Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በሚኒሶታ የሚገኘው ሪሳላ ኢንተርናሽናል በሊቢያ በየመን እና በደቡብ አፍሪካ ከወደቁት ኢትዮጵያውያን ጎን እንደሚቆም አስታወቀ

$
0
0

የአቋም መግለጫ

ሪሳላ ኢንተርናሽናል በሚኒሶታ የሚገኝ ማእከል ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥየሃይማኖት መብት ጥሰት በመቃወም በሚኒሶታ ዋና ከተማ ሴንትፖልህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል::
Risala International
ባለፉት ሶስት ፈታኝ አመታት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች እና ክልሎች ህዝባዊ ሰላማዊ ተቃውሞዋቸውን በመግለጽ መንግሥት ከውጪ ያስገባውን አህባሽ የሚባለዉን መጤ ሃይማኖት ህዝቡ በግድ እንዲቀበል ጫና ማድረጉን እንዲያቆሙ ጠይቋል::ተቃውሞውን የቀሰቀሰው መንግስት እና ሃይማኖት እንደሚለያዮ የምናደርገውን የህገ መንግስትን በመጻረር በመዲናይቱ የሚገኘውን ታዋቂየእስልምና ትምህርት ማእከል አወሊያ ኮሌጅን በቁጥጥር ስር ለማዋልየወሰደው እርምጃ ነው። ተቃዋሚዎቹ በመንግስት የተወከሉ የመንግስትአመራሮች ከሃላፊነታቸው ወርደው በምትኩ የኣማኙ ነጻ ፈቃድና ምርጫ የሚወክል አካለ እንዲመራ ቢጠይቅም መንግሥት እነኚህን ጥያቄዎች በቀና መንፈስ ተቀብሎ ማስተናገድ ሲገባው ሙስሊሙ ይህንን ጉዳይ እንዲያስፈጸሙለት የመረጣቸው ተወካዮች በማሰርና ማንኛውም አይነት ተቃውሞ በማፈን ጸረ ሽብርተኝነትን አዋጅ ተንተርሶ በሀገር መክዳት ክስ መስርቶባቸዋል::

ይህ እርምጃ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፉን እንዲቀላቀሉ አድርጓል ለዚህም የመንግስት ምላሽ በዜጎች ላይ የሽብር ማዕበል በመክፈት ከህግ ዉጪ ንጹሃን ዜጎችን ማስፈራራት፣ ማሰር፣መደብደብ እና መግደል የቀን ተቀን ስራው አደረገው፤ ይህም ህገ ወጥ እርምጃ በአለም የዜና አውታሮች ተድጋግሞ ተዘግቧል። ህዮማን ራይትዎች፣
አምኒስቲ ኢንተርናሽናል፣ በአለም አቀፍ የሀይማኖት መብት የአሜርካኮሚሽን፣ የሰብኣዊና የህዝቦች መብት እንዲሁም የአፍርካ ኮሚሽን በህገ ወጥ መንገድ የታሰሩትን አመራሮችን እና ሰላማዊ ተከተዮቻቸውን አሳዛኝ እጣ አስመልክቶ የተለየዮ መግለጫወችን አዉጥቷል።
በአሁኑ ጊዜ እነኚህ ንጹሃን የምእመናኑ የህዝብ ተወካዮች የፈጠራ ክስ ተመስርቶባቸው በህግ ሳይሆን በፖለቲካ ፍላጎት የሚመራ ፍርድ ቤት ብይን እየተጠባበቁ ናቸዉ። ሰልፉን አስመልክቶ በማንኛውም ቦታ የሚደረግ የፍትህ ጥሰት በሁላችንም ላይ የተቃጣ ነው። ስለሆነም ታሳሪዎቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እንጠይቃለን በማለት የሪሳላኢንተርናሽናል ሊቀመንበር አቶ ወዚር ጃዋር ተናገሩ ። በማስከተልም የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ ጣሃ ሰመሩ ድምጻቸውን ለተነፈጉት ድምጽ ለመሆን ያለን የሞራል ግዴታ በኢትዮጵያ ድምጻቸውን ከተቀሙት የህሊና እስረኞች ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር በአጋርነት እንድንቆም ያስገድደናል ። በሰብአዊ መብት ጥሰት እየታወቀች የመጣችው ኢትዮጵያ በጸረ ሽብር ዘመቻ ስም የአሜሪካ የጦር እርዳታ ከሚጎርፍላቸዉ የአፍሪካ ሃገሮች መካከል ዋነኛዋ ናት።

ይሄም እየሆነ ያለው የነጻነት ቤት freedom house ኤፕሪል 17/2015 ወይንም በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሚያዚያ 9/2007 ባወጣው የአቋም መግለጫ የብዙሃን ፖለቲካ እና ኢትዮጵያውያን የመሰብሰብ፤ የመደራጀት ብሎም ሃሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ መብታቸው ከዛሬ አስር አመት በላይ መገደቡን እና ይሄውም የሚያሳየው መንግስት ለመሰረታዊ ህዝባዊ እና የፖለቲካ መብቶች በአደገኛ ሁኔታ ማሻቀቡ ነው ሲል ገልጿል ።

በመሆኑም በሚኒሶታ ክፍለ ግዛት የመንግስት ምክር ቤት ፊት ለፊት የሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በአሜሪካኖች የሚሰበሰበው ግብር ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገውን የመብት ጥሰት እንዳያግዝ የሚጠይቅ ነው።

በማከልም ሰልፈኞቹ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሄደዉ የመብት ረገጣና በስራ እጦት ተገደው ለስደት ለተዳረጉ በየመን፣ በሊቢያ እና በድቡብ አፍርካ ለተገደሉት እንዲሁም ከፍተኛ አደጋ ስር ለወደቁት ወገኖቻችን ያለንን አጋርነት መግለጽ ይሆናል ።

ሪሳላ ኢንተርናሽናል ሚኒሶታ

The post በሚኒሶታ የሚገኘው ሪሳላ ኢንተርናሽናል በሊቢያ በየመን እና በደቡብ አፍሪካ ከወደቁት ኢትዮጵያውያን ጎን እንደሚቆም አስታወቀ appeared first on Zehabesha Amharic.


Sport: ዮሃንስ ሳህሌ የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ሆኖ ተመረጠ

$
0
0

sport
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ኮሚቴ ክፍል ለሶስት ቀናት ከፈጀው ስብሰባ በኃላ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መርጧል። ለብሔራዊ ቡድኑ ምርጫ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ፣ ፋሲል ተካልኝ ፣ፀጋዬ ኪዳነማሪያም በተወዳዳሪነት የቀረቡ ሲሆን በምክትል አሰልጣኝነት ፣ፀጋዬ ኪዳነማሪያም እንደተመረጠ መረጃዎች ያመላክታሉ።

ምንጭ ኢትዮ-ኪክ

The post Sport: ዮሃንስ ሳህሌ የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ሆኖ ተመረጠ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአይሲኤል ሊቢያ ውስጥ ሕይወታቸውን ካጡት ኢትዮጵያውያን መካከል እንዳልክ ሐጎስ አየለ

$
0
0

Endalk
በሊቢያ በአይሲኤል የተገደሉትን ኢትዮጵያውያን ማንነትን የመለየቱ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል:: እስካሁን የ11 ሰዎች ማንነት የታወቀ ሲሆን አሁን ደግሞ የአንዱ ወንድማችን ማንነት ታውቋል:: ናትናኤል መኮንን እንዳስታወቀው የሰሜን ጎንደር ላይ አርማጭሆ ወረዳ ልዬ ስሙ ወርቅ ምድር ቀበሌ ተወላጅ እንደሆነ የሚነገርለት ወንድማችን እንዳልክ ሐጎስ አየለ በትክል ድንጋይ ከተማ የወንዶች ፅጉር ቤት እና ሞተር ማከራየት ስራ ይሰራ እንደነበርና በቅርቡ በስደት ከሃገር የወጣ መሆኑና በሊቢያ በ ISIS በግፍ ከተገደሉት ኢትዩጵያዊያን መካከል አንዱ መሆኑ ተረጋግጦ ቤተሰቦቹ ስለልጃቸዉ አሰቃቂ ሞት ተረድተዋል፡፡

ለቤተሰቦቹ ፤እንዲሁም ለወገናችን ለላይ አርማጭሆ ትክል ድንጋይ ከተማ ህዝብ መጽናናትን እንመኛለን፡፡
እስካሁን ያወቅናቸው፦
1. ኢያሱ ይኵኖአምላክ
2. ባልቻ በለጠ
3. ዳንኤል ሐዱሽ
4. ቡሩክ ካሳሁን
5. ኤልያስ ተጫኔ
6. በቀለ ታጠቅ
7. በቀለ አርሰማ
8. ዳዊት ሐድጉ
9. መንግሥቱ ጋሼ
10. ጀማል ራህማን
11. አወቀ ገመቹ
12. እንዳልክ ሐጎስ አየለ

The post በአይሲኤል ሊቢያ ውስጥ ሕይወታቸውን ካጡት ኢትዮጵያውያን መካከል እንዳልክ ሐጎስ አየለ appeared first on Zehabesha Amharic.

“ልጄ! እንኳን አንተ፤ እኔም ባልተወለድኩ!” –የንጎቻው

$
0
0

yengochaw…. ስሙን ሞት ይጥራውና እንኳን በአንደበቴ በህሊናዬ ሲንከላወስ እጅጉን የሚኰሰኩሰኝ ያ! መናጢ፤አናጢ፤ ግምበኛ፤አትክልተኛ ነኝ’ ባይ ‘መጤ’ ‘የቀን ሠራተኛ’ ለካስ ዋናው ሙያው ‘የጨለማ ሠራተኛ’ ኖሮ ወያኔዎች ኢትዮጵያን ወረው መዲናንችንን ሲቆርጣጠሩ ይኸ ‘እንግዳ ሰው’ ከምንጊዜው እንደ እስስት ተቀያይሮ፤ የቀን ቱታውን አውልቆ፤ዪኒፎርሙን ጠርንቆ፤መትረየሱን ታጥቆ ሰፈራችንን ፊታውራሪ ሆኖ ሲያምሰን፤ ሲያተራምሰን ከረመ። አይ እኛ! ምንኛ ተላላዎች፤ሰው አማኞች፤ የዋሆችም ኖረናል።

ይባስ ብሎ ለሥራ ክብር ባላቸው የተከበሩ ጎረቤቶቻችንና የሰፈራችን አረጋዊያን፤ አባ ምንተስኖትና እማማ ገላኒ በትልቁ ግቢያቸው አስጠግተው እንዳቅሙ መጠነኛ ክፍል አከራይተው ቡናና፤ጠላ አብረው እየጠጡ፤ወሬ እየለጠጡ፤ዓመት ባል፤አውዳ ዓመት እንደ ዘመድ፤እንደ ሃገር ሰው የተገኘውን ሁሉ እኩል ተካፍለው፤ አክብረው ቢያኖሩት ‘ባለቀን’ ሆነና ለውለታቸው ምላሽ ግቢያቸውን በሙሉ ወርሶ እነርሱን ከከተማ ዳርቻ አልባሌ ቦታ ቀበሌ ቤት ጣላቸው። በዘመኑ ሰዎች ቋንቋ አፍ መፍታቱን ሲያስረግጠን ከጆሯችን አልፎ በአናታችን የገደል ማሚቶ እስኪያስተጋባ ያምቧርቅብን ጀመር። —-[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—

The post “ልጄ! እንኳን አንተ፤ እኔም ባልተወለድኩ!” – የንጎቻው appeared first on Zehabesha Amharic.

“ባልቻና ኢያሱ አብረውኝ ያደጉ የሠፈሬ ልጆች ነበሩ…ሕይወታቸው ሊቢያ ውስጥ እንዲህ ባለው ሁኔታ ማለፉ አስለቅሶኛል”–ኮሜዲያን ተመስገን መላኩ (ባትሪ)

$
0
0


“ባልቻና ኢያሱ አብረውኝ ያደጉ የሠፈሬ ልጆች ነበሩ… ሕይወታቸው ሊቢያ ውስጥ እንዲህ ባለው ሁኔታ ማለፉ አስለቅሶኛል” – ኮሜዲያን ተመስገን መላኩ (ባትሪ)
“ባልቻና ኢያሱ አብረውኝ ያደጉ የሠፈሬ ልጆች ነበሩ… ሕይወታቸው ሊቢያ ውስጥ እንዲህ ባለው ሁኔታ ማለፉ አስለቅሶኛል” – ኮሜዲያን ተመስገን መላኩ (ባትሪ)

The post “ባልቻና ኢያሱ አብረውኝ ያደጉ የሠፈሬ ልጆች ነበሩ… ሕይወታቸው ሊቢያ ውስጥ እንዲህ ባለው ሁኔታ ማለፉ አስለቅሶኛል” – ኮሜዲያን ተመስገን መላኩ (ባትሪ) appeared first on Zehabesha Amharic.

አይሲኤል ኢትዮጵያውያኑን መግደሉን ተቃውሞ ሰልፍ ከተደረገ በኋላ አለቃ ጸጋዬ በርሄ ትግረኛ ተናጋሪዎችን ሰብሰበው ያደርጉት ምስጢራዊ ንግግርን ሳዲቅ አህመድ ይፋ አደረገው

$
0
0

ህወሃት ሚስጥራዊ ስብሰባ ቢቢኤን እጅ ገባ::
በሐለቃ ጸጋይ የተመራዉ ስብሰባ ትግሪኛ ተናጋሪዎች ብቻ የተጠሩበት ነበር።
የሙስሊሙ ትግል ሊፈረጅ ተሞክሯል፣ሰማያዊ ፓርቲ ጣት ተቀስሮበታል።
ዝርዝሩን ባልደረባችን ሳዲቅ አህመድ በሰበር ዜና ዘግቦታል


Sadik Ahmed

The post አይሲኤል ኢትዮጵያውያኑን መግደሉን ተቃውሞ ሰልፍ ከተደረገ በኋላ አለቃ ጸጋዬ በርሄ ትግረኛ ተናጋሪዎችን ሰብሰበው ያደርጉት ምስጢራዊ ንግግርን ሳዲቅ አህመድ ይፋ አደረገው appeared first on Zehabesha Amharic.

(ለትውስታ) አቡበከር አህመድ ከመታሰሩ በፊት ከራድዮ ፋና ጋር ያደረገው ቃለምልልስ – [ሊደመጥ የሚገባና አዲሱን የወያኔ ሴራ የሚያጋልጥ]

ኢትዮጵያ ውስጥ የግብረሰዶማዊነት ትምህርት እየተሰጠ ነው –አደጋ ላይ ነን!

$
0
0

gay-flag
ካስደነገጥኳችሁ አዝናለሁ ግን በጣም መደንገጥ አለባችሁ፡፡በመላው የአዲስ አበባ የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምርህት ቤቶች ማለት ይቻላል በነSave The Children ፊት አውራሪነት እየተሰጠ ያለው የግብረሰዶማዊነት ትምህርት ተጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑን ሳረዳችሁ ከፍተኛ ሀዘን እየተሰማኝ ነው፡፡እስካሁን ከ40 በላይ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ት/ቤቶች ውስጥ ለውስጥ በአንድ ክፍለ ጊዜ በ120 ብር በተቀጠሩ የየትምህርት ቤቱ የባዮሎጂና የአይሲቲ መምህራን አማካኝነት እየተሰጠ ነው፡፡ሁለት አይነት ነው ትምህርቱ፡፡Life Skill (ላይፍ እስኪል) እና Comprehensive Sexuality Education (ከምፕሬኤንሲቭ ሴክሽዋሊቲ ኤጁኬሽን) የሚባሉ፡፡በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመጀመሪያ ዙር ስልጠናው አልቋል፡፡ሁለተኛ ዙሩ የተግባር ትምህርት ነው፡፡ በቪዲዮና በተግባር እንቅስቃሴ የተደገፈ፡፡ ከሚሰጡት ትምህርቶች መካከል FREE KISSING (በፍሪ ኪሲንግ) እና MASTERBATION (ማስተርቤሽን)የሚባሉ የልቅ ወሲብ አይነቶች አሉበት፡፡ ልቅ ስል በ FREE KISSING (በፍሪ ኪሲንግ) ጊዜ ጾታ ሳይለይ የፈለጉትን ደፍሮ መሳም ሲሆን በ MASTERBATION (ማስተርቤሽን) የሚለው ደግሞ ሴቶችም ወንዶችም በቪዲዮ የታገዘ የ Pornography (የፖርኖ) ፊልሞች እያዩ እንዲተገብሩት የታሰበ ነው፡፡ ለዚህም አላማ ከየትምህርት ቤቱ ጎበዝ የተባሉ ተማሪዎች ተመርጠው ተዘጋጅተዋል፡፡

ጉዳዩ እስከ ትምህርት ሚኒስተርና ቢሮ ቢደርስም እስካሁን መልስ ሊሰጡ አልቻሉም፡፡አንዳንድ የክፍለ ከተማ ሀላፊዎች እንዳሉት እነSave The Childern (ሴቭ ዘቺልድረን) በኢትዮጵያ የተለያዩ ስራዎች ስለሚሰሩልን አቁሙ ብንላቸው ግንኙነታችን ይበላሻል፡፡በላይ አመራሩም ዘንድ ያለው እሳቤና አቋም ይሄ ነው ብለዋል፡፡የተከበራችሁ የአዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያ የምትገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ፤ ወላጆች ፤ቤተሰቦች ይህ የምነግራችሁ ነገር ተራ አሉባልታ አለመሆኑን በተለያየ ጊዜ ለማሳያ የተለጠፉ መረጃዎችን አይታችሁ መፍረድ ትችላላችሁ፡፡ የተከበራችሁ ተማሪዎች ወላጆች እና በዚህ ጉዳይ እንደ እኔ የተንገበገባችሁ ሁሉ አደጋ ላይ ነን፡፡በተለይ ድርጅቶቹ ነገሩን እንዲሰሩላቸው የመረጧቸውን ሰዎች ለመግዛት እያወጡት ያለው ምራቅ የሚያስውጥ ገንዘብ በየክፍሉ ከሚያስተምሩላቸው መምህራንና ከተባባሪ የትምህርት ቤት አስተዳደሮችም አልፎ እስከ ላይ ድረስ ኪስ ሳያሞቅ አልቀረም፡፡ የእናንተ እርዳታ ቆፍጠን ያለ ውሳኔ ያስፈልጋል፡፡

ተማሪዎችና ወላጆች በአዲስ አበባ በብዛት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ላይ ቢያነጣጥርም ነገሩ በኦሮሚያ፣ በአማራና በሌሎች ክልልሎች ግን እስከ ታችኛው ክፍል ድረስ በስነተዋልዶ፣በጸረኤድስና በስርአተ ጾታ ሰበብ የግብረሰዶማዊነት ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን ሳረጋግጥላችሁ በአውነት ነው፡፡ ስለዚህም ተማሪዎች፣ ወላጆች የሚመለከታችሁ ሁሉ አይናችሁን ወደ ትምህርት ቤት አንሱ!! ተማሪዎች በገንዘብ በተደለሉ ግለሰቦች እተረጨባቸው ያለውን መርዝ አስቁሙ፡፡በተለይ በአሁኑ ወቅት አስረኛና አስራ ሁለተኛ ክፍሎች ትምህርት በጨረሱበት ጊዜ እየሆነ ያለው ተማሪዎችን በክረምት ትምህርትና ስልጠና ሰበብ ለዚህ ተግባር እየመዘገቡ ያሉ ትምህርት ቤቶች እንዳሉ ልነግራችሁ እችላሁ፡፡ሴቭ ዘቺልድረን በክረምት ወራት ትምህርት ቤቶችን በክረምት ትምህርት አሳቦ በመከራየት የሰዶማዊነት ትምህርት ሊሰጥ መሆኑን ስነግራችሁ ያለምንም ጥርጥር ነው፡፡አስካሁን የግብረሰዶማዊነት ትምህርት ሁለተኛ ዙር ለመስጠት ፈቃደኛ ሆነው ካሉ ትምር ቤቶች መካከል፡ ሚኒሊክ፤መድሀኒአለም፣ባልቻ አባነፍሶ፣ኤስኦኤስ፣ህዳሴ፣አፍሪካ ህብረት፣የካቲት 23 ፣መነን፣አየርጤና እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ይህ ነገር ሀሰትነው ብላችሁ የምትጠራጠሩ ከሆነ በተለይ ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተለይ ወላጆች አንደኛ በየክፍለ ከተማ የሚገኙ የስርአተ ጾታ ሀላፊዎችን ፣በአዲስ ትምህርት ቢሮ በተለይ አቶ ሀይለ ስላሴ የተባሉ የስራ ሀላፊን መጠየቅ ይቻላል፡፡በተጨማሪም በኢትዮጵያዊነት ድምጽ ላይ የተለጠፉ የመማሪያ ሰነዶችን ማየት ይቻላል፡፡ወላጆች ልጆቻችሁን አድኑ!!

የተከበራችሁ ተማሪዎች በየትኛውም አጋጣሚ በትምህርት ቤትም ሆነ ከትምህርት ቤት ውጪ በስነተዋለዋልዶና ስርአተ ጾታ ስም የሚሰጠውን ፍጹም የግብረሰዶማዊነት ትምህርት አንማርም ንድትሉ ብትሉም እራስን የማዳንና የመከላከል ተግባርና እርምጃ መሆኑን አውቃችሁ በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፉ መምህራንም ሆኑ በገንዘብ ተደልለው ሊያስተምሩ የተዘጋጁ ተማሪዎችን አምርራችሁ እንድታገሉ ሁላችንም በፈጠረን አምላክ ስም እለምናቿለሁ!!

ኢትዮጵያ የግብረሰዶማዊነት መቀበሪያ ትሆናለች እንጂ መቼም ከግብረሰዶማዊነት ጋር አትጋባም!!

ጭንቀት ካደረበት መምህር

The post ኢትዮጵያ ውስጥ የግብረሰዶማዊነት ትምህርት እየተሰጠ ነው – አደጋ ላይ ነን! appeared first on Zehabesha Amharic.


የታሰርኩ ለታ ‹‹ለሁለት አመት ያላየሁትን ጓደኛዬን ላገኘው ቀጠሮ ነበረኝ›› በፍቃዱ ኃይሉ

$
0
0

እኔ እና አጥኔክስ 10፡45 አካባቢ ከቀነኒሳ ሆቴል እየወጣን ነበር፣ ያን ቀን አብረን ነው የዋልነው፡፡ መንገድ ላይ እንዳለን ስልክ ተደውሎ ማሂ በፖሊሶች መያዟን ሰማን፡፡ ወዲያው የማሂን መያዝ በተመለከተ ቲዊት ላደርግ ስልኬን ስነካካ የማላውቃቸው ሰዎች ሁለታችንንም ከበቡን፤ ስልካችንና ላፕቶፓችንንም ነጠቁን፡፡ ምንም አይነት የተለየ እንቅስቃሴ አላደረግንም፡፡ ዙሪያ ገባየን ሳይ ሰው የተለመደ እንቅስቃሴውን ቀጥሏል፡፡

(ጋዜጠኛ በፈቃዱ ኃይሉ)

(ጋዜጠኛ በፈቃዱ ኃይሉ)


የሚገርመው ለሁለት አመታት ያህል አግኝቼው የማላውቀው ጓደኛዬ ጋር ቀጠሮ ስለነበረኝ ወደዚያ እየሄድኩ ነበር፡፡ ከጓደኛየ ጋር ብዙ ጊዜ ለመገናኘት ፈልገን አልመችህ ሲለን ረጅም ጊዜ ሳንገናኝ ቆየን፡፡ በዛ ዕለትም ሳላገኘው ወደእስር ተጋዝኩኝ፡፡ የነጠቁኝ ስልክ በተደጋጋሚ ሲደወል እና መልዕክት ሲገባ ይሰማኛል፡፡ የቀጠርኩት ጓደኛየ ይሆናል እያልኩ አስባለሁ፡፡

ሰዎቹ እኔን እና አጥኔክስን መኪና ውስጥ አስገብተው ወደ ቦሌ መድሃኒያለም ወሰዱን፡፡ ከዚያም ሌላ መኪና መጣችና አጥኔክስን ከእኔ ለይተው ወደሌላኛዋ መኪና ወሰዱት፡፡ አጥኔክስ ጋር ሲለያዩን አይዞን፣ አይዞን ተባብለን ተለያየን፡፡ ከዚያ እኔን የያዘችው መኪና ወደ እኔ ቤት ይዛኝ ከነፈች፡፡ የቤት ብርበራ ሊደረግ መሆኑ ገባኝ፡፡

ቤት ደርሰን የእኔን ክፍል እያንዳንዷን ነገር መፈተሽ ጀመሩ፡፡ አንደኛው በተለያየ ጊዜ የጻፍኳቸውን ጽሑፎች እያነበበ አየዋለሁ፡፡ ፍተሻው ቀጠለ፡፡ የሚፈትሹት ሰዎች ቀስ በቀስ እየወደዱኝ እንደሆነ ገባኝ፡፡ ማነጋገር ጀምረዋል፡፡ ቤቴ ውስጥ ያለኝ ብዙ ሀብት መጽሐፍ ነው ማለት እችላለሁ፡፡ የቆዩ መጽሐፎችን ሳይቀር እያገላበጡ እያዩ የሚፈልጉትን ይይዛሉ፡፡ እኔ የጻፍኳቸውን ጽሑፎች እያገላበጡ ‹ለምን አታሳትማቸውም› ማለት ሁሉ የጀመሩ ነበሩ፡፡ የእውነት ሰዎቹ እየወደዱኝ ነበር (በሳቅ)፡፡ ፈታሾቹ ሳጥን ውስጥም መጽሐፍ፣ ካርቶን ውስጥም መጽሐፍ፣ ጠረጴዛ ላይም መጽሐፍ ሲያገኙ እየተገረሙ እንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡ የእኔን ክፍል ፈትሸው ሲጨርሱ ዋናው ቤት ገቡ፡፡ እናቴም አባቴም ቤት ውስጥ ነበሩ፡፡ የዛን ሰሞን ሁኔታ ስላላማረኝ፣ ሊያስሩኝ እንደሚችሉና ቤቱም ሊፈተሽ እንደሚችል እነግራቸው ስለነበር ሳይዘጋጁ አልቀሩም፡፡ ቢሆንም ግን መደንገጣቸውና ፣ ማልቀሳቸው አልቀረም፡፡ ቤት ውስጥ ማየት የሚፈልጉትን እያዩ እያለ እራት እንድበላ አሳሰቡኝ፡፡ እራት ቀርቦልኝ እንዴት ይበላልኝ!

ፍተሻው አልቆ ከቤት ስወጣ ቤተሰቦቼን ለማረጋጋት ያህል ‹በጥርጣሬ ነው የያዙኝ፣ ሰኞ እወጣለሁ ይለቁኛል› አልኳቸው፡፡ ከዛም በመኪና ይዘውኝ ማዕከላዊ ወሰዱኝ፡፡ ማዕከላዊ እንደደረስኩ ሰውነቴ ድንዝዝ ሲል ይታወቀኛል፡፡ በቃ ራሴን የመጣል ስሜት ነበር የወረረኝ፡፡ ደሞ ድካሙ! ማዕከላዊ ተመዝግቤ ሌሎች እስረኞች ወዳሉበት ክፍል አስገቡኝ፡፡ በሩ ከኋላዬ ሲዘጋ ቀፈፈኝ፡፡ ወዲያው ውስጥ ያሉት እስረኞች ስለራሴ ጠየቁኝ፤ ነገርኳቸው፡፡ ሊያረጋጉኝ ሞከሩ፡፡

The post የታሰርኩ ለታ ‹‹ለሁለት አመት ያላየሁትን ጓደኛዬን ላገኘው ቀጠሮ ነበረኝ›› በፍቃዱ ኃይሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: 8 ነጥቦች ስለ አጥንት መሳሳት

$
0
0

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
1) የአልኮል መጠጥ አለመውሰድ ምክንያቱ የሰውነታችንን ካልሲየም መጠን ስለሚቀንስ
2) ሲጋራን ማጤስ ማቆም ምክንያቱ በደም ውስጥ የሚገኝን ካልሲየም መጠን እንዲሁ ስለሚቀንስ
3) ወተት እና የወተት ተዋጽኦ የሆኑ ምግቦችን ማዘውተር
4) በካልሲየም የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ለምሳሌ፣ ቆስጣ እና አሣ የመሣሠሉትን
5) የጠዋት ፀሐይን መሞቅ ይህም ቫይታሚን ዲ እንዲመነጭና ካልሲየም በሰውነታችን እንዲወስድ ይረዳል
6) የሚወስዱትን የካፊን መጠን ይቀንሱ ምክንያቱም ካፊን ካልሲየም ከሰውነታችን እንዲወጣ ስለሚያደርግ ነው
7) ቀለል ያለ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ ይህም ሰውነትዎን ጥንካሬ እና መፍታታትን ስለሚሰጥ በቀላሉ ወድቀው ለስብራት እንዳይጋለጡ ይረዳል
8) ወደ ሐኪም በመሄድ ቅድመ ምርመራ ያድርጉ በተለይ ከ65 ዓመት ዕድሜ በላይ ያሉ ሴቶች ምርመራ ቢያደርጉ ይመከራል፡:
osteoporosis
Three factors essential for keeping your bones healthy throughout your life are:

Adequate amounts of calcium
Adequate amounts of vitamin D
Regular exercise
Calcium

Men and women between the ages of 18 and 50 need 1,000 milligrams of calcium a day. This daily amount increases to 1,200 milligrams when women turn 50 and men turn 70. Good sources of calcium include:

Low-fat dairy products (200 to 300 milligrams per serving)
Dark green leafy vegetables
Canned salmon or sardines with bones
Soy products, such as tofu
Calcium-fortified cereals and orange juice
If you find it difficult to get enough calcium from your diet, consider taking calcium supplements. However, too much calcium has been linked to heart problems and kidney stones. The Institute of Medicine recommends that total calcium intake, from supplements and diet combined, should be no more than 2,000 milligrams daily for people older than 50.

Vitamin D

Vitamin D improves your body’s ability to absorb calcium. Many people get adequate amounts of vitamin D from sunlight, but this may not be a good source if you live in high latitudes, if you’re housebound, or if you regularly use sunscreen or avoid the sun entirely because of the risk of skin cancer.

Scientists don’t yet know the optimal daily dose of vitamin D. A good starting point for adults is 600 to 800 international units (IU) a day, through food or supplements. If your blood levels of vitamin D are low, your doctor may suggest higher doses. Teens and adults can safely take up to 4,000 international units (IU) a day.

Exercise

Exercise can help you build strong bones and slow bone loss. Exercise will benefit your bones no matter when you start, but you’ll gain the most benefits if you start exercising regularly when you’re young and continue to exercise throughout your life.

Combine strength training exercises with weight-bearing exercises. Strength training helps strengthen muscles and bones in your arms and upper spine, and weight-bearing exercises — such as walking, jogging, running, stair climbing, skipping rope, skiing and impact-producing sports — affect mainly the bones in your legs, hips and lower spine.

Swimming, cycling and exercising on machines such as elliptical trainers can provide a good cardiovascular workout, but because such exercises are low impact, they’re not as helpful for improving bone health as weight-bearing exercises are. There is evidence that competitive cyclists have reduced bone mineral density. They should combine strength training and weight-bearing exercises and consider a test for osteoporosis.

The post Health: 8 ነጥቦች ስለ አጥንት መሳሳት appeared first on Zehabesha Amharic.

በባህር ዳር መስቀል አደባባይ እና የህዝብ ተቋማት መፍረሳቸው ተረጋገጠ

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ባለፈው ታህሳስ 2007 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮች ሀይማኖታዊ በዓላትን የሚያከብሩበት (በተለይ ጥምቅትና መስቀል በዓላትን) ስፍራ መስቀል አደባባይ በከፊል እና የተለያዩ የህዝብ ተቋማት ‹‹ለመንገድ ልማት›› በሚል ሊፈርሱ ይችላሉ መባሉን ተከትሎ የከተማዋ ህዝብ ለተቃውሞ ወጥቶ ዜጎች በመንግስት ታጣቂዎች መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ እነዚህ ህዝብ የሞተላቸው ተቋማትና የሐይማኖት ቦታ ከሰሞኑ መፍረሳቸው እርግጥ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ዘጋቢ በቦታው ተገኝቶ በመመልከት አረጋግጧል፡፡

(የባህር ዳር ከተማ)

(የባህር ዳር ከተማ)


በከተማዋ ከአዝዋ ሆቴል እስከ ግዮን ሆቴል በሚወስደው መስመር የሚገኙት የባህር ዳር የህዝብ ቤተ-መጽሐፍት ሙሉ ለሙሉ፣ የባንክ ስራ የሚሰራበት እድሜ ጠገብ ህንጻ ሙሉ ለሙሉ፣ እና የህዝቡ ተቃውሞ ዋና ምክንያት የሆነው መስቀል አደባባይ በከፊል ፈርሰዋል፡፡ የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት እና ሙሉዓለም የባህል ማዕከል ደግሞ አጥሮቻቸው እንዲፈርሱ ሆኗል፡፡

የነገረ ኢትዮጵያ ዘጋቢ በስፍራው ተገኝቶ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚገልጹት ከተማ አስተዳደሩ እነዚህን የህዝብ ተቋማት ሲያፈርስ ዙሪያ ገባውን በፌደራልና በክልሉ ፖሊስ አጥሮና የሚቆረጡ ዛፎችንና ሌሎች ፍርስራሾችን በፖሊስ መኪና ብቻ እያጓጓዘ ነው፡፡ ይህም አስተዳደሩ ከፍተኛ የጸጥታ ስጋት ውስጥ ሆኖ ተቋማቱን ማፍረሱን ያመለክታል ይላሉ ነዋሪዎቹ፡፡
ታህሳስ ወር ላይ ተቀስቅሶ በነበረው የህዝብ ተቃውሞ ወቅት የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ አቶ ላቀ አያሌው ‹‹ህዝብ ያልፈለገውና በተቃውሞ ድምጽ ያሰማበት ፕሮጀክት ተፈጻሚ አይሆንም፤ ስለዚህ ካልፈለጋችሁ ይቀራል›› በሚል ህዝቡን ለማረጋጋት መሞከራቸው የሚታወስ ሲሆን፣ አሁን ግን ህዝቡ ይሁንታ ሳይሰጣቸው ወደማፍረስ መግባታቸው ተመልክቷል፡፡

አስተዳደሩ ህዝቡን በኃይል እያስፈራራ ነው የሚሉት የከተማዋ ነዋሪዎች፣ የፌደራል ፖሊስ መስቀል አደባባይ ጎን በሚገኘው ሁለገብ የወጣቶች ማዕከል ውስጥ ከትሞ በተጠንቀቅ መቀመጡን ለንግግራቸው እንደ ዋቢ ያነሳሉ፡፡ ይህን የነዋሪዎችን ጥቆማ በማስመልከት ወደ ወጣት ማዕከሉ ያመራው የነገረ ኢትዮጵያ ዘጋቢም የፌደራል ፖሊስ አባላት በማዕከሉ በብዛት እንደሚገኙ ማረጋገጥ ችሏል፡፡

The post በባህር ዳር መስቀል አደባባይ እና የህዝብ ተቋማት መፍረሳቸው ተረጋገጠ appeared first on Zehabesha Amharic.

በሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ለአይሲኤል ሰለባዎች በአንድ ቀን ከ20 ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ

$
0
0

debereselam-medhanialem
(ዘ-ሐበሻ) በሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ በአይሲኤል የተገደሉትን 28 ኢትዮጵያውያን ለማሰብ በተጠራው የፍትሃት ስነ-ስርዓት ላይ ከኢትዮጵያውያኑ ከ20 ሺህ ዶላር በላይ መሰብሰቡ ታወቀ::

የቤተክርስቲያኑ አስተዳደር ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ እንዳስታወቀው ይህ እርዳታ የመጀመሪያው እንጂ የመጨረሻው አይደለም:: እንደ አስተዳደሩ ገለጻ ትናንት እሁድ በቤተክርስቲያኑ በተደረገው የፍትሃትና የጸሎት ስነስርዓት ላይ ሕዝቡ ሃዘኑን በሰፊው የገለጸ ሲሆን በሊቢያ ለሚገኙና ሕይወታቸውን በአይሲኤል ላጡ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች መርጃ የሚሆን ከ20 ሺህ ዶላር በላይ መሰብሰቡን አስታውቋል::

The post በሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ለአይሲኤል ሰለባዎች በአንድ ቀን ከ20 ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ appeared first on Zehabesha Amharic.

(የሊቢያው እልቂት ጉዳይ) እኛ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ነን!!

$
0
0

አፈንዲ ሙተቂ

ISIL የሚባለው ሰይጣናዊ ቡድን በምድረ ሊቢያ በዜጎቻችን ላይ የፈጸመው አረመኔያዊ ድርጊት ያስቆጣኝ በሁለት ምክንያቶች ነው፡፡ የመጀመሪያው ምክንያቴ በጥይት የተረሸነውና በስለት የታረደው ኢትዮጵያዊ ወንድሜ መሆኑ ነው፡፡ አዎን!! “ዘወትር በድህነት ከምንገላታ ወደ ውጪ ሄጄ ዕድሌን ብሞክር ይሻላል” በሚል የሃሳብ ምጥ ተነሳስቶ በምድረ ሊቢያ በኩል ወደ አውሮጳ ለመሻገር ሲሞክር በአረመኔው ቡድን የተያዘው ወገኔ ደም በረሃ አሸዋ ላይ እንደ ጎርፍ መፍሰሱ በእጅጉ ያንገበግበኛል!! ያስቆጣኛል!! ያስቆጨኛል!! ከአስከፊው የሰሃራ በረሃ የውሃ ጥም እና የሞት መልዕክተኛ ከሆነው የሜዲትራኒያን ባህር ጉዞ ተርፎ ወደ ማልታና ኢጣሊያ መድረሱ እንኳ እያሳሰበኝ ሳለ ከሁለቱ ሰይጣኖች በሺህ እጥፍ የሚብሰው ISIL የተባለ ሶስተኛ ሰይጣን በሊቢያ ምድር ላይ ወገኔን ጠልፎ እንደ በግ አጋድሞት ሲያርደው ማየቱ ይቅርና መስማቱ ራሱ ሲቃው የማይቻል ህመም ነው የሆነብኝ፡፡ የፈሰሰው ክቡር የሆነው የወገኔ ደም ነውና ስለርሱ ሞት እኔ ታምሜአለሁ (ብታምኑም ባታምኑም ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ የምርምር ስራዬን አቁሜአለሁ፤ እንኳንም የቢሮ ሰራተኛ አልሆንኩ)!!

(ፎቶ ፋይል)

(ፎቶ ፋይል)


ሁለተኛው ምክንያቴ ይህ ISIL የተሰኘ “ከላባ” የሰይጣኖች ቡድን ዘወትር እንደለመደው በወገኖቼ ላይ የፈጸመውንም አረመኔያዊ አድራጎት እኔ በምከተለው የእስልምና እምነት ላይ ማላከኩን መቀጠሉ ነው፡፡ በዚህም ሳያበቃ “ይህንን የፈጸምኩት ለናንተ ብዬ ነው፤ በየትኛውም የዓለም ክፍል የምትኖሩ ሙስሊሞች አዳኛችሁ እኔ ብቻ እንደሆንኩ አውቃችሁ ልትቀበሉኝ ይገባል” እያለ ማላገጡም ቁጭቴን ከፍተኛ ደረጃ ላይ አድርሶታል፡፡ እንደዚያ ዓይነት ድርጊቶችን የሚፈጽምበት ዓላማም የእስልምና እምነትን ጥላሸት መቀባት እና በሙስሊሙ እና በሌሎች ወገኖች መካከል ግጭት እንዲቀሰቀስ ማድረግ እንደሆነም በደንብ ስለምረዳ “አንተ አረመኔ! በእስልምና ስም የምትነግድ የሰይጣን ማህበርተኞች ስብስብ” ብዬ እናገረው ዘንድ የተገባም ነበር (በአማርኛ የጻፍኩትን እርሱ ባይረዳውም እንኳ)፡፡

እንግዲህ ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ ሰይጣናዊው ISIL በወገኖቻችን ላይ ያደረሰውን አደጋ ተከትሎ አንዳንድ ጽሑፎችን ስንጽፍ የነበረው በነዚህ ሁለት መነሾዎች ነው፡፡ ወደፊትም በተጠቂ ወገኖቻችን ቤተሰቦች ላይ የደረሰውን መሪር ሐዘን ለማሻር በሚደረገው ርብርቦሽ ውስጥ የተቻለንን ሁሉ ማድረጋችንን እንቀጥላለን፡፡ ታዲያ የተወሰኑ ሰዎች ይህንን መጠነኛ እንቅስቃሴአችንን ፍርሃት የወለደው ራስን የመደበቅ መፍጨርጨር አድርገውት ሲመለከቱት ለመታዘብ በቅተናል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ “ይህ ጉዳይ እናንተን ስለማይመለከት አርፋችሁ ተቀመጡ” ዓይነት ጽሑፎችን ሲበትኑ ተስተውሏል፡፡ አንዳንዶች ጭራሽ ISIL በኛ እጅ የተፈጠረ እንደሚመስላቸው ለማየት ችለናል፡፡ ጥቂቶች ደግሞ ከእስልምና እምነት ጋር ተያያዥነት የሌላቸው ትረካዎችንና ሀሳብ-ወለድ አመክንዮዎችን እያነሱ ነገሩን በእምነታችን ላይ ለማላከክ ሞክረዋል፡፡

በእውነቱ እነዚህ ወገኖች በሦስት ነገሮች አስገርመውናል፡፡ አንደኛ በጉዳዩ ዙሪያ በአማርኛ ቋንቋ ስንጽፍ የነበርነው ሙስሊሞች ኢትዮጵያዊያን መሆናችንን መርሳታቸው ነው፡፡ አዎን!! ኢትዮጵያዊ መሆናችን ብቻ ለወገኖቻችን እንድንናገር ያስገድደናል፡፡ “ኢስላም” እምነታችን እንጂ ዜግነታችን አይደለም፡፡ እምነቱ ጥንት ከዐረቢያ ወደ ኢትዮጵያ የገባ ቢሆንም ዜግነታችን ወደ ሳዑዲያ አልተቀየረም፡፡ የብሄር መለያችንም ወደ ዐረብ አልተለወጠም፡፡ የጥቁር አፍሪቃዊነት መታወቂያችንም ተፍቆ ወደ ነጭነት አልተለወጠም፡፡ ከሌሎች እምነቶች መካከልም የሚበዙት ከውጪ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ቢሆንም የየእምነቶቹ ተከታዮች በዜግነታቸው ኢትዮጵያዊያን ናቸው፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ “ኢትዮጵያዊያን በእምነት ብንለያይም ተፋቅረን ነው የኖርነው” እያልን ስንጽፍና ስንናገር የነበረው ከድሮም ጀምሮ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለፕሮፓጋንዳ ብለን የምንጽፈው ሳይሆን በተግባር የኖርነው ህይወታችን ነው፡፡ ዛሬ ለወገኖቻችን መቆርቆራችንም በደማችን ውስጥ ሲዘዋወር የነበረው ህብርነታችን የቀሰቀሰው ብሄራዊ ወኔ ነው፡፡ ይህ በሌላ ዓለም የማይታየው ጥብቅ የወንድማዊነት ቃል-ኪዳናችን የዜግነት ግዴታችንን እንድንወጣ ቢያንቀሳቅሰን በአንዳንዶች ዘንድ “ፍርሃት ወለድ ነው” ተብሎ መታሰቡ በጣም አሳዛኝ ነው፡፡

ሶስተኛው ነጥብ ደግሞ እነዚህ ወገኖች እስከዛሬ ድረስ ISIL ስለሚባለው ቡድን ተገቢ ግንዛቤ አለመውሰዳቸው ነው፡፡ ቡድኑ “ከእስልምና የወጣ አፈንጋጭ የእስልምና ጠላት ነው፤ የሰይጣን ወኪል ቢሆን እንጂ በጭራሽ የእስልምና ወኪል ሊሆን አይችልም” ተብሎ በዓለም ሙስሊሞች የተወገዘው ገና ከመነሻው ነው፡፡ ሌላው ይቅርና ጽንፈኛ እና አሸባሪ ተብለው በምዕራባዊያን የተፈረጁት አል-ቃኢዳ እና “ጣሊባን” እንኳ ISIL ከእስልምና ውጪ ነው ማለታቸው በዓለም ሚዲያዎች በተደጋጋሚ ጊዜያት ተዘግቧል፡፡ ይህንን ሰይጣናዊ ቡድን የእስልምና ወኪል አድርጎ ማሰብ በጣም ያሳምማል፡፡

እንደምታስታውሱት ስለዚህ ጨፍጫፊና ሰይጣናዊ ቡድን በየጊዜው ስንጽፍ ነበረ፡፡ እኔም ሆንኩ ሌሎች ሙስሊም ወንድሞቼ የአንጃው ድርጊቶች ከእስልምና ጋር ሆድና ጀርባ መሆናቸውን ማሳወቅ ከጀመርን አንድ ዓመት ሊሞላን ነው፡፡ እርግጥ ያኔ ስለቡድኑ አረመኔነት ስንጽፍ የነበረበት ዋነኛ ምክንያት በርካታ ወገኖች (ኢትዮጵያዊያን አይደሉም) የአንጃውን አድራጎት ከእስልምና ጋር ማያያዛቸው ስላበሳጨን ነው፡፡ ዛሬ ሳይታሰብ 30 ዜጎቻችን የአረመኔያዊው ቡድን ሰለባ ሲሆኑብን ደግሞ ቁጭታችን እጥፍ ድርብ ሆኗል፡፡ በመሆኑም ለወገኖቻችን በጋራ መጮኻችን የዜግነትነት ግዴታችንን ከመወጣት እና አንጃው የእምነታችንን ስም ከመጥፎ ድርጊቶች ጋር እያገናኘ ሲያደርስብን የነበረው የስነ-ልቦና ጉዳት ምን ያህል ግዙፍ እንደሆነ ከማስረዳት ውጪ ከሌላ ትርፍ ጋር የሚያያዝበት ምክንያት ሊኖር አይገባም፡፡

*****
ከላይ የገለጽኳቸው አንዳንድ የተዛነፉ አመለካከቶች የታዩት በጥቂቶች ዘንድ ነው፡፡ አብዛኛው ህዝባችን እንዲህ ዓይነት ነገር ሲያልፍም አይነካው፡፡ እነዚህንም ጥቂቶች አይቶ እንዳላየ ሆኖ ማለፍ ይቻል ነበር፡፡ ነገር ግን እነዚህ ጥቂቶች ነገሩን እየመላለሱት የዋሃን ዜጎቻችንን ሊበክሉት ይችላሉ በማለት ለዛሬ ብቻ በጉዳዩ ላይ ይህቺን ማስታወሻ ጽፌአለሁ፡፡ ስለዚህ እህት ወንድሞቼ አንዳንዶች በሚያሳዩት ያልተገባ ጸባይ ሳትለወጡ በጋራ የጀመርነውን ወገንን የመርዳት ጥረት ከግብ እንድናደርሰው በትህትና እጠይቃችኋለሁ፡፡

*****
ማስታወሻዬን ከማሳረጌ በፊት ጥቂት ነጥቦች ለማውሳት እፈልጋለሁ፡፡

• ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ISIL ስለተባለው ቡድን ስጽፍ የነበረው ከናንተ የተለየ እውቀት ኖሮኝ አይደለም፡፡ ከላይ እንደጠቀስኩት ቡድኑ ለሚፈጽማቸው የጭራቅ ድርጊቶች እስልምናን መጥቀሱ በጣም ስለሚያናድደኝ ነው በዚህ ግድግዳ ላይ የተሰማኝን ስጽፍ የነበረው፡፡ ቡድኑ በልዩ ልዩ ሀገራት ውስጥ የሽብር ድርጊቶችን እየፈጸመ እነዚህን ድርጊቶች ተከትለው ሊፈጠሩ በሚችሉ ቅራኔዎች በኩል ማህበራዊ መሰረቱን ለማስፋት የሚጥር መሆኑ ደግሞ የአደባባይ ሚስጢር ነው፡፡ ይህንን ከይሲ ምኞቱን ለማምከን ያለን ዋነኛ መሳሪያ ከጥንት እስከ ዛሬ ያለንን ፍቅርና ህብርነት የበለጠ ማጠናከር ነው፡፡

• አንዳንዶቻችሁ ስለጂሃድ የጻፍኩትን ጽሑፍ ካነበባችሁ በኋላ ልዩ ልዩ የቁርኣን አንቀጾችን እየጠቀሳችሁ “አንጃው የሚፈጽመው ድርጊት በቁርኣንም የተነገረ ነው” የሚል አዝማሚያ ያለው የመከራከሪያ ሃሳብ አምጥታችኋል፡፡ አንዳንዶቻችሁም በዚህ ዙሪያ አንድ ነገር ጻፍልን ብላችሁኛል፡፡ በእውነቱ ሃሳቡ መነሳቱ ተገቢ ነው፡፡ ይሁንና ሀገር በተጨነቀችበት በዚህ ቀውጢ ጊዜ ውስጥ በእንዲህ ዓይነት አጀንዳ ዙሪያ መነጋገሩ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ ISIL የሚባለው አንጃ አንዱ ፍላጎትም ይህንን በመሳሰሉ ጥያቄዎች ዙሪያ ሰዎችን ማወዛገብና ማበጣበጥ ነው፡፡ ስለዚህ “ለጊዜው ጥያቄው ይለፈኝ” እላችኋለሁ፡፡ ለወደፊቱ ግን በዚህ ርዕስ ዙሪያ አንድ መጣጥፍ አዘጋጅቼ ላስነብባችሁ ቃል እገባለሁ፡፡ ለዝግጅት የሚረዷችሁ ጥቂት ነጥቦችን ግን ወርወር ላድርግላችሁ፡፡
1. ቅዱስ ቁርኣን በመጽሐፍነቱ በሁሉም ሙስሊሞች ሊነበብ ይችላል፤ “አል-ፉስሓ” የሚባለውን ጥንታዊ ዐረብኛ የሚናገር ሰው ደግሞ የቁርኣንን አንቀጾችን ቃል በቃል ሊተረጉም ይችላል፡፡ ነገር ግን ቁርአንን ማንበብ የሚችል ሰውም ሆነ እና የዐረብኛ ቋንቋ በቂ እውቀት ያለው ሰው የቁርኣንን ትክክለኛ መልዕክት እና ፍካሬያዊ ይዘት (inner meaning) ለመተንተን አይችልም፡፡ የቁርኣን አናቅጽ ያላቸውን ፍካሬና የሚያስተላልፉትን ትክክለኛ መልዕክት የመተንተን ስልጣን ያለው ለዚህ የሚያገለግለውን የእውቀት ዘርፍ በስፋት ያጠና ምሁር (ዓሊም) ነው፡፡ ይህ ኢስላማዊ የትምህርት ዘርፍ “ተፍሲር” ይባላል፡፡ በእንግሊዝኛ Qur’amic Exegesis ይሉታል፡፡ አንድ ሰው እዚህ ደረጃ ላይ የሚደርሰው ብዙ ሂደቶችን ካለፈ በኋላ ነው፡፡

2. ቁርኣን 6236 አንቀጾች (አያት) አሉት (6666 አንቀጾች ነው ያሉት የሚለው መረጃ ስህተት ነው)፡፡ ከነዚህ አንቀጾች መካከል የሸሪዓ ህግ ምንጭ ሆነው የሚያገለግሉት ግን 500 ብቻ ናቸው፡፡ እነዚህ አናቅጽ የሰላት አፈጻጸም፣ ዘካት፣ ሐጅ፣ የረመዳን ጾም፣ ውል መዋዋል፣ ንግድ፣ ጋብቻ፣ ከሌሎች ህዝቦች ጋር ግንኙነት መመስረት፣ ጂሃድ እና ሌሎችንም የህይወትና የአምልኮ ዘርፎችን ይመለከታሉ፡፡

3. እነዚህ 500 አንቀጾች በየዘርፉ ቢከፋፈሉ ጂሃድን የሚመለከቱት ስንት ይሆናሉ?…. ቁጥራቸው ትንሽ እንደሚሆን አያጠራጥርም፡፡ ስለጂሃድ የሚያወሱት ጠቅላላ የቁርኣንን አንቀጾችስ ስንት ይሆናሉ…?. ቁጥራቸው ብዙ ነው፡፡ ከዚህ ልዩነት እንደምትገነዘቡት ስለጂሃድም ሆነ ስለሌሎች የህይወት ዘርፎች የሚያወሱት በርካታ የቁርኣን አንቀጾች የመጽሐፉ አካል ቢሆኑም ሁላቸውም የህግ ምንጭ ሆነው አያገለግሉም፡፡ ይህ ለምን ሆነ…?. ሰፊ መነሻ አለው፡፡ ሁሉንም ወደፊት እናወጋለን!! ኢንሻ አላህ!!

4. ሌላኛው መሰረታዊ ነጥብ ደግሞ ይኸውላችሁ!! ከቁርኣን አንቀጾች መካከል መልእክታቸውም ሆነ ይዘታቸው በግልጽ ትርጉም እና ትንታኔ የማይደረስባቸው አሉ፡፡ እነዚህን አናቅጽ ለመፍታት የሚችለው ስልጣን የተሰጠው “ሙፍቲ” ብቻ ነው፡፡
እንግዲህ እስልምናን የሚያሳብቡ ጽንፈኛ ቡድኖች ከስህተት ላይ እየወደቁ ዓለምን ሲያተራምሱ የነበሩት ከላይ ባነሳናቸውና በሌሎችም መሰረታዊ ነጥቦች ከጥራዝ ነጠቅ ያልዘለለ እውቀት ይዘው ስለሚነሱ ነው፡፡ አንዳንዶቹ ጭራሽ እነዚህ ነጥቦች በሃይማኖቱ ውስጥ መኖራቸውን ይክዳሉ፡፡ ሆኖም ከላይ የጠቀስኳቸው ነጥቦች ሁሉ ከነቢዩ ሙሐመድ ሲወርድ ሲዋረድ በመጣው አስተምህሮ ውስጥ በጥብቅ የተከበሩ ናቸው፡፡ ብዙሃኑ የዓለም ሙስሊምም በዚሁ ያምናል፡፡እነዚህን ነጥቦች እምቢ ብሎ ከህዝበ ሙስሊሙ ያፈነገጠ ግለሰብም ሆነ ቡድን በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አንደበት “አፈንጋጭ” ተብሎ ተወግዟል፡፡ ነቢዩ ከዚህ የአፈንጋጭነት ባህሪ እንድንታቀብ ሲያስጠነቅቁን እንዲህ ብለዋል፡፡

“ከጀመዓው ያፈነገጠ (የተነጠለ) ወደ ጀሃነም ብቻውን ተገነጠለ”
አላህ ከዚህ የአፈንጋጭነት ባህሪ ይጠብቀን፤ ለአፈንጋጮችም አደብ ይስጣቸው፣ እምቢ ካሉም አላህ ያጥፋቸው፡፡ ISIL ግን ከመነሻው ሰይጣናዊ በመሆኑ አላህ ድምጥማጡን ያጥፋው፡፡ ሀገራችንንና ወገናችንን ከክፉ ነገር ይጠብቅልን፡፡ አሚን!!
——-
አፈንዲ ሙተቂ
ሚያዚያ 18/2007

The post (የሊቢያው እልቂት ጉዳይ) እኛ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ነን!! appeared first on Zehabesha Amharic.

መከራችን መፍትሄ ሳያገኝና ሃዘናችንም ሳይበርድልን ሌላ ከባድ መርዶ ከወደ ሊቢያ ተሰማ

$
0
0

ከአብርሃም ተፈሪ (ሚኒሶታ)

ወዳጆች በቅድሚያ በያላችሁበት የከበረ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ!
ከዚህ ቀጥሎ የምታነቧት አጭር ጽሁፍ በስራ ገበታየ ላይ ሳለሁ በሃሳብ ወዲህ ወዲያ ስባዝን የሞነጫጨርኳት ሰሞንኛ ማስታወሻ ነች።
Abreham D
ሰሞኑን በኛ ኢትዮጵያኖች ላይ የደረሰብንን የሃዘን ማእበል እንዲህ ነው ብሎ ለመግለጽ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው። በደረሰብን ሃዘን ምክንያት ሁላችንም ልባችን ተሰብሯል ውስጣችንም በቁጭት ተቃጥሎ አሯል። የመን ውስጥ በጦርነት መሃል እየተሰቃዩና እየተገደሉ ስላሉ ወገኖቻችን አዝነን ምን ብናደርግ ይሻላል እያልን እየተወያየን ባለንበት ሁኔታ ሌላ አሰቃቂና ጥላቻን መሰረት ያደረገ ኢ-ሰብዐዊ ድርጊት ከደቡብ አፍሪቃ ተሰማ። በደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ከሃገራቸው ኢትዮጵያ በተለያየ ምክንያት ተሰደው በሰው ሃገር ደከመኝ ሳይሉ ቀን ከሌት ሰርተው በላባቸው የሚኖሩ መሆናቸውን ቀናው የሃገሬው ህዝብ የመሰከረበት የአደባባይ እውነት ነው። ይህንን የኢትዮጵያውያኑን ጥንካሬና ችሎታ ተመልክተው የዙሉ ጎሳ የሆኑት የደቡብ አፍሪቃ ዜጎች ለስራ ሊነሳሱ ሲገባ፤ በተቃራኒው ፍጹም ጥላቻን መሰረት ባደረገ ስሜት ካገራችን ይውጡልን በማለት ሲፎክሩ ተሰምተዋል። ይህም አልበቃ ብሏቸው ኢ-ሰብዐዊ ድርጊታቸውን በወገኖቻችን አንገት ላይ ጎማ በማስገባት በጠራራ ፀሃይ እመንገድ ላይ ቤንዚን አርከፍከፍክፎ በመግደል አሳይተዋል። በዚህም ኢ-ሰብዐዊ በሆነ አሰቃቂ ድርጊት ስድስት የሚሆኑ ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ከነዚህም ሶስቱ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን መሆናቸውን የተለያዩ የዜና አውታሮች ዘግበውታል። (እዚህጋ ኢትዮጵያ ደቡብ አፍሪቃ ላደረገችው የነፃነት ትግል ከፍተኛ አስትዋፆ ማድረጓን ልብ ይሏል።)

(Photo File)

(Photo File)


ይህ መከራችን መፍትሄ ሳያገኝና ሃዘናችንም ሳይበርድልን እንደድንገት የድንገት ሌላ ከባድ መርዶ ከወድ ሊብያ ተሰማ። እልም ባለው የሊብያ በርሃና የሜድትራኒያን ባህር ዳርቻ አይሲስ የተባለው ሰይጣናዊ ቡድን ፴ የሚሆኑ የመስቀሉ ተከታይ ኢትዮጵያውያኖችን አንገታቸውን በካራ ቀልቻለሁ በጥይትም ደብድቤ ገድያቸዋለሁ ሲል አወጀ። ይህንንም ስለማድረጉ ማሳያ የሚሆነዉን ወደ ፪፱ ደቂቃ የሚሆን በምስል የተደገፈ ቪድዮ ለቀቀ። ይህንንም ተከትሎ ትላልቆቹ የመገናኛ አውታሮች ወሬውን ተቀባብለው ዘገቡት። እኝም ኢትዮጵያውያን ይህን ዜና እንደሰማን ሃዘናችን እጥፍ ድርብ ሆነ። በሀገር ውስጥም ከሃገር ውጭም ያሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ዳግም ልባቸው በከፍተኛ ሃዘን ተሰበረ። ንፁህ ወገኖቻችን እንደ በግ እየተጎተቱ ወደ እርድ ቦታቸው ሲወሰዱ ማየት እጅግ በጣም ያማል። በ፪፩ኛው ክ/ዘመን ይፈፀማል ተብሎ የማይታሰብ ጭካኔ በኢትዮጵያኖች ላይ ሲደርስ ሰው ሆኖ መፈጠርን ያስመርራል። ይህ ከሆነ በኋላ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከያለበት ቁጣውን፣ ሃዘኑንና ቁጭቱን ማስተጋባት ጀመረ። ይህ ነው በማይባል ሃዘን ሁላችንም እንደተመታን ግልፅ ሆነ። በተለያዩ ሚድያዎችና ማህበራዊ ድህረ ገፆች ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከአድማስ ጥግ እስከ ጥግ እንባውን ረጨ፣ ማቅ ለበሰ።
በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዳለን ጎበዙ መንግስታችን ከተደበቀበት የአራት ኪሎ ጫካ ግቢ ውስጥ ፍፁም ሃላፊነትና ሰብዐዊነት ስሜት በጎደለዉ መንገድ “ስለምን እንደምታወሩ አላውቅም፣ የሰዎቹንም ማንነት በተመለከተ ግብፅ ካይሮ የሚገኘውን ኤንባስዬን አነጋግሬ ኢትዮጵያዊ ስለምሆንና ስላለመሆናቸው ያገኘሁት ማረጋገጫ የለም” በማለት መሪር ሃዘናችን ላይ ተሳለቀብን። ከዛም በመቀጠል ሃዘናቸውን ለመግለፅ በወጡት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ላይ እንደተለመደው የፌደራል ፖሊሶችን በማሰማራት ድብደባና እስራትን አካሄደ። ከዚህም ለመረዳት የሚቻልው የሕወሀት ባለስልጣኖች እንዲሁ በድፍረት እንመራለን እናስተዳድራለን ብለው ወንበር ላይ ተቀመጡ እንጂ የአመራር ጥበብና ችሎታ የሌላቸው፣ ለወቅታዊ ክስተቶች አፋጣኝ የሆነ መፍትሄ መስጠት የማይችሉ፣ በግድ ካልመራንህ እያሉ ከሚያስገድዱት ህዝብ ወደ ኋላ ስልሳና ሰባ ዓመት ርቀው የሚገኙና ከምንም በላይ ሰብዐዊና ሞራላዊ ስሜት የሌላቸው ፍጡሮች መሆናቸውን ነው። በነዚሁ ቡድኖች ምክንያት ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ከፍተኛ ችግር ውስጥ መግባቷ በግልፅ የሚታወቅ ቢሆንም የችግሮቹ ጥልቀትና ስፋት ማለትም ( የሰብዐዊ መብት ጥሰቱ፣ የሙስናው፣ የዘር ክፍፍሉ፣ ሰዎችን ያል አግባብ ማሰሩና መወንጀሉ፣ የብሄራዊ ማንነት መዋረዱና ወዘተረፈ) ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ጉዳዩን እጅግ በጣም አሳሳቢ ያደርገዋል።

በዚህ አጭር ፅሁፌ የችግሮቹን መንስኤዎች ሁሉ ለመዘርዘርና ለመተንተን አልደፍርም ነገር ግን የአብዛኛዎቹ ችግሮች መንስኤ መንግስት ነኝ የሚለው የሕወሃት ቡድን የሚከተለው የተበላሸ ፖለቲካ እንደሆነ ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ። ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብም ሰብዐዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቹን ተጠቅሞ ብሄራዊ ኩራትና ማንነቱን ሊያስመልስ ይገባል ስል አጥብቄ እከራከራለሁ። ከዚህ ጋር ተያይዞ እግረ መንገዴን አንዳንድ የማምንባቸውን የምፍትሄ ሃሣቦች እንደሚከተለው አስቀምጣለሁ።

የመፍትሄ ሃሳብ ፩፡ በሃገሩስጥም ሆነ በውጭ ሃገር የምንገኝ ኢትዮጵያኖች ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በአንድነት አብረን ልንቆምና ልንተባበር ያስፈልጋል። ካለንበት ዘመን ጋር አብረው የማይሄዱትን፣ ኋላ ቀርነታችንን ካልሆነ በስተቀር ምንም አይነት እሴትና ኩራት የማይጨምሩልንን ጠባብ የሆኑ የዘርና የፖለቲካ አመለካከት ጭምብሎቻችንን አውልቀን ልንጥላቸው ይገባል። አይጠቅሙንም! የትም አያደርሱንም። ይልቁንም በዘር በሃይማኖት ሳንለያይ ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን በሕብረት ልንቆም ይገባል። ምናልባትም አስቀድመን ይህን አድርገን ቢሆን ኖሮ እንዲህም አይነቱ መሪር ሃዘን ባልመጣብን ነበር።

የመፍትሄ ሃሳብ ፪፡ ሁላችንንም ኢትዮጵያዉያንን ሊያስተሳስር የሚችል ጠንካራ የሆነ አቋም ሊኖረን ይገባል። ችግርና ሰቆቃ ሲደርስብን ብቻ ሳይሆን በአዘቦቱም ግዜ የህዝባችንና የሃገራችን ሁኔታ ሊያሳስበን ይገባል። ለምሳል፡ ሰብዐዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻችን ላይ ሁላችንም ቁርጥ ያለ አቋም ሊኖረን ይገባል። የመብት ጥሰት ትንሽ ትልቅ የለውምና ሁላችንም ለመብታችን መቆምና መታገል አለብን። ይሄ ጉዳይ ትንሽ ነው ብለን ልናልፈው የሚገባ ነገር መኖር የለበትም። በዛ ደረጃ ልዩ ትኩረት መስጠት ስንችል ነው እንዲህ አይነት ከባድ ችግሮችን ማስወገድ የምንችለው።

የመፍትሄ ሃሳብ ፫፡ በሃገራችን የፖለቲካም ይሁን የማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የያገባኛልና የባለቤትነት ስሜት ሊሰማን ግድ ይላል። እንደዛ ሲሆን ነው እኛን የሚመጥን ዘመናዊ የሆነ መሪም ሆነ አስተዳድር ልናገኝ የምንችለው። በተራ የፖለቲካ ዲስኩርም ልንታለል አይገባም። ይሕንን ማድረግ ስንችል ነው ብሄራዊ ክብርና ኩራታችንን የምናስመልሰው። አለበለዚያ ሁሌም ከሌሎች በታች ሆነን አንገታችንን ደፍተን እንኖራለን።

በመጨረሻም ብዙዎቻችን የተለያዩ ጠቃሚ የመፍትሄ ሃሳቦች እንደሚኖሩን በመገመት ፅሁፌን በዚሁ አጠናቅቃለሁ።
ከመቼውም በላይ ተነቃቅተን የመፍትሄ ሃሳቦቻችን ላይ ልናተኩር ይገባል እላለሁ!
አመሰግናለሁ!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
አብርሃም ተፈሪ

The post መከራችን መፍትሄ ሳያገኝና ሃዘናችንም ሳይበርድልን ሌላ ከባድ መርዶ ከወደ ሊቢያ ተሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

በጨካኞች ሰማእታት በመሆን ሕይወታቸውን ላጡት ወገኖቻችን የተላያዩ ዝግጅቶችን በማቅረብ በስቮልቫር ከተማ ተደረገ!!!

$
0
0

በህወሓት አገዛዝ የአንድ ብሄር የበላይነት በሚንፀባረቅበት ሰዎች በዕውቀታቸው ደረጃ በዜግነታቸው ሳይሆን ለወያኔ ሎሊ ወይም አገልጋይ ካልሆኑ የስራም ሆነ የመኖር መበታቸው በማይረጋገጥበት አገር መኖር ስይችሉ ሲቀሩ ሰደትን እንደአማራጭ በመጠቀም የትም በርሃ ሲቀሩ እናያለን ከሁሉም በላይ የከፋው የአለምን ቀልብ የሳበው በ 30 ንፁሀን ወግኖቻችን ላይ በአይሲስ የተወሰደባቸው የጨካኔ ግድያ ለዚሁሉ ጥፋት በመጀመሪያ ደርጃ ተጠያቂው የወያኔ ስርአት ነው። የወንድሞቻችን ደም ያለአግባብ መፍሰሱ የተቆጨን ህዝቦች ሁሉ ሀዘናችንን በተለያየ መልኩ እየገለፅነው፣፣
ethiopian killed by isil 1
ኤፕሪል 25/4/2015 ፍፁም ሰባዓዊነት በጎደለው መልኩ ባአሰቃቂነት ለተሰውት ወገኖቻችን በማሰብ የሻማ ማብራት እና በቤተክርስቲያን የተለያዩ ዝግጅቶችን በማቅረብ በስቮልቫር ከተማ የምንኖር የኢትዮጵያ ስደተኞች ከኤርትራ እህቶቻችን ወንድሞቻችን በጋራ በመተባበር ሀዘናችን በመግለፅ ነፍሳቸውን ይማር በማለት አስበናቸው ውለናል።
በፕሮግራሙላይ በስቮልቫር ከተማ ነዎሪዎች የሆኑ ኖርዌያኖች የተወሰነ ቁጥር ያላቸው ጥሪያችንን በማክበር እና ማስታወቂያውን በማየት የፕሮግራሙ ተካፋይ በመሆን አጋርነታቸውን አሳይተዋል በተለይም ወደቤተክርስቲያን ድረስ አብረውን በመጓዝ እስከመጨረሻ ድረስ የተሳተፉትን ከልብ አናመስገናለን።

ከአበባ ማስቀመጡ እና ከሻማ ማብራቱ በተጎዳኝ በግፍ የትገደሉ ወገኖቻችን የሚገልፅ ምሰልና ገዳዮቻችው ተሽፋፍነው የሚያሳየውን ፎቶ አይሲስ የልቀቁትን ፎቶ በማያዝና የምስሉ ገላጨ የሆነ ፅሁፍ በመፃፍ ለማህብረሰቡ አምፊ (AMF) የገቢያ አደራሽ በር ላይ በመቆም የደርሰባቸውን መከራና ሰቃይ በገላጨ ፎቶው ለማሰየት ሞክረናል ትልቁ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው አብይጉዳይ አይሲሰ እንወክለዋልን በለው የሚያምኑትን የእስለምና ሀይማኖትን የማይወክሉና ትልኮቸው ፍፁም ደቢሎሳዊ ሰለሆነ የአለም ህዝብ በጋራ በመቆም በተለይም አሜሪካና የተቀረው የምዕራቡ ዓለም ትኩረት ሰጥተው ማጥፋታ አለባቸው ይህንንም መልእክት ለኖርዌይ ማህበረሰብ አስተላልፈናል።
Libya ethiopia
ከአንድ ስዓት ቆይታ በኃላ በመቀጠልም በተያዘው ፕሮግራም መሰረት ወደ ሁለተኛው ፕሮግራም የያዝነውን ምስል ወይም ፎቶ በመያዝ ዋናውን ከትማ በምዞር በህብረት ጉዞ ወደ ቤተክሪስቲያን እዛም ስንደርስ ፕሮገራሙን የያዙልን ቄስ እንኳን ደህና መጣቹሁ በማለት በመንፈሳዊ መዙሙር ኦርጋን በመጫውት በፈገግታ ተቀብለውናል ከዛም በመቀጠል ብደጋሚ ቄስ ጉናኣር አንደርሰን (Gunnar Andersen) እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት አጭር የምግቢያ ንግግር ካደረጉ በሆላ በደጋሚ የምስጋና መዝሙር ጋብዘውናል ከዛም በመቀጠል የፕሮግራሙ መሪ ወንድማችን ሳምሶን ወደመድርክ በኤርትሪያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ እህቶቻችን ወንድሞቻችን በመጋበዝ ለእለቱ የሆናል በለው የተዘጋጁበትን 3 መንፈሳዊ መዝሙሮችን በተከታታይ አቅርበዋል በማስከተልም አንድ ውንደማችን ኤርትራዊ ግጥም አዘጋጅቶ አቅርቦልናል በመጨረሻም የፕሮግራሙ መሪ በራሱ የተዘጋጀውን የስደትን አስከፊነት የሚገልፅ በወንድሞቻችንላይ የደረሰው አሰቃቂ መከራና ግድያ በእያንዳንዳችን ቢደርስብን ምንሊሰማን እንደሚችል የሚያሳስብ ግጥም በማቅረብ ገልጿል በስተመጨረሻ ሻይ ብና በማለት ፕሮግራሙ በታያዘለት ስዓትና ደቂቃ በሰላም ተጠናቋል ።

በሰተመጨረሻ ምስጋና ለዝግጅቱ መሳካት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ በእውቀታቹሁ ፣ በጉልበታቹሁ ፣በመልካም ሀሳባቹህ ለተባበራችሁን የሻማ ማብሪያ ቦታ ለፈቀዱልን ለአምፊ (AMF)የግቢያ አዳራሽ ፣ፎቶውን በ ከለር ፕሪንት በማደርግ ለትባበረችን የትምህርት ቤቱ ሰራ አስኪያጅ ፣ለቄስ ጉናኣር አንደርሰን (Gunnar Andersen) ላደርጉልን መልካምና በጎ ሀሳብ እርዳታ ከልብ እና መሰግናለን።

በግፍ በጨካኞች የተገደሉትን ወገኖቻችን ወንድሞቻችንን ነፍስ የማርልን !!!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
Dawit Wondimu
SVOLVÆR 25/4/2015

The post በጨካኞች ሰማእታት በመሆን ሕይወታቸውን ላጡት ወገኖቻችን የተላያዩ ዝግጅቶችን በማቅረብ በስቮልቫር ከተማ ተደረገ!!! appeared first on Zehabesha Amharic.


(በዚህ ሳምንት የተማርናቸው ሦስት ነገሮች) 1ኛ) “ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለምን ኬክ አይበሉም?”… 2ኛ) የኢትዮጵያ መንግሥት ሲያፍን እንደ አንበሳ ሲጠብቅ እንደ ሬሳ ኾነ… 3ኛ) ፕሮፌሰር መስፍን ምሁራዊ አይበገሬ ናቸው

$
0
0

(የቡና ቁርስ)

በዚህ ሳምንት የተማርናቸው ሦስት ነገሮች
habesha in libya

1ኛ) “ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለምን ኬክ አይበሉም?”

ታዋቂው ገጣሚ እና ጸሐፊ በዕውቀቱ ሥዩም ከሦስት ዓመታት በፊት የለንደን ኦሎምፒክን በማስመልከት በተዘጋጀ የሥነ ጽሑፍ ፌስቲቫል ላይ ተሳታፊ ነበር። በጊዜው ካቀረባቸው ግጥሞች መካካል ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኘለት “ኀሠሣ ሥጋ” የተባለው ነበር።

“እልፍ ከሲታዎች ቀጥነው የሞገጉ ፥
በየሸንተረሩ በየጥጋጥጉ፥
“ስጋችን የት ሄደ?” ብለው ሲፈልጉ ፥
አስሰው አስሰው በምድር በሰማይ፥
አገኙት ቦርጭ ኾኖ ባንድ ሰው ገላ ላይ። ”

ግጥሙ በዩናይትድ ኪንግደም እና በሌሎች ያደጉ አገራት ወስጥ ኢ-እኩልነትን በሚመለከት የሚደረገው ክርክር እና የነበረው ጭንቀት በተጧጧፈበት ጊዜ የቀረበ ስለነበር የጊዜውን መንፈስ መያዝ ችሏል። በዚያን ወቅት ኦኩፓይ ዎል ስትሪት ንቅናቄ ናኝቶ ነበር። ከንቅናቄው ዋነኛ ዓላማዎች መካከል አንዱ የኢኮኖሚ ልዩነቱን ከነመዘዙ ለሕዝብ በግልጽ ማሳየት ነበር። አንዳንድ ጊዜ ፊት ለፊታችን ያለ ችግርን በጥሞና መመልከት ያዳግተናል። የበዕውቀቱ ሥዩም ግጥም ይህን ችግር በጣፋጭ እና አጭር ቋንቋ ያስቀምጣል።

የውስጥና የውጭ መሬት ነጣቂዎች እና ጥቂት ከበርቴዎች በተንሰራፉባት ኢትዮጵያ የኢ-እኩልነት እና የኢኮኖሚ መደብን ጉዳይ ማንሳት እና የፖለቲካ ኢኮኖሚ ፍጭት ዋነኛ አካል ማድረግ አግባብነት ያለው ቢኾንም እስካሁን በተገቢው መጠን አልተዳደሰሰም፤ ሙግት አልተደረገበትም። በ1995 ዓ. ም የጀመረው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ሁሉንም የጠቀመ አይደለም። በርካታ የኢኮኖሚክስ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በእድገቱ የመጀመርያዎቹ ዘጠኝ ዓመታት የታየው አስደንጋጭ የዋጋ ግሽበት የድኻ ሠራተኞችን ኹነኛ ገቢ (real income) ክፉኛ ያዳቀቀ ነበር። በተጨማሪም እድገቱ ከኢንደስትሪያላይዜሽን እና በርካታ ሠራተኞችን ለመቅጠር ከሚችሉ የአገልግሎት ዘርፍ አካላት ጋር የተፋታ በመኾኑ በከተሞች የተንሰራፋውን ሥራ አጥነት ትርጉም ባለው ደረጃ ለመቀነስ እንዳይችል አድርጎታል። እነዚህ እና ሌሎች ምክንያቶች ተደራርበው በተለይ የከተማ ድኾች (urban poor) የእድገቱ ጦስ (development cost) ተሸካሚዎች ኾነዋል “አሁን ተሰውተን ለመጪው ትውልድ ሀብታም አገር ማውረስ” የሚለውን መፈክር ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ኹኔታ አንጻር ስንመረምረው መስዋዕትነቱን እንዲፈጽሙ የሚጠበቅባቸወቅም ኾኑ የተገደዱት የከተማ ድኾች ኾነው እናገኛቸዋለን። በተቃራኒው ይኼን መፈክር ጮኽ ብለው የሚያሰሙት ደግሞ በዋጋ ግሽበት በሰከረ እና በሥራ አጦች በተሞላ ዕድገት ተጠቃሚ የኾኑት ናቸው።

ይህ ግልጽ የኾነ የኢኮኖሚ እውነታ ቢኾንም ለብዙዎች ተሰውሮባቸው ቆይቷል። ነገር ግን ባለፈው ሳምንት በደቡብ አፍሪካ፣ በሊቢያ እና በሜድትራንያን-በኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ የደረሰው ሞት እና እንግልት የቀሰቀሰው ብሔራዊ ሐዘን ሳይበርድ መዘራት የጀመረ አንድ አመለካከት አፍንጫችን ሥር ከነበረው የኢ-እኩልነት መዘዝ ጋር እንድንፋጠጥ ያደረገ ነው። የፌስ ቡክ እና ትዊተር ያላሰለሰ ተሳታፊ የኾኑትን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ጨምሮ በርካታ የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የአገዛዙ ደጋፊዎች እንዲሁም የመንግሥት የፕሮፖጋንዳ ጣቢያዎች በተደጋጋሚ ካስተጋቧቸው አመለካከቶች አንዱ “ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አገር ውስጥ ሠርተው መኖር ሲችሉ ከ40 እስከ 90 ሺሕ ብር እየከፈሉ አደጋ ላይ የሚጥላቸውን የስደት ሕይወት መርጠዋል “የሚል ነው። ነገር ግን ይህ አመለካከት የአገዛዙ ብቻ ነው ብሎ መደምደም ከእውነት የራቀ ነው። በተለይ በተለምዶ የመካካለኛ መደብ አባላት ተብለው የሚጠሩ ገቢያቸው የተደላደለ ኑሮ እንዲኖሩ የሚፈቅድላቸው አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ሐሳቡን እንደሚጋሩት በተለያዩ መድረኮች በሚሰጧቸው አስተያየቶች ተስተውሏል።

የዚህ ሐሳብ ዋነኛ ችግር ጥያቄውን መጠየቁ ሳይኾን ‘ ርግጠኝነት የተሞላበት መልስ በቅጽበት ለመስጠት መሞከሩ ነው። ማኅበራዊ ሳይንቲስቶች ኢ-እኩልነት ሲጨምር ሁለት ነገሮች እየተሸረሸሩ እንደሚመጡ ይጠቁማሉ። አንደኛው ማኅበራዊ ንቃት (social consciousness) ነው። ይህ በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ኾነን በምናደርገው የኢኮኖሚ መስተጋብር ምክንያት የሚፈጠር የጋራ ንቃት ነው። ይህ ንቃት ባልንጀሬነትን እና ወገንተኝነትን የሚያጸና ነው። የኢኮኖሚ መደብ ልዩነት እየሰፋ ሲመጣ እነዚህ ውጤቶች እየኮሰመኑ ይሄዳሉ። ኢ-እኩልነትን የሚሸረሽረው ሁለተኛው እሴት ደግሞ ማኅበራዊ ኅሊና (social conscience) ነው። ይህ ለፍትህ መጨነቅን፣ ራስን ሌላ ሰው ጫማ ውስጥ በማስገባት በበጎ ልቡና ለመረዳት መፈለግን (empathy) ወዘተ ይመለከታል። በዚህ ሳምንት ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ላይ የተነሱ ችኩል ጥያቄያዊ ትችቶች የእነዚህ እሴቶች ቀስ በቀስ መሸርሸር ነጸብራቅ ነው። በብድር፣ በመዋጮ እና ጥሪት አሟጠው አገር ለቀው የሚሰደዱ ሰዎች እና ቤተሰቦቻቸውን በጥንቃቄ በመጠየቅ እና በማነጋገር ለመረዳት ከመጣር፣ ሕይወታቸውን ለመመርመር ከመሞከር እና የኑሯቸውን የትርፍ እና የኪሳራ ስሌት መዋቅር (risk and reward structure) በጥሞና ከማጥናት ይልቅ “ኢንፎርሜሽን የላቸውም፣ ተሸውደዋል፣ ያላቸውን ዕድል መጠቀም አልሞከሩም” ወዘተ የሚሉ መረጃ ላይ ያልተመሠረቱ-ከወንድማማችነት፣ ከወገንተኝነት እና ከባልጀሬ መንፈሶች ጋራ የተጻረሩ የሩጫ ፍርዶችን አስተውለናል። ከመደብ ልዩነት ከመነጩ ከእነዚህ ፍርዶች-በ13 ዓመት የእድገት ሂደት ውስጥ እንዲህ ያለውን ክፍፍል ካየን ጥቂት ቆይተን “ለምን ኬክ አይበሉም?” የሚል አሳፋሪ ትችትን ልንሰማ እንችላለን።
yilikal

2ኛ) የኢትዮጵያ መንግሥት ሲያፍን እንደ አንበሳ ሲጠብቅ እንደ ሬሳ ኾነ

የኢትዮጵያን የመንግሥት ሥርዐት ለመረዳት የሚፈልግ ሰው በዚህ ሳምንት የተፈጠሩ ሁለት ነገሮችን እና የእነርሱን ግንኙነት እንደ ምሳሌያዊ ማስተማርያ ሊወስድ ይችላል። የመጀመርያው፦ መንግሥት ሐዘንተኞች ከቁጥጥር ውጪ ወደኾነ ዐመጽ እንዳይገቡ የወሰደው ፈጣን እና ቁርጠኛ ርምጃ ነው። ሁለተኛው፦ የሐዘኑ ምንጭ ለኾነው የኢትዮጵያውን ስደተኞች ጥቃት ዘገምተኛ፣ አሻሚ እና የተዘበራረቀ መልስ መስጠቱ ነው። የመጀመርያውን የተመለከተ የኢትዮጵያን መንግሥት ብቃት (competence) ያስተውላል። ሁለተኛው ደግሞ የአስተዳደሩን ችግሮች አጉልቶ የሚያሳይ ነው። እነዚህ ልዩነቶች ከምን መነጩ? አምባገነን መንግሥታትን የሚያጠኑ የፖለቲካ ሳይንቲስቶች ከሚሰጧቸው መልሶች መካከል አንዱን እነኾ፦

የአምባገነን መንግሥታት ዋነኛ ዓላማ ዕድሜን ማራዘም (survival) ነው። ሌሎች ዓላማዎች ቢኖሯቸውም ሁሌም ከዕድሜ ማራዘም ያነሰ ቦታ ያላቸው ናቸው። ዕድሜ ለማራዘም ደግሞ ዋነኛ ስልታቸው አምባገነናዊ ቁጥጥር (authoritarian control) ነው። የአምባገነናዊ ቁጥጥር ሁለት መሣርያዎች አፈና (repression) እና ደልሎ መማረክ (co-optation) ናቸው። እነዚህ መንግሥታት ሁለቱን መሣርያዎች በጥንቃቄ እና በጥናት አቀናጅተው ይጠቀሙባቸዋል። የሁለቱ ቅንጅት ሚዛን ከጨቋኝ ጨቋኝ ይለያያል። አንዳንድ አምባገነኖች ከአፈናው ቀነስ፣ ከማባበያው ጨመር ያደርጋሉ። ሌሎቹ ደግሞ ወደ አፈና ያዘምማሉ። ለምሳሌ በሶቭየት ሕብረት አምባገነናዊ ቁጥጥር ላይ ጥናት ያደረጉት ዲሚትሪ ገርሸንሰን የቅንጅቱን ሚዛን በተመለከተ በስታሊን እና በብሬዥኔቭ መካከል ያለውን ሰፊ ልዩነት ያትታሉ። የአምባገነኖች ዓላማ ዕድሜን ማቆየት በመኾኑ አገዛዞቻቸው ከሁሉም በላይ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጧቸው እና የሚያፋፏዋቸው እነዚህን ሁለት የቁጥጥር መሣርያዎች በተግባር የሚያውሉትን ተቋማት ነው። እነዚህ ተቋማት የተሻለ የሰው ኃይል እና ሌሎች እምቅ ሀብቶች (resource) ያገኛሉ፤ ተወርዋሪ እና አዳዲስ ነገሮችን መፍጠር የሚችሉ ይኾናሉ። በረዥም ጊዜ ዕውቀት እና ብልኃት ያከማቻሉ። ቀልጣፋም ይኾናሉ። ይህ ልዩነት ያለው በተቋማት መካከል (inter-institutional) ብቻ ሳይኾን በተቋማት ውስጥም (intra-institutional) ነው። አንዳንድ ተቋማት አምባገነናዊ ቁጥጥርን ከሌሎች ተግባራት ጋር ቀላቅለው ይሠራሉ። እንዲያ ሲኾን ይህን ሥራ የሚሠሩ ዲፓርትመንቶች እና ዴስኮች ከሌሎቹ ይልቅ ልዩ ትኩረት እና ክብካቤ ይደረግላቸዋል።

በዚህ ምክንያት ብዙ አምባገነን መንግሥታት አምባገነናዊ ቁጥጥርን የማይመለከቱ ድንገተኛ ቀውሶች እና ችግሮች ሲገጥሟቸው በዝግጁነት እና በአቅርቦት ችግር ምክንያት ፈጣንና ቁርጠኛ መልስ ለመስጠት ይቸገራሉ። በሜክሲኮ፣ በኒከራጓ፣ በበርማ፣ በግብጽ እና በሶቭየት ሕብረት የተሠሩ ጥናቶች እንደዚህ ዐይነቱን የተቋማት አለመመጣጠን እና የሚያስከትሉትን ችግር ይዳስሳሉ። ሙሉ ለሙሉ አምባገነንነት ውስጥ የተዘፈቀው የኢትዮጵያ መንግሥትም ከአምባገነን ቁጥጥር ውጪ ያልታሰቡ የቤት ሥራዎች ሲደነቀሩበት ቢንገዳገድና ቢውተረተር ሊያስገርመን አይገባም። ያልተዘራ አይታጨድም።

mesfin
3ኛ) ፕሮፌሰር መስፍን ምሁራዊ አይበገሬ ናቸው

የ82 ዓመቱ ማርክሲስት ፈላስፋ ሮበርት ፖል ዉልፍ በሳምንት ሁለት ጊዜ በታዋቂው ብሎጋቸው (The Philosophers Stone) የዘመኑን ፖለቲካዊ ጥያቄዎች እያነሱ የሰላ አስተያየቶች ይሰነዝራሉ። አልፎ አልፎ አወዛጋቢ ሐሳቦችን እያነሱ ተከታዮቻቸውን ያሟግታሉ። በተጨማሪም ግሩም መጻሕፍት ያሳትማሉ። አንዳንድ ጊዜ በየዩኒቨርሲቲው እየዞሩ ሌክቸር ይሰጣሉ። ከሁለት ዓመታት በፊት ሰማንያኛ የልደት በዐላቸውን ሲያከብሩ በአዛውንትነታቸው እንዲህ ያለ ሕይወት (vitality) ያለው የሐሳብ እና የኮሚዩኒኬሽን ኑሮ የሚኖሩበትን ምክንያቶች አቅርበው ነበር። አንደኛ፦ በእርሳቸው ትውልድ ካሉ ጓደኞቻቸው ይልቅ ከወጣቶች ጋር መዋል፤ ሁለተኛ፦ ከዩኒቨርሲቲዎች እና ከሐሳብ መድረኮች አለመራቅ፤ ሦስተኛ፦ ውዝግብን እና ሙግትን አለመፍራት፤ አራተኛ፦ በሶሻል ሚዲያ እና ሌሎች ሚዲያዎች ላይ በንቃት መሳተፍ።

በዚህ ሳምንት ድፍን ሰማንያ አምስት ዓመት የኾናቸው ፕሮፌሰር መስፍን ከሁለተኛው በስተቀር ሌሎቹን የሮበርት ዉልፍ መመርያዎች በሃይማኖታዊ ወኔ የሚከተሉ ናቸው። ሁለተኛውን መመርያም የገደፉት ተገደው እንጂ ፈቅደው አይደለም። 60 ዓመታት ከቆየ የአደባባይ ምሁራዊ ኑሮ በኋላም እንኳ ፕሮፌሰር መስፍን በሐሳብ እና በፖለቲካ ሕይወት ያለመታከት መሳተፋቸውን አላቆሙም። አሁንም ልክ እንደ ቀድሟቸው ይጎነትላሉ፣ ይነቁራሉ፣ ያወዛግባሉ፣ ያበሳጫሉ፣ ያስጨበጭባሉ። ሐሳቦቻቸውንም ይኹን የፖለቲካ አቋሞቻቸውን የሚቃወሙ በርካታ ናቸው። የፖለቲካ ተሳትፏቸው የውጤት ምስክር ወረቀት (scorecard) ቢመረመር በቀይ እስኪሪብቶ የተጻፉ ብዙ ውጤቶች ይገኛሉ። አሜሪካዊው ታላቅ ዳኛ ጀስቲስ ኦሊቨር ዌንደል ሆልምስ እንደሚሉት የምሁር ሕይወት “በማያቋርጥ የጥይት እሩምታ መካከል ውስጥ ኾኖ ማሰብ ነው” ፤ አንዳንዴ ጥይቱ ያቆስላል። ሕይወት ያለው ምሁር ቁስሉን ሲያክ እና ሲደባብስ አይቆይም። በፍጥነት ተነስቶ ወደ ፍልሚያው ይመለሳል። ዕድሜ ሲገፋ እንዲህ ዐይነቱ ጽናት እና ጉልበት እየቀነሰ ይመጣል። ለምሁራዊ ኑሮ መልካም ዋጋ የሚሰጡ ማኅበረሰቦች የአዛውንት ምሁራንን ጉልበት ለመደገፍ እና ጽናታቸውን ለማደስ ብዙ ነገሮች ያደርጋሉ። በዩኒቨርሲቲዎች፣ በጥናት ተቋማት እና በሚዲያዎች ተቀማጫ ፌሎው (resident fellow) እየተደረጉ ከወጣት ምሁራን እና ከተማሪዎች ጋራ ንቁ መስተጋብር እንዲያደርጉ ዕድል ይመቻችላቸዋል። በኮንፈረንስ እና በየሌክቸሮች ይጋበዛሉ። የምርምር ረዳቶች ተመድበውላቸው መጽሐፍ ይጽፋሉ። ፖለቲከኞች እና ፖሊሲ አውጪዎችን ያማክራሉ። ፕሮፌሰር መስፍን ይኼን ማጣታቸው ብቻ ሳይኾን በሐሳባቸውን እና በፖለቲካ ተሳትፏቸው ምክንያት በአዛውንትነታቸው ዘብጥያ ከመውረድ አንስቶ ብዙ እንግልት አስተናግደዋል። ከእነዚህ ገደቦች እና ጫናዎች ጋር ተገዳድረው በጋዜጣ፣ በመጽሔት፣ በመጻሕፍት፣ እና በማኅበራዊ ሚዲያዎች መሳተፋቸውን ቀጥለዋል። ይህን ጽናታቸውን ለማድነቅ የአይዲዮሎጂያቸው ወይም የሐሳቦቻቸው ደጋፊ መኾን አያስፈልገንም። ሕይወት ላለው ምሁራዊ ኑሮ ጽዋችንን እናነሳለን፤ ለፕሮፌሰር መስፍን ደግሞ መልካም ልደት!!

Source: 7-killo Magazine

The post (በዚህ ሳምንት የተማርናቸው ሦስት ነገሮች) 1ኛ) “ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለምን ኬክ አይበሉም?” … 2ኛ) የኢትዮጵያ መንግሥት ሲያፍን እንደ አንበሳ ሲጠብቅ እንደ ሬሳ ኾነ… 3ኛ) ፕሮፌሰር መስፍን ምሁራዊ አይበገሬ ናቸው appeared first on Zehabesha Amharic.

በጃክሰንቪል ፍሎሪዳ የሻማ ማብራት -ሜላት መኮንን ለሐበሻ ሬዲዮ ከጃክሰንቪል ፍሎሪዳ

$
0
0

በጃክሰንቪል ፍሎሪዳ የሻማ ማብራትና የጸሎት ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

mela(ሐበሻ ሬዲዮ) በቅርቡ በሊቢያ የባህር ዳርቻ ፣ በግፍ የተረሸኑትንና የታረዱትን፣ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ፣ በየመን እና በሌሎችም የዓለማችን ክፍሎች በችግርና በስቃይ ውስጥ ያሉትን ወገኖችን ለማሰብ የተዘጋጀ የሻማ ማብራትና የጸሎት ስነ ሥርዓት፣ በጃክሰንቪል ፍሎሪዳ ተካሄደ። በዚሁ ከ መቶ የማያንስ የኢትዮጲያ እና ኤርትራዊያን ነዋሪ በተገኘበት ስነ ሥርዓት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ፣ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተወካይ እና ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን አባቶች ተገኝተው በየተራ ጸሎት በማድረግ መርሃ ግብሩን ከፍተዋል በዚሁ የጸሎትና የሻማ ማብራት ስነ ሥርዓት ፣ በሁሉም አባቶች መንፈሳዊ ምክር ተሰጥቷል የወገኖቻችን ሞትና እስራት፣ መከራና ችግር፣ ስቃይና መቃተት የሁላችንም ስሜት እንደሆነ በተነገረበት በዚህ ዝግጅት፣ የዕምነት ተቋማት  መቀራረብና አንድ መሆን ወሳኝነት አለው ብለዋል።በንግግራቸውም በሊቢያ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያን አስታውሰው በአይሲስ ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ተቃውሞ አሰምተዋል:: በደቡብ አፍሪካ እና በየመን እያለቁ ስላሉት ኢትዮጵያውያንም ተጸልይዋል:: ሁሉም የሃይማኖት መሪዎች ያሳሰቡት ነገር ቢኖር አንድነት እና ፍቅርን ሲሆን ሁሉም አንድ ሆኖ ለሃገሩና ለሕዝቡ እንዲቆም ጠይቀዋል::

ሜላት መኮንን ለሐበሻ ሬዲዮ ከጃክሰንቪል ፍሎሪዳ

The post በጃክሰንቪል ፍሎሪዳ የሻማ ማብራት -ሜላት መኮንን ለሐበሻ ሬዲዮ ከጃክሰንቪል ፍሎሪዳ appeared first on Zehabesha Amharic.

መሰቦ ስሚንቶ ለአባይ ግድብ ስሚንቶ ማቅረቡን ማቋረጡ ተሰማ

$
0
0

ኢሳት ዜና :-የህወሃት የልማት ድርጅት ፣ ኢፈርት ንብረት የሆነው መሶቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ላለፉት ሶስት አመተት ያለተቀናቃኝ በከፍተኛ ዋጋ ለአባይ ግድብ ስሚንቶ ሲያቀርብ ከቆየ በሁዋላ ፣ ስራውን አቋርጧል።

የአባይ ግድብ ግንባታ የኢኮኖሚ አዋጭነት ጥናት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ይፋ ከተደረገ በኃላ በባለስልጣናት መካከል ውዝግብ መነሳቱ ታውቋል። ጉባ የሚገኘው የስሚንቶ ማምረቻ በመሰቦ ስር እንዲሆን መወሰኑ የውዝግቡ መነሻ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
Mesobe Cemnet
ይህን ተከትሎ ፋብሪካው ላልተወሰነ ጊዜ አቅርቦቱን አቋርጧል፡፡ በህወሃት ባለስልጣናት ተፅኖ ያለምንም ጫረታ ያሸነፈው መሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ፣ ትራንስ እና ጉና በሚባሉ የህወሃት የትራንስፖርት ድርጅቶች ስሚንቶ ወደ ግድቡ በማመላለስ ባለፉት 3 አመታት
9 ቢልዮን 345 ሚልዮን 289 ሺ ብር ገቢ አግኝቷል። መሰቦ የሲሚንቶ ፋብሪካ በ240 ሚሊዩን ብር የተከፈለ ካፒታል ከመቀሌ 15 ኪሜ እርቆ በሚገኝ ስፍራ ላይ በፈረንጆች አቆጣጠር በ1995 የተመሰረተ ነው፡፡

1 ሺ 1 መቶ 95 ቆሚ ሠራተኞች ፣ 240 ኮንትራት ሠራተኞችና 51 ጊዜያዊ ሠራተኞች ያሉት መሰቦ በአመት 900 ሺ ቶን ስሚንቶ ያመርታል።

ፋብሪካውን የቻይና ማኔጀሮች በኮንትራት ሲያስተዳድሩት ቆይተው እኤአ በ2000 ውላቸው ተቋረጠ፡፡ እስከ 2003 ፋብሪካው በኪሳራ ለመዘጋት ተቃርቦ የነበረ ሲሆን፣ ማኔጅመንቱን ፓኪስታኖች እንዲወስዱት ተደርጓል።

ከ6 አመታት በፊት መሶቦ ፋብሪካ የማስፋፍያ ስራውን ሃንፊ ለሚባል የቻይና ኩባንያ በ3 ቢሊዩን ብር ወይም 180 ሚሊዩን ዶላር በመስጠት ምርቱን አሁን በቀን ከሚያመርተው 3 ሺ ኩንታል ስሚንቶ ወደ 6 ሺ ኩንታል ስሚንቶ ለማሳደግ እቅድ ነድፎ ነበር።
ኩባንያው ለዚህ ስራው 141.6 ሚሊዩን ብር ወይም 8.4 ሚሊዩን ዶላር ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ተበድሯል።

መሰቦ የሲሚንቶ ፋብሪካ ሲቋቋም የደንበኛ ጥናት ባለማካሄዱ ለብዙ አመታት በኪሳራ ተንቀሳቅሷል፡፡ የፋብሪካው ርቀት በመላ ሀገሪቱ ምርቶቹን ለማከፈፈልና መሸጥ አላስቻለውም ነበር፡፡ ህወሃት የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለሚያሰሩዋቸው ፕሮጀክቶች ስሚንቶ ከመሶቦ እንዲገዙ በማድረግ ኪሳራውን በህዝብ ኃብት ለመሸፈን መሞከሩን የውስጥ ምንጮች ይናገራሉ።

ህወሃት በመሰቦ፣ በትራንስ ፣ በጉና ድርጅቶች በቀጥታ ከአባይ ግድብ ግንባታ ተጠቃሚ ሲሆን፣ የወ/ሮ አዜብ መስፍን የእህት ልጅ የሆኑት የወ/ሮ አኪኮ ስዩም ንብረት የሆነው ኦርኪድ ኩባንያ ደግሞ ማሽነሪዎችን ያቀርባል። የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንም እንዲሁከግድቡ ግንባታ ከፍተኛ ገንዘብ ያገኛል።

The post መሰቦ ስሚንቶ ለአባይ ግድብ ስሚንቶ ማቅረቡን ማቋረጡ ተሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

በ ሲንትልዩስ የሻማ ማብራት እና የጸሎት ስነ-ስርዓት አደረጉ

$
0
0

st 2

(ሐበሻ ራዲዮ) አረመኔው አይሲኤል በሊቢያ 30 ኢትዮጵያውያን አርዶ እና በጥይት ከገደለ በኋላ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውን ከዳር እስከ ዳር ተቆጥተዋል:: ስሞኑን በመላው ዓለም ኢትዮጵያውያን በየሚኖሩበት ሃገር የሻማ ማብራት እና የጸሎት ስነ-ስርዓት አካሂደዋል::

st1

በ ሲንትልዩስ ሐበሻ ራዲዮ ዘጋቢንት የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ የጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በሊቢያ… በደቡብ አፍሪካና በየመን የተገደሉ እና እየተሰቃዩ ያሉ ታስበዋል::ከአንድ መቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ኤርትራውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በተገኙበት በዚህ ስልፍ

ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም በሊቢያ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያን አስታውሰው በአይሲስ ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ተቃውሞ አሰምተዋል:: በደቡብ አፍሪካ እና በየመን እያለቁ ስላሉት ኢትዮጵያውያንም ታስበዋል:: ሁሉም ተናጋሪዎች ያሰመሩበት አንድ ነገር ቢኖር “አንድነት”ን ሲሆን ሁሉም አንድ ሆኖ ለሃገሩና ለሕዝቡ እንዲቆም ጠይቀዋል::አያይዘውም በኢትዮጵያውያኑ መካከል የእምነት ልዩነት ሳይኖር በአንድ ላይ እንዲህ ያለው ትልቅ ዝግጅት መደረጉ ብዙዎችን ያስደሰተ ሲሆን ይህ መተባበርና አንድ መሆን በችግር ጊዜ ብቻ ሳይሆን በደስታውም ጊዜ አንድነቱ እንዲቀጥል ሕዝቡ ጠይቋል:: ከዚህ ጋር አያይዞ አሁድ እለት አፕሪል 26 የሻማ ማብራት ፕሮግራም አንደሚኖር አቶ ኢፍሬም አምደማሪያም አስታውቀዋል

The post በ ሲንትልዩስ የሻማ ማብራት እና የጸሎት ስነ-ስርዓት አደረጉ appeared first on Zehabesha Amharic.

(የሊቢያው ጉዳይ) ‹‹አሁንም የመሄድ ሐሳባችንን አልቀየርንም›› በግፍ የተገደሉት የሠፈር ጓደኞች

$
0
0

በየማነ ናግሽ

አሸባሪው አይኤስ ምንም ከለላ በሌላቸው ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ላይ በሊቢያ ሜዲትራንያን ባህር ዳርቻ ላይ የፈጸመውን አሳፋሪ ድርጊቱን የሚያሳይ ቪዲዮ ከተለቀቀ በኋላ፣ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ተቀባብለውታል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን ይኼ አስደንጋጭ ዜና ያጥለቀለቀው ማኅበራዊ ሚዲያውን ነበር፡፡
yemane Nagish
ሰላሳ ወጣት ኢትዮጵያውያን የዚህ አስከፊ ግፍ ሰለባ በመሆናቸው በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ቁጣ ቀስቅሷል፡፡ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ሥፍራ የሚሰጠው የዳግማይ ትንሳዔ በዓል ዕለት በአሸባሪው በአይኤስ የተለቀቀው ቪዲዮ፣ እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ከተፈጸሙት አሰቃቂ የሽብር ድርጊቶች እጅግ የከፋው ነው እየተባለ ነው፡፡ ይኼ አረመኔያዊ ድርጊት ቀደም ብሎ በሌላ መጥፎ ዜና ከወደ ደቡብ አፍሪካ የታጀበ ነበር፡፡ የደቡብ አፍሪካ በዘር ጥላቻ የተለከፉ ግለሰቦች፣ ‹‹የውጭ አገር ስደተኞች ከአገራችን ይውጡልን፤›› በማለት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ አፍሪካውያን ላይ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናት ምላሾች ተለሳልሰዋል በማለት ብዙዎችን ሲያበሳጭና ሲያናድድ አንድ ሳምንት አልሞላውም ነበር፡፡

ጥቃቱም በዚሁ አላበቃም፡፡ የመንግሥት ለመንግሥት ግንኙነት በልጦባቸዋል እየተባሉ ሲተቹ የቆዩት የመንግሥት ባለሥልጣናት ምላሽም በዚህ አላበቃም፡፡ በሊቢያ የኢትዮጵያውያን ምሥል እየታየ የተለቀቀው ቪዲዮ እውነትነት ጥርጣሬ ገብቶዋቸው ይሁን ወይም በሌላ ምክንያቱ ባይታወቅም፣ ብዙዎቹ በሊቢያ የተፈጸመውን ድርጊት ፈጥነው ማውገዝ አልቻሉም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የአንዱ የአይኤስ ሰለባ እህት የወንድሟን አገዳደል ቀድማ መለየት በመቻሏ፣ በተለይ በተለምዶ ጨርቆስ (ቂርቆስ) በመባል በሚታወቀው አካባቢ ሐዘንና ቁጣ ቀሰቀሰ፡፡

በፀጉሩ ምክንያት ቤተሰቡ በቀላሉ መለየት የቻሉት ኢያሱ ይኩኖአምላክ ነው፡፡ ጓደኛው አብሮ መጓዙን የሚያውቁ የወጣት ባልቻ በለጠ ቤተሰቦችም መጠርጠር ጀመሩ፡፡ እሱም የሰለባው አካል መሆኑ ታወቀ፡፡ ድንኳኑ በጋራ ተጣለ፡፡ የቂርቆስ አካባቢም ድባብ በሐዘን ተዋጠ፡፡ ይህ የሆነው ሰኞ ጠዋት ሲሆን፣ መንግሥት የሰጠው መግለጫ አልነበረም፡፡ በተለይ ‹‹የሟቾቹን ማንነት እናጣራለን፤›› የሚል መግለጫ መባሉ ብዙዎችን አስቆጣ፡፡ በሐዘን ቤት የተገኙት ለቀስተኞች በመንግሥት መግለጫ ማዘናቸውን ገልጸው ነበር፡፡ ማኅበራዊ ሚዲያው ደግሞ ማውገዙን ቀጠለ፡፡ በኢሕአዴግ ደጋፊነታቸው የሚታወቁ ፌስቡከሮች ሳይቀሩ መንግሥትን አወገዙ፡፡ አንዱ፣ ‹‹መንግሥታችን ለመሆኑ የሰብዓዊ ፍጡር ስብስብ ነው ወይ?›› አለ የኢሕአዴግ የምርጫ ቅስቀሳ ሰኞ ማታ ሲተላለፍ አይቶ፡፡ በእርግጥ ወደ ኋላ መንግሥት ስህተቱን ያረመ ይመስላል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሐዘን መግለጫ አሰሙ፡፡ በነጋታውም የአገሪቱ ፓርላማ የሦስት ቀናት ሐዘን አወጀ፡፡ የአገሪቱ ባንዲራም ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ተደረገ፡፡ የመንግሥትን አቋም የለወጠው የማኅበራዊ ሚዲያ ንቅናቄ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት ተሰማ፡፡

የሟች ኢያሱ እናት ወ/ሮ አኸዛ ካሳዬ፣ ልጃቸው ወደ ሊቢያ መጓዙን የሰሙት ዘግይተው ነበር፡፡ የበለጠ ቤተሰቦችም ቢሆኑ አላወቁም ነበር፡፡ ጉዳዩ በሁለቱ አብሮ አደጐችና ጓደኞች በሚስጥር የተደረገ ነበር፡፡ አሁን የሰሙትን መቀበል አቅቷቸዋል፡፡ የሰለባዎቹ ቤተሰቦች በሥርዓቱ አልነበረም የተረዱት፡፡ በፌስቡክና በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ነበር ያወቁት፡፡

ሐዘኑ በዚህ አላበቃም፡፡ በትግራይ ክልል የእንትጮ ከተማ 02 ቀበሌ ነዋሪ የሆነው የ25 ዓመቱ ወጣት ዳንኤል ሐዱሽ ፎቶም ተለይቶ ተለቀቀ፡፡ ዳንኤል ባለፈው ዓመት ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በዲግሪ የተመረቀ ነው፡፡ በ1982 ዓ.ም. በአስመራ ከተማ የተወለደው ዳንኤል፣ የሁለት ዓመት ሕፃን ሆኖ ወደ አገሩ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን ከቤተሰብ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ተወልደ ተክሉ ከተባለው (አሁን ያለበት ሁኔታ አልታወቀም) ጓደኛው ጋር ነበር ወደ ሊቢያ የተጓዘው፡፡ በዚሁ አረመኔያዊ ድርጅት አራተኛ ልጃቸውን ያጡ እናት ወ/ሮ ዛፏ ገብረ ኢየሱስ እንደ ሌሎቹ እሳቸውም የልጃቸውን ወደ ሊቢያ መሄድ አያውቁም፡፡ ሑመራ የስኳር ፋብሪካ ውስጥ እንደሚሠራ ነግሯቸው ነበር የሄደው፡፡ ‹‹በአካባቢው ኔትወርክ አይሠራምና አልደወለም ብለሽ እንዳታስቢ፤›› ብሏቸው ጥር 25 ቀን 2007 ዓ.ም. መሄዱን ይናገራሉ፡፡ ሪፖርተር ያናገራት አንዲት ዘመዱ እንደምትለው፣ ‹‹ሥራ አላገኘሁም፡፡ ሰው በዘመድ ነው ሥራ የሚገባው፡፡ እኔ ዘመድ የለኝም፤›› ብሎ ነበር፡፡ ሑመራና መቐለ ተመላልሶ ሥራ በማጣቱ ምክንያት ስደትን አማራጭ አድርጐ መወሰኑን ትናገራለች፡፡

አሁንም መርዶ

በዚሁ አላበቃም፡፡ ባለፈው ሳምንት እሑድ ጀምሮ በሐዘን በቁጣና በተቃውሞ በተጨናነቀው ቂርቆስ፣ አሁንም ሌላ መርዶ ተሰማ፡፡ ከሦስት ወራት በፊት የካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀደም ብለው ወደ ሊቢያ ያመሩት ሦስት ወጣቶች ከሰለባዎች መካከል መሆናቸው ታወቀ፡፡ ኤልያስ ተጫነ፣ ብሩክ ካሳና በቀለ ታጠቁ ይባላሉ፡፡ ሁሉም ኑሮ የከበዳቸውና ምንም የሥራ አማራጭ ያጡ እንደነበሩ የሠፈር ጓደኞቻቸው ይናገራሉ፡፡

ከእነዚህ መካከል የበቀለ ታጠቁ የአጐት ልጅ የሆነውን ታምራት ታረቀኝን ሪፖርተር አናግሮት ነበር፡፡ በቀለ ከወልቂጤ ነው የመጣው፡፡ ቤተሰቡ አሁንም ድረስ እዚያው ነው ያሉት፡፡ ሲሄድ አልነገረውም፡፡ መተማ ዮሐንስ እንደደረሰ ግን ደውሎ 11,000 ብር እንዲልክለት ይነግረዋል፡፡ ዱብ ዕዳ ሆኖበት አገር ቤት ልጆች በሰንበት ትምህርት ቤት ተሰብስበው ቲሸርት ያሳትሙ ነበር፡፡ ኃላፊውም በቀለ ራሱ ነበር፡፡ በቀጣይ ዓመት ተመሳሳይ ነገር ለመሥራት ያተረፉትን 3,600 ብርና የቀረውን ጨምሮ ይልክለታል፡፡ ቀጥሎም ከሁለት ቀናት በኋላ ሱዳን ካርቱም ላይ ሆኖ 34,000 ብር እንዲልክለት በደላሎቹ ያስነግራል፡፡ ካልሆነም ወንድሙ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ይነግሩታል፡፡ ሊያገናኙት ግን አልቻሉም፡፡ ወልቂጤ ድረስ በመሄድ ለወላጆቹ ነግሮ ከዚያም ከዚህም ተበድሮ አሰባስቦ አሁንም ሕይወቱን ለማትረፍ ይልክለታል፡፡ እንደምንም ደውሎ አንድ ጊዜ ድምፁን ሰምቷል፡፡ ከዚያ በኋላ አላገኘውም፡፡ አሸባሪው አይኤስ ይህንን ዘግናኝ ድርጊት የፈጸመ ዕለት እሑድ ታምራት አገር ቤት ነበር፡፡ ቀደም ብሎ ያያትን ልጅ ለማጨት ከጓደኛው ጋር ነበር የሄደው፡፡ እንደ አገሩ ባህል ሽማግሌዎች የላከ ሲሆን፣ ከመካከላቸው የሟቹ የወጣት በቀለ አባት አቶ ታጠቁ ይገኙበታል፡፡

እሑድ ከሰዓት በኋላ ‹‹ሰጠናችሁ›› ተብሎ እዚያው የደስ ደስ ፍንጥር አድርገው ነበር ያደሩት፡፡ ሰኞ እዚህ እንደመጣ ይህንን መጥፎ ዜና ታክሲ ውስጥ ይሰማል፡፡ ይደነግጣልም፡፡ ‹‹ቀልቤ ልክ አይደለም፤›› ይላል፡፡ በቀለ መሄዱን ከእሱ ውጪ እምብዛም ሰው አያውቅም ነበር፡፡ ለጓደኞቹ በቀለ እንደሄደ ነግሯቸው በፌስቡክ እንዲያዩ ይጠይቃቸዋል፡፡ ‹‹እኔ ማየት አልቻልኩም፡፡ ድፍረቱም የለኝም፤›› ይላል፡፡ ከዚያ ሐሙስ ጠዋት ሌላ አጐቱ ዘንድ በመሄድ እሱም ከሌሎቹ ጋር እንደሞተ ይናገራል፡፡ በኃላፊነት ከአገር ቤት አስመጥቶ በዕዳ የላከው ልጅ ሐዘን በርትቶበት እንባ እየተናነቀው፣ ከዚያ ውጪ መናገር አልቻለም፡፡ የሦስቱ ወጣቶች ሐዘን የተከናወነው በአንድ ድንኳን ሲሆን፣ የሌሎችም ታሪክ አሳዛኝና ተመሳሳይ ነው፡፡ አንዳች ዕርዳታና ድጋፍ ካልተደረገላቸው በቀላሉ የሚፅናኑ አይመስልም፡፡

በአካባቢው ከተቀመጡት ወጣቶች መካከል መናገር የሚፈልገው ነገር እንዳለ እያሳበቀበት ነው፡፡ ‹‹እባካችሁ ሕገወጥ ስደተኞች አትበሉ፡፡ ልጆቹ ሕገወጥ አይደሉም፡፡ እንጀራ ፈላጊ ናቸው፡፡ ሱዳን ኤምባሲ ከፌዴራል ፖሊስ ጽሕፈት ቤት መቶ ሜትር አይርቅም፡፡ በሕጋዊ መንገድ ነው የሚወጡት፡፡ በሰላምና በስካይ ባስ ነው ተሳፍረው በሱዳን የወጡት፤›› ይላል የሰለባዎቹ ጓደኛ ወጣት ያሬድ አሰፋ፡፡ ‹‹እዚህ አካባቢ ያለው ሰው በሙሉ መሥራት ይፈልጋል፡፡ መንጃ ፈቃድ ማውጣት ይፈልጋል፡፡ አልቻለም፡፡ ክፍያው ቀላል አይደለም፡፡ ለመንግሥት ንገሩልን፡፡ ይቀንስልን፤›› በማለት በተስፋ መቁረጥ መንፈስ ተናግሯል፡፡

የሠፈሩ ልጆች ብሎኬት አምርቱ ተብለው ለሥራ ተሰማርተው እንደነበር ያስረዳል፡፡ የሚሠሩበት የኮንዶሚንየም ሳይት ቃሊቲ አካባቢ በመሆኑ የባሰ ዕዳ አመጣችሁ ተብለው የመንግሥት ትራንስፖርት ተከልክለው በራሳቸው እንዲጓዙ መደረጋቸው፣ በዚህም ተስፋ ቆርጠው ሥራውን እንዳቆሙ ይናገራል፡፡

‹‹እኛም ለመሄድ ነው የምናስበው››

ሮቤል ደፋሩ የኤልያስና የብሩክ ጓደኛ ነው፡፡ ከዋሊያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ እስከ ስለሺ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አብሮአቸው ተምሯል፡፡ በ2002 ዓ.ም. በኮብልስቶን ሠልጥነዋል፡፡ ‹‹ነገር ግን ቁጭ ብለናል፤›› ይላል፡፡ ‹‹እኛም ለመሄድ ነው የምናስበው፡፡ ልንከተላቸው ነበር፤›› በማለቱ ‹‹አሁንስ ምን ታስባላችሁ?›› የሚል ጥያቄ ቀረበለት፡፡ ሮቤል ብቻ ሳይሆን አጠገቡ የነበሩት ሌሎችም የሠፈሩ ልጆች አንድ ላይ፣ ‹‹አሁንም እንሄዳለን፡፡ ምንም ተስፋ የሚሰጥ ነገር የለም፡፡ ዕድላችንን እንሞክራለን፤›› አሉ፡፡

በአሸባሪዎች ሊቢያ ውስጥ የተጨፈጨፉ ጓደኞቻቸውን እየተመለከቱ አሁንም ለመሄድ ያስባሉ፡፡ እዚህ አገር ባለው ነገር ተስፋ መቁረጣቸውን ይናገራሉ፡፡ ሄደው ጣሊያንና ጀርመን ገብተው ያለፈላቸው እንዳሉም ያስረዳሉ፡፡

አሸናፊ ቦጋለ የተባለው ወጣት ከመካከላቸው በጣም ተስፋ የቆረጠ ይመስላል፡፡ ‹‹እኛ ምርጫ በመጣ ቁጥር ነው መንግሥት የሚፈልገን፤› በማለት እሱም በኮብልስቶንም፣ በኤሌክትሪክም ሠልጥኖ ምንም መሥራት አለመቻሉን ይናገራል፡፡ ‹‹አንዳንድ ጊዜ የምናገኛትን ብር አጠራቅመን እንሄዳለን፡፡ ሕጋዊ መንገድ ተዘጋ፡፡ እዚህ ያለው ወጣት በሙሉ በዚሁ መንገድ ለመሄድ የተዘጋጀ ነው፤›› ይላል፡፡

ሪፖርተር በአካባቢው ተዟዙሮ ያነጋገርናቸው ወጣቶች ጥያቄያቸው ተመሳሳይ ነው፡፡ ምንም የሥራ አማራጭ እንደሌላቸው ይናገራሉ፡፡ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ወሮአቸዋል፡፡ አንድ ስሙን መጥቀስ ያልፈለገ ወጣት፣ ‹‹ሌላስ ይቅር እባካችሁ መንግሥት ሊቢያ በአደጋ ላይ ያሉትን ሕይወት ለመታደግ ምን እየሠራ እንደሆነ ጠይቁልን፤›› ይላል፡፡ ‹‹አገር ውስጥ ስላለው ችግር ብናገር ምንም አዲስ ነገር ስለሌለው ባልናገር ይሻላል፤›› በማለት ተንሰቀሰቀ፡፡

ዓምደ ዲኖ የተባለው ሌላው ጓደኛው ግን ጣልቃ ገብቶ፣ ‹‹ስብሰባ ጠርተው ሃምሳ ሃምሳ ብር ሰጥተው ወጣቱ እየሠራ ነው የሚል ፕሮፓጋንዳ ከሚሠሩብን ምን አለ ሥራ ቢፈጥሩልን?›› በማለት ይጠይቃል፡፡

ዳዊት ላቀው የተባለው ሌላው ወጣት ግን ችግሩ ከመንግሥትም አቅም በላይ እንደደረሰ ይናገራል፡፡ ‹‹ምንም ዓይነት የሥራ ዕድል የለም፡፡ የሚወራውና መሬት ላይ ያለው ተጨባጭ ነገር ለየቅል ነው፡፡ ያልፍልናል ብለው ነበር የሄዱት፡፡ አሁን ግን ከቤተሰብም አልፈው አገር አሳዝነዋል፡፡ ከዚህ በፊት ብዙ ሰው ተሳክቶለታል፡፡ ያንን ስኬት አይተው ነው የተሳሳቱት፤›› ይላል፡፡ እሱም ከመንግሥት የሚጠብቀው አንዳች ነገር የለም፡፡

‹‹ምን ማድረግ እንደሚቻል አይታወቅም፡፡ መንግሥትም የሚቻለው ነገር አይመስለኝም፡፡ ስደት ይብቃ ብለህ የምታስቆመው አይደለም፡፡ ይህንን ያህል ሥራ አጥ ወጣት ማብቃት ከባድ ነው፡፡ መንግሥት እንዴት እንደሚቋቋመው አላውቅም፡፡ ከባድ የቤት ሥራ ነው ያለበት፤›› ብሏል፡፡

ሌላ ‹‹ሕገወጥ›› የሚለው አገላለጽ እጅግ ያስከፋው ወጣት፣ ‹‹ደልቶት ወይም ከመንግሥት ጋር ተጣልቶ አይደለም የሄደው፡፡ ይኼ ነገር ቢታረም ደስ ይለኛል፤›› ብሏል፡፡ የአንድ የመንግሥት ባለሥልጣን አነጋገርንም በመተቸት ‹‹እባክህ ምን አለበት አንድ የሚያሳርፍ ቃል ቢጠቀም፤›› ብሏል፡፡

‹‹ያመለጠው››

በአካባቢው ከተገኙት የሟቾች ጓደኞች መካከል ወጣት ልዑል ሰገድ ንጉሥ አንዱ ነው፡፡ ጉዳት ከደረሰባቸው ጓደኞቹ በፊት ከሌሎች ሦስት የሠፈር ልጆች ጋር ነበር ወደ ሊቢያ የተጓዘው፡፡ ታሪኩን ይናገራል፡፡ ከአዲስ አበባ ትኬት ቆርጠው ባህር ዳር ይደርሳሉ፡፡ ከዚያም መተማ ከደላሎች ጋር ተገናኝተው ወደ ገለባት ሄዱ፡፡ ገለባት ላይ የኢትዮጵያና የሱዳን ሲም ካርድ ተሰጣቸው፡፡ ሁለቱም ይሠራሉ፡፡ ከመተማ ወደ ካርቱም 12,000 ብር ተጠይቀዋል፡፡ ብሩ የሚከፈለው ካርቱም ሲገባ ነው፡፡ እዚህ ያለ ቤተሰብ ነው የላከለት፡፡ የሚቀበሉዋቸው ደላሎች ሱዳናውያን ሲሆኑ፣ አልፎ አልፎ ሐበሾችም አሉ፡፡ ጉዞ በመኪና በመሆኑ በሌሊት ነው፡፡ ገዳራት የሚባል ቦታ ላይ 15 ቀናት ያህል ቆይተዋል፡፡ ‹‹ምንም ምግብ አይሰጡንም፡፡ በረሃብ አልቀን ነበር፤›› ይላል፡፡

ከዚያ ካርቱም ላይ ከሚጠብቃቸው ልጅ ጋር ተገናኝተው፣ ከሌሎች በጐንደር አቋርጠው ከመጡ ሦስት ልጆችም ጋር ተቀላቅለው ሰባት ሆኑ፡፡ በልጁ ቤት አራት ቀናት ቆዩ፡፡ ከዚያ ወደ ሊቢያ ተነሱ፡፡ 28,000 ብርም ተጠየቁ፡፡ ‹‹የተጓዝነው በፒካፕ ሲሆን፣ ደህና ብር የከፈሉት ጋቢና ሌሎቻችን ከ30 በላይ የምንሆን ከኋላ ተጫንን፤›› ይላል፡፡

ለሁለት ቀናት ከተጓዙ በኋላ ሊቢያ ድንበር ላይ የሱዳን ፖሊሶች ይይዟቸዋል፡፡ ፖሊሶቹ ከደላሎች ጋር እያወሩ እንዲከፈላቸው ቢጠይቋቸው አልተስማሙም፡፡ ከዚያ ሦስት ጊዜ አስቁመው ጠየቁአቸውና አልተስማሙም፡፡ ቀጥሎ ወደ ፖሊስ ጣቢያ አስገቡዋቸው፡፡ እስር ቤቱ ውስጥ ብዙ ኤርትራውያንንና ኢትዮጵያውያንን ተመልክተዋል፡፡ አድራሻቸው አዲስ አበባ መሆኑን ተናግረው ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ አምስት አምስት ጅራፍ ተገርፈው ወጡ፡፡

ከዚያ ለ15 ቀናት ‹‹ጉዳ›› የሚባለው ማረሚያ ቤት ላይ ታሰሩ፡፡ በቀን ሁለት ሁለት ቂጣና የተቀቀለ ምስር ይሰጡዋቸዋል፡፡ ‹‹እዚያ ውስጥ ብዙ ነገር ብዙ ፈተና ይገጥምሃል፤›› በማለት ለመናገር ያዳገተው ነገር እንዳለ ማስተዋል ይቻላል፡፡ ከዚያ ወደ ካርቱም መለሱዋቸው፡፡ ስደተኞች ካምፕ ውስጥ ገቡና ወደ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ወሰዱዋቸው፡፡ እነሱም መክረውና የይለፍ ወረቀት ሰጥተው ወደ መተማ መለሱዋቸው፡፡

ልዑል ሰገድ እንደሚለው በዚሁ ጉዞ ላይ ምንም ዓይነት ሕጋዊ መታወቂያም ሆነ ፓስፖርት መያዝ አይቻልም፡፡ ለዚህም ነው መንገድ ላይ አደጋ ሲገጥም ሰው ማንነቱ የማይታወቀው፡፡ ሁለቱ ጓደኞቹ ከመተማ ተመልሰው ወደ ሊቢያ የሄዱ ሲሆን፣ እሱና ጓደኛው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡ አንዱ ጓደኛው ጣሊያን ሲገባ፣ አንዱ ወደ ጣሊያን ለመሻገር መርከብ የሚጠበቅበት ሥፍራ ላይ መሆኑን ነግሮታል፡፡ አሁን የደረሰውን አደጋ እያሰበ ‹‹ለበጐ ይሆናል›› በማለት ታሪኩን ቋጨ፡፡ ዋይታው ግን ቀጥሏል፡፡

Source: Ethiopian Reporter Newspaper

The post (የሊቢያው ጉዳይ) ‹‹አሁንም የመሄድ ሐሳባችንን አልቀየርንም›› በግፍ የተገደሉት የሠፈር ጓደኞች appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live