Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ስለ ኮሎኔል ታደሰ ጥቂት ልበል፡ ከፍል1 በይታያል የሩቅሰው

$
0
0

ከፍል1
ይታያል የሩቅሰው

መነሻዬ ሰመረ ዓለሙ የተባሉ ሰው፡ ካቀረቡት ጽሁፍ መካከል፡ አንዱን በማንበቤ ስለተጠቃሹ ከማውቀው እውነት ጥቂት ቆንጥሪ
በሚከተሉት አርእዕስቶች በመክፈል፡ የነጠረውን ሀቅ እያነሳሁ አንድ ሁለት ለማለት ነው።

ስለዚህ

1/ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ፡ ምን ሰርቶ ነበር?

2/የመሰወሩ ምክናያቶችስ ምንና እነማን ናቸው?

3/እኛስ ስለ እሱ ምን ብለናል?

4/ወደፊትስ ምን ማለት አለብን?

የሚሉ ሃሳብና ጥያቄዎችን እያነሳሁ ባጭሩ ለመዳስ ልሞክር።

 ለዛሪ

1.1.ኮሎኔል ታደሰ ምን ሰርቶ ነበር፡

Colo. Tadesse Muluneh_

Colonel Tadesse Muluneh

ገና በለጋ እድሜው ዝነኛውን፡ የኢትዮጵያ አየር ሃይል የተቀላቀለው፡ ታደሰ ሙሉነህ በኮሌጁ የሚሰጠውን ትምህርት አጠናቅቆ፡ በምክትል፡ መቶ አለቅነት ማህረግ እንደተመረቀ ነበር፡ በሲያድባሪ የሚመራው የሶማሌ ተስፋፊ ጦር ኢትዮጵያን የወረረው፡ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ እንደሚያስታውሰው፡ ወቅቱ የሃይለስላሴ መንግስት፡ ወድቆ ደርግ ስልጣን የያዘበት ስለነበር ሀገራችን ለመከላከል የምታደርገውን እንቅስቃሴ፡ የሚደግፍላት ባልነበረበት ሁኔታላይ ስትሆን፡ ባንጻሩ ሶማልያ የረጅም ጊዜ የወረራ ዝግጅት ከማድረጓም በላይ ሶቬት እስካፍንጫዋ ያስታጠቀቻት በመሆኑ፡ በሁሉም ዘርፍ የእኛና የጠላት ሐይል አሰላልፍ፡ የሰማይና የመሪት ያክል፡ የተራራቀ ነበር ማለት ያስደፈራል።

ደርግ በአንድ በኩል ከምዕራባውያን መንግስታት መሳሪያ ለማግኘት፡ በሌላበኩል ወታደር መልምሎ በማሰልጠን ለውጊ ዝግጁ ለማድረግ፡ በሚሯሯጥበት ወቅት፡ የሶማሌ ታንክና ልዩ ልዩ ከባድ መሳሪያዎችን፡ የጫኑ በሺ የሚቆጠሩ፡ተሽከርካሪዎች ባይድዋ መድረሳቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ይደርሰዋል፡ ይህ ሃይል ወንዙን ከተሻገረ፡ ከአንድ ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አዲስ አበባ ከመግባት የሚያግደው፡ ነገር እንደማይኖር ሰለሚገመት፡ ምንም እነኳን በተጠናከረ የአየር መቃወሚያና፡ እጅግ ዘመናዊ ተዋጊ አውሮፕላኖች የሚጠበቅ ቢሆንም፡ የተከፈለው ዋጋ ተከፍሎ ያ እንደጉንዳን የሚርመሰመስ ታንክና ከባድ መሳሪያ የጫነ መኪና ሳይሻገር፡ ድልድዩ መፍረስና ተመልሶ እስኪሰራ፡ ጥቂትም ቢሆን የዝግጅት ጊዜ መገኘት እንዳለበት፡ በባለስልጣናቱ ስለታመነ ለአየር ሃይላችን የውጊያ ትህዛዝ በመሰጠቱ፡ ግዳጁ ለም/ መቶ አለቃ ታደሰ ሙሉነህና ለበዛብህ ጴጥሮስ፡ በመሰጠቱ ወደ ቦታው ይከንፋሉ፡ በተጠንቀቅ ይጠባበቅ የነበረው የሶማሌ ወራሪም ገና በርቀት አየር መቃዎሚያውን ቢያስወነጭፍም፡ 2ቱ ጀግኖችና እውነተኛ የ ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች፡በድፍረት ገስግሰው ተፈላጊውን ኢላማ መትተው ድልደዩን በማፍረስ፡ ፊታቸውን ወደሃገራቸው ሲያዞሩ ታደሰ ያበረው የነበረው ተዋጊ አውሮፕላን፡ በሶማሌ አየር መቃወሚያ በመመታቱ መንደድ ሲጀምር ወጣቱ ፓይለት በፓራሱት በመውረድ፡ በጉዞ ላየም ብዙ አስደናቂ ታሪኮችን እያከናወነ በጣም አስቸጋሪ ጉዞ በማድረግ፡ ኦጋዴን የሚገኜውን የወገን ጦር በመቀላቀሉ፡ የኢትዮጵያ ጀግና መዳሊያ የተሸለመ ከመሆኑም በላይ፡ከም/ መቶ አለቅነት አንድ ደረጃ በመዝለል የሻበልነት ማህረግ የተሰጠው፡ ጀግና ነው።

ኮሌኔል ታደሰ ሙሉነህ፡ ከዚያም በሗላ  በርካታ ሃገራዊ ግዳጆችን የተወጣና ጠቃሚ ቁም ነገሮችን ያከናወነ፣ በትምህርት ዝግጅቱም የ2ኛ ዲግሪውን በማዕረግ ያጠናቀቀ፡ ፍጹም ሐገር ወዳድ፣ቅንና እሩህ ሩህ፣ አርቆ አስተዋይ፡ ባጠቃላይ እንከን የለሽ ስብናን የተጎናጸፈ፡ ሲሆን ወያኔ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር፡ የጠላትን ፊት ላለማየት፡ ከድሪድዋ አውሮፕላን አስነስተው፡ ኬንያ ከገቡት የአየር ሃይል አብራሪዎቻችን አንዱ ነበር።

ከዚያም የሀገሩ ውድቀት የእግር እሳት የሆነበት፡ ኮሎኔል ታደሰ ኬንያ እየኖረ የፖለቲካ እንቅስቃሴ፡ ለማካሄድ ሲጀምር ሁኔታዎች ለህይወቱ አድገኛ ሆነው ስላገኛቸው፡ የተሻለ ከለላ ለማግኘት ባደረገው ጥረት የዑጋንዳ ባለስልጣናትን አነጋግሮ ባገኜው ይሁንታ መሰረት ወደዚያው ሄዶ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንዳለ፡ የወያኔና የሻብያ ግንኙነት፡ በመበላሽት ላይ እንደሆነና፡ ሻብያ ወያኔን በጦር ሃይል ለማበርከክ፡ ሚስጥራዊ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ፡ በአንድ የድሮ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ባልደረባና ኤርትራ ከተገነጠለች በሗላ የኤርትራ ባለስልጣን በሆነ ግለሰብ፡ ይነግረውና፡ ኢትዮጵያን ከወያኔ ነጻ የማውጣት እቅዱን በኤርትራ በኩል ቢያደርግ እንደሚሻል ያግባባዋል፡፡

ኮሎኔል ታደሰም፡ የጠላቴ ጠላት የእኔ ወዳጄ ነው ወይንም ጅብን ለመውጋት አህያን መጠጋት እንዲሉ፡ ከስልት አንጻር ከዚህ የተሻለ ቦታ የለም በማለት፡ ጥያቄውን ተቀብሎ ወደኤርትራ በማምራት የሃገሪቱን መሪ በአካል አግኝቶ ሲያነጋግር፡ ሁኔታወች እስኪመቻቹልህ ድረስ፡ የኤርትራ ተዋጊጀት አብራሪዎችን ሲያሰለጥን እንዲቆይ፡ ትብብር ስለተጠየቀ እሽ ብሎ እያሰለጠነ  ለሁለት አመት ያህል እንደቆዬ፡ ወያኔ ሳያስበው፣ ሻብያ ግን ከ3አመት ባለነሰ ዝግጅት ጦርነቱ በሻብያ ተንኳሽነት ይፈነዳል።

ይህነን ተከትሎ ደግሞ በኬንያም፣ በሱዳንም፣ በሃገር ቤትም፡ ይንቀሳቀሱ የነበሩ፡ የወያኔ ተቃዋሚዎች ኤርትራ ገብተው፡ ከእዚያ እየተንደረደሩ ወያኔን መውጋት ይችሉ ዘንድ፡ ለኤርትራ መንግስት ጠያቄ አቅርበው ስለተፈቀደላቸው፡ ጠቅልለው እንደገቡ   ከኦነግና ከኦቭነግ በቀር፡ ሌሎቹ ግንባር ፈጥረው በአንድ ድርጅት ጥላ ስር በመሰባሰብ ለውጊያ እንዲዘጋጁ፡ በሻብያ መመሪያ ስለተሰጣቸው፣

1ኛ/በአቶ ዮሴፍ ያዘው፡ ይመራ የነበረው፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች ዲሞክራ ግንባር፡

2ኛ/በአቶ ተስፋዬ ጌታቸው ይመራ የነበረው፡ የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ንቅናቄ፡

3ኛ/በአቶ ቱሗት ፖል ይመራ የነበረው፡ የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር፡

4ኛ/በአቶ ጁማ እሩፋኤል ይመራ የነበረው፡ የቤንሻንጉል ንቅናቄ፡ በጋራ ባደረጉት የውህደት ጉባኤ ላይ ኮሉኔል ታደሰ ሙሉነህም ተካፋይ እንዲሆን ትደርጎ ስለነበር፡ ተዋህደው አዲሱን ድርጅት የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የሚል ስያሜ በመስጠት የመጀመሪያ ጉባያቸውን ሲያጠናቅቁ፡

1ኛ/ ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህን፡ የግንባሩ ሊቀመንበር፡

2ኛ/ አቶ ቱሗት ፖልን፡ የግንባሩ ም/ሊቀመንበረ፡

3ኛ/አቶ ጁማ እሩፋኤልን የግንባሩ ጽሃፊ፡

4ኛ/አቶ ዮሴፍ ያዘውን የግንባሩ ድርጅት ጉዳይ፡

5ኛ/አቶ ተሰፋዬ ጌታቸውን የግንባሩ የእርዕዮታለም ጉዳይና ሌሎች 2 ሰወችን በማከል፡ 7 ያመራር አካላትን መርጠው ነበር። ኮሎኔል ታደሰ ያካበተውን የጠለቀ እውቀትና ሰፊ የስራ ልም፡ ሳይሰስት ተግባር ላይ ስላዋለው፡ አርበኛ ግንባር ባጭር ጊዜ በብዛትም ሆነ በጥራት ጠላቱን ወያኔን ብቻ ሳይሆን፡ አስተናጋጇን  የኤርትራን መንግስትም፡ ከማስፈራት ደረጃ ላይ ከመድረሱም በላይ፡ በዲፕሎማሲውም ዘርፍ ኮሎነል ታደሰ ወደ አውሮፓና አሜሪካን በመጓዝ፡ ኢትዮጵያውያንንና የውጭ ሀገር መንግስታትን፡ አነጋግሮ በማሳመን ሰፊ ድጋፍን ያስገኘ ሰው ነው።

ኮሎኔል ታደሰ ወደ አሜሪካን ባቀናበት ወቅት፡ሻብያን በጥርጣሪ አይን የሚያዩ፡ ኢትዮጵያውያን፡ ተሰባስበው መኝታ ክፍሉ ድረስ በመሄድ፡ በሻብያ ድጋፍ ኢትዮጵያ ነጻ ትወጣለች ብለህ አትድከም ይልቅ፡ ሻብያ እንደበግ አስብቶ ሳያርድህ፡ አሁን እንደወጣህ በእዚሁ ቅርና ልጆችህን አሳድግ፣ ሚስትህም፡ ኢትዮጵያም ያንተ ብቻ አይደለችም፡ ወ.ዘ.ተ. በማለት ቢለምኑት፡ የሰጣቸው መልስ፡ ሁሉም ኢዮትጵያ ለእኔብቻ አይደለችም፡ እያለ ጥሏት ከሸሸ የጎርቤት ሀገር ዜጋ መጥቶ ሊታደጋት ነውን? ባለቤቴም ሆኑ ልጆቸ አሜሪካን ገብተዋል፡ የተሻለ ኑሮ እየኖሩ ነው ወደፊትም ቢሆን እኔ ኖረሁም አልኖርሁም ይኖራሉ፡ ሌላው ኢትዮጵያዊ ግን ይህንን እድል ማግኘት አይደለም በሀገሩ ላይ በሰላም የመኖር መብቱ ተገፍፎ 2ኛ ዜጋ ሆኖ በመማቀቅ ላይ ከመሆኑም በቀር፡ ወያኔ ውሎ ካደረ ኢትዮጵያ የምትባል ሃአገር አትኖርም፡ እናም ቢሆን ከጥፋት አድናታለሁ፡ ካልሆነም ጥፋቷን ሳላይ ማንም ያጥፋኝ ማን ስከላከልላት እኔ ቀድሜያት፡ እጠፋለሁ፡ ሞት እንደሁ ፈራንም ደፈርን የማይቀር የተፈጥሮ እዳችን ነው። የሚል እንደነበር ካነጋገሩት ሰዎች መካከል አንዱ ሰሞኑን በቁጭት አጫውተውኛል።

ለዛሪ በዚህ ላብቃ ቀሪውን በክፍል ሁለት ሳምንት እመለስበታለሁ፡ የሳምንት ሰው ይበለን፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይታደጋት አሜን!!!!

                                                          

 


የእናት ጡት ነካሾቹ ህወሃት ና ጀሌወቹ

$
0
0

berhane-assebe
ከብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ

ከዛሬ 21 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ህዝቦች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ስልጣን የተቆናጠጠው ህወሃት/ወያኔ ገና ከጅምሩ የሃገርና የህዝብ ሃብትና ንብረት መዝረፍና ማውደም መለያ ባህሪው የሆነው የእናት ጡት ነካሹ ህወሃት በሆድ አደር ጀሌዎቹ ተባባሪነት እንሆ ለ21 ዓመታት የሃገራችንን ቁሳዊይና አካላዊ ሃብቶች እያራቆታት ይገኛል
ህወሃት/ወያኔ በ 17 አመታት የጫካ የሽፍትነት ዘመኑ በቀመረው ፀረ-ኢትዮጵያ የጫካ ሕጉ በትግል ጎራ ሳይቀር አብረወት ሲቆስሉና ሲዋደቁ ከነበሩት እውነተኛ ታጋዮች መካከል፣ በሃገራቸው አንድነትና ልኡላዊነት ላይ ጽኑ እምነት የነበራቸውን፣የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትንና ዴሞክራሲ ስርአት በኢትዮጵያ መገንባት አለበት የሚል አቋም ያላቸውን እና የህዝብ ወገናዊነት የነበራቸን በየጊዜው በማሶገድ ፀረ-ኢትዮጵያ አቋም ያላቸው ሃይሎች ተሰባስበው ና ተማምለው እንሆ ዛሬ በአዝማቹ ህወሃት እና ከየብሄር ድርጅቱ ተወክለናል ባዮቹ ጀሌዎች በዚህ ትውልድ ላይም ለዜጎች መብትና ነጻነት የሚታገሉትን፣ በጹሁፍ ላይ የሰፈረው ሕገ መንግስት በተግባር ሊተገበር ይገባል የሚል ጥያቄ የሚያነሱ አካላትን፣ የህዝብ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ምላሽ ሊያገኝ ይገባል በማለትጥያቄ የሚያነሱ የህብረተሰብ ክፍልን፣በሃይማኖታችን ጣልቃ አይገባብን፣በሃገራችን ሁላችንም እኩል ልንስተናገድ ይገባናል፣የሠብአዊ መብት ሊከበር ይገባል፣ የመሰብሰብና የመደራጀት መብታችን ሊገደብ አይገባውም ወዘተ በማለት ጥያቄ የሚያነሱ የህብረተሰብ ክፍሎችን አሸባሪ ፣ነውጠኛ፣ ሙሰኛ፣ የአመለካከት ችግር ያለበት ወዘተ በሚሉት ተለጣፊ ቃላቶቹ በመጠቀም ትውልዱን በመግደል፣ በማሰር፣ ከሃገር በማባረር እያመከነው ይገ ኛል
የዛሬ የእናት ጡት ነካሾቹ ህወሃት ማ! ያ- ን- ዬ በታጋይ ስም በሚሉበት በዚያን ዘመን ደጉ ያገሬ ሰው የውስጥ የልባቸውን መርዝ ሳይረዳ የተባለለት ዴሞክራሲ ከፊቱ እየታየው ለተራበው በማጉረስ ፣ለተጠማው በማጠጣት፣መንገድ ለጠፋው መንገድ በማሳየት፣የተመታን ሸሽጎ ሂዎት በማትረፍ፣ገደል ፈንቅሎ መንገድ በመስራት፣ጅረት ጫካውን በማሻገር ፣ስንቅ ቋጥራ/ሮ/ ይቅናችሁ ብላ /ሎ/ ለመረቀ እናት/አባት፣እህት/ወንድም ህወሃት/ወያኔ በሃብት ላይ ሃብት አካብተው በዘረፉት ሃብት ደንዝዘው የህዝብን ጥያቄ ወደጎን ትተው ያ ሂዎታቸውን የታደጋቸውና ለድል ያበቃቸውን ህዝብ በፀረ-ዴሞክራሲ ህጋቸው መፈናፈኛ አሳጥተውታል ፥ ህዝቡይህንን ብሶቱን በንጉርጉሮ እንዲህ ሲገልጸው ይደመጣል
እሾህ ብቻ ሆኗል እግሬን ብዳብሰው
እንዴት መራመጃ መሄጃ ያጣል ሰው
ወ–ገ–ን በዚያን ዘመንታጋይ አይራብም ብላ ፈትፍታ ያጎረሰች እናት በኖረችበት ቀዬ /ቦታ/ ያረገዘችውን ልጅ እንኳን ሳትወልድ ቤንሻንጉል ጉምዝ አገርሽ አይደለም በሚል ከቤቷ ተፈናቅላ /ተገፍትራ /ጫካ ስትወልድ ዝምእንበል?
- የሃገር አለኝታ የሆነው አርሶ አደሩ ያ ትልቅ ሰው በግዳጅ ከ ቤንችማጅዞን ውጣ ሲባል ቤንችማጅዞን ሃገሬ ካልሆነማ ! ቀን ይሰጠኝ ሃብትና ንብረቴን ሰብስቤ እወጣለሁ ብሎ እጁን ዘርግቶ ሲማፀን እጣ ፋንታው ዱላ ሲሆን ምን እንፍጠር ? ምንእንበል ?
በሃገራችንና በህዝባችን ላይከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ የመጣውን የሰብአዊ መብትጥሰት፣ እየደረሰ ያለውን የሃገር ውድመትእና የሕዝባችንን ሰቆቃ ለመታደግ ይህንን እኩይ ስርዓት ማሶገድ አማራጭ የሌለው ተግባር ነው
በመሆኑም በየትኛውም ቦታ የምንገኝ የህዝባችን ሰቆቃና ስቃይ የሚቆረቁረን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ልብ ለልብ ተገናኝተን ይህን ፀረ-ዴሞክራሲና ፀረ-ህዝባዊነት የተንሰራፋበትን ስርአት ሁለገብ ትግል ለማድረግ እንነሳ
ሁላችንም ለሃገራችን የድርሻችንን እናበርክት!
አዘጋጅ ብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ
21/07/2013

ኢትዮጲያ፣ ሃይማኖት እና ብሄር ካለፈው እና ከአሁኑ ታሪካችን ተምረን ለእውነተኛ ዲሞክራሲ እንታገል

$
0
0

By: Ephrem Shaul

የዚህ ጹሁፍ አላማ ከታሪክ ስህተቶቻችን ተምረን ወደፊት የማይደገምበትን እውነተኛ ዲሞክራሲ ለሁላችን መፍጠር ላይ ትንሽ ሀሳቤን ለማካፈል ነው። የኢትዮጲያ ህዝብ ታሪክ ጥሩም መጥፎም ታሪክ እንደማንኛውም ሀገር አለን። አኩሪ ታሪክ ያመሰገብን እንደመሆናችን ሁሉ ክፉ የታሪክ አሻራም አለን። ዜጎች በነጻነት ለመኖር ያልታደልንበት አሳዛኝ እና አስከፊ ግዚያቶች በታሪካችን ጎልተው ይታያል። አሁንም በአስከፊ ሁኔታ በወያኔ ኢሃዴግ ተጠናክሮ አፈናው ቀጥላል። በዚህ እውነት ውስጥ የሚነሳው የኦሮሞ ህዝብ መበደል፣ አስከፊ እንዲሁም አሳዛኝ ሰቆቃ ነው። ይህ አስከፊ እንዲሁም አሳዛኝ ሰቆቃ መከሰቱ እጅግ አሳዛኝ ነው። መከሰቱን መካድ መፍትሄ አይደለም። የተፈጠረውን ግፍና ችግር በአግባቡ ተረድተን ስናበቃ ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጣውን መንገድ መምረጥ ብልህነትና የዚህ ትውልድ የታሪክ ሃላፊነት ነው። የሰውነትና የዜግነት ግዴታም ነው። በተመሳሳይ የምናነሳው የኢትዮጲያ ሙስሊሞችን አሳዛኝ በደል ነው። አስልምና በአርብ ሀገራት ከፍተኛ ችግር በገጠመው የታርክ ዘመን ኢትዮጲያ ተቀብላ ያቆየችበት ታሪክ እንደመኖሩ ሁሉ አሳዛኝ ችግሮችም አሉ። ይህን በደል ተረድቶ ለሁሉም ዜጋ የምትሆን ኢትዮጲያን መፍጠር ግዴታችን ነው። ይህ የታሪክ ክፉ ኣሻራ በኦሮሞ ክርስቲያኖችም ላይም ተፈጽማል። የሁሉም ብሄር ተወላጅ በሆኑ ፕሮተስታንት ተከታዮች ላይ ተፈፅማል። ኣርቶዶክስ ኢትዮጲያዊያን ላይ አሁን ያለው ስርአት ጣልቃ ገብቶ መቆጣጠሩ የታወቀ ነው። በሃገራችን ታሪክ ኦሮሞ፣ ሶማሌው አፋሩ ጋንቤላው አማራው ትግሬው ውላይታው ጉራጌው ሲዳማው ከንባታው ሱሪው ኮንሶ ኮሬ አደሬዉ ቤንሻንጉሉ ወዘተ ተበድላል። ሁላችን በታሪካችን ውስጥ ብሶት አለን። ይህን እውነት (fact) በአግባብ መረዳትና ማስረዳት ወሳኝ የአክቲቪስትና የፖለቲከኛ ስራ ነው። በአንጻሩ ደግሞ እምነትን መስበክ በሰላማዊ ትምህርት ማስፋፋት የሃይማኖት አባቶች (ቄስ ሽክ ፓስተር ወዘተ) ስራ ነው።

ፓለቲከኞች የራሳቸውን እምነት ለራሳቸው ይዘው ለሁሉም ዜጋ የሚሆን (ለሁልም ብሄር እና እምነት) በነጻነት እና በክብር የምንኖርበትን ሀገር እውን ለማድረግ መረባረብ አለባቸው።  ግዜን እውቀትን ገንዘብን አቅምን ማዋል ያለብን እዚ ላይ ነው። የሚባክን ግዜ የለንም የዜሮ ድምር ፓለታካም አያስፈልገንም። የእምነት ትንታንኔ ስራና አስተምህሮት የሃይማኖት አባቶች ስራ ነው። የፖለትቲከኛ ስራ ጨርሶ አይደለም። ይህን ብሄር ያንን እምነት የበላይነት ለማምጣት መሞከር ኢፍትሃዊና ኢዲሞክሪያሲያው ነው። የታሪክን ችግር መድገም ነው። የዲሞክራሲ ትግሉን አላማ መሳትና ግዜውን ማርዘም ነው። የራስን በደል ብቻ መመልከት ሌላውን አይመለከተኝም ማለት የታሪክን በደል እንደመካድ ይህም ስህተት ነው። የሁሉንም በደል ተረድተን በጋራ መስራት አርቆ አሳቢነትና አስተዋይነት ነው። ለሁላችንም ነጻነትና ፍትህ የምትሆን አገርን መገንባት ትክክለኛ ራዕይ: ድፍረት: ቆራጥነት ይጠይቃል። የአመራር ችሎታ ግድ ይላል። ይህ ወያኔ ኢሃዴግ እንደሚለው በወሬ ሳይሆን ተግባራዊ ቁርጠኛነት ይጠይቃል። ይህ የትላንት እና የዛሬ በደሎችን እንዳይደገም ዋስትና ይሰጣል ዘላቂ መፍትሄውም ይህ ብቻ ነው። ቅንነትን ሁላችን ከያዝን ከባድ አይደለም። የአመራር ችሎታ ማለት (leadership quality) ህዝብን ፍትሃዊ በሆነ ስርአት የዜጎችን ነጻነት አክብሮ እና አስከብሮ መምራት ማለት ነው። ግጭት አምጪ ሀሳብችን ወይም ድርጊት ማስፋፋት ለማንም አይጠቅምም የአመራር ችሎታም ጨርሶ ኣይደለም። አሳዛኝ የታሪክ ስህተቶችን ተረድተን ካለፈው ስህተት መማር ወሳኝ ነው። ነገር ግን የተፈጠሩ ስህተቶችን ተከትለን ሌላ ኢፍትሃዊ ስርአት ለማምጣት ማስብ የለብንም በጣም አደገኛ ስህተት ነው። ከችግሩ ሳንወጣ እዛው እንድንዳክር ከማድረጉም በላይ እንደ እስተሳስብም የተሳሳተ አካሃድ ነው።

በኢትዮጲያ ውስጥ ለኢትዮጲያ አንድነትና ነጻነት የታገሉ የታሪክ ደማቅ አሻራ የጻፉ የተለያየ ብሄር ተወላጅ ኢትዮጲያዊያን (ሙስሊምና ክርስትያን) በገዛ ሀገራችን በታሪክ ተበድለን መቆየታችን አሳዛኝ ነው። ያልተበደለ ህዝብ የለም በዳዪ ደግሞ አንድ ቡሄር አይደለም። በአንድ ብሄር ስም ስልጣን ላይ የወጡ ገዥ መደቦች ናቸው (የተለያዮ አምባገነን ስርአቶች ናቸው) በስልጣልን ላይ ያለው የወያኔ ሰርአት ከትግራይ ህዝብ ተለይቶ መታየት አለበት። ስርአትንና ብሄርን ለይቶ ማየት ለአክትቪስት ወይም ፖለቲከኛ ሀሁ/ABCD ነው። አሁን ስልጣን ላይ ያለው ሰርአት በኦሮሞ ላይ የሚያደርሰውን በደል የሚያስፈፅምለት ኦህዴድ ተብሎ የተደራጀው የኦሮሞ ተወለጅ ናቸው። በተመሳሳይ በአዴን በአማራው ላይ፣ ህውሃት በትግራይ ህዝብ ላይ ደህዴን በደቡብ ፤ አጋር የሚላቸው ድርጅቶች በሶማሌው፣ በጋምቤላው በአፋሩ በቤንሻንጉሉ ላይ ተጋግዘው ነው ህዝቡን ስቃይ የሚያበሉት። ይህ እውነታው ነው፤ ይህንንም መቀበል የተሳሳተ መስመር ከመከትል ያድናል መፍትሄውም የአሁኑን የአንባገነንነት ስርአት የመጨረሻ አድርጎ ዲሞክራሲ ለሁሉም ለማስፈን መታገል ነው። ከታሪክ በአግባብ ተምረን ስናበቃ ስህተቱን አውግዘን መልካሙን ደግም ለማበልጸግ መስራት አለብን። ከታሪክ መማር እንጂ የታራክ እስረኛ መሆን የለብንም። ራእይ ያለው ትውልድ መሆን ያስፈልጋል። ራዕያችን ደግሞ ዲሞክራሲያዊና ሁሉን ያሳተፈ መሆን አለበት (inclusive democracy)። ውድድር የበዛበት አለም ውስጥ ነው የምንኖረው። ችግራችንን ለዘለቄታው በአፋጣኝ ፈተን አስከፊ ስርአትን ለውጠን በአዲስ መንፈስ በፍትህና ዲሞክራሲ መመራት አለብን። ከታሪክ መማር ወሳኝ የመሆኑን ያህል ፤ የታሪክ እስሪኛ መሆን ለግለሰብም፣ ለቤተሰብም፣ ለብሄርም፣ ለእምነትም፣ ለሃገርም ሆነ ለአለምም አይጠቅምም።  ወደ ሃላ እያዪ ወደ ፊት በትክክል መሄድ አይቻልም። አንድ ምሳሌ ልጨምር የመኪና ሹፌር በጎን መስታወቶቹ ወደሃላ አይቶ አደጋ እንዳይጥመው ይከላከላል ነገር ግን ወደፊት በአግባቡ ካላየ አደጋ የገጥመዋል፤ ወደፊትም መሄድ አይችልም። በዘላቂ በመፍሄ ላይ ያተኮረ አቅጣጫ ላይ ሙሉ አቅምን ማዋል አስፈላጊና ወሳኝ ነው። የምንታገለው ስርአት ሌት ተቀን ተግቶ ስልጣን ላይ ለመቆየት ይሰራል። ሲለው ይገላል ሲያሻው ያስራል የሃገሪቱን ሰልጣን ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ በሙሉ ተቆጣጥራል። ይህ ስልጣን ሊያረጋግጥ ፈፅሞ አይችልም። ወሳኙ የህዝብ ድጋፍ ነው። ይህ ደግሞ አንባገነን ስርአቶች ጨርሶ የላቸውም የህዝብ ድጋፍ ኖራቸው አያውቅም ሊኖራቸውም አይችልም።

ዲሞክራሲ እና ነጻነትን ለማምጣት ነው ትግሉ። ከዚህ የወጡ እርስ በርስ የሚያጋጩ አስትያየት ሲስነዘር ወደ መፍሄ እንደማይወስድ በግልጽ መንገር የሁላችንም ግዴታ ነው። ወደ መፍሄው እንጂ ወደ ብጥብጥ የማይወስደውን መንገድ መምረጥ  ደግሞ በሳልነት ነው። ስህተትን ተቀብሎ ማረም ስህተቱን የሰራው ወይም ሊሰራ ያሰበ አካል ሃላፊነት ነው። ከወያኔ ስህተት ተቃዋሚ መማር አለበት። የወያኔን አድሎአዊና ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲን ስንቃውም እኛ እንደማይደገም ማረጋገጥ መቻል አለብን። በታሪክ ጎልተው የሚታዩ አስከፊ በደሎች ኣሁን ባለንበት ዘመን በወያኔ ኢሃዴግ ተባብሶ ቀጥላል። ዜጎች በነጻነት እንዳያምኑ በእምነት ተቍማት ጣልቃ ገብነቱ ከፍታል። ዜጎች በነጻነት ሀሳባቸውን እንዳይገልፁና በነጻነት በሚመርጡት መሪዎች እንዳይተዳደሩ አፈናው ቀጥላል። ጋዘጠኞች፣ የፖለቲካ ድርጅት አመራሮች ኣባላትና ደጋፊዎች አሸባሪ ተብለው በሃሰት ተከሰው ታስረዋል። የሃይማኖት ነጻነት የጠየቁ ሙስሊም ኢትዮጲያዊያን አሸባሪ ተብለው በሃሰት ተከሰው የድራማ ፕሮፓጋንዳ በአደባባይ ተሰርቶባቸው በግፍ ታስረዋል። ሁሉ ብሄር በግፍ ተጨቁኖ ጥቂት የስርአቱ ደጋፊዎች ተንደላቀው የሚኖሩበት ሀገር ሆናለች ኢትዮጲያ። ይህ ፈጽሞ ፈትሃዊ አይደለም። መጻፍ እና ሀሳብን በነጻነት መግለጽ አሽባሪነት ተብሎ የሚያስፍርጅበት ክፉ ስርአት ተፈጥራል። ይህ ለማንም አይበጅም ለሀገር፣ ለህዝብ፣ ለራሱ ስልጣን ላይ ላለው አስከፊ ስርአት አደጋ ነው።

በተመሳሳይ ለሃይማኖት ነጻነት የሚደረግ ትግል የሌላውን እምነት ነጻነት ማክበር አለበት። እዚህ ላይ ትክክለኛውን መንገድ መምረጥ የሁሉም እምነት አባቶች እና የእምነቶቹ ተከታዮች ሃላፊነትና ግዴታ ነው። የሃይማነት ነጻነት ትግል ወሳኝ ነው ነግር ግን አካራሪነትን ጨርሶ በየትኛውም እምነት ውስጥ ማስከተል የለበትም። ሀይማኖት የግል ሀገር የጋራ እንደሚባለው። ሀይማኖትና ፖለቲካ መደበላለቅ የለባቸውም። ሀይማኖት የግል ስብእናችን ነው። እያንዳንዳችን ፈጣሪያችንን የምናመልክበትን መርጠን የምንከተለው ነው። በኛና በፈጣሪያችን መሃል የምንከተለውን መንገድ የሚመራን ነው። ለሁሉም እምነት መከበር ደግሞ በጋራ ሁላችን መስራት አለብን። በተመሳሳይ የተሳሳተ አስተሳሰብንም በጋራ ሁላችን መቃወም አለብን። የጋራ በሆነችው አገራችን ደግሞ ለሁላችን በፍትህና በነጻነት እንድንኖር በጋራ የምንመራበት ሁሉን አሳታፊ ዲሞክሪያሲያዊ ስርአት መገንባት አለብን። ሀይማኖትና ፓለቲካ መደባለቅ የለበትም ፤ የእምነት ነጻነትንም ለሁሉም ለማምጣት አይችልም። ይህ እውነታን ለመገንዘብ ፖለቲካል ሳይንስ ማጥናት አያስፈልግም ፤ ስፔስ ሳይንስም አይደለም። ይህን ችግር ለዘለቄታው መፍታት የዚህ ትውልድ የታሪክ ሃላፊነትና ግዴታ ነው። ሀገር እንድታድግ የዜጎች ነጻነት መከበር አለበት ፤ ይህ ደግሞ ዜጎች ያላቸውን በጥረት ራስን የማሳደግና የማበልጸግ ራእይ ለማሳካት ወሳኝ ነው። የሃገርም እድገ መሰረት ነው። ለብሄራዊ ራዕይ እና መግባባት ወሳኝ ነው። ባለንበት ግሎባላይድ አለም ተፎካካሪና ውጤታማ ለመሆን ትክክለኛ ራዕይ እና ጠንክሮ መስራት ወሳኝ ነው ። ለዚህ ደግሞ ዜጎች የምንሰራበትን እደል ለመፈጠር የዜጎች ነጻነት ያለማወላወል መከበር አለበት።  የምንመኛት ኢትዮጲያ ለሁላችን ሀገር መሆን አለባት። ለኦሮሞው፣ ለአማራው፣ ለሶማሌው ለትግሬው ለአፋሩ ለጋምቤላው ለሃረሬው ለቤንሻንጉሉ ለሲዳማው ለጉራጌው ለወላይታው ለሃዲያው ለኮንሶው ለሱሪው ለኒያጋቶም … ወዘተ  እንዲሁም ለክርስትያኑ ለሙስሊሙ ለባህል እምነት ተከታዩ እምነት ለሌለው በአጠቃለይ ለሁላችንም የምትሆን ኢትዮጲያን እውን ማድረግ ነው መፍትሄው።

አንድነታችን ሁሉንም ያከበረና ያቀፈ መሆን አለበት። የሁላችንም ኩራት የሆነች ኢትዮጲያን እውን ማድረግ አለበት። ለዚህ ደግሞ የውስጥ ችግሮቻችንን እውነትኛ ዲሞክራሲ ስርአት ላይ መስርተን በአፋጣኝ መፈታት አለብን። እውነተኛ ዲሞክራሲ ከገነባን አብዛኛውን ህዝብ ከሚውክለው ኦሮሞ፣ አማራ፣ ሶማሌ፣ ትግሬ ብሄሮች እስከ አነስተኛ ህዝብ ቁጥር ያላቸውን ቤንች፣ኮንሶ፣ አላባ፣ እና በጣም ጥቂት ህዝብ ቁጥር  ያላቸውን ኒያንጋቶም፣ ሙርሲ፣ ካሮ የሁሉም መብት ተከብሮ በሰላም በፍቅርና አንድነት የምንኖርባት ኢትዮጲያን እውን ማድረግ ነው ያለብን። በዚህ አይነት መሰረት ላይ የቆመ አንድነት ተሰሚነት ያላት በአካብያዊ ፖለቲካም ሆነ በአለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የራስዋን አውንታዊ ሚና የምትጫወት ጠንካራ ኢትዮጲያን እውን ማድረግ ያስችላል።

እንደ አገር አንድ መሆን ይበጀናል አንድነታችን ደግሞ ሁሉያን ያቀፍ እና ያሳተፈ (inclusive) እንዲሆን ሁላችንም መስራት አለብን። አሁን ያለንበት የአለም እውነታ የሚያሳየን የአንድነትን ጥቅም ነው። ሀገራት ጥቅማቸውን ማስጠበቅ የሚችሉት በጠንካራ መሰረት ላይ የቆመ አንድነት ሲኖር ነው። አለም ላይ ያለው ተጨባጭ እውነታ የሚያሳየን ይህን ነው። በአለማችን ጠንካራ አቅም ያላት ሀገር ስንሆን ተሰሚነታችን ይጨምራል። ፈተናዎችን በተሻለ አቅም ማሸነፍ ያስችለናል። አውሮፓ(EU)፣ አፍሪካ (AU)፣ ደብቡ አሜሪካ (ECLAC) የአንድነትን ጥቅም አስልተው አንድነቱን አጠናክራል። በአንድ ድምጽ በአለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር አየሰሩ ነው።  አውሮፓ የተለያዮ ሀገራትን አሰባስቦ ጠንካራ አቅም ገንብታል። እነዚህ ሀገራት በጣም አስከፊ የእርስ በርስ ግጭት አሳልፈዋል። ያሳለፉት ታሪክ እስረኛ ሳይሆኑ ከታሪክ ተምረው ጥቅማቸውን ለማስከበር በጋራ እየሰሩ ነው። እስያም በተመሳሳያ የራሳን ብዙ የትብብር መድርኮች ፈጥራለች (SASEC, ACD, APDC..)። አረብ አገራት የራሳቸውን የትብብር መድረክ ፈጥረዋል (Arab League, GCC )። አገራት የጋራ ጉዳያቸውን እየፈለጉ በጠንካራ ትብብር እየሰሩ ነው። ከዚህ ሪጅናል ትብብር (regional cooperation) በተጨማሪ በተለያየ አካባቢ እና በተለያየ አለም ክፍል የሚገኙ ሀገራት የተለያየ የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊ፣ ውታደራዊ እና የጽጥታ ትብብር መስርተው ይሰራሉ። ጥቅማቸውንም በጋራ ያስከብራሉ። አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ (EU-US) ትራንስ አትላንቲክ ኮኦፐሬሽን፣ ኢስት ኤዥያ ላቲን አሜሪካ ኮኦፐሬሽን፣ ቻይና አፊሪካ ፣ ሰሜን አሜሪካ አፍሪካ ወዘተ። በዚህ በትብብር አገራት ጥቅማቸውን በሚያሰጠብቁበት አለም ጠንካራ አንድነት ከሌለን ተወዳዳሪ መሆን ይቅርና ተሰሚነትም አይኖረንም። መበታተን የራሳችንንም ሰላም አያስገኝልንም። መበታተን ዲሞክራሲን ፈጽሞ ጋራንቲ አያደርግም።

ይህን አለማቀፋዊ ሁኔታ፣ ተፈላጊውን ከፍተኛ ደረጃ ጠንካራ ፉክክርና ትብብር ግምት ውስጥ ያላስገባ ጥላቻን የሚያባብስ እርስ በእርስ የሚያጋጭ አክራሪነትን የሚያበረታታ አስተያየት ሲሰጥ ከየትም ይምጣ ከየትም፡ ከማንም ይምጣ ከማንም ስህተት መሆኑን ሁላችን በጋራ አንድ ሆነን ልንናገር ያስፍልጋል። ከታሪክ ስህተት መማር እንጂ የታሪክን ስህተት ማስቀጠልም ሆነ በሌላ አካል መድገም የለብንም። የምንኖረው ግሎባላይድ በሆነ አለም ነው (globalized world). ሀገራችን በውስጥ ትክክለኛ ዲሞክራሲ ላይ ተመስርታ ስታበቃ፤ ከምስራቅ አፍሪካ፣ አፊሪካ እንዲሁም ከመላው አለም ጋር ጤናማ ግንኙነት መፍጠር አለብን። በጅብቲና በአካባቢው ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ገብተን የምንበጠብጥበት (intervening in other countries internal affairs) በፓለቲካም ይሁን በኢኮኖሚ ወይም ሀይማኖትን መሰረት አድርገን ማስብም ይሁን ማቀድ ጤናማ አስተሳሰብ አይደለም፤ መልካም የጉርብትና ትብብር እና ሰላም አይፍጥርም። ከአለም አቀፍ ህግጋትም ጋር ይጣረሳል ከፍተኛ ችግርም ያስከትላል (severely violets international laws and results serious and long term consequences on our country).

በሃገራችን የውስጥ ጉዳይ ለፍትህ መታገል ለነጻነት መታገል ይገባል ትክክልም ነው። ይገባልም። ይህ ትግል ለኦሮሞ ሙስሊሞች ብቻ ሳይሆን ለኦሮሞ ክርስቲያኖች፤ ሙስሊምም ክርስቲያንም ለልሆኑ ኦሮሞዎች፤ ኦሮሞ ለልሆኑ ክርስያኖች፤ ኦሮሞ ላልሆኑ ሙስሊሞች በአጠቃላይ ለሁሉም ኢትዮጲያዊያን ነጻነትና ፍትህ መታገል የሰውነት፣ የኢትዮጲያዊነት የሞራል ግዴታ ነው። ለመብት ስንታገል የህዝቦችን አብሮ የመኖር አሴት (solidarity, coexistence, and multiculturalism, merits of unity) ፍቅር፣ መዋድድና መከባበር (love, tolerance, respect for diversity) ለግል ክብር፣ ተዋቂ ለመሆን፣ ለስልጣን ስንል ለመናድ መሞክር ማናችንም ጨርሶ ማድረግ የለብንም። እኛ ስናልፍ ሀገርና ህዝብ አያልፍምና።  ለኦሮሞ መብት መከበር ሁላችን መታገል አለብን። ለአማራውም፣ ለትግሬውም ለሱማሌው ለወላይታው  ወዘተ ፤ እንዲሁም ለሙስሊሙ ለክርስትያኑ ለማያምነው ወዘተ በአጠቃላይ ለሁላችን መብት ሁላችን በጋራ መስራት አለብን። ከአለንብት የበድል አዙሪት የምንወጣው ያኔ ብቻ ነው።

 

ያለፉ የታሪክ ስህተቶችን መካድም አይጠቅምም (denial of historical injustice) ። ችግሩን የፈጠሪው አንድ ብሄር ደግሞ አይደለም (blaming one ethnic group for historical injustice is unjust)። ጥቂት ገዥ መደቦች (few ruling group) ናቸው ። በተመሳሳይ በግል ጥቅምና ለተዋቂነት በሚደረግ ርጫ እንዲሁም በስሜት ላይ የተመሰረተ የጥላቻ ፖለቲካ (emotion driven politics) ፤ ግትርነትና (rigidity) አግላይ የፖለቲካ አቁአም (exclusionist  politics) ለማንም አይጠቅምም። የአጭር ግዜ ፓለቲካ (short termism) የጥላቻ ፖለቲካ (spreading of negative consciousness and hatred) ለማንም አይጠቅምም።

ለፍትሕና ለነጻነት መታገላችን ሰብአዊነትን እና ሁሉን ያሳተፈ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን። ኢንፓውርመንት (empowerment) ማለት ህዝብ መብቱን እንዲጠይቅ ማሳወቅ እና ማስተባበር ማለት ነው። ፈትሃዊነትን ከልብ የተቀበለ ህዝብና ህዝብን በሃይማኖት ማበጣበጥን ያወገዘ መሆን አለበት። ጤናማ አክቲቪዝም (activism for democracy, freedom, sustainable & long term peace and justice) እና ኢንፓወርመንት (empowerment) ትርጉሙ ይህ ነው። ለእውነተኛ ዲሞክራሲ እንታገል።

ይህን ጽሁፍ ወደ ኦሮመኛ እና ሌሎች የሃገራችን ቋንቋዎች በቀጥታ ለሚተርጉምልኝ ምስጋናዬ ወደር የለውም።  እንደ አስፈላጊነቱ የእንግሊዘኛ ትርጉሙን ከተጨማሪ ማብራሪያ ጋር አዘጋጅቼ ብቅ እላለሁ።

ከምስጋና እና ታላቅ አክሮት ጋር በዚህ ላብቃ።

ቤልጂየም (Belgium)

አስተያየቶን በሚከተለው ኢሜል ይላኩልኝ።   fiftoze@yahoo.co.uk

 

 

‘የአረቡ ዓለም አብዮት ኢትዮጵያ ውስጥ ይመጣል ብለህ ታስባለህ ብለው ጠይቀውኛል”–ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

$
0
0

woloዝግጅቱ የነበረው አሜሪካ ኤምባሲ ውስጥ ነው፡፡ ጥሪውም የደረሰን በአሜሪካ ኤምባሲ በኩል ነው፡፡ የተነገረኝም ቀደም ብሎ ነው፡፡ ከሦስት ሣምንት ወይም ከአንድ ወር ቀደም ብሎ ነው፡፡ ጊዜውን በትክክል ስለማላስታውሰው ነው፡፡ እኛ በዛ መሠረት ስብሰባውንም ይመሩ የነበሩት የአሜሪካ አምባሣደር ነበሩ፡፡ ስለዚህ እኔ የደረስኩት ግማሽ ላይ የእነሱ ስብሰባ እያደረጉ /አመታዊ ስብሰባ/ የለጋሽ ሀገሮች ስብሰባ፡፡ ስለዚህ ለኛ የተያዘው ፕሮግራም ከዘጠኝ ሰአት እስከ 10፡30 ነበር፡፡ እና የአሜሪካ አምባሣደር ንግግር እንዳደረጉ የእለቱ ልዩ እንግዳቸው እንደሆንኩ ካስተዋወቁ በኋለ ይዤ የቀረብኩትን ንግግር አቀረብኩ፡፡
ይዤ የቀረብኩት ፅሁፍ መጀመሪያም ስጋበዝ እንደተናገረኝ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ፖለቲካና ቀጠናው ላይ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ ወደፊት ምን ሊያደርግ አስቧል እንደ አንድ አማራጭ የፖለቲካ ኃይል ሲመጣ ይዟቸው የተነሣቸው መሠረታዊ ሀሣቦች ዝርዝር የፖሊሲ አማራጮች ምንድን ነው የሚለውን አጠቃላይ የሆነውን የመጨረሻ እይታ ለማሣየት ነው የሞከርኩት፡፡ አቅጣጫውን የኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ አሠላለፍ ፣ የመንግስትን እርምጃዎችና ከ1997-2005 የሆኑትን ነገሮችን በእኛ እቅድ ላይ ያሉትን አጠቃላይ ሁኔታዎች ለማሣየት እንዲሁም ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ ናት፡፡ የምስራቅ አፍሪካ ውስጥ ትልቅና የረጋ የብሔር ስብስብ ነው ያለው፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ሰላሙና ኃይሉ ለምስራቅ አፍሪካ ቅርብ ነው፡፡ ሜድትራኒያን አለ፣ ቀይ ባህር አለ፣ አባይ አለ፡፡ ሁለተኛ ነገር ይሄ ሽብርተኝነት የሚባለው ነገር አለ፡፡ ነዳጅ አለ እነዚህ ሁሉ ያሉበት ቀጠና ስለሆነ፣ እንደ አንድ የፖለቲካ አማራጭ ስንመጣ እንደዚህ ያሉት ችግሮች ሁሉ አጠቃላይ የሆነ እይታ ሊኖረን እንደሚችል ጠይቀውኛል፡፡ እኔም በፅሁፌ አብራርቻለሁ፡፡
በወቅቱ የነበረው የአምባሣደሮች ቁጥር ወደ 35 አካባቢ ይሆናሉ፡፡ የትላልቅ ሀገሮች አምባሣደሮች በሙሉ አሉ፡፡ ፈረንሣይ፣ ጀርመን፣ አውስትራሊያ፣ እንግሊዝ፣ ስፔን እንደመሰለኝ እንደውም የምእራባውያን ብቻ ይመስለኝ ነበር፡፡ ዳሩ የለጋሽ ሀገሮች ቡድን ግን እንግሊዘኛ በደንብ የማይናገሩ መልካቸው ወደ ጃፓን የሚያደላ ሲናገሩ ነበር፡፡ እዛ ውስጥ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ለጋሾች ናቸው፡፡ ማን ነው ያለው ፣ ማን ነው የሌለው የሚለውን ባላውቅም የፖሊሲ አፈፃፀማቸውን የሚገመግሙበት ስብሰባ መሆኑን አውቃለሁ፡፡
እዛ ካገኙኝ በኋላ ብዙ ነገር ጠይቀውኛል፡፡ እኔ አጠቃላይ እይታዬን ነው ያቀረብኩት፡፡ እነሱም ቢሆን በጣም ብዙ ጥያቄ ጠይቀውኛል፡፡ “የአረቡ አለም አብዮት ኢትዮጵያ ውስጥ ይመጣል ብለህ ታስባለህ ወይ; እንደዛ አይነት ሰፊ የተቃውሞ ሰለፍ እንዴት በአጭር ጊዜ ውስጥ ማደራጀት ቻላችሁ; በብዛት ወጣቶች ላይ ትኩረት እንደማድረጋቸው ወጣቶች ላይ የፖሊሲ ትኩረት አላች ወይ; እዛ ሰልፍ ውስጥ የወጣው የተለያየ የሕብረተሰብ ክፍል አይነት ነው፡፡ እስራትን በመቃወም የሚጠይቅ አለ፣ የኑሮ ውድነቱን በመቃወም የሚጠይቅ አለ፣ የታሰሩ ሰዎች እንዲፈቱ የሚጠይቅ አለ፡፡ ስለነፃነት የሚጠይቅ አለና እነዚህ ሁሉ በሰማያዊ ፓርቲ የፖሊሲ አቅጣጫ እንዴት ነው ሊፈቱ የሚችሉት” እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ጠየቁኝ፡፡ ብዙ አይነት ዝርዝር ጉዳዮችንም ጠይቀውኛል፡፡ ብዙ ነው ያነሱት በጣም ትኩረት ሰጥተው ነው የሚጠይቁት፡፡ ከዛም በኋላ ስለ 2007 ምርጫ ሁሉ ጠይቀውኛል፣ እንዴት ነው ተሣትፏችሁስ ዝግጅታችሁስ ሲሉኝ እኔም ያው እንደምናሸንፍ መጠነኛ የሆነ እንኳን መስፈርቱን የሚያሟላ ምርጫ ከተገኘ ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ኃይል አላቸው ተብለው የሚታዩ፣ የሚታመኑ፣ በሙሉ በኃይማኖት መሪዎቹም ዘንድ ፣ በእስልምናና በክርስትናም እንዲሁም በአደባባይ ምሁራን ዘንድ በሌሎቹም የሕብረተሰብ ክፍሎችም ውስጥ በሙሉ ትልቅ ድጋፍ በዩንቨርስቲዎችም ሆነ በተቋሞች ውስጥ ድጋፍ ያገኘ በሚዲያውም ጭምር በአለም አቀፉ ኮሚቴውም ከዛ ሲያልፉ ደግሞ ወጣቱን የሚያንቀሣቅሰው ፓርቲ በሙሉ ወጣቶች በመሆናቸው እነዚህ ኃይሎች ተዳምረው ውጤት ለማምጣትና ለውጥን ለመሸከም ዝግጁ ናቸው፡፡ ስለዚህ ሰማያዊ ፓርቲ በ2007 እንደሚያሸንፍ ነገርኳቸው፡፡
ስታሸንፉስ ማለትም ኢህአዴግን በልጣችሁ ድል ብታገኙ ከኢህአዴግ ጋር የሚኖራችሁ ግንኙነት እንዴት ነው; ብለው ጠየቁኝ፡፡ እኛ ጋር ችግር እንደሌላ እኛ ለይቅርታ ዝግጁ እንደሆንን ወደፊትም እንደምናይ ምናልባት ከቦታቸው ላይ የሚለቁት ምርጫ ሲመረጥ የተሸነፉት ብቻ እንጂ ወታደራዊ ክፍሉም፣ ፖሊሱም፣ ደህንነቱም፣ ሲቪል ሰርቪሱም እንደሚቀጥል፡፡ ለብሔራዊ እርቆች ለመነጋገር ዝግጁ እንደሆንን ተቋማት እንደተቋማት እንደሚቀጥሉ አስረድቻቼዋለሁ፡፡
በወቅቱ ተገኝቼ ያየሁት መንፈስ አሁን እንግዲህ እኔ እንደሚመስለኝ ኢህአዴግ የማታለል ፖሊሲውና ተግባራዊው ነገር እየተራራቀ እንደሆነ ነው የምረዳው፡፡ ኢህአዴግ ሁሌ ማታለል ነው ስራው፡፡ የሚላቸው ዳታዎቹና የሚሰራቸው ነገሮች እጅግ የተራራቁ ናቸው፡፡ ስለዚህ በአንፃሩ ደግሞ ካለው መንግስት ጋር መስራት አለባቸው፡፡ ያለውን ብሔራዊ ጥቅማቸውን በቀጠናውም ሆነ የአገራቸውን ነገር ለማስጠበቅ፡፡ ስለዚህ ከእነሱ ጋርም ያላቸው ነገር በቀላሉ እንዲበላሽ የሚፈልጉ አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ ዲፕሎማሲ ሲበዛ በጣም ጣጣ አለው፡፡ ሚዛን ጠብቀህ መሂድ አለብህ፡፡ ለአንድ የተለየ አድሎ እንዳለህ አሣይተህ መሄድ የለብህ፡፡ ስለዚህ ካለው ኃይል ጋር ዋናው ነገር ብሔራዊ ጥቅማቸውን ማስጠበቅ ስለሆነ ያንን ሚዛን ጠብቀው ይሄዳሉ፡፡ ግን የኢትዮጵያዊያን ዋናው ጥሩ ነገር አሁን ያገኘነውን እድል እንዲታወቅ የምፈልገው፣ የኢትዮጵያም ሕዝብ እንዲያውቀው የምፈልገው ከጠነከርን አማራጩንም የአገራችንን ጉዳይ በራሣችን ኃላፊነት መፍታት እንደምንችል ሲረዱ እነሱ ለኛ ለመስራት ይመጣሉ፡፡ እነሱ ይጫኑልናል፣ መንግስትን ይገፉልናል አይደለም፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ይልቃል የሚባል ፓርቲም አልነበረም፡፡ መጣን ተነቃነቅን ፣ ተስፋ አሣየን፣ ሚዲያውም ስለኛ ፃፈ ፣ ወጣቶችም ተነቃቁ፡፡ ጥያቄያቸውን አንሣንላቸው ወጡ፣ ከዛ በኋላ ደግሞ ኢንተርናሽናል ኮሚኒቲውም ከኛ ጋር ለመስራት መጣ ፣ ማየት ያለብን እኛ ኢትዮጵያዊያን ከጠነከርን ከአለም ጋር ለመስራት ጥሩ ባህሪ አለን፡፡ ሚዛናዊነት አለን፣ አስተዋይነት አለን፣ ስስት የለብንም ፣ ከጐረቤቶቻችን ጋር የመኖር ጥሩ ባህል አለን፡፡ ይህንን ጠብቀው ከኛ ጋር ለመስራት ይመጣሉ፡፡ ነገር ግን እኛ በተዳከምን ቁጥርና ኢህአዴግ ዘላቂነቱን ካረጋገጠ ግዴታ ከኢህአዴግ ጋር ለመስራት ይገደዳሉ፡፡ ስለዚህ እኛ ጋር ነው ቁም ነገሩ ያለው፡፡ የለውጥ አማራጭ ሆነን በታየን ጊዜ ሕዝባችንን ማንቀሣቀስ የምንችል ሆነን በታየን ጊዜ ፣ መሠረታዊ ድጋፉ እንዳለን ባወቁ ጊዜ ከኛ ጋር ይሰራሉ፡፡
ባለፈው ሰልፍ በወጣንበት ጊዜ ያነሣናቸው ጥያቄዎች ላይ የታሰሩ ሰዎችን በሚመለከት ጥያቄ አንስቻለሁ፡፡ የኢትዮጵያን አጠቃላይ ሁኔታ ስገልፅ ሰዎች ያለአግባብ እንደሚታሰሩ፣ ስለኃይማኖት ነፃነት የጠየቁ ፣ የመንግስትን አሠራር የተቹ እስክንድር ነጋን የመሳሰሉ፣ በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት የታሰሩ እንደ አንዱላምን የመሰሉ፣ ርዕዩትን የመሰሉ ጋዜጠኞች እንዲሁም በእስልምና እምነት ላይ ነፃነት ያስፈልገናል በኃይማኖታችን ጉዳይ መንግስት ጣልቃ አይገባ፣ ኃይማኖትና መንግስት የተለያየ ስለሆነ ይህንን ነገር ኢህአዴግ ያቁም ብለው የራሣቸውን መሪዎች እንምረጥ በማለታቸው እስር ቤት የወረዱ የሙስሊሙ ማህበረሰብ የመፍትሄ አፈላላጊዎች በብዛት ወጣቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ ይህንን ነገር በአስቸኳይ እንዲያስተካክል እኔም ጠይቂያለሁ፡፡ አሁንም ቢሆን እኛ የምንሰራበት ሁኔታ ግፊት አይነት መሆኑን እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲደርስ ደግሞ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ዝም ማለት እንደሌለበት በሞራልም ፣ በሀሣብም ከኛ ጋር መቆም እንዳለበት መንግስትንም መጠየቅ እንዳለበት ደጋግሜ አስረድጃለሁ፡፡

ብርቱ ሰው! (The Iron Man) – (ከተመስገን ደሳለኝ)

$
0
0

eskindir
ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ
…አራት ኪሎ በሚገኝ አንድ ካፍቴሪያ ከጓደኞቼ ጋር የደራ ወግ በመያዜ፣ የእጅ ስልኬ የ‹‹መልስ ስጠኝ›› ጩኸቱን ደጋግሞ ሲያሰማ ልብ አላልኩትም፤ እናም ጮኾ ጮኾ ሲጨርስ፣ እንደገና ይጀምራል፡፡ ይኼኔ ጥሪውን እንዳላስተዋልኩ የተረዳው ጓደኛዬ ወደ ስልኩ ሲያመላክተኝ፣ ቁጥሩን አየሁት፤ አውቀዋለው፡፡ የእስክንድር ነጋ ባለቤት የጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ነው፤ አነሳሁት፡፡
‹‹በጣም ይቅርታ! ከሰዎች ጋር ጨዋታ ላይ ሆኜ ነው ያልሰማሁት…››
‹‹ለአስቸኳይ ጉዳይ ፈልጌህ ነበር፤ የት ነህ?››
‹‹ምነው? ምን ተፈጠረ?››
‹‹በስልክ አልነግርህም፤ መገናኘት አለብን››
‹‹እኔ አራት ኪሎ አካባቢ ነኝ››
‹‹ጥሩ! እኔም ፒያሳ ስለሆንኩ ‹ቲሩም ካፌ› እንገናኝ››
‹‹አሁኑኑ መጣሁ፡፡››
የሆነ ሆኖ የስልክ ንግግራችን ቢቋረጥም ድምጿ ከወትሮ የተለየ ስለሆነብኝ በእጅጉ ግራ ተጋባሁ፤ ምን አጋጠማት? እስክንድር ምን ሆነ? መቼም ኢህአዴግ ‹‹አስተዳድረዋለሁ›› የሚለውን ህዝብ ከፋሽስቱ ጣሊያንም በከፋ ጭካኔ እያሰቃዩ መደሰትን መገለጫው አድርጎታል፤ ታዲያ ዛሬ ደግሞ ምን ፍጠሪ እያላት ይሆን? ጥቂት ጥያቄዎች በውስጤ ቢመላለሱም፣ ጓደኞቼን በአጭሩ ተሰናብቼ በፍጥነት ‹‹ቲሩም ካፌ›› ደረስኩ፤ ቀድማኝ ስላገኘኋትም ወንበር ከመያዜ በፊት፡- ‹‹እስክንድር ከነበረበት ዞን ተቀይሯል!›› ስትለኝ በደንብ አልሰማኋት ኖሮ ‹‹ወደ ዝዋይ ተቀየረ›› ያለች መስሎኝ ደነገጥኩ፤ በሁኔታዬም የተናገረችውን አለመረዳቴ ገባትና፡-
‹‹ወደ ሌላ ዞን ተቀይሯል›› ብላ ደገመችው፡፡ ኡፍ-ፍ… በእፎይታ ተንፍሼ ሳበቃም፣ ወንብር ከሳብኩ በኋላ ወዴት እንደተቀየረ ጠየኳት
‹‹ወደ ዞን ሁለት››
‹‹ማን ነገረሽ?››
‹‹ዛሬ አግኝቼው ነበር፤ ‹በጣም ስለምፈልገው፣ ነገ ምንም ጉዳይ ቢኖረው ይሰርዝና ይዘሽው ነይ› ብሎኛል፤ ከባድ ጉዳይ ከሌለህ ሄደን እናግኘው›› አለችና መልሴን መጠበቅ ጀመረች፡፡ …ለጥቂት ደቀቃዎች ያህል በፀጥታ ከራሴ ጋር ተነጋገርኩ፡፡ ‹‹ከባድ ጉዳይ ከሌለህ…››
ያለችውን አስፈላጊ ስላልሆነ ችላ አልኩት፤ ምክንያቱም እስክንድር ነጋ ለምን እንደታሰረ እና ይህ ሁሉ መዓት ለምን እንደወረደበት ጠንቅቄ አውቃለው፤ ታዲያ! ነገ እርሱን ከማግኘት የከበደ ምን አይነት ጉዳይ ሊኖረኝ ይችላል? ያልገባኝ ነገር ግን የቃሊቲ ኃላፊዎች ከቤተሰቡ ውጪ ማንም እንዳይጠይቀው ከልክለውት እያለ እንዴት ብዬ ላገኘው እንድምችል ነው? ለደቂቃ ያህል በውስጤ ባስበውም መግቢያ ቀዳዳ አልታይህ ስላለኝ ይህ እንዴት ሊሳካ እንደሚችል እርሷኑ መልሼ ስጠይቃት፣ በፈገግታ ተሞልታ፡-
‹‹ከነገ ጀምሮ ማንም ሰው እንዲጠይቀው ተፈቅዷል፤ ሆኖም ፍቃዱ ብዙ ላይቆይ ይችላል የሚል ጥርጣሬ ስላለው ሌላ ሰው ከመስማቱ በፊት መጀመሪያ አንተን ማግኘት ፈልጓል›› አለችና ምርጊት የሆነብኝን ስጋት ገፈፈችው፡፡ መሀል ፒያሳ ድንገት የወረደ-ታላቅ የምስራች! …አቤት! ጀግናዬ! እንዴት ናፍቆኝ ነበር? ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት በህዳር ወር 2004 ዓ.ም ሲሆን፣ ያን ጊዜ ከታሰረ 45ኛ ቀኑ ነበር፡፡
ዛሬስ? በልቤ መቁጠር ጀመርኩ፤ ታህሳስ፣ ጥር፣ የካቲት… ድፍን አስራ ዘጠኝ ወር (አንድ ዓመት ከሰባት ወር) አልፎታል፡፡ …በመጨረሻም ከስርዓቱ ተለዋዋጭ ባህሪ አኳያ በ‹‹አማኝነት›› እና በ‹‹መናፍቅነት›› መሀል ብዋልልም፣ ጠዋት ሁለት ሰዓት ቃሊቲ እንድንገናኝ ተቀጣጥረን ተለያየን፡፡
በቀጥታ ወደ ‹‹አሲምባ›› (መኖሪያ ቤቴ) አመራሁ፡፡
ከአንድ ቀን በፊት ደብረዘይት ሄደው የነበሩት ባልደረቦቼ ሙሉነህና ዳዊት በፍጥነት ወደ ‹‹አሲምባ›› እንዲመጡ በስልክ ነገሬያቸው ሳበቃ አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ነገን መናፈቅ ጀመርኩ፡፡ ኦ! እንዴት አይነት ግሩም ቀን ነው! ብቻዬን አወራለሁ፤ እስቃለሁ፡፡ እስክንድር ሆይ! በአይነ ስጋ ልንተያይ የሰዓታት ዕድሜ ብቻ ቀርቶናል!!
…በኢትዮጵያ ምድር፣ በኢህአዴግ መንግስት ‹‹ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት›› እንዲከበር እና ስርዓቱ ከጠመንጃ ማምለክ ህግን ወደ ማክበር ይመጣ ዘንድ የከፈለው መስዕዋትነት በአንድ መጣጥፍ ተዘርዝሮ እንደማያልቅ ለውጥ ፈላጊው ወገን ብቻ ሳይሆን፣ እንደ‹‹ክፉ እንጀራ አባት›› ከስር-ስሩ እየተከተሉ በሾኬ የሚጥሉት እነበረከት ስምዖንም ያውቃሉ፡፡ በፍርድ ቤት የአስራ ስምንት ዓመት እስር የተወሰነበትም ለ‹‹ጥፋተኝነቱ›› ማስረጃ ተግኝቶበት እንዳልሆነም ጨምረው ያውቃሉ፡፡ ሀገሬውም ያውቃል፡፡ እኔም አውቃለሁ፤ ወዳጄ እስክንድር ንፁህ ነው፤ በተለይም ‹‹በህቡዕ ህገ-ወጥ ድርጅት መስርቶ ፀረ ህገ-መንግስት እንቅስቃሴ ሊያደርግ ሲል ደረስንበት›› ያሉት ውንጀላ ፍፁም ሀሰት ለመሆኑ በነፍሴም በስጋዬም እምላለሁ፤ ዘመኔን ሙሉ እንዲህ አይነት ነጭ ውሸት ሰምቼ አላውቅም፡፡ ምክንያቴን በአዲስ መስመር ልንገራችሁ፡፡
(ታሪኩ የሚጀምረው ግንቦት 22/2003 ዓ.ም ከቀኑ አምስት ሰዓት አካባቢ ስልክ ደውሎ የት እንዳለው ጠይቆኝ፣ በአስር ደቂቃ ውስጥ ተገናኘተን ለምን እንደፈለገኝ ካስረዳኝ በኋላ ነው፤ እናም በዕለቱ የተነጋገርነውን እንደወረደ ላስቀምጠው)
‹‹ምን ታስባለህ?››
‹‹ስለምኑ?››
‹‹ስለአጠቃላይ ሁኔታው››
‹‹እስኬ! አልገባኝም?››
‹‹ከዚህ በኋላም ዝም ብለን እየፃፍን ነው መቀጠል ያለብን ብለህ ታስባለህ?››
‹‹ታዲያ! ሌላ ምን አማራጭ አለን?›› በአግራሞት ጠየኩት፡፡ ያሰበውን ዘርዝሮ ነገረኝ፡፡ …ለየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ የማይወግን የ‹ሲቪክ ማህበር› መስርተን ህዝቡ መብቱን እንዲጠይቅ ከመቀሰቀስ ጀምሮ ፓርላማው ህጋዊ ስላልሆነ ፈርሶ በአስቸኳይ (ሁሉንም የፖለቲካ ድርጅቶች በዲሞክራሲያዊ መንገድ የሚያሳትፍ) አዲስ ምርጫ እንዲደረግ የአደባባይ ስብሰባና ሰልፍ ማዘጋጀትና የመሳሰሉትን እንቅስቃሴ መፍጠር እንደሚቻል ጆሮ-ገብ በሆነ ድምፁ አብራራልኝ፡፡ በተመስጦ አዳመጥኩት፡፡ እፁብ ድንቅ አሳብ!
በመጨረሻም በተግባራዊው እንቅስቃሴ ላይ ከተነጋገርን በኋላ፣ ኢህአዴግ ለውንጀላው ክፍተት እንዳያገኝ እያንዳንዷን ድርጊት በህጋዊ መንገድ ብቻ እንዲሆን ጥንቃቄ ማድረግን ጨምሮ ስራችንን ለመጀመር የሚያስፈልገውን ገንዘብ ከሀገር ውስጥም ሆነ ውጪ ካሉ ኢትዮጵያውያን ሳንጠይቅ በጋራ ለመሸፈን ተስማምተን፣ መስራች አባል የሚሆኑትን ስድስት ሰዎች የማሰባሰቡ ስራ የእኔ ሆኖ (ይህንን ሰበብ አድረገው ፍትህ ጋዜጣን ሊነጥቁን ስለሚችሉ እኔ በቀጥታ የቡድኑ አባል እንዳልሆን ያቀረበውን ስጋት ተቀብዬ) ከአራት ቀን በኋላ ምስረታው እውን መሆን እንዳለበት ወስነን ተለያየን፡፡
በቀጠሮው ቀን እስክንድርና ስድስቱ ወጣቶች ተገናኝተው ስለጉዳዩ በስፋት አብራርቶላቸው፤ በሃሳቡ ከተስማሙ በኋላ እስክንድርን ሰብሳቢ፣ የጋዜጣችንን ምክትል አዘጋጅ ሙሉነህ አያሌውን ም/ሰብሳቢ፣ ሪፖርተራችንን ዳዊት ታደሰን ፀሀፊ አድርገው መርጠው፣ በቃለ- ጉባኤው ላይ ፈርመው ቀጠሮ ይዘው ተለያዩ (በተሰበሰቡ ቁጥር በሁለት ኮፒ ቃለ-ጉባኤ ይያዛል፣ አንዱ እስክንድር ጋ፣ አንዱ እኔ ጋይቀመጣል) ደግመው ተገናኙ፤ ሰለሱ…፡፡ ከዚህ በኋላ እቅዱን የተመለከተ ዝርዝር መግለጫ በጋዜጣችን ላይ የሚወጣበት ቀን ተወሰነ፡፡ ሆኖም መግለጫው አርብ ከመውጣቱ በፊት ረቡዕ እስክንድር ‹‹የግንቦት ሰባት አባል እና የህዕቡ ድርጅት መስርተሃል›› በሚሉ ክሶች ከደረዘን በሚልቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት ተከቦ ተያዘና ማዕከላዊ ምርመራ ጣቢያ ታሰረ፡፡ መርማሪ ፖሊሶቹም የእምነት-ክህደት ቃሉን ሲጠይቁት ህጋዊ የ‹‹ሲቪክ ማህበር›› ከስድስት ወጣቶች ጋር በመመስረት ላይ መሆኑን አስረድቶ ሲያበቃ የግንቦት ሰባት አባልም ተባባሪም አለመሆኑን አፅንኦቶ ሰጥቶ ተናገረ፡፡ ምርመራውም ተጠናቆ ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ሲጀምር ሙሉነህና ዳዊት በመከላከያ ምስክርነት ቀርበው ማህበሩን አብረው እንደመሰረቱ፣ ሃሳቡ የእስክንድር ብቻ ሳይሆን የእነርሱም መሆኑን ህዝብ በታደመበት ችሎት መሰከሩ፤ ግና! ለ‹‹ካንጋሮ ፍርድ ቤት›› ከዕውነታው ይልቅ የእነበረከት ስምዖን ድራማ ይበልጣልና ሀቁን ሊቀበል አልወደደም፡፡ …በቃ!
እውነታውም የንፅህና ማረጋገጫውም ይህ ነው፤ ሌላ አይደለም (አሁን ወደ ርዕሰ-ጉዳያችን እንመለስ) መንግዶች ሁሉ ወደ ቃሊቲ…
እሁድ ጠዋት
ከጋዜጠኛ ሰርካለም ቀድመን በመድረሳችን እንደ ሊማሊሞ ዳገት ጠመዝማዛና ረጅም የሆነውን የእስረኛ ጠያቂዎች ሰለፍ ተቀላቅልን ተራችንን መጠበቅ ጀመርን፤ ከድፍን ሀምሳ አምስት ደቂቃ ጥበቃ በኋላ ተራችን በመድረሱ አሰልቺውን ፍተሻ አልፈን ወደ ውስጥ ገባን፤ ስለፍትህ የሚጮኸው ሰው ወደ ተጣለበት-‹‹ዞን ሁለት››
‹‹እስክንድርን አየዋለሁ›› ብዬ እርግጠኛ ስላልሆንኩ፣ ሙሌ ወደ ዲጄው (ጠያቂዎች የሚፈልጉትን እስረኛ ስም ሲነግሩት በማይክራፎን የሚጠራ ታሳሪ ነው) ተጠግቶ ‹‹እስክንድር ነጋን›› ሲለው በስጋት ነበር የማስተውለው፤ ይኹንና ዲጄው የተነገረውን ተቀብሎ ‹‹እስክንድር ነጋ፣ እስክንድር ነጋ….›› እያለ ሲጮኽ ድንገተኛ ደስታ አጥለቀለቀኝ፤ ኦ አምላኬ! ምኞቴ እውን ይሆን ዘንድ እርዳኝ! …በስሜት ተሞልተን እስረኞች በሚወጡበት በር ላይ ለበርካታ ደቂቃዎች አፈጠጠን፤ ሆኖም ጥቂት ታሳሪዎች ተከታትለው ከመምጣታቸው በቀር እስክንድር የለም፤ ዝምታ በተጫነው ገፅታ እርስ በእርስ ተያየን፤ ኩም-ኩምሽሽ ልንል ይሆን? …የዲጄው ድምፅ ‹‹ታምራት ገለታ፣ ታምራት ገለታ…›› ብሎ ያሰመጠንን የስጋት ፀጥታ አደፈረሰው፤ ይህን ስም አውቀዋለሁ፤ አንድ ሰሞን ከዜናነትም አልፎ፣ የመፅሄቶች እና የጋዜጦች ዋነኛ ማሻሻጫ ሆኖ እንደ ነበር አስታውሳለሁ፤ የጥሪው ድምፅ አየር ላይ ናኝቶ አፍታም ሳይቆይ ‹‹እያንገዋለለ/ አባባ ታምራት›› ውሃ ሰማያዊ ቀለም ያለው ሙሉ ልብስ በጥቁር ከረባት ለብሶ፣ አይኑ ላይ ጥቁር መነፅር ሰክቶ በፈገግታ ወደ ሚመለከቱት ሶስት ወጣት ሴቶች ወደ ቆሙበት አቅጣጫ ሲሄድ አየሁት፤ ሶስቱም ብስል ቀይ ናቸው፡፡ የሰውየው አለባበስ የእስረኛ አይመስልም፤ ምናልባት ተከታዮቹ ሊጠይቁት ሲመጡ ‹‹ዛሬም አምላክ ነኝ-አርጋለሁ፣ እበራለሁ›› ብሎ እያጭበረበረ ሊሆን ይችላል፡፡
…እስክንድር ግን አሁንም አልመጣም፡፡ ለዲጄው ነገርኩት፤ በተሰላቸ ድምፅ፡-
‹‹ጠብቀው ይመጣል›› አለኝ፤
‹‹ከእርሱ በኋላ የተጠሩ እስረኞች እየመጡ ነው›› መለስኩለት፤ በፀበኛ አስተያየት ገረመመኝና ‹‹እስክንድር ነጋ፣ እስክንድር ነጋ…›› ሲል አምባረቀ፤ ሰከንዶች አለፉ፡፡ አንድ ደቂቃ፣ ሁለት ደቂቃ… ሰዓታት ያለፉ ቢመስለኝም፣ አይኖቼን ከእስረኛ መውጫው ላይ አልነቀልኩም፤ ሸምገል ያሉ አንድ እስረኛ መጡ፤ ከኋላቸው ደግሞ ሌላ ሰው ተከትሏል፤ አየሁት፤ እርሱ ራሱ ነው፤ ልቤ በደስታ ወከክ ሲል ይታወቀኛል፡፡ አይን-ለአይን ተያየን፤ ደግሜ አየሁት፤ አላመንኩም፡፡ አዎን! ራሱ እስክንድር ነጋ ነው፡፡ ባርኔጣውን አጥልቋል፤ ፊቱ በማራኪ ፈገግታ ተሞልቷል፤ እርሱም በጣም የተደሰተ ይመስላል (ለነገሩ እንዴት አይደሰት! ከአስራ ሰባት ወራት በኋላ ከቤተሰቡ ውጪ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጠያቂዎች ጋር ሲገናኝ!) አጠገባችን እስኪደርስ አፍጥጬ ተመለከትኩት፤ በጭራሽ እስር ቤት የቆየ አይመስልም፤ አብሬው በዋልኩባቸው ጊዜያት ሁሉ ከራሱ አልፎ በእኔም ላይ ይጋባ የነበረው ያ ጠንካራ መንፈሱ ዛሬም አብሮት አለ-ክቡድ መንፈስ፡፡ ‹‹ብሶት የወለደው›› ገዥው ፓርቲ ለሃያ ዓመታት የመከራ ናዳ ቢያወርድበትም-አልተበገረም፡፡ ይህ ሰው መቼም የሚሸነፍ፤ መቼም እጅ የሚሰጥ፤ መቼም የሚከሽፍ አይመስለኝም፡፡ የእስር ቤት ኑሮም የትግል ፍላጎቱን ይበልጥ ኃያል አድርጎታል፡፡ ብርቱው-ሰው (The Iron Man) እስክንድር ነጋ፡፡
የሆነ ሆኖ መሀላችን ያለው የሽቦ አጥር የፈቀደልንን ያህል እጅ-ለእጅ ተነካክተን ሰላምታ ተለዋወጥን (ናፈቆትን የማያረካ-ሰቀቀን) እና ያሰብኩትን ያህል ባይሆንም ለተወሰኑ ደቂቃዎች አውርተን ስናበቃ ለምን እንደፈለገኝ ነገረኝ፡፡
‹‹ትግሉ መቆም የለበትም፤ እጅ አንሰጥም፤ አሁን የምነግርህን በሙሉ በአእምሮህ እንድትይዘው እፈልጋለሁ››‹‹ግዴለም፤ ንገረኝ ለሶስት ተረዳድተን እናስታውሰዋለን››
‹‹በጣም ጥሩ! መልዕክቱን ራስ ከፃፍከው በኋላ ለአሜሪካ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ እንዲደርስ እና በመረጥከው ሚዲያ ላይ እንዲታተም አድርገው›› አለና ከሸሚዝ ኪሱ የተጣጠፈ ወረቀት አወጥቶ ከዚህ በታች የምታነቡትን መልዕክት ያለ ማስታወሻ ደብተር እንድይዘው አብራራልኝ፤ (በድጋሚ ወደ ቃሊቲ አምርቼ፣ መልዕክቱን በትክክል መረዳቴን አረጋግጫለሁ)
ልፅ ደብዳቤ ለኦባማ አስተዳደር!
ሁላችንም እንደምናውቀው በሀያኛው ክፍለ ዘመን የመጨረሻ ዓስርታት በተለያዩ ክፍለ አህጉራት ውስጥ ባሉ ታዳጊ ሀገር ህዝቦች የተነሱ የፖለቲካ እና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች በቀዳሚነት በጠመንጃ ኃይል የተደገፉ ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያም በተመሳሳይ የታሪክ ክስተት ማለፏን የሚመሰክረው ዛሬም ወታደራዊ ስርዓቱን ብቻ ሳይሆን፣ ይህንን መንገድ የመረጡትን ጥቂት የተቃዋሚ ድርጅቶችንም በጦር ኃይል ድል አድርጎ ስልጣን ላይ ያለው ኢህአዴግ መሆኑ ነው፡፡ ይሁንና የቀዝቃዛው ዓለም ጦርነት ማብቃትና የአሜሪካ ብቸኛ ልዕለ ሀያል ሀገር ሆኖ መውጣት በኃይል የሚደረጉ ‹‹ፀረ-አምባገነን›› ንቅናቄዎች ሰላማዊውን መንገድ ብቻ እንዲከተሉ ሁኔታዎችን አመቻችቷል፡፡ የለውጡም ዋነኛ መግፍኤ አሜሪካ ለሰላማዊ ትግል የምትሰጠው ከፍ ያለ ቦታ ብቻ ሳይሆን የምታደርገው እገዛም መሆኑ አከራካሪ አይደለም፡፡ በእርግጥ የአሜሪካ አስተዳደር በሰላማዊ ትግል ላይ ያለው አቋምና ለትግሉ የሚያደርገው ቀጥተኛ አበረታችነት የሀገሪቱ መስራች አባቶች ካነፁት የሞራል እና የፖለቲካ እሴት እንደሚነሳም አውቃለሁ፡፡ በኢትዮጵያ የ1983 ዓ.ምን የመንግስት ለውጥ ተከትሎ የተስተዋለው ‹‹ሰላማዊ የትግል አማራጭ›› እምነት አውድም ከዚሁ የአሜሪካ መንግስት አቋም ጋር የተዛመደ ሲሆን፣ ባለፉት ሀያ ሁለት ዓመታትም በሀገራችን ዓላማቸውን በሰላማዊ ትግል ያራመዱ ወገኖች በሙሉ በዚህ ከመሰረታዊ የነፃነተ እሴቶች የሚነሳውን የአሜሪካንን ድጋፍ እውነተኝነት በፍፁም ልብ በመቀበል መሆኑ አይሳትም፡፡ ነገር ግን በዚህ እምነት ተቀኝተው የትግሉን አማራጭ ለመከወን ሲታትሩ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ስቃይ እንደደረሰባቸው ለማወቅ ‹‹ስቴት ዲፓርትመንት›› በየዓመቱ የሚያወጣውን ሪፖርት መመልከት ብቻ በቂ ነው፡፡ እናም ሞት፣ እስር፣ ስደት እና ሌሎች መከራዎች በትግሉ አራማጆች ላይ የደረሰ (እየደረሰ) መሆኑ ለአሜሪካን የተደበቀ ጉዳይ አይደለም፡፡
ይኽም ሆኖ በግሌ የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አስተዳደር ‹‹ካለ ዲሞክራሲ ዕርዳታ የለም!›› የሚለውን መሰረታዊ የውጪ ጉዳይ መርሁን ለማስከበር አሁንም ቢሆን ጊዜው አልረፈደበትም የሚል እምነት ስላለኝ፣ ኢህአዴግ ለህግ የበላይነት ተገዢ እንዲሆን ከሀገሪቱ ነባራዊ የፖለቲካ ሁኔታም ሆነ በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ካለው አጠቃላይ ግንኙነት አንፃር፣ አሜሪካ የሚከተሉትን ተፅእኖ መፍጠሪያ አማራጮች ብትከተል በሀገር ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የነፃነት እንቅስቃሴ በእጅጉ ይጠቅማል ብዬ አስባለሁ፡፡
1.የኢኮኖሚ ማዕቀብ
አሜሪካ በየዓመቱ የምታደርገውን ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ደረጃ በደረጃ የሚቀንስ ኢኮኖሚያዊ ማዕቀብ ብትተገብር ኢህአዴግ ህግ አክባሪ እንዲሆን የሚገደድበትን ሁኔቴ ማመቻቸት ትችላለች ብዬ አምናለሁ፡፡ ሆኖም ማዕቀቡ ዋነኛ ግቡ ማድረግ የሚኖርበት ስርዓቱ ለአፈና የሚጠቀምባቸውን (ምንም አይነት የኢኮኖሚ ፋይዳ የሌላቸውን) ተቋማትና መንገዶች መሆን ይኖርበታል፡፡
2.የበረራ ማዕቀብ /Flight Embargo/
በሁለተኛነት መተግበር ያለበት ማዕቀብ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ከሀገር ሀገር የመዘዋወር መብትን የሚያግድ ቢሆን አስፈላጊውን ውጤት ያመጣል፡፡ ይህ የበረራ እግድ የተወሰኑ የስርዓቱ ቀዳሚ ባለስልጣናትን ብቻ የሚመለከት መሆን ይኖርበታል፡፡
3.የሰብዓዊ ዕርዳታ /Humanitarian Aid/
ሁለቱ ማዕቀቦች ሲጠነክሩ ሀገሪቱ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ሰብዓዊ ዕርዳታዎችን /Humanitarian Aid/ ማቋረጥ አይኖርባትም፡፡ ምክንያቱም የዚህ አይነቱ የዕርዳታ መስተጓጎል ዜጎችን ለከፋ ስቃይ ሊዳርግ የሚችልበት ዕድል ሰፊ ነውና፡፡ ዩናይትድ ስቴት ኦፍ አሜሪካ እነዚህን ማዕቀቦች በኢህአዴግ አስተዳደር ላይ ከጣለች፣ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ ያለውን ሁሉን አቀፍ የዲሞክራሲ መብቶችን የማስከበር ትግል በከፍተኛ ሁኔታ ታግዛለች፡፡ ይህን ማድረግ ደግሞ ሀገሪቷ ከቆመችበት ስለሰው ልጆች ነፃነት የመቆርቆር የሞራል ኃላፊነት ጋር በጥብቅ ይተሳሰራል፡፡የማዕቀቦቹ መተግበር ለኢትዮጵያ አምስት ዋና ዋና ጥቅሞችን ያስገኛል፡፡
1.የሰላማዊ ትግል ተዓማኒነትን ያጠናክራል በኢትዮጵያ ውስጥ እየተሞከረ ያለው ሰላማዊ ትግል የተሻለ አማራጭ እንደሆነ የትግሉ አራማጆችና ደጋፊዎች እንዲያምኑ ያደርጋቸዋል፡፡
2. ለለዘብተኞቹ
ይህ አይነቱ ጫና ከሚፈጥራቸው አዎንታዊ ለውጦች አንዱ በኢህአዴግ ውስጥ ያሉ ለዘብተኛ የአመራር አባላት እና ካድሬዎች ለበለጠ የፖለቲካ መብቶች መከበርና የተሻለ ስርዓታዊ ክፍትነትን ለማበረታታት ያላቸውን ተነሳሽነት እንዲያጠናክሩ ማድረግ ማስቻሉ ነው፡፡
3. ለአክራሪዎቹ
በድህረ-መለስ ኢህአዴግ ውስጥ ለዘብተኛ እና እጅጉን ፅንፈኛ ኃይሎች እንዳሉ ተስተውሏል፡፡የዚህ ማዕቀብ ተፅዕኖም ፅንፈኞቹ የስርዓቱ ባለስልጣናት ከሚያቀነቅኑት ኢ-ዲሞክራሲያዊ አካሄድና የጥላቻ ፖለቲካ እንዲታቀቡ አድርጎ ፖለቲካዊ መቻቻልን እንዲቀበሉ ያስገድዳቸዋል፡፡
4.ለሲቪክ ማህበራት እና ጋዜጠኞች
በሰላማዊው መንገድ በነፃነት እንቅስቃሴው ውስጥ በጉልህ ሲሳተፉ የነበሩትን እና እየተሳተፉ ያሉትን ጋዜጠኞች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ሲቪክ ማህበራት እየከፈሉ ያለው መስዕዋትነት ከፍ ያለ ዋጋ እንዳለው ከማረጋገጡም በላይ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ብቸኛው መንገድ ሰላማዊና ህገ-መንግስታዊ የትግል አማራጭ እንደሆነ እንዲያምኑና ትግላቸው ውጤት ሊያመጣ እንደሚችል እርግጠኛ ሆነው በመንገዳቸው እንዲፀኑ ያደርጋቸዋል፡፡
5. ለአሜሪካ መንግስት
የአሜሪካ መንግስት እነዚህን ሀገራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን እርምጃዎች መውሰዱ፣ ለኢትዮጵያውያን አሜሪካ ያለባትን የሞራል ኃላፊነት እየተወጣች መሆኑን ከማሳመን በዘለለ የገባችውን ቃል በመተግበር በሰላማዊ መንገድ አላማቸውን ሲያራመዱ ለስርዓቱ ጥቃት የተጋለጡ ፖለቲከኞች እና የመብት ተሟጋቾችን መታደግ አስችሎ፣ ከታሪክ ተጠያቂነት ዕዳ ነፃ ያወጣታል፡፡ በጥቅሉ እነዚህ ተመጋጋቢ ሂደቶች ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት የሚደረገውን ትግል በማፋጠን ሰብዓዊና ፖለቲካዊ መብቶች የተከበሩባት ሀገር ለመፍጠር ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖራቸው የማይናወፅ እምነት አለኝ፡፡
እስክንድር ነጋ /ከቃሊቲ እስር ቤት/
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

በወረባቡ የአንድነት አባላትን ጨምሮ 45 ወጣቶች መታሠራቸውን ፓርቲው ገለፀ

$
0
0

MillionsVoice1በደቡብ ወሎ ዞን በረባቡ ወረዳ በስግደት ላይ የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ አብዱ መሐመድ እና አቶ እንድሪስ አህመድን ጨምሮ 45 ወጣቶች መታሰራቸውን ምንጮቻችን ከስፍራው በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡

ከታሰሩት መካከልም ወጣት ሱልጣን መሐመድ በከፍተኛ ህመም እየተሰቃየ እንደሚገኝና እስካሁንም የህክምና እርዳታ እንዳልተደረገለት ተጠቁሟል፡፡ መንግስት የወረዳውን ነዋሪዎች የደሴው ሼህ ኑሩ ይማምን መገደል በሰላማዊ ሰልፍ ካላወገዛችሁ የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ አይሰጣችሁም፣ ዘርና ማዳበሪያም አታገኙም የሚል ማስፈራሪያ በካድሬዎች አማካኝነት እየተሰጠ መሆኑንም ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

በተለይ ከታሰሩት 45 ወጣቶች መካከል 3ቱ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች በመሆኑ የእድሜ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ እና ወጣቶቹ ከመስኪድ ውጭ በአካባቢው ሜዳ ላይ ሲሰግዱ ስለተወሰዱ አብዛኞቹ ቤተሰቦቻቸው እንደማያውቁና እስካሁንም እየፈለጓቸው መሆኑ ታውቋ፡፡ ወጣቶቹም ከታሰሩ ከሳምንት በላይ የሆናቸው ሲሆኑ እስካሁን ክስ እንዳልተመሰረተባቸው ተጠቁሟል፡፡ ይህን ዜና እስክናሰራጭ ድረስ ከታሳሪዎች መካከል  ከፊሉ በደሴ ቀሪዎቹ ደግሞ በሐይቅ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ እስር ላይ እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አመልክቷል፡፡ የዝግጅት ክፍሉም ከወረዳውና ከደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደርና የፀጥታ ክፍል ስለጉዳዩ ለማጣራት ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን በረባቡ ወረዳ በስግደት ላይ የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ አብዱ መሐመድ እና አቶ እንድሪስ አህመድን ጨምሮ 45 ወጣቶች መታሰራቸውን ምንጮቻችን ከስፍራው በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡

ከታሰሩት መካከልም ወጣት ሱልጣን መሐመድ በከፍተኛ ህመም እየተሰቃየ እንደሚገኝና እስካሁንም የህክምና እርዳታ እንዳልተደረገለት ተጠቁሟል፡፡ መንግስት የወረዳውን ነዋሪዎች የደሴው ሼህ ኑሩ ይማምን መገደል በሰላማዊ ሰልፍ ካላወገዛችሁ የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ አይሰጣችሁም፣ ዘርና ማዳበሪያም አታገኙም የሚል ማስፈራሪያ በካድሬዎች አማካኝነት እየተሰጠ መሆኑንም ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

በተለይ ከታሰሩት 45 ወጣቶች መካከል 3ቱ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች በመሆኑ የእድሜ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ እና ወጣቶቹ ከመስኪድ ውጭ በአካባቢው ሜዳ ላይ ሲሰግዱ ስለተወሰዱ አብዛኞቹ ቤተሰቦቻቸው እንደማያውቁና እስካሁንም እየፈለጓቸው መሆኑ ታውቋ፡፡ ወጣቶቹም ከታሰሩ ከሳምንት በላይ የሆናቸው ሲሆኑ እስካሁን ክስ እንዳልተመሰረተባቸው ተጠቁሟል፡፡ ይህን ዜና እስክናሰራጭ ድረስ ከታሳሪዎች መካከል  ከፊሉ በደሴ ቀሪዎቹ ደግሞ በሐይቅ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ እስር ላይ እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አመልክቷል፡፡ የዝግጅት ክፍሉም ከወረዳውና ከደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደርና የፀጥታ ክፍል ስለጉዳዩ ለማጣራት ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም፡፡

- See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5043#sthash.3wJCeMzM.dpuf

የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት እና የአንድነት መሪዎች እንደ ጋንዲ! በግርማ ሞገስ

$
0
0

በግርማ ሞገስ (girmamoges1@gmail.com)
ሰኞ ሐምሌ 15 ቀን 2005 ዓ.ም.

 

የሚሊዮኖች-ድምጽ-ለነጻነት የሚለው ስትራተጂካዊ ዘመቻ ግቡ ምን እንደሆነ እና እድሜው ሶስት ወሮች እንደሚሆን አንድነት ፓርቲ ግልጽ አድርጓል። ከመግለጫው እንደተረዳሁት አንድነት ፓርቲ ጊዜ ወስዶ ብዙ አውጥቶ እና አውርዶ ያሰላው ለነፃነት እና ለዴሞክራሲ የሚደረግ ዘመቻ ነው። አንድ ነገር ግልጽ መሆን የጀመረ ይመስለኛል። ከንዋዮች መንግስት ፍንቀላ ጀምሮ ኢትዮጵያችን ለ50 አመቶች ያህል ብዙ ህይወት እየከፈለች በፖለቲካ ስርዓት ለውጥ ትግል ጎዳና ስትወድቅ እና ስትነሳ ከርማ ዛሬ ትክክለኛውን ወደ ዴሞክራሲ
MillionsVoice1የሚያደርሳትን ጎዳና ያገኘችው መሰለኝ። ወደፊትም መውደቅ መነሳት ሊኖር ይችላል። መንገዱም አልጋ ባልጋ አይሆንም። ይሁን እንጂ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ ኢትዮጵያ ትክክለኛውን ጎዳና ማግኘቷን አብስሯል። የዚህ ዘመቻ ስሌት የፖለቲካ ትግል ባህላችንን እድገት ያመለክታል። የስልጣኔም ምልክት ነው። የሚሊዮኖች-ድምጽ-ለነፃነት ዘመቻ በርቀት ብርሃን አሳይቷል። በዚህ ጉዳይ ላይ ሶስት ተከታታይ ክፍሎች ያሉት ጽሑፍ በማቅረብ የተሰማኝን ለአንባቢ አጋራለሁ። ክፍል ሁለት በሽብር ህግ እና በሽብርተኛነት በታሰሩት የሰላማዊ ትግል ሐዋርያት ዙሪያ ያተኩራል። ክፍል ሶስት ደግሞ ዛሬ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ እና ወደፊት የሚካሄዱ ተመሳሳይ ዘመቻዎችን ከብክለት እና ከውድቀት ለመጠበቅ ይረዳሉ የምላቸውን ምክሮች አንድ ሁለት እያልኩ ለአንባቢ አቀርባለሁ። ክፍል አንድ ግን የፖለቲካ ትግል ባህል ሽግግር በማድረግ ላይ መሆናችንን እንደሚከተለው ያቀርባል።

የትናንቱ እንደሚከተለው ነበር። የገደልን እኛ (The People)። የሞትን እኛ (The People)። የትግሉ እና የድሉ ባለቤት ግን እርስ በርስ ካጫራሱን ቡድኖች ውስጥ በጦርነቱ የቀናው ቡድን ሲሆን የመሰረተው መንግስት ደግሞ የጋራ አገራችንን የግል የጓሮ እርሻው ያደረገ እና ከቀድሞው የከፋ ሽብርተኛ አምባገነን ነው የሚል ነበር የትናንት የፖለቲካ ትግላችን ታሪክ። የትናንቱ የፖለቲካ ለውጥ ትግል ጎዳና በጦርነት የተሞላ ነበር። ብዙ ትምህርት ቤቶች ፈርሰዋል። መንገዶች ወድመዋል። የጦር ካምፖች እና የጦር መኪናዎች ጋይተዋል። ያ ሁሉ የኛ ንብረት ነበር። በህዝባችንም መካከል መቃቃር እና ክፍፍል እያደገ እንዲሄድ በማድረጉ የተወሰኑት ጥለውን እንዲሄዱ እና ከቀረነው ውስጥም ወደ ውጭ የሚመለከቱ እንዲፈጠሩ አድርጎ አንድነታችንን ክፉኛ አዳክሟል የትናንቱ የፖለቲካ መንገዳችን። አዲሱን አምባገነን መንግስት አብዣኛው የአገሪቱ ዜጎች ህጋዊ አድርገው ስለማይቆጥሩት እሱ ስልጣን የጨበጠበትን የመጨራረስ አዙሪት ጉዞ እንድንደግም የሚሰብኩን አዳዲስ ቡድኖች ተፈጥረዋል። የፖለቲካ ትግል ባህላችንም ቢሆን በመገዳደል ደም የተጨማለቀ በመሆኑ የመንግስት ስልጣን የጨበጡት ግለሰቦች ስብዕናቸው የተሟጠጠ ነው። ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ደግሞ በስልጣን ላይ የሚገኙት መሪዎች ፖለቲካ ባህል ከደም መጽዳት እና ስብዕናቸው የተሟላ መሆን ወሳኝ ነው። ባጭሩ ከሶስት ሺ አመቶች በላይ አብሮን የቆየው የፖለቲካ ትግል ባህላችን ከዴሞክራሲ ጋር ጸበኛ ነው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲኽ ግን ህዝባችን የትናንቱን ደም አፋሳሽ የፖለቲካ ትግል ባህል አዙሪት ሰብሮ በመውጣት አዲስ የፖለቲካ ትግል ባህል ጀምሯል። ይኽ አዲስ ክስተት በትልቁ እውቅና እና ድጋፍ ሊለገሰው የሚገባ የፖለቲካ ትግል ባህል እድገት ምልክት ነው። ስልጣኔም ነው። የሙስሊሙ ማህበረሰብ ከአንድ አመት በላይ በበርካታ የኢትዮጵያ ከተሞች ያካሄዳቸው እና ዛሬም የሚያካሂዳቸው በድስፕሊን የታነጹ እንከን የለሽ ሰላማዊ የመብት ትግሎች የፖለቲካ ትግል ባህላችን ማደጉን ያመለክታሉ። መንግስት ለህዝብ ጥያቄዎች መልስ እንዲሰጥ ጫና ለማድረግ ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን በአዲስ አበባ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ አጀማመር እና አፈጻጸም የፖለቲካ ትግል ባህላችን ሰላማዊነትን እንደመረጠ ይጠቁማል። በተለይ ‘የሚሊዮኖች ድምጽች ለነፃነት‘ በሚል ቀዳሚ መርህ አንድነት ፓርቲ የኢትዮጵያን ሽብር ህግ እዲሰረዝ እና የህጉ ሰለባ የሆኑት የሰላማዊ ትግል ባህል ሐዋሪያት እንዲፈቱ በመንግስት ላይ ጫና ለማድረግ ሐምሌ 7 ቀን በጎንደር እና በደሴ ከተሞች ያካሄዳቸው ሰላማዊ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች የፖለቲካ ትግል ባህላችን መብሰሉን እና መሰልጠኑን ያመለክታል።

በተጨማሪ ሐሙስ ሐምሌ 12 ደግሞ አንድነት ፓርቲ ከሐምሌ 21 እስከ መስከረም 5 ቀን 2006 ዓመተ ምህረት የሚዘልቁ አዲስ የሚሊዮኖች-ድምጽ-ለነፃነት ዘመቻ ስምሪቶች ይፋ አድርጓል። እነሱም፥ በወላይታ ሶዶ፣ በመቀሌ፣ በድሬ ደዋ፣ በአዋሳ፣ በአምቦ፣ በደብረ ማርቆስ እና በአዲስ አበባ ያቀዳቸው ህዝባዊ ስብሰባዎች እና በባህር ዳር፣ በጅንካ፣ በአርባ ምንጭ፣ በአዳማ፣ በባሌ፣ በወሊሶ፣ በፍቼ፣ በአምቦ፣ በጋምቤላ፣ በአሶሳ እና በአዲስ አበባ ያቀዳቸው ሰላማዊ ሰልፎች ናቸው። እያንዳንዱ ዘመቻ ስኬታማ እንዲሆን እራሳችንን የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ሰራዊት አባል አድርገን የምንቆጥር በሙሉ የተቻለንን ያህል ተሳትፎ ማድረግ አለብን።

እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የአደባባይ ተቃውሞ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ በተካሄዱት ሰላማዊ ትግሎች እርስ በርስ አልተላለቅንም እኛ (The People)። ትምህርት ቤት፣ መንገድ፣ ፋብሪካ አልፈረሰም። ስራ አልተቋረጠም። የአንድነት ፓርቲ መሪዎች ሳይቀሩ በአደባባይ ከህዝብ ጎን ቆመው ሲታገሉ፣ ከህዝብ ጋር ሲታሰሩ እና ሲፈቱ አስተውለናል። አንድነት ፓርቲ አንድ የፓርላማ አባል (ግርማ ሰይፉ) ብቻ ቢኖረውም ካለምንም ስስት እሱንም በደሴው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ አሰማርቶት ነበር። እንግዲህ በአለማችን ታዋቂዎቹ የሰላም ትግል መሪዎች እነ ጋንዲ፣ ማርቲን ሉተር ኪንግ እና ሌሎችም ሌላ ምን አደረጉ? ያደረጉት ይኽንኑ ነበር። ከህዝባቸው ጋር እየታሰሩ እና እየተፍቱ መታገል። የሰላማዊ ትግል መሪዎች ከትግሉ ሂደት ውጭ አይሆኑም። ግባቸው እራሳቸውን መረማመጃ አድርገው ህዝቡን የአገሩ እና የስልጣን ባለቤት ማድረግ ነው። ይኽ የሰላማዊ ትግል ባህል ህዝብን ከማቀራረብ አልፎ የትግል እና የድል ፍሬ ባለቤት ያደርገዋል። ህዝብ መሪዎቹን በቀርብ እንዲያውቃቸው ያደርጋል። እንደ ትጥቅ ትግል የእውቀታቸው እና የአዕምሮዋቸው ጤንነት ደረጃ የማይታወቁ ካለ ህዝብ ተሳትፎ ብድግ ብለው አገር የሚያፈርሱ እንደ መለስ ዜናዊ አይነት መሃይም እና ንክ (እብድ) የትጥቅ ትግል መሪዎች ገዢዎቹ አይሆኑም። አዎ! መሐይም። አዎ! ጥራዝ ነጠቅ ነበር። የአልቤንያ እና የሲቪየት ህብረት አምባገነኖች የጻፉትን የፖለቲካ መመሪያ ቃል በቃል ገልብጦ ኢትዮጵያ ላይ በመድፋት የኢትዮጵያ ህዝብ በሽብር አስፈራርቶ አመራሩን እንዲቀበል ማድረግ አዋቂ መሪ አያደርግም። በአውሮፓ ከተሞች ስለ አየር ጸባይ በእንግሊዘኛ ቋንቋ መናገርም ብቻውን አዋቂ መሪ አያደርግህም። ተሳዳቢነት እና አጭበርባሪነትም አዋቂ አያደርግህም። የአዋቂ መሪ መስፈርቱ ሌላ ነው። የራስን አገር ህዝብ ታሪክ ሳትንቅ በጥልቀት አጥንተህ እና አውቀህ፣ ኢትዮጵያዊ የሆነ የአመራር አሳብ አመንጭተህ፣ ከተቃዋሚዎችህ ጋር አብረህ መስራት ችለህ፣ ቀደም ባለው ታሪካችን የተፈጸሙ ስህተቶችን አርመህ፣ ህዝብን አግባብተህ እና አቀራርበህ ፊቱን ወደ ዴሞክራሲ እና እድገት እንዲመልስ ማድረግ ከቻልክ ብቻ ነው ምናልባት አዋቂ መሪ የምትባለው። መለስ ዜናዊ ግን ችግራችንን አባብሶ ሄደ። የሆነው ሆኖ በጎንደር እና በደሴ እንዳስተዋልነው የአንድነት ፓርቲ መሪዎች እንደ ጋንዲ በህዝባቸው መካከል ሆነው መብት እንዲከበር ታግለዋል። ይኽ ሁኔታ ህዝባዊ ስብዕናቸው እንዲያድግ እንጂ እንዲሟጠጥ አያደርግም። የፖለቲካ ባህላቸውም ከገዳይነት ደም የጸዳ እንዲሆን ያደርጋል። በዚህ አይነት የትግልም ሆነ የድል ባለቤት የሚሆነው እራሱ ህዝቡ ነው። ማለትም በምርጫ የመንግስት ስልጣን ባለቤት የሚሆነው እራሱ ህዝቡ ነው። ስለዚህ ሰላማዊ ትግል እና ዲሞክራሲ የማይነጣጠል ዝምድና አላቸው።

ወሳኙ የውስጥ ትግላችን ነው። ዜናዎች እንደሚያመለክቱት የአውሮፓ ህብረት፣ አምንስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂውማን ራይትስ ዋች፣ ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች ሳይቀሩ በኢትዮጵያ ውስጥ መብት ለማስከበር እየተካሄደ ባለው በሳል እና እንከን አልባ ሰላማዊ ትግል ተደንቀዋል። ድጋፋቸውን ለግሰዋል። እየተጠናከረ በሄደ ቁጥር ትግሉ የሚያገኘው ድጋፍ እንደሚጨምር አትጠራጠሩ። እንግሊዝ እና አሜሪካም ለምነውን የሚደጉን ቀን ቅርብ ነው። ወሳኙ የውስጥ ትግላችን መጠናከር እንደሆነ ለአንዲት ደቂቃ እንኳን እንዳንዘነጋ።

ስለዚኽ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጭ የምንኖር የሰላም ትግል ሰራዊት እና የዴሞክራሲ አርበኞች ኢትዮጵያውያን በመካሄድ ላይ ያለውን አገር አቀፍ የሚሊዮኖች-ድምጽ-ለነፃነት ዘመቻ በሙሉ ልብ መደገፍ እና መሳተፍ አለብን። እያንዳንዱን ዘመቻ ለማደራጀት (ለማዘጋጀት እና ለማኪያሄድ) ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ግልጽ ነው። የገንዘብ እርዳታ በማድረግ የዚህ ታላቅ የፖለቲካ ባህል ለውጥ ታሪክ አካል እንሁን! ነፃነት ገፋፊው የሽብር ህግ እንዲሰረዝ እና የህጉ ሰለባ የሆኑት የሰላማዊ ትግል ሐዋሪያት እንዲፈቱ በመንግስት ላይ ጫና ለማድረግ በተጀመረው ዘመቻ ካለ ምንም ስስት እንሳተፍ። በአሳብ ወይንም በገንዘብ! በተለይ በውጭ ያለን ዜጎች ዘመቻውን በገንዘብ በመርዳት ኢትዮጵያ በመስራት ላይ ባለቸው ታሪክ ላይ ማህተማችንን እናስቀምጥ!

በክፍል ሁለት እንገናኝ።

ሰበር ዜና: በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

$
0
0

mekelle_university_tigraiበመቀሌ ዩኒቨርስቲ ዛሬ ሐምሌ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3 ሰዓት በፕሬዘዳንቱ ቢሮ አካባቢ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ፡፡ ሰልፉን ያካሄዱት የዚህ ዓመት የክረምት የተፈጥሮ ሳይንስ የድግሪ መርሃ ግብር የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡ ተማሪዎቹ በዩኒቨርስቲው ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ ያካሄዱበት ምክንያት ቀደም ሲል ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት ትምህርቱን የሚከታተሉት ለ 6 ዓመታት እንደሆነ እና 4 ዓመቱን ከተከታተሉ በኋላ የባችለር ኦፍ ሳይንስ ድግሪ የምስክር ወረቀት እንደሚሰጣቸው፤ ቀሪው 2 ዓመት ደግሞ መምህር ለመሆን የሚያስችላቸውን የስነ ትምህርት ዘዴ(ፔዳጎጂ) እንደሚወስዱ መዋዋላቸው ተጠቁሟል፡፡ በዚህም ምክንያት 4 ዓመት የክረምት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችም በተዋዋሉት መሰረት ድግሪያቸው እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

የዪኒቨርስቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ክንዴ በበኩላቸው ተማሪዎቹ ሰልፉን እንዲበትኑ እና ከተወካዮቻቸው ጋር መነጋገር እንደሚቻል በገቡት ቃል መሰረት እንዳናገሯቸው ምንጮቻችን በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡ በመጨረሻም የተማሪዎቹ ተወካዮች ከፕሬዘዳንቱ ጋር ከተወያዩ በኋላ ፕሬዘዳንቱ አሰራሩን እንደማያውቁና በሌሎች የሀገሪቱ ዩኒቨርስቲዎችም ተመሳሳይ አሰራር ካለ አጣርተው ከ3 ቀናት በኋላ ምለማጣራትላሽ ለመስጠት ቀነ ቀጠሮ መያዛቸው ታውቋል፡፡ የዝግጅት ክፍሉም የዪኒቨርስቲው ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት እና ፕሬዘዳንት ጽህፈት ቤት ስለ ጉዳዩ ለማጣራት ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም፡፡

 

 


I am Ethiopian first – By Abebe Gellaw

$
0
0

emama

 

By Abebe Gellaw

It has come to my attention that my brief Facebook comment regarding a few controversial statements made by Jawar Mohammed has been posted on ECADF’s website as an article. I had no intention of writing a series piece on the issue. Quite obviously, there is a big difference between a well-thought out lengthy commentary and a brief message in a particular context.

My intention was just to appeal for calm and harmony, a necessary effort lacking in our political discourse. Often times, a message without its context is open to misinterpretation and misunderstanding. So there seems to be a need to clarify.

Politics, as far as I understand, is a mechanism of managing conflict of interests. It is a means of building consensus through dialogue and compromise. Since the early 1960s, the major political conflict in Ethiopia has been between ethno-nationalists and nationalists. The forces on both ends of the political spectrum have not still found a middle ground that can bring them towards consensus and compromise.

My understanding is that Jawar is an ethno-nationalist. As an ethno-nationalist, he says he is an Oromo first. Unlike him, I am a nationalist. But that is not the major problem. The problem is the way he has chosen to articulate and present his views in question that have been widely perceived as inflammatory and divisive.

I firmly and fervently believe that I am an Ethiopian first. I do not wish to allow the ethnic origin of my predecessors and parents to define me as a human being and overshadow my Ethiopian identity.

Jawar said Ethiopian identity was imposed on him. On the contrary, I argue that such a position is fundamentally flawed. Nowhere in the world is anyone given choices of national identity.

The Chinese-American writer, Eric Liu, once said: “The next time someone uses denial of citizenship as a weapon or brandishes the special status conferred upon him by the accident of birth, ask him this: What have you done lately to earn it?” Our predecessors, who have bequeathed us a country called Ethiopia with all its faults, challenges and problems, have made huge sacrifices in blood and flesh so that we’ll never be stateless. We should rather make sacrifices to reclaim our country and make our citizenship more meaningful by winning our rights, as citizens, to live in our country with full dignity, freedom and equality. We should make Ethiopia a country where every citizen and ethnic group is equal.

Unfortunately, our birthplaces also define the major problems and opportunities we inherit. Ethiopia is not a perfect nation. Far from it, it is defective and faulty as a result of the age-old tyrannies and injustices we have been condemned to suffer collectively.

Like any nation, it offers unique challenges as well as opportunities. With all its problems and baggage, Ethiopia is a nation of 80 million people. Our destiny is intertwined. We are diverse and yet we are all Ethiopians, whether we like it or not. I believe that rejecting Ethiopia as our country is not a solution to any of the problems we are supposed to confront. We should rather make strenuous efforts to reconstruct Ethiopia as a country where all of its citizens live in freedom, harmony, justice, peace and prosperity.

In the new Ethiopia we envision, there should be no room for inequality, injustice and tyranny. It should never be a prison for its children, regardless of their political, ethnic or cultural backgrounds. No ethnic or political group should be allowed to impose hegemony at the detriment of the majority.

The worst challenges all citizens of Ethiopia, except the oppressors, face are political oppression, grinding poverty, indignity, inequality, injustice and discrimination, just to mention a few among so many. At this time and age, what has been imposed on us is not national identity but the tyranny of the TPLF, an extremist ethno-nationalist group whose aim was nothing more than seceding Tigray. That is why we should continue struggling to throw off this backbreaking tyranny from our shoulders.

As I have clearly stated in another Facebook post, addressed to Jawar, “No nation-state was formed through consensus and democratic deliberations. Nation-states emerged out of conflicts, conquests, occupations and colonialism. While almost all African states were created by the colonial powers, Ethiopia was formed through internal processes. It was a painful process but not even as painful as what Native Americans and Europeans, who had gone through two devastating [world] wars.”

“We Ethiopians do not need to be bitter about the past. We are not part of the old history. But we certainly need to preserve our country and make it a nation for all correcting past injustices and mistakes. We need to move forward with a united spirit. As long as we can bring about real equality, justice, freedom and democracy, we will be fine. That is what we should all fight for rather than dwelling on the past [and gnaw old bones]. It is the present and the future that really matter….”

While I called for unity rather than condemning each other, making such inflammatory and controversial statements that turned out to be divisive are not only wrong but also damaging to our common cause for freedom. I said Jawar had misspoken. The dictionary definition of misspeak is not to endorse or approve. It means, “To speak mistakenly, inappropriately, or rashly.” I think that should be clear enough. It was particularly wrong for Jawar to speak in such a divisive ethno-religious tone at a time when we desperately need to unify to overcome and overwhelm the divide-and-rule tyranny of the TPLF. That is where he misspoke, in my humble opinion, without completely disregarding so many positive contributions.

I was under the impression that calling for sanity and unity at this critical juncture in our struggle would not also be misconstrued as a sign of weakness. I always see myself as a moderate. Compromise for the sake of the greater good is at times a mechanism to avoid unnecessary conflict and feelings. Even if that was my intention, I believe that we Ethiopians should never compromise on anything that undermines our unity, freedom, harmony and peace.

After all, our aspiration is to rebuild a united nation that will accommodate every citizen as equal and guarantee the freedom of every individual citizen including those who believe that they are the byproducts of their cultural and ethnic heritage. For that to happen, we need to preserve Ethiopia, a country that we will all be proud of when we claim our freedom despite its troubles and predicaments.

Anyone is not entitled to apologize on behalf of Jawar. If any apologies are needed, no one but only Jawar is entitled to make. As far as I am concerned, I am nobody’s apologist.

That said, I will be disingenuous if I do not repeat my main message. Let us move on with a united spirit and focus on our just cause for freedom, equality and justice. That is much more important than the war of attrition and divisiveness that is derailing our gains. Whenever we have problems, we should first have the courage to address them in a civilized manner. Again let us move on united as Ethiopians…

ትውልድ የማድን ሃላፊነት የማን ነው? በይበልጣል ጋሹ

$
0
0

 በይበልጣል ጋሹ

16916781ትውልዱ ከበፊቱ በበለጠ መሪ የሚፈልግበት ዘመን ነው። ጊዜውንና ዘመኑን የዋጀ ወላጅ፣ መሪና ህብረተሰብ ይፈልጋል። የዘመኑን ትውልድ በጥሩ ሥነ ምግባር፣ ለአገር ተቆርቁሪና በማንነቱ የሚኮራ አድርጎ ለማሳደግ ሃላፊነት ሊወስድ የሚችል አካል ያስፈልጋል። የነገ ሃገር ተረካቢ ትውልድ ግን ወደየት እሄደ እንደሆነ የሚያሳዩ በርካታ ምልክቶችን መጥቀስ ይቻላል። የትናቱንና የበፊቱን ትውልድ በማነኛውም መልኩ በእጅጉ የሚያስመሰግን ከሆነ ውሎ አድሯል/የበፊቱን ስርዓት ናፋቂ ባትሉኝ ደስ ይለኛል/። ትውልዱ በአለማዊነት ተፅዕኖ ውስጥ ወድቆ ማንነቱን የረሳ ትውልድ እንደሆነ በመሰረተ ሃሳቡ የምንስማማ ይመስለኛል። ከተስማማን መንስኤውና መፍትሄው ምን ይሁን? የሁላችን መሰረታዊ ጥያቄ ይሆናል።

መንስኤው፦

  1. አለማዊነት፦ ትውልዱ አለማዊነት የሚለውን ጽንሰ ሃሳብ በሚገባ ከአለማወቅ የመጣ ችግር ነው። ይህንን ሃላፊነት ወስዶ ሊያስገነዝበው የሚችል አካል በማጣቱ የመጣ ትልቅ ክስረት ነው። ወላጅ እንደ ወላጅ፣ መንግሥት እንደ መንግሥት፣ እያንዳንዱ ዜጋ እንደ ዜጋ ሃላፊነቱን በየደረጃው መወጣት ስላልቻለ አንድ ትውልድ በማጣት ላይ እንገኛለን። ይህን ደግሞ በአካባቢያችንና በሰፈራችን የምናያቸውን ነገሮች መጥቀስ ከበቂ በላይ ማስረጃዎች ናቸው። ልጅን በሃይማኖት ማሳደግ እንደኋላ ቀርነት ተቆጠረ፤ልጆችም ስለእምነትና ባህል መነጋገርንና መወያየትን ትተው ስለአለማዊነት “ስለ ግብረ ሰዶምና ሰይጣናዊነት” መነጋገር ከጀመሩ ውለው አድረዋል። ይህንና መሰል አስነዋሪ ድርጊቶች ሲከናወኑ እያየን ዝም በማለታችን ለትውልዱ መጥፋት በየደረጃው ተጠያቂዎች ነን። የመጀመሪያዉና ትልቁ ለትውልዱ መጥፋት መንስኤው ይህ ነው።
  2. ትምህርት ቤቶች፦ ተማሪዎችን በጥሩ ሥነ ምግባርና ባህልን ከማሳዎቅ አንጻር አስተምሯቸው ዝቅተኛና ከዚህ ግባ የማይባል መሆኑ ለትውልዱ መጥፋት ሌላው መንስኤ ነው። እንደሚታወቀው ትውልዱ ጥሩ ዜጋ እንዲሆንና እምነቱንና ባህሉን አክባሪ አድርጎ በማነጽ በኩል ት/ቤቶች ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ። ዛሬ ግን ትምህርት ቤቶችን ስንመለከት ከተቀረጸላቸው ሥርዓተ ት/ት ጀምሮ ትውልድን ለመቅረጽ ቀርቶ በዜግነት ደረጃም እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚናገር ትውልድ እንዳይጠፋ ስጋቴ ከፍ ያለ ነው።  ከዚህ ባለፈም አንዳንድ ት/ቤቶች የብልግና ድርጊት ተባባሪዎች በመሆናቸው ለትውልዱ መጥፋት ተቆርቋሪ አካል መጥፋቱን ያመላክታል /በህጻናት ላይ ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ መምህራን የሚገኙበት ት/ትቤቶች/። ወላጅም ልጆቻቸውን የሃይማኖት ት/ት ቤት ልኮ ሥነ ምግባር እንዲማሩ የማድረጉ ተግባር አናሳ ነው።    ከፍተኛ  ት/ት ተቋማትም የተማረና አገርን ሊረከብ የሚችል ዜጋ ይፈራበታል ብሎ ማሰብ ቅዥት እየሆነ መጥቷል፤ የመጥፎ ሱስ ተገዥዎች ቁጥር በግቢ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመር ላይ ነው፤ እንደ አንዳንድ ከተሞች በግቢ ውስጥም የዝሙት መፈጸሚያ ቦታውች ስም ተሰጥቷቸው እና እንስሳዊ ባህሪ ሲፈጸምባቸው እየታየ  ችግሩን ለመቅረፍ ግን የሚወሰድ እርምጃ የለም።
  3. መንግሥት፦ ትውልዱ ጥሩ ዜጋ እንዲሆን የማድረግ ሃላፊነትም ግዴታም ያለበት መንግሥት ነው። አገሪቱን እያስተዳደረ ያለው እርሱ እስከሆነ ድረስ አገር ተረካቢ ዜጋ የመፍጠሩ ስራ በዋናነት የመንግሥት ነው፤ ምንአልባት “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” ካልሆነ ነገሩ። ሃገራዊ ስሜት ያለው ዜጋ ለመፍጠር ይህን ስሜት ሊፈጥር የሚችል ሥርዓተ ት/ት፣ ሊተገብሩ የሚችሉ ትምህርት ቤቶችንና የማስተማር ብቃት ያላቸው  መምህራንን ማደራጀት እንዲሁም ለተማሪዎች ከምረቃ በኋላ የሥራ ዕድል ማመቻቸት የመንግሥት ግዴታ ነው። አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ግን ለትውልዱ መጥፋት የመንግሥት ተቆርቋሪነት ጎልቶ የሚታይበት አጋጣሚዎች ባለመኖሩ ችግሩ ሥር መስደዱና በእጅጉ አሳሳቢ መሆኑን እንመለከታለን። መንግሥት ግን ትውልዱ ጥሩ ዜጋ እንዲሆን ራዕይ የለውም? የዘወትር ጥያቄዬ ነው።
  4. ወጣቶችን ወደ አልተፈለገ ህይወት የሚመሩ ነገሮችን ቸል ማለት፦ በት/ት ቤቶችና ወጣቶች በሚያዘወትሩበት አካባቢ የሥነ ምግባር ብልሹነት ሊያጋልጡ የሚችሉ ነገሮችን ተቆጣጣሪ  አካል በመጥፋቱ ችግሩ እንዲባባስ አድርጎቷል። ለምሳሌ ጫት ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ አሽሽ ቤቶችና የሴተኛ አዳሪ ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ መጨመሩና ወደ እነዚህ ቦታወች መሄድ ከነውርነት አልፎ እንደ  ዘመናዊነት በመቆጠሩ ትውልዱ በግልጽና በድፍረት የድርጊቱ ተሳታፊ ሁኗል።
  5. ማህበራዊ መገናኛዎች/ social medias/ ማህበራዊ መገናኛዎች ትውልዱን የማዳንም የመግደልም አቅም አላቸው። ይህን ተገንዝቦ ለትውልዱ መዳን የሚሰሩ መገናኛዎች ግን ጎልተው አይታዩም። በተለይ የዘመኑ  መገናኛ ዜዴ በእጅጉ ትውልዱን ሰነፍና በአለማዊነት ተጽኖ ውስጥ እንዲገባ አድርጎቷል። ወደ አገራችን ኢትዮጵያ ስንገባ ደግሞ ጥበብ የሞላበት አጠቃቀም አይደለም የምንጠቀምው ከጊዜ ማጥፋት ጀምሮ እስከ አጉል ሱስነት ውስጥ እንድንገባ አድርጎናል። የፌስ ቡክና ትዊተር ተጠቃሚዎች በእጅጉ ታውቁታላችሁ። ትውልዱ ወደ አልተፈለገ ህይወት ውስጥ እንዳይገባ በማህበራዊ መገናኛ ዙርያም ትልቅ ሥራ ሊሰራ ይገባል።

መፍትሔው፦ በአጠቃላይ ከላይ በጥቂቱ የተዘረዘሩትን ችግሮች በሚገባ ማጤንና አገራዊ ጉዳቱን በመረዳት ትውልዱን ለማዳን ከቤተሰብ፣ ከጎረቤትና አካባቢ በመጀመር ግዴታችንን መወጣት መቻል ነው። ልጆቻችንን ዘመኑን በዋጀ መልኩ ማሳደግ፣ መከታተልና በመንከባከብ በጊዜ ሂደት ችግሩን ልንቀንሰው እንችላለን፤ ፈጽሞ  ማጥፋት ግን የሚታሰብ አይሆንም። ምክንያቱም ዓለም ሰይጣናዊነትን አሜን ብላ ስለተቀበለችሁ የዛ ነጸብራቅ ወደ ልጆቻችን መድረሱ አይቀርምና። ቢሆንም ግን ወላጆች ልጆቻችንን የት፣ ከማን ጋር እና በምን መልኩ መሄድ እንዳለባቸው ቀስ አድርገን በሚገባቸው መልኩ በማስረዳት በጥሩ ሥነ ምግባር ማሳደግ ይቻላል። ችግሩ ግን እኛስ ማን ነንና ለልጆቻችን አርያ የሚሆን ህይወት አለን? በፍቅርና ግልጽ በሆነ መልኩ ልጆቻችንን እያሳደግን ነው? ፍቅር የሞላበት የትዳር ህይወት፣ የጸሎት ህይወት አለን?

Hiber Radio: ግብጽ ኢትዮጵያ በአባይ ጉዳይ ጀርባዋን ሰጠችኝ ስትል ስጋቷን ገለጸች

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ሐምሌ 14 ቀን 2005 ፕሮግራም

>

በአሜሪካን አገር ጠበቃ የሆኑት አቶ ሳህሉ ሚካኤል የ17 ዓመቱን ወጣት

ትራይቮን ማርቲን በጥይት የገደለው ራሱን ለመከላከል ተብሎ ነጻ መባሉን አስመልክቶ ለህብር ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ

>

የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት አስተባባሪ ግብረ ሀይል ም/ል ቃል አቀባይ አቶ ሀብታሙ አያሌው ከሰጡን ወቅታዊ ቃለ ምልልስ (ሙሉውን ያዳምጡ)

ፕ/ት ኦባማ ያለ ወንጀሉ በጥይት የተገደለውን የ17 ዓመቱን ትራይቮን አስመልክቶ በይፋ ተናገሩ > (ከመቶ በላይ የአሜሪካ ከተሞች የተደረገውን የገዳይን ነጻ መባል የተቃውሞ ንቅናቄ በዘገባችን ቃኝተነዋል)

የአውሮፓ ሕብረት የፓርላማ አባላት እና የሰብዓዊ ጥበቃ ኮሚቴ አባላት በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው በአገዛዙ ሰብዓዊ መብት ላይ ስለሚያደርሰው በደል ጠቅሰው የሰላ ሂስ ሰንዝረዋል ።ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሁሉም የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ ጠይቀዋል

(ሙሉ ዝርዝሩን ከወቅታዊው ዘገባ ያዳምጡ)

ሌሎችም ቃለ መጠይቆች አሉን

ዜናዎቻችን
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከእስር ቤት ለፕ/ት ኦባማ የሚደርስ ግልጽ ደብዳቤ ጻፈ

አሜሪካ ሰብዓዊ ዕርዳታን የማይነካ የኢኮኖሚ ማዕቀብና በባለ ስልጣናቱ ላይ የበረራ ማዕቀብ እንድትጥል ጠይቋል

መድረክ በመቀሌ የተሳካ ሕዝባዊ ስብሰባ ማካሄዱ ተገለጸ

በአገር ውስጥ በበረራ ላይ የነበረ አውሮፕላን በድንገት አረፈ

ግብጽ ኢትዮጵያ በአባይ ጉዳይ ጀርባዋን ሰጠችኝ ስትል ስጋቷን ገለጸች

አሜሪካ በሟች ጥቁር ወጣት ትራይቮን ማርቲን ገዳይ የፍርድ ቤት ውሳኔ ሳቢያ ከመቶ በላይ ከተሞች ተቃውሞ ተደረገ

ቢዮንሴና ጄዚም ተሳትፈዋል

ፍሪያስ ኩባንያ ያባረራቸውን የስራ ማቆም አድማ ተሳታፊዎችን ወደ ስራ ለመመለስ በተመለከተ ከሽማግሌዎች ጋር ለመወያየት ጥሪ አቀረበ

ሌሎችም ዜናዎች አሉን

Art: ሁለገቧ አርቲስት አዳነች ወ/ገብርኤል

$
0
0

በማስረሻ መሀመድ

አርቲስት አዳነች ከአባቷ ወ/ገብርኤል ገብረ ማርያም እና ከእናቷ ፋና አምባው በ1952 ዓ.ም ይህችን አለም ‹‹ሀ›› በማለት ይፋትና ጠሞ በሚባል አውራጃ ካራቆሬ በተባለ ትንሽ ከተማ ውስጥ ተወለደች፡፡ እንደማንኛውም ልጅ እናትና አባቷን በቤት ውስጥ በማገልገል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በዚችው ካራቆሬ በተባለች ትንሽ ከተማ ውስጥ ተከታተለች፡፡ ከዛም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ደብረሲና ከተማ ውስጥ ከተከታተለች በኋላ 9ኛ ክፍል ሠንዳፋ ጅማ ሰንበቴ ትምህርት ቤት ከታላቅ እህቷ ኮማንደር ብርቄ ወ/ገብርኤል ጋር በመሆን እዛው ትምህርቷን እንድትከታተል ሆነ፡፡ ይሁንና የነበሩበት ከተማ በተለያዩ ምክንያቶች ስላልተስማማቸው አዳነችና እህቷ ብርቄ ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት ተገደዱ፡፡
Adanech
አዲስ አበባም አጎቷ ሻንበል ባሻ ተረፈ አንባ ጋር በመሆን ያቋረጠችውን ትምህርቷን ማለትም ከ9ኛ ክፍል በግዜው የፈጥኖ ደራሽ ካንፕ (ሙዚቃ ክፍል) አጠገብ ከነበረው ቅዱስ ጳውሎስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መማር ቀጠለች፡፡ ‹‹እንዴት ነበር ለትምህርት የነበረሽ ፍላጎት››? የሚል ጥያቄ አቀረብኩላት ‹‹ኦ ይሄ ነው ልልሽ አልችልም ብቻ ተመጣጣኝ ነው ማለቱ ይቀለኛል፡፡ እኔ በተለይ በቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት ቤት ስማር በግዜው በጣም ወጣት ነኝ ፍላጎቴ በሙሉ የነበረው ስፖርት ላይ ነው፡፡ እንዲሁም
ከዚሁ ትምህርት ቤት በፊት በተማርኩባቸው ት/ቤቶች በጠቅላላ ስፖርት ከመስራቴ ባሻገር ውድድር ውስጥ ሁሉ እገባ ነበር፡፡ እንደውም ጅማ ሰንበቴ ትምህርት ቤት ስማር ለስፖርት ተመርጬ ለውድድር ወደ አዲስ አበባ ስቴድየም የመጣሁበት ግዜ ሁሉ አለ፡፡ የምድር ዝላይ፣ ሪሌይ፣ 100 ሜትር ሩጫ እና ሌሎችንም ተወዳድሬ ወደ አራት ሜዳሊያዎችን ለትምህርት ቤቴ ያስገኘሁበትን ግዜ አልረሣም›› የሚል መልሷን ሠጠችኝ፡፡
ከዚህ በኋላ አዳነች በቅዱስ ጳውሎስ ትምህርቷን እየተከታተለች ቢሆንም ከፈጥኖ ደራሽ ካንፕ ሙዚቃ ክፍል የሚንቆረቆረው የባንድ ዜማ እና ከፍተኛ ድምቀት የነበረው የማርሽ ቡድኑ ጣዕመ ዜማ ከግዜ ወደ ግዜ ቀልቧን እየገዛ መጣ፡፡ ታዲያ በዚህ መሀል ፈጥኖ ደራሽ የሥራ ማስታወቂያ ለጠፈ፡፡
ይህን በመከተል ታዲያ 1968 ዓ.ም አዳነች በ16 አመቷ ትምህርቷን በማቋረጥ ፈጥኖ ደራሽ ያወጣውን መስፈርት በብቁነት በማለፍ ወደ ውትድርናው አለም ‹‹በእድሜ ትንሽ ብትሆንም እዚሁ ታድጋለች›› በማለት የሙዚቃ ክፍሉ ሀላፊ ኮረኔል አያሌው አበበ፣ ተስፋዬ አበበ እና ኮረኔል ግርማ በተወዛወዥነት እንድትቀላቀል አደረጓት፡፡ በዚህም ግዜ ፒያኖ፣ የማርሽ ሙዚቃና የተለያዩ በካንፑ ይሰጡ የነበሩ ትምህርቶችን በፖሊስነት ተምራና ሠልጥና ብቁ ሆና ተመረቀች፡፡ የፖሊስ ተወዛዋዥ ሆና ለስድስት ወር ሠልጥና ከተመረቀች በኋላ በህጉ መሠረት በግዜው የሚሞላ ቃል የመግቢያ ፎርም ነበረና በፎርሙ መሠረት ለሠባት አመት ላታገባ፣ ላትወልድና፣ የሰውነት አቋሟ ላይለወጥ ቃል ገባች፡፡ በህይወት ላይ መቼም አንዳች አይጠፋምና አዳነች ስራዋን ለተወሠኑ ግዜያት ከሠራች በኋላ በውዝዋዜው በግዜው ያሠለጥናት የነበረው ሻንበል ባሻ ጌታቸው አንዳርጌ በፍቅሯ በመውደቁ ጠልፏት እቤቱ ይዟት ገባ፡፡ ይህ ሲሆን ታዲያ በካንፕም በመሠማቱ ከፍተኛ ቁጣን አስነሣ፡፡ ይህን ተከትሎም የህግ ጥሠት ተካሄዷል ተብሎ አዳነችና ጌታቸው ቻርጅ እንዲሞሉ ተደረገ፡፡ ቅጣትም ተላለፈባቸው፡፡ ቅጣቱ በግዜው ጦርነት ወደነበረበት አስመራ ክፍለ ሀገር ጌታቸው ባሰልጣኝነት አዳነች ደግሞ በረዳት አሠልጣኝ ሆነው ወደ አስመራ ፖሊስ ሙዚቃ ክፍል እንዲዘዋወሩ ተደረገ፡፡
‹‹ለግዜው ቅጣቱ ሲወሰንብሽ ምን አይነት ስሜት ተሠማሽ›› የሚል ጥያቄ አነሣሁላት ‹‹እንደማንኛው ሰራዊት ህጉን በመጣሴ ቅጣት ተላልፎብኛል፡፡ ለምን ቅጣቱ ተላለፈብኝ ብዬ አላዛንኩም፣ ቅሬታም አላሠማሁም፣ ጥፋቴንም አምኛለሁ፣ ለመቀጣትም ዝግጁ ነበርኩ›› በማለት በራስ የመተማመን ስሜቷ ፊቷ ላይ በግልፅ እያሣየችኝ ለጠየኳት ጥያቄ መልሷን ለገሠችኝ፡፡
አዳነች በአዲስ አበባ ፈጥኖ ደራሽ ሙዚቃ ክፍል የተወሠኑ ጊዜያት ብቻ የቆየች ቢሆንም ኤርትራ ክፍለ ሀገር አስመራ ፖሊስ ሙዚቃ ክፍል ግን ብዙ ግዜያትን አሣልፋለች፡፡ ከዛም አልፎ ከሌሎች ለየት ባለ ብዙና አጥጋቢ እንቅስቃሴዎችን ታደርግ ነበር፡፡ ይህን የምታደርገው ታዲያ አንደኛ በፖሊስነት ሌላም ደግሞ በሲቪልነት ነበር፡ ፡ ታዲያ ከምታደርገው ጠንከር ያለ እንቅስቃሴ የተነሣ የአራት ሲኒማ ቤቶች ማለትም ሲኒማ ካፒቶል፣ ሲኒማ ኢትዮጵያ፣ ሲኒማ ሮማ እና ሲኒማ አባ አሉላ አባ ነጋ አዳራሽ የተባሉ ሲኒማ ቤቶችን አስተዳድራለች፡፡
በዚህ ግዜ ታዋቂ አርቲስቶች የተባሉ አርቲስት አማኒ ኢብራሂም፣ ይገዙ ደስታ እና ሌሎች ሌሎችም ከአዲስ አበባ ራስ ቲያትር እየመጡ እሷ የምታስተዳድራቸው ሲኒማ ቤቶች ዝግጅታቸውን በሚያቀርቡ ሠዓት የተለያዩ የሙዚቃ መሣሪያዎች የምታቀርብላቸው እሷ ስለነበረች ከነሱ ጋር የመተዋወቅ እድሉ ተከፍቶላታል፡፡
አዳነች ከ1969 እስከ 1974 ዓ.ም ድረስ በኤርትራ ከላይ የጠቀስኳቸው ሲኒማ ቤቶችን ስታስተዳድር አያሌ የሚባሉ አስደማሚ ግዚያቶችን ማሳለፏን ትናገራለች፡፡
አዳነች ሲኒማ ካፒቶል እያለች ‹‹ጭቁኗ ሴት ተነሽ›› የሚል ድርሠት በመፃፍ ለእይታ አብቅታለች፡፡ በሠዐቱ አስመራ ውስጥ 107 ቀበሌዎች የነበሩ ሲሆን በነበራት ጠንከር ያለ እንቅስቃሴዎች ከሚሊተሪ ውጪ የሴቶች ሊቀመንበር በመሆን አገልግላለች፡፡ ታዲያ በወቅቱ ስለነበረው የሻዕብያ ጦርነት ቤት ለቤት በመዞር ሴቶችን በማነሣሣትና የተለያዩ ኪነ ጥበብ ነክ ስራዎች በመስራት የማነቃቃት ስራዎችን ሠርታለች፡፡ ይህ ታዲያ ታይቶ ከተራ ወታደርነት የ50 አለቃ ማዕረግን ለማግኘት በቅታለች፡፡ በግዜው ጀነራል ግርማ አየለ የማዕረግ ሽልማቱን (አበርክተውለታል፡፡)
ከዚህ በኋላ አዳነች አስመራ የነበራትን እንቅስቃሴ ወደአዲስ አበባ ለመቀየር በማሰብ ለአራቱም ሲኒማ ቤቶች ባለቤት አቶ ሀይሉ የስራ መልቀቂያ በማስገባት ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ሲኒማ ራስ ተቀጥራ ማገልገል ጀመረች፡፡ ከ1974 በኋላ ወሩን በትክክል ባታስታውሰውም ከላይ እንደጠቀስነው በአሁኑ ራስ ቲያትር ቤት በቀድሞው ስሙ ራስ ሲኒማ ማገልገል ጀመረች፡፡ ወደዚህ የመጣችበትን ዋና ምክንያት ብላ እንደገለፀችው አዲስ አበባ ያለው ሲኒማ ኢትዮጵያና ራስ ቲያትር ከተስፋዬ አበበ ጋር ግንኙነት ስለነበራቸውና ደሞዟም ሞዴል እየተባለ ከአስመራ እየተላከ ይከፈላት ስለነበር ነው፡፡
‹‹በዚያን ግዜ ደሞዝ ስንት ይከፈልሽ ነበር?›› የሚል ጥያቄ አነሣሁላት እሷም እየሳቀችና የአግራሞት ስሜትን እያንፀባረቀች ‹‹የያኔ ብር እንዳሁን ግዜ አልነበረም፤ እኔ እንዳውም ትልቅ ደሞዝ ይከፈላቸው ከነበሩት ውስጥ አንዷ ነበርኩኝ፤ 375 ብር ይከፍሉኝ ነበር›› የሚል መልስ ሠጠችኝ፡፡
ከዚህ በኋላ አስቴርዬ ክለብ ማገልገል ጀመረች፡፡ ክለቡ በሲሊንደር ፍንዳታ ምክንያት በመቃጠሉ በራስ ቲያትር የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ በመሆን ተቀጥራ በዚሁ ቦታ ላይ ለ15 ዓመታት ያህል አገለገለች፡፡ ከዚያም ወደ ሀገር ፍቅር ቲያትር በመዘዋወር ከ1994 ዓ.ም እስከ 1996 ዓ.ም ድረስ በዚሁ ሞያዋ አገለገለች፡፡
ከ1996 ዓ.ም በኋላ በኢትዮጵያ መገናኛ ኤጀንሲ ውስጥ ተቀጥራ የፕሮሞሽን ስራዎችን ፣ መፅሔቶችንና የተለያዩ ኪነ ጥበብ ነክ ስራዎችን በመስራት ለተወሰኑ አመታት ካገለገለች በኋላ ከመስሪያቤቱ በግሏ ስራ የመልቀቅ ፍላጎቷን በመግለፅ ከስራዋ ለቀቀች፡፡
ከዚህ በኋላ እንግዲህ አዳነች ስራዎቿን ሁሉ ከተቀጣሪነት ይልቅ በግሏ ለመስራት በመወሠን ‹‹ጀአዲ አርት ፕሮሞሽን›› የሚል ድርጅት መሠረተች፡፡ በዚህ ድርጅት ውስጥ ታዋቂ የነበረውንና የመዝናኛና የኪነጥበብ ስራዎች ይቀርብት የነበረውን ‹‹ጠብታ›› የተሠኘውን መፅሔት በ2000 ዓ.ም መሠረተች፡፡ ይህ መፅሔት በአዲስ አበባ ውስጥ ጎልተው ከወጡ መፅሔቶች ውስጥ አንዱ የነበረ ሲሆን በውስጡም እነ ፕሮፌሠር አብይ ፎርድር ፣ሀይሌ ገሪማ፣ የሼክ አላሙዲን ባዬግራፊና ሌሎች ታዋቂ ሠዎችን
ይዞ የሚወጣ መፅሔት ነበር፡፡ መፅሔቱን አዳነች ለሁለት አመታት አሣትማ ለህዝብ ያቀረበች ቢሆንም በወቅቱ የነበረውን የህትመት ዋጋ መቋቋም ባለመቻሏ በ2002 ዓ.ም መፅሔቷን ከመታተም እንዲቆም አደረገች፡፡ ከ2002 ዓ.ም ላይም ‹‹ሳሎን ኢትዮጵያ›› የተባለ ጋዜጣ በበአሜሪካ ሲያትል ከተማ ውስጥ በየ15 ቀኑ አሳትማ ለኢትዮጵያውያን ታቀርብ የነበረ ቢሆንም ከአሳታሚዎች ጋር በነበራት አለመስማማት ጋዜጣዋን ልታቆም ችላለች፡፡
‹‹በነገራችን ላይ እዚህ ደረጃ ላይ እንድደርስ፣ መሠረት እንድጥልና በራሴ እንድተማመን ያደረገኝ የፖሊስ ሠራዊት ቤት ነው፡፡ ትልቁን በስነ ምግባር እንድታነፅና ህይወቴን እንድመራ ያደረገኝ ይሄው የፖሊስ ቤት ስርዓት ነው፡፡›› የምትለው አዳነች እሷ የነበረችበት ግዜ የነበረው የፖሊስ ሥነ ስርዓት እንዲህ በቃላት ልትገልፀው እንደማትችል ታስረዳለች፡፡ በሚሊተሪ ውስጥ የማትረሣው ነገር አዳነች ሙዚቃ ክፍል እያለች የነበረው መተሣሠብ፣ መፈቃቀርን፣ መከባበሩንና ሰርዓቱን ነው፡፡ ‹‹እስከ ዛሬም ድረስ በፈጥኖ ደራሽ ነባር የነበሩትን መኮንን መርሻን፣ እና ዳንኤልን ሣይ እንባዬ ይመጣል›› ትላለች፡፡
አዳነች በአሁኑ ሠዓት በራሷ ድርጅት ‹‹ጀአዲ አርት ፕሮሞሽን›› ላይ እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች፡፡ በቅርቡም የልጇ ባለቤት የሆነው አርቲስት አለማየሁ ታደሠ የደረሠው ድርሰት ላይ አብራ ለመስራት እንቅስቃሴ እያደረገችም ትገኛለች፡፡ ‹‹በቅርቡ የሠው ለሠው ድራማ ላይ እየተወንሽ ትገኛለሽ እንዴት ነው እንቅስቃሴው?›› አልኳት ‹‹ኦው! የሰው ለሰው ቤተሠቦች እጅግ ጎበዝና የቀልጣፋ ተዋናዬች ስብጥር ሲሆን አንጋፋና ወጣት ተዋንያን የተሣተፉበትም ጭምር ነው፡፡ እንዳውም ‹የአስናቀ ሚስት› እያሉ መንገድ ላይ ስሜን ቀይረውት ይጠሩኛል፡፡
በይበልጥ በድራማው ታዋቂነትን አትርፌያለው ብዬ አስባለሁ›› የሚል መልስ ሰጠችኝ፡፡ አዳነች ከባለቤቷ ጋር የነበራት ኑሮ እጅግ መራራ እንደነበረ ትገልፃለች፡፡ እሷ ወጣት በመሆኗና ባለቤቷ ሻንበል ባሻ ጌታቸው በእድሜ ስለሚበልጣት እንደ ልጅ በየግዜው ይደበድባት እንደነበር ትገልፃለች ይህ ያማረራት አዳነች፤ ቢኒያም ጌታቸው እና ማርታ ጌታቸው የተሠኙ ልጆቿን ከወለደች ከተወሰኑ አመታት በኋላ ከባለቤቷ ጋር ልትለያይ ችላለች፡፡ ባለቤቷም ሌላ ቤተሰቦችን መስርቶ ልጆችን ያፈራ ቢሆንም ከዚህ አለም በሞት የተለየ መሆኑና ልጆቹንም እንደ ልጆቿ እያየች እንዳሳደገች ታስረዳለች፡፡ ሻይና ዳቦ ከማንኛውም የምግብ አይነቶች የምታስበልጥ ሲሆን እስፓርታዊ እንቅስቃሴንም አሁንም ድረስ አላቋረጠችም፡፡
አርቲስት አዳነች ወ/ገብርኤል በቲቪ ድራማዎች ላይ ያልተሄደበት መንገድ፣ ቅብብል እንዲሁም አሁን በሚታየው የሠው ለሰው ድራማ ላይ የተሣተፈች ሲሆን የራሷ ድርሰት በሆነው የሳት ዕራት፣ ክብረነክ፣ ኮሞሮስ፣ አልደወለም፣ አልነግራትም እንዲሁም ፊደል አዳኝ የተሠኙ ፊልሞችን ሠርታለች፡፡ አማጭ፣ ዲያስፖራ፣ ሩብ ጉዳይ እንዲሁም የብዕር ስም የተባሉ ቲያትሮች ላይም ተውናለች፡፡ ከዚህ በተረፈ የሸዋንዳኝ ሀይሉን፣ የሄኖክ አበበን፣ የሄሎ አፍሪካ ጄሪን፣ የነዋይ ደበበን (አሜን)፣ የፀሐዬ ዩሀንስን (ሳቂልኝ) አልበሞችን ፕሮሞት ያደረገች ሲሆን የቴዲ አፍሮን እና የሸዋንዳኝን፣ ኮፒ ራይት ማህበር ያዘጋጀውን፣ የከተሞች ቀን የተከበረበትን፣ ስፖርት ለሠላም የተሠኙ ኮንሰርቶችን ፕሮሞት አድርጋለች፡፡ ቻቺ ታደሰ እንዲሁም የሌሎች ታዋቂ አርቲስቶች ፕሮሞተር በመሆን ሠርታለች፡፡ ‹‹ሥራዬን መቼም አላቆምም ወደፊትም ለህዝብ የማቀርበው ሥራዎች አሉኝ›› በማለት የወደፊት ዕቅዷን ነግራኛለች፡፡ እነሆ አዳነች 53ኛ ዓመት ዕድሜዋን በደመቀ ሁኔታ አክብራለች፡፡ በእርግጥም የብዙ ሙያዎች ባለቤት መሆኗን አስመስክራለች፡፡
ቸር እንሠብት፡፡S

Sport: ኃይሌ ገ/ሥላሴ በ2007 ለወርቅ ሜዳሊያ ሣይሆን ለፓርላማ መቀመጫ ይሮጣል

$
0
0

Haile
(በአዲስ አበባ የሚታተመው ወርልድ ስፖርት ጋዜጣ እንደጻፈው)

ባለፉት 25 እና 26 አመታት በአለም የአትሌቲክ መድረክ ታላላቅ ውጤቶችን በማስመዝገብ አለምን ያስደመመውና ለወጣት አትሌቶች ተምሳሌት መሆን የቻለው ኃይሌ ገ/ስላሴ ፊቱን ወደ ፖለቲካው አለም ሊያዞር ነው፡፡ ኢትዮጵያን በፕሬዝዳንትነት መምራት እንደሚፈልግና የፓርላማ አባል ለመሆን እቅድ እንዳለው ዘ ኦብዘርቨር ከተባለው የእንግሊዝ ጋዜጣ ጋር ባደረገው ሰፊ ቃለ ምልልስ ገለፀ፡፡ የ40 አመቱ ጐልማሣ ኃይሌ ገ/ስላሴ በስፖርቱና በቢዝነሱ ተሣክቶለታል በቅርቡም ከፍተኛ የቡና እርሻ ጀምሯል፡፡ ከሁለቱ አመት በኋላ ደግሞ ፊቱን ወደ ፖለቲካው አለም በማዞር በ2007ቱ ሀገራዊ ምርጫ የግል ተወዳዳሪ ሆኖ እንደሚቀርብ ከጋዜጣው ጋር ባደረገው የስልክ ቃለ ምልልስ ጠቁሟል፡፡ ፕሬዝዳንት ለመሆን ትፈልጋለህ ወይ ተብሎ ጥያቄ የቀረበለት ኃይሌ ገ/ስላሴ ያንን ማን የማይፈልግ አለ ሲል ሀገሩን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት ቁርጠኛ አቋም እንዳለው ተናግሯል፡፡ 547 መቀመጫ ያለውን የኢትዮጵያ ፓርላማ ለመቀላቀል በግሉ የሚወዳደረው ኃይሌ ገ/ስላሴ እድሉን ሊያገኝ እንደሚችልም ተንታኞች ከወዲሁ ይጠቁማሉ፡፡ በአሁን ወቅት በፓርላማው አንድ ግለሰብ በግል አባል ለመሆን መቻላቸው አይዘነጋም፡፡ እኚህ ግለሰብ የቀድሞ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕ/ት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ናቸው፡፡ ኃይሌ በ2007ቱ ምርጫ ፓርላማ የሚገባ ከሆነ ሁለተኛው የስፖርት ሰው ይሆናል ማለት ነው፡፡

‹‹ጋዜጠኞች ከእስር ቤት እንደወጡ በአንድ የፖለቲካ ድርጅት ጥላ ስር ሲሰባሰቡ መመልከት ያሳዝናል›› ዳዊት ከበደ [ጋዜጠኛ]

$
0
0

“ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት?” በተሰኘውና በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ታትሞ በገበያ ላይ በዋለው መፅሀፍ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ የሰጠው ቃለ – ምልልስ የሚከተለውን ይመስላል፡፡
ይህቺን ምድር መስከረም 1 ቀን 1972 ዓ.ም. በአድዋ ከተማ የተቀላቀለው ዳዊት ከበደ፣ ከምርጫ 97 ጋር በተፈጠረ ቀውስ በዋና አዘጋጅነት ይሠራበት በነበረው ሀዳር ጋዜጣ ላይ ‹‹አመፅ በማነሳሳት እና ሕገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ ሙከራ በማድረግ›› ተከሰው በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለ21 ወራት ከታሰሩ ጋዜጠኞች አንዱ ነው፡፡ በየካቲት 2000 ዓ.ም. ሰፊ ተነባቢነት የነበራትን አውራምባ ታይምስ ጋዜጣን መሥርቶ ለሦስት ዓመት ከዘጠኝ ወር ሲሠራ የሲ.ፒ.ጄ. የ2010 የፕሬስ ነፃነት አሸናፊ ነበር፡፡ ‹‹ይቅርታዬ ተነስቶ ድጋሚ እንደምታሰር ከፍትሕ ሚኒስትር ታማኝ ምንጮች መረጃ ደረሰኝ›› በማለት ኅዳር 7/2004 ዓ.ም. የስደትን መንገድ ተቀላቀለ፤ ወደ አሜሪካም በመኮብለል በጋዜጣዋ ስም ድረ-ገፅ ከፍቶ (awrambatimes.com) በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ ኤልያስ ገብሩ የዳያስፖራ ጋዜጠኝነት እና ፖለቲካን መሠረት ያደረጉ ጥያቄዎች አቅርቦለት ከዳያስፖራ ፖለቲካ በተቃርኖ መቆሙን የሚያሳይ ምላሽ በጽሑፍ ሰጥቶታል፡፡ ዘ-ሐበሻም እንደወረደ ቃለምልልሱን አቅርባዋለች
dawit kebede
ከአገር ከመሰደድህ በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ በፕሬስ ጋዜጠኝነት ስትሠራ ነበር። አሁን ደግሞ በድረ-ገጽ አዘጋጅነት እየሠራህ ነው። በሁለቱ መሀከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
ልዩነቱ ግልጽ ነው። የጋዜጣ ሥራ በሣምንት አንድ ጊዜ ለሚወጣ የኅትመት ውጤት በመሆኑ ሣምንት ሙሉ መዘጋጀትን ይጠይቃል። በሣምንት ውስጥ ብዙ ነገር ይፈጠራል። እነዚያ ክስተቶች ጠቅለል ብለው እና ዳብረው ለአንባቢያን ይቀርባሉ። ወደ ድረ-ገጽ ስትመጣ ግን ክስተቶችን ሣምንት ሙሉ የምትጠብቅበት ሁኔታ አይፈጠርም። ማንኛውንም ክስተት [ክስተቱ በትክክል መፈጸሙን ለማረጋገጥ ጊዜ ካልፈጀብህ በስተቀር] ወዲያውኑ በደቂቃዎች ውስጥ አንባቢ ጋር ማድረስ ትችላለህ። ልዩነቱ በፍጥነት አንባቢ ጋር መድረሱ ብቻ ሳይሆን የድረ ገጽ ጋዜጠኝነት ከኅትመት ይልቅ ብዙ ቦታ የመዳረስ ዕድሉም ሰፊ ስለሆነ ነው። ለምሳሌ፣ የአውራምባ ታይምስ ድረ-ገጽ ዕለታዊ ጎብኚ፣ ጋዜጣው በአገር ቤት ሲታተም ከነበረው ሣምንታዊ የአንባቢ ቁጥር ጋር ሲነጻጸር፣ የድረ-ገጽ አንባቢው ብልጫ እንዳለው ጥያቄ የለውም። በእርካታ ደረጃ ግን የሚገናኝ አይደለም። የድረ-ገጽ አንባቢ አርቲፊሺያል የሚባል ዓይነት ነው። ጠላትህም ወዳጅህም ሊሆን ይችላል። አገር ቤት ያለው የጋዜጣ አንባቢ ግን አንደኛ፣ መረጃህን የሚገዛው ገንዘቡን አውጥቶ ነው። ሁለተኛ፣ ‹‹ጋዜጣህን የምገዛው ገንዘቤን አውጥቼ ነው?›› ብሎ እጅ ጥምዘዛ ውስጥ አይገባም። ልዩነቱ ድረ-ገጽ የሚቀርበው በሰለጠነ አገራት ውስጥ ለሚገኝ ያልሰለጠነ ሀበሻ ሲሆን፣ ጋዜጣው ደግሞ ባልበለጸገች አገር ለሚገኝ የሰለጠነ ማኅበረሰብ መሆኑ ነው።
ማንኛውም ዜና የመዘገብ ሥራ አቋራጭ መንገድ ባይኖረው ይመረጣል። ብዙ ጊዜ የተወሰደባቸው እና ከባድ ጥረት የተደረገባቸው ዘገባዎች ምንጊዜም ትልቅ ፋይዳ እና ጠቀሜታ አላቸው። ከዚህ አኳያ የአገር ውስጡን እና ከአገር ውጪ ያሉትን የጋዜጣ እና የድረ-ገጽ ሥራዎች [ያንተን ጭምር] እንዴት ትገልጻቸዋለህ? አንባቢን የሚመጥን ሥራ እየተሠራባቸው ነው?
ከኢትዮጵያ ውጪ ሆነህ ከስደት ጋር እየታገልክ የምትሠራው ሥራ ሁሌም ሁለተኛ ደረጃ (Secondary) የምትሰጠው ስለሆነ እና ‹‹የበሰለ ሥራ ነው›› ብለህ በኩራት የምትናገረው አይደለም። ዞሮ ዞሮ አገር ቤት ያላችሁም እዚህም ያለን ሰዎች የምንሠራው ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነህ እና ከኢትዮጵያ ርቀህ እኩል ልትሠራ አትችልም። ስለ ሌሎች ድረ- ገጾች መናገር አልፈልግም። ‹‹ስለ አውራምባ ታይምስ ንገረኝ?›› ካልከኝ ግን ጋዜጣው የ20 ሰው ልፋት እና ድካም ውጤት ነበር። ድረ-ገጹን የማዘጋጀት ኃላፊነት ግን ያለው በአንድ ሰው ትከሻ ላይ ነው። ዋሺንግተን ዲ.ሲ. እያለሁ ሪፖርተር፣ ቪዲዮ ቀራጭ፣ ቃለ-ምልልስ አድራጊ፣ ዜና ጸሐፊ፣ ዲዛይነር፣ ፎቶግራፈር እኔ ብቻ የሆንኩበትን አጋጣሚ አልረሳውም። በዚህ ሁኔታ የበሰለ ሥራ ሊሠራ አይችልም። ያ ማለት ግን ድካም እና ልፋት የለም ማለት አይደለም። አብዛኛው ልፋት በአንድ ሰው ትከሻ ላይ ነው።
ድረ-ገጽን በአንድ ሰው ብቻ የምትሠራው ለምንድን ነው? ይኼ የአንባቢን ብዝሐ ሐሳብ የማግኘት ዕድሉን አይገድብም? የጋዜጣ እና የመጽሔት ገቢ በሽያጭ እና በማስታወቂያ እንደሆነ ይታወቃል። ከድረ-ገጽ የምታገኘው ገቢ ምንድን ነው? [ከቻልክ የሌሎቹን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ድረ-ገጾች ገቢ ምን እንደሆነ ብትነግርኝ መልካም ነው።]
በአንድ ሰው ይሠራል ሲባል በአንድ ሰው ትከሻ ላይ እየወደቀ ያለው የማዘጋጀቱ (የሥራው) ኃላፊነት ነው እንጂ የድረ ገጹ ይዘት የአንድ ሰው አቋም አይደለም። ለምሳሌ አገር ቤት እያለን እኔ ኖርኩ አልኖርኩ ጋዜጣው ይሠራ ነበር። በ2010 አሜሪካን አገር ለሽልማት መጥቼ ሁለት ወር ገደማ ስቆይ ጋዜጣው ቀኑን እና ይዘቱን ጠብቆ ይወጣ ነበር። ያ የሆነበት ምክንያት ዘጋቢ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ አዘጋጆችም ስለነበሩት ነው። ድረ-ገጹ ግን ዘጋቢ ካልሆነ እኔን ተክቶ የሚሠራ አዘጋጅ የለውም። አገር ቤት እያለሁ የነበረኝ በቡድን ሥራ የማመን ጥብቅ አቋም አሁንም አልተለወጠም። አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን በውጪ አገር አዘጋጆችን ልቅጠር ብትል የማይሆን ነገር ነው። በአገር ቤትም አዘጋጅ ልቅጠር ብትል ይህ አዘጋጅ እንዴት አድርጎ ነው የተዘጋን ዌብሳይት ከፍቶና የምስጢር ቁጥር አስገብቶ የአዘጋጅነት ሚናውን ሊወጣ የሚችለው? ነገሩ መታየት ያለበት ከነዚህ መሰናክሎች አንጻር ነው። ድረ-ገጹ በአገር ቤት እንደ መዘጋቱ እንኳን አዘጋጅ ይቅርና በሪፖርተርነት እንኳን ሰዎችን ለማሠራት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ፖለቲካውን ጠንቅቀህ ታውቀዋለህ። ፍርሃቱ ደግሞ ዝም ብሎ የመጣ አይደለም። እነ ውብሸትን ያየ በዚህ ቢደነግጥ አይገርምም። እኔም ደግሞ ለማንም መታሰር ምክንያት መሆን አልፈልግም። እንደዚያም ሆኖ ያንን ስጋት ተቋቁመው እየዘገቡ ያሉ የአገር ቤት ዘጋቢዎቼን ሳላመሰግን አላልፍም።
የድረ-ገጾችን ገቢ በተመለከተ ሙሉ ለሙሉ ማወቅ ባይቻልም በአብዛኛው ግን ድረ-ገጾቹ የሚደግፏቸው የፖለቲካ ድርጅቶች በሚያዘጋጇቸው የገቢ ማሰባሰቢያ ምሽቶች የሚገኝ ገቢ ነው። እዚህ ዋሽንግተን በሚገኝ አንድ የኢትዮጵያ ጎረቤት ኤምባሲም የሚደገፉ እንዳሉ አውቃለሁ። ከጠቀስኩት ኤምባሲ ድጋፍ የሚያገኙት ድረ-ገጾች ታዲያ ከዚያች አገር ጋር በቅርብ የሚሠራ እና ስሙን መጥቀስ የማልፈልገውን የፖለቲካ ድርጅት በግልጽ መደገፍ አለባቸው። ኢትዮጵያ እያለሁ የ‹‹እከሌ ተላላኪዎች›› እየተባለ በቴሌቭዥን ሲለፈፍ እውነት አይመስለኝም ነበር። ኢቴቪ አብዛኛውን ጊዜ ውሸት ስለሚያወራ በእነዚያ ውሸቶች መሀከል ጥቂት እውነት ይወራል ብለህ አትጠብቅም። አሜሪካ በመጣሁ በሣምንቴ ከአንድ የፖለቲካ ተንታኝ ጋር ስናወራ የተጠቀሰው ኤምባሲ እንዴት ድረ-ገጾችን እንደሚረዳ በቁጭት ሲያጫውተኝ በጣም ነበር የተገረምኩት። በኋላ እኔም ዌብሳይት ስጀምር ተመሳሳይ የ‹‹እንደግፍህ›› ጥያቄ በሰዎች አማካኝነት ሲቀርብልኝ በጣም አዘንኩ። ‹‹ለሻዕቢያ ድጋፍ እጄን ከምዘረጋ ልማታዊ ዘገባዎችን ብቻ እያቀረብኩ ኢትዮጵያ ውስጥ ማንም ሳይነካኝ አልኖርም ነበር እንዴ?›› የሚል ምላሽ ሰጠሁ። አጋጣሚው ግን በዳያስፖራ ያለው የተቃውሞ ፖለቲካ በማን እየተጠለፈ እንደሆነ ለመረዳት አስችሎኛል። ለማንኛውም አውራምባ ታይምስ ድረ-ገጽ ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ጋር የድጋፍ ውል የለውም። በርካታ ትራፊክ (ጎብኚ) ካላቸው ዌብሳይቶች አንዱ እንደመሆኑ ከጉግል መጠነኝ ገቢ ያገኛል። በተጨማሪ ደግሞ ለፕሬስ ነጻነት መከበር ድጋፍ የሚያደርጉ (ምንም ዓይነት የፖለቲካ አጀንዳ የሌላቸው) ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም አልፎ አልፎ ይደግፉኛል። ከእነዚህ የምናገኘው ድጋፍ ድረ-ገጹን ለማንቀሳቀስ የምናወጣውን ወጪ ይደጉምልናል።
በስደት ላይ የምትገኙ ጋዜጠኞች ‹‹የስም እንጂ የተግባር ጋዜጠኞች›› ናችሁ ማለት ይቻላል?
አሁንም ደግሜ ልንገርህና ስለ ሌሎች የድረ-ገጽ አዘጋጆች አቋም መናገር አልፈልግም። እኔ ግን ነኝ ማለት እችላለሁ።
በአገር ውስጥ አብዛኞቹ የኅትመት ሚዲያ ተቋማዊ መሠረት እንዳይኖራቸው ምን ያገዳቸው ይመስልሃል? በምሳሌነት የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ መቀጠል አለመቀጠል በአንተ መኖር እና አለመኖር ተወስኖ ነበር። ‹‹የጋዜጣ ባለቤቶችስ የሚዲያ ተቋም መገንባት ይሻሉን?›› የሚል ጥያቄም ይነሳል።
ይህ እኮ የመንግሥት እንጂ የአሳታሚ ግለሰቦች ችግር አይደለም። የአውራምባ ታይምስ አሳታሚ በሆነው ብሉ ኧርዝ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር ውስጥ እኔ የነበረኝ ድርሻ 90 ከመቶ ነበር። በዚያ ላይ ሥራ አስኪያጁም እኔ ነበርኩ። ስለዚህ እኔ ከአገር ስወጣ ድርጅቱ ተቋማዊ መሠረት ይዞ እንዲቀጥል እኔ መስጠት የምችለው ውክልና ብቻ ነው። ተቋም እንዲመሠረት በኛ በኩል የፈለገውን ያህል ሕልምና ፍላጎት ቢኖር፤ በኢትዮጵያ መንግሥት ባህሪ እና በአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ሊሆን የሚችል አይደለም። እንኳን አውራምባ ታይምስ የሚለውን ስም በውክልና ይዛችሁ ልትቀጥሉ ቀርቶ፤ የአውራምባ ታይምስ ባልደረቦች ስለነበራችሁ ብቻ አዲስ ጋዜጣ ለማውጣት ፍቃድ ተከልክላችሁ የለም እንዴ?
ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት በተለያዩ ጊዜያት ሲዘጉ እና አሳታሚዎች ወይም ጋዜጠኞች ከአገር ሲሰደዱ የአንድ ሰሞን ርዕስ ይሆንና ዝምታ ይውጠዋል። የዝምታው አንድምታ ምን ይመስልሀል?
የዝምታው አንድምታ፣ ያው ፍርሃት እንጂ ሌላ ምን ትለዋለህ። መቼም በመንግሥት እርምጃ ‹‹መስማማት ነው›› ልንል አንችልም።
ኑሮ ሲወደድ፣ መብቱ ሲገፈፍ፣ ሕልውናው ፈተና ላይ ሲወድቅ ሕዝብ በተመሳሳይ ዝምታን ይመርጣል። ምንጩ ‹‹ፍርሃት ነው›› ብለን መደምደም እንችላለን?
ታዲያ ከዚህ ሌላ ምን ይባላል። ስደትን አማራጭ ያደረገ እንደኔ ዓይነት ሰው ከዚህ ያለፈ ምን መረጃ ሊኖረው ይችላል?
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ‹‹በኢትዮጵያ ውስጥ የታሠረ ጋዜጠኛ ይሸለማል!›› የሚሉ ንግግሮች በቁም ነገር እና በቀልድ መልክ ሲነገሩ ይደመጣል። ሳይታሰር በላቀ ሥራው የሚሸለም ጋዜጠኛ በኢትዮጵያ ሊፈጠር አይገባም? በኢትዮጵያችን በጋዜጠኝነት የሙያ ዘርፍ ‹‹ጀግና›› የምንላቸውስ እነማንን ነው ብለህ ታምናለህ?
‹‹በላቀ የጋዜጠኝነት ተግባር ላይ መሳተፍ›› የሚለው አባባል በእኛ አገር ተጨባጭ ሁኔታ እንዴት ነው የሚገለጸው? እንደኔ እንደኔ ሙስናን ማጋለጥ፣ ፍትሕ ሲዛባ መጮህ፣ የሕግ የበላይነት እንዲከበር ሙያዊ ኃላፊነትን መወጣት ነው። አሜሪካዊያን እነዚህ መሠረታዊ ነገሮች በአገራቸው እንዲከበሩ ስላደረጉ ‹‹ፐልቲዘር››ን የመሳሰሉ ሽልማቶችን ለጋዜጠኞቻቸው ይሰጣሉ። እኛ አገር መሠረታዊ የሰው ልጅ ነጻነት በበቂ ሁኔታ ሳይከበር፤ ‹‹የሰው ልጅ መሠረታዊ መብት ይከበር!›› ብለው የሚጠይቁ ጋዜጠኞች እንደጥጃ በሚታሰሩበት ሁኔታ ‹‹በሥነ-ጽሑፍ ክህሎት፣ ውበትና ፍሰት›› ጋዜጠኛን መሸለም ቅንጦት ይሆናል። ገና ለገና ‹‹የታሠረ ይሸለማል›› በሚል ጉጉት ‹‹ካላሠራችሁን›› ብለው የሚማጸኑ ሰዎችም ሊኖሩ ይችላሉ።
ሰማያዊ መጽሔት ላይ በዚህ ዓመት … የሰጠኸውን ቃለ-ምልልስ ተንተርሰው ሁለት የአገር ውስጥ መጽሔቶች ጽሑፍ በማዘጋጀት ለንባብ አብቅተው ነበር። አንደኛው፣ ‹‹ዳዊት፣ የዳያስፖራውን ፖለቲካ ተቋቁሞ በሙያው እየሠራ ይቀጥል ይሆን?›› ዓይነት ጠያቂ ይዘት የነበረው ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ‹‹ይቅርታዬ ተነሥቶ እንደምታሰር ከፍትሕ ሚኒስቴር አስተማማኝ መረጃ ደረሰኝ›› ብለህ የተናገርከውን ከመጠራጠር ባለፈ፣ በጋዜጠኝነት ሙያ እስር እንደሚኖር መጀመሪያ እየታወቀ፣ ከመጀመሪያውም ወደ እዚህ ሙያ መግባት እንደማይገባ ስምህን ሳይጠቀስ ተቺ ጽሑፍ ቀርቦብህ ነበር። ምን ምላሽ አለህ?
አስቀድመህ የጠቀስከውን ጽሑፍ ወዳጆቼ መጽሔቱን ልከውልኝ አንብቤዋለሁ። ‹‹የዳያስፖራውን ፖለቲካ ተቋቁሞ ይቀጥል ይሆን ወይ?›› የሚለው ተገቢ ስጋት ነው። ስጋታቸው ምን ያህል ተገቢ እንደሆነ ለማረጋገጥ ከዚያ በኋላ በተከታታይ በእኔ ላይ የደረሱ የስም ማጥፋት ዘመቻዎችን መመልከቱ ብቻ በቂ ነው። እዚህ በዳያስፖራ አንድ ሰው ‹‹የሌላውን የፖለቲካ ስትራቴጂ አልተቀበለም›› ማለት ጦርነት እንደሚታወጅበት ግልጽ ነው። እንደ አለመታደል ሆነና የፖለቲካ አካሄዳችን ‹‹የአጥፍቶ መጥፋት›› ነው። ሁለተኛውን ጽሑፍ ግን በዝርዝር አላነበብኩትም። ሰዎች ናቸው አንብበው ‹‹ኧረ! ጓደኞችህ እንዲህ እያሉህ ነው..›› ያሉኝ። እንደተነገረኝ ከሆነ ጽሑፉ የተስተናገደው ከአንድ አመት በፊት እኔ ስሰደድ ‹‹ጓደኞቻችንን መልሱልኝ›› ብለው የተማጸኑ ወዳጆቼ በሚያሳትሙት መጽሔት ላይ ነው። እነዚህ ሰዎች ያኔ በምን ምክንያት እንደተሰደድኩ፣ እነማን እንዳባረሩኝና ያባረሩኝ ሰዎችም በነካ እጃቸው ወደ አገሬ እንዲመልሱኝ ለሚመለከተው አካል በጽሑፋቸው ጥያቄ ያቀረቡ የማከብራቸው ጓደኞቼ እንደመሆናቸው ከአንድ ዓመት በኋላ መልሰው ‹‹የለም ማንም አላባረረውም!›› ብለው ጣታቸውን ወደኔ ይቀስራሉ የሚል እምነት የለኝም። እንደው አንባቢ የላከላቸውን ጽሑፍ ሳያዩት ወጥቶ ይሆናል እንጂ ‹‹በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ መስዋዕትነት ሊኖር እንደሚችል ዳዊት ፈጽሞ አያውቅም›› የሚለው ዐረፍተ ነገር ዐይናቸው እያየ ያሳልፉታል አልልም።
በአሜሪካ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንደተደረገብህ ገልጸሃል። [ኢትዮ ሚዲያ ድረ-ገጽ ዳዊት የሕወሃት/ኢሕአዴግ ደጋፊ መሆኑን ያሳያሉ ያላቸውን 11 ዝርዝሮችን አቅርቦ ተችቶት ነበር] አንተም የኢትዮ ሚዲያ ድረ-ገጽ ኤዲተር አብርሃ በላይን ስም በመጥራት መጻፍህ ተገቢ ነው?
ነገሩ እንደዚያ አይደለም። ድረ-ገጹ 11 ያህል ገጽ ያለውና በብዕር ስም የተጻፈ በጣም የወረደ ጽሑፍ ይዞ ወጣ። እንዳየሁት ወዲያውኑ ኤዲተሩን አነጋገርኩት። ‹‹ይህ ጽሁፍ እኔን እንደማይወክል ባለን የግል ወዳጅነት ጠንቅቀህ ታውቃለህ። አዲስ ዘመን በገጽ 3 ላይ የሚፈጽመውን ስህተት አንተ የ’ዴሞክራሲ ጠበቃ ነኝ’ የምትል ሰው ልትደግመው አይገባም›› አልኩት። እሱም ‹‹እዚህ ስንኖር የሚኖረን አማራጭ ሁለት ብቻ ነው፤ ወይ ዳያስፖራ ያለውን የፀረ-ወያኔ ትግል መደገፍ፤ ወይም ደግሞ ወያኔን መቀላቀል›› አለኝ። ጽሑፉ የእሱም እምነት እንደሆነ ነገረኝ። እዚህ ላይ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ በ2001ዱ የሽብር ጥቃት ማግስት የተናገሩትን አስታወሰኝ። ‹‹You are either with us or with the terrorists›› (እናንተ ወይ ከእኛ ወይም ከሰሸባሪዎች ጋር ናችሁ) ነበር ያሉት። ጉዳዩ የሽብርተኝነት ጉዳይ እስከሆነ ድረስ ቡሽ እንዲህ ዓይነት አማራጭ ቢያቀርቡ ብዙም ላያስተቻቸው ይችላል። ‹‹በኤርትራ አማካኝነት የሚደረግን ትግል ካልደገፍክ›› ተብሎ እንደዚህ ዓይነት ጭፍን አማራጭ መስጠት ነውረኝነት ነው። ግለሰቡ በደርግ ጊዜ የሳንሱር ክፍል ኃላፊ ሆኖ እንደማገልገሉ እና በኢሕአዴግ ዘመንም የኢትዮጵያን ሄራልድ አዘጋጅ ሆኖ እንደ መሥራቱ የተለያዩ ሐሳቦችን ማስተናገድ እንደ ‹‹አላማጣ ዳገት›› ቢከብደው አይገርመኝም። ‹‹ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ ብዙ የጋራ ጉዳይ እያለን እርስ በርሳችን ጭቃ መቀባባት የለብንም›› በማለት በዚህ አቋሙ የሚቀጥል ከሆነ ግን ራሴን ለመከላከል እንደምገደድ ነገርኩት። በዚያ ላይ ደግሞ የኔንም ሐሳብ መስማት የሚፈልጉ በርካታ ኢ-ሜይሎች ደርሰውኛል። ስለዚህ ምላሼን ሰጠሁ። መጀመሪያ ላይ ‹‹የእኔም ጭምር እምነት ነው›› ያለ ሰውዬ እኔ ምላሽ በሰጠሁ በሦስት ሰዓታት ውስጥ ይቅርታ የሚመስል ‹‹ኤዲተርስ ኖት›› አስቀምጦ ጽሑፉን ሰረዘው። እኔም እነ ኦባንግ ሜቶ፣ አበበ ገላው፣ የአትላንታው ዳዊት ከበደ፣ ዶ/ር ሼክስፒርና ሌሎችም ሰዎች ባቀረቡት ተማጽኖ ለእሱ የሰጠሁትን ምላሽ ከድረ-ገጼ አነሣሁት። እውነታው ይኼ ነው።
ይህ ታዲያ ሚዲያህን ለራስ ፍላጎት መሙያ ማዋልህን አይገልጽም?
የእኔ ምላሽ በቀጥታ አውራምባ ታይምስ ላይ ከመውጣቱ በፊት የሙያው ሥነ-ምግባር በሚጠይቀው መሠረት በራሱ ድረ- ገጽ ላይ እንዲስተናገድልኝ ልኬለታለሁ። መላኬንም በሞባይል የጽሑፍ መልዕክት አሳውቄዋለሁ። ፈቃደኛ ሳይሆን ሲቀርና መድረክ ሳጣ ታዲያ ምን ማድረግ ነበረብኝ? የኔ ምላሽ እኮ የወጣው ከ24 ሰዓታት በኋላ ነው። ይህም በምንም መመዘኛ ሚዲያውን ለራስ ፍላጎት ማዋል ሊሆን አይችልም።
የዳያስፖራ ጋዜጠኝነት በኢሕአዴግ ደጋፊነት እና በፀረ-ኢሕአዴግ ካምፕ (ለሁለት) የተከፈለ ነው። አንተ የቱ ጋር ነህ?
ሁለቱንም አይደለሁም።
የጋዜጠኝነትን ‹‹ABC›› እየተገበሩ (አንድ ጽንፍ ሳይዙ) የዳያስፖራ ሚዲያ ላይ እየሠራህ እስከመቼ ትዘልቃለህ? በፊት በኢትዮጵያ በሽብርተኝነት የተፈረጁ ሰዎችን ሐሳብ አታስተናግድም ነበር። በኋላ ላይ ግን ማስተናገድ ጀመርክ። ግፊት የበረታብህ አያስመስለውም?
አንድ ጽንፍ ሳይዙ መሥራት ፈታኝ እንጂ አስቸጋሪ አይደለም። ወደ ማብራሪያው ከመሄዴ በፊት ግን ጥያቄህን ላስተካክለው። ‹‹በሽብርተኝነት የተፈረጁ ሰዎችን ሳታስተናግድ ቆይተህ በኋላ ላይ ማስተናገድ ጀመርክ›› የሚለው ስህተት ነው። ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን ቃለ-ምልልስ ያደረግኩት ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ የተነገረ ዕለት ነበር። የእኔ ችግር በሽብርተኝነት መፈረጃቸው እና አለመፈረጃቸው አይደለም። የኢትዮጵያ የፀረ- ሽብር አዋጅ የሚሠራው በኢትዮጵያ ግዛት ስር ነው። አውራምባ ታይምስ ድረ-ገጽ በአሪዞና ስቴት የንግድ ሕግ የተመዘገበ የሚዲያ ተቋም ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይታይ ደግሞ መንግሥት አግዶታል። ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አዋጆች በሥራዬ ላይ ተጽዕኖ የሚፈጥሩት ለምንድን ነው? ወደ ዋናው ነጥብ ስመለስ፣ እዚህ ዳያስፖራ ያሉ ሚዲያዎች በአብዛኛው በሁለት ፅንፍ የተሰለፉ ናቸው። በየፅንፋቸው ‹‹አክራሪ›› እና ‹‹ለዘብተኛ›› የሚባሉም አሉ። ሁለት ድረ-ገጾችን ምሳሌ አድርጌ ላቅርብልህ፤ ‹‹ትግራይ ኦንላይን›› እና ‹‹ኢካድፎረም››ን፤ ‹‹ትግራይ ኦንላይን›› በኢሕአዴግ ስር ያለችው ኢትዮጵያ የፕላኔታችን መንግሥተ-ሰማያት እንደሆነችና መሪዎቿም መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸው መላዕክት እንደሆኑ አድርጎ ያቀርባል። ‹‹ኢካድፎረም›› በበኩሉ አዲስ አበባን ሲገልጻት ማንም በነጻነት የማይንቀሳቀስባት፤ ከትግራይ ተወላጆች ውጪ የሌላ ብሔረሰብ ተወላጆች በጠራራ ፀሐይ የሚረሸኑባት የሲኦል ከተማ ያደርጋታል። መሪዎቿን ከተለያዩ አደገኛ የእንስሳት ዝርያ ጋር እያመሳሰለ የሚያቀርብ እና ለዴሞክራሲ እታገላለሁ የሚል ድረ-ገጽ ነው። ‹‹ትግራይ ኦንላይን›› እና ‹‹ኢካድፎረም›› የሚስሏትን ኢትዮጵያ እኔ አላውቃትም። ሌሎቹ ሚዲያዎችም በእነዚህ ግራ እና ቀኝ ባስቀመጥኳቸው ሞዴል ድረ-ገጾች ስር ለዘብ ባለ አኳኋን የተሰለፉ ናቸው። በአውራምባ ታይምስ እና በኢትዮ-ሚዲያ መካከል ግጭት ሲፈጠር ‹‹ኢካድፎረም››፣ ‹‹የሁለት ወያኔዎች ጠብ›› ሲል፤ ‹‹ትግራይ ኦንላይን›› ደግሞ ‹‹የብርሃኑ ነጋ ግራ እጅ እና ቀኝ እጅ ጠብ›› ብሎ ነበር የዘገበው። አውራምባ ታይምስ ድረ-ገጽን ከእነዚህ ‹‹ሚዲያዎች›› ጎን እንድትሰለፍ ማድረግ ሞራላዊ አይደለም። ስለዚህ እነዚህን ሁኔታዎች በመመርመር አውራምባ ታይምስ ባለፈው ጥቅምት ወር አንድ የፎርማት ለውጥ አደረገች። ይህም ሚዛናዊ በሆነ መንገድ በተለይ ደግሞ አገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎችን በሚያበረታታ ሁኔታ ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲ እንዲጎለብት፣ የፕሬስ ነጻነት እንዲያብብ፣ ከአንድ የሚዲያ ተቋም የሚጠበቅ አስተዋጽኦ በጨዋነት ማበርከት›› የሚል ነው።
ዞሮ ዞሮ ያው ሆነ… ተቃዋሚዎችን ማበረታታት የአንድ ሚዲያ ተቋም ተግባር ሊሆን ይገባል?
ተቃዋሚዎችን ማበረታታት ስንል የተቃዋሚዎችን ፖሊሲ ከመደገፍና ከመቃወም አንጻር ሳይሆን የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት እንዲኖር ከመፈለግ ነው። ተቃዋሚው አንድ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ሚዲያው ማበረታታት አለበት። በአንድ አገር ዴሞክራሲ የመኖሩ አንዱ መገለጫ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት መኖር እና ሕዝብ ደግሞ በምርጫ ወቅት የሚበጀውን እንዲመርጥ ምቹ የሆነ ሁኔታ መፍጠር ነው። ስለዚህ ‹‹ተቃዋሚዎች መጠናከር አለባችሁ›› ሲባል ‹‹ለመራጩ ሕዝብ ጥሩ አማራጭ መሆን የሚችሉበት ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ሚዲያው ሊያበረታታቸው ይገባል፤ ፖሊሲዎቻቸውንና አማራጮቻቸውን ሕዝቡ ጋ እንዲያደርሱ ተገቢውን ድጋፍ ሊሰጣቸው ይገባል›› ለማለት ነው። እዚያ ደረጃ ላይ ከደረሱ በኋላ የመምረጥ እና ያለመምረጥ ኃላፊነት የሕዝቡ ስለሚሆን እንደሚዲያ ባለሙያዎች ላያገባን ይችላል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረጉ ያሉ ምርጫዎችን ተመልከት። ‹‹ዴሞክራሲ ሂደት ነው›› እየተባለ 22 ዓመት ያስቆጠረው የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት መጨረሻው እንዲህ ሲሆን መመልከት ነበረብን? አሁን ባለፈው ወር (ሚያዚያ 2005 ዓ.ም.) የተደረገው ምርጫ ምርጫ ነው? እውነት የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት በዚህ ውጤት መኩራት አለባቸው? በ21ኛው ክፍለ ዘመን በዚህ መንገድ ምርጫን ‹‹ማሸነፍ›› ትክክል መሆኑን የሚያረጋግጥ ማሳመኛ በቅንነት ሊያቀርቡልን ይችላሉ? ዴሞክራሲ እንዲያብብ የሚፈልግ የሚዲያ ተቋም ይህን ቢያደርግ ምንድነው ችግሩ?
‹‹የእኔ ችግር በሽብርተኝነት መፈረጃቸው እና አለመፈረጃቸው አይደለም›› ብለሃል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን በኢትዮጵያ በሽብር በተፈረጁ በአንዳንድ ቡድኖች ላይ የሰላ ትችት ትሰነዝራለህ። ምክንያትህ ምንድነው?
ለምሳሌ ‹‹ግንቦት 7››ን በተመለከተ፣ አገር ቤት ያለ ሰው ትልቅ ድርጅት አድርጎ ይመለከተው ይሆናል። በእኔ እምነት የ‹‹ግንቦት 7›› ታላቅነት ኢሕአዴግ የሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች ደጋግመው ስለሚያወሩለት ብቻ ነው። በተረፈ በዓምስት አመት ውስጥ ‹‹ግንቦት 7›› ያበረከተው አስተዋጽኦ ምንድን ነው? ካልከኝ ኢሳት የተባለ ‹‹የሳይበር ቴሌቭዥን›› ማቋቋሙ ብቻ ነው። ከዚያ ውጪ የራሱ የሆነ ስትራቴጂ የለውም። ጥቂት የመከላከያ ጄኔራሎች እና ኮሎኔሎች በራሳቸው መንገድ ሲደራጁ ‹‹አለሁበት›› ይላል። የሰሜን አፍሪካ አመጽ ሲነሣ ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ አመጹ እንዲደገም ጠንክረን እየሠራን ነው፤ ግንቦት 21/2003 ነጻ ትወጣላችሁ›› ይላል። ‹‹የኔሰው ገብሬ ራሱን አቃጠለ›› ሲባል ‹‹ኢትዮጵያዊው ቡአዚዝ የለኮሰውን እሳት በሳምንታት ውስጥ አራት ኪሎ እናደርሰዋለን›› ሲል ይደመጣል። ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የ‹‹ሃይማኖት ነጻነት ይከበር!›› ሲሉ ‹‹ጥያቄው የእኛም ነው›› በማለት ክርስቲያን የፓርቲው አመራሮች በአደባባይ ‹‹አላሁ አክበር!›› ማለት ጀመሩ። የአማራ ተወላጆች ከጉራፈርዳ እና ከቤንሻንጉል ክልል ሲባረሩ ‹‹የአማራ ጠላቶችን ድል እንንሣ፤ ተነሡ!› ይላል። እንዲህ እያለ ይቀጥላል። በነገራችን ላይ ሙስሊሞች ላነሱት የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄና ለአማራ ወገኖቻችን መፈናቀል አጋርነት ማሳየት ተገቢ እንደሆነ አምናለሁ። ነገር ግን፣ የፓርቲው አመራሮች ከእያንዳንዱ ክስተት ፖሊቲካዊ ትርፍ ለማግኘት የሚያደርጉት አስቂኝ ጥረት ደግሞ በጣም ይገርመኛል። ስትራቴጂያቸው ኢሕአዴግ የሚፈጥራቸውን ስሕተቶችና በየአጋጣሚው የሚፈጠሩ ክስተቶችን ለራሱ ዓላማ ማዋል ብቻ ነው።
እንደምታስታወሰው፣ አውራምባ ታይምስ ጋዜጣን ስንሠራ አየለ ጫሚሶን ለመሳሰሉ ተቃዋሚዎች ‹‹ሽፋን አንሰጥም›› እንል ነበር። ለምን ከተባለ የራሳቸው የሆነ አጀንዳ ስለሌላቸው ነው። በአየለ እና በብርሃኑ መካከል ያለው አንድነት የኢሕአዴግን አጀንዳ ከማራገብ ውጪ እውነተኛ ለውጥ እንዲመጣ አለመፈለግ ሲሆን ልዩነታቸው ደግሞ አ… በኢሕአዴግ እየታዘዘ ብርሃኑ ግን በሻዕቢያ እየተጠመዘዘ መሆኑ ነው።
ትውልደ ሩሲያዊው ባለቅኔ፣ የኖቤል ሽልማት ባለድል፣ ሟች ጆሴፍ ብሮድስኪ ‹‹አንድ ነጻ ሰው ሲወድቅ ማንንም አይወቅስም›› በማለት ጽፏል። ይህ አባባል ራሳቸው ሊኖሩበት ለመረጡት ኅብረተሰብ ዕጣ ፈንታ የመጨረሻውን ኃላፊነት መቀበል ባለባቸው የዴሞክራሲ ዜጎችም ላይ የሚፀና ሀቅ ነው ተብሎ ይገለጻል። በአንጻሩ በአገራችን በመንግሥት፣ በተቋማትና በግለሰቦች ደረጃ አንዱ አንዱን አጥብቆ ሲወቅስ ይታያል።
ይህ ዓይነቱ የመወቃቀስ ባህል ገንቢ በሆነ መልኩ ቢሆን እንደ አገር እና እንደ ማኅበረሰብ ተጠቃሚ እንጂ ተጎጂ አንሆንም ነበር። መወቃቀሱ በፖለቲካ ልዩነት ደረጃ ሲሆን ከመተራረም ያልፍ እና ወደ መጠፋፋት ይቀየራል። በአገራችን፣ በ1960ዎቹ መጨረሻ የነበረው የፖለቲካ አሰላለፍ እና ልዩነት ቤተሰባዊ እና ማኅበራዊ ግንኙነትን ሁሉ በጣጥሶ ያልፍ ነበር። እህት እና ወንድም በሁለት የአስተሳሰብ (የርዕዮተ ዓለም) ልዩነት ምክንያት ለመገዳደል ሲፈላለጉ አይተናል ወይም አንብበናል። ‹‹ማኅበራዊ ግንኙነት ሁሌም ፖለቲካን ማለፍ አለበት›› የሚባለውን የሰለጠነው ዓለም አካሄድ ከመከተል ይልቅ በአገራችን ያለው የፖለቲካ ልዩነት ወደ መጠፋፋት ሲያመራ ታያለህ። ያ ልዩነትን በ‹‹አጥፍቶ መጥፋት›› ለመፍታት ይደረግ የነበረው ጥረት ዛሬም ድረስ ዘልቆ በዚህኛው ትውልድ ላይም እየተንፀባረቀ ነው። የ‹‹አጥፍቶ መጥፋት›› ፖለቲካ የግድ ከፖለቲካ ልዩነት ጋር ተያይዞም ላይመጣ ይችላል። ልዩነትም ሳይኖር ሰውን ለመፈረጅ (ብላክ ሜይል ለማድረግ) የተካኑ የፈጠራ ባለሙያዎች ካሉ እንደተፈጸመ ተደርጎ ሊወራ ይችላል። ካንተ የሚጠበቀው፣ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ለአሻሚ ትርጉም ተጋላጭ የሆነች ዓረፍተ-ነገርን ብቻ መተንፈስ ነው። በጋዜጠኝነት ውስጥም የምትመለከተው ተመሳሳይ መፈራረጅን ነው። በደጉ ጊዜ አብሮህ የበላ እና አብሮህ የጠጣ ባልደረባህ ያንተን አቋም በተሳሳተ ሁኔታ ተርጉሞ ለገበያ በማቅረብ መጠነኛ የስደት ፖለቲከኛነት ትርፍ ለማግኘት ሲጥር ታያለህ። እንደ አለመታደል ሆነና ከዚህ ያለፈ ገንቢ መወቃቀስ ብዙም አትመለከትም። ምናልባት ይህ እንዲለወጥ ማድረግ የሚችሉት የዳያስፖራ ፅንፈኞች ያልበከሏቸው የአገራችን ፖለቲከኞች ብቻ ናቸው።
በፅንፈኝነት አልተበከሉም የምትላቸውን የአገራችንን ፖለቲከኞች በምሳሌነት ልትነግረኝ ተችላለህ?
በጣም በርካታ ፖሊቲከኞችን ልጠራልህ እችላለሁ። ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ አቶ ስዬ አብርሃ፣ አቶ ያሬድ ጥበቡ፣ ዶክተር ያዕቆብ ኃይለ ማርያም፣ አቶ ግርማ ሰይፉ… በጣም በርካታ ሰዎችን መጥራት ይቻላል።
በእነዚህ የጠቀስካቸው ስሞች አማካኝት የአገራችን የፖለቲካ ሂደት አንድ ደረጃ ፈቀቅ የሚል ይመስልሀል?
ተስፋ አለኝ።
‹‹ዴሞክራሲ ለነጻነት ተቋማዊ ይዘት መስጠት ነው›› ይባላል። ከዚህ አኳያ ዴሞክራሲያዊ ነጻነትን በአሜሪካ፤ እንዲሁም በኢሕአዴግ ዴሞክራሲ እየተገነባባት መሆኑ በሚነገርባት አገራችን ‹‹አለ›› የሚባለውን የነጻነት ገጽታ እንደ ጋዜጠኛ ትዝብትህን ንገረኝ?
በዚህ ረገድ እኮ ያለው አንዱ መሠረታዊ ችግር፣ ኢሕአዴግ ነጻነትን የሚሰጥ እና የሚከለክል ሆኖ መገኘቱ፣ ‹‹ሰጪ›› እና ‹‹ከልካይ›› መሆኑንም ጭምር አምነን መቀበላችን ነው። አንድ አሜሪካዊ ነጻነቱን ተግባራዊ ሲያደርግ ፖሊስ በቁጥጥር ስር የሚያውለው የአሜሪካ ሕገ መንግሥት ከሚፈቅድለት ውጪ ከተንቀሳቀሰ ብቻ ነው። ከዚያ ውጪ ኋይት ሀውስ ፊት ለፊት መፈክር ይዘህ ባራክ ኦባማን ስትራገም ብትውል ማንም አይነካህም። ዛሬ አራት ኪሎ በሚገኘው የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ፊት ለፊት ቆመህ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምን ልትቃወም ቀርቶ ‹‹ጣሊያን አገር ለግራዚያኒ የመታሰቢያ ሐውልት ሊሠራ አይገባም!›› ብለህ በሰላማዊ ሰልፍ ወደ ጣሊያን ኤምባሲ መሄድ ያሳስራል። ይህ እርምጃ የተወሰደው፣ ‹‹ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት›› በሕገ መንግሥቱ ስላልተካተተ አይደለም። አሊያም ዋቢ ሸበሌ ሆቴል እራት ለመመገብ ከማዘጋጃ ቤት ፍቃድ ማግኘት አስፈላጊ ስለሆነም አይደለም። ‹‹አባይን እየገደብን ስለሆነ፣ በቃ! ሕገ መንግሥታዊ መብቶችን አትጠይቁ!›› እያሉን ነው።
እዚህ የምታገኘው ነጻነት ምን ያደርግልሀል? ምንስ ትለውጥበታለህ? እዚህ ያሉ ተቃዋሚዎችም ቢሆኑ እዚህ ያገኙትን የአሜሪካ ሕገ መንግሥት ነጻነት የፖለቲካ ባላንጣቸውን ሲሰድቡበት እና ሲያዋርዱበት እንጂ ቁም ነገር ሲሠሩበት አይታይም። ያ ደግሞ ከየትም የመጣ ችግር አይደለም። ሌሎችን የምንተቸውን ያህል በውስጣችን ነጻነት አለመኖሩ ነው። ‹‹ነጻነት የማያውቅ ነጻ አውጪ›› ብለን መጽሐፍ ከመጻፍ ውጪ ወደ ስልጣን እየተጓዝን ያለነው ሌሎች በነጻነት እንዲተቹን መፍቀድ ሳንችል ነው። የፕሬስ ነጻነትን ማፈን የምንጀምረው ገና መንግሥታዊ ሥልጣን ሳንይዝ ነው። የዛሬ ሦስት ዓመት አካባቢ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም አምባገነንነትን ስለመቃወም የተናገሩትን ነገር ሁሌም አልረሳውም። ‹‹እኛ እኮ በሥልጣን ላይ ያሉትን የምንቃወመው አምባገነንነታቸውን እንጂ በግለሰብ ደረጃ ጥላቻ ኖሮን አይደለም፤ ስለዚህ በተቃዋሚውም ጎራ አምባገነኖች ሲኖሩ ‘ትግሉ ይጎዳል’ በሚል ሽፋን ካበረታታናቸው ነገም የስም ለውጥ ባደረጉ አምባገነኖች ነው የምንገዛው›› ብለው ነበር። ኢሕአዴግ የራሱን ሕግ እንዲያከብር ከመታገል ጎን ለጎን የፕሮፌሰርንም ምክር መስማት ተገቢ ይመስለኛል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ነባራዊ ሁኔታ ሚዲያ አራተኛው የመንግሥት አካል ተደርጎ አልተቆጠረም። ሚዲያ 4ኛ የመንግሥት አካል መሆን እንዲችል ወሳኙ እውነት ምንድን ነው? ከሚዲያ ባለሙያዎች ምን ይጠበቃል ትላለህ?
ኢሕአዴግ ሚዲያውን እንደ አራተኛው የመንግሥት አካል ሊቆጥር ቀርቶ [ድሮ እንደሚያደርገው] በጠላትነት ፈርጆ እንኳን ሊያሠራው አልቻለም። የፕሬስ አዋጁ በ1985 ዓ.ም. ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ ያሉትን 20 ዓመታት ስትመለከት በነጻ ሚዲያው እና በመንግሥት ሹማምንት መሀከል የነበረው ግንኙነት የአይጥ እና ድመት ዓይነት ነው። ጋዜጠኞች ሲታሰሩ እና ሲፈቱ፣ ጋዜጦቹም ‹‹ሕጋዊ እና ፖለቲካዊ›› እርምጃ ሲወሰድባቸው አስተውለናል። ስለዚህ ጋዜጠኛው ‹‹እንደ አራተኛ የመንግሥት አካል ልቆጠር!›› የሚል የቅንጦት ጥያቄ ሊጠይቅ ቀርቶ ‹‹ሳልታሰር፣ ሳልሰደድ፣ ድርጅቴ ሳይዘጋ በነጻነት ልሥራ›› ለሚለው መሠረታዊ ጥያቄ እንኳን አዎንታዊ ምላሽ አላገኘም። ዛሬም የምናወራው ስለ እስክንድር የይግባኝ ውሳኔ፣ ስለ ውብሸት ወደ ዝዋይ እስር ቤት መዘዋወር፣ ስለ ርዕዮት ሕክምና ማጣት ነው። ‹‹ከሚዲያ ባለሙያዎች ምን ይጠበቃል?›› ላልከው ግን ምንም እንኳን ችግሮች ቢኖሩም ሚዲያው ሚዛናዊ ሆኖ መቀጠል አለበት እንጂ የአጸፋዊ ምላሽ መስጫ መድረክ መሆን የለበትም የሚል እምነት አለኝ።
ሚዲያውስ ‹‹አራተኛው የመንግሥት አካል›› ለመሆን ‹‹ማድረግ ያለበትን አድርጓል›› ብለህ ታስባለህ?
ያ ደግሞ የ20 ዓመት ዕድሜ ብቻ ባስቆጠረው የኢትዮጵያ ፕሬስ ይቅርና ከ200 ዓመት በላይ ታሪክ ባለው የአሜሪካ ፕሬስም ችግሮች ይታያሉ። ሁሌም በክልከላ የሚታረም ነገር አይኖርም። መብቱ ሲሰጥህ ኃላፊነት እየተሰማህ ይመጣል። ሕዝቡ ይበልጥ እየሰለጠነ በመጣ ቁጥር ስልጡን ፕሬስ ወደ መምረጥ ይሄዳል። በሰለጠነው ዓለም ያሉት ፕሬሶች የመጡበት ታሪክ በክልከላ ሳይሆን ኃላፊነት እየተሸከሙ መሆኑን ያሳያል።
አቦይ ስብሃት በአንድ ወቅት በሰጡት ቃለ-ምልልስ ‹‹…እጅግ የሚገርመው ለኋላቀርነታችን መሠረት የሆነው ይኼ ነጻ ፕሬስ ነው። አብዛኛው ነጻ ፕሬስ ኢትዮጵያዊ አይደለም። የሚነሳው አገርን ማዕከል አድርጎ አይደለም። ጥላቻን ነው የሚሰብከው። የኢትዮጵያን የጥላቻ ፖለቲካ ለማጥናት የተትረፈረፈው መረጃ የሚገኘው ከኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ነው። በአንድ ጋዜጣ አራት እና አምስት ዕትም ለማስተርስ ድግሪ የሚሆን የመመረቂያ ጽሑፍ መጻፍ ይቻላል። …ከሥነ-ምግባር አኳያ ተለክተው የመንግሥትም ሆነ ነጻ ፕሬስ ፍርድ ቤት ቢሄዱ ቅር አይለኝም።›› ብለው ነበር። ለዚህ ምን ምላሽ ትሰጣለህ?
በአቦይ ስብሃት አባባል ውስጥ መጠነኛ እውነት የለም ማለት አይደለም። ‹‹አብዛኛው የነጻ ፕሬስ›› የሚለው ድምዳሜ ግን ትክክል አይመስለኝም። በተለይ በ1980ዎቹ ብዙ የሥነ-ምግባር ችግር እንደነበር አይካድም። ‹‹ፕሬሱስ በምን ዓይነት አስቸጋሪ ሁኔታ [ፖሊቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች] ውስጥ ሆኖ ነበር የሚሠራው?›› የሚል ጥያቄ ማንሳት ተገቢ ይመስለኛል። እንደ አንድ ጀማሪ የዴሞክራሲ ተቋም፣ በወቅቱ ነጻው ፕሬስ እንዲጠናከር የአቦይ ስብሃት መንግሥት ምን ዓይነት አስተዋጽኦ አደረገ? እንደ ሌሎች አገሮች የገንዘብ ድጎማ ማድረግ ባይቻል እንኳን ቢያንስ ጋዜጠኛውን ባለማሰር ነጻ ፕሬስ እንዲያብብ ማድረግ ይቻል ነበር። አቦይ ስብሃት በሚገልጹት ደረጃ ፕሬሱ ፕሮፌሽናል አለመሆኑ ‹‹የሚያስወቅሰው ሙያተኛውን ብቻ ነው›› ካልን ተሳስተናል። ሌሎች የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በተለይ ከውጪ አገር ዲፕሎማቶች ጋር ሲያወሩ ስለ ነጻው ፕሬስ ያላቸው ዕይታ እና ድምዳሜ እንደ አቦይ ስብሃት የተንሸዋረረ ነው። እሺ! እውነታው አቦይ እንዳሉት ይሁን እንበልና ማነው ተጠያቂው? ‹‹የአገሬ ፕሬስ ኋላቀር ነው›› ብሎ ለውጭ ሰዎች አፍን ሞልቶ መናገርስ መንግሥትን ያስከብራል?
ኢትዮጵያን እና አውራምባ ታይምስ ጋዜጣን ስታስብ ምን የሚቆጭህ ነገር አለ?
አውራምባ ታይምስ እንደ አንድ ነጻ ሚዲያ በሦስት ዓመት ከስምንት ወር ዕድሜዋ ብዙ የዳሰሰቻቸው ርዕሠ ጉዳዮች ነበሩ። ከመጀመሪያ ጀምሮ እስከ መጨረሻ ድረስ አብረውን የዘለቁት አንባቢዎቻችን የብርታታችን ምንጭ ነበሩ። የበለጠ ሥራ እንድንሠራ አበረታተውናል፣ ገስጸውናል፣ መክረውናል። እንደምታስታውሰው፣ በመጀመሪያው እትም ላይ የነበረ የጋዜጣዋ ባልደረቦች ቁጥር ቁጥራችን አምስት ነበር፡፡ ከዚያ ቀስ በቀስ ወደ 20 ገደማ አደገ። መጀመሪያ ስንጀምር በ16 ገጽ ነበር፤ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ወደ 24 ገጽ አሳደግናት፤ ከሁለት ዓመት በኋላም ባለቀለም ጋዜጣ እንድትሆን ተደረገ… እንዲህ እንዲህ እያልን ብዙ ነገር እያሻሻልን ነበር። እስከ ዛሬ ብንቆይ ኖሮ ምናልባትም በሣምንት ሁለት ጊዜ እንድትወጣ ማድረግ ችለን ሊሆን ይችል ነበር። በምንወዳት አገራችን በአስር ሺህዎች ከሚቆጠሩ ሳምንታዊ አንባቢዎቻችን የምንወደውን ሥራ እየሠራን፣ የጎደለውን እየሞላን መሥራትን የመሰለ የሚያረካ ነገር የለም፤ ግን አልሆነም። የምንሠራው በኃላፊነት መንፈስ ሕገ- መንግሥቱን እና በየደረጃው ያሉ ሕጎችን አክብረን ነበር። ግን እኛ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መጎልበት የምናበረክታት ሚጢጢ ድርሻ በአዎንታዊ መንገድ አልታየችም። ‹‹አውራምባ ታይምስ የተዘጋችው ከስራ ነው፤ እኛ አልተጫንናችሁም›› ያሉ ሰዎች ዌብሳይታችንን ወዲያውኑ በማፈን ‹‹ጫና ወይስ ኪሳራ?›› የሚለውን እንቆቅልሽ ራሳቸው ፈትተውታል። እኔ ከመላው የአውራምባ ታይምስ ባልደረቦች [በፕ/ር አለማየሁ ገብረማሪያም አገላለጽ ‹‹ቲም አውራምባ››] ጋር የነበረኝ የሦስት ዓመት ከስምንት ወር አስደሳች ቆይታ መቼም ቢሆን በሕይወት ዘመኔ ተመልሶ የሚመጣ አይመስለኝም። እስኪ አስበው፣ የፍጼን የ‹‹መርሕ›› ጥያቄዎች፣ የግዛውን ነገሮችን በተለያየ አቅጣጫ የማየት ችሎታ፤ የውብሸትን የሥራ መንፈስ አነቃቂ ጨዋታዎች፣ የአቤልን እልህ አስጨራሽ ክርክር፣ የነብዩን የግራፊክስ ክህሎት፣ ያንተን ጤና ነክ ትንታኔዎች፣ የወሰንን የደስታ እና የመከራ ዘመን ወዳጅነት፤ (እንዲሁም የሌሎች ባልደረቦቻችን ትዝታዎች ተጨማምረው) ሁሉም ለአውራምቢት [በፍጼ አጠራር] የነበረው ፍቅር መቼም ከኅሊናችን አይጠፋም!!!
ጋዜጠኛ እና ፖለቲከኛ ከአገሩ ከወጣ ወይም ከተሰደደ ‹‹ከባህር የወጣ አሳ ማለት ነው›› ከአገር የተሰደዳችሁ ጋዜጠኛች ተፅዕኖ የመፍጠር አቅማችሁ ‹‹ኢምንት ነው›› ይባላል። ድረ- ገጾች ስለሚታፈኑ፣ ኅብረተሰቡም ድረ-ገፆች የመከታተል ልምዱ ዝቅተኛ ስለሆነ በሥራችሁ የምትደርሱት የኅብረተሰቡ ክፍል ዝቅተኛ አይሆንም? ከ97 ምርጫ በፊትም ሆነ በኋላ ከአገር የተሰደዱ ጋዜጠኞች ከተለያየ የዓለም ክፍል የቻሉትን ያህል ቢተጉ ተፅዕኖ ይፈጥራሉ ብለህ ታስባለህ?
ይሄ ምንም አያጠያይቅም። ፖለቲከኛም ይሁን ጋዜጠኛ ከአገሩ ከወጣ ምንም የሚፈጥረው ተጽዕኖ የለም። ውጪ ሆነህ የምትሠራውን ሥራ በብዛት የሚያነበው ስደተኛ ነው፤ እሱ ደግሞ ተለወጠ/ አልተለወጠ ምንም የሚያመጣው ተጽዕኖ የለም። ላለመመለስ አገር ለቀህ ስትወጣ ሁሉም ነገርህ የሚቀረው እዚያችው ኤርፖርት ኬላ ላይ ነው።
የአንተም ሆነ የሌሎች በኢትዮጵያ ላይ የሚያጠነጥኑ የድረ-ገጽ ዜና እና ሀተታዎች ብዙዎቹ በራስ የተሰሩ ዘገባዎች (ኤክስክሉሲቭ) አይደሉምና የዳያስፖራ ሚዲያዎች በሌላ ድረ-ገጽ ጉዳይ የመጠቀም (Copy–Paste) ሥራን የምትከተሉ አይመስልህም?
በእርግጠኝነት የምነግርህ ነገር ይህን ጥያቄ አውራምባ ታይምስ ድረ-ገጽን ተመልክተህ የሰነዘርከው አይመስልም። ምክንያቱም የኛ ድረ-ገጽ በይዘት እና በሚሳተፉ ጸሐፊዎች ማንነት ረገድ ካየኸው ከሌሎቹ ፍጹም የተለየ ነው። ከሌሎቹ የተሻለ ወይም የበለጠ ነው ግን እያልኩህ አይደለም። ‹‹የተለየ ነው›› ስልህ በሌሎች ድረ-ገጾች ላይ አዘውትረው የሚጽፉ ጸሐፊዎችን እኛ አናስተናግድም። ያንን የምናደርግበት ዋናው ምክንያት ከሌሎቹ የተለየ ነገር ይዘን ለመቅረብ እንጂ ጸሐፊዎቹን ሳንፈልጋቸው ቀርተን አይደለም። አንዳንዶቹ አድርጉ እንደሚሉን የ‹‹ሥርዓቱ ሰለባ ነን›› ብለን ከጋዜጠኝነት መርህ አንወጣም። በተቻለ መጠን ሚዛናዊ ለማድረግ እንጥራለን። ያ ደግሞ ልዩ ያደርገናል ብቻ ሳይሆን በአንዳንድ ጭፍኖች ዘንድም እያስተቸን ነው።
‹‹በራስ የተሰሩ ዘገባዎች (ኤክስክሉሲቭ) አይደሉም›› ያልከው ነገር ትንሽ ፈገግ ያሰኛል። እስኪ ሌሎች ትልልቅ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን ተከታተል። በራሳቸው ዘጋቢ የሚሠራ ነገር የሚያቀርቡት ምን ያህሎቹ ናቸው? በተረፈ እንደ ምንጭ እየጠቀሱ የሚያወጡት ሬውተርስ፣ አሶሺየትድ ፕሬስና አጃንስ ፍራንስ ፕሬስን ከመሳሰሉ ሚዲያዎች የሚያገኙትን መረጃ አይደለምን? ሌሎቹን ተዋቸው፣ እዚያው አጠገብህ ያለውን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች ያሉት ኢቴቪ እንኳን አብዛኛዎቹ ዜናዎቹ ከዋልታ እና ከኢዜአ የሚወሰዱ አይደሉም? ይህ ማለት ግን ‹‹ኤክስክሉሲቭ›› ነገር አውራምባ ታይምስ ላይ አይሠራም ማለት አይደለም። የምንሠራው ሥራ ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ እንደመሆኑ ኤክስክሉሲቭ ሥራ ለመሥራት በቋሚነት የሚሠሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው ዘጋቢዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ሊኖሩህ ይገባል። ያ ደግሞ በእኛ ውስን አቅም አስቸጋሪነቱ ምን ድረስ እንደሆነ አንተም ታውቀዋለህ።
ከዲሲ ወደ ፊኒክስ አሪዞና ሄደህ መኖር ጀምረሃል። በዲሲ ያለው የዳያስፖራው ተጽዕኖ ከብዶሀል ይባላል። በአንድ ወቅት በማኅበራዊ ድረ-ገጽ ላይ ራስን መሆን ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ ገልፀህ ነበር። እስኪ አስቸጋሪነቱን በደንብ ግለጸው?
በዋናነት ወደ አሪዞና የመጣሁት በ‹‹ዩኒቨርሲቲ ኦፍ አሪዞና›› ያገኘሁትን የትምህርት ዕድል ለመጠቀም ቢሆንም ዲሲ አካባቢ ካለው የፖለቲካ ሙቀት ለመራቅም አጋጣሚውን ተጠቅሜበታለሁ። አገር ቤት እያለን መንግሥት ልማታዊ ዘገባዎችን አቅርቡ እያለ እንደሚወተውተን ሁሉ እዚህም ያሉ ፖሊቲከኞች እኛ ስለምናውቃት ኢትዮጵያ ሳይሆን እነሱ በምናባቸው ስለሚስሏት ኢትዮጵያ እንድንጽፍ ይፈልጋሉ። ‹‹ዳያስፖራ ያለ ጋዜጠኛ ወይ ወያኔን አሊያም እከሌ የተባለን ድርጅት መደገፍ አለበት›› ብለው በአደባባይ የሚናገሩትን ጨምሮ ማለቴ ነው። በቅርቡ ከወዳጄ መስፍን ነጋሽ ጋር ስናወራ፤ በንግግሩ መሀል አንድ እጅግ የሚማርክ አገላለጽ ሲጠቀም ሰማሁት። ‹‹እኛ ጋዜጠኞች ገና ለገና ኢሕአዴግ ስላባረረን እና ስለከሰሰን አንዳንድ ተቃዋሚዎች የእነሱ የግል ንብረት የሆንን ይመስላቸዋል፤ ከኢሕአዴግ ጋር ተጣላን ማለት እኮ ተቃዋሚዎች የሚሉት ሁሉ ይስማማናል ማለት አይደለም›› ብሎ ነበር። የሚሰደዱ ጋዜጠኞችን በተመለከተ፣ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ አንድ የተሳሳተ ግንዛቤ አለ። መከራን ሸሽቶ የመጣ ጋዜጠኛ ‹‹ዳያስፖራ ያሉ ጽንፈኛ ፖሊቲከኞችን በባርነት ሊያገለግል ይገባል›› የሚል ያልተጻፈ ሕግ አለ። አንዳንዶቹ የተሰደዱ ጋዜጠኞች ኢሕአዴግን ማገልገል እንጂ ተቃዋሚን ማገልገል እንደ መጥፎ ነገር አድርገው አይመለከቱትም። የእነዚህን ጥቂት ጋዜጠኞች ደካማ ጎን የተመለከቱ ተቃዋሚዎችም ሁሉም የተሰደደ ጋዜጠኛ የእነሱ የግል ንብረት እንደሆነ አድርገው ማመን ጀመሩ። ይህንን እምነታቸውን የሚፈታተን ጋዜጠኛ ካለ በተለመደው የፍረጃ ስትራቴጂያቸው በወያኔነት ይፈርጁታል። በየቦታው ያሉ ፓልቶኮቻቸው፣ ብሎጎቻቸውና ዌብሳይቶቻቸውም ያንን ፈጠራ ያስተጋቡታል። በዚህ መልኩ ሁሉም አንገቱን መድፋት ይመርጣል። ከ1997 ዓ.ም. በፊት በነጻው ፕሬስ ውስጥ በነበራቸው ተሳትፎ እጅግ የምናደንቃቸው እና በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲያጋልጡ የኖሩ ጋዜጠኞች ከእስር ቤት እንደወጡ በቀጥታ በአንድ የፖለቲካ ድርጅት ጥላ ሥር ሲሰባሰቡ መመልከት ያሳዝናል። ‹‹ከቅንጅት መሪዎች ጋር ተባብራችሁ መንግሥትን ልትገለብጡ ነበር›› የሚለውን ክስ ሐሰትነት በተደጋጋሚ የተናገርን ሰዎች፤ ‹‹ክሱ እውነት ነበር እንዴ?›› በሚያስብል መልኩ በ1997 ዓ.ም. ከቅንጅት መሪዎች መካከል አንዱ የነበሩ ግለሰብ ባቋቋሙት የስደት የፖሊቲካ ድርጅት እና በእሱ ስር ባለ የሚዲያ ተቋም መሰባሰብ ሙያውን ማዋረድ ነው።
እውን ‹‹ሚዛናዊ ጋዜጠኛ ነኝ›› ብለህ ታምናለህ?
አቅሜ በፈቀደ መጠን ሚዛናዊ ለመሆን እጥራለሁ። በአገራችን ተጨባጭ የፖሊቲካ ሁኔታ በተለይ በዳያስፖራ ሚዛናዊ መሆን የራሱ የሆነ የሚያስከፍለው ዋጋ እንዳለ እሙን ነው። ለምሳሌ፣ በአገር ቤት ያለ አንባቢ ገለልተኛ ሆነህ መረጃውን እስካቀረብክለት ድረስ ይቀበልሀል። ምሳሌ፣ እንደምታስታውሰው በጋዜጣችን ላይ በርካታ የመንግሥት ባለሥልጣናት [ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም፣ አቶ ሴኩቱሬ ጌታቸው፣ አቶ ሽመልስ ከማል፣ ኮሚሽነር ዓሊ ሱሌይማን፣ ዶ/ር ደብረፅዮን ...ና ሌሎች] እንግዳ ሆነው ቀርበዋል። የአቦይ ስብሐት መጣጥፎችም በፍትሕ ጋዜጣ ላይ በተከታታይ ይስተናገዱ ነበር። አንባቢ ግን ወቀሳ ሲያቀርብ አላስታውስም። እዚህ ዲያስፖራ ያለው ሁኔታ ደግሞ ፍጹም የተለየ ነው። የመንግሥት ባለሥልጣናትን ማቅረብ ቀርቶ አቶ ስዬ አብርሃን ቃለ-ምልልስ በማድረጌ የደረሰብኝን ውግዘት እኔ ነኝ የማውቀው። በቃ ፖሊቲካችን እንደዚህ ሆኗል።
ለኢትዮጵያ የሚበጃት ማን ነው? ምንድን ነው? አሁን ላለችበት ችግር፣ ፈተና፣ ድህነት…ማን ይታደጋት?
በእርግጠኝነት የምነግርህ፣ ለነገዋ ኢትዮጵያ ተስፋ እና ቤዛ ሊሆኑ የሚችሉት በአገር ቤት ያሉ ጋዜጠኞች፣ ተቃዋሚዎችና የለውጥ አራማጆች ብቻ ናቸው። ዋጋ የሚከፍሉት፣ መከራ የሚቀበሉት ጫናው የሚበረታባቸውም እነሱ ላይ ነው። አንድ ችግር ቢፈጠር ቀድመው ክፍተቱን የሚሞሉትም እነሱ ናቸው። እዚህ ያሉ ፖለቲከኞች የቤት ሥራው ከተሠራ በኋላ መምጣት የሚፈልጉ ናቸው። አስታውሳለሁ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ መሞታቸው ሲነገር የአውሮፕላን ትኬት ለመቁረጥ የዳዳቸው የተቃዋሚ አመራሮች ነበሩ። እንደኔ እንደኔ በኢሕአዴግ ላይ አንዳች አስገዳጅ ነገር ቢመጣ እና ፈተና ቢጋረጥበት፣ ሕዝቡን አንቀሳቅሰው አንድ ለውጥ ለማምጣት ቅርብ የሆኑት በአገር ቤት ያሉት ፖሊቲከኞች ናቸው። ከኢሕአዴግ ሴራ ጎን ለጎን በ1997ቱ ምርጫ የተገኘው የዴሞክራሲ ጭላንጭል በድጋሚ እንዲጨልም ያደረገው የስደት ፖለቲከኞች ጣልቃ ገብነት ነው። ፓርላማ አለመግባት፣ አዲስ አበባን አለመረከብ የማንም ሳይሆን የዳያስፖራው ፍላጎት ነበር። እዚህ ሆነው የአገር ቤት ታጋዮችን እጅ ለመጠምዘዝ የሚዳዳቸው ፖለቲከኞች ለትግሉ ቁርጠኛ ሊሆኑ ቀርቶ የኢትዮጵያን ዜግነት ይዘው ለመቆየት እንኳን ወኔ የላቸውም። ከ‹‹ግንቦት 7›› የሥራ አስፈጻሚ አባላት መካከል 80 ከመቶ የሚሆኑት ዜግነታቸውን ቀይረዋል። እዚህ ሆነው ግን እርስ በርሳችን እንድንተላለቅ የሚያደርግ የእልቂት ነጋሪት ሌት ተቀን ይጎስማሉ። በሆነ አጋጣሚ አገር ቤት ቢገቡ እና አንድ ችግር ቢከሰት እንኳን የሚሸሹበት አገር ስላላቸው ያለ ምንም ችግር በቻርተር አይሮፕላን ይወጣሉ። ገና ለገና ‹‹ድጋፍ የሚሰጠን በውጭ ያለው ማኅበረሰብ ነው›› በሚል ጊዜያዊ ፈተና በአገር ቤት የሚደረገው ትግል የስደት ፖለቲካ መጠቀሚያ መሆን የለበትም። ‹‹ኢሕአዴግም ቢሆን በሩን ለድርድር ክፍት አድርጎ የፖሊሲ ማሻሻያ ሊያደርግ የሚችለው ከስደተኛቹ ፖለቲከኞች በሚመጣበት ጫና ነው›› የሚሉ የዋሆች ካሉ ተሳስተዋል። የአገር ቤት ፖለቲከኞች በሚያራርቃቸው ሳይሆን በሚያቀራርባቸው ጉዳይ ላይ ጊዜ ማጥፋት አለባቸው። ከፖለቲካዊ ፅንፍ እና ከመጠፋፋት ወጥተን የሰለጠነ ፖለቲካዊ ንግግር ወይም ውይይት ለማድረግ ዝግጁነቱ ሊኖር ይገባል። በዚህ መንገድ አገር በቀል የፖለቲካ ለውጥ/መሻሻል ቢመጣ ችግራችን እና ድህነታችንም አብሮ መፍትሄ ያገኛል።
ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ከፖለቲካው ሜዳ ጠፍታለች በማለት ተስፋ በመቁረጥ የሚተቿት አሉ። በቅርብም ያስተዋልከው ነገር ስለሚኖር በዚህ ላይ ምን ትላለህ?
እንዳልከው የብርቱካንን ወቅታዊ አቋም በተገቢው ሁኔታ ያልተረዱ ሰዎች እዚህም ሲተቿት ይደመጣል። ምን ማድረግ ነበረባት? እዚህ እንደመጣች እዚህ ያሉ ተቃዋሚዎችን መቀላቀል ነበረባት? ይኼ ብርቱካንን እስከ ወዲያኛው ያጠፋታል እንጂ ወሳኝ ስፍራ ኖሯት እንድትወጣ አያደርጋትም። እሷም ያንን እንደማታደርግ ከመነሻው አዲስ አበባ ሆና ተናግራለች። የአንዳንዶቹ ምክንያት ‹‹ድምፅዋን አጠፋች›› የሚል ነው። ይህም ቢሆን ከፖለቲካ መውጣቷን የሚያረጋግጥ አይደለም። እዚህ እንደመጣች ‹‹የዴሞክራሲ ፌሎው›› ሆና የተቀላቀለችው ‹‹National Endowment for Democracy›› የተባለ ትልቅ ዓለም አቀፍ ተቋምን ነው። በዚህ ተቋም ለአንድ ዓመት ያህል ቆይታለች። ከአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ፖሊሲ አስፈጻሚዎች፣ የተለያዩ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ የምርምር ተቋማት ኃላፊዎች፣ በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ እውቅ የለውጥ አራማጆች፣ አንግ ሳን ሱቺን ከመሳሰሉ ዓለም አቀፍ የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብት ታጋዮች፤ ከታወቁ የፖለቲካ አቀንቃኞች ጋር የልምድ ልውውጥ ስታደርግ እና ዕውቀት ስትቀስም ነበር።
ዴሞክራሲያዊ ተቋማት እንዴት እንደሚገነቡ፣ በበለጸጉ አገራት ስላሉ የሲቪክ ድርጅቶች ሚናና ስለ ሰላማዊ ትግል መሠረታዊ አካሄድ በተለያዩ የ‹‹ቲንክ ታንክ›› መድረኮች እየተገኘች ልምዷን ስታካፍልና ልምድ ስትቀስም ነው የቆየችው፡፡ ይሄ በብርቱካን ደረጃ ላለ ወጣት ፖለቲከኛና በአገራችን ላለው ያልተቀናጀ የሰላማዊ ትግል አካሄድ ወሳኝ ይመስለኛል። እንዲህ ዓይነቱ ልምድ ለወደፊቱ የፖለቲካ ሕይወቷ ቀላል ልምድ አይደለም። ማንም በእሷ የእውቅና ደረጃ ላይ ያለ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ድርጅት መሪ ይህ ዓይነቱን ልምድ የመቅሰም አጋጣሚ አግኝቷል ብዬ አላስብም። በቅርቡ የሚጠናቀቀው የሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የአንድ ዓመት ቆይታዋም የዚህ አንድ አካል ነው። በቀጣይ ደግሞ በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሜሪላንድ ትምህርቷ ይቀጥላል።
እንግዲህ ‹‹ከፖለቲካ አልወጣም፤ ብርቱካን ከፖለቲካ ትወጣለች የሚባለው አባባል ፈጽሞ የማይታሰብ ነው፤ ለሦስት ወይም ለአራት ዓመታት ያህል ግን አቅሜን በእውቀት መገንባት እፈልጋለሁ›› ብላ የመጨረሻውን ጋዜጣዊ መግለጫ ለሚዲያዎች ሰጥታ ከአገር የወጣችው ብርቱካን ጊዜዋን በዚህ መልኩ እየተጠቀመችበት ነው። ታዲያ በአንድ ዓመት ውስጥ የትኛውን ቃሏን አጥፋ ነው ተወቃሽ የምትሆነው?
ብርቱካን የ‹‹ከሰረች ፖለቲከኛ›› ማለት አይቻልም?
አይቻልም፤ ቃሉም አይገልጻትም። እንዲህ የሚሏትን ሰዎች አስተያየት አከብራለሁ። በእኔ እምነት ብርቱካን ማድረግ የሚገባትን እያደረገች ነው ብዬ አምናለሁ። በእርግጠኝነት ይህን ፕሮግራሟን አጠናቃ በዚህ ልምዷ ወደ ፖለቲካ ስትመለስ የተቃውሞ ፖለቲካውን ትግል አንድ ደረጃ ከፍ ታደርገዋለች የሚል ተስፋ አለኝ።
አውራምባ ታይምስ ስትጀመር ‹‹ዝክረ- ቃሊቲ›› በሚል አምድ ስር የ21 ወራት የእስር ቤት ቆይታህን በተከታታይ ትጽፍ ነበር። በኋላም ተቋረጠ። ጽሑፉ ቢቀጥል ኖሮ ‹‹እጽፈው ነበር›› የምትለውን የ‹‹ቃሊቲ›› አጋጣሚ ልትነግረኝ ትችላለህ?
አብረውን የታሰሩ አራት ያህል የአዕምሮ በሽተኞች ነበሩ። የእነዚህ ምስኪኖች ታሪክ አንባቢ ጋር ባለመድረሱ ሁሌም ይከነክነኛል። እነዚህ የአዕምሮ በሽተኞች ሁሉም የየራሳቸው የሆነ ባህሪ ነበራቸው። አንዱ ደስታ ይባላል። ደስታ መንገድ ላይ ህጻን ልጅ በመግደል ወንጀል ተፈርዶበት የመጣ ነው። ነገር ግን የአዕምሮ በሽተኛ መሆኑ ከአማኑኤል ሆስፒታል ቢረጋገጥም የሚረከበው ቤተሰብ በመጥፋቱ ነው እኛ ጋር እንዲቆይ የተደረገው። ደስታ ማለት ቡና እና ሲጋራ ከገዛህለት የማያጫውትህ ታሪክ የለም። በእሱ እምነት ለእስር የበቃው ሰው በመግደሉ ሳይሆን የተባበሩት መንግሥታት ከሱዳን መንግሥት ጋር ተመሳጥሮ እዚህ እንዲቆይ ስላደረገው እና የኢትዮጵያ መንግሥትም ‹‹ከሱዳን ጋር ምን አጨቃጨቀኝ›› ብሎ ዝም እንዳለው ደጋግሞ ይናገራል። ሌላው እስረኛ ደግሞ አባስ ይባላል። አባስ ሁሌም አድመኛ ነው። በስጦታ መልክ የሚሰጡትን ሱሪዎች እየቆረጠ ወደ ቁምጣነት ካልቀየራቸው በስተቀር የሚሰጠውን የሰው ልብስ አይለብስም። አንድ ጊዜ የእስረኛ አስተዳደሩ በእርዳታ ከተገኙ አልባሳት መካከል አንዱን ሱሪ አንስቶ ለአባስ ይሰጠዋል። እንዳይቆርጠው ጥብቅ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው አድመኛው አባስ አማራጭ ሲያጣ የተሰጠውን ሱሪ ገልብጦ ለበሰው። አባስ ‹‹ለምን እንዲህ ያደርጋል›› ብዬ ሰዎችን ስጠይቅ የፖለቲካ እስረኛ በመሆኑ ምክንያት ያዳበረው እልህና ‹‹አልሸነፍ ባይነት›› በዚህ መልኩ እንደሚገልጸው አጫወቱኝ።
አባስ የታሰረው በ1993 ዓ.ም የፒያሳው አንበሳ ጫማ ሲዘረፍ ነው። ከጓደኞቹ እንደሰማሁት፤ ፒያሳ አካባቢ በሊስትሮነት ሲተዳደር የነበረው አባስ አንድ ደንበኛው ጫማውን አስጠርጎ ሲያበቃ እዛው እንደተቀመጠ የግራ እግር ጫማውን አውልቆ ‹‹ስፋልኝ›› በማለት ለአባስ ይሰጠዋል። አባስ ተቀብሎ ጫማውን እየሰፋ እያለ አካባቢው ቀውጢ ይሆናል። ደንበኛ ሆዬ የግራ እግር ጫማውን አባስ ጋር ትቶ እግሬ አውጪኝ ይላል። በአካባቢው የደረሱ ፖሊሶች ግን በአባስ እጅ ላይ ያለው አንድ እግር ጫማ በቸልታ አልተመለከቱትም። ‹‹ከአንበሳ ጫማ የተዘረፈ ነው›› በማለት አባስን በአመጽ እና ሁከት ማነሳሳት ወህኒ ቤት ይጨምሩታል… እንዲህ እንዲህ አይነት ብዙ አሳዛኝ ታሪኮች ነበሩ።
ጋዜጠኛ ዘጋቢ፣ ፀሐፊ እና ታዛቢ ብቻ ሳይሆን አንባቢ መሆንም የግድ ይገባዋል። የሚያነብ ጋዜጠኛ ደግሞ ዕይታው ሰፍቶ ነገሮችን በጥልቀት የመጻፍ አቅምን ያዳብራል። ዳዊት አንባቢ ነህ? የንባብ ልምድህ ምን ይመስላል?
የማንበብ ልምድ የሌለው ጋዜጠኛ መጀመሪያውኑ ጋዜጠኛም መሆን አይችልም። የሚጻፍም ነገር አይኖረውም። እኛ አገር እንደምታወቀው የውጭ መጽሐፎችን ለማግኘት ያለው ችግር ራሱ በጣም ከባድ ነው። ቡክ ወርልድ እና የኤድናሞሉ ስቶር ብቻ ነው ወቅታዊ መጽሐፎችን የሚያቀርበው። እነሱም በበቂ ሁኔታ አያቀርቡም። ለምሳሌ፣ አዲስ አበባ በነበርኩበት ጊዜ የኖአም ቾምስኪይ፣ የጆን ግሪሻምና የታሪቅ ዓሊ መጽሐፎችን በነዚህ ስቶሮች ውስጥ ፈልጌ ማግኘት አልቻልኩም ነበር። ወደ ጥያቄህ ስመለስ፣ እንኳንና እኛን ቀርቶ ዘመናቸውን በሙሉ በንባብ ያሳለፉ ሰዎች ብዙ ባነበቡ ቁጥር ብዙ ያላነበቡት ነገር እንዳለ ነው እየተገነዘቡ የሚሄዱት። በተለይ ለማንበብ ደግሞ ጊዜ በጣም ወሳኝ ነው። እስር ቤት በነበርኩበት ጊዜ የነበረኝ ጊዜ እና አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ላይ እየሰራሁ እያለ የነበረኝ ጊዜ እኩል ሊሆን አይችልም። የጋዜጠኝነትን ስራ እየሰራህ መጽሐፎችን በበቂ ሁኔታ ለማንበብ ጊዜ ባይኖርህ እንኳን ሳታስበው ከንባብ ጋር ያለህ ቁርኝት እንዳለ ይሆናል። ለምሳሌ፣ በሣምንት ውስጥ አንድ የሀተታ (ፊቸር) ጽሑፍ ለመስራት የሚያስፈልጉህን ግብአቶች ለመሰብሰብ ብቻ ብዙ ነገሮችን ታነባለህ፤ ታገላብጣለህ። የትርጉም ሥራዎችን ለመሥራት የምታነባቸው ጽሑፎች ዞሮ ዞሮ ውስጥሀ እየቀሩ ይሄዳሉ። አውራምባ ታይምስ ውስጥ የሳምንቱ ሥራችንን ጨርሰን ቅዳሜ እና እሁድ የሚኖረን የእረፍት ጊዜ በራሳችን እና በሌሎች ጋዜጦች ላይ የተዘገቡ ጽሑፎችን ከማንበብ ባሻገር የሚተርፈንን ጊዜ መጽሐፍ በማንበብ እናውለዋለን። የጋዜጣ ሥራ በበቂ ሁኔታ ለማንበብ አዳጋች መሆኑ ጥርጥር የለውም። ከተሰደድኩ በኋላ ያለኝን ጊዜ ግን ከዚህ ቀደም ከነበረው እጅግ በተሻለ ሁኔታ (የመጽሐፍ አማራጭ እዚህ ያለገደብ ስለሚገኝ) ለንባብ እየሰጠሁ ነው። እንደዛም ሆኖ ግን ‹‹አንባቢ ነኝ›› ብዬ በድፍረት ለመናገር ይከብደኛል።
ቃሊቲ እያለህ የነበረው የንባብ ል ምድ ምን ይመስል ነበር?
አሳሪዎችህ እስርቤት ሲያስገቡህ ዋናው አላማ እንድትጎዳ ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ አሳሪዎችህ የማያስተውሉት አንድ እድል ግን አለህ። እሱም ከሌላው ጊዜ (ባትታሰር ኖሮ ከሚኖርህ ሁኔታ) የበለጠና የተትረፈረፈ ጊዜ ታገኛለህ። አንተ ብልጥ ከሆንክ ግን ሁኔታውን ለራስህ በሚጠቅም መልኩ ተጠቅመህበት የተሻልክ ሰው ሆነህ መወጣት ትችላለህ። ከተለያየ ቤተሰብ ወዳጅና ዘመድ ለእስረኛ የቅንጅት አመራሮችና ጋዜጠኞች የተለያዩ መጽሐፍቶች ይገቡ ነበር። በተለይ ከሌላው እጅግ በተሻለ ሁኔታ ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ጋር ብዙ መጽሐፎች ተከማችተው ነበር። ከማዕከላዊ ወደ ቃሊቲ ስንዘዋወር ዶ/ር ብርሀኑ አንድ ሀሳብ አቀረበ። ‹‹ሁላችንም ጋር ያሉ መጽሐፎች ተሰብስበው በኃላፊነት አንድ ሰው ጋር ይቀመጡ፤ ከዚያ ማንበብ የሚፈልግ ሰው ስሙንና የመጽሐፉን ርዕስ እያስመዘገበ ወስዶ ያንብብ›› የሚል ነበር። በዚህ መልኩ በመቶዎች የሚቆጠሩ በርካታ መጽሐፎች ተሰባሰቡ። በዚህ ፋይል የተከሰስን ሰዎች በየቀኑ የላይብረሪ ሰዓት መድበን ማንበብ ጀመርን። ከመጽሐፎቹ በተጨማሪ ወቅታዊ የሚዲያ ውጤቶችን (ኒውስ ዊክ፣ ዘ-ኢኮኖሚስትና ታይምን የመሳሰሉ) በስፋት የማግኘት እድል ነበረን። ይህ እንግዲህ የእስር ቤቱ ላይብረሪ ከሚያቀርበው የመጽሐፍ አቅርቦት በተጨማሪ ነበር። ይህ ሁኔታ በአንድ ዞን ውስጥ ለነበርነው አምስት ጋዜጠኞች እና 14 የቅንጅት አመራሮች ቀላል አማራጭ አልነበረም።
ስለታሰርክ ትጎዳለህ ብቻ ማለት አይደለም። እስር ከራስህ ጋር ይበልጥ እንድትቀራረብ ያደርግሃል። ውጪ ብትሆን ግን ጊዜህን በመዝናናት ልታጠፋው ትችላለህ። እስር ቤት ለንባብ ይጠቅማል። ቃሊቲ ውብሸትን ለመጠየቅ የሄድን ጊዜ የምንልክለትን መጽሐፍ በሚፈልገው መጠን እንዳይገባለት ማረሚያ ቤቱ የተለያየ ሰበብ እየፈጠረ ሲከለክለው እንደነበር አስታውሳለሁ። ይህ ትልቅ ችግር ነው። ከስቪል መብቶች መታገድ ሲባል አንዳንድ ኃላፊዎች ይህንንም የሚጨምር ይመስላቸዋል መሰለኝ። በተለይ በዚያን ጊዜ ስለ እስክንድር የማስታውሰው ነገር ልንገርህ። ሰዎች ‹‹ምን እናምጣልህ›› ሲሉት ሁሌም ምርጫው የነበረው ‹‹ዘ-ኒውዮርከር›› የተሰኘው ታዋቂው የኒውዮርክ ጋዜጣ ነበር። ሁል ጊዜም የእስክንድር ምርጫ እሱ ነበር። በነገራችን ላይ ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ እኔና የሲፒጄው መሐመድ ኬይታ ለ‹‹ዘ-ኒውዮርከር›› ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሁኔታውን ከገለጽንለት በኋላ በጣም ተደስቶ በቋሚነት ጋዜጦቹ እንዲላኩለት ሁኔታውን አመቻችቷል።
አስገራሚ የማስታወስ ችሎታ እንዳለህ አውቃለሁ። ከረዥም ዓመታት በፊት የተጻፈ ጽሑፍ ረዥም ዐረፍተ ነገርና እና የሥርዓተ ነጥብ ግድፈትን ሁሉ አስታውሰህ በፍጥነት ትገልጻለህ። ይኼ በተፈጥሮ ያገኘኽው ወይስ በልምድ ያዳበርከው? በሌላ በኩል ደግሞ ትችት ሲሰነዘርብህ ስሜታዊነት የታከለበት ፈጣን ምላሽ እንደምትሰጥ ይነገራል። ስሜታዊ ነህ ማለት ይቻላል።
እንግዲህ እንዳንተ ዓይነት አብሮኝ ብዙ ዓመት የሠራ ሰው ስለ እኔ ባህሪ (ስሜታዊ መሆንና አለመሆን) መናገር ይችላል። እንደ ማንኛውም ሰው ጥቃትን አሜን ብዬ አልቀበልም። እንደምታስታውሰው፣ እዚያ እያለ ሁ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የሚጻፉ ጽሑፎች በጣም ስ ሜታዊ እንድንሆን ያደርጉን ነበር። በአዲስ ዘመን፣ ገጽ 3 ላይ እንደዚያ የዘለፉን ሰዎች ነገ በሆነ አጋጣሚ ወደ አሜሪካ ሲመጡም ሁለት አማራጭ ብቻ የሚያቀርቡልን አምባገነኖች እንደሚሆኑ ጥርጥር የለውም። እንዲህ ዓይነቶቹ የራሳቸው መርሕ የሌላቸው፣ ይሉኝታ ቢሶች ለፖለቲካ ትርፍ ሲሉ የሚደፈጥጡት መሠረታዊ የሰው ልጅ ነጻነት ስሜታዊ እንደሚያደርግ አያጠራጥርም። የማስታወስ ችሎታ ላልከው ተፈጥሯዊ ነው፡፡
ስለ ነበረን ቆይታ በጣም አመሰግናለሁ።
እኔም ዕድሉን ስለሰጣችሁኝ አመሰግናለሁ።

Sport: ሞውሪንሆ ፕሪሚየር ሊጉን ሊያመሰቃቅሉት ይችላሉ – (የስፖርት ተንታኞች አስተያየት)

$
0
0

የ2012/13 የውድድር ዘመን መገባደጃ በርካታ ክስተቶችን ያስተናገደ ነበር፡፡ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ከአሰልጣኝነት ጡረታ መውጣታቸውና በዴቪድ ሞዬስ መተካታቸው፡፡ ሮቤርቶ ማንቺኒ ከማንቸስተር ሲቲ የመሰናበቱ እንዲሁም የራፋ ቤኒቴዝ ከቼልሲ የሚለቁበት ቀን መቆረጡ አበይቶቹ ነበሩ፡፡ ክስተቶቹ እንደ ትልቅ ድግስ ነበሩ፡፡
በፕሪሚየር ሊጉ አዳዲስ አሰልጣኞች መጥተዋል፡፡ አዳዲሶቹ አሰልጣኞች በክለቦች ይሳካላቸው ይሆን? ማንንም ያስፈርማሉ? ማንን ያሰናብታሉ? ምን አይነት ውጤት ይገጥማቸዋል? የሚሉት ጥያቄዎች ይከተላሉ፡፡ የውድድር ዘመኑን መጠናቀቅ ተከትሎ መጪው 2013/14 ጥሩ የውድድር ዘመን እንደሚሆን በማሰብ ወደ እረፍት አቀናሁ፡፡ ነገር ግን ፔትር ቼክ በፕራግ ከሚገኝ አካዳሚው የሰጠውን ቃል መጠይቅ አነበብኩ፡፡ ቢዘገይም የሆነ ነገር እንዳስብ አደረገኝ፡፡ በቼልሲ ጆዜ ሞውሪንሆ በመመለሳቸው ምናልባት ሁኔታዎች ወደ ቀድሞ ቦታቸው ሊመለሱ ይችላሉ፡፡
የቼልሲው ግብ ጠባቂ ስለሞውሪንሆ መመለስ የገለፁባቸው ቃላት በ2013/14 ክፍት ፉክክር ይካሄድበታል ብዬ የሰነቅኩት ተስፋ ላይ ውሃ ቸልሶበታል፡፡ ‹‹ሞውሪንሆ አቻ ከመውጣት ይልቅ መሸነፍን የሚመርጥ አሰልጣኝ ነው፡፡ አንዳንዶች ማሸነፍ ካልቻልክ እንዳትሸነፍ ይላሉ፡፡ ሞውሪንሆ ጋር ግን ይህ አይሰራም፡፡ እርሱ የሚያስበው በትክክለኛው መንገድ ስለማሸነፍ ነው፡፡ ትክክለኛ የሚለው በማራኪ አጨዋወት ላይሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜያት መጥፎ ተጫውተህ ማሸነፍ ይኖርብሃል›› የሚለው ቼክ ማብራሪያውን በመቀጠል ‹‹በአካላዊ ጥንካሬ ላይ አመዝነው የሚጫወቱ ቡድኖች ሲገጥሙህ ለመፎካከር መንገድ መፈለግ አለብህ፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ ቡድኖች የተለያየ አጨዋወት ዘይቤ ስለሚከተሉ ማራኪ አጨዋወት ለመተግበር የማይቻል ሊባል ይችላል፡፡ በትክክለኛ አካሄድ ማለት በታክቲኩ ረገድ በመዘጋጀት ተጋጣሚህን ማሸነፍ ነው፡፡ የምትችለውን እና ሲመለከቱት ማራኪ ያልሆነ እግርኳስን ልትጫወት ትችላለህ፡፡ ነገር ግን ዋንጫ ለማንሳት የግድ ማሸነፍ ይጠበቅብሃል፡፡ ትክክለኛው መንገድም ይኸው›› ይላል፡፡
jose-mourinho_1812989c
ይህ የሞውሪንሆ አካሄድ ነው፡፡ ፕሪሚየር ሊጉን ሊያመሰቃቅሉት ይችላሉ፡፡ በቼልሲ ሌላ አሰልጣኝ አስቀምጣችሁ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን እስከ አምስተኛ የጨረሱ ቡድኖች ለዋንጫ ፉክክሩ ውስጥ እንደሚኖሩ መገመት ቀላል ነው፡፡ ቀደም ብዬ ፉክክሩ ክፍት ይሆናል ያልኩት በሊጉ እስከ አምስተኛ ባጠናቀቁት ቡድኖች መካከል ያለው ልዩነት ሰፊ አለመሆኑን ተከትሎ ነው፡፡ ባለፉት አምስት የውድድር ዘመናት በአንደኛውና አምስተኛ ሆኖ በጨረሰው ቡድን መካከል አማካይ የነጥብ ልዩነቱ 21 ነው፡፡
የሞውሪንሆ ሹመት ሲረጋገጥ የውይይቱ አብዛኛው ርዕስ በሰውየው ባህሪይ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ ምክንያቱም ጆዜ በ2004 ወደ እንግሊዝ ሲመጡ በስኬታቸው ተቀባይነታቸው አግኝቶ ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን የሞውሪንሆ ተቀባይነት ወርዷል፡፡ አሁን ልንጠብቅ የምንችለው ጠብ ፈላጊነታችንን ነው፡፡ የቼልሲ ደጋፊዎች ፖርቹጋላዊው እንዲመለሱ በጥብቅ ይፈልጉ ነበር፡፡ ሌሎች ግን በሰውዬው መመለስ እርግጠኛ አይደሉም፡፡
ስለሞውሪንሆ የምናስበው ለጥቃቅን ነገሮች ትልቅ ትኩረት የሚሰጡና ቡድናቸውን በጥንቃቄ የሚገነቡ አሰልጣኝ አድርገን ነው፡፡ ‹‹ሞውሪንሆ በዝግጅት ወቅት ለጥቃቅን ነገሮች ሰፊ ትኩረት ይሰጣል፡፡ ከአንተ ብዙ ነገር ይጠበቃል፡፡ በስሩ ያሉት የበለጠ ለመስራት እንዲነሳሱ ያደርጋል›› ሲል ቼክ የሞውሪንሆን አካሄድ ያብራራል፡፡ ጆዜ ስህተት ፈላጊ መሆናቸው ወደ ቼልሲ ለመመለስ ትክክለኛው ጊዜ ስለመሆኑ እጠራጠራለሁ፡፡
በፕሪሚየር ሊጉ ትልቅ ለውጥ አለ፡፡ በተለይ ባለፉት አንድና ሁለት የውድድር ዘመናት የቡድኖች መከላከል በአንፃራዊነት መዳከሙ ሊጉን እንድደሰትበት አድርጎኛል፡፡ ማንቸስተር ዩናይትድ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን 43 ጎሎች ተቆጥረውበታል፡፡ ከአምስት የውድድር ዘመናት በፊት ግን ዩናይትድ ያስተናገደው 22 ጎሎች ብቻ ነበር፡፡ ሬዲንግና ሳውዛምፕተን በ2012/13 በስታምፎርድ ብሪጅ እያንዳንዳቸው ሁለት ጎሎች አግብተዋል፡፡ ሞውሪንሆ የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫቸውን ሲያነሱ በሜዳቸው የተቆጠሩባቸው ጎሎች ስድስት ብቻ ነበሩ፡፡ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን አርሰናል በሁለት ግጥሚያዎች ቶተንሃምን 5-2 ማሸነፍ ችሏል፡፡ ሞውሪንሆ ዳግም ወደ እንግሊዝ በመምጣታቸው ይህ የጎል ናዳ ማብቂያ ሊያገኝ ይችላል፡፡
ሞውሪንሆ ሁልጊዜ ጠንካራ ቡድን ከመስራታቸው ባሻገር ለማሸነፍ ያላቸው ተነሳሽነት ሌሎች ፍላጎታቸውን እንዲያልፉ ያደርጋቸዋል፡፡ በ2004 ሴፕቴምበር ላይ ጆዜ የቶተንሃሙን ጥብቅ መከላከል ቢተቹም በ2007 በኤፍኤካፑ ፍፃሜ ጨዋታ በሙሉ መከላከል ካሸነፉ በኋላ ከጨዋታው ይልቅ በድሉ መደሰት የበለጠ ይሻላል የሚል አስተየየት ሰጥተው ነበር፡፡ የሞውሪንሆ የማሸነፍ ድርሻ የላቀ ነው፡፡ በማድሪድ 72%፣ በኢንተር ሚላን 62%፣ በቼልሲ 67% እንዲሁም በፖርቶ 73% ነበር፡፡ ተፎካካሪዎቻቸው በራሳቸው መንገድ እየተጓዙ ባሉበት ወቅት ያልተጠበቀውን በመከወኑ በኩል ግን ሞውሪንሆ አስገራሚ ናቸው፡፡

(በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ላይ ታትሞ የወጣ)


Health: በወሲብ ወቅት ብልቴን ያቃጥለኛል፣ ያመኛል፣ ይቆስላል፣ ይላላጣል

$
0
0

እድሜዬ 25 ሲሆን የወንድ ጓደኛ አለኝ፡፡ ለአንድ ዓመት ያህል ጥሩ የወሲብ ግንኙነት ነበረን፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላ አዲስ ነገር ተፈጠረ፡፡ በመጀመሪያ በግንኙነት ጊዜ ከእኔ ብልት የሚወጣው ፈሳሽ አይወጣም ነበር፡፡ ይህን ተመርምሬ መድሃኒቱን ተከታትዬ ለተወሰነ ጊዜ ተሻለኝ፡፡ ቀጥሎ የጓደኛዬ ብልት ብልቴ ውስጥ ሲገባ ያቃጥለኛል፣ ያመኛል፣ ይቆስላል፣ ይላላጣል፣… ለአንድ ዓመት እንደዛ ሆነብኝ፡፡ ከዛ ተመርምሬ ዶክተሩ (ሐኪሙ) ይህን ችግር ሊያስከትልብሽ የቻለው ማህፀንሽ ውስጥ ዕጢ ስላለ ነው አለኝ፡፡ ይህን እጢ ሳታስወጭ መፀነስ የለብሽም፡፡ ዕጢውን ካስወጣሽ በኋላም ለመፀነስ ሐኪምን ማማከር አለብሽ ተባልኩኝ፡፡ የኔ ጥያቄ ታዲያ፡-
1. ማህፀን ውስጥ ዕጢ ሊፈጠር የሚችለው እንዴት ነው?
2. በግንኙነት ጊዜ የሚቆስለው የሚላጠው ዕጢው ሲወጣ ይተውሻል ብላችሁ ታምናላችሁ?
3. ከቀዶ ጥገና በኋላ እንደፈለጉ ግንኙነት ማድረግ እና ያለስቃይ ልጅ መውለድ ይቻላል? ይህን ሁሉ የምላችሁ ፍቅረኛዬን ማጣት ስለማልፈልግ ነው፡፡ የማይሆን ከሆነ እወደዋለሁ ግን ምን ላድርግ? መልሳችሁን እጠብቃለሁ፡፡ S.K

ask your doctorየዶ/ር ዓብይ ዓይናለም ምላሽ፡ ውድ S.K ሰላምታሽ ደርሶናል እናመሰግናለን፡፡ የእኛም ሰላምታ ከመልካም ምኞታችን ጋር ይድረስሽ እያልን ዛሬ ያንቺን ደብዳቤ ለመመለስና አንዳንድ መረጃዎችን ላንቺ እንዲሁም ለሌሎች ለማድረስ ወደድን፡፡
በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ሆነም ከግንኙነት በፊት ወይም በኋላ በብልትና አካባቢው የሚሰማ ህመም በህክምናው Dys-pareunia በመባል ይታወቃል፡፡ የዚህ ህመም ስሜት ከመጀመሪያው የግብረ ስጋ ግንኙነት ጀምሮ የሚሰማ ወይም የግብረ ስጋ ግንኙነት ከመጀመሩ ከብዙ ጊዜያቶች ያለ ህመም ከቆየ በኋላ የሚመጣ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ የህመም ስሜት በማንኛውም ጊዜና ከተለያዩ ሰዎች ጋር በሚደረግ የግብረ ስጋ ግንኙነት ሲመጣ ወይም አልፎ አልፎ ሊከሰት የሚችል የበሽታ አይነት ነው፡፡
ምክንያቱም ከብልትና አካባቢው (ከማህፀን ጭምር) በሚኖሩ ችግሮች እና ከስነ ልቦና ችግር ጋርም የመያያዝ ባህሪ ሊኖረው ይችላል፡፡
ለዚህ ችግር ተጠያቂ ምክንያቶች ተደርገው የሚነሱ ጉዳዮች፡-
- የሴት ልጅ ግርዛት፣
- የማህፀን በሽታ (ኢንፌክሽን)
- ያረጡ ሴቶች
- የጭንቀት በሽታ
- የድብርት በሽታ፣ እና
- በልጅነት ዕድሜ የተከሰተ የፆታ ጥቃት ወይም አስገድዶ መደፈርን የመሳሰሉ ናቸው፡፡
የዚህን በሽታ ምክንያቶች ዘርዘር አድርገን ስንመለከት ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በታች በሆኑ ሴቶች ላይ Vestibulsodyria የተባለው የበሽታ አይነት ሲሆን ከ50 ዓመት በላይ በሆኑት ላይ ደግሞ የብልት መሳሳት (Vulvavaginal atrophy) ይህንን የህመም ስሜት በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ያስከትላሉ፡፡
ተራ በተራ የዚህን በሽታ ምክንያቶች እስከ ህክምናቸው ስናይ፡-
1. Vaginismus:- የዚህ ችግር መንስኤ አንዲት ሴት የብልቷና አካባቢ ጡንቻ ሳታስበው በሚፈጠርባት መኮማተር የሚያስከትለው ነው፡፡ ለዚህ ችግርም የስነ ልቦና ችግር እንደ ምክንያት ይቆጠራል፡፡ ስለዚህ የዚህች ሴት የብልት አካባቢ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት በሚነካበት ወይም የወንዱ ብልት ወደ ብልቷ ሊገባ ሲል የብልቷ ጡንቻዎች ይኮማተራል ወይም ይወጣጠራል፡፡ በዚህም የህመም ስሜት ይፈጠራል፡፡ የብልቷ ይወጣጠራል፡፡ በዚህም የህመም ስሜት ይፈጠራል፡፡ የብልቷ አካባቢም ሳይነካ ይህ ችግር ሊታይ ይችላል፡፡ ህክምናውን በተመለከተ ቀስ በቀስ የብልትና አካባቢውን ጡንቻዎች አዕምሮን በማዘዝ ለማላላት በመሞከር የሚደረግ የህክምና አይነት ነው፡፡ በዚህም የብልትን ጡንቻዎች ወይም በብልት አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎች ቀስ በቀስ በአዕምሮ እንዲታዘዙ ማድረግ ስለሚቻል በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የህመም ስሜትን መቆጣጠር ይቻላል፡፡
ሌሎች ህክምናዎች ደግሞ Sex therapy የሚባለው የህክምና አይነት ሲሆን ህመሙን ለማለዘብ ጓደኛሞች ቀስ በቀስ ግብረስጋ ግንኙነቱን እንዲያላምዳት ማድረግ ነው፡፡ በዚህም ጊዜ የጓደኛዋ ብልት ቀስ እያለ ወደ ብልቷ እንዲገባ በመርዳት በሂደት የሚከናወን ድርጊት ሲሆን ወንዱም ያለመ ሰላቸት የሚያከናውነው መሆን ያለበት የህክምና አይነት ነው፡፡
በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የሚወሰድ የጡንቻን መላላት የሚያመጣውን መድሃኒት መጠቀም ሌላው አማራጭ ነው፡፡ ይህንንም ከሐኪም ጋር በመወያየት መጠቀም ይቻላል፡፡
2. Vulvar vestibulodynia:- ይህም ችግር ልክ እንደ ከላይ እንዳለው አይነት በሽታ ሲሆን ምክንያቱ ግን ተደጋጋሚ የብልት ኢንፌክሽን ወይም አደጋ የሚያስከትለው የበሽታ አይነት ነው፡፡ ህመሙ የሚመጣው የብልት አካባቢ ሲነካ ብቻ ነው፡፡ የላይኛው ግን ሳይነካም ሊመጣ ይችላል፡፡
ህክምናውም የግብረስጋ ከመፈፀም በፊት (ከ10 ደቂቃ በፊት) እና ከፈፀሙም በኋላ የሚቀባ ቅባት በመጠቀም ከህመሙ መላቀቅ ይችላል፡፡ የዚህ ቅባት ስም ዛሎኬን ይባላል፡፡ ወይም ከዚህ ላቅ ያሉ የመድሃኒት አማራጮችን በመርፌ የሚሰጥ መድሃኒት በባለሙያ እርዳታ በብልት አካባቢ በመወጋት ህመሙን መቀነስ ይቻላል፡፡ ይህም በመጀመሪያው ቀን፣ ከሳምንት በኋላ እንደገና ከ15 ቀን በኋላ የሚሰጡ ናቸው፡፡ ሌሎችም መድሃኒቶች ስለሚኖሩ በዚህ አይነት በሽታ የተጠቁ ሴቶች የማህፀን ሐኪምን እርዳታ መጠየቅ አለባቸው፡፡
ተጨማሪ ምክሮች፡-
- የብልትን አካባቢ ንፅህና መጠበቅ፣
- ላላ ያለና አለርጂ የማይፈጥር ፓንትና ልብስ ማድረግ፣ ከጥጥ የተሰራ ቢሆን ይመረጣል፡፡
- ሽታ፣ ቀለማቸው የሚለቅ፣ ኬሚካል ያላቸውን ልብሶች አለመልበስ፣
- የብልትን አካባቢ ሊጎዱ የሚችሉ እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ ብስክሌት መንዳት ማቆም፣
- የብልት ፈሳሽ የሚያስቸግራቸው ሴቶች ፓድ ከማድረግ የውስጥ ሱሪያቸውን ቶሎ ቶሎ መቀየር ይጠበቅባቸዋል፣
- የብልት አካቢን ሞቅ ባለ ውሃ መዘፍዘፍና በተለይም የብልት አካባቢ ድርቀት የሚታይባቸው ከሆነ፣
- የግብረ ስጋ ግንኙነት በሚደረግበት ጊዜ የአትክልት ዘይት መቀባትም ድርቀቱን ሊያስወግድ ይችላል፣
- የተሰባበረ በረዶ በላስቲክ በማድረግ ብልት ላይ ማድረግ ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ የሚከሰተውን የብልት ማቃጠል ሊያስወግድ ይችላል፡፡
- Oxolate የተባለውን ቅመም የያዙ ምግቦችን ለምሳሌ ፍራፍሬዎች አትክልቶችንና ጥራጥሬዎችን ከምግቦቻቸው ላይ መቀነስ፡፡
1. Vulvovaginal atrophy (የብልት መሳሳት)
ይህ ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት ወይም ባረጡ ሴቶች ላይ ይታያል፡፡ ምክንያቱም ኤስትሮጅን የተባለው ሆርሞን እጥረት ሲሆን፣ በዚህ እጥረት የብልት አካባቢ ቅባት ይቀንሳል፡፡ ስለሆነም የብልት አካባቢ መድረቅ ይከሰታል፡፡ በዚህም የተነሳ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ህመም ይሰማል፣ የብልት አካባቢ ያቃጥላል፣ የብልት መቁሰልና ከግንኙነትም በኋላ መድማት ይታያል፡፡ የኤስትሮጅን ቅባት በቀን አንድ ጊዜ ለአራት ሳምንታት መቀባት ያስፈልጋል፡፡
2. በቂ የብልት ቅባት አለመኖር
በቁጥር 3 እንዳየነው ሆኖ አንዳንድ ጊዜ ከ50 ዓመት በታች በሆኑ ሴቶች ላይ የሚታይና በቂ የስሜት አለመነሳሳት፣ ከጓደኛ ጋር በተለያየ ምክንያት አለመጣጣም ወይም ያልተፈታ የስነ ልቦና ችግር ሲኖር የአንዳንድ መድሃኒቶች የጎንዮሽ ችግሮች (የደም ግፊት፣ የድብት በሽታ መድሃት እና ሌሎችም) ይህንን ችግር ያስከትላሉ፡፡
መፍትሄዎቹ በመጀመሪያ ደረጃ ያሉትንና አጋላጭ ችግሮችን ማስወገድ ከግብረ ስጋ ግንኙነት በፊት የሚደረግ የፍቅር ጨዋታ ያስፈልጋል፡፡
3. የፊኛና የኩላሊት ኢንፌክሽን ሲኖር፡- በባለሙያ እርዳታ በመታገዝ ህክምና ማድረግ
4. የብልት ኢንፌክሽን ሲኖር፡- የብልት ፈንገስ በሽታ ወይም ሌላ የብልት በሽታ መኖር፣ የብልትና አካባቢው ፈሳሽ መኖር፣ መቁሰል፣ ማቃጠል፣ ማሳከክ ሌሎችም ምልክቶች ይኖራሉ፡፡ ህክምና ሳይደረግ የሚፈፀም ግንኙነት ህመም ያስከትላል፡፡ በባለሙያ እርዳታ ህክምና ማድረግ ለበሽታውም ለህመሙም መፍትሄ ያስገኛል፡፡
5. በወሊድ ጊዜ የሚደረግ የብልት መቆረጥ ወይም መለጠጥ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ህመም ሊያመጣ ይችላል፡፡ ይህም ችግር በቀዶ ጥገና መስተካከል አለበት፡፡
6. የማህፀን ዕጢ፡- የማህፀን ዕጢ ያላቸው ሴቶች ከሌላቸው ሴቶች ጋር ሲነፃፀሩ በግንኙነት ወቅት የህመም ስሜት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ በተለይ ትልቅ የሆነና በማህፀን ጀርባ አካባቢ የወጣ ዕጢ ከሆነ የማህፀን ዕጢውን ማውጣት ከዚህ ችግር ያድናል፡፡
7. የስነ ልቦና ችግር ያላቸው ሴቶች በዚህ ህመም ሊጠቁ ይችላሉ፡፡ በተለይ የተቃራኒ ፆታ ጥቃት ከደረሰባቸው፣ በቂ እውቀት (ስለ ግንኙነት) የሌላቸው ከሆኑ አብዛኛውን ጊዜ ስለ ግብረ ስጋ ግንኙነት የተሳሳተ ግምት ካላቸው ለዚህ ሰዎችም የስነ ልቦና ህክምና፣ የግብረ ስጋ ግንኙነት ምን እንደሆነ የሚ ሰጥ ትምህርት፣ የፆታ ትምህርት፣ እና ሌሎችም ያስፈልጋቸዋል፡፡
ውድ ጠያቂያችን የማህፀን ዕጢ የሚፈጠርበት በውል የታወቀ ምክንያት ባይኖርም ከቤተሰብ በዘር የሚወረስና በአንዳንድ ምክንያቶች ጤነኛ የነበሩት የማህፀን ሴሎች ወደ ዕጢ ይለወጣሉ፡፡ እነዚህ ዕጢዎች የተለያዩ ምልክቶች ሊያሳዩን ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ለረጅም ጊዜ ወይም ብዙ የወር አበባ መፍሰስ፣ ወደ ታች የሚጫን ስሜት ወይም የህመም ስሜት መኖር፣ ከእርግዝና ጋር የሚከሰቱ ችግሮች ለምሳሌ በመጀመሪያው 3 ወራት ውስጥ የደም መፍሰስ መኖር፣ የእንግዴ ልጁ ከማህፀን ግድግዳ መለየትና እርግዝናው ላይ ችግር ማስከተል፣ በምጥ ጊዜም ምጡ ከጠናና የሚያስቸግር መሆንን ያመጣል፡፡ እነዚህ በእርግዝና ጊዜ የሚመጡ ችግሮች እንደ ማህፀን ዕጢው ትልቅነትና ያለበት ቦታ ይወሰናል፡፡ በተለይ የእንግዴ ልጁ በዕጢው ላይ ካለ ችግሩ ይከፋል፡፡
የማስወረድና ልጅ የመውለድ ችግር በማህፀን ዕጢ ምክንያት ሊመጣ የሚችለው ዕጢው የማህፀንን የውስጥ ክፍል አቀማመጥ ሲያዛባው ነው፡፡ ስለዚህ ዕጢውን ማስወገድ (በቀዶ ጥገና) ከላይ የጠቀስናቸውንና ሌሎችንም ችግሮች እንዳይኖሩ ያደርጋል፡፡
ውድ ጠያቂያችን፡- በአጠቃላይ በግንኙነት ወቅት የሚደርስብሽ ችግር የሚመጣው በዚህ በማህፀን ዕጢ ብቻ ላይሆን ስለሚችል ተጨማሪ የባለሙያ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የቀዶ ጥገና ከተደረገ ያለ ስጋት ግንኙነት ማድረግ ይቻላል፡፡ ልጅ መውለድም እንደዚሁ፡፡ S

ኢህአዴግ አንድነት ፓርቲን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ ሲል አንድነት ፓርቲ አስታወቀ

$
0
0

eprdfበደቡብ ወሎ ዞን በሚገኘው ኩታበር ወረዳ አንድነት ፓርቲ ሐምሌ 7 ቀን 2005ዓ.ም. በደሴ ያካሄደውን ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በመቃወም ህዝቡ ሰላማዊ እንዲወጣ ኢህአዴግ እያስገደደ መሆኑን ምንጮቻችን በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡

የኩታበር ወረዳ ነዋሪ ሰልፍ እንዲወጣ የተደረገው ነገ ረቡዕ ሐምሌ 17 ቀን 2005 ዓ.ም. ጠዋት መሆኑም ታውቋል፡፡ በተለይ ሰፊ የማስፈረሳሪያና የቅስቀሳ ስራ እየተካሄደ ያለው በወረዳው ቀበሌ 05፣06 እና 07 መሆኑንም ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢህአዴግ ካድሬዎች ገበሬውን በግድ ከአቅሙ በላይ የዘር ማዳበሪያ ውሰዱ እያሉ ከፍተኛ ገንዘብ ከማስከፈላቸው በተጨማሪ ለአልማ(ለአማራ ልማት ማኀበር)፣ለአባይ፣ ለመሬት ግብር እየተባሉ ከፍተኛ ዋጋ በመጠየቃቸው እና ነዋሪዎቹ አቅማቸው እንደማይፈቅድ ሲናገሩ ወደ እስር ቤት እየተወሰዱ በመሆኑ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ከአካባቢው እየተሰደዱ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡ ማዳበሪያና ዘር አንወስድም ያሉ ገበሬዎችንም መሬታችሁ ይነጠቃል በሚል የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ደምሴን ጨምሮ የወረዳው ሹማምንት እያስገደዱ እንደሆነ ነዋሪዎቹ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡

ስለጉዳዩ የዝግጅቱ ክፍሉ የወረዳውን አስተዳደር አቶ ደምሴን እና የወረዳውን ግብርና ጽህፈት ቤትና የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችን ለማናገር ጥረት ቢደረግም አልተሳካም፡፡

#milloinsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ

 

ዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ እና ዶ/ር በያን ሱባ -በገበየሁ ባልቻ

$
0
0

በገበየሁ ባልቻ

Fikire-tolosa-OLF-and-Ethiopiaባለፈዉ ጊዜ ሁለቱ ልሁቃን ዶፍቶሮች በፈረንጂ እዉቀታቸዉ የተመሰከረላቸዉ ምሁራን (በኢትዮሚዲያ) የተመላለሱትን በመመልከት የበኩሌን በጉዳዩ ዙሪያ ሀሳብ ልሰጥ አስቤ የአባይ ጉዳይ በረድ ይበል በማለት በጋዉን ስጠብቅ ባጀሁ።

ዶ/ር ፍቅሬ ዶ/ር በያን የሚመሩት ድርጅት ኢትዮጵያዊ ይዘት ያለዉ መስሎ ስለታያቸዉ መሰለኝ ዘመን ተሻግረዉ ማህደር ፈልፍለዉ ልዩ ጥናት አካሂደዉ በዘመኑ ያለነዉን ሁሉ የሚያስደምም የምርምር ድርሳን አቀረቡ። በጥናቱ መሰረት ኦሮሞ እና አማራ የአንድ ቤተሰብ ልጆች ከመሆናቸዉም በላይ በየጊዜዉ የኦሮሞ ተወላጆችንን አንገት የሚያስደፋዉን አሉባልታ ወደጎን በመተዉ በማንኛዉም የኢትዮጵያ አስተዳደር ኦሮሞ ያልተሳተፈበት ወይም ደግሞ ኦሮሞ ያልገዛበት ዘመን እንደሌለ በርቀት ተጉዘዉ መረጃ አስደግፈዉ ገለጹልን ። በዚሁ መልእክታቸዉ  ለዶ/ር በያን እንዲህ ያለ የምርምር ሰነድ ካሻችሁ ከጎናችሁ ነኝ ሌሎች ኢትዮጵያዉያንም በኢትዮጵያ ምድር ለሚደርሰዉ ማንኛዉም በደል ዘር፤ ወገን፤ ጎሳ፤ሀይማኖት ሳንለይ አብረን እንታገላለን በማለት ቃላቸዉን ሰጡ። ነገር ግን ማንኛዉም እንቅስቃሴ፤ሀሳብ፤መመሪያ አሉባልታ ላይ ያተኮረ ወይም ደግሞ ፈረንጂን እና የኢትዮጵያ ጠላቶችን የሚያስደስት ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ይዘት ያለዉ የእኛዉ መሆን አለበት በሚል አገላለጽ አድናቆታቸዉን፤ ምስጋናቸዉን፤ ምክራቸዉንና ትብብራቸዉን ለ/ዶር በያን እና ይመሩታል ለተባለዉ ድርጅታቸዉ አበሰሩ እኛም በእጅጉ ደስ አለን።

ዶ/ር በያን ለዚህ ሀገራዊ ጥያቄ መልሳቸዉ ሲጠበቅ ብዙም ሳይቆይ ከመቅጽበት ብቅ አለ። በእዉነቱ የዶ/ር በያን መልስ በእጅጉ ይጠበቅ ነበርና ስማቸዉንና ምስላቸዉን ስንመለከት ልባችን ቀለጠ በስንት መከራ ከፈረንጅኛ ወደ አማርኛ ገልብጠን ስንረዳዉ በተቻለ መጠን ልዉዉጡን እኩል በማድረግ  የዶ/ር በያን መልስ ስምን ሆነ ብሎ በመለወጥ እና ስምን አሳስቶ በመጻፍ ላይ የተነጣጠረ ዉንጀላ እና ክስ ሁኖ ቀረበ (ሼክስፒር ፈይሳ እንዴት ያዩት ይሆን ይህን ነገር?)። በዉነቱ ዶ/ር ፍቅሬ ያን ያህል የተጉዋዙ እና ታሪክን ያብላሉ በፈረንጂ እርሶ የተባሉ ምሁር ይህ ጠፍቷቸዉ አልመሰለኝም። ስምን በተመለከተ ራሺያኖች ኢትዮጵያን ኢፊዮፒያ፣ ጃፓንን  ያፖኒያ…….ሲሉ የኛ የጥንቶቹም ለንደንን  ሎንዶን፤ግብጽ ምስር፤አዉስትሪያ ነምሳ…….ጣሊያኖች ኢትዮጵያን  አቢሲኒያ እንግሊዝን ኢንግልቴሪያ…….እያለ ይቀጥላል። ሌሎቻችሁም በስደት በያላችሁበት እንዲሁ እናንተ ከምታዉቁት አጠራር ዉጭ የአገሬዉ ሰዉ የሚጠራበትን  አጠራር ሳትስሙ የቀራችሁ አልመሰለኝም። እዚህ ላይ አሁን የምንሰማዉ ቋንቋ ዶ/ር በያን እንደሚፈልጉት ወደፊት አሁን ባለበት ሁኔታ ሊቀጥል አይችልም። ቁዋንቁዋ በንግድ፤በትምህርት፤በሀይል፤ከዉስጥና ከዉጭ ባለዉ ግፊት፤በስልጣኔ፤በወረራ አጠራሩ እና አጠቃቀሙ ይለዋወጣል፤ይዳቀላል፤ ካልጠቀመም ይጠፋል ለምሳሌ መኪናን የሚተካ ቴክኖሎጅ ተፈልስፎ መኪና ከጠፋ ያንን ጽንሰ ሀሳብ የሚተካዉ መኪና ከጊዜ ብዛት መጥፋቱ ግድ ይላል።

በዚህ መልኩ የምስራቅ ፍልስፍና አራማጆች፤ ብሄረተኞች፤ ነገድን ለመቀስቀሻነት ለመጠቀም ሲሉ ቋንቋን  ከዳቦ በላይ አቅርበዉታል። እዚህ ላይ በእርግጠኛነት ለመናገር የ/ዶር በያን ልጆችም (ካላቸዉ)  ኦሮምኛዉን ከእንግሊዝኛ በላይ ያዉቁታል ማለት ይከብደኛል ለዛዉም ኦሮምኛዉን ካወቁት። በዚህ በዘመናችን እንኳን ፔሪስትሮይካ የሩሲያኖች ቁዋንቁዋ ወደ እንግሊዝኛዉ ተጠቃልሏል። በጀት፤ካልሲ፤እስክሪፕቶ፤አስቢዳሌ እንደዉ ሌላም ሌላም።ይህ ሁሉ ቅይጠት እና አጠቃቀም የመጣዉ የቁዋንቁዉን ባለቤት ለማስቀየም ሳይሆን ቋንቋ የተናጋሪዉ እንጂ የማንም ባለመሆኑ ነዉ። ወደ ምእራብ ኢትዮጵያ ብዙ የአማራዉ ብሄረሰብ አባሎች ዛሬ ጆሯቸዉን ቢቆርጧቸዉ አማርኛን አይሰሙም በሌላ አካባቢ የተወለዱ ኦሮሞዎችም በአንጻሩ እነዲሁ ከትዉልድ ቋንቋቸዉ በላይ የመጠቀሚያ ቋንቋቸዉን አጥብቀዉ ይዘዋል።

ቁዋንቋ ሀሳብን የመግለጫ ልሳን እንጂ ምንም ማለትም አይደለም። ለምሳሌ የአዉሮፓ ማህበረሰብ አባሎች ቁዋንቋቸዉ እንግሊዝኛ እንዲሆን ወስነዋል። ማንኛችንም እንደምናዉቀዉ እንግሊዝ የአዉሮፓ ማህበረሰብ አገር ወዷትም አይደለም ኢኮኖሚዋም ቢሆን ከሌሎች የበለጠ ስለሆነም አይደለም እንግሊዝ የአዉሮፓ ሀገሮችንም ወርራ ቋንቋቸዉንም እንግሊዝኛ እንዲሆን አስገድዳም አይደለም ነገር ግን በተለያዩ መስፍረቶች እንግሊዝኛ ለማህበረሰቡ ከሌሎች ቁዋንቁዎች በላይ አገልግሎት ይሰጣል በሚል ግምት እንጂ። የህዋት አስተዳደር አማርኛ እና አማራ ላይ ካለዉ ጭፍን ጥላቻ የተነሳ አማርኛን ከስሩ መንግሎ ለመጣል ያላደረገዉ ጥረት አልነበረም ሆኖም ተጠቃሚዉ የሚጠቅመዉን በማወቁ እነሱኑ ጨምሮ አማርኛ አማርኛ እንደሆነ ቆይቷል። አቶ መለስ ወደ ሁዋላ ላይ የአማርኛቸዉ አጠቃቀም ከዋሸራ የተመረቁ አስመስሏቸዉ ነበር ብቻ ለመልካም ስራ ስላልተጠቀሙበት የቋንቋዉ ባለቤት ጠራቸዉ።እዚህ ላይ ከመሰረቴ ሳልወጣ ታላቁ ሎሞኖሶቭ የሩሲያን የቁዋንቁዋ ህግጋት ሲያወጣ የኢትዮጵያን የቋንቋ ህጎች (አማርኛን) ተጠቅሟል ይላሉ ሩሲያኖች በመጻፋቸዉ እንግዲህ ምን ልንሆን? ሩሲያኖች ተዋረዱ ማለት ነዉ? አይ የኛ ፍልስፍና።

ብቻ በማይረባዉ ስትነጫጩ ኑሩ ስላለን በማይረባዉ ስንክሳር ሁሉ ስንባላ እንኖራለን። ህዋትም መርዙን እኛ ዉስጥ እየረጨ መኸሩን ይሰበስባል ፈረንጅም፤አረብም እንዲሁ።  በአጠቃላይ ዶ/ር በያን ዶ/ር ፍቅሬ በዝርዝር የጠቀሱትን መልካም ነገር በመዝለል  ለምን በሱባ እና ጅክሳ ላይ አይናቸዉ እንዳረፈ ከሳቸዉ በስተቀር ማንም ሊያዉቅ አይችልም። አኝህ አንድ ድርጅት እንዲመሩ ስልጣን እና ሃለፊነት የተሰጣቸዉ ሰዉ በዚህ መልሳቸዉ ማንነታቸዉን አመላክተዉናል።

በአዉሮፓም ሆነ አሜሪካ ተፎካካሪ መሪዎች ወደ ስልጣን ሊመጡ ሲሉ ጠያቂዎች እልህ አስጨራሺ፤ የሚያበሳጭ፤ እዉቀትን፤ ድፍረትን፤ አርበኝነትን፤ ማስተዋልን እና መሪነትን የሚለካ ጥያቄ ይጠይቋቸዋል። የዚህ አይነት የከረረ ጥያቄ መሪዉ በዉጥረት ጊዜ የአመራር ችሎታዉን፤ ትእግስቱን፤እዉቀቱን፤ማመዛዘኑን ለመለካት እድል የሚሰጥ አጋጣሚ ነበር። እስቲ እንግዲህ እግዜር የሳያችሁ ዶ/ር በያን እና ዶ/ር ፍቅሬ በአንድ መድረክ ላይ ተገኛኝተዉ ቢሆን ኑሮ ሊደርስ የሚችለዉን በአይነ ህሊና እንገምት ወይም ደግሞ ዶ/ር በያን ትልቅ ጦርና አገር እንዲመሩ እድል ቢሰጣቸዉ  ሊደርስ የሚችለዉን መገመት አስቸጋሪ አይሆንም።

እድል ሆነና እኛ አካባቢ ግን በድርጅትም ሆነ በሀገር አቀፍ ምርጫ መሪዎቻችን በእኛ ተመርጠዉ አያዉቁም እንዲሁ በተንኮል፤ በጭካኔ እና በቡድን ስልጣን ላይ ቁጭ ብለዉ በዉርደት ወይም ይድፋዉ እየተባለ በእርግማን ይወርዳሉ። አቶ መለስ እና ዶ/ር ጳዉሎስን ማለቴ አይደለም የነሱ ከእዚህ በላይ ነዉ።

እንግዲህ ዶ/ር በያንን ልብ እና ትእግስት ይስጥልን እያልን ዶ/ር ፍቅሬን ደግሞ በጎደለን የእዉቀት ክፍተት እንዲሞሉልን እንጠይቃለን የጀመሩትንም የፍቅር ተልእኮ በጀመሩት መንገድ እንዲቀጥሉም አደራ እንላለን ከቂም፤ ከጥላቻ፤ ከመከፋፈል፤ ከተንኮል ምን ይተርፋል?። በዘመናችን ከሻቢያ ብዙ መማር አንችልም ነበር?  ሲንጋፖር ሊሆን የታሰበዉ አገር ዛሬ ፓስታ እና በርበሬ በፖስታ ከአዉሮፓ እና አሜሪካ እየተላከለት አሁን ኑሮ ነዉ ይሄ?። በዉነቱ የህዋት መንግስት አቅፎ ደግፎ ባይዛቸዉ ዛሬ ኤርትራ ዘጠኝ ቦታ አይከፋፈልም ነበር? ለማንኛዉም መቻቻል እና አርቆ ማሰብን ይስጠን። ማነዉ አማራን እና ኦሮሞን ወይም ደግሞ ደቡብን እና ትግሬን ወይም ሱማሌን እና ወላይታን አፋርን የሚለየዉ? ኢትዮጵያዊ ሁሉ በስነልቦናዉም ሆነ መልኩ ጠባዩ ተመሳሳይነት ያለዉ ነዉ ይህም ተፈልጎ ሳይሆን አብሮ በመኖር የፈጠርነዉ ትስስር ነዉ።

ለማንኛዉም በቸር ይግጠመን gebeyhubalcha@yahoo.com ካጠፋሁ በዚህ አናግሩኝ

ገበየሁ ባልቻ

 

ስለ ቂሊጦ ዝም አልልም! ከ ሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት »

$
0
0

ስለ ቂሊጦ ዝም አልልም!
==============
በቂሊጦ እስር ቤት በርካታ ወንድሞቻችን በጸረ ሽብር አዋጁ ተገን በኦነግ ስም ታስረው መከራቸውን እያዩ ነው፡፡ አሁን በቅርቡ የምግብ ማቆም አድማ አድርገው የነበሩት እነዚህ ወንድሞቻችን የርሃብ አድማ ሲያደርጉ የመጣላቸው ሀኪም አይደለም፡፡ ልዩ ሀይል የሆነ ወታደር ነው እንጂ… ልብ በሉልኝ፤ በርሃብ ለደከመ ሰውነት ገራፊ ወታደር!!!

ይሄ አይነቱን ጭካኔ ሰይጣን እንኳን አድርገው ቢባል “አረ ፈጣሪ ምን ይለኛል” ብሎ መፍራቱ አይቀርም፡፡ ፈጣሪን መፍራት የተሳናቸው ሰዎቻችን ግን በድፍረት እንዲህ ጨከኑ…

በብረት ክርችም ካሰሩ በኋላ በርሃብ የደከሙ ሰዎችን መደብደብ ጀግና ያስብል ይሆን…! ወይስ “ጀግንነቱን ቀድመን ተብለናል እስቲ ደግሞ በእርኩሰት ሳጥናኤልን አንብለጠው” ብለው እየተወዳደሩ ነው…! ግራ ገብቷቸው ግራ አጋቡንኮ…

እንደሰማነው ገድል ከሆነ… (መሆኑን ግን አንጃ…) ህውሃት ያኔ ጫካ እያለች የሚታኮሷትን ወታደሮች የያዘቻቸው እንደሆነ እንክብካቤዋ በጦርነት ሳይሆን በፍቅር የማረከች ነበር የምትመስለው ብለው ድርሳን ፀሀፊቿ እና ኢቲቪዋ ነገሮናል፡፡

ታድያ ያኔ ሲታኮሷት የነበሩ ሰዎችን ስትንከባከብ የነበረች ድርጅት ዛሬ ከትምህርት ቤት እና ከሰላማዊ መስሪያ ቤት የሰበሰበቻቸው ሰዎች ላይ እንዲህ መሆኗ … አብዳ ነው ተናዳ….!?

“እስቲ ጠይቁልኝ ይቺን ሰው በሰው…

አያያዟ ሁሉ እንደማሆን ነው… ”

(እስቲ ተቀበል…)

እውነቱን ለመናገር ይሄ መካሪ ማጣት ነው፡፡ በዚህ ርግጫ መሰል ርምጃ፤ በእስር ላይ ያሉትን ፀጥ ማሰኘት ይቻል ይሆናል፡፡ በውጪ ያሉትን ግን ያበረታል፡፡ የበረቱት ሲታሰሩ ደግሞ ሌሎች ይበረታሉ፡፡ እነርሱም ሲታሰሩ ሌሎች ይበረታሉ… ያ ማለት ምን ማለት እንደሆነ… ከተረሳ የህዳሴው ዋዜማ የሚለውን ቪዲዮ ድጋሚ መመልከቱ ሳይበጅ አይቀርም…!

ለማንኛውም በቂሊጦ የሚገኙ ወንድሞቻችን እየደረሰባቸው ላለው ስቃ የህዝ ለህ እያሉ ነው…! እኔ ስለ እነርሱ ዝም አልልም…. ኪቦርድ ያለህ በኪቦርድህ ድምጽ ለህ በድምፅህ አግዘኝ…. ስለ ወንድሞቼ እጮሃለሁ…!

ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ….!!!

https://www.facebook.com/MillionsOfVoicesForFreedomUdj

ቂሊጦ

የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከዩቲዩብ (Youtube) ተባረረ

$
0
0

etv
(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በዩቱዩብ የተለያየ ፕሮፓጋንዳዎቹን የሚያስተላልፍበት የዩቲብ ቻናል ተዘጋ። ዩቲዩብ ኢትዮጵያ ቴሌቭዥንን ማባረሩን የገለጸበት መልዕክት “YouTube account ethiopiantv has been terminated because we received multiple third-party notifications of copyright infringement from claimants including: David Tesema” ይላል።
ከዚህ ቀደም በቴሌቭዥን ጣቢያው የአፍሪካ ዋንጫን ሰርቆ በማስተላለፍ የሃገሪቱን ስም አንገት ያስደፋው የኢትዮጵያ ቲሌቭዥን አሁንም ከዩቲዩብ የተባረረው በተደጋጋሚ በኮፒ ራይት ሲመከርና ማስጠንቀቂያ ሲሰጠው አልሰማ በማለቱና ከድርጊቱም ባለመቆጠቡ እንደሆነ የዩቲብ አሰራር ያመለክታል።
ኢቲቪ ለዘፋኞች 5 ሳንቲም ክፍያ ሳይከፍል ሥራዎቻቸውን በሕብረትርዒት ላይ እንደሚያቀርብ፤ የውጭ ሃገር ፊልሞችንም ምንም ክፍያ ሳይፈጽም በታላቅ ፊልም ላይ እንደሚያሳይ የሚታወቅ ሲሆን ይህን ስርቆቱን በመቀጠል ዩቲዩብ ላይ ገንዘብ ለማካበትና ፕሮፓጋንዳውን ለማስተላለፍ መጠቀሙ እንዲባረር ምክንያት ሆኗል።
የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የዩቲዩብ ቻናል ከፕሮፓጋንዳዎች በተጨማሪ ለአርቲስቶች ክፍያ የማይፈጸምባቸው ድራማዎች፣ ዘፈኖች፣ አስገራሚ ታሪኮችና ሌሎችም ይቀርቡበት ነበር።
ይህን የሰሙ አስተያየት ሰጪዎች”ሕዝብን መስረቅ የለመደ መንግስት በኢንተርኔት እሰርቃለሁ ሲል እጅ ከፍንጅ ተያዘ” ሲሉ ተሳልቀዋል።
ዘ-ሐበሻ በተደጋጋሚ ወደ ኢቲቪ የዩቲዩብ ቻናል በመሄድ እንዳረጋገጠቸው አካውንቱ ሲከፈት YouTube account ethiopiantv has been terminated because we received multiple third-party notifications of copyright infringement from claimants including: David Tesema” ይላል። ይህን ለማረጋገጥም፦
http://www.youtube.com/user/ethiopiantv

 

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live