Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የሰላማዊ ሰልፍ 04.06.2015 Munich G7 ኃይለማሪያም ደሳለኝ

$
0
0

ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ

ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ 04.06.2015 Munich  ሰአት 13:00 

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካህደውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣ፣ የዲሞክራሲ እና የነጻ ፕረስ መታፈን፣ ኢንዲሁም የምርጫ  ማጭበርበር በመቃወም ሁሉም  ለኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት እና የ ዲሞክራሲ እንዲሁም የሰላም ተቆርቋሪ የሆናችሁ ሁሉ ኑ በአንድ ላይ ድምጻችንን እናሰማ  

የሰላማዊ ሰልፍ አላማ

በጀርመን የአመቱ ፕሬዚደንትነት አዘጋጅነትና ጋባዥነት በዚህ አመት 2015 06.-07.June 2015 በ ሙኒክ ከተማ ጀርመን በሚካህደው የ G 7 ስብሰባ ላይ በአፍሪካ ዉስጥ ጋዘጠኞችን በብዛት በማሰር  እና ምርጫ ማጭበርበር እንዲሁም በከፍተኛ ሰብአዊ መብት መጣስ የሚከሰሰውን ኢንዲሁም በከፍተኛ ደረጃ ስደተኛ አመንጪ የሆነዉን የኢትዮጵያን አምባገነን ስርአት ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝን መገኘት አጋጣሚ በማድረግ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተዘጋጅቶዋል

የሰላማዊ ሰልፍ አላማ

፩፣ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገውን የሰብአዊ መብት ረገጣ እንዲቆም

፪፣በኢትዮጵያ ውስጥ የታሰሩት የፖሊቲካ  እስረኞች በጠቅላላ ባስቸኩዋይ  እንዲፈቱ

፫፣የጀርመን መንግስት እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት እና የ G7 አገሮች ሁሉንም አምባገነን በእኩል አይን እንዲይዩ ለቆሙለት በቆሙበት ለሚመሰክሩለት ደሞክራሲ እና ሰብአዊ መብት ለኢትዮጵያ ሲሆን ፊታቸውን ማዞር የሚያቆሙበት ጊዜ መሆኑን ተረድተው በኢትዮጵያ ውስጥ በስልጣን ላይ ላለው አምባገነን ስርአት የሚሰጡትን ድጋፍ እንዲያቆሙ እና በአንጻሩ ለዴሞክራሲ ለህግ የበላይነት ለስብአዊ መብት መከበር ድጋፋቸውን እንዲሰጡ እንጠይቃለን ፦፦፦

የጀርመን እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት እና የ ጂ፯ አገሮች መራጭ ዜጎች መንግስቶቻቸው     በከፍተኛ ደረጃ ሰብአዊ መብትን ከሚረግጥ ፣የዲሞክራሲን እና የነጻ ፕረስን አፍኖ ከሚያጠፋ፣ለህግ የበላይነት ለማይገዛው በኢትዮጵያ ውስጥ በስልጣን ላይ ላለው አምባገነን ስርአት የሚሰጡትን ድጋፍ
እናጋልጣለን

 

 

 

ሰልፉ የሚጀምርበት ሰአት 13:00

ሰልፉ የሚጀምርበት ቦታ Stachus (Karlsplatz), München 

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ

 

Contact Tel:. +49 160 4357232
E-mail:menschenrecht-ethiopia@hotmail.de

 

220px-2379_-_München_-_Residenz

 

The post የሰላማዊ ሰልፍ 04.06.2015 Munich G7 ኃይለማሪያም ደሳለኝ appeared first on Zehabesha Amharic.


ኦ! –ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

02.05.2015 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

ይድረስ ለፓን አፍሪካኒስቱ ወገኔ ለተከበሩ አቶ ቴወድሮስ ዳኜ –

„እንዳላፍር ልቤ በሥርዓትህ የቀና ይሁን“ / መዝሙር ምዕ. 118 ቁ. 80/

እንዳያመም ጥራው እንዳይበላም ግፋው“

Cry-ethiopiaበቅድሚ እንዴት ሰነበቱ። ለአፍሪካውያን የስደትና የሰቆቃ መከራ የበኩለዎትን ድርሻ ለመወጣት በማድረግ ላይ ያሉትን ዬሰብዕዊነት  ጥረት አብዝቼ አከብራለሁ፤ ኢምንት ብሆንም አመሰግናለሁ። ከመልካም ነገር ፍቅርና ተስፋ መኖርና መሆን አሉና።

እኔ ብዙን ጊዜ የኢትዮጵያ ሙሑራን በሰብዕዊ መብት እረገጣ፤ በዘበጠ አስተዳደር ጉዳይ ላይ ያላቸው ተስትፎ አናሳ ነው፤ የበቃም አይደለም በማለት ወቀሳን ከወገኖቼ ሳዳምጥ የአያያዝ አቅም ከሙሁራዊ ሥነምግባር ውስጠት ጋር የማጣጣም ብቃት አንሶን ሊሆን ይችላል የሚል ዕድምታ ስለነበረኝ ምንም ብዬ አላውቅም። ዛሬ ግን ተናጠሉን ሙሁርነት ብቻ ሳይሆን እንደ ቀደምቶቹ ኢትዮ – አፍሪካውያን ዕንቁዎች መስመሩን ለመከተል መቁረጥ ብቻ ሳይሆን ተግባር ላይ በተገኙት ወንድሜ ላይ ቅሬታዬን ከዕንባዬ ጋር ልልክለው እንሆ ወደድኩኝ። ሃዘኔ የምር ልቅሶዬም ከቁስለት – የተቀዳ ነው።

ውድና የተከበሩ ኢትዮ አፍሪካዊው አቶ ቴወድርስ ዳኜ – ጎሰኝነት ወይንም መንደርተኝነት ያልተመጣጠነ የአስተሳሰብ እድገት ወይንም የአስተሳሰብ ድህነት ጽንስ ነው። እድገቱም ከቤተሰብ ቀጥሎ ያለ ስለሆነ ሁለመናው በእንጭጭ ዕጭ ተፈጥሮው ላይ ስለሚወሰን አህጉራዊ ኃላፊነትን በተቆርቋሪነት ላበሰለ ወገን፤ በወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ አሳሯን በመክፈል ላይ የምትገኘው ልዕልት ኢትዮጵያና ልጆቿ ጉዳይ ከማንም በላይ ከፍ ካለው አህጉራዊ መንፈስ ላለው አብነት እኩያው አይደለም። ምስክርነት ለመሰጠትም አቻው አይደለም። … በማናቸውም የወያኔ ሃርነት የጎሳ ሶሻሊስታዊ ፖሊሲ ሰብዕነትን በይ  – አህጉራዊው አምክንዮ ጋር ለመወዳጀት እድገቱም አይፈቅድም። አህጉርና -ጎጥ?! እንዴት ግን ግጥመወትም ቅኔዎትም መሆን ይቻል?! ለክብሩነተዎት የወያኔ ሃርነት የጎጥ ማንፌስቶ መንፈስ አይመጥነዎትም – በፍጹም እንደ እኔ። ልዩው ጸጋዎት ሊጸዬፈው ይገባል መንደር ላይ የተተከለው የመርዝ ማንፌስቶ። ክብሩነተዎት ላቅ ብለው – ለግለግ ብለው – አፍሪካ ላይ ያሉ ሲሆን፤ ዬኢትዮጵያ ዘረኛ ጸረ ሰብዕ፤ ፀረ አብሮነት፤ ጸረ ፍቅር፤ ጸረ ታሪክ፤ ጸረ ትውፊት፤ ጸረ ሰንደቅዓላማ አስተዳደር ደግሞ ደረጃው አሰር ውሃ ላይ ስለሆነ ቁጭ ብሎ ለመነጋገር እንኳን ዳገት ነው። እንኳንስ ጠበቃ በመሆን ሸማ ማልበስ  ይቅርና ….

የተከበሩ ፓን አፍሪካኒስቱና የአፍሪካ ህይወት ከፍተኛ ባለሙያ ሆይ! – የቅድመ ምርጫ መሰናዶ ዕይታዎትን ቃለ ምልልስ አዳመጥኩት – እጅግ በተመስጦ። እንደሚመለከቱት ንዑስ እርእሱን ሲያዩት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ጋር መስመረኛ እንደሚሆን – አስባለሁ። የብሄራዊ ዜግነት መፍጫ፣ የማንነት መቅጫ የሆነው የወያኔ ሃርነት ትግራይ የምርጫ ልጋጫንም ንዑስ እርእሱ አሳምሮ ይገልጠዋል ብዬም አስባለሁ። ስለዚህ ንዑስ እርሱ ድርብ ሚናን ተሸክሞ ነው ጉዳዩን አህዱ የሚለው። ከኢትዮጵያ ሀገራችን በስተቀር አፍሪካ ሀገሮችን በሚመለከት ባለበዎት የሥራ ኃለፊነት ምክንያት በቅርበት እንደሚከታተሉት ብቻ ሳይሆን የሰጡት አስተያዬትም የውጭ የዜና አውዶች በተለይም „ሰው“ የሚለውን የሁለመና ፍጥረት ልዑቅ ጸጋ እንደሚያከብሩት ወገኖችና የሚዲያ አውታሮች ከሚሰጡት ጋር መሳ – ለመሳ ስለሆነ ውስጥወት ስላደረጉት አልሄድበትም። ትክክል – ነውና።

ገለፃዎትን ሁለመናዬን በፍቅር ሰጥቼ ነበር የተከታተልኩት። እንጃ „ክርስቶስ ለሥጋው አደላ“ ሆኖበዎት እንደሆነ አላውቅም  የእትብትዎትን፣ የደመዎትን ጉዳይ በሚመለከት የሰጡት አስተያየት ግን እጅግ የሚያሳዝን ድርብ በደል ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ድርብ በደል የሚያደርገው እንደ አፍሪካውያን ስደተኛ ተቆርቋሪነተዎትና የፋውንዴሽን መሥራችነተዎት፤ እንዳ ዓለምአቀፉ የማህበረሰብ ድምጽ ሚዛን ዕይታ ዳኛነተዎትና ኃላፊነዎት በሳል ተመክሮ፤ እንደ የግል ሥያሜ መጠሪያዎት ሚስጢራዊነት ወይንም የመንፈስ ቅዱስ መንፈስ ጠብታ ረቂቅነት „ሥምን መላዕክ ያወጣዋል“ እንዲሉ „ቴወድሮስ ዳኜ“  በእናት ሀገራችን በኢትዮጵያ የወያኔ ሃርነት ትግራይ የ2007 ምርጫን አስመልክቶ ብቻም ሳይሆን፤ የሰብዕዊ መብት ረገጣ፣ የሌሎችን የዘመናዊ ባርነት ጨካኝ አስተዳድር ያልሰለጠነ – እምቅ የበቀልና የቋሳ ማወራራጀ በሆነው ወገነዎት ላይ የደረሰው መከራን በሚመለከት የአፍሪካ ሀገሮችን ያህል ተቆርቋሪነት ወይንም ቅርበት ወይንም የእኔነት መንፈስ በቃለምልልሱ እንብዛም አላደመጥኩም። ቃናው ባዕዳዊ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ስለዚህም ከፍቶኛል። ከሁሉ በላይ ሄሮድስ መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ ለማለት ይጸዬፉት ነበር። „ሀገሪቱ፣ እዛ በነበርኩበት ጊዜ እያሉ“ የገለጹት በቀጥታ መጤ እንደራሴ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። በተጨማሪም „ጠንካራ ተፎካካሪ የለንም“ ያሉትን የሄሮድስ መለስ ዜናዊ የትበት ቅላጼ እርስዎ በመድገም „እነሱ ያቀረቡት ቪዥን የተሻለ የሌላቸው፤ በመጨቃጨቅ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉ፤ መዋቅራቸው ሥር ሰደድ ያልሆነ“ በማለት በሄሮድስ መለስ አቃላይ – አጣጣይ – አገላላጽ ሥር የወደቀ የመንፈስ ተጠቂ የሆነ አገላለጸዎት ከፈኝ ከምል ከረፋኝ ብል ይገልጠኛል። ከእርስዎ በፍጹም ሁኔታ የማልጠበቅውስለነበር

በቃለ ምልልሱ ላይ መንፈሱ ቁስል ያለው ጋዜጠኛ፤ ጋዜጠኛ ሰለሞን አባተ ክቡርነተዎት እዬተናገሩ እሱ ማህል ላይ የገባበትን እንዲሁም ክቡርነተዎት ድምጸዎትን ቀነስ አድርገው የገለጹት ብቻም ሳይሆን፤ ዝንቅ በሆነው የሁለት ቋንቋ ምላሽዎት የልተደመጡኝ ጥቂት ነገሮች ሲቀሩ በስተቀር መንፈሱን ሙሉውን አቅርቤዋለሁ። ለነገሩ ያልተደመጠኝ ከምፈልገው ነጥብ ላይ ባለመሆኑ እምብዛም አስፈላጊ አልነበረም። የምፈልጋቸውን በቅጡ ለማድመጥ ስለቻልኩኝ። ያው በዝንቁ እንደወረደ እንግሊዘኛውንም አማርኛውንም –  በአማርኛ ጽፌዋለሁ። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/41765 ታሪክ ነውና ትውልዱ ታሪኩን ማድመጥ – መተርጎም – ማመሳጠር ብቻም ሳይሆን ሚዚናኑን የጠበቀ ግንዛቤ ይኖረው ዘንድ በጥቅሉ ሲያሰፍልግም በተን እያደርኩኝ አቀርበዋለሁ።

ውስጡን ከብዙኃን ዕንባ ጋር ያገባው የተግባር ታላቄ ጋዜጠኛ ሰለሞን አባተ እጅግ እርቀው ከተመሰጡበት ከሌሎች አፍሪካዊ ሀገሮች ውስጣዊ የውስጥነት ጉዳይ መለስ አደረገወትና —- የአፍሪካ ጉዳይ ስፔሻሊስት፤ በተመክሮ የበሰለ ብቃትን እንዲህ ነበር ዬጠዬቀዎት ….

„ …. ወደ ኢትዮጵያ መለስ አልና ለመሆኑ ቴድ በኢትዮጵያ የዛሬ 20 ዓመትና ከዛ በፊት ከነበረው ሁኔታ የዲሞክራሲያዊና የሰብዕዊ መብቶች አያያዝ ፓለቲካው የተሻለ ነው ብለው ያስባሉ አልኳቸው?“ አለ ጋዜጠኛ ሰለሞን አበተ።

„ ይመስለኛል እኔ አክሮስ ኢትዮጵያ ስመለከተው አንዳንድ የነበሩ ጦርነቶች ቆመዋል። ዌስተርን ኢትዮጵያም ቢሆን ወደ ኡጋዴንም በሚመለከት መንግሥት ፍላጎቱን አሳይቷል። ተቀምጠው ለመነጋገር እንደሚፈልጉ፤ ከኡጋዴ ናሽናል ሊቬሬሽን ፍሮንት ጋር፤  ሌላም ቦታ ብትመለከት ውስጥ ብትመለከት ስታቢሊቴ አለ። መንገድ ላይ ሄደህ መታሰር ነገር የለም። ሰው ሥራውን ይሠራል ትምህርቱንም ይማራል። ያ እንደ ፕሮግረስ ብዬ ነው የማዬው ኦፍ ኮርስ ሂዩማን ራይትስ ኦድቦኬት ኦር ተቃዋሚ ኃይሎች ሞር ኖሌጅ ይኖራቸዋል። ስለዚህ እና የእኔ አሰስመንት ከእነሱ አስሰምነት ጋር ሊለያይ ይችላል። ግን እኔ አዝ እንደ ኦርዘርቨር ስመለከተው ኦቨር ኦል ፒክቸሩ ደህና ነው ብዬ ነው የምመለከተው። ኢብን ኮንፒዬር 5 እና ከ7 ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ሞር ስቴብል ነው። እራሱ አሁን ለምሳሌ ስትመለከተው ትራንዝሽኑ ፕራይም ሚንስተር መለስ ከሞተ በኋላ ወደ አሁን ወደ አሉት ፕራይም ሚኒስተር ትራንዝሺኑ ፒስፉል ነበር።“ በማለት ካለወታደራዊ ጣልቃ ገብነት በሰላም ተከወነ እንደማለት፤ ቀጠሉ ፓን አፍሪካኒስቱ አቶ ቴወድሮስ ዳኜ „ፕሮግሬስና ማቹሪቲ ነው ያ አይ ቲንክ ቢ …. ማቹሪቲና ፕሮግሬስ ነው ብዬ ነው የምለው። ሌላም …. ምንድነው ኢትዮጵያ ኢሌክሽን ይደረጋል ኢፒዲአርፒ ዶሚነት ነው ግን ይህ ዶሚነት የሆነው አይ ቲንክ ዊ ሹድ ቢ ኬርፉል ኖት የትቱ ብሌሙ ብሎ  ኢንተርያሉ የፖለቲካ ስፔሱ ተዘግቷል ኦፖዚሽኑ ሃራስ ይደረጋል ብሎ መገምግም ትክክል አይደለም ብዬ ነው ። የዛሬም 5 ዓመትም እንዳልኩት ኮንግረሱ ጀስቲፋይድ ሲደረግ ተቃዋሚ ኃይሉ ሪስፖንስቢሊቴውን መውሰድ አለበት። ብዙዎቹ ውጪ ነው ያሉት። ብዙውንም ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት እርስ በርሳቸው ሲጣሉ ነው። እነሱ ያቀርቡት ቪዢን ለሀገሪቱ ብዙ የሚታይ የለም። ያዬሁትም የለም። እንዴት ተብሎ ነው ዜን ኢሌክሽን ሲደረግ ለማሸነፍ የሚቻለው የዛ ዊክነስ፤ የዛ ሪዛልት ሁልጊዜ መታዬት ያለበት ኖት ጀስት ተቃዋሚ ኃይሎች እንደሚሉት ሃራስ ተደርገናል  ኖ! ሃራስመንት ሊኖር ይችላል“ ጥርጣሬ … „ግን እነሱ ያደረጉት ነገርም ኮንትሪቢዩት አድርጓል አላደረግም ተብሎ መጠዬቅ አለበት?!  ….. የዛሬ 5 እና አመት አንዳልኩት አሁንም እላለሁ። ብዙውን ጊዜ የታለፈው እርስ በእርስ ሲጣሉና ማጆሪቲው ደግሞ ውጭ ነው ያሉት። ሃራስ አይደረጉም ለማለት ሳይሆን ኤግዛጁሬት ባናደርገው ጥሩ ነው።“

ቀጠለ ሳተናው ጋዜጠኛ ከውስጡና ከመንፈሱ ጋር ሆኖ „ እህም! ለመሆኑ ከዚህ አጠቃላይ ግምጋሜዎት ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ነፃ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማድረግ የሚያስችል የፖለቲካ ዝግጅነት ወይንም ተክለ ቁመና አላት ብለው ያምናሉ? ክቡሩ ፓን አፍሪካኒስት አቶ ቴውድሮስ ዳኜ ቀጠሉ „ ዌል! ስትራክቸሩ አለ። ኦርዘርበሮች ይኖራሉ። ሌትራል ኮሚሽኑ አለ የተቃዋሚ ኃይሎች ያላቸውን ኮንፕሌኖች አቅርበዋል፤ ፓብሊክ ላይ በቴሌቪዥን ላይም ወጥቷል፤ እና ፎር ሚ የለም ለማለት አንድ ሰው ኢቢደንስ አቅርቦ ኮንቢንስ እንዲያደርገኝ ያስፈልጋል“

ቀጠለ የመንፈስ ሃብቱን ያልተዘረፈው ሳታናው ጋዜጠኛ „ስለዚህ አለ?“ አቋረጡት ፓን አፍሪካኒስቱና ሙሁሩ ኢትዮጵያዊ „ ዴፊኔትሊ! አለ ግን ብትጠይቀኝ የተቃዋሚ ኃይሉ ጠንካራ ነው ወይ? ተቃሚዊ ሃይሉ ፓርላመንቱ ውስጥ ብዙ ፎከሶች ሊወስድ ይችላል መልሱ አይደለም! ነው። ተቃዋሚ ፓርቲ ነው አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን ጠቅላላ በሀገሪቱ ውስጥ የስትራክቸር ከሌለለህ ኮንፒት ለማደረግ ከባድ ነው ለማሸነፍም በጣም ከባድ እዬሆነ ነው የሚመጣው“

ቁስለቱና መግሉ

  • „ተቀምጠው ለመነጋገር እንደሚፈልጉ፤ ከኡጋዴ ናሽናል ሊቬሬሽን ፍሮንት ጋር ሌላም ቦታ ብትመለከት ውስጥ ብትመለከት ስታቢሊቴ አለ።“

ኡጋዴ ናሽናል ሊቨሬሽን ፍሮንት ብቻ ነውን ከፋኝ ያለውን? „ስቴብሊቲ“ የሚባለውስ በቀን 500 ዜጋ እዬታሰረ፤ ጋዜጠኞች፤ የፖለቲካ መሪዎች፤ የእስልምና ዕምነት ሃይማኖት መሪዎች፤ ጦማርያን በገፍ እስር ቤት መግባት ብቻ ሳይሆን እስር ቤት ውስጥ፤ መንገድ ላይ ኢ – ሰብዕዊ፤ ኢ – ሞራላዊ ግፍ እዬተፈጸመባቸው፤ ሚሊዮኖች ከመኖሪያቸው እዬተፈናቀሉ፤ ገበሬዎች ከመሬታቸው ተነቅለው መሬታቸው ለሌላ ሀገር ዲታ እዬተቸበቸበ፤ ህጻናት በገብያ እዬተቸረቸሩ፤ እህቶቾዎት ሞትን ጥበቃ ማታ ማታ መንገድ ላይ ተገትረው እያደሩ …. ይህ ሁሉ እምቅ የደም ዕንባ ይሆን „ስታብሊቲ“ የሉን? አይመስለዎት ቀን የሚጠብቅ ፈንጅ ያረገዘ የመረቀዘ የሙት ቀን የሚጠብቅ ነው።

  • „መንገድ ላይ ሄደህ ምትታሰር ነገር የለም“

መንገድ ላይ መታሰር አይደለም ሞት ነው ያለው። ዜጎች ወጥተው ለመመለስ እርግጠኛ የሚያደርጋቸው አንዳችም የኑሮ ዋስትና የላቸውም። ሃላፊነት ያለው አስተዳደርም የላቸውም። ገዳዮችም የወያኔ ሃርነት ትግራይ ልዩ የጥበቃ ኃይሎች በስውር ነው የሚፈጽሙት። ታዳጊ ወጣቶች ይደፈራሉ – ህክምና በሀገራቸው መሬት ተነፍገው ያልፋሉ፤ ይህ አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በመላ ኢትዮጵያ ከእውነት በላይ እውነት ነው። በዘራቸው ብቻ ተነጥለው በመኖሪያ ቀያቸው ግድያ ይፈጸምባቸዋል። አዲስ አበባ ከተማ ላይ ታክሲ ውስጥ ዶር. ስዩም አምሩ ተገድለዋል። እንዲሁም ሌሎቹ። ከዚህም በላይ አዋቂ ወንዶች ሳይቀሩ – ይደፈራሉ። ይህን አሰቃቂ ቃል ስጽፈው ይዘገንነኛል። ስለ ቃሉ ሎቱ ስብኃት፤

  • „ሰው ሥራውን ይሠራል ትምህርቱንም ይማራል።“

አዲስ አበባ ከተማ ብቻ የወደቀ ለቅሞ ለመብላት የተሰለፉ ሺ ልጆቻችን አሉ። ለዛውም ተርፎት የወደቀ የሚጥለው ዘመንተኛው ብቻ ነው። የሆነ ሆኖ የነገ ተስፋዎቻችን አዳራቸው ሆነ ውሏቸው፤ ትምህርት ቤታቸው መንገድ እና የመንገድ ሞራል ብቻ ያስተዳድራቸዋል። ይህ በነገ ማህበራዊ ህይወት ላይ የሚፈጥረው የሥነ ምግባር ቀውስ የኒኩሌዬር ቦንብ መርዝ ያህል ነው። መንፈሱን የተቀማ ምህበረሰብ የትውልደን ሃላፊነት እንዲወጣ አድርጎ ለመቅረጽ ግዙፍ ፈተና ነው። በዬክፍለሀገሩ ከተሞች ሆነ በገጠሮች ሊለምኑ ያፈሩ ሚሊዮኖች መጠለያ – ከፈን – የዕለት ጉርስ አጥተው ከሞት ጋር አፈር ለብሰው አፍር እዬሆኑ ነው። የሚነግሩን ኬክ ስለሚበሉት ይሆን? ወይንም ልጆቻቸውን ለመውለድ አሜሪካና አውሮፓ ለተሰናዳላጀቸው የትግራይ ሹሞች ቤተሰቦች ይሆንን? ይህ ነው ለእርሰዎ እድገት – ብልጽግና – መረጋጋት – ሥራና ትምህርት ብለው የሚያስቡት፤ እንደ አንድ ፓን አፍሪካኒስት …. ልጆቾዎት እርቃናቸውን ነው ያሉት በመንፈሰቸውም በአካላቸውም። ይህን ረመጥ አስፈንጥረው ከመወርውር ደመዎት ነውና ጠጋ አድርገው – ይቅመሱት። ኮሶ ነው ከርቤ ነው – ይመራል።

  • „ኦፍ ኮርስ ሂዩማን ራይትስ ኦድቦኬት ኦር ተቃዋሚ ኃይሎች ሞር ኖሌጅ ይኖራቸዋል። ስለዚህ እና የእኔ አሰስመንት ከእነሱ አስሰምነት ጋር ሊለያይ ይችላል። ግን እኔ አዝ እንደ ኦርዘርቨር ስመለከተው ኦቨር ኦል ፒክቸሩ ደህና ነው ብዬ ነው የምመለከተው።“

መለዬት ሳይሆን – አንገናኝም። ጉዳዬ ብለው አላዩትምና። እንጃ እንደ ወገነዎትም የማዬት ጠረን አላዬሁበትም – በገለፃዋት።  ክቡርነተዎት ከደላው ገነት ላይ እኛ ደግሞ ብትን አፈር ለማኝ ብናኞች ነን። ምን አልባት እርስዎ አራት ኪሎ ላይ ስለ አለው የፓርላማ መቀመጫ እንጂ፤ ፓርላማው ከተመሰረተ ጀምሮ እንኳንስ ሶስት ጊዜ አንድ ጊዜም ለማብላት ከድሃ ሀገሮች የመጨረሻ ተርታ ለጣላት ሀገር ተጠያቂነቱን ትልሙንና ውጤቱን፤ የግል ነጻነቱን ተቀምቶ ሁሉም ዜጋ በሥነ ልቦና ቀውስ ጥቃት ላይ መኖሩን ለእኔና ለእርስዎ እኩል ትርጉም ሊሰጠን አይችልም። ዬፓርላማው ወንበር አንድ ነፃ ጋዜጠኛ ሊያስፈታ ያልቻለ፤ የሃይማኖቱን መብት ለማሰከበር ያልቻለ፤ ወረቀት ላይ በሰፈረው የቁጥር ድርድር ብቻ የተሰለበ -እንደ ጉርሽጥ እንሶስላ የተሰለሰለ፤ እውክለዋለሁ ለሚለው ዜጋ ሳይሆን ለታላቋ ትግራይ ቅዠት የሚማስን ገበርም የሆነ፤ ልብስ – መጠለያ ፤ ዜጎቹ እንዲያገኙ ያላስከበረ፤ ኃላፊነት የማይሰማው፤ እራሱን ማድመጥ የተሳነው የኩበት ድርድር ላይ የከተመ ወንበር ነው። የዕንባ ዕለታዊ የምልዕቱ ትንፋሽ መሆኑ ይሆን „ደህና ነው“ ያሰኘዎትን? ወይንም እራህብ፤ መታረዝ ጎርፍ ላይ ፕላስቲክ አንጥፎ መተኛትን መተርጎም ስላቃተዎት? ወይንም ድልድይ ውስጥ መኖሬያቸው አድርገው ድሪቶን ለነፍሳቸው መጠግያ ያደረጉት ወገኖቻችን የክር እስትንፋስ፤ ሞት አፋፍ ላይ ያለው የሲቃ መቃሰት ድምጹ አልደረሰበዎት – ይሆን? ዕድለኛ ነዎት¡

  • „እራሱ አሁን ለምሳሌ ስትመለከተው ትራንዝሽኑ ፕራይም ሚንስተር መለስ ከሞተ በኋላ ወደ አሁን ወደ አሉት ፕራይም ሚኒስተር ትራንዝሺኑ ፒስፉል ነበር።“

እንደሚገባኝ እርስዎ ያሉት ወንበሩ ላይ ብቻ መሰለኝ። በሌላ በኩል ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የፈርኃ እግዚአብሄር ባለቤት ነው። ሌላው ቀርቶ „የድምጻችን ይሰማ“ የአርብ የድዋ በዓለት በሰሞናቱ ዝግ ነበሩ። ስለምን? ሞቱ አስደንጋጭ የሰማይ ቅጣትና ቅስፈት ስለነበረ። አይደለም ለኢትዮጵያ የኃያሉ እግዚአብሄር ቅጣት አብረዋቸው ከሄሮድስ መለስ ዜናዊ ጋር የተቀመጡትንም አላተረፈም ነበር። እጬጌዎና ዓፄውን በአንድ ሰሞን መቃብር ሲጠራቸው ይህን ፈንድሻ እዬረጨ አልተቀበለውም – የኢትዮጵያ ህዝብ። ኢትዮጵያና ህዝቧ ህግ ናቸውና። ስለዚህም በአርምሞ፤ በሱባኤ፤ በፆም፤ በጸሎትና በሰጊድ ነበር የታደመው። ደህና የዕድምታ ሚስጢር ተርጓሚ አልጻፈውም እንጂ ዓለምን ያስተማረ የሰማይ ቅጣትና ገድል፤ የ21ኛው ምዕተ ዓመት ታምርም ነበር። ልጅ እያለሁ ግብጽ ላይ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ታዬች የሚል ገድል ሰምቼ ነበር። የዛን ያህል ነበር የሰማዩ ቁጣና የአባታችን መዳህኒተአለም – ታምር። አንድ ታናሽ ብላቴና ሥሙን እንኳን በአግባቡ የማናውቀው የዕንባ ተቆርቋሪ ወታደር አስነሳ ፈጠሪ በጥበቡ = ታምሩንም በእሱ በመረጠው ብላቴና በዓለም አደባባይ ናኘው። ጎልያድ – በብላቴናው ቅዱስ ምሩቅ መንፈስ ተረታ። ስለዚህ እርስዎ የጠበቁት የወታደራዊ ፍጣጫ ሊኖር አልቻለም። የሰማዩን ሚስጢር መተርጎም የቻለው ህዝብ ሂደቱን የታምር አህዱ ብሎ ነበር የተመለከተው። ቅጣቱ  – ይበቃዋል ለሄሮድስ ብሎ ነው ጸጥ ብሎ በተደሞ ያሳለፉት። በሌላ በኩል ስማቸውን ለመጥራት ያልደፈሩትም ተተኪው ጠ/ሚር ቢሆን „በ5 የወያኔ ሃርነት ምርኩዞች መቆም አልሻም፤ ህሊናዬም መንፈሴም ብቁ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን፤ ከእኔ ጋር እንደሉ አውቃለሁ“ በማለት እርግጠኛ ቢሆኑና ምርኩዞቹን ቢሰብሩ ይፈንዳ ነበር። ነገር ግን የራሳቸው መንፈስ የሌላቸው፤ በጥገኝነት የሚማቅ የሙት መንፈስን የሙጥኝ ያሉት ጠ/ሚር ኃይለማርያ ደስአለኝ የተሰጣቸውን የእስር ጊዜ በጸጋ ስለተቀበሉ እንደ ትናንቱ ኢትዮጵያ በግፍና በዘረኝነት መተዳደሯን ስለወደዱ ብቻ ….. እንዳሉት እንደ እርስዎ ላለ ለሚያዳለ ሙሁር የመነሻ ድጋፍ መሆን ችሏል። ግን ውስጡ የአምክንዮ እምቅ ሚስጥራት ማዕድን ነው። በመደዴ የሚኬድበት አይደለም። …. ሌላው ቀርቶ የ2014 የዬመን፤ የሳውዲ ግፍ በኢትዮጵውያን ላይ በ2015 ዓይናችን በሌላ ባልተጠበቀ ታምር እንሆ ተገለጠ። መንፈስ ለተገለጠለት የሰማዩን ፕሮቶኮል ማንበብ ይቻለዋል። ግን እኛ ሰብዕና ሰብዕዊነትን ስለዋጥን ሃዘኑን እንደ ሃዘናችን እንጂ እንደ ቅንጦተኞች አለደረግነውም። የትኛውም ዓለም ህዝብ፤ ህጻነት ሰቆቃ ጉዳያችን ነውና።

  • „ምንድነው ኢትዮጵያ ኢሌክሽን ይደረጋል ኢፒዲአርፒ ዶሚነት ነው ግን ይህ ዶሚነት የሆነው አይ ቲንክ ዊ ሹድ ቢ ኬርፉል ኖት የትቱ ብሌሙ ብሎ ኢንተርያሉ የፖለቲካ ስፔሱ ተዘግቷል ኦፖዚሽኑ ሃራስ ይደረጋል ብሎ መገምግም ትክክል አይደለም ብዬ ነው ። የዛሬም 5 ዓመትም እንዳልኩት ኮንግረሱ ጀስቲፋይድ ሲደረግ ተቃዋሚ ኃይሉ ሪስፖንስቢሊቴውን መውሰድ አለበት። ብዙዎቹ ውጪ ነው ያሉት። ብዙውንም ጊዜያቸውን የሚአሳልፉት እርስ በርሳቸው ሲጣሉ ነው።“

አንድ ምሳሌ ብቻ ይበቃወታል። የመጀመሪያዋን ሴት የብሄራዊ ፓርቲ መሪን በድምጽ ብልጫ የመረጠው እጅግ መጠነ ሰፊ ዓላማና ራዕይ የነበረውን አንድነትን ሊቀመንበሩን ወያኔ አሰራት፤ ከ2010 ምርጫ በፊት ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳን መንፈሷን ቀጠቀጠ፤  ይተካታል ተብሎ የታሰበውን አቶ አንዷአለም አራጌንም ደገመ፤ እሱን ማን ሊተካው ሲባል ወጣት ሃብታሙ መጣ እሱንም ቀማ፤ አቶ ናትናኤል አቶ ዳንኤልም ማገር ነበሩ ለፓርቲው። ይህን የሚያደርገው አስርጎ በሚያስገባቸው ካድሬዎቹ ነው። አሁን እርስዎ ስትራክችር /መዋቅር/ የተሟላ ነው የሚሉት ምርጫ ኮሚሽን – አንድንት ያህል ብሄራዊ ፓርቲ ዘርፎ፣ አፍርሶ የራሱን መንፈስ – ተከለ። ድራማው ይሄ ነው። ከዚህ በላይ ከመታሰር፤ ሀገር ከመልቀቅ፤ ከመደፈር፤ ከመደብደብ፤ ከመዘረፍ በላይ ምኑን ይሆን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኃላፊነት አልወሰዱም የሚሉት? የሞትና የዕድሜ ልክ እስራት እኮ የተበዬነባቸው በእነሱ ላይ ነው። ባለፈም ከትውፊታችን ውጪ አዛውንት የፓርቲው መሪዎች አባት ወንዶች በግረ ሰዶም የተደፈሩበት …. ሂደት እ! ትንሽ አንደ ሰው —-

ይሄን እንደ ምሳሌ አነሳሁት እንጂ ሌሎችም እጅግ የከፋ ግፍ ተፈጽሞባቸዋል። አንድነት ብሄራዊ  ጉባኤውን ሲያካሂድ ያስተውሉ የብሄራዊ ጉባኤው ውክል አካላትን ያስተናገደው በሚያሳዝን ሁኔታ ነበር። የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጉባኤቸውን ለማካሄድ የሚያስችል የኢኮኖሚ የሎጅስቲክ አቅም የላቸውም። በልመና ገንዘብ ከአፈሙዝ ጋር እዬታገሉ።  የጉባውኤው ተሳታፊዎች በራሳቸው ወጪ መጥተው አዲስአባባ ላይ ልብሳቸውን አንጥፈው ነበር መሬት ላይ እያደሩ የተሳተፉት፤ የወያኔ ደግሞ ዝቅ ሲል ሂልተን ከፍ ሲል ሸራተን ነው። እዬራባት እንጀራ ጋግራ ልጇን በመቁንን ቀንታ በምትክፈለው ገንዘብ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ከላይ እስከታች ሠርግና ምላሹ ይሆኗል። ልጆቹ ውጪ ሄደው ይማራሉ፤ እረፍታቸውን ከፈለጉት ሀገር ያሳለፋሉ ወጪው በህዝብ ሃብት ይከወናል። ለማንኛውም ህጋዊ ፓርቲውና ዕጣውን በሚመለከት፤ ከህጋዊነቱ ተነስተው ህገዎጦቹ የወያኔ መዋቅሮች የበደሉትን በንጽጽር በዚህ ሊንክ ይመልከቱት … መስማማት ባንችል እንዳንረጋገም መቀራረብ ከኖረ …..

http://en.wikipedia.org/wiki/Unity_for_Democracy_and_Justice

http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com

  • „ማጆሪቲው ደግሞ ውጭ ነው“

ከቶ ሞት የተፈረደባቸው ገመድ ላይ ተንጠልጠለው ማዬትን ይሆን የናፈቀዎትን? ለእርቅና ለሰላም ጉባኤ ጠርቶ እኮ ካቴና ነው የጠበቃቸው። አይደለም ሌላው። ውጪ ስለሚኖሩት ደጋግመው በቁጭትና በእልህ ጠቅሰዋል – ለወያኔ ሃርነት ትግራይ በተቆርቋሪነት መቆመዎት የሚያሽልም ይመስለኛል። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ደንበር አልፎ ከሞት እስከ 18 ዓመት የተፈረደባቸው ወገኖቸዎት ለሞት መሄድ ነበረባቸውን? የሽብር ህጉስ ለማን የወጣ ይመስለዎታል? ተቃዋሚ ሃይሎችን በፍርሃት –  በሰቀቀን – በስጋት – መንፈሳቸውን በማሰር የማይናገሩ ድንቡልቡሎች ለማድረግ የታቀደ ነው። የላቲን አሜሪካ ሀገሮች ምርጫ ሲኖር ዜጎቻቸውን ያሳትፋሉ – በውጪ ሀገር። ይህ እኔ ካለሁበት ሲዊዘርላንድ በተደጋጋሚ ያዬሁት ሃቅ ነው። የእኛ ደግሞ በግል በነፍስ ወከፍ ከሚላኩብን ሰላዮች በላይ የሞት ፍርድም አለ፤ የእድሜ ልክ እስራትም ውጭ ሀገር በሚኖሩ የፖለቲካ መሪዎች፤ ጋዜጠኞች፤ የሰብዕዊ መብት ተሟጋቾች። ጥብቅና የቆሙለት ፋሽስት ሥርአት ቅምጥል ያለ፤ ልኩንም የሳተ ገደል ነው። ውጪ ባሉት ላይ እስራት ሞት ሲፈረድ – በሌሉበት ነው። ሀገር ቤት በሚኖሩ ቤተሰብ ላይ ምን ያህል መንፈስን እንደሚጎዳ – እንደሚቀድ፤ ሥጋት ላይ እንደሚጥል ቅርበዎት የሥነ ልቦና ሙሁር ካለ ይጠይቁና ይረዱ – በትህትና። ለነገሩ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እኮ የሥነ ልቦና ጥቃት ሰለባ እንዲሆን – ተበይኖበታል። አሁን አላውቅም እስከ 2006 እ.አ.አ ድረስ ኢትዮጵያ ከ10 የበለጡ የሥነ ልቡና ባለሙያች አልነበራትም፤ እርግጥ ከአፍሪካ የተሻለ ቁጥር ነበራት። የሆነ ሆኖ ስለማይገልጠው ነው እንጂ በዘመነ ወያኔ ሃርነት የጭንቀት በሽታ ተጠቂው ፍጥረት ብቻ ሳይሆን አዬሩም ጣሪያ ግድግዳውም ነው። ተጠያቂውም ደግሞ „ኤግዛጁሬት አናድርገው“ በማለት የሚያቆለባብሱት የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ነው።

ከዚህ ሌላ ውጪ ያሉት እኮ ምርጫ እንሳትፍ አላሉም …. መግቢያ ቢዛ የላቸውም። ስለዚህ ወቀሳው አግድም ላይ እንዲቀር ያደርገዋል። ትንትም ይዘፍንበታል። ወንድሟ በድንገት የመን ላይ ተጠልፎ የሄደባት ወገነዎት፤ ሥጋና ደምወት – በ24 ሰአት ሀገሯን ጥላ እንድተወጣ ተገዳለች፤ የነገ ፍሬዎች ከእናታቸው ጋር ሀገራቸውን ናፍቆተ – ኢትዮጵያን ለማዬት ቢሄዱ አባታቸው የኢሳት ጋዜጠኛ በመሆኑ ብቻ በአስቸኳይ ወደ ለንደን ከወላጅ እናታቸው ጋር እንዲመለሱ ተበይኖባቸዋል፤ ይህ ለቀንበጦቹ ህጻናት ጮርቃ መንፈስ መሸከም እንዴት እንደሚችሉት ይመዝኑት? ልክ መስፈሪያ ካለዎት – አሁንም በትህትና፤ ምን አልባት ለእርስዎ ተነጥፎ – ተጎዝጉዞለዎት ሊሆን ይችላል? የክትና የዘወትር – ወርቅና ነሃስ መለዬት የወያኔ ሃርነት ትግራይ ትንፋሹ ነውና።

ሀገር ቤት ያሉት መድረክና ሰማያዊውንስ ከምን መድበዋቸው ይሆን? ዱላውንም – እስሩንም – ስቃዩንም – ግልምጫውንም – መገፋቱንም ችለው ሀገር ቤት ናቸው ያሉት። ሌላው ቀርቶ አብዬት አደባባይ /መስቀል አደባባይ/ ላይ ህዝባቸውን መጥራትና መሰብሰብ አይፈቀድላቸውም። ለትግራይ አፓርታይድ አገዛዝ ብቻ የወርቅ ምንጣፍ ተነጥፎለት እሱ ብቻ ነው በህዝብ አደባባይ የሚፈነጥዘው። ይህ ለእርስዎ የሃኒ ሙን ሳውና ሆኖ ይሆን?! – በአክብሮት።

የተከበሩ ፓን አፍሪካኒስት አቶ ቴወድሮስ ዳኜ – በፖለቲካ ድርጅቶች ፉክክር ውሰጥ ጥላቻ የሚጠበቅ ባይሆንም ግጭት ግን ግድ ነው። ፉክክር – ነዋ። ከዚህም ጋር የትግል ስልትና የአጋዥ ሀገሮች ምርጫም ሆነ የፖሊስ ጉዳይ ያፋትጋቸዋል። ነገም ቢሆን በፓለቲካ ህይወት ውስጥ ሰጥ -ለጥ፤  ጭጭ እረጭ የሚል ነገር አይጠበቁ ….

ይልቁንም ስለምን አይሳመሙም የሚለውን፤ ማጠቃለያ ለመድረስ ግራ – ቀኝ ሁነቶችን፤ አገናኝ መስመሮችን፤ ገፊ ሃይሎችን፤ የዘመን አስተዋፆችን፤ የተመክሮ ማሳዎችን፤  በአግባቡ ፊት ለፊት አስቀምጦ መመርመር ያስፈልጋል።

የትግል ስልት ምርጫ

ሀ. ሰላማዊ

ለ. የትጥቅ

ሐ. ሰላማዊና ትጥቅ /ሁለገብ/

የአደረጃጀት ባህሪ

ሀ. ብሄራዊነት

ለ. ጎሳዊ /አካባቢያዊነት/

የፓሊሲ ጉዳይም አለ —-

ሀ. ፓሊሲውን በግልጽነት ፕሮግራሙ ላይ ያቀረበ፤

በዚህ ዙሪያ ሌላም ልዩነት የሚያመጡ አምክንዮዎች አሉ …. የመሬት፤ የውጪ ግንኙነት፤ ህገ -መንግስታዊ ጉዳዮች፤  የኢኮኖሚ ጉዳዮች ወዘተ ….. ለምሳሌ የመሬትን ቢነሳ የመንግስት/ የህዝብ/ መንግስትና የህዝብ እነዚህ በራሳች ሰፊ ቅርንጫፎችን ከነግጭታቸው እንዲያስተናግዱ ግድ – ይላቸዋል።

ለ. ፓሊሲ አይስፈልገኝም መጀመሪያ ከባርነት መላቀቅ ነው አቅጣጫዬ የሚለው ደግሞ አዲስ መንገድ ነው። ቀድመው የሚፋልሙ የፖሊሲ ጉዳዮች እረፍት ሰጥቶ አቅምን ከብክነት ለማዳን የተተለመ ይመስላል። ያላቸው ደግሞ ወቀሳውን ያስኬዱታል —-

ትጥቅን መራጮች ስፖንሰር የሚደርጋቸው ድርጅትና ሀገር ምርጫ ጉዳይ –

ሁሉም ጎረቤት ሀገር ጥገኝነት አይሰጣቸውም። የወያኔ የኢንትሪግና /የሸር/ ፖለቲካ ቀለል ያለ መናፈሻ ላይ ነጭ ሸሚዝ ተለብሶ ወክ እንዲህ የሚባልበት የሠርግ ግጥግጥ አይደለምና። ስለዚህ በሀገር ምርጫ ላይም እንዲሁ ስምምነት – የለም። አሁን ኤርትራን በመረጡት ላይ የሰላማዊ ትግልን የመረጡት ሳይቀሩ ይህን አካሄድ ትክክል አይደለም በማለት  -ይወቃቀሳሉ ////

የመንግሥት አደረጃጃት ዕይታ ንድፍ ልዩነት …..

/የህግ አውጪ/ ህግ ተርጓሚና አስፈጻሚ ባህሪና ግባቶቹም ሌላው የሚያፋጥጥ የክርክር አጀንዳ ሲሆን …. ከሁሉ በላይ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሴራን በፖሊሲ ደረጃ የነደፈ አስተዳደር በመሆኑ በውጭ ለሚገኙት ሰፊ የዘመቻ ፓሊሲ አለው። በሀገርም አንድ ለአምስት ….. አስርጎ ያስገባል። በትዳር፤ በጓደኝነት፤ በሃይማኖት መሪነት፤ በተገኘው ቀዳዳ ሁሉ። ድርጀቶችን – ተቋማትን ይከፋፍላል፤ ያተራምሳል፤ ጦር ያማዝዛል፤ እኔም የሰለባዎቹ አባል በመሆኔ ነው ይህን ሃቅ እምገልጽልወት፤ ተፈጥሮዬ እራሱ ሰብሰብ ያለ – ብልህና ቁጥብ ነው። ያም ሆኖ ግን ከጥቃት ሰለባነት አልወጣሁም። በራሴ በምከፍለው ኔት ላይ ነፃነቴን ተቀምቼላሁ። ስጽፍ ኔቱን አጥፍቼ ነው። እሰከዚህ ድረስ በነፃነት ሀገር ነፃነቴን ቀምቶኛል የወያኔ ሃርነት ሸር። እርግጥ በሰለጠነ ዓለም ስላለሁ መስመር ማስያዝ – በህግ ይቻላል። ግን ሩቅ አስባለሁ። በዛ ቤተሰብ ሥር በልተው የሚያድሩ አሮጊቶች፣ ነፍሰጡር እህቶች፣ ህመምተኞች፤ ህጻነት ይኖራሉ ስለዚህ እኔው ብጎዳ ይሻላል – ለመንፈሴ በማደር።

የዕውነት —-  ግን እርስዎ ለመሆኑ …. የት ላይ ይሆን ክቡርነተዎት የሚኖሮት ሌላ ፕላኔት ላይ ይሆን? የእርስ በርስ ጦርነት – ጎሳ ላይ የተቸከለ አስተዳደር በባህሪው እሾኽ ስለሆነ እንዲህ ቁጥርጥሩን በቀላሉ መፍታት አይቻልም። የተጋባው – የተዋለደው – ክርስትና የተናሳው – በጡት ልጅነት ያለው – የጉርብትናው፤ የውለታ አደሩ ሁኔታ ሁሉ የወያኔ ፖለቲካ የማስፈጸሚያ ሃዲዶቹ ናቸው። የትውልዱ ኃላፊነት ከእናቱ ማህጸን ውስጥ ዓይን ሳይኖረው የተፀነሰውን ሲወለድ ዓይናማ ማድረግ ነው። ይህ ይቻላልን?! ከዚህ ሃቅ ጋር እስኪ ይቀመጡና ይወያዩ … እባክዎትን?

ሌላው ፈታኝ ጉዳይ ብስጩ የሚያደርገው ደግሞ ኢትዮጵያን ያህል ተናፋቂ ሀገር ሂዶ ማዬት አለመቻል፤ ወላጅ ሲታመም ሩጦ አለመድረስ፤ ሲያልፍም ቁሞ አለመቀብር ከዚህም ባለፈ በፖለቲካ ህይታቸው እንዳሉ ሲያልፉ የ ሀገርን ብትን አፈር ያለመግኘት ስጋት፤ የትግሉ ጊዜ መርዘም ትዳር – ልጅ – ትምህርትም ሁሉም ይቅርበኝ ያሉት ከሁሉም ሳይሆን ዘመን እዬጨረሳቸው ሲሄድ ከውስጥ መከፋት ጋር የሚመነጩ የሥነ ልቦና ሆነ የመህበራዊ ጥቅል ፈተናዎች ጋር መፋጠጥ – በስምምነቱ ሂደት ሆነ በትግል ጉዞ ላይ የራሱ ተጽዕኖ አለው። ግን ራህብን የሚያውቀው የተራበው ብቻ ነው።

የማከበረዎት ወገኔ አቶ ቴወድሮስ ዳኜ ሁሉንም ወቀሳ አንከባለው – አድቦልቡለው – ጠፍጥፈው ናዳውን የለቀቁት በዕንባ ላይ ነው። ትዝብት ነው ትርፉ። „ሃራስ ሊደረጉ“ ይቻላሉ ብለው እንኳን የወያኔ ሃርነት ትግራይ አስተዳደር ማስተካከል ያለበትን ዘለዎታል? ከዚህ ላይ ነው የፓን አፍሪካኒስትነተዎት ካባ ብልዝ ነቁጥ እንዲኖረው የሚፈተነው። እንዲያውም እኔን ሌላ ጥርጣሬ ውስጥ ጨመረኝ። የአፍሪካን የስደት ሰቆቃ ለመጋራት ባቋቋሙት ፋውንዴሽን ስምሪት፤ ኢትዮጵያዊ ስደተኞችን እንዴት ይሆን የሚመለከቷቸው – ልክ እንደ ሱማሊያ፤ ኬንያ ስደተኞች እኩል ይሆን ስል? መልሱ ድፍርስ ነው የሆነብኝ። ምክንያቱም የቃለምልልሱ ፊድባክ /ምላሽ/ ጉሽ እና አብዝቶ የተስረከረከ ስለሆነ። ኢትዮጵያዊ ስደተኞች ከማናቸውም በላይ የተገፉ ናቸው። ስለምን? ሀገራቸው ላይ በመሬታቸው ላይ ባይተዋር ናቸው፤ ዬቅቡ የቁጥር ስታስቲክ ድርድር ሰለባ የሆኑ ሀገሮችም እንደ ክቡርነተዎት „ስቴቢሊቲ አለ፤ ጦርነት የለም ሰለሙን ሰዉ አግኝቷል ኢትዮጵያ እድገት ላይ ናት“ በማለት የጥገኝነት ጥያቄቸውን ውድቅ ያደርጉታል። ስለዚህም ወገኖቻችን – ዜግነታቸውን አሳልፈው ለሌላ መንፈስ እዬሸለሙ – ይገኛሉ። እነሱም በመንፈስ ምጥ ላይ ይገኛሉ። ይህ ደምን – ይቆጠቁጣል። የእርሶዎም ገለጣ እንደነገረኝም መጋፋታቸውን፤ መከፋታቸውን አልተቀበሉትም …. ስለዚህ ፋውንዴሽነዎት ሥሙ የአፍሪካ ሆኖ ኢትዮጵያን የማይጨመር ዓይነት …. ይሆን -? ይሆን -?

  • „እነሱ ያቀርቡት ቪዢን ለሀገሪቱ ብዙ የሚታይ የለም። ያዬሁትም የለም። እንዴት ተብሎ ነው ዜን ኢሌክሽን ሲደረግ ለማሸነበፍ የሚቻለው የዛ ዊክነስ የዛ ሪዛልት ሁልጊዜ መታዬት ያለበት ኖት ጀስት ተቃዋሚ ኃይሎች እንደሚሉት ሃራስ ተደርገናል ኖ! ሃራስመንት ሊነር ይችላል ጥርጣሬ … ግን እነሱ ያደረጉት ነገርም ኮንትሪቢዩት አድርጓል አላደረግም ተብሎ መጠዬቅ አለበት።“

ምን እድል አግኝተው ነው የሀገሪቱ ቪዥን ላይ ተጽዕኖ ማሳደር የሚቻሉት፤ ይህን ቢያዳምጡት መልካም ነው ቀደም ሲል እንደገለፅኩለዎት አንድነት የተባለው ለዛውም ወያኔ የፈረሰውን ብሄራዊዊ ፓርቲውን ሳይጨመር፤ መሪዎቹን አስሮና አሰድዶ ንጡሑ አንድነት ባይኖርበትም ተቀጥላው አንድነት አለበት የአቶ ትግስቱ በቃለምልሱ፤ ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ በአጭር የቃኘውን ያዳምጡት እስኪ „ የግንቦቱ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር ተጀመረ ፤ፍልሚያው ጓንት አልባ ነበር፡፡”/አዋዜ/

https://www.facebook.com/pages/Alemneh-Wasse-News/259948420841915?sk=timeline&ref=page_internal

“የግንቦቱ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር ተጀመረ ፤ፍልሚያው ጓንት አልባ ነበር፡፡”/

https://www.facebook.com/pages/Alemneh-Wasse News/259948420841915?sk=timeline&ref=page_internal

ደግሞስ በአምስት አመት ውስጥ 9 መደበኛ 4 ምራቂ ደቂቃ ብቁ ነውን? ይህ የህሊና ጉዳይ ይመስለኛል ጥያቄው የመመለስ አቅም ያለው። መልሰዎት የግብር ይውጣ ዓይነት ነው የሆነው።

ሌላላም ልከል ፋና ራዲዮ ማለት የወያኔ ሃርነት ትግራይ የጫካ ራዲዮ ከኢንጂነር ይልቃል ጋር ቃለ ምልልስ አደረገ። እራሱ ጠያቂው አጋዚ ከሰለጠነበት –  የሰለጠነ ነው የሚመስለው። ለአንድ ቃለ ምልልስ አድረጊ ቀዳሚው ትህትና አክብሮት ሆኖ ሳለ ካቴናውን አስቀምጦ ጅራፉን እያጮኽ ነበር የጠዬቃቸው ኢንጂነሩን —-  ያም ሆኖ እንዳይተላላፍ ታገደ። ይሄንስ ምን ይሉት ይሆን? የርትህ ማህደር ይሉትን ይሆን ¡?

„ስለ ስትራክቸር“ /መዋቅር አንስተዋል። አዲስ አበባ ከተማ ላይ ቢሮ ለመከራዬት ፈቃድ የማያገኙ፤ አዲስ አበባ ከተማ ላይ መኪና ለመንቀስቀሻ ለመከራዬት ፈቃድ የማይሰጣቸው፤ በማናቸው ሰአት ቢሯቸውን ወታደር ገብቶ ሰብሮ ዘርፎ ሲሄድ ሃላፊነቱን የሚወስድ ተቆርቋሪ አስተዳደር በሌለበት ስለ ስትራከችር /መዋቀር/ አስፈላጊነት ይነግሩናል። መደረጀት እኮ ሲባል ስትራክቸር /መዋቅር/ መዘርጋት ነው። ስትራክችሩ /መዋቅሩ/  ከቀበሌ እስከ ብሄራዊ።

  • የቀበሌ ጠቅላላ ጉባኤ / ሥራአስፈጻሚ ሙሉ አባለቱ ይገኛሉ።
  • የወረዳ ጠቅላላ ጉባኤ/ ምክር ቤት/ ሥራ አስፈጻሚ –
  • የ አውራጃ ጠቅላላ ጉባኤ/ ምክር ቤት/ ሥራ አስፈጻሚ
  • የብሄራዊ ጠቅላላ ጉባኤ / ማዕከላዊ ምክር ቤት/ ሥራ አስፈጻሚ ይህን ነው የሚሉን አይደለ?

ወያኔ ሃርነት ትግራይ በደርግ ጊዜ የከሸፉ ቀላሃዎችን ሰባስቦ ጨፍልቆ የሠራቸው „ህዝቦች“ እያለ አደራጅቶ ለማላገጫው የተጠቀመበት ህብረት እራሱ የሚተዳደረው በህዝብ አንጡራ ሃብት፤ መዋቅሩን እስከ ሥር ዘርግቶ በበጀት ነው የሚያስተዳድራቸው። ሥልጠና፤ የውጭ የትምህርት ዕድልና ዕድገት ይደጎማሉ ካድሬዎቹ – ከመደበኛው ማህያ በላይ። የተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን ለሃገራቸው አንጡራ ሃብት ባይታዋር ናቸው። ግብር ቀረጠ ግን ይከፍላሉ። ማናቸውም መንግስታዊ መዋቅር በወያኔ ሃርነት ማንፌስቶ ሥር የሚተዳደር ግን በጀቱ በህዝብ አንጡራ ሃብት ነው። ፖሊስ ሃይል/ ደህንነት/ ሰራዊት/ የሚ/ር መስሪያ ቤቶች፤ ተቋማት፤ ፍርድቤቶች ሁሉ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሃብት ናቸው – መንፈሳቸውም።

ተቃዋሚ ሃይሎች ወደ ታች ሲወርዱ  …. ዋርካ ላይ ነው የሚሰበሰቡት፤ የሚተዳደሩትም በራሳቸው ማህያ ነው። እንዲያውም የተቃዋሚ ፓርቲ አገልጋይ ከሆኑ ይባራራሉ – ከሥራቸው፤ ከእድገት ይታገዳሉ …. አሁንም እርስዎ ክቡርነተዎት የት ነው ያሉት? ስለምኑ ይሆን የሚነግሩን? …. ይህም ሆኖ በሁሉም ዘርፍ ጥረዋል አውሬው ግን አውሬ ነው። ተመክሮው ጫካ እድገቱም ፕርሜቴቢ …. ይሄ „ኦቨዘርበሮች ይኖራሉ፤ መዋቅር የላቸውም“ ያሉት ነገር ቅልጣን ይመስለኛል።

  • “ተቃዋሚ ኃይሎች እንደሚሉት ሃራስ ተደርገናል ኖ! ሃራስመንት ሊኖር ይችላል ጥርጣሬ … አለበት። „ግን እነሱ ያደረጉት ነገርም ኮንትሪቢዩት አድርጓል አላደረግም ተብሎ መጠዬቅ አለበት።  ….. የዛሬ 5 እና አመት አንዳልኩት አሁንም እላለሁ። ብዙውን ጊዜ የታለፈው እርስ በእርስ ሲጣሉና ማጆሪቲው ደግሞ ውጭ ነው ያሉት። ሃራስ አይደረጉም ለማለት ሳይሆን ኤግዛጁሬት ባናደርገው ጥሩ ነው።“
  • „አንድ ሰው ኢቢደንስ አቅርቦ ኮንቢንስ እንዲያደርገኝ ያስፈልጋል“

ምን እኛ ኮንቢንስ እናደርገዎታለን የአውሮፓው ማህበረሰብ በማናቸውም የሀገሪቱ ሰቆቃ፤ የዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ ያቀረበውን ዘገባ ጊዜ ወስደው ያዳምጡት። እኔ እንደማስበው የመረጃ እጥረት አብዝቶ አለበዎት፤ ከሀገረዎት ከኢትዮጵያ ዕንባ ይልቅ የለማና ያፈራ ግንዝቤ ከኢትዮጵያ ውጪ ስላሉት አፍሪካ ሀገሮች አለዎትና። የሚያምረው የራስን ሲያከብሩት፣ ከራስ ላይ ሲነሱ ነው – ጌጡ የሚደምቀው። ጆሮ አልባ የጆሮ ጌጥ፤ አንገት አልባ ሰው መሆን የለምና። ዕንባን የምልዕትን የመተርጎም አቅም ፈጠሪ እንዲሰጠዎት ቢተጉ የለመኑትን ይሰጥወታል። እኛም መመኪያችን እንለወታለን – ወደ እኛ ለማዬት ልበዎት ሲከፍቱ መንፈሰዎትን ሲፈቅዱልን እንናፍቀዎታለን፤ በስተቀር ግን ከመጤ እንደራሴ ጋር የሚከትም እኛነት አይኖርም መሃን ነው።

http://ecadforum.com/ethiopianvideo/2015/02/03/u-s-policy-ethiopia-a-failed-state-documentary/

  • ይህም ብቻ አይደለም በሲዊዲን ከደም ጋር የከተሙትን ለፍርድ ለማቅረብ በቀለማቸው የማይመስሉን እዬሰሩ ነው። ከእኛ ጋር በደም የማይገናኙት። ‚ሰውን“ ግን ከቃል አልፈው መሆን በጸጋ የተረጉሙት፤ እንደ እርስዎ ያለው ፓን አፍሪካኒስት ደግሞ ወቀሳ ለዕንባ ይገባዛል – ማዘን ቃሉ አይገልጸውም፤ መቁሰልም ቃሉ አይገልጸውም፤ ማረርም ቃሉ አይገልጸውም የፍሬ መርገፍ ልበለውን? ከአላወቁን ስለምን ቃለምልስ አደረጉ?!
  • https://www.facebook.com/ESATtv/posts/816604948371589 „13 የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣኖችና የጦር መኮንኖች በስዊድን አለማቀፍ የጦር ፍርድ ቤት ክስ ተመሰረተባቸው“

ልሰናበተዎት እንደ ከፋኝ። ቁስል ላይ ሚጥሚጣ – ቁስል ላይ የፋመ ማረሻ —–

ያለፉ ጥቂት ሊንኮችን ጊዜ ካላዎት ይከታተሉት ዘንድ ከምርጫ ጋር የተያያዙትን ለጥፌያለሁ። አንዱን ሲከፍቱት ተያያዡም ሰለሚመጣ የወደዱት ወይንም ለቀልበዎት የተመቸወትን ቢያነቡ አፍሪካዊ ሃላፊነትዎትን ሚዛናዊ ሊያደርግ ይችላል። እናትዎትና አይነጥሏት፤ ጣል – ጣልም አያድርጓት፤ የክብረዎት መሰረት ማርዳ ጌጠዎት ናትና፤ በማን ላይ ይሆን ተዚህ – የተደረሰው?!

ምርጫና ልግጫውን የዓለም የዜና አውታሮች የዘገቡትንም …. ባይገርመዎት የናይጀርያን በሚመለከት የጀርመን፤ የኦስትርያ፤ እንዲሁም የሲዊዝ ራዲዮና የተለያዩ ቴሌቪዥን ፕሮግራሞች እዬተቀባበሉ ዘግበውት ነበር። ኢትዮጵያ ላይ ግን ቃልም ትንፋሽም አላወጡም „ሰው“ ስለሆነ – አጀንዳቸው።

„ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው። እግዚአብሄር በክፉ ቀን ያድነዋል“ /መዝሙር 40 ቁጥር 1/

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል፤

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/41705

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/41705#sthash.v011En2U.dpuf

http://www.ethiofreedom.com/amharic/

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/39189

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/41765

http://ecadforum.com/Amharic/archives/15131

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/41700

http://www.zehabesha.com/amharic/

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/41678

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/41648

The post ኦ! – ከሥርጉተ ሥላሴ appeared first on Zehabesha Amharic.

ለአፍሪካ አርዓያ የሆነዉ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫና ሰላማዊ የስልጣን ርክክብ (በሳዲቅ አህመድ) –ሊያደምጡት የሚገባ

ግልፅ ደብዳቤ ለጀነራል አበበ ተከለሀይማኖትና ጀነራል ፃድቃን –ከሽሕ ጦረኛ አንድ ወረኛ ትጥቅ ያስፈታል

$
0
0

Tsadkan Gebretensae

ህወሓት ነበር ጀነራል አበበ ተክለሀይማኖት በአቶ ገብሩ ላይ ያቀረበው የአሉቧልታ ዘመቻ

በአንድ መንደር ከኔ በላይ ቆንጆና ጀግና የለም ብላ የምትመካ አንዲት ዝንጀሮ ነበረች:: አንድ ቀን በመንገድ ላይ እየተንጎራደደች ስታልፍ ወደ ገበያ መደብር ጎራ ብላ ድንገት በግድግዳ ላይ የተሰቀለ ትልቅ መስተዋት ስትመለከት ፊትዋን ወለል ብሎ ታያት:: የራሷን ተፈጥሮ መሆኑን አልገባትም ነበርና ቆም ብላ በመገረም ደጋግማ ስታየው “ወይኔ ጉዴ”!! ይህ አስቀያሚ መልክ የኔ ቢሆን ኖሮ አንገቴን በገመድ አንጠልጥዬ ታንቄ እሞት ነበር” አለች ይባላል:: ( ከታሪክና ምሳሌ የንባብ መፅሐፍ የተወሰደ ሀገሪኛ አባባል)

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

The post ግልፅ ደብዳቤ ለጀነራል አበበ ተከለሀይማኖትና ጀነራል ፃድቃን – ከሽሕ ጦረኛ አንድ ወረኛ ትጥቅ ያስፈታል appeared first on Zehabesha Amharic.

በዘውዲቱ ሆስፒታል የ5 ልጆች እናት በህክምና ስህተት ሕይወቷ አለፈ

$
0
0

zewditu

zewditu hospital
በዘውዲቱ ሆስፒታል የመህፀን እጢ እንዳለባቸው የተነገራቸው የ 5 ልጆች እናት እጢው ወደ ካንሰር እንዳይለወጥ አስቸኳይ ቀዶ ጥገና እንዲደረጉ ይታዘዛሉ ። ለዚህም ቀዶ ጥገና ሆስፒታሉ መሳሪያ ስለሌለው ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የምርመራ ውጤታቸውን አባሪ በማድረግ ይልካቸዋል። የተጠቀስው ሆስፒታል እደደረሱም እናት ለህክምና ከአቅማቸው በላይ የሆነ ክፍያ ሰለተጠየቁ «ያለአባት የሚያሳድጓቸው የ 5 ልጆች እናትና የቤተሰብ ሃላፊ መሆናቸውን ጭምር በመግለጽ ሆስፒታሉ ከሞት እንዲታደጋቸው ይማፀናሉ ። የሆስፒታሉ አስተዳደር እናት ከቀበሌ ደብዳቤ ካመጡ በነጻ ህክምና የሚያገኙበትን መላምታ እንደሚያመቻቹላቸው ቃል በመግባት ያሰናብቷቸዋል። የጤና ጉዳይ ነውና እናት የተባለውን ሁሉ አሞልተው ዳግም ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በማቅናት ለነጻው ህክምና ተራ ያሲዛሉ ። ከወራት ቆይታ በኃላ እናት የቴሌፎን ጥሪ ከሆስፒታል ይደርሳቸዋል « ተራዎ ስለደረሰ መጥትው ነጻ ህክምናውን ይውሰዱ የሚል» ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በቁሙ የገባ ታካሚ እንደዋዛ በሬሳ ሳጥን ታሽጎ በአስከሬን በር የሚወጣበት ፤ የመኪና ግጨትን ጨምሮ በተለያያ ድንገተኛ አደጋዎች እግርጥሎት ወደ ሆስፒታሉ ያቀና «ዘመድ አዝማድ የሌለው የኔ ቢጤ » የሰውነት ክፍሉ ተበልቷ ለሃብታሞች ጫራታ የሚቀርብበት ፡ በአጠቃላይ ሆስፒታሉ ወደ ሰው ቄራነት የተለወጠ ፤ የህክምና መሳሪያን ጨምሮ በ መደሃኒትና በባለሙያ እጠረት ያለበት መሆኑን ቀደም ብለው የተረዱ እናት ሁኔታው ደስ ስላላቸው « እሱ እንደፈጠረኝ እሱ ይግደለኝ » ብለው ምንም አይነት የህመም እንደማይሰማቸው ገልጸው የቀዶ ጥገና ሃሳባቸውን መለወጣቸውን ለሆስፒታሉ ያስረዳሉ። የኚህን እናት ሙሉ መረጃ የያዙ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ዶ/ሮች በተደጋጋሚ ስልክ በመደውል እጢው ቀላል እንደሆነና በዛው ልክ ቀዶ ጥገና እንደሚያደርጉላቸው ያግባቦቸዋል።

እናት ያለአባት የቀሩ ልጆቼን ላሳድግ ኽረ ! ጉድ ታደርጉኛላችሁ ! ቢሉ ማን ሊሰማ ። በዶ/ክተሮች ተማጽኖ ሆስፒታል የገቡት እናት ግን የፈሩት አልቀረላቸውም። ዕለቱ ማክሰኞ ረፋዱ ላይ ነው ። ከሶስት ቀን በፊት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አልጋ ተይዞላቸው የቀዶጥገና ቀናቸውን የሚጠብቁት የ 5 ልጆች እናት ስጋታቸው ጨምሯል። እናት ፍረሃት ፍረሃት እንዳልቸው ለገኙት ሁሉ ቢገልጹም ደሃ ታሞ በማይድንባት ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም እንደሆነ የሚነገርለትን የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ባዶ ህንጻና ነጫጭ ገዋን በለበሱ የጤና ባለሙያዎች በተማረኩ ወገኖች አበረታችነት እናት በተጠቀሰው ቀን ከቀኑ 8 ሰዓት ልጆቻቸውን ተሰናብተው ወትሮም ወደ አላመኑበት ቀዶ ጥገና ክፍል ገቡ ። ልጆቻቸውን ጨምሮ ሁሉም ቤተሰብ ቀዶ ጥገና ክፍል በሩ ላይ በጭንቀት ተውጦ ፈጣሪውን ይማፀናል ። የቀዶ ጥገና ክፍሉ መግቢያ ላይ ዶ/ሮቹ ቀዶ ጠገናውን መጀመራቸውን የሚያመላክተው ቀይ መብራት በርቷል ።ሶስት ሰዓት ይፈጃል ይተባለለት ቀዶ ጥገና ሳይጥናቀቅ ከቀዶ ጥገና ክፍሉ አንድ በወጣትነት እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ የህክምና ባለሙያ እይተቻኮለ ወጣ ፤ በጭንቀት ተመስጥው በር ላይ ለታደሙት ቤተሰቦች በተርበተበተ አንደበት « ሴትየዎ ብዙ ደም ስለፈሰሳቸው ደም ስለሚያስፈልግ ፈልጋችሁ አምጡ » የሚል ትዕዛዝ ቢጤ አስተላልፎ እየተቻኮለ ወደ መጣበት ክፍል ተመለስ ።ሁሉም ቤተሰብ በየአቅጣጫው ደም ፍለጋ ከተማ ውስጥ ያሉትን ሆስፒታሎች ማካለል ጀመር ወትሮስ ምክንያት እንጂ ችግሩ የደም አልነበረም ። የናታቸው ህይወት አደጋ ውስጥ መውደቅ የተነገራቸው ልጆች እሪታቸውን አቀለጡት የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህንጻ እንደዚህ አይነት ጩህቶችን በየግዜው መስተናገድ የተለመደ ቢሆንም የልጆቹ ጩኽት ግን ከወትሮው ለየት ያለ ነበር ፤ በአካባቢ የነበረውን ሁሉ ደረት በማስደቃት የሆስፒታሉን ድባብ ለወጠው ።በሁኔታው የተደናገጡት ዶ/ር ተብዬዎች ከአካባቢው ተሰወሩ ችግሩ ወደ ተፈጠረበት የቀዶ ትገና ክፍል የመጡ የሆስፒታሉ ህላፊዎች በቀዶ ጥገና ወቅት በደም ስር ላይ ጉዳት ሳይደርስ እንዳልቀረና ሴትየዋ የማይተርፉ መሆናቸውን ቢረዱም የዜጎች ህይወት በተደጋጋሚ በቀዶ ጥገና ስህተት መጥፋት የተለመደ ነውና በአካባቢ የነበረውን ቤተሰብ ከማስተዛዘን ውጭ ዴታም አልነበራቸውም ፤ በተለይ ልጆቻቸውን ለማረጋጋት በእድሜ የገፋውን ልጅ ቀዶ ጥገና ክፍል ውስጥ ይዘውት በመግባት ከማደነዘዣ የነቁትን እናት እንዲያይ ፈቀዱለታል ።

የአባት ፍቀር እንደተራበ እናቱን ለማየት ወደ ቀዶ ጠገና ክፍል የዘለቀው ልጅ ከእናቱ አንደበት « ብርድ ብርድ አለኝ ፤ ተጫወቱብኝ የሚለውን ቃል ከመስማት ባሻገር »እናት ጤና እያሉ ይለግሱት የነበረውን የእናትነት ፍቅር ዳግም መስማት አለታደለም ። የማህጸን እጢ አለባቸው ተብለው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተለምነው የገቡት እናት ይህይወት ፍጻሜ በቀዶ ጠገና ስህተት ሁሉም ነገር አበቃ ። በዛው ቅጽፈት የቀዶ ጠገና ክፍሉ ዘግናኝ የደውል ድምጽ አቃጨለ ተጠያቂነትና የህግ የበላይነት በሌለበት ሃገር ተተኪ የሌላት የ 5 ልጆች እናት ላትመለስ እስከ ወዲያኛው አሸለበች ። በፖለቲካ አመመለካከታቸው አያሌ የሃገሪቷን እውቅ ዶክተሮች ከሃገር እንዲሰደዱ ያደረገው « የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት » በጤና ፖሊሲው የፖለቲካ ቱሩፋት ለማግበስበስ ያለ በቂ ባለሙያ ፤ የህክምና መሳሪያና መደሃኒት በየክልሉ ለይስሙላ ባስገነባቸው ባዶ ህንጻዎች ውስጥ ህይወታቸው እንደዋዛ ያጡትን ዜጎቻችንን ቤት ይቁጠራቸው::

The post በዘውዲቱ ሆስፒታል የ5 ልጆች እናት በህክምና ስህተት ሕይወቷ አለፈ appeared first on Zehabesha Amharic.

ዳኛ ብርቱካን አቶ ማሙሸት አማረን ክሱ ተቋርጦ ይፈቱ ስትል ፖሊስ አለቅም አለ

$
0
0

Zehabesha News
* የአይ.ሲ.ስን ግድያ ለማውገዝ ሰልፍ የወጣው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ከሶስት ዓመት በላይ እስር ተፈረደበት

(ሕብር ሬዲዮ-ላስ ቬጋስ ) የመኢአድ ሕጋዊው ፕ/ት አቶ ማሙሸት አማረ ሚአዚአ 14 ቀን 2007 በመስቀል አደባባይ በተጠራው ሰልፍ ላይ ብጥብጥ አስነስተዋል በሚል ለተከሰሱበት የፈጠራ ክሱንና የሀሰት ምስክርነቱን ዋጋ የሚያሳጣ በዕለቱ በሌላ ፍርድ ቤት ምርቻ ቦርድን ከሰው ሙግት ላይ መሆናቸውን የሚአስረዳ የሰውና የሰነድ መከላከያ ምስክር ባለፈው አርብ ያቀረቡለት ቦሌ ምድብ የመጀመሪአ ፍርድ ቤት ሶስተና ችሎት ዛሬ በሰጠው ትዕዛዝ አቶ ማሙሸትን ያሰረው ቦሌ ፖሊስ መምሪያ ክሱ በመቋረጡ እንዲፈታቸው ትዕዛዝ ቢሰጥም ፖሊስ ሳይፈታ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳዛወራቸው ያገኘነው መረጃ ይገልጻል።

አቶ ለገሰ ወ/ሃና የዛሬውን የአቶ ማሙሸት የፍርድ ቤት ውሎ ተከታትለው በላኩልን መረጃ መሰረት ባለፈው አርብ በዋለው ችሎት የአቶ ማሙሸት አማረን የመከላከያ ምስክር የሰማው የፌዴራል መጀመሪአ ደረጋ ቦሌ ምድብ ሶስተኛ ችሎት ለዛሬ ለውሳኔ ቀጥሮ የነበረ ሲሆን ክሱን ሲያዩ የቆዩት ዳኛ ብርቱካን ገላው በሰጡት የፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረት አቶ ማሙሸት አማረ ድልነሴ በተከሰሱበት ስብሰባን ወይም ጉባዔን ማወክ ክስ ተከሳሹ የተከሰሰበት መዝገቡ የተቋረጠ ስለሆነ ይፈታ ሲል ማክሰኞ ጠዋት በሶስት ሰኣት ሲል ያዛል።

የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ማክበር የነበረበት ፖሊስ ውሳኔውን ወደ ጎን በማድረግ የቦሌ ፖሊስ መምሪአ ቤተሰብና የአቶ ማሙሰት አማረን የትግል አጋሮች ጠብቁ ሲል ቆይቶ ሌላ ክስ ሳይቀርብ ፣የፍርድ ቤቱም ውሳኔ ሳይከበር ከሰኣታት ጥበቃ በሁዋላ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከእስር ቤት ወደ እስር ቤት ተዛውሯል መባላቸውን የደረሰን መረጃ ያስረዳል።

የመኢአድ ሕጋዊው ፕ/ት አቶ ማሙሸት አማረ ግንቦት 5 ቀን 2007 ከመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ በደህነቶች ታፍነው ተወስደው በዚሁ ፍርድ ቤት በሊቢያ ለሞቱት ወገኖች ሐዘን ለመግለጽ ሚአዚአ 14 ቀን 2007 መስቀል አደባባይ የወጣውን ሕዝብ አሳምጸዋል ብትብት አስነስተዋል በሚል የፈጠራ ክስ ተከሰው አገዛዙ የሀሰት ምስክሮች አቅርቦ አስመስክሮ የነበረ ቢሆንም ባለፈው አርብ አቶ ማሙሰት አማረ ባቀረቡት የመከላኬአ የሰነድና የሰው ማስረጃ በዕለቱ መስቀል አደባባይ እንዳልነበሩ ይልቁንም ምርጫ ቦርድ በመኢአድ ላይ የወሰደውን አመራሩን በሕገ ወጥ የማባረር እርምጃ በመቃወም በቦርዱ ላይ ያቀረቡትን ክስ ለመከታተል ልደታ ምድብ የፌዴራሉ አንደና ደረጃ ፍርድ ቤት እንደነበሩ ፍርድ ቤቱ በሰነድ ያረጋገጠውንና በዕለቱ አብረዋቸው የነበሩትን አስመስክረዋል። ይሄን የአርብ ምስክርነት የሳው ፍርድ ቤት በዛሬው ቀጠሮ ክሱን አቋርጦ ይፈቱ ቢልም ፖሊስ ሳይፈታ ቀርቷል።

አገዛዙ ፍርድ ቤት የሚፈልገውን ካልወሰነ ቱንም ትዕዛዝ የማያከብር ሲሆንየዛሬዋ ዳኛ ብርቱካን ገላው የሰቱትን ውሳኔ አለመከበር ከዚህ ቀደም በስፋት የሚታወቀውን የዳኛ ብርቱካን ሚደቅሳን ውሳኔ የሚአስታውስ ሆኗል። ዳና ብርቱካን ሚደቅሳ የቀድሞው የአገዛዙ ባለስልጣን አቶ ስዬ አብርሃን የቀረበውን የሙስና ክስ መዝገብ በመመልከት በጊዜ ቀጠሮ ፖሊስ አለ በቂ ምክንያት የምርመራ ጊዜ እየጠየቀ ተገቢውን ባለመስራቱ የመሀል ዳኛ በሆነችበት አራዳ ምድብ በችሎት ፖሊስ በዋስ ይፈቱ የተባለውን ውሳኔ ባለማክበሩ በነጻ ማሰናበቷ ይታወሳል። ይሁንና ፖሊስ ውሳኔውን ተግባራዊ ላለማድረግ የፍርድ ቤቱን ግቢ በር ለጊዜው ዘግቶ መልሶ ከአለቆቹ ትዕዛዝ ሲደርሰው ከፍርድ ቤቱ እንደወጡ ጥቂት በእግራቸው እንደተጓዙ ሁኔታውን ለመከታተል ካጀባቸው ሕዝብ፣ቤተሰቦችና ጠበቃቸው ነጥሎ መልሶ ማሰሩ ይታወሳል። ዛሬ አቶ ማሙሸት በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሳይፈቱ ከእስር ቤት ወደ እስር ቤት ተዛውረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ወጣት በሚያዚያ 14/2007 በሊቢያ በአይ.ሲስ አሸባሪ ቡድን በሊቢአ በግፍ የተገደሉ ወገኖች ላይ ተወሰደውን በመቃወም በተጠራው ሰልፍ ላይ አደባባይ በመገኘቱ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ›› ፈጥረሃል በሚል ተይዞ የቆው ናትናኤል የዓለም ዘውድ የ3 አመት ከ3 ወር እስራት ዛሬ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ የመናገሻ ፍርድ ቤት እንደተፈረደበት ፓርቲው ይፋ አድርጓል።

ከፓርቲው የተገኘው መረጃ እንደሚገልጸው ናትናኤል የኣለም ዘውድ ዛሬ ግንቦት 25ቀን 2007 ዓ.ም የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት የቀረበው ወጣት ናትናኤል የዓለም ዘውድ ላይ የቀረበው ክስ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ መፍጠር›› የሚል ሲሆን አቃቤ ህግ ከፍርዱ በፊት ‹‹ሁከትና ብጥብጡን የፈጠረው ኢትዮጵያውያን ላይ ግድያ የፈፀመውን አይ ኤስ አይ ኤስ ለማውገዝ የተጠራው ሰልፍ ላይ በመሆኑ፣ በተፈጠረው ረብሻ በርካታ ሰዎች የተጎዱ በመሆኑ እና ረብሻውን የፈፀመው አምስተኛው አገራዊ ምርጫ እየተቃረበ ባለበት ወቅት በመሆኑና ይህም አደጋውን ያባብስ የነበር መሆኑን በማገናዘብ›› የሚል የቅጣት ማክበጃ መጨመሩንም ይሄው መረጃ ገልጿል።

በሌላ በኩል በተመሳሳይ ክስ ተከሰው በዚሁ ፍርድ ቤት የቀረቡት ማቲያስ መኩሪያ፣ ብሌን መስፍን፣ ተዋቸው ዳምጤና መሳይ የተባለ ሌላ ወጣት መከላከያ ምስክር ለማቅረብ ለሰኔ 4 ተቀጥረዋል፡፡ እነ ማቲያስ ‹‹ሰልፉ ላይ ሀሰተኛ ወሬ በማውራት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተናገሩ በነበረበት ወቅት ወደ ፖሊስ ድንጋይ በመወርወር፣ ህዝቡን አትነሳም ወይ በማለት…›› የሚል ክስ እንደቀረበባቸው ያስታወሰው ይሄው ፓርቲው መረጃ በጉዳዩ ላይ ዛሬ ይቀርባል ተብሎ የነበረው የቪዲዮ ማስረጃ ባለመቅረቡ በሚቀጥለው ቀጠሮ እንዲቀርብላቸው መጠየቃቸው ታውቋል።

The post ዳኛ ብርቱካን አቶ ማሙሸት አማረን ክሱ ተቋርጦ ይፈቱ ስትል ፖሊስ አለቅም አለ appeared first on Zehabesha Amharic.

መኢአድና ኢራፓ የምርጫውን ውጤት አንቀበልም አሉ

$
0
0

aeupየመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. የተካሄደውን ጠቅላላ ምርጫ ውጤት እንደማይቀበሉት፣ ግንቦት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. በየጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ፡፡

መኢአድ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው ዋና ጽሕፈት ቤቱ ምርጫውን አስመልክቶ በፕሬዚዳንቱ አቶ አበባው መሐሪና በሌሎች የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች መግለጫ ሲሰጥ፣ በምርጫው ወቅት ገጠመኝ ያላቸውን ችግሮችና ጫናዎች ዘርዝሮ አቅርቧል፡፡

‹‹ባለፉት አራት ምርጫዎች በተከሰቱ ችግሮች ዙሪያ መፍትሔ አስቀምጦ ሙሉ በሙሉ ተሻሽሎ ይካሄዳል የሚል ዕምነት ቢኖረንም፣ ራሱን ሙሉ በሙሉ ወደ አምባገነንነት በቀየረው ገዥ ፓርቲ አፈና፣ ወከባ፣ እስራትና ግድያ የተነሳ ምርጫው ሳይሳካ ቀርቷል፤›› በማለት መኢአድ አስታውቋል፡፡

መኢአድ በምርጫው ዕለትና ከዚያ ቀደም ብሎ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ደረሰብኝ ያላቸውን ችግሮች ዘርዝሯል፡፡ ከአዲስ አበባ በስተቀር ኦሮሚያ፣ አማራና ደቡብ ክልሎችን ጨምሮ አባላቱ መታሰራቸውንና ታዛቢዎቹ ከምርጫ ጣቢያ መባረራቸውን ገልጿል፡፡

‹‹ምርጫው ነፃ፣ ፍትሐዊና፣ ሰላማዊ እንደሆነ ይገለጽ እንጂ በተግባር የታየው ግን የዚህ ተቃራኒ ነው፤›› ብሏል፡፡ ‹‹ሰው እየደበደቡ፣ እያሰሩ፣ እያንገላቱ፣ ከመኖሪያ እያፈናቀሉና የግድ ንብን ምረጡ ብለው ለማስፈራራታቸው ተጨባጭ መረጃ ባለበት ሁኔታ እንዴት ብሎ ነፃ፣ ፍትሐዊና ሰላማዊ ምርጫ እንደተካሄደ የሚያውቀው አፋኙ ሥርዓት ብቻ ነው፤›› በማለት መኢአድ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

በምርጫው ምክንያት የታሰሩ የፓርቲ አባላትና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል፡፡ ‹‹ምርጫው ታዋቂ የሆኑ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎችና ከፖለቲካ ገለልተኛ የሆኑ የሲቪክ ማኅበራት ባልተገኙበት ኢሕአዴግ ባደራጃቸው የሲቪክ ማኅበራትና አባብሎ ወደ ታዛቢነት ያሰማራቸው የምርጫ ታዛቢዎች በተገኙበት የተካሄደ በመሆኑ፣ ይህንን የፖለቲካ ድራማ የተከናወነበት ምርጫ የማንቀበለው መሆኑን እናስታውቃለን፤›› በማለት መኢአድ መግለጫውን አጠቃሏል፡፡

የፓርቲውን የወደፊት አቅጣጫ በተመለከተ የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ አበባው ሲገልጹም፣ ‹‹ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር መክረን ዘክረን ወደፊት የምናሳውቀው ይሆናል፤›› ብለዋል፡፡

በተመሳሳይም በዋና ጽሕፈት ቤቱ መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ)፣ የዘንድሮው ምርጫ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መካሄዱን ያስረዱልኛል ያላቸውን የተለያዩ ክስተቶች በማንሳት አስረድቷል፡፡ በፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮና በሌሎች ኃላፊዎች በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተገለጸው፣ ለምርጫ ቦርድ ፓርቲው ያቀረባቸው ዕጩዎች ቁጥራቸው ያለምንም አሳማኝ ምክንያት ተቀንሶ ፓርቲው በተወሰኑለት ዕጩዎች ብቻ እንዲወዳደር መደረጉ ከፍተኛ ጫና ፈጥሮበታል፡፡

እንዲሁም በአማራ፣ በደቡብና በኦሮሚያ ክልሎችና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዕጩ ምዝገባ ወቅት፣ በቅስቀሳና በምርጫው ዕለት አጋጠሙኝ ያሏቸውን ችግሮች በባለ 6 ገጽ መግለጫው አስታውቋል፡፡ አብዛኛዎቹ ችግሮችም ከዕጩዎች አለመመዝገብ፣ ከአባላት መዋከብና መታሰር እንዲሁም የታዛቢዎች በሥፍራው ተገኝተው መታዘብ ከመከልከላቸው ጋር የሚያያዙ ናቸው፡፡

‹‹ጠጣር ግድፈቶች በተንፀባረቁበትና በተስተዋሉበት ሁኔታ የሕግ የበላይነት ተሟልቷል ተብሎ ከነጉድፉ መቀበል የፖለቲካ ቃር የሚያስይዝ ከመሆኑም በላይ፣ ከቀደምቶቹ ምርጫዎች 2002 እና 2005 (ማሟያና አካባቢያዊ) ባልተለየ መልኩ በአንድ ቅርጫት የተቀመጠ የቅድመ ምርጫ ሒደትና ውጤት በመሆኑ ፓርቲው አልተቀበለውም፤›› በማለት አስታውቋል፡፡

ቀጣይ አቅጣጫቸውን በተመለከተ ከሪፖርተር ለቀረበላቸውም ጥያቄ፣ ‹‹በትግል ደክመን ሳይሆን በመንግሥት ጫና ምክንያት መፈናፈን ባለመቻላችን ምንም እንኳን ዛሬ በዝረራ ብንወጣም፤ ዝረራው ግን ለነገው ቁጭት ጭሮብናል፤›› በማለት መልሰዋል፡፡

ፓርቲው ለወደፊቱ ሁለት አቅጣጫዎች ማዘጋጀቱን ገልጿል፡፡ አንደኛው ብሔራዊ መግባባትን ማስገኘት የሚል ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር አብሮ መሥራት የሚሉ ናቸው፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

The post መኢአድና ኢራፓ የምርጫውን ውጤት አንቀበልም አሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስድስት ሠራተኞች በጥይት ተገደሉ

$
0
0

–ግድያውን ፈጽሟል የተባለው ተጠርጣሪ እጁን ሰጥቷል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመቀሌ ዲስትሪክት የማይፀብሪ ቅርንጫፍ ዋና ሥራ አስኪያጅን ጨምሮ፣ ስድስት የባንኩ ሠራተኞች ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. በባንኩ የጥበቃ ሠራተኛ በጥይት ተገደሉ፡፡

national bank of ethiopiaግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. የተለመደ ሥራቸውን በማከናወን ላይ እያሉ፣ በባንኩ የጥበቃ ሠራተኛ በጥይት ተደብድበው የሞቱት የቅርንጫፉ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ወልዳይ ገብሩ፣ የባንኩ ኮንትሮለር አቶ አትንኩት ደምሴና የደንበኞች አገልግሎት ኦፊሰሮች የነበሩት ወ/ሮ ለምለም ግደይና አቶ አስማማው ገብረ ማርያም መሆናቸውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም መኩሪያ አረጋግጠዋል፡፡ አቶ ንጉሤ ግርማና አቶ ጌትነት ባዩ የተባሉ በኮሜርሻል ኖሚኒስ አማካይነት የተቀጠሩ የባንኩ ሠራተኞችም መገደላቸውን አቶ ኤፍሬም አክለዋል፡፡

የባንኩ ሠራተኞችን በመግደል የተጠረጠረው የጥበቃ ሠራተኛ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሆኖ፣ ግድያውን ሊፈጽም የቻለበት ምክንያት እየተጣራ መሆኑን የገለጹት አቶ ኤፍሬም፣ ግድያውን የፈጸመው ግለሰብ የሥራ አፈጻጸሙን በሚመለከት ምክር፣ ተግሳጽና ማስጠንቀቂያ ከተሰጠው ከደቂቃዎች በኋላ መሆኑን መረዳታቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጥበቃና የፅዳት ሠራተኞችን የመቅጠርና የመቆጣጠር ሥራን ለኮሜርሻል ኖሚኒስ መስጠቱን የጠቆሙት አቶ ኤፍሬም፣ የባንኩን ሠራተኞች በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብም የተቀጠረው ከዚያው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ተጠርጣሪው በሥራው ላይ ተገቢ ያልሆነ ባህሪያትን በማሳየቱ በባንኩ ኃላፊዎች ቢመከርም ሊስተካከል ባለመቻሉ፣ የቅርንጫፍ ዋና ሥራ አስኪያጁ መቐለ ለሚገኘው የኮሜርሻል ኖሚኒስ ጽሕፈት ቤት ደብዳቤ በመጻፍ፣ የጥበቃ ሠራተኛውን በሌላ እንዲተካላቸው ጠይቀው እንደነበር ገልጸዋል፡፡

የኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃላፊዎች በሠራተኞቻቸው ላይ ቅሬታ ሲደርሳቸው በቦታው በመገኘትና ሠራተኞቹንና የተቋሙን ኃላፊዎች በማነጋገር፣ ሠራተኛው ተገስጾና ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ሥራውን እንዲቀጥል ወይም እንዲባረር እንደሚያደርጉ የገለጹት አቶ ኤፍሬም፣ ተጠርጣሪውም በዕለቱ ተመክሮ፣ ተገስጾና ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት በዕለቱ ተረኛ ስለነበር መሣሪያውን ይዞ ወደ ሥራው መሰማራቱን ተናግረዋል፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ ግን ሁለት የፍተሻ ሠራተኞችን አቁስሎ ሌሎቹን መግደሉን አስረድተዋል፡፡

የተገደሉት የባንኩ ሠራተኞች የቀብር ሥነ ሥርዓት መፈጸሙን ያስታወቁት አቶ ኤፍሬም፣ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ወልዳይ ገብሩ ቤተሰቦቻቸው በሚኖሩበት በዓደዋ ልዩ ስሙ ወርኢ ዳጋብር ቀብራቸው እንደተፈጸመም አክለዋል፡፡ ኮንትሮለሩ አቶ አትንኩት ደምሴ በትውልድ ሥፍራቸው ባህር ዳር የቀብራቸው ሥርዓት ተፈጽሟል፡፡ ወ/ሮ ለምለም ግደይና የኮሜርሻል ኖሚኒስ ሁለቱ ሠራተኞች አቶ ንጉሤና አቶ ጌትነት፣ በዚያው በማይፀብሪ ቀብራቸው ሲፈጸም፣ አቶ አስማማው ከማይፀብሪ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ዲማ በሚባለው አካባቢ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡

ባንኩ በሠራተኞቹ ላይ በደረሰው ያልታሰበና ድንገተኛ አደጋ ጥልቅ ሐዘን እንደተሰማው የገለጹት አቶ ኤፍሬም፣ ሠራተኞቹ መገደላቸው ከተሰማበት ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ቀብራቸው እስከተፈጸመበት ዕለት ድረስ፣ የመቀሌ ዲስትሪክት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አሻግሬ አስመላሽ በሥፍራው ተገኝተው ያደረጉት አስተዋጽኦም ከፍተኛ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ የንግድ ባንክ ጠቅላላ የጥበቃዎች ሥራ አስኪያጅም እዚያው ሆነው ጉዳዩን እየተከታተሉ መሆኑን አቶ ኤፍሬም አስታውቀዋል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

The post የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስድስት ሠራተኞች በጥይት ተገደሉ appeared first on Zehabesha Amharic.


የአለም ሀገራት ባሰፈኑት የህግና ፍትህ ስርአት ምዘና ኢትዮጵያ ከ102 የአለም ሀገራት 94ተኛ ደረጃ ተሰጥቷታል

$
0
0

Justiceዎርልድ ጀስቲስ ፕሮጀክት የተባለው በአለም ላይ ፍትህና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እሰራለሁ የሚል ተቋም የ 102 የአለም ሀገራትን የፍትህና ህግ ስርአት ደረጃ ይፋ አድርጓል፡፡ ከተለያዩ ሀገራት ከ 100 ሺህ የማያንሱ ህዝቦችን መጠይቅ በማድረግ ጭምር የተጠናቀረው ይህ የተቋሙ ሪፖርት በዚህ ረገድ የኢትዮጵያችንንም ደረጃ ይፋ አድርጓል፡፡

የፍትህና ህግ የበላይነት ጉዳይ ብዙ ጊዜ የህግ ሰዎች ስራ ብቻ ተደርጎ ሊታይ ይችላል ነገር ግን ሁላችንንም በየእለቱ የሚያጋጥም የእለት ተእለት ጉዳይ ነው ያለው ተቋሙ የአለም መንግስታት ለዜጎቻቸው ያላቸው ግልጽነትና ተጠያቂነት የሚለካውም በዚሁ መስፈርት እንደሆነ ነው ያስቀመጠው፡፡

ሪፖርቱ በዋናነት የአለም መንግስታት ለዜጎቻቸው የቱን ያክል ግልጽነትና ተጠያቂነት አስፍነዋል የሚለውን ሲያስቀምጥም በአራት መስፈርቶች እንደመዘናቸው ነው የገለጸው፡፡ መንግስታቱ በተጻፉ ህጎችና መረጃዎች ነው ወይ ህዝባቸውን የሚያስተዳድሩት የሚለው ቀዳሚው መስፈርት ሲሆን፣ የዜጎች መረጃ የማግኘት መብት፣ የሲቪክ ማህበራት ተሳትፎ፣ እንዲሁም ቅሬታና አቤቱታ አፈታት በሚሉ አራት መመዘኛዎች ሀገራቱ መገምገማቸው ታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት ከአጠቃላይ 102 ሀገራት ውስጥ ስዊድን፣ ኒውዚላንድና ኖርዌይ እጅግ ግልጽ የሆኑ የመንግስት ስርአት የሰፈነባቸው ተብለው የህግና ፍትህ ስርአታቸው ሲወደስ እንደ ማይናማር፣ ኡዝቤኪስታንና ዚምባብዌ ያሉ ሀገራት ደግሞ መንግስታቶቻቸው ዝግ በሆነና ፍትህና ህግ ባልሰፈነበት ሁኔታ ህዝባቸውን የሚያስተዳድሩ ተብለው በመጨረሻዎቹ እርከኖች ላይ ሰፍረዋል፡፡

የኢትዮጵያችንንም ደረጃ ያስቀመጠው ይህ ሪፖርት በአራቱም መስፈርቶች መልካም የሚባል ውጤት እንዳላገነች ነው ይፋ ያደረገው፡፡

በተጻፉ ህጎችና መንግስታዊ መረጃዎች 73ተኛ፣ በመረጃ ማግኘት መብት 79ኛ፣ በዜጎች ተሳትፎ 97ተኛ፣ እንዲሁም በቅሬታ አፈታት ስርአት 89ኛ ደረጃዎችን ያገኘችው ኢትዮጵያችን ይህ ደግሞ በዚህ ሪፖርት በአጠቃላይ ውጤት ከ 102 ሀገራት በ 94ኛ ደረጃ ላይ እንድትሰለፍ እንዳደረጋት ነው የተነገረው፡፡

The post የአለም ሀገራት ባሰፈኑት የህግና ፍትህ ስርአት ምዘና ኢትዮጵያ ከ102 የአለም ሀገራት 94ተኛ ደረጃ ተሰጥቷታል appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢትዮዽያዊው በአሜሪካ 122 አመት ተፈረደበት

$
0
0

በአሜሪካን ሀገር በሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮዽያዊያን ስደተኞች ይኖራሉ! እነዚህ ስደተኞች ከጥቃቅን ስራዎች አንስቶ እስከ_ታላላቅ ካምፓኒዎች በወዛቸው ያገኙዋትን ዶላር አጠራቅመው አንድ ቀን ሀገሬ እገባለው ከሚል ተስፋ ጋር ሕይወትን ይገፋሉ::Ethiopians

ህልሙ የሞላለት ጥቂቱ ጠቅልሎ ሲመጣ አብዛኛው ግን በዥዋዥዌው የአሜሪካ ህይወት ባለበት ሰምጦ ይቀራል! ስደት የእድሜ ወፍጮ ነው! በአምስት አመት ውስጥ ሀገሬን አያታለው ያለ ዲያስፖራ ሳይታሰብ ስምንት የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ምርጫ መታዘቡን ሲያሰላው ስደት ከወጣም ከሰላሳ አመት መዝለሉ ትዝ ይለዋል! ነገ ያሉት እቅድ ተራራ የመግፋት ያህል ይከብድና የተስፋ ሞተርም እየቀዘቀዘ ይመጣል! ይሄ ሁሉ “ምን ይዤ ልግባ?” ከሚል ይሉኝታ የሚፈጠር ሰውኛ ጭንቀት ነው! በእርግጥ ዲያስፖራዎች ያሳዝናሉ::

ለአንድ ራሳቸው የሚሆን ቅሪት ቢፈጥሩ እንኩዋን አናት_እያከከ የሚጠብቃቸው ነብሳት ብዙ ነውና ሀገር ቤትን እንደ_ናፍቆታቸው ሊመለሱበት ይፈሩታል! እናም “ወይ_ሀገሬ” ከሚል የትዝታ ዜማ ጋር የአሜሪካ ሰፊ ከርስ ውጦዋቸው ይቀራል! እንደዚህም ሆኖ ሀገራዊ ምስላቸው ሸጋ ገፅታ ይዞ ኖሮዋል! ሰሀንም አጥበው ነገን ለፈጣሪ ይተውታል እንጂ ገንዘብ ፍለጋ አጉል መንገድ አይሞክሩም! ባለፈው ማርች ወር ግን እውነት ይሄ ሰው የአበሻን ውሃ የጠጣ ነው? ያስባለ ጋንግስተር ኢትዮዽያዊ የአሜሪካ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር! ኢትዮዽያ ውስጥ የተወለደው የ42 አመቱ “ወሰን_አሳየ” እ.ኤ.አ ከ2013 ኦክቶበር አንስቶ 12 ባንኮችን መዝረፉ ሳያንሰው በህግ ጥላ ውስጥ ከዋለ በዋሃላም ጀብዱ መስራቱን አላቆመም! በፖሊስ ታጅቦ ከሄደበት ሆስፒታል የፖሊሱን ሽጉጥ ነጥቆ በማምለጥ በሂሊኮፕተር ሳይቀር በተደረገበት ክትትል ተይዞ ዛሬ 122 አመት ተፈርዶበታል::

The post ኢትዮዽያዊው በአሜሪካ 122 አመት ተፈረደበት appeared first on Zehabesha Amharic.

  መውደቂያ ያጣ እንባ

$
0
0

ውሀ በጠማው በረሀ በደረቀ የምድር ሀሩር
የሠማይ ዝናብ ይመሥል የወንድሜ ደም ሲገበር
ኑሮ ለገፋው ወገኔ ሰይፍ ካፎቱ ሲመዘዝ
የሰው ልጅ ልክ እንደስሳ አንገቱ አንዲህ ሲገዘገዝ
ሀዘኑ ሆዴን ቢያምሠው ስቀት አንጀቴ ቢገባ
ቁስለቴ ሽቅብ አንስቼ የውስጤን ህመም ላሠማ
አንድባይ ገላገይ ሽቼ ወጣሁኝ ከአገሬ ማማ
ግን ጩኸቴ  እንደመናኛ እንኳንስ ሊሠጠው ስፍራ
እንዳጠፍ ወንጀለኛ ልባቸው ጥቂት ሳይራራ
ማልቀሻ ነሱኝ በአገሬ ሀዘኔም እንዳያባራ
ያብሡልኛል ያልኳቸው ለአይኖቼ ውሀ ግደባ
ወታደር ልከው አሠሩኝ ቁስሌ ልባቸው ሳይገባ
እንኳን ከፊቴ ሊታበስ መውደቂያ ያጣው የእኔ እንባ
ቁልቁል ደረቴን ሰንጥቆ ደም ከሞላው ልቤ ገባ ፡፡

ይርጋለም ዘለቀ

KONICA MINOLTA DIGITAL CAMERA

 

The post   መውደቂያ ያጣ እንባ appeared first on Zehabesha Amharic.

ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው ክስ ተመሰረተባት- በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

$
0
0

11257577_718473044945023_8620623119912413467_nሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም በመንግስት ተጠርቶ ከነበረው ሰልፍ ጋር በተያያዘ በምርጫ ማግስት ግንቦት 19/2007 ዓ.ም ለእስር የተዳረገችው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው ክስ ተመሰረተባት፡፡
ዛሬ ግንቦት 26/2007 ዓ.ም በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ችሎት የቀረበችው ወ/ሮ ንግስት፣ በፌደራል አቃቤ ህግ ከሳሽነት በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና 490/3/ የተመለከተውን በመተላለፍ የሚል ክስ ቀርቦባታል፡፡
ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም በነበረው ሰልፍ ላይ ‹‹ወያኔ ሌባ፣ መንግስት አሸባሪ፣ ታርዷል ወገኔ፣ ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ፣ ወያኔ አሳረደን፣ ናና መንግስቱ ናና፣ ወያኔ አሸባሪ…በማለት እጅን አጣምሮ ወደላይ በማድረግ ታስረናል›› በማለት ሰላማዊ ሰልፉ እንዲታወክ አድርጋለች በሚል ተከሳለች፡፡ በተጨማሪም በሚያዝያ 13/2007 ዓ.ም ቂርቆስ አካባቢ ‹‹ስብሰባን ወይም ጉባኤን›› በማወክ እንደተከሰሰች የክስ ቻርጁ ያሳያል፡፡
ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም ፍርድ ቤት በቀረበችበት ወቅት ፍርድ ቤቱ ለግንቦት 28/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶ የነበር ቢሆንም ‹‹በምስክሮች ላይ ማስፈራራት እየተፈጸመ ስለሆነና ምርመራየንም ስለጨረስኩ›› በሚል ፖሊስ ዛሬ ቤተሰቦቿ እንኳ ሳይሰሙ ወ/ሮ ንግስትን ፍርድ ቤት አቅርቦ ክስ መስርቶባታል፡፡
ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው በቀጣይ አርብ ግንቦት 28/2007 ዓ.ም ለሶስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ትቀርባለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

The post ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው ክስ ተመሰረተባት- በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር appeared first on Zehabesha Amharic.

የወያኔ 100% የምርጫው ድራማ –ከደምሰው ደስታ

$
0
0

34መላዋ ኢትዮጵያ እስር ቤት በሆነችበት ከአሳሪዎቹ ከወያኔ ኢህአዴግ በስተቀር ከ 82 በላይ ብሄር በሄረሰቦች በጠቅላላ በጽኑ እስር ላይና አሳራቸውን በመብላት ላይ ይገኛሉ። ለናሙና ያህል ብንመለከትም ኦልባና ለሊሴና ጓደኞቹ ከኦሮሞ፤ አንዷለም አራጌ፣ የሽዋስ አሰፋና ጓደኞቹ ከአማራ፤ አብርሃ ደስታ ከትግራይ፤ ኦኬሎ አኳይና ጓደኞቹ፣ ከጋምቤላ፤ ባሽር ማክታልና ጓደኞቹ፣ ከሶማሌ ጂጅጋ፤ ዳንኤል ሽበሺና ጓደኞቹ ከደቡብ፤ እስክንድር ነጋ፣ ርእዮት፣ ዉብሸት፣ አቡበክር ፣ከአዲስ አበባ እና ሌሎች ወዘተ ስብጥር ስናይ በእስር ቤት የብሄር ብሄረሰቦችን ተዋጽኦ ለማረጋገጥ በሚመስል መልኩ ወገኑ ያልታሰረበት የሃገሪቱ ክልል በሌለበት ሁኔታ እንዴት ወያኔ 100 % ተመረጡኩኝ ሲለን ትንሽ እንኳን ኢትዮጵያዊ ይ ሉንታ የለበትም።

ከእስር ቤት በስተቀረ የመከላከያ አዛዥነትን ብንመለከት ግን ከ 60 ከፍተኛ መኮንን ውስጥ 58 ቱ ከትግራይ ብቻ በጤናውም እንደዛው የተመደቡ ናቸው ። በየሃይማኖት ተቋማት፥ ብ አዴንም ሆነ በሌሎችም መሰሎች የኢህዲግ ፓለቲካ ድርጅቶች፥ በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የመሪነቱን ሚና በሞኖፓሊ የሚሾፍረረው ወያኔና ወያኔ የሆነ ብቻ ነው።

አባዱላ የተወዳደሩበትን ጨምሮ በበርካታ የምርጫ ጣቢያዎች በህጉ ከተቀመጠው ከመራጭ ቁጥር በላይ ድምፅ ተሰጥቷል ይለናል ሪፖርተር። ነገርዬዋ ግን የድምር ስህተት ናት ወይስ የአስመራጮቹ የኮሮጆ አሞላል ልምድ እጥረት ??? መቼም ከ 1000 በላይ መራጭ ባልተመዘገበበት ጣቢያ ከ 1400 ሰው በላይ ድምፅ ሰጥቶ ኢህአዴግ አሸነፈ ብሎ ማወጅ “ሁሉን አቀፍ” ተቀባይነት አግኝቷል ከተባለለት ቦርድ የሚጠበቅ ሊሆን አይችልም ። ወይ አላጋጭ ቦርድ።

ኢትዮጵያን በገጠርና በከተማ ከፍለን ብናይም መላ ገጠሬው መላ ከተሜው ታስሯል። ገበሬውን አንድ ለአምስት በሚሉት የትብተባ ገመድ በመተብተብ ወሬኛ አድርጎታል። በሰንበት ሳይቀር የሃይማኖት ተቋማትን እንዲተው በማደረግ የክህደት አብዮታዊ ወያኔነትን በግድ ይግቱታል። ከወያኔ መዋቅር አልታቀፍም ካለ የእህል ማዳበሪያ ይከለከላል ስለዚህ ይታሰራል።አንዱ ገበሬ ሌላውን እንዲሰልል በማድረግ ጥንታዊ አብሮነቱን እየሸረሸሩት ነው።

በከተማ ያለው የትራንስፓርት ችግር ሰልፈኛ አድርጎናል። የኑሮ ውድነት የስራ አጥነት ገዝፎ ስራ ለመቀጠር ዬኢ ህ አ ዴ ግ አባል መሆን የግድ ነው። የወጣት ሊግ የአዛውንት ሊግ የሴቶች ሊግ ፎረም ወዘተ የወያኔ የመዋቅር እስር ቤቶች ናቸው። መደገፍ እንጂ መቃወም አይችሉም። ጠቅላይ ምኒስትሩ ኃይለማሪያም ደሳለኝም አሻንጉሊት ናቸው። ሌሎቻችን የበይ ተመልካች መባሉ ቀርቶ ሲበሉ እንዳናያቸው ጭለማ እስር ቤት አጉረውናል። ተፈጥሮኣዊ በሆነው የመናገር የመጻፍ መብታችንን በመጠቀም ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ይኑር፣ ዜጎች በእኩልነት ይታዩ፣ መልካም አስተዳደር ይስፈን፣ የሀገር አንድነት ይጠበቅ ብለን ስንናገር ስንጽፍ እንቀሰፋለን። ይባስ ብሎ ነጻነታችንን ለመለጎም ባወጣው የጸረ ሽብር ህጉ ሰበብ ስለ ፍትህ ስለነጻነት፣ ስለዲሞክራሲ ማቀንቀን ግንቦት ሰባት ወይም ኦነግ አሰኝቶ በአሸባሪነት እድሜ ልክ ያስወነጅላል።

ስድስት ሰላማዊ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንና ሶስት ጋዜጠኞችን ያገተው የካድሬነት ስራ የሚሰራው ፖሊስ የረባ የሃሰት ክስ መጎንጎን አቅቶት ለሁለት ወራት ያህል የፍርድ ቤት ቀጠሮ ሲያራዝም ነበር። ጦማሪያኑ በየብእሮቻቸዉ የሃይል አማራጭ የሚወስዱትን ግንቦት ሰባትንና ኦነግን የሚቃወሙና በሰላማዊ ምርጫ መንግስት እንዲለወጥ የሚወተውቱ መሆናቸው እየታወቀ ግማሾቹን ከግንቦት ሰባት ገሚሶቹን ከኦነግ ጋር ግንኙነት የነበራቸው በማለት የክስ ድራማ ስክሪፕት ከሁለት ወራት መጉላላት በኋላ ጽፎ ሰጥቷቸዋል። የግንቦት ሰባት የፍትሕ የነጻነት የዴሞክራሲ ንቅናቄ መስራችና ዋና ጻሃፊ የነበሩት አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ ታፍነው መያዛቸው በተገለጸበት ቅጽበት በሰላማዊ መንገድ ሲታገሉ ከነበሩ የፓለቲካ ፓርቲዎች አባላት በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች ከሆኑት መካከል አቶ ሐብታሙ አያሌው እና ዳንኤል ሺበሺ ከአንድነት፣አቶ የሺዋስ አስፋ ከስማያዊ ፓርቲ፣አቶ አብርሃ ደስታ ከአረና ትግራይ ተይዘው ወደ ሰቆቃው ማእከላዊ ተወርውረዋል።የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን ከግንቦት ሰባት እና ከአንዳርጋቸው ጋር አቆራኝቶ ለመወንጀል እየሮጠ ያለው ወያኔ ጉልበቱን እና የሃገር አንጡረ ሃብትን በመጠቀም ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል በዜጎች ላይ እየፈጸመ ይገኛል።

እያንዳንዱን ሰው ባሰሩ ቁጥር አሽባሪ የሚል ሰም ይለጥፉበታል። የጸረ ሽብር ህጉ በጣም ልቅ የሆነ ስልጣን አጎናጽፏቸዋል ።ሕገ መንግስቱ ሰው በተያዘ በ 48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ አለበት ቢልም የጸረ ሽብር ህጉ ፓሊስ ከ ሁለት ወር እስከ አራት ወር ጊዜ በላይ ፍርድ ቤት ሳያቀርብ ማገት እንደሚችል ሰለሚፈቅድ ህገ መንግስቱ ተጥሷል። በተጨማሪም ፓሊስ በዘፈቀደ መንገድ ላይ አካሄዱ ያላማረውን ማንኛውም ሰው መያዝ እንዲሁም ያለ ፍርድ ቤት ፈቃድ ግለስብን መበርበር እንደሚችል መብት ሰጥቶታል።ፓሊስ ይህን መስል የካድሬነት ስራ እንዲሰራ ያደረገው ህገ መንግስቱ ተጥሶ ነው።

በሰላማዊ መንገድ እንንቀሳቀሳለን የሚሉት ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች ወያኔ በሰራው አጥማጅ ህግ ከመከሰስ አላመለጡም። ሃሳባችሁን በግል ሚዲያዎች ጋዜጦች፥በኢሳት ቴሌቪዥን በኢንተርኔት ወዘተ ለምን ገለጻችሁ ተብሎ ፓለቲከኞቻችንና የግል ጦማርያንም ታስረዋል።በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ኢብኮ) እንዳይጠቀሙ ማድረጉ ሳያንስ የግል ሚዲያዎች ኢሳትን ጨምሮ መከልከሉ ምንም አትተንፍሱ ሙቱ ማለት ነወ። ሃገር ቤት ያሉ የመጽሄት የጋዜጣ አዘጋጆች የጸረ ሽብር ህጉ ማንኛውም ጽሁፍ አንቀጸ ፮ ሊያስጠይቃቸው ሰለሚችል በጣም እየፈሩ ይገኛሉ። ሁላችንም የፖሊስን ዱላና እስር ቤት ጸበል ጸዲቅ እየተጋፋ እየቀመስን ነው። መንግስት በግልጽ ጣልቃ በሃይማኖት ውስጥ በመግባት የራሱን ካድሬ ቄስና ካድሬ ሼክ ሾሟል ። ይህንን የተቃወሙ ሙስሊሞች በየጁምአው እየታስሩ ይገኛሉ ።ድምጻችን ይስማ እያልናቸው ያፍኑናል። እስከመቼ አንዱ ሲታስር አንዱ ቆሞ ያያል። ቆሞ የሚያያውም ሰለማያገባው ሳይሆን የወያኔን ዱላና እስር በመፍራት ነው። እስከመቼ ሁላችንም በፍርሃት ተሽብበን እንኖራልን ????? የፍርሃት ድባብን በመስበር የታሰርንበትን የፍርሃት ሰንሰለት እንበጥስው።

ከቃሊቲ፥ከማዕከላዊ፥ከዝዋይ፥ከብርሽለቆና ሌሎችም ቦታዎች የታስሩት ወገኖቻችንን ማስፈታት የምንችለው በዞን አስር ታስረን በተወሰነ መልኩ የምንንቀሳቀሰው ሰዎች ነን። ኑሮ ተወደደ ዘረኝነት ስር ሰደደ ብለን ስለተቃወምን የሚገድለን ዘረኛ ፋሺስት ቅኝ አገዛዝ ተወግዶ በዲሞክራሲያዊ በህጋዊ መንገድ የተመረጠ የመንግስት ስርዓት እንዲኖረን የምንፈልግ ፍትህ የናፈቀን ለራሳችን ነጻነት ስንል ለፍልሚያ መዘጋጀት ግድ ይለናል።

The post የወያኔ 100% የምርጫው ድራማ – ከደምሰው ደስታ appeared first on Zehabesha Amharic.

በኢትዮጵያና ሱማሊያ ድንበር ውጥረቱ አይሏል * በትናንትና ዛሬ ጠዋት ጦርነት 19 ሰዎች ሞቱ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) 2ኛ ሳምንቱን የያዘውና በሶማሊያና በኢትዮጵያ ድንበር ባሉ መንደሮች አካባቢ በተነሳ ጦርነት ትናንት ረቡዕ እና ዛሬ ሐሙስ በተደረጉ ውጊያዎች የ19 ሰዎች ሕይወት ማለፉን እና ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ዜጎች ቁስለኛ መሆናቸውን ዘ-ሐበሻ ከስፍራው ያገኘችው መረጃ አመለከተ::

boarder

በድንበሩ አካባቢ ትናንትና ዛሬ በ3 መንደሮች አካባቢ 2 ውጊያዎች መደረጋቸውን ያስታወቁት የአካባቢው የዜና ምንጮች በዚህ ውጊያ ሳቢያ የአካባቢው ነዋሪዎች ንብረታቸውን እና ቤታቸውን ጥለው ለመሰደድ በቅተዋል::

በሶማሊያና በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ባሉት መንደሮች አካባቢ የተነሳው ጦርነት እስካሁን ግልጽ አለመሆናቸውን የሚጠቁሙት የዜና ምንጮች በደፈናው የዘር ግጭት ነው ሲሉት ይገልጹታል:: በዚህ ጦርነት ዙሪያ የሶማሊያም ሆነ የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን ለማርገብ ምንም አይነት ንግግር አለማድረጋቸውም ተዘግቧል::

በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር ባሉ መንደሮች ላለፉት ዓመታት በዘር ግጭት የተለያዩ ጦርነቶች ሲደረጉ የቆዩ መሆናቸውን የሚጠቁሙት የዜና ምንጮቹ የኢትዮጵያም ሆነ የሱማሊያ መንግስታት ዜጎቻቸው እየተላለቁባቸው ጉዳዩን በዝምታ ማለፋቸው በጣም አሳፋሪ ነው ብለውታል::በተለይም የኢትዮጵያ መንግስት ጦሩን ወደዚያ ከማስጠጋት ውጪ ጉዳዩን ለማረጋጋት ያደረገው ይኸ ነው የሚባል ሥራ አለመስራቱ እየተተቸ ነው::

The post በኢትዮጵያና ሱማሊያ ድንበር ውጥረቱ አይሏል * በትናንትና ዛሬ ጠዋት ጦርነት 19 ሰዎች ሞቱ appeared first on Zehabesha Amharic.

ዛሬም አይመረንም –ይገረም አለሙ

$
0
0

ግንቦት 2005

electionምርጫ 2007 ከተጠናቀቀ በኋላ የተለያዩ ነገሮች እየሰማን ነው፡፡ምርጫ ማለት በእለቱ ጠዋት 12 ሰአት ተጀምሮ ምሽት 12 ሰአት የሚጠናቀቀው ሂደት አይደለም በሚል በተለያዩ ምሁራን የተሰጠው አስተያየት እውነትም ትክክልም ነው፡፡  ከወያኔ በስተቀር የሌሎቹን ተወዳዳሪዎች ዝግጅትና ሂደት እንደታዘብነው ሙሉ ትኩረታቸው የድምጽ መሽጫ እለቱ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ ይህም በመሆኑና በቂ ቅድመ ዝግጅት ባለማድረጋቸው ወያኔ በቀላሉ ታዛቢዎቻቸውን ከጨዋታ ውጪ በማድረግ በየምርጫ ጣቢያው የተቀዋሚዎቹን ውጤት ዜረ0 ማድረግ ቻለ፡፡

አራት አመት ሙሉ ምንም ሳይሰራ ወይንም ለምርጫ ተወዳዳሪነት የሚያበቃ ቅድመ ምርጫ ሥራ ሳይሰራ( በወያኔ ጫናም በራስ አቅም ማጣትም) የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔን ስለሚጠላ ይመርጠናል በሚል ብቻ ወያኔ የራሱንም የምርጫ ቦርድንም ስራ አጠናቆ በቦርዱ ስም የምርጫ የግዜ ሰሌዳ ሲያወጣ የምርጫ ሥራ የሚጀምሩ ፓርቲዎች እንዲህ አሳፋሪ ለሆነ ውጤት ይዳረጋሉ፡፡ የምርጫ አንዱ ዝግጅት ማጭበርበርን ማስቀረት የማይቻል ቢሆንም መግታት የሚያስችል መሆን አለበት፡ለዚህ የሚያበቃ ዝግጅት ከሌለ ወይንም የወያኔ የማጭበርበር ዝግጅትና ድፍረት የማይቻል መሆኑ ከታወቀ ወደ ምርጫ አይገባም፤ ቢገባም ጫናው ሲበረታ ይወጣል፡፡ የምርጫው ውጤት አስቀድሞ የታወቀ ነው እያሉ አጃቢ ሆኖ መዝለቅ ግን ምን ይሉት ስትራቴጂ እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ ሌላ ቀርቶ ይህ ካልሆነ እንዲህ መደረጉ ካልተገታ ከምርጫው እንወጣለን (ለአፋቸው እንኳን) ያሉ የሉም፡፡

በምርጫ ተወዳድሮ ስልጣን መያዝ ወይንም መጋራት ሲታሰብ፤

በአራት ዓመታት ውስጥ

1-ድርጅታዊ አቅምን ማጎልበት; ማለትም በፕሮፓጋንዳ ሳይሆን በተግባር መሬት መርገጥ፡

2-ለምርጫ ተወዳዳሪነት የሚያበቁ ተግባራትን ማከናወን፤ማለትም

ሀ-ዓላማቸውን በአጭሩና በግልጽ የሚያስረዱ ሰነዶችን ማዘጋጀት፤ማሰራጨት፡

ለ-እምነት ጽናትና ብቃት ያላቸውን ዕጩ ተወዳዳሪዎች ማዘጋጀት፤

ሐ-ታዛቢዎችን በብዛትና በጥራት ማዘጋጀት፤

3-የፖለቲካ ምህዳሩ ሁሉን በእኩል ደረጃ ማወዳደር የሚችል እንዲሆን ጉድለቱን፤አድሎአዊነቱን ወዘተ በበቂ ማስረጃ እያሳዩ አማራጭ ሀሳብ እያቀረቡ በሁሉም መንገድ መታገል፤ ሕዝቡን የዚህ ትግል ኣካል በማድረግ ማንቀሳቀስ፡፡

4-ነጻ ፍትሀዊና ተአማኒ ምርጫ ለማካሄድ የሚያበቁ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ አማራጭ ሀሳቦችን በማቅረብ ሁለንተናዊ ትግል ማካሄድ፡፡ (ምርጫ ቦርድ ነጻ ተቋም እንዲሆን ማስቻልን ዋና ስራ ያደረገ)

5-በጠመንጃ የያዘውን ሥልጣን በጠመንጃ አስጠብቆ የሚኖረው ወያኔ ለነጻ ምርጫ ፈቃደኝነቱም ዝግጁነቱም እንዳማይኖረው ስለሚታወቅ ምርጫ ሊያጨበረብርባቸው የሚችሉ ቀዳዳዎችን ሁሉ ለመድፈን ካልሆነም አስቀድሞ በተአማኒ ማስረጃ ለማጋላጥ መስራት፡፡

እነዚህና ተመሳሳይ ተግባራት በአራት ዓመታት ውስጥ ተከናውነው  የመጨረሻው ምርጫ የሚካሄድበት ዓመት ላይ  የተሰሩ ስራዎች ተገምግመው በሚገኘው ውጤት መሰረት በምርጫ መወዳደር ወይንም አለመወዳደር ይወሰናል፡፡ ውሳኔው መወዳደር ሆኖ ወደ ምርጫ ፉክክር ከተገባ ደግሞ  የእለት ተእለቱ እንቀስቃሴ በቅጡ እየተፈተሸ የመወዳደሩ ፋይዳ እየተገመገመ ወያኔ ሥልጣን ወይም ሞት በሚለው መርሁ እስከምን ድረስ የከፋ ተግባር  ሊፈጽም እንደሚችል እየተጤነ እስከ መጨረሻው መዝለቅ አለያም በማናቸውም ግዜ ከምርጫው የመውጣት ውሳኔ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡

የምርጫ 2007ን ሂደት ግን ከዚህ በተቃራኒ ነው፡፡ ተቀዋሚዎች በምርጫው ማግስት የሚሉትን ማለትም ድምጽ ተዘረፈ፤ታዛቢ ታሰረ ታፈነ፤ተወዳዳሪ ተከለከለ፤ነጻነት በሌለበት ነጻ ምርጫ ማካሄድ አይቻልም ወዘተ ከምርጫው በፊት አያውቁትም ነበር ማለት አይቻልም፡፡ ነገር ግን ከምርጫ 2002 እስከ ምርጫ 2007 በነበሩት አመታት እነዚህ ነጻ ምርጫ ለማካሄድ የማያበቁ ያሉዋቸው ጉዳዮች እንዲለወጡ ወይንም እንዲሻሻሉ ምን ሰሩ ብለን መለስ ብለን ብንቃኝ የምናገኘው ብዙም ነገር የለም፡፡ በወቅታዊ ትኩሳቶች ላይ የተሳካም ያልተሳካም ሰላማዊ ሰልፍ ሲያዘጋጁ አንድም ቀን “ለነጻ ምርጫ ነጻ  ምርጫ አስፈጻሚ” ብለው አያውቁም፡፡ እንደውም ወያኔ ሌላ ሌላው የሰራው አልበቃ ብሎት ምርጫ 97ን እያሰበ በቅዠት መንፈስ  የሰላማዊ ሰልፍ ቦታ በየጽ/ቤቶቻቸው ጓሮ  መርጦላቸው የሚሄዱበትንም መንገድ ሲወስንላቸው በጸጋ ተቀብለው ሰልፍ እየወጡ ትልቅ የፖለቲካ ስራ እንደሰሩ ያናገሩ ነበር፡፡ እሱ ይህንን ያደረገው ምርጫን እያሰበ ሲሆን እነርሱ ከጊዜያዊ ፕሮፓጋንዳ በዘለለ ስለምርጫ አስበውና የዝግጅታቸው አንድ አካል አድረገው ነበር ብሎ ደፍር መናገር የሚቻል አይመስለኝም፡፡

በምርጫ 2002 ተቀዋሚው አንድ ወንበር ባገኘበት፤ ወያኔ ያንን ውጤት ለማስጠበቅ አይደለም አንድም ተቀዋሚ በፓርላማ ላለማየት የራሱን አውራ ፓርቲነት አውጆ መኖር ያለባቸው ታማኝ ተቀዋሚዎች ብቻ ናቸው ብሎ በይፋ ነግሮ ሌሎች እንዳይንቀሳቀሱ መንገዱን ሁሉ ዘግቶ ባለበት ምን ሰርተው ምን ጥንካሬ ፈጥረው ምን ተማምነው ወደ ምረጫ ገቡ ብለን ብንጠይቅ ቀናና ተገቢ ምላሽ የሚኖራቸው አይመስለኝም፡፡የማስተዋል ችግር ካልሆነ በስተቀር አንድነትን ባፈረሱበት ወቅት ፕ/ር መርጊያ “ለሚታዘዙንና ከእኛ ጋር ተስማምተው ለሚሰሩ ሰጥተናል” በማለት አስበውትም ይሁነን አምልጦአቸው የተናገሩት ለምርጫ 2007 ውጤት ግልጽ አመላካች ነበር፡፡

ምርጫ ከገቡ በኋላም ምርጫ ቦርድና ወያኔ አንድም ሁለትም ሆነው ለምርጫ ቅስቀሳ ቃላትን ሳይቀር ሲመርጡላቸው፤እጩዎቻቸውን አለመዘግብ ሲሏቸው፤ ተወዳዳሪ ፓርቲዎችን አሸባሪ የውጪ ተላላኪ ወዘተ እያሉ ፕሮፓጋንዳ ሲሰሩባቸውና አባሎቻቸውን ሲያስሩ ወዘተ የሚሆነውን እየተቀበሉ አድርጉ የተባሉትን እያደረጉ(ለምሳሌ እንዲህ ብላችሁ እንዳትቀሰቅሱ፤በክርክር መድረክ ላይ እንዲህ አይነት ቃላትን አንዳትጠቀሙ ወዘተ)  እስከ መጨረሻ የመቀጠላቸው ዓላማ ግልጽ አይደለም፡፡

በምርጫው እስከ መጨረሻው በመቆየታችን ወያኔን አጋልጠናል የሚል ቃል ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች እየሰማን ነው፡፡ በጣም የሚገርም ነው፡፡ ለመሆኑ ወያኔ ከምርጫ 97 ያለፈና ከምርጫ 2002 የቀረ ምን የተደበቀ ማንነት ነበረው፡፡በምርጫ 2007 አስቀድሞ የማይታወቅ ከዚህ በፊትም ያልሰራው ምን አዲስ ነገር አደረገ ፣ ምን አዲስ ባሕርይ አሳየ፡፡ ፖለቲከኞቻችን ራሳቸውን አጋልጠው ካልሆነ በስተቀር ወያኔን ያጋለጡበት አንድም ነገር የለም፡፡

ባለፉት 24 ዓመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ ያላወቀው አንድም የወያኔ ማንነትና ምንንት የለም፡፡ በምርጫ ተወዳድረው ያሸነፉትን የሚያስር፤ስለ ሰላም የሚዘምሩትን ጦረኛ የሚል፤ስለ ሀገር አንድነት ነጻነትና ሉዐላዊነት የሚታገሉትን በሀገር ክህደት የሚከስ፤ስለ ሰው ልጅ እኩልነት፣ ስለ አንድ ሀገር ልጅነት ስለ አብሮነት የሚያስተምሩትን በዘር ማጥፋት ወንጀል የሚከስ እጃቸው ከብእርና ከኪቦርድ ውጪ ነክቶ የማያውቅ አዳዲስ ሀሳብ አፍላቂዎችን አሸባሪ ብሎ የሚከስ ወዘተ ወያኔ ምን የተደበቀ ማንነት ኖሮት ነው በምርጫው እስከ መጨረሻው በመዝለቃችን አጋለጥነው የሚባለው፡፡

እንዲህ አይነቱን ራስን ለማጽናኛና ወቅታዊውን መነጋገሪያ ጉዳይ ለማድበስበሻ የሚቀርቡ ረብ የለሽ ነገሮችን ተወት አድርገን እውነቱን ለመናገርም፡ የሚነገሩና የሚጻፉ እውነቶችን ለማዳመጥም ወኔ፣ድፍረት ቅንነት ይኑረን፡፡ትግላችንን ውጤት አልባ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ በእውነት ስለ እውነት ለመነጋገር መድፈር አለመቻላችን ነው፡፡ ስራችን የታይታ፣ጽሁፍ ንግግራችን የፕሮፓጋንዳ፤አስተሳሰባችን ከራስ በላይ ነፋስ ጉዞአችን በጥላቻ የተተበተበ ፖለቲካችን የሴራ ሆኖ በድል አልባ ትግል ለወያኔ አገዛዝ በየአምስት አመቱ ህጋዊነትን እያላበስን እንኖራለን፡፡ እስቲ አሁን አንኩዋን ይቆጨን፤ከመማረር አልፈን ለማምረር እንሞክር፡፡ እናም ሰበብ መደርደሩ ምክንያት ማብዛቱ ይቆየንና 24 ዓመት ሙሉ በተደረገው ትግል ለውጥ ማምጣት ያልተቻለው  ለምንድን ነው ብለን መነጋገር እንጀምር፡፡ የነገ ጉዞ እቅድ ዝግጅታችን ከዚህ ውጤት ይመንጭ፡፡

 

 

The post ዛሬም አይመረንም – ይገረም አለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.


ወጣት መሆን በኢትዮጵያ (ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ)

$
0
0
(ፍቅሬ ቶሎሳ፥ ፒ ኤች ዲ – የሁማኒቲስ ፕሮፌሰር)

(ፍቅሬ ቶሎሳ፥ ፒ ኤች ዲ – የሁማኒቲስ ፕሮፌሰር)

ወጣት መሆን ወንጀል ነው

በኢትዮጵያ ምድር፤

ደም ያስተፋል፥ ያስከፍላል ከባድ ዋጋ፥

ያስቀፈቅፋል ያልተበደሩትን ብድር።

ወጣት መሆን ያስኮንናል፥

ኢትዮጵያ በሚሏት ሃገር፥

የመከራ አዘቅት ውስጥ ይፈጠፍጣል፥

ባልዋሉበት ዋሉ አሰኝቶ፥ አስበይኖ ባልሠሩት ነገር

[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

 

 

The post ወጣት መሆን በኢትዮጵያ (ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ) appeared first on Zehabesha Amharic.

ሰማያዊ የG-7 መሪዎች በኢህአዴግ ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳሰበ

$
0
0

semayawi 2

semayawi
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ነገ ግንቦት 29/2007 ዓ.ም በሚካሄደው የG-7 ስብሰባ መጋበዛቸውን ተከትሎ የወቅቱ የጉባኤው መሪ ለሆኑት የጀርመን ቻንስለር ለአንጌላ ሜርክል በፃፈው ደብዳቤ መሪዎቹ በኢህአዴግ ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በስብሰባው ላይ መጋበዛቸው ቅር እንዳሰኘው የገለፀው ፓርቲው 24 አመት በስልጣን ላይ የቆየው የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ፓርቲ አፋኝ ለመሆኑ የ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫን በምሳሌነት ጠቅሷል፡፡ ምርጫው ልምድ ያላቸው የውጭ ታዛቢዎች ያልተገኙበትና የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድንም ‹‹ነፃና ፍትሓዊ›› ነበር ለማለት ያልደፈረበት፣ ሰማያዊን ጨምሮ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተጭበረበረ መሆኑን ማረጋገጣቸውን በደብዳቤው አስታውሷል፡፡

ምርጫው ገዥው ፓርቲ 100% አሸነፍኩ ያለበት፣ ተቃዋሚዎች ላይ ከፍተኛ ጫናና እስር ከዚህም ሲያልፍ ለሞት የተዳረጉበት ነበር ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ገለልተኛ ሲቪክ ማህበራት እንዳይታዘቡ መከልከላቸውን ገልጾአል፡፡ ጋዜጠኞችን፣ ጦማሪያንን፣ የሀይማኖት አባቶችንና ፖለቲከኞችን ለማጥቃት በወጣው የፀረ ሽብር ህግ ምክንያት ኢትዮጵያ በፖለቲካ እስረኞች ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚዋ መሆኗን ፓርቲው አስታውሳል፡፡

የጉባኤው አባላት ከኢትዮጵያ ጋር ባላቸው የንግድ ግንኙነትና በሚያበረክቱት እርዳታ ምክንያት በሰብአዊ መብት፣ ዴሞክራሲና ልማት ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችሉ ቢሆንም የኃይለማርያም ደሳለኝ ፓርቲ የሚመራው መንግስት ለሰብአዊ መብት፣ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እየገደበና ተቃዋሚዎች ላይ ከፍተኛ በደል እያደረሰ ይገኛል ብሏል፡፡

ጉባኤው ሰብአዊ መብትና ዴሞክራዊያዊ መብትን ለልማትና የኢኮኖሚ ግንኙነት በቅድመ ሁኔታነት በመውሰድ ጫና ማድረግ ካልቻለ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ግንባታን እንደሚጎዳም ሰማያዊ ፓርቲ አሳስቧል፡፡ በመሆኑም ጉባኤው የፖለቲካ እስረኞች ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፣ ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን ማሰርና እንቅስቃሴያቸውን ከመገደብ እንዲቆጠብ እና አፋኝ አዋጆች ላይ ማሻሻያዎች እንዲደረግባቸው በኢህአዴግ መንግስት ላይ ጫና እንዲያደርግና ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል፡፡

The post ሰማያዊ የG-7 መሪዎች በኢህአዴግ ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳሰበ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሰበር ዜና መርካቶ ሸራ ተራ እየተቃጠለ ነው

$
0
0

ለዘሃበሻ የደረሰው ሰበር መረጃ እንዳመለከተው መርካቶ የሚገኘው ሸራ ተራ እየተቃጠለ ይገኛል። የእሳቱ መነሻ ባይታወቅም እሳቱን ለመቆጣጠር እንዳልተቻለ ይህ ዜና እስከ ተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የደረሰን መረጃ ኣመልክቱአል።
shera tera 2

shera tera 4

shera tera merkato

shera tera

merkato addis

merekato 2

markato 43

The post ሰበር ዜና መርካቶ ሸራ ተራ እየተቃጠለ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢሳት ዜና ሰበር ዜና –በደቡብ ክልል እና ጋምቤላ አዋሳኝ ቴፒ ከተማ ታጣቂዎች ጥቃት ፈፀሙ 

$
0
0

news ”በደቡብ ክልል እና ጋምቤላ አዋሳኝ ኢትዮጵያ ቴፒ ለፍትህ እና ለነፃነት የቆምንነን ያሉ ታጣቂዎች ዛሬ ማለዳ ላይ ጥቃት ፈፀሙ”
ኢሳት ቴሌቭዥን የዛሬ ሰበር ዜና።በሰበር ዜናው ውስጥ የሚከተሉት ነጥቦች ተነስተዋል –
– ታጣቂዎቹ ከአንድ መቶ እስከ አንድ መቶ ሃምሳ ናቸው፣
– ትናንት ጥቃት እንደሚፈፅሙ ቀድመው አሳውቀው ነበር፣
– በሶስት ክፍል ውስጥ ያሉ ከአንድ መቶ በላይ እስረኞችን እና በከተማው የሚገኝ
የፖሊስ ጣቢያ ሰነድ እና በርካታ የጦር መሳርያ ይዘው ሄደዋል።
– የቴፒ ከተማ ነዋሪ በታጣቂዎቹ ጥቃት ደስታውን ሲገልፅ ታይቷል።
– ታጣቂዎቹ ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ አላቸው።”

The post ኢሳት ዜና ሰበር ዜና – በደቡብ ክልል እና ጋምቤላ አዋሳኝ ቴፒ ከተማ ታጣቂዎች ጥቃት ፈፀሙ  appeared first on Zehabesha Amharic.

ሰማያዊ የG-7 መሪዎች በኢህአዴግ ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳሰበ

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ነገ ግንቦት 29/2007 ዓ.ም በሚካሄደው የG-7 ስብሰባ መጋበዛቸውን ተከትሎ የወቅቱ የጉባኤው መሪ ለሆኑት የጀርመን ቻንስለር ለአንጌላ ሜርክል በፃፈው ደብዳቤ መሪዎቹ በኢህአዴግ ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በስብሰባው ላይ መጋበዛቸው ቅር እንዳሰኘው የገለፀው ፓርቲው 24 አመት በስልጣን ላይ የቆየው የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ፓርቲ አፋኝ ለመሆኑ የ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫን በምሳሌነት ጠቅሷል፡፡ ምርጫው ልምድ ያላቸው የውጭ ታዛቢዎች ያልተገኙበትና የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድንም ‹‹ነፃና ፍትሓዊ›› ነበር ለማለት ያልደፈረበት፣ ሰማያዊን ጨምሮ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተጭበረበረ መሆኑን ማረጋገጣቸውን በደብዳቤው አስታውሷል፡፡

ምርጫው ገዥው ፓርቲ 100% አሸነፍኩ ያለበት፣ ተቃዋሚዎች ላይ ከፍተኛ ጫናና እስር ከዚህም ሲያልፍ ለሞት የተዳረጉበት ነበር ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ገለልተኛ ሲቪክ ማህበራት እንዳይታዘቡ መከልከላቸውን ገልጾአል፡፡ ጋዜጠኞችን፣ ጦማሪያንን፣ የሀይማኖት አባቶችንና ፖለቲከኞችን ለማጥቃት በወጣው የፀረ ሽብር ህግ ምክንያት ኢትዮጵያ በፖለቲካ እስረኞች ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚዋ መሆኗን ፓርቲው አስታውሳል፡፡

የጉባኤው አባላት ከኢትዮጵያ ጋር ባላቸው የንግድ ግንኙነትና በሚያበረክቱት እርዳታ ምክንያት በሰብአዊ መብት፣ ዴሞክራሲና ልማት ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችሉ ቢሆንም የኃይለማርያም ደሳለኝ ፓርቲ የሚመራው መንግስት ለሰብአዊ መብት፣ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እየገደበና ተቃዋሚዎች ላይ ከፍተኛ በደል እያደረሰ ይገኛል ብሏል፡፡

ጉባኤው ሰብአዊ መብትና ዴሞክራዊያዊ መብትን ለልማትና የኢኮኖሚ ግንኙነት በቅድመ ሁኔታነት በመውሰድ ጫና ማድረግ ካልቻለ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ግንባታን እንደሚጎዳም ሰማያዊ ፓርቲ አሳስቧል፡፡ በመሆኑም ጉባኤው የፖለቲካ እስረኞች ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፣ ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን ማሰርና እንቅስቃሴያቸውን ከመገደብ እንዲቆጠብ እና አፋኝ አዋጆች ላይ ማሻሻያዎች እንዲደረግባቸው በኢህአዴግ መንግስት ላይ ጫና እንዲያደርግና ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል፡፡

ሰማያዊ የG-7 መሪዎች በኢህአዴግ ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳሰበ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ነገ ግንቦት 29/2007 ዓ.ም በሚካሄደው የG-7 ስብሰባ መጋበዛቸውን ተከትሎ የወቅቱ የጉባኤው መሪ ለሆኑት የጀርመን ቻንስለር ለአንጌላ ሜርክል በፃፈው ደብዳቤ መሪዎቹ በኢህአዴግ ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በስብሰባው ላይ መጋበዛቸው ቅር እንዳሰኘው የገለፀው ፓርቲው 24 አመት በስልጣን ላይ የቆየው የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ፓርቲ አፋኝ ለመሆኑ የ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫን በምሳሌነት ጠቅሷል፡፡ ምርጫው ልምድ ያላቸው የውጭ ታዛቢዎች ያልተገኙበትና የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድንም ‹‹ነፃና ፍትሓዊ›› ነበር ለማለት ያልደፈረበት፣ ሰማያዊን ጨምሮ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተጭበረበረ መሆኑን ማረጋገጣቸውን በደብዳቤው አስታውሷል፡፡

ምርጫው ገዥው ፓርቲ 100% አሸነፍኩ ያለበት፣ ተቃዋሚዎች ላይ ከፍተኛ ጫናና እስር ከዚህም ሲያልፍ ለሞት የተዳረጉበት ነበር ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ገለልተኛ ሲቪክ ማህበራት እንዳይታዘቡ መከልከላቸውን ገልጾአል፡፡ ጋዜጠኞችን፣ ጦማሪያንን፣ የሀይማኖት አባቶችንና ፖለቲከኞችን ለማጥቃት በወጣው የፀረ ሽብር ህግ ምክንያት ኢትዮጵያ በፖለቲካ እስረኞች ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚዋ መሆኗን ፓርቲው አስታውሳል፡፡

የጉባኤው አባላት ከኢትዮጵያ ጋር ባላቸው የንግድ ግንኙነትና በሚያበረክቱት እርዳታ ምክንያት በሰብአዊ መብት፣ ዴሞክራሲና ልማት ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችሉ ቢሆንም የኃይለማርያም ደሳለኝ ፓርቲ የሚመራው መንግስት ለሰብአዊ መብት፣ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እየገደበና ተቃዋሚዎች ላይ ከፍተኛ በደል እያደረሰ ይገኛል ብሏል፡፡

ጉባኤው ሰብአዊ መብትና ዴሞክራዊያዊ መብትን ለልማትና የኢኮኖሚ ግንኙነት በቅድመ ሁኔታነት በመውሰድ ጫና ማድረግ ካልቻለ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ግንባታን እንደሚጎዳም ሰማያዊ ፓርቲ አሳስቧል፡፡ በመሆኑም ጉባኤው የፖለቲካ እስረኞች ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፣ ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን ማሰርና እንቅስቃሴያቸውን ከመገደብ እንዲቆጠብ እና አፋኝ አዋጆች ላይ ማሻሻያዎች እንዲደረግባቸው በኢህአዴግ መንግስት ላይ ጫና እንዲያደርግና ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል፡፡

 

11407238_719529988172662_9201368755983019763_n

11416333_719529974839330_3281869570455127392_o

The post ሰማያዊ የG-7 መሪዎች በኢህአዴግ ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳሰበ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live