Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ኢትዮጵያ –የምርጫ ቀጣና ሳይሆን የጦርነት ቀጠና እየመሰለች ነው

0
0

Bahrdar

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዉጥ ይፈልጋል። የነገዉን ምርጫ እንደ መሳሪያ በመጠቀም፣ ለዚህ ግፈኛ መንግስት ተቃዉሞዉን ይገልጻል ተብሎ ይጠበቃል። ህወሃት/ኢህአዴግ ህዝብ እንደተፋው ያውቃል። ከዚህም የተነሳ በብዙ ቦታዎች ፣ የምርጫ ጣቢያዎች ሁሉ ተዘግተዋል። እንደ አዲስ አበባ፣ ባህር ዳር ያሉ ከተሞች የጦርነት ቀጠናዎች ይምስሉ። ቁጥሩ እጅግ በጣም ብዙ የሆነው የታጠቃ ኃይል ተሰማርቷል። ቁጥራቸው እጅግ በጣም ብዙ የሆነ ኢትዮጵያዉይን እየታፈሱ ነው።

bahrdar 1
በአገር ቤት ያለው ሁኔታ እንዲህ እንዳለ ህወሃት/ኢሕአዴግ ከፍተኛ የአለም አቀፍ ተቃዉሞ ገጥሞታል። በርካታ የዉጭ ጋዜጦች ምርጫው የዉሸት እንደሆነ እየዘገቡ ነው። የአቶ ኃይለማሪያም የአልጃዚራም ቃል ምልልስ በአገዛዙ ላይ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ዉርደትን አከናንቧል። አቶ ኃይይለማሪያ የአንድ አገር መሪ ሳይሆኑ ሃሺሻ ሳያገኝ ሲቀር የሻሺሽ ሱሰኛ እንደሚሆው ፣ የሚቀጠቀጡ ዱርዬ ነበር የሚመስሉት።

ሕወሃት/ኢሕአዴግ በራዲዮና ቲቪ በመዛት፣ የወታደር ብዛት በማከማቸት፣ ታንኮች በማሰማራት በ1997 እንዳደርገው የሕዝቡን ጥያቄ አፈቤ እገዛለሁ የሚል እምነት ይኖረዋል። ሆኖም 2007 እንደ 1997 አይደለም።

ይሄ በአገዛዙ ላይ የደረሰው ዉጥረትና ውርደት ፣ የሕዝብ ትግል ያመጣው ነው። ይሄ የሕዝብ የትግል መነሳሳት ደግሞ በአገራችን የነጻነት ጮራ የሚፈነጥቅበት ጊዜ ቅርብ መሆኑ የሚያሳይ ነው። በርግጥም የሕዝብ ጉልበት ያሸንፋለ። እነርሱ ጥቂቶች ናቸው። እነርሱ እስከ አሁንም የኖሩት እየከፋፈሉ ነው። እኛ ግን ሚሊዮኖች ነን። እኛ ግን ዘር፣ ኃይይማኖት ሳንለይ አንድ ሆነናል።

The post ኢትዮጵያ – የምርጫ ቀጣና ሳይሆን የጦርነት ቀጠና እየመሰለች ነው appeared first on Zehabesha Amharic.


እውን የዘንድሮው ምርጫ ፍታሀዊ ነውን? –ምርጫ እንደ ዕድሜ ማራዘሚያ

0
0

መድረክ በሆለታ ከተማ አድርጎት የነበረው ስብሰባ ይህንን ይመስል ነበር

መድረክ በሆለታ ከተማ አድርጎት የነበረው ስብሰባ ይህንን ይመስል ነበር


ከኢብራሒም ሻፊ

ከ10 ዓመታት በፊት ምርጫ ሲከወን አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ከአራት ዓመታት በፊት “በስብሰዋል” ብሎ ስላሰናበታቸው የትግል ግዜ ወዳጆቹ እና ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በኋላ ስለተፈጠረው የሰላም ድርድር እንዲሁም የፍትህ ሂደት እንጂ ምንም ያሰበው ነገር አልነበረም፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተገኝቶም ለሰበሰባቸው ምሁራን “ቀጣዩ ምርጫ ፍትሐዊ እና ዲሞክራሲያዊ ይሆናል፤ ለዚህም ቃል እገባለሁ” ሲል ምን ይመጣብኛል አላለም፡፡ የትግል ወዳጁ ገብሩ አስራት “ሉዓላዊነት እና ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ” በሚለው መፅሐፋቸው ይህን በሚገባ ተረድተውት “የኢህአዴግ ተሃድሶ ተግባራዊ ይሆናል ብለው ተስፋ ያደረጉ በርካታ የአዲስ አበባ እና የሌሎች ዩኒቨርስቲ የቀድሞ እና የወቅቱ ምሁራን ወደ ምርጫው መጡ” በማለት በጥልቀት ያላሰበበት አምባገነኑ መለስ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ስርነቀል ለውጥ ሊፈጥሩ የሚችሉ ሰዎችን ወደ ፖለቲካዊ ምህዳሩ ጋብዞ እንደነበር ያወሳሉ፡፡

በወቅቱ አምባገነኑ መለስ እንዳሰበው የምርጫ ውይይቱ እና ክርክሩ ከስርዐቱ መበስበስ እና መታደስ ጋር የተያያዘ አልነበረም፡፡ ስለ ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት መዘዞች፣ውጤት እና የፍትሕ ሂደትም ብዙ አልተነሳም፡፡ በቁንፅል በመገናኛ ብዙሐን ስለሚወሳው ሙስና እና ስርዐቱ ሙስናን ለማስወገድ በቁርጠኝነት አለመንቀሳቀሱ ላይም ብዙ አላጠነጠነም….ውይይቱ…..ክርክሩ፡፡ ይልቅ መንግስት ያልተዘጋጀባቸው የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አፍጠው መጡ፣ የኢኮኖሚ ችግሩ ተነሳ፣ ችጋሩ እና ድህነቱ ተወሳ፤ የሀይማኖት ነፃነት ጥያቄዎች በረድፍ ይቀርቡ ጀመር፣ የኢትዮጵያን አንድነት የነቀነቀው “በልዩነት አንድነት” የኢህአዴግ ፖሊሲ ብዙ ጥያቄዎችን አንግቦ ብቅ አለ፡፡ ኦሮሞው የታለ የኢኮኖሚ እኩልነቱ የሚል ጥያቄን ሲያነሳ፣ አማራው እስካዛን ወቅት ለምን ነፍጠኛ እና የቀድሞ ገዢ መደቦች አካል ተደርጎ እንደሚወሰድ መጠየቅ ጀመረ፡፡ መንግስት ምሁራንን ከፊታቸው አድርገው ባልተዘጋጀበት ጥያቄ ያጣደፉትን ተፎካካሪ ፓርቲዎችን “ኢንተርሀሞይ” የሚል ኃይለ ቃልን ጭምር ተጠቅሞ ቢያስፈራራም ጥያቄው ገፋ፡፡ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ድጋፍ በአዲስ አበባ የወጣው ህዝብም ኢህአዴግ በምርጫው ተሸናፊ ሊሆን እንደሚችል የቅድሚያ ምስክርነትን ሰጠ፡፡ ስለዚህም አምባገነኑ መለስ ሊያሸንፍበት የሚችለውን አንድ ነገር ከምርጫው በኋላ ተጠቀመ፡፡ ህፃናትን ጭምር በጥይት አስደብድቦ ገደለ፣ ህዘብን በገፍ አሰረ፣ የተፎካካሪ ፓርቲዎችን አመራሮችን ወህኒ ወረወረ፣ ጋዜጠኞችን እስር ቤት አጎረ፣ አሰደደ እንዲሁም እንዲዘጉ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡

ህዝብ በፍርሃት በተወጠረበት እና ነፍስ ውጪ፣ ነፍስ ግቢ በሚባልበት በዚያው ዓመት አምባገነኑ መለስ የስልጣን ዕድሜውን ማራዛሚያ ቀመርን ይቀምም ጀመር፡፡ አምሳያ አምባገነን ሀገራት እንዴት ስልጣን ላይ ረጅም እድሜን አስቆጠሩ? በተለይ የቻይናው ኮሚዩኒስት ፓርቲ ይህን ሁሉ ዘመን አንዴት ስልጣን ላይ መቆየት ቻለ? ብሎም የኩረጃ ፖለቲካውን ጀመረ፡፡ የበጎ አድራጎት ማህበራት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ህግ ወጣ፡፡ በርካታ ለእርዳታ፣ ፍትህ፣ ዲሞክራሲ፣ እኩልነት እና ሰብዐዊነት የቆሙ ተቋማት ተዘጉ ………ከኢትዮጵያም ተሰናበቱ፡፡ የፀረ-ሽብር ህግ ተብሎም በተረቀቀው ህግ ጋዜጠኞች፣ ተቃዋሚዎች እና የሰብዐዊ መብት ተሟጋቾች ኢላማ ተደርገው ለእስር ተዳረጉ፣ ተገደሉ እንዲሁም ተሰደዱ፡፡ የመገናኛ ብዙሓን መረጃ የማገኘት እና ነፃነት አዋጅ ተብሎም እጅግ አፋኝ ህግ ወጥቶም የህዝብ ድምፅ የሚባሉት ጋዜጦች እና መፅሔቶች ተዘጉ፡፡ ባለቤቶችን እና ጋዜጠኞቹን ማንገላታት፣ ማሰር፣ ማስፈራራት እና ሀሳዊ ፍርድ ቤቶች አቅርቦ ለረጅም ዓመታት ወህኒ መወርወር ተለመደ፡፡

የትኛውም ዓይነት ጥያቄ ሲቀርብ በኃይል መጨፍለቅ ምላሽ ተደርጎ ይወሰድ ጀመር፡፡ በጋምቤላ መሬቴን ተነጠቅሁ ያለን ገበሬ ያለ ርህራሄ መጨፍጨፍ በአምባገነኑ መለስ ትክክለኛ ተደርጎ ይወሰድ ጀመር፡፡ በኦጋዴን እና ሲዳም ለትንሽ ኮሽታ እናት፣ አባት፣ ሴቶች፣ ህፃናት ተገደሉ፡፡ አወሊያ አስተዳደራዊ ዝቅጠት ውስጥ ከገባው መጅሊስ ተላቆ የሙስሊሙ ይሁን፣ መንግስት በሀይማኖት ጉዳያችን ጣልቃ አይግባ እንዲሁም ሙስሊሙ በመስጂድ የሚመርጣቸው እውነተኛ የሀይማኖቱ ተወካዮችን እናግኝ ብለው ሶስት ቀላል ጥያቄዎችን ይዘው በመረጧቸው ኮሚቴዎች በኩል የቀረቡትን ሙስሊሞች “ኢስላማዊ መንግስት የመመስረት ሀሳብ አላችሁ” ብሎ ድራማ ሰርቶባቸው ወህኒ ወረወራቸው፤ በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ሙስሊሞችም ህይወታቸውን ከፈሉ፡፡ የአዲስ አበባ ኦሮሚያ የተቀናጀ የጋራ ፕላን “ገበሬን በዝቅተኛ ገንዘብ አፍናቅሎ ድህነትን የበለጠ ያስፋፋል” ብለው የተቃወሙ የኦሮሚያ ሰዎችን እንደተለመደው ህፃን፣ አዛውንት፣ አሮጊት፣ ሴት ሳይመረጥ የጥይት እራት አድርጎ አለፋቸው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ውስጥ ሳይቀር እጁን አስገብቶ ህዝበ ክርስቲያኑን “በምን ታመጣለችሁ?” ደነፋባቸው፡፡

መንግስት በዚህ ሁሉ ወንጀል ውስጥ ተዘፍቆ ግን ሁለት የይስሙላ ምርጫን አድርጎ ወደ ሶስተኛው ተጉዟል፡፡ እሁድ ግንቦት 16/2007 እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠርም ይኸው ምርጫ ተደርጓል፡፡ የ2000 የማሟያ ምርጫን 100% እንዲሁም የ2002 አጠቃላይ ምርጫን 99.6% አሸንፌያለሁ ብሎ ባደደባይ የሚደሰኩረው አምባገነኑ መንግስት ከሙስሊሙ፣ ክርስቲያኑ፣ ከሁሉም ዘር (የትጥቅ ትግል የጀመረበት ቦታን ጨምሮ)፣ ከወጣቱ፣ አዛውንቱ እና ሴቶች ጋር ተጋጭቶ፤ ሙስናው አይን አውጥቶ፣ በእግሩ ድሆ እና ቆሞ አፍጥጦ እየታየ፣ በየሳምንቱ እምባን የሚጋብዙ ኢትዮጵያዊ ነክ ዜናዎች እየተሰሙ ለምን ምርጫ ላይ ሙጭጭ ይላላ? የብዙዎች ጥያቄ ነው፡፡

የስልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም ከ1997 ምርጫ በኋላ የኩረጃ ፖለቲካ ውስጥ የተፈቁት ሟቹ አምባገነን መለስ “እንዴት ብዙ መቆየት እችላለሁ?” ብለው ሲኮረጁ 66 ዓመታት የቆየውን የቻይናን አምባገነን መንግስት ብቻ አላዩም፡፡ 69 ዓመታት የቆየው የጆርዳን፣ 35 ዓመታት ያስመዘገበው የዙምቧቡዌ እንዲሁም 21 ዓመታት የዘለቀውን የቤላሩስ አምባገነኖችን ኮርጀዋል፡፡ እግረ መንገዳቸውንም የዩኒቨርስቲ ኦፍ ካሊፎርኒያ የፖለቲካል ሳይንቲስቷ የዶክተር አንድሬያ ኬንዴላ-ታይለር እና የብሪጅዋተር ስቴት ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰሯን ኤሪካ ፍራንትዝ ጥናትን የተመለከቱም ይመስላሉ፡፡

ለሁለቱ እንስት ምሁሮች፤ እንደ ሟች መለስ ዜናዊ አይነት አምባገነን እና እንደ ኢህአዴግ አይነት የተጠላ መንግስት ዕድሜውን ማራዘም ከፈለገ ምርጫ አይነተኛ “መድኃኒት” ነው፡፡ ከምርጫ በተጨማሪ የውሸት (Pseudo) ዲሞክራሲያዊ ተቋማት ዕድሜያቸውን ያረዝሙላቸዋል፡፡ በሚፈልጉት መጠን ለክተው የቆረጧቸው ተቃዋሚ (ተፎካካሪ) ፓርቲዎች የሚያጫውቷቸው ከሆነ ደግሞ ዕድሜያቸው መንግስታዊ “ማቱሳላ” መሆኑ አይቀርም ይባልላቸዋል፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከላይ የተጠቀሱት ምሳሌዎች እንዳሉ ሆነው ዘንድሮ ምርጫን ያደረጉ አምባገነኖች እንደዚህ ናቸው፡፡ ዑዝቤክስታን፣ ሱዳን፣ ቶጎ እና ካዛክስታን ፖለቲካዊ አምሳያቸውን ከፈለጉ ኢትዮጵያን ማየት ይበቃቸዋል፡፡ ኢትዮጵያም እንዲህ የሆነችው እነሱን ኮርጃ ነው፡፡

እንደ ዶክተር አንድሪያ እና ረዳት ፕሮፌሰር ኤሪካ ገለፃ ለእንደ ኢትዮጵያ አይነቱ አምባገነን ምርጫ “ነፃ፣ ፍትሐዊ እና በውድድር የተሞላ” መሆኑ አያሳስባቸውም፡፡ እነርሱ የሚፈልጉት ዓመቱን ጠብቆ ምርጫ መደረጉ፣ በሚፈልጉት መጠን የተለኩ የተፎካካሪ ፓርቲዎች መኖርን እና ስልጣናቸውን ህጋዊ (Legitimate) የሚያደርጉላቸውን ተቋማት ብቻ ነው፡፡ በተለይ ከቀዝቃዘው የዓለም ጦርነት በኋላ አምባገነኖች ይህን አሰራር በደንብ ተላምደውታል፡፡ ሁለቱ አንስት ምሁራን እንዳጠኑት ከ1946-1989 የአምባገነኖች አማካይ ዕድሜ 12 ዓመታት ብቻ ነበር፡፡ ሆኖም ከቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት በኋላ ይህ አማካይ ዕድሜ ወደ 20 ዓመታት ከፍ ብሏል፡፡አምባገነኖቹ ዕድሜያቸውን ለማርዘም ምርጫ፣ ህግ፣ ደንብ፣ ስርዐት ይሏችኋል፡፡ እናም የሚፈልጓቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሏቸው፡፡ ይህ ዲሞክራሲያዊ ጭምብልን ያላብሳቸዋል፡፡ ዓለምዓቀፍ እና የሀገር ውስጥ ተቀባይነትን (Legitimacy) በግድ ይወስዱበታል፡፡ “የተረጋጋ መንግስት አለኝ፤ በሀገሬ መጥታችሁ ኢንቨስት አድርጉ” ብለው ይቀሰቅሱበታል፡፡ በርካሽ የቸበቸቡትን የሰው ጉልበት፣ መሬት፣ የንግድ ዘርፍ እና የንግድ ተቋምን ከግምት ሳያስገቡ ዜጎቻቸው ላይ “እድገት” ብለው ያላዝኑበታል፡፡ እንዲሁም ወደ ምዕራባዊያን ሀገራት ለጉብኝት ሲያቀኑ ስለ ኮሞዩኒዝም መውደቅ፣ ስለ ምርጫ እና ሊብራሊዝም ማበብ ሊደሰኩሩም ይችላሉ፡፡ የይስሙላ ምርጫን አድርጎ ሳያስበው እና ሳይዘጋጅበት በህዝብ አመፅ እውነተኛ ውድቀት ውስጥ ከተዘፈቀው የሲሪላንካው ማሂንዳ ራጃብካ መንግስት ውጪ በቅርብ አምባገነኖችን ምሉዕ በሙሉ በውሸት የተገነባው ምርጫቸው ጥሏቸው አያውቅም፡፡

የኢትዮጵያ መንግስትም መተማመኛው ይሄው ነው፡፡ ሟች አምባገነኑ መለስ የሁለቱ እንስት ጥናትን ተመልክተው ከ1951-1989 አምባገነኖች ከተቃዋሚ ፓርቲ ጋር በአማካይ ጭማሪ ስድስት ዓመታት፤ ሳያሰልሱ ምርጫን ካደረጉ ጭማሪው 12 ዓመታት እንደሚኖሩ ይህ ቁጥር ግን ከቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት በኋላ አምባገነኖች ከተቃዋሚ ፓርቲ ጋር በአማካይ 14 ዓመታት፤ ግዜን ጠብቀው ምርጫን ካደረጉ ግን 22 ተጨማሪ ዓመታት ሊቆዩ እንደሚችሉ አምብበውም፤ ስለዚህም ምሉዕ በሙሉ የውሸት ምርጫ ማድረግን ያዋጣኛል ብለው ተቀብለው ይሆናል፡፡ ለኢህአዴግ ከሙስሊሙ ጋር ቢጋጭ፣ በክርስቲያኑ ሀይማኖታዊ ጉዳዮች እጁን ቢያንቦጫርቅ፣ የትጥቅ ትግል የጀመረበት ቦታ ዘር ሳይቀር “ጠላሁህ” ብሎ ጠብመንጃ ቢያነሳበትም፣ ወጣቱ ጠልቶት በገፍ ስደትን ቢመርጥም፣ እስር ቤቶች ኢ-ፍትሐዊ በሆነ መንገድ በተያዙ እና በታሰሩ ሰዎች ቢሞሉም፣ ህዝብ በሹክሹክታ አምባገነንት በቃኝ ቢል፣ በሀገሪቷ ብሶትን የሚያሰማ አንዲትም ጋዜጣ ይሁን መፅሔት ባይኖርም፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ባለዝና ሰዎች እና ምሁራን በፍርሃት ተሸብበው አጎብዳጅ ቢሆኑም፤ ምርጫው ይደረጋል፡፡ ምክንያቱም “ምርጫው እድሜ ማራዘሚያ መድኃኒቱ” ነው፡፡ ህዝብ ይህን ምርጫ ታኮ ልተንፍስ ካለም ከእንሰሳ ብዙም የማይለዩ ለመግደል ብቻ የሰለጠኑ፣ ቀጭን ትዕዛዝ ተቀባዮች ይላኩበታል፡፡

The post እውን የዘንድሮው ምርጫ ፍታሀዊ ነውን? – ምርጫ እንደ ዕድሜ ማራዘሚያ appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: የተሰነጣጠቀ ተረከዝን በቀላሉ ማስወገድ የሚቻልባቸው 5 መንገዶች

0
0

eger
(ጤናማ ውበት በቤታችን)
1. ሎሚ glycerin እና ጨው
• ሞቅ ባለ ዉሃ በጥቂቱ የሎሚ ጭማቂ :glycerin: እና ጨው: ከጨመሩ በኃላ እግርን ከ 15-20 ደቂቃ ማቆየት::
• pumice stone ወይም foot scrubber በመጠቀም ቀስ አድርጎ መፈግፈግ::
• 1 ማንኪያ glycerin እና 1 ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ በመቀላቀል ተረከዝን መቀባት:: ከዚያ ካልስ አድርጎ መተኛት::
• ጥዋት በሙቅ ዉሃ በደንብ መታጠብ
• ይሄን በየቀኑ ተረከዝ ለስላሳ እስኪሆን መደጋገም::
2. የአትክልት ዘይት
• እግርን ከታጠቡ በኃላ በደንብ ማድረቅ::
• የአትክልት ዘይት ተረከዝን መቀባት:: ከዚያ ካልስ አድርጎ መተኛት::
• ጥዋት በሙቅ ዉሃ በደንብ መታጠብ
• ይሄን በየቀኑ ተረከዝ ለስላሳ እስኪሆን መደጋገም::
3. ሙዝ
• የሙዝ ልጣጭ በመጠቀም የተሰነጣጠቀውን ተረቀዝ መቀባት::
• ከአስር ደቂቃ በኃላ መታጠብ
4. ቫዝሊን እና የሎሚ ጭማቂ
• እግርን ከታጠቡ በኃላ በደንብ ማድረቅ::
• እግርን ለ 15-20 ደቂቃ መዘፍዘፍ::
• 1 ማንኪያቫዝሊን እና 1 ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ በመቀላቀል ተረከዝን መቀባት::
• ከዚያ ካልስ አድርጎ መተኛት:: (የሚጠቀሙት ካልስ cotten ቢሆን የመራጭ ነው )
• ጥዋት በሙቅ ዉሃ በደንብ መታጠብ
• ይሄን በየቀኑ ተረከዝ ለስላሳ እስኪሆን መደጋገም::
5. ማር
ማር ከማለስልስ በተጨማሪ ፅረ-ባክቴሪያ ጠቀሜታ አለው (ስለ ማር ጠቀሜታዎች ከዚህ በፊት ያካፈልነዉን መመልከት ይችላሉ)
• የተዎሰነ ማር ሞቅ ካለ ዉሃ ጋር መቀላቀል
• እግርን ለ 15-20 ደቂቃ መዘፍዘፍ::
• ቀስ አድርጎ መፈግፈግ::
ጤናዎ ይብዛልዎት!
ማጋራት ደግነት ነው

The post Health: የተሰነጣጠቀ ተረከዝን በቀላሉ ማስወገድ የሚቻልባቸው 5 መንገዶች appeared first on Zehabesha Amharic.

ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በሚኒሶታው ቅዱስ ዑራኤል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ

የ”ምርጫው”ውሎ ምን ይመስላል? –ከተለያዩ ከተሞች የተጠናቀረ

0
0

election
-‹‹እየተከተሉ እስከ ድምጽ መስጫው በመግባት ጫና ያደርጋሉ፡፡ ታዛቢ የሚባል ነገርም አላየሁም፡፡›› ሰሜን ወሎ ራያቆቦ

-‹‹በጣም ያሳዝናል፡፡ ራሳቸው ናቸው የሚመርጡት፡፡ ምልክት የሚያደርጉት እነሱው ናቸው፡፡ እንደ አጠቃላይ ፍትሃዊ አይደለም፡፡›› ደቡብ ወሎ ወግዲ ወረዳ
-ደብረማርቆስ ከተማ ላይ መንበረ ዘውዴ የሚባል የብአዴን ፀኃፊ ተዘዋዋሪ ታዛቢዎችን የሚጓጓበትን መኪና በማስቆም እንዳይታዘቡ አድርጓል፡፡ ታዛቢዎች ምዕርባ ጎጃም ፈረስ ቤት የሰማያዊ ፓርቲ ምልክት እንዳይኖር ተደርጓል፡፡

-‹‹ከንብ ውጭ ምልክት የለም፡፡ ከዛም ካርድ ይቀዳሉ፡፡ ሶስት ቀበሌዎች ተዘዋውሬ አይቻለሁ፡፡ መምህራን ስለሚጠይቁ ችግር እየደረሰባቸው ነው፡፡ ይህ ምርጫ ይበላል?›› ኦሮሚያ ክልል አደሬ ጮሌ ቀበሌ

-በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የሰማያዊ ፓርቲ ምልክት የለም እየተባሉ እንደተመለሱ መራጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

-‹‹ምክትል ሊቀመንበሩ ከምርጫ አስፈፃሚዎች ጋር በመሆን እያጠቆረ ለመራጩ ይሰጣል፡፡ የመራጩ ስራ ኮሮጆው ውስጥ ማስገባት ብቻ ነው፡፡ የሚሰማ ሰው ካለ አድርሱልን፡፡›› ምስራቅ ጎጃም ዞን ፈለገ ብርሃን ከተማ
-ደቡብ ጎንደር ዞን ወረታ ከተማ ላይ ከፍተኛ አፈና እና ወከባ እየተፈፀመ ነው
-በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ዕጩ የሆኑት አቶ መለሰ ተሸመ ትናንት ማታ በደህንነቶች ታፍነው የተወሰዱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የት እንዳሉ አልታወቀም፡፡ በተመሳሳይ በደቡብ ጎንደር ስቴ ወረዳ ሁለት የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰባቸው ታውቋል፡፡ ሁለቱም ታዛቢዎች እግርና እጃቸው ላይ ከፍተኛ ስብራት አጋጥሟቸው ሆስፒታል መግባታቸው ታውቋል፡፡
-ባህርዳር ላይ የድምፅ አሰጣጡ ሚስጥራዊ አይደለም ተባለ:..በአንድ ምርጫ ሳጥን ላይ አንድ ጊዜ የሚመርጡትም በካድሬዎች 1ለ5 የተጠረነፉት ነዋሪዎች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሎአል፡፡
-አዲስ አበባ ውስጥ የወረዳ 12ና 13 የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የሆነው አቶ ይድነቃቸው አዲስ መራጮች ጣት ላይ የሚቀባው ቀለም በሶፍትም እንደሚለቅ ማረጋገጡን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

-መታወቂያ የሌላቸው ነዋሪዎች እየመረጡ ነው

ወረዳ 20 ምርጫ ጣቢያ መታወቂያና የምርጫ ካርድ የሌላቸው ነዋሪዎች እየመረጡ ነው ተብሏል፡፡ ነዋሪዎች በዚህ አካባቢ ነዋሪ ከሆኑ ስድስት ወር ሆኗቸዋል በሚል ያለ ቀበሌ መታወቂያ እየመረጡ እንደሆነ ተገልጾአል፡፡ ንፋስ ስልክ ላፍቶ 5ና 8 ምርጫ ጣቢያ ላይ መታወቂያና የምርጫ ካርድ ያልያዙ ነዋሪዎች እየመረጡ እንደሆነ የአካባቢው የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የሆነት አቶ እስክንድር ጥላሁን ገልጾአል፡፡

-‹‹የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነኝ፡፡ ካለ ንብ ሌላ የሚመረጥ ምልክት አያሳዩንም፡፡ ሌላ ምልክት አሳዩን ስንል ከፈለክ ይህን ምረጥ ከዚህ ውጭ የሚመረጥ የለም ነው የሚሉን፡፡ ይህ ምኑ ምርጫ ይባላል?›› ከደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ (ነገረ- ኢትዮጵያ)

The post የ”ምርጫው” ውሎ ምን ይመስላል? – ከተለያዩ ከተሞች የተጠናቀረ appeared first on Zehabesha Amharic.

ካድሬዎች መራጮችን እያስገደዱ ነው * እራሳቸው መራጮቹ ይናገራሉ * የመድረክና የሰማያዊ ተወዳዳሪዎች ይናገራሉ (መደመጥ መጋለጥ ያለበት የኢህአዴግ የምርጫ ሴራ)

0
0

ካድሬዎች መራጮችን እያስገደዱ ነው * እራሳቸው መራጮቹ ይናገራሉ * የመድረክና የሰማያዊ ተወዳዳሪዎች ይናገራሉ (መደመጥ መጋለጥ ያለበት የኢህአዴግ የምርጫ ሴራ)
ቢቢኤን ግንቦት 16/2007 ሰበር ልዩ የምርጫ ዘገባ
(ያዳምጡ ያጋልጡ ለሌሎችም ያስተላልፉ)


election 2015 addis ababa

The post ካድሬዎች መራጮችን እያስገደዱ ነው * እራሳቸው መራጮቹ ይናገራሉ * የመድረክና የሰማያዊ ተወዳዳሪዎች ይናገራሉ (መደመጥ መጋለጥ ያለበት የኢህአዴግ የምርጫ ሴራ) appeared first on Zehabesha Amharic.

4 የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ታዛቢዎች ተደበደቡ * በክፍለሃገራት ኢሕአዴግ ራሱን በራሱ እየመረጠ ነው

0
0

election 2015 ethiopia
ሰማያዊ ፓርቲ የመደባቸው 4 የምርጫ ታዛቢዎች በገዢው ፓርቲ ተላላኪዎች መደብደባቸው ተዘገበ::
ምስራቅ ስቴ የተበደቡ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች
1. ታደለ ግዛው (ዳጉት ቀበሌ)
2. እሱ ያውቃል በላይ (ለዋዬ ቀበሌ)
3. ገብሬ ተፈራ (ደንጎልት ቀበሌ)
4. መልካሙ ነጋ (አበርጉት ቀበሌ)

በተጨማሪም ይስማው ወንድሙ የተባለ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢ በጥይት መሳቱን የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
*****
‹‹ጋሞ ጎፋ አርባ ምንጭ ከተማ ብርብር ምርጫ ክልል የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎችን አዋክበው እንዳይታዘቡ አድርገዋል፡፡ ካቢኔ ኮሮጆው ክፍል ድረስ ገብተው ኢህአዴግ ላይ ምልክት እንዲያደርግ ጫና አድርገዋል፡፡ በተለይ ሴቶችንና ሽማግሌዎችን በግዳጅ ነው ያስመረጧቸው፡፡ በአጠቃላይ በጋሞጎፋ የህዝብ ታዛቢዎች የተመረጡት በኢህአዴግ ነው፡፡ ይህን ቀድመንም ተናግረናል፡፡›› አቶ ወንድሙ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ

*****

‹‹ከ8 ሰዓት በኋላ ካርዱን ራሳቸው ነው እያጠፉ እያስገቡ ያሉት፡፡ ማንን ነው የምትመርጡ ሲባል የምንመርጠውን እኛ እናውቃለን ያሉት ተደብድበዋል፡፡ በተለይ አንዱ ይህን የሞተ መንግስት አልመርጥም ብሎ በመናገሩ ክፉኛ ተደብድቧል፡፡ ህዝብ በዱላ ሊያልቅ ነው፡፡›› ከስናን ወረዳ

*****
‹‹ትናንት ቤቴ ተከቦ አደረ፡፡ እንደምንም ምርጫ ጣቢያ ልመርጥ ስሄድ መምረጥ አትችልም ተብዬ ተመለስኩ፡፡ የቀበሌ አመራሮች ናቸው የሚመርጡት›› ቄስ ዋልተንጉስ አባተ የሰማያዊ ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ዕጩ/ከደጀን
*****
ገዳም ሰፈር ምርጫ ጣቢያ አንድ እና ምርጫ ጣቢያ ዘጠኝ ሰማያዊ ፓርቲ በዕጣ ምክንያት ዕጩ ባለማቅረቡ ምክንያት ሰማያዊ የለም የተባሉ 10 ወጣቶች ‹‹ሰማያዊ ከሌለማ ማንንም አንመርጥም›› ብለው ሲወጡ ታፍነው ታስረዋል፡፡
****
‹‹የኢህአዴግ አባላት ናቸው የምርጫ ወረቀቱን እየተቀበሉ ምልክት የሚያደርጉት፡፡ ታዛቢ የሚባሉት ራሳቸው የኢህአዴግ አባላት ናቸው፡፡›› ከዱር ቤቴ
*****
‹‹ባለስልጣናት ምርጫ ጣቢያው በር ላይ ቁጭ ብለው እጅ ይዘው እያስፈረሙ ነው፡፡ ከኢህአዴግ ውጭ እንመርጣለን ያሉ ወጣቶች ከአካበቢው ተባረዋል፡፡ ችግሩን ለሌሎች ይገልጻል የተባሉ ወጣቶች ስልካቸውን ተነጥቀናል፡፡ እኛ ከአካባቢው ርቀናል፡፡›› ስልጤ ዞን ላንፎሮ ወረዳ አርጢማ ቡላ ቀበሌ

(ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው)

The post 4 የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ታዛቢዎች ተደበደቡ * በክፍለሃገራት ኢሕአዴግ ራሱን በራሱ እየመረጠ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

በጉደር አምቦ ጸጥታው ደፍርሷል::ምርጫው ቆሟል::

0
0

Gondorበአቦ በባድዮ ጉደር አምቦ ምርጫ ጣቢያዎች ምርጫውን ከቁጥጥር ውጪ ያደረጉ ችግሮች የተፈጠሩ ሲሆን በየምርጫ ጣቢያዎቹ የኢሓዴቅ የቅስቀሳ ፖስተሮች ተለጥፈዋል::ይህን ተከትሎ በጉደር ከፍተኛ የሆነ የጸጥታ መደፍረስ ተፈጥሯል::በታዛቢዎች እና በምርጫ ባለስልጣናት መካከል ከፍተኛ አለመግባባቶች ተፈጥረው እስከ ድብድብ ተደርስል::‹‹ከንብ ውጭ ምልክት የለም፡፡ ከዛም ካርድ ይቀዳሉ፡፡ ሶስት ቀበሌዎች ተዘዋውሬ አይቻለሁ፡፡ መምህራን ስለሚጠይቁ ችግር እየደረሰባቸው ነው፡፡ ይህ ምርጫ ይበላል?›› ኦሮሚያ ክልል አደሬ ጮሌ ቀበሌ
‹‹ከ8 ሰዓት በኋላ ካርዱን ራሳቸው ነው እያጠፉ እያስገቡ ያሉት፡፡ ማንን ነው የምትመርጡ ሲባል የምንመርጠውን እኛ እናውቃለን ያሉት ተደብድበዋል፡፡ በተለይ አንዱ ይህን የሞተ መንግስት አልመርጥም ብሎ በመናገሩ ክፉኛ ተደብድቧል፡፡ ህዝብ በዱላ ሊያልቅ ነው፡፡›› ከስናን ወረዳ
ገዳም ሰፈር ምርጫ ጣቢያ 1 እና ምርጫ ጣቢያ 9 ሰማያዊ ፓርቲ በዕጣ ምክንያት ዕጩ ባለማቅረቡ ሰማያዊ የለም የተባሉ 10 ወጣቶች ‹‹ሰማያዊ ከሌለማ ማንንም አንመርጥም›› ብለው ሲወጡ ታፍነው ታስረዋል፡፡ ከደጀን ‹‹ትናንት ቤቴ ተከቦ አደረ፡፡ እንደምንም ምርጫ ጣቢያ ልመርጥ ስሄድ መምረጥ አትችልም ተብዬ ተመለስኩ፡፡ የቀበሌ አመሮች ናቸው የሚመርጡት›› ቄስ ዋልተንጉስ አባተ የሰማያዊ ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ዕጩ

The post በጉደር አምቦ ጸጥታው ደፍርሷል::ምርጫው ቆሟል:: appeared first on Zehabesha Amharic.


ህወሃትና ሌቦክራሲ በኢትዮጵያ ።ምርጫ ሳይሆን ግዳጅ –ከቢላል አበጋዝ፡ ዋሽግቶን ዲ፡ሲ

0
0

ሌቦክራሲ የሚለው የፖለቲካ ስርዓት ስያሜ የወያኔን ከ “ነጻ አውጭ ነት” ወደ ሌብነት ስርዓት መመስረት ያደረገውን ሽግግር አመልካች ነው። የሌቦች አገዛዝ ለማለት ነው። ሌቦክራሲ በስልጣን የባለጉ፤በሙስና የተዘፈቁ የሚመሩት ስርዓት ነው። በኢትዮጵያ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ከስልጣን ወጥቶ እንዲህ የህዝብ ንብረት በድፍረት የዘረፈበት ታሪክ የለም።እንዲህም አድርጎ ህዝብ ያፈነ ስርዓት አልነበረም። ይህ ምርጫ የሌቦች ስም ማደሻ ሰልፍ ማስተካከያ እንጂ ሌላ አይደም።የዚህ ስያሜ የሰጠነው ስርዓት እሰነብትበታለሁ የሚለው ትዕይንት ነው።የምናውቀው እባብ አዲስ ቆዳ የሚለብስበት።


police ethiopiaአፍ ተሸብቦ፤በግድ ምረጥ ብሎ፤ካልመረጥ ደግሞ “ይከተልሃል” ተብሎ ምን ምርጫ ይባላል? ግዳጅ እንጂ።የቀድሞ ታዛቢ ያፈረበት፤የተቸበት ምርጫ በኢትዮጵያ እየካሄድ ነው። ህወሃት መሩ መንግስት ያለሀፍረት ተመረጥኩ፤ህዝቡ እምነቱን ሰጠኝ ብሎ ለመደንፋት እየተመቻቸ ነው።

መጀመሪያ ዲሞክራሲን ምርጫ፤መመረጥ፤በየአራት፡ አምስት ዓመት፡ የሚመጣ፤ የሚሄድ አድርገን እንዳናይ በኛው ታሪክ እንኳን ቢያንስ የሁለት ዓሰርት ዓመታት ልምዳችን በቂ ትምህርት ሰጥቶናል።ከወያኔ ስርዓት ሌላ የነበረውን ትተን ማለት ነው።በምርጫ መሪዎች ማውጣት፤በምርጫው ጊዜ በሙሉ ፍላጎትና ስሜት መካፈልን አስመስክረናል።ኢትዮጵያውያን የዲሞክራሲ ስርዓት ናፍቆታቸውን የሁለት መቶ ዓመታት ልምድ አለን ከሚሉት ለምሳሌ አሜሪካ እንደማናንስ አሳይተናል።ኢትዮጵያዊው መራጭ ማለዳ የወጣ ጀምበር እስክትጠልቅ ድምጹን ለመስጠት ተራውን በመጠበቅ ጽናቱን አሳይቷል።

election 2015 addis ababaዲሞክራሲ የሚገነባ ስርዓት ነው።ሸፍጠኞችም የሚያንጹት አይደለም።ላገር ለህዝብ የሚሉ ከዝቡ ጋር ሆነው የሚያቆሙት ያገር መውደድ ፍሬ እንጂ ለወሬ ፍጆታ የሚቀርብም አይደለም።ዲሞክራሲ የባህል ለውጥ ማዕከል ነው።መከባበርን ወግ የሚያደርግ ነው።ለአገር እድገት መሰረት ነው።በህግ መገዛትን መሰረት ያደረገ ነው።የሰው አክብሮት፤ፈሪሃ እግዚአብሄርም አጥሩ ነው። እውን ጠባብ ብሄርተኞች፤ክፋትና ጥላቻ አስፋፊዎች ዲሞክራሲን ያበስራሉ ? ህወሃት መሩ መንግስትና ዲሞክራሲ ተቃራኒዎች ናቸው።

ዛሬ ኢትዮጵያ  የሚካሄደው ትእይንት የምርጫ አቸናፊው ቀድሞ የታወቀበት ነው።እግር ተወርች የታሰረ ተወዳዳሪ ጡንቻውን ሊያሳይ ሁሉን ከሚያደርግ የመንግስት ፓርቲ ጋር ይወዳደራል። ይህ መሆኑን በግልጥ እያወቁ በኢትዮጵያ ፍትሃዊ ምርጫ ይደረጋል ብለው ሲመሰክሩም ታዝበናል።ምርጫማ አፍሪካ ሁሉ ያደርገው የለ? በአሜሪካ መንግስት አስተያየት በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እያደገ፤እየጎለበተ ነው። ይህን ያለ አምባገነን ሁሉ የሚያካሂደው “ውድድር” መልካም ነው እንደማለት ነው። እንኳን አሁን ፋሺሽት ኢጣሊያም ስትወረን ማን ከማን ጋር እንደቆመ የሚሳየው ታሪክ የሩቅ ጊዜ አይደለም።ኢትዮጵያ በውጭ ወዳጅ የታለች ሆና አታውቅም።ወዳጅ አለኝ ብለው ካልተማመኑት አባቶቻችን ለመማር ጊዜ የሚወስድ አይደለም። ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት ወዲህ ያለው ታሪካችን ብቻ በቂ ትምህርት ይሰጣል።

ሰሞኑን በቡሩንዲ ሶስተኛ ጊዜ ለመወዳደር ህጉን የቀየረውን መሪ ህዝቡ ለመቋቋም ሲታገል ተመልክተናል። “አታረጋትም !” ብሎ ሆ ብሎ ወጥቷል።ይህ እምቢታ ዛሬ ተሳካ አልተሳካ የጊዜ ጉዳይ ነው።የቡሩንዲ ህዝብ መልክቱን አስተላልፏል።በሚካሄደው የህወሃት የምርጫ ቲያትርም  የኢትዮጵያ ህዝብ የሚለውን እየጠበቅን ነው።የጠላውን፤ያንገሸገሸው፤ያስመረረው የህወሃት መንግስት “ከነምርጫ ቲያትርህ ጥርግ በል” ሊለው ይችላል። ከዚህ ከውጭ ያለነው የምንታዘበው የኢትዮጵያ ህዝብ በትዕስግቱ፤እየደማ፤ እየታሰረ፤ሰብዕናው እንዲደፈር ቢደረግም ህወሃት መሩ መንግስትን ዛሬ አዳከሟል:: የውጭ ሀይሎችን የሙጥኝ እንዲል አድርጎታል። ህወሃት መሩን መንግስት በስርቆት ፋፍቶ መንቀሳቀስ የማይችል ዝሆን አድርጎ አዝሎታል።ገፍትሮ የሚጥለው ጊዜ መቃረቡን አመልካች ምክንያቶች ብዙ ናቸው።

ይህ ምርጫ ወትሮ ከሚደረጉት ልዩ የሚሆንበት ካጀቡት ሁኔታዎች አንጻር ሲታይ ነው።ወያኔ ሙሉበሙሉ የዲፕሎማሲ ክስረት እያናጋው አይደለም።የስለላ መዋቅሩ በትላልቅ ከተሞች አስልቷል።ተቃዋሚዎች በአድጎራ መቆም እየጀመሩ እንጂ ገና በህብረት በጥንካሬ አልቆሙም። ይህም ቢሆን ግን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ህዝባዊ አመጽን የሚጭር ሁኔታ ቢከሰት ቶሎ የሚቀየር፤ መንግስቱን የሚያርድ ሁኔታ አይፈጠርም ማለት አይደለም።የንጉሳዊ ስርዓትና ደርግን የሸኗቸው ምክንያቶች በጣም ጨምረው ዛሬ በአገራችን ይገኛሉ። የኑሮ ውድነቱ ለከት የለውም::ወጣቱም ሆነ ሌላው ተስፋ ቆርጧል። የህዝቡ እሮሮ አንገሽግሿቸው ወያኔ በሚያውቀው መንገድ ሊገጥሙት የቆረጡ ህዝቡን አይዞህ የሚሉት ሀይሎች መኖር ዋናው ነው። ይህን ህወሃት መሩ መንግስት አታንሱብኝ ብሏል።በውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ልጆች በቁጭት ለተግባር መነሳታቸው አንዱ ትልቅ ክስት ነው።በኢትዮጵያ ህዝቡ በሚችለው ሁሉ በከተማ በገጠር ይህን የክፋት ስርዓት እየተቋቋመ ነው።የሌቦክራሲው ስርዓትን የሚሰናብቱ እኒሁ ሶስት ረድፎች ናቸው።የህዝብ ትግል በከተማ በገጠር፤በውጭ ያለነው እርዳታ፤ህወሃት መሩን መንግስት በሀይል እያጫነቁት ያሉት ወንድሞቻችን ጽናት አይነተኛ ነው።ከነዚህ ሀይሎች ማንም  ደገፍኩህ ቢለው የህወሃትን መንግስት ሊያሰነብተው አይችልም።

በመጨረሻ ይህ ምርጫ ሲያልፍ ያው የተለምዶው ይቀጥላል እንጂ ወዲያው የሚቀየር ነገር ይኖራል ማለት ዛሬ አይቻል ይሆናል።አንድ ትልቅ ትምህርት ግን ትቶ ያልፋል። ህወሃት መሩ መንግስት በሰላም፤በምርጫ ይቀየራል የሚሉትን ግንዛቤአቸው ቀይሮ ያልፋል። ይህ ደግሞ ለወሳኙ ፍልሚያ ጠቃሚ ነው። ወያኔን አንበረካኪ ሁኔታ ሳይኖር የሰላም ሽግግር የማይሆን መሆኑን አስገንዝቦ ማለፉ ለዲሞክራሲ ትግላችን ያቀረበው ትምህርት ይሆናል።

ምርጫን ለህዝብ ቅንጣትም ደንታ የሌላቸው መንግስታትም ያደርጋሉ። ወጉ ምርጫ መካሄዱ ሳይሆን እንዴት ባለ ስርዓት ተካሄደ ነው።ምርጫ ሲደረግ ህዝብ የወደደውን ያሰነብታል።የጠላውን ያሰናብታል።ሁሉም በስልጣን ያለ “ተመርጨ ነው” ማለትን ይወዳል።ተመረጠ ተወደደን አመልካች በመሆኑ።ለዚህ ገና አልታደልንም።የተቀናጀ ትግል ይጠይቃል።

 

የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!ምርጫ ከመካፈል በፊት ይህ ይቀድማል።

ኢትዮጵያ በክብር፤በአንድነት፤ተረጋግታ በነጻነት ትኖራለች።የጃዙር ቅኝ ግዛት አትሆንም!!!

 

 

 

 

 

The post ህወሃትና ሌቦክራሲ በኢትዮጵያ ።ምርጫ ሳይሆን ግዳጅ – ከቢላል አበጋዝ፡ ዋሽግቶን ዲ፡ሲ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአ.አ. አቃቂ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የተቃጠለው የአረቄ ፋብሪካ የኩማ ደመቅሳና አዲሱ ለገሰ ንብረት መሆኑ ታወቀ

0
0

በአዲስ አበባ አቃቂ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የአረቄ ፋብሪካ የኢህአዴግ ባለስልጣኖች መሆኑን ያወቁ ሰዎች እንዳቃጠሉት ታወቀ።በአዲስ አበባ አቃቂ ክፍለ ከተማ የሚገኘው አረቄ ፋብሪካ ንብረትነቱ የከፍተኞች የኢህአዴግ አመራሮች የኩማ ደመቅሳና አዲሱ ለገሰ መሆኑን የተገነዘቡ ወገኖች ይህ ፋብሪካ በሃገርና በህዝብ ገንዘብ ተሰርቶ ለባለስልጣኖች ጥቅም ብቻ መዋል የለበትም በማለት ግንቦት 11/2007 ዓ.ም እንዳቃጠሉት የሚስጥሩ አዋቂ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለፁ።
fire
ፋብሪካው እየተቃጠለ በነበረበት ወቅት ሲመለከት የነበረው ነዋሪው ማህበረስብ፣ እሳቱን ለማጥፋት ምንም አይነት እገዛ ማድረግ ያለመቻሉን የተመለከቱት የስርዓቱ ካድሬዎች ወሮበላ ተከታዮቻቸውን በማሰባሰብ ነዋሪውን ህዝብ ማን አቃጠለው ከእናንተ አልፎ ሌላ የሚያውቅ የለም ተናገሩ እያሉ ላይና ታች ቢሉም እንኳን ነዋሪው ህዝብ ግን እኛ የምናወቀው የለንም የምታውቁት ካለ ደግሞ እናንተ ንገሩን በማለት ለጥያቄአቸው በጥያቄ መልክ በመመለስ ምንም አይነት መረጃ ከመስጠት እንደተቆጠበ ለማወቅ ተችሏል።

The post በአ.አ. አቃቂ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የተቃጠለው የአረቄ ፋብሪካ የኩማ ደመቅሳና አዲሱ ለገሰ ንብረት መሆኑ ታወቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

በእሑዱ ምርጫ አንዳንድ ነጣጥቦች – ዶ/ር ኀይሌ ላሬቦ

0
0

election 2015
ኀይሌ ላሬቦ ዶ/ር

ከፊታችን ባለው እሁድ በኢትዮጵያ ውስጥ ምርጫ ይካሄዳል። በዚህ ቀን በሕገ መንግሥቱ መሠረት ዐምስት መቶ ዐምሳሹማምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለፈደረሽኑ ሸንጎ ቤት ደግሞ አንድ መቶ ዐሥራ ሰባት አባላት ከሃያ ሁለቱ አነሳ ብሔረ-ስቦች በነፍስ ወከፍ አንዳንድ፣ የቀሩት በሌሎች አንኳል ክልሎች በሚሰጠው ድምፅ ይመረጣሉ። ተመራጮቹ ዐምስት ዓመት ካገለገሉ በኋላ የአላፍነታቸው ጊዜ ያበቃና ወይ እንደገና በዕጩነት ላዲስ ምርጫ ይወዳደራሉ፤ ካልፈለጉ ደግሞ ባሰኛቸው የሥራ ዘርፍ ይሰማራሉ። የእሁዱ ምርጫ ገዢው መንግሥት ደምብ ሠርቶ ሥነ-ሥርዐቱን አደላድሎ ከጀመረበት ወቅት አምስተኛ መሆኑ ነው። የመጀመርያው በ፲፱፻፹፯ ዓ.ም. ነበር። ከዚያ በኋላዐምስት ዐምስት ዓመቱን እየቈጠረ በ፲፱፻፺፪፣ ቀጥሎም በ፲፱፻፺፯ና በ፳፻፪ ዓ.ም. ተካሂዷል። —[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—-

The post በእሑዱ ምርጫ አንዳንድ ነጣጥቦች – ዶ/ር ኀይሌ ላሬቦ appeared first on Zehabesha Amharic.

48 የምርጫ ታዛቢዎች በቁም እስር ላይ ናቸው * 26 ታዛቢዎች ታስረው የታዛቢነት መታወቂያቸውን መለሱ

0
0

election 2015 ethiopia addisዛሬ 12 ሰዓት የጀመረው ምርጫ በወከባ ተጀምሯል፡፡ ኢህአዴግ ካድሬዎች መራጮቹን በመጠርነፍ እንዲመርጡ እያስገደዱ እንደሆነ አዲስ አበባ ውስጥ ከምርጫ ጣቢያ 03 የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በዚሁ ምርጫ ጣቢያ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች እንዳይገቡ ታግደው በማርፈዳቸው ወረቀት ሳይቆጠር ምርጫው ተጀምሯል፡፡ በተመሳሳይ በወረዳ 15 ምርጫ ጣቢያ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች ‹‹አትገቡም!›› ተብለው ወከባ እንደደረሰባቸው የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የሆኑት አቶ ተገኔ ጌታነህ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ወረዳ 6 ምርጫ ጣቢያ 20 መራጮች ጣት ላይ የሚደረገው መርገጫ ቀለም የሚለቅ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች ቀለሙ የሚለቅ መሆኑን ገልጸው ቃለ ጉባኤ እንዲያዝላቸው ቢጠይቁም የምርጫ አስፈጻሚዎቹ ፈቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች በገዥው ፓርቲ ካድሬዎችና ደህንነቶች ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝና አንዳንዶቹ በወከባው ምክንያት በቦታው አለመገኘታቸውን ዕጩዎቹ ገልጸውልናል፡፡

ሲዳማ ቦርቻ ወረዳ ደግሞ 26 የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች ታስረው የታዛቢነት መታወቂያቸውን እየመለሱ ሲለቀቁ፣ ሶስቱ መታወቂያን አልመልስም በማለታቸው አሁንም እንደታሰሩ ናቸው፡፡ በጉራጌ ዞን የም ልዩ ወረዳ ደግሞ 48 የሰማያዊ ታዛቢዎች በቁም እስር ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡

The post 48 የምርጫ ታዛቢዎች በቁም እስር ላይ ናቸው * 26 ታዛቢዎች ታስረው የታዛቢነት መታወቂያቸውን መለሱ appeared first on Zehabesha Amharic.

የወያኔው ሚዲያ ኢሕአዴግ አ.አን እና ጎንደርን 100% አሸነፈ ሲል ዘገበ * ዶ/ር መራራና ዶ/ር በየነ ተሸነፉም አለ የወያኔው አይጋ

0
0
የማያፍረው ወያኔ ይህ ሁሉ ሕዝብ ዶ/ር መረራ ጉዲናን ደግፎ አደባባይ ወጥቶላቸው ዶ/ር መረራ ተሸነፉ ሲል ከምርጫ ቦርድ በፊት በአይጋ ፎረም በኩል ይፋ አድርጓል::

የማያፍረው ወያኔ ይህ ሁሉ ሕዝብ ዶ/ር መረራ ጉዲናን ደግፎ አደባባይ ወጥቶላቸው ዶ/ር መረራ ተሸነፉ ሲል ከምርጫ ቦርድ በፊት በአይጋ ፎረም በኩል ይፋ አድርጓል::

የወያኔው ምርኩዝ ምርጫ ቦርድ የምርጫውን ውጤት ይፋ ሳያደርግ አይጋ ፎረም የተሰኘው አፍቃሪ ወያኔ ድህረ ገጽ፣ ወያኔ በአዲስ አበባ በአዲስ አበባ፣ በጎንደር ዞኖች 100% እንዳሸነፈ ገለጸ። ቁጥሩ እጅግ በጣም በርካታ ነዋሪ ድጋፉን ለመድረክ በሰጠበት፣ ዶር መራራ ጉዲና በተወዳደሩበት በአምቦ/ጉደር፣ እንዲሁም ዶ/ር በየነ በተወዳደሩበት ሃዲያ ዞን ኢሕአዴግ እንዳሸነፈም አይጋ ጠቅሷል። አዲስ አበባ፣ ሙሉ ጎንደር ዞኖችን 100% ወይኔ እንዳሸነፈ ነው የተገለጸው።

አይጋ ከህወሃት ጋር በቅኝት የሚሰራ ድህረ ገጽ እንደመሆኑ፣ ወያኔ ይፋ ሊያደርገው የሚችለው ዉጤት ምን ሊሆን እንደሚችል የሚያሳይ እንደሆነ አንድንዶች ይናገራሉ።
ሆኖም የሕዝቡን ስሜት አስቀድሞ ለመለካት ሆን ተብሎ እንደ ታክቲክ የተደረገ ዘገባ ሊሆንም ይችላል።
አይጋ የሚከተለውን ነው የዘገበው
“Although some expected Dr Merara and Dr Beyene to reclaim their lost seat in parliament preliminary count suggests EPRDF has won both seats and 100% sweep in the Capital City as well as other regions! The only region opposition has a chance to win some seats is in Amhara Kilil but that is not certain either so far Gondor is all gone to EPRDF”
ከዚህ ቀጥሎ ያለው በአምቦ/ጉደር መድረክን ደግፎ የተሰበሰበው ህዝብ ነው። እንግዲህ ይሄ ሁሉ ህዝብ እያለ ነው ወያኔ አሸነፍኩ የሚለው።

The post የወያኔው ሚዲያ ኢሕአዴግ አ.አን እና ጎንደርን 100% አሸነፈ ሲል ዘገበ * ዶ/ር መራራና ዶ/ር በየነ ተሸነፉም አለ የወያኔው አይጋ appeared first on Zehabesha Amharic.

Hiber Radio: ዶ/ር አክሎግ ቢራራ እና የአረናው አምዶም ገ/ሥላሴ ልዩ ቃለምልልስ ስለምርጫው * አገዛዙ የሕዝቡን ድምጽ ወደጎን አድርጎ ለራሱ የሰጠውን የምርጫ ውጤት ይፋ ለማድረግ ተዘጋጅቷል * በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ተማሪዎች የሕዝብ ድምፅ እንዲከበር መጠየቅ ጀምረዋል * በአዲስ አበባ የ17 ዓመቷን ወጣት ሃና ሌላንጎን የደፈሩት ከ17 ዓመት እስከ እድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸውና ሌሎችም

0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ የግንቦት 16 ቀን 2007 ፕሮግራም

ዶ/ር አክሎግ ቢራራ የአገር ቤቱን የይስሙላ ምርጫ አስመልክቶ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

የአረና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ወጣት አምዶም ገ/ስላሴ (ከመቀሌ ምርጫውን አስመልቶ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ማብራሪያ የተወሰደ )

በየመን ያሉ ኢትዮጵያውያን አጣብቂኝ እና የተባበሩት ሀይሎች የአየር ድብደባ ያደረሱት ጉዳቶች(ልዩ ዘገባ)

የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ በቬጋስ(ከበዓሉ አዘጋጆች አንዱ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ)

አስተያየት በአገር ቤቱ ውጤቱ አስቀድሞ የታወቀ ምርጫ ላይ

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የተቃዋሚ የምርጫ ታዛቢዎች ጥቃት ሲፈፀምባቸው ዋለ

አገዛዙ የሕዝቡን ድምጽ ወደጎን አድርጎ ለራሱ የሰጠውን የምርጫ ውጤት ይፋ ለማድረግ ተዘጋጅቷል

ሕዝቡ በተዘረፈው ድምጹ ጉዳይ ተቃውሞ እንዳያቀርብ በሚል የሰብዓዊ ጥሰቱ ቀጥሏል

በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ተማሪዎች የሕዝብ ድምፅ እንዲከበር መጠየቅ ጀምረዋል

በአዲስ አበባ የ17 ዓመቷን ወጣት ሃና ሌላንጎን የደፈሩት ከ17 ዓመት እስከ እድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው

ኬኒያዊው ጠበቃ ፕሬዝዳንት ኦባማ ልጃቸውን ከዳሩልኝ ለጥሎሽ 50 ከብቶች 70 በጎችና 30 ፍየሎች እሰጣለሁ ማለቱ ተሰማ

የኤርትራ መንግስት ለአገሪቱ ወጣቶች ስድትና ሞት የሰብዓዊ ተሟጋች ድርጅቶች ጭምር ይጠየቃሉ አለ

ኢትዮጵያና ኤርትራ በኮንፊዴሬሽን እንዲዋሃዱ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ጠየቁ

የሔጉ ውሳኔ በአዲስ መልክ እንዲቀየር አንድ ታማኝ የተቃዋሚ መሪ ገልፀዋል

ሁቨር በኔቫዳ ስራ እንዲጀምር ህጉ ፀደቀ

ስራ ከመጀመሩ በፊት ለተቆጣጣሪው ኩባንያ ማመልከት አለበት ተብሏል

የሚሉና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

The post Hiber Radio: ዶ/ር አክሎግ ቢራራ እና የአረናው አምዶም ገ/ሥላሴ ልዩ ቃለምልልስ ስለምርጫው * አገዛዙ የሕዝቡን ድምጽ ወደጎን አድርጎ ለራሱ የሰጠውን የምርጫ ውጤት ይፋ ለማድረግ ተዘጋጅቷል * በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ተማሪዎች የሕዝብ ድምፅ እንዲከበር መጠየቅ ጀምረዋል * በአዲስ አበባ የ17 ዓመቷን ወጣት ሃና ሌላንጎን የደፈሩት ከ17 ዓመት እስከ እድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸውና ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.

የሻዕቢያ “የተሀድሶ” ስትራተጂ አካሄዱና አንደምታው

0
0

issayas afewerki
አክሊሉ ወንድአፈረው
ሜይ 22፣ 2015

በአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራው አስመራ ላይ የተሰየመው የሻዕቢያ መንግሥት ለ 23 ዓመታት የተከተለውን አካሄድ እንዳላዋጣው በመገንዘብ ይመስላል በተወሰነ ደረጃ ለየት ያለ ገጽታን ለማሳየት እና ራሱን አለሳልሶና የሰላም አባወራ ሆኖ ለመቅረብ በመሯሯጥ ላይ ይገኛል። ይህ ምን መልክ ይዞ ነው የሚራመደው? ለሀገራችን ኢትዮጵያስ ምን እንደምታ አለው? የሚለው የዚህ ጽሑፍ ዋና Aላማው ነው።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

The post የሻዕቢያ “የተሀድሶ” ስትራተጂ አካሄዱና አንደምታው appeared first on Zehabesha Amharic.


ለ50 ዓመታት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ትልቅ ሥፍራ የነበራቸው አርቲስት ሻምበል መኮንን መርሻ አረፉ

0
0


(ዘ-ሐበሻ) በዘፋኝነት; በሙዚቃ አቀናባሪነትና በሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋችነት የሚታወቁት ታዋቂው አርቲስት ሻምበል መኮንን መርሻ አረፉ::

በፖሊስ ኦርኬስትራ ውስጥ የትራንፔት ሙዚቃ ተጫዋች የነበሩትና “አደሉላ (የዘማች እናት)” በሚለው ታዋቂ ዘፈናቸው የሚታወቁት ሻምበል ወደ ሙዚቃው ዓለም ከመግባታቸው በፊት የወርቅ ሰራተኛ ነበሩ:: ሻምበሉ በአንድ ወቅት ለዘ-ሐበሻ ዘጋቢ እንደገለጹት ወርቅ ሰሪነት የተቀጠሩት በወቅቱ 15 ብር ነበር::

ድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ዛሬ የተለዩት እኚሁ ባለጥምር የሙዚቃ ክህሎት ባለሙያ ሻምበል መኮንን ለሂሩት በቀለና ለተለያዩ የሙዚቃ ሰዎች ሙዚቃ አቀናብረዋል:: ለ50 ዓመታት በሙዚቃ ዓለም ቆይታቸውም በርከት ያሉ ሥራዎችን ሰርተዋል:: ሃመልማል አባተ ከሃረር መጥታ በአዲስ አበባ የሙዚቃ ሥራ እንድትሰራ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ትልቅ ሲሆን የቴዲ አፍሮ አባት አቶ ካሳሁን ገርማሞ የቴዲ አፍሮን እናት ባገባ ጊዜ ሚዜም ነበሩ::

የእኚሁ ታዋቂ አርቲስት የቀብር ስነስርዓት በኖሩበት ኮልፌ አካባቢ በሚገኝ ቤተክርስቲያን ነገ ይፈጸማል ተብሎ ይጠበቃል::

ቭዲዮውን ይመልከቱ::

shambel Mekonen Mersha

The post ለ50 ዓመታት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ትልቅ ሥፍራ የነበራቸው አርቲስት ሻምበል መኮንን መርሻ አረፉ appeared first on Zehabesha Amharic.

በኦሮሚያ ሁለት የምርጫ ታዛቢዎች ተገደሉ * “ምርጫ ሳይሆን ዘረፋ ነው የተካሄደው”–ዶ/ር መረራ ጉዲና

0
0

Gudina
(ዘ-ሐበሻ) ትናንት እሁድ የተካሄደው ምርጫ በመሳሪያ የተደገፈ ዘረፋ እንጂ ምርጫ አልነበረም ሲሉ ዶ/ር መረራ ጉዲና አስታወቁ:: የመድረክ የወቅቱ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስም የምርጫውን ሂደት አወገዙ::

ምርጫው በፌደራል ፖሊስ እና በልዩ ሃይሎች የሕዝብ ድምጽ እንዲሰረቅ መድረጉን ያጋለጡት ዶ/ር መረራ ጉዲና በአምቦ አካባቢ የተቃዋሚ ፓርቲ 2 የምርጫ ታዛቢዎች መገደላቸውንም ለኢሳት ገልጸዋል:: ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስም በደቡብ ክልል በተለያዩ ቦታዎች በመንግስት ታጣቂዎች የምርጫ ኮሮጆ ከመሰረቁም በላይ በርካታ የምርጫ ታዛቢዎች መደብደባቸውና ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው አስታውቀዋል::

በአሪሲ ኮፈሌ እንዲሁም አምቦ ሚደጋን ቶላ ላይ ሁለት የምርጫ ታዛቢዎች መገደላቸውንና በሌሎች ላይም ጥቃት መፈጸሙን ዶ/ር መረራ ገልጸዋል:: ዶ/ር መረራ ጉዲና ሕዝቡ በሰላማዊ መንገድ የተሰረቀውን ድምጹን ለማስመለስ እንዲታገልም ጥሪያቸውን አቅርበዋል::

The post በኦሮሚያ ሁለት የምርጫ ታዛቢዎች ተገደሉ * “ምርጫ ሳይሆን ዘረፋ ነው የተካሄደው” – ዶ/ር መረራ ጉዲና appeared first on Zehabesha Amharic.

ምርጫ 2007: የአለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሗን ዘገባና መሬት ላይ ያለዉ እዉነታ (ሊያደምጡት የሚገባ የሳዲቅ አህመድ ትንታኔ)

የቴዲ አፍሮ ባለቤት አምለሰት ሙጩ የሆስፒታሎች አምባሳደር ልትሆን ነው

0
0

teddy afro and ameslet
ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሆስፒታሎችን ንፁህና ፅዱ /Clean and save Hospital- CASH/ በማድረግ
ለታካሚዎች፤ለጤና ባለሙያዎችና ለተገልጋዩ ህብረተሰብ የተሻለ የጤና አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል የጤና ተቋማትን ምቹ የማድረግ ዘመቻ የጀመረ ሲሆን ለዚሁ ዘመቻ በሙያዋ ቅስቀሳ እንድታካሂድ የዝነኛው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ባለቢኤት አርቲስትና ሞዴል አምለሰት ሙጩን አምባሳደር አድርጎ መርጧል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ይህንን ትግበራ ከጀመረባቸው ሆስፒታሎች መሀከል አንዱ የሆነው በራስ ደስታ ሆስፒታል ሲሆን የአዲስ አባባ ጤና ቢሮ ከአብት አሶስየት ፕሮጀክት Abt project Associate-HSFR/HFG project ጋር በጥምረት የሚያካሂደው ዘመቻ ሆስፒታሎችን ንፅህና ፅዱ በማድረግ ምቹ አካባቢን የመፍጠር ዓላማ አለው፡፡ አዳዲስና ዘመናዊ ሆስፒታሎች እስከሚገነቡ ድረስ ያሉትን ሆስፒታሎች ለአገልግሎት ንፁህና ምቹ በማድረግ የተሻለ የጤና አገልግሎት ለህብረተሰቡ የመስጠት እቅድም ተይዟል፡፡
ባለፈው ግንቦት 9 ቀን 2007 ዓ.ም የራስ ደስታ ሆስፒታል ማኔጅመንት አባላትና የአብት አሶስየት ፕሮጀክት ሃላፊዎች እንዲሁም አርቲስት አምለሰት ሙጩ በተገኘችበት የጉብኝት ፕሮግራም ተካሂዷል፡ ፡ የራስ ደስታ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ምትኩ ጨመዳ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር አርቲስት አምለሰት ሙጩ በራስ ደስታ ሆስፒታል የተጀመረውን የህክምና አካባቢን ንፁህና ምቹ የማደርግ ዘመቻ ላይ ለመሳተፍና በአምባሳደርነት ሀላፊነቷን ለመወጣት ፍቃደኛ መሆኗን አድንቀው ሆስፒታሉ ንፅህና ምቹ መሆኑ ሆስፒታሉ የእናቶችንና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ እያደረገ ላለው እንቅስቃሴ አጋዥ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ameleset
የአብት አሶስየት ፕሮጀክት ዋና ዳይሬክትር አቶ ሉዑልሰገድ አገዘ እንደተናገሩት ግንቦት 23 ቀን 2007 ዓ.ም የራስ ደስታ ዳምጠው ቤተሰቦች፤የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና የአዲስ አበባ የጤና ቢሮ የስራ ሀላፊዎች፤ የራስ ደስታ ሆስፒታል ማኔጅመንትና የአስተዳደር ሰራተኞች በሚገኙበት ሥነ ሥርዓት ላይ አምለሰት አምባሳደር ሆና እንድትሰራ ሃላፊነቱ እንደሚሰጣትና ይኸውም ለህዝቡ በይፋ እንደሚገለፅ ተናግረዋል፡፡ አርቲስትና ሞዴል አምለሰት ሙጩ በበኩሏ ይህንን ሀላሀፊነት ከፍ ባለ አክብሮት እንደምትቀበል ገልፃ ከዚህ ቀደምም በተለያዩ አጋጣሚዎች ወደየሆስፒታሎች ስትንቀሳቀስ ከንፅህና ጋር ተያያዞ ጉድለቶችን በማየቷ በዚሁ ዘመቻ ላይ የተቻላትን ያህል እንደምትሰራ ተናግራለች፡፡

አምለሰት ቀደም ሲል በአካባቢ ጥበቃ ላይ የራሷን እንቅስቃሴ ማድረጓና በውበት ኢንዱስትሪ ውስጥ ባላት ተሳትፎ ሳቢያ ለዚህ ሀላፊነት መመረጧ ታውቋል፡፡

ምንጭ – ቁምነገር መጽሔት ከአዲስ አበባ

The post የቴዲ አፍሮ ባለቤት አምለሰት ሙጩ የሆስፒታሎች አምባሳደር ልትሆን ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

(አሁንም ስለአነጋጋሪው የጥላሁን መጽሐፍ) ሁለት ማንነት በአንድ ራስ –ጥላሁን ገሠሠ የሙዚቃው ንጉሥ

0
0

tilahun

ርዕስ፡ ጥላሁን ገሠሠ የሕይወቱ ታሪክ እና ምሥጢር
ጸሐፊ፡ ዘከሪያ መሐመድ

ሲሳይ ጫንያለው እንዳነበበው


የመጀመሪያ ስሜት እንደመንደርደሪያ “እንዲህ ካለ መራራ የሕይወት ገጽ ውስጥ ኮኮብ ሆኖ መፈጠር ፤ ንጉሥ ተብሎ መዘከር እንደምን ይቻላል?” የሚለው ጥያቄ አዕምሮዬ ውስጥ ብቅ ያለው የጥላሁን ገሠሠን የሕይወት ታሪክና ምሥጢር የሚተርከውን የዘከሪያ መሐመድ መጽሐፍ ካነበብኩ በኋላ ነው፡፡ ከጨቅላ ዕድሜው አንስቶ የሐዘን አንቀልባ እንዳዘለ ሃምሳ አመታትን በኢትዮጵያ ኪነት ውስጥ በክብር ለኖረ ሰው 69 ዓመት ትንሽ ዕድሜ ነው፡፡ ኅልፈተ ሕይወቱ በሚዲያ ሲነገር አገር በዕንባ ታጥቧል፡፡ ያኔ እኔም እርሜን አውጥቻለሁ፡፡ ከስድስት ዓመታት በኋላ የጥላሁንን ሁለት የማንነት ገጾች በፍካሬ ለማሳየት የተጋውን የዘከሪያን መጽሀፍ ሳነብ ደግሞ በስኬቱ ተገርሜ በስቃዩ ታምሜያለሁ፡፡

ጋሽ ጥላሁን የምር አሳዝኖኛል፡፡

በገጾቹ ምን ይዟል?

“ጥላሁን ገሠሠ የሕይወቱ ታሪክና ምስጢር” በዘከሪያ መሐመድ ተጽፎ ለንባብ
የበቃ አነጋጋሪ የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ ነው፡
፡ መጽሐፉ አቶ ፈይሳ ኃይሌ ሀሠና የተባሉ የጥላሁን ቅርብ የስጋ ዘመድ ከ1934 ጀምሮ ያሰፈሩትን የቤተሰብ ማስታወሻ ቀዳሚ የመረጃ ምንጩ አድርጓል፡፡ ጸሐፊው የትውልድ ሥፍራው ሶየማ ድረስ ተጉዞ የባለታሪኩን ዘመድ አዝማዶች ፣ አብሮ አደጎች እና ጎረቤቶች ቃለ መጠይቅ በማድረግ መረጃዎቹን አጠናክሯል፡፡ በተጨማሪም የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያው እና የህትመት ሚዲያው ስለ ጋሽ ጥላሁን የዘገቡትን ፣ በሙዚቃው ንጉሥ ሕይወት ውስጥ የነበሩ ሌሎች ግለሰቦች የነገሩትን በመተንተንና በመፈከር በአራት ክፍሎች እና በሃያ ዘጠኝ ምዕራፎች የጥላሁንን ሕይወት ከልደቱ እስከ ኅልፈቱ ተርኳል፡፡

በአምስትምዕራፎችየተደራጀውና“መሠረት” የሚል ርዕስ የተሰጠው የመጀመሪያው ክፍል ከአቶ ፈይሳ ኃይሌ ሀሠና ዳራ ተነስቶ የጥላሁንን ልደት እና ቤተሰባዊ መሠረት የሚቃኝ ነው፡፡ ሁለተኛው ክፍል የጥላሁን የሙዚቃ አጀማመር ከኢትዮጵያ የዘመናዊ ሙዚቃ ታሪክ ጋር በማስተሳሰር ሙያዊ እና ግለሰባዊ ሕይወቱ ተሰናስለው በአስራ ስድስት ምዕራፎች ቀርበውበታል፡፡ ሰፋ ያለውን ገጽ የሸፈነውም “የሕይወቱ ሕይወት” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይኸው ክፍል ነው፡ ፡ ክፍል ሶስት በጥላሁን የመጨረሻ አልበም መጠሪያ የተሰየመ ነው ፤ አንዳንድ ነገሮች፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ጥላሁን ከግል ሕይወቱ ጋር የሚገናኙ ዜማዎች ፣ ስለሌሎች ድምጻውያን ያደነቀባቸውን ስሜቶች ፣ ስለድምጽ አጠቃቀሙና ብቃቱ ፣ ከመደበኛ መድረክ ውጪ ስለተጫወተባቸው አጋጣሚዎችና ስለግለሰባዊ ባህርይው የሚተርኩ አጫጭር ሁነቶችን የያዙ ሦስት ምዕራፎችን አካቷል፡፡ ክፍል አራት የሚተርከው የልጅነት ሕመሙ የፈጠረው ስነ-ልቦናዊ ቀውስ ግዘፍ ነስቶ የሚታይበትን የፍቅር ሕይወቱን ነው፡፡ ከመጀመሪያ የልጅነት ባለቤቱ ወ/ሮ ፈለቀች ማሞ አንስቶ በመጨረሻው የሕይወቱ ምዕራፍ ላይ አብራው እስከነበረችው ወ/ሮ ሮማን በዙ ድረስ አስራ ስድስት ልጆች ያፈራባቸውን ሰባት የትዳር ሕይወቶች ይቃኛል (ከፈለቀች ማሞ እና ከብርሃኔ ዘለቀ ብቻ ነው ጥላሁን ልጅ ያላገኘው)፡፡

tilahun Gesese
ደራሲው የጥላሁንን ሕይወት እንዴት ቀረበው የሕይወት ታሪክ እጅግ ጥንታዊ መሠረት አላቸው ከሚባሉ የስነጽሁፍ ዘሮች አንዱ ነው፡፡ በይዘቱ ኢ-ልቦለዳዊ ይሁን እንጂ የባለታሪኩን ሕይወት በመልሶ ፈጠራ በውብ ቃላት እየሳለ ከትክክለኛው የታሪክ እውነት ጋር በማይቃረን መልኩ አቀራረቡን ልቦለዳዊ ሊያደርግ ነጻነት አለው፡፡ ይህ ግን በባለታሪኩ የሕይወት ታሪክ አካሄድ እና በደራሲው ምርጫ የሚወሰን ነው፡ ፡ በዘመናዊ የሕይወት ታሪክ አጻጻፍ ውስጥ ደራሲው በአቀራረቡ ስነልቦናዊ ፣ ምግባራዊ እና ስነውበታዊ አካሄዶችን ሊያጤን እንደሚገባ ፖልሙራይን የመሰሉ የዘርፉ ምሁራን ያስረዳሉ፡ ፡ ባለታሪኩን የተመለከቱ ታሪካዊ መረጃዎችን በቅደም ተከተል መደርደር ብቻ የሁነቶችን ቢጋር እንጂ የግለሰቡን ሕይወት አያሳዩም፡፡ ስለዚህ ደራሲው አስፈላጊ የሚላቸውን መረጃዎች ከሰበሰበ በኋላ ጥልቅ የሆነ ስነልቦናዊ ፍተሻ በማድረግ መረጃዎቹን እያዛመደ በመተንተን እና በመተርጎም የባለታሪኩን ሰብዕና መገንባት ይጠበቅበታል፡፡
በዚህ ሂደት ውስጥ ዘመናዊ የሕይወት ታሪክ ጸሐፊ የሚጋፈጠው ምግባራዊ ፈተና አለ፡፡ የተለያዩ የስነልቦና ንድፈ ሀሳቦችን ተግባራዊ አድርጎ በትርጓሜ ያገኘውን እውነት ሁሉ እንዲታተም ያደርግ ይሆን? ምን ያህሉን አውጥቶስ ምን ያህሉን ይተወው? እነዚህ ጥያቄዎች ከ18ኛው ክፍለ ዘመን አንስቶ በሕይወት ታሪክ ጥናት ውስጥ ሲነሱ የኖሩ ምላሽ አልባ ጥያቄዎች ይመስላሉ፡፡

ሌላው የሰበሰባቸውን ፣ የተነተናቸውንና የተረጎማቸውን ጥሬ መረጃዎች ሕይወት አከል እንዲሆኑ ምስል የመፍጠር እና ቅርጽ የማበጀቱ ጉዳይ ነው፡፡ እዚህ ጋር ሽግግር አለ በቅደም ተከተል የተሰደሩ የታሪክ እውነታዎችን የባለታሪኩን ሰብዕና ወደሚያሳይ ውብ ትረካ ማሸጋገር ያስፈልጋል፡፡ ጥሬ ሐቆቹን ልቦለዳዊ አድርጎ ሲያቀርብ ከእውነታው ሊጋጭ ይችላል፡፡ ልቦለዳዊ አቀራረቡን ትቶ ጥሬ ሐቆቹን ቢደረድር የሕይወት ታሪኩ ኪነት አልባ ይሆናል፡፡ አንድ የሕይወት ታሪክ ደራሲ የሚመዘነውም በዋናነት ለእነዚህ ጥያቄዎች በሚሰጠው የተመቻመቸ ምላሽ (compromised response) ነው፡፡
Tilahun Legend
ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋዜጠኛ የነበረው ዘከሪያ መሐመድ እንደ ደራስያን ማህበሩ የደቦ ድርሰት ገራገር አቀራረብ ይዞ አልመጣም፡ ፡ ያገኛቸውን መረጃዎች በሙሉ በቅደም ተከተል ሲሰድር ታሪካዊ እና ስነልቦናዊ አንድነታቸውን እየፈከረ ነው፡፡ ልቦለዳዊ ውበቱ እና ታሪካዊ እውነቱም እርስ በእርስ እንዲደጋገፉ እንጂ አንዱ ከአንዱ ጋር እንዲቃረኑ አላደረገም፡፡ አልያም እንደ ደራስያን ማህበሩ ድርሰት የተነገረውን ብቻ የሚተፋ በቀቀን አልሆነም ፤ በፍጹም !

“ጥላሁን ገሠሠ የሕይወቱ ታሪክ እና ምሥጢር” በዋናነት ሦስት የማህበራዊ ሳይንስ ዲሲፕሊኖች ( ሙዚቃ ፣ ስነልቦና እና ታሪክ) እንደየአስፈላጊነቱ ተዛምደው የቀረቡበት መጽሐፍ ነው፡፡ የዚህ ዳሰሳ አቅራቢ ይበልጡን የተሳበው ግን በስነልቦናዊ ፍከራው ላይ ነው፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ስነልቦናዊ ፍካሬ ያላቸው የሕይወት ታሪኮች ተቀባይነታቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ ምክንያቱም ባለታሪኩ አውቆም ይሁን ሳያውቅ የደበቃቸውን ስውር የታሪክ ገጾች የማሳየት አቅም አላቸው፡፡ በዚህ ረገድ የሊዎናርዶ ዳቬንቺን እና የልጅነት ትዝታውን በፍካሬ ልቦና (psycho analysis) ያሳየው የሲግመን ፍሩድ መጽሐፍ ፈር ቀዳጅነቱ ይጠቀሳል፡፡ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ላይ የነበረውን የአዶልፍ ሂትለርን ሰብዕና የሚተነተነው የዶ/ር ሙራይ መጽሐፍም ከሚጠቀሱ ስነልቦናዊ የሕይወት ታሪኮች አንዱ ነው፡፡

የእኛው ዘከሪያ መሐመድ ከእነዚህ መጽሐፍት ጋር የቅርብ ዝምድና ያለው ይመስለኛል፡፡ የአቶ ፈይሳ ኃይሌ ሀሠና የቤተሰብ ማስታወሻ ያዘለውን የጥላሁንን የልጅነት ቀውስ የበዛበት ታሪክ መሳሪያ በማድረግ የጥላሁንን ሙሉ ሰብዕና በፍካሬ ለማሳየት የተጋው በእነዚህ መጽሐፍ ተጽዕኖ ይሆን ? መልሱን ለደራሲው ትቻለሁ፤

ሁለት ማንነት ለምን ?
መሳቁን ይስቃል ጥርሴ መቼ አረፈ፣
ልቤ ነው በጣሙን እጅግ ያኮረፈ፡፡
አልጠፋልህ ብሎኝ የልቤ ውስጥ እሳት፣
ጥርሴ እንዲያምር ብዬ ተወጋሁ ንቅሳት፡፡
ይሄ ነው ጥላሁን ማለት ! ልቡ ውስጥ የቀበረውን እውነት በአንደበቱ

ይሽራል፡፡ በአስታወሰው ቁጥር እሳት ሆኖ ይፈጀዋልና አርቆ ጥሎታል፡፡ በጨቅላነት ዕድሜ የእናቱን ጉያ እየሞቀ ማደግ ቢፈልግም ፣ በአባቱ መዳፍ እየተዳበሰ ልጅነቱን ማየት ቢሻም አልቻለም፡፡ እናቱ ስድስት ዓመት ሳይሞላው ጥላው ኮበለለች፡፡ አባቱ የእናቱን ፈለግ ተከትሎ አድራሻውን ሳይናገር ጠፋ፡ ፡ ጥላሁን በአያቱ እጅ ለማደግ ተገደደ፡፡ ይህን የልጅነት ቁስል ነው ላለፉት 50 ዓመታት ሲደብቅ የኖረው እና የዘከሪያ መሐመድ መጽሐፍ ይፋ ያደረገው፡፡ ጥላሁን መዘንጋት ፣ መተው ያመዋል፡፡ በልጅነቱ የተከሰተው ስነልቦናዊ ቀውስ በትዳሩም የተረጋጋ ሕይወት እንዳይኖረው አድርጎታል፡፡ እናት እና አባቱ እሱን ጥለውት እንደኮበለሉ ሁሉ እሱም ሻንጣውን እየያዘ ያለበትን ሳይናገር የትዳር አጋሮቹን እስከነልጆቻቸው ጥሎ ሸሽቷል፡፡ በዚህ መጽሐፍ ትንታኔ መሠረት ጥላሁን ከሰባት ሴቶች ጋር የፍቅር ሕይወት የመሠረተው ሴት የመቀያየር አባዜ ይዞት ሳይሆን የተዳፈነው የልጅነት ቁስል ውጤት ነው፡፡ የዚህ መጽሐፍ ትልቁ ትሩፋትም ይህን በትንታኔ ማሳየቱ ነው፡፡

ከጥላሁን አንደበት ያገኙትን በሙሉ በተዝረከረከ ቋንቋ የጻፉት የደራስያን ማህበር ጸሐፍት (ይህ ወቀሳ የሠርጸ ፍሬስብሐትን መጣጥፍ አይመለከትም) ከዘከሪያ መሐመድ ! ከአንዱ ግለሰብ ! ጥረት የሚማሩት በርካታ ነገር አለ፡፡

እንደ ደራስያን ማህበር መጽሐፍ ቢሆን ኖሮ ጥላሁን የተወለደው ጠመንጃ ያዥ ሠፈር ነው ፤ የጥላሁን ሕጋዊ ሚስቶች ቁጥር አምስት ብቻ ነው ፤ የመጀመሪያ ሚስቱም ወ/ሮ አስራት አለሙ ናት ፤ የእናቱ ሙሉ ስምም ወ/ሮ ጌጤነሽ ጉርሙ ነው፡፡ በዘከሪያ መሐመድ መጽሐፍ እነዚህ ስህተቶች እርማት ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ጥላሁን ገሠሠ የተወለደው ከወሊሶ 12 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ጉሩራ እልፍ ብሎ በሚገኘው ሶየማ የገጠር ቀበሌ ነው፡፡ እናቱም ወ/ሮ ጌጤነሽ ኢተአ ትባላለች፡፡ የጥላሁን ሕጋዊ ሚስቶች ቁጥር ስድስት ሲሆን የመጀመሪያ ባለቤቱ በአስራ ሰባት ዓመት ዕድሜው ያገባት ወ/ሮ ፈለቀች ማሞ ናት፡፡ በ1970ዎቹ አጋማሽም አራተኛ ሚስቱን ፈሪያል መሐመድን ከፈታ በኋላ ከወ/ሮ ብርሃኔ ዘለቀ ጋር ከሁለት ዓመት በላይ አብሮ ኖሯል፡፡ ይህም የሚስቶቹን ቁጥር ወደ ሰባት ከፍ ያደርጋል፡፡ እነዚህን ሁሉ አሳማኝ የታሪክ ሐቆች ነው የደራስያን ማህበሩ መጽሐፍ የገደፈውና የዘከሪያ መሐመድ መጽሐፍ ይፋ ያደረገው፡፡

ለሃምሳ ዓመታት ሲተረክ የነበረው የጥላሁን ተለጣፊ ማንነት በስነልቦናዊ ትንታኔ ሽሮ የእውነተኛውን የሙዚቃ ሰው ታሪክ ለአስኮመኮመን ዘከሪያ በእውነት ክብር ይገባዋል፡፡

የሆድ ይፍጀው ነገር

“ጥላሁን ገሠሠ የሕይወቱ ታሪክ እና ምሥጢር” የተሰኘውን መጠሪያ የተመለከተ ሰው ሁሉ የዚህ መጽሐፍ ትልቁ ምሥጢር አድርጎ የሚወስደው የሆድ ይፈጀውን ትረካ ይመስለኛል፡፡ ለእኔ ግን ከሆድ ይፍጀውም በላይ ትልቁ ምሥጢር ለሃምሳ ዓመታት ተደብቆ የኖረው የጥላሁን የልጅነት እና የትዳር ሕይወት ነው፡፡
ሚያዝያ 10 ቀን 1985 ዓ.ም የፋሲካ ዕለት የጥላሁን ገሠሠን በስለት የመወጋት ዜና ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ ጥላሁንን ሦስት ቦታ ወግቶ የመግደል ሙከራ ያደረገው ማን እንደሆነ ማወቅ አልተቻለም ነበር፡፡ ዘከሪያ መሐመድ ለዚህ ጥያቄ ዘወርዋራ በሆነ መንገድ ምላሽ ለመስጠት ሞክሯል ፤ ወንጀሉን የፈጸመው እና የፈጸመበትን መንስኤ በትርጓሜ ጠቁሟል፡፡ አብዛኛውን አንባቢ ምን ያህል ያረካል ? እርግጠኛ አይደለሁም፡፡

የመጨረሻው ቃል

በአንድ ኢትዮጵያዊ የኪነት ሰው ላይ በዚህ ደረጃ የሕይወት ታሪክ ተጽፎ ያነበብኩት የዘከርያ መሐመድን “ጥላሁን ገሠሠ የሕይወቱ ታሪክ እና ምሥጢር” የተሰኘውን መጽሐፍ ነው፡፡ የጥላሁን ገሠሠ ውስጣዊ ዓለም በቃላት ስሎ አሳይቶናል፡፡ ስነልቦናዊ ፍካሬው አንጀት ያርሳል ቅደም ተከተላዊ ታሪኩን የገለጸበት ቋንቋ ጥቃቅኖቹን ሁነቶች ሳይቀር ልቦና ውስጥ እንዲቀሩ ያደርጋል፡፡ ይህ መጽሐፍ ፈቃደኛ የሆኑ መረጃ አቀባዮችን ካገኘ የበለጠ እየፋፋና እየጎለበተ መሄድ የሚችል ይመስለኛል፡፡ ለአገራችን የሕይወት ታሪክ ጸሐፍትም ዘከሪያ መሐመድ “የተገኘውን ጥሬ መረጃ እንደወረደ መጻፍ ጸሐፊ አያሰኝም ፤ ጥሬውን መረጃ ከተለያዩ ዲሲፕሊኖች በተገኙ ንድፈ ሐሳቦች መተንተንና መፈክር ነው የስኬታማ የሕይወት ታሪክ ጸሐፊ ብቃት መታያው፡ ፡” ያለ ይመስለኛል ፤ በሥራው፡፡

የዘከሪያን መጽሐፍ ማንበብ መታደል ነው ፤ ትርፉ ብዙ ነውና፡፡

ቁምነገር መጽሔት ላይ ታትሞ የወጣ

The post (አሁንም ስለአነጋጋሪው የጥላሁን መጽሐፍ) ሁለት ማንነት በአንድ ራስ – ጥላሁን ገሠሠ የሙዚቃው ንጉሥ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live