Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ሕወሃት አይኑን በጨው አጥቦ፣ ራሱ መራጭ፣ ራሱ ተመራጭ፣ ራሱ ታዛቢ፣ ራሱ ምርጫ ቦርድ (ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበራት የተሠጠ መግለጫ)

0
0

አንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበር

ANDENET NORTH AMERICA ASSOCIATION OF SUPPORT ORGANIZATION

     8121 Georgia Avenue, Silver Spring, MD 20910 ste 10, Tell: (301) 585-7700

ሰኔ ፲, 2007 ዓ/ም (June 12, 2015)

udjየደርግ ስርዓት ሲገረሰስ  ሕወሃት/ኢሕአዴግ የዲሞክራሲ ስርዓት እንደሚገነባ ቃል ገብቶ ነበር። ሆኖም፣ ይኸው ሃያ አራት አመታት አለፈ፤ ኢትዮጵያዉያን የግፍ ቀንበር በላያቸው ላይ ተጭኖ፣ መብታቸዉንና ነጻነታቸውን ተገፈው፣ በአገራቸው በፍርሃትና በሰቀቀን እየኖሩ ነው። ምንም እንኳን እጅግ በጣም ጥቂት የሆኑ የስርአቱ ተጠቃሚዎች ቢከብሩም፣ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የኑሮ ዉድነት፣ ዜጎችን ከቅያቸው የማፈናቀል ተግባራት፣ አድልዎና ዘረኝነት፣  ከጊዜ ወደ ጊዜ ኢትዮጵያን ለብዙዎች ሲኦል እያደረጋት ነው።

ምርጫ ዜጎች ልዩነቶቻቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የሚረዳ እንደመሆኑ አገር ቤት ያሉ የሰላማዊ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ምርጫውን ተጠቅመው ለዉጥ ለማምጣት  በርካታ እንቅስቃሴዎችን አድርገዋል። ሆኖም አገዛዙ  የፖለቲካ ምህዳሩን በማጥበብ ከፍተኛ ጫና እያደረገ አላሰራ እንዳላቸው የአደባባይ ሚስጠር ነው። ጫና ከማሳደር ባለፈም፣ የሚዘረጋበትን መሰናክል በማለፍ፣ ጠንካራ ድርጅታዊ መዋቅር የዘረጋዉንና  በሕዝቡ  ዘንድ በሁሉም ክልሎች ተቀባይነት ያገኘውን የአንድነት ፓርቲ፣ አገዛዙ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ እስከማገድም ደርሷል። ብቸኛ ተቀናቃኝ የሆነዉን እና ምርጫውን ሊያሸንፍ የሚችል ድርጅት በታገደበት ሁኔታ የተደረገ ምርጫ ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም። በምርጫው ወቅትም፣  ምርጫ ሳይሆን የድምጽ ዘረፋ በይፋ እንደደተደረገ፣ የምርጫ ጣቢያዎች የጦርነት ቀጠና ይመስሉ እንደነበረ፣ ኮረጆዎች እንደተገለበጡ በስፋት ተዘግቧል።  ምርጫዉን የአዉሮፓ ሕብረትም ሆነ የካርተር ማእከል ያልታዘቡት ሲሆን፣ የአሜሪካን ኤምባሲም የምርጫውን ሂደት ለመከታተል ሰራተኞች ለመላክ ቢጠይቅም ፍቃድ አላገኝም። በብዙ ቦታዎች የተቃዋሚ ፓርቲ ታዛቢዎች አልተገኙም። በተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች የታዘበው፣ የአገዛዙ አጋር ተደረጎ የሚቆጠረው የአፍሪካ ሕብረት ታዛቢዎች ሁሉ ሳይቀሩ፣  ምርጫው ሰላማዊ ነበር ቢሉም፣  ነጻና ዴሞክራሲያዊ እንዳልሆነ አረጋግጠዋል።

ሕወሃት አይኑን በጨው አጥቦ፣ ራሱ መራጭ፣ ራሱ ተመራጭ፣  ራሱ ታዛቢ፣ ራሱ ምርጫ ቦርድ ፣ ራሱ ፖሊስ፣ ራሱ ዳኛ  ሆኖ  ባደረገው የምርጫ ድራማ፣ መቶ በምቶ አሸነፍኩም ብሎ አውጇል። የሕወሃት ቅርንጫፍ የሆኑት የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎችም  የምርጫው ዉጤት አለመቀበል በሕግ እንደሚያስቀጣ በመግለጽ እያስጠነቀቁ ነው።ሆኖም፣ የብዙ ድርጅቶች ግንባር የሆነው መድረክ፣ ኢዴፓ፣ ሰማያዊ፣ መኢአድ እና ኢራፓ ምርጫውን እንደማይቀበሉ  በይፋ አሳወቀዋል።

አገር ቤት ያሉ ድርጅቶች፣ በምርጫውው ሂደት ላበረከቱት አስተዋጾና  ለከፈሉትን መስዋትነት ያለንን አክብሮት እየገለጽን፣  ምርጫውን እንደማይቀበሉ በመግልጽ የወሰዱትን አቋም እንደምንደገፍ ለመገልጽ እንወዳለን። እኛም ከዚህ ምርጫ የሚገኝ ምንም አይነት ሕጋዊነት እንደሌለ በማስረገጥ፣ ሕወሃት ያለ ህዝብ ፍቃድ በጉልበት የሚገዛ ግፈኛ አገዛዝ እንደመሆኑ  የምንታገለው መሆናችንን እናረጋግጣለን።

አለም የትናይት በደረሰበችበት፣ በቅኝ ግዛት ሥር የነበሩና እኛ ስንረዳቸው የነበሩ እንደ ጋናና ናይጄሪያ ያሉ አገራት  የዲሞክራሲና የነጻነት አየር እየተነፈሱ ባለበት ዘመን፣ ሕወሃት መቶ በመቶ አሸነፍኩ ብሎ ማወጁ፣  ምን ያህል ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ ንቀት እንዳለው በግልጽ ያመላከተ ሲሆን፣  ይሄን ሕዝብን የሚንቅ አገዛዝ የመሸከም ትከሻ ማንም ኢትዮጵያ ሊኖረው  አይገባም ብለን እናምናለን።በመሆኑም ለዉጥ እንዲመጣ የለዉጥ እንቅስቃሴን ለማገዝ ማድርረግ ያለብንን ሁሉ ለማድረግ ቁርጠኝነት እንዳለን ልናረጋግጥ እንወዳለን።

አገር ቤት ያሉ ድርጅቶች፣  ትግሉ የርዮት አለም ሳይሆን የነጻነት መሆኑን ተረድተው፣  ኃይላቸውን በማስተባበር በጋራ እንዲንቀሳቀሱም በአጽንኦት እናሳስባለን። ተመሳሳይ ፕሮግራሞች  ያላቸው ወደ ዉህደት፣ ካልሆነም ደግሞ መስማማት በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ የጋራ ግንባር በመፍጠር፣  መግለጫ ከማውጣትና ብሶት ከማውራት አልፎ በመሄድ፣  ስርአቱን የሚያስጨንቅ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ወደ ማድረግ እንዲሸጋገሩ እየጠየቀን፣ በማንኛው  ጊዜ በጋራ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ኢትዮጵያዊ አጋርነታንን እንደማይለያቸው ቃል እናሳውቃለን።

 

ድል ለኢትዬጵያ ሕዝብ!

የአንድነት ድጋፍ ማህበሮች በሰሜን አሜሪካ አስተባባሪ ኮሚቴ

 

The post ሕወሃት አይኑን በጨው አጥቦ፣ ራሱ መራጭ፣ ራሱ ተመራጭ፣ ራሱ ታዛቢ፣ ራሱ ምርጫ ቦርድ (ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበራት የተሠጠ መግለጫ) appeared first on Zehabesha Amharic.


በቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለም ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት አባላት በዋና ሥራ አስኪያጅ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ጥያቄ እየታሰሩ ነው

0
0
  •   በጥያቄአቸው፣ በአስተዳደር ይኹን በልማት ሥራ ምንም ችግር የለም ብለዋል፤ በሌለ ልማት!
  • ምእመናኑንም ‹‹ምንም ዓይነት ድርሻ የሌላቸውና ማንነታቸው የማይታወቅ›› ሲሉ ገልጸዋቸዋል
  • የታሰሩት ምእመናን በፖሊስ ጣቢያ ‹‹ማዕተባችኹን በጥሱ መስቀላችኹን አውልቁ›› ተብለዋል
  • የቀድሞው የደብሩ አለቃ ዘካርያስ ሓዲስና ኃይሌ ኣብርሃ ከውዝግቡ ለማትረፍ እያሰሉ ነው

bole bulbula medየቤተ ክርስቲያን ይዞታ ከቤተ ክርስቲያን አቋም ጋር በሚስማማ እና ሀብቷን በሚያስጠብቅ አኳኋን እንዲለማ በመጠየቅ በቅንጅት የተንቀሳቀሱ የቦሌ ቡልቡላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ደብር ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት አባላትበሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጥያቄ እየታሰሩ እና ለእንግልት እየተዳረጉ ነው፡፡

ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ለቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና በክፍለ ከተማው ለወረዳ 12 ፖሊስ ጣቢያ በጻፉት ደብዳቤ፣ በምእመናኑ እና የሰንበት ት/ቤት አባላቱ ተበይዶ የታሸገው የደብሩ ቢሮዎች በፖሊስ ርምጃ እንዲከፈቱ ምእመናኑም በወንጀል ድርጊት እንዲጠየቁ አመልክተዋል፡፡

ጥያቄአቸውን ተከትሎ ባለፉት ኹለት ቀናት ከኻያ የማያንሱ ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት አባላት መታሰራቸው ታውቋል፡፡ ትላንት እና ከትላንት በስቲያ ታስረው ከተለቀቁት ውጭ እስከ አኹን በእስር የሚገኙ ስምንት ምእመናን (አራት ምእመናን እና አራት የሰንበት ት/ቤት አባላት) በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ተገልጧል፡፡ ከታሳሪዎቹ መካከል ደብሩን በስብከተ ወንጌል ሲያገልግሉ ቆይተው በጡረታ የተገለሉ የ70 ዓመት ሕመምተኛ አዛውንት ይገኙበታል፡፡ ወደ ፖሊስ ጣቢያው ሲገቡ በአዛዡ ‹‹ማዕተባችኹን በጥሱ፤ መስቀላችኹን አውልቁ›› መባላቸውን ከእስር የተፈቱት ምእመናን ተናግረዋል፡፡

በደብሩ የልማት እና የመካነ መቃብር ይዞታዎች የሚገኙ የንግድ ቦታዎች እና ሱቆች ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ግለሰቦችን በሚጠቅም አኳኋን በከፍተኛ ዋጋ እየተከራዩ ባለበት ኹኔታ የደብሩ ገቢ እና ልማት እየተዳከመ መምጣቱ በምእመናን እየተገለጸ እና ይኸውም በጠቅላይ ቤተ ክህነት የአስተዳደር ጉባኤ በተሠየመ አጥኚ ቡድን ተረጋግጦ እርምት እንዲደረግ ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ቢሰጥም፣ ዋና ሥራ አስኪያጁ በደብሩ የአስተዳደር ይኹን የልማት ሥራዎች ምንም ዐይነት ችግር እንደሌለ ነው በደብዳቤአቸው የጠቀሱት፡፡

በሌላ በኩል ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ‹‹ችግር አለ ተብሎ የሚታሰብ ከኾነ ሊፈታ የሚችለው በሀገረ ስብከቱ ነው›› ቢሉም በትላንትናው ዕለት በጽ/ቤታቸው ላነጋገሯቸው 12 የምእመናን ተወካዮች፣ ‹‹አያገባኝም፤ የጻፍኹትም ደብዳቤ የለኝም፤ ሰንበት ተማሪ አድርግ የሚባለውን ከማድረግ በቀር ሌላ ሥልጣን የለውም›› ብለው እንደመለሷቸው ምእመናኑ በከፍተኛ ሐዘን ገልጸዋል፡፡

ዋና ሥራ አስኪያጁ ሊቀ ማእምራን የማነ፣ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የምእመናን እና የሰንበት ት/ቤቶች ሚና yemane zemenfes‹‹አድርጉ የተባሉትን ብቻ ከማድረግ ያለፈ አይደለም፤ ልካቸውን ሊያውቁ ይገባል››በሚለው ንቀት የተመላበት ንግግራቸው ይታወቃሉ፡፡ በዚኽም ደብዳቤአቸው ምእመናኑን ‹‹በቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር ምንም ዐይነት የሥልጣን ድርሻ የሌላቸውና ማምነታቸው የማይታወቅ›› ሲሉ ነው የገለጧቸው፡፡ አካሔዱን አላርምም ባለው የደብሩ አስተዳደር ላይ የቤተ ክርስቲያንን ሀብት ለማስጠበቅ እና ተጠቃሚነቷን ለማረጋገጥ በማስገዳጃነት የወሰዱትንም ርምጃ፣ ‹‹የቤተ ክርስቲያንን መብት የሚጋፋ እና በቤተ ክርስቲያን ላይ የተፈጸመ በደል ነው››ብለውታል፡፡

በዋና ሥራ አስኪያጁ ‹‹ማንነታቸው አይታወቅም›› የሚባሉት ምእመናን ግን የደብሩ አስተዳደር በየምክንያ የሚጠይቀውን ድጋፍ ከመስጠት የማይሰስቱ እና በበጎ አድራጎታቸው የሚታወቁ ናቸው፡፡ ልማት በሚል ለሦስተኛ ወገን እየተላለፈ በአስተዳደሩ የሚሰበስበው በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠር ወርኃዊ ገቢም ሓላፊዎቹንና ግለሰቦችን ከመጥቅም በቀር በተጨባጭ የሌለ ለመኾኑ ‹‹በደብሩ አካውንት ያለው ተቀማጭ ማሳያ ነው፤ ባዶ እጁን የመጣ መኪና ገዝቶ እየወጣ ነው››ይላሉ – ምእመናኑ፡፡

ምእመናኑን በመረዳት ችግሩን በትክክለኛ ገጽታው ተመልክቶ ከመፍታት ይልቅ ‹‹ልማቱን ለማስቀጠል›› በሚል እንዲታሰሩና በወንጀል ድርጊት እንዲጠየቁ ዋና ሥራ አስኪያጁ የወሰዱት ርምጃ ከአማሳኞች ጋር በተግባር ያልተፋቱ ለመኾናቸው ማረጋገጫ ነው፡፡ ለዚኽም ነው የቤተ ክርስቲያንን መብት ለማስጠበቅ ከተንቀሳቀሱት ምእመናን ይልቅ በእንቅስቃሴው ጥቅማቸውን ካጡ ተከራዮች ጋር ዳኝነት የተቀመጡትንና በውዝግቡ አጋጣሚ እንዴት እንደሚያትርፉ የሚያሰሉትን አማሳኝ ባለሟሎቻቸውን – የቀድሞው የደብሩ አስተዳዳሪ ዘካርያስ ሐዲስን እና ቀንደኛው ሌባ ኃይሌ ኣብርሃን እየሰሙ የሚገኙት፡፡

በሀ/ስብከቱ ሥር በሚገኙ 69 ገዳማት እና አድባራት የመሬት፣ የሕንፃ፣ የመካነ መቃብር ኪራይ እና የመኪና ሽልማት ጉዳዮችን አጥንቶ የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያቀርብ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ የተቋቋመው ኮሚቴ ጥር ፳፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ባቀረበው ሪፖርት፣ የደብሩ አስተዳደር ሱቆችንና ሰፊ ቦታዎችን በሕገ ወጥ መንገድ በማከራየት የቤተ ክርስቲያንን ጥቅም አሳልፎ መስጠቱን አረጋግጧል፡፡ የደብሩ አስተዳደር የቀሩትን ባዶ ይዞታዎች በማከራየት ሕገ ወጥ አካሔዱን ሊቀጥል እንደሚችል የጠቆመው ሪፖርቱ፣ በሀገረ ስብከቱ በኩል ጥብቅ መመሪያ እንዲሰጠው ጠይቆ ማሳሰቢያው እንደተላለፈ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

እንደ ቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለም ባሉ አድባራት ሰፊ ይዞታዎች ላይ ዐይናቸውን የጣሉት የዋና ሥራ አስኪያጁ የሙስና ባለሟሎች እነኃይሌ ኣብርሃ፣ ዘካርያስ ሐዲስ እና ተስፋ ፍሥሓ በልማት ስም በሚካሔዱ ግንባታዎች በየደብራቸው ያካበቱትን የዘረፋ ልምድ የሚያስፋፉበት ስልት ሲቀይሱ፣ ዋና ሥራ አስኪያጁም በልማት ስም በየአድባራቱ ጉብኝት እያካሔዱ እንደኾነ ተጠቁሟል፡፡ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነትን የመልካም አስተዳደር፣ የፍትሕ እና የዕቅበተ እምነት ንቅናቄ በተለያዩ ክሦች ለማዳፈን በመቶ ሺሕ ብሮች(እስከ ብር አምስት መቶ ሺሕ) መድበው የሚንቀሳቀሱትም ለዚኽ ነው፡፡

ይኹንና የአማሳኞች በደል እና የፍትሕ ዕጦት ያንገሸገሻቸው የአጥቢያው ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤቶች ግንቦት ፴ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የጽ/ቤቱን ቢሮዎች በይደው በማሸግ፤ የአድባራቱን ሓላፊዎች በማባረር እና መኪኖቻቸውን በመቆጣጠር የያዙት አቋም ንቅናቄውን አንድ ርምጃ ወደፊት ያራመደ፤ ችግሩ በሚጠይቀው ልክ ለመሥዋዕትነት የተዘጋጁ፤ የታዘዙትን ብቻ የሚፈጽሙ ሳይኾኑ መልሰው እንደሚጠይቁም ያሳዩበት ኾኗል፡፡

*          *          *

The post በቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለም ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት አባላት በዋና ሥራ አስኪያጅ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ጥያቄ እየታሰሩ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

የአላሙዲና የአርቲስት ማህደር አሰፋ ግንኙነት አደባባይ መታየት ጀምሯል (ፎቶ ይዘናል)

0
0

(ዘ-ሐበሻ) ሼህ መሃመድ አላሙዲ ከአርቲስት ማህደር አሰፋ ጋር ግንኙነት ጀምረዋል የሚለው ወሬ ሲወራ ከቆየ ሰንበትበት ብሏል:: በተለይም ማህደር ለትዳር ከምታስበው ጓደኛዋ ጋር ከተለያየች በኋላ ብዙ ጊዜ ከሼኩ ጋር ታይታለች:: በትናንትናው ዕለት ደግሞ ይህን የሁለቱ ግንኙነት በአደባባይ ታይቷል:: የአርቲስት ማህሙድ አህመድ 50ኛ ዓመት የሙዚቃ አገልግሎት ዘመን ሲዘከር አላሙዲና ማህደር በሕዝብ ፊት ወጥተው እየተቃቀፉ ሲደንሱ ታይተዋል:: ይህም ፎቶ ለዘ-ሐበሻ ደርሷል – በጨለማ ውስጥ የተነሳ በመሆኑ ለፎቶው ጥራት ይቅርታ::
alamudi

alamudi

alamudi and mahder

alamudi and mahder asefa

 

 
Mahder asefa

The post የአላሙዲና የአርቲስት ማህደር አሰፋ ግንኙነት አደባባይ መታየት ጀምሯል (ፎቶ ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.

የእስክንድር ነጋ መልዕክት ከቃሊቲ እስር ቤት –“ለህዝባዊ እምቢተኝነት ሁኔታዎች ተመቻችተዋል”

0
0

የእስክንድር ነጋ መልዕክት ከቃሊቲ እስር ቤት

በሰላማዊ ትግል ውስጥ ሁለት አብይት የትግል ስልቶች አሉ፡፡ አንደኛው ገለልተኛ የዴሞክራሲ ተቋማትና ህግጋት ባሉበት ነባራዊ ሁኔታ የሚደረግ ህዝብን ያሳተፈ ምርጫ ነው፡፡ ምርጫ ሲባል ዝም ተብሎ ለማስመሰልና የአምባገነኖችን የስልጣን እድሜ ለማራዘሚያነት የሚደረገውን አይጨምርም፡፡ ምርጫ ሲባል ዓለም አቀፍ መመዘኛዎች ያሉት ነው፤ መመዘኛዎችን ባሟላ መልኩ የሚደረግ ምርጫ፣ ምርጫ ሊባል ይችላል፡፡
Eskinder-Nega
አምባገነን ስርዓቶች ምርጫ ሲያደርጉ አስተውለናል፤ ግን የይስሙላ ነው፡፡ ግብጽ በሙባረክ ጊዜ ምርጫ ታደርግ ነበር፡፡ ብዙ አምባገነኖች ምርጫ አደረግን ይላሉ፡፡ ኢህአዴግም ምርጫ አደረግሁ ይላል፡፡ በእነዚህ ስርዓቶች የተደረጉት ምርጫዎች ግን ዴሞክራሲያዊ ሆነው አላየናቸውም፡፡ በዚህ ምክንያት ምርጫን እንደ ሰላማዊ የትግል ስልት አማራጭ አድርገው ይመለከቱ የነበሩ ዴሞክራሲያዊ ኃይላት ፊታቸውን ወደ ሌላኛው ስልት እንዲያዞሩ ይገደዳሉ፤ እሱም ህዝባዊ እምቢተኝነት ነው፡፡ በግብጽ የሆነው ይኸው ነው፡፡

አንድ ነገር ማስተዋል አለብን…የምርጫ ስልት ተዘጋ ማለት ሰላማዊ ትግል አበቃለት ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንስ ወደሌላኛው ምዕራፍ ተሸጋገረ ማለት እንጂ፡፡ ምርጫ ሲያበቃለት ህዝባዊ እምቢተኝነት አማራጭ ይሆናል፡፡ አሁን በኢትዮጵያ ሁኔታዎች ለህዝባዊ እምቢተኝነት ተመቻችተዋል፡፡ አሁን ህዝቡ በምርጫ ላይ ያለውን አሰራር አስረጅ ሳያስፈልገው ራሱ አይቶታል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በኋላ አማራጩ ህዝባዊ እምቢተኝነት እንደሆነ መገንዘብ ግድ ይለናል፡፡ ህዝባዊ እምቢተኝነት ህጋዊና ሰላማዊ የትግል ስልት መሆኑን ዓለም ይገነዘባል፡፡

በዚህ ወቅት ስለህዝባዊ እምቢተኝነት የሚሰሩ አካላት ካሉ መንገዳቸው ልክ ነው፤ ሊገፉበትም የሚገባ ነው፡፡ በእርግጥ ህዝባዊ እምቢተኝነት ላይ በቅድሚያ መግባባት ላይ መድረስ ያለባቸው አካላት አሉ፣ ዋነኛዎቹ ‹አክቲቪስቶች› ናቸው፡፡ አክቲቪስቶች መግባባት ላይ ደርሰው ህዝቡን የማነቃነቅ ስራቸውን በጋራ ቢያከናውኑ አንድነቱን ያጠናከረ እንቅስቃሴ መተግበር ይቻላል፡፡

እስካሁን በተገለጸው የ2007 ‹‹ሀገራዊ ምርጫ›› (በትምህርተ ጥቅስ አስገባልኝ) ውጤት እጅግ ደስተኛ ነኝ፡፡ አዎ፣ የተለያየ ፍላጎትና ጥቅም ያላቸው ኢትዮጵያውያን በሙሉ ተስማምተው አንድ ፓርቲ መረጡ ቢባል ለሰሚውም ቀልድ ነው፡፡ ይህ ተፈጥሯዊ ያልሆነ ውጤት ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው ኢህአዴግ ለማጭበርበር እንኳ አቅም እንዳጠረው ነው፡፡ ለዚህም ነው በውጤቱ ደስ የተሰኘሁት፡፡ ውጤቱ በግልጽ የሚነግረን ከዚህ በኋላ ለሚመጣው ህዝባዊ እምቢተኝነት ዋናው ገፊ ምክንያት ኢህአዴግና የኢህአዴግ ስርዓት መሆኑን ነው፡፡ እናም ህዝባዊ እምቢተኝነት በኢትዮጵያ ‹ጀስቲፋይድ› ነው፡፡

በእርግጥም አሁን ያለው የኢህአዴግ ስርዓት ለራሳቸው ለኢህአዴግ አባላት እንኳ አሳፋሪ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ የማስመሰል ካባው እንኳ አላስፈለገውም፤ ሁሉንም ነገር ከርችሞታል፡፡ እናም ቀጣዩ ትግል የነጻነት ትግል ነው፡፡ ይህን የነጻነት ትግል ዳር የሚያደርሰው ማሳረጊያ ደግሞ ህዝባዊ እምቢተኝነት እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ህዝባዊ እምቢተኝነት ኢህአዴግ ራሱ መርጦ ለህዝቡ የተወው እንደሆነ መረዳት አለብን፡፡ የታፈነ ህዝብ ሲነሳ ማዕበል ነው፣ አምባገነኖችን ይጠራርጋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አፈና ህዝባዊ እምቢተኝነት አይቀሬነቱን በግላጭ ያረጋግጣል፡፡

The post የእስክንድር ነጋ መልዕክት ከቃሊቲ እስር ቤት – “ለህዝባዊ እምቢተኝነት ሁኔታዎች ተመቻችተዋል” appeared first on Zehabesha Amharic.

መሪ ያጣ ሕዝብ ምን ያድርግ  – ይገረም አለሙ

0
0

በዘሀበሻ ገጽ ላይ የተነበበ አንድ ጽሁፍ ለወያኔ አገዛዝ መራዘም የሕዝብ ድክመት እንደሆነ በመግለጽ ተራበ ተጠማ ተጨቆነ ወዘተ ተብሎ ሊጮኸለት እንደማይገባ ገልጾ ለሕዝብ ሲሉ መስዋዕትነት የከፈሉም ሆነ እየከፈሉ ያሉ ለማን ብለው ነው በማለት ይጠይቅና መስዋዕት ሊሆኑለት የማይገባ ሕዝብ ነው ወደሚል ድምዳሜ ያመራል፡፡

follow-leaderየጽሁፉ መነሻ ምክንያትም ሆነ መድረሻ ድምዳሜ ትክክል ሆኖ ስላልተሰማኝና ራስን ከሕዝብ አካልነት ለይቶ ሕዝቡ እያሉ መውቀስና ተጠያቂ ማድረግ በተለያየ ግዜ ከተለያየ ሰዎች የሚሰማ በመሆኑ ሀሳብ የምናቀርበው ከምር ለውጥ ከመሻት ከሆነ ጉዳዩን እንነጋርበት ዘንድ የበኩሌን ለማለት ፈለግሁ፡፡ በርግጥ ሕዝቡ ተወቃሽ ተከሳሽ ነው? የዚህ አይነት ሀሳብ ባለቤቶችስ እነርሱ የሚወቅሱት ሕዝብ አካል አይደሉም? በተለመደው ተራ የመዘላለፍ ስሜት ሳይሆን ለመማርና ቁም ነገር ለማትረፍ እንነጋገር፡፡

በየትኛውም ዘመን በማናቸውም ሀገር በሰላማዊም መንገድም ይሁን በጦር ሕዝብ በአንድ ግዜ ተነስቶ ሥርዐት የቀየረበትና ከአገዛዝ የተላቀቀበት ታሪክ የለም፡፡ መነሻ ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምን (ሥልጣን መፈለግ፡በጭቆና መማረር፤ለሕዝብ አለኝታ መሆን፤ለውጥ መሻት ወዘተ) ጥቂት ግንባር ቀደሞች ዓላማ አልመው፤ እቅድ አውጥተው፤ ስትራቲጂ ቀይሰው ትግል ይጀምራሉ ሕዝቡን ያስተባብራሉ፡፡ ይህም ሆኖ መላው ሕዝብ ተከታያቸውም ሆነ ደጋፊያቸው አይሆንም ሊሆንም አይችልም፡፡

የተሻለ ድጋፍ ለማግኘትና ትግልቸውን ለውጤት ለማብቃት ታጋዮቹ እቅድ ዝግጅታቸውም ሆነ የተግባር እንቅስቃሴያቸው የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ የህብረተሰቡን ባህል፤ ታሪክና ስነ-ልቦና እንዲሁም የሚታገሉትን ኃይል ማንነትና ምንነት ብሎም ሥልጣኑን ለማስጠበቅ ሲል እስከምን ድረስ ሊሄድ እንደሚችል ወዘተ ያጤነ መሆን አለበት፡፡

በዚህ መልኩ የተደራጁና የሚያምናቸውና ተስፋ የሚጥልባቸው ፓርቲዎችም ሆነ ግንባር ቀደም ግለሰቦች በማጣቱ ተስፋ ያደረገባቸውም ብቅ ብለው የሚጠፉ፤ ሳያብቡ የሚቀጠፉ እየሆኑበት ተቸግሮ ያደርገው አጥቶ በሚኖርበት ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊወቀስ ሊከሰስ አይገባም፡፡ ሌላው ሌላው ቢቀር በ1997 ምርጫ የታየው የሕዝብ ትግል ምንግዜ ተረስቶ ነው ሕዝቡ መስዋዕትነት ሊከፍሉለት የማይገባ እስከመባል የሚደረሰው፡፡

ከራስ በላይ ማሰብ የተሳናቸው ለሥልጣን ጥማቸው እንጂ ለሕዝብ ስቃይ ቅድሚያ መስጠት አልሆንልህ ያላቸው ፖለቲከኞች የሚያብጡትን ፖለቲካ መልክ በማስያዝ፤ ወያኔ የሚያላግጥበትን ምርጫ የምር ምርጫ ለማድረግ የቆረጡ ጥቂት ምሁራን የጎሪጥ የሚተያዩ ፖለቲከኞችን አቀራርበው ሀራምባና ቆቦ የቆሙ ፓርቲዎችን አገናኝተው ቅንጅትን በመመስረት ባሳዩት እንቅስቃሴ ሕዝቡ አምነት አሳድሮ፤ የለውጥ ተስፋ ሰንቆ፤ ሴት ወንድ ወጣት አዛውንት ሳይል ያሳየው እንቅስቃሴ የሚዘነጋ አይመስለኝም፡፡

በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ከጠመንጃ እየተጋፋ ቅንጅትን ደግፎ ሰልፍ ወጣ፤የቅንጅትን የምርጫ ምልክት የእለት ተእለት የሰላምታ መለዋወጫው እስከ ማድረግ ደረሰ፤ድምጹን ሰጠ፤ድምጼ ይከበር ብሎ አደባባይ ወጥቶ በአረመኔ ጦረኞች ተፈጀ፤የቅንጅት አመራሮች ሲታሰሩ፤የመረጥናቸው ለፓርላማ እንጂ ለቃሊቲ አይደለም በማለት እስኪፈቱ ድረስ በቻለው መንገድና ዘዴ ከጠመንጃ ጋር እየታገለ ጮኸ፡፡ ትግሉ በሀገር ውስጥ ሳይወሰን በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም ልዩነታቸውንና መቃቃራቸውን ወደ ጎን ብለው ጸኃይና ብርድ ሳይበግራቸው ሰልፍ እየወጡ አንድ ሆነው በአንድ ላይ ጮኹ ይፈቱ ብለው ጠየቁ፡፡

የተጮኸላቸው፤ መሪዎቻችን ተብለው የተሞገሱ የተደነቁት ሰዎች ግን እድሜ ለኢ/ር ኃይሉ ሻውል በተፈቱ ማግስት የእንቧይ ካብ ሆኑ፡፡ ሕዝቡ ግን በዚህም ተስፋ ሳይቆርጥ ተለያይተው በየመንገዳቸው የቀጠሉትን  ዛሬም ለአለመበታተናችሁ ምን ዋስትና አለ እያለ እየጠየቀ ድጋፉን ቢቀንስም አይናችሁን አልይ ግን አላላም፡፡

እናም የኢትዮጵያ ሕዝብ ጽናት፤ተአማኒነት፤ብቃት ወዘተ ያለው እራሱን ቤተ መንግሥት ማየትን ሳይሆን የህዝብን የሥልጣን ባለቤትነትን ማረጋገጥን ቀዳሚ ዓላማው ያደረገ፤ ተባብሮና ተከባብሮ ወደ ድል  የሚመራው አጣ እንጂ የለውጥ ፍላጎቱን፤ለሚፈልገው ለውጥም እስከ ሕይወት መስዋእትነት መክፈሉን በተግባር አሳይቷል፡፡

ሎሬት ጸጋየ ገብረ መድህን ከምርጫ 97 በፊት የካቲት 1/97 ለንባብ ከበቃችው  ጦቢያ መጽሔት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ከተናገረው የሚከተለው ከላይ ለማሳየት የሞከርኩትን ሀሳቤን ይበልጥ የሚገልጽልኝ ይመስለኛል፡፡

{  የሕዝብን እውነት በልብ ሳይቋጥሩ ሕዝብ ግንባር ፊት መቆም እንደ ወያኔ ድፍረት ሕዝብን ማርከስ ነው፡፡ መተባበር ያቃተው ‹ኀብረትና ቅንጅት›ደግሞ ሕዝብን ሊያስተባብር አይችልም፡፡ አለንልህ የሚሉት ፖለቲከኞች ርስ በርሳቸው ሲጠላለፉ እያየ ሕዝቡ በመራራ ትዝብት ያስተውላቸዋል፡፡ አይቆስሉ ቁስለት ማለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁስለት ነው፡፡አይችሉ መቻል ማለትም የኢትዮጵያ ሕዝብ መቻል ነው፡፡ ‹በላይ እሳት በታች እሳት› እንደ ድፎ ዳቦ እየነደደ በፅናቱ ብቻ ሳይሆን ሕዝቡ በትእዝብቱም ቀድሞናል}

እንዲህ የተመሰከረለትን ሕዝብ ነው ዛሬ መስዋእት ሊከፍሉለት የማይገባ የተባለው፡፡ ነፍሱን ይማረውና  ከርሱ ሞት በኋላ የተፈጸመውን የፖለቲካ መመሰቃቀል፤የፖለቲከኞች መጠላለፍና መከዳዳት የወያኔን መቶ በመቶ አሸናፊነት ቢያይ   ጸጋዬ ምን ይል ነበር!

The post መሪ ያጣ ሕዝብ ምን ያድርግ  – ይገረም አለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.

እሷ ያየችው ሰሙን እኔ የነገርኳት ወርቁን –ከተማ ዋቅጅራ

0
0

 

Ketemaሰም የሚገኘው ከማር ነው። ወርቅ የሚገኘው ከመሬት ነው። ማሩን ማር እንዲሆን ያደረገችው ከአበባ እና ከውሃ ቀምማ ንብ ናት። ወርቁን ወርቅ ያሰኘው ከአፈር ለይቶ  በእሳት አቅልጦ ሰው ነው። ታዲያ ሰምና ወርቅን ምን አገናኛቸው ቢሉ ፊደል። በምን ቢሉ በሰሌዳ።

አንዷ ወዳጄ በተደጋጋሚ ያየችውን ነገርና የገጠማትን ሁሉ ታወጋኝ ነበር። እኔም የምችለውን ያህል ሳይሰለቸኝ የሰማኋትን እንዳይሰለቻት አድርጌ እነግራት ነበረ። ታዲያ በእንደዚ ጨዋታ መሰላቻቸት በሌለበት መዝለቅ በተለይ በዘመነ ወያኔ መታደል ነው።

እናም ይቺ ወዳጄ እንዲ ብላ ያየችውን ጀመረችልኝ። ዛሬ ብታይ አለችኝ አፏን እየጠራረገች ዛሬ ብታይ በትልቅ ሙቀጫ ውስጥ ከቶኝ ሲሸከሽከኝ ነው ያደረው አለችኝ።

እኔም፡- ይኽውልሽ ምን መሰለሽ ለወገን የማያስብ መሪ ለህዝብ የማይጨነቅ ንጉስ ነግሶብን ኢትዮጵያ  የምትባል ትልቅ አገር መሃል ገብቶ በተለያየ አቅጣጫ እንደ ሙቀጫ ያለ እስርቤት አዘጋጅቶ ገሚሱን አንተ ኦነግ ነህ ሲለው ገሚሱን  አንተ ግንቦት 7 ነህ ሲለው ገሚሱን ደግሞ አንተ ኦብነግ ነህ እያለ ወዳዘጋጀው የእስር ሙቀጫ ይከታል። ጋዜጠኖችን እና የተለያየ ጽሁፎችን በመጻፍ የሚታወቁትን ጸሃፊዎችን ብቻ ምን አለፋሽ ለአገዛዙ  የማይመቹትን ከሆኑ የኛን ዓላማ ለማሰናከል ነው የሚንቀሳቀሱት በማለት  አሸባሪ የሚል  ታርጋ እየለጠፈ ስንቱ ያለ ሐጥያቱ ላገሩ በለፋ ለእውነተኛ ለውጥ ስለታገለ ሙቀጫ እስር ቤታቸው አስገብተው ስንቱን ንጹሃንን ሸከሸኩት መሰለሽ።

ሌላው ምን መሰለህ ብላ ቀጠለች….  ምጣድ ላይ ጥዶ ሲያምሰኝ ነው ያደረው አለችኝ

እኔም፡- አልኳት ፌድራል የሚባሉ ህዝብን ሊጠብቁ የተመረጡ ነገር ግን በተገላቢጦሽ ህዝብን ለሚጨቁኑ ባለስልጣን ተብዬዎች አገልጋይ የሆኑ ታሪክ የማይረሳው ስህተት እየሰሩ ያሉ አድርግ የተባሉትን ብቻ  የሚያደርጉ ከበላይ ትእዛዝ ከመጣላቸው ሴት ነሽ ህጻን ነሽ ትልቅ ነህ ትንሽ ነህ ሳይሉ በያዙት ዱላ ያገኙትን ሁሉ መቀጥቀጥ እንደ ስራ የቆጠሩት  ስንቱ ወገኔ በነዛ አረመኔ ተደበደበ  ወገኖቻችንን በየቦታው ስንቱን ያላመሱት አለ መሰለሽ አገር በየግዜው በነዚህ አረመኔዎች ስትታመስ አይደለ የምትውለው።

እንዲህ በማለት ቀጠለች የዛሬ ይገርማል ብላ ቀጠለች ትልቅ ብረት ምጣድ ላይ ጥዶ በትልቅ መቁያ ሲቆላኝ ሲቆላኝ ነው ያደረው አለችኝ

እኔም፡- አዪዪ አልኩኝ የኢትዮጵያ ህዝብ መቆላት ከጀመረ እኮ ቆየ የምንስ ወገን ያልተቆላ አለ ብለሽ ነው ፈጁን እንጂ ነው የሚባለው። መንግስትንም ተቃውመው ሰልፍ ይውጡ በጥይት መቁላት ነው። የፖለቲካ ለውጥም ፈልገው ሰልፍ ይውጡ መቁላት ነው። ገበሬን አታፈናቅሉ መሬታችንንም ያለአግባባ መዝረፍ ይቁም ብለው ሰልፍ ይውጡ መቁላት ነው። የሐይማኖት ቦታችን ይከበርልን አትንኩብን ብለው ሰልፍ ይውጡ መቁላት ነው። ISISንም ተቃውመው ሰልፍ ይውጡ መቁላት ነው። ህዝባችን ተቆልቶ  አልቋል እኮ ምን ቀረ ብለሽ ነው ጋንቤላ ብትዪ ኡጋዴን ብትዪ ቤንሻጉል ብትዪ ባሕር ዳር ብትዪ አንቦ  ብትዪ አዲስ አበባ ብትዪ በወያኔ የግፍ ጥይት ማን ያልተቆላ አለ ብለሽ ነው እና …ብዬ ልቀጥል ስል አቋርጣኝ

አልተግባባንም እኔ የምልህን ምንም አላዳመጥከኝም አለችኝ

እኔም፡- ኽረ በድንብ አድምጬሻለው አልኳት

እሷም፡- እሺ ምንድነው ያልኩህ

እኔም፡- ያልሽኝን ነዋ  እኔ ደግሞ የሆነውንና የሚሆነውን ነገርኩሽ

እሷም፡- ጮክ ብላ አልነገርከኝም! አልሰማህኝም! እኔ ያልኩህ እንደሱ እንድትለኝ አይደለም!!!

እኔም፡- እና ምንድነው? ያልሽኝ አልኳት አይን አይኗን እያየኋት

እሷም፡- ሲሸከሽከኝ አየው ነው ያልኩህ

እኔም፡- እሺ የሸክሽክሽ

እሷም፡- ሲያምሰኝ አየው ነው ያልኩህ

እኔም፡- እሺ ያምስሽ

እሷም፡- ሲቆላኝ አየው ነው ያልኩህ

እኔም፡- እሺ ይቁላሽ

እሷም፡- ታዲያ የዚህን ፍቺ ነው ንገረኝ ያልኩህ እንጂ ሌላ አይደለም አለችኝ ቆጣ ብላ

እኔም፡- አይ አንቺ አልኳት በመገረም አኳኃን እያየኋት አንቺ የፈለግሽው ሰሙን እኔ የነገርኩሽ ወርቁን አልተግባባንም የገባው ወርቁን ይከተል ያልገባው በሰሙ ይቀጥል ምን እላለው ይኸው ነው ቃሌ አልኳት።

እሷም፡- በል ደህና ሁን ብላኝ ትታኝ ሄደች

እኔም፡- ይኸውልሽ እህቴ የምልሽን አድምጠሽኛል ወዳጅህ ሲታማ ለኔ ብለህ ስማ ይላል ያገረ  ሰው እናም በኢትዮጵያ  ውስጥ የሚደርሰው ግፍና በደል ሁላችንን ተሰምቶን ሊያስቆጣን እና በቆራጥነት አስነስቶን በህዝባችን ላይ ግፍ ፈጻሚዎችን በማስወገድ ህዝባችን በነጻነት፣ በሰላም፣ በፍቅር የሚኖርባትን አገር እንዲኖረን የማድረጉ  የሁላችንም ድርሻ  ነውና ይታሰብበት። በይ ደህና ሁኚ በድል ያገናኘን ብያት ተሰናበትኳት።

ከተማ ዋቅጅራ

13.06.2015

Email- waqjirak@yahoo.com

 

The post እሷ ያየችው ሰሙን እኔ የነገርኳት ወርቁን – ከተማ ዋቅጅራ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሕወሓት መንግስት ወታደሮች ጭልጋ ላይ ገበያ ውስጥ በከፈቱት ተኩስ 3 ሰዎችን ገደሉ * በርካቶች ቆስለዋል

0
0

ሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ በአይከል ከተማ ዛሬ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የሚመራው መንግስት ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ 3 ሰዎች መገደላቸው ታወቀ።
news
ከስፍራው የሚወጡት ዜናዎች እንደሚያረጋግጡት በአይከል ከተማ መሀል ገበያ ህዝብ ላይ ተኩስ የከፈቱት የህወሀት ወታደሮች በርካታ ሰዎችንም ማቁሰላቸው ተገልጿል።

ከሶስቱ ሟቾች የሁለቱ ስም የታወቀ ሲሆን የአስር አለቃ ውቤ እና አቶ ብርሌ በህወሀት ወታደሮች ዛሬ ተገድለዋል።

የአይከል ከተማ ነዋሪ የሆኑ አንድ ሙስሊምም መገደላቸው ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች አስታውቀዋልል::

እንደ ዘገባው ከሆነ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል እየተነገረ ነው። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በአይከል ከተማ ውጥረቱ ተባብሶ ቀጥሏል።

በማንነት ጉዳይ የተነሳው የህዝብ ጥያቄ በመንግስት ምላሽ ተስጥቶታል ቢባልም አከባቢውን ወደትግራይ ክልል ለመጠቅለል በህወሀት መንግስት እየተደረገ ያለው ድብቅ ሴራ ህዝቡን እንዳስቆጣው ይነገራል።

ባለፈው ቅዳሜ የሱዳን ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በአብደራፊ የሚገኘውን የሁለት ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች የእርሻ ይዞታ ሲያቃጥሉ የእኛ ድንበር የሚዋሰነው ከትግራይ ክልል እንጂ ከአማራ አይደለም ማለታቸው መዘገቡ የሚታወስ ነው።

The post የሕወሓት መንግስት ወታደሮች ጭልጋ ላይ ገበያ ውስጥ በከፈቱት ተኩስ 3 ሰዎችን ገደሉ * በርካቶች ቆስለዋል appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢትዮጵያን ባሰብኳት ግዜ አለቀስኩኝ!!!

0
0

ከ-ሳሙኤል አሊ (ኖርዌይ)
ፍቅር እንደ ሻማ የተላበሰች አገር፤ ጀግነትን እንደ ባህል የያዘች አገር፤ ጥበብን ለልጆቿ ስታስተምር የኖረች አገር፤ ፍልስፍናን ለአለም ስትገልጽ የቆየች አገር ፤ በሁሉ ቀዳሚ የሆነች አገር መሆናን በአፍ ሳይሆን በተግባር ገልፃ ያሳየች እንደሆነች እናውቃለን። ፍደልን ቀርፃ ዘመንን ቀምራ የተገኝች ብችኛዋ አፍሪካዊት አገር ፤ ኢትዮጵያ የዜማና የፍልስፍና አስተምሮ የበቀለባት አገር፤ በቀኝ ያልተገዛች ቅኝ ገዢወችን አሳፍራ ያባረረች የአፍሪካ ፈር ቀዳጅ ውዷ አገራችን ኢትዮጵያ ናት። ይሄንን ለመግቢያ ያክል አልኩኝ እንጂ ዛሬ ግን ይህ ሁሉ ክብርና ዝና ሀይልና መፈራት ፍቅርን እና መዋደድን አንድነት እና መስማማትን ከኢትዮጵያ አገሬ ጠፍታል። ለምን ይሆን? ማን ነው አጥፍው? ተጠያቂውስ ማን ይሆን በዚህ ዙርያ ትንሽ ልበል፦
samuel
ኢትዮጵያ የሀዘን ካባዋን ደርባ ነጠላዋን አዘቅዝቃ ሀዘን ከተቀመጠች ድፍን 24 አመታትን አስቆጥራለች። ከ24 አመት በፊት ኢትዮጵያን ሲያስተዳድሩ የነበሩት መንግስታቶች በህዝብ ላይ አንባገነን ሆነው ከፍተኛ በደል ቢያደርሱም ቅሉ በኢትዮጵያ ጉዳይ ግን አይደራደሩም ነበር። ኢትዮጵያ የሚለው ስም ከ24 አመት በፊት የምትፈራ የምትከበር ህዝቡም በፍቅር የሚኖርባት ነበረች። አሁን ላይ ግን በዘመነ ወያኔ ዜጎች በማንነነታቸው ከየት አካባቢ ብሄር የመጣኸው/ሽው? እዚህ ለመኖር፣ ለመስራት፣ ለመሳሰሉት የመኖሪያ ፈቃድ አለህ/ሽ ወይ? በሚል ብሄርን ከፋፍሎ መለያ በመስጠት ተከባብሮ የኖረን ህዝብ በትውልድ ሀገሩ እርስ በርሱ እንዲጋጭ እየተደረገ ነው ።

እትዮጵያ ማለት ከአንባገነንም በላይ አንባገነን የነገሰባት የአንድ ዘር የበላይነት የታወጀባት ሆና እርስ በርሳችን እንደንጠላላ የማድረግ ስራ እየተሰራባት ኢትዮጵያ የምትባል አገር በአለም የተናቀች አድርጎ ሕዝባችንን በሃገሩም የተገፋ በስደትም የተናቀ እንዲሆን ሌት ተቀን እየሰሩ ነው።

ከኢትዮጵያ በፊት ዘሬን ላስቀድም የሚል ትውልድ መፍጠር ለዚህም በዘር ከፋፍሎ ለሁሉም ዘር ባንዲራ መስጠት እና ያንን ባንዲራ በየክልሉ እንዲውለበለብ በማድረግ ልዩነት እንዳለን በማስመሰል የእከሌ ዘር ይህንን ባንዲራ የእከሌ ዘር ያንን ባንዲራ ብሎ ከኢትዮጵያዊነት ዝቅ ብሎ ዘር ተራ አውርዶ ዘሩን እንዲያስብ ማድረግ ወያኔ ያመጣው ሰይጣናዊ አመለካከት ነው።
Cry Ethiopia in Saudi
በመሰረቱ ወያኔንም እስከአሁን በስልጣን ላይ ያቆየው የዘር ፖሊሲው ነው ይህ ቁማር ለጊዜው የሚጠቅመው ለወያኔወች ሊሆን ይችላል በሃላ ግን ለልጅ ልጆቹ የማይፋቅ እዳም እያስቀመጠ ያለውም ወያኔ ነው። ክልል ብሎ በከለለው እንኳን ብንሄድ ድንጋያማዋን ትግራይን ይዞ ቁጭ ብሎ የደም እንባ የሚያነባውና የሚራበው ወያኔ ቆሜለታለው የሚለው የራሱ ሰዎች ናቸው። ሌሎቹን ብንመለከት ግን ሰፊ ለም መሬት ሰፊ የውሃ ሃብት አላቸው ዛሬ ደስ ብሎህ የምትንጫጫ የወያኔ ጉጅሌ ሁላ ነገ እንደ ወንዝ የማያባራ እንባህን ትዘራታለህ ሁሉም የእጁን ነው የሚያገኝው እዚህ ላይ ግን በዚህ አካሄድ ላሰምርበት የምፈልገው ብዙ ያልተረጋጉ ሁኔታወች አመኔታ ያላገኙ የክልል ክለላወች እንዳሉ እሙን ነው። ይሄ ነው የኔ፡ እዚህ ድረስ ነው፡ የኔ የሚል እሰጣ ገባ ውስጥ ከወያኔ ውጪ ሌላው ህብረተስብ መግባት እንደሌለበት ለመናገር እወዳለው። አይ የለም መገባት አለበት የሚባል ከሆነ ግን ተመልሰን እንደጋርዮሽ ስረአት ቀድሞ የኔ ቦታ እዚህ ድረስ ነበርና ማስመለስ አለብኝ የኔ ግዛት ትንሽ አንሳለች እና ማስፋፋት አለብኝ ወደሚለው መሄዳችን ግልጽ ነው። በፍቅርና በአንድነት ስንኖር እንኳን ለኛ ኢትዮጵያን ቀርቶ ለአለም የሚተርፍው አገራችንን በይገባኛል ተራን የማይረባ ነገር አገራችንን ሲኦል እንዳናደርጋት አደራ እላለው ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ኢትዮጵያ ጠፈታለች አንድ ዘር ከአንድ ዘር ጋር በጎን እንዲተያዩ እየተደረገ ነው። አንዱ ሃይማኖት ከሌላው ሃይማኖት ጋር ጥላቻ እያስፈኑ ነው። ክልል ድንበር እያለ በኢትዮጵያ ምድር በነፃነት እንዳንቀሳቀስ እያደረጉን ነው። ይህን ሁሉ የኢትዮጵያ ሰላም ያናጋ የኢትዮጵያን ፍቅር ያጠፋ ወያኔ የተባለ የተደራጀ ዘራፊ ሰይጣናዊ ቡድን ነው። ይህንን ዘራፊ ቡድን ባስቀመጠልን የመከራ ክልል ሳንወናበድ፧ ወያኔ በዘረጋው የዘር ከዘር ልዩነት ሳንከፋፍለን፧ ኢትዮጵያን የማዳኑን ስራ የመስራት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጉዳይ ነው። ከወገኔ አንድ ሰው ቢሞትብኝ አልቅሼ የምቀብረው አገር ሲኖር ነው። አገር ከሞተች ግን እንኳን በደስታ መኖር ይቅርና በክብርም መቀበርያ እናጣለን አገር እየገደለ ያለው ወንበዴ ወያኔን ቀድመን ልንገለው ግድ ይለናል።

ኢትዮጵያን ሁሉ ዘር ሳይለያየን ሃይማኖት ሳይከፋፍለን ከዳር እስከዳር እጅ ለእጅ ተያይዘን በደስታ፧ በነፃነት ፧ በእኩልነት፧ የምንኖርባትን አገር ለመመስረት ኢትዮጵያን እየገደላት ያለውን ወያኔ የተባለውን ገዳያን እንግደልላት ከጸጋዋ ተካፍለን በፍቅራ እንድንጠለል ፍቅር አጥፊውን ወያኔን እናጥፋ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!
ከ -ሳሙኤል አሊ ( ኖርዌይ)
Email samilost89@yahoo.com
June 14.2015

The post ኢትዮጵያን ባሰብኳት ግዜ አለቀስኩኝ!!! appeared first on Zehabesha Amharic.


ደቡብ አፍሪካ አልበሽርን ለICC አሳልፋ ትሰጥ ይሆን? –የአለምነህ ዋሴ ትንታኔ (ያድምጡ)

የአንድነቱ አብርሃም ልጃለም በረሃ ወርዶ የብረት ትግሉን ተቀላቅሏል

0
0

የሰላም በሮች ሲዘጉ የአመጽ በሮች ይከፈታሉ

ከዳዊት ሰለሞን

የቀድሞው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከዓመት በፊት ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ ሲያከናውን ከየክልሉ የመጡ ተሳታፊዎችን የማግኘትና በክለላቸው ስለሚያደርጓቸው እንቅስቃሰዎች፣ስለሚደርስባቸው እስራት፣ወከባ፣ድብደባና ስለሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዲያካፍሉን የፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ባልደረቦች እንወተውታቸው ነበር፡፡
Abreham 2

Abreham
አብርሃም ልጃለም ከጎንደር አካባቢ ወደ አዲስ አበባ ለጠቅላላ ጉባኤው የራሳቸውን የትራንስፖርት ወጪ ችለው ከመጡ የክልሉ የአንድነት አመራሮች አንዱ ነው፡፡ጎንደሮች አዲስ ሲመጡ ባዶ እጃቸውን አልመጡም፡፡ገበሬውን ወላጅ አባቷን በመኖሪያ ቤቱ በጥይት ደብድበው ከገደሉት በኋላ በተኛችበት የመደብ አልጋ በተተኮሰባት ጥይት የቀኝ እጇን ለመቆረጥ የበቃችን የስምንት ዓመት ታዳጊ ወጪዋን ሸፍነው አምጥተዋት ነበር፡፡

አብርሃም ልጃለምና ጓደኞቹ በክልላቸው ስለሚፈጸም የመብት ጥሰት የሚያወሩት በቃል አይደለም፡፡ስለሚያወሩት ነገር በሙሉ መረጃዎች አጠናቅረው ዶሴ አዘጋጅተው ሌላው ቀርቶ ኢህአዴግ አካባቢውን ከተቆጣጠረበት ግዜ አንስቶ ጠቅላላ ጉባኤው እስከተደረገበት ወቅት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የተገደሉ ሰዎችን ስም ዝርዝር እስከ አያታቸው መዝግበው ይዘዋል፡፡

የ2007 ምርጫ ለኢህአዴግ በክልላቸው የመጨረሻ እንደሚሆን በድፍረት የሚናገሩት እነ አብርሃም ምርጫው ከመድረስ አስቀድሞ ምርጫ ቦርድ የተባለ መራጭ አንድነትን ለትዕግስቱ መስጠቱን ተከትሎ ህልማቸው ተዘረፈ፡፡አፍታም ሳይቆይ የአብርሃም አካባቢ የአንድነት አባላት በገዢው ፓርቲ ፖሊሶች ታስረው ማዕከላዊ ተወሰዱ፡፡
አብርሃምና ከአፈናው የተረፉት የአርማጭሆ ልጆች ተማከሩ፡፡ከአሁን በኋላ ምን ቀረን የሚለው ጥያቄ የምክራቸው ማጠንጠኛ ነበር፡፡ፓርቲያቸው ፈርሷል፣ሰላማዊ ትግልን የቆረቡበት ያህል ጸንተው ያጸኗቸው ጓዶቻቸው ‹‹ሽብርተኛ››ተሰኝተው ደብዛቸው እንዲጠፋ ተደርጓል፡፡እናማ ቀሪዎቹን የወሰዱ እግሮች እያንዳንዳቸው ደጃፍ ከመድረሳቸው አስቀድሞ ቀደሟቸው፡፡

አብርሃምን በምስሉ እንደምትመለከቱት በረሃ ወርዶ ከሐሳቡ ውጪ የነበረውን መንገድ ተቀላቅሏል፡፡ከ15 የማያንሱ የጎንደር አካባቢ የቀድሞ የአንድነት አባላትም ዛሬ በአብርሃም መንደር ይገኛሉ፡፡

The post የአንድነቱ አብርሃም ልጃለም በረሃ ወርዶ የብረት ትግሉን ተቀላቅሏል appeared first on Zehabesha Amharic.

የፍቅር ትርያንግል አዙሪት(Lovers Triangle) (በሥዩም ወርቅነህ)

0
0

ሼህ መሐመድ አላሙዲ-ከመንግስት ባለስልጣናት-ከልማታዊ አርቲስቶቻችን

 

unnamedቱጃሩ ‘ሼክ’ መሐመድ አል አሙዲን፤ጋጠወጦቹ የወያኔ መንግስት ሹማምንቶች፦ የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ የፌደረሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ በረከት ስምዖን፣ እንዲሁም ታላላቅ ‘የተከበሩ’ እንግዶችና የአርቲስት ቤተሰቦች በተገኙበት፤ በትላንትናው እለት የትዝታው ንጉስ ጋሽ ማህሙድ አህመድ 50ኛ ዓመት የሙያ ጉዞ በማስመልከት የተዘጋጀ ዝግጅት ሲከበር፤ ከወጣቷ አክትረስ ማህደር አሰፋ ጋር ከትዳራቸው ውጭ ሲማግጡ ታይተዋል። ይህ ከሃገራችን ባህልና ወግ በእጅጉ የሚፃረርና የወደፊት ተተኪውን ትውልድን ወደ አልባሌ ድርጊት የሚገፋፋ ነውረኛ ተግባር ነው።

 

ማህደርና ሼሁ ለብዙ ጊዜ ሲታሙ መቆየታቸው ይታወቃል። ነገር ግን ንቀት ካልሆነ በቀር እንደዚህ ጋጠወጥ የሆነን ድርጊት በአደባባይ ማድረጉ ለምን አስፈለገ? የወያኔ ሊቀመናብርት ባለስልጣናትን በመዳፋቸው በማስገባት የሃገሪቱን ሃብት የሚዘርፋት ሼክ መሃመድ አል አሙዲን በልማታዊ አርቲስቶቻችን ሰይፉ ፋንታሁን፣ ሰራዊት ፍቅሬ፣ ሙሉዓለም ታደሰ፣ ማዲንጎ አፈወርቅና በሌሎችም አማካኝነት ታዳጊ ወጣት የሃገራችን ልጃገረዶችን በሃብታቸው በማማለል ከአላማቸው በማሰናከል ንፅህናቸውን እንዲያረክሱ ያስገድዷቸዋል። ይህን ህገ-ወጥ ድርጊት የሚያውቁት የወያኔ ቁንጮ ባለስልጣናት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ከማድረግ ይልቅ በተጋበዙበት ግብዣ እንኳን ከትዳራቸው ውጭ እየማገጡ እያዩ በጭብጨባ አጅበዋቸዋል።

 

ወያኔና ጀሌዎቹ ላለፉት 24 ዓመታት የኃገራችን ሃብትና ንብረትን የዘረፉት አንሷቸው፤ ታሪካችንን ሲያጠለሹ፣ ሲያጠፉ፣ የታሪክ መፅሃፍትና ቅርስ ለባዕድ ሲሸጡ፣ ሲያቃጥሉ፣ ባህልና ወጋችንን ሲያንኳስሱ፣ የእምነትና ሃይማኖት ስፍራዎችን ሲያረክሱና ሲያቃጥሉ፣ እንዲሁም አያሌ ወንጀሎችን ሲፈፅሙ መቆየታቸው ፀሃይ የሞቀው የአደባባይ ሚስጥር ነው። እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ለእኔ በዚህ ደረጃ ተንኮታኩታ ጥበብ በአደባባይ ረክሳ፣ ሃገር ተደፍራና አንገታችንን አስደፍታ ማየት ያመኛል። ልማታዊ አርቲስቶቹና የወያኔ ቁንጮ ባለስልጣናት በሼሁ ፍርፋሪ ገንዘብ ህሊናቸው ታውሯል። ልማታዊ አርቲስቶቹም በጥቅም በመደለል የወያኔ ሎሌ ሆነዋል። በቅኝ ግዛት ተገዝታ የማታውቀው ሃገራችን ኢትዮጵያም ሼክ መሐመድ አል አሙዲን እንደፈለጉ የሚፈነጩባትና እሚያዙባት ሃገር ሆናለች።

 

ሼህ መሐመድ አል አሙዲን 28 ክርስቲያን ወንድሞቻችን ISIS በሚባለው እስላማዊው አሸባሪ ቡድን ከታረዱ ወዲህ ለብዙ አርስቲስቶች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ብሮች በስጦታና በሽልማት መልክ አበርክተዋል። ለአብነት ያህል ለአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅና ለንዋይ ደበበ ሁለት ሁለት ሚሊዮን ብር፣ ለመሳፍንት 9 ሚሊዮን ብር እንዲሁም በትላንትናው ዕለት ለአርቲስት ማህሙድ አህመድ 5 ሚሊዮን ብር በሽልማት መልክ ለግሰዋል። እውን ይህን ሁሉ የሚያደርጉት ለአርቲስቶቻችን እውነተኛ አክብሮት ኖሯቸው ይሆን!? እውነተኛ ምክንያታቸው ይህ ቢሆን ኖሮ በርካታ ታላላቅ አርቲስቶቻችንና እውቅ ዜጐቻችን በሼሁ ብሮች በተጥለቀለቁ ነበር። ይልቁኑስ በዙሪያቸው የተሰባሰቡት አርቲስት ተላላኪዎቻቸውና ሎሌዎቻቸው በወንጀል ያደፈ ልባቸውን፣ በዝርፊያ የተጨማለቀ እጃቸውንና፣ ውስጠ ሚስጥራቸውን ስለሚያውቁ በውለታ መልክ ጠፍረው ለመያዝና አንዳንድ የዋህ ዜጐችን ለማምታታት ይመስላል።

 

ሼሁ በእውነት ለሃገራችን ደራሽ የሆኑ ቅን ሰው ቢሆኑ ኖሮ፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሃዘን ቅስሙ በተሰበረበት፣ መሪር ሃዘኑ በከፋበት፣ የልጆቹ አንገት በቢላዋ ሲቀላ በአደባባይ ተመልክቶ ባዘነበት በዛ ድቅድቅ ጨለማ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሃዘናቸውን በገለፁ ነበር፤ እንደሌላውም ቅን ኢትዮጵያዊ ልጆቻቸው ለታረደባቸው ቤተሰቦች እርዳታ ባደረጉ ነበር። ዛሬ ደግሞ አይናቸውን በጨው አጥበውና የኢትዮያን ህዝብ ንቀው፤ የልጅ ልጃቸው ከምትሆነው ከወጣት ተዋናይት ማህደር አሰፋ ጋር፤ ከኢትዮጵያ ባህልና ወግን ባልተከተለ መልኩ ባደባባይ ባልባለጉ ነበር። ሼሁ በISIS ልጆቻቸው ለተጎዳባቸው ቤተሰቦች ሃዘናቸውን ያልገለፁትና  ያለመርዳታቸው፣ ያለሃፍረትም እንዲህ ያስፈነጠዛቸው ምክንያት በሃዘናችን ተደስተው ይሆን!? ወይንስ ሌሎችም እንደሚታሙት ለISIS አጋርነታቸውን እየገለፁ!?~መጠርጠር አይከፋም!።

 

የኢትዮጵያ ታሪክና ወግን አስጠብቀን ለተተኪ ትውልድ ለማስተላለፍ ወያኔን ማስወገድ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው።

ኢትዮጵያ ለዘላለም በልጆቿ ተከብራ ትኑር!

እናቸንፋለን!

The post የፍቅር ትርያንግል አዙሪት(Lovers Triangle) (በሥዩም ወርቅነህ) appeared first on Zehabesha Amharic.

የሕወሓት መንግስት የግንቦት 20ን በዓል በ20 ሰው በድብቅ በሚኒሶታ አከበረ

0
0

Girma biru
(ዘ-ሐበሻ) የሕወሓት መንግስት የሚኒሶታን ሕዝብ እንደ ጦር ነው የሚፈራው – ለዛም ነው ሕዝባዊ ስብሰባና በዓል ሲያደርግ በድብቅ የሚያደርገው:: ከዚህ ቀደም በአደባባይ ፖስተር ለጥፎ ስብሰባ ሲጠራ ሕዝቡ ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት በማወኩ ስብሰባው ሳይካሄድ ቀርቷል::

ትናንት June 13 በሚኒሶታ የሕወሓት መንግስት የግንቦት 20ን በዓል ለማክበር በሚኒሶታ በድብቅ ስብሰባ ጠርቶ ነበር:: በሚኒሶታ 5ለ1 በሚል ጥርነፋ የተደራጁ የሕወሓት መንግስት ደጋፊዎች ያሉ ሲሆን እነዚህ ሰዎች የየራሳቸውን ኮኔክሽን ቢጠሩም በስብሰባው ላይ ከ20 የበለጠ ሰው ሳይገኝ ቀርቷል:: በረመዳ ሆቴል በተደረገው በዚሁ በከሰረው የግንቦት 20 በዓል ላይ የሕወሓቱ ተላላኪና ከደንበል ሲቲ ሴንተር ጋር በተያያዘ በሙስና የሚታሙት አቶ ግርማ ብሩ የመጡ ቢሆንም በኪሳራ ወደመጡበት ተመልሰዋል::

ከአቶ ግርማ ብሩ የቀረቡ ምንጮች ባገኘነው መረጃ መሠረት በስብሰባው ላይ ከ20 ሰው በታች መገኘቱ በጣም ከመበሳጨታቸው የተነሳ በድብቅ የተጠሩት ሰዎች ሁሉ ባለመገኘታቸው “ምን አድርገናቸው ነው?” የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውን ነው::

የሕወሓት መንግስት በዓል የሆነው የግንቦት 20 በዓል በሚኒሶታ በባዶ አዳራሽ መካሄዱ ለሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ትልቅ ድል ነው::

The post የሕወሓት መንግስት የግንቦት 20ን በዓል በ20 ሰው በድብቅ በሚኒሶታ አከበረ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢትዮጵያን ባሰብኳት ግዜ አለቀስኩኝ!!! –ከ-ሳሙኤል አሊ

0
0

ከ-ሳሙኤል አሊ (ኖርዌይ)

ሳሙኤል አሊ

ሳሙኤል አሊ

ፍቅር እንደ ሻማ የተላበሰች አገር፤ ጀግነትን እንደ ባህል የያዘች አገር፤ ጥበብን ለልጆቿ ስታስተምር የኖረች አገር፤ ፍልስፍናን ለአለም ስትገልጽ  የቆየች አገር ፤ በሁሉ ቀዳሚ የሆነች አገር መሆናን በአፍ  ሳይሆን በተግባር ገልፃ ያሳየች እንደሆነች እናውቃለን። ፍደልን ቀርፃ ዘመንን ቀምራ የተገኝች ብችኛዋ  አፍሪካዊት አገር ፤ ኢትዮጵያ የዜማና የፍልስፍና አስተምሮ የበቀለባት አገር፤ በቀኝ ያልተገዛች ቅኝ ገዢወችን አሳፍራ ያባረረች የአፍሪካ  ፈር ቀዳጅ ውዷ አገራችን ኢትዮጵያ ናት። ይሄንን ለመግቢያ ያክል አልኩኝ  እንጂ ዛሬ ግን ይህ ሁሉ ክብርና ዝና  ሀይልና መፈራት   ፍቅርን እና መዋደድን አንድነት እና መስማማትን  ከኢትዮጵያ አገሬ ጠፍታል። ለምን ይሆን? ማን ነው አጥፍው? ተጠያቂውስ ማን ይሆን በዚህ ዙርያ ትንሽ ልበል፦

ኢትዮጵያ የሀዘን ካባዋን ደርባ  ነጠላዋን አዘቅዝቃ  ሀዘን ከተቀመጠች ድፍን 24 አመታትን አስቆጥራለች። ከ24 አመት በፊት ኢትዮጵያን ሲያስተዳድሩ የነበሩት መንግስታቶች በህዝብ ላይ አንባገነን ሆነው ከፍተኛ በደል ቢያደርሱም ቅሉ በኢትዮጵያ  ጉዳይ ግን አይደራደሩም  ነበር።  ኢትዮጵያ የሚለው ስም ከ24 አመት በፊት የምትፈራ የምትከበር ህዝቡም በፍቅር የሚኖርባት ነበረች። አሁን ላይ ግን በዘመነ ወያኔ  ዜጎች በማንነነታቸው ከየት አካባቢ ብሄር የመጣኸው/ሽው? እዚህ ለመኖር፣ ለመስራት፣ ለመሳሰሉት የመኖሪያ ፈቃድ አለህ/ሽ ወይ? በሚል ብሄርን ከፋፍሎ መለያ በመስጠት ተከባብሮ የኖረን ህዝብ በትውልድ ሀገሩ እርስ በርሱ እንዲጋጭ  እየተደረገ ነው ።

እትዮጵያ ማለት ከአንባገነንም በላይ አንባገነን የነገሰባት የአንድ ዘር የበላይነት የታወጀባት ሆና እርስ በርሳችን እንደንጠላላ የማድረግ ስራ እየተሰራባት ኢትዮጵያ የምትባል  አገር በአለም የተናቀች አድርጎ ሕዝባችንን በሃገሩም የተገፋ በስደትም የተናቀ እንዲሆን ሌት ተቀን እየሰሩ ነው።

ከኢትዮጵያ በፊት ዘሬን ላስቀድም የሚል ትውልድ መፍጠር ለዚህም በዘር ከፋፍሎ ለሁሉም ዘር ባንዲራ መስጠት እና ያንን ባንዲራ  በየክልሉ እንዲውለበለብ በማድረግ ልዩነት እንዳለን በማስመሰል የእከሌ ዘር ይህንን ባንዲራ የእከሌ ዘር ያንን ባንዲራ  ብሎ ከኢትዮጵያዊነት ዝቅ ብሎ ዘር ተራ አውርዶ ዘሩን እንዲያስብ  ማድረግ ወያኔ ያመጣው ሰይጣናዊ አመለካከት ነው።

በመሰረቱ ወያኔንም እስከአሁን በስልጣን ላይ ያቆየው  የዘር ፖሊሲው ነው  ይህ ቁማር ለጊዜው  የሚጠቅመው ለወያኔወች ሊሆን ይችላል በሃላ ግን ለልጅ ልጆቹ የማይፋቅ እዳም እያስቀመጠ  ያለውም ወያኔ ነው።  ክልል ብሎ በከለለው  እንኳን  ብንሄድ  ድንጋያማዋን ትግራይን ይዞ ቁጭ ብሎ የደም እንባ የሚያነባውና የሚራበው ወያኔ  ቆሜለታለው የሚለው የራሱ ሰዎች ናቸው። ሌሎቹን ብንመለከት ግን ሰፊ ለም መሬት ሰፊ የውሃ  ሃብት አላቸው ዛሬ ደስ ብሎህ የምትንጫጫ የወያኔ  ጉጅሌ  ሁላ  ነገ እንደ ወንዝ የማያባራ  እንባህን ትዘራታለህ ሁሉም የእጁን ነው የሚያገኝው  እዚህ ላይ ግን በዚህ  አካሄድ ላሰምርበት የምፈልገው ብዙ ያልተረጋጉ ሁኔታወች  አመኔታ ያላገኙ የክልል ክለላወች  እንዳሉ እሙን ነው።  ይሄ ነው የኔ፡ እዚህ ድረስ ነው፡ የኔ የሚል እሰጣ ገባ ውስጥ ከወያኔ ውጪ ሌላው ህብረተስብ መግባት እንደሌለበት ለመናገር እወዳለው።  አይ የለም መገባት አለበት የሚባል ከሆነ ግን  ተመልሰን እንደጋርዮሽ ስረአት ቀድሞ  የኔ ቦታ  እዚህ ድረስ ነበርና  ማስመለስ አለብኝ  የኔ ግዛት ትንሽ አንሳለች እና   ማስፋፋት አለብኝ  ወደሚለው መሄዳችን ግልጽ ነው።  በፍቅርና በአንድነት ስንኖር  እንኳን ለኛ ኢትዮጵያን ቀርቶ ለአለም የሚተርፍው አገራችንን በይገባኛል ተራን የማይረባ ነገር አገራችንን ሲኦል እንዳናደርጋት  አደራ  እላለው ።

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ኢትዮጵያ ጠፈታለች  አንድ ዘር ከአንድ ዘር ጋር በጎን እንዲተያዩ  እየተደረገ ነው።  አንዱ ሃይማኖት ከሌላው ሃይማኖት ጋር ጥላቻ እያስፈኑ ነው። ክልል ድንበር እያለ  በኢትዮጵያ ምድር  በነፃነት እንዳንቀሳቀስ  እያደረጉን ነው።  ይህን ሁሉ የኢትዮጵያ ሰላም ያናጋ የኢትዮጵያን ፍቅር ያጠፋ ወያኔ የተባለ የተደራጀ ዘራፊ ሰይጣናዊ ቡድን ነው።  ይህንን ዘራፊ ቡድን  ባስቀመጠልን የመከራ ክልል ሳንወናበድ፧ ወያኔ በዘረጋው የዘር ከዘር ልዩነት ሳንከፋፍለን፧ ኢትዮጵያን የማዳኑን ስራ የመስራት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጉዳይ  ነው።  ከወገኔ አንድ ሰው ቢሞትብኝ አልቅሼ የምቀብረው   አገር ሲኖር ነው። አገር ከሞተች ግን እንኳን በደስታ መኖር ይቅርና   በክብርም መቀበርያ  እናጣለን አገር እየገደለ ያለው ወንበዴ ወያኔን ቀድመን ልንገለው ግድ ይለናል።

ኢትዮጵያን ሁሉ ዘር ሳይለያየን ሃይማኖት ሳይከፋፍለን  ከዳር እስከዳር  እጅ ለእጅ ተያይዘን  በደስታ፧ በነፃነት ፧ በእኩልነት፧ የምንኖርባትን አገር ለመመስረት  ኢትዮጵያን እየገደላት ያለውን ወያኔ የተባለውን ገዳያን እንግደልላት ከጸጋዋ  ተካፍለን በፍቅራ እንድንጠለል ፍቅር አጥፊውን ወያኔን እናጥፋ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

ከ -ሳሙኤል አሊ ( ኖርዌይ)

Email samilost89@yahoo.com

June 14.2015

The post ኢትዮጵያን ባሰብኳት ግዜ አለቀስኩኝ!!! – ከ-ሳሙኤል አሊ appeared first on Zehabesha Amharic.

Hiber Radio: በሰሜን ጎንደር በታጣቂዎች በተወሰደው እርምጃ አምስት ንጹሃን ሲገደሉ ስድስት መቁሰላቸው ተነገረ፣ በእንግሊዝ ሁለት የጥበቃ ሰራተኞች ትገል ነበር ተብሎ ኢትዮጵያዊው ከሰባት ዓመት በላይ ተፈረደበት፣የአፍሪካ ህብረት የጦር ቃል አቀባይ በአልሸባብና በኢትዮጵያ ወታደሮቹ መካከል የደፈጣ ውጊያ መኖሩን ማመኑ፣ ደቡብ አፍሪካዊው በስጦታ ያገኘው ብልት ለእጮኛው ተርፎ ማስረገዙ መዘገቡ፣ በሆንግ ኮንግ የሚገኘው ቆንስላ በህግ ወጥ ንግድ መሰማራቱ መጋለጡ የሚሉና ሌሎችም አሉን

0
0

የህብር ሬዲዮ ሰኔ 7 ቀን 2007 ፕሮግራም
Habitamuአቶ ወረታው ዋሴ የሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ጉዳይ ሀላፊ በድህረ ምርጫ የተቃዋሚዎች ዝምታን አስመልክቶ ጠይቀናቸው ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ  (ሙሉውን ያዳምጡ)

<…በቀጥታ አይከል ከተማ ከላይ አርማጭሆ የመጡ ሶስት ወጣቶች ሻይ ቤት ተቀምጠው እያለ ታጣቂዎቹና ፖሊሶች በአንድነት መጥተው ወጣቶቹ ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ ሰው ግልብጥ ብሎ አትነኳቸውም ልጆቻችንን አለ በዚህ ጊዜ ወደ ሕዝቡ ተኮሰው አምስት ገለው ስድስት ቆስለዋል..እንዴት ሰላማዊ ሰው ላይ በመሳሪያ ጭፍጨፋ ይደረጋል?..> በሰሜን ጎንደር የተፈጸመውን ግድያ አስመልክቶቃለ መጠይቅ (ሙሉውን ያዳምጡ)

<…ሁበር ኤክስ ለቬጋስ አያዋጣም የሚያዋጣው ብላኩ ነው እሱ እንዲፈቀድ መታገል ጥሩ ነው ካልሆነ የቲፕ ነገር የግድ በስብሰባ መነሳት አለበት…>

አሌክስ አበራ ከሳን ፍራሲስኮ ስለ ሁበር የግል ልምዱን መሰረት አድርጎ ከሰጠው ማብራሪያ  (ውይይቱን ያዳምጡት)

ከኒዮርኩን እስር ቤት ያመለጡት መጨረሻ ያለመታወቅ የፈጠረው ጭንቀት እና ያልተሳካው በመቶዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶች አሰሳ( ልዩ ዘገባ)

በውጭ የሚኖረው ነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊ በጭብጨባ ተገቢውን ትኩረት አግኝቷል? (ምልከታ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የአፍሪካ ህብረት የጦር ቃል አቀባይ አልሸባብ ከኢትዮጵያ ወታደሮች ጋር መዋጋቱን አመነ

ኢትዮጵያዊው በእንግሊዝ ሁለት የጥበቃ ሰራተኞችን በጠርሙስ ልትገድል ነበር በሚል ከሰባት ዓመት በላይ እስር ተፈረደበት

በሆንግ ሆንግ የኢትዮጵያን ቆንስላ የሚመሩት ባለስልጣን በህገ ወጥ የዝሆን ጥርስ ዝውውር እንዳሉበት ተዘገበ

በሰሜን ጎንደር የአገዛዙ ታጣቂዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩሰው አምስት ሲገድሉ ስድስት ማቁሰላቸው ታወቀ

የደቡብ አፍሪካው ፍርድ ቤት በአልበሽር ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ አለመከበር ቅሬታ ፈጠረ

 የሰው ብልት በበስጦታ ያገኘው ደቡብ አፍሪካዊ ከእጮኛው ልጅ ማግኘቱ ተዘገበ

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የይስሙላውን ምርጫ የመቶ በመቶ አሸነፍኩ ማለቱ  አገዛዙ የማጭበርበር አቅም ማጣቱን ያያል ብሏል

የኢትዮጵያው ዋሊያ የሌሴቶን ቡድን 2 ለ1 አሸነፈ

የሱዳኑ ፕሬዝዳንትን የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናት የፍርድ ቤት ውሳኔ በመጣስ ከአገር እንዲወጡ መፍቀዳቸው ተዘገበ

 ሌሎችም ዜናዎች አሉ

(ህብርን ከዘሐበሻ፣አፍሮ አዲስ ድህረ ገጾችእና በሌሎችም ያዳምጡ።  በተጨማሪ  በማንኛውም ቀን በስልክ ለማዳመጥ 2139924347 ይደውሉ)ነ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢውሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8  ሰዓት 1340 .ኤም  የአየር ሞገድ ያዳምጡ። በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው።

The post Hiber Radio: በሰሜን ጎንደር በታጣቂዎች በተወሰደው እርምጃ አምስት ንጹሃን ሲገደሉ ስድስት መቁሰላቸው ተነገረ፣ በእንግሊዝ ሁለት የጥበቃ ሰራተኞች ትገል ነበር ተብሎ ኢትዮጵያዊው ከሰባት ዓመት በላይ ተፈረደበት፣የአፍሪካ ህብረት የጦር ቃል አቀባይ በአልሸባብና በኢትዮጵያ ወታደሮቹ መካከል የደፈጣ ውጊያ መኖሩን ማመኑ፣ ደቡብ አፍሪካዊው በስጦታ ያገኘው ብልት ለእጮኛው ተርፎ ማስረገዙ መዘገቡ፣ በሆንግ ኮንግ የሚገኘው ቆንስላ በህግ ወጥ ንግድ መሰማራቱ መጋለጡ የሚሉና ሌሎችም አሉን appeared first on Zehabesha Amharic.

የአማራው ኤሊትና የኤርትራ ጉዳይ –ኃይለገብርኤል አያሌው

Previous: Hiber Radio: በሰሜን ጎንደር በታጣቂዎች በተወሰደው እርምጃ አምስት ንጹሃን ሲገደሉ ስድስት መቁሰላቸው ተነገረ፣ በእንግሊዝ ሁለት የጥበቃ ሰራተኞች ትገል ነበር ተብሎ ኢትዮጵያዊው ከሰባት ዓመት በላይ ተፈረደበት፣የአፍሪካ ህብረት የጦር ቃል አቀባይ በአልሸባብና በኢትዮጵያ ወታደሮቹ መካከል የደፈጣ ውጊያ መኖሩን ማመኑ፣ ደቡብ አፍሪካዊው በስጦታ ያገኘው ብልት ለእጮኛው ተርፎ ማስረገዙ መዘገቡ፣ በሆንግ ኮንግ የሚገኘው ቆንስላ በህግ ወጥ ንግድ መሰማራቱ መጋለጡ የሚሉና ሌሎችም አሉን
0
0

shambe  zewduየአማራው ኤሊትና የኤርትራ ጉዳይ ኃይለገብርኤል አያሌው የቀድሞው የመዐህድ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሕብረት ም/ሊቅመንበርና የሞረሽ መስራች አባል ከፋሽስት ወረራ በሃላ በሃገራችን በፖለቲካ አጀንዳነት ያቆጠቆጠው የብሄረትኝነት እንቅስቃሴ በተለይ በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል የነበረው የኤርትራ ክፍለሃገር ከረጅም ዘመን የጣልያን ቅኝ አገዛዝ ነጻ ወጥቶ ከእናት ሃገሯ ጋር ከተቀላቀለች በሃላ የተከተለው የእንድነትና የራስገዝ አስተዳደር ጥያቄ ውስጥ ውስጡን ሲብላላ ቆይቶ የኤርትራን ነጻነት በሃይል ለማስመለስ ወድ ትጥቅ ትግል የገባው ጀብሃና ተከትሎት የተነሳው ሻአብያ የፖለቲካቸው የማዕዘን ድንጋይ የፀረ ቅኝ አገዛዝ ትግልና የፕሮፓጋንዳቸው መሰረት ባደረጉት የአማራው ሕዝብ ቅኝ ገዥነት ላይ በከፈቱት የሃሰት ጦርነት ይህ ነው የማይባል ስም ማጥፋትና ሰቆቃ መፈጸማቸው ታሪክ የማይዘነጋው ሃቅ ነው። በኤርትራ በርሃዎች የተጀመረው የአማራውን ስም —–[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]——

The post የአማራው ኤሊትና የኤርትራ ጉዳይ – ኃይለገብርኤል አያሌው appeared first on Zehabesha Amharic.


ሰበር ዜና –አልበሽር “ተለቀው”ወደ ሱዳን በረሩ

0
0

alebeshir
በደቡብ አፍሪካዋ ፕሪቶሪያ ግዛት ውስጥ በቁም እስር ላይ የነበሩት የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተላልፈው ሳይሰጡ ከደቂቃዎች በፊት ወደ ሱዳን መብረራቸውን የተለያዩ የዜና ምንጮች ዘግበዋል:: በቅርብ ሰዓት ውስጥ ካርቱም ይደርሳሉ የተባሉት እኚሁ ፕሬዚዳንት እዚያም እንደገቡ ለጋዜጠኞች መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል::

The post ሰበር ዜና – አልበሽር “ተለቀው” ወደ ሱዳን በረሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

በደ/ብሥራት ቅ/ገብርኤል: ሰበካ ጉባኤውን በማዳከም በካህናት እና ምእመናን ላይ ግፍ የፈጸሙት አለቃ ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ ተጠየቀ

0
0

bisrate-gabriel-church00የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን: በልማት ስም ከጥቅመኛ ግለሰቦች ጋር በመመሳጠር የቤተ ክርስቲያንን ሀብት እና ንብረት ለግሉ በማካበት በሚታወቀው የቀድሞው አለቃ ኃይሌ ኣብርሃ፥ በግንባታ እንዲኹም የባለቤትነት እና የተጠቃሚነት መብቱን አሳልፈው በሚሰጡ የኪራይ ውሎች ከመመዝበሩም በላይየሚልዮኖች የባንክ ባለዕዳ አድርጎት ያለተጠያቂነት ለመሰል ዘረፋ ወደ ሌላ ደብር ተዘዋውሯል፡፡

በእግሩ የተተኩት ግብታዊው እና ዐምባገነኑ መልአከ ብርሃን ዘመንፈስ ቅዱስ (የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ አባት)፥ በቃለ ዐዋዲው ደንቡ መሠረት በሰበካ ጉባኤው ሙሉ ተሳታፊ የኾኑትን እና የወሳኝነት ድርሻ ያላቸውን የማኅበረ ካህናት፣ የማኅበረ ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮችን በማሳደድ እና ከልጃቸው ጋር ተማክረው ሥልጣን በሌለው የክፍለ ከተማው የሰው ኃይል አስተዳደር ሓላፊ በኩል ወደ ሌላ አድባራት በማዘዋወር ሀብቱንና ይዞታውን ከሚነጥቁ ቀማኞች ጋር እየሠሩ ነው፡፡

* * *

  • በአለቃው ከሰበካ ጉባኤው የተባረረው የማኅበረ ምእመናን ተወካዩ እና የሰንበት ት/ቤቱ አባሉ ዲ/ን ሰሎሞን የኋላሸት ‹‹ወረቀት በትኗል፤ አድማ አነሣስቷል›› በሚል በአለቃው ጥያቄ ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮ በእስር ላይ ነው
  • በጥፋታቸው ስለሚቃወሟቸው፣ በዋና ሥራ አስኪያጁ ልጃቸው ተመክተው በግፍ ያዘዋወሯቸው ካህናት በሳምንት ጊዜ ውስጥ እንዲመለሱ፤ ሰበካ ጉባኤውም እንደ ቃለ ዐዋዲ ደንቡ በተሟሉ ተወካዮች እንዲጠናከር ምእመናኑ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል
  • በደብሩ የጠበልተኞች ማደርያ የኾነው ቦታ እንዲከበር የሚጠይቁትን የጠበል ዕድርተኞች ፊት በመንሳት ለግለሰብተላልፎ እንዲሰጥ እየተባበሩ ነው
  • በሰበካ ጉባኤው የሰንበት ት/ቤቱ ተወካይ በመልቀቁ በሌላ እንዲተካ ሰንበት ት/ቤቱ ለወራት ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አይደሉም
  • ምክትል አስተዳዳሪ በሚል ተቀምጦ ቀድሞ ደብሩን ለመዘበረው ኃይሌ ኣብርሃ መረጃ የሚያቀብለው ግለሰብ ተጨማሪ ምእመናንን በጥቆማ ለማሳሰር እየሠራ ነው

Source:: haratewahido

The post በደ/ብሥራት ቅ/ገብርኤል: ሰበካ ጉባኤውን በማዳከም በካህናት እና ምእመናን ላይ ግፍ የፈጸሙት አለቃ ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ ተጠየቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

አቶ አላሙዲንን እንደ በጎ አድራጊ፣ ቸር እና ደግ ሰው የምትቆጥሩ ሰዎች በጣም አስቂኝ ናችሁ

0
0

alamudi 1
ዓበጋዝ ዤዓንግት

አላሙዲ ሞራል እና ስነምግባር የጎደለው ሰው ነው፣ አላሙዲ የብዙ ኢትዮጵያውያንን ትዳር አፍርሷል፣ አላሙዲ ወርቅን ያክል የኢትዮጵያ ሀብት በብቸኝነት ያለ ማንም ከልካይ እየዘረፈ ያለ ሰው ነው።

ብዙዎች አላሙዲ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያንቀሳቅሰው ንግድ ትርፍ እንደሌለው እና ይልቁንም በተለያየ ጊዜ ለግለሰቦች በሚያደርገው የገንዘብ ዳረጎት ብዙ ሚሊዮን ብሮች የሚከስር ግለሰብ አድርገው ማየታቸው አንድም ካለማወቅ ነው በሌላ በኩል ደግሞ ስለ ሰውየው በተደራጀ መልኩ በጎ ነገሮች በሚያወሩ እና በሚያስወሩ ሰወች ተሸውደው ነው ብለን እናስባለን።

ቢሆንም ግን አላሙዲ ህወሀት/ወያኔወች በራሱ ምንም ሊያደርጉት የማይችል ግለሰብ ነው፤ ምክንያቱም እሱ የአይነኬወቹ ሰይጣን አምላኪ ኢሉምናቲወች አባል ነው (ይህን አላምንም የሚል ሞባይል እና ለፕቶፕ ላይ አፍጥጦ ፎቶ ላይክ ከማድረግ ይመርምር)፤ እስከዛሬ ህወሀት/ወያኔወች በእሱ ምክንያት አይናቸው እየቀላ ምንም ሊያዳርጉት ያልቻሉት ሰው ነው፤ ስለዚህ ምርጫቸው እና የሚያዋጣቸው አብረው ተሞዳሙደው መዝረፍ ነው።
bereket alamudi demeke
በአጠቃላይ አቶ አላሙዲ (ሼኽ የማልለው ሙስሊም ስላልሆነ ነው) መታየት ካለበት እንደ በጎ አድራጊ ሳይሆን እንደ ሞራል እና ምግባር የሌለው ዘራፊ ሰው ነው፤ ሊመሰገን አይገባውም። ምናልባት የወሎ ሰወች ከሚዘርፈው ነገር ቆንጥሮ ስታዲዬም ገንብቶላቸዋል፣ ኮምቦልቻ ላይ የህወሀት/ወያኔን መሰፍን ኢንጅነሪንግ ጉሮሮ የሚዘጋ በአፍሪካ ተወዳዳሪ የሌለው የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ሊገነባላቸው መሰረት ድንጋይ ጥሏል፣ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሚሆን ቴሪሸሪ/ ሦስተኛ ደረጃ የህክምና ማዕከልም ሊገነባላቸው ስለሆነ ቢያመሰግኑት አይከፋኝም።

ይህን የፃፍኩት አሁን በታክሲ ስሄድ ማንነቱን ባላወቅኩት ኤፍ ኤም ራዲዮ አንድ የሰውየውን ዳረጎት የሚፈልግ አይነት ጋዜጠኛ ሰውየውን ሲያቆለጳጵስ፣ ሲክብ እና ሲያሽቃብጥ ሳልፈልግ ሰማቼ አድርባይነታችን አብሽቆኝ ነው።

The post አቶ አላሙዲንን እንደ በጎ አድራጊ፣ ቸር እና ደግ ሰው የምትቆጥሩ ሰዎች በጣም አስቂኝ ናችሁ appeared first on Zehabesha Amharic.

አስር አለቃ ጫላ ጋዲሳ ራሱን አጠፋ

0
0

ትህዴን ባሰራጨው ዘገባ ለሃምሌ ወር 2007 ዓ/ም የቆይታ ጊዜአቸውን ጨርሰው በሚገኙ የሰራዊት አባላት ላይ እየተካሄደ ባለው የከፋ የዘረኝነት ምልመላ ምክንያት አንድ የኦሮሞ ተወላጅ የሆነ የአስር አለቃ ማዓረግ አይገባህም በመባሉ የተነስ እራሱን እንዳጠፋ ተገለፀ።

newsለትህዴን በደረሰው መረጃ መሰረት- የ23ኛ ክፍለ ጦር የ2ኛ ሬጅመንት በ3ኛ ሃይል ውስጥ የቲም ምክትል አዛዥ የነበረ አስር አለቃ ጫላ ጋዲሳ የተባለው ወታደር በተለያዩ መድረኮች ላይ ተቃራኒ የሆነ ሃሳቦችን ያቀርባል ለህገ መንግስቱ ታማኝ አይደለም መንግስትን ያማርራል የሚሉ ነጥቦችን አስቀምጠው ማዕረግ አይገባህም ተብሎ ከሃይል አመራር በላይ ያሉ አዛዦች ውሳኔውን በማስተላለፋቸው ምክንያት ስሜቱ የተጎዳው ይህ ወታደር ስብሰባው እንዳለቀ ዋርዲያ ነኝ በሎ በመውጣት እራሱን እንዳጠፋ ከእዙ የደረሰን መረጃ አመለከተ።

በአሁኑ ጊዜ በኢህአዴግ የሰራዊት አባላት ውስጥ ያለው የከፋ የዘረኝነት አድሎዎ ለማዕረግ እድገትና ለተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ሲባል በሚደረጉ ምልመላዎች ላይ የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች በሰራዊት ውስጥ ኢ- ፍትሃዊ የሆነ አሰራር እየሰሩ መሆናቸውን በተለያዩ የሰራዊት እዞች ውስጥ የሚገኙ ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ ያስረዳል ሲል ትህዴን መረጃውን ቋጭቷል::

The post አስር አለቃ ጫላ ጋዲሳ ራሱን አጠፋ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሰማዕት መንግሥቱ ጋሼ – ከወለጋ እስከ ሊቢያ

0
0
 አይ እናት እስቲ ተመልከቷት ። እናት ምንጊዜም እናት ናት ። ፍቅሯ እስከመቃብር የሚዘልቀውን የእናት ብቻነው ።


አይ እናት እስቲ ተመልከቷት ። እናት ምንጊዜም እናት ናት ። ፍቅሯ እስከመቃብር የሚዘልቀውን የእናት ብቻነው ።

※ በእኔ በኩል በሊቢያ ሰማዕታት ጉዳይ ላይ የምጽፈው ማስታወሻዬ ላይ ሌላ ሰማዕት እስካልተገኘ ድረስ ይህ ታሪክ የመጨረሻዬ ነው ብዬ አስባለሁ ※

” ዘ ሐበሻ እና ድሬ ትዩብ የተባሉ ድረገጾችን ሳላመሰግን አላልፍም ። ምክንያቱም እግር በእግር እየተከታተሉ በፌስቡክ ፔጄ ላይ የምጽፈውን የሰማዕታቱን ታሪክ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ አንባቢዎቻቸው መረጃ በማቅረብ የሰማዕታቱ ቤተሰቦች እንዲረዱ ስላደረጉ ከልብ አመሰግናለሁ” ።

መንግሥቱ ጋሼ ሩቅ አልሞ ቅርብ ያደረው ሰማዕት ።

መንግሥቱ ጋሼ ሩቅ አልሞ ቅርብ ያደረው ሰማዕት ።

” በተለይ በየክፍለ ሀገሩ ለማደርገው ጉዞዬ በስዊዘርላንድ በሚኖረው ወንድሜ ጴጥሮስ አሸናፊ አማካኝነት የተዋወቁኳቸው ኢትዮ ዙሪክ የእግር ኳስ አባላትና ደጋፊዎች ፣ በመጨረሻው ጉዞዬ ወንድሜ ዘማሪ ቀሲስ ወንድወሰን በቀለና የሚኒሶታዎቹ አንድነት የሙዚቃ ባንድ አባላት ሙሉ የሆቴልና የትራንስፖርት ፣ እንዲሁም የስልክ ካርድ መሙያ ይሆንሀል ብላችሁ የላካችሁልኝን በአግባቡ ተጠቅሜበታለሁ እናም ምስጋናዬ ካለሁበት ይድረሳችሁ ” ። ይህ ጉዳይ ያለ እናንተ ተሳትፎ የመሳካቱ ነገር አጠራጣሪነቱ ከፍ ያለም ነበር ። ምክንያቱም አሁን እኔ አሁን ባለሁበት ሆኔታ አቅም ኖሮኝ ሁሉንም እንዲህ በተሟላ መልኩ ማቅረብ እችላለሁ ብዬ ማሰቡ ስለሚከብደኝ ማለት ነው ።

ከዚህ በኋላ የሁሉንም የሰማዕታት ቤተሰቦች የመገኛ አድራሻና የባንክ ሒሳብ ጭምር ፖስት ስላደረግሁ ገንዘብንና ሌሎች ጉዳዮችን ከእኔ ጋር ጭምር በትነካኩ ይመረጣል ። አሁን የሰማዕት መንግሥቱ ጋሼን ታሪክ በእርጋታ እንዲያነቡ ልጋብዝዎት ። መልካም ንባብ ።

※※※★★★※※※★★★※※※

ሐሙስ ከረፋዱ 4 ሰዓት ላይ ራሴን አቶ ሙክታር ከድር የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ቢሮ ውስጥ አገኘሁት ። በፕሬዘዳንቱ ቢሮ የመገኘቴ ምክንያቱ ደግሞ ወደ ወለጋ ለመሄድ መዘጋጀቴን የሰሙ አንድ አባት በትግራይ ክልል ወደ ሰማዕታቱ ቤት ስሄድ የአክሱምና የኢንቲጮ ከንቲባዎች እና አስተዳዳሪዎች ያደረጉልኝን ትብብር ከፌስቡክ ገጼ ላይ አንብበው ስለነበር አሁን ደግሞ የኦሮሚያ ክልል ትብብር እንዲያደርግልኝ ለማድረግ በማሰብ ነበር እኔን መውሰዳቸው ።

ፕሬዚዳንቱ በስብሰባ ምክኒያት አልነበሩም ። ነገር ግን ስለ አላማው እኝህ አባት ለፕሬዚዳንቱ ጸሐፊ ሲያስረዱዋቸው ምክትል ፕሬዘዳንቱ በቢሮአቸው በመኖራቸው ወደ እሳቸው እንድንሄድ አደረጉን ። በዚያም ለምክትል ፕሬዘዳንቱ አቶ አብዱልአዚዝ የመጣንበትን ጉዳይ እኚሁ አባት አስረዱዋቸው ። ምክትል ፕሬዘዳንቱም እጅግ በሐሳቡ መደሰታቸውን ገልጸው ነገር ግን መኪኖች በሙሉ ለስብሰባ ናዝሬት በመሄዳቸው እንደምንም ብለን እስከ አርብ አምስት ሰዓት እንድንቆይ ጠየቁን ። እኔ በሁኔታው ብገረምም የማልደብቃችሁ ነገር በማግሥቱ የምፈጽመው የግል ጉዳይ ስለነበረኝ መቆየቱን አልጠላሁትም ።

ነገር ግን ምክትል ፕሬዘዳንቱ አስከምሽት ድረስ ከሥራ ሰዓት ውጪ ጭምር መኪና ቢፈልጉም ሊያገኙኝ አልቻሉም ። ይህንንም ጥረታቸውን በየሰዓቱ እየደወሉ ያሳውቁን ነበር ። እኔም ቅዳሜን መዋል ሰኞ ያለኝን የኤምባሲ ቀጠሮ ያዛባብኛል ብዬ ስላሰብኩ ማንንም ሳልጠብቅ ቅዳሜ በሌሊት ጉዞዬን ወደ ነቀምት አደረግሁ ። በመሃል ግን ምክትል ፕሬዘዳንቱ ነዳጅ የተሞላ V-8 መኪና ከነሹፌሩ አዘጋጅተው ለእኚያ አባት ይምጡና ጉዞአችሁን ጀምሩ ቢሏቸው እኔ ግን አምቦ ደርሼ የነቀምቴ መኪና ተሳፍሬ ነበር ። ከቡር አቶ አብዱልአዚዝ እግዚአብሔር ያክብርልኝ ። የእኔ ጊዜዬን ለመሻማት መቸኮል እንጂ እንዳደረጉልኝ ነው የምቆጥረው ።

ወሮ አለሚቱና የልጅ ልጆቻቸው ።

ወሮ አለሚቱና የልጅ ልጆቻቸው ።


ለማንኛውም በሰማዕታተ ሊቢያ ላይ ለጀመርኩት ጽሑፍ ይህ የወጣት መንግሥቱ ጋሼ ታሪክ የመጨረሻዬ ነው ብዬ እገምታለሁ ። ትናንት ከአዲስ አበባ ተነስቼ ነቀምት ገብቼ አዳሬን በነቀምት አደረግሁ ። በነቀምት የፌስቡክ ጓደኛዬና በወለጋ ዩኒቨርስቲ መምህርት የሆነችው መምህርት ስርጉት እና በመንግሥቱ ጋሼ ሕይወት ዙሪያ ለሁለት ጊዜ ያህል ፕሮግራም የሠራው አሁን ደግሞ ወደ ሥፍራው የሚወስደኝ በነቀምት ፋና ኤፍኤም ራዲዮ ጋዜጠኛ የሆነው ጋዜጠኛ ኬነሳ አመንቴ አስቀድመን ተደዋውለን ስለነበር በግንባር ተገናችተን ሰለ ጉዞአችን ተወያይተን ወደ የማደሪያችን አመራን ።

በማግስቱ ትናንት ሰኔ 7/10/2007 ዓም እሁድ ከንጋቱ ሁለት ሰዓት ያረፍኩበት ሆቴል ድረስ የመጣው ጋዜጠኛ ኬነሳ ወደ አውቶብስ ተራ ይዞኝ ይሄዳል ብዬ ስጠብቅ ለካስ አስቀድሞ ተነጋግሮ ኖሮ በቀጥታ ወደ ምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ተፈሪ ጢያሮ ቢሮ ይዞኝ በመሄድ ለአስተዳዳሪው የመጣሁበትን ጉዳይ በማስረዳት የምንሄድበት ሥፍራም ያለ መኪና በእግር ሩቅ መሆኑን በመንገር አስተዳደሩ መልካም ፈቃዱ ሆኖ መኪና እንዲፈቅድልን በትህና ጠየቀ ።

በዕለተ ሰንበት ስብሰባ ሊገቡ በዝግጅት ላይ የነበሩት ባለሥልጣናት በሙሉ በሁኔታው በመደሰት መኪና ከነሹፌሩ ፣ እንዲሁም የዋዩ ቱቃ የወረዳዋን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ለቺሳ በቀለ ስብሰባውን አቋርጠው ከእኛ ጋር በመሄድ በመንገዳችን ሁሉ እንዲረዱን በመንገር ጉዞአችንን እኔ ፣ ኬነሳ ፣ ምክትል አስተዳዳሪው አቶ ለቺሳ በቀለ መምህርት ስርጉት እና ጓደኛዋ መምህርት መአዛ ሆነን ከነቀምት ወደ ምስራቅ አቅጣጫ ጉዞ ጀመርን ። አርብ ገበያ የምትባል ከተማ እንደደረስን በቀኝ በኩል ታጥፈን ወደ ደቡብ አቅጣጫ የጥርጊያ የገጠር መንገድ በመጓዝ “ጋረ ሁዳ ” የገጠር መንደር ከተባለ ቦታ ስንደርስ መኪናዋን አቁሙን እኛ መኪና የማይገባውን የእግር መንገድ ተያያዝነው ።

አካባቢው ለምለም ነው ። ግራናቀኙ ሰሞኑን በዘነበው ዝናብ አማካኝነት ምድር አረንጓዴ ምንጣፍ የተነጠፈባት መስላ ትታያለች ። የበቆሎ ቡቃያ ከመሬት ብቅ ብቅ ብሎ መታየት ጀምሯል ። በሚያምረው መስክና በገጠር መንደሮች እያቋረጥን ፣ መንገድ ላይ የምናገኛቸውን ሰዎች ” አሸም ፣ አሸም አከም ቡልተን ” እያልን ሰላምታ እየተለዋወጥን ከሰማዕቱ መንግሥቱ ጋሼ ቤተሰቦች ዘንድ ደረስን ።

የመምጣታችን ዜና አስቀድሞ ደርሶዋቸው ስለነበር ቤተዘመድና ጎረቤቶች ሁሉ ተሰብስበው ነበር የጠበቁን ። ወንበር ተደርድሮ ፣ አጎዛ ተነጥፎ ፣

ሁላችንም ቦታ ቦታችንን ያዝን ። የመንግሥቱ ጋሼ ወላጅ እናት አጠገቤ ተቀመጡ ። እንደ አስተርጓሚ ሆኖ ጊዜያዊ አገልግሎት ለመስጠትም ጋዜጠኛ ኬነሳ ተሰይሟል ። እኔም ቢሆን የዋዛ አይደለሁም ስናገረው ስብርብር ላድርገው እንጂ የሐረርጌ ልጅም በመሆኔ ኦሮምኛ ያደግሁበት ቋንቋዬ በመሆኑ ብዙም አልቸገርም ። እናም ቢያንስ ቱርጁማኑ ቢሳሳት እንኳን ለማረም እችላለሁ ማለት ነው ። አሁን ወደመጣንበት ጉዳይ ልንገባ ነው ። ወላጅ እናት ወሮ አለሚቱ ገለታ ስለሁሉም ነገር እንዲህ ይነግሩናል አድምጡዋቸው ።

ወሮ አለሚቱ ገለታና በሞት የተለዪዋቸው ባለቤታቸው አቶ ጋሼ ጉዲና በሕይወት በነበሩ ጊዜ 9 ወንዶችና 3 ሴቶች ልጆችን አፍርተዋል ። መንግሥቱ ጋሼ ደግሞ 6ተኛ ልጃቸው ነው ። የአባት በጊዜ ማረፍ 12 ልጆችን የማሳደግ ኃላፊነት በወሮ አለሚቱ ትከሻ ላይ ወደቀ ። ልጆች የጀመሩትን ትምህርት አቋረጡ ፣ ብዙዎቹ በላይ በላዩ በተከታታይ የተወለዱ በመሆናቸው የእድሜ ልዩነትም የላቸውም ።

በኦሮምኛ ረቢ ኢሲኒ ሀኬኑ ተብላችኋል ። እግዚአብሔር ይስጣችሁ ነው የሚሉት እማማ አለሚቱ ።

በኦሮምኛ ረቢ ኢሲኒ ሀኬኑ ተብላችኋል ። እግዚአብሔር ይስጣችሁ ነው የሚሉት እማማ አለሚቱ ።

ማብላት ፣ ማጠጣቱ ፣ ማልበስ ፣ ማስተማሩ ለወሮ አለሚቱ ጭንቅ ሆነ ። ነገር ግን ባይፈልጉትም ሳይወዱ በግዳቸው መንግሥቱ ጋሼን ጨምሮ 3 ልጆቻቸውን በእረኝነት ለተለያዩ ሰዎች በህፃንነታቸው ለእረኝነት አሳልፈው ሰጡ ። በዚህ የእረኝነት ሕይወት ግን መንግሥቱ አንድ አመት ብቻ ነው መቆየት የቻለው ። በአንድ በኩል የእናቱ ፍቅር በሌላ በኩል የሰው ቤት የሰው ነው ቢርብ መሶብ ተከፍቶ የማይበላበት ፣ ቢከፋ የልብን አውጥቶ ለመናገር አቅም የማይገኝበት ፤ ብቻ ብዙ ምክንያቶችን ይዞ ዓመት ሙሉ ፀሐይና ዝናብ ፣ ረሃብና ጥም ተፈራርቀውበት የሰራበትን ደምወዙን አንድ ፍየል ገዝቶበት ወደ እናቱ ተመለሰ ። አሁን መንግሥቱ እድሜው 11 ደርሷል ።

መንግሥቱ ትምህርቱን ከ3 ተኛ ክፍል እንዳቋረጠ አልተመለሰበትም ። ታላላቆቹ ትዳር መመስረት በመጀመራቸው የሰው ኃይል ጫና ለእናት መቀነስ ቢጀምርም እድሜያቸው እየገፋ በመምጣቱ ማረፍ ሲገባቸው የቤቱንም የውጪውም ሥራ የሚጠብቀው እሳቸውን ሆነ ። መሬቱ እኮ አለ ። ነገር ግን ማን ይረሰው ። ችግር ሆነ ። በዚህ ላይ ከመሬቷ ላይ ትዳር ለያዙት ድርሻቸውን እየሰጡ ሳሳ እያለ መጥቶባቸዋል ።

ለዚህ ደግሞ መንግሥቱ እናቱን ለማገዝ መሬት ያላቸው ነገር ግን በስንፍናም ቢሉ በጥጋብ ለማያርሱ ባለመሬቶች የእኩል በማረስ ምርት ሲደርስ በመካፈል በቀለብ በኩል እናቱን ማገዝ ጀመረ ። ይህም ቢሆን ባለመሬቶቹ በሚቀጥለው የምርት ዘመን እራሳቸው ያርሷታል እንጂ ለመንግሥቱ አያስደግሙትም ። እንደሚፈልገው እናቱን መርዳት ያለመቻሉ ያንገበግበው ጀመር ።

አዴ አለሚቱ ባለቤታቸው ከሞቱ በኋላ ሌላ ባል ለማግባት አልፈለጉም ። ዶሮ ከክንፎቿ በታች ጫጩቶቿን አቅፋ እንደምትኖር እሳቸውም መላ ዘመናቸውን እንደ አናትም እንደ አባትም ሁነው ልጆቻቸውን ለማሳደግ ሲሉ ዋጋ ከፍለዋል ።

እማማ አለሚቱ በተነጋገርነው መሠረት ጥቁር ልብሳቸውን አውልቀው ነቀምት በመምጣት የባንክ ሒሳብ ቡካቸውን ከባንኩ ሥራ አስኪያጅ ተቀብለዋል ።

እማማ አለሚቱ በተነጋገርነው መሠረት ጥቁር ልብሳቸውን አውልቀው ነቀምት በመምጣት የባንክ ሒሳብ ቡካቸውን ከባንኩ ሥራ አስኪያጅ ተቀብለዋል ።

መንግሥቱ አሁን እድሜው 14 ደርሷል ። ከአንድ ፍየል ተነስቶ 10 ከብቶችን ለማፍራትም በቅቷል ። ሆኖም ግን በመንደሯ ውስጥ በአንደኛው ግቢ ውስጥ የጎጆ ቤት ወደ ቆርቆሮ ቤት መለወጡ በመንደሯ ውስጥ መነጋገሪያ ሆኖአል ። ቆርቆሮ ቤቷ የተሰራችው በመጀመሪያ ሱዳን ከዚያ ሊቢያ በመቀጠል አውሮፓ ገባ የተባለ ልጅ በላከው ብር ነው መባሉ ደግሞ መንግሥቱና ጓደኞቹ ቅንአት ቢጤ ፈጥሮባቸዋል ። ነገር ግን እንዴት እንደሚኬድ ደግሞ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም ።

15 ኛ ዓመቱን ሲያከብር ግን እስካሁን አርብ ገበያ በምትባለው ከተማ ውስጥ የሚኖር አብዱ የተባለ ህገወጥ ደላላ እጅ ይወድቃል ። መንገዱም አልጋ በአልጋ እንደሆነ ይሰበካል ። ከአስሩ ከብቶችም ሰባቱን በመሸጥ ሦስቱን ደግሞ ለእናቱ በመስጠት 4 ሆነው እያንዳንዳቸው ለደላላው አስር አስር ሺ ብር በመስጠት ጉዞ ወደ ሱዳን ካርቱም ያደርጋሉ ።

መንግሥቱ በሱዳን ላለፉት አራት አመታት ተቀምጦ ለመሥራት ጥረት አድርጓል ። እንዳሰበው ለእናቱ የተመኘውን የቆርቆሮ ቤት ለመሥራት የሚያስችል ጥሪት መቋጠር ግን አልቻለም ። በመሃል ግን ከሱዳን ወደ ሊቢያ ከመሄዱ አስቀድሞ ለእናቱ 8 ሺህ ብር በመላክ የተመኘውን የቆርቆሮ ቤት ማሰራት ጀምሮ ነበር ። እንደውም ጠባብና ትንሽ እንዳይሆን ብሎ በሰፊው ነው ያስጀመራቸው ። ሳይጨርሰው ፍፃሜውንና የእናቱንም ደስታ ሳያይ ቀረ እንጂ ።

ከጓደኞቹ ሁለቱ ከሱዳን ወደ ሊቢያ ከዚያም ባህሩን ተሻግረው እድል ይቀናቸውና ጀርመን ይገባሉ ። ከጀርመንም ሱዳን ለቀሩት ለመንግሥቱና ጓደኛው እንዴት አድርገው ሊቢያ ከዚያም ባህር ተሻግረው አውሮፓ እንደሚመጡ ይነግሯቸዋል ። እነ መንግሥቱም ሐገር አማን ብለው በተነገራቸው መሰረት ከሱዳን ወደ ሊቢያ መንገድ ይጀምራሉ ። በመሃል ጉዞ እንደጀመሩ ከሌሎች ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ጋር ተቀላቅለው ጉዞ ወደፊት ወደ ትሪፖሊ ።

የሊቢያ ክልል እንደገቡ አሸባሪው ቡድን ተኩስ ከፍቶ ቁሙ ሲል መንግሥቱና ጓደኛው በተለያየ አቅጣጫ ለማምለጥ ሮጡ ። ጓደኛው የሄደበት መንገድ ሲያስመልጠው መንግሥቱ የሮጠበት መንገድ ግን ከጨካኞቹ እጅ ጣለው ። መንግሥቱ ከታረዱት ከእነ ዳንኤል ሐዱሽና ተስፎም ታረቀኝ ጋር ሳይሆን ጭንቅላታቸውን በጥይት ከፈረሰው ከሁለት ህፃናት አባቱ ብርሃኑና ከቂርቆሱ ባልቻ ጋር ሆነ ። ህልሙን እውን ሳያደርግ እናቱን ለማስደሰት እንደተመኘ በሰው ሐገር ቀባሪ እንኳን ሳያገኝ በምደረበዳ አሸዋ ውስጥ ከነህልሙ ተቀበረ ።

እኒህ የወሮ አለሚቱ ቀሪ ልጆች ናቸው ። ሦስቱ በቦታው ባለመኖራቸው ነው ።

እኒህ የወሮ አለሚቱ ቀሪ ልጆች ናቸው ። ሦስቱ በቦታው ባለመኖራቸው ነው ።

የመንግሥቱን መሞት ሸሽቶ ያመለጠው ጓደኛውና በኢንተርኔት አሰቃቂውን ድርጊት ያዩ የሚያውቁት ሰዎች መጥተው ለእናት አረዷቸው ። ያለ አባት 12 ልጆች ያሳደጉት የ60 ዓመቷ እናት ዛሬ ሀዘኑ ከልባቸው ባይወጣም ኢትዮጵያውያን በሙሉ በልጃቸው ሞት ማልቀሳቸው አፅናንቷቸዋል ።

አሁን እማማ አለሚቱ የሚያሳስባቸው ሌላ ነገር ነው ። እድሜዬ አልቋል ። አሁን ምንም ቀረኝ ብዬ አልጓጓም ። የሚያሳስበኝ ከአስራአንዱ ልጆቼ የሥስቱ ብቻ ነው ። አንዱ ወደ 11ኛ ክፍል አልፎ አንዴ ከእርሻው እናቱን በማገዝ አንዴ ከትምህርቱ ሲል ሲኦሲ ተፈትኖ ማለፍ አቅቶት ከቤት ውሏል ። አንደኛው ወንድ ልጃቸውና አንዷ ሴት ግን በትምህርት ላይ ናቸው ። የሚረዳቸው እና የሚያበረታታቸው ካገኙ ተስፋ የሚጣልባቸው ናቸው ።

እኔም የመጣሁበትን ምክንያት አስረድቼ ። ጆሲ ሄዶ ከረዳቸው በቀር ማንም እንዳልጎበኛቸው በነበረኝ መረጃ መሠረት የሚኒሶታ የአንድነት የሙዚቃ ቡድን አባላት በአቶ ሰሎሞን በኩል ይሰጥልን ያሉትን 50ሺህ ብር እና የኢትዮ ዙሪክ የእግር ኳስ ቡድን አባለት እንደተለመደው የላኩትን 8,520 ብር ጨምሮ ከሀገረ አሜሪካን እነ ሕይወት ፣ አቶ አማረ ፣ አቶ ሚናስ ፣ ባልና ሚስቶቹ ሔለን ነጋሽና ፈረደ ዓለሙ ዘማሪ ቀሲስ ወንደሰን በቀለ ፣ ቤተልሔም ከቱርክ ውቢት ከግሪክ እና ስሜ አይጠቀስ ያለች እህት ከሳዑዲ የላኩትን በአጠቃለይ 92500 ብር ያስረከብኩ ሲሆን ወንድሜ ዘማሪ ቀሲስ ወንድወሰን በቀለ ፣ ሚኒሶታዎች እንዲሁም ኢትዮ ዙሪክ የእግር ኳስ ቡድን አባላት ለመንገድና ይህን ጉዞ ስታደርግ ለምታወጣው ወጪ ይሁንህ ብለው ከላኩልኝ ሳንቲም ላይ በእኔ የማይታሰብ በሰጪዎቹ የሚደመርልኝ 2480 ብር በመጨመር በአጠቃላይ ለእማማ አለሚቱ 95000 ብር አስረክቤአለሁ ። የቀረውን ጥቂት ብር ለትርሓስ ፣ ለሮዚና ፣ ለደንኤል ሐዱሽ ፣ ለተስፎም እና ለዲያቆን እንዳልክ ቤተሰብ በየባንካቸው አስገባለሁ ።

እዚህ ላይ እንደተለመደው ቢሰሙኝም ባይሰሙኙም ወቀሳዬን የማቀርብባቸው አካላት አሉ ። እነሱም ።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አመራሮች ✔ ሀዘኑ ብሔራዊ ነው ። ግን ደግሞ እንደ ክልል ምን አደረጋችሁ ? በተለይ ለገበሬ ልዩ ፍቅር እንዳላችሁ ትናገራላችሁ ሁሌም የምንሰማው ነው ። ታዲያ እኚህ ያለ ባል ብቻቸውን 12 ዜጋ ያሳደጉ አዛውንት ሴት ይህ ከባድ ሐዘን በደረሰባቸው ጊዜ ከምን ደረሳችሁ ? ሌላው ቢቀር እንኳን የሴቶች ጉዳይ ወዘተ ተብላችሁ የምትጠሩ ምነው ድምጻችሁ ጠፋሳ ! በእርግጥ የወረዳውና የዞኑ አስተዳደር ከሀዘኑ ቤት ተገኝተዋል ነገርግን ምን ያደርጋል መንግሥትን ያህል ትልቅ አካል ደሀ ቤት ያውም ከባድ ሐዘን የደረሰባቸው አዛውንት ቤት ገብቶ የቡና መግዣ እንኳን ሳይሰጥ መሄዱ ነውር ነው ። ባህላችንም አይደለም ። በዚህ በኩል የአዲስ አበባ መስተዳደር ለተጎጂዎቹ ቤተሰቦች ያደረገው ያስመሰግነዋል ።

የኦሮሚያ ቴሌቪዥን ✔ ጣቢያችሁ ምርጥ ምርጥ የተባሉ ድራማዎችን እና ፕሮግራሞችን እንደሚያቀርብ ብዙዎች ያዩዋችሁ ይናገራሉ ። በዚህ ሐዘን ላይ ግን አለመገኘታችሁ ያስወቅሳችኋል ። እርግጥ ኦሮሚያ ሰፊ ናት ። ነገር ግን ምንም ሰፊ ብትሆንም ነቀምቴ ሩቅ አይደለችም ። ፕሮግራም ብትሰሩ አዛውንቷ ይረዳሉ ፣ እግረመንገዳችሁንም የስደትን አስከፊነትና እስከአሁን በአርብ ገበያ የድለላ ሥራውን እየሰራ ያለውን አቶ አብዱንም ታነጋግሩት ነበር ። ምናልባትም ማን ያውቃል ይህ ደላላ ጌታውን የተማመነና ላቱን ከደጅ የሚያሳድር እንደሆነም ትነግሩን ነበረ ።

የኦሮሚያ አርቲስቶች ✔ አፈርኩባችሁ የሙያ አጋራችሁና ጓደኛችሁ ጆሲ ከአዲስ አበባ ፣ አራት አርቲስቶች ከሚኒሶታ ለእኚህ አዛውንት ሲደርሱ እናንተ በሐገር ውስጥ ያላችሁ ምን ነካችሁ ? አደራ ነገ ደግሞ ያ መከረኛ ጋዜጠኛ መጥቶ ሲጠይቃችሁ እኛ ቀሪ ሃብታችን ሕዝባችን ነው እያላችሁ በሳቅ ፍርድ አድርጋችሁ እንዳትገድሉን ብቻ ።

ባለሃብቶቻቸው ✔ ምን አለበት በሚሊዮን የሚቆጠር ብር እንኳን ባትሰጡ ጥቂት መቶ ብሮችን ብትወረውሩላቸው ብዬ ልጠይቃችሁ አሰብኩና ተውኩት ። ምክንያቱም የሞቱት ለካስ ዘፋኞች አይደሉም ። አፉ በሉኝ አለ የአፋር ሰው ። እናም ይቅርበሉኝ ወይ አለማወቅ ። አንዳንዴ ሳስበው ግን ብር ወረቀት ነው ያልቃል ። የማያለቅው ፍቅርና ለሰማዕታቱ የተሰጠውን ክብር ሳስበው ከሚያልቀው ብር የሚበልጥ የማያልቅ የአምላክ ፀጋ ነው በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለሰማዕታቱ ቤተሰቦች የሰጡዋቸው ። እናም ይቅር በሉኝ ። ከተቻላችሁ ግን ሦስቱን ልጆች ሥራ ብታገኙላቸው መልካም ነው ። አይይይይ የእኔ ነገር ደግሜ አስቸገርኳችሁ አይደል ምን ላድርግ ብላችሁ ነው ቢጨንቀኝ ያየሁትም እረፍት ቢነሳኝ ነው ።

የፕሮቴስታንት ቸርች አመራሮች ✔ ሟች መንግሥቱ ጋሼን ጨምሮ ቢያንስ ፎቶው ላይ የምታዩዋቸውን የእምነታችሁ ተከታዮች አድርጋችኋቸዋል ። ታዲያ እንዲህ በሆኑ ጊዜ ቢያንስ ሌላው ቢቀር የሚለበስ እንኳን አታጡምና እስቲ ጎብኟቸው ።
ፍጻሜው ይመር እንጂ አብረውኝ የሄዱትን የወረዳዋን ምክትል አስተዳዳሪ ገንዘቡ ዝም ብሎ ከሚቀመጥና ከሚጠፋ በከተማዋ ላይ ትንሽ መሬት ብትሰጡዋቸው እና ልጆቻቸውም ሥራ የሚያገኙበት በዚያውም አዛውንቷም የሚጦሩበት ወፍጮ ቤት ብንከፍት ብዬ ጥያቄ አቅርቤላቸው ነበር ። እሳቸውም በቅርቡ እናደርገዋለን ካቢኔው እንዲወስንበት ጥያቄ አቀርባለሁ ። መልሱንም እነግርሃለሁ ብለውኛል ። እንጠብቃለን ኦቦ ለቺሳ ።

በመጨረሻም ዛሬም ነቀምት መዋሌ ነው ። የቸኮልኩበት የኤምባሲ ቀጠሮም ቀለጠ ፣ ውኃ በላው ማለት ነው ። ምክንያቱም እማማ አለሚቱ ከገጠር መጥተው የባንክ አካውንት መክፈት አለባቸው ። ጆሲ የሰጣቸው 40 ሺ ብር እንኳን እስከአሁን በቃጫ አስረው ከቤት ነው ያስቀመጡት ። ይሄ ደግሞ አደጋ አለው ። እሱም ባንክ መግባት አለበት ። እኔ ይዤው የሄድኩ በባንክ ያለ ነው እሳቸው የባንክ አካውንት ሲያወጡ ጠብቄ የግድ ማዘዋወር አለብኝ ።

እፎይ ሁሉንም ጨርስኩ ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የንግድ ባንክ ሰራተኞች ሥራ አስኪያጁን ጨምሮ መላው የባንኩ ሰራተኞች በሚገባ አስተናግደውናል ። ለሟች እናትም ክብር ሰጥተው አስተናግደውኛል ። በእጃቸው ያለውን ገንዘብና እኔ ያመጣሁትንም ገንዘብ በመጨረሻ ከባንክ ገብቶላቸዋል ።

ይኸው ሁሉንም በእግዚአብሔር ቸርነት በእመቤታችን አማላጅነት በቅዱሳን ተራዳኢነት በእናንተ በጓደኞቼ ጸሎት እንደዋዛ የጀመርኩት ነገር አልለቅህ ብሎኝ በመጨረሻ ወለጋ ላይ ፍጻሜውን አግኝቷል ።

ነጋቲ ጋ አዴ አለሚቱ !! ጀባዳ !!

ነጋቲ ጋ አዴ አለሚቱ !! ጀባዳ !!

በቀጣይ በዚህ ዙሪያ አጠቃላይ የእርዳታችሁን መጠንና ቀሪ ሥራዎችን እጠቁማችኋለሁ ።

የሚቀረኝ ነገር ቢኖር የሰማዕቱ ባልቻ እህት የነገረችኝና በአሜሪካ ከምትገኙ ሰዎች መካከል አንድ ሰው ሊፈጽመው የሚችለው ቀላል ነገር ማስቸገር ብቻ ነው ጉዳዩ ገንዘብ ነክ አይደለም ።

ሌላው የሰማዕቱ የኢያሱ ሚስት የሮዚና ጉዳይ ነው ። ሮዚና ወጣት ናት ። በዚህ ዕድሜዋ የወጣት ተጧሪ መሆን አለባት ብዬም አላምንም ። ይህን እድሜዋን በመስራት ማሳለፍ አለባት ። በዚህ መሰረት ጀርመን የሚገኙት የአቢሲኒያ የጉዞ ወኪል ባለቤት ወሮ መሠረት አዲስ አበባ የሚገኝ የአንድ ካምፓኒ ባለቤት እንዳነጋግር በነገሩኝ መሠረት የካምፓኒውን ባለቤት አነጋግሬ ፍጹም ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸውልኛል ።

ስለዚህ ከነቀምት መልስ ሮዚና ሥራ ይኖራታል ማለት ነው ። የሚቀረው ከሽንት ቤት ላይ ያለውን የመኖሪያ ቤቷን የክልሉን መስተዳደር ጠይቆ ቤት የምታገኝበትን መንገድ መፈለግ ነው ። ይሄም እንደ አዋሬዋ ብርቱኳን ይሳካል ብዬ አምናለሁ ። የትርሓስ ጉዳይም መቋጫ ይፈልጋል ። ለዛሬ አበቃሁ ።

ወሮ አለሚቱ ገለታ ጂራታን መርዳት የምትፈልጉ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ነቀምቴ ቅርንጫፍ
የባንክ ሒሳብ ቁጥር
1000129744147 ነው ። ካላችሁበት አገር ሆናችሁ ባለችሁበት ሐገር ባንክ በኩል ከማናችንም ጋር ንክኪ ሳትፈጥሩ በ Swift Coode : CBETETAA መላክም ትችላላችሁ ።

ወይም ታሪኩ ጋሼ ብላችሁ በስልክ ቁጥር +251921199718 በተለይ ኦሮምኛ የምትችሉ ሰዎች ደውላቭጉጥ አፅናኑዋቸው ።

በተረፈ ውድ ጓደኞቼ በዚህ ጉዳይ የምትጠይቁኝ እና እንድመልስላችሁ የምትፈልጉት ነገር ካለ ። ያው እንደተለመደው በእጅ ስልኬ +251911608054 ላይ ደውሉልኝ ። ሰላም ሁኑልኝ ። አክባሪ ወንድማችሁ ።

ዘመድኩን በቀለ ነኝ
ሰኔ 8/10/2007 ዓም
ከነቀምት ወደ አዲስ አበባ በጉዞ ላይ ።

The post ሰማዕት መንግሥቱ ጋሼ – ከወለጋ እስከ ሊቢያ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live