Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

“ይታደሏል እንጅ….!” –አሰፋ ጫቦ

$
0
0
አቶ አሰፋ ጫቦ

አቶ አሰፋ ጫቦ

አሰፋ ጫቦ Dallas Texas USA

  • ታየች በዛብህና ሻምበል ሐብተ ገብርኤል ጫቦ የጋብቻቸውን ኢዮበልዩ በአል አርባ ምንጭ መድኃኔነ ዓለም ቤተክርስቲይን ሚያዚያ 27,2007 የዳግመ ትንሳዔ ዕለት አከበሩ።ግርማ ሐብተ ገብርኤል በስልክ ነገረኝ። “ታዩንና ሐብቴን እንኳን ለዚህ በቃችህ ብለህ ሳምልኝ!” አልኩት። “አሁኑኑ እሔዳለሁ !”አለኝ። ከድምጹ ቃና  ኢዮበልዩ  በአሉ  አሁንም በመከበር ያለ  አስመስለው።እኔ ባልኖርበትም ቤተክርስቲያኑ በልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው እንዲሁም በከተማዋ ኗሪ ምእመነና እነደተጣበበ ታየኝ። በቂ አትረፈዋል!
  •   የታላቅ ወንድሜን የሻምበል ሐብተገብርኤል ጫቦን  ፎቶ My Brother! MY Hero!   ብዬ  Facebook ላይ ለጥፌ ነበር። ፕሮፌሰር መስፍን ለሎችም ጎብኝዎች  ስለወንድምህ ከዚያ የተሻለ በል እንጅ አለኝ። እኔማ አንድ ቀን ስለሀብቴ መጽሐፍ እጽፋለሁ እላለሁ።ወንድሜ ስለሆነም ብቻ አይደለም። ሀብቴ አሁን አሁን “ወሰላም በምድር ስመረቱ ለስብ “ “በምድር ላይ ለሰው ዘር ሰላም ይስመር/ያብብ “ያለውን ያስታውሰኛል።“አሁን አሁን “ ያልኩት ልጅ ሆኜ ያ ሰላሙ ያናድደኝ ነበር  ነበር:: አይቆጣ፤አይናነደድ፤አይፈጥን፤  አይቾኩል:: ሁሌም ሰላም! ያው ነው!

Read Full story in PDF

The post “ይታደሏል እንጅ….!” – አሰፋ ጫቦ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

↧

ዛሬም አይመረንም

$
0
0

ይገረም አለሙ ( ግንቦት 2005)

ምርጫ 2007 ከተጠናቀቀ በኋላ የተለያዩ ነገሮች እየሰማን ነው፡፡ምርጫ ማለት በእለቱ ጠዋት 12 ሰአት ተጀምሮ ምሽት 12 ሰአት የሚጠናቀቀው ሂደት አይደለም በሚል በተለያዩ ምሁራን የተሰጠው አስተያየት እውነትም ትክክልም ነው፡፡ ከወያኔ በስተቀር የሌሎቹን ተወዳዳሪዎች ዝግጅትና ሂደት እንደታዘብነው ሙሉ ትኩረታቸው የድምጽ መሽጫ እለቱ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ ይህም በመሆኑና በቂ ቅድመ ዝግጅት ባለማድረጋቸው ወያኔ በቀላሉ ታዛቢዎቻቸውን ከጨዋታ ውጪ በማድረግ በየምርጫ ጣቢያው የተቀዋሚዎቹን ውጤት ዜረ0 ማድረግ ቻለ፡፡
clash
አራት አመት ሙሉ ምንም ሳይሰራ ወይንም ለምርጫ ተወዳዳሪነት የሚያበቃ ቅድመ ምርጫ ሥራ ሳይሰራ( በወያኔ ጫናም በራስ አቅም ማጣትም) የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔን ስለሚጠላ ይመርጠናል በሚል ብቻ ወያኔ የራሱንም የምርጫ ቦርድንም ስራ አጠናቆ በቦርዱ ስም የምርጫ የግዜ ሰሌዳ ሲያወጣ የምርጫ ሥራ የሚጀምሩ ፓርቲዎች እንዲህ አሳፋሪ ለሆነ ውጤት ይዳረጋሉ፡፡ የምርጫ አንዱ ዝግጅት ማጭበርበርን ማስቀረት የማይቻል ቢሆንም መግታት የሚያስችል መሆን አለበት፡ለዚህ የሚያበቃ ዝግጅት ከሌለ ወይንም የወያኔ የማጭበርበር ዝግጅትና ድፍረት የማይቻል መሆኑ ከታወቀ ወደ ምርጫ አይገባም፤ ቢገባም ጫናው ሲበረታ ይወጣል፡፡ የምርጫው ውጤት አስቀድሞ የታወቀ ነው እያሉ አጃቢ ሆኖ መዝለቅ ግን ምን ይሉት ስትራቴጂ እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ ሌላ ቀርቶ ይህ ካልሆነ እንዲህ መደረጉ ካልተገታ ከምርጫው እንወጣለን (ለአፋቸው እንኳን) ያሉ የሉም፡፡

በምርጫ ተወዳድሮ ስልጣን መያዝ ወይንም መጋራት ሲታሰብ፤
በአራት ዓመታት ውስጥ
1-ድርጅታዊ አቅምን ማጎልበት; ማለትም በፕሮፓጋንዳ ሳይሆን በተግባር መሬት መርገጥ፡
2-ለምርጫ ተወዳዳሪነት የሚያበቁ ተግባራትን ማከናወን፤ማለትም
ሀ-ዓላማቸውን በአጭሩና በግልጽ የሚያስረዱ ሰነዶችን ማዘጋጀት፤ማሰራጨት፡
ለ-እምነት ጽናትና ብቃት ያላቸውን ዕጩ ተወዳዳሪዎች ማዘጋጀት፤
ሐ-ታዛቢዎችን በብዛትና በጥራት ማዘጋጀት፤
3-የፖለቲካ ምህዳሩ ሁሉን በእኩል ደረጃ ማወዳደር የሚችል እንዲሆን ጉድለቱን፤አድሎአዊነቱን ወዘተ በበቂ ማስረጃ እያሳዩ አማራጭ ሀሳብ እያቀረቡ በሁሉም መንገድ መታገል፤ ሕዝቡን የዚህ ትግል ኣካል በማድረግ ማንቀሳቀስ፡፡
4-ነጻ ፍትሀዊና ተአማኒ ምርጫ ለማካሄድ የሚያበቁ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ አማራጭ ሀሳቦችን በማቅረብ ሁለንተናዊ ትግል ማካሄድ፡፡ (ምርጫ ቦርድ ነጻ ተቋም እንዲሆን ማስቻልን ዋና ስራ ያደረገ)

5-በጠመንጃ የያዘውን ሥልጣን በጠመንጃ አስጠብቆ የሚኖረው ወያኔ ለነጻ ምርጫ ፈቃደኝነቱም ዝግጁነቱም እንዳማይኖረው ስለሚታወቅ ምርጫ ሊያጨበረብርባቸው የሚችሉ ቀዳዳዎችን ሁሉ ለመድፈን ካልሆነም አስቀድሞ በተአማኒ ማስረጃ ለማጋላጥ መስራት፡፡

እነዚህና ተመሳሳይ ተግባራት በአራት ዓመታት ውስጥ ተከናውነው የመጨረሻው ምርጫ የሚካሄድበት ዓመት ላይ የተሰሩ ስራዎች ተገምግመው በሚገኘው ውጤት መሰረት በምርጫ መወዳደር ወይንም አለመወዳደር ይወሰናል፡፡ ውሳኔው መወዳደር ሆኖ ወደ ምርጫ ፉክክር ከተገባ ደግሞ የእለት ተእለቱ እንቀስቃሴ በቅጡ እየተፈተሸ የመወዳደሩ ፋይዳ እየተገመገመ ወያኔ ሥልጣን ወይም ሞት በሚለው መርሁ እስከምን ድረስ የከፋ ተግባር ሊፈጽም እንደሚችል እየተጤነ እስከ መጨረሻው መዝለቅ አለያም በማናቸውም ግዜ ከምርጫው የመውጣት ውሳኔ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡

የምርጫ 2007ን ሂደት ግን ከዚህ በተቃራኒ ነው፡፡ ተቀዋሚዎች በምርጫው ማግስት የሚሉትን ማለትም ድምጽ ተዘረፈ፤ታዛቢ ታሰረ ታፈነ፤ተወዳዳሪ ተከለከለ፤ነጻነት በሌለበት ነጻ ምርጫ ማካሄድ አይቻልም ወዘተ ከምርጫው በፊት አያውቁትም ነበር ማለት አይቻልም፡፡ ነገር ግን ከምርጫ 2002 እስከ ምርጫ 2007 በነበሩት አመታት እነዚህ ነጻ ምርጫ ለማካሄድ የማያበቁ ያሉዋቸው ጉዳዮች እንዲለወጡ ወይንም እንዲሻሻሉ ምን ሰሩ ብለን መለስ ብለን ብንቃኝ የምናገኘው ብዙም ነገር የለም፡፡ በወቅታዊ ትኩሳቶች ላይ የተሳካም ያልተሳካም ሰላማዊ ሰልፍ ሲያዘጋጁ አንድም ቀን “ለነጻ ምርጫ ነጻ ምርጫ አስፈጻሚ” ብለው አያውቁም፡፡ እንደውም ወያኔ ሌላ ሌላው የሰራው አልበቃ ብሎት ምርጫ 97ን እያሰበ በቅዠት መንፈስ የሰላማዊ ሰልፍ ቦታ በየጽ/ቤቶቻቸው ጓሮ መርጦላቸው የሚሄዱበትንም መንገድ ሲወስንላቸው በጸጋ ተቀብለው ሰልፍ እየወጡ ትልቅ የፖለቲካ ስራ እንደሰሩ ያናገሩ ነበር፡፡ እሱ ይህንን ያደረገው ምርጫን እያሰበ ሲሆን እነርሱ ከጊዜያዊ ፕሮፓጋንዳ በዘለለ ስለምርጫ አስበውና የዝግጅታቸው አንድ አካል አድረገው ነበር ብሎ ደፍር መናገር የሚቻል አይመስለኝም፡፡

በምርጫ 2002 ተቀዋሚው አንድ ወንበር ባገኘበት፤ ወያኔ ያንን ውጤት ለማስጠበቅ አይደለም አንድም ተቀዋሚ በፓርላማ ላለማየት የራሱን አውራ ፓርቲነት አውጆ መኖር ያለባቸው ታማኝ ተቀዋሚዎች ብቻ ናቸው ብሎ በይፋ ነግሮ ሌሎች እንዳይንቀሳቀሱ መንገዱን ሁሉ ዘግቶ ባለበት ምን ሰርተው ምን ጥንካሬ ፈጥረው ምን ተማምነው ወደ ምረጫ ገቡ ብለን ብንጠይቅ ቀናና ተገቢ ምላሽ የሚኖራቸው አይመስለኝም፡፡የማስተዋል ችግር ካልሆነ በስተቀር አንድነትን ባፈረሱበት ወቅት ፕ/ር መርጊያ “ለሚታዘዙንና ከእኛ ጋር ተስማምተው ለሚሰሩ ሰጥተናል” በማለት አስበውትም ይሁነን አምልጦአቸው የተናገሩት ለምርጫ 2007 ውጤት ግልጽ አመላካች ነበር፡፡

ምርጫ ከገቡ በኋላም ምርጫ ቦርድና ወያኔ አንድም ሁለትም ሆነው ለምርጫ ቅስቀሳ ቃላትን ሳይቀር ሲመርጡላቸው፤እጩዎቻቸውን አለመዘግብ ሲሏቸው፤ ተወዳዳሪ ፓርቲዎችን አሸባሪ የውጪ ተላላኪ ወዘተ እያሉ ፕሮፓጋንዳ ሲሰሩባቸውና አባሎቻቸውን ሲያስሩ ወዘተ የሚሆነውን እየተቀበሉ አድርጉ የተባሉትን እያደረጉ(ለምሳሌ እንዲህ ብላችሁ
እንዳትቀሰቅሱ፤በክርክር መድረክ ላይ እንዲህ አይነት ቃላትን አንዳትጠቀሙ ወዘተ) እስከ መጨረሻ የመቀጠላቸው ዓላማ ግልጽ አይደለም፡፡

በምርጫው እስከ መጨረሻው በመቆየታችን ወያኔን አጋልጠናል የሚል ቃል ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች እየሰማን ነው፡፡ በጣም የሚገርም ነው፡፡ ለመሆኑ ወያኔ ከምርጫ 97 ያለፈና ከምርጫ 2002 የቀረ ምን የተደበቀ ማንነት ነበረው፡፡በምርጫ 2007 አስቀድሞ የማይታወቅ ከዚህ በፊትም ያልሰራው ምን አዲስ ነገር አደረገ ፣ ምን አዲስ ባሕርይ አሳየ፡፡ ፖለቲከኞቻችን ራሳቸውን አጋልጠው ካልሆነ በስተቀር ወያኔን ያጋለጡበት አንድም ነገር የለም፡፡

ባለፉት 24 ዓመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ ያላወቀው አንድም የወያኔ ማንነትና ምንንት የለም፡፡ በምርጫ ተወዳድረው ያሸነፉትን የሚያስር፤ስለ ሰላም የሚዘምሩትን ጦረኛ የሚል፤ስለ ሀገር አንድነት ነጻነትና ሉዐላዊነት የሚታገሉትን በሀገር ክህደት የሚከስ፤ስለ ሰው ልጅ እኩልነት፣ ስለ አንድ ሀገር ልጅነት ስለ አብሮነት የሚያስተምሩትን በዘር ማጥፋት ወንጀል የሚከስ እጃቸው ከብእርና ከኪቦርድ ውጪ ነክቶ የማያውቅ አዳዲስ ሀሳብ አፍላቂዎችን አሸባሪ ብሎ የሚከስ ወዘተ ወያኔ ምን የተደበቀ ማንነት ኖሮት ነው በምርጫው እስከ መጨረሻው በመዝለቃችን አጋለጥነው የሚባለው፡፡

እንዲህ አይነቱን ራስን ለማጽናኛና ወቅታዊውን መነጋገሪያ ጉዳይ ለማድበስበሻ የሚቀርቡ ረብ የለሽ ነገሮችን ተወት አድርገን እውነቱን ለመናገርም፡ የሚነገሩና የሚጻፉ እውነቶችን ለማዳመጥም ወኔ፣ድፍረት ቅንነት ይኑረን፡፡ትግላችንን ውጤት አልባ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ በእውነት ስለ እውነት ለመነጋገር መድፈር አለመቻላችን ነው፡፡ ስራችን የታይታ፣ጽሁፍ ንግግራችን የፕሮፓጋንዳ፤አስተሳሰባችን ከራስ በላይ ነፋስ ጉዞአችን በጥላቻ የተተበተበ ፖለቲካችን የሴራ ሆኖ በድል አልባ ትግል ለወያኔ አገዛዝ በየአምስት አመቱ ህጋዊነትን እያላበስን እንኖራለን፡፡ እስቲ አሁን አንኩዋን ይቆጨን፤ከመማረር አልፈን ለማምረር እንሞክር፡፡ እናም ሰበብ መደርደሩ ምክንያት ማብዛቱ ይቆየንና 24 ዓመት ሙሉ በተደረገው ትግል ለውጥ ማምጣት ያልተቻለው ለምንድን ነው ብለን መነጋገር እንጀምር፡፡ የነገ ጉዞ እቅድ ዝግጅታችን ከዚህ ውጤት ይመንጭ፡፡

The post ዛሬም አይመረንም appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

“ሙስሊሙን ህብረተሰብ መናቅ ከባድ ዋጋን ያስከፍላል!”–ድምጻችን ይሰማ!

$
0
0

የተፈረደው እኛው ላይ ነው!
ሙስሊሙን ህብረተሰብ መናቅ ከባድ ዋጋን ያስከፍላል!
አርብ ግንቦት 28/2007

ሶስት መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎችን አንስተን ‹‹ድምጻችን ይሰማ!›› ማለት ከጀመርን 175 ሳምንታት አለፉ። እነዚህ ጥያቄዎች እንኳንስ ግድያ፣ እስራት፣ ማሰቃየት፣ ማንገላታት፣ ስደት፣ ሃብት ዘረፋ፣ ወሲባዊ ትንኮሳ፣ ሃይማኖትን ማራከስ፣ የእምነት እሴቶቻችንን ማብጠልጠል፣ በአደባባይ ስምን ማጥፋት አና ሌሎች በደሎችንም ሊያስከትሉ ይቅርና መጀመሪያውኑ ሳይጠየቁ መከበር የነበረባቸው ናቸው። ሆኖም ሙስሊሙ ህብረተሰብ እንደ ቀደምት አባቶቹ ዛሬም ቢሆን በሃገሩ ላይ እንደ ዜጋ ሳይቆጠር እጅግ ያነሱና አሻሚ ያልሆኑ፣ቢከበሩ ማንንም የማይጎዱ ጥያቄዎችን በማንሳቱ ብቻ ላለፉት 3 ዓመታት በጅምላ በተለያየ ደረጃ የመከራ ገፈት እየቀመሰ ይገኛል።
Muslim in ethiopia
በመንግስታት ደረጃ እንኳን ሊታሰቡና ሊጠበቁ ያልቻሉ የስነ-ስርአት መርሃ-ግብሮችን ለሃገር ሰላምና ለህብረተሰብ ደህንነት ባሰበና ባከበረ መልኩ ስንተገብር ቆይተናል። ይህንን ሁሉ ስናደርግ አማራጭ በማጣት፣ አልያም የመንግስትን እርምጃ በመፍራት ሳይሆን ለአገራችን ካለን ጥልቅ ፍቅርና
የሰላምን ዋጋ ካለፈው ታሪካችን እጥብቀን በመረዳታችን ብቻ ነበር፡፡

ባለፉት ቀናት በወንድም ዓሊ መኪ እና በወንድም ዓብዱልዓዚዝ ጀማል ላይ የተላለፈው የፖለቲካ ውሳኔ በመላው ሙስሊም ህብረተሰብ ላይ የተላለፈ ቅጣት ነው። ሰደቃ ማዘጋጀት እና ‹‹ንጹሃን እስረኖች ይፈቱ›› ማለት 15 ዓመታት የሚያስፈርድ ወንጀል ከሆነ በእርግጥም የተፈረደው በእኛው ላይ ነው… በፍትህ ፈላጊዎች ሁሉ ላይ! የ‹‹ድምጻችን ይሰማ!›› እንቅስቃሴ የግለሰብ እና የቡድን ጥያቄ ሳይሆን የመላው ሙስሊም ህብረተሰብ እና የፍትህ ወዳዶች በሙሉ ጥያቄ ነው። በሃሰት ክስ ወንድሞቻችን ላይ የተፈረደው የፖለቲካ ፍርድ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ የተወረወረ የንቀት መልእክት ነው። ሕዝብን መናቅ እና ህዝብን ማስቆጣት ደግሞ መጨረሻው ምን እንደሆነ ከታሪክም ባለፈ መንግስት የተቀመጠበትን የስልጣን ወንበር ማየት ብቻውን በቂ ምስክርነት ነው።በመሆኑም በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገራት የሚኖሩ ሰላም ወዳዶችና ፍትህ ፈላጊዎች በሙሉ ይህንን ህዝብን የመናቅ ተግባር አጥብቀው ሊያወግዙት እና ሊታገሉት ይገባል። ሁላችንም ‹‹የተፈረደው እኛው ላይ ነው! የተናቅነው እኛው ነን! ሕዝብን መናቅ ደግሞ ዋጋን ያስከፍላል!›› ልንል ይገባል!

የፖለቲካ ፍርድ አንቀበልም!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

The post “ሙስሊሙን ህብረተሰብ መናቅ ከባድ ዋጋን ያስከፍላል!” – ድምጻችን ይሰማ! appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

በዋሽንግተን ዲሲ የሚደረገው 32ኛው የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ዋና ዋና ዝግጅቶች ይፋ ሆኑ

$
0
0

ከፊታችን ጁን 28 እስከ ጁላይ 4 ድረስ በዋሽንግተን ዲሲ የሚደረገው 32ኛው የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ዝግጅት ላይ ከሚቀርቡ ዋና ዋና ዝግጅቶች መካከል የተወሰኑትን ፌደሬሽኑ ለዘ-ሐበሻ ልኳል:: ወደዚያው ጉዞ ለሚያደርጉ ወገኖች ይጠቅማልና በራሪ ወረቀቶቹን ተመልከቱ::
Opening Day

Beharawi Theater

Teddy and Gossaye

Golf Final

Ethiopian Day Final flyer

Jacky Final

The post በዋሽንግተን ዲሲ የሚደረገው 32ኛው የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ዋና ዋና ዝግጅቶች ይፋ ሆኑ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ለዚህ ሕዝብ መሰ-ዋት ይገባል – (ሔኖክ የሺጥላ)

$
0
0

እማዬ ለዚህ ሕዝብ መሰ-ዋት አይገባውም ትለኝ ነበር ! ( ያቺ የኔ እማዬ ካረፈች ቆየች ፣ ቀብሯ ደብረ ሊባኖስ ገዳም እንደነበር ዜና ዕረፍቷን ሲያረዱኝ ነግረውኛል ፣ አዎ ያቺ እማዬ ፣ በአይበሉባዋ ቂጣ ጠፍጥፋ ፣ በቅቤ እና በበርበሬ ቀብታ ትመግበኝ የነበረችው እማዬ ፣ ያቺ በፋሲካ እኩለ ሌሊት ፌጦ በእንጀራ አረስርሳ የጠዋቱ ዶሮ እንደ አባይ ግድብ በቦንድ እንጂ በዶሮነት አልወርድም እንዳይለኝ ወይም በፋሲካ ጾምና በሰፈራችን አቧራ ሉዓላዊ እና አንጀታዊ ቅባቱን ነጥፎ የከረመው ሆዴ ፣ ከዱለት ጋ በሚያደርገው ግብግብ ተረቶ በሸርተቴ እና በምግብ ፍንቀላ ዕለተ ፋሲካውን እንዳያሳልፍ ብእር ባልያዙ ፣ በፍቅር በተያዙ እጆቿ ትመግበኝ የነበረችው እማዬማ ከሞተች ሁለት ዓመት አለፋት ፣ የኢትዮጵያን ትንሣዔ እንደተመኘች !! አይ እማዬ ስላንቺ ሳስብ እንዴት ልቤን ሃዘን እንደሚያከው ፣ እንዴት ሁሌም በለቅሶና በእልህ መሃል እንደምናጥ ባየሽ !
ታዲያ አንዳንዴ ይገርመኛል ፣ እነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ይሄን ሕዝብ ተነስ ሲሉ ! አንዳንዴ ግራ ይገባኛል እነ ሊቀ-ሊቃውንት ( ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ) ለዚህ ሕዝብ ሲሉ መስዋት እንደሆኑ ሳስብ ፣ አንዳንዴ እጅግ በጣም ይገርመኛል እነ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህንም እነ ሌንጮ ለታም ሁለቱም በአንዲት ኢትዮጵያ በተባለች ሀገር ላይ መፈጠራቸውን ሳስብ ። እንደው ረጋ ብላችሁ ካሰባችሁት እኮ ፣ ይሄ ሕዝብ ተራበ ፣ ተጠማ ፣ ተቸገረ ብሎ መጮህ እብደት አይመስላችሁም በእማዬ ሞት ?! አንዳንዴ የሰማያዊ ፓርቲ ልፋት ፣ የእስክንድር መከራ ፣ አንዷለም ላይ የሚደርሰው ግፍ ” ዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ፣ ወዘተ ወዘተርፈ ፣ ይሄ ሁሉ መከራን እና ስቃይን የሚቀበሉት ፣ ለምን ሲባል ይሆን ” ብዬ ራሴን እጠይቀዋለሁ ።
nega berehanu
ድሮ ድሮ ሰርግ ላይ ይዘፈን የነበረ ዘፈን ( እርግጠኛ አይደለሁም አሁንም ድረስ ይዘፈን ከሆነ ) የዚህን ሕዝብ ሁኔታ ( ስነ ልቦናዊ ቁምጥና እና አቀማመጥ ለማለት ነው ) የሚያሳይ ይመስለኛል ። እየበሉ እየጠጡ ዝም ! አዎ እያሳሰሩ ፣ እያስገደሉ ዝም ፣ ከተባለ የዚህ ሕዝብ ሁነኛ መገለጫ ነው !

እንደው በማዬ ሞት ለዚህ ሕዝብ መሰ-ዋ ይገባል ? ይሄ ሕዝብ እኮ አይደለም በ- አደባባይ ፣ በፌስ ቡክ ላይ የተጻፈ ፣ በልቡ የሚያምንበትን እውነተኛ ሃሳብ ፣ በኮምፒዩተር ስር ፣ ከቤቱ ቁጭ ብሎ ፣ ጋቢ ለብሶ ፣ ቡና እየጠጣ ፣ ቆሎ እየቆረጠመ ላይክ ( like ) የሚለውን ዶቃ መጫን የሚፈራ ሕዝብ ነው ፣ ” ፈርቼ ነው ጽሁፍህን ላይክ ያላደረኩት በርታ !”የሚል መልክት በሚስጥር ሳጥን የሚልክ ሕዝብ እኮ ነው ። በእማዬ ሞት አፉን ሞልቶ ” በርታ !” ሲል ምንም አይቀፈውም ! ። እባክህ አን-ፍሬንድ ( ኢ-ጏደኛ ) አድርገኝ ተሳስቼ ነው ጏደኛ ያረኩህ ፣ እኔ የልጆች አባት ነኝ ብሎ አፉን ሞልቶ የሚያወራ ሕዝብ እኮ ነው ። የልጆች እበት ማለቱ ይሆን አላለሁ ! ( ሳቁ እንጂ !)። ይሄ ሕዝብ እኮ የዶሮ ዘንቢል የሚመስል ቤት ውስጥ እየኖረ ፣ ፒያሳ ከዘመኑ ሰዎች ወርቅ ቤቶች ጋ እንድ ግድግዳ ተጋርቶ እያደረ ፣ ራበኝ የሚል ሕዝብ እኮ ነው ፣ እሱ ያመጣውን እሱ እስኪመልሰው ምን ይደረጋል ብሎ የሚኖር ሕዝብ እኮ ነው ። እንዴ! ይሄ ሕዝብ እኮ አማሪካን እየኖረ በኢትዮጵያ መንግስት ሕግ የሚተዳደር ነው ፣ ለሚያምንበት ነገር ሰልፍ ለመውጣት መፈክር ሳይሆን ጥቁር መነጽር ለመግዛት ከሰልፉ ቀደም ብሎ ሞል ( የገባያ አዳራሽ ) የሚሄድ ሕዝብ እኮ ነው ፣ ይሄ ሕዝብ እኮ መለስ ሲሞት ያለቀሰ ሕዝብ ነው (ገንዘብ ተከፍሎት ፣ ገለመኔ ፣ ገለመኔ ፣ ምንም ይሁን ምክንያቱ !) ፣ ይሄ ሕዝብ እኮ ከፌዴራል ፖሊስ ዱላ ለማምለጥ ፣ በኢትዮጵያ ከነገሰው ቸነፈር ለመሸሽ ፣ ወደ ቦንብ ቀጠናዋ የመን የሚተም ነው ፣ በእርግጠኝነት ኢትዮጵያን ነቅለህ አሜሪካ ላይ ብትተክልለት ይሄ ሕዝብ ከአማሪካም ይሸሻል ። ሽሽቱ ከማንነቱ ይሁን ፣ ከፍርሃቱ ምንም አይገባኝም ። ታዲያ በእማዬ ሞት ይሄ ሕዝብ አሁን መስዋትነት ይገባዋል ።

እንዴ! ይሄ ሕዝብ እኮ መብቱን በአደባባይ በሳቅ እና በስላቅ ሲቀሙት ፣ ቦርሳውን እንደጣለ ሰው መሬት መሬት እያየ እኮ ነው ወደ ቤቱ የገባው ! ይሄ ሕዝብ እኮ ዘንድሮን ለማምለጥ ስለ ትናንትና የሚያወራ ነው ( አኖሌ አንዱ ምሳሌ ነው !)። ሌላ ብዙ ምሳሌዎች መጥቀስ እንችላለን ።

ይሄ ሕዝብ እኮ ከራሱ በላይ ፍርሃቱን የሚያምን ነው ። እነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ” የምርጫ ካርድህን ቀደህ ጣል !” ሲሉት ደሞ ለመቅደድ ! ብሎ ራሱን በአደባባይ ቀዶ የጣለ ሕዝብ እኮ ነው ! ለዚህ ሕዝብ በትግል ፣ በነጻነት እና በሰይጣን መሃከል ያለው ልዩነት ፣ ሰይጣን ከገነት ሲባረር ነጻነት ግን ከኢትዮጵያ መባሩሩ ነው እንጂ ሁሉም ለሱ አንድ ነው ! ወገኖቼ ይሄ ሕዝብ እኮ ሽምብራ ዱቤ በቆርቂ አሰፍሮ ገዝቶ እየበላ፣ አድገሃል ሲሉት ፣ የጠዋት ጥላውን የሚያይ አይነት ቀበሮ ነው ። ከትግስት እና ፍርሃት ዛይት ቢጨመቅ ፣ ምናልባት ኢትዮጵያ ባለም አንደኛ የቅባት እህል አምራች ትሆን ነበር ። 90 ማንምን ሚሊዮን ቅባታም ! ይገርማል ወፍ እንኳ ሲርባት ትናከሳለች ! ውሃው የደረቀበት ወንዝ እኮ ፣ ቀየሜታውን በመገልማት ይገልጻል ፣ አረ ሬሳ እንኳ ይሸታል ! እንዴ ! መሚ ( የሬሳ ማድረቂያ ) ተቀብተን ነው እንዴ ቁመን የምንሄደው ?
ገንዳ ላይ ከውሻ ጋ ስጋ ተጋፍቶ የሚበላ ፣ ደሞ በዛ ላይ ፈሪሃ እግዚያብሄር ያለኝ ምናምን ይልሃል። እንዴት አይነት የምነት ሰው ነው ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሆነውን እያየ ዛሬም ስለ ” ግራህን ሲመቱ ቀኝህን ስጣቸው የሚሰብከው ?” ምን አይነት እውነት ነው “። የንጹሃን ሞትን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ውጭ ( ያም ለስርዓቱ የሚስማማ ጥቅስ ) ፣ ሌላ ሊገልጥበት የሚችልበት ስሜት በሰብአዊ ማንነቱ ላይ አምላክ ያልፈጠረበት ቅዱስ አውሬ ማለት ይሄ “ሕዝብ” ነው!

ለዚህ ሕዝብ እንኳን ሕይወቴን እንቅልፌን አልሰዋም ነበር ያለው እንዳለ ጌታ ! ምርጥ ጸሐፊ !

አይ እማዬ ” ልጄ አትቃጠል ይሄ ሕዝብ በልጅነትህ የነገርኩህ ሕዝብ አይደለም እኔም ተሳስቼ አሳስቼህ ነው !” ነው ያልሽኝ አንድ ቀን ! አይ እማዬ !

The post ለዚህ ሕዝብ መሰ-ዋት ይገባል – (ሔኖክ የሺጥላ) appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

በደራሸ ወረዳ 15 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታሰሩ (ዝርዝራቸውን ይዘናል)

$
0
0

Zehabesha News
(ነገረ ኢትዮጵያ) በደቡብ ክልል ደራሸ ወረዳ አርጎባጠና ቀበሌ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የሆኑት አቶ ከተማ ካሳን ጨምሮ በርካታ ወጣቶች መታሰራቸውን የወረዳው አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን እያደነ እያሰረ መሆኑን የገለጹት አስተባባሪዎቹ ከ27 በላይ ወጣቶች የደረሱበት እንዳልታወቀ ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ግንቦት 29/2007 ዓ.ም በደራሸ ወረዳ አርጎባጠና ቀበሌ በፖሊስ ተይዘው በደራሸ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ከሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. አቶ ከተማ ካሳ (ዕጩ ተወዳዳሪ)
2. ወጣት ሙሉጌታ ሙንጣዮ
3. ወጣት ይበልጣል አቡሽ
4. ወጣት ኢሳሞ ሽብሩ
5. ወጣት ጨንቄ ሻንቆ
6. ተማሪ ገብሬ ኩሴ
7. ተማሪ ደረቡ ካሳ
8. ወጣት ደግነት ደነቀ
9. ወጣት የኋላሸት
10. ወጣት ሙሉጌታ ጢኖ
11. ወጣት አርቢኖ ታየ
12. ወጣት ታሪካ ጭንጌ
13. ወጣት ጥጋቢ ጭልጌ
14. አቶ ጭንቃዮ ካሳሁን
15. አቶ ሙሉቃ በርበሶ ናቸው
በደራሸ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ከሚገኙት በተጨማሪ በሌሎች የወረዳው አካባቢዎችም በርካታ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እየታደኑ እየታሰሩ እንደሚገኙ አስተባባሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

The post በደራሸ ወረዳ 15 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታሰሩ (ዝርዝራቸውን ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

አባቱን እንደናፈቀ ሳያገኘው ያለፈው ሰማዕት (ዳንኤል ሐዱሽ) “በዐይኔ አይቼ በጆሮዬም ሰምቼ ከሥፍራው በመገኘት ጻፍኩላችሁ”

$
0
0

ዘመድኩን በቀለ

ቅድስቲቱ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ከተማ ፣ ጥንታዊቷ የታላቋ ሐገር ኢትዮጵያችን የቀድሞ ዘመን ዋና መናገሻ ከተማ ፣ የታቦተ ጽዮን የዘለዓለም ማረፊያ ፣ የስልጣኔአችን ምንጭ ፣ የሥነ ዜማ ፣ የሥነ ፊደል ፣ የሥነ ጥበብ ፣ የሥነ ሕንፃ መገኛ ፣ የሊቃውንተ ቤተክርስቲያን መፍለቂያ ዋነኛዋ ምንጭ በዘመነ ኦሪትም ኋላም በዘመነ ሐዲስ የአምልኮተ እግዚአብሔር መፈጸሚያ ማዕከል ወደ ሆነችው አክሱም ጽዮን ከተማ በትናንትናው ዕለት በሰላም መግባቴን ፣ በዚያም እንደደረስኩ እኔ ባልጠበኩት ሆኔታ የከተማዋ ከንቲባ አቶ ካህሳይ እና አማካሪያቸው አቶ ሐጎስ አውሮፕላን ጣቢያ ድረስ በመምጣት ተቀብለውኝ ፣ የማረፊያ ሆቴልንና የምግብ አገልግሎትም ጭምር እንዲሰጠኝ አድርገውልኝ እንደነበር ነግሬያችሁ ነበር ለዛሬ ቀጠሮ ይዘን የተለያየነው ።
የዛሬ ውሎዬን ደግሞ እነሆ ብያለሁ ።

hadush

hadush daniel
እንደ እኔ ሐሳብ ዛሬ ከአክሱም ከተማ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደ ምትገኘው ኢንቲጮ ከተማ በትራንስፖርት በመሄድ ከዚያም ጾረና ግንባር ወደሚገኘው ሰማዕት ቤትም ከዚያው ከኢንቲጮ ከተማ ትራንስፖርት ይዤ ለመሄድ ነበር እቅዴ ። እኔ እንዳሰብኩት መች ሆነና ብላችሁ እኔ ያላሰብኩት ሆነ እንጂ ።

የአክሱሙ ሲደንቀኝ የኢንቲጮው ከንቲባ አቶ ሰሎሞን በጠዋት መኪና እንደሚልኩልኝ ነግረውኝ ስለነበር በቃላቸው መሰረት ሾፌር ከነ መኪናው በጠዋት ልከውልኝ ረጅም ቀናት ይፈጅብኝ የነበረውን ጉዞዬን በአንድ ቀን እንዳጠናቅቅ ረድተውኛልና እባካችሁ ጓደኞቼ በሰማዕታቱ ስም አመስግኑልኝ ።

አሁን ሹፌሬ ክብሮም ቶዮታ ፒካፕ መኪናውን ይዞ ከአክሱም ወደ ምስራቅ አቅጣጫ በሚወስደው መንገድ ወደ ኢንቲጮ ከተማ ይዞኝ እየተጓዘ ነው ። በመንገዳችን ላይም ኢትዮጵያ ሃገራችን ነጻ ሆና እንድትኖር እነሱ አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰው የህይወት ዋጋ ከፍለው ነፃነት አግኝተን እንድንኖር ያደረጉበትን የአድዋን የጦርነት ሥፍራና እኒያን ሰማይ ጠቀስ የአደዋ ተራሮች እያየሁ ሥለ ቀደሙት ሰማዕታት እያሰብኩ በእኔ ዘመን ደግሞ አንገታቸውን ከነ ማዕተባቸው በመስጠት ለኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ እምነታቸው ያላቸውን ታማኝነት ወደገለፁት ብርቅዬ የዘመኑ ሰማዕታት ወንድሞቻችን ወላጆች ቤት ጉዞዬን ቀጥያለሁ ።

በኢንቲጮ ከተማ መግቢያ ላይ ቆመው ይጠብቁኝ የነበሩትን የከቲማዋን ከንቲባ ክቡር አቶ ሰሎሞንን በመያዝ ወደ ሰማዕቱ ዳንኤል ሐዱሽ ቤት አመራን ።
በቤቷ ውስጥ ቀድሞ እኔ እንደምመጣ ታላቅ ወንድሙ ያውቅ ነበርና ጥቂት እንግዶችም ተገኝተው ነበር ። የእመቤታችን ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ፣ የአቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪና የወረዳዋ ሰባኬ ወንጌልም በቦታው ነበሩ ።

የሰማዕቱ እናት ወሮ ዛፉ ገብረየሱስ ሐጎስም በሚያሳዝን ሁኔታ ከሁለት እናቶች መሐል ኩርምት ብለው ተቀምጠዋል ። ጥቂት አረፍ እንዳልን እናት ማልቀስ በመጀመራቸው ታላቅ ልጃቸው አቶ ጌታቸውም ፣ እንግዶቹም መገሰፅ መጀመራቸው እኔ ጥቂት ለመናገር በር ስለከፈተልኝ የሰማዕትነትን ጥቅም ፣ ልጃቸው ከቀደሙት ሰማዕታት ከነ ቅዱስ እስጢፋኖስ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስና ፣ ቅዱስ ቂርቆስ ጋር ያለውን ክብር በመጠኑ በመግለጽ ከእንግዲህ ማልቀስስ ለእኛ ነው እንጂ ፣ በምን እንደምንሞት ለማናውቀው ምስኪኖች ፤ በማለት ጥቂት ካጽናናሁ በኋላ ስለ ሰማዕቱ ዳንኤል ሐዱሽ እንዲነግሩኝ አግባባሁዋቸው ። እናት አማርኛ መስማት እንጂ ብዙም መናገር ባለመቻላቸው ልጃቸው ጌታቸው ሐዱሽ ስለ ሰማዕቱ ዳንኤል የነገረኝን እነሆ እናንተም ስሙት ብዬ በእንዲህ አይነት መልኩ አቅርቤላችኋለሁ እና ተከታተሉት ።

ጥቅምት 7 1982 ዓም ከምሽቱ ሦስት ሰአት ሲሆን የዛሬው ሰማዕት ዳንኤል ሐዱሽ አስመራ ከተማ እዳጋ አርቢ በተባለ ስፍራ ነው የተወለደው ። በ40ኛው ቀኑ ህዳር 12 ቀን በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስርዓት መሠረት እዚያው አስመራ ከተማ እንዳ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ስርዓተ ጥምቀትን በመፈጸም የክርስትና ስሙም ተስፋ ሚካኤል ተባለ ።

ይህ ኦርቶዶክሳዊ ህጻን ብዙም ሳይቆይ የመንግሥት ለወጥ በኤርትራ በመከሰቱ እንዳሊቁ በመባል ከሚታወቁ አባት ዘንድ የጀመረውን የቄስ ትምህርት በማቋረጥ በ1985 ዓም ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ይውጡ ሲባል ከቤተሰቦቹ ጋር ወደ ኢንትጮ ተመለሰ ።

የዳንኤል አባት ግን እንዴት በእድሜዬ ሁሉ የለፋሁበትን ሃብትና ንብረት እንዲሁ ከሜዳ ላይ በትኜው እቀራለሁ በማለት ተመልሰው ብቻቸውን ወደ አስመራ ያቀናሉ ። በዚያም በንብረታቸው ላይ ይገባኛል የሚል አካል ተነስቶባቸው ስለነበር በአስመራ ፍርድቤት እንደዋዛ የጀመሩት ክርክር መቋጫ በማጣቱ ከአስመራ ሳይወጡ የኢትዮ— ኤርትራው ጦርነት በመጀመሩ ይባስ ብለው ከቤተሰባቸው ተቆራርጠው ቀሩ ።

ዳንኤል ግን ምንም አባቱ ከአጠገቡ ባይኖሩም ከ1ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል በዚሁ ባደገባት ኢንቲጮ በእናቱ አጋዥነት ተምሮ ባመጣው ከፍተኛ ነጥብ ወደ ጅማ ዩኒቨርስቲ በማምራት 4 ዓመት ሙሉ በትጋት ትምህርቱን በመከታተል በ2006 ዓም በኮምፒዩተር ሳይንስ ተመርቆ ትምህርቱን አጠናቅቋል ።

ዳንኤል ተመርቆ ሥራ ያለማግኘቱ ቢያስከፋውም እሱ ግን እንዲሁ ዝም ብሎም አልተቀመጠም ። መሆኒ ከተማ የምትገኘው እህቱ ዘንድም በመሄድ የእህቱ ባል እንዲያው ከፍ ወዳለ ሥራ እስክትሸጋገር ፎቶ ቤትም ቢሆን ልክፈትልህ ብሎትም እንደነበር ወንድሙ ጌታቸው ይናገራል ።

በመሃል ላይ ጆርጅ ከተባለ ስትሬት A ያመጣ ጎበዝ ተማሪ ጓደኛው ጋር ጠበቅ ያለ ጓደኝነት ከመመስረታቸውም በላይ መቐለ ላይ በማኅበር ተደራጅተው ሥራ ሊጀምሩ እንደሆነ እና ለዚህም እያንዳንዳቸው ከ10 ሺህ እስከ 12 ሺህ ብር እንደሚያስፈልጋቸው በመወሰኑ ለእርሱም ሠርቶ የሚከፍለው ብር እንዲያበድረው ታላቅ ወንድሙን ጌታቸውን ያግባባውና ያሳምነዋል ።

ለመጀመሪያ ጊዜ 2ሺህ ብር ይቀበለውና ወደ መቐለ ያመራል ። መቐለ እንደገባም ቀሪውን 10ሺ ብር ይልክለታል ። በቃ እፎይ ሥራ ጀመረ ብሎ ቤተሰቡም ተረጋግቶ ሳለ በመሃል ዳንኤል ሁመራ ነው ያለሁት ሥራው ሰፋ እያለ ስለመጣ ተጨማሪ 5 ሺህ ብር ያስፈልገኛል ብሎ ወንድሙን ይጠይቀውና ብሩን ወንድሙ ይልክለታል ።

በመሃል የዳንኤል ስልክ ዝም ጭጭ ይላል ። 2 ሳምንት ሙሉ በኔትወርክም እየተሳበበ ትንሽ ጊዜ ከቆዩ በኋላ ድንገት ለጌታቸው ይደውልና ሱዳን ካርቱም መግባቱን ፣ ለእናቱ እንዳይነግር ፣ እሱም በቅርቡ አውሮፓ በመግባት የተበደረውን ገንዘብ ጭምር እጥፍ አድርጎ እንደሚከፍለው በመንገር በሰላም ካሰበበት እንዲገባ ጭምር እንዲጸልይለት ለወንድሙ በመንገር ተሰነባበቱ ። ወንድሙ ጌታቸው ምንም በሁኔታው ቢያዝንም ምንም ማድረግ የማይችለው ነገር በመሆኑ ዝም ከማለት ውጪ ምንም አማራጭ ስለሌለው ደንግጦ ይቀራል ።
ከቤት እናት ወሮ ዛፉ ገብረየሱስ ደግሞ ይህን ሁሉ የታላቅና የታናሽን ምስጢር ባይሰሙም ውስጣቸው እየተረበሸ ተቸግረዋል ። “ልጄ ምነው ድምፁ ጠፋ ” መቐለ ሆኖ ነው እንዲህ የጠፋው? ብለው ይጠይቃሉ እውነታውን የሚነግራቸው የለም እንጂ ። የእናት አንጀት አይደል የሚባል ። ወደ ኋላ ላይማ በግልፅ ” ህልም አይቻለሁ ። ልጄ ታስሯል ። አደጋም ደርሶበታል እያሉ ቢናገሩም ማን አድምጧቸው ።

በመጨረሻም የዳንኤል የመጨረሻ ወንድሙ ሃኒ ኢንተርኔት ሲጎረጉር የወንድሙን የግፍ አገዳደል አይቶ ደነገጠ ። ለማን እንደሚነግር ቢጨንቀው ወንድሙ ጌታቸውን በመጥራት ዳንኤል ታርዷል ብሎ ምስሉን ያሳየዋል ። ከዚያ በኋላ የሆነውን ጌታቸው ማስታወስ አይፈልግም ። እስካሁን ድረስ ምነው ያን ገንዘብ ባልሰጠሁት እያለ ይንገበገባል ። የእናቱን ፊት እንኳን በሙሉ አይኑ ለማየት አይደፍርም ። ጥቁር ልብሱን እንኳን ዛሬ ነው እንዲያወልቅ በካህናቱ አስመክሬ እሺ ያሰኘሁት።

ምናልባት ተሳስቼ ወይም ተመሳስሎብኝ እንደሆነ ብሎ ደብረዘይት በኢንጅነሪንግ ተመርቆ በማስተማር ላይ ወዳለው ታናሽ ወንድሙ ጋር ቢደውል ወንድሙ ጣዕመ ሐዱሽ ለካ ቀድሞ በኢንተርኔት አይቶ ኑሮ ትኬት እንደቆረጠና በበነጋው እንደሚመጣ ፣ እናታቸውንም እንደሚያረዱ ተነጋግረው በማግሥቱ እናት በህልማቸው ያዩትን የልጃቸውን አደጋ በገሐድ አረጋገጡላቸው ።

አባት አቶ ሐዱሽ ገብረ ኪዳን አሁንም አስመራ ናቸው በቅርብ ርቀት ድንበር የሚሉት ጣጣ አይሻገሩት ነገር ችግር ሆኖባቸው የወለዱትን ልጅ አድጎ ዩኒቨርስቲ ገብቶ ተመርቆ እስኪወጣ እንደናፈቃቸው ዓይኑን ለማየት እንደጓጉ በሊብያ በረሃ በጨካኞች እጅ ወድቆ ሰማዕትነትን ተቀበለ ። ባለፈው ዓመት ጅማ ዩኒቨርስቲ ዳንኤል ሲመረቅ በባህርም በየብስም ብዬ እንደምንም ብዬ መጥቼ የልጄ የምርቃት ፕሮግራሙ ላይ እገኛለሁ ቢሉም አልተቻለም ።

ልጅ ዳንኤል ከኢትዮጵያ አባቴን እንዳለ ፣ አቶ ሐዱሽም ከአስመራ ልጄ እንዳሉ ፣ ላይገናኙ እንደተነፋፈቁ ተላለፉ አባትና ልጅ ። ወይ ነዶ አለ ያገሬ ሰው ።
አቶ ሐዱሽ እንደምንም ብለው አሁን መውጫ ቀዳዳ አግኝተው ከኤርትራ ምድር ወጥተው ጎረቤት ሐገር ገብተዋል ። እግዚአብሔር ካለ ሰሞኑን ኢትዮጵያ ይገባሉ ። ዳንኤልን በሕይወት ባያገኙትም ቀሪ ዘመናቸውን ከተቀሩት ልጆቻቸው ጋር ለማሳለፍ ሃገራቸው ለመግባት ቀናት እየቆጠሩ ይገኛሉ ።

ዳንኤል በክርስትና ህይወቱ የተመሰከረለት ፣ ለሃይማኖቱ እጅግ ልዩ ቅንአት ያለው ልጅ እንደነበረ አሁን በሕይወት የሚገኙት ጓደኞቹ ጭምር ይናገራሉ ። ISIS እጅ ከወደቀበት ጊዜ ጀምሮ በረሃብና በጥም ጭምር ብዙ የተሰቃዩ ቢሆንም እንኳ ከፊቱ ላይ ወዙ እንዳለ እንደነበር ሁላችን ያየነው ነው ። አንገቱን ከአካሉ ቆርጠው ወገቡ ላይ አስቀምጠውት እንኳ የተቆረጠው ፊቱ ላይ ፈገግታና ወዙ እንዳለ ነበር የሚታየው ።

ዳንኤል ሐዱሽ ማዕተቡን ከአንገቱ ሳይበጥስ ከነማዕተቡ አንገቱን የሰጠ ጀግና ሰማዕት ነው ። ቁም ነገር የላችሁም ለምንባል ለእኛ ፣ አዬ የ8ተኛው ሺህ ልጆች ለምንባል ለእኛ ኩራት የሆነን ። ቀና ብለን እንድንሄድ ያደረገን ምርጥና ብርቅዬ የተዋህዶ ልጅ ፣ የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም ሰማዕት ነው ።

በ ስዊዘርላንድ የሚገኙት የኢትዮ ዙሪክ የእግር ኳስ ቡድን አባላት የላኩትን 8520 ብር አቶ አምሀ ከአሜሪካን እነ ህይወትም እንዲሁ ከአሜሪካን ብፁዕ አቡነ ማትያስ የካናዳ ሐገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በሀገረ ስብከታቸው ከሚገኘው የካናዳ ቫንኮቨር ሆህተ ሰማይ ቅድስት ማርያም ምእመናን ልጆቻቸው ተቀብለው እንዳደርስ የሰጡኝን 4100 ብር በአጠቃላይ 25177. 95 ብር በኢንቲጮ ከተማ አስተዳሩ በአቶ ሰሎሞን እጅ አስረክቤላችኋለሁ ። ለሰጣችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ይስጣችሁ ።

የሰማዕቱ ዳንኤል እናት ያቀረቡልኝን ነጭ ወተት የመሰለ ማር በአንባሻ ከተቀበልኩ በኋላ ክቡር ከንቲባው በረሃው ሳይበረታባችሁ በጊዜ ወደ ጾረና ግንባር ወደሚገኘው ሰማዕቱ ተስፎም ታረቀኝ በስመ ጥምቀቱ ተስፋማርያም ቤተሰቦች ዘንድ እንድንሄድ መኪናዋን ከነ ሹፌሩ ስለፈቀዱልኝ ከአባቶች ቡራኬ ተቀብዬ የሰማዕቱ ዳንኤል ወንድም ጌታቸውም አብሬህ ነው የምሄድ ብሎኝ ጉዞ ወደ ገርሁ ስርናይ አድርጌያለሁ ።

ኦ አምላኬ ምን አይነት ምስቅልቅሉ የወጣና የሚያሳዝን ቤተሰብ በዚያ እንደገጠመኝ ሰሞኑን አወጋችኋለሁ ። በትእግስት ጠብቁኝ ።

አሁን ከሌሊቱ 5 ሰዓት ሆኗል ። ነገ ሰንበት ስለሆነ አክሱም ጽዮን የማስቀደስ እድሉን አግኝቻለሁ ። በረራዬ ከምሽቱ 11 ሰዓት ላይ መሆኑ አክሱም እቆያለሁ ።
የሰማዕቱን ዳንኤል ሐዱሽን ቤተሰቦች ለመርዳት የምትፈልጉ በእናትየው ስም በተከፈተው የባንክ አካውንት ካላችሁበት ሆናችሁ አስገቡላቸው ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አኒቲጮ ቅርንጫፍ
የባንክ ሂሳብ ቁጥር
Z 21 S 010007346
ሞባይል +251917872705 አቶ ጌታቸው ሐዱሽ ብላችሁ ደውላችሁ አጽናኗቸው ።

ይህን ጽሑፍ ካነበቡ በኋላ ሼር ቢያደርጉት ከበረከቱ መካፈል ለሚፈልግ ሰው እድል እንደመስጠት ይቆጠራልና ላልሰማ ሼር በማድረግ እናሰማ ።
ማንኛውንም አስተያየታችሁን እቀበላለሁ ። በዚህ ዙሪያ ለምትጠይቁኝ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ ። የእጅ ስልኬ +251 911608054 ነው ።

ከሁሉ የማንስ እኔ አክባሪ ወንድማችሁ
ዘመድኩን በቀለ ነኝ
ግንቦት 29/9/2007 ዓም
አክሱም — ኢትዮጵያ

The post አባቱን እንደናፈቀ ሳያገኘው ያለፈው ሰማዕት (ዳንኤል ሐዱሽ) “በዐይኔ አይቼ በጆሮዬም ሰምቼ ከሥፍራው በመገኘት ጻፍኩላችሁ” appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

በትናንቱ የመርካቶ ቃጠሎ 7 ሰዎች ተጎድተዋል ተባለ

$
0
0

በአዲስ አበባ መርካቶ ወረዳ 8 ሸራ ተራ ተብሎ በሚታወቀው ቦታ ላይ ትናንት የደረሰው የእሳት ቃጠሎ ግምቱ ያልታወቀ ንብረት ያወደመ ሲሆን 7 ሰዎች በጭስ የመታፈን አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡
የፕላስቲክ ጫማ ማምረቻ ጨምሮ ወደ 50 የሚጠጉ የብርድልብስና የተለያዩ የላስቲክ ውጤቶች፣ የንግድ መደብሮችና መጋዘኖች መቃጠላቸውን ጉዳቱ ከደረሰባቸው ወገኖች ያገኘነው መረጃ ያመለከተ ሲሆን የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ መቆጣጠር ባለስልጣን በበኩሉ፤ የአደጋው መንስኤና በአደጋው የወደመው የንብረት መጠን እየተጣራ መሆኑን ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡
katello
እሳቱ የተነሳው ከቀኑ በ8፡50 ገደማ ላይ መሆኑን ከአካባቢው ሰዎች ያገኘነው መረጃ ሲያመለክት የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠሪያ የኮሙዩኒኬሽን ኦፊሰር አቶ ንጋቱ ማሞ፤ ለመ/ቤታቸው ጥሪ የደረሰው 8፡57 ደቂቃ መሆኑንና በ3 ደቂቃ ውስጥ የአደጋ መከላከያ ተሽከርካሪዎችና ሰራተኞች በስፍራው ተገኝተው እሳቱን የማጥፋት ስራ እንደጀመሩ ገልፀዋል፡፡
ከ3 ሰዓት በላይ የዘለቀውን የእሳት ቃጠሎ የእሳትና ድንገተኛ ተሽከርካሪዎች በምልልስ ለማጥፋት ርብርብ ያደረጉ ሲሆን የአየር መንገድ የእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪም ትብብር ማድረጉን አቶ ንጋቱ ጠቁመዋል፡፡ በአካባቢው ተገኝተን እንደተመለከትነው የአካባቢው ህብረተሰብ አደጋውን ለመቆጣጠር እንዲሁም ከእሳት ቃጠሎብ ንብረት ለማትረፍ ከፍተኛ ርብርብ ያደረጉ ሲሆን በርካታ ሸቀጦችም በዚህ መልክ ማትረፍ መቻሉን ለማየት ችለናል፡፡
እሳቱን በፍጥነት ለመቆጣጠር የቦታው ለተሽከርካሪዎች አመቺ አለመሆንና እንደ ፕላስቲክና ጨርቃጨርቅ ያሉት ተቀጣጣይ ቁሳቁሶች በብዛት መኖር አዳጋች እንዳደረገባቸው የጠቆሙት አቶ ንጋቱ፤ የአደጋ መቆጣጠሩን ስራ ለባለሙያዎች አለመተውም አንዱ ችግር ነበር ብለዋል፡፡

Source: Addis Admass Newspaper

The post በትናንቱ የመርካቶ ቃጠሎ 7 ሰዎች ተጎድተዋል ተባለ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

Health: ማር እና ሎሚን ቀላቅሎ መጠቀም ለጤና፣ ለቆዳ ውበት እና ለጸጉር ያለው ጠቀሜታ

$
0
0

honey
ማር በጣፋጭነቱ እና ባለው በርካታ የጤና ጠቀሜታ በብዙዎቻቸን ዘንድ ይዘወተራል።

ሎሚም በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት በተለያዩ ጊዜያት የተሰሩ ጥናቶች ይመከራሉ።

ማር እና ሎሚ በውስጣቸው አንቲኦክሲዳንት እና አንቲባክቴሪያ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን በመያዛቸው የሰው ልጅን በሽታ የመከላከል አቅም በመጨመር ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ።

ሁለቱን አንድ ላይ በማዋሃድ መጠቀም ደግሞ ክብደትን ለመቀነስ፣ ለቆዳ ውበት እና ለጸጉራቸን እንዲሁም ለጤናችን በርካታ ጠቀሜታዎችን ያስገኝልናል።

ማር እና ሎሚን በመቀላቀል የምናገኛቸው ጠቀሜታዎች፦

አስም፣ ጉንፋንና ብሮንካይትን ለማከም፦ ማር እና ሎሚን አንድ ላይ ቀላቅለን በመጠጣት ከመተንፈሻ አካላት ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ እንደ አስም፣ ብሮንካይት እና ጉንፋን አይነት ህመሞችን ለማከም ይቻላል።

ለዚህም ይረዳ ዘንድ 2 የሻይ ማንኪያ የሎሞ ጭማቂና 1 የሻይ ማንኪያ ማር አንድ ላይ በማድረግ በ1 ብርጭቆ ውሃ ውስጥ አንድ ላይ በመደባለቅ በቀን ውስጥ ደጋግምን መጠጣት ይመከራል።

በፊትና በቆዳ ላይ የሚወጡ እንደ ብጉር እና ሌሎች ችግሮችን ለማከም፦ ማር እና ሎሚ በተፈጥሮ የጸረ ባክቴሪያ ነጥረ ነገር ስላላቸው በባክቴሪያ እና ተያያዥ ነገሮች አማካኝነት በቆዳ ላይ ሚከሰቱ እንደ ብጉር እና ሌሎች የቆዳ ህመሞችን ለማከም ወይም ለማስወገድ ይረዳሉ።

እንዲሁም ለስላሳ እና ጤነኛ ቆዳ እንዲኖረንም ይረዳሉ።

ለዚህም ይረዳ ዘንድ የሎሚ እና ማርን በአንድ ላይ በመደባለቅ ቢያንስ በሳመንት ሁለት ጊዜ መጠቀም አለብን ተብሏል።

የሰውነት ቁስልን ለመፈወስ፦ የሎሚ እና የማር ውህድ ቁስልን ቶሎ ለመፈወስ እና ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር በማድረግ ረገደም ጠቀሜታ አላቸው ሲሉ ተመራማሪዎች ይናገራሉ።

ማር በተፈጥሮ ባለው የስኳርነት ባህሪ አማካኘነት ማይክሮ ኦርጋኒዝሞችን የሚከላከል ሲሆን፥ ሎሚ ደግሞ ባክቴሪያዎች እንዳየራቡ በማደረግ ቁስል ቶሎ እንዲድን ያደርጋሉ።

ስለዚህ የሎሚ እና የማር ውህድ በመጠጣት ከቁስል ቶሎ መፈወስ እንችላለን።

ከልክ ያለፈ ውፍረትን እና ቦርጭን ለመቀነስ፦ ማር ከስብ ነጻ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፥ ሎሚ ደግሞ ዝቅተኛ የክሎሪክ መጥን እንዳለው ይነገራል።
ታዲያ የነዚህ ሁለቱ ውህድ በሰውነታቸን ስጥ ያለውን የስብ መጠን ለመቀነስ ይረዳሉ ተብሏል።

ስለዚህ ከልክ ያለፈ ውፍረትን እና ቦርጭን በቀላሉ ለመከላከል ለብ ባለ አንድ ብርጭቆ ውሃ ውስጥ 3 የሻይ ማንኪያ የሎሚ ችማቂ እና 1 የሻይ ማንኪያ ማር በመጨመር በደንብ አዋሀዶ መጠጣት ይመከራል።

ለጸጉር እንክብካቤ፦ የሎሚ ጭማቂ ጸጉርን ለመንከባከብ እንደሚረዳም ተነግሯል።

በተለይም የጸጉር መድረቅና የማሳከክ ስሜት ለሚሰማቸው ሰዎች የሎሚ ጭማቂ አይነኛ መፍትሄ ነውም ተብሏል።

የሎሚ ጭማቂን በቀጥታ የጸጉር ራስ ቅላቸን ላይ በመቀባት ጸጉር የማሳከክ ስሜትን ለመከላከል የሚረዳ ሲሆን፥ እንዲሁም ጸጉራችን ተፈጥሯዊ ውበት እንዲኖረው ይረዳል ተብሏል።

ምንጭ፦ healthdigezt.com

የተርጉሞው፦ በሙለታ መንገሻ

The post Health: ማር እና ሎሚን ቀላቅሎ መጠቀም ለጤና፣ ለቆዳ ውበት እና ለጸጉር ያለው ጠቀሜታ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

ቴዲ አፍሮ የተለያየው ማናጀሩ የፌስቡክና የዩቲዩብ አካውንቱን ፓስወርድ እንዲመልስ ጠየቀ

$
0
0

989TeddyAfro_NYC_26
(ዘ-ሐበሻ) ዝነኛው አርቲስት ቴዲ አፍሮ ከማናጀሩ ከዘካሪያስ ጌታቸው የመለያየታቸው ዜና ከተሰማ በኋላ በየሥፍራው የተለያዩ መረጃዎች እይወጡ ይገኛሉ:: የቴዲ አፍሮ እና የማናጀሩ የመለያየት ምክንያት ራድዮ ፋና የገለጸው አይደለም እየተባለ ባለበት በዚህ ወቅት የዘ-ሐበሻ የቅርብ ምንጮች እንዳረጋገጡት ቴዲ አፍሮ ማናጀሩ የፌስቡኩን እና የዩቲዩብ ፓስወርዱን እንዲመልስ ጠይቋል::

ወደ 417 ሺህ ሰዎች ላይክ ያደረጉት የቴዲ አፍሮ ዋና የፌስቡክ ገጽን የሚያስተዳድረው ዘካሪያስ ጌታቸው የነበረ ሲሆን ቴዲ አፍሮ የዚህን ፓስወርድ እንዲመልስ ማናጀሩን በሽማግሌ ቢያስጠይቅም ዘካሪያስ ፓስፖርቱን ለመመለስ ከፍተኛ ገንዘብ መጠየቁን ምንጮች ለዘ-ሐበሻ አስታውቀዋል::

በቴዲ አፍሮ በኩል ይህን ፓስወርድ ለማስመለስ ዘካሪያስ የጠየቀውን ከፍተኛ ክፍያ ለመክፈል ፈቃደኛነት የለም:: የቴዲ አፍሮ የዩቲዩብ አካውንትም እንዲሁ በዘካሪያስ ጌታቸው እጅ የሚገኝ ሲሆን 9,529 ሰዎች ተመዝግበዋል:: ይህንንም ፓስወርድ እንዲመልስለት በሽማግሌዎች እየጠየቀ ባለበት በዚህ ሁኔታ እንደውም ዘካሪያስ ፓስወርዱን የማይመልስ ከሆነ አዲስ የፌስቡክ ላይክ ገጽ እንከፍታለን በሚል በባለቤቱ በኩል እንቅስቃሴ መጀመሩም ተሰምቷል::

ከሰሞኑ የተከፈተው አዲሱ የቴዲ አፍሮ ዋና የፌስቡክ ገጽ በርካታ ተከታዮችን እያፈራ ሲሆን እርስዎም ላይክ ማድረግ ከፈለጉ ሊንኩ የሚከተለው ነው::

Teddy Afro Offical

The post ቴዲ አፍሮ የተለያየው ማናጀሩ የፌስቡክና የዩቲዩብ አካውንቱን ፓስወርድ እንዲመልስ ጠየቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የሕወሓት መንግስት ስርዓቱን የከዱትን 9 የጦር መኮንኖች እያደነ ነው * መኮንኖቹ ኦነግን ተቀላቅለዋል እየተባለ ነው

$
0
0

(ምንሊክ ሳልሳዊ) ከደቡብ ምስራቅ እዝ የከዱ ዘጠኝ የባሌ ክፍለሃገር ተወላጅ የሆኑ የሰራዊቱ መኮንኖችን ለመያዝ ማደኑን አንደቀጠለ አና አስካሁን ከኦነግ ኣማጽያን ጋር ተቀላቅለዋል ከሚባል ውጪ ያሉበት ቦታ ምንም ፍንጭ እንደሌለ ለጦር ሃይሎች መምሪያ የደህንነት ክፍል የመጣ መረጃ መጠቆሙን የመከላከያ ምንጮች ገልጸዋል::
clash
በተለያዩ ጊዜያት ከባለፉት ሳምንት ጀምሮ ድንበር ዘለል ወረራ በኬንያ ላይ ያደረገው የወያኔ ሰራዊት ከኦነግ ኣማጽያን ጋር ጦርነት ገጥሞ አንደነበር ሲታወስ የከዱ የመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ከኦነግ ኣማጽያን ጋር ተደባልቀው የወያኔን ሰራዊት አንደወጉ ቢገለጽም አስካሁን ድረስ የኦነግ ታጣቂ ሃይሎችን ያሉበትን ኣከባቢ ለማግኘት ኣለመቻሉን መረጃዎቹ ሲጠቁሙ ኣሉበት የተባሉ ኣከባቢዎችን በሃገር ውስጥ ደኖች ላይ ኣንደተለመደው አሳት በመልቀቅ አና ጎረቤት ሃገሮችን በመውረር በሃይል ለማዳከም ስራዎች አየተሰሩ አንደሆን ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::

ሰራዊቱን ከድተው ወተዋል ከተባሉት ከፍተኛ መኮንኖች ውስጥ ሶስቱ ኮሎኔሎች የጦር መሪዎች መሆናቸው ሲታወቅ አነሱም
፤ ፩ = ኮሎነል ያሲን ሁሴን
፪ = ኮሎኔል ነገራ ኢደሳ
፫ = ኮሎኔል ኑሩ ኣስሊ ይገኙበታል::

የሰራዊቱ የዘመቻ እንቅስቃሴ መረጃዎች በጃቸው አንደሆነ የሚነገርላቸው የጦር መሪዎች መክዳት ከፍተኛ ድንጋጤ አንደፈጠረ ታውቋል፥፥ይህ በእንዲህ አንዳለ በሶማሊያ አና በኢትዮጵያ ድንበር ኣከባቢ በወያኔ ሰራዊት እና በኦብነግ ኣማጽያን መካከል ግጭቱ የቀጠለ ሲሆን በክዐንያው ድርድርም አስካሁን የተገኘ ውጤት አንዳሌለ ታውቋል:

The post የሕወሓት መንግስት ስርዓቱን የከዱትን 9 የጦር መኮንኖች እያደነ ነው * መኮንኖቹ ኦነግን ተቀላቅለዋል እየተባለ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

Sport: ዋሊያዎቹ በዛምቢያ‬ ተሸነፉ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከዛምቢያ አቻቸው ጋር ባደረገው የወዳጅነት ጨዋታ 1-0 ተሸነፈ። ዛምቢያ በአላን ሙኩካ አማካኝነት 45 ኛው ደቂቃ ጎል ማስቆጠር ችለዋል። 75ኛው ደቂቃ ኢትዮጵያ የፍፁም ቅጣት ምት ብታገኝም ቢንያም አሰፋ ሳይጠቀምበት ቀርቶ ጨዋታው በዛምቢያ 1- 0 አሸናፊነትም ተጠናቋል::

ፎቶ ክሬዲት - ለኢትዮ-ኪክ

ፎቶ ክሬዲት – ለኢትዮ-ኪክ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በተለይም ጋቶች ፓኖም እና ምንተስኖት አዳነን በብሩክ ካልቦሬ እና ፍሬው ሰለሞን በመቀየር ከእረፍት መልስ የተሻለ ቢንቀሳቀስም ግብ ማስቆጠር ተስኖት ታይቷል ያሉት የስፖርት ተንታኞች ጨዋታው ሊጠናቀቅ አምስት ደቂቃ ሲቀርም ሙጂብ ቃሲም ሆን ብሎ ኳስ በእጅ በመንካቱ በቀይ ካርድ ከሜዳ መሰናበቱን ገልጸዋል::

ፌዴሬሽኑ ይህን የወዳጅነት ጨዋታ የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን ወጪ በመቻል ወደ ኢትዮጵያ ያመጣው ጨዋታው የተካሄደው አዲሱ አሰልጣኝ ዩሃንስ ሳህሌ የሚመሩት ዋልያዎቹ የፊታችን ሰኔ 7 ለ2017ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ከሌሴቶ ጋር ለሚያደርጉት የምድብ ጨዋታ ቅድመ ዝግጅት እንደሚረዳቸው ታስቦ ነበር::

ፊፋ በየዓመቱ በሚያወጣው የዓለም የ እግር ኳስ ደረጃ 8 ደረጃዎችን በማሽቆልቆል 68ኛ ደረጃ ሲቀመጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአንጻሩ 2 ደረጃዎችን ወደ ላይ በማሻሻል 99ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል::

The post Sport: ዋሊያዎቹ በዛምቢያ‬ ተሸነፉ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የኖርዌይና የኢትዮጵያውያን ስደተኞቻችን ፍልሚያ –በአበራ ለማ

$
0
0
Photo File

Photo File

የዛሬ አራት ዓመት በኖርዌይ ተቀስቅሶ የነበረው የ500 ጥገኝነት ጠያቂ ኢትዮጵያውያን ስደተኖች ጉዳይ በኦስሎ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት 127ኛ ችሎት በቅርቡ ሲታይ ሰንብቷል፡፡ ይህ ቀደም ሲል በዶ/ር ግሩም ዘለቀ የግል ተነሳሽነት በኖርዌይ ጠበቆች አማካኝነት በየደረጃው ላሉ የኖርዌይ ፍርድ ቤቶችና በኋላም ለአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረው ጉዳይ አሁን የታየው እ.አ.አ. ከሜይ 4 – 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ነው፡፡ የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት መቀመጫውን ለንደን ባደረገው ”ዘ አየር ሴንተር – The AIRE Center” (Advice on Individual Rights in Europe) በተሰኘው መንግሥታዊ ባልሆነው የሕግ ባለሙያዎች ድርጅት አማካኝነት የቀረበለትን ይህን ጉዳይ፣ ከሦስት ዓመታት ተኩል በላይ ለሆነ ጊዜ ሲመለከተው መቆየቱም ይታወሳል፡፡

Read Full Story in PDF

The post የኖርዌይና የኢትዮጵያውያን ስደተኞቻችን ፍልሚያ – በአበራ ለማ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

ተመስገን ደሳለኝ –ለጥላቻ እና ጠልፎመጣል ፖለቲካ አራማጆች አዲስ መንገድ ያሳየ ጀግና ጋዜጠኛ

$
0
0

Temesgen Desalegn behindbar
ስለ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጋዜጠኛ ኤድመን ተስፋዬ (በኢትዮ – መኅዳር ጋዜጣ ላይ ከፃፈው)

ሰው ማለት ሰው የሆነ ነው ሰው የጠፋለት !
በመንቃት ላይ ባሉ፣
ፍጡራን መሀከል- ህይወት የምንለው፣
እንደ ጥሬ እህል፣ በኑሮ ምጣድ ላይ፣
ቢቆላ ቢማሰል -የበሰለው ያራል ፣ ጥሬው እስኪበስል፡፡ (ኃይሉ ገ /ዩሐንስ)

አምላክ ለሌሎች ፍጡራኑ ያልሰጠውን ፣ ነገር ግን ለሰው ልጆች ብቻ የሰጠውን የማሰብ ጸጋ ተግባራዊ በማድረጉ የተነሳ ነጻነቱን ለድርድር የማያቀርበው የፈክት መጽሔት ባልደረባዬ የነበረው ተመስገን ደሳለኝ ለኔ ማሰብ የጀመረ ሰው ከምንም በላይ ለነጻነቱ ቅድያ እንደሚሰጥ ማሳያ የሆነ ግለሰብ፡፡

በእኔ እምነት የአባት እዳ ለልጅ እንዲሉ፣ መጠላለፍ እና አሸናፊነትን እና ጸሸናፊነትን ብቻ ፖለቲካዊ ባህሉ ላደረገው እና አሁንም የሀገሪቷ ፖለቲካ ከሚዘውረው የያ ትውልድ የፖለቲካ ባህል ውስጥ ፣ ከመጠላለፍ ውስጥ ህብረትን ፣ ከአሸናፊነት እና ተሸናፊነት ውስጥ አሸናፊነትን እና አሸናነትን ችቻ ያሳየ የአዲሱ ትውልድ አንደበት ነው፡፡

ከጳጳስ እስከ ሼካ፣ ከሼካ እስከ ምሁር ፣ ከምሁር እስከ ኪነጥበብ ባለሙያ ወዘተ ሀገርን እና ህብረተሰብን ወደ ጎን በመተው ፣ ለጓዳው ብቻ በማሰብ ምናገባኝ ባይ በሆነበት ሀገር ውስጥ ከአንባገናዊ ስርዓተ መንግስት በላይ የሚያስጨንቀው እንደ እኔ እምነት አርአያ የሚሆን ግለሰብ ያጣችው እና የሞራልን ዋጋ የናዱ ግለሰቦች የሚፈነጩባት ሀገር እጣ ፈንታ ነው፡፡
እንደ እኔ እምነት፣ ተመስገን ደሳለኝ አርአያ የሚሆን ግሰብ ላጣችው እና የሞራን ዋጋ የናዱ ግለሰቦች መፈንጫ ለሆነችው ሀገሩ ሀገሬ በግለሰቦች የግል ፍላጎት የተነሳ ህልውናዋ አደጋ ላይ ሊወድቅ አይገባም በሚል ብእሩን የግልሰቦች ስብስብ በሆነው ስርዓት እና የስርዓቱ አንቋላጮች ላይ ያነሳ የሀገሩ እጣ ፈንታ ያስጨነቀው ግለሰብ ነው፡፡

ከህዝብ በሚሰበሰብ ቀረጥ የሚከናወነው የልማት እንቅስቃሴ ወደ ግለሰቦች ጓዳ በሚገባበት፣ ከኢህአዲግ አባልነት ውጪ ስራ ማግኘት ከባድ በሆነበት፣ የወጣት ጥቃቅን እና አነስተኛ ማህበራት የፋይናንስ ዋስትና አደጋ ላይ በወደቀበት ባለሀብቱ ዛሬ ደግሞ ምን ሊሉን ይሆን በሚል በነጋ በጠባ በሚጨነቅባት ባል እና እሴቶቻችን ጠፍተው የህዝቡን እና የሀገርን ሀብት የዘረፈ ደረቱን ነፍቶ በአደባባይ በሚሄድበት እና በሚከበርበት ፍትህን ለገንዘብ ብሎ ያዛባ ያሻውን በሚያደርግበት ከዲግሪ እስከ ፒኤች ዲ በዘረፈው ገንዘብ ገዝቶ በማን አለብኝነት በአስተዳዳሪነት በተቀመጠበት በዘመነ ኢህአዴግ ላይ ለአቅመ አዳም የደረሰው ተሜ የአዲሱ ትውል አካል እንደ መሆኑ ለአዲሱም ሆነ ለነባሩ ትውልደ በመረጃ የተደገፈ ሚዛናዊ ሂስ እና ትችት ከፍ ሲልም ማስጠንቀቂያና መፍትሄን ከድፍረትጋር ማቅረብ እንደሚቻ ያሳየ ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያዊነትን ማንም መስጠትም ሆነ መንፈግ እንደማይችል በተግባር ያሳየ ሰላማዊ ባለሞያ ነው ለኔ ፡፡

ለሆዱ አዳሪ የሆነ ማህበረሰብ በበዛበት እና ሀገር አርአያ የሆነ ግለስ ባጣችበት በዚህ ዘመን ኢትዮጵዊ ማንነትን ማንም የሚሰጠውም ሆነ የሚነጥቀው አይደለም የሚለው ጽኑ እምነቱ እንዳ ሆኖ እንዲህ መጻፍህን አቁም አልያም ሀገርህን ለቀህ ውጣ የሚል ማስፈራሪያም ሆነ መደለያ ቀርለት እንኳ አሻፈረኝ ያለው ተመስገን ደሳለኝ ለኔ ከአዲሱ ትውልድ የወጣ የዚህ ትውልድ ፈርጥ ነው፤፤ ማህበረሰቡ ውስጥ ሆኖ የማህበረሰቡን በደል በአደባባይ በማውጣት መንገስትን በሰላ ብእሩ የሚተቸው ተሜ ከምንም በፊት የህዝብ እና የሀገርን ህልውና በማስቀደም የመንግሰትን ገመና በመረጃ እና በአካዳሚካዊ ትንታኔ በአደባባይ ማውጣቱ በእኔ እምነት ተሜን ለጥላቻ እና ጠልፎመጣል ፖለቲካ አራማጆች አዲስ መንገድ ያሳየ ወጣት የሚያደርገው ይመስለኛል፡፡

ተመስገን ደሳለኝ ከፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል እስከ አንባገነናዊ የግለሰቦች ጭቆና በብእሩ መግለጹ በአንድ በኩል እንደ ህዝብ የደረሰበትንም ሆነ ወደፊት ስለሚጠብቀው አደጋ ለህዝቡም በማሳወቅ ረገድ በሌላ በኩል ለጭቆናውም ሆነ ለሌብነቱ መንስኤ ለሆኑት ግለሰቦች በነሱ የተነሳ በህዝቡ እና በሀገሪቷ ላይ ስላደረሰው እና ስለሚያደርሰው ሁነታ ለገዢዎቹ በማሳየት ረገድ ከፍተኛ ሚና ያበረከተ ብቻ ሳይሆን ገና የሚያበረክት ስመሆኑ ሳስብ ፊቴ ላይ ድቅን የሚለው እና የሚያሳስበኝ ተሜ ሰው በጠፋበትሀገር ሰው በመሆኑ የተነሳ በዝዋይ እስር ቤት ታስሮ በጀርባ ህመም የመሰቃየቱ ነገር ነው፡፡

ለዚህ ጽሑፍ መግቢያ ያደረኩትን ድንቅ ግጥም ያበረከተልን የዛ ዘመኑ ታጋይ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ኃይሉ ገብረየሁአንስ በህይወት ኖሮ የተሜን ህመም ቢሰማ ኖሮ ምን ይል ነበር?

በመንቃት ላይ ባሉ፣ ፍጡራን መሀከል
ህይወት የምንለው ፣ እንደ ጥሬ እህል፣
በኑሮ ምጣድ ላይ፣ ቢቆላ ቢማሰል የበሰለው ያራል፣ ጥሬው እስኪበስል፡፡

The post ተመስገን ደሳለኝ – ለጥላቻ እና ጠልፎመጣል ፖለቲካ አራማጆች አዲስ መንገድ ያሳየ ጀግና ጋዜጠኛ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ታዋቂው የአውሮፓ እግር ኳስ ተጫዋች ኢትዮጵያ ውስጥ ንጹህ ውሃና መጸዳጃ ፕሮጀክት ላይ ለመስራት ኢትዮጵያ ይገኛል

$
0
0

ኢትዮ-ኪክ እንደዘገበው የጀርመኑ ቦርሲያ ዶቱመንድ ክለብ የመሀል ተከላካይ ተጨዋቾ ኢትዮጵያ ይገኛል። 27 አመቱ Neven Subotic ኢትዮጵያ የመጣበት ዋነኛው ምክንያት በንፁ ውሃ አቅርቦት እና በመፀዳጃ ቤት ችግር የሚሰቃዪ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚገኙ ወገኖቻችን በተለይም ህፃናትን ከዚህ ችግር እንዲላቀቁ ለመርዳት Neven Subotic Foundation በሚል ያቌቌመውን ፋውንዴሽን ስራውን ሂደት ለመጎበኘት ነው።
Borsia Dortumund

dortumund

Dortumund

dortumund 2
Neven Subotic Foundation ፕሮጀክት ስራውን እየሰጠ የሚገኘው በትግራይ ክልል አዲግራት ላይ ሲሆን ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች ውስጥ ንፁ የመፀዳጃ ቤት አግልግሎት ለመቅረፍና የንፁ ውሃ በቅረበት የሚያገኙበት ፕሮጀክቶችን እየረዳ ነው ።

የተቸገሩን መረዳት የሚያስደስተው Neven አስከ June 17 በኢትዮጵያ ቆይታ ያደርጋል።
ስለ ተጨዋቹ ማንነት እና የፋውንዴሽኑ e:mail አድርሻውን ለማወቅ ይህንን ያንብቡ
About Neven:—:
Neven Subotic was born on December 10, 1988 in Banja Luka, Bosnia. Together with his parents and his sister, he came to Germany in 1990, where they lived until 1999, near
Pforzheim.
To avoid having to return to the kriegserschĂźtterte Yugoslavia, the family emigrated in 1999 to Salt Lake City in Utah, USA, from. There lay Neven Subotic with inserts in the national youth team laid the foundation for his football career.
He completed his first professional contract in 2006 from the first division Mainz 05. In 2008 he moved to Dortmund BVB. Since 2009 he has also player of the Serbian national team. He has already realized many important career dreams at an early age. His great desire is also to make use of his role models to help children.
Contact
info@nevensuboticstiftung.de

The post ታዋቂው የአውሮፓ እግር ኳስ ተጫዋች ኢትዮጵያ ውስጥ ንጹህ ውሃና መጸዳጃ ፕሮጀክት ላይ ለመስራት ኢትዮጵያ ይገኛል appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

በሰሚት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን መታመሱ ቀጥሏል * የሰንበት ት/ቤት አባላት እስር ወደ ምእመናን ተሸጋገረ

$
0
0

‹‹ጉዳዩን በፌስቡክ እያጋጋላችኹ ነው›› የተባሉ 16 የሰንበት ት/ቤት አባላትና ምእመናን ከቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል

በሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መመሪያ፣ ያለው ፈርሶ በአዲስ ምዝገባ በሚቋቋመው ሰንበት ት/ቤት ዕድሜአቸው ከ30 በላይ የኾኑ ይባረራሉ

‹‹አዲስ ሰንበት ት/ቤት እንዲቋቋም ያዘዝኹት እኔ ነኝ፤ ዑራኤል ጸሐፊ ኾኜ 700 ሰንበት ተማሪ በትጥቅ ድጋፍ አስበትኛለኹ››/ሥ/አስኪ. ሊ/ማእ. የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ/

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመካነ ሰላም ሰሚት መድኃኔዓለም ፍኖተ ሰላም ሰንበት ት/ቤት አመራር እና አባላት ላይ እየደረሰ ያለው ወከባ፣ እስር እና እንግልት ወደ አባላቱ ወላጆች ተሸጋገሮ እየከፋ መሔዱ ተገለጸ፡፡

የፖሊስ ጣቢያውን እንዳሻቸው የሚያዙበት አለቃው መልአከ ሰላም አባ ገብረ ሥላሴ አማረ

የፖሊስ ጣቢያውን እንዳሻቸው የሚያዙበት አለቃው መልአከ ሰላም አባ ገብረ ሥላሴ አማረ

የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም አባ ገብረ ሥላሴ አማረ ዛሬ፣ ግንቦት ፴ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ከጸሎተ ቅዳሴው ፍጻሜ በኋላ፣ በአገልግሎት ላይ የነበረውን ሰንበት ት/ቤት በማፍረስ ሌላ እንደሚቋቋም እና የአባላት ምዝገባ እንደሚያካሒዱ ሲገልጹ የሰንበት ት/ቤቱ አባላትና ምእመናኑ በአንድ ድምፅ ተቃውመዋቸዋል፡፡

‹‹ያለው ሰንበት ት/ቤት ምን ኾኖ ነው አዲስ ምዝገባ የሚካሔደው?›› ብለው በአንድ ድምፅ በመጠየቅ ተቃውሟቸውን በብርቱ ካሰሙት መካከል፣ ዘጠኝ ምእመናንና ሰባት የሰንበት ት/ቤት አባላት በስም እየተጠሩ ከቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጎሮ ፖሊስ ጣቢያ በአስተዳዳሪው ትእዛዝ ተይዘው ተወስደዋል፡፡

ከሦስት ዓመት በፊት ወደ ደብሩ የመጡት አለቃው መልአከ ሰላም አባ ገብረ ሥላሴ፣ በቃለ ዐዋዲው ለሰንበት ት/ቤቱ የተደነገገውን ወጣቶችንና ሕፃናትን የማደራጀት እና የማቋቋም ሓላፊነት በመጣስ በየአጥቢያው የምእመኑን ልጆች በሀብት መደብ እየከፋፈሉ የሀብታም ልጆችን እናስተምራለን ለሚሉ ግለሰቦች አስተዳደራዊ ድጋፍ በመስጠታቸው የተጀመረው ውዝግብ፣ ለሰንበት ት/ቤቱ አመራሮች እና አባላት መታሰር፣ መከሠሥ እና መታገድ፤ ለጽ/ቤቱና ለአዳራሹም መታሸግ ምክንያት ኾኗል፡፡

ከሰንበት ት/ቤቱ ጽ/ቤት መታሸግ ወዲኽ የአባላት ወላጆች የኾኑ ምእመናንንም ጭምር በማካተት ዛሬ የተፈጸመው እስር፣ ወከባ እና እንግልት በአንድ ሳምንት ለሦስተኛ ጊዜ የደረሰ ነው፡፡ ትላንት ጠዋት ሰባት አባላት ‹‹ለምን ጥያቄ ትጠይቃላችኹ›› በሚል ታስረው ወዲያው የተለቀቁ ሲኾን ባለፈው ረቡዕ ደግሞ ‹‹የአዲስ ምዝገባውን ማስታወቂያ ገንጥላችኋል›› በሚል አምስት አባላት ከ5፡00 – 8፡00 በጎሮ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው መለቀቃቸው ታውቋል፡፡

ምእመናኑንና የሰንበት ት/ቤት አባላቱን በተደጋጋሚ በማሰር የአለቃው ፈቃድ ፈጻሚ የኾነው የጎሮ ፖሊስ ጣቢያ ለቀረበለት የዘፈቀደ እስር እና የጣልቃ ገብነት ጥያቄ፣ ‹‹አባ ገብረ ሥላሴ አዝዘውኛል፤ እርሳቸው ያዘዙኝን ብቻ ነው የምፈጽመው›› ቢልም ከቀትር በኋላ ከአቅሜ በላይ ነው በሚል ምእመናኑንና የሰንበት ት/ቤት አባላቱን አምቼ አካባቢ ወደሚገኘው ወደ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ እንደወሰዳቸው ተገልጧል፡፡

በምእመናን የተመረጠውን ሰበካ ጉባኤ በማዳከም ደብሩን በዓምባገነንነት የሚመሩት አለቃው መልአከ ሰላም አባ ገብረ ሥላሴ፣ በማስታወቂያ በሚያቋቁሙት አዲስ የሰንበት ት/ቤት የሚመዘገቡት ዕድሜአቸው እስከ ሠላሳ ያሉትን ብቻ ሲኾን ይኸውም በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የተላለፈላቸው መመሪያ እንደኾነ ተጠቅሷል፡፡

ይህንኑ መመሪያ በኹሉም የሀገረ ስብከቱ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን በማስፈጸም ከሠላሳ ዓመት በላይ ያሉትን ወጣቶች እና ጎልማሶች ከሰንበት ት/ቤቶች እንደሚያባርሩ የዛቱት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ከፓትርያርኩ ዘንድም ይኹንታ እንዳገኙበት ተመልክቷል፡፡

locked-finot-selam-sunday-school-gates
የሰሚት መካነ ሰላም መድኃኔዓለም ፍኖተ ሰላም ሰንበት ት/ቤት÷ አባላቱ በሀብታም እና ድኻ መከፋፈላቸውንና በማስተማርያ ቦታ የሚደረገውን አድልዎ በመቃወሙ አመራሩ እንዲታገድ እና ጽ/ቤቱ እንዲታሸግ በማዘዝ በአዲስ ምዝገባ ሌላ ሰንበት ት/ቤት እንዲቋቋም መመሪያ የሰጡት ዋና ሥራ አስኪያጁ ሊቀ ማእምራን የማነ፣ በጸሐፊነት በሠሩበት የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያንም ሰንበት ት/ቤቱን በመሣርያ ኃይል በማፍረስ 700 አባላትን መበተናቸውን በጀብደኝነት ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡

፬ኛው የሰንበት ት/ቤቶች ሀገር አቀፍ አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ፣ ከጥቅመኛ ግለሰቦች ጋራ በዓላማ የተሳሰሩ አማሳኝ አለቆች እና እነርሱን የሚተባበሩ አካላት በሰንበት ት/ቤት አባላት ላይ ከሚያደርሱት እስር፣ ወከባ እና እንግልት እንዲቆጠቡ በአቋም መግለጫው አሳስቧል፡፡

በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያው ሥር የሚገኘው ሀገር አቀፍ አንድነቱ በጥቅምት ፳፻፮ ዓ.ም. በጸደቀለት የውስጥ መመሪያ፣ ሰንበት ት/ቤቶች ከሕፃናት እና ወጣቶች በተጨማሪ ጎልማሶችንም እንዲያደራጁ የተፈቀደላቸው ሲኾን የቅ/ሲኖዶሱን መምሪያ ኹሉም የበታች መዋቅሮች የመፈጸምና የማስፈጸም ግዴታ እንዳለባቸው ግልጽ ነው፡፡

በሌላ በኩል ሰንበት ት/ቤት፣ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮዋን ለተረካቢው ትውልድ የምታስተላልፍበትና የምታስጠብቅበት የትምህርት እና የልማት ማእከል በመኾኑ በግንቦት ፳፻፬ ዓ.ም. በተወሰነው የቃለ ዐዋዲው ማሻሻያ በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጀት እና ማቋቋም ድንጋጌ፣ ከ4-30 በሚል ለሕፃናት እና ወጣቶች የተቀመጠው የዕድሜ ገደብ እንዲጤን በሀገር አቀፍ አንድነቱ የአምና እና የዘንድሮ የአቋም መግለጫዎች ተደጋጋሚ ጥያቁ የቀረበበት ጉዳይ መኾኑ ይታወሳል፡፡

 

ምንጭ – ሐራ ተዋሕዶ

The post በሰሚት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን መታመሱ ቀጥሏል * የሰንበት ት/ቤት አባላት እስር ወደ ምእመናን ተሸጋገረ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የአርመን ቤተ ክርስቲያን ተምሳሌታዊ የፍትሕ ትግልና የኢትዮጵያ ጉዳይ –ኪዳኔ ዓለማየሁ

$
0
0

የአርመን ቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ እርምጃ፤

5cbefb19-064e-425a-a108-2477fb210ddfHiResበኒው ዮርክ ታይምስ (New York Times) እ.አ.አ. ግንቦት 19 ቀን 2015 በተዘገበው ዜና ቱርኮች ከ100 ዓመታት በፊት ስለ ዘረፉባት ንብረት የአርመን ቤተ ክርስቲያን በቱርክ መንግሥት ላይ በሐገሩ ውስጥ ክስ አቅርባለች። የቤተ ክርስቲያኗ መሪ፤ ቀዳማዊ አቡነ አረም (Aram I) በሰጡት ቃለ መጠይቅ መሠረት በደቡብ ቱርክ በአዳና (Adana) አውራጃ የሚገኘው በ1293 የተቋቋመው የአርመን ክርስቲያኖች ማእከል የነበረው ቤተ ክርስቲያንና ገዳም በቱርኮች ነጠቃ ተይዞ ስለሚገኝ በቱርክ ሕገ መንግሥት ፍርድ ቤት ክሱ ቀርቧል። ያ የአርመኖች ቤተ ክርስቲያን ማእከል በአስር ሺዎች ከሚቆጠሩ በኦቶማን ቱርኮች ከተመዘበሩት ብዙ ንብረቶች አንደኛው እንደ ነበር ገልጸዋል። የተረፉት አርመኖች እ.አ.አ. በ 1930 የቤተ ክርስቲያናቸውን ቤተ ክሕነት ማእከል አንተሊያስ (Antelias) ወደምትባል የሌባኖን ከተማ አዛውረው እንደ ነበር ተገልጿል።

በኒው ዮርክ ታይምስ* እንደ ተገለጸው የ68 ዓመት እድሜው አቡነ አረም በቱርክ መንግሥት ላይ የተወሰደው ሕጋዊ እርምጃ ከ30 የሕግ ሊቆች ጋር በመመካከር መሆኑን አረጋግጠዋል። በተጨማሪም የአርመን ቤተ ክርስቲያን እስካሁን ያተኮረችው ቱርኮች በፈጸሙት የዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ ቢሆንም ባሁኑ ጊዜ ለአርመኖች ስለሚያስፈልገው ካሣ መጠየቅ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። ለዚህም ሒደት የመጀመሪያው የንብረት ካሣ ጥያቄ ከላይ በተጠቀሰው የቤተ ክርስቲያን ንብረት ላይ ሲሆን ለወደፊቱ በሌሎች በቱርኮች በወደሙና በተዘረፉ ቤተ ክርስቲያኖች እንዲሁም የግል ቤቶችና ንብረቶች ላይ የሚያተኩር መሆኑን ገልጸዋል።

*”Aram I…..said he had decided to proceed with a lawsuit after having consulted with 30 legal experts, including some from Turkey. While the church’s efforts to achieve an international acknowledgment of the genocide were important, “after 100 years, I thought it was high time that we put the emphasis on reparation,” he said.

ቱርኮች አርመኖች ላይ ስለ ፈጸሙት ወንጀልና ስለ ፍትሕ ትግሉ ውጤት፤

በአርመኖች መግለጫዎች በይፋ በታተተው መሠረት እ.አ.አ. በ1915 የኦቶማን ቱርኮች በአርመኖች ላይ በፈጸሙት የጦር ወንጀል 1.5 ሚሊዮን አርመኖች ተጨፍጭፈዋል፤ እጅግ ብዙ አርመኖችም ለስደት ተዳርገዋል። ከአርመኖቹ ስደተኞች ውስጥ 40 ቤተሰቦች በኢትዮጵያ ተስተናግደው እንደ ነበር የታወቀ ነው። ምንም እንኳ የቱርክ መንግሥት የወንጀል አኃዙን የተጋነነ ነው ቢልም ቱርኮች በአርመኖች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙ መሆኑን የአውሮፓ ምክር ቤትና የቫቲካኑ ቀዳማዊ ፖፕ ፍራንሲስ እውቅና ሰጥተውላቸው የአርመኖችን የ100 ዓመት የፍትሕ ትግል ፍሬያማ አድርገውላቸዋል።

ላለፉት 100 ዓመታት የአርመኖች የፍትሕ ትግል በቱርኮች አማካኝነት ስለ ተፈጸመባቸው የዘር ማጥፋት ወንጀል ዓለም አቀፍ እውቅና ለማስገኘት ብቻ ሲሆን አሁን ደግሞ፤ በአርመን ቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴ የተጀመረው የካሣ ጥያቄ ጉዳይ ተጀምሯል ማለት ነው። ይህ እንቅስቃሴም በተመሳሳይ ሁኔታ በፋሺሽቶች አማካኝነት ብዙ ቤተ ክርስቲያኖች ለወደሙባት ለኢትዮጵያ ምሳሌነት ያለበት ሒደት ነው።

በኒውዮርክ ታይምስ በተዘገበው መሠረት የቱርኩ ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት እስካሁን ድረስ የሰጠው መልስ የለም። ለማንኛውም ከፍርድ ቤቱ ተገቢው ምላሽ ካልተገኘ በታዋቂው የማክጊል ዩኒቨርሲቲ (McGill University) ፕሮፌሰር (መምሕር)ና ስለ ዘር ማጥፋት ወንጀል ጉዳይ የሕግ ሊቅ የሆኑት ፓያም አክሃቫን (Payam Akhavan) በአርመን ቤተ ክርስቲያን የቀረበውን ክስ የቱርኩ ፍርድ ቤት ውድቅ ካደረገው ጉዳዩን ወደ አውሮፓ ሰብአዊ መብት ፍርድ ቤትሊያቀርበው ማቀዱን ገልጿል። በተጨማሪም ሌሎች አርመናዊ ምሑራን ለሐገራቸው ስለሚያሰፈልገው ካሣ ጠለቅ ያለ ጥናት አከናውነው ሰፊ ትንተና ያሰራጩ መሆኑን እ.አ.አ. ሚያዚያ 14 ቀን 2015 በወጣው የኒውዮርክ ታይምስ ተዘግቧል።

በኢትዮጵያ ላይ ስለ ተፈጸመው የጦር ወንጀል የፍትሕ ትግል፤

እንደሚታወቀው፤ ፋሺሽት ኢጣልያ፤ በቫቲካን ያልተቆጠበ ድጋፍ፤ እ.አ.አ. በ1935-41 አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ከመጨፍጨፋቸው በላይ፤ 2000 ቤተ ክርስቲያኖችን፤ 250 000 ቤቶችንና 14 ሚሊዮን እንስሳትን አውድመዋል። እንዲሁም መጠነ ሰፊ ንብረቶችን ዘርፈዋል። ከነዚሁ ውስጥ አሁንም ከ500 በላይ የሚቆጠሩ በቫቲካን ይዞታ የሚገኙ ሰነዶች አሉ። “ፀሀይ” የተሰኘች አውሮፕላንም በኢጣልያ አየር ኃይል ቤተ መዘክር ትገኛለች። ሌላም ብዙ የተዘረፈ ንብረት እንዳለ የታወቀ ነው።

ለተፈጸመባት አሰቃቂ ወንጀልና ዝርፊያ ኢትዮጵያ እስካሁን ያገኘችው ኢምንት የሆነ ቆቃ ግድብ የተሠራበት $25 ሚሊዮን እና በቅርቡ ከሮም፤ ኢጣልያ የተመለሰው የአክሱም ኃውልት ነው። ኢጣልያ ለሊቢያ $5 ቢሊዮን፤ ለዩጉዝላቪያ $125 ሚሊዮን፤ ለግሪክ ሐገር $105 ሚሊዮን እና ለሶቪየት ዩኒየን $100 ሚሊዮን ከከፈለችው ካሣ ጋር ሲወዳደር፤ በተለይ በነዚህ ሐገሮች ላይ የፈጸመችው ወንጀል ኢትዮጵያ ላይ ካከናወነችው ጋር ሲነጻጸር ለኢትዮጵያ ተገቢ የሆነ ካሣ እንደሚገባት በፍትሕ ለሚያምን ሁሉ ግልጽ ነው። እጅግ ብዙ ንብረት የወደመባትና የተዘረፈባት እንዲሁም እነአቡነ ጴጥሮስና አቡነ ሚካኤል በተጨማሪም በደብረ ሊባኖስ ገዳም ከ2000 በላይ መነኮሳትና ምእመናን፤ ሌሎችም የተሰዉባት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ያገኘችው ካሣ የለም።

በኢትዮጵያ ላይ ለደረሰው የጦር ወንጀል በመከናወን ላይ ያለው ትግል ከኢትዮጵያ አርበኞች ማሕበር የተሰማው አቤቱታና የዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ – የኢትዮጵያ ጉዳይ (Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause)  (www.globalallianceforethiopia.org) የተሰኘው ተቋም በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር በመተባበር በመፈጸም ላይ ያለው እንቅስቃሴ ነው። ይህ ድርጅት እየተንቀሰቀሰባቸው ያሉት መሠረታዊ ዓላማዎችም የሚከተሉት ናቸው፤

(ሀ) የኢጣልያ መንግሥት ተገበዊን ካሣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲከፍል፤

(ለ) ከኢትዮጵያ የተዘረፉት በኢጣልያ መንግሥትና በቫቲካን ይዞታዎች የሚገኙት ንብረቶች ለኢትዮጵያ እንዲመለሱ፤

(ሐ) ቫቲካን ፋሺሽቶችን በመደገፏ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ፤

(መ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመውን የፋሺሽት ጦር ወንጀል እንዲመዘግብ፤ እና

(ሠ) ለፋሺሽቱ ወንጀለኛ ለሮዶልፎ ግራዚያኒ በኢጣልያ፤ አፊሌ ከተማ በቅርቡ የተሠራው መታሰቢያ እንዲወገድ።

ከላይ የተጠቀሱትን ዓላማዎች ለማሳካት ድርጅቱ ለሚመለከታቸው ሁሉ፤ ማለትም፤ ለኢጣልያ መንግሥት፤ ለቫቲካን፤ ለአውሮፓ አንድነት ድርጀት፤ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት፤ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፤ እንዲሁም ለኢትዮጵያና ለአሜሪካ መንግሥቶች በተጨማሪም ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና ለዓለም ቤተ ክርስቲያኖች ምክር ቤት የአቤቱታ ደብዳቤዎች አቅርቧል።

በተጨማሪም፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሻለ ግንዛቤና ድጋፍ እንዲገኝ 30 ከተሞች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የኢጣልያ ፋሺሽቶች በሶስት ቀኖች ብቻ አዲስ አበባ 30 000 ኢትዮጵያውያንን የጨፈጨፉበትን የየካቲት 12ን 3 ዝክረ በዓል ምክንያት በማድረግ በጸሎት፤ በጉባኤዎች እና/ወይም በሰላማዊ ሰልፎች እንዲሳተፉ ክፍተኛ ጥረት አድርጓል። በዚህ ምክንያት ከተገኙት ተጨባጭ ውጤቶች መሀል፤ (ሀ) በቅርቡ በኢጣልያ፤ የላዚዮ አውራጃ ምክር ቤት የግራዚያኒ ኃውልት ስያሜ እንዲወገድ ያስተላለፈው ውሳኔ፤ (ለ) በኢትዮጵያ የካቶሊክ ካርዲናል ከሆኑት ከአቡነ ብርሃነየሱስ የተሰጠው ቀና መልስ፤ (ሐ)የአውሮፓ አንድነት ምክር ቤት ጉዳዩን የሚመለከተው መሆኑን በመግለጽ የሰጠው መልስ፤ እና (መ)በድርጅቱ ድረ- ገጽ (www.globalallianceforethiopia.org) ላይ የሚገኘው ቫቲካን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ የሚያመለክተው በ4500 ሰዎች የተፈረመው አቤቱታ ሊጠቀሱ የሚገባቸው ናቸው።

እንዲሁም ለኢትዮጵያ ስለሚያስፈልገው ፍትሕ በበለጠ ጥልቀት ግንዛቤ እንዲገኝ ድርጅቱ በቅርቡ የሚከናወን አንድ ዓለም አቀፍ ጉባኤ እያዘጋጀ ነው።

ከላይ የተጠቀሱት ጥረቶች የሚያበረታቱ ቢሆኑም፤ የፍትሕ ትግሉ የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የታወቀ ነው። ለዚህም ተግባር የሚመለከታቸው መንግሥታዊ የሆኑና ያልሆኑ ድርጅቶች መንፈሳዊዎቹም ጭምር፤ በዓለም ዙሪያ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የአርመን ቤተ ክርስቲያንን ምሳሌነት በመመልከት ለሐገር ክብርና ፍትሕ ጠንክረን የዘለቄታ ትግል ማከናወን ይጠበቅብናል።

ቸሩ የኢትዮጵያ አምላክ ይርዳን።

 

 

The post የአርመን ቤተ ክርስቲያን ተምሳሌታዊ የፍትሕ ትግልና የኢትዮጵያ ጉዳይ – ኪዳኔ ዓለማየሁ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

አርበኞች ግንቦት 7ን ጨምሮ በኤርትራ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ታጋዮች –ሊያዩት የሚገባ ቭዲዮ

≫ Next: Hiber Radio: ምርጫ 97ን ተከትሎ ሰኔ አንድ በአጋዚ ጥይት የተገደሉ ሰማዕታት ሊታሰቡ መሆኑ፣ የሰማዕታቱ ቤተሰቦች በጋራ እንዳይዘክሩ ማስፈራሪያ መኖሩ፣አሜሪካ አይ.ሲ.ስን በመሳሪያ ረድታለች የሚል ወቀሳ መቅረቡ፣ አሸባሪው ቡድን በሊቢያ ሁለት ኤርትራውያንን በጭካኔ ገደለ ከታፈኑት ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሳይሆኑ አይቀርም መባሉ፣ኢትዮጵያ ፍትህ በማዛባት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጠቃሽ መሆኗን ሪፖርት ማመልከቱ፣ ቃለ መጠይቅ ከምርጫ 97 የሰማዕታት ቤተሰቦች ሰብሳቢ ጋር እና ሌሎችም
$
0
0

በኢትዮጵያ ጫና ላይ ቁጭ ብሎ ሕዝቡን በማተራመስ በመግዛት ላይ ያለውን የሕወሓት መንግስት ለመጣል ብረት አንስተው ትግል ላይ ያሉት ኢትዮጵያውያን ታጋዮች በኤርትራ በልምምድ ላይ ያሉበትን ፎቶዎች ቴዎድሮስ መይሳው በቭዲዮ በሙዚቃ አቀናብሮ ለቆታል:: የአርበኞች ግንቦት 7 ወታደሮችን ጨምሮ ሌሎች በአስመራ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ታጋዮችን በአንድ ላይ አቀናብሮታል – ይህንን ስሜት ቀስቃሽ ቭዲዮ ይታደሙት:: ያካፍሉት::
Arbegnoch Ginbot 7

The post አርበኞች ግንቦት 7ን ጨምሮ በኤርትራ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ታጋዮች – ሊያዩት የሚገባ ቭዲዮ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

Hiber Radio: ምርጫ 97ን ተከትሎ ሰኔ አንድ በአጋዚ ጥይት የተገደሉ ሰማዕታት ሊታሰቡ መሆኑ፣ የሰማዕታቱ ቤተሰቦች በጋራ እንዳይዘክሩ ማስፈራሪያ መኖሩ፣አሜሪካ አይ.ሲ.ስን በመሳሪያ ረድታለች የሚል ወቀሳ መቅረቡ፣ አሸባሪው ቡድን በሊቢያ ሁለት ኤርትራውያንን በጭካኔ ገደለ ከታፈኑት ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሳይሆኑ አይቀርም መባሉ፣ኢትዮጵያ ፍትህ በማዛባት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጠቃሽ መሆኗን ሪፖርት ማመልከቱ፣ ቃለ መጠይቅ ከምርጫ 97 የሰማዕታት ቤተሰቦች ሰብሳቢ ጋር እና ሌሎችም

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ የግንቦት 30 ቀን 2007 ፕሮግራም

አቶ ኢዮብ ከበደ የምርጫ 97 ሰማዕታት ቤተሰቦች ኮሚቴ ሰብሳቢ ለህብር ሬዲዮ ሰኔ 1 ቀን 1997 በአጋዚ ጦር ወንድሙን ጨምሮ በርካታ ንጹሃን የተገደሉበትን ቀን በተመለከተ ካደረግንለት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)

ወይዘሮ ፀዳለ እጅጉ የቀድሞ የኢህአፓ ታጋይ በተቃዋሚው ጎራ ስላሉ ተቃዋሚን መቃወምና ተራ ስም ማጥፋትን እንደ ትግል የሚቆጥሩትን አንዳንድ የስም ተቃዋሚዎች ሁኔታ በተመለከተ አነጋግረናቸው ከሰጡን ሰፋ ያለ ማብራሪያ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

አቶ ለገሰ ወልደሃና ከመኢአድ በምርጫ ቦርድ ህገወጥ ውሳኔ የተባረረው ህጋዊው አመራር ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ጋር ያደረግነው ቃለ መጠይቅ (ሙሉውን ያዳምጡት)

በሊቢያ በአሸባሪው ቡድን የታፈኑ ኤርትራዊያንና ኢትዮጵያዊያን እጣ ፈንታ ምን ይሆን? (ልዩ ዘገባ)

የፊፋው ፕሬዝዳንት ላይ ኤፍ. ቢ. አይ የሙስና ምርመራ ጀምሮ ይሆን? ታዋቂ የቀድሞ ተጫዋቾች እና የስፖርት ባለስልጣናት ፊፋን ስላተራመሰው የሙስና ቅሌት እየሰጡት ያለው አስተያየት ( ልዩ ዘገባ )

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የምርጫ 97 ሰኔ 1 ቀን ሰማዕታት አስረኛ ዓመት በአዲስ አበባ ይዘከራል

ሰማያዊ ፓርቲም ጥሪ አቅርቧል ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የህግ የበላይነት ከሌለባቸውና የፍትህ ስርዓት ከተዛባባቸው አገሮች በስተመጨረሻ ላይ መገኘቷን ሪፓርት አመለከተ

አሸባሪው የአይሲስ ቡድን ሁለት ኤርትራዊያን ስደተኞችን በዘግናኝ ሁኔታ መግደሉ ተዘገበ

አሜሪካ ለአሸባሪው ቡድን በተዘዋዋሪ የጦር መሳሪያ አቀብላለች ተብላ ተወነጀለች

ኬኒያ ከኢትዮጵያ ለምትወስደው የኤሌክትሪክ ሐይል በዜጎቿ እንቅፋት ገጠመኝ ስትል አማረረች

ዜጎች የሚደርስባቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በፍ/ቤት እንኳ መግለጽ ተከለከሉ

በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ለፍርድ ቤት ያለውን ንቀት በይፋ አሳየ የሚሉና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በቀጥታ በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽና በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው።

The post Hiber Radio: ምርጫ 97ን ተከትሎ ሰኔ አንድ በአጋዚ ጥይት የተገደሉ ሰማዕታት ሊታሰቡ መሆኑ፣ የሰማዕታቱ ቤተሰቦች በጋራ እንዳይዘክሩ ማስፈራሪያ መኖሩ፣አሜሪካ አይ.ሲ.ስን በመሳሪያ ረድታለች የሚል ወቀሳ መቅረቡ፣ አሸባሪው ቡድን በሊቢያ ሁለት ኤርትራውያንን በጭካኔ ገደለ ከታፈኑት ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሳይሆኑ አይቀርም መባሉ፣ኢትዮጵያ ፍትህ በማዛባት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጠቃሽ መሆኗን ሪፖርት ማመልከቱ፣ ቃለ መጠይቅ ከምርጫ 97 የሰማዕታት ቤተሰቦች ሰብሳቢ ጋር እና ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ኣብራሃ ደስታ –ከቅሊንጦ…!

≪ Previous: Hiber Radio: ምርጫ 97ን ተከትሎ ሰኔ አንድ በአጋዚ ጥይት የተገደሉ ሰማዕታት ሊታሰቡ መሆኑ፣ የሰማዕታቱ ቤተሰቦች በጋራ እንዳይዘክሩ ማስፈራሪያ መኖሩ፣አሜሪካ አይ.ሲ.ስን በመሳሪያ ረድታለች የሚል ወቀሳ መቅረቡ፣ አሸባሪው ቡድን በሊቢያ ሁለት ኤርትራውያንን በጭካኔ ገደለ ከታፈኑት ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሳይሆኑ አይቀርም መባሉ፣ኢትዮጵያ ፍትህ በማዛባት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጠቃሽ መሆኗን ሪፖርት ማመልከቱ፣ ቃለ መጠይቅ ከምርጫ 97 የሰማዕታት ቤተሰቦች ሰብሳቢ ጋር እና ሌሎችም
$
0
0

Abrha Destaህወሓት ከኒኩለር በላይ የሚያስፈራት ብእርን እንደ ጉድ የሚያናግራት ጀግናው ኣብራሃ ደስታ በህወሓት ከታሰረ ወራቶች ኣለፉ።
በ”ሽብር” ክስ ተከሶ ቅሊንጦ ወህኒ ቤት የሚገኘው የዘመናችን ጀግና ኣብራሃ ደስታ እስር ቤት ሁኖም ህወሓቶችን እያስጨነቃቸው ይገኛል። ምክንያቱም እነሱ እንዳሰቡት የኢትዮዽያ ህዝብ “ኣብራሃ ኣሸባሪ ነው” ብሎ የሚያምን ሁኖ ኣላገኙትም። ባይሆን ሃሳብህን በነፃነት የመግለፅ መብት በኣግባቡ ከተጠቀምክበት እንደሚያሳስር ሊረዳ ችለዋል።
ይህ ኪሳራ የተረዱት ህወሓቶች ኣንድ መላ ይዘው ወደ ኣብራሃ ደስታ ሂደው “..ኣብራሃ ደስታ ኣሁኑኑ ከእስር ብንፈታህ መፃፍህን ታቋርጣለህንን…? የሚል የጭንቅ ጥያቄ ጠየቁት።
ጀግናው የመለሰው መልስ “…እንኳን ከእስር ተለቂቄ ላፕቶፔ ብታቀብለኝ እዚሁም እፅፍ ነበር…” በማለት ቅስማቸው ስብርብር ኣድርጎ ጣለው።
እንደነሱ ግምት ይሄ ሁሉ ግፍ እያወረድንበት እያለን ግፉን መሸከም ኣቅቶት “..ልቀቁኝ እንጂ ካሁን በሗላ እጄ ከእስኪርቢቶና ከላፕቶፕ ጋር ኣላገኛኝም..” እንዲላቸው ነበር።
ጀግናው ኣብራሃ ደስታ ያኔ ስንት የሚፃፍ ሃሳብ ፍንትው ብሎ ታይቶት ኖሮ ይሆናል…!
ኣብራሃ ደስታ ገዢዎች ሲረግጡት የሚረገጥ ቄጠማ(ጉዝጓዝ) ኣይደለም ሲረግጡት መለሶ የሚወኣጋ ጀግና ነው።
ነፃነታችን በእጃችን ነው..!
IT IS SO..!

The post ኣብራሃ ደስታ – ከቅሊንጦ…! appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live