Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

አ.አ በግድግዳ ጽሁፎች (ግራፊቲ) ተሸፍና አደረች

0
0

demesachin-yesema3
ድምፃችን ይሰማ እንደዘገበው
እሁድ ምሽት ለሰኞ አጥቢያ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ቦታዎች የሙስሊሙን ህብረተሰብ ጥያቄዎች በሚያንጸባርቁ ጥቅሶች ተጽፎባቸው አደሩ፡፡ በከተማዋ የተለያዩ መንገዶች፣ የመንገድ አካፋዮች እና አጥሮች ላይ መንግስት ሕገ መንግሰቱን እንዲያከብርና በእምነት ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም የሚጠይቁ ጽሁፎች በትላልቅ ቁመት ለህዝብ በሚታይ መልኩ ተጽፈው የተገኙ ሲሆን ይህ በተጻፈባቸው ቦታዎችም ሰዎች ሁኔታውን በትኩረትና በግርምት ሲመለከቱ እንደነበር ታውቋል፡፡

demesachin-yesema

በካዛንቺስ፣ በጦርሀይሎች በውንጌት አስኮ መንገድ እንዲሁም ገና በውል ባልታወቁ ቦታዎች ደምጻችን ይሰማ፣ ኮሚቴው ይፈታ፣ ሕገ መንግስቱ ይከበር፣ ጥያቄያችን ይመለስ፣ በእምነታችን ጣልቃ አትግቡብን የሚሉ ጽሁፎች ተጽፈው የታዩ ሲሆን በካባቢው የሚገኙ የወረዳ አስተዳደሮችም በተፈጠረው ነገር በመደናገጥ ጽሁፎቹን ለማጥፋት ጥረት እያደረጉ ይገኛል፡፡ የጎዳና እና የግድግዳ ጽሁፎች በአለም የታወቁ የመቃወሚያ ዘዴዎች በመሆናቸው ህብረተሰቡ መልእክቱን ለሚመለከተው አካል ለማድረስ የሚጠቀምባቸው ናቸው፡፡

ሙስሊሙ ህብረተሰብ ሕጋዊ የመብት ጥያቄዎቹን አግባብ ባለው መልኩ ለመንግስት ሲያቀርብ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን አሁንም በዚህ እርምጃው በመቀጠልና ወደ ሌላ ሂደትም በመሸጋገር መንግስት ለሚወስዳቸው ማንኛውም እርምጃዎች እጅ እንደማይሰጥ በማሳየት ላይ የሚገኝ መሆኑን ይህ የዛሬ ክስተት ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡ መንግስት የሙስሊሙን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ሙስሊሙን በአክራነትና አሸባሪነት በመፈረጅ ላይ የሚገኝ ቢሆንም ሙስሊሙ ህብረተሰብ በተገኙት አጋጣሚዎች ሁሉ ድምጹን ለማሰማትና መንግስት ምላሹን እንዲሰጥ ለማድረግ ጥረቶች በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

demesachin-yesema2

በዚህ አይነቱ ስልትም ሆነ በሌሎች ሰላማዊ መንገዶችና የመታገያ ስልቶች የሙስሊሙን ህብረተሰብ ሕጋዊ ጥቄዎች ብቻ የሚያንጸባርቁና ከትግሉ መንፈስ ያልወጡ መልእክቶች ሊተላለፉበት እንደሚችሉ ይታሰባል፡፡


የሚሊዮኖች-ድምጽ-ለነፃነት ዘመቻ የዜጎችን ፊርማዎች ለመሰብሰብ! –ግርማ ሞገስ

0
0

ግርማ ሞገስ (girmamoges1@gmail.com)
እሮብ ሐምሌ 17 ቀን 2005 ዓ.ም. (Wednesday, July 24, 2013)

MillionsVoice1የዜጎችን ፊርማዎች ማሰባሰብ የብዙ መቶ አመቶች ታሪክ ያለው ሰላማዊ ትግል ነው። የሚሊዮኖች-ድምጽ-ለነፃነት ዘመቻ አንዱ ግብ በኢትዮጵያ ሽብር ህግ ላይ ዜጎች ያላቸውን አቅዋም በፊርማቸው እንዲገልጹ ማድረግ ነው። እንደሚታወቀው አንድ መንግስት ዜጎቹን በሽብር ህግ የሚገዛው ከፖለቲካ ተፎካካሪዎቹ የተሻለ አሳብ በማቅረብ የህዝብ ድጋፍ ማግኘት ሲያቅተው ነው። የአዲስ አሳብ ምንጮቹ ሲደርቁበት ነው። የአሳብ ኪሳራ ሲደርስበት  ፊቱን ወደ ሽብር ያዞራል። በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው ይኼው ነው። በፊርማችን አቅዋማችንን እንግለጽ።

አለም አቀፍ ሽብር ለመከላከል ነበር የኢትዮጵያ ፀረ-ሽብር ህግ የተደነገገው የሚለው ምክንያት ሃሰት ነው። የኢትዮጵያ ፀረ-ሽብር ህግ የተደነገገው አልቃይዳ እና ሌሎች አለም አቀፍ ሽብርተኞች ጥቃት ደርሶባቸው በሽሽት ላይ በነበሩበት ጊዜ ነበር። እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከ2001 ዓመተ ምህረት ማለቂያ ጀምሮ አሜሪካ እና ምዕራብ አውሮፓ በየአገራቸው ፀረ-ሽብር ህግ ሲደነግጉ አቶ መለስ ኢትዮጵያ አያስፈልጋትም ይል ነበር። ነገር ግን እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2005 ዓመተ ምህረት በኢትዮጵያ የተካሄደው ምርጫ (ምርጫ 97) አስደነገጠው። ሌላ ምርጫ 97 ቢደገም ስልጣን ከዕጁ ሊያመልጥ እንደሚችል ወለል ብሎ ታየው። በዚህን ጊዜ ነበር የመለስ ዜናዊ ህውሃት አለም አቀፍ ፀረ-ሽብር ህግ ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል ማለት የጀመረው። የፖለቲካ ባላንጣዎቹን ለመወንጀል እና ከስልጣን ፉክክር ሜዳ ለማስወጣት። ህዝብን በሽብር አስፈራርቶ እንደ እንሰሳ ለመግዛት።

ቀደም ሲል ቀጥተኛ የሽብርተኞች ጥቃት የደረሰባት እና በግንባር ቀደምትነት ፀረ-ሽብር ህግ ከደነገጉት አገሮች ውስጥ አንዷ የሆነቸው አሜሪካ ሳትቀር የኢትዮጵያን ፀረ-ሽብር ህግ ከመስመር የወጣ እና የፖለቲካ ተቃዋሚዎቹን ኢላማ ያደረገ መሆኑን ገለጸች። የኢትዮጵያ መንግስት ህጉን እንዲከልስ አሳሰበች። የአውሮፓ ህብረት፣ አምንስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂውማን ራይትስ ዋች፣ ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች የኢትዮጵያን ፀረ-ሽብር ህግ ፀረ-ሰብዓዊ መብት እና ፀረ-ዲሞክራሲ ነው በማለት በአደባባይ ተቃወሙ። እንዲሻሻል ጠየቁ። ስመ ጥሩው ኢሰመጉም ተመሳሳይ ተቃውሞ እና ጥያቄ አቀረበ። በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ተመሳሳይ ተቃውሞ እና ጥያቄ አቀረቡ። ተቃውሞዎቹ እና ጥያቄዎቹ ዛሬም አላቋረጡም። የዛሬው የሚሊዮኖች-ድምጽ-ለነፃነት አገር አቀፍ ህዝባዊ እንቅስቃሴም የእነዚሁ አለም አቀፋዊ እና አገራዊ ተቃውሞዎች እና ጥያቄዎች ቅጥያ ነው።

የኢትዮጵያ ፀረ-ሽብር ህግ የህጎች ሁሉ የበላይ የሆነውን የአገሪቱን ህገ-መንግስት ይፃረራል። ህጉ የተዘጋጀው አምባገነኖቹ ገዢዎች እንደፈለጉ መተርጎም እና ፖለቲካዊ ጥቃት መፈጸም እንዲችሉ ተደርጎ ነው። ህጉ በህገ-መንግስቱ ውስጥ የተዘረዘሩትን መብቶች ይሰርዛል። ጸረ-ዴሞክራሲ ነው። ጸረ-ነፃ ፕሬስ ነው። ፀረ-ነፃ ምርምር ነው። ፀረ- አዳዲስ አሳብ አፍላቂነት ነው። ፀረ-ሲቪክ ማህበራት ነው። የነፃነት አድማስ አፋኝ ነው። የዴሞክራሲ አድማስ አጥፍቷል። ነፃ ምርጫ ያደናቅፋል። እንደ ከብት መንጋ መገዛትን ህጋዊ ያደርጋል የኢትዮጵያ ሽብር ህግ። ባጭሩ ከአቀራረባቸው እና ከአፈጻጸማቸው በስተቀር የዛሬው የኢትዮጵያ ሽብር ህግ እና የትናንቱ የደርግ ሽብር ህግ ተመሳሳይ ናቸው። ሁለቱም ህጎች የዜጎችን የማሰብ መብት ሳይቀር የሚያስቀጣ ወንጀል ያደርጋሉ። ስለዚኽ የኢትዮጵያ ፀረ-ሽብር ህግ መሰረዝ አለበት። የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት አገር አቀፍ እንቅስቃሴ ግቡ ይኽን ህግ ለማሰረዝ እና የዚህ ህግ ሰለባ የሆኑትን ሰላማዊ ታጋዮች እና ጋዜጠኞ ማስፈታት ነው። በዚህ ሰላማዊ ትግል ብንሳተፍ የሚጠቀሙት በአገር ቤት ያሉት ወገኖቻችን ናቸው። የሚጠቀሙት በሽብርተኛነት የታሰሩት የድምጻችን ይከበር መሪዎች፣ የኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል መሪዎች እና ጋዜጠኞች ናቸው። የሚጎዳው ህውሃት ብቻ ነው።

በሽብርተኛነት የታሰሩት ሽብርተኞች አይደሉም። ላብራራ! ዛሬ የሽብርተኞች ባህሪ ብዙ የተጠና እና የተጻፈበት ጉዳይ ነው። በኢትዮጵያ በሽብርተኛነት የታሰሩት የሙስሊም እምነት መሪዎች እነ አቡበከር፣ የአንድነት ፓርቲ አባላት እነአንዱዓለም አራጌ፣ እነናትናኤል መኮንን እና ሌሎች፣ የኦፌዴን ም/ሊቀመንበር በቀለ ገርባ፣ የኦሕኮ ጽ/ቤት ኃሊፊ አቶ ኦሌባና ላሉሳ እና ሌሎች፣ እንዲሁም ጋዜጠኛቹ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ፣ ርዕዮት ዓለሙ የሽብርተኛነትን ባህሪ እና ታሪክ የላቸውም። ሌላ ማብራሪያ! ሽብርተኞች በአለማችን የፈጸሙዋቸውን አሰቃቂ የሽብር ተግባሮች ብናስታውስ ሽብር ለመፈጸም የተደራጀ የሰው ኃይል፣ የሰለጠነ ድርጅት፣ ሃብት፣ የጦር መሳሪያ፣ ሚስጥረኛነት (የድብቅ ስራ) እና በሽብርተኛ የፖለቲካ ትግል ባህል መጠመቅን ይጠይቃል። በሽብርተኛነት ህውሃት ያሰራቸው በሙሉ እንዲዝኽ አይነት የተደራጀ ኃይል የላቸውም። እስኪ አሁን በምን ሂሳብ ርዕዮት ዓለሙ ሽብርተኛ ናት ማለት ይቻላል? በከፊል እየሰራች በከፊል ትምህርት እና ተጨማሪ ድግሪ በማሳደድ ላይ ነበረች እንጂ የሽብር ድርጅት በመምራት ላይ እንዳልነበረች ይታወቃል። ያልፈቷትም ይቅርታ ጠይቂ ብለዋት ሳላጠፋ ይቅርታ አልጠይቅም በማለቷ ነው። በቀለ ገርባም ቢሆን ክብሩን ጠብቆ እያስተማረ በጎን ከፍተኛ ትምህርቱን የሚከታተል እና ቤተሰብ የሚያስተዳድር ሽብርን የሚኮንን ዜጋ ነበር። አንዱአለም አራጌ ደፋር የሰላማዊ ትግል ሐዋሪያ ነበር። እስክንድር ነጋም ሃሳቡን በአደባባይ ሲናገር የነበር የነፃ ፕሬስ ታማኝ ወታደር ነበር። መለስ ዜናዊን አምባገነን ለዴሞክራሲ እንቅፋት ስለሆንክብን ከስልጣን ውረድ ብሎ እዚያው አዲስ አበባ በይፋ የፃፈ ነው። በሽብር የታሰሩት በሙሉ አዲስ ሰላማዊ የትግል ባህል ለኢትዮጵያ ያበረከቱ ናቸው። በዚኽ አስተዋጽዋቸው ኢትዮጵያ ልትሸልማቸው እንጂ ልታስራቸው አይገባም። በሙሉ ሊፈቱ የገባል።

የህውሃት ካድሬዎች እስክንድር ነጋን ሽብርተኛ ለማስመሰል በህፃን ልጅ ፊት የሰሩት ድራማ እጅግ አሳፋሪ ነበር።  ሽብርተኛ አስመስለው ሊያስሩት በመንገድ ላይ ሳለ ግርግር ሲፈጥሩ እስክንድር ነጋ ፍቅር የተባለውን የ5 አመት ልጁን ከትምህርት ቤት ወደ ቤት በማድረስ ላይ ነበል። እንደ ጥሩ ዜጋ አባት። እስክንድር ሲያዝ አብሮት የነበረው ፍቅር አባቱን ከፖሊሶች ለማስለቀቅ እያለቀሰ ፖሊሶቹን እግር እግራቸውን በእግሩ ሲመታ እንደነበር በሰፊው ተዘግቧል። ሽብረተኛው እስክንድር ሳይሆን ስብዕናቸው የተሟጠጡት የመለስ ዜናዊ መልክተኞች የህውሃት ካድሬዎች ናቸው። ከአይን ምስክሮች ባሻገር ወጣት ናፍቆት አባቱን ከፖሊሶች ለማስለቀቅ ያደረገውን ትግል የሚያሳይ ቪዲዮ ወይንም ፎቶ ቢኖር ከፍተኛ ታሪካዊነት እና የፖለቲካ ፋይዳ አለው።

ስለዚኽ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጭ የምንኖር ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ውስጥ በመካሄድ ላይ በሚገኘው አገር አቀፍ የሚሊዮኖች-ድምጽ-ለነፃነት ዘመቻ በመሳተፍ በኢትዮጵያ ፀረ-ሽብር ህግ ላይ ያለንን ተቃውሞ እንግለጽ። አለአግባብ የታሰሩትን ለማስፈታት በመንግስት ላይ ጫና እናድርግ። መሳተፍ ማለት ከሚከተሉት ሁለት ነገሮች ውስጥ አንዱን ወይንም ሁለቱንም ማድረግ ማለት ነው።

(1)    www.andinet.org ድረ-ገጽ በመሄድ ፊርማችንን መስጠት፣
(2)   እያንዳንዱን ህዝባዊ ስብሰባ እና ሰላማዊ ሰልፍ ዘመቻ ለማደራጀት ገንዘብ ስለሚያስፈልግ የገንዘብ እርዳታ ማድረግ፣

http://www.thepetitionsite.com/174/997/377/millions-of-voice-

ከፍ ብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ አንዱን ወይንም ሁለቱንም በማድረግ በሃሰት በሽብርተኛነት ታስረው አላግባብ እድሜያቸውን በእስር ቤት እንዲያባክኑ ለተገደዱት ለእነ አቡበከር፣ አንዱዓለም አራጌ፣ ናትናኤል፣ በቀለ ገርባ፣ ኦሌባና ላሉሳ፣  እስክንድር፣ ውብሸት፣ ርዕዮት እና ሌሎች የትብብር እጃችን እንዘርጋላቸው። በመንግስት ላይ ጫና በማድረግ ከእስረኞቹ ጎን መቆማችንን እንግለጽ። ኢትዮጵያ በመስራት ላይ ባለቸው አዲስ የዲሞክራሲ ጉዞ ታሪክ ላይ ማህተማችንን እናስቀምጥ!

በክፍል ሶስት እንገናኝ።

ክፍል ሶስት የሚሊዮኖች-ድምጽ-ለነፃነትን ከበካይ ተግባሮች ለመጠበቅ ያስችሉናል የሚላቸውን አሳቦች ለአንባቢያን በማቅረብ ዜጎች ውይይት እንዲከፍቱበት ይጋብዛል።

 

ዶ/ር ነጋሶ መድረክን ወደ ውህደት መግፋት ጥቅሙ አይታየኝም ሲሉ ደብዳቤ ጻፉ (ደብዳቤውን ይዘናል)

0
0

(ዘ-ሐበሻ) የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በመድረክና አንድነት መካከል ስላለው ግንኙነት የእርሳቸውን አቋም የሚያስረዳ ግልጽ ደብዳቤ በተኑ። በርከት ያሉ ህብረብሄራዊ ፓርቲዎች የሚገኙበት መድረክ ወደ ውህደት ይምጣ የሚለውን አቋም እንደማይደግፉ ለተለያዩ ሚድያዎች በበተኑት ግልጽ በደብዳቤያቸው ላይ ይፋ አድርገዋል። “ግንባር ምንድን ነው?” በሚል ትንታኔ የሰጡት ዶ/ር ነጋሶ አቋማቸውን የሚያሳየው ደብዳቤያቸው ደርሶናል። ዘ-ሐበሻ እንዲህ አስተናግዳዋለች።

የግንባርነት መስፈርትና መድረክ

በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
የግል አስተያየት

በግንቦት ወር በአንድነትና በመድረክ መካከል ይፋዊ ውይይት ተከፍቷል፤ ቀጥለውበታልም። በዚህ ውይይት ውስጥ እስከ ዛሬ ድረስ አስተያየት አልሰጠሁም። በአንድነት ውስጥ ግን በግሌ ያለኝን አቋም፣ አመለካከትና አስተያየቶችን ማንፀባረቄ አልቀረም። በግሌ ሳንፀባርቃቸው የነበርኳቸውን አቋሞች፣ አመለካከቶችና አስተያየቶችን በጽሑፍም ለማስቀመጥ እሞክራለሁ።

አንድ በሰኔ ወር ያጠናቀቅሁት ጽሑፍ “በመድረክ ዙሪያ የተጀመረው ውይይት መድረክን ህዝባዊ ድርጅት ያደርገዋል ወይስ ይጎዳዋል? ዝምታዬ ስምምነት እንዳይመስልብኝ” የሚል ርዕስ አለው። ይህ ጽሑፍ ዛሬ በሙሉ ይፋ ማድረግ አልፈለግሁም። ይልቁንም ከጽሑፉ አንዲት ክፍል ብቻ ቀንጭቤ አቅርቤአለሁ። ይህችም ያቀረብኳት አጭር ጽሑፍ ስለ መድረክ ግንባርነት ነው። የቀሩትን ክፍሎች እንዳስፈላጊነቱ እያየሁ ለአንባቢያን አቀርባለሁ።
negaso gidada
መጀመሪያ ግን ለመሆኑ “ግንባር” ምንድው? የሚለውን ጥያቄ ባለኝ ትንሽ ዕውቀትና ተሞክሮ ላይ በመመርኮዝ ኀሳቤን ለማቅረብ እሞክራለሁ፤

የግንባር ቃለ አመጣጥ ከሰውነታችን ክፍሎች ከፊታችን ወጣ ብሎ የሚታየው የአካል ክፍል ነው፤ የፊት ለፊት ዘርፍ ነው ማለት ነው። በውጊያ ጊዜ ኃይል የሚከማችበት የሠራዊት የፊት መስመር ነው። ለምሳሌ የቡሬ ግንባር፣ የባድመ ግንባር፣ የዛላንበሳ ግንባር፣ የከረን ግንባር ሲባል እንደነበረው።

ከታሪክ አንፃር ስናየው በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ የፖለቲካ ግንባሮች እንደተፈጠሩ እናስታውሳለን። ለምሳሌ በቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት ጊዜ የኮሙኒስቶችና የፀረ-ኮሚኒስቶች ግንባሮች ተፈጥረው ነበር። የሠራተኛ ማኅበራት፣ የሶሻሊስት ፓርቲዎች፣ የነሱም ሕዝባዊ አደረጃጀቶች በርዕዮተ ዓለም መቀራረብ ላይ የተመሠረተ የአንድነት ግንባሮች ሲመሠረቱ ነበር። በአሜሪካና በአውሮፓ ለእስራኤል ድጋፍ ሰብሳቢ ግንባሮች ተመስርተው እንደነበር ታሪክ ያስተምረናል።

የግንባር መሠረተ ሃሳብ የጋራ አጀንዳ ያላቸው፣ ግን የተለያዩ ፍላጎት ሊኖራቸው የሚችሉ የፖለቲካ ድርጅቶችና ቡድኖች (የግራ ዘመም፣ የመሀልና የሊብራል ቡድኖች ሊሆኑ ይችላሉ) የጋራን አጀንዳ ለማራመድና ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ ተመሳሳይ ርዕዮተ ዓለም ያላቸው ድርጅቶች፣ ወይም የተለያዩ ርዕዮተ ዓለም ያላቸው ድርጅቶች ሰፋ ያለ (Broad) አንድነት የሚፈጥሩበት አደረጃጀት ነው።

የግንባር ዓላማና መርህ ሲፈተሽ የሚከተሉት ባህሪያት አላቸው። የጋራ ጠላትን በጋራ ለመዋጋት፣ የጋራ ተቃዋሚን በጋራ ለመከላከል፣ የጋራ ተፃራሪን በጋራ ለመጋፈጥና የጋራ ዓላማን በጋራ ለማራመድ የሚፈጠር የአንድነት አደረጃጀት ነው። የግንባር አባል ድርጅቶች ኃይል ለመፍጠርና ውጤታማ ለመሆን “አንድነት ኃይል ነው” የሚለውን መርህ ይከተላሉ። አንድ ፓርቲ ብቻውን መንግሥት መያዝ አይችልም፣ ትክክልም አይደለም ይላሉ። አንድ ፓርቲ ብቻውን መንግሥትን አጠቃልሎ መያዙ ጥሩ አይደለም የሚል እምነት በመያዛቸው በሰጥቶ መቀበል መርህ ላይ የተመሰረተ አቅጣጫን ይከተላሉ።

ግንባርና ጥምረቶች (ቅንጅቶች) ይለያያሉ። ጥምረት /ቅንጅት ለተወሰነ ዓላማ ብቻና ለተወሰነ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል የአንድነት አደረጃጀት ነው። የጥምረት /ቅንጅት ዓላማ በምርጫ ገዢውን ፓርቲ ለማሸነፍና ለአንድነት የምርጫ ዘመን የጋራ መንግሥት (coalition government) ለማቋቋም የሚመሠረት ጊዜያዊ አንድነት ነው።

ግንባር ግን የረጅም ጊዜ ዓላማ ያለው ስትራቴጂአዊ አንድነት ነው። በረጅም ጊዜ ወይም በዘላቂ ስትራቴጂካዊ እቅድ ውስጥ ወደ ዓላማውና ወደ ግቡ የሚያደርሱ በየደረጃው የሚፈፀሙ የአጭር ጊዜ ስትራቴጂዎች አሉ።

በግንባር አንድነት አደረጃጀት ውስጥ የሚታቀፉ ድርጅቶች አንድ ወይም የተለያየ ርዕዮተ ዓለም ያላቸው ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ፡- እንደ ኢህአዴግ በቋንቋና በአካባቢ ላይ የተመሠረቱ ፓርቲዎች ቢኖሩበትም ድርጅቶቹ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ርዕዮተ ዓለም ላይ የተመሠረተ የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪ አብዮታዊ ዴሞክራት አባሎች የተሰበሰቡበት ድርጅት ነው። የዚህ ዓይነት በአንድ ወጥ ርዕዮተ ዓለም ላይ የተመሠረቱ የላብ አደሩና የኮሙኒስት ሶሻሊስት አደረጃጀቶች በዓለም ላይ ሲፈጠሩ አዲስ አይደለም። በርዕዮተ ዓለም ባይስማሙም የጋራ አጀንዳ ያላቸው፣ የጋራ ጠላት፣ ተቃዋሚ ወይም ተፃራሪ አቋም ያላቸው ኃይሎች በፈቃደኝነት ተስማምተው ገብተው አንድ የጋራ ፕሮግራም ነድፈው ለረጅም ጊዜ አብሮ ለመስራት የሚቋቋሙ የግንባር አደረጃጀቶችም ሊፈጠሩ ችለዋል። ይችላሉም ከዚህ አኳያና የአገሪቱ ሕግ በደነገገው መሠረት መድረክ ግንባር ሆኖ ተመዝግቧል።

የመድረክ ግንባርነት ባህሪይን ስንመለከት ግንባርነቱ የተመሠረተው በሰፊ (Broad) አንድነት ላይ ነው እንጂ በርዕዮተ ዓለም አንድነት ላይ የተመሠረተ አይደለም። ከመድረክ ሰነዶች እንደሚታየው በምርጫ ጊዜ በአንድ የምርጫ ምልክትና በአንድ ማኒፌስቶ በመወዳደርና በፕሮግራሙ የተቀመጠን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ዓላማዎችን መድረክ በምርጫ ካሸነፈ በሚቋቀመው መንግሥት በኩል በዚያ የምርጫ ዘመን ተግባራዊ እንዲሆን ለማድረግ ቢያልምም የረጅም ጊዜ ወይም ስትራቴጂአዊ ዓላማውና ግቡ፡-

1. የኢትዮጵያ ህዝብ በዘላቂነት የሥልጣን ባለቤት እንዲሆን ለማድረግ፣

2. ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ፍትህ የሰፈነበትና የበለፀገች አገር ለመገንባት፣

3. ከተጨባጭ የኢትዮጵያ ሁኔታ በመነሳት በብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች እኩልነት ላይ የተመሠረተች ኢትዮጵያን መገንባት፣

4. የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚከበሩባት ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚል ነው።

የግንባሩ አባል ድርጅቶች ይህን የረጅም ጊዜ (ስትራቴጂያዊ) ዓላማና ግብ በመያዝ በጋራ ተግባራዊ ለማድረግም በልዩ ሁኔታ ተስማምተዋል። እነዚህም ስምምነቶች እንደሚከተሉት ናቸው።

1. የኢትዮጵያ አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነትን ለማስከበር ለማስጠበቅ በጋራ መስራት፣

2. ኢፍትሓዊና አድሎአዊ አሠራሮች የተወገዱባት ኢትዮጵያን መገንባት፣

3. በመከባበር ላይ የተመሠረተ አንድነት እንዲጠናከር በጽናት መቆም፣

4. የግለሰቦች፣ የብሔር ብሔረሰቦች፣ ህዝቦችና የቡድን መብቶች እኩል እንዲከበሩ ሳይታክቱ አብሮ መሥራት፣

5. ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚከበሩባት፣ ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ፍትሕ የሰፈነባት የበለፀገች ኢትዮጵያን መገንባት የሚሉ ናቸው።

መድረክ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚከተለው የትግል ስልት ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡-

1. ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ለማክበርና ለማስከበር ይሰራል፣ የአገሪቱን ሕጎች ያከብራል፤

2. በሕገ-መንግስታዊ ጉዳዮች በቀጣይነት ውይይት እንዲካሄድ ይሰራል፣ ሕገ-መንግሥቱ በሕገ-መንግሥታዊ መንገድ፣ በሕዝበ ውሳኔ ጭምር፣ የሚሻሻልበት ሁኔታ እንዲፈጠር ይታገላል፤

3. በሰላማዊ ትግል ያምናል፣ ሠላማዊ ትግል ለማጠናከር ሳይታክት ይሰራል፣

4. ምርጫ ሠላማዊ፣ ነፃና ፍትሓዊ እንዲሆን የፖለቲካ ምህዳሩ ለሁሉም እኩል የተመቻቸ እንዲሆን እንደሚታገል ገልጿል።

በእነዚህ የመድረክ ግንባርነት ባህሪይና የትግል ስልት አንፃር ሲታይ መድረክ ወይ የመድረክ አባል ድርጅቶች በርዕዮተ ዓለም አንድነት ላይ የተመሠረተ ውህድ ፓርቲ መሆን አለበት፣ ያለበለዚያ በቅንጅትነት (ጥምረትነት) ደረጃ መንቀሳቀስ አለበት የሚሉ ሰዎች ምክንያታቸውን የበለጠ ቢያብራሩ አስተማሪነቱ የሚናቅ አይደለም። በእኔ ትንሽ ዕውቀትና የዕድሜ ተሞክሮ የሚነግረኝ ግን መድረክ የግንባርነት መስፈርት ማሟላቱ የሚያጠራጥር አይደለም። ሆኖም ግን ከግንባር ደረጃ ሲታይ መድረክ የሰፊ ግንባር (Broad Front) መስፈርትን እንጂ የጠበበ (Narrow or Limited Front) ግንባር ደረጃ ላይ የደረሰ ነው ለማለት አያስደፍርም።

ይህን ለመረዳት እንዲረዳን የፀረ-ደርግ ትግል ጊዜ አንድ ክስተትን ማስታወሱ ጥሩ ነው። ልክ እንደዛሬው የኢህአዴግ ተቃዋሚ የሆኑ ብዙ ፓርቲዎች እንዳሉ ሁሉ፣ በዚያን ጊዜም ኢህአዴግንና ኦነግን ጨምሮ ብዙ ፀረ-ደርግ የፖለቲካ ድርጅቶች ነበሩ። በዚያን ጊዜም የጋራ ጠላትን ለማስወገድ ቀላል ይሆን ዘንድ የተቃዋሚ ድርጅቶች መሰባሰብ አስፈላጊ ነበር። በመሆኑም፣ ለምሳሌ ሕወሓት ከኦነግ ጋር ግንባር ለመፍጠር ብዙ ጥረት ሲያደርግ ነበር። ሆኖም ግን ሕወሓት የነበረው አቋም ከኦነግ አቋም የተለየ ነበር። ሕወሓት ፍላጐቱ ደርግ ከተወገደ በኋላ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት የተከበረበት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መገንባት ነበር። ማኅበረ-ኢኮኖሚና የፖለቲካ ፍላጐቱ ደግሞ የሶሻሊስት ኢትዮጵያ ግንባታ ሁኔታን ማመቻቸት ነበር። ለዚህም እንዲረዳው አብዮታዊ ዴሞክራሲን ማስፈን ይፈልግ ነበር። ከውጭ ግንኙነት አንፃር ያኔ የነበረውን ሶቪየት ኅብረትን እንደ ሶሻል ኢምፔሪያሊስት ያይ ነበር። የምኒልክን እንቅስቃሴ ደግሞ እንደፊውዳል ተስፋፊነት ይመለከት ነበር።

በአንፃሩ ግን፣ ኦነግ የሚኒልክን እንቅስቃሴ እንደ ቅኝ ግዛት መስፋፋት ያይ ስለነበር የፀረ-ኮሎኒያሊዝም ትግል በማካሄድ ነፃ የኦሮሚያን ሪፐብሊክ ለመመስረት ይታገል ነበር። ከማኅበረ-ኢኮኖሚ-ፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም አንፃር ደግሞ የማኦን አዲሱ ዴሞክራሲያዊ አብዮት ይከተል ነበር። ሶቪየት ኅብረትን ግን እንደ ኢምፔሪያሊስት ኃይል አይወስደውም ነበር።

ግንባር የመፍጠር አስፈላጊነት ላይ ሁለቱም ያምኑ ነበር። ችግሩ ግን የነበረው ምን ዓይነት ግንባር እንፍጠር በሚለው ላይ ነበር። ከዚህም የተነሳ ህወሓት ሁለት አማራጮችን አቀረበ። አንደኛው አማራጭ፣ ኦነግ አቋሙን ቀይሮ የሕወሓትን አቋም በመከተል ሁለቱ “ዴሞክራሲያዊ ግንባር” መፍጠር የሚል ነበር። ይህ የጠበበ (Narrow or Limited) ግንባር የምንለው ዓይነት ነው። ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ ደርግን ለመጣል ያለመ አንድነትን መፍጠር ነው። ይህ ሰፊ ግንባር (Broad Front) የምንለው ነው።

የዚህ ግንባር ዓላማ ደርግን መጣልና ከዚያ በኋላ በሚፈጠረው የኃይል ሚዛን ጉልበተኛ የሆነው ቡድን ሌላውን አስወግዶ የቆመለትን ዓላማ ተግባራዊ ማድረግ ነበር። ኦነግ የመጀመሪያውን አማራጭ አልፈለገም። በ1983 በነበረው የኃይል ሚዛን ኦነግ በጉልበት ተመጣጣኝ ስላልነበረ ደርግ ከወደቀ በኋላ ሕወሓት ያጠፋኛል ብሎ ስለፈራ ሁለተኛውም ዓይነት ግንባር ውስጥ ለመግባት አልፈለገም። በመሆኑም የተፈጠረው ሁኔታ ከብዙ ውስብስብ ሁኔታዎችና ችግሮች ጋር የታጨቀ ሰፊ ትብብር ነበር። በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነበር የሽግግር መንግሥት የተመሠረተው።

ወደ አሁኑ ሁኔታ ስንመለስ መድረክ ሰፊ (Broad) ግንባር ነው። ሆኖም ግን በምርጫ ኢህአዴግ ከተሸነፈ በኋላ ኢህአዴግን ጨምሮ (ኢህአዴግ በፓርላማ ወንበር ካገኘ) ከሌሎች የፓርላሜንታዊ ፓርቲዎች ጋር የብሔራዊ አንድነት መንግሥት ለማቋቋም ይፈልጋል። በዚያን ወቅት ሆነ ከዚያም በኋላ አንድነትዋ፣ ነፃነትዋና ሉዓላዊነትዋ የተጠበቀች፣ ሁሉም የግለሰቦችና የቡድኖች መብቶች እኩል የተከበሩባት፣ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት የተረጋገጠባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ይታገላል ብሎ የመድረክ ግንባር ቃል ገብቷል። ስለሆነም የመድረክ ግንባርነት፣ ከርዕዮተ ዓለም አንድነት በመለስ ከኢህአዴግ ሰፊ ግንባርነት (Broad Front) ከፍ ያለ ነው። ስለሆነም መድረክ በዚያው ደረጃ ቢቆይ ይሻላል እንጂ ወደ ጥምረት /ቅንጅት ደረጃ እንዲወርድ መፈለጉም ሆነ ወደ ውህድ ፓርቲ መግፋት መፈለጉ በአሁኑ ወቅት ጠቀሜታው አልታየኝም። ያም ሆነ ይህ ዋናው ቁም ነገር ለአንድ ዓይነት ዓላማ በጋራ መስራት ጠቃሚ የመሆኑ ጉዳይ ነው።

ይህ በግንባር ዙሪያ የሚካሄደውን ውይይት ለከፈተው አንድነት ፓርቲ፣ ለመድረክ፣ ለ33 ፓርቲዎች ስብስብና ለሌሎችም በአገር ቤት በውጭ ላሉ ተናጠልና ስብስብ ፓርቲዎች በኀሳቡ (Concept) ላይ ግልጽነት እንዲኖረን ከሚረዳን በላይ ለምናደርገው ተግባራዊ እንቅስቃሴ ድክመትና ጥንካሬ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያደርግ ስለሚችል ውይይቱ ይቀጥል። በሌላ በኩል ግን ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ተረስተው በዚህ ርዕስ ላይ ተጠምደን ጊዜ ማባከኑ ትክክል እንዳልሆነ ኀሳቤን እየሰጠሁ፣ የምናደርገው ውይይት ግን ገንቢ እንጂ አፍራሽ እንዳይሆን አደራ እላለሁ።

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ።

የፓርላማው ውይይት መታፈኑን በይፋ ያጋለጠው የኢቲቪ ጋዜጠኛ ከሥራ ተባረረ

0
0

(በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው)

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናና የአስፈፃሚ ተቋማት ኃላፊነት” በሚል ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም ያደረገውን ውይይት በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በኩል ተቆራርጦና ተዛብቶ እንዲተላለፍ ተደርጓል በሚል አንድ ዜና መዘገቡ ይታወሳል።

ይህን ዜና በሰንደቅ ጋዜጣ የህዳር 5 ቀን 2005 ዓ.ም ዕትም “ኢቲቪ የከፍተኛ ባለሥልጣናትን ውይይት በማፈን ተወቀሰ” በሚል ርዕስ ከቀረበ በኋላ፤ በዚህ ዘገባ ላይ ተመድቦ የሠራው የቀድሞ የኢቲቪ ባልደረባ ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ ረቡዕ ህዳር 12 ቀን 2005 ዓ.ም በጉዳዩ ላይ ለዝግጅት ክፍላችን ምላሹን ሰጥቷል።

ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ (ፎቶ ከሰንደቅ ጋዜጣ)

ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ
(ፎቶ ከሰንደቅ ጋዜጣ)

እነዚህ ዘገባዎች ከተስተናገዱ በኋላ፣ ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ ለሰንደቅ ጋዜጣ መረጃ እንደሰጠና ሚስጢር እንዳወጣ ተቆጥሮ የዲስፒሊን ክስ ቀርቦበታል። ኢ.ሬ.ቲ.ድ በዲስፒሊን ክሱ ላይ አራት ከፍተኛ የሥራ አመራሮች በምስክርነት ዘርዝሮ አቅርቧል። የድርጅቱ የዲስፒሊን ኮሚቴ በከሳሽ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እና በጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ መካከል የክስ ዝርዝር እና የመልስ መልስ ደብዳቤዎች ሲያዳምጥ ከሰነበተ በኋላ ግንቦት 9 ቀን 2005 ዓ.ም በቁጥር ቴ02.1/131-304/02/8/ በተፃፈ ደብዳቤ ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ ከግንቦት 10 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ከሥራ የሚያሰናብተውን ቅጣት አሳልፏል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ባለቤትነት በጠ/ሚኒስትሩ ቢሮ ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም የተካሄደው ስብሰባ በመልካም አስተዳደር፣ በተጠያቂነት፣ በሙስና ችግሮችና በመሳሰሉት ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት የተካሄደ ሲሆን በዚህ ውይይት ላይ የኢፌዲሪ ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጨምሮ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይ ፀሐዬ፣ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል፣ የእምባ ጠባቂ ተቋም ዋና እምባ ጠባቂ ወ/ሮ ፎዚያ አሚን፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዓሊ ሱሌይማን፣ የአ/አ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አበባው ስጦታው እና ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የጠራውና የአስፈፃሚ አካላትና የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናን በተመለከተ የተደረገው ውይይት፣ በዕለቱ በሥፍራው ባልነበረ ጋዜጠኛ ተገቢ ባልሆነ መልኩ ተቆራርጦና ተዛብቶ ለሕዝብ መቅረቡ ትክክል እንዳልነበረ በይፋ በመግለፁ ምክንያት ከሥራ የተሰናበተው የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት ባልደረባ የነበረው ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻን ስለሁኔታው ፋኑኤል ክንፉ አነጋግሮታል።

ሰንደቅ፡- የዚህ ዜና መነሻ አንተን አድርገው ለመውሰድ ያስቻላቸው ምክንያቶች ምንድን ናቸው?

ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ይህን ምላሽ መስጠት የሚችሉት እነሱ ናቸው። በሰጡኝ የክስ ዝርዝር ላይ ግን ሌላ ምክንያት ነው ያስቀመጡት። ወይም ደግሞ ላነሳኸው ጥያቄ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችለው የዚህ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ብቻ ነው።

ሰንደቅ፡- እንዴት?

ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ምክንያቱም “ኢቲቪ የከፍተኛ ባለሥልጣናትን ውይይት በማፈን ተወቀሰ” ለሚለው ዜና መነሻ ለሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በእኔ በኩል ያልኩትም አንዳች ነገር የለም። እንደማንም አንባቢ ይህ ዜና በሰንደቅ ጋዜጣ ከወጣ በኋላ ነው የተመለከትኩት። ስለዚህም መረጃ ከእኔ አግኝታችሁ ከሆነ አግኝተናል፤ ካላገኛችሁ አላገኘንም ለሚለው ምላሽ መስጠት የሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ይመስለኛል።

ሰንደቅ፡- በርግጥ የሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ለዚህ ዜና መነሻ መረጃውን ያገኘው ከሌላ ሶስተኛ ወገን መሆኑን ማረጋገጥ እንችላለን። ሆኖም ግን ይህ ዜና በወጣ በሳምንቱ ህዳር 12 ቀን 2005 ዓ.ም. እርሶ ለሰንደቅ ጋዜጣ ማስተባበያ መስጠትዎ የሚታወስ ነው። በወቅቱ ከዜናው ጋር በተያያዘ ለምን ማስተባበል ፈለጉ?

ጋዜጠኛ አዲሱ፡- “የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናና የአስፈፃሚው ተቋማት ኃላፊነት” በሚል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያዘጋጀውን ፕሮግራም የቀረጽኩት እኔ በመሆኔ ነበር። በሰንደቅ ጋዜጣም የተሰራው ዜና “የባለስልጣናት ድምጽ ታፈነ” የሚል በመሆኑም ጭምር ነው። ከዚህ አንፃር እንደአንድ ጋዜጠኛ ውይይቱን አፈነ ተብሎ መወንጀል በጣም አደገኛ ነው። እንዲሁም ማንስ አፈነው? እንዴት ታፈነ? ለሚሉት ጥያቄዎችም ምላሽ የሚፈልጉ መሆናቸው ግልፅ የሆነ ነገር ነው። በተለይ በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩትን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ኃላፊነት ታሳቢ ስታደርግ በእኔ ውስጥ ሊፈጠር የሚችለውን ድንጋጤ መገመት ከባድ አይደለም። የእነዚህን ከፍተኛ ባለስልጣናት አንደበትን ለማፈን በእኔ በተራ ረዳት አዘጋጅ ቀርቶ በሌላው የተቋሙ ከፍተኛ አመራር የሚሞከር ተግባር ተደርጎ የሚወስድ አካል ያለ አይመስለኝም።

ይህ ችግር ከተፈጠረ በኋላም ከስራ ባልደረቦቼ ጋር ተወያይቻለሁ። እንዲሁም አንድ የተቋሙ ከፍተኛ አመራር ለማግኘት ጥረት ባደርግም አልተሳካልኝም። የሆኖ ሆኖ ከባልደረቦቼ ጋር ከመከርኩ በኋላ ፕሮግራሙ ታፍኗል ብሎ ለዘገበው ጋዜጣ ማስተባበያ በመስጠት እራሴን ከጉዳዩ ነፃ ማድረግ እንዳለብኝ ተማምነናል። የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናቱም እኔ አለማድረጌን ሊገነዘቡ የሚችሉት ፕሮግራሙ ታፍኗል የሚለውን ዜና ባሰራጫው ሚዲያ መሆኑ አሻሚ አይደለም። ስለዚህም በዚህ ጉዳይ ላይ ንፁህ መሆኔን ለማረጋገጥ ለሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በጉዳዩ ላይ ያለኝን መረጃ ለመስጠት ተገድጃለሁ።

ሰንደቅ፡-እርሶ እንደዚህ ቢሉም፣ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ታህሳስ 01 ቀን 2005 ዓ.ም. በተፃፈ ደብዳቤ የዲስፕሊን ኮሚቴው “አቶ አዲሱ መሸሻ በየነ በፕሮግራሙ ኢ.ሬ.ቴ.ድ የባለስልጣኖች ድምጽ አፍኗል። ፕሮግራሙ ቆራርጧል የሚል የተሳሳተና ከኃላፊነት የራቀ እና በሀሰት የተሞላ መግለጫ ለሰንደቅ ጋዜጣ” ሰጥቷል ሲል ይከሳል። በዚህ ላይ የእርሷ አስተያየት ምንድን ነው?

ጋዜጠኛ አዲሱ፡- እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት የኢ.ሬ.ቴ.ድ “የከፍተኛ ባለሥልጣናትን ውይይት በማፈን ተወቀሰ” ያለው ሰንደቅ ጋዜጣ እንጂ እኔ አዲሱ አይደለሁም። በወቅቱም በሰጠሁት ማስተባበያ ተቋሙን በተመለከተ ያልኩት አንዳች ነገር የለም። የማፈን ነገር ተፈጽሟል ከተባለም ግለሰቡ እንጂ ተቋሙ ሊሆን አይገባም በማለት ነበር ተቋሙን የተከላከልኩት። በሌሎችም ተቋማት ግለሰቦች ከተቋሙ ዓላማ በመውጣት የሚፈጽሙት ስህተት በእኛም ተቋም በተመሳሳይ ሁኔታ ተፈጽሟል። ይህ ማለት ግን ግለሰቦች ከተቋም በላይ ናቸው ማለት አይደለም። ስለዚህም ግለሰቦች በሰሩት ጥፋት በግል መጠየቅ አለባቸው እንጂ በተቋም ደረጃ ስህተቱ ሊታይ አይገባም። ስለዚህም አንድ ሰው በራሱ መነሻ በፈጸመው ተግባር የተቋም አድርጎ መውሰድ ከሕግም ከሞራልም አንፃር የሚያስኬድ አይመስለኝም።

ሰንደቅ፡- የተከሰስክበት የደብዳቤ ይዘት ሚስጥር በማውጣት የሚል ነው። የሰጠኸው ማስተባበያ ከሚስጥር መጠበቅ ጋር እንዴት ትገልፀዋለህ?

ጋዜጠኛ አዲሱ፡- በመጀመሪያ ደረጃ ሚስጥር ማባከን ከመጥፎ ፍላጎት (intention) የሚመነጭ ነው። ሚስጥር የሚባክነው ተቋምን ወይም ግለሰብን ለማጥቃት ከመፈለግ የሚመጣ ክፉ መንፈስ ነው። ከዚህ አንፃር ስትወስደው፣ እኔ በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ የሰራሁትን ፕሮግራም የሚመለከት ዜና በመሰራቱ ብቻ ማስተባበያ ሰጠው እንጂ ምን አጠፈሁ። ከእኔ ጋር ተያያዥነት ያለው ዜና ባይወጣ እኔም ባልተናገርኩ፤ እነሱም ክስ ያሉት ክስ ባልመሰረቱብኝ ነበር። ስለዚህም የጋዜጠኝነት ሙያዬን (integrity) በሚያጠፉ “አፋኝ” ተብሎ በተሰየመ ሁኔታ ስሜ ጠፍቶ፣ ስሜን ለመመለስ መከላከሌ ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ። ይህ ከሚስጥር ማባከን ከመጠበቅ ጋር ምን ያገናኘዋል?

ሁለተኛው፣ “የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናና የአስፈፃሚው ተቋማት ኃላፊነት” በሚል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተካሄደው ውይይት ዋናው ዓላማው፣ ውይይቱ ለሕዝብ እንዲቀርብ ነበር። ተደራሽነቱም ለሕዝቡ ነው። ለሕዝቡም ግልፅ መረጃ ለማቅረብ የተዘጋጀ ውይይት ነበር። ከሁሉ በላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነበረው የስብሰባ ይዘት፣ የኪራይ ሰብሳቢነት አደጋ በዚህች ሀገር ውስጥ የደረሰበትን ከፍተኛ ደረጃ ለሕዝብ ማሳየት ነበር። ሕዝቡም አደጋውን በመረዳት ከመንግስት ጎን በመሰለፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ግንዛቤ ለማስጨበት ያለመ ስብሰባ ነበር። ይህ ታዲያ ምን ሚስጥር አለው? ሚስጥር ከሆነ መጀመሪያውኑ ሚዲያውን አይጋብዙም ነበር። በወቅቱም ፕሮግራሙ ሲቀረጽም ሚስጥር ነው ያለ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን አልነበረም።

ሌላው በዚህ ተቋም ውስጥ በቆየሁበት የስራ ዘርፎች ሚስጥር ተብለው የሚቀረፁ ስራዎችን ጠንቅቄ አውቃለሁ። በሚስጥር ደረጃ የተቀረፁ ስራዎችንም ሰርቼ አውቃለሁ። በዚህ ደረጃ የሰራኋቸውን ስራዎች እንኳን ለሶስተኛ ወገን፣ በተቋሙ ውስጥ ማወቅ ከሚገባቸው ሰዎች ውጪ ዉይይት አድርጌም አላውቅም። አለቆቼም ይህን ጠንቅቀው ያውቁታል።

ሰንደቅ፡- የዲሲፕሊን ኮሚቴው እንደሚለው ከሆነ “በስሜት ያደረኩት ነው” ሲሉ አቶ አዲሱ በኢዲቶሪያል ስብሰባ ላይ ገልጸዋል ይላል። በዚህ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?

ጋዜጠኛ አዲሱ፡- በነገራችን ላይ የነበረው ኢዲቶሪያል ስብሰባ በአዋጅ ከተሰጠው ስልጣን ብዙ ርቆ የሄደ ነው። ግልፅ የፖሊስ ምርመራ ነበር የተደረገብኝ። አስራ አራት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ባሉበት የተደረገ ስብሰባ ሲሆን አውጣ፣ አታውጣ የሚሉ ጥያቄዎች ነበሩ። እኔ ለማስፈራራት፣ ለማሸማቀቅ የተደረገ ኢዲቶሪያል ስብሰባ ነበር። የቀረበብኝ ውንጀላ እስከሀገር ክህደት የሚደርስ መሆኑ ነበር የተነገረኝ። የፖለቲካ ይዘት ፈጥረውለት እኔ አንገት ለማስደፋት በአደባባይ ውጣና ማስተባበያ ስጥ ብለውኛል። የሚገርመው እኔ ነኝ ፕሮግራሙን የቆረጥኩት ያለው አመራር በዚህ ስብሰባ ውስጥ አንዱ ወቃሽ ሆኖ የተገኘበት ነበር።

ሰንደቅ፡-በዚህ ስብሳባ ደረሰብኝ የሚሉት ጉዳት አለ?

ጋዜጠኛ አዲሱ፡- አለ እንጂ። ከዚህ በፊት የኢዲቶሪያል ስብሳባ የምናደርገው አየር ላይ የዋሉ ፕሮግራሞችን ጠንካራና ደካማ ጎናቸውን ለመገምገም ነው። ከዚህ ዜና ጋር በተያያዘ የተደረገው ኢዲቶሪያል ግን መንፈሱን የተለየ ነው። የአንድ ተቋም ኃላፊዎች ተሰብስበው የፖሊስን ስራ በመተካት ያን ሁሉ ወከባ ማስፈራራት ሲፈጥሩ መመልከት በጣም አሳዛኝ ተግባር ነው። በእኔ ውስጥ የፈጠረው ስሜት ለረጅም ጊዜ ውስጤን ጎድቶታል። በተለይ የኢ.ሬ.ቴ.ድ ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑ ይታወቃል። የምክር ቤቱን ውይይት መቁረጡን በግልፅ መናገሩን ሳይፈራ፣ ለምን እኔን ውይይቱ ተቆርጧል ብልሃል ብሎ ከስራ ሊያሰናብተኝ እንደፈለገ አልገባኝም።

ሰንደቅ፡-በታህሳስ 01 ቀን 2005 ከዲሲፕሊን ኮሚቴው ወጪ በሆነው ደብዳቤ ላይ “ፕሮግራሙን ያዘጋጁት ባልደረባችን አቶ አዲሱ መሸሻ” የሚል ሲሆን፣ በጥር 20 ቀን 2005 ከዲሲፕሊን ኮሚቴው የወጣው ደብዳቤ በበኩሉ “ፕሮግራሙን ከ90 በመቶ በላይ የሰራው አቶ ሳሙኤል ከበደ” ናቸው ይላል። ከዲሲፕሊን ኮሚቴው በዚህ መልኩ ደብዳቤዎቹ ሊዘጋጁ ቻሉ? ፕሮግራሙን የሰራው ማነው ሊባል ይችላል?

ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ዲሲፕሊን ኮሚቴው ያወጣው ደብዳቤ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነው። ለክሱ እንዲረዳቸው አንድ ደብዳቤ በእኔ አዘጋጁ። ለመከላከል እንዲረዳቸው ደግሞ ፕሮግራሙን ከ90 በመቶ በላይ የሰራው አቶ ሳሙኤል ከበደ ናቸው የሚል ደብዳቤ አዘጋጅ። ይህ በራሱ የሚነግርህ ነገር አለ። በማኛውም ዋጋ እኔ መክሰስ እና ከስራ ማፈናቀል ለዲሲፕሊን ኮሚቴው የተሰጠው ተልዕኮ ነው። አቶ ሳሙኤል በወቅቱ ትምህርት ላይ ነበሩ። እንዴትም እንደመጡ አላውቅም።

እውነቱ ግን ጥቅምት 24 ቀን 2005 ዓ.ም. ቅዳሜ ፕሮግራሙን ሰርቼ ሙሉ ዝግጅቱ እሁድ ጥቅምት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ዜና በኋላ የሚቀርብ መሆኑ ነው። በዚህ ዕለት የሚተላለፍ መሆኑን የሚገልፅ ከውይይቱ የተወሰዱ አጫጭር ንግግሮች የሚያሳይ ማስታወቂውን /ስፖት/ የሰራሁትም እኔው እራሴ ነኝ።

ሰንደቅ፡- አሁን በዚህ መልስ በእርሶ ላይ የተወሰደው እርምጃ በሌላው ሰራተኛ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ምንድን ነው?

ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ይህ ጥያቄ ከነሳህልኝ በውይይቱ ላይ አንድ የተሰነዘረ ነጥብ ልንገርህ። በዚህ ውይይት ከተሳተፉት ተሳታፊዎች መካከል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ዓሊ ሱሌማን አንዱ ናቸው። እሳቸው ከገጠማቸው አስቸጋሪ የፀረ-ሙስና ትግል ሲገልፁ፤ “የመልካም አስተዳደርን ለማስፈን የሚታገሉ እና የሙስና ተግባራትን የጠቆሙና ያጋለጡ ሰዎች በአለቆቻቸው የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እየተወሰዱባቸው ቤሰቦቻቸው ተበትነዋል። በዚህም የተነሳ እነዚህ ግለሰቦች ምነው ይህን ባልተናገርኩ እያሉ አንገታቸውን ደፍተው ተሸማቀው እየሄዱ ነው። እነዚህ ሃይሎች ገነው ወጥተው ለፀረ-ሙስና ትግል የተሰለፉ ኃይሎች ግን አንገታቸውን ደፍተው ይገኛሉ” ነበር ያሉት።

ሰንደቅ፡- አሁን እርሶ ላይ የደረሰውን ነገር ከዚህ ከአቶ አሊ ሱሌይማን አባባል ጋር እንዴት ያስታርቁታል?

ጋዜጠኛ አዲሱ፡- የኮሚሽነሩን አስተያየት በእኔ ላይ መፈጸሙን ስመለከት በጣም አስገርሞኛል። ምክንያቱም በውይይቱ ላይ ተገኝቼ የቀረጽኩት ውይይቱን ለሕዝብ ለማቅረብ እንጂ፣ በዚህ የውይይት ፕሮግራም መቆራርጥ መነሻ እና በመልካም አስተዳደር ዕጦት ሰለባ ለመሆን አልነበረም። የሆነው ግን በእውነት አስገራሚ ነው። ከስራ ተፈናቅያለሁ። ልጆቼን ለጊዜው ለወላጆቼ ሰጥቻለሁ። ባለቤቴን ከፍዬ ነው፤ የማስተምረው። የፓርላማውን ውይይት በፈለጉት መንገድ የቆረጡት ግን ደረታቸውን ነፍተው ለእኔ የስንብት ደብዳቤ ፅፈው ሰጥተውኛል። ኮሚሽነሩም ያሉት ከላይ የዘረዘርኳቸውን ሂደቶች ነበር። ለእሳቸው አስተያየት ከእኔ በላይ ማረጋገጫ ማን ሊያቀርብ ይችላል?

እዚህ ላይ ማወቅ ያለብህ በጋዜጣችሁ ዝግጅት ክፍል ይህን እድል አግኝቼ ለመናገር ቻልኩ እንጂ ስንቶቹ የሆዳቸውን ይዘው የቢሮክራቶች ሰለባ ሆነው ቁጭ ማለታቸውን መዘንጋት የለብንም።

ሰንደቅ፡- ተጠሪነታችሁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው። አሁን ደርሶብኛል የምትለውን የመልካም አስተዳደር ችግር በአካል ሄደህ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባህል፣ የቱሪዝምና መገናኛ ብዙሃን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያመለከትከው ነገር የለም?

ጋዜጠኛ አዲሱ፡- በመጀመሪያ የወሰድኩት እርምጃ እራሴን ማረጋጋት ነበር። በዚህ ጉዳይ አንተ ሶስተኛ ወገን ስለሆንክ እንጂ የተፈጠረው ሁኔታ እጅግ ድፍረት የተሞላበት ነው። መዋሸት የማልፈልገው ከስራ ተሰናብተሃል የሚለውን ውሳኔ ስሰማ ደንግጫለሁ።

ሰንደቅ፡- ለምን?

ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ምክንያቱም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጠራው ስብሳባ ታማኝ ባለመሆኑ ይቅርታ መጠየቅ የነበረበት ኢ.ቴ.ሬ.ድ ነው። ይህን የምለው የእኛ ተቋም አስፈፃሚ መስሪያቤት በመሆኑ ተጠሪ ለሆነበት ተቋም በሰራው ስህተት ይቅርታ መጠየቅ ይገባዋል የሚል እምነት ስለነበረኝ ነው። የሆነው ግን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት በአግባቡ አልተስተናገደም የሚል መከራከሪያ ባነሳሁት ግለሰብ ላይ፣ የስራ ስንብት ደብዳቤ ሲሰጥ ምን ሊሰማህ ይችላል። እንደዚህ ዓይነት ድፍረት የተሞላበት እርምጃ እንዴት ይወስዳሉ ብለህ ትገምታለህ። ስለዚህም ግራና ቀኙን ለመመልከትና የተፈጠረብኝን ጫና ለመርሳት ወደ ሆነ ቦታ ዞር ማለትን ነበር የመረጥኩት።

ሰንደቅ፡- ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ ጉዳይ ምን ትጠብቃለህ?

ጋዜጠኛ አዲሱ፡- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ ጉዳይ ላይ ከእኔ ስራ መፈናቀል በላይ አጀንዳ ያለው ይመስለኛል። ምክንያቱም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ የሆነ ተቋም፣ በምን ምክንያት ውይይቱን ሊቆርጠው ይችላል? ውይይቱ መቆረጡንም ምክር ቤቱ ያውቃል። እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ ምክር ቤቱ ውይይቱ እየተቆራረጠ መቅረቡን እንደሚያውቅ እየታወቀ፣ ለምን የሃሰት መረጃ እንዳቀረብኩ ተቆጥሮ ከስራ ገበታዬ እስናበታለሁ? የፓርላማው ውይይት በትክክል አለመዘገቡን በመቃወም ምላሽ መስጠቴ ዋጋው ከስራ መሰናበት ከሆነ፣ ከእኔ የስራ ዋስትና በላይ ፓርላማው ሊመለከተው የሚገባ ጉዳይ ነው። ይህን መሰል ብልሹ የመልካም አስተዳደር ከተለመደ ተቋሙም ወዴት እየሄደ እንደሆነ ቆም ብሎ ማሰብ ተገቢ ይመስለኛል።¾

(ምንጭ፡- ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር 411 ሀምሌ 17/2005)

Sport: የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለወሳኙ ጨዋታ ነገ ወደ ኪጋሊ ይጓዛሉ

0
0

national team(ወርልድ ስፖርት) በደቡብ አፍሪካ አስተናጋጅነት በሚካሄው 3ኛው የቻን ውድድር ተሣታፊ የሚያደርገውን ትኬት ለመቁረጥ የመጨረሻው ምእራፍ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊታችን ቅዳሚ ለሚደርገው ወሣኝ ጨዋታ ነገ ወደ ኪጋሊ ይጓዛል፡፡ አሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው ለዚህ ጨዋታ ስኳዳቸውን ይፋ ያደረጉ ሲሆን ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ከቡድኑ ተቀንሶ የነበረው ኡመድ ኡክሪ ለክለቡ ተሰልፎ በተጫወተባቸው ጨዋታዎች ያሣየውን ድንቅ አቋም ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ጠርተውታል፡፡ አሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው ለሩዋንዳው ወሣኝ ጨዋታ የመረጧቸው ተጨዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡፡
ግብ ጠባቂዎች
ጀማል ጣሰው፤ ሲሳይ ባንጫና ሳምሶን አሰፋ
ተከላካዮች
ደጉ ደበበ ፤አይናለም ሀይለ ፤አበባው ቡጣቆ ፤ስዩም ተስፋዬ ፤ብርሀኑ ቦጋለ ፤ቶክ ጀምስ ፤ሳላዲን በርጊቾ ፤ሞገስ ታደለ
አማካዮች
አዲስ ህንፃ፤ተስፋዬ አለባቸው፤ሽመልስ በቀለ፤ምንያህል ተሾመ፤በሀይሉ አሰፋ
አጥቂዎች
አዳነ ግርማ፤ኡመድ ኡክሪና ዳዊት ፈቃዱ

“አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል!” (ከ የአርአያ ጌታቸው)

0
0

araya
2005 ዓ.ም ከ1998 ዓ.ም በኋላ በተግባር ሊታይ የሚችል የፖለቲካ እንቅስቃሴ የታየበት አመት ነው ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም ፡፡ በተለይ በግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ፣ም የሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ምንአልባትም ወደኋላ ይጓዝ የነበረውን የሀገር ውስጥ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከማስቆም በዘለለ ወደፊት እንዲጓዝ ያደረገው ይመስለኛል፡፡ ከዚህ እለት በኋላ ባሉት ቀናቶች ውስጥ በርካታ ፓርቲዎች ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ። በተለይ አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ለዚህ ማሳያ ነው፡፡ ድርጅቱ በደሴና በጎንደር የተሳኩ ሁለት ሰልፎችን በአንድ ቀን አድርጓል፡፡
ለዛሬ ይህን እንድጽፍ ያነሳሳኝ ግን ይህን እንቅስቃሴ ተከትሎ እየተነሱ ያሉት እንዳንድ አሉታዎችን ለማየትና የራሴን ምልከታ ለመጠቆም ያህል ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው የፕሬስ እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ ማለት በሚቻልበት ሁኔታ አለ ብሎ ለመናገር አያስደፍርም (ያ ጉምቱ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እየያዘ ከሚመጣቸው መጽሄትና ጋዜጦች በቀር፤ እነሱንም አንብበን ሳናጣጥም እና በጽሁፎቹ ዙርያ ሳንወያይ ያው የስርአቱ ጡጫ ያርፍባቸዋል) ታዲያ በዚህ ክፍተት ውስጥ ትልቅ የመነጋገሪያና የመያያ መድረክ እየሆኑ የመጡት ማህበራዊ ገጾች እና ድረ ገጾች ናቸው፡፡ እነዚህ ሚዲያዎች ይህንን ክፍተት በመሙላት ደረጃ ትልቅ እተዋጽኦ እያበረከቱ የመሆናቸውን ያህል ሰዎችንም ወደ ተሳሳተ መንገድ እና አመለካከትም የመምራት እድል አላቸው፡፡
ሰሞኑን እየተደረጉ ካሉት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ጎን ለጎን በነዚህ ማህበራዊ ድረ ገጾች አንዳንድ ግለሰቦችና ግሩፖች በተለይ የሰማያዊ ፓርቲና የአንድነት ፓርቲ በተናጥል እያደረጉ ያሉትን እንቅስቃሴ ወደ ፉክክር መንፈስ በመውሰድ አላስፈላጊ ቃላቶችንና በመጠቀም ድርጅቶችን ወይም ግለሰቦችን ሌብል እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ በሌላ ወገን ደግሞ ድርጅቶቹን ወደ ተለመደው “ተባበሩ ወይም ተሰባበሩ” የሚል አሰልች ዝማሪያቸው የተመለሱም በብዛት አሉ፡፡
ለመሆኑ ህብረት ወይም ትብብር ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ያልተሞከረ ነውን? የኢትዮጵያንስ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የጎዳው ህብረት አለመኖሩ ነውን? እነዚህ ጥያቄዎች ምንም እንኳ ጥልቅ ጥናት የሚፈልጉ ቢሆኑም ለኔ በደፋናው አይመስሉኝም (ከተሳሳትኩ ለመታረም ዝግጁ ነኝ) በኢትየጵያ ፖለቲካ ከፓርቲዎች ብዛት እኩል ለቁጥር አሰልቺ የሆኑ ህብረቶችና ጥምረቶችን ሀገር ወስጥ ባሉም ከሀገር ውጭ ባሉም ድርጅቶች መካከል አይተናል፡፡ አንዳቸውም ግን መሰረታዊ ለውጥ ሲያመጡ አልታዩም ወይም የተጣመሩበትን ግብ እስኪመቱ እንኳ መቆየት አላቻሉም፡፡ እንደኔ በኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ ፓርቲ እንዳይኖር ካደረጉት ምክንያቶች እንዱ ይህ “የህብረት” መንፈስ ይመስለኛል፡፡ አንድ ድርጅት ጠንክሮ የመውጣት አዝማሚያ ሲያሳይ ደካሞች የሚጠፉ ወይም የለመዱትን ጥቅማጥቅም የሚያጡ ስለሚመስላቸው ያንን ድርጅት ከነሱ ቁመት እንዳይበልጥ ወይም እራሳቸውን ከነችግራቸው እና ከነድክመቶቻቸው ካለ እነሱ እንዳይጓዝ ለማድረግ ሁሌ በኋላ ኪሳቸው የሚያስቀምጧትን ካርዳቸውን ይመዛሉ “ህብረት” ከዛም የጥፋት ዘራቸውን ይበትናሉ፡፡
መጀመሪያ ወደ ተነሳሁበት እና ወቅታዊ ወደ ሆነው ጉዳይ ስመለስ በተለይ በቅርቡ እየተካሄዱ ባሉት ሰልፎች ዙርያ የተጀመረው ሰማያዊንና አንድነት ፓርቲን (ሶሊ እንዳለችው “ለትልቅ አላማ ሲባል”) ተባብራችሁ አንድ ላይ ስሩ ጥሪ ጊዜውን የጠበቀ አለመሆኑን ጉዳትም እንዳለው በግርድፉ ለማሳየት እሞክራለሁ፡፡
የመጀመሪያው ከትግል ስትራቴጂ አንጻር እንየው፡፡ የሁለቱ ተቋማት በተናጥል ትግል ማድረጋቸው በተወሰነም ደረጃ ድርጅቶቹ ላይ ስርአቱ የሚሰነዝርባቸውን ዱላ ወይም ውንጀላ ይቀንሰዋል፡፡ ትላንት ሰማያዊ ፓርቲ ባደረገው ሰልፍ የስርአቱ አጋፋሪዎች እስኪነጋ አላደርስ ብሏቸው የዛኑ እለት ድርጅቱን ከአሸባሪ ቡድኖች ጋር መድበውት እንደነበርና በአመራሮቹም ላይ ክስ ለመመስረት በዝግጅት ላይ እንደነበሩ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ሰማያዊ ፓርቲ በ3 ወር ውስጥ መንግስት መልስ ካልሰጠ ከፍ ባለ ደረጃ ሰልፍ ለመጥራት ቃል መግባቱን ተያይዞ መንግስት ትኩረቱ ሁሉ በሰማያዊ ላይ ያደረገ ይመስል ነበር፡፡ ሆኖም ይህንን ህዝባዊ ንቅናቄ አንድነት በፍጥነት በመቀላቀሉ መንግስትን ክፍኛ ስላስደነገጠው የትኩረነት አቅጣጫውን በተወሰነ ደረጃ ከሰማያዊ ፓርቲ ወደ አንድነት አዙሯል ለማለት ይቻላል፡፡ ነገር ግን እንዚህ ድርጅቶች በጋራ እንቅስቀቃሴ ቢያደርጉ የስርአቱን አቅጣጫ እና ሀይል በአንድ መሰመር ስለሚያደርገው የእንቅስቃሲያቸውን እድሜ የማጠሩ እድል ከማስፋቱም በዘለለ መንግስት በአንዱ ተቋም ላይ እርምጃ ቢወስድ ሌላው ጥያቄዎቹን አንስቶ የመቀጠል እድሉን ያጠበዋል፡፡
ሁለተኛው አንድነት አሁን የሚገኝበት ሁነት በመነሳት ሰማያዊ ብቻውን ቢጓዝ በግሌ እመርጣለሁ፡፡ አንድት አሁን ያለበት ሁነት ስል ድርጅቱ ከመድረክ ጋር የጀመረው እንቅስቃሴ (የመድረከ ግንባር አባል ነው) በተለያዩ ሚዲያዎች እንደምናየው ገና እልባት ያላገኘና በፓርቲው የውስጥ ስነስርአትና መዋቅር ውይይቶችና ጥናቶች እየተካሄዱ በመሆናቸው እንዲሁም ከ33 የፓርቲዎች ህብረትም ጋር የጋር የትግል እንቅስቃሴ እየነደፉ ስለሚገኙ፤ ሰማያዊ ደግሞ በወጣቶች የተመሰረተና ገና አዲስ ድርጅት እንደመሆኑ እንደዚህ ያሉ የማይመለከቱት እና አላስፈላጊ የውስጥ ፖለቲካ ንትርኮች ውስጥ ገብቶ እድሜውን እንዳያሳጥር ስለምሰጋ በጀመሩት ጠንካራ የፖለቲካ ባህል ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ፍጹም በመከባበር ትግላቸውን ወደፊት ቢቀጥሉ እመርጣለሁ፡፡ ለረጅም አመታት የቆሰልንበት የውስጥ ፖለቲካ ሽኩቻ ሰለባ እንዳይሆን ከመስጋቴ የተነሳ እንደሆን ተረዱልኝ፡፡
ሶስተኛው ምክንያቴ በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ ያሉት አንዳንድ ወጣቶች ከዚህ ቀደም በአንድነት ፓርቲ ውስጥ የነበሩና በድርጅቱ ውስጥ በተፈጠረ አለመግባባት “ዝም አንልም” በሚል ከፓርቲው የወጡ እንደመሆናቸው ከአንድነት ፓርቲ ጋር በአሁኑ ወቅት ያለው መልካም ግንኘነትን በጥንቃቄ መያዝና ይህንንም ግንኘነት ወደፊት አጠንክሮ ማስቀጥል ከተፈለገ ነገሮች በእርጋታ እና ለተጨማሪ ንግግሮችና የጎንዮሽ ግንኙነቶች ጊዜ መስጠት በጣሙን አስፈላጊ ነው ብዬ ስለማምን ይህንን ጊዜውን ያልጠበቀ “ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ” ድርጅቶቹ በራሳቸው ጊዜ እያሻሻሉት ያለውን ግንኙነት አጉል ተቆርቋሪ ነኝ በሚል ያለወቅቱ በማንሳት የተጀመረውን ጠናካራ ሀገራዊ ንቅናቄ ወደኋላ ከመጎተት ውጭ ጥቅም ይኖረዋል ብዬ አላምንም፡፡
በአጠቃላይ በፓርቲዎች መካካል የሚደረጉ ህብረቶች ወይም ጥምረቶች በድርጅቶቹ በራሳቸው ግንኙነት እና እምነት ጊዜውን ጠብቆ መምጣት ይኖርበታል፡፡ አለበለዚያ ከዚህ በፊት እንደለመድነው “ለትልቅ አላማ” በሚል በግድ በሙጫ ለማጣበቅ የሚደረግ ጥረት ነገ በትንሽ ንቅናቄ እንደሚገነጠል ጥርጥር የለኝም፡፡
ደግሜ እላችኋለሁ መተባበር ባንችል አንጠላለፍ!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
(ይህ ጽሁፍ የአርአያ ጌታቸውን አቋም ብቻ የሚያንጸባርቅ ነው፡፡ እንዲሁም ይህን እንድጽፍ ያነሳሳኘ “በስመ ተቃዋሚ ተቃቅፎ መሳሳም” – ለትልቁ ዓላማ? በሚል በሶሊያና ሽመል የተፃፈውን ካነበብኩ በኋላ ነው )
majiesty02@gmail.com

https://www.facebook.com/araya.getachew

እስላም ኦሮሞች፣ እስላም ያልሆኑ ኦሮሞች፣ ኦሮሞ ያልሆኑ እስላሞች እና ኢትዮጵያኖች ፣

0
0

(አዩም አያኔ ዘ ኢትዮጵያ)
16916781
ከላይ ያለዉ ቃል የተጳፈዉ በእንግሊዝኛ ነዉ። እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ። ዘሬም ነገዴም ከኢትዮጵያ ነዉ።ደግሞም ኦሮሞ ነኝ።
ለዝህ ጦማር መንሻ የሆነኝ አስከዛሬ ድረስ ኦሮሞ የሚባል አገር ፣ ወይንም ኦሮሞ የሚባል ዜግነት መኖሩን አለማዎቄ ነዉ። ኦሮሞ ነኝ በማለት ለነፃነት ቆረጠናል የሚሉትም የያዙት የኢትዮጵያን ፓስፖርት ነዉ።
እንግድህ ከላይ የትጳፈዉን ቃል የተጠቀመዉተ ጁሀር መሐመድ የተባለ ሰዉ ነዉ። ኦሮሞ ማለት አትዮጵያዊ አልምሆኑን ስለነግረኝ ፣ እኔ ደግሞ አትዮጵያዊ ሰልሆንኩ ፣ ኦሮሞ ሆኘ አና እሰላም ሳልሆን ግን አትዮጵያዊ መሆኔ እንደሱ አመለካከት ምን አንደሚባል ለማወቅ ነዉ። ወይንም ለመጠየቅ ነዉ።
ጁሀር መሐመድ፣
እኔ ኦሮሞ ነኝ፣ ያደኩት በኦሮሞቹ ዘሞዶቼ ተከብቤ ነዉ፣ የተወለደኩት የኦሮሞ ያልሆነ መሬት ላይ ነዉ። ኦሮሞ፣ አማራ፣ ሲዳማ፣ ከንባታ፣ ጉራጌ፣ ሀዲያ ፣ ዎላይታ፣ ሱማሌ፣ አደሬ ፣ አፋር፣ አና ሌሎችም ብዙ ጎሳዎች የሚኖሩባት አገር አለች ፣ እነዝህ ሁሉ አንድ ላይ ኢትዮጵያዊያኖች ተበልዉ የጠራሉ። ዜግነታቸዉም አትዮጵያዊ ነዉ። ላንተ ያለኝ ጥያቄ ሶስት ነዉ።
1. ለእስላም ኦሮሞች አና እስላም ላልሆኑ ኦሮሞች ያለህን ህልም ፣
2. እነዚሁ ሰዎች የትምድር ላይ አንድሚኖሩ አና
3. እስላም የሆኑም ያልሆኑ ኦሮሞዎች አትዮጵያዊ አንዳልሆኑ የገልጠልህን ነብይ ልትነግረኝ ትችል አንድሁ ብዬ ነዉ።
አትነገረግኝም ። ኦሮሞ ሰላልሆንክ የኦሮሞን ታሪክ አትዉቅም ። እስላምም ሰላልሆንክ ነብይህንም አታውቅም። ከሁሉም በላይ አትዮጵያዊነትን ስልምትጠላ ሰለኢትዮጵያ ነገድ ማዉራት አትቺልምና ነዉ። አኔ ግን እነግርሃለሁ። እስላም የሆኑም ያልሆኑም ኦርሞች ኢትዮጵያውያኖች አንድሆ ሰልማዉቅ ። ነብይህንም መገመት አይቅተኚም ቶራቦራ ሳልሄድ። ለዛረዉ ህልምህን ልንገርህና ሌላዉን ሌላ ቀን።
ሕልምህ እንድህ ነዉ፣
ከሰንሰልታማዉ የቶራቦራ ተራሮች የተነሳች ቁራ ወደላይ ትበርና የፓኪስታንን ምድር አቃርጣ ፣ የሳዑድን፣ የግብፅን ፣ የየመንን፣ የሶሪያን፣የኢራንን በረሃ አልፋ ቁልቁል አይትምዘገዘግች አንተ ነጭበነጭ ሺርጥ አሸርጠህ ኢቆምከበት ሠፈር በጥቁር ጨርቅ የተሸፈነ ስል ሜንጫ ታቀብልሃልች። ከዚያም ወደ ምእራብ አቅጣጫ አንድትመልከት ትነግረሃለች። አናም ታያልህ፣ ድምፅ ይመጣል ‘ሰ ‘ሰ ‘ ስራልዮን የሚል። ከዝያም “the bloody dimond” ፊልም ባይነህልናህ ይመጣል። ህልምህ የቀጥላል ፣ ሴት ሳይባል ወንድ፣ ህፃን ሳይባል ሺማገሌ በ AK 47 ኢንደቅጠል ሲረግፉ መካከል ሆንህ ሰትደሰት ደም አንደጎርፍ ስፈስ ፣ ለመሞት የምያጣጥሩትን ሰዎቺን አያስጎተትክ አጅ አጃቸዉን በሜንጫ ስትቀነጥስ።
ህልምህ የቀጥላል፣ ህፃናት ሴቶችና ወንዶች ሺማገሎዎችና አሮጊቶች ከንጎጆያቸዉ እንድቺቦ ስነዱ፣ በረት ከነከብቱ ፣ ጎተራ ክንእህሉ ስጋይ፣ መንደሩ በእቶን አሳት ስንበልበል ፣ ደስታህ ከፍ እያለ ህልምህ ይቀጥላል ። ህዝቡ ተሰብሰቦ ነብይ ሲያደርግህ፣ ወንዶቺን በሜንጫ አና በ AK-47 ስታስታጥቅ ፣ ሴቶቺን ከነነብሳቸዉ አስቀብረህ በድጋይ ሰታስዎግር ምኞትህ ስሰመር ፣ የቀጥላል ህልምህ ። ክርስትያን አምቦቃቅላ ሴቶች ስመጡልህ የስጋ ፍላጎትህን ጨርሰህ አንገታቸዎን ሰታስቀላ፣ ስትቀላ ።
ህልምህ የቀጥላል ፣ ቁራዉ ከንድምፁ ይመጣል ወደ ሰሜንም ዙር የልሃል ትዞራልህ፣ ቦ ቦ ቦ ቦኩሃራም ይልሃል የታይሃል። ታልማልህ ቤትክርስትያን በቦምብ ሰጋይ ፣ መስጊድ በፈንጂ ሰናድ ፣ አዉቶቡሶች ከነተሳፍርያቸዉ በሳት ስንበልበሉ ፣ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ላይ ሰደርመሱ። የአበሻ ምደር ሰናጥ ፣ ደስታህ እየጨመረ ህልምህ የቀጥላል ። ቁራውም የመለሳል የጃራ አባገዳን ድምፅ ይዞ። የኔ ወራሽ ነህና የነገርኩህን ቀጥል አያለ ፣ የበደኖን የወተርን ፣ የአርባጉጉን ታርክ አትረሳ አያለ።ህልምህ የቀጥላል ፣ቁራዉ የመለሳል፣ በመለስም የመሰላል፣ የነወራሽነህና ኢትዮጵያን ያሉትን አሳድ ፣ አንገታቸዎን ቁረጥ ኢትዮጵያን አትራምስ፣ የደም መሬት የደም ምድርም አደርግ አያለ ።
ህልምህ የቀጥላል ፣ ቁራዉም የመጣል አሳፍሮህም ይከንፋል፣ ወደቶራቦራም ይበራል ። አዛም ጥቂት ታርፋለህ ህልምህንም ታጠናለህ አጥንተህም ታልማለህ ። በፓኪስታን በሳዑድ፣ በግብፅ ፣ ከፍ ከፍ ያለ ስፈራ ስሰጥህ ፣ ገንዘብም በገፍ ስጎርፍልህ፣ ህልምህ የቀጥላል። ቁራዉም ይመጣል ወደ ምስራቂም ዙር የልሃል። ትዞራለህ ኢትዮጵያንም ፣ታያለህ ። ባለጎፈረ ፈርሰኞች ሰጋልቡ ፣ ራባዶርንም ባራቴርንም ስያንበረክኩ፣ አረንጎዋዴ፣ ብጫ፣ ቀይ ቀለማትን የተሸለሙ የኦሮሞ ፈርሰኞች፣ ለመጀመርያ ጊዜ ነጭን ያንበርከኩ ፣ የጥቁር አንበሶች፣ ወዳንተ ስግሰግሱ ታያለህ አይተህም ትደነግጣለህ ደንግጠህም ትባንናለህ። ትናደዳለህ የበታችነትም ይሰማሀል ፣ተመልሰህም ትተኛለህ ። አንድገናም ታልማልህ፣ ኦሮሞ አማራ፣ጉራጌ፣ ከንባታ፣ ሀዲያ፣ ወላይታ፣ አደሬ ፣ ሱማሌ፣ ጋምቤላ ፣ሺናሻ፣ሲዳማ፣ትገሬ፣አፋር፣ ሌሎቺም ሌሎቺም አንድላይ ሆነዉ አንድላይቆመዉ አንድላይ ወድቀዉ ኢትዮጵያን ሲሉ ታያለህ አሁንም ተናደዳለህ ። ህልሙን ለማስተካከል ተመልሰህ ትተኛለህ ፣ አሁን ላትመለስ እንደ መለስ አንተም አስከ ወድያኛዉ ታሸልባልህ ፣ ኢትዮጵያ ግን ለዘላለም ትኖራለች፣ ከነልጆቹዋ ከእስላሞቹ ከክርስትያኞቹ ጋር። ያንተም የነብዮችህም ፣ የጃራም፣ የመለስም፣ የህወሃትም ፣የኦሆድድም፣የብአዴንም ህልማችሁ ህልም አንድሆነ ኢትዮጵያ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ ትኖራለች ተሻገራለች።
ከዝህ በላይ ባንተ ህልም ላይ ግዜ ማጥፋት እንዳንት ሃርቫርድ አንድመሄድ ከንቱ ስለሚሆን ብበቃኝስ ።

ሰለኮሎኔል ታደሰ ጥቂት ልበል፡

0
0

Moving-picture-Ethiopia-flag-flapping-on-pole-with-name-animated-gif
ከፍል2
ይታያል የሩቅሰው
ወደ እለቱ ተግባራዊ ቅኝቴ ለመግባት፡ ባለፈው ሳምንት በዚህ አርእዕስት የከተብሗትን፡ ጦማሪን ስደመድም፡ ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ፡ ወደአሜሪካን ባቀናበት ወቅት፡ በዚያው እንዲቀር ለቀረበለት ጥያቄ፡ የሰጠው መልስ፡ወያኔ ውሎ ካደረ ኢትዮጵያ የምትባል ሃአገር አትኖርም፡ እናም ቢሆን ከጥፋት አድናታለሁ፡ ካልሆነም ጥፋቷን ሳላይ ማንም ያጥፋኝ ማን ስከላከልላት እኔ ቀድሜያት፡ እጠፋለሁ፡ ሞት እንደሁ ፈራንም ደፈርን፡ የማይቀር የተፈጥሮ እዳችን ነው። የሚል እንደነበር በመጥቀስ ነበር፡፡ ወደዛሪው የምገባው ደግሞ የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ በመሞከር ነው።
2.1.የመሰወሩ ምክናያቶችስ ምንና እነማን ናቸው?
ነገሩ እንዲህ ነው፣በኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ፡ የሰከነና፡ በእውቀት ላይ የተመሰረተ አመራር፡ በእነ ቱሗት፣ በእነ ጁማ፣ በእነ ዮሴፍ፣ በእነተ ስፋዬ፡ ትጋትና የዓላማ ጽናት፡ ያልተለየው የሌት ከቀን እንቅስቃሴ፡ በክፍል አንድ ማብራሪያዬ፡ እንደጠቀስሁት፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፡ በአጭር ጊዜ ተጠናክሮ፡ ጥቃት መሰንዘር ከሚያስችለው ደረጃ ላይ እየደረሰ ሲመጣ፡ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ በርካታ፡ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን፡ እቦታው ድረስ በመሄድ ጎብኝተው፡ ትግሉን በማበረታታት ወደ እየመጡበት ሲመለሱ፡ ፕ/ር ሙሴ ተገኝ ግን፡ ጓዙን ጠቅልሎ አስመራ በመግባት፡ አይዟችሁ በማለት ፋንታ፡ ከተማ ቁጭ ብሎ፡ የግንባሩ መሪ ለመሆን ባለው ህልም፡ ይሁን በሌላ ልዩ ተልዕኮ፡ ባለየለት ምክናያት፡ በኤርትራ ባለስልጣናት ቢሮዎች እየዞረ፡ እነኮሎኔል ታደሰን፡ እነዚህን ደርጎች፡ እንዴት ታምኗቸውአላችሁ፡ በማለት ማጥላላትን ስራየ ብሎ ይይዛል፡ አመራሩ ግን፡ ከሗላው እየተለቀለቀበት ያለውን ጥላሽት፡ በማያውቅበት ሁኔታ ላይ ሆኖ፡ ብዙ ኩነቶችን ከዳሰሰና፡ ካጠና በሗላ የውጊያ እቅድ ሲነድፍ፡ አንድ መደምደሚያላይ ይደርሳል። እሱም የትግሉ መሰረት የጎረቤት ሀገር ሳይሆን ሃገር ቤት መሆን አለበት። የወደቀው ወድቆና ያለቀው አልቆ፡ ሀገራችን ላይ ነጻመሪት ሊኖረን ይገባል፡ የሚለው ተወስኖ ጠቅልሎ ለመግባት የ6ወር ጊዜ ገደብ ተቀምጦለት፡ ዝግጅት ይጀመራል፡ ጉዳዩም በሚስጥር እንዲያዝና ከስራ አመራሩ በቀር ለማንም እንዳይወራ፡ ተስማምተው በእየተመደቡበት የስራ ዘርፍ ደፋቀና በማለት ላይ እንዳሉ፡ ከ7ቱ አመራር አባለት መካከል አንዱና በገንዘብ ያዥነት፡ የተመደበው አበሩ አታላይ ማለት ዛሪ ስሙን ቀይሮ መስከረም ነኝ ያለውና፡ ጀርመን ሃገር የሚኖረው፡ ለህክምና ብሎ አስመራ በሄደበት ከፕ/ር ሙሴ ተገኝ ጋር ተገናኘቶ 2ቱ የተንኮል ሴራ ሽርበው፡ በጋራ ከአንድ የሻብያ ቱባ ባለስልጣን ቢሮ ቀጠሮ አስይዘው በመግባት፡ እነዚህ ደርጎች እነ ኮሎኔል ታደሰን ማለት ነው፡ ጓዛቸውን ጠቅልለው ሀገራቸው ሊገቡ ወስነው እየተዘጋጁ ነው ያሉት፡ እንዲያውም፡ በመጀሪያ፡ ወያኔን ቀጥለን ሻብያን፡ እንደመስሳለን፡ ሀገራችን ወደብ አልባ ሆና አትቀርም ነው የሚሉት፡ በማለትና ሌሎች ሻብያን ሊያበሳጭ ይችላል ያሉትን ውሽት በመደርደር፡ መረጃ ሰጥተውና ለቀጣይ መመሪያ ተቀብለው ይወጣሉ። ከዚያች እለት ጀምሮ እነ ኮሎኔል ታደሰ በሻብያ አይነ ቁራኛ መጠበቅ ይጀምራሉ፡፡ አበሩ አታላይም ወደግንባር ተመልሶ፡ የጎንደር አካባቢ ተወላጅ ሲያገኝ፡ ጎነደሬ፡ የትግራይ ካባቢ ተወላጅ ሲያገኝ፡ ትግሬ ነኝ በማለት፡አቅሙ በፈቀደ መጠን ሰራዊቱን፡ በመንደር መከፋፈሉን ያጧጡፋል።
ነገር ከስሩ ውሃ ከጥሩ እንዲሉ፡ ለአነባብያን፡ የበለጠ ግልጽ እንዲሆን፡ ትንሽ ወደሗላ ሄጄ፡ ሰለ አበሩ አታላይ፡ ማንነት በአጭሩ፡ አንድ ሁለት ልበል፡ ተጠቃሹ፡ ወልቃይት ውስጥ ነው ተወልዶ ያደገው፡ ትምህርት፣ የሚሉት ነገር ባህላዊዩም ሆነ ዘመናዊዩ አልነኩትም በፍጹም አይተዋወቁም፡ በማህበራዊ ኑሮውም በአካባቢው የተጠላ ነበር፡ ያነን ማንነቱን የፋቀልኝ መስሎት ሳይሆን አይቀርም ስሙን መቀየር ያስፈለገው። ይህ ግለሰብ የሚኖርባት መንደር የጎንደር ክፍለሀገር ክልል ሆና፡ የትግራይንና የኤርትራን ክፍላት ሀገራት በቅርብ እርቀት የምታዋስን በመሆኗ፡ በደርግ ዘመን፡ በሚፈጽማቸው አስነዋሪ ተግባራት፡ ምክናያት በፖሊስ፡ ጎንደር ሲፈለግ ትግራይ፣ ትግራይ ሲፈለግ ኤርትራ፡ እያለ በማስቸገር ሲኖር፡ በአንድ ወቅት ብልሁ የሀገሪ ሰው በዘዴ ለመገላገል፡ሲል ለአካባቢ ህዝባዊ ሰራዊትነት መልምሎ እንዲሰለጥን ይልከዋል፡ አበሩ ከተላከበት ጠፍቶ ወደመንደሩ ሲገሰግስ አዘዞ ላይ ተይዞ፡ በሀገር ክህዕደት ወንጀል ተፈርዶበት እስር ቤት ይገባል፡ ጨርሶ ሲወጣ፡ ወደመንደሩ ሄዶ የተለመደ ስራውን ሲያከናውን፡ ወያኔ ሀገሪቷን ይቆጣጠራል፡ ወያኔዎች እንደገቡ ሌባ ይገድሉ ስለነበር እንዳይገደል ፈርቶ፡ ወደሱዳን ይሸሻል፡ እዚያም ከፋኝን ተቀላቅሎ፡ እያለ የከፋኝ መስራችና ነባር አባላቱም ሆኑ መሪዎቹ በዩ.ኤ.ን. አማካኝነት፡ ወደተለያዩ ምእዕራባውያን ሀገራት ሲሄዱ፡ እሱ በመቀረቱ፡ በአቶ ዮሴፍ ያዘው የሚመራውን፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች ዲሞክራሴያዊ ግንባርን፡ተቀላቅሎ ኤርትራ ይገባና፡ የትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪነቱን፡ እንደ ማንነት መገለጫ በማቅረብ፡ በድብቅ በአካባቢው፡ ላገኛቸው የኤርትራ ባለስልጣናት ኤርትራዊ እነቱን በመንገር፡ የሻብያ አባል ይሆንና፡ አብረውት የተሰደዱ ኢትዮጵያንን፡ እንዲሰልል ግዳጅ ተሰጥቶት እያለ ነው ተጨማሪ ሐይል ሙሴ ተገኝን ያገኘ።
ስለ መስከረም አታላይ፡ ከብዙው በጥቂቱ፡ ይህነን ያህል ካልሁ ወደ ኮሎኔል ታደሰ ልመለስ፡ እነኮሎኔል ታደሰ ባላወቁት ነገር በሻብያ ጥርስ ተነክሰው፡ የሚደነቀርባቸውን ሁሉ መሰናክል በትግስት እያለፉ፡ ስራቸውን በማፋጠን ላይ እንዳሉ፡ ከእለታት አንድ ቀን በሻብያ ሰራዊት ተከብበው፡ አመራሩ እንዲበተን ይደረጋል፡ ከዚህ በሗላ ኮሎኔል ታደሰ፡ ከአስመራ እንዳይወጣ ሲደረግ ቱሗት ፖልና ጁማ እሩፋኤል፡ ከኤርትራ እንዲወጡ፡ ዮሴፍ ያዘው ከተሰኔይ ከተማ እንዳይወጣ፡ ሲደረግ ተስፋዬ ጌታቸው፡ አዚያው ሃሪና በርሀውስጥ እንዲታሰር ተወሰነበት፡፡ይህ ከመከናወኑ ቀደም ብሎ ግን የግንባሩ አመራር ከነደፈው፡ መርሃግብር አንዱ የሆነውን አርበኛው፡ ከኤርትራ ነቅሎ ሲወጣ፡ መሰረቱን የሚጥልበትን ቦታ፡ አጥንቶ እንዲመለስ የተመደበውን ቃኝ ሃይል፡ በሃላፊነት መርቶ የሚሄድ አንድ ሰው ለመምረጥ፡ በተደረገ ውይይት ላይ፡ አበሩ ወይንም መስከረም አታላይ፡ በእራሱ ፈቃድ እኔ ልሂድ ስለአለ፡ በሃላፊነት መርቶ እንዲሄድ ይደረጋል፡ አበሩ ከፊሉን አስገድሎና ከፊሉን፡አስማርኮ፡ እሱ ብቻውን፡ ጥይት አይደለም እንቅፋት ሳይመታው፡ ከመመለሱም በላይ ኪሱ ውስጥ በርካታ ዶላር በመገኘቱ፡ ጉዳዩ አጠራጣሪ ሆኖ ስለተገኘ፡ እስኪጣራ አመራሩ አስሮት ከነበረበት፡ በሻብያ ትእዕዛዝ ተፈትቶ፡ አሁንም ያለምርጫ፡ በሻብያ ትእዛዝ የግንባሩ፡ አዛዥ እንዲሆን ሲመደብ፡ በአንድ በኩል የፕ/ር ሙሴ ተገኝ የመሪነት ህልምን ሲያከስም፡፡ በሌላበኩል ሰራዊቱን፡ አስቆጥቶ፡ ከመበታተን፡ ደረጃ አደረሰውና፡ የተበተነው የሰው ሐይል፡ ከፊሉ ሱዳን ሲገባ ከፊሉ ደግሞ ወደሀገሩ የተመለሰ ሲሆን፡ ሁለቱንም ማድረግ ያልቻለው፡ መሀይም አይመራንም፡ አበሩ አታላይ፡ ታደሰ ሙሉነህን ሊተካ አይችልም፡ በማለት፡ የደቡብ ህዝቦች፡ የሲዳማ ህዝቦች፣ የጋቤላ፣ የቤንሻንጉል ወ.ዘ.ተ. በሚል ተከፋፍሎ፡ እነሆ ዛሪ የምንሰማውን 8 የብሄረሰብና የቋንቋ ድርጅት አቋቁሞ፡ እዚያው ኤርትራ ውስጥ እየኖረ ይገኛል። አበሩ አታላይም፡ በጣም ጥቂትና በግንዛቤም ሆነ በአቅም የሚመሳሰሉተን፡ የመንደሩን ልጆች አሰባስቦ፡ የአርበኛ ግንባር የሚለውን ስም፡ እንደያዘ አዛዥ ነኝ በማለት፡ ተስፋዬ ጌታቸውን ጉድጓድ ውስጥ አስሮ እንደውሻ በዱላ ደብድቦ ገደለው። በዚያን ጊዜ በአበሩ አታላይ፡ የተጀመረው፡ ወያኔን የምንጠላበት፡ የመንደርተኝነት፡ አባዜ እረ ወያኔስ ቢያንስ ከፍ አድርጎ፡ በቋንቋ ነው የከፋፈለን፡ አበሩ ግን አውርዶ፡በቀበሌ ገነጣጥሎን፡ አርበኛ ግንባር ውስጥ አሁንም ድረስ ተጠናክሮ እየሰራ ሲሆን፡ አመራር አይደለም፡ የአርበኛ ግንባር ታማኝ አባል ለመሆን፡ ቢሆን ወልቃይት፣ ካልሆነም ጎንደር መወለድ የግድ ይላል፡፡ ባልተጻፈው በእነ መስከረም፣ ማእዛው መመሪያና ደንብ፡ መሰረት፡፡ ለዚህም ነው አረበኛ ግንባር በተለያየ ጊዜ ከገደላቸው፡ ሁሉ ምሁራን፡ መካከል ከካሳሁን ወንዴ በቀር ጎንደር ክፍለሀገር የተወለደ፡ ሌላ2ኛ ሰው የማይገኝበት።
ከእነ ታደሰ ሙሉነህ፡ በሗላ ያለው አርበኛ ግንባር፡ ተስፋዬ ጌታቸውን ብቻ አይደለም የገደለው ወደፊት ታሪክ የሚያወጣቸው፡ ለመታገል የገቡ በመቶወች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ምሁራንን፡ እንክት አድርጎ በልቷል፡ ለዚህ ድርጅት አመራር አካላት ፊደል የቆጠረ ሰው፡ ከወያኔ በላይ ያስፈራቸዋል፡፡
መስከረም አታላይ፡ እሱ በሻብያ እንደተሾመ ሁሉ ከ3 አመት ቆይታ በሗላ፡ ወደጀርመን ሲጓዝ በተራው ደገሞ፡ መጻፍና ማንበብ የማይችለውን፡ የታላቅ እሀቱን ልጅ፡ ማእዛው ጌቱን፡ ሾሞት ስለሄደ 9 አመት ሙሉ አርበኛ ግንባር፡ የሚመራው በእሱ ነው፡ ያሳያችሁ እንግዴህ በተራቀቀ ሳይንስና ቴክኖለጅ፡ የሚጠቀምን ጠላት ለማስወገድ እታገላለሁ የሚል ጦር አዛዡ፡ ይህ ሰው ነው፡ ታዲያ፡ ለምን አይዳከም? ለምንስ አይክሰም? በእውቀት የበሰሉ፣ በሙያው የተካኑ፣ ኢትዮጵያውያን ሲቀላቀሉት፡ ፈጥኖ
ይበላቸዋል፡ ለእነማዛው ስልጣን ስለሚያሰጉ። የኮሎኔል ታደሰ መሰወር መንስኤው ሌላ ምንም ሳይሆን ይኸው ነው፡ ለእነማእዛው ስልጣን እንዳያሰጋ ገለል ማለት አለበት። ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ፡ ከአስመራ እንዳይወጣ ተወስኖበት ሲኖር፡ ከዲያስፖራ አርበኛውን ለመጎብኘት የሚሄድ፡ ሁሉ ኢትዮጵያዊ የአመራሩን ደካማነት ሲያይ፡ በማዘንና ተስፋ በመቁረጥ፡ ምናለ ኮሎኔል ታደሰ አመራሩን እንዲረከባችሁ ብታደርጉ የሚል ከቅንነትና ከመቆርቆር የመነጨ፡ አስተያይት፡ ተደጋግሞ እየተሰነዘረ ስላስቸገራቸውና፡ኮሎኔል ታደሰ አመራሩን ተረክበ ማለት ደግሞ፡ በምርጫ የማይቀየረውና፡ በማእዛው፡ የሚመራው 7ቱ የስራአመራር፡ ኮሚቴ ከዲያስፖራ እየተዋጣ፡ የሚላክላቸውን ዶላር በማዘርዘር፡ ተሰነይና ጉልሽ ከተሞች ላስቀመጧቸው የኤርትራ ቆነጃጅት፡ አልባሳትና ከእግር ጥፍራቸው እስከ እራስ ጸጉራቸው፡ የሚንቀለቀሉበት ወርቅ፡ መግዛቱ የሚቆም ከመሆኑም በላይ፡ ያመራር ቦታው፡ ወልቃይት በመወለድ ሳይሆን፡ በብቃት በሹመት ሳይሆን በሰራዊቱ የተመረጡ ሰዎች የሚይዙት ስለሆነ፡ ከአዛዥነት ወደታዛዥነት ሊወርዱ ነው፡፡ ይህ እንዳይሆን ዘላቂ መፍትሄና፡ ስጋትን አስወጋጅ ነው ብለው ያሰቡት፡ ኮሎኔል ታደሰን፡ ወንጅሎ ቢሆን ተላልፎ ለእነሱ ተሰጥቷቸው፡ እንደተስፋዬ ጌታቸው፣ እንደ ካሳሁን ወንዴ እንደ ጌታቸው ብርሃኑ እንደ ወርቅነህ መበሩ፡ ወ.ዘ.ተ.ጉርጓድ ውስጥ አስረው በውሃጥምና በእራብ አሰቃይተው፣እንደውሻ ዱላ ደብድበው በመግደል፡ አለዚየም፡ እንደ ሌሎች በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን፡ ታጋዮች በጥይት መረሸን፡ ካልሆነም በማሳሰር፡ ብቻ በሆነ ነገር ኮሎኔሉን ከአካባቢው፡ በማጥፋት እሱ ይምራችሁ የሚለውን ጥያቄ፡ ማንም እንዳያነሳባቸው ማድረግ ስለሆነ፡ ለዚህ ግባቸው መሳካት ደግሞ ውሸት ፈብርኮ ለኤርትራ መንግስት ታደሰ ሊያሰራን አልቻለም፡ በማለት የማያቋርጥ አቤቱታ ማቅረብ፡ ስለነበረባቸው፡ ከእረጅም ጊዜ ጥረት በሗላ እርኩስ ዓላማቸው ተሳክቶላቸዋል።
እስካሁን ግልጽ ያልሆነው ግን ኮሎኔል ታደሰን፡ የኤርትራ መንግስት እራሱ አስሮታል? ወይንስ አሳልፎ ለዚህ ወልዶበላ ድርጅትና፡ ግብዝና መሀይም መሪዎች ሰጥቶታል? የሚለው ነው። ይህነን እርዕስ ለማጠቃለል መነሻዬን ማስታወሱ ተገቢ ይመስለኛልና፡ የመሰወሩ ምክናያቶችስ ምንና እነማን ናቸው፡ የሚለውን ከዚህ በላይ በዝርዝር ለማሳየት ሞክሪያለሁ፡ ጠቅለል አድርጌ ለማስቀመጥ፡ ደግሞ ለዚህ ጀግና እና እውነተኛ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ መሰወር፡ መነሻውም መድረሻውም፡ አንድና አንድ ብቻ ነው፡ እሱም በስሟ እየነገደ ከወያኔ ባልተናነሰ ሁኔታ ብርቅዬ ልጆቿን እንደምስጥ እንክት አድርጎ የበላውና እየበላ ያለው፡ ካልተነቃበት ለወደፊትም ከመብላት የማይገታው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ነው።
ለዛሬ በዚህ ላብቃ ቀሪውን ሳምንት በክፍል3 እመለስበታለሁ ለዚያ ሰው ይበለን ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅ አሜን


ለመለስ ሙት አመት ማስታወሻ (ከፋሲል የኔአለም) ጋዜጠኛ

0
0

meles
ከመለስ ሞት በሁዋላ ያለው የኢትዮጵያ ሁኔታ ከሌኒን ሞት በሁዋላ የነበረውን የሩስያ ሁኔታ ያስታውሰኛል። ሌኒን በቦልሼቪክ ፓርቲ ውስጥ የገዘፈ ስም ነበረው፣ በፓርቲው ውስጥ ያሰፈነው የዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነት አሰራር የምእራቡን ዲሞክራሲን ለማይቀበለው የኮሚኒስት ታጋይ ሁሉ የሚመች ነበር ፤ በዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነት መርህ መሰረት ማንም የድርጅቱ አባል የሆነ ሰው እንደልቡ መናገር ይፈቀድለታል፣ ውሳኔ ከተላለፈ በሁዋላ ግና ውሳኔውን ያለምንም ማቅማማት ይተገብራል። ሌኒን ሲሞት የሌኒንን ቦታ ለመያዝ ይቋምጥ የነበረው ስታሊን የመጀመሪያ እቅዱ ይህን የዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነትን አሰራር ማፍረስ ነበር። ስታሊን ተናግሮ የማሳመን ወይም አዳዲስ ሃሳቦችን የማፍለቅ ስጦታ ወይም ችሎታ አልነበረውም። ትሮትስኪን የመሳሰሉ፣ ከስታሊን የተሻለ አስተሳሰብ እና ብቃት የነበራቸው፣ ሰዎች የዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነትን አሰራር ተጠቅመው ወደ ስልጣን የሚመጡበት እድል ከፍተኛ ነበር፤ ስታሊን ይህንን አሰራር ካላስቆመው በስተቀር በክርክር የመሪነቱን ስልጣን ሊይዝ የሚችልበት እድል አልነበረውም፣ አፈረሰው።
ዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነትን ማፍረስ ብቻውን ለስታሊን በስልጣን ላይ መቆየት ዋስታና የማይሰጥ በመሆኑ ስታሊን የፓርቲውን መስራችና የአብዮቱ መሪ የነበረውን የሟቹን የሌኒንን ስም ለመጠቀም ወሰነ። የመንግስት የመገናኛ ብዙሀን ሌኒን የተለየ ፍጥረት እንደነበር እንዲሰብኩ አዘዘ፣ ዜና መክፈቻና መዝጊያው ሁሉ “በሌኒን ራእይ” የታጀበ ሆነ። ጎዳናው ሌኒን፣ ካፌው ሌኒን.. ሆስፒታሉ ሌኒን፣ መጸዳጃው ሌኒን፣ ሌኒን.. ሌኒን… ሌኒን… እነትሮትስኪ በሌኒን ሙት መንፈስ መነገዱ እንዲበቃ ቢወተውቱም ለእነስታሊን የሚያሳምን አልሆነም፣ እንዲያውም ሌኒን ወደ “ሌኒኒዝምነት” ከፍ አለ…። ስታሊን የሌኒን የሙት መንፈስ ብቻውን ለረጅም ጊዜ በስልጣን ላይ እንደማያኖረው የተገለጠት ዘግይቶ ነበር፤ ይህ መገለጥ እንደታየው ወዲያውኑ ተቃዋሚዎችን አንድ በአንድ ጨረሳቸው።
ከዚህ በሁዋላ ስታሊን አስገራሚ የሆነ የ5 አመታት የኢኮኖሚ እቅድ ነደፈ፣ አገሪቱን በከባድ ኢንዱስትሪዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ( 10 አመታት) ከምእራባዊያን ጎን እንደሚያሰልፋት ቃል ገባ ። ይህንን የሚቃወሙ ፖለቲከኞች ” ከሀዲዎች፣ ጸረ ልማት ሀይሎች” ተባሉ፤በመጀመሪያዎቹ 5 አመታት የስታሊን እቅድ ተሳካ። የአገሪቱ እንዱስትሪ በ2 አመታት ውስጥ በ300 ፐርሰንት አደገ ፤ ግብርናውም እንዲሁ ተመነደገ። ብዙም ሳይሄድ ነገሮች መቆም ጀመሩ፣ በተለያዩ ምክንያቶች። ከእነ አሜሪካ ቀድማ መንኮራኩር ( ስፑትኒክ) ለመጀመሪያ ጊዜ ያመጠቀችው ሩስያ ከ70 አመታት የተወለካከፈ ጉዞ በሁዋላ ተንገራግጫ ቆመች፤ ቆመች ብቻ አይደለም በማፊያዎች ተዘረፈች።
መለስ ዜናዊ ተቀናቃኞቹን ካስወገደ በሁዋላ የዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነትን አሰራር አሽመደመደው ( እነስየን ማለቴ ነው)፣ መድረክ አዘጋጅ፣ ተናጋሪ፣ ወሳኝ መለስ ብቻ ሆነ። ተቀናቃኝን ማጥፋት ብቻውን በስልጣን ላይ የመቆየት እድሜን አያረጋግጥምና መለስም እንደስታሊን የ5 አመታት የትራንስፎርሜሽን ረቂቅ መዝሙር ቀምሞ ብቅ አለ፣ ውጤቱን ሳያይም በድንገት አረፈ፣ እነሆ ኢህአዴግም በተራው የመለስን ራእይ አስፈጽማለሁ ብሎ ተነሳ ፤ የአንዱ ሞት ለሌላው የስልጣን ማራዘሚያ መቅስቀሻ በሚሆንበት ስታሊናዊ አሰራር መሰረት ፓርቲው መለስ ካለፈበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ “መለስ መለስ” ማለቱ ለራሱም እንኳ የሰለቸው አይመስልም፣ መቼ እንደሚያቆምም እግዚአብሄር ይወቅ።
የሌኒን የሙት መንፈስ ስታሊንን ረጅም ርቅት እንዳልወሰደው ሁሉ፣ የመለስም ሞት ኢህአዴግን ረጅም ርቀት አይወስደውም፤ ከተወሰኑ አመታት በሁዋላ መለስም ይረሳል( እስካሁንም ካልተረሳ ነው)። በመለስ መረሳት ጭንቀት ውስጥ የሚገባው ኢህአዴግ ምናልባትም ስታሊን ተቃዋሚዎቹን ለማጥፋት በሄደበት መንገድ ሊሄድ ይችላል፣ አዝማሚያውም ወደዛው ነው።
በመጨረሻም፣ የኢህአዴግ የ 5 አመታት የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን ፖሊስ ከስታሊን የመጀመሪያዎቹ የ5 አመታት የእድገት ፖሊሲ ጋር በብዙ ነገሮች ይመሳሰላል፤ የመመሳሰሉ ብዛት ደግሞ አወዳደቁንም እንዳይ ረድቶኛል፣ እግዜር ቢፈቅድ አንድ ቀን እመለስበታለሁ።

እስቲ እረጋ ብለን ደግሞ እንነጋገር… “ጭርቁምፈምቶታ ኡመታ ኢትዮጵያ” (ከአቤ ቶክቻው)

0
0

jawar
እስቲ እረጋ ብለን ደግሞ እንነጋገር… ”ጭርቁምፈምቶታ ኡመታ ኢትዮጵያ”

ወንድማችን

ጃዋር መሀመድ እኔን ጨምሮ በርካቶች የሚያደንቁት ወጣት ነው፡፡ ሀሳቦቹ አንጀት ላይ ጠብ የሚሉ ገዢ ሀሳቦች ናቸው፡፡ የሚገዙት ታድያ እንደ ገዢው ፓርቲ አስገድደው አይደለም፡፡ ጃዋር ወደው ፈቅደው የሚገዙላቸው

ሀሳቦች ባለቤት ነው፡፡ እኔ ከጃዋር ሀሳቦች ጋር በቅጡ የተዋወቅሁት የቱኒዚያ አብዮት የተቀሰቀሰ ሰሞን ነበር፡፡ ስለ ቱኒዚያ እና ግብፅ አብዮቶች መንስኤ፤ አስፈላጊነታቸው እና ውጤታማነታቸው ጃዋር ከፃፈው በተሸለ ገብቶኝ እና ተመችቶኝ ያነበብኩት መኖሩን እንጃ…

ከዛም በኋላ ጃዋር የሚሰጣቸውን ትንታኔዎች ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ እሰማለሁ፡፡ ሰምቼም እስማማለሁ፡፡ ምን መስማማት ብቻ፤ የሆነ ቀን ጃዋር ምርጫ
ቢወዳደር ይምራኝ ብዬ የምመርጠው ሁሉ እስኪሆን ድረስ አክባሪው ሆኛለሁ…!

ከእለታት በአንዱ ቀን እኛ “በፌስ ቡክ አስተዳደር የኢህአዴግ ዋና የስራ ሂደት ባለቤት” የምንለው ዳንኤል በርሄ በአሁኑ ሰዓት በአልጀዚራ የሚተላለፈውን እባክችሁ ቅዱልኝ ብሎ ተማፅኖ ሲያሰማ “እኔ እንደ እናንተ አይደለሁም” በሚል “ሙድ” ልቀዳለት ወደ አልጀዚራ ጎራ አልኩ… የማከብረው ጃዋር በአልጀዚራ ስቱዲዮ ጉብ ብሏል፡፡ እውነቱን ለመናገር ጃዋርን ባየሁት ጊዜ ኖራ… ብዬ አባቴ የሚያከብረው ሰው ሲመጣ እንደሚያደርገው በአክብሮት ከመቀመጫዬ ተነስቻለሁ…

እንግዲህ ይሄኔ ነው፡፡ ኦቦ ጃዋር እስከዛሬ ሲናገር ይስማሙኝ ከነበሩት በተቃራኒው የማይስማማኝን ነገር ሲናገር የሰማሁት፡፡ የተረገመቺቱ የአልጀዚራ ጋዜጠኛ አንድ የተረገመ ጥያቄ ጠየቀችው… ኦሮሞ ፈርስት ወይስ ኢትዮጵያ ፈርስት… አለችው… እርሱም ኦሮሞ ፈርስት አለ፡፡ ጃዋር ይሄንን የማለት መብት አለው፡፡ ኢትዮጵያዊነት በግድ የተጫነብኝ ነው ሲልም ተናገረ፡፡ ይሄንንም የማለት መብት አለው፡፡ እኔ ደግሞ መብቴን በመጠቀም፤ አንድ ውሳኔ ላይ ደረስኩ… ጃዋር ምርጫ ቢወዳደር አልመርጠውም፡፡ እንኳንም ቀድሞ ተወዳድሮ ጉድ አላደረገኝ አልኩ… (አልጀዚራንም እረገምኩ እንድንከፋፈል አድርጎናልና፤ ዳንኤል በርሄንም ረገምኩ አልጀዚራን እንድመለከት አድርጎኛልና፤ ጃዋርንም አሽሟጠጥኩ ሀሳቡ አልረባልኝምና!)

ጃዋርን ያሰብኩት ለክልሉ አስተዳዳሪነት ሳይሆን ለሀገሪቷ መሪነት ነበር፡፡ ታድያ ለቤተዘመዶቹ ቅድሚያውን የሚሰጥ መሪ አማራሪ እንጂ ምኑን መሪ ሆነው… ለመሆኑስ የብሄርተኝነት ጥጉ የት ድረስ ነው…. ስልም… ሽሮሜዳ ደረስኩ… እናም የመጣው ምጣ ብዬ አሽሟጠጥኩ!

ይለይልህ ብለው የጃዋርን ሌላ ንግግር ሰዎች ካለበት ፈልፍለው አሳዩኝ… ይሄኛው ደግሞ የባሰበት ነው፡፡ ጃዋር ባደገበት አካባቢ ዘጠና ዘጠኝ በመቶው ሙስሊም ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ሙስሊም ያልሆነ ኦሮሞ ቀና ቢል “በሜንጫ ነው አንገቱን የምንለው” አለን፡፡ ልብ አድርጉልኝ ጃዋር “ኦሮሞ ፈርስት” ብሎ አላቆመም ደግሞ “ሙስሊም ኦሮሞ ፈርስት” አለን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ እኔ እና ሌላው ዋቄፈታ ኦሮሞ ጃዋርን ይምራን ብለን መርጠነው ቢሆን ኖሮ እጣ ፈንታችን ቀና ስንል ሜንጫ ነበር ማለት ነው፡፡

አንድ ጊዜ ቤተሰባዊ ዝምድናውን ያስቀደመ ሰው ማብቂያ አይኖረውም፡፡ የምለው ለዚህ ነው፡፡ በደሉ የሁላችንም ነውና በደል የሌለባት ሀገር እንድትኖረን ሁላችን በአንድ ላይ ብንተባበር የተሸለ ነው የምለውም ለዚህ ነው…! “ሁላችንም ነፃ ካልወጣን አንዳችንም ነጻ አይደለንም” የሚለው የኦባንግ ሜቶ ንግግር የሚማርከኝ ለዚህ ነው፡፡

በኦነግ ትግል ምስረታ ወቅት ከመስራቾች አንዱ የነበሩት ሀጂ ሁሴን ሱራ፤ ትግላችንን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲሆን፤ “ጭርቁምፈምቶታ ኡመታ ኢትዮጵያ” (የተጨቆኑ የኢትዮጵያ ህዝቦች) እንበለው እና በጋራ በደልን እንታገል ሲሉ ቀደምት የኦሮሞ ታጋዮችን ለማሳመን አጥብቀው ሲከራከሩ እንደነበር ስለኦነግ ሚጢጢ እውቀት ያለው ሁሉ የሚያስታውሰው ነው፡፡ እናም ይህ ሀሳብ በኦሮሞ ዘንድ አዲስ ሀሳብ አይደለም፡፡

በአሁኑ ጊዜ ያሉ ኦሮሞ ታጋዮች የቀድሞ ንጉሳ ንጉሶችን በመኮነን በኦሮሞ ህዝብ ላይ የደረሰውን በደል ሲዘረዝሩ ይሰማሉ፡፡ እውነቱን ለመናገር በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የአማራም የኦሮሞም የጉራጌም የትግሬም ገበሬ ደልቶት የሚያውቅበት ጊዜ አላነበብኩም፡፡ ከንጉሳውን ቤተዘመዶች ውጪ አብዛኛው ህዝብ ጭቁን ነበር፡፡ ለዚህም ነበር በእነ ሃጂ ሁሴን ሱራ ዘንድ “ጭርቁምፈምቶታ ኡመታ ኢትዮጵያ” የሚለው ሃሳብ የተወለደው፡፡

በአፄዎቹ ዘመን የተበደለው እና የተጨቆነው ኦሮሞው ብቻ እንኳ ቢሆን፤ እንደ ጃዋር የመሰሉት ምሁራን ያለፈውን ታሪክ ለታሪክ ፀሀፊዎች ትተው እነርሱ በሽሙጡም ሳይደነግጡ በሙገሳውም ሳኩራሩ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ የሚበጀውን የመቻቻል መንገድ በመቀየስ ታሪክ ቢሰሩ መታደል ነበር፡፡

ዛሬ በወዳጃችን ጃዋር ድረ ገፅ ላይ “በዲያስፖራ ያለውን የወቅቱን የኢትዮጵያ ፖለቲካ በማስመልከት በአውሮፓ የኦሮሞ ወጣቶችና የሴቶች ማህበራት የጋራ መግለጫ” የሚል ፅሁፍ ተመለከትኩ፡፡

በተለይ ደግሞ ይቺ አንቀፅ ቀልቤን ሳበችው፡፡

“እኛ በአውሮፓ የኦሮሞ ወጣቶችና የሴቶች ማህበራት በአሁኑ ወቅት በአልጀዚራ ላይ ቅድሚያ ኦሮሞ ነኝ በማለቱ ብቻ በፖለቲካ ምሁሩ ጀዋር ላይ የተከፈተውን የሀሰት ዘመቻ ማውገዝ ብቻ ሳይሆን ለመከላከልም በመገደዳችን ይህ አይነቱ አጼያዊ ዘመቻ እስኪያቆም ድረስ ከቅርብ ጊዜ በፊት ከሰላም ወዳድ የአንድነት ሀይሎች ጋር የጀመርነውን የቅርርብ ዲያሎጎችና የሀሳብ ልውውጦች በይበልጥ ልንገመግምው ወስነናል። ”

እኔ ጃዋርን ብሆን ኖሮ ይህንን ፅሁፍ በራሴ ድረ ገፅ ላይ አላትምም ነበር፡፡ ምክንያቱም ጃዋር የዚህ ማህበር አባል አይደለም እርሱ የሚኖረው አሜሪካ ነው፤ መግለጫው ደግሞ “በአውሮፓ የኦሮሞ ወጣቶችና የሴቶች ማህበራት“ ያወጡት ነው፡፡ የአደባባይ ሰው ሲሆኑ ትችትም ሙገሳም እንደሚመጣ የታወቀ ነው፡፡ ለሚሰነዘርብን ትችት በሙሉ ዘመዶቻችን መግለጫ እንዲያወጡልን ከመጋበዝ ራሳችን ነጥብ በነጥብ ለመመለስ መሞከር የተሸለ ነው፡፡

ማህበሩም ቢሆን ጃዋር ላይ የሚሰነዘር ትችት ኦሮሞ ላይ የተሰነዘረ አድርጎ በማየት “…ከሰላም ወዳድ የአንድነት ሀይሎች ጋር የጀመርነውን የቅርርብ ዲያሎጎችና የሀሳብ ልውውጦች በይበልጥ ልንገመግምው ወስነናል።” የሚል ትልቅ ፖለቲካዊ አንድምታ ያለው መግለጫ ማውጣቱ አስገራሚ ነው፡፡ ትልቅ ሀገራዊ ራዕይን አንድ ሰው ተነካ ብሎ እንደውም አንጫወትም ብሎ ለማቋረት መዳዳት ለማን እንደሚጠቅም ፈጣሪ ይወቅ…!

ጃዋር ወደፊትም ቢሆን ጥሩ ሲሰራ መመስገኑ መጥፎ ሲሰራ መተቸቱ የማይቀር ነው፡፡ ለትችቱ ምለሽ ለሙገሳውም ምስጋና መስጠት ያለበት ጃዋር እንጂ ዘመዶቹ አይደለንም፡፡

በአሁኑ ወቅት ትልቁ አሳሳቢ ችግር “ጭርቁምፈምቶታ ኡመታ ኢትዮጵያ” (የተጨቆኑ የኢትዮጵያ ህዝቦች) አለመተባበራቸው ነው፡፡ እኔ ብቻ ነኝ የተበደልኩት ብሎ የራስን ችግር ብቻ አግዝፎ ማየት እና ማሳየት የትም አያደርስም፡፡ (ብዬ አስባለሁ… ማሰብ መብቴ ነው! (በሌላ ቅንፍ ደግነቱ ይሄንን ችግር ሀገር ውስጥ ብብዛት አላየሁትም…))

ጎበዝ ለማንኛውም “በስጫው”ን ትተን እስቲ ረጋ ብለን እንነጋገር…!

“በስጫ”… ማለት የአራዳ ብሄረሰብ ቋንቋ ሲሆን ትርጓሜውም ብስጭት ማለት ነው፡፡

ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 53 – PDF

በሙስና የተጠረጠሩት የደብረ ጽጌ ቅ/ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሐፊ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ

0
0

ሐራ ተዋሕዶ ብሎግ እንደዘገበው፦

  • በተጭበረበረ ውል ደብሩን ከ3 ሚልዮን ብር በላይ በማሳጣትና ሰነድ በማሸሽ ይጠየቃሉ
  • ከጥቂት የሙዳይ ምጽዋት ገቢ ምርመራ ብቻ ከ2 ሚልዮን ብር በላይ ጉድለት ተገኝቷል
  • የአብዛኛዎቹ የደብሩ ሕንጻ ሱቆች የኪራይ ውል በትክክለኛ ሰነድ የተፈጸመ አይደለም
  • ለማተሚያ ቤት አገልግሎት በተከራየው ክፍል በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የማይታወቅ ሞዴላሞዴል እንደሚታተምበት ተጠቁሟል
  • የፕሮቴስታንት ቤተ ጸሎት እንደሚያዘወትሩ የሚያሳዩ መረጃዎች ወጥተዋ

 

musnaበአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሐፊ ዲያቆን ምሩፅ ትኵዕ በተጭበረበረ ሰነድ ከተፈጸመ የኪራይ ውልእና ለሒሳብ ምርመራ የሚፈለጉ የሙዳይ ምጽዋት የገንዘብ ቆጠራ ቃለ ጉባኤዎችን ከማሸሽ የሙስና ወንጀል ጋራ በተያያዘ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ፡፡

ዋና ጸሐፊው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ባለፈው ሳምንት ዐርብ፣ ሐምሌ ፲፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ረፋድ ላይ በደብሩ ጽ/ቤት ባሉበት ሲኾን ከዋና ጸሐፊው ጋራ በተጭበረበረው የኪራይ ሰነድና ውል ለደብሩ የሚገባውን ክፍያ ሳይፈጽሙ የግል ጥቅማቸውን አካብተዋል የተባሉ ሌሎች ሁለት የሕንጻው የንግድ ቤቶች ተከራዮችም በተመሳሳይ ቀን መያዛቸው ተመልክቷል፡፡

በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ከዋሉበት ቀን ጀምሮ በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙት ዋና ጸሐፊው ዲያቆን ምሩፅ እና ሁለቱ ተጠርጣሪዎች፣ ሐምሌ ፲፮ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት መቅረባቸው ተገልጧል፡፡

ዋና ጸሐፊውና የጥቅም ተባባሪዎቻቸው ፈጽመውታል የተባለውን ማጭበርበርና ምዝበራ  የሚያረጋግጡ የሰነድ ማስረጃዎችና የሰው ምስክሮች እንዳሉት ለችሎቱ የገለጸው ፖሊስ፣ በዋና ጸሐፊው ላይ ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለማሰባሰብና የሰው ምስክሮችን ለማዘጋጀት የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡

ቤተ ክርስቲያን ያቀረበችባቸው ክሥ እንደሌለና ከሣሻቸው እንደማይታወቅ በመጥቀስ የፖሊስን የተጨማሪ ጊዜ ጥያቄ በጠበቃቸው በኩል የተቃወሙት ዲያቆን ምሩፅ÷ የሰባት ቤተሰብ አስተዳዳሪ መኾናቸውን፣ የሚጠየቁትን ማስረጃ ቤተሰቦቻቸው እያቀረቡ መኾኑን፣ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሲውሉ ቢሯቸውን ለመዝጋት እንዳልተፈቀደላቸው እና ሐምሌ ፳፪ ቀን በደብሩ የቅዱስ ዑራኤል ክብረ በዓል በመኾኑ ሥራዎች እንዳይስተጓጎሉ በመጥቀስ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ጉዳያቸውን በውጭ መከታተል እንዲችሉ እንዲፈቀድላቸው አመልክተዋል፡፡ ዮሐንስ አይዳኝ እና ዓለም ፍሥሓ የተባሉት ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በበኩላቸው፣ እነርሱ ውል የያዙበት ሰነድ ከሌሎች ተከራዮች የተለየ እንዳልኾነ በመጥቀስ የዋስ መብታቸው እንዲከበር ጠይቀዋል፡፡

የደብሩን ሕንጻ አራት የንግድ ሱቆች በተጭበረበረ ሰነድ በተፈጸመ የኪራይ ውል በመያዝ ሕገ ወጥ ጥቅም ሲያካብቱ ቆይተዋል ከተባሉት ሁለት ተጠርጣሪዎች ተፈላጊውን ማስረጃ መሰብሰቡን የገለጸው ፖሊስ÷ ተጠርጣሪዎቹ ለምርመራ ሥራው ጠቃሚ ማስረጃዎችን በመስጠት አደርገውታል ባለው መተባበር በዋስ ተለቀው በውጭ ኾነው ጉዳያቸውን መከታተላቸውን እንደማይቃወም፣ ዋና ጸሐፊው ዲያቆን ምሩፅ ግን የደብሩ ጽ/ቤት ሓላፊ በመኾናቸው በተለይ ከሒሳብ ምርመራ እንዳሸሿቸው የሚገመቱት የሙዳይ ምጽዋት ገንዘብ ቆጠራ ቃለ ጉባኤዎችእስኪገኙ ድረስ ‹‹ማስረጃ ያጠፋሉ፤ ምስክር ያባብላሉ›› በሚል የዋስትና ጥያቄያቸውን ተቃውሟል፡፡

ዮሐንስ አይዳኝና ዓለም ፍሥሓ የተባሉት ተከራዮች በብር 50 ሺሕ ዋስ እንዲለቀቁ ያዘዘው ፍ/ቤቱ፣ የዲያቆን ምሩፅን የዋስትና ማመልከቻ ውድቅ በማድረግና የፖሊስን የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጥያቄ በመቀበል ተጠርጣሪው ለሐምሌ ፴ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም እንዲቀርቡ ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል፡፡

በቀደመው ዘገባችን እንዳስታውቅነው÷ ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት እና ከመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የተውጣጡ ልኡካንበደብሩ የፋይናንስ እንቅስቃሴና አሠራር ላይ ምርመራ እያካሄዱ ባሉበት ኹኔታ የደብሩ ዋና ጸሐፊ ዲያቆን ምሩፅ ትኵዕ በቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ ከሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ለፖሊስ በቀረበ ጥያቄ እንደኾነ ሲዘገብ፣ ይህም ዲያቆን ምሩፅ በጋብቻ ሰበብ ከአገር ለመውጣት እየተሰናዱ ለመኾናቸው ከመሰማቱ ጋራ ሳይያዝ እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡

St Urael Church YeHulegeb Agelgelot Hintsa

የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ሁለገብ ሕንጸ

ሐራዊ ምንጮች ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ የደብሩ አካላት ለአብነት ካቀረቧቸው ማስረጃዎች እንደተረዱት፣ ዲያቆን ምሩፅ ከሁለቱ ተጠርጣሪ ተከራዮች ጋራ የተጭበረበረ የኪራይ ውል የፈጸሙት ነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም እና መስከረም ፲፭ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ነበር፡፡ በቤት ቁጥር 43 የተለየው የደብሩ ሁለገብ ሕንጻ ክፍል ለአኒሜሽንና ግራፊክስ ቴክኖሎጂ ማሠልጠኛ፣ በቤት ቁጥር 27 እና ቨረንዳ ቁጥር 4 የተለዩት የሕንጻው ክፍሎች ደግሞ ለዓለም ጠቅላላ ፋይበር ግላስ ሓላ/የተ/የግ/ማ ተከራይተዋል፡፡

ለአራት ዓመት የሚቆየው የኪራይ ውል የተፈጸመበት ሰነድ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ በኪራይ ውል አሰጣጥ/ውል ማራዘሚያ ከሚጠቀምበት ሕጋዊ ሰነድ የተለየና የውል መለያ ቁጥር የሌለው ነው፡፡ በሰነዱ ላይ የሚታየው ክብ ማኅተም የደብሩ ቢኾንም ቲተሩና ፊርማው ግን ውሉ ከመፈጸሙ በፊት ከአስተዳዳሪነት ሓላፊነታቸው የተነሡትና ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የደብሩ አለቃ ነው፡፡

ኹኔታው የበለጠ ሊከፋ÷ እኒህ ሁለት ተከራዮች የደብሩ ሰበካ ጉባኤ የአካባቢውን የኪራይ ዋጋ ባማከለ አኳኋን በአዲስ መልክ ባስጠናው የኪራይ ተመንና አዲስ የውል ሰነድ መሠረት ውል እንዲያድሱ፣ በዚህ አግባብ የማይዋዋሉ ከኾነ ደግሞ ያለባቸውን ውዝፍ ዕዳ አጠናቅቀው የንግድ ቤቱን ለደብሩ እንዲያስረክቡ በወቅቱ አስተዳዳሪ በቆሞስ ፀባቴ መሓሪ ሀብቴ መጋቢት ፴ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ደርሷቸው የነበረ መኾኑ ነው፡፡ ‹‹ማስጠንቀቂያ በክቡር ቆሞስ ፀባቴ መሓሪ ሀብቴ ውል ደግሞ በአባ ተስፋ ማርያም መከናወኑ ግልጽ ጥፋት መኖሩን ያሳያል፤›› ይላል የኪራይ ውሎቹን አፈጻጸም ስሕተት ያጠናው የሰበካ ጉባኤው መንፈሳዊ አስተዳደር ያቋቋመው ኮሚቴ ያቀረበው ሪፖርት፡፡

ከተከራዮች ጋራ የጥቅም ተካፋይ በመኾን የተፈጸሙት የኪራይ ውሎች በሐሰተኛ ሰነድ መስጠታቸው የተረጋገጠባቸው ዋና ጸሐፊውና የቀድሞው የደብሩ ዋና ተቆጣጣሪ በሰበካ ጉባኤው ፊት ጥፋተኝነታቸውን አምነው ይቅርታ መጠየቃቸው በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የይቅርታ ቤት ብትኾንም፡- የደብሩን ንብረትና የኪራይ ውሎች እየተከታተሉ ጥቅሙን ማስጠበቅ የሚገባቸው ዋናው ተቆጣጣሪ የተጭበረበረው ውል አዘጋጅና ምስክር በመኾን በፈጸሙት ጥፋት የአንድ ወር ደመወዛቸውን እንዲቀጡ፣ ሀ/ስብከቱም በዋና ጸሐፊው እና ዋና ተቆጣጣሪው ላይ ሕጋዊ ርምጃ እንዲወስድ፣ ተከራዮቹም በ30 ቀን ገደብ ውላቸው ተቋርጦና የሚፈለግባቸውን ውዝፍ ዕዳ ከፍለው ሱቆቹን እንዲያስረክቡት ጥር ፳፫ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም የደብሩ የሕግ ባለሞያ ባለበት በድጋሚ ተወስኖ እንደነበር ሪፖርቱ ያትታል፡፡

ይኹንና ዋናው ተቆጣጣሪ የተወሰነባቸው ቅጣት ሳይፈጸም ከነበደላቸው ወደ ሌላ ደብር በተመሳሳይ ሓላፊነት መዛወራቸውን፣ ተከራዮቹም አለመልቀቃቸውን ሪፖርቱ ገልጾ በዚህም ደብሩ በአዲስ መልክ ባስጠናው የኪራይ ተመን መሠረት ቢያንስ ከሚያዝያ ፳፻፬ ዓ.ም ጀምሮ ማግኘት የሚገባውን ከብር 2,637,603.30 /ብር ሁለት ሚልዮን ስድስት መቶ ሠላሳ ሰባት ሺሕ ስድስት መቶ ሦስት ከሠላሳ ሳንቲም/ ማጣቱን አስታውቋል፡፡

የቀድሞው የምሥራቅ አዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት በፋይናንስ አሠራርና በሕንጻው ኪራይ ዙሪያ ተፈጸመ የተባለውን ምዝበራ አጣርተው የሚያቀርቡ ልኡካንን ከአንድም ሁለት ጊዜ ልኮ የነበረ ቢኾንም ለማጣራቱ ሥራ ግንባር ቀደም ተባባሪ መኾን የነበረባቸው ዋና ጸሐፊው ዲያቆን ምሩፅ የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ ለማጣራቱ ሥራ ተባባሪ አልኾኑም፡፡ ዋና ጸሐፊው ለተመደቡት አጣሪዎች እንዲያቀርቡ ከተፈለጉት ማስረጃዎች መካከል፣ ከሐምሌ ፳፻፫ ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ የሚገኘው ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የያዛቸው የ22 ወራት 44 የሙዳይ ምጽዋት ቆጠራ ቃለ ጉባኤዎች/ቬርቫሎች/ ይገኙበታል፡፡

ዲያቆን ምሩፅ በሚያቀርቡት ‹‹ሕጋዊ እና በቂ ያልኾነ›› ምክንያት መጥፋታቸው ተገለጹት በእኒህ 44 የገንዘብ ቆጠራ ቃለ ጉባኤዎች መሠረት፣ ደብሩ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ  በመባዕ፣ ስእለት፣ በወርቅና በውጭ ምንዛሪ የተሰበሰበውን ሳይጨምር ከብር 12 ሚልዮን ብር ያላነሰ የሙዳይ ምጽዋት ገቢ ሊኖረው ይገባ ነበር፡፡ ለሐራዊ ምንጮች የደረሱት መረጃዎች ግን ደብሩ በአሁኑ ወቅት በባንክ ያለው ተቀማጭከብር 5 ሚልዮን የበለ እንዳልኾነ የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ከዚሁ ብር 5 ሚልዮን ውስጥም 3.5 ሚልዮን ብሩ ካለፈው የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር የዞረ ነው፡፡ ይህም በወቅቱ የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ወደ ደብሩ ካዝና የገባው የሙዳይ ምጽዋት ገቢ ከ1.5 ሚልዮን ያለፈ እንዳልኾነ ያስረዳል፡፡

የሙዳይ ምጽዋቱ ገቢ ከሕንጻው ኪራይ እና ሌሎች የደብሩ የገቢ ምንጮች ጋራ ተደማምሮ በአጥቢያው ቋት መኖር ከነበረበት ሒሳብ ጋራ ሲነጻጸር በተጨባጭ ያለው መጠን በማነሱ የተደናገጡ የሰበካ ጉባኤ አባላት ተቆርቋሪ ምእመናንን በማስተባበር ለሀ/ስብከቱ አቤቱታቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል፡፡ አቤቱታቸው በብዙ ጥረት ሠምሮ ከሀ/ስብከቱ እና ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ተውጣጥቶ ወደ ደብሩ የተላከው መርማሪ ልኡክ የማጣራቱን ሥራ እየሠራ ይገኛል፤ ‹‹ያለቃለ ጉባኤ አንመረመርም›› በሚል ለተጠያቂነት ያስቸገሩት ዋና ጸሐፊው ዲያቆን ምሩፅም በሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጥያቄ በሕግ ጥላ ሥር ውለዋል፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት የሒሳብ ምርመራ ሥራቸውን የጀመሩት የሀ/ስብከቱ ልኡካን እስከ አሁን ባደረጉት ማጣራት ከሚፈለጉት 42 የገንዘብ ቆጠራ ቃለ ጉባኤዎች 14ቱን አግኝተዋል፤ ከዚህም ተቀባይነት ያገኙት ስድስት ቃለ ጉባኤዎች ብቻ ሲኾኑ ሌሎቹ የተጭበረበሩና በማስመሰል የተዘጋጁ መኾናቸው ታውቋል፤ መርማሪ ልኡኩ በስድስቱ ቃለ ጉባኤዎች ላይ ብቻ ተመሥርቶ ባደረገው ማጣራት ከብር 2.7 ሚልዮን በላይ የገቢ ልዩነት/ጉድለት እንደተመዘገበ መገለጹ የሰበካ ጉባኤውን አባላት አቤቱታ የሚያጠናክር እንደኾነ ተመልክቷል፡፡ የሙዳይ ምጽዋት ገንዘብ ከተቆጠረና አጠቃላይ ገቢው ከታወቀ በኋላ ወደ ሞዴል ፷፬ እንዲሰፍር ተደርጎ በገንዘብ ያዡ አማካይነት በሞዴል ፮  ተጠይቆ ወደ ባንክ ገቢ እንደሚደረግ ይታወቃል፡፡

the alleged underground printing house

ሞዴላሞዴሎች በድብቅ ይታተሙበታል የሚባለው ማተሚያ ቤት

የደብሩ ሰበካ አስተዳደር ጉባኤ የተጭበረበረውን የኪራይ ውል እንዲያጣራ ያቋቋመው ኮሚቴ ከዘረዘራቸው የውል አሰጣጥ ችግሮች መካከል÷የውል ጊዜያቸው አልቆ በአዲሱ ውል ያልገቡ፣ ፈጽሞ ውል የሌላቸውና ኪራይ የማይከፍሉ፣ በውላቸው የጊዜ ገደብ ያልተቀመጠላቸውና ያልታደሰላቸው፣ ውል ኖሯቸው ክፍያ የማይፈጽሙ /ውዝፍ ያለባቸው/ እንዳሉ መጠቀሳቸው በመርማሪ ልኡኩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች የዋስትና መብታቸው ለማስጠበቅ ለፍ/ቤቱ ሲናገሩ እንደተደመጡት፣ ከ40 ያላነሱት የሁለገብ ሕንጻው ክፍሎች የኪራይ ውል ሰነዶች እነርሱ ውል ከያዙበት ሰነድ ጋራ ተመሳሳይ ስለመኾኑ የተናገሩት ቃል ቸል ሊባል አይገባም፡፡

ከሁለቱ ተጠርጣሪ ተከራዮች አንዱ ለማተሚያ ቤት አገልግሎት በተከራዩት ክፍል፣ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የቤተ ክርስቲያንን ንብረትና ገንዘብ እንቅስቃሴ የሚቆጣጠርባቸው ሞዴላሞዴሎች በድብቅ እንደሚታተሙባቸው በስፋት እየተወራ ነው፡፡ የምስጢር ኅትመት የኾኑት እኒህ ሞዴላሞዴሎች ግን በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት ቁጥጥር በትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት ብቻ መታተም ያለባቸው ናቸው፡፡ እንደ አንዳንድ ምንጮች ጥቆማ ከኾነ ይህ ክፍል ‹‹ሞዴል ፴ እንደማያውቀው››ና ጨርሶ ኪራይ እንደማይከፈልበት መነገሩ ያሳስባል፡፡ የሀ/ስብከቱ ልኡክ የሒሳብ ምርመራ ሥራ ይህን ጉዳይ በሚገባ እንደሚዳስስ ይጠበቃል፡፡

በአጠቃላይ በገቢ አቅሙና ደረጃው ከሀ/ስብከቱ ዐበይት አድባራት በቀዳሚነት በሚጠቀሰው በደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የፋይናንስ እንቅስቃሴ ላይ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የወሰደው ርምጃ በሀ/ስብከቱና በሌሎች አድባራት ለተንሰራፉት ሙሰኞች/መዝባሪዎች መልእክት የሚያስተላልፍና እንደ አገባቡም የሕግ ተጠያቂነቱ መቀጠል ያለበት ነው፡፡

በሌላ በኩል ከሚያዝያ ፳፻፫ ዓ.ም ጀምሮ የደብሩ ዋና ጸሐፊ በመኾን ተዛውረው የመጡት ዲያቆን ምሩፅ በአዋሬ አካባቢ የሚገኝና ‹‹ብርሃነ ኢትዮጵያ›› ተብሎ የሚጠራ የፕሮቴስታንት ቤተ ጸሎት እንደሚያዘወትሩ ለሐራዊ ምንጮች ተያይዞ ከደረሰው የቪሲዲ ማስረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በቪሲዲው ‹ዲያቆን› ምሩፅ በቤተ ጸሎቱ ከተሰበሰቡት ሰዎች ጋራ ቆመው ‹ሲዘምሩ› ይታያል – ከቤተ ክርስቲያን እየጎረሱ ወደ መናፍቃን መዋጥ፡፡ የዲያቆን ምሩፅን በለምድ የተሸፈነ ፕሮቴስታንታዊነት የሚያጋልጠው ቪሲዲ የሚሰጠን ፍንጭ አዘውትረን እንደምንለው በቤተ ክህነታችን ውስጥ ሙስናና ኑፋቄ ያላቸውን ትስስር ነው፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ በወባ ከሚሞተው ይልቅ በፖለቲካ ጦስ እና ችግር የሚጎዳው በቁጥር ይልቃል›› ተመስገን ደሳለኝ – [ጋዜጠኛ]

0
0

ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት? በተሰኘውና በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ታትሞ በገበያ ላይ በዋለው መፅሀፍ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ  የሰጠው ቃለ – ምልልስ የሚከተለውን ይመስላል፡፡ ዘ-ሐበሻ ድረገጽ ለግንዛቤ በሚል ለአንባቢዎቹ እንደወረደ አቅርቦታል

 

 

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

‹‹ተመስገን ደሳለኝ ጋዜጠኛ ሳይሆን የፀረ-ኢሕአዴግ ፖለቲካ አቀንቃኝ ነው›› ሲሉ ጋዜጠኛነቱ ላይ ጥያቄ የሚያቀርቡ ወገኖች የመኖራቸውን ያህል ከብዙ ፓርቲዎች በተሻለ ገዢው ፓርቲን በብዕሩ የታገለ፣ ጋዜጣ አንባቢው ኅብረተሰብ ከፖለቲካዊ ፍርሃት እንዲላቀቅ በጽናት የጣረ፣ የቁርጥ ቀን ጋዜጠኛ መሆኑን ምስክርነት የሚሰጡለትም አሉ። አራት ዓመት ገበያ ላይ በቆየችው ፍትሕ ጋዜጣ፣ ታይተው በጠፉት አዲስ ታይምስ መጽሔትና ልዕልና ጋዜጣ ላይ ባሰፈራቸው መጣጥፎቹ የመነጋገሪያ ርዕስ የነበረው ተመስገን ለእሱ በተሰጡ ቀጣይዎቹ ገጾች ላይ ከእዚህ መጽሐፍ አዘጋጆች የቀረቡለትን ሞጋች ጥያቄዎች በመመለስ የ‹‹ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት?›› አካል ሆኗል።

 

በልጅነትህ ምን መሆን ትፈልጋለህ ስትባል ምላሽህ ምን ነበር?

ያደግኩት ፊት በር አካባቢ ነው። ይህ ሰፈር ደግሞ በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ በርካታ የደሀ ሰፈሮች አንደኛው ነው። ያደግነውም ሆነ የምንጫወተው በቡድን ነበር። ልጅ ሆኜ ሁሌም ማታ ማታ አባቴ ጋዜጣ ገዝቶ ስለሚመጣ ቡና እየተፈላ ጋዜጣ እንዳነብላቸው ያበረታታኝ ነበር። ሁለተኛ እና ሦስተኛ ክፍል እያለሁ ለቤተሰቡ ጋዜጣ ማንበብ የዘወትር የማታ ተግባሬ ነበር። ታላቅ ወንድሜ ቢኖርም አባቴ የሚያስነብበኝ እኔን ነበር። ትምህርት ቤትም ክፍል ውስጥ አነብ ነበር።

አባትህ ማንበብ አይችሉም?

ይችላል። እስከ ዘጠነኛ ክፍል ተምሯል። በኃይለ ሥላሴ ጊዜ እስከ ዘጠነኛ ክፍል መማር ከአሁን ጋር ሲነፃፀር ያው እንደምታውቁት ነው። [ሳቅ]

ጋዜጣ ማንበቤ፣ ጋዜጠኛ እንድሆን አድርጎኛል እያልክ ነው?

አነብ ነበር እንጂ ጋዜጠኛ እሆናለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር። አድጌ መሆን እፈልግ የነበረው መከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ገብቼ እስከ ጄኔራል ማዕረግ መድረስ ነበር።

የሆንከው የማትፈልገውን ነው ማለት ነው?

ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው ጋዜጠኛ በመሆኔ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ። ሁለትም፣ ሦስትም ሰዎች ቢሆኑ እኔ በምሠራው ሥራ ደስተኛ በመሆናቸው ደስ ይለኛል። በልጅነታቸው የተመኙትን ሲያድጉ የሚሆኑ ጥቂቶች ናቸው። የምንኖረው ደግሞ የተመኘነውን ሳይሆን የተጻፈልንን ነው። እናንተም ቢሆን ጋዜጠኛ እንሆናለን ብላችሁ ተመኝታችሁ እንደማታውቁ እገምታለሁ። [ጠያቂዎቹ የፈለጉትን እንደሆኑ ተናግረዋል።]

በልጅነትህ ቶሎ ደምህ የሚሞቅ፣ ከኪስህ ጩቤ የማይጠፋ የፍልውሃ እና የአራት ኪሎ የታወቅክ ተደባዳቢ መሆንህን ሰምተናል። ትክክል ነን?

[በጣም ሳቀ] አ… ማለት… እእእ… እንትን ነው… ወሬው ትንሽ ግነት አለው ብዬ አስባለሁ። እንደ ማንኛውም ልጅ ሰፈር ውስጥ ስትውል ‹‹ሰፈሬን አላስደፍርም›› ከሚል እሳቤ ፀብ አይጠፋም። በእኛ ጊዜ ደግሞ የቡድን ፀብ ፋሽን ነበር። ጩቤ ይዤ የምዞር ተደባዳቢ ግን አልነበርኩም።

ለተለያዩ መገናኛ ብዙኃን በሰጠሀቸው ቃለ-ምልልሶች ላይ እንደተናገርከው ወደ ጋዜጠኝነቱ ያመጣህ የሙያው ፍላጎት ሳይሆን ከ1997 ዓ.ም. በኋላ መንግሥትን የሚሞግቱ ጠንካራ ጋዜጦች አለመኖር አስቆጭቶህ እንደሆነ ገልጸሀል። አመጣጥህ መንግሥትን ለመቃወም ወይም ተቺ ፖለቲካዊ ሀሳቦችን ለማንሸራሸር ብቻ አይመስልም?

አይመስልም ሳይሆን ነውም፤ ይህ ግምት ሳይሆን እውነታ ነው። ቅድም እንዳልኩት ጋዜጠኛ የሆንኩት ተጽፎልኝ አይደለም። የጋዜጠኝነት ስሜቱም እንደነበረኝ እርግጠኛ አይደለሁም። ያመጣኝ ጎርፉ ነው። እንደ ማንኛውም ሰው አገሬን እወዳለሁ። በማንኛውም ቀዳዳ፣ በምችለው መልኩ ለአገሬ የሆነ ነገር ማበርከትን አስብ ነበር። 1997 ዓ.ም. የተፈጠረው ማዕበል፣ ያመጣበት ጎርፍ ያደናገጠው ኢሕአዴግ በርካታ ጋዜጦችን ከጥቅም ውጪ አደረጋቸው። ከዚያ በኋላ የተፈጠሩት ጥቂት ጋዜጦች ደጋግሜ እንደምለው አቅሙ ቢኖራቸውም ከኢሕአዴግ ባሕሪ አኳያ ‹‹ዶማን ዶማ፣ አካፋን አካፋ›› ከማለት ይልቅ ቅኔ ለበስ ያደርጉት ነበር። ስለዚህም ይህን የፍርሃት ቆፈን ለመግፈፍ መሞከር አለብኝ በሚል እንጂ ጋዜጠኛ ለመሆን ስወድቅ ስነሣ ቆይቼ አልመጣሁም። የ97 ጎርፍ ባይመጣ ኖሮ እሆን የነበረው ጋዜጠኛ ሳይሆን ኦዲተር ነበር፤ ከ1999 ዓ.ም. ጀምሮ በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ የውጪ ኦዲተር ነበርኩ።

ፍትሕ ምን ዓይነት ጋዜጣ ነበረች?

የፖለቲካ ጋዜጣ!

አንድ ጋዜጣ፣ ጋዜጣ ለመባል ሊያሟላቸው የሚገባቸው ነገሮች አሉ። ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የዓምድ ስብጥር ነው። በሙሉ ወይም በከፊል ፍትሕ ይህን ይዛ ነበር ብለህ ታስባለህ?

አይ …. እንደሱ ብዬ ላስብ አልችልም። ምክንያቱም የአገራችን ሚዲያ ገና እያደገ ስለሆነ እኛም አንድ ጋዜጣ ሊያሟላ ያስፈልገዋል ወደሚባለው ደረጃ ለመድረስ ሌት ተቀን እየሠራን ባለንበት ሁኔታ ነው ጋዜጣዋ እንድትቆም የተደረገው እንጂ እጅግ በጣም ብዙ እንደሚቀረን እናውቃለን።

በአገራችን ያሉ ጋዜጦች አቋማቸው፣ የገጽ ብዛታቸውና የዓምድ መጠናቸው ቢለያይም የሚይዟቸው ነገሮች አሉ። ለምሣሌ ጤና የአገሪቷ ትልቅ ችግር ነው። በዚያ ዙሪያ የሚደረጉ ወንጀሎች፣ ሙስናዎች፣ በግል ሕክምና ተቋም የሚካሄዱ ሕጋዊ የሚመስሉ ዘረፋዎች… ብቻ ብዙ ናቸው። የምትሠሩት ለሕዝብ እስከሆነ ድረስ በቀጥታ ከመንግሥት ጋር የተገናኘው ፖለቲካ ላይ ከማተኮር ባለፈ ሌሎች ችግሮችን ወደ ማጋለጥ ለምን አታተኩሩም?

ኢትዮጵያ ውስጥ በወባ በሽታ ከሚሞተው ይልቅ በፖለቲካ ጦስና ችግር የሚጎዳው በቁጥር ይልቃል። ለዚህ ነው ከወባው ይልቅ ለፖለቲካው ቅድሚያ የሰጠነው።

[ሳቅ] ፍትሕ ጋዜጣ፣ አዲስ ታይምስ መጽሔት እና ልዕልና ጋዜጣ ላይ ከ12 ሰዎች በላይ የግል ሃሳባቸውን ይገልጹበታል፤ ከድርጅታችሁ ሠራተኞች ብዛት ይልቅ የዓምደኞቻችሁ ቁጥር ይልቃል። ይሄ ደግሞ የጋዜጣውን ኤዲቶርያል ሐሳብ ለማንሸራሸር ዕድል አይፈጥርም። ሁሉም አገሪቷ ላይ ያሉ ችግሮችን አስቦ መጥቶ ይተነፍሳል እንጂ ‹‹ሳምንታዊ አጀንዳችን እነዚህ ናቸው›› ተብለው የመሠራት ዕድላቸው አናሳ ነው።

ይሄ የሚታየው ከጋዜጣው አሠራር አኳያ ነው። ኤዲቶሪያላችን የሚያስቀምጠው ነገር አለ። ሃይማኖትን የተመለከቱ በጣም ስስ የሆኑ ነገሮች አሉ። ከዚያ በተረፈ ጋዜጣው ሙሉ በሙሉ ሐሳብን በነፃነት መግለጽ ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት ስላልን ከርዕስ አንቀጻችን ውጪ ሁላችንም የተለያየ ሐሳብ የምናንፀባርቀው ከዚያ ተነሥተን ነው። ከላይ እንደገለጽኩት ፍትሕ የተመሠረተችው የጋዜጠኝነት ሙያ ባንገበገባቸው ወይም ባቃጠላቸው ሰዎች ሳይሆን ጭራሽ ጋዜጠኛ እንሆናለን ብለው ባላሰቡት ነው።

የሆነ ሆኖ ትልልቅ አገራዊ አጀንዳዎች ሲኖሩን ኤዲቶሪያል ቡድናችን ተነጋግሮ በጋራ የሚሠራበት አጋጣሚ አለ። አዲስ ታይምስ ላይ በ‹‹አባይ ግድብ›› ዙሪያ የሠራነውን መጥቀስ ይቻላል። ልዕልና ላይ ወቅታዊውን የሚዲያ ሁኔታ በተመለከተ ሠርተናል። ፍትሕ ላይም ደጋግመን ኤዲቶሪያላችን ወስኖ የሠራናቸው አጀንዳዎች አሉ። ስለዚህም ከሞላ ጎደል የጋዜጣዋን ኤዲቶሪያል ሐሳብ ማንሸራሸር ችለናል ብለን መናገር እንችላለን። አንዱን ሃይማኖት ከሌላው ሃይማኖት አናጣላም፤ በብሔርም እንደዚሁ ነው። ከእነዚያ ውጪ የሚከለክለን/የማይከለክለን ኤዲቶርያል አቋም አለን ብለን የምንራቀቅበት ሁኔታ የለም። የጋዜጣው ዋነኛ የማዕዘን ድንጋይ ፍርሃትን መግፈፍ ስለሆነ አሁን የምንከተለው ስልት ትክክል ነው ብዬ አስባለሁ።

ይህ ምን ያህል ተሳክቶልናል ብለህ ታስባለህ?

ይሄንንም የምናገረው በግምት ነው እንጂ በዚህ ጉዳይ ላይ የተደረገ ወይም ያካሄድነው ጥናት የለም። ነገር ግን የተሻለ ነገር አምጥተናል ብዬ አስባለሁ። ሌላ ሰው መጥቶ ‹‹ይሄን … ይሄን ፍትሕ የፈጠረችው አይደለምን?›› እስከሚል ድረስ ማለት ነው። የመምህራን ተቃውሞ፣ የፀረ- መጅሊስ እንቅስቃሴ የመሳሰሉት ‹‹ስትነጠቅ እምቢ በል›› የሚለው ፍትሕ የፈጠረችው ለውጥ እና መነቃቃት ነው ብዬ አስባለሁ። በሁለቱም በኩል ፍትሕን እንደሞዴል አንሥተው በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ጽፈው አይተናል።

ስትፅፍ ሐሳብን ገልጸህ መገላገልህን ነው ወይስ የሚያስከትለውን ውጤት (Consequence) ታሰላዋለህ?

ጋዜጠኝነት አርበኝነት አይደለም፤ ጦር ይዘህ ጠላትን ስታይ የምትወረውረውርበት/የምትሰካበት ተግባር አይደለም። ጋዜጠኛ ከሆንክ የምታነሣቸው ትችቶች እውነትን መሠረት ያደረጉ እና ሕዝብ ሊያውቃቸው ይገባል የምትላቸውን ነው። መፍትሄ ማግኘት አለባቸው ያልናቸውን ጉዳዮች እናነሣለን። ገዢው ፓርቲ እየሄደበት ያለውን ስሕተት መጠቆም እና የተሻለ መንገዶችን ማሳየት ላይ አተኩራለሁ። ኢሕአዴግ ብልጥ አምባገነን ነው። የእኛ ጋዜጣ (ፍትሕ) ታተኩር የነበረው የኢሕአዴግን የብልጠት ሴራዎችን ለሕዝብ በማሳየት እና በማጋለጥ ላይ ነው። የእኔም ጽሑፎች የሚቃኙት በዚሁ መልኩ ነው።

‹‹ተቃዋሚ›› ከሚባሉት ከአንዳንድ ፓርቲዎች በተሻለ መንግሥትን በጽሑፎችህ ለመገዳደር ትሞክራለህ። መጣጥፎችህም የጋዜጠኛ ሳይሆን የአርበኛ ወይም የተቃውሞ ፖለቲካ አቀንቃኝ ዓይነት ናቸው።

እንደምታውቁት አደባባያችን ጭር ብሏል። ጠንካራ ተቃዋሚ የለም፤ ጋዜጣዊ መግለጫ ከመስጠት በዘለለ በሰላማዊ ትግል ውስጥ ያሉ አማራጭ የትግል ስልቶችን አንዱንም አይጠቀሙም። ተቃዋሚዎች ትልቅ ነገር አደረጉ ከተባለ መግለጫ ማውጣት ነው። መሪያቸው ሲታሰር፣ አቧራ የሚያስነሣና ለትችት የሚዳርግ ፖሊሲ ሲወጣ የእነሱ ሥራ መግለጫ ማውጣት ነው እንጂ በሰላማዊ ትግል ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ አማራጮችን አይጠቀሙም። ወደ እኛ ስትመጣ አንድ ጋዜጠኛ ሊያደርጋቸው የሚገቡ አማራጮችን ሁሉ በመጠቀማችን ከፓርቲዎቹ የተሻለ ግምት አስይዞልን ‹‹አርበኛ›› ሊያስብለን ይችላል። ይህን የሚያመጣው የአርበኝነት ሚና መጫወት የነበረባቸው ፓርቲዎች ጭርታን በመፍጠራቸው እና አንተ የድርሻህን በመወጣትህ ነው። እኔ ግን ከጋዜጠኝነት የዘለለ ሚና አለኝ ብዬ አላስብም።

ፍትሕ ላይ አስፍረኸው የነበረውን ‹‹የፈራ ይመለስ›› የሚለውን ጽሑፍህን ለአብነት ማንሣት ይቻላል። [ጠያቂው ጋዜጣውን ገልጦ እያሳየው] በሰላማዊ መንገድ ቢሆንም ‹‹መብትህን ለማስከበር ውጣ፣ ተንቀሳቀስ›› የሚል ጥቅል ሐሳብ አለው። ይሄ የአንድ ጋዜጠኛ ተግባር ሊሆን ይገባዋል?

ከፖለቲካ ገለልተኛ የሆነ አገር የሌለው ብቻ ነው። አገር የሌለው ደግሞ ማን አለ? ማንም የለም። ጋዜጠኛ ብሆንም የራሴ የሆነ የፖለቲካ አቋም አለኝ። ጽሑፎቼ ላይ አቋሞቼ ሊንፀባረቁ ይችላሉ። ሥርዓቱ ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለመተቸት ያልከውን ጽሑፍ ጽፌዋለሁ። አምስት ዓመት ያህል የጻፍኩት ግን ‹‹የፈራ ይመለስ›› ብቻ ብዬ አይደለም።

የአንድነት ፓርቲ ልሳን ከነበረችው እና ስትንፋስዋ ከተገታው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ፣ የፖለቲካ አቀንቃኝ (Political Activist) ስለ መሆንህ ጥያቄ ቀርቦልህ ‹‹አዝማሚያው ሊኖር ይችላል›› ብለህ ነበር። ታዲያ ይህ ከጋዜጠኝነት መርሕ ጋር በእጅጉ አይጋጭም?

‹‹የፖለቲካ አቀንቃኝ ነህ?›› ያለው ጠያቂው እንጂ እኔ አይደለሁም።

አንተም ግን ‹‹አክቲቪስት ነኝ ባልልም እስከ ዛሬ ፍትሕ ታደርግ የነበረው ከዚህ የዘለለ አይደለም›› ስትል ምላሽ ሰጥተሀል።

‹‹ጽሑፎቼ ያንን ስያሜ ለማሰጠት አጋድለው ሊሆን ይችላል›› ነው ያልኩት። አንባቢ ከጽሑፍህ ተነሥቶ አርበኛ ሊልህ፣ ፅንፈኛ ሊልህ፣ የተቃውሞ ፖለቲካ አቀንቃኝና ሌላም ሊልህ ይችላል። እነዚህ ሁሉ ምድቦች ግን እኔ ውስጥ የሉም። ራሴን የምቆጥረው በአገሩ ላይ የተሻለ ነገር እንዲፈጠር የሚጥር አንድ ጋዜጠኛ አድርጌ ነው።

ስለ ስደተኛ ጋዜጠኞች ያለህ አቋም ምንድን ነው?

ኧኧኧ… [ሳቅ… የቁጥብነት ስሜት እየታየበት] ማንም ሰው ‹‹ለምን የእኔን ፅዋ አልጠጣም?›› ብለህ ልትወቅሰው አይገባም። የራሱ መከራ የመቀበል አቅም የት ድረስ እንደሆነ ያውቀዋል። እዚያ ደረጃ ሲደርስ ማንም ሰው ይሰደዳል። ለእኔ ግን መሰደድ የሚወገዝ ተግባር ነው።

ጋዜጠኛ መፍራት/መሸሽ የለበትም እያልክ ነው?

የመፍራት ጉዳይ ብቻ ሆኖ ሳይሆን ችግሩ እኮ ያለ ነገር ነው። እናንተ ጋዜጣ ለመጀመር ፈቃድ ጠይቃችሁ የነበረው የአውራምባ ታይምስ ማኔጂንግ ኤዲተር ‹‹ልከሰስ ነው›› ብሎ በሸሸበት፣ አዲስ ነገሮች የተሰደዱበት ሁኔታን እያወቃችሁ ነው። እና ታዲያ ‹‹ይህ ጸበል ለእኛ አይደርሰንም›› ብላችሁ ታስባላችሁ? ታዲያ ልከሰስ ነው፣ ልታሰር ነውን ምን አመጣው?

ስለዚህ ለተሰደዱ ጋዜጦች ምንም ክሬዲት አትሰጥም ማለት ነው?

[እየሳቀ] ያው ገልጬዋለሁ ‹‹የተሰደዱ ጋዜጠኞች ለፍተዋል፣ ሠርተዋል›› ብዬ ላስተካክለው? [ሳቅ] የእውነት ሠርተዋል፤ ለፍተዋል። ሲሰደዱ መከራን የመቀበል አቅማችን እዚህ ድረስ ነው ብለው ነው። ባይሰደዱም ያሉት ነገር (እስር) ሊተገበርባቸው ይችል ነበር። የእኔ ቅሬታ ኢሕአዴግ የለየለት አፋኝ በመሆኑ የጋዜጣ ፈቃድ ሲወስዱ ይህ እንደሚሆን ስለሚያውቁት ከመሰደድ ይልቅ ፊት ለፊት መጋፈጡ የተሻለ ነው የሚል ነው። የምንፈልገውን ውጤት የምናመጣው መስዋዕትነት በመክፈል ነው። ጋዜጠኛ የሐሳብ ተዋጊ ነው፤ ምሽጉ ደግሞ ሚዲያው ነው። ስለዚህ መስዋዕትነቱን እየከፈለ ምሽጉን መልቀቅ አይገባውም። ከአገር የተሰደዱ ጋዜጠኞችን ግን በምንም መልኩ ጥፋተኛ ልናደርጋቸው አይገባም። የሸሹ ሰዎች ጥፋተኛ ናቸው አለማለቴ እንዲታወቅልኝ ግን እፈልጋለሁ።

አገር ውስጥ ሆነው የሰላ ትችት ለሚሰነዝሩት ክብር ሰጥቶ በተቃራኒው የተሰደዱትን ክሬዲት ማሳነስ ልክ ይሆናል? አገር ውስጥ ካሉት ከተሻለ በውጪ ወጥተውም አበርክቷቸው ያልተቋረጠ (እየሠሩ ያሉ ጋዜጠኞች) አሉ ብዬ ስለማስብ ነው። እንዳሉት የሚታሰሩ ከሆነስ ወጥተው የሚችሉትን ማበርከታቸው ተገቢ አይሆንም?

ግልፅ እንዲሆን የምሻው ስደተኛ ጋዜጠኞች ፈሪዎች፣ የማይሸሹ ጋዜጠኞች ደግሞ ደፋሮች ናቸው አላልኩም። ድፍረት እና ፍርሃትን ከዚህ ውስጥ እናውጣው! ነገር ግን የቁርጠኝነት ጉዳይ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። መከራ የመቀበል ደረጃ ልዩነት እና የስልት ጉዳይም ነው። እኛ (ፍትሖች) ‹‹እዚሁ ቆስለን፣ እዚሁ ደምተን እንሠራለን›› ስንል፣ ሌሎች ጋዜጠኞች ደግሞ ‹‹ከመታሰር ከአገር ውጪ ሆኖ አስተዋፅኦ ማድረግ የተሻለ ነው›› ይላሉ። ይሄ የምርጫ ጉዳይ ነው። በእኔ እምነት ግን ከአገር ውጪ ሆኖ መሥራት የተሻለ አይደለም፤ እዚህ ሆኖ የመጣውን በጸጋ መቀበሉ የለውጡን ቀን ያቀርበዋል። በተረፈ ትክክሉ ለየራሳችን የሚተው ነው።

የቀድሞውን ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊን አስመልክቶ ‹‹ከጥቂት ቀናት በኋላ አንድ ነገር ይኖራል ጠብቁ›› ብለህ ፌስቡክ ላይ ገልጸህ ነበር። በሁለተኛው ቀን ማረፋቸው ተነገረ። የኢሕአዴግ የውስጥ ምንጮች አሉህ?

ምንም የማያከራክረው ፍትሕ በአገሪቷ ትልቅ ጋዜጣ ነበረች፤ ዋና መስፈርቱ የኅትመት ቁጥር በመሆኑ። የብዙ ሰዎችን ትኩረት ስለሚስብ መረጃዎች ወደ እኛ ይመጣሉ። ሥርዓቱ አገርን እየጎዳ እንደሆነ የሚገነዘቡ የሥርዓቱ ወሳኝ የሆኑም/ያልሆኑም ሰዎች አገርን ከማዳን አኳያ፣ እኛን በማመን አንዳንድ መረጃዎችን ያቀብሉናል።

ጽሑፎችህ ጥልቀት እንደሌላቸው እና ሰዉ ‹‹የእኔ›› ብሎ እንዲያነብ ሰሞነኛ ብሶታዊ ስሜትን ማንፀባረቅ ላይ እንደምታተኩር የሚተቹህ አሉ።

ሁሉም ጽሑፎቼ ላይ ባይሆንም ይሄ ዓይነት ነገር አለ ብዬ አስባለሁ። ፍርሃትን በመግፈፍ ሕዝብን ወደ አደባባይ መሰብሰብን ስለማልም፤ [አደባባይ ስል አብዮት አደባባይ አይደለም] ሕገ- ወጥነትን እምቢ እንዲል የማንቃት ባሕሪ ዋና ዓላማዬ ስለሆነ ሕዝባዊ እና ስሜታዊ ጉዳዮች ላይ አተኩራለሁ። በአገራችን ላይ የጠፋው ነገር የርዕዮተ ዓለም ዳሰሳ እና ትንተናዎች ሳይሆን [ይሄን በቂ ምሁራን ብለውታል] ፍርሃትን ማሸነፍ ነው። ለዚህ ደግሞ መፍትሄው አብዮታዊ ዲሞክራሲን ከሊበራል ዴሞክራሲ ጋር እያነፃፀርክ መተንተን አይደለም። የጠቀስካቸውን ጉዳዮች መዳሰስ ነው። ከዚህ አኳያ እንዳልከው ጥልቅ ትንታኔ ላይኖረኝ ይችላል። ‹‹የፈራ ይመለስ›› ለማለት ጥልቅ ትንታኔ አያስፈልግህም። አምስት ዓመት የተጻፉት ጽሑፎች ሁሉ ጥልቀት የሌላቸው ናቸው ብዬ ግን አላስብም።

ከሐሳብ ሙግት ይልቅ ግለሰቦችን ‹‹መጭረፍ›› ላይ ታተኩራለህ። መለስ ዜናዊ፣ ስብሀት ነጋ፣ ፕ/ር አንድሪያስ እሸቴ፣ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ፣ ሬድዋን ሁሴን፣ ፋሲል ናሆምና ሌሎችም ላይ ግላዊ መሠረት ያለው ትችት አቅርበሀል። ችግሮች ያሉት ግለሰቦቹ ጋ ነው ወይስ ተቋማዊ አሠራሩጋ?

ገበያ ላይ ከዋሉ 197 የፍትሕ ኅትመቶች ውስጥ ቢያንስ በሳምንት አንድ ጽሑፍ ላይ እኔ አለሁ። [በነገራችን ላይ የፍትሕ የመጀመሪያዎቹ ሕትመቶች ላይ ተመስገን በስሙም ሆነ በብዕር ስም የጋዜጣዋን ከግማሽ በላይ ገጾች ይሸፍን ነበር።] ከዚያ ውስጥ ግለሰብ ላይ ያተኮርኩት በጣም ጥቂት ጽሑፎች ላይ ነው። ግለሰቦች ላይ የጻፍኩት እኮ አምስት ጊዜ ብቻ ነው።

ልልህ የፈለግኩት ለውይይት የሚጋብዙ ሓሳቦች (Arguments) ላይ ከማተኮር ይልቅ የቀድሞውን ጠ/ሚኒስትር መለስን ጨምሮ በርካቶች ግላዊ ኹነት ላይ ትንተራሳለህ ነው። [የተቋምም ሆነ የሲስተም ፈጣሪ ሰው መሆኑ እንዳለ ሆኖ ማለት ነው።]

በርዕዮተ ዓለሞች ላይ፣ በፍትሕ ሥርዓቱና በመሳሰሉት ላይ ለሁለት ዓመት ያህል ሀተታዎች (Features) ጽፌያለሁ። ስለዚህ ፍትሕ ከመግነኗም በፊት ያለውን ማሰብ/ማየት ያስፈልጋል።

‹‹እስኪ በስብሀት ሙድ እንያዝባቸው፣ ንዋይ ገብረ አምላክ በረሃ እንዳልገቡ አውቃለሁ ምናልባት ውቤ በረሃ ካልገቡ በስተቀር…›› መሰል ከሞራል እና መገናኛ ብዙኃን ከሚቀርብ ጽሑፍ አንፃር (በተለይ ኮስታራ ጽሑፍ ላይ) ተገቢ ያልሆኑ ቃላትን ትጠቀማለህና ይህ ሐሳብህን ወደ ስድብ ደረጃ አያወርደውም?

ኧ… ኧ… ኦኬ! ቃላቶቹን የተጠቀምኩት ትንሽ ዘና ለማድረግ ያህል ነው። ለምሳሌ ንዋይ ገብረ አምላክ የኢሕአዴግ ታጋይ አይደሉም፣ የደርግ ባለሥልጣን ነበሩ። ያንን ይበልጥ ለመግለጽ ‹‹ንዋይ ገብረ አምላክ በረሃ አልገባም፤ ምናልባት ውቤ በረሃ ካልሆነ›› ብያለሁ። ስድብ ነው ብዬ አላስብም ነበር። በዚያ መልኩ ተተርጉሞ ከሆነ በጣም አዝናለሁ። ምናልባት ቃላቶቹ ወደ ስድብ ወርደው ከሆነ በእጅጉ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ለመሳደብ አልነበረም፤ ከባሕሪም አኳያ የመሳደብ ነገር የለብኝም።

አፍሮጋዳ የሚል መጽሐፍ አንብበሀል? ‹‹ዘመኑ የሚወደው ጥልቀትን አለዝበህ ስሜቱን እንድትነግረው ነው። ቴዲ አፍሮ እና ይስማዕከ ወርቁ (ዴርቶጋዳ) የተወደዱት ለዚህ ነው›› ይላል፤ ታሪክ ሠሪው ከግልቡ እኩል አይታወቅም የሚል ይዘት አለው ጽሑፉ። ይሄንን በአንተ ላይ እንዴት ታየዋለህ?

የ‹‹ጥልቀት›› እና የ‹‹ግልብ›› መስፈርቱ ምንድን ነው? የሚለው አንድ ነገር አለ። በእኔ እምነት የቴዲ አፍሮም ሆነ የዴርቶጋዳ ሥራዎች ግልብ አይደሉም። እነዚህን ‹‹ግልብ›› እንበላቸውና የንዋይ ደበበን ወይም የሰለሞን ተካልኝን ሥራዎች ‹‹ጥልቀት›› አላቸው እንበል? [የአግራሞት ሳቅ] ጥያቄውን ለመመለስ ግን ምናልባት አገር እና ሕዝብን የመናቅ ነገር ይመስለኛል። ቴዲ አፍሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አድማጮች አሉት እነዚህን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አብረህ መተቸት ነው። እነዚህ ኢትዮጵያኖች የወደዱትን ሥራ አናንቀን የተሻለው የትኛው ነው?

ሕዝብ የወደደው ነገር ሁሉ ትክክል ነው ማለት ይቻላል?

እንደ ሕዝብ ስሕተት አለው ብዬ አላስብም። አንድ መጽሐፍ ጥልቅም ይሁን ግልብ ሆኖ ይውጣ፣ ገበያ ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥረው ጋዜጦች ላይ ከሚወጣው ማስታወቂያ ይልቅ ሕዝብ የሚያወራው ነው። የአንተን መጽሐፍ በጣም አሪፍ ነው እያለ የሚያወራው ከሆነ በቃ አከተመ፤ በጥሩ ሁኔታ ይሸጣል። ‹‹ኡ… የአቤል መጽሐፍ የሞተ ነው›› ብሎ ሕዝብ የሚያወራ ከሆነ ታቅፈኸው ትቀራለህ። ዴርቶጋዳ በእኔ እምነት ጥሩ መጽሐፍ ነው። ያንን ሁሉ ሰው ማሳማን የቻለ ሥራ ግልብ ነው? ይሄ ሁሉ ሰው ግልብ እና ጥልቀት መለየት አይችልም? የሚሉ ነገሮች አብሮ ሊታዩ ይገባል ባይ ነኝ።

ሁሌም መንግሥትን የሚያጠለሹ ጽሑፎችን ብቻ በመጻፍ ትተቻለህ። ይህ ሥርዓት ምንም አልሠራም ብለህ ታስባለህ?

ሩቅ ሳትሄድ ለምሳሌ አዲስ ነገር፣ አውራምባ ታይምስ፣ ፍትሕ ጥቂት ጊዜ ቢኖሩም የዚህ ሥርዓት ውጤት ናቸው፤ እንደ ድመት ራሱ ወልዶ በላቸው እንጂ። ምንም የምትክደው ነገር አይደለም። በደርግ ጊዜ ‹‹ሠርቶ አደር፣ አዲስ ዘመን፣ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ›› እያልክ ትሄዳለህ እንጂ የግል ሚዲያ ሽታውም አልነበረም። በዚህ 22 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሚመስሉ ነገሮች ብዙ አሉ። ለምሳሌ እናንተ የአውራምባ ታይምስ ባልደረቦች ነበራችሁ። ምንም ይሁን ምን አውራምባ ታይምስ የተዘጋው በኢሕአዴግ ጫና ነው። ስለዚህ ስለ ፕሬስ ነፃነት የሚኖራችሁ ግንዛቤ እዚያ ላይ መሠረት ያደረገ ነው። አውራምባ ታይምስ አራት ዓመት ያህል ለመሥራትዋም ቢሆን ምንም ሳያከራክር ክሬዲቱን መውሰድ ያለበት ኢሕአዴግ ነው። ‹‹ነፃ ፕሬስ›› ብሎ፣ አዋጅ አቋቁሞ፣ ፈቃድ የሰጠው ኢሕአዴግ ነው። ፍትሕ ተዘግታለች ነገር ግን እስከ ነበረችበት ጊዜ ድረስ ፈቃድ የሰጣት ኢሕአዴግ ነው። እነዚህ እነዚህ በጎ ጎኖች በትልልቅ ጥፋቶች፣ ውድመቶችና ኪሳራዎች ስለሚጋረዱ ያንን ማየት የማትችልባቸው ሁኔታዎች አሉ።

ፍትሕ ከተዘጋችና አዲስ ታይምስ መጽሔት ላይ ተሻግራችሁ ሥራ ከመጀመራችሁ በፊት 300 ሺህ ብር ወጪ እንዳወጣህ ፌስቡክ ላይ ጽፈህ አንብበናል። የማስታወቂያ ገቢ አልነበረህምና ጋዜጣ ሸጦ ይሄንን ሁሉ ወጪ መሸፈን ይቻላል?

ጋዜጣ እየሸጥክ እያለህ ድርጅትን ልታሻሽል ትችላለህ። አቁመህ ግን ይሄን ያህል ትርፍ ወጪ መሸፈን አትችልም። እንደምታውቁት ባለፈው ዓመት (2004 ዓ.ም.) ግንቦት ወር ላይ ከወጣው መጽሐፌ (የመለስ አምልኮ) ብዙ ብር አግኝቼበታለሁ። ንገረኝ ካልከኝ መጠኑን ልነግርህ እችላለሁ።

ይቻላል!

እስካሁን ባለው ሁኔታ ከስድስት መቶ ሺህ (600,000) ብር በላይ አግኝቼበታለሁ። ጋዜጣው ቢዘጋም የደጎመኝ ይሄ ብር ነው። ‹‹300 ሺህ አወጣሁ›› ያልኩት ፍትሕ ማተሚያ ቤት ስትያዝብን 84 ሺህ ብር ከፍለን ነበር። በተጨማሪም ጋዜጣውን ለማዘጋጀት የከፈልናቸው ወጪዎች ነበሩ። በአዲስ ታይምስ እስክንመለስ ድረስ ማንም ሠራተኛ ስላልተባረረ ደመወዝ እንከፍል ነበር። 300 ሺህ ብር የደረሱት እነዚህ ወጪዎች ተደማምረው ነው። መቆየት የቻልነውም በመጽሐፉ ገቢ ነው።

ፍትሕ እንደቆመች በተሻለ ፍጥነት በአዲስ ታይምስ መጽሔት ተመለሳችሁ፣ ለስምንት እትም የሄደችው አዲስ ታይምስ ስትቆምም አራት እትም በሄደችው ልዕልና›› ለሦስተኛ ጊዜ መጥታችሁ ነበር። በዋነኝት ኦርኬስትራውን የምትመራው አንተ ነህና ይህ ትጋትህ ለፕሬስ ነፃነት ነው ወይስ ለገንዘብ ነፃነት? [የንግድ ሱቁ የተዘጋበት ሰው ገቢው እንዳይቆም በፍጥነት ሱቅ አፈላልጎ እንደሚይዘው ሁሉ የእናንተም ወደ ሌላ ፕሬስ የምትጓዙት በፍጥነት ስለሆነ ጥርጣሬ በመፍጠሩ ነው።]

ትልቁ ስሕተትህ የሚጀምረው [ጠያቂው አቤልን ቆጣ ብሎ እያየ] በኢትዮጵያ የጋዜጣ ንግድ ለገንዘብ ነፃነት ያበቃል ብለህ መገመትህ ነው። ሐሳቡ የአንተ ካልሆነም ‹‹ሐሳባችሁ ስሕተት ነው›› በልልኝ። በኢትዮጵያ ፕሬስ ውስጥ ያለህን ይዘህ ገብተህ፣ ባዶ እጅህን ትወጣለህ እንጂ እውነት አትራፊ የምትሆንበት ነው?

ፍትሕ አትራፊ አልነበረችም?

ፍትሕ አትራፊ ነበረች። ለአራት ዓመት ያህል ርምጃዋን ጠብቃ መጓዝ በመቻልዋ በሂደት አትራፊ መሆን ችላለች። ነገር ግን አዲስ ታይምስን ስምንት ጊዜ ስናሳትም እና ልዕልናን በከፍተኛ (በተጋነነ) ወጪ ንግድ ፈቃድዋን ከግለሰብ ላይ ስንገዛው ቁማር እንደሆነ እናውቃለን። ከኢሕአዴግ አፋኝ ባሕሪ አንፃር አንድ እትምም ሳንሄድ ሊዘጋት እንደሚችል እናውቃለን። በተለይ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሞት በኋላ ሥርዓቱ ሆደ ባሻ በመሆኑ ያገኘውን ነገር ሁሉ መርገጥ እና ማፈን ጀምሯል። ይህ ባለበት ሁኔታ ብዙ ወጪ አውጥቶ፣ በኪሳራ ምክንያት የቆመን ጋዜጣ ከግለሰብ ላይ በተጋነነ ገንዘብ መግዛቱ ለገንዘብ ያለህን ሐሳብ በፍጹም አያሳይም። ልናተርፍ ይቅርና ያወጣነውን ገንዘብ እንኳን ለማስመለስ ዋስትና የለንም። የሚገርመው ደግሞ የቃለ-ምልልሱን ተከታይ ክፍል በምታደርጉበት በዚህ ወቅት ልዕልና መቆሟን የምነግራችሁ የመጀመሪያ ሰዎች ሆናችኋል። ስለዚህ፣ ያወጣነውን ወጪ እንኳን ማስመለስ አልቻልንም ማለት ነው። እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ‹‹ለገንዘብ ነፃነት ነው የምትሠሩት›› መባል የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ አለማወቅ ይመስለኛል። ያለንን እያወጣን መቆመራችን፣ ለፕሬስ ነፃነት እንታገላለን ከሚል እሳቤ የመነጨ መሆኑን ያለጥርጥር እናገራለሁ።

ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ራሳቸውን ሳያከብሩ ሌላውን ማክበር፣ ለራሳቸው አድናቆት ሳይኖራቸው ሌላውን ማድነቅና ጥቂት ግለሰቦች ላይ መንጠልጠል ይፈልጋሉ። መናገር እየቻሉ ‹‹ተመስገን በዚህ ጉዳይ ጻፍበት፣ ተችበት፣ ንገርልኝ›› ሲሉ በጎንዮሽ መልዕክት ማስተላለፍን ይመርጣሉ። ትቀበለዋለህ?

እንዳልኳችሁ እንደ እነዚህ ዓይነት ሰዎች እና ሁኔታ አገራችን ላይ በመኖሩ ነው እኔ ጋዜጠኛ የሆንኩት እንጂ ፍላጎቱ ኖሮኝ ከየትኛውም የጋዜጠኝነት ትምህርት ቤት ተመርቄ አይደለም። እንደዚህ ዓይነት ድባብና ፍርሃት ስላለ የግድ የተወሰንን ሰዎች ሰንደቅ ማንሳት አለብን፤ ሰዎቹ ቢሉም ትክክል ናቸው። የምንሠራው ለእነሱ፣ ለሌላው ሕዝባችንና ለአገራችን ነው። በዚህ ላይ ደግሞ ለአንድ አገር መስዋዕት ሊሆኑ የሚገቡት ጥቂት ሰዎች ናቸው እንጂ 80 ሚሊዮን ሕዝብ መስዋዕት ከሆነ ታዲያ ማን ነው በመስዋዕትነት በተገኘ ድል ላይ የሚረማመደው? የአረብ ዓለም አብዮት በተነሣ ጊዜ ሆን ብለው የመንግሥት የፀጥታ ሠራተኞች ‹‹ይሄ ሕዝብ አንተ ሞተህለት እንዲያልፍለት ነው የሚፈልገው›› የሚል አፍራሽ ቅስቀሳ ጀምረው ነበር። አገራችን የተሻለች ልትሆን የምትችለው፣ የተወሰንን ሰዎች መከራውን ከተቀብለን ነው። ፈረንጆቹ ‹‹ነጻ ምሳ የለም›› እንደሚሉት ሕዝቡ በሙሉ መከራና ችግር የሚቀበል እና የሚቸነከር ከሆነ ከትርፉ ይልቅ ኪሳራው ያመዝናል። ስለዚህ በጥቂቶች ላይ ቢንጠለጠሉም ተገቢ ነው።

ዱላውን የሚቀበል በሌለበት፣ ለእውነት መታገል እና መስዋዕትነት መክፈል ኪሳራ አይሆንም?

ፍትሕን የመሠረትኩትና እኔ ጋዜጠኛ የሆንኩበት ምክንያት የዚህ ዓይነት ዱላ የሚቀበሉ ዜጎችን ለማፍራት ነው። እቅዴ ፍርሃትን አሸንፈው እና ከቀንድ አውጣ ዛጎላቸው ውስጥ ወጥተው ዱላ ሊቀበሉ የሚችሉ የፍትሕ ቤተሰቦችን ማፍራት ነው።

ዱላ ተቀባይ ከሌለስ?

ማፍራት አለብን። እስኪፈራ ድረስ አቅም እስካለ እንሠራለን። እኛ ብናልፍ በርካታ ሰዎች ይቀጥሉታል። ቢያንስ በዚህ አራት ዓመታት ውስጥ ሁለትና ሦስት ማፍራት እንችላለን ብዬ አስባለሁ። በሂደት እንዲህ አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት እየተባለ ይቀጥላል።

‹‹ዱላ ተቀባዮችን በሂደት እናመጣለን›› ብለሀልና አሁን ዱላ ተቀባዮች ከሌሉ፣ ብዙዎች በፍርሃት ቆፈን ውስጥ ከባተቱ፣ አንተ ወይም ጥቂቶች ጠንካራ እና ሞጋች ሐሳቦችን መሰንዘራችሁ እናንተን እያገነነ ወደ ጀብደኝነት ደረጃ ከፍ ያደርጋችኋል እንጂ ተከታዮችን ለማግኘት ያስችላችኋል?

‹‹ተመስገን አርአያዬ ነው›› የሚሉ ሰዎች አሉ። እንዲህ ካሉ እኔ አናጢ፣ ግምበኛ ወይም አስተማሪ አይደለሁም። አርአያነቴ በጋዜጠኝነት ሥራዬ ነው። ስለዚህ ይህንን አርአያ ይከተላሉ ማለት ነው።

የሠራህባቸው የኅትመት ውጤቶች ከተቋማዊ አሠራር ይልቅ በአንተ ትከሻ ላይ መንጠልጠል ይታይባቸዋል። ጥናት ባንሠራም፣ ባለን መረጃ መሠረት ከጋዜጣችሁም ጥቅል ፍሬ ነገር ይልቅ አንተ ርዕስ ነህ። በሆነ አጋጣሚ ለአንድ ወይም ለሁለት ሳምንታት ተመስገን ባይጽፍ የጋዜጣችሁ ሽያጭ አደጋ ውስጥ የሚወድቅ አይመስልህም? [የፍትሕ/አዲስ ታይምስ/ልዕልና አንባቢያን ማዳመጥ የሚፈልጉት ያንተን ትኩሳት ነው ብዬ ነው።]

ይሄ ሁኔታ ተቋማዊ ሁኔታን ካለመገንባት የሚመጣ ሳይሆን ጋዜጣው ለረዥም ዓመት እንደ አሁኑ ‹‹በድል ጎዳና›› መራመድ ሳይጀምርና በቂ የሠራተኛ ኃይል ሳይኖረው፣ ለረዥም ዓመት በችግርና በብድር [አራጣ እስከ መበደር ደርሼ] ጋዜጣውን ይዤ የተጓዝኩት እኔ ስለሆንኩ ነው። በ2004 ዓ.ም. ሙሉ ዓመት ግን ጋዜጣው ተቋማዊ ሰውነት ይዞ እየተጓዘ ነበር። በእኔ እምነት ፍትሕ የተለያዩ ሐሳቦችን ታነሣለች፣ ታስተናግዳለች። አቅም ኖሮንም መክፈል ችለናል። ይሄ ጋዜጣዋ በድል ጎዳና መጓዝ ከጀመረች በኋላ የመጡ ለውጦች ናቸው። ይሄ ጥያቄ የተነሣው 2004 ዓ.ም. ሳይገባ በፊት ቢሆን ትክክል ነበር። ከስሜ ውጪ በብዕር ስም ስድስትና ሰባት ጽሑፍ በሳምንት የምጽፍበት ጊዜ ነበር።

‹‹ፍትሕ በድል ጎዳና…›› ካልከው ጋር ልንተራስና፣ በተደጋጋሚ ጊዜ በኅትመት መጠን ቀዳሚ መሆንን እንደ ብቃት ጥግ ማሳያ ትመለከተዋለህ። ፍትሕ ታብሎይድ ስለሆነች እና ስሜት ቀስቃሽ (Sensational) ጉዳዮችን ስለምታንፀባርቅ (ስለምታነሣ) እንጂ የጋዜጣዋን በደረጃ ቀዳሚነት እና ጥልቀት፣ ተነባቢነቷን ፈጽሞ አይገልጽም ብልህ ተሳስቻለሁ?

አዎን! ሙሉ በሙሉ ተሳስተሃል። ምክንያቱም ምንም የማያከራክረው ነገር 2004 ዓ.ም. ሙሉ ፍትሕ በኅትመት መጠን ቀዳሚ ነበረች። በታብሎይድ ስታይል ብትሄድ፤ አንድ ሳምንት ስሜት ቀስቃሽ ርዕሰ ጉዳይ ስታገኝ ሊሳካልህ፣ ሳታገኝ ደግሞ ላይሳካልህ ነው። ከሳምንት ሳምንት በቋሚነት አንባቢ አፍርተህ መጓዝ ማለት ግን የተሻለ አማራጭ ይዘህ መጥተሃል ማለት ነው። ስሜት ቀስቃሽ ነገሮች በጣም ውስን እና ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር የሚያያዙ ናቸው። ለምሳሌ፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሞት ስሜት ቀስቃሽ አጀንዳ ሊሆን ይችላል። ጥሩ አድርገህ ልትሠራበት ትችላለህ። ሁልጊዜ ግን እሳቸው አይሞቱም። ዓመቱን ሙሉ በቀዳሚነት መጓዛችን የሚያሳየው ቋሚና ታማኝ አንባቢ ማግኘታችንን ነው። ታማኝ አንባቢ ማግኘት ደግሞ ቀዳሚ መሆን ማለት ነው።

በአገራችን ነፃ ፕሬስ ስሙ ነው እንጂ በአሁን ወቅት አለ ብለህ ታምናለህ?

የለም ብዬ አምናለሁ።

ማሳያህ ምንድን ነው?

ጋዜጠኛው በራሱ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቱ ምን ያህል ተከብሯል? እስክንድር ነጋ፣ መስፍን ነጋሽ፣ ዳዊት ከበደ፤ አቤል፣ ኤልያስ፣ ውብሸት ወይም አቤ ቶኪቻውን ምን ያህል ነፃ አድርገዋቸዋል? በሚል ነው የሚለካው እንጂ ‹‹ኢሕአዴግ አምባገነን ነው›› ብቻ ብሎ በመጻፍ የጋዜጣህ ነፃነት ወይም ነፃ ጋዜጠኝነት አይለካም። ከዚህ አኳያ አሁን ወዳሉት የኅትመት ውጤቶች ስትመጣ ‹‹ነፃ ጋዜጣ አለ›› ለማለት ይከብደኛል። [የቃለ ምልልሱን የመጀመሪያ ክፍል ያደረግነው ፍትሕ ጋዜጣ ከቆመች በኋላ በነሐሴ 2004 ዓ.ም. እንደነበር ልብ ይሏል።] ‹‹ከዚህ በኋላ በዚህ ርዕስ ላይ እንዳትሠራ›› የሚሉ የጋዜጣ ባለቤቶች ናቸው ያሉት። ዋና አዘጋጆቹም የባልደረቦቻቸውን ሸክም (መስቀል) መሸከም የማይችሉ ናቸው። በአገሪቱ የፕሬስ ሕግ መሠረት የሚጠየቀው ዋና አዘጋጁ ነው። ፍትሕ ላይ ሁሉም በሚጽፉት ጽሑፍ አንዳች ነገር እንደማይደርስባቸው ያውቁታል። ስለዚህ እነዚያ ጋዜጠኞች እንዳሻቸው በነፃ ሜዳ ላይ ይቦርቁበታል ማለት ነው። ማንኛውም ዋና አዘጋጅ ለባልደረቦቹ ያንን ያህል ኃላፊነት መውሰድ አለበት። በዋነኛነት ‹‹ነፃ ጋዜጣ የለም›› የምልህ አፈናው የሚጀምረው ከውስጥ፤ ከባለቤቱና ከዋና አዘጋጁ በመሆኑ ነው። ጋዜጦቹን በደንብ ተከታተሏቸው፤ የሚጮሁበትና የማይጮሁባቸው ጉዳዮች አሉ። የሚሠሩት ‹‹ይሄ ኢሕአዴግን ያስቆጣዋል/አያስቆጣውም›› እያሉ በማማረጥ ነው።

ነፃ ሚዲያ አለ ብለህ አታምንም ነገር ግን የኅትመት ውጤቶችህ/ቻችሁ ሲዘጉ እነዚህኑ የፕሬስ አካላት ሁኔታውን ይፋ እንዲያደርጉ እና አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ትጠይቃለህ። አይጣረስም?

ግልፅ እንዲሆን የምፈልገው ነገር… የሕወሃትን አጀንዳ የሚያራምዱ መገናኛ ብዙኃን እንዳሉ አምናለሁ። ሌሎቹ ግን ራሳቸው ላይ ቅድመ ቁጥጥር እያደረጉ ራሳቸውን በራሳቸው አዳክመዋል። አንድ ሚዲያ ራሱን ከገደበ፣ ኤዲቶሪያል ነፃነቱ ላይ ከተደራደረ፣ ‹‹ይዘጉብኛል›› ብሎ ራሱን ከቆጠበ ደካማ ነው። በርግጥ ይህ የሆነው በሥርዓቱ ጫና ፈጣሪነት ነው። ይህ ማለት ግን ሕወሃት ጠፍጥፎ ሠርቷቸዋል ማለቴ አይደለም። ስሕተታችንን ነግረኸናል በሚል ቅር ተሰኝተው፣ ከእናንተ ጎን አንቆምም የሚሉ ካሉ የአቶ መለስን አባባል ልዋስና [አቶ መለስ የሚነሡለት በጎ ነገር ባይኖርም፣ ተረቶቹ ይነሣሉ] ‹‹በሊማሊሞ ማቋረጥ ትችላላችሁ›› እላቸዋለሁ።

እኛ አገር ባለው ሁኔታ አሳታሚዎች ወይም ጋዜጠኞች የጋራ ችግር ሲመጣ፣ የማተሚያ ቤት ዋጋ ሲወደድና መሰል ችግሮች ሲፈጠሩ ለይምሰል ማኅበር ይቋቋማል፣ ‹‹ኅብረት›› ለመፍጠር ይጥራሉ እንጂ በጥቅሉ አጋርነት (Solidarity) አለ ለማለት ይቻላል?

እንዳልኳችሁ ምን ያህል ጋዜጦች ነፃ ናቸው? ከ2003 ዓ.ም. በኋላ ገበያ ላይ እስከነበርንብት ጊዜ ድረስ ከአውራምባ ታይምስ ውጪ ነፃና በራሱ ቆሟል ብዬ የማምነው ሌላ ጋዜጣ አልነበረም። ይሄ የአደባባይ ሃቅ ነው። ሌሎቹ የየራሳቸው ፍላጎት ያላቸው ናቸው። ራሳቸውን ነፃ ካላወጡ ሰዎች ጋር አብሬ፤ ነፃ ማኅበር መስርቼ እንቀሳቀሳለሁ፣ የፕሬስ ካውንስል መስርቼ እንቀሳቀሳለሁ ብትል አያስኬድም። የፕሬስ ካውንስል በየትኛውም አገር የሚታየው ከሥነ-ምግባር አኳያ ነው። አፍሪካ ውስጥ ትልቅ የፕሬስ ካውንስል ያለበት የመጀመሪያ አገር ዛምቢያ ትመስለኛለች። እዚያ ፕሬዝዳቱ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩና ከፍተኛ ባለስልጣናት በአንድ ጋዜጣ የወጣ ዘገባ በደለን፣ ጎዳን፣ ስማችንን አጠፋው ብለው ሲያስቡ ወደ ፍ/ቤት አይሄዱም። ፕሬስ ካውንስሉ ጋ ሄደው መርምሮ የሥነ-ምግባር ጉድለት ካለበት ቅጣት ይወስናል። ‹‹ለሦስት ወር አትዘግብ›› ሊል ይችላል። ፕሬስ ካውንስል ይሄንን የሚያደርግ ትልቅ ኃላፊነት የተሸከመ ድርጅት ነው። ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ካውንስል አደራጅ ሊቀ-መንበር ሚሚ ስብሐቱ ትባላለች። የምናወራው ስለ ስነ-ምግባር ነው፤ ከግለሰቧ ጋር ምንም ችግር የለብኝም። አንዳንዴ ትራንስፖርት ውስጥ ድምጿን በሬድዮ ከመስማት ውጪ ስለእሷ ብዙም መረጃ የለኝም። በአካልም ተገናኝተን አናውቅም። ነገር ግን ከአሜሪካ ሬድዮ ጣቢያ በሥነ-ምግባር ጉድለት የተባረረች፣ በ1998 ዓ.ም. ጋዜጠኞች ሲታሰሩ ‹‹እነዚህ ጋዜጠኞች ሞት ሊፈረድባቸው ይገባል›› ብላ ስትከራከር የነበረች፣ ጋዜጠኞች በተሰደዱ ቁጥር ‹‹ከሥረው ነው፣ አሸባሪዎች ናቸው›› የምትል፣ ፍትሕ ሲዘጋም ‹‹መንግስት ዘገየ›› ያለች ሴትዮ ሌላውን ጋዜጠኛ እንዴት አድርጋ እንደ ምታስተምር እግዚአብሔር ነው የሚ ያውቀው።

እንደዚህ አይነት ካውንስልን ስለማታምነው እና ነፃነት እንደሌለው ስለምታውቅ አብረኸው ልትሠራ አትችልም። በሙሉ መልዕክተኞች ናቸው። በአብዛኛው የመንግሥት አስፈጻሚዎች ናቸው። እነሱ ነፃ መሆን ቢፈልጉም ኢሕአዴግ በባህሪው ምንም ነገር ነፃ እንዲሆን አይፈልግም። እነዚህ ሠዎች ደግሞ የሥርዓቱ ቀንደኛ አገልጋዮች እና ዋና ተጠሪዎች ናቸው። ስለዚህ ከእነዚህ ጋር ልትሠራ አትችልም። ይሄ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ አጋርነት እንዳይኖር ያደረገው።

ከመንግሥት ትዕግስት አልባነት አንፃር ብዙዎች ጋዜጣ ለመጀመር ፈቃድ ማግኘት ባልቻሉበት አገር እናንተ ሦስት ‹‹መለያ›› ቀያይራችሁ [አዲስ ታይምስ እና ልዕልና ላይ የቆያችሁት ለአጭር ጊዜም ቢሆን] ስትጫወቱ መታየቱ ጥርጣሬ የጫረባቸው ወገኖች አሉ። ‹‹የኢሕአዴግ አንድ ክንፍ “ነጻ ሚዲያ አለ” ለማስባል ከጀርባቸው ሆኖ ያግዛቸዋል›› የሚሉ ድምጾችም ይሰማሉና ምን ትላለህ?

እንዲህ እያሉ የሚያራግቡት ሕሊናቸው በጥቅም የታወሩ ሠዎች ናቸው። ምክንያቱም እኛ በ‹‹አዲስ ታይምስ››ም ሆነ በ‹‹ልዕልና›› ስንመለስ በሥርዓቱ (በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን) ፈቃድ አይደለም። ሁለቱንም ከባለቤቶቹ ጋር ተደራድረን ገዝተን ወደ እኛ ከዞረ በኋላ የአንድ ዓመት ፈቃድ ስለነበራቸው በሕጉ መሠረት ለብሮድካስት ባለስልጣን ያደረግነው ‹‹ዋና አዘጋጅ እና ሥራ አስኪያጅ መቀየራችንን ማስታወቅ እንጂ ማስፈቀድ አይደለም። በማስታወቅ እና በማስፈቀድ መሀከል ሰፊ ድልድይ አለ።

ስታሳውቁ እናንተ መሆናችሁን ሲረዱ እንዳትንቀሳቀሱ እንዴት አላደረጓችሁም?

ያው ዘጉት እኮ። ከታኅሳስ 30 በኋላ የሥራው ፈቃድ ስለሚቃጠል የአዲስ ታይምስን ፈቃድ ልናድስ ስንል ‹‹ሥም ያዞራችሁት በሕገ-ወጥ መንገድ ስለሆነ አናድስም›› ብለው ዘጉት። ልዕልናንም የጀመርነው አዲስ ፈቃድ አውጥተን አይደለም በውልና ማስረጃ ማድረግ የሚገባንን ከጨረስን በኋላ ጋዜጣው ነገ ሊወጣ እንደዛሬ ባለቀ ሰዓት ዋና አዘጋጅ መቀየራችንን በደብዳቤ አሳወቅን። ሦስት ዕትም ከሄድን በኋላ ብሮድካስት ላይ ያሉ የሥርዓቱ ሎሌዎች ‹‹በሕገ ወጥ መንገድ ነው ጋዜጣውን ወደ እናንተ ያዞራችሁት›› ብለው ደብዳቤ ጻፉልን። በጣም የሚገርመው ግን ከልዕልና ባለቤት ጋር ስምምነት ነው እንጂ የፈጸምነው ገና ሥም ወደ እኛ አልዞረም ነበር። አራተኛውን ዕትም ካወጣን በኋላ በንግድ ሚኒስቴር በኩል ‹‹የንግድ ፈቃዳችሁ ተሰርዟል›› የሚል ደብዳቤ ላኩልን።

እውነታው ይህ ስለሆነ የሚወራውን በማስተባበል ራሴን አላደክምም። እንዲህ ብለው የሚጽፉትም እውነታውን ያውቁታል። በሦስቱም የኅትመት ውጤቶች ላይ እኛ የምናነሳቸው ርዕሰ ጉዳዮች የእውነት ሥርዓቱ የሚፈልጋቸው ወይም ለማስተንፈሻነት የሚጠቀምባቸው ናቸው? አንባቢ ስለሚፈርድ ይህን በማስተባበል ጉልበቴን አላደክምም።

በነገራችን ላይ… ልዕልና ላይ ባሰፈርካቸው መጣጥፎች ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን  አንቱታን ትተህ ሁለተኛ መደብ ነጠላ ስም በመጠቀም ‹‹አንተ›› እያልክ ትገልፃቸው ነበር። ይህ ተገቢ ነው?

ተሳስቼ ሳይሆን ሆን ብዬ ያደረግኩት ነው። ፍትሕ ላይ እያለን ሥርዓቱ በተወሰነ መልኩ ሕግ እንደሚያከብር የማስመሰል አካሄድ ስለነበረው ለዚያች እውቅና ሰጥቼ ‹‹አንቱ›› እላቸው ነበር። አሁን የተፈጠረው ግን ጭልጥ ያለ አፈና እና ጉልበተኛነት ስለሆነ እነዚህን ሰዎች አንቱ ማለቱ አግባብ አይደለም ብዬ ስለማስብ ነው። የምታከብረው እኮ የሚከበርን ሠው ነው። አፋኝ፣ ሕገ ወጥና ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለሱ ጭፍን አምባገነን ስለሆኑ ‹‹አንተ›› ከማለት ባለፈ በአፋጣኝ ከሥልጣናቸው እንዲለቁም እፈልጋለሁ። ‹‹ከሥልጣንህ ውረድ›› እንጂ ‹‹ከሥልጣንዎ ይውረዱ›› አትልም። ጋዳፊ፣ ሙባረክ ‹‹ውረድ›› ነው የተባሉት።

ጋዜጠኛ ከሥልጣን ሲወርዱ ይዘግባል እንጂ ‹‹ከሥልጣን ውረድ›› ማለት ይገባዋል?

ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ የጋዜጠኝነትን መርህ አክብረህ የምትሠራበት ስላልሆነ ነው። ጋዜጠኝነት መታየት ያለበት ከአውዱ አኳያ ነው ብዬ አስባለሁ።

ባለፈው ነሐሴ 2004 ዓ.ም. በጀርመን ድምፅ ሬዲዮ ላይ አንተ፣ አቶ አማረ አረጋዊ [የሪፖርተር ጋዜጣ ከፍተኛ ባለድርሻ እና ሥራ አስኪያጅ] እና ዶ/ር መሠረት ቸኮል [በዊስኮንሲን ሪቨር ፎልስ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ፕሮፌሰር የነበሩና በሕዳር/2005 ዓ.ም. በጉበት ካንሰር ሕይወታቸው ያለፈ] ለቃለ ምልልስ ቀርባችሁ ነበር። አቶ አማረ ‹‹ሚዲያ ካውንስሉ የፕሬስ ነፃነትን እየታገለ ነው መጓዝ ያለበት›› ሲሉ አንተ እና ዶ/ር መሠረት ደግሞ ‹‹መጀመሪያ የፕሬስ ነፃነቱ መቅደም አለበት›› ስትሉ ነበር።

ጋዜጠኞች ናችሁና ብዙ መረጃ አላችሁ። ለረዥም ጊዜያት አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ጨምሮ ‹‹አገሪቱ ላይ የቀሩት ሁለት ነፃ ጋዜጦች ናቸው›› ይሉ ነበር። አውራምባ ታይምስ ከተዘጋች በኋላ ደግሞ አንድ ጋዜጣ ብቻ መቅረቱን ተናግረዋል። አሁን ደግሞ ‹‹የቀረችው አንድ ጋዜጣ ተዘጋች›› ብለዋል፤ ፍትሕን። ስለዚህ መጀመሪያ የሚያስፈልገው ሚዲያው ነው። ካውንስሉ የሚያስፈልገው ሚዲያ ሲኖር ነው፤ ሚዲያ ከሌለ ደግሞ ካውንስሉ ምንም አይሠራም። ሚዲያ የሚኖረው ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ሲረጋገጥ በመሆኑ፣ መጀመሪያ መታገል ያለብን ሚዲያ እንዲኖር ነው። እናንተ የጋዜጣ ፍቃድ ተከልክላችኋል። ታዲያ እንዴት ስለ ካውንስል ይወራል? ማውራት ያለብን [ቆጣ ብሎ] ፍቃድ ስለ መከልከል/አለመከልከል ነው። ፍቃድ ተከልክለህ ካውንስሉ ምን ያደርግልሀል? ካውንስሉ የሚያያዘው ከሥራ ጋር ነው፤ ስትሠራ፣ ስታጠፋ ካውንስሉ ያስፈልጋል። ‹‹የዐይንህ ቀለም አላማረኝም›› ተብለህ ፍቃድ በምትከለከልበት አገር ላይ እንዴት ስለ ካውንስል እናወራለን? ካውንስሉ አያስፈልግም ሳይሆን በሁለተኛ ደረጃ የሚመጣ ነው። መጀመሪያ ሚዲያው በእግሩ መቆም አለበት። የእነ አማረ አረጋዊና የእነ ሚሚ ስብሐቱ የሚዲያ ካውንስል ዕቅድ ዝም ብሎ ተራ ቅዠት ነው። ዝም ብለው ድርጅት አቋቋምን ብለው መንፏለል ካልሆነ በስተቀር ግብዝነት ነው። እኔ አማረ አረጋዊን ከሚሚ ስብሐቱ ጋር አንድ ላይ ደርቤ አላየውም። አማረ የራሱ ፍላጎት ቢኖረውም፣ የራሱ ኤዲቶሪያል ነፃነት ያለው ጋዜጠኛ አለው። ሚሚን ግን እንደ ጋዜጠኛ ልወስዳት አልችልም፤ ጋዜጠኛ አይደለችምም። ‹‹ጋዜጠኛ አይደለሽም፤ አትችይም›› ተብላ የተባረረች ነች፤ እየሠራች ያለውንም የምታዩት ነገር ነው። ‹‹ካውንስል መሠረትን›› ብለው በየመድረኩ ለታይታ ለመቅረብ ካልሆነ በስተቀር የትም ሊደርስ እንደማይችል ከእኔ የበለጠ እነሱ ያውቁታል።

በአንድ ወቅት ላይ ከአንድ የመንግሥት ባለሥልጣን ጋር ፖርላማ ስብሰባ ላይ ተገናኝተን ስናወራ ‹‹ተመስገንን አስረን አናጀግነውም›› ብለውኝ የነበረ ቢሆንም ለስድስት ቀንም ቢሆን መታሰርህ አልቀረም። ታስረህ ‹‹መጀገን››፣ መሸለም እንደምትፈልግ፣ ለመታሠር ጉጉ እንደሆንክ የሚደመጡ አስተያየቶች አሉ። ምን መልስ አለህ?

ይሄ እንደ ሰውየው የማሰብ መጠን ይወሰናል። ሲ.ፒ.ጄ. ከሸለማቸው ሰዎች ውስጥ [ከዳዊት ውጪ ያሉት] አብዛኛዎቹ ታስረው የማያውቁ ናቸው፣ እስር ቤት ሆነው የተሸለሙ በጣም ጥቂቶች ናቸው። በሲ.ፒ.ጄ ለመሸለም ትልቁ መስፈርቱ በአምባገነን መንግሥት ውስጥ ሳትሸሽ፣ በድፍረት መሥራት ብቻ ነው እንጂ ‹‹መታሰር›› የሚል ቅድመ ሁኔታ የለውም። ምናልባት መታሰርን እንደ ሁለተኛ መስፈርት ሊወስዱት ይችላሉ። አቶ ሽመልስ ከማል አንተ [ኤልያስ] በጥያቄህ ላይ እንዳነሳኸው ሁሉ እኔንም ቢሯቸው ጠርተው ‹‹የዳዊት ሽልማት አማልሎህ ከሆነ በጣም ተሳሰተሃል›› ብለውኛል። ንግግራቸው እና ከንግግራቸው ጀርባ ያለው እውነታ የሚያሳየው ‹‹አሳሪ፣ ጨፍላቂ፣ ደምሳሽ ነን›› የሚል ነው እንጂ አንድ ጋዜጠኛን ጠርተህ ‹‹ለመታሰር ፈልገሃል›› የምትልበት ምንም ምክንያት የለም። ጋዜጠኛ ካጠፋ መታሰር አለበት። ወንጀል የሠራ ሰው መመከር ሳይሆን መታሰር ነው ያለበት። የአቶ ሽመልስ ንግግር የሚገልጸው እሳቸው የሚያገለግሉት ሥርዓት ምን ያህል ጨቋኝ፣ አፋኝና የነፃውን ፕሬስ ምኅዳር አጥባቢ መሆኑን ነው።

… ታስሬ ጀግና መሆን የምፈልገው መቼ ስፈታ ነው? ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ውሰደው! 18 ዓመት ተፈርዶበታል። ከእነዚህ ዓመታት በኋላ 60 ዓመት ሲሆነው [አሁን አርባ ሁለት ዓመቱ ነው] ወጥቶ የሚያገኘውን የጀግንነት ክብር ፈልጎ ይታሰራል? ‹‹የማገኘው ክብር አለ›› ብለህ መታሰር፣ ሕይወትህን ልትበላበት የምትችለው ቁማር ነው። አሁን 34 ዓመቴ ነው። 15 ዓመት ቢፈረድብኝ ከእስር ቤት የምወጣው በ50 ዓመቴ ነው። በዚያ 15 ዓመታት ውስጥ የማጣቸው ብዙ ነገሮች አሉ። የማገኘው ክብር ምንድን ነው? ሁሉንም ነገር ከዜሮና ከአዲስ ነው የምትጀምረው። አቶ ሽመልስ የሚያንፀባርቁት ነፍሳቸውን ይማረውና የሟች ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ጉልበታም ሐሳብ ነው። ይሄ የአምባገነኖች ባሕሪ ነው።

(ዘ-ሐበሻ ድረገጽን በየቀኑ በማንበብ ራስዎን በመረጃ ከሰው እኩል ያድርጉ)
በቃሊቲ የስድስት ቀን አክራሞትህ እነማንን አገኘህ? ምንስ ተማርክ?

የታሰርኩት የቀድሞ መንግሥት ባለሥልጣናት ታስረው በነበረበት ‹‹ዞን አራት›› ነው። ዋና ዋናዎቹ ተፈትተዋል፣ ጥቂት ሚኒስትሮች ነበሩ። ለምሳሌ የኢኮኖሚ እና የጡረታ ዋስትና ሚኒስትር የነበሩት ኮሚሽነር ገሠሠ ወልደኪዳን ነበሩ። ሻለቃ መላኩ ተፈራ [የጎንደር አስተዳዳሪ] እነ ሻምበል በጋሻው አታላይ [የወሎ አስተዳዳሪ] ነበሩ። በርካታ እስረኞች አሉ። ዶ/ር ተስፋዬ ብሩ፣ የአዋሽ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ለይኩን ነበሩ፤ ብዙ ብትቆይ ከእነሱ ብዙ ትማራለህ።

የቀድሞ የቤንሻንጉል ጉምዝ ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ያረጋል አይሸሹምን አግኝቻቸዋለሁ። ከእሳቸው የምትማረው ነገር አለ ብዬ አላስብም፤ ሙስናን ካልተማርክ በስተቀር። [ሳቁ መጣበት] ከብዙዎቹ ጋር አውርተናል፤ ግን ለጊዜው ባልገልጻቸው ጥሩ ነው። የእስር ዘመንና ሰቆቃቸውን ማበርታት ይሆናል። ብዙዎቹ ከእኔ ጋር የሚያወሩት ስለ ዕድርና ዕቁብ አይደለም። አስቀድመው የፖለቲካ ጋዜጣ አዘጋጅ መሆኔን ስላወቁ፣ ያወጋነው ፖለቲካዊ ወሬ ስለሆነ፣ ይሄንን መናገር አስቸጋሪ ነው።

‹‹ለምን እንዳሰሩኝ፣ ለምን እንደፈቱኝ›› አላውቅም ብለህ ከወጣህ በኋላ ጽፈሀል። ዞን 4 ተስማምቶህ ነበር እንዴ?

[ከሳቀ በኋላ] አይደለም። በጥፊ አጩዬህ ይቅርታ መጠየቅ የለብኝም። ሲጀመር መማታት የለብኝም። ዝም ብለህ ማንንም ሰው እየጠራህ፣ ከቤቱ እየወሰድክ፣ እስር ቤት እየከተትክ፣ የምትፈታበት ሁኔታ መቆም አለበት። መብቴ ሊከበር ይገባል። የተለቀቅኩት ስድስት ቀን ያለአግባብ ታስረሀል ተብዬ አይደል? ለዚህ ካሳ ማግኘት ነበረብኝ፤ መንግሥትም በይፋ ይቅርታ ሊጠይቀኝ ይገባ ነበር።

ዳግመኛ ወደ እስር ቤት የምትመለስ አይመስልህም? [ይህ ጥያቄ የቀረበለት በድጋሚ በዚህ ጉዳይ ከመከሰሱ በፊት ነበር።]

በዚህ ጉዳይ ተመልሼ እገባለሁ ብዬ አላስብም።

በድህረ መለስ ኢትዮጵያ ምን ገጽታ የሚኖራት ይመስልሀል? ለኢትዮጵያ የሚጠቅማት ማን እና ምንድን ነው ብለህስ ታስባለህ?

ከፋፍለን እንየው፣ መጀመሪያ ከእውነታው እንነሣ። ስገምት ‹‹ድህረ-መለስ›› አስቸጋሪ ሁኔታ ይኖረዋል ብዬ አስባለሁ። አራቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሥልጣን ሲይዙ ባልተመጣጠነ ጉልበት ነው። ሕወሃት አስኳል ነው። ወሳኝ ወሳኝ ነገሮችን ይዟል። የመሪነት ባሕሪ አለው። ልክ በደርግ ጊዜ ስትመጣ መፈክሩ ሁሉ ‹‹በጓድ መንግሥቱ ኃይለማርያም ማዕከላዊነቱ ኢሠፓን እንመሠርታለን…›› ነበር የሚሉት። ኢሕአዴግም ሲመሠረት በሕወሃት ማዕከላዊነት ነው። ከ1993 ከሕወሃት መሰንጠቅ በኋላ ግለሰብ (አቶ መለስ) ማዕከላዊ ሆነዋል። ይሄ ሁኔታ ጉዳቱን በግልጽ ያመጣዋል። በተለይ ደግሞ አማራንና ኦሮሞን የሚወክሉ ሁለት ድርጅቶች አሉ። ኦሕዴድ እና ብአዴን ወክለውት ወደ ግንባር የመጡት የሕዝብ ቁጥር አለ። ከፍተኛ ሥልጣን ይዞ የነበረው ሕወሃት ይዞ የመጣው የሕዝብ ቁጥር አለው። ምናልባት አሁን የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ ‹‹በቁመታችን ልክ ግንባሩ (ኢሕአዴግ) ውስጥ ቦታ ልናገኝ ይገባል።›› የሚል ጥያቄ ያነሣሉ ብዬ አስባለሁ። አሁን የሥልጣን ትግል (Power Struggle) ይፈጠራልም፤ ተፈጥሯልም። በተለይ ደግሞ በትግሉ ላይ ተቀራራቢ ዕድሜ ያስቆጠሩ ፓርቲዎች አሉ፤ ሕወሃትና ብአዴን። ኦሕዴድ ከ1981፣ ደኢሕዴን ከ1983 ወዲህ ስለሆኑ፣ በዚሁ ልክ ነው ግንባሩ ውስጥም የእኔነት ስሜትና የበላይነት ቁመት የሚኖራቸው። አሁን ያለው የድህረ መለስ ክፍፍል በብአዴንና በሕወሃት መካከል ከፍተኛ ትንቅንቅ ፈጥሯል። ይሄ ትንቅንቅ የቱ ጋር ሄዶ ሄዶ ያቆማል ሌላ ጉዳይ ነው። ወይ ደግሞ ትንቅንቁ ወደ አደባባይ በወጣ ጊዜ የሥርዓቱ መጨረሻ ይሆናል። ጉልበት መለካካቱ አይቀርም።

በምኞት ደረጃ የምትለኝ ከሆነ፣ መንግሥት ብሔራዊ ዕርቅ መፍጠር አለበት። ለደርግ ባለሥልጣናት የተሰጠው ምሕረት ጥሩ ነው። ኢሕአዴግ ብዙውን ጊዜ ፈልጎ፣ የተወሰነ ጊዜ ደግሞ በስሕተት በርካታ ዜጎችን አሰቀይሟል፣ አስኮርፏል፣ በድሏል፣ ለስደት ዳርጓል። እነዚያን ለማምጣት ዕርቁ ያስፈልጋል። ከፖለቲካ ፓርቲዎች [ኦነግ እና ግንቦት 7ን ጨምሮ] ጋር ምሕረት ነግሦ፣ ‹‹አሸባሪ›› ለሚሉት ምሕረት አውርደው፣ የምርጫ ጊዜ ከመድረሱ በፊት ሁሉም ፓርቲዎች ፓርላማውን አፍርሠው፣ በእኩል ምኅዳር፣ በእኩል የሚዲያ አጠቃቀም የሚወዳደሩበትን ዕድል መንግሥት ፈጥሮ፣ ምርጫ እንዲደረግ ቢያደርግ የተሻለ ነው ብዬ አስባለሁ።

ስለ አንገት ልብስዋ እናውራ። ፍትሕ ላይ ፎቶህን ለጥፈህ መጻፍ ከጀመርክበት ጊዜ ጀምሮ አንገትህ ላይ የምትታየው የአንገት ልብስ (Scarf ) በተለያየ አጋጣሚ ስናገኝህም ወልቃ ተመልክተን አናውቅም። አንተ ብቻ ሳትሆን ባልደረቦችህና የፍትሕ ቤተሰቦችም የአንገት ልብስ አይለያቸውም። የአንገት ልብስዋ መልዕክት ምንድን ነው?

ሻርፑ ራሱን የቻለ መልዕክት አለው።

ልትነግረን ትችላለህ?

ጊዜው ገና በመሆኑ አሁን ልናገረው አልችልም።

‹‹የአንገት ልብስ አብዮት›› የማስነሳት ዓላማ አላችሁ?

በአገራችን ላይ ማንም የማይፈቅድልን፣ ማንም የማይነሳን የፈለግነውን ሕጋዊ እንቅስቃሴ የማድረግ ሙሉ መብት አለን። ይሄ ጥያቄ ከላይኛው ጋር ስለሚያያዝ ለጥቂት ወራት ቢቆይ የተሻለ ነው ብዬ አስባለሁ። ነገር ግን፣ የአንገት ልብሱ ለብርድ ወይም ለጌጥ የሚደረግ አለመሆኑን መናገር እችላለሁ።

ከዚህ በኋላ በሌላ የፕሬስ ውጤት ትመለሳለህ?

CNNን እንደ ሞዴል ወስደን ከሰዎች ጋር በሽርክና ግዙፍ የሆነ የኦን ላይን ሚዲያ (ድረ-ገጽ) ለመመሥረት ብዙ መንገዶችን ተጉዘናል። አራት የኢትዮጵያ ክልሎች ላይ ቢሮዎች ይኖሩናል። የምንመለሰው በዚህ መንገድ ነው።

ከመሰናበታችን በፊት በኪስህ ስንት ብር እንደያዝክ ልታሳየን ትችላለህ?

አደጋ ይደርስብኛል፣ አንድ ነገር ያጋጥመኛል ብዬ ስለማስብ ከአምስት ሺህ ብር በታች አልይዝም። ብሩን ላሳያችሁ እችላለሁ፤ ግን አንድ ነገር ላይ መግባባት አለብን። [ሳቅ] ‹‹አበድረን›› የሚል ነገር አልፈልግም። [ስድስት ሺህ አራት መቶ (6,400) ብር የታሰረ፣ ሦስት ሺህ (3,000) ብር ያልታሰረ መያዙን ፊታችን ቆጥሮ አረጋግጠናል] የሥርዓቱ ባሕሪ በፈጠረው የተለያዩ ምክንያቶች ከቤቴ ስወጣ ቀና ነገር ይገጥመኛል ብዬ አስቤ አላውቅም። በተወሰነ መልኩ ገንዘብ ያስፈልጋል ብዬ አስባለሁ።

ጨርሰናል። ስለ አብሮ ቆይታችን ከልብ እናመሰግናለን። መልካሙን ሁሉ እንመኝልሀለን።

እኔም አመሰግናለሁ። በእውነቱ ብዙ ጊዜ መናገር የማልፈልጋቸውን ነገሮች እንድናገር ስትገፋፉኝ ስታስገድዱኝ ነበር፤ አስገድዳችሁኛልም። ‹‹Hard Talk›› እንደማለት ነው። ቢሆንም እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ጨለማ በነገሠባቸው አገራት፣ ሕዝብ እንዲያውቅ የመረጣችሁበት መንገድ በእጅጉ የሚያስመሰግን እና ፈር ቀዳጅ ነው ብዬ አስባለሁ።

Sport: ቬንገር በማባረር አልተቻሉም

0
0

በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ የሐምሌ እትም ቁጥር 53 ላይ ታትሞ የወጣ።

Arsene-wenger (1)ከባድ ሸክም ከአርሰን ቬንገር ትከሻ ተነሳ፡፡ በጣም ከባድ፤ ለዚያውም የ10 ሚሊዮን ፓውንድ ሸክም፡፡ ሴባስቲያን ስኩዊላቺ፣ ዴኒልሰን እና አንድሬ አርሻቪን ያለምንም ጥቅም ክለቡን በደመወዝ መልክ በዓመቱ በድምሩ 10 ሚሊዮን ፓውንድ ሲያስወጡ ኖረዋል፡፡ አሁን የአርሰናል ንብረት አይደሉም፡፡ ይህም ለደጋፊዎች መልካም ዜና ነው፡፡ ሆኖም ወሬው በእርግጥም መልካም እንዲሆን አሰልጣኙ 10 ሚሊዮን ፓውንድን መልሰው ለቡድኑ ማጠናከሪያ ሊያደርጉ ይገባል፡፡ ፈረንሳዊው ከዚህ ቀደም እንደሚያደርጉት የተሸረፈ እና የተቆጠበውን ገንዘብ ለማይወደደው የክለቡ ቦርድ አሳልፈው ከሰጡ የተጨዋቾቹ ሽያጭ የፈጠረው ደስታ ከደጋፊዎቹ ጋር አይቆይም፡፡

ይሁን እንጂ አርሰናል ለዓመታት ያለአግባብ ታቅፎ የያዛቸውን እና ላልተገባ የደመወዝ ወጪ የዳረጉትን ተጨዋቾች መሸኘት መጀመሩ እንደበጎ ጅምር ተወስዶለታል፡፡ በተለይ አሰልጣኙ እነዚህን ሂያጆች በአዳዲስ እና በተሻሉ ተጨዋቾች ካልተተኩ እርምጃቸው ሙሉ አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ቬንገር ተጫዋቾችን ለመሸጥ ወይም በነፃ ለመልቀቅ አዲስ አይደሉም፡፡ ሆኖም ሰውዬው ምርጥ ተጫዋቾቻቸውን ከሸኙ በኋላ ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ያሉ ከዋክብትን ለመተካት ሲቸገሩ ኖረዋል፡፡ ለዓመታትም በተመሳሳይ መልኩ ተጉዘዋል፡፡

ቬንገር ዴኒልሰን ትቶት የሄደውን 50 ሺ ፓውንድ ሳምንታዊ ደመወዝ እንዲሁም የስኩዊላቺን 60 ሺ ፓውንድ እና የአርሻቪንን 85 ሺ ፓውንድ ተቀብለው አርሰናልን መጥቀም የሚችሉ ጥሩ ጥሩ ተጨዋቾች ማምጣት ይችላሉ፡፡ የዝውውር ሂሳቡን ትተን ስለደመወዝ ብቻ ካወራ አሰልጣኙ የሶስቱን ተሰናባቾች ገንዘብ ተጠቅመው ሁለት ትልልቅ ስም ያላቸው ተጨዋቾችን በ90 ሺ ፓውንድ ሳምንታዊ ደመወዝ ሊያስፈርሙ እድል ይፈጥርላቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ትልቅ ተጨዋች እና ሁለት ሌሎች የቡድኑን ጥልቀት እና ጥራት ከፍ የሚያደርጉ ከዋክብትን ደመወዝ ቀጥ አድርጎ ይይዝላቸዋል፡፡

አርሰን የማይጠቀሙባቸውን ተጨዋቾች መሸኘታቸው እና በሌሎች መተካታቸውን በጀታቸውን በተሻለ መንገድ እንዲጠቀሙ ከማድረጉም ሌላ የቡድናቸውን ጥራት በትልቁ ያሳድግላቸዋል፡፡ ቬንገር በግብ ጠባቂ ቦታ ወጣቶችን ቢይዙም አንዳቸውም በደጋፊዎች እምነት የሚጣልባቸው አልሆኑም፡፡ በኢምሬትስ ከቮይቾች ቼዝኒ እና ሉካስ ፋቢያንስኪ በመቀጠል የቡድኑ ሶስተኛ ግብ ጠባቂ የነበረው ቪቶ ማኖኔ ወደ ሰንደርላንድ ሲያመራ የተሸጠበት ዋጋ ይፋ ባይሆንም አርሰናል 2 ሚሊዮን ፓውንድ ሳያገኝበት እንዳልቀረ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ መድፈኞቹ በንፅፅር ወጣት የሚባልን የ25 ዓመት በረኛ ቢያጡም የጣልያናዊው ክለቡን መልቀቅ ለሌላ ልምድ ያለው ግብ ጠባቂ በር መክፈቱ እርግጥ ይመስላል፡፡ በተለይ ከአርሰናል ጋር ድርድር ላይ መሆኑ የሚነገርለት ዡሊዮ ሲዛር ክለቡን ከተቀላቀለ ለሌሎቹ ሁለት ወጣት ፖላንዳዊያን ጥሩ ልምድ ሊያካፋል እና ቡድኑንም ወደ ውጤት ሊያመራ ይችላል፡፡

ሌላኛው የክለቡ ተሰናባች በኤምሬትስ ረጅም ጊዜ የቆየው ዮሀን ዡሩ ነው፡፡ ስዊዘርላንዳዊው ተከላካይ በተለይ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ከሁለት የካፒታል ዋን ግጥሚያዎች ውጪ በቋሚነት የጀመረው ግጥሚያ የለም፡፡ በጃንዋሪ ወደ ጀርመኑ ሆኖቨር በውሰት አቅንቶ 16 ጨዋታዎች ካደረገ በኋላ ክለቡ ዝውውሩን ቋሚ ለማድረግ ፍላጎት አሳይቷል፡፡ ሆኖም የ26 ዓመቱ ዡሩ ከሀኖቨር ይልቅ የክለቡን ተፎካካሪ ሀምቡርግን መቀላቀል የመረጠ ሲሆን አዲሱ ክለቡም አሁን ዝውውሩ በውሰት ውል ተይዞ በውድድር ዘመኑ መጨረሻ በቋሚነት ሊገዛው እንደሚችል ተስማምቷል፡፡ ይህም በመሀል ተከላካይ ቦታ የስዋንሲውን አሽሊ ዊልያምስ ለማስፈረም ያለውን ፍላጎት ያጠናከርለታል፡፡

የ2012/13 የውድድር ዘመንን በውሰት ውል በጁቬንቱስ ያሳለፈው ኒክላስ ቤንድትነርም በኤምሬትስ እህል ውሃው አልቋል፡፡ በገዛ ፈቃዱ ወደ አርሰናል እንደማይመለስ በትዕቢት ሲናገር የቆየውን ዴንማርካዊ ደጋፊዎቹ ማየት አይሹም፡፡ ባለፉት ቀናት በወጡ መረጃዎች መሰረት የጀርመኑ ኢንትራክት ፍራንክፈርት በግዙፉ አጥቂ ላይ ያለውን ፍላጎት አጠናክሯል፡፡ የተጫዋቹ ወኪል ቶም ብሩክስም ‹‹አሁን ብዙ ባልናገር እመርጣለሁ፡፡ ሆኖም ዝውውሩ በቀናት ውስጥ እውን እንደሚሆን ተስፋ አለኝ›› ሲል ጉዳዩ እያለቀ መሆኑን አብራርቷል፡፡

ቬንገር ለወቀሳ ያደረገው ሌላኛው የቅርብ ጊዜ ግዢ ፖርክ ቹ ያንግ ኤምሬትስን እስከመጨረሻው የመሰናበቱ ነገር እርግጥ ይመስላል፡፡ ባለፈው ሳምንት በወጡ መረጃዎች መሰረት ክለቡ በደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ የዜግነት ግዴታውን እየተወጣ ያለውን ተጨዋች ሊሸኝ ወስኗል፡፡ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በውሰት ለሴልታቪጎ የተሰጠው እና በአርሰናል የሁለት ዓመት ቆይታው በሊግ ካፕ ቦልተን ላይ የተቆጠረችን አንድ ጎል ብቻ ያስመዘገበው እስያዊ አርሰናልን ለኪሳራ ቢዳርግም በደመወዝ መልክ ሊወጣበት ይችል የነበረውን 5.5 ሚሊዮን ፓውንድ ያድናል፡፡ በዚህ ሀሳብ የተስማሙ የሚመስሉት የቆረጡ መስለዋል፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ተሰናባቾች በተጨማሪ በክለቡ እንዲቆይ የማይፈለገው አንድሬ ሳንቶስም በቡድኑ የሚሰነብትበት ምክንያት የለም፡፡ በጁን አጋማሽ በውሰት ከቆየበት ሀገሩ ብራዚል ሲመለስ ቅር መሰኘቱን በይፋ የገለፀው ፉልባክ ምናልባትም ወደ ቱርክ ሊጓዝ እንደሚችል ተነግሯል፡፡

ሳንቶስ በ2011 6 ሚሊዮን ፓውንድ ወጥቶበት ከፌኔርባህቼ ከመጣ በኋላ ለክለቡ 25 ጨዋታዎች ቢያደርግም በደጋፊዎቹ ልብ የሚያቆየው መልካም ትዝታ አላተረፈም፡፡ በእርግጥም ሳንቶስ ከአርሰናል በውሰት ከመልቀቁም በላይ በብራዚል ለግማሽ የውድድር ዘመን የቆየው ግሬሚዩም ተጨዋቹን ለማስፈረም ብቁ ነው ብሎ አለመመልከቱ ተከላካዩ በጭራሽ ለእንግሊዙ ክለብ እንደማይመጥን ይጠቁማል፡፡ አሁንም በዝውውር ገበያው ሳንቶስ ፈላጊ ማጣቱ ቬንገርን ቅር አሰኝቷል፡፡

እነዚህ ተጨዋቾች አርሰናልን ምን ያህል እንደጎዱት መመልከት ከባድ አይደለም፡፡ ሆኖም አሰልጣኙ የማይጠቀሙባቸውን እና የተጠቀሱትን ተጨዋቾች ጨርሰው ከሸኙ እንዲሁም ከሰሞኑ ሌሎቹን እንደተጠበቁ ያልሆኑ ሁለት ተጨዋቾች (ማርዋን ሻማክ እና ዠርቪንሆ) ሸጠው ገንዘብ ካገኙ ትልቅ ስራ እንደሰሩ ይቆጠርላቸዋል፡፡

እንደ እንግሊዙ ዴይሊ ሜይል ዘገባ ከሆነ የስፔኑ ክለብ ሌቫንቴ ሞሮኳዊውን ለመግዛት 1 ሚሊዮን ፓውንድ ለመክፈል ፈቃደኛ ነው፡፡ በ2010 ከቦርዶ በነፃ አርሰናልን የተቀላቀለው አጥቂ በመጀመሪያዎቹ አራት ወራት 10 ጎሎች አስቆጥሮ ተስፋ ቢያጭርም በቀጣዮቹ ጊዜያት ችሎታውን ብቻ ሳይሆን በራስ መተማመኑንም ጨርሶ አጥቶታል፡፡ ተጨዋቹ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በውሰት ውል ለዌስትሀም ቢጫወትም ምንም ተፅዕኖ መፍጠር ሳይችል ወደ ኢምሬትስ ተመልሷል፡፡ የሻማክን የሌቫንቴ ዝውውር ሊያደናቅፍ የሚችለው በአርሰናል ሊያገኘው የነበረው 65 ሺ ፓውንድ ሳምንዊ ደመወዝ ቢሆንም አጥቂው ደመወዙን ለመቀነስ የሚስማማበት እድል አለው፡፡

የአርሰናል ደጋፊዎች በቅርቡ ሰምተው ከተደሰቱባቸው ዜናዎች መካከል የዠርቪንሆ በማርሴይ መፈለግ ይገኝበታል፡፡ የፈረንሳዩ ክለብ ኮትዲቯራዊውን ቀድሞ ይጫወትበት ወደነበረው ሊግ ሊመልሰው ተዘጋጅቷል፡፡ ዠርቪንሆ በ2011 ከሊል ከመጣ በኋላ በአርሰናል ወጥ የሆነ አሳማኝ ብቃት ማሳየት እና ተመልካቾቹን ማሳን አቅቶታል፡፡ አርሰናል ከሁለት ዓመት በፊት 11 ሚሊዮን ፓውንድ የከፈለበት እና በ63 ጨዋታዎች 11 ጎሎች ያስቆጠረለትን አፍሪካዊ በኪሳራ ሊያጣው ፍላጎት ያለው ይመስላል፡፡

የ26 ዓመቱ ተጨዋች ከማርሴይ በተጨማሪ በቱርኩ ፌኔርባህቼ ቢፈለግም የፈረንሳዩ ክለብ ከሰሜን ለንደኑ ክለብ ጋር ድርድር ለመጀመር ቅድሚያውን ወስዷል፡፡

አርሰናል በክረምቱ ከዡሩ፣ ስኩዊላቺ፣ አርሻቪን፣ ዴኒልሰን እና ማኖኒ በተጨማሪ ቤንድትነር፣ ሻማክ፣ ፓርክ፣ ሳንቶስ፣ ባካሪ ሳኛ እና ፋቢያንስኪን ካሰናበተ በየሳምንቱ ወደ 700 ሺ ፓውንድ የሚጠጋ የደመወዝ ወጪ ያድናል፡፡ ይህ በዓመት ወደ 31 ሚሊዮን ፓውንድ ይጠጋል፡፡ ይህ ገንዘብ በአቡኑ የዌይን ሩኒ የማንቸስተር ዩናይትድ ደመወዝ እርሱን መሰል ሶስት ትልልቅ ተጨዋቾችን የዓመት ደመወዝ ይከፍላል፡፡ ተጨዋቾቹ መጠነኛ በሚባል ገንዘብ ቢሸጡ ደግሞ በግምት በድምሩ እስከ 28 ሚሊዮን ፓውንድ ያስገኛሉ፡፡ ይህ ገንዘብ ሩኒን ለመግዛት በቂ ሊሆን ይችላል፡፡ በአጠቃላይ የሽያጩ እና የደመወዝ መጪው ለአርሰናል ሶስት ወይም ትልልቅ ተጨዋቾችን ገዝቶ ክለቡን ለዋንጫ እንዲፎካከር ያስችላል፡፡

የእንግሊዝ ጋዜጦች ቬንገር ለዝውውር 70 ሚሊዮን ፓውንድ እንደተፈቀደላቸው መዘገባቸውን ቀጥለዋል፡፡ ባለፉት ዓመታትም እንደዚሁ አርሰናል የተሻለ የዝውውር ገበያ እንደሚያሳልፍ እየተነገረ በዋዛ ያለፉ ጊዜያት ነበሩ፡፡ በእርግጥም ሰውየው የተባለው በጀት ካላቸው እና የማይጠቅሙ ተጨዋቾቻቸውን ሸኝተው ገንዘብ ማትረፍ ከቻሉ አርሰናልን ወደ አደገኛ ተፎካካሪነት ለመለወጥ አቅም ያገኛሉ፡፡

ሆኖም አርሰናል ተጨባጭ የገንዘብ ምንጭ አለው፡፡ ከፑማ ጋር ለአምስት ዓመት ከተፈራረመው ሪከርድ የትጥቅ ማቅረብ ስፖንሰርሺፕ ውል 170 ሚሊዮን ፓውንድ የሚያገኝ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 20 ሚሊዮን ፓውንዱ በቅድሚያ ተከፍሎታል፡፡ በተጨማሪም ከኢምሬትስ አየር መንገድ ጋር ለአምስት ዓመት የፈረመው 150 ሚሊዮን ፓውንድ ትልቅ ገንዘብ አስገኝቶለታል፡፡ የስታዲየሙ ግንባታ ዕዳ በእጅጉ መቀነሱ ከግምት ሲገባ ቬንገር ለዝውውር በቂ ገንዘብ እንዳገኘ መገመት አሳማኝ ነው፡፡

ጋዜጦች ስለሚያወሩት የ70 ሚሊዮን ፓውንድ በጀት ማረጋገጫ ባይገኝ እንኳን ክለቡ ከተጨዋቾች ሽያጭ 28 ሚሊዮን ፓውንድ እና ከፑማ ቅድመ ክፍያ 20 ሚሊዮን ፓውንድ መቀበሉን ለተመለከተ በዚህ ክረምት ቢያንስ ቬንገር የዚህን ገንዘብ ድምር እንደሚያወጡ መጠበቅ ስህተት የለውም፡፡

 

የለሊት ወፍን ማን ገደላት? – (ከደራሲና ገጣሚ መኳንንት ታዬ)

0
0

ሚኒሶታ

በአንድ ወቅት  የምድር አራዊትና የሰማይ አእዋፋት  ወገን ለወገንህ ተባባሉና  ሁሉም ከእያሉበት  ተጠራርተው  ሲያበቁ  በአንድ ችግር ላይ መወያት  ጀመሩ። ይኸውም በአራዊቱ  እና በአኢዋፍቱ ዘንድ ችግር እንዳለና  እራሳቸውንም  ማስከበር እንዳለባቸው ይመክሩ ጀመር ። በአእዋፋቱ ዘንድም አራዊቱ ዘንድ ችግር እንዳለ እና ደኑን ተማምነው  ያልተገባ ነገር እያደረጉ እንደሆነ እንደሚጠራጠሩ ለዚህ ደሞ መፍትሄው  ጦርነት ብቻ እንደሆነ  እየተነጋገሩ እያሉ የለሊት ወፍ መጣች። ሁሉም በድንጋጤ  ቢያያትም ቅሉ የማን ወገን ናት  በሚል መልኩ እርስ በእርሳቸው ቢተያዩም  ደፍሮ ግን  ሊጠይቃት የወደደ ግን ስላልነበር  እርሷም የማንነቷን  ገልፃ አልተናገረችም። ብቻ ግን አንድ ነገር አስባለች፤ ጦርነቱ ሲጀመር  ብዙም  ወደሰማይ ከፍ ሳትል  ብዙም  ወደ መሬት  ሳትቀርብ  በረራዋን ለማድረግ።

nightbird2ይሁን እና  በዚህ መሃል ጉባዬው ጋር ለመገኘት የረፈደባቸው ይቅርታ እየጠየቁና ያጋጣማቸውን እየነገሩ ተቀላቀሉ። የእለቱ ፀሃይ በጣም የሚያቃጥል  ቢሆንም  ከህልውና የሚበልጥ የለም በሚል ይመስላል  በሁለቱም ወገን  ምክከሩ  የአሰላለፍ አካሄዱ የ እለቱን  ውሎ በሚመለከት ተነጋገሩ። ከአእዋፍ ወገን ፤ እነ- እርግብ ፤ እነ-ንስር  ፤እነ -ጥንብ አንሳ  እነ- አሞራ ብቻ  ሁሉም ከያሉበት ተጠራርተው የመገናኘታቸውን ያህልም ፤ ጦሩን ማን ይምራ የሚለውም ነገር  ብዙ ካነታረካቸው በሓላ፤ በስተመጨረሻ ንስር የጦሩ መሪ ሊሆን ተማምለው ባሉበት  ሠኦት ፤ የለሊት ወፍ  ፈንጠር ብላ ተቀምጣ ነበርና ፤”አንቺ የማን ወገን ነሽ?ሲል ንስር በቁጣ ቃል ጥያቄ አቀረበላት። እርሷም ፈጠን ብላ “ምን ጥያቄ አለው  ክንፌን ስታይ የማን እመስልሃለው ብላ ጥያቄውን በጥያቄ መለሰችለት። በዚህ ሁኔታ እያሉ የአራዊቱን አሰላለፍ ማን ይሰልል እያሉ አእዋፋቱ ሲነጋገሩ ይህቺው የለሊት ወፍ “እኔ ብሄድስ? ምክንያቱም  ጡት ስላለኝ  አጥቢ ናት  እና ከእኛ ወገን  ነች ብለው  ስለሚያስቡ ያለውን ነገር ሁሉ በሚገባ አጤነዋለው” ብላ እንደጨረሰች  የሁሉም  ሃሳብ አንድ ሆነና  የለሊት ወፍ ተላከች።

እዛም እንደደረሠች  አራዊቱ በመልክ በመልክ ተሰብስበው ይወያያሉ። ሁሉም አሉ፤ አንበሳ ፤ ነብር አያጅቦ፤ ተኩላ  እነ ዝሆን  ብቻ አራዊቱ ወገን የቀረም የለ። ይሁንና በውይይታቸው መሃል እንዳሉ የለሊት ወፍ  ደረሰች ። ሁሉም አፈጠጡ፤ አንበሳ ነበርና  የጦሩ አበጋዝ “ምን ፈለግሽ?’’ ሲል አፈጠጠባት። የለሊት ወፍም  ምንም እንዳልተፈጠረ በመቁጠር ለማርፈዷ ይቅርታ ጠይቃ  ለመቀላቀል ስትሞክር አንበሳ ጠንከር ባለ ንግግር “የማን ወገን ነሽ?” ሲል አፈጠጠባት። የለሊት ወፍም ፈጠን ብላ ምን ጥያቄ አለው !

ከአራዊቱ ወገን ለመሆኔ ጡቴን ማየት ብቻ አየበቃም? ስትል በማፍጠጥ በመመለሷ ሁሉም በይሁንታ ተቀብሉዋት።  ስለሚያደርጉት ጦርነት እና  የቦታ አያያዝ ብሎም ማን ፊት አውራሪ  እንደሚሆን እና  ማን ጦር መሳሪያ  አቀባይ  እንደሚሆን  ፕላኑን  አውጥተው ከጨረሱ በሓላ ፤ አንበሳ ወደ ለሊት ወፍ ዞር ብሎ ፡አጅሪት እስቲ ሂጅና ያለውን ነገር ሰልለሽ ያላቸውን ሃይልና እና  የታጠቁትን የጦር መሳሪያ አይነቱን ንገሪን አላት። መላኩ  ያስደሰታት የለሊት ወፍ  ስትበር ሄዳ ‘የአራዊቱን አቅም ምን ያህል ደካማና በአሰላለፍም ከኣኢዋፍቱ  እንደማይበልጡ አፏን እያጣፈጠች  ነገረቻቸው። በሁኔታው የተደሰቱት አእዋፍቱም  በፍጥነት ጦርነቱን ቢጀምሩ አራዊቱ ካለቸው ብቃት ማነስ ጋር ተጨምሮ በድንጋጤ ሊረበደበዱ እንደሚችሉ ነግራ ፤ ለመጀመር እየተዘጋጁ ባሉበት ሰዐት ለፊት አውራሪው ንስር ጠጋ ብላ “ምንም እንኳን ሁኔታው ባይመችም ቅሉ ጦርነቱ ባሸናፊነት እንዲወጡ እርሷ  ለአስር ደቂቃ  ፀሎት አድርጋ መምጣት እንደምትፈልግ አሳምናው በራ  ወደ አራዊቱ ዘንድ በመሄድ ለእነኛ የነገረቻቸውን  ሁሉ ለእነዚህም  ነግራ ጦርነቱን አስጀመረች። በሁለቱም ወገን ከባድ ውጊያ ሆነ። የለሊት ወፍም ከፍ ብላ በበረረች ግዜ ኣኢዋፍቱን በርቱ እንጂ መጠቃታችን ነው ስትል ዝቅ ብላ አራዊቱን በርቱ እንጂ መጠቃታችን ነው፤ እያለች ቀኑን ስታዋጋ ዋለች። ከሁለቱም በኩል በጣም ብዙ ሰራዊት ወደቀ። ሬሳ በሬሳ ላይ ተደራረበ። የሚገርመው በእለቱ ከሁለቱም ወገን የጦርነቱ ሚስጠር ያልገባቸው እንዲሁ በየወገንህ ሲባል ብቻ ሰምተው የተሰለፉም ነበሩበት። ባላወቁትም  የሞት ሰለባ ሆኑ። ግና በዚህ ሁሉ ምሀል ስትሽሎኮለክ  የነበረችው የለሊት ወፍ  የምታደርገውን ንስር ከሩቅ ሆኖ ይመለከት ነበርና ሳታስበው አደጋ ጥሎ ከሙታን ጋር ቀላለቀላት።

በዚህ ሁሉ መሃል አንበሳ በድንገት  ዞር ብሎ ቢያይ   የለሊት ወፍ  የለችም። ከሓላው ይከተለው ለነበረው ወታደር በቁጣ “የለሊት ወፍ የታለች ?” ብሎ ጠየቀው። ወታደሩም ፈጠን ብሎ ከንስር በተጣለ ቦንብ ስትጋይ አይቻታለሁ አለ።” ለነገሩ እኔም ላጋያት ነበር የፈለኳት ብሎ ጦርነቱ እየመራ ቀጠለ። በዚህ ሁኔታ ሆዱን መሸከም ያቃተው አያ ጅቦ ከሞቱት ወገኖች መሃል የሞተውን  (እርሙን) ሊበላ ወደሓላ ቀረ። ከአእዋፍቱም ወገን እንዲሁ እነ ጥንብ አንሳ ሆን ብሎ እጁን በመስጠት ከተማረከ በሓላ የሞተውን መብላት ጀመረ። በስተመጨረሻ ጦርነቱን የሰሙት  የቤት  እንሰሳት  በገላጋይነት በመግባት “ለሊቱን  ለአራዊት  ቀኑን  ለአእዋፋት” ብሎ አምላካችሁ ከፍሎ ሰጥቶአችሁ እያለ ውጊያው ምንን በተመለከተ ነው? ሲሉ በዝርዘር የውጊያው አላስፈላጊነት አስረዱአቸው። በሆነውም ከልብ እንዳዙኑ ገልፀው ሁሉን አሳምነው ሲያበቁ በጦርነቱ ወቅት ችግር ፈጣሪ እና ታማኝታቸውን በአቅም ማጣት ምክንያት  እና በመምሰል ለመሆን  የሞከሩትን ጦር ወንወጀለኞች፤ እንደ ለሊት ወፍ ያለው  ከሁለቱም ወገን እንዳትገባ፤ ጥንብ አንሳና ጅብ ዜግነታቸው ተነጥቆ በቁም አስር እንዲቆዩ ተወስኖ፤ ከእንግዲህ የሰላም አገር መስርተው ሊኖሩና የጋራ ጠላታቸውን በጋራ  እንደሚከላከሉ ተስማምተው ሊስታርቋቸው የመጡትንም አመስገኑ::

በስተመጨረሻም ለአስታሪቀነት ከመጡት አንዷ እመት በግ ተነስታ “እስቲ የጦርነቱን መንስሄ ከሁለቱም ወገን ብታስረ ዱን“ ስትል ሁሉንም አይን አይናቸውን እያየች ጠየቀች። በሁለቱም ወገን ይሄ ነው ብሎ ምክንያት የሚሰጣት በመጥፋቱ አፍረው አንገታቸውን በደፉበት ግዜ አሞራ ከሩቅ ሆኖ”መሳሪያ ሻጮች ናቸው የሚያጣሉን” ሲል ሁሉም በምክንያቱ ተገርመው ሳቁ። በግም በነገሩ ተገርማ  ስታበቃ ”ይገርማል የሚያፈስ ጣራ ያላት ሃገር ይዘን ብዙ ግዜ የምንጣላው ለአጥር በሚሆን እንጨት በሚደረገው  ፍለጋ ስለሆነ ነው። ነገር ግን መጀመሪያ መቅደም የነበረበት ጣራን መሸፈን ነው ወይስ አጥር? ብላ ሁሉንም አፍጣ ጠየቀች። ሁሉም በአንድነት አሱማ ጣራ ይቀድማል አሉ። አዎ አንዲህ ስላችሁ አጥር አትጠሩ ማለቴ ሳይሆን ከጦርነት በፊት ለምን የሚል ቃልና ትርፉስ የሚለውን አስተሳሰብ አትርሱ። በማለት የእለቱን የማስታረቂያ ንግግር ስታደርግ ሁሉም ተመስጠው በመስማት አድንቀው ሲያበቁ ከዚህ በሓላ ስለሁሉም በማሰብ ስልጣኔን አየር እየዛቁ ለሃገር ለወገን በሚሆን ነገር ላይ በማተኮር ዘመናቸውን እንደሚኖሩ ተነጋግረው  ተሳስመው ተለያዩ።

ቸር እንሰብትS

 


የረመዳን ፆም

0
0

(በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 53 ላይ ታትሞ የወጣ፤ ሚኒሶታ)

በዓለማችን ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው እምነቶችና ኃይማኖቶች የመገኘታቸው ነገር እሙን ቢሆንም ካላቸው የረዥም ዓመታት ታሪክ፣ ወግ፣ ስርዓትና ባህል አኳያ ኢስላም (እስልምና)፣ ክርስትናና የአይሁድ እምነቶች በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህ እምነቶች፡-

በተለምዶ ሰማያዊ ሃይማኖቶች ወይም ዋና መሰረተ ምንጫቸው ከሰማይ መለኮታዊ ኃይል ነው የሚባሉ እምነቶች ናቸው፡፡ በእርግጥም ይህን ዘልማዳዊ አነጋገር ከእውነታው ጋር ሲነፃፀር በእውነትም ሰማያዊ እምነቶች (ሃይማኖቶች) እንደሆኑ በቀላሉ ለማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ሃይማኖቶቹ ለፈጣሪያቸው አልያም ለአምላካቸው ቅንነታቸውንና ታዛዥነታቸውን የሚገልፁበት የተለያዩ አምልኮታዊ ተግባራት ያላቸው ከመሆኑ ባሻገር እነዚህ አምልኮታዊ ተግባራት በምን መልኩ እንደሚፈፀሙ የሚያመላክት የየራሳቸው የሆነ ሰማያዊ መመሪያዎች አላቸው፡፡ ይህ ሰማያዊ መመሪያቸው በሚያመለክተው መሰረትም የአምልኮ ተግባራቸውን ይፈጽማሉ፡፡

ለዛሬ እንደ ርዕስ የያዝነው በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞች እየፈፀሟቸው ከሚገኙት የአምልኮ ተግባራት መካከል አንዱ ስለ ሆነው የረመዳን ፆም አንዳንድ ነገሮችን ለማንሳት ነው፡፡

 

remedan kerim ethiopiaየፆም ትርጓሜ በኢስላም ሃይማኖት

በኢስላማዊው የስነ ቃላት ትርጓሜ መሰረት ፆም ማለት ጎህ ከቀደደበት ጊዜ አንስቶ ፀሐይ እስከምትጠልቅበት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ከምግብ፣ ከመጠጥ፣ ከወሲባዊ ፍላጎት እና ከሌሎች መሰል ድርጊቶች በልበ ውሳኔ ተነሳሽነት ከአላህ ዘንድ ምንዳ አገኛለሁ በሚል እምነት መታቀብ (መከልከል) ማለት ነው፡፡

በእስልምና ሃይማኖት የተለያዩ የፆም አይነቶች ያሉ ሲሆን እነዚህ የተለያዩ የፆም አይነቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

ሀ. ግዴታ የሆኑ ፆሞች

ለ. ግዴታ ያልሆኑና በፍላጎት የሚፆሙ ፆሞች

- ክልክል የሆኑ ጾሞች

ፆም የሚሰጣቸውም ጠቀሜታዎች እንደሚከተለው በአጭሩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡

ሀ. በመንፈሳዊ ጠቀሜታዎች

1. በልቦና ውስጥ የአላህ ፍራቻ እንዲሰርፅ ከማድረጉ ሌላ ህሊና ወደር የማይገኝለትን የውስጣዊ ደስታ እንዲቀዳጅ ያደርጋል፡፡

2. ትዕግስትን ሲያላብስ፣ ፍላጎትን ያጠነክራል፡፡

3. ማንኛውም ሰው በማናቸውም ክስተቶችና ሁኔታዎች ውስጥ ራሱን እንዲቆጣጠር በማድረጉ ሂደት ፆም ከፍተኛውን ሚና ይጫወታል፡፡

4. ፆም የሰው ልጅ ህይወት ስርዓት ባለው መልኩ እንዲጓዝ ያደርጋል፡፡

5. ፆም አዕምሮ ለትንሽ ጊዜያትም ቢሆን ስለ መልካም ነገሮች እንዲያስታውስ ብሎም የሰው ልጆች አላህን አስበው እንዲፈሩና ቅን ታዛዥ እንዲሆኑ መንፈሳዊ ስልጠናን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ይሰጣል፡፡

6. ፆም አንደበትንና መላ አካላትን እንዲሁም ስጋዊ ስሜትን በማድከም ሰዎች ለሰይጣን (ዲያቢሎስ) ታዛዥ እንዳይሆኑ ስለሚከለክል ሰዎች መልካምና ቀጥታውን የኢስላም መንገድ እንዲከተሉና ከትንሣኤ በኋላ ባለው ዘልዓለማዊ ህይወት ተደሳች እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡

ለ. ማህበራዊ ጠቀሜታዎች

1. ፆም ሙስሊሞች በአንድነት አንድ ወጥ ለሆነ ስርዓት ተገዢ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡

2. በሰዎች መካከል ፍትህና እኩልነት እንዲሰፍን ይረዳል፡፡

3. ማንኛውም ሙስሊም በመልካም ስነ ምግባር የታነፀና ለሌሎች ሰዎች አርአያነት ያለው ሰው እንዲሆን በማድረጉ በኩል ፆም ከፍተኛውን ሚና ይጫወታል፡፡

4. ፆም ማንኛውንም ባለሀብት አላህ የገለሰውንና የቸረውን ሀብቶች በይበልጥ የሚያስታውስበት ልዩ አጋጣሚ ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር የተቸገሩ ወገኖቹን በማስታወስና ህመማቸውን በጋራ በመቅመስ ከጎናቸው እንዲቆም ይረዳል፡፡

ሐ. በጤና መስክ የሚሰጠው ጠቀሜታ

1. ፆም የስኳር ህመምን በመከላከሉ ረገድ የሚሰጠው ጠቀሜታ፡-

ሰውነታችን በተመጣጣኝ ሁኔታ ከሚፈልጋቸው ንጥረ ነገሮች መካከል ስኳር አንዱ ነው፡፡ ሰውነታችን የሚፈልገውን ይህን ስኳር በሚፈለገው መጠን ተዘጋጅቶ በተመጣጠነ ሁኔታ የሚቀርበው በጉበት አማካኝነት ነው፡፡

የስኳር ክምችት መጠኑ ከሚፈለገው በላይ ከሆነ በጤንነት ላይ ችግር ይፈጥራል፡፡ ስለዚህ የጤና ችግር እንዳይፈጠር በፆም ምክንያት የተከማቸው ስኳር በደም ውስጥ በመቀላቀል ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ስለ ሚሰራጭ፣ ፆም የስኳር ክምችት በጤናነት ላይ ከሚያደርሰው የጤና መታወክ ይታደጋል፡፡

2. የልብን ጤንነት በመጠበቁ ረገድ፡-

የጤነኛ ሰው ልብ ምት ከ70-80 በደቂቃ ያመለክታሉ፡፡ ነገር ግን ዕድሜ እየጨመረና እየገፋ በሄደ ቁጥር የልብ ምት ድክመትን እንደሚያመለክትና በአብዛኛው ዕድሜአቸው ከሃምሳ በላይ የሆኑ ሰዎች በልብ ድካም በሽታ እንደሚጠቁ የህክምና መረጃዎች አረጋግጠዋል፡፡ ሆኖም ግን በፆም ጊዜ ወደተለያዩ የሰውነታችን ክፍሎች የሚሰራጨው የደም መጠን ከሚፈለገው መጠን በላይ ስለሚያንስ የልብን ስራ ያቃልላል፡፡ ስለዚህ የልብ ምት መጠን 60 በደቂቃ ይደርሳል፡፡ ይህ ደግሞ ልብ የተወሰነ የስራ ጫናንና መጨናነቅን አስወግዶ ለጥቂት ጊዜ እረፍት እንዲያገኝ ይረዳል፡፡

 

የረመዳን ፆም

የረመዳን ወር ፆም ከዚህ በላይ እንደተመለከትነው ግዴታዊ ፆም ከሚባሉት የፆም አይነቶች አንዱ ነው፡፡ የረመዳን ወር ፆም በሙስሊሞች ላይ ግዴታዊ የአምልኮት ተግባር ሆኖ የተደነገገው ነብዩ መሐመድ ከመካ ወደ መዲና በተሰደዱ በሁለተኛው ዓመት ነው፡፡ የረመዳን ወር ፆም ግዴታ የተደረገው በሚከተሉት የቁርአን አንቀጽ ሲሆን ነብዩ በህይወት ዘመናቸው ዘጠኝ የረመዳን ፆሞችን ብቻ እንደ ፆሙ ታሪካቸው ያስረዳል፡፡

‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ፆም ለነዚህ ከናንተ በፊት በነበሩት (ህዝቦች) ላይ እንደተፃፈ በናንተም ላይ ተፃፈ ልትጠነቀቁ ይከጀላልና›› (አአል በቀራህ፡ 183)

‹‹(እንድትፆሙ የተፃፈባችሁ ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀፆች) ሲሆን ቁርአን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው)›› (አል-በቀራህ 185)

የረመዳን ወር የጨረቃን የዘመን አቆጣጠር ቀመር ተከትሎ እንዲፆም የተደረገበት ዋና ምክንያት የሚከተለው ነው፡፡

ጨረቃ በመሬት ዙሪያ ዙር ለመፈፀም የሚወስድባት ጊዜ 29 ቀናት ከ12 ሰዓት ከ44 ደቂቃ 03 ሰከንድ ሲሆን በዚህ የጨረቃ አቆጣጠር አንድ ዓመት ማለት 354 ቀኖች ከ8 ሰዓት ከ48 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ ነው፡፡ አላህ የሰው ልጅ ይህን ተመልክቶ በቀላሉ ሊጠቀምበት የሚችለውን የዘመን አቆጣጠር በኢስላም ውስጥ ላሉና የተወሰኑ ወራትን ጠብቀው ለሚፈፀሙ አምልኮታዊ ተግባራት የዘመን መለኪያ አድርጎ አስቀምጧል፡፡ ይህንንም ጠቀሜታ አላህ ለሰው ልጆች ሲያብራራ በቁርአን ላይ እንዲህ ብሏል፡፡

‹‹(ሙሐመድ ሆይ!) ስለ ለጋ ጨረቃዎች ይጠይቁሃል ሰዎች

(ለዚህችም ሆነ ለቀጣዩ ዓለም ክንውኖቻቸው) ጊዜያቶችን የሐጅንም ወቅት (የሚያውቁባቸው) ምልክቶች ናቸው በል›› (አል-በቀራ 189)

ጨረቃዊው የዘመን አቆጣጠር ቀመር እንደ ፀሐያዊው የዘመን አቆጣጠር ቀመር በዓመት ውስጥ ባሉ የተለያዩ ወቅቶች (seasons) የተከፋፈለ አይደለም፡፡ በዚህም የተነሳ ለምሳሌ ያህል ለሰላሳ ዓመታት የረመዳንን ወር ፆም የፆመ ግለሰብ በአንድ ዓመት ውስጥ ባሉት የተለያዩ ወቅቶች ማለትም በበጋ፣ በክረምት፣ በፀደይና በበልግ ውስጥ የአየር ሁኔታዎቹ የሚፈጥሩበትን ተፅዕኖዎች ተቋቁሞ ግዴታ የሆነበትን ይህን የአምልኮ ተግባርን እንዲፈፅም ያደርገዋል፡፡ ይህም የግለሰቡ ሰውነት የአየር ለውጥ የሚያስከትለውን የጤና ችግር እንዲቋቋምና እንዲላመድ ያደርገዋል፡፡ ከዚህም ሌላ ማንኛውም ሙስሊም አመቺና አስቸጋሪ በሆኑ ወቅቶች ሁሉ ለጌታው ቅን ታዛዥ እንዲሆን በማድረግ ሂደት የጨረቃ የዘመን አቆጣጠር ቀመር ጉልህ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ፆም በፀሐያዊው የዘመን አቆጣጠር ቀመር የሚፈፀም ቢሆን ኖሮ ማንኛውም ሙስሊም ምን ጊዜም በተወሰነ የአየር ሁኔታ ውስጥ የተጣለበትን አምልኮታዊ ተግባር እንዲፈፅም በተገደደ ነበር፡፡ ይህ ደግሞ በእርሱ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ችግር በቀላሉ ለመገመት አያስቸግርም፡፡

በኢስላም ኃይማኖት ሙስሊም ሆነ ወይም መፆሙ ግዴታ ያልሆነባቸው ሰዎችም አሉ፡፡ እነዚህም ሰዎች እንዳይፆሙ የተደረገበት ምክንያት ካሉባቸው ችግሮች አንፃር እንጂ በሌላ አይደለም፡፡ እነርሱም፡-

1. በሽኞች (ህሙማን)

2. የአዕምሮ ህመምተኞች

3. ለረዥም ጉዞ የሚያደርግ መንገደኛ

4. በወር አበባ ደም ላይ ያለች ሴት

5. በወሊድ ደም ላይ ያለች ሴት

6. ለአቅመ አዳም ወይም ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ ህፃናት፡፡

በኢስላም ሴቶች በወር አበባ ወይም በወሊድ ደም ላይ ሳሉ እንዳይፆሙ ያደረገበት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉ፡፡ እነርሱም፡-

1. አንዲት ሴት በወር አበባ ወይም በወሊድ ደም ውስጥ ካለች ከሰውነቷ የሚፈሰው ደም አብዛኛውን ጊዜ ራሷን የመቋቋም ችሎታዋን እንድታጣ ስለሚያደርጋትና የመቋቋም ችሎታዋን ለመመለስ ተጨማሪ ምግቦችንና መጠጦችን መውሰድ ይኖርባታል፡፡ ያለዚያ ህይወቷ ለአደጋ እንደሚጋለጥ ጥርጥር የለውም፡፡ ስለዚህ ህይወቷን ከከፋ አደጋ ለመታደግ ኢስላም በዚህ ጊዜ ሴቶች እንዲፆሙ አያስገድዳቸውም፡፡ እንደውም መፆማቸውን ውግዝ (ፍፁማዊ ክልክል) ‹‹ሐራም›› አድርጎባቸዋል፡፡

2. አንዲት ሴት በወር አበባ ወይም በወሊድ ደም ላይ ካለች ባህሪዋ እንደሚለዋወጥ የስነ ልቦና እና በመስኩ ላይ ጥናት የሚያደርጉ ባለሙያዎች በጥናቶቻቸው አረጋግጠዋል፡፡ ስለዚህ ሴቶች በዚህ አይነት ሁኔታ ላይ እያሉ የባህሪ መለዋወጥ የሚያጋጥማቸው ከሆነ በቅንነት ለፈጣሪያቸው አላህ ቅን ታዛዥ ግዴታ የሆነባቸውን የረመዳን ፆምና ሌሎች የአምልኮ ተግባራትን ስርዓታቸውን ጠብቀው መፈፀም አይችሉም፡፡ ስለዚህ በሙሉ አንደበት፣ በሰከነ አዕምሮና መንፈስ የአምልኮ ተግባራትን ይፈፅሙ ዘንድ የኢስላም ሃይማኖት እንዲጾሙ አላስገደዳቸውም፡፡

እንግዲህ ከዚህ በላይ እንደተመለከትነው የኢስላማዊ ፆም ትርጓሜ፣ ስርዓትና ጠቀሜታዎች ይህን ይመስላሉ፡፡ በዚህ ፅሑፍ ላይ ያልተነሱትንና መነሳት የነበረባቸውን ነጥቦች አጋጣሚውን ጠብቀን በሌላ ጊዜ ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡ እስከዚያው ድረስ ግን ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አልፈጥር ረመዳን በዓለም በሰላም አደረሳችሁ እላለሁ፡፡

ቸር እንሰንብት፡፡

 

የቁልቢ ገብርኤል ንግስና የመንግሰት አቅጣጫ (መልካም አስተዳደር፣ ሙስና እና ስደት) በግርማ ሠይፉ ማሩ

ጆሮ ያለው ይሰማል! አይን ያለው ይመለከታል! ጆሮ ኖሮት የማይሰማ፣ ዓይን ኖሮት የማያደምጥስ? –ከድምፃችን ይሰማ

0
0
ታሪኩ ተፅፏል!
ጁምአ ሐምሌ 19/2005

የኢቴቪ ከ‹‹ጥቂቶች›› ወደ ‹‹የተወሰኑ›› የቃል ሽግግር!

እያንዳንዷ ጁምአ ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ታሪክ የሚጻፍባት ገጽ ከሆነች ቆይታለች። ጁምአ የፍትሕ፣ የነጻነትና የህዝብ ድምጽ ቀን ናት ለእኛ። የዛሬዋ ጁምአ ደግሞ በበኩሏ ታሪካዊ ሆና ውላለች። እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ በአለም አቀፍ ደረጃ አገሪቱ ውስጥ እየተፈጸመ ላለው የሃይማኖት ጭቆና ድምጹን አሰምቷል። ዛሬ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በተጠራው አለም አቀፍ ተቃውሞ በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እለቱን ስለ ፍትህ በመጣራት ሲያሳልፉት ውለዋል፡፡

muslimበኢትዮጵያ ያለው የሃይማኖት ነጻነት እጦት፣ ተደጋጋሚ ፖለቲካዊ ክሶችና እስሮች፣ ሙስሊሞች ላይ እየተፈጸመ ያለው የሰብአዊ መብት ረገጣ፣ የህገ መንግስት ጥሰት፣ የመስጊድ ቅሚያ እና መታሸግ፣ በመንግስት ሚዲያዎች ሙስሊሞች ላይ የሚሰነዘረው የፕሮፖጋንዳ ጦርነት፣ የመሪዎቻችን እስርና ወዘተ የመብት ጥሰቶችን በአንድ አንደበት ግን በተለያዩ አሕጉራት ሆኖ ለመቃወም የተጠራው የዛሬው ተቃውሞ እጅግ ባማረና ባስደነቀ ትእይንቶች ታጅቦ ተካሄዷል፡፡ በዚህ ሪፖርታዣችን በአገር ውስጥ ብቻ የተካሄዱትን የተቃውሞ መርሐ ግብሮች አፈጻጸም የምናስቃኛችሁ ሲሆን በነገው ሪፖርታዣችን ከአገር ውጪ የተካሄዱትንና ዛሬ ምሽት እንዲሁም ነገ ቀጥለው የሚካሄዱትን የቤት ውስጥና ከቤት ውጪ ተቃውሞዎች ሙሉ ዘገባ እናቀርባለን፡፡

አዲስ አበባ ገና ከማለዳው ነበር የተለመደ መንገዳቸውን ትተው ወደ ፒያሳው ኑር መስጂድ በሚፈሱ ሙስሊሞች መሞላት የጀመረው፡፡ ለወትሮው በአንዋር መስጂድ ጁምአን ለመፈጸም የሚሄደው ሙስሊም ህብረተሰብ በሚሊዮን ሆኖ የተቃጠረበትን ኑር መስጂድን በማሰብ ነበር ወደ ኑር መስጂድ የነጎደው፡፡ ኑር መስጂድ ከመርካቶ፣ ቦሌ፣ ልደታ ካዛንቺስ እና ፒያሳ አቅጣጫ የሚመጡ ሙስሊሞች ለመሞላት የጁምአ ሰላት መድረስ እንኳ አላስፈለገውም ነበር፡፡ ገና በጊዜ መስጂዱ ሞልቶ ጎዳና ላይ መፍሰስ የጀመረው ሙስሊም በፒያሳ፣ ተ/ሃይማኖት እና አንዋር መስጂድ አቅጣጫ መፍሰሱን ተያያዘው፡፡ ሕዝቡ እንደጉድ ይመጣል፤ ጎዳናውም መሙላቱን ቀጥላል፡፡ ከጁምአ ሁለተኛ አዛን በፊት ወደ ተ/ሃይማኖት የወረደው ሙስሊም በላይ ዋናውን ጎዳና ለመዳረስ ጥቂት ቀርቶት ነበር፡፡

የጁምአ ሰላት እንደተጠናቀቀም ሁሉም በየፊናው የያዘውን መፈክር ከፍ በማድረግ ‹‹አላሁ አክበር›› በማለትና አላህን በማተለቅ ተቃውሞውን አሀዱ አለ፡፡ አንድ ሁለት እያሉ መፈክሮች ተከተሉ፡፡ የአካባቢው ድባብም ተቀየረ፡፡ መብቱ የተነካው ሙስሊም ‹‹ኢ-ፍትሃዊነትን የምሸከምበት ትከሻ የለኝም!›› በማለት እየተፈጸመበት ያለው በደል እንዲያከትም፣ የመንግስት ያልተገደበ ጣልቃ ገብነት እንዲያበቃ ደጋግሞ በመፈክሩ አስተጋባ፡፡ ደቂቃዎች እየነጎዱ፣ ጾመኛ የሆነው ሕዝብ ሀይልና ወኔ ግን እየጨመረ ነበር የሄደው – እስከ ተቃውሞው መጠናቀቂያ ወቅት ድረስ፡፡ ሙስሊሙ ተቃውሞውን አጠናቆም ዱአውን በማስከተል ወደየአካባቢው መመለስ ጀመረ፡፡ በአካባቢው የነበረው ሕዝብ ብዛት በታሪክ ያልታየና አካባቢውም ሆነ ኑር መስጂድ አስተናግዶት የማያውቅ እንደነበርም በብዙ የአይን እማኞች ምስክርነት ተሰጥቶታል፡፡ የአዲስ አበባውን የኑር መስጂድ ተቃውሞ ለታደመ መንግስት ባለበት ሃገር ዳግም ህዝባዊ ተቃውሞ መጥራት እንደማያስፈልግ ይረዳል። የህዝብ ሃላፊነት ድምፁን ማሰማቱ፣ የመንግስት ግዴታው ደግሞ የህዝቡን ድምፅ ማድመጡ ነውና። መቶ ሺዎች በአዲስ አበባ ብቻ ሲጠሩት ያልሰማ መንግስት የቱን ሃላፊነት በመወጣት ላይ ይሆን? ህዝብስ መብቱን እንዴት እንዲጠይቀው እየገፋፋ ይሆን?

በህብረተሰብ ስብጥር እና በማህበረ ፖለቲካው ረገድ ትልቅ ግምት የሚሰጣት ሻሸመኔ በልዩ ትኩረት የምትታይ ነች። በዚህች ከተማ የሚኖር መልካምም ሆነ መጥፎ ተሞክሮ እጅግ በርካታ በሆኑ የከተማና የገጠር ቀበሌዎች ላይ ቀጥተኛ ተፅእኖ አለው። እናም ሻሸመኔዎች ድምፃቸውን የወታደር ከበባ ጥሰው ሲያሰሙ የሃይል እርምጃ ፈፅሞ እንደማያዋጣ እና መዘዙም የከፋ መሆኑን በዙሪያቸው ባሉ ከተሞችና ቀበሌዎች ስም እያስደመጡ ነበር። በከተማዋ አል ሂከም መስጂድ ዛሬ የተደረገውን ተቃውሞ ተከትሎ ፌደራል ፖሊሶች መሰጂዱን ከበውት የቆዩ ሲሆን ህዝበ ሙስሊሙ ያካሄደው ሰላማዊ ተቃውሞ ከተጠናቀቀ በኋላ መስጂዱን ለቆ ለመውጣት ሳይችል ቀርቷል፡፡ ወደ ቤቱ ለመመለስ የሚወጣውንም ሕዝብ ፖሊስ ሲያፍን የነበረ በመሆኑ ሙስሊሙ እስከ አስር ሰላት ድረስ በመስጂዱ ለመቆየት ተገዷል፡፡ ከአስር ሰላት መጠናቀቅ በኋላ ህዝበ ሙስሊሙ በጋራ በመሆን ከመስጂድ ቢወጣም ፖሊስ ግለሰቦችን ነጥሎ ያስር እንደነበር የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፡

በሂላል መስጂድ የተሰባሰቡ የአጋሮ ከተማ ሙስሊሞች አንደባለፈው ሳምንት ተቃውሞውን ለሴቶች ብቻ ከመተው ይልቅ በወንዶች በኩል የሳምንቱን በደል ለመካስ ሲሰባሰቡ ሴቶች ማንም ዝም ቢል ዝም ላይሉና ታሪክ ለመድገም ቃል ተግባብተዉ ነበር የመጡት፡፡ ዉጤቱ ወንዶች በደላቸዉን ሲክሱ ሴቶችም ወንዶችን አንድ እርምጃ በመቅደም በጀግንነት መዝገባቸዉ ላይ ስማቸዉን በደማቅ ቀለም ለሁለተኛ ግዜ አስመዝግበዋል፡፡ የመንግስት ኢማሞች ሕዝቡን ለማስፈራራት ቢሞክሩም ‹‹መብቴን ተነጥቄ ዝም አልልም›› ያለው የአጋሮ ሕዝብ ከሰላት መጠናቀቅ በኋላ በተክቢራ የጀመረውን ተቃውሞ በሌሎች መፈክሮች ታጅቦ በሰላም አጠናቆታል፡፡ የአጋሮ ድምፆች በመላው ሀገሪቱ የተሰሙ የመብት ጥያቄ ድምፆችን ተቀላቅለው ኢትዮጵያዊ ህብር ሰርተው ከተማው ደምቆ ውሏል።

በኦሮሚያዋ መቱ የነበረው የተቃውሞ ትእይንትም ልዩና የአገሬው ሕዝብ በሌሎች የአገሪቱ ክልሎች እንደሚገኙት ሙስሊሞች ፍትህ መነጠቁን የመሰከረበትና ለፍትህ እንደሚሟገት ያሳየበት ነበር፡፡ በከተማዋ ዋና መስጂድ ነጃሺ የተገኘው በርካታ ሕዝብ በእልህና በንዴት በተናጠ ገጽታ መሪዎቻችን እንዲፈቱ፣ መንግስት ሕገ መንግስቱን እንዲያከብር፣ ሙስሊሞችን መጨቆን እንዲያቆም ጠይቋል፡፡ በመቱ የነበረው ተቃውሞም የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድምፅ ሃገራዊ ጥሪ መሆኑን ለሚያስተባብሉ ሁሉ ተግባራዊ ምላሽ የሰጠ ደማቅ ተቃውሞ ነበር።

በደሌም ታላቅ ተቃውሞ አስተናግዳ ነበር፡፡ የኢሊባቡር ዞኗ በደሌ በረህማ መስጂድ ሲሆን በበደሌ ከተማ እስከዛሬ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እጅግ በጣም ብዛት ያላቸው በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ሰላማዊ ተቃውሞ አከናውነዋል፡፡ የዛሬው የበደሌ ተቃውሞ የተለያዩ መፈክሮች የተስተጋቡበት ሲሆን፤ ከግማሽ ሰዓታት በላይም ቆይቷል – እንደ ዘገባዎች፡፡ በኢሊባቡር ዞን በምትገኘውና ከበደሌ ከተማ 36 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ጮራ ከተማ ከረጅም ጊዜ ዝምታ በኋላ ተቃውሞ ተካሂዶባታል፡፡ የድምጽ ተቃውሞ በተካሄደባት በጮራ ከተማ ትዕይንቱ በሁለት ቀበሌዎች በሚገኙ በፈትህ እና በኑር መስጂዶች መካሄዱን ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡

በኢሊባቦር ዞን በገቺ ከተማም እንዲሁ ከጁምአ ሰላት በኋላ ከባድ ተቃውሞ ተደርጓል:: የገቺ ከተማ ህዝበ ሙስሊም ተቃውሞውን እንዲያቆም የከተማው የፀጥታ ቢሮ ሃላፊዎች የከተማውን ሽማግሌዎች እና የከተማዋን ህዝብ ለያይተው ስብሰባ በመጥራት ማስፈራራታቸው የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ጁምአ ግን ማስፈራሪያው ቦታ እንደሌለው በተግባር አሳይተዋል፡፡ በከተማዋ የፀጥታ ቢሮ ሃላፊዎች የተደረገው ማስፈራራት ሳይበግረው የገቺ ከተማ ህዝበ ሙስሊም እልህ እና ወኔ በተሞላበት ሁኔታ ከበፊቱ ይበልጥ በነቂስ በመውጣት ድምፁን ሲያሰማ መዋሉን ምንጮቻችን ዘግበዋል፡፡ የጁምአ ሰላት ከመሰገዱ በፊትም ለኮሚቴዎቻችን ዱአ የተደረገ ሲሆን በመስጂዱ የተገኘው ህዝበ ሙስሊምም በለቅሶ እና በእምባ ‹‹አሚን›› ሲል እንደነበር ተሰምቷል፡፡ በተካሄደው ተቃውሞ የሴቶች ተሳትፎ ከፍተኛ የነበረ ሲሆን የተለያዩ መፈክሮችም ተብለዋል፡፡

ጅማዎች በፖሊስ ተከበው በዋሉበት በዛሬው ጁምአ የፈጸሙት ጀግንነት በቃላት ብቻ የሚገለጽ አይደለም፡፡ በከተማዋ ፈትህ መስጂድ ከረፋዱ ጀምሮ ከቧቸው የነበረውን ታጣቂ ሀይል ሳይሰጉ ወደ መስጂድ አል ፈትህ ያመሩት ጅማዎች የሰላት መጠናቀቅን ተከትሎ በነፍስ ወከፍ ያዘጋጁትን መፈክር ከፍ አድርገው የድምጽ ተቃውሞአቸውን ጀመሩ፡፡ ‹‹ድምጻችን ይሰማ!›› ከሚለው መፈክር ተነስተው ‹‹አሻእቡ ዩሪድ ኢስቃጠል መጅሊስ›› የሚለውን መፈክር አቋርጠው ለታሳሪ ኮሚቴዎቻችን ጥብቅና እንደሚቆሙ ከፍ ባለ ድምጽ መስክረዋል፡፡ ‹‹መብትን በማሰር መንጠቅ አይቻልም!›› እያሉም ለመንግስት ግልጽ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የጅማ የመብት ታጋዮች የእነሱን፣ በዙሪያቸው ያሉ ከተማ እና ገጠር ቀበሌዎችን ድምፅ ይዘው ሲወጡ ድምፃቸው ሃገራዊውን ተቃውሞ በሚደንቅ ውበት ተቀላቅሎ ውሏል።

ብዙዎች ‹‹ያልተጠበቀ ጀግንነት ነው›› ያሉት የወልቂጤው አስደማሚ ተቃውሞ ደግሞ እጅግ ውጥረት በሞላበትና የጦር ቀጠና በመሰለ ከባቢ ውስጥ በድምቀት ተካሂዷል። ወልቂጤዎች በዲናቸው የማይደራደሩ መሆናቸውን ለሚያውቅ ግን ‹‹ታሪክ ራሱን ደገመ›› እንጂ ሌላ አይልም፡፡ ውጥረት ነግሶበት የተከናወነው የወልቂጤው ተቃውሞ ባልተጠበቀው የህዝብ ማዕበል የበድረዲን መስጂድ ሜዳ በከተማው ሙስሊም ተጨናንቆ የጁመዓን አለም አቀፍ ተቃውሞ በከፍተኛ ድምቀት አከናውኗል፡፡ የጁመዓ ሰላት እንደተጠናቀቀ በተክቢራ የደመቀው በድረዲን መስጂድ ወዲያው ነበር ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ልዩ ሀይሎችና ፖሊሶች የተከበበው፡፡ ከበባውን ተከትሎ የተቃውሞው ድምፅ ከመቼው ጊዜ በበለጠ ከፍ ብሎ መሰማት ቀጠለ፡፡ ‹‹ጥያቄው ይመለስ!››፣ ‹‹ኮሚቴው ይፈታ!››፣ ‹‹ድምጻችን ይሰማ!››፣ ‹‹በአቋማችን እንፀናለን!›› እና ሌሎች መፈክሮች ተስተጋቡ፡፡ በስተመጨረሻ ህዝቡ ተቃውሞውን አጠናቆ አካባቢውን ከበውት የነበሩትን ልዩ ሀይሎችና ፖሊሶችን በመሀል ሰንጥቆ በማለፍ ከመስጂዱ ወጥቷል፡፡ ሆኖም ወደ 10 የሚጠጉ ሙስሊሞች መታሰራቸው የተሰማ ሲሆን ከፊሎቹም ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ተዘግቧል፡፡

ምእራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ወረዳ በዶዶላ ወረዳ ስር በሚገኘው ሄረሮ ከተማ በሦስት መስጂዶች ዛሬ ከጁምዓ ሰላት በኋላ ከፍተኛ የሆነ የድምፅ ተቃውሞ መደረጉና በሰላም መጠናቀቁም ተነግሯል፡፡ ተቃውሞው የተደረገው በኡሙ ቱርኪ ትልቁ መስጊድ፣ በቢላል መስጊድና በሳፊ መስጊድ ሲሆን በተቃውሞው ላይ ጎልተው ከተሰሙት መፈክሮች መካከል ‹‹አላሁ አክበር!››፣ ‹‹ድምፃችን ይሰማ!››፣ ‹‹ኮሚቴው ይፈታ!››፣ ‹‹መጅሊስ አይወክለንም!››፣ ‹‹ድራማው ይብቃ!››፣ ‹‹ህገ-መንግስቱ ይከበር!›› እና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ ሕዝቡ በተያዘው መርሀ ግብር መሰረት ተቃውሞውን አሰምቶም በሰላም ወደ መጣበት ተመልሷል፡፡

የሰሞኑ የፓሊስ እስር፣ ፍተሻ፣ ማስፈራራት፣ ዘመቻ እና የመንግስታዊው እስልምና ተከታታይ ፕሮፓጋንዳ ያልገደበው የወራቤ ሙስሊም የተቃውሞ መርሃ ግብሩን በብቃት አሳክቶ በድል ወደቤቱ ተመልሷል፡፡ በወራቤው ተቃውሞ ህጻን፣ አዋቂ፣ ሴት፣ ወንድ ሳይለይ በጋራ ‹‹ፍትህ ይከበር!›› ድምጹን ያስተጋባ ሲሆን የአካባቢው አስተዳደሮችም ሁከት በመፍጠር የተወሰኑ ሙስሊሞችን ለመያዝ ጥረት ሲያደርጉ ነበር፡፡ ነቀምቴዎችም በአለም አቀፉ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ እለት ከቀሪው ኢትዮጵያዊ ጋር በዱዓ ተቃውሞ ተቀላቅለዋል። ከእነዚህ ከተጠቀሱት ከተሞች በተጨማሪ በሌሎች በርካታ ከተሞች ከበር መልስ የዱአ እና የመሰባሰብ ተቃውሞዎች ተደርገዋል፡፡

ይህ ህዝብ ድምጹን እንክን የለሽ በሆነና በሰለጠነ ሰላማዊ መንገድ እያሰማ ቢሆንም እስካሁንም ግን በመንግስት ባለስልጣናት ‹‹ጥቂት›› እየተባለ ከመሸርደድ፣ ‹‹አክራሪ›› እየተባለ ከመሸንቆጥ አለማለፉ ለብዙዎች የሚያሳዝናቸው እውነታ ሆኗል። ‹‹ጥቂት›› የሚለው ቃል ሌላ አዲስ ትርጉም የተበጀለት ይመስላል። በቀበሌ ካድሬዎች ማስፈራሪያ ተገደው ለሰልፍ የሚወጡ አንድ እፍኝ የማይሞሉ ሰዎችን ‹‹የእገሌ ከተማ ሙስሊም ህዝብ›› እያለ የሚያጭበረብረው ኢቲቪ የአዲስ አበባንና የሌሎች ከተሞችን ጎዳናዎች ሞልተው የፈሰሱና በየሳምንቱ ድምጻቸውን የሚያሰሙ ሚሊዮኖችን ግን ‹‹ጥቂት አክራሪዎች›› ለማለት አያመነታም። ዛሬ ደግሞ ይሄ ቃል ‹‹የተወሰኑ›› ወደሚል ቃል ተለውጦ አይተነዋል፡፡

መንግስት ሁለት አመት ሙሉ የሄደበትን የሀሰት አዘጋገብ በመከተል ሕዝቡን የተወሰነ ከማለቱ በተጨማሪ ሕዝበ ሙስሊሙን በጸረ ሰላምነትና ኢትዮጵያዊነት የማይሰማቸው ዜጎች አድርጎ ለማቅረብ ጥረት አድርጓል፡፡ ዛሬ በአንዋር መስጂድ የተቃውሞ ፕሮግራም ያልነበረ ቢሆንም የተቃውሞ ፕሮግራም እንደነበርና ሰላማዊው ህዝብ የመንግስትን ንብረት አወደመ ብሎ እጅግ አሳፋሪ ዜና ለሕዝቡ አቅርቧል፡፡ ምንም እንኳ የኢትዮጵያ ሕዝብ በዚህ መሰሉ የሀሰት ዜና የማይደለል ቢሆንም መንግስት እውነታውን ከማውራት ይልቅ በዚህ አይነቱ ‹‹አልሰማም አላይም›› ሁኔታ መቀጠሉ እንደ አገሪቱ ዜግነታችን በጣም ያሳስበናል፡፡ አንድ መንግስት የህዝቡን ልብ ትርታ በትክክል ለማዳመጥ ከዚህ የተሻለ ምን እድል ሊያገኝ ይችላል? የህዝበ ሙስሊሙን ፍላጎት በትክክል ለማወቅስ ከዚህ የተሻለ አጋጣሚ ይኖር ይሆን?

አዎን! የዛሬዋም ጁምአ ‹‹ህዝብን ማሸነፍ አይቻልም!›› የሚል መልእክቷን ነው ያስተላለፈችው! እናም ህዝብን ማሸነፍ አይቻልምና በከንቱ አትድከሙ። የሃይል እርምጃም ሆነ የግዳጅ ጠመቃ እንዳላዋጡ ለማየት የዛሬውን ተቃውሞ ብቻ ማየት ይበቃል። አዎን! እኛ ለምትወስዱብን የሃይል እርምጃ ምንዳችንን አናጣውም… ትግላችን ለፍትህና ለነጻነት እሴቶች ነውና! እናንተ ሰላማውያንን በመደብደብና በመግደል እያጣችሁት ያለው ተቀባይነትና እያተረፋችሁት ያለውን የህዝብ ቁጣ ግን በምን ታካክሱት ይሆን!?

አላሁ አክበር!

Sport: ኢትዮጵያ ለቻን ዋንጫ አለፈች

0
0

Ethiopia national team
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ደ ደቡብ አፍሪካ እ.አ.አ በ2014 ዓ.ም ለምታስተናግደው የአፍሪካ ሀገሮች ሻምፒዮና (CHAN) ውድድር ለማለፍ የሩዋንዳ አቻውን ኪጋሊላይ በመለያ ምት 6 ለ 5 በሆነ ውጤት አሸንፏል። በመጀመሪያው ጨዋታ አዲስ አበባ ስታዲየምላይ በአስራት መገርሳ ብቸኛ ጎል የሩዋንዳ አቻውን 1 ለ 0 ያሸነፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋሊያዎቹ የተሻለ እድል ይዘው ነበር ወደ ኪጋሊ የተጓዙት።

በጨዋታው የመጀመሪያው አጋማሽ የተሻለ የጨዋታ እንቅስቃሴ የነበረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የነበረ ቢሆንም ተጨማሪ ጎል ማስቆጠር ሳይችሉ 0 ለ 0 የመጀመሪያ አጋማሽ ተጠናቋል። በሁለተኛ አጋማሽ ተመጣጣኝ የሆነ ፉክክር ያደረጉ ሲሆን በ68ኛው ደቂቃ ዋሊያዎቹን ሩዋንዳዎች ጎል አስቆጥረው ጨዋታው በአጠቃላይ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት 90ው ደቂቃ ተጠናቋል። ሁለቱን ሀገሮች ለመለየት በተደረገው የመለያ ምት ዋሊያዎቹ 6ለ5 በሆነ ውጤት የደቡብ አፍሪካ ትኬታቸውን ቆርጠዋል።

በፍጹም ቅጣት ምቱ የግብ ጠባቂው ሲሳይ ባንጫ ድንቅ ብቃት የታየበት ነበር። በጨዋታው ላይ ጉዳት የደረሰበት ጀማል ጣሰውን የተካው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ሲሳይ ባንጫ ሁለት መለያ ምቶችን በማክሸፉም ከፍተኛ አድናቆትን እየተቸረው ይገኛል።

ጎሎቹን ለማየት ይኸው – ከኢትዮ ቲዩብ፦

ለጸረ ሙስና እና ቤቲን እንከሳለን በማለት ለዛቱ አቃቢያነ ህጎች የቀረበች ቆንጆ ፈተና =>ሰምሃል መለስ ዜናዊ

0
0
SEMEHAL

ዳዊት ሰለሞን በፌስቡክ ገጹ ያሰፈረው አስተያየት፦ 

የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ የሚያበላሽና ለህዝቡ ማህበራዊ ሞራል ተቃራኒ የሆነ ድርጊት በመፈጸሟ በወንጀል እንከሳታለን በማለት በቢግ ብራዘርስ አፍሪካ ወሲብ ስትፈጽም የታየችውን ቤቴልሄም አበራን ለመሞገት መዘጋጀታቸውን አቃቢያነ ህጎች መናገራቸውን አቤ ቶክቻው አስር አለቃ በማለት የሚጠራው አንድ የቅዳሜ ጋዜጣ ማስነበቡ አይዘነጋም፡፡
እኔ ለማህበራዊ ዕሴቶቻችን ጥብቅና ለመቆም እንዲህ ትንታግ አቃቢያነ ህጎች አለን ማለታቸውን ውድድ አድርጌዋለሁ፡፡መቼም ባለሞያዎቹ ለወሲብ ጊዜ ብቻ የህግ አንቀጽ መምዘዝ ያለባቸውም አይመስለኝም፣እናም ሰዎቹን በየትናችሁ ለማለት የሰምሃል መለስ ዜናዊ ሰሞነኛ ጉድ አሪፍ መፈተኛ ትመስለኛለች፡፡አቃቢያነ ህጎቹ የአባትን ስልጣን ተገን በማድረግ ይህችን ደሃ አገር እንደ ሸንኮራ መምጠጥ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ተቀባይነት ያገኘ የኢትዮጵያዊያን ትውፊት ነው ካላሉን በስተቀር መለስም ይሁኑ አዜብ በ2011 ኒውዮርክ ውስጥ በሚገኝ ባንክ 5 ቢልዮን ዶላር በልጃቸው ሰምሃል ስም ማስቀመጣቸውን ዶክተር መኮንን ወንድሙ ለእንግሊዝ ፓርላማ በመግለጽ የምለውን የምትጠራጠሩ ከሆነ ዶላሩ በስሟ ገቢ የተደረገበትን የቼክ ኮፒ ተመልከቱልኝ ብለዋል፡፡
በቅርቡ ሙሰኞችን ወህኒ እያወረድኩ ነው ያለን ጸረ ሙስናስ ቢሆን እንዲህ አይነት ጥብስ መረጃና ማስረጃ እየቀረበለት ምን ይጠብቃል? ዜናው ለአደባባይ የበቃበት ወቅት ግጥምጥሞሽም ሌላው አስቂኝ ነው፡፡ሰምሃል በኒውዮርክ ያጨቀችውን ዶላር ቤሳቤስቲን ሳትነካ ለአባቷ ሙት አመት የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ኪስ ለመዳበስ መንቀሳቀስ ጀምራለች፡፡እንዴት ነው ነገሩ ?ሼም የለም?

 

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live