Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

Sport: ፋብሪጋስ ወደ ማን.ዩናይትድ?

$
0
0

fabrigas
(ዘ-ሐበሻ) ከአርሰናል ወደ ባርሴሎና ለ5 ዓመታት በመፈረም የሄደው ስፔናዊው የመሃል ሜዳ አቀጣጣይ ሴስክ ፋብሪጋስ ባርሴሎና የሚሸጠው ከሆነ ወደ ማን.ዩናይትድ መዘዋወር እንደሚፈልግ አስታወቀ። ማን.ዩናይትድ ተጫዋቹን ለማዘዋወር 25 ሚሊዮን ፓውንድ ግዢ ለባርሴሎና ያቀረበ ሲሆን የባርሴሎና ውሳኔ እየተጠበቀ ይገኛል።

በባርሴሎና ቋሚ ተሰላፊነትን ማግኘት ያልቻለው ፋብሪጋስ በተለይም በሚቀጥለው ዓመት በብራዚል በሚደረገው የዓለም ዋንጫ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ በመሆኑ በክለብ ደረጃ በበርካታ ጨዋታዎታዎችን መሰለፍ ይፈልጋል። ተጫዋቹ በባርሴሎና በቀጣዩ ሲዝን በበርካታ ጨዋታዎች ላይ የማይሰለፍ ከሆነ በስፔን ብሄራዊ ቡድን ውስጥ መካተቱ አጠራጣሪ ይሆናል። በመሆኑም ማን.ዩናይትድ ልጁን ከወሰደው በተለይም ፖል ስኮልስን ለመተካት ጥሩ አማራጭ ስለሚሆን በበርካታ ጨዋታዎች ላይ ስለሚያሰልፈው ፋብሪጋስ ባርሴሎና የሚሸጠው ከሆነ ወደትያትር ኦፍ ድሪምስ መዘዋወርን ይፈልጋል።

ማንቸስተር ዩናይትድ በግልጽ ፋብሪጋስን ለመውሰድ 25 ሚሊዮን ፓውንድ የግዢ ጥያቄ ለካታሎናዊው ክለብ አቀርቧል።

Manchester United have bid £25m for Barcelona’s ex-Arsenal midfielder Cesc Fabregas but the Gunners have first refusal on him at the same price.
United’s offer is being considered but is understood to be below the Spanish club’s valuation of the player.
While Fabregas is not pushing for a move, it is believed he is open to a return to England.
Fabregas facts
He became Arsenal’s youngest player aged 16 years and 177 days against Rotherham United in League Cup in October 2003
He was part of Arsenal team which beat Manchester United on penalties in 2005 FA Cup final – their last trophy
The 26-year-old will be guided by whether Barcelona are prepared to accept an offer for him.
Fabregas came through the Spanish club’s La Masia academy before Arsenal signed him as a 16-year-old in 2003.
He developed as one of the London club’s key players under manager Arsene Wenger before becoming Arsenal captain in November 2008.
The Spain international spent eight years with the Gunners, playing 303 games and scoring 57 goals.
However, he returned to the Nou Camp when he signed a five-year deal with Barcelona in a £25.4m move in August 2011.
He has since helped the Catalan club win the Copa del Rey in 2011-12 and La Liga in 2012-13.
Fabregas has played 96 times in two seasons with Barcelona, including 60 league games, but has rarely featured in his preferred midfield role, with Xavi, 33, and Andres Iniesta, 29, ahead of him.
Fabregas has made 83 appearances for Spain, winning the 2010 World Cup and the European Championship twice


ፖሊስ ማሰሩን የአንድነት አባላትም ወረቀት መበተኑን ገፍተውበታል (ዛሬ የታሰሩት 4 ደረሱ)

$
0
0

8611_669727903043674_1400680652_n(ሰበር ዜና ከፍኖተ ነፃነት) ዛሬ ሐምሌ 9, 2005 ዓ.ም የታሰሩት አባላት 4 ደርሰዋል፡፡ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የታሰሩ 3 የአንድነት አባላትን ለማስፈታት ወደ ስፍራው የሄደውን የአዲስ አበባ ዞን ስራ አስፈፃሚ የሆነው አዲሱ ካሳሁንን ከታሳሪዎቹ ጋር ቀላቅለውታል፡፡
ከአንድነት አዲስ አበባ ዞን ለፍኖተ ነፃነት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ዛሬ የተሰማሩት አባላት በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች በተሳካ ሁኔታ ወረቀት የመበተን ተልዕኳቸውን በአግባቡ ተወጥተዋል፡፡ በትላንትናው እለት 42 የአንድነት አባላትና ለአንዱ ታሳሪ ዋስ ለመሆን የሄደ ግለሰብ መታሰራቸው አይዘነጋም፡:
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የፀረሽብር ህጉ እንዲሻርና በሌላ እንዲቀየር እያሰባሰበ ስለሚገኘው ፊርማ የሚያብራራ በራሪ ወረቀት በመበተን ላይ የነበሩት ባይሳ ደርሳ፣ አለማየሁ በቀለ፣ ግርማ ሹቤ የተባሉትን የአንድነት አባላት ዛሬ ሐምሌ 9 ቀን 2005 ዓ.ም በፖሊስ ታስረዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቀው በዛሬው ዕለት ሁለት መቶ የሚሆኑ የፓርቲው አባላት በተለያዩ የአዲስ አበባ የክፍሎች በራሪወረቀቶችን በመበተን ላይ ናቸው፡፡

ከኦሮሞ ፖለቲካ ወደ ጃዋር ፖለቲካ? (ከመስፍን ነጋሽ )

$
0
0

“የኦሮሞ ሕዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር በአንድነት መኖር የሚፈልግ ይመስለኛል” – ጃዋር መህመድ (አዲስ ቃለ-ምልልስ)
ወንድሜ ጃዋር (Jawar Mohamed) ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በኦሮሞ ፖለቲካ እና አሁን ደግሞ ስለኦሮሞ-ኢስላም ያቀረባቸው ንግግሮች ኮርኳሪ ሆነዋል። ኮርኳሪነታቸው የሚመነጨው ግን ሐሳቦች አዲስ ስለሆኑ አይደለም፤ በአቀራረባቸውም ቢሆን ያልተለመዱ አይደሉም። “የአግራሞቱ” ወይም የንዴቱ ምንጭ ጃዋር የገነባው ወይም እየገነባው የመሰለን የፖለቲካ ማንነት እና በቅርብ ያንጸባረቃቸው አቋሞቹ እጅግ የሚቃረኑ ስለሚመስሉ ነው።

የኢትዮጵያን ፖለቲካ ውስብስብ ከሚያደርጉት ቁልፍ ጉዳዮች አንዱ የኦሮሞ ፖለቲካ ነው። ኢትዮጵያ ዜጎች ቢያንስ በመጠኑ ሐሳባቸውን በነጻነት የሚለዋወጡባት አገር ብትሆን ኖሮ ጉዳዩን ነጋ ጠባ በተነጋገርንበት፣ በተከራከርንበት ነበር። ይህ ባለመሆኑ ግን ከትልቁ የኦሮሞ ጉዳይ ይልቅ ጃዋር የተነፈሳት አንድ አረፍተ ነገር የበለጠ ቁም ነገር ያላት ሆና ተቆጠረች። መፍትሔው ጃዋርን ማውገዝ አይመስለኝም፤ ስለኦሮሞ ፖለቲካ መነጋገርና መደማመጥ ያስፈልጋል።

ጃዋር በአልጀዚራ ላይ ባቀረበው ሐሳብና በወሰደው አቋም ዙሪያ ሌላ ውይይት/ጽሑፍ የሚያስፈልገው ሆኖ ቢያንስ በክርክሩ ሐልዮታዊ መነሻዎች ላይ ግን ቢይንስ በግማሹ ከጃዋር ጋራ እስማማለሁ። መጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ነህ ወይስ ኦሮሞ የሚለው ጥያቄም በግለሰቦች ታሪክ፣ ከባህላቸው ጋራ ባለቸው ትስስር እና በፖለቲካዊ ርእዮታቸው የሚወሰን በመሆኑ ውይይትና ዴሞክራሲያዊ የአገር ግንባታ የሚፈታው አድርጌ እወስደዋለሁ። እኔ ያደኩበት ከባቢ ጃዋር ከኖረበት ፈጽሞ የተለየ ነው። ይህ በፖለቲካዊ ማንነታችን ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖ በኑሮና በእውቀት ሊለወጥ የሚችል ቢሆንም በቀላሉ የሚታይ ግን አይደለም። እኔ ባደኩበት ከባቢ ኖረው የጃዋርን ስሜት የሚጋሩ፣ እንዲሁም በተቃራኒው የሚሆኑ ሰዎች አሉ። አንዱ ከሌላው የበለጠ ትክክል አይመስለኝም።

ከብዙ የኦሮሞ የፖለቲካ ልሂቃን ጋራ ያለኝ ልዩነት፣ በዋናነት ያለፈውን ታሪክ በምገመግምበት መንገድ ሳይሆን መጪውን ዘመን በማልምበት ስልት ላይ የተመሰረተ ነው። ዴሞክራሲያዊት እና ፌዴራላዊት ኢትዮጵያ የችግሩ መውጫ ናት እላለሁ፤ ሌላ ምርጫ የለም። የኦሮሞ ሕዝብ በመገንጠል (የራስን እድል በራስ መወሰን) የራሱን መፍትሔ ሊያገኝና ብቻውን በሰላም ደሴት ላይ ሊኖር እንደሚችል የሚያስቡ ይኖራሉ። ቁም ነገሩ መገንጠል በራሱ ከሆነ ቢሞክሩት የሚከፋ አይደለም፤ ሆኖም መገንጠል የታሪኩ መጨረሻ አይሆንም። አሁን ያለው የኢትዮጵያ ባህላዊና ማኅበረሰባዊ እውነታ የኦሮሞንም ሆነ የሌሎቹን ሕዝቦች ችግሮች በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል የታመቀ አቅም እንዳለው አምናለሁ። እንደ ማኅበረሰብ ይህን አቅም ለመጠቀምና የጋራ ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችለን የፖለቲካ ብስለት ላይ ግን ገና አልደረስንም።

ሁለተኛው የጃዋር ንግግር የኦሮሞና የእስልምናን ግንኙነት፣ ከዚህ ግንኙነት የሚፈልቀው ፖለቲካዊ አንደምታ፣ እንዲሁም ሙስሊም ኦሮሞ ሙስሊም ከሆነ ሌላ ኢትዮጵያዊና ሙስሊም ካልሆነ ኢትዮጵያዊ ጋራ የሚኖረውን ግንኙነት የሚያጣቅስ ነው። ይህ ንግግር በአቀራረቡ በሚገባ የታሰበበትና የተደራጀ አይመስልም። በይዘቱም ስሜታዊነት አብዝቶ የተጫነው ነው። ጃዋር የሰነዘራቸው ሐሳቦችና “መረጃዎች” አሁንም ቢሆን አዲስ አይደሉም፤ የኖሩ ናቸው። አቀራረባቸው ግን አስፈሪ ነው። አስፈሪነቱ ከጃዋር በማልጠብቀው መንገድ የቀረበ ነው። የአፍ ወለምታ ነው ብዬ እንዳላልፈው ደግሞ ስብራት ሆነብኝ።

ኢሉ አባቦራም ላይ ይሁን ቶራቦራ ላይ፣ በቁጥር አብላጫ መሆን ሜንጫ የመምዘዝ ነጻ ፈቃድ እንደሚያቀዳጅ እንደዋዛ ሲነገር እደነግጣለሁ። ሰብአዊ ድንጋጤ። እኔም ሆንኩ ማንም ሰው ሜንጫ መዛዡም የሜንጫ ሰለባውም እንዲሆን ስላማልፈልግ። ጃዋር ያለው ነገር የትኛውንም የኢትዮጵያ ክፍል፣ ኦሮሞውን ሙስሊም ጨምሮ እንደማይወክል እርግጠኛ ነኝ። ነገር ግን ጃዋር እንዲህ ያለው ሜንጫ መዘዛ ተራ ክስተት የሆነበት አካባቢ ኖሮ ቢሆን እንኳን ነገሩ ሳያስደነግጠው ቀርቶ፣ ጭራሹን በአደባባይ ለሌሎች የሚሰብከው አኩሪ ስልት ሲሆን ያስደነግጣል። ነገሩ ኦሮሚያ ውስጥ በእውነት የሚፈጸም ቢሆን እንኳን ጃዋር ድርጊቱን ማውገዝ በተገባው ነበር። በጣም ሐላፊነት የጎደለው፣ አስተውሎት የተለየው እምነትና አነጋገር ነው። ሜንጫ መዘዛ ዛሬ “በሌሎች” ላይ ስለሚፈጸም ፈቃድ ከተሰጠው ነገ ለራሱ ለሙስሊም ኦሮሞ መጥፊያ መሆኑ አይቀርም።

ሌላው እጅግ በጣም አስደንጋጩ ነገር የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ብሶት” ያቀረበበትና የለካበት መንገድ ነው። ስለሙስሊሞች መገፋት በመርህና ላይ ተመስርተው የተናገሩና የታገሉ ክርስቲያኖች በሚሊዮን በሚቆጠሩባት ኢትዮጵያ በማንኛውም መንገድ የሙስሊሞች ትግል ከክርስቲያኖች ጋራ የሚደረግ አስመስሎ ማቅረብ ስሕተት ነው። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የተፈጸመባቸውን ታሪካዊ በደል ማቅረብ፣ በደሉ እንዳይደገም፣ ሙስሊሞች ከቀሪው ኢትዮጵያዊ ወገናቸው እኩል ተከብረው የሚኖሩባት አገር እንድትፈጠር መቀስቀስ የተገባ ነው። አሁን የሚፈጸመውንም በደል ማቅረብ፣ ሰላማዊና ሕጋዊ ጥያቄዎችንም መደገፍ ያባት ነው። በዚህ ሁሉ ከጃዋርና ከሌሎቹም ሙስሊም ወገኖቼ ጋራ እቆማለሁ። ይህን ሲያስረዱ የሚያቀርቡትን ምሳሌ መምረጥ ግን የተናጋሪ ሸክም መሆኑን ጃዋር ዘንግቶታል፤ ወይም የታናገረው የሚያምነውን ነው። እውነት የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ቁልፍ ጥያቄና ህልም አክሱም ላይ መስጊድ መገንባት ነው? ለሌሎች ታሪክና ባህል ክብር ካለን፣ ዜጎች በተቻለ መጠን ተከባብረውና ተቻችለው እንዲኖሩ ማድረግ ቀዳሚ ፍላጎታችንስ ከሆነ በዚህ ጥያቄ ወደ ግጭት መግባት ይኖርብናል? የጃዋር ኢትዮጵያ ብትፈጠርና የፖለቲካ ስልጣን ሁሉ እርሱ በሚላቸው አይነት ሙስሊሞች ቢያዝ፣ አንዱ አጃንዳቸው አክሱም ላይ መስጊድ መስራት ነው ማለት ነው? አክሱም ላይ መስጊድ ቢገነባ ለአንድ በአካባቢው ለማይኖር ኢትዮጵያዊ ሙስሊም የሚሰጠው የድል ስሜት ከምን የሚመነጭ ነው? መካ ላይ ቤተ ክርስቲያን ወይም ምኩራብ፣ ቫቲካን ውስጥ መስጊድ ወዘተ እንዲሰራ መታገልና ማለም እውነት ሊታገሉለት የሚገባ ምድራዊ ዓላማ ነው? (ሰማያዊ ዓላማ ከሆነ ሌላ ጥያቄ ነው።) በድጋሚ እጅግ ሐላፊነት የጎደለው የተሳሳተ አስተሳሰብና አነጋገር ነው።

የጃዋርን ንግግሮች ስሰማ በተደጋጋሚ የሚታወሰኝ በቀለ ገርባ ነበር፤ በግልጽ ምክንያት። (ስለበቀለ የፍርድ ቤት ንግግር የጻፍኩትን ማስታወስ።)

ለማጠቃለል፣ ውይይቱ ስለጃዋር ከመሆን አላመለጠም። (ፖለቲካዊ) ማንነት የእቅድና የአጋጣሚዎች ድምር ውጤት ነው። ጃዋርም ማንነቱን በዚሁ መንገድ እየቀረጸ ይታያል። ጥያቄው ጃዋር አንዳንዶቻችን ያሰብነው አይነት፣ በዴሞክራሲያዊ መርሆች የምሩን የሚያምን፣ ስለኦሮሞ ሕዝብ መብትና ነፃነት ሲታገልና ተረዱኝ ሲል በተራው ለሌሎች ማንነትና ፍላጎት ክብር የሚሰጥ፣ በመስጠትና በመቀበል የፖለቲካ መርህ የሚገዛ፣ ከቅርብ ነጠላ ድሎች ይልቅ ለረጅም ጊዜ ሰላምና ነጻነት የበለጠ ክብደት የሚሰጥ፣ ወይም ይህን ሁሉ የሚሞክርና የሚመኝ ይሆናል ወይስ ተቃራኒውን የሚል ነው። ጃዋርን በፊትም አሁንም ከእነዚህ አንዱንም አይደለም የሚሉ ወዳጆች አሉኝ። በፊት የነበረውም ሆነ አሁን ያለው ጃዋር ምንም ይሁን፣ የወደፊቱን ተክለ ቁመናውን መወሰን ለእርሱ ብቻ የተከለለ መብቱ ነው። እርግጥ ጃዋር እዚህ እኔ ከተመኘሁት የተለየ ሰው እንዲሆን የሚመኙና የሚጋብዙት ሌሎች ወገኖቼም እንዳሉ አውቃለሁ። ምርጫው የባለቤቱ ነው። ምርጫው የትኛውም ቢሆን ግን ስለሜንጫ መዘዛው ይቅርታ ቢጠይቅ ጃዋር ይከበርበታል እንጂ ይዋረድበታል ብዬ አላምንም። ጥያቄው መሆን አለመሆን ነው፤ አንዱን ወይም ሌላውን።

ከዚህ ቀደም እንደሆነው ሁሉ ከነልዩነቶቻችን ከጃዋር ጋራ ውይይታችንና ግንኙነታችን ይቀጥላል።

ከነመላኩ ፈንታ በኋላ የቆመ መርከብ የሆነው ፀረ –ሙስና ኮሚሽን

$
0
0

ከሰናይ ቃል

 መላኩ ፈንታ እኚህ ናቸው።

መላኩ ፈንታ እኚህ ናቸው።

በኢትዮጵያ ውስጥ በጣም አስከፊ እየሆኑ ከመጡት ነገሮች መካከል የሙስና ተግባር በጣም በጣም አሣሣቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ሰዎች በአንድ ጀምበር የሚመነጠቁበት ይህ የሙስና ተግባር ታዲያ በአግባቡ ቁጥጥር ተደርጐበታል ወይም ክትትሉ የሁሉንም አካል ጥያቄ ያማከለ ነው ለሚለው ብዙ አሻሚ የሆኑ ነገሮች አሉበት፡፡ ለዋቢነት መጥቀስ የሚቻለው የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዜና በረጅም አመት ሙሰኛ ተገኘ ብሎ አንድ ትልቅ ባለስልጣንን የማያዝ እንጂ በትክክለኛው መንገድ መስመር ተከትሎ የሚሰራ ባለመሆኑ ነው፡፡ ባለፈው ሰሞን እንደሚታወቀው ከሆነ ትልቅ ዜና ሆኖ የሰነበተው የገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን በአቶ መላኩ ፈንታ የሚመራው ቡድንና ሌሎች ነጋዴዎች ከሙስና ተግባር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉበት ሁኔታ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ምናልባትም ሲደረግ ወይም ሲተገበር ያስደነገጠው የሕብረተሰብ ክፍል የለም፡፡ እንዴት ይህ ሊደፈር ቻለ ይህ እርምጃስ አሁን በምን ታወሰ የሚል አልጠፋም፡፡
ኢህአዴግ አንድ የሚገርም ባህሪ አለው ነገሮችን የማስቀየሻ ተግባራትና ለመስዋእትነት የሚያቀርባቸው ባለስልጣናት፡፡ በወቅቱ አንድ በመንግስት ላይ ፍጥጫ የሚፈጥር ወይም የሕዝብ ትኩረትን የሚስብ ነገር ካለ ያንን ነገር ለማስለወጥ ወይም ለጋሽ ሀገራትን ሀሣብ ለማስቀየስ ይህንን ተግባር ይፈፀማል፡፡ በወቅቱ ታዲያ ትልቅ ዜና የነበረው የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አንዱአለም አራጌ ያቀረቡት የይግባኝ ጥያቄ በሕዝቡ ውስጥ ትልቅ ቦታ ተሰጥቶት ሲጠበቅ የነበረ ጉዳይ ነበር፡፡ እናም ግን ታዲያ ይህ የይግባኝ ጥያቄ ውድቅ ሆነ፡፡ በተለይ የእስክንድር ነጋ ንብረት ምንም በማይገናኝ መልኩ እንዲወርስ መደረግ ደግሞ ይበልጥ የሕዝብን ትኩረት ስቦ ነበር፡፡ ይህንን ጉዳይ ለማጨለምና ለማጥፋት ታዲያ ኢህአዴግ አጋጣሚው ከተጠቀመባቸው መንገዶች መካከል አንዱና ዋንኛው ነገር ምንም ሣይሆን ይህ እነመላኩ ፈንቴ በሙስና የተያዙበት ጉዳይ ነው፡፡
ሌላው ደግሞ እንደነ “UNDP” ያሉ ተቋማት በሀገሪቱ ለሚደረገው የፀረ ሙስና ዘመቻ የገንዘብ ድጐማ ያደርጋሉ፡፡ ይሁንና ግን እነሱ በኢትዮጵያ ያለውን የሙስና ጉዳይ በሚመረምሩበት ወቅት በ15 ወይም በአስር አመት ጊዜ ውስጥ ብቻ 20 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ገንዘብ በሕገ ወጥ መንገድ መውጣቱን ገልፀዋል፡፡ ይህ ብቻም አይደለም የዚህ ገንዘብ መውጫና የወጣበት አካልም ማንም ሣይሆን የመንግስት አካል መሆኑ በቀጥታ ጣቱን ቀስሮ የመጣው ወደ መንግስት ሆነ፡፡ እናም ይህን ጉዳይ ማስተባበል የሚቻለው ለመላምትነት በሚቀርቡ ባለስልጣናት ዙሪያ ነው፡፡ በዚህም መሠረት የገቢዎች ሚኒስትር አቶ መላኩ ፈንቴ የሚመራ ቡድን በሙስና ተጠርጥሮ ወህኒ ወረደ፡፡ ሙስና በዚህች ሀገር ላይ አይፈፀምም ሣይሆን ሙስና ሌላው የመተዳደሪያ ደንብ ተደርጐ ሁሉ እስከመቆጠር ተደርሷል፡፡ ታዲያ አቶ መላኩ ላይ ይህ በትር ሲያርፍ እሣቸው በበርካታዎች ዘንድ በዚህ ነገር ስለማይጠረጠሩ ጉዳዩን ግራ የሚያጋባ እንዲሆን አድርጐታል፡፡ እንደውም አሁን በአንዳንድ ወገኖች በኩል እሣቸው እንዲፈቱ ፒቲሽን ሁሉ ሣይቀር የሚያስፈርሙ ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
አዜብን የሚጠረጥር ደፋር ጠፋ?

አዜብን የሚጠረጥር ደፋር ጠፋ?

እንደሚታወቀው ታዲያ የነአቶ መላኩ ፈንቴ የሙስና ጉዳይ ከተፈጠረ በኋላ “ትላልቆቹን አሳዎች” አጠምዳለሁ ሲሉ የተነሣው የፀረ ሙስና ኮሚሽን ጉዳይ ውስጥ ያለውን የሙስና ተግባር ለማጣራት ተደስቻለሁ ሲል ገልጿል፡፡ እንደሚታወቀው ከሆነ በርካታ በሙስና የሚገቡ ባለስልጣናት የተካሰሱበት ነገር በሙስና ሣይሆን ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ በርግጥም የዚህ አይነት ነገሮች ይኖራሉ፡፡ ለምሣሌ በ1993 ዓ.ም. አቶ ስዬ አብርሃ ሲታሰሩ የሙስና ጉዳይ ተባለ፡፡ የፀረ ሙስና ኮሚሽን እየመራሁ ነው ቢልም ከነመላኩ ፈንቴ በኋላ የተቋረጠ የሚመስለው ሙሰኞችን የማፈላለጉና የመያዙ ሁኔታ ብዙም አርኪ የሚባል አይደለም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከፖለቲካው አሠራር ነፃ መሆን ይኖርበታል፡፡ ሕዝብ እንኳን የትኛው ባለስልጣን ምን አይነት ሀብት እንዳለው፤ የማን ባለስልጣን ህንፃ እንደሆነ በደንብ ያውቃል፡፡ ይህን ጉዳይ ደግሞ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጠፍቶት ነው ብሎ በድፍረት ለመናገር የሚከብድ ነው የሚሆነው ምክንያቱም እያንዳንዱን ነገር ውስጥ ድረስ በመግባት የመመርመር ስልጣን አለውና፡፡ ፀረ – ሙስና ግን ይህን ነገር አይቶ በማለፍ የማይረቡና የዚህን ያህል አንጀት የሚያረሱ ጉዳዮች ላይ ጊዜውን ሲያባክን ይስተዋላል፡፡ በአሁኑ ወቅት በዚህች ሀገር ሁሉም ነገር የተሳሰረ ሆኗል፡፡ ኢህአዴግ ፈፅሞ ነፃ ሆነው እንዲሰሩ የሚፈቅድላቸው ተቋማት የሉም፡፡ እነ አምነስቲና ሌሎች የሰብአዊ መብት ጉዳዮች የሚቆጣጠሩ ተቁማት ላይ የኢህአዴግ አባል የሆኑ ግለሰቦችን ቢያስገባ ሁሉ ደስታው ነው፡፡ የማይሆን ነገር ሆኖበት ነው እንጂ ታዲያ አሁን ያለው የሙስና ሁኔታ ምን ያህል የሚያስኬድ ነው; ምን አይነት ለውጥስ ያመጣል; የሚለውን ከታዘብን፡፡
በፀረ ሙስና ኮሚሽን የሚገኝ ሙስናን የማፈላለግና ለውጥ የሚመጡት ነገር ምናልባትም በኢህአዴግ ችሮታና፣ እሱ ይህንን አድርጉ ሲል የሚፈጠር ነው የሚመስለው፡፡ ይህ ነገር ደግሞ ቀደም ብሎ አፈትልኮ በወጣ ምስጢር አማካይነት የተሰማ ነው፡፡ በጥቅምቱ የባህርዳር ጉባኤ ወቅት “አቶ መላኩ ፈንቴ ምን ብለው ተናግረው ነበር; እነማንንስ አጋልጠው ነበር; ማን ነው ይህንን እንዲናገሩ ሁኔታዎችን ያመቻቸላቸው; ከዛስ በማን ተጠልፋው ለዚህ ነገር በቁ;” እነዚህ እነዚህ ጉዳዩች በሙሉ ተጋልጠው ሲታዩ በውስጣቸው የፖለቲካ መንፈስ እንዳለበት በግልፅ የሚያሣይ ነው፡፡ ዛሬ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሙስና ተነክረዋል፡፡ አንዳንደች የግምገማ በትሩ ሲበረታባቸው ካላቸው ወይም በሙስና ከገነቡት ቤት አንዱን ለፓርቲዬ ብለው ያስረክባሉ፡፡ የፀረ ሙስና ኮሚሽን የዚህ አይነት ነገሮችን ለምንና እንዴት በማለት መጠየቅ ቢገባውም ይህንን አልደፈረም፡፡ የፀረ ሙስና ኮሚሽን ባይነግረንም ከዚህ በኋላም ምናልባት ከአንድ አመት በኋላ አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጠን ይወርዳል፡፡ ከኢህአዴግ ጋር አብሮ ከመኖር የገባን ነገር ነው፡፡ ከአንድ አመት ተኩል በኋላ ፓርቲው የአምስት አመት የስራ ጊዜውን ይጨርሳል፡፡ እናም ኢህአዴግ የሚፈልገውን ከማይፈልገው ሲለያይና ሲመዳደብ ለፀረ ሙስና ኮሚሽንም የሚሰጠው ቦታ ይኖረዋል፡፡ በቃ እንዲህ እንዲህ እየተባለ ነው ታዲያ ፀረ ሙስና ኮሚሽንም ስራ ወይም እንቅስቃሴ አደረገ የሚባለው፡፡ እናም ከነመላኩ ፈንቴ በኋላ ፀረ ሙስና ኮሚሽን የቆመ መርከብ ሆኗል፡፡ ሌሎች ሙሰኞች መረጃቸውን እንዲያሸሹ ከነመላኩ ጓደኞች ስህተት ተምረው እንዲዘጋጁ ያደረገ ነው የሚመስለው፡፡ ብዙ መሄድ ሲገባው በትንሹ ተጉዞ ለጊዜው በቃኝ ሲል የወሰነ ተቋም ሆኗል፡፡

የካህናት ጉባኤ በሚኒሶታ በቅዱስ ጳዉሎስ ከተማ!

$
0
0

ourael
የደብረ ብርሃን ቅዱስ ኡራኤል ዓመታዊ ንግሠ በዓል ሐምሌ 7/28/2013 ለአስረኛ ጊዜ በደማቅ ይከበራል። በእግዚአብሔር መልካ ም ፈቃድ በቅዱስ ጳዉሎስ እና ሚናፖሊስ ከተማዎች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ታዳሚወች ሁነዉ የበረከቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለህዝበ ክርስቲያን ጥሪያችንን ስናስተላልፍ በታላቅ ደስታ ነዉ። የቅዱስ ኡራኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከተቋቋመ ጀምሮ በእግዚአብሔር ቸርነት ከእለት ወደእለት አገልግሎቱን በማስፋት ላይ ይገኛል ፤ የአባቶችን ቡራኬና በረከት እያገኘን የሰላም እና የፈዉስ ቦታ ሁኗል። የቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን ባለፉት ዓመታት ታላላቅ ጉባኤወችን አስተናግዷል፤ ይኸዉም በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፓትርያርክ ዘኢትዮጲያ የሚመራዉን ቅዱስ ሰኖዶስ ጉባኤ እና የሰንበት ትምህርት ቤት የአንድነት ጉባኤን በማስተናገድ ህዝበ ክርስቲያኑ የመንፈሳዊ መድረክ ተሳታፊ ሁኗል። አሁንም ከሐምሌዉ ንግሠ በዓል ጋር አብሮ የተያዘዉ ታላቅ ፕሮግራም 1ኛ የካህናት ጉባባኤ ከሐምሌ 22-26/2013፦እንዲሁም የሰንበት ት/ቤት የአንድነት ማህበር የመሃከለኛዉ ምዕራብ ጉባኤ ሐምሌ 7/27/2013 በቅድሱ ኡራኤል በተክርስቲያን ይከናወናል።
የመርሃ ግብሩ ቀናት፦
- ማክሰኞ (7/22/2013) እስከ ሐሙስ (7/25/2005) የካህናት ጉባኤ ይጠናቀቃል።
- አርብ እና ቅዳሜ (26-27/2013) ለህዝበ ክርስቲያኑ የትምህርት ፕሮግራም ከ5pm-7pm
በ7/27/2013 ሙሉ ቀን የሰንበት ት/ቤት ጉባኤ
እሁድ ሌሊት ስርዓተ ማህሌት፤ ጸሎተ ኪዳን ፤ጸሎተ ቅዳሴዉ በብጹዓን ሊቃነጳጳሳት ተመርቶ በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
ሁላችንም በአንድነት በቅዱስ ኡራኤል ንግሠ በዓል ተገኝተን የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን ጥሪያችንን እያቀረብን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ከጊዜዉ ከሰዓቱ በሰላም ያድርሰን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ደብረ ብርሃን ቅዱስ ኡራኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን።

1144 Earl Street Saint Paul Minnesota 55106

(ሰበር ዜና) ቋሚ ሲኖዶሱ ፓትርያርኩ አስተዳደር ነክ ውሳኔዎችን ብቻቸውን እንዳይሰጡ የውሳኔ ሃሳብ አቀረበ

$
0
0

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በተቃውሞ ላይ

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በተቃውሞ ላይ

(ዘ-ሐበሻ) ቋሚ ሲኖዶሱ ሳይሰበሰብ፣ የተማሪዎቹ ጥያቄ በአግባቡ ሳይመለስና ሳይጠና ከአቡነ ጢሞጢዎስ ጋር ባላቸው ጥብቅ ወዳጅነት የተነሳ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እስከ መስከረም ድረስ እንዲዘጋ ፓትርያርኩ አቡነ ማቲያስ ወስነዋል በሚል ቋሚው ቅዱስ ሲኖዶስ ተቃውሞውን ማሰማቱን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ። ከአዲስ አበባ ለዘ-ሐበሻ ሾልከው የመጡት የቤተክህነት መረጃዎች እንዳመለከቱት የቋሚው ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አስቸኳይ ጉባኤ እንዲጠራ አድርገዋል።
ጉባኤው መቼ እንደሚደረግ የዘ-ሐበሻ የቤተክህነት ምንጮች ያልደረሱበት ቢሆኖም በቅርብ ቀናት ውስጥ እንደሚደረግ ግን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። የቋሚ ቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ባወጡት የውሳኔ ሃሳብ መሰረት ፓትርያርኩ ቡራኬ ከመስጠት በቀርቭ አስተዳደራዊ የሆኑ ውሳኔዎችን ብቻቸውን እንዳይሰጡ ይከለክላል። ይህ አዲስ የውሳኔ ሃሳብ እንደሚለው ፓትርያርኩ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን ሲሰጡ በቅድሚያ ከቋሚው ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር እንዲነጋገሩበትና በጋራ እንዲወሰን ያዛል። ይህ ፓትራይርኩ በአስተዳደራዊ ውሳኔዎች ላይ ስህተት እንዳይፈጽሙ ወይም የሚደርስባቸውን ወቀሳም ይቀንሳል በሚል የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በተጠራው ጉባኤ ላይ ከጸደቀ ሕግ ሆኖ እንደሚያገለግል የዘ-ሀበሻ የቤተክህነት ምንጮች አጋልጠዋል።
በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተነሳው የተማሪዎች ተቃውሞ እስካሁን እልባት አላገኘም። ዘ-ሐበሻ አሁንም ጉዳዩን ተከታትላ መረጃውን ለሕዝብ ታደርሳለች።

ግልጽ ደብዳቤ ለሃይሌ ገብረሥላሴ (ከአበበ ገላው)

$
0
0

haile

ውድ አትሌት ሃይሌ፣ ከነመላው ቤተሰብህ እንደምን ከርመሃል? ልጆቹ እንዴት ናቸው፣ አለምስ እንዴት ሰንብታለች?
ሰሞኑን የወዳጅ የዘመድ ምክር አላዳምጥ ብለህ እንደነ ጋሼ ግርማና ጋሼ ሃይለማርያም ደሳለኝ የህወሃቶች አሻንጉሊት መሆን እንዳማረህ ስሰማ በጣም ተገረምኩ። በመላው አለም ዝና ያተረፍክበትን እሩጫ ትተህ “ቤተመንግስት” ወይንም “ፓርላማ” ቁጭ ብለህ ዝንብ ማባረር ምን ይጠቅመኛል ብለህ ነው? አንተም እንደነጋሼ ግርማና ሀይለማሪያም በቁምህ ከመሞትህ በፊት ምክሬን ባትሰማ እንኳን ለማንኛውም ይቺን አጠር ያለች ጦማር ልጽፍልህ ወሰንኩ።
እኔ ያቺን “ሪከርድ” የሰበርክባትን ቲሸርት ነፍሳቸውን ይማርና ለዛ ህዝብ ላፈኑ፣ ላሰቃዩ፣ ለረገጡና ለጨረሱ፣ እንኳን በቁማቸው ሞተውም ላስመረሩን የሂትለርና የሞሶሊኒ ግልባጭ በአደባባይ ስትሸልም መካሪ ማጣትህን ገምቻለሁ። ግለሰቡ መሸለም ሳይሆን ተይዘው እንደ ናዚዎቹ ኑረንበርግ ለፍርድ መቅረብ ይገባቸው እንደነበር ጠፍቶህ ነበር ማለት አይቻለኝም። ግን ሃያሉ ፈጣሪ ፍርዱን እንደማያዘገይ አሳየን።
alamudi

ከሁሉ የገረመኝ ደግሞ ልክ እንደ ህወሃት ካድሬዎች በኢቲቪ ቀርበህ “ታላቅ መሪ” አጣን እንባ አዋጡ እያልክ ካሜራ ፊት እንባ ስትጨምቅ ማየቴ ነበር። ያቺን የዋህ ደራርቱ “ለኛ ብሎ ታገለ፣ መስዋት ሆነ፣” ምናም እያለች ስታነባ በኢቲቪ ሳይ አንተ ሳታሳስታት እንዳልቀረህ በልቤ ገምትኩ። ከተሳሳትኩ ይቅርታ!
ውድ ሀይሌ፣ በህዝብ ዘንድ መከበርና መወደድ በቢሊዮን ዶላር እንኳን እንደማይገዛ ከቱጃሩ አላሙዲን መማር ይቻላል። ቱጃሩ አላሙዲን ሰሞኑን ወደ ዋሽንግተን ከአስር አመት በሁዋላ ሲመጡ የተከራዮት ታላቅ እስታዲየም በህዝብ ይጨናነቃል ብለው ጠብቀው ነበር። ይሁንና ነበር ባይሰበር ሆነና ነገሩ ያን ያሚያህል ስታዲየም እንኳን ሰው ወፍ ዝር ሳይልበት እንደሰማነው ከሆነ አራት ሚሊዮን ዶላር የፈሰሰበት ድግስ ከንቱ ቀርቶ የሚበላው ጠፍቶ ተደፋ:: ቱጃሩም በሃፍረት ተሸማቀው መሰወራቸውን ስነግርህ በታላቅ ሃዘን ነው። ይህ ቱጃር በህዝብ ዘንድ ምን ያህል የተከበሩና የተወደዱ እንደነበር፣ የዛሬን አያድርገውና፣ ሁሉም የሚያውቀው ጉዳይ ነው። ሁሉ አልሳካ ቢላቸው ምስኪኑ ቱጃር ከሩቅ ሆነው አፋችንን ለማዘጋት እየዛቱ ነው። ዝርዝሩን ሰሞኑን አጫውትሃለሁ::
2
ቱጃሩ ድንገት በምርጫ 97 (ዝ)ንባቸውን በኩራት ደረታቸው ላይ ለጥፈው “ለህወሃት እሞታለሁ እያሉ ያዙኝ ልቀቁኝ” አበዙ። አስተዋዩ ህዝባችን ፊቱን አዞረባቸው። በቃ፣ ያሁሉ ቢሊዮን ከንቱ መሆኑ ታየ። ገንዘባቸውም አድናቂ አጣ፣ እርሳችውም ክብር እና ፍቅር በገንዘብ እንደማይሸመት ተረዱት። ዛሬ የሚያጅቧቸውም ጥቂት ግለሰቦች እርሳቸውን ሳይሆን ገንዘባቸውን ያፈቀሩ መሆኑ ያደባባይ ሚስጥር ነው። በዚህ በክፉ ቀን ህዝብን ከከዳህ ቀባሪህ ጅብ እንጂ ሰው አይሆንም።
ወደ ተነሳሁበት ቁም ነገር ልመለስና ስለምኞትህ ትንሽ አስተያየት ልሰንዝር። ከሚድያ መረዳት እንደቻልነው ሁለት ምኞቶች አሉህ። አንደኛው የመቶ አለቃ ግርማን መቀመጫ መረከብ ሲሆን ሌላው ደግሞ የፓርላማ አባል ለመሆን ነው። እኔንም የገረመኝ የምኞቶችህ ከንቱነት ነው።
እንደምታውቀው “ፕሬዚዳንት” ተብሎ የሚሰየመው ሰው የህወሃቶች አሻንጉሊት ሆኖ ዋና ስራው እንግዶች መቀበልና መሸኘት ነው። ዶሮን ሲያታልሏት ሆነና ነገሩ አቶ መለስ ይህ “ስልጣን” የሚገባው ኦሮሞ ለሆነ ሰው ነው ብለው ባደባባይ ወስነው ስለነበር ቦታውን ሁለት የኦህዴድ አባላት ይዘውት ቆይተዋል። ኦህዴድ እንደሚታወቀው የፈጣሪው የህወሃት ሎሌ እንጂ ታላቁን የኦሮሞን ህዝብ ፈጽሞ አይወክልም። ኦሮሞ ኢትዮጵያዊያን የጠየቁት እውነተኛ እኩልነት እንጂ አሻንጉሊት እንዳልሆነ እንኳን አዋቂ አፍ ያልፈታ ህጻን የሚያውቀው ጉዳይ ነው።
የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ነጋሶ የነበሩ ሲሆን እርሳቸውም አሻንጉሊትነት በቃኝ ብለው ጥያቄ መጠየቅ ሲጀምሩ እንዲነሱ ተደረገ። አንተ ጎበዙ እሯጭ በምን መስፈርት ነው ታዲያ ፕሬዚዳንት መሆን ያማረህ? የዘር መሰፈርትን ካላሟላህ፣ እጅና እግር እያለህ፣ ሕሊና ካለህ እንደ ኳስ መንከባለል እንዴት ይቻልሃል?
ነጋሶ ቢያንስ ከመሰናበታቸው በፊት መለስን “መንግስቱ መንግስቱን ሸተትከኝ” ማለታቸው የሰሩትን ስህተት ማረሚያ ሲሆናቸው ገነት ዘውዴን ግን ማስለቀሱን ተጽፎ አነበብን። እንደ ሰማነው ገነትን ያንሰቀሰቃቸው ላቶ መለስ ያላቸውን ፍቅር ለመግለጥ ብቻ ሳይሆን የነጋሶን ወንበር ይመኙ ስለነበር ነው። “ፕሬዚዳንት ገነት ዘውዴ” ምናምን እያሉ እራስ ለማታለል ማለት ነው።
ነጋሶ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ ለመጀመሪያ ግዜ በኢትዮጵያ ታሪክ ስልጣን በሰላማዊ መንገድ በህዝብ ለተመረጠ ሰው ሲሰጥ በአይኔ በብረቷ አየሁ ብለው የድንቢጥ ማስክርነት ሰጥተው የነበሩት ገነት ዘውዴ፣ ለመለስ ምን አስለቀሳቸው ብለን መመራመር አያስፈልገንም። ነገሩ “ሆድ ሲውቅ…” እንደሚባለው መሆኑ ነው። ግን ያዞ እንባቸውም ከንቱ ቀረ። የወይዘሮ ገነት ዘውዴም ጌታ በዚያው አሸለቡ፣ እኛም ታዝበናቸው ቀረን። ምስኪን!
ነጋሶ ሲሰናበቱ ያተንኮለኛ አንባገነን ጥያቄ የማይጠይቅና አሻንጉሊትነቱን ሙሉ በሙሉ የሚቀበል ሰው አፈላልገው መቶ አለቃ ግርማን ፕሬዝዳንት ብለው ሰየሙ። ጋሽ ግርማ መቼም ድሮም ወስላታ እንደነብሩ አብረዋቸው የሰሩ ሁሉ የሚመሰክሩት ጉዳይ ነው። ህሊናቸው አይወቅሳቸውም። ይኸው እስካሁን አልጋ ላይ ሆነው፣ በዊል ቼይር እየተገፉ የህወሃቶች ላንቲካ እንደሆኑ መሞቻቸው ተቃርቧል። መቶ አለቃ ግርማ ወደ መቃብራቸው በህወሃቶች ሰረገላ ታጅበው ሲጋዙ ዶ/ር ነጋሶ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠይቀው ለህዝባችን አንድነትና ነጻነት እየታገሉ ይገኛሉ። ከጥፋቱ የሚማር ሁሉ ታላቅ ሰው ነው።
ሃይሌ ሆይ፣ ያንተ ዋናው ጉብዝና እሩጫ ነው። እንኳን አጸያፊውንና የሚከረፋውን የህወሃቶች የዘር ፖለቲካ መፈትፈት ይቅርና ሽምግልናም አልሆነልህ። ታስታውስ እንደሁ አቶ መለስ በግፍ ያሰሯቸውን አገር ወዳዶች ለማስፈታት ከነፕሮፌሰር ኤፍሬም ጋር
3
ሆነህ ያደረከው ጥረት መልካም ቢሆንም ምንም ያልበደሉ ንጽሃን ዜጎች ስንት ግፍና ጭፍጨፋ የፈጸሙትን መለስ ዜናዊን ይቅርታ እንዲጠይቁ ተደርጓል። ይሄ ደግሞ በታሪክ ያስወቅሳል።
በርግጥ ህወሃቶች ምን ቃል እንደገቡልህ አላውቅም። ይሁንና እንኳን ፕሬዚዳንትነት ጠቅላይ ሚኒስትነት ፈጽሞ አይመጥንህም። ጠቅላይ ሚኒስቴር ስል ጋሼ ሃይለማሪያም ትዝ አሉኝ። እኚህ ግለሰብ ገና አርባ ምንጭ ሲሰሩ ጀምሮ የሚታወቁበት አንድ መለያቸው ለህወሃቶ ጭራ መቁላት ነበር። ቀስ በቀስ ወደ ባለራዩ መሪ ቢሮ ጠጋ ሲሉም ስራቸው ከጭራ መቁላት ወደ ምንጣፍ አንጣፊነት ከፍ እንዳለ የሚውቋቸው ሁሉ የሚናገሩት ጉዳይ ነው።
ዛሬ በህወህት ጄኔራሎችና አማካሪዎች ታጅበው የመሪነት ስልጣን ሳይሆን የአሻንጉሊትነት ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ። እኚህ ሰው የሌለና ያልነበረ ራእይ እጠብቃለሁ ብለው ደፋ ቀና ሲሉ በቁሙ የሞተው “መሪ” የሚል ቅጽል ወጥቶላቸው ተከብረው ሳይሆን የህወሃቶች ላንቲካና መጫውቻ ሆነው ሲሽከረከሩ ይውላሉ። ሰው ለህሊናው ማደርን ትቶ ሆድ ለመሙላት ብቻ ከኖረ የሚያዳምጠው ህሊናው የሚናገርውን እውነት ሳይሆን የሆዱን ፍላጎት ብቻ ነው። ጋሽ ሃይለማሪያም ህሊናቸውን አፍነው ሆዳቸውን እያዳመጡ መኖራቸው የሚያስከብራቸው ሳይሆን ለዘላለም የሚያስንቃቸው የታሪክ እውነታ ነው።
ውድ ሃይሌ፣ ሌላው ምኞትህ ደግሞ ፓርላማ ገብቶ ህግ ማውጣት ነው። ለመሆኑ ይሄ የህወሃቶች አዳራሽ ከመቼ ወዲህ ነው ለሃገርና ለወገን የሚጠቅም ስራ ሰርቶ የሚያውቀው። ወያኔዎች ዴሞክራሲ አመጣን ብለው ሁሉን ነገር ሙሉ በሙሉ እንደፈለጋቸው ተቆጣጥረው፣ ህዝብ እያስለቀሱ ፣ እያፈኑ፣ እየገደሉ፣ እያሰቃዩና እየዘረፉ ሲኖሩ ለመሆኑ መቼ ነው ፓርላማ ተብዬው የህዝብ ብሶት ተወያይቶ የሚያውቀው? የትኛውን መብት ነው ያስጠበቀው?የትኛውን ህግ ነው ያስከበረው? እኛ እስከምናውቀው ፓርላማ ማለት የህወሃቶች የቧልት አዳራሽ ነው። ቧልት ካማረህ፣ ለህወሃቶች ጭራ እየቆላህ፣ እያጨበጨብክ መኖር ካማረህ ወደ አዳርሹ ግባና የሚሉህን ሁሉ አድርግ። እኔ ግን ኪሳራ እንጂ ትርፍ እንደማታገኝ ከወዲሁ ልነግርህ እወዳለሁ።
እንደሰማሁት ከሆነ የሙስና እናት በመባል የሚታወቁት አዜብ መስፍን ከፓርላማ አባልነታቸው፣ ከኤፈርት ቁንጮነታቸው በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከንቲባና የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት መሆን ይፈልጋሉ። አዜብ ከባላቸው ሞት በሁዋላ ፍላጎታቸውም በጣም እንደጨመረ እንደውም የመለስን እራእይ አስጠባቂ እኔ ነኝ ማለታቸው ትክክል ነው። በዘር ላይ ተመስርቶ የኢትዮጵያን ህዝብ ደም እየመጠጠ ያለው ኤፈርት ባለቤቶ ጋር መወዳደር በፖለቲካው ብቻ ሳይሆን በንግዱም ዘርፍ ብዙ ኪሳራ ስለሚያስከትልብህ ጠንቀቅ ብትል ይሻልሃል። ፕሬዚዳንትነቱንም ሆነ ፓርላማውን ለነአዜብ ተውላቸው። የነሱ የፍርድ ቀን እሩቅ አይደለም…
አንተም የኢትዮጵያን ህዝብ ማገልገል ከፈለክ ህዝባችን ከህወሃቶች የአፓርታይድ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት የሚያደርገውን ትግል በሙሉ ልብህ ደግፍ። ትንሽም ብትሆን መሰዋእትነትና ዋጋ ክፈል። ፓርላማም ሆነ ቤተምንግስት ገብተህ የህወሃቶች ጉልቻ አትሁን።
ለማንኛውም የኔን ምክር ተውና የባለቤትህን የአለምዬን ምክር ስማ። ሴት መቼም ሁል ጊዜም ብልህ ነችና፣ አለም አያዋጣህም ብልሃለች። “ጨው ለራስህ ብትል…” ነው ነገሩ።
እኔ በበኩሌ የምመኘው በአገሬ እንደማንም ተራ ዜጋ ተከብሬ የነጻነት አየር እየተነፈስኩ መኖር ብቻ ነው። ከቤተ መንግስት ይልቅ የእናቴ ደሳሳ ጎጆ ትናፍቀኛለች።
ነጻነታችን ሲታወጅ ቤተመንግስት ሳይሆን አዲስ አበባ መንገድ ላይ እንደምንገናኝ ተስፋ አደርጋለሁ።የሰው ምክር ብትሰማ መልካም፣ ካልሰማህ ግን አንተንም እንደ አቶ መለስ በአደባባይ ካገኘሁህ ቀልብህን ገፍፌ….በማለት በፈገግታና በደስታ አጭሯን ጦማሬን አጠቃልላለሁ። …ለአለምዬ ልባዊ ሰላምታዬን አድርስልኝ። ያንን ቱጃር ግን ካገኘኸው እንደማለቀው ንገርልኝ!
ለማንኛውም መልካም እድል ለሁላችን!

ግልጽ ደብዳቤ ለሃይሌ ገብረሥላሴ -ከአበበ ገላው

$
0
0

haileውድ አትሌት ሃይሌ፣ ከነመላው ቤተሰብህ እንደምን ከርመሃል? ልጆቹ እንዴት ናቸው፣ አለምስ እንዴት ሰንብታለች?
ሰሞኑን የወዳጅ የዘመድ ምክር አላዳምጥ ብለህ እንደነ ጋሼ ግርማና ጋሼ ሃይለማርያም ደሳለኝ የህወሃቶች አሻንጉሊት መሆን እንዳማረህ ስሰማ በጣም ተገረምኩ። በመላው አለም ዝና ያተረፍክበትን እሩጫ ትተህ “ቤተመንግስት” ወይንም “ፓርላማ” ቁጭ ብለህ ዝንብ ማባረር ምን ይጠቅመኛል ብለህ ነው? አንተም እንደነጋሼ ግርማና ሀይለማሪያም በቁምህ ከመሞትህ በፊት ምክሬን ባትሰማ እንኳን ለማንኛውም ይቺን አጠር ያለች ጦማር ልጽፍልህ ወሰንኩ።  ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


አክራሪነት በኢትዮጵያ –ጥያቄዎች ለሃጂ ናጂብ

$
0
0

አማኑኤል ዘሰላም
amanuelzeselam@gmail.com

July 17, 2013

ከማከብራቸው የዲሞክራሲ አክቲቪስት መካከል አንዱ የሆኑት፣ አቶ ተድላ አስፋዉ፣ አቶ ጃዋር መሃመድ ለተናገራቸው አንዳንድ አባባሎች የሰጡትን ምላሽ አነበብኩ። አቶ ጃዋር የተወለደው በአርሲና በሃረርጌ ድንበር አካባቢ ነዉ። በዚያ አካባቢ ነዉ አርባ ጉጉ (ምእራብ አርሲ) እና በደኖ (ምስራቅ ሃረርጌ) የሚገኙት። ወያኔ/ኢሕአዴግና ኦነግ ስልጣን በጨበጡ ጊዜ፣ በአርባ ጉጉና በደኖ የተፈጸሙትን ሁላችንም የምናወቀዉ ነዉ። አካባቢዉን ከክርስቲያኖችና ከ«አማራዎች» ለማጽዳት ፣ ብዙዎች በቤታቸው ተቆልፎባቸው ተቃጥለዋል። ብዙዎች፣ ነፍሰ ጡር እህቶቻችን ሳይቀሩ፣ ጥልቅ በሆነ ጉድጓድ ዉስጥ፣ አይኖችቸው በጨርቅ ታስረዉ፣ በሕይወት ተወርውረዋል። አርባ ጉጉን ኦሕዴድ/ኢሕአዴግ ፣ በደኖን ደግሞ ኦነግ ነበር የሚያስተዳድሩት። በዚያን ወቅት ከፍተኛ ፀረ-አማራና ፀረ-ክርስቲያን የጥላቻ ዘመቻ ይደረግ ነበር። ብዙ ያልተማረው ሕዝብ፣ ተማሪዎች፣ ልጆች ፣ የዚህ ጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ሰላባዎች እንዲሆኑ፣ ይህን አይነት የጥላቻና የአክራሪነት አስተሳሰብ እንዲኖራቸው ተደርጓል።
haji negib
አቶ ጃዋር መሃመድ የዚህ ዉጤት ናቸው። አሁን የሚያንጸባርቁት፣ ያኔ በልጅነታቸው ከኦሕዴድና ኦነግ አክራሪዎች የተማሩት ነዉ። ይህ አይነቱ የጥላቻና የአክራሪነት ፖለቲካ በኢትዮጵያ ዉስጥ ቦታ ሊኖረው የማይገባ፣ ለአገር ትልቅ ጠንቅ የሆነ ፖለቲካ ነዉ። አቶ ተድላም በዚህ ጉዳይ ላይ ጊዜያቸዉን ወስደው አክራሪነትን እና ጥላቻን ለማጋለጥ ላደረጉት አስተዋጾ ላመሰግናቸው እወዳለሁ።

በቅድሚያ አክራሪነት ላይ ትንሽ ልበል። በአለማችን የሙስሊም አክራሪዎች በርካታ ጥፋቶች እየፈጸሙ እንደሆነ ሁላችንም የምናወቀዉ ነው። እነዚህ አክራሪዎች ዋሃቢስት ወይንም ሳላፊስት ይባላሉ። አላማቸው ሰው ሁሉ ሙስሊም እንዲሆን ነዉ። «ከሙስሊም (ይሄ ሱፊዎችና ሺያዎችን አይጨምርም) ውጭ ያሉ በሙሉ፣ እዉነተኛ ሙስሊም መሆን አለባቸው። አሊያም መጥፋት ይኖርባቸዋል» የሚል እምነት ነዉ ያላቸው። ሁሉንም በፍቃደኝነት ሆነ በሃይል ካሰለሙ በኋላ፣ በአንድ ከሊፋ የሚመራ፣ የሽሪያ እስላማዊ መንግስት ማቋቋም ነዉ አላማቸው።

የግብጹ ሙስሊም ወንድማማቾችን እንመልከት። አካባቢዉን ሁሉ (ግብጽ፣ ሶሪያ፣ ሳዉዲ አረቢያ፣ ዮርዳኖስ ፣ ሊባኖስ …) በሙሉ ተቆጣጥሮ፣ ዋና ከተማዉን ኢየሩሳሌም አድርጎ ፣ አካባቢዉን ሙስሊም ካልሆኖት ቃፊሮች አጽድቶ፣ አንድ ታላቅ እስላማዊ የከሊፋ ግዛት ለሟቋቋም ነዉ ሲሰሩ የነበሩት። በየቦታዉ፣ ዉስጥ ዉስጡን የተደራጁ ናቸው። ከሰማኒያ አመታት በኋላ ፣ የግብጽ ወጣቶች በቀሰቀሱት አብዮት ላይ ተረማምደው በግርግር ስልጣን ጨበጡ። የክርስቲያኖችን እና አክራሪ ያልሆኑ ሙስሊሞች ጥያቄ ወደ ጎን አደረጉ። እስላማዊ ሕገ መንግስት አጸደቁ።

አላማቸው ሕዝቡን በሙሉ ማገልገል፣ ግብጽን ማሳደግ ቢሆን ኖሮ፣ የሁሉንም መብት የሚያስከበር ሕግ መንግስት እንዲኖር ያደርጉ ነበር። ነገር ግን አላማቸው አገራዊ ሳይሆን አክራሪነት በመሆኑ፣ የማታ ማታ ከሕዝባቸው ጋር ተጋጩ። ሞርሲ ከስልጣን ወረዱ። ይኸው ግብጽም በነዚህ አክራሪዎች ምክንያት እየታመሰች ነዉ።

አንድ ነገር አንርሳ። እነ ሞርሲ ለምርጫ ይወዳደሩ በነበረበት ወቅት፣ ስዉር አላማቸውን ደብቀዉት ነበር። ስልጣን ከያዙ በኋላ ነዉ እዉነተኛ ማንነታቸው የተጋለጠው።

ኢትዮጵያ ዉስጥም አክራሪዎች አሉ። ለጊዜው ማንነታቸውን ደብቀዉ፣ ኃይላቸዉን እስኪያፈረጥሙና ስልጣን እስኪጨብጡ ድረስ ሞደሬቶች ሊመስሉን ይችላሉ። የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበረ፣ አንድ አክራሪ የኢሕአዴግ ባለስልጣን ሙስሊም ነበር። (በዚህ አጋጣሚ ኢሕአዴግ እራሱ በአክራሪዎች የተሞላ ድርጅት መሆኑን የሚያሳይ ነው) አብያተ ከርስቲያናት እንዳይገነቡ እየከለከለ፣ መስኪዶች እንዲገነቡ ይፈቅድ ነበር። መስኪዶች መሰራታቸው ችግር ባይኖረዉም፣ ቤተ ክርስቲያናት እንዳይሰሩ እያከላከሉ መስኪድ እንዲሰራ መፍቀድ ግን፣ ሌሎች እምነቶችን ለማዳከምና ለማጥፋት የሚደረግ አክራሪነት ነዉ።

እነ ጃዋር መሃምድ፣ እስላማዊ ኦሮሚያን፣ ብሎም እስላማዊ ኢትዮጵያን ለማቋቋም አላማቸው አድርገዉ ሲንቀሳቀሱ፣ ብዙ ልንደነቅ አይገባም። እነዚህ ከአለምአቀፉ የሙስሊም ወንድማማች ጋር እየተመካከሩ፣ እጅና ጓንት ሆነው የሚሰሩ ናቸው። ወጣት ጃዋር መሃምድ፣ ቸኩሎ የረጅም ርቀት አላማቸዉን አጋለጠባቸው እንጂ፣ በአሁኑ ጊዜ በአብዛኛዉ፣ ሰላማዊ፣ ሞደሬት ፣ ከሁሉም ጋር መስራት እንደሚፈልጉ፣ አድርገዉ ነዉ እራሳቸውን የሚያቀርቡት። በአሁኑ ጊዜ ትኩረታቸው ሙስሊም ያልሆነው ክርስቲያኑ ላይ ሳይሆን፣ ሞደሬት ሙስሊሞች ላይ ነዉ። ከዋሃቢዝም ዉስጥ የተሳሰተ እስልምና የሚከተሉ የሚሏቸውን ማጥራት፣ ለዚህ ዘመቻም መሰናክል የሚሆኑትን፣ ታላላቅ የሙስሊም አባቶችን፣ ማስወገድ ዋና አላማቸው ነዉ።
ይሄንን ኢትዮጵያዉያን ሁሉ ከወዲሁ ማገናዘብ ያለብን ይመስለኛል። ጉግል እያደረግን ትንሽ ጥናት ብናደርግ ብዙ የአክራሪዎችን ታክቲኮች እንረድለን።

አብዛኛው ኢትዮጵያዊ፣ ለዜጎች መብት መከበር፣ ለእምነት ነጻነት፣ ለዴሞክራሲ ያለዉን ቁርጠኝነት እያሳየ የሚገኝበት ወቅት ነዉ። እነ ኡስታዝ አቡበከር፣ ከመታሰራቸው በፊት ሲያስተምሩት በነበሩ ትምህርቶች ላይ ተቃዉሞ የሚኖርን ብዙ አለን። ነገር ግን የሚያስተምሩትን ብንቃወምም፣ ትምህርታቸውን በትምህርት መመክት ሲቻል፣ ሃሳባቸውን በነጻነት የመግልጽ መብታቸው ተረግጦ፣ አንዲት ጠጠር ሳይወረዉሩ ሽብርተኛ ተብለዉ፣ አሳፋሪ በሆነ መንገድ፣ በኢቲቪ ስብእናቸውና ክብራቸው ተዋርዶ ማየታችን እንደ ሰው፣ እንደ ኢትዮጵያዊ አሳዝኖናል። በነርሱም ላይ የደረሰው ግፍ ፣ የሃይማኖት ጉዳይ መሆኑ ቀርቶ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ በመሆኑም፣ ከነእስክንድር ነጋ፣ አንዱዋለም አራጌ ጋር፣ የነአቡበከርንም መፈታት ሕዝቡ እየጠየቀ ነዉ።

በእስረኞች መፈታት፣ በእምነት ነጻነት፣ በሰብዓዊ መብት መከበር፣ በሕግ የበላይነት ዙሪያ፣ በአንድ ድምጽ መናገር እንደጀመርነዉም፣ በአክራሪነት ዙሪያም አንድ ድምጽ መናገር አለብን። በጋራ ሁላችንም ዋሃቢዝም አክራሪነትን መቃወም ይኖርብናል።

የመጀመሪያው ከጂራ ፋንዉንዴሽን መሪ ለሆኑት ለሃጂ ነጂብ መሃመድ አቶ ተድላ በጻፉት ደብዳቤ «It is unfortunate you did not condemn Jawar Mohamed hateful speech » ብለዋል። ሃጂ ነጂብ መሃመድ፣ በተለያዩ የዳያስፖራ ኢትዮጵያዉያን ጉባዔዎች ላይ ሙስሊም ማሀብረሰቡን ወክለው የሚናገሩ ናቸው። በርግጥም እነ አቶ ጃዋርና መሰሎቻቸው የሚያራግቡትን አክራሪነት አለማውገዛቸው ተገቢ አይደለም። «ምናልባት ሃጂ ነጂብ ከላይ ሞደሬት ከዉስጥ ግን እንደ ጃዋር አክርራሪ ይሆኑ ይሆን ?» የሚል ጥያቄም ሊነሳ ይችላል።

የሳዉዲ ታላቅ ሙፍቲ (የዋሃቢስቶች ፓትሪያርክ እንደማለት ነዉ) ፣ ሼክ አብዱል አዚዝ ቢን አብደላ፣ ያለፈው አመት፣ በአካባቢዉ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲጠፉ ጥሪ አቅርበዉ ነበር። አንድ ተራ አክራሪ ይሄን አይነት አስተያየት ቢሰጥ፣ ብዙ ትኩረት ላይሰጠው ይችላል። ነገር ግን እኝህ ሰው ዋና መሪ ሆነው ነዉ፣ በነጃዋር የተንጸባረቀዉን አክራሪነት በይፋ ሲያወጁ የምንሰማዉ።

http://rt.com/news/peninsula-saudi-grand-mufti-701/

እንግዲህ ለሃጂ ነጂብ ያሉኝ ጥያቄዎች «እርሳቸውና የሚመሩት የሃይማኖት ተቋም ፣ ይሄንን አክራሪነት ለምን በይፋ አይቃወም ? ዋሃቢዝምን ለምን አያወግዝም ? በርግጥ ዋሃቢዝምና አክራሪነት የሚቃወሙ ከሆነ ደግሞ አክራሪነትን ለመወጋት በተግባር አስተምህሮ ይሰጣሉ ወይ ? » የሚሉት ይሆናል።

ለነዚህ ጥያቄዎች ግልጽ ምላሽ ባልተገኘበት ሁኔታ፣ ከነዚህ ሰዎች ጋር መንቀሳቀስ በተዘዋዋሪ መንገድ አክራሪነትን ማጠናከር ሊሆን እንደሚችል መገንዘብ ያለብን ይመስለኛል። የሃይማኖት ነጻነትን በማስከበር ስም፣ አክራሪነትን በማስፋፋት የሃይማኖት ነጻነትን እንዲገፈፍ መስራት የለብንም።

እዚህ ላይ አንድ ነገር ግልጽ ላድርግ። ዜጎች የፈለጉትን የመሆን መብት አላቸዉ። እምነታቸውን የማስፋፋት፣ ክርስቲያኖችን አስተምሮና አሳምኖ ሙስሊም የማድረግ፣ መስኪድ የመከፈት ሙሉ መብት አላቸው። ክርስቲያኖችም ፣ ቤተ ክርስቲያን የመክፈት፣ ሙስሊሙን ክርስቲያን የማድረግ፣ ወንጌልን በሁሉም ቦታ የማስተማር ሙሉ መብት እንዳለቸው መረጋገጥ አለበት። ሙስሊሞች ክርስቲያን በመሆናቸው የሞት ፍርድ ሊፈረድባቸው አይገባም።

እንግዲህ አብረን እንድንሰራ ከተፈለገ «ሃይማኖት የግል አገር የጋራ» በሚለው መርህ ተስማምተን፣ አገራችንን እንደ አንድ ሕዝብ እያሳደግን፣ በፊናችን ደግሞ የምናምንበትን እምነት በሰላም ማስተማር፣ የምንከተለዉን ሃይማኖት ይዘን በሰላም መቀጠል ያስፈልጋል። ሰው የመረጠዉን የወደደዉን ሃይማኖት ይያዝ።

በአክራሪነት ላይ ይሄን ካልኩ ይበቃል። በጠባባ ብሄረተኝነት ላይ ያተኮረዉን ክፍል ሁለት በሚቀጥለው ጊዜ ይዤ እቀርባለሁ። ያኔም ጃዋር «ኢትዮጵያዉያን ከኦርሚያ ይዉጡ» ያለው አባባል በክልል ሕገ መንግስቶች በሰነድ የተንጸባረቀ መሆኑን ለማሳየት እሞክራለሁ።

ትንሽ ስለጃዋራዊያን (ለፋሲል የኔአለም መልስ)

$
0
0

ጎሳዬ(ጆሲ) ደስታ
አቶ ፋሲል የኔአለም እጄን ጠምዝዞ ክፉ ነገር ሊያናግረኝ እየገፋፋኝ ነው። “ትንሽ ስለጃዋራዊያን” በሚል ርእስ የጻፈው አስደናቂ ጽሁፉ ከልብ አስደስቶኛል። ሆኖም ግን አመለካከቱ አሁንም ሌላ ጀዋርን ከማስተናገድ የሚቆጠብ ስላልመሰልኝ አንድ ሁለት ነገር ላክልበት ተገድጃለሁ። በመጀመርያ ደረጃ በኛተቃዋሚ ውስጥ በሚድያ ገነህ ስላለህ ብዙ ግዜ ታግሼሃለሁ። ሆኖም ላርምህ ብሞክር ብዙ ሰው ቢያስቆጣም የመጣው ይምጣ ብዬ ልነግርህ መጥቻለሁ።
jawarጽሁፍህ ወደ መሃል ላይ እንድህ ይላል “አንድ ግዜ እናቴን አንቺ እኮ የኦሮሞ ደም አለሽ ፣ ይህ አካባቢ እኮ በኦሮሞዎች የተያዘ ነበር አልኩዋት”። አንተ ያንን ያልከው የጀዋርን ልብ ለማማለል ከሆነ ስለ ብሄርተኝነት የጠበቀ ግንዛቤ የለህም ማለት ነው። ታይለኖል ተውጦ ሚዳን ቢሆን ኖሮ እነ አቶ መለስበደዌው ተለክፈው ባልሞቱ ነበር። ኦሮሞ መሆን የሚያኮራ መሆኑን ማንም አይክድም። ግን ኦሮሞ ያልሆኑትን ሴትዮ በግድ ኦሮሞ ነሽ ማለት እራሱ ከኦነግ ጠባቦች አስተሳሰብ የተለየው ምኑላይ ነው? አንተ በግልህ ኦሮሞ መሆን ከፈለክ ሙሉ መብህ አለህ። ግን ያልሆኑትን አጉል ለመወደድ ብቻ በሚልሂሳብ ማስላቱ አስፈላጊነቱ አይገባኝም። አንድ ኢትዮዽያ ካልን ዘንዳ ምን ከዚ ነሽ ወይም ከዛ ነሽ አመጣው? ሁለትና ሶስት ትውልድ ከተዋለዱበት ቦታ ሰላማው ዜጎችን ያፈናቀለው ይህ አይነት አያትሽ/ህ ከዚ ብሄር ነው የመጣው የሚል አስተሳሰብ መስሎኝ? ደሞ ባክብሮት የምነግርህ ፥ የራስህትንአይደንቲቲ ክራይሲስ ሳትጨርስ ሌውን ለመስበክ ባትሞክር ጥሩ ይመስለናል።
ጽሁፍህ ወደመጨረሻ እንዲህ ይነበባል “…ፖለትከኞች ስልጣን ሲያምራቸው ታሪክን አጣመው ደጋፍዎችን ለማሰባሰብ ይሻሉ…”። እንደውም በተለይ አንተን ብዙ ግዜ በዚ ጉዳይ ኢሜል ላደርግህ ፈልግ ነበር። ለምሳሌ ያክል አንድ የአማራ ተውላጅ ድሮ ጫካ የነበረና በህዋላም ብአዴን ሆኖ ደሞ አሁንየከዳ ወጣት ኢንተርቪውን በሚያደርግበት ሰአት ደግመህ ደጋግመህ ኦነግ አልገደለም ወያኔ ነው የገደለው ብሎ እንዲናገር ስታጣድፈው ታይትዋል። እንድሁም በሌላ ግዜ ደሞ መምህር ኣባ ኒቆዲሞስ ኣስፋው ስለኦነግ አሰቃቂ ድርጊት ሲተነትኑ ወያኔ ብቻ ነው ያደረገው ብለው እንዲናገሩ ስታስጨንቃቸውነበር። ያንን ደሞ ስታደርገው የነበረው ከኦነግ ጋር የጀመራቹት ሰርግ ድግሱ ገና ስላላለቀ ነበር። አንተ የተደረገን ታሪክን በፈለከው መንገድ እየጠመዘዝክ ሌላውን እንዴት ልትገስጽ ታስባለህ። እኛ ዘመዶቻችን መሄጃ አጥተው ከዶዶላና ካርሲ አካባቢ እንደ እባብ እየታደኑ ሲጨፈጨፉ ማደርያ ቦታ አጥተውየዘመድ ቤት ሞልቶ ግቢ ሳር ላይ ሲያድሩ የምናውቀው የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው። ባህርዳር በሰላሙ ሃገር አንተ አኩኩሉ ስትጫወት ሌላው ሲታደን ነበር። ከፈለክ የብሄር ብጥብጥ ያስነሳል ብዬ ነው እንጂ ዝርዝሩን ማፍረጥረጥ ይቻላል። ላሁን ግን የዚህ ጽሁፍ አላማ ስላልሆን ቁስሉን አንካው።
ሃሳብህን ስታጠቃልል “አንድነት የሚሰብኩት ወገኖች ጃዋርያውያንን በመሳደብ ፣ በማውገዝ ፣ በማግለል ወይም ፎቶግራፋቸውን በማበላሸት ማሸነፍ እንደማይቻል ልብ ሊሉት ይገባል። እንድህ አይነቱን አስተሳሰብ ማሸነፍ የሚቻለው የተሻለ አስተሳሰብ በማምጣትና በመሞገት ነው” ብለሃል። በሃሳብደርጃ እስማማለሁ። ግን ታድያ ያንተ አይነት ፍልስፈና የሚሰራ ከሆነ ለምን ጀዋር የጥግ ፖለቲካ አራማጅ ሊሆን ቻለ? ወይንስ በቲቪ ስታሰድቡን ስለነበር ሃፍረትህን ለመሸፈን ምታደርገው መርበድበድ ነው? ሆነም ቀራም ጀዋር በገጀራ እንደማይመለስልን ነግሮናል። አቶፋሲል ደሞ ወረቀት ላይ ታሪክእየዘረዘርን መምዋገቱ ያዋጣናል ነው ምትለን። የፖለቲካ ተንታኝ ተብዬው የዘላበደው የተወሰነ ያፍ ወለምታ ቢሆን ኖሮ አቶ ፋሲል ያለው ይሰራ ይሆናል። ግን ግለሰቡ ጅማቱን ገትሮ በሜጫ አንገታችንን እንደሚለን እየነገረን ታድያ እንዴት ነው የታሪክ እና የፖለቲካ ፍልስፍና በማንጋጋት የምንወጣው?ፈረንጆች ለንደዚ አይነቱ ቀልድ ሲተርቱ “Don’t bring a knife to a gun fight” ይላሉ። ጠመንጃ ለሚያስፈልገው ውግያ ቢላዋ አታምጣ እንደማለት ነው።
እንደውም አቶ ፋሲል አልሰማውም ይሆናል እንጂ ባለፈው ሰይፈ ነበልባል በሚባል ሬድዮ ላይ ጀዋር ቀርቦ ካንድነት ሃይሎች ጋር መስራት እንደማይቻል ሲናገር ነበር። እናም እንዴት አድርገህ ነው ታድያ እሱንና መሰሉን የምታክማቸው? ያንተ ፕለቲካዊና ታሪካው ትንታኔ እንከን ማይወጣለት ሆኖ ሳለ ፣አንተን ከመሰለ የበሰለ ፖለቲካኛ የዚህን ግለሰብ ድብቅ አላማ ለማወቅ ይከብድሃል ብዬ አላምንም። እናም ልቦናህ እያወቀው ለምን እኔንም ግዜዬን ትገድላለህ አንባቢንም ታደክማለህ። እስከመቼ ነው እንደዚ አይነት አመለካከትን ተሽክመን እንድንሄድ ምንደረገው? አደባብሶና አለባብሶ የታለፈው ሁሉግዜውን እየጠበቀ ሲፈነዳ ፍንጣሪው አካላችንን እያሰናከለው ይገኝኛል። አንገታችንንም እያስደፋን ነው።
የሆነ የፖለቲካ ነውጥ በመጣ ቁጥር ተስፋዬ ገ/አብ ጋር ተሩጦ ትንታኔ መጠየቅ ምን አመጣው? የቡርቃ ዝምታን ጨምሮ ሌሎችንም መርዛማ መጽሃፎችንና መጣጥፎችን በማምረት የሚታወቀውን ግለሰብ እግር ስር መርመስመስንስ ምን ይሉታል? ደሞ ሌላ ነገር ሲመጣ በብሄርና በሃይማኖት የሰከሩግለሰቦችን ካሉበት በሻማ እየፈለጉ ባደባባይ እኛን ማሰደቡ አስፈላጊነቱ ምኑ ላይ ነው? ዳዊትም ቢሆን ቀኑን ጠብቆ ተናከሰ። ይሄ ሁሉ ትልቅ ትምህርት ሊሆንህ ይገባል። የሚናደፍ እባብን ለምድዋል ብለህ ኪሳህ ውስጥ ጨምረህ ስቴድ ነደፈህ። ጀዋር ላንተ አዲስ ሆነብህ እንጂ ድሮም አሁንም ያው ነው።ደሞ ያንያክል ወረቀትና ግዜ ፈጅቶ የፖለቲካና የታሪክ ጋጋታ ሚያስፈልገው ጉዳይ አልነበረም።
አሁን የፖለቲካው ትንተና ጅብ ከሄደ በህዋላ ምን ጮህች ነው ሚያስብለው። ያለፈው አልፍዋል ግን ኪኒንህን ዋጥ አድርገህ ለመወደድ ሳይሆን ላላማህ መስራት ይጠበቅብሃል። ይሄ እንደምክር ቢጤ ይሁንህ። አልሰማም ካልክ ደሞ ለጀዋር ያቀድነው ድግስ ላይ አናንተን እንሞሽርበታለን። ላሁኑ በሁለትብጫ አልፈንሃል። በተጨማሪ ደሞ ለኛ ወጣቶች ስትል ሃሳብህን አጠር አድርገህ ጻፈው። ያንሁሉ ለማንበብ ግዜ የለንም። የኦቶዋን ኢምባዬር ቱርኮች ይጨነቁበት እኛ በፊልም ካየነው ይበቃናል። በቸር እንሰንብት

አንድነት ፓርቲ በደሴ ያካሄደው ታላቅ ሰላማዊ ክፍል ቪዴኦ1, ቪዴኦ 2, ቪዴኦ 3

$
0
0

አንድነት ፓርቲ በደሴ ያካሄደው ታላቅ ሰላማዊ ክፍል 3

አንድነት ፓርቲ በደሴ ያካሄደው ታላቅ ሰላማዊ ክፍል 2

አንድነት ፓርቲ በደሴ ያካሄደው ታላቅ ሰላማዊ ክፍል 1

Sport: ታይሰን ጌይ እና አሳፋ ፖል አበረታች መድኃኒት ተገኘባቸው

$
0
0

ከቦጋለ አበበ

በአጭር ርቀት ስመ ገናና የሆኑት አሜሪካዊው ታይሰን ጌይ እና ጃማይካዊው አሳፋ ፖል ሰሞኑን ባደረጉት ምርመራ አበረታች መድኃኒት ተጠቃሚ መሆናቸው እንደተረጋገጠ ቢቢሲ ዘገበ፡፡
pawel and gay
የምንጊዜም የመቶ ሜትር ሁለተኛው ፈጣን አትሌት የሆነው ጌይ አበረታች መድኃኒት እንደተጠቀመ ይፋ ያደረገው የአሜሪካ ፀረ-አበረታች መድኃኒት ኤጀንሲ ነው፡፡ ተቋሙ ባለፈው ዓርብ ይፋ እንዳደረገው የሰላሳ ዓመቱ ጌይ ባለፈው ግንቦት ከውድድር ውጪ ባደረገው ምርመራ አበረታች መድኃኒት ተጠቃሚ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
አራተኛው የዓለምአችን ፈጣን አትሌት ፖል ደግሞ ባለፈው ሰኔ በተካሄደው የጃማይካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ አበረታች መድኃኒት መጠቀሙ ተደርሶበታል፡፡ በዚህም ቅጣት ይጠብቀዋል ተብሎ እንደሚገመት ዘገባው ያስረዳል፡፡
ባለፈው የለንደን ኦሊምፒክ የአራት በአራት መቶ የብር ሜዳሊያ አሸናፊ የሆነው ጃማይካዊው ሺሮን ሲምሰን ከፖል ጋር ተመሳሳይ የሆነ አበረታች መድኃኒት ተጠቅሟል መባሉ ይታወሳል፡፡ ይህም በጃማይካ አትሌቶች ላይ ጣት እንዲቀሰርባቸው አድርጓል፡፡
ፖል በአሁኑ ወቅት የአገሩ ልጅ ዩሴን ቦልት የመቶ ሜትርን ክብረወሰን ከመጨበጡ በፊት የርቀቱ ንጉስና አገሩን በቤጂንግ ኦሊምፒክ የአራት መቶ ሜትር አሸናፊ እንድትሆን ያስቻለ አትሌት ነው፡፡
ፖል እና ጌይ አበረታች መድኃኒት ተጠቃሚ ሆነው መገኘታቸው የስፖርት ቤተሰቡን ያስደነገጠ ክስተት ሆኗል፡፡ የስፖርቱ ባለሞያዎችም በሁለቱ አትሌቶች ላይ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን አስተያየት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
የቢቢሲው የአትሌቲክስ ተንታኝ ኮሊን ጃክሰን በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከሰነዘሩ አንዱ ነው፡፡ ፖልና ጌይ ታላላቅ አትሌቶች መሆናቸውን በመግለፅ አስተያየቱን የጀመረው ኮሊን ሁለቱ አትሌቶች በስፖርቱ ውስጥ የማይሽር ጠባሳ ጥለዋል ብሏል፡፡
«አበረታች መድኃኒት የተገኘባቸውን አትሌቶች ይቅርታ ልናደርግላቸው አይገባም፣ እነዚህ አትሌቶች ላይ ከባድ ቅጣት መጣል ስፖርቱን ሊጎዳው ይችል ይሆናል፣ ይሁን እንጂ ለስፖርቱ መልካም ገፅታ ስንል ጉዳዩን ችላ ልንል አንችልም፣ መጪውን ትውልድ ማስተማር የምንችለውም በዚህ መንገድ ነው» በማለትም ኮሊንስ አስተያየት ሰጥቷል፡፡
ፖል በዘንድሮው ዓመት መቶ ሜትሩን በ9፡88 ቢሮጥም ጃማይካን ወክሎ ከወር በኋላ በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ አይሳተፍም፡፡ ፖል አበረታች መድኃኒት ተጠቃሚ እንደሆነ ከተረጋገጠ በኋላ በሰጠው አስተያየት፤ መድኃኒቱን ሆን ብሎ እንዳልተጠቀመ አስረድቷል፡፡
«ለቤተሰቦቼ፣ ጓደኞቼና በዓለም ላይ ላሉ ደጋፊዎቼ መናገር የምፈልገው አበረታች የተባለውን ንጥረነገር ሆን ብዬ ወይንም አውቄ እንዳልተጠቀምኩኝ ነው፣ ያልተፈቀደ ነገር እንዳላደረኩም እርግጠኛ ሆኜ መናገር እችላለሁ» በማለት ፖል አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
እ.ኤ.አ በ2007 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በመቶ፣ ሁለት መቶና አራት በአራት መቶ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ የሆነው ጌይ አበረታች ንጥረነገር ለመጠቀሙ ማስረጃ የሚሆን ሁለተኛውን የናሙና ምርመራ ውጤት እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡
ጌይ የመጀመሪያው የምርመራ ናሙና ላይ በተገኘበት አበረታች መድኃኒት ጉዳይ በሰጠው አስተያየት፤ አበረታች መድኃኒት በራሱ እጅ እንዳልተጠቀመና የሆነ ሰው ሆን ብሎ ሰጥቶት ሊሆን እንደሚችል አብራርቷል፡፡
«ከዚህ በፊት በእንደዚህ ዓይነት ጉዳይ ላይ ስሜ ተነስቶ አያውቅም፣ አበረታች መድኃኒት ተጠቅሜ አላውቅም የሆነ ሰው ግን በማላውቀው መንገድ እንድጠቀም አድርጎኝ ሊሆን ይችላል» በማለት ጌይ አስተያየቱን ለቢቢሲ ሰጥቷል፡፡
ጌይ ከሁለተኛው የናሙና ምርመራ ውጤት በኋላ የትኛውንም ቅጣት ለመቀበል ዝግጁ እንደሆነ በመናገር በሌላ ጊዜ ዳግም ወደ ውድድር እንደሚመለስ ያለውን ተስፋ ገልጿል፡፡
ጌይ በጉዳዩ ላይ የሰጠውን አስተያየት ተከትሎ ምርመራውን የሚያካሂደው ኤጀንሲ አትሌቱ በሰጠው መልካም አስተያየት እንደተደሰተ ገልፆ የሁለተኛውን የናሙና ምርመራ ውጤት ሕጋዊ በሆነ መልኩ በቅርቡ እንደሚያሳውቅ አረጋግጧል፡፡
ጌይ በመቶ ሜትር 9፡69፣ በሁለት መቶ ሜትር ደግሞ 19፡58 የሆነ የራሱ ምርጥ ሰዓት ያስመዘገበ አትሌት ነው፡፡ ጌይ ባለፈው የለንደን ኦሊምፒክ አራት በአራት መቶ ውድድር የብር ሜዳሊያ አሸናፊና በዓለም አሉ ከሚባሉ ታዋቂ አትሌቶች አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ፖል በመቶ ሜትር 9፡72፣ በሁለት መቶ ሜትር ደግሞ 19፡90 የሆነ ፈጣን ሰዓት ከማስመዝገቡ በተጨማሪ እ.ኤ.አ 2007 ላይ የአጭር ርቀት ክብረወሰኖችን በስሙ ማስመዝገብ የቻለ አትሌት ነው፡፡
ፖል በቤጂንግ ኦሊምፒክ የአራት መቶ ሜትር ዱላ ቅብብል የወርቅ ሜዳሊያ፣ እ.ኤ.አ በ2004ና 2008 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በተመሳሳይ ርቀት የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ትኩረቱ ወደ ጀግናዉ አጼ ዮሐንስ ከተማ –መቀሌ !

$
0
0

ግርማ ካሳ
Muziky68@yahoo.com

ሐምሌ 11 ቀን 2005 ዓ.ም

Arena-Tigray-logoሐምሌ 7 ቀን ደሴና ጎንደር የኢትዮጵያዉያንን ትኩረት ስበውት ነበር። በነዚህ ከተሞች የአንድነት ፓርቲ በጠራዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በሺሆች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን፣ በአገዛዙ ካድሬዎች የደረሰባቸዉን ጫናና ማስፈራሪያ ወደ ጎን በማድረግ፣ የሰላም፣ የዴሞክራሲ የነጻነት ጥያቄዎቻቸውን አሰምተዋል። «አምባገነንነት፣ ጭቆና፣ ዘረኝነት በቃን» ብሎ ሕዝቡ እንደተነሳ፣  በገልጽ የተያበት ሁኔታ ነዉ የነበረዉ። የኢትዮጵያዊ ጨዋነት መንፈስ በገሃድ የተንጸባረቀበት ቀን ነበር።

ሐምሌ 14 ቀን ትኩረቱ መቀሌ ይሆናል። ከአንድነት ፓርቲ ጋር በቅርበት የሚሰራዉ፣ በአቶ ገብሩ አስራት የሚመራው፣ አረና ትግራይ ለሉዓላዊነት ወይንም በአጭሩ አረና፣ በመቀሌ ማዘጋጃ ቤት ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ ጠርቷል። መቀሌ – የጀግናዉ አጼ ዮሐንስ ከተማ!!!!!

አረናዎች በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ጠንካራ አቋም ያላቸው፣ የሕወሃት/ኢሕአደግ በዘር የመከፋፈል ፖለቲካን የሚቃወሙ፣ በትግራይ ዉስጥ ጠንካራ ሰላማዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ታጋዮች ናቸው።

ከአቶ መለስ ዜናዊ ሕልፈት በኋላ ሕወሃቶች የአረና አመራሮችን ወደ ሕወሃት እንዲመለሱ ጥሪ እንዳቀረቡላቸው ፣ ነገር ግን  «ጠባችን እኮ ከመለስ ጋር አልነበረም፤ ግን ሕወሃት ከሚያራምዳቸዉ ፖሊሶዎች ጋር  ነዉ እንጂ» የሚል ምላሽ በመስጠት፣ ጥያቄዎቹን አረናዎች ውድቅ እንዳደረጉ  ከታመነ ምንጭ መረጃ ደርሶኛል።

አረናዎች፣ መድረክ በተባለዉ ስብስብ ዉስጥ በመስራት፣  መድረኩ ወደ ዉህደት እንዲመጣ ትልቅ ጥረት ያደረጉ ናቸው። በትግራይ ያሉ የአንድነት አባላትና አስተባባሪዎች፣  ከአራና ወገኖቻቸው ጋር፣ አንድ ጽ/ቤት እየተጋሩ፣  በጣም በተቀራረበ መልኩ እንደሚሰሩ ነዉ የምንሰማዉ። ከዚህም የተነሳ፣  አንድነትና አረና ይዋሃዳሉ የሚል ግምት ያላቸው ወገኖችም አሉ።

የትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵያን የሚወድ፣  ለኢትዮጵያ አንድነት መስዋእትነት የከፈለ ጀግና ሕዝብ ነዉ። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም፣ በአንድ ጽሁፋቸው፣  ስለትግራይ ሕዝብ የጻፉትን ላዉጋችሁ። ሕወሃት/ኢሕአዴግ ስልጣን እንደጨበጠ ነበር። በመቀሌ የሕወሃትን ባንዲራ እንጂ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማን ማውለብለብ አይቻልም ነበር። «አንድ መቀሌ ሄዶ የመጣ፣ አንድ የኔ ተማሪ የታዘበዉን ልንገራችሁ» ሲሉ ነዉ ፕሮፌሰር መስፍን የጻፉት። በየቤቱ ሰዉ በትንሹ፣  የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ሰቅሏል። «በዉጭ ብንከለከልም፣ በቤታችን ግን እንሰቅላለን» ነበር ሕዝቡ የሚለው።

አዎ፣ ለሕወሃት/ኢሕአዴጎች ኢትዮጵያዊነት ቢናቅም፣ ኢትዮጵያን ባህር አልባ ማድረግ ቀላል ቢሆንም፣ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ እንደ ተራ ጨርቅ ቢቆጠረም፣ ለትግራይ ሕዝብ ግን ኢትዮጵያዊነቱ በልቡ የተቀረጸ ማንነቱ ነዉ። በሰርግ፣ በቀብር ስነ ስርዓት በገጠሪቷ ትግራይ ሁሉ ሳይቀር የኢትዮጵያ ባንዲራ ነዉ። ኢትዮጵያን በተመለከተ የትግራይ ሕዝብ ቀዳሚ እንጂ ደጀን ሆኖ አያውቅም። አይሆንንም። ኢትዮጵያዊነትን ያኔም ሕወሃት ሊያጠፋው አልቻለም። አሁንም ደግሞ አያጠፋዉምም።

ከትግራይ የሚደርሱ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ሕዝቡ በሕወሃት አገዛዝ የተማረረ ይመስላል። ለዉጥ ይፈልጋል። አማራጭ ይፈልጋል። የሕዝቡን ጥያቄ በማዳመጥ፣  አረና ትግራይና አንድነት አማራጭ ሆነው ቀርበዋል። ለዚህም ነዉ በገዢው ፓርቲና በነርሱ መካከል ያሉትን የጎላ ልዩነቶች ለማሳየት፣ ሐምሌ 14 ቀን በሚደረገዉ ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ ሕዝቡ እንዲገኝ ቅስቀሳ እየተደረገ ያለዉ።

መቀሌም እንደ ደሴና ጎንደር፣  እንደገና የዲሞክራሲና የፍህት ደዉልን ትደዉላለች። እንደገና የትግራይ ሕዝብ በመቀሌ ማዘጋጃ ቤት ኢትዮጵያዊነቱን ያወጃል። እንደገና ታሪክ ይሰራል።

አንድ ብዙ ጊዜ የማስታወሰው አቶ ገብሩ አስራት የተናገሩትን አንድ አባባል ልጥቀስ። ከጥቂት አመታት በፊት ነዉ፣ አራና እንደ አሁኑ፣  ሕዝባዊ ስብሰባ ጠርቶ ነበር። ብዙ ሕዝብ ይሰበሰባል። የጥያቄና መልስ ወቅት አንዱ ይነሳና «እንዴት ከትግሬ ጠላቶች ጋር አብረህ ትሰራለህ? » የሚል ጥያቄ ይጠይቃል። ትግሬ፣ ኦሮሞ ፣ ከንባታ … እያሉ፣ ሰውን በዘር የሚለዩ፣ በአይምሮ የታመሙ፣  ብዙ ጠባቦችና ጎጠኞች መቼም  በየቦታዉ አይጠፉም።

አቶ ገብሩ አስደናቂ መልስ መለሱ። «ማን ነዉ ትግራይን ለትግሬዉ ብቻ የሰጠዉ? ትግራይ የአማራዉም የኦሮሞውም ናት። የአማራ ክልል የትግሬዉ፣ የጉራጌው የኦሮሞው ነዉ። ኦሮሚያ የሶማሌ የአማራም የትግሬም ነዉ ….ማንም ኢትዮጵያ የማንም ጠላት አይደልም» ነበር ያሉት። ይሄ ነዉ እንግዲህ የሰለጠነው፣ የወንድማማችነትና የኢትዮጵያዊነት ፖለቲካ።

አረናም ሆነ አንድነት፣  «ሁሉም ኢትዮያጵያዊ በሁሉ የአገሪቷ ግዛት የመኖር፣ የመስራት፣ የመነገድ፣ የመምረጥ፣ የመመረጥ መብት አለው» ብለው ያምናሉ። አረናም ሆነ አንድነት «ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባህር በር እንዲኖራት መደረግ አለበት» ብለዉ ያማናሉ። አረናም ሆነ አንድነት ለሰላም፣ ለዲሞክራሲ፣ ለፍትህ፣ ለሕግ የበላይነት ይታገላሉ። አረናም ሆነ አንድነት የታሰሩ የሕሊና እስረኞች ሁሉ እንዲፈቱ፣ ሕዝቡን እያሸበረ ያለው የጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ ተሽሮ ወይም ተሻሽሎ ዜጎችን በአገራቸው በነጻነት ቀና ብለዉ እንዲኖሩ ይታገላሉ።

እንግዲህ አስቡት ወገኖቼ፣ የምርጫ ወቅት አይደለም።  ነገር ግን በአዲስ አበባ የተጀመረውን እንቅስቃሴን ተከትሎ በደሴና በጎንደር ሕዝቡ ድምጹን አሰምቷል። ወደፊትም ያሰማል። የፊታችን እሁድ ደግሞ በመቀሌ አረና በጠራዉ ስብሰባ የዲሞክራሲ ችቦ ይበራል።  ከአስራ አምስት ቀናት በኋላ ደግሞ፣ ሐምሌ 28፣  እንደገና በመቀሌ፣ እንዲሁም በወላይታ ሶዶ የአንድነት ፓርቲ ሕዝቡን ይሰበስባል። በዚያኑ ቀንም በጂንካ፣ አርባ ምንጭና ባህር ዳር ሰላማዊ ሰልፎች ይደረጋሉ። ብዙ ሥራ እየተሰራ ነዉ። መስዋእትነት እየተከፈለ ነዉ።

እንግዲህ ኢትዮጵያዉያን በሁሉም መስክ፣ ድጋፋችንን ለአረና ሆነ አገር ቤት ለሚታገሉ ወገኖች ልንሰጥ ይገባል። በከፍተኛ ወከባ፣  በመቀሌ ጠንካራ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ከሚያደረጉት የአረና ወገኖቻችን ጎን እንቁም። በዚያ ያሉ ዘመድ ጓደኞቻችን ወደ ስብሰባው እንዲሄዱ እናበረታታ። በምንችለው መልኩ ትግሉን እንቀላቀል። ይሄ የፖለቲካ ጉዳይ አይደለም። ጉዳዩ የሰብአዊነትና የኢትዮጵያዊነት ጉዳይ ነዉ።

አለን ብለን እንዳናወራ!

$
0
0

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

“እናት ሀገሬ ኢትዮጵያ አንዲት ናት!” ብሎ ለአሃዳዊ ግዛቷ ዐፄ ቴዎድሮስ ቆላ ደጋ የተንከራተተላት ኢትዮጵያ፣ “ኢትዮጵያዬ…” እያለ ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) በ‹ጃ ያስተሰርያል› አልበሙ የሚያለቅስላት ኢትዮጵያ፣ “እምዬ ኢትዮጵያ … ተራራሽ አየሩ…” እያለ ቴዎድሮስ ታደሰ ያቀነቀነላት ኢትዮጵያ፣ … አሁን የገባችበትን ማጥ ስናይ ናላችን የሚበጠበጥ የወዲያኛው ትውልድ አባላት ጥቂቶች አይደለንም፡፡ በሀገር ውስጥ የምኖረው እኔ ለጉድ የጎለተኝ ሰውዬ በዐይኔ በብረቱ የማየውን ሀገራዊ ስንክሣር xenedtlmdwe እንደተለመደው ጥቂት ላዋራችሁ ነውና ትንሽ ትቆዝሙ ዘንድ ፈቃዳችሁ ይሁንልኝ፡፡

ethiopian youngበመጀመሪያ ‹ኢትዮጵያ ዐፄው ህመሟን አባባሱባት – ደርጉ ጣዕረ ሞቷን አጣደፈው – ወያኔው ገደላትና ቀበራት› በሚለው የብዙዎች እሳቤ የማምን መሆኔን መግለጽ እወዳለሁ – እየሞቱ ይሉኝታ የለም፡፡ ትንሣኤ ሙታን የመኖሩ ዕድል በታሳቢነት ተይዞልኝ የዘመኑ ግልጽ እውነት ታዲያን እንደዚያ ይመስለኛል፡፡ ይህችን ሀገር አንዳቸው ከአንዳቸው እየተቀባበሉ ወረደ መቃብሯን እንዳፋጠኑት ለማንም ግልጽ ነው፡፡ በአገዛዛቸው ወቅት የሚለብሱት ፖለቲካዊ ካባ ይለያይ እንጂ፣ በሀገርና በሕዝብ ያደረሱት ወይ የሚያደርሱት ጥፋትና በደል በደረጃ አይመሳሰል እንጂ፣ ለሕዝብና ለሀገር ያላቸው ፍቅርና ብሔራዊ ስሜት የአንዳቸው ከአንዳቸው በተለይም የሁለቱ ከሦስተኛው የሚቀራረብ አይሁን እንጂ ለጥፋተኝነቱ ሁሉም በየደረጃው ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ በቀ.ኃ. ሥላሤ ህመሟ እንደጸናባት፣ በደርግ ጣዕረ ሞት ውስጥ እንደገባችና በወያኔው የማፊያ ቡድን የከፋፍለህ አውድም ዘመነ ጽልመት ደግሞ ለይቶላት እንደሞተችና በምዕራባውያንና ምሥራቃውያን የፖለቲካ ሊቃነ ጳጳሣት ጉዞ ፍትሓት አማካይነት የቀብር ሥነ ሥርዓቷ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ መመሥከር ይቻላል፡፡ (ዐፄው በሥልት ያስወገዷቸውን አንጎሎች፣ ደርጉ በምሕረት የለሽ ጭካኔው የጨፈጨፋቸውን ሀገር ገምቢ ወጣቶችና የጦር አበጋዞች ስናስታውስ የመረገማችን ዕዳና ባሳለፍናቸው ጥቂት የማይባሉ አሠርት ዓመታት ውስጥ የዕዳችን ተከፍሎ አለማለቅ ክፉኛ ይሰማናል፤ አለመታደላችን በሚያስከትልብን ጸጸትም ለማንወጣው ውስጣዊ ቁጣ እንዳረጋለን – ጨጓራን ለመላጥ፡፡ የቀደሙት ሁለቱ አመቻችተውት በሄዱት ገላጣ ቦታ ላይ ወያኔ ያለ ተቀናቃኝ ጉብ አለበት፤ ይሄ የወያኔ ጥፋት አይደለም፡፡ ጥፋቱ መደላድሉን አበጅተው የጠፉት ወገኖች ነው፡፡ ሀገር በስንት ወጪ ያሰለጠነቻቸውን በተለያዬ የሙያ ዘርፍ የሰለጠኑ ምሁራንን በቀይ ሽብር መፍጀትና በርካታ የጦርና የፖሊስ ጄኔራሎችን በአንድ ቀን ጀምበር መረሸን ማለት የጠላትን የ500 ዓመት ጦርነት በ500 ዓመታት ማሳጠር ማለት መሆኑን ዛሬ ላይ ሆነን ሳይሆን ያኔውኑ ማሰብ ይገባ ነበር፡፡ ለአንድ ሰው የሥልጣን ጥም እርካታ ወይም ወንዝ ለማያሻግር ርዕዮተ ዓለማዊ ፍልስፍና ሲባል ሀገር ጠፋች፤ ወገን ተሰደደ፤ ርሀብና ድርቅ፣ ጦርነትና ግዞት ባል ሆኑ፤ በስተመጨረሻም ዘረኝነትና ጎጠኝነት አዲስ የፖለቲካ ዘይቤ ሆነው በመተከላቸው አካማሌ ሆነን ከሀገርም ከሰውም ተራ ወጥተን ቀረን፡፡)

ትናንትና ወደ አንድ ወንድሜ ቤት ሄድኩ፡፡ ወንድሜ የምለው ላለማራቅ እንጂ የብዙ ዘመን ጓደኛየ ነው፡፡ እቤቱ ስደርስ የአሥር ዓመት ዕድሜ ልጁን አጠገቡ አስቀምጦ ጋቢውን ለብሶ ልቅሶ የተቀመጠ መስሏል፡፡ የወረወርኩለትን የተለመደ ሰላምታም በቅጡ ሊቀበለኝ አልቻለም፡፡ ደነገጥኩ፡፡ “እንዲህ ሆነን ዐረፍነው!” ይለኛል – የሚለው ሳይሆን ያለበት ምክንያት ሳይገባኝ፡፡

“ይሄውልህ ዳግምዬ፡- ጉዴን ስማልኝ – አሁን እኔ ሰው ነኝ? ከአሁን በኋላስ በሕይወት መኖር አለብኝ? ሀገርስ አለኝ? መንግሥትስ አለኝ? ኧረ ምንድን ነኝ ለመሆኑ? ወዴት እየሄድን ነው? ከእንግዲህ ምን ይዋጠኝ? …”

መነሻው በማይታወቅ የብሶት እሩምታ ብዙ መቆየቱ አስጨነቀኝና አቋርጬው “እንዴ! ምን ሆነሃል? አለወትሮህ ዛሬ ምን ነክቶሃል?” ስል ጠየቅሁት፡፡ ሊያዳምጠኝ አልቻለም፡፡ ብሶቱን ማዥጎድጎዱን ቀጠለ፡፡ የአፍንጫና የጉንጭ አምላክ ባይታደጋቸው ኖሮ በሚያስፈራ አኳኋን ተጉረጥርጠው ከማኅደራቸውም ወጥተው የሚታዩት ዐይኖቹ ወደመሬት ወርደው ሊፈጠፈጡ ምንም አልቀራቸውም፡፡ እንዲሰክን ውትወታየን አላቋረጥኩም፤ ተሳካልኝ – ቀስ እያለ በረድ ማለት ጀመረ፡፡

“ይሄውልህ፡፡ እንደምታውቀው ይህ የመጨረሻው ልጄ ነው፡፡ ዕድሜው አሥራ አንድ ዓመት ነው፡፡ ገቢየ አነስተኛ በመሆኑ የማስተምረው በመንግሥት ትምህርት ቤት ነው፡፡ እንደ መጥፎ ልማድ ሆኖብኝ ልጆቼን የመከታተል ባህል ከዱሮውም  አላዳበርኩም፡፡ በዚህ አዝናለሁ፡፡ በስንትና ስንት ሀገራዊና የመሥሪያ ቤት ችግር ስለምወጣጠር እቤት ገብቼ እንደብዙ አባቶችና እናቶች ‹ዛሬ ምን ተማርክ? ሰሞኑን ምን ተማርሽ?› ማለቱን አላዘወተርኩም – እንዲያው በደፈናው እመክራለሁ ፣ እንዲተጉ አስጠነቅቃለሁ እንጂ ጠለቅ ብዬ የምከታተለው ነገር የለኝም፡፡ እናታቸውም ከኔ የበለጠች ሰነፍና ዝንጉ ናት፡፡ ዛሬ ታዲያ በጋው ከመድረሱ እስኪ አንዳንድ ነገር ላስጠናው ብዬልህ መጽሐፍ ገዝቼ ላስነብበው ስል በመጪው የ2006 መስከረም አምስተኛ ክፍል የሚገባ ልጅ ከነአካቴው ማንበብ አይችልም፡፡ እነ ‹ጀ፣ኀ፣ኸ፣ጨ፣ጰ›ን ይቅርና የ‹ሀ›ንና የ‹ለ›ን ዘሮች እንኳን አልለየም፡፡ እንግሊዝኛውንማ ተወው፡፡ ይገርምሃል – የመጀመሪያውን ሆሄ ስትጠራለት ብቻ በሽምደዳ የያዘውን እንደበቀቀን ያነበንባል እንጂ ፊደላቱን ለይቶ በዘር በዘራቸው አያውቃቸውም፤ በዚያም ምክንያት ማንበብ ፈጽሞ አይችልም፡፡ ይሄ ታዲያ አያሳንቅም ትላለህ? ሞት ሲያንሰኝ ነው!”

ችግሩ አሁን ገባኝ፡፡ ‹ያሳንቃል› ብዬ አስተያየቴን ለመስጠት ግን ከበደኝ – ሆድ ለባሰው ማጭድ አታወሰው ይባላል፡፡ ወዳጄ ዛሬ ገና አንድ ነገር የገባው ይመስላል፡፡ በየቤታችን ያለውን ጉድ ቢሰማ ምን ሊል ነው? በደመ ነፍስ የምትነዳ ሀገር ውስጥ መኖራችን ዛሬ ገና ነው የታየው መሰለኝ፡፡ አሁን ምን ማድረግ እንደሚችል አላውቅም፡፡ ምን ብዬ እንደምመክረውም ግራ ገባኝ፡፡ “የምትችለውን አድርግለት እንጂ ያን ያህል ዕብድ አትሁን፤ አንተ ብታብድ ልጆችህም አንተም ሁላችሁም ትጎዳላችሁ እንጂ የሚጠቀም የለም፤ አይዞህ – በሁላችንም ቤት ያለ ነው” እያልኩ አጽናናው ገባሁ፡፡ ብዙ አብነቶችንም እየጠቀስኩ ያለንበት አደገኛ ሁኔታ እገልጥለት ያዝኩ፡፡

ይሄውልህ – የአንድ ዘመዴ ሴት ልጅ ሰባተኛ ክፍል ደርሳለች፡፡ በዕውቀት ግን አዲስ ከተወለደ እንኳን ሕጻን አትሻልም፡፡ አታነብም፤ አትጽፍም፡፡ ግነት እንዳይመስልህ – አታነብም ፤ አትጽፍምም፡፡ እንዴት ሰባተኛ ክፍል ደረሰች ብሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ ይህን ጥያቄ የሚመልስልን ግን ጊዜው ሲደርስ ራሱ ወያኔ ይሆናል – ለአሁኑ ግን “ ባልተማረ መምህር ስለሚማሩ፣ በአብዛኛው የሙያና የሀገር ፍቅር በሌለውና አነስተኛ ክፍያ በሚከፈለው  መምህር ስለሚማሩ…” ብለን እናልፋለን፡፡ በሠፈሩት ቁና መሠፈር አለና ያኔ እነማን ማይም ሆነው ቀርተው እነማን እንደተማሩ፣ እነማን መንገድ ጠራጊ ሆነው ቀርተው እነማን መሀንዲስና ዶክተሮች ሆነው ከፍተኛ ደረጃ እንደተቆጣጠሩ ሲጠየቁ ወያኔዎች ራሳቸው ሊመልሱት የሚገደዱበት ምድራዊና መለኮታዊ ጥያቄ ነው፡፡ ሰው ለሆነ ፍጡር የኢትዮጵያ ሁኔታ እጅግ የሚዘገንን ነው፡፡ ጣሊያን እንኳን ይህን ያህል አልጨከነም፤ ይህን ያህል ሕዝብን አላደደበም፤ ይህን ያህል ሰውን ከእንስሳት በታች ቆጥሮ ወደ ድንጋይነት አልለወጠም፡፡ ይህን ያህል ዜጎችን ለይቶ አንዱን በሃሳብም በቋንቋም እንዲበለጽግ ሌላውን በሁሉም እንዲደኸይ አላደረገም፡፡ የወያኔን ይህን መሰል ኃጢኣትም እንበለው ወንጀል ሰይጣን ራሱም ቢሆን ከአሁን ቀደምም ሆነ ወደፊት ሊሠራው አንጀቱ የሚጨክንለት አይመስለኝም፡፡ የነዚህ ወያኔዎች አንጀት የተሠራው ግን አይገባኝም፤ ምናልባት ከጅብ ቆዳና ከባሌስትራ ሳይሆን አይቀርም፡፡

እኔ ያጽናናሁት እየመሰለኝ እንዲህና እንዲያ እያልኩ የማውቀውንም የሰማሁትንም ዘለባበድኩለት፡፡ በዲግሪ ከተመረቁ ወጣቶች ብዙዎቹ ስማቸውን በእንግሊዝኛ ይቅርና በሌላ በቅርብ በሚያውቁት ሀገርኛ ቋንቋ አስተካክለው እንደማይጽፉ አከልኩለት፡፡ ዛሬ ዛሬ ዕድሜ ለወያኔ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ይቅሩና የኮሌጅ ተማሪዎች ሳይቀሩ የለዬላቸው ማይማን ናቸው፡፡ በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ የሚበረታቱት ጫት ቤት እንዲውሉ፣ ሺሻ እንዲምጉ፣ አረቂና ጠላ እየተጋቱ በመስከር ጭንቅላታቸውን እንዲያላሽቁ፣ ሀሽሽና ቁማር ቤት እንዲያዘወትሩ፣ ከሃይማኖትና ከሞራል እንዲያፈነግጡ፣ ወጥ ማንነት ኖሯቸው ለአብሮነት የጋራ ሕይወት እንዳይጥሩ ነው…፡፡ ወያኔ የውጪ ወራሪ ኃይል ይመስል ከውጪ ወራሪና ቅኚ ገዢም በከፋ ደረጃ የራሴ በሚላቸው “ሕዝቦቹ” ላይ እየፈጸመ የሚገኘው ግፍና በደል ተዘርዝሮ አያልቅም፡፡ ለዚህም ነው የሀገሩ ባንዲራ የተበጣጠቀችበት ወጣቱ ትውልድ በማንነት ኪሣራ እየዳከረ የራሱን ሰንደቅ ሳይሆን በህልም የሚቀላውጣቸውን የፈረንጆችን ዕራፊ ጨርቅ የሚመስል ባንዲራ ግንባሩ ላይ አሥሮ የሚታየው፤ ለዚህም ነው ወጣቱ የአነጋገር ሥልቱ፣ አካሄዱና አለባበሱ ሳይቀር በፊልም የሚያየውን እየኮረጀ ከነሱም ከራሱም ሳይሆን በመሀል ከራዳር እንደወጣ አውሮፕላንና ኮምፓስ እንደሌላት መርከብ የትሚናውን ጠፍቶ ራሱንም ለመፈለግ ፍላጎት አጥቶ በሁለት ዓለማት ስብዕና እየባዘነ የሚታየው፡፡ ምን አለ በለኝ – ወጣቱን ለዚህ ያበቁት ወያኔዎችና ለወያኔዎች ምቹ ሁኔታን የፈጠሩ እርጉማን ሁሉ ዋጋቸው ይሠፈራል፡፡

ወዳጄን ለማስተዛዘን በምሥጢር መያዝ የሚገባኝን ብዙ ዘግናኝ ሀገራዊ እውነቶችን ዘከዘክሁለት – ሴትዮዋ ‹መንግጌ አባስኳት› እንዳለችው ጓደኛየ ሶበረልኝ ብዬ ላጥናናው በምነግረው እውነተኛም የተጋነነም ታሪክ በቀላሉ ሊጽናናልኝ ግን አልቻለም፤ “ወደዚህ ቤት ያመጣኝን እግሬን በሰበረው” አልኩና ተማረርኩ – መማረር ችግርን የሚፈታ ይመስል፡፡

እኔ ግን ቀጠልኩ፤ አልኩም፡- ቢኤውን ከያዘ ገና አራት ዓመት በቅጡ ያልደፈነ የአንድ ጓደኛየ ልጅ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በእንግሊዝኛ ቋንቋ በማስተርስ ዲግሪ ይመረቅና ማመልከቻ እንድጽፍለት ወደኔ ዘንድ ይመጣል፡፡ ይህን ምን ይሉታል?

 

ማመልከቻ ጻፍልኝ፤

የምን ማመልከቻ?

የሥራ ማመልከቻ፤

ለየትኛው መሥሪያ ቤት?

ለ … ት/ቤት ነው የምትጽፍልኝ፤ አንድ የእንግሊዝኛ መምህር ይፈልጋሉ አሉ፤ በራፖርተር ጋዜጣ ወጥቷል፡፡

በ‹ሪፖርተር› ማለትህ ነው? ታዲያ አንተው አትጽፍም እንዴ? በቋንቋ አይደል እንዴ የተመረቅኸው?

አይ፣ ግዴለህም አንተው ጻፈውና ባይሆን እኔ የምጨምረውን እጨምራለሁ ወይ እቀንሳለሁ፡፡

የለም፣ እንደሱማ አይሆንም፤ አንተው ጻፍና እኔ ኋላ ላይ ልይልህ፡፡

በዚህ ተስማማንና የሚከተለውን የማመልከቻ ደብዳቤ በእንግሊዝኛ ጽፎ አሳየኝ፡፡

 

Deer Sirs or deer madams:

I was written these letter for apply to the teacher post advertising on the reporters newspaper printed dated on julay 18, 2013(hamillie 11/2005). I am interesting to hire you in your school, if possible.

My name is Gudayehu Zendro and I am 27 old. I am graduation from Addis Ababa University in MA degree for about english. I can writting  and speeking English very good and I can teaches these languge on your school if you gives me the chances to accepted me their and allow me to work with no matter salary amount to paid me.

As high school english teacher, I worked in Zebider school for 2 yers. On top of that I have been written two modules and I have been served another school for six months. And I had made unit ledder their four a month.

If you chose or selects me to your butifull school, by the way I love it, I will is happy to becoming interviewed on your inconvenient time and don’t afraid me to contact me anytime you may dislikes.

Semisterly yours,

Tank you very match

 

ማሽላ እያረረ ይስቃል እንላለን – አበውም ይሉት ነበር፡፡ ይህ ማመልከቻ ቀልድ ቀመስ መሆኑን የሚያጣው ያለ አይመስለኝም – ግን ጠጣር እውነትን ያዘለ ነው፡፡ አንድ ሂስ እቀበላለሁ – ‹ትንሽ ጨከን ብለሃል› ለሚለኝ እውነት ነው እላለሁ፤ የጨከንኩ ይመስላል፡፡ ሆድ ቢብሰኝ ነውና አትታዘቡኝ፡፡ ነገር ግን መሬት ላይ ያለው እውነት ከዚህ ብዙም የሚለይ እንዳልሆነ ብዙ ተጨባጭ ማስረጃዎችን በማቅረብ ማስረዳት ይቻላል፡፡ ከበርካታ ‹ምሁራን› ይህን መሰል ወይም ወደዚህ የሚጠጋ አስደንጋጭ የማመልከቻ ወይም የሌላ ጉዳይ ጽሑፎችን ማየት ከጀመርን ውለን አድረናል፡፡ ዘመኑ የቴክሎጂ በመሆኑ ዕድሜ ለዚህ ለኮፒ/ፔስት አዳሜ ከየድረገ ገጹ እየኮረጀ ወይም በተቀጣሪ አሰለጦች እያሠራ በዲግሪ ይንበሸበሻል – ሥራው ዓለም ላይ ግን ከዜሮ በታች ነው – የዱሮ ስምንተኛ ክፍል የዛሬን የዲግሪ ምሩቅ ሰጥ ለጥ አድርጎ ያሰለጥነዋል ይባላል፡፡ በቴክኒክ ሥራዎች ከሆነ በተለይ ልዩነታቸው ሰማይና መሬት ነው – ደመወዙ ግን ግፍ የሚታይበት ነው – ዲግሪ የሌለው ነገር ግን ሥራውን በዘመኑ ቋንቋ አድምቶ የሚሠራው የሚከፈለው መሃያ በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ እይዐርግ እይወርድ – ወጣም ወረደ – ይህ በወያኔ ሆን ተብሎ የታወጀ የትምህርት ጥራት ዝቅጠት – መቅሰፍትም ሊባል ይችላል – ሀገሪቱን ሰው አልባ የሚያደርግና የነገ ሀገር ተረካቢ የሚያሳጣ ከችግሮች ሁሉ የከፋው አደገኛ ችግር ነው – ርሀብና ጠኔ የሚገድለው አካልን ነው፤ ያልፍማል፡፡ የትምህርት ጉዳይ ግን ከሀገር ኅልውና መቀጠል አለመቀጠል ጋር በቀጥታ የተቆራኘና መንፈስን የሚገድል ነው፡፡ ብዙዎቻችን በዚህ ረገድ ጠፍተናል፡፡ያልጠፋን እንዳይመስለን፡፡

በዚህ ላይ አንድ አስገራሚ ነገር ለመጨመር ያህል – የዘመኑ ምሩቃን አለማወቃቸውን በጭራሽ አያውቁም፡፡ አለማወቅን አለማወቅ የመሰለ ጠንቀኛ ችግር ደግሞ የለም፤ አለማወቅን አለማወቅ አንድም ዕብሪታዊ ደደብነት ነው አንድም ትዕቢት ነው – ወይም የሁለቱ ቅልቅልም ሊሆን ይችላል፡፡ አለማወቅን አለማወቅ ያልታወቀ በሽታ እንደማለት ነው – መድሓኒት የማይገኝለት፡፡ በሁሉ ዘርፍ ሀገር እየጠፋች የምትገኘው አለማወቃቸውን ባለማወቅ እነሱ የሚያውቁት ሁሉ እንደትክክለኛ ዕውቀት እንዲወሰድ በሚፈልጉ ጭንቅላታቸው በትምክህት ሞራ ወይም በማይምነት ጥቁር ሱቲ በተሸፈነ ሰዎች ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ማስታወቂያ የሚጽፍ ድርጅት ከደንበኛ የተሰጠውም እንኳን ቢሆን ተማክሮ ይለውጣል እንጂ ”enklish gramer school”  የሚል ማስታወቂያ ትልቅ ቢልቦርድ ላይ ጽፎ ሊሰጥና በዕውቀትና ጥበብ አምባ ላይ ልግጫና ፌዝ እንዲበረታ ሊያደርግ አይገባም፡፡ በዚህ ረገድ የምናያቸው ብዙ ጥፋቶች እንግዲህ ‹ዕውቀት ከኔ በላይ ላሣር!› ባሉ የወቅቱ ምሁራን ወይም ‹ኮሌጅ የበጠስን ነን› በሚሉ ሰዎች የተሠሩ ናቸው ማለት ነው – መዝገበ ቃላትን እንኳን ማገላበጥ ማንን ገደለ? ኧረ ወዴት እየሄድን ነው ጎበዝ! ለማለት የፈለግሁት ይበልጥ ግልጽ እንዲሆን እፈልጋለሁ – አንሳሳት ወይም ሰው አይሳሳት እያልኩ አይደለም፡፡ ስንሳሳት ግን ስህተትን ባህላችን ለማድረግ ቆርጠን የተነሣን መሆናችንን በሚያሳብቅ ሁኔታ መሆን የለበትም ነው እያልኩ ያለሁኝ፡፡ እንጂ ያልሞተ ይሳሳታል -  ቆም ብሎና በምክክር ግን ይታረማል፡፡ የአሁኑ ዘመን ግን በሁሉም አቅጣጫ ሲመዘን ስህተት እንደቅቡል ይትበሃል በመንሠራፋት ላይ የሚገኝ ይመስላል፡፡ መሳሳት እንደጀብድ የሚቆጠርበት ዘመን ላይ ሳንገኝ አልቀረንም፡፡ ሰውን ስህተቱን ስትነግረው ‹ምን ይጠበስልህ!› ለማለት “So what?” ይልሃል፤ ታፍራለህ – ትደነግጥማለህ፤ ለሌላ ጊዜ አፍህን በዳቦ ወይም ዳቦም ባቅሙ ካረረብህ በመዳፍህ ትይዛለህ፡፡ አቤት! አቤት! አቤት! ያለንበት ዘመን!!

የአዲስ አበባን የመንገድ ላይ ማስታወቂያዎችን፣ የንግድና የአግልግሎት ማግባቢያና ማሻሻጫ በራሪ ወረቀቶችን … ብንመለከት ብዙዎቹ የሚታዩባቸው የፊደላት ስህተትና የሃሳብ ፍሰት አለመጣጣም የወያኔው የማፊያ ቡድን ትምህርትን በማውደም ሀገርን ተረካቢ አልባ አድርጎ ለማስቀረት የነደፈው ዕቅድ ምን ያህል እንደተሳካለት ያሳያሉ፡፡ ከዚህ ጎን ለጎንም ለንግድ ቤቶችና ለትምህርት ቤቶች የሚሰጡ ስያሜዎችን ስንመለከት ሀገራችን ምን ያህል በማንነት ኪሣራ ውስጥ እንደተዘፈቀች እንረዳለን፡፡ በሀገር ውስጥ እያሉ በሀገር ውስጥ መኖራቸውን ማመን በማይፈልጉ ኢትዮጵያውያን ለልጆች የሚወጡ ስሞችና ለተቋማት የሚሰጡ መጠሪያዎች በግልጽ የሚያሳዩን ነገር ቢኖር ከሞላ ጎደል ሁሉም ሰው በገዛ ሀገሩና በገዛ ቋንቋና ባህሉ ላይ ማመጹን ወይም መሸፈቱን ነው፡፡ አለበለዚያ እነታንጉትና አንጓች እነጫልቱና ዘርመጪት ተዘንግተው ባልጠፋ የሰው ስም ‹ሊሊ፣ ቲቲ፣ሊዱ› ባልተባለ፤ ባልጠፋ የትምህርት ቤት ስም ‘School of Americana’ ፣ እነመቻልና ቡቺ ተረስተው ባልጠፋ የውሻ ስም ‹ጃኪ. ሮኪ› ባልተባለ፣ ባልጠፋ ሀገርኛ የንግድ ቤት ስም ‘ቴክሳስ ጫማ ቤት›ና ‹አልባንያ ቁርስ ቤት’ ማለቱም ለትዝብት ከመዳረግ ውጪ የሚፈይደው አንዳች ነገር እንደሌለ በታወቀ፡፡ ቦሌ መንገድ ብትሄድ ከቋንቋው ጀምሮ አለባበሱና የሰውነት መለወጫ ኮስሞቲክሱ ድረስ ሲታይ “ኢትዮጵያ ውስጥ ነው እንዴ ያለሁት? ለመሆኑ ይህች ሀገር የማን ናት?› ማለትህ አይቀርም – እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ፤ የውጪውማ ቢያንስ ርቀዋልና ግዴለም ሊባል ይችላል፡፡ የትናንት አበቅየለሽ ወይ አምለሰት ዛሬ ቦሌ ገብታ በሞተ ከዳ የነጭ ጋለሞታዎች ፀጉርና ሰይጣናዊ ቅብዓ-ርኩስ ፈረንጅ መስላና ስሟን ወደ ቲና ለውጣ መቀመጫዎቿን ቆላ ደጋ ደንገላሣ እያዝበጠበጠች ስታዩ በትውልዱ የቁም ሞት ታለቅሳላችሁ – ወይኔ ምነው ይህን ሳላይ እንዳያት ቅድማያቶቼ አፈር ውስጥ ገብቼ በመሸግሁ – እያላችሁ፤ ‹ይህችን ሀገር ማን ነው የሚረከብ?› ብላችሁም የሚረከባት የሚጠፋ ይመስል በ‹ከንቱ› ልትጨነቁ ትችላላችሁ – ‹ይብላኝ ለእኛ እንጂ ተረክቦ የሚግጥ ውሻና ግሪሣማ መች ጠፍቶ ያውቅና!› ለማለት ፈልጌ ነበር ግን ቀና ሀገራዊና ሕዝባዊ ዓላማቸውን ያልተረዳሁላቸው መስያቸው ከወደፊት መሪዎቼ ጋር ያቃርነኛልና ይሄኛውስ ይቅርብኝ – ግን ግን ሳስበው ‹ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከምቢያው ቂጢጥ› እያለ ተቸገርን እኮ ምዕመናን፡፡ መጥኔ ለሚቆዩ! መጥኔ ለወጣቶች፡፡

ጎበዝ – ተወርረናል! እነዚህ ወያላ ወያኔዎች ሀገራችንን ሙሉ በሙሉ አዋርደዋታል፡፡ ሰው ራሱንና ሀገሩን እስኪጸየፍና አምርሮ እስኪጠላ በሀገሩ ላይ አመጽ እንዲያስነሳ አስገድደውታል፡፡ ከቦሌ እስከ ጉለሌ፣ ከኮተቤ እስከ ካራቆሬ፣ ከሳሪስ እስከ እንጦጦ መላዋን አዲስ አበባ ብትጎበኙ ብዙ ጉድ ታያላችሁ፡፡ ቋንቋችንን መጠየፍ፣ ባህላችንን መጠየፍ፣ ራሳችንን መጠየፍ፣ አብሮነታችንን መጠየፍ፣ መተሳሰብንና መተዛዘንን መጠየፍ፣ ሰብኣዊነትን መጠየፍ፣ ወገናዊ ፍቅርን መጠየፍ፣ ዕውቀትን መጠየፍ፣ ጥበብን መጠየፍ፣ ዕርቅን መጠየፍ፣ ተቻችሎ መኖርን መጠየፍ፣ አማራ ትግሬን መጠየፍ፣ ትግሬ አማራን መጠየፍ፣ ኦሮሞ – አማራ – ትግሬ – እርስ በርስ መጠያየፍ… ሁሉን መልካም ነገሮች መጠየፍ አብዝተናል፡፡ የእርግማኑ ዑደታዊ ጡዘት ከመቼውም ጊዜ በላይ ከርሯል – ለጤናም አይመስልም ፡፡ በምትኩ በራስ ወዳድነትና በግለኝነት ሱስ መለከፍ፣ በሴሰኝነት ዳንኪራ መጠመድ፣ በሥልጣን አራራ መቃተት፣ በዘረኝነት የደዌ  ልክፍት መንጠራወዝ የዘመኑ ፋሽናችን የሆኑ ይመስላል፡፡ (በነገራችን ላይ በአዲሱ የወያኔ ቤተ ሙከራዊ የሕዝብ ቆጠራ ትግራይ ክልል የመሪነቱን ሥርፋ – ማለትም ሥፍራ – ስትይዝ ሶማሌ ሁለተኛ – ኦሮሞ ሦስተኛ – አማራ አራተኛ እንደሆኑ ሰማሁ፡፡ የዕብድ ቀን አይመሽም፡፡ የወያኔ ቀንም አልመሽ ብሎ በቴዲ አፍሮ ምናባዊ ግሩም አገላለጽ – በእያነቡ እስክስታ ውስጣችን እያረረና በሀዘን እየተኮማተረ በዕድለቢሶቹ የወያኔ ተውኔቶች ግን መገልፈጣችንን ቀጥለናል – አንድ ቀን እንኳን ተኣማኒ ትያትር መድረስ እንዴት ያቅታቸዋል? ለምን ሰው አይቀጥሩም፡፡ ይህን የ‹ቁጥር መበላለጥ› አሁን ቢያስጠጉት፣ ትንሽ ቆይተው ቢያቀርቡት፣ ከዛም ቢደርቡት… አሁን ምን አጣደፋቸው? ለነገሩ ማን ነው ወንዱ “ የጅብ ችኩል …” ብሎ ስማቸውን በከንቱ የሚያነሳ ? ከፉኛ ንቀውናል እኮ!

አነሳሴ ትምህርት ሞታለች ነው፡፡ በአዲስ አበባ ሁለት ትምህርት ቤቶች እንዳሉ ልጠቁም፡፡ እጅግ ውድ የሆኑ የግል ት/ቤቶችና የመንግሥት የሚባሉ የተዋጣላቸው ትውልድ ገዳይ ት/ቤቶች፡፡ የግሎቹ ዋጋቸው ለድሃው ቀርቶ ለንዑስ ከበርቴ ተብዬውም አይቀመሱም፡፡ የማኅበረሰብ ክፍፍሉ ሁለት መደብ ሆኗል – አንድም ያለው አንድም የሌለው፡፡ በያለውና በየሌለው መካከል ያለው ክፍተት የሰማይና ምድርን ርቀት ያስከነዳል፡፡ በድሆች ትምህርት ቤት ከነአካቴው ትምህርት የለም ማለት እንችላለን – ያለው ኮታና ቀልድ ነው፡፡ ወያኔ ለወሽካታው የእስታትስቲክስ መዝገቡ ሲል ይህን ያህል ት/ቤት ተከፈተ፤ ይህን ያህል ልጅ ተመዘገበ … ለሚለው የማስመሰያና ፈንድ ማወራረጃ ድራማው እንጂ ከአንጀት አዝኖ ትውልድን በተገቢው ዕውቀት ለመቅረጽ የሚፈልግ መንግሥት አይደለም፡፡ የትምህርት አመራሩ በጠቅላላውና በየትኛውም እርከን በወያኔዎች መያዙ ችግር እንደሌለው ቆጥረን ሥራው ሲታይ ግን የግብር ይውጣና እውነትም የጠላት ሤራ ትግበራ ይመስላል፡፡ የትምህርት ባለሞያ ይባልና ሰውዬው የሰለጠነው ግን ውትድርና ወይም ቆዳ አፋፋቅና ዓሣ ማስገር ሊሆን ይችላል፡፡ ለነገሩ የፖሊስ አዛዥን የትራንስፖርት ሚኒስትር ከማድረግ የማይመለስ የጉዶች መንግሥት እንጨት ጠራቢን አልጋ አንጣፊ፣ የቢሮ ጸሐፊን ገንዳ ጠባቂ አድርጎ ቢመድብ አይገደውም – አድርገውታልም፡፡ ዋና ዓላማው ሀገርን ማውደምና ትውልድን በቀቢጸ ተስፋ ሀሽሽ ማደንዘዝ፣ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተብዬውንም በሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ማታለል ነው፡፡ ይህ ሀገራዊ አሳዛኝ ቲያትር እስከመቼ ይዘልቃል? ጊዜና እግዚአብሔር የሚፈቱት ነው፡፡ እኛ ግን ግዴለም ዝም ብለን በባዶ ቦታ እንፋጅ፤ ባገኘነውም መድረክ ሁሉ እናምቧትር – ሕዝቡንም ከምጣድ በማይወጣ የተስፋ ዳቦ እንቀብትት፡፡ አየ እኛ!! መጨረሻችንን ያዬ፡፡

በግሉ ዘርፍ ብዙ ት/ቤቶች አሉ – ጥሩዎችም አስመሳዮችም፤ በጣም ውዶችም መለስተኛ ውዶችም (ወላጅን ለማታለል በተማሪ መግቢያና መውጫ ሰዓት ያልተማረ ደንቆሮ ፈረንጅ ቀጥረው በር አካባቢ የሚያቆሙ ት/ቤቶች እንዳሉ ሰምታችኋል? ለማስታወቂያ፡፡ የገዛውን ትልቅ አሮጌ አውቶቡስ ያላንዳች ሥራ ባዶውን ከተማዋን የሚያዞር የኮሌጅ ባለቤት እንዳለስ ታውቁ ነበር? ከመሪ እስከ ነጋዴ፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ፣ ከነጭ እስከ ቢጫ – ደካማ ሥነ ልቦናችንን የማይጠቀም የለም፡፡) በነዚህ የግል ትምህርት ቤቶች ከሚማሩት ተማሪዎች ውስጥ በጨዋ ግምት ከ90 በመቶ የማያንሱት የወያኔ ልጆች መሆናቸው በስፋት ይወራል፡፡ ሌላው አቅም ስለሌለው ልጆቹን የሚልከው አንድም ወደ መንግሥት ት/ቤቶች አለዚያም ወደሸቅልና ወደ ጎዳና ተዳዳሪነት – ወደሽርሙጥና – እልፍ ሲልም ወዳረብ አገር ግርድና … ነው፤ በወያኔ አልፎልናል(ሴቷ ልጄ ለአቅመ -ዐረብ ግርድና አልደርስ ብላኝ ተቸግሬያለሁ – ወያኔ ሌላ ምን አመጣልኝ?)

[ኅያው አባት ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ! የኔን የባርያህንና የመሰል ወንድምና እህት ኢትዮጵያውያን ወገኖቼን ዕንባ አብስ! በቃችሁ በለንና ከነዚህ የሲዖል ትሎች ነጻ የወጣን እንድንሆን አድርገን፤ ከዚህ ውጥንቅጥና የተደራረበ ችግር የሚያወጣን በቅዱስ መንፈስህ የሚመራ አንድ ሙሤያዊ ኃይል በአፋጣኝ ላክልን፤ እንደኛ የኃጢኣት ቁልል ሣይሆን እንደምሕረትህ ብዛት ይሁንልን፤ አሜን፡፡]

ኢትዮጵያ ሳያናግሯት ብዙ እየተናገረች ናት፡፡ ወደ በረንዳዎች ሂዱ፤ ወደ ት/ቤቶችም ሂዱ፤ ወደ ንግድ ቤቶች ሂዱ፤ ወደ መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሂዱ… ብቻ እናንተ ለመሄድ አትሰልቹ እንጂ ወደ የትም ሂዱ፡፡ ወደ ገጠርም ውጡ፤ ወደከተሞችም ግቡ፡፡ በምትሄዱባቸው ጥቅም የሚያስገኙ ቦታዎች ሁሉ ቀድመው የሚጠብቋችሁ ወያኔዎች ናቸው – ‹የታገልንበት የደም ዋጋችን ነው› እያሉ በግልጽ ሲቦጠቡጡ ታያላችሁ፡፡ በዚህ ታሪካዊ ስብራታችን ልባችሁ ይነካል፡፡ ‹ሰው እንዴቱን ያህል ክፉ ቢሆን ነው መሰል ወንድሞቹንና እህቶቹን ከሁሉም ማዕዶች አውጥቶ በኅሊናዊና እውናዊ ርሀብ እየገረፈ የራሱን ኑሮ ብቻ የሚያመቻቸው?› ብላችሁ ለሰው ልጅ አጠቃላይ ተፈጥሮ ትጨነቃላችሁ፡፡ ይህን ግላዊ ምቾቱን ለማረጋገጥ ሲልም የሚሠራውን የመቶና የሁለት መቶ ዓመታት ሲአይኤያዊና ሞሳዳዊ ሸርና ተንኮል ስታስቡ ደግነቱ እግዚአብሔር በመሃል በመኖሩ እንጂ ተስፋ ቆርጣችሁ እናንተም የክፋትን መንገድ ልትከተሉ ትከጅላላችሁ፡፡ ግን እንተማመን – እንደጠቢቡ አባባል ሁሉም ነገር ከንቱና የከንቱ ከንቱ ነው፡፡

እዩልኝ እንግዲህ – በግል ት/ቤቶች የሚማሩ የወያኔ ልጆችን የማውቅበት መንገድ አለኝ፡፡ እውነት እላችኋለሁ – ቁም ነገረኛ ልጅ የወጣላቸውን ቱባ ወያኔዎች ማስታወስ አልችልም፤ ስም እያነሳሁ ማፍረጥረጥ ባላቃተኝ – ነውር ባይሆንብኝ፡፡ ገንዘብና ሥልጣን አላግባብ ከተያዘ እንደማባለጉ የነዚህ ወያኔዎች አብዛኞቹ ልጆች ገና ከአሁኑ ጠፍተዋል፡፡ ለመጥፋት የወላጆቻቸውን ዕድሜ ያህል መጠበቅ አላስፈለጋቸውም – አሸዋና ድንጋይ ላይ በዕለተ ሰንበት የተዘሩ የእርኩሳን ዝሪቶች ናቸውና፡፡ ሕዝብ የረገመው፣ ሀገር ያሳቀለው ዜጋ መቅኖ የለውምና እነዚህ ልጆች ምንም እንኳን በልዩ ትምህርት ቤቶች እንዲማሩ ቢመዘገቡም ገንዘቡ አናታቸው ላይ ወጥቶ ስላሰከራቸው አይማሩም፤ ትምህርት ቤት አይገቡም፤ ቢገቡም በዲሲፕሊን ችግር ት/ቤቱን ያውካሉ፡፡ ሊባረሩ ሲወሰን የትምህርት ቢሮ ባለሥልጣናት ከሚኒስትር ጀምሮ ተረባርበውና የት/ቤቶችን ባለቤቶች በ‹ት/ቤታችሁን እንዘጋባችኋለን› አስፈራርተው ራሳቸው ያወጡትንና ያሰራጩትን ሕግ በመጣስ ያስመልሷቸዋል፡፡ ሕግ በየትም አይሠራም፡፡ በትምህርትም ሆነ በሌላው ዘርፍ ወያኔን በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ የሚነካ ሕግ ሥራ ላይ አይውልም፡፡ ሀገሪቱ በወለድ አግድ በነሱው ሥር ስለዋለች ሕግ የሚሠራው ለሌሎች ምሥኪኖች እንጂ ለወያኔዎች አይደለም፡፡ የምለው የምታውቁትን እንደሆነ ባውቅም እንደመምሬ አውግቼው እየደጋገምኩ ላውጋችሁ ብዬ ነው፡፡ በዚህ እንኳን ቢወጣልኝ፡፡ ጨስን እኮ ምዕመናን!!

በአንድ ‹ምሁር› አነጋገር ፈገግ ላሰኛችሁ ልሞክርና አንዳንድ ነገሮችን ጣል ጣል አድርጌ ልሰናበታችሁ፡፡ ሰዎች አንዱን ጓደኛቸውን ሲተርቡት የሰማሁት እውነተኛ ታሪክ ማለትም ገጠመኝ  ነው፡፡ የዩኒቨርስቲ ጓደኛውን ለበርካታ ዓመታት ሳያየው የኖረ አንድ ሰው ያን ድራሹ የጠፋበትን ጓደኛውን መንገድ ላይ አገኘው አሉ፡፡ ያኔ እንደምንም ለየው(ዐወቀው)ና “እንዴ! አንተ እንትና የምትባለው የዩኒቨርስቲ ጓደኛየ አይደለህም እንዴ? በስማም! በጣም develop አድርገሃል፤ በድምጽህ እኮ ነው ያወቅሁህ!” ብሎት ዕርፍ፡፡ ምን ማለቱ መሰላችሁ ‹ ወፍረሃል፤ ተለውጠሃል፤ ተስማምቶሃል…› ማለቱ ነው፡፡ አንዱ ምሩቅ ደግሞ እንዲህ ብሏል አሉ፡- ‹ፐ ፐ ፐ ያ ልጅ እንዴት ያለው cooked የሆነ ልጅ መሰለህ!› – የዚህኛውስ ገባችሁ? የአማርኛውን በቀጥታ ተርጉሞ ‹በሳል ልጅ› ለማለት ነው፡፡ የወያኔን ጊዜ ምሁራን – ሁሉም አይደሉም በነገራችን ላይ – ገድል እንጻፈው ብንል አውሎ ያሳድረናል፡፡ እዚህ ላይ በራሳቸው ጥረት በግል በሚያደርጉት ጥናትና ምርምር ምክንያት ራሳቸውን በዕውቀት ያደረጁ፣ በየትኛውም የተሰማሩበት መስክ የማያሳፍሩ ወጣትና ጎልማሣ ምሁራን መኖራቸውን መጠቆም እፈልጋለሁ – በደረቅ አበሳ እርጥብ መቃጠል የለበትም፡፡ እነዚህኞቹ ወገኖች በልዩ ድካማቸውና ያልተቆጠበ ጥረታቸው ከወያኔ ሀገርንና ትውልድን የማምከን ሤራ ያመለጡ ናቸውና የምሥጋና ብፅዓት ይገባቸዋል፡፡

በሌላ አቅጣጫ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው እንዳይኖሩ ሲገደዱ ወደ ውጪ በመፍለስና በመሰደድ በነዚያ ሀገሮች በሚገበዩት ዕውቀትና ጥበብ ለወደፊቱ ሀገራቸውን የሚጠቅሙና በእንደገና ግንባታው በከፍተኛ ደረጃ የሚሣተፉ እንደሚሆኑ ከፍተኛ ግምት አለኝ – በበኩሌ፡፡ እናም ተስፋዎቻችን ናችሁና በርቱልን እላለሁ – ፍሉሳንን፤ ደግሞም ከብት እንጂ በየሄደበት እሚለምድ እናንተ ሰዎች በመሆናችሁ ቆንጆና ገና ያልተነካ የተፈጥሮ ሀብት ያላት ሀገር ባለቤትም ስለሆናችሁ ልቦናችሁን ወዳገራችሁ ማቅናት ይኖርባችኋል፤ ጠፍታችሁ እንደምትቀሩ ሳይሆን አንድ ቀን የራሳችሁ ሀገር ባለቤት እንደምትሆኑ አስቡና ዓላማችሁን ከዚህ ቅዱስ ሃሳብ ጋር ቃኙ፡፡ በሀገር ቤቱ ግን ብዙም ተስፋ አናድርግ፡፡ በጣት ከሚቆጠሩ ጥቂቶች በስተቀር ብዙዎቻችን ራስ ወዳዶችና ለወያኔው ሥርዓት አጎብዳጆች ነነ፡፡ ቄስ የለ፣ ገበዝ የለ፣ ጳጳስ የለ፣ ኤጲስ ቆጶስ የለ፣ ምሁር የለ፣ ጨዋ የለ፣  ከሞላ ጎደል ሁላችንም ተንበርካኪዎች ሆነናል፡፡ ‹ጊዜው ነው› ልበልና በጊዜ ላላግጥ ይሆን? እኛው ነን! ጥፋተኞች እኛው ነን፡፡ ቆይ ልኮርጅ፡- የውድመታችን መሃንዲሶች እኛው፤ የመጥፋታችን የገንዘብ ምንጮች እኛው፤ የችግሮቻችን መፍትሔዎች እኛው … ታላቁን ግድብ በሚመለከት ‹ታላቁ› መሪያችን እንዲህ የመሰለ ቀልድ ሲናገር ሰምቻለሁ፡፡

ሀገር ስትጠፋ ሃይ የማይል የሃይማኖት አባት የጥፋት ተባባሪ ከመሆን አይዘልም፡፡ ሀገር ስትጠፋ ሃይ የማይል በሀገር ሀብት የተማረ ምሁር የጥፋት ተባባሪ ከመሆን አይድንም፡፡ ግፍና በደል ሲፈጸም ዝም ብለን ያየን ሁሉ – በቻልነው ያልተቃወምን ሁሉ – ኋላ ላይ የየድርሻችን ወዮታ አለብን፡፡ ስለዚህም ነው በኢትዮጵያ ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ የዘመናዊ ትምህርት ምሁርና የሃይማኖት አባትም ሆነ ተራ አገልጋይ የለም በሚለው የማምነው፡፡ ውሸት ነው፤ ሁላችንም ማለት በሚቻል መልክ ለሩህያችን እንሳሳለን – ሥጋችንንም ከሁሉም አስበልጠን እንወዳለን፡፡ ለኅሊናውና ለነፍሱ ያደረ ሰው ሥጋውን ይጠየፋል፤ ለኅሊናውና ለነፍሱም አድሮ ግፍን ይቃወማል – በዚያም የጽድቅ ሥራው የሞት ጽዋንና የእሥራት መቁነን ሳይቀር ይጋፈጣል፡፡ እነ አንዷለም አራጌና እስክንድር ነጋ የነፍሳቸውን መክሊት ተረድተው የኢትዮጵያዊነታቸውን አሥራት ብኩራት እየከፈሉ በመገኘታቸው እቀናባቸዋለሁ፡፡ የነሱን ያህል በማይሆን አነስተኛ ወጪ ሀገራችንን ከክፋት መታደግ የምንችል ሚሊዮኖች ዝም ብለን ተቀምጠን ስመለከት ደግሞ በራሴ አፍራለሁ፡፡ የእናት ሆድ ዥንጉርጉር መባሉም ለዚህ ነው፡፡ በሀገር ደረጃ ግፍና በደል ናኝቶ ሕዝብ ሲረገጥና ሲጨቆን ዝም የሚል የሃይማኖት አባት ካለ ያ ሰው የሰይጣን ተባባሪ መሆኑን ለመገንዘብ መጽሐፍ መግለጥ ወይ ጠንቋይ መቀለብ አያስፈልግም፡፡ ለሥጋው ያደረ ነፍሱን እንደሚያጣ ከኔ የበለጠ ቀሲስ አስመሮምና ደብተራ ጓንጉል ያውቃሉ፤ ግፍ ሲፈጸም ‹ተው! በሠይፍ የሚገድሉ በሠይፍ ይገደላሉ› ብሎ የማይገስጽ የሃይማኖት አባት ለዓለማዊ ኑሮው የተሸነፈና ለመብል መጠጥ እንዲሁም ለርክብክብ ሥጋ የተንበረከከ መሆኑ ግልጽ ነው – ቃሉም ጠፋኝ፡፡ ሰውንና ሥልጣኑን በመፍራት የእግዚአብሔርን ቃል የሚሽሩ ካህናትና ጳጳሳት በእግዚአብሔር ኅልውና ስለማመናቸው ማወቅ ይከብዳል፡፡ እውነትን የሚቀብሩ ሀሰትን ግን የሚያነግሡ ካህናትና ሊቃነ ጳጳሣት በእግዚአብሔር የማያምኑ ለጨለማው ንጉሥ ግን ቅን ታዛዥ የሆኑ የሥጋዊው ዓለም ሰዎች ናቸው – በዚያ ላይ ‹ለሁለት ጌቶች አትገዙ› የሚለውን ቅዱስ ቃል ለሥጋቸው ሲሉ ሽረውታልና ጽድቅ ከነሱ ጋር አትገኝም፡፡ እንቅልፍ የሞት ታናሽ ወንድም እንደሆነ ሁሉ ኃጢኣተኝነትም የሰይጣናዊነት መገለጫ ነውና ከሚባርኩን ውስጥ የትኞቹ በወዲያኛው ሊባረኩ እንደሚችሉ ለማወቅ ጥልቅ መንፈሳዊነትንና ልባዊ ጸሎትን ይጠይቃል፡፡ ይህን በማይም ቃሌ የምናገረውን ማስተባበል የሚቻለው አንድም ካህን ሊኖር አይችልም፤ ቢኖር እርሱ አንድም ገነት ውስጥ ነው አንድም እኔ አላውቅም፡፡ መሀል ቤት እንደሌለ ግን ይገባኛል፡፡ በተጠየቁ መሠረት ጽድቅና ኩነኔ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ሊሆኑ አይችሉም፤ ጧት ማጉራትና ማታ ዳዊት መድገም እንደማይቻል ሁሉ በእግዚአብሔር ስም እየነገዱ ፍጡራኑን ለአረመኔዎች ጅራፍ አጋልጦ ከአረመኔዎች ጋር መሞዳሞድና ዲያብሎሳዊ ቅኔ ማኅሌት መቆም አይቻልም፡፡ ይህን እውነት ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖረ ነግር ግን ለሥጋው ተሸንፎ መስቀሉን ለኃጥኣን ግሣጼ ያላዋለ የሃይማኖት አባት ነኝ የሚል ሐሳዊ መሢሕ ሁሉ ይገንዘብ፡፡ ደረታቸውን ለጦር አንገታቸውን ለሠይፍ የሰጡ እነቅዱስ ጳውሎስንና መጥምቁ ዮሐንስን ያስቧል፡፡ ባማረ ፎቅ እየኖሩ፣ ያማረን እየለበሱ፣ በዲኤክስና በቪታራ እየተንፈላሰሱ የክብር አክሊል ይገኛል ማለት ዘበት ነው – እንደዚህስ የዚያኛው ጎራ አባላትም አያቅታቸውም፡፡ ቀደምት ጻድቃንና ሰማዕታት ያን ሁሉ መለኮታዊ ክብር የተጎናጸፉት የተላጠ ሙዝ እንደሚመስሉት እንደኋለኞቹ ዘበናይ አባቶች በወርቅና በነሐስ መስቀል እየተሸሞነሞኑ፣ ከእግዚአብሔር ይበልጥ በምዕመናን ዘንድ እንደጣዖት ሊከበሩ እየቃጡ፣ መንፈሣዊ ተልእኳቸውን ንቀው (ፈጣሪን ንቀው) ከዓለማዊ መንግሥታት ጋር በመሻረክ ለዓለማዊ ድሎታቸው እያደሉ፣ ከቃለ ዐዋዲው ውጪ አሥሩ ቦታ እየደቀሉና በድብቅ ልጅ እያሳደጉ የሁለት ዓለም ሰዎች ሆነው  ሳይሆን የተቆጠረች ውሱን ሽምብራ እያንቀራጩና ዐይን ያላያት ሥጋ ያልሳሳባት የበረሃ ቅጠል ተሲያት ላይ ቀንጥሰው እየቀመሱ፣ ከእባብና ዘንዶ እንዲሁም ከአንበሣና ከነብር ጋር በዱር በገደል እየታገሉ፣ ከከሃዲያንና ከአረመኔ መንግሥታት ጋር እየተፋለሙ ነው፡፡ መንፈሣዊ ተጋድሎ ቀላል አይደለም፤ በዘረጥ እምቦጥም የሰማያዊ መንግሥት ወራሽ አይኮንም፤ ልብ እንበል – ከዚህ አኳያ ቤተ ክርስቲያናችን ብዙ የምታወራርደው ዕዳ ከፊት ለፊቷ ተደቅኗል፡፡ በግልቡ ለየዋሃን እንደሚታየው ነገሩ ጥምጥም የማሳመርና ቃለ እግዚአብሔርን የማነብነብ ወይም በያሬዳዊ ዜማ ምእመናንን የመመሰጥ ጉዳይ አይደለም … ብዙ ማለት ይቻላል፡፡ በዚህ ረገድስ ጊዜው ሲደርስ በግልጽ ለመነጋገር ያብቃን፡፡

ልጨረስ ነው አይዞህ፡፡ የኑሮ ውድነቱ እንደወትሮው ሁሉ ህዝብን ባልተወለደ አንጀቱ እየሸነቆጠ ነው፡፡ ቲማቲምም ባቅሙ 25 ብርን ከዘለለ ሰነበተ፡፡ ዱሮ የሥጋ ቁርጥ ነበር የሚያምረን፡፡ አሁን ደግሞ የቲማቲም ቁርጥ – ሰላጣ ከሥጋ ቁርጥ ሊስተካከል ተቃርቧል፡፡ ሥጋ ለብዙዎቻችን የመዝገበ ቃላት ቃል ከሆነ ከረመ፡፡ የ300 ብር ደሞዝተኛ በአማካይ የ150 ብር ቁርጥ ሲበላ ይታይህ፡፡ የ600 ብር ደሞዝተኛ የ180 ብር ኪሎ ቅቤ ሲገዛ ይታይህ፡፡ የ1000 ብር ደሞዝተኛ የ40ና 50 ብር እዚህ ግባ የማይሉት አንድን ሕጻን እንኳን የማያጠግብ የበሬ ይሁን የበግና የፍየል ወይም ለባህላዊና ሃይማኖታዊ የአመጋገብ ሥርዓታችን እንግዳ የሆነ የሌላ ፍጡር ሥጋ ጥብስ እቡና ቤት ገዝቶ ሲመገብ ይታይህ፡፡ የ1500 ብር ደሞዝተኛ በደህናው ቀን ለገዛው አልጋው የ700 እና የ800 ብር ብርድ ልብስ ወይም የ450 እና የ600 ብር አንሶላ ሲገዛ ይታይህ፡፡ የ400 ብር የጽዳት ሠራተኛ በታክሲና በከተማ አውቶቡስ ስትጓዝና የ15 ብር የፍራፍሬ ጭማቂ ስትጠጣ ትታይህ፡፡ እኔ ዳግማዊ መጠኑን በጭራሽ በማልነግርህ የሦስት ሺህ ብር ወርሃዊ የተጣራ ደመወዜ ለአሥር ቤተሰቤ የሚበቃ (ለሥጋና ወተቱ ዐርብና ረቡዕን ሳይጨምር) በየቀኑ 3 ኪሎ ሥጋ፣ 3 ኪሎ ጤፍ፣ ግማሽ ሊትር የምግብ ዘይት፣ ለአንድ የወንድና ለአንድ የሴት በድምሩ ለሁለት ዕድሮች የሚከፈል፣ አንድ ሊትር ላምባ፣ 3 ነጠላ ሻማዎች፣ 3 ሊትር ወተት፣ 3 ኪሎ አትክልትና ፍራፍሬ፣ 3 ጃምቦ ድራፍት፣ 3 ለስላሳ (ከውኃ ጋር አብቃቅቶ ለመጠጣት)፣ 3 ቡና፣ 6 ኪሎዋት ኮረንቲ፣ ሩብ ኪዩቢክ ሊትር ውኃ፣ በአማካይ አሥር የቤት ሥልክ ጥሪ፣ በቤተሰብ የሚከፋፈል የ100 ብር ሞባይል ካርድ፣  አንድ ኪሎ ከሰል፣ ግማሽ ኪሎ ስኳር ከነቀጠፉ፣ የ30 ኪሎ ሜትር ቤት/መሥሪያ ቤት ደርሶ መልስ ጉዞ፣ ኦ! ደከመኝ … ይህን ሁሉ ስገበይ ይታይህ፡፡ ባይገርምህ ከ40 ዓመታት በፊት በነበረ ገበያ እነዚህንና ሌሎችንም ጨምሮ ቤትን ለማሟላት በከፍተኛ ግምት የ200 ብር ደሞዝተኛ ብቻ መሆን ነበር የሚያስፈልግ፡፡ ዛሬ ወያኔ መጣና ሁሉን ነገር እንዳይሆን እንዳይሆን አደረገና የአሥር ሺህ ብር ደሞዝተኛ ሳይቀር በኑሮው ብዙ እየጎደለበት ከድሃው ጋር የሚያላዝን ሆኗል፡፡ አልፎለት የምታየው ኅሊናውን በየቤቱ ታዛ ሸጉቦ አቅሉን ለገንዘብ ሸጦ በመጣው ይምጣ ከወያኔ ጋር የወየነ ብቻ ነው – ወቅቱ ራስን የማዳን ነው፡፡ ተንደላቅቀህ ለመኖር ኅሊና፣ አእምሮ፣ አስተሳሰብ፣ አመለካከት፣ ምናምን እንዲኖርህ አያስፈልግም፡፡ ሌላውና ብዙኃኑ ይልሰውንና ይቀምሰውን አጥቶ በሞትና በሕይወት መካከል እየተንጠራወዘ በሆዳቸው የሚያስቡና ነገን የማያውቁ ብቻ በቆንጆ ሁኔታ እየኖሩ ናቸው፡፡

ባክህን ትንሽ ላክል – መለየቱ አሳሳኝ፡፡ የ700 ብር ደሞዝተኛ ፖሊስ የ800 ብር ቤት ተከራይቶ ከነቤተሰቡ ሲኖር ይታያችሁ፡፡ የ500 ብር ደሞዝተኛ ርካሹን የ300 ብር ጫማና የ16 ብር ካልሲ ሲገዛ ይታያችሁ፡፡ ዛሬ ሸሚዝ ለመግዛት ቁብ መግባት አለብህ – ጥሩ ሸሚዝ ከብር 400 ይጀምራል፡፡ የጥንቱ የ120 ብር የሎንዶን ሱፍ ዛሬ ከ12000 ብር በላይ ነው፤ የቻይና ፍርጅድ ሱፍ ራሱ ከ2000 ብር በላይ ይሸጣል – እንደዝምብ አማካይ ዕድሜ አገልግሎታቸው በ15 ቀናት ውስጥ በሚጠናቀቅ የፎርጅድ ዕቃዎች ተጥለቅልቀናል – ለነገሩ ሁሉም ነገራችን ፎርጅድ ሆኗል፤ ትምህርቱ፣ ሰው ሁሉ ፎርጅድ፣ መስተንግዶው ፎርጅድ፣ ፈገግታው ፎርጅድ፣ አገልግሎቱ ፎርጅድ፣ ቅዳሤውና ማኅሌቱ ፎርጅድ፣ ንስሃ አባቱ ፎርጅድ፣ ስብከቱ ፎርጅድ፣ … ፎርጅድ ያልሆነውና ጄኒውን የምንለው እንደእንስሳት ኖረን እንደሰው መሞታችን ብቻ ነው፡፡ ምን አለፋህ ወንድሜ – የምንኖረው በተዓምር ነው፡፡ የሰዎችን ገቢ ስትሰሙና ቀኑ እንዴት ነግቶላቸው እንደሚመሽ ስትታዘቡ ከአእምሮ በላይ በሆነ አንዳች ስሜት ትወጠራላችሁ፡፡ የመንግሥትን ጭካኔ አይታችሁ፣ የግል ኢንቬስተሮችንና ሀብታሞችን አረመኔነት ተመልክታችሁ በሥራቸው የሚገኙ ምዝብር ድሆች እንዴት እንደሚኖሩ ስታጤኑ መፈጠራችሁን ትጠላላችሁ፤ የዓለምን  ፍጻሜም ትመኛላችሁ – ልክ እንደኔ፡፡ ‹ሰውን መግዛት እያስራቡና እያሰቃዩ ነው› የሚለው ነባር የኢትዮጵያው ብሂል ይከሰትላችኋል፡፡ መንግሥትና አብዛኛው ኢንቬስተር sadist ናቸው ተብሎ ቢታመን ድርብርብ እውነት ነው፡፡

ሰሞኑን ደግሞ ይሄ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚባል የቅዱሱን ስም አላግባብ አስካሪ መጠጡ ላይ የለጠፈ ቢራ ኮማሪ ድርጅት አብዝቶታል፡፡ ከወያኔ ጋር እየተባበረ በብሻን ጮረሬ የፋብሪካ ጠላው ሕዝብን መግፈፉ አነሰውና በየስድስት ወሩ በሚጨምረው ዋጋው ምድረ መኢጠማን (መላው የኢትዮጵያ ጠጪዎች ማኅበር) እያማረረው(ን) ይገኛል፡፡ ነሸጥ ባረገው ጊዜ ሁሉ እየባነነ በሚጨምረው ዋጋ የአንድ ነጠላ ድራፍት ዋጋ ከ85 ሣንቲም እኔ የማውቅለት ዋጋ ተነስቶ ዛሬ 6 ብር እንዲደርስ አድርጎታል፡፡ ከግንቦት 97 በፊት ባማካይ 2.70 የነበረው ጃምቦ ዛሬ በብዙ ቦታዎች 12 ብርን አሻቅቧል፡፡ የሚገርመው ጊዮርጊሶች ከጨመሩ ሌሎቹም እንዲጨምሩ መገደዳቸው ነው፡፡ የሕዝቡን – ማለትም የጠጪውን ማኅበረሰብ የልብ ትርታና የሥነ ልቦና ቀመር ሳይረዱት አልቀሩም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ዋጋ ሲጨምር ገበያ ይደራል፡፡ በውሰት አገላለጽ ባሕርያችንን ለመጠቆም ያህል – እኛ ኢትዮጵያውያን ወደ አውሮፓውያን የገበያ ሥሪት ከምንገባና መብታችንን በጋርዮሻዊ አድማ ከምናስከብር ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብትሾልክ ሳይቀላት አይቀርም፡፡ የምንገርም ሕዝብ ነን፡፡ ድራፍትና ቢራ የዕድሜ ማራዘሚያ ኤ.አር.ቪ የሆነ ያህል፣ ድራፍት ለአንድ ሣምንት ባንጠጣ የምንሞት ይመስል፣ አልኮል መጠጣትን ለአንድ ቀን ብንተው የምንዋረድና ድህነታችንን ለ‹ጠላት ለወዳጅ› የገለጥን ይመስል … በራሳችን ገንዘብና በድንቁርናችን ምክንያት ሻጮችና ኮማሪዎች በላያችን ላይ ለዘላለሙ እንዲነግሡብን ተመቻቸንላቸው፡፡ አህያና አጋሰስ መጋጃ ሆንልናቸውና አምቡላቸውንና አተላቸውን በፈለጉት ዋጋ ይቸረችሩልን ያዙ፡፡ በመሠረቱ ይሄ የኛ እንጂ የነሱ ጉዳይ አይደለም፡፡

እነሱማ ከመንግሥት ጋር እየተመሳጠሩ ገቢያቸውንም በስንጥቅ ትርፍ እያሳደጉ በሚከፍሉት ከኛው አላግባብ የሚዘረፍ የመንግሥት ግብርም መትረየስ ከነአረሩ እየተገዛ በኛው በድሆቹ ልጆች አናት ላይ ይርከፈከፋል – መብታችንን በጠየቅን ቁጥር፡፡ በእግረ መንገድም በቡና ቤት ለመዝናናት አቅም ያጣን ዜጎች እንደዶሮ በጊዜ ወደየቤታችን ስንሰተር መንግሥትን አናማም፤ አንቦጭቅም፡፡ ያኔ ወያኔው አንጻራዊ ዕረፍት ያገኛል፡፡ ለአንድ ቡና ወይ ማኪያቶ  8 እና 10 ብር ካልከፈልክ፣ በተለይ በቦሌ መስመር ለአንድ ኬክ ሃያና ሠላሣ ምናምን ብር ካልተዘረፍክ፣ ከጉሮሮ ለማያልፍ በአረፋ የተሞላ አንድ ድራፍት አሥራ ምናምን ብር ቁጭ ካላደረግህ፣ … እንዲያው ተጎልተህ የማንን ወንበር ታሞቃለህ? ማንስ ያስቀምጥሃል? ኤዲያ! የኢትዮጵያ ነገርስ … ምነው እግዜሩም እንደሰው ጨከነ ግን? እነዚህ ወያኔዎች እኮ የማይገቡበት የለም፤ እሱንም ‹ሆስቴጅ› አድርገውት ይሆን እንዴ? መጠርጠር ነው! ለማንኛውም እንዲህ ማለቴን አትፍረዱብኝ – ቢጨንቀኝ ነው – “እስከማዕዜኑ ትረስዓኒ ሊተ” ብሏል አሉ  ዳዊት እንደኛው ቢጨነቅ፡፡ ኢዮብም ክፉኛ ይወቅስ ነበር፡፡

ያገሬ ባላገርስ እንዲህ ያለው ወዶ ነው?

 

ቀና ብዬ ባየው ሰማዩ ቀለለኝ፤

አንተንም ሠፈራ ወሰዱህ መሰለኝ፡፡

 

እርግጥ ነው – የእግዚአብሔርን ሥልጣንና ኃይል አይዘባበቱበትም፤ ሰው ሲጨነቅ ብዙ ይላል እንጂ የፍርዱ ቀን መምጣቱ በጭራሽ አይቀርም፡፡ እንዲያውም ወንጀልና የክፋት ሥራ ሲበዛ ቀኑ እንደቀረበ ምልክት ነውና ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ የሚገኝ እንደኔ ዓይነቱ ሆደ ባሻ ሰው ብዙ ያስቀይማልና በድምብርብር አነጋገሬ የተከፋችሁ ይቅርታ ታደርጉልኝ ዘንድ ከልብ እለምናለሁ፡፡ ቻው፡፡

አዜብ መስፍን ከአቶ ገ/ዋህድ፣ አቶ ነጋና ምህረተአብ ጋር በመመሳጠር በ3 መርከብ ስሚንቶ አስጭነው በማስገባት የሙስና ወንጀል መፈፀማቸውን ምንጮች አጋለጡ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

$
0
0

azeb(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከአቶ ገ/ዋህድ፣ አቶ ነጋና ምህረተአብ ጋር በመመሳጠር በሶስት መርከብ ስሚንቶ አስጭነው አገር ውስጥ በማስገባት ከፍተኛ የሙስና ወንጀል መፈፀማቸውን ምንጮች አጋለጡ። በተከለከለ ፍራንኮ ቫሉታ ፈቃድ አገር ቤት የገባው ስሚንቶ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ትርፍ አዜብና ግብረአበሮቻቸው እንደዛቁበት ያረጋገጡት ምንጮቹ፣ አያይዘውም ጉዳዩ በደህንነት ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ እጅ እንደገባ አስታውቀዋል። በሕገወጥ መንገድ የውጭ ምንዛሪ በከፍተኛ ደረጃ በመመደብና አስፈላጊውን ትእዛዝ በመስጠት እንዲሁም የጥቅም ተካፋይ በመሆን ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱት አዜብ መስፍን ከዚህ ድርጊታቸው በተጨማሪ ከዚህ ቀደም ከስሚንቶው ጋር በተያያዘ ተመስርቶ የነበረውን ክስ እንዲቋረጥ ማድረጋቸውን የጠቆሙት ምንጮች፣ ይህና ሌሎች ተያያዥ የወንጀል ድርጊቶችን የሚያስረዱ ማስረጃዎች በአቶ ጌታቸው እጅ እንደገቡ አረጋግጠዋል። አቶ ነጋ ገ/እግዚያብሄር በኮንትሮባንድ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው ወደ አገር ውስጥ ያስገቧቸው የህክምና መሳሪያዎች ተይዘው ክስ ከተመሰረተባቸው በኋላ ክሱ እንዲቋረጥ ያደረጉት አዜብ መሆናቸውን የገለፁት ምንጮቹ፣ በተለያዩ ጊዜያት የገቡና የነጋ ገ/እግዚያብሄር ንብረት የሆኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ያለቀረጥ እንዲገቡ በማድረግ አዜብ መተባበራቸውን አያይዘው ገልፀዋል። ጉዳዩም «ክስ በማቋረጥ..» በሚል በሰነድ ተደግፎና ከሌሎች መሰል ድርጊቶች ጋር ተያይዞ በታሳሪዎች ላይ ክስ የቀረበ ቢሆንም፣ ዋናው ተዋናይ ግን አዜብ ሳይጠየቁ መቅረታቸው አነጋጋሪ መሆኑን ምንጮቹ አልሸሸጉም። ከስሚንቶው ጋር በተያያዘ አስተያየት የጠየኳቸው ታዋቂ የሆኑ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ባለሙያ ፥ « መንግስት ስለ ፍራንኮ ቫሉታ ሕግ አውጥቷል፤ ይህን በመተላለፍ ሶስት መርከብ ስሚንቶን የሚያክል ነገር በታሳሪዎቹ ብቻ ሊፈፀም አይችልም፤ ከዚህ ሕገወጥ ድርጊት በስተጀርባ ትልቅና ቁልፍ ስልጣን ያለው ሰው እጁ እንዳለበት ግልፅ ነው።» ብለዋል።
በተያያዘም ስለ ነጋ ገ/እግዚያብሄርና ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስ የጀርባ ታሪክ በተመለከተ ምንጮቹ ተከታዩን መረጃ አስቀምጠዋል፤ “ ሕወሐት/ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ሲመጣ የአቶ ነጋ ስራ የመኪና ድለላና ኮረዶችን ከባለስልጣናት ጋር የማገናኘት የድለላ ተግባር ላይ ተሰማርቶ እንደነበረ ይገልፃሉ። በተለይ ሴቶችን እየመረጠ ለበርካታ የገዢው ሹማምንት ለወሲብ ከማቅረብ ጎን ለጎን የሕወሐት ቁልፍ ባለስልጣናትን በእጁ የማስገባት አጋጣሚ ፈጥሮለታል ፥ ይላሉ ምንጮቹ። ከባዶ ተነስቶ ሚሊየነር የሆነበት ምስጢሩ አዜብ መስፍን መሆናቸውን ያሰምሩበታል። ለዚህም «ነፃ ትሬዲንግ፣ ባሰፋና…» ሌሎች ከፍተኛ የቢዝነስ ተቋማቱና በሕገወጥ የዘረፋ ተግባር በድፍረት ተሰማርቶ መቆየቱን ከሞላ ጎደል ይጠቅሳሉ። በባለስልጣናቱ ተረማምዶ ከአዜብ ጋር በፈጠረው <ልዩ ቁርኝት> የተገኘ ሃብት እንደሆነ ይገልፃሉ። ከአዜብ ጋር በማሌዢያና ለንደን የፈፀሟቸው አስነዋሪ ተግባራት የሚያሳዩ የምስል ማስረጃዎች በደህንነት ሃላፊው እጅ እንደገቡ የጠቆሙት ምንጮቹ፣ የሁለቱን ግንኙነት በተመለከተ አብዛኛው የሕወሐት አመራር ጠንቅቆ እንደሚያውቀው አስታውቀዋል። አቶ ነጋ በቁጥጥር ስር ሲውሉ ማመን ተስኗቸው ከማንገራገራቸው ባሻገር፥ «..ለአዜብ ስልክ እንድደውል ፍቀዱልኝ?» በማለት መማፀናቸውንና ደህንነቶቹ እንዳልተቀበሏቸው ምንጮቹ አመልክተዋል። በሌላም በኩል ከአዜብ ጋር ተመሳሳይ <ግንኙነት> ያላቸው ሌሎች ሁለት ባለሃብቶች፥ አንዱ 40 ሚሊዮን የፈጀ ባለስድስት ፎቅ የቢዝነስ ተቋም (ቦሌ ከሜጋ አጠገብ) አዜብ በለገሱት ገንዘብ እንዲገነባ ሲደረግ፣ ከዚህ ግለሰብ ጋር በተደጋጋሚ በዱባይ በውቂያኖስ ላይ በተገነባውና የቱጃሩ አልወሊድ ቢንጣለል ንብረት በሆነው “ኪንግደም” ባለ4 ኮከብ እጅግ ዘመናዊ ሆቴል እንደተገናኙ፣ እንዲሁም ሌላኛው የአንድ ቢሊየን ብር ባለሃብት ሆኖ ከፍተኛ ደረጃ እንዲደርስ አዜብ ማድረጋቸውን ምንጮቹ አጋልጠዋል።
የአቶ ገ/ዋህድ ማንነት በተመለከተ ምንጮቹ ይህን ይላሉ፤ « ገ/ዋህድ የኢሰፓ አባል ሆኖ በአስመራ እስከ 1982ዓ.ም ያገለግል ነበር። በዚሁ አመት መጨረሻ በራማ በኩል አድርጎ ሕወሐትን ተቀላቀለ። በወቅቱ በመቀሌ እንዲቋቋም በተደረገውና የቀድሞ የደርግ ከፍተኛ መኮንኖች (ምርኮኛ) የተካተቱበት <ኢዴመአን> የተባለ ድርጅት መስራች አባል ነበር – ገ/ዋህድ። በ1983 ዓ.ም የሁለት ሳምንት ወታደራዊ ስልጠና ወይም በድርጅቱ አጠራር “ተአለም” ከወሰደ በኋላ በአጋጣሚ ፓርቲው መላ አገሪቱን እንደተቆጣጠረ ምንጮቹ ያመለክታሉ። በሲቪል ሰርቪስ አልፎ ደቡብን ከጀርባ እንዲመሩ ከተመደቡት አቶ ቢተው በላይ ጋር በአዋሳ ተመደበ። በ1993ዓ.ም በተፈጠረው የፓርቲው መሰንጠቅ አመቺ አጋጣሚ የተፈጠረለት ገ/ዋህድ የክልሉን ፕ/ት አቶ አባተ ኪሾን፣ ቢተው በላይና ሌሎችም እንዲታሰሩ በማድረግ ከፍተኛ ሚና ተጫወተ። ለዚህ ታማኝነቱ የላቀ ቦታ በመለስ ማግኘት እንደቻለና ከዛ በኋላ በየቀኑ ከአዜብና መለስ ጋር በስልክ ይገናኝ እንደነበረ በፈለገው ጊዜ ቤተመንግስት ይገባና ይወጣ እንደነበረ ምንጮቹ አረጋግጠዋል። በአዜብ መልካም ፈቃድ በጉምሩክ ወሳኝ ስልጣን እንዲጨብጥ መደረጉንም አክለው ገልፀዋል። ከአዜብና ሸሪኮቻቸው ጋር በመነጋገርና በመመሳጠር ስሚንቶና ሌሎች ቁሳቁሶች በህገወጥ መንገድ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው አገር ቤት እንዲገቡ በማድረግ ከፍተኛ ሚና የተጫወተው ገ/ዋህድ፣ በሚሊዮን የሚገመት ሃብት ከዘረፋው እንዳተረፈም ተመልክቷል። ባለቤቱ ኮ/ል ሃይማኖትም እንዲሁ አዜብ በሚመሩት የሴቶችና ፀረ-ኤድስ ተቋም በምክትል ሃላፊነት እንዲመደቡና በየአመቱ ከአሜሪካ ብቻ እስከ 240 ሚሊዮን ዶላር በእርዳታ መልክ የሚገኘውን ገንዘብ በግልፅ በመዝረፍ ተባባሪ ሆነው መቆየታቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል።


አሸባሪዉ ኢህአዴግና የፀረሽብር ህጉ መወገድ አለባቸዉ

$
0
0

ከተስፋዬ ተካልኝ


ዘዋይ እስር ቤትኢትዮጵያንና ህዝቧን የአብሮነትን መሠረት ለመሸርሸርና ብሎም ለማጥፋት ሌተ ቀን የማይተኛዉ የህወሀት ኢህአዴግ አሸባሪ መራሹ መንግስት በህዝብ ጫንቃ ላይ ተቀምጦ ዜጎችን ማሰቃየት ከጀመረእነሆ ፪፪ አመት ተቆጥሮዋል።ነገር ግን የ፪፪ አመት ቆይታዉ ህዠብን ከማሸበር፣ ከመግደል፣ከማሰር ከማሰደድ፣ከመግረፍና ከማፈናቀል አልፎ በተመቸዉና የጥፋት ምርቃናዉ በመጣለት ቁጥር በዘረኞች መሪዎቹአማካይነት በፈለገዉ ሰዐት ከራሱ ህግና ስርአትዉጪ ከእንቅልፋ እንደሚነቃና የሚያደርገዉን እንደማያቅ ህፃን ልጅ የተለያዮ ህጎችን በማዉጣት ጭምር ህዝባችንን ከህዝባችን እንዲሁም ሀገሪቱዋን ባለቤትየሚያሳጣ አስነዋሪ ህጎች በማርቀቅና ድራማ በመስራት ማፍያ ስርአት መሆኑ ይታወቃል።

ከእነዚህ የህወሀት ኢህአዴግ አስነዋሪ ህጎች አንዱ እኤአ ፪፻፱ በሙዋቹ ቀንደኛ ማፍያ መሪያቸዉ መለስ ዜናዊ መሪነትና በሌሎች አጭበርባሪ ሆዳም የሀገር ፍቅር በሌላቸዉ ተከታዮች አማካይነት የፀረ ሽብርህግ አዉጥቶ ፭፬፩ እጅ በሚያነሱለት የፓርላማ አሻንጉሊቶቹ ድጋፍ ማፀደቁ የሚታወቅ ነዉ።

ይህ ህግ አሁንም በባለ ጥፋቱ መሪያቸዉ የሙት መንፈስ ራእይ ስምና በተተካዉ አሻንጉሊት መሪ ሀይለማርያም ደሳለኝ ህጉ እንደቀጠለ ሲሆን ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚያሸብረ ወያኔ ሆኖ ሳለ ነገር ግን በመሣርያየበላይነት በሀገሪቷ ዉስጥ ከወያኔ የተለየ ሀሳብ ያላቸዉ በህጉ የስቃይ ሰለባ እየሆኑ ነዉ ዛሬም።

ለዚህም ማስረጃ ሰሞኑን ወገናችን ተስፋዬ ተካልኝ በአንድነት ፓርቲ ጽህፈት ቤት ዉስጥ የሚሊዮኖች ድምፅ በሚል በሰጠዉ ቃለ ምልልስ ፪፫ ወራት፣ ለ፫ ወር ማዕከላዊ ለ፩፱ ወር ደግሞ በዝዋይ እስርቤት በወያኔ ኢሰብአዊና አረመኔያዊ የጭካኔ በደል ፍዳዉን አብልተዉ የቁም ሞት ገለዉ ከለቀቁት በዉኃላ በዚህ የፀረ ሽብር ህግ ምክንያት ህይወቱ ጉዳና ላይ ወድቋል ንፁሀን ዜጎች ከሱ ጭምር የህጉ ሠለባመሆናቸዉን ከአንደበቱ ሰምተናል።

ስለዚህ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት ዛሬ ነገ ሳይል እንደ ተስፋዬ ተካልኝ እይነት ሚሊዮኖችን ከተለያዮ ግልፅና ስዉር የማሰቃያ ቦታዎች ሊታደጋቸዉ እንዲሁም አሸባሪዉ ህወሀት ኢህአዴግንና ፀረሽብር ህጉን ከኢትዮጵያ ማስወገድ አለበት።

እኔ ተስፋዬ ተካልኝ ነኝ እናንተስ

በህወኃት ወያኔ ሞት

የኢትዮጵያ ነፃነት።

 

“ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የምናደርገው ትግል በስም ማጥፋትና በፍረጃ አይገታም”–ሰማያዊ ፓርቲ

$
0
0

semayawi partyከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ሰማያዊ ፓርቲ በሃገራችን የሚፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰትና የአስተዳደር ብልሹነት እንዲስተካከል የመንግሥት አካላት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ነገርግን እነዚህ ጥያቄዎቻችን በመንግሥት በኩል ምላሽ ስለተነፈጋቸው ጥያቄዎቹ ከፍ ባለደረጃ ትኩረት እንዲያገኙ ሆነው መቅረብ እንዳለባቸው ተገንዝበናል፡፡ በዚህም መሰረት ጥያቄዎቹን በሰላማዊ ሰልፍ መጠየቅ እንዳለበት ወስኖ ግንቦት 25 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በአዲስ አበባ ባካሔደው ታላቅ ሠላማዊ ሠልፍ ጥያቄዎቹ እንዲመለሱ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ በተጨማሪም ጥያቄዎቻችን ከመንግሥት በኩል በሦስት ወር ጊዜ ምላሽ የማያገኙ ከሆነ ሌላ የተቃውሞ ሠልፍ ከፍ ባለ ደረጃ የሚጠራ ስለመሆኑ ፓርቲው አቋሙን በሰልፉ ዕለት አሳውቋል፡፡
ይሁንእንጂ ሰልፉ ከተጠናቀቀበት ዕለት ጀምሮ በገዥው ፓርቲና በመንግሥት ተወካዮች የተሠጡ መግለጫዎች ያስገነዘቡን መፍትሔ እንዲሠጣቸው ለቀረቡ ጥያቄዎች መንግስት ተገቢውን መልስ ለመስጠት ምንም ዓይነት ፍላጐት እንደሌለው ነው፡፡ ከዚህም አልፎ መንግስት ጥያቄዎቹ የቀረቡበትን መንፈስ እንኳ በቀናነት ለመቀበል ያልፈለገ መሆኑን ያሳያል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ፓርቲያችንን ለመጫንና ስሙን ለማጉደፍ በፕሮግራሙም ሆነ በሥራ እንቅስቃሴው የሌለበትን በአክራሪነትና በአሸባሪነት ለመወንጀል ተደጋጋሚ ጥረት እያደረገ መሆኑን ከሚሠጣቸው መግለጫዎች ተረድተናል፡፡
ይህ የመንግስት አካሔድ የጥያቄዎቻችንን አቅጣጫ ለማስቀየር ከሚደረግ ሙከራ ውጭ የትግሉን እንቅስቃሴ ሊገታው እንደማይችል ዛሬ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች እያደረጉ ያሉት የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ አብይ ማስረጃ ነው፡፡ በተጨማሪም መንግስት የሚያደርጋቸውን ፍረጃና ስም ማጉደፍን በመፍራት የኢትዮጵያ ህዝብ የሚደርስበትን የሰብአዊ መብት ጥሰትና የአስተዳደር ብልሹነት ከዚህ በላይ ተሸክሞ ለመኖር የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ያሳያል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በአሁኑ ወቅት ለነፃነትና ለፍትህ መገኘት እያደረጉ ያለውን እንቅስቃሴ ፓርቲያችን እያደነቀ ትግላቸንን አጠናክረን እንድንቀጥል መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2ዐዐ5 ዓ/ም. ካካሄደው ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ዕለት ጀምሮ በገዥው ፓርቲና በመንግሥት የተወሰዱ አቋሞችን በመገምገም ፓርቲው ላቀረባቸው ጥያቄዎች የተሠጠ ምላሽ አለመኖሩንና አንዳንዶቹም ችግሮች እየተባባሱ መሔዳቸውን ተገንዝቧል፡፡

ስለሆነም ፓርቲያችን ለሕዝብ በገባው ቃል መሠረት ነሀሴ 26 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም ከፍ ያለ የተቃውሞ ሰልፍ በማካሄድ አሁንም በሃገራችን የሚካሄዱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና የአስተዳደር ብልሹነቶች እንዲስተካከሉ፣ በተለይም የፖለቲካና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፣ የመንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ገብነት እንዲቆም፣ የተፈናቀሉ ዜጐች ወደመኖሪያቸው እንዲመለሱና አፈናቃዮችም ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ ሙስናና የተበላሹ አሰራሮች እንዲወገዱ ላቀረባቸው ጥያቄዎች ምላሽ እስኪያገኙ ድረስ ትግሉን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
በዚሁም መሰረት መንግስት በፓርቲዎች ላይ ከሚነዛው ስም ማጥፋትና ፍረጃ እንዲቆጠብና ፓርቲያችን ላነሳቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፣ የፓለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማሕበራት ነሀሴ 26 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በምናደርገው ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በመሳተፍ የየበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ሐምሌ 12 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ

“በስመ ተቃዋሚ ተቃቅፎ መሳሳም” – ለትልቁ ዓላማ? (ሶሊያና ሽመልስ)

$
0
0

 

zone9

ከጥቂት ጊዜያት በፊት አንድ የመጽሐፍ ዳሰሳ ዝግጅት ላይ ተገኝቼ ነበር፡፡ መጽሐፉ “ፌኒክሷ ዛሬም፣ ሞታም ትነሳለችች” ሲሆን ጸሐፊዋ የቀድሞው የሕወሓት አባልና አመራር የአቶ ገብሩ አስራት ባለቤት ወ/ሮ ውብማር ናቸው፡፡ በዳሰሳው ወቅት በትግል ጊዜ ለምን መጽሐፉ ላይ የተጠቀሱትን ችግሮች እንዳልፈቱ ሲጠየቁ ወይዘሮዋ እንዲህ ብለው መልሰው ነበር፡፡“ደርግን የሚያህል ጠላት ከፊት ለፊታችን እያለ እንዴት እርስ በርስ በመጣላት ጊዜ እናባክናለን? ነጻ ስንወጣ የሕወሓት ፖሊሲና ፕሮግራም ሁሉንም ነገር ይፈታዋል::” ብለን ተውነው ይላሉ፡፡በኋላ ላይ ደግሞ ሕወሓትን ስለመለወጥ ሲጠየቁ ‹‹ሕወሓት ከዚህ በኋላ የሚለወጥ ድርጅት አይደለም አርጅቷል፡፡ 40 ዓመት በኋላ የድርጅት ባሕሪይ አይቀየርም›› ሲሉ ይከራከራሉ፡፡

Zone9 young Ethiopian bloggers

Zone9 is an informal group of young Ethiopian bloggers working together

 

የትኛው ጠላት? የትኛው ትልቁ ዓላማ?

አሁንም ሕወሓት ሥልጣን ከያዘ ከ20 ዓመት በኋላም ቢሆን የዋናው ጠላት ወይም “ትልቁ ዓላማ” ክርክር እንደ መተባበርያ እና እነደመቻቻያ ሰበብ እንዲሁም እንደአለመተቺያ ምክንያት ይነሳል፡፡ ተቃዋሚዎች እንዲተባበሩ የሚጠየቁት “ዋናውን ጠላት” ለማንበርከክ ነው፡፡ የትልቁ ጠላት መኖር አገራዊ የፖለቲካ ክርክራችንንም ሆነ የፓርቲ ፖለቲካችንን የሚበጠብጥ ትልቅ ችግራችን እየመሰለኝ መጥቷል፡፡ መንግሥት/ገዥው ፓርቲ የተሰኘውን ይህንን ጠላት ለማባረር በሚደረገው ጥረት ውስጥ ለትልቁ ዓላማ ተብሎ የምናጣቸውን ነገሮች ሳናስተውል የምናልፍበት ጊዜ ብዙ ነው፡፡ ምሳሌ እናንሳ ብንል ለትልቁ ዓላማ ሲባል የማይተች ጋዜጠኛ አለን፣ ለትልቁ ዓላማ ሲባል የተቃዋሚ ፓርቲ አይነካም፣ ለትልቁ ዓላማ ሲባል ውስጠ ፓርቲ ልዩነቶች ይታፈናሉ (ሲፈነዱ የሚያመጡት አደጋ መባሱ ላይቀር)፡፡ ለትልቁ ዓላማ ሲባል ሐሳብን በነጻነት መግለጽ መብትን የሚያፍኑ ሌሎች ትንንሽ ጨቋኞችን ማበረታታት የተለመደ ሆኗል፡፡ ለትልቁ ዓላማ ሰበብ ሲባል ጋዜጠኞች ላይ የጥላቻ ፓሮፖጋንዳ ይነዛል፡፡ ትልቁ ዓላማ ሁላችንም ስህተቶቻችንን የምንሸፍንበት አገራዊ የተቃውሞ ሰበብ ሆኖልናል፡፡

“ትልቁ ዓላማ”ና ትርጉሙ

አብዛኛው ተቃዋሚ ፓርቲዎች/ግለሰቦች ዓላማቸው ቢጠየቁ ሃገሪትዋ አሁን ካለችበት ሁኔታ በሁሉም መልኩ ተሻሽላ እንድትገኝ ማድረግ እንደሆነ ቢያንስ በግርድፉ ይናገራሉ ብዬ እገምታለሁ፡፡ አሁን ላለን የፖለቲካዊ ሁኔታ ትኩረት እንሰጣለን የምንል ቡድኖችም ሆነ ግለሰቦች በቋንቋ ብንለያይም፣ ብንጠየቅ የምንናገረው ሐሳብም ከዚህ የተለየ አይሆንም የሚል ግምት አለኝ፡፡ (የገዥው ፓርቲ ደጋፊዎች አሁን ባለችው ኢትዮጵያ እንደሚስማሙና እንደማይመለከታቸው ባስብም ኢሕአዴግም ራሱ በተቃዋሚዎች ቦታ ቢሆን የተሻለ አቅም እንደማይኖረው በመገመት ይህንን ውይይት ወደራሳቸው ቢተረጉሙት አልጠላም፡፡) ነገርግን አሁን ያለውን ነባራዊ የፓለቲካ ሁኔታ ከመቀየር ረገድ እየሠራን ነው የሚሉት አካላት ሁሉ የሚስማሙበት የሚመስለው ሌላው ነገር ሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት መቀየር የሚለውን አካሄድ ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ሠላማዊዎቹንም ነፍጥ ያነሱ ቡድኖችንም የሚያስማማ ሁለተኛው የጋራ ሐሳብ መሆኑ ነው፡፡ እንግዲህ ከላይ በተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ የሚስማሙት ተቃዋሚዎች በተመሳሳይ ሁኔታ መንግሥት ለመቀየር የሚያደርጉትን ጥረት ባለማስተባበር ሲታሙ ኖረዋል፡፡ “ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ” ተብለው ሲተቹ ከርመው ቢተባበሩም ደግሞው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከመሰባበር አላመለጡም፡፡

እኔ እንዳስተዋልኩት ተቃውሞው ጎራ ያሉ አብዛኛው ቡድኖች ከሚስማሙባቸው ጉዳዮች አንዱ መንግሥት ማንኛውንም ተቃራኒ ድምፅ ለማፈን ጥረት ማድረጉን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ይህንን ስርዓት ለመቀየር (ትልቁ ዓላማ) ሲባል እርስበርስ የሚፈጠሩ ክፍተቶችን መተው/ማለፍ እንደሚገባ ነው፡፡ ይህ ያልተጻፈ የመግባቢያ ሐሳብ በሕዝቡም በፓርቲዎችም በግለሰቦችም ውስጥ ሰርፆ በተቃውሞ ቡድኖች መካከል ልዩነቶች በተፈጠሩ ቁጥር ሕዝቡንም የሚያስከፋው “እነዚህ እርስበርስ መስማማት ያልቻሉ እንዴት ነገ መንግሥት ይሆናሉ?” “ እንዴት በዚህ ጊዜ እንኳን ለትልቁ ዓላማቸው ሲሉ ችግሮቻቸውን አያመቻምቹም? ”የሚሉት ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ጉዳዩን ከላይ ከላይ ያየነው እንደሆነ የሚረባ ጠንካራ ፓርቲ አለማግኘት የማንኛውም ሕዝብ የተስፋ መቁረጥ ምንጭ ሊሆንበት ይችላል፡፡ ስለዚህ ጠንካራ ፓርቲዎችን ለማየት መመኘትና ደካማ የሚያስመስሉ ችግሮችን መሸሽም ተገቢ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን መጀመሪያ ትልቁ ዓላማችን አገራችንን ዴሞክራያዊ የተሻለች አገር ማድረግ ነው ወይስ መንግሥትን መቀየር ብቻ? መንግሥትን መቀየር የተሻለ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማምጣት አስፈላጊ ነው ብዬ ባምንም ይህንን የምናደርገው ለወደፊትዋ ዴምክራሲያዊት ኢትዮጵያ የሚስፈልጉ እሴቶችን በመሸርሸር መሆኑ ግን ያሳስበኛል፡፡ ከነዚህ መሸርሸሮች አንዱ ደግሞ ልዩነትን እንደአማራጭ ያለመቀበል አዝማሚያ ነው፡፡ በመሆኑም አሁን ባለን የተዛባ የመቻቻልና ተስፋ ያለማስቆረጥ ጽንሰ ሐሳብ ከቀጠልን እንደአገር በዴሞክራሲያዊ ስርዓቱ ውስጥ የምናጣው ነገር ከመብዛቱም በተጨማሪ የሚመጣው ስርዓት የተሻለ ለመሆኑ ማረጋገጫ አይኖረንም ብዬ እከራከራለሁ፡፡

መተባበሮች ለምን ይፈርሳሉ?ለ”ትልቁ ዓላማ” ሲባል ቅድሚያ የሚሰጣቸው የማይመስሉ ነገሮችን መሸፋፈን ባሕላችን እስከዛሬ ውጤታማ ሆኖ አላገኘነውም፡፡ ይህ የአለባብሶ የማረስ ትብብር በአረም ሲያስመልሰን ብዙ ጊዜ አስተውለናል፡፡ እየተሸፋፈኑ የማለፍ ፖለቲካ ከውስጥ ፓርቲ ጀምሮ እስከ አገሪትዋ ወሳኝ የፖለቲካ ጊዜያት ድረስ ብዙ ጊዜ ዋጋ ሲያስከፍለን ቆይቷል፡፡ እነዚህ ያልተተቹ ያልተፈተሹ እርስ በርስ መተባበሮች መካከል በተወሰነ መልኩም ቢሆን ለምርጫ 97 ውድቀት አስተዋእፆ ማድረጉ የሚታወስ ነው:: ለ”ትልቁ ዓላማ” ሲባል የሚደረጉ ያልተጠኑ መስማማቶች “ለትልቁ ዓላማ” ሲባል የታለፉ ልዩነቶች ምርጫ 97ትን የሚያህል ስኬት ለማጣት አስተዋፅዖ አድርገዋል፡፡ስለዚህ ለ”ትልቁ ዓላማ” ሲባል የሚታለፉ ልዩነቶቸ መጨረሻውን ውጤት ስኬታማነት ስለሚቀንሱት ለምንድነው የምንተባበረው? ከነማን ጋር ነው አብረን መሥራት የምንችለው? የሚለውን ነገር ማጣራትና ልዩነትን በግልጽ ማስቀመጥ ከማይዘልቅ መተባር የተሻለ ለወደፊቱ ለፓለቲካ ባሕል ጥቅም ይኖረዋል፡፡ አሁን ባለን አካሄድ የመተባበር ሙከራዎቹ ችግሩንም ጭንቀቱንም ከመቀነስ አንጻር የሰጡት ጥቅም አይታየኝም፡፡ እንደውም ደካማ ተስፋ እየሰጡ እርሱንም በአጭሩ እያከሰሙት ብልጭ ድርግም የምትለው የተቃውሞ ፓለቲካ ላይ ተስፋ ለማሳጣት ዋነኞቹ ምክንያቶች ናቸው፡፡

የምናወርሰው የፖለቲካ ባሕል ምንድነው?

በባሕል ደረጃ ሊገለጽ የሚችል የፖለቲካ ልምድ ባይኖረንም እነደአገር ለምናደርገው የመማር ሒደት መታሰብ ያለበት የምናሳድገውና የምናወርሰው የፖለቲካ ባሕል ምን ይሆናል የሚለውንም ጭምር ነው፡፡ አሁን ባለን ሁኔታ የፖለቲካ ባሕላችን በጠላትና በወዳጅ ልዩነት ብቻ የተወሰነ ሲሆን መሐል ላይ የሚቀመጥ ግራጫ ባሕሪይ የለውም፡፡ ይህ መሐል ያለመቀመጥ ችግር ፖለቲካ ፓርቲዋችን በግድም ቢሆን ወደተለባበሰ መተባበር ሲገፋቸው ይታያል፡፡ ልዮነቶችን የምናተናግድበት መንገድ የንግግር ባሕልን፣ ልዩነትን የማክበርን ሳይሆን ጎራ የመለየትን ከሆነ ለመጪው ትውልድም ቢሆን የምናወርሰው የፖለቲካ ባሕል ደካማ ይሆናል፡፡

እንደአገር ከ50 ዓመት በፊት የነበሩ ጥያቄዎችን መመለስ ያልቻልን ሕዝቦች ጥያቄዎቹን ለለመለስ የምንጠቀማቸው መንገዶች እንዲህ ደካማ መተባበሮች ላይ የተመሠረቱ ሆነው ከቀጠሉ ችግሮቹን ብቻ ሳይሆን ለመተባበር ሲባል ብቻ የሚነሱ ደካማ ውሕደቶችንም እንደ ባሕል አስተላልፈን ልናልፍ እንቸላለን የሚል ስጋት አለኝ፡፡ እነዚህን ኃላፊነቶች ከግምት ውስጥ ያላስገባ የፓለቲካ ተቃውሞም እስካሁን ውሕደት/አብሮ የመሥራት ችግሮች ምክያትን ሲያጠናም ሆነ ለመፍታት ሲሞክር አይታይም፡፡ የኅብረቶችን መፍረስ በሌላ ኅብረት በመተካት መፍታት የፓለቲካ ባሕሉ ሳይሻሻል እንዲቀጥል ከሚያደርጉት ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡ ጥቃቅን ልምዶችን (መፍረስ መደራጀት) ችላ ማለት የተበላሸና ለማስተካከል ጊዜ የሚፈጅ የፖለቲካ ባሕል ይዘን እንድንቀር እንደማያደርገን እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡

ለ”ትልቁ ዓላማ “ ሲባል መሰረታዎ እሴቶችን መጨፍለቅ

ልናመጣቸው የምንከራከርላቸው ሰው ልጆች መብት፣ ፍትሕ፣ እኩልነት እሴቶችን ራሳችን ለትልቁ ዓላማ በመቆርቆር ስያሜ እንደረምሳቸዋለን፡፡ ይህንን ለመረዳት ከፖለቲካ ፓርቲ እስከ ሚዲያ ከግለሰብ እስከ ብሎግና ማኅበረሰብ ሚዲያ አይቶ መመስከር ይቻላል፡፡ በዚህ ባህሪያች የተነሳ በየቀኑ የምንጥሳቸው እሴቶች ብዙ ሰዎችን ገፍተው ዓላማ ሲያስቱም አስተውለናል፡፡ (መቼም ትችቴን ተቹብኝ እንደሰበብ ተቀባይነት ባይኖረውም ተፅዕኖውን ዕውቅና መስጠቱ አስፈላጊ ነው) “ትልቁ ዓላማ” የሚባለው ሰበብም የእሴቶች እሴት ሆኖ ሁሉም ንግግር የመብት ጥያቄና ትችት ከሱበታች ካልሆነ በስተቀር የማናተናግድበት ባሕል ፈጥረንና ብዛኛዎቻችን ተስማምተን ተቀምጠናል፡፡ ምን ነካት/ው? ለዚህ ሲል ምናለ ቢያልፈው? ይሄንን መናገሪያ ጊዜ አሁን ነው? የሚሉ ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ይነሳሉ፡፡የአብዛኛዎቹ የዚህ ክርክር ደጋፊዎች የምናስቀድመው “ትልቁን ዓላማ” መሆን አለበት ከማለት በተጨማሪ ጊዜንና ቅድሚያ አሰጣጥን እንደተያያዥ ምክንያች ያነሳሉ፡፡ እነዚህ ምክንያቶች በቂ ሆነው ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት፣ የግለሰቦች መብት በቀላሉ ይጣሳል፡፡ ይህ ባሕል ደግሞ በየቦታው የምናነሳቸውን እሴቶች ተቃራኒ የመሆንን እና ተደራራቢ መመዘኛዎችን የመጠቀም ያጋልጠናል፡፡ የምንቆምላቸው እሴቶች ለእኛ ዓላማ ሲሆን የሚሸረፉ፣ ሌሎች ሲያደርጉት የሚያስወቅሱ ከሆነ ምኑን ቆምንላቸው?

ትንንሽ አምባገነኖች ማሳደግ

ዛሬ ለትልቁ ዓላማ ሲባል ዝምታን የምንመርጥባቸው ጥቃቅን መሳይ ጉዳዮች የምናፈራቸው መሪዎች ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖም መገመት ቀላል ሥራ አይደለም፡፡ ዛሬ እሴቶች እና መርሕዎቸ ሲሸራረፉ ዝም ማለታችን በትንሽ ሥልጣን ትንሽ አምባገነንነትን ሊያበረታታ ይችላል የሚል ስጋት አለኝ፡፡ ይህ ትንንሽ አምባገነኖችን የማበረታታት አዝማሚያ ነገ ትልቅ ሥልጣን ላይ ትልቅ አማባገነንነት ላለመፍጠሩ ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡ የአመራር ብቃትና ባሕርይ ማጣት ችግር በሰፊው የሚታይበት የተቃውሞ ፓለቲካ ከገዥው ፓርቲ ከሚደርስበት ጫና በተጨማሪ የሚጋፉት ችግሮች አንዱ አመራሩ አለመገራቱ እና በገዥው ፓርቲ ስም ለስህተቶችቹ በቀላሉ የማርያም መንገድ ማግኘቱ ነው፡፡ ለ”ትልቁ ዓላማ” ሲባል የምናልፋቸው ስህተቶች ሌላ አምባገነን መሪዎችን መፍጠር አደጋ ውስጥ ገብተን እንዳይሆን አሁንም ቢሆን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

የዚህ ጽሑፍ ዓላማ የመንግሥት ተቃውሞውን የማዳከም ተፅዕኖ አሳንሶ ማየት አይደለም፡፡ እንደኽዝብ የምንፈልገውን በግልጽ ማወቅና ለዚያ መሽራትና መኖርንና መለማመድ እንደአንድ የክርክር ሐሳብ ለማቅረብ ብቻ ነው፡፡ ለ”ትልቁ ዓላማ” የሚደረጉ ማመቻመቾችም የት ድረስ መሄድ አለባቸው? የምናጥፋቸውና የማናጥፋቸው መርሕዎች የትኞቹ ናቸው? የትኛው ላይስ ማስተካከያ መውሰድ ይገባናል? የሚለውን ለመለየትና ከአሁኑ እርምጃመውሰድ ካልቻልን “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ” የሚለው የአበው ምሳሌ እንዳይደርስብን ከመጨነቅ የመነጨ ነው፡፡ የሐሳብ ልዩነታቸውን ተከትሎ ብቻ “ትልቁ ዓላማ” አልተከተላችሁም በሚል ሰበብ ያጣናቸውና የምናጣቸውን ሰዎችም እያሰብኩ እንደጻፍኩት ይታሰብልኝ፡፡ማስታወሻ፡- “ትልቁ ዓላማ”- The bigger picture የሚለውን የእንግዘኛ ቃል ተክቶ የገባ ነው፡፡

—–

የዚህ ጽሑፍ ዋና ቅጂ በኢትዮጵያእንዳይነበብ በታገደው በዞን ዘጠኝ ጦማር ላይ ይገኛል፡፡

በዳያስፖራ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

ሐምሌ  13 ቀን 2005 ዓ.ም

MillionsVoice1«ነጻነትን ማንም አይሰጥህም። እኩልነትና ፍትህንም ማንም አይሰጥምህ። ሰው ከሆንክ፣ አንተዉ እራስህ  ተቀበለው» ነበር ያሉት፣  የሰብአዊ መብት ተሟጋች ማልኮም ኤክስ። ነጻነትና ሰላም፣  ዴሞክራሲና ፍትህ፣ እኩልነትና መልካም አስተዳደር፣ ሌሎች የሚሰጡን ሳይሆን፣  ፈጣሪ በቸርነቱ የለገሰን፣ ደፍረንና ፈቅደን የምንቀበላቸው፣  የኛዉ የሆኑ በረከቶች ናቸው።

ነገር ግን ለአመታት መብታችንና ነጻነታችን፣  በጥቂቶች ተገፎ፣ ሁላችንም በየጓዳችን ስንናደድ፣ ስናማርር፣ ስናዝን፣ ስንራገም፣ ልባችን ሲደማ፣ «እንደዉ ምን ይሻላል? » እየተባባልን ስናወራ ቆይተናል። ለዜጎቿ ሁሉ እኩል የሆነች፣ ሕግ የበላይ የሆነባት፣ ፍትህ የሰፈነባት፣ ሕዝቡ ለመሪዎች ሳይሆን መሪዎች ለሕዝብ የሚንበረክኩባት፣ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለማየት ትልቅ ጉጉት አለን።

ማልኮም ኤክስ እንዳሉት፣ ፍትህንና እኩልነትን እንዲያመጡልን፣  ሌሎችን መጠበቅ የለብንም። እያንዳንዳችን መንቀሳቀስ ይኖርብናል። በአገር ቤት፣ በጎንደርና በደሴ እንደታየው፣  ከፍተኛ፣ ሰላማዊ፣ የሰለጠነ የፍቅር ፖለቲካ ላይ ያተኮረ፣ እንቅስቅሴ እየተደረገ ነዉ። እንቅስቅሴዎቹ በባህር ዳር፣ በፍቼ፣ በጂንካ፣ በአርባ ምንጭ፣ በአዳማ፣ በመቀሌ፣ በወላይታ ሶዳ፣ በጋምቤላ በአሶሳ .. እያለ ይቀጥላል። በአገሪቷ ክልሎች ሁሉ ያለው ሕዝቡ  መብቱንና ነጻነቱን እንዲያስከብር ቅስቀሳ ይደረጋል። ለምን ? የምንፈልጋት ኢትዮጵያ ልትመጣ የምትችለው እኛን ጨምሮ ሕዝቡ ቀን ሲል ብቻ በመሆኑ።

በዉጭ አገር ያለነዉ ፣ አገር ቤት ያለው ሕዝብ አካል ነን። «ምን ተደረገ?» እያልን የምንከታተል ብቻ ሳይሆን፣ የሚደረጉት እንቅስቃሴዎች አካል መሆን መቻል አለብን። እምነት ያለን በጸሎታችን፣ ገንዘብ ያለን በገንዘባችን፣ ጠቃሚ፣ ትግሉን ወደፊት ሊያስኬዱ የሚችሉ ምክሮችና አስተያየቶች ያሉን፣  ሃሳቦቻችን በማቅረብ፣  ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረግ እንችላለን። ይገባናልም።

የአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ግብረ ኃይል፣  ለሕዝብ ይፋ ያደረገዉን የሶስት ወራት እንቅስቃሴ ለመደገፍና ለማገዝ፣ በዳያስፖራ የሚሊየኖች ድምጽ ለነጻነት ግብረ ኃይል ተቋቁሟል። ግብረ ኃይሉ የተለያዩ መርሃ ግብሮችን  አውጥቶ፣ ዳያስፖራዉ እንዴት ሊረዳ፣ ሊደግፍና የሚሊዮኖች አንዱ ሊሆን እንደሚችል መረጃዎች የሚያቀርብና አቅጣቻዎችን የሚያሳይ ይሆናል። በዉጭ አገር የሚገኙ ሬዲዮች፣ ቴሌቭዥኖች ፣ ድህረ ገጾች፣  የሲቪክ ማህብራትና በዉጭ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ ድጋፋቸዉን እንዲሰጡንም በአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን።

በኢትዮጵያ ወገኖቻችን ትልቅ ዋጋ እየከፈሉ ነዉ። በዉጭ አገር ያለን ኢትዮጵያውያን፣  ከዚህ በፊት ብዙ ለአገራችን ደክመናል። አሁን ወሳኝ ወቅት ላይ እንዳለን ተረድተን፣ ከዚህ በፊት ካደረግነዉ በላይ ለማድረግ እንነሳ። ትላንት ወድቀን ቆስለን ሊሆን ይችላል። የትላንቱ ጠበሳ ወደፊት እንዳንሄድ ሊያግደን ግን አይገባም። ከወደቅንበትና ከተኛንበት ተነስተን፣ ከቆምንበት ተንቀሳቅሰን፣ ወደፊት በመሄድ መቻል አለብን።

ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን ! በዚህ ወቅት እኛ ካልተባበረን ማን ? ?  ዛሬ ካልሆነ መቼ ?

 

 

ሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያ የቤት ሰራተኞች ላይ የጣለችው እገዳ እና አንድምታው . . .

$
0
0

በነቢዩ ሲራክ

YeMaleda Weg

በማለዳው ከእንቅልፍ ስነቃ ለዛሬው ለማለዳ ወግ ቅኝቴን ሁለት ሰሞነኛ ትኩስ ወጎች ከፊ ለፊቴ ገጭ ብለው ጠበቁኝ ! . .  አንዱ ሰሞነኛ ወግ ስልጣኔ ዘመነኛ የመገናኛ ዘዴዎችን ማግኘት የታደለው የሃገሬ ሰው አይኑን አፍጦ በማህበራዊ ገጾች እና በተለያዩ     የኢንተር ኔት ድህረ ገጽ ስር ባሉ የመረጃ መረቦች ሲከታትለው የሰነበተው የጁሃር መሃመድ ሃይማኖትና ዘርን ቀላቅሎ የተናገረበት     አሳፋሪ፣ አሳዛኝ እና አነታራኪ ንግግር ነው። ሁለተኛው ሳውዲ ነዋሪውን የሃገሬ ሰው ግራ ያስደነገጠ ያስደሰተው ሲሆን ጉዳዩም  የሳውዲ መንግስት የቤት ሰራተኞች ከኢትዮጵያ እንዳይመጡ ጊዜያዊ እገዳ የጣለበት ጉዳይ ነው ! ሁለቱንም ሰሞነኛ ጉዳዮች መነጋገሪያ ሆነው ሰንበተዋልና መረጥኳቸው ! ያም ቢሆንም የማተኩረው ባንዱ ርዕስ ላይ ብቻ ይሆናል ! እናም የዛሬ ወግ ትኩረቴን በአያሌው   ስለሳበውና ሚዛንም ወደደፋብኝ የሳውዲ እገዳ ጉዳይ ላቅና.  . .

የእገዳው ሰበብ …
በያዝነው ወር ብቻ ሁለት ህጻናት በሳውዲ ዋና ከተማ ውስጥ በኢትዮጵያውያን  የቤት ሰራተኞች የመገደላቸውን ዜና ተከትሎ የሳውዲ መንግስት ከኢትዮጵያ የቤት ሰራተኛ ማስመጣቱን የማስቆም ፍላጎት እንደለ ጭምጭምታ የሰማሁን ከሁለት ቀናት በፊት ቢሆንም የመታገዱን እርግጠኛነት የሰማሁት ግን ባሳለፍነው ሮበ አመሻሹ ላይ ነበር ።  ይህንን ለማረጋገጥ  ወደ ጅዳ ቆንስል ሃላፊ ደጋግሜ ብደውልም ሃላፊው ስልካቸውን አያነሰሱም ። ውሎ አደረና   የደረሰኝ የጓሮው ሁነኛ ምንጭ እውነት ሆኖ ትናንት ሃሙስ ማለዳ  እገዳው በይፋ ታወቀ !      በተደበላለቀ ስሜት ተናጥኩ ፣ ሌላው ሁሉ ቢቀር የብዙውን ድሃ ወገን በልቶ የማደር ህልም   እውን ማድግ የሚቻለበት መልካሙን እድል መጠቀም አለመቻላችን በቁጭት አደበነኝ።      በሌላ ጎኑ በቤት ሰራተኞች ዙሪያ መንግስት ትኩረት ባለመስጠቱ በኮንተራት ሰራተኛ ስምህጋዊ  የሳውዲ እና የኢትዮጵያ መንግስት ስምምነት አለመኖርን፣በዜጎች መብት ጥበቃ የተሟላ ስራ   በመንግስታችን በኩል ያለመፈጸሙ ህጸጽ እና የምሰማው፣የማየው የወገን ስቃይና በደል       አውጥቸ አውርጀ “በእገዳውን ቢያንስ እረፍት ይገኛል!” ስል የእፎይታ ደስታ ተሰማኝ !         መረጃ ለማቀበል ካለኝ ፍላጎት አንጻር በእገዳው አንድምታ ዙሪያ ገብ መረጃዎችን ለመሰባሰብ በጾምና በጸሎት ለፈጣሪው በሚገዛው ነዋሪ መካከል በተረጋጋግቸ መረጃ ስብሰባየን   ገፋሁበት! ራስ ሰንጠቆ ከሚገባው ከጅዳ የበጋ ሙቀት ጋር የቀይ ባህር ወበቅ ከጭንቀትን የማይሸሸውን የስደተኛ ነፍስ ይፈትናል ።

ስለ ሳውዲ መንግስት እገዳ መረጃ መሰብሰቡ ባያደክመኝም አንዱን አንዱን ስል የተኛሁት ሊነጋጋ ቢሆንም በማለዳው ከአልጋየ ሳልወርድ በማቀርበው ወግ ዙሪያ ማብሰልሰል ይዣለሁ.  . . ሁሌም እንደማደርገው የማለዳ ወጌን ከመጀመሬ እና የወጌን ሁነኛ     ርዕስ ከመምረጤ አስቀድሞ የመረጃ ግብአት ይሆኑኝ ዘንድ ቅኝቴን የጀመርኩት እለታዊ ጋዜጦችን በመዳሰስ ነበር። የአረቡ አለም ዋና ዋና የሚባሉትን መገናኛ ብዙሃን ድህረ ገጾ እጎበኛቸዋለሁ። የመካከለኛ ምስራቅን ፖለቲካው አድፍጣ የምትዘውረው ሃገር የሳውዲ አረቢያ ጋዜጦች ከቅርብ አመታት ወዲህ ማናቸውንም አይንት ጽንፈኝነት ከመቃዎም ጀመሮ ድሮ ድሮ ሊነኩ ቀርቶ ሊወሱ አዳጋ ያስከትላሉ በሚባሉ የመንግስት ተቋማት ይተቻሉ፣ መገናኛ ብዙሃኑ ከዚህ አልፈው ሄደው ከመንግስት እኩል ባይባልም ከፍ ያለ ቦታ ያላቸው የሃይማኖቱ ተቋማት አሰራርና በአካሔዱ ላይ ነጻ አስተያየት ጥቆማዎችን ያቀርባሉ። ከመንግስት ተቋማትን ዝርክርክነት እስከ አካባቢ አረብ ሃገራትን የፖለቲካ አሰላለፍ ዘልቀው የሚተቹ የፖለቲከኞች ትንታኔ ጽሁፎችን በግልጽ ያወጣሉ። በዚህ ረገድ የሚቀርቡ   መረጃዎችን በቅርብ ለተመለከተ መረጃዎቹ በሳውዲ ንጉሳውያን ቤተሰብ አመራር ስር በሚተዳደር ሃገር ስር የወጡ ናቸው ብሎ  እስከመጠራጠር ሊያደርስዎ ይችል ይሆናል። ይህም አካሔድም የሳውዲ መንግስት የተለያዩ ምክንያቶች ደርድሮ ነጻ መገናኛ ብዙሃንን  አስሮም ቢሆን እንደመልቀቅ የሚያደርግበትን አካሄድ መኖሩን ማስተዋል ይቻላል ! እናም ይብዛም ይነስ መረጃዎችን ትንፋሸን ዋጥ አድርጌም ቢሆን ማንበቡን ለምጀዋለሁ ! እናም በጀመርኩት ርዕስ ዙሪያ የምፈልጋቸውን መረጃዎች ስብሰባ ቅኝቴን አገባድጀ ወደ   እኔው የማለዳ ወግ ሙንጨራ ገባሁ !      እርግጥ ነው በሳውዲዋና ከተማ ሪያድ ካሳለፍነው ወር ወዲህ ለሚስ የተባለች የ6 አመት ሳውዲ ህጻንንና ሌላ ኢስራ የተባለች       የ 11 አመት ሶርያዊት ታዳጊ ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ወንጀል በየትኛውም ሚዛን መወገዝ ያለበት ድርጊት ነው።  በኢትዮጵያውያን ተገደሉ መባሉ ድግሞ ያሳዝናል ፣ ያሳፍራል! ይህንንም ተከትሎ ሳዊዲ ጊዜያዊ እገዳ አድርጋለች ።  የሳውዲ መንግስት ኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኛ ቅጥር በጊዜያዊነት ማስቆሙን በሚመለከት በሃሙስ ምሽቱ የጀርመን ራዲዮ ዜና መጽሄት ላይ ከጋዜጠኛ ተክሌ የኋላ ጋር ያደረግኩትን ቃለ ምልልስ ሰምቸ ጨረስኩ። ወዲያውኑ በራዲዮ መረጃው የደረሳቸው በርካታ ወዳጆቸ በስልክ ፣በፊስ ቡክ ገጼና በጓሮ መልዕክት መላኪያ ሳጥን በርካታ አስተያየቶችን ልከውልኛል።

የእገዳው ድጋፍ ፣ ተቃውሞ እና ሰሚ ያጣው ጩኸት ኑሮ. . . .

             ከደረሱኝ አስተያየቶች መካከል “እገዳውን እንደግፋለን! ” ያሉኝ አብዛኛው ኢትዮጵያውያን “ያለ ህጋዊ የስራ ኮንትራት መጥተው ግፍና በደል ሲፈጸምባቸው የሚደርስላቸው የመንግስታቸው አካል አለ ማለት አይቻለም።  ”ያሉኝ አስተያየት ሰጭዎች ስለደገፉበት ምክንያት ባስረዳት ሲቀጥሉ ” አቅም አዳም ያልደረሱ ታዳጊ እህቶቻችን ሳይቀሩ በደላላ ተግዘው እየመጡ ከሚደርስባቸው ግፍ አንጻር ባይመጡ ይሻላል !” በሚልየሳውዲ መንግስተ  የጣለውን  እገዳ እንደሚደግፉ ገልጸውልኛል።  በኮንትራት ሰራተኞች ቅጥርና ዝውውር ዙሪያ ያለውን መጠነ ሰፊ ችግር የሚገልጹ  አስተያየት  የሰጡኝ ወገኖች መንግስት ሌላው ቢቀር  ዜጎቹን ከድህነት ማላቀቅ ባይችል በአረብ ሃገራት የተገኘውን የስራ እድል ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ አልቻለም ሲሉ ቅሬታቸውን በመግልጽ “በመታገዱ የምንሰማው የመከራ ጩኸት እስኪ ይብረድልን! “በማለት ወቀሳቸውን በመብት ማሰከበሩ “አልሰራም! !” ባሉት መንግስት ላይ አነጣጥረው መታገዱ ጥሩ ሆኗል የሚል አስተያየት የሰጡኝ በርካታ ናቸው ።

      በመታገዱ የተከፉትም ሃሳባቸውን ገልጸውልኛል ።  መንግስት ስራውን ባለመስራቱ ለችግሩ ሁሉ ምክንያት ነው በማለት መንግስትን የሚወቅሱት አስተያየት አቅራቢዎች  ኮንተራት ስራ ብሎ እንቅስቃሴ ሲጀመር በሃገራት መካከል ሁለትዮሽ ስምምነት አለመደረጉ ትልቁ ስህተት መሆኑን ያስረዳሉ።  ከዚያም ቀጥሎ ስራው ሲጀመር ባልተቀናጀ በቂ ጥናት ፣ ያለ በቂ ቅድሚያ ዝግጅት ፣ ያለ በቂ     ስልጠናና የመሳሰሉትን ዝግጅቶች አለማድረጉ በማመላከት ስህተቶቹ ለእገዳ ምክንያት መሆናቸውን በአጽንኦት ያስረዳሉ።  ” የሳውዲ ሰራተኛ ቅጥሩ እገዳ ይጎዳናል! ” የሚለውን ሃሳብ የሚደግፉት እኒሁ ነዋሪዎች አጥፊው መንግስታችን ነው ሲሉ ደጋግመው ይወቅሳሉ። ተጠያቂዎቹ ከማዕከላዊ መንግስት ቸልተኝነት እስከ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢንባሲና ቆንስል ሹሞች ይወርዳል በማለት ሲያስረግጡ ” መንግስት ለዜጎች የመጣውን እድል እንዲጠቀሙ ማድረግ አልቻለም !” ብለውኛል።  ወደዚህ መሰል መደምደሚያ ምን እንዳደረሳቸው ጠይቄያቸው ሲመልሱ  ”መንግስት ዜጎችን የመደገፉ ሃላፊነት ተዘንግቶታል እንኳ ቢባል ከገቢ አንጻር ያልተመለከተበት አካሄድ አውጥቶ ላወረደው ግራ ያጋባል!” በመለት የመጣውን ወርቃማ እድል መንግስት እንዳልተጠቀመበት እና ይህም እንዳሳዘናቸው         ገልጸውልኛል ።

       እርግጥ ነው የሰራተኞች አቅርቦት ኮንትራት ሰም መንግስት     የማመልከቻ ደብዳቤ ለማጻፍ   ከሚያስከፍለው ጀምሮ ፖስፖርት በማደስ ፣ ቪዛ በማጽደቅ ፣ በውክልና ፣ በምስክርነትና በመሳሰሉት ከፍተኛ የሆነ በአመታዊ ሪፖርት ተለይቶ ባይነገረንም ከቆዳና ሌጦ     ያላነሰ ገቢ አስገብቷል ። ጥቅሙ ከመንግስትም ወርዶ  ከህጋዊ እስከ ህገ ወጥ ደላላ ከግለሰብ የሁሉንም ካዝናዎች ማጣበቡ እውንት   ነው!  ዜጎችም ቢሆን ብዙ መከራ እና ስቃይ እያዩም ቢሆን የተወሰነ በሚያገኙት ገቡ የደፈኑት የወላጅ ዘመድ አዝማድ የችግር ቀዳዳ መጠነ ሰፊ መሆኑን መካድ አይቻለም። በድህነት እየተጠበሰ ያለ ወላጅ በኑሮ ውድነት ኑሮው ይባስ ሲከፋበት ከፋ ህይወቱን በልጆቹ መስዋዕትነት ሊያልሳልፍ በእድሜ ያልበሰሉ ገና ያልጠነከሩ  ታዳጊ ልጆችን ከህገ ወጥ ደላሎች ቀቢጸ ተስፋ ተደልሎ ወደ አረብ ሃገር እየላከ ነው ። ከሁሉም የሚሳዝነው  ወላጅም ሆነ መንግስት ታዳጊዎች የሚላኩባቸው ሃገራት በሰራተኛ ሰብአዊ መብት ይዞታ በማይመሰገኑ ፣ ቤት ሰራተኛ አያያዝ የሚወገዙ የአረብ ሃገራት ያለ ህግና ስርአት መላካቸው ስለመሆኑ ብዙ ማለት ይቻላል።  በአደጋ በተከበበት መንገድ የሚገፋው በአረቡ አለም የቤት ሰራተኝነተ  ህይዎት በተለያዩ ምክንያቶች ግፍ ተፈጽሞባቸው ስንኩል ሆነውና ሞተው በድናቸው ሃገር ሲገቡ ማየት ተለምዷል።  የታደሉት ሬሳቸው የሚታወቅበት፣ ያልታደሉት  ሬሳቸው ሳይቀር የማይታወቅበት  አስከፊ  የአረብ ሃገሩ ስደት ለመሆኑ ወላጅና መንግስት ከበቂ በላይ መረጃ አላቸው።  ወላጅ ድህነት ችግሩ ብሶበትና በደላሎች ቀቢጸ ተስፋ ተታሎ በአብራኩ ክፋዮች ላይ ጨክኗል!  መንግስት ችግሩ ትውልድን እያጠፋ ለመሆኑ በእማኝ እያየና እየሰማ ችግሩን ለመከታተልና ለማስቆም ብጣሽ ህግ ማውጣት ተስኖታል። ለተበዳዮች መብት ማስከበርም ሆነ ሲበደሉ ፍትህ መጠየቁን ትቶታል። የሁሉም ስደተኛ ሰራተኛ ህይወት ይህን ሁሉም ይህን ይመስላል አይባልም። ያም ሆኖ ቁጥራቸው ይህ ነው የማይባል የአረቡ ስደት ተጠቂዎች መሆናቸው የሚታበል ሃቅ አይደለም። እስካሁን በዜጎች ላይ እየደረስ ያለው ግፍና መከራ ግን ለቀሪው ትምህር ሆነው ስደቱን ሊገድበው አልቻሉም።

የሳውዲ መንግስትን የሰራተኛ ማስገባት ጊዜያዊ እገዳ ጠልቀን ማየት ከሞከርን እርምጃውን ደገፍነም ተቃወምን ፣ አስደሰተንም   አስከፋን አንድ እውንታ ድጋፍ ፣ ደስታ፣  ተቃውሞ ፣ መከፋቱን አንድ ያደርጋቸዋል !  በእገዳውን የመደሰትና የመደገፋችን ስሜት ምንጩ መንግስት ለዜጎች ተቆርቁሮ የመብት ጥበቃ አለማድረጉ ሲሆን  በአንጻሩ እገዳውን ያስከፋን መንግስት በድህነት አረንቋ ውስጥ ያሉ   ዜጎች በመጣውን እድል መታደግ ባለመቻሉ ነው ብሎ መደምደም ይቻላል ባይ ነኝ  ! በዚህም ጎን ለጎን በያዝነው ሳምንት አጋማሽ የወጣው የሳውዲ መንግስት ጊዜያዊ እገዳ መንግስታችን እያፈሰው ያለው ገቢ  ጋብ ብሎ ኢኮኖሚውን ከማሽምድመድ ባይደርስም በዙሪያው ተጠቃሚ ለሆኑት ደላሎች ታላቅ መርዶ ነው!  በባለጊዜዎች ከለላ ሲንቀሳቀሱ ለከበሩት የምስለኔዎቻችን ወዳጆችም እገዳው   ዱብ እዳ ነው  !   በአንጻሩ የ ፈልግው ይምጣ ብለው ሰርተው ለመለወጥ ቋምጠው ለመሰደድ በቋፍ ላይ ላሉት ዜጎች መልካም የምስራች አይደለም ! መርዶ እንጅ ! የሳውዲ በቅርቡ የሳተውን የምህረት አዋጅ ተከትሎ መኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት በወረፋ ላይ ላሉትም ቢሆን ዜናው መልካም አይደለም !  ገጽታችን እንገንባ እያሉ ገጻችን እያበላሹ ለዚህ ላበቁን ይብላኝላቸው እንጅ በሳውዲ ለከተምን እየተሰራ ያለው አንገታችን አስደፍቶናል ! በአረብ ባገሩ ስደት ህይወት የዜጎችን በደል ፣መከራና ሰቆቃ ከባለቤቶቹ ስቀበል ለባጀሁት ጎልማሳም ስሜቱ ከላይ የገለጽኩት አይነት የተቀላቀለ ነው ! አገዳው ያስደስታልም! ያሳዝናል ፣ ያስቆጫልም ! እየሆነ ያለው ደፍሞ ያሳፍራል ! መንግስት ሆይ ! በደል ፣ ጭንቀት  ሃዘናችን ስማ  !

በጎ በጎውንም አስብልን!

ነቢዩ ሲራክ

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live