Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የፌዴራል ፖሊሶች እና የከተማዋ ፖሊሶች ከነሞባይል ስልካቸው ተገመገሙ ተፈተሹ ተሰረዙ

$
0
0

Federal p0ባሳለፍነው ቀናት ጀምሮ በፌዴራል ፖሊሶች እና በአዲስ አበባ ፖሊሶች ላይ ጠንከር ያለ ግምገማ እየተካሄደ መሆኑን ሲታወቅ የፖሊሶቹ ሞባይል ስልኮች ሳይቀሩ ድንገት በደህንነት ሃይሎች እየተፈተሹ እና አላስፈላጊ የተባሉ እና ለወያኔ የማይመቹ የተጫኑ ዘፈኖች ፎቶዎች እና የተለያዩ ዶክመንቶች ሲሰረዙባቸው የነበረ ሲሆን በርካታ ፖሊሶች በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ሲደረግ የተወሰኑ ደሞ ክትትል እንዲደረግባቸው ታዟል:ከስራቸው የታገዱ እና የታሰሩ እንዳሉም ተጠቁሟል::

በአዲስ አበባ ለከተማው ፓሊስና ለፊደራል ፓሊስ ድንገት የተጀመረው ገምገማ እረፍት አንዳይወጡ በእረፍት ላይ ያሉት እንዲመጡ ተደርጎ በድንገት ሞባይል ተሰብስቦ በውስጡ የተለያዩ በመንግስትና በባለስልጣን የሚያላግጡ ቀልዶች የቴዲ አፍሮ ከሊፕ የተገኝበት የአማርኛና የኦሮምኛ ሀይለኛ ቀሰቃሽ ዘፈኖች የተገኘበት ከተለያዩ ሰዎች ጋር የተላላኩት መልክቶች ተጎርጉረው የተገኙባቸው እንዳስፈላጊው እርምጃ እንደተወሰደባቸው ሲገለጽ የታገዱ የታሰሩ ደሞዛቸውን የተቀጡ ሲኖሩ ወደፊት በድጋሚ ቢገኝባቸው ትልቅ ችግር ሊፈጠርባቸው እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ተሰቷቸዋል::

የለውጥ ሃይሎች በወታደሩ እና በፖሊስ ሃይሉ ዙሪያ ጠንካራ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ያሉት የመረጃው አድራሾች ፖሊሶች የሚያቀናጅ ሃይል እና የሚያስተባብር ሃይል ማጣታቸው እንዲሁም እንደ ደርግ ሃይል ትበተናላችሁ ሌላ ስልጣኑን ቢይዝ በማለት የሚደረገው ማስፈራሪያ በወያኔ እየተደረገባቸው መሆኑ ስለሆነ ከለውጥ በኋላ በስራቸው እንደሚቀጥሉ እና ከለውጥ ሃይሎች ጎን ቆመው ይህንን አምባገነን ስር አት እንዲገረስሱ አስፈላጊ የሆነ የግንዛቧ ማስጨበጫ ስራዎች እንዲሰሩ አሳስበዋል::

The post የፌዴራል ፖሊሶች እና የከተማዋ ፖሊሶች ከነሞባይል ስልካቸው ተገመገሙ ተፈተሹ ተሰረዙ appeared first on Zehabesha Amharic.


ሰማያዊ ፓርቲ በሀድያ ዞን ቅስቀሳ እንዳያደርግ ተከለከለ

$
0
0

ሰማያዊ ፓርቲ ነገ መጋቢት 27/2007 ዓ/ም በሃድያ ዞን ሆሳና ከተማ ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ እንዳያደርግ መከልከሉን የሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡

(photo file)

(photo file)


የሰማያዊ ፓርቲ የሀድያ ዞን አስተባባሪዎች ፓርቲው ነገ መጋቢት 27/2007 ዓ.ም በዞኑ ከተማ ሆሳና ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ እያደረጉ በነበረበት ወቅት ‹‹በቅዳሜ ቀን ቅስቀሳ ማድረግ አትችሉም›› በሚል ስድስት የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን ጨምሮ ሌሎች አባላት ሲታሰሩ መኪናን ጨምሮ የመቀስቀሻ መሳሪያዎቻቸው በፖሊስ ተይዘውባቸው እንደዋሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ህዝባዊ ስብሳባው እውቅና ያለው በመሆኑና ለቅስቀሳም የሚያስፈልጉ ህጋዊ መስፈርቶችን ቢያሟሉም በህገ ወጥ መንገድ ታስረው እንደዋሉ የገለጹት ዕጩዎች፤ የመኪና፣ የሞንታርቮና የሌሎች ወጭዎችን አውጥተው ዕቅዳቸውን እንዳያሳኩ ካድሬዎች እንቅፋት እየፈጠሩናቸው እንደሚገኙና ህዝቡ ስብሰባውን እንዳይታደም መከባና መሰናክል እንደተፈፀመባቸው ገልጸዋል፡፡

ምንም እንኳ ለህዝባዊ ስብሰባው ቅስቀሳ እንዳያደርጉ ክልከላና እንቅፋት ቢፈጠርባቸውም ህዝባዊ ስብሰባው በነገው ዕለት ሆሳና ከተማ ውስጥ ጎፎር ሜዳ በተባለ ቦታ ከቀኑ 7 ሰዓት -11 ሰዓት ተኩል ድረስ እንደሚካሄድ የስብሰባው አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡

The post ሰማያዊ ፓርቲ በሀድያ ዞን ቅስቀሳ እንዳያደርግ ተከለከለ appeared first on Zehabesha Amharic.

የዘንባባው እሑድ –የሆሳዕና በዓል

$
0
0

ሔኖክ ያሬድ

የዘንድሮው ትንሣኤ በዓል ሊከበር አንድ ሳምንት ቀርቶታል፡፡ የሚያዝያን አራተኛ ቀንን ይጠብቃል፡፡ ዛሬ መጋቢት 27 ቀን ሆሳዕና ከእግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና ዋና በዓላት መካከል አንዱ ነው፡፡

ክርስቶስ ኢየሱስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም የገባበት ዕለት ይታሰብበታል፡፡ በወቅቱ ተሰባስበው የነበሩት የዘንባባና የወይራ ዝንጣፊ ይዘው በደስታ በዝማሬ ‹‹ሆሳዕና የዳዊት ልጅ›› እያሉ በምስጋና ተቀብለውታል፡፡
hosaena
‹‹ሆሳዕና›› የአራማይስጥ (አራማይክ) ቃል ሲሆን ፍችውም ‹‹አድነን›› ማለት ነው፡፡ በዕብራይስጥም በግእዝም ተመሳሳይ ፍች አለው፡፡ በዚያ ዘመን አይሁዶች በሮማውያን ቀንበር ውስጥ ወድቀው ነበርና ምድራዊ ንጉሥ መጥቶ ነፃ እንደሚያወጣቸውና እንደሚያድናቸው ይጠብቁ ነበር፡፡ በመጻሕፍት እንደተጻፈው፣ በዚሁ ቀን እንዲሁ እግዚእ ቤተ መቅደስ ውስጥ ገብቶ ሃይማኖት የንግድ ቦታ አይደለም በማለት ቁጣውን ያሳየበትና ነጋዴዎችንና ቀራጮችንም ያባረረበት ነበር፡፡

ቤተመቅደሱ የጸሎት ቤት መሆኑን ያወጀበትና ክብሩንም የገለጸበት ነው፡፡ የሆሳዕና ሥርዓት ዐቢይ ጾም በተጀመረ በስምንተኛው ሳምንት፣ ከትንሣኤ (ፋሲካ) አንድ ሳምንት በፊት የሚከበረው ሆሳዕና ከጌታ ዐበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ሆሳዕና እሑድ በሁለት ነገሮች ይዘከራል፡፡ አንደኛው በቅዳሴ ጊዜ ‹‹ያለ ሕማምና ያለ ደዌ፣ ያለ ድካምም ለከርሞም ያድርሰን ያድርሳችሁ›› እያሉ ካህናቱ ዘንባባ የሚያድሉበት ሲሆን፣ ሁለተኛው ካህናቱና ምዕመናኑ በቤተ ክርስቲያኑ ዙርያ የሚያደርጉት ዑደት ነው፡፡ ‹‹በታወቀችው በዓላችን መለከቱን ንፉ›› እያሉ የቅዱስ ያሬድ መዝሙር እየተዘመረ በዐራቱም ማዕዘናት ዕለቱን በተመለከተ ዐራቱ ወንጌላት እየተነበቡ ይከበራል፡፡

ዕለቱ የሰሙነ ሕማማት ዋዜማ ስለሆነና ሰሙነ ሕማማት ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረው ‹‹የዓመተ ፍዳ የዓመተ ኩነኔ›› መታሰቢያ ሳምንት በመሆኑ ጸሎተ ቡራኬ ለሙታን የፍትሐት ጸሎት ስለማይፈጸምበት በሆሳዕና እሑድ በሳምንቱ ውስጥ ለሚያርፉት የሚገባው ሁሉ አስቀድሞ ይፈጸማል፡፡

ከሆሳዕና በኋላ ከትንሣኤ በፊት ያሉት ሰሙነ ሕማማትና ዓርብ ስቅለት በተለይ በጾምና በስግደት የሚከበሩ ናቸው፡፡ በወይራ ቅጠል ጥብጠባ በማሳረጊያው ይደረጋል፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትውፊትና ሥርዓት መሠረት ከሆሳዕና ሰኞ እስከ ጸሎተ ኀሙስ ያሉት ቀናት ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበሩትን 5500 ዓመታት (አምስት ተኩል ቀናት) “የዓመተ ፍዳ” መታሰቢያ ሆነው ተሠርተዋል፡፡ ሆሳዕና ባህላዊ ገጽታዎች የሚታዩበት ነው፡፡ በሁሉም የአገሪቱ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ዐውደ ምሕረት ምእመናኑ እየተገኙ የዘንባባ ዝንጣፊ ከመያዝ ባሻገር፣ ከአዋቂ እስከ ሕፃን በዘንባባው ቅጠል ለጣታቸው ቀለበት፣ ለእጃቸው እንደ አልቦ፣ ለራሳቸው እንደ አክሊል የሚጠለቅ አድርገው ያዘጋጃሉ፡፡ ምዕመናኑም የመስቀል ምልክት በመሥራት በቤታቸው ይሰቅሉታል፡፡

በሆሳዕና እሑድ ኢየሱስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁነት በማስታወስ በአንዳንድ አድባራት ተመሳሳይ ሥርዓት ይከናወናል፡፡ በአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ ትርዒቱ የተካሄደው ከ109 ዓመት በፊት ነበር፡፡ ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ “የዘመን ታሪክ ትዝታዬ በዳግማዊ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት” በሚለው የትዝታ ድርሳናቸው እንደጻፉት፣ የሆሳዕና በዓል በአክሱም ሥርዓት ዓይነት ሆኖ እንጦጦ ላይ መከበር የተጀመረው በ1898 ዓ.ም መጋቢት 30 በሆሳዕና ዕለት ነው፡፡ ከአክሱም የመጡ አንድ መምህር ከበዓሉ ቀን ቀደም ብለው ጀምረው የሥነ ሥርዓቱን አፈጻጸም ለደብሩ ካህናትና ለሕፃናት መዝሙር አስጠንተዋል፡፡

በበዓሉ ዕለት አንዲቱን የበቅሎ ግልገል በወርቅ ጥልፍ የተለጠፈ ባለመረሻት (የበቅሎ የማዕርግ ልብስ፣ በልዩ ልዩ ሐሮች ተጠልፎ የተዘጋጀ ወርቀ ዘቦ) ኮርቻ ተጭኖባት ድባብ ደብበውላትና አጅበዋት ወደ ቤተ ክርስቲያን አመጡዋት፡፡ ዑደት ተደረገ፡፡ ከአክሱም የመጣው ያ የሆሳዕና በዓል ሥነ ሥርዓት ጃንሆይ ዳግማዊ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ መኳንንትም ሁሉ ባሉበት መከበሩ ተመዝግቧል፡፡

The post የዘንባባው እሑድ – የሆሳዕና በዓል appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለማሰልጠን አሰልጣኝ ቶም ቀዳሚው የውጪ ዜጋ?

$
0
0

tom national tea,
” ዋሊያዎቹን ለማሰልጠን ለፌዴሬሽኑ ማመልከቻ አስገብቻለሁ፤ ከ4 አመት በፊት የጀመርኩትን እንድጨርስ እድሉ ይሰጠኝ” —–>አሰልጣኝ ቶም ሴንትፊት

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶን ማሰናበቱ በይፋ ጋዜጣዊ መግለጫ ለስፖርት ቤተሰቡ ሳያሳውቅ የተለያዩ የአገር ውስጥ አሰልጣኞች በእጩነት መታሰባቸው መሰማቱ ይታወሳል። ለኢትዮ- ኪክ በደረሰው ታማኝ መረጃ መሰረት የቀድሞ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ቤልጂዬማዊው ቶም ሴንትፊት በእጩነት ለመወዳደር ማስረጃዎቻቸውን አንደላኩ በመስማታችን ጉዳዮን ለማጣራት አሰልጣኙን አነጋግረናል። እንድታነቡት እንጋብዛለን:–

ኢትዮ-ኪክ:- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለማሰልጠን ማሰረጃዎትን ለፌዴሬሽኑ እንዳስገቡ ሰምተን ነበር፤ የተባለው ነገር ምን ያህል እውነት ነው?
አሰልጣኝ ቶም:- የተባለው መረጃ ትክክል ነው። ኢትዮጵያን በጣም እወዳታለው። ስለዚህም ዶኩመንቶቼን ለፌዴሬሽኑ ሰሞኑን አስገብቻለው። በ2011 ኢትዮጵያ ጥሩ ጊዜ ነበረኝ።
ኢትዮ-ኪክ:- አሰልጣኝ ባሬቶ መባረራቸው እኮ በይፋ ፌዴሬሽኑ ለህዝብ ሳያሳውቅ እንዴት እርሶ ማመልከቻዎቱን ላኩ ?
አሰልጣኝ ቶም:- እኔ ከሳምንታት በፊት ጭምጭምታ ሰምቼ ነበር። ይሄ እንደሚሆን ደግሞ ከአንድ አመት በፊት አውቅ ነበር፣ በተጨማሪም ከፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለኝ። ስለዚህ ልኪያለው።
ኢትዮ-ኪክ:- ዋሊያዎቹን ድጋሚ የማሰልጠን እድሉን ቢያገኙ ምን የተለየ ነገር ለማድረግ አቅደዋል?
አሰልጣኝቶም:- በ2011 የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን ስረከብ የተሸነፈ ቡድን ነበር። በናይጄሪያ 4-0 እና በጊኒ 4-1 ነገር ግን ቡድኑን ከተረከብኩ በኃላ ከናይጄሪያ ጋር 2-2 አቻ ወጥተን በጊኒ ጠባብ ውጤት 1-0 ተሸነፍን። ከዛ ቀጥሎ ከማላዊ 0-0 ማዳጋስካርን 4-2 አሸንፈናል። የኢትዮጵያን ተጨዋቾችን አውቃለው፤ባህሉን እና አሰተሳሰባቸውን ስለዚህ ከአራት አመት በፊት የጀርኩት ስራ እንድጨርስ እድሉ ይሰጠኝ። የማሰልጠን እድሉን ካገኘው ደግሞ አላማዬ የማሰለጥነውን ቡድን ለAFCON የአፍሪካ ዋንጫ እና ለ2018 የአለም ዋንጫ ማብቃት ነው።
ኢትዮ-ኪክ:- ማሪያኖ ባሬቶም እኮ ለአፍሪካ እና ለአለም ዋንጫ ዋልያዎቹን አበቃለው ብለው ነበር ?
አሰልጣኝ ቶም:- ትክክለኛ አሰልጣኝ ከተገኘ ይቻላል።
ኢትዮ-ኪክ:- አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ትክክለኛ አሰልጣኝ አይደሉም እያሉኝ ነው?

አሰልጣኝ ቶም:- በዚህ ጉዳይ ላይ እኔ አሳብ ከመስጠት ብቆጠብ እና ጉግል ላይ መላሹን ማየት….
ኢትዮ-ኪክ:- ከአራት አመት በፊት ለምን ከስራዎት ተባረሩ?
አሰልጣኝ ቶም:- በ2011 ቡድኑ መልቀቅ መለየት አልፈለኩም፤ ነገር ግን የኢት.እግርኳስ ፌዴሬሸን በወቅቱ የምንከፍልክ ገንዘብ የለንም አሉኝ። ባለፈው አመትም ፈልጌ ነበር። እኔ በጣም ለቦታው የምመጥን አሰልጣኝ ነኝ። በአፍሪካም ሆነ በአውሮፖም በቂ ልምድ አለኝ። የ UEFA Pro የአሰልጣኝነት ፍቃድ አለኝ፤ በአለም ላይ አንድ አሰልጣኝ ሊኖረው የሚገባው ትምህር አለኝ። በ UEFA- A እና UEFA -B ዲግሪ ፤ የአካል ብቃት አሰልጣኝ ኮርስ ፤ Skill Development ስልጠና እና የስፖርትሳይኮሎጂ የዮኒቨርስቲ ዲግሪ አለኝ። በአፍሪካ የሚገኙ አምስት አገራት አሰልጥኛለው። ቁጥራቸው 37 የሚደርሱ በፊፋ እውቅና ባላቸው ጨዋታዎች ያሰለጠንኩት ቡድን አንድም በሜዳው የተሸነፈ የለም።

ኢትዮ-ኪክ:- ስለዚህ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለማሰልጠን ድጋሚ እድል ይሰጠኝ እያሉ ነው?
አሰልጣኝ ቶም:- አዎ !የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን በድጋሚ ማሰልጠን እፈልጋለው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአፍሪካ ሻምፖዮናዋ ናይጄሪያ ጋር ተጫውቶ ጥሩ ውጤት እንዲያመጣ ያደረኩኝ ነኝ ። በ2011 እኮ በFIFA ድህረገፅ እና ኪክ ኦፍ ደቡብ አፍሪካ ድህረገፅ ላይ ኢትዮጰያ በ2013 የአፍሪካ ዋንጫ እና በ2014 የአለም ዋነጫ ማጣሪያ እንደምታልፍ ቀድሜ ተነግሬ ነበር። ይህን ያልኩት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ጠልቄ ስለማውቀው ነው።
ኢትዮ-ኪክ:- የኢትዮ.እ ፌዴሬሽን ላስገቡት የአሰልጣኝነት ጥያቄ የሰጦት ምላሽ ካለ?
አሰልጣኝ ቶም: – የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ምላሹን እንኳን ገና አልነገሩኝም እየጠበኩ ነው።
ኢትዮ-ኪክ:- አሰልጣኝ ቶምን በአንባቢዎቼ ስም አመሰግናለው!

The post Sport: የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለማሰልጠን አሰልጣኝ ቶም ቀዳሚው የውጪ ዜጋ? appeared first on Zehabesha Amharic.

“በታሰርኩ ጊዜ አብረውኝ ለነበሩ ሁሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ”–በቀለ ገርባ ከቢቢኤን ራድዮ ጋር

$
0
0

አቶ በቀለ ገርባ ከእስር ቤት ከተፈቱ በኋላ ለቢቢኤን ራድዮ ቃለምልልስ ሰጥተዋል:: በቃለምልልሳቸውም ለሕዝቦች አብሮ መኖር መታገላቸውን አስታውሰዋል:: የከፈሉት መስዋዕትነት በክብር እንደሚመለከቱት ገልጸው በዚህም ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል:: አቶ በቀለ ሌሎች ጉዳዮችንም አንስተዋል ያድምጡት::

Bekele Gerba

The post “በታሰርኩ ጊዜ አብረውኝ ለነበሩ ሁሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ” – በቀለ ገርባ ከቢቢኤን ራድዮ ጋር appeared first on Zehabesha Amharic.

ታሪክ ይፋረደናል!

$
0
0

አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ
ቅዳሜ፤ መጋቢት ፳፮ ቀን ፳፻፯ ዓመተ ምህረት – 04/04/2015

እንደ እውነቱ ከሆነ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ገዥ ቡድን በእብሪት ተወጥሮ ሀገራችንን ሲጫወትባት፤ “እኛ የኔ ድርጅት! የለም የኔ ድርጅት!” “እኔ ልምራ እናንተ ተከተሉኝ! የለም እኔ ልምራ እናንተ ተከተሉኝ!” “እኔ እበልጣለሁ! የለም እኔ እበልጣለሁ!” እየተባባልን፤ በሌለ ሥልጣን ሽሚያ ልባችን ተወጥሮ፤ ዛሬ ትናንት፤ ነገ ደግሞ ዛሬ እየሆነ ዓመታትን አስቆጠርን። ለምን? የሀገር ጉዳይ እያንዳንዳችንን የሀገሯ ተወላጆች እኩል አይሸነቅጠንም? ምን እንስኪሆን ድረስ ነው የምንጠብቀው? በየድረገጹ የማነበው፣ በየፓልቶኩ ክፍል የማዳምጠው፣ በየሬዲዮኖች የሚተላለፈው፤ በአንድነት እስካልተነሳን ድረስ፤ ትግሉ አይሳካም! የነገውም ሂደት አያስተማምንም! ነው። ለምን በዚህ አውቶቡስ ሁላችን አንሳፈርም? ኧረ ተው! ታሪክ ይፋረደናል!
Tensaye
አሜሪካ ፈልጌውና ጓጉቼለት የመጣሁበት ሀገር አይደለም። የዴሞክራሲ ሥርዓቱ ናፍቆኝም አይደለም የመጣሁት። የተሰማራሁበት ትግል ሂደት ተሰናክሎ፣ ቀኑ ጨልሞብኝ፣ በሰደት ከነበርኩበት የኑሮ ዝግመት ማምለጫ ስለሆነልኝ ነበር። መጥቼ ደግሞ በአድናቆት ተውጬ ማንነቴን ረስቼ አልቧረቅሁበትም። በርግጥ ያገኘሁትን ዕድል በመጠቀም ኑሮዬን ገፍቻለሁ። ይኼው ከመጣሁ ሰላሳ ዓመታት አልፈዉኛል። የአሜሪካን የዴሞክራሲ ሥርዓት አካሄድ ስገነዘብ፤ ያላቸውን ድክመት ደግሞ በዚያው ጎን ለጎን አጢኛለሁ። ለሀገሬ ከማደርገው መሯሯጥ ጋር፤ በአሜሪካ ሀገር ያለሁበትን ሀገር የፖለቲካ ሀቅ ለማስተካከል፤ እንዲህ መሆን ሲገባው ለምን አልሆነም? እያልኩ ከማማረር አልቦዘንኩም። አሜሪካኖች የራሳቸውን የዴሞክራሲ አካሄድ “ፍጹም ወደ መሆን እያዘገምን ነው።” ብለው ነው የሚያምኑት። “ፍጹም ነው!” አይሉም። በምችለውና ባጋጠመኝ መንገድ ሁሉ፤ ይኼን ፍጹም ወደመሆን የሚጓዘውን ሂደታቸውን፤ በንቃት በመሳተፍ እየረዳሁ ነው።

አሁን በሀገራችን የኑሮ ሀቅ፤ የወሃ ጥማት፣ የምግብ ማጣት፣ በሰላም የገበያ አገልግሎት፣ የመንገድ አለመሠራት፣ የትምህርትና ሕክምና አለመስፋፋት፣ የመናገርና የመጻፍ፣ የመሰባሰብና ተቃውሞን የመግለጽ፣ የአድልዕና ሙስና መንገሥ፤ መሠረታዊ የኅብረተሰቡ ጥያቄዎች፤ የፖለቲካውን መድረክ ማዕከላዊ ቦታ አልያዙም። ለዚህ ተጠያቂ የሆነውን መንግሥት በመወንጀል ባንድነት የመነሳት ግዴታችንን በውል አልጨበጥነውም። በርግጥ ከአሜሪካ ጋር የኛን ሀገርና የኛን ሁኔታ እያወዳደርኩ አይደለም። አዎ እንደነሱ በሀብት የበለጸግን አይደለንም። ግን ይኼ ላለንበት ሁኔታ ወሳኝነት የለውም።

የሀብት ጉዳይ ከተነሳ፤ በሀብት ያልበለጸግን መሆናችን አዲስ አይደለም። ከሕዝቡ ጥቅምና ከሀገሪቱ ዕድገት ይልቅ የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም ቅድሚያ የሠጡ ገዥዎች በነበሩበት ዘመን፤ አጠቃላይ የሀገሪቱን እውነታ ፈትሸው፤ ለረጅሙ የወደፊት ብልጽግና በማቀድ እርምጃ ስላልወሰዱ፤ ድኅነቱ አብሮን ኖሯል። እዚህ ላይ አንዳንዶቹ ያደረጉትን የልብ አስተዋፅዖ በምንም መንገድ ልስት አልችልም። ከነዚህ መካከል ባገኘሁት ዕድል ሁሉ፤ መጽሐፍትን በማገላበጥ ለማወቅ ጥረት ከማደርጋቸው መሪዎች መካከል፤ አፄ ዘርዓ ያዕቆብንና አፄ ቴዎድሮስን እጠቅሳለሁ። በአፄ ቴዎድሮስ ዘመን ምን ነበር? ያሁኑስ ዘመን ከዚያ ዘመን በምን ይለያል?

ከአፄ ቴዎድሮስ ዘመን የአሁኑ ዘመን የሚለየው፤ ያኔ ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያ፤ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ትልቅ ክብር የነበራቸው ሲሆን፤ አፈሩ እንኳ ሳይቀር የተከበረበት ዘመን ነበር። አፄ ቴዎድሮስ፤ ከሕዝቡ በመጠቀ ደረጃ፤ ከራሳቸው የወቅቱ ክብር ይልቅ፤ የሀገራቸው እድገትና በአካባቢያቸው የተኮለኮሉት የውጭ ጠላቶች እንቅስቃሴ፤ የዕለት ተዕለት ጭንቀታቸው ነበር። የተበታተነች ኢትዮጵያን ለመመለስና የቀድሞ ቦታዋን ለማስያዝ የሕይወታቸው ዋና ማዕከላዊ ትርጉም አድርገው ጣሩ። ለራሳቸው የስም ማስጠሪያ ግንብ ወይንም ቤተክርስትያን ከማሠራት ይልቅ፤ ለሀገራቸው መጠበቂያ የጦር መሣሪያ እንዲያበጁላቸው ነበር የውጭ ሀገር ሰዎችን የጠየቋቸው። ምንም እንኳ አሁን ምሁር ነን ባዮች፤ የአፄ ቴዎድሮስ ጠላቶች በውጭም ሆነ በውስጥ የነበሩት የጻፉትንና ያሉትን ተሸክመው ቢይጥላሏቸውም፤ እኒህ መሪ በተወለዱበት ዘመንና በቦታው የነበራቸውን የፖለቲካ ድርሻ አጢነው ቢመረምሩ፤ ከማንም መሪ የበለጠ ሊያደንቋቸው በተገባ ነበር።

የበዕደ ማርያም መምህሬ ዶክተር ገብሩ አስራት ለቀረበላቸው ጥያቄ የሠጡት መልስ እጅግ በጣም አርክቶኛል። ከነበሩት መሪዎች ሁሉ አንደኛ አድርገው የሚያደንቁትን ቃለ መጠይቅ አቅራቢዋ እንድትነግራቸው ስትጠይቃቸው፤ ያለምንም ማመናታት “ፄ ቴዎድሮስ ናቸው!” በማለት በኩራት አስቀምጠውላታል። ልክ ድሮ ሲያስተምሩኝ እንዳደነቅኋቸው ሁሉ፤ አሁንም መምሬ ሆነው አገኘኋቸው። ከመሬት ተነስተው፤ ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት ሀገራዊ ሕልውና፤ የመሠረቱን ደንጋይ ያስቀመጡ አፄ ቴዎድሮስ ናቸው። ከግለሰብ ማንነታቸው ይልቅ፤ የሀገራቸው መሪነታቸው ነበር ልባቸውን የሞላው። ያኔ በሕዝቡም መካከል፤ ከግለሰብ ምንነታችን ይልቅ የስብስብ ማንነታችን ማዕከላዊ ቦታውን የያዘ ነበር። ዛሬ በኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያዊነት አፈር የተንከባለለበት፤ ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ኢትዮጵያዊ አለመሆን የተወደደበት፣ ከኢትዮጵያዊያን ስም ይልቅ የውጪ ሀገር ስሞች የተመረጡበት፣ ከራሳችን ቋንቋ ይልቅ የውጪ ቋንቋ፣ ከራሳችን እምነት ይልቅ የውጪ እምነት፣ ከራሳችን ምግብ ይልቅ የውጪ፤ ባጠቃላይም ከራሳችን ማንነት ይልቅ የውጪውን መቅዳትና መስሎ መገኘት የጎላበት ክስተት፤ ሀቅ ሆኖ ይታያል። ለምን? ዋናውን ማዕከላዊ ቦታ ይዞ በተጠያቂነት የቆመው ያለው ገዥ ቡድን ነው። ዋና ሥራዬ ብሎ የያዘው፤ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ማጥፋት ነው። ይኼንንም በትውልድ ማንነት ተክቶታል። እናም ከራሱ የገማን አሣ . . . እንደሚባለው ቆርጦ መጣል ያለበት ገዥው ክፍል ነው።

አሁንም ያኔም ኢትዮጵያዊነት፤ ኢትዮጵያዊነት ነው። አሁን ግንዛቤያችን ፈሩን ለቋል። የብሔር ብሔረሰብ ጥያቄ የፖለቲካውን ማኅደር አጥለቅልቆታል። ምኑም ሆነ ምኑ የሀገራችን ሀቅ፤ ከዚህና ከዚህ ብቻ እንዲታይ ተደርጓል። ይህ ደግሞ በገዥው ክፍል ብቻ ሳይሆን በታጋዩም ወገን ያለ እውነታ ነው። በዚህ ተለጉመን፤ መሠረታዊ የመኖርና ያለመኖር የሕልውና አምዶች፤ ቦታ ተነፍገዋል። የፍትኅ መጓደል፣ የትምህርት ጥራትና ዕድገት ወደ ታች ማሽቆልቆል፣ የሕክምና አለመሟላት፣ የምግብ እጥረትና ረሃብን የመቋቋም ዕቅዶች አለመኖር፣ የሴቶችን እኩልነት አለመቀበልና ተሳትፏቸውን አለማሳደግ፣ አድልዕና ሙስና፤ እነዚህ መሠረታዊ የሕልውና ጥያቄ ናቸው። መስመሩ የተዘጋበት የውሃ ፈሰስ፤ ዙሪያውን ይዳስሳል። የተገደበበትን መዝጊያ መጋፋቱን፤ በጎን መፋሰሻ ከመፈለግ ጋር በእኩል ይዳስሳል። ተገድቤያለሁ ብሎ ተስፋ በመቁረጥ አይረጋም። ከግድቡ ጋር ብቻም አይታገልም። ዙሪያውን በሙሉ ነው ጥረት የሚያደርገው። በግድቡ አናት፣ በግድቡ ሥር፣ ከታቆረበት ዙሪያ ይውዘገዘጋል። የታፈነ በመሆኑ ቦርቅቆ ለመውጣት ይፍጨረጨራል።

ወገኖቻችን በየበረሃው መንገላታታቸው፣ እህቶቻችን በአረብ ሀገሮች መጎሳቆላቸው፣ በገዛ ሀገራቸው ወገኖቻችን መፈናቀላቸው፣ በገዛ ሀገራቸው ወንድምና እህቶቻችን በረሃብ ተጠምደው ለማኝና ሀገሪቱ በሞላ የውጭ ሀገር ምጽዋተኛ መሆናቸው፤ አእምሯችንን በማስጨነቅ የፖለቲካ ምኅዳሩን ሊያናጉት ይገባል። በርግጥ በአሁኑ ሰዓት የፖለቲካ ውይይቱ ተጧጡፏል። ይህ በምን ዓይነት ውጥረት ላይ መሆናችንን አመልካች ነው። ነገር ግን መፍትሔ አፈላለጉ ላይ ለየብቻ እየሮጥን ነው። ለየብቻ ሮጦ የግብ መሰመሩ ላይ ለየብቻ ነው የሚደረሰው። ታዲያ ምን ዋጋ አለው? ግቡ የማንም ግለሰብ ወይንም ቡድን የግል መኖሪያ አይደለም። የሁላችንም ነው። ባንድ ላይ መሯሯጥ አለብን። የተጎተቱ ካሉ፤ አብረን መሳብና መሳሳብ እንጂ፤ እኔ ቀድሜ ሄጄ እሸለማለሁ ወይንም ሌሎችን እጎትታለሁ የሚባልበት አይደለም። አብረን ስንነሳ፤ ቀዳሚ ሆነው የቆሙት ሲመሩ፤ የተጎተቱት ደግሞ ሲከተሉ፤ ባንድነት ከግባችን እንደርሳለን። ታሪክ ደግሞ ከኛ ጋር አብሮ ይኖራል። ተወቃሽ አያደርገንም። ከታሪክ ተወቃሽነት መዳን አለብን። በሕይወት እስካለን ድረስ፤ ሆዳችን መሙላቱን ሳይሆን፤ በሕይወት የኖርንበትን ወቅት ትርጉም መሥጠቱ ላይ ማተኮር አለብን። ቆመን እንቆጠር። አብረን እንሰለፍ። eske.meche@yahoo.com

The post ታሪክ ይፋረደናል! appeared first on Zehabesha Amharic.

(መልካም ዜና) የፋሺሽቱ የግራዚያኒ ኃውልት ስያሜ እንዲወገድ ውሳኔ ተላለፈ

$
0
0

ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ – የኢትዮጵያ ጉዳይ
4002 Blacksmith Drive, Garland, TX 75044; Tel: (214)703 9022
www.globalallianceforethiopia.org; E-mail: info@globalallianceforethiopia.com

ጋዜጣዊ መግለጫ
የፋሺሽቱ የግራዚያኒ ኃውልት ስያሜ መወገድ

እንደሚታወቀው፤ “የኢትዮጵያ ጨፍጫፊ” በመባል ለሚታወቀው ለሮዶልፎ ግራዚያኒ፤ አፊሌ በምትሰኝ የኢጣልያ ከተማ አንድ የመታሰቢያ ኃውልትና መናፈሻ ተቋቁሞለት፤ የቫቲካን ተወካይ በተገኙበት፤ እ.አ.አ. በነሐሴ 2012 ተመርቆለት ነበር። በኢትዮጵያ ላይ እጅግ አስከፊ የጦር ወንጀል በማስፈጸም ለታወቀው ፋሺሽት ይህንን የመስለ ተግባር ተቀባይነት ስለ ሌለው ማሕበራችን፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ፤ በሚገኙ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንዲሁም በመንፈሳዊና በሌሎችም ድርጅቶች ድጋፍ ጭምር ተቃውሞውን በልዩ ልዩ መንገድ ሲገልጽ ከርሟል።

Graziani (left) is seen here with German Field Marshal Albert Kesselring in October 1944

Graziani (left) is seen here with German Field Marshal Albert Kesselring in October 1944


ጥረቱም ሁሉ፤ በቸሩ የኢትዮጵያ አምላክ እርዳታ፤ መልካም ውጤት ማስገኘት ጀምሯል። ባለፈው ወር፤ እ.አ.አ. መጋቢት 13 ቀን 2015 አፊሌ ከተማ የምትገኝበት የላዚዮ አውራጃ ምክር ቤት ባሳለፈው ውሳኔ የግራዚያኒ ስያሜ በ15 ቀን ውስጥ እንዲወገድ፤ አለበለዚያ ለመታሰቢያ ኃውልቱ የወጣው ገንዘብ እንዲመለስና ተጨማሪ እርምጃም እንደሚወሰድ ገልጿል። የውሳኔውን ዋና ዋና ነጥቦች ከዚህ በታች መመልከት ይቻላል።

በዚህ አጋጣሜ፤ ስለ ኃውልቱ ለተገኘው መልካም ውጤት በድጋፋቸው ለተባበሩት ሁሉ ማሕበሩ ጥልቅ ምሥጋናውን በትሕትና ይገልጻል።
የላዚዮ አውራጃ ኦፊሴያላዊ መግለጫ፤ (ቁ. 24/1) ዋና ዋና ነጥቦች
(ዶር. ግርማ አበበ በኢጣልያንኛው ሰነድ መሠረት በእንግሊዝኛ ባቀረቡት መሠረት)
ጉዳዩ፤ የአፊሌ ከተማ ማሕበራዊ ምክር ቤት ለማርሻል ሮዶልፎ ግራዚያኒ አፌሌ
ስለ መረቀው ትንሽ የሚሊታሪ ሚዩዚየም፤ እ.አ.አ. ሐምሌ 21 ቀን 2012
ያስተላለፈውን ውሳኔ እንዲሰርዝ የቀረበ ጥሪ፤

በላዚዮ አውራጃ የተወሰደ እርምጃ
እ.አ.አ. መጋቢት 13 ቀን 2015
እ.አ.አ. ሕዳር 11 ቀን 2004 የወጣውን የላዚዮን አውራጃ ሕግና ሌሎችንም ጉዳዮች በመመልከት፤
በተጨማሪም እ.አ.አ. በየካቲት 18 ቀን 2002 የወጣውን የክልሉን ሕግ በማስታወስ፤

የአፊሌ (ከተማ) ማሕበረሰብ ምክር ቤት እ.አ.አ. በሐምሌ 21 ቀን 2012 አንድ ትንሽ የሚሊታሪ ሚዩዚየም ለማርሻል ሮዶልፎ ግራዚያኒ እንዲመረቅ የወሰነ መሆኑን በማሰብ፤ ሮዶልፎ ግራዚያኒ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የወንጀለኞች ዝርዝር የተመዘገበ፤ በሰዎች ላይ የመርዝ ጋዝ የተጠቀመና በኢትዮጵያ የቀይ መስቀል ሆስፒታል በቦምብ እንዲደበደብ ትእዛዝ ያስተላለፈ በፋሺሽት ኢጣልያ ቁልፍ መሪ የነበረ መሆኑን በማስታወስ፤

የአፊሌ ማሕበረሰብ ምክር ቤት ትንሹን የሚሊታሪ ሚዩዚየም ለማርሻል ሮዶልፎ ግራዚያኒ በመመረቅ ያስተላለፈውን ውሳኔ እንዲሰርዝ፤ ይህንንም ተግባር፤ የላዚዮ ባለሥልጣን እ.አ.አ. በመጋቢት 13 ቀን 2015 ከወሰነበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀኖች ውስጥ እንዲፈጽም ታዟል።
የማሕበረሰቡ ምክር ቤት ውሳኔውን እንዲሰርዝ የተላለፈለትን ትእዛዝ በተፈቀደለት ጊዜ ውስጥ ካላጠናቀቀ፤ ለትንሹ የሚሊታሪ ሚዩዚየም መሥሪያ በአውራጃው ባለሥልጣን የተሰጠውን ገንዘብ እንዲመልስ ይጠይቃል።

በመጨረሻውም፤ የአፊሌ ማሕበረሰብ ምክር ቤት በአውራጃው ባለሥልጣን የተጠየቀውን ሳይፈጽም ቢቀር፤ ባለሥልጣኑ ጉዳዩን፤ የአፊሌ ከተማ ምክር ቤትን ውሳኔ፤ ወደ ፍርድ ለማቅረብ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል።

ማሳሰቢያ፤ ፋሺሽት ኢጣልያ በውድ ሐገራችን በኢትዮጵያ ላይ በፈጸመችው የጦር ወንጀል ስለ ተጨፈጨፉት አንድ ሚሊዮን ወገኖቻችን፤ ስለ ወደመውና ስለ ተዘረፈው ንብረት ተገቢው ፍትሕ፤ ብቁ የሆነ ካሣና ይቅርታ የመጠየቅ ተግባር እንዲከሰት በመከናወን ላይ ስላለው ጥረት ዝርዝሩን በwww.globalallianceforethiopia.org መመልከት ይቻላል።

The post (መልካም ዜና) የፋሺሽቱ የግራዚያኒ ኃውልት ስያሜ እንዲወገድ ውሳኔ ተላለፈ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሰማያዊ ፓርቲ በወልዲያ እና በሆሳዕና ሕዝባዊ ስብሰባዎችን አደረገ

$
0
0

ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተሳኩ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማድረጉን አስተባባሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ፓርቲው ቅዳሜ መጋቢት 26/2007 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ቀኑ 7 ሰዓት በወልደያ ከተማ፣ እንዲሁም እሁድ መጋቢት 27/2007 ዓ.ም በሆሳና ከተማ ከ7 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት ተኩል ህዝባዊ ስብሰባዎችን በማድረግ አማራጩን ለህዝብ እንዳቀረበ የስብሰባዎቹ አስተባባሪዎቹ ገልጸዋል፡፡
semayawi party
ወልደያ ከተማ ላይ ለተካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ዝግጅት ወቅት የገዥው ፓርቲ ካድሬዎችና ፖሊስ ከፍተኛ ጫና እንዳደረገባቸው የገለጹት የፓርቲው የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ወረታው ዋሴ በቅስቀሳ ወቅት ፖሊሶች ‹‹ቅስቀሳ በይፋ መፈቀዱን የምናውቀው ነገር የለም›› በሚል በቅስቀሳ ላይ የተሳተፉትን አባላት በማወከብ እንቅፋት እንደፈጠሩባቸው ገልጸዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር የከተማውን ከንቲባ ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት ሰማያዊ ስብሰባ ያደረገበት አዳራሽ በር ድረስ በመምጣት ወደ ስብሰባው የሚገባውን ህዝብ ለማሸማቀቅ እንደሞከሩ ገልጸውልናል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ስብሰባውን እንዳያደርግ ከገዥው ፓርቲ ካድሬዎች የተፈፀመበትን ወከባና እንቅፋት ለምርጫ ቦርድ ቢያሳውቅም የምርጫ ቦርድ ተወካዮች ምንም ማድረግ እንዳልቻሉ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ይህም ሆኖ ሰማያዊ ፓርቲ ከ250 በላይ ህዝብ የተገኘበት ስኬታማ ህዝባዊ ስብሰባ እንዳደረገ አቶ ወረታው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ሰማያዊ ፓርቲ እሁድ መጋቢት 28/2007 በሀድያ ዞን ሆሳና ከተማ ጎፈር ሜዳ ላይ የአደባባይ ደማቅ ህዝባዊ ስብሰባ እንዳደረገ የሰማያዊ ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ተሰማ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ምንም እንኳ የገዥው ፓርቲ ካድሬዎችና ፖሊስ በቅስቀሳ ወቅት አባላትን በማሰር፣ የመኪና ቅስቀሳዎችን በማደናቀፍ እንቅፋት ለመፍጠር ቢሞክሩም የሆሳና የሰማያዊ ፓርቲ ቅርንጫፍ ባደረገው ጥረት ከ500 በላይ ህዝብ የተገኘበት ስኬታማና ደማቅ ህዝባዊ የአደባባይ ስብብሰባ አድርገናል›› ሲሉ አቶ ሰለሞን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ህዝባዊ ስብሰባዎቹ የሰማያዊ ፓርቲን የምርጫ ቅስቀሳ አካልና አማራጩን ለህዝብ ያስተዋወቀበት እንደሆኑ የገለጹት ኃላፊዎቹ በገዥው ፓርቲ በኩል ህገ ወጥ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነና እነዚህ ህገ ወጥ ተግባራት መቆም እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡ ‹‹አስፈጻሚው ኃይል ለህገ ተገዥ አይደለም፡፡ በማናለብኝነት የመምረጥና አማራጭ የማቅረብ መብት እየተደፈጠጡ ነው›› ያሉት አቶ ወረታው ዋሴ አሁንም ሰማያዊ ፓርቲ ገዥው ፓርቲ ለህግ ተገዥ እንዲሆን የበኩሉን ጫና እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡

አቶ ሰለሞን በበኩላቸው ‹‹አፈናውን ተቋቁመን ህዝቡ ሰማያዊ ጎን እንደቆመ ለማሳየት ችለናል፡፡ ህዝቡ በገንዘብ፣ በሞራልም ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን እንደሚቆም አሳይቶናል፡፡ እኛም ዜጎች ያለ መድሎ የሚኖሩበት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንደምንመሰርት ቃል የገባንበት ነው›› ብለዋል፡፡

The post ሰማያዊ ፓርቲ በወልዲያ እና በሆሳዕና ሕዝባዊ ስብሰባዎችን አደረገ appeared first on Zehabesha Amharic.


“ሰዎች በውስጥ ባለህ ነገር ሳይሆን በውጭ አለባበስህ ነው የሚለኩህ”–ብርሃኑ ተዘራ (ከታማኝ ሾ ጋር)

$
0
0

ተወዳጁ ድምፃዊ ብርሃኑ ተዘራ ከታማኝ ሾው ጋር ያደረገው ሁለተኛ ክፍል ቃለምልልስ ተለቋል:: በቃለምልልሱም አዳዲስ ነገሮችን ተናግሯል:: “በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የምሳተፈው በአስተዳደጌ የተነሳ ነው” ይለናል:: ያድምጡት::

“ሰዎች በውስጥ ባለህ ነገር ሳይሆን በውጭ አለባበስህ ነው የሚለኩህ” – ብርሃኑ ተዘራ (ከታማኝ ሾ ጋር)

The post “ሰዎች በውስጥ ባለህ ነገር ሳይሆን በውጭ አለባበስህ ነው የሚለኩህ” – ብርሃኑ ተዘራ (ከታማኝ ሾ ጋር) appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢንጂነር ይልቃል “የጠመንጃው ትግል ሰላማዊ ታጋዮችን ከማስበላት ውጭ በ24 ዓመታት ውስጥ ያመጣው ለውጥ የለም”አሉ

Next: Hiber Radio: “በሳዑዲ አረቢያው ላይ እንደተደረገው በየመን ላሉ ኢትዮጵያውያን መጮህ አለብን ተባለ.. የቻይና የባህር ሀይል አባላት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከየመን ከ200 በላይ የ10 አገር ዜጎችን ታደጉ…አቶ እንዳርጋቸው ፅጌን ለማስለቀቅ የእንግሊዝ መንግስት ዛሬም ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየ.. የግብጹ ሚድያ ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያና ሱዳን ጋር የፈረሙትን ፊርማ የግብፅን ህዝብ አይወክልም አለ…የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ልደት ፕሮፌሰር መስፍንን ጨምሮ የተለያዩ የተቃዋሚ መሪዎችና ጋዜጠኞች በተገኙበት ተከበረ…እና ሌሎችም
$
0
0

Hiber Radio Interview with Eng Yilkal Getnet
ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በቦስተን ለኢትዮጵያውያን በስካይፕ ባደረጉት ንግግር የጠመንጃ ትግል ለ24 ዓመታት ተደርጎ አንዳችም ውጤት አላመጣም ሲሉ ተናገሩ:: ኢንጂነሩ በንግግራቸው በጠመንጃ ይደረጋል የተባለው ትግል ሰላማዊ ታጋዮችን ከማስበላት ውጭ ያመጣው ውጤት የለውም ብለዋል::

‹‹ሰላማዊ ትግል አያዋጣም የሚባለው ትክክል አይደለም፡፡ ጠመንጃ ያወጣል የሚሉት የራሳቸውን መንገድ መምረጥ መብታቸው ነው፡፡ ነገር ግን ለ3000 አመት የጠመንጃ ትግል ውስጥ ነን፡፡ ግን ምንም አይነት ውጤት አላመጣም፡፡ ለ24 አመት የጠመንጃ ትግል አለ፡፡ ግን አንድ ቀበሌ ሲቆጣጠር አላየንም፡፡ እንዲያውም ብዙዎቹን ሰላማዊ ታጋዮች አስበልቷል፡፡ ይህ ሁሉ ፖለቲከኛና ጋዜጠኛ የታሰረው ሰላማዊ ትግሉ ስጋት ስለፈጠረበት ነው፡፡ ይህንን ስንል ግን ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ ለትግሉ ቅን ናቸው ከሚል አይደለም›› የሚሉት ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹ሰማያዊ ትግሉ የፖለቲከኞች ሳይሆን የህዝብ እንዲሆን እየሰራ ነው፡፡›› ብለዋል::

‹‹ዋጋ በከፈልን ቁጥር ይህ የከፈልነው ዋጋ ወደ ህዝብ እየወረደ እየበዛን እየመጣን ነው፡፡ እነ እስክንድርና እነ አንዱዓለም ሲታሰሩ እኔ የግል ስራዬን ነው የምሰራ ብዬ ትግሉን ብተወው፣ ሌሎቹም እንደዛው ቢያደርጉ ተስፋ ያስቆርጥ ነበር፡፡ አሁን ግን እየተበራከትን ነው፡፡ አንድነትን ሲያፈርሱት አባላቱ ከትግሉ አልሸሹም፡፡ እናም የምንከፍለው ዋጋ እየባከነ አይደለም፡፡›› ያሉት የሰማያዊ ፓርቲው ሊቀመንበር ‹‹እኛ ሊያስሩን ይችላሉ፡፡ ከምርጫው ወጥተዋል ብለው ሊያወሩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ይህ ለራሳቸው ነው የሚብቸው፡፡ በደላቸው ይበልጡንም የሚያጠናክር ነው የሚሆነው፡፡ ዛሬ ስልጣኑ ላይ ቢሆኑም አፈናው በእነሱ ጩኸት እንዲበዛባቸው የሚያደርገው፡፡ ነውረኛ ተግባራቸው ይበልጡን እህልና ቁጭት ይፈጥራል እንጅ ከትግል አያባርረንም፡፡›› ብለዋል::

‹‹እኛ የምንለው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ይደረግ ነው፡፡ ኢህአዴግ እኛ በምርጫ ስም ብጥብጥ እንደምንፈጥር ነው የሚሰጋው፡፡ ነገር ግን ይህ እነሱ የሙፈሩት ነገር የሚመጣው እነሱ ሲፈሩና ይበልጡንም ነገሮችን ሲያበላሹ ነው፡፡ ህዝብ በገዥውም ሆነ በተቃዋሚዎች ተስፋ ሲያጣ ያንን መንገድ መምረጡ አይቀርም፡፡ እኛ ይህ ችግር እንዳይከሰት ነው እየሰራን ያለነው፡፡›› ያሉት ኢ/ር ይልቃል ፓስፖርታቸው ካልተመለሰ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ተይዞላቸው የነበረው ስብሰባ በስካይፕ እንደሚቀጥል ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ጠቁሟል::

The post ኢንጂነር ይልቃል “የጠመንጃው ትግል ሰላማዊ ታጋዮችን ከማስበላት ውጭ በ24 ዓመታት ውስጥ ያመጣው ለውጥ የለም” አሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

Hiber Radio: “በሳዑዲ አረቢያው ላይ እንደተደረገው በየመን ላሉ ኢትዮጵያውያን መጮህ አለብን ተባለ.. የቻይና የባህር ሀይል አባላት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከየመን ከ200 በላይ የ10 አገር ዜጎችን ታደጉ…አቶ እንዳርጋቸው ፅጌን ለማስለቀቅ የእንግሊዝ መንግስት ዛሬም ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየ.. የግብጹ ሚድያ ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያና ሱዳን ጋር የፈረሙትን ፊርማ የግብፅን ህዝብ አይወክልም አለ…የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ልደት ፕሮፌሰር መስፍንን ጨምሮ የተለያዩ የተቃዋሚ መሪዎችና ጋዜጠኞች በተገኙበት ተከበረ…እና ሌሎችም

$
0
0
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ መጋቢት 28 ቀን 2007 ፕሮግራም

ዶ/ር መራራ ጉዲና የመድረክ ምክትል ሊቀመንበር እና የውጭ ግንኙነት ሀላፊ ስለ ናይጀሪያው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጠይቀናቸው ከሰጡን ማብራሪያ

<...>አቶ ወረታው ዋሴ የሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ሃላፊና ለፓርቲው የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት እጩ(ሙሉውን ያዳምጡት)

<...>ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከሳውዲ ጅዳ

በኬኒያ የደረሰው የአልሸባብ የሽብር ጥቃት (ልዩ ዘገባ)

ባሻ ይገዙ (ልዩ ግጥም)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በጣሊያን የፋሽስት የግራዚያኒ ስም እንዲሰረዝ ታዘዘ

አቶ እንዳርጋቸው ፅጌን ለማስለቀቅ የእንግሊዝ መንግስት ዛሬም ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ

የቻይና የባህር ሀይል አባላት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከየመን ከ200 በላይ የ10 አገር ዜጎችን ታደጉ

አንድ አሜሪካዊ የመን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መገደሉ ታወቀ

በኬኒያ ዩኒቨርስቲ በተፈፀመው ጥቃት ላይ አንድ የአካባቢው የአገሪቱ ባለስልጣን ወንድ ልጅ ከአልሸባብ ጎን መሰለፉ ታወቀአረብ ኢሚሬትና እስራኤል ከአወዛጋቢው የኢትዮጵያው ህዳሴ ግድብ ጀርባ እጃቸው አለበት ሲል አንድ የግብፅ መገናኛ ብዙሃን ዘገበ

ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያና ሱዳን ጋር የፈረሙትን ፊርማ የግብፅን ህዝብ አይወክልም ብሏል

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ልደት ፕሮፌሰር መስፍንን ጨምሮ የተለያዩ የተቃዋሚ መሪዎችና ጋዜጠኞች በተገኙበት ተከበረ

ከአገር እንዳይወጡ የታገዱት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ዋሽንግተንና ቦስተን ለተሰበሰቡ ኢትዮጵያውያን ከአገር ቤት ንግግር አደረጉ

“ገዢዎቻችን ትግሉን ለማደናቀፍ የሚያደርጉት መሰናክል ሁሉ ይበልጡን ያጠናክረናል” ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

The post Hiber Radio: “በሳዑዲ አረቢያው ላይ እንደተደረገው በየመን ላሉ ኢትዮጵያውያን መጮህ አለብን ተባለ.. የቻይና የባህር ሀይል አባላት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከየመን ከ200 በላይ የ10 አገር ዜጎችን ታደጉ… አቶ እንዳርጋቸው ፅጌን ለማስለቀቅ የእንግሊዝ መንግስት ዛሬም ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየ.. የግብጹ ሚድያ ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያና ሱዳን ጋር የፈረሙትን ፊርማ የግብፅን ህዝብ አይወክልም አለ… የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ልደት ፕሮፌሰር መስፍንን ጨምሮ የተለያዩ የተቃዋሚ መሪዎችና ጋዜጠኞች በተገኙበት ተከበረ… እና ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.

“ያሳደግኹት ውሻ አሳጣኝ መድረሻ” ፥ የአቶ ገብሩ ዐሥራት እና ሊነበብ የሚገባው አነጋጋሪ መጽሐፋቸው

Previous: Hiber Radio: “በሳዑዲ አረቢያው ላይ እንደተደረገው በየመን ላሉ ኢትዮጵያውያን መጮህ አለብን ተባለ.. የቻይና የባህር ሀይል አባላት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከየመን ከ200 በላይ የ10 አገር ዜጎችን ታደጉ…አቶ እንዳርጋቸው ፅጌን ለማስለቀቅ የእንግሊዝ መንግስት ዛሬም ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየ.. የግብጹ ሚድያ ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያና ሱዳን ጋር የፈረሙትን ፊርማ የግብፅን ህዝብ አይወክልም አለ…የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ልደት ፕሮፌሰር መስፍንን ጨምሮ የተለያዩ የተቃዋሚ መሪዎችና ጋዜጠኞች በተገኙበት ተከበረ…እና ሌሎችም
$
0
0

(ኄኖክ የማነ)
ከአቶ ገብሩ ሕይወት ጋራ የሚመሳሰሉ ታሪኮችን ከገሃዱ ዓለም ይልቅ በልብ ወለዶች ወይም በሕይወት ትርጉም ላይ በሚያተኩሩ የፍልስፍና መጽሐፍት ውስጥ በቀላሉ ማግኘት ሳይቀል አይቀርም። የሕይወትን ትርጉም የተለያዩ ጸሐፍት አያሌ መመዘኛዎችን በመጠቀም ለማብራራት ይሞክራሉ። ከነዚህ አከራካሪ መመዘኛዎች አንዱ ሰዎች በኋለኛው የዕድሜ ዘመናቸው ላይ ኾነው ያሳለፉትን የሕይወት ዘመን የኋልዮሽ በመመልከት “ሕይወቴ የተሳካ ነበረ?” ለሚለው ጥያቄ በሚሰጡት መልስ ላይ ይመሠረታል። በዚህ ውጤት አግናኝ መመዘኛ ከተለካ የአቶ ገብሩ ሕይወት “እዚህ ግባ” የሚባል ትርጉም አልነበረውም ብሎ መከራከር ይቻላል። ለዚህ አስተያየት እንደ ምክንያት ሊቀርብ የሚችለው ነገር ደግሞ የቀድሞው የሕወሓት ባለሥልጣን ከዐሥራዎቹ ዕድሜያቸው ጀምሮ መላ ሕይወታቸውን የገበሩለት የትጥቅ ትግልም ኾነ የፖለቲካ ዓላማ በ64 ዓመታቸው በተሻለ ብስለት እና ስክነት ሲገመግሙት “ኢትዮጵያ በፍጥነት ሊቀየር የሚገባው አሳሳቢ ኹኔታ ላይ ትገኛለች።” የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሳቸው ነው።
gebru-book
አቶ ገብሩ በቅርቡ “ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ባሳተሙት መጽሐፋቸው መግቢያ ላይ የትግልና የፖለቲካ ሕይወታቸውን ትርጉም የሚመለከቱ ከባድ ጥያቄዎች ያነሳሉ፤ “ያለፈውን ጊዜህን ይኼን ያህል ከተቸህ ጉዞህ ኹሉ ከንቱ ነበረ ወይ?፥ ባደረግኸውስ ትጸጸታለህ ወይ?” ፥ እና “ለመብትና ለነጻነት ሲሉ በሕወሓት/ኢሕአዴግ ተደራጅተው የተፋለሙትን፥ አካላቸውን እና ሕይወታቸውን ያጡትን ወገኖች አስተዋጽዖ መና አስቀረኸው ወይ?” ሊባሉ እንደሚችሉ ይጠቅሳሉ። ጸሐፊው ለነዚህ ጥያቄዎች የሚሰጡት መልስ ለሦስት ዐሠርት ዓመታት ከልቡ አምኖበት ብዙ መስዋዕትነት የከፈለለት ዓላማ ያመጣውን ውጤት አጥብቆ የሚቃወም ሰው ሊፈጠርበት የሚችለውን አስጨናቂ የተቃርኖ ስሜት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው። ይኼም ብቻ አይደለም፤ መልሱ በመጽሐፉ ውስጥ የሚስተዋለውን የአቶ ገብሩን በፖለቲካው ዓለም ብርቅ የኾነውን ቀጥተኝነትም ያንጸባርቃል። “በኔ ዕምነት በሕወሓት/ኢሕአዴግ የተሰለፍነውም ኾነ በሌሎች ድርጅቶች ተሰልፈው ደርግን የተፋለሙት ታጋዮች ኹሉ ታሪክ በአዎንታ መዝግቧቸዋል። እዚህ ላይ መታየት ያለበት እነዚህ ታጋዮች ያስገኙት ውጤት ሳይኾን ያነገቡት አምባገነንነትን ገርስሶ ፍትሐዊ ሥርዐትን የማስፈን ዓላማቸው ነው። ለዚህ ክቡር ዓላማ ማንኛውንም መስዋዕትነት የከፈለ ዜጋ ክቡር በመኾኑም በአገራችን ታሪክ ሊዘከር ይገባዋል።” ይላሉ አቶ ገብሩ ምላሻቸውን ሲሰጡ። በማስከተልም “ ይኽ ማለት ግን በዚህ የትግል ጉዞ የነበረው የፖለቲካ አካሄድ ቢያንስ ከዴሞክራሲ እና ከአገር ጥቅም አንጻር የነበረበትን መሠረታዊ ጉድለት መመርመር የለበትም ማለት ኣይደለም። የዕውነተኛ የፖለቲካ መጽሐፍ ፋይዳም ያሁኑንም ይኹን ያለፈውን ታሪክ ያለምንም ፍርሐት እና ወገናዊነት በነጻነት እንዲታወቅ ማድረግ ነው። ስለኾነም በዚህ መጽሐፍ ለኅሊናዬ ትክክል የመሰለኝን ኹሉ ለማስፈር በመሞከሬም ሰማዕታቱ የተሰዉለትን ዓላማ ለማክበር ሞክሬአለሁ” በማለት አቋማቸውን ይገልጻሉ።
ይህ የአቶ ገብሩ አመለካከት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ካሉ የተለያዮ አቋሞች አንጻር ሲታይ አወዛጋቢ ሊኾን ቢችልም፤ የታገሉለት ዓላማ አቅጣጫውን ስቶ አገሪቷን ከባድ ችግር ውስጥ እንደከተታት ቢያምኑም ቢያንስ በአንድ መመዘኛ ሕይወታቸው ጉልህ ትርጉም እንዳለው መከራከር ይቻላል። የቀድሞው ታጋይ እና ባለሥልጣን ዘግይተውም ቢኾን (በተወሰነ መልኩ ሳይፈልጉም ቢኾን) ራሳቸውን በጥልቀት መርምረው፥ ስህተት ነው የሚሉትን ተቀብለው፥ እንደ ጣዖት ይመለክ የነበረውን የቀድሞ ድርጅታቸውን በአደባባይ ለመተቸት እና ንስሐ ለመግባት፤ እንዲሁም ለሌላ ለውጥ ለመታገል እና ስህተታቸውን ለማረም ዕድል አግኝተዋል። ብዙ ነገር ቢያጡም ትልቅ ዋጋ ያለው አንድ ነገር አግኝተዋል ማለት ይቻላል።
Gebru Asrat
በዚህ ኹሉ መካከል ግን አንድ በማሻማ ኹኔታ ግልጽ የኾነ ነገር አለ፤ በአቶ ገብሩ ሕይወት ውስጥ የሚስተዋለው መራር የፖለቲካ እና የታሪክ ምጸት። እርሳቸው እንደሚያምኑት አምባገነናዊ ሥርዐትን እና ኢፍትሐዊነት ለማስወገድ የተደረገው መራር ትግል ያስከተለው ነገር ቢኖር- በደምሳሳው ሲታይ- በቅርጽ የተለየ በይዘቱ ግን አምባገነናዊ እና ኢፍትሐዊ የኾነ ሥርዐት “ማንገስ” ነው። ይኽ እጅግ መራር ምጸት ነው።
በመጽሐፋቸው ምረቃ ላይ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኝ አንድ አዳራሽ ውስጥ ከመገናኘታችን በፊት አቶ ገብሩን የማውቃቸው እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በመገናኛ ብዙኃን ነበር። ስለ እርሳቸው የነበረኝ አመለካከት ደግሞ ከሕወሓት ክፍፍል በኋላ አሸናፊው ወገን ስለ “አንጃው” መሪዎች በሚያሰራጫቸው መረጃዎች ተጽዕኖ ሥር የወደቀ ነበር። “ በድሮ በሬ ለማረስ የሚሞክሩ ተቸካይ ማርክሲስት ሌኒኒስት”፥ እንዲሁም ጽንፈኛ የትግራይ ብሔረተኛ እንደኾኑ አምን ነበር። ወደ ምረቃ አዳራሹ የሄድኹት በበርካታ ንዑስ ርዕሶች ከተከፋፈለው የመጽሐፉ ማውጫ ወደ ዐራት የሚጠጉ ትኩረቴን የሳቡ ጉዳዮችን ብቻ በዋዜማው አንብቤ ነበር። ዐራቱ ጉዳዮች የተደበላለቀ ስሜት የፈጠሩብኝ ቢኾንም፥ የመጽሐፉ ድርጁ ይዘት መጽሐፉን ሙሉ በሙሉ ለማንበብ ከፍተኛ ፍላጎት ፈጥሮብኝ ነበር። በምረቃው ላይ ለተነሱት ጥያቄዎች ደራሲው መልስ የሰጡበት መንገድ ደግሞ የማንበብ ፍላጎቴን ብቻ ሳይኾን ጸሐፊውን የማግኘት ፍላጎቴን አነሳሳው። በቀድሞው የ”ኢትኦጵ” ጋዜጠኛ አርዐያ ተስፋማርያም በኩል አንድ ቅዳሜ ተገናኝተን ለዐራት ሰዓታት ያህል ጥያቄዎቼን ሳዥጎደጉድባቸው ቆየኹ። ጥያቄዎቼን በተለመደው ‘ርጋታቸው በተቻላቸው ኹሉ ቀጥተኛ እና ግልጽ በኾነ መንገድ በትዕግስት መለሱልኝ። ይከተሉት የነበረው ርዕዮተ ዓለም ስህተት መኾኑን ለመረዳት ለምን የሕወሓት መከፋፈል አስፈላጊ እንደ ነበር፥ የአቶ መለስ አንዳንድ አስገራሚ ግለሰባዊ ባህርያት፥ ከሕወሓት ከተሰናበቱ በኋላ ስለደረሰባቸው ችግር እና ስለ ሌሎችም መጽሐፋቸው ውስጥ ያልተካተቱ ብዙ አስገራሚ ነገሮች አጫውተውኛል። አቶ ገብሩ እጅግ ትሑትም ናቸው። ተቋማዊ፥ ቤተሰባዊ፥ እና ግለሰባዊ ንቅዘት በተንሰራፋበት አገዛዝ ውስጥ በከፍተኛ ባለሥልጣንነት ቆይተው በሙስና ጨርሶ አለመታማታቸውን ሳስብ ደግሞ መጽሐፋቸውን የመገምገም ሥራዬን ወገናዊነት እንዳይጫነው መስጋቴ አልቀረም።

በቅርብ ዓመታት ውስጥ በቀድሞ ባለሥልጣናት ከተጻፉ የፖለቲካ ግለታሪክ እና የትውስታ መጻሕፍት “ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ” ከአገራዊ ፋይዳ፥ ከግልጽነት እና ከተጠያቂነት፥ ከስፋት እና ከጥልቀት አንጻር ሲታይ ከሁሉም ከፍ ብሎ በሚገኝ ማማ ላይ ለብቻው ተቀምጧል ቢባል ማጋነን አይመስለኝም።በነዚህ መስፈርት በማያጠራጥር ኹኔታ ከወለል በታች የሚገኘው (አሁንም ሥልጣን ላይ እንዳሉ የሚያስቡ በሚመስሉት) በኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም የተደረሰው “ትግላችን” የተባለው መጽሐፍ ነው። በግል፥ በውስን፥ እና በጠባብ አጀንዳዎች ላይ የሚሽከረከረው የአቶ ስየ አብርሃ “ነጻነት እና ዳኝነት በኢትዮጵያ” ፥ የግብር ይውጣ በሚመስል ኹኔታ ይቅርታ ለመጠየቅ የሚዳዳው እና የደርግን ሥርዐት ወደ መከላከል የሚያዘነብል የሚመስለው የሻምበል ፍቅረሥላሴ “እኛና አብዮቱ” ከፍተኛ ትኩረት እና ተቀባይነት ያገኘው ነገር ግን “ይቅርታ” የሚባል ቃል የማይወጣው የአቶ ኤርምያስ ለገሠ “የመለስ ትሩፋቶች” ፥ ጠንከር ያለ የትንተና ችግር የሚታይበት እና የሕወሓትን የሽምቅ ውጊያ ታሪክ በማንቆለጳጰስ የተጠመደው የአቶ አስገደ ገብረሥላሴ “ጋሕዲ” እና የመሳሰሉት የየራሳቸው ሊጠቀሱላቸው የሚችሉ ጠንካራ ጎኖች እንዳሏቸው ባይካድም (ይኽ ምልከታ“ትግላችን” የሚመለከት አይመስለኝም) አቶ ገብሩ በመጽሐፋቸው በተደጋጋሚ እና በየአጋጣሚው አቋማቸውን እየፈተሹ ስህተት ኾኖ ያገኙትን “ ስህተት ነው” ማለታቸው፥ አስፈላጊ ሲኾንም ኃላፊነት መውሰዳቸው፤ በተጨማሪም ትልቁን አገራዊ ሥዕል በመመልከት ይበጃል የሚሉትን አቅጣጫ በጥናት ላይ ተመሥርተው ለማቅረብ መሞከራቸው መጽሐፋቸውን ልዩ ያደርገዋል።
“ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ”ም ቢኾን ግን እንከን አልባ አይደለም፤ በጭራሽ። እንደውም ያደነቅኹትን ግልጽነታቸውን እና ሃቀኝነታቸውን እስከ መጠራጠር ያደረሱኝ በመጽሐፉ ውስጥ ኾን ተብለው የተድበሰበሱ የሚመስሉ ፥ ፈጽሞ ያልተስተዋሉ እና ያልተወሱ አንገብጋቢ ጉዳዮችን ታዝቤአለሁ። ታዲያ አቶ ገብሩ ዐሥራትን ተጣድፌ አወድሻቸው ይኾን?

አቶ ገብሩ የድርሰታቸውን ጽሕፈተ-ምክንያት በሁለት ዐበይት ዓላማዎች ዙሪያ እንደሚያጠነጥን ያወሳሉ። አንደኛው “በሕይወት እያለን የምናውቀውን ታሪክ የሕወሓት/ኢሕአዴግ አመራር እያዛባው እና እየከለሰው ለአገዛዙ እንደሚመች የሚያቀርበውን ታሪክ በማስተካከል ረገድ የበኩሌን አስተዋጽዖ ለማድረግ” ሲኾን ኹለተኛው ደግሞ “ዕውነትን ፍለጋ ለሚሯሯጡት ይኼን ዐይነት መጽሐፍ ማዘጋጀቱ እንደ መነሻ እና እንደ አማራጭ ሊጠቅማቸው ይችላል” በሚል ዕምነት ነው። የመጽሐፉ ስኬት ከነዚህ ዓላማዎች አንጻር ከተለካ አቶ ገብሩ እጅግ ስኬታማ ኾነዋል ማለት ይቻላል። በዚህ ዳሰሳ “ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ”ን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ጭብጦች አንጻር ለመቃኘት እሞክራለሁ።

1. ቅርጽ፥ አቀራረብ፥ መጠነ-ቅኝት (Scope)፥ እና ጥልቀት

እነዚህ ነጥቦች ከመጽሐፉ ይዘት ጋራ ቀጥተኛ ግንኙነት ባይኖራቸውም፤ ይዘቱ ሊፈጥረው በሚችለው ተጽዕኖ ላይ የማይናቅ ሚና ሊኖራቸው ይችላል። ከዚህ አንጻር ሲታይ መጽሐፉ የተለያዩ የአጻጻፍ ዘርፎች (Genres) ባህርያትን ቀላቅሎ የያዘ መኾኑ ደራሲው የሚፈልጉትን መልዕክት በጥሩ ኹኔታ ለማስተላለፍ ‘ረድቷቸዋል፤ ኾኖም አንዳንድ እንከኖችም ይታዩበታል።

2. ማርክሲዝም- ሌኒኒዝም እና ሕወሓት

አቶ ገብሩ በዝርዝር እና በተደጋጋሚ ከሚያነሷቸው ቁልፍ ጉዳዮች አንዱ የማሌ ንድፈ-ኃሳብ እና በሕወሓት፥ አልፎም በኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ውስጥ የተጫወተው ወሳኝ ሚና ነው። በመጽሐፉ ውስጥ ከሠፈሩት ነገሮች ሰቅዘው ከያዙኝ (ካሳዘኑኝ እና ካሳቁኝ) መካከል ይገኙበታል።

3. አቶ መለስ ዜናዊ
“ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ” ውስጥ የሚገኙት አቶ መለስ ዜናዊ ፍጹም አስደናቂ ከመኾናቸው የተነሳ መጽሐፉን ለመክደን አዳጋች ያደርጉታል። አቶ መለስ ኒኮሎ ማኪያቬሊን ራሱን በመቃብሩ ውስጥ በኩራት ደረት ሊያስነፉ የሚችሉ፥ ከማኪያቬሊም በላይ ማኪያቬላዊ ናቸው። አቶ ገብሩም አንድ ቦታ ላይ አቶ መለስን በቀጥታ ሳይኾን ተግባራቸውን “ማኪያቬላዊ” በማለት ይገልጹታል። ከአቶ ገብሩ መጽሐፍ ለመረዳት እንደሚቻለው ሟች የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር በአንድ ጉዳይ ላይ ብቻ ወጥ አቋም ያሳያሉ፤ ለሥልጣናቸው አደጋ ሊፈጥር እንደሚችል እያወቁም ጭምር። በአዕምሮ ብቃታቸው እና በንድፈ ኃሳብ ትንተና ችሎታቸው ደግሞ በሕወሓት ውስጥ እምብዛም የሚገዳደር ተፎካካሪ የነበራቸው አይመስሉም።

4. ሉዓላዊነት እና ማኅበረ – ኢኮኖሚያዊ ፍትሕ

የ“ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ” አንኳር ድክመቶች በአብዛኛው ሉዓላዊነት እና ማኅበረ – ኢኮኖሚያዊ ፍትሕ ላይ ያጠነጥናሉ። ለአቶ ገብሩ “ሉዓላዊነት ማለት በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መካከል በቻ ያለ የድንበር ጥያቄ ነው እንዴ?” የሚል መጠይቅ የሚያጭሩ ከመጽሐፉ ሽፋን ጀምሮ በርካታ ጉዳዮች ማንሳት ይቻላል። ውስጣዊ ሉዓላዊነት እና በሌሎች የኢትዮጵያ ጠረፎች ያሉ የድንበር ውዝግቦች የአቶ ገብሩን ትኩረት ብዙም የሳቡ አይመስሉም። ስለ ኢትዮጵያ የወደፊት አቅጣጫ በሚናገሩበት የመጽሐፉ የመጨረሻ ክፍል ደግሞ የማኅበረ – ኢኮኖሚያዊ ፍትሕን ወሳኝነት አስረግጠው ቢያብራሩም ከጉዳዩ ጋራ የተቆላለፈ እና ለማኅበረ – ኢኮኖሚያዊ ፍትሕ ግዙፍ እንቅፋት የኾነን ዐብይ ጉዳይ ቀደም ባሉት የመጽሐፉ ገጾች እንደነገሩ አከክ-አከክ አድርገው ያልፉታል።

Source: 7killo Magazine

The post “ያሳደግኹት ውሻ አሳጣኝ መድረሻ” ፥ የአቶ ገብሩ ዐሥራት እና ሊነበብ የሚገባው አነጋጋሪ መጽሐፋቸው appeared first on Zehabesha Amharic.

በምስራቅ ጎጃም ዞን የምረጡን ቅስቀሳውን ይዞ የቀረበው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጠመው

$
0
0

በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ አማኑኤል ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የመምህራን ስብሰባ ላይ የምረጡን ቅስቀሳውን ይዞ የቀረበው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጠመው፣
በደረሰን መረጃ መሰረት የማቻከል ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የኔነህ እና የወረዳው የትምህርት ዝሕፈት ቤት ሃላፊው አዲሱ የተባሉት በወረዳው እየተካሄደ በነበረው የመምህራን የርዕሳነ መምህራንና የሱፐርቫዘሮች ስብሰባ ላይ በአጀንዳነት የቀረበውን የትምህርት ጥራትና የውጤት ተኮር ግምገማ በመቀየር ወቅታዊ በሆነው ምርጫ ዙሪያ ላይነው መወያየት ያለብን በማለት እንዲቀየር ያቀረቡትን አዲስ አጀንዳ በመቃወም ከትምህርት ጽህፈት ቤት ሃላፊው በስተቀር የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አጀንዳውን ይዞ እንዲወጣ መደረጉን አስረድቷል፣
መምህራኑ አክለውም በወረዳችን በተደጋጋሚ የሚታየው የሰው ሞትን ያስከተለ መፈናቀል የመልካም አስተዳድር ችግር በመሆኑ መጀመሪያ አካሄድህን አስተካክል በአቅራቢያችን ከቤተሰቦቻችን በኢንቨስትመንት ስም የተነጠቀው የእርሻ መሬት መመልስ አለበት በማለት መቃወማቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል፣

መረጃ ለነፃነት

The post በምስራቅ ጎጃም ዞን የምረጡን ቅስቀሳውን ይዞ የቀረበው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጠመው appeared first on Zehabesha Amharic.

በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን የማውጣት እንቅስቃሴ አልተጀመረም

$
0
0

ኢሳት ዜና :- በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በየመን የሚካሄደውን የእርስ በርስ ጦርነት ተጋፍጠው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቢሆንም፣ ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉትን ከ2 ሺ ያላነሱ ፈቃደኛ ኢትዮጵያውያንንን
ለመመለስ እንቅስቃሴ እየታየ አይደለም ሲሉ የመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያውያኑ ኢምባሲው ባቀረበው ጥሪ መሰረት ምዝገባ አካሄዱ ቢሆንም ፣ መቼና እንዴት እንደሚሄዱ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።
Mideast Yemen Perils Ahead Analysis
አንዳንድ አገራት የባህር እና የአየር ሃይላቸውን በመላክ ዜጎቻቸውን ቢያወጡም ፣ በኢትዮጵያ በኩል ስለሚደረገው እንቅስቃሴ መንግስት አስቸጋሪ ነው ከማለት በስተቀር መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።
ሱዳን ዜጎቿን በአየር ለማውጣት ያደረገችው ሙከራ ከሰአነ መሪዎች የማረፍ ፈቃድ በመከልከሉዋ ሳይሳካላት ቀርቷል። ሱዳን ከሳውድ አረቢያ ጎን በመቆም በሃውዚ አማጽያን ላይ የሚደረገውን የአየር ድብደባ ከሚደግፉት አገራት መካከል ናት። ፓኪስታን ዜጎቿን በአየር
ማስወጣት የቻለች ሲሆን፣ ግብጽ፣ ቻይና፣ ሩሲያና በርካታ አገራት ዜጎቻቸውን በተሳካ ሁኔታ እያወጡ ነው። አልጀሪያና ህንድ ደግሞ ዜጎቻቸውን በሙሉ ማውጣታቸው ታውቋል።
የኢህአዴግ መንግስት በሳውድ አረብያ የሚመራውን የአየር ድብደባ ደግፎ መግለጫ መስጠቱ ይታወቃል። ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ኢትዮጵያ ከስልጣን የተባረሩት ፕ/ት ሃዲ ተመልሰው ወደ ስልጣን እንዲመጡ እንደምትፈልግና ከሱዳንና ጁቡቲ ጋር
በመሆን ስለምትወስደው ቀጣይ እርምጃ እንደምትመክር ተናግረዋል። የአቶ ሃይለማርያም መግለጫ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ በየመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ህይወት አደጋ ላይ ይጥላል በሚል ተተችቶአል።
ጦራቸውን ከአማጽያን ጎን ያሰለፉት እና የሃውዚ ሚሊሺያዎችን የሚደግፉት የቀድሞው ፕሬዚዳንት አሊ አብዱላ ሳላህ ኢትዮጵያ ውስጥ በጥገኝነት ይኖራሉ። ሳላህ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ በሳውዲ የሚመራው የአየር ድብደባ ተገቢ አለመሆኑን ተናግረዋል።
ኢህአዴግ በሳላህ ላይ ያለው አቋም ግልጽ አይደለም።
በሌላ በኩል ደግሞ የኢህአዴግ ደጋፊ የሆነቸው ቻይና በሳውዲ መሪነት የሚወሰደውን እርምጃ እየተቃወመች ነው።

The post በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን የማውጣት እንቅስቃሴ አልተጀመረም appeared first on Zehabesha Amharic.

የአራዳ ልጅ ብሔር? –‎ሁኔ አቢሲኒያ‬

$
0
0

የአራዳ ልጅ ብሔር? ሲባል ምን እንደሚል ታውቃላችሁ? ”አልቦ ብሔር ” ነው። አልቦ ብሔር ማለት ብሔር የሌለኝ ግን ኢትዮዽያዊ ነኝ ሲላችሁ ነው። በ1960 ዎቹ መጨረሻ ላይ የተነሳው እና በ ¨ት ሃ ቶች¨ ታሽቶ በ 1987 ዓም ¨እስከ መገንጠል¨ የሚል ቃል አክሎ፤ በ ህገ መንግስቱ ላይ ጨምሮ ፤አስጨብጭቦ፣ ሰው በቋንቋ መከፋፈልን (¨ከ¨ ሲላላ) እና መከፋፈልን (¨ከ¨ ሲጠብቅ) በሃገሪቱ ላይ የነገሰው አስተሳሰብ በትክክል ግብአተ መሬቱ ሊከናወን ሰዓታትን መቁጠር ግድ ይለዋል። ይህ የሚሆነው በ ተፈጥሯዊ ሂደት ነው።

የ ዘር ፖለቲካ ለ አለማችን አዲስ ክስተት አይደለም።የ አምባገነኖች መሸሸጊያ ጉረኖ ዘረኝነት እና የዘር መርዝ መንዛት ነው። ሂትለር የጦርነት ጥማቱን ለማርካት የ ጀርመንን ህዝብ የተለየ ህዝብ አድርጎ ማቅረብ ነበረበት። ¨እናንተ የ ጀርመን ህዝቦች የ ‘አርያን’ዘሮች ¨ እያለ ይሸነግል ነበር። መለስ ዜናዊም እንኳን ከእናንተ ተፈጠርኩኝ በማለት የትግራይ ህዝብ የተለየ ምርጥ ዘር ለማስመሰል ሲናገር ተደምጧል፡፡ ሰዎች በባህሪያችን ብልህ የመሆናችንን ያህል የመሆኑን ጅልነትም አያጣንም።ሰው እኮ በዛፍ የማመን፣ አምላክ ነው የማለት አስቂኝ ሞራል ያለው ፍጡር ነው።¨አንተ ዘርህ የ እገሌ ነው፤ታላቅ ነህ፤ ያንተ ዘር እገሌ ድሮ እንዲህ ያደረገ፤ እገሌ የተባለው መሪህ ካንተ መንደር የተወለድ¨ ሲባል ልቡ ደንገጥ የሚል ይጠፋል ብለን አናስብ።

የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) “ሁሉም የሰው ልጆች ዝርያቸው አንድ ሲሆን ሁሉም ከአንድ የዘር ግንድ የመጡ ናቸው” ብሏል።—የዘርና የዘር ጥላቻ አዋጅ፣ 1978

ሼክስፒር የተባለው ደራሲ ደግሞ ምን አለ መሰላችሁ ” ትዕቢት ምቀኝነትና ዘረኝነት ከእውቀት ማነስ የሚመጡ መርዘኛ አመል ናቸው ።
እናም በመጨረሻ እኔ የአራዳ ልጅ ነኝ አልቦ ብሔር
‪#‎ሁኔ_አቢሲኒያ‬

Comment

The post የአራዳ ልጅ ብሔር? – ‎ሁኔ አቢሲኒያ‬ appeared first on Zehabesha Amharic.


የምርጫ አስፈፃሚዎች የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አንቀበልም አሉ

$
0
0

ነገረ ኢትዮጵያ /

‹‹ሰበር ሰሚ ችሎት የሚባል አናውቅም›› የምርጫ አስፈጻሚዎች

ethiopia-blue-party-300x164በምዕራብ ጎጃም ዞን የወንበርማ ወረዳ ምርጫ ክልል የምርጫ አስፈጻሚዎች የአማራ ብሄራዊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠውን ውሳኔ አንቀበልም ማለታቸውን የምዕራብ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ አቶ አዲሱ ጌታነህ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

የአማራ ብሄራዊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መጋቢት 18/2007 ዓ.ም በምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ የተሰረዙት የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ‹‹ከምርጫ የተሰረዙት ያለ አግባብ በመሆኑ፣ መምረጥና መመረጥ ህገ መንግስታዊ መብታቸው ነው›› በሚል ወደ ዕጩነት እንዲመለሱ ውሳኔ መስጠቱ ይታወቃል፡፡

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እስካሁን 16 ያህል የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ወደ ዕጩነታቸው እንዲመለሱ ቢያዝም የምርጫ አስፈጻሚዎች ‹‹ሰበር ሰሚ ችሎት የሚባል አናውቅም›› በሚል የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አንቀበልም ማለታቸውን አቶ አዲሱ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ አቶ አዲሱ አክለውም ‹‹የምርጫ አስፈጻሚዎች በብቃታቸው ሳይሆን በታማኝነታቸው ስለሚመረጡ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆኑም›› ብለዋል፡፡

The post የምርጫ አስፈፃሚዎች የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አንቀበልም አሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

ትዮጵያ ሁሉንም የትምህርት ተደራሽነት ግብ መመዘኛዎች አላሳካችም ተባለ

$
0
0

“ትምህርት ለሁሉም” በሚል መርህ ከ2000 እስከ 2015 እ.ኤ.አ በአለማቀፍ ደረጃ የተያዘውን የትምህርት ተደራሽነት ግብ ኢትዮጵያ በሁሉም መመዘኛዎች ዝቅተኛ ውጤት በማምጣት ማሳካት አለመቻሏን ዩኔስኮ በግሎባል ሞኒቴሪንግ ሪፖርቱ ይፋ አደረገ፡፡ ሃገሪቱ በሁሉም መመዘኛዎች ስኬታማ ባትሆንም በተለይ 7 ሃገራት ብቻ ማሳካት የቻሉትን ጥቅል የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ሽፋንን በተሻለ ደረጃ ልታሳካ መቃረቧንና በዚህ ረገድ ያስመዘገበችው ውጤት አመርቂ መሆኑን ሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡ አለማቀፉ የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም (UNESCO) ከ15 ዓመት በፊት ታዳጊ ሃገራት የትምህርት ተደራሽነትን ይበልጥ እንዲያስፋፉ በ6 መመዘኛ ነጥቦች የሚገመገሙበት ግቦች ያስቀመጠ ሲሆን ሰሞኑን ይፋ ባደረገው የግምገማ ሪፖርት፤ አብዛኛዎቹ ታዳጊ ሀገራት የገቡትን ቃል አለማሳካታቸውን ጠቁሟል፡፡
Saudi Arabia ethiopian school
“ኢትዮጵያ አያያዟ መልካም ነው፤ እስከ 2030 በሚቆየው የልማት ትልም ጊዜ ውስጥ ግቦቹን ልታሳካ ትችላለች” ብሏል – ሪፖርቱ፡፡
በዚህ ሪፖርት ኢትዮጵያ በሁሉም መመዘኛዎች ከተቀመጡት ግቦች በእጅጉ ወደ ኋላ የቀረ አፈፃፀም ማስመዝገቧ ተጠቁሟል፡፡ በ2015 ሃገሪቱ የጎልማሶች የትምህርት ተደራሽነትን በማስፋፋት በሃገሪቱ ያለውን መሃይምነት ከ50 በመቶ በታች ትቀንሳለች ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም ከተቀመጠው ግብ መፈፀም የቻለችው 21 በመቶውን ብቻ ነው፡፡

በሃገሪቱ የ1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን መከታተል ሲገባቸው ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ህፃናት የእድሉ ተጠቃሚ መሆን እንዳልቻሉ የጠቆመው ሪፖርቱ፤ ትምህርት ከክፍያ ነፃ በመሆኑ የሴቶች ተሳትፎ መጨመሩን አመልክቷል፡፡

በፊት 61 በመቶ የሚሆኑ ታዳጊዎች የ1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ሳያጠናቅቁ ያቋርጡ እንደነበር የጠቀሰው ሪፖርቱ፤ በአሁን ወቅት አኀዙ ወደ 37 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጠቁሞ ውጤቱ ከተቀመጠው ግብ አንፃር ዝቅተኛ አፈፃፀም ነው ብሎታል፡፡

ኢትዮጵያ እስከ ዘንድሮ የፈረንጆች ዓመት ድረስ የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ሽፋንን በማሳደግ ታሳካዋለች የተባለውን ግብ ባለማሳካቷ በሁለተኛው ምዕራፍ እስከ 2030 በሚዘልቀው የ15 ዓመት ግብ ማሳካት ይጠበቅባታል ያለው ሪፖርቱ፤ ለዚህም በየዓመቱ 22 ቢሊዮን ዶላር (ከ440 ቢሊዮን ብር በላይ) በጀት ለዘርፉ መመደብ እንዳለባት ጠቁሟል።

ዩኔስኮ የ15 ዓመት የትምህርት ልማት ግብ ብሎ ያስቀመጣቸው መመዘኛዎች፡- የህፃናት የትምህርት እድል መስፋፋት፣ የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ሽፋንን ማሳደግ፣ ለወጣትና ጎልማሶች በእኩል ትምህርትን ማዳረስ፣ መሃይምነትን ከ50 በመቶ በታች መቀነስ፣ የፆታ ተሳትፎ እኩልነትን ማረጋገጥና የትምህርት አጠቃላይ ጥራት ማሳደግ የሚሉት ሲሆኑ ኢትዮጵያ በሁሉም መመዘኛዎች ዝቅተኛ ውጤት ካስመዘገቡት ሃገራት ምድብ ውስጥ ተካታለች። ከስኬት ለመድረስ ብዙ ርቀት መጓዝ ይቀራታል ሲልም ሪፖርቱ አክሏል፡፡

The post ትዮጵያ ሁሉንም የትምህርት ተደራሽነት ግብ መመዘኛዎች አላሳካችም ተባለ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ ማንኛዉም አዲስ የእምነት ተቋም እንዳይገነባ መመርያ ወጣ

$
0
0

አቡበከር አህመድ እንደዘገበው:-

መንግስት በሴኩላሪዝም ስም ህብረተሰቡን በተለይ ሙስሊሙን ማህበረሰብ ከእምነቱ ለማስወጣት የሚያደርጋቸውን ጥረቶች አጠናከሮ የቀጠለ ሲሆን የዚህ እቅድ አንደ አካል የሆነውን ድርጊቱን ማንኛዉም አይነት የእምነት አዲስ ተቋማት በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ እንዳይገነቡ በሚል መመሪያ ማዉጣቱን ምንጮች አስታዉቀዋል።
Ethiopia-Addis-Ababa-2
በየትኛዉ እምነት አማኞች ፈጣሪያቸውን በአንድነት የሚያመልኩበት ቦታና የእምነቶቻቸውን ጥሪ የሚያደርጉበት ቦታ የእምነት የእምነት ተቋማቸዉ ሆኖ እያለ ከተማዋ እጅጉን እያሰፋችበት በሚገኘው በዚህ ወቅት ላይ ይህ አይነቱ ወሳኔ መተላለፉ መንግስት ህብረተሰቡን ከእምነቱ ለማራቅ ያለውን ፍላጎት የሚያሳይ ነው ተብሎ እየተተቸ ነው::

ዉሳኔው ሌላ መመሪያ እስኪመጣ ድረስ እንዲሰራበት የተላለፈ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በቅርቡ በተለያዩ እምነቶች ለእምነት ተቋም መገንቢያ ተብለው የተከለሉ ቦታዎችን መንጠቅ እንደተጀመረም ምንጮች አካተዉ ገልፀዋል።

The post በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ ማንኛዉም አዲስ የእምነት ተቋም እንዳይገነባ መመርያ ወጣ appeared first on Zehabesha Amharic.

ገዢው ፓርቲ የጦርነት ያክል ዘምቶብናል ሲሉ የኦፌኮ ሊቀመንበር ተናገሩ

$
0
0

news
ኢሳት ዜና :-የመድረክ አባል የሆነው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊ/መንበር አቶ በቀለ እንደተናገሩት በመጪው ምርጫ ለመሳተፍ ድርጅታቸው በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች እጩዎችን ቢያሰማራም፣ እጩዎቹ እየታሰሩና
እየተደበደቡ በመሆናቸው መድረክ ቀጣዩን ሂደት ለመወሰን እየተነጋገረ ነው።
አቶ በቀለ በሆድሩ ጉድሮ አባሎቻቸው ቅስቀሳ እንዳያደርጉ መከልከላቸውን፣ በሜታ ሮቢ ከ50 ያላነሱ ወጣቶች መታሰራቸውን፣ በግንደበረት የወረዳው አስተዳደር ሽጉጥ በማውጣት አባሎችን ማስፈራራታቸውን ፣ ግንጭ ላይ ጽ/ቤታቸው መሰበሩን እና ሌሎችንም
እየደረሱባችው ያሉትን ችግሮች ተናግረዋል። ምርጫ ቦርድም ሆነ ፖሊስ መልስ ሊሰጡዋቸው እንዳልቻሉ የገለጹት አቶ በቀለ፣ ጥቃቱና ዘመቻው የማይታገስ ከሆነ መድረክ ስለሚወስደው እርምጃ እየተነጋገረ ነው ብለዋል።
የፊታችን ግንቦት የሚደረገው ምርጫ አለማቀፍ ትኩረት አልሳበም። የአውሮፓ ህብረትም ሆነ የካርተር ማእከል ምርጫውን እንደማይታዘቡ ይታወቃል ገዢው ፓርቲ አንጻራዊ የሆነ ፉክክር ከሰማያዊ ፓርቲ እና ከመድረክ ይገጥመዋል ተብሎ ቢጠበቅም፣ በድርጅቶች ላይ
የሚደረሰው ጫና ብዙዎች ነጻ ምርጫ ይካሄዳል ብለው ተስፋ እንዳይጥሉ አድርጓቸዋል።

The post ገዢው ፓርቲ የጦርነት ያክል ዘምቶብናል ሲሉ የኦፌኮ ሊቀመንበር ተናገሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

ባንኮች የተከፈለ ካፒታላቸው ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ሊሆን ነው

$
0
0

national bank of ethiopiaበኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ለመግባት የሚያስፈልገው የመነሻ ካፒታል መጠን እንደገና ስለሚከለስ ባንኮችም ለዚህ እንዲዘጋጁ ተነገራቸው፡፡ ምንጮች እንደገለጹት፣ የባንኮች መመሥረቻ ካፒታል መጠን አሁን ካለበት 500 ሚሊዮን ብር ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ከፍ በማድረግ ሥራ ላይ ለማዋል ታቅዷል፡፡

የባንኮች መነሻ ካፒታል መጠንን ለማሳደግ መንግሥት ያለውን ዕቅድ በቅርቡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከባንኮች ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር አድርጎት በነበረው የውይይት መድረክ ላይ ማስታወቁን፣ ለዚህም እንዲዘጋጁ ያሳሰበ መሆኑን ምንጮች አስረድተዋል፡፡

በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የፋይናንስ ተቋማት ሊደርሱበት ይገባል የተባለውን ግብ ለማሳካት፣ አንዱ የባንኮችን ካፒታል አቅም ማሳደግ የሚያስፈልግ መሆኑ ስለታመነበት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ ለባንኮቹ ኃላፊዎች ባደረጉት ገለጻ፣ በሥራ ላይ ያሉት የግል ባንኮች ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ያሉዋቸውን ቅርንጫፎች በ25 በመቶ እንዲያሳድጉ ነግረዋቸዋል፡፡ ከተጨማሪዎቹ ቅርንጫፎች ውስጥ ሁለት-ሦስተኛው ከአዲስ አበባ ውጪ መክፈት እንደሚገባቸው ማሳሰባቸው ተሰምቷል፡፡

በብሔራዊ ባንክና በባንኮች ሥራ አስፈጻሚዎች መካከል በነበረው ውይይት ይህንን ሐሳብ ባንኮች እንዲያውቁት መረጃ ከመስጠት ያለፈ ዝርዝር መረጃ ባይቀርብም፣ የባንኮች የመነሻ ካፒታል ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ እንዲሆን ፍላጎት ያለ መሆኑን የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡ ይህ መጠን አነስተኛው ሊሆን እንደሚችልና ምናልባትም ከዚህ ከፍ ሊል እንደሚችልም ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

የባንኮች ካፒታል መጠን እንደታሰበው አንድ ቢሊዮን ብር እንዲሆን ከተወሰነ፣ አብዛኛዎቹ ባንኮች ችግር ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ የሚል ሥጋት አሳድሯል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንዳንድ የባንክ የሥራ ኃላፊዎች፣ የባንኮች ማቋቋሚያ ካፒታል መጠንን ለማሳደግ ስለመፈለጉ መረጃው እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ በየትኛውም ደረጃ የመነሻ ካፒታል መጠኑ ቢያድግ ለአብዛኛዎቹ ባንኮች ፈታኝ እንደሚሆንባቸው ተናግረዋል፡፡ በተለይ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ የተቋቋሙ ባንኮች ከሦስት ዓመት በፊት የባንኮች መመሥረቻ ካፒታል ከ100 ሚሊዮን ብር ወደ 500 ሚሊዮን ብር እንዲያድግ ሲወሰን፣ ካፒታላቸው 500 ሚሊዮን ብር ያልደረሱ ባንኮች በአምስት ዓመታት ውስጥ ወደዚህ ደረጃ እንዲደርሱ የወጣውን ሕግ ለማሟላት በሚታትሩበት ወቅት፣ ይህ አዲስ ሐሳብ መቅረቡ ሳያሳስባቸው አልቀረም፡፡

ለ500 ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታል እስካሁን አክሲዮን እየሸጡ ያሉ ባንኮች በመኖራቸውና ይህንንም ለማሟላት አድካሚ የሚባል ጉዞ እየተጓዙ መሆናቸውን የገለጹት አንድ የባንክ ባለሙያ፣ በእርግጥም አዲሱ መመርያ በተግባር ላይ ከዋለ የአብዛኛዎቹ ባንኮች ዕጣ ፈንታ ውህደት እንዲሆን ያደርጋል የሚልም ሥጋት አላቸው፡፡ ጠንካራ ለሚባሉትም ፈታኝ ነው ብለዋል፡፡

ባንኮች አትራፊ መሆናቸው ቢታወቅም የካፒታል መጠናቸውን እንዲያሳድጉ በወጣው አስገዳጅ መመርያ መሠረት፣ 500 ሚሊዮን ብር ካፒታሉን ለማሟላት እያደረጉ ያሉት የአክሲዮን ሽያጭ በተፈለገው ፍጥነት እየተጓዘ ባለመሆኑ፣ እንደገና ካፒታላችሁን አሳድጉ ከተባሉ በአክሲዮን ሽያጭ ለመሙላት የሚቸገሩ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ብቸኛው አማራጭ የሚሆነው አነስተኛ ካፒታል መጠን ያላቸው ባንኮች ወደ ውህደት እንዲገቡ ሊያስገድዳቸው እንደሚችልም እኚሁ ባለሙያ ገልጸዋል፡፡

‹‹የመጨረሻው ውሳኔ ውህደት ቢሆን አሁን በሥራ ላይ ካሉ የባንኮች ባህሪ አንፃር አንዱን ከአንዱ ለማዋሀድ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፤›› የሚልም ሥጋት አላቸው፡፡ የካፒታል ዕድገቱ ለሎች ተፅዕኖዎችም እንዳለው የሚናገሩት እኚሁ ባለሙያ፣ የማቋቋሚያ ካፒታሉ አንድ ቢሊዮን ብር ይሁን ቢባል እንኳን አሁንም አዳዲስ ባንኮች እንዳይፈጠሩ ጋሬጣ ይሆናል ይላሉ፡፡

የመመሥረቻ ካፒታሉ 500 ሚሊዮን ብር ይሁን የሚለው መመርያ ሥራ ላይ ከዋለ ወዲህ እንኳን ይህንን ያህል ካፒታል ለማሰባሰብ አስቸጋሪ ነው ተብሎ በመታመኑ አዲስ ባንክ አለመቋቋሙን አስታውሰዋል፡፡ ባንክ ለማቋቋም አክሲዮን ሲሸጡ የነበሩ ሦስት ባንኮች ሳይቀሩ 500 ሚሊዮን ብሩን መሙላት አንችልም ብለው እንቅስቃሴያቸውን ማቋረጣቸውንም በምሳሌነት አስረድተዋል፡፡

አሁንም የካፒታል መጠኑ ካደገ አዳዲስ ባንኮች እንዳይመሠረቱ በማድረግ፣ በኢንዱስትሪው ውስጥ ያሉት ባንኮች ብቻ እንዲቆዩና ካፒታላቸውን አንድ ቢሊዮን ለመድረስ የሚገደዱትም ቀጣይ ጊዜያቸው ሕጉን ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንዲወጠሩ ያደርጋቸዋል የሚል ግምት አላቸው፡፡ የአዳዲስ ተወዳዳሪ ባንኮች እንዳይፈጠሩ ማድረጉ ደግሞ ሌላው ተፅዕኖ ነው የሚሉት የባንክ ባለሙያዎች፣ እንደ ኬንያ ያሉ አገሮች ከ45 በላይ ባንኮች ያላቸው መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

በሌላ በኩል ለአገሪቱ የባንኮች ዕድገት ከታሰበ የመመሥረቻ ካፒታሉ ማደጉ ይጠቅም ይሆናል እንጂ ጉዳት የለውም የሚሉም አሉ፡፡ የአገሪቱ ባንኮች ከሌሎች ባንኮች ጋር በንፅፅር ሲታዩ ያላቸው ካፒታል እዚህ ግባ የሚባል ባለመሆኑ፣ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ማድረጉ አግባብ ነው ይላሉ፡፡ ይህንን ካልቻሉ ተጣምረው ጠንካራ ባንክ ካቋቋሙም ጠቃሚ ስለሚሆን ሥጋቱ ተገቢ አይመስላቸውም፡፡ ካፒታሉን የሚያሟሉበት መንገድ የተመቻቸ እንዲሆን ማድረግ እንደሚገባ፣ አቅማችሁን አሳድጉ የሚለው ሐሳብ ትክክል ነው የሚል እምነት ያላቸው መሆኑን ይናገራሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት 16 የግል ባንኮች በሥራ ላይ ናቸው፡፡ እስከ 2007 ዓ.ም. የመጀመርያ ስድስት ወራት ድረስ አራት ባንኮች እስካሁን ያሰባሰቡት የካፒታል መጠን ከ500 ሚሊዮን ብር ያነሰ ነው፡፡ ስምንት ያህሉ ደግሞ የተከፈለ ካፒታላቸው ከአንድ ቢሊዮን ብር በታች ነው፡፡ እንደ መንግሥት ዕቅድ አዲስ በሚወጣው መመርያ ተግባራዊ እንዲሆን የሚፈለገው የካፓታል መጠን፣ እስከ ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መጨረሻ ድረስ ነው፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

The post ባንኮች የተከፈለ ካፒታላቸው ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ሊሆን ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live