Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በደም የጨቀየች ካርድ! * በትግራይ የአረና-መድረክ አባላትና የምርጫ ተወዳዳሪዎች ደም ፈሰሰ

0
0

አምዶም ገብረሥላሴ ከትግራይ እንደዘገበው

በ11 / 09 / 2007 ዓ/ም በዓፅቢ ወንበርታ ወረዳ በቅስቀሳ የነበሩ ኣባሎቻችን ላይ በገዢው ፓርቲ በምስራቃዊ ዞን ኣመራሮች ትእዛዝና መሪነት የተፈፀመው ኣሰቃቂ ድብደባ 9 ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።በቅስቀሳ ላይ የነበሩ ኣባሎቻች የምስራቃዊ ዞን የፕሮፖጋንዳ ሃላፊ የሆነው ኣቶ ደሳለኝ ተፈራ መጥቶ ከኣፅቢና ሌሎች ኣካባቢዎች ወጣቶች ኣደራጅቶ ድብደባ እስኪፈፅም ቅስቀሳው ሰለማዊ ነበር።ኣባሎቻች በኣፅቢና ደራ ከተሞች ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍና ተቀባይነት ያገኙና ሲበረታቱ ነበር።በእጅ የሚያዝ ማይክሮፎንና በመኪና የተጫነ ሜጋፎን ኣድርገው በሰላምይቀሰቅሱ ነበር። የህዝቡ የለውጥ ፍላጎት ለዓረና መድረካባላት ከፍተኛ መነሳሳት ሲፈጥር ለምስራቃዊ ዞንና ለወረዳው ኣስተዳዳሪዎች ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠረ ነበር።
arena tigrai

tigrai arena medrek

tigrai arena 2

Tigrai arena 1

Tigrai Arena

tigrai 3

tigrai
የዚህ ድንጋጤኣቸው መገለጫም ተደባዳቢ ሰዎች በማደራጀት በ9 ኣባሎቻችንና በሜጋፎን ጭና ስትንቀሳቀስ ይንበረችውን መኪና የድንጋይ ናዳ በማውረድ በሰውና በመኪናዋ ኣካል ከፍተኛ ጉዳት ኣድርሰዋል።

በዚህ መሰረትም 8 ኣባሎቻችን ከፍትኛ ጉዳት የደረሳቸው ሲሆን የመኪናዋ መስተዋትና ሌሎች ኣካልዋ የመሰበር ጉዳት ኣድርሰዋል።

ጉዳት የደረሳቸው ኣባሎቻን

1) ሕድሮም ሃይለስላሴ ከባድ ጉዳት የደረሰው ከኣፅቢ ጤና ጣብያ ሪፈር ትብሎ፣ በውቕሮ ሆስፒታልም ሪፈር ተብሎ መቐለ በህክምና ያለው..

2) ወልደ ኣብራሃ ገብረመድሂን ከባድ ጉዳት የደረሰው ከኣፅቢ ጤና ጣብያ ሪፈር ትብሎ፣ በውቕሮ ሆስፒታል በህክምና ያለው

3) ወልደገብርኤል ሃይሉ የፌደራል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ከባድ ጉዳት የደረሰው ከኣፅቢ ጤና ጣብያ ሪፈር ትብሎ በውቕሮ ሆስፒታል በህክምና ያለ.

4 ) ነጋሲ ክንፉ ከባድ ጉዳት የደረሰው ከኣፅቢ ጤና ጣብያ ሪፈር ትብሎ፣ በውቕሮ ሆስፒታል በህክምና ያለ

5) ካሕሳይ ተስፋይ ጉዳት የደረሰው ከኣፅቢ ጤና ጣብያ እየታከመ ያለው

6) ሓጎስ ገብረስላሴ የክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ጉዳት የደረሰው ኣፅቢ ጤና ጣብያ እየታከመ ያለው.

7) ሙሉ ኣባይ የክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ጉዳት የደረሰው ኣፅቢ ጤና ጣብያ እየታከመ ያለው.

8) ኣበራ ኣስገዶም የክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ጉዳት የደረሰው ኣፅቢ ጤና ጣብያ እየታከመ ያለው

9) ሃይለማርያም ግደይ ጉዳት የደረሰው ኣፅቢ ጤና ጣብያ እየታከመ ያለው ናቸው።

በመኪና ሁነው ቅስቀሳ ሲያካሂዱ የነበሩ እነ ሃፍታይ ገብረሩፋኤል እንደምንም በሹፌሩ ብቃት ከጉዳት ድነዋል። የዚህ ኣረመኒያዊ ተግባር ኣደራጅ የነበረው ኣተ ደሳለኝ ተፈራ በዓዲግራት፣ በኣብረሃ ወ ኣፅበሃ፣ በኣፅቢና ሓወዜን የደረሱብን ድብደባዎች የመራ ኣምባገነንና ወንጀለኛ ሰው ነው።

ይህ ከነ ለገሰ ኣስፋው የማይተናነስ ኣምባገነን ሰው ከድርጅቱ የተሰጠው ትእዛዝ በመፈፀም የኣባሎቻችን ደም እንደ ጎርፍ ያፈሰሰ ወንጀለኛ ነው። ህወሓት በመላ ትግራይ በኣባሎቻችን ላይ እያደረሰች ያለው ግፍ ፍፁም የኣንባገነን ስርዓት መገለጫና ጭፍጨፋ ነው።

በታሕታይ ቖራሮ በመምህር ገብረስላሴ፣ ኣቶ ደመቀ ገብረስላሴና በ4 የምርጫ ታዛቢዎቻችን ከፍተኛ ድብደባ ፈፅመዋል።

በኮረምም ከምርጫና ዓረና-መድረክበተያያዘ ትናንት12/09/ 07 ዓ/ም ኣንድ ምልሻ በጥይት ሂወቱ ኣልፈዋል።

በኣላማጣ ባላ በተባለች ቀበሌ ህዝቡ በሙሉ”ዓረናነን” በማለቱ በስብሰባ ላይ ከወረዳ የተላከች ካድሬ “ዓረና ከመረጣቹ ወደ ጦርነት እንገባለን ለልጆቻቹ ስትሉ ህወሓት ምረጡ” ብለዋል።

የኣላማጣ ምርጫ ታዛቢዎቻችን በወረዳ ኣስተዳዳሪዎች የታዛቢነት መታወቅያ ተቀምተው ባዶ እጃቸው እንዲቀሩ ተደርገዋል፣ በውቕሮና ኣግበ ምርጫ ክልል የታዛቢነት ካርዱ “ራሳችን ነው የምናከፋፍለው” ብለው የምርጫ ኣስፈፃሚዎች ከልክለውናል፣ በመላ ትግራይ ያሉ ታዛቢዎቻችን ከታዛቢነት እንዲወጡ በፖሊስ፣ ምልሻ፣ ካድሬዎች፣ የሃይማኖት ኣባቶች፣ ቤተሰቦች ከፍተኛ ጫናና እንግልት እየደረሰባቸው ይገኛሉ።

ታዛቢዎቻችን ከፍተኛ ጫና በመ ፍጠር ከታዛቢነት እንዲያገሉና “ያለፍላጎታችን ነው ታዛቢ እንድንሆን የተደረግነው” ብላቹ ክሰሱ” እየትባሉ የክስ ደብዳቤ እንዱያስገቡእየተደረገ ነው። ብለው ብለው በስም መመሳሰል ወይም በስም ሞክሼነትም እስከ እስራት የደርሰ መንገላታት እያደረሱባቸው ይገኛሉ።

የዘንድሮ ምርጫ ዓረና-መድረክ ከፍተኛ ዝግጅት ያደረገበት እንደመሆኑ በተወዳደርንባቸው የምርጫ ክልሎች በቂ ታዛቢዎች ኣቅርበናል። ገዢው ፓርቲ ይህ የፈጠረበት ድንጋጤ ለመከላከል ከፍተኛ የወንጀል ተግባራት በመፈፀም ይገኛል።

የህዝባችን ድጋፍ ደግሞ እጅግ የሚያኮራ ነው። የመቐለ ህዝብ እንደ ምሳሌ ብንወስድ ድምፁ ለዓረና-መድረክ እንደሚሰጥ በተለያየ መንገድ እየገለፀልን ገኛል።
ህወሓት በትግራይ ህዝብ ፍፁም ተቀባይነትዋ ተማጦ ጠፍተዋል። ህወሓትም በትግራይ ህዝብ የነበራት እምነት ጨርሳለች። ለዚህ ነው ከወር በፊት በምርጫ መሰረት ኣድርጎ ይሰጥ የነበረው ስልጠና ምርቃት የተገኙ ኣቶ ሓሰን ሹፋው “ህወሓትና መንግስት በቸኛው እምነት የጣለው በፖሊስ ብቻ ነው፤ ህልውናችንም ጥፋታችንም በናንተው ነው።..” ብለው ንግግር ያሰሙት።

የኣፅቢ ወንበርታ ፖሊስም ይህ ጭፍጨፋ በኣባሎቻችን ሲደርስባቸው እያየ እንዳላየ የሆነው ከሓሰን ሽፋ ንግ ግር የተያያዘ ነው።

የዘንድሮ ካርድ በደም የጨቀየች እያደረጋት ያለው ገዢው ፓርቲ ኢህኣዴግ ለራሱ፣ ለኛም ለሃገራችንም ጥቅም ብሎ ከጀመረው የጥፋት መንገድ ሊመለስ ይገባል። ምርጫው ሰለማዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲያልፍ በዓረና-መድረክና ኣባላቱ መስዋእትነት እየከፈልንም ቢሆን የተቻለን ጥረት እናደግርጋለን።

ካርዷ ከደም የፀዳች ለማድረግ የተቻለንን ጥረት እናድረግ።

ነፃነታችን በእጃችንነው..!

The post በደም የጨቀየች ካርድ! * በትግራይ የአረና-መድረክ አባላትና የምርጫ ተወዳዳሪዎች ደም ፈሰሰ appeared first on Zehabesha Amharic.


ወንድሟ በዝዋይ ማረሚያ ቤት በግፍ የተገደለባት የኢትዪጲያ ህዝብ ይፍረደኝ ትላለች (ሊደመጥ የሚገባ)

Health: በቀላል አማራጮች ክብደትዎን ይቀንሱ

0
0

በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ላይ ታትሞ የወጣ

መፍትሄ ከታጣለት እና ለመቆጣጠር ከሚከብድ የውፍረት ችግር ለመላቀቅ ሰዎች የመረጡትን የመፍትሄ መንገድ ለመከተል በዚህ ወቅት የተመቻቸ አማራጭ አለ፡፡ ጊዜው እንኳን ወፍረውለት እንደ ሳር ቀጥነው ተፍ ተፍ ብለውለት እንኳን አብረውት የሚሄዱት አይነት አልሆነም፡፡ ለጤና ጥንቅነቱን ወደ ጎን ትተን የወፈርን እለት እኮ ፀሐዩ ለእኛ ብቻ የተሰየመ ይመስል የሚበረታብን ተፈጥሮውም የተፈጠረውም የሚጨክንብን እየመሰለን ሆድ ይብሰን ይሆናል፡፡ ስለዚህ ጨከን ብሎ አማራጮችን መፈለጉን ያስቡበት፡፡
የሚከተሉት ነጥቦች በተለያዩ የሳይንስ እና የተፈጥሮ የምርምር ውጤቶች ከሚሰፍሩባቸው ታማኝ የመረጃ ገፆች ላይ የተገኙ በመሆናቸው ከምንሰጋቸው የጎንዮሽ ጉዳቶች በፀዳ መልኩ ጤናዎን ጠብቀውና አላስፈላጊ ክብደት ቀንሰው የተስተካከለ አካላዊ ቁመና ያላብስዎታል፡፡
loose weight
– በቂ እንቅልፍ ያግኙ፡፡ የእንቅልፍ እጦት ግሄሬሊን የተሰኘ እና ምግብ ፍላጎትን የሚጨምር ሆርሞን በውስጥዎ እንዲመነጭ የሚያደርግ ሲሆን ለምግብ አመንጪ ውፍረት እራስዎን አጋለጡ ማለት ነው፡፡ በቂ እንቅልፍ አለማግኘት የሚያመጣው ድካምም ማለዳ ላይ ለማከናወን እቅዶ ላይ የነበረን የዋና እንቅስቃሴና ሩጫ፣ እንዲዘሉ ምክንያት ሲሆንዎ ዘወትር ማለዳ መነቃቃትን ፍለጋ ስኳርን እና ካፍዬንን የመውሰድ ግዴታ ውስጥ ይገባሉ፡፡ ስለዚህ መደበኛውን የእንቅልፍ ክፍለ ጊዜ በተቻለ መጠን ላለመዝለል ከፍተኛ ጥረት እንዲያደርጉ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

– ሰናፍጭ ያልታወቀለት ውፍረት መቀነሻ መንገድ መሆኑን ያውቃሉ? ሰናፍጭ ኤፓድሪን የተሰኘ እና በውስጣችን ስብን ለማቅለጥ የሚረዳንን ሆርሞን በተፈጥሯዊ መንገድ እንድንገነባ ይረዳናል፡፡ በኦክስፎርድ ብሩክስ ዩኒቨርሲቲ የሰው ልጅ አመጋገብ ላይ የሚመራመሩት ፕሮፌሰር አንድ ሾርባ ማንኪያ ሰናፍጭ ልፍስፍስ ወገብ ካለዎት በ20 በመቶ ችግርዎን እንዲቀርፉ ያስችሎታል ነው የሚሉት፡፡

– የምግብ ፍላጎትዎ መቆጣጠር ከሚችሉትም በላይ ነው? ረሃብን ሆድዎ የሚጠይቅዎ ሲሆን ህይወቶን ለማቆየት መብላትም ግዴታ ነው፡፡ ነገር ግን አዕምሮዎ ከሰውነትዎ ጋር በመናበብ ከፍተኛ የምግብ ፍጆታ ይጠይቅዎ ይሆናል፡፡ የእርስዎ ችግር ሱሰኝነትዎ በተለይ ለጣፋጭ እና ስብ አመንጪ ምግብ ከሆነ ለበሽታ የመጋለጥ ዕድልዎ የሰፋ ስለሆነ መፍትሄ ያሻዎታል፡፡ በዚህ ረገድ ተመራማሪዎች በዚህ ችግር ተጠቂ የሆኑ ሰዎች በከፍተኛ ፍጥነት ወደ አንጀት የማይዘዋወሩና ከፍተኛ የፋይበር መጠን ያላቸው ምግቦችን መጠቀም አማራጭ እንደሆነ ያስቀምጣሉ፡፡ ከፍተኛ ፋይበር፣ አፕል፣ ብርቱካን፣ ጎመን፣ ዝኩኒ እና ሌሎች አትክልት ፍራፍሬዎች ውስጥ እንዲሁም ባቄላ ውስጥ ያገኙታል፡፡
እነዚህን የመመገብ ባህል ማዳበር ለስኳር ህመም የሚወስድ የኢንሱሊን መድሃኒት በአጭር ጊዜ ልዩነት የመውሰድ አጋጣሚን ከማስቀረቱም ባለፈ በቀላል መንገድ መፍትሄ የተጣለበትን ውፍረትዎን በመቀነስ ረገድ የተዋጣለት አማራጭ ሆኖ ተቀምጧል፡፡

– ባገኙት አጋጣሚ ማለትም ሲራመዱ፣ ሲቀመጡ እንዲሁም ምግብ ሲያበስሉ ሆድዎን ወደ ውስጥ ይሳቡት፤ ይሄም የሆድዎ አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች እንዲጠነክሩ በማድረግ ቦርጫምነትን ይከላከላል፡፡

– ባቄላን ያዘውትሩ በአንፃራዊነት በሀገራችን በዝቅተኛ ዋጋ ከሚገኙ የምግብ አማራጮች መካከል ሲሆን እንደውም የብዙዎቻችን የዘወትር ብፌ ነው፡፡ ሆን ተብሎም ሆነ ዕድል ባመቻቸው ሁኔታ ይሄን ፍሬ ማዘውተር ጥቅሙ የበዛ አስተዋፅኦ ያጎናፅፋል፡፡

ባቄላን ማዘውተር ለልብዎ ከሚሰጥዎ ጥቅም በላፈ የአጠቃቀምዎ ሁኔታ ባደገ ቁጥር በዛው ልክ ውፍረት ለመቀነስ ይረዳዎታል፡፡ በፋይበር የበለፀገ እንዲሁም ወደ አንጀትዎ የመከማቸት የጊዜ ምጣኔው ዝቅተኛ መሆኑ ሆድዎ በፍጥነት እንዳይጠይቅዎ በማድረግ ለረዥም ጊዜ እንደጠገቡ መቆየት ያስችልዎታል፡፡
– በራስዎ ይተማመኑ፡፡ ምን ያህል ጊዜ የሸንቃጣዎችን ስኬት በማድነቅ እንዲሁም ‹‹እኔም እንደዚህ መሆን እፈልጋሁ ነገር ግን አልችልም›› በማለት ራስዎን በመገደብ ይቆያሉ? የስኬትዎን ጫፍ አይገድቡ፡፡ የፈለጉትን ከማሳካት የሚገድብዎ የእርስዎ አመለካከት ብቻ ነው፡፡
– በማንኛውም አጋጣሚ ጨውን ከምግብዎ ለማራቅ ይሞክሩ፡፡ ሶዲየም (ጨው) የደም ግፊትዎን በመጨመር እና ደምዎን በማቀዝቀዝ ብቻ አይገድብም ተፅእኖው ይልቁንም ከፍተኛና ከሚያስፈልግዎ መጠን በእጅጉ የላቀ ውሃ እንዲወስዱ በማድረግ ለበሽታና ክብደት መጨመር ያጋልጦታል፡፡ ውሃ መጠጣት ለጤና ከሚያበረክተው አስተዋፅኦ ባልተናነሰ መልኩ ጉት ማስከተሉን መዘንጋት እንደሌለብን የሚያስገነዝብ ነጥብ ነው፡፡

– የመመገቢያ እና የልምምድ ወቅትን በጊዜ መገደብ ያስፈልጋል፡፡ ከእንቅስቃሴ በፊት በምንም ሁኔታ መመገብ አደገኛ ነው የተባለ ሲሆን ከ30 እስከ 60 ደቂቃ ከእንቅስቃሴ በኋላ ቆይቶ መመገብ የተሻለው አማራጭ ነው፡፡ ይሄም የሚፈልጉትን ሰውነት ለመገንባት የሚረዳዎ አካሄድ ነው፡፡

– ውፍረታቸውን ለመቀነስ ያቀዱ ሰዎች ቲማቲም፣ አረንጓዴ አትክልቶችን ስብ የሌለባቸውን ፕሮቲኖች በአመጋገብ እቅዳቸው ውስጥ ያካትታሉ፡፡ ከእቅዳቸው ውጪም አይመገቡም፡፡

– ሁለት ፍሬ እንቁላል ውፍረቶን ለመቆጣጠር ለጠዋት ቁርስዎ ዳቦን ከመጠቀም ጥሩ አማራጭ ተደርጓል፡፡

The post Health: በቀላል አማራጮች ክብደትዎን ይቀንሱ appeared first on Zehabesha Amharic.

አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ሕዝቡ በይስሙላው ምርጫ ድምጽ መስጫ ላይ ለስርዓቱ ያለውን ተቃውሞ እንዲገልጽበት ጥሪ አስተላለፉ

0
0

የተቃዋሚ ታዛቢዎች ለፓርቲያቸው የተሰጠውን ድምጽ መቁጠር ብቻ ሳይሆን የተበላሹትን ገዢው ፓርቲ እንዳይጠቀምባቸው ተከላከሉ ሲሉ አስጠነቀቁ
ermias copy
(ሕብር ሬዲዮ -ላስቬጋስ )አስቀድሞ ውጤቱ የታወቀውና የህዝቡ ድምጽ የማይከበርበት ኢህአዴግ ለራሱ የፈለገውን ድምጽ የሚወስድበት የይስሙላ ምርጫ እለት አማራጭ ጠፍቶ ወደ ምርጫ ጣቢያው ለመሄድ የተገደደ እና ገዢውን ፓርቲም ሆነ ተቃዋሚን የማይመርጡ በተለይም የታቃዋሚ ምንም ዕጩ የሊለባቸውም ሆነ ቢኖሩም ታዛቢ እንዳይገኝ የተደረገባቸው ቦታዎች ህዝቡ ወት በሆነ መንገድ በድምጽ መስጫው ወረቀት ላይ በምስጢር ተቃውሞውን እንዲገልጽ አቶ ኤርሚአስ ለገሰ የቀድሞው የአገዛዙ የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታና የመለስ ቱርፋቶች ደራሲ ገለጹ።

አቶ ኤርሚያስ ለገሰ የተግባር ሳምንት ብለው በምርጫው ዋዜማ ባወጡት ጽሑፍ በዚህ ወቅት በምርጫው ዕለት ሊከወኑ የሚችሉ ጉዳዮችን ዘርዝረው ለሕዝቡና ለተቃዋሚ መሪዎች ጥሪ አስተላልፈዋል። በዚህ ጽሁፋቸው ተቃዋሚዎች በሁሉም ዕጮዎቻቸው ባሉበት ቦታዎች ታዛቢ እንዲያስቀምጡ እና በምርጫ 2002 የተቃዋሚ ታዛቢዎች እንዳደረጉት ሳይሆን ለፓርቲያቸው የተሸጠውን ድምጽ ብቻ ሳይሆን የተበላሹትን ለብቻ ቆጥረው ለይተው ድምጽ አልባ እንዲሆኑ የማስደረግ እና በፍጥነት ለፓርቲያቸው ሪፖርት የማድርግ ግዴታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል። ያ ካልሆነ ገዢው ፓርቲ ከዚህ ቀደም እንዳደረገው የተበላሺትን ወረቀቶች ድምጽ አልባ እንዳይሆኑ በማስደረግ ለራሱ ይጠቀምባቸዋል ብለዋል።

በድምጽ መስጫው ላይ የሚደረጉ ተቃውሞዎችን ወጥ እንዲሆኑ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የጠቆሙት የቅድሞ የአገዛዙ የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ ወደ ምርጫ ጣቢያ መሄድ የህልውና ጉዳይ ሆኖበት ስርዓቱን መምረጥ የማይፈልገው ሌላው ቀርቶ የራሱ የድርጅት አባል ሆነው ለስራ ዋስትና ሲሉ የሚመርጡ ያላቸውን የውስጥ ተቃውሞ በምስጢር ድምጽ በሚሰጥበት የድምጽ መስጫ ወረቀት ላይ ተቃውሞን በመጻፍ ለስርዓቱ ያለን ተቃውሞ መግለጫ ብቸኛና ለደህንነት የማያሰጋ መሆኑን ገልጸዋል።

የተቃውሞው መልዕክቶች ወጥ እንዲሆኑ ማድረግ ላይ ስምምነት ከተፈጠረ ለዚሁ የሚሆን ዘዴ መቀየስ አስፈላጊነቱን የጠቆሙት አቶ ኤርሚያስ የሙስሊሙ ማህበረሰብ > የሚለውን ወይም ጨረቃን መሳልና ሌሎችንም የተስማማባቸውን ክርስቲያኑም በሊቢያ መስዋዕት የሆኑትን ለማሰብ መስቀል አሊአም ሌላ በጋራ በመጠቀም ተቃውሞን መግለጽ ሲሆን ከዚህ ውጭ ለውጥ በኢትዮጵአ በትጥቅ ትግል ነው የሚመጣው ብለው የሚአምኑም በተመሳሳይ ወጥ በሆነ መንገድ በምስጢር ሀሳባቸውን በመግለጽ የውስጥ ተቃውሟቸውን ለማሳየት የይስሙላውን ምርጫ ይጠቀሙበት ሲሉ በጽሁፋቸው ገልጸዋል።

> ያሉት አቶ ኤርሚያስ ዋጋ የሚያስከፍለው ነገር ግን ጉልህ የተቃውሞ ማሳያ መንገድ ያሉትንም በጽሁፋቸው ጠቅሰው ያም ወደ ምርጫ ጣቢያው ዝር አለማለት በተለይ ይህ የተቃዋሚ ታዛቢዎች በሌሎበት አካባቢ ትርጉም ያለው የተቃውሞ ማሳያ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል። መሰረታዊ የዲሞክራሲና የሰብኣዊ መብት በተገፈፈበት የሲቪል ተቋማት በተሽመደመዱበት ፣ የገዢውን ፓርቲ ፕሮፖጋንዳ የሚያሰራጩ ሚዲያዎች ብቻ ባሉበት፣የብዕር አርበኞችና የሀይማኖት ነጻነት ታጋዮች በአሸባሪው ጸረ ሽብር አዋጁ በተከሰሱበት ፣ገዢውን ፓርቲ በተወሰነ መልኩ ሊገዳደሩ የሚችሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በፖለቲካ ውሳኔ ተላልፈው በተሰጡበት የምርጫ ካርድ ተሸክሞ ወደ ምርጫ ጣቢያ መሄድ የሞራል ጥያቄ ማስነሳቱ አይቀርም ብለዋል።

አቶ ኢርሚያስ በመጪው ዕሁድ ለምርጫ ህ/ሰቡ ምን ፈልጌ ነው ድምጽ ምሰጠው ? ምን ለማትረፍ? የተጠቀሱት መሰረታዊ ችግሮች በኔ ድምጽ ይፈታሉ ብሎ እያንዳንዱ እራሱን ሊጠይቅ የሚገባበት ሳምንት ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ በምርጫ 2002 የሆነውን በማሳያነት አጣቅሰው ለምርጫ ከተመዘገበው ውስጥ 43.8 በመቶ ብቻ ለምርጫ ሲወጣ የቀረው ለምርጫ ባለመውጣት ተቃውሞውን አሳይቷል ሲሉ የፕ/ር መስፍን ወልደማሪያምን ጥናትን መሰረት ያደረገውን > የሚለውን መጽሐፍ አብይ ማስረጃዎች ጠቅሰዋል። ለምርጫ አለመውጣት በገጠራማ አካባቢዎች እንደ አፋር፣ሱማሊ ክልል፣ጋምቤላ፣ቤንሻንጉል እና ትግራይን በመሳሰሉ አካባቢዎች አስቀድሞ ኮሮጆ ተሞልቶ ስለሚያልቅ ትርጉም እንደሌለው ገልጸዋል።

አቶ ኤርሚያስ ለገሰ የመለስ ቱርፋቶች ባለቤት አልባ ከተማ በሚል መጽሐፋቸው ውስጥ ኢህአዴግ በምርጫ 2002 የሕዝብ ድምጽ እንዴት እንደዘረፈ እና ምርቻውም አስቀድሞ የተበላ ዕቁብ እንደነበር ጠቅሰው የጻፉትን መሰረት አድርገን ለሕብር ሬዲዮ በሰጡን ቃለ መጠይቅ የዘንድሮውም ምርቻ ከተበላ ዕቁብነት የማይዘልና በስልታን ላይ ያለው ስርዓት በምርጫ ይወድቃል ብለው እንደማያምኑ ነገር ግን በሰላማዊ መንገድ እንታገላለን የሚሉትንም እንደማይቃወሙ መግለጻቸው ይታወሳል።

The post አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ሕዝቡ በይስሙላው ምርጫ ድምጽ መስጫ ላይ ለስርዓቱ ያለውን ተቃውሞ እንዲገልጽበት ጥሪ አስተላለፉ appeared first on Zehabesha Amharic.

መንግስት በምርጫ ዋዜማ የሀይማኖት ጣልቃ ገብነቱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል * ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ከአዲሱ መጅሊስ ጋር በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ አህባሽን ከምርጫ በሁላ የማስቀጠያ መንገዶቹን ተነጋገሩ

0
0

yisema

Muslim
ሰበር ዜና ቢቢኤን

ቢቢኤን፡- ግንቦት 13/2007

መንግስት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ሃይማኖት ጣልቃ በመግባት የአህባሽ አስተምህሮን በፌድራል ጉዳዪች አስተባባሪነት፤በመጀሊስ ሽፋንነት የህገ-መንግስቱን አንቀጾች በመጣስ የሚፈጽመውን አስነዋሪ ተግባር አጠናክሮ መቀጠሉ ታወቀ
ከግንቦት7 እስከ 8 የፌድራል ጉዳዪች ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ከአዲሱ በርሳቸው ትእዛዝ ከተመሰረተው አዲሱ የአህባሽ መጅሊስ ፕሬዝዳንትና ሌሎችም በተገኙበት ከዚህ ቀደምም የአህባሽ ጠመቃ በተካሄደበት የሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ስልጠና ሰጥቷቸዋል፡፡
”የአክራሪነትና ጽንፈኝነት አደጋ እና የመታገያ ስልቶች ” በሚል ርእስ በተሰጠው ስልጠና ላይ ዶክተር ሽፈራው ያስቆመጧቸውን የመንግስት መጅሊሶች ኢህአዴግ እንዲመረጥ የሚችሉትን እንዲያደርጉና ከዚያ በሁላ የአህባሽ አስተምህሮትን በሰፊው ለማዳረስ ያላቸውን እቅድ ተነጋግረዋል፡፡
ምርጫ ሊደረግ ጥቂት ቀናት በቀረቡት ዶክተር ሽፈራው የተለመደ ጣልቃ ገብነታቸወን መቀጠላቸው ኢህአዴግን ምረጡ አህባሽን በግዳጅ እንድጠመቁ የሚል መልክት እያስተላለፉ ነው ሲሉ ታዛቢዎች ተችተዋል፡፡ ይህም የሚያሳየው ኢህአዴግ ዛሬም ከሙስሊሙ እምነት ላይ እጁን እንዳላወረደ አመላካች ነው ተብሏል፡፡
በሌላ በኩል ከነዶክተር ሽፈራው ጋር የህዝብን ጥያቄ ይዘው ሂደው ሲወያዩ የነበሩት የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በአሁኑ ጊዜ በማረሚያ ቤቱ በኩል በህወሃት ደህንነቶች ትእዛዝ ከፍተኛ በደል እየተፈጸመባቸው ይገኛል፡፡
ድምጸችን ይሰማ በበኩሉ ትላንት ባወጣው መግለጫ ከምርጫ በፊትም ሆነ በሁላ ህዝበ ሙስሊሙ የጀመረውን ሰላማዊ ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥለበት መግለጹ ይታወቃል፡፡

The post መንግስት በምርጫ ዋዜማ የሀይማኖት ጣልቃ ገብነቱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል * ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ከአዲሱ መጅሊስ ጋር በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ አህባሽን ከምርጫ በሁላ የማስቀጠያ መንገዶቹን ተነጋገሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ የሚታወቀው የህወሓት/ኢህአዴግ የምርጫ ድራማን አስመልክቶ የተሰጠ የጋራ መግለጫ

0
0

 

ቀን ግንቦት 13፣ 2007

shengoENTCየኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነቱን ተነፍጎ ባገር በቀሉ የወያኔ አፓርታይድ አገዛዝ ስረ ወድቆ ፍዳውን እያየ ነው። ስርአቱ ላለፉት  24 አመታት በሃገራችን ውሰጥ በፈጠራቸው ፖለቲካዊ፤ ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ስነልቦናዊ ቀውሶች ምክንያት ተተኪው ወጣት ትውልድ ባስደንጋጭ ሁኔታ በየጊዜው አገሩን ጥሎ ሲወጣ በባህር ውስጥ በመስመጥና፤ ከዛም የተረፈው በአፍሪካና በአረብ አገሮች እጅግ አሰቃቂ ለሆኑ ውርደት ስቃይና ግድያ ተጋልጧል።

ከምርጫ ሂደት ጋር በተያያዘ፤ ምርጫውን ተከትሎ ሊፈጠር የሚችለውን የህዝብ አመጽ አስቀድሞ ለማምከን በሚል ስልት በሀገር ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችን ወጣት በመሆናቸው ምክንያት ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ በመታፈስና ወደ ተለያዩ እስር ቤቶች በመታጎር ላይ ናቸው።  በመላው አገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ አመራር አካላትም ይሁኑ አባላት በእስርና ወከባ ላይ ይገኛሉ። በአጠቃላይ የምርጫ ምህዳሩ ዝግ መሆኑ እየተገለጸ በሚገኝበት ሂደት ውስጥ ያለነጻነት ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ማድረግ ስለማይቻል ህዝባችንን ወደ ፍትሃዊና ዲሞክራሲዊ ስርአት የሚያሸጋግረው ውጤት ይገኛል ብለን አናምንም።

በማንኛውም አገር በሚደረጉ የምርጫ ሂደት ላይ የጎላ ሚና ሊጫወቱ የሚችሉ ተቋማትና ድርጅታዊ እንቅስቃሴዎች  ምን አህል እንደታፈኑ በአጭሩ በማስረጃ ለማስደገፍ ያህል፤ በርካታ የህዝብ ወገንተኛና የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎች፤ አባላትና ደጋፊዎቻቸው፤ ጋዜጠኞች ጦማሪያን በግፍ ታስረው በድቅድቅ ጨለማ በእስር ቤት ውስጥ ባስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከውጭ የመጣ መንግሥታዊ ሃይማኖት ሊጫንብን አይገባም በማለታቸው ብቻ መሪዎቻቸው በአሸባሪነት ተፈርጀው በእስር ቤት እየተሰቃዩ ነው። ህወሓት ከጥንስሱ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፤ የኢትዮጵያ አንድነት መሰረት ነው ከሚል መነሻ፤ በዋና ጠላትነት በመፈረጅ መንበረ ስልጣኑን ከመቆጣጠሩ በፊትና በሗላ በካህናት፤ ምእመናንና በታሪክ ላይ ተከታታይና ከፍተኛ ወንጀል በመፈጸም ላይ ነው። የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲፈርሱ ሆነዋል። ተቃዋሚውን የሚደግፉ ዜጎች ሥራ አያገኙም፤ ከሥራም ይባረራሉ። እጩነት በእጣ ሆኗል። የምርጫ ቦርዱ በአገዛዙ ቁጥጥር ሥር ነው። ተቃዋሚዎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው ማደራጀት አይችሉም። ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች የሉም። መገናኛ ብዙሃንን አገዛዙ ተቆጣጥሮታል። ጋዜጠኞች ተሰደዋል። ነፃ የፍትኅ ተቋም የለም። ሰብዓዊ መብትን እያፈነ ሽብርተኝነትን እዋጋለሁ በሚል ሰበብ ከምዕራቡ ዓለም በሚያገኘው ዕርዳታ ተቃዋሚውን ያፍናል፤ ምዕራባውያንን ያሞኛል። እነኚህን መሰረታዊ ችግሮች በመረዳት ለመጀመሪያ ጊዜ  የአውሮፓ የጋራ ማህበር በምርጫው አንደማይሳተፍ ይፋ አድርጓል።

ከላይ በጥቂቱ የተዘረዘሩትን ኩነቶች ስንገነዘብ የምርጫው ውጤት አስቀድሞ መታወቁን ለማወቅ አዳጋች አይሆንም።  አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ ይህንን ምርጫ ለይስሙላ ዲሞክራሲ ለውጭ መንግስታት ገጸ በረከት ለማቅረብና ዓለም አቀፍ እውቅና በማግኘት  ለቀጣይ ተመሳሳይ አስርተ ዓመታት ሀገሪቷን በመግዛት የስልጣን ጥሙን ሊያረካበት የተዘጋጀ መሆኑን በግልጽ እንረዳለን።

ህዝባችን ላለፉት 24 አመታት ያለነጻነት በወያኔ የግፍ አገዛዝ ስር ፍዳውን በሚያይበት በዚህ ወሳኝ ወቀት ስርአቱን ለማስወገድ ህዝብን መሰረት ያደረገ ባንድ ማከል የሚንቀሳቀስ ሁሉን አቀፍ ያማራጭ አካል በማቋቋም የህዝባችንን እምቢተኝነት በተማከለ ሁኔታ ለመምራት የተቃዋሚው ኃይል በሙሉ ባስቸኳይ ተሰባስቦ አማራጭ ኃይል ሆኖ መቅረብ የወቅቱ ጥያቄ መሆኑን በመረዳት የእንሰባሰብ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ቀጥለው የተዘረዘሩት ድርጅቶች፤ ከላይ የተገለፁትን ችግሮች የኢትዮጵያ ህዝብ ለነፃነቱ የሚያካሂደው ትግል ላይ የሚያስከትሉትን አስከፊ አደጋዎች ከወዲሁ በመረዳት፤ በዋነኝነት ደግሞ ብሄራዊና ወቅታዊ ጉዳዮችን በማስቀደም፤ የአማራጭ ሃይል ባስቸኳይ የሚቋቋምበትን ሁኔታዎች ለማመቻቸት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን እየገለፅን፤ ሁሉም የፓለቲካ ድርጅቶች የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት የጋራ አቋም ላይ እንዲደርሱ ጥሪያችንን በአክብሮት እናቀርባለን።

በዚህ አጋጣሚ ነጻነት ናፋቂ ለሆነው ወገናችን ለማሳሰብ የምንወደው፤ ይህ መሰረታዊ ጉዳይ የፖለቲካ ድርጅቶች ሀላፊነት ብቻ አለመሆኑን ተገንዝቦ አገርና ህዝብን ለነጻነት ለማብቃት አስፈላጊውን ተሳትፎ እንዲያደርግ አገራዊ ጥሪያችንን በአክብሮት እናስተላልፋለን።

ይህን አደገኛ የቁልቁለት ጉዞ እንዲገታ በጋራ እንቁም!

የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (SHENGO)

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት (ENTC)

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት (UEM-PMSG)

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ (EYNM)

The post ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ የሚታወቀው የህወሓት/ኢህአዴግ የምርጫ ድራማን አስመልክቶ የተሰጠ የጋራ መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.

[ሰበር ዜና ቢቢኤን] በኢህአዴግ መንግስትና በግብጽ መንግስት ግፊት የቢቢኤን ሳተላይት ስርጭት ተቋረጠ

0
0

BBN
የናይል ሳት ድርጅት ለቢቢኤን ሬድዪ ዛሬ በጻፈው ደብዳቤ ይህኑኑ ግልጽ አድርጓል
ሰበር ዜናውን ዳውንሎድ አድርገው ያድጡ


ቢቢኤን በላይቭ ስትሪምና በሞባይል አፕሊኬሽን የሚያደርገውን ስርጭት አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል

The post [ሰበር ዜና ቢቢኤን] በኢህአዴግ መንግስትና በግብጽ መንግስት ግፊት የቢቢኤን ሳተላይት ስርጭት ተቋረጠ appeared first on Zehabesha Amharic.

ፈካረ ዘመን ትንቢተ ወቅት –የጐንቻው!


የኦፌኮ/መድረክ መሪ ተከታታይ ጥቃቶች እንደደረሱባቸው አስታወቁ

0
0

በወለጋ፣ በኢሉባቦርና በጂማ የተለያዩ አካባቢዎች የምርጫ ዘመቻ ሲያካሂድ የነበረ የፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሙድረክ ቡድን ትናንትና ከትናንት በስተያ በአካባቢው የፀጥታ ኃላፊዎችና የገዥው ፓርቲ ደጋፊዎች ባሏቸው ሰዎች ተከታታይ ጥቃቶች እንደተፈፀሙበት የቡድኑ መሪ የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡ ሁኔታውን እያጣሩ መሆናቸውን የተናገሩት የኦሮሚያ ምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር አምባሣደር ዲሳሳ ድርብሳ እስከአሁን “…ችግር ደርሶባቸዋል፤ ይጓዙበት የነበረ መኪና ተሰብሯል፤ ድብደባና ዝርፊያ ደርሶብናል ያሉት እውነት አይደለም ማለት አይቻልም…” ብለዋል፡፡  ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

 

Bekele Gerba

The post የኦፌኮ/መድረክ መሪ ተከታታይ ጥቃቶች እንደደረሱባቸው አስታወቁ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች እየታሰሩ ነው

0
0

blue partyበደቡብ ክልል የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች እየታሰሩ እንደሚገኙ የፓርቲው አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፁ፡፡ በሀድያ ዞን ጌጃ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ታዛቢ የሆኑት አቶ በየነ ጫፎን የደኢህዴን ካድሬዎች የንግድ ቤታቸውን በማሸግ እንዳሰሯቸው በሀድያ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ አቶ ሳሙኤል አቦቼ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ የሰማያዊ ፓርቲ ለታዛቢነት ያቀረባቸውን ሰዎች ስምና አድራሻ ለደኢህዴን ካድሬዎችና ደህንነቶች አሳልፎ ስለሚሰጥ ታዛቢዎች በስፋት እየታሰሩና ወከባ እየደረሰባቸው እንደሆነም አቶ ሳሙኤል ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ሚዛን ቴፒ ላይ መንግስት ‹‹የሸፈቱ ሰዎች አሉ›› በሚል ሰራዊቱን በማስፈሩ ምክንያት በህዝብና በሰራዊቱ መካከል ውጥረት እንደተፈጠረና ነዋሪዎች ግጭት ይነሳል በሚል ከአካባቢው እየለቀቁ እንደሚገኙ ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በዚህ ስጋት ውስጥ ታዛቢዎች ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው ምርጫውን ለመታዘብ እንዳይችሉ እንቅፋት እንደተፈጠረባቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሰብሳቢዎች ገልጸዋል፡፡ በስጋቱ ምክንያት አካባቢው እስኪረጋጋ ምርጫው እንዲራዘም ቢጠይቁም ደኢህዴን ፈቃደኛ እንዳልሆነ ገልፀዋል፡፡

The post የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች እየታሰሩ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

“የምርጫውን ካርድ ቀዳችሁ ጣሉት”–ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ

0
0

nega birhanu zehabesha Ginbot 7
May 22, 2015

የተከበራችሁ እናቶቼና አባቶቼ፤ እህቶቼና ወንድሞቼ እንዲሁም ልጆቼ የምትሆኑ ወጣቶች!! አገራችን የምትገኝበትን አስጨናቂ ሁኔታ ሁላችንም እንረዳለን። የህወሓት/ኢሕአዴግ ፋሽስቶች ቡድን እየገረፈ፣ እያሰረና እየገደለ በካርዳችሁ መርጣችሁ የምርጫ ድግሴን ካላሞቃችሁልኝ እያለ ነው። እንኳንስ ዛሬ ታዛቢ በሌለበት፤ ታዛቢ እያለም እንኳን ወያኔ የሕዝብን ድምጽ በትክክል ቆጥሮ አያውቅም። ወያኔ ለህዝብ ድምጽ ምንም ደንታ የሌለው የኋላቀር ወሮበሎች ቡድን ነው::

ለስንት አስርት ዓመታት ለወያኔ ባርነት እንገብራለን? ለሀያ አስምስት ዓመታት ተገዛን፣ ተገደልን፣ ተቀጠቀጥን፣ ታሰርን፣ ተሰቃየን፣ ልጆቻችን በአገራቸው ተስፋ ቆርጠው ሲሰደዱ በበረሀ ንዳድ አለቁ፤ በባህር ሰጥመው ቀሩ፤ በባዕዳን አረመኔዎች እንደከብት ታረዱ፤ ቤንዚን ተርከፍክፎባቸው ተቃጠሉ። ሀይማኖታችን ተዋረደ፤ ባህላችን ረከሰ፤ ታሪካችን ተናቀ። በልማት ስም ወልደን ከከበድንበት ተፈናቀልን፤ አገራችን አደገች እያለ ሕዝብ በኑሮ ውድነት ተሰቃየ። በልቶ ማደር ብርቅ ነው። እንደሙጫ የሚያጣብቀንን ማህበረሰባዊ ትስስር በስልጣን ለመቆየትና ህብረተሰቡን ለመዝረፍ ሲል ሆን ብሎ እያፈራረሰው ነው:: ይኽ ሁሉ አይበቃንምን? ይኸ ሁሉ አይመረንምን?

ወላጆቼ፣ እህት ወንድሞቼ!ውርደት ይብቃን። የተረገጥንና የተገደልን አንሶን ፍጹም ማንንም ሊያሞኝ በማይችል የለበጣ ምርጫ ወደን የተረገጥን፤ ፈልገን የተገዛን ለማስመሰል ወያኔ የሚያደርገውን ሩጫ እናክሽፈው:: ከፊታችን ያለውን ምርጫ ባለመሳተፍ ምሬታችንን እንግለጽ።

ዛሬ በግሌ እና በአርበኞች ግንቦት 7፡ የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ስም ጥሪዬን አቀርባለሁ። በዚህ ምርጫ አትሳተፉ። የምርጫ ካርዳችሁን ቀዳችሁ ጣሉት። እናምርር። ካላመረርን ለውጥ ሊመጣ አይችልም። ይልቅስ ለማይቀረው የመጨረሻው ትግል ራሳችንን እናዘጋጅ::

አርበኞች ግንቦት 7፣ ከትግራይ፣ ከኦሮሞ፣ ከአፋር፣ ከኦጋዴን፣ ከጋምቤላ፣ ከቤሻንጉል ድርጅቶች ጋር ትብብር በመፍጠር የአገር አድን ኃይል በመገንባት ላይ ነው። እኛ ልጆችህ በብሔርም ሆነ በሀይማኖት አንከፋፈልም። ከትግራይ እስከ ኦጋዴን፤ ከአፋር እስከ ጋምቤላ ሁሉንም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ያካተተ ስብስብ ፈጥረን በኅብረት አገዛዙን እየታገልን ነው። ይህ ትግል ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ ትግል ነው። የትግሉም ባለቤት የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ነው። ክርስቲያን ሙስሊም፤ ወንድ ሴት፤ ወጣት አረጋዊ ሳንል፤ በብሔርም ሆና በቋንቋ ሳንከፋፈል ሁላችንም ይህን አስከፊ ሥርዓት በቃህ እንበለው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ይህንን የውሸት ምርጫ ባለመሳተፍ ለለውጥ ያለህን ዝግጁነት አሳይ! ደግሜ እለዋለሁ – የምርጫ ካርድህን ቅደድ!!!

የጦርና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ሆይ!

እናንተ የሕዝብ አካላት ናችሁ። በወገኖቻችሁ ላይ አትተኩሱ። ይልቁንስ አፈሙዛችሁን አገራችንን ለውርደት በዳረገውና በሙስና በተጨማለቀው ዘራፊው የህወሓት አገዛዝ ላይ አዙሩት። ታሪካችሁን ከምታበላሹ፤ ታሪክ ሥሩ። ለራሳችሁ፣ ለቤተሰቦቻችሁ፣ ለልጆቻችሁ እና ለሕዝብ የሚጠቅም አገርና መንግሥት እንዲኖረን የእናንተ የግልም ሆነ የጋራ ተነሳሽነት ወሳኝ ነው። ወያኔ ህዝቡን የሚዘርፈው በእናንተ ትከሻ ላይ ቆሞ እንደሆነ ላንዳፍታም አትርሱት:: እንደመላው ህብረተሰብ እናንተም በነጻነትና በኩራት የምትኖሩበት ሀገር እንደምትሹ አልጠራጠርም:: ስለዚህም ይህን የህወሓት የውሸት ምርጫ ተቃወሙ። ዛሬውኑ ነፃነትና ፍትህ ከጠማው ወገናችሁ ጎን ቁሙ።

የኢትዮጵያ ወጣቶች፤ ትግላችን እስከ ነፃነት ድረስ ይቀጥላል። ነፃነታችንን በእርግጠኝነት በትግላችን እንቀዳጃለን። የምትወዷት፣ የምትኮሩባት አገር – ኢትዮጵያ – ትኖረናለች። ለዚህ ግን ዛሬ ተደራጅተን፣ ፀንተን መታገል የሁላችንም ኃላፊነት ነው። ዛሬ ሁላችንም በፍላጎትና በመንፈስ የተገናኘን ነንና ሁሉም በያለበት ትግሉን ያጧጡፍ። ውጤቱ ቀድሞ በታወቀው በዚህ ምርጫ አለመሳተፍ ለትግሉ ያለንን ቁርጠኝነት ማሳያ ነውና ለውሸት ምርጫ ያለን የመረረ ተቃውሞ በምርጫው ባለመሳተፍ እናሳይ።

ነፃ እንወጣለን!

የኢትዮጵያ ሕዝብ የነፃነቱ ባለቤት ይሆናል! ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

The post “የምርጫውን ካርድ ቀዳችሁ ጣሉት” – ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ appeared first on Zehabesha Amharic.

በሚኒሶታ ለጊዜው ባልተረጋገጠ ሁኔታ ተገድሎ የተገኘው ኢትዮጵያዊ የቀብር ሥነሥርዓት ዛሬ ይፈጸማል

0
0

Abiyuአብዩ ተከሥተብርሃን ይባላል:: ኤፕሪል 16 (ሚያዝያ 20 ቀን 2007 ዓ.ም) ከሥራ ውሎ ከተመለሰ በኋላ ከቤት እንደወጣ ሳይመለስ ስለቀረ ምን እንደደረሰበት ሳይታወቅ ሲፈለግ ሰንብቶ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ለጊዜው ባልተረጋገጠ ሁኔታ ተገድሎ እንደተገኘ ቤተሰቦቹ ለቀብር ካዘጋጁት በራሪ ወረቀት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል:: መረጃው እንደሚለው ይህ ወጣት ኢትዮጵያዊ በሚኒሶታ እንዴት እንደሞተ ፖሊስ እያጣራ ያለበት ሁኔታ ሲሆን የቀብር ስነስርዓቱም የፊታችን ሜይ 22 (ግንቦት 20 ቀን 2007) ይፈጸማል::

በሚኒሶታና አካባቢው የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያውያን ወዳጆች በአሳዛኝ ሁኔታ ተገድሎ የተገኘውን ወጣት ወንድማችን ቀብር ስነሥርዓት ላይ እንድትገኙ ጥሪ ቀርቦላችኋል::

ሜይ 22 በሚኒሶታው ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ከቀኑ 12:15 ጀምሮ የፍትሃት ስነስር ዓት የሚደረግ ሲሆን 2:45 ላይ ደግሞ በሜንዶታ ሃይትስ የመቃብር ሥፍራ ሥር ዓተ ቀብሩ ይፈጸማል::

አድራሻውም

2101 Lexington Ave South

Mendota Heights

MN 55120. ነው::

 

 

abyu tekestebirhan

The post በሚኒሶታ ለጊዜው ባልተረጋገጠ ሁኔታ ተገድሎ የተገኘው ኢትዮጵያዊ የቀብር ሥነሥርዓት ዛሬ ይፈጸማል appeared first on Zehabesha Amharic.

መነሻውን ከህውሃት ጉያ ውስጥ ያደረገው የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ታሪክ መፅሃፍና አነጋጋሪው ክህደት

0
0

በሰሜን አሜሪካና በተቀረው ዓለም የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ህብረትethiopian airforce

የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሃሰት ውንጀላ በጅምላ ወደ ህውሃት ማጐሪያ እንዲጋዝ ከተደረገና በኋላም በጨፍጫፊነት ተፈርጆ በአዋጅ ከስራ ውጪ እንዲሆን የፈረደበትን ግንቦት 1983 ዓ/ምን እሳቤ በማድረግ ከምስረታው እስከ አሳዛኝ ብተናው ድረስ የነበረውን ታሪክ በመፅሃፍ መልክ ለማዘጋጀት የተደረገው ጥረት አስርተ ዓመታትን አስቆጥሯል።

በቅብብሎሽ አንዱ በፃፈው ላይ ሌላኛውም እያከለ የተቋሙን ታሪክ ወደ ሙሉዕነት ለመቀየር ከፍተኛ ድካም ተደክሞበታል ። መፅሃፉን አንድ ሰው ያሳተመው ይምሰል እንጂ ባለቤትነቱ በህብረት ነው ።

ከእዚህ ወደ እዚያ ሲንከባለል የቆየው የመፅሃፍ ዝግጅት መነሻ አየር ኃይሉ በደረሰበት ዕጣ ፈንታ በእጅጉ በመቆጨት –

1. የአገር አንድነትን ለማስከበር የተሰዋበትን
2. በአኩሪ ታጋድሎውም በህዝብ ዘንድ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ አክብሮት የተቸረበትን ፣
3. በአሳዛኝ መልኩ ስመጥር ታሪኩን በሬት በመለወስ በትውልድ እንደ ጨፍጫፊና ወንጀለኛ እንዲቆጠር የተደረገበት ሁኔታ ሌት ተቀን እንቅልፍ የነሳቸው የሰራዊቱ አዛውንት አባላት ተሰባስበውና ተማክረው እውነተኛውን ገፅታ ለማቅረብ ጊዜአቸውንና ሃብታቸውን መስዋዕት አድርገዋል ።

ይህንን በጐ ዓላማ ይዞ የተነሳው የታሪክ መፅሃፍ ታትሞ አደባባይ ከመውጣቱና በዚያ ታላቅ የሃገር ሃብት የሆነ የመከላከያ ተቋም ላይ የተወሰደው ፖለቲካዊ ብያኔ የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ስሜትና ቀልብ እንደሚስብ ፣ ሃላፊነት የጐደለውም ፍርደ ገምድላዊ ብያኔ ምን ያክል አገር የማፍረሱ አካል መሆኑን ቁልጭ አድርጐ በማሳየት በስልጣን ላይ ያለውን ዘረኛ ስርዓት ከማሳጣቱ በፊት ፖለቲካዊ ማድበስበስ ተደርጐ ለዳግም ክህደት ተዳርጓል ።

የተቃውሞው መነሻ –

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሙሉዕ ታሪክ ተፅፎ ለትውልድ ቢተላለፍ የሚጠላ አንድም ኢትዮጵያዊ እንደማይኖር ሁሉ ታሪኩ ጐዶሎና በፖለቲካዊ ደባ የተንሸዋረረ እንዲሆን ሲፈረድበት ዝም ብሎ መመልከት ደግሞ ለአገራቸው መስዋዕት የሆኑ ዛሬ ግን እራሳቸውን ሊከላከሉ የማይችሉትን ሰማዕታትንም አገርንም መክዳት ነው ።
የአየር ኃይል ታሪክ በቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ዘመነ መንግስት መመስረቱ ብቻ ሳይሆን በዘመነ ህውሃት/ኢህአደግ ዘመን በውርደት መፍረሱን ፣ በአባላቱም ላይ የደረሰው ወደር የለሽ ሰቆቃና እንግልት ፣ እስርና ረሃብን የማይገልፅ የታሪክ መፅሃፍ ሙሉዕነቱ የተጓደለ ብቻ ሳይሆን እውነትን ፈፅሞ ለመጋፈጥ የሸሸ አሳዛኝ አድርባይነት ይሆናል ።

የአየር ኃይሉን አመሰራረትና የስልጠና ታሪክ ማሳየት ብቻ ሳይሆን አኩሪ ታሪክ የፈፀሙ ጀግኖች እኩሌታው በአሳዛኝ ሁኔታ ከአገር እንዲሰደዱ ተደርጐ ፣ ቁጥሩ ቀላል ያልሆነው ደግሞ በፍርደ ገምድልነት የሞትና የእድሜ ይፍታህ ፍርደኛ ሆነው በመካከላችን ቆመው በሉበት ሁኔታ ፤ ከሁሉም በላይ ድሃዋ ኢትዮጵያ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የደከመችበትንና የሃገር ሃብት የፈሰሰበትን ፣ ሃላፊነት በጐደለው ስርዓት ገደል እንዲገባ የተደረገበትን እንዳላየና እንዳልሰማ በዳሰሳ ብቻ ማለፍ ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል ነው ።

ለመሆኑ በወንጀለኝነትና በጨፍጫፊነት ተወንጅሎ ለነጋሪ እንዳይተርፍ ሆኖ በጅምላ ታስሮ ፣ በሞትና በእድሜ ልክ እስረኝነት ፍርድ የተፈረደበት የአየር ኃይል ታሪክ መነሻውን ከህውሃት ቤተመንግስት እንዴት አደረገ ?

እንዲህ የሚከበርና ለአገርም አለኝታ እንደነበረ የሚተረክለት አየር ኃይል ስለምንስ ዛሬ ድረስ በጅምላ ወንጀለኛ የሚለውን ስም እንዲሸከም ተደረገ ? እንዴትስ አባላቱ የሞትና የእድሜ ልክ ፍርደኛ ሆነው ሊቀሩ ቻሉ ? በምንስ መመዘኛ አየር ኃይሉ በጅምላ ይህንን ያክል ፍዳና መከራ ሲሸከምና ሲከፍል ከዳር ሆነው የተመለከቱት የህውሃት/ኢህአዴግ ባለስልጣናት መፅሃፉ ሲመረቅ በክብር እንግድነት ተስተናገዱ ? ጥቂት ከዘረኛው ስርዓት ጋር የደም ትስስርና ዝምድ ካላቸው የቀድሞው ሰራዊት አባላት በስተቀረ ብዙሃኑ ተወንጃይ የአየር ኃይል አባላትስ የታሉ ? እንዴትስ የዚህ የተወነጀለው አየር ኃይል አባላትና የቀድሞው ስርዓት ጀነራል መኰንኖች የቤተ መንግስት ደጃፍ ያለከልካይ ክፍት ሆነላቸው ?

እነዚህን የመሳሰሉትን ሁሉ ያላገናዘበና ምላሽ ያልሰጠ ፣ ይልቁንም ዘረኛው ስርዓት በጐ እንደሚሰራ ለማስመሰል የሚደርግ ርካሽ የልወደድ ባይነት የተንፀባረቀበት ሆኖ አግኝተነዋል ።

አሁንም ታሪኩ ለትውልድ እንዲተላለፍ የሚደረገውን ጥረት እያደነቅን ነገር ግን ምስረታውንና እድገቱን ለመዘከር የደፈርነውን ያክል በአሳዛኝና ኃላፊነት በጐደለው መልኩም እንዲፈርስና እንዲወድም መደረጉንም ለመግለፅ ድፍረቱ ያስፈልገናል እያልን የህውሃትን ቡራኬ ለማግኘት ሲባል ብቻ ይህንን ታላቅ ዓላማና ስራ ወስዶ ህውሃት ጫማ ስር ማዝረክረኩን አጥብቀን እየተቃወምን ይህ የማይሆን ከሆነ ግን የቀድሞውን የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት ያላማከረና ያልወከለ ተግባር በመሆኑ አጥብቀን እናውግዛለን ።

በሰሜን አሜሪካና በተቀረው ዓለም የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ህብረት

The post መነሻውን ከህውሃት ጉያ ውስጥ ያደረገው የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ታሪክ መፅሃፍና አነጋጋሪው ክህደት appeared first on Zehabesha Amharic.

የዞን 9 ማስታወሻ

0
0

zoneeጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ምርጫውን አስመልክቶ ከአልጀዚራ ቴሌቭዥን ጋር ቆይታ ባደረጉበት ወቅት በተደጋጋሚ ስለዞን9 ጦማርያን አና ሶስቱ ጋዜጠኞች ተጠይቀው በጥቅሉ የሚከተሉትን ምላሾች ሰጥተዋል፡፡
1. ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር አንደሚሰሩ እርግጠኞች ነን ብሎገርነት ስም ሽፋን ነው
2. ፓርላማ በሽብር ከመደባቸው ድርጅቶች ጋር እንደሚሰሩ ማስረጃ አለኝ የድርጅቱን ስም ግን አሁን አልናገርም ምክንያቱም የፍትህ ሂደቱ ላይ ተጽእኖ ላመጣ እችላለሁ
3. ከሽብርተኛ ድርጅት ጋር ላለመስራታቸው (ለፍርድ ቤቱ) ማስረዳት አለባቸው
4. አንድ ዓመት እስር ለሽብር ህግ ምንም ማለት አይደለም

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር አስመልክቶ ከዚህ በፊት በእስር ላይ ከሚገኙት ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ግልጽ ደብዳቤ የጻፍን ቢሆንም ጠቅላይ ሚንስትሩ በዛሬውን ንግግራቸው የተለመደውን የአመክንዮ፣ የሃቅ እና የህግ ስህተቶች ፈጽመዋል

1. የዞን9 ጦማርያን የሽብርተኛ ድርጅት አባል ለመሆናቸው የቀረበባቸው ምንም የአባልነት ማስረጃ የለም ፡፡ ፍርድ ቤት ላይ የቀረቡ ማስረጃዎችም ይህንን አያስረዱም ፡፡
2. በፍርድ ቤት የተከሰስነው የግንቦት ሰባት እና የኦነግ አባልነት መሆኑ በግልጽ ተቀምጦ ሳለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚስጥር ማስመሰላቸው ጉዳዩ ላይ እውቀት አንደሌላቸው ያስረዳል፡፡
3. በመሰረታዊ የህግ መርሆ መሰረት ከሽብርተኛ ድርጅት ጋር አለመስራታችንን ማስረዳት ሳይሆን መንግስት በአቃቤህግ በኩል ወንጀል መስራታችንን ነው ማስረዳት ያለበት ፡፡ የማስረዳት ሸክሙን እኛ ላይ በመጣል መሰረታዊ የህግ ጥሰት ከመፈጸማቸውም ውጪ መንግሰታቸው የሚሰራበትን “ሁሉም ሰው ወንጀለኛ ነው ወንጀለኛ አለመሆኑን ማስረዳት አለበት” የሚል ትችት የሚሰነዝሩ ዜጎችን አንደወንጀለኛ የማየት አቅጣጫ ፍንትው አድርጎ ያሳያል ፡፡ በዚህም ወጣት የህግ ባለሞያዎች እንዳሉበት ስብስብ አፍረናል፡፡
4. መሰረታዊ የሆነው አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብት በተራዘመ ምርመራ እና የፍርድ ቤት ቀጠሮ መጉላላት መጣሱ መንግስትን አንደማያሳስበው ማየታችን አሁንም አሳፍሮናል፡፡ አገራችን በፈረመቻቸው አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ህጎች መሰረት አፋጣኝ ፍትህ ማግኘት የዜጎች መብት ሲሆን የመንግሰት ከፍተና አመራረር ያለምንም ማፈር የመብት ጥሰቱን መከላከላቸው አስገራሚ ነው ፡፡

በመሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሰት ባለስልጣናት ያልተፈረደባቸውን ተከሳሾች ሽብርተኛ በማለት መፈረጃቸው አንዲያቆሙ ፣ መሰረታዊ የወንጀል ህጎቸን አንዲያከብሩና አንዲያስከብሩ ልናሳስብ አንወዳለን፡፡

የዞን9 ጦማርያንም ሆነ ወዳጅ ጋዜጠኞች በምንም አይነት ወንጀል ተሳትፈው የማያውቁ ሲሆን ክሳቸውም ፓለቲካዊ ነው ፡፡ ተከሳሾቹን በነጻ ማሰናበት ለመንግሰት በጣም ቀላሉ ችግሩን የመፍቻ መንገድ ነው ፡፡

ስለሚያገባን እንጦምራለን!
ዞን 9

The post የዞን 9 ማስታወሻ appeared first on Zehabesha Amharic.

ምርጫ ውጤታማ የሚሆነው አስፈፃሚዎቹ ከወገንተኝነት ሲፀዱ ነው –ትዝታ በላቸው

0
0

29B7870E-08AB-41FB-B990-96E2A689EBC0_w640_r1_s_cx0_cy31_cw0“ምርጫ ዓለምአቀፍ ተቀባይነት ያለው የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገለጫ ነው። አንድ ሃገር ነፃ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማካሄድ የሥልጣን ዝውውር ካላደረገ ዴሞክራሲያዊ ተብሎ ሊገለፅ አይችልም” ዶክተር ዓለምአንተ ገብረሥላሴ ስለ ምርጫ ምንነትና መገለጫዎቹ በሰጡትን ትንተና ነው ይህንን ያሉት።

“ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማለትም አንድ ሕዝብ በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት የሥራ ክንውኖች ጥሩውን ከመጥፎው ለይቶ የሚገመግምበት፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሥልጣን ይገባናል የሚሉ አዳዲስ ተወዳዳሪዎችን የፖለቲካ ፕሮግራም መርምሮ ለራሱ የሚበጀውን በማመዛዘን ውሣኔ የሚሰጥበት ሥርዓት ነው” ብለዋል ዶ/ር ዓለምአንተ።

“አንድ ምርጫ ውጤታማ የሚሆነውም የምርጫ አስፈፃሚ አካላት ከወገንተኝነት የፀዱና የዴሞክራሲያዊ ምርጫ መሥፈርቶችን ሁሉ በማሟላት ሕዝቡን ወክለው ሲሠሩና የምርጫ ውጤት ምንም ይሁን ምን ተወዳዳሪዎች የሕዝቡን ውሣኔ ሲቀበሉ ነው” ብለዋል።

ዶክተር ዓለምአንተ ገብረሥላሴ ለሃያ ዓመታት ያህል ዩናይትድ ስቴትስ ቨርጂንያ ግዛት በሚገኘው ዊልያም ኤንድ ሜሪ ኮሌጅ ሕግና ሕገ መንግሥትን አስተምረዋል፡፡ አሁን ጡረታ ላይ ናቸው።

ዕሁድ፤ ግንቦት 16 ኢትዮጵያ ከምታካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ዋዜማ ትዝታ በላቸው ሰለ ነፃ ምርጫ ፋይዳና መገለጫዎቹም አነጋግራቸዋለች።

ለሙሉው ውይይት የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Source:: voanews

The post ምርጫ ውጤታማ የሚሆነው አስፈፃሚዎቹ ከወገንተኝነት ሲፀዱ ነው – ትዝታ በላቸው appeared first on Zehabesha Amharic.


ኢህአዴግ ሆይ ነቄ ነን ተቀየስ! – ርዕዮት አለሙ- ከቃሊቲ እስርቤት

0
0

አራት ሆነን ወደምንኖርበት የአሁኑ የማግለያ ክፍል ከመግባቴ በፊት በርካታ እስረኞች በተለምዶ የአራድኛ ቃላት የሚባሉትን በመጠቀም ሲነጋገሩ የመስማት እድል ነበረኝ፡፡ ለርዕሴ የመረጥኳቸው ቃላትንም ያገኘሁት ከነሱው መሆኑን መግለፅ ይኖርብኛል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፤ አንዳንድ እስረኞች የሚፈልጉትን አንዳች ነገር ለማግኘት በጉልበታቸው ወይም ጤፍ በሚቆላ ምላሳቸው ይጠቀማሉ፡፡ ሀይልን በመጠቀም ያስገድዳሉ ወይም ያታልላሉ ማለት ነው፡፡ እንዲህ አይነቶቹ እስረኞች እንደለመዱት ለማድረግ ሲሞክሩ አንዳንዴ ደፋርና የማይታለሉ እስረኞች ላይ ይወድቃሉ፡፡ እናም ለማታለል ወይ ለማስገደድ የሞከረች ባለጌ የሚጠብቃት መልስ “ነቄ ነን እባክሽ! ተቀየሽ! ንኪው!”የሚል ይሆናል፡፡ እኛን ማታለልም ሆነ ማስፈራራት ስለማትችይ ይቅርብሽ፡፡ ዞርበይልን እንደማለት ነው፡፡ ኢህአዴግም እያደረጋቸው ያለው የማታለል ሙከራዎችና ተገቢ ያልሆኑ የሀይል እርምጃዎች ተመሳሳይ ምላሽ ሊያሰጡት እንደሚገባ አምናለሁ፡፡ የዘንድሮውን ምርጫ ለማለፍ ከወትሮው በከፋ ሁኔታ እየሄደባቸው ያሉት እነዚህ ሁለት ጠማማ መንገዶች መጨረሻቸው አውዳሚ ነው፡፡ በመሆኑም “ኢህአዴግ ሆይ ነቄ ነን ተቀየስ!” በማለት እኛና ሀገራችንን ይዞ ወደጥፋት እያደረገ ያለውን ግስጋሴ መግታት ይገባል፡፡
reeyot alemu
ጠማማ መንገድ አንድ የፈሪ ዱላውን የመዘዘው ኢህአዴግ ኢህአዴግ የተቃዉሞ ድምፆችን በሰማበት አቅጣጫ ሁሉ ዱላውን ይዞ የሚሮጥና ያለሀሳብ የፈሪ ምቱን የሚያሳርፍ ደንባራ መሆኑን በተደጋጋሚ በተግባር አይተናል፡፡ በሰሜን አፍሪካ አመፅ ተቀሰቀሰ ሲባል ለአመፅ ምክንያት የሚሆኑ ድክመቶቹንና ጥፋቶቹን ከማስወገድ ይልቅ ነቅተው ሊያነቁብኝ ይችላሉ ብሎ የጠረጠረንን ጋዜጠኞችንና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን ለእስር መዳረጉ ከቅርብ ጊዜ ተዝታዎቻችን ውስጥ ይጠቀሳል፡፡ የሩቁን ብንተወው እንኳ ማለት ነው፡፡ በሀይማኖት ተቋማት ውስጥ እንኳ ሳይቀር ገብቶ ያለአግባብ ያሰራቸው የሙስሊም ሀይማኖት መሪዎችና አማኞች የማደናበሩ ማሳያዎች ናቸው፡፡ ካለፈው አመት ጀምሮ የምርጫውን ዝግጅት ማድረግ የጀመረው እንደለመደው ከሱ የተለየ ሀሳብ የሚያንፀባርቁ ጋዜጦችንና መፅሔቶችን በመዝጋትና፣ ጋዜጠኞችንና ፖለቲከኞችን በማሰርና በመደብደብ ነበር፡፡ በምሳሌነት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንና የሶስቱን ጋዜጠኞች ጉዳይ ማንሳት ይቻላል፡፡ ዘንድሮ ደግሞ ኢህአዴግን በድፍረት በመሄስ የሚታወቀውን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ጨምሮ ምርጫ ቦርድን በመጠቀም ያለአግባብ ከፓርቲያቸው እንዲገለሉ ያደረጋቸውን የአንድነት ፓርቲ አባላትን በግፍ ማሰሩን ተያይዞታል፡፡ በተመሰረቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለኢህአዴግ ፈተና የሆኑበት ደፋሮቹ የሰማያዊ ወጣቶችም የኢህአዴግ ሰለባ እየሆኑ ነው፡፡ የየትኛውም ፓርቲ አባላት ያልሆኑና ቅሬታቸውን በተለያዩ መድረኮች ያሰሙ በርካታ ግለሰቦችም ተመሳሳይ እጣ ገጥሟቸዋል፡፡ ኢህአዴግ ይሄን ሁሉ የፈሪ ዱላውን እያዘነበ የሚገኘው በሚወስዳቸው እርምጃዎች ከተቃዉሞ ድምፆችና እንቅስቃሴ የሚገላገል እየመሰለው ነው፡፡ እንደተሳሳተ ማን ቢነግረው ይሻል ይሆን? የራሱን ዜጎች ማክበር ስለማይሆንለት የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንድትነግርልን ብናደርግ ሳይሻል አይቀርም፡፡

ለማንኛውም የሚኒስትሯን ጉዳይ ለጊዜው እንተወውና በሀገራችን ዴሞክራሲ ሰፍኖ ለማየት የቆረጥን እኛ ግን ከትግላችን ለሰከንድም ቢሆን እንደማናፈገፍግና በዚህም ምክንያት የሚደርስብንን ሁሉ ለመቀበል ፍቃደኞች እንደሆንን ልንነግረው ያስፈልጋል፡፡ “ኢህአዴግ ሆይ እየበዛኸው ያለኸው ግፍና በደል ይበልጥ ጠንካሮች ያደርገናል እንጂ አንተ እንደፈለከው አያንበረክከንም ነቄ ነን ተቀየስ” ልንለውና ጥንካሬያችንንም በተግባር ልናሳየው ይገባል ጠማማ መንገድ ሁለት “አይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛቹ” ማለትን የሚወደው ኢህአዴግ ኢህአዴግ እንደጠቀስኳቸው አይነቶችና ሌሎች የሀይል እርምጃዎችን በአብዛኛው የሚወስደው ሊያሞኛቸው እንደማይችል በተረዳው በነቁ ሰዎች ላይ ነው፡፡ እንዳልነቅ የገመታቸውን ደግሞ እንደጨለመባቸው እንዲቀሩ የሚያደርግ የሚመስለውን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ያዘጋጅላቸዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ታዲያ ይሄ ግምቱ ግቡን መምታቱ ይቀርና እንደሚያታልላቸው እርግጠኛ በሆነባቸው ዘንድ ሳይቀር መሳቂያ ሲያደርገው ይስተዋላል፡፡ ሌሎቹን ትቼ ለምርጫው ካዘጋጃቸው ማታለያዎቹ ውስጥ እጅግ በጣም ጥቂቶቹን ላንሳ፡፡ 2.1 ተቃዋሚዎች አማራጭ የላቸውም፡፡ በተለይ በዘንድሮው ምርጫ ጆሮአችን እስኪያንገሸግሸው ድረስ ኢህአዴግ ሊግተን ከሞከራቸው ሀሳቦች ውስጥ “ተቃዋሚዎች አማራጭ የላቸውም” የሚለው ዋነኛው ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ በእውነተኛና ጠንካራ ተቃዋሚዎች ላይ እየፈፀመ ያለውን ደባ የሚያውቅ ሁሉ ይሄ ሀሳብ በውስጡ በርካታ ሴራዎችን የያዘ መሆኑን ይረዳል፡፡ እንዴት ማለት ጥሩ! ኢህአዴግ ሰራኋቸው ብሎ የሚመፃደቅባቸውን ስራዎች በሙሉ ከነድክመቶቻቸውም ቢሆን መስራት የጀመረው ባለፉት አስርት አመታት መሆኑ ይታወቃል፡፡

ዕድሜ ለ1997ዓ.ም የተቃዋሚዎች ድንቅ አማራጭና እንቅስቃሴ! ከዚያ በፊትማ ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ነበር፡፡ በዚያ የምርጫ ወቅት ከተቃዋሚዎች ጋር ባደገረው ክርክሮች ባዶነቱ የታየበት ኢህአዴግ ራቁቱን ከመሸፈን ይልቅ ተቃዋሚዎችን መግፈፍ መፍትሔ አድርጎ ወሰደ፡፡ ያለፉትን አስር አመታት ሙሉ ጠንካራ አማራጭ ያላቸውንና በሀሳብ የተገዳደሩትን ፓርቲዎች በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የማፍረስ፣መሪዎችን የማሰርና የማሳደድ እርምጃዉን ገፋበት፡፡ በዚህ ድርጊቱም በርካታ ጠንካራ ፖለቲከኞችን ከጫዋታ ዉጪ አደረጋቸው፡፡ ባደረሰባቸው ከባድ ኩርኩም ተቃዋሚዎችን ድንክ እንዳደረጋቸው እርግጠኝነት የተሰማው ገዢው ፓርቲ “ተቃዋሚዎች አማራጭ የላቸውም” ብሎ ለመፎከር በቃ፡፡ ድሮስ በራሱ የማይተማመን ሰው ሁሌም ትልቅ ለመምሰል የሚሞክረው ጠንካሮችን በማስወገድና በደካሞች ራሱን በመክበብ አይደል? የተቃዉሞው ሰፈር በየቀኑ ከኢህአዴግ በሚሰነዘርበት የሀይል ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት አያጠያይቅም፡፡ ሆኖም ዛሬም ቢሆን የኢህአዴግ ባለስልጣናት ጉንጫቸው እስኪቀላ ድረስ የሚገዳደሩና መልስ የሚያሳጡ ሰዎች አላጣንም፡፡ የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ እንዲሉ ኢህአዴጎች ግን “ተቃዋሚዎች አማራጭ የላቸውም” የሚለዉን ነጠላ ዜማቸውን ለማቆም አልፈለጉም፡፡ ጠንካራ አማራጭ ያላቸውን ከጎዳናው ላይ በማስወገድ ብቸኛ ባለአማራጭ ሆነው ለመታየት በተግባር የሚያደርጉትን ሙከራ ማጀቢያ ሙዚቃ መሆኑ ነው፡፡ በመሆኑም “ኢህአዴጎች ሆይ ነቄ ነን ተቀነሱ!” ብለን ልናስቆማቸው ይገባል፡፡ 2.2 በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ምርጫ ይሄ ምርጫ አልፎ ከመስማት ልገላገላቸው ከምፈልገው ሸፍጥ የተሞላባቸው የኢህአዴግ ፕሮፓጋንዳዎች አንዱ “የምርጫ ቅስቀሳውና ክርክሩ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ምርጫ ለማካሄድ እንደረዳቸው የእንትን ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ” የሚለው ይገኝበታል፡፡

አስቀድሜ እንደገለፅኩት ገዢው ፓርቲ ተቃዋሚዎች አማራጭ እንደሌላቸው ደጋግሞ ነግሮናል፡፡ እንግዲህ በዚህ ስሌት መሰረት ከሄድን እየተፎካከሩ ያሉት ባለአማራጭ ኢህአዴግና አማራጭ የሌላቸው ተቃዋሚዎች ናቸው ማለት ነው፡፡ ከውድድሩ ሜዳ ላይ ሊገዳደሩት የሚችሉትን ሁሉ ለማስወገድ የሞከረው ኢህአዴግ በሱ ቤት ብቸኛና ምርጥ ቀስቃሽ የሆነ መስሎታል፡፡ “በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ምርጫ” እያለ የሚያደረቁረንም ለዚህ ነው፡፡ አይ ኢህአዴግ! በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ምርጫ እንዲካሄድ እንደማይፈልግ ተግባሩ እንደሚመሰከርበት እንኳ አይታየውም፡፡ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ፡፡ በገዢው ፓርቲ የሚሽከረከሩ የሚዲያ ተቋማት የተቃዋሚ ፓርቲዎችን የምርጫ ቅስቀሳ ሳያስተናግዱ የቀሩባቸው ግዜያት ነበሩ፡፡ ህገመንግስቱ ገለልተኛ መሆናቸውን የገለፀውን ተቋማት ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ይዘት ያለው ቅስቀሳ ነው በሚል፡ አሳዛኝና አስቂኝ ምክንያት! እንደምርጫ ቦርድ፣ ፍርድቤትና የመሳሰሉት ያሉትን ገለልተኛ መሆን የሚገባቸውና በተግባር ግን ሆነው ያልተገኙ ተቋማትን መሞገት እንኳን የማይችል ተቃዋሚ መፈለግ ምን የሚሉት አምባገነንነት ነው? ሁሉም ነገር በአንድ በእርሱ የተበላሸ መስመር እንዲሄድ የሚፈልግና የተለዩ ሀሳቦችን ለማስተናገድ ያልፈቀደ ፓርቲ የሚያካሂደው ምን አይነት በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ምርጫ እንደሚሆን አይገባኝም፡፡ ፅድቁ ቀርቶ በወጉ በኮነነኝ እንዲሉ በመጀመሪያ ደረጃ ለውጥ የምንፈልግበት ምክንያት በዋናነት ያን ያህል ምሁራዊ ንድፈሀሳቦችን የሚጠይቅና የተወሳሰበም አይደለም፡፡ ኢህአዴግ ሆይ አይደለህም እንጂ ጎበዝ ተከራካሪ ብትሆን እንኳ እንደሰውና እንደዜጋ የመኖር መብታችንን የገፈፍክ አምባገነን ሆነህ ሳለ አፈጮሌ ስለሆንክ ብቻ እንድታስተዳድር የምንፈልግ ጅሎች መስለንህ ከሆነ ተሳስተሀል፡፡ ነቄ ነን አልንህ እኮ! 2.3 ከ “የህዝቡን ድምፅ መቀበል” እስከ “አስፈላጊው እርምጃ” የምርጫውን መቅረብ ተከትሎ ኢህአዴግ እየነገረን ያለው ሌላው ጉዳይ የህዝቡን ድምፅ መቀበል እንደሚገባ ነው፡፡ ድምፄ ይከበርልኝ ብሎ አደባባይ የወጣን ህዝብ በመግደል ስልጣኑን በደም ያራዘመው ኢህአዴግ ይሄን ለማለት ምን የሞራል መሰረት አለው? ፈፅሞ ሊኖረው አይችልም፡፡

ነገሩ ወዲህ ነው፡፡ ኢህአዴግ አጭበርብሮም ሆነ በስልጣን ለመሰንበት ማንኛቸውንም ጉዳይ ፈፅሞ ካበቃ በኋላ በምርጫ ቦርድ “አሸናፊነቱ” ሲታወጅለት የህዝቡ ድምፅ እንደሆነ ተቆጥሮ እንዲወሰድለት ይፈልጋል፡፡ ስቴድየም “ድሉን” ምክንያት በማድረግ በሚያዘጋጀው ዝግጅት ላይም “መሾምና መሻር ለሚችለው የህዝቡ ሉአላዊ ስልጣን ” እጅ ለመንሳትም በእጅጉ ቋምጧል፡፡ የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትሪያችን እንደ ቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኮፍያቸውን አንስተውና ከወገባቸው ዝቅ ብለው ላልመረጣቸው ህዝብ “የእንኳን መረጥከን” ምስጋና ሲያቀርቡ እንደምናይ ለመገመት እደፍራለሁ፡፡ ይሄንን ድርጊት ለማሰናከል የሞከረ ሰው ደግሞ “አስፈላጊዉ እርምጃ” እንደሚወሰድበት አንዴ ኮሚሽነር፣ ሌላ ጊዜ ምክትል ኮሚሽነር ሲያሻው ደግሞ በርካታ ኮማንደሮችን ዋቢ እያደረገ ሰሞኑን ኢብኮ ሊያስጠነቅቀን ሞክሯል፡፡ ከፍተኛ መኮንኖቹም በቂ ትጥቅ እንዳሟሉና ከ2006ዓ.ም ጀምሮ ዝግጅት ሲያደርጉ እንደከረሙ በኩራት ሊነግሩን ሞክረዋል፡፡ ዝግጅታቸው ለእውነተኛ የሀገር ጠላትና አሸባሪ ቢሆን ኖሮ ኩራታቸው ኩራታችን ይሆን ነበር፡፡ ግን ዝግጅታቸው ለኢህአዴግ ተቀናቃኞች መሆኑን በሚገባ ስለምናውቅ ስሜታቸውን ልንጋራቸው አልቻልንም፡፡ ኢብኮ ከመኮንኖቹ ንግግር መሀል እያስገባ ሲያሳየን የነበረው የታጣቂና የትጥቅ ብዛትም የ “አርፋቹ ተቀመጡ” መልዕክትን ያዘለ ነው፡፡ በእኔ በኩል ለውጥ ያለፅናት ሊታሰብ እንደማይችልና ቦግ ድርግም በሚል አይነት ትግል ድል እንደማይገኝ ስለማምን ሁሌም በመስመሬ ላይ ነኝ፡፡ በትግሉ ውስጥ ያሉትን ሁሉ የምመክረውም ይሄንኑ ነው፡፡ ይሄ አቋማችን ህይወታችንን እስከመስጠት የሚያደርስ መስዕዋትነት ሊጠይቀን እንደሚችል አሳምሬ አውቃለሁ፡፡ ለሀገራችንና ለህዝቡ መልካም ለውጥ ለማምጣት እስከሆነ ድረስ ይሁን፡፡ ነገር ግን በትግሉ ውስጥ ያላችሁትን ሁሉ ትግሉን ወደፊት ሊያራምድ ከማይችልና ኢህአዴግን የበለጠ ስልጣን ላይ እንዲደላደል ከሚያደርግ አጉል መስዕዋትነት እንድትቆጠቡ አደራ እላለሁ፡፡ የምታደርጉት እንቅስቃሴ የተጠና፣ የለውጥ ሀይሎችን በሙሉ በአንድነት ያሰባሰበ፣ ቀጣይነት ያለውና በተቻለ መጠን አደጋን የሚቀንስ እንዲሆን ያስፈልጋል፡፡

ይሄንን በማድረግ ትግሉን ሊያስቆም ወይም ደግሞ የጅምላ እስርን ሊፈፅምና ሀገራችንን በደም አበላ ሊነክር የተዘጋጀውን ኢህአዴግ የትኛውም ፍላጎቱ ቢሆን እንዲሳካ ባለመፍቀድ “ነቄ ነን ተቀየስ! ” ልትሉት ይገባል፡፡ በመጨረሻም ኢህአዴግን “ነቄ ነን ተቀየስ” ልንልባቸው የሚገቡንና ሌሎችንም እንዲነቁበት ማድረግ የሚገባን በርካታ ጉዳዮች ቢኖሩም ያለሁበት ሁኔታ ብዙ ለመፃፍም ሆነ እናንተጋ እንዲደርስ ለማድረግ ፈፅሞ አመቺ አይደለም፡፡ አሁን አሁንማ የምርጫውን መቃረብ አስመልክቶ የሚፈትሹኝ፣ የሚያጅቡኝ ሆነ ቤተሰብ የሚያገናኙኝ በሙሉ የህወሓት ሰዎች ብቻ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ ራሱን የብሔረሰቦች መብት አስከባሪ አድርጎ የሚያቀርበው ገዢው ፓርቲ ምነው እኔን ለመፈተሽና ለመጠበቅ እንኳ ሌሎቹን ብሔረሰቦች ማመን አቃተው?የፖለቲካ እስረኛ የሆኑ ወገኖችም ላይ ተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚፈፀም ይገባኛል፡፡ ኢህአዴግ እንዲህ ከሚያደርግበት በርካታ ምክንያቶች አንዱ ሌላው የህብረተሰብ ክፍል የትግራይ ወገኖቹ ላይ ጥርጣሬና ጥላቻ እንዲያድርበት ለማድረግ እንደሆነ እገነዘባለሁ፡፡ የትግራይ ህዝብ ሌላው ብሔረሰብ በጥሩ አይን አያየኝም የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲኖረውና ሳይወድ በግዱ የህወሓት ባርያ ሆኖ እንዲቀር መሆኑ ነው፡፡ አይ ኢህአዴግ! ፓርቲና ህዝብ መለየት የምንችል ነቄዎች መሆናችንን ረሳኸው እንዴ? የትግራይ ልጆችም ቢሆኑ ሴራህ ገብቷቸው አብረውን እየታገሉህ በመሆናቸውና ያልነቁትንም እያነቁ በመሆናቸው የሚሳካልህ አይመስለኝም፡፡ እንደው እንደው ግን እናንተዬ ከላይ የጠቀስኩት ከፋፋይ ባህርይው ብቻ እንኳን ኢህአዴግን ለመታገል ከበቂም በላይ ምክንያት አይሆንም? ይሆናል እንደምትሉኝ አውቃለሁ፡፡ በመሆኑም ይሄን በዜጎች መሀከል ጥላቻን ለመዝራት የሚሞክር መርዘኛ መንግስት ከትከሻችን ላይ አሽቀንጥሮ ለመጣልና ነፃነታችንን ለማወጅ በአንድ ላይ እንቆም ዘንድ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

The post ኢህአዴግ ሆይ ነቄ ነን ተቀየስ! – ርዕዮት አለሙ- ከቃሊቲ እስርቤት appeared first on Zehabesha Amharic.

ፍርሃትን ድል የነሳ ታጋይ ሕዝብ!!! ቅዳሜ ግንቦት 15/2007 ድምጻችን ይሰማ!

0
0

ferehat
አምባገነን ስርዓቶች የህዝብን ጥያቄ በመመለስና ብሶቱን በማድመጥ ህዝብ ዘንድ ከመከበርና ከመወደድ ይልቅ የህዝብን ጥያቄዎች በሀይል በማፈንና ለብሶቱ ምላሻቸውን ሌላ ብሶት የሚፈጥር በደል በማድረግ መፈራትን ይመርጣሉ፡፡ አምባገነኖች ቀና ብሎ የሚሄድ፣ ብሶቱን በአደባባይ የሚያሰማ፣ ግዴታዎቹን በማክበር መብቱን የሚጠይቅ ህዝብ ፈፅሞ አይሹም፡፡ ይልቁንም የሰጡትን የሚቀበል፣ የከለከሉትን የማይጠይቅ፣ የተናገሩትን ሁሉ እውነት ብሎ የሚቀበልን ህዝብ ለመፍጠር የፍርሀትን ድባብ በሁሉም አቅጣጫ ይዘረጋሉ፡፡

አሕባሽ ከተሰኘው መንግስታዊው እስልምና መምጣት በኋላ «የሀይማኖት ነፃነታችን በህገ-መንግስቱ መሰረት ይከበር!» ሲል አደባባይ የወጣው ህዝበ ሙስሊም አምባገነኖች የዘረጉትን የፍርሀት አጥር ማለፍ ችሏል፡፡ከመነሻው ህዝቡ ተቃውሞውን እንዲገታ ማስፈራሪያዎች የነበሩ ቢሆንም ህዝበ ሙስሊሙ ለእምነቱ ያለው ቀናዒነት የፍርሀት ድባቡን ማፍረስ አስችሎታል፡፡ መንግስትን ህዝባዊ ወኪሎቻችንን ጠርቶ እንዲያወያይ ያስገደደው ይኸው በፍርሀት ያልተለጎመው የሙስሊሙ አንደበት ነው፡፡

የፍርሀት ድባቡን አልፈው የህዝብን ሀላፊነት ከዳር ለማድረስ ያለ እረፍት ሲደክሙ የነበሩ ኮሚቴዎቻችን ደግሞ በአንጻሩ ለህዝቡ ተጨማሪ ጀግንነትን ያላበሱ ህያው ተምሳሌቶች በመሆናቸው ነበር የከፋ የበደል በትር ያረፈባቸው፡፡ በፍርሀት የማይሸበቡ፣ ቀና ብለው ተራምደው ለሌሎች ቀና ማለት ምሳሌ የሚሆኑ መሪዎች ያሉት ትግል መዳረሻ ድል መሆኑን በመረዳትም ነው ህዝብን ከመሪዎቹ ለመነጠል የሞከሩት፡፡ በተደጋጋሚ አስከፊ ጥቃቶችን በመፈፀም በህዝብ ሙስሊሙ ልቦና ውስጥ የሚዘዋወረውን የፍርሀት አልበኝነት ስሜት በፍርሀት ለመቀየር ጥረት አድርገዋል፡፡ በኮሚቴዎቻችን እና ለዚህ ህዝባዊ የመብት እንቅስቃሴ በጎ አመለካከት ባላቸው ላይ በየእስር ቤቱ የተፈፀመው ግፍ በአደባባይ «መብቴ ይከበርልኝ!» ሲል እያስተጋባ ያለውን ህዝበ ሙስሊም አንደበት ለመለጎም የታሰበ ነበር፡፡ ግና የሆነው በተቃራኒው ነው። የእነርሱ ግፍና በደል በበረታ ቁጥር የህዝብ ወኔ፣ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት እየጨመረ በመሄድ ሊፈጥሩ ሲሞክሩ የነበሩትን የፍርሀት አጥር መናድ ችሏል፡፡

በተቆጣጠሯቸው የህዝብ ሚዲያዎች የሚተላለፉት መሰናዶዎች በዋነኝነት ዓላማ ያደረጉት ህዝበ ሙስሊሙን ማሸማቀቅና አንገት ማስደፋት፣ ብሎም የፍርሀት ማቅን ተከናንቦ ከጀመረው የእምነት ነፃነቱን በህገ-መንግስቱ መሰረት የማስከበር ሰላማዊ ትግል እንዲያፈገፍግ ማድረግን ነው፡፡ እነዚህ ፍርሀትን እንዲወልዱ ተጠንቶባቸው የሚሰሩ ዝግጅቶች ለእምነቱ ባለው ቀናዒነት የደነደነውን ልቡን አልፈው መግባት ግን አልቻሉም፡፡ በስም ማጥፋቱ፣ በእስሩ፣ በድብደባው፣ በግድያው ማግስትም ድምፁን ከማሰማት ወደኋላ ባለማለት ፍርሀትን ማሸነፉን አመላክቷል፡፡ አምባገነኖች የሚፈጥሩትን የፍርሀት ድባብ ድል የነሳ ህዝብ ዘወትር ቀና ብሎ ይኖራል። የኢትዮጵያ ሙስሊምም በበደል ወጀብ መካከል ለመፍጠር የሞከሩትን የፍርሀት ድባብ ድል ነስቶ ቀና ብሎ እየኖረ በዳዬቹን አሳፍሯል!

ትግላችን በአላህ ፈቃድ እስከድል ደጃፎች ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

The post ፍርሃትን ድል የነሳ ታጋይ ሕዝብ!!! ቅዳሜ ግንቦት 15/2007 ድምጻችን ይሰማ! appeared first on Zehabesha Amharic.

ዓለምነህ ዋሴ የኃይለማርያም ደሳለኝን የአልጀዚራ ቃለምልልስ ይተነትነዋል (ያድምጡ)

0
0


ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከአልጀዚራ ቴሌቭዥን ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ አለምነህ ዋሴ እንደሚከተለው ተንትኖታል:: ክፍል አንድ ከላይ ክፍል ሁለት ደግሞ ከታች ቀርቧል:: አድምጣችሁ አስተያየት ሰጡበት::

ክፍል ሁለት

du_pm_haile_mar_des

The post ዓለምነህ ዋሴ የኃይለማርያም ደሳለኝን የአልጀዚራ ቃለምልልስ ይተነትነዋል (ያድምጡ) appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: 3 ጠቃሚ መረጃዎች ስለ ጉሮሮ ሕመም

0
0

Guroro
(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም)
የጉንፋን ሕመም በሚይዘን ጊዜ የሚከማቸው አክታ ወደ ጉሮሮ በመውረድ የጉሮሮ ሕመምን ያስከትላል፡፡
የጉሮሮ ሕመም በቫይረስ ወይም በባክቴሪያ ኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰት ሲሆን እነዚህ ቫይረስና ባክቴሪያዎች በአፍና በአፍንጫችን አድርገው በመግባትም ጭምር የጉሮሮ ሕመምን ያስከትላሉ፡፡
1.የጉሮሮ ሕመም ምልክቶች ምንድን ናቸው?
✔ የጉሮሮ መከርከር
✔ ለመዋጥ መቸገር
✔ ትኩሳት
✔ ሳል
✔ የራስ ምታት
✔ የምግብ ፍላጎት መቀነስ
✔ የድካም ስሜት መሰማት
✔ ብርድ ብርድ ማለት
✔ በጆሮና እናባንገት አካባቢ ሕመም መሰማት
2. በአንዳንድ ሰዎች ላይ ከላይ ከተጠቀሱት ምልክቶች በተጨማሪ
✔ ማቅለሽለሽ
✔ ማስመለስ
✔ መጥፎ የአፍ ጠረን
✔ የድምፅ መለወጥ
✔ አፈን ለመክፈት መቸገር ሊኖሩ ችላሉ
የጉሮሮ ሕመም ሕክምና ሕመሙን እንዳስከተለው ተህዋስያን ዓይነት ይለያያል፡፡
በቫይረስ ምክንያት የሚመጣን የጉሮሮ ሕመም ሰውነታችን ባለው የበሽታ መከላከል አቅም የሚዋጋ ሲሆን መድኃኒት መውሰድ አስፈላጊ አይሆንም፡፡
በባክቴሪያ ምክንያት የሚከሰትን የጉሮሮ ሕመም ሕክምና ቦታ በመሄድ ባክቴሪያ አጥፊ መድኃኒቶችን (Antibiotics) መውሰድ ተገቢ ነው፡፡
3. ከዚህ በተጨማሪ የሕመሙን ሁኔታ እንዲያስታግስልን፤
✔ በቂ ዕረፍት መውሰድ
✔ ትኩስ ፈሳሽ መውሰድ፡- ሻይ፤ወተት፤አጥሚት
✔ ለስለስ ያሉ ምግቦችን መመገብ፡- ሾርባ
✔ ለብ ባለ ውሃ በጨው እና በዝንጅብል መጉመጥመጥ
✔ ሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን መውሰድ ጠቃሚ ነው፡፡

Tonsillitis is inflammation of the tonsils, two oval-shaped pads of tissue at the back of the throat — one tonsil on each side. Signs and symptoms of tonsillitis include swollen tonsils, sore throat, difficulty swallowing and tender lymph nodes on the sides of the neck.

Most cases of tonsillitis are caused by infection with a common virus, but bacterial infections also may cause tonsillitis.

Because appropriate treatment for tonsillitis depends on the cause, it’s important to get a prompt and accurate diagnosis. Surgery to remove tonsils, once a common procedure to treat tonsillitis, is usually performed only when tonsillitis occurs frequently, doesn’t respond to other treatments or causes serious complications.

Causes

Tonsillitis is most often caused by common viruses, but bacterial infections can also be the cause.

The most common bacterium causing tonsillitis is Streptococcus pyogenes (group A streptococcus), the bacterium that causes strep throat. Other strains of strep and other bacteria also may cause tonsillitis.

Why do tonsils get infected?

The tonsils are the immune system’s first line of defense against bacteria and viruses that enter your mouth. This function may make the tonsils particularly vulnerable to infection and inflammation. However, the tonsil’s immune system function declines after puberty — a factor that may account for the rare cases of tonsillitis in adults.

Risk factors

Risk factors for tonsillitis include:

Young age. Tonsillitis is most common from the preschool years to the mid-teenage years.
Frequent exposure to germs. School-age children are in close contact with their peers and frequently exposed to viruses or bacteria that can cause tonsillitis.

Symptoms

Tonsillitis most commonly affects children between preschool ages and the mid-teenage years. Common signs and symptoms of tonsillitis include:

Red, swollen tonsils
White or yellow coating or patches on the tonsils
Sore throat
Difficult or painful swallowing
Fever
Enlarged, tender glands (lymph nodes) in the neck
A scratchy, muffled or throaty voice
Bad breath
Stomachache, particularly in younger children
Stiff neck
Headache
In young children who are unable to describe how they feel, signs of tonsillitis may include:

Drooling due to difficult or painful swallowing
Refusal to eat
Unusual fussiness
When to see a doctor

It’s important to get an accurate diagnosis if your child has symptoms that may indicate tonsillitis.

Prevention

The germs that cause viral and bacterial tonsillitis are contagious. Therefore, the best prevention is to practice good hygiene. Teach your child to:

Wash his or her hands thoroughly and frequently, especially after using the toilet and before eating
Avoid sharing food, drinking glasses or utensils
To help your child prevent the spread of a bacterial or viral infection to others:

Keep your child at home when he or she is ill
Ask your doctor when it’s all right for your child to return to school
Teach your child to cough or sneeze into a tissue or, when necessary, into his or her elbow
Teach your child to wash his or her hands after sneezing or coughing

The post Health: 3 ጠቃሚ መረጃዎች ስለ ጉሮሮ ሕመም appeared first on Zehabesha Amharic.

የቻለ ፓርላማ ያልቻለ ፓልቶክ ይግባ (ሄኖክ የሺጥላ)

0
0

Birhanu Nega
የሆነው ይህ ነው
ወያኔ-ትግሬ ( የትግራይ ሰው የሆኑ የሀገረ ኢትዮጵያ ብሔር ሽፍቶች ) ፣ ስልጣን ላይ ወጡ ፣ ህዝቡ አጨበጨበ ፣ ሙህራኖች ከሚኖሩበት ሃገረ አማሪካን ፣ እንግሊዝ ፣ ጀርመን ወዘተ፣ ወዘ-ተርፈ ተጏዙ ፣ የተማሩት ሀገራቸውን ሊያገለግሉ ፣ እውቀታቸውን ሊያካፍሉ በየ ትምህርት ተቋማቱ ገቡ ፣ የቻሉት ቤተ- መንግስት ድረስ ዘለቁ ፣ ከያኔው ጠቅላይ ሚንስትር ጋ ተጨባበጡ ፣ ብርጭቆ አጋጩ ፣ አብረው ለመስራት ተስማሙ ፣ እንደውም አንዳንዶች እንደ ቀብድ አማራን የሚኮንን መጽሐፍ ጻፉ ።
ጊዜው ነጎደ ፣ ህውሃት ከተማ ሲገባ ፣ በሰላምና መረጋጋት ስም ሌባ በአደባባይ በመረሸን ፣ በአንቀጽ 39 ስር ፣ በሽግግር መንግስት እና ወዘተ ስር ደብቆት የነበረው ቀንዱ ወጣ ። ከሀገረ አማሪካ ከህውሃት ጋ ለመስራት የሄዱትን ሙህራኖች አሰረ ፣ ውዳሴ ህውሃት ወይም እርግማነ አማራ መጽሐፍ እንደበረከት ያቀረቡለትን አባረረ ፣ ከዚያ ድብድቡ ተጀመረ ።

ቀጠለ ። ታላላቅ የዩንቨርስቲ መምህራንን አባረረ ፣ እነ ዶክተር ታዬ ወ/ሰማ’ትን እና እነ ፕሮፌስር አስራት አሰረ ፣ በላዩ ላይ እኔ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋንና እነ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያምን ጨመረበት ። ጥሉ ከረረ ። አሁንም ቀጠለ ። እነ አንዳርጋቸው ጽጌን ተፋታ ፣ እነ ብርሃነ መዋ እና እነ ክቡር ገናን አብጠለጠለ ። በዚህ ውሃ ውስጥ ሌሎች የኢሰመጉ አመራር አካሎች ፣ የመኢአድ ባለስልጣናት ፣ የሃይማኖት ሰዎች ተበሉ ። ሁኔታው ቀጠለ ፣ ሌባ በአደባባይ ከግንቦት 22 1983 እስከ ዛሬ እየገደለ ያለው ስርዓት ፣ ራሱ የወጣለት ሌባ ሆነ ።

ሲጀመር አብረው ለመስራት ከዚህ ከአማሪካ ተሳፍረው የሄዱት እነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ማርሽ ቀየሩ ፣ ፊታቸውን እስከ ምርጫ 97 በከፊል አዙረው የምርጫ 97 ለት ጎራ ለዩ ። ባንድ ወቅት እጁን የጨበጡትን ጠቅላይ ሚንስቴር ስልጣኑን እንዲለቅ ሞገቱት ፣ ሞግተውትም አልቀረም ዘረሩት ። የዘረሩት ህውሃት ግን ከካርቶን ፌንቱ ተነስቶ የቅንጅት አመራሮችን አሰረ ። እነሱም ባጋጣሚ ባገኙት ድል እንደ ባቢሎን ሰዎች ልሳናቸው ተዘበራርቆ ስለነበር ተቦጫጨቁ ። ኃይሉ ነው ፣ ብርቱካን ናት ፣ ብርሃኑ ነው ፣ ወዘተ ወዘተ ተባባሉ ። ( በነገራችን ላይ ስለዚህ ሁኔታ ሳስብ ዛሬም ድረስ ያሳፍሩኛል ፣ ሀፍረቴ የሚመጣው ደሞ በጥቅምት 22እና 23 1998 በአደባባይ የተገደሉት ልጆች ሰልስት ሳይወጣ እነሱ ንትርክ በመጀመራቸው ነው ) ። በነገራችን ላይ ቀኑን ጠብቀን ” ቅንጅትን ማን አፈረሰው !” የሚል ጽሑፍ እናወጣለን ። በይበልጥ የኔ ብርሃነ መዋ እና የሌሎች የዛሬ ጀግኖቻችን አስተዋጾ ምን እንደነበር እናትታለን ። ምክንያቱም የስራ ልምድ () ማንነትን በደንብ ስለሚገልጥ ። አሁን አላማችን እሱ ስላልሆነ ወደ ዋናው ሃሳብ እንገስግስ ።
ከፈርሱት የቅንጅት አመራሮች ውስጥ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ አማሪካን በመምጣት ፣ በሃሳብ፣ በራእይ፣ ርዮት እና በወዳጅነት አብረው ከዘለቋቸው ሰዎች ጋ በመሆን ግንቦት ሰባትን መሰረቱ ። የግንቦት ሰባት እውቅና በሚድህበት ሰሞናት ፣ ህውሃት ግንቦት ሰባትን ማስተዋወቅ ጀመረ ። አሸባሪ ብሎ ሰየመው። ሊቀመንበሩን እና ሌሎች የማዕከላዊ ኮሚቴ አባሎቹን በአሸባሪነት ከሰሰ ። አሁን ላይ ሆኘ ሳስበው ህውሃት ይህንን ያደረገው የሚመስለኝ ለአንድ ነገር ሲል ነበር ። እንደምናቀው “አሸባሪ እዚህ አገር ታየ!” ብለው ያለ ምንም እውነት የሰው ሀገር እንደሚደበድቡት ምዕራባውያን ፣ ወያኔም ግንቦት ሰባትን የሚፈልገውን ለማሰር እና ለማጥፋት ማሳበቢያ ለማድረግ ነበር ። በዚህም የተንሳ ብዙ የብሔረ አማራ የጦር አዛዦች ከስልጣን ተባረዋል ፣ በየ መአከላዊው ታስረዋል ፣ ተገለዋል ። ብዙ ነጻ ጋዜጠኞች ( ምሳሌ እስክንድር ነጋና እና አንዷለም አራጌ ) ፣ እንደ ዞን 9 ያሉ የድህረገጽ ሞገደኞች ፣ እና ወዘተን ። ( በነገራችን ላይ ህውሃት አሸባሪነትን የማይፈልገውን ትግሬ ያልሆነ ብሔር ከስልጣን ማባረሪያ ምክንያት አድርጎ ሲጠቀም ግንቦት ሰባት የመጀመሪያው ድርጅት አይደለም ፣ እንደውም ከግንቦት ሰባት ቀደም ብሎ ብዙ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ባለስልጣናትን በኦነግ ስምነት አስሯል ፣ ገሏል ፣ ወዘተ )።

ታዲያ በዚህ ሁናቴ ላይ እያለ ነው ህውሃትን የማይመጥን ስህተት የተሰራው ። ግንቦት ሰባትን ከመንግስት ግልበጣ ጋ ያያያዘ ዜና አፈትልኮ ወጣ ። ያቺ ቀን ለግንቦት ሰባት ከፍተኛ የፕሮፖጋንዳ ሥራ ሰርታ አለፈች ። በዛ ውለታው ውስጥ ግን ብዙ የጦር መኮንኖችን መአከላዊ አስገብታ ማሰቃየት ጀመረች ። እንግዲህ በዚህ ሁኔታ ሰሞን ላይ ነው ኢሳት የተመሰረተው ። ( ምን ያህል እውነት እንደሆነ ባላውቅም ፣ ይህንን ኢሳት የሚባለውን ነገር በሃሳብነት ካፈለቁት ሰዎች መሃከል አንዱ አቶ ክንፉ አሰፋ ( የኢትዮጵያ ሚዲያ ፎረም ድህረ ገጽ ዋና አዘጋጅ ) እንደሆነ ሰምቻለሁ ። ምስጋና ሃሳቡን ላፈለቁት ። ሌላ ምስጋና ያንን ሃሳብ ላላባከኑት ! ( ለሰረቁት አላልኩም !) የግንቦት ሰባት ምናባዊ ጥንካሬ ወደ ቁሳዊ ህልውና ቀስ እያለ መቀየር ጀመረ ። በተለይም ትኩስ ሁኔታዎችን ለማብራራት በኢሳት መስኮት ላይ በተደጋጋሚ ብቅ እያሉ አስተያየታቸውን የሚሰጡት ዶ/ ር ብርሃኑ ነጋ ፣ ስለ አስመራ ጉዟቸው እና ቆይታቸው የነገሩን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፣ የራሱ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታሰር ፣ የነ-መሳይ መኮንንና ፋሲል የኔ ዓለም የአስመራ ቆይታ ፣ ጦሩ ፣ ሳንጃው ፣ የግራር ክላሹ እና ወዘተ ነገሩን አሟሟቀው ። ግንቦት ሰባት ከአርበኞች ጋ ተዋሐደ ፣ ኢሳት እያንዳንዷን ነገር አስተላለፈ ። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ወጣቶች ይህንን መጀመሪያ መስማት ከዚያ ማዳመጥ ጀመሩ ። አንዳንድ ወዳጆቼ (የማቃቸው እና የማላውቃቸው ሰዎች ) ፣ በየት በኩል ጫካ ልግባ የሚል ጥያቄ ያጎርፉልኝ ጀመር ። ታዲያ በዚህ ሁኔታ ላይ እያለን ፣ ከዚህም ሁኔታ ቀደም ብሎ ፣ ምርጫ 2007 ድሆ ድሆ ከተፍ አለ ፣ ወያኔ-ትግሬ የለመደውን ውንብድና ጀመረ ። በቀን ጆሯቸው ምርጫውን በግራ ጆሯቸው ኢሳትን ሲያዳምጡ የከረሙት የአንድነት እና መኢአድ አባሎች ፍትህን ሲነፈጉ ፣ ፍትህ ልናገኝበት እንችላለን ወዳሉት ወደ ኤርትራ ጫካ ገቡ ። እንደኔ እምነት ( ከሚደርሰኝ መልእክት እና መረጃ ኢሳት ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ ጋ ያደረገውን ቃለ ምልልስ ጥበብ በተሞላበት መንገድ አድርጎት ቢሆን ምናልባት ዛሬ አሁን ካየነው በተሻለ “የሰው ጎርፍ ” አርበኞች ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል በሄደ ነበር )። አሁንም ቢሆን የምወደው እና የማከብረው ኢሳት እዚህ ጉዳይ ላይ በጥንቃቄ ይሄድ ዘንድ እንመክራለን ።

ምርጫው ቀጠለ ፣ መድረክ እንደለመደው ዛሬም ፓርላማ ገብቶ መሰዳደቡ እንደናፈቀው እገምታለሁ ( መድረክ ስል በተከታዮቹ እና መሪዎቹ መሃል ያለ የነጻነት አስተሳሰብ ልዩነት እንዳለ እጅግ ስለሚገባኝ ነው )። አንቦ ላይ መድረክን ደግፎ የወጣውን ሕዝብ አዲስ አበባ ላይ ቅንጅትን ደግፎ ከወጣው የ 1997 ሕዝብ በምንም ለይቼ አላየውም ። ሁለቱም ስርዓቱን ከመጥላት እና በስርዓቱ ተስፋ ከመቁረጥ የታየ እና አጋጣሚውን በመግለጽ ንዴቱን ለመግለጽ የወጣ ሕዝብ ስለመሆኑ ዶ/ር መራራ ጉድና በደንብ ያወቀዋል ። ብልጥ ፖለቲከኛ ስለሆነ እንደለመደው ያንን ኃይል ወደ ወንበር ለመቀየር እየትጋ ነው እንጂ !

ሰማያውዊም እስሩን ፣ እንግልቱን ፣ ስቃዩን እና መከራውን ተቋሙሞ ዛሬ ላይ ደረሰ ። ምርጫው ደረሰ ሰማያዊ ም አለሁ አለ ። እስከሚገባኝ ታዲያ የሰማያዊ ሃሳብ ኢፍትሃዊ በሆነ ምርጫ ተሳትፎ የተሰጠውን ድምጽ ይዞ ፓላማ መግባት እና የመንግስት ደሞዝተኛ መሆን ፣ ከዚያም በቴሌቪዥን በሳምንት ወይም በወር አንዴ እየቀረቡ ወያኔ ወስኖ ለጨረሰው ጉዳዮች ድምጽ አለመስጠት አይመስለኝም ። እሱ ከሆነ እኔም እንደ ብርሃኑ ነጋ የምርጫ ካርዳቹን ቅደዱት በሚለው ሃሳብ ላይ እስማማለሁ ። እኔ እማስበው ሰማያዊ ከዚያ የተለየ ማንነት አለው ብዬ ነው ። ጫካ መግባት አማራጩ የማይሆን የሚሆነው ፓርላማ ለምግባት ሰለወሰ ነው ብዬ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ አላስብም ። ምክንያቱ ግን ያ ከሆነ አሁንም የምርጫ ካርዱን ቅደዱት በሚለው ሃሳብ እስማማለሁ ። ባንጻሩ ግን በአሁኑ ሰዓት እንደ አንድ ተቃዋሚ ፓርቲ በጭንቅላታችሁ የያዛችሁት ሃሳብ ” የሆነለት ፓርላማ ፣ ያልሆነለት ፓልቶክ ይግባ ” የሚል እንዳልሆነ ስለማምን የምርጫ ካርዱን ቅደዱት በሚለው ሃሳብ ብዙም አልስማማም ።

እስከ መጨረሻው መጀመሪያ ድረስ በመታገል አምናለሁ ። የናንተ መንገድ ዛሬ የናንተ ብቻ ነው ፣ ነገ በምትወሱነት አካሄድ ወይ የናንተ ብቻ ሆኖ ይቀራል ወይም ደሞ ወደ ሕዝብ የኛነት ይቀየራል ።

ሄኖክ የሺጥላ

The post የቻለ ፓርላማ ያልቻለ ፓልቶክ ይግባ (ሄኖክ የሺጥላ) appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live