Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

አይሲስ በሊቢያ ተጨማሪ ኢትዪጲያንን መያዙን ከአይሲስ ያመለጠው ኢትዪጲያዊ ለቪኦኤ ገለጸ

$
0
0

እኛን ከአይሲሲ ያዳኑን ኢትዪጲያዊያን ሙስሊሞች ናቸው፡፡ በሀገራችን በፍቅር ነው የኖርነው ክርስቲያኖቹን ለይታችሁ አትወስዱም በማለት ሲል ከአይሲስ ያመለጠው ተናግረዋል::

(Photo File)

(Photo File)


ቪኦኤ በዛሬው እለት ባስተላለፈው ስርጭት ከሊቢያ ያነጋገረው ኢትዪጲያዊ ቁጥራቸው ያልታወቀ ኢትዪጲያዊያን በአይሲስ መያዛቸውን ገለጸ፡፡

እሱም በአይሲሶች ተይዞ እንደነበር የገለጸው ነዋሪ ክርስቲያንና ሙስሊሙን ለያይተው ሊወስዱ ሲሉ ኢትዪጲያዊያን ሙስሊሞቹ ለይታችሁ እነሱን አትወሱም እኛንም አብራችሁ እረዱን፡፡ በሀገራችን ሙስሊምና ክርስቲያን ተፈቃቅረን ነው የኖርነው ሊቢያ ላይ ታሪካችንን አናበላሽም ክርስቲያኖቹን ብቻ ነጥላችሁ አትወስዱም በማለት እንዳስጣሏቸው ለቪኦኤ ገልጸዋል፡፡

የቪኦኤው ጋዜጠኛ ሰለሞን አባተ ተጠያቂውን አንተ እምነትህ ምንድን ነው ሲል ጠየቀው እሱም ክርስቲያን መሆኑን የገለጸለት ሲሆን ቤንጋዚ ላይ ከአይሲሲ ጩሄው ያስጠሏችሁ ኢትዪጲያዊያን ሙስሊሞች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የኢትዪጲያ ሙስሊሞች እኛን ለማዳን በሊቢያ ህይወታቸውን አሳልፈው እየሰጡ ለኢትዪጲያን ክርስቲያንኖች ብዙ ብዙ ነው የሚያደርጉልን፡፡ እስላም ክርስቲያን ሳንባባል በፍቅር ነው የምንኖረው በማለት አይሲስ ያለየውን የኢትዪጲያዊያን የሊቢያን አስገራሚ ትንቅንቅ ለቪኦኤ ተርክዋል፡፡

በሌ በኩል አይሲስ በዛሬው እለት ቁጥራቸው ያልታወቁ ኢትዪጲያዊያንን አፍኖ መውሰዱና እነሱም በአሁኑ ጊዜ ተደብቀው እንዳሉ ገልጸዋል፡፡ ቪኦኤ ከአይሲስ ካመለጠው ስደተኛ ጋር ያደረገውን ቆይታ ያድምጡ::

The post አይሲስ በሊቢያ ተጨማሪ ኢትዪጲያንን መያዙን ከአይሲስ ያመለጠው ኢትዪጲያዊ ለቪኦኤ ገለጸ appeared first on Zehabesha Amharic.


የዛሬ ቀትር –በጨርቆስ ሀዘን ቤት

$
0
0

ከኤልያስ ገብሩ

——
‹‹ልጆቼ፣ እኛ በታረድን››
በጨርቆስ የነበሩ አንድ እናት ለቅሶ
‹‹ወያኔ አታለለን … ወያኔ ሌባ …ይለያል ዘንድሮ …ወይኔ ወይኔ››
በጨርቆስ የነበሩ ወጣቶች ያሰሙት ተቃውሞ እና ሀዘን
—-

ከሰሞኑ በአይሲስ በዘግንኝ ጭካኔ አንገታቸው በተቀሉት ሁለት ኢትዮጵያዊ ወጣቶች ወገኖቼ ቤት ሀዘን ለመድረስ ወደጨርቆስ ረፋድ ላይ አምርቼ ነበር፡፡
yilikal
ከሜክሲኮ ታክሲ ብይዝም ወደጨርቆስ የሚወስደው መንገድ በፌዴራል ፖሊሶች በመዘጋቱ በውስጥ ለውስጥ መንገድ ታክሲው ተጉዞ ጨርቆስ ቤተ/ክርስቲያን ጋር ተሳፋሪዎቹን አደረሰን፡፡ የታክሲ ፌርማታው አከባቢ በበርካታ ፌዴራል ፖሊሶች ተከብቧል፡፡ ገሚሶቹ ፖሊሶች ባዶ እጃቸውን ሲሆኑ ጥቁር ዱላ የያዙም ነበሩ፡፡ አንድ ፖሊስ ማይክራፎን ይዞም ተመልከቻለሁ፡፡

ብዛት ያላቸው ወንድና ሴት ሀዘንተኞች፣ ወደለቅሶ ቤቱ እያለቁሱና የተለያዩ የተቃውሞ ድምጾችን እያሰሙ በእርጋታ ነበር የሚሄዱት፡፡ በሰልፉ መሃል የነበሩ ወጣቶች የተቃውሞ ድምጽነ በቃላት ጮክ ብለው ከማሰማት ባለፈ ሁለት እጆቻቸውን በማቆላለፍ ወደላይ ሲያደርጉም ነበር፡፡ ‹‹ወያኔ አታለለን … ወያኔ ሌባ …ይለያል ዘንድሮ … ወይኔ ወይኔ›› የሚሉት ከሰማኋቸው የተቃውሞና የሀዘን ድምጾች መካከል ይገኛሉ፡፡ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮችም በተደጋጋሚ ተደምጠዋል፡፡

ወደለቅሶ ቤቱ ድንኳን ጋር ስንደርስ ሁሉም ባለበት ቆሞ እንባውን አውጥቶ የሚያለቅሰው እያለቀሰ እና በሀዘን ስሜት ተውጦም ‹‹ወይኔ ..ወይኔ›› የሚለውም ሀዘኑን ገለጸ፡፡ በርካታ ሰዎች በሞባይላቸው የሀዘን ድባቡን በቪዲዮ ካሜራም ሲቀርጹ ነበር፡፡

በዚህም ስፍራ በርካታ ፖሊሶች ከሀዘንተኛው በቅርብ ርቀት ሆነው ሁኔታውን ይከታተላሉ፡፡ አንዱ ፖሊስ ሞባይሉን አውጥቶ በሥርዓቱ ላይ የሚደመጠውን የተቃውሞ ድምጽ ሲቀርጽም አስተውያለሁ፡፡ እዚህ መሳሪያ የታጠቁ ፖሊሶችም ነበሩ፡፡ ፊታቸው ላይ ሀዘን የሚነበብባቸው ጥቂት ፖሊሶችን መኖራቸውንም ታዝቤያለሁ፡፡

አንዲት እናት ከጎኔ ቆመው ምርር ብለው እንዲህ ሲያለቅሱ ነበር፡- ‹‹ ልጆቼ ታረዳችሁ? እናንተ እኮ የእናት እና አባቶቻችሁ ብቻ አይደላችሁም፤ የእኛም ልጆች ናችሁ! ልጆቼ እኛ እንታረድ፣ እኛ ምን እናደርጋለን …››

በቦታው የነበርን ድጋሚ እንባችንን መቆጣጠር አልተቻለንም፡፡ …ብቻ እጅግ ያሳዝናል፡፡

ወዲያው አንድ ፒክአፕ የፌዴራል ፖሊስ መኪናም ፖሊሶችን ጭኖ በስፍራው ደረሰ፡፡ ዕድሜዋን ሙሉ የጨርቆስ ነዋሪ የሆነች አንድ አክስቴን ወንድ ልጇንና ባለቤቱንም አገኘኋቸው፡፡ ሁለቱንም ሟቾች ከነቤተሰቦቻቸው ያውቋቸዋል፡፡ አክስቴ ስለልጆቼ የሚያውቁትን እያለቀሰች ጥቂት አወጋችኝ፡፡

በርካታ ሰዎች ከተለያየ ቦታ በመምጣት በለቅሶ ቤቱ ሀዘናቸውን ገልጸዋል – እያለቀሱ ጭምር፡፡ የኢትዮጵያ ቡናን እግር ኳስ ቡድን ማሊያ የለበሱ በርካታ ሴት እህቶቻችን በለቅሶ ቤቱ ደርሰው ሲያለቅሱ በለቅሶ ቤቱ ድጋሚ የለቅሶ ጩኸትም ተደመጠ፡፡

የሁለቱ ሟች ወገኖቻችን ፎቶ ግራፍ፣ በትልቅ ተሰርቶ ወደድንኳን ከመገባቱ በፊት በሁለት ቦታዎች ላይ ተቀምጠዋል፡፡ በድንኳኑ በር ላይ ‹‹ሉዓማዊነት በሁሉም ቦታ ያሉ ወገኖችን መብት ማስጠበቅ ነው›› የሚል ይዘት ያለው ባነር ተሰቅሎ ይነበባል፡፡ የለቅሶ ቤቱን አካባቢ ከቀኑ 08፡30 ሰዓት ላይ ለቅቄ ስሄድም በርካታ ፌዴራል ፖሊሶች በተለያዩ ቦታዎች ላይ ቆመው እና ተቀምጠው ነበር፡፡ በግፍ አንገታቸው ለተቀሉ ወገኖቻቸው እጅግ በማዘን፣ እርማቸውን ለማውጣት እና ሀዘን ለመድረስ የሚሄዱ ወገኖችን በፖሊስ በቅርብ ርቀት አስከብቦ ማስጨነቅ ግን ለምን?

ለማንኛውም የወገኖቻችንን ነፍስ ፈጣሪ በገነት ያኑርልን!

The post የዛሬ ቀትር – በጨርቆስ ሀዘን ቤት appeared first on Zehabesha Amharic.

የISIS ሰለባ ከሆኑት መካከል አንዱ የሆነው ወንድማችን ዳንኤል ሓድሽ

$
0
0

አይሲኤል በሊቢያ አንገታቸውን ከቀላቸው እና ከገደላቸው ኢትዮጵያውያን መካከል የ3ኛው ኢትዮጵያዊ ማንነት ታውቋል:: የሌሎቹም ማንነት እንዲሁ ማጣራቱ እየቀጠለ ሲሆን በአይሲኤል ሕይወቱን ሊቢያ ውስጥ አንገቱን በመቀላት ያጣው ወንድማችን ዳንኤል ሓድሽ እንደሚባል በሶሻል ሚዲያዎች የተሰራጩት መረጃዎች አመልክተዋል:: ከትግራይ የመጣው ወጣቱ ዳንኤል ፎቶ ግራፉ የሚከተለው ነው::
hadish

dan El dan El

The post የISIS ሰለባ ከሆኑት መካከል አንዱ የሆነው ወንድማችን ዳንኤል ሓድሽ appeared first on Zehabesha Amharic.

ፓትርያሪክ አቡነ መርቆሬዎስ በአይሲኤል; በደቡብ አፍሪካውና በየመን ላለቁት ወገኖች ያስተላለፉት መንፈሳዊ መልዕክት

“በወገኖቼ ላይ የተፈፀመዉ ድርጊት አሳዝኖኛል አስቆጥቶኛልም”–ቴዲ አፍሮ

$
0
0

teddy afro
ከቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የተላከ መልዕክት

ሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም በተለያዮ ሀገራት በሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን ላይ እና የሌላ ሀገር ተወላጅነት ባላቸዉ ንፁሀን ዜጉች ላይ በተፈፀመዉ አሰቃቄ የግድያ ወንጀል አዝነን ሳናበቃ ፦ በሊቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመዉን እጅግ አሳዛኝ ፤ አረመኔያዊ ተግባር ሳይና ስሰማ የተሰማኝን ሐዘን ለመግለፅ ቃላትም ሆነ ቋንቋ ያጥረኛል።

እንኳን የኔ በሚሉት የራስ ወገን ይቅርና ክቡር በሆነዉ የትኛዉም የሰዉ ልጅ ፍጡር ላይ እንዲህ አይነቱ ፍፁም ርሕራሔ የሌለዉ ኢሰብአዊ ተግባር ሲፈፀም ማየትም ሆነ መስማት የሚፈጥረዉን ጥልቅና መሪር የሀዘን ስሜት ለመረዳት ወገን ሆኖ መገኘት ብቻ ሳይሆን ሰዉ ሆኖ መፈጠር ይበቃል።

እንደ ሰዉ ሰዉ በመሆኔ ብቻ ሳይሆን በተለይ እንደ ኢትዮጵያዊነቴ በወገኖቼ ላይ የተፈፀመዉ ድርጊት አሳዝኖኛል አስቆጥቶኛልም።
ከመቼዉም ጊዜ በበለጠም እኛ ኢትዮጵያዊያን ማንኛዉም አይነት ልዮነት ሳይወስነን በግፍ ለተጠቁት ወጉኖቻችን በአንድነት ቆመን ወገናዊነታችንን የምናሳይበት ወቅት አሁን ነዉ።

የኛ አለመግባባትና አንድ አለመሆን እንዴህ ላለ መጠቃት አሳልፎ ሲሰጠን ዛሬ አዲስ ባይሆንም መደጋገሙ እና ተጠናክሮ መቀጠሉ ግን እዚህጋ ይበቃል ልንል ይገባል።

ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን መንካት የእሳት ዘንግ መጨበጥ እንደሆነ የሁለተኛዉ የዓለም ጦርነትን ጨምሮ በዘመናት የቀደመ ታሪክ የታየና ወደፊትም የሚቀጥል የመሆኑ ሐቅ ከአለት የፀና ነዉ። ይህም ቃል ኪዳን በልኡል እግዚአብሔር የታተመ የማይቀየር ቃል ነዉ።

ላስተዋለዉ የምስራቹ ደጅ ላይ ሲደረስ ይህ የጣሩ ድምጽ ጅማሬ ስለሆነ የኢትዮጵያ ብርሀን ዓለምን ሊሞላ የተጣሏትም፤ ያዋረዷትም ፈፅመዉ ሊከደኑ እጅግ ጊዜዉ ቀርቧልና አይዟቹሁ ፅኑ ። ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ አንድነታችን ሊጠናከር የሚገባበትም ጊዜ አሁን ነዉ።

በመጨረሻም በግፍ የተገደሉትን ንፁሀን ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችንን ነፍስ እግዛአብሔር በቀኝ መንግስቱ እንዲያሳርፍ እየተማፀንኩ ለሟች ቤተሰቦችና ለመላዉ ኢትዮጵያን ወገኖች መፅናናትን እመኛለዉ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
ፍቅር ያሸንፋል
ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)

The post “በወገኖቼ ላይ የተፈፀመዉ ድርጊት አሳዝኖኛል አስቆጥቶኛልም” – ቴዲ አፍሮ appeared first on Zehabesha Amharic.

በሂውስተን ቴክሳስ ኢትዮጵያውያኑ በሊቢያ, በደቡብ አፍሪካ እና በየመን ያለቁትን ኢትዮጵያውያን በሻማ ማብራት አሰቡ

$
0
0

ዛሬ ማምሻውን በሂውስተን ቴክሳስ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በመሰባሰብ አይሲ ኤል ሊቢያ ውስጥ የቀላቸውን; እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ በስደት ሥራ ላይ የነበሩትን እና የተገደሉትን ኢትዮጵያውያን እና በየመን እየተገደሉ ያሉትን ኢትዮጵያውያን በማሰብ ታላቅ የሻማ ማብራት እና የመታሰቢያ ፕሮግራም ተካሂዷል:: በዚህ ስነስርአት ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል -በፎቶ ግራፍ ይመልከቱ:: ይህ የመታሰቢያ; የጸሎት እና የሻማ ማብራት ምሽት በተለያዩ ከተሞች በቀጣይ ቀናት ይቀጥላል::
texas

texas 1

texas 3

texas 5

The post በሂውስተን ቴክሳስ ኢትዮጵያውያኑ በሊቢያ, በደቡብ አፍሪካ እና በየመን ያለቁትን ኢትዮጵያውያን በሻማ ማብራት አሰቡ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከ33 በላይ አርቲስቶች በአንድ ላይ በመሰብሰብ በሊቢያ አይሲኤል ኢትዮጵያውያን ላይ ያደረሰውን ግድያ አወገዙ

$
0
0

ethiopian artist 1
artist

abeba

tem

temu

siyum

mesfin bekele

(ዘ-ሐበሻ) በሰሜን አሜሪካ የሚገኙትና ከ33 የሚበልጡት ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች በአንድ ላይ በመሰባሰብ በቨርጂኒያ Falls Church በመገኘት አይሲኤል በኢትዮጵያውያኑ ላይ ያደረሰውን ግድያ አወገዙ:: ለወገኖቻቸው ያላቸውን ክብርና ፍቅርም ገለጹ::

በዚህ ኢትዮጵያውያኑን ለማሰብ ከተሰባሰቡት አርቲስቶች ውስጥ
1ኛ. አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ
2ኛ. አርቲስት ፋሲል ደመወዝ
3ኛ. አርቲስት አበባ ደሳለኝ
4ኛ. አርቲስት ትዕግስት ፋንታሁን
5ኛ. ኮሜዲያን ክበበው ገዳ
6ኛ. አርቲስት አብዱ ኪያር
7ኛ. አርቲስት አብዮት (ካሳነሽ)
8ኛ. አርቲስት ሕብስት ጥሩነህ
9ኛ. አርቲስት ጌራወርቅ ነቅአጥበብ
10ኛ. አርቲስት መስፍን በቀለ
11ኛ. አርቲስት ስንታየሁ ሂቦንጎ
12ኛ. አርቲስት ዳንኤል ወልደገብርኤል
13ኛ. ዲጄ ሉዳ
14ኛ. አርቲስት ደሳለኝ መልኩ
15ኛ. የሙዚቃ ገምጋሚና ጋዜጠኛ ተቦርነ በየነ
16ኛ. አርቲስት ተመስገን ገ/እግዚአብሔር
17ኛ. ትንሹ ጥላሁን
18ኛ. ትንሹ ቴዲ አፍሮ
19ኛ. አርቲስት አሸብር
20ኛ. አርቲስት ጠረፍ (ቴሪ)
21ኛ. አርቲስት እንዳለ አድምቄ
22ኛ. አርቲስት ስዩም ተፈራ እና ስማቸው ያልተገለጸ ከ33 በላይ አርቲስቶች ተገኝተዋል::

እነዚሁ ተወዳጅ አርቲስቶች በተጨማሪም በቅርቡ በሊቢያ በደቡብ አፍሪካ በየመን እና በሌሎችም ሃገራት ሕይወታቸው በስደት እየጠፋ ላሉት ኢትዮጵያውያን የሕሊና ጸሎት አድርገዋል ሲል የዘ-ሐበሻ ዘጋቢ ጠቁሟል::

The post ከ33 በላይ አርቲስቶች በአንድ ላይ በመሰብሰብ በሊቢያ አይሲኤል ኢትዮጵያውያን ላይ ያደረሰውን ግድያ አወገዙ appeared first on Zehabesha Amharic.

መንግስት በአ.አ የጠራው ሰልፍ ወደ ተቃውሞ ተለወጠ * ሴቶች እና አዛውንቶችን ሳይቀር ደብደበ * አስለቃሽ ጭስ ተተኮሰ * የሕዝቡ ቁጣ አልበረደም

$
0
0

የአይ ኤስ አይ ኤስን ጭካኔ ለመቃወም ሰልፍ የወጡ ኢትዮጵያውያን አገራቸው ውስጥ ሌላ ጭካኔ ገጥሟቸዋል

(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ለፖለቲካ ጥቅም ማግኛ ሲል የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ወደ ተቃውሞ ተለወጠ:: ማንኛውም ሕዝብ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳያደርግ የሚከለከለው ኢሕአዴግ ሕዝብን ወዳጅ መስሎ ቢቀርብም በመስቀል አደባባይ ዳግም ሕዝብን በመደብደብ ዳግም ራሱን ማዋረዱን ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ አመልክቷል::

agazi

TPLF 1

tplf 2

TPLf 3

በዛሬው ኢሕአዴግ በጠራው ሰልፍ ላይ ሕዝቡ ተቀላቅሎ በመግባት ተቃውሞውን በመንግስት ላይ ያሰማ ሲሆን “እኛን ከምትደበድቡ አይሲስን ደብድቡ” “ወታደር ዳርፉር ከምትልኩ ሊቢያ ላኩ” እያለ ተቃውሞውን አሰምቷል:: “ወኔ የሌለው የሃገር ሸክም ነው” እያለ ተቃውሞውን ያሰማው የአዲስ አበባ ሕዝብ ከደህንነቶች ጋር ግብግብ የገጠመ ሲሆን በዚህም በርካታ ወጣቶች በፌደራል ፖሊሶች ተይዘው መታሰራቸው ታውቋል::

የአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከልን እንደ እስር ቤት በመጠቀም ስርዓቱ በርካታ ወጣቶችን ያሰረ ሲሆን በቆመጥ ሴቶችን እና አዛውንቶችን ሳይለይ ቀጥቅጧል:: አስለቃሽ ጭስ በመጠቀምም ተቃውሞውን ለማብረድ ጥሯል::

በጨርቆስ፣ መስቀል አደባባይ፣ ተክለሃይማኖት እና ሌሎችም አካባቢዎች ተቃውሞው እንደቀጠለ ይገኛል::

በሰልፉ ላይ ንግግር ለማድረግ የመጡት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሊናገሩ ሲሉ ሕዝቡ በጩኸት ተቃውሞውን
‹‹ውሸት ሰለችን ሰለችን!››
‹‹ዋ! ዋ! ዋ!››
‹‹ታርዷል ወገኔ!››
‹‹መንግስት የሌለው እዚህ ብቻ ነው!›› ሲል ተቃውሞን ከመግለጹ በተጨማሪ ጆሮውን በመያዝና ፊቱን በማዞር ቁጣውን ገልጿል ሲል ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመልክቷል::

ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው የመንግስት ፌደራል ፖሊሶች አሁንም በአራቱም አቅጣጫ ህዝቡን እየተከታተለ እየደበደበና እያሰረ ነው፡፡ በርካታ አዛውንቶችና ወጣቶች ራሳቸውን ስተው ወድቀዋል፡፡
ከተበተነው ህዝብ መካከልም ፖሊስ የተቃውሞው መሪ ናቸው በሚል ወጣቶችን እየነጠለ ማሰር ጀምሯል፡፡ በሰልፉ ላይ ተሳታፊ የነበሩት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና ዕጩዎች እየታሰሩ መሆኑ የተሰማ ሲሆን የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የሆነው ይድነቃቸው አዲስን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችና አባላት ታስረዋል፡፡

በኢትዮጵያውያን ላይ የጭካኔ እርምጃ የወሰደው አይ ኤስ አይ ኤስ ላይ እርምጃ አልወሰድክም፣ ለዜጎች ትኩረት አልሰጠህም በሚል ተቃውሞ የገጠመው መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ ሌላ ጭካኔ እየፈፀመ መሆኑ የራሱን የስር ዓቱን ደጋፊዎች ሳይቀር አሳዝኗል::

ፖሊስ አይሲስን እና ኢሕ አዴግን ለመቃውም የመጣውን ሕዝብ ሲመልስ

ፖሊስ አይሲስን እና ኢሕ አዴግን ለመቃውም የመጣውን ሕዝብ ሲመልስ

The post መንግስት በአ.አ የጠራው ሰልፍ ወደ ተቃውሞ ተለወጠ * ሴቶች እና አዛውንቶችን ሳይቀር ደብደበ * አስለቃሽ ጭስ ተተኮሰ * የሕዝቡ ቁጣ አልበረደም appeared first on Zehabesha Amharic.


በአዲስ አበባ ሕዝቡ “ወያኔ ሌባ”እያለ ሲዘምር የሚያሳይ የተቃውሞ ቭዲዮ

አይሲስን ለመቃውም አደባባይ የወጡት የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች፣ አመራሮችና አባላት ታሰሩ

$
0
0

addia ababa
(ነገረ ኢትዮጵያ) ዛሬ መንግስት በጠራው የተቃውሞ ሰልፍ በርካታ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት፣ አመራሮችና እጩዎች ታስረዋል፡፡ ሰልፉን ለመቀላቀል በጠዋቱ ወደ መስቀል አደባባይ በማቅናት ላይ የነበረችው ወይንሸት ሞላ ሰልፉ ላይ ሳትደርስ የታሰረች ሲሆን አሁን የት እንዳለች አልታወቀም፡፡

ዕጩ ተወዳዳሪ የሆነው ጠና ይታየውን ጨምሮ በርከት ያሉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች የታሰሩ ሲሆን ከእነዚህም መካከል
ዳንኤል ተስፋዬ፣ ምዕራፍ ይመር፣ ኤርሚያስ ስዩም እና ቴዎድሮስ አስፋው ይገኙበታል፡፡

The post አይሲስን ለመቃውም አደባባይ የወጡት የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች፣ አመራሮችና አባላት ታሰሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሻማ ማብራት እና የጸሎት ጥሪ በአትላንታ እና አካባቢው ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች (ፍላየር)

ኢትዮጵያዊ ክርስቲያን ወንድሞቼን አሳልፌ አልሰጥም በሚል በአይሲኤል ሕይወቱን ያጣው ጀማል ራህማን

$
0
0

በሙስሊም ወገኖቻችን ኮራን

አበበ ገላው እንደጻፈው:-
ISIL
አረመኔዎቹ ወያኔዎች ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን ከISIS ጋር የተሰለፉ ለማስመሰል አደገኛ ፕሮፓጋንዳ በመርጨት ላይ ናቸው። ይሁንና እውነታው ሙስሊም ወገኖቻችን ክርስቲያን ወገኖቻቸውን ከእርድና ጥይት ለመታደግ መስዋእት እየሆኑ መሆኑን ተረጋግጧል። ክርስትያን ወንድሞቼን አሳልፌ ለሞት አልስጥም ብሎ አብሮ ከተሰውት ኢትዮጵያዊያን መሃል ወንድማችን ጀማል ራህማን ይገኝበታል። ክርስቲያን ወንድሞቹን ለማትረፍ ከአረመኔዎች ጋር ሲሟገት እራሱ ተሰዋ። በታሪክ ለዘላለም የሚዘከር ታላቅና ቅዱስ መሰዋእትነት!! ነፍስህ ለዘላለም በገነት ስለምትኖር ይማርክ ልንህ ልንልህ አይቻለንም።

እኛ ኢትዮጵያዊያን እንዲህ ነን! ምንም ገዢዎች ቢከፋፍሉን አብረን እንኖራለን፣ አብረን እንቆማለን፣ አብረን እንሰዋለን። በዚህ የመከራ ግዜ ሁላችንም በዘር በሃይማኖት ሳንከፋፈል አንድነታችንን አጠንክረን ከውጭም ከውስጥም እንታገል። የክርስቲያኑም የሙስሊሙም አምላክ ይርዳን!!

The post ኢትዮጵያዊ ክርስቲያን ወንድሞቼን አሳልፌ አልሰጥም በሚል በአይሲኤል ሕይወቱን ያጣው ጀማል ራህማን appeared first on Zehabesha Amharic.

ከሰማያዊና ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበራት የተሠጠ መግለጫ

$
0
0

udj-Blueበዚህ ባሣለፍነው ሣምንት በኢትዮጵያውያን ላይ በሊቢያና ደቡብ አፍሪካ የደረሰው እጅግ በጣም ዘግናኝ ጭካኔ የጅምላ ግድያ ማለትም በሊቢያ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን ወደ ዕስልምና እንዲቀየሩ ጠይቀዋቸው እምቢ ስላሏቸው ብቻ ግማሾቹን በቢላዋ አንገታቸውን አርደዋቸዋል፡፡  ግማሾቹን ደግሞ በጥይት እራሣቸውን በመምታት ሠላሳ(30) ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን በግፍ አይስል (ISIL) ተብሎ በሚጠራው የእስላማዊ አሸባሪ ቡድን ተሰውተዋል፡፡ በደቡብ አፍሪካም እንዲሁ ኢትዮጵያውያን ሰደተኞች ላይ ቤንዚን በማርከፍከፍ ከተሽከርካሪ ጐማ  ጋር በማሰር ሦስት ኢትዮጵያውያን በእሣት ተቃጥለው እንዲሞቱ ተደርጓል፡፡ በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውን ስደተኞችን በእሣት ያቃጠሉት የደቡብ አፍሪካ ጥቁር ዜጐች ናቸው፡፡ በሁለቱም አገሮች የደረሰው አሠቃቂው የኢትዮጵያውያን ጅምላ ሞት ምከንያት ስር መሠረቱ ቁጥጥር ያጣው የአገሪቱ ሕዝብ ስደት ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ከየትኛውም የአገሪቱ ክልሎች በየቀኑ በጣም ከፍተኛ ሕዝብ በሕገ-ወጥ ደላሎች ከቤታቸው እንዲኮበልሉ እየተደረገ የስደት ገፈት ቀማሽ እንዲሆን ተገዷል፡፡

ህውሃት/ኢህአዴግ የሚቆጣጠራት የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ለዜጐቿ ምቹ አልሆነችም፡፡ አገዛዙ በራሱ በሚቆጣጠረው የመገናኛ ብዙሃን እንደሚለፈፈው አገሪቱ በሁለት እጥፍ እያደገች ሣይሆን በተቃራኒው ኢትዮጵያ ለዜጐቿ የማትመች፣ ፍትህ የሌለባት፣ ሰው በነፃነት የማይኖርባት፣ ችግርና መከራ የበዛባት፤ ለአብዛኛው ዜጎቿ  የማትመች የመከራ ምድር በመሆኗ የአገዛዙን የጭቆና ቀምበር መሸከም ስላልቻለ፣ ኑሮ ስለከበው እልፍ-አእላፍ  ዜጐች በስደት መከራ እንዲሰቃዩ ተደርገዋል፡፡ የአገዛዙ ባለስልጣኖች ሠሞኑን በስደተኛ ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን እጅግ አሠቃቂ ግድያ ማውገዝ እንኳን ሲያቅታቸው ተስተውለዋል፡፡ የኢህአዴግ የዘዉግ መንግሥት ዘመንኛ ገዢዎች የተጐጅ ወገኖቻችንን ኢትዮጵያዊነት እውቅና ላለመስጠት የፈለገበት ምክንያት ለሕዝቧና ለአገሪቱ ካላቸው ስር የሰደደ ጥላቻና ግድየለሽነት የመነጨ ነው፡፡ ገዳዮቹ አሸባሪዎች “የጠላታችን የኢትዮጽያ ቤተክርስቲያን የመስቀል ጦረኞች ልጆች” ብለው ሲነግሩን ከሁሉም በላይ ደግሞ የወገኖቻችን ደምና መልካቸው እየታዬ የኢህአዴግ አምባገነን ገዢዎች ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን ለመቀበል ተስኗቸዉ ተስተውሏል፡፡ ይህም ድርጊታቸው ኢትዮጵያውያንን እጅግ አሣዝኗል፤ አበሣጭቷልም፡፡ የአዲስ አበባና የአካባቢው ሕዝብ ሃዘኑን ለመግለፅ ከሰኞ ዕለት ጀምሮ  ወደ ጎዳና በመውጣት ምሬቱን ሲያሠማ ተስተውሏል፡፡ ይሁን እንጂ ትናትናና ዛሬ በአዲስ አበባ ሠልፈኞች ላይ እጅግ ከፍተኛ ድብደባ በፀጥታ አስከባሪ ቅልብ ፖሊሶች ተፈጽሟል፡፡ አገዛዙ እራሱ ሠልፍ ጠርቶ መልሦ ሕዝቡን በዱላና በጥይት እያሠቃየው ይገኛል፡፡ በባዕዳን የፈሰሰው ደም ሣይደርቅ ዓለም እንኳን ይታዘበናል ብለው ሣያፍሩ ሣይሰስቱ በሰልፈኛው ሕዝብ ላይ መሣሪያ በመተኮስ ብዙ ወገኖች ከፍተኛ አደጋ ደርሦባቸዋል፡፡ ብዛት ያላቸዉ ሠልፈኞች ታሥረዋል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ፡-

የዚህ ሁሉ የማያልቅ መከራ የዕለት-ተዕለት ክስተት ዋናው ምክንያት አገሪቱ ውስጥ ያለው የመልካም አስተዳደር እጦት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለጥቂቶች ገነት ለብዙሃኑ ገሃነም የሆነች አገር ሆናለች፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢህአዴግ አገሪቱን ከተቆጣጠረ ጀምሮ  ፍትሕ የለም፣  ነፃነት የለም፣ ሰዎች ባገራቸው ከቦታ ቦታ መዘዋወር አይችሉም፣  የአገዛዙ ካድሬዎች  ሕዝቡን በዘርና በቋንቋ በመከፋፈል እርስ በርሱ እንዳይተማማንና እንዳይግባባ አድርገውታል፡፡ ኢትዮጵያውያን በነፃነት በእኩልነት መብታቸው ተከብሮ የመኖር ዋስትናቸው እንዲረጋገጥና ስደት እንዲቀር እንዲሁም አገራችን የጥቂቶች ሣይሆን የሁሉም ኢትዮጵያውያን እንድትሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በነቂስ አገዛዙን መቃወምና ስርዓቱን ከስር መሠረቱ መቀየር ያስፈልጋል፡፡ስለሆነም ኢትዮጵያውያን በውስጥም በውጭም ያሣለፍነው የመከራ ዘመን ከኋላችን እንዲቀር ከተፈለገ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በሌላው ዓለም እንደታየው ሁሉ እኛም ዕጅ ለዕጅ ተያይዘን አገዛዙን በመቃወም በጋራ አሽቀንጥረን መጣል ይገባናል፡፡

ድል ለኢትዬጵያ!

 

የአንድነትና የሠማያዊ ድጋፍ ማህበሮች በሰሜን አሜሪካ አስተባባሪ ኮሚቴ

The post ከሰማያዊና ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበራት የተሠጠ መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.

መድሐኒአለም ይፋረደኝ ! –ነቢዩ ሲራክ

$
0
0
tiwa
================
ማጣቱ ዘልቆ ሳይጎዳኝ ፣
ድህነቱን ችየ በኖርኩኝ ፣
እህ ብየ ተመስገን ብየ ኑሮ በገፋሁኝ ፣
የመኖሬን ተስፋ ቀማችሁኝ ፣
ልጀን ወዳጀን ነጠቃችሁኝ  ፣
ደጋፊየ ጠዋሪየን በግፍ ቀማችሁኝ !
እኔማ  …. ደካማ እናት ነኝ ፣
ልጀን በጨካኞች በግፍ ያጣሁኝ ፣
አሳቢ ልጀን የተቀማሁ ፣ የጎደለብኝ ፣
እኔማ አድሜ ጠገብ ፣ ደከማ ነኝ  ፣
ለበቀል የሚሆን ጉልበት የከዳኝ ፣
የተገፊ እናት ነኝ ፣ ሀዘን ጠልቆ የተሰማኝ ፣
አዎ! አቅም ያጣሁ ምንዱብ እናት ነኝ !
ብቻ ተስፋየ በሱ ነው ፣ በማይተወኝ ፣
የፈጠረኝ መድሐኒአለም ይፋረደኝ  ፣
በቀል አይቀርም ተስፋ አለኝ  !
እሱ አንድየ ይድረስልኝ  !
መድሐኒአለም ይፋረደኝ ! ”
አዎ እናታለም ፣ መድሐኒአለም ይፋረደን  !!!
አዎ እናት አለም  …
የበቀል አምላክ ዝም አይልም ፣
መድሐኒአለም ይፈርዳልም !ነቢዩ ሲራክ
በጨለመው ሚያዝያ 15 ቀን 2007 ዓም

 

The post መድሐኒአለም ይፋረደኝ ! – ነቢዩ ሲራክ appeared first on Zehabesha Amharic.

ለፌዴራል ፖሊሲ አባላት

$
0
0

ፖሊስ የሆናችሁት ሕዝቡን እንድትጠበቁና ሕዝቡን እንድታገለግሉ ነው። የሕወሃት ባለስልጣናት ሕዝቡን እንድትደበድቡ፣ እንድታሸበሩ፣ እንድታወኩ መመሪያ ሲሰጧችሁ፣ መመሪያዉን ተቀብላችሁ ተግባራዊ ለማድረግ መሯሯጣችሁ አሳዛኝ እና ትልቅ ወንጀል ነው።

በአሁኑ ዘመን የምታደርጉት ሁሉ በፎቶና በቪዲዮ እየተቀረጸ ነው። አለም ሁሉ እያየው ነው። ማንነታችሁ እየተመዘገበ ነው። ከእኩይ ተግባራችሁ እንድትቆጠቡ፣ የአለቆቻችሁን ኢሰብዓዊ መመሪያ አንቀበልም እንድትሉ እናሳስባለን።

ሕዝቡ ድምጹን ማሰማቱን ይቀጥላል። ተቃዉሞው ይቀጥላል። ለውጥ መምጣቱ የግድ ነው። ሕወሃት ለ24 አመታት ገዝቶ፣ በስብሶ ሊወድቅ ትንሽ ነው የቀረው። ሕወሃት አገር የማስተዳደር አቅምና ብቃት የለዉም። በሕዝቡ ከዳር እስከ ዳር የተጠላ ነው። የዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ በማያሻማ መልኩ አረጋግጧል። ከሕዝባችሁ ጎን ብትቆሙ ይሻላቹሃል !!!!!

ነገ ሚያዚያ 15 ቀን “ስራ የለም” ተብሏል። ነገ ቤታችሁ ተቀመጡ !!!!

የሕውሃት ባለስልጣናት አንድ ነገር ቢፈጠር እናንተን አጋልጠው ነው አገር ለቀው የሚሄዱት። ከሕዝቡ ገንዘብ ዘርፈው ወደ ዉጭ አውጥተዋል። ልጆቻቸዉን ወደ ዉጭ ልከዋል። እናንተ ናችሁ ሜዳ ላይ የምትቀሩት !!!!! ስለዚህ ለራሳችሁና ለቤተሰባችሁ ስትሉ መልካሙን መንገድ ምረጡ። ከሕዝብ ጎን ቁሙ!!!!!!!

19

 

The post ለፌዴራል ፖሊሲ አባላት appeared first on Zehabesha Amharic.


‹‹ልጆቻችን፣ ማዕተቤን አልበጥስም፤ ወደ ሌላ አንለወጥም አሉ፤ በሰማዕትነታቸው ልንጽናናባቸው ልንማርባቸው እና ልናወድሳቸው ይገባል›› – የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የማጽናኛ ቃለ ምዕዳን

$
0
0

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡

‹‹ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዝንጉርጉርነቱን ሊለውጥ ይችላልን? ልጆቻችን የምንኮራባቸው መጻሕፍቶቻችን፣ የምንማርባቸው ዩኒቨርስቲዎቻችን ናቸው፤ አስተምረውናል፤ አኩርተውናል፤ አስከብረውናል››

the-martyr-daniel-hadush(ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤ የሰቲት ሑመራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ)

የልጆቻን የኃይለ ሚካኤል(ኢያሱ ይኵኖ አምላክ) እና የኃይለ ኢየሱስን(ባልቻ በለጠ) ነፍስ ይማርልን፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን የሐዘን ዳርቻ ያድርግልን፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን የቤተሰቡን ሕይወት፣ የቤተሰቡን ሐዘን በመልካም ነገር፣ በፍቅር ነገር ይለውጥልን፡፡ ቤተሰቡን ያለምልምልን፡፡ ቤተሰቡን ያጽናልን፡፡ ደግ ያልኾኑ ሰዎችን ወደ ደግነት፣ ወደ ምሕረት፣ ወደ ቸርነት ይመልስልን፡፡ ለዓለሙ ኹሉ ሰላም መረጋጋትን ያድልልን፡፡ አገራችን ኢትዮጵያን በክብር በረድኤት ይጠብቅልን፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤

የውድ ልጆቻችን የሰማዕታቱ፣ የታማኝ ልጆቻችን፣ የጀግኖች ልጆቻችን፣ በኢትዮጵያዊ ባህላቸው፣ በኢትዮጵያዊ ትውፊታቸው፣ በእምነታቸው፣ በሥርዐታቸው፣ በወጋቸው ጸንተው፣ ለማንም ሳይበገሩ እና ለማንም ሳይደለሉ፣ ለሌላ እጃቸውን ሳይሰጡ፣ ሳይቀለበሱ ጀግንነትን ያስተማሩ ልጆቻችን፣ መጻሕፍት የኾኑ ልጆቻችን ወላጆች እና እዚኽ የተሰበሰባችኹ ውድ ወገኖቼ፤

His Grace Abune Lukasከክርስቶስ ልደት በፊት ሰባት መቶ ዓመታት ቀድሞ የነበረው ነቢዩ ኤርሚያስ፣ በዚያን ጊዜዋ ባቢሎን በዛሬዋ ኢራቅ፤ በዚያን ጊዜዋ ፋርስ በዛሬዋ ኢራን እየዘዋወረ ባስተማረበት ዘመን ስለ ኢትዮጵያውን አድናቆት፣ ክብር፣ ጀግንነት፣ አይበገሬነት በትንቢቱ ምዕራፍ 13 ቁጥር 23 ላይ እንዲኽ ብሏል፡- ‹‹ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዝንጉርጉርነቱን ሊለውጥ ይችላልን?››

ኢትዮጵያዊ ባህሉን፣ ኢትዮጵያዊ እምነቱን፣ ኢትዮጵያዊ አንድነቱን፣ ኢትዮጵያዊ ጀግንነቱን፣ ኢትዮጵያዊ ትውፊቱን በሌላ ሊቀይር ይችላልን? አይቀየርም፡፡ ነቢዩ ሠቆቃው ኤርሚያስ በተባለ መጽሐፉም ይህን በስፋት እየገለጸ ይናገራል፡፡

ውድ ወገኖቼ፤ ልጆቻችን እኮ ጀግኖች ናቸው፤ ልጆቻችን እኮ እጃቸውን አልሰጡም፤ ልጆቻችን እኮ አልተንበረከኩም፤ ልጆቻችን እኮ መጻሕፍቶቻችን ናቸው፤ ልጆቻችን እኮ አርበኞቻችን ናቸው፤ አልተማረኩም፤ የጀግና እናት አታለቅስም እንደተባለው ኹሉ፣ እናንተም የጀግኖች እናቶች ናችኹ፤ ልትኮሩ ይገባችኋል፤ ስማቸውን ለውጠው፣ ሃይማኖታቸውን ለውጠው፣ ሥርዐታቸውን ለውጠው፣ ተማርከው ቢኾን ኖሮ ነበር ማልቀስ የሚገባን፡፡

ውድ ወገኖቼ፤ የጀግኖች ወላጆች ናችኹና ልትኮሩ፣ ልትጽናኑ ይገባችኋል፡፡ እሰይ ልጄ፤ ተባረክ ልጄ፤ ለመንግሥተ ሰማያት ያብቃኽ ብላችኹ ልትመርቁ፣ ልትጸልዩ፣ ልትጽናኑ ይገባል፡፡ የመጽናኛ ዕለት ነው፤ ልጆቻችን አስተምረውናል፤ ልጆቻችን አኩርተውናል፤ ልጆቻችን አስከብረውናል፤ አስወድደውናል፤ በዓለም ደረጃ አገራችንን አስተዋውቀዋል፡፡

ውድ ወገኖቼ፤ እንዲኽ ላሉት ነው እንዴ የሚለቀሰው? አገር አጥፍቶ ለሔደ፣ በሙስና ተዘፍቆ ለሔደ፣ ሰክሮ ለሔደ፣ አመንዝሮ ለሔደ፣ ቀምቶ ለሔደ÷ ‹‹በምድር ኑሮው ተበላሽቶ፣ በሰማይ እንዴት ይኾን ከቶ›› ተብሎ የሚለቀስለት ለዚኽ ነው፡፡ ብዙ ልጆቻችን በየመልኩ ኸሉም አርበኛ ነው፡፡ አካሉን፣ ሕይወቱን፣ ወላጁን፣ ልጁን፣ ዘመኑን፣ ንብረቱን የሰጠ ስንት አለ? ውድ ወገኖቼ፤ እንዴ፣ እነዚኽማ ልጆቻችን የምንኮራባቸው መጻሕፍቶቻችን ናቸው!! የምንማርባቸው ዩኒቨርስቲዎቻችን ናቸው ልጆቻችን!! ብርሃናችን ናቸው ልጆቻችን!! ማዕተቤን አልበጥስም፤ ወደ ሌላ አንለወጥም፤ አንበገርም አሉ፤ ይኼ ነው ወይ የሚያስለቅሰው? የሚለቀስበትን ነገር እንወቅ እንጂ!

ውድ ወገኖቼ፤ ስለዚኽ ልጆቻችንን በሰማዕትነታቸው፣ በጀግንነታቸው ልናከብራቸው፣ ልንማርባቸው፣ ምሳሌአቸውን ልንወስድ፣ ልናወድሳቸው ይገባል፡፡ ስለዚኽ ይኼ የመረጋጋት፣ የሰላም‹ የፍቅር ቦታ ነው፡፡ ልጆቻችን የአገር ፍቅር፣ የአገር ሰላም፣ የአገር አንድነት አስተምረውናል፡፡ በልጆቻችን ተምረናል፤ ጠግበናል፤ ረክተናል፤ ኮርተናል፡፡

የልጆቻችንን ነፍስ በገነት በመንግሥተ ሰማያት ያሳርፍልን፤ ይማርልን፤ ወላጆቻቸውን ይጠብቅልን፤ ከክፉ ነገር ይሰውረን፤ መልካሙን ነገር ያምጣልን፤ ልጆቻችንና ወገኖቻችንን በሰላም ወደ ቤታቸው ይመልስልን፡፡ ኹላችንም ተጽናንተን የሚያኮራ ሥራ እንድንሠራ ቅዱስ ፈቃዱ ይኹንልን፡፡ ነፍሰ ገብሩ ኃይለ ኢየሱስ፣ ኃይለ ሚካኤል ሀገረ ሕይወትን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን፡፡

* * *

‹‹ወገኖቻችን ሰማዕታት፣ ታሪክ አትርፈው ስለሔዱ ለዘላለም ስማቸውና ሥራቸው ሲወሳ ይኖራል››

(ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፤ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ፤ የወላይታ ኮንታ እና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ)

አኹን ያለንበት አካባቢ ቤተ መቅደሱ [ደብረ ፍሥሓ መካነ ሰማዕት]ቂርቆስ ነው፡፡ እንደምታውቁት ቂርቆስ ሕፃን ነው፡፡ በምን መልክ እንደ ዐረፈ ታውቃላችኹ፡፡ ሕፃኑ ቂርቆስ፣ ዓላውያን ነገሥታት በእኛ እምነት እመን፤ እኛ የምናዝዝኽን ፈጽም ባሉት ሰዓት አልተቀበላቸውም፡፡ እሳት ነደደ፤ በበርሜል ውስጥ ውኃ ፈላ፡፡ በዚኽ ሰዓት እናቱ ደንግጣ ወደ ፈላው ውኃ ለመግባት ስትፈራ ሕፃኑ ቂርቆስ፣ ‹‹እናቴ ጨክኚ፤ ዛሬ መንግሥተ ሰማያት የምንገባበት ቀን ነው፡፡ አባቶቻችን በሰጡን፣ ባወረሱን፣ ባስተማሩን እምነት ጸንተን ወደ መንግሥተ ሰማያት የምንገባበት ነውና ከዓላዊው ንጉሥ አትፍሪ›› ብሎ እናቱን ወደ እሳት የጋበዘ ነው፡፡ እስከ መጨረሻው እስከ ዘላለሙ ሰማዕቱ ቂርቆስ ሲባል ይኖራል፤ ታሪክ ሲዘክረው ይኖራል፤ ታሪክ አይደመሰስም፡፡

አኹንም እነዚኽ ወንድሞቻችን፣ ወገኖቻችን ሰማዕታት የታሪክ ባለቤቶች ስለኾኑ፣ ታሪክ አትርፈው ስለሔዱ ከእነርሱ በፊት እንደነበሩት ኹሉ ለዘላለም ስማቸው፣ ሥራቸው ሲወሳ ይኖራል፡፡ ሐዘን ኹልጊዜ ሲያነሡት ልብ ይሠቀጥጣል፡፡ ይኼን እያነሡ መናገር በጣም ይከብዳል፡፡ ጭንቅላት ሊሸከመው አይችልም፡፡ እናም እዚኽ ያሉትን እያጽናናችኹ፣ እዚያ የቀሩት ደግሞ በሰላም እንዲወጡ ምሕላ እያደረግን ልንጸልይ ይገባል፡፡ እኛ እዚኽ ፀሐይ እየሞቅን፣ እየተነጋገርን እናዝለን፤ እዚያ እነርሱ ከወጡበት ሰውነታቸው አልቆ ነፍሳቸው የምትጨነቅ አለችና በሰላም እንዲያወጣቸው ላለፉት ብቻ ሳይኾን ለቀሩትም ጸሎት እያደረጋችኹ በዚኽ እንድትጽናኑ ነው አደራ የምንለው፡፡

ወላጆች ወለዱ እንጂ የኹላችን ልጆች ናቸው፤ ሐዘኑ የኢትዮጵያ ነው፤ እግዚአብሔር ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጽናቱን ይስጥልን፡፡ እዚያ የቀሩትንም በሰላም ያውጣልን፡፡

ስድስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት÷ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ዘካናዳ፣ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ፣ ብፁዕ አቡነ ኄኖክ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ፤ ሚያዝያ ፲፫ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. በደብረ ፍሥሓ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ሰበካተገኝተው የመስተጋድላን ሰማዕታትን ኢያሱ ይኵኖ አምላክ እና ባልቻ በለጠ ቤተ ሰዎች እና ወዳጆች ያጽናኑበት ቃለ ምዕዳን

Source:: haratewahido

The post ‹‹ልጆቻችን፣ ማዕተቤን አልበጥስም፤ ወደ ሌላ አንለወጥም አሉ፤ በሰማዕትነታቸው ልንጽናናባቸው ልንማርባቸው እና ልናወድሳቸው ይገባል›› – የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የማጽናኛ ቃለ ምዕዳን appeared first on Zehabesha Amharic.

በአይሲኤል ሕይወታቸውን ከተቀጠፉት መካከል አንዱ አወቀ ገመቹ

$
0
0

በሊቢያ በአይሲኤል ሕይወታቸውን ካጡት ኢትዮጵያውያን መካከል የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ማንነት ማረጋገጡ ቀጥሏል:: የተወሰኑትን ማንነት ዘ-ሐበሻ ባለፉት ቀናት ስታስተዋውቅ ቆይታለች:: የሁሉም በደረሰን ጊዜ ለማቅረብ እንሞክራለን:: በዚህም መሠረት ሕይወታቸውን ካጡት ውስጥ አወቀ ገመቹ ቡባ ይገኝበታል:: ከምስራቅ ወለጋ ሆሮጉድሩ ወደ ሊቢያ የተጓዘው አወቀ ሕይወቱ በ እንዲህ ያለው ሁኔታ ማለፉ በጣም ያሳዝናል::

እስካሁን ያወቅናቸው፦
1. ኢያሱ ይኵኖአምላክ
2. ባልቻ በለጠ
3. ዳንኤል ሐዱሽ
4. ቡሩክ ካሳሁን
5. ኤልያስ ተጫኔ
6. በቀለ ታጠቅ
7. በቀለ አርሰማ
8. ዳዊት ሐድጉ
9. መንግሥቱ ጋሼ
10. ጀማል ራህማን
11. አወቀ ገመቹ
ለቤተሰቦቹ መጽናናትን እንመኛለን::
aweke

aweke horo gudru

The post በአይሲኤል ሕይወታቸውን ከተቀጠፉት መካከል አንዱ አወቀ ገመቹ appeared first on Zehabesha Amharic.

ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የእምነት ቦታዎችን ማራካሱን ቀጥሎበታል

$
0
0

kirkos

ማምሻውን ፖሊሶችና ፌድራል ፖሊሶች ጨርቆስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በመግባት በምእምናን ላይ ድብደባ መፈጸማቸውን ጉዳት የደረሰባቸው ለቢቢኤን ገለጹ::

ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የእምነት ቦታዎችን በማርከስ ከዚህ ቀደም በገዳማት በመስጅዶች ውስጥ በመግባት በምእምናን ላይ ድብደባ ሲፈጸም መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው እለት በጨርቆስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ድረስ በመዝለቅ ከፍተኛ ድብደባ መፈጸማቸውን በቦታው ላይ ድብደባ የተፈጸመባቸው ለቢቢኤን ገልጸዋል፡፡

በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ከሚስቱ ጋር እንደነበር የገለጸው ወጣቱ ፖሊሶቹ ሴት ወንድ ሳይሉ ከሁለት መቶ በላይ በሚሆኑት ምእምናን ላይ ድብደባ እንደፈጸሙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቤተክርስቲያኑ የነበሩትን አማኞች በከደበደቡ በሁላ በየክፍለ ከተማቸው በመለየት በመኪና ጭነው እንደወሰዷቸው በድጋሚ እንደደቧቸው ተናግረዋል;፡

በመጨረሻም ፎቶ አንስተው አሻራ ተቀብለው ከምሽቱ 5፤45 እንደለቀቋቸው ለቢቢኤን ገልጸዋል፡፡ መንግስት የሃይማኖት ነጻነት አክብሪያለሁ እያለ የእምነት ተቋማትን ክብር ጭምር በመዳፈር የዚህ አይነት አስነዋሪ ድርጊት በመፈጸማቸው ማዘናቸውን ምእምናኑ ገልጸዋል፡፡

The post ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የእምነት ቦታዎችን ማራካሱን ቀጥሎበታል appeared first on Zehabesha Amharic.

በሲድኒ አውስትራሊያ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ እና የሻማ ማብራት ምሽት

$
0
0

በሲዲኒ አውስትራሊያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሊቢያ በአይሲኤል አማካኝነት ሕይወታቸውን ለተቀጠፉ; እንዲሁም በየመን እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ሕይወታቸውን ላጡት ኢትዮጵያውያን መታሰቢያ የሚሆን የተቃውሞ እና የሻማ ምሽት የፊታችን እሁድ ጠርተዋል:: ፍላየሩን በመጫን አሳድገው ይመልከቱት::
Sydney Ethiopians australia

The post በሲድኒ አውስትራሊያ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ እና የሻማ ማብራት ምሽት appeared first on Zehabesha Amharic.

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታድነው መታሰራቸው ታወቀ • 500 በላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ታስረዋል

$
0
0

self
(ነገረ ኢትዮጵያ) መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰልፈኛው ‹‹መንግስት በዜጎቻችን ላይ ለተፈፀመው አረመኔያዊ እርምጃ በቂ ምላሽ እየሰጠ አይደለም›› በሚል ባሰሙት ተቃውሞ በርካቶች ተደብደበው ከተሳሩና ሰልፉ ካበቃ በኋላ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው በሚል በርካቶች እየታደኑ መታሰራቸውን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

ሰልፉ ካበቃ በኋላ ታድነው ከታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መካከል ብሩክ የኔነህ ማታ 12 ሰዓር ላይ የተያዘ ሲሆን በአሁኑ ወቅት አራዳ መምሪያ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ በተመሳሳይ ዜና ከሰልፉ በኋላ ከ500 በላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተይዘው አራት ኪሎ አካባቢ በሚገኘው 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ታስረው እንደሚገኙ ተማሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ጠና ይታየው፣ ይድነቃቸው አዲስና እስክንድር ጥላሁን የተባሉት የሰማያዊ ፓርቲው ዕጩዎች ሌሊት 6 ሰዓት ላይ ከአባላት ተለይተው መፈታታቸውን አቶ ዮናታን ገልጸዋል፡፡

The post የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታድነው መታሰራቸው ታወቀ • 500 በላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ታስረዋል appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live