Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

Hiber Radio: በአሜሪካ ኢትዮጵያዊው የታክሲ ሺፌር በወሮበላዎች ተገደለ

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ሚያዚያ 13 ቀን 2005 ፕሮግራም
>
ባለቤታቸው ከሱዳን ስደተኞች ካምፕ ተጠልፋ ከሲና በረሃ ስላለችበት ሁኔታ ለህብር ሲገልጹ
ማርጋሪት ታቸር(ልዩ ዘገባ)
በቬጋስ የታክስ አሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ ላይ የተለያዩ ቃለ መጠይቆች

ዜናዎቻችን:-
- የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ በዘፈቀደ እስራትና ግድያን ጨምሮ ልዩ ልዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን በዓመታዊ ሪፖርቱ በዝርዝር ገለጸ
- በአሜሪካ ኢትዮጵያዊው የታክሲ ሺፌር በወሮበላዎች ተገደለ
- የግልገል ግቤ 3ኛ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ዛሬም እያወዛገበ ነው
- በ117ኛው የቦስተን ማራቶንን ተከትሎ የተከሰተው የሽብር ተግባር ሲዳሰስ
- በኢትዮጵያ የሕክምና ባለሙያዎች የቲቪ ድራማ እየተመለከቱ ለወሊድ የሔዱ ወይዘሮን ተገቢውን እርዳታ ሳይሰጡ ሕይወታቸው ማለፉን ቤተሰቦቻቸው ገለጹ
- ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ወደ ዝዋይ ማረሚያ ቤት ሊዛወር ነው
- ርዮት አለሙ የተከለከለችው ሕክምና እንዲፈቃድላት ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ጠየቀ
- በቬጋስ በኔሊስ ኩባንያ የሚሰሩ አሽከርካሪዎች ዩኒየን አንፈልግም ሲሉ ለኩባንያው ድምጽ ሰጡ

↧

↧

ሞረሽ ወገኔ አዲስ ጽሁፍ በተነ!! የትግሬ-ናዚዎች አዋጅ፦ «ዐማራን ከምድረ-ገፅ እናጠፋለን!»

$
0
0

1. ናዚዝም በጀርመን ፣ ፋሽዝም በጣሊያን ቢቀበሩም በኢትዮጵያ ትንሣኤ አግኝተዋል

moreshናዚዝም እና ፋሽዝም በአውሮፓ እንዲያቆጠቁጡ ምክንያት የሆናቸው አንድ ዓይነት መንስዔ ብቻ ነበር ብሎ ለመደምደም ያስቸግራል። ሆኖም ጀርመን በአንደኛው የዓለም ጦርነት በተባባረው የእንግሊዝ እና ፈረንሣይ ኃይል ተደቁሳ፣ ወርራ ከያዘቻቸው የቅኝ ግዛቶቿ በተጨማሪ ከራሷም ግዛት እንድታጣ በመደረጉ፣ እንዲሁም ጦርነት መቀስቀሷ ምክንያት ተደርጎ ለአሸናፊዎቹ ለእንግሊዝ እና ለፈረንሣይ እንድትከፍል የተገደደችው የጦርነት ካሣ ቁልል ኢኮኖሚዋን መቀመቅ ከትቶት ሰለነበረ በጀርመኖች ዘንድ «ተጠቃን ፣ ተዋረድን ፣ የእኛ የነበረውን አሣጡን» የሚል ቁጭት እንዲፈጠር አድርጎ ነበር። ስለዚህ አዶልፍ ሒትለር እና የፖለቲካ አጋሮቹ ያንን የጀርመን ሕዝብ ቁጭት፣ የተከሠተውን ኢኮኖሚያዊ ችግር፣ እርሱንም ተከትሎ በጀርመን ሕዝብ ላይ የደረሠውን የተመሠቃቀለ የማኅበራዊ ሕይወት ቀውስ በፈጣን እና «በአስተማማኝ የጀርመን ብሔረተኝነት» መፍትሔ ለመስጠት እንደሚችሉ ከፍተኛ ፕሮፓጋንዳ ማዝነብ ጀመሩ። በቤኔቶ ሙሶሊኒ ይመራ ለነበረው ለጣሊያን ፋሽስቶች አነሣሥም አመቺ ሁኔታ የፈጠረላቸው ከሮም አገዛዝ በኋላ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ አዲስ ከተዋቀረችው የኢጣሊያ ሪፓብሊክ አመሠራረት ጀምሮ የዘለቀው ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ምስቅልቅል ሲሆን ያም «ፈጣን ለውጥ እናመጣለን» ለሚሉ አጭበርባሪ ፋሽስቶች የተመቻቸ የፖለቲካ ድባብ መፍጠሩ አልቀረም።
ናዚዝም እና ፋሽዝም በሁለት የተለያዩ የአውሮፓ አገሮች ተፈጥረው በሁለት የተለያዩ ሥያሜዎች ቢጠሩም መገለጫ ባህርይዎቻቸው ተመሣሣዮች ነው። ናዚዝምም ሆነ ፋሽዝም የፓርላማ ዲሞክራሲን አይቀበሉም። ለእነርሱ ብሔረተኝነት የሚገለፀው በዘር (በጎሣ ወይም በነገድ) ላይ በተመሠረተ መሥፈርት ላይ ስለሆነ የርዕዮታቸው መሠረት ሁሉ ዘረኝነት ነው። ለናዚዎች እና ለፋሽስቶች የቡድን ማለትም «የጎሣ ወይም የነገድ» መብት ከሁሉም መብቶች በላይ ስለሆነ የግለሰብ መብት ሥፍራ የለውም። በተለይ ደግሞ ናዚዎች «ምርጥ የሆነው የአርያን ዘር ነን» ብለው ስለሚያምኑ ዘራቸውን ከሌላው ዘር ሣያቀላቅሉ ማራባት መርሆዋቸው ነበር፣ ነውም። ናዚዎች ለፖለቲካ ግባቸው መቀስቀሻ ፀረ-አይሁዳዊነት ዋና መፈክራቸው ስለነበረ ከ6 ሚሊዮን የማያንሱ አይሁዶችን በአሠቃቂ ሁኔታ በግፍ ጨፍጭፈዋል። ለፋሽስት ጣሊያኖች ዋና ጠላታቸው «ኢትዮጵያዊ» በተለይም ደግሞ «ዐማራ» የሚባለው ዘር ስለነበረ ኢትዮጵያን በወረራ በያዙበት 5 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን የማያንሱ ኢትዮጵያውያንን በመርዝ ጋዝ፤ በቦንብ፣ በመጥረቢያ፣ በእሣት በማጋዬት እና በሌሎችም አሠቃቂ መንገዶች ጨፍጭፈዋል። በታሪክ ተመዝግቦ እንደሚገኘው በፋሽስት ጣሊያኖች በብዛት የተጨፈጨፉት ዐማራዎች ነበሩ። ናዚዎች እና ፋሽዝቶች በነፃ ገበያ መርሆ የሚመራ የኢኮኖሚ ሥርዓት አይቀበሉም። ስለዚህ የመሠረቱት የኢኮኖሚ ሥርዓት በዘር ትሥሥር እና በሥውር ሤራ ላይ የተመሠረተ የፋይናንስ ካፒታሊዝምን የጀርባ አጥንት አድርጎ የሚንቀሣቀስ የማፍያ ካፒታሊዝም ነበር። በፖለቲካ አመለካከታቸውም ዜጎቻቸውን ለፍፁም አምባገነናዊ አመራር ታዛዥ የሚያደርግ ሥርዓትን ያራምዳሉ። ስለሆነም የሊበራል ዲሞክራሲንም ሆነ በተፃራሪ የቆመው የግራ ርዕዮተ-ዓለም «ኮሚኒዝምን» አምርረው የሚጠሉ እና የሚታገሉ ነበሩ፣ ናቸውም። ሁለቱም እኒህን የርዕዮተ-ዓለማቸውን ምሦሦዎች ያቆሙት «ውሽት ሲደጋገም ወደ እውነቱ ይጠጋል» በሚሉት የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ መሠረት ላይ ነበር። ከላይ የተዘረዘሩትን ለሚመለከት የትግሬ-ወያኔዎች ቀዳሚውን የርዕዮተ-ዓለም መሠረታቸውን ያገኙት ከጀርመን ናዚዎች እና ከጣሊያን ፋሽስቶች መሆኑን ለመገንዘብ ይችላል። ለትግሬ-ወያኔዎች ሁለተኛው የርዕዮተ-ዓለማቸው መሠረት ደግሞ የኮሚኒዝም አመለካከት ነው። አንድ ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው «እንዴት ተደርጎ እኒህን ሁለት ፍፁም ተፃራሪ የሚመስሉ ርዕዮቶች አንድን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለመምራት በተጣመረ ሁኔታ መርሆ አድርጎ መቀበል ይቻላል?» ብሎ ሊጠይቅ ይችላል፣ ተገቢ ጥያቄም ይሆናል። መልሱ ደግሞ «የትግሬ-ወያኔዎች በሚሄዱበት አቅጣጫ ከተሄደ ይቻላል፤» ነው። ለዚህ እንዲረዳ የትግሬ-ወያኔዎችን የመጀመሪያውን የ1968 ዓ.ም. ማኒፌስቶ በከፊል መመልከቱ ይጠቅማል።
የቀድሞው ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተ.ሓ.ህ.ት.) የአሁኑ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት.) ወይም በተለምዶ አጠራሩ «ወያኔ» በ1968 ዓ.ም. ባወጣው ማኒፌስቶ በግልፅ እንዳሠፈረው፦ ሙሉውን ጽሑፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

New Picture (6)

↧

በዋልድባ ገዳም ማይለባጣ እና ዶንዶሮቃ ላይ በታጣቂዎች ዘረፋ ተካሄደ

$
0
0

 Save Waldiba እንደዘገበው

·         ማይለበጣ ቤተ-እግዚአብሔር በታጣቂዎች ተዘረፈ
·         ዶንዶሮቃ ላይ የሚገኘው የዋልድባ ገዳም ወፍጮ ቤትም በተመሳሳይ ታጣቂዎች ተዘርፏል
·         አባ ፍቅረማርያም የተባሉ አባት በደረሰባቸው ከባድ ድብደባ በህክምና ላይ ናቸው
·         መናኝ ገብረመድኅን የተባሉ ስመ እግዚአብሔር ጠርተው ለምነው ከድብደባ ድነዋል
·         መናኝ ኅይለመለኮት የተባሉ አባት “ታጣቂዎች ዘረፉን፣ ደበደቡን፥ ታጣቂዎችም ሊዳኙን መጡ” ብለዋል በሚል ወደ እስር ቤት ተጥለዋል
የዋልድባ ገዳም አባቶች የድረሱልኝ ጥሪያቸውን ያሰማሉ

የዋልድባ ገዳም አባቶች የድረሱልኝ ጥሪያቸውን ያሰማሉ

እለቱ አርብ ሚያዚያ ፲፩ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ማታ ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ሲሆን ጭልም ድቅድቅ በሆነበት ሰዓት ላይ ማይለበጣ በሚገኘው ቤተ እግዚአብሔር ላይ በከባድ የሚሊተሪ ልብስ እና ትጥቅ የታጠቁ በግምት ስድስት የሚሆኑ ታጣቂዎች በውጪ በረንዳ ላይ ተኝተው የነበሩትን መነኮሳት እና መናንያን ደብድበው እና ብዙ እንግልት አድርሰውባቸው ገንዘብ ያለው የት ነው ተናገሩ በሚል ብዙ እንግልት እና ድብደባ እንዳደረሱባቸው ከቦታው በደረሰን መረጃ መመልከት ችለናል። በመጨረሻም ታጣቂዎቹ ከመሄዳቸው በፊት ጽ/ቤቱን በሰደፍ ሰብረው ሲያበቁ በጽ/ቤት ውስጥ ያለውን ንብረት በመወርወር ሲያምሱ ቆይተው ምንም ባለማግኘታቸው ተበሳጭተው መነኮሳቱን ደብደበው እና አንገላተው ጥለው ወጥተው ለመሄድ ችለዋል።

በዚሁ አርብ ምሽት በማይለበጣ ምንም ያላገኙት ታጣቂዎች ከእኩለ ሌሊት በኃላ ማለትም ከሌሊቱ 1:00 ሰዓት ሲሆን በዳንዶሮቃ በሚገኘው የገዳሙ እህል ወፍጮ  ቤት ለነፍሳቸው በረከት ለማግኘት የሚጣደፉ ምዕመናን እገዛ ከገዳሙ ውጪ የአካባቢው ምዕመናን እህል በማስፈጨት የሚገኘውን ገቢ ለገዳሙ መጠቀሚያ እንዲሆን በተዘጋጀው መሰረት እነዚህ ታጣቂዎች በዶንዶሮቃ በሚገኘው የገዳሙ ወፍጮ ቦታ በመሄድ፥ በወፍጮ ቤቱ ውስጥ በጥበቃ እና በግልጋሎት ላይ ያሉትን ሁለት ማናንያን ፩ኛ. አባ ፍቅረ ማርያም የሚባሉትን ክፉኛ ደብድበው በሞት እና በሕይወት መካከል እስኪሆኑ ድረስ ድብደባ ደርሶባቸዋል፣ ሌላው መናኝ ገብረመድኅን የተባሉት በመስኮት ዘለው ለማምለጥ ሙከራ ሲያደርጉ ከታጣቂዎቹ አንዱ ደርሶባቸው ነበር ነገር ግን ስመ እግዚአብሔርን ጠርተው በመለመናቸው ምንም ሳይሆኑ ተርፈዋል። ታጣቂዎቹም በዘረፋቸው ወቅት ግምቱ ከ$6000.00 ብር በላይ የሆነ ገንዘብ ከወፍጮ እና የተለያየ ገቢ እጃቸው ላይ የነበረውን በሙሉ ዘርፈው አባ ፍቅረማርያምን በሞትና በሕይወት መካከል ትተው ጥለው ለመሄድ እንደሄዱ ለመረዳት ችለናል።
በሚቀጥለው ቀን የአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናት በታጣቂዎች ታጅበው ነገሮቹን ለማጣራት ነው በሚል መጥተው ተጠቂዎቹን ሲያዋክቡ፣ ምን እያደረክ ነበር? የት ነበርክ ዘረፋው ሲፈጸም፣ ለምን አንተስ አልተደበደብክም? እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች በመጠየቅ ሲያዋክቧቸው እንደነበር ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚሁ የምርመራ ሰዓት ታጣቂዎቹ ገዳማውያኑን በሚጠይቁበት ጊዜ አንድ መናኝም በእነዚህ ታጣቂዎች ወደ እስር ቤት ተወስደው እስከ አሁን ድረስም በእስር ቤት እንደሚገኙ ለመረዳት ችለናል። የታሰሩበትን ምክንያት ለማጣራት ስንሞክር እንደተረዳንው፥ የመንግሥት ታጣቂዎቹ መናኝ ኅይለመለኮትን ለእስር ያበቃቸው የተባለው “የሚዘርፉን ታጣቂዎቹ ፥ የሚዳኙንም ታጣቂዎች ምን ይሻለናል” ነገር ግን የታሰሩት መናኝ እንደተናገሩት ምንም የተናገሩት ነገር እንደሌለ በአካባቢው የነበሩት መነኮሳት ወንድሞቻቸው ምስክርነታቸውን ቢሰጡም ለእስር መዳረጋቸው ብዙዎችን አሳዝኗል፥ ሁልጊዜም እንደሚያደርጉት የሚደርስባቸውን ግፍ እና እንግልት ለመድኃኒዓለም በጸሎት እና በምኅላ ገልጸዋል።
ከዚሁ ከዋልድባ አካባቢ ሳንወጣ፥ ባለፈው ጥቂት ሳምንታት እንደዘገብነው በዋልድባ ሸንኮራ ለማልማት ይገደባል የተባለው ግድብ በመድኃኒዓለም ፈቃድ ሳይገነባ (ሳይገደብ) በመቅረቱ መንግሥት ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት በዛሬማ ወንዝ አካባቢ ያሉትን ዛሮች እያስቆረጠ ከሰል አክሳዮችን በማምጣት በከፍተኛ ሁኔታ ደኑን እየመነጠሩ ከሰል በማክሰል ላይ ይገኛሉ የአካባቢው  ነዋሪም የመጠየቅ ባይችልም ነገሩን በግርምት እየተመለከተው እንደሚገኝ እና ምን ሊመጣ እንደሚችል ለመተንበይ ባይችልም ነገሩ ግን መጠነኛ የሆነ ስጋት ሊያስድርባቸው ችሏል። እርግጥ ነው እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥትም ሆነ የመንግሥት ባለሥልጣናት የፈለጋቸውን ነገር ያደርጋሉ፣ ሲያሻቸው ያርሳሉ፣ ሲያሻቸው ይቆፍራሉ፣ ሲያሻቸው ቤተ እግዚአብሔርን ያፈርሳሉ፣ ሲያሻቸው የቅዱሳን መካናትን ይፈነቅላሉ ይህ ሁሉ ሲደረግ የገዳሙን መነኮሳት ሆነ የቤተክርስቲያን ተወካዮች ተጠይቀው አያውቁም፥ የፈለጋቸውን ነገር በፈለጉበት ሰዓት እና ቦታ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታሰሳል ነገር ግን የቦታው ባለቤት መድኃኒዓለም፥ የርስቱ ጠባቂዎች መነኮሳቱ ስለሆኑ የቦታው ባለቤት በጊዜው ሊጠይቃቸው እንደሚችል እናምናለን ነገር ግን ሁልጊዜ እግዚአብሔር አምላክ እርሱ እሳት ልብሱ እሳት የተባለለት አምላክ ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው እርሱ እሳት ልብሱ እሳት ነው፣ ማንም ፍጥረት እፊቱ ሊቆም ቀርቶ ሊቀርብ ባልቻለ ነበር፥ ነገር ግን ምሕረቱ ደግሞ ያንን እሳት አቀዝቅዞት ዛሬ አረማውያን እንደፈለጋቸው ሲሆኑ እና ሲያደርጉ ዝም ብሏቸዋል እድሜ ለንሰሐ ይሰጣቸዋል አልመለስ ቢሉ ግን በሰዶም እና ገሞራ የወረደው እሳት እና መከራ ዛሬም በእነዚህ አረማውያን ላይ እንዳይወርድ ፍራቻችን ነው ያም ከመሆኑ በፊት ወደ ልቦናቸው ተመልሰው የሀገርን ቅርስ፣ ሃይማኖትን ከማጥፋት፣ አረጋውያን መነኮሳትን ከማንገላታት እና ከማሰቃየት፣ ለወገን መኩሪያ እና ለመጪው ትውልድ ኩራት የሚሆኑትን ብርቅዬ ሃብቶቻችንን እንዲያከብሩ እና እንዲያስከብሩ ልቦናውን ይስጥልን እንላለን።
ይቆየን
ቸር ይግጠመን

IUEOTCFF
Let’s save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

↧

የመሠረታዊ ነፃነት ቀበኞች! (በሰሎሞን ተሰማ ጂ)

$
0
0

Email: solomontessemag@gmail.com or  semnaworeq.blogspot.com

UDJ Uniteየነፃነት ቀበኞች (ፀሮች) የተደራጁትም ያልተደራጁትም ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አንዳንዶቹ ጡንቻቸውን አፈርጥመው፣ ክራንቻቸውን ስለው፣ ጥፍሮቻቸውን ወድረው ሊዘነጣጥሉ የሚችሉበት አቅምና ጉልበት አላቸው፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ያ ጉልበት ስለሌላቸው፣ ቀበኛ ባሕሪያቸውን በጩኸትና በስም ማጥፋት ተግባር ላይ ተሰማርተው ያከናውኑታል፡፡ በልዩ ልዩ መልክና ቅርጽ የተደራጁት “የመሠረታዊ ነፃነት ጠሮች (ቀበኞች)” ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ገሚሶቹ በገዢነት (በፓርቲነት)፣ አንዳንዶቹ በሃይማኖታዊ ማኅበራት ሽፋን፣ ሌሎቹ ደግሞ በአነስተኛና ጥቃቅን ቡድንነት የተደራጁ አዳሚዎችና አሳዳሚዎች ናቸው፤ ቀሪዎቹ ደግሞ በአንድ-ለአምስት ሕዋስ ሥር (as a gangster) የተደራጁ “የጎበዝ አለቆች” ናቸው፡፡ በነዚህ አካላት ጭፍን አካኼድ የተነሳ፣ የዜጎች መሠረታዊ ነፃነትና መብት ይደፈጠጣል፡፡ የሥልጣናቸውና የመጉዳት አቅማቸው መጠን የተለያየ ይሁን እንጂ፣ ሁሉም የመሠረታዊ ነፃነት ቀበኞች (ፀሮች) ናቸው፡፡ ለምን እንደሆኑና እንዴትስ ከዚህ ደረጃ እንደደረሱ ለማሳየት ጥረት አደርጋለሁ፡፡
የሥነ-መንግሥት ተመራማሪዎች፣ ልዩ ልዩ ዓይነት ነፃነት አለ-ይላሉ፡፡ ሁሉንም ለመዘርዘር አልቃጣም፡፡ ለምሳሌ ያህል፣ የሐሳብ መስጠት ነፃነት፣ አንድ ሰው አምላኩን ሃይማኖቱ በሚፈቅደው መንገድ የማምለክ ነፃነት፣ ተሰብስቦ የመወያየት ነፃነት፣ የመናገርና የመፃፍ ነፃነት፣ እና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትና ነፃነት፣የመሳሰሉት እያሉ ይዘረዝራሉ፡፡ ሁሉም ታዲያ “ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ነው የሚከወኑት” ይላሉ፡፡ አልተተገበረም አንጂ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ-መንግሥት በአንቀጽ 27 መሠረት፤ የሃይማኖት፣ የእምነትና የአመለካከት ነፃነት የዜጎች መብት እንደሆነ ይደነግጋል፡፡ በተጨማሪም፣ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 30 መሠረት፣ የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የመድረግ ነፃነትና አቤቱታንም የማቅረብ መብትን በተመለከተ ነጩ ወረቀት ላይ ሰፍሯል፡፡ ግን አልተተገበረም፡፡ የከፋ በደል ነው፡፡ የበደልም በደል! (“የሰው ልጅ በሠለጠኑትም ሆነ ባልሰለጠኑት አገሮች መሠረታዊ ነፃነት እንጂ ፍፁም ነፃነት ሊያገኝ እንደማይችል የሚታወቅ ነው፤” ሲሉ ተመራማሪዎቹ ያክላሉ፡፡)
ስለ“መሠረታዊ ነፃነት” ምንን ከመጻፌ በፊት፣ ስለዚህ የነጻነት ዓይነት ለመፃፍ ያሳሰቡኝን ምክንያቶች ላነሣ እፈልጋለሁ፡፡ የመጀመሪያው የሩዶልፎ ግራዚያኒ ደጋፊዎች በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 30 መሠረት፤ “የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የመድረግ ነፃነትና አቤቱታንም የማቅረብ መብትን” እንዴት በካልቾ እንደመቱት በመመልከቴ ሲሆን፤ ሁለተኛው ምክንያቴ ደግሞ፣ አንዳንድ ሰዎች (በግልም በቡድንም ሆነው) እንዴት የሌሎችን መሠረታዊ ነፃነት እንደሚጣረሩ ለማሳየት ነው፡፡ ከሁሉ አስቀድሜ ግን፣ “ነፃነት ማለት ምንድነው?” የሚለውን ጥያቄ ለመመለስም እሞክራለሁ፡፡ በአቦ ሰጡኝ የመጣልኝ መልስ፣ “ነፃነት የሰው ልጅ ከአላህ ወይም ከእግዚአብሔር (አዳላህ እንዳትሉኝና ከእግዚአብሔር ወይም ከአላህ) በተፈጥሮ የተሰጠውን ክብር መጠበቂያው ሚዛን ነው፡፡” የሚል ሆነ፡፡ መሠረታዊ ነፃነት የሌለው ሰው፣ በሰው ፊት ሰው የበለጠው፣ ከሰው በታች የሆነም ነው፡፡ ነፃነት የሌለው ሰው፤ በሰው ፊት የተዋረደ፣ የተናቀ፣ ሕቁር (Inferior) ፍጥረት ነው፡፡ ነፃነት የሌው ሰው በአፀደ ሕይወት ቢኖር እንኳን፣ መኖሩ እንደሰው ሳይሆን እንደዕቃ፤ እንደ“እንትና” ሳይሆን እንደ“እንትን” የሚታይና የሚቆጠር ፍጡር ነው፡፡ “እንትን” የሚል ቅጽል የሚሰጠው፣ መሠረታዊ ነፃነት ለሌለው ሰው ነው፡፡ እንትንነት ክብራቸውን በፍርፋሪ ለሸጡና መሠረታዊ ነፃነታቸውን ለተገፈፉ የሚሠጥ ቅጽል ነው፡፡ ለሕቁር ፍጥረታት የሚሠጥ ቅጽል ነው፡፡ እንደዔሳው የብኩርና ክብራቸውን በምስር ንፍሮ ለሸጡና ለለወጡ ፍጥረታት የሚሠጥ ስያሜ ነው፡፡ እነዚህ አምላክ/ፈጣሪ በተፈጥሮ የሰጣቸውን ክብር የቸበቸቡ ፍጥረታት ደግሞ፣ ሰላማዊ ሰልፎችን የሚከለክሉ፣ የመናገርንና የመጻፍን መብት ለመገደብ የሚንጠራወዙ፤ ፖሊስ ወይም የፀጥታና ደኅንነት ኃይል ተቀጣሪዎች ሲሆኑም ሌሎችን በዱላ የሚደበድቡ፣ የሚሳደቡና በተራ ስም አጥፊነት ተግባር የሚጠመዱ ናቸው፡፡ ኅቁር ፍጥረታት ክብር ስለሌላቸው፣ ማንንም አያከብሩም፡፡
ኅቁር ፍጥረታት ሰላማዊ ሰልፍ ሲሏቸው፣ እፊታቸው ድቅን የሚልባው የአመጽ ሰልፍ ነው፡፡ ለኅቁር የፀጥታና የዘመኑ ሹሞች የሚታያቸው፣ በሕግ ፊት ሰዎች እኩል መሆናቸው ሳይሆን፣ ተደብዳቢነታቸው ነው፡፡ ኅቁራን ሹሞችና አሽቃባጮቻቸው፣ ሰብዓዊ መብትን መጣስና መሠረታዊ ነፃነትን ማሳጣት የእንጀራ ገመዳቸው እንዳይበጠስ ማረጋገጫ ነው፡፡ ኅቁራን ባለሥልጣኖች፣ የጉልበት ሥልጣን እንጂ የመንፈስ ሥልጣን የላቸውም፡፡ ለኅቁር ፍጥረታት፣ ካላግባብ በአሸባሪን ስለታሰሩ ወገኖቻችን ሲነገራቸው፣ እንደሰረሰር ሰርሳሪ የቄራ ለማጅ፣ ዋናውንና ሙዳውን ስጋ ትተው አገጭና ሌንጬጭ ይፈልጣሉ፡፡ ኅቁራን ፍጥረቶች፣ “ለአህያ ማር አይጥማትም” እንደሚባለው፣ ትልቁ ዓላማ አይጥማቸውም፡፡ ለኅቁር ፍጥረታት፣ መሳደብና ስም ማጥፋት ቋሚ ተግባራቸው ነው፡፡ ለኅቁራን፣ መቼም ቢሆን የቃላት ስንጠቃና “ከቁንጫ መላላጫ” ማውጣት የተለመደ ተግባር ነው፡፡
እንደአለመታደል ሆኖ ብዙዎቹ የኢትዮጵያ ገዢዎች የዔሳው የመንፈስ ልጆች ናቸው፡፡ የእነሱ አጫፋሪዎችና ሎሌዎቻቸው ደግሞ የባሰባቸው “ኅቁሮች” ናቸው፡፡ ኅቁርነት፣ “ከመምህሩ ደቀ-መዝሙሩ” እንደሚባለው እየከፋና እየሰፋ የሚሄድ ነቀርሳ (Cancer) ነው፡፡ በቅርቡ ፕሮፌሰር መስፍን እንዳሉት፣ ኅቁራን “በቆብ ላይ ሚዶ” የሚሽጡም ናቸው፡ በዚህ አላዋቂነትና ጠብደል መታወር ውስጥ እየኖሩ እንደምን የሌሎችን መሠረታዊ ነፃነት ሊያከብሩ ይችላሉ? ፈጽሞ ፈጣሪ ለሰው ልጆች ስለሠጠው መሠረታዊ ነፃነት ስለማያውቁ፣ ወይም በያውቁም ሆን ብለው ስለሚክዱት፣ የሌሎችን ነፃነትና ክብር የገፋሉ፡፡ (ኋላ እመለስበታለሁ፡፡) አባቶቻችን አገራችን በተወረረች ጊዜ ነፃነትን አጥቶ ሆድን በፓስታና በሹታ ጎስሮ፣ ገላን በአቡጀዲና በጨርቅ ሸፍኖ ከመንቀዋለል ይልቅ፣ መሠረታዊ ነፃነትን ማጣት ምን እንደሚደርስባቸው ስላወቁ፤ “ነፃነት ወይም ሞት!” ብለው በጀግንነት ተጋድለው አለፉ፡፡ በፍርሃትና በጥቅመኝነት ታውረው፣ “ከመሞት መሰንበት” ያሉትም ቢሆኑ፣ ያለመሠረታዊ ነፃነት መኖር ምን ምን እንደሚል አሳምረው ቀምሰውታል፡፡ በዱር በገደል የተጋደሉትና በእስር አዚናራ የተጋዙት ምንኛ እድለኞች ነበሩ?
በነሐሴ 1960 ዓ.ም በወጣው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ላይ ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ፣ ስለመሠረታዊ ነፃነት ሲያወሱ፣ “የባሕል ነፃነት ነው” በማለት ሊገልፁት ሞክረዋል (ገጽ 5 ላይ ይመልከቱ)፡፡ “በሀገራችንና በሕዝባችን ዘንድ የባሕል ነፃነት ወይም የመሠረታዊ ነፃነት ከነትርጉሙም አይታወቅም፡፡ ነገሩ ግን የሀገርን ነፃነት የማጣትን ያህል ደም የሚያፋስስ ነው፤” (የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ ነሐሴ 9/1960)፡፡ ይሄው የመሠረታዊ ነፃነትን የማጣትና የማሳጣት ተንኮል፣ ከጥንት ጀምሮ በምዕራባውያን (በቄሳራውያን ሃይሎች) ዘንድ የተለመደ ተግባር ነው፡፡ መሠረታዊ ነፃነት ገፈፋው ዘዴ በጣም ረቂቅና ስልታዊም ነው፡፡ ከባሕልና ከመሠረታዊ ነፃነት ገፈፋ ስልቶች መካከል አንዳንዶቹን ለመጥቀስ እፈልጋለሁ፡፡ የመጀመሪያው ዘዴ፣ የገዢዎችን መብት ለአንዳንድ ተገዢዎች መስጠት ነው፡፡ ሁለተኛ፣ ተገዢዎች ማንነታቸውን ክደው፣ የሀገርና የብሔራዊ ስሜታቸውን ማስካድ ነው፡፡ ሦስተኛውና ዋናው ችግር ደግሞ፣ ተገዢው ባሕሉንና ወጉን እንዲንቅና በራሱ እንዳይተማመን የማድረግ የሥነ-ልቦና ክሽፈት ነው፡፡
ከመጀመሪያው ነጥብ ጀምሮ መተንተን ያለበት ነው፡፡ ገዢዎቹ ለአንዳንድ ተገዢዎች፤ “በብሔር፣ በዘር ወይም በሃይማኖት ተዋጽዖ ስም” የይስሙላ የገዢነት መብት ይሠጧቸዋል፡፡ የአገሩን ሰርዶም በአገሩ በሬ ማለት እንደዚህ ነው እያሉ ይደልሏቸዋል፡፡ ጣሊያን አንዴ ልጅ አያሱን ልጅ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ የአፄ ዮሐንስን ወይም የንጉሥ ተክለ ሃይማኖትን ልጆች ከተገዢነት አውጥታ ገዢ ልታደርጋቸው ያልፈነቀለችው ድንጋይ አልነበረም፡፡ ገዢዎች የሚከተሉት ስልትና ብልሃት ተመሳሳይ ነው፡፡ መሠረታዊ ነፃነቱን የተገፈፈው ሰው፣ የነፃነት ገፋፊውን ቋንቋና አነጋገር በቅጡ እንዲኮርጅ ከተደረገ በኋላ፣ የነፃነት ገፋፊውን አገር ዜጎች ያላቸውን ክብርና የይስሙላ ማዕረግ ይሰጡትና፣ የትውልድ አገሩንና የወገኖቹን መሠረታዊ ነፃነት የሚንድ “ምልምል አሽከር” ይሆናል፡፡ እንደዚያ ለመሆን የሚጠበቁበት ነገሮች ቀላል ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ቋንቋውን ማጥናት፣ ሁለተኛ፣ የወራሪውን ሀገር ዜጎች አክባሪ መሆኑን ለማሳየት መስገድ/እጅ መንሳት፣ ሦስተኛ፣ የወራሪውን አገር ከትውልድ አገሩ በላይ እንደሚያፈቅርና እንደሚወድ ማሳየት ነው፡፡ በተቻለ መጠን የሀገሩ ሕዝብና የሀገሩን ፍቅር ክዶ የብሔራዊ ስሜቱን አንጠፍጥፎ ደፍቶ ሞራለ-ቢስ መሆን በቂው ነው፡፡ ያን ጊዜ፣ ከተገዢነት ወጥቶ፣ የፈረስ ስም ተሰጥቶት፣ (ማጆር፣ ወይ ሰር፣ አልያም ደግሞ አፈ-ቄሳር፣ ማንትሴ እየተባለ) የይስሙላ ገዢ/ሹም ይሆናል፡፡ እንዴት ዓይነት አዘቅት ነው ጃል!
ሌላው ከተገዢነት ደረጃ ወጥቶ ወደ ይስሙላ ገዢነት መብት የሚደርስ ሰው፣ ከአፋፉ ጫፍ ላይ ለመድረስ ክህደትን የሙጥኝ ማለት አለበት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የይሁዳ ሰው ሆኖ ሳለ፣ የገዢዎቹን ሮማዊነት መብት ያገኘውና ከእስር ቤት የተለቀቀው በዚሁ መንገድ ነው፡፡ እንደጳውሎስ ያለውን መብት ያገኘ ሰው፣ ከእስር ቤት ወጥቶ ስለፎለለ ነፃነትን ያለገደብ ያገኘ ይመስለዋል፡፡ ለሌሎች ተገዢዎችም ትልቅ ሰው መስሎ ስለሚታያቸውና በየአደባባዩም ስለሚወጣጠርና ስለሚበጣጠስም ጭምር፣ እርሱን መስሎ ለመገኘትና እርሱ የደረሰበት የክህደት አፋፍ ላይም ለመቆም ብዙ ወገኖቹ በማመጽ ፈንታ ጀርባቸውን ለሸክም፣ ኅሊናቸውንም ለሎሌነት ይሰጡታል፡፡ ተገዢዎች መሠረታዊ ነፃነታቸውን ለማግኘት ከመታገል ይልቅ፣ የገዢነትን መብት ለማግኘት ይንጠራወዛሉ፡፡ ብዙዎችም ነፃነት የሚባለውን አኃዝ ከነመኖሩም ይረሱታል፡፡ ትግሉ ሮማዊ፣ እንግሊዛዊ፣ አሜሪካዊ፣ ፈረንሳዊ፣ ጣሊያናዊ፣ ሳዑዲአረባዊ ወይም ሊባኖሳዊና ኳታራዊ ምንትስ ለመሆን መንጠራራት ይሆናል፡፡ ገዢዎች ከሚሠሩት ሃጢያት ሁሉ እንዲዚህኛው ዓይነት በክፋት የተሞላና የረጅም ጊዜ ቀውስ የሚያስከትል መርዝ የለም፡፡
ነፃነት ገፋፊዎች ይሄንን ሳያደርጉ ሁለት ዓላማዎችን ይዘው ነው፡፡ 1ኛ) የገዢዎቹን (የራሳቸውን) ትልቅነትና የሌላውን ትንሽነት አሳምኖ የበላይም ሆኖ ለመኖር የተዘየደ ደባ ነው፡፡ 2ኛ) አገሩና ሕዝቡም የኋላ ኋላ የይስሙላ ነፃነት ሲሰጠው፣ የባሕል ተገዢ ሆኖ እንዲቀርና የመሠረታዊ ነፃነት ጣዕም ሳይቀምስ እንዲቀር ለማድረግ የተሸረበ ታክቲክ ነው፡፡ በመሆኑም ነፃነት ገፋፊዎች በእቅድና በብልሃት ወደ ዓላማቸው ይደርሳሉ፡፡ አንዱ ዘዴ ከላይ የጠቀስነው የገዢነት መብት መስጠት ሲሆን፣ ሁለተኛው ዘዴ ደግሞ የነሱንና የባሕላቸውን ትልቅነት እንዲሁም ከፍተኝነት የተገዢዎቹንና የባህላቸውን ትንሽነትና ዝቅተኝነት ከልጅነታቸው ጀምሮ በማስተማር ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ትምህርት በአንድ ሕዝብ አእምሮ ውስጥ ሲቀረጽ ባሕል ለዘላለሙ ይጠፋል፡፡ አብሮትም መሠረታዊ ነፃነት ድራሹ ይጠፋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በየአውደ ምህረቱ፣ በየመስጂዱ፣ በየማኅበር ቤቱና በየመንዙማ ዝየራው፣ በየጽዋውና በየወዳጃ ቤቱ ሳይቀር የባሕል ወራሪዎቹ ትልቅነት ስለሚሰበክና ስለሚደሰኮ ዜጎች ከማይወጡት የመሠረታዊ ነፃነት እጦት ውስጥ ገብተው እንዲዘፈቁ ይዳርጋሉ፡፡ የፖሊስና የወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ ስለገዢዎች የበላይነትና ስለሠልጣኞቹ የበታችነት በዘዴ እንዲማሩ ይደረጋል፡፡ ከዚያ ፀጥ-ለጥ ብለው ተገዢ ከመሆን ውጭ ምርጫ አይኖራቸውም፡፡ ጃስ ሲሉት የሚናከስ፣ ጭላጭ ሲያቀርቡለት የሚልስ ውሻና ድመት ይሆናል፡፡
የተገዢዎቹን ሥነ-ልቦናም የበለጠ ለማኮስመንም ሲባል፣ ገዢው በተገዢው ዓይን ከታምራት የማያንሱ ነገሮችን ሲሰራ እንደነበረና እየሠራም እንዳለ ተደርጎ በየመድረኩና በየአደባባዩ ይደሰኮራል፡፡ ተገዢው ሕዝብ የፈለገውን ያህል ቢማርና ጥበበኛ ቢሆን እንኳን፣ ገዢዎቹ የሚሠሩትን ምትሃት ከቶም የማይደርስበት “ራዕይ” መሆኑን እንዲገነዘብ ተደርጎ ይሰበካል፡፡ የገዢዎቹ ራዕይና አርቆ-አሳቢነት ከሞቱም በኋላ በመገናኛ ብዙሃን እየተደሰኮረለት፣ ለሙት መንፈስ ሳይቀር ታማኝ ሆኖ እንዲገዛ ይደረጋል፡፡ ዱሮ-ዱሮ “ሰማይ አይታረስ፣ ንጉሥ አይከሰስ” ነበር የሚባለው፡፡ አሁን ደግሞ “ከጓድ አብዮታዊ መሪያችን ጋር ወደፊት!” ወይም “ከባለራዕዩ መሪ ጋር ወደፊት!” በሚል ሽፋን፣ ሕዝቡ መሠረታዊ ነፃነቱን እንዳይጠይቅ፣ አልፎ-ተርፎ ነፃነቱን ሲገፈፍም ዝም ብሎ እንዲያይ፣ “አሜን” ብሎ እንዲገዛም ያመቻቹታል፡፡ (ብቻቸውን አይደለም፣ ጭፍራና ጀሌ አስከትለው ነው፤ ካድሬዎቻቸውን አስደግድገው ነው፡፡)
ፕ/ር ጌታቸው እንደጠቀሱት፣ ገዢዎች የሚፈጽሙት ሦስተኛው መቅሰፍት ከሁሉ የባሰ ነው፡፡ ተገዢዎች ነፃ ቢወጡ እንኳን ራሳቸውን ችለው የሚያድሩም እንዳይመስላቸው አድርገው በባዶ ፕሮፓጋንዳ ያሸብሯቸዋል፡፡ ገዢዎቹ (ከሃሊዎቹ) የሌሉበት ነገር እንደሚዘባረቅ፤ “እነርሱ ያልገዙት አገር እንደሚበታተን፤ ዜጎች እንደ ሩዋንዳና ቡሩንዲ እንደሚተላለቁ፣” ሟርትና ጥላቻን  ይደሰኮራሉ፡፡ ባዶ ሟርትና ፕሮፖጋንዳ መሆኑን ለመረዳት ተገዢዎች ለማመን እስኪቸገሩ ድረስ ፕሮፓጋንዳ ይሠራባቸዋል፡፡ ያንንም ለማወቅ፣ “በእርግጥ ባህላችንና እምነታችን የተመቸ ነውን?” ብሎ የሚጠየቅ ሰው ያስፈልጋል፡፡ ያን ጊዜም፣ የገዢዎቹ ሟርትና ማስፈራሪያ በሥልጣን ከመቆየት የዘለለ ቁብ እንደሌለው ይረዳል፡፡ “ጠመንጃ ነካሾች፣ በሥልጣን ኮርቻው ለመፈናጠጥና ለመቆየት ብለው የሚነዙትን ሽብር ፋይዳ-ቢስነት ለመረዳት፣ በመጀመሪያ ባህልን ጠንቅቆ ማወቅ” እንደሚያስፈልግ ኤድዋርድ ሳይድ Orientalism በተባለው መጽሐፉ ይመክራል፡፡
ስለባህል ምንነት ለመረዳት የሚፈልግ ሰው ካለም፣ “ባሕል ማለት ቋንቋ፣ ዜማ፣ ዘፈን፣ የአለባበስ ዓይነትና ዘዴ፣ የጸሎት ወይም የአምልኮ ሥነ-ሥርዓት፣ ከቤተሰብና ከጎረቤት ጋር ያለው ተራክቦ፣ በአረጋውያንና በልጆች ብሎም በወራዙት መካከል ያለውን ግንኙነትና ሥርዓት እንዴት ነው?” ብሎ መጠየቅና መመርመር አለበት (ፕ/ር ጌታቸው፣ 1960)፡፡ እስከምናውቀውና እከተረዳነው ድረስ፣ የኢትዮጵያውያን ባሕል በፈሪሃ እግዚአብሔር ላይ የተመሠረተ ነው በመሆኑ፣ ዕልቂትን አያስከትልም፡፡ እልቂት ቢከሰት እንኳን የእልቂቱና የግድያዎቹ ፈፃሚዎች ራሳቸውንና ሀገራቸውን ክደው፣ የገዢዎቹ ደረጃ ላይ ደርሰናል በሚሉት የነፃነት ገፋፊዎች ጭካኔ የሚፈፀም ነው፡፡ የእውነተኛ ኢትዮጵያውያን መዋግደ ኅሊና የተገራና ፈሪሃ-እግዚአብሔር ያለው በመሆኑ፣ ለጭካኔ ብርታት የለውም፡፡ ትክክለኛ ኢትዮጵያውያን ኅቁር ፍጥረታት አይደሉም፡፡ ከነፃነታቸውና ከሰብዐዊነታቸው ያለፈ፣ የሚያስቀድሙት ሃብትም ሆነ ሥልጣን የላቸውም፡፡ ኅቁር ፍጥረታት ከፈረሱ በፊት ጋሪውን ያስቀድማሉ፡፡ “ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ይቅደም!” ሲሏቸው፣ “መልካም አስተዳደር እናሰፍናለን!” ይላሉ፡፡
ምዕራባዊያኑም ሆኑ አንዳንድ የምስራቅ አገሮች በአገራችን ላይ የባሕልና የመሠረታዊ ነፃነት ገፈፋን ስፖንሰር ያደርጋሉ፡፡ በከተሞቻችን አካባቢ እንደምናየው፣ ኦርቶዶክስሰ ክርስቲያኖቹ እንደሶሪያና ሊባኖስ ካህናት፣ ሙስሊሞቹም እንደ ሳዑዲና የመን ሼኪዎች፣ ካቶሊኮቹም እንደቫቲካን ቀሳውስት፣ ፕሮቴስታንቶቹም እንደጀርመንና አሜሪካን ፓስተሮች ለመሆን ይቸጋገራሉ፡፡ የሃይማኖትና የፖለቲካ መሪዎቹ፣ ራሳቸውን ክደው በሌሎች ባሕል ኮራጅነት ተጠምደው እሽቅድምድም ይዘዋል፡፡ ከራሳችን አለባበስ የእነርሱ አለባበስ፤ ከራሳችን ዜማና ዘፈን የነርሱ ጋጠወጥ ስልት፣ ከራሳችን የቤተሰብ ኑሮ የነርሱ ቤተሰባዊ ኑሮ፣ ከራሳችን ወግና ሥርዓት የነርሱ ወግና ሥርዓት፣ ከራሳችን አገር የነርሱ አገር የሚሻል መሆኑን ሊያሳምኑን ጥረዋል፡፡ የዚህ የዚህ ታዲያ፣ በዓድዋና በማይጨው ለምን የብዙ ኢትዮጵያውያን ንፁህ ደም ፈሰሰ? በሽንብራ ኩሬና በመተማ፣ በዶጋሊና በኦጋዴን ለምን ጀግኖች ተሰው? አገራችን እንዳትገዛና በእነርሱ እንዳትተዳደር አልነበረምን?!” እንጂ፤ “አገሪቱማ ሳትገዛና ሳትተዳደር መቼ አድራ ታውቃለች! ዋናው ምክንያት እነሱ በምንም መልኩ እንዳይገዙን መሰረታዊ ነፃነታችንን እንዳናጣ አልነበረም እንዴ? የራሳችን ባህል እንድንጠብቅና የነሱን ባህል እንዳንይዝ አልነበረምን?” አሁን ታዲያ ምን ነካን? ምን ዓይነትስ ጥንጣን በላን? ምን አነቀዘን? (ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ፣ 1960፡፡)
ከላይ በጠቀስነው መጣጥፋቸው ላይ ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ እንደገለጹት ከሆነ፣ “በማናቸውም ረገድና በየትኛውም ሥርዓት ውስጥ መሠረታዊ ነፃነት እንጂ ነፃ ነፃነት የለም፡፡” ነፃ ነፃነት (Absolute Freedom) የሌለው፣ በነፃ ነፃነት ውስጥ መኖርም ስለማይቻል ነው፡፡ ነፃ ነፃነት አለ ካልን፤ የሕዝቡ የርስ በርስ ግንኙነት ባዶ (ዜሮ) ነው ማለታችን ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ኃላፊነትና ግዴታ እስካለ ድረስ “ነፃ ነፃነት” የለም፡፡ ያለው መሠረታዊ ነፃነት ነው፡፡ አንዱ ከሌላው የሚቀበለውና ለሌላውም የሚሠጠው እስካለው ድረስ ነፃ ባህልም የለም፡፡ አንዱ ከሌላው ይዋሳል፤ ያውሳልም፡፡ ነፃ ባህል የለም፤ ነፃ ነጻነትም የለም፡፡ ያለው መሠረታዊ ባህልና መሰረታዊ ነፃነት ነው፡፡ ግራዚያኒን ለመቃወም ሰልፍ መሰለፍ አትችሉትም የሚሉትና የሚያስሩት ወገኖች፣ የመሠረታዊ ነፃነት አፈና እያካሄዱ ነው፡፡ አንድ ሃሳብ ወይም አጀንዳ ሲነደፍ የሚጮኹና የሚፎክሩትም ወገኖች፤ መሠረታዊ ነፃነትን ለመግፈፍ በአነስተኛና ጥቃቅን ገዢነት ተግባር ላይ የተሰማሩ ናቸው፡፡ ሃሳቡን ሳይሆን አሳቢውን የሚዘልፉና የሚሳደቡም ኅቁራን ካሉም፤ አንድ ለአምስት የተደራጁ የገዢዎቹ አባሪዎችና ተባባሪዎች ናቸው፡፡ ከዚህ ሌላ አይደሉም፡፡
መሠረታዊ ነፃነትን የሚገድበው መንግሥት የሚባለው አካል ብቻ አይደለም፡፡ የመንደር ጎረምሳ፣  የቀዬ ጠብደልና የአጥቢያም ጎበዝ አለቃ ጭምር ናቸው፡፡ በግሌ መሠረታዊ ነጻነትን የሚገፍን አገዛዝ፣ ሥርዓትና መንግሥታዊ መዋቅር ለማጋለጥና አላህ ወይም እግዚአብሔር የሰጠኝንም ነፃነት ለማስከበር እጥራለሁ እንጂ፤ በአንድ ለአምስት ወይም በአነስተኛና ጥቃቅን ከተደራጁ የመሠረታዊ ነፃነት ገፋፊዎች ጋር ቅንጣት ሴኮንድም አላጠፋም፡፡ በአንድ ለአምስት ወይም በአነስተኛና ጥቃቅን የጎበዝ-አድማ ላይ ለተሰማሩት ወገኖቼም ሆነ ለሌሎች ኢትዮጵያውያን የምናገረው ሃይለ-ቃልም የሚከተለተው ነው፡፡ “እርስ በርስ መፎካከታችንን ትተን፤ መሠረታዊ ነፃነታችንን የሚገፉትንና እያወናበዱ እንግዛችሁ የሚሉንን፤ ካድሬ ሆናችሁ፣ ሎሌ ሆናችሁ ቋንቋችንን ተናገሩ፤ የእኛን ባሕል ተከተሉ፣ የእኛን ሃይማኖት እመኑ፣ እናንተ ምንም ስለማታውቁ፣ እኛ ሁሉንም እናውቅላችኋለን፤ በአጠቃላይ “እኛን ምሰሉ” ባዮችን የአገዛዝ ዘመን እናሳጥር፡፡ እርስ በርስ ስንቦቃቀስ፣ የገዢዎቻችን እድሜ አራዝመን የእኛንም ሆነ የሕዝባችን ስቃይ ከማራዘም፣ የመሠረታዊ ነፃነት ገፋፊዎችን ጎራ ከማጠናከር በስተቀር የምናተርፈው ቅንጣት ታክል ፍርፋሪም ሆነ ሰደቃ እንደሌለ ማወቅ አለብን፡፡ አይመስላችሁም ጎበዝ?! (የሳምንት ሰዎች ይበለን!)
↧

በዉጭ ያሉ ተቃዋሚዎችን ለማሰባሰብ የሚረዱ ነጥቦች –ክፍል አንድ

$
0
0

አማኑኤል ዘሰላም
ሚያዚያ 11 ቀን 2005 ዓ.ም
amanuelzeselam@gmail.com

በዉጭ አገር የፖለቲካ ድርጅቶች ነን የሚሉ ፣ የፖለቲካ ድርጅቶች አይደለንም ብለውም በፖለቲካዉ ጨዋታ ድምጻቸውን የሚያሰሙ ጥቂቶች አይደሉም።  የኢሳት ቴሌቭዥን አለ። በርካታ ድህረ ገጾች አሉ። ራዲዮ ጣቢያዎችማ በተለይም በዲሲ በሽበሽ ናቸው። በተለያዩ ጊዜ ፣ በተለያዩ ጉዳዮች የተለያዩ የአቋም መግለጫዎች፣ በተለያዩ ድርጅቶች ይወጣሉ። መግለጫዎቹ በሙሉ «ተቃዋሚዎች በአንድ ላይ መሰባሰብ አለብን፤ በአንድ ድምጽ መናገር መቻል አለብን፤ ከሌሎች ጋር አብሮ ለመስራት ድርጅታችን ያለዉን ቁርጠኝነት ያረጋግጣል» የሚል ይዘት ነበራቸው።

ሰሞኑን ከቤኔሻንጉል በተፈናቀሉ ወገኖቻችን ላይ የተከሰተዉን የዘር ማጥፋት ወንጀል አስመልክቶ፣ እንደለመድነዉ፣ የመግለጫ ናዳዎች ከተለያዩ በዉጭ አገር ካሉ ማእዘናት እያነበብን ነዉ።  ዜጎች፣ ድርጅቶች የተሰማቸዉን ስሜት መግለጻቸው በራሱ ችግር የለዉም። ተገቢም ነዉ። ነገር ግን ዛሬም ትግላችን፣ መግለጫዎች በማውጣት ላይ ብቻ የተወሰነ መሆኑ ግን በጣም ያሳዝናል።

እንግዲህ መግለጫዎች ከማውጣት ያለፈ ሥራ ለመስራት፣ አንዱና ዋናዉ አስፈላጊ ነገር ትብብር ነዉ። በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ተሰሚነት እንዲኖረን፣ ዉጭ ያለዉም ሕዝባችን በኛ ላይ ያለዉ ድጋፉ እንዲበዛ፣  በሚያስማሙ ነጥቦች ላይ አብረን መስራት መቻል አለብን። ለዚህም አብረን እንዳንሰራ መሰናክል የሆኑብንን  ችግሮች ማስወገድ ይገባል።

በኢትዮጵያዉያን መካከል መሰባሰብና መስማማት እንዳይኖር ያደረጉ ሶስት ችግሮች አሉ። የመጀመሪያዉ ከሻእቢያ ጋር አብሮ የመስራቱ ሁኔታ ነዉ። «ወያኔን ለመጣል እስከረዳን ድረስ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነዉ» በሚል የተሳሳተ መርህ፣ ሁለቱም የኦነግ አንጃዎች እና የግንቦት ሰባት ንቅናቄ የመሳሰሉቱ  ከአቶ ኢሳያስ መንግስት ጋር በቅርበት የሚሰሩ ናቸው።

አብዛኞቻችን ሻእቢያን ከኢሕአዴግ ያልተሻለ እንደዉም የባሰ አድርገን ነዉ የምናየዉ።  በኤርትራ በኩል የሚደረገዉንም ትግል አጥብቀን እንቃወማለን።  በዚህም ምክንያት አፍቃሪ ሻእቢያ በሆኑና በተቀረነዉ መካከል ትልቅ ገደል ተፈጥሮ ነበር።

ይሄ እንግዲህ እስከአሁን የነበረው ነዉ። ከሻእቢያ ጋር በመስራቱ ዙሪያ፣  ከአሁን በኋላ መከፋፈል ይኖራል ብዬ ግን አላስብም። ከሻእቢያ ጋር እንስራ የሚሉ ሰዎች እንደተሳሳቱ የተረዱበት ሁኔታ ነዉ ይመስለኛል። በተለይም የአርበኞች ግንባር አመራር አባላት መገደላቸዉና መሰወራቸው፤ የጀነራል ከማል ገልቹና ጀነራል ሃይሎ ጎንፋ መታሰር፣ የግንቦት ሰባት ጥቂት ሰራተኞች አስመራን ለቆ መዉጣት፣ አንጋፋ የተባሉ፣ አፍቃሪ ሻእቢያ የነበሩ፣ የኦነግ መስራቾችና የአመራር አባላት ኦነግን በአዲስ መልክ በአዲስ ስም አዋቅረዉ፣ ከሻእቢያ ጥገኝነት ነጻ የሆነ እንቅስቃሴ መጀመራቸው፣ የተባበሩት መንግስታት በኤርትራ ላይ የዘረጋዉ ማእቀብ፣ በአስመራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየታየ የመጣዉ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣  በኤርትራ በኩል የመታገል ፖለቲካ የማያዋጣ፣ የማያስኬድና እራስን እንደማጥፋት ያህል የሚያስቆጥር መሆኑ የሚያመላክቱ ናቸዉ።

በመሆኑም «ትግል በኤርትር በኩል ይደረግ አይደረግ» የሚል ክርክር፣  ከአሁን በኋላ ሊነሳ ይችላል ብዬ አላስብም። እንዳንስማማ ያደረገ ይሄ አንዱ ትልቁ መሰናክል ተወገደልን ማለት ነዉ።

ሁለተኛው መሰናክል የትጥቅ ትግል ወይስ ሰላማዊ ትግል የሚለዉ ነዉ። የትጥቅ ትግል ለማድረግ ቤዝ ያስፈልጋል። በርካታ የትጥቅ ትግል እናደርጋለን የሚሉ ቡድኖች አስመራ መጀመሪያዉኑ የተከሉት በዚሁ ምክንያት ነበር። መሳሪያ፣ መድሃኒት፣ ምግብ የሚያቀብላቸው፤ ወታደሮቻቸዉን የሚያሰለጥኑበት ኮሪዶር ያስፈልጋቸዋል። በኤርትር በኩል መስራቱ የማያወጣ በመሆኑ፣ ኤርትራን ካልተጠቀመን ደግሞ ሌላ ሊረዳ የሚችል ጎሮቤት አገር ባለመኖሩ፣ የትጥቅ ትግል ማድረጉ፣ ብንፈልገዉም፣ የማይቻል ነዉ።

«አይ የትጠቅ ትግሉን በአገር ዉስጥ ማካሄድ ይቻላል» የሚል ሃሳብ ሊቀርብ ይችላል። ይሄ ደግሞ በስድሳዎቹ እንደ ኢሕአፓ ያሉ የሞከሩት፣ ብዙ ወጣቶች ያሰጨረሰዉ  አይነት፣ አሁን ደግሞ በሲሪያ እያየን እንዳለነው፣  እንኳን ሊሞከር ሊታሰብ የማይገባ ነዉ።

ስለዚህ የትጥቅ ትግል ማድረጉ ዉጤት ካላመጣና ጠቃሚ ካልሆነ፣ እንቀጥለው እንኳን ብንል መቀጠል የምንችልበት ሁኔታ ከሌላ፣ ጥይት፣ መድሃኒት  የሚያቀርብለን የጎሮቤት አገር  ድጋፍ ካለገኘን፣ የትጥቅ ትግሉን እንደ አንድ አማራጭ መዉሰድ አይቻልም። በመሆኑም «ሰላማዊ ትግል ወይስ የትጥቅ ትግል» የሚል ክርክር ከአሁን በኋላ የሚነሳበት ምክንያት የለም። እንዳንስማማ ያደረገ ሁለተኛዉ ትልቁ መሰናክል በዚህ መልኩ ተወግደልን ማለት ነዉ።

ሌላዉ በዳያስፖራ ያሉ ተቃዋሚዎች እንዳይተባበሩ መሰናክል የሚፈጥረዉ ጉዳይ ቢኖር የአገር ቤቱ ትግል ነዉ። አንዳንዶቻችን በዉጭ ሆነን የአገር ቤት ትግሉን መምራት እንፈልጋለን። ይሄ ትልቅ ስህተት ነዉ። ከዉጭ በሚደረግ ትግል በኢትዮጵያ ለዉጥ ማምጣት አይቻልም። አራት ነጠብ። ዉጭ አገር ያለነዉ ማተኮር ያለብን የአገር ቤቱን ትግል በማገዙና በመርዳቱ ዙሪያ መሆን አለበት።

ኢሕአዴግ በሃያ አመታት እድሜዉ ለመጀመሪያ  ጊዜ የተነቃነቀዉ በቅንጅት እንቅስቃሴ ነዉ።  ያኔ በዉጭ አገር የሚገኘዉ ኢትዮጵያዊ  በድጋፍ ድርጅቶች በመሰባሰብ፣ የአገር ቤቱን ትግል ይረዳ ነበር። ያኔ በዉጭ ያሉ ተቃዋሚዎቾ በሕብረት ሥር በመሰባሰብ፣  የአገር ቤት ትግሉን ይረዱ ነበር። በዚህም ምክንያት ነዉ፣  ያኔ ያየነዉን ያየነዉ።

 

እርግጥ ነዉ ቅንጅት/ሕብረት መድረስ የነበረባቸው ደረጃ አልደረሱም። ነገር ግን ብዙ መንገድ ተኪዶ ነበር። እንግዲህ የሚያዋጣን በቅንጅት ጊዜ የተሰሩት መልካም ስራዎችን በመድገም ፣ የተሰሩ ስህተቶችን በማረም፣ የአገር ቤቱን ትግልና የዉጭ አገሩን ትግል አቀናጅቶ መቀጠሉ ነዉ እንጂ፣  ከዚህ በፊት በተሰሩ ስህተቶች ተስፋ ቆርጠን፣ ለዉርደት እራሳችንን አሳልፈን መስጠት የለብንም። እርግጥ ነዉ ከዚህ በፊት ወድቀናል፣ ቆስለናል። ገር ግን ከአሁን ለአሁን እንደገና እንወድቃለን ብለን፣  በፍርሃትና በጥርጣሬ ተሞልተን ለመነሳት ካልሞከርን፣ በወደቅንበት በስብሰን  ሞተን ነዉ የምንቀረዉ።

እንግዲህ በሰላማዊ የእምቢተኝነት ትግል የሚያምኑ፣ ከሻእቢያ ጋር ግንኙነት የሌላቸው ወይንም ግንኙነታቸውን በኢፊሴል የበጠሱ፣ የኢትዮጵያን አንድነት የሚያምኑ፣ ትግሉ አገር ቤት እንደሆነ ተረድተዉ፣  አንዳንዶች እንደሚያደርጉት ፣ የአገር ቤት ትግሉን ማሳነስ ሳይሆን፣  የሚደግፉ ኃይላት በሙሉ በአንድ ላይ መሰባሰብ አይቸግራቸውም። አለባቸውምም።

ድነት/መድረክ የድጋፍ ድርጅቶችና በነአቶ ኦባንግ ሜቶ የሚመራዉ የሶሊዳሪት ንቅናቄ፣ በሰላማዊ ትግል የሚንቀሳቀሱ መሆናቸዉ ይታወቃል። በነ ዶር ፍስሃ የሚመራዉ የሽግግር መንግስት ምክር ቤትም በይፋ የትግል ስልቱ ሰላማዊ እምቢተኝነት እንደሆነ አሳዉቋል። በዘጠና ሰባት ወቅት ከነዶር መራር ጉዲና ጋር በቅርበት ይሰሩ የነበሩ ድርጅቶች ያሉበት፣ ሸንጎ፣ በዉስጡ ያሉ ድርጅቶች አንዳንዴ «ሁሉ ገብ» ትግል የሚል ያለፈበት ፈሊጥ ቢኖራቸውም፣  ሸንጎ እንደ ሸንጎ በሰላማዊ ትግል የሚያምን ስብስብ ነዉ። በቀድሞ የኦነግ አመራር አባላት በቅርቡ የተቋቋመዉ፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባርም፣ ኦነግ ላለፉት በርካታ አመታት፣ ኦሮሞዎችን ከማስጨረስ ዉጭ በትጥቅ ትግሉ ዘርፍ ያስገኘው ዉጤት እንደሌለ በመረዳት ይመስለኛል፣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ ካስፈለገም ከገዢዉ ፓርቲ ጋር በመደራደር ለመንቀሳቀስ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።

እንግዲህ ከላይ የዘረዘርኳቸው አምስት ድርጅቶች ወይም የድርጅት ስብስቦች ሁሉም በሰላማዊ ትግል የሚያምኑ፣ ለኢትዮጵያ አንድነት የቆሙ፣ በሻእቢያ የማይታዘዙ እንደመሆናቸው ፣ በጋራ በሚስማሙበት ነጥቦች ላይ አብረው የሚሰሩበትን መድረክ ለማመቻቸት መሰናክሎች ያጋጥማቸዋል ብዬ አላምንም። በተለይም የዲፕሎማሲና የዉጭ ግንኑነትን በተመለከተ፣  በዳያስፖራ ያለዉን ኢትዮጵያዊ በማስተባበር ዙሪያ፣ የሚስራ አንድ ግብረ ኃይል በቀላሉ ሊያቋቅሙ ይችላሉ። እርግጠኛ ነኝ እንደ ዶር ዲማ ነግዎ፣ አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ ዶር ፍስሃ፣ አቶ አክሎግ ልመንህ፣ ዶር አቻሜልህ የመሳሰሉ፣ የበሰሉ፣ ኢትዮጵያዉን የሚወዱ፣ የነዚህ ድርጅቶች አመራር አባላት ብቃቱ፣ ቅንነቱና  ቁርጠኝነቱ አላቸዉ ብዬ አምናለህ።

ይህ ግብረ ኃይል በዉጭ አገር የሚደረገዉን ትግል የሚመራ ይሆናል። ተቃዋሚዎችን ወክሎ ከምእራባዉያን ጋር ይነጋገራል። የተቃዋሚዉ ኃይል ተሰሚነት እንዲኖረው በአንድ ድምጽ ይናገራል። ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ፣ ሰላማዊ ሰልፎችን  ይመራል።  ከገዢው ፓርቲ ጋር መደራደር ካስፈለገ፣ አገር ቤት ካሉ ጋር በመቀናጀት፣ ዳያስፖራዉን ወክሎ ይደራደራል።  እኛም ከተለያዩ ማእዘናት የሚለቀቁ፣ አሰልቺና «እኔም ከማን አንሼ»  መግለጫዎችን ማንበባችን፣  ከተለያዩ ማእዘናትም እየተጎተትን  ግራ መጋባታችን ይቀራል።

ይህ ግብረ ኃይል፣ አገር ቤት የሚደረገዉን ትግል የሚመራ አይሆንም። ነገር ግን አገር ቤት የሚደረገዉን ትግል የሚያግዝ ይሆናል። በኢትዮጵያ የመንግስት ለዉጥ የሚመጣዉ አገር ቤት ያለዉን ሕዝብ ተደራጅቶች ሲንቀሳቀስ ብቻ ነዉ።

በፊታችን ጁላይ «የሽግግር ምንግስት ምክር ቤት»  የተሰኘው ድርጅት ሁሉንም የሚያሰባስብ ኮንፍራስ ጠርቷል። ይሄን አጋጣሚ መጠቀሙ ጥሩ ይመስለኛል። ይሄን በተመለከተ  ወደፊት በስፋት የምመለስበት ይሆናል።

 

እስከዚያዉ ሁላችንም ቸር ይግጠመን !

 

↧
↧

!.. በህወሓት የጉባኤ ኣጀንዳ ዙርያ ስብሰባ ሊጠራ ነው..!

$
0
0

Abrham Destaከኢህኣዴግ ጉባኤ በኋላ መሪዎቻችን (ከበፊቱ ብሶባቸው) መግባባት ኣቅቷቸዋል። በፌደራል ደረጃ የሚደረጉ ስብሰባዎች ያለ ዉጤት ይጠናቀቃሉ። ለምን ኣይግባቡም? (‘ቀሽም ጥያቄ’)። የሚያግባባ ነጥብ የላቸውማ። ድሮ (ከ‘ባለራእዩ መሪ’ ዕረፍት በፊት) ሁሉም ነገር እሳቸው ይሰሩት ስለነበር) በመሪያቸው ነበር ‘የሚግባቡት’ (አብረው የሚጓዙ)። በሰው ‘ይግባባሉ’ (ሌላ ሊያግባባቸው የሚችል ሓሳብ ወይ መርህ አልነበራቸውም፣ የላቸውም)። አሁን ታድያ እንዴት ይግባቡ?

‘ባለራእዩ’ ሰውዬ መመርያ ይሰጣል፣ ‘ፖሊሲ ነው ተግብሩት’ ይላቸዋል፣ እነሱም እሱ የተናገረውን ‘ቃል’ እየደገሙ (ከላይ እስከ ታች) ይዘምራሉ። ስሕተት መሆኑ (ሊተገበር የማይችል መሆኑ) ሲረዱ ‘ስሕተቱ ያለው አፈፃፀም ላይ ነው’ ብለው ራሳቸው ያፅናናሉ። ህዝቡ በማይፈፀሙ ፖሊሲዎች ተስፋ እንዳይቆርጥ መሪዎቻችን ሁሌ ስለ አዲስ ፖሊሲ ወይ አሰራር ይሰብካሉ። ሁሌ ስለ ‘አዲስ ኣሰራር’ ወይ ዕቅድ ሲወራልን ለውጥ የመጣ ያህል እንዲሰማን ለማድረግ ያህል ነው።

አሁን ሰውየው ‘አርፈዋል’። ለተከታዮቻቸው የተውት መርህ መሰረት ያደረገ የፖለቲካ አቅጣጫ የለም። የኢህኣዴግ ካድሬዎች ታድያ አሁን የሚግባቡበት ቋንቋ የላቸውም። የኣምስት አመቱ ‘የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን አቅድ’ ይዘት ወይ መሰረታዊ ፅንሰ ሓሳብ ምን እንደሆነ የሚያውቀው የለም። በዚህ ጉዳይ ተደጋጋሚ ውይይት ተደርጎ ያለ ዉጤት ተበትነዋል። (ዕቅዱ ግን ድሮውም ቢሆን ምንም የሚጨበጥ ሓሳብ አልነበረውም ….. የሚሰማን አጣን እንጂ)። ዕቅዱ ‘Ambitious’ ብለን በተደጋጋሚ አሳስበን ነበር (‘ሊተገበር የሚችል ዕቅድ አሳዩን’ ብለን ተማፅነን ነበር)። አሁን ግን ካድሬዎቹ ራሳቸው (በተለያዩ ስብሰባዎች) ‘የተለጠጠው (ዝተለጠጠ)’ ዕቅድ ማለት ጀምረዋል።

በኢህኣዴግ ደረጃ ያለው ችግር የስልጣን ሽኩቻ ነው (የባለስልጣናቱ ዓላማ ስልጣን ነው)። ህወሓቶች በኢህኣዴግ የነበራቸው ሚና ማጣት አይፈልጉም። ግን ይህንን ሚና ሊጫወት የሚችል ደህና ሰው የላቸውም። (ዓቅም የነበራቸው የፓርቲው ሰዎች በተለያየ ምክንያት እንዲጠፉ ተደርገዋል ) ። ራሳቸው በራሳቸው ችግር ፈጥረው (በሁለት ተከፍለው፣ ጓደኞቻቸው ኣባረው) ተዳክመዋል (አሁን ትግራይ እንኳ መቆጣጠር በሚችሉበት ሁኔታ ኣይገኙም)።

በኣሁኑ ግዜ በኢህኣዴግ ዉስጥ የተሻለ የስልጣን ተፎካካሪ ብአዴን ነው። ግን ብአዴን ከሌሎች ሦስቴ የኢህኣዴግ አባል ድርጅቶች ተቀባይነት የለውም። የህዝብ ድጋፍም በሰፊው የለውም። የሚጠበቀው ያህል (ኢህኣዴግ ለመቆጣጠር የሚያስችል) ጠንካራ አባላትም የሉትም። ግን በኢህኣዴግ ስርወ መንግስት የህወሓት አልጋ ወራሽ ብአዴን ይመስላል። በህወሓትና ብኣዴን ከፍተኛ ውዝግብ አለ።

ኦህዴድ በኢህኣዴግ ዉስጥ በጣም ያኮረፈ ቡድን ነው። የተለያዩ ምክንያቶች እየደረደረ ስልጣን ለኦህዴድ መሰጠት እንዳለበት ይወተውታል። ግን ኦህዴድ ሁለት ችግሮች ተደቅነውታል። (አንድ) በኦህዴድ ውስጥ መግባባት ብሎ ነገር የለም። (ሁለት) በሌሎቹ የኢህኣዴግ አባል ድርጅቶች እምነት ባለፈው የኦህዴድ ጉባኤ ወደ ሓላፊነት የወጡ ሰዎች ከኦነግ ጋር ግንኙነት አላቸው። በነሱ እምነት ኦነግ የኦህዴድ መዋቅር ተቆጣጥሮታል። ስለዚ ለኦህዴድ ስልጣን መስጠት እጅግ ያስፈራቸዋል።

ሌላው ደኢህዴን ነው። ደኢህዴን ጠንካራ ኣይደለም። በሁለት ቡድኖች ተከፍሎ ትርምስ ላይ ነው። ከቡድኖቹ አንዱ ከህወሓት ጎን መሰለፍ ይፈልጋል። ብቻውን (ህወሓት ከዚህ በፊት እንዳደረገው) የኢህኣዴግ ስልጣን መቆጣጠር የሚችልበት ዕድል የለውም። ህወሓትም ቢሆን ደካማ ሁነዋል። ዶር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በኢህኣዴግ ጉባኤ ሲናገር “በቃ ወድቀናል” ብሎ ነበር። ይሄ ከህወሓት ጋር መጠጋት ለሚፈልግ ቡድን ራስ ምታት ነው።

ህወሓቶች ጉዳዩ ኣስጨንቋቸዋል። የነ አባይ ወልዱ ቡድን የነ አርከበ ዕቁባይ ቡድን ካባረሩ ወዲህ የባሰ ንትርክ ዉስጥ ገብተዋል። እርስበርሳቸው አይግባቡም፣ ይናናቃሉ። የኣሁኑ መሪዎች ማንም አያከብራቸውም። በህወሓት ጉባኤ የተሳተፉ አባላት በነ ኣባይ ወልዱ የተመለመሉ ቢሆኑም በጉባኤው ወቅት በነኣርከበ የተወሰደው እርምጃ ግራ አጋብታቸዋል። ጉባኤተኞቹ ‘እነ ኣርከበ ከውጡ ህወሓት ከማን ጋ ትቀራለች?’ የሚል ጥያቄ ነበራቸው።

የፓርቲው ሊቀመንበር የሚመረጠው (በፓርቲው ደንብ መሰረት) በጠቅላላ ጉባኤ ነው (በቀጥታ ግን አይደለም)። እንዲህ ነው። ጉባኤተኞቹ አርባ አምስት የፓርቲው የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ይመርጣሉ። በውጤቱ (ባገኙት ድምፅ) መሰረት በቅደም ተከተል (የተመረጡት ሰዎች) ስማቸው ይገለፃል። የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት የፓርቲው ስራ ኣስፈፃሚ (ፖሊት ቢሮ) ይመርጣል። ፖሊት ቢሮ አባላት ደግሞ የፓርቲው ሊቀመንበርና ምክትል ይመርጣሉ።

በምርጫው ከፍተኛ ስልጣን ያለው (በመርህ ደረጃ) ጉባኤተኛው ስለሆነ ከፍተኛ ድምፅ ያለው (By Default) የፓርቲው ሊቀመንበር ይሆናል። የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ይሄንን አውቀው ባገኙት ድምፅ መሰረት ዘጠኙ (Top Nine) ለፖሊት ቢሮ ይመርጣሉ። ፖሊት ቢሮ አባላትም በተሰጠው ድምፅ መሰረት ከፍተኛውን ያገኘ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርገው ይመርጣሉ።

በጉባኤው የተሳተፉ አባላት ሊቀመንበር (ከተሰጣቸው አማራጭ) አድርገው የመረጡት ዶር ደብረፅዮን ነበር። ዶር ደብረትፅዮን የኣንደኛነት ድምፅ ሲያገኝ አባይ ወልዱ ሁለተኛ ነበር። (ደብረፅዮን ለኣባይ በ23 ድምፅ ይበልጠዋል)። ውጤቱ ግን ጉባኤተኞቹ እንደጠበቁት ኣልሆነም። የፖሊት ቢሮ አባላት ሁነው የተመረጡት (top nine) ዘጠኙ ኣልነበሩም። በውጤቱ መሰረት የህወሓት ሊቀመንበር መሆን የነበረት ዶር ደብረፅዮን ሲሆን ዉጤቱ ተገልብጦ አቶ ኣባይ ተመረጠ። ይሄ የሆነው የኣቶ አባይ ቡድን አብዛኛው የማእከላዊ ኮሚቴ ወንበር መያዝ በመቻሉ ነበር። (ጉባኤተኞቹ የነኣባይ ቡድን ደጋፊዎች ሲሆኑ አባይ ፓርቲው ይመረዋል ብለው ግን አያምኑም። ስለዚህ ጉባኤተኞቹ ደብረፅዮን ሊቀመንበር አድረገው መርጠው እንደሄዱ ነው የሚያውቁ)።

ይሄን ዉሳኔያቸው ታድያ በጉባኤተኞቹ ጥሩ ስሜት አልፈጠረም። የኣሁኑ መሪዎች የህዝብ አመኔታም የላቸውም። ይሄን ችግር ለመፍታት ሲሉ ከነገ እሮብ (ሚያዝያ 16, 2005 ዓም) ጀምሮ ጉባኤው በተመለከተ በመላው ትግራይ (በየደረጃው ከከፍተኛ የክልል ቢሮዎች ጀምሮ እስከ ቀበሌ አስተዳደር ድረስ) ስብሰባ እንደሚደረግ ታውቋል። ለስብሰባው ማስኬጃ ብዙ ሚልዮን ብር ተመድበዋል (ከመንግስት ካዝና መሆኑ ነው)።

ኣየ ህወሓት! በቃ ስብሰባ ነው። እኔ ደግሞ ስብሰባ ስጠላ! (እንኳን የህወሓት አባል አልሆንኩ)።

↧

ድምፅ ለሌለው ወገናችን በጋራ ድምፅ እንሁን !!!

↧

የማረሚያ ቤቱ ድራማ በርዕዮት እምቢተኝነት ከሸፈ

$
0
0

reeyot alemu(ፍኖተ ነፃነት) ባሳለፍነው እሁድና ሰኞ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትገኘውን ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን ለመጠየቅ በዛ ያሉ የሞያ አጋሮቿና አድናቂዎቿ በስፍራው ተገኝተው ነበር፡፡የጠያቂዎቹ በዛ ብሎ የመገኘት ዋነኛ ምክንያት ደግሞ ርዕዮት በቅርቡ የዩኔስኮን የ2013 አለም አቀፍ ሽልማት በማግኘቷ እንኳን ደስ አለሽ በማለት የደስታዋ ተካፋይ መሆናቸውን ለመግለጽ ነበር፡፡ የባልንጀሮቿን የደስታ ምኞት እየተቀበለች ለሁሉም ሽልማቱ የእርሷ ብቻ እንዳልሆነም ትገልጽ ነበር፡፡

ርዕዮት ጠያቂዎቿን በመቀበል እያነጋገረች በነበረችበት ሰዓት(ሰኞ ዕለት) የቪዲዩ ካሜራ በመደገን ለመቅረጽ ይሞክር የነበረ አንድ ሰው በጋዜጠኞች እይታ ስር ይወድቃል፡፡ርዕዮት ላይ ያነጣጠረው ካሜራ የፈለገውን እንዳያገኝም በስፍራው የነበሩ ሰዎች ጋዜጠኛዋን በመክበብ ምስሏን እንዳይቀርጽ አድርገዋል፡፡በጠያቂዎቿ እንደተከበበች ርዕዮትን መቅረጽ ያልሆነለት ስውሩ ጋዜጠኛ በመጨረሻ ርዕዮትን ነጥሎ ለማናገር ይሞክራል፡፡በዚህ ወቅት ግን የጠያቂዎች ሰዓት በማለቁ የርዕዮት ጠያቂዎች ማረሚያ ቤቱን ለቅቀው እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡

የፍኖተ ነጻነት ምንጮች እንዳረጋገጡት ጋዜጠኛው ርዕዮትን በማግኘት ‹‹አንቺ ጋዜጠኛ አይደለሽ፣በራስሽ የምትተማመኚ ከሆነስ ለምን ለመቀረጽ እምቢ ትያለሽ›› ይላታል፡፡ርዕዮትም ‹‹ከአንተ ጋር ከመነጋገሬ በፊት የማረሚያ ቤቱን ሃላፊዎች ማነጋገር እፈልጋለሁ›› በማለቷ ሃላፊዎቹ ይመጣሉ፡፡ርዕዮት ቀጠለች‹‹ይህ ጋዜጠኛ የሚፈልገውን ቃለ ምልልስ የመስጠት ችግር የለብኝም፣ ነገር ግን የተናገርኩትን ቆራርጦና ጨማምሮ ሊያቀርበው የሚችል በመሆኑ የነጻ ሚዲያ አባላት በቃለ ምልልሱ ወቅት እንዲገኙ ይደረግ ፣ ከዚህ ውጪ ግን ለጥያቄው ምንም አይነት ትብብር እንደማላደርግ ይታወቅልኝ››በማለት አቋሟን ግልጽ አድርጋለች፡፡

እንደሚታወቀው መንግስት በሽብርተኝነት ከስሶ በእስራት እንድትቀጣ እያደረጋት የምትገኘው ጋዜጠኛ የጤንነቷ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መገለጹን ተከትሎ በአገር ውስጥና በውጪ መንግስት ላይ ከፍተኛ ጫና እየተደረገ ይገኛል፡፡የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄን ጨምሮ የአውሮፓ ፓርላማ አባል የሆኑት ሚስ አና ጎሜዝ፤የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንትና ሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት ጋዜጠኛዋ ተገቢውን የህክምና ክትትል እንድታገኝ መጠየቃቸው አይዘነጋም፡፡

ከዚህ ቀደም ፖለቲከኛና ዳኛ የነበሩት ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ በታሰሩበት ወህኒ ቤት ለህመም ተጋልጠዋል የሚሉ መረጃዎች በመውጣታቸው ጫና የተፈጠረበት መንግስት ብርቱካን በጤንነት ላይ ይገኛሉ ለማለት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አማካኝነት አንድ ዘገባ መስራቱ አይዘነጋም፡፡ርዕዮት ማረሚያ ቤቱ ያስገባው ስውሩ ጋዜጠኛ ከእውቅናዋ ውጪ ሊሰራው የነበረውን ድራማ ቀድማ በመንቃቷ ሊሳካ አልቻለም፡፡

ባሳለፍነው እሁድና ሰኞ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትገኘውን ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን ለመጠየቅ በዛ ያሉ የሞያ አጋሮቿና አድናቂዎቿ በስፍራው ተገኝተው ነበር፡፡የጠያቂዎቹ በዛ ብሎ የመገኘት ዋነኛ ምክንያት ደግሞ ርዕዮት በቅርቡ የዩኔስኮን የ2013 አለም አቀፍ ሽልማት በማግኘቷ እንኳን ደስ አለሽ በማለት የደስታዋ ተካፋይ መሆናቸውን ለመግለጽ ነበር፡፡ የባልንጀሮቿን የደስታ ምኞት እየተቀበለች ለሁሉም ሽልማቱ የእርሷ ብቻ እንዳልሆነም ትገልጽ ነበር፡፡

ርዕዮት ጠያቂዎቿን በመቀበል እያነጋገረች በነበረችበት ሰዓት(ሰኞ ዕለት) የቪዲዩ ካሜራ በመደገን ለመቅረጽ ይሞክር የነበረ አንድ ሰው በጋዜጠኞች እይታ ስር ይወድቃል፡፡ርዕዮት ላይ ያነጣጠረው ካሜራ የፈለገውን እንዳያገኝም በስፍራው የነበሩ ሰዎች ጋዜጠኛዋን በመክበብ ምስሏን እንዳይቀርጽ አድርገዋል፡፡በጠያቂዎቿ እንደተከበበች ርዕዮትን መቅረጽ ያልሆነለት ስውሩ ጋዜጠኛ በመጨረሻ ርዕዮትን ነጥሎ ለማናገር ይሞክራል፡፡በዚህ ወቅት ግን የጠያቂዎች ሰዓት በማለቁ የርዕዮት ጠያቂዎች ማረሚያ ቤቱን ለቅቀው እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡

የፍኖተ ነጻነት ምንጮች እንዳረጋገጡት ጋዜጠኛው ርዕዮትን በማግኘት ‹‹አንቺ ጋዜጠኛ አይደለሽ፣በራስሽ የምትተማመኚ ከሆነስ ለምን ለመቀረጽ እምቢ ትያለሽ›› ይላታል፡፡ርዕዮትም ‹‹ከአንተ ጋር ከመነጋገሬ በፊት የማረሚያ ቤቱን ሃላፊዎች ማነጋገር እፈልጋለሁ›› በማለቷ ሃላፊዎቹ ይመጣሉ፡፡ርዕዮት ቀጠለች‹‹ይህ ጋዜጠኛ የሚፈልገውን ቃለ ምልልስ የመስጠት ችግር የለብኝም፣ ነገር ግን የተናገርኩትን ቆራርጦና ጨማምሮ ሊያቀርበው የሚችል በመሆኑ የነጻ ሚዲያ አባላት በቃለ ምልልሱ ወቅት እንዲገኙ ይደረግ ፣ ከዚህ ውጪ ግን ለጥያቄው ምንም አይነት ትብብር እንደማላደርግ ይታወቅልኝ››በማለት አቋሟን ግልጽ አድርጋለች፡፡

እንደሚታወቀው መንግስት በሽብርተኝነት ከስሶ በእስራት እንድትቀጣ እያደረጋት የምትገኘው ጋዜጠኛ የጤንነቷ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መገለጹን ተከትሎ በአገር ውስጥና በውጪ መንግስት ላይ ከፍተኛ ጫና እየተደረገ ይገኛል፡፡የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄን ጨምሮ የአውሮፓ ፓርላማ አባል የሆኑት ሚስ አና ጎሜዝ፤የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንትና ሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት ጋዜጠኛዋ ተገቢውን የህክምና ክትትል እንድታገኝ መጠየቃቸው አይዘነጋም፡፡

ከዚህ ቀደም ፖለቲከኛና ዳኛ የነበሩት ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ በታሰሩበት ወህኒ ቤት ለህመም ተጋልጠዋል የሚሉ መረጃዎች በመውጣታቸው ጫና የተፈጠረበት መንግስት ብርቱካን በጤንነት ላይ ይገኛሉ ለማለት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አማካኝነት አንድ ዘገባ መስራቱ አይዘነጋም፡፡ርዕዮት ማረሚያ ቤቱ ያስገባው ስውሩ ጋዜጠኛ ከእውቅናዋ ውጪ ሊሰራው የነበረውን ድራማ ቀድማ በመንቃቷ ሊሳካ አልቻለም፡፡

↧

ጎጃም አዘነ –ክየጐንቻው!

↧
↧

በደም የተከበረ የዓለም ሠራተኞች ቀን፤ ሜይ ዴይ

$
0
0

eprpyl

“ሚያዝያ 21 ቀን 1969 ዓ.ም. ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ በአራቱም አቅጣጫ የተኩስ ድምጽ አልፎ አልፎ ማስተጋባቱ ታውቋል።…በ22/8/69 ጠዋት ባደረግነው መከታተል…በቀጨኔ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን አካባቢ የ31 ተማሪዎች አስከሬን፣ በየካ ወረዳ አሥመራ መንገድ የ42 ተማሪዎች አስከሬን ወድቆ መገኘቱና በአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አንሽነት ተለቅሞ ወደ ምኒልክ ሆስፒታል መወሰደን…በ23/8/69 እንደዚሁ በገፈርሳ ወረዲ ሳንሱሲ ከሚባለው አካባቢ የ19 ተማሪዎች አስከሬን በጫካ ውስጥ ተጥሎ በአካባቢው ሕዝብ ስለተገኘ…በ24/8/69 በየካ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የ22 ተማሪዎች አስከሬን ተቀብሮ መዋሉን…ይህን መሰል ድርጊት የተፈጸመው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በክፍለሀገራትም ጭምር መሆኑንም ተጨማሪ መረጃ ደርሶናል።”  ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

 

 

↧

“ሕፃን ካቦካው –ልጅ ያቦካው ይሻላል” (ለተክለሚካኤል አበበ አስተያየት የተሰጠ ድጋፍ)

$
0
0

ይህ ፅሑፍ የኢሳት ባልደረባ ተ/ሚካኤል አበበ “የኢሳት 3ኛ ዓመት ክብረ በአል የሙስሊሞች ብቻ ነው እንዴ?( http://www.zehabesha.com/amharic/archives/1923) ’’ በሚል ርዕስ ላቀረበው ፅሑፍ አቶ  ቶፊቅ ጀማል ከቼክ ሪፖብሊክ(ፕሪግ) መልስ እንዲሆን ብለው “ልጅ ያቦካው (http://www.zehabesha.com/amharic/archives/2039) ” በሚል ርዕስ “  ለሰጡት  ባለ 12 ነጥብ (የቃላት ጨወታ) የተሰጠ ምላሽ ነው፡፡

ESAT 3

  1.  ውድ አቶ  ቶፊቅ ጀማል “የአብዬን ወደ እምዬ ልክክ” እንዲሉ በኢሳት 3ኛ ዓመት ክብረ በአል ዝግጅት ላይ በሙስሊም  ( እዚህ ላይ አወልያን መሰረት አድርጎ የተነሳውን የሙስሊም እንቅስቃሴ የማትደግፉ ወይም አካሄዱን የማትቀበሉ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች እንድትረዱኝ አደራ የምለው በዚህ ፅሑፍ “የሙስሊም ተወካዮች” እያልኩ የምጠቅሰው አወልያን መሰረት አድርጎ የተነሳውን የሙስሊም እንቅስቃሴ ደግፋው “በዲያስፖራ” የሚንቀሳቀሰውን ቡድን መሆኑን እንድትረዱኝ አደራ እላለሁ ) ተወካዮች ብቻና ብቻ እንዲሞላ መደረጉ ተገቢ አይደለም ከዚህ ይልቅ የሁሉም ሃይማኖት ተወካዮች ጥሪ ሊደረግላቸው ይገባል የሚል ግልፅ የሆነ የእርምት መልዕክት ያለውን ፅሑፍ የኢሳት ባልደረባ የሆነው ተ/ሚካኤል አበበን ቁምነገር አዘል ምክር “ልጅ ያቦካው” ነው ብለህ ለመተቸት በመድፈረህ “ልጅ” ማን እንደሆነ ምላሽ እንድሰጥህ ግድ ሆኖብኛል፡፡

አንተ ግን ያደረገውንና የተናገረውን  ፈጥኖ እንደሚረሳ ሕፃን በዚህ ፅሑፍ አልተበሳጨሁም ወይም አያበሳጭም ብለህ ከፃፍክ ከጥቂት መስመሮች በኋላ ቀለሙ እንኳን ሳይደርቅ ወዲያው “ኧረ በጣም ያበሳጫል” ብለህ መፃፍህንና ተ/ ሚካኤል አበበ የጻፈዉን  ጽሑፍ አንብበህ ሳትጨርስ ለትችት መንደርደርህን የተመለከትን ማለትም የኢሳት ባልደረባ ተ/ሚካኤል አበበ የፃፈውን ባለ 15 (አስራ አምስት) ነጥብ ፅሑፍ ባለ 12 (አስራ ሁለት) ነጥብ የአቋም መግለጫ ብለህ ከጅምሩ ስትቀባጥር የታዘብን አንባብያን የአንተን ፅሑፍ “ልጅ ያቦካው” ነው ወይስ “ሕፃን ያቦካው” ነው የምንለው?

ተ/ሚካኤል አበበ የተጠቀመበት የአነጋገር ስልት ገና ከጅምሩ ሊገባህ እንዳልቻለ ስለ ማበሳጨት እና ስለ ማስጨብጨብ  የሰጠኸው ትንታኔ ያሳብቅብሃል እንዲያው በከንቱ ያለአቅምህ ተወጣጠርክ እንጂ::  አንድ ግለሰብ ወይም ቡድን በሚተቸው ፥ በሚገስፀውና ስህተቱን በሚያርመው የማይደሰት ከሆነ መስተካከልና መታረም ባለመፍቀዱ “ያበሳጨዋል”። እንዲሁም ምክር አዘል መልዕክቶችን አንብበው ከስህተታቸው ለመታረም : ለችግራቸው መፍትሄ ሰጪ ይሆናል ብለው ለሚያምኑና ለሚያነቡ ደግሞ “አስጨብጫቢ” ይሆናል ማለት እንጂ “ማበሳጨት” ማለት ፊትህ እስኪቀላ መኮሳተርን ወይም “ማስጨብጨብ” ማለት ደግሞ እጅህ እስኪቃጠል በመዳፍህ አጋና መምታትን የሚመለከት አለመሆኑን ለመረዳት ከፈለክ ለማቡካት የሚጣደፉትን የህፃን እጆችህን ሰብሰብ ብታደርጋችው መልካም ነው’።

  1. የኢሳት ባልደረባ ተ/ሚካኤል አበበ ከዜና አንባቢነት ጀምሮ በኢሳት በሚተላለፉ የተለያዩ ፕሮግራሞች ላይ ግዜውን ፥ እውቀቱንና ጉልበቱን ያፈሰሰ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ከመሆኑም በላይ በተለያዩ የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች ላይ በበርካታ የሰሜን አሜሪካ ክፍለ ሃገራት ( states) በመገኘት የታወቀ ሆኖ ሳለ መሰረታዊውን የፅሑፉን መልዕክት በተ/ሚካኤል መጋበዝና ባለመጋበዝ ዙሪያ ለማቡካት መከጀልህ አንተን የመሳሰሉ ህፃናቶችን ልትቀልድባቸው አልመህ ካልሆነ በስተቀር ኢሳት የኢትዮጵያውያን ሁሉ እንደ መሆኑ መጠን የሃይማኖት ተወካዮች መጋበዛቸው አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የሁሉንም ኃይማኖት ተወካዮች ማካተት አለበት የሚለውን ጭብጥ ሊያጠፋው አይችልም።

አቶ  ቶፊቅ ጀማል ስታቦካ የረሳኸውን ነገር ላስታውስህ የኢሳት ባልደረባ ተ/ሚካኤል አበበ ጳጳስ ነኝ ፥ ቄስ ወይም ፓስተር ነኝ ወይም የሃይማኖት ተወካይ ነኝ አላለም ነገር ግን የሃይማኖት ተወካዮችን መጋበዝ ካስፈለገ ኢሳት የኢትዮጵያዊያን ሁሉ እንደመሆኑ መጠን ኢትዮጵያዊያንን ሁሉ የሚያካትት መሆን ስለሚገባው የሁሉንም ሃይማኖት ተወካዮች መጋበዝ  ነበረባቸው በማለት ምክር አዘል እርምት መስጠቱ በየትኛውም የአፈታት ወይም የአተረጓጎም ስልት(ተፍሲር) ተ/ሚካኤል አበበ እኔ ጳጳስ በመሆኔ የሃይማኖት ተወካይ ነኝና ጋብዙኝ ማለትህ ነው ሊያስብለው የሚያስችል ጭብጥ የለውም።

  1. Teklemichael-Abebeበ3ኛው ነጥብህ ላይ ኢሳት ለዲያስፖራ የሙስሊም ተወካዮች ሽፋን የሰጣቸው የኢትዮጵያዊያን የመብት ትግል ሲያቀጣጥሉት በመገኘታችው ነው ብለሃል  ነገር ግን የሙስሊም ተወካዮች ትግሉን ለማቀጣጠል መነሳታችው የሚለካው ከሃይማኖት ጎራ ወጣ ብሎ ለዜግነት ክብር በመቆም በሁሉም  ኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ ለሚደርሰው የመብት ጥሰትና ጭቆና በጋራ መቆም ሲችሉ እንጂ ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ዜጎች ለምሳሌ ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ፥ አንዷለም አራጌ ፥ ጋዜጠኛና መምህር ወ/ት ርዮት አለሙ ፥ አቶ በቀለ ጎረባና ለሌሎችም የህሊና እስረኞች መቆምና መታገል ካልቻሉና ልባቸው ካልተነካ እንዲሁም በየሄዱበት ቦታ በዋነኛነት የሚያነሱት የሙስሊም እስረኞችን ጉዳይ ብቻ ከሆነ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን መብትና ነፃነት የሚታገለው ኢሳት ተጠቃሚ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው? ይልቅስ ኢሳት የአንድ ሃይማኖት ተወካዮችን ብቻና ብቻ በዓመታዊ ክብር ባዓሉ ላይ ለመጋበዝ መወሰኑ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ዘንድ ኢሳት የኢትዮጵያዊያን ሁሉ ሳይሆን አወልያን መሰረት አድርጎ ለሚንቀሳቀሰው የሙስሊም ተወካዮች ብቻ የሚሰራ የፕሮፖጋንዳ ማሽን ያስመስለዋል እንጂ።
    1. አቶ ቶፊቅ ጀማል በአራተኛው ነጥብ ላይ ምጡቅ ሃሳብ ልታመነጭ የምትንደረደር በሚመስል መልኩ “ያልተረዳኸው ወይም ልትረዳው ያልፈለከው ወይም ያልሞከርከው ጉዳይ ያለ የመስለኛል” ብለህ ከጀመርክ በኋላ የሙስሊሙ ችግር የሃይማኖት እንጂ የፖለቲካ አይደለም የሚንቀሳቀሰውም ይህንኑ የሀይማኖት  ችግር  ለመፍታት ብቻ ነው” ብለሃል።አስተሳሰብህ የሕፃን ቡኮ ሆኖብህ ነው እንጂ ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ በጥራት የሚገባህ ሰው ብትሆን ኖሮ በዚህ ነጥብ ላይ ያነሳኸው የተ/ሚካኤልን  ስጋት የሚያጠናክር ነው።

ሙስሊሙ የሚመለከተው የሙስሊሙን ሃይማኖታዊ ጉዳይ ብቻ እንጂ የመላው ኢትዮጵያውያ ህዝብ ያለበት የኢኮኖሚ ፥ የፖለቲካና ማህበራዊ ቀውስ አይመለከተውም የምትል ከሆነ አንተና አንተን መሰል አስተሳሰብ ያላቸው ግለሰቦች ኢትዮጵያውያንን ሁሉ በዜግነት አጀንዳ ዙሪያ ወደ ላይ ከፍ ለማድረግ በተቋቋመው በኢሳት ዙሪያ ሳይሆን መሰብሰብ የሚገባቸው በሃይማኖት ጣራ ስር ወይም በመስጊድና በመስጊድ ብቻ ነው።

አንተ ሊገባህ ያልቻለው ኢሳት  የኢትዮጵያውያን ሁሉ የዜግነት አጀንዳ የሚስተናገድበት ሚድያ እንጂ ከሙስሊሙ ጥያቄ ውጪ የሌላው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ችግር አይመለከተንም ለሚሉና እንዲሁም በኢሳት ዓመታዊ ክብር በዓል ላይ መጋበዝ ያለባቸው  የሙስሊሙ ተወካዮች ብቻ ናቸው ብለው ለሚያስቡ  ወገንተኛ አስተሳሰብ ላላቸው የጠባቦች ንብረት አይደለም።

  1. እዚህ ላይስ እኔም መልስ መስጠት የለብኝም ብዬ አሰብኩና  “ለዚህ መልስ መስጠት ያለብኝ አይመስለኝም”  ካልክ በኋላ  ወዲያው ከቼክ ሪፖብሊክ የአማርኛ ሰዋሰው እርማት ለማድረግ መከጀልህን አይቼ “መልስ በመስጠትና ባለ በመስጠት” መካከል ያለው ልዩነት የማይገባህ ህፃን መሆንህ ትዝ ስላለኝ አንድ ሁለት ነገር ልጠቁምህ ወሰንኩ።

ኢሳት በዜግነት ክብር እንጂ እንዳንተ በሃይማኖት ብቻ የማያስቡ ውድ  ኢትዮጵያዊያን የተሰባሰቡበት በመሆኑ ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ላይ የሚጋበዙ እንግዶችም ይህንኑ የሚያንፀባርቁ ሊሆን  ይገባል ስለዚህም  የሃይማኖት ተወካዮችን መጋበዝ ካስፈለገ ሁሉም ቤተ እምነቶች በመወከል በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ እየተፈጠረ ያለውን ስጋት እና ጥርጣሬ ያገናዘበ ቢሆን እንደዜጋ በኢትዮጵያዊነታቸው

: ዜግነትን መሰረት አድርጎ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት ለመታገል ለቆመው እንደ ኢሳት ዓይነት ተቋም ጠንቅ መሆኑን መቀበል ፥ መረዳትና መገንዘብ አቅቶህ ብትዘባርቅ ሃይማኖታዊ ብቻ እንጂ ብሔራዊ አጀንዳ የለንም ከምትለው  ከአንተ እና ከመሰሎችህ ሌላ ምን ይጠበቃል።

  1. በ6ተኛ ነጥብ ላይ ያነሳኸውን ሃሳብ “የራስዋ አሮባት የሰው ታማስላለች” የሚለውን ቁም ነገር አዘል ምሳሌ እንዴት እንዳስታወስከኝ እንደሚከተለው ላመላክትህ:: በዚህ ነጥብ ጅማሬ ላይ “መንግስትና ሃይማኖት አይለያዩ ማለታችን ነው..” የሚለውን አረፍተ ነገር ጠቅሰህ የአማርኛ ቋንቋ አጠቃቀም ላይ ትችት ለመስጠት በማሰብ ያልገባህ በመምሰል የህፃን ነገር ሆኖብህ ነውረኛና ነገረኛ ለመሆን ሞክረሃል ነገር ግን በዚሁ  አረፍተ ነገር ላይ በዚህ ነጥብ አንተው ራስህ “በእርግጥም ምን ለማለት እንዳወብህ አልገባኝም” ስትል ምን ማለት ፈልገህ ነበር? “እንዳወብህ” የሚል አዲስ የአማርኛ ቃል አንተ ፈጥረህ ነው? ወይስ ከመኖሪያ ሃገርህ ከቼክ ሪፖብሊክ ቃላት ተውሰህ ነው? አየኸው የራስዋ አሮባት የሰው ታማስላለች ይሉሃል እንዲህ ነው።

እንዲያው ለነገሩ ነው  እንጂ ከአረፍተ ነገሩ አሰካክና ከአውደ ንባቡ አንፃር ለማለት የፈለከውን ለመረዳት በጣም ቀላል ነው የሚጠይቀው ቅንነት ብቻ ነው አንተ ለማለት የፈለኩት ሌላ ነው ካላልከኝ በስተቀር መጠቀም የፈለግከው ቃል በታይፕ ግድፈት  “ሰ” በ “ወ” ቢቀየርብህም  “እንዳሰብህ” ለማለት ፈልገህ እንደሆነ ይታየኛል  ከዚህ የምረዳው  የተ/ሚካኤልን ጽሑፍ በቅንነት ለማንበብ አለመሞከርህንና በዚህም ምክንያት ለአላስፈላጊ ትችትና ጥላቻ መዳረግህን ብቻ ነው።

ተ/ሚካኤል በ7ተኛው ነጥብ ላይ የገለፀውን ሃሳብ አንተ ለጥላቻ መልዕክትህ እንደቆረጥከው ወይም ለመጠምዘዝ እንደሞከረከው ሳይሆን አውደ ንባቡ በግልፅ እንደሚያስረዳው መንግስትና ሀይማኖት የተለያዩ መሆናቸውን ነው:: በተ/ሚካኤል ፅሑፍ በ6ተኛው ነጥብ መጀመሪያ ላይ “… ሀይማኖትና መንግስት የተለያዩ ናቸው፤ መንግስት Secular ይሁን፤ የሚለውን መሰረታዊ የፖለቲካ መርህ አምነንበት…” ነው ይላል:: በተጨማሪም በ 7ኛው ነጥቡ ላይ “ አሁንም መንግስትና ሀይማኖት ይለያዩ፤ መንግስት በሙስሊሞች ጉዳይ ጣልቃ አይግባ ስንል ያ ብዙ ወጣት ኢትዮጵያውያን የሞቱለት መርህ ይከበር ማለታችን ነው ”ይላል:: እነዚህን አረፍተ ነገሮች ያነበበ ቅን ሰው

 

ከላይ “አይለያዩ ” የሚለው ቃል “አ” በታይፕ ግድፈት የገባች እንጂ በግንዛቤ ችግር የገባች አለመሆንዋ እየታወቀ ይህን ያህል በጥላቻ የተሞላህና በእድሜ ብቻ የገፋህ በአስተሳሰብህ ጨቅላ ህፃን ያስመሰለህን ጉዳይ ቆም ብለህ እንድታስብበት እጠይቅሃለሁ።

 

  1. ለነገር ከመቸኮልህ ብዛት ናላህ ስለዞረ  የተ/ሚካኤል 6ተኛ እና 7ተኛ ነጥብ ከአንተ 6ተኛ እና 7ተኛ ነጥብ ጋር የተለያዩ ቢሆኑም “ህፃን ያቦካው” እንዲሉ አገለባብጠከኸዋል ስለዚህም ነጥቦቹን እየተከታተሉ ለሚያነቡ አንባቢያን አደናጋሪ እንዳይሆን በበኩረ ፅሑፉ ቅደም ተከተል ሳይሆን መልስ የምሰጠው ላንተ በመሆኑ አንተ የፃፍክበትን ቅደም ተከተል መርጫለሁ።  የኢሳት ባልደረባ ተ/ሚካኤል አበበ የኢሳት ዓመታዊ ክብረ በዓል የሁሉም ኢትዮጵያውያን በመሆኑ የሁሉም ሀይማኖት ተወካዮች ሊጋበዙ ይገባል የሚል ምክር በማቅረቡ “የልጅ ራዕይ ነው” ብለህ ከተሳለቅክበትና ለማጣጣል ከሞከርክ ፣ በበዓሉ ላይ መጋበዝ ያለባቸው የሙስሊም ሀይማኖት ተወካዮች ብቻና ብቻ መሆን አለበት ብለህ ሽንጥህን ገትረህ የምትሟገተውን ያንተን ህልም “የሕፃን ቅዥት ነው” ከማለት የተሻለ ምን ማለት ይቻላል?

 

  1. በዚህ ነጥብ ላይ የሚገርመው ይሄን ሁሉ ትችት ስትደረድር ከቆየህ በኋላ በእርግጠኝነት ባልገባህ ጉዳይ ስትፅፍ መቆየትህን  “…በእርግጥ አልገባኝም …“በማለት ማመንህ ነው። በእርግጠኝነት ባልገባህ ጉዳይ ላይ ስትቸከችክ መቆየትህ ዘባራቂ መሆንህን አረጋገጠልኝ። በእርግጥም ሊገባህ ያልቻለውን ነገር እኔ ልንገርህ አንተ ያልገባህ ኢሳት የኢትይጵያዊያን ሁሉ መሆኑና በዓመታዊ ክብረ በዓሉ ላይ መጋበዝ ያለባቸው የአንድ እንቅስቃሴ ተወካዮች ብቻ መሆን እንደማይችል ነው። በዓመታዊ ክብረ በዓሉ ላይ የሃይማኖት ተወካዮችን መጋበዝ ካስፈለገ  ሁሉም የሃይማኖት ተወካዮች ቢጋበዙ ኢትዮጵያዊነትን ከማንፀባረቅ በስተቀር ሌላ ምን ችግር ይኖረዋል?

 

አንተ ግን አንዳንድ የአክራሪ ኢስላም አቀንቃኞች እንደሚናገሩት ኢትዮጵያዊነትን በሚያንፀባርቁ ጉዳዮች ላይ ቀስ በቀስ መታየትና መገኝት ያለባቸው የሙስሊም ተወካዮች ብቻና ብቻ መሆን አለባቸው በሚል በሸሪያ ፍልስፍና የተጠመቁ ሰዎችን አስተሳሰብ ለማራመድ የምትከጅል ሕፃን በመሆንህ ነው።

ተ/ሚካኤል በተደጋጋሚ ለማስረዳት የሞከረው ኢሳት ኢትዮጵያዊ ዜጎችን ሁሉ በሚያካትት መልኩ ሊሆን ስለሚገባ የሃይማኖት ተወካዮችን መጋበዝ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የሁሉም ሃይማኖት ተወካዮች ቢገኙም ባይገኙም መጋበዝ ተገቢ ሆኖ ሳለ የአንድ ሃይማኖት ተወካዮችን ብቻ ነጥሎ መጋበዝ አደጋ ከመፍጠር በስተቀር ጠቃሚ ሊሆን አይችልም:: በተለይ ደግሞ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ በጥርጣሬ የሚመለከቱ ኢትዮጵያዉያን እንዳሉ በተረዳንበት ግዜና ወቅት::

9.  በዚህ ነጥብ ላይ ያነሳኸው ነጥብ በአጭሩ “የእርጎ ዝምብ” መሆንህን ከማሳየት በስተቀር ሌላ ምንም ቁም ነገር የለውም በ5ተኛው ነጥብህ ላይ የአማርኛ ሰዋሰው ሊቅ ለሞሆን ሲቃጣህ አንብቤ ሲገርመኝ አሁን ደግሞ የታማኝ በየነ በኢትዮጵያዊነቱ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የቆመበትን አላማ በመጠምዘዝ አሳፋሪ አፈቀላጤ ለመሆን ሞከርህ ከዚህም በላይ ኢሳት የኢትዮጵያውያን ሁሉ ዓይን ፥ ጆሮና አንደበት እንጂ እንደ አንተና እንደ  መሰሎችህ በኢሳት ክብረ በዓል ላይ መጋበዝ ያለባቸው የአወልያ እንቅስቃሴ ተወካዮች ብቻና ብቻ ናቸው ብለው ሽንጣቸውን ገትረው ለሚሟገቱ ሕፃናቶች መፈንጫ አይደለም።

የሃይማኖት ተወካዮችን መጋበዝ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የሙስሊሙን ተወካዮች ብቻ ነጥሎ መጋበዝ ታላቅ አደጋ አለው በተለይ ደግሞ አወልያን መሰረት አድርጎ የተነሳውን የሙስሊም እንቅስቃሴ በጥርጣሬ የሚመለከቱ እና  የማይደግፉ ሙስሊሞችንም ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እንዳሉ በሚታወቅበት በዚህ ወቅት ጥንቃቄ ማድረጉ ተገቢ መሆኑን መጠቆሙ ሊገባህ ያልቻለበት ምክንያት አንድም ኢትዮጵያዊያንን ሁሉ እንደ ዜጋ ለመቀበል ችግር ያለብህ ከመሆኑም በላይ ሙስሊም ላልሆነው ኢትዮጵያዊ ክብር የሌለህ መሆኑን ነው።

10. የኢሳት ባልደረባ ተ/ሚካኤል በፅሑፉ 11ኛ ነጥብ ላይ “የሀይማኖት መሪዎች ከጋበዝን ደግሞ ቢመጡም ባይመጡም የኦርቶዶክሱንም የፕሮቴስታንቱንም፤የይሁዲውንም፤ የካቶሊኩንም ነው እንጂ፤ በምን መስፈርት ነው የሙስሊሞቹን ብቻ የምንጋብዘው? ይሄአደገኛና መታረም ያለበት አካሄድ ነው። “  እንዲሁም በ12ተኛ ነጥብ ላይ ኢትዮጵያ “ የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች ያሉባት ሃገር “ መሆኗን በግልፅ ጠቅሷል። ይህም ኢትዮጵያ የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች የሚኖሩባት አገር መሆኗን የሚያስረዳ ሆኖ ሳለ ነገር ግን አንተ ከአውደ ንባቡ ውጪ የሆነ መደምደምያ ይዘህ ለዚህ ትችት መነሳትህ ቀደም ሲል ደጋግመህ እንዳረጋገጥክልኝ የኢትዮጵያዊነት ፅንሰ ሃሳብ ያልገባህ መሆንህን ነው።

ለነገሩ “የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል” እንዲሉ አንተ እስከ 12ተኛው ነጥብ ብቻ በማየት የፅሑፉን መዳረሻ ሳትረዳ በመዘባረቅህ ይቅርታ መጠየቅ ይገባሃል። ምክንያቱም የተ/ሚካኤል ፅሑፉ ሙሉው አንተ እንዳልከው ባለ 12  (ኣስራ ሁለት) ነጥብ ብቻ ሳይሆን 15 (ኣስራምስት) ናቸውና :: ለምሳሌ ስለ ብሔር ብሔረሰቦች ስብጥር ለመግለጽ ቢያስፈልገን ከ80 በላይ የሆኑትን የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች  በንግግሩም ሆነ በፅሑፉ ላይ ሁሉንም ካልጠቀሰ በስተቀር በአንተ የ “ህፃን” አስተሳሰብ መሰረታዊ የጠባብነት ማስረጃ ሆኖ ከተወሰደ እስከ ዛሬ ድረስ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ የብሔር ብሔረሰቦችን የሚመለከት ንግግር ሲያደርጉ ወይም ሲፅፉ ለናሙና ያህል የተወሰኑትን ጠቅሰው በማለፋቸው በአንተ የጠባብነት መስፈርት መሰረት ሁሉንም ባለ መዘርዘራቸውና የተወሰኑትን ጠቅሰው ሌሎቹን ግን “የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች” በማለታችው በአንተ የ”ሕፃን” መስፈርት መሰረት በጠባብነት ጎራ ተፈርጀው ላልበሰለ ትችትህ ተጋልጠዋል ማለት ነው።

አንተ በመግቢያህ ላይ ማንንም አልወክልም ብትልም የተፅዎ ስምህ አልያም የብዕር ስምህ “ቶፊቅ ጀማል” እንደሚያሳብቅብህ ሙስሊም ልትሆን ትችላለህ ነገር ግን ኢትዮጵያ የጀግና ሙስሊሞችም አገር ናት ብለን ለምናምን እንደኔ ላሉ እንደዜጋ በኢትዮጵያዊያነት ለምናምን ወገኖች አንተና አንተ ያለህበት ማህበረሰብ ምናልባትም እንዳንተ የሚያስቡ ከሆነ የኢትዮጵያ ግማሽ አካል ተበላሽቷል ፥ ታሟል፡ በድን ሆኗል ፥ አልያም ከርፍቷልና የወገን ያለህ ብዬ ጩኸቴን አሰማለሁ።

11.    በ11ኛው ነጥብ “ኢሳት በህዝብ ድጋፍ የሚተዳደር ነፃ ሚድያ ይመስለኛል” ብለሃል እዚህ ላይ “ይመስለኛል” ስትል መቼ ይሆን “ነው” ብለህ የምታምነው? በዜግነት የሚያምኑ ኢትዮጵያዊያን የሚሰባሰቡበት መሆኑ ቀርቶ ኢሳት ሙሉ በሙሉ በሙስሊሙ ተወካዮች ብቻና ብቻ ሲሞላ ነው? ሌላው ደግሞ ኢሳት “በህዝብ ድጋፍ የሚተዳደር ነው” ብለሃል እንግዲያውስ ኢሳት በህዝብ ድጋፍ የሚተዳደር ከሆነ በኢሳት ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ የሚገኘው ሁሉም ህዝብ ማለትም በሙስሊሙ እንቅስቃሴ ላይ ጥርጣሬ ያለውም ጭምር ማለት እንጂ ኢትዮጵያዊ ህዝብ ማለት የሙስሊም ተወካዮች ማለት ብቻ ሊሆን አይችልም።

ወይስ አንዳንድ ቅዠታሞች እንደሚደሰኩሩት ከአቡጃ አዋጅ (Abuja declaration of 1989 http://en.wikipedia.org/wiki/Abuja_Declaration) ወዲህ ኢትዮጵያ ኢስላማዊ አገር ሆናለችና መወከል ያለባት በሙስሊም ብቻ ነው ብለው ከሚያስቡት ቡድን በመሆንህ ምክንያት እንጂ በኢትዮጵያዊያን ስብሰባ ላይ መጋበዝ ያለባቸው የሁሉም ሃይማኖት ተወካዮች ናቸው የሚለው የተ/ሚካኤል አበበ ጥሪ ባልጎረበጠህ ነበር።

ስለዚህም ኢሳት ሕዝባዊነቱን ጠብቆ ረጅሙን ጉዞ መጓዝ እንዲችል የሃይማኖት ተወካዮችን መጋበዝ ሲያስፈልግ የሁሉንም የሃይማኖት ተወካዮችን መጋበዝ አለበት እንጂ የሙስሊም ተወካዮችን ብቻ  መጋበዙ የአወልያን እንቅስቃሴ በጥርጣሬ ለሚመለከቱ ኢትዮጵያዊያን ተጨማሪ ስጋትና አደጋ መፍጠር ስለሆነ የሁሉንም ሃይማኖት ተወካዮች መጋበዙ እውነታና ጥበብ መሆኑን የሕፃን አይምሮህ ከልክሎህ ካልሆነ በቀር በቀላሉ ሊገባህ የሚገባ ገዢ ሃሳብ ነበር።

12.   በአስራሁለተኛው ነጥብህ ላይ ከላይ ከፃፍካቸው 11 ነጥቦች በባሰ ሁኔታ የተሳከረ ሃሳብ አንፀባርቀሃል። በአጠቃላይ እርግጠኛ ባልሆንክባቸው ጉዳዮች ሁሉ እንደ እርጎ ዝንብ ዘለህ እየገባህ የምታስቸግር ዘባራቂ መሆንህን ዳግም ያሳየህበት ነጥብ ነው።

በ12ተኛው ነጥብህ ላይ “እንዳልሆኑ ቢናገሩስ?” “ከማሳወቃቸው በፊት ቢሆንስ?” “ተነሳሽነት አሳይተው ቢሆንስ?” በሚሉ ኀረጎች የተሞላ በመሆኑ ስለምትጽፍበት ጉዳይ በቂ ግንዛቤ የሌለህ ለዜግነት ክብር ያላቸውን ሰዎች ለኢትዮጵያዊነት መጎልበት የሚሰጡትን ሃሳብና እርማት የማጣጣልና የማብጠልጠል አባዜ ይዞህ በጽንፈኝነት ለአንድ ቡድን ከመቆም የመነጨ ደካማና መጥፎ ባህሪ በመሆኑ ለወደፊቱ ቆም ብለህ ራስህን እንድትገመግም አደራ እላለው።

ፅሁፌን ለማጠቃለል ሳስብ በጣም የሚገርሙ ከላይ ከፃፍካቸው በበለጠ ማንነትህን ያጋለጥክበት ሃሳብ በማጠቃለያ ፅሑፍህ ውስጥ በማግኘቴ ለማጠቃለያህም ማጠቃለያ መፃፍ አስፈላጊ ሆነ:: ነገር ግን የአማርኛ ሰዋሰው ሊቅ በመሆንህ በሮማኖች ቁጥር (Roman number)  መጠቀም ትቼ ትንሽ ደስ ይልህ እንደሆን ብዬ የነጥቦቹን ተራ ቁጥር በአማርኛ ፊደላት እንደሚከተለው ገልጫቼዋለው:-

ሀ.  ተ/ሚካኤል በግልፅና በተደጋጋሚ ኢትዮጵያዊነትን አጉልቶ በማሳየት የፃፈውን ፅሑፍ አንኳር ሃሳቡን አውርደህ አውርደህ የቃላት ጨዋታ ለማድረግ ስትሞክር “የአማርኛ ክፍተት ይታይብሃል” ብለሃል ጉዳዩ ግን የአማርኛ ክፍተት ጉዳይ ሳይሆን ኢትዮጵያዊያን በዜግነታቸው ተሰብሰበው በሃገራቸው ላይ ለሚከሰቱ ችግሮች የጋራ መፍትሔ እንዲፈልጉ የማድረግ ጉዳይ ሆኖ ሳለ አንተ ግን ጭብጡ ላይ ከማተኮር ይልቅ የአማርኛ ቋንቋ ውድድር ልታስመስለው መሞከርህ እጅግ በጣም ያሳዝናል :: ነገር ግን እግረ መንገድህን  “የኢሳት ባልደረቦችን የአማርኛ ክፍተት ለመሙላት” የአማርኛን ቋንቋ ለማስተማር ሃሳቡ ካለህ ለኢሳት አስተዳደር ማመልከቻ ብታስገባ የተሻለ ነው።

ለ.     አቶ  ቶፊቅ ጀማል በኢሳት ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያንን በሚያካትት መልኩ መዘጋጀት አለበት ብሎ ተ/ሚካኤል አበበ መፃፉ ኢሳትን ማጠልሸት ነው ብለሃል::  ለመሆኑ በኢሳት ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ የሃይማኖት ተወካዮችን መጋበዝ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ  የሁሉም ሃይማኖት ተወካዮችን መጋበዙ ጣቃሚ ነው መባሉ በየትኛው አተረጓጎም (ተፍሲር) ነው ኢሳትን ማጠልሸት የሚሆነው?

የማጠልሸት ጉዳይ ከተነሳ ግን በግልፅ እንዲገባህ የሚያስፈልገው  ነገሩ “የእምዬን ወደ አብዬ ልክክ”መሆኑን ነው ። አንተንና አንተን የሚመስል ሃሳብ ያላቸው አንዳንድ በሙስሊሙ ስም የሚነግዱ ቅዠታሞች ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያ ኢስላማዊ በመሆንዋ ልትወከል የሚገባው በሙስሊሞች ብቻ ና ብቻ መሆን አለበት እያሉ በተለያዩ ሚዲያዎች እንደሚደሰኩሩት ( http://www.selamta.net/Downloads/Letter_to_International.pdf )  አንተም የነዚህን የቀን ህልመኞች ፈለግ ተከትለህ በቂ ግንዛቤ ሳይኖርህ ይህንን ተራ ቱልቱላ ተሸክመህ ኢትዮጵያዊያንን ሁሉ በዜግነት የሚያሰባስበንን ኢሳትን ለማጠልሸት የተነሳኸው አንተ ሆነህ ሳለ የኢሳትን ገፅታ እንዳይበላሽ ምክርና እርምት የለገሰንን ሰው ጥፋተኛ ለማድረግ በመሞከርህ “የእምዬን ወደ አብዬ” ብዬ ከማለት በቀር ሌላ አማራጭ የለም። ነገር ግን በዚህ “የህፃን” አስተሳሰብህ በአንተም ፥ አንተን በሚመስሉህም በተጨማሪም እንደዚህ ዓይነት አስተሳሰብ እንዲኖርህ ተፅኖ ባደረገብህም የማህበረሰብ ክፍል እጅግ በጣም አዝኛለሁ።

ሐ.   በመጨረሻም በአንተና የአንተን አስተሳሰብ ተከትለው በሚነጉዱ ሰዎች እኔንና እንደ እኔው ለኢትዮጵያዊ ዜግነት ክብር ላለን ሰዎች ተስፋ አስቆራጭ የሆነውን ማጠቅለያ ስትፅፍ እንዲህ ነበር ያልከው “ ሌላው ልትረዳው እምፈልገው ጉዳይ ቢኖር እንደው ግላዊንት ካልሆነ በስተቀር ምንን ምክንያት አድርገው ነው የሌላው የሃይማኖት አባቶች ሊሳተፉ የሚችሉት በብዙ ሺህ የታሰሩት ሙሰሊሞች፣ ከአመት በላይ ደምፃቸውን ያለማቋረጥ በሰላማዊ መልኩ እያሰሙ ያሉት ሙሰሊሞች፣ ከትምህርት ገበታቸው በጅምላም በችርቻሮም እየታፈኑ ያሉት ሙሰሊሞች፣ በምሽት እየተዋከቡ የሚገኙት ሙሰሊሞች ወንድሜ ቆም ብለህ ማሰብ ያሻሃል፡፡”

በዚህ አስተሳሰብህ አንተን ኢትዮጽያዊ ዜጋ ነህ ብሎ ለመቀበል አይቻልም ወይም ለኢትዮጽያዊያን በችግራቸው ወቅት ከጎናቸው ልትቆምላቸውና ልትደግፋቸው የሚገባህ በሀይማኖታቸው አይነት ሳይሆን በዜግነታቸው ብቻ መሆኑን የማታምን የዜግነት ክብር የሌለህ “ጨቅላ ህጻን” መሆንክን ክማረጋገጡም በላይ ለሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ችግሮች; በሃይማኖታቸው ሳይሆን በዜግነታችሀው ብቻ ለሙስሊሙ መብት ቀንና ሌሊት ሲጮሁ የከረሙትን የሃይማኖት መሪዎች : የፖለቲካ መሪዎች:  የሲቪክ ማህበራት : ታዋቂ ግለሰቦች:  የሰባዊ መብት ተሟጋቾች:  የሚዲያ ተቋማት : ጋዜጠኞችና እንደ ኢሳት አይነቱን የቴሌቪዥን ጣቢያ በግልጽ ያቃለልክበትን: ያላገጥክበትና ለኢትዮጵያዊያን ያለህን ንቀት  ያረጋገጥክበት የማንነትህ መገለጫ ነው::

v አቶ(ሼክ) ቶፊቅ ጀማል ለሙስሊሞች ችግር ሙስሊሙ ብቻ ከሆነ  መቆም ያለበት ለመሆኑ እነዚህ ሁሉ “ምንን ምክንያት አድርገው ” ነበር ለሙስሊሙ ጥያቄዎች ክሙስሊሙ ጋር አብረው በየ አደባባዩ ሲጮሁ የከረሙት?

v በዚህ ጽሁፍ ላይ በስም የጠቀስከው “አርቲስትና አክቲቪስት” ታማኝ በየነ ምንን ምክንያት አድርጎ ነበር በየ አደባባዩና በየ ሚድያው ድምጹን ሲያሰማ የነበረው?

v በኢትዮጵያዊነት ብቻ አንዳችን ለአንዳችን በመቆም የማታምን ከሆነ ታድያ እንደ አንተ አይነቱን “እጅ ነካሽ” አምነን ለዜግነት ክብር ያለውንና ኢሳትም ይህንኑ መስመር ይዞ እንዲቀጥል ሃሳቡን  ያካፈለንን የወንድማችንን የተ/ሚካኤል አበበን ምክር አዘልና የተቀደሰ ሃሳብ  አጣመህና አወላግደህ በማቅረብ ልታወናብደነን የሞከርከው?

v አንተንና ስምህ እንደሚያመለክተው ምናልባት ሙስሊም ከሆንክ የአንተ አይነት አስተሳሰብ ያላቸውን ሙስሊሞች ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆናችሁን እንዴት ለማመን ይቻላል?

v አንተንና አንተን የመሰሉ ሰዎች በሚኖሩባት ኢትዮጵያ አወሊያን መሰረት አድርጎ የተነሳውን የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ኢትዮጵያዊ ዜግነትን አጥፍተው በኢስላማዊ ዜግነት ለመተካት ነው የሚፈልጉት ብለው የሚጠራጠሩና ስጋት ያለባቸው ኢትዮጵያዊያን ቢኖሩ ጥፋታቸው ምንድነው?

v በኢትዮጵያ ውስጥ በሃይማኖታቸው ዙሪያ ችግር የገጠማቸው ሙስሊሞቸ ብቻ መሆናቸውን በዝርዝር አስቀምጠሃል ነገር ግን የኢትዮጵያ ኦርተዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ከሃገር ተሰደው የሚኖሩት በሃይማኖታቸው ሙስሊም ስለሆኑ ነው?

v አቶ(ሼክ)  ቶፊቅ ጀማል እነ እስክንድር ነጋ ፥ አንዷለም አራጌ ፥ ርዮት አለሙ ፥ አቶ በቀለ ጎረባና በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በየ እስር ቤቱ የሚሰቃዪት  በሙሉ በሃይማኖታቸው  ምስሊሞች ናቸውን?

መካሪ ህሊና ወይም ለመካሪነት የደረሱ ሰዎች በዙሪያህ ካሉ በዚህ ሃላፊነት በጎደለው አባባልህ በሀይማኖት ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ከሙስሊሙ ጋር አብረው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ሲያሰሙ የነበሩትን ወገኖች ሁሉ የሚያሳዝን አፀያፊ ስራ ሰርተሁልና በአደባባይ ይቅርታ ልትጠይቅ ይገባሃል::

ኢትዮጵያዊያን በገጠማቸው ማናቸውንም ችግሮችና  የሰብዓዊ መብት ረገጣ ላይ አፋጣኝ መፍትሄ ሊያመጡ የሚችሉት በሃይማኖት ፥ በጎሳና በፖለቲካ ሪዮተ ዓለም ሳይሆን ከምንም በላይ በኢትዮጵያዊ ዜግነት ላይ መሰረት ሲያደረጉ ብቻ ነው።አንተ ግን ይሄ እውነታ እንዲገባህ ያልፈቀድህ በኢትዮጵያዊንት ላይ የምትቀልድ “ህፃን” ብቻ መስለኸኝ ነበር በዜግነት ክብር ላይ ያልህን ንቀት ካረጋገጥክልኝ በኋላ ግን “ሕፃን” ብቻ ሳትሆን “ከሕፃንም ሕፃን” እንጂ።

ኢሳት ለዜግነት ክብር ላላቸው ኢትዮጵያውያን ሁሉ የጋራ ሃብት በመሆኑ በኢሳት ክብረ በዓል ላይ የሙስሊም ተወካዮች ብቻ እና ብቻ የሚጋበዙበት መስጊድ አይደለም!!!

አስተዋይ: ታዛቢ

Asteway.tazabi@gmail.com

↧

ስለ ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም የሚወራው ምንድን ነው?

$
0
0

zehabesha 50
እንደፌስቡክ ያሉ የማህበራዊ ድረገጾች ማጥፊያም ማልሚያም ከሆነ ሰነባብቷል። ከአንድ አመት በፊት የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሞቱ ተብሎ በሰፊው በየማህበራዊ ድረገጾች ከተወራ በኋላ ህዝቡ ‘ሞቱ አልሞቱም በሚል ሲወዛብ ቆትሮ በኋላም ፕሬዚዳንቱ በቲቪ ቀርበው ለረዥም ሰዓታት ተኝቼ ብነሳ ይህ እንዲህ ተወራብኝ ብለው ነበር።

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ደግሞ በኢትዮጵያ የስነጽሁፍ ታሪክ ግዙፍ ታሪክ ካላቸው ጸሐፊያን መካከል በዓሉ ግርማ በጣና ሀይቅ ላይ ከሚገኙት  ደሴቶች ካሉ በአንዱ ገዳም በሕይወት አለ ተብሎ እንዲሁ በሰፊው በማህበራዊ ድረገጾች ከተወራ በኋላ መጨረሻው ምን እንደሆነ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። (በዚህ ዙሪያ በውስጥ ገጻችን ሰፋ ያለ ዘገባ ይዘናል – ይመልከቱት)

ሸሽተው በስደት ዘምባብዌ የሚገኙት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት መንግስቱ ሃይለማርያምም ሞተዋል የሚለው ዜና መወራት የጀመረው ከሳምንታት በፊት ነበር። የኢሳት ራድዮ ይህ ወሬ ሲዛመት ወደ ዙምባዌ ደውሎ የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ባለቤት ወ/ሮ ውባንቺ ቢሻውን አግኝቶ አነጋግሯቸው ነበር። ወ/ሮ ውባንቺም መንግስቱ በመልካም ሁኔታ በሕይወት እንዳሉ ሲናገሩ ጋዜጠኛው እርሳቸውን አገናኙን ሲል ቢጠይቃቸውም እርሷቸው ግን ፈቃደኛ አለመሆናቸው ይታወሳል።

ዘ-ሐበሻን ይዘን ወደ ማተሚያ ቤት ለመግባት በዝግጅት ላይ እንዳለን ደግሞ ማንም ሰው ተንስቶ የፈለገውን ነገር ሊጽፍ በሚችልበት topix.com (የመወያያ ፎረም ነው) ላይ በሰበር ዜና መንግስቱ ኃይለማርያም በልብ በሽታ በተወለዱ በ75 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ተጽፏል። ወዲያው ወሬው እንደፌስቡክን በመሳሰሉ የማህበራዊ ድረገጾች ላይ ተሰራጭቶ በሰፊው ህዝብን እያወያየ ሲሆን መሞታቸውን ያመነ፣ መሞታቸውን ያላመነ እና በጥኑ ህመም ላይ እንዳሉ ያመነ እንዳሉ ከሚሰጡ አስተያየቶች ለመረዳት ይችላል።

ዘ-ሐበሻ ይህን ዜና ወደ ህትመት እስከገባችበት ጊዜ ድረስ የተከታተለች ሲሆን የቀድሞውን ፕሬዚዳንት መሞት ግን ልታረጋግጥ አልቻለችም። የትኛውም ትላልቅ ሚዲያም ይህን ጉዳይ አልዘገበም።
“ሰውን ማመን ቀብሮ” የሚባለው አባባል “ፌስቡክን ማመን ቀብሮ” ወደሚለው ቢስተካከል ምን ይመስላችኋል?

 

 

↧

የኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያም ዜና ምንጭ ወያኔ ነው

$
0
0

zehabesha 50 (በፌስቡክ የተለቀቀ አስተያየት)

በርካታ የኤርትራና አፍቃሪ ህወሀት/ኢህአዴግ ብሎጎች፣ የህወሀት/ኢህአዴግ ደጋፊ ካድሬዎች እንዲሁም የተቃዋሚ ደጋፊ መስለው የሚንቀሳቀሱ ድረ-ገጾች በአንድላይ “መንግስቱ Mengistu_Haile_Mariam ሀይለማርያም አረፈ” የሚል ዜና በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ ጉዳዩን አንድም ነብስ ያለው የዜና አውታር አልዘገበውም።

ይህን አስመልክቶ ታዋቂው የኢሳት ራድዮ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን የሚከተለውን በፌስቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል፣

ኮነሬል መንግስቱ ኃይለማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ፌስቡኩን ድረ-ገጹን የወረረ ምንጭና ፍንጭ የሌለው ወሬ በግሌ ወረርሽኙ ሲዛመት ለማጣራት ያሉኝን መንገዶች በሙሉ ተጠቀምኩ ደወልኩ ነዘነዝኩ ምንም የለም ሊንክ ተደርገው የተለጠፉና ምንጭ ተብለው የተጠቀሱትን በሙሉ አየሁ በረበርኩ ዋንኛ ምንጭ የተባለው ድረ ገጽ ከሶስት ሳምንት በፊት የለቀቀውና ውሸት መሆኑ ወዲያውኑ ኢሳት ያረጋገጠው ነበር ሌላው የዙምባቡዌ ቴሌቪዥን ተናገረ የተባለው ነው ሲከፈት ግን ምንም የለም እና ወሬው ከየት መጣ የበዓሉ ግርማ በህይወት አለ ወረርሽኝ ለማንኛውም እስከዚህ ሰዓት ድረስ ባለኝ መረጃ ኮነሬል መንግስቱ ኃይለማያም በህይወት አሉ።

ሀና መታሰቢያ በመባል የምትታወቅ የፌስቡክ ተተቃሚ ደግሞ እንዲህ ብላለች፣

ፌስቡክን ሙሉ ለሙሉ መዝጋት ፖለቲካል ኪሳራው ከባድ መሆኑን የተረዱ የሚመስሉት ወያኔዎች ከዚህ ይልቅ ለየት ያለ መንገድ እየተከተሉ ነው።ፌስቡክ ውስጥ እየተፈጠሩ ያሉት አባዛኛዎቹ አሉባልታዎች ምንጭ ወያኔዎች ይመስሉኛል። በአጠቃላይ ፌስቡክን በተመለከተ የወያኔ ፕሮፐጋንዲስቶች እየተከተሉ ያሉት መንገድ፦

1. ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የሚካሄድባቸውን ግሩፖችና ገፆችን ነጥሎ መዝጋት(ምንም እንኳን በhttps://መከፈት ቢችሉም)

2. ፌስቡክ ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ ግለሰቦችን አካውንት መዝጋት

3. መንግስትን የሚያወግዙ ፖስተሮችና ፅሑፎች ስር ከርዕሱ ባፈነገጠ መልኩ ፖስት ያደረገውን ግለሰብ በመዝለፍ የውይይቱን አቅጣጫ ማሳት

4. ፌስቡክ ላይ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉ ግለሰቦችን ሜሴጅ እየላኩ ማስፈራራት፣ በስድብና በዛቻ ማሸማቀቅ

5. ምንም እንኳን ማንኛውንም ነገር ያለ ፕሮግራም መጠቀም ጊዜን ማባከኑ እሙን ቢሆንም ወያኔዎች ስለፌስቡክ ጊዜ አጥፊነት የሚሰብኩት ለኛ በማዘን አይደለም ስለሚጠፋ ጊዜ ከምር ቢጨነቁ ሀገሪቷን የወረሯትን ጫት ቤቶች በዘጉ ነበር እስካሁን የፌስቡክን ጉዳት እና ጊዜ አጥፊነት በተመለከተ በወያኔ ሚዲያዎች ከ3 ጊዜ በላይ ፀረ ፌስቡክ ዝግጅቶች ቀርበዋል

6. አዲሱ የወያኔ ፕሮፐጋንዲስቶች ታክቲክ መያዣ መጨበጫ የሌላቸውን አሉባልታዎች በፌስቡክ በመንዛትና በማሰራጨት የፌስቡክን ተአማኒነት በመቀነስ ፌስቡክ የቦዘኔዎች ብቻ መሰብሰቢያ የሚመስል ገፅታ እንዲላበስ ማድረግ በዚህ መንገድ ከተነዙ አሉባልታዎች ውስጥ የልመንህ ሞት፥ የበአሉ ግርማ በህይወት ተገኘ መባል እና የዛሬው የመንጌ ሞት ይጠቀሳል።

እኛ ጭቁን ኢትዮጵያውያን ጉዟችን እሩቅ ነውና በጅላጅል አሉባልታዎች ሳንዘናጋ ፌስቡክን እንደ መወያያ እና መገናኛ መድረክ እንጅ እንደዋነኛ የትግል አውድ ሳንወስድ ትግላችንን እናበርታ።

↧
↧

ደደቢት ባይቀናውም የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመጨረሻዎቹ 16 ክለቦች ተለይተዋል

$
0
0

የሞሮኮው ክለብ ፋርሪካት የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሻምፒዮን ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፤

የሞሮኮው ክለብ ፋርሪካት የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሻምፒዮን ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፤


በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የተለያዩ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ሲካሄዱ ቆይተው የመጨረሻዎቹ አስራ ስድስት ክለቦች የመጨረሻው የጥሎ ማለፍ ተፋላሚዎች መሆናቸው ታውቋል።
ወደ መጨረሻው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ካለፉት አስራ ስድስት ክለቦች መካከል አምስቱ ቀደም ሲል የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ያነሱ ናቸው።
ከአምስቱ ክለቦች መካከል የሞሮኮዎቹ ፋር ራባትና ዋይዳድ ካሳብላንካ ግንባር ቀደሞቹ ሲሆኑ፤ የኮትዲቯሩ ኤ ኤስ ኢ ሲ ሚሞሳህ አስራ ስድስት ውስጥ የገባ ሌላኛው ክለብ ሆኗል።የቱኒዚያው ኢቶይል ሳሌህና የግብፁ ኢስማኤሊ ከአምስቱ የቀድሞ የአፍሪካ ሻምፒዮኖችና የአሁኑ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመጨረሻው የጥሎ ማለፍ ተፋላሚዎች ሆነዋል።
ከአስራ ስድስቱ ክለቦች መካከል የቱኒዚያው ኤስ ሲ ፋዚየን መካተት ችሏል።ይህ ክለብ አህጉራዊ ዋንጫ ከማንሳቱም ባሻገር በተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች አፍሪካን ወክሎ መሳተፍ የቻለ ውጤታማ ክለብ እንደነበር ይታወሳል።
ወደ መጨረሻው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ከገቡ ክለቦች መካከል የሞዛምቢኩ ክለብ ሊጋ ሙከልማና መካተቱ የስፖርት ቤተሰቡን ያስገረመ ጉዳይ ሆኗል።ይህ ክለብ የመጨረሻውን ጥሎ ማለፍ ውድድር የተቀላቀለው የናይጄሪያውን ሎቢ ስታርስ ክለብን ማፑቶ ላይ ሰባት ለአንድ በሆነ ውጤት አሸንፎ ነው። ሊጋ ሙከልማና ክለቡ ይህ ነው የሚባል ስም የሌለው እንደመሆኑ መጠን በሰፊ ውጤት ማሸነፉ ያልተጠበቀ ነበር።
የጋቦኑ ዩ ኤስ ቢታም ክለብ አስራ ስድስት ውስጥ መግባት ከቻሉት ክለቦች አንዱ ሆኗል።ይህ ክለብ በቀደሙት ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች አስራ ሰባት ግቦችን በማስቆጠር ባለ ክብረወሰን ነው። በመጪዎቹ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎችም ውጤታማ ይሆናል ተብሎ ግምት ተሰጥቶታል።
ዩ ኤስ ቢታም ክለብ ካስቆጠራቸው ግቦች መካከል አራቱ ግቦች ሶኒቶ የተባለው ተጫዋች ኳስን ከመረብ ያዋሃዳቸው ናቸው። በእዚህም የዋነጫው ኮከብ ግብ አግቢ በመሆን ይመራል።
የሞሮኮው ፋር ክለብ የአፍሪካ ሻምፒዮን በመሆን በሞሮኮ ክለቦች ታሪክ የመጀመሪያው ነው።ይህ ክለብ የአፍሪካ ሻምፒዮን የሆነውም እ.ኤ.አ በ1985 እንደ ነበር ይታወሳል። ክለቡ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫን ከስምንት ዓመት በፊት ለሁለተኛ ጊዜ ማንሳቱም አይዘነጋም።
በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የተሻለ ታሪክ ያለው የታንዛኒያው አዛም ክለብ በሜዳው ግብ ባልተቆጠረበት ሕግ የሊቢያውን አል ናስር ክለብን ጥሎ አስራ ስድስት ውስጥ ገብቷል። አዛም ከእዚህ በፊት በነበረው ጥሎ ማለፍ የላይቤሪያውን ባራክ ያንግ ኮንትሮለርስ ክለብን በጥሎ ማለፍ ማሸነፉ ይታወሳል።
«ዘ ነርሰሪ» በመባል የሚታወቁት ኤ ኤስ ኢ ሲ የኮትዲቯርን በርካታ ከዋክብት ያፈራ ክለብ ነው።ይሁን እንጂ በኮንፌደሬሽን ዋንጫ ተጠቃሽ ታሪክ የለውም።ይህ ክለብ የአፍሪካ ሻምፒዮን የነበረበት ጊዜም እ.ኤ.አ በ1998 ነው።
የአገራችንን ክለብ ደደቢትን በሜዳው አንደ ለባዶ በማሸነፍ አዲስ አበባ ላይ ደግሞ ባዶ ለባዶ በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቶ ወደ ቀጣይ ዙር ያለፈው የሱዳኑ አል አህሊ ሸንዲ ክለብ አስራ ስድስት ውስጥ መግባት ከቻሉ ክለቦች አንዱ ነው።አል አህሊ ሸንዲ በቀጣይ ጥሎ ማለፍ ጨዋታም የግብፁን ኢስማይሊ ክለብን እንደሚገጥም ታውቋል።
↧

የረጅም ርቀት ንጉሡ ኃይሌ ገ/ሥላሴ አይረሴ ውድድሮች

$
0
0

Haile-Vienna በአሰግድ ተስፋዬ

የሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴን አርባኛ የልደት በዓል አስመልክቶ ስፓይክስ የተባለው ድረ ገጽ የአትሌቱን አስር አይረሴ ውድድሮች ዝርዝር ለትውስታ ማቅረቡ ይታወሳል።እኛም ከእነዚህ ውድድሮች መካከል አምስቱን ባለፈው ቅዳሜ እትማችን ማቅረባችን ይታወሳል።ዛሬ ደግሞ ቀሪዎቹን አምስቱን እንደሚከተለው አቅርበናቸዋል።

1999 የማዕባሺ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በእዚህ ውድድር « ሁለ ገብ » መሆኑን ያሳየበት ነበርና አውሮፓውያኑ « Multi-eventer » የሚል ቅጽል ከስሙ በፊት እንዲጨምሩ አስገድዷቸዋል።
በውድድሩ ብዙ ጊዜ በማይስተዋል መልኩ ሻለቃ ኃይሌ በአንድ ሺ አምስት መቶና በሦስት ሺ ሜትር ውድድሮች ምርጥ ችሎታውንና ለረጅም ርቀት ሩጫ የተፈጠረ አትሌት መሆኑን አሳይቷል።

የሦስት ሺ ሜትር ርቀት ውድድር የሚታወቅበትና በበርካታ ውድድሮች ላይ ችሎታውን ያሳየበት በመሆኑ ማሸነፉ ብዙም አስደናቂ ባይሆንም በውድድሩ የአንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር ውድድርን በተደጋጋሚ በመርታቱ የተነሳ « ስፔሻሊስት » ለመባል የበቃውን ላባን ሮቲችን መርታቱ በወቅቱ እንደተአምር ተቆጥሮ ነበር ።

1999 የዓለም ሻምፒዮና ሲቪያ

ይህ የዓለም ሻምፒዮና አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በአስር ሺ ሜትር ተፎካካሪዎቹን በሙሉ ተስፋ ያስቆረጠበት ነበር።
በውድድሩ የመጨረሻውን ዙር ከአንድ ደቂቃ በታች ማለትም በ54 ነጥብ 5 ሰከንድ በመሮጥ በተከታታይ ለአራተኛ ጊዜ በአስር ሺ ሜትር የዓለም ሻምፒዮን መሆን የቻለበት ነው። በእዚህ ውድድር ሁለተኛ የወጣው ማን እንደሆነ አንባቢ ግምቱን ይስጥ ቢባል ኬንያዊው ፖል ቴርጋት ከተባለ መልሱ ትክክል ይሆናል ።

ተአምረኛዋ ሰኞ 2000ሲድኒ ኦሊምፒክ

የአውስትራሊያዋ ሲድኒ ያስተናገደችው ይህ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በተሳትፎዋ ለመጀመሪያ ጊዜ በርካታ ሜዳሊያዎችን ያገኘችበት በመሆኑ ለኢትዮጵያውያን ልዩ ነበር።በመሆኑም ነው ከልጅ እስከ አዋቂ ባለድል አትሌቶቹ ወደ አገራቸው ሲመለሱ አደባባይ ወጥቶ የጀግና አቀባበል ያደረገላቸው።
ይህ ኦሊምፒክ ለኢትዮጵያውያን ልዩ ስፍራ የሚሰጠው ቢሆንም ሻለቃ ኃይሌ ደግሞ ተስፋ አለመቁረጥን ፣ ኢትዮጵያዊ ወኔን ለዓለም ያሳየበት ነው ማለት ይቻላል።
ልክ የሪያል ማድሪዱ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ችሎታ በአርጄንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ ችሎታ እንደተሸፈነው ሁሉ በኃይሌ ገብረሥላሴ ተአምራዊ ብቃት ሁል ጊዜ ሁለተኛ መውጣትን የተለማመደ የሚመስለው ኬንያዊው ፖል ቴርጋት የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ለመውሰድ አስራ አምስት ሜትሮች ብቻ ሲቀሩት ድሉን ለማስጠበቅ በመወዳደር ላይ የነበረው ኃይሌ ከኋላ መጥቶ የወርቅ ሜዳሊያውን የነጠቀበት ሁኔታ የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች ሁሌም የሚያስታውሱት ክስተት ሆኗል።
የስድኒ ኦሊምፒክ በአስር ሺ ሜትር ያስመዘገበው አስደናቂና ልብ አንጠልጣይ ድል አትሌት ኃይሌ የአትላንታ ክብሩን ያስጠበቀበት ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያ በተከታታይ ሁለት ኦሊምፒኮች በርቀቱ የወርቅ ሜዳሊያ እንድታገኝ ያስቻለ ነበር ።

ለንደን ግራንድ ፕሪ 2004

በእዚህ ጊዜ ኃይሌ ሜዳ ላይ ምርጥ ብቃቱን የሚያሳይበት ጊዜው ያለፈበት ቢመስልም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ግን የቀድሞ ብቃቱን ማሳየት አልተሳነውም።
በእዚህ ውድድር ላይ ባለምርጥ ብቃቱ ወጣት አውስትራሊያዊ ክሬግ ሞትራም ተሳታፊ ነበር። ወጣቱ እንደተጠበቀውም ኃይሌን ቀድሞ በመግባት ለማሸነፍ ከጫፍ ደርሷል።ይሁንና ኢትዮጵያዊው ተለይቶ የሚታወቅበትን ፈጣን የአጨራረስ ብቃት ተጠቅሞ አንደኛ ወጣ።
ኃይሌ ውድድሩን በ12 ደቂቃ ከ55 ነጥብ 51 ሰከንድ ቢያሸንፍም ከወጣቱ አውስትራሊያዊ የነበረው የሰዓት ልዩነት የዜሮ ነጥብ 25 ሰከንድ ብቻ መሆኑ አውስትራሊያዊውና ኢትዮጵያዊው ያደረጉት ፍልሚያው ከባድ እንደነበረ ለመገመት አያዳግትም።

« የማራቶኑ ሰው » በርሊን 2008
haile
በአትሌቲክስ ስፖርት ዓለም ትልቁና የመጨረሻው በሆነው የማራቶን ውድድር ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ በበርሊን ጎዳናዎች ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም ክብረ ወሰን ያስመዘገበበት ውድድር ነው፡፡ ይህ ውድድርበራሱ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በ27 ሰከንዶች ከማሻሻሉም በላይ ርቀቱን ከሁለት ሰዓት ከ04 ደቂቃ በታች በመሮጥ የዓለማችን የመጀመሪያው ሰውም የሆነበት ውድድር ነው።
አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ርቀቱን በሁለት ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ59 መሮጡን ተከትሎ « ርቀቱ ከሁለት ሰዓት በታች በሆነ ጊዜ ሊሮጥ ይችላል ? » የሚል ጥያቄ እንዲያነሱ አድርጓቸዋል።

↧

“በሀገሪቱ የተደረገው ምርጫ የቧልትና የቀልድ ምርጫ መሆኑን ለህዝብ አሳውቀናል”

$
0
0

አቶ አስራት ጣሴ

አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ አስራት ጣሴ የዛሬ እንግዳችን ናቸው፡፡ አቶ አስራት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ዋና ጸሐፊና የመድረክ አመራር አባል ናቸው፡፡ የ33ቱ ፔቲሽን ፈራሚ ፓርቲዎች ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴም ሰብሳቢ ናቸው፡፡ በወቅታዊ  የሀገሪቱ  ጉዳይ  ላይ  ከፍኖተ ነፃነት ጋር ቆይታ አድርገዋል  መልካም  ንባብ

ፍኖተ ነፃነት፡- የ33ቱ ፓርቲዎች ስብስብ እስካሁን ምን ምን አከናወኑ?

Asrat Tassie

አቶ አስራት ጣሴ -የአንድነት ፓርትይ ዋና ፀሐፊ

አቶ አስራት፡- ከተፈራረምን 6 ወር የሆነን ሲሆን ተጨባጭ ሆኑ የስራ እንቅስቃሴዎችን አድርገናል፡፡ ከዚህም መካከል የሚያዚያ 2005 ዓ.ም. ምርጫን አስመልክቶ ለሀገሪቱ ይጠቅማሉ ያልናቸውን 18 ጥያቄዎችን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ ለኢፌድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ፣ ለኢህአዴግ ጽህፈት ቤት በማቅረብ ምርጫውን ነፃ፣ፍትሃዊ፣ ተዓማኒና ሰላማዊ እንዲሆን ትልቅ ትግል አድርገናል፡፡ ነገር ግን ከእነሱ በኩል ምንም ዓይነት ምላሽ ባይገኝም በእኛ በኩል ውጤታማ ስራ ሰርተናል ብለን እናስባለን፡፡ በርግጥ ከ33ቱ ውስጥ 5ቱ ከተፈራረምን በኋላ ወደ ምርጫ ቢገቡም የቀሩት 28ቱ በሙሉ ይህ ምርጫ ፍትሃዊና ተዓማኒ ስለማይሆን አጃቢ መሆን አንፈልግም በሚል ከምርጫው ወጥተናል፡፡
ከምርጫው የወጣነውም ተገደን እንደሆነና ቢያንስ 18ቱም ጥያቄዎች ባይመለሱም እንኳ በመሰረታዊ ሐሳቦች ዙሪያ ውይይት ቢደረግበትና የተወሰኑ ጥያቄዎች እንኳ ቢመለሱና በትንሹ ምርጫው ከፈት ቢል ወደ ምርጫው እንገባ ነበር፡፡ በመሐል ፒቲሽን ፈርሞ ወደ ምርጫው የገባው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ(ሲአን) ተመልሶ ወጥቷል፡፡ስለዚህ በሀገሪቱ የተደረገው ምርጫ የቧልትና የቀልድ ምርጫ መሆኑን ለኢትዮጵያ ህዝብና ለዓለም አቀፉ ማኀበረሰብም አሳውቀናል፡፡ በዚህ ምርጫ መሳተፍ ለሰብዓዊ መብት መሻሻል፣ ለሀገሪቱ ዴሞክራሲያዊ ዕድገት፣ የህግ የበላይነትና ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ለውጥ ምንም ጥቅም እንደሌለው ነው የተረዳነው፡፡ በተፃፃራሪ መልኩ ያየነው እንደሆነ በዚህ ምርጫ መሳተፍ ማለት የሰብዓዊ መብት ጥሰትን፣ የዜጎች መፈናቀልን፣የዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰትን እንዲቀጥል መፍቀድና መቀበል ማለት ነው፡፡ ይህን ደግሞ የማንኛውም ሰው ህሊና የሚቀበለው ተግባር ስላልሆነ የጠቀስኳቸው የመብት ጥሰቶች በሀገሪቱ እንዲቀጥሉ ስለማንፈልግ ከምርጫው መውጣታችን ተገቢ ነው፡፡ ሌላው ትልቁ ውጤታማ ስራ የሆነው ሁሉም ፈራሚ ፓርቲዎች በየፓርቲያችን ከምርጫ ጉዳይ ባለፈ ወደፊት በጋራ ልንሰራቸው ስላሰብናቸው ስራዎች በሰፊው ተወያይተን የካቲት 23 ቀን 2005ዓ.ም በመኢአድ ጽህፈት ቤት በርካታ እንግዶች በተገኙበት የጋራ የስምምነት ሰነድ ተፈራርመናል፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- ወደ ፊት ሊያሰራችሁ የሚችል የመጨረሻ ሰነድ ነው ወይስ ከምርጫ ጉዳይ ውጭ ልትሰሩ አላሰባችሁም?

አቶ አስራት፡- የመጨረሻ የሚባል ሳይሆን በጋራ ለመስራትና ወጥ የሆነ አቋም ለመያዝ እንጂ  ከምርጫ ጉዳይ ባለፈ ወደፊት በተጠናከረ መልኩ በጋራ ሊያሰራ የሚችል ሰፊ ጥናት የተደረገበት ረቂቅ ተዘጋጅቶ ለየፓርቲዎቹ ተበትኗል፤ ፓርቲዎቹም ተነጋግረው ለሚቀጥለው ስብሰባ ይቀርባል፡፡
ከላይ ከጠቀስኩት ውጭ ሰነዱን የፈረምን ፓርቲዎች በጋራ ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ ወስነን ስናበቃ እንቅፋቶች ገጥመውናል፡፡ ከገጠሙን ችግሮች መካከል ጥር 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ህዝባዊ ስብሰባውን ለማካሄድ አዳራሾች ፈልገን በመጨረሻ ኢየሩሳሌም ሆቴልን አግኝተን ከተስማማን በኋላ እንደውም እኔው ራሴ 5ሺህ ብር ቀብድ ይዤ ስሄድ በመጨረሻ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ ከዛ በኋላ የወሰድነው እርምጃ አዲስ አበባ ባሉ የፒቲሽን ፈራሚ ፓርቲዎች አዳራሽን በመጠቀም ከህዝብ ጋር መወያየትን እንደ አማራጭ በመውሰድ በመድረክ፣ በአንድነት፣ በመኢአድ እና በሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤቶች ግቢ ውስጥ መጋቢት 29 ቀን 2005 ዓ.ም. በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት የተለያዩ አመራሮች ከህዝቡ ጋር ተወያይተናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በዕለቱ በሺህዎች የሚቆጠሩ በራሪ ወረቀቶችን ለህዝቡ በመበተን የአዲስ አበባ፣ የድሬዳዋ እና የአካባቢ ምርጫ ነፃ፣ተዓማኒ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ እንዳልሆነ በመግለፅ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን ባጭሩ ለማሳወቅ ችለናል፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- ከህዝቡ ያገኛችሁት ግብረ መልስ ምን ነበር?

አቶ አስራት፡- በአራቱ አባል ፓርቲዎች ያደረግነው ህዝባዊ ስብሰባም የተሳካ ነበር፡፡
እንደውም በወቅቱ ከተነሱ በርካታ ገንቢ ሐሳቦች መካከል 33ቱ የሚለው መቼ ነው ወደ አንድ የምትቀየሩት፣ እናንተ እንደዚህ መሰባሰባችሁን እንደግፋለን፤ በርቱና ጠንክራችሁ ስሩ፤ አብረናችሁ ነን የሚሉና እስካሁን የሚጠበቅባችሁን ያህል አልሰራችሁም፤ ፈርታችኋል፤ ደክማችሁብናልም የሚል ወቀሳም መጥቶብናል፤ ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ያሉን ቢሆንም ወቀሳውን አምነን ተቀብለናል፤ በዚህ ችግር የለብንም፡፡ ለወቀሳው በእኛ በኩል የተሰጠው መልስ ጠንካራ ፓርቲና አመራር ሊወጣ የሚችለው ከጠንካራ ህዝብ መሐል እንደሆነ እና ለዚህም ህዝቡ ጠንካራ መሆን እንዳለበት ጠቁመናል፡፡ ከዚህ ውጭ አብራችሁ ወደፊት ለመቀጠላችሁ ምን አሳማኝና ተጨባጭ ዋስትና ትሰጡናላችሁ? ሀገሪቱ በአሁን ወቅት ከፍተኛ ችግር ላይ ነችና ከጋዜጣዊ መግለጫ ባለፈ ምን ልትሰሩ አስባችኋል? የሚሉና በርካታ ጥያቄዎችም ተነስተዋል፡፡ ይህም ለእኛ ትልቅ ስኬታማና ውጤታማ ውይይት ነበር፡፡ ከዚህ ውጭ በወቅቱ የታዘብነው ህዝቡ ምን ያህል ብሶት ውስጥ እንዳለ አይተናል፡፡  አመራሩ ጠንክሮ ከወጣና ጥሩ አመራር ካለ ህዝቡ እንከተላለን የሚል ምላሽ ሰጥቶናል፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- አሁን ያለው ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ መቼ ነው ኃላፊነቱን የሚያስረክበው?

አቶ አስራት፡- የፊታችን ሚያዚያ 20 ቀን 2005 ዓ.ም. ነው፡፡ ያኔ አሁን ሲሰራ የነበረው እኔም ያለሁበት ጊዚያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ በወቅቱ ለሚመረጥ ቋሚ ኮሚቴ ያስረክባል፡፡ አሁን እኔም ያለሁበት ኮሚቴ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ነበር፡፡ አሁን ግን ይሄ ሰነድ ከተፈረመ በኋላ ጊዜያዊ አስተባባሪ የሚለው ኮሚቴ ቀርቶ ከየፓርቲዎቹ ሁለት ሁለት ሰዎችን ወክሎ ከዛ ውስጥ በመተዳደሪያ ደንባችን መሰረት በስድስት ወር አንዴ በሚደረግ ምርጫ በቋሚነት ዘጠኙ ተመርጠው አብይ ኮሚቴ በሚል ይተካል፤ ስራውም የተግባር ነው የሚሆነው፡፡ እዚህ ላይ ጉባዔው ከነባሮቹ ተወሰኑትን ሊወስድ ይችላል አሊያም ሙሉ በሙሉ ሊቀይርና ሊወስድም ይችላል፤ ይሄ ያኔ የሚታይ ነው፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- እራሳችሁን ከምርጫው አግልላችኋል፤ የሚያዚያውን ምርጫ እንዴት ታዘባችሁት?

አቶ አስራት፡- ይሄንን በሁለት መልኩ ነው የምናየው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ምርጫ ጣቢያዎቹ እጅግ ቀዝቅዘው ህዝቡ “ምን ተወዳዳሪ አለና ነው የምንመርጠው?” በሚል አብዛኛው ህዝብ እራሱ አለመሳተፉን ሂደቱን ከቃኙ አንዳንድ ጋዜጠኞችና ከህዝቡም ለማወቅ ችለናል፡፡ የነበረው ሂደት የመራጭነት ካርድ ይዘው የነበሩትን በግድ በየቤቱ በመሄድ ካርዱን አምጡ በማለት የማስፈራራት፣ የመቆጣትና የማዋከብ ሂደት እንደነበር የታዘብንበት ሁኔታ እንዳለና አሁንም ድረስ በህዝቡ እየተነገረ መሆኑ ምርጫ ነበረ ለማለት አያስደፍርም፡፡
ምክንያቱም ምርጫ እኮ የራሱ ደረጃ አለው፤ ህዝቡ በፍላጎቱ ሲፈልግ ይመርጣል ሳይፈልግ ይተዋል እንጂ በግድ በየቤቱ እያንኳኩ ምረጡ ማለት ህዝቡ መብቱን አያውቅም ማለትና ህዝቡን የመናቅ ያህል ይቆጠራል፡፡ ስለዚህ ምርጫው አሳፋሪና አሳዛኝ ነበረ፤ ቀልድም ነው ማለት ይቻላል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ ህዝብ ሃብት፣ ንብረት፣ ጊዜና ጉልበት በከንቱ የባከነበት ነው፡፡
ሌላው ምርጫውን የገመገምነው ከ33ቱ ፈራሚ አባል ፓርቲዎች መካከል በአመራርም የነበረው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ(ሲአን) በመርህ ደረጃ ምርጫው ነፃና ፍትሃዊ እንደማይሆን ቀድመን ብናውቅም የሲዳማ ህዝብ 5 ሚሊዮን በላይ የሆነ ብዙ ህዝብ ለምርጫ ወስኖና ቆርጦ በመነሳት ተዘጋጅቻለውና ወደ ምርጫው ግቡ ብሎ ባቀረበለት ጥያቄ መሰረት ወደ ምርጫው ሊገባ መሆኑን ባሳወቀ ጊዜ ፓርቲው የህዝቡ እንደመሆኑ መጠን እኛም ህዝቡ ለምርጫው ከተዘጋጀና ድምፁን ንቁ ሆኖ ለመጠበቅ ከበቃ ለሌሎች ወገኖቻችንም ትልቅ ትምህርትና ተሞክሮ ስለሚሆን ተስማምተን ሲአን ወደ ምርጫው ገብቶ ነበር፡፡ ሁኔታውን በጥብቅ በጋራ እየተከታተልን ሳለን ሲአንም በራሱ አባላትና በእኛም አመራሮችና አባላት ትልቅ ድጋፍ እየተደረገ ለምርጫው ቢዘጋጅም የኢህአዴግ የተለመደው አፈና፣ ግድያ፣ እስርና ስቃይ ተጠናክሮ በመቀጠሉ ምርጫው እሁድ ሊደረግ አርብ ዕለት እራሱን ከምርጫው ማግለሉን ይፋ አድርጓል፡፡
ለዚህም በርካታ ተጨባጭ ማስረጃዎች ከነ ሙሉ ሰነዶች እጃችን ላይ ገብቷል፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- አለ የሚሉትን መረጃ ማግኘት ይቻላል?

አቶ አስራት፡- አዎ፤ በተጨባጭ አለን፡፡ እንደውም እነኚህን ማየት ትችላልህ ( ከላይ የተጠቀሱትን ተፈፀሙ የተባሉ ችግሮችን ሰነድ ማየት ችለናል) የደኢህዴን/ኢህአዴግ አባላት የህዝብ ታዛቢ ሆነው ተመርጠዋል፣ የኢህአዴግ አባላት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ አስፈፃሚ ሆነው ተመድበዋል ይህም አባል የሆኑበትና የከፈሉበት ሰነድ ይኸው እጃችን ላይ ይገኛል፣ ከምርጫ ቀናት በፊት  ምልክት የተደረገባቸው የምርጫ ወረቀቶች ታድለዋል፣ አንድ ለአምስት በሚል ጥርነፋ ኢህአዴግን ለማስመረጥና እንዲመርጡ ለማድረግ ቃል በመግባት የተግባር ስራ የሚሰሩ ከነሙሉ ስም ዝርዝራቸው እና ግዴታቸው ሰነድ ከነ እጅ ፅሑፋቸው አለ፣ ሌላው ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ እንዲመርጡ ተመዝግበዋል፣ አንድ መራጭ ከአንድ በላይ የመራጭነት ካርድ እንዲወስድ ተደርጓል፣ የመራጩ የመኖሪያ ቀበሌ እና የቤት ቁጥርም ሆነ ሌላ አድራሻ የሌላቸው ተመዝግበዋል፡፡  በዚህ ሁኔታ በሀገሪቱ ላይ ምንም ዓይነት ነፃ፣ ተዓማኒና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ሊኖር አይችልም፡ገዥው ኢህአዴግም ሆነ በስልጣን ላይ ያሉት ቁንጮዎች ድፍረት ያነሳቸው በአዋጅ በሀገሪቱ ላይ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት የለም ብለው ማስነገር ነው እንጂ በተግባር በኢትጵያ የመደበለ ፓርቲ ስርዓት የለም ብዬ አፌን ሞልቼ መናገር እችላልሁ፡ስለዚህ ከላይ የጠቀስኩልህ ጥሩ ማሳያ ስለሆነ ፒቲሽን ፈራሚዎች ከአባላችን ሲአን ጋር በመሆን ያለውን እውነታ ከነሙሉ ማስረጃው አርብ ሚያዚያ 11 ቀን 2005ዓ.ም. የተሰጠውን መግለጫ ማየቱ በቂ ነው፡፡
ሌላው እጃችን ላይ ያለው ሰነድ ኢህአዴግ በድፍረት በየወረዳው ለምሳሌ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት በመንግስት ማህተም በመጠቀም መጋቢት 20 ቀን 2005 ዓ.ም. …ባለሃብቶች፣ ኩባንያዎች፣ ሪልስቴቶችና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በግድ 368 ሺህ ገንዘብ እንዲያዋጡ ደብዳቤ ፅፎላቸዋል፡፡ በደብዳቤው ማጠቃለያ ላይ እራሱ”…. ማሳወቅ ነው “ የሚል አስገዳጅ ነገር ነው የተቀመጠው፡፡
ይሄ ከዚህ በፊት በኢህአዴግና በመንግስት መካከል ልዩነት የለም፤ ሊኖር ግን ይገባል ብለን በተደጋጋሚ መጮሃችን ይታወቃል፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- ከምርጫው እራሳችሁን ማግለላችሁ ትክክል ነው ማለት ነው?

አቶ አስራት፡- አዎ፡፡ በዚህ ሁኔታ እንዴት ምርጫ ማካሄድ ይቻላል? ስለዚህ ከምርጫ መውጣታችን ተገቢ ነው ብለን እናምናለን፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- ህዝባዊ ውይይቱንስ ከአዲስ አበባ ውጭ አድርጋችኋል?

አቶ አስራት፡- ይሄ የ 33ቱ ፓርቲዎች ጥምረት የገንዘብ አቅም ችግር አለበት፡፡ አሁን የምንንቀሳቀሰው ከራሱ ከየፓርቲዎቹ በሚሰበሰብ አነስተኛ ገንዘብ ነው፡፡ በርግጥ ዕቅዱ ቢኖረንም ካለብን የገንዘብ አቅም እጥረት የተነሳ በቅርቡ በክልሎች ውይይት ማድረግ አስቸጋሪ ቢሆንም ማድረጋችን አይቀርም፡፡ ለምሳሌ ከ33ቱ አባል ፓርቲዎች መካከል የሲዳማ አርነት ንቅናቄ(ሲአን) በቅርቡ በሐዋሳ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ ታስቧል፡፡ እዚህ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ የ33ቱም ፓርቲ ተወካዮች ይገኛሉ፡፡
ይሄ ካለቀ በቅርቡ ወደ ሐዋሳ እንሄዳለን ብለን እናስባለን፡፡ በዚህም ህዝቡ እያጋጠመ ያለውን ችግርና በመጨረሻው ሰዓት ለምን ከምርጫው እንዲገለል እንደተደረገና በአጠቃላይ ሀገራዊና አካባቢያዊ ጉዳይ ላይ ሰፊ ውይይት እናደርጋለን የሚል እምነት አለን፡፡ ያኔ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የሚያካትት ሀገር አቀፍ ህዝባዊ ንቅናቄ ለመፍጠር ሰፊ ስራ መስራት ይጠበቅብናል፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- ከዚህ በኋላስ ይሄ የ33ቱ ፓርቲዎች ጥምረት ወዴት ያመራል ብለን እንጠብቅ?

አቶ አስራት፡- በርግጥ ይህን ተንብይ ብባል መገመት ያስቸግረኛል፡፡ ምክንያቱም ገና በበርካት ሀገራዊ ጥያቄዎች ዙሪያ በሰፊው መነጋገር፣ መተማመን እና መግባባት አለብን፡፡ ምክንያቱም አሁን 33ቱ ፓርቲዎች ጠንክረው መውጣታቸውን በማየት ለመከፋፈል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንዳሉ እናውቃለን፡፡ ስለዚህ የአብሮነት ስራችን ተጠናክሮ መቀጠልና ከምርጫ ጉዳይ ባለፈ በርካታ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም ላይ በግልፅ በሰፊው መወያየት ያስፈልጋል፡፡
ይህ ማለት ግን በመሐከላችን ጥርጣሬ አለ ማለት አይደለም፡፡ ስለዚህ በአጭሩ ወዴት ያመራል የሚለውን ለመመለስና ወደ ግንባርና ውህደት ለማምራት በእርግጠኝነት ለመናገር ጊዜ ስለሚያስፈልግ ወደፊት አብረን የምናየው ነው የሚሆነው፡፡ በርግጥ በተለያየ ጊዜ በምናደርጋቸው ስብሰባዎች ላይ መቼ ነው 33ቱ፣ 28ቱ መባላችን ቀርቶ በአንድ ማኀተም የምንተዳደረው የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ ይነሳል፡፡ የህዝቡም ግፊት ይሄው ነው፡፡ ይህንን እኛም የምንደግፈውና የምንቀበለው ጉዳይ ነው፡፡
ስለዚህ በጥንቃቄ ጊዜ ተወስዶ መሰራት አለበት፤ ይህም እንደሚሳካ ጥርጥር የለውም፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- አሁን ካላችሁት 33 ፖለቲካ የፓርቲዎች ውጭ ሌሎች ፓርቲዎችም መምጣት ቢፈልጉ ምንድነው ምታደርጉት? አባል መሆን ይችላሉ?

አቶ አስራት፡- ጥሩና ተገቢ ጥያቄ ነው፡፡እዚህ ላይ ግልፅ መሆን ያለበት ጉዳይ ቢኖር በምርጫ መሳተፍና ከምርጫ እራስን ማግለል ጋር በተያያዘ ማንም ዘሎ እሚገባበት ቦታ አይደለም፡፡

እኛም የራሳችን መስፈርት ይኖረናል፡፡
ምክንያቱም እኛ የሀገራችን ኢትዮጵያን ጉዳይ ከምርጫ በላይ ነው የምናየው፡፡ ሌለው በግድም ይሁን በተለይየ ምክንያት ወደ ምርጫ የገቡም ቢሆኑ ከእነሱም ጋር መነጋገርና መስራት ይቻላል፤ ችግር የለብንም፡፡
ይህ ማለት ግን ያመለከተና እገባለሁ ያለ ሁሉ አባል ሆኖ ይገባል ማለት አይደለም፤ መስፈርት ይኖረናል፡፡ ነገር ግን እስካሁን ጥያቄ ያቀረበ አካል ስለሌለ ወደ ዝርዝር መስፈርቱ መግባት አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡
በአጠቃላይ አብሮ መስራት የሚፈልግ አካል ካለ እናበረታታለን፣ እንደግፋለን፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- በመጨረሻ ከምርጫው ጋር በተያያዘ መናገር የሚፈልጉት ካለ ዕድሉን ልስጥዎት፡፡

አቶ አስራት፡- ማለት ያለብኝን ብዙ ብያለሁ፡ነገር ግን በስልጣን ላይ ያለው አካል ምርጫን ከስልጣን ጋር ብቻ ማያያዝና ማየት ትልቅ ስህተት ነው፡፡ ምክንያቱም የዴሞክራሲም ጉዳይ ነው፡፡ የዴሞክራሲ ጉዳይ ደግሞ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ፣ የእኩልነት፣ የሰላምና መረጋጋት ፣የሰብዓዊ መብትና የሀገር ህልውና ጉዳይ ነው፡፡ስለዚህ ዴሞክራሲንና የህዝብን ጥያቄ አፍኖ በጦር መሳሪያ አስፈራርቶ ሁሉንም ነገር እንደፈለገ አደርጋለሁ ማለት ለማንም ለምንም አይጠቅምም፡፡ ኢህአዴግ እየሄደበት ያለው መንገድ አምባገነናዊ ስርዓትና በጦር መሳሪያ የሚደረግ ስልጣን ኪሳራ እንጂ ጥቅም የለውም፡፡ ስለዚህ ይሄ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከሀገራችን ተወግዶ ስልጣን የህዝብና ለህዝብ መሆን አለበት፡፡ ይሄ ደግሞ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ ባለመሆኑ ሁላችንም ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ ይገባናል እላለሁ፡፡

የዜናው ምንጭ  : http://www.fnotenetsanet.com/?p=4117

 

 

↧

የኢትዮጵያ ማነቆዎች

$
0
0

ኢትዮጵያ በቀላሉ ሊቀረፉ በማይችሉ ሁለት አጣብቂኝዎች ውስጥ ገብታለች። ኢትዮጵያ በአንድነቷ፣ በጀግንነቷና በበርካታ ታሪካዊ ክስተቶችና ሁነታዎች የምትታወቅ ቢሆንም የአሁኑ ትውልድ ግን በሁለት ከባድ ፈተናወች/አጣብቂኝዎች/ ውስጥ ገብቶ አንዱን ክንፉና አንዱን እግር እንደተሰበረ አሞራ መብረርም መጓዝም አቅቶት ሲቃትት ይታያል። እነዚህ ማነቆዎች ሰብረን መውጣት ከአልቻልን ነገና ከነገ በኋላ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ በአንደበቱ የሚመሰክር ትውልድ እንደሚጠፋ ምንም ጥርጥር የለውም ከእዚህም አልፎ ኢትዮጵያ በኢትዮጵነቷ የመቀጠሏ እጣ ፈንታ አስቸጋሪ እንደሚሆን ነብይነት የሚሻ ጉዳይ አይመስለኝም።

ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ሊያሰኛት የሚችለው እምነቷ፣ ባህሏ፣ አንድነቷ በአጠቃላይ ከእነሙሉ ታሪኳ ስትኖርና ወደፊትም ስትጓዝ ብቻ ነው። ከዚህ በአለፈ ግን አዲስ ኢትዮጵያ እንጂ አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ሰንደቃላማዋን የአውለበለቡላት ያቺ ታሪካዊዋ ኢትዮጵያ አትሆንም። ዛሬ ላይ ያለነው ትውልድ ግን ይችን አገር አባቶቻችን በአስረከቡን መልክ ሳይሆን እየኖርንባት ያለነው አዲስ ገፅና አዲስ መልክ ሰጠን አገራዊ ወኔ ጠፍቶብንና ኢትዮጵያዊ ማንነታችንን አጥተን የምራቡን ባህል ተከትለን ልንወድቅ በመንገዳገድ ላይ እንገኛለን። “ተቀምጠው የሰቀሉት ቁሞ ለማዉረድ ያስቸግራል” እንደሚባለው ዛሬ ላይ ዝም ብለን ያየነው ነገር ነገ ለማስተካከልም ሆነ ለአገሩ የሚያስብ ዜጋ ለማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው የሚሆነው። ምንም እንኳ ይህ ችግር የሚያሳስባቸው እና  እንቅልፍ የሚነሳቸው በርካታ እውነተኛ የኢትዮጵያ ልጆች በተዋበ ስነ ጽህፋዊ አጻጻፍና ከመረጃ ጋር የጻፉ ቢኖሩም እኔም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ችግሩ ስለሚመለከተኝና ስላሳሰበኝ እነዚህ ለኢትዮጵያ ከባድ ማነቆዎችን እና መፍትሔዎችንም ለመጠቆም ወደድኩ።

እነዚህ ሁለት ማነቆዎች ብዬ በርዕሴ ላይ ያስቀመጥኳቸው ዘረኝነትና ግሎባላይዜሽን/Globalization/ ዓለም አቀፍ ትስስር ናቸው። እንዲሁ ከላይ ስንመለከታቸው ብዙም ፈታኝና አስቸጋሪ ላይመስሉን ይችሉ ይሆናል። ነገር ግን በጥልቀትና በስፋት ከአየናቸው በጣም አስቸጋሪና አሳሳቢ ጉዳዮች እየሆኑ ከመጡ ዘመናትን አስቆጠሩ።

1.    ግሎባላይዜሽን/Golobalization/

የነገ አገር ተረካቢ የምንለው ትውልድ በዘረኝነት የቀረውም በግሎባላይዜሽን ውስጥ ገብቶ ለኢትዮጵያዊነት የማይጨነቅ፣ የማይገደውና የማያስብ የኢትዮጵያንም ታርክ ማወቅ የማይፈልግ ትውልድ እየሆነ ከመጣ ዘመናትን አስቆጠረ። በእርግጥ ግሎባልይዜሽን በጥበብና በማስተዋል መቀበልና መተግበር ቢቻል ለአገር እድገት በር ይከፍታል እንጂ ጉዳቱ ባልጎላ ነበር ምንም እንኳ ኃያላን አገሮች የራሳቸው  የሆነ ውስጣዊ ትልዕኮ ቢኖራቸውም፤ ዳሩ ግን እኛ በትክክለኛ ዓላማው ሳይሆን በሌላ በኩል እየተጓዝን ስለሆነ ነው አስቸጋሪ እና ማነቆ ብዬ ከዘረኝነት ጎን ማስቀመጥ የፈለኩት። ኃያላን አገሮች ዓለምን እየመሩና በእነርሱ ስር ለማድረግ ይመቻቸው ዘንድ ትናትና በቅኝ ግዛት የራሳቸውን ባህልና እምነት በግድና በግፍ ለማስፋፋት እንደሞከሩት ሁሉ ዛሬ ደግሞ በዘመናዊ መልክ ግሎባላይዜሽን ብለው የእነርሱን ባህልና እምነት በውዴታ እንድንቀበለው እያደረጉን ይገኛሉ። እኛ ኢትዮጵያውያን ደግሞ የራሳችን የሚያኮራ ባህል፣ እምነትና ታሪክ ያለን እንጂ ከሌላ የምንዋስበት ምንም ምክንያት የለንም። በነገራችን ላይ የአደጉ አገሮችን ብንመለከት በእድገት ደረጃቸው ሁሉ ባህላቸውን፣ታሪካቸውንና ቋንቋቸውን ጨምረው ነው ያደጉት እንጂ የእነሱን በመተው በሌላ ባህልና ታሪክ አይደለም ያደጉት።በእርግጥ ዛሬ ዛሬ የአደጉ አገሮች በደመ ነፍስ ብቻ የሚንቀሳቀስ ትውልድ በመገንባት ውድድር ላይ ናቸው።

ዛሬ የኢትዮጵያ ወጣት ስለ ምዕራቡ ዓለም የሚያውቀውን ሩብ ያክል ስለ ኢትዮጵያ አያውቅም። የሌላ አገር ታሪክ ማወቁ ባልከፋ  ነበር ግን የራሳችንን ታሪክና ባህል መናቅና ማንቋሸሽ ከየት የተማርነው ታሪክ ነው፣ ወደየትስ እየተጓዝን ነው? የትስ ለመድረስ ነው? ባህልና ታሪክ የሌላትን አገር ለመመስረት? የትናት አኩሪ ታርኳን ረስተን ሌላ ኢትዮጵያ ለመመስረት? የመከባበረ፣የመቻቻል፣ የመረዳዳት፣ አብሮ የመብላት ባህሏን ረስተን ሌላ የማናውቀንና የምዕራባውያንን ባህል ለማሳደግ? ግሎባላይዜሽን እንዲህ ከሆነ ባህልን፣ ታሪክን፣ እምነትንና ቋንቋችንን የሚደበላልቅብን ከሆነ ባናድግ ቢቀርብን ይሻለናል። “ጎመን በጤና” ይላል ያገሬ ሰው እውነት ነው ያገኙትን በሰላም፣ በፍቅርና በጤና እየበሉ የአገርን ባህልና ታሪክ እየጠበቁ መኖር ታላቅ ጀግንነት ነው። ታሪክ ነውና አይረሳም ትናት መንግስት ሳይቀር ግብረ ሰዶምን ለማስፋፋትና ለማበረታታት የውጭ አገር ግብር ሰዶማውያንን እንዲዎያዩና እንዲመካከሩ ኢትዮጵያን ባርኮ  ሰጣቸው፡፡ በእርግጥ አይደንቅም ትውልዱ የምዕራብያውያንን ባህል ቢናፍቅ ምክንያቱም መንግስት በኢትዮጵያ ባህል ፈጽሞ የማይታሰበውን ድርጊት እንዲወያዩባት አገራችንን ከፈቀደ። ለዚህ ትውልድ መጥፋት ተጠያቂው ማነው? ምናልባት በዋናናት ተጠያቂ የምናደርገው አንድ አካል ልንል እንችላለን ነገር ግን ሁላችንም በትንሹም ቢሆን ከተጠያቂነት አናመልጥም። ምክንያቱም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፤ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ለችግሩ መባባስ አስትዋጾ እያደረግን ስለሆነ። የአገር ሃላፊነትን ለመወጣት በትንሹም ቢሆን ይህን ትውልድ ባገኘነው አጋጣሚ ኢትዮጵዊነቱን እንዳይለቅ ማስተማርና ማስረዳት እንዲሁም ዘመናዊነትን በትክክል ከባህላችን ጋር አስተሳስሮ አብሮ እንዲያስኬደው  ትውልዱን የማስረዳት ሂደት ከእያንዳንዳችን የሚጠበቅ ታላቅ ተግባር ነው።

2. ዘረኝነት

መቼም ስለ አንድነት ለኢትዮጵያ ህዝብ መናገር ለቀባሪ ማርዳት እንዳይሆንብኝ እፈራለው። ሁላችንም እንደምናውቀው አንድነት ማለት መለያየት፣ መከፋፈልና መጠቋቆም የሌለበት ህብረት፤ እንዲሁም ለአገርና ለወገን እድገትና ብልፅግና በጋራ መስራት ማለት ነው። ዘመናዊና አገር ተረካቢው ትውልድ ግን እየተጓዘ  ያለው ከዚህ ፈጽሞ ተቃራኒና በተለየ አካሔድ ነው። ዛሬ አዲሱ ትውልድ እንደ ኢትዮጵያነታችን ሳይሆን እያሰብን፣ እየሰራን ያለነው፤ በብሔር፣ በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖትና በቋንቋ ፍጹም ተለያይተን እንደ አንድ አገር ህዝብ ማሰብና መናገር ተስኖናል። ይህ አካሄድ ደግሞ በዚሁ ከቀጠለና ችግሩን ከወዲሁ መፍታትና ማስቆም ካልቻልን ለአገራችን ኢትዮጵያ እጅግ አስቸጋሪና መድኃኒት የሌለው በሽታ እንደሚሆን ዛሬ ላይ የምናያቸው ነገሮች ከበቂ በላይ ማስረጃዎች ናቸው። ለአገራችን ማነቆ ብዬ ርዕስ የሰጠሁበት ምክንያትም ይህን ጠባብ አመለካከታችንን በቀላሉ ትተን ወደ ቀደመ አንድነታችን ለመመለስ እጅግ ከፍተኛ ዋጋ የሚጠይቅ በመሆኑ ነው። ጎሳዊና አካባቢያዊ ስሜታችንን ትተን ወደ አገራዊ ስሜት ከአልተሸጋገርን፣ መለያየትን ትተን አንድነትን ከአልሰበክን፣ መጠቋቆርና መተቻቸትን ትተን መተራረምንና መረዳዳትን ባህል ከአላደረግን፣ በቋንቋ በዘርና በሃይማኖት መለያየትንና መከፋፈልን ትተን ለአገር እድገትና ብልጽግና ህብረት መፍጠር ከአልቻልን በቀላሉ የወጋን እሾህ በቀላሉ አይነቀልም። ይባስ ብሎ እያመነቀዘ አካለ ጎደሎ ሊያደርገን ይችላል እንጂ። ስለዚህ ከወዲሁ ከምንም በላይ ትኩረት በመስጠት ሃይ ልንለው የሚገባ ተግባር ነው ባይ ነኝ።

ይህ የዘረኝነት በሽታ በጣም አሳሳቢና አስከፊ መሆኑን የምንረዳው የነገ አገር ተረካቢ ትውልድ የእውቀት ባለቤት ሁኖ ይወጣበታል ተብሎ በሚታሰብበት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሳይቀር በዚህ የዘረኝነት መንፈስ መጠቃቱ ነው። ተማርዎች ብቻ ሳይሆን መምህራንም ሳይቀሩ በዚህ በሽታ መለከፋቸው ችግሩን ይበልጥ ትኩረት እድንሰጠው አመላካች ነገሮች ናቸው። በሚገርም ሁኔታ ግን የአልተማረው የህብረተሰብ ክፍል የዚህ ችግር ተጠቂ አይደለም ብሎ መናገር ይቻላል፤ እዚህ ላይ ግን ሁሉም የተማረው ክፍል የዘረኝነት መንፈስ አለበት እያልኩ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ። እንዳው ብዙ አወራህ እንዳትሉኝ እንጂ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ለዘረኝነት መንፈስ መስፋፋት ትልቅ አስትዋጾ እያደረጉ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። አንድ የከፍተኛ ት/ት ተቋም ተማሪ የሚያጠናውን የት/ት መስክ ጨርሶ በሚመረቅበት ወቅት በዘረኝነት መንፈስም አብሮ  ጎን ለጎን እንደሚመረቅ ተማሪዎች ከተመረቁ በኋላ የሚያሳያቸው እንቅስቃሴዎች ማስረጃዎች ናቸው። ስለዚህ መንግስትም ሆነ/የትኛውን መንግሥት እንዳትሉኝ እንጂ/ ሁላችንም ጉዳዩ ለአገር በጣም አደገኛ ስለሆነ በከፍተኛ ት/ት ተቋማት ላይ ልዩ  ትኩረት በመስጠት የዘረኝነት መንፈስ ሊቀንስ የሚችልበትን ሁኔታ ማየቱና አስፈላጊ የሆነ ጥናት መደረግ አለበት የሚል አቋም አለኝ።

እንዲሁም ለአገራችን ኢትዮጵያ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቀው በውጭ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዋን ከአገር ውስጥ በከፋና በባሰ ሁኔታ በዘረኝነት በሽታ በክፉ ተጎድተዋል። በዚህ በውጭው ዓለም እናተ እና እኛ እያሉ የሚያወሩ የዘረኝነትን በሽታ በወረርሽኝ መልክ የሚያስፋፉ ብዙዎች እንዳሉ በተለያየ መልክ ከማገኛቸው ሰዎች ተመልክቻለው፤ ስምን እና የሚያወራውን ቋንቋ ከሰሙ በኋላ እነሱ ከሚፈልጉት ወገን ከአልሆነ ፊታቸው የሚጠቁርና ደስቶኞች የማይሆኑም በቁጥር ጥቂቶች አይደሉም። ግን እስከ መቼ በዚህ መልኩ እንቀጥላለን? የሚለው ጥያቄ መልስ ባላገኝም የዘወትር ጥያቄዬ ነው።

እጅግ የሚገርመው ደግሞ ሃገር እመራለሁ እያለ ያለው ‘መንግሥታችን’ የብሔር እኩልነት እያለ ሲያዎራ ትንሽ አለማፈሩ ነው። በእውነት ሁሉም ብሔሮች በመንግሥት በኩል እኩል ናቸው??? እንደ እኔ ግን የብሔር እኩልነት ተብሎ  ከሚወራ “የብሔር ልዩነት ተረጋግጧል” ተብሎ ቢወራ ሥራቸውን በሚገባ ይገልጠዋል ብየ አስባለሁ። ትናት እና ከትናት በስተያ በይፋ የተፈጸመው የብሔረ አማራ ከቦታቸውና ከአገራቸው መፈናቀል ዘረኝነቱ ምን ያክል ጎልቶ  እንደወጣ ጥሩ ማሳያ ነው። እንግዲ እኛም ዘረኝነቱ ያለብን ሰዎች የመንግሥት ዋና አስፈጻሚ አካላት መሆናችንን መገንዘብ ይኖርብናል።

አንድ ያጋጠመኝን ገጠመኝ ላውራችሁ። በስደት የምኖርበት አካባቢ ከዋናው ከተማ ትንሽ ወጣ ይላል፤ ለዋናው ከተማ አዲስ ነኝ ማለት እችላለው። በትራንስፖርት ምክንያት አልፌበታለው እንጂ ብዙ አላውቀውም። አንድ ቀን ከምኖርበት ከተማ ወደ ዋናው ከተማ ለግል ጉዳይ ሄድኩኝና አውቶብስ ተራ/ buss station/ አካባቢ ሰው እየጠበኩ ቁሚያለው፤ አበሻ ማየት በዛን ስዓት ለእኔ ብርቅ ሁኖብኛል ምንም እንኳ በመልክ አበሻ የሚመስል ሰው ባይም አይኑን ወደ እኔ የሚያዞር ማንም አልነበረም። እኔም የአገሬን አውቶብስ ተራ እያሰብኩ እስካሁን እዛ ብሆን ኑሮ የስንት ሰው አይን ያርፍብኝ ነበር እያልኩ በትዝታ አገር ቤት ገብቻለው። በዚህ ሁኔታ እያለው አንድ በእድሜ ሸምገል የአሉ ሰውዬ ከርቀት አየሁኝ። አበሻ ለመሆናቸው ከቁመና እስከ መልካቸው ይናገራል።  እኔም እንደማነኛውም ሰው ዝም ብለው ያልፋሉ ብዬ ብዙም ትኩረት አልሰጠዋቸውም ነበር፤ እርሳቸው ግን ያ የናፈቀኝን የአበሻ ፈገግታ ከቅርብ እርቀት ቸሩኝ እኔም በደስታ የፈገግታውን አፃፋ ጋበዝኳቸው። እርሳቸውም ወደኔ ጠጋ አሉና የመጀመሪያውን ማንኛውም ሰው የሚጠይቀውን ጥያቄ “አበሻ ነህ” ብለው ጠየቁኝ። እኔም ኢትዮጵያዊ አክብሮት የተሞላበት ሰላምታ ለመስጠት እየተዘጋጀው በፈገግታ አዎ ብዬ መለስኩላቸው። ጥያቄያቸው አሁንም አላቆመም “ኤርትራዊ ነህ ኢትዮጵያዊ” አሉኝ እኔም ኢትዮጵያዊ በማለት በአጭር መለስኩላቸው። ሦስተኛውና እጅግ የገረመኝንና ያልጠበኩትን ጥያቄ ቀጠሉ “ምንድነህ አሉኝ” ጥያቄአቸው ግራ አጋባኝና  ጥያቄ በሚመስል አነጋገር አቤት አልኳቸው እርሳቸውም ትግሬ ነህ አማራ ወይስ ኦሮሞ አሉኝ። እጅግ በጣም ደነገጥኩኝ እኔ ከእርሳቸ ስጠብቅ የነበረው ለአገሩና ለከተማው እንግዳ መሆኔን ተረድተው ምን ልርዳህ? ኑሮ እንዴት ነው? የሚል ጥያቄ ስለነበረ የእርሳቸውን ጥያቄ በስዓቱ ለመመለስ ቃላት አጠረኝ። ከብዙ ዝምታ በኋላ “ኢትዮጵያዊ  መሆኔ በቂ አይሆንም” ብዬ ስመልስላቸው በመጀመሪያ ያሳዩኝን ፈገግታ ደግመው ሳያሳዩኝና ሰላም ዋል የሚል የስንብት ድምፅ ሳያሰሙ መንገዳቸውን ቀጠሉ እኔም እዛው ለተወሰነ ጊዜ በሃሳብ ተክዤ ለምን ይህን ጥያቄ ጠየቁኝ ብዬ እራሴን ጠየኩት መልስ ግን ማግኘት አልቻልኩም። አሁን ላይ ግን እርሳቸውንም የዘረኝነቱ መንፈስ በእጅጉ እንደጎዳቸው ተረዳው። እናተ ብትሆኑ ምን ትሏቸው ነበር?

ይህ ነው እንግዲህ የኢትዮጵያ የእድገት ደረጃ፤ ህጻን፣ ወጣት፣ ትልቅ፣ አዛውንት፣ ተማሪ፣ ሙህር ሳይቀር በዘረኝነት መንፈስ መመታት። ታዲያ ይህ ለኢትዮጵ አገራችን ከማነቆም በላይ ማነቆ አይሆንባትም ትላላችሁ? ከወዲሁ መፍትሔ ማፈላለጉ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑን ተረድተን በበሽታው የተጠቁትን ህክምና፤ ያልተጠቁትን ደግሞ  የመከላከል ስራ ለመስራት ቆርጠን መነሳት ይኖርብናል።

 

 

 

 

 

 

↧
↧

የሰንደቅ ጋዜጣ ገጽ ሶስት፣ የአዲስ ዘመን ገጽ ሶስት መንትያ

$
0
0

በዳዊት ሰለሞን 
 (ምንጭ: ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ)  http://www.fnotenetsanet.com/?p=4112)

sendek addis zemen

አመታዊ በጀት የተያዘለት፣ባለቤቶቿ ከመጋረጃው በስተጀርባ የሚዘውሯትና እራሷን የነጻ ጋዜጦች ‹‹ምድብ ›› ውስጥ የምትቀላቅለው ‹‹ሰንደቅ›› ጋዜጣ (በነገራችን ላይ ፋናም የግል መሆኗን ወገቧን ገትራ እንደምትከራከርና  አንባቢ መርሳት አይገባውም) ሰርግና ምላሽ ሆኖላታል፡፡ ሰርግና ምላሹም አንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲን በውድቀት አፋፍ እንዳገኘችው ጋዜጣዋ ማመኗን ተከትሎ የተፈጠረ ነው፡፡

ሰንደቅ የሚያዚያ ወር ቁጥር 397 ዕትም ‹‹በቃኝ›› በሚል ርዕስ የአንድነት ፓርቲ አመራር የነበሩት ኢንጅነር ዘለቀ ረዲ የሰጡትን እርስ በእርሱ የተጣረሰ ቃለ ምልልስ፣ የኢንጅነሩን ከአመራርነት መልቀቅ በድጋሚ በዜና መልክና ከአዲስ ዘመን ገጽ ሶስት ተዛምዱ ባለው መልኩ ሰንደቅም በገጽ ሶስቷ ‹‹ኪራይ ሰብሳቢነት ፣በአንድነት ፓርቲ ›› በሚል ዐቢይ ርዕስ ፓርቲው ላይ በማነጣጠር የሳምንቱን አጀንዳዋን አንድነትን አድርጋለች፡፡

ኢንጅነሩ ለምን ‹‹በቃኝ›› ማለታቸውን ሰንደቅ ዘገበች በማለት ለወቀሳ አልቸኩልም፡፡‹‹በቃህ››የተባሉት ሰው ፣ሁሉን ቀድሜ ‹‹በቃኝ›› አልኩኝ ማለታቸውን ለምናውቅ ሰዎችም ጋዜጣዋ ለኢንጅነሩ መድረክ  እንደምትሆን እንጠብቀው የነበረ ነገር እንጂ እንግዳ አይደለም፡፡

በገጽ 3 አንድነትን የገዢውን ፓርቲ ልሳን በመዋስ ‹‹በኪራይ ሰብሳቢነት›› ለመወንጀል ስማቸው ያልተጠቀሰው ‹‹የጋዜጣዋ ሪፖርተር›› ዙራዙሩን ዞረው እርባና ያለው መረጃ ሳያቀርቡ ለፓርቲው በመጨረሻው መጨረሻ አዛኝ ቅቤ አንጓች በመምሰል ‹‹ራሱን ማጽዳት አለበት››በማለት ጽሁፋቸውን ቋጭተዋል፡፡ ሰንደቅ የጋዜጠኞቿን  ሃላፊነት በምትጠቅስበት ግርጌ ‹‹ሪፖርተር ››እንዳላት ባትክድም ስያሜያቸው ‹‹ከፍተኛ ሪፖርተር››እንደሆነ ትነግረናለች፡፡ ገጽ ሶስት ላይ የወጡት ጸሀፊ ግን ‹‹የጋዜጣው ሪፖርተር ነኝ ››ማለታቸውም የሰንደቅንና የአዲስ ዘመንን ቤተሰባዊነት ቅርብ ያደርገዋል፡፡
(እረስቼው ለካ አዲስ ራዕይም ስሙ የተጻፈ ዋና አዘጋጅ የነበራት ቢሆንም ዋና አሰናጇ ግን መለስ ዜናዊ ነበሩ፡፡)

አንድነት ‹‹በሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች ላይ የሚሰነዝረው የኪራይ ሰብሳቢነት ውንጀላ ተቀባይነት የሚኖረው ፓርቲው ከኪራይ ሰብሳቢነት ፣አመለካከት ሙሉ ለሙሉ ራሱን ማጽዳት ሲችል ብቻ መሆኑ ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል፡፡ መልእክቱ ግልጽ፣ ቋንቋውም አንድና አንድ ነው፡፡

እርግጥ ነው አንድነት ገዢውን ፓርቲ በሙሰኝነት ሲከስ ቆይቷል፡፡ ኢህአዴግም ቢሆን በአንድ መድረኩ ‹‹ዋነኛ ችግሬ ኪራይ ሰብሳቢነት ነው፡፡)በማለት ተናግሯል፡፡ አሁን ሰንደቅ አንድነት ሌሎችን በሚከስበት ሚዛን ላይ ሲቀመጥ ቀልሎ ስለ መገኘቱ በሚጮህ ርዕስ ስር አገኘሁ ያለችውን መረጃ አቅርባለች፡፡

ኪራይ ሰብሳቢነትን በአንድነት ቀረበ ከተባለው ማስረጃ አንጻር የሚመዝኑ ሰዎች ‹‹ኪራይ ሰብሳቢዎችን በፓርቲው የማያገኙ በመሆናቸው ጋዜጣዋን መታዘባቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የኪራይ ሰብሳቢ ፖለቲካ ኢኮኖሚ ምን ማለት እንደሆነ እንመልከት፡፡

ለኪራይ ሰብሳቢነት አቻ ትርጉም ለመስጠት የሞከሩ ባለሞያዎች የጋራ ስምምነት ላይ በመድረስ አንድ አይነት ድምዳሜ ላይ ባይደርሱም አንድ የሚያደርጋቸውን ትርጓሜ ከመስጠት አልተቆጠቡም፡፡
Rent-Seeking When a company, organization or individual uses their resources to obtain an economic gain from others without reciprocate any benefits back to society through wealth creation.(ኪራይ ሰብሳቢነት፤ አንድ ካምፓኒ፣ድርጅት ወይም ግለሰብ የኢኮኖሚ ጥቅም ከሌሎች ለማግኘት በእጁ  የሚገኘውን ሀብት  ለማህበረሰቡ ምንም አይነት ጥቅም ሳያበረክትበት ሀብቱን ለራሱ ብቻ  ለማከማቸት መፈለግ ነው፡፡) በዚህ ትርጓሚ መነሻነት ሰንደቅ አንድነት ውስጥ ተገኘ ያለችውን ኪራይ ሰብሳቢነት ብንፈልገው ዱካውን እንኳን ማግኘት አንችልም፡፡

የፓርቲው የፋይናንስ ኮሚቴ ለፓርቲው ማጠናከሪያ የገቢ ማሰባሰቢያ እቅድ በመንደፍ በ2004 አንድ ምሽት የእራት ፕሮግራም በማዘጋጀት የትኬት ሽያጭ ያቀርባል፡፡ በዚህም መሰረት እያንዳንዱ የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ 15,000 ብር የሚያወጡ ኩፖኖችን እንዲሸጥና ገንዘቡን ገቢ እንዲያደርግ ያዛል፡፡ (ሰንደቆች የፓርቲው ጸሀፊ 24.000ብር አላስገቡም በማለት መዘገባቸው በዚህ አጋጣሚ ፍጹም ውሸት መሆኑን ከፓርቲው የፋይናንስ ኮሚቴ ማጣራት እንደሚቻል መጠቆም እወዳለሁ፡፡) ኮሚቴው በቅርቡ ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ ከኩፖን ሽያጭ ገቢ መደረግ ከነበረበት ውስጥ የተወሰነው ተሟልቶ አለመግባቱን በመጠቆም ያልተሸጠ ኩፖን በእጁ የሚገኝ አመራር ያልተሸጠውን ኩፖን ገቢ እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡ እንግዲህ ሰንደቅ ይህንን ሪፖርት በመውሰድ ‹‹አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በኪራይ ሰብሳቢነት ተጨማልቋል›› ለማለት የደፈረችው፡፡
(በነገራችን ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የፋይናንስ እንቅስቃሴውን በውጪ ኦዲተር በማስመርመር ከምርጫ ቦርድ የምስክር ወረቀት ያገኘ አንድነት ብቻ መሆኑን ሰንደቆች ያውቁ ይሆን?)

እኛ አገር ሁሉም ነገር በራስ አረዳድና በአድርባይነት ከታመነለት ወገን ፍላጎት በመነሳት ትርጉም የሚሰጠው በመሆኑ ኪራይ ሰብሳቢነት ወይም (Rent-Seeking)ሁሉንም አይነት ትርጉም በመያዝ ውዥንብር እየፈጠረ ይገኛል፡፡ በአንድ ወቅት ታዋቂው አትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገ/ስላሴ ‹‹ህንጻ በመስራት እያከራየሁ ገቢ አገኛለሁ፣እና እኔ ኪራይ ሰብሳቢ ነኝ ›› በማለት መጠየቁን ሰምቼ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ሰንደቅ ተሸጦ ይሁን ሳይሸጥ ገቢ ያልተደረገበትን ምክንያት ያልታወቀ ኩፖን በስራ አስፈጻሚዎቹ እንደተበላ በመቁጠር ‹‹በትንሹ ያልታመኑት አንድነቶች በትልቁ እንዴት ይታመናሉ፡፡›› በማለት ለመሳለቅ ትሞክራለች፡፡ ለመሆኑ በሰነድ ደረጃ የሚገኝን ኩፖን እንደ ገንዘብ በመውሰድ ድምር ወጥቶለት እንዴት ለኪራይ ሰብሳቢነት ውሏል ይባላል? እርግጥ ነው የፋይናንስ ኮሚቴው በሪፖርቱ ገንዘቡና ያልተሸጠው ኩፖን ገቢ ይደረግ ብሏል፡፡

ሰንደቅ እነዚህን እውነታዎች በተጣረሰ መልኩ የራሷንና የጌቶቿን የቃላት ፍቺ በመጠቀም‹‹ኪራይ ሰብሳቢነት በአንድነት ነግሷል ትላለች፡፡
ግጥምጥሞሹ ለአንዳንድ የዋሃን የአጋጣሚ ሊመስላቸው ቢችልም የአዲስ ዘመን ገጽ ሶስትና የሰንደቅ ገጽ ሶስት ድብቅ አላማን በማንገብ ተመሳሳይ ውጤት ላይ ለመድረስ ብዕራቸውን ከወረቀት ባገናኙ ዙምቢዎች ሀሳብ እንዲሞሉ ተደርገዋል፡፡

 

↧

ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ በብራስልስ!! በአማራ ተወላጆች ወገኖቻችን ላይ ወያኔ የሚያካሂደውን የዘር ማጥፋትና ማጥራትን ለመቃወምና ለማስቆም በኅብረት እንነሳ !!!

↧

“መሬትህን ሊቀሙ ነው የመጡት”በሚል የቤንሻንጉል ነዋሪ ተመላሽ አማራዎችን እንዲያገል በመንግስት ተላላኪዎች እየተሰበከ ነው

$
0
0

New Picture (6)ወደ ቤንሻንጉል የተመለሱት የአማራ ተወላጅ ተፈናቃዮች እጅግ በከፋ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን የመንግስት ሃይሎች የአካባቢው ነዋሪዎች አማሮቹን እንዲያገሉ በተዘዋዋሪ መንገድ እየተወተ እንደሚገኝ ፍኖተነፃነት ጋዜጣ ከአዲስ አበባ ዘገበ።
እንደ ጋዜጣው ዘገባ ከሆነ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቅለው በፍኖተሰላምና በተለያዩ አካባቢዎች ተበትነው ከቆዩ በኋላ ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው እንዲመለሱ የተደረጉት የአማራ ተወላጅ ተፈናቃዮች እስካሁን እርሻ አለመጀመራቸውን አስታውቀዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ እንዳስታወቁት ወደ ቀድሞው ቦታቸው እንደሚመለሱ ተነግሯቸው ቢመጡም፣ ስፍራው ሲደርሱ የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ለህብረተሰቡ አስቀድመው የተከራየነውን መሬት እንዳያስረክቡን በመቀስቀሳቸው ሊቀበሏቸው እንዳልፈለጉ አስረድተዋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግስት አካላት “ተመልሰው የመጡት መሬታችሁን ሊቀሟችሁ ነው እንዳታቀርቧቸው” ተብለዋል የሚሉት ተፈናቃዮቹ “እርሻችንን እንዳትነኩ ወደ መሬታችንም እንዳትደርሱ” መባላቸውን ለጋዜጣው ተናግረዋል።
“በዚሁ ምክንያት እጅግ ለከፋ ችግር እንደተጋለጡ የሚናገሩት ተፈናቃዮቹ መንግስት በአካባቢው በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈፃመውን ግፍ እንዲያስቆም ተማፅነዋል፡፡” ያለው ዘገባው አክለውም “እኛ ያለ ባለመሬቱና ያለ መንግስት ፈቃድ የሰው መሬት አንነካም፤ ይህንን የአካባቢው የመንግስት አካላት ለህብረተሰቡ ሊያስረዱልን ይገባል፡፡ ሰርተን ለመኖ ተቸግረናል” ብለዋል ሲል ዘገባውን አጠናቋል።

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live