Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

Health: ኮሌስትሮልዎ ከፍ ያለ ከሆነ ዓመት በዓሉን የግድ በሥጋ ብቻ ማክበር የለብዎትም

$
0
0

ከዶ/ር ዓብይ ዓይናለም
ኮሌስትሮል ከተለያዩ ምግቦች ወደ ሰውነት ዘልቆ እና ከመጠን አልፎ ሲጠራቀም የደም ባንቧዎች ግድግዳና መንገዳቸው ላይ በመለጠፍና መንገዱን በማጥበብ ደም እንደልቡ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች እንዳይደርስ ያግዳል፡፡ ይህም ለህዋሳቶች በህይወት መቆየት ወሳኝ የሆኑት ንጥረ ነገሮችና ኦክስጅንም አይሄዱም ማለት ነው፡፡ በጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስና ኦክስጅን ማጠርን ተከትሎ የሚመጣው እንደኩላሊት ድክመት አይነት ክፉ ህመሞችም ከሚከሰቱባቸው መንስኤዎች ዋነኛውም ይኸው የኮሌስትሮል ጠንቅ ነው፡፡ ኮሌስትሮል በተፈጥሮው ክፋት ያለው ቅባት አይደለም፡፡ የተለያዩ የፆታ ሆርሞኖችን ጨምሮ የሚዘጋጁበት ንጥረ ነገር በመሆኑ ለሰውነታችን እጅግ በጥቂት መጠኑ ያስፈልገዋል፡፡ ነገር ግን በተለያዩ ምግቦች ስንወስደው ይጠራቀምና መዘዝ ያመጣል፡፡ እሾህን በእሾህ ነውና ባለሞያዎች ዋነኛዎቹ ኮሌስትሮልን ከደም ውስጥ በከፍተኛ ምጣኔ ለማውረድና ከመዘዞቹ ለመጠበቅ ከሚመክሩዋቸው ማርከሻዎች ውስጥ ዋናኛዎቹ ምግቦች ሆነው ተቀምጠዋል፡፡ በተለያዩ በሳይንስ በተረጋገጡ መንገዶች ከመድኃኒት ይልቅ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው የኮሌስትሮል ምጣኔያቸው ከፍተኛ ለሆኑ ሰዎችና ለሌሎች ወደዚያው እየተንደረደሩ ላሉትም እንዲያዘወትሩዋቸው የተመከሩ ምግቦች ላይ በዛሬው ሜዲካል ፊቸራችን ትኩረት አድርገናል፡፡ እነዚህ ከመድኃኒት ይልቅ የተመረጡት የኮሌስትሮል መቀነሻ ምግቦች የትኞቹ ይሆኑ? በምን አይነት አሰራር? -ይህ የኢድ በዓልና መጪው ጊዜ ኮሌስትሮላችንን የምንቀንስበት ይሁን!
aokado
1. አፕል
አፕል በተለይ መጥፎ የሚባለውን አይነት የኮሌስትሮል አይነት ከሚቀንሱ ፍራፍሬዎች ይመደባል፡፡ አፕል ሟሚ የሆነ ፔክቲን የተባለ ቅመም ያለው ሲሆን ኮሌስትሮልን ከደም የመምጠጥ ባህሪ ስላለው ደም ውስጥ ያለውን ኮሌስትሮል ይቀንሳል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም አፕል ውስጥ ያሉት ፍላቪኖይድስ የሚሰኙ ፀረ መርዛማ ኬሚካሎች ኮሌስትሮል ቅባት በደም ውስጥ እንደልቡ እንዳይንቀሳቀስ መንገዱን በመቁረጥም ይሳተፋል፡፡ አንድ አፕል ዶክተርን ያስጥል የሚባለው ብሒል እውነት ከሚሆንባቸው የአፕል የጤና ጥቅሞች አንዱ ይኸው የኮሌስትሮልን መጠን የመቀነስ ተግባሩ እንደሆነ በጥናት መረጋገጡን ሃርቫርድ ኒውስሌተር የሐምሌ ወር እትም በዝርዝር ያትታል፡፡
2. ቡናማ ሩዝ
ቡናማው የሩዝ አይነት በውስጡ ልዩ ዘይት አለው፡፡ ይህ ዘይት ነው ኮሌስትሮልን የመቀነስ ብቃት ያአለው፡፡ በተለይ ቡናማ ሩዝን እንደ አተር እና መሰል ጥራጥሬዎች ጋር ቀላቅሎ መመገብ ምርጥ የፕሮቲን ቅልቅል እንደሆነ እና ኮሌስትሮልንም መዋጊያ መሆኑን ባለሞያዎቹ ይጠቁማሉ፡፡ ቡናማ ሩዝ ማግኒዥየም፣ ቫይታሚን ቢ እና ፋብየርን የያዘ በመሆኑም ከልብ ጋር ተስማምቶ የሚዋሃድ ለልብ ጤና የሚጠቅም እንደሆነ በስፋት ይገለፃል፡፡
3. ቀረፋ
ስለቀረፋ ጠቀሜታ የቀደሙት ሰዎችም በስፋት ሲያወጉ እና ከበረከቱም ሲካፈሉ ቆይተዋል፡፡ የህክምናው ሳይንስ ሰዎችም ያደረጉት ጥናት ይህንን ያረጋግጣል፡፡ ጆርናል ዲያቤትስ ኬር የተሰኘ የምርምር ውጤቶች ማስፈሪያ መጽሔት ላይ የወጣ ጥናት እንደሚለው በቀን ግማሽ ማንኪያ ቀረፋ መጠቀም በስኳር ህሙማን ዘንድ አብዝቶ የሚታየውን የደም ግፊት ህመም በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ይቻላል፡፡ መጥፎ የሚባለውን አይነት ኤልዲኤል ኮሌስትሮልም ከደም ውስጥ ማውረድ መቻሉን ማረጋገጣቸውን አጥኚዎቹ በመጽሔቱ አስፍረዋል፡፡ ስለሆነም በሻይም ይሁን በሌላ የአመጋገብ መልክ ቀረፋን ማዘውተር ኮሌስትሮልን ይዋጋል፣ ከምግብ ዝርዝርዎት ይጨምሩት ይላሉ ባለሞያዎች፡፡
4. ነጭ ሽንኩርት
ስለነጭ ሽንኩረት ጥቅሞች ዘርዝሮ መጨረስ ይከብዳል፡፡ በነጭ ሽንኩርት ውስጥ ታምቀው ከሚገኙ ንጥረ ነገሮች አንዱ የሆነው አሊሲን ባክቴሪያ እና ፈንገሶችን ከመግደሉ በተጨማሪ ለአንዳንድ የጨጓራ ችግሮችም ሁነኛ መፍትሄን ይሰጣል፡፡ የደም መርጋትን ማስቀረቱም ልዩ ጥቅሙ ነው፡፡ ከእነዚህ ቀደም ብለው ከሚታወቁ ጥቅሞች በተጨማሪ በምን አይነት ስርዓት እንደሆነ ባይታወቅም ለጤና ጎጂ የሆነውን ኮሌስትሮልን መጠን የመቀነስ ጥቅም እንዳለው ሳይንቲስቶች በቅርቡ በጥናት ጽሑፎቻቸው አሳይተዋል፡፡ ግምቶች እንደሚያሳዩት ግን ነጭ ሽንኩርት ኮሌስትሮልን የሚቀንሰው የጉበትን ኮሌስትሮል የማምረት አቅም በማዳከም ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ነጭ ሽንኩርትን የማይደፍሩ ከነበረና የውፍረትና የኮሌስትሮል ጉዳይ የሚያሳስበዎት ከሆነ ወደ ነጭ ሽንኩርት ቢያዘነብሉ ከጠቀሜታውን ይቋደሳሉ፡፡
5. አጃ
አጃን በተለያየ መልክ ለሚጠቀሙት ኢትዮጵያውያን ጠቀሜታዎቹ ብዙም እንግዳ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ ከኮሌስትሮል ቅነሳ ጋር ስለመያያዛቸው ግን ብዙም የሚታወቅ አልነበረም፡፡ እንደ ጥናቶች ጥቆማ ግን አጃ ውስጥ ያሉ ፋይበሮች የኮሌስትሮልን ምጣኔ በከፍተኛ መጠን ይቀንሳሉ፡፡ አጃ ውስጥ ያሉት ግሉካጎን የሚሰኙ ንጥረ ነገሮች ይህን ቁልፍ ስራ ይሰራሉ፡፡ ቀን ከ5 እስከ 10 ግራም አጃ መውሰድ የኮሌስትሮልን መጠን በቀን ቢያንስ በ5 በመቶ እንደሚቀንሰው ባለሞያዎቹ ይገልፃሉ፡፡ በየትኛውም መልክ ቢወስዱት በጣም እሳት ሳያጠቃው ሲወሰድ አጃ ውጤቱ ከፍተኛ ነው ይባላል፡፡ አሜሪካን ጆርናል ኦፍ ክሊኒካል ኒውትሪሽን ላይ የሰፈረው ጥናት ይህን ያረጋግጣል፡፡
6. ኦሜጋ ፋቲ አሲድ ከነጭ ዓሣ
ቅባት ያላቸው ዓሣዎች በተለይ ኦሜጋ ፋቲ አሲድ በብዛት ያላቸው ሲሆን ይህም ለልብ በሽታ፣ ለመዘንጋት ችግር እና ለሌሎችም ጭምር በመዋጋት በኩል ከፍተኛ ጠቀሜታዎችን ስለመስጠቱ ከዚህ ቀደም ብዙ የተባለለት ነው፡፡ ሳይንቲስቶች ጥቅሞቹ በዚህ ብቻ እንደማይቆም ጠቁመው ለኮሌስትሮል ቁጥጥርም ሚናው የላቀ እንደሆነ እየገለፁ ይገኛሉ፡፡ በአሜሪካው የሎማ ሊንዳ ዩኒቨርሲቲ የተሰራ ጥናት እንደጠቆመው መጥፎ ቅባቶችን ከዓሣ በሚገኙ ጤናማ ቅባቶች መተካት የጥሩውን አይነት ኮሌስትሮል ምጣኔ በ6 በመቶ ጨምሮ ተገኝቷል፡፡ ይህም በተዘዋዋሪ መጥፎው አይነት ኮሌስትሮል ምጣኔ እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡
7. ሻይ
ሻይ ካንሰርን በመከላከል በኩል ያለው አስተዋፅኦ ከታወቀ ረዘም ያሉ ጊዜያትን አስቆጥሯል፡፡ በቅርቡ የተደረጉ ተጨማሪ ጥናቶች ደግሞ በደም ውስጥ የሚገኝ ኮሌስትሮል መጠንን በመቀነስ የደም ፍሰትን የማቀላጠፍ ሚናውም አቻ የማይገኝለት መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ በተለይም ጥቁር ሻይ ላይ በተደረገው ጥናት በሶስት ሳምንታት በተከታታይ ጥቁር ሻይን የጠጡ ባለከፈተኛ ኮሌስትሮል ሰዎች ደም ኮሌስትሮል ቅባት መጠናቸው በ10 በመቶ ሊቀንስ መቻሉ በዩኤስዲኤ የምርመራ ውጤቶች ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡
8. ጎመን
ጎመንና ሌሎቹም አረንጓዴ ቅጠል ያላቸው ምግቦች ዘንድ የሚገኘው ሊውቲን የተባለው ንጥረ ነገር ከማርጀት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ የአይን ጡንቻዎች መድከም ሁነኛ መፍትሄ ሆኖ ያገለግላል፡፡ በዚህም በርካቶችን ከአይነ ሰውርነት ሲጠብቅ መኖሩን ባለሞያዎች በጽሑፎቻቸው አስፍረውታል፡፡ ተጨማሪ ጥቅሞቹ ደግሞ የልብ በሽታን ከመዋጋት ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ ይህንንም የሚያደርገው የደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ ተለጥፈው የሚገኙ የኮሌስትሮል ቅባት ክምችቶችን እያጠበ በማውጣት ብቃቱ ነው፡፡ በሚቀጥለው ጊዜ ወደ ገበያ የሚወጡበት ምክንያት ካለ ከፌስታልዎ ውስጥ ጎመን አብሮ ተገዝቶ መምጣቱን ያረጋግጡ፡፡ ለልብዎ ጤና ወሳኝ ቅመሞች አሉትና፡፡ በዚህ መልክ ከኮሌስትሮል ጥርቅምና ተያይዘው ከሚመጡት በሽታዎች ራስዎን ይጠብቃሉ፡፡ የቤተሰብ ኃላፊ ከሆኑም ለቤተሰብዎ አባላት ይህን በረከት እንዲያካፍሉ ባለሞያዎች ይመክራሉ፡፡ ታዲያ ጎመኑ ለዛው እስኪሟጠጥና ጠቃሚው ቁልፍ ንጥረ ነገር ተጠቃሎ እስኪሄድ አያብስሉት፡፡
9. አቮካዶ
አጎካዶ ሞኖሳቹሬትድ የሚሰኙት ጤናማ ቅባቶችን በብዛት የያዘ ፍሬ ሲሆን ይህ ተፈጥሮውም ጤናማ የሚባለውን የኮሌስትሮል አይነት ከደም ውስጥ ለመጨመርና መርዛማውን ባለዝቅተኛ ግዝፈት ኮሌስትሮል ለመቀነስ ይረዳዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሲቶስትሮል የተባለ ከምግብ የምንወስደውን ከፍተኛ ኮሌስትሮል መጥጦ የማስቀረት ከፍተኛ ብቃት ያለው ንጥረ ነገር ስለሚይዝ ጠቀሜታውን ከፍ ያደርገዋል፡፡ ይሁንና አቮካዶ ከፍተኛ የቅባትና ካሎሪ ይዘት ያለው ፍሬ ስለሆነ ማዘውተሩ ለውፍረት ሊዳርግ ስለሚችል አለፍ አለፍ እያሉ ቢጠቀሙበት የበለጠ እንደሚመከር የሐምሌው ወር 2011 የሃርቫርድ ህክምና ትምህርት ቤት ኒውስ ሌተር ያሳስባል፡፡
10. ቸኮሌት
ቸኮሌት ቅባት እንዳለው በብዛት ቢነገርም በውስጡ ያለው የፀረ መርዛማ ኬሚካሎች (አንቲኦክሲዳንትስ) ምጣኔ የሚበልጥ በመሆኑ ጠቀሜታው የበለጠ ይጎላል፡፡ በተለይ ጥቁር ቸኮሌት ይህን በብዛት ስለሚይዝ የኮሌስትሮል ቁጥጥር ውስጥ የራሱን ጠቃሚና ጣፋጭ ሚና ይወጣል፡፡ የአሜሪካ ክሊኒካል ጆርናል መጽሔት ይህን በማስረጃ አስደግፎ ጽፎታል፡፡ ጥቁር ቸኮሌት በ12 ሳምንታት ጊዜ ውስጥ 24 ከመቶ የሚሆነውን የኮሌስትሮል መጠን ሊቀንስ መቻሉ በጥናቱ ታውቋል፡፡ የደም መርጋትንና የህዋሳት መጣበቅን የመግታት ተጨማሪ ጥቅሞቹንም የሚያስታውሱት ባለሞያዎች ከወተት የተደባለቀው ቸኮሌት ጠቀሜታው ያን ያህልም ስለሆነ ጥቁሩን ቸኮሌት የሙጥኝ ይበሉ ብለዋል፡፡ ቸኮሌት ለፍቅረኛ ብቻ ያለው ማነው? ለራስዎም ጤንነት ሁነኛ መፍትሄ ነው፡፡ መጥፎ ሙድን በመለወጥ ዘና የማድረግ ብቃቱን ታዲያ እንዳይዘነጉ፡፡ ትንሽ ድብርት ቢጤ ከሞካከረዎት ቸኮሌት ጥሩ መፍትሄ ነው፡፡µ

ኢድ ሙባረክ።

The post Health: ኮሌስትሮልዎ ከፍ ያለ ከሆነ ዓመት በዓሉን የግድ በሥጋ ብቻ ማክበር የለብዎትም appeared first on Zehabesha Amharic.


የማለዳ ወግ…በኳታር ታምና ያኮራችን እህት አንድነት * ”ታማኝነት የህይወት መመሪያየ ነው! “

$
0
0

የማለዳ ወግ…በኳታር ታምና ያኮራችን እህት አንድነት
* ታማኟ ኢትዮጵያዊት አንድነት ዘለቀው በክብር ተሸለመች
* ” ታማኝነት የህይወት መመሪያየ ነው! “
ታምና ያኮራችን እህት አንድነት ዘለቀው

ነቢዩ ሲራክ

አንድነት ዘለቀው ትባላለች ፣ አንድነት የ 32 ዓመት ዕድሜ ያላት ኢትዮጵያዊት ስትሆን በኳታር ዶሀ ውስጥ በሚገኘውና ኳታር ብሄራዊ ኮንቬንሽን ሴንተር Qatar National Convention Center (QNCC) ተብሎ በሚታወቀው አንድ ታዋቂ መስሪያ ቤት ውስጥ በጽዳት ሥራ ተቀጥራ መስራት የጀመረችው እጎአ ከ2011 ጀምሮ ነው ።
Quatar
ታማኟና ታታሪዋ ኢትዮጵያዊት አንድነት ዙሪያ ካሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ በሰፊው እየተሰራጨ ያለው የሚያስደስት መረጃ ማረጋገጫ የተገኘው ግን ከትናንት በስቲያ ነበር ። አንድነት በመታጠቢያ ቤት የዘወትር የጽዳት ሥራዋን በመከወን ላይ ሳለች ሁለት በእንቁ ፈርጥ የተሸላለሙ የጋብቻ ቀለበቶች ታገኛለች ። የከበረ አልማዝ ያጌጡት ቀለበቶች ስለመሆናቸው ጠቋሚ ዋጋቸው የኳታር ገንዘብ QR470,000 US$129,000 ( አንድ መቶ ሀያ ዘጠኝ ሺ የአሜሪካ ዶላር) መሆኑ በቀለበቶቹ ላይ ተጽፏልና አውቃለች ። ታማኝ ናትና እንቁ አልማዙ አንድነትን አላጓጓትም ። እናም ሳታመነታ ወዲያውኑ ለምትሰራበት መስሪያ ቤት ኋላፊዎቿ ያገኘችውን የጣት ቀለበቶችን አስረከበች ። ስለ መልካም መግባሯና ታምኝነቷ የከብር ሽልማትን ተቀብላለች !

ሽልማቱን ያስረከቧት የድርጅቱ ዋና ኃላፊ ሲናገሩ አንድነት የቀለበቶች ዋጋ ስላለባቸው ለሁለት ደቂቃ ያህል በእጆችዋ ለማቆየት አለመፈለጓን በእግራሞት የገለጹት ኃላፊው ኢትዮጵያዊቷ አንድነት ” ታማኝነት የህይወት መመሪያየ ነው! “I believe in my life that honesty is the best policy.” ማለቷን ጠቅሰዋል !

ኳታር ብሄራዊ ኮንቬንሽን ሴንተር Qatar National Convention Center (QNCC) ተብሎ በሚታወቀው አንድ ታዋቂ መስሪያ ቤት ኃላፊዎችና አስተዳደሩ የአንድነትን ታማኝ ሰራተኝነት በአደባባይ ከመመስከር አልፈው ጠቀም ያለ የገንዘብ ዳረንጎት እንዳደረጉላት ከኳታር ዶሃ የአንድነትን ታማኝነት የተሰጠውን ክብር አስመልክተው ባሰራጯቸው መረጃዎች አስታውቀዋል !

አንድነት ከዚህ ቀደምም ትሰራበት ከነበረው አል ሙክታር የጽዳት ኩባንያ Al Mukhtar Cleaning company በጽዳት ስራ ላይ እንዳለች ውድ እቃ አግኝታ ለአለቆቿ በማስረከብ ታማኝነትቷን ማረጋገጧ በመገናኛ ብዙሃኑ ተወስቷል … !
ደስ አይልም ? ኮራሁብሽ እቱ !
ከብር ለሚገባው ክብር እሰጣለሁ!
ነቢዩ ሲራክ
ሚያዝያ 2 ቀን 2007 ዓም

The post የማለዳ ወግ…በኳታር ታምና ያኮራችን እህት አንድነት * ” ታማኝነት የህይወት መመሪያየ ነው! “ appeared first on Zehabesha Amharic.

መተማመን በጠፋበት መከላከያ ሠራዊት ውስጥ ሹም ሽሩ ቀጥሏል * ኮረኔል ጋይም እና ኮረኔል እሸቴ ከስልጣናቸው ዝቅ ተደረጉ

$
0
0

በስልጣን ላይ ያለው ገዢው ስርዓት በከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ላይ እምነት በማጣቱ ምክንያት እንዱን በማውረድ ሌላኛውን በመሾም ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝ ምንጮቹን ጠቅሶ ደህሚት ዘገበ:: ዜናው እንደወረደ እንደሚከተለው ተስተናግዷል::

Photo File

Photo File


ከመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ በደረሰን መረጃ መሰረት ውስጣዊ አሰራሩ በስብሶ በሰራዊቱ አዛዦች እምነት አጥቶ የሚገኘው የኢህአዴግ ስርዓት በ31ኛ ክፍለ ጦር ውስጥ እየሰራ የቆየውን ኮነሬል ጋይም የተባለውን አዛዥ በስርዓቱ ላይ እምነት የለውም በሚል ምክንያት ከነበረበት የአዛዥነት ደረጃ በማውረድ። በምትኩ ኮነሬል ዘነበ የተባለውን ከ23ኛ ክፍለጦር በማስመጣት ኮነሬል ጋይም ምክትል ሆኖ አዲሰራ መደረጉን የተገኘው መረጃ አስረድቷል::

የኢህአዴግ ገዢ ስርዓት የአመራር ለውጥ በማድረግ ካጋጠመው ስጋት የሚላቀቅ ስለመሰለው የ7ኛ ሜካናይዝድ አዛዥ የነበረውን ኮረኔል እሸቴ ከነበረበት የአዛዥነት ደረጃ በማውረድ የአመራር ለውጥ እየተደረገላት ባለችው የ31ኛ ክፍለጦር በሦስተኛ ደረጃ አዛዥ ሆኖ እንዲሰራ መመደቡን የገለፀው መረጃው እየተካሄደ ባለው ከሃላፊነት የማውረድና የመሾም ተግባር ያልተደሰቱት አዛዦች በስርዓቱ ላይ የከፋ ጉዳት ማድረስ እንደሚችሉ ከቦታው የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል::

The post መተማመን በጠፋበት መከላከያ ሠራዊት ውስጥ ሹም ሽሩ ቀጥሏል * ኮረኔል ጋይም እና ኮረኔል እሸቴ ከስልጣናቸው ዝቅ ተደረጉ appeared first on Zehabesha Amharic.

አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የትንሣኤን በዓል በማስመልከት ቃለ ቡራኬ ሰጡ (ይዘነዋል)

$
0
0

Ledet Message from His Holiness Abune Merkorios
አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የትንሣኤን በዓል በማስመልከት ቃለ ቡራኬ አስተላለፉ:: ፓትርያርኩ ለዘ-ሐበሻ በላኩት ቡራኬ “ቤተ ክርስቲያናችን ኢትዮጵያውያንን ሁሉ አንድ አድርጎ የኢትዮጵያን የአንድነቷን ትንሣኤ እንዲያሳየን; ጥልቅን በመስቀሉ ገድሎ; ሞትን በሞቱ ድል ነሥቶ ወደ ተነሳው ጌታ ትጸልያለች” ብለዋል::

ሙሉን ቃለ ቡራኬ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

The post አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የትንሣኤን በዓል በማስመልከት ቃለ ቡራኬ ሰጡ (ይዘነዋል) appeared first on Zehabesha Amharic.

አብዱ ኪያር አዲስ ነጠላ ዜማ ለቀቀ (ዘፈኑን እና ግጥሙን ይዘናል)

$
0
0

መርካቶ ሠፈሬ በሚለው ታዋቂ ዘፈኑ ከሕዝብ ጋር የተዋወቀው አብዱ ኪያር አዲስ ነጥላ ዜማ ለቀቀ:: አዲሱ ነጠላ ዜማው “መልካም አመት በዓል” ሲሆን መል ዕክቱም ጠንካራ እንደሆነ ግጥሙን ያነበቡ ሰዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል::

ዘፈኑን ይመልከቱ; ከዘፈኑ በታች ደግሞ ግጥሙን አስተናግደናል:-

መልካም አመት በዓል – አብዱ ኪያር

ተሰብስበን እንዳማረብን
በአውዳመቱ ፍቅር ያዝንብብን
ቤት ለሌሉት ለራቁት በአካል
በያሉበት መልካም አመት በዓል

አንቺ የኢትዮጵያ እናት ይለፍልሽ
ከአመት እስከ አመት ይሙላ ጓዳሽ
አንተ የኢትዮጵያ አባት እሺ ይበልህ
ከሰው እንዳታይ እንዳይጎድልህ

ጀግናዋ እህቴ የናቷ ልጅ
ከብረሽ ቆይልን ውለጅ ክበጅ
ወንድሜ አንበሳው ያባቱ ልጅ
ክፉ አያሳይህ ደጋጉን እንጂ

ከአገር ርቀው ለተሰደዱት
በህመም በስቃይ ካልጋ ለዋሉት
በህግ ተይዘው እስር ቤት ላሉት
ያድርግላቸው እንደሚመኙት

እንዲሁ እንዳለን እንዳይለየን

ካለም ሚለየን ከማንም ዜጋ
የሚያሳምመን ልክ እንደ አለንጋ
ልብ ውስጥ ታትሞ የማይዘነጋ
ያገር ፍቅር ነው የነፍሶች ዋጋ
ያገር ፍቅር ነው የነፍሶች ዋጋ
ከእየሩሳሌም ደግሞም ከመካ
እኛን አክብሮ ከሩቅ ጃማይካ
ኢትዮጵያን ብሎ በኛ ሲመካ
ተቀብለናል ትመስክር አፍሪካ
ተቀብለናል ትመስክር አፍሪካ

እንዲሁ እንዳለን እንዳይለየን

የወንጌሉ ሰው ላገሬ እስላሙ
ወገኑ አይደል ወይ ደራሽ ወንድሙ
የቁርአኑ ሰው ለክርስቲያኑ
ወንድሙ አይደል ወይ ደራሽ ወገኑ
ወንድሙ አይደል ወይ ደራሽ ወገኑ
ረመዳን ስፆም በርታ የሚል ጓዴ
አይዞህ የምለው ሲሆን ኩዳዴ
የኔና የሱን ታላቁን ፍቅር
ኢትዮጵያን ያየ ወጥቶ ይመስክር
ኢትዮጵያን ያየ ወጥቶ ይመስክር

እንዲሁ እንዳለን እንዳይለየን

ABDU_KIAR

The post አብዱ ኪያር አዲስ ነጠላ ዜማ ለቀቀ (ዘፈኑን እና ግጥሙን ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.

በደቡብ አፍሪካ መሲና ከተማ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ኮሚቴው ነፃ መሆኑን መሰከሩ

$
0
0

south africa

south africa ethiopia
(ዘ-ሐበሻ) ድምፃችን ይሰማ ባስተላለፈው ጥሪ መሠረት በደቡብ አፍሪካ የድንበር ከተማ ላይ የምትገኘው መሲና ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በ እስር ላይ የሚገኙት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ነፃ መሆናቸውን መሰከሩ::

በስፍራው የሚገኘው የዘ-ሐበሻ ዘጋቢ በፎቶ ግራፍ አስደግፎ በላከው ዜና መሰረት ኢትዮጵያውያኑ ሙስሊሞች ሕዝባዊ ስብሰባ ጠርተው በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ከተወያዩ በኋላ የታሰሩት የኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ ጠይቀው ነፃ ናቸው ብለዋል::በስብሰባው ላይ የታደሙት ወገኖች “የታስርነው እኛ ነን” የሚል ቢጫ ቲሸርት ለብሰው ለስብሰባው ድምቀት ሰጥተውታል::

ሕወሓት የሚመራው መንግስት በካንጋሮው ፍርድ ቤት በኩል ከሰሞኑ በነዚህ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ፍርድ ለማስተላለፍ ዝግጅ መሆኑን ተከትሎ በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በመሰባሰብ ኮሚቴው ነፃ መሆኑን በመመስከር በነፃ እንዲለቀቁ እየጠየቁ ነው:: እንዲህ ያለው ስብሰባም እስካሁን ባልተደረገባቸው ሃገራት እንደሚቀጥል ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ጠቁሟል::

The post በደቡብ አፍሪካ መሲና ከተማ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ኮሚቴው ነፃ መሆኑን መሰከሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

በፋሲጋችን። –ዳዊት ዳባ

$
0
0

እንኳን በደህና ከዘመን ዘመን  አሸጋግሮ ለፈሲጋ በዓል  አደረሰን። በአሉን የፍቅር የሰላም ያድርግልን።

Anger at injustice as martin luter king wrote. Is the political expression of love?
የፋሲጋ ሳምንት (ህማማት)  ድንቅና አስገራሚም ነው። ፍቅር፤ መሰዋትነት፤ ክህደት፤ ታማኝነት፤ ፅናት፤ፍርደገምድልነት፤ምቀኝነት፤ ተንኮል፤ ደባ፤ አፍቅሮ ሰልጣን፤ አፍቅሮ ንዋይ፤ ሰም ማጥፋት፤ ይቅርታ፤ አብሮ መብላት፤ ጉቦ፤ ተስፋ፤ ሀዘን፤ ደስታ፤ ስቃይ፤ሞት፤ ይሰቀል{Mop Justice}፤  ብቻ ጠቅለል ባለ የዚህን አለም  ሂወታችንን በአንድ ሳምንት ውስጥ ሲከወን እናይበታለን።

ህማማቱ ከተፈፀመ ረጅም ጊዜ ሆነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ አለም የሰው ልጅም በእጅጉ ተቀይሯል።  ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶ በዚህ ምድር ላይ የተመላለሰው በዚህ ዘመን ቢሆንስ ኖሮ ብለን ብንጠይቅ?። የሰው ልጆች ይህ ሁሉ ግፍ እንዲፈፀምበት፤ በመጨረሻም እንዲሞት አይፈቅዱም ማለት የሚቻልበት ደረጃ ድረስ ተለውጧል ማለት ይቻላል።  ሞቱም ሆነ ያን ሁሉ መከራን መቀበሉ ከንቱ አልቀረምና ስለተለገስነው ዘላለማዊ ሂወቱ ብቻ ሳይሆን ምድርን በዚህ ደረጃ ስለቀየረው  ደስ ያሰኛል። ይህ ግን ጠቅለል አድርገን በአለም ደረጃ ከወሰድነው ነው።  የዘመኑ ሀያል ህዝቦች በአደገ ስብእና ላይ እና ለሰው ልጅ ሂወት ክብር የሚሰጡ በመሆናቸው ነው ። ብቃት ደረጃ ደርሰዋል ባይባልም ፍትህ እንዳይጓደል አሰልሰው የሚጥሩና ለእውነት የሚቆሙ ስለሆነ ነው። አቅሙ ለሌላቸው ተቆርቋሪ መሆንን ስራቸው ያደረጉ ብዙዎች ያለቡት ማህበረሰብ ስለሆነም ነው። በዋናነት ክርስትናቸው ይህንኑ ታላቅ ቁም ነገር መሰረት ያደረገና  በሚታይ በሚጨበጥ  ስራ የታገዘ ስለሆነ ነው። ነጣጥለን በየሀጉሩና በየአገሩ  የሰው ልጅ ምን ደረጃ ላይ ነው ያለው? ብለን ካየነው ግን ግምታዊም ቢሆን የምንደርስበት ድምዳሜ በእጅጉ የተራራቀ በዙም በህማማቱ ዘመን ከነበሩ የሰው ልጆች ከነበራቸው  ስብእና ያልተለወጠ ሊሆን ይችላል።

አያድርገውና መመላለሱ በዚህ ዘመን ኢትዬጵያ ውስጥ ሆኖስ ቢሆን?። ጥያቄው ለበዛው አማኝ አናዳጅ የሚሆን አይመስለኝም። ሲጀመር ጥያቄውን ያስነሱት ሰባኪ ነን ያሉ ናቸው። ዝም ሲባል ይባስ ብለው ትንኮሳ ስለበዙ ነው። አሁንም ለምን ተነሳ ብለው  ይሰቀሉ የሚሉና አዋራ ሊያስነሱ ይችላሉ። መነሳት ግን የግድ አለበት። አዎ በዚህ በኛ ዘመን ህማማቱ  ኢትዬጵያ ውስጥ ቢሆንስ ኖሮ?።

ከሳሾች፤ አስገዳይና፤ ገዳዬች አሉን።  በእርግጥ በሰለጠነው ማህበረሰብ ውስጥ እነዚህን  በመንግስት ስልጣን ላይ አናገኛቸው ይሆናል። ቢኖሩም ስልጣናቸው የተገደበ ስለሆነ አይችሉም።  በየትኛው የአለም ክፍል ላይ ሊኖሩ ግን ይችላሉ። የውሸት ምስክሮችንም መግዛቱም ሆነ ፈራጆችን ማግኘቱ ቀላል እንደሆነ ከኑሯችን የምናያው ነው። ይህን አይነት እኩይ ወንጀል ቅቤ ቀብተው የሚያሰማምሩና ህዘብን የሚያደናግሩም የካድሬ መአት፤ ጋዜጠኛ ተብዬና አደርባይ ምሁራን ሞልተዋል። በዋናነት በየእምነቱ የቁጩ ሀዋርያቶችም እንዲሁ። ያም ሆኖ እነዚህ ሁሉ ተደምረው ከጠቅላለው ህዘብ ጥቂቶች ናቸውና እንደህዘብ ከሌሎች የሚያሳንሱን አይሆንም።

መክሰሻውም በገፍ ነው ያለን። ከአስተምሮቶቹ ውስጥ በቀላሉ በመምዘዝና ትርጉም በመስጠት።  በእምነቶች መሀል ግጭት በመፍጠር። በሽብርተኛነት፤ በአገር ክህደት፤ መንግስት ላይ በማሴር፤ የህዳሴ ጉዟችንን በማደናቀፍ  የሚለው ሁሉ በቀላሉ መክሰሻና ማሰቃያ ሲያልፍም መግደያ ሊሆን እንደሚችል ያለንበት ሁኔታ መስካሪ ነው። አይደለም አገርን አልፎም አለምን የሚያነቃንቅና የሚለውጥ መልካም ሀሳብ ይዞ የመጣው መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ትንሽ የሆነች አገራዊና ህዝባዊ  መልክም ሀሳብ ለዛውም ምድራዊ አላችሁ ተብለው ብዙ ንጹሀን ዜጎቻችን እየተገደሉ፤ ሰቆቃ እየተፈፀመባቸው በየማጎርያ መኖራቸው የማንክደው ነው።  ያም ሆኖ ይህንኛውም በመንግስት ደረጃ የሚራመድ ስለሆነ እንደ ህዘብ  አያሳንሰንም ብለን እንውሰደው።

ዛሬም “ይሰቀል”፤ “ይሰቀል” ልንል የምንችል ምን ያህላችን ነን የሚለው ላይ ብዛታችን ነው  አስፈሪም አሳፋሪም ሊያደርገን የሚችለው ። ሲጀመር የመጠየቅ እድሉም ስለሌለን ይሰቀል ማለቱንም አንችልም። ወናው ጉዳይ  ይህ ሰው ንጹህ ነው፤  ሰቆቃ ሊፈጸምበት አይገባም  ብለን ልንመሰክር የምንችል ምን ያህላችን ነን?።  አጥብቀን የምንቃወም፤ ፍትህን የምንጠይቅና ድምጻችንም የምናሰማስ?። ወጋም የሚያስከፍል ቢሆን ለመክፈል የምንፈቅድስ?።  ንጽህናውን ልቦናችን እያወቀ  እሷስ ብትሆን በመጀመርያ “አጭር ቀሚስ ማን ልበሺ አላት” አይነት አመክነዬ መደርደሩም ሆነ የተካንበት ተጠቂው ላይ ጉድፍ መፈለጉ  ዘመንኛ መሆኑ ነው እንጂ ያው “ስቀለው” ውስጥ  የሚካተት ነው።

አምላክ በማቲዌስ ወንጌል 25፤31-46 ግልጽ አድርጎ ነግሮናል። አመክንዮ ለመደረድር  እንኳ እንዳያመቸን አድርጎ። ለተራቡት፤ ለተጠሙት፤ ለተጨቆኑት፤ ፍርድ ለተጓደለባቸው፤ ለሚሳደዱት፤ ባጠቃላይ ለሰው ልጆች አሁን በምድር ላይ የምናደርገውን ለሱ እንዳደረግነው አድርጎ እንደሚወስደው ነግሮናል። በዬሀንስ 4፤20 ደግሞ አጠገብህ ያሉ ወንድምና እህቶችህን ሳትወድ አምላክን እወዳለው ብትል እየቀጠፍክ ነው ብሎ መፈናፈኛ እንዳይኖር  ቁም ነገሩን አጠናክሮ ዘግቶታል። ቃሉን ላመሰጠርው ልሞክር። መንፈሳዊ ስራችን ሲገለፅ ስለውለታ፤ ስለጉልበተኛነት፤ ስለትውውቅ ሳይሆን  ስለሰባዊነት፤ ስለፍትህና ስላእውነት ለዛውም ከልባችን ደስ እያለን ብቻ የምናደርገው ይሁን ነው የሚለን።

ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር ከመጣ አይደል ‘ሀ’ ተብሎ ቀን መቆጠር የተጀመረው። አሁን 2007  ላይ ነን ።  በዚህ ረጅም ጊዜ ክርስትናው በአገራችን ብዙ ተከታዬች አፍርቷል። ብዙ አብያተ ቤተክርስትያናትና የአምልኮ ቦታዎች አሉን። ብዙ አስተማሪዎች ሰባኪዎች እንዲሁ። ጿሚው አገሬው ነው። ስሙን ከፍ ከፍ የሚያደርገውም እንዲሁ። በቀን ውስጥ ብዙ ጊዜ ሰላት የሚያደርሰውም ያገሬው ግማሽ ነው። ሁሉም አይነት እምነቶቹ ረጅም ዘመንን አገራችን ውስጥ አስቆጥረዋል። ታዲያ ለምን ነፃነት የበዛልን ዜጎች መሆን አልቻልንም?። ማን ሀላፊነቱን በአግባቡ ስላልተወጣ? ምንስ ስለጎደለ ነው?።

በዬሀንስ ወንጌል 2፤20 ላይ የአምላክ ቃል “ስራ የሌለው እምነት ሙት ነው ይላል።” በሌላ አገላላጽ ፍቅሩ አለ እንበልና እምነቱና ፍቅሩ መኖሩ የክርስትናው ግማሹ ነው። ሌላኛው ግማሽ ያን እምነትህና ፍቅርህን በስራ ላይ ማዋሉ ነው።  እምነታችን ስራ የሌለበት ቢሆን ነው እንጂ ይህ ሁሉ ችግረኛ፤ ይህን ያህል ጥላቻ፤ በዚህ ደረጃ የፍርድ መጓደል። ቆጥሮ መስፈርት የሌለው ተሰዳጅ፤ አድሎ፤ዘረኝነት…. ባጠቃላይ ስቃይና መከራ በአገራችን ባልነገሰ ነበር።

የዘመኑ ስልጣኔ እንደሁሉም ነገር የአምላክን ቃል ማግኘቱንና መረዳቱንም ቀላል አድርጎታል። ኮንቢዩተሬን ስለሌሎች መብት መከበርና ስለነፃነት ስለመቆም ቅዱስ መፀሀፍ ምን ይላል ብዬ ጠየኩት?። ከሰባ በላይ ጥቅሶች ሰጠኝ።  ለፍትህ ስለመቆምስ ምን ይላል ብዬ ጠየኩት። ከየትኛውም ቁምነገር በበዛ ወደ ሁለት መቶ ቦታዎች ላይ ስለፍትህ ግልፅ አድርጎ ይነግረናል። እንዲሁ  በራስ ስለመተማመንና አንገትን ቀና አድርጎ ስለመሄድስ ምን ይላል ብዬ ጠየኩት። ዘረገፈልኝ። እንዲህ እንዲህ እያልኩ ስጠይቅ አብዝቶ መልስ ሲሰጠኝ በመጨረሻ የደረሰኩበት ድምዳሜ የዚህ ዘመን ኢትዮጵያዊ አማኝና ፖለቲከኛ  ልዩነት የሌለው መሆኑን ነው።

ሲጀምር የበዛነው አይደለንም እያልን በግድ  ፖለቲከኛ መባላችን ይሰመርበት። ይህ እንግዲህ ለነጻነት፤ ለመብት፤ ስለፍትህና ስለእውነት የሚጮህው ሁሉም ባይሆን እንኳ የበዛው አማኝ መሆኑን ያውቃሉ። ከዘም በላይ አመነም አላመነም  ክርስትናው የሚያዘውን ነው የምናደርገው። እንደሚመስለኝ ፖለቲከኛና ፖለቲካ የሚለው ዘመቻ መልካም በሆነው ስራችን እያሳጣን ስለሆነ ያልተመቻቸው ክፍሎች አሸማቀው ዝም ሊያሰኙን ነው ፍላጎታቸው።   የሚገርመው ግን መሳጣቱ የተፈራው ለአምላክ  ወይስ ለምእመኑ?።

እወቁት መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር የተመላለሰው በዚህ ዘመን ኢትዬጵያ ውስጥ  ቢሆን ኖሮ። ይህው ፖለቲከኛ ተብሎ ልታሳንሱት የምታስቡት ወገናችሁ   በግፍ ለሚገደሉት፤ ፍትህ ለተነፈጉት፤ ከቄያቸው ለሚሳደዱት፤ አገር ለቀው ለተሰደዱት ወገኖቹ መቆምን ደስ እያለው የሚያደርገው፤ የሚታወቅበትና ለምድም ያደረገው ነው። በእርግጠኛነት ካሳዳጆቹ  ወገን አይቆምም ። ሌላው የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ጽዋው በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለሁላችንም መዳረሱ አይቀርም። ነገ ለሁላችንም የሚጮህው ይህው ወገን ነው።  አለቀ።

 

Comment

 

The post በፋሲጋችን። – ዳዊት ዳባ appeared first on Zehabesha Amharic.

የትንሣኤ ዋዜማ ቀጥታ መርሃግብር ከሚኒያፖሊስ ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ (Live Stream)


ኢትዮጵያዊያኑ የኬንያን ፍርድ ቤቶች እያጣበቡ ነው

$
0
0

ዳዊት ሰለሞን ከኬንያ እንደዘገበው:-

ከኢትዮጵያ በቀጥታ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለሚደረግ በረራ ቪዛ ማግኘት ካለፉት አስር ዓመታት ጀምሮ ለኢትዮጵያዊያን ፈጽ ሞ የማይታሰብ ሆኗል፡፡በደቡብ አፍሪካ የተለያዩ ከተሞች ኢትዮጵያዊያን በከፍተኛ ደረጃ ቁጥራቸው እየተበራከተ በመምጣቱ አዲስ አበባ የሚገኘው የኔልሰን ማንዴላ አገር ኢምባሲ ቪዛ መስጠት ዳገት ሆኖበታል፡፡
ethiopia1

ethiopia2

ethiopia3
ህጋዊው መንገድ እየጠበበ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ የሚያስፈልገውን ፈቃድ ማግኘትም 100.000 ብሮችን መስዋዕት ማድረግን ሲጠይቅ የተሻለ ህይወት በደቡብ አፍሪካ እንደሚገኝ የሚሰሙት ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ወደ ኬንያ በማቅናት በህገ ወጥ አስተላላፊዎች አማካኝነት ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ናይሮቢን እንደመተላለፊያ መጠቀም ከጀመሩ አመታት ተቆጥረዋል፡፡

ከኬንያ ምድረ ርስት ተደርጋ ወደ ተሳለችው ደቡብ አፍሪካ የሚደረገው ጉዞ ብዙ እንቅፋት የሞላበት ቢሆንም ወጣቶቹ ገንዘባቸውን ከስክሰው ሞትን ፊት ለፊት ለመጋፈጥ በመምረጣቸው ለአስተላላፊዎቻቸው ጥሩ እንጀራ ፈጥረውላቸዋል፡፡

‹‹አስጨዳጅ››የሚል መጠሪያ የተሰጣቸው አስተላላፊዎች ከአገር ቤት እስከ ደቡብ አፍሪካ መድረሻ ሰንሰለት የሰራ ግኑኝነት በመፍጠር የተደራጁ መሆናቸውም የሰው ንግዱን ውጣ ውረድ የማይጠይቅ ቀላል ቢዝነስ አድርጎላቸዋል፡፡

‹‹አስጨዳጆቹ››በየድንበሩ ከሚገኙ የፊናንስ አባላት፣ከፖሊሶች፣ከኢምባሲ ሰራተኞችና ከመኖሪያ ቤት አከራዮች ጋር ቁርኝት መፍጠራቸውም የሰው ንግዱን ሰንሰለት መበጠስ ለየትኛውም ወገን አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡

ኢትዮጵያና ኬንያ ካላቸው ስምምነት የተነሳ ከአንዱ አገር ወደ ሌላኛው ለመተላለፍ ቪዛ የማይጠየቅ መሆኑም በዛ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን አስተላላፊዎቹ ወደ ናይሮቢ ለማዘዋወር ተመችቷቸዋል፡፡የአልሻባብ ዱላ በተደጋጋሚ ጊዜያት ያረፈባት ኬንያ በበኩሏ ድንበሯንና ከተሞቿን በጸጥታ ሰራተኞቿ በስፋት ማስጠበቅ መጀመሯም ለአስጨዳጆቹ ያልተጠበቀ እንቅፋት እየፈጠረባቸው ይገኛል፡፡ኢትዮጵያዊያንን የኬንያ ፖሊሶች በድንበርና በከተሞች አካባቢ ሲያገኙም በህገ ወጥ መንገድ ወደ አገራችን ገብታችኋል በሚል ሰበብ አፋፍሰው እስር ቤት በመወርወር ፍርድ ቤት መገተርን የቀን ተቀን ተግባራቸው አድርገዋል፡፡ባለፈው አንድ ወር ብቻ ከ485 የሚልቁ ደቡብ አፍሪካ ለመድረስ ናፍቀው ከቤታቸው የወጡ ወጣቶች በፖሊሶች ተይዘው ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

አስጨዳጆቹ ለደምበኞቻቸው የሚያደርጉት አቀባበል

ከኬንያ ጉዳያቸውን ጨርሰው ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚያሻግሯቸው ደላሎች ከመኪና እንደወረዱ እንደሚጠብቃቸው ተነግሯቸው በሞያሌ አቋርጠው ናይሮቢ የሚገቡት መንገደኞች የሚደረግላቸው አቀባበል አስከፊ የሚለው ቃል ከመጠነው የምንጠቀምበት አይነት ብቻ ነው፡፡ፖሊሶች አይደርሱበትም በሚባለውና በአለማችን በድሆች መኖሪያነቱ ተለይቶ በሚታወቀው የናይሮቢ ኪቢራ ሰፈር በሚገኝ መጠለያ በመውሰድ በአንድ ክፍል ውስጥ ከ50 -125 የሚደርሱ የደቡብ አፍሪካ ተስፈኞችን ያሳድሩበታል፡፡

አስጨዳጆቹ ለደምበኞቻቸው ደረቅ ዳቦ ከወረወሩና ጉዳያቸው እስኪያልቅ መንቀሳቀስ ፈጽሞ የማይታሰብ መሆኑን በማስጠንቀቅ ከአካባቢው ይሰወራሉ፡፡ርሃብ፣ተፋፍነው ከመቀመጣቸው ጋር ተደማምሮ በሚፈጠር የአካል መዛል ተስፋ የሚቆርጡ ቀላል ቁጥር የሌላቸው ወጣቶች ዳቦ ፍለጋ በወጡበት በሌቦች ይዘረፋሉ አልያም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ይውላሉ፡፡

የኬንያ ፍርድ ቤት ከዚህ በፊት በቀላል ማስጠንቀቂያ ታሳሪዎቹን ይለቅ የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ግዜያት ወዲህ ‹‹በህገ ወጥ መንገድ በመግባታችሁ ››በሚል ሰበብ እስከ ከ500 -1000 ዶላር ወይም ከ6 ወር – 2 ዓመት የሚደርስ ቅጣት መበየን ጀምሯል፡፡አስጨዳጆቹ ፍርድ ቤት በቀረቡ ደምበኞቻቸው ላይ የሚበየነውን ገንዘብ ለመክፈል ቀርቶ በእስራታቸው ወቅት ስንቅ ለማቀበል እንኳን ድራሻቸው አለመገኘቱም ጭካኔያቸውን ያሳያል፡፡

የተጨዳጆቹ ዕጣ ፈንታ

ዕድል ቀንቷቸው የኬንያ ፖሊስ እጅ ያልወደቁ ተጨዳጆች ወደ ሶስተኛ አገር እንደተዘዋወሩ ተመሳሳይ ፈተና ይጠብቃቸዋል፡፡እኛም ኢትዮጵያዊያኑ ድንበር ሊያቋርጡ ሲሉ ተያዙ የሚሉ ዜናዎችን ከደቡብ አፍሪካ ጎረቤት አገራት እንሰማለን፡፡በናይሮቢ ከጠበቁት በላይ ጉዟቸው ተጓትቶ ወይም ፖሊስ ይዟቸው እስር ቤት የተጣሉ ወጣቶች በእስር ቤቶች በሚደርስባቸው ጥቃት የተነሳ ራሳቸውን እስከመጥላት በመድረስ ወደ አገር ቤት እንኳን ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆኑ መንገድ ተዳዳሪዎች ሆነው አስቸጋሪውን ህይወት ይገፋሉ፡፡

ትንንሾቹን አሳዎች የሚያጠምደው መንግስት

በቅርቡ ሁለት ሴት አስጨዳጆችን በኢንተርፖል አማካኝነት መንግስት ይዞ ከናይሮቢ መውሰዱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ሰዎቹን በቅርበት የሚያውቁ በናይሮቢ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በበኩላቸው አሳው አንጂ አሳ አንበሪዎቹ አሁንም ባህሩ ውስጥ መኖራቸውን ይናገራሉ፡፡አሳ አንበሪዎቹ በናይሮቢ ከአስጨዳጅነት ተግባራቸው በተጨማሪ በተለያዩ ታላለቅ የንግድ ኢንቨስትመንቶች የተሰማሩ፣ናይሮቢ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጋር ጥሩ ግኑኝነት በመፍጠር ኢምባሲው በሚያዘጋጃቸው የተለያዩ ዝግጅቶች ቀድመው በመገኘት ሪከርድ የሰበሩ፣ያለ ችግር አገር ቤት ገብተው ተጨዳጆችን መልምለውና ዲያስጶራ በሚል ስያሜ ኢንቨስትመንት ላይ ተሰማርተው የተንደላቀቀ ህይወት የሚመሩ መሆናቸውን ያወሳሉ፡፡የኬንያን ፖሊሶች በወዳጅነት የቀረቡት አሳ አንበሪዎች እጃቸው ከዚህም በላይ ረዥም መሆኑን የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም፡፡

መፍትሔው በየት ነው?

በአብዛኛው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር ድንበር የሚሻግሩት ወጣቶች የአንድ አካባቢ ተወላጆች ናቸው ፡፡ከደቡብ ክልል የበቀሉ ተስፈኛ ወጣቶች፡፡እነዚህን ወጣቶችን በመመልመል ስራ የተሰማሩትም የዚያው ክልል ተወላጆች ናቸው፡፡የአስጨዳጆቹ የአገር ቤት ወኪሎችም የደቡብ ልጆች ናቸው፡፡መምህራን፣ፓስተሮች፣ካድሬዎችና በየአካባቢው የሚታወቁ ሽማግሌዎችና ልጆቻቸው ቀደም ብለው በደቡብ አፍሪካ ኑሮ የመሰረቱላቸው ቤተሰቦች ናቸው፡፡መንግስት ለአካባቢው ትኩረት በመስጠትም የስደት ጎርፉን መቀነስ የሚያስችለውን ፖሊሲ ሊቀርጽ ይችላል፡፡
እርግጥ ነው ስደተኞቹ በአገራቸው ሰርተው ለመኖር የሚያስችላቸው ዕድል ቢፈጠርላቸው ይህን ያህል የኬንያን ፍርድ ቤት የሚያጣብቡበት መንገድ ሊፈጠር አይችልም፡፡እናም አስጨዳጆቹን ለቃቅሞ በማሰር ብቻ ነገሩን ማቆም የማይቻል በመሆኑ የስራ ዕድል ለሁሉም እኩል የሚፈጠርበትን ሁኔታ ማመቻቸት ለዜጎቼ አስባለሁ ከሚል ስርዓት ይጠበቃል፡፡

The post ኢትዮጵያዊያኑ የኬንያን ፍርድ ቤቶች እያጣበቡ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

በስለላ ከሆላንድ የተባረረው የጋዜጠኛውን አንገት እቆርጣለሁ አለ (ድምጹን ይዘናል)

$
0
0


ክንፉ አሰፋ

እለተ እሁድ ከቀትር በሁዋላ አንድ የስልክ ጥሪ ደረሰኝ። ቁጥሩ +251 945226530 ነበር። ስልኩን አነሳሁት።
“ሃሎ”
“አቤት”
“አለማየሁ ነኝ። መን አባክ ነው የምትጽፈው። እኔ አላማዬ ነው። አንተን ግን አንገትህን ቆርጬ ነው የማሳይህ። ለማየት ያብቃህ። ያን የምትጽፈውን ጽሁፍ… እኔ ምንም ልሁን ምን እንደዚህ አይደለሁም። እሺ። እናትክን ልብ… (ይህንን ጸያፍ ቃል በድምጽ ስሙት)። … ደግሞ ኢህአዴግ ዘርህን ይበ… (ይህንንም ጸያፍ ቃል በድምጽ ስሙት)።
alemayehu-sentayehu
ይህ ጸያፍ ዘለፋ እና ማስፈራርያ እንግዲህ ወያኔ ምን ያህል እንደወረደ ያሳየናል። ከነውረኛ ስድቡ ባሻገር ደግሞ ቀላል የማይባል ድንበር ዘለል ሽብር ነው። ለዚህ ሽብር ተጠያቂ የሚሆነውም ተላላኪውና ሆድ አደሩ ብቻ ሳይሆን ላኪውም ጭምር ነው። ህወሃትን በመጠለል ልክ እንደ ISIS አንገትህን እቆርጥልሃለው ሲል መናገሩ መንግሥታዊ አሸባሪነት ለለመሆኑ ግልጽ ነው። ለዚህ ሰው ሲከራከር የነበረው ተሾመ ቶጋም ይህንን ሰምቶ ዝም የሚል ከሆነ የወንጀሉ ተባባሪ ይሆናል።

በዚህ አይነት ማስፈራራት አላማቸውን ማስፈጸም ካሰቡ ግን በጣም ተሳስተዋል። እንዲህ አይነቱ ነገር የበለጠ እልህ ውስጥ ያስገቡናል እንጂ በስራችን ላይ ቅንጣት ያህል ተጽእኖ ሊፈጥሩ አይችሉም። እንደጋዜጠኛ ለመስራት ስንነሳ ፍርሃትን ከእትብታችን ጋር ቀብረነው ነውና ይህንን የምትሞክሩ ተስፋ ቁረጡ ነው የምንላችሁ።

ይህ ሰው ከሆላንድ የመኖርያ ፈቃዱ ተነጥቆ ወደ ኢትዮጵያ እንደተመለሰ በተለያዩ የዜና አውታሮች መዘገቡ ይታወሳል። ስለዚህ ሰው ጉዳይ ተሾመ ቶጋ (የወያኔ አምባሳደር) ከብራስልስ ማስተባበያ ሰጥቶ ነበር። ማስተባበያው ባጭሩ፣ “አለማየሁ ስንታየሁ ሰላይ አልነበረም። ከሆላንድም አልተባረረም። የተሰደደውም ከኢሃዴግ ዘመን በፊት ነው። … ይህ ደጋፊዎቻችንን ለማሸማቀቅ በአሸባሪ የተፈረጁ ሰዎች የሚያወሩት ወሬ ነው።” ይላል።

የሶስት ልህጆች አባት የነበረው አለማየሁ (ዘለቀ ፖላ) የሆላንድ የመኖርያ ፈቃዱን እና መኖርያ ቤቱን ተቀምቶ ከሄደ ሶስት ወራት አልፈዋል። ጉዳዩን ከሚመለከተው ክፍል በማጣራት የዜናውን እውነተኝነት አረጋግጠናል።

ዜናው በውጭ ያሉ የስርዓቱ ደጋፊዎችን በእጅጉ ያስደነገጠ በመሆኑ የተሾመ ቶጋ ማስተባበል የግድ ነበር። ውሸት ነው ማለታቸውም አይደንቅም። እውነት ተናግረው ሰምተናቸው ስለማናውቅ። አለማየሁ ስንታየሁ ችግር እንደነበረበት እና አስፈላጊውን ደብዳቤ ከኤምባሲው ተቅብሎ ወደ ኢትዮጵያ መሄዱን አቶ ተሾመ በቃለ-ምልልሱ አልሸሸጉም።

የተሾመ ቶጋን ውሸት ከሰማሁ በኋላ ጉዳዩን ለማጣራት የሚመለከታቸው የሆላንድ መንግስት አካላትን አነጋግሬአለሁ። ሶስት ክሶች ተመስርተውበት ነበር። አንደኛው ከወያኔ ካድሬዎች ጋር በመመሳጠር አንድ ኢትዮጵያዊ ባለሃብትን እንዲታፈን በማድረጉ፤ ሁለተኛው ክስ የአሱን ስም በማጭበርበር እና፤ ሶስተኛ የሆላንድ መንግስትን ዋሽቶ የስደት ፈቃድ ከገኘ በህዋላ ለገዢው ፓርቲ ይሰልላል የሚሉ ነቸው።
ጭንቀት ውስጥ በነበረ ጊዜ ከአንዴም ሁለቴ ደውሎ በጉዳዩ ላይ አነጋግሮኛል። ከሚኖርበት አካባቢ እንዳይርቅ በሆላንድ መንግስት ታግዶ በነበረበት ወቅትም ከመገኛኛ ብዙሃን፤ በተለይ ከጀርመን እና ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋር እንዳገናኘው ጠይቆኝ ነበር።

ይህ ሰው ወደ ሆላንድ የገባው በ1994 (ወያኔ ስልጣን ከያዘ ከአንድ አመት በህዋላ) በሰላም ተጓዥ ስም ነበር። ከዚያ ለበርካታ አመታት በስውር ከዚያም በግልጽ ለወያኔ ሲሰራ ነበር።

ጋዜጠኛ አፈወርቅ አገደው በፌስቡክ ገጹ ላይ ስለዚህ ሰው እንዲህ ሲል አስነብቦናል። “ይህን ግለሰብ በአካል አውቀወለሁ። ብዙ የቅርብ ጓደኞቼም ስለሚሠራቸው የስለላ ሥራዎቹ ያውቃሉ። ከራሱ አፍ እንደሰማሁት ትክክለኛ ስሙ ዘለቀ ፖላ ነው። እዚህ ስደት የጠየቀበት ስሙ ዓለማየሁ ስንተሰየሁ ነው። የወላይታ አካባቢ ተወላጅ ነው። ተቃዋሚ መስሎ ለህወሓት ኤምባሲ ብዙ የስለላ መረጃዎችን የወያኔ ተቃወሚዎችን በሚመለከት እንደሚያቀብል ይታወቃል። … አንዳንዴ ስብሰባዎቹ ሌሎችን በሚያገልል መልኩ በትግርኛ ሲደረግ ዘለቀ ፖላ ይሳተፋል። ምኑ ገብቶህ ነው በማታውቀው ቋንቋ የምትሳተፈው ስንለው ጆሮዬ ክፉ ክፉውን ስለሚሰማ ለእናንተ ወሬ ለማቀበል ነው ይል ነበር።”

The post በስለላ ከሆላንድ የተባረረው የጋዜጠኛውን አንገት እቆርጣለሁ አለ (ድምጹን ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.

በአዲስ አበባ ኤድና ሞል በጣም አጭር ቀሚስና ቁምጣ በሚለብሱ ሴቶች ላይ አወዛጋቢ ሕግ አወጣ

“ሁሉም ሰው ንግግሬን ወዶታል; ግን ባትናገር ጥሩ ነበር አሉኝ”– (ብርሃኑ ተዘራ ከታማኝ ሾ ጋር ክፍል 3) ስለድምጻችን ይሰማም ተናግሯል

$
0
0

በቅርቡ ተወዳጁን ‘ወገኔን’ ነጠላ ዜማ የለቀቀው ብርሃኑ ተዘራ ከታማኝ ሾ ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ ክፍል 3 ላይ “ሁሉም ሰው ንግግሬን ወዶታል; ግን ባትናገር ጥሩ ነበር አለኝ” አለ:: የትኛውን ንግግር? – ቃለ ምልልሱን ያድምጡ::

“ሁሉም ሰው ንግግሬን ወዶታል; ግን ባትናገር ጥሩ ነበር አለኝ” – (ብርሃኑ ተዘራ ከታማኝ ሾ ጋር ክፍል 3) ስለድምጻችን ይሰማም ተናግሯል

The post “ሁሉም ሰው ንግግሬን ወዶታል; ግን ባትናገር ጥሩ ነበር አሉኝ” – (ብርሃኑ ተዘራ ከታማኝ ሾ ጋር ክፍል 3) ስለድምጻችን ይሰማም ተናግሯል appeared first on Zehabesha Amharic.

በቤተመንግስት አካባቢ አለመተማመኑ በገሃድ እየታየ ነው * የቤተመንግስቱ ጠባቂዎች በሙሉ ወደ ቤንሻንጉል ተላኩ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ሕወሓት በሚያስተዳድረው መንግስት ውስጥ እርስ በ እርስ በባለስልጣናቱ መካከል ያለው አለመግባባት እና አለመተማመን እያየለ መሄዱ ቤተመንግስትም መድረሱ ተሰማ:: በተለይም የመለስን ራዕይ ገደል ይግባ የሚለው የአቶ አርከበ ቡድን ሃይለማርያም ደሳለኝን ይዞ እያየለ መሄዱና በሌሎች የሕወሓት አባላት ላይ ያለው አለመግባባት ወደ አለመተማመን ደርሶ የቤተመንግስት ጠባቂዎችን እንዳስቀየረ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አጋለጡ::

Photo File

Photo File


ቤተመንግስቱን ሲጠብቁ የነበሩ የሕወሓት ተላላኪ ወታደሮች በጠቅላላ ወደ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ጉባ ወረዳ መላካቸውን ያጋለጡት የዘ-ሐበሻ ምንጮች እነዚህ ጠባቂዎች ደግሞ የአየር ሃይል አባላት መሆናቸው ጉዳዩን ከረር አድርጎታል:: ሕወሓት በሚመራው አየር ኃይል ውስጥ ያለው መታመስና በርካታ የአየር ሃይል አባላትም እየከዱ ወደ ጎረቤት ሃገራት መሰደድና ተቃዋሚዎችን መቀላቀል ያስደነገጠው መንግስት የአባይን ግድብ ትጠብቃላችሁ በሚል ሰንካላ ምክንያት መሳሪያቸውን በጠቅላላ አስቀምጠው ወደ ቤንሻንጉል እንዳዘዋወራቸውና በምትካቸውም ጆሮዋቸውን ቢቆርጧቸው ያለውን መከፋፈል የማያውቁ ወታደሮችን በቤተመንግስቱ አካባቢ አስፍሯል::

በገዢው ፓርቲ ውስጥ ያለው መከፋፈል ወደ እርስ በ እርስ መበላላት ሊያደርስ እንደሚችል ከውስጣቸው የሚወጡ መርጃዎች ይጠቁማሉ::

The post በቤተመንግስት አካባቢ አለመተማመኑ በገሃድ እየታየ ነው * የቤተመንግስቱ ጠባቂዎች በሙሉ ወደ ቤንሻንጉል ተላኩ appeared first on Zehabesha Amharic.

ስለቤተክርስቲያን ዝም አንልም!!! –ከምእመናን የተላለፈ የትንሳዔ መልእክት

$
0
0

08/01/2007 ዓ.ም
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አኃዱ አምላክ አሜን

” በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ” ሐዋ.20፡28
eotc-members
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለረጅም ዘመናት አንድነቷን ጠብቃ ኖራለች፤እስካሁንም ደርሳለች። አሁን ባለንበት ዘመን ግን በአባቶቻችን ጳጳሳት መካከል በተፈጠረው መለያየትና መወጋገዝ የተነሳ አንድነቷ እየታወከ ተከታዮቿም እርስ በርሳቸው እየተለያዩ ይስተዋላል። በተለይም በውጪው ዓለም የሚኖሩ የቤተክርስቲያኗ አማንያን በሚያሳዝን ሁኔታ እርስ በርሳቸው ሲጣሉና ሲከፋፈሉ ማየት፤ በ አህዛብ ፊት መሳለቂያ መሆናችን ልብ ያደማል አንገት ያስደፋል። በለንደን ቅድስት ማርያም፣ በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል፣ በሚኔሶታ መድኃኔዓለም፣ በላስቬጋስ ቅዱስ ሚካኤል፣በቴናሲ፣ በስዊድን፣በጀርምን ፣ ወዘተ የታዩት መለያየቶች እጅግ አሳዛኝ ከስተቶች ናቸው። ለዚህ ሁሉ አሳዛኝ ሁኔታ መከሰት ደገሞ በግንባር ቀደምትነት ተጠያቂዎቹ አባቶቻችን ጳጳሳት ናቸው።

በክርስቶስ ምሳሌ የተሾሙበትን የሰላምና የአንድነት ተምሳሌትነት ትተው የተሰጣቸውን ታላቅ አደራና ኃላፊነት ዘንግተው ረብ ለሌለው ሥልጣን ሲሉ እርስ በርሳቸው በመለያየታቸው ምእመናኑም የዚህኛው እና የዚያኛው ወገን ደጋፊ ሆነው ክርስቶስ የሞተለትን ሰላም፣ አንድነትና ፍቅር ባደባባይ ሲያስነቅፉ ይስተዋላል።

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃሉ እነዳስተማረን እስከ መስቀል ሞት ያደረሰው የነገር ሁሉ ፍጻሜ ፣ የተግባራት ሁሉ ቁንጮና መጨረሻ የሆነው ፍቅር ነው። ፍቅር ኃያል ወልድን ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው እንዳለ ሊቁ።

እርሱ ራሱ አምላካችን ሕግጋትን ሁሉ በሁለት ከፍሎ አስቀምጧቸዋል። ፍቅረ እግዚአብሔር እና ፍቅረ ቢጽ/የባልንጀራ ፍቅር ብሎ ነው። የሚያስደንቀው ደግሞ የመጀመሪያው ሕግ ፍቅረ እግዚአብሔር የሚታወቀውና የሚገለጸው በፍቀረ ቢጽ ነው።

ፍቅረ ቢጽ ፍቅረ እግዚአብሔርንም ጨምሮ የያዘ ከሕገጋተ ሁሉ በላይ የሆነ ሕግ ነው። የሰው ልጅም በግርማ መለኮቱ ሲመጣ ፍጥረትም በፊቱ ለፍርድ ሲሰበሰብ የፍርድ ውሳኔ የሚተላለፈው በዚሁ በፍቅረ ቢጽ መመዘኛነት ነው። የተራበን ማብላት ፣የተጠማን ማጠጣት ፣ የታመመን መጠየቅ፣ የታሰረን መጎብኘት፣ ያዘነን ማጽናናት ፣የታረዘን ማልበስ፣ወዘተ እነኝሀን ነገሮች በማደረግና ባለማድረግ ነው ፍጥረት ሁሉ የሚጸድቀው ወይንም የሚኮነነው ።

” የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል።
ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና። ጻድቃንም መልሰው ይሉታል። ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ? እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ?ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን?ንጉሡም መልሶ። እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።” ማቴ. ም.25 ቁ. 31-40

እንግዲህ ፍቅር በተለይ ለክረስቲያኖች ይህን ያህል የመጨረሻ እጣ ፋነታችን የሚወሰነበት ከሆነ ሰላምን አንድነትን እና ፍቅርን ምን ያህል ልንጠብቅ እንደሚገባን ዘወትር ልብ ልንልና ልናስተውል ያሰፈልጋል። በጠቢቡም አድሮ እግዚአብሔር ስድሰት ነገሮችን እንደሚጠላ ሰባተኛውንም ነፍሱ ፈጽማ የምትጸየፈው መሆኑን ይህም በወንድማማቾች መካከል ጸብ የሚዘራውን እንደሆነ አበከሮ ተናገሯል።
“እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤
ትዕቢተኛ ዓይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥
በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር፣ በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።” ምሳሌ 6፡16-19።

በአንድ መቅደስ ውስጥ ሆነው ለብዙ አመታት በአነድነት እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ፣ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበሉ የነበሩ ሰዎችን አሁን ምን እና ማን ለያያቸው??? ይህን ያህልስ የኖሩበትን ቤተክርስቲያን ለማፍረስ ምን እዚህ አደረሳቸው? ክርስትና ያስነሱበትን ቤተክርስቲያን፣ያኢግዚአብሔር ማደሪያ የሆነውን ታቦት የለም አይሰራም፣ የተቀበሉትን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም ትክክል አይደለም ብለው እጅግ ከባድ የድፍረት ነገር እንዲፈጽሙ ያደረጋቸው ማነው? አላልንም አላደረግንም እንዳይሉ ፈጽሞ ከቤተክረስቲያን ሥርዓት በወጣ መልኩ በሥላሴ ላይ መድኃኔዓለምን ፣በሚካኤል ላይ ሚካኤልን ማድረጋቸው ሥራቸው ይመሰክርባቸዋል።

ሰዎች በጊዜ በተፈጠረ አንዳንድ ጊዚያዊ እና ጥቃቅን ነገሮች ላይ የሃሳብ መለያየት ቢኖራቸው ነገ ሁሉም ነገር የሚቀየር ነውና የዛሬውን የግድ ዛሬ እንደ እኛ ካላሰባችሁ ሊባሉ አይገባም። በተለይም በዚህ በአባቶች መለያየት ዙሪያ ባለው ሁኔታ ከዚህም ሆነ ከዚያ ወገን ያሉትን አባቶች እንደ አባትነታቸው ተቀብሎ ልዩነታቸውን እስኪያስወግዱና አንድ እስኪሆኑ ድረስ ዶግማና ቀኖና ያልሆነውን ኢምነት የስም መጥራት ነገር እንደ ትልቅ ጉዳይ ሆኖ ለምን ክርስቲያኖችን ይለያያሉ? ይህ አይነቱ የ አባቶች መጣላት በቀድሞ ጊዜም ይከሰት ነበር። በዚህም የተነሳ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ እነዲህ ያለ ነገር በተከሰተ ጊዜ ሰዎችን ሳይሆን አነዱን ጌታ ብቻ እንድንመለከት እንዲህ ሲል ይመክረናል።

” ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ በአንድ ልብና በአንድ አሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ። ወንድሞቼ ሆይ፥ በመካከላችሁ ክርክር እንዳለ ስለ እናንተ የቀሎዔ ቤተሰዎች አስታውቀውኛልና። ይህንም እላለሁ። እያንዳንዳችሁ እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ እኔስ የአጵሎስ ነኝ፥ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፥ እኔስ የክርስቶስ ነኝ ትላላችሁ። ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቀለን? ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠመቃችሁን?” ስለዚህ ሁላችን የቤተክርስቲያን ልጆች በስም መጥራትና አለመጥራት መከፋፈል አይገባንም። ደስ ያለው ደስ ያለውን ይጥራ። አንድነት እስኪመጣ የሁለቱንም ወገን አንጠራም ያሉም መልካም እንደቃሉ ይኑሩ።

አባቶችም እባካችሁ ስለመረጣችሁ አምላክ ብላችሁ ይህን መለያየት አስወግዱ። አንድነትን እና ሰላምን አሳዩን፤ አስተምሩን። ልጆች አባቶቻቸውን ነውና የሚመስሉት።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፤አሜን።

The post ስለቤተክርስቲያን ዝም አንልም!!! – ከምእመናን የተላለፈ የትንሳዔ መልእክት appeared first on Zehabesha Amharic.

8 የፖለቲካ ፓርቲዎች ራሳቸውን ከምርጫው ሊያገሉ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ (መግለጫውን ይዘናል)

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

በወላይታ ዞን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤት ዕጩዎችን ያቀረቡ 8 የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዞኑ እየደረሰባቸው የሚገኘው አፈና እና በደል መፍትሄ ካልተሰጠው ራሳቸውን ከመጭው ግንቦት 2007 ዓ.ም ምርጫ ራሳቸውን ሊያገሉ እንደሚችሉ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለዞኑ ምርጫ ማስተባበሪያ፣ ለምርጫ ቦርድና ሌሎች የመንግስት ተቋማት ባስገቡት ደብዳቤ አስጠንቅቀዋል፡፡
ከመጭው ምርጫ ራሳቸውን ሊያገልሉ እንደሚችሉ ያስጠነቀቁት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰማያዊ፣ የኢትዮጵያ ፍትሕና ዴሞክራሲ ሃይሎች ግንባር (ኢፍዴሃግ)፣ የወላይታ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ወሕዴግ)፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ (አትፓ)፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) ናቸው፡፡

ማስጠንቀቂያውን ያቀረቡት ፓርቲዎች ለምርጫ ምቹ የሆነ አጋጣሚ እንዳለ በሚዲያ የሚገለፀው ትክክል እንዳልሆነ፣ ያለ ገደብ መብት የሰጠው ገዥው ፓርቲ ሰሆን በእነሱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጫና እና በደል እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ በደብዳቤያቸው ገልጸዋል፡፡ ፓርቲዎቹ አክለውም ምህዳሩ እጅግ የጠበበ መሆኑን በየጊዜው አቤቱታቸውን ለምርጫ ክልሎችና ለጋራ ምክርቤት ቢያቀርቡም ምንም አይነት ምላሽ እንዳላገኙና በአባላቶቻቸው ላይ የሚፈፀመው በደል ከአቅማቸው በላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

‹‹የወረዳና የዞን የምርጫ አስተባባሪዎች የገዥውን ፓርቲ ድምጽ ከመስማት በስተቀር ምንም አይነት ውሳኔ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡›› ያሉት ፓርቲዎች በዚህም ምክንያት ምህዳሩ እጅግ መጥበቡንና ከችግር ላይ ችግር እየተደራረበ በመምጣቱ ከፍተኛ አደጋ ላይ መሆናቸውን በደብዳቤው ገልጸዋል፡፡

ፓርቲዎቹ ለጠቅላይ ሚኒስትር፣ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ለደቡብ ክልል ምርጫ ቦርድና ሌሎችም አገራቀፍና የክልሉ ተቋማት በላኩት ደብዳቤ:-
welayeta 1

welayeta 2

welayeta 3

The post 8 የፖለቲካ ፓርቲዎች ራሳቸውን ከምርጫው ሊያገሉ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ (መግለጫውን ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.


ሞያሌ ከትናንት ምሽት እስከ ዛሬ እኩለቀን ድረስ በተኩስ ተናጠች

$
0
0

ኢሳት ዜና :- የከተማዋ የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጹት ከትናንት ሰኞ ምሽት ጀምሮ እስከ ዛሬ ማክሰኞ እኩለቀን ድረስ ከተማዋ በተኩስ ስትናወጥ ውላለች።

Moyale Main Street (Photo file)

Moyale Main Street (Photo file)


አንዳንድ ነዋሪዎች እንደሚሉት የተኩሱ ልውውጡ የተካሄደው በመከላከያ ሰራዊት አባላት እና በሶማሊ ክልል ልዩ ሚሊሺያዎች መካከል ነው፡፡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት አንድ የክልል 5 ጠባቂ መግደላቸውን ተከትሎ፣ የክልሉ ልዩ ሃይል ሚሊሺያዎች በየሰዎች ቤት እየገቡ እቃዎችን ከመሰባበርና ከመዝረፍ በተጨማሪ ከተማዋን በተኩስ ሲበጠብጡዋት አድረዋል።

ጧት አካባቢ በአማርኛ ፣ በኦሮምኛና በሶማሊኛ የተጻፉ ወረቀቶች መበተናቸውን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ ጽሁፎቹ በከተማው ያሉትን ባንዶች ለመቅጣት መጥተናል የሚል ይዘት እንዳለው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በማግስቱ ለገዢው ፓርቲ ቅርበት አላቸው የሚባሉ ድርጅቶች ጥቃት ደርሶባቸዋል።

አንዳንድ ወገኖች እንደሚሉት የሶማሊ ክልል ተጣቂዎች ምሽት ላይ ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላትን አስቁመው በሚፈትሹበት ጊዜ፣ አንደኛው ለምን ትፈትሹታላችሁ በማለት ፈታሹን የገደለው ሲሆን፣ መረጃው በሶማሊ ክልል ታጣቂዎች ዘንድ በመድረሱ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ መነሳሳታቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የክልሉ ታጣቂዎች ሌሊት ላይ በወሰዱት እርምጃ ከገዢው ፓርቲ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የሚጠረጠሩ የንግድ ድርጅቶች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ማክሰኞ ጠዋት ደግሞ የከተማዋ የሶማሊ ተወላጆች የመከላከያን ድርጊት በመቃወም ወደ አደባባይ የወጡ ሲሆን፣ በመኪኖች እና በተለያዩ ድርጅቶች ላይ ባደረሱት ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶአል። የፌደራል ፖሊሶች ተከታታይ ጥይቶችንና አስለቃሽ ጪስ በመተኮስ ተቃውሞውን ለመቆጣጠር ቢችልም፣ ውጥረቱ እስከ ምሽት ዘልቋል። ትምህርት ቤቶች፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና የንግድ ድርጅቶች ተዘግተው ውለዋል።

የፌደራል ፖሊስ አባላት ከረብሻው ጋር እጃቸው አለበት ብለው የሚጠረጥሩዋቸውን ሰዎች ይዘው በማሰር ላይ ናቸው።

The post ሞያሌ ከትናንት ምሽት እስከ ዛሬ እኩለቀን ድረስ በተኩስ ተናጠች appeared first on Zehabesha Amharic.

በኢትዮጵያ የንግድ ሚዛን ጉድለቱ እየጨመረ ነው

$
0
0

ሚያዝያ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት ባለፉት አምስት አመታት ተግባራዊ ባደረገው የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሰረት ምርቶችን ውደ ውጭ በመላክ በያመቱ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለማግኘት አቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ በአምስቱ አመታት ውስጥ ያሳካው ሩቡን ያክል መሆኑን መረጃዎች አመልክተዋል።
national bank of ethiopia
መንግስት በያመቱ ከኤክስፖርት ከ2 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን እስከ 3 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዶ ሲንቀሳቀስ ቢቆይም፣ በአምስት አምት ውስጥ ያገኘው አጠቃላይ ገቢ ከ3 ቢሊዮን ዶላር ያልበለጠ ነው። በተቃራኒው መንግስት በአምስት አመቱ ውስጥ ወደ አገር ውስጥ ያስገባው ገቢ ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሲሆን፣ በአምስት አመቱ መጨረሻ የንግድ ሚዛን ጉድለቱ ከ8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ከፍ ብሎአል።

የወጪ ንግድ ገቢው ዝቅተኛ መሆን በአንድ በኩል የ5 አመቱ የልማት እቅድ ህዝቡን ሆን ብሎ ለማደናገር በምኞት ላይ ተመስርቶ የታቀደ መሆኑን ሲያመላክት፣ በሌላ በኩል ደግሞ እቅዱን ያወጡ ሰዎች ችሎታውና ብቃቱ የሌላቸው መሆኑን ኢኮኖሚስቶች ይናገራሉ።
የንግድ ሚዛን ጉድለቱ መስፋት የውጭ ምንዛሬ እጥረቱን ማባባሱንም ኢኮኖሚስቶች ይናገራሉ። ለጊዜው መንግስት እዳዎቹን ለመክፈል ከአይ ኤም ኤፍና ከሌሎች አበዳሪ ድርጅቶች ለመበደር ቢችልም፣ እዳው እየሰፋ ሲሄድ ለመከፍል የሚቸገርበት ሁኔታ እንደሚፈጠር ኢኮኖሚስቶች ይገልጻሉ።

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የንግድ ድርጅቶች በውጭ ምንዛሬ እጥረት የሚቸገሩትም በዚሁ የተነሳ መሆኑን ኢኮኖሚስቶች ይገልጻሉ።
በሌላ በኩል ደግሞ ባለፉት 5 አመታት አገሪቱ ወደ ውጭ ልካ ካገኘቸው አጠቃላይ ገቢ ይልቅ፣ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአንድ አመት ብቻ ወደ አገራቸው ከሚልኩት ጋር እኩል መሆኑ ፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአገሪቱ ኢኮኖሚ መሰረት መሆናቸውን ያሳያል። ባለፉት 5 አመታት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከ12 -15 ቢሊዮን ዶላር ወደ አገራቸው ልከዋል።

The post በኢትዮጵያ የንግድ ሚዛን ጉድለቱ እየጨመረ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

በደቡብ አፍሪካ በውጭ አገር ዜጎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንደቀጠለ ነው

$
0
0

south africaሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፉት ሁለት ቀናት በደቡብ አፍሪካዋ የቱሪስት ከተማ የደርባን ተወላጆች_የውጭ አገር ዜጎች ከአገራቸው እንዲወጡ ለማስገደድ በወሰዱት ጥቃት 3 ኢትዮጵያውያን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን አጇንስፍራንስፕሬስዘግቧል።

ኢትዮጵያዊያኑ ሱቆቻቸው ውስጥ እንዳለ በጋስ በተሞላ ቦንብ መቃጠላቸውን አንዳንዶች ተደብድበው መሞታቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል። በደርባንና አካባቢዋ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በጭንቅ ውስጥ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ቢቢሲ ባቀረበው ዘገባ ደግሞ አንድ ኢትዮጵያዊ አገራችን ችግር ላይ ነች፣ አገር የለንም የት እንደምሄድም አላውቅም ብሎአል።

የአሁኑ ተቃውሞ የዙሉ ባህላዊ ንጉስ ጎድ ዊል ዝዌልቲኒ የውጭ አገር ዜጎች ሻንጣዎቻቸውን ሸከፍው እንዲወጡ ትእዛዝ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ የተፈጠረ ነው። የፕሬዚዳንት ዙማ ልጅ በበኩሉ ” የውጭ አገር ዜጎች አገሪቱን በረጅም ጊዜ ሊቆጣጠሩዋት ይችላሉ” በሚል የሰጠው መግለጫ ለግጭቱ መባባስ አስተዋጽኦ ማድረጉ ተገልጿል። ማላዊ ዜጎቿን ከደቡብ አፍሪካ በማውጣት የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች።

Source:: Ethsat

The post በደቡብ አፍሪካ በውጭ አገር ዜጎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንደቀጠለ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት እና የአየር ሃይል የበረራ አስተማሪዎች ታሰሩ

$
0
0

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን ከፍተኛ የደህንነት ሃላፊዎች  ያስተላለፉትን ድንገተኛ ትእዛዝ ተከትሎ በፌደራል ፖሊስ አባላት የእጅ ስልኮችና የኢሜል አካውንቶች ላይ በተደረገ ፍተሻ፣ የተቃዋሚ መሪ ፎቶዎችን፣ አገራዊ ሙዚቃዎችንና ማንኛውም ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ጽሁፎች ከኢንተርኔት አውርደው በስልካቸው ላይ ያስቀመጡ ፖሊሶች ተይዘው የተወሰኑት ማእከላዊ ሲገቡ፣ የተወሰኑት ደግሞ ጃንሜዳ አካባቢ በሚገኝ እስር ቤት መታሰራቸውን የፖሊስ ምንጮች ገልጸዋል።

ethiopian airforceበድንገት የተደረገውን ፍተሻ ተከትሎ በአጠቃላይ ከ120 ያላነሱ ፌደራል ፖሊስ አባላት ሲታሰሩ፣ በፍተሻው በቀጥታ የተቃዋሚ መሪዎች ፎቶዎች ወይም ፖለቲካ ነክ የያዙ ጽሁፎች የተገኙባቸው 37 የሚሆኑ ፖሊሶች ማእከላዊ ተወስደው ታስረዋል።

ከ80 በላይ የሚሆኑት ደግሞ አጠራጣሪ የሆኑ ጉዳዮች አሉ በሚል ለተጨማሪ ምርመራ ጃን ሜዳ አካባቢ በሚገኝ ማቆያ እንዲታሰሩ ተደርጓል።

የፌደራል ፖሊስ አዛዦች የሚሰጡትን ትእዛዝ ላለመቀበል ያንገራግራሉ ተብለው አስቀድመው በተለዩ ፖሊሶች ላይ ደግሞ ክትትሉ መጨመሩን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በዚህም መሰረት በአርማጭሆና ሰሜን ጎንደር የጸረ ሽብር ግብረሃይል ሃላፊዎች የሆኑት ኢንስፔክተር ስንታየሁ፣ ሳጅን አበበ እና ም/ል ሳጅን ብርሃኑ ተይዘው ወደ ማእከላዊ ተወስደዋል።

በእስር ላይ የሚገኙት የግንቦት7 ዋና ጻሃፊ የአቶ አንዳርጋቸውን ፎቶ ግራፍ በብዙ ወታደሮች ሞባይል ስልኮች ላይ መገኘቱን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

ከድምጻውያን ደግሞ የቴዲ አፍሮ፣ የብርሃኑ ተዘራና የፋሲል ደሞዝ ሙዚቃዎችን ከኢንተርኔት አውርዶ ማዳመጥ ኢህአዴግን እንደመክዳት እያስቆጠረ ነው ተብሏል።

በተመሳሳይ ዜና  ድሬዳዋ ውስጥ በበረራ አስተማሪነት ይሰሩ የነበሩ ሁለት መኮንኖች ሰሞኑን ተይዘው ማእከላዊ መታሰራቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ስማቸውን እስካሁን ለማወቅ ባይቻልም፣ አብራሪዎቹ ቀድም ብሎ ከታሰሩት 4 አብራሪዎች ጋር ግንኙነት ነበራችሁ ተብለው መታሰራቸው ታውቋል።

የኤም 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር የበረራ አስተማሪ የነበረው የሻለቃ አክሊሉ መዘነ ወንድም ሰይፉ መዘነም ማእከላዊ ታስሮ በመሰቃየት ላይ ነው። የቀድሞው አንድነት ፓርቲ የአመራር አባል የነበረው መሳይ ትኩም ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰበት ነው።

ገዢው ፓርቲ በደህንት ተቋማት ላይ ያለው ጥርጣሬ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ እያለ መምጣቱን የሚናገሩት ምንጮች፣ ተጨማሪ ፍተሻዎች፣ ድንገተኛ ግምገማዎችና እስሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ይገልጻሉ።

የጥርጣሬው መነሻ ምን እንደሆነ በውል ለማወቅ አልተቻለም። ይሁን እንጅ ስራቸውን እየለቀቁ የሚጠፉ የፌደራል ፖሊሶች ቁጥር መጨመር ስርአቱን ስጋት ላይ ሳይጥለው እንደማይቀር ምንጮች  ይገልጻሉ።

The post በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት እና የአየር ሃይል የበረራ አስተማሪዎች ታሰሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአማራ ክልል ሊመደብ የነበረው የኮማንዶ ጦር እቅድ ተሰረዘ * አለመተማመኑ በርትቷል

$
0
0

(ምንሊክ ሳልሳዊ) – የመጭው ምርጫ ጋር በተያያዘ ስጋቱ እያየለበት የመጣው የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ አምባገነን ቡድን በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር እና በጎጃም ክፍለሃገራት ሊመድበው የነበረው የኮማንዶ ጦር እቅድ በጦሩ ውስጥ ያለውን ጉምጉምታ እና አለመተማመን ስላሳሰበው መሰረዙን እና ጦሩ ወደ ካምፕ እንዲመለስ መደረጉን ለጄኔራል ሰአረ መኮንን ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::

(ፎቶ ከፋይል)

(ፎቶ ከፋይል)


ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በጦሩ ውስጥ የተከሰተው አለመተማመን እና ሕዝቡ በጦሩ ላይ ጫና እንደፈጠረ እንዲሁም የከተማ ፖሊሶች የሕዝብ ወገንተኝነት ማሳየታቸው የፌዴራል ፖሊሶች ግምገማ የፈጠረው ችግር የደህንነቶች መክዳት የህዝቡ ለውጥ መሻት ተደማምሮ አለመተማመኖች በስርአቱ ውስጥ እየሰፋ እንዲሄድ አድርጎታል::በሰራዊቱ ውስጥ የተከሰተው አለመተማመን እየሰፋ እና እርስ በእርስ በጥርጣሬ መተያየት እየነገሰ መምጣቱ ሰራዊቱን በሕዝቡ መሃል ብናሰፍረው መሳሪያውን በመንግስት ባለስልጣናት ላይ ሊያዞር ስለሚችል በካምፕ እንዲቆይ እና በታትኖ ከአጋዚ ጦር ጋር መቀላቀል እና በተለያዩ አከባቢዎች ላይ እንዲመደብ የሚል ሃሳብ ቀርቧል::

የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ እየዳከረ በጠበንጃ ሃይል ሕዝብን ፈጅቶ ስልጣኑን ለማስረዘም እየሰራ መሆኑን ይታወቃል::ሰሞኑን የደረሱ መረጃዎች አዲስ አበባ በአጋዚ ጦር እና በፌዴራል ፖሊሶች እየተሸበረች መሆኗን መግለጹ ይታወሳል::

The post በአማራ ክልል ሊመደብ የነበረው የኮማንዶ ጦር እቅድ ተሰረዘ * አለመተማመኑ በርትቷል appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live