Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የክስ መቃወሚያ አቀረቡ * ብርሃኑ “እንዴት ማረሚያ ቤቱን ትከሳለህ”ተብሎ ወረቀቱን ተነጥቋል

0
0

birhanu tekle
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

መንግስት የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን ተሻግረው ኤርትራ የሚገኘውንና በተወካዮች ም/ቤት በሽበርተኝነት የተፈረጀውን የግንቦት ሰባት ወታደራዊ ክንፍ ሊቀላቀሉ ሲሉ በጸጥታ ኃይሎች ማይካድራ ላይ በቁጥጥር ስር አውያቸዋለሁ ያላቸው እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ክስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያቸውን አስገቡ፡፡

ዛሬ ሰኔ 9/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የቀረቡት በእነ ብርሃኑ ተክለያሬድ የክስ መዝገብ የተካተቱት አራት ተከሳሾች ማለትም፣ ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማውና ደሴ ካህሳይ በጋራ ያዘጋጁትን የክስ መቃወሚያ አስገብተዋል፡፡ አራቱ ተከሳሾች ጠበቃ ማቆም አንፈልግም በማለታቸው ያለጠበቃ የቀረቡ ሲሆን፣ ተከሳሾቹ በክስ መቃወሚያቸው ላይ ሁለት አብይት ነጥቦችን በመጥቀስ ክሱ ውድቅ ተደርጎ በነጻ እንዲሰናበቱ ጠይቀዋል፡፡

ተከሳሾቹ በክስ መቃወሚያቸው ላይ እንደጠቀሱት አቃቤ ህግ ያቀረበባቸው ክስ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚጣረስና (ጸረ-ሽብር አዋጁ ከህገ መንግስቱ ጋር እንደሚጣረስ በመጥቀስ) በወ/መ/ሥ/ሥ/ህጉ መሰረት ያልቀረበ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ እንደ ህጉ ያልቀረበን ክስ ውድቅ በማድረግ በነጻ ያሰናብተን ብለዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ በተከሳሾች የቀረበው አቤቱታ ላይ አቃቤ ህግ መልስ እንዲሰጥ በሚል ለሰኔ 19/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በሌላ በኩል አንደኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ተ/ያሬድ በተደጋጋሚ በእስር ቤት በሚደርስበት በደል ላይ አቤቱታ ማሰማቱን ቀጥሏል፡፡ በዚህም ፍርድ ቤቱ አቶ ብርሃኑ አለኝ የሚለውን አቤቱታ በጽሑፍ እንዲያቀርብ አዝዞ የነበር ቢሆንም አቶ ብርሃኑ የማዘጋጀውን አቤቱታ ‹‹እንዴት ማረሚያ ቤቱን ትከሳለህ›› በሚል ጽሑፉን እየተነጠቀ እንደሆነ በመግለጽ አቤቱታውን በጽሑፍ ማቅረብ እንዳልቻለ አስረድቷል፡፡

ይህን የአቶ ብርሃኑን አቤቱታ በተመለከተ የማረሚያ ቤቱ ተወካይ ችሎት ፊት እንዲቀርቡ ተደርገው ‹‹ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ያለውን አቤቱታ እንዲያቀርብ አዝዘናል፤ ስለዚህ እናንተ መልስ ካላችሁ መልሳችሁን እንቀበላለን፣ አሁን ግን ተከሳሹ የሚያዘጋጀውን አቤቱታ እንዲያቀርብ አድርጉ›› በማለት በፍርድ ቤቱ ተነግሯቸዋል፡፡ በመሆኑም አቶ ብርሃኑ በቀጣዩ ቀጠሮ በእስር ቤት አያያዝ ላይ ያለውን አቤቱታ በጽሑፍ ይዞ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

The post እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የክስ መቃወሚያ አቀረቡ * ብርሃኑ “እንዴት ማረሚያ ቤቱን ትከሳለህ” ተብሎ ወረቀቱን ተነጥቋል appeared first on Zehabesha Amharic.


2.36, የ1 ለ5 አደረጃጀትና በሀገር ላይ የጋረጠው አደጋ! –ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

0
0

ሰኔ 2007ዓ.ም.

 

Amsalu

ከአምሳሉ ገ/ኪዳን

በዚህ ጽሑፍ የ1 ለ5 አደረጃጀት ማለት ምን ማለት ነው?፣ የ1 ለ5 አደረጃጀት ዓላማ ምንድን ነው? ይህ አደረጃጀት አገዛዙ እንደሚለው ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ዓላማ የለውም ወይስ አለው?፣ አደረጃጀቱ ሕጋዊ አሠራር ነው ወይስ አይደለም?፣ ይህ አደረጃጀት ከሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ (በይነ ሕዝባዊ) መብቶች አንጻር የጋረጠው አደጋ አለ ወይስ የለም? የሚባሉ ነጥቦችን በዝርዝር ዕናያለን፡፡

ይህ አደረጃጀት መጀመሪያ ላይ ሥራ ላይ የዋለው ትግራይ ላይ ነበር፡፡ በእርግጥ ይሄንን ዓይነት አደረጃጀት ወይም ጥርነፋ ወያኔ በረሀ እያለ ጀምሮ ሲጠቀምበት የነበረ አሠራሩ ነው፡፡ ወያኔ የህልውናየ መሠረት የሚለው የትግራይ ሕዝብ በሌሎች ተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች እንዳይወሰድበት ለመከላከል ለመጠበቅ ሲል ነበር እዚያ ሥራ ላይ አውሎት የነበረው፡፡ ይህን አደረጃጀት በተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይም መተግበር ያስፈለገበት ምክንያት ወያኔ ሕዝቡን በየ ብሔረሰቡ ስም ባደራጃቸው የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች እንደ ብአዴን ኦሕዴድና የመሳሰሉት የሕወሀት አሻንጉሊት ድርጅቶች በተለያየ መንገድ እያስገደደ አባል እንዲሆን ያደረገው ጥረት እንብዛም የፈለገውን ያህል ውጤት ስላላመጣለት ሌላ ዘዴ በመጠቀም ጥቅሙን ለማስጠበቅ ትግራይ ላይ ውጤታማ አድርጎኛል ብሎ የሚያስበውን የ1 ለ5 አደረጃጀት “ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ዓላማና ተልዕኮ የለውም” እያለ በተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል ላይም ተግባራዊ ለማድረግ አስቦ ነው ይሄንን ያደረገው፡፡ ዛሬ ላይ ከ3ኛ ክፍል ሕፃናት ጀምሮ እስከ መንደር ሽማግሌና አሮጊቶች ድረስ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከገጠር እስከ ከተማ ከመንግሥት ሠራተኛ እስከ የግል ድርጅት ሠራተኛ አልፎም የሃይማኖት ተቋምንም በማጠቃለል አባቶችና አገልጋዮች ድረስ በ1 ለ5 አደረጃጀት ያልተጠረነፈ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ብትፈልጉ አታገኙም ወይም ቢፈለግ እንዳይገኝ በብርታት እየሠሩ እየጣሩ ይገኛሉ፡፡

1 ለ5 አደረጃጀት ማለት ምን ማለት ነው?

ብዙ ሰዎች 1 ለ5 አደረጃጀት ሲባል አምስቱ የሕዝቡ ወገን ሆነው አንዱ ጠርናፊው ደግሞ የወያኔ አባል ይመስላቸዋል፡፡ በእርግጥ በአጋጣሚ አልፎ አልፎ እንዲህ ዓይነት ሁሌታ ሊያጋጥም ቢችልም አደረጃጀቱ ግን እንደዚህ አይደለም፡፡ የሚበዛው የ1 ለ5 አደረጃጀት 6ቱም የሕዝብ አባላት የሆኑበት ነው፡፡ ሕዝቡን በሥራ ቦታ ወይም በመንደር እንዳለው ቅርበት በስድስት በስድስት ያቧድኑና ከመሀላቸው አንዱን ትምህርት ያለውን ወይም ነቃ ያለውን መሪ በእነሱ አማርኛ ጠርናፊ ያደርጉታል፡፡ በዚህ አደረጃጀት የመታቀፍ ያለመታቀፍ ጉዳይ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ አይደለም፡፡ እንቢ አልደራጅም ማለት አይቻልም ክልክል ነው ቀለል ሲል ከወያኔ ተጻራሪ ከበድ ሲል ከአሸባሪነት ያስቆጥርና ከሥራ ከትምህርት ከመሳሰሉት ያስባርራል፣ የተለያዩ የዜግነት ጥቅሞችንና መብቶችን ያሳጣል፡፡ ይሄ ግን በድርጊት ሲሆን ታዩታላቹህ እንጅ በይፋ በአዋጅ አይነገርም፡፡ አሠራሩ ሕገ ወጥ በመሆኑ አገዛዙ በይፋ እንዲህ ማለት ስለማይችል እንቢ ያለውን ዜጋ ሌላ ሰበብ እየፈለገ የሚያጠቃበትና የሚያሳምንበት አኪያሔድ አለው የአሠራር ስልት መሆኑ ነው፡፡ ቀደም ሲል እነኝህን ቅጣቶች የሚያስቀጣው የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባል ሆኖ በመገኘት መንቀሳቀስና አገዛዙ የኔ አባል ሁን ወይም ሁኝ ሲል አልሆንም አልፈልግም ሲባል ነበር፡፡ በየ ፓርቲው ሔዳቹህ ብትጎበኟቸው የዚያ ፓርቲ አባል ሆነው በመንቀሳቀሳቸው ከሥራ ገበታቸው የተባረሩ ከከፍተኛ ትምህርታቸው የተባረሩ የከፍተኛ ትምህርት ዕድል የተነፈጋቸው የተለያየ የሕገ ወጥ ጥቃት ሰለባ የሆኑ ዜጎችን በብዛት ታገኛላቹህ፡፡

እሩቅ ሳልሔድ እኔ እራሴ አንዱ ምሳሌ ነኝ፡፡ እኔ እንዲያውም የማንም የፖለቲካ ድርጅት አባል አይደለሁም፡፡ ነገር ግን የዜግነት ግዴታየን ለመወጣት፣ በማያቸው በምታዘባቸው ጉዳዮች ላይና በሚታየኝ ነገር ሁሉ ላይ በመጽሔቶች ጋዜጦችና ድረ ገጾች ላይ ስለምጽፍ (ምን ስለምጽፍ አሁንማ እነዚያ እጽፍባቸው የነበሩ መጽሔቶች ሁሉም በአገዛዙ አንባገነናዊና አፋኝ ትዕዛዝ ስለተዘጉ እጽፍ ስለነበር ብል ይሻላል መሰል) በዚህ የያገባኛል እንቅስቃሴየ ምክንያት “እየተሰለልን ነው” በሚል ለ12 ዓመታት ስሠራበት የነበርኩበት ድርጅት ከአራት ዓመታት በፊት ከሥራየ አባረረኝ፡፡ በዚሁ እንቅስቃሴየ ምክንያት ሌላ ቦታም የሚቀጥረኝ ማግኘት አልቻልኩም፡፡ አሁን አሁንማ የእግዜር ሰላምታ የሚሰጠኝ ሰውም እያጣሁ ነው በተለይ መጽሔት ላይ በጻፍኩት ጽሑፍ ታስሬ ከተፈታሁ በኋላ፡፡ ኑሮየ በጣም ነው የተመሰቃቀለው፡፡ አንደኛየን ብረት ወዳነሡት ጀግኖች ወገኖቸ ተቀላቅየ እንዳልታገልም እውነቱን ለሕዝብ ለማስገንዘብ ለማሳወቅ፣ የሀገሬን ጥቅም ለማስጠበቅ ስል ሸአቢያና ኢሳይያስ ፍጹም የተሳሳቱና አጥፊ እንደሆኑ ወይም “እንደነበሩ” ጠንካራ ጠንካራ የመከራከሪያ ነጥቦችን በመጥቀስ መታረማቸው የግድ እንደሆነ በጻፍኳቸው ጽሑፎች አስተሳሰቤን ዓላማየንና አቋሜን በማስታወቄና የኢሳይያስን ወይም የሸአቢያን ጥቅምንም ስለጎዳ በዚህም ምክንያት ስላቄሙብኝ የውስጤን በውስጥ አድርጌ ለሀገሬ ያለኝን ዓላማ ከነሱ ደብቄ እዚያ ገብቸ እንድታገል የሚያስችለኝ ዕድል ስለሌለኝ መቀላቀል አልቻልኩም፡፡

ወደ ኬንያ እንዳልሰደድ አሁንም የሀገሬን ጥቅም ለማስጠበቅ ያለውን እውነታ ለሕዝብ ለማሳወቅ ለማስገንዘብ ስል በጻፍኳቸው ጠንከር ደፈር ያሉ ጽሑፎች ኦነግና እስልምናን ተንተርሰው ዓለምን የሚያሸብሩት አሸባሪ ቡድኖች ሊያስተባብሏቸው በማይችሏቸው አመክንዮዎችና የመከራከሪያ ሐሳቦች ድንቁርናቸውና ሰይጣንን አገልጋይነታቸው ቁልጭ ብሎ በመታየቱ በዚህ በመበሳጨት አርደው እንደሚጥሉኝ ክፉኛ ዝተውብኛልና ኬንያ እንደገባሁ አፍነው ስለሚወስዱኝ እዚያም መሔድ አልችልም፡፡ ምን እባካቹህ እኔ በሀገሬ ላይ ሰይጣናዊ ጦሩን የወረወረውን ማንኛውንም አካል ሁሉ እኔም መልሸ ያልወጋሁት ያላቆሰልኩት አለ እንዴ! የጸፍኩባቸው ሁሉ አቂመውብኝ በተለያየ መንገድ ጥርስ እንደነከሱብኝ አሳውቀውኛል፡፡ አይሁዶቹም አልቀሩ ዝተውብኛል፡፡ የምዕራባዊያኑን ባላውቅም እነሱም ለውድቀት ጥፋታችን ዋነኛ ጠንቆች እንደመሆናቸው ከብዕር ሰይፌ አላመለጡምና እስከ አሁን ያሉኝ ነገር ባይኖርም ጥርስ አልነከሱብኝም ማለት ግን አልችልም፡፡ ይሄንን ስል አንዳንድ ሰዎች “ራስህን ማን ታደርጋለህ ባክህ! አንተ ማን ነህና ለእነዚህ ሀገራትና ቡድኖችስ ምን ያህል ሥጋትና አደጋ ሆነህ ነው ይሄንን ያህል ትኩረት የሚሰጥህ?” የሚሉ ሰዎች ይኖሩ ይሆናል፡፡ እኔ ማንም ስለሆንኩ አይደለም፡፡ ይሄንን የሚሉ ሰዎች ብዕር ያለውን ኃይል ካለማወቅ የተነሣ ነው እንዲህ የሚሉት፡፡ አውሮፓውያን “ከእልፍ ጦር አንድ ብዕር” የሚል አባባል አላቸው ናፖሊዮን ቦና ፓርቲም ተመሳሳይ ጥቅስ አለው “The pen is mightier than the sword, ከሰይፍ ይልቅ ብዕር ያይላል” የሚል፡፡ በእኛም ሀገር “ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው” ይባላል፡፡ ብዕር ማለት ክብሪት ማለት ነው፡፡ ክብሪት ትንሽ ናት ተብላ አትናቅም ሀገር ልታቃጥል ትችላለች፡፡ ምዕራባዊያን የብዕርን አቅም ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ በእነሱ መርሕ ምንም ዓይነት መረጃ አይናቅም ምንም ዓይነት ትችት ቸል አይባልም፡፡ ከዚህ አንጻር ከምትገምቱት በላይ እነኝህ ሀገራት ኤምባሲ (የመንግሥት እንደራሴ ጽ/ቤት) እና ቆንሲላ (የመንግሥት ጉዳይ አማካሪ ጽ/ቤት) ባላቸው ሀገራት ሁሉ የየሀገሮቻቸውን ጥቅም የሚጋፉ ማንኛውም ዓይነት መጣጥፎችን በከፍተኛ ትኩረት ይከታተላሉ ይመለከታሉ፡፡ በተለያየ መንገድ የመልሶ ማጥቃት እርምጃን ይወስዳሉ ወይም በጥቅም ሊይዟቹህ ይሞክራሉ፡፡ በግል የሚደርሱኝ ዛቻና ማስፈራሪያዎች ያረጋገጡልኝ ነገር ቢኖር ይሄንን ነው፡፡ በተለይ የምትጽፉት ነገር በአሳሳቢ ጉዳዮች ላይ ጠንካራና አሳማኝ ከሆነ ፕሮፌሰር ሆናቹህ ታራ ዜጋ የናንተ ደረጃ ለነሱ ጉዳያቸው አይደለም፡፡ የሚያተኩሩት በጽሑፉ ጥንካሬ የተነሣ በጥቅማቸው ላይ ሊያመጣ የሚችለው አሉታዊ ውጤት በምን ያህል ደረጃ ጥቅማችንን ይጎዳል? የሚል መሆኑ ነው የሚያሳስባቸውና በቸልታ መመልከት የማይፈልጉበት ምክንያት፡፡

እናም እንግዲህ ያለኝ አማራጭ ወያኔ እስኪያጠፋኝ ድረስ እየራበኝም እየጠማኝም እዚሁ መታገል ነው፡፡ የግል ሕይዎቴን እንዳይጎዳብኝ፣ እራሴን ለአደጋ እንዳላጋልጥ፣ በራሴ ላይ ጠላት እንዳላበዛ ብየ ስልታዊ አኪያሔድ አልከተልም፤ ማድረግ ካለብኝ ነገር አልታቀብም፡፡ ዓላማየ መቸ እንደምሞት አላውቅምና በሕይዎት እስካለሁ ድረስ ሀገሬ ከኔ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ መጣር፣ ሕዝባችን ማወቅ መገንዘብ መረዳት ያለበትን ነገር ሁሉ በሰዓቱ እንዲያውቅ ማድረግ፣ የሀገሬን ጥቅም ለማስጠበቅ የመጨረሻ አቅሜን በመጠቀም መጣር ነው፡፡ ስንት ወገን መቸ በምን ምክንያት እንደሚሞት የሚያውቅ ይመስል ምቹ ጊዜን ሲጠብቅ አንዳችም ነገር ሳያበረክት ሳይጠቅም አፈር የገባ አለ መሰላቹህ፡፡ ሀገርም ከነሱ ማግኘት የነበረባትን ስንት ጥቅም በማጣቷ እንዴት ተጎድታለች መሰላቹህ?

የፖለቲካ ፓርቲ አባል ተሁኖ ወይም ሳይኮን ወያኔን እታገላለሁ፣ ሀገሬን አገለግላለሁ፣ የዜግነት ኃላፊነቴንና ግዴታየን እወጣለሁ፣ ለሆዴ አድሬ ኅሊናየን በማርከስ እራሴን በማዋረድ ከሰውነት ወደ እንስሳነት አልለውጥም፣ ባሪያ አልሆንም፣ የሀገሬ ጠላት አልሆንም ማለት እንግዲህ ይሄንን ይሄንን ለመሳሰለ ፈተናና መከራ ይዳርጋል፡፡ ይሁን እንጅ እኔ በበኩሌ በእነኝህ ውርደቶች የጎደፈ የረከሰ ሰብእና ስለሌለብኝ ውሳጣዊ ሰላም አለኝና ፈጽሞ አልጸጸትም፡፡ በተለየ ምክንያት ወይ ባላቸው ጉብዝና በንቁነታቸው ወይም ደግሞ ወያኔ በራሱ ምክንያት አባሌ ሁኑ ብሏቸው እንቢ አንሆንም አንፈልግም በማለታቸው ብቻ ከከፍተኛ ትምህርት ገበታቸው የተባረሩ በርካታ ዜጎች አሉ፡፡ ከእነኝህ አንዱን ብቻ ለምሳሌ ያህል ላቅርብ፡፡

መጋቢት 6, 2004ዓ.ም ላይ አንድ በሀገራችን ውስጥ ሥራ ላይ ካሉ ሕጎች ውጭ በሆነ ወይም በማይፈቅዱት ሁኔታ ተቋቁሞ በሕገ ወጥ መንገድ ሲሠራ በቆየና እየሠራም ባለ የራሱን ከተለያየ አቅጣጫ የተቀናጀ የኢኮኖሚ ኢምፓየር (የሀብት ግዛት) እስከ መገንባት የደረሰ ቀደም ሲል የሕወሐት ፓርቲ የነበረ የገዛ ሕጋቸው እንደማይፈቅድ ከየአቅጣጫው አቤቱታ ሲበዛባቸው የአክሲዮን (የማኅበር) ነው ቢሉም ባለንብረትነቱ እነማን እንደሆኑ በማይታወቀው ፋና በሚባል የሬዲዮ (የነጋሪተ-ወግ) ጣቢያ ላይ አንድ ሳምንታዊ ዝግጅት በመተላለፍ ላይ ነበር፡፡ ይህ ምስናድ የቀጥታ ዝግጅቱን በሚያስተላልፍበት በዚህ ዝግጅቱ ስቱዲዮ (መከወኛ ክፍል) እስኪገኙላቸው ድረስ የምስናዱ አዘጋጆች ለሥራቸው መቃናት ሲሉ ሌላ ሌላ ምክንያቶችን በመስጠት ለምን ጉዳይ እንዳመጧቸው አያውቁ የነበሩት መከወኛ ክፍል ውስጥ እንዲገኙ የተደረጉት እንግዳ ከልጃቸው ጋር እንዲታረቁ እዚያ እንደተገኙ ከተነገራቸው በኋላ አዘጋጆቹ ለሚጠይቋቸው ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ ከቆዩ በኋላ በድንገት በብሶት በመገፋት ሁላችንም የምናውቀውን ደፍረን ግን በአደባባይ የማናወራውን ነገር መናገር ጀመሩ፡፡

እንዲህም አሉ “እኔ ልጀን ጠልቸ አይደለም ልጀን እንዴት እጠላለሁ? ለ26 ዓመታት በረሀ ተቃጥዬ ነው ያሳደኳቸው ነገር ግን የት ይደርሱልኛል ያልኳቸው ተስፋ የጣልኩባቸው ልጆች ከንቱ በመሆናቸው ውስጤ በጣም ስለተጎዳ ጤና አሳጥቶኝ፤ ይህች እንደምታይዋት ጎረምሳ አታሏት ካስወለዳት በኋላ “ዞር በይ አላውቅሽም” ብሎ ሸኛት ሕይወቷን አበላሸብኝ ያኛው የሷ ታላቅ ጥሩ ጭንቅላት ነበረው ጎበዝ ተማሪ ነበር አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የዲግሪ ተማሪ ነበር “አባል ካልሆንክ አትማራትም” እያሉ ይሄው ለሦስተኛ ጊዜ በተከታታይ ዓመታት እያባረሩት ዘንድሮም እዲያቋርጥ አደረጉት እስካሁን ተመርቆልኝ ነበር” እያሉ እንባ በተናነቀው ተስፋ በቆረጠ ድምፅ እየተናገሩ እንዳሉ ጋዜጠኞቹና የነጋሪተ-ወጉ ኃላፊዎች ሰውየው እንዲናገሩ የማይፈልጉትንና የማይፈቅዱትን የአገዛዙን ግፍ ሳያስቡት በመናገር ላይ እንዳሉ በድንገቱ የተደናገጡት አዘጋጆቹ ተጣድፈው አቋረጧቸው፡፡ አሁን እንግዲህ ይሄ ልጅ በገዛ ሀገሩ ላይ ተምሮ መለወጥ ሠርቶ ማደር ባለመቻሉ ያለመሰደድ ሌላ አማራጭ አለውን? ይሄኔ ተሰዶም ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ተማሪ የደረሰበት ችግር ሁሉም ላይ የሚደርስ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ዜጎች እንዲህ ዓይነት መሥዋዕትነቶችን እየከፈሉ ወያኔ የፈለገው ነገር ሊሆን ስላልቻለ ለሽፋን ያህል “ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ዓላማ የለውም ዓላማው የልማት ሠራዊትን መፍጠር ብቁ ተወዳዳሪና ታታሪ ሠራተኞችን ማፍራት ነው” እያለ የ1 ለ5 አደረጃጀትን አመጣ፡፡

የ1 ለ5 አደረጃጀት ዓላማ ምንድን ነው?

የዚህ አደረጃጀት ዓላማ ሕዝብ ያለውን ሰብአዊና ሕገ መንግሥታዊ መብቶችና ነጻነቶችን በማሳጣት መበንጠቅ በአገዛዙ ፈቃድና ፍላጎትና ቁጥጥር ሥር ቀፍድዶ ለመያዝና ተቃዋሚ ወይም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ወያኔ የደህንነቴ ሥጋት ናቸው የሚላቸው ሕዝባዊ ማኅበራት ሕዝባዊ መሠረት እንዳያገኙ ማድረግ መከላከል ነው፡፡ አገዛዙ ግን እያለ ያለው “የልማት ሠራዊት ለመፍጠር” ነው፡፡ ይህ ግን ሽፋን ነው፡፡ በእርግጥ ከገጠር እስከ ከተማ ከተማሪ እስከ ሠራተኛ ሕዝቡን ሲያደራጀው አንዳንድ የልማት እንቅስቃሴዎችንና ርእሰ ጉዳዮች (አጀንዳዎች) አድርጎ በማንሣት እንዲንቀሳቀሱበት ያደርጋል፡፡ ለምሳሌ ተማሪዎችን ከ3ኛ ክፍል ጀምሮ ካደራጀሁበት ምክንያቶች አንዱ የሚለው፡- “የተሻለ ዕውቀት ያለው ተማሪ ደከም ያሉትን አምስቱንም በማስረዳትና በማስጠናት እሱ ካለበት ደረጃ ላይ ማድረስ አንዱ ኃላፊነቱና ግዴታው ነው” በማለት ነው፡፡ ይሄ አሠራር ምንም እንኳ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ባይንም የሚበረታታ እንጅ የሚነቀፍ የሚኮነን አልነበረም ችግሩ ያለው እዚህ ላይ አይደለም፡፡

ይህ አደረጃጀት አገዛዙ እንደሚለው ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ዓላማ የለውም ወይስ አለው?

አገዛዙ ፖለቲካዊ (እምነተ አሥተዳደራዊ) ዓለማ የለውም የሚለው ሐሰት ነው፡፡ ዋነኛ ዓለማው ፖለቲካዊ ነው፡፡ ፖለቲካዊ ነው ስል የሀገርንና የሕዝብን ሳይሆን የሕወሐት ኢሕአዴግን ጥቅምና ዓላማ ለማስጠበቅ ሲባል የተዘረጋ ሥራ ላይ የዋለ አደረጃጀት አሠራር ነው ማለቴ ነው፡፡ እንዴት ሆኖ ነው ከተባለ አገዛዙ “የአካባቢ ሰላምና መረጋጋት” የሚል አጀንዳን (ርእሰ ጉዳይን) ለየ1ለ5ቱ አደረጃጀት በማንሣት የፖለቲካ ፓርቲዎችንና በክርስትናውም በእስልምናውም ያሉ አገዛዙ በግልጽ “አክራሪ ብሎም አሸባሪ” በሚል የሚጠራቸውን ማኅበራትንና በውስጣቸው ያሉ ግለሰቦችን የአካባቢ የሀገር ሰላምና መረጋጋት ሥጋቶችና ጠንቆች እንደሆኑ አድርጎ ይሰብካል ስም ያጠፋል፡፡ ይሄንን ማለቱ የሚለው ነገር በሕዝቡ ዘንድ ታምኖለት ሕዝቡ እነኝህን አካላት እሱ እንደሚለው ፀረ ሰላምና መረጋጋት አድርጎ ይወስዳቸዋል ከሚል እምነት ሳይሆን ሕዝቡን የእነኝህ አካላት አባል ደጋፊ እንዳይሆን ለማሸማቀቅ ለማራቅ “የእነኝህ አካላት አባል ደጋፊ ብትሆን ወዮልህ!” የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ለማስያዝ የሚያደርገውና በአጭር ጊዜ እንዲከስሙ ለማድረግ የሚጠቀምበት ዘዴ ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ ሕዝቡ የወያኔን ሐሰተኛ የስም ማጥፋት አምኖበት ሳይሆን በ1ለ5 በመጠርነፉ ብቻ በፈጠረበት የበእንተእፍረት ስሜት ሊከበርለት የሚገባውን ሰብአዊና ሕገመንግሥታዊ መብቶቹን ለመጠየቅና በሕጋዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችም ደፍሮ እንዳይሳተፍ ከእንደዚህ ዓይነቶች እንቅስቃሴዎች ራሱን እንዲያርቅ እንዲያገል አድርጎታል፡፡ ወያኔም እያስገደደ ሕዝቡን በዚህ አደረጃጀት ሲጠረንፍ ቢያንስ ይህችን የሥነ ልቡና መሸበብ ውጤት እንደሚያስገኝለት በመተማመን ነው፡፡

እነኝህ ወያኔ ስማቸውን የሚያጠፋባቸው አካላት ለአገዛዙ “ልብ በሉ” ለአገዛዙ አደጋ ይሆኑ ይሆናል፡፡ ለዚህ አገዛዝ አደጋ ናቸው ማለት ግን ለሀገርና ሕዝቧ አደጋ ናቸው ማለት በፍጹም አይደለም፡፡ ወያኔ ለዚህች ሀገርና ሕዝቧ ቅን አሳቢ አይደለምና ከእሱ በተሻለ አልልም እንጅ ላቅ ያለ የሀገርና የወገን ፍቅር የሚያቃጥላቸው ለሀገርና ለወገን የሚያስቡ የዜግነት ድርሻቸውንም ለማበርከት የሚታትሩ መሆናቸው በሕዝብ ዘንድ በሚገባ ይታወቃል፡፡ የአገዛዙና የእነኝህ አካላት መሠረታዊ ልዩነትና የጥቅም ግጭትም ይሄው ነው፡፡ እሱ ሊያፈርሰው ሊንደው ሌት ተቀን የሚጥርበትን የሚለፋበትን የሀገር ፍቅር ስሜት፣ ዘርና ሃይማኖት ያልተለየበት የአንድነትና ትስስር ጥንካሬንና ሌሎች እሴቶቻችንን እሱ በናደ ባፈረሰ ቁጥር ከስር ከስር የሚገነቡ መሆናቸው ነው፡፡ አሁን ታዲያ ለዚህች ሀገር ሰላምና መረጋጋት አደጋው ማን ነው? መንግሥት ነኝ ከሚል አይደለም ከጠላት እንኳን በማይጠበቅ ደረጃ መርዘኛ ሴራ እየሸረበ ሕዝቡን በዘርና በሃይማኖት ሊያፋጀን እየጣረ ያለው፣ ከሕዝብ ዕውቅናና ይሁንታ ውጪ የሀገርን ሉዓላዊ መሬታችንን እየቆራረሰ ለጎረቤት ሀገራት እያደለ ያለው፣ ከአንድም ሁለት ሦስት ብሔረሰቦችን በጠላትነት ፈርጆ ጨርሶ ለማጥፋት የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን እየፈጸመ ያለው፣ ሌላም ሌላም በርካታ የሀገር ክህደቶችንና አደጋዎችን እየፈጸመብን ያለው ወያኔ ወይስ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ (ሕዝባዊ) ማኅበራት? ሕዝቡ ይሄንን ጠንቅቆ ያውቃልና አይሳሳትም፡፡ ወያኔም ሕዝቡ ያምነኛል ብሎ አይደለም ይሄንን ሐሰተኛ ወሬ የሚነዛው፡፡ ነገር ግን “እንዲህ ናቸው ብያለሁ እኔ የማውቃቸው በዚህ መልኩ ነው እያንዳንድህ ሔደህ ብትቀላቀል አንተም አሸባሪ ፀረ ሰላምና መረጋጋት ነው ብየ ፍዳህን አሳይሀለሁ!” የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ነው፡፡

በመሆኑም ወያኔ ይሄንን አደረጃጀት ያዋቀረው እንዲህ ዓይነት ፖለቲካዊ ጥቅሙን ሊያስጠብቅበት ህልውናው ለአደጋ እንጋይጋለጥ ሊከላከልበት በመሆኑና እየሠሩት ያለውን ሥራ የመሥራት ሕገ መንግሥታዊና ሰብአዊ መብታቸው የሆኑ አካላትን እያጠቃበት ያለ አደረጃጀት በመሆኑ ይህ አደረጃጀት ዋነኛ ዓለማውና ግቡ ፖለቲካዊ እንጅ ልማታዊ አይደለም፡፡ ወያኔ የእነኝህ ፖለቲካዊና ሕዝባዊ ማሕበራትና ድርጅቶች ሥራ መብታቸው እንደሆነ ተረድቶ በዚህ አደረጃጀት ላይ ይሄንን የስም ማጥፋት አጀንዳ እያነሣ እነኝህ አካላትን ሕዝባዊ ተቀባይነት እንዳይኖራቸው የሚሠራበት አደረጃጀት ባይሆንና ንጹሕ የልማት ሥራ ብቻ የሚሠራበት አደረጃጀት ቢሆን ኖሮ ይህ አደረጃጀት ፖለቲካዊ ዓላማ የለውም ልማታዊ ነው ባልን ነበር፡፡ እየሆነ ያለው ግን የዚህ ተቃራኒ በመሆኑ የሚወገዝና የሚኮነንም ነው፡፡

ወያኔ እሱን የማይመስሉትን ሁሉ ለሀገርና ለወገን ተቆርቋሪ እንደሆኑ ልቡ እያወቀ የፈጸመብንንና እየፈጸመብን ያለውን የሀገር ክህደቶችና ወንጀሎቹን ስለሚያጋልጡ ከዚህም የተነሣ ለህልውናየ አደጋና ጠንቅ ናቸው ብሎ ስለሚያስብ ብቻ ለሀገርና ለወገን ተቆርቋሪ የሆኑትን ሁሉ “ፀረ ሰላም ፀረ ሕዝብ በመሆናቸው፣ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ በመሞከራቸው” የሚል ክስ እያነሣ በርካታ ንጹሐን ወገኖቻችንን በግፍ ገሏል አስሯል አንገላቷል፡፡ ሕዝብ ግን እውነቱን ያውቃል፡፡ በዚህች ሀገር ሕገ መንግሥቱንና የሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትን በኃይል የሚያፈራርስ የሚያመሰቃቅል ጠላት ከወያኔና መሰሎቹ በላይና ሌላ ማንም የለም፡፡ ወያኔ እኮ የገዛ የራሱን ሕገ መንግሥት ለአንድም ቀን እንኳን አክብሮ የማያውቅ ለ24 ዓመታት ሲያፈራርሰው ሲሸራርፈው የኖረ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት እንዳይመሠረት ደንቃራ የሆነ አካል ነው፡፡ ሲጀመር ሕገ ምንግሥታዊ ሥርዓት በዚህች ሀገር የለም፡፡ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት በሌለበት ሁኔታ “ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመጣል” የሚለው ክስ አስቂኝና አሳፋሪ ነው፡፡

የምለው ነገር ቢኖር የሀገራችንና የሕዝባችንን ጥቅምና ህልውና አለመቀናቀናቹህን አለመቃረናቹህን እርግጠኛ ሁኑ እንጅ በወያኔ ላይ ብታምፁና ለማመፅ ባታስቡ ብረት ብታነሡና በወያኔ ላይ ብትተኩሱ “ፀረ ሕዝብና ፀረ ሰላም” ወይም “ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመጣል” የሚል ክስ ይነሣብኛል እንዲህ እባላለሁ እፈረጃለሁ ብላቹህ ቅንጣት እንዳትሠጉ እንዳታስቡ ወይም በወያኔና በጌቶቹ “አሸባሪ” የምትባሉ በመሆናቹህ ቅንጣት ታክል ሊደንቃቹህ ሊገርማቹህ ሊያሳስባቹህ በፍጹም በፍጹም የሚገባ እንዳልሆነ መረዳት ይሆርባቹሀል፡፡ እየሠራቹህ ያላቹህት እንደ እናት አባቶቻችን ሀገርንና ሕዝብን የመታደግ የአርበኝነት ተግባር እንጅ እንደ ወያኔ የውንብድና ተግባር አይደለምና፡፡ ወያኔ የሀገርና የሕዝብ ጠላት እስከሆነ ጊዜ ድረስ ወያኔንና መሰሎቹን መዋጋት ጥቅማቸውን መጉዳት ለአንድ ዜጋ መብቱ ብቻ ሳይሆን የዜግነት ግዴታውም ነው፡፡ ሀገር አልባ ሆነናል ሀገራችንን ተቀምተናል ሕዝባችን ባለቤት እንደሌለው ውሻ የትም ተቅበዝባዥ ሆኗል፣ ውርደት መለያችን ሆኗል፣ ሀገሪቱ የአንድ ጎሳ ብቻ ሆናለች ይሄንንም ዘለዓለማዊ ለማድረግ በከፍተኛ ደረጃ እየተሠራበት ይገኛል፣ በሀገራችን መኖር የማንችልበት ሁኔታ በመኖሩ ከሞት ማዶ ያለችን መንማና የሕይዎት ተስፋን የማግኘት አደገኛን የስደት አማራጭ ለመጠቀም ተገደናል፣  በገዛ ሀገራችን በውጭ ዜጎች በሰብአዊ ክብራችን ላይ አስነዋሪና ዘግናኝ ጥቃቶች እንዲፈጸምብን እየተደረገ ቅስማችንንና ብሔራዊ የማንነት ክብራችንን ለመግደል ለመሰባበር፣ በውርደት ስሜት አፍረን ተሸማቀን እንድንቀር ለማድረግ በየዕለቱ ሊባል በሚችል ደረጃ ጥረቶች ተደርገውብናል እየተደረጉብንም ይገኛል፡፡

በእርግጥ ላሚቱ ላይ ተተክሎ ደሟን የሚመጠውን መዥገር እናንሣ እናስወግድ እንንቀልላት ሲባልና ሲነቀል መዥገሩ ላለመነቀል ነክሶ ስለሚይዛት በግድ ስትነቅሉት የላሚቱ ገላ ተቦጭቆ መጎዳቱና መድማቱ አይቀርምና፤ ወይም ደግሞ ከላሚቱ አካል ላይ ያለውን መግልና ደም የያዘ እባጭ አፍርጠን አፍሰን ላሚቱን ከዚህ ሰላሟን ካሳጣት ሕመሟ እንገላግላታለን እፎይ እናሰኛታለን ብላቹህ ይሄንን ስታደርጉ ላሚቱን ለጊዜው ሕመም ሊሰማት መቻሉ አይቀርምና የዚህችን ሀገርና ሕዝብ ጠላት ወያኔን ለማስወገድ ወያኔን እናጠቃለን ስንል የሀገር ጥቅም መነካቱ መጎዳቱ አይቀርም ይሆናል፡፡ ነገር ግን ጉዳቷ መግሉ ተፍረጥርጦ እስኪፈስ መዥገሩ እስኪነቀል ድረስ ጊዜአዊና ለዘለቄታዊ ጥቅም ደህንነትና እፎይታ ሲባል የሚደረግ ነውና እንደ ጉዳት የሚቆጠር ባለመሆኑ ይሄ አያሳስባቹህ፡፡ የሀገር ጥቅም ተነካ ብላቹህም አትዘኑ፡፡ ይህ ሳይሆን ቁስሏን ማከም መዥገሯን ማንሣት አይቻልምና፡፡

ስለሆነም ወያኔ የራሱን ጠላት ነገር ግን ለሀገርና ለወገን የሚታገሉትን የሀገርንና የሕዝብን ልጆች የሆኑ አካላትን የሀገርና የሕዝብ ጠላት እንደሆኑ አድርጎ ሊፈርጅና የኢትዮጵያም ሕዝብ እንደዚያ አድርጎ እንዲቆጥራቸው እንዲያስባቸው ማድረግ የሚያስችለው ምንም ዓይነት ሕጋዊና ሞራላዊ (ቅስማዊ) መብት ጨርሶ የለውም፡፡ ሕዝብ ማን ጠንቅ ማን ጠቃሚ ማን ጠላት ማን ወዳጁ እንደሆነ በሚገባ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ “አንተ አታውቅም እኔ ነኝ የማውቅልህ” ሊል ፈጽሞ ፈጽሞ አይችልም፡፡ ይሄንን ሊል የሚችልበት መብትም የለውም፡፡ ይሄ አንባገነናዊ አስተሳሰብ እንጅ ዲሞክራሲያዊ (በይነ ሕዝባዊ) አስተሳሰብ አይደለም፡፡ ወያኔ እንዲህ ብሎ የሚያስበው አንባገነን ስለሆነ ነው፡፡ የዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ መሠረቱ ሕዝብ አዋቂ ነው ሕዝብ ባለ መብት ነው ሕዝብ ወሳኝ ነው ሕዝብ የሁሉም ነገር መሠረት ነው ብሎ ማሰብ ነው፡፡ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሕዝብን ውሳኔ የመጨረሻውና የማይቀለበስ አድርጎ ይቆጥራል ይቀበላል፡፡ የመጨረሻው ባለሥልጣን ሕዝብ እንደሆነ ያምናል፡፡ ወያኔ ግን አንባገነን እንጅ ዲሞክራት (በያኔ ሕዝብ) አይደለምና ከተጀመረ ጀምሮ ሕዝብን “እኔ ነኝ የማውቅልህ አንተ አታውቅም” የሚል ነው፡፡ ወያኔ ለየት የሚልበት ነገር ቢኖር እንደ አንባገነንነቱ በራሱ ውሳኔ ማድረግ የሚችለውን ጉዳይ ሁሉ ሕዝብን ለማጨስ የራሱን የሕዝቡንና የሀገሪቱን ጥቅም በሚጎዱ ነገሮች ላይ “የሚጎዳህ መሆኑን ብታውቅም አንተ ባትልም እኔ ብያለሁና አንተ እንዳልክ ተቆጥሮ ይፈጸማል!” ብሎ እያወናበደ “ሕዝብ ብሏል” እያለ የሚያስፈጽም መሆኑ ነው፡፡ ይሄ የወያኔ የራሱ የብቻው መገለጫ ባሕርይው ነው፡፡

ይህ አደረጃጀት ሕጋዊ አሠራር ነው ወይስ አይደለም?

በፍጹም አይደለም ምክንያቱም የአደረጃጀቱ ዓላማና ግብ የመንግሥትን መዋቅር በመጠቀም የፓርቲን አጀንዳና ጥቅም ማስጠበቅ መከወን ስለሆነ፡፡ አንድ መንግሥት እንደ መንግሥትነቱ ሊከውናቸው የሚገቡ በርካታ ጉዳዮች አሉ፡፡ ልማት አንዱ ነው፡፡ ወያኔ ላይ ስንመጣ ግን ወያኔ የመንግሥት አቅል ፣ ሥነ ሥርዓት (discipline) ሰብእና (personality)፣ ቅርጽ (formation)፣ ሥርዓት (system)፣ ኃላፊነት (responsibility)፣ ቃል አጠባበቅ (commitment) አስተሳሰብ (Mentality) ተአማኒነት (credibility) ተቀባይነት (acceptability) የሕዝብ ውክልና (public representation) ኖሮት ስለማያውቅና ወደፊትም እንደነዚህ ዓይነት ለመንግሥትነት የሚያበቁ ብቃቶች ችሎታዎችና ሰብእና ሊኖረው የሚችልበት ዕድል ከምንም ወይም ከዜሮ በታች ስለሆነ ወያኔን መንግሥት ብሎ መጥራት አይቻልም፡፡ በመሆኑም ወያኔን ስንገልጽ መንግሥት ሳይሆን አገዛዝ የሚለውን ቃል ለመጠቀም እንገደዳለን፡፡ እናም ይሄ አገዛዝ በዚህ የ1 ለ5 አደረጃጀት የመንግሥትን ሥልጣንና መዋቅር በመጠቀም የመንግሥትን ወይንም የሕዝብን ጥቅሞች የሚያስጠብቁ ሳይሆን የሀገርንና የሕዝብን ጥቅሞች የሚጎዱ የሕወሐት ኢሕአዴግን አጀንዳና ዓላማ እያራመደበት እያስፈጸመበት በመሆኑ አደረጃጀቱ የለየለት ሕገ ወጥ አሠራር ነው፡፡

የወያኔ ሕገ መንግሥት ልክ እንደ ምዕራባዊያን ሕገ መንግሥታት ሁሉ መንግሥትና ፓርቲ የተለያዩ መሆናቸውንና አንዱ የሌላውን መዋቅርና ንብረት መጠቀም መገልገል እንደማይችል ይደነግጋል፡፡ ወያኔ በሕገ መንግሥቱ ላይ ይሄንን ብሎ ይደንግግ እንጅ በተግባር ግን እያደረገ ያለው የገዛ ሕገ መንግሥቱ ከሚለው ፍጹም የተቃረነ ነው፡፡ የመንግሥት ንብረትና መዋቅር ሁሉ ስንጥር ሳትቀር የሕወሐት ኢሕአዴግ ንብረትና መጠቀሚያ ነው፡፡ ወያኔ ፈጽሞ ፓርቲና መንግሥት እንዲነጣጠሉ አይፈልግም፡፡ ከአንባገነናዊ ማንነቱ አንጻር ጥቅሙ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጎዳበት ለህልውናውም አደጋ እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃልና፡፡ ይሄንን አደረጃጀት ለሽፋን እያለው እንዳለው ሁሉ የልማት ሠራዊትን ለመፍጠር ሕዝቡን ለልማት ለማነሣሣት ቢሆን ኖሮ አደረጃጀቱ በግዳጅ ከመሆኑ በቀር ምንም ችግር አልነበረውም፡፡ ከዚህ አሳፋሪ አንገት ሰባሪ አዋራጅ ድህነት ለመውጣት የመጨረሻ አቅማችንን አሟጠን እስከመጠቀም ድረስ መትጋት የግድ ይኖርብናልና፡፡ ሕዝቡ የራሱን መንግሥት ቢያገኝ እስኪያስገድዱትም የሚጠብቅ ሕዝብ አልነበረም፡፡ መንግሥትን ቀድሞ ከፊት ከፊት እየሔደ ነፍሱንም እስከመስጠት ለእናት ሀገሩ የማይሆነው ነገር እንደሌለ የማይከፍለው የመሥዋዕትነት ዓይነት እንደማይኖር ከታሪኩ መረዳት ይቻላል፡፡

ሕዝባችን ያጣው የራሴ የሚለው የሚሰማው የሚታዘዘው መንግሥት ነው፡፡ ሕዝባችን ያጣው ክብርና ፍቅር ሰጥቶት ድርሻውን ሥልጣኑን አውቆለት ምን እናድርግ? ምን ይሻላል? ብሎ ፋንታ የሚሰጠውን መንግሥት ነው፡፡ ሌላው ሁሉ በእጁ ነበር የሚቸግረው ነገር ባልነበረ፡፡ ምክንያቱም ሕዝባችን ሞራል (ቅስም) ያለው ሕዝብ ነውና ቅስም የመነቃቃት አቅም ያለውን ሕዝብ ለምንም ጉዳይ ቢሆን ያሳምኑት ብቻ እንጅ ተራራን ይገፋል ኮረብታን ያፈልሳል፡፡ ቅስም ማለት ለአንድ ሀገር ሕዝብ ምንም ነገር የማይተካው የትም ሊያደርሰው የሚችል ኃይል አቅም ጉልበት ነው፡፡ የእኛ ሕዝብ የትኛውም ሕዝብ ሊወዳደረው በማይችለው ደረጃ ይህ ሀብት አለው፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ በሥርዓቶች መበላሸት ምክንያት ይሄንን አቅሙን እንዲጠቀምበት ማድረግ አልቻልንም፡፡ የእኛ ችግራችን የሕዝብና መንግሥትህ ነን የሚሉት አካላት ልብና ቋንቋ አለመገናኘት አለመጣጣም ነው፡፡

እናም ይህ አደረጃጀት የተፈጠረበት ወይም ሥራ ላይ የዋለበት ዓላማ የሀገሪቱንና የሕዝቧን ጥቅም ለማስጠበቅ ለማሳደግ ለማበልጸግ ሳይሆን ከሀገርና ከሕዝብ ጥቅም በተጻራሪ ያለን የፓርቲን ሕልውናና ጥቅም ለማስጠበቅ ነው፡፡ ሲጀመር ከላይ እንደገለጽኩት የወያኔ ሰብእናና ማንነት በአንድ ጎጥ ላይ ጠቦና ተወስኖ ያለ እንጅ በኢትዮጵያና ብሔረሰቦቿ ልክ በእኩልነት ሰፍቶ ያለና ለኢትዮጵያ የሚበቃ ኢትዮጵያን የሚመጥን አይደለም፡፡ ወያኔ በምንም ነገር ላይ ቢሆን ቅድሚያ የሚሰጠው የራሱን (የፓርቲውን) ጥቅምና ጉዳይ እንጅ የሀገርንና የሕዝብን አይደለም፡፡ ለአንድም ጊዜም እንኳ ተሳስቶ ከራሱ ጥቅም ይልቅ የሀገርንና የሕዝብን ጥቅም አስቀድሞ አያውቅም፡፡ ይልቁንም የራሱን ነውረኛ ጥቅም ለማስጠበቅ ሲል ከባባድ የሀገርንና የሕዝብን ጥቅም አሳልፎ በመስጠት የፈጸማቸው የሀገር ክህደቶቹ በርካቶች ናቸው፡፡ የወያኔ ማንነትና ሰብእና ይሄ ሆኖ እያለ የ1 ለ5 አደረጃጀትን የሀገርንና የሕዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ ነው ብሎ ማሰብ ፈጽሞ የማይቻል ነው፡፡ እንደ ወያኔና መሰሎቹ ሁሉ ከሀገርና ከሕዝብ ጥቅም ጋር የሚጋጭ ዓላማና ግብ ያለው የሕዝብ ተቀባይነት ያገኘ የፖለቲካ ፓርቲም ሆነ ሕዝባዊ ማኅበር በዚህች ሀገር የለምና ቢያንስ በግልጽ የምናውቀው የለምና የጥቅም ግጭቱ ያለው በወያኔና በማኅበራቱ እንጅ በሀገር ወይም በሕዝብ ጥቅምና በማኅበራቱ መካከል ባለመሆኑና ወያኔም የመንግሥትን መዋቅር በመጠቀም የራሱን (የፓርቲውን) አጀንዳ እያስፈጸመበት በመሆኑ ይህ አሠራር ሕገ ወጥ እንጅ ሕጋዊ አይደለም፡፡ አቶ መለስ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ላይ ማኅበረ ቅዱሳንን ያህል ለሀገርና ለሕዝቧ እሴቶች ጥቅሞችና ማንነቶች ተቆርቋሪ ማኅበር በስም ጠርቶ በአሸባሪ ድርጅትነት ፈርጆ መወንጀሉ ይታወሳል፡፡

ይህ አደረጃጀት ከሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ (በይነ ሕዝባው) መብቶች አንጻር የጋረጠው አደጋ አለ ወይስ የለም?

በሚገባ እንጅ! ዋናው የፈጠረው ችግር ምን ሆነና? ዜጎች የመሰላቸውን ፖለቲካዊም ሆነ ማኅበራዊ አስተሳሰቦች የመከተል የማንጸባረቅ ሕገ መንግሥታዊና ሰብአዊ የሆነ መብት አላቸው፡፡ ይሄንን መብት በመጠቀም የመሰላቸውን የፖለቲካ ፓርቲ እንዳይደግፉ በአባልነት እንዳይሳተፉ በመሰላቸው ሕዝባዊ ማኅበራት ታቅፈው ለሀገራቸው ሊያበረክቱት የሚፈልጉትን አስተዋጽኦ እንዳያበረክቱ የሚከለክል የሚያሸሽ አገዛዙ እኔ የማስብላቹህን እኔ የምነግራቹህን አስተሳሰብ ብቻ ተቀበሉ የሚልበት አደረጃጀት በመሆኑ ይህ አደረጃጀት ከሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ (በይነ ሕዝባዊ) መብቶች አንጻር የጋረጠው ብቻ ሳይሆን ያደረሰውና እያደረሰ ያለው ጉዳትና አደጋ አለ፡፡ ወደፊት ወያኔ ዕድሜ ከሰጠው ይሄንን አደረጃጀት በመጠቀም ኢትዮጵያዊነትን አጥፍቶ ወያኔያዊነትን በቦታው ሊተካበት ያስባል፡፡ የምላቹህ ገብቷቹሀል? ወያኔ ምን ብሎ ያምናል መሰላቹህ? “ኢትዮጵያዊነትን ደብዛውን አጥፍቸ ወያኔያዊነትን በቦታው ስተካ ብቻ ነው ከተጠያቂነት ከታሪክ ተወቃሽ ተከሳሽነት ላመልጥ የምችለው” ብሎ ያምናል፡፡ ይህ የ1 ለ5 አደረጃጀት ማለት ኢትዮጵያዊነትን የሚያጠፋ በአንድ ጊዜ ሳይሆን ቀስ በቀስ በተለያየ ጊዜ እየፈነዳ ኢትዮጵያዊነትን የሚያፈራርስ በኢትዮጵያዊነት አካል ላይ የተጠመደ የሰዓት ፈንጅ (time bomb) ነው፡፡

ይሄ የገባው በርካታ ዜጋ መኖሩን እጠራጠራለሁ፡፡ የወያኔን ጥቅም የሚጻረሩ እንደ ታሪክ ያሉ የኢትዮጵያዊነት እሴቶች በዚህ አደረጃጀት ፊት እየተለቀሙ ይረሸኑና ከኢትዮጵያ ምድር እንዲጠፉ ይደረጋሉ፡፡ ወያኔ በራሱ ፍላጎትና ዓላማ ልክ የሚፈጥራት ታሪክና ማንነት አልባ አዲስ ሀገር ብቻ እንድትቀር ይደረጋል፡፡ ይሄንን አደረጃጀት ወያኔ እዚህ ድረስ ተስፋ ጥሎበታል፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ይህ አደረጃጀት ለወያኔ ሠራዊቱ በላይ “ለህልውናየ ትልቅ አቅምና ዋስትና ይሆነኛል” ብሎ ያስባል፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ በዚህ አደረጃጀት ያልታቀፈ ዜጋ በዚህች ሀገር መኖር እንዳይችል ኅብረተሰቡ ወዶም ይሁን ተገዶ እንዲያገለው እንዲተፋው የሚያስችል፣ ምንም ዓይነት መንግሥታዊ አገልግሎት እንዳያገኝ እንዳይፈጸምለት የሚያደርግ አጋንንታዊ ተንኮል ሸር አሻጥር የተሞበት አሠራር ቀርጾ አስቀምጧል፡፡ ይህ ነገር የመጽሐፍ ቅዱሱን የአውሬውን ማለትም የ666ን አሠራር አደረጃጀት ዓይነት መዋቅር የያዘ ነው፡፡ ለነገሩ እነሱስ የሱ መንገድ ጠራጊዎችም አይደሉ? ለዚህ ማስረጃ መጥቀስ አያስፈልግም ፀረ ቤተክርስቲያን መሆናቸውን ፍጹም እንግዳ በሆነ መልኩ በሸር ክፋት ሸፍጥ የተካኑ ቅንነት ደግነት ታማኝነት ፈጽሞ ያልፈጠረባቸው ጭካኔ የተሞሉ እኩዮችና እርኩሶች መሆናቸውን ማየቱ ብቻ በቂ ማስረጃ ነው፡፡ ወገኔ አንቀላፍተህ ዝም ብለህ በማየትህ ወያኔ የከፋ አውሬ ሆኖ እራሱን እንዲፈጥር ዕድል እንዲያገኝ አደረከው፡፡ ከዚህ በኋላ እያንዳንዷ ቀን ወያኔን እያበረታች እያፈረጠመች እያገዘፈች ትሔዳለች፡፡ ልናደርገው የምንችለው ነገር ካለ በተቻለ ፍጥነት ቶሎ ማድረግ ካልቻልንና ጊዜ ከሰጠነው አትድከሙ ወያኔ የሚነቀል አይሆንም፡፡

የቅድስት ድንግል ጽዮን ማርያም ልጅ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሆይ! በቃ ላትታደገን ነው? በቃ ላትምረን ነው? በቃ ይቅር ላትለን ነው? እባክህን ካንተ ይቅር? የፍጻሜ ዘመን ሰዎች መሆናችንን አስብ? ለንስሐ በቅተን ምሕረትህን እናገኝ ዘንድ ጸጸትና ትጋት ጨርሶ የማይጎበኘን የጥፋት ዘመን ትውልድ ነን፡፡ ደስ ስላሰኙህ ስለ ደጋግና ቅዱሳን እናት አባቶቻችን ብለህ ይቅር በለን? የአውሬው ኃይል ፍጹም ይበረታብን ይሠብረን ያደቀን ዘንድ አትፍቀድ? አንሣን? ነጻ አውጣን? ማረን? ይቅር በለን? አንተን የሚፈራ ለአንተ የሚገዛ ልብ ስጠን? ደስ የማያሰኘውን ሊመጣ ያለውን ክፉ የጨለማ ዘመን ከእኛ አርቅ? እባክህ ስለ እናትህ ስለ እናትህ ስለ እናትህ ብለህ? እንዲያው እ ባ ክህ? እባክህ? አሁንስ ተስፋ ቆረጥኩ ከሥራችን፣ ወደ አንተ ከመመለሳችን አንጻር ዐይተህ ከሆነ ልትምረን ይቅር ልትለን የምትፈልገው የዘመኑ ፍጻሜ ሰዎች እንደመሆናችን መጠን መቸም ልናደርገው አንደማንችል ስለማስብ እየባሰን እንጅ እየተሻለን አይሔድምና ምሕረትህ መቸም ላይጎበኘን ነው ማለት ነውና ተስፋ የመቁረጡ ስሜት ክፉኛ ተጫነኝ ትንፋሽ አሳጠረኝ፡፡ መቸ እንደሆነ ባላውቅም በምሕረት ወደኛ እንደምትመለስ ከቅዱስ ቃልህ አውቃለሁ፡፡ እባክህን ሩቅ አይሁን? አሁን ማር? አሁን ይቅር በለን? አሁን በቃቹህ በለን? ምህረትህን አሁን አድርገው?

ልዑል እግዚአብሔርን “የሠራዊት ጌታ ሆይ! እነኝህን ሰባ ዓመታት የተቆጣሀቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቸ ነው?” ትን. ዘካ. 1፤12-17 ብለህ ጠይቀህ ለምነህ ተማጽነህ እግዚአብሔር በመልካምና በሚያጽናና ቃል ለልመናህ መልስ የሰጠህ፤ ኢይሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች ልዑል እንደማረ ይቅር እንዳለ ያወጅክና ነቢዩ ዘካርያስ ሕዝቡን እንዲያበስር የላክ የእግዚአብሔር መልአክ ሆይ! ለእኛም እንደ ኢየሩሳሌምና የይሁዳ ከተሞች ሁሉ “ኢትዮጵያን የማትምራት እስከ መቸ ነው?” ብለህ ለምነህ እግዚአብሔር በምሕረት ወደኛ እንደተመለሰ ይቅር እንዳለ የምታውጅልን መቸ ነው? እባክህን ፍጠንልን?

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

 

The post 2.36, የ1 ለ5 አደረጃጀትና በሀገር ላይ የጋረጠው አደጋ! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው appeared first on Zehabesha Amharic.

ምርጫ ማላገጫ (ሰኔ 2007 ዘሀበሻ)  –ይገረም አለሙ

0
0

 

electionበቅድሚያ የወያኔን ሕገ ወጥና ሞራለ ቢስ እንዲሁም ወራዳና እኩይ ተግባር ሁሉ ተቋቁመው እዚህ በሀገር ቤት ሰላም በሌለበት ሰላማዊ ብለው የህግ የበላይነት በሌለበት ራሳቸውን ህጋዊ አድርገው ለሚታገሉት ፖለቲከኞች አክብሮትም አድናቆትም ያለኝ መሆኑን እገልጻለሁ፡፡ይህ ስሜት ግን ድክመታቸውን ለማየት ስህተታቸውን ለመተቸት የሚጋርድና የሚከለክል መሆን የለበትም፡፡ የሚወዱትና የሚደግፉት ይበልጥ እንዲጎለብት በግልጽና በድፍረት መተቸት፣ ድክመት ስህተትን ማሳየት ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም፡፡ የሚያሳዝነው ለዚህም አልታደልን፡ ከሚጥመን ውጪ ሌላ ለመቀበል ቀርቶ ለመስማት ፍላጎቱ ብዙም የለንም፡፡

ምርጫ አንድም ሕዝብ በድምጹ ያሻውን መርጦ የሥልጣን ባለቤትነቱን የሚያረጋግጥበት፣ አንድም አምባገነኖች ለሕገ ወጥ ሥልጣናቸው ሕጋዊ ካባ የሚያላብሱበት ክንውን ነው፡፡ ምርጫ አስፈጻሚ ተቋም ተቋቁሞ ተወዳዳሪዎች ተሰይመው መራጭ ተመዝግቦ ካርድ ኮሮጆ ውስጥ መክተቱ ብቻ አይደለም የምርጫን እንዴትነት የሚወስነውና ምንነቱን የሚያሳየው፡፡

ከመነሻው የሥልጣን ባለቤቱ ሕዝብ መሆኑን አምኖ፣ የሥልጣን መያዣው አንድና ትክክለኛ መንገድ ምርጫ መሆኑን ተቀብሎ፣ በሕዝብ ውሳኔ ለመገዛት ራስን አዘጋጅቶ፣ የሀገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ነጻ ተአማኒና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል እንዲሆን ከማድረግ ነው የሕዝብን የሥልጣን ባለቤትነት የሚያረጋግጥ ትክክለኛ ምርጫ የሚጀምርው፡፡

ወያኔ ከደደቢት ተነስቶ ለአስራ ሰባት ዓመታት ገድሎና ሞቶ ለምኒልክ ቤተ መንግሥት ከበቃ እነሆ ዘንድሮ አምስተኛውን ምርጫ አካሂዷል፡፡ በ1997 ዓም ከተካሄደው ሶስተኛ ምርጫ በስተቀር ሌሎቹ ለውጥ ሊታይባቸው ቀርቶ በሰው አዕምሮ ውስጥ ጥለውት ያለፉት ትውስታ የለም፡፡ አለ ከተባለ የ2002ቱ 99.6 በመቶ ወያኔ አሸናፊ መሆኑ በአንጻሩ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ 20 ዓመት ወደ ኋላ መመለሱ ነው፡፡

እንደ ወያኔ በሁለንተናዊ ተግባሩ የህዝብ ድጋፍ የተለየው ፓርቲ ቀርቶ ከፊል የህዝብ ድጋፍ ያለው ፓርቲ እንኳን ቢሆን በተከታታይ አምስት ምርጫ ሊያሸንፍ አይችልም፡፡ የሰው ልጅ ለውጥ መፈለጉ የተፈጥሮ ህግ ነውና የጎደለው እንዲሟላለት፣ ቅር የተሰኘበት እንዲስተካከልለት አለያም በስልጣን ላይ የቆየው ፓርቲ ተምሮ ለወደፊት የተሻለ ሆኖ እንዲቀርብ ወዘተ ሌላ ይመርጣል፡፡ እናም በዴሞክራሲያዊ ሀገራት ሕዝቡ በሚያዝበት የሥልጣን ወንበር ላይ አንዱን ከአንዱ እያፈራረቀ ያያል ይፈትናል፡፡

በኢትዮጵያ ግን ይህ የለም፤ብሎ ብሎ የዘንድሮው ውጤት መቶ በመቶ ወያኔ አሸናፊ የተባለበት ሆኗል፡የሚገርመው በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች የወያኔ ተወዳዳሪ ሙሉ ድምጽ አገኘ ሲባል ለሌሎቹ ተወዳዳሪዎች አገኙት ተብሎ የተገለጸው የእያንዳንዳቸው ውጤት ዜሮ በድፍረት ተጽፎ መገለጹ ነው፡፡ ተወዳዳሪዎቹ ራሳቸውን አልመረጡም ?ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ የላቸውም? ወያኔ ሀፍረት ብሎ ነገር አያወቅም እንጂ ይህ ማስተዋል የሌለበት አሳፋሪ የድንቁርና ስራ ነው፡፡ ሲዋሽ ትንሽ እውነት ይዞ ማጭበርበር ሲፈጽም ትንሽ ትንሽ እያስመሰሉ እንጂ እንዲህ ግልጽ ሆኖ የሚታይ እኩይ ስራ አይሰራም፡፡ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ምርጫ ቦርድን ያመሰገኑት በዚህና ለዚህ ተግባሩ ነው፡፡

እስካሁን የተደረጉትን ምርጫዎች (ምርጫ 97ን ትተን) ብንፈትሽ የምናገኘው ምርጫ ማላጋጫ መሆኑን ነው፡፡ ቅንጅቶች በምርጫ 97 ወያኔ የሚያላግጥበትን ምርጫ የምር ምርጫ ለማድረግ በመቻላቸው ሕዝብ የለውጥ ፍላጎቱን በምርጫ ካርዱ አሳይቶ  ወያኔን ላልተዘጋጀበት አይደለም ፈጽሞ ላላሰበው ሽንፈት ሲዳርጉት ብዙዎቹ የወያኔ ሹማምንት ለጭንቅላት በሽታ እንደተዳረጉ ከራሳቸው ጭምር ሰምተናል፡፡ ምርጫ ቃሉን እንኳን ሲሰሙ ያ በሽታቸው ስለሚነሳባቸው ነው በምርጫ ወቅት የሚያቀበጠብጣቸው፡፡

በዛ ታሪካዊ ምርጫ ወያኔ  በእውር ድንብር ህገ ወጥ ተግባር ጉልበት ከሥርዓት ተጠቅሞ በፈጸመው ድርጊት “ሥልጣን ወይም ሞት፣ በጠመንጃ የተገኘ ስልጣን በምርጫ አይነጠቅም፣ በዮሀንስ ዘመን የተፈጸመው የሥልጣን ንጥቂያ በእኛ ዘመን አይደገምም”ወዘተ የሚልና እሱን ከስልጣን ለማንሳት የሚደረገውም ትግል ከባድ መስዋእትነት የሚያስከፍል መሆኑን አሳይቷል፡፡

በጠመንጃ ኃይል ሽንፈቱን ቀልብሶ አሸናፊዎቹን አስሮ ሥልጣኑን ካረጋገጠ በኋላ   ሽንፈት ብሎ ነገር ከዛ በኋላ ላለማየት ለሽንፈት የበቃበትን ምክንያትና መንገድ መርምሮ ምክንያቶቹን አስወግዷል፣ መንገዶቹንም ዘግቷል፡፡ ይህን የማያውቅ ፖለቲከኛ የለም ሊኖርም አይችልም፡፡ ስለሆነም በዚህ ሁኔታ ውስጥ ወያኔ የሚያካሂደው ምርጫ ማላጋጫ ከመሆን ያለፈ ፋይዳ ሊኖረው የሚችለው ተፎካካሪ ፖለቲከኞቹ የተዘጋውን አስከፍተው፣ የጠበበውን አስፍተው፣ የተከላውን መልሰው፣ ለእድሜ ማራዘሚያ የሚያዘጋጀውን ምርጫ ለሥልጣን ዘመኑ ማክተሚያ እንዲሆን ለማስቻል በየግል ጠንክረው በጋራም ተባብረው መቅረብ ሲችሉ ብቻ ነው፡፡

ወያኔ ለአሯሯጭነትና ለአጨብጫቢነት የፈጠራቸውንና ምርጫ ቦርድም ይህን ያህል ፓርቲ ተወዳድሯል ለማለት እንዲያስችለው የፓርቲነት መስፈርት ሳያሟሉ(አቶ በረከት በመጽኃፉ የቤተሰብ ፓርቲ ያላቸው) ፓርቲ እያለ እየደገፈ ያስቀመጣቸውንና ወያኔ እስትንፋስ የሚሰጣቸውን ትተን  ሕዝብ የሚያውቃቸውና እውቅና የሰጣቸውን ፓርቲዎች ብንወስድ በዘንድሮው ምርጫ አንዳቸውም ለሥልጣን የሚያበቃ የዕጩ ተወዳዳሪ ብዛት አላቀረቡም፡፡ይህን ሲያውቁ የአቅማቸውን ውስንነት ሲረዱ ደግሞ ተመካክረውና ተጋግዘው ሊቀርቡ ሲገባ ይህንንም ማድረግ አልቻሉም፡፡ እንደውም በተግባር የሚታየው  እያንዳንዳቸው ከወያኔ ጋር ከሚፎካከሩት በላይ ርስ በርሳቸው የሚፎካከሩ መሆኑ ነው፡፡ የምኒልክን ቤተ መንግሥት ሁሉም ይመኙታል ግን ሁሉም ያጡታል፡፡ ከዚህ አንጻር ካየነውና ከማለባበስ ወጥተን በእውነት ስለ እውነት ከተነጋገርን ምርጫውን ማላገጫ ያደረገው ወያኔ ብቻ ሳይሆን አጅበው ያዘለቁት  ተዋሚዎችም ናቸው ለማለት ያሰደፍራል፡፡

በምርጫ መወዳደር በራሱ ግብ አይደለም፡፡ የምርጫ ሰሞን ብቅ ብሎ ሆይ ሆይ ማለትም በቂ የፖለቲካ ሥራ አይደለም፡፡ የፖለቲካ ስራውም ሆነ የምርጫ ውድድሩ ምርጫን ምርጫ ለማድረግና አሸንፎ የመንግሥትን ሥልጣን ለመረከብ ካልሆነም በቂ ወንበር አግኝቶ ፓርላማውን የአንድ ፓርቲ መፈንጫ ከመሆን ለማላቀቅ የሚያስችል መሆን ይኖርበታል፡፡ 547 መቀመጫ ላለው የተወካዮች ምክር ቤት ቁጥራቸው ከ200 ያልዘለለ ዕጩዎችን ይዞ ምርጫ መግባትና እናሸንፋለን ብሎ መፎከር አለያም የምርጫው ውጤት አስቀድሞ የታወቀ ነው እያሉ ማላዘን  ምርጫን ማላገጫ ማድረግ እንጂ ምን ይባላል፡፡

እንግዲህ ልብ እንበል፣በየግል ተወዳድሮ ለማሸነፍ የሚያስችል አቅም የላቸውም፡፡ይህን ተረድተው ከግል የሥልጣን ጥም ተላቀው ተባብረው ለምርጫ የሚቀርቡ አይደሉም፡፡ የሥልጣን መና ቢወርድላቸው ተስማምተው ይሄ ለአንተ ይሄ ለእኔ ብለው ስልጣን ተጋርተው መንግስት ለመመስረት የሚያስችል ቁመናም ባህርይም አይታይባቸውም፡፡ታዲያ ምን ሊሆኑ ወደ ምርጫ ገቡ? እነርሱም እንደ ወያኔ በምርጫው ሊያላግጡ? የሚያሳዝነው የፖለቲካ መሪዎቹ በሚያላግጡበት ምርጫ ለእስር ለስደት ለሞትና ለእንግልት የሚዳረገው ዜጋ ነው፡፡

ወያኔ በሥልጣን ከሚቀጥል የምንችለውን ሁሉ እናድርግ ብለው ከልብ ወስነው በቁርጠኝነት ቢነሱ ምርጫ የወያኔ ማላገጫ እንዳይሆን ማድረግ በቻሉ ነበር፡፡ እያንዳንዱን የወያኔ ሴራ እያጋለጡና የተንኮል ስራውን እያመከኑ ለዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማንበርከክ ባይቻላቻው ከማን አለብኝነት አይን አውጣ ስራ ሊያቅቡት በተቻላቸው ነበር፡፡ አንዱ ሲጠቃ ሌላው እልል እያለ፤አንዱ ከጨዋታ ውጪ ሲደረግ ሌላው ሜዳው የሰፋለት ያህል እየቆጠረ፣የአንዱ ዕጩ ሲሰረዝ ሌላው እሰይ እያለ ወዘተ ወያኔ የሚያላግጥበትን ምርጫ የምር ምርጫ ማድረግ አይቻልም፡፡ በሌላ በሌላው መተባበር ቢቀር ምርጫው የወያኔ ማላገጫ እንዳይሆን ለማድረግ  የጋራ እቅድ ነድፎ ተባብሮ መስራት ይጠይቃል ፡፡ ከፖለቲከኞቻችን አድራጎት የምናያውና ከየንግግራቸው የምንረዳው ግን ከእነርሱ ሌላ ተቀዋሚ ከሚያሸንፍ ወያኔ ቢቀጥል የሚመርጡ መሆናቸውን ነው፡፡ ታዲያ እነዚህ ከወያኔ ባልተናነሰ ምርጫን ማላገጫ ያደረጉ ናቸው ቢባል እውነትን ላለመቀበል ማንገራገር ካልሆነ በስተቀር የሚያከራክር ይሆናል?

የተቃውሞ ፖለቲካ መሪነት ሥልጣን ሆኖ በውስጣቸው ርስ በርስ ይታመሳሉ፤ፓርቲ ከፓርቲ ይናቆራሉ፤ባይናቆሩም ፍቅር የላቸውም፤አብረው ሲሆኑም ሆነ ተለያይተው በቃላት ሲሸናቆጡ በቂ ምክንያት የላቸውም፡፡ በዚህ አቋምና ቁመናቸው ምርጫ እያሉ ከወያኔ ባልተናነሰ በምርጫ ያላግጣሉ፡፡ምንግዜም የማይረሳውን ምርጫ 97 ብንወስድ አራት ፓርቲዎች ቅንጅት ፈጥረው አንድ ሆነው ለምርጫ ቀረቡ፡፡ እኛ ስንዋደድ እግዜሩም ይረዳልና ያልታሰበ የምርጫ ምልክት ሁለት ጣት ሰጣቸው፤ልጅ አዋቂ ሳይል የቅንጅት መንፈስ ሰረጸበት፡፡ ምርጫ ቦርድ ሰባ ሰማኒያ ፓርቲዎች አሉ ሲል ሕዝብ በድምጹ የሚጠራው በምልክት የሚያሳየው ቅንጅትን ብቻ ሆነ፡፡ከዛ ቀጥሎ በተለይ በኦሮሚያና በደቡብ አንዳንድ ቦታዎች ህብረት፡፡ እነዚህ ሁለቱ ፓርቲዎች ደግሞ የምርጫ ሂደታቸውን አቀናጅተው በጋራ መግለጫ ከመስጠት አድማ እስከ መጥራት ደረሱ፡፡ እናም ምርጫውን ከወያኔ ማላገጫነት ወደ ትክክለኛ ምርጫነት ቀይረው ለአሸናፊነት በቁ፡፡ መጨረሻው አሳዛኝና አሳፋሪ ቢሆንም፡፡

ዛሬ መተባበሩ ቀርቶ የምርጫውን እንከን ለማሳየት እንኳን በጋራ መግለጫ መስጠት የሚችሉ ፓርቲዎች አላየንም፣ አልሰማንም፡፡ ታዲያ በየግል በቂ ዝግጅት አድርገው በበቂ ቁጥር ዕጩ አቅርበው ታዛቢ አዘጋጅተው የወያኔን ማጭበርበሪያ መንገዶች ለመዝጋት ወይንም በአቋራጭ ለማለፍ ስልት ነድፈው ለውድድር ካልቀረቡ፤ወይ ደግሞ አቅማቸውን ገምተው ከአንድ ብርቱ ሁለት መድሀኒቱ ብለው ተባብረው ካልሰሩ፡ምርጫ ስለተባለ ብቻ ወደ ምርጫ በመግባት የወያኔ አድማቂ ከመሆን ያለፈ ፋይዳ ከሌላቸው ምርጫውን ከወያኔ ባልተናነሰ ማላገጫ አድርገውታል ከማለት ሌላ ምን ሊባል ይቻላል፡፡

ሕዝቡ በወያኔ አገዛዝ ተማሯል፣እናም ለውጥ ይፈልጋል፣ይህንንም አሳይቷል፡፡ወያኔ በሕግና በሥርዓት አይደለም በጠመንጃም መግዛት የማይችልበት ደረጃ ቢደርስም ምርጫ 97ን እያስታወሰና እየቃዠ የዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንገዶችን ሁሉ ዘግቶ  በስመ ምርጫ   የአገዛዝ ዘመኑን እያደሰ ቀጥሏል፡፡ ተቀዋሚዎች ደግሞ በተናጠል አይጠነክሩ ወይ ተባብረው አይሰሩ የወያኔን የማላገጫ ምርጫ እያደመቁ ለአገዛዝ ዘመኑ መራዘም ቡራኬ ይሰጣሉ፡፡ ከሁለት ያጣ የሆነው ሕዝቡ ነው፤ የሥልጣን ባለቤትነቱን የሚያረጋግጥለት ቀርቶ ሰዋዊ ክብሩን የሚያከብር የሚያስከብርለት መንግሥት አላገኘ፤ወይንም ከአምባገነን አገዛዝ የሚያላቅቀው ታግሎ የሚያታግለው መርቶ ወደ ለድል የሚያበቃው ተቀዋሚ/ተቀዋሚዎች አላገኘ ፡፡

 

The post ምርጫ ማላገጫ (ሰኔ 2007 ዘሀበሻ)  – ይገረም አለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሰማያዊ ፓርቲ የፓርላማ እጩ ተወዳዳሪ ሳሙኤል አወቀ ተገደለ

0
0

Samuel Aweke

"በመጨረሻም ተገደለ በቅርብ ከማውቃቸው ቆፍጣና: ሀገሩን ከምንም በላይ በማስቀደም የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል ሊታገልላት ቆርጦ በመነሳት ምስክርነቴን ከምሰጣቸው ወጣት ታጋዮች አንዱ ነበር:: ለቃለመጠይቅም ሆነ መረጃ ፍለጋ በደወልኩለት ጊዜ ሁሉ በልዩ የሀገር ፍቅር ስሜት ትብብር በማድረግ የስርዓቱን ግፍና ጭካኔ በማጋለጥ ግዴታውን በሚገባ እየተወጣ የነበረ ብረት የሆነ ወጣት:: ደበደቡት: አሰሩት: በአካሉ ላይ የሚችሉትንና የሚፈልጉትን ሁሉ ጉዳት አደረሱበት:: ሳሙኤል ካመነበት ንቅንቅ የሚል አልነበረም:: በመጨረሻም የወጣትነት ህይወቱን አጠፉት:: ታጋይ ይሞታል:: ትግል ግን........ሳሙኤል ነፍስ ይማር!" - ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን

“በመጨረሻም ተገደለ
በቅርብ ከማውቃቸው ቆፍጣና: ሀገሩን ከምንም በላይ በማስቀደም የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል ሊታገልላት ቆርጦ በመነሳት ምስክርነቴን ከምሰጣቸው ወጣት ታጋዮች አንዱ ነበር:: ለቃለመጠይቅም ሆነ መረጃ ፍለጋ በደወልኩለት ጊዜ ሁሉ በልዩ የሀገር ፍቅር ስሜት ትብብር በማድረግ የስርዓቱን ግፍና ጭካኔ በማጋለጥ ግዴታውን በሚገባ እየተወጣ የነበረ ብረት የሆነ ወጣት:: ደበደቡት: አሰሩት: በአካሉ ላይ የሚችሉትንና የሚፈልጉትን ሁሉ ጉዳት አደረሱበት:: ሳሙኤል ካመነበት ንቅንቅ የሚል አልነበረም:: በመጨረሻም የወጣትነት ህይወቱን አጠፉት:: ታጋይ ይሞታል:: ትግል ግን……..ሳሙኤል ነፍስ ይማር!” – ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን

ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ እንደዘገበው የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፀኃፊና በ2007 ዓ.ም ምርጫ የፓርቲው ዕጩ ተወዳዳሪ የነበረው ወጣት ሳሙኤል አወቀ ተገደለ፡፡ ወጣት ሳሙኤል አወቀ ትናንት ሰኔ 8/2007 ዓ.ም ምሽት ላይ ወደ ቤቱ እየገባ በነበረበት ወቅት በሁለት ግለሰቦች ከፍተኛ ድብዳባ ከተፈፀመበት በኋላ ሆስፒታል ውስጥ ነፍሱ አልፋለች፡፡

ወጣት ሳሙኤል ከቀድሞው አንድነት ጀምሮ ሲታገል የቆየ ሲሆን የሰማያዊ ፓርቲ መስራች አባል ነው፡፡ በአካባቢው የሚፈፀሙ በደሎችን ለሚዲያ በማጋለጥ ሲያበርክተው ከነበረው ሚና ባሻገር በፓርቲው በነበረው ጠንካራ እንቅስቃሴ ምክንያት በተደጋጋሚ እስርና ድብደባ ተፈፅሞበታል፡፡

የወጣቱን ግድያ ተከትሎ የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ አዘጋጅ ጌታቸው ሽፈራው በፌስቡክ ገጹ የሚከተለውን አስፍሯል:: እንደወረደ ይኸው:-

ሳሙኤል ይህ አረመኔያዊ እርምጃ እንደሚወሰድበት ያውቅ ነበር፡፡ ግን ትግል ነውና ወደኋላ አላለም፡፡ ከሳምንታት በፊት እግሩን ሰብረውታል፡፡ ከዛ በፊት በተደጋጋሚ ታስሯል፡፡ ህዝብ በዳኞች ላይ ተማርሮ የጻፈውን የህዝብ አስተያየት አንተ ነህ የጻፍከው ተብሎ ታስሯል፡፡ እንደሚገድሉት ዝተውበታል፡፡ ይህ ሁሉ አልሆንላቸው ሲል ከሀገር እንዲወጣ ወትውተውታል፡፡ እሱ ግን እስከ ትናንትናዋ ማታ ድረስ ፀንቶ ቆይቷል!

ከሁለት ሳምንት በፊት ደግሞ በፌስቡክ ገጹ እኔን ቢገድሉኝም እናነተ ግን ፅኑ ብሎ አደራውን አስተላልፎ ነበር፡፡
samuel aweke lem

ውድ የደብረማርቆስ ከተማ ኗሪዎች!

ሰማያዊ ፓርቲን የመረጣችሁ ከ25’0000 በላይ መራጮች(ኮረጆውን) እርሱት እና በተጨማሪም በ31 ዩኒቨርስቲ የምትገኙ ከ14,000 በላይ ሰማያዊ ፓርቲን የመረጣችሁ ሌሎች ደጋፊዎች እና የኢሕአዴግ አባላትም የማያፍረው ብአዴን / ኢሕአዴግ ድምፅ መቀማቱ ሳያንስ በ21/08/2007 ዓም አፍነው ደብድበው ከሞት መትረፌ ቆጭቷቸው እሰር ቤት ለመወርወር ያለመከሰስ መብቴን እንኳን ተዳፍረው የሀሰት ክሰ እየፈጠሩ ነው!

በስልኬ እደተደወለም ያለፍላጎቴ ደሕንነት እያስገደደኝ ይገኛል፡፡

ተገደልሁም፣ ታሠርሁም፣ ታፈንኩም ነፃነት አይቀርም እና ለማሰረጃነት የደሕንነቶችን ስም፤ ፎቶግራፍ ፤ እና አድራሻ እንዲሁም በሐሠት ምሰክርነት እና ከሳሽነት የተደራጁ አካላት እና ዋና ተወካዮች የደብረማርቆስ ከተማ 04 ቀበሌ አመራሮች እና ፖሊስ ለታሪክ አሰመዘግባለሁ፡፡ ማንኛውም የምከፍለው ዋጋ ለሀገሬ እና ለነፃነት ነው፡፡ ከታሠርሁም ሕሊናዬ አይታሰርም ከገደሉኝም ትግሌን አደራ በተለይ የኔ ትውልድ አደራ! አገራችን የወያኔ ዘረኞች ብቻ መፈንጫ መሆን የለባትም! ትግላችን የነፃነት ጉዟችን ጎርባጣ መድረሻችን ነፃነት ታሪካችን ዘላለማዊ ነው!

(ከሳሙኤል አወቀ ዓለም –
የሰማያዊ ፓርቲ የደብረ ማርቆስ የሕዝብ ተወካዮች እጩ ተወዳዳሪ)

The post የሰማያዊ ፓርቲ የፓርላማ እጩ ተወዳዳሪ ሳሙኤል አወቀ ተገደለ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሰበር ዜና –የወያኔው ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር «ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ» ትላንት ምሸት በድብቅ ጅዳ ገቡ

0
0

የወያኔው ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር «ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ»

የወያኔው ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር «ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ»

ሰኔ 8 ቀን 2007 ምሸት ሳውዲ አረቢያ የገቡት የኢትዮጵያው ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚንስተር ጉብኘት ያለተጠበቀና እንግዳ መሆኑን የሚናገሩ የጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ምንጮች በዲፕሎማቱ ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥ መፈጠሩን  ገልጸዋል፡፤ ሚንስትሩ ከሳውዲ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ለመገናኘት  ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤት ቢሄዱም   የኢ.ህ.አ.ዴ.ጉ ከፍተኛ  ባለስልጣን ጉብኝት ኦፊሴላዊ ይሁን በድብቅ እስካሁን የሚታወቅ ነገር እንደሌለ   ጅዳና ሪያድ ያሉት የመንግስት ዲፕሎማቶች ምንም አይነት ነገር  እንደማያውቁ   ከቆንስላው ጽ/ቤትና ከሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

13የሚንስትሩን ድንገተኛ ጉብኝት ተከትሎ   ማምሻውን ከውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ጋር ለመወያየት ሽርጉድ ይሉ የነበሩ የጅዳና አካባቢው ካድሬዎች ፡ የልማት ማህበራት ተወካዮች ለደጋፊዎቻቸው በሚስጠር ጥሪ ማስተላለፋቸውን የሚቃወሙ  ኢትዮጵያውያን  ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኑ በዚህ መልክ ወደ ጃዳ  መግባታቸው  ዲፕሎማት ብለው ለሾሞቸው አገልጋዮቻቸው ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን በዲፕሎማቱ  ላይ እምነት እንደሌላቸው  አመላካች መሆኑን ይናገራሉ። ከቀርብ ግዜ ወዲህ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ ባለ ስልጣናት ለስራ ጉብኘትም ይሁን ለህክምና ወደ ሳወዲ አረቢያ ሲገቡ የኤንባሲው ዲፕሎማቶች  መረጃ የሚያገኙት ከተለያዩ  ድህረ ገጾች መሆኑን የሚናገሩ ውስጥ አዋቂዎች ከአንድ አመት በፊት አቶ በረከት ስመኦን በሚስጠር ለህክምና ሲገቡ ዲፕሎማቱ በተመሳሳይ ሁኔታ መረጃ እንዳልነበራቸው   ያስታውሳሉ ፡፤
12በሳውዲያዊው ቱጃር ሼክ አላሙዲን የግል አውሮፕላን ተጭንው  እኩለ ለሊት ሳውዲ  የገቡት አቶ  በረከት ስመኦን  ጅዳ ከተማ  የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ላይ መሆናቸውን የቆንሳላ ጽ/ቤቱም ይሁን  በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ  ያወቁት  ጎልጉል እና ዘሃበሻ ሚዲያ ላይ በተለቀቀው መረጃ  መሆኑን  የሚገልጹ እነዚህ ወገኖች  በዲፕሎማቱና በመንግስት መሃከል ከፍተኛ የሆነ የመረጃ ክፍተት መኖሩን በማውሳት  የመረጃ ክፍተቱን ለማሞላት ዲፕሎማቱ ሚስጥራዊ  መረጃዎችን  ለማግኘት የተጠቀሱትን ሚዲያዎች  መከታተል አማራጭ የሌለው መፍትሄ እንደሆነባቸው  ይነገራል። ዛሬ በጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት በተደረገው ስብሰባ ላይ የታዩት ሚንስቲር ገብረክርስቶስ በሙስና ስለ ሚታመሰው በጅዳ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤትና ህልውናው ስላከተመው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ንብረት መባከን  ምንም መረጃ እንደሌላቸው ለማወቅ ተችሏል ።
አንድ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤት ሰራተኛ አስከትለው ትላንት ጅዳ ሳውዲ አረቢያ ስለገቡት ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚንስቲር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ጉብኘት  በሳውዲም ይሁን በኢትዮጵያ መንግስት መገናኛ ብዙሃን እስካሁን  ምንም የተባለ ነገር እንደሌለ ለማወቅ ተችሎሏ፡፤ አሁን ዘግይቶ በድረሰን ዜና ሚንስትሩ ወደ ሪያድ ከተማ ያቀናሉ ተብሎ ይጠበቃል

Ethiopian Hagere Jed

The post ሰበር ዜና – የወያኔው ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር «ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ» ትላንት ምሸት በድብቅ ጅዳ ገቡ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአቢሲኒያ ባንክ ሰራተኞች የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊ ናቸው ተብሎ በኢሕ አዴግ ባለስልጣናት ተፈረጀ

0
0

የትህዴን ድምጽ እንደዘገበው ባህርዳር ከተማ ውስጥ የሚገኙ የአቢሲኒያ ባንክ ቅርጫፍ ሰራተኞች የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊዎች ናችሁ ተብሎው በኢህአዴግ ባለስልጣናት መነገራቸው ተገለጸ።
bank of abissinya
ለዜና ምንጩ በደረሰው መረጃ መሰረት በባህር ዳር ከተማ የኢህአዴግ ባለስልጣን በሆነው በአዲሱ ለገሰ በተደረገው የስብሰባ መሪነት አብዛኛው የአቢሲያ ባንክ ሰራተኞች የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊዎች ናችሁ፤ ከመንግስት ጋር ያላችሁን ችግር በውይይት እንፋታው ብሎ በከፈተው ስብሰባ ላይ የባንኩ ሰራተኞች እኛን የቀጠረን ባንክ የግል ተቋም ነው። ስለዚህ ላንተ የምንሰጠው መልስ የለንም ብንናገርም የሚመጣ ለውጥ የለም በማለት ያለምንም ፍሬ ነገር ሳይግባቡ ከስብሰባው እንደተበተኑ ለማወቅ ተችሏል።

በአሁኑ ሰዓት አብዛኛው የመንግስት ሰራተኛ ምንም ዓይነት ወንጀልና ጥፋት ሳይኖረው ስርዓቱ በውስጡ ካለው ያለመተማመንና መጠራጠር ሁኔታ በመነሳት ንፁሃን ዜጎችን እያንገላታና በቂ ማስረጃ ሳያገኝ እያሰቃያቸው እንደሚገኝ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።

ለዘ-ሐበሻ በደረሰው መረጃ መሰረት ደግሞ አቢሲኒያ ባንክ የአማሮች ባንክ ተብሎ በሕወሓቶች ተፈርጇል:: ሕወሓቶች በአሁኑ ወቅት ወጋገን ባንክን እንደራሳቸው ባንክ የሚቆጥሩ ሲሆን አቢሲኒያ ባንክን ለማክሰም የአማሮች ባንክ በሚል ስያሜ እየሰጡ ሰዎችን እንደሚያሸማቅቁ ታውቋል::

The post የአቢሲኒያ ባንክ ሰራተኞች የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊ ናቸው ተብሎ በኢሕ አዴግ ባለስልጣናት ተፈረጀ appeared first on Zehabesha Amharic.

የጀግና ሞት ጀግናን ይወልዳል!

0
0

awke
ከይድነቃቸው ከበደ


———-
አምቦገነኖችን በሰላማዊ እምቢተኝነት መፋለም ሕይወትን የሳጣል ! በትግሉ ሜዳ እስካለን ድረስ የሚከፈለው መሰዋትነት እስከዚህ ድረስ ነው፡፡ ጓድ ሳሙኤል አወቀ ሰማያዊ ፓርቲ እንዲመሰረት የበኩልን ድርሻ የተወጣ፣ፓርቲያችን ከተመሰረተበት ቀን ጀምሮ የፓርቲውን ዓላማና ግብ ለማሳካት የተቻለሁን ሁሉ ያደረገ ወጣት የህግ ባለሙያ ነው፡፡ ሳሙኤል በፓርቲያችን ውስጥ ጠንካራ እና ደካማ ጎን በመለየት በዴሞክራሲያዊ መንገድ ከሚተች እና ከሚያበረታቱ መካከል አንዱ ነው፤በፓርቲያችን ውስጠ-ዴሞክራሲ እንዲዳብር ላደረጋቸው ጥረቶች እኔ ምስክርነቴን ለመስጠት እወዳለሁ፡፡

ሳሙኤል በፖለቲካ አስተሳሰቡ እና የተቃዋሚ ፓርቲ አባል በመሆኑ ብቻ ከዚህ ቀደም ይደርስበት የነበረው ጫና እንዲሁም እንግልት የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቀው ሃቅ ነው፡፡የሚፈፀምበት አሰቃቂ እንግልቶች በአገር ውስጥና በውጪ ለሚገኙ የኢትዮጵያዊያን ሚዲያ ሲገለፀ የቆየ የአደባባይ እውነት ነው ፡፡በተለይ ለመጨረሻ ጊዜ ድብዳባ ተፈፅሞበት በደረሰበት የአካል ጉዳት ሳይንበረከክ ከኢሳት ከ“ሰብአዊ መብቶች” ፕሮግራም አዘጋጅ Wendmagegne Gashu ወንድምአገኝ ጋሹ ጋር ያደረገው ቃለ መጠየቅ ሳሙኤል ጠበንጃ አልባ በሆነ ትግል አምባገነኑን የህውሓት/ኢህአዴግን ሥርዓት ለመጋፈጥ ምን ያህል ቁርጠኛ እንደነበር የሚያስታውሰን አጋጣሚ ነው፡፡በሚያደርጋቸው ሰላማዊ ትግል ሕይወቱን ሊያጣ እንደሚችልም ግን እስከመጨረሻ ድረስ እንደሚታገልም በዚኹ ፕሮግራም ላይ ገልፆኦ ነበር፡፡

ወንድማችን ሳሙኤል በቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይ በሆኑ በአካለ-ሥጋ አሁን ከአጠገባችን የለም ! ሰው እንደመሆናችን መጠን ይሄን የመሰለ ቆራጥ ጓድ ከእጃችን ሲያመልጥ ሐዘንና ቁጭታችን እጅግ መራር ነው፡፡ ማንም ምንም የሆነ ሞት ይሞታል፣ ሳሚ ግን የጀግና ሞት ሞተ !ጅግና አይሞትም ሞቱ ጀግናን ይወልዳል እንጂ !!!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላላም ትኑር !!!

The post የጀግና ሞት ጀግናን ይወልዳል! appeared first on Zehabesha Amharic.

ለእውነት እንዳንታገል አዚም የሆነብን ምንድር ነው? –ዘጠኙ ምክንያቶችን እንሆ -(በይበልጣል ጋሹ)

0
0

ስለ እውነት በተግባር እንጂ በቃል ደረጃ ብዙ ማለት ከባድ ቢሆንም ብዙዎች ብዙ ጽፈዋል ተናግረዋል። እውነት ማለት ያዩትን፣ የሰሙትን፣ የሚያውቁትን፣ የተረዱትን፣ የሆኑትን እና የሚያምኑበትን ነገር ሳይጨምሩ ሳይቀንሱ በግልም ሆነ በአደባባይ በይፋ መናገርና መመስከር መቻል እንደሆነ የዘርፉ ሙህራን ያስረዳሉ። በሌላ መልኩ ደግሞ ያላዩትን፣የማያውቁትን፣ ያልሰሙትን፣ ያልሆነን ነገር ሳያረጋግጡ እና የማያምኑበትን ጉዳይ አለመናገር ማለት እንደሆነም አክለው ያስረዳሉ፡፡ በአጭሩ እውነት የሀሰት ተቃራኒ ነው። እውነት ለመናገር፣ ስለ እውነት ለመመስከር በመጀመርያ ሀሰትን መቃወም ይኖርብናል። ስለ እውነት ለመናገር ያልቆሸሸ ንጹህ ሕሊና ሊኖረን ይገባል። ንጹህ ሕሊና እውነተኛ ዳኛ ነውና። ያልተበረዘ፣ያልቆሸሸ እና ንጽህ ሕሊና ሀሰትን የማስተናገድ ባህሪ የለውም።
Tensaye
ሀቀኝነት፣ ታማኝነት፣ እርግጠኛነት፣ ትክክለኛነት፣ ተጠያቂነትን መቀበል እና ሀላፊነትን መወጣት የእውነት መገለጫ ባህሪያት ናቸው። በሌላ አነጋገር እውነት ማለት ጽድቅን ማድረግ፣ መልካም ሥነ ምግባርን መላበስ እና ለነጻነት፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ግንባታ መታገል ማለት ነው። እውነት ማለት ሀገር፣ ታሪክ፣ ባህል እና ማንነት ነው። እውነት አድሎ የማይታይበት፣ ርህራሄና ቸርነት በተሞላበት ለሰው ልጅ ሁሉ መልካም ነገር እንዲያገኝ መመኘትና በጎ ተግባራትን ማከናወን ነው። እውነት የሰው ልጅ ዘላቂ ሰላም እና የተረጋጋ ህይወት እንዲያገኝ ከፍተኛ አስትዋጾ ያደርጋል።

ቀደምት አባቶቻችን ስለእውነት ሲሉ ውድ ህይወታቸውን በሰማዕትነት አሳልፈው ሰጠዋል፤ ብዙ መከራና ስቃይ ተቀብለዋል። ለእውነት ሲሉ ከጊዜያዊ ጥቅም ታቅበዋል። ዛሬም ለእውነት ሲሉ ዋጋ እየከፈሉ የሚገኙ እውነተኛ የእውነት ምስክሮች በብዙ ስቃይና መከራ ውስጥ ይገኛሉ። በብዙ ውጣ ውረድ እውነትን መናገር እጅግ መልካምና ልብን የሚያስደስት ቢሆንም እውነትን የሚወዷትን ያህል የሚፈሯትና ከቻሉም በሀሰት ለውጠው ለማጥፋት የሚመኙ ብዙዎች ናቸው፡፡ በተለይ ጥቅምና ስልጣን ፈላጊዎች እንዲሁም አምባገነን መሪዎች በዋናነት ለእውነት መጥፋት ዋነኛ ተዋናኞች ናቸው፡፡

አምባገነን መሪዎች እውነትን መከተልም ሆነ መስማት አይፈልጉም። መነሻቸውና ግብራቸው ሀሰት ስለሆነ እውነትን ፈጽመው አያውቋትም። እርግጥ ነው እውነት ለእነሱ ጠላት ናት፤ ታጠፋቸዋለች። እነርሱ የሀገር መጥፋት፣ የታሪክ መዛባት፣ የህዝብ ሰላምና ደህንነት አያስጨንቃቸውም። ለሥልጣን ማራዘሚያ ሀገር ይሸጣሉ፣ ህዝብን ይጨቁናሉ፣ ይገድላሉም።
በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ስለ ነጻነት፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ማውራትና መስበክ ወንጀል ከሆነ ዘመናትን አስቆጥሯል። በዚህ ዙርያም ለምን እና እንዴት ብለው የሚጠይቁ ዜጎች እጣ ፈንታቸው እስር፣ እንግልትና ሞት ሆኗል። በኢትዮጵያም ያለው ይህ እውነትን የሚፈራ እና ከእውነት ፈጽሞ የተጣላ የህወሓት አገዛዝ ለሀቅ፣ ለእውነት የቆሙትንና ሕዝብ እውነትን ያውቅ ዘንድ ያለመታከት እየሰሩ የሚገኙ ጋዜጠኞችን፣ ጦማርያንን፣ የፖለቲካ መሪዎችን እና ንጹሃን ዜጎችን ማሳደድና ማሰር ቀጥሎበታል፡፡ በአጠቃላይ ለነጻነት፣ፍትህና ዲሞክራሲ የሚታገሉ ውድ ኢትዮጵያውያንን ወያኔ ማንኛውንም ዋጋ ከፍሎ ወደ ግዞት እንዲወረወሩ ማድረግ፣ መግደልና ማሰቃየት የሥርዓቱ ተቀዳሚ ተግባር አድርጎታል። ወያኔዎች ሰባዊነት የሚባል በውስጣቸው ቅንጣት ስለሌላቸው በነጻነት ታጋይ ኢትዮጵያውያን ላይ የአካልና የሥነ ልቦና አሰቃቂ እና ኢ_ሰባዊ ድርጊት ካለ ምንም ርህራሄ ይፈጽማሉ፤ ዛሬም በመፈጸም ላይ ይገኛሉ።

የወያኔ ፈላጭ ቆራጭ፣ ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ በህብረተሰቡ ላይ የሚያደርሰው ግፍና ሰቆቃ ከመብዛቱ የተነሳ ለእውነት እንዳንቆም እንቅፋት ሆኖብናል። ብዙዎች እውነት መናገር ቢፈልጉም እንዳይናገሩ የተለያዩ አመክንዮ ይሰጣሉ። ከፊሎችም በወያኔ አምባገነን አገዛዝ ተጠልፈው የሥርዓቱ ከዳሚና ደንገጡር በመሆን ከእውነትና ከእራሳቸው ጋር ተጣልተው የሕሊና እስረኞች ሆነው መኖር ጀምረዋል። አብዛኛው ህዝብ ደግሞ ከእውነት ጋር ለመቆም፣ ለእውነት ለመታገል ጊዜና ወቅት በመጣባበቅ ላይ ይገኛል። ብዙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የወያኔን የውንብድና አገዛዝ ተቋቁመው ለእውነት ሲሉ ሰማዕትነትን እየተቀበሉ ይገኛሉ። እውነት ዘላለማዊ ሰላም የምታጎናጽፍ ከመሆኗም በላይ ድልን የምታቀናጅ አሸናፊ ናትና።

በዋናነት ለእውነት እንዳንታገል አዚምና እንቅፋት የሆነብን ወሮበላው የወያኔ ቡድን አምባገነናዊ አገዛዝ መሆኑ ግልጽ ቢሆንም በተለያዩ ዘርፈ ብዙ ምክንያቶች ለእውነት እንዳንታገል ሆነናል። እውነትን በቃል ከመግለጽ ባሻገር በተግባር መኖር እንዳንችል ምክንያቶችን በመደርደር ከእውነት ታቅበናል። ለእውነት እንዳንታገል አዚም ከሆኑብን ምክንያቶች መካከል የተወሰኑትን ማንሳት እንችላለን።

1. ፍርሃት

ፍርሃት በአካል እና በሥነ ልቦና እንዲሁም በእለታዊ ኑሮያችን ላይ እንቅፋት ሊፈጥርብን/ሊደርስብን ይችላል ብሎ በማሰብ ከማነኛውም ድርጊት ወይም ማድረግ ካለብን ነገር መቆጠብ/መከልከል ማለት ነው። ፍርሃት ከነጻነትና ፍትህ እጦት የሚመጣ በሽታ ነው። ፍርሃት ቅጣትን ወይም ብቀላን በመፍራት ማድረግ ከምንፈልገው ሁሉ መታቀብ ማለት ነው። ፍርሃት በቡድንም ሆነ በግለሰብ ሊከሰት ይችላል፤ በሀገርና ህዝብ ላይ ግን ሊከሰት አይችልም። ፍርሃት በግለሰብና በቡድን ደረጃ ብቻም ሳይሆን በአምባገነን መንግሥታት ላይም ይከሰታል። ስልጣንና ገንዘብ በእጅጉ ስለሚፈልጉ ይህንን ሊያሳጣ የሚችል ማንኛውንም ኃይል ይፈራሉ። ስለዚህም ህዝብን በማሰቃየት፣ በማሰርና በመግደል ስልጣናቸውን ያራዝማሉ። ግለሰቦች ይህን መከራና ስቃይ ስለሚፈሩ ለእውነት ከመታገል ወደ ኋላ ይሸሻሉ። ፍርሃት እንደ ህወሓት አምባገነን ገዥዎችን በህዝብ ላይ ስቃይና መከራን የበለጠ እንዲያጸኑ ያደርጋቸዋል፤ ብዕር ይዘው ስለ እውነት የሚታገሉትን፣ ለነጻነት ስርዓቱን የሚቃወሙ የፖለቲካ መሪዎችን፣ ጦማርያንን እና ወጣቱን ትውልድ በአሸባሪነት ተከሰው ግዞት እንዲወርዱ አድርጓቸዋል። የሃይማኖት መሪዎች ሳይቀሩ እውነት ከመናገር ይልቅ ተቋሜ ችግር ሊገጥመው ይችላል በማለት በፍርሃት ተውጠው አምልኮታቸውን እንኳ በስርዓት ማካሄድ እንዳይችሉ አድርጓቸዋል። ስለዚህ ፍርሃት በሁሉም በኩል ለእውነት እንዳንታገል ትልቅ እንቅፋት ሆኖብናል።

2. አድርባይነት/ጊዜያዊ ጥቅም መሻት

ለእውነት እንዳንታገል ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል አድርባይነት አንዱ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተዘግቦ እንደምናገኘው ኤሳው ለሆዱ ብሎ በምስር ወጥ ብኩርናውን አሳልፎ ለወንድሙ ለያዕቆብ እንደሸጠው ሁሉ ዛሬም በዚህ ዘመን ለጊዜያዊ ጥቅም ተብሎ ማንነትንና ሕሊናን በመሸጥ ለእውነት ከመቆም ይልቅ አድርባይነትን ተቀብለው ከእውነት ጋር የተጣሉ በርካቶች ናቸው። አድርባይነት ዛሬ የጀመረ ብቻም ሳይሆን በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አሉታዊ ተጽኖ ከፈጠሩ ጉዳዮች መካከል ትልቁን ስፍራ ይዞ እናገኘዋለን። በአድርባይነት ታውረው በጣሊያን ወረራ ዘመን መንገድ እየመሩ ወደ መሀል ሀገር ከማስገባት በተጨማሪም የንጉሠ ነገሥቱ የቅርብ ባልሙዋል ከነበሩ መኩዋንንቶች እና መሳፍንቶች መካከል ሳይቀሩ ለጣሊያን ያደሩ ሰዎችን እንደምሳሌ ማንሳት ይቻላል። እነዚህ በአድርባይነት የተጠቁ ወገኖች ወይም ሹማምንቶች ህዝቡ ተቃውሞውን በማቆም መሰሪዋ ጣሊያን ይዛው የመጣችውን የይምሰል እውቀት እና ስልጣኔ በመቅሰም ሀገሩን ያለማ ዘንድ በሀሰት ለመሸንገል ሞክረዋል። መረጃ በመስጠት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ደማቸው በግፍ እንዲፈስ ያደረጉት አድርባዮች/ጥቅመኞች ናቸው። ዛሬም አድርባኞችና ጥቅመኞች ጊዜያዊ ሥልጣንን እና የወያኔን ትርፍራፊ በመልቀም የሀሰት “ልማታዊ መንግስት” የሚል ስም ለጥፈው ሀገርን በመሸጥ፣ ታሪክን በመበረዝ፣ ህዝብን በመበደል፣ በማሰርና በመግደል ዋነኛ ተባባሪዎች እነርሱ ናቸው። ስለዚህ ከአድርባይነት ተላቀን ማንነትንና ሕሊናን በጥቅም ሳንሸጥ እንደ ዜጋ ለሀገር በማሰብ ለነጻነት፣ ፍትህና ዲሞክራሲ በጽኑ መታገል ይኖርብናል።

3. ምን አገባኝነት

እኔ ከሞትኩ ሰርዶ/ግጦሽ አይብቀል እንዳለች አህያ እኔ ከበላሁ፣ ከጠጣሁ፣ ኑሮዬ ከተሟላልኝ ለሌላውና ለሚቀጥለው ትውልድ አይመለከተኝም በማለት ለነጻነት ከሚደረገው እውነተኛ ትግል የሚርቁት ጥቂቶች አይደሉም። የራሳቸው በር እስካልተንኳኳ ድረስ የሌሎች ስቃይ፣ በደል፣ ሰቆቃ፣ እንግልትና ስደት አይመለከተንም በማለት ከሰባዊነት ወጥተው ከዳር የቆሙ በርካቶች ናቸው። ምን አገባኝነት የማንነት፣ ሀገራዊና የነጻነት ጥያቄ እንዳናነሳ እና ሆድ አምላኪዎች በማድረግ ለእውነት እንዳንታገል ያደርጋል።

4. የእውቀት ማነስ

በእውቀት የበለጸገ ትውልድ ሀገርን የመለወጥ አቅም ይኖረዋል። እውቀት ሙሉ ሰው በማድረግ ሀገርን ከማነኛውም አሉታዊ ተጽኖ በመታደግ ወርቃማ ታሪክ መስራት ይችላል። አባቶቻችን በዚህ ተክህነውበት ነበር፤ ተፈጥሯዊና በልምድ የቀሰሙትን እውቀት ለሀገር ጥቅም በማዋል በተግባር አሳይተዋል። የሀገርን ታሪክ፣ ባህልና ቋንቋ እንዲሁም የህዝብን ምንነት መረዳትና ጠንቅቆ ማወቅ ሀገራዊ ፍቅር እንዲኖረን ያደርጋል። የበለጸጉ ሀገራት ታሪክንና ብሄራዊ ስሜትን በማስረጽ እያንዳንዱ ትውልድ ለሀገሩ ፖሊስ (እንደ ኢትዮጵያ ፖሊስ ማለቴ አይደለም) እንዲሆን አድርገዋል። ወያኔ ግን ትውልዱ እውቀት አልባ፣ ታሪክ የለሽ ለማድረግ በጎጥና በመንደር ከፋፍሎ ሀገራዊ ስሜት እንዳይኖረው በከፍተኛ ደረጃ እየሰራ ይገኛል። ይህ የእውቀት ማነስ ትውልዱ ሀገራዊ ፍቅር ተላብሶ ለእውነት እንዳንታገል አድርጎናል። ወያኔዎች “በጣሊያን ቅኝ ግዛት በተገዛን ኑሮ” የሚል ትውልድ በማፍራት ሥልጣናቸውን ለማስረዘም እየጣሩ ነው። እውቀታችንን በማዳበር እንደ አባቶቻችን ታሪክ መስራት እንኳ ቢያቅተን ታሪካችንን አስጠብቀን ለተተኪው ትውልድ ማስተላለፍ ሀገራዊ ኃላፊነት አለብን የሚል እምነት አለኝ።

5. ተስፋ መቁረጥ

የህግ የበላይነት ባልሰፈነበት፣ አምባገነን መንግሥት በሰለጠነበት፣ ድህነት በተንሰራፋበት ሀገር እውነት መናገርም ሆነ ለነጻነት መታገል ውጤት አይኖርም በሚል ተስፋ የቆረጠ የህብረተሰብ ክፍል በግልጽ ይታያል። ይህ ችግር በተለይ ወጣቱን ትውልድ ለእውነት ከመታገል ይልቅ ስደትን አማራጭ መፍትሄ አድርጎ እንዲጓዝ አድርጎታል። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ዘረኝነት፣ ማን አለብኝነት፣ ሙስና እና ብልሹ አሰራር በእጅጉ ገዝፎ በመታየቱ ብዙዎችን በቀላሉ የማይቀረፍ ስለሚመስላቸው ተስፋ መቁረጥ ይታይባቸዋል። ተስፋ መቁረት መፍትሄ እንዳልሆነ ቢያውቁትም ለጊዜ ጭቆናን በጸጋ ተቀብለው ሰማያዊ ኃይል በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ብዙዎች ይመስሉኛል። ለውጥ ለማምጣት፣ ተስፍ ለመሰነቅ፣ እውነትን ለማንገስ፣ ነጻነት፣ ፍትህና ዲሞክራስን ለማስፈን ችግሮቻችንን ተቋቁሞ ወደፊት መጓዝ ይኖርብናል እንጂ ተስፋ በመቁረጥ ለስደት እና ለባርነት መጋለጥ የለብንም።

በአጭሩ ከላይ የዘረዘርናቸው ምክንያቶች/ችግር ለወሮበላውና ማፍያ ቡድን ወያኔ አሳልፎ በመስጠት ስቃይና መከራ፣ እንግልትና ሰቆቃ፣ እስራትና ግርፋት፣ ሞትና ስቅላት እንድንቀበል አድርጎናል። ብዙኃኑ ህዝብም ይበላው ይጠጣው አጥቶ፣ ነጻነቱን ተገፎ በድህነት ይሰቃያል፤ ለእውነት እንዳንታገል ትልቅ እንቅፋት ሆኖብናል። ታሪክ እንደሚያስረዳን አባቶቻችን ለእውነት ሲሉ ህይወታቸውን አሳልፈው ሰጠዋል። ዛሬም ብዙዎች መከራን እየተቀበሉ ይገኛሉ። እኛም የእነሱን ዓርያ ለመከተል እና ሀገርን ነጻ ለማውጣት የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይኖርብናል። ለእውነትኛ ትግል እንደ መፍትሄ ሊደረጉ ከሚገባቸው ተግባራት መካከል የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል።

6.እራስን መሆን/ ለሕሊና መኖር

ማንኛውንም ተግባር ለመፈጸም ቀዳሚው ነገር እራስን መሆን ነው። እራሳችንን በሚገባ ሳናውቅና ሳንረዳ የምናከናውናቸው ነገሮች ዘላቂነት ላይኖራቸው ይችላል። በይምሰልና በሌላ አካል ተጽኖ የምንፈጽማቸው ጉዳዮችም እንዲሁ ውጤታቸው አያምርም። ስልጣን፣ ገንዘብ፣ ጥቅም ዜያቸውን ጠብቀው ይጠፋሉ። እራስን ለመሆን ሕሊናን ማዳመጥ ይኖርብናል። ሕሊና በእድሜ ዘመናችን ሁሉ እውነተኛ ዳኛ በመሆኑ ትክክለኛ ፍርድ ይሰጣናል፤ ሕሊና ዘላለማዊ ሰላም አልያም ደግሞ ዘላለማዊ ጸጸት ያጎናጽፈናል። እራችንን መሆን ከቻልን ለእራሳችን፣ ለእውነት፣ ለነጻነት፣ ለፍትህ፣ ለሀገር እና ለወገን መታገል እንችላለን። እውነተኛ ትግልን ከእራስ እንጀምር፤ ያኔ ለውጥ ማምጣ እንችላለንና።

7. ታሪክን በሚገባ መረዳት

ኢትዮጵያ አኩሪ ታሪክ፣ ባህል እና ኩሩ ህዝብ ያላት ሀገር ናት። የህዝቧ ጀግንነት፣ አይበገሪነት፣ ዳር ድንበር ጠባቂነት እና የጥቁር አፍሪካውያን ተምሳሌነት በዓለም የተመሰከረላት ብርቅዬ ሀገር ናት። ሀገራችን የመለያየት፣ የሙስና፣ የዘረኝነት እና ተስፋ ያጣ ትውልድ መፍለቂያ አልነበረችም፤ እንደ ሀገር ዛሬም አይደለችም። ይኸን ታሪኳን ብዙ መዛግብት ይመሰክራሉና ማስተባበል አይቻልም። ቀደምት አባቶቻችን የከፈሉት ዋጋ እንዲሁ በታሪክ ሲወሳ ህያው ሆኖ ይኖራል። ታሪካችንን በሚገባ ተገንዝበን እንደ ዜጋ መክፈል የሚገባንን ዋጋ በመክፈል ለእውነት/ለሀገር መቆም አለብን። ታሪክ ሰርተን እንጂ ታሪክ በርዘን ወይም አጥፍተን ለልጆቻችን ማስተላለፍ የለብንም።

8. በእውቀት እራስን ማነጽ

ከላይ እንዳየነው የእውቀት ማነስ ሀገርን ወደኋላ ያስቀራል፤ ማንነትን ያሳጣል፤ ደካማና ፈሪ ያደርጋል። በእውቀት ከታነጽን ግን ለምን፣ እንዴት እና መቼ እንደምንታገል በደንብ ተረድተን ከዓላማችን እንደርሳለን። እውቀት በዓላማና በስልት እንድንታገል ይረዳናል። ነጻነት፣ፍትህ፣ ዲሞክራሲ እና ልማት ምን ማለት እንደሆነ እንረዳለን። እውቀት ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ለይቶ ያወጣል። እውቀት ወያኔ እንደሚያወራው ህንጻ መገንባት፣ መንገድ መስራት፣ ግድብ መገደብ፣ የሀገሪቱን ለም መሬት ለውጭ ባለሃብቶች ማቀራመት፣ ህዝብ ሃብት ንብረት አፍርቶ ከሚኖርበት ማፍለስ እና ወዘተ የዘላቂ ልማት መገለጫ እንዳልሆነ እንድንረዳ ያደርጋል። እውቀት ከምንም በላይ ለሰባዊ መብት፣ ለነጻነት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ እንድንቆም እና በጽኑ እንድንታገል ከፍተኛ አስተዋጾ አለው። ስለዚህ በእውቀት መታነጽ ያስፈልጋል።

9. አንድነትን መፍጠር

ስለ አንድነት ብዙ መተንተን አስፈላጊ መስሎ አልታየኝም፤ በተግባር እንጂ በቃላት የሚገለጽ አይደለም። አባቶቻችን በተግባር አሳይተውናልና። በእውነት ወያኔን ከህዝብ ጫንቃ ላይ አሶግዶ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ለመገንባት ከሆነ የማስመሰል ሳይሆን እውነተኛ ህብረት/አንድነት ይኑረን። በዘር፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት ተለያይተን ለውጥ ማምጣት በፍጹ የማይታሰብ ነው። “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” እንደሚባለው ተባብረን በአንድ ላይ ከቆምን እንኳን ወያኔን ጣሊያንን ድባቅ የመቱ ኢትዮጵያውያን አርበኞች ልጆች ነንና ጊዜ ሳይፈጅብን ሀገራችንን ነጻ ማውጣት እንችላለን። ስለዚህ አንድነት ይኑረንና ከዘረኛው ወያኔ እራሳችንና ሀገራችንን ነጻ እናውጣ!

በአጠቃላይ ለእውነት እንዳንታገል አዚም የሆነብንን ነገር አሶግደን ከእኛ የሚጠበቀውንና ጊዜው የሚጠይቀውን ማንኛውንም ዋጋ በመክፈል ለእውነት ከቆሙ እና ከነጻነትና ፍትህ ታጋዮች ጋር በመቀላቀል በይፋ እውነትን መስበክ ሀገራዊ ግዴታ አድርገን እንነሳ። እኛ በውጭም በውስጥም የምንኖር ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያን የወያኔ ተራ የሃሰት ወሬና ማስፈራሪያ ሳይገድበን ለነጻነትና ፍትህ በጽናት እንታገል። ለእውነት፣ ለሀገር፣ ለነጻነትና ፍትህ ብለው ስቃይና መከራ፣ እስራትና ግርፋት እንዲሁም ሞት የተፈረደባቸውን እውነተኛ ታጋዮችን በማሰብ የእነርሱን ራዕይ እና ሀገራዊ ተልእኮ ከግብ ለማድረስ እኛ ለእውነትና ለእውነት ብቻ በመታገል ሀገርራችንን ከወያኔ ዘረኛና አምባገንን አገዛዝ እንታደግ።
ለእውነትና ለእውነት ብቻ እንታገል! አዚም የሆነብንን ወያኔን በነገር ሁሉ እንቃወም!!!

አስተያየታችሁን በ gashuy@gmail.com ብትጽፉልኝ ይደርሰኛል።

The post ለእውነት እንዳንታገል አዚም የሆነብን ምንድር ነው? – ዘጠኙ ምክንያቶችን እንሆ -(በይበልጣል ጋሹ) appeared first on Zehabesha Amharic.


Sport: የሊቨርፑል ፀሐይ ጠልቃ ይሆን?

0
0

ለከርሞ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ለሊቨርፑል ቦታ የለውም፡፡ ለእንግሊዝ ክለብ በትልቁ መድረክ ተሳታፊ የሚያደርገውን ዕድል ማግኘት አልቻለም፡፡ የአሁኖቹ የክለቡ ባለሀብቶች ወደ እንግሊዝ ሲመጡም ሊቨርፑል የቻምፒዮንስ ሊግ ተወዳዳሪ አልነበረም፡፡ ብሬንዳን ሮጀርስ በአንፊልድ ሲሾሙም ክለቡ በፕሪሚየር ሊግ እስከ አራተኛ ደረጃ ይዞ አልጠበቃቸውም፡፡ ዘንድሮም የተለወጠ ነገር የለም፡፡ አምና በአስደናቂ ሁኔታ ያሳኩትን የቻምፒዮንስ ሊግ ሊቆዩበት አልቻሉም፡፡ በፕሪሚየር ሊግ ብቃታቸውን መጠበቅ ተስኗቸው ቀርቷል፡፡
liverpool copy
አሁን ሊቨርፑል በሊጉ እስከ አራተኛ ደረጃ ውስጥ የለበትም፡፡ በእንግሊዝ የክለቦች የሀብት ደረጃም እንደዚሁ ከአራቱ ሀብታሞች መካከል አይገኝም፡፡ በሊቨርፑል ቦታ ሆኖ ትልልቅ ተጨዋቾችን ማስፈረም ያስቸግራል፡፡ ሊቨርፑል ትልቅ ተጨዋች ለማስፈረም የተሻለ ዕድል የነበረው ባለፈው ክረምት ነበር፡፡ ሆኖም አልተሳካለትም፡፡ ክለቡ አጥብቆ የፈለገው አሌክሲስ ሳንቼዝም አርሰናል መረጠ፡፡ ሊቨርፑል ተጨዋቾችን ወደ ክለቡ ለመሳብ የተጋነነ ደመወዝ ማቅረብ ቢጀምር በቀጣይ የሚጠብቀው ቅጣት የከፋ ይሆናል፡፡ የፋይናንሳዊ ጨዋነት ደንብ ክለቡ ወጪውን በገቢው መጠን እንዲያደርግ ያስገድዳል፡፡
ሊቨርፑል ለተጫዋቾች ከ100 ሺ እስከ 150 ሺ ፓውንድ መክፈል ቢጀምር ለሌላ አዲስ እና ደረጃው እጅግ የላቀ ሌላ ፈራሚው እስከ 254 ሚሊዮን ፓውንድ ለመክፈል ይገደዳል፡፡ ይህንን ያህል ገንዘብ የሳምንቱ የሚከፈለው ኮከብ በላቀ ብቃት መጫወት ቢሳነው የተቀሩት ጥሩ ተጨዋቾች ሁሉ ቢያንስ 250 ሺ ፓውንድ እንዲከፈላቸው ቢጠይቁ አያስገርምም ይሆናል፡፡

የክለቦች የደመወዝ መዋቅር ብዙ የተወሳሰቡ ጉዳዮች አሉበት፡፡ የተጫዋቾች ደመወዝ ከብቃት ደረጃቸው እና ከሚያስፈልጋቸው ገንዘብ መጠን ጋር የተያያዘ ብቻ አይደለም፡፡ ተጨዋቾች አብረዋቸው የሚጫወቱ የቡድን ጓደኞቸው የሚከፈላቸውን የገንዘብ መጠን በመመልከት ብቻ የደመወዝ ጭማሪ ይጠይቃሉ፡፡ ለምሳሌ 30 ሺ ፓውንድ ብቻ ሳምንታዊ ደመወዝ የሚከፈለው ተጨዋች የተንደላቀቀ ኑሮ መግፋት ይችላል፡፡ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥም ሚሊየነር መሆን አያቅተውም፡፡ ነገር ግን በቡድኑ ሌላ ሳምንታዊ 150 ሺ ፓውንድ ደመወዝ የሚያገኝ ተጨዋች ካለ እርሱም በችሎታው እንደማያንስ እና ተመሳሳይ ገንዘብ ሊከፍለው እንደሚገባ መጠየቅ ይጀምራል፡፡ አለበለዚያም በወኪሉ በኩል ያስጠይቃል፡፡

በ2011 ሊቨርፑል ምርጡን ሉዊስ ሱአሬዝ በዝቅተኛ ሳምንታዊ ደመወዝ ሲያስፈርም ዕድለኛ ነበር፡፡ ምናልባትም ኡራጓያዊው በሆላንድ ሰው መንከሱ ለሊቨርፑሉ መልካም አጋጣሚ ሳይሆን አልቀረም፡፡ የሆነ ሆኖ ሱአሬዝ በእያንዳንዱ ጨዋታ ያለውን ብቃት ሁሉ አውጥቶ እየተጫወተ በሊቨርፑል ደመወዙን ከፍ አደረገ፡፡ ሱአሬዝ በሊቨርፑል ሳለ ክለቡ የወጣበት ገንዘብ ተገቢነት ላይ ጥያቄ የሚያነሳ ሰው አልነበረም፡፡ ነገር ግን ሊቨርፑል ራዳሚኤል ፋልካኦን ቀደም ብሎ በውሰት አስፈርሞት ቢሆን ኖሮ ሳምንታዊ የ260 ሺ ፓውንድ ደመወዙ በሌሎች የቀዮቹ ተጨዋቾች አዕምሮ ምን ሊፈጥር ይችል እንደነበር መገመት ይቻላል፡፡ የማሪዮ ባሎቴሊ የውድድር ዘመን ደካማ መሆን ተመሳሳይ አደጋ ሊፈጥር ይችል የነበረ ቢሆንም የጣልያናዊው ሳምንታዊ ደመወዝ ከ90 ሺ ፓውንድ አለመብለጡ ክለቡን ጠቅሞታል፡፡

ሊቨርፑል የተለየ አጋጣሚ ካልተፈጠረ በስተቀር የደመወዝ ጣሪያውን አይቀይርም፡፡ ከከፍተኛ ደመወዝ ይልቅ በቦነስ ክፍያዎች ላይ ይደራደራል፡፡ በእርግጥ አለመፈለግ ብቻ ሳይሆን ሊቨርፑል እንደሌሎቹ ሀብታም ክለቦች የተጋነነ ደመወዝ ለመክፈል አቅም የለውም፡፡

የሲቪያ ሞዴል
ሮጀርስ ከክለቡ ባለሀብቶች ጋር ስብሰባ ይቀመጣሉ፡፡ በስብሰባው የአሰልጣኙ የ2014/15 የውድድር ዘመን ይገመገማል፡፡ በተለይም አሰልጣኙ በቅርብ ጊዜ ባስፈረሟቸው ተጨዋቾች ውጤታማነት ላይ ምላሽ እንዲሰጡ ይደረጋሉ፡፡ በእርግጥ የሮጀርስ የዝውውር ሪከርድ ጆን ሄንሪ በቦስተን ሬድ ስኮስ ውጤታማ ከሆኑበት አሰራር ለየት ይላል፡፡
ሮጀርስ ለከርሞ የሊቨርፑል አሰልጣኝ ሆነው የመቀጠላቸውን ዕድል ‹‹በ150% እርግጠኛ ነኝ›› ሲሉ ያረጋግጣሉ፡፡ በእርግጥ ሰውዬው የሚቆዩ ከሆነ ግን ቢያንስ የዝውውር ስትራቴጂያቸው ለውጥ የሚፈልግ ይመስላል፡፡ ሊቨርል የላሊጋውን ክለብ ሲቪያ መንገድ ቢከተል ሲሉ ምክራቸውን የሚሰጡ አሉ፡፡ ለዚህ ደግሞ የስፔኑ ክለብ እግርኳስ ዳይሬክተር ቁልፍ ሰው ናቸው፡፡
ሊቨርፑል በ2012 ክረምት ያስፈረመውን አንዲ ካሮል እንኳን መተካት አልቻለም፡፡ ነገር ግን ሄንሪ ለደጋፊዎች በላኩት ግልፅ ደብዳቤ የፌንዌይ ስፖተስ ስትራቴጂ ወጪ መቆጠብ ብቻ አለመሆኑን ገልፀዋል፡፡ ‹‹የዝውውር ፖሊሲያችን ወጪ ቁጠባ ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁኑ ላወጣነው ወጪ ወደ ፊት የላቀ ዋጋ ማግኘት እና ጥራትን ከፍ ማድረግ እንፈልጋለን፡፡ ብልሃት የተሞሉ ግዢዎች እንፈፅማለን፣ ገንዘብ አናባክንም፣ የተጋነነ የዝውውር ሂሳብ እና የማያሳምን ደመወዝ አናወጣም››
ሊቨርፑል እና አዲሶቹ ባለሀብቶች ሶስት መጥፎ የማይባሉ የውድድር ዘመናትን ቢያሳልፉም ገንዘቡን ባለማባከን በኩል ምን ያህል እንደተሳካላቸው ያከራክራል፡፡

ሊቨርፑል ካሮልን ለዌስትሃም ሲሸጥ የከሰረው 20 ሚሊዮን ፓውንድ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ እንግሊዛዊው አጥቂ አንፊልድን እንዲለቅቅ የመደረጉ ተገቢነት ባያጠያይቅም የሊቨርፑል ኪሳራ ግን ጥቂት የሚባል አይደለም፡፡ ክለቡ ሱሶ እና ስቲዋርት ዳውኒንግን ሸጦ ያገኘው ገንዘብ እንዲሁም ፋቢዮ ቦሪን፣ ዴያን ሎቨሪን፣ አዳም ላላና፣ ሉዊስ አልቤርቶ እና ኢያጎ አስፓስን ሲያመጣ ያወጣው ሂሳብ የክለቡ ቡድን የገንዘብ አጠቃቀም ጥያቄ ውስጥ ይጥለዋል፡፡

በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ሲቪያ የፈፀማቸውን ዝውውሮች እንመልከት፡፡ የስፔኑ ክለብ ከ2012 እስከ 2014 ያስፈረማቸው ተጨዋች ጂኦፍሪ ኮንዶግቢያ (3.5 ሚሊዮን ፓውንድ)፣ ካርሎስ ባካ (6 ሚሊዮን ፓውንድ)፣ ማርኮ ማሪን (በውሰት)፣ ቪቶሎ (3 ሚሊዮን ፓውንድ)፣ ስቴፋን ሞቢያ (በውሰት በኋላም በቋሚነት)፣ ዳኒኤል ካሪክ (በውሰት በኋላም በቋሚነት)፣ ኤቨር ባኔጋ (2 ሚሊዮን ፓውንድ)፣ ቲሞቲ ኮሎድዜዬዛክ (5 ሚሊዮን ፓውንድ)፣ ዤራርድ ዴልፉ (ውሰት)፣ ዴኒስ ሱአሬዝ (ውሰት) ናቸው፡፡

እነዚህ ተጨዋቾች ሁሉ በአሳማኝ ወጪ የተሰበሰቡ እና ቆይቶም በአሰልጣኝ ኡናይ ኢምሬ ስኬታማ ቡድን ጥሩ ብቃታቸውን ያሳዩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ባካ በላሊጋ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ሊዮኔል ሜሲ፣ ኔይማር እና አንቶኒ ግሪዝማን ቀጥሎ አምስተኛው ከፍተኛ ጎል አግቢ ሆኖ የውድድር ዘመኑን የሚያጠናቅቅ ይመስላል፡፡

ሲቪያ በሽያጭ ያገኘውም ገንዘብ የዝውውር ስትራቴጂውን ስኬታማነት ያሳያል፡፡ ማርቲን ካሴሬስ (7 ሚሊዮን ፓውንድ)፣ አልቫሮ ኔግሬዶ (22 ሚሊዮን ፓውንድ)፣ የሶስ ናቫስ (17.5 ሚሊዮን ፓውንድ)፣ ጋሪ ሜዴል (11 ሚሊዮን ፓውንድ)፣ ኢቫን ራኪቲች (16 ሚሊዮን ፓውንድ)፣ ፌዴሪኮ ፋዚዮ (9 ሚሊዮን ፓውንድ) እና አሁን የሊቨርፑል ንብረቶች የሆኑት ሁለቱ አልቤርቶዎች አልቤርቶ (7 ሚሊዮን ፓውንድ) እና አልቤርቶ ሞሮኖ (16 ሚሊዮን ፓውንድ) በሆነ ዋጋ ተሽጠዋል፡፡

ባለፉት ሶስት የውድድር ዘመናት ሲቪያ 9ኛ፣ 5ኛ እና ዘንድሮም 5ኛ ደረጃን ይዞ በላሊጋው አጠናቅቋል፡፡ የዩሮፓ ሊግን ሲያሸንፍ አሁንም ድሉን ሊደግም ቀርቧል፡፡ ከተጨዋቾች ሽያጭም 32 ሚሊዮን ፓውንድ አግኝቷል፡፡ ለመሆኑ ክለቡ ይህንን ስኬት ያገኘበት ምስጢር ምንድነው?

ከሲቪያ የዝውውር ስኬት በስተጀርባ ያሉት ሰው ‹‹ሞንቺ›› ወይም በሙሉ ስማቸው ሮማን ሮድሪጌዝ ቬርዴጆ ይሰኛሉ፡፡ ለሲቪያ የቅርብ ጊዜ ስኬቶች አሰልጣኙ ኢምሬ አድናቆት ቢገባቸውም ከክለቡ ሂደቶች በስተጀርባ ግን ቁልፉ ሰው ‹ሞንቺ› ናቸው፡፡ የቀድሞ የሲቪያ ግብ ጠባቂ የነበሩት ሞንቺ በ2009 በ30 ዓመታቸው ከተጨዋችነት ከተገለሉ በኋላ የክለቡ የእግርኳስ ዳይሬክተር ሆነዋል፡፡ ሰውየው ወደዚህ ኃላፊነት ከመጡ በኋላ ሩተን ራኪቲች፣ ሜዲል፣ ኔግሬዶ፣ ኮንደግቢያ፣ ፋዚዮ፣ ሉዊስ ፋቢያኖ፣ ጃሊዮ ባፕቲስታ፣ ፍሬዲ ካኑቴ፣ ሴይዱ ኬይት እና ኦድሪያኖን በክለቡ የተሻለ ደረጃ ላይ ደርሰው ጥሩ ዋጋ እንዲያወጡ አድርገዋል፡፡

ሞንቺ በአንድ ወቅት ስለሚከተሉት ስትራቴጂ የማብራራት ዕድል አግኝተዋል፡፡ ‹‹እኔ ለአሰልጣኙ መሳሪያ እንደሆንኩ አድርጌ ራሴን እቆጥራለሁ፡፡ ኡናይ ኢዋሬ ምን አይነት ተጨዋች እንደሚፈልግ ይነግረኛል፡፡ ከዚያም የእኔ የምልመላ ቡድን ስራውን ይጀምራል፡፡ ለዚህም ከአሰልጣኙ ጋር ያለን መናበብ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በምልመላ ቡድናችንም እንደዚሁ አይነት የተቀናጀ አሰራር አለ፡፡››

የሞንቺ ጥብቅ የሆነ የተጨዋቾች መመዘኛ ሂደት በእንግሊዝ ክለቦች ብዙም አይስተዋልም፡፡ በተለይም በሊቨርፑል ይህ እንደ ችግር ሊጠቀስ ይችላል፡፡ በሲቪያ ግን የእግርኳስ ዳይሬክተሩ በዚህ በኩል የነበሩቱ ሆነው ድንቅ ችሎታ ያላቸውን ተጨዋቾች ማስፈረም ችለዋል፡፡ ‹‹የምልመላ ቡድናችን ተጨዋችን በጥልቀት ይመለከታል፡፡ በተጫወተባቸው የተለያዩ ቦታዎች የነበረውን ብቃት ይመዝናል፡፡ በየቦታው ብዙ መልማዮችን አናሰማራም፡፡ በሲቪያ የ16 ሰዎች ቡድን አለን፡፡ ከደቡባዊቷ ስፔን እየተነሳን የተጨዋቾችን ለመመልከት የማንደርስበት የለም፡፡

‹‹በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚደረጉ ጨዋታዎችን እንመለከታለን፡፡ የቤልጂየም፣ ፈረንሳይ፣ ቺሊ እና ሌሎችንም እንቃኛለን፡፡ መልማዮች የግድ በላቲን አሜሪካ ሀገሮች ሊኖሩን ያስፈልጋል ብለን አናምንም፡፡ በቴሌቪዥን ሁሉንም ጨዋታዎች የመመልከት ዕድል እያለን ሰዎችን ወደ ሌሎች ሀገሮች መላክ አይጠበቅንም፡፡››

የሲቪያን የዝውውር ስትራቴጂ ስኬት ለማሳየት የተሻለው ምሳሌ ዳኒ አልቬስ ነው፡፡ ከብራዚሉ ባሂያ በ2003 በ500 ሺ ፓውንድ ብቻ ተገዝቶ የነበረው ተጨዋች በስድስት የውድድር ዘመን ለሲቪያ 175 የሊግ ጨዋታዎችን ካደረገ በኋላ በ2008 በ23.5 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ ባርሴሎና ተዘዋውሯል፡፡ በሽያጭ ውሎ ውስጥ ሌሎችም የተጨማሪ ክፍያ አንቀፆች የተካተቱበት የአልቬስ ዝውውር በአጠቃላይ ወደ ሲቪያ ካዝና የሚገባውን ገንዘብ በሂደት 28.5 ሚሊዮን ፓውንድ ሊያደርሰው ይችላል፡፡ በእርግጥ አልቬስ በ2006 በ8 ሚሊዮን ፓውንድ የሊቨርፑል ንብረት ሊሆን ቢቃረብም የመርሲ ሳይዱ ክለብ የተጠየቀውን ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆኑ ዝውውሩ ተደናቅፏል፡፡

ሲቪያ በላሊጋ እና በአውሮፓ መሻሻሉን ቀጥሏል፡፡ ለትልልቆቹ ተጋጣሚዎቹም አስፈሪ ነው፡፡ በስፔን ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ከወገብ በላይ ሆኖ ማጠናቀቅ የለመደው ክለብ ከ2000/01 ወዲህ ሁለት ጊዜ የኮፓ ዴል ሬይ እና ሶስት ጊዜ ዩሮፓ ሊግን አሸንፏል፡፡

ሊቨርፑል ከሲቪያ ሊኮርጅ የሚችለው መልካም ነገር የዝውውር ስትራቴጂውን ብቻ አይደለም፡፡ ሲቪያ ሞንቼን እንደተጠቀመው ሁሉ የመርሲ ሳይዱ ክለብም ተመልሰው መጥተው በተለያየ ሚና ሊያገለግሉት የሚችሉ የቀድሞ ጀግኖች አሉት፡፡ ለዚህ ደግሞ አያክስ እና ባየርን ሙኒክ ጥሩ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ሁለቱ ክለቦች ከሜዳ ውጪ ያለውን የመሪነት ሚና ለቀድሞ ተጨዋቻቸው ሰጥተው ጥሩ የሚባል ውጤት አግኝተዋል፡፡

የአያክስ እና ባየርን ተሞክሮ

የሊቨርፑልን ባለቤትነት የያዘው ኤፍ.ኤስ.ጂ ወይም ኢያን አይሬ ለክለቡ መጥፎዎች አይደሉም፡፡ አንፊልድን የሚያስተዳድሩበት መንገድም ደካማ ሊባል አይችልም፡፡ ነገር ግን ውጤታማነታቸው አንድ ወጥ አይደለም፡፡ እንዲያውም ከቢዝነስ አቅጣጫ ከታየ ሰዎቹ ስኬታማ ናቸው፡፡ የአንፊልድን ተመልካች የመያዝ አቅም ከፍ እያደረጉ ነው፡፡ የክለቡን ዕዳ በእጅጉ መቀነስ ችለዋል፡፡ በርካታ የስፖንሰርሺፕ ውሎችን እየተፈራረሙ የሊቨርፑልን ፋይናንሳዊ አቅም አጠንክረዋል፡፡ በዚህ የክለቡ ባለስልጣናት የሚያስመሰግን ሥራ ሰርተዋል፡፡

በእግርኳሳዊው መመዘኛ ግን ይህንን መድገም አልቻሉም፡፡ በተለይ ከተጨዋቾች ዝውውር ጋር በተያያዘ ሊቨርፑል እጅግ ተፈትኗል፡፡ ምርጥ ተጨዋቾችን ማስፈረም ካለመቻሉም በላይ ያገኛቸውን ድንቅ ከዋክብት ማቆየት ይቸግራል፡፡ ይህ ደግሞ ቡድኑ እየተጠናከረ ወደ ስኬታማነቱ እንዳይመለስ እንቅፋት ሆኖበታል፡፡

አያክስ እና ባየርን ለቀድሞ ተጨዋቾቻቸው የሰጡት ሚና በሊቨርፑል ቢደገም የክለቡ በርካታ ችግሮች መስመር መያዝ እንደሚጀምሩ የሚናገሩ አሉ፡፡ ግዙፉ የእንግሊዝ ክለብ ለዚህ ቦታ ያለው አይመስልም፡፡ ሌላው ቀርቶ በክለቡ ታሪክ ረጅም ዓመታት ያገለገለው አምበላቸው ስቲቭን ዤራርድ በአንፊልድ የስንብት ስነ ስርዓት ሲደረግለት የሊቨርፑል ባለቤቶችም ሆኑ ሊቀመንበሩ በስታዲየሙ አለመገኘታቸው ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው፡፡ ሰዎቹ የእግርኳስ ሳይሆን የቢዝነስ ሰዎች መሆናቸውን ያመላክታል፡፡ ስለዚህ ክለቡ እግርኳሳዊ ጎትን እግርኳስን ለሚያውቁ ሰዎች ቢተው ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል መገመት አያስቸግርም፡፡

በባየርን ሙኒክ የቀድሞ ኮከባቸው ካርል ዌይንዝ ሩሚኒንግ የሊቀመንበርነቱን ቦታ ይዟል፡፡ ከእርሱ ዝቅ ብለው የተቀመጡትም የቀድሞ ተጨዋቾች ናቸው፡፡ ማቲያስ ሳመር የስፖርት ዳይሬክተር ነው፡፡ ገርድ ሙለር በሁለተኛው ቡድን ምክትል አሰልጣኙ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ በ1970ዎቹ ክለቡ የቀድሞ ኮከቡን ኡሊ ሆኔሽ ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርጎት እስካለፈው ማርች ወር ድረስ በስኬት ዘልቀዋል፡፡

ወደ አያክስ ብንሄድ የሆላንዱ ክለብ ይበልጥ በዚህ የተጠቀሙ መሆኑን እንረዳለን፡፡ በክለቡ ቦርድ ካሉት ሰዎች ውስጥ አንድ የቀድሞ ተጨዋች እና የቀድሞ መልማይ፣ አሰልጣኝ እናገኛለን፡፡ ማርክ አቨርማርስ አሁን የክለቡ ቴክኒክ ዳይሬክተር ነው፡፡ ኤድዊን ቫንደር ሳር የማርኬቲንግ ዳይሬክተርነቱን ቦታ ይዟል፡፡ ዋና እና ምክትል አሰልጣኞቹ ፍራንክ ደ ቦር እና ዴኒስ ቤርካምፕ የቀድሞ ተጨዋቾች ብቻ ሳይሆኑ በክለቡ አካዳሚ ያለፉ ናቸው፡፡

በባየርንም ሆነ በአያክስ የተጠቀሱት ሰዎች ለምሳሌ ያህል የተነሱ ናቸው፡፡ ወደ ታች ወርደን ብንመለከት በክለቦቹ መዋቅር የተለያዩ ቁልፍ ሚና የወሰዱ የቀድሞ ተጨዋቾች እናገኛለን፡፡ እነዚህን ሰዎች ሙያውን ማወቅ ብቻ ሳይሆን የሚሰሩትን ሥራ ይወዱታል፡፡ የክለባቸውን ባህል እና ማንነትም በጥልቀት ይገነዘባሉ፡፡ ይህ አሰራር በሚገባ ተሞክሮ ውጤታማ መሆኑ የታየ ነው፡፡

በእርግጥ እግርኳስ ክለቦች አሁን ቢዝነስ መሆናቸው ተደጋግሞ ይደመጣል፡፡ ደጋፊዎች በክለባቸው ላይ ያላቸው ተሰሚነት፣ የክለቡ ታሪክ እና ባህል እየደበዘዘ መጥቶ ወደ መጥፋቱ ተቃርቧል፡፡ ሊቨርፑል ታሪክ እና ባህል አለው፡፡ የደጋፊዎቹ ብዛትም በዓለም ዙሪያ ነው፡፡ የክለቡን ማሊያ የለበሱ እና አሁንም ስለ ሊቨርፑል ግድ የሚላቸው የቀድሞ ተጨዋቾች በርካቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች በየዓቱ፣ በየወሩ፣ በየሳምንቱ በሚዲያ እና በተለያዩ መንገዶች ለክለቡ ተቆርቋሪነታቸው የሚያሳዩ አስተያየቶችን ይሰጣሉ፡፡

ጃሚ ካራገር ባለፈው ሳምንት ስለ ረሂም ስተርሊንግ የተናገረውን መመልከት በቂ ነው፡፡ ጆን አልድሪጅ የሊቨርፑልን የዝውውር ጉዳዮች ኮሚቴ ትቶ እና ለውጥ እንደሚፈልግ አበክሮ የገለፀበትን ፅሑፍ ማስታወስ ይቻላል፡፡ ጄራርድ ወደ አንፊልድ እንደሚመለስ ሲናገር መስማት የቀድሞ ተጨዋቾች ክለባቸውን በተለያየ ሚና ለማገልገል ዝግጁ እንደሆኑ ያሳያል፡፡
ተጨዋቾች እና ደጋፊዎች ጠንካራ ግንኙነት የሚፈጥሩባቸውን ክለቦች ብንቆጥር ሊቨርፑል ከቀዳሚዎቹ ተርታ ይቀመጣል፡፡ ይህ ግንኙነት ተጨዋቾች ክለቡን ሲለዩ ሊያበቃ አይገባም፡፡ ይህ የክለቡ መልካም ጎን ከታሪክነት አልፎ የሊቨርፑል የወደፊት ስኬት መሰረት ሊሆን ይችላል፡፡ ሮቢ ፎውለር፣ ሮብ ጆንሰን እና ስቲቭ ማክናማን ከታዳጊ ቡድኖች ጋር ብዙ ሰርተዋል፡፡ እነዚህ ከዋክብት በ30ዎቹ መጨረሻ እና በ40ዎቹ መጀመሪያ ዕድሜያቸው ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ በሙሉ አቅማቸው ለረጅም ዓመታት ለማገልገል ዝግጁ ናቸው፡፡

በእርግጥ ሁሉም የቀድሞ ተጨዋቾች አስፈላጊ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ የቀድሞ ምርጥ ጎል አስቆጣሪ በቡድኑ አሁን ምር የማጥቃት አቅም ያለው ቅንጅት ላይፈጥር ይችላል፡፡ የዋንጫ አሸናፊ ቡድንን መገንባት ይቸገር ይሆናል፡፡ ሆኖም ሊቨርፑል አሁን በቡድኑ ምን እንደሚጎድለው መመልከት ያሻዋል፡፡

ሊቨርፑል ምርጥ ተጨዋቾችን ለማስፈረም ሲነሳ ድርድሩን የሚመሩትን ሰዎች ተመልከታቸው፡፡ ኢያን አይሬ እና ብሬንዳን ሮጀርስ ደረጃቸው ላቅ ያሉ ተጨዋቾችን የሚስብ የቀደመ ስም እና ዝና የላቸውም፡፡ በቡድኑ ከዤራርድ በኋላ አውራ ሆኖ እየታየ ያለው ጆርዳን ሄንደርሰንን የጥቂት ወራት የቻምፒዮንስ ሊግ ልምድ አይተው አብረውት ለመጫወት የሚጓጉ ከዋክብት ብዙ ይኖራሉ?

ይልቁን እነዚህን ድርድሮች የቀድሞ የክለቡ የቻምፒዮንስ ሊግ ጀግኖች ቢያካሂዱት ብለን ማሰብ እንችላለን፡፡ ለሊቨርፑል ሶስት የቻምፒዮንስ ሊግ ያሸነፉትን አምበሎች ዤራርድ፣ ፊል ቶምሰን እና ግሪዬም ሶነስ ድርድሮች ቢመሩ ምን ያህል በተሻለ አቅም ተጫዋቾችን ሊያሳምኑ እንደሚችሉ መገመት አያስቸግርም፡፡ ክለቡ ከቀደሙ ጀግኖቹ በከፊል የአሰልጣኞች ስታፍ እና የአስተዳደር ቦታዎች ላይ ቢያስቀምጥ ማንነቱን እንደጠበቀ ወደ ትልቅነቱ ለመመለስ መንደርደር ይችላል፡፡ በፋይናንስ እና በሌሎችም ችግሮች ያጣውን ምርጥ ተጨዋቾች የመሳብ አቅምም መመለስ ይችላል፡፡ ቢያንስ ክለቡ ሥራውን መጀመር ይችላል፡፡ የአሁኑ ሊቨርፑል መሪዎች ይጎድሉታል፡፡ የቀድሞ ተጨዋቾች አሁን ሜዳ ገብተው ቡድኑን ማገዝ አይችሉም፡፡ ነገር ግን እነዚህ አሸናፊዎች፣ መሪዎች እና ታሪካዊ ልጆች ለክለቡ የሚሰጡት አላቸው፡፡

በእርግጥ ጉዳዩ የቀድሞ ተጨዋቾችን የመመለስ አይደለም፡፡ ዋናው ነገር እግርኳስን ለሙያው ሰዎች መስጠት ነው፡፡ ይህ የቡድኑ አሰልጣኞች ቦታ ይጨምራል፡፡ የቀደሙት ተጨዋች ያለፉበት ጊዜ እና የአሁኑ እግርኳስ ብዙ ታክቲካዊ ለውጦች አሉት፡፡ ወጣቶቹ አሰልጣኞችአሌክስ ኢንግሊትሮፕ፣ ኒል ክሪትቻሊ እና ፔፕጂን ለንደርስ በዘመናዊ እግርኳስ ፍልስፍናዎች የወጣቶችን ስልጠና ሊያስኬዱ ይችላሉ፡፡ ሌሎቹም የአሰልጣኝነት ፈቃዳቸውን ከጨረሱ በተለያየ ደረጃ የአሰልጣኞች ስታፍ ቦታ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡

በተጨማሪም የደጋፊ ማህበራት ተሳትፎ እና ሃሳብ ሊቨርፑልን የሚያግዝ አቅም አለው፡፡ ሆነሽ የባየርን ፕሬዝዳንት በነበሩበት ወቅት ደጋፊዎችን እንደሚታለቡ ላሞች ብቻ መመልከት እንደማይፈልጉ ተናግረዋል፡፡ ኬኒ ዳልግሊሽ እና ኢያን ረሽ ለአንፊልድ ታዳሚዎች ተመሳሳይ አመለካከት እንዳላቸው መገመት አያስቸግርም፡፡

የዝውውር ስትራቴጂ
የአስተርሊንግ ጉዳይ ለሊቨርፑል ምርጥ ተጨዋቹን ከማጣትም በላይ ነው፡፡ የወጣቱ ኮከብ ክለቡን ለመልቀቅ መቃረብ አጠቃላይ የሊቨርፑል የዝውውር ስትራቴጂ ላይ ጥያቄ ያስነሳል፡፡ ስተርሊንግ በክለቡ መቆየት አለመፈለጉ የሊቨርፑል ተፈላጊነት መቀነሱን እና ከውጪ ምርጦችን መሳብም እንደማይችል ፍንጭ ይሰጣል፡፡

በእርግጥ ስትርሊንግም ሆነ ወኪሉ ኢዲ ዋርድ ከሊቨርፑል መለያየት የፈለጉበትን ምክንያት ከመጀመሪያ አንስቶ በአንድ ቃል አልገለፁም፡፡ ቀደም ሲል ጉዳዩ ሊቨርፑል ሳምንታዊ 150 ሺ ፓውንድ ለመክፈል ፈቃደኛ ካለመሆኑ ጋር የተያያዘ ይመስል ነበር፡፡ ቆይቶ ደግሞ ጉዳዩ ከገንዘብ ጋር ሳይሆን ተጨዋቹ ያለቦታው እንዲጫወት ከመደረጉ ጋር እንደሚገናኝ ተሰማ፡፡ በኋላ ደግሞ ስትርሊንግ ወደ ሌላ ክለብ ተጉዞ ዋንጫዎችን ማንሳት እንደሚሻ ተገለፀ፡፡

እውነተኛው ሰበብ ምንም ይሁን ምን ሊቨርፑል ገና በብቃቱ ጫፍ ላይ ያልደረሰውን ድንቅ ተጨዋቹን ሊያጣ በእጅጉ ተቃርቧል፡፡ ይህ ለደጋፊዎች አስፈሪ ስሜት ይፈጥራል፡፡ ሊቨርፑል የተጋነነ ሂሳብ ካልከፈለ በስተቀር ቡድኑን ከዚህ የተሻለ ማጠናከር የማይችል ይመስላል፡፡ የክለቡ ባለስልጣናት ምርጥ ወጣቶችን በግዢ እና በአካዳሚ አሳድጎ የመጠቀም ስትራቴጂ መያዛቸውን ይናገራሉ፡፡ ሆኖም ወጣቶቹ በዕድገት ቆይተው የመጨረሻ ትልቅ የሚባለው ብቃታቸው ላይ ሳይደርሱ እንደ ስተር ሊንግ የሚሰናበቱ ከሆነ እና ክለቡም ሊያቆያቸው አቅም ካጣ ስትራቴጂው ላይ ጥያቄ ይነሳል፡፡ ክለቡ የሌሎች ተቀናቃኞቹ መጋቢ እንዳይሆንም ያስፈራል፡፡

የሊቨርፑል ባለስልጣናት ስቴርሊንግ እንደማይሸጥ መናገራቸውን ቀጥለዋል፡፡ ሆኖም ተመሳሳይ ውዝግቦች እንዴት ፍፃሜ እንደሚያገኙ ከልምድ የሚያውቁት ደጋፊዎች ሁኔታው አላማራቸውም፡፡ ምናልባትም ሊቨርፑል በክረምቱ ስኬትማ የሚባል የዝውውር ግብይት ካልፈፀመ ስትርሊንግ ቀዩን ማሊያ ለማውለቅ የመጨረሻው ኮከብ አይሆንም፡፡

ይህ ጽሁፍ በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ የጁን ዕትም ላይ ታትሞ ወጥቷል::

The post Sport: የሊቨርፑል ፀሐይ ጠልቃ ይሆን? appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: ለአፍ ጠረን መንስኤ የሆኑ 16 ክስተቶችና ህመሞች -የዶክተሩ ትንታኔ

0
0

ይህ ጽሁፍ በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ የጁን ዕትም ላይ ታትሞ ወጥቷል::

የህክምና ባለሙያዎቹ ‹‹ሃሊቶሲስ›› ይሉታል፡፡ ቃሉ ‹‹ትንፋሽ›› የሚል ትርጉም ካለው ሃልተስ ከተባለው የላቲን ቃልና መጥፎ ሁኔታን ከሚያመለክተው ኦሲስ ከተባለው ባዕድ መድረሻ ነው፡፡ ብዙው የህብረተሰብ ክፍል መጥፎ የአፍ ጠረን በሚል ያውቀዋል፡፡ መጥፎ የአፍ ጠረን አለዎት? ሌሎች ሰዎች መጥፎ የአፍ ጠረን እንዳላቸው ለማወቅ አስቸጋሪ ባይሆንም የራስዎን ሁኔታ ማወቅ ግን ሊያዳግትዎ ይችላል፡፡ የአሜሪካ የጥርስ ህክምና ማህበር መጽሔት ከራሳችን መጥፎ የአፍ ጠረን ጋር እንደምንለማመድና ‹‹አፋቸው በጣም የሚሸት ሰዎች እንኳ ችግራቸውን ላያውቁት እንደሚችሉ›› ገልጿል፡፡ ስለዚህ አብዛኞቻችን መጥፎ የአፍ ጠረን ያለን መሆኑን የምናውቀው አንድ ሰው ስለሁኔታው ሲነግረን ነው፡፡ ምንኛ ያሳፍራል፡፡
bad breath
መጥፎ የአፍ ጠረን የብዙ ሰዎች ችግር መሆኑ ብቻ መጽናኛ የአፍ ጠረን አስነዋሪና ተቀባይነት የሌለው ነገር ተደርጎ ይታሰባል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከባድ የስሜት መቃወስ ሊያስከትል ይችላል፡፡ በእስራኤል የቴል አቪቭ ዩኒቨርሲቲ፣ የአፍ ማይክሮባዮሎጂ ላቦራቶሪ ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ሜል ሮዘንበርግ እንዲህ በማለት ገልፀዋል፡፡ ‹‹መጥፎ የአፍ ጠረን ግምታዊም ሆነ እውነተኛ ከህብረተሰቡ ለመገለል፣ ከትዳር ጓደኛ ለመፋታትና ራስን ለመግደል ምክንያት ሊሆን ይችላል›› ታዲያ ዛሬ ዛሬ በአዲስ አበባ በርካታ ፋርማሲዎችና ሱፐር ማርኬቶች፣ ‹‹መጥፎ የአፍ ጠረን መድሃኒት እንሸጣለን›› የሚል ማስታወቂያ ማንበብ አዲስ አይደለም፡፡ መድሃኒቶቹ ካለሐኪም ትዕዛዝ የሚሸጡ ከመሆኑ ጋር አይነትና አጠቃቀማቸው ሁሉ፣ ለራሳቸው ለሻጮቹና ሸማቾቹ ጭምር ደናገር ሲፈጥሩ ይታያል፡፡ ባለሙያዎቹ ግን ድርጊቱ ተራ የገበያ ሥራ ሲሉ ያጣጥሉታል፡፡ አንድ የጥርስና አፍ ህክምና ስፔሻሊስት ስለዚሁ ጉዳይ የሚሉት አላቸው፡፡

ጥያቄ፡- የአፍ ውስጥ ህክምና ሲባል ምን ማለት ነው?
ዶ/ር፡- ጥሩ፤ ብዙው የህብረተሰብ ክፍል የአፍ ውስጥ ህክምና ሲባል የጥርስ ሐኪም ወይም ዴንቲስት በሚል ነው የሚረዳው፡፡ ነገር ግን ዴንቲስት ከአፍ ውስጥ ህክምና አንዱ እንጂ ሁሉንም አይወክልም፡፡ ስለዚህ አፍ እና በአጠቃላይ ከአንገት በላይ ያለው የሰውነታችን ክፍል በተመለከተው ‹‹ከአንገት በላይ ህክምና›› የሚባለው አጠራር ትክክል ሳይሆን አይቀርም፡፡ በእንግሊዝኛውም ENT በሚባል አህጽሮተ ቃል ይታወቃል፡፡ E- ear N- nose T- throut የሚባለው መሆኑ ነው፡፡ ከዚህ በቀር ግን ኢፍታሞሎጂስት (ዓይን)ን እንዲሁም በህክምናው ዓለም ጠጣሩ የአዕምሮ /ኒውሮሎጂስት/ ሳይንስ፣ ራሳቸውን የቻሉ የአንገት በላይ ህክምና ክፍሎች መሆናቸውን መዘንጋት አይገባም፡፡ የእኛ ስፔሻሊቲ ግን አፍ ውስጥ እና የፊት አካባቢ አጥንቶች ናቸው፡፡

ጥያቄ፡- የአፍ ውስጥ በሽታ መንስኤን ቢነግሩን?
ዶ/ር፡- የአፍ ውስጥ በሽታ /ፓረንዶንታል ዲዚስ/ የምንለው ጥርስ አቃፊ አካባቢ ያለው ህመም ነው፡፡ የሰው ልጅ ከተወለደ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ጀምሮ ከ300 ባክቴሪያዎች በላይ ሰውነታችን ውስጥ ገብተዋል፡፡ እነዚህ ባክቴሪያዎች በተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን ከመሰራጨታቸው ጋር በአፍ ውስጥም ቦታ አላቸው፡፡ ስኳር ነክ የሆኑ ምግቦችን ስንመገብ ቶክሲክ የሆኑ ባክቴሪያዎች ወደ አሲድነት ይለውጡታል፡፡ ለጥርስ መቦርቦርም እነዚህ አሲዶች ዋና ድርሻ አላቸው፡፡ ስለዚህ ምግብ ተመግቦ ሳያፀዳ የተኛ ማንም ሰው በዚህ አሲድ ምክንያት ጥርሱ ሊቦረቦር ይችላል ማለት ነው፡፡
ሁለተኛውና ትልቁ ደግሞ ሌሊት ስንተኛ የምራቅ መጠናችን ስለሚያንስ ካልሲየምና ፎስፈረስ በየጥርስ ዙሪያችን ይከመራሉ፡፡ እነዚህም በተገቢው ሁኔታ ከቁርስ በኋላ ካልፀዱ የጥርስ በሽታን አምጪ ናቸው፡፡ ስለዚህ ማንም ሰው በ24 ሰዓት ውስጥ ሁለት ጊዜ ጥርሱን እንዲያፀዳ ይመከራል፡፡ በመሀሉ ምንም አይነት ምግብ ከተመገብን በኋላ አፋችንን በውሃ መጉመጥመጥ አለብን፡፡ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ጥርሱን ያላፀዳ ሰው በአራተኛው ቀን ማጽዳት ቢሞክር ቆሻሻው ስለሚለጠፍ ብሩሹም ሊያስወጣለት አይችልም፡፡ ስለዚህ ከግል እንክብካቤ ባሻገር በየስድስት ወሩ ደግሞ ሐኪም ዘንድ ቀርቦ ስኬሊንግ /ማጽዳት/ የአፍ ውስጥ ጤንነትን ማረጋገጥ ይችላል፡፡

ጥያቄ፡- የአፍ ውስጥ ህክምና ከጥርስ ህክምና ይለያል ማለት ነው?
ዶ/ር፡- አዎ! ይሄንንም በቅጡ መረዳት ይገባል፡፡ አንድ ካርዲዮሎጂስት ጋ የሚሄድ ታካሚ ልቤን ስላመመኝ መድሃኒት ጻፍልኝ፣ እኛ ጋ የሚመጠውም ጥርሴን ሙላልኝ ማለት የለበትም፡፡ ጥርስ መሙላት ማለት ህክምና ማለት አይደለምና፡፡ ለሁሉም በሽታዎች የየራሱ ሐኪም ስላለ ምን ያስፈልጋል አያስፈልግም ለሙያተኛው ቢተው ነው የሚሻለው፡፡

ጥያቄ፡- ለጥርስና ለአፍ ውስጥ በሽታዎች ምክንያት የሆኑትን ምግቦች ማወቅ እንችላለን?
ዶ/ር፡- አይ! ይሄ በአጠቃላይ ከህብረተሰባችን የአኗኗርና የአመጋገብ ዘዬ መለወጥ ጋር ተያይዞ መታየት ያለበት ነገር ነው፡፡ እንደሚታወቀው ሁሉ በአሁኑ ወቅት ብዙ የምግብ ግብአቶቻችን የገበያ ወይም የሱፐር ማርኬት ውጤቶች ናቸው፡፡ እነዚህ የምግብ ግብአቶች ደግሞ ቀጥታ ፕሮቲናቸው የወጣ በመሆኑ ለሰውነት ያላቸው ጠቀሜታም የዚያን ያህል አይደለም፡፡ ለምሳሌ ቀደም ባለው ዘመን እናቶች በቤት ውስጥ ጋግረው ሲያበሉን የቆየው ኦርጋኒክ ዳቦና አሁን በዳቦ ቤቶች ወይም ሱፐር ማርኬቶች ተዘጋጅተው የምንመገባቸው ዳቦዎ እኩል ጠቀሜታ አላቸው አይባልም፡፡ ሌሎቹንም የምግብ አይነቶች እንዲሁ ማየት ይቻላል፡፡ በጥቅሉ ፕሮሰስድ የሆኑ ምግቦች በቀላሉ ጥርስ ላይ የመጣበቅና የመጠራቀም ባህሪይ እንዳላቸው ነው፡፡ ስለዚህ ከላይ እንዳልኩት እነዚህን በወቅቱ ካላፀዳን ይለጠፉና ወደ ፓራንዶንታል ዲዚስ /ጥርስ ዙሪያ/ በሽታ ይሸጋገራል ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ይህን ስል በሽታውን ያመጣው ምግቡ ሳይሆን ምንም ተመገብን ምንም ጽዳት ካደረግን ምንም በሽታ አይኖርም ነው፡፡

ጥያቄ፡- በባህል ሁኔታ ጥርሳችን የምንፍቅባቸው እንጨቶችስ ምን ያህል ጠቀሜታ አላቸው?
ዶ/ር፡- እስካሁን የተናገርኩት ከምግብ በኋላ ጥርስን ማጽዳት ተገቢ መሆኑን ነው፡፡ በዚህ ረገድ ጥርሱን ምንም ከማያፀዳ ባህላዊ ጥርስ መፋቂያዎች የተሻሉ መሆናቸውን አውቃለሁ፡፡ እርግጥ የጥርስ መፋቂያ እንጨቶች ቆሻሻል በመቀነስ አስተዋፅኦ ያላቸው ቢሆንም፣ ጫን ተብለው በተያዙ ቁጥር ድድን በመክፈት ሌላ ችግር ማስከተላቸው አይቀርም፡፡

ጥያቄ፡- የጥርስ ብሩሽ ሳሙና አፍ ያሸታል የሚባለውስ?
ዶ/ር፡- ስህተት ነው፡፡ ብሩሽና ሳሙናውን ያዘጋጁት እኮ በሳይንስ የኖቤል ተሸላሚ የሆኑ ሳይንቲስቶች ናቸው፡፡ በብሩሹ ደረጃ ጠንካራ፣ ለስላሳና መካከለኛ የሆኑ አሉ፤ ይህም እንደ አመራረጡ ነው፡፡ ሳሙናውም በይዘት ያካተተው ፍሎራይድ የመሰለ ለጥርስ ተፈላጊ የሆነ ኤለመንትና ፀረ ባክቴሪያዎች አሉት፡፡

ጥያቄ፡- በአሁኑ ወቅት በብዙ የከተማችን ፋርማሲዎችና ሱፐር ማርኬቶች ‹‹የአፍ ጠረን መድሃኒት እንሸጣለን›› የሚል ማስታወቂያ ጽፈው እያየን ነው፡፡ እስቲ ስለ አፍ ጠረን መድሃኒት ትንሽ ቢያብራሩልን?

ዶ/ር፡- ‹‹የአፍ ጠረን መድሃኒት አስመጥተናል›› ማለት በሌላ አነጋገር የሞተ አይጥ ሽታ የሚያጠፋ መድሃኒት እንሸጣለን ማለት ነውኮ፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሰዎች የአፍ ሽታ ምክንያቱን አላውቁም፡፡ ባለማወቃቸውም ጉዳዩን ለገበያ ተጠቅመውበታል ማለት ነው፡፡ ባይሆን እንኳ ሐኪሙ የአፍ መጉመጥመጫና ሌሎች የሚያዛቸው አሉ፡፡ አሁን እያየን እንዳለነው አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍል ሐኪም ቀርቦ ከመታየት ይልቅ በገበያ ማስታወቂያዎች ተማልሎ በራሱ ላይ ተጨማሪ በሽታ በመሸመት ላይ ይመስላል፡፡ አንዳንድ ፋርማሲስቶችም ከሐኪም ትዕዛዝ ውጭ መሸጥ የሌለባቸውን መድሃኒቶች እንደሚሸጡ ይታወቃል፡፡ አንድ ጊዜ የታዘዘ መድሃኒትን ደጋግመው የሚገዙና የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥርም ቀላል የሚባሉ አይደሉም፡፡ እንደዚሁ ሁሉ የሀገር ውስጥና የውጭ መድሃኒቶች በሚል ተጨማሪ ዋጋ የሚጠይቁ እንዳሉ የማናውቅ አይደለንም፡፡ ለእኔ ግን ይህ ሁሉ ከባድ ስህተት ነው ባይ ነኝ፡፡

እንግዲህ በገበያ ላይ የሚገኙ የአፍ መጎመጥመጫዎች ሊጠቅሙ ቢችሉም መጥፎ የአፍ ጠረንን በመከላከል ረገድ ሙሉ በሙሉ ልትተማመንባቸው እንደማትችል በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ እንዲያውም ብዙውን ጊዜ አልኮል ባለባቸው መጉመጥመጫዎች መጠቀም የአፍ ድርቀት ሊያስከትል ይችላል፡፡ አንዳንድ በጣም ውጤታማ ናቸው የሚባሉ የአፍ መጉመጥመጫዎች በጥርስ ላይ የሚላከኩ ቆሻሻዎችን መቀነስ የሚችሉት 28 በመቶ ብቻ ነው፡፡

ስለዚህ የምትመርጠውን የአፍ መጉመጥመጪያ ከተጠቀምክ በኋላም ቢሆን በአፍህ ውስጥ ከነበሩት ባክቴሪያዎች ውስጥ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑቱ ላይጠፉ ይችላሉ፡፡ በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ ሙከራዎች መሰረት በአፍ መጉመጥመጪያ ተጠቅሞ ጥርስንም ካፀዱ ከ10 ደቂቃ እስከ አንድ ሰዓት ባሉት ጊዜያት ውስጥ መጥፎ የአፍ ጠረን እንደሚያገረሽ ነው፡፡

በግልጽ መረዳት እንደሚቻለው መጥፎ የአፍ ጠረንን በመከላከል ረገድ ግዴለሽ መሆን አያስፈልግም፡፡ ከዚህ ይልቅ አፍህንና ጥርስህን ዘወትር እንክብካቤ እንደሚያስፈልጋቸው ውድ መሳሪያዎች አድርገህ መያዝ ይኖርብሃል፡፡ ስለዚህ የሚገባቸውን እንክብካና ጥንቃቄ አድርግላቸው፡፡ እንደህ ካደረግህ መጥፎ የአፍ ጠረንንና በዚሁ ሳቢያ የሚመጣውን ጭንቀትና ሐፍረት ትቀንሳለህ፡፡ ከዚህም በላይ አፍህ ንፁህና ጤነኛ ይሆናል፡፡
ጥያቄ፡- አመሰግናለሁ፡፡
ዶ/ር፡- እኔም አመሰግናለሁ፡፡

The post Health: ለአፍ ጠረን መንስኤ የሆኑ 16 ክስተቶችና ህመሞች -የዶክተሩ ትንታኔ appeared first on Zehabesha Amharic.

እርዱን ፍረዱልን አንልም፤ በነፃነት ተጋድሎአችን አይግቡብን! –ከጸጋዬ ገብረመድህን አርአያ

0
0


Wendy-Sherman-Ethiopian-Election-628x329በመካከለኛዉ ምስራቅ ዝነኛ የሆነዉ ጋዜጠኛ ድንቅ የስነጹሁፍ ሰዉም ነዉ። በኮሎኔል ጋማል አብዱልናስር የቅርብ ሰዉነትነትና አማካሪነትም ይታወቃል። ሖስኒ ሙሃመድ ሃይከል እንደዳቦ የሚገመጡ መጻሕፍትን በመጻፉ፥ ከመካከለኛዉ ምስራቅ ባሻገር የእንግሊዝ አንባቢዎቹ የጹሁፎቹ እስረኞች ናቸዉ። አሁንም በጋርዲያን ጋዜጣና በስፔክቴተር መጽሄት የሚወጡ መጣጥፎቹ እንደጆን ላካሬ ልብወለድ መጻሕፍት የሚያማልሉ ናቸው። በእኛ በኩል ከዚህ ደራሲ-ጋዜጠኛ The Sphinx and the Commissar መጽሃፉ በቀልድም በቁም ነገርም የተጠቀሰ አንድ አጭር ‘ኤፒሶድ’ ለመዋስ እንወዳለን።

ሐይከል እንደጻፈው ከሰባቱ ቀን የአረቦችና የእስራኤል (1967) ጦርነት ማብቂያ አካባቢ የግብፁ መከላከያ ሚኒስትር ማርሻል ፋዉዚ ሰፋ ያለ የጦር መሳሪያ ሸመታ ሊስት ይዘዉ ወደ ሞስኮ ይሄዳሉ። በክሬምሊን የተቀበሉአቸው የሶቪየቱ የመከላከያ ሚኒስትር ማርሻል ግሬችኮ ነበሩ። በሰባቱ ቀን የሞስኮ ቆይታቸዉ ወቅት እስራኤል ስላወደመችባቸዉ ታንኮች፥ ኤፒሲዎች፥ አውሮፕላኖች – ስለማረከችባቸዉ ስፍር ቁጥር የሌለው የጦር መሳሪያዎች አንስተው እነዚያን እንዴት መተካት እንደሚቻል ሲነጋገሩ ሰንብተዋል።

በዉይይቱ ፍጻሜ ላይ ሁለቱ ማርሻሎች ብቻ ሳይሆኑ በሁለቱም ልዑካን ቡድኖች ዉስጥ አባላት የነበሩ የሁለቱም አገሮች ሹማምንት መለኪያ በማጋጨት “ናዝድራቬ ናዝድራቬ” ሲባባሉ ቆይተዉ የሶቪየቱ የመከላከያ ሚኒስትር የማሳረጊያ ንግግር ያደርጋሉ። የፖለቲካ ባህል ስለሆነ የሶቪየት ኅብረት ቀይ ሰራዊት የጀርመን ናዚዎችን እንዴት እንዳሸነፈ፤ አገሩን ብቻ ሳይሆን መላውን ምስራቅ አዉሮፓን ለድል እንዳበቃና ፒፕልስ ዲሞክራሲዎችን እንዴት እንዳቋቋሙ ደሰኮሩ። ከዚያም ማርሻሉ “አሁንም ከግብፅ ሰራዊት ጎን ተሰልፈን ጽዮናውያንን “እንደመስሳለን! እናሸንፋለን!” ብለው መለኪያ አጋጩ። መፈክር ቀረበ፤ ተፎከረ። (የልዑካን ቡድን አባላት ሆናችሁ ወደሞስኮ የሄዳችሁ ሁሉ የተከታተላችሁት ስነ-ስርዓት ሁሉ ተከናወነ። እንደምታዉቁት በስራ ሰአት በቢሮዎች የሚሾመው ቮድካ፥ ኮኛክ፥ ቪኖ ወዘተ ልክ የለዉም። ትንሽ የአካል ጥንካሬ ከሌለዎ የመጠጡ መጠን አለመኖር ሳይታሰብ ጉድ ያፈላል። ለማንኛዉም ፉከራዋም አለች።)

ትርዒቱ አላለቀም። የሶቪየቱ ማርሻል የግብጹን ማርሻል አውሮፕላን ማረፊያ ድረስ አጅበው በመሄድ በመጨረሻ ሞቅ ያለ ሰላምታ ተሰጣጡ። የግብፁ መከላከያ ሚኒስትር ለጊዜው መሳሪያ ጭነው ባይመለሱም፤ መስፈሪያ ሚዛን የሌለው ተስፋ ተሸክመው ሊሄዱ ነዉ። ያንን ተስፋ ከመሳፈራቸው በፊት እንደገና ለመስማት ፈለጉና፤ “ዛሬ ጠዋት የገቡልን ቃል ልቤን አሙቆታል” ይላሉ። በዚህ ጊዜ የሶቪየቱ አቻቸዉ “የቱ ነው ልብዎን ያሞቀው?” ሲሉአቸዉ ፋውዚ “ከእናንተ ጎን ተሰልፈን ፅዮናውያንን እንወጋለን፥ ያሉትን መጥቀሴ ነዉ” ይሏቸዋል። የሶቪየቱም ማርሻል እዚህ ላይ ሲደርሱ “ያንንኮ የጠቀስኩት ‘አንድ ለመንገድ’ ይሆንዎታል ብዬ ነዉ። “One for the Road አያዉቁም?” አሉአቸዉ ይባላል። ማሾፍ ወይም እንደፈረንጆቹ “bluff” ማድረጋቸዉ ኖሯል።

ባለፈው ወር ላይ የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (ስቴት ዲፓርትመንት) ረዳት ሚኒስትር ወደ አዲስ አበባ የሚወስድ ተልዕኮ ነበራቸውና ወደዚያው ዘልቀው ተመልሰዋል። ለምን ነበር የሄዱት? ተብሎ የሚጠየቅ አይመስለኝም። በዚያ አካባቢ ትልቅ የጦርነት ቋያ አለ። በአረቢያን ፔኒንሱላ ያለውን አልቃይዳ እንዲከላከል ተመድቦ የነበረዉ የየመኑ ፕሬዚዳንት አብደላ ሳለህ፥ በአረብ ስፕሪንግ ባይበላም በህይወት ወጥቶ የመለስ ዜናዊ እንግዳ ሆኖ ነበር። አሁንም በዚያው አካባቢ ብቅ ጥልቅ ይላል። የመንን በተለይ ሆዴይደንና ሳንዓን ከአሰብ ድንጋይ ወርውረህ አንድ ሰው ልታቆስል ትችላለህ። አሜሪካ ደግሞ የእኛ ቤተኛ ስለሆነች ጋሞ ጎፋ (አርባ ምንጭ) በርከት ያሉ ሰው አልባ አዉሮፕላኖች (drones) አሰማርታ እነዚያ እንደዳክዬ ጉብ ጉብ ብለው ተቀምጠዋል። ስድስት ሺህ የአሜሪካ ሰራዊት ጅቡቲ ላይ መሽጓል። ባራክ ኦባማ ደግሞ የተመረጡበት አንድ ዓቢይ ቃል ኪዳን (ፕላትፎርም) በአመራራቸዉ ዘመን አንድ አሜሪካዊ በየትም አገር የጦር ሜዳ ላለማስገባት ስለሆነ ምንደኞችን በበጎ ፈቃድም ይሁን በግዥ ለማሰማራት አዘጋጅታ ያስቀመጠች የሃይለማርያም አስተዳደር አለች። እግረ-መንገዳቸዉን ወሃቢስቶችም ኤርትራን እንዲያግባቡ በዚያዉም (በነካ እጃቸው) ኢሳያስን ከርቀት ሆነው ከሚሳደቡበት አቅጣጫ እንዲመልሱ ልዩ ተልእኮ ተቀብለው ኤርትራዊውን መሪም በሪያድ አነጋግረዋል። ስንቅና ትጥቅ በማቀበል ረገድ (የመንን በኢራኖች ከሚደገፈዉ ደብረ በጥብጥ ኢስላማዊ ሃይል ለመታደግ) ዘመቻ ማስተባበር ያስፈልጋል። ምን ያስፈልጋችኋል? ምን ይሟላላችሁ? የሚል መልእክት ከማስተላለፍ ባሻገር ዌንዲ ሸርዉድ ጥቃቅን የመሰላቸዉን ራሳቸዉ ለመፈጸም ቃል ይገባሉ። ለነገሩ አዲስ አበባ ላይ ብሄራዊ ባንኩ የዉጭ ምንዛሪ የለኝም ማለት ከያዘ ሰንብቷል። አሜሪካ በዓመት የሚሰፍርልን ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ የት እንደደረሰ እንግሊዝ ብቻ ለበጀት ማስተካከያ፥ ለዕዳ መክፈያና ለመሳሰሉት የምትሰጠዉ ሶስት መቶ ዘጠና ሶስት ሚሊዮን ፓዉንድ የአዲስ አበባን መንገድ አለማየቱን ሴትዮዋ እያወቁ አያውቁም። የአዉሮፓ ኅብረት አባል አገሮች በአጠቃላይ ለዚያ “ቀበኛ” እያሉ ለሚያሙት መንግስት ከቢሊዮን ዶላርስ በላይ ያፈሳሉ። እዉነትም ቀበኛ? “አየሁን” አያውቅም። ገንዘቡ የሚገባበት የበርሙዳ ትሪያንግል አለ። ለዌንዲ ያ ሁሉ ኢምንት ነዉ። ወያኔ ስለሚያስራቸዉ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ሰዎች – በአደባባይ ስለሚረሸኑ ኢትዮጵያዉያን ደንታ የላቸዉም። ያልተነሳም። አይነሳም። ጠባቸው ከአለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ተከታታይ ሃይላት ጋር ነው። የዌንዲ ደንበኞች አይን ለአይን መተያየት የማይችሉ፥ ለምስክርነት የማይበቁና ከህሊናቸዉም ጋር የተሰነባበቱ ናቸው። ሴቲቱ ግራ የገባቸውና የሚያሳዝኑ ናቸው። ሀይለማሪያምና ጭፍሮቹ በምንም አይነት ሊደገፉ አይችሉም። ለአሜሪካኖቹ ደግሞ ስለነሱ የሚሰጡት ድጋፍ ሁሉ የሚያስገምታቸውና የሚያሸማቅቃቸው ነው። ወራዳና ባለጌ ባቆለጳጰስኸው ቁጥር ውርደቱ ሁሉ ወዳንተ ትከሻ ይዛወራል። ዌንዲ የዚህ ሰለባ ናቸው።

 

መጽሃፋችን “የሚያበራየዉን ወይፈን አፍ ማሰር አይገባህም” ይላል። የመንግስታችን እምነትም ይኸዉ ነዉ። የዉጭ ምንዛሬ በዉጭ፥ ለዉጭ ይቀመጣል። በአገር ከአገር የሚገኘዉ ገንዘብ ክርስቶስ እንዳለዉ የ “ቄሳር” ነዉ። ያም ሆነ ይህ የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ይህን ለመተሳሰብ ስልጣንም ዉክልናም የላቸዉም። ቢሆንም የመንግስታችንን ቀማኛነት፥ ፍርደ-ገምድልነትና፥ ተራ ሽፍትነት ­– ወደር የሌለው ወንጀለኝነት አያውቁትም አንልም። እኛ እንኳ ማስረጃ ስንጠይቅ ዋቢያችን የዌንዲ መስሪያ ቤት ሪፖርት ነዉ። በአጭሩ በኦባማ ፍልስፍና መመሪያ መሰረት ­– በተለይ ኦባማ “America should lead the world” የሚል አቋም በሰፊው እያራመዱ እንደ መሆናቸው አለምን የሚመሩበት አንደኛው አቋም የአሜሪካንን ጦርነት ደሀ ልጆቻችን በጦርነት መሰውያዉ እሳት ላይ ማንደድ ብቻ ሊሆን ነዉ::

 

በወያኔ በኩል አሁንም በመስዋዕትነት የሚቀርብ አለ። ስራዊቱ የእሳት ራትና የመድፍ ቀለብ እየሆነ ይዋጋላቸዋል። አሁንም ይዋጋል። ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ የወያኔ ባለስልጣኖች ለሴቲቱ ያቀረቧቸዉ ጥያቄዎች ምን እንደነበሩ መገመት ይቻላል። ጠንቋይ በመቀለብ ወይም በጸሎት የሚገኝ አይመስለኝም። ወያኔ ለአሜሪካም ሆነ ለሌላ ሀይል የኢትዮጵያ ልጆች የሆኑትን የሰራዊቱን አባላት በምንደኝነት ለማከራየት ዝግጁ ናቸው። በእውነቱ በእነ ሐይለማሪያም ደሰለኝ በኩል ሳይቀፍፋቸው፥ ለአፍታ እንኳን መንፈሳቸውን ሳይረብሸው ከቶውንም ጮቤ እየረገጡ የሚፈጽሙበት ይህን መሳይ ወራዳ ሰራ ነው። አሜሪካኖች በፈንታቸው ሊያስነኩ የማይፈልጉት እንዲህ ያሉ ወገኖቻቸውን የሚሸጡ ብቻ ሳይሆን የራሳቸውንም ሕሊና፥ መንፍስና፥ ነፍስ ለመሸጥ የተዘጋጁ ሰዎችን ነው ። እንዲህ ያሉ መሪዎች ከየትም አናገኝም ቢሉ አይደንቀንም። የአሜሪካ ድጋፍ ምክንያት ይህ ነው ።

 

የእኛዉ መሪዎች ከጦር መሳሪያ ሸመታዉ ዝርዝር፥ በመካከለኛዉ ምስራቅ በተለይም በሶማሊያና በየመን ባህረ ሰላጤ ከአሜሪካ ጋር ለመቆም ከሚያሳዩት ስምምነት ባሻገር ለመሄድ ዝግጁ ናቸው። ዌንዲ እንደሚሰማቸዉ ዛሬ አሜሪካ ከኢትዮጵያ የምትፈልገዉን ሁሉ ለማቅረብ የሚችለው ወያኔ ብቻ ነው። ያ መንግስት ለኢትዮጵያ ህዝብና ለኢትዮጵያ ያልቆመ በጥቃቅን ጥቅም ሊታለል የሚችልና “ብሄራዊ ክብር” የሚባል እምነት የሌለዉ መሆኑን ያውቃሉ። በገበያ የሚፈለገው አይነት መንግስት ተገኝቷል ማለት ነው። እንዲያም ሆኖ በጊዜ ማህፀን ዉስጥ ያለ መንግስት መፈለጋቸው እዉነት ነዉ። ጨረታው ከወጣ ደግሞ ቆይቷል። የተቃዋሚ ሃይሎችን ባነጋገሩ ቁጥር “ግልፅ አማራጭነታችሁን አረጋግጡ” እንዳሉ ነዉ። በዚህ አንጻር እነሱ ከአሜሪካ የሚያገኙት ጥቅም ሁሉ ተደማምሮ የእነ ብርሃኑ ነጋ ግንቦት ሰባት የማታ ማታ ምን ሊያደርስባቸዉ እንደሚችል አይዘነጉትም። የህልዉና ጥያቄ ነው ለወይዘሮይቱ ያነሱት። አዎን በየቦታዉ ሰራዊቱን እየላኩ የመድፍ ቀለብ፥ የእሳት ራት እያደረጉት ነዉ። ለኢትዮጵያ ጦርነትና ጥቅም ሳይሆን ለትልቁ ወንድም (ቢግ ብራዘር) የመስዋዕትነት ጠቦት እየሆንን ነዉ። በነገራችን ላይ ከዚህ ቀደም ለበርካታ አመታት (ከ1945 ወዲህ) የአሜሪካ መሪዎች “ይህ የአሜሪካ ዘመን ነዉ። አሜሪካ ዓለምን መምራት አለባት የሚለዉ የፖለቲካ ፈሊጥ በኦባማ የግዛት ዘመንም የበለጠ እየተራገበ መሆኑ ይደንቀናል። በ21ኛ ምዕተ አመት ሌሎች የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች አሜሪካን ወታደሮችን በጦር ሜዳ እያሰማሩ ሲሆን ኦባማ ግን ለአሜሪካ የዓለም ገዥነት የሌሎችን ሕዝቦች ነፍስና ደም የሚፈልጉ መስለዋል። “አሜሪካ አለምን መምራት አለባት” “America should lead the world” ያለይሉኝታ የሚነገር፥ አለም በሙሉ ለአሜሪካ መገበር እንዳለበት በእብሪት የሚገለጥ መፈክር ሆኗል። ከቀዝቃዛዉ ጦርነት ወዲህ አሜሪካ ብቸኛዋ ልዕለ-ሃያል በመሆንዋ ዓለም በሙሉ በእስዋ ፈቃድና ትዕዛዝ መሰረት መገዛት አለበት የሚል እብሪት የተሞላዉ አቋም ተፈጥሯል። አዎን! ነፍሰ ገዳዮችና የአራዊት ልብ የገባላቸው አምባገነኖችን አሜሪካ እያደነች በሕዝቦች ላይ በመጫን አለምን የመግዛትዋን አቋም ማንም ህሊና ያለው የአለም ዜጋ አይቀበለውም። በ21ኛው ክፍለዘመን አዲሱን የባርነትና የተራቀቀ ኒዮኮሎኒያሊዝም ለመቀበል ያዳግታል።

 

ወደ ሚስ ሸርዉድ እንመለስ

 

ሴቲቱ ከወያኔ መንግስት ባለሟሎች ጋር በሰፊዉ ሲወያዩ በአጀንዳዉ ውስጥ የወያኔ ጠላቶች ጉዳይ እንደሚያዝ ሳይታለም የተፈታ ነዉ። ስለሆነም ግንቦቶችና በዚያ የገለማ ስርዓት ላይ የተነሱ ሃይሎች ሁሉ ስለነሱ የተባለና የሚባል ጉዳይ መኖሩን መገመት አለባቸው። እንዲያዉም ማንም የአሜሪካና የአዉሮፓ መንግስት ባለስልጣን ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝና የወያኔ ሹማምንት ወደ እነዚህ አገሮች ሲሄዱ ከልመናና ከግዥ ሰነዳቸዉ ሊስት ዉስጥ ይህ ጥያቄ ዋነኛዉ መሆኑን መገመት አለ።

 

የዚህ መጣጥፍ መክፈቻ ካደረግነዉ የአልአህራም ጋዜጣ አዘጋጅ “አንድ ለመንገድ” አንጻር የሚስ ሸርዉድን መግለጫ መውሰድ እያመች ይሆናል። ይሁንና ሴቲቱ ለወያኔ አመራር ከሰጡት ተልዕኮና ሃላፊነት አንጻር የተወሰኑ የወያኔን ጠላቶች ማስፈራራት ትንሹ ውለታ ነበር። ወይም እስከ እናካቴዉ ግሬችኮ ለፋዉዚ የሰጡት የሽንገላ ቋንቋ ይሆናል። ፈረንጅ “የማሾፍ ፖለቲካ” ወይም bluff የሚለዉ ነዉ። ይህንን የፈረንጆች “የማሾፍ ፖለቲካ” ከራሳችን ታሪክ እንደሚከተለው እናቀርባለን።

 

የቪክቶር ኢማኑኤልና የቤኒቶ ሙሶሊኒ ኢጣልያ የመንግስታትን ማህበር ቃል ኪዳን ጥሳ ኢትዮጵያን ስትወረር በደፈጣ ፖለቲካ ውስጥ ገብተዉ የፋሽስቶች ረዳት ለመሆን ከአለም አቀፍ ሴራው ዋነኛ ተዋንያን መካከል የእንግሊዙ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰር ሳሙኤል ሖርና የፈረንሳዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ፒየር ሳቫል ነበሩ። እነዚህ ሁለት ዲፕሎማቶች የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ዋና ጸሃፊና የአንዳንድ ሌሎች መንግስታት ወኪሎች አምታተው ሴራቸውን ተያይዘውታል። በዚሁ መሰረት ፈረንሳይና እንግሊዝ የሙሶሊኒ ሰራዊትና የጦር መሳሪያ በስዊዝ ካናል በኩል ወደሞቃዲሾና ምጽዋ እንደተሸኘ ያውቃሉ። የሙሶሊኒ ሰራዊትና የጦር መሳሪያ፥ የአየር ቦምቦችና የነርቭ ጋዝ በስዊዝ ካናል ፀሃይ እየሞቀዉና 140 የእንግሊዝና የፈረንሳይ መርከቦች እያዩአቸዉ ኢትዮጵያዉያንን ለመጨረስ ተጭኖ አልቋል። በዚህ መካከል ቀና አመለካከትና ሰብዕና የነበራቸዉ በሊጉ የእንግሊዝ ቋሚ መልእክተኛ የነበሩት አንቶኒ ኢደን በሴራዉ በመብሸቅ አንጀታቸዉ ቆስሎ አልሰሩ አላስበላ አላስጠጣ ብሏቸዋል። በመካከሉ ሁሉ ነገር ለኢጣልያ ከተመቻቸና በሽሬና በአምባአላጌ እንዲሁም የጦር ሚኒስትሩ ራስ ሙሉጌታ በነበሩበት ግንባር (50ሺ ጦር) ሩቡ ያህል በቦምብና በጋዝ ሲያልቅ ላቫልና ሖር የፖለቲካ ትርኢት ማሳየት ይጀምራሉ። በዚህም መሰረት ሰር ሳሙኤል ሖር ወደ ጄኔቫ በመሄድ ወደሊጉ ስብሰባ ገብቶ “የሊጉ ቃል ኪዳን ይከበራል! አይታጠፍም! ሊጉ ለቆመለት ቁም ነገርና አላማ አገሮች ማናቸዉንም መስዋዕትነት ይከፍላሉ። እንግሊዝ ወረራውን በቀላሉ አትመለከተዉም” በማለት ጉባዔውን አንጫጫው። አዳራሹ በጭብጨባ ተቃጠለ። በዚሁ ልክ ፒየር ላቫልም ከሊጉ አዳራሽ ውጭ ሆኖ “ፈረንሳይም ከሊጉ ጋር ትቆማለች” እያለ ሲጮህ ዋለ። (በነገራችን ላይ የታሪክ ፍርድ ሲገመገም ሳቫል ማታ ላይ ፓሪስ ውስጥ የተለመደ እንቅልፉን ማለዳ ሲጨርስ ፈረንሳይ የሂትለር ግዛት ሆናለች።)

 

ሁለቱም የፖለቲካ አሻጥረኞች በጄኔቫ እንዲያ ሲናገሩ ብዙ የመንግስታት ወኪሎች ተቀብለዋቸዉ ነበር። ታዲያ ሳሙኤል ሖር በሊጉ ጉባዔ ላይ ያደረገዉን “ታሪካዊ ንግግር” በተመለከተ በትዝታ መጽሃፉ ውስጥ ማሾፌ ነበር፥ “It was all a bluff” ብሎታል። ራሱ ቤኒቶ ሙሶሊኒ ሳሙኤል ሖር ያንን ንግግር ካደረገ በኋላ በማግስቱ በእንግሊዙ Morning Star ላይ ባወጣዉ ጽሁፍ “ሰራዊታችን ያለ ችግር ምስራቅ አፍሪካ ገብቷል! ጉዳዩ የሁለት ቢሊዮን ሊሬ ጥያቄ ነበር። ያንን ሁሉ በሰማይ ከዋክብት የሚለካ ገንዘብ ያወጣነዉ ለለበጣ መሰላችሁ?” ብሎአል። በዚሁ አይነት እኒህም የአሜሪካ ዲፕሎማት የተናገሩትን ያናገራቸው የከዋክብት ግምት ያለው ጣጣ ካልሆነ እንዲሁ የፖለቲካ bluff ነው ትላላችሁ? የአዉአሎም ልጆች አካሄድኮ አይታወቅም። በመልካም ልግስና ብዙ ስራ ለመስራት እንደሚፈልጉ አንዳንድ ጊዜም በእህቶቻችንና በሚስቶቻቸዉ አማካኝነት ወፍራም አስበ ደነስ (ግዕዙን ቀሲስ አስተርይ ካልተቃወሙት) እንደሚያፍሱ ይታወቃል። ተክነዉበታልም። እንዲያም ሆኖ እንደ ሳሙኤል ሖር It was a bulff ወይም እንደ ማርሻል ግሬችኮ It was one for the road የሚሉበትም አጋጣሚ አይጠፋም። ኣድሮ ማየት ነዉ። ታዲያ ብዙዎቻችን ሚስ ዌንዲን የወቀስናቸዉንና የተቸናቸዉ፥ “እንዴት ለወያኔ እንዲህ ያለ ምስክርነት ይሰጣሉ?” በማለት ነዉ። ከፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ መግለጫዎች አንዲቱን ይዤላቸዋለሁ። አሜሪካኖች ለመስማት ሲፈልጉ ይሰማሉ፤ ለማየት ሲፈልጉ ያያሉ። ለማየት ሲፈልጉ በሳር ክምችት ዉስጥ ያለች መርፌ ያያሉ። ካልፈለጉ ደግሞ በእልፍኝ ዉስጥ የሚጎማለል ዝሆን አይታያቸዉም ብለዋል። ዌንዲ አስመሳይና የዉሸት ተለማማጅ እንጂ በደደብነት የሚታሙ አይመስለኝም። (በነገራችን ላይ ሴትዮዋ ተገፍተው ወጥተዋል። ዕድል ሌላ ጊዜ ይህን የመሰለ ስራ የምትሰጣቸው አይመስልም። የምዕራቡ የፖለቲካ አምላክ የጻፈላቸው የፈረደባቸው እንዲሁ ዘወር ማለትን ብቻ ነው።

 

እነዚህ ልምድ ያላቸዉ ምዕራባውያን ለምሳሌ አሜሪካ ከአንድ መንግስት ጋር የጠበቀ ግንኙነት አለው ተብሎ በሚገመትበት ሰአት ላይ እንኳ ዉስጥ ለዉስጥ ሌላ ስዉርና በተጠባባቂነት የተቀመጠ ሃይል እስከማደራጀት ይይዛሉ። በአለም ዙሪያ በዚህ መልክ ሲያካሄዱ የኖሩትን ለአብነት ማቅረብ ይቻላል። ለቦታና ለጊዜ፥ እንዲሁም ጹሑፍ ላለማንዛዛት ከኢትዮጵያ ሁኔታ አንድ ማስረጃ እናቀርባለን።

 

በ1950ዎቹ (እስከ 1958 ይመስለኛል) በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ኮሪ ትዝ ይሉኛል። ጆን ኬኔዲ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በሆኑበት ስዓት ከመረጧቸዉ ወጣት የሐርቫርድ ምሩቃን መካከል አምባሳደር ኮሪ አንዱ ናቸዉ። ከንጉሠ ነገስቱ እልፍኝ ከአዳራሽ፥ የዙፋን ችሎትና እንዲያ ባሉ ስፍራዎች የሚሽከረክሩ ናቸዉ። ይህ ብቻም ሳይሆን በመኖሪያ ቤታቸዉ በየጊዜዉ ድግስ ያደርጋሉ። ለምሳሌ በወር አንድ ቀን የጋዜጦች አዘጋጆች ይጋብዛሉ። እሳት ግር ብሎ ይነድዳል። የፈለገ ጥሬ ስጋ ያወራርዳል። አለዚያ ቄንጠኛ ጥብስ በኮኛክ ይጠበሳል። ፍሌመኞን ነዉ የሚባለዉ? ቲቦን ወዘተ ይቀርባል። ማወራረጃዋ ኮኛክ በእድሜዋ ትመጣለች። ኦን ዘ ራክስ ተለምዷል። በአጭሩ የአምባሳደር ኮሪ ግብዣ የምትናፈቅ ናት። የፕሬዚዳንት ሩዝቬልት የኋይት ሃዉስ “ባህል” እየተባለ በሚጠቀሰዉ ስልት ከመኖሪያ ቤታቸዉ ጎምቱ ጎምቱ የሆኑ ሰዎችን እየጠሩ፥ እያበሉና እያጠጡ ለነገና ለተነገ ወዲያ ስራ የሚጠቅማቸዉን ጉዳይ መተኮሻ ኣድርገዉታል።

 

አንድ ቀን (1959?) ለጦር አዛዦች የሚሰጥ ግብዣ ነበር። ጄኔራል መኮንኖች በተለይ የሃይል አዛዦች በብዛት እንደነበሩ አይጠረጠርም። ለእነዚህ ደግሞ ወደ አሜሪካ የሚወስድ ስያሜዉ “ሊደርሺፕ ቱር” በተሰኘ ፕሮግራም እየመጣ ሁሉም የአሜሪካ ልጅነት እስኪሰማው ድረስ የሚቀብጥበት አጋጣሚ ነበር። ከዝርዝሩ እንመለስና በአንዱ የግብዣ ወቅት ሁሉም ከንጥረ-ነገሩ ገፋ አድርጎ ሲወስድ አምባሳደሩ ከዋናዉ ጄኔራል ጋር ድምጻቸዉን ቀንሰው ማዉራት ይጀምራሉ። “ሆድ ያባዉን ብቅል ያወጣዋል” የሚባለዉ አነጋገር በፈረንጅም አለ “In wine comes the truth” ። ታዲያ አምባሳደሩ ሌተና ጀኔራሉን ከልብ ማጫወት ይዘዋል። “ጄኔራል ዛሬ እኮ በሁሉም የአፍሪካ አገሮች ወታደራዊ መፈንቀለ-መንግስት እየተካሄደ ነው። ይህ የወታደር መንግስት መቋቋም ጉዳይ ማቆሚያ አጥቷል። ለዚህም መንግስት ሳያሰጋ አይቀርም። ያስቡበት። ያንን የመሰለ ሁኔታ እንዳይፈጠር እርስዎን ልንረዳዎት እንችላለን” በማለት አንድ ትልቅ ኳስ ከሜዳቸዉ ዉስጥ ይጥሉላቸዋል። ጄኔራሉ ግን ነጋ አልነጋ ብለዉ ወደ ንጉሰ-ነገስቱ ዘንድ ሄደዉ “አሜሪካኖች” ምንኛ የማይታመኑና ወዳጃቸዉ የሆነዉን ይህን መንግስትም እንደምንም ለመለወጥ እንደሚሹ ይገልጡላቸዋል። የፖለቲካው የጊዜ ጨዋታ አጤ ዮሃንስ ወይም አጤ ሃይለስላሴ “ለአሜሪካ ታማኝ አይደሉም” የሚል አይደለም። ዋናው ጉዳይ የሃይለስላሴ መንግስት መገልበጡ የማይቀርና ባይሆን የሚመጣዉን መንግስት አዋላጆች አሜሪካኖች ራሳቸው ይሆኑ ዘንድ የሚቀይስ ፖለቲካ ነዉ። (በነገራችን ላይ አምባሳደር ኮሪን ጃንሆይ ሲያስጠሯቸው ሰዉየዉ ጉዳዩን በመጠርጠር ወደላንጋኖ ሄደዋል አሰኙ፤ ጃንሆይ ደግሞ ለፕሬዚዳንት ጆንሰን ስልክ ደዉለዉ ዲፕሎማቱ ሳይዉል ሳያድር “እንዲጠራ” ተደረገ። ምን ሆነ መሰላችሁ? አምባሳደር ኮሪ ለጥቂት ጊዜ ዋሽንግተን አካባቢ ሲሽከረክሩ ቆይተዉ ሳልቫዶር አየንዴ በቺሌ ሶሻሊስት መንግስት እንዳቋቋሙ ያንን ለመገልበጥ ሁሉንም ሴራ ጎንጉነዉ በመጨረሻ ላይ ያለዉን ምዕራፍ ለናትናኤል ዴቪስ አስረክበዉ ወደዋሽንግተን ተመለሱ። ናትናኤል ዴቪስ ከጄኔራል ፒኖቼ ጋር ሁሉን ነገር ጨርሰዉ ከቅልበሳዉና እልቂቱ አንድ ቀን በፊት ወደ ዋሽንግተን ተመለሱ። ከዚያ አንድ ወር ሳይሞላቸዉ በአዲስ አበባ የአሜሪካ አምባሳደር እንዲሆኑ “አግሪማ” (ስምምነት) ተጠየቀ። በነካ እጃቸዉ አብዮት ይቀለብሱ ዘንድ ነዉ። ይህ እንቅስቃሴ ረጃጅም ጽሁፎች የሚቀርቡበት ሲሆን ምናልባትም ሊሰመርበት የሚገባዉ አንድ ሃቅ አምባሳደር ኮሪ እንዳሉትና እንደፈሩት ሁሉ “የማይታወቁና እንዲያዉም በየጦሩ ካምፕ የተናቁ” ወታደሮች ያንን የሶስት ሺህ ዘመን ታሪክ ገረሰሱት። ስዩም ሐረጎት “Serving Emperor Haile Selassie” በሚለዉ መጽሃፉ እንደገለጠዉ ደግሞ “የክብረ-ነገሥት ፍጻሜ” ሆነ።

 

ሚስ ሸርዉድ ግንቦት 7ን ሽብርተኛ አድርገዉ ሲያቀርቡ ከልባቸዉ ላይሆን ይችላል። የምለዉ ይህ እንቅስቃሴ ኣድጎና ተጠናክሮ ይህን ዛሬ የሚረዱትን መንግስት ጨምድዶ ወደታሪክ መጣያ ቅርጫት ሲወረውረው ለማየት ቢችሉ ደስ ይላቸዋል ባይ ነኝ። ከዚያም በፊት ጥንካሬውንና “ግልፅ አማራጭነቱን” በማየት “እሹሩሩ” ቢሉት አይድነቃችሁ። ብቻ ሴቲቱ የእኛ ሰዉ እንደናቃቸዉና እንዳዘነባቸዉ ሁሉ የኦባማም አስተዳደር የፈቀዳቸዉ አልመሰለኝም። በቃሽ ተብለዋል። የታላላቅ መንግስታት ፖለቲካ በመሰረቱ ይህን ይመስላል። ረቂቅ ፖለቲካና ጠለቅ ያለ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ከነዚህ መንግስታት ስትጠብቁ ሳታስቡ አንሰዉ ስታገኟቸዉ አለመደነቅ ነዉ። የሚስ ሸርዉድ መስሪያ ቤት ቢያንስ ባለፉት አስር አመታት ሰለወያኔዎች ፖለቲካ አሳፋሪነት፥ ስለሰብአዊ መብት ሬከርዳቸዉ አስቀያሚነትና ስለ ኢኮኖሚ ያላቸዉ ዝቅተኛ የሞራል ደረጃ የራሳቸዉ መንግስት ያወጣውን ተደጋጋሚ መግለጫ አያዉቁትም፤ አልሰሙትም ብሎ ማሰብ አያመችም። ምናልባትም በዝግጅቱ በስተጀርባም ሊኖሩ ይችላሉ። እኔ የሎርድ Parlmerston “ነፍስ አይማረዉ” የምልበት ጊዜ ሞልቷል። በ 1848 የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረዉ ይህን ግለሰብ ንግስት ቪክቶሪያ “ለመሆኑ በዛሬዉ ዕለት የእንግሊዝ ወዳጆችና ጠላቶች እነማን ናቸዉ?” ብለዉ ይጠይቃሉ። ያን ጊዜ ነዉ “እንግሊዝ የዘለቄታ ጠላትም ሆነ የዘለቄታ ወዳጅ የላትም።  የዘለቄታ ጥቅም እንጂ” በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት።

 

ስለዚህ በፖለቲካቸዉ ውስጥ ጥቅም እንጂ ሞራሊቲ የሚባል ቅመም የለም። ሰብአዊነት ብርቅ እሴት ነዉ። ይልቁንም ለጥቅማቸዉ መከበር ሚሊዮንና ትሪሊዮን የሆነ ነፍስ ቢጠፋ ቁብ አይሰጣቸውም። የሕዝብ የሕሊና ቁስል አይሰማቸውም። የሚዘረፍ የለም እንጂ ከዚች ደሃ የኢኮኖሚ ቋታችን ኣድፋፍተዉ ቢወስዱብን የሚሰማቸዉ እንዳች የህሊና ወቀሳ የለም። ለነገሩ ታላላቆቹ መንግስታት በፖለቲካ ቀመራቸው ዉስጥ ህሊና የለም። የህሊና ወቀሳ “ላም ባልዋለበት” ነዉ። ሚስ ሸርዉድ እንደሌሎቹ የአሜሪካ ፖለቲከኞች ሁለት ነፍስ ናቸዉ። በአደባባይ ወያኔ የሚወደዉን በመናገር ሊሸዉዱት ይወዳሉ (ይፈልጋሉ) ። በግል የተወሰኑ ሰዎች ህሊናቸዉን የሚወቅስ ጉዳይ ሲያቀርቡላቸዉ “ወንጀላቸዉን ሁሉ ከእናንተ የበለጠ አዉቃለሁ” የሚሉ ናቸዉ። አንድ ሰዉ አንድ ጭንቅላት ሁለት ምላስ! ይህን መሳይ የፖለቲካ ዘማዊነት ከታላላቆቹ መንግስታት ደጋግማችሁ ትሰማላችሁ። ማፈሪያ! እንዲህ ሲያደርጉ መንግስታቸዉን እንደሚጎዱ ለማወቅ አይፈልጉም። ወያኔዎችን “እሹሩሩ” ካላሉና bluff ካላደረጉ ወደብጫዉ መንግስትና ብጫዉ ጎዳና (ቻይና) ይሄዳሉ ብለዉ ተራ ፍርሃት ይመጣባቸዋል። የፖለቲካው ዘማዊ ባህርይም ይህ ከንቱ ስጋት ነው።

 

አዎን ትላልቆቹ አገሮች – ድሮ የምናዉቃት ሶቪየት ኅብረትና አሁንም ጣዕሟን የበለጠ እየተረዳን የመጣነዉ አሜሪካም ወሮበላ መሪዎችንና አምባገነኖችን ይወድዳሉ። ያስጠጓቸዋል። እነዚህ ግለሰቦች የሞራል ትልቅነትና የነፍስ ‘ንፅሕና’ ስለሌላቸው ለባርነትና ለአገልጋይነት የተመቹ ናቸው። ዝግጁ ናቸው። የሚዋረድ ኩራት የላቸውም። እንደምታዩት እነ ስብሐት ነጋ ከእንስሳዊ ሰብዕናቸው የት ይወርዳሉ? አንዳንድ ደማካ ነፍስ የሆኑትንም በአምባገነንነት ይቀርጿቸዋል። የእነሱን ተልዕኮ እስከፈጸሙ ድረስ ማናቸዉም ድጋፍ ይሰጧቸዋል። ህዝባዊ ወንጀሎቻቸውን የሚያዩ አይኖች የሏቸዉም። የአሜሪካ ቅምጥሎች የነበሩ እነ ሞቡቱ ሴሴ ሴኮን፥ እነ ሳሞዛን፥ እነ ባቲስታን፥ እነ ሻህ ኤንድሻህ ፓሕላቪን ይጠቅሷል።

 

ከዚህ እኩል አምባገነን በመፍጠር ሂደት የአሜሪካኖችን ሚናም እንዲሁ ማንሳት ይቻላል። ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት በኋላ ከሚደነቁት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው መካከል ዲን አክሰን (Dean Acheson) ይገኛሉ። እንደሚታወሰው በ1952 የግብፅ ወጣት መኮንኖች ቡድን ፋሩቅን ከስልጣን አባርሮ የብዙሃን ፓርቲ አመራርን ለማስፈን ይንደፋደፍ በነበረበት ሰዓት ከዲን አኬሰን በኩል የቀረበዉ አሳብ እኔ መልቲ-ፓርቲ በምትሉት ዉዥንብር ዉስጥ ስዳክር አልገኝም። ከሺ ሰዎች ጋር መደራደር አልፈልግም። ይልቁን ከመሃላቸዉ ጉልበት ያለዉ አንድ ሰዉ ይውጣና ልንረዳዉም ልንንከባከበዉም እንችላለን” ብሏል። የዲን አኬሰንን የትዝታ መጽሃፍና በቅርቡ ስለግብጽ ሬቮሉስዮን የተጻፈዉን Soldiers, Spies and Statesmen ይመለከቷል። ናስርን በአምባገነንነት የመፍጠሩን ሃላፊነት የወሰዱት ዲን አኬሰን ነበሩ ማለት ይቻላል።

 

ራቅ ባለ ዘመን (ምንአልባትም 47 አመት) ያነበብሁት “The Boss” የተባለዉ መጽሃፍም የአሜሪካ የስለላ ድርጅት (በመንግስት ውስጥ ያለው መንግስት) እና ዲን አኬሰን እንደሚነግሩን ለአሜሪካ ጥቅም ተቀዳሚነት የሚተማመኑበት አምባገነን እስከመፍጠርና እሱንም እስከመንከባከብ የደረሰ (የሚያደርስ) የቅብጠት አያያዝ ሊሰጡ ይገደዳሉ። በካይሮ ለናስር መንግስት በሚሰጡት ክብካቤ በመጀመሪያ ላይ ይህንን አጽንተዋል። በኢራን ህጋዊዉንና በህዝብ የተመረጠዉን ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሞስዴህን በመገልበጡና ሻህ ኤንድ ሻህ ፓህላቪን በማንገሡ ሂደት (1953) የአሜሪካ ሲአይኤና የእንግሊዝ መንግስት (ኤም አይ ሲክስ) ሚና በሃፍረት የሚታወስ ነዉ። ቀደም ባለዉ ገለጻ በቺሊ በህዝብ የተመረጠዉን ሳልቫዶር አየንዴን በመግደልና መንግስቱን አስገልብጦ ጨካኝና ጨቋኝ የሆነዉን ጄነራል ኦግስቶ ፒኖቼን መጎለቱን አንስተናል።

 

እነዚህ አምባገነኖች በህዝቦች ላይ የፈጸሙት ደባ፥ ያቋቋሙአቸዉ የሽብር ሪፐብሊኮች (ግዛቶች) ታሪክ በትክክለኛ መልኩ ተዘግቦ የሚገኘዉ በሲአይኤ መስሪያ ቤት ነዉ። የአሜሪካም የፖለቲካ ነውር ማስረጃ ሁሉ የሚገኘዉ በዚያዉ ባህረ-መዝገብና የፖለቲካ ሰነድ ዉስጥ ነዉ። ሌላዉ ቀርቶ ሲአይኤ ከተመሰረተበት ክ1948 አንስቶ ከ52 የማያንሱ በህግ የተመረጡ የዓለም መሪዎች ለአሜሪካ ጥቅም ባለመመቸት ሰበብ ተገድለዋል። እነ ሉሙምባና የፓናማ ሶስት መሪዎች ከዚህ ተራ ዉስጥ ይመደባሉ። ታዲያ ፕሬዚዳንት ኒክሰን የኒካራጉዋን ህዝብ ደም እያስለቀሰና በአንዳንድ ጸሃፊዎችም አገላለጽ “ደም እየጠጣ” የገዛዉን የአናስታሲያ ሶሚዛን (ደባልዬ) አምባገነንነት ተጠይቀዉ የሰጡት መግለጫ በትምህርት ማዕድ ላይ እንኳን የሚጠቀስ ነዉ። ኒክሰንን እንጥቅሳቸዉ፤ “Yes I know Somosa is a son of a bitch፥ but he is our son of a bitch” ነበር ያሉት።

 

እኔ የወቅቱን ወንጀለኛና “ማፈሪያ” የኢትዮጵያ መሪዎች (ገዢዎች) በኒክሰን ቋንቋ ላዉቃቸዉ አልፈልግም። ለፕሬዚዳንት ኦባማና ለዌንዲ ግን የግላቸዉ sons of bitches ናቸዉ። አሽከርነታቸዉንና ነፍስና ስጋቸዉን ለእነሱ አገልግሎት ማዋላቸውን እቀበላለሁ። “የዉሻ ልጅ” የምትለዋ ቋንቋ ለአማርኛዉ አገላለጥ ስለማትስማማ ሌላ አማርኛ ልናመጣ እንችላለን (በዚያ ትክ ማለቴ ነዉ)። የዛሬ 267 ዓመት ወደ ፖለቲካዉ መዝገበ ቃላት የገባዉ “ዘላለማዊ የወዳጅነትና የጠላትነት መለኪያና የዉጭ ጉዳይ ፖሊሲ እምብርት የአሜሪካ ወይም የእንግሊዝ ጥቅም” የመሆኑ ጉዳይ ዛሬም እየተሰመረበት ነዉ። ውብ ቋንቋና ጥዑም አነጋገር ያላቸዉ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ አሜሪካ አለምን መምራት አለባት” እያሉ ደጋግመው ይነግሩናል። በሚመች ጊዜ ይህን አገላለጥ በራሱ ባሕርያትና ይዘት በሰፊው ብመለስበት ደስ ይለኛል። አገሬ በእድገትና በሰላም ገስግሳ ከአሜሪካ ብትስተካከል እጅግ እደሰታለሁ። የመጨረሻ ህልሜ ግን አለምን ትገዛ ዘንድ አይደለም። የእኛ ከወያኔ ነጻ መዉጣት የአሜሪካንን የአለም መሪነት የሚያቃዉስ መስሎ ከታያቸዉ ግን እዚሁ ዉብ አሜሪካ ሆኜ ያስጠጋችኝን አሜሪካ መንግስት አምርሬ ብፋለመዉ ደስ ይለኛል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዉያን ዘላለም በወያኔ የእሳት መሰውያ ላይ መንደድ መቃጠልና ከስሎ ማለፍ ግዴታችን መሆኑን አልቀበልም በማለት እምዬ አሜሪካን እፋለማለሁ። አገሪቱም እንዲሁ ለወያኔ ቆሌና የወርቅ ጥጃ አምላክ በእሳቱ መሰውያ ላይ እየነደደች ስታልቅ እሳቱን ለማጥፋት የዌንዲን፥ የሱዛን ራይስንና የኦባማን ፈቃድ መጠየቅ እንዳለብን ለማወቅም ለመቀጠልም አልሻም። ይልቁንም እዚህ ላይ ቆም ብለን ማሰብ የሚገባን ከእንግዲህ ወዲያ ህዝባችን ያልተስማማዉንና የሚያፌዝበትን መንግስት ለመቅጣትና ከስራም ማባረር ያለዉን ነጻነት ማወጅ ነዉ። እንደአሜሪካ፥ እንግሊዝ፥ አለም ባንክ፥  የአዉሮፓ ህብረት፥ ወዘተ ያሉ መንግስታትና የቅኝ አገዛዝ ድርጅቶች  “የግልና ተወዳጅ የዉሻ ልጆች ወይም የማንወደድ የዉሻ ልጆች” አድርገዉ እንዳያዩን ጠረጴዛዉን ልንገለብጥባቸዉ ይገባናል። ተወዳጅ “የዉሻ ልጅነትም” ሆነ “የማንወደድ የዉሻ ልጅነት” ይቅርብን። በአፍንጫችን ይዉጣ። ከሁለቱ የትኛዉን ትመርጣለህ? ብባል ሁለቱንም መጥላቴን አዉጃለሁ። ኢትዮጵያዊነትን ማንም የሚሰጥህ መብት ወይም የሚነፍግህና የሚነጥቅህ ምድራዊ ሃይል የለም። በእኔ በኩል በወያኔ የዜግነት ሰጪነትና ነሺነት ስልጣን አዋቂነት ባልታማም ይልቅስ እነሱ ኢትዮጵያዊ በመባላቸዉ ብቻ የቆሰለ አንጀት ይዤ ወደመቃብር እሄዳለሁ። እፋለማለሁ! ተፋለሙ!

 

ዌንዲ ሸርዉድ ግንቦት ሰባትን እንደሚቃወሙና እንደ አልቃይዳና እንደ አይሲስ አሸባሪ ከማለት ባሻገር የሄዱ አይመስለኝም። ለዚህ መግለጫ አጻፋዉን ከግንቦት ሰባት አመራር ብንጠብቅም አቅጣጫዉ ወያኔን የሚቃወምና የሚቋቋም ሁሉ አሸባሪ የሚባል እንደመሆኑ ሁላችንንም በአንድ ቅርጫት ዉስጥ የሚያስቀምጠን ይመስለኛል። ስለሆነም አንድ ግዴታ ዉስጥ ልንገባ የምንገደድ ይሆናል። እኛ አይደለንም የአሜሪካን ጥላቻ የምናተርፈው። አሜሪካ የኢትዮጵያን ህዝብ ፍቅር ጨርሳ እዳታጣ እፈራለሁ። የዘመኑ ፖለቲካ ይህን እየመሰለ መምጣቱን የአሜሪካ የፖለቲካ መሪዎች ማጤን አለባቸዉ ባይ ነኝ። አሜሪካና እንግሊዝ ከ Palmerston ፍልስፍና (ቋሚ ጠላትና ቋሚ ወዳጅ የለንም፤ ቋሚ ጥቅም እንጂ) ከሚለዉ ወጥተዉ በ21ኛዉ ክፍለዘመን እንኳን በሰዉ ልጆች በአጠቃላይና በመንግስታትም እኩልነት ለማመን አልቻሉም። ፕሬዚዳንት ኦባማ በግልፅ ቋንቋ አለምን እንገዛለን፥ መግዛት አለብን ይሉናል። እዚያ ላይ ልንለያይ ነዉ። ወያኔ ሊገዛ ይችላል፤ እየታየም ነዉ። የኢትዮጵያ ህዝብ ግን አይገዛም፥ አይነዳም። የመጨረሻዉ ትልማችን የኢትዮጵያ ህዝብ ራሱን ይገዛ – ራሱን ይመራ ዘንድ ነዉ። የመጨረሻው ፈታኝ ችግር ቢመጣ እንኳን፥ ኢትዮጵያ በማንም እንድትገዛ አልስማማም።

 

ከላይ እንደጠቀስኩት ሴቲቱ የሰጡት መግለጫ አልተቋጠረም። ወያኔን የነካ (ግንቦት ሰባትን ጨምሮ) ምን ይደርስበታል? የተንጠለጠለ አቋም እንጂ በግልጽ የተነገረ ነገር የለም። በመለስ ቋንቋ እንመለስበትና “ጣቶች፥ እጆችና፥ አጽቆች እንቆርጣለን” አላሉም። በዋሽንግተን የሚገኙ የወያኔ መንግስት ጠላቶችን እያነቅን ወደአዲስ አበባ በመላክ እናስደስታቸዋለን እንዳልተባለ እገምታለሁ። እዚህ ላይ ስንደርስ በእርግጥ የአሜሪካን ዲሞክራሲ ዉበት ማሰብ አለብን። የዚችን ታላቅ አገር መስተንግዶ አክብሬና ዲሞክራሲ በስራ ላይ የሚዉልበትን የየቀኑን ህይወቴን እያየሁ፥ አሜሪካንን እያደነቅሁና እያፈቀርኩ እኖራለሁ። ማንም እንዲነካት ነክቶአትም አደጋ እንዲያደርስባት አልሻም። አሜሪካ ለሁላችንም የስደት ቤታችን ናት። እኛም የአሜሪካ ህልም ተቋዳሾች ነን። መንፈሳዊ ቤቴ ናት። በዚህ አንጻር በዲሞክራሲ ስም መሪዎቿ በየአገሩ የሚያደርሱት ጉዳት ይቀፈኛል።

 

ከህዝብ ይልቅ አምባገነንነት የሚመረጥበትና “በእግዚአብሄር እንታመናለን” (In God we trust) የሚል መሪ መፈክር ያነሳ መንግስት አላማና መርሁ በአሳማ ፊት የወደቀ እንቁ ይሆንብናል። የሴቲቱ ዌንዲ ሸርዉድ ንግግግር በዕንጥልጥል ነዉ የቀረበዉ። ከዉግዘት ባሻገር ሌላ (ሌሎች) እርምጃዎች አሉ? ይኖራሉ? አነጋገራቸዉን በሚመለከት እሸት እሸት የሆነ ማስረጃ በማቅረብ ሰዉ ፊት ለመቅረብ በማይችሉበት ሁኔታ ያሳፈሯቸው ምሁራንና ድርጅቶች ነበሩ። እንደ ዋሽንግተን ፖስት ያሉ የሚዲያ አውታሮች ሳይቀሩ ከዚህ ሁሉ በኋላ ለወያኔ አገዛዝ መቀጠል ሲባል በኢትዮጵያዉያን ታጋዮችና ተቋሞቻቸዉ ላይ አንድ አይነት ስውር ይሁን ገሃድ ርምጃ ቢወሰድ የአሜሪካንን አመራር ውስልትና የሚመሰክርና በሁላችንም ኢትዮጵያዉያን ላይ የተቃጣ ጥፋት አድርጌ እወስደዋለሁ። አቅሜ ደካማ ሊሆን ይችላል፤ መንፈሴ ጠንካራ ነው።

 

ለአሜሪካ የምንነግራት ኢትዮጵያውያን ጦርነት ላይ ናቸው። ከእንግዲህ ወዲያ ገላጋይ የሚፈልጉ አይመስለኝም። ይህም ሲባል ሰላምን አንፈልግም ማለት አይደለም። የጦርነት ፖለቲካ መለጠጥና ከሰላም ባሻገር ማደግ መሆኑንም እናውቃለን። ጦርነቶች የሚፈጸሙት እንደገና በሰላማዊ አደባባዮች በሚደረግ ምክክርና ውይይት መሆኑንም አንስተውም። ወያኔ ከዚያ በላይ ሄደ – ከሒትለርም ጉዞ አልፎ ዜጎቻችንን ጨፍጭፏል። አገር ሸጦአል። አንድነታችንን አቃውሶአል። ጦርነት አውጇል። በህዝቡ ላይ። ስለዚህ ግንቦት ሰባትና ሌሎች ሃይሎች ይህን በእግዚያብሔርና በህዝቡ ስም የሚያካሄዱትን ትግል ማንም ለመቃወም የሞራልና የትውልድ መብት የለውም። ተውን!

 

የኦባማ አመራር በእነ ግንቦት 7 ላይ አንድ አይነት የሚሳዝን አቋም ከያዘ (አያደርገዉም እንጂ) ወያኔን የነካ አሜሪካንን ነካ ማለት ይመስላል። ሐቁ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ በግንቦት ሰባት ሆነ በሌላ ድርጅቶቹ ወያኔን ይፋለማል፤ ያንበረክካል። ለታሪክ የፍትህ አደባባይም ያቀርበዋል። ይህንን መሰረታዊ የአገሬን ህዝብ መብት ኦባማ፥ ዌንዲ፥ ካርተር….. ባርተር ሊቀሙ ሊያቆሙ አይችሉም። በየጆሮዎቻቸዉ ሹክ ብለን ሳይሆን በጩኸት ልናስቀር የሚገባን ሐቅ ይህን ይመስላል። አትርዱን፤ አትፍረዱልንም። ግን ትግላችንን አክብሩልን። አትንኩን። ዳግመኛም የአሜሪካ አባቶች ለእዉነት ስለመቆም፥ ከተገፉ ህዝቦች ጎን ስለመሰለፍ፥ በጭቆናና በግፍ ላይ በመዝመቱ ሒደት የነበራቸዉን አቋም መርምሩ። አሜሪካ ለዘላለም ትኑር!

 

 

The post እርዱን ፍረዱልን አንልም፤ በነፃነት ተጋድሎአችን አይግቡብን! – ከጸጋዬ ገብረመድህን አርአያ appeared first on Zehabesha Amharic.

“ትግሌን አደራ!” –የጐንቻው!

መኮንን ጌታቸው ጌይል ስሚዝን በምስክርነት መስሚያ መድረክ ላይ ተቃወማቸው

0
0

mekonen
ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን እንደዘገበው የዲሲ ወጣቶች ግብረ ሃይል አባል መኮንን ጌታቸው የህወሀት ደጋፊ በመሆን የሚታወቁትና ለUSAID ሃላፊነት የታጩትን ጌይል ስሚዝን በመቃወም በምስክርነት መስሚያ መድረክ ላይ ተቃውሞ አሰምቷል።

ጌይል ስሚዝ በኢትዮጵያ የሚፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ የአሜሪካን መንግስት ጀርባ እንዲሰጥ ከሚያደርጉ ሰዎች አንዷ ናቸው።

መኮንን የሟቹን ሳሙኤል አወቀን ፎቶግራፍ በመያዝ ተቃውሞውን አሰምቷል።

መኮንን ጌታቸው ከዚህ ቀደም የሕወሓትና ተላላኪ ባለስልጣኖቻቸው ወደ አሜሪካ ሲመጡ የገቡበት ገብቶ ሲጋፈጣቸው መክረሙ የሚታወስ ነው::

The post መኮንን ጌታቸው ጌይል ስሚዝን በምስክርነት መስሚያ መድረክ ላይ ተቃወማቸው appeared first on Zehabesha Amharic.

የአረናው አመራር አባል በ3 ሰዎች ታንቀው ተገደሉ

0
0

ዓምዶም ገብረስላሴ ከመቀሌ እንደዘገበው: ኣቶ ታደሰ ኣብርሃ የተባሉ የዓረና-መድረክ ኣባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና ኣመራር ኣባል ትናንት ማታ 09 / 10 / 2007 ዓ/ም በሶስት ሰወች ታንቀው ተገደሉ።

Tadese Aberhaኣቶ ታደሰ ኣብራሃ በቓፍታ ሑመራ ወረዳ ማይካድራ ቀበሌ ኑዋሪ ሲሆኑ በዘንድሮው ምርጫ ወቅት በቀበሌው ኣስተዳዳሪዎች፣ ካድሬዎች፣ የሚቀርቧቸው ሰዎች ከዓረና-መድረክ ኣባልነታቸው እንዲለቁ የተሸመገሉ፣ የተለመኑና በመጨረሻም ዛቻዎች ሲደርስባቸው እንደነበረ ይታወቃል።

ኣቶ ታደሰ ማታ 03:00 በ 3 ሰዎች ኣንገታቸው የታነቁ ሲሆን ሶስቱ ሰዎች ሙቷል ብለው የተዋቸው ቢሆኑም ሂወታቸው እስከ 09:15 ኣላለፈችም ነበር። ኣቶ ታደሰ ኣብራሃ የ48 ዕድሜ ጎልማሳ ነበሩ።

ኣደጋው 3 ሰዎች እንደፈፀሙባቸው፣ በኪሳቸውም 300 ብር የነበረ ቢሆንም ሰዎቹ ሊወስዱት እንዳልቻሉ ተናገረው ነበር።

የኣቶ ታደሰ ሬሳ በሑመራ ሆስፒታል ላለማስመርመር የማይካድራ ፖሊስ ትራፊክ በዓረና ኣባላት ላይ ከፍተኛ ጫና የፈጠሩ ሲሆን የተለያዩ የመንግስት ኣካላትም ምርመራው እንዳይካሄድ የተለያዩ ጫናዎች እንደፈጠሩ ኣባሎቻችን ከስፍራው ገልፀውልናል።

ሬሳው ወደ ሑመራ ወስዶ ለማስመርመር የሚጠቅም መኪና ለመከራይ ሲባል ኣባሎቻችን የተካራት ሞተር ሳይክ በፖሊስት ትራፊክ ተከልክላለች።

የኣቶ ታደሰ ኣብራሃ ቤት ኣካራይና ሌሎች ሰዎች ከኣደጋው በተያያዘ ጫና እየተፈጠረባቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችለዋል።

የኣቶ ታደሰ ኣብራሃ ግድያ በሳምንት ውስጥ የወጣት ሳሙኤል ኣወቀን ጨምሮ ለሁለተኛ ግዜ በፖለቲከኞች ላይ የተፈፀመ ግድያ ሲሆን ከ2007 ዓ/ም በዓረና-መድረክ ኣባላት ለሁለተኛ ግዜ የተፈፀመ ግድያ ያደርገዋል።

ባለፈው ታህሳስ ወር የደቡባዊ ዞን የዓረና-መድረክ ኣስተባባሪና የማእከላይ ኮሚቴ ኣባል የነበረው ኣቶ ልጃለም ኻልኣዩ በኣዲስ ኣበባ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች መገደሉ ይታወቃል።

ይህ ተግባር በስፁም የሚወገዝና በሰላማዊ ትግል ላይ ሽብር የሚፈጥር ተግባር ነው።

በሰለማዊ መንገድ የሚታገሉ ፖለቲከኞች የሚፈፀም ግድያ ይቁም…!

መንግስት ነብሰገዳዮች ወደ ፍርድ ያቅርብ…!

ፈጣሪ ነብሳቸው ገነት ውስጥ ያኑርልን ኣሜን።

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

IT IS SO..!

– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/7865#sthash.EPhkL0ka.dpuf

The post የአረናው አመራር አባል በ3 ሰዎች ታንቀው ተገደሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሳሙኤል አወቀ መገደል የነፃነት ትግሉን አያስቆመውም !!

0
0

semawi

“ለማንኛውም የምከፍለው ዋጋ ለለሃገሬና ለነፃነት ነው፡፡ በአካል ብታሰርም ህሊናዬ አይታሰርም፡፡ ከገደሉኝም ትግሌን አደራ!!! አገራችን የወያኔ ዘረኞች ብቻ መፈንጫ መሆን የለባትምትግላችን የነፃነት፤ ጉዞአችን ጎርባጣ፤ መድረሻችን ነፃነት፤ ታሪካችን ዘላለማዊ ነው፡፡  ሳሙኤል አወቀ ፊስቡክ ገፅ ላይ የተገኘ ሰኔ 8/2ዐዐ7 ዓ.ም፡፡

awkeምስራቅ ጎጃም ግንደ ወይን 1978 ዓ/ም ተወልዶ – በህግ የዲፕሎማ እና ዲግሪውን ሰርቷል፡፡ ሣሙኤል አወቀ የሠማያዊ ፓርቲ መስራች አባልና ከዚያም በፊት እንደ ሌሎች ጓደኞቹ ከቅንጅት ጀምሮ በአንድነት ፓርቲ ውስጥ ሲታገል የቆየ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ ነበር፡፡ ሣሙኤል በሙያው የህግ ባለሙያና በጥብቅና ስራ በግል እየሠራ ጎን ለጎን ደግሞ ለአገሩ ከነበረው ፅኑ ፍቅር የተነሣ በሠላማዊ ትግል በማመን ገና በልጅነቱ ትግሉን ተቀላቅሎ በግፍ እስከተገደለ ድረሥ በንቁ የፖለቲካ አመራር ሲታገል ቆይቷል፡፡ ሣሙኤል የሠማያዊ ፓርቲ ከተመሠረተ ጀምሮ በከፍተኛ ኃላፊነት  በንቃትና በተደራጀ መልኩ  በተወከለበት ቀጠና በምስራቅ ጎጃም ዞን ሲያደራጅና ሲያስተባብር ነበር፡፡

ሳሙኤል አወቀ በአካባቢው ዘንድ የተከበረ እና ምስጉን ወጣት ነበር፡፡ በቅርቡም በተደረገው ሃገራዊ ምርጫ ፓርቲውን ወክሎ የዞኑ የተወካዬች ም/ቤት ጠንካራ ተወዳዳሪ እንደነበር አስመስክሯል፡፡  ሣሙኤል በምሰራቅ ጎጃም አካባቢ እታች አርሦ አደሩ መንደር በመዝለቅ በንቃት ሲያደራጅና ሲያስተባብር የነበረ በየአካባቢው ይደርስ የነበረውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ አስተዳደራዊ ጭቆናና በደል እየተከታተለ ለሕዝብ መረጃ ሲያቀብል እንደነበረ! በተለይም በፓርቲው ልሣን በነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ላይ አምደኛ በመሆን ተከታታይ መረጃዎችን ሲያቀብል የነበረ ጠንካራ የማይበገር ታጋይ እንደነበር ተገንዝበናል፡፡

በትናትናው ዕለት ማለትም ሰኔ 8 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም የወያኔ ኢህአዴግ የፀጥታ ሃይሎች ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል አካባቢ ከሚኖርበት ቤት አጠገብ ደ/ማርቆስ ከተማ ውስጥ እጅግ አሠቃቂ ድብደባ ተፈጽሞበት በግፍ ለተገደለው የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባል ሣሙኤል አወቀ አለም ሃዘናችን ፅኑ፣ መራርና ፈጽሞ ለአፍታም ያህል የማይረሳ የዘመናችን የነፃነት ትግል አርዓያ ዋና ተምሣሌት፣ እንዲሁም ለኢትዮጵያችን እንደቀደሙት ጀግኖች እንደነ አቡነ ጴጥሮስ የታሪክ ባለአደራ የወቅቱ የትግል ጥሪ ፈር ቀዳጅ ጀግናችን ነው፡፡  ለሣሙኤል አወቀ ቤተሰቦች እግዚአብሔር እንዲያፅናናቸው እየተመኘን ዛሬ ሣሙኤል በአካል ከትግል አጋሮቹ ጋር ባይኖርም የሥራው ተምሣሌት ግን ለነፃነት ትግሉ ጉዞ ህያው ሥንቅ ሆኖ ይቀጥላል፡፡

ሣሙኤልን በጥቅም ሣይደለል በኃይል በማስፈራራት ወይም በአካሉ ላይ ድብደባ በመፈጸም ትግሉን ለማስቆም ያልቻሉት የወያኔ ኢህአዴግ ቅልብ ወንጀለኞች በአካሉ ላይ ያደረሱት ጉዳት አልበቃ ብሏቸው በትናትናው ዕለት በስለት ፊቱንና አካሉን በመቆራረጥ ማንነቱን መለየት እስከማይቻል ድረስ በጭካኔ ገድለው ጥለውታል፡፡  ይህ ዓይነቱ የመንግስታዊ አሸባሪነት የመጀመሪያ ሣይሆን በተደጋጋሚ የታዬና አገዛዙ ጠንካራ ተቃዋሚ አመራሮችን በተመሣሣይ ጥቃት ሲያደርስ እንደቆየ ሕዝቡ ያውቃል፡፡ በኢትዮጵያ ተንሠራፍቶ ያለው ኢሰብአዊ አምባገነን ዘረኛ መንግስት በሕዝቡ ላይ በተለይም በተቃዋሚ ፓርቲ  አመራሮችና  በነፃው ኘሬስ አባላት ላይ ከፍተኛ በደሎች ማለትም እስራት፣ ድብደባ፣ግድያና ሁለገብ የሆነ የስነ ልቦና፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሃይማኖታዊ ወንጀል እየፈጸመ ይገኛል፡፡ የሣሙኤል አወቀ የግፍ ግድያ ከላይ እነደተጠቀሰው አገዛዙ ሕዝቡን የሚያጠቃበት መለያ ባህረው አንድ አካል መሆኑን አስረጅ ሊሆን የሚችልና  አገዛዙ ምን ያህል በጥላቻ እንደተጠመደና እጅግ አሣሣቢ ደረጀ ላይ መድረሱን ያሣያል፡፡  የወንድማችን የሣሙኤል የግፍ  አገዳደል አልበቃ ብሏቸው የአገዛዙ ቅልብ ነፍሰ ገዳዬች በሣሙኤል ቀብር ላይ የተገኙትን ሌሎች አመራር አባላት ከቀብሩ ስነስርዓት ሲመለሱ አግተው አስረዋቸዋል፡፡

ውድ የኢትየጵያ ሕዝብ ሆይ፦

ይህ አይነቱ እጅግ ዘግናኝ በደል ሃዘናችንንና ቁጭታችንን ያባብሰዋል እንጅ ለነፃነት የተጀመረውን መራር ትግል ለአፍታም አያስቆመውም፡፡ በአገርቤትም በውጭም የምንኖር የሠላማዊ ትግል ደጋፊዎችና አራማጆች እንዲሁም መላው አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የአገዛዙን ሰይጣናዊ ስራ በአንድ ድምፅ ማውገዝና መቃወም ይገባናል፡፡ ዛሬ በሣሙኤል ሞት ልባችን እንደቆሰለ ነገ በሌሎች ሣሙኤሎች ተመሣሣይ ግፍ እንዳይፈጸም ሁላችንም በአንድ ላይ እንነሣ!  አገዛዙን በጋራ ታግለን ማስወገድ ይኖርብናል፡፡

 

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

እግዚአብሔር የሣሙኤልን ነፍስ በገነት ያኑርልን!

 

The post የሳሙኤል አወቀ መገደል የነፃነት ትግሉን አያስቆመውም !! appeared first on Zehabesha Amharic.


ሰሞናቱ። ዳ እና ቃ ….

0
0

SAmuel awee bu

ከሥርጉተ ሥላሴ 17.06.2015 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

ሰሞኑን በርከት ያሉ ጸሐፊዎች በነፃነት ፍለጋ ሂደት ዙሪያ በርካታ ጹሑፎችን ጽፈው – አስተዬቶችን አነበብኵኝ። ወቀሳዎቹም ቢሆኑ መምህር ሆነው አግኝቻቸዋለሁ። በሌላም በኩል ላቅ ባለ ዝግጅት የተካሄደውን የኢሳት ዓለምአቀፋዊ ጉባኤንም ጊዜ ወስጄ – አዳመጥኩት። እርግጥ በጉባኤው እርዕስና ጭብጥ ላይ ቅሬታ ያለበት አንድ በፒዲኤፍ ጹሑፍ እዚህው ዘሃበሻ ላይ አንብቤያለሁ። ያም ነፃነት ነው። በሌላ በኩል ግን  አይደለም ለአፍሪካ ቀንድ ለመካከለኛው አፍሪካ፣  ለአህጉራችን ለአፍሪካና ለዓለም ሰላምና መረጋጋት በጠቃሚ ሃሳቦች ዙሪያ መወያዬቱ የሚበጅ እንጂ የሚጎዳ ሆኖ አላገኘሁትም – ተገኝቶ ነው። ከዚህም ሌላ በጸሎት መረዳዳቱም ይገባል። አባቶቻችን ስለሀገረ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ስለ ዓለምም ነው አብዝተው የሚጸልዩት። የዓለም ሰላም ለእኛም ሁነኛ ነውና። ዛሬ ዓለም እንዲህ በስጋት በተወጠረችበት ወቅት ችግሮችን ቁጭ ብሎ መነጋገሩ መልካም ነው። ዛሬ ያልተነሱ ሰበነክ ጉዳዮች ደግሞ ነገ ቀልብ ያገኛሉ። ዋናው መጀመሩ ነው። ወያኔ ሃርነት ትግራይ እያደባ ነው ትልሙን የሚፈጽመው እንጂ ለመካከለኛውም ምስራቅም ቢሆን ጊዜ የሚጠብቅ ፈንጅ ይኖረው – ይሆናል። ጠጠር ጥጥር እንጂ ጥጥ አይደለምና። ለማንኛውም እንደ እኔ እንደ ሥርጉተ ዕይታ ኢሳት ያሰናዳው ስብሰባ ምራቁን የዋጠ ነበር ማለት እችላለሁ፤  ከጊዜ ማነስ በስተቀር … ሳልጠግባቸው የቀሩ ዕርእሰ ጉዳዮች ነበሩ። ለአፍሪካም ቢሆን ጉልበታም ጉልህ የተመክሮ ማሳ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። እንዲሁም ለሚዲያ ታሪካችንም፤ በተለይ የእንግሊዘኛው ውይይት ዓይን የከፈተ ሃላፊነትን የተጋራ ማለፊያ ዬአቅም ጅምር ነው። …

በስብሰባው ላይ አዳዲስ ሃሳቦች ተነስተዋል „እርቅ፤ ዬንጉሣዊ ሥርአት ዘመኑ በሚፈቅደው መልክ እንደ እስካንድብያ ሀገሮች ቢሞከሩ ወዘተ ..“ የሚል ጫሪ ሃሳቦች። እንደነዚህ ዓይነት ሃሳቦች መልካም ናቸው። እርግጥ ግጭት ይፈጥራሉ፤ የሃሳብ ጦርነት ያውጃሉ፤ ፍትጊያን ይልካሉ፤ ተከክተው – ተሰልቀው – ግን እንጀራን ይፈጥራሉ። ስለዚህ በህሊና ውስጥ የሚጉላሉትን ሃሳቦች እንዲህ አደባባይ አውጥቶ ከወዲሁ ወለሉን መደልደል ከተቻለ ነገ የሰመረ ይሆናል። እኔ ተመሳሳይ ሃስብና ውይይት አይማርከኝም፤ ይልቁንም ፍጭትና ግጭት ያላቸው፤ አቧራውን የሚያጨሱ ጠቃሚ ዕይታዎች ይመርኩኛል፤ ለዚህም ነው ግጭት ፍልጋ ብዕሬን የመንፈሴ ልዩ መልእክተኛ ያደረግኳት። ወጣ ያሉና የተለዩት አምክንዮዎች ቀልቤን ይስቡታል – ይማርኩኛልም።  ዬእኔማ – የእኔ ነው፤ የእኔውን ቀለማም ውብ የሚያድርግ ነው የሚፈለገው። ምክንያቱም የራሴ ብቻ ከሆነ – ይሰለቸኛል፤ አዲስ ሃሳብ ከእኔ ለዬት ያለ ሲቀርብ ግን ለመንፈሴ ድሎት ነው – ይመቸዋል። ስለዚህ አዳዲስ ሃሳቦች መፍለቃቸውን – ወድጀዋለሁ፤

ሌላው የሰሞናቱ ንፋስ ደግሞ የ2007 የምርጫን ሸሩባው በሚመለከት ምላጭ ላጥ አድርጎ አዲሱን ሹርባ እንደበላው ዜናዎች በግራ በቀኝ ይደመጣሉ። ያገባኛል የሚሉ ወገኖቼም አስተያዬታቸውን በቅናነትና በታታሪነት እዬሰጡበት ነው። እንዲያውም አዲስ ሥም በተካታታይ ጭብጥ ዙሪያ አይቻለሁ – በተቆርቋሪነት። ማለፊያ ነው።

ሁሉም የምርጫ ስኬት፤ የድል እርቀት፤ የተስፋ ዝግመት፤  ምከንያታዊ ናቸው። ከመነሻው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥልጣን ላይ ከመውጣቱ በፊት ማንፌስቶውን ሲያዘጋጀው ነበር የገማ እንቁላል የነበረው። መቼም ከገማ እንቁላል የሚያድግ ጫጩት አይጠበቅም። ይህን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ጫካ በነበረበት ጊዜ በቅርበት ይከታተሉት ከነበሩት እጅግ በጣም ጥቂት ወገኖች በስተቀር ወያኔ ሃርነት ትግራይን የርትህ አደባባይ አድርጎ የተመለከተው ምልዐት ነበር። „ከደርግ የባሰ“ አይታሰብም ነበር። ስለሆነም ይህ የምልዕት ታዳሚነት መወቀስ አለበት ወይንስ የለበትም? ለሚለው – ሳያዩ የሚያምኑ ጥቂቶች በመሆናቸው መወቀስ የለበትም። ማንም ዜጋ ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ጋር ይሆናል መስሎት የሠራው – የተባበረው  – መንገድ የደለደለ፤ ጥሪውን የተቀበለ ሁሉ … ለወቅቱ ህሊናው የፈቀደለትን ተግባር መፈጸሙ ማንም የማይሰጠው ህጋዊው የነፃነቱ ማዕድ ነውና።

ለምን ተርቦ ማዬትና ስለ ራህብ ማድመጥ፤ ሰክሮ ማዬትና ሰካራም ማዬት፤ ሙሽራ ሆኖ ማዬትና ታዳሚ መሆን፤ መስማትና ማድመጥ፤ ማዬትና መስማት፤ ታስሮ ማዬትና እስረኛ መጠዬቅ አንድ አይደሉምና። ስለዚህም በስማበለው ሳይሆን ቀርቦ ማዬቱ ለውሳኔም ለመንገድም መልካም ነው።  „ቁርጥ ያጠግባል“ ይላሉ ጎንደሬዎቹ ሲተርቱ። ካዩት በኋላ ወጣ ገብ ያልሆነ፤ ቀጥ ባለ ውሳኔ የሰጡትን ድጋፍ መንጠቅ ብልህነት ነው። ወጣ ገብ ከሆነ ግን ጊዜ ይበላል ተስፋንም እያማለለ – እንዲህ ይሸረሽራል።

ያው እንደሚታወቀው ምርጫ በመጣ ቁጥር አዲስ ህብረት፤ አዲስ ፓርቲ ይኖራል። ያላዬነው – ያልሄድንበት መንገድ አለና እኛ የያዝነው ሃሳብ አሸናፊ ነው በማለት አዲሶቹ በአዲስ ተስፋ ጉዞውን ይጀምራሉ። ይህ ደግሞ አዲሱ በተፈጠረበት ጊዜ ወቅቱን አይቶ ስለሆነ ፕሮግራሙን የሚተለመው አዲስነቱን ያጎላውና ደጋፊ ይቸረዋል። በነገራችን ላይ – ወያኔ ሃርነት ትግራይ ዕድል ለቀጣይ ምርጫ ከኖረው ቀደም ብሎ አዲስ ፓርቲ ይፈጠራል። በሆነ አዲስ ሥያሜ።  አረንጓዴ ቢጫ ቀይ፤ ግሪን የለው ሬድ ወይንም ሰንደቅዓላም ወይንም ኢትዮጵያ ብቻ በሆነ ሥም ይፈጠራል። የዛሬ አዲሶች ከአምስት ዓምት በኋላ በሥራቸው የታሰረው ታስሮ፤ የተሰደደው – ተሰዶ፤ የበቀል መከርከሚያ የሆነው – ታጭዶ፤ የሞተው  – ሞቶ፤ የተፈታው ቤት ተፈቶ ቀሪው ነባሩ አሮጌ ይሆናል። ስለዚህ አሮጌው እኛ አይተነዋል አያዋጣም ቢል አዲሱ ደግሞ ኖ! እኔ የተሻለ አለኝ ብሎ ያው ፍልሚያውን – ይቀጥላል። ነባሮችን – ይወቅሳል። ወያኔም አጋጠመኝ ይልና አዲስ ገብ በማግኘቱ – ይፈነጫል። በዙርና በፈረቃ የሚደቃ ፈቃድ ማግኘት ሎተሪ ነው። … ስለሆነም ወያኔ ሃርነት ትግራይ ያዝ ለቀቅ እያደረገ አዲሱን እያባበለ መጋረጃ ጠባቂ ያደርገዋል። መጨረሻ ላይ ጉሩቦውን ተረግጦ ሚሊዮኖች ከኑሯቸው ያፈናቅላል ….. ያሻውን ደባ ማወራረጃ ያደርገዋል፤ ይህ በዙር የታየ የአምክንዮ ቁንጮ ነው።
awke
ይህ ለምን ሆነ? የወያኔ ሃርነት ትግራይን ተፈጥሮ  ዕውቀት ላይ „ሀ“ ላይ ስላለን፤ ምንአልባት አቡጊዳ የደረሱ ካሉ ዕድለኞች ናቸው። ቀላል ዬገበጣ ጨዋታ የሚመስላቸውም አሉ። „አብዮት አደባባይ የዛሬ ዓመት እንገናኛልን – የሚሉ።“ መሰረታዊ ችግራችን የወያኔ ሃርነት ትግራይን ተፈጥሮ፤ ሁለገብ የተከደነ አሉታዊ ሚስጢረ – ገብ ሴራ አናውቀውም። ከእኛ ይልቅ ክብርት ወ/ሮ አና ጉምዝ አሳምረው ያውቃሉ። ለዛውም ሃበሻ ሳይሆኑ። ሊቀል የሚገባው ግን ለእኛ በነበር። ምክንያቱም እኛ በደማችን ውስጥ ባሉ ጥበቦች ተመራምረን ልንደርስበት የሚያስችሉን ረቂቅ ህዋሶች – ስለነበሩን። ነገር ግን ሁልጊዜም ዳ  እና ቃ

ቀድሞ ነገር በሽታን ለማዳን ሃኪሞች በመዳህኒት ካልሆነም በገዶ ጥገና – ይገላግላሉ። እኛ በሽታችን እራሱ ገና አላወቅነውም። ሥም የለሹን በሽታ ካለማወቅ በመነጨ ለማናቸውም ጉዳይ „ቅድመ ሁኔታ“ ይጠዬቅበታል። ለታመመ መዳን ብቻ ነው አጀንዳው እንጂ ከመዳኔ በፊት ቅድመና ድህረ ድርድር ይደረግልኝ አይልም – በሽተኛው። እንዲያውም በሽተኛ „በሽታው“ የታወቀ ዕለት መዳኑን – መኖር መቻሉን ያረጋግጣል፤ ስለሆነም ደስ ይለዋል። ለዚህ ነው እንግሊዞች ችግርን ማወቅ 50% መፍትሄው እንደተገኘ የሚቆጥሩት።

ችግርን መሞከር ያስፈልጋዋልን?

ብዙ ጊዜ ስለወያኔ ሃርነት ትግራይ ተገልፆል በእሱ ላይ ጊዜ ማጥፋት አይገባም፤ ተዘውትሮ የሚደመጥ ክስተት ነው። እኔስ እላለሁ  ወያኔን – አናውቀውም። የምናቀለውም በዚህ ምክንያት ነው። ስለዚህ ቁጭ ብሎ መማር ያስፈልጋል። ለዚህም ነው ኢሳት አዘጋጅቶት በነበረው ጉባኤ  „ህግን“ በሚመለከት እነዛ ፍሬዎች – የተስፋ ገለጣቸው በአጭር ሲሆን ክፍት ያለኝ። ለምን? ወሳኙ ጉዳይ መማር አለመቻላችን በመሆኑ። በህግ ጉዳይ ምን መብት ምንስ ግዴታ እንዳለ አለማወቅ ብዙ ነገርን ያሳጣል። ዜጋ ነኝ። በዜግነቴ ላገኝ የምችለው ምንድን ነው? ዜግነቴ ብቻ ለእኔ ሊሰጠኝ ከሚገባው ምን ያህሉን አግኝቻለሁ? በዜግነቴ ብቻ በቀጥታ ላገኘው የሚገባኝን የከለከለኝ – ያገደኝ ምንድነው? አላውቀውም። ስለዚህ ትራሴን ከፍ አድርጌ ተኛሁ። ወይንም መነሻዬን የዜግነቴን አምክንዮ የጠቀጠቀው ማዕከላዊ አመክንዮዊ ጉዳይ ላይ አትኩሮት – ነፈግኩት፤ ወይንም ተስማሚ ብርሃን እንዳያገኝ አደረኩት፤ ወይንም ጠውልጎ እንዲረግፍ – ፈቀድኩኝ እኔው እራሴ ተከሳሽ በሌለበት ሁኔታ። እኔ ዜጋ መሆኔ ሳይኖር ነው ሌላ ጥያቄ የማነሳው። እነኛ ጥያቄዎች ግን ዜጋ መሆኔ ሲረጋገጥ በቀጥታ ከዜግነት መብቴ ጋር ካለ ፍርፋሪ ለማኝነት ማግኘት ያስችለኝ ነበር – ግን ተራራቅን። ስለምን ዜግነት ጽንሰ ሃሳቡን ከህግ አንፃር የመተርጎም ዕውቀት የለኝም። አልተማርኩ – ማ። ዜጋ መሆን ካልቻልኩ ግዴታ የለብኝም ማለት ነው። መብቴን ዬነጠቀኝ ግዴታውን አስኪያሟላ ድረስ ቁጥር አንድ ጥያቄዬ ዜግነቴን ማስከበር ይሆናል። መብቴን ሲያከብር ግዴታዬን እወጣለሁ። ግን ግንዱ ሥሩ ተዘሎ ቅርንጫፍ ጭፍጫፊው ላይ ነው አቅም እንዲህ የሚባክነው – የ“ዳ“ ዕዳ የ“ቃ“ም ግብዕት ተመቻችቶ መሰንጠቅ – መተርተር እንደ ግራምጣ፤ እንደ ሰበዝ – መሰበዝ።

ትልቅ ጉባኤ አይስፈልገውም፤ አጫጭር በራሪ ጹሑፎች፤ ፓስተሮች፤ አሰባሳቢ – አባባሎች፤ ውይይቶች፤ ንግግሮች ሁሉ የራሳቸው አስተዋፆ አላቸው። „አክሱም ለጋንቤላው ምኑ ነው“ ይህ ሠርቷል። የሄሮድስ መለስ የምጻት አገላላጽ የአራት ቃል – ትርፍ። ጋንቤላ እሳት ቢነድ፤ ጋሞ በአውሎ ቢናጥ፤ ድሬ በረዶ ቢወርድባት፤ ባህርዳር ነጎድጓድ ቢሰነጥቃት፤ መተማ የሱዳን ብትሆን ለሌላው ባዕዱ ነው። አያችሁ አንድ የአራት ፊደል ስንኝ ምን ያህል መንፈሳችን እንደ ቦረቦረው – ተሸናፊም እንዳደረገው? እንዴትም እንደዘረፈው – እትብታዊ የግንኙነት ሃዲዳችን። ስለዚህ ከአባባሎች ጀምሮ አዳዲስ መንፈስን የሚገሩ ተግባራት ላይ ማተኮር በእጅጉ ያስፈልገናል። አብሶ ፓርቲዎች፤ ንቅናቄዎች፤ ግንባሮች፤ ተቋማት ዬአባሎቻቸውን ህሊና በመገንባት እረገድ ተከታታይነት ያለው ተግባር ለመከወን ማቀድ ግድ ይላቸው – ይመስለኛል። ምክንያቱም የትናንት ችግር ዛሬም መኖሩ ብቻ ሳይሆን፤ ችግሩን ሊፈቱ በሚችሉት ላይ ሳይሆን አቅም የሚባከነው ችግሩን እንሞክረው በማለት – የሚቀጠፉት ነፍሶች በግፍ መርገፍ የልብ እሳት ነው። ለመሆኑ ችግር ስንት ጊዜ ነው የሚሞከረው? ዓመታት ጥለውን እዬሸራረፉን እዬነጎዱ ነው ያሉት። ወያኔ ሃርነት ትግራይን ያላገላጠ አንድም ዓለምአቀፍ የሰብዕዊ መብት ድርጅት የለም። ስለዚህ – የምናጋልጠው ወያኔን አብጠርጥረን በማወቅ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ሽወዳ በራችን ስንቀረቅር ብቻ ነው። እንጂ ወያኔ ሃርነት የዘር አስተዳደር፤ እና አሸባሪ መሆኑ አሳምሮ አለም ያውቀዋል። ዓለም ባገለጠው ዕውነት ላይ የምልዕት መንፈስን ማደራጀት ነው ያነሰን። የፕሮፖጋንዳ ተግባር በር አያስከፍትም። ከተጨባጩ ከምድጃ የተነሳ የሃቅ አውድ እንጂ …..

ደወላትን (signal ‚ ponter) የማዳመጥ አቅምን ማሳደግ –

ድወሎችን የመተርጎም አቅም ማነስ ሌላው ችግራችን ይመሰልኛል። በ2002 ምርጫ „መድረክ“ የሚል ህብረት ስለነበር ህብረቱ አቅም ጉልበት አለው ስለዚህም አብላጫውን ወንበር የማግኘት ዕድሉ ሰፊ ነው ተባለ – ተሞከረ፤ ዛሬ የዛን ጊዜ የነበሩት አብዛኞቹ የሉም። ግን ካሳና ግብር ማገዶዎቹ አቶ አንዷለም አቶ ናትናኤል ሆኑ። አቶ አንዷአለም አራጌ ሲታሰር ጨዋታው አብቅቷል። በቃ! ወደ ክ/ሀገር ሲወረድ ደግሞ ገላጭ፣ ተገርጓሚ፣ ቃል አይገኝለትም። እስከ ዘንድሮው ምርጫ ድረስ የቋሳው ፖሊሲው – ይፈጫል። አሳዛኙ ነገር ሌላ አዲስ የቋሳ ስብስብ መንፈስ ሳይታከት በማሰናዳት ለወፍጮ ምርት አቅራቢ ከመሆኑ ላይ ነው።

መምጣት አይቀርም 5 ተቆጥሮ — 2007 መጣ። „የ2007 እንደምናሸነፍ እርግጠኛ ነን – እናውቀዋለን። ወያኔ ጓዙን ይጠቅልል“ የሚሉ መሪ ቃሎች ተደመጡ። ዋጥ ተደርገው ቢያዙ መልካም በሆነ ነበር። „ዬሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነትም“ ሰፊ ተግባር ከውኗል። በነገራችን ላይ አውሮፓ በዬአመቱ የሙዚቃ ውድድር ያደርጋል – በወል። ኢሮ ሶንግ ኮንቴስት /euro song contes / ይባላል። ከጉዳዬ ጋር ብቻ የሚያያዘውን ነው የማነሳው። ግን እጅግ በሰብዕዊነት ዙሪያ አብልጎ የሚሰራ፤ መንፈሱ ውብ ጠርን ያለው፤ ፉክክሩም ልብ ሰቃይ ብቻ ሳይሆን የአውሮፓውያኑን ባህልና መሰል ግንዛቤዎችን የሚያስጨበጥ ነው። ስለሆነም እኔ እታደምበታለሁ። ሰው – ሰው ነው። ሰው ጥበብን፣ በጥበብ ለማኖር እራሱ ጥበብ መሆኑን ማረጋገጥ ሲችል ብቻ ነውና።
Samuel Aweke
በዚህ ዓመት 60ኛ ዓመቱን ሲያከበር በ2014 አሸናፊ በነበረው ኦስትሪያ ቬና ላይ 40 የአውሮፓ ሀገሮችን፤ ከአህጉሩ ውጪ አውስትራልያን ለመጀመሪያ ጊዜ አሳትፎል። ቻይናም በቀጥታ ዝግጀቱን ታስተላልፍ ነበር። ማጠሪያውን ያለፉት 27 ሀገሮች ነበሩ። ከ27 ሀገሮች እስከተወሰነ ደረጃ በአንድነት መርቶ ሁለተኛ የወጣው „የሚሊዮኖች ድምጽ A Million Voices“ ዬPolina Gagarina የአርቲስት ፖሊና ጋጋሪን የራሽያዊቷ ነበር። አውስትርልያን ጨምሮ አውሮፓ ሀገሮች በሁለተኛ ደረጃ በፍቅር የመረጡት። እርግጥ አንደኛ የወጣው ዬሲዊዲን ነው። መንፈሱ „ሰው ጀግና ነው በተፈጥሮው“ የሚል ነበር። እርእሱ „ጀግና“ ይል ነበር። አርቱም ቅንብሩም እጅግ ያደገ ሥልጡን ነበር።  ወደ ጉዳዬ ስመለስ እንዴት ያለ ህሊናና መንፈስ „የሚሊዮኖችን ድምጽ ለነፃነት“ መርህ እንደ ነደፈ እጅግ ..  እጅግ በጣም ነበር ዬገረመኝ። በመንፈሴ ውስጥ የአንድነት ዓርማ ቤተኛ ነበር። አውሮፓውያንን መንፈስ በፈቃደ – ፍቅር ሰጥ አድርጎ የገዛም፤ በቂ አድማጭና አትኩሮት የተለገሰው ክብሩ ነበር። ይሄን ሞገድ ነበር –  ወያኔ ከሥሩ የነቀለው። ወያኔን  …. አቅልለን ስለምናዬው እንጂ እራሱን ለማቆዬት የሚያስችለውን በርግጫም በፍጥጫም የሚያዋጣውን መስመር እንደሚተልም – ይታወቃል። የላቀና የበለጠ – ተወዳጅና ተናፋቂ ነገ ማዬት ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ምጡ ነው።

ደወል አንድ – ወጣት ተደማጭነት ያላቸው ታሰሩ አብርሽ፤ ሃብታሙ አያሌው፤ የሽዋስ አሰፋ፤ ዳንኤልን ሺበሺ /አቶ/

ደወል ሁለት – የወያኔ ጋዜጠኞች ቢጨፈለቁ የማይተኩትን አንደበታችን ተመስገን ታሰረ /ጋዜጠኛና ጸሐፊ/

ደወል ሦስት – አንድነት ፈረስ / ብሄራዊ ተደማጭነት ያለው መጠነ ሰፊ ትልም ቀብር ተበዬነበት/

ደወል አራት – አርበኛ አንዳርጋቸው ታሠሩ – የኢትዮጵያን ህዝብ ምርጫ አልቦሽ በማድረግ ብቸኛ ሃብቱን ድምጹን ለታላቋ ትግራይ ህልም እንዲያውል – መንፈሱን ተዘረፈ …

ደወል አራት – የአውሮፓ ማህረሰብ ሆነ ሌሎችም ምርጫውን እንደማይታዘቡ አሰገነዘቡ።

ደወል አምስት – በቅድመ ምርጫ መሰናዶ ላይ ተፎካካሪዎች ሰፊ አፈና እስር እንግልት ተፈጸመባቸው ግን ጆሮ አልባ ነበርን?

ከዚህ ላይ ክብርት ወይዘሮ አና ጉምዝ ከአሜሪካ ድምጽ አማርኛው ፕሮግራም ጋር ካደረጉት ቃለምልልስ እንደተረዳነው ያልተገኙበት ምክንያት ዕውቅና ለወያኔ ሃርነት አለመስጠት ብቻ አልነበረም። „ወያኔ ሃርነት ትግራይን ለሚያቆላምጡ ዲታ ሀገሮችም እውቅና በመስጠት ሽፋን አንሆንላቸውም፤ የደራ የዜና ገብያ አንከፍትላቸውም“ ነበር ያሉት ግን አብዛኛውን ወንበር እንሸንፋልን በሚል ሙሉዑ ተስፋ ተሞከረ። ድምጽ ለተፎካካሪዎች የሰጡት ምን ይደርስባቸዋል በሚለው ላይ ብዙም ትኩረት ያልሳበ ዕሴት ነበር። እነኛ የነፃነት ናፊቂዎች አሁን ሦስተኛ ዜጎች ናቸው። ተራው የወያኔ ሃርነት ትግራይ አባል ሳይቀር ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ቁጫኑን – ይወጣባቸዋል። የመንፈስ ድቀቱና የሥነ ልቦናው ጫና ሌላው ያልተከፈለ ዕዳ ነው።

ጆሮ ቢኖር ሂደቱ ብቻውን ዬወያኔን የምርጫ ትልም ልናስተውልበት የምንችለው ቀዳሚ የህሊና ሰብል በነበር። ነገር ግን ችግር ፈተና ይሁን ሞት ተሞከረ – ሆነም። ለምን? አበጥረን አናውቀውማ – ወያኔ ሃርነት ትግራይ የተመሰረተበትን አመክንዮ። ሥሙን እንኳን በድፈረት ለመጥራት አንችልም – እንኳንስ ጥንስሱን – ዝልሉን – የመርዝ ድፍድፉን ለመተርጎም …. እና እኔው እምለው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ቁጭ ብሎ ማንበብ፤ ማጥናት፤ ተያያዥ ህጎቹ፤ የአፈጻጸም መመሪያዎቹ ለምን? ስለምን? እንደተረቀቁ እንደ ጸደቁም ልብ ገዝቶ መመርምር ያስፈልጋል። አሁን በዚህ ምርጫ ዘመዱ የሆኑትም ቢሆኑ ለአሁን ብቻ ነው። በሚቀጥሉት ጊዜ አይስፈልጉትም – እረክሳዋል ብሎ ቆሻሻ ውስጥ ይጨመርና አዲስ አመላቸው የማይታወቁትን ዱቅ ያደርጋል። ወያኔ ሃርነት ትግራይ በትጋትና በታታሪነት እዬሠራ ነው – ለታላቋ ትግራይ ህልሙ። ተፎካካሪዎች አብዛኛውን ወንበር እንሸንፋልን ዬሚል ተስፋ ነበራቸው – ባልከፋ፤ ግን ቀድሞ በህግ የታሰረ ስለሆነ ሰማይ ከፍ ምድር ዝቅ ቢል እንዲህ በቀላል የወረቀት ቅልቅል ማስፈታት አይቻልም – ተቆልፏል። „ቁርጥ ያጠግባል“ – ሃቁ ይህ ነው።… በተአምር ወያኔ ሃርነት ትግራይ ስለ ሰብዕዊ መብት፤ ስለመናገር ነፃነት፤ ስለ ህዝብ በደል ብናኝ ጊዜ በክርክር ሸንጎው ላይ ማቃጠል አይሻም። በጎጥ በተጠረገ አስፓልት እራሱን እያዳመጠ ሌላውን መዳጥ ….

የሚገርመው አቤቱታ አቅራቢም እኛው፤ አቤቱታም ሰሚው እኛው፤ እለቅሶ ተደራሾችም እኛው፤ አልቃሾችም እኛው — ከሁሉ የሚከፋው ግን ቀደም ብዬም በተከታታይ ጹሑፎቼ በራዲዮ ፕሮግራሜ እንደገለጽኩት ይሆናል መስሎት ጥግ አልባ የረዳ፣ የተባበረ እዬታደና እስር ቤት መወርወሩ የባሩድ እራት መሆኑ —- .። እንደርስለታለን ….? ለራሳችንም አቅም የለንም እንኳንስ በዬምርጫ ጣቢያው ከጥርስ የገባውን ህዝብ እና ሰፈር ለማዳን …. በብሄራዊ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ሊቀመናብርት ላይ ወያኔ ካቴና የሚያስበው ሲያሰጉት ብቻ ነው። ካላሰጉት ታች ያለውን መሠረቱን ለመናድ ሴሉን – ያፈርሳል። ለፕሮፖጋንዳውም „ከእነሱ አልደረስኩም ያጠፋ ግለሰብ ነው ያሰርኩት“ ይላል። የተፎካካሪ ሊቀመናብርት እንደልባቸው – ይናገሩታል፤ አያስራቸውም፤ ለውጪ ዜና መልካም – ቅዳሜ ገብያ //// ለነገሩ ቧልትም ጎጥም ሀገርን በመምራት ደረጃው ቧልት ይመሰልኛል። መሻል – ይጠይቃል።

መማር ያለመቻላችን መሰረታዊው ምክንያት የወያኔ ሃርነት ትግራይ የተፈጠረበትን መሰረታዊ ሥነ ምግባር አለማወቅ ብቻ ነው። አሁን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥልጣን ላይ ስላለ ብቻ አይደለም፤ ሌላማ ጎሳዊ ድርጅት ወንበሩን ቢይዝ ይሄው ነው። የሚያስበው ለራሱ ብቻ ነው። የሚቆረቆረው ለራሱ ብቻ ነው። የሚያሳድገው የራሱን ልጆች ብቻ ነው። ስለዚህ ከዚህ የራስና የግልዮሽ ጥብቆ ዕዬታ መውጣት የሚቻልበትን መንገድ ስንተልም ብቻ ወያኔን ማሸነፍ እንችላልን። ወያኔ ሃርነት ትግራይን አወቀነዋል ማለት የሚቻለውም ድል የሚደርጉትን እርምጃዎች ስናሰብል ብቻ ይሆናል። በሥነ ልቦና ማሸነፍ በራሱ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥልጣኑን ከመልቀቁ በፊት መንፈሱን ማሟሸሽ ያስቻላል። ጎሳን አንጋሽዎች ጎሳና ጎጥ ዋጋ ቢስ መሆኑን ስንመሰክር፤ ቁመን ስንሰብክ፤ ሐዋርያ  ሆነን ስንገኝበት ብቻ ሃይላችን ከዛ ይቀዳል። ዬትም ቦታ መከራን አብዝተው የሚቀበሉት ወገኖቻችን „ኢትዮጵያዊ“ በመሆናቸው ብቻ ነው። መፍትሄ አምንጪውም ሆነ መንገድ ጠራጊውም፤ የስሜትና የፍላጎት ገዢውም በዚህ ማዕፍ ውስጥ የተጠቃለልን ዕለት ሚስጥርና እኛ እኛና ሚስጢር ጥምረት አይደለም እእ – ጋብቻም አይደለም እእ በአህቲነት  – እንፈጠራለን። እንደገና መፈጠረ —– ችግርን ለመመንጠር – የጎጥን ሴራ ስንንድ — ግን ነገር ግን – አሁንም ቅድምም “ኢ“ ተትታ – ተንቃም ኦ. ት. ኡ. ሱ. አ እያልን እምንተክዝ ከሆነ ዕንባን ዋጥ አድርጎ መቀመጥ።

የሚከብዱ – ስምምነቶች፤ የሚያቃቱ – ፈተናዎች መበራከት የመግባባት ሂደቶች ጨዋታው ያለው ዬወያኔ ሃርነት ትግራይን ተፈጥሮ ካለማወቅ የሚመነጭ ነው። የወያኔ ሃርነት ትግራይን ሥነ ደንብ ለመተርጎም አቅም ስለሚያነስን ብቻ ነው። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ተልዕኮን ከጥላቻ አልፈን የጥላቻው ችግኝ ዕድገት እንዲገባን ለራሳችን ስለማንፈቅድለት ነው፤ እንጂ ማንይሙት እፍኞች 24 ዓመት እንዲህ አንበርክከው መፍለጥ ባልቻሉ ነበር። ለእኔ የግንዛቤ ችግር አለብን – የወያኔ ሃርነት ትግራይን የመሰሪነት – ህጋዊነት፤ የተንኮለኝነት ሴራው ምንጩ መነሻው መድረሻው ሆኖ ሳለ፤ እኛ ላዩን እንጂ ነፍሱን ገና አለገኘነውም። ለዚህም ነው አድጎ መሄድ የቻለውን እንኳን ለማስተናገድ ህሊናችን አሻም በማለት ራሳችን የራሳችን የህሊና ሃብት ስንነቅፍ፤ ስናሳድድ የምንገኘው። ባደገው ወይንም ለግለግ ብሎ በወጣው ላይ ያነሰው ምንድን ነው? አፈር? ማዕድን? ውሃ? የጸሐይ ብርሃን? ያ አይደለም ጭንቀቱ —- እህሳ – ኮፒራይት … ወያኔ ሃርነትን ያህል ጠላት አስቀምጦ – ለመደርምስ መፍቀድ፤ ለመፍለስም።

ስለዚህ አቅም ያላቸው ወገኖች ሌላ ቦታ ሳይሄዱ፤ ወጪም ሳያቃጥሉ እራሳቸውን – ይዳኙ። እራስን መዳኘትም – ሌላው የአቅም አመክንዮ ነው። ምክንያት መሆን የለባቸውም – ለብርሃን ግርዶሽ በመሆን። አንድ ታሪክ ትዝ አለኝ። አንድ ወንድሜ የሚሆን መርጌታ አሞት ሁዳዴን ገደፈ እና ለእኔ ነገረኝ። ታዲያ ምን አለበት ለሌሎችስ ብትነግራቸው ታመህ ነው አልኩት „ለሌሎች መሰናከያ አልሆንም“ አለኝ። ብልህነት ነው። ሌላም አንድ ልከል ጀርመን ውስጥ ቤፋውቤ (BVB) የሚባል የእግር ኮስ ቡድን አለ። በጣም ታዋቂ ነው። ታዋቂነቱ ዘንድሮ እዬቀነሰ፣ አቅሙም እዬመነመነ ሲመጣ – ባልታሰበ ቀን ከ7 ዓመት በላይ ያሰለጠኑት ጀርመንን ለዋንጫ ያበቀውን ጎትሰንና መሰሉን ሳተና ወጣቶችን ያፈረቱ ታላቅ አሰልጣኝ በድንገት „እለቃለሁ“ አሉ። ሥራ ፈላጊም እሆናለሁ አሉ። አስደንጋጭ ነበር። ጋዜጣዊ መግላጫቸው አጭር ነበር „ …. እኔ ከዬትኛውም የእግር ኳስ ቡድን ቡድን ጋር ውል የለኝም። ስለሆነም በቀጥታ ሥራ ፈላጊ ነው የምሆነው። ቁጭ ብዬ ሳስበው እኔ ከቦታው እያለሁ እያደገ መሄድ የሚገባውን የቡድኑን ዕድል ላጨናግፍ አይገባም። እኔ ስለቀው ያድጋል“ በቃ የአንድ እግር ኳስ አስልጣኝ ደሞዝ በወር ምን ያህል እንደሆነ ታውቁታላችሁ። ክብሩም ሞገሰም ወዘተ …. ለዛውም በ2015 በለስ ቀንቶት BVB ለሀገሩ የዋንጫ ውድድር መድረስ ችሎ ነበር ባያሸንፍም ….

ስለዚህ እንቅፋት የሆንባቸው ቦታዎች ካሉም፤ በቅንነት – በሙያችን፣ በተመክሯችን እያገዝን ዞር ማለቱም የሚበጅ ይመስለኛል። ይህን ማለቴ የአመራር ተከታታይነት ይሰረዝ ማለቴ አይደለም። መርህ ብቻ ሳይሆን ካለእርሾ ሊጥ አይቦካምና …. የሆነ ሆኖ ሁልጊዜ አዲስ የምንሆንበት ምክንያት፤ አዲስ ፓርቲዎች በመፍጠር ችግሮችን የምንፈታቸው የሚመስለን ምክንያቶች ዕልባት ሊሰጣቸው ይገባል። ወይንም ህብርት በፈጠርን ቁጥር ድሉን ቅርብ አድርገን ተስፋ የምንደርገው ሁነት ሁሎቹም ሲደመሩ ሲባዙ የወያኔ ሃርነት ትግራይን ተፈጥሮ ካለማወቅ ይቀዳሉ። ስለዚህ መሥራት ካለብን መሠረታዊ ጉዳይ ትልቁ መንፈስን በመስኖ ማልማቱ ላይ ነው። ከዚህም በላይ ባለቤት የሌላቸው ጹሑፎች ይበተናሉ እነሱም የሚያሳድሩት ተጽዕኖ ቀላል አይደለም። ለምን? የሚመከት ተግባር ለመከወን አቅምን ስለሚበሉ …. ከእነዚህ መሰል ጉዳዮችም ነፃነት ፈላጊ ቅን ዜጋ መታቀብ በእጅጉ አለበት። መከራው ከመረረን፤ መርዶው ከጎመዘዘን፤ የዛሬ 20 ዓመት በጎሳ ዛሬም በጎሳ ተደራጅቶ ጎሰኝነትን አምልኮ ጎሰኛውን ዘውደኛ ማሸነፍም አይቻልም – በፍጹም። ኢትዮጵያ ኢትዮጵያውያን ሳታዳላ የመገበች የግብር – ማዕዶት ናት። ዛሬ መከራውን ለመሸምገል ግን እንደ ሥጋ ቀረመት ላይ ተሆኖ ሳይሆን ውስጧን በመሆን ብቻ ነው። የምትፈልገው እናት የልጆቿን አብሮነትና አንድነት ብቻ ነው።

ወቀሳ።

ወቀሳው እራስን፤ ነቀሳው እራስን ….. ዳኝነቱ እራስን፤ ኩነኔውን ወደ እራስ፤ ሃጢያቱን ወደ እራስ እንጂ ሃይልና አቅምን ነፃነት የተፈለገበት ምክንያት ላይ …. መለቀቅ የተገባ አይደለም። አለሎ ድንጋይ እዬፈለጉ አናት ሲፈልጡ እራስን በዙር እንደሚፈልጥ ማስተዋል የሚገባ ይመስለኛል። „ወያኔ ሃርነት ትግራይ ኮረጆውን በሙሉ ዘረፈ፤ ሟጠጠ¡“  ምን አዲስ ነገር አለው? ከጎሳ ድርጅት ፓሊሲ የሚጠበቅ ነው። እኛም በጎሳ መንፈስ ውስጥ ነው ያለነው። … „የዘንድሮው የባሰ የበዛ ነው¡“  ትናንትም በሞት ተሞከረ ዛሬም በሞት 2007 ተዘከረ። ምንአልባት የትናንቱን የእኔ ወይንም የእኛ ብለን ሳናስጠጋው ቀርተን ካልሆነ በስተቀር ሲጀመር ጀምሮ ይሄው ነው። 4 ዓመት ተስድስት ወር የለሁም፣ ከዛ እባንና ከማይክ ጋር እገናኛለሁ። በማይኩ ጀርባ ግን በድምጹ ልክ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ የበቀል ፓሊሲ ጥሬ ሃብት አቀርባለሁ – ለዛውም የሰው ልጅ። ከእኔ እስካልደረሰ ሌላው መሞከሪያ ይሁን በቃ — አራት አመት ከስድስ ወሩን ግን ደሙ ሲፈስ፤ ሲታሰር፤ ተደብድቦ ሆስፒታል ሲገባ፤ ለድርጅቱ ሲል በካቴና ሲጠረነፍ ቤተሰቡን ተገኝቶ በማጽናናት፤ ህዝቡን በአብሮነት ላይ በማሰለፍ፤ መንፈሱን ለማልማት ሰሚናሮችን፤ ወርክሾፖችን እስከ ታች ድረስ ወርዶ መልክ ለመልክ ለመተያዬት ሙከራው – እሩቅ ነው። ሌላው ቀርቶ በክንድ እቅፍ ውስጥ አንድን የነፃነት ራህብተኛ መቆዬት እራሱ እኮ ልዩ መንፈስን ይለግሳል።

መቋጫ – አንድ ጹሑፍ ላይ „ማረድ“ የሚል አንብቤ ነበር። ስለቃሉ ከብራናዬ ላይ ለማዋል እዬሰቀጠጠኝ ነው የጻፍኩት። በጉልህ ይህ አስፈሪ ቃል የሚያመልክተው ፋይዳ ህሊናን የማልማት ተግባር ምን ያህሉን እንደከወን የሚያሳይ አሉታዊና አዎንታዊ ናሙናችን ነው። —አዎንታዊ የተገበርነውን ሪፖርት ገላጭነት መሆኑ ሲሆን፤ አሉታዊ ደግሞ በሰውና በአራዊትነት መሃከል ያለውን ልዩነት በጥበት ስለሚወጥረው ነው። ሰው እንዴት ይታረድ? አንደኛ ደብዳቢነቱ – በማህያ ነው ይሸጎጥለታልም – በፋሽስት በምትመራ ሀገር። ሁለተኛ ደብዳቢነቱ በበቀል በወረዛ ፖሊሲ ሥር ነው። አንድ ወንጀለኛ „በማረድ“ ይወገድ። ሥርዓቱ ፓሊሲው ስለሆነ ሌላ ይተካበታል ሌላ ነፍሰ በላ። ስለዚህ መቀዬር መለወጥ ያለበት የሥርዓቱ ፓሊሲ መሠራች የሆነው ማንፌስቶው ነው። ያም የወያኔ ሃርነት ትግራይ የጎሳ ማንፌስቶ፤ እሱን እንታገለዋለን የሚሉትም እራሳቸውን እንዲዳኙ በአክብሮት አሳስባለሁ። ከጎጥ የሚመነጭ ማናቸውም መንፈስ ለብዙሃኑ ኢ- ሰብዕዊ፤ ኢ – ህጋዊ ነው። ጎጠኝነት ለጥቂት ድሎት ለብዙኃን መከራን በህግ ማረጋገጥ ነው። ስለሆነም ከጎጥ መንፈስ ጋር የሙጥኝ ያሉት ሁሉ ቁጭ ብለው እራሳቸውን ለመዳኘት ጊዜ ይኑራቸው። ደም ማዬት ስቃይ ማድመጥ ከአንገፈገፋቸው –

የሆነ ሆኖ ወንጀለኛነትን  „በማረድ“ መፍትሄ አይገኝለትም። ለዛ ሰውኛ ላልሆነ መንፈስ እራሱን ዳኛ በማደረግ እንደገና ከአራዊትነት ወደ ሰውነት በማሸጋገር በሚካሄድ ተከታታይ የመንፈስ ተግባር ነው መለወጥ የሚቻለው፤ „አራጁም“፤ ደብዳቢውም፤ ገዳዩም፤ ኮረጆ ገልባጩብም፤ ጭካኔው እራሱን እንዲደበድበው መልሶ እንዲጎርሰው ህሊናውን በሰብዕነት ተፈጥሮ መግራት፤ እንዲጸጽተው፤ እንዲያርመጠምጠው፤ እንዲወቅሰው በማድረግ ፈቃደ ህዝብ ነፃ ይወጣል። ከቀላል ጠላት ጋር አይደለም ግብግቡ – ሁሉም ካለው ዘመንተኛ ጋር ነው። ለራሳችን መልስ የሚሆነው ብቸኛው ዘዴ ከበዳዩ የጎጥ ድርጅት የተለዬ አቅምን ማሳደግ ሲቻል ብቻ ነው። ምርጫ ለአንድ ሀገር አንድ ዘላላ ጉዳይ ነው። ከዛ የገዘፉ በርካታ መንገዶች ላይ ቢተኮር የዛሬ የወያኔ ሃርነት ትግራይ መሪ ተዋናይ የነገ የአብነት አጋር ሊሆን ይችላል። ፍላጎታችን ስናዘገዬው „ዳ“ ራዕያችን በዝግመት ስናድርቀው „ቃ“ የሁሉ መከራ ተሸካሚ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ – ። ቁልምም እንዳለ ድፍት ክፍት እንዳለ እርግፍ ….

ለነበረን መልካም ጊዜ መልካሙን ተመኘሁ። መሸቢያ – ጊዜ።

  • „ማረድ“ እባካችሁን ወገኖቼ እንዲህ ያለ ጥቅርሻማ መንፈስን አታስጠጉት – መንፈሱ የባህሩ ነውና። እኔ እንጃ ሀገሬ ኢትዮጵያ ብሄድ ከእንግዲህ በኋላ ዶሮ ወይንም በግ ከፊቴ ታርዶ ደሙን አይቼ በፍጹም አልበላውም። ተመጣጣኝ እርምጃ፤ የሚመክት እርምጃ ማለትም ይቻላል …. ይህን የገሃነም ቃል ወደ ድርጊት ተለውጦ የማዬት ራዕይ ማለም ነገን አያመጣም ዛሬንም አያሰጥም።

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል። እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

The post ሰሞናቱ። ዳ እና ቃ …. appeared first on Zehabesha Amharic.

የመላው ኢትዮጵያአንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) ፕሬዝደነንት አቶ ማሙሸት አማረ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤት ውሎ

0
0

ለገሰ ወ/ሃና
Mamushet-Amare (1)የመላው ኢትዮጵያአንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) ፕሬዝደነንት አቶ ማሙሸት አማረ ፍርድ ቤት ከእስር እንዲፈታ ቢወስንም ፓሊስ ሳይፈታው ቀረ ዘሬ ሰኔ 10/10/2007 ዓም በአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርቦ በዝግ የታየው ችሎት ማሙሸት አማረ በ5000:00 ዋስ ከእስር ይለቀቅ ቀጣይ ሀምሌ 02/2007 ዓም ይቅረብ ብሎ አዟል እኛም ለዋስትና የተጠየቀውን ገንዘብ ከምሳ በፊት ገንዘቡን አስይዘን የማስፈቻ ወረቀት ብናወጣም ከህግ በላይ የሆነው ፓሊስ ግን ማሙሸትን አለቅም ብሎ ለሁለተኛ ጊዜ የፍርድ ቤት ውሳኔ ሽሮ አስሮታል በዛሬው ችሎት ዋስትና አስይዘው ይዉጡ የተባሉት ሁሉ ሲወጡ ማሙሸት ግን አልወጣም የተጠየቀውን ዋስትና አስይዘን ለምን አይለቀቅም ብለን ላቀረብነው ጥያቄ የተሰጠን መልስ ማሙሸት ይለቀቅ የሚለውን መፈረም የሚችለው ሰው የለም የሱ ጉዳይ የሚመለከታቸ ሠዎች ተመካክረው ነው የሚፈታው የሚል መልስ ሰጥተውናል በትዕዛዙ መሠረት ነገም ተጨማሪ ጥረት እናደርጋለን ፓሊስ እንዳለፈው በእንቢተኝነቱ ከፀና እስከ ሀምሌ 02/2007 ዓም ድረስ በእስር ሊቆይ ይችላል ከዛስ በኋላ ያለው ምን ታውቆ የመላው ኢትዮጵያአንድነትድርጅት ( መኢአድ ) አባላትና ቤተሰቡ ለሁለተና ጊዜ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማመን አቀባበል ለማድረግ የመጣውን ሰው አሳፍረው መልሰውናል ሁኔታው እጅግ አሳዛኝ ነበር ፡፡

The post የመላው ኢትዮጵያአንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) ፕሬዝደነንት አቶ ማሙሸት አማረ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤት ውሎ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ጥልቅ የሐዘን መግለጫ!

0
0

ethiopia-blue-party-300x164አንድ በስልጣን ላይ የተቀመጠ አካል ተቀዳሚ ተግባር የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ መሆኑን ጤነኛ አዕምሮ ያለው የሰው ልጅ የሚገነዘበው ጥሬ ሃቅ ነው፡፡ እንደ እርግማን ዛሬ በኢትዮጵያ የስልጣን እርካቡን የተቆጣጠረው ቡድን የሚገዛቸውን ዜጎች የሚያያቸው እንደጠላት እንጅ የመንግስትን ጥበቃ እንደሚፈልጉ፤ በጠላትነት የፈረጃቸው ዜጎች በከፈሉት ግብር ስልጣን ላይ መቆየት መቻሉን እንኳን ባለስልጣናቱ መረዳት ተስኗቸዋል፡፡

ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ እጅግ በሚሰቀጥጥ ጭካኔ እንደ እባብ ተቀጥቅጦ የተገደላው የሰማያዊ ፓርቲ ቆራጥ ታጋይ ሳሙኤል አወቀ የስርዓቱ አገልጋዩች ለዓመታት ሲያስፈራሩት፣ ሲደበድቡት፣ ሰርቶ የመኖር መብቱን ሲጋፉት፣ ያልተሳከ የመግደል ሙከራ በተደጋጋሚ ጊዜ ሲፈፅሙበት መቆየታቸውን የሚያረጋግጡ በርካታ ማስረጃዎች ተይዘዋል፡፡ ሳሙኤል ሕይወቱ አደጋ ላይ እንደሆነችና ጥበቃ እንዲያደርጉለት የጠየቃቸው የፀጥታና የፍትህ አካላት በተገላቢጦሽ ተጨማሪ ዛቻና ማስፈራሪያ ያደርሱበት እንደነበር አይዘነጋም፡፡ አንድ ወጣት በተወለደበት ምድር በሕይወት የቆየባቸውን ጊዚያት በስጋት እንዲኖር ከተፈፀመበት ግፍ በተጨማሪ በሕይወት የመኖር መብቱ በአረመኔዎች እጅ ስትነጠቅ የህዝብን ፀጥታና ደሕንነት እናስከብራለን የሚሉ አካላት በመሃል ከተማ እንኳን ደርሰው ለመታደግ አቅሙም ሆነ ፍላጎቱ አልነበራቸውም፡፡

ሳሙኤል በአሰቃቂ ሁኔታ ከመገደሉ በፊት በተለያዩ ጊዚያት ለሚመለካታቸው አካላትና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያስተላልፋቸው የነበሩ መልዕክቶች እንደተጠበቁ ሆነው በተለይ ግንቦት 25 2007 ዓ.ም በራሱ ገፅ በሆነው “የፌስ ቡክ” ማህበራዊ ሚዲያ ካስተላለፈው መልዕክት መረዳት እንደሚቻለው በተደራጀ ሁኔታ ሕይወቱ አደጋ ላይ እንደሆነች አስረግጦ ተናግሯል፡፡ ሆኖም የሚሰማውና የሚጠብቀው ምንም አካል እንዳልነበረ ይልቁንም ለመገደሉ ተባባሪ የሆኑ የመንግስት አካላት እንደነበሩ ስጋቱን በገለፀ በቀናት ውስጥ ሕይወቱ በአሰቃቂ ሁኔታ መቀጠፏ ጉልሕ ማስረጃ ነው፡፡

በሰላማዊ ትግል ፅኑዕ እምነት የነበረው ሳሙኤል አወቀ ይደርስበት የነበረውን ለቁጥርና ለዓይነት አታካች የሆነ በደል ተቋቁሞ፣ ትግሉን እንዲያቆም ወይም የሚወዳትን ሕይወቱን አሳልፎ የሰጠላትን ሐገሩን ለቆ እንዲሰደድ ይህ ካልሆነ ግን የእሱን ሕይወት ለማጥፋት እጅግ ቀላል መሆኑን የስርዓቱ ባለስልጣናት እና ካድሬዎች ደጋግመው ቢነግሩትም በጭቆና ስር ለሚማቅቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ የገባውን ቃል ከማጠፍ ይልቅ ሕይወቱን ለመሰዋት እንደሚቀለው የገባውን ቃል በተግባር አስመስክሮ አልፏል፡፡ በማሰርና በመደብደብ አላማውን እንደማያስቀይሩት፤ ከገደሉት ግን ቀሪ ታጋዮች በተለይም የእድሜ አቻዎቹ የሆኑ የእርሱ ትውልድ የሚሰዋለትን ዓላማ ከግብ እንዲያደርሱ “ትግሌን አደራ!! አደራ!!” በማለት ተማፅኖ አስቀምጧል፡፡

እኛም እንላለን፡፡ አደራህ ከባድ ነው፡፡ ቃልህን እናከብራለን፡፡ አላማህንም እናሳካለን!!!!

ይህ ስርዓት በህግም በሞራልም ኢትዮጵያን የማስተዳደር ብቃት የለውም፡፡ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ እያልንም አናላዝንም፤ ወንጀለኞቹ የመንግስት አካላት ናቸውና፡፡ በወንድማችንና ገና በለጋ እድሜው በተቀጨው የትግል አጋራችን ላይ የተፈፀመውን ግፍ አይቶ እንዳላዬ ዝም ያለ መንግስት ከዚህ የተሻለ መልካም ነገር ያመጣል ብለን አንጠብቅም፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግን መልዕክት አለን፡፡ እስከ መቼ በግፍ እንገደላለን?!! ሸፍጠኞችስ እስከ መቼ ይዘባበቱብናል?!! ትግል ለውጤት የሚበቃው በተወሰኑ ቡድኖች ወይም ግለሰቦች መፍጨርጨር ብቻ ባለመሆኑ የግፍ ስርዓት እንዲያበቃ ሁላችንም የሚገባንን የዜግነት ድርሻ እንድንወጣ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በአባላቱና በደጋፊዎቹ በአጠቃላይም የተለየ አስተሳሰብ ስላላቸው ብቻ በካድሬዎች የሚታሰሩ፣ የሚገረፉ፣ የሚሳደዱ፣ የሚዋረዱና የሚገደሉ ዜጎች ለከፈሉት መራራ ፅዋ ክብር ይሰጣል፡፡ መስዋዕትነታቸውም በከንቱ እንዳይሆን እሰከመጨረሻው ይታገላል፡፡

ሳሙኤል “ብታሰርም፣ ብገደልም ይህን ሁሉ የማደርገው ለሐገሬና ለነፃነቴ ነው” ያልከው ቃልህ ከመቃብር በላይ ነው!!!! ቃልህን እናከብራለን፡፡ አላማህንም እናሳካለን!!! ትግል ይቀጥላል . . .

ሰኔ 10 ቀን 2007 ዓ.ም

አዲስ አበባ

The post ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ጥልቅ የሐዘን መግለጫ! appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: የቴምር (Dates) 10 የጤና በረከቶች

0
0

dates  copy
በርካቶቻችን በብዛት የምንጠቀመው እና በተለይም በረመዳን ጾም ወቅት በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድየሚዘወተረው ቴምር በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች አሉት።

በቫይታሚን፣ ማዕድናትና የተለያዩ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ መሆኑ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዲኖሩት አስችሎታል፡፡…ለምሳሌ ያህል…

1) ስብና ኮልስትሮል፡ ከየትኛውም የኮልስትሮል ዓይነቶች የጸዳና በጣም አነስተኛ የስብ መጠን ያለው መሆኑ ክብደት መቀነስ ለሚፈልጉ ተመራጭ ነው፡፡

2) ፕሮቲን፡ ቴምር በፕሮቲንና አስፈላጊ ማዕድናት የበለጸገ መሆኑ ለሰውነት እጅጉን ጠቃሚ ያደርገዋል፡፡

3) ቫይታሚን፡ በቫይታሚን የበለጸገ ነው ቴምር፡፡ ከቫይታሚን ዓይነቶች ቢ1፣ ቢ2፣ ቢ3፣ ቢ5፣ ኤ1 እና ሲ ንም አካትቶ ይዟል፡፡

4) ሀይል እና ጉልበት፡ ቴምር ቀላል የማይባል የሀይል ክምችት ስላለውም ንቁና በሀይል የተሞላን እንድንሆን ያስችለናል፡፡

5) ፖታሲየምና ካልሲየም፡ ቴምር የፖታሲየም ክምችቱ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህም በልብ በሽታ እንዳንጠቃና አካላችን ውስጥ ያለው የኮልስትሮል መጠን እንዲቀንስ ይረዳል፡፡ ቴምር በአንጻሩ አነስተኛ የሶዲየም መጠን ነው ያለው፡፡ ብዙ ፖታሲየምና ትንሽ ሶዲየም ደግሞ ለጤናማ የነርቭ ስርዐት ወሳኝ ነው፡፡

6) ብረት፡ ቴምር በብረትና በፍሎሪን የበለጸገ መሆኑ ደግሞ ብረቱ የብረት ማዕድን እጥረት ላለባቸው ሰዎች፣ ፍሎሪኑ ደግሞ ጥርስን ከመበስበስ ይከላከላል፡፡

7) ድርቀት፡ ለድርቀትም ቢሆን ውሀ ውስጥ የተነከረ ቴምር መመገብ ፍቱን እንደሆነ ይታወቃል፡፡

8) ሰውነትን ማጽዳት፡ በአልኮል መጠጣት ሳቢያ ሰውነት ውስጥ የሚከማቸውን መርዛማ ኬሚካሎች ከሰውነታችን ውስጥ በማስወገድም ይረዳል – ቴምር !

9) ካንሰር እና የዓይን ችግር፡ የዓይን ህመም ችግርንና የሆድ ነቀርሳ (ካንሰር)ን ለማከምም ብቃት እንዳለው ይታወቃል – ቴምር፡፡

10) (የቆዳ ችግር) ቴምር የቆዳ ችግሮችን በማስወገድም መልካም ዝና አለው፡፡ ጸጉርን በማፋፋት የጸጉር መሳሳትንም ይከላከላል፡፡

በርከት ያሉ ቪታሚኖችን እና ሚኔራሎች በመያዙ ለጤናችን በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ይነገርለታል። ሀይል ሰጪ፣ ፋይበር፣ እንዲሁም ካልሺየም፣ አይረን፣ ፎስፈረስ፣ ሶዲየም፣ ፖታሲየም፣ ማግኒዚየም፣ እና ዚንክ ሚኔራሎች በቴምር ውስጥ የሚገኙ በመሆኑ ቴምርን ለጤና ጠቃሚ ያደርጉታል። ስለዚህም ቴምርን አዘውትረን መመገብ ለጤናችን ከሚሰጠው ጠቀሜታዎች ውስጥም፦
የሆድ ድርቀትን ይከላከላል
ቴምር በባህሪው የማለስለስ ባህሪ ስላለው ምግብ በአንጀታችን ውስጥ በቀላሉ እንዲዘዋወር በማድረግ የሆድ ድርቀት ለመከላከል ይረዳል። ለዚህም ይረዳን ዘንድ ቴምሩን በውሃ
ውስጥ ዘፍዝፈን በማሳደር ጠዋት ላይ መመገብ ይመከራል።

ለአጥንት ጤንነት እና ጥንካሬ
በቴምር ውስጥ የሚገኙት ሚኔራሎች ለአጥንታችን ጥንካሬ እና ጤነነት እጅጉን ጠቃሚ እንደሆኑ ይነገራል። ቴምር እንደ ሴሌኒየም ማንጋኒዝ፣ ኮፐር እና ማግኒዚየም ማእድናትን በውስጡ በመያዙም ለአጥንት ጤናማ እድገት እና ጥንካሬ ጠቃሚ ነው።

ደም ማነስን ይከላከላል

ቴምር በውስጡ በያዘው ከፍተኛ የምግብ ማእድናት ንጥረ ነገቾች ክምችት የደም ማነስ ችግር ላለባቸው ሰዎች እጅጉን ጠቃሚ ነው።

አለርጂን ይከላከላል
ቴምርን ከሌሎች ለየት የሚያደርገው አለርጂን ለመከላከል የሚረዳውን ሰልፈር ንጥረ ነገር በውስጡ በመያዙ ነው። ስለዚህም ቴምርን አዘውትረን የምንመገብ ሰዎች ለተለያዩ አይነት አለርጂዎች የመጋለጥ እድላችን እጅጉን እንዲቀንስ እንደሚያደርገው ይነገርለታል።

ለነርቭ ጤንነት

በቴምር ውስጥ የሚገኙት ቪታሚኖች የተስተካከለ እና ጤናማ የነርቭ ስርዓት እንዲኖረን ስለሚያደርግም ለጤናችን ጠቃሚ ያደርገዋል።

ለልብ ጤንነት
ቴምር ለልባችን ጤንነት በርካታ ጠቀሜታዎች ስላሉት ተመራጭ ያደርገዋል።

ቴምር የልብ ጤንነትን ይጎዳል የሚባለውን የኮሌስቴሮል መጠን የመቀንስ እቅም ስላለው ለድንገተኛ የልብ ህመም እንዳንጋለጥ በመርዳትም ለልባችን ጤንነት ጠቀሜታ አለው።
ስንፈተ ወሲብን ይከላከላል

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ቴምር በውስጡ በያዘው ንጥረ ነገሮች አማካኝነት የሰዎችን የወሲብ ፍላጎት ከፍ እንዲል እና የወሲብ ፍራቻ ላለባቸው ሰዎች ድፍረትን እንዲያገኙ በማድረግ ስንፈተ ወሲብን ለመከላከል ይረዳል።

በእርግዝና እና ወሊድ ወቅት ተመራጭ ምግብ ነው

ቴምር በእርግዝና ወቅት ለጽንሱ ጤንነት ብሎም በወሊድ ጊዜ ምጥ አስቸጋሪ እንዳይሆንና የተሻለ የማማጥ አቅም እንዲኖረን ያስችላል።

የአዕምሯችንን ጤንነት ያሳድጋል
ጥናቶች በቴምር የምናገኘው ቫይታሚን ቢ6 የተሻለ የአዕምሮ ተግባራት እንዲኖርና ሰዎች በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘገቡ ማገዙን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ http:// naturalsociety.com

The post Health: የቴምር (Dates) 10 የጤና በረከቶች appeared first on Zehabesha Amharic.

ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው የታሰሩት 7 የዓየር ኃይል አባላት ነገ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው

0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል የሽብርተኝነት ክስ የቀረበባቸው ሰባት የአየር ኃይል አባላት ነገ ሰኔ 12/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ይቀርባሉ፡፡
ethiopian airforce
አቃቤ ህግ በሰኔ 7/2007 ዓ.ም ባቀረበባቸው ክስ ላይ እንደተመለከተው፣ ተከሳሾቹ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 32(1)(ሀ)ን እና የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጅ አንቀጽ 7(1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በሽብተኝነት ተከስሰዋል፡፡ በክሱ የተመለከቱት ተከሳሾች የሚከተሉት ናቸው፣

1ኛ. መ/አ ማስረሻ ሰጤ……አድራሻ ድሬዳዋ
2ኛ. መ/አ ብሩክ አጥናዬ……. ›› ድሬዳዋ
3ኛ. መ/አ ዳንኤል ግርማ…… ›› ድሬዳዋ
4ኛ. ገዛኸኝ ድረስ………. ›› ድሬዳዋ
5ኛ. ተስፋዬ እሸቴ…….. ›› ምስራቅ ጎጃም
6ኛ. ሰይፉ ግርማ……. ›› አዲስ አበባ
7ኛ. የሻምበል አድማው…… ›› ምስራቅ ጎጃም፣ ናቸው፡፡

በአቃቤ ህግ ክስ ላይ እንደተመለከተው ተከሳሾች ‹‹….ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል የማፈራረስ ዓላማ ይዘው ….በሽብር ድርጅት ውስጥ አባል በመሆንና በሽብር ድርጅት ተግባር ላይ ለመሳተፍ በማሰባቸው….›› የሽብርተኝነት ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡

ተከሳሾች ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል በመክዳት ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ሊያመሩ ሲሉ ባህር ዳር እና ጎንደር ላይ እንደተያዙ በክሳቸው ላይ የተመለከተ ሲሆን፣ በአጠቃላይ የሽብር ድርጅት አባል በመሆን፣ ተልዕኮ በመቀበል፣ አባላትን በመመልመል እና መረጃ በማቀበል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡
የአየር ኃይል አባላት ተከሳሾቹ በነገው ዕለት አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ክስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ተከሳሾች ለወራት ከቆዩበት ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ወጥተው በአሁኑ ወቅት ቂሊንጦ እስር ቤት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

The post ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው የታሰሩት 7 የዓየር ኃይል አባላት ነገ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live