Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ፍ/ቤቱ በጦማርያኑ እና ጋዜጠኞች ላይ የቀረቡ የሲ.ዲ መረጃዎችን ውድቅ አደረገ

$
0
0

zone9-bloggers6በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ዛሬ ግንቦት 19/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ መዝገቡ የተቀጠረው አቃቤ ህግ አሉኝ ባላቸው ሲ.ዲዎች እና ቀሪ ምስክሮቹን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ብይን ለመስጠት ነበር፡፡
በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል፡፡ ቀሪ ምስክሮቹን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ምስክሮቹን ለማቅረብ ፍርድ ቤቱ በተደጋጋሚ የሰጠውን እድል ባለመጠቀሙ እና ምስክሮቹን ላለማቅረቡ የሰጠው ምክንያትም በቂ ባለመሆኑ አቃቤ ህግ ያቀረበውን የተጨማሪ ጊዜ ባለመፍቀድ ከዚህ በኋላ ምስክሮቹን እንደማይሰማ አመልክቷል፡፡
አቃቤ ህግ በኤግዚቢትነት ይዟቸው የቆያቸውን የ12ቱን ሲ.ዲዎች ጉዳይ በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ሲ.ዲዎቹ በማስረጃ ዝርዝሩ ውስጥ ፕሪንት ተደርገው የተያያዙ ሰነዶችን እንደያዙ ስለተገለጸ ሲ.ዲዎቹ ከማስረጃነትም ሆነ ከኤግዚቢትነት ውድቅ መደረጋቸውን ገልጹዋል፡፡
አቃቤ ህግ በአንደኛ ተከሳሽ ላይ የሲ.ዲ ዶክሜንተሪ ማስረጃ ማቅረቡን በመግለጽ ፍርድ ቤቱ እንዲመለከትለት የጠየቀ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ አቃቤ ህግ ሲ.ዲውን በጽ/ቤት በኩል እንዲያስገባ በማዘዝ በአንደኛ ተከሳሽ ላይ የቀረበውን ዶክሜንተሪ በቢሮ ዳኞቹና ጠበቆቹ እንዲመለከቱት ከተደረገ በኋላ ሲ.ዲው ሌሎችን ተከሳሾች ይመለከታል ወይስ አይመለከትም የሚለውን አይቶ ብይን ለመስጠት ለሰኔ 8/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል ተከሳሾች ጥያቄያቸውን ለፍርድ ቤቱ ለማስረዳት በሞከሩበት ጊዜ ፍርድ ቤቱ የመናገር እድል ሲነፈጉ የተስተዋለ ሲሆን፣ ተከሳሾቹ ፍርድ ቤቱ እንዲፈቅድላቸው ሲጠይቁ ‹‹ስነ-ስርዓት አድርጉ!›› ባለ ጊዜ ጦማሪ አቤል ዋበላ ‹‹እናንተ ራሳችሁ ስነ-ስርዓት አድርጉ….እንናገርበት! ይህ የመብት ጉዳይ ነው…በግልጽ ችሎት ላይ ህገ መንግስታዊ መብታችንን አክብሩ እንጂ…ጥያቄ አለን ተቀበሉን›› ሲል በመናገሩ ችሎት ደፍረሃል ተብሏል፡፡ በዚህም ፍርድ ቤቱ በአቤል ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ለግንቦት 25/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

The post ፍ/ቤቱ በጦማርያኑ እና ጋዜጠኞች ላይ የቀረቡ የሲ.ዲ መረጃዎችን ውድቅ አደረገ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

↧

Health: 4 ቁምነገሮች ስለ ቃር (Heartburn)

$
0
0

heart burn
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

ቃር የምንለው ወይንም በህክምና አጠራሩ ሃርትበርን (Heartburn) በመባል የሚታወቀው የህመም አይነት ሲሆን አብዛኞችን የሚያጠቃ እና እጅግ የተለመደም ችግር ነው።

በደረት አካባቢ የማቃጠል ስሜት መሰማት በአብዛኛው ከምግብ በኃላ እና እንቅልፍ ስንተኛ የሚብስ ነው። ይህም የሚከሰተው የጨጓራ ውስጥ አሲድ ወደ ላይኛው የምግብ አስተላላፊ ቱቦ (esophagus) ሲገባ ነው።
1. ለቃር ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች
* ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ
* ሽንኩርት
* ሲትረስ ያላቸው ምግቦች
* ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች
* ቸኮሌት
* የአልኮል መጠጦችን መውሰድ
* ካፊን ያላቸውን መጠጦች መውሰድ
* ከጥጋብ በላይ መመገብ
* ከመጠን ያለፈ ውፍረት
* ነፍሰጡርነት ናቸው።
2. ሃኪምዎን ማማከር የሚገባው መቼ ነው
ቃር በአብዛኛው አመጋገብን በማስተካከል እና ቀስቃሽ ሁኔታዎችን በማስወገድ የሚድን ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የደረት ማቃጠል፣ ውጋት፣መጨምደድ ስሜት እና ወደ ትከሻ የሚሰራጭ የህመም ስሜት ከትንፋሽ ማጠር ጋር ከተከሰተ በአፋጣኝ ሃኪም ማማከር ተገቢ ነው ምክንያቱም የድንገተኛ ልብ ህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ነው።
3. ከዚህ በተጨማሪ
* በሳምንት ውስጥ ከሁለት ጊዜ በላይ የሚያቅርዎ ከሆነ
* ለመዋጥ የሚችገሩ ከሆነ
* ማቅለሽለሽና ማስመለስ ካልዎት
* የምግብ ፍላጎት በማጣት ወይንም ለመመገብ በመቸገር ምክንያት የሰውነት ክብደትዎ ከቀነሰ ሃኪምዎን ማማከር ይኖርብዎታል።
4. ቃርን ለማስታገስ መደረግ ያለባቸው የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች
* የሰውነት ክብደትዎን ማስተካከል
* ቃርን የሚይያስነሱ ምግቦችን አለመመገብ
* የአልኮል መጠጦችን አለመውሰድ
* ሲጋራን አለማጤስ
* በመኝታ ጊዜ ጭንቅላትዎን ከፍ ባለ ትራስ ላይ ማሳረፍ ናቸው።

The post Health: 4 ቁምነገሮች ስለ ቃር (Heartburn) appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

አርቲስት ጎሳዬ ተስፋዬና ባለቤቱ 8ኛ ዓመት የትዳር ሕይወታቸውን አከበሩ

$
0
0

Gosaye Tesfaye

Gosaye tesfaye 2

Gosaye tesfaye2
ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በብስራተ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የአቡነ ዓቢየ እግዚእ ታቦተ ህግ በትናንትናው ዕለት ከበሯል። ይህ ጻዲቅ አባት በጎንደርና በትግራይ ብቻ ነበር የሚከብረው። ትናንት ግንቦት 19 እረፍቱ ስለነበረ በአዲስ አበባ ውስጥ በዚህ ደብር ብቻ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከብሮ ውሏል።

ዲያቆን ሉኡልሰገድ ጌታቸው እንደገለጸው ለዚህ ክብረ በዓል መሳካት አርቲስት ጎሳዬ ተስፋዬና ባለቤቱ ወሮ አፀደ ሥላሴ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል። በተለይ ወሮ አፀደ የጻድቁን ገድል በማጻፍ፣ ታቦተ ሕጉም በደብሩ እንዲኖር ከአባቶች ጋር በመሆን ከፍተኛ ጥረት ያደረገች ታላቅ ሴት ነች። አጋጣሚው ደግሞ እጅግ ደስ ይላል፣ ለእነዚህ ለተባረኩ ጥንዶች ይህ ግንቦት ወር የተጋቡበት ወር መሆኑ ነው። ስለዚህ 8ኛ ዓመታቸውን በታቦቱ ስር አስበውት ውለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰሩት መልካም ትሩፋት ደብሩ ያዘጋጀላቸውን የክብር ካባ ብጹዕ አቡነ ሰላማ ባርከው ደርበውላቸዋል ሲል ዲያቆን ልዑልሰገድ ጌታቸው ዘገባውን አጠናቋል::

The post አርቲስት ጎሳዬ ተስፋዬና ባለቤቱ 8ኛ ዓመት የትዳር ሕይወታቸውን አከበሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

“የአባዬ ስልክ እና ባዮሎጂ”–ተራኪ ፈቃዱ ተክለማርያም (በጣም አስቂኝ)

$
0
0

በየወሩ የመጀመሪያው ሮብ በራስ ሆቴል ‹‹ጦቢያ ግጥምን በጃዝ›› የስነፅሁፍ ፕሮግራም ይካሄዳል:: የግንቦት ወር 2007 ዓ/ም ተጋባዥ እንግዳ ሆኖ ለታዳሚው አንድ ፅሁፍ እንዲተርክ ወደመድረክ የወጣው ደግሞ አርቲስት ፈቃዱ ተክለማሪያም ነበር:: ዶ/ር አሸብር ከሚለው የአሌክስ አብርሃም አጭር ልብወለድ መጽሐፍ “የአባዬ ስልክና ባዮሎጂ” የሚለውን መጣጥፍ ተርኮታል:: ለመሳቅ ከፈለጉ ይመልከቱት::

fekadu

The post “የአባዬ ስልክ እና ባዮሎጂ” – ተራኪ ፈቃዱ ተክለማርያም (በጣም አስቂኝ) appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የዛሬ 24 ዓመት ኢህአዴግ አዲስ አበባን ባይቆጣጠር ኖሮ ዛሬ የኢትዮያ እድገት ከብራዚል ጋር ይስተካከል ነበር

$
0
0

(የጉዳያችን ማስታወሻ)

ደርግ 17 ዓመታት ሙሉ በህወሓት እና ሻብያ የተከፈተውን ጦርነት ሲዋጋ እንደነበር እና ጦርነቱ በቀን ብቻ በሚልዮን የሚቆጠር ብር ያስወጣ ነበር።በመቶሺዎች የሚቆጠር ሰራዊት መግቦ፣ታንክ እና ብረት ለበስ ተሽከርካሪ ነዳጅ
እና ግዥ ፈፅሞ ማደር በራሱ ከፍተኛ ወጪ ነበር።ይህ ገንዘብ እንዳሁኑ የእርዳታ እና የብድር ገንዘብ ሳይሆን ህዝቡ ለእናት ሀገር እያለ ከሚያዋጣው እንደነበር ይታወቃል።በእርግጥ የሩስያ እርዳታ እና ብድር እንዳለ ሆኖ።
addis-ababa-realethiopia-141
በአንድ ወቅት ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርይም የሰሜኑ ጦርነት ባይኖር በጥቂት አመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ በባቡር ማገናኘት በተቻለ ነበር።ሲሉ መደመጣቸው ይታወሳል።በተለይ ህወሓት በዋነኛነት ድልድዮች እና መንገዶችን ማፍረስ ስራዬ ብሎ ይዞ ስለነበር እነርሱን ተከታትሎ መጠገን ሌላው ሥራ ነበር።የመከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅት (መኮድ) የተሰኘው ድርጅት አንዱ ስራው ህወሓት ያፈረሰውን
ድልድይ እና መንገድ መልሶ መጠገን ነበር።

በደርግ የመጨረሻ አመታት ታድያ ኮ/ል መንግስቱ የመንግስታቸውን ቅርፅ ለመቀየር ወስነው ነበር።ቅይጥ ኢኮኖሚ ታወጀ።ሚኒስትሮች በአዲስ መልክ ተሾሙ።ብዙዎቹ በምዕራብ ዓለም የተማሩ ነበሩ።ኢኮኖሚውም ሆነ ፖለቲካው ለቀቅ ያለ መስሎ ነበር።በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ዕድል እንዳላቸው ምህረት እንደሚደረገም ተወራ።ፕሮፌሠር መስፍን ወ/ማርያምን ጨምሮ ሌሎች ምሁራን ከአመታት በኃላ እንደገና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን የማናገር፣በሀገሪቱ መፃኢ ዕድል ላይ የመነጋገር ዕድል አገኙ።

በወቅቱ በተያዘው መልክ የሀገሪቱ ሰላም ቢረጋጋ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ የህወሃትን የጎሳ ፖለቲካ እና የሻብያ ኤርትራን የመገንጠል አጀንዳ እንደመጥላቱ በነበረው ሕብረት ቢቀጥል ኖሮ፣በውጭ ይኖር የነበረው ሕብረተሰብ ወደሀገር ቤት ገብቶ የመስራት፣በሀገር ውስጥ ያለው ካለ ምንም የጎሳ ክፍፍል የመስራት እና ትላልቅ ኩባንያዎችን የመመስረት እድሉ ሰፊ ነበር። ዛሬ ኤፈርት እና ጥቂት ባለ ሀብቶች የሃገሩትን ሀብት ሁሉ እንዲህ ጠቅልለው ሚልዮን ኢትዮጵያውያን በድህነት ውስጥ አይዳክሩም ነበር።

አሁንም በተጀመሩ የሽግግር ሂደት ደርግ ስልጣኑን ቢለቅ እና የሽግግር መንግስት ተመስርቶ ቀጥሎም ወደ እውነተኛ ምርጫ ኢትዮጵያ ሄዳ የእራሷ የሆነ መንግስት ቢኖራት ኖሮ ዛሬ ከ 24 ዓመታት በኃላ ኢትዮጵያ ካለምንም ጥርጥር ብራዚል ከደረሰችበት የእድገት ደረጃ የመድረስ ዕድል ነበራት።እዚህ ላይ ብራዚል ቀደም ብላ በውጭ ኃይሎች የመገዛቷ እና በርካታ የባህል ተቃርኖ ቢኖርም እኛ ካለን የባህል ሀብት ጋር በምጣኔ ሀብት ደረጃ እና በፈጠራ እንዲሁም በአዲስ ቴክኖሎጂ ክህሎት ሁሉ በእጅጉ የምንራመድበት የመነቃቃት አመታት ነበሩ።በእነኝህ 24 አመታት ውስጥ ከተባለው ደረጃ ለመድረስ እንችል እንደነበር እንደማሳያ የምረዳኝን ኢትዮጵያ ሊኖሯት እና ላይኖሯት የሚችሉት ነገሮች ሁለት ክፍል ከፍዬ ለማሳየት እና እነኝህ ጉዳዮች ማለትም ኢትዮጵያ ሊኖሯት የሚችሉት ነገሮች ምን ያህል ወደፊት እንደሚያራምዱን እና ላይኖሩ የሚችሉት ደግሞ ምን ያህል ወደኃላ እንደወሰዱን ለመመልከት ይረዳናል።እነኝህን ነጥቦች ለመንደርደርያ አነሳሁ እንጂ ጠለቅ ያለ ጥናት ቢደረግ ብዙ ጉዳዮችን ሊያሳየን እንደሚችል መረዳት ይቻላል።
ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ ሊኖሯት የሚችሉት
eth Bank
1/ የባንክ ኢንዱስትሪያችን ቢያንስ በ 5 የአፍሪካ ሁለት የመካከለኛው ምስራቅ እና አንድ አውሮፓ እንዲሁም 3 በአሜሪካ ቅርንጫፍ ከፍተው ግዙፍ የፋይናንስ ተቋም በሆኑ ነበር፣

2/ እነ ጣና በለስ የመስኖ ልማት በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ ሞደል የተባለ ምርቶቹ ከኢትዮጵያ አልፈው ለመላው ዓለም የሚልክ በአውሮፓ የስቶክ ኤክስቸንጅ ገበያ የሚገባ ኩባንያ ይሆን ነበር፣

3/ ኢትዮጵያ ከሻብያ ጋር በኤርትራ ጉዳይ ባትግባባ ቢያንስ በአሰብ ጉዳይ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደራድራ ወደቧን ታስከብር ነበር።በሌላ በኩል እንደ ህወሓት በመሃል ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኤርትራውያንን ከሀገር ስለማታስወጣ በሂደት እነኝሁ ትውልደ ኤርትራውያን የኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር አብሮ መኖር ሽንጣቸውን ገትረው የሚከራከሩ በሆኑ ነበር።እዚህ ላይ በደርግ ዘመን ከፍተኛ ተደማጭ የነበሩ የኤርትራ ቆላው ተወካዮች የነበራቸውን ተሰሚነት ማሰብ ይገባል።እነኝህ ሁሉ በህወሓት ስሳደዱ እና ሲገፉ 24 ዓመታት ተቆጠሩ።

4/ ኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይሏ ጠንካራ ስለነበር በደቡብ ሱዳን ጉዳይም ሆነ የሱማልያ አልሸባብ ፈፅሞ ስጋት ሊሆኑ አይችሉም ይልቁንም በአካባቢው ሃያል ሀገርነቷ እስከ ግብፅ እና መካከለኛው ምስራቅ ድረስ ይናኝ ነበር።የአይኤስ ኤስ ጥቃት መፈፀሙ በተሰማ በ24 ሰዓታት ውስጥ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከደብረ ዘይት ተነስተው የሱዳንን የአየር ክልል ጥሰው በርካታ የአሸባሪው ይዞታዎችን ሊብያ ውስጥ ያጠቁ ነበር።በእዚህም ሌሎች ተቀናቃኝ ሀገሮችን ሊያስደምም ይችል ነበር።

5/ በጦርነት ውስጥ የነበረ ኢኮኖሚ ያንን ያህል የስራ ዕድል ለወጣቱ መፍጠር ከቻለ ከጦርነት በኃላ ላለፉት 24 ዓመታት ውስጥ ቢያንስ ከ አስር ያላነሱ ከባድ የብረት ኢንዱስትሪዎች፣የነዳጅ ማውጣት ሥራ (ሱዳን ባቅሟ ነዳጅ ስታወጣ ኢትዮጵያ በሙስና ያልባለገ መንግስት ቢኖራት ኖሮ እስካሁን የነዳጅ ምርት በጀመረን ነበር)፣

6/ በኢትዮጵያ ተጀምረው የነበሩት የመካናይዝድ እርሻ ልማቶች በሰፊ ይስፋፉ ነበር።ኢትዮጵያ ጤፍ በብዛት በማምረት ለዓለም ብቸኛ አምራች እና ላኪ ሀገር ትሆን ነበር።

7/ የበርካታ ሃገራት ትላልቅ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋለ ንዋይ ለማፍሰስ ይጎርፉ ነበር።በተለይ ደርግ የወደቀበት ወቅት የምስራቅ አውሮፓ ሃገራት ገና ከሩስያ ተፅኖ እየወጡ፣በርካታ የአፍሪካ ሀገራትም እየተነቃቁ ስለነበር ከወቅቱ ጋር የሚሄድ የድርጊት መርሃ ግብር እና ከሙስና በተቻለ መጠን የፀዳ መንግስት ስለሚኖር ኩባንያዎቹ ከማንም የአፍሪካ ሃገራት ኢትዮጵያን እንደሚመርጡ ሳይታለም የተፈታ ነበር።ይህም ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ከብራዚል እኩል የምትጠራ ሀገር ትሆን ነበር።

8/ ናዝሬት የተጀመረው የትራክተር መገጣጠምያ ፋብሪካ ምርቱን አሻሽሎ በሌሎች ቦታዎች ማምረት እና የኢትዮጵያን ገበሬ በከፊልም ቢሆን ከበሬ አስተራረስ ዘዴ እንወጣ ነበር።

9/ ወላጆቻቸው የሞቱባቸው ማሳደጊያ እና መንከባከቢያ ማዕከል ”ሕፃናት አምባ” በሁሉም ክፍለ ሀገሮች ተመስርቶ እናት አባት የሞቱባቸውን በተለይ ባለፉት 24 ዓመታት ቁጥራቸው በመቶ ሺዎች የሆኑትን ሕፃናት ወደ ማዕከሉ አስገብቶ ኃላፊነት የሚሰማቸው ትውልድ ማፍራት ይቻል ነበር።የማዕከሉም አስተዳደር በባለሥልጣን ደረጃ ተዋቅሮ ኢትዮጵያውያን በወር ከደሞዛቸው እያዋጡ በርካታ እናት አባት ያጡ ሕፃናትን ሕይወት መታደግ ይቻል ነበር።ኢህአዴግ ማዕከሉ የነበሩ ሕፃናትን የደርግ ልጆች ብሎ በምሽት እንዳባረራቸው እና ማዕከሉን አንዴ የካድሬ ማሰልጠኛ ሌላ ጊዜ የግብርና ማሰልጠኛ እያደረገው መሆኑ ይታወቃል።

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ ላይኖሯት (ላይሆንባት) የሚችሉት

1/ ሀገሪቱ በጫት እንዲህ አትበከልም ነበር።ወጣቶቿ በስፖርት እና በልዩ ልዩ ሙያ ላይ እንጂ የጫት ተገዢ አይሆኑም ነበር፣

2/ ከሶስት መቶ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለግዳጅ ሥራ አይጋዙም ነበር፣

3/ የጣና በለስ ፕሮጀክት አይፈርስም ነበር፣

4/ ኢትዮጵያ የባህር በር የሌላት ሀገር አትሆንም ነበር፣

5/ ኢትዮጵያ በጎሳ የተደራጀ ፓርቲ አይኖራትም ነበር።ሀገሩም በጎሳ የተከፋፈለ አስተዳደር አይኖራትም ነበር።
6/ ኢትዮጵያውያን ጎሳቸው ሳይሆን ኢትዮጵያዊነታቸው ብቻ በፈለጉት ቦታ ሄደው የመስራት መብት ይኖራቸው ነበር፣

7/ ኢትዮጵያውያን በመላው ዓለም ክብራችን ዝቅ ተደርጎ እንዲታይ አይደረገም ነበር። አንድ ችግር ሲገጥመን ወደ ኤምባሲያችን ሄደን ችግራችንን እንፈታ ነበር፣

8/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለሁለት የተከፈሉ አባቶች አስተዳደር አይኖራትም ነበር፣

9/ ከ11 ቢልዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ከሀገር በሕገ ወጥ መንገድ አይወጣም ነበር፣

10/ የብሔራዊ ባንክ በቀትር ፀሐይ ወርቁን ለሌቦች አስረክቦ አርተፍሻል ወርቅ አይቀበልም ነበር፣

11/ የተማረ የሚከበርባት እና ሥራ የምያገኝባት እንጂ ኮብል ስቶን ተራቢ እንዲሆን አይደረገም ነበር፣

12/ የሕፃናት አምባ ወላጆቻቸው የሞቱባቸው ሕፃናት በምሽት በኢህአዴግ ወታደር አያባረሩም እና ሴቶች ለሴተኛ አዳሪነት ወንዶቹ ለጎዳና ተዳዳሪነት አይዳረጉም ነበር።
national bank of ethiopia
13/ ኢትዮጵያ ሕፃናቶቿን በጉዲ ፈቻነት በመሸጥ በአፍሪካ ቀዳሚ አትሆንም ነበር።

ባጠቃለይ ኢትዮጵያ በህወሓት አገዛዝ ስር እሩብ ክ/ዘመን (25 ዓመታት) ሊሞላት አንድ ዓመት ብቻ ቀራት።ሃያ አምስት አመታት በርካታ ሃገራት ወደ መካከለኛ ገብ ደረጃ የደረሱበት ነው።የዛሬ 24 ዓመት አንጎላ ጦርነት ላይ ነበረች።ዛሬ አንጎላ በከፍተኛ እድገት ላይ የምትገኝ ሀገር ነች። የዛሬ 24 ዓመት ቦትስዋና ብዙም የምትደነቅ ሀገር አልነበረችም ዛሬ ቦትስዋና የአልማዝ አምራች ሀገር ነች።የዛሬ 24 ዓመት ጋና ስሟ እምብዛም አይነሳም። ዛሬ ጋና በዲሞክራሲያዊ ምርጫ መንግስት የምትቀይር እና የነዳጅ ሀብት ባለቤት የሆነች ሀገር ነች።ሃያ አራት ዓመት እንደ ኢትዮጵያ ላለ ጠንካራ ሰራተኛ ሕዝብ፣በብዙ ውጣ ውረድ ላለፈ ሕዝብ እና በርካታ እድሎች ከፊቱ ላሉት ሕዝብ ዛሬ ብራዚል ለደረሰችበት ደረጃ የመድረስ አቅም ነበረው።ነገር ግን በጎሰኛ መንግስት ተጠልፎ የጥቂቶችን የተንደላቀቀ ሕይወት እየተመለከተ እንዲኖር ተፈርዶበታል።አሁንም ከነገ ዛሬ ይቀድማል እና ለኢትዮጵያ ነፃነት አንድነታችንን እናጠናክር።ከጎሰኞች ማዶ ለምትመሰረተው የሁላችንም ኢትዮጵያ የበኩላችንን እናድርግ።

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
ግንቦት 20/2005 ዓም (ሜይ 28/2015)

The post የዛሬ 24 ዓመት ኢህአዴግ አዲስ አበባን ባይቆጣጠር ኖሮ ዛሬ የኢትዮያ እድገት ከብራዚል ጋር ይስተካከል ነበር appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

ስለቀጣዩ ትግል ሳስብ ! –ከይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ ፓርቲ አመራር)

$
0
0

holeta
ዲሞክራሳዊ ምርጫ ሰላማዊ ወይም ጠበንጃ አልባ የትግል ስልት ከሆኑት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ሆኖም ግን በአገራችን ለሃያ አንድ አመት ወይም ለ5 ዙር ምርጫ የተካሄደ ቢሆንም ህውሓት/ኢህአዴግ የግንቦት ሃያ 24ኛ አመት በሚያከብሩበት ማግስት 100 % በምርጫ ተወዳዳሪ አሸናፊ ሆኛለው ማላት፣ ህውሓት/ኢህአዴግ ለዲሞክራሳዊ ምርጫ የተዘጋጀ አለመሆኑ በሚገባ ያረጋገጠ አጋጣሚ ነው ፡፡የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር እና አባላት የህውሓት/ኢህአዴግ አምባገነናዊ የምርጫ ሥርዓት እግር-በእግር በመከተል ለማጋለጥ ችለዋል ! ለዚህም አኩራ ተግባራቸው አድናቆት እና ምስጋና መስጠት ተገቢና አስፈላጊ ነው፡፡

ሆኖም ግን ከዚህ በኋላ ሌሎች ጠበንጃ አልባ ወይም ሰላማዊ የሆነ ትግል ስልቶችን በመተግበር ሕዝባዊ መንግስት አስኪቋቋም “በአገር ውስጥ” የሚንቀሳቀሱ የዲሞክራሲ ሃይሎች አማራጭ የሰላማዊ ትግል ስልት በመከተል፣ ከሌላው ጊዜ በተሻለ እና በተቀናጀ መልኩ የተጀመረው ከአምባገነን አገዛዝ ወደ ዲሞክራሲ የሚደረገውን ሰላማዊ ትግል መምራት እንደሚያስፈልግ ከምንፈልገው ለውጥ አንፃር ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም፡፡ይህን ሃቅ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር እና አባላት አጥብቀው የሚረዱት እውነት እንደሆነ እምነቴና ተስፋዬ የበዛ ነው፡፡

ለውጥ ፈላጊው የሆነው ጭቁኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሣይሰለች የለውጡ ሂደት እንዲፋጠን ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጎን በመቆም ያሣየው ጥረት እና ፍላጎት እንዲሁም ድጋፍ ለዲሞክራሲ ሃይሎች የሁል-ጊዜ ብርታትን የሚሰጥ ነው !ለዚህም የላቀ ተግባር ከበሬታ መስጠት ድጋፍ ለተቸራቸው የተቃወሚ ሃይሎች በፖለቲካ ሥራችን በግብረ-መልስ የሚሰጡት በጎ ምላሽ መሆን እንዳለበት ማረጋገጥ አለብን ፡፡ ይህም በመሆኑ የህብረተሰቡ የለውጥ ፍላጎት ለዲሞክራሲ ሃይሎች ከምንም በላይ ዋንኛ ግባት ነው፡፡
በውጪ ሀገር የሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በገንዘብ እና በሃሳብ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በአገራችን በሰላማዊ መንገድ የመንግሰት አስተዳዳር ለውጥ እንዲመጣ የከፈሉት መሰዋትነት ቀላል የሚባል አይደለም ! ይህ-ቀረ የማይባልበት የሁል ጊዜ ድጋፋቸውም በቀጣይም ከሰላማዊ ትግል ጎን የማይለይ መሆኑ እርግጥ ነው፡፡

ማስታወሻ ፡- ይህ ፁሑፍ የእኔን አስተሳሰብ እንጂ የፓርቲዬን አቋም የሚመለከት አይደለም፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!

The post ስለቀጣዩ ትግል ሳስብ ! – ከይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ ፓርቲ አመራር) appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

በምርጫ ቦርድ ውጤት የኢህአዴግ ደጋፊዎች ከሁለት ተከፍለዋል * ፊደል ቀመስ አባሎች ውጤቱን አልተቀበሉትም

$
0
0

ግንቦት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ የግንቦት15ቱን ምርጫ መቶ በመቶ ማሸነፉ ከተገለጸ በሁዋላ የኢህአዴግ ደጋፊዎች ከሁለት ተከፍለዋል። ምንጮች እንደገለጹት በርካታ ፊደል ቀመስ አባሎቹ ኢህአዴግ አሸነፍኩ
ያለበትን የድምጽ ልዩነት አልተቀበሉትም። ውጤቱን የሚቃወሙ የግንባሩ አባላት ” ህዝቡ ከእንግዲህ በሰላም መንግስት እቀይራለሁ የሚለው እምነቱ ተሟጦ የሃይል አማራጭን ብቻ እንዲመለከት ከማድረጉም በላይ፣ የሃይል አማራጭን
የሚከተሉ ሃይሎች በህዝቡም ሆነ በአለማቀፉ ማህበረሰብም የተሻለ ተቀባይነት እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል” በማለት ለድርጅቱ አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው።
election 2015
በሌላ በኩል ደግሞ ተገኘ የተባለውን ውጤት ከመደገፍ አልፈው፣ ህዝቡ እንዴት ለተቃዋሚዎች ይህን ያክል ድምጽ ሊሰጥ ቻለ በማለት በቁጭት አስተያየት የሚሰጡ ደጋፊዎች መኖራቸውንም ምንጮች ገልጸዋል።

ኢህአዴግ እያሰባሰበ ባለው መረጃ ላይ እንደተገለጸው፣ አንዳንዶች ” ይህ ህዝብ ምን አይነት ልቡ የማይታወቅ ከሃዲ ህዝብ ነው! እንዴት ይሄን ሁሉ ልማት እያዬ ለተቃዋሚ ድምጹን ሊሰጥ ቻለ?” የሚል አስተያየት ሰንዝረዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ምርጫ ቦርድ ራሱ ባወጣው ሰሌዳ መሰረት የምርጫውን ውጤት መግለጽ የነበረበት ግንቦት21 ቢሆንም፣ የግንቦት20 በአልን ለማድመቅ እንዲረዳ በሚል ከእቅዱ በፊት እንዲገለጽ መደረጉን ምንጮችን ዋቢ በማድረግ
ዘጋቢያችን ገልጿል።

ኢህአዴግ በየክልሉ ከፍተኛ ወጪ የወጣበት የፌሽታ በዓላትን አዘጋጅቷል። ትናንት የገዢው ፓርቲ ደጋፊ አርቲስቶች ያዘጋጁት የኪነጥበብ ምሽት በብሔራዉ ቲያትር ተካሂዷል፡፡፡ በርካታ የፌዴራል የመንግስት መ/ቤቶች በተለያዩ ሆቴሎች
በዓሉን ለማክበር ጥሪ አስተላልፈዋል።

ምርጫ ቦርድ የኢህአዴግን አሸናፊነት ቢያውጅም መድረክ የተባለው የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ስብስብ የምርጫውን ውጤት አልተቀበለውም። ድርጅቱ ምርጫው አነስተኛ የሚባሉ መስፈርቶችን እንኳ ያላሟላ በማለት አጣጥሎታል። መድረክ
በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ገለልተኛ የሚባሉ ሰዎች ተመርጠው መምርራ እንዲያካሂዱ ጠይቋል።
ሰማያዊ ፓርቲ ምርጫውን በተመለከተ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ያለው ነገር የለም። መንግስት የሰማያዊ ፓርቲ ደጋፊዎችን እያዋከበ በማሰር ላይ መሆኑ፣ ፓርቲውን አጣብቂኝ ውስጥ ሳይከተው አልቀረም። ሰማያዊ የምርጫውን
ውጤት ይቀበለዋል ተብሎ አይጠበቅም።

የአሜሪካ መንግስትና የአውሮፓ ህብረት ምርጫውን በተመለከተ በርካታ እጸጾችን አውጥተው ቢገልጹም፣ ከኢህአዴግ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንደማያቋርጡ አስታውቀዋል። የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ባወጣው መግለጫ ዲፕሎማቶች
በምርጫ ታዛቢነት እንዳይሰታፉ መከልከላቸው፣ ምርጫው አሳታፊ አለመሆኑንና የተለያዩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች መታሰራቸውን በመግለጫቸው አመልክተዋል።

በምርጫው ሂደት ያጋጠሙ በርካታ አስገራሚ ክስተቶች ለኢሳት እየደረሱ ነው። ግንቦት12 ቀን 2007 ዓም በአዲስ አበባ ልዩ ቦታው ላንቻ ወይም ጠመንጃ ያዥ ነዋሪ የሆነ አንድ የ12 ዓመት ህፃን የኢህአዴግን የምርጫ መልዕክት ያየዘ
ፖስተር ከተለጠፈበት ግድግዳ ላይ ቀደሃል በሚል 6 ወር ተፈርዶበታል።

በአዲስ አበባ ችሎት በሚባል ቦታ አርብ ግንቦት 14 ቀን 2007 ዓ.ም ሁለት ማየት የተሳናቸው ወጣቶች ተይዘው ታስረዋል። ወጣቶቹ የተያዙት አንደኛው ሙሉ ሰማያዊ ልብስ ለብሶ በመውጣቱ በተፈጠረው አተካራ ነው። የአካባቢው
ሴት ካድሬ አንደኛውን ማየት የተሳነው ወጣት “ለምን ሰማያዊ ልብስ ለበስክ የሰማያዊ ፓርቲ አባል ነሆይ?” በማለት ጥያቄ ስታቀርበለት፣ ጓደኛው “ምን አገባሽ ምንስ ብለብስ!” የሚል መልስ መስጠቱን ተከትሎ፣ ግለሰቧ በብስጪት
ለደህንነቶች ባስተላለፈችው ጥቆማ መሰረት ሁለቱም ወጣቶች በድንገት ታፍነው የተወሰዱ ሲሆን እስከዛሬ ድረስ ታስረው ይገኛሉ።
መነን መሰናዶና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም ፀሃይ ጮራ ት/ቤት ውስጥ የሚገኙ ቁጥራቸው 20 መምህራንና 30 ተማሪዎች የሰማያዊና የአንድነት ፓርቲ አባላት ናቸው በሚል ዝርዝራቸው ለጸጥታ አካላት ተልዕኮ በልዩ ሁኔታ ክትትል እንዲደረግባቸው ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከምርጫ በፊት ትዕዛዝ ተላልፎ እንደነበርም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

The post በምርጫ ቦርድ ውጤት የኢህአዴግ ደጋፊዎች ከሁለት ተከፍለዋል * ፊደል ቀመስ አባሎች ውጤቱን አልተቀበሉትም appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበለው አስታወቀ • ‹‹በሂደቱ በመቆየታችን የኢህአዴግን አውሬነት አሳይተናል›› ኢ/ር ይልቃል

$
0
0

‹‹በኃይል የተቀማ ድምፅ የሚመሰረት መንግስት በህዝብ ተቀባይነት የለውም››
• ‹‹በሂደቱ በመቆየታችን የኢህአዴግን አውሬነት አሳይተናል›› ኢ/ር ይልቃል
• ‹‹የአፍሪካ ህብረት ራሱንም ሌላም ማዳን የማይችል የእንጨት ድስት ነው›› አቶ ስለሽ
ሰማያዊ ፓርቲ የ2007 ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫ ሂደቱንም ሆነ ውጤቱን እንደማይቀበለው አሳወቀ፡፡ ፓርቲው ዛሬ ግንቦት 21/2007 ዓ.ም በጽ/ቤቱ ‹‹ነጻነት በሌለባት ኢትዮጵያ ሕዝባዊ አስተዳደር መትከል ዘበት ነው!›› በሚል ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ምርጫው ‹‹ከዚህ ቀደም ከተካሔዱት ምርጫዎች ጋር እንኳ ሊወዳደር የማይችል እጅግ ኢ-ፍትኃዊ፣ ወገንተኛና ተዓማኒነት የሌለው በመሆኑ ሰማያዊ ፓርቲ ሂደቱንም ሆነ ውጤቱን አይቀበለውም፡፡›› ብሏል፡፡
semayawi Party
በ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ ሲወስን ገለልተኛና ብቃት ያላቸው ተቋማት እንደሌሉና ገዥው ፓርቲም እውነተኛ ምርጫ እንደማይፈቅድ እያወቀ መሆኑን የገለፀው ሰማያዊ በሂደቱ የተሳተፈው የስርዓቱን ችግሮች ለማጋለጥ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹በሂደቱ ውስጥ በመቆየታችን እጩዎቻችን በህገ ወጥ መንገድ ሲታገዱ፣ ታዛቢዎች ሲከለከሉና ሲታሰሩ አሳይተናል፡፡ በሂደቱ በመቆየታችን የኢህአዴግን አውሬነት አሳይተናል፡፡ ከመጀመሪያው ጀምሮም ሆነ በምርጫው ወቅት የነበረውን ማጭበርበር ለኢትዮጵያ ህዝብና ለዓለም አጋልጠንበታል፡፡›› ብለዋል፡፡ የፓርቲው ም/ሊቀመንበር እና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስለሽ ፈይሳ በበኩላቸው ምርጫው መትረየስ ተጠምዶ፣ ብረት ለበስ በየ መንገዱ ቆሞ፣ የአጋዚ ጦር አባላት ከተማ ውስጥ ተሰማርተው ከመካሄዱም ባሻገር ከፍተኛ የድምጽ ማጭበርበር የነበረበት ነው ብለዋል፡፡ የምርጫው ብቸኛ የውጭ ታዛቢ የሆነውን የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድንም ራሱንም ሌላም ማዳን የማይችል ‹‹የእንጨት ድምጽ ነው!›› ሲሉ ተችተዋል፡፡
ምርጫው በህገ ወጥ አሰራሮች የታጀበ፣ በማንኛውም መመዘኛ ፍትሃዊ፣ ነፃና ተአማኒ ሊሆን እንደማይችል ሒደቱ በግልፅ አመላካች ነበር ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹በውጤቱም በሐገራችን የዲሞክራሲና የመድብለ ፓርቲ ስርዓት መኖርን ወደ መቃብር የከተተና ኢትዮጵያ የአንድ ፓርቲ ስርዓት ሐገር መሆኗን ያረጋገጠ ነው፡፡..ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ የጨለማ ዘመን መምጣቱን ከማሳየቱ ባሻገር ኢህአዲግ በፍርሃት ተውጦ ሁሉንም ለመቆጣጠር ባደረገው ሩጫ ለመግለፅ እስኪያፍር ድረስ የሚያሸማቅቅ ውጤት እንዲከናነብ ሆኗል፡፡›› ብሏል፡፡ በኃይል በተቀማ ድምፅ የሚመሰረት መንግስትም በሕዝብ ተቀባይነት እንደሌለውም ገልጾአል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ በአፈና እና ጭቆና ውስጥ ሆነው ድምጽ ለሰጡት መራጮች ምስጋናውን አቅርቧል፡፡ በምርጫው ሂደት የተንገላቱ፣ የታሰሩትን፣ የተደበደቡና የተሰደዱትን አባላቱንም ፓርቲያቸው በኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋ የተጣለበት እንዲሆን ለደረሰባቸው መከራና በደል ክብር ይገባቸዋል ብሏል፡፡ የዜጎች ነፃነት ሳይከበር ነጻና ፍትኃዊ ምርጫ ሊደረግ አይችልም ያለው መግለጫው ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻችን እስከሚከበሩ ድረስ ሰማያዊ ፓርቲ በሚያካሂደው የነጻነት ትግል ኢትዮጵያውያን ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪ አድርጓል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጾአል፡፡

The post ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበለው አስታወቀ • ‹‹በሂደቱ በመቆየታችን የኢህአዴግን አውሬነት አሳይተናል›› ኢ/ር ይልቃል appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ከጥፋት ሰረገላ  ውረዱ!!! –ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

Ketemaክፋት ተዘርቶ ክፋት ከሚታጨድበት፣ ጥፋት ተከምሮ ጥፋት ከሚወቃበት ከሰረገላው ውረዱ። ምርጫው መላገጫ ከሆነበት፣ አሸናፊው ከሚሸነፍበት ከውሸት ሰረገላው ውረዱ። ህዝቡ የኔ የሚላቸው የሚታሰሩበት፣ መሪዬ የሚላቸው ከሚታፈኑበት ከሰረገላው ውረዱ። ይሄንን የውሸት ሰረገላ አዘጋጅቶ ለበደሉ አድማቂ ለጥፋቱ ተባባሪ የሆኑትን የወያኔ ጭፍሮችን አሳፍሮ ከበሮ  የሚያስደልቀውን፣ ለማፈኑ ተግባር አጋዚ ለረገጣው መሰረት ምርኩዝ የሆኑትን የታጠቁ ወታደሮች በሰረገላው ያሳፈረው፦ የህዝብ እንባ አፍሳሽ፣ የህዝብ መብት ረጋጭ ነውና ሰረገላውን የሞሉት…. አንተ  ህሊና ያለህ ከሁሉ በላይ ህሊናህ ዳኛህ ነውና  ያለ ሞጋች የሚሞግት፣ ያለ ከሳሽ የሚከስህ፣ ያለ ዳኛ የሚፈርድብህ፣ ህሊናህ እዳ ነውና ከህሊና ፍርድ ለመውጣት ከጥፋት ሰረገላው ውረድ። የህዝብ ቁጣ ወደ ግለት፦ ግለቱ ወደ እንፋሎት፦ እንፋሎቱ ወደ ፍንዳታ ተለውጦ ሰረገላው ከመጥፋቱ በፊት ከሰረገላው ከጥፋት ሰረገላው ውጡ።

ነጻነትን የማያውቅ መሪ ለህዝቡ ነጻነትን ይሰጣል ወይም ያመጣል ማለት ዘበት ነው። መብላትና መጠጣት ሆድን ሊያጠግብ እንዳትራብም ሊያደርግ ይችላል። ነጻነት ሊሆን ግን አይችልም። ነጻነት ማለት ከመብላት እና ከመጠጣት በላይ ለአእምሮ እውነትን የምትነግርበት፣ የተሰማህን ያለምንም  ፍራቻ የምትገልጽበት፣ ሃሳብህን በነጻነት የምትገልጽበት፣ የመናገር፣ የመጻፍ፣ ነጻነት የሚጸባረቅበት ከፈጣሪ የተሰጠህ ጸጋ ነው። ይህንን ከፈጣሪ የተሰጠህ ነጻነትህን አንባ ገነኖች በግድ ማፈን እና ሊነጥቁህ ሲፈልጉ የነጻነት ፈላጊው ድምጽ ከውስጥ ፈንቅሎ  በመውጣት ማየል ይጀምራል። ወያኔም ይህንን የህዝቡን ነጻነት ያፈነው። ይህንን የሰፊውን ህዝብ ሰላም ያናጋው። የሰላም እጦት ሰላም አደፍራሹን ካላጠፋ እንደማያቆም ጠንቅቆ ለመረዳት ታሪክን መመልከቱ በቂ ነው።

መረጥን ያሉ እጆች የመረጡት ሳይሆን ያልመረጡት ያሸነፈበት፣ የፈለጉት ሳይሆን ያልፈለጉት ሊገዛ መነሳት ማለት ምን ያህል ህመም እንደሆነ ሁሉም የሚያውቀው ጉዳይ ነው። ባልመረጡት መመራት ማለት ነጻነትን መነጠቅ ማለት ነው። ረጋጭ እና አፋኝ፣ አሳሪና ገዳይ፣ በራስ ላይ በግድ መሾም እንደሆነ ይታወቃል። ታዲያ ይሄንን በጠራራ ጸሃይ የተነጠቀውን የህዝብ ድምጽ ሊቀበል የሚችል እና እውቅና የሚሰጠው የትኛው አካል ነው። በግድ እራስ ላይ የወጣን ባለጌ በግድ ከእራስ ላይ ትወርዳለህ ብሎ ባለጌን ፊት ለፊት ተናግሮ በሚገባው ቋንቋ በማናገር ነጻ የመውጣት ትግሉ ትርጉም እንዲኖረው ማድረግ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጉዳይ ነው። ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ፈትፍቶ ያጎርስሃል እንደተባለው ተረቱ።

ህዝቤ ሆ!!! ከፊትህ ያለውን የጥፋት ሰረገላ አፍርሰው። ሰረገላው ላይ ተሰቅለው ግፍና በደልን በመስራት ማንም ከኛ በላይ ያሉትን በማሳፈር ከህዝብ በላይ ማንም እንደሌለ እናሳየው። ከአሁን በኋላ ህዝባችን ከቶውን ተሸማቆ እና ተሳቆ፣ ታስሮ እና ተገድሎ፣ ተርቦ እና ተጎሳቁሎ መኖር ይብቃ። በሰረገላው የተሰቀሉት በህዝብ ቀልደው የሚኖሩበት ግዜን ፍጻሜውን እናምጣው። ሰረገላውን መስበር ቀላል ነው። ያም የሚጓዝበትን መንገድ መስበር፣ በካድሬ የተሳሰረውን የስለላ መረብ መቁረጥ፣ አንድ ለአምስት ብሎ የጠረነፈውን ወጥመድ በመጠስ ስር ስራችን ያሉትን የአቃጣሪዎችን መስመር በመበጣጠስ ህዝቡ የማያዳግም ርምጃዎችን መውሰድ ያስፈልጋል። ህዝብን በማሰቃየት፣ በማፈን፣ በመሰለል፣ የተሰማሩት የሰረገላው ተሳፋሪዎች በአጭር ግዜ መቆጣጠር የሚቻልበት ግዜ ላይ ስለሆንን ለዚህም ድል እንደ ሸረሪት ድር በቀለበት በመተሳሰር ጠላትን እያጠመድን በመጣል ታሪክን እናስመዝግብ። ድር ቢያብር አንበሳን ያስር ነውና ።

ሃያ አራት አመት ሙሉ ሰረገላው ላይ የተሳፈሩት ሲፈሩ ነበረ። የፈለጉትን ያስራሉ፣ የፈለጉትን ይገድላሉ፣ ለዚህም ማንም ጠያቂ የላቸውም። ምክንያቱም ፍርድ ቤቱ የራሳቸው፣ ዳኛውም የራሳቸው በመሆኑ እውነትን በሃሰት ተለውጦ የህዝብ ደምና እንባ በከንቱ ፈሷል። አሁን ግን አይተናቸዋልም አውቀናቸዋልም። ከአሁን በኋላ የሚጠበቅብን በሰረገላው ተጭነው በደልን ለማድረስ የሚሯሯጡትን ህዝብን የሚያፍኑትን በሙሉ ዋጋቸውን ሊያገኙ ይገባል። የበደል ሰረገላ ይፈርሳል። የገዳዮችም ሰረገላ ይጠፋል። የአፋኞች ሰረገላም ይመታል። ለሰረገላው መንገድ ለሰረገላዎቹም ቦታ ከእንግዲህ በኢትዮጵያ ምድር ቦታ አይኖረውም። የታፈነ የህዝብ ድምጽ የተረገጠ የህዝብ ነጻነት እራሱን ነጻ አውጥቶ በግልጽ የሚታይበት ግዜ ቅርብ ነው።

ከተማ ዋቅጅራ

29.05.2015

Email waqjirak@yahoo.coma

The post ከጥፋት ሰረገላ  ውረዱ!!! – ከተማ ዋቅጅራ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

ሥነ-ስርዓት! –የአቤል ማስታወሻ ከቅሊንጦ

$
0
0

“they say that time heals all things,they say you can always forget;
but the smiles and the tears across the years
they twist my heart strings yet!”
― George Orwell, 1984
የመታሰሬ ምክንያት መናገሬ ነው ፡፡ መንግሰት በሬ ወለደ “ሽብር” የሚል ክስ ሳይመስርትብኝ በፊት ይጠይቀኝ የነበረው በማህበረሰብ ሚዲያ የምጽፍበትን የምናገርበት አላማ ነበር፡፡ አላማዬ ተፈጥሮአዊ የመናገር መብቴን ማከናወን አንደሆነ ስናገር ከዚህ ተጨማሪ ሌላ ምክንያት ያለኝ ይመስል የተረፈኝ ድብደባ ነበር ፡፡ በዚህ ሂደት ወትሮም ገመምተኛ የነበረውን ግራ ጆሮዬን አጥቻለሁ፡፡ የሚቆጨኝ ነገር የለም፡፡ የሚያስቆጭ ነገር ካለም መቆጨት ያለብኝ የመናገር ነጻነት ያለውና ያን ነጻነቱን የሚጠቀም ሰው ሆኜ በመፈጠሬ ነው ፡፡

ጦማሪ አቤል ዋበላ

ጦማሪ አቤል ዋበላ


አላማዬ መናገር ነው ፡፡ አላማዬ መማር መማማር፣ ግድየለሽነትን በእውቀት ማስወገድ ነው ፡፡ ይህ አላማዬ ከማንም ያልተቀበልኩት ሰው በመሆኔ ብቻ ያገኘሁት ነው፡፡ ይህንን መሰረታዊ የሰውነት መብቴን ማንም አንዲነፍገው አልፈቅድለትም ፡፡ የመንግሰት ሹመኛ ይሁን ተራ ግለሰብ ፣ ተቋም ይሁን ማህበረሰብ የመናገር መብቴን ልሰጠው አልደራደርም ፡፡
የምናገረው በአደባባይ ፣ በገዛ ቤቴ ፣ በማህበራዊ ሚዲያ በእስር ቤት በፍርድ ቤት በፓሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል በአጠቃላይ በአካባቢዬ ያለውን ግለሰብና ቡድን ሳላውክ በሃላፊነት ነገር ግን በማንኛውም ቦታ ነው ፡፡ ይህንን እነዳላደርግ ቁጣ ፣ ማስፈራሪያ፣ የማሰቃየት ተግባር እስርና ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከልከል አላገደኝም ለወደፊትም እንዲያግደኝ አይሆንም ፡፡
ጓደኞቼም ሆነ እኔ አሁን ያለንበትን እስር ማስወገድ እንድንችል ስደትና ሌሎች መንገዶች አንድንመለከት ሥርዓቱ በደህንነት ሰራተኞቹ ጥቆማ ሰጥቶን ነበር፡፡ የመጨረሻዋ ሰአት ስትቃረብ ከልብ የሆነ አእምሮን የሚፈታተን ውይይት አድርገን ነበር፡፡ ከመታሰራችን ቀናት ቀድሞ ሚያዝያ 15/2006 በገጻችን ዞን9 አንዳስነበብነው“ ተፈጥሮአዊና ህገ መንግሰታዊ መብታችንን ማስረከብ “ እጅግ ስለበዛብን የምንከፍለውን ዋጋ እና የስርአቱን ቂመኝነት እያወቅን መናገራችንን አንደምንቀጥል አውስተን ነበር፡፡

የተራዘመው የእስር ጊዜም ይሄንን አቋም አልለወጠውም፡፡ አሁንም መናገር አሁንም ሃሳቤን መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ ይህ ሰው ሆኖ የመወለድ መብት በምንም አይነት ላባክነው አልፈልግም፡፡ግንቦት 19/2007 በዋለው ችሎትም የተፈጸመውም ይሄ ነው፡፡

ይህንን ክስ የሚከታተል ሰው ሁሉ አንደሚያውቀው19ኛ ወንጀል ችሎት በቀረብንባቸው ጊዜያት ዳኞቹ ንጽህናችንን የምናረጋግጥበትን እድል የሚያጣብቡ ውሳኔዎቸን መወሰናቸው ፣ የራሳቸውን ውሳኔ መልሰው መካዳቸው ፣ አቃቤ ህግ በቸልተኝነት የፍትህ ሂደቱን አንዲያዘገይ መፍቀዳቸው ፣ ማረሚያ ቤት የሚደርሱብንን የመብት ረገጣዎች ሰምተው አጥጋቢ እርምጃ አለመውሰዳቸው ሳያንስ ከሁሉም የከፋው ደሞ ችሎት ውስጥ እነዳንናገርና ሃሳባችንን እንዳንገልጽ ማፈናቸው ነው ፡፡

ይህንን ተከትሎ መፍትሄ ይሆናል በማለት ሃሳባችንን በችሎት እንዳንገልጽ መታፈናችንን በመግለጽ የመሃል ዳኛው አንዲቀየሩ አቤቱታም አቅርበን ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ ጥያቄያችንን ውድቅ ቢያደርገውም መሃል ዳኛው በራሳቸው ፍቃድ ከእኛ ( ከነሶልያና ሽመልስ) የክስ መዝገብ ራሳቸው አግልያለው ብለው የነበረ ቢሆንም አሁንም ድረስ የሚሰየሙት ራሳቸው ናቸው :: ችሎቱም አንደተለመደው ለአቃቤ ህግ እንደፈቀደ ለእኛም ሆነ ለዳኞቹ ለራሳቸው የማይገቡ ነገሮች የሚናገርበት እኛም አንዳንዴ ካልሆነ በስተቀር እንዳንናገር የምንታፈንበት ሆኖ በኤሊ ፍጥነት እያዘገመ ነው ፡፡

ይህ መዘግየት አንደሚያሳስበን ዳኞቹ የተረዱ አይመስለኝም፡፡ በነጻነት ልናደርጋቸው የምንፈልጋቸው ነገሮች አንዳሉን ከሚወዱንና ከምንወዳቸው ሰዎች እስር ቤቱ አንደነጠለን ዘንግተውታል፡፡
የአገሪትዋን የማረሚያ ቤቶች ሁኔታ እና የማረሚያቤቶቹን የእስረኞች አያያዝ አያውቁት ይመስል፣ እኛ የተፈጠርንበትን የጉድ ዘመንና የምንተውንበት ወለፈንድ ድራማ አስገርሞን ፈገግ ማለታችንን አይተው እስሩ የተመቸን እየመሰላቸው በቀጠሮ ላይ ቀጠሮ መደራረባቸው አግባብ አለመሆኑን መናገር ነበረብኝ ፡፡ መታሰራችን ጤናማ መንፈሳችንን እያደከመ መሆኑን አቃቤ ህግ እስከዛሬ አለኝ ሲል ያልተደመጠውን በድንገት ያመጣውን አንድ ዶክመንተሪ ሲዲ (አንደኛ ተከሳሽ ሶልያና ሽመልስ ላይ የቀረበ) ለማየት ሃያ ቀናት መውሰዱ ፣ በአጭር ቀናት ውስጥ አይተው በፍጥነት ወደቀጣዩ የፍርድሂደት እንድንሄድ አንዲደርጉ ለመግለጽ በፍርድ ቤቱ ሥርአት መሰረት እጄን አውጥቼ አውጥቼ አሳየሁ። አንደተለመደው እነዳንናገር ዳኞቹ እቀባ በማድረግ የመሰማት እድላችንን ነፈጉን ፡፡ ለመናገር ፍቃድ ስንከለከል ሳይፈቀድልን መናገር ጀመርን ፡፡ “ የምጣዱ ሳለ የእንቅቡ ተንጣጣ” አንዲል ያገሬ ሰው ተበድለን በተናገርን “ስነስርአት አድርጉ” የሚል ትእዛዝ ከዳኞቹ መጣ፡፡ በዚህ ሰአት “እናንተ ራሳችሁ ሥነ-ስርዓት አድረጉ” በማለት ስርአት አልበኛ የሆነው የንጹሃን ዜጎችን መብት ለማፈን የተዘጋጁት እነሱ መሆናቸውን ተናግሬያለሁ፡፡ ይህንን ስናገር ስሜት ተጭኖኝ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በዚያ ችሎት የሚፈጸመውን በደል ትውልድ እንዲረዳው ታሪክም መዝግቦ አንዲያቆየው መዘከር ነበረብኝ፡፡

ሥነስርዓት ምን እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ወላጆቼ በገባቸው መጠን ጥብቅ በሆነ ስነስርዓት አሳድገውኛል፡፡ ይህ ታላቅን ብቻ ሳይሆን ታናሽንም ማክበር አንደሚገባ ሥነ-ስርዓትና ደንቦችን መጣስ አንደማይገባ ይጨምራል፡፡ ( በሁለት አመት የዞን9ሥራቸንም ለማንኛውም የአገሪቷንህግ ሳንጥስ ህጋዊ ሆነን የቆየነው ለዚያምጭምር ነው ) ነገር ግን መታፈንን በጻጋ መቀበልና በደልን መሸከምን አይጨምርም፡፡ የማንም ሰብአዊ መብት ተሟጋች ወይም ነጸ አውጪአይደለሁም ፡፡ የግለሰብ መብቴ ሲነካ ግን ዝም ማለት አልወድም ፡፡ በተለይም ደግሞ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብቴ አንዲከለከልአልፈልግም ፡፡ ስለዚህም ይህንነ ከዚህ በፌት ላደረገ ፣ ከአሁን በማድረግ ላይ ያለ ፣ ወደፌትም ለማድረግ የሚያስብን ሁሉ::

The post ሥነ-ስርዓት! – የአቤል ማስታወሻ ከቅሊንጦ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

5ቱ ካሮትን የመመገብ ጥቅሞች የጤና ጥቅሞች

$
0
0

carrot
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
1. የምግብ መፍጨት ሂደትን ያግዛል
ካሮት በፋይበር የበለፀገ ስለሆነ የምግብ መፈጨት ሂደትን በማገዝ እንደ ሆድ ድርቀት ያሉ ችግሮችን እንዳይከሰቱ ያደርጋል።
2. ለአይናችን የሚሰጠው ጥቅም ከፍተኛ ነው
ካሮት በሻይታሚን ኤ የበለፀገ ስለሆን እይታችን የተሻለ እንዲሆን ያግዛል
3. በሽታን የመከላከል አቅምን ያዳብራል
ካሮትን መመገብ በሽታን የመከላከል አቅማችን እንዲዳብርና ጤናማ እንድንሆን ይረዳል
4. ስትሮክን ይከላከላል
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ በቀን አንድ ካሮትን መመገብ ለስትሮክ ያለንን ተጋላጭነት በ፮፰ % የመቀነስ አቅም አለው።
5. ካንሰርን ይከላከላል
ካሮት በውስጡ በያዛቸው ልዩ ልዩ ንጥረ ነገሮች ምክንያት ካንሰርን የመከላከል አቅም እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ

The post 5ቱ ካሮትን የመመገብ ጥቅሞች የጤና ጥቅሞች appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የዘረኝነት ጥቃት የደረሰበት ኢትዮ-እስራኤላዊው ወታደር የ100 ሺህ ዶላር ካሳ ጠየቀ

$
0
0

netanyahu

natanyahu 2
ገንዘቡን ለፍትህና እኩልነት ለሚታገሉ ድርጅቶች እሰጣለሁ ብሏል

ባለፈው ወር መጨረሻ ላይ በእስራኤሏ ባት ያም ከተማ በፖሊስ የድብደባ ጥቃት የደረሰበት ኢትዮ-እስራኤላዊው ወታደር ዳማስ ፓካዳ፣ የተፈጸመብኝ ጥቃት ከዘረኝነት የመነጨ ነው ሲል በአገሪቱ ፖሊስ ላይ ክስ መመስረቱንና ለደረሰበት ጉዳት የ100 ሺህ ዶላር ካሳ እንዲሰጠው መጠየቁን “ታይምስ ኦፍ እስራኤል” ዘገበ፡፡የ19 አመት ዕድሜ ያለው ግለሰቡ ባለፈው ማክሰኞ በቴል አቪቭ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአገሪቱ ፖሊስ ላይ በመሰረተው ክስ፣ ለደረሰበት ጉዳትና ጉዳዩን በህግ ለመከታተል ላወጣው ወጪ ካሳ እንዲሰጠው የጠየቀ ሲሆን፣ ጠበቃውም በግለሰቡ ላይ የተፈጸመው ጥቃት የአገሪቱ ፖሊስ በዜጎች ላይ በተደጋጋሚ የሚፈጽመውን ስነምግባር የጎደለውና ሃይል የተቀላቀለበት ጥቃት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

ግለሰቡ በፖሊሶች ጥቃት ሲፈጸምበት በካሜራ ባይቀረጽና ለማስረጃነት ባይቀርብ ኖሮ፣ ምናልባትም ፖሊስን በመድፈር ከባድ ወንጀል ተከሶ ሊቀጣ ይችል እንደነበር የገለጸው ክሱ፣ ጥቃቱ በግለሰቡ ላይ አካላዊና መንፈሳዊ ጉዳት ከማድረሱ ባሻገር የመላውን ኢትዮጵያዊ ቤተ እስራኤላዊ ልብ የሰበረ ነው ብሏል፡፡ ፓካዳ በፍርድቤት ተከራክሮ ካሸነፈና የጠየቀውን የገንዘብ ካሳ የሚያገኝ ከሆነ፣ የተወሰነ ያህሉን ገንዘብ ለፍትህና ለእኩልነት ለሚታገሉ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ድርጅቶች ለመስጠት ማሰቡን ተናግሯል፡፡

ሁለት የፖሊስ ባልደረቦች በግለሰቡ ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ የሚያሳየው አጭር የቪዲዮ ምስል፣ በስፋት መሰራጨቱንና በቴል አቪቭ በሚኖሩ ቤተ እስራኤላውያን ዘንድ ከፍተኛ ቁጣና ተቃውሞ መፍጠሩን ተከትሎ፣ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁና የፖሊስ ኮሚሽነሩ ዮሃናን ዳኒኖ ግለሰቡን በአካል አግኝተው ለተፈጸመበት ጥቃት በፖሊስ ስም ይቅርታ መጠየቃቸውና ከሁለት ሳምንታት በፊትም ጥቃቱን የፈጸመው አንደኛው ፖሊስ ከስራ መባረሩ ይታወሳል፡፡

ምንጭ አዲስ አድማስ ጋዜጣ

The post የዘረኝነት ጥቃት የደረሰበት ኢትዮ-እስራኤላዊው ወታደር የ100 ሺህ ዶላር ካሳ ጠየቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ግለሰቡ በትግራይ ክልል 6 ሰዎችን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ ገደለ

$
0
0

tigrai
(ዘ-ሐበሻ) በትግራይ ክልል ከሚሰራበት ባንክ መስሪያ ቤት የተባረረው ግለሰብ በፊት ይሰራበት ባንክ ገብቶ 6 የባንኩን ሠራተኞች መግደሉ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ::

በትናንትናው ዕለት ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም በሰሜን ምዕራብ ትግራይ በምትገኘው ማይ ፀብሪ በተባለች ከተማ ይኸው ቀድሞ በዘበኝነት ባንኩን ያገለግል የነበረው ግለሰብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማይፀብሪ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅና የወንድ ዘበኛ ጨምሮ 6 የባንኩ ሰራተኞችን ሲገድል አንዲት የባንኩ ሴት ዘበኛም ማቁሰሉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል::

እንደ ዜናው ከሆነ ይኸው ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ቅርንጫፍ ለተወሰኑ ሰዓታት ተቆጣጥሮት ቆይቶ በመጨረሻም በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ለዘ-ሐበሻ የመጣው መረጃ ጠቆሟል:: ሰዎቹን የገደለው ይኸው የቀድሞ የባንክ ሠራተኛ ለምን ከሥራው እንደተባረረ የደረሰን መረጃ የለም::

The post ግለሰቡ በትግራይ ክልል 6 ሰዎችን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ ገደለ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

“የሰለሞን ዴዜዴራታ!!”–ከኤርሚያስ ለገሰ (የመለስ ትሩፋቶች መጽሐፍ ደራሲ)

$
0
0

በሀገረ አሜሪካ መስፍን በዙ የሚባል ትንሽ ሰው አለ። ይህ ሰው ” ቲጂ ቴሌቪዥን” የሚባል በህውሀት የሚደገፍ ተንቀሳቃሽ መንኩራኩርና እሷን የሚሸከምበት ኮልኮላታ አለችው። የሁለቱም ቴክኒሻን፣ ፓይለት፣ ኮፓይለት፣ አስተናጋጅ፣ ተስተናጋጅ እሱ ብቻ ነው። ማንንም ስለማያምን አያሳፍርም። ለነገሩ የሀገሬ ልጆች እንደሰው ሰለማይቆጥሩት አይጠጉትም። በደንብ የሚያውቁት ደግሞ ” ከራሱ የተጣላ፣ግማሽ ሰው” ይሉታል። ቀትረ ቀላል!
ermias copy
እናም ህውሀት የሸለመውና ግርማ ብሩ ወጪውን የሚሸፍንለት መንኩራኩርና ኮልኮላታ አለው። ታዲያ! መንኩራኩሯን ሲሾፍራት በጣም ስለሚፈራና ድንጉጥ ስለሆነ የቀድሞ ክልል አንድን የሚያክል ባይነኩላር በሁለት አይኖቹ ላይ ይገጥማል። ባይነኩላሩ ካሜራ ስለተገጠመለት የድፍረቱ ምንጭ ሆኖ ያገለግለዋል። በጥርጣሬ ለተመለከተውና መንኩራኩሯን ለተጠጋ ሁሉ ” እስቲ ወንድ ከሆንክ ጫፌን ንካ! ” እያለ በተደጋጋሚ ይማፀናል። ጫፋን ሲነኩት እንደ ጐማ ተጠቅልሎ ለመተኛት እየተዘጋጀ። በነገራችን ላይ ወገቡም ላይ ሻጥ ያደረጋት ዲሞፍተር አለችው። ርግጥ ዲሞፍተሯ ቀጥረው እንደሚያሰሩት ጌቶቹ የክርኑን እርዝመትና ክብደት ማሳየት አልቻለችም። አይቻላትም። ምድሪቷ የጌቶቹ ( የድሮ ጓደኞቼ) አይደለችምና! …ይህ አሜሪካ ነው!!

መቼም የድሮ ጓደኞቼ እንደዚህ አይነት ከራሳቸው የተጣሉ ትናንሽ ሰዎችን ለፕሮፐጋንዳ መጠቀም የመጨረሻ አማራጫቸው እየሆነ መሄዱን ስመለከት ያሳዝነኛል። ርግጥ ምንጩን ስለማውቀው ሀዘኔታዬ ገደብ አለው። ደጋግሜ እንደምናገረው ምንጩ የበታችነት ስሜት ( inferiority complex) ነው። ይሁን እንጂ ይህ ስሜት የሚፈጥረው የፍርሀት ጐርፍ ራሳቸውን ተሸክሞ እንደሚሄድ ስለማውቅ እምብዛም አይገርመኝም። በሌላ በኩል የበታችነት ስሜቱ ዘረኝነት የፈጠረውና ከዘመኑ ጋር መለወጥ እንደማይችል ሳስብ ደግሞ ሀገራዊ አደጋው እየታየኝ እደነግጣለሁ። በየጊዜው የሚፈለፈለው የበቀል እርግዝና ማቆሚያው የት ነው?… ጠመንጃና ጉልበት እስከ መቼ መፍትሔ ይሆናል?… በየቦታው ” ጥቁር ባንዲራ” ይዘው በሚቆሙ ጃርቶች መከበብ ምን ይፈይዳል?……

የቀድሞ ጓደኞቼን ባህሪ ትተን ወደ መስፍን በዙ እንመለስ። መነሻችን እሱ በመሆኑ። የሌላችሁን ባላውቅም ባጋጣሚ የተመለከትኳቸው ” ቲጂ ቴሌቪዥን” ፕሮግራሞቹ ” የሞኝ ዘፈን ሁልጊዜ አበባዬ!” የሚለውን ያስታውሰኛል። የመስፍን “አበባዬ” ክቡር ዶክተር አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ ነው። አልፋና ኦሜጋው። በጥላሁን ስም ካልነገደ የራሱን ቀፎነት መደበቅ አይችልም። እስኪሰለቸን ጥላሁን ገሰሰ አሜሪካን ሀገር ቱር ሲያደርግ የሚያዞረው እሱ እንደሆነ ይነግረናል። የማሞ ቂሎ ነገር ጌቶቹን እንዳስቀየመ እንኳን ሳያውቅ ጥላሁን አሁን አምባሻ ያለበትን በንዲራ እንደሚጠላና እንደ ኢትዬጲያ ባንዲራ እንደማይቆጥር ሀይለማርያም ደሳለኝን ፊት ለፊቱ አስቀምጦ ይነግረዋል። ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ ጋሽ ሀይሌ መልስ የመስጠት አቅሙ እንዳሁኑ አልጐለበተም እንጂ ቢጐለብትማ ኖሮ፣

” አምባሻዋን ጠፍጥፈው የፈጠሯት የሰሜን ሰዎች ናቸው። በአንባሻዋ ላይ በሌላው አካባቢ ያለው ህዝብ ምንአይነት ስሜት እንዳለው አያውቁም ነበር” የሚል የግመሏን ምላሽ የሚያስታውስ ታሪካዊ መልስ ይሰጥ ነበር።

መስፍን በዙ ሰሞኑን ለፈፀመው ቂላቂል ስራ እንደሱ ወረድ ብዬ መልስ መስጠት ሳስብ አንድ ነገር አገኘሁ።በአንድ ወቅት ንዋይ ደበበ በድምጳዊ ሰለሞን ተካልኝ ላይ የሰጠው አስተያየት። የሚገርም ምላሽ ነው! ብራቮ ንዋይ!! እንደ እውነቱ ከሆነ መቀነስም መጨመርም አላስፈለገኝም። የመጨረሻዎቹ መስመሮች ” የፓለቲካ ጨዋታ እንዴት በጣም ለትናንሽ፣… ላልበሰሉ… ከሁሉም በላይ ሆዳም ሰዎች” በማለት የገለፀውን ለመስፍን በዙ ምላሽ ይሁንልኝ። አንቀጱ በሙሉ አርቲስት ንዋይ ለተናገረለት ሰው ቋሚ ንብረት ሆኖ ይቀመጥ። ስያሜውንም ” የሰለሞን ዴዜዴራታ” ይበለው።

እነሆ! ንዋይ ” የሰለሞን ዴዜዴራታን” እንዲህ ነበር ያስቀመጠው፣

” … አሁን ላይ ሆኞ ስገመግመው ሙያተኛ ነው?… ወይንስ ፓለቲከኛ ነው?… ወይንስ የትግሉን አምባ ዝም ብሎ እዛም፣ እዛም እየገባና እየሄደ የሚበጠብጥ ያበደ ሰው ነው?… ግራ ይገባኛል። ሰውየውን በቀጥታ ለመተርጐም ግራ ያጋባል። ምክንያቱም እጅግ ከማናችንም በፊት ቀድሞ የከረረ ትግል ለማድረግ የወሰነ የሚመስል ሰው ነበር። እንደውም አሁን በስልጣን ላይ ያለውን መሪ ( አቶ መለስ መሆኑ ነው) የጡት ማስያዣና ፓንት አልብሶ በሲዲው ላይ አድርጐ እየዞረ የመሸጥም ጠንካራ የትግል ስሜት ነበረው። ኧረ! እንደውም እጁን በሰንሰለት አስሮ ፣በብረት ውስጥ ቁጭ ብሎ የእነማንዴላን የትግል አርአያነት ሊላበስ የሞከረ ነው። እኛን ሁሉ መንፈሳችንን የሚያበረታታ ፣ አሳምኖ አብረነው እንድንቆም ካደረገ በኃላ ባልታሰበ ጊዜ ውስጥ ዛሬ እንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ገባ። እንደዚህ አይነት ፍጡር አለወይ የሚያሰኝ ይመስላል። ለምን? …ከማንም በላይ በአትኩሮት ሲከታተሉትና ማንነቱን ሲመረምሩ የነበሩት እነሱ ናቸው። ታሪኩ በሙሉ እጃቸው ላይ አለ።… የፓለቲካ ጨዋታ እንዴት በጣም ለትናንሽ ሰዎች እንደሚጠቅም!… እንዴት ላልበሰሉ ሰዎች እንደሚጠቅም!… ከሁሉም በላይ እንዴት ለሆዳም ሰዎች ምቹ እንደሆነ ነው።…ታሪክና የኢትዬጲያ ህዝብ ጊዜውን ጠብቀው ፍርድ እስኪሰጥ ድረስ መጠበቅ ነው!!…”

The post “የሰለሞን ዴዜዴራታ!!” – ከኤርሚያስ ለገሰ (የመለስ ትሩፋቶች መጽሐፍ ደራሲ) appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የምስራች! ምስር ሳይሆን እርሳስ ብላ –የጐንቻው

$
0
0

yengochawአንት? ‘የቀን ሰው’ ጊዜ ሎቶሪ ቢያወጣልህ፤

የአገር ካባ ቀዳደህ ሕዝብ ማቅ ያልበስክ ወይነህ፤

እነሆ! ‘ሩብ-መቶ ዓመት’ በዙፋን ላይ ዘምነህ፤

ስርዎ-ዘር ያነገስክ ዝርፊያን በምርጫ ሰይመህ፤

በየ አምስት ዓመት የደም ግብር ታፈሳለህ፤

ዘንድሮ ግን ቆርጠናል እራስህን በኮሮጆህ ታገኛለህ፤

የምስራች እንኳን ‘ደስ ያለህ’! ከምስር እርሳስ ከቀናህ።

——የምስራች! ምስር ሳይሆን እርሳስ ብላ——

 

The post የምስራች! ምስር ሳይሆን እርሳስ ብላ – የጐንቻው appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

በሀገራችን ኢትዮጵያ ስላለው ሁለንተናዊ ቀውስ በመወያየት ሁሉን አቀፍ የአማራጭ ኃይል የሚቋቋምበትን ሂደት ለመምከር ከጁላይ 2-3 በዋሽንግተን ዲሲ የሀገር አድን ጉባዔ በጋራ ይዘጋጃል

$
0
0

shengoENTCየኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፤ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ኅብረት ጋር በተደረጉ ተከታታይ የሁለትዮሽ ውይይቶችና ስምምነቶች፡ ህዝባችን ላለፉት 24 ዓመታት ያለነፃነት በህወሓት የግፍ አገዛዝ ሥር ፍዳውን የሚያይበት ዋና ምክንያት፤ ሕዝብን መሠረት ያደረገና ብሄራዊ ጥቅምን ያስቀደመ፤ በአንድ ማዕከል የሚንቀሳቀስ ሁሉን አቀፍ የአማራጭ አካል በማቋቋም ሥርዓቱን ለማስወገድ አስፈላጊውን ትግል የማድረግ ቁርጠኝነቱ በተቃዋሚው ጎራ ያለመኖሩ ዋና ጉዳይ መሆኑን የጋራ ግንዛቤ ላይ ደርሰናል። ይህን አዙሪት በመስበርና ሁኔታዎችን በጋራ በማመቻቸት የአማራጭ ኃይሉ በአስቸኳይ እንዲቋቋም ስምምነት ላይ መድረሳችንንም በተከታታይ ባወጣናቸው የሁለትዮሽ መግለጫዎች ይፋ መሆናቸው የሚታወስ ነው።

ሥርዓቱ ባሳለፍነው ሳምንት ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል አስቀድሞ የታወቀውን የህወሓት/ኢህአዴግ የምርጫ ድራማ በማካሄድ፤ ሕዝብን ተስፋ በማስቆረጥና ግፉን አሜን ብሎ በመቀበል፤ ቀደም ሲል ሲያደረግ የነበረውን ሀገር የማፈራረስ ሂደትና የሕዝብን ስቃይ የሚያበዛ አገር በቀል የአፓርታይድ አገዛዝ ለቀጣይ አምስት አመታት ለማስቀጠል የሚያስችለውን ህጋዊ ሽፋን በማመቻቸት ላይ በሚገኝበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፤ አገር አድን የምክክር ጉባዔ በማድረግ በሕዝብ ተቀባይነትና ታማኝነት ያለው ሁሉን አቀፍ የአማራጭ ኃይል በማቋቋም ትግሉን በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠል ወቅታዊና አስቸኳይ ነው።

ከላይ በመግቢያው ላይ የተዘረዘሩት ድርጅቶች፤ ከተለያዩ አክቲቪስቶችና ታወቂ ግለሰቦች ጋር በመሆን ከጁላይ 2-3 የምክከር ጉባዔ በጋራ ያዘጋጃሉ። የጉባዔውን ውጤት ለማሳወቅ ሕዝባዊ ስብሰባም ይዘጋጃል። የመሰብሰቢያ ቦታ፤ ዝርዝር ፕሮግራሞችና ተያያዥ እንቅስቃሴዎችን በተከታታይ እንደምናሳወቅ ከወዲሁ መግለጽ እንወዳለን።

ስለዚህ፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የፓለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ መኅበራት፣ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆናችሁ ወጣቶች፤ በሀገራችን ነፃነት ሠላም እኩልነትና ፍትኅ ይሰፍን ዘንድ የምትተጉ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ አዘጋጆች፣ የፓልቶክ ክፍሎች፣ ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች፣ ምሁራንና የሀገር ሽማግሌዎች፣ የእምነት አባቶች፤ እንዲሁም ለሀገር ደህንነት ተቆርቋሪ የሆናችሁ ዜጐች በሙሉ፤ የሚገነባው የተባበረ አማራጭ ኃይል ባለቤት እንደመሆናችሁ መጠን የሂደቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆን፤ በሀገራችን ነፃነት እውን እንዲሆን በሚደረገው ወሳኝ ሕዝባዊ ትግል ውስጥ የበኩላችሁን አስተዋፅዖ ታበረክቱ ዘንድ፤ እንዲሁም በሕዝባዊ ስብሰባው ላይ ንቁ ተሳትፎ እንድታደርጉ አደራ እያልን በአክብሮት ሀገራዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

 

ይህ አደገኛ የቁልቁለት ጉዞ እንዲገታ በጋራ እንቁም!

የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (SHENGO)

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት (ENTC)

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት (UEM-PMSG)

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ (EYNM)

 

ግንቦት 22፤ 2007 (May 30, 2015)

The post በሀገራችን ኢትዮጵያ ስላለው ሁለንተናዊ ቀውስ በመወያየት ሁሉን አቀፍ የአማራጭ ኃይል የሚቋቋምበትን ሂደት ለመምከር ከጁላይ 2-3 በዋሽንግተን ዲሲ የሀገር አድን ጉባዔ በጋራ ይዘጋጃል appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ለአፍሪካ ልማት ባንክ የተወዳደሩት አቶ ሱፍያን አህመድ ሳይመረጡ ቀሩ

$
0
0

sofian_ahmedየአፍሪካን ልማት ባንክን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ዕጩ ሆነው የቀረቡት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ አቶ ሱፍያን አህመድ ሳይመረጡ ቀሩ፡፡

ናይጄሪያዊ የግብርናና የገጠር ልማት ሚኒስትር የ55 ዓመቱ ኦኪንውሚ ኦዴሲና የባንኩ ፕሬዚዳንት አድርጎ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ግንቦት 20 ቀን 2007 ዓ.ም. መርጧቸዋል፡፡

ባንኩን ላለፉት አሥር ዓመታት ሲያስተዳድሩት የቆዩትን ሩዋንዳዊውን ዶናልድ ካቤሩካን ለመተካት አቶ ሱፍያንን ጨምሮ ስምንት ዕጩዎች ቀርበው የነበረ ቢሆንም፣ በምርጫ ሥነ ሥርዓቱ አቶ ሱፍያን በሁለተኛ ዙር ከውድድር ውጪ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

አቶ ሱፍያን ቀደም ብሎ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ሆነው ባስመዘገቡት ስኬት የማሸነፍ ዕድላቸው ከፍተኛ እንደሚሆን ተጠብቆ ነበር፡፡ አቶ ሱፍያን ከ20 ዓመታት በላይ በመሩት ሚኒስቴር ካከናወኗቸው ዓበይት ተግባራት መካከል፣ በአገሪቱ ሲከሰት የነበረውን ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ወደ ነጠላ አኃዝ በማውረድ ረገድ የተጫወቱት ሚና ይነገርላቸዋል፡፡ በአገሪቱ አዲስና የቅርብ ክስተት ከሆኑት ውስጥ፣ አገሪቷ በዓለም ቦንድ ገበያ ውስጥ ተሳታፊ መሆኗም ከሚጠቀሱላቸው ተግባራት መካከል ይካተታል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ አቶ ሱፍያን የባንኩ ሁለተኛ የሥራ ቋንቋ የሆነውን ፈረንሳይኛ ቋንቋ መናገር የማይችሉ በመሆናቸው ከፍተኛ ፈተና ሊገጥማቸው እንደሚችል የገመቱም ነበሩ፡፡ በተለይ አንዳንድ የመስኩ ባለሙያዎች የፕሬዚዳንትነቱን ውድድር ለምዕራብ አፍሪካ አገሮች ተወካዮች የተሻለ ቅድመ ግምትን ሰጥተውም ነበር፡፡

በስምንተኛው የባንኩ ጉባዔ ላይ ይፋ በሆነው የምርጫ ሥነ ሥርዓት ላይ አሸናፊ በመሆን የተመረጡት ናይጄሪያዊው ኦዴሲና ‹‹ዛሬ ታላቅ ኃላፊነትን ተቀብያለሁ፤›› በማለት ደስታቸውን ከሚጠብቃቸው ኃላፊነት ጋር በማያያዝ ገልጸዋል፡፡

በቅድመ ምርጫ ወቅት ስምንቱ ዕጩዎች ለውድድሩ የየራሳቸውን ስኬትና አሸናፊ ከሆኑ ለባንኩ ይበጃል ያሉዋቸው ዕቅዶች አቅርበው ነበር፡፡ በተለይ አቶ ሱፍያን ኢትዮጵያ ላለፉት አሥር ዓመታት አስመዝግባዋለች ያሉትን የኢኮኖሚ ዕድገትና የገንዘብ ግሽበትን በመቆጣጠር ልማትን እንዴት ማፋጠን ያስችላል ያሉትን ዕቅድ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ካቤሩካ በበኩላቸው በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ለተተኪያቸው የእንኳን ደስ ያለህ መልዕክት በማስተላለፍ መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል፡፡ ‹‹ለተተኪዬ መልካሙን ሁሉ እመኝለታሁ፡፡ አሥር ዓመት በፍጥነት መሄዱን አይቻለሁ፡፡ እጅግ ውስብስብና ውጥረት የተሞላበት ሥራ ነበር፡፡ ቢሆንም ግን አስደሳች የሥራ ወቅት ነበር፡፡ በእርግጥ ይኼን ሥራ ብዬ ከምጠራው ተልዕኮ ብለው ይሻለኛል፤›› ሲሉ ባንኩን ለአሥር ዓመት ያስተዳደሩት ዶናልድ ካቤሩካ በባንኩ ስላሳለፉት የሥራ ዘመን ተናግረዋል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

The post ለአፍሪካ ልማት ባንክ የተወዳደሩት አቶ ሱፍያን አህመድ ሳይመረጡ ቀሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

በሚኒሶታ የዘ-ሐበሻ 7ኛ ዓመት በዓል በአስገዳጅ ሁኔታ እንዳይከበር ተሰረዘ!

$
0
0

ውድ የዘ-ሐበሻ ወዳጆች! ጁን 20 የዘ-ሐበሻን 7ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በሚኒሶታ ለማክበር ዝግጅታችንን አጠናቀን ነበር:: ሆኖም ግን በአስገዳጅ ምክንያት የዘ-ሐበሻ 7ኛ ዓመት በዓል እንደማይካሄድ ከይቅርታ ጋር እየገለጽን ዘ-ሐበሻን ለመርዳት የምትፈልጉ በድረገጻችን በመግባት በፔይፓል መጠቀም እንደምትችሉ ለመጠቆም እንወዳለን:: እውነት ያሸንፋል! የሚለው መርህዋን ተከትላ የምትቀሳቀሰው ዘ-ሐበሻ 7ኛ ዓመቷን ወደፊት የትና መቼ እንደምታደርግ በቅርቡ እንደምታሳውቅም በዚሁ አጋጣሚ እየጠቆምን ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን::

በዚሁ አጋጣሚም ለዘ-ሐበሻ 7ኛ ዓመት በዓል በክብር እንድነት ለመገኘት ፈቃደኛነታቸውን ገልጸውልን ለነበሩት ለኤርሚያስ ለገሰ (የመለስ ትሩፋቶች መጽሐፍ ደራሲ) እና ለጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ያለንን ክብርና ፍቅር ለመግለጽ እንወዳለን::

የምንወዳት ሃገራችንን ፈጣሪ ይጠብቅልን

የዘ-ሐበሻ ቡድን
Zehabesha

The post በሚኒሶታ የዘ-ሐበሻ 7ኛ ዓመት በዓል በአስገዳጅ ሁኔታ እንዳይከበር ተሰረዘ! appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

በፓትርያርኩ መቀመጫ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቅርሶች እና ንዋያተ ቅድሳት ጉዳይ ምርመራ እንዲካሔድ ተጠየቀ

$
0
0

ታሪካዊው የቅዱስ እንጦንስ ጽሌ በአርተፊሻል ተቀይረዋል ከተባሉት አንዱ ነው
የስእለት እና የስጦታ ወርቆች እና የብር ጌጣጌጦች በየመሸታ ቤቱ እየተሸጡ ነው
የውጭ ኦዲት እንዲካሔድ በፓትርያርኩ የተሰጠው መመሪያ ተግባራዊ አልተደረገም
በየመሸታው አስነዋሪ ሥራ የሚያዘወትሩ ካህናት ለምእመናን መራቅ ምክንያት ኾነዋል
የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ለችግሩ መባባስ ተጠያቂ ተደርገዋል

(ኢትዮ-ምኅዳር፤ ቅጽ 03 ቁጥር 107፤ ቅዳሜ ግንቦት 22 ቀን 2007 ዓ.ም.)

በምሥረታ ታሪኳ እና በሕገ ቤተ ክርስቲያኒቱ ድንጋጌ የፓትርያርኩ መንበር በሚገኝባት ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም፣ በቅርስነት የሚታዩ ጥንታውያን የቤተ ክርስቲያን ንዋያተ ቅድሳት፣ አልባሳት፣ መጻሕፍት እና ልዩ ልዩ ንብረቶች እየተለወጡ እና እየተሸጡ በመጥፋት ላይ ናቸው ያሉ የገዳሟ አገልጋዮች እና ምእመናን ምርመራ እንዲካሔድ ጠየቁ፡፡
ባለፈው ሚያዝያ ወር መጨረሻ የገዳሙ አገልጋዮች እና ምእመናን ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የጻፉት ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ገዳሟ የበርካታ ንዋያተ ቅድሳትና ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት ስትኾን ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያን ተሰርቀው በእግዚአብሔር ኃይል የተገኙና ወደ ስፍራቸው እስኪመለሱ ድረስ በአደራ የተቀመጡ ብዙ ንዋያተ ቅድሳትም ያሉባት ነች፡፡
ከታቦተ ሕጉ ጀምሮ የገዳሟ ንዋያተ ቅድሳትና ታሪካዊ ቅርሳ ቅርሶች ተመርጦ በተመደበው ካህን በየዓመቱ እየተቆጠሩ በጥንቃቄ ተመዝግበው መጠበቅ ሲገባቸው፣ ‹‹የመልካም ሥነ ምግባር አብነት መኾን በተሳናቸው›› አንዳንድ የገዳሟ ሠራተኞች በአምሳላቸው እየተለወጡና እየተሸጡ የመጥፋት አደጋ እንደተጋረጠባቸው ተገልጧል፡፡
Ethiopian_Orthodox_Church_Siege_Addis_Abeba_2
ካለፈው ዓመት ጀምሮ እየተባባሰ መምጣቱ በተነገረው በዚኽ ዓይነቱ ዘረፋ፣ ጥንታውያን ጽሌዎች በአርተፊሻል እንደተቀየሩ፣ ጥንታውያን የብራና መጻሕፍት እና የወርቅ ጽንሐሕ እንደ ወጡ በጥያቄው ተጠቁሟል፡፡ ‹‹እኔ የማውቃቸው ብዙ ንብረቶች ጠፍተዋል›› ሲል ለኢትዮ-ምኅዳር የተናገረ አንድ የገዳሙ አገልጋይ፣ ድርጊቱ የሚፈጸመው ጥንታውያኑን ንዋያተ ቅድሳት እና ቅርሶች በአሳቻ ጊዜ በማውጣት፣ በዕቃ ማጣርያ እና ሽያጭ ሰበብ እንዲኹም ሰነዶችን በመደለዝ እና በማጥፋት እንደኾነ አስረድቷል፡፡ ጥገና እየተደረገላቸው በቅርስነት ተከብረው ለአጠባበቅ ምቹ በኾነ ዕቃ ቤት ተቀምጠው መጎብኘት የሚገባቸው የመጀመሪያውን ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ ጨምሮ ቀደምት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የለበሷቸው ካባዎች፣ ቀጸላዎች፣ አክሊሎች፣ መጎናጸፊያዎች፣ መጋረጃዎችና ጽዋዎችበግምጃ ቤቱ ስለመኖራቸው በንብረት ዓመታዊ ምዝገባ እና ቁጥጥር ማጣራት እንደሚያስፈልግ አገልጋዩ በሐዘን ጠይቋል፡፡
የድርጊቱ ዋነኛ ፈጻሚዎች እንደኾኑና የማጣራቱ ርምጃ እንዲካሔድባቸው የተጠየቀው÷ በገዳሙ የቁጥጥር ክፍል ሓላፊ፣ በንብረት ክፍል ሓላፊ እና በቄሰ ገበዙ ላይ ነው፡፡ የሦስቱን ሓላፊዎች ድርጊት የሚያውቁ አንዳንድ የገዳሟ መነኰሳትም ‹‹የድርሻችን›› በማለት ሲጠይቁ እንደሚስተዋሉ የጠቀሱት አመልካቾቹ፣ ‹‹የቢሮ ሥራ እንሰጣቸኋለን፤ የሙዳይ ምጽዋት ቆጠራውን ወደነበረበት እንመልሰዋለን›› በሚል ሕገ ወጥ አካሔድ እና ጥቅም በማማለል ማባበያ እየተደረገለቸው እንዳለ ገልጸዋል፡፡
በሚልዮኖች የሚቆጠር የገዳሟ ገንዘብ እና ንብረት በአስተዳደር ሓላፊዎች እና ሠራተኞች መመዝበሩን ተከትሎ በኅዳር ወር አጋማሽ የተቋቋመው የሙዳየ ምጽዋት ቆጠራ ኮሚቴ፣ የስድስት ወራት የሥራ ጊዜው ቢጠናቀቅም በእጁ ያለውን ንብረት አስረክቦ ለመቀየር ዝግጁ ካለመኾኑም በላይ በኮሚቴው የሰበካ ጉባኤው ምክትል ሊቀ መንበር እና ቄሰ ገበዙ ተካተውበት ቆጠራው በካሽ ካውንተር አጋዥነት በባንክ ባለሞያዎች ድጋፍ እንዳይቆጠር አባላቱ መቃወማቸው ተመልክቷል፡፡
ኮሚቴው ከምእመናን በስእለት የተሰጡ ንብረቶች በአግባቡ እየተመዘገቡ ግምታቸው ታውቆ በሕጋዊ መንገድ ገቢ እንዲኾኑ በማድረግ በኩል ከፍተኛ ድክመት ማሳየቱ የአመልካቾቹ ሌላው ትኩረት ነው፡፡ በተለይም ካለፈው ሚያዝያ ወር ወዲኽ እየተባባሰ በመጣው የንብረት ምዝበራ፣ ከበጎ አድራጊዎች ለገዳሙ የተለገሠ ላፕቶፕ ኮምፒዩተር እና ጸሎተ ቅዳሴውን ለብዙኃን ለማስተላለፍ ያገለግላል የተባለ ፕሮጀክተር ተመዝግቦ ገቢ ሳይደረግ በግለሰቦች ወጥቶ መሸጡ ተገልጧል፡፡
በደብዳቤው እንደሰፈረው÷ ከመቶ ኻያ ግራም በላይ የአንገት እና የጣት ወርቆች፣ መጠናቸው የማይታወቅ የብር ጌጣጌጦች በደንቡ እና በመመሪያው መሠረት በሕጋዊ ሰነድ ለንብረት ክፍሉ ገቢ ሳይደረጉ መልአከ ብሥራት አባ ወልደ ትንሣኤ አዳሙ በተባሉ የቆጠራ ኮሚቴው አባል በተለያዩ መሸታ ቤቶች መሸጣቸው በዓይን እማኞች ተረጋግጧል፡፡
ከሰማኒያ በላይ ካህናት ባሉበት ገዳም የቃለ ዐዋዲ ደንቡን የሥራ ሓላፊዎች ምርጫ እና የአገልግሎት ዘመን ድንጋጌ በመቃረን ተመሳሳይ ያልኾኑ ሓላፊነቶችን ደራርበው ይዘዋል የተባሉት መልአከ ብሥራት አባ ገብረ ሥላሴ፣ የልማት ኮሚቴው ለሚያሠራው ኹለ ገብ እና የአገልግሎት ሕንፃ ያለፕሮፎርማ በተፈጸመ ጥራቱን ያልተጠበቀ የብረት ግዥ ተገቢ ያልኾነ ጥቅም (ቢያንስ ከብር 200,000 በላይ) ማግኘታቸው ተጠቁሟል፡፡ የገዳሟ የሥራ ማስኬጃ ገንዘብ ያዥ፣ የልማት ገንዘብ ተቀባይ፣ ዕቃ ግዥ እና ንብረት ቁጥጥር ሓላፊየኾኑት የመልአከ ብሥራት አባ ወልደ ሥላሴ ስም ከቄሰ ገበዙ አባ ሳሙኤል ቀለመ ወርቅ እና ሌላ ካህንን ጨምሮ ለምንኩስና ሥርዐት በማይስማማ ተግባር በአልባሌ ቦታ ከመገኘት ጋር ተያይዞም ተነሥቷል፡፡
መነኰሳቱ፥ ‹‹ልናጠምቃቸው ነው›› በሚል እና በምግብ አብሳይነት ሰበብ በገዳሙ ቅጽር በሚገኘው ማረፊያ ቤታቸው የሚገቡ ሴቶችን እስከ መንፈቀ ሌሊት እያቆዩ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስነቅፍ ነውር በመፈጸም፤ በየግሮሰሪው ዓምባጓሮ እየፈጠሩ ከአስተናጋጆች ጋራ ለድብድብ በመጋበዝ፤ በስካር ወደ ገዳሙ ተመልሰው እየገቡ ከምእመናን ጋራ በክፉ አንደበት በመመላለስ፤ በዘር አንዳንዴም በመንደር እየተከፋፈሉ ቅጽሩን የአሉባልታ እና የአድማ መናኸርያ በማድረግ ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን ነቅፈው አስነቅፈዋል፤ ክብረ ቤተ ክርስቲያንን ደፍረው አስደፍረዋል ተብሏል፡፡ አዲሱ የገዳሟ ሰበካ ጉባኤ ይህን ለመከላከል የጊዜ ወሰንን ጨምሮ ያወጣው ዝርዝር የመተዳደርያ ደንብ ‹‹ሕጉ እኛን ለመገደብ ነው፤ እስከ ከዛሬ እንደኖርነው እንኖራለን እንጂ ሕግ አያስፈልግንም፤›› ባሉት በሦስቱ መነኰሳት ግንባር ቀደምነት ተግባራዊነቱ መስተጓጎሉ ተዘግቧል፡፡
ከሰማኒያ ዓመታት በላይ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎት ስትሰጥ የቆየችው ገዳሟ አኹን ያለችበት የቤተ መቅደስ የውስጥ አገልግሎት ‹‹መንፈሳዊ ሕይወት በማይታይባቸው እና ሞያዊነት በሚያንሳቸው ካህናት የተነሣ ደረጃዋን የማይመጥን ነው፤›› ይላሉ አመልካቾቹ፡፡ የውስጥ አገልግሎቱ እና የክህነቱ ተግባር በቂም በቀል፣ በጥላቻ ለደመወዝ ሲባል ብቻ እንጂ መንፈሳዊነቱ ተጠብቆ እና ሥነ ሥርዐቱ ተሟልቶ እየተፈጸመ አይደለም፤ ከጥምቀት እስከ ጸሎተ ፍትሐት አስፈላጊውን መንፈሳዊ አገልግሎት ለምእመናን መስጠት የካህናቱ ኹሉ ሓላፊነት እንደመኾኑ የተመደቡበትን ተልእኮ በሙሉ ኃይላቸው እና ችሎታቸው ለበላይ ሓላፊ በመታዘዝ ከማከናወን ይልቅ ደጀ ጠኚዎችን እየተኩ በውክልና የሚያስፈጽሙ፤ ‹‹ተረኛው የለም፤ ጊዜው አልፏል›› በሚል ግልጋሎት ፈላጊ ምእመናንን ግብረ ገብነት እና ቅንነት በጎደለው ቃል እየተናገሩ የሚያስመርሩ ካህናት ጥቂቶች አይደሉም፡፡ አመልካቾቹ፣ ‹‹በአገልግሎት ከአረጀንባት ቅድስት ስፍራ የሰበካዋ ምእመናን እንዲርቋትና ወደ ሌሎች አድባራት እንዲሔዱ ምክንያት ኾነዋል፤›› በማለት ካህናቱን ይወቅሳሉ – በደብዳቤአቸው፡፡
ምእመናንን በሃይማኖት የመጠበቅ ግዴታቸውን የዘነጉት ካህናት፣ ከተጠያቂነት ለመዳን የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊን ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃን ጨምሮ ቅርበት አላቸው የሚባሉ ሓላፊዎችን መከታ እንደሚያደርጉም ተገልጧል፡፡ የገዳሙን ሀብት እና ንብረት ከመጠበቅ ጀምሮ ለገዳሙ አስተዳደር እና አገልግሎት የበላይ ሓላፊና ተጠሪ የኾኑት አስተዳዳሪው በተጠቀሱት ካህናት እና መነኰሳት ዘንድ ሥልጣን አልባ መደረጋቸው ተነግሯል፡፡
St Marry Bulding comp.
የገዳሟ ያለፉት ስድስት ዓመታት የሒሳብ አያያዝና የንብረት አጠባበቅ በውጭ ኦዲተር እንዲመረመር የልማት ኮሚቴው የበላይ ጠባቂ በኾኑት በፓትርያርኩ ባለፈው ኅዳር ወር የተሰጠው መመሪያ እስከ አኹን ተግባራዊ አለመኾኑ የአስተዳዳሪው ሥልጣን ውሱንነት እና የተጠቀሱት ዋልጌ መነኰሳት የበላይነት መገለጫ ተደርጎ ታይቷል፡፡ በታኅሣሥ ወር አጋማሽ በተመረጠው አዲሱ ሰበካ ጉባኤ ገዳሟ፣ የኻያ በመቶ የሀገረ ስብከት ፈሰስ ውዝፏን በመክፈልና ተቀማጯን ወደ 1 ነጥብ 8 ሚልዮን በማሳደግ የተጓተተው የባለስድስት ፎቅ ሕንፃ ግንባታ እየተፋጠነ ቢኾንም ለውጭ ኦዲቱ ‹‹እየተዘጋጀን ነው›› ከማለት ያለፈ በተግባር ለማስፈጸም አለመቻሉ ታውቋል፡፡
የንብረት እና የቁጥጥር ክፍሎች ሓላፊዎች ከቄሰ ገበዙ ጋራ በመኾን ‹‹አዲሱ ሰበካ ጉባኤ ኦዲት አስደርጎ እኛን ሊያባርረን ነው፤ አንገታችንን እንሰጣለን እንጂ ኦዲቱ አይካሔድም›› በሚል የውጭ ኦዲት ምርመራው እንዳይፈጸም በተለያዩ ስልቶች እየተከላከሉ እንዳሉ ነው የተገለጸው፡፡ ፈቃድ እየጠየቁ ዕረፍት በመውጣት በሥራ ገበታ አለመገኘት አንዱ ስልት መኾኑ ተጠቁሟል፡፡
መንበረ ፓትርያርክ በኾነችው በገዳሟ በውስጥ አገልግሎቷ ከሚታይባት በቂ ሞያ እና ቁጥር ያላቸው ካህናት ጉድለት ባሻገር በቢሮ ሠራተኞች ዘንድም ከፍተኛ የዕውቀት ማነስ እና የአቅም ውስንነት እንዳለ ተጠቅሷል፡፡ ለአብነት ያኽል፣ ለኦዲቱ ሥራ የሚያስፈልገውን የሒሳብ ሪፖርት በጥራት እንዲያቀርቡ የሚጠበቁት የሒሳብ ሹሙ የትምህርት ደረጃ ከዐሥረኛ ክፍል ያለፈ አይደለም፡፡ ሰበካ ጉባኤው ለቦታው በዕውቀት የሚመጥን ባለሞያ እንዲላክ ከአንድ ወር በፊት በጉባኤ ወስኖ ሀገረ ስብከቱን የጠየቀ ቢኾንም ክፍተቱ እንዳይደፈንና ‹‹ከእኛ በላይ ሰው የለም›› በሚል ከቢሮ ሠራተኞች ጋር በጥቅም በተቆራኙት ሦስት ካህናት ክፋት እንዳይፈጸም መደረጉ ነው የተገለጸው፡፡
‹‹ሰበካ ጉባኤው አይጠቅመንም፤ ይውረድልን›› በሚሉ አድማዎች ሳቢያ ሰበካ ጉባኤው አርቅቆ ያቀረባቸው የሰው ኃይል፣ የፋይናንስ፣ የንብረት እና የግዥ ዝርዝር መመሪያዎቹ÷ ‹‹መተዳደርያ ደንብ፣ ማኑዋል የሚባል ነገር አያስፈልገንም፤ እንዲያስቀሩልንም ለሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ነግረናቸዋል›› በሚሉት ሦስቱ ግንባር ቀደም መነኰሳት የተነሣ ሊሠራባቸው እንዳልቻሉና ተጨባጭ ለውጥ ለማሳየት የሚያደርገው ጥረት ዕንቅፋት እንደገጠመው ተመልክቷል፡፡ ይኸውም የአድኅሮት አቋማቸው ‹‹ሕገ ቤተ ክርስቲያን፣ ቃለ ዐዋዲ እና የሠራተኛ መተዳደርያ ደንብ አለን፤ ሌላ ምንም አያስፈልገንም›› የሚሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ ሳይተባበሩበት እንዳልቀረ ተጠቁሟል፡፡
በገዳሟ ‹‹ሃይማኖት ጎድሏል፤ ግብረ ገብነት ጠፍቷል፤ ምዝበራ ተንሰራፍቷል›› የሚሉት አመልካቾቹ፣ በመጋቢት ወር ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጥያቄአቸውን ለማቅረብ ሞክረው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ ይኹንና የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ‹‹ጾም ሲፈታ እንጂ አኹን አይቻልም›› ብለው በማለታቸው ችግሩ እየተባባሰ እንዲሔድ ምክንያት መኾናቸውን በመጥቀስ ጉዳዩ ፖሊስን ጨምሮ በሚመለከታቸው አካላት እንዲጣራ ያደርጉላቸው ዘንድ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስን መጠየቃቸው ታውቋል፡፡
የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው በበኩሉ ባለፈው ሳምንት ኀሙስ ወደ ፓትርያርኩ ቀርቦ ከተመረጠበት ታኅሣሥ ወር ወዲኽ በአስተዳደር እና በልማት ያከናወናቸውን ተግባራት በሪፖርት ማቅረቡ ዘግይቶ ተሰምቷል፡፡ በተለይም በአሠራር መመሪያዎቹ ዝግጅት ‹‹ከጠበቅኹት በላይ ነው የሠራችኹት›› የሚል ማበረታቻ ከፓትርያርኩ ማግኘቱ ተገልጧል፤ ለተግባራዊነቱ ስለገጠመው ዕንቅፋትም ‹‹በቃለ ዐዋዲው መሠረት ሕግ እና ሥርዐት ተከትላችኹ ርምጃ ከመውሰድ የሚያግዳችኹ ነገር የለም›› የሚል መመሪያ መቀበሉ ተነግሯል፡፡
St Marry Church
የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ስያሜዋን ያገኘችው በ፲፱፻፳፪ ዓ.ም. ስትመሠረት የቅዱሳን ፓትርያርኮች መንበር ስለሚገኝባትና በመንበረ ፓትርያርክ ግቢ ስለምትገኝ መኾኑን ታሪኳ ይገልጻል፡፡ ስፍራው ቀደም ሲል የሥርዐተ ምንኵስና መሥራቾቹ የቅዱስ አባ እንጦንስ እና አባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶበት የግብጻውያኑ ሊቃነ ጳጳሳት ማረፊያ እና ዕጨጌው እንዲኹም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጸሎት የሚያደርሱበት በመኾኑ አቡን ቤት እየተባለ ይጠራ ነበር፡፡ በግብጻዊው ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ከኢየሩሳሌም መጥቶ በመናገሻ ማርቆስ ተቀምጦ የቆየው የቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ጽላት እስከገባበት ድረስም ምእመናን አምልኮታቸውን ይገልጹበት ነበር፡፡
ጥር ፳፩ ቀን ፲፱፻፳፪ ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ትእዛዝ መሠረቱ የተጣለው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ሥራው የተጠናቀቀው መስከረም ፲፱፻፳፰ ዓ.ም ነው፡፡ በወቅቱ በፋሽስት ኢጣልያ ወረራ ምክንያት ሌሎች በርካታ ታቦታትም በቤተ መቅደሱ ተቀምጠው እንደነበር ይነገራል፡፡ ገዳሟ የግብጽ ኦርቶዶክስ ካህናት እና የሕንድ ኦርቶዶክስ ካህናት በየራሳቸው ቤተ መቅደስ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚፈጽሙባት ብቸኛዋ ቤተ ክርስቲያን ነበረች፡፡ ግብጻውያን ኦርቶዶክሳውያን ዛሬም በገዳሙ ደቡባዊ አንቀጽ ከክርስትናው ቤት ፎቅ ላይ በመገኘት መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን ሲፈጽሙ ይታያሉ፡፡
በሚያዝያ ወር መጨረሻ ለፓትርያርኩ በተጻፈው የገዳሟ ካህናት ደብዳቤ ‹‹በአርተፊሻል ተቀይረዋል›› ከተባሉትና ምርመራ እንዲካሔድ ከተጠየቀባቸው ጥንታውያን ጽላት አንዱ ታዲያ የአበ መነኰሳት ቅዱስ እንጦንስ መኾኑ ነው እየተነገረ የሚገኘው፡፡
Source:: haratewahido

The post በፓትርያርኩ መቀመጫ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቅርሶች እና ንዋያተ ቅድሳት ጉዳይ ምርመራ እንዲካሔድ ተጠየቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ከጁላይ 2-3 በዋሽንግተን ዲሲ የሀገር አድን ጉባዔ በጋራ ይዘጋጃል

$
0
0

በሀገራችን ኢትዮጵያ ስላለው ሁለንተናዊ ቀውስ በመወያየት ሁሉን አቀፍ የአማራጭ ኃይል የሚቋቋምበትን ሂደት ለመምከር ከጁላይ 2-3 በዋሽንግተን ዲሲ የሀገር አድን ጉባዔ በጋራ ይዘጋጃል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፤ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄና
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ኅብረት ጋር በተደረጉ ተከታታይ የሁለትዮሽ ውይይቶችና
ስምምነቶች፡ ህዝባችን ላለፉት 24 ዓመታት ያለነፃነት በህወሓት የግፍ አገዛዝ ሥር ፍዳውን የሚያይበት ዋና ምክንያት፤
ሕዝብን መሠረት ያደረገና ብሄራዊ ጥቅምን ያስቀደመ፤ በአንድ ማዕከል የሚንቀሳቀስ ሁሉን አቀፍ የአማራጭ አካል
በማቋቋም ሥርዓቱን ለማስወገድ አስፈላጊውን ትግል የማድረግ ቁርጠኝነቱ በተቃዋሚው ጎራ ያለመኖሩ ዋና ጉዳይ
መሆኑን የጋራ ግንዛቤ ላይ ደርሰናል። ይህን አዙሪት በመስበርና ሁኔታዎችን በጋራ በማመቻቸት የአማራጭ ኃይሉ
በአስቸኳይ እንዲቋቋም ስምምነት ላይ መድረሳችንንም በተከታታይ ባወጣናቸው የሁለትዮሽ መግለጫዎች ይፋ
መሆናቸው የሚታወስ ነው።
shengoENTC
ሥርዓቱ ባሳለፍነው ሳምንት ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል አስቀድሞ የታወቀውን የህወሓት/ኢህአዴግ የምርጫ
ድራማ በማካሄድ፤ ሕዝብን ተስፋ በማስቆረጥና ግፉን አሜን ብሎ በመቀበል፤ ቀደም ሲል ሲያደረግ የነበረውን ሀገር
የማፈራረስ ሂደትና የሕዝብን ስቃይ የሚያበዛ አገር በቀል የአፓርታይድ አገዛዝ ለቀጣይ አምስት አመታት ለማስቀጠል
የሚያስችለውን ህጋዊ ሽፋን በማመቻቸት ላይ በሚገኝበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፤ አገር አድን የምክክር ጉባዔ በማድረግ
በሕዝብ ተቀባይነትና ታማኝነት ያለው ሁሉን አቀፍ የአማራጭ ኃይል በማቋቋም ትግሉን በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠል
ወቅታዊና አስቸኳይ ነው።
EYNM New Logo
ከላይ በመግቢያው ላይ የተዘረዘሩት ድርጅቶች፤ ከተለያዩ አክቲቪስቶችና ታወቂ ግለሰቦች ጋር በመሆን ከጁላይ 2-3
የምክከር ጉባዔ በጋራ ያዘጋጃሉ። የጉባዔውን ውጤት ለማሳወቅ ሕዝባዊ ስብሰባም ይዘጋጃል። የመሰብሰቢያ ቦታ፤
ዝርዝር ፕሮግራሞችና ተያያዥ እንቅስቃሴዎችን በተከታታይ እንደምናሳወቅ ከወዲሁ መግለጽ እንወዳለን።
ስለዚህ፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የፓለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ መኅበራት፣ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆናችሁ ወጣቶች፤
በሀገራችን ነፃነት ሠላም እኩልነትና ፍትኅ ይሰፍን ዘንድ የምትተጉ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ አዘጋጆች፣ የፓልቶክ ክፍሎች፣
ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች፣ ምሁራንና የሀገር ሽማግሌዎች፣ የእምነት አባቶች፤ እንዲሁም ለሀገር ደህንነት ተቆርቋሪ
የሆናችሁ ዜጐች በሙሉ፤ የሚገነባው የተባበረ አማራጭ ኃይል ባለቤት እንደመሆናችሁ መጠን የሂደቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ
በመሆን፤ በሀገራችን ነፃነት እውን እንዲሆን በሚደረገው ወሳኝ ሕዝባዊ ትግል ውስጥ የበኩላችሁን አስተዋፅዖ ታበረክቱ
ዘንድ፤ እንዲሁም በሕዝባዊ ስብሰባው ላይ ንቁ ተሳትፎ እንድታደርጉ አደራ እያልን በአክብሮት ሀገራዊ ጥሪያችንን
እናቀርባለን።

ይህ አደገኛ የቁልቁለት ጉዞ እንዲገታ በጋራ እንቁም!
የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (SHENGO)
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት (ENTC)
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት (UEM-PMSG)
የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ (EYNM)
ግንቦት 22፤ 2007 (May 30, 2015)
ďżźďżźďżź

The post ከጁላይ 2-3 በዋሽንግተን ዲሲ የሀገር አድን ጉባዔ በጋራ ይዘጋጃል appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live