Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ድምጻችን ይሰማ:- ትግላችን ከየት ወደየት?

$
0
0

ክፍል 1 –

ላለፉት 3 ዓመታት በጽናትና በህዝባዊነቱ እያደገ የሄደው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሃይማኖት መብት የማስከበር ህዝባዊ ትግል ከእርከን እርከን እየተሸጋገረ አሁን ያለበት ደረጃ ደርሷል፡፡ ገና ከጅምሩ መንግስት የሙስሊሙን የመብት ማስከበር ትግል ለማኮላሸት ያላደረገው ጥረት አልነበረም፡፡ መንግስት የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ከውስጥ ለመሰንጠቅ በመሞከር እና የሙስሊሙ የመብት ጥያቄ በሌላው እምነት ተከታይ እና በሃገር ላይ የተቃጣ አደጋ እንደሆነ አድርጎ በማቅረብ ያካሄደው የከሸፈ ፕሮፓጋንዳ በቀላሉ የሚረሳ አይደለም፡፡ ግና የመንግስትን የጥፋት ተልዕኮ ገና ከጅምሩ የተረዳው ህዝባችን ሁለቱንም ሰንኮፎች ለመንቀል ያደረገው ጥረት የተሳካ ነበር፡፡
muslim 1
በእነዚህ ውጣ ውረድ በተሞላባቸው ዓመታት ህዝባዊ ትግሉ የተሳኩ መስጂድ ተኮር ተቃውሞዎችን ከማካሄድ አልፎ አቻ የማይገኝላቸው የአደባባይ ትዕይንተ ህዝቦችን በሁለቱ የዒድ በዓላት በተደጋጋሚ ለማካሄድ ችሏል፡፡ በእነዚህ እንቅስቃሴዎች የሙስሊሙን አንድነት ከማጠናከር በተጨማሪ የመንግስት የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ማሽኖች በማህበረሰባችን ዘንድ ሊያሰርጹት የሞከሩትን እኩይ ሴራ በብቃት ለመመከት ተችሏል፡፡ በመላው የሃገሪቱ ክፍሎች በተካሄዱ የተቃውሞ መርሃ ግብሮች የህዝበ ሙስሊሙን የሰለጠነና ህገ መንግስታዊ አካሄድ ለማመስከር የተቻለ ሲሆን የመንግስትን ፕሮፓጋንዳም ባዶ ለማስቀረት ተችሏል፡፡ እንቅስቃሴው በአዲስ አበባ በተጀመረበት ሰሞን በክልል ከተሞች የሚገኘው ማህበረሰብ በመንግስት ፕሮፓጋንዳ ምክንያት ተፈጥሮበት የነበረው ብዥታ እንዲጠራ ማድረግ የተቻለውም ብዙም ሳይቆይ እንቅስቃሴውን ወደ ክፍለ ሃገራት በማሳደግና ማህበረሰባችን እውነቱን በአይኑ አይቶ የሚፈርድበትን እድል በመፍጠር ነበር፡፡
muslim1
በእርግጥ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ በአፋኝ አምባገነናዊ ስርዓት ውስጥ የሚካሄድ እንደመሆኑ መጠን በስጋት የተሞላ ነበር፡፡ ሆኖም ህዝባችን በስነ ልቦናም ሆነ በተከተለው ስልት መንግስትን በልጦ በመገኘቱ በኢትዮጵያ ምድር የሰላማዊ ትግል ፈር ቀዳጅነትን ተጎናፅፏል፡፡ መንግስት መንግስት ከሚያሰኙ ባህሪያት ወጡ ጋጠወጥነቶችን በሚፈጽምበትና ሰላማዊውን የትግል መስመር ለማደፍረስ ከደህንነት ሃይሎቹ አልፎ ፖሊሶችና መከላከያ ሓይሎችን ጭምር ባሳተፈበት ወቅት ሁሉ ሰላማዊነቱን ጠብቆ ከሁለት ዓመታት በላይ የተሳኩ የተቃውሞ ትዕይንቶች ማካሄድ ፈታኝ ቢሆንም ህዝባችን ግን የሚቻል የማይመስለውን አድርጓል፡፡ የመርሃ- ግብሮቹ ስኬት በተሳታፊው ማህበረሰብ የንብረት፣ የአካል፣ ብሎም የህይወት መስዋዕትነት የተገኘ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ አሳሳ፣ ገርባ፣ አወሊያ፣ ደሴ፣ ከሚሴ፣ ሻሸመኔ፣ ወልቂጤ፣ አንዋር፣ ፍልውሃ… የፈሰሰው ደም፣ የተደፈረው ሰብዓዊ መብት፣ የተዘረፈው ንብረት ሁሉ ህዝባችን ለሃይማኖቱ ያለው ቀናኢነት እና ሃይማኖታዊ መብቱን ለማስከበር የማይከፍለው መስዋዕትነት እንደሌለ ያሳየበት የማይፋቅ የመስዋእትነት አሻራ ነው፡፡ (ይቀጥላል…)

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!

The post ድምጻችን ይሰማ:- ትግላችን ከየት ወደየት? appeared first on Zehabesha Amharic.


ከኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ለኢትዮጵያ ወጣቶች የተላለፈ ማሳሰቢያ!!!

$
0
0

ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚገነዘበው በጥቂት ጠባብ አምባገነኖች የሚመራው የህወሓት/ኢ ህአዴግ ሥርዓት ላለፉት 23 አመታት በህዝብ መካከል የጥላቻና የጥርጣሬ መርዙን እየረጨ፤ ለዘመናት ተፋቅሮና ተከባብሮ የኖረውን ጠንካራ ህዝብ በተለያዩ ጐራዎች በመከፋፈል፤ እምቅ ጉልበቱን በማዳከም፤ ብሎም ትውልድ የማምከን ሰይጣናዊ አላማውን ለማሳካት ነጥሎ በማጥቃት፤ በሃገርና በህዝብ ላይ እጅግ ዘግናኝ ጭካኔዎችንና በደሎችን አየፈፀመና፣ ለከፍተኛ ስቃይና መከራ እየዳረገ እንደሚገኝ ይታወቃል። ይህ አርቆ ማየት የተሳነው ሥርዓት በተለይ ወጣቱ ትውልድ በራስ የመተማመንና አርቆ የማሰብ እምቅ ችሎታው እንዲዳከምና ባክኖ እንዲቀር፤ ብሄራዊ ስሜቱ ጨርሶ እንዲጠፋና ከግለኝነትና ከጐጠኝነት የማያልፍ ጠባብ አስተሳሰብ ውስጥ ሰጥሞ እንዲቀር፤ ብሎም ትውልድን የማምከንና ሃገር የማጥፋት እኩይ አላማውን ለማሳካት፤ በትምህርት ካሪኩለሙ ላይ ሳይቀር መርዙን ለመርጨት ሌት ከቀን እየኳተነ ይገኛል። በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማህበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት በጥቂት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች መካከል እያየን የምንገኘው አላስፈላጊና ዋጋቢስ ንትርክ፤ የሥርአቱ ትውልድን የማምከን እኩይ አላማ መገለጫ ተብሎ የሚገለፅ ቢመስልም፤ እውነታው ግን ሥርአቱ አላማውን ለማሳካት ቀጥሮም ሆነ አሳስቶ፤ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ፤ የተፅዕኖው ሰለባ በማድረግ እየተጠቀመባቸው ባሉ ጥቂት ወጣቶች አማካኝነት የሚካሄዱ መሰሪ ተግባራት ናቸው። ይሁንና ዛሬ ይህ ትዕይንት መረን እየለቀቀ የመጣበት ደረጃ ላይ ይገኛል።
EYNM New Logo
ሃገራችን ኢትዮጵያ ከ85 ያላነሱ ብሄር ብሄረሰቦችና ጐሳዎች የሚኖሩባት፤ የ92 ሚሊዮን ህዝብ መኖሪያ ውብ ሀገር ነች። ኢትዮጵያ ከ3000 ዓመት በላይ ታሪክ ያላት ሀገር ስትሆን፤ በአለም ላይ ከታየና ከተመዘገበ ታሪክ ሁሉ፤ ልዩ በሆነ መልኩ የተለያዩ ጎሳ/ዘር፣ ኃይማኖት፣ እምነት፣ አመለካከት ያላቸው ዜጐች የሚኖሩባት ቢሆንም፤ ለዘመናት ተከባብረው፣ ተቻችለውና፣ ተዋደው፤ በፍቅርና በአንድነት በመኖር እንደምሳሌ የሚጠቀሱና የሚወደሱ ናቸው። ልዩነቶች ኖሮባቸው እንኳን ጠላት በመጣ ጊዜ በኢትዮጵያዊነታቸው አንድ ላይ በጽናት በመቆም፤ ጠላትን አሳፍሮ በመመከትና ድባቅ በመምታት፤ የሀገር ሉዓላዊነትን ጠብቀው፤ ህዝባቸውን ከጠላት ጥቃት ለመከላከል ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን አድቅቀው መስዕዋትነትን በመክፈል፤ የምንወዳትና የምንመካባት ኢትዮጵያን በክብር አስረክበውናል።

ይህን ማለት ግን ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋና ሰላማዊ ነበር ማለት አይደለም። እውነታው በተለያዩ ጊዜአት የመጡ ስርዓቶች በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በደል በመፈፀም የታሪክ አሸራ ጥለው አልፈዋል። እዚህ ጋር ግልፅ ሊሆንልን የሚገባው፤የተፈፀመው በደል በወቅቱ የነበሩት ገዢዎች ተግባር እንጂ፤በሃገራችን ኢትዮጵያ ታሪክ አንድም ጐሳ በምንም ሁኔታ በሌላው ላይ ለማጥቃት ተነስቶ አያውቅም። ይህ ታሪካችን በሃገራችን ኢትዮጵያ ዜጐች በፍቅርና በአንድነት ለዘመናት ተቻችለው ሊቆዩ የቻሉበት ዋንኛ ሚስጢር ከመሆኑም በላይ፤ ልንሸሽገው የማይቻለን፤ለአንድነታችን አይነተኛ ማረጋገጫ የሆነ እውነት ነው።

በመሆኑም በወጣትነታችን የዚህ ትውልድ ፈርጥ መሆናችንን አውቀን፤ አእምሮአችንን አስፍተን ታሪካችንን በጥልቀት በመመርመርና በመረዳት፤ብሎም እውነታውን ለይተን በማገናዘብ፤ በታሪክ የነበሩ ችግሮቻችንን አሶግደን፤ የተሻሉ መፍትሄዎችን በሰከነ ውይይት በማፍለቅ፤ አባቶቻችን በክብርና በአንድነት ያስረከቡንን ታላቅ ሃገር በክብር ለመጪው ትውልድ የማስረከብ ታሪካዊ ግዴታችንን እንድንወጣ ሲል፤ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ በአብሮት ጥሪውን እያቀረበ የወያኔ መሳሪያም እንዳይሆን ያሳስባል።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ

The post ከኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ለኢትዮጵያ ወጣቶች የተላለፈ ማሳሰቢያ!!! appeared first on Zehabesha Amharic.

(የሳዑዲ እና የመን ጉዳይ) “ወሳኙ ማዕበል”የ7ኛ ቀን መግለጫ … (ነብዩ ሲራክ)

$
0
0

Mideast Yemen Perils Ahead Analysis
የመረጃ ግብአት

* “የ መዝራ መጠለያና የወተት ፋብሪካ ጥቃት ፈጻሚዎች የሁቲ አማጽያን ናቸው !” የዘመቻው ቃል አቀባይ

* በሳውዲ መራሹ ጦር የአየር ጥቃት እንደደረሰበት ሲነገር ስለነበረውና አነጋጋሪ ሆኖ ስለሰነበተው በተባበሩት መንግስታታ የስደተኞች በመዝራ መጠለያ ጥቃት ዙሪያ ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ መግለጫ ሰጥተዋል ። ጀኔራሉ ከቀናት በፊት በጥቃቱ ዙሪያ ተጠይቀው በመጠለያው አካባቢ የመሸጉ የሁቲ አማጽያን ላይ ጥቃት መደረጉን አምነው ነበር ። በወቅቱ ዝርዝር መግለጫ አልሰጡም ነበር ።

* ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ የዘመቻውን 7ኛ ቀን ዘመቻ መግለጫ በሰጡበት የትናንት ረቡዕ መጋቢት 23 ቀን 2007 ዓም ጋዜጣዊ መግለጫቸው አነጋጋሪ ስለሆነው የንጹሃን ጥቃት መረጃ አሰምተዋል::

* ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ ባሳለፍነው ሰኞ ከ40 በላይ ስለሞቱበት እና ከ200 በላይ በቆሰሉበት በአነጋጋሪው የተባበሩት መንግስታታ የስደተኞች ድርጅት UNCR በሃጃ ክልል በሚገኘው የመዝራ መጠለያ ጣቢያ ጥቃን አጣርተው እንደሚያቀርቡ በገቡት ቃል መሰረት ተጣርቷል ባሉት መረጃ ጥቃት ፈጻሚዎቹ በጥቃቱ ክፉኛ የተጎዱት ሁቲዎች መሆናቸውን አብራርተዋል ።

* ዘመቻው በተጣራ መረጃዎችን እንጅ ሰላማዊ ነዋሪዎች የሚገኙባቸው ቦታዎች ኢላማ እንደማያደርግ በማስረዳት በተለይም በተባበሩት መንግስታታ የስደተኞች ድርጅት UNCR በመዝራ መጠለያ ጣቢያን ጥቃት በሚመለከት ሲናገሩ በንጹሃን ላይ ጥቃት የተፈጸመበት ሞርታር መሳሪያ የሁቲ ሸማቂዎች ይጠቀሙበት እንደነበር መረጋገጡን በአጽንኦት አስታውቀዋል ። ከዚሁ ጋር አያይዘው ሁቲዎች በጥቃቱ ሲዳከሙ በንጹሃን እልቂት አዘኔታ ለማግኘት የረከሰ ስልት መጠቀም መጀመራቸውን አሳፈሰሪነት ” የቆሸሸ ስልት! ” ሲሉ አንቋሸውታል ! ብ.ጀኔራል አሲሪ ስለ መጠለያው ጥቃት ማብራሪያቸውን ሲያጠቃልሉ በሁቲ ሽማቂዎች የሞርታር ጥቃት የተፈጸመ እንጅ የአየር ድብደባ ጥቃት አለመሆኑ መረጋገጡን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል::

* ጥቃት የደረሰበት መጠለያ የሞቱት ዜጎች ዝርዝር መግለጫ ባይወጣም መጠላያው በየመን እርስ በርስ ጦርነት የተፈናቀሉ የመናውያንና ከምስራቅ አፍሪካ ወደ የመን የመጡ ስደተኞች መጠለያ እንደሆነ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ተጠቅሷል::

* በመዝራ መጠለያ ጣቢያ በደረሰው ጥቃት የሞቱትና የቆሰሉት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ስለመሆናቸው አለመሆናቸው ግን እስካሁን ምንም የተጨበጠ መራጃ በአረቡ አለምም ሆነ በምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን አልተጠቀሰም::

* በተመሳሳይ ሁኔታ በጠንካራው የአየር ጥቃት የተሸበሩት የሁቲ አማጽያን ንጹሃንን መሸሸጊያ የማድረግ ስልት መጠቀማቸውን የጠቆሙት ቃል አቀባዩ በአልሆዴዳ የወተት ፋብሪካው በተመሳሳይ ሁኔታ የሁቲ አማጽያን ተንኮል የተፈጸመ እንደሆነ አልደበቁም::

* የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥቃቱ አለም አቀፍ ህግን የጣሰ ነው በማለት ጥፋተኞች በተፈጸመው ወንጀል በኃላፊነት መጠየቅ አለባቸው የሚል መግለጫ ማውጣቱ አይዘነጋም …
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
መጋቡት 24 ቀን 2007 ዓም

The post (የሳዑዲ እና የመን ጉዳይ) “ወሳኙ ማዕበል” የ7ኛ ቀን መግለጫ … (ነብዩ ሲራክ) appeared first on Zehabesha Amharic.

የሳኦል ፍሬዎች ፊልም ተመረቀ  

$
0
0

seol2በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ ‘የሳኦል ፍሬዎች’ በሚል ርዕስ በበርገን ቅርጫፍ የኢሳት ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ አስተባባሪነት የተዘጋጀው ፊልም በርካታ እንግዶች በተገኙበት በማርች 28 ቀን 2015 ዓ.ም በኖርዌይ በርገን ከተማ በቢከስ  አዳራሽ ተመረቀ።

ይህ ፊልም በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰባዊ መብት ጥሰት ፣የአካዳሚ ነፃነት ማጣት፣የፍትህ መጓዋደል እና በስደት አለም ውስጥ ዜጎች የሚገጥሙዋቸውን የህይወት ውጣውረዶች ከፍቅር ጋር በማስተሳሰር ይዳስሳል::

በእለቱ ዝግጅቱን የመሩት በበርገን ቅርጫፍ የኢሳት ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ ህዝብ ግንኙነት አቶ ዳዊት እያዩ የፊልም ምርቃት ዝግጅት መጀመሩን ያበሰሩ ሲሆን  በበርገን ቅርጫፍ  የኢሳት ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ ሊቀመንብር አቶ ሰለሞን አሸናፊ  እና ጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን   በአዳራሹ ውስጥ ለተገኙት እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡  ይህ በውጪው አለም  ብዙም ያልተሞከረው በሀገራችን እና በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና በደል ኪነጥበብን በመጠቀም መረጃወን ለህዝብ የማዲረስ ዘዴ  “ በሳኦል ፍሬዎች ”  ፊልም  ፈር ቀዳጂነት ለተመልካች ቀርቧል ፡

ከዚህ በመቀጠል የሳኦል ፍሬዎች ፊልሙ ላይ ወደ በርገን አመጣጡን ፣ የተዋንያኑን መረጣ ፣ ከጥናቱ ጀምሮ  እሰከ ፊልም ቀረጻው ስላከናወናቸው ውጣ ውረዶች ቀረጻው የፈጀውን የግዜ ርዝመት ፣ የሰው ሃይል ብዛት እና ፊልሙን እስኪጠናቀቅ ድረስ የነበረውን ውጣ ውረድ ጠቅለል አድርገው ገለጻ ያደረጉት የበርገን ቅርጫፍ ኢሳት ድጋፍ ሰጪ ሊቀመንበር አቶ ሰለሞን አሸናፊ ሲሆኑ በቀጣይ በፊልሙ ላይ ተዋናይ እና ዳይሬክተር ጋዜጠኛ እና ተዋንያን ገሊላ መኮንን የፊልም ፅሁፉን በድጋሚ በማስተካከል (script rewrite) በማድረግ ለፊልሙ ሙያዊ እገዛ በመስጠት ፊልሙ ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ በመቆጣጠር፡አሰልቺውን እና አድካሚውን የኤዲቲንግ ስራ ከባለሙያቹ ጎን ሳትለይ  በመከታተል እና ለመጀመሪያ ግዜ ፊልሙ መመረቅ ያለበት በተሰራበት ቦታ በኖርዌይ በርገን ከተማ ነው በማለት ይህን እድል በማመቻቸት የነበራት ድርሻ ጉልህ ነው : ይህ ድርሻዋም ከአንዳርጋቸው ጽጌ ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ከሌሎቹም ጀግኖቹ ጀርባ ላሉት ሴቶች እህቶቼ መታሰቢያ ይሁንልኝ በማለት ፊልሙ ስላሳለፈው ሁኔታ ገለጻ አድርጋለች ፡፡

ለሳኦል ፍሬዎች ደራሲና ተዋንያን አይንሸት ገበየሁ ካሳ ምንም እንኳ  በእለቱ በዝግጅቱ ላይ ባይገኝም  ፊልሙን የተመለከቱት እንግዶች ለደራሲና ተዋንያን አይንሸት ገበየሁ  ወቅታዊ ሁኔታን የሚያሳውቅ፣ አርዓያና ምሳሌ  የሚሆን  ፊልም ነው በማለት  በመደነቅ ሞቅ ያለ አድናቆታቸውን  በጭብጨባ ገልፀውለታል ፡፡

የበርገን ቅርጫፍ ኢሳት ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ ከዛሬ 4 ወር በፊት ባሳወቀው ኢሳት ይቀጥላል መርህ መሰረት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ከሚያደርጉት ድጋፍ ጎን ለጎን እኛም የአቅማችንን ለመወጣት በተሰራው በዚህ በሳኦል ፍሬዎች ፊልም በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ መተንበታል ብለዋል  ፡፡

  1. ይህ ፊልም ከምረቃው በሃላ ኢሳት በሚደርስባቸው ቦታዎች ሁሉ ፣ በአውሮፓ እንዲሁም በአሜሪካ በሁሉም የኢሳት ቤተሰቦች ባሉበት ቦታ ሁሉ በሚያዝለት የግዜ ሰሌዳ መሰረት ለእይታ ይቀርባል ከዚህ ከሚያገኘው ገቢ በሃገራችን ላይ በመረጃ እጥረት በወያኔ የሃሰት ማታለያ እየተጨብረበረ ላለው ወገናችን ኢሳት የህዝባችን አይንና ጆሮ ሆኖ እንዲቀጥል የኢኮኖሚ ድጋፍ በመሆን ያገለግላል እንዲሁም በኢሳት ቴሌዚዠን ይተላለፋል በተጨማሪም ከእይታ ሲወርድ በቪሲዲና በዲቪዲ ተባዝቶ ለህዝቡ ለሽያጭ ይቀርባል ፡፡
  2. በወያኔ እየደረሰብን የሚገኘውን አፈና ግድያ ስደት የህዝባችንን በደል በተወሰነ መልኩ አሳይተንበታል ይህ ፊልም የመጀመሪው በመሆን ብዙ የተደበቁ እውነተኛ ታሪኮችን መሰረት ያደረጉ ሌሎች ፊልሞችም እንዲሰሩ መነሻ ይሆናል ፡፡

በአጠቃላይ በዚህ ደረጃውን ጠብቆ በተሰራው ፊልም ላይ ለተሳተፉ የውዲቷ ሃገራችን  ልጆች ከኢሳት ማኔጅመንት እና ከበርገን ቅርጫፍ የኢሳት ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ የተዘጋጀላቸውን አበባ እና የምስጋና የምስክር ወረቀት ፡ አዘጋጁ ኮሚቴ በ 3 ክፍል ከፍሎ አበርክቶላቸዋል ፡፡

በምረቃው ላይ ከተገኙ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መካከል  ለ3ቱ ስጦታውን የሰጡልን በበርገን ቅርጫፍ  የኢሳት ድጋፍ ሰጪ ሊቀመንበር አቶ ሰለሞን አሸናፊ ሲሆኑ
በአንደኛ መደብ ተሸላሚ ደራሲና ተዋንያን የፊልሙ መሰረት መነሻ የሆነው  ወጣት ደራሲ አቶ አይንሸት ገበየሁ ካሳ          / ተፈሪን ሆኖ የተወነው / ሲሆን ምንም እንኳ በእለቱ  ባይገኝም በተወካይ በኩል ስጦታው ተሰጥቶታል ፡፡ ሁለተኛዋ  ተሻላሚ ፊልሙ ደረጃውን ጠብቆ እንዲሰራ ፣ የፊልሙን ድርሰት ሪ ራይት እና ዳይሬክት በማድረግ ሙያዊ እገዛ ስታደርግ  የነበረችው ሪ ራይተር እና ተዋንያን ገሊላ መኮንን ነበረች ፡፡ በሶስተኛ ደረጃ ተሸላሚ የነበረው ይህ ፊልም  ለታሪክ እንዲተላልፍ ከንብረቱ ከሙያው በተጨማሪ ከሳኦል ፍሬዎች ደራሲ ጋር በመነጋገር ለኮሚቴው ሃሳቡን ይዞት የመጣው እንዲሁም በተዋንያን መረጣ ሰፊውን ድርሻ ወስዶ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የቀረጻውን ስራ ሲያከናውን የነበረው ካሜራ ማን አቶ ቶማስ አለባቸው ነበሩ  ፡፡

በሁለተኛ መደብ ተሸላሚ የነበሩት መሪ ተዋንያኑ  ሲሆን ስጦታውን የሰጡልን በበርገን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀ መንበር አቶ ተስፋዬ ኮርፊል ነበሩ ፡ የመጀመሪያው ተሸላሚ በፊልሙ ላይ ዋናውን ገጸ ባህርይ ወክሎ የተወነው ወጣት መክብብ ሙሉጌታ ( ሃይሉን ሆኖ የተወነው) ሲሆን  ሁለተኛው ተሸላሚ ለፊልሙ ማማር የራሱን ድርሻ በሚገባ የተወነው አቶ ሳሙኤል ተወልደ ( መሃሪ) በሶስተኛ ተሸላሚ አቶ አንተነህ አማረ (ወዲ ጠቆ) በአራተኛ ተሸላሚ የሴቶችን ተሳትፎ በማሰደግ ላይ የምትገኘው ወ/ሪት ሜሮን አድማሱ (ማስተዋል) በመሆን ስጦታቸውን ተቀብለዋል ፡፡

በሦስተኛ መደብ ተሸላሚ የነበሩትን ተዋንያን ስጦታው የሰጡልን በበርገን ነዋሪ የሆኑት በሃገራዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ሁሌም ከወገናቸው ጎን በመቆም የሚታወቁት ወ/ሮ ምስራቅ ነበሩ ፡፡ የመጀመሪያው ተሸላሚ አቶ ብሩክ ጌታነህ (ዋሴን ሆኖ የተወነው ) ሁለተኛው ተሸላሚ አቶ ሰለሞን አሸናፊ (ቦጋለን ሆኖ የተወነው) ሦስተኛዋ ተሸላሚ ከነቤተሰብዋ ወ/ሮ ሰላም በጋሻው (የመሰረት ጓደኛ ሆኖ የተወነችው) አራተኛ ተሸላሚ አቶ ዳዊት እያዩ ( ደህንነት ) አምስተኛ ተሸላሚ አቶ ማንደፍሮ መንግስቱ (የደህንነት ሹፌር) ስድሰተኛ ተሸላሚ አቶ ሺበሺ ጌታቸው (ፖስተር ዲዛይነር) ሰባተኛ ተሸላሚ አቶ ዮናስ በመሆን ስጦታቸውን ተቀብለዋል ፡፡ በመቀጠልም በምረቃው ላይ ከተገኙ እንግዶች አርቲስቶች አንዲሁም ከተሣታፊዎች መካከል በፈልሙ ዙሪያ ወይይት ተደርጓል።

በፊልሙ ምርቃት ላይ ከአመስተርዳም ጋዜጠኛ እና አርቲስት ገሊላ መኮንን ፣ በበርገን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር አቶ ተስፋዬ ኮርፊል፣ ጥሪ የተደረገላቸው የኢትዮጵያ ወዳጆች  እንዲሁም የበርገን ነዋሪዎች እና በፊልሙ የተሳተፉና ተጋባዥ አርቲስቶች ተገኝተዋል።
በመጨረሻም የበርገን ቅርጫፍ የኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ ፊልሙ እንዲሰራ በማስተባብር ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ልምድና ትምህርት አግኝቶበታል በቀጣይም ከዚህ የተሻለ ስራ ይዞ ለመቅረብ በእቅዱ ውስጥ አስገብቶ እየሰራበት ይገኛል ፡፡ የሳኦል ፍሬዎች ፊልም መነሻነት፡ ደፍረው ያልተነገሩ የወያኔ የአደባባይ ሚስጢሮች በሰፊው ለህዝብ ቀርበው ህዝቡ ፍርድ እንዲሰጥበት ማድረግ የአገዛዙን ድብቅነትና ውሸት ማጋለጥ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው ፡፡ ይህ ፊልም የፍርሃታችንን ድባብ አስወግዶ በሌላም ቦታ እንደዚህ የመሰሉ ስራዎች እንዲሰሩ ፈር ቀዳጅ ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ፡፡ የሳኦል ፍሬዎች ቧልትና ቀልድ በበዛበት ዘመን ደፍሮ የተሰራ ኮስተር ያለ ፊልም ነው ፡፡ የማይነካውን ነክቶ ያሳየ መንገዱን ያመላከተ ፊልም ነው እኛ የምንችለውን አድርገናል ከዚህ በላይ የተሻሉ ስራዎች እንደሚሰሩ ተሰፋ እናደርጋለን ፡፡

የበርገን ቅርጫፍ ኢሳት ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ ህዝብ ግኑኘነት

አቶ ዳዊት እያዩ

The post የሳኦል ፍሬዎች ፊልም ተመረቀ   appeared first on Zehabesha Amharic.

የሠላማዊ ትግላችን የፓለቲካ አመራሮችን ውጭ እንዳይወጡ በማገድና በምርጫ ቦርድ ፖርቲዎችን የማፍረስ ሴራ በፍጹም አይቋረጥም፤ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!

$
0
0

semawi

ከሰማያዊና ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበራት የተሠጠ መግለጫ

ውድ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፤ ከውጭም፣ ከውስጥም፣ ያላችሁ፦

ሕውሃት/ኢህአዴግ ጠንካራ ተቃዋሚ የለም በማለት በብቸኝነት በሚቆጣጠራቸው የመገናኛ ሚዲያዎች በሕዝቡ እያላገጠ በስተጀርባ ግን የፖለቲካ አመራሮችንና የፖርቲዎችን ሕልውና ማሣደድ ቀጥሎበታል፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት የአንድነት ፓርቲን ማፈራረሣቸው አልበቃ ብሏቸው አሁን ደግሞ በትናትናው ዕለት የሰማያዊ ፖርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ወደ ውጭ እንዳይመጣ በማንአለብኝነት በእብሪት በመወጠር ከቦሌ አለም አቀፍ አውሮኘላን ማረፊያ ከልከለው መልሰውታል፡፡ በሃሰት ሚዲያዎች ሕዝቡን አፍኖ በመያዝ አገዛዙን ለመቀጠል እየተውተረተረ በሚገኝበት በአሁኑ ሰዓት ቆራጥ የሆኑ የሠላማዊ ትግል አመራሮችንና አባላትን እያዋከበ ትግሉን ለማሰናከል ከመቼዉም ጊዜ በላይ ቀጥሎበታል፡፡ የኢንጂነር ይልቃል የውጭ በሪራ ጉዞ የመከልከል ህገ-ወጥ ድርጊትም ከነዚህ ዕኩይ ተግባራቸው አንዱ ነው፡፡

የኢህአዴግ ባለስልጣናትና የቢሮ ኃላፊዎቻቸው በመንግስታዊ መዋቅር ሥልጣናቸዉን በመጠቀም የተለመደውን የማታለልና የህገ-ወጥነት ተግባራቸውን ተግተው ቀጥለውበታል፡፡ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ህልውና ቀምቶ ለታማኝ ግለሰቦች በመስጠት የሚደረገውን የነፃነት ትግል ለማኮላሸት በሃሰት በመወንጀል በህገ-ወጥነት አባሎቻቸውን ማሣደድና ማሠር፣ ሃብታቸውን መዝረፍ፣ ግድያ፣ እስር፣ ማዋከብና፣ ከቦታ ማፈናቀል የዕለት፡ዕለት ተግባራቸው ሆኗል፡፡

ውድ ነፃነት ናፍቂ ኢትዮጵያውያን፦

የኢህአዴግ ዘረኛ መንግስት በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ጭቆና/ስቆቃ ለመከላከል ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት፣ በአንድ ድምፅ ፣አገዛዙን መቃወም ይገባናል፡፡ አምባገነኖች በሚያደርሱብን ጭቆና እና አስተዳደራዊ ግፍ ተሠላችተን ተስፋ መቁረጥ በየትኛውም መስፈርት መፍትሔ አይሆንም፤ መፍትሔው ጨቋኙን ኃይል ታግሎ አሸቀንጥሮ መጣል ነው፡፡ ስለሆነም የፖርቲዎችን ሕጋዊ ህልዉና በማሣጣት፣ ሠለማዊ ትግሉን በማደናቀፍና የፖለቲካ አመራሮችን ወደ ወጭ እንዳይወጡ በመከልከልና በተለያዩ የአገዛዙ የውንብድና ድርጊቶች ሠላማዊ ትግላችን ለአንድም ሰከንድ አይቋረጥም!  እንዳውም የበለጠ እልህ እንድንገባና ትግላችንን አጠናክረን ድጋፋችንን ለሠላማዊ ትግል ኃይሎች  የማቴሪያልና የሞራል ትብብራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ በትናትናው ዕለት የሠማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ወደ ውጭ እንዳይወጣ አገዛዙ በማንአለብኝነት ቢከለክለውም እኛ እዚህ በውጭ አገር ያለን ደጋፊዎችና አባላት በየከተሞች በወጡት የስብሰባ ቀኖች መርሐ-ግብር መሠረት በየዕለቱ በየቦታው በመገኘት መላው ደጋፊያችንና የነፃነት ናፋቂ ኢትዮጵያውያን ሁሉም በነቂስ በመውጣት ስብሰባዎቻችንን በደማቅ ሁኔታ ከመሪዎቹ ጋር ከአዲስ አበባ ዘመኑ ባፈራው የጥበብ ውጤት በመጠቀም እንድናከናውን በቂ ዝግጅት አድርገናል፡፡ ሕዝባችንም በየስብሰባዎቹ በመገኘት ድጋፋን በበለጠ ሁኔታ እንደሚያሣይ አንጠራጠርም፡፡ በዚህ አጋጣሚም ጥሪያችንን በአክብሮት እናስተላልፋለን፡፡

የስብሰባዎች መርሐ ግብር ከዚህ ደብዳቤ ጋር ተያይዞ ቀርቧል፡፡

የአንድነትና የሠማያዊ ድጋፍ ማህበሮች በሰሜን አሜሪካ አስተባባሪ ኮሚቴ

The post የሠላማዊ ትግላችን የፓለቲካ አመራሮችን ውጭ እንዳይወጡ በማገድና በምርጫ ቦርድ ፖርቲዎችን የማፍረስ ሴራ በፍጹም አይቋረጥም፤ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል! appeared first on Zehabesha Amharic.

ፍትህ መረገጡን ባደባባይ አስመስክረናል፤ሃላፊነታችንንም ተወተናል!!

$
0
0
ተክሌ በቀለ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት

ተክሌ በቀለ 

ለኔ እዉነተኛዉ የአንድነት ፓርቲ ትናንት በፍ/ቤት ዉሳኔ ተቀብሯል፡፡ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል እንደሆን ቀድም ሲል አዉቀናል፡፡ዳኛ ብርቱኳንም ፍርህይወትም ዳግም አልተከሰቱም፡፡እንደ ኢህአዴጉ የምርጫ ዉጤት 99.6 ከመቶዉ አመራሩና አባላቱ በምርጫ ቦርድ እንዲበተኑ የተበየነበት እንዲሁም በደጋፊዎች የተገዛ ንብረት ያለፍ/ቤት ትእዛዝ በመንግስት ታጣቂ ፖሊሶች የተዘረፈበት አንድነት የፍትህ ተቋሙን ለመፈተሸ ም/ቦርዱን መክሰሱ ይታወቃል፡፡

ም/ቦርድን መክሰሳችን አግባብ እንዳልሆነ አንቀጽ ተጠቅሶ ከማስፈራሪያ ጋር ክሱ ዉድቅ ተደርጓል፡፡ መፍትህ መረገጡን ባደባባይ አስመስክረናል፤ሃላፊነታችንንም ተወተናል፡፡ቀጣዩን በቀጣይ ሂደት የምናየዉ ይሆናል፤እንደሚፈልጉት ተበትነን አንቀርም፡፡አንድነቶች በያለንበት እንረጋጋ!!
ታላቋ ምእራብ አፍሪካዊት ሃገር ናይጀሪያ እዚህ የደረሰችዉ ዉድ ዋጋ ከፍላ ነዉ፡፡ከናይጀሪያም በላይ ዋጋ ብንከፈልም በልተዉ በማይጠግቡ በሎች ትግሉ እየተነጠቀ ዛሬም እዛዉ ላይ ነን፡፡ታላቅዋ የምስራቅ አፍሪካ ኮከብ ሀገረ ኢትዮጵያ በልማት ስም ክብሯ እንዲወርድ እየተደረገች ትገኛለች፡፡እናም በዲፕሎማሲ፤በዲሞክራሲ፤በኢኮኖሚም ይሁን በሁለንተናዊ ልማት የአለም ማህበረሰብ በአፍሪካ ትኩረት ናይጀሪያ ሆናለች፡፡ኢትዮጵያ የምትፈለገዉ ለክፍለአሁጉሩ የደህንነት አጋርነት ብቻ ነዉ፡፡

የናይጀሪያ ተፎካካሪ ፓርቲዎችና(የተቀናቃኝ ፓርቲዎች ትብብርና ዉህደት ያስከተለዉን ዉጤትም ልብ ይሏል) የተወዳዳሪ ግለሰቦች ሚና ቀላል ባይሆንም ለናይጀሪያ ተስፋ የሆናት ግን ህዝቡ ነዉ፡፡የኢትዮጵያችንም የለዉጥ ተስፋ ህዝቡ ነዉ፡፡በዚህ ወቅት የተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎች አሰላለፍም የጎላ ድርሻ ይኖረዋል፡፡

The post ፍትህ መረገጡን ባደባባይ አስመስክረናል፤ሃላፊነታችንንም ተወተናል!! appeared first on Zehabesha Amharic.

የጊፍት ሪል እስቴት ጉዞ በስም ማጥፋት ዘመቻ ወደኋላ አይመለስም

$
0
0

ከጊፍት ግሩፕ ኩባንያ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ

nlmqi6fn76e6fjt0pj5uይህ ጽሁፍ “ጊፍት ሪል እስቴት  ወደፊት ወይስ ወደኋላ” በሚል ርዕስ ‘አበበ ወርዶፋ’ በተባሉ ግለሰብ  ለተጻፈውና ጸሃፊው ‘ሪል እስቴቱ ጉዳት ያደረሰብኝ ደንበኛ ነኝ’ በሚል ሽፋን የኩባንያውን መልካም ስም ያለአግባብ ለመጉዳት በማሰብ እ.ኤ.አ ማርች  24 እና 25 ቀን 2015 ze-habesha.com እና satenaw.com ድረገጾች ላይ ለንባብ ላበቁት ሃተታ  የተሰጠ ምላሽ ነው።

ጸሃፊው በቂ ማስረጃ ሳይኖራቸው ግነት የተሞሉና ከሃቅ የራቁ መረጃዎችን በመደርደር በስሜት ብቻ ተነሳስተው ላቀረቡት ትችት መልስ ከመስጠት በፊት “ጊፍት ሪል እስቴት ማነው?” የሚለውን ጥያቄ መመለስ ተገቢ ይሆናል። ይህን ማድረግ የሚያስፈልገው በብዙዎች ዘንድ የታወቀ መልካም ስምና ዝና ያለውን ጊፍት ሪልእስቴትን እንደአዲስ ኩባንያ ለማስተዋወቅ ሳይሆን አንባቢ የሁለቱንም ወገን ጽሁፎች ሲያነብ በጉዳዩ ላይ ሙሉ ስዕል እንዲኖረው ማድረግ ተገቢ በመሆኑ ጭምር ነው።

በኢትዮጵያ የግል የሪል እስቴት ዘርፍ ለመሰማራት ቀዳሚ ከሆኑት ኩባንያዎች አንዱ ጊፍት ሪል እስቴት ነው፡፡ ጊፍት ሪል እስቴት ሲኤም ሲ እና ሃያት አካባቢ በተረከበው 16.3 ሄክታር መሬት ላይ በሶስት ፌዞች የተለያየ ዲዛይን ያላቸው ከ300 በላይ ዘመናዊ ቪላዎችንና ታውን ሃውሶችን እንዲሁም 44 ብሎክ         አፓርትመንቶችን በአጠቃላይ እስከ አንድ ሺህ የሚደርሱ አባወራዎችን መያዝ የሚችሉ መኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ በተለያየ ደረጃ ለተጠቃሚዎች እያስተላለፈ ሲሆን አሁንም በመጠናቀቅ ላይ ያሉትን ጨምሮ አዳዲስ ግንባታዎችን በማካሄድ ላይ የሚገኝ ኩባንያ ነው።

ጊፍት ሪል እስቴት የሚያከናውነው የቤቶች ግንባታ ስራ ሰፊና በካፒታል ደረጃ ሲሰላም 2 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ኢንቨስትመንት ነው። በግንባታው ሂደት እስከ 2ሺህ የሚደርሱ በተለያየ የሙያ ደረጃ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞችን በማሳተፍም ለዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር የቻለ ሃገርበቀል ኩባንያ ነው።

ጊፍት እንደ ቢዝነስ ግሩፕ ኩባንያ በሪል እስቴት ልማት ዘርፍ ላይ ለመሰማራት እቅድ ሲነድፍና ምክረሃሳቡን ለአዲስ አበባ አስተደደር አቅርቦ መሬት ሲረከብ ዓላማው ቢዝነሱን ማስፋት ብቻ አልነበረም።  ኩባንያው በመመስረቻ ሰነዱ ላይ ካስቀመጣቸው ተቀዳሚ አላማዎች (core objectives) ዋናው በሃገር ውስጥ እየኖሩ ደረጃውን የጠበቀ ምቹና ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ባለቤት መሆን ለሚፈልጉ እንዲሁም በውጭ ሃገራት እየኖሩ በሃገራቸው ውስጥ ማረፊያ የሚሆናቸውና ከሰለጠነው ዓለም ጋር ተመጣጣኝ ደረጃ ያለው መኖሪያ ቤት እንዲኖራቸው ለሚመኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ፍላጎታቸውን የሚያረካ አገልግሎት የሚሰጥ ሃገር በቀል ሪልእስቴት አልሚ መሆን ነው። ጊፍት ሪል እስቴት እስካሁን እያከናወነ ያለው ስራ ይህንኑ ዓላማ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ያተኮረ ነው።

ሪል እስቴቱ ግንባታ የሚያካሂድባቸው ሲኤምሲና ሃያት አካባቢዎች ለመኖሪያነት አንደኛ ደረጃ ተመራጭ  ከሆኑት የአዲስ አበባ አካባቢዎች በቀዳሚዎቹ ተርታ ላይ የሚገኙ መሆናቸውና የቦታውና የቤቶቹ ኢንቨስትመንት በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መሄዱ በደንበኞች ዘንድ የጊፍትን ቤቶች ቀዳሚ ተመራጭ ሊያደርጓቸው ከቻሉት ምክንያቶች ዋናው ነው።ይህንን ሃቅ በሃገር ውስጥም ይሁን  በውጭ ሃገራት የሚኖሩ ኩባንያው ቤት የገነባላቸው ደንበኞች በተደጋጋሚ የሚናገሩት ነው።

ጊፍት ሪልእስቴትን በተመለከተ  እንደመረጃ ከላይ የሰፈሩትን ነጥቦች ካነሳን ከዚህ በመቀጠል  ጸሃፊው በሰነዘሯቸው ትችቶች ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ በማትኮር አንባቢ ሃቁን አገናዝቦ ይረዳ ዘንድ እውነታውን ለማሳየት እንሞክራለን።

ጸሃፊው የሪል እስቴቱ ደንበኛ አይደሉም

ጊፍት ሪል እስቴት ካሉት ከ300 የሚበልጡ ቤት የገዙት ደንበኞች ዝርዝር ውስጥ አበበ ወርዶፋ የሚባሉ ግለሰብ የሉም።ጸሃፊው ‘አበበ ወርዶፋ’ በሚል ስም የሪል እስቴቱ ደንበኛ እንደሆኑ በመግለጽ ሃተታ የመጻፋቸው ዋነኛ ዓላማ በአንባቢያን ዘንድ እምነት በማግኘት የስም ማጥፋት እቅዳቸው እንዲሳካ ከማድረግ የዘለለ አይሆንም። ሪል እስቴቱ ካልገለጸ በቀር አንባቢያን የኩባንያውን ደንበኞች ዝርዝር ለማወቅ አጋጣሚው እንደማይኖራቸው የሚገነዘቡት ጸሃፊው ይህንን ክፍተት በመጠቀም ራሳቸውን ጉዳት እንደደረሰበት ደንበኛ አድርገው ማቅረባቸው ትችታቸው በቀላሉ ተዓማኒነትን እንዲያገኝ መንገድ ይከፍታል። ነገር ግን ጸሃፊው አሳንሰው እንዳዩት ሳይሆን አንባቢ ይጠይቃል፣ያገናዝባል፤ይፈርዳልም።

በሌላ በኩል ጸሃፊው ጊፍት ሪልእስቴት ቤት የሚገነባላቸው ደንበኛ መሆናቸው እንዳይታወቅባቸው ሲሉ ወይም በራሳቸው የተለየ ምክንያት (መቼም ሪልእስቴቱ ለደህንነቴ ያሰጋኛል እንደማይሉ ተስፋ እናድርግና )  በብዕር ስም ተጠቅሜያለሁ ቢሉ እንኳን  ለሃቀኝነታቸው ጥቂት ማሳያዎችን ብቻ ማቅረብ ዳገት አይሆንባቸውም ነበር።

ለምሳሌ ከሪልእስቴቱ ገዝቻለሁ ያሉት መኖሪያ ቤት ጊፍት ከሚገነባቸው የተለያየ ዓይነትና ዋጋ ካላቸው ቤቶች ውስጥ የትኛው መሆኑ፣ለግንባታው ምን ያህል ዋጋ እንደከፈሉ ፣ቤቱ ከሶስቱ የጊፍት ሳይቶች የትኛው ሳይት ላይ እንደሚገኝና ከመሰል ተያያዠ መረጃዎች አንዱን እንኳን  ሳይገልጹ በደፈናው ‘ደንበኛ ነኝ’ ብለው ማለፋቸው ትችታቸው ገንቢ ሳይሆን አፍራሽ ዓላማ ያለው መሆኑን በግልጽ ያሳያል።ይህም በደንበኛ ስም አንባቢንና የጊፍትን ደንበኞች በማሳሳት ስም የማጥፋት አጀንዳ እንደያዙ ይመሰክራል። ይህን ሁሉ መረጃ መግለጽ አያስፈልገኝም ቢሉ እንኳን ኩባንያው ደንበኝነታቸውን ለማወቅና ያቀረቧቸውን ትችቶች ለመመዘን የሚችልበትን አንድም ተጨባጭ እውነት አለማስቀመጣቸው ግን ፍላጎታቸው መፍትሄ ማግኘት ሳይሆን ድርጅቱን በመልካም ዝናው የሚያውቁትን በውጭ ሃገራትና በሃገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለማሳሳትና የተዛባ ግንዛቤ እንዲይዙ የማድረግ ዓላማ ይዘው መነሳታቸውን ይመሰክራል።

 

የተዛቡና የሚጋጩ መረጃዎች

ይህንን እንዳለ ብንቀበለው እንኳን  የዛሬ 7ዓመት ከጊፍት ሪል እስቴት ቤት ገዝቻለሁ ያሉት እኚሁ ጸሃፊ “መቶ በመቶ ብትከፍሉ በፍጥነት ይደርስላችኋል ተብለን ስለነበር የቤቱን ዋጋ 100% ከፍያለሁ” ብለዋል። እውነቱ ግን የዛሬ 7 ዓመት 100% ከፍሎ ከሪል እስቴቱ ቤት የገዛ ደንበኛ የሌለ መሆኑ ነው። ከ 3 ዓመት ወዲህ ባሉት ጊዜያት ቅድሚያ 100% ክፍያ ከፍለው ቤት ለገዙ ደንበኞቹም ሪል እስቴቱ 6 በመቶ ቅናሽ አድርጎላቸው ቤታቸውንም ገንብቶ አጠናቆ አስረክቧቸዋል።

ጸሃፊው “ቤታችሁ በፍጥነት ይደርስላችኋል ተብለን 100% ከፈልን” ያሉትም ቢሆን ከእውነት የራቀ ነው።ሪልእስቴቱ ቅድሚያ ሙሉ ክፍያ ለሚፈጽሙ ደንበኞች  6% የዋጋ ቅናሽ ከማድረግ  ውጪ ቤታችሁን  ከ18 ወራት በታች በሆነ ጊዜ በፍጥነት ሰርቼ አስረክባለሁ የሚል ስምምነት ከየትኛውም ደንበኛ ጋር አልገባም። እኚህ ጸሃፊ በየትኛውም የጊፍት ደንበኛ እጅ ውስጥ የሚገኘውን ውል በማየት በቀላሉ መረጋገጥ ከሚችለው ከዚህ እውነት ተቃራኒ የሆነ ቃል እንደተገባላቸው በማስመሰል በተዛባና እርስ በርሱ በሚጋጭ መረጃ አንባቢን ለማሳሳት ሞክረዋል።

የጸሃፊው ሌላ ግድፈት የዛሬ 7 ዓመት 100% ከፍያ ፈጽመው ነገር ግን የቤታቸው ግንባታ መሰረት ከማውጣት አለማለፉን መግለጻቸው ነው። ጊፍት ሪል እስቴት ውል ገብቶ የቤታቸውን ግንባታ ከሚያከናውንላቸው ደንበኞች መካከል ብዙዎቹ ቤታቸውን በተለያየ የግንባታ ደረጃ ተረክበዋል። በቅርብ ጊዜ ከኩባንያው ቤት ለገዙ ደንበኞች እየተገነባ የሚገኘው መኖሪያ ቤት የደረሰበት ደረጃ የተለያየ ቢሆንም ቅሉ ጊፍት ሪልእስቴት በራሱ ወጪ ገንብቶ ሊሸጣቸው እየገነባቸው ከሚገኙ ቤቶች በቀር ደንበኛ ክፍያ ፈጽሞበት ሳይገነባ የቀረ አንድም ቤት የለም። በጽሁፉ ውስጥ  ይህንን ፍጹም የተጋነነና ከተዓማኒነት የራቀ ትችት ለማስፈር የተፈለገበትን ዓላማ የሚያውቁት ራሳቸው ጸሃፊው ብቻ ናቸው።

የባለቤትነት ማረጋገጫ ያለው ማን ጋር ነው!

ጸሃፊው በሃተታቸው ውስጥ “ጊፍት  ቤት ላስረከባቸው ህጋዊ ገዠዎች የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለም” የሚል ጭፍን ትችት አስፍረዋል።ከዚህ በተጨማሪም “የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ሲጠየቅ የሚያመካኘው በመስተዳድሩ ላይ ነው” ብለዋል። ጸሃፊው በርግጥም የጊፍት ደንበኞችን አነጋግረው ከሆነ (እርሳቸው የጊፍት ደንበኛ ስላልሆኑ) የባለቤትነት ማረጋገጫ የመስጠት ሃላፊነት የማን እንደሆነና እስካሁን የዘገየውም በምን ምከንያት እንደሆነ በሚገባ ይገነዘቡ ነበር።

ጊፍት ለገነባቸውና ለደንበኞቹ ላስረከባቸው ቤቶች የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር እንዲሰጠው በአሰራሩ መሰረት የየካ ክፍለከተማንና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽህፈት ቤቶችን በተደጋጋሚ ጊዜ ጠይቋል። በአፈጻጸሙ መዘግየት ሳቢያም እስከላይኛው የአስተደደሩ የስልጣን እርከን የደረሱ ተደጋጋሚ አቤቱታዎችን አቅርቧል። ድርጅቱ በክፍለከተማው በኩል የገጠመውን የአገልግሎት መዘግየት ችግር ለመፍታትና የጀመረውን የቤቶች ልማት በውሉ መሰረት አጠናቅቆ ለደንበኞቹ ለማስረከብ ያደረጋቸው ጥረቶች ተገቢ ባልሆኑ አሰራሮች ተጓተዋል። ይህንንም ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቋል።ጊፍት ምን ያህል ጊዜ በጉዳዩ ላይ ከአስተዳደር አካላቱ ጋር ውይይት እንዳደረገ ከተጻጻፋቸው ደብዳቤዎች ጭምር ጉዳዩን መረዳት ለሚፈልግ አካል ማሳየት ይችላል።

ያም ሆኖ እስካሁን ኩባንያው ጉዳዩ ሲጓተትበት ቢቆይም በቅርቡ በተደረጉ ጥረቶች ግን ችግሩ እልባት ለማግኘት ወደሚችልበት መስመር ገብቷል።በአሁኑ ወቅት ከኩባንያውና ከክፍለከተማው የህግ ክፍል ጋር በመሆን  በጋራ የማጣራት ስራዎች እየተሰሩ ነው።ጊፍት ይህ ችግር በቅርብ ጊዜ አልባት እንደሚያገኝ ያምናል።

ጸሃፊው እንዳሉት ጊፍት ለደንበኞቹ ካርታ ባለመስጠት ተጠቃሚ አይደለም። በተቃራኒው በቅርቡ መፍትሄ የሚያገኝ ቢሆንም ካርታው ከላይ በተገለጹት ምክንያቶች በመዘግየቱ ምክንያት የተወሰኑ ቤታቸውን የተረከቡ ደንበኞች የመጨረሻውን ክፍያ እንዳይፈጽሙ እንቅፋት ሆኗል። በዚህም ኩባንያው  ከተወሰኑ ደንበኞች ገቢ መሰብሰብ አልቻለም። ይህም የኢንቨስትመንቱን ወጪ ሸፍኖ ስራውን ለማቀላጠፍ በገቢ አሰባሰብ ስርዓቱ ላይ ጫና አሳድሯል። በሌላ አነጋገር አስተዳደሩ  የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ አለመልቀቁ ለኩባንያውም ጉዳት ነው።

እውነቱ የህ ሆኖ ሳለ ጸሃፊው  ጊፍት የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተሩን በእጁ ይዞ ለደንበኞቹ መስጠት እንዳልፈለገ አስመስለው ተችተዋል። ዓላማቸው የኩባንያውን ስም ማጥፋት ባይሆን ኖሮ “ጊፍት የደንበኞቹን ካርታ መያዙ የራሱን ገቢ ከማስቀረት የዘለለ ምን ይጠቅመዋል?” የሚል ቀላል ጥያቄ በመጠየቅ ብቻ መልሱን ከራሳቸው ማግኘት ይችሉ ነበር።

የመንገዱ ጉዳይ

ጸሃፊው ወደጊፍት ሪልእስቴት ፌዝ ሁለት ሳይት የሚወስደው መንገድ አለመሰራቱን በተመለከተ ኩባንያውን ተጠያቂ ለማድረግ የግራውን ከቀኝ እያጋጩ ማስረጃ አልባ ክስ ዘርዝረዋል። እንደእውነቱ ከሆነ “ቤቴ መሰረቱ ብቻ ነው የወጣው” በሚል አቤቱታ ትችታቸውን የጀመሩት ግለሰብ ‘ወደቤቴ የሚወሰድ መንገድ አልተሰራልኝም’ የሚል ክስ መጨመራቸው ራሳቸውን በራሳቸው አቃርኗቸዋል።

ጊፍት አሁን ሙሉ በሙሉ ቤት ወደገነባበት ፌዝ ሁለት ሳይት የሚወስደው መንገድ በሪልእስቴት ፕላኑ ላይ በግልጽ ተለይቶ የተቀመጠና የተፈቀደ ነው። ነገር ግን በመንገዱ ላይ ጥቂት ነዋሪዎች በህገወጥ መንገድ ቤት የገነቡ በመሆኑ አስተዳደሩ ወይ ህገወጥ ግንባታውን እንዲያስነሳ ካልሆነም ተለዋጭ መንገድ እንዲያዘጋጅ ከበላይ አካላት ጭምር በደብዳቤ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል። እስካሁን ድረስ ግን ትዕዛዙን ተፈጻሚ አላደረገም። ይህም የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ባለስልጣናትን ጨምሮ የከተማ ስራ አመራርና ማኔጅመንት ኢኒስቲቲዩት ባለሙያዎች ጭምር ያጠኑትና ችግሩ የአስፈጻሚው አካል በመሆኑ ላይ መግባባት ላይ የተደረሰበት ፣በፍጥነት መስተካከል  እንደሚገባውውም ውሳኔ የተሰጠበት ጉዳይ ነው። ጊፍት በዚያ ሳይት ያሉትን ቤቶች ለደንበኞቹ ሙሉ በሙሉ አስረክቦ እስኪያጠናቅቅ የመንገዱ ጉዳይም እልባት እንደሚያገኝ ተስፋ ተሰጥቶታል።

ጸሃፊው ወደዚሁ ሳይት በጊዜያዊነት የሚገባበት መንገድ ኮብልስቶን ያልተነጠፈው ጊፍት መዋጮ ባለመክፈሉ ነው የሚል ትችት አስፍረዋል።አስተዳደሩ ወደሪልእስቴቱ የሚገባውን በማስተርፕላን ተለይቶ የተቀመጠ መንገድ አስከብሮ ነጻ ማድረግ ባለመቻሉ ሳቢያ ግለሰቦች ለህገወጥ ተግባራቸው መጠቀሚያነት ቢያውሉትም ሪልእስቴቱ ግን ውሳኔው ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ ለግንባታ ስራው በጊዜያዊነት የሚጠቀምበትን መንገድ አልምቷል። ይህንን መንገድ በበጋና በክረምት ለመጠቀም በሚያስችል ሁኔታ በኮብል ስቶን ለማሰራትም ከአስተደደሩና በሳይቱ አካባቢ ከሚኖሩት ግለሰቦች ጋር በተደረገ ውይይት ጊፍት ለልማት ከተጠየቀው ገንዘብ ውስጥ 150ሺህ ብር ያለምንም ማቅማማት አዋጥቷል። ከአካባቢው ነዋሪዎች የተሰበሰበው ገንዘብ 40ሺህ ብር ብቻ ስለነበር በቂ ገንዘብ እስኪሰበሰብ ድረስ ኮብልስቶኑ ሳይነጠፍ ዘግይቷል። ከአንድ ወር በፊት ኩባንያው የመንገዱ ስራ ያልተጀመረበትን ምክንያት በተመለከተ የሚያስተባብረውን የአካባቢውን  አስተዳደር ማብራሪያ ሲጠይቅም የልማት ኮሚቴው ላይ በነበሩት  ክፍተቶች ሳቢያ ስራው መዘግየቱ ተነግሮታል።ጊፍት ስራው ከተጀመረ ለአካባቢ ልማት ማንኛውንም ድጋፍ ከማድረግ የማይቆጠብ መሆኑን አሳውቋል።የባለሙያና የማሽን እገዛ ካስፈለገም ድጋፍ እንደሚያደርግ በቅርቡ ከክፍለከተማው ስራ አስፈጻሚ ጋር በጉዳዩ ላይ ባደረገው ውይይት ቃል ገብቷል። ከብዙ ጊዜያት መባከን በኋላ በቅርቡ የፍሳሽ ማስወገጃ ትቦ የመቅበር ስራ እየተሰራ ነው።

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ጸሃፊው ግን ሁሉንም ችግሩን ወደጊፍት ሪልእስቴት በመግፋት ደንበኞች በኩባንያው ላይ እምነት እንዲያጡና የአካባቢው ነዋሪዎችንም ከሪልእስቴቱ ጋር በማቃቃር  እንደህልውናቸው ጠላት እንዲያዩት ሆን ተብሎ የታቀደ ማስረጃ አልባ ሃተታ አቅርበዋል። ይባስ ብለው “ለወረዳው አስተዳደርና ለክፍለከተማው  ሪልእስቴቱ እምቢ ባይ በመሆኑ ከአቅማቸው በላይ ሆኗል” የሚል ኢተዓማኒ መረጃ ተጠቅመዋል።አካባቢውን ለማስተዳደር፣ ህግና ደንብ ለማስከበርና ለማስፈጸም ሃላፊነት የተሰጠው አስተደደር ለሚመራው ህዝብ አንድን ኩባንያ “ከአቅሜ በላይ ነው” ብሎ አቤቱታ ሲያቀርብ ምናልባት ከእኚህ ጸሃፊ በቀር ማንም ሰምቶ አያውቅም።

ጸሃፊው በአላዋቂ አተያይ የቃኙት የአካባቢ ልማት ለኩባንያዎች የኮርፖሬት ማህበራዊ ሃላፊነትን የመወጣት የሞራል ሃላፊነት እንጂ በውልና በአስተደደራዊ ጫና የሚተገበር ስራ አይደለም። ጊፍት በውዴታ አስተዋጽዖ አደርጋለሁ ብሎ የገባበት ይህ የአካባቢ ልማት በጋራ ርብርብ ተፈጻሚ ሆኖ ህብረተሰቡ ሲጠቀም ማየት ከአላማዎቹ አንዱ ነው።ጊፍት በአካባቢያዊና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ሁሌም ቀዳሚ ተሰላፊ የሆነ ፣ ማህበራዊ ሃላፊነቱን በመወጣት በኩል የተከበረ ስም ያለው ተቋም ነው። ለቀይመስቀል ህንጻ ማሰሪያ የለገሰውን ከ6መቶ ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ቤት ጸሃፊው ራሳቸው በጽሁፋቸው ማጠናቀቂያ ለአሉታዊ ሃሳባቸው ማጠናከሪያ ምሳሌ ቢያደርጉትም አልካዱትም። ጊፍት  ማህበረሰቡን አግልሎ ገንዘብ ለመሰብሰብ ብቻ ያለመ ኩባንያ ቢሆን ኖሮ አንጋፋ ሆኖ የሚሳተፍበትን የሪልእስቴት ኢንቨስትመንት ዛሬ ድረስ ማቆየት ባልቻለ ነበር።

የመሰረተ ልማት ጥያቄ  የጊፍት ጥያቄ ብቻ ነውን?

ጸሃፊው በመጨረሻ ላይ በግልጽ በሚያስታውቅ ግነት ያነሱት የውሃ፣የመብራትና የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች ጉዳይ የጊፍት ሪልእስቴት ብቻ ሳይሆን የመላው አዲስ አበባ ችግር መሆኑ ጠፍቷቸው አይደለም። በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የትኞቹም የሪልእስቴት አልሚዎች ከገጠሟቸው ዋና ዋና ችግሮች ተጠቃሾቹ እነዚህ ጸሃፊው ከላይ የጊፍት ስህተቶች አስመስለው ሊያቀርቧቸው የሞከሯቸው የመሰረተ ልማት ችግሮች ናቸው።ዛሬ እንኳን በከተማ ማስፋፊያ አካባቢ አዲስ የሚመሰረት መንደር ቀርቶ በመሃል ከተማ የሚገኝና ከ50 ዓመት በላይ የቆየ ነባር መንደር ጭምር የውሃ መጥፋትና የመብራት ሃይል መቆራረጥ ችግር ያጋጥመዋል።ይህ ከከተማው መስፋት፣ከህዝብ ቁጥር መጨመርና ከውሃና ከሃይል ፍላጎት ማደግ ጋር በተያያዘ የተከሰተ የጋራ ችግር ነው። መንግስት ለሪልእስቴት አልሚዎች መሬት ሲሰጥ የውሃና የመብራት መስመር የመዘርጋት ሃላፊነት እንዳለበት ቢያውቅም በአቅም ማነስና በሃብት ውስንነት ሳቢያ በተፈለገው ጊዜ አገልግሎቱን ማድረስ አልቻለም። ማንኛውም አካል ይህ ችግር ተፈትቶ ከተማዋ ለኑሮና ለነዋሪዎቿ ምቹ ሆና ማየት ይናፍቃል።

ጊፍት ሪልእስቴትም ቤት የገነባው አዲስ አበባ ውስጥ አንደመሆኑ በከተማው ቤት ልማት ላይ የተሰማሩ  አቻ ኩባንያዎች ከገጠማቸው የተለየ ችግር አልገጠመውም። የጊፍት ሪልእስቴት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ይህን ጊፍትን ብቻ ሳይሆን የሃገሪቱ ሪልእስቴት ዘርፍ በሚፈለገው ሁኔታ ላለማደጉ እንቅፋት የሆኑበትን መሰረታዊ ችግሮች በተመለከተ በአዲስአድማስ ጋዜጣ ለቀረበላቸው መሰል ጥያቄ በሰጡት ምላሽ በግልጽ ያስቀመጧቸውን ነጥቦች መጋቢት 5 ቀን 2007 ዓ.ም ከወጣው የጋዜጣው እትም ገጽ 14 በንግድና ኢኮኖሚ አምድ ላይ በማንበብ እውነቱን መረዳት በዚያውም አዕምሯቸው ውስጥ ላለው ጥያቄ መልስ ማግኘት ይችላሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፉት ዓመታት ጊፍት ግንባታ ወዳካሄደበት ፌዝ ሁለት ሳይት የውሃና የመብራት መስመር እንዲዘረጋለት በተደጋጋሚ ጊዜ ጠይቋል። የሚመለከታቸው አስፈጻሚ አካላት ዛሬ ነገ ከሚሉ ተስፋዎች የዘለለ አጥጋቢ  ምላሽ መስጠት ባይችሉም።ያም ሆኖ ኩባንያው ሳያሰልስ ጉዳዩን በመከታተሉ  ከዓመታት ጥረት በኋላ ችግሩን ከመሰረቱ ለመቅረፍ ወደሚቻልበት ምዕራፍ አድርሶታል። በአስፈጻሚ መስሪያቤቶቹ የተጀመሩት ስራዎች ሲጠናቀቁ የደንበኞች ጥያቄ ምላሽ ያገኛል የሚል ዕምነትም አለ።

እንዲያም ሆኖ ቤታቸውን ተረክበው የገቡ ነዋሪዎች በውሃና በመብራት እጦት እንዳይቸገሩ ኩባንያው ተጨማሪ ወጪ በማውጣት ጊዜያዊ መስመር በመዘርጋት አገልግሎቱን እንዲያገኙ ለማድረግ ሞክሯል። ለስራ የሚጠቀምበትን የኤሌክትሪክ ሃይል ለነዋሪዎች በማከፋፈል ችግራቸውን በጊዜያዊነት ለመፍታትም ጥሯል። ይህ ችግር የጋራ ችግር መሆኑን ደንበኞቹ ይገነዘባሉ። ጸሃፊው የግራውን ከቀኝ እየቀላቀሉ ‘የምርጫ ክርክር ማየት አልቻልንም’ ብለው እንዳጋነኑትና ፍሪጅ አስነስቶ ቴሌቪዠን የማያሰራ ሃይል  እንዳሉት ሳይሆን ሊጠቀሙበት የሚችሉትን ሃይል ነው ያከፋፈላቸው። ጸሃፊው ለወቀሳቸው ማጠናከሪያ አጋንነው ቢያቀርቡትም ይህንን ማድረግ የኩባንያው ሃላፊነትም ጭምር ነውና ምስጋና የሚሻበት ጉዳይም አይደለም ።

ጸሃፊው በመጨረሻ “የኩባንያው ሃላፊዎች ደንበኞችን አያነጋግሩም” የሚል ጭብጥ ለአንባቢ ለማስያዝ “ሃላፊዎቹ ቢሮ  ዘግተው ይጠፋሉ” የሚል ቃል ተጠቅመዋል። እሳቸው በጽሁፋቸው መግቢያ ላይ “በተደጋጋሚ ጊዜ አነጋግሬያቸዋለሁ” ያሏቸውን የድርጅቱን ባለቤትና ዋና ስራ አስኪያጅ ከቢሮ ውጪ የት አግኝተው አነጋግረዋቸው እንደሆን ቢጠቅሱት የራሳቸውን ሃሳብ በራሳቸው ከማፍረስ ያድናቸው ነበር። በመሰረቱ የሪልእስቴቱ ሃላፊዎችም ሆኑ ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ ከስራ ሰዓት ውጪም ቢሆን ሁልጊዜ በቢሯቸው ደንበኞችን እንደሚያስተናግዱ ራሳቸው ደንበኞች ምስክር ናቸው። በጊፍት ሪል እስቴት ደንበኞች ቀን ሳይወሰንባቸው ስድስቱንም የስራ ቀናት መጠቀም ይችላሉ፣እየተጠቀሙበትም  ነው። ጸሃፊው በይመስላል ከመጻፍ ይልቅ የአዲስ አበባ ነዋሪ ከሆኑ ቢሮ መጥተው የሚያነጋግራቸው አጥተው ከሆነ በግልጽ ቢናገሩት መልካም ነበር። ማስረጃ አልባ ክስ ክፋቱ ከስም ማጥፋት አለመዝለሉ ነው።

እንደማጠቃለያ

አንባቢ ይህንን ለጸሃፊው የተሰጠ ምላሽ ሲያነብ “ጊፍት ሪልእስቴት ከማንኛውም ችግር የጸዳ ነው” የሚል መልዕክት ለማስጨበጥ ታልሞ የተጻፈ አድርጎ እንዲገነዘበው ኩባንያው ፍላጎቱ አይደለም። ከላይ ለመግለጽ እንደተፈለገውና ጸሃፊው ራሳቸው በመንደርደሪያቸው እንዳስቀመጡት በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍ ከጀማሪነት ደረጃው ከፍ ባለ እርከን ላይ እንዳይቀመጥ ባደረጉት በብዙ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች ውስጥ ያለ ዘርፍ ነው። እነዚህ ችግሮች በኩባንያዎቹ ላይ ሲጫኑ ደንበኞችም ችግሩ የሚያስከትለውን ጫና በከፊልም ቢሆን መሸከማቸው እውነት ነው።ያም ሆኖ ጊፍት ሪል እስቴት በተቻለ መጠን ደንበኞች ለከፈሉት ገንዘብ እርካታ አግኝተው የሚወጡበት ሰርዓት እንዲፈጠር ጥረት እያደረገ ነው።ቅሬታዎች ቢኖሩም ቅሬታዎቹን “ደንበኛ ሁሌም ትክክል ነው” በሚለው የኩባንያው መርህ መሰረት በማስተናገድ  በጋራ መግባባት የተጀመሩትን ስራዎች ለማጠናቀቅ ቁርጠኛ ፍላጎትና አቋም አለው። ነገር ግን ሆን ተብሎ የኩባንያውን መልካም ስምና ዝና በሃሰት መረጃዎች ለመጉዳትና በደንበኞቹ ዘንድ እምነት እንዲያጣ ለማድረግ እንደ ‘አበበ ወርዶፋ’ ባሉ ግለሰቦች የሚፈጸሙትን ደባዎችን ኩባንያው በዝምታ ሊያልፈው አይችልም። አንድን በህግ የህግ ሰውነት የተሰጠው ኩባንያ ስም ማጥፋት በህግም በሞራልም ተቀባይነት የሚኖረው አይሆንም።

ጸሃፊው በውጭ ሃገራት ሰፊ ጎብኚዎች ባሏቸው ze-habesha.com እና satenaw.com ድረገጾች ላይ ጽሁፋቸው እንዲታተም ያደረጉት ሆን ብለው የሪልእስቴቱን ደንበኛ የሆኑ ኢትዮጵያውያንንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን አመለካከት ለመበረዝና ድርጅቱን ለማጣጣል እንዲሁም ኩባንያው ላይ እምነት እንዳይኖራቸው ለማድረግ መሆኑን ጊፍት ሪል እስቴት ይገነዘባል። ጸሃፊው “የኩባንያው ብዙ ደንበኞች በውጭ ሃገራት ስለሚኖሩ ቢበዛ ጮኸው ይሄዳሉ በማለት ሃላፊዎቹ ምላሽ አይሰጡም” ላሉት በርግጠኝነት የድርጅቱ ደንበኛ አለመሆናቸውን ያመለክታል። ምክንያቱም ኩባንያው በዘረጋው የመረጃ ግልጽነት ስርዓት እያንዳንዱ ደንበኛ በኩባንያው ኦፊሺያል ዌብሳይት ላይ በተከፈተለት አካውንት የቤቱ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ በፎቶግራፍ ጭምር እንዲያይ የሚደረግ ከመሆኑ በተጨማሪ የተለያዩ መረጃዎችን እንዲሁም ደንበኛው ያለውን ማንኛውንም አስተያየትና ቅሬታ በኢሜይል መልዕክቶች በመለዋወጥ የየዕለት ክትትልና ግንኙነት ያደርጋል።

እነዚህ ሁሉም የጊፍት ሪልእስቴት ደንበኛ የሚያውቃቸው ከላይ የተጠቀሱት መረጃዎች የጸሃፊውን መረጃ ትክክለኛ አለመሆን ያሳያሉ። ከዚህ በተጨማሪም ዌብሳይቱ ላይ የሰፈረው ጽሁፍ የሁሉም የጊፍት ደንበኞች እምነት አለመሆኑን ቢያንስ ይህ ጽሁፍ ለድረገጹ እስከተላከበት ቀን ድረስ የጸሃፊውን ሃሳብ ደግፎ አስተያየት የሰጠ አንድም ሰው አለመኖሩ  ቀላል ማሳያ ነው። በመጨረሻም  ጸሃፊው በርዕስነት ለተጠቀሙበት “ጊፍት ሪል እስቴት ወደፊት ወይስ ወደኋላ?” የሚል ጥያቄ ኩባንያው አጭር ምላሽ ሊሰጣቸው ይወዳል። “የጊፍት ሪል እስቴት ጉዞ በስም ማጥፋት ዘመቻ ወደኋላ አይመለስም !”

በዚህ አጋጣሚ ጊፍት ሪል እስቴት ስሙ ተጠቅሶ ለወጣበት ጽሁፍ ተገቢ ነው ያለውን ምላሽ ሲልክ ze-habesha.com እና satenaw.com ድረገጽ ሃላፊነት እንደሚሰማቸው ሚዲያዎች ተቀብለው ለንባብ በማብቃታቸው ኩባንያችን ከፍ ያለ ምስጋናውን ሊያቀርብላቸው ይወዳል።

 

The post የጊፍት ሪል እስቴት ጉዞ በስም ማጥፋት ዘመቻ ወደኋላ አይመለስም appeared first on Zehabesha Amharic.

በየመን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጥቃት ተፈጸመበት

$
0
0

መንግስታዊው ሚድያ ራድዮ ፋና እንደዘገበው በየመን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጥቃት ተፈፀመበት በየመን ሰንዓ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ለትናንት አጥቢያ ጥቃት እንደተፈጸመበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ እንዳስታወቁት በጦር መሳሪያ ጥቃቱ ጉዳት የደረሰበት ኢትዮጵያዊ የለም።
yemen1
አምባሳደሩም ሆኑ ሌሎች ዲፕሎማቶች በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ነው ያስታወቁት። ኢምባሲ በየመን ያላቸው አብዛኛዎቹ አገራት ኢምባሲዎቻቸውን ከዘጉ ሳምንታት ተቆጥረዋል።

በሌላ ዜና ከየመን ተመላሽ የሆኑ የመጀመሪያዎቹ 30 ኢትዮጵያውያን ጅቡቲ ደርሰዋል። እስካሁን ወደ አገራቸው ለመመለስ ከ2 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ተመዝግበዋል። የተመዘገቡትን ዜጎች በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ አገራቸው ለመመለስም መንግስት የተቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ መሆኑን ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያስታወቀው።

በየመን የሆቲ አማፂያን እና የአልቃይዳ ክንፍ ሰፊ ግዛት እየተቆጣጠሩ በመምጣት የአገሪቱ መዲና ሰነዓን ይዘዋል። በአገሪቱ መንግስት ደጋፊዎች እና በአማፂያኑ መካከል የሚደረገው ግጭት የቀጠለ ሲሆን፥ በተለይም በባህር ዳርቻዋ ከተማ ኤደን ጦርነቱ ተባብሷል ነው የተባለው። በህጋዊ መንገድ የተቀመጠውን የአገሪቱን መንግስት ወደ መንበሩ ለመመለስም በሳዑዲ አረቢያ መሪነት የአከባቢው አገራት ተጣምረው የዓየር ጥቃት በመፈፀም ላይ ይገኛሉ።

The post በየመን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጥቃት ተፈጸመበት appeared first on Zehabesha Amharic.


ኢሜግሬሽን በኢ/ር ይልቃል ጌትነት ጉዳይ ላይ መልስ መስጠት አልቻለም • ‹‹ይህ ሁሉ ከአቅመ ቢስነታቸው የመነጨ ነው›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት 

$
0
0

Hiber Radio Interview with Eng Yilkal Getnet
የኢሜግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ጉዳይ ላይ መልስ መስጠት አለመቻሉንና ይህም ሆን ተብሎ ጉዟቸውን ለማጓተትና እንቅስቃሴያቸው ለመግታት የተደረገ ነው ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ የኢሜግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ በትናንትናው ዕለት ቀጠሮ ሰጥቷቸው የነበር ቢሆንም ምንም አይነት ምክንያትና መፍትሄ ሳይሰጥ ለዛሬም ሌላ ቀጠሮ ተሰቷቸው እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ይሁንና በዛሬው ዕለትም የኢሜግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ሲሄዱ ‹‹ፓስፖርቱ እኛ ጋር አልደረሰም፡፡ ቆይተው ደውለው ይጠይቁ›› ብለው ስልክ እንደሰጧቸው ገልጸዋል፡፡ ይህም ሆን ተብሎ ጉዞውን ለማጓተት የተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ሊቀመንበሩ አክለውም ‹‹ይህን ሁሉ የሚያደርጉት አገር የማስተዳደር ብቃት ስለሌላቸው፣ የፖለቲከኛን እንቅስቃሴ በማጓተትና በማገድ የተፈጠረባቸው ስጋት የሚቀርፉ ስለሚመስላቸው ነው፡፡ እንደ አጠቃላይ ከአቅመ ቢስነታቸው የመነጨ ነው›› ብለዋል፡፡ በምርጫ ክርክር ወቅት ኢህአዴግ ሰማያዊ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ጋር ያለውን ግንኙነት አሉታዊ አድርጎ እንዳቀረበ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ የኢህአዴግ ሚዲያዎችም ይህን አቋም እየተደጋገመ እንደሆነ የገለጹት ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ሰማያዊ ፓርቲ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያለው ተቀባይነት፣ እነዚን ኢትዮጵያውያን እያንቀሳቀሰ መሆኑና አቅማቸውን ለመጠቀም ዝግጁ መሆኑ በጣም አስፈርቶታል ብለዋል፡፡

The post ኢሜግሬሽን በኢ/ር ይልቃል ጌትነት ጉዳይ ላይ መልስ መስጠት አልቻለም • ‹‹ይህ ሁሉ ከአቅመ ቢስነታቸው የመነጨ ነው›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት  appeared first on Zehabesha Amharic.

የጦርነት ድባብ ያቀዘቀዘው ምርጫ! –አምዶም ገብረሥላሴ ከመቀሌ

$
0
0

የዘንድሮ ምርጫ ኣሸንፎ ለመውጣት የህወሓት መንግስት ኣርባው ሲያስወጣ “…ከፍተኛ ህዝባዊ ንቅናቄ ፈጥሬ ድጋፍ ኣገኛለው…” ብሎ ኣስቦ ነበር። ይሁን እንጂ ከድጋፍ በላይ ተቃውሞ በመውለድ ያሁሉ ጥረቱ መና ሁኖ መቅረቱ ህወሓት ተረድተዋል። ድሮም በወከባ የሚገኝ ህዝባዊ ድጋፍ እንደሌለ የሚታወቅ ነው።
Ethiopian soldiers ride on an army truck on the road to Afgooye, south of Mogadishu
ህወሓት ጥረቱ ከንቱ ሲቀር የዘየደው መላ በትግራይና የሚያዋስኑት የኢትዮ ኤርትራ ድንበር ኤርትራ የጦርነት ድባብ በመፍጠር የምርጫው ኣቅጣጫ ለማስቀየስ እየሞከረ ነው። የዚህ ማሳያ “..የኢትዮዽያ ኣየር ሃይል የወርቅ መዓድንና የትጥቅ መጋዘን ደብድበው ጉዳት ኣድርሰዋል..” የሚል በፌስቡክ ካድሬዎቹና በድህንነት ኣካላት በሰፊ እንዲወራ ኣድርገዋል።

የዚህ ምላሽ ተብሎ የተገለፀው ደግሞ “..ሻእብያ ሶሎዳ ተራራን(ኣድዋ ከተማ ኣጠገብ የሚገኝ) በሚሳይል እንደደበደበ..” እነ ዳኒኤል ብርሃነ ኣበሰሩን። ምድረ ካድሬም “..ኣሸው..” እያሉ ለኣየር ሃይላችን ኣንቆለዻዸሱት።

ኣቶ ሃይለማርያም ደሳለይም ስለ የኣየር ጥቃቱ ሲጠየቁ “..ተደበደብኩ የሚል ኣካል ሲኖር መልስ እንሰጣለን…” የሚል ኣመላካች የእምነት ቃል ገለፁ።

“…በኣንዳንድ የኢትዮ-አርትራ ድንበር የተወሰነ ወተሃደራዊ እንቅስቃሴ መኖሩና ይህንን ተከትሎ የህብ መፈናቀል እንደተስተዋል..” የፌስቡክና ምንጭቻቸው በግልፅ የማይታወቁ ወሬዎች በትግራይ ክልል እንዲወሩ ተደረገ።

የመቐለ መስተዳደርም የዚህ ወሬ ከሚያራግቡ ኣካላት ኣንዱና ዋነኛው ነበር። በከተማዋ የሚገኙ የባጃጆችና የታክሲ ሹፌሮች በማዘጋጃ ቤት ኣዳራሽ በመሰብሰብ “..ፀጉረ ለወጥ ሰው ስታስተናግዱ መታወቅያ ጠይቁ፣ መኪኖቻቹና ባጃጆቻቹ ፈንጅና ሌላ ተቀጣጣይ ነገር እንዳይጠመድባቸው በንቃት ጠብቁ..” የሚል ማስጠንቀቅያ ሰጣቸው።

በማስቀጠልም “..በመከላከያችን ጥቃት ደረሰ፣ ይህን ያክል ሰው ሞተ፣ ቆሰለ የሚል ኣሉባልታ እንዳታምኑ፣ እንዳታወሩ..” ወዘተ የሚሉና የውትድርና ምልመላ ማስታወቅያዎች በማስተዋወቅ ህዝቡ የጦርነት ስጋት እንዲያድረው እየተደረገ ነው።

እነዚህ ወሬዎች የትግራይ ክልል ህዝብ ትኩረቱ ከምርጫው ይልቅ በሚናፈሱ ወሬዎች እንዲያደርግና የጦርነት ድባብ እንዲሰማው እየተደረገ ነው።
ይህ ህዝቡ በጦርነት፣ ወተሃደራዊ ጥቃት፣ የሽብር መንፈስ እንዱያድረውና የነዚህ ክፉ ወሬዎች ውጤት የሆኑት መልኣከ ሞት፣ ስደትና ችጋር ወደ ህሊናው እንዲመጡና የምርጫው ትኩረቱ እንዲቀይር እየተደረገ ነው።

በዚህ ኣካሄድ በትግራይ ክልል ምርጫ ማካሄድ በማይቻልበት ሁኔታ ላይ ነው ያለው። ህዝቡ በተረጋጋ ሁኔታ መብቱን መጠቀም እንዲችል የምርጫው የግዜ ሰሌዳ ለሌላ ግዜ ማራዘም ግድ ይላል።

በተለያዩ ኣካላት እየታነፈሰ ያለው ወሬ ሃቅነት ይኑረው ኣይኑረው ህዝቡን በተረጋጋ ሁኔታ ይበጀኛል የሚለው እጩ ተወዳዳሪና ድርጅት መምረጥ ካልቻለ ለኣገራችን ሰላምና እድገት ኣሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩ ግድ ይሆናል።

የህወሓት መንግስት ከምርጫ ይልቅ የጦርነት ድባብ ማስፈኑ ምክንያት ከትግራይ ህዝብ ያጣው ድጋፍ ተረድቶ ምርጫው ኣጨናግፎ ለማለፍ ነው።

ምርጫው ሊጨናገፍ ኣይገባም።

ነፃነታችን በእጃችን ነው..!

IT IS SO..!

The post የጦርነት ድባብ ያቀዘቀዘው ምርጫ! – አምዶም ገብረሥላሴ ከመቀሌ appeared first on Zehabesha Amharic.

በዚህ ሳምንት የተማርናቸው አምስት ነገሮች

$
0
0

ከ7 ኪሎ መጽሔት

1ኛ) ፖለቲካ ለብዙሃን “ውስጡን ለቄስ ነው”
ከሰባት ዓመታት በፊት የቅንጅት እስረኛ የነበሩት አቶ አንተነህ ሙሉጌታ “የሁለት ዓለም ሰዎች” በሚል ርእስ የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞችን የሚመለከቱ የፍርድ ቤት ድራማዎች ላይ ያነጣጠረ መጽሐፍ ጽፈው ነበር። መጽሐፉን ያነበበ በዚህ ሳምንት በዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች የፍርድ ሂደት ላይ የታየው ትዕይንት አይገርመውም። ችሎታ የሌላቸው አቃቤ ሕጎች፣ የመንግሥት ታዛዥ ዳኞች፣ ግራ የተጋቡ እና ያልተዘጋጁ የአቃቤ ሕግ ምስክሮች ላለፉት ኻያ ሦስት ዓመታት የፖለቲካ ችሎቶች ቋሚ ንብረቶች ኾነው ቆይተዋል። ታዲያ ከእነዚህ የፍርድ ቤት ሂደቶች ጋራ ተያይዞ በተደጋጋሚ የሚነሳው ጥያቄ “መንግሥት ራሱን በዚህ ደረጃ ከሚያዋርድ፤ እንዲሁም የማይረባ አማተር የደረሰው እና ያዘጋጀው የሚመስለውን ቴአትር ትቶ፤ ለምን ማሰር የሚፈልጋቸውን ያለ ፍርድ ቤት ሂደት ዘብጥያ አውርዶ አይገላገልም?” የሚል ነው። ጥያቄው ከሕጸጽ (fallacy) የመነጨ ነው። ይህ ሕጸጽ በእንግሊዝኛ ኢ-መደበኛ ስሙ Ubiquitous Political Junkie Fallacy ይባላል። ሕጸጹ አብዛኛውን ሰው የፖለቲካ ሱሰኛ አድርጎ የማየት አባዜ ነው። የዚህ ሐሳብ ተጠቂዎች በአብዛኛው ፖለቲካን በቅርቡ የሚከታተሉ አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች ናቸው።

እንደዚህ ዐይነት ግለሰቦች ሌሎች ሰዎች ልክ እንደ እነርሱ ፖለቲካን ቀን ከሌት የሚያመነዥኩ ይመስላቸዋል፤ ሐቁ ግን ከዚህ የተለየ ነው። የማሕበራዊ ሳይንስ ጥናቶች እንደሚያሳዩት አብዛኞቻችን ፖለቲካን በቅጡ አንከታተልም፤ ከተከታተልንም ላይ ላዩን ነው። አምባገነን መንግሥታት ይህን ጠንቅቀው ያውቃሉ። ፖለቲካን ከላይ ከላይ ለሚከታተሉ ብዙሃን ማሳየት የሚፈልጉት መንግሥታቱ ሥርዐት እና ሂደት የሚያከብሩ፤ ውሳኔዎቻቸውን በመደበኛ ተቋማት የሚያስወስኑ እና በዘፈቀደ የማይመሩ መኾናቸውን ነው። ይህን ለማሳየት ማስመሰል ይበቃቸዋል። ሥርዐት እንዳለ ማስመሰል የዐይነተኝት መንፈስ (aura of legitimacy) ያላብሳቸዋል። የፍርድ ቤት ትዕይነቱ በጥልቅ ሲመረመር ለመንግሥት አሳፋሪ ነው። ይኹንና ይህን ጥልቅ ምርመራ የሚያደርጉ ጥቂቶች ናቸው። የእነርሱ ድምጽ ብዙሃኑ ጋር የሚደርስበት መንገድ ከተዘጋ ንጉሡ ራቁቱን ቢኾን እንኳ ልብስ እንደለበሰ እያስመሰለ መቆየት ይቻለዋል።
Nile Countries
2ኛ) አቴናዊው ቱስይዲዴስ በአባይ ጉዳይ ልክ ነው
እ.እ.ኤ ከ460 እስከ 395 ዓ.ዓ የኖረው አቴናዊው የፖለቲካ ፈላስፋና ጄነራል ቱስይዲዴስ የጌም ቲዎሪ አባት ተደርጎ ይወሰዳል። ከቱስይዲዴስ ታላላቅ ሐሳቦች መካከል አንዱ የሐይል ልዩነትን አንጻራዊነት የሚያትት ነው። ጊዜና አውድን በሚገባ የሚያጤን እና የሚጠቀም ደካማ ባለጋራ በረዥም ጊዜ በብልሃት ጠንካራ ባላጋራን ሊገዳደር ይችላል። የአባይ ፖለቲካ ለዚህ ተምሳሌት ነው። የግብጽንና የኢትዮጵያን ፍጹማዊ ሐይል በግልጽ መለኪያዎች ብንገመግም ልዩነቱ በጣም ሰፊ ነው። ይህ ልዩነትም በአባይ ፖለቲካ ጉዳይ ላይ ለረዥም ጊዜ ሲንጸባረቅ ቆይቷል። እ.ኤ.አ. በ1959 ግብጽ ኢትዮጵያን ወደ ጎን አድርጋ ከሱዳን ጋር አባይን ለሁለት ለመጠቀም ስትስማማ ኢትዮጵያ ስምምነቱን አጥብቃ ብትቃወምም ከጩኸት አልፋ ጠጠር ልትገፋ አልተቻላትም። ዐፄ ሐይለሥላሴና ደርግ ግድብ ለመገንባት ቢነሱ ግብጽ የተለያዩ መንገዶችን (እርዳታ ማስከልከል፣ አማጽያንን መርዳት ወዘተ) ተጠቅማ ፈቅ እንኳ ሳይሉ እንዲያቆሙ አድርጋቸዋለች።

እ.ኤ.አ. በ2011 በግብፅ የሕዝብ አመጽ ተቀስቅሶ የመንግሥት አለመረጋጋት ማስከተሉ ለኢትዮጵያ ያልታሰበ ዕድል ፈጠረላት። ብርታኒያዊው አድሚራል ዊልያም ሄልሲ ለደካሞች እንዲህ ዐይነት ዕድል ሲፈጠር “strike fast, strike hard” ሲሉ እንደመከሩት ኢትዮጵያ ዕድሉን ለመጠቀም በፍጥነት ተንቀሳቀሰች፤ የግድቡ ግንባታ ተጀመረ፤ የአባይ ተፋሰስ አገሮችን ከግብጽ በተቃራኒ ማስተባበር ቀጠለ። በውስጥ ችግር ተወጥሮ ያልተረጋጋው የግብጽ መንግሥት ለዚህ እንቅስቃሴ ፈጣን አጸፋ ለመስጠት የሚያስችል ትንፋሽ አልነበረውም። ጀነራል ሲሲ ሥልጣን ላይ ወጥተው መንግሥትን ሲያረጋጉ ደግሞ መሬት ላይ ያሉት ኹኔታዎች ተቀይረዋል። ለ2014 ኹኔታዎች እንጂ ለ2010 ኹኔታዎች መልስ መስጠት እንደማይቻላቸው አውቀው ወደ ድርድር መጡ። የድርድሩ ውጤት የኾነው የፖለቲካ ስምምነት ግብጽ ሳታወላውልና ሳታመነታ ስትከላከለው የነበረውን የ1959 ኪዳን በጽንሰ ሐሳብ ደረጃ ጥያቄ ውስጥ ከቶታል። 2010 ላይ ኾነን ከአምስት ዓመት በሁዋላ ኢትዮጵያ እና ግብጽ የ1959ን ስምምነት አደጋ ላይ የሚጥል የፖለቲካ ውል ይገባሉ ተብሎ ቢነገረን ለማመን እንቸገር ነበር። የቱስይዲዴስን ነፍስ ይማር።
ali birra
3ኛ) ዐሊ ቢራ ብረት ነው
ለፖለቲካ ዘፋኞች ክብርና ተምሳሌትነትን እንደተጎናጸፉ ዘመንን መሻገር እጅግ አስቸጋሪ ነው። መጠነኛ የሐሳብ ለውጥ ካሳዩ ወይም ያሳዩ ከመሰሉ አድናቂዎቻቸው በድንገት ይገለበጡባቸዋል። ፖለቲካ የጋለ ስሜት የሚቀሰቅስ ጉዳይ በመኾኑ ከቀድሞ ተከታዮቻቸው የሚደርስባቸው ነቀፌታ ምሬት ያዘለ ነው። አንዳንዴ አደጋው የሚመነጨው ሐሳብን ከመቀየር ብቻ ሳይኾን ካለመቀየርም ነው። ዘመን ሲቀየርና ደጋፊዎቻቸው ሐሳባቸውን ሲለውጡ የፖለቲካ ዘፋኞች የቀድሞ አቋማቸውን ይዘው የሚቀጥሉ ከኾነ ዕጣ ፈንታቸው በሐሳብ ለውጥ ችግር ውስጥ ከሚገቡቱ የተለየ አይደለም። ተጠንቅቆ መጓዝም ዕድሜን በመጠኑ ያራዝም እንደኾን እንጂ ዘመን አያሻግርም። ዝናቸውንና ክብራቸውን ጠብቀው ዘመን የሚሻገሩ የፖለቲካ ዘፋኞች በአብዛኛው አጠቃላይ እና ዕቡይ በኾኑ ሐሳቦች ላይ የሚያተኩሩቱ እንጂ መሬት የሚነካ ጭብጥ የሚያነሱቱ አይደሉም። መዝፈን የጀመረበት ኢዮቤልዩ እየተከበረለት ያለው ታላቁ ዐሊ ቢራ የኦሮሞ ብሔርተኝነትን እና ጸረ ጭቆናን ያነገቡ መሬት የወረዱ ዘፈኖችን በማቀንቀን ይታወቃል። ሃምሳኛ ዓመቱን እያከበሩ ያሉት በተለያዩ ተቀናቃኝ ድርጅቶችና ጎራዎች ውስጥ የተሰለፉ እና ያልተሰለፉ ኦሮሞዎች ናቸው። የኦፕራይዱ ጸሐፊ መሐመድ አዴሞ እንዳስቀመጠው “ብሔራዊ ተምሳሌት፣ ጀግና፣ ፈር ቀዳጅ፣ የኦሮሞ ሙዚቃ ንጉስ” እያሉ የሚያንቆለጳጵሱት የአንድ ወይም የጥቂት የፖለቲካ ቡድን/ቡድኖች አባላት ብቻ ሳይኾኑ በፖለቲካዊ አቋማቸው እዚያና እዚህ የቆሙት ጭምር ናቸው። የኦሮሞ ብሔርተኛ ፖለቲካ ባለፉት ሃምሳ ዓመታት በነውጥና በውዝግብ ውስጥ እያለፈ ነው። ዐሊ በዚህ ታሪክ ውስጥ ቢያልፍም የተጎናጸፈው ሕየንተ ክብር ሳይፈርስ ለወርቅ ኢዮቤልዩ መብቃቱ ከድንቆች ያስመድበዋል።
bob geldof ethiopia
4ኛ) ቦብ ጌልዶፍ በጎ አድራጎትና ኢንቨስትመንትን እያምታታ አስቸግሯል

አየርላንዳዊው አቀንቃኝ ቦብ ጌልዶፍና ኢትዮጵያ የጋብቻ ቀለበት ካሰሩ ድፍን ሰላሳ ዓመት ሞልቷል። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ጋብቻው የተመሠረተው በጌልዶፍ ደግ ሳምራዊነት ላይ ነበር። አሁን ግን ጌልዶፍ በኢትዮጵያ ስም ርዳታ መሰብሰብ እና ርዳታ ሰጪዎችን ሎቢ ማድረግ ትቶ ምዕራባውያን ባለ ሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ ሄደው ኢንቨስት እንዲያደርጉ መወትወት ጀምሯል። በዚህ ሳምንት በተለያዩ ዓለማቀፍ ሚዲያዎች ቀርቦ ሐሳቡን አስረድቷል። ነገር ግን ጌልዶፍ “ኢትዮጵያ ሄዳችሁ ኢንቨስት አድርጉ” ሲል ፈላስፋውና ኢኮኖሚስቱ አዳም ስሚዝ ባስቀመጠው የኢንቨስትመንት ጽንሰ ሐሳብ መንፈስ አይደለም። ስሚዝ እንደሚለው ኢንቨስትመንት ኢንቨስተሩ ለራሱ ጥቅም ሲል የሚገባባት ከግል ፍላጎት (private interest) የሕዝብ ጥቅም (public virtue) የሚገኝበት ነው። ጌልዶፍ የሚቀሰቅሰው ግን እንዲህ ሲል ነው። “ትኩረት ሳትሰጣቸው ቀርተህ በርካቶች መሞት የለባቸውም፤ አፍሪካ ውስጥ ኢንቨስት ማድረግ ሊያስገኝ የሚችለው ጥቅም ሌላ ቦታ ከሚገኘው የላቀ ነው።” ይህ ሐሳብ ኢንቨስትመንትንና ደግ ሳምራዊነትን የሚቀላቅል ነው። ‘ድመት መንኩሳ ዐመሏን አትረሳ” ብለን እንለፈው።

abay Tsehaye
5ኛ) የቃላት ዕብሪተኝነት ያለመረጋጋት ውጤት ነው

ውስጣዊ ጽናት የማጣት (insecurity) ስሜት ችግር ያለባቸው መሪዎችና ፖለቲከኞች ችግራቸውን ለመሸፈን ከሚጠቀሙባቸው ማካካሻ ጠባያት መካከል አንዱ የቃላት ዕብሪተኝት እንደኾነ ሳይኮሎጂስቶች ይነግሩናል። ሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር፤ በመግለጫቸው ሲደነፉና ዕብሪት የተቀላቀላበቸውን ቃላቶች በተደጋጋሚ ሲጠቀሙ አስተውለናል። እነዚህንም መልሶች የሰጡት መፈናፈኛ ለሚያሳጡ ብቻ ሳይኾን ለገራገር የማብራርያ ጥያቄዎችም ነበር። ለኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እንዲህ ዐይነት መረን የለቀቀ ዛቻና ስድብ መጠቀም፣ ማንጓጠጥ እና ንቀት መደርደር ያልተለመደ አይደለም። አቶ መለስ ዜናዊ በዚህ የተካኑ ነበሩ። ሬድዋን ሁሴን፣ አባይ ጸሐዬ፣ ሽመልስ ከማልና በረከት ስምዖን ካላሽሟጠጡና ካልዛቱ የቦተለኩ አይመስላቸውም። ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘ 24 ዓመት ኾኖታል። በእነዚህ ዓመታት ከ1997 በስተቀር በትረ ሥልጣኑን የሚነቀንቅ ከውጪ የመጣ ጠንካራ ግፊትና ጥቃት አልደረሰበትም። እንደብዙ የአንድ ፓርቲ አምባገነኖች የኢሕአዴግ መንግሥትም የተረጋጋ ረዥም ዕድሜ አሳልፏል። ነገር ግን የባልሥልጣነቱ የማይለወጥ ዕብሪተኝነት በስጋትና ባለመጽናት ስሜት እንደተዘፈቁ ጠቋሚ ነው። ናሲም ታሌብ የተባሉ ምሁር በአምባገነን ሥርዐቶች ዝግ መኾን ምክንያት የሚፈጠሩ የኢንፎርሜሽን ችግሮች (information problems) ተጠቂዎች ተገዢዎች ብቻ ሳይኾኑ የአገዛዙ መሥራችና አንቀሳቃሾችም ጭምር እንደኾኑ ያስረዱናል። እንደ ምሑሩ ከኾነ አምባገነኖች ስለ ራሳቸው ያላቸው እውቀት ከምናስበው በታች ደካማ ነው። የኢትዮጵያ ባለ ሥልጣናት የማያባራ የቃላት ዕብሪት ራስን ካለማወቅ የመነጨ አለመረጋጋት የፈጠረው ይኾን?

The post በዚህ ሳምንት የተማርናቸው አምስት ነገሮች appeared first on Zehabesha Amharic.

የአባይን ልጅ ውሃ ጠማው!”–የጐንቻው

$
0
0

yengochaw

ማስታወሻነቱ፡-

አባይ ከብሄራዊ ስነ- ልቦናችን፤ ማንነታችን፤ ከታሪካችን፤ መልካ ምድራዊ አሰፋፈራችን፤ተፈጥሯዊ ትሥሥራችን ጋር ተቆራኝቶ ሺህ ዘመን አብሮን የነጐደ ከወንዝ የበለጠ ትርጉም፤ስላለውም እንደየዘመኑ የኑራችንን ፈተና ልንሻገርበት ምኞትና ሕልም ቋጥረን የምንፈታበት፤የእድገትና የልማታችንን ቁጭት የምንገልጽበት ሚስጥራዊ ኃይል መሆኑን የተረዱ የዘመኑ ‘ብልጣብልጥ ገዥዎች’ በቀውጢው ሰዓት፤በፊታውራሪነት ከሚስጥር ኪሳቸው ሳይታሰብ ‘ህዳሴ ግድብ’ ብለው የመዘዙት ካርድ፤ነበርና አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ከኪስ ባለፈ፤በገዘፈ ብዙ፤ብዙ አስወጥቶታል።

[ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—

 

 

 

The post የአባይን ልጅ ውሃ ጠማው!” – የጐንቻው appeared first on Zehabesha Amharic.

(የየመን ጉዳይ) ዘመቻ “ወሳኙ ማዕበል ”በ8ኛው ቀን ክንውኖች …እና በየመን ሁከትና የኢትዮጵያውያን ይዞታ !

$
0
0

Mideast Yemen Humanitarian Toll
የመረጃ ግብአት …
ዘመቻ “ወሳኙ ማዕበል ” በ8ኛው ቀን ክንውኖች …
እና በየመን ሁከትና የኢትዮጵያውያን ይዞታ !
=
nebyu sirak> ” ኤደን በሁቲዎች እጅ አልወደቀችም! ” የሳውዲ መራሹ ዘመቻ ቃል አቀባይ
> ” በየመን ሰንአ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ተደብድቧል፣ 2000 ተመዝግበው 30 ጅቡቲ ገብተዋል ” ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖም
> በስደተኞች መጠለያ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር የመግባት ፍላጎት አላሳዩም፣ የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ ነው፣ በፖለቲካ የሸሹት የምህረት ጥሪ ይደረግላቸውም እየተባለ ነው

8ኛው ቀን የዘመቻ ክንውን መግለጫ …
========================
ኤደን በሁቲ አማጽያን ስር መሆኗን አልጀዚራና የተለያዩ የአረብ መገናኛ ብዙሀን የጠቆሙ ቢሆንም ትናንት ማምሻውን በሪያድ የአየር ኃይል የጦር ሰፈር ሆነው ለጋዜጠኞች ስለ 8ኛው ቀን የዘመቻ ክንውን መግለጫ የሰጡት የዘመቻው ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ ኤደንን ለመያዝ ውጊያው እንደቀጠለ መሆኑን ያስረዱ ሲሆን ኤደን ሙሉ በመሉ በሁቲዎች ቁጥጥር ስር አለመውደቋን አስታውቀዋል።።
በ8ኛው ቀን የአየር ጥቃት ዘመቻ መግለጫ የሰጡት ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ በኤደን አካባቢ እግረኛ ጦር ጀምሯል ወይ ? ተብለው ተጠይቀው ፣ እግረኛ ጦር አለጀመሩን አስረግጠው ተናግረዋል ። በዚሁ መግለጫቸውም በኤደን ዙሪያ ስለተደረገውና እየተደረገ ስላለው የዘመቻው ክንውን ሲያስረዱ በዋናነት በምድርና በባህር የሁቲ አማጽያን ስንቅና ትጥቅ አቅርቦት እንዳያገኙ መንገዶችን የመዘጋጋት ስራ መሰራቱን ጠቁመዋል። ከዚህ ባከፈ የእግረኛ ጦር ዘመቻ አለመጀመሩን ቃል አቀባዩ አስረድተዋል ።

“ከወሳኙ ማዕበል” የአየር ጥቃቱን አፋፍሞ በቀጠለበት ሁኔታ በየመን የድንበር ከተማ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ በምትገኘው አሲር ክልል በሚያዋስን ድንበር ግጭት መቀስቀሱ ተጠቁሟል። ባልታወቁ ታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስም ሰልማን አልመልኪ የተባሉ አንድ የበታች ሹም የድንበር ጠባቂ ወታደር መገደላቸውንና 10 ያህል መቁሰላቸውን የሀገር ውስጥ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ ሜጀር ጀኔራል መንሱር አልቱርኪ አስታውቀዋል ። የአየር ጥቃት ከተጀመረ ወዲህ በድንበር ይህን አይነት ክስተት ሲታይ የመጀመሪያው ሲሆን በተባለው ግጭት የሞቱት የድንበር ጠባቂ የቀብር ስነስርአትም ትናንት ሀሙስ በአብሃ ከተማ ተከናውኗል !

*የኢትዮጵያ ኢንባሲ መደብደብና
አሳሳቢው የኢትዮጵያውያን ይዞታ…

======================
በየመን ሰንአ የኢትዮጵየ ኢንባሲ ባሳለፍናቸው ቀናት በጦርነቱ የድብደባ ጥቃት የተፈጸመበት መሆኑን የኢፊድሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖም ባሰራጩት መረጃ አስታውቀዋል። በተፈጸመው ድብደባ የተጎዳ ሰው የለም ከማለት ውጭ በጦር መሳሪያ ተደበደበ ስላሉት ኢንባሲ የጉዳት መጠን የሰጡት ዝርዝር ማብራሪያ ግን የለም ።
በየመንን ሁከት ተከትሎ በኢትዮጵያ ኢንባሲ በኩል ወደ ሀገር ለመመለስ የተመዘገቡት 2000 ኢትዮጵያውያን መኖራቸውን የጠቆሙት ሚኒስትሩ ከተመዘገቡት መካከል 30 ያህል በጦርነት ከምትናጠው ከኤደን ተነስተው ጅቡቲ መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መረጃ ያስረዳል። በየመን እያደር የጦርነቱ መባባስ ስደተኞችን የመመለስ ስራውን እንዳወሳሰበው የጠቆሙት ዶር ቴዎድሮስ በሚቀጥሉት ቀናት የተመዘገቡትን ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር የመመለሱ ስራ በተቻለው መጠን እንደሚደረግ አስረድተዋል። በመጨረሻም ባስተላለፉት መረጃ የብዙ ሀገር ዲፕለማቶች የመን ሰንአን ለቀው ሲወጡ ” ከዜጎቻችን በፊት አንወጣም !” ብለው እስካሁን የመን አሉ ላሏቸው የኢትዮጵያ ኢንባሲ ዲፕሎማቶች ምስጋና አቅርበዋል ።

በሌላ በኩል በስደተኞች መጠለያ የሚገኙት ከ5000 ስደተኞች ጨምሮ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ በየመን በኩል ወደ ሳወዲ ለመግባት አስበው በተለያዩ የየመን ክልሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ አዳዳቢ እንደሆነ ቀጥሏል። ወደ ሶስተኛ ሀገር እንጅ በኑሮው ውድነትና በፖለቲካው አለመረጋጋት ተማረው በ UNHCR የስደተኛ ማረጋገጫ የተሰጣቸው ግን ወደ መጡባት ሀገራቸው ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ፍላጎት እንደሌላቸው እየተናገሩ ነው። እኒሁ በጭንቅ ላይ ሆነው ወደ ሀገር የመግባቱ ነገር እንደ ተሻለ አማራጭ የማያዩት ወገኖች አማራጩ ጥሏቸው ከየመን የወጣው በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን UNHCR ወደ ሶስተኛ ሀገር ያሸጋግራቸው ዘንድ የተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶችን እንዲማጸኑላቸው በተለያዩ አለማት ላሉ ኢትዮጵያውያን የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ ነው!

በየመን ሁከቱ እያየለ ከሄደና የሳውዲ መራሹ የ10 አረብ ሀገራት የምድር ጦር እግረኛ ማዝመት ከጀመረ ያለውን አማራጭ መጠቀም ባልፈለጉ ኢትዮጵያውያን ላይ የከፋ አደጋ እንዳያጋጥማቸው ስጋት ተደቅኖባቸዋል ። በተለያየ ምክንያት ፖለቲካውን ሸሽት ሀገር ለቀው አሁን አደጋ ላይ ሲወድቁ ወደ ሃገራቸው እንዳይመለሱ የእስራት ፍርዱን የፈሩ ዜጎች ቁጥር ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል። ይህን መሰሉን ችግር ማቅለል ይቻል ዘንድ የኢትዮጵያ መንግስት ከችግሩ ቀጠና ወደ ሃገር ለሚመለሱ ማናቸውም ስደተኞች የምህረት ጥሪ ያቀርብ ዘንድ በዚሁ ዙሪያ ያነጋገርኳቸው ወገኖች ያስረዳሉ !
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 25 ቀን 2007 ዓም

The post (የየመን ጉዳይ) ዘመቻ “ወሳኙ ማዕበል ” በ8ኛው ቀን ክንውኖች … እና በየመን ሁከትና የኢትዮጵያውያን ይዞታ ! appeared first on Zehabesha Amharic.

በበደል ላይ በደል የከሳውን መግደል !! የወያኔ ጥቅም ለማጋበስ የሚደረግ ሩጫ እስካሁን አልተሳካም::

$
0
0

tewodros adhanomወያኔ ወደ የመን የሰላም አስከባሪ ሊኮ ዶላሮች ለመዛቅ ሳኡድ አረቢያን እየተለማመጠ ከሆነ በበደል ላይ በደል የከሳዉን መግደል ያሰኛል::ዜጎችን ለማስወጣት ያልተረባረበ ወንጀለኛ ስርአት በየትኛው ሞራሉ ሰላም አስከባሪ ልኮ የመኖችን ሊታደግ? የወያኔ ጥቅም ለማጋበስ የሚደረግ ሩጫ እስካሁን አልተሳካም:: አረብ ሊግ እኮ እንደማይፈልግ በተደጋጋሚ እየተናገረ ሳኡዲን መለማመጥ ለምን አስፈለገ?የወያኔ አገልጋይ የሆነው ሃይለማርያም ደሳለኝ የሳኡዲ አረቢያን የአየር ድብደባ በተመለከተ የሰጠው ድጋፍ የሰሙት የመናውያን በኤምባሲው ላይ ጥቃት እንዳደረሱ እና ኢንዲሁም ኢትዮጵያውያንን በየመንገዱ እየተሳደቡ እንደሚገኙ ከሰነአ የሚገኙ ወገኖች ጠቁመዋል::የሳኡዲ አየር ሃይል ኤምባሲውን አልመታም::በተሳሳተ መረጃ ለማደናበር ወያኔ እየሞከረ ነው::

'ዜጎችን እያስፈጁ ዜጎችን ማጭበርበር የወንጀል ሁሉ ትልቅ ወንጀል ነው::</p>
<p>@[1479450082325389:274:Minilik Salsawi] - በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ በአለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ጭንቀት ውስጥ ባሉበት ወቅት እንደ ቴዎድሮስ አድሃኖም ያሉ ውሸታሞች ያልተደረገ ተደረገ ያልተመለሱ ተመለሱ ወዘተ በማለት በሃሰት ሕዝብን እያጭብረበረ ይገኛል::ከባድመ የሃሰት ድል ጀምሮ እንከ 20 ሚሊዮን ዶላር የውሸት ፕሮፓጋንዳ ቅሌት ውስጥ የተዘፈቁት እነ ቴዎድሮስ አድሃኖም በህዝብ ላይ የሚቀልዱ አምባገነኖች አሁንም የሃሰት ወሬያቸውን መርጨት አላቆሙም::ከወያኔ ሃሰት እንጂ እውነት አይሰማም::</p>
<p>ከዚህ ቀደም በሳኡዲ የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ለፖለቲካ ፍጆታ እና ለፎቶ ታይታ የተጠቀመበት ወዲ አድሃኖም አሁንም የየመኑን ግጭት ተከትሎ ሕዝብን ለማጭበርበር ከፍተኛ መወራጨት እያደረገ ነው:: ሕዝብ መንቃቱን ሳያውቅ የሚያላዝነው ወዲ አድሃኖም ለፖለቲካ ትርፍ እና በወያኔ ውስጥ ለተከሰተው አጣብቂኝ ለመሸፋፈኛነት የሚነዛው ሃሰት እያንዳንዱ ዜጋ የሚያውቀውን እውነት ለመደበቅ መሞከር ወያኔ ምን ያህል እንደዘቀጠ ይታያል::እንኳን 30 ኢትዮጵያውያን ጅቡቲ ሊደርሱ ይቅርና ደውሉ ተብሎ የተሰጠው ስልክ የማይሰራ እንዲሁም ጦርነቱ ሳይጀምር የተዘጋ ኤምባሲ እና የወጡ የወያኔ ወኪሎች እንዳሉ አድርጎ ማቅረብ ብሎም እየመዘገብን ነው ማለት ያልተፈተለውን እንደመሸመን ነው::ያልተመታውን ኤምባሲ ተመታ ያሌሉ ዲፕሎማቶች አሉ የሚል ወሬ እንዲነዛ በማድረግ .... የወያኔ አገልጋይ የሆነው ሃይለማርያም ደሳለኝ የሳኡዲ አረቢያን የአየር ድብደባ በተመለከተ የሰጠው ድጋፍ የሰሙት የመናውያን በኤምባሲው ላይ ጥቃት እንዳደረሱ እና ኢንዲሁም ኢትዮጵያውያንን በየመንገዱ እየተሳደቡ እንደሚገኙ ከሰነአ የሚገኙ ወገኖች ጠቁመዋል::የሳኡዲ አየር ሃይል ኤምባሲውን አልመታም::በተሳሳተ መረጃ ለማደናበር ወያኔ እየሞከረ ነው:: .... ወያኔ የለመደውን የማደናበሪያ ፕሮፓጋንዳውን መንዛት ዜጎችን እያስፈጁ ዜጎችን ማጭበርበር የወንጀል ሁሉ ትልቅ ወንጀል ከመሆኑም በላይ ነገ ከተጠያቂነት አያድንም::'

The post በበደል ላይ በደል የከሳውን መግደል !! የወያኔ ጥቅም ለማጋበስ የሚደረግ ሩጫ እስካሁን አልተሳካም:: appeared first on Zehabesha Amharic.

የሰማያዊ ፓርቲ አደራጆችና የሰልፉ ተሳታፊዎች ድብደባ ተፈፀመባቸው

$
0
0

Gamu Gofaበደ/ጎንደር ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አደራጆች፣ መጋቢት 20/2007 ዓ.ም በደብረታቦር ከተማ በተካሄደው ሰልፍ ላይ የተሳተፉ ዜጎች ድብደባ እንደደረሰባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አደራጆችን ጨምሮ በሰልፉ ከተገኙት መካከል 20 ያህል ዜጎች በገዥው ፓርቲ የደህንነት ኃይሎች ድብደባ የደረሰባቸው ሲሆን በደ/ጎንደር ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ፀኃፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ በትናንትናው ዕለት በደህንነቶች ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰበት ገልጾልናል፡፡

ትናንት መጋቢት 24 ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ ‹‹ትፈለጋለህ›› ተብሎ በደህንነቶች ከተያዘ በኋላ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመበት የገለጸው አቶ ሰለሞን ታደሰ በከተማው ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ እንዲያድር ከተደረገ በኋላ ዛሬ ጠዋት መፈታቱን ገልጾአል፡፡ በተመሳሳይ በሰልፉ ላይ የተገኙት ዜጎችና የሰማያዊ ፓርቲ አደራጆች ‹‹ሁከትና ብጥብጥ ልትፈጥሩ ሞክራችኋል›› በሚል እስርና ድብደባ ተፈጽሞብናል ብለዋል፡፡

ማታ ላይ ያለምንም ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከተያዘ በኋላ ደብደባ ተፈፅሞበት ታስሮ ያደረው አቶ ሰለሞን ጠዋት 2፡30 ላይ የከተማው የፖሊስ አዛዥ መቶ አለቃ ፈንቴ እና የፀጥታ ሰራተኛው ትዕዛዝ ‹‹ልቀቁት›› ተብሎ እንደተፈታ ገልጾአል፡፡

Negere Ethiopia

The post የሰማያዊ ፓርቲ አደራጆችና የሰልፉ ተሳታፊዎች ድብደባ ተፈፀመባቸው appeared first on Zehabesha Amharic.


ድምጽ ከመስጠት ደም መስጠት   (አብርሃም Hታዬ)

$
0
0

በቅድሚያ ይሄን አስተማሪ ቀልድ ጀባ ልበላችሁ

electionአንድ ግለሰብ ይሞትና ነፍሱ ዳኞች ፊት ቀረበ።እንደ አጋጣሚ ለወደፊት የሚኖርበትን ገነትን ወይም ሲኦልን ገብኝቶ የመምረጥ እድል ተሰጠው።በመርሐ-ግብሩ መሰረትም በመጀመሪያ ሲኦልን እንዲጎበኝ ይጋበዝና ገና ከበሩ ላይ በመልካም አለባበስ የተሸቆጠቆጠው ሳጥናኤል በሞቀ ሰላምታ ተቀብሎት ወደ ውስጥ ይዞት ይገባል።ገሃነም ውስጥ የሟች የድሮ ወዳጆች ሁሉ ተሰብስበው እየጠጡ፣ ከረንቦላ እየተጫወቱ፣ ዲኤስ ቲቪ እያዩ እና በሙዚቃ እየጨፈሩ አስደሳች ጊዜ ሲያሳልፉ ተመለከተ።

ከዚያም ወደ ገነት ተወሰደ። ገነት እንደ ገባ አንድም የድሮ ጓደኛውን ሊያገኝ አልቻለም። ከዚያም በላይ ሲያስበው ያስመረረው ግን በገነት ያሉ ሰዎች ነጫጭ ለብሰው ስራቸው  ማሸብሸብ፣መጸለይና መስገድ ብቻ መሆኑ ነው ።

ሟች ሁለቱንም ሁኔታዎች አመዛዝኖ ሲያበቃ ገሃነም ከወዳጆቹ ጋር ለመቀላቀል ወስኖ ፊርማውን አኖረ። በማግስቱ ወደ ገሃነም ሲወሰድ ግን የጠበቀው ነገር ሌላ ነበር። ሳጥናኤል በአስፈሪ ዕርቃኑ ቆሞ እህል-ውሃ የማያሰኝ ጅራፍ ይዞ እየዠለጠ ወደ ውስጥ አስገባው። ውስጥ የነበሩት ጓደኞቹም ግማሽ ሰውነታቸው በእሳት ተዘፍቆ ሲሰቃዩ ተመለከተ።  ወደ አንድ ጓደኛው ጠጋ አለና ‹‹ትላንትና ያየሁት ደስታ የት ሄደ?›› ብሎ  ቢጠይቀው። ‹‹አይ እሱማ የምርጫ ቅስቀሳ ነው›› ብሎት እርፍ!

በሃገራችንም ምርጫ ሲደርስ ገዢው ፓርቲ የኮንዶሚኒየም ቤት ዕጣ ደርሷችኋል ይለናል ቤቱ ግን ኣልተሰራም ወይ አላለቀም።የገባንባቸው ቤቶችም ፍሳሽ ከላይ ወደታች ሰው ላይ ይንጠባጠባል:: ምርጫ ሲደርስ ሰላማዊ ሰልፍ ይፈቅድልናል ስንወጣ ግን መንገድ ይዘጋብናል፥ የምርጫ ቅስቀሳ ፖስተሮች ይቀዱብናል፤ያስሩናል፤ ይደበድቡናል። እስከምርጫው ዋዜማ በየቀበሌው በየሰፈሩ እየዞሩ ድጎማ ይሰጡናል ይደልሉናል በምርጫው ማግስት አይናችንንም ማየት ይቀፋቸዋል።

ባለፉት አመታት ሊሰሩ ታቅደው የመሰረት ድንጋይ የተጣለባቸውን ቦታዎች እስካሁንም ሳይሰራ ተጎልቶ ምርጫ ሲደርስ ተጠቅላይ ምኒስተር ሃይለ ማርያም ደሳለኝ በወሎ መሰረት ድንጋይ ጣሉ ወይም ባላፈው የተመረቀ የዉሃ ማቆሪያ መረቁ ይሉናል በድጋሚ።ሃገር አቀፍ ምርጫ በደረሰ ቁጥር ወተት እንደ ዉሃ በቧንቧ አስገባለው እያለ የሚለፈልፈው መንግስታችን የተዋጣለት ፎጋሪ መሆኑን የሚያንጸባርቀውን የቀላል ባቡር ምርቃ እንመልከት።  አዲስ አበባን የበርሊን ግንብ ኣስመስሎ ለሁለት የከፈላት  የባቡር መንገድ ግንባታ አንድ ሰው ከሳሎን ቤቱ ወደመኝታ ቤቱ ለመሄድ የአንድ ሰአት ታክሲ መንገድ ርቀት ሆኖበታል። ሃዲዱ  ተመርቋል ተብሎ የካቲት ላይ ተነግሮን አገልግሎት የሚጀምረው ግን  ከሶስት ወር ኋላ ምርጫ ሲቃረብ  ነው ያሉን ያው ለምርጫው ማሟሟቂያ ዘገባ ካንድም ሁለቴ ሲመረቅም ሲጀመርም በመተረክ ህዝቡን በወሬ ለማጥገብ ነው። በተግባር ግን መንገዱ ከመሰራቱ ከ 6 ጊዜ በላይ ከባባድ የመኪና ግጭቶች ደርሰውበታል። አሰራሩ የይድረስ ይድረስ ስለሆነ የብረት አጥሩም የባቡሩ ሃዲድም ገና በድምጽ ይደረመሳል። የነቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ የሚለው አባባል ለፎጋሪው ወያኔ የተጠቀሰ እስኪመስል ድረስ ቻይና ሰራሽ መንገዶች ድልድዮች ሲልም ህንጻዎች ገና አመት ሳያገለግሉ ይሰነጣጠቃሉ ከጥቅም ውጭ ይሆናሉ።የቀለበት መንገድም ሆነ ቀላል ባቡር  የእግረኛ መንገድ ስለሌለው  በታጠረው የባቡር እና የመኪና   መንገድ እግረኞች  ሲዘሉ ሲሻገሩ ለአደጋ ይጋለጣሉ።

ገና ከመሰራታቸው ከተቆፈሩት መንገዶች አንዱ ዛሬ ባቡር መንገድ ተብሎ የታጠረው ከመስቀል አደባባይ ወደ ሳሪስ የሚወስደው ሰፊ የአስፋልት መንገድ መሆኑ መረሳት የለበትም። ከ2005 አም በፊት ለመኪና ብቻ ተብሎ የመስቀል አደባባይ ሳሪስ መንገድ ሲሰፋ በርካታ ሰዎች ካካባቢው ተነስተዋል ከቁፋሮ ጀምሮ  እስከ  አስፋልት የማልበስ ድረስ ከፍተኛ የዉጪ ብድር ገንዘብ ተከስክሶበታል። ይሁንእና  ስንት ወጪ ፈሶበት በተሰራው ባለሶስት መስመር መንገድ መኪኖች ሸር ማለት እንደጀመሩ ለባቡር መሆን አለበት የሚል ሃስብ በደንገት ብልጭ ባለበት የመለስ  የትራንስፎርሜሽን ቅዠት ምክንያት  ያው አስፋልት በድጋሚ ለባቡር ተብሎ ታጠረ ተቆፈረ አሁን ደሞ ተመረቀ ሲባል  አንድም ባቡር ሳይሄድበት ተሰባበረ።እንግዲህ ወያኔዎች ለ አዲስ አበባ ህዝብ በአምስት አመቱ የ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሰረት ሰራንልህ የሚሉት  ፉከራ ፉገራ ሲሆን እያየነው ነው። እውነታው ግን ድንጋይ መንገድ ላይ ከምሮ ሰውን ሁሉ ቃሊቲ አስሮ ማሰቃየት ነው::

በድፍረት ምርጫ ዲሞክራሲያዊ የሚያሰኘው ሂደቱ ነው እንጂ ውጤቱ አይደለም የሚለን የመንግስት የኮሚኒኬሽን ሃላፊ የእስካሁኑ ሂደት ዲሞክራሲያዊ ነው ብሎ መግለጫ ይሰጣል። ለመሆኑ  ጽሁፍን ሳንሱር ማድረግ ህገመንግስቱን የሚጻረር አይደለምን? ይሄው እስካሁን እንኳ ሰማያዊ ፓርቲ ከ10 ጊዜ በላይ የምረጡኝ ቅስቀሳውን በአንድዬዋ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ እንዳያቀርብ ተከልክሏል። ተለጣፊ የሚባለው መ ኢ ኣ ድ እና የተቃዋሚ ካባ ለብሶ የሚጫወተው ኢህአዴጉ ኢዴፓም የቅስቀሳ መልክቶቼ ሳንሱር እየተደረጉብኝ ነው ሲሉ ስንሰማ ወያኔ የራሱ የሆኑት እንኳ ለዘብተኛ ተቃውሞ ወይ ውዳሴ  ላለማዳመጥ መቁረጡ አምባገነንነቱ የከፋ ደረጃ ላይ መድረሱን ያረጋግጣል።

ህወሃት ኢህኣዴግ ሙሉ ሃያ አራት አመት ሙሉ ሃያ አራት ሰዓት እየደሰኮረ  በአምስት አመት አንዴ ለዛውም አንዲት ሰዓት  ለማይሞላ የተፎካካሪ ፓርቲ የሚሰጥ የአየር ሰዓት  ከተከለከለ  ህዝቡ ተፎካካሪ ፓርቲን መኖሩን ካልሰማ ቀጣይ አመታትን በድህነት፥ በ ኢ-ፍትሃዊነት፥በዘረኛው  ስርዓት ወስጥ መክረሙ አሌ ኣይባልም።

ምንም የግል ሚዲያ በሌለበት ሁኔታ በብቸኛው የመንግስት ቲቪ እና ራዲዮ ካመት ኣመት የሚሰለቸውን ወሬ መስማት ብዙ ኢትዮጵያውያንን አስመርራል ። ተፎካካሪ ፓርቲዎች ኣላማቸውን ባላስተዋወቁበት ሁኔታ ህዝቡን ንብን ይምረጡ ሲል ግራ ያጋባል። ሌሎቹን ከልክሎ ኣፍኖ እና አስሮ ብቻውን ምረጡኝ እያለ የህዝቡን የመዝናኛ ፕሮግራሞች የማየት ፍላጎቱን ገድቧል።

የኢትዮጵያ ህዝብ በምርጫ ዘጠና ሰባት ተመሳሳይ የኮንዶሚኒየም ቤት ምርጫ ሲደርስ የተሰጠው እና  በገንዘብም የተደለለ ቢመስልም በነበረችው ትንሽ ቅስቀሳ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን መርጦ ነበረ።ይሁንእና በማግስቱ ለምን ቅንጅትን መረጣቹ ብሎ ለምርጫ ቅስቀሳ ያሳየንን ፊት ነስቶ በርካታ ኢትዮጵያውያን ታስረዋል ተገድለዋል አሁንም የበቀል ሰለባ ሆነዋል::  ያኔ የተሰለፍነው የሚመረጥ ስለነበረ ሲሆን አሁን ግን ደም መጣጩን ከምንመርጥ ብንታቀብ ይበጃል::ሃሳብን የመግለጽ መብት በይፋ በተዘጋበት በዚህ ወቅት መከራከር ራስ ላይ ሰበብ መጠምጠም ነው::

በ አሁኑ ኣለም ቀፍ ታዛቢዎች በማይገኙበት የኣውሮጳ ህብረት ምርጫውን እንዳይታዘብ በተከለከለበት በዚህ ወቅት ከምንም በላይ ታዛቢው ህዝብ  የወያኔን እንጂ የሌላን ፓርቲ ኣላማ እንዳይሰማ ገድበው፥ የምርጫ ቆጣሪዎች ሳይቀሩ ከወያኔ ሴት ሊግ ወጣት ሊግ ያለህዝብ ይሁንታ ተመርጠው የምርጫ ድምጽ ለመስረቅ ለማዛባት ኣቆብቁበው፥ የሰማያዊን ከሁለት መቶ በላይ ዕጩዎች መወዳደር ኣትችሉም ብለው ያለህግ አግደው፥ በአጠቃላይ በዘንድሮው ምርጫ የመወዳደሪያ ሜዳው ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየጠበበ መምጣቱን የሚያሳይ ተግባራት ተከምረውብን የሚቆሰቁሱን ድምጽ ለመስጠት ሳይሆን ደም ለመስጠት  ነው።

ከገባን የምርጫ አጃቢ አድርጎን በሗላ ጅብ ሆኖ ከሚበላን ለወንበዴ ወያኔ ድምጽ ከመስጠት ለነጻነት ደም ብንሰጥ ይቀላል።

የቀድሞው የ አሜሪካ ፕረዚዳንት እብርሃም ሊንከን Ballot is stronger than bullet የምርጫ ካርድ ከጥይት የጠነከረ ነው ቢልም በሃገራችን የምርጫ ሳጥኖች በጠበንጃ ሲቀየሩ ስላየን  We are forced to use bullet instead of ballot የሃይል አማራጭ እንድንጠቀም እንገደዳለን።

እነ እስክንድር ነጋ ወይ ርእዮት አለሙ ብቻ ሳይሆን መላ ኢትዮጵያውያን ስለታሰርን በቅድሚያ ልንፈታ ይገባል።

ከአብርሃም ታዬ

The post ድምጽ ከመስጠት ደም መስጠት   (አብርሃም Hታዬ) appeared first on Zehabesha Amharic.

የፌዴራል ፖሊሶች እና የከተማዋ ፖሊሶች ከነሞባይል ስልካቸው ተገመገሙ ተፈተሹ ተሰረዙ

$
0
0

ከምኒልክ ሳልሳዊ

ባሳለፍነው ቀናት ጀምሮ በፌዴራል ፖሊሶች እና በአዲስ አበባ ፖሊሶች ላይ ጠንከር ያለ ግምገማ እየተካሄደ መሆኑን ሲታወቅ የፖሊሶቹ ሞባይል ስልኮች ሳይቀሩ ድንገት በደህንነት ሃይሎች እየተፈተሹ እና አላስፈላጊ የተባሉ እና ለወያኔ የማይመቹ የተጫኑ ዘፈኖች ፎቶዎች እና የተለያዩ ዶክመንቶች ሲሰረዙባቸው የነበረ ሲሆን በርካታ ፖሊሶች በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ሲደረግ የተወሰኑ ደሞ ክትትል እንዲደረግባቸው ታዟል:ከስራቸው የታገዱ እና የታሰሩ እንዳሉም ተጠቁሟል::

photo file

photo file


በአዲስ አበባ ለከተማው ፓሊስና ለፊደራል ፓሊስ ድንገት የተጀመረው ገምገማ እረፍት አንዳይወጡ በእረፍት ላይ ያሉት እንዲመጡ ተደርጎ በድንገት ሞባይል ተሰብስቦ በውስጡ የተለያዩ በመንግስትና በባለስልጣን የሚያላግጡ ቀልዶች የቴዲ አፍሮ ከሊፕ የተገኝበት የአማርኛና የኦሮምኛ ሀይለኛ ቀሰቃሽ ዘፈኖች የተገኘበት ከተለያዩ ሰዎች ጋር የተላላኩት መልክቶች ተጎርጉረው የተገኙባቸው እንዳስፈላጊው እርምጃ እንደተወሰደባቸው ሲገለጽ የታገዱ የታሰሩ ደሞዛቸውን የተቀጡ ሲኖሩ ወደፊት በድጋሚ ቢገኝባቸው ትልቅ ችግር ሊፈጠርባቸው እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ተሰቷቸዋል::

የለውጥ ሃይሎች በወታደሩ እና በፖሊስ ሃይሉ ዙሪያ ጠንካራ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ያሉት የመረጃው አድራሾች ፖሊሶች የሚያቀናጅ ሃይል እና የሚያስተባብር ሃይል ማጣታቸው እንዲሁም እንደ ደርግ ሃይል ትበተናላችሁ ሌላ ስልጣኑን ቢይዝ በማለት የሚደረገው ማስፈራሪያ በወያኔ እየተደረገባቸው መሆኑ ስለሆነ ከለውጥ በኋላ በስራቸው እንደሚቀጥሉ እና ከለውጥ ሃይሎች ጎን ቆመው ይህንን አምባገነን ስር አት እንዲገረስሱ አስፈላጊ የሆነ የግንዛቧ ማስጨበጫ ስራዎች እንዲሰሩ አሳስበዋል::

The post የፌዴራል ፖሊሶች እና የከተማዋ ፖሊሶች ከነሞባይል ስልካቸው ተገመገሙ ተፈተሹ ተሰረዙ appeared first on Zehabesha Amharic.

የመረጃ ግብአት…የ”ወሳኙ ማዕበል”ዘመቻ 9ኛ ቀን ውሎ አበይት ክንውኖች –ነቢዩ ሲራክ

$
0
0

መጋቢት 26 ቀን 2007 ዓም

የመረጃ ግብአት…

የ” ወሳኙ ማዕበል” ዘመቻ 9ኛ ቀን ውሎ አበይት ክንውኖች

Nebiyu Sirak* በ9ኛ  ቀን በሳውዲ መራሹ  ” ወሳኙ ማዕበል !” የአየር ማጥቃት ዘመቻ በየመን  ሰማይ በተጠኑ ወታደራዊ የሁቲ አማጽያን ይዞታዎች ላይ አየር ድብደባው መቀጠሉን የዘመቻው መምሪያ ቃል አቀባይ ብ.ጀኔራል አህመድ አሲሪ ናቸው ፣ ጀኔራሉ በዚሁ መግለጫች በወደብ ከተማዋ በኤደንም የሁቲ አማጽያ አልበገርላቸው ካለው የአካባቢ ሚኒሽያ ጋር ውጊያ መግጠማቸውን አስረድተዋል

* ከሁቲ አማጽያንን ኤደንን እንዳይቆጣጠሩ በአካባቢው ሚኒሽያ በመሬት ቃታ እየሳበ እንቅስቃቀሴያቸውን ሲያሽመደምደው በሰማይ የህብረቱን ጦር በተጠኑ  ኢላማዎች ላይ እንዲያተኩር በማድረግ በሚከወነው ድብደባ አማጽያኑን አቅመ ቢስ አድርጎ እንዳዳከማቸው ቃል አቀባዩ ተናግረዋል

*  ቃል አቀባዩ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ሰርጎ የሚገባባትን በሚዮን ደሴት Meon Island የሚገኙ የባህርና ሃይሉና የእግረኛው  ጦር መሳሪያዊች በሳውዲ መራሹ የአየር ድብደባ ኢላማ ገብተው ተደምስሰዋልም ብለዋል

* በአየር ድብደባው ተስፋ የቆረጡና የተዳከሙት የሁቲ አማጽያን በመገናኛ ብዙሃንን ከእውነት የራቁ መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝቡን በማሳሳት ላይ ናቸውም ብለዋል ብ.ጀኔራል አህመድ አሲሪ

* በሌላ በኩል እየተካሔደ ስላለው ዘመቻ ማብራሪያ የሰጡት በአሜሪካ የሳውዲ አንባሳደር አድል አልጃብሪ  ዘመቻው በጥሩና በመጥፎ መካከል እንጅ በሱኒና በሸአ የእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል ሚካሔድ ጦርነት አለመሆኑን ተናግርዋል።  አምባሳደሩ በማከልም የሳውዲ መራሹ አረብ ሃገራት ዋና አላማ በኢራን በሂዝቦላህ የሚመራውን የሁቲ አማጽያን ከስልጣን አስወግዶ ፣  ህጋዊው የፕሬዚ አብድልረቡ መንግስት ወደ ቦታው መመለስ ነው ብለዋል ። አንባሳደሩ የቀድሞው የየመን ፕሬዚ አሊ አብደላህ ሳላህን በሚመለከት ሲናገሩ አሊ አብደላ ሳላህ ከሁቲዎች ጎን መሰለፋቸው  የተሳሳተ አካሄድ ነው ሲሉ ነቅፈውታል

በሳውዲ የመን ደንበር ድንበር መገዳደል …

* በሳውዲ የመን ድንበር ባሳለፍነው ረቡዕ አንድ ድንበር ጠባቂ በሳውዲ የመን ድንበር ሁለት የድንበር ጠባቂ መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን ትናንት አርብ ተጨማሪ ሁለት ወታደሮች መሞታቸውን ተጠቅሷል ። መረጃውን የድንበር ጦሩ ዳይሬክተር ሌተናል ኮሎኔል  አዎል ቢን ኢድ አል በላዊ አረጋግጠውታል

* የሳውዲው ንጉስ  ሰልማን ቢን አብድልአዚዝ የሟች የድንበር ወታደር ቤተሰቦችን ልዩ የሀዘን መልዕክተኞች በመላክ  አጽናንተዋል

ከዘመቻው ድጋፍ እስከ የመንን መልሶ መገንባት  ….

* በሳውዲ ታላላቅ ምሁራንና ታላላቅ የሐይማኖት አባቶች በሳውዲ መራሹን የየመን አየር ድብደባ ድጋፋቸውን እየሰጡ ነው

* የመን ከሁቴ አማጽያን ጠርታ የፕሬዚደንት አብድል ረቡ መንሱር ሃዲ መንግስት በሁቲ አማጽያን የተቀማውን ስልጣን ተቀብሎ የመን ስትረጋጋ የባህረ ሰላጤው ባለ ሃብቶች 150 በላይ ፕሮጀክቶችን በመክፈት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የማፍሰስ እቅድ መያዛቸው ተጠቅሷል
( መቸ ይመጣ ይሆን?  ብቻ ለዚያ ቀን ያድርሰን …)

በየመን የኢትዮ ይዞታና  የ” እውነት ፣ ውሸቱ”  እሰጣ ገባ

* በየመን የኢትዮጵያ ኢንባሲ ጥቃት እንደደረሰበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖምና መስሪያ ቤታቸው ከቀናት በፊት ፣ ቀጥሎም የኢትዮጵያ ቴሌቪዠን ቢያስታውቁም የተላለፈው መረጃ አነጋጋሪ ሆኗል።  በተባራሪ ጥይት በኢንባሲው የሚገኝን አንድ መኪና ጎማ መታ ተብሎ ጥቀሰት ብሎ ማቅረቡ የተጋነነ መሆኑን ከየመን ሰንአ የደረሱኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ

* በየመን ሰንአ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ዲፕሎማቶች ሳይሆኑ የኮሚኒቲ  ሰራተኞች ለመመለስ ፍላጎት ያላቸውን ተመላሽ ዜጋዎች በመመዝገብ ላይ መሆናቸው ተጠቅሷል ። የኢንባሲውን መደብደብ ዜና የሰሙት በቦታው ያሉትን የኮሚኒቲ ተወካዮች ሳይቀር በሚኒስትሩ ኢንባሲው ተጠቃ በሚል በቀረበው መረጃ ግራ የተጋቡ እንደነበር የአይን እማኞች ጠቁመዋል

*  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖም ” በየመን ሰነአ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ጥቃት ደረሰበት!”  ያሉትን ሰሞኛ ዝርዝር መረጃ ያልቀረበበት አነጋጋሪ መረጃቸውን  ተከትሎ ” ከአውስትራልያ የመጣች ታዳጊ 20 ሚሊዮን… ለገሰች !” እንደተባለችው ታዳጊ ወጣት ስጦታ ገንዘብ ምንጭ ዙሪያ የተደረገውን ያህል ሙግት እሰጣ ገባ የየመኑ ጥቀሰት ባይገንም  ” እውነት ፣ ውሸቱ ”  ግን ቀጥሏል
( አሜሪካ ቢሆን ይህ ይደምቅ ነበር ያሉኝ አሉ: )  )

* ከቀናት በፊት በኤደን የመን አድርገው ጅቡቲ የገቡት 30  ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገር ቤት መግባታቸው ተጠቁሟል ፣ ”  ወደ ሃገር ቤት መግባቱ ለደህንነታችን ያሰጋናል !”  ያሉት ግን ወደ ሶስተኛ ሃገር የሚሻገሩበትን መንገድ በመላ አለም የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ድምጻቸውን እናሰማላቸው ዘንድ በመማጸን ላይ ናቸው   !

እስኪ ቸር ያሰማን  !

ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 26 ቀን 2007 ዓም

The post የመረጃ ግብአት… የ” ወሳኙ ማዕበል” ዘመቻ 9ኛ ቀን ውሎ አበይት ክንውኖች – ነቢዩ ሲራክ appeared first on Zehabesha Amharic.

ጋዜጠኝነት የማሰብ ጥበብ ልቅና ነው! –ሥርጉተ –ሥላሴ

$
0
0

ሥርጉተ – ሥላሴ 4.04.2015 /ዙሪክ ሲዊዘርላንድ/

„እንቅልፍ ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም“ – ከአቨው ብሂል

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

እንዴት ናችሁ የኔዎቹ  ሐገር ሰላም ነውን? ዬዛሬ መነሻዬ “ኢትዮጵያዊቷ የISIS ሙሽራ እና “ጽንፈኛ” ሆነው የተገኙት አባቷ” ይህ እርእሱ ሲሆን በውስጡ ብንሄድበትም እርገቱ እንዲህ ይላል “ድምጻችን ይሰማ በዚህ ውዥንብር „ሳይደናገር” ላለፉት 3 ዓመታት ያሳየንን ሰላማዊ እና ስልጡን ተቃውሞ እንደሚቀጥል ቅንጣት ታህል ጥርጥር የለኝም።” ዬፁሑፉን ምንጭ ፌስ ቡክ ላይ ከካሳሁን ይልማ(የኢሳት ጋዜጠኛ) ሲል ዘሀበሻ ባጠናቀቅነው ሳምንት የመጀመሪያ ቀናት ጹሑፉን ለጥፎታል።http://www.zehabesha.com/amharic/archives/40100 እኔ የፌስ ቡክ ተሳታፊ ባለመሆኔ መልካም ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ለምን? ሚሊዮን አድናቂ አለና ብዙ ሰው አንብቦታል፤ በውስጡም አስቀምጦታል ብዬ ስለማስብ ብቻም ሳይሆን የዋህ ወገኖች ባልሆነ መልክ ሊተርጉሙትም ስለሚችሉ “ህልም እንደፈቺው” አይደል የሚባለው እንዲሁ ተንጠልጥሎ ከሚቀር ቅርጥምጣሚ ስጋቶች መሬት ላይ ወርደው በቅጡ መያዝ ስላለባቸው ልንሸራሸርበት እንዲህ አሰኜኝ። በቅድሚያ ግን ላመስግነው ዘሃበሻን – እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

እኔ የፌስ ቡክ ተሳታፊ ባለመሆኔ መልካም ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ለምን? ሚሊዮን አድናቂ አለና ብዙ ሰው አንብቦታል፤ በውስጡም አስቀምጦታል ብዬ ስለማስብ ብቻም ሳይሆን የዋህ ወገኖች ባልሆነ መልክ ሊተርጉሙትም ስለሚችሉ “ህልም እንደፈቺው” አይደል የሚባለው እንዲሁ ተንጠልጥሎ ከሚቀር ቅርጥምጣሚ ስጋቶች መሬት ላይ ወርደው በቅጡ መያዝ ስላለባቸው ልንሸራሸርበት እንዲህ አሰኜኝ። በቅድሚያ ግን ላመስግነው ዘሃበሻን – እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ጹሑፉ „ድምጻችን ይሰማን” አክብሯል። ለዚህም ለታናሼ ምስጋና ይድረሰው እላለሁ። ያልተመቸኝ ነገር ግን አለ። ለዚህም ነው ከእሜቴዋ ጋር ተመካክረን የምንለውን ልንል የተሰናዳን። እንዲህ ዓይነት ጉዳዮች በተፈጠሩ ቁጥር ከሌሎች ነገሮች ጋር ዬምናያይዘው ነገር ፈጽሞ አይገባኝም። ባለቤቶች እኮ አሉ። በተጠያቂነት የሚቀርቡ። እኔ ሥርጉተ በእንደነዚህ ዓይነት ጉዳዮች ጋር አብሬ አልቆዝምም። ለወያኔ የፈጠራ ክስ አጨብጫቢነት የሰናፍጭ ታክል ክፍተት – ድንኳን ሰብርነትንም አልፈቅደውም። እኔ በግሌ ንቅናቄ፤ ድርጀት፣ ግንባር በአጠቃላይ ተልዕኮውና በውላዊ ሂደቱ ብቻ ነው የምለካው። “ሳይደናገር” ምን ያደናግረዋል? የተነሳበት ንፁህና ቀጥ ያለ ግልጽ የነፃነት ዓላማ አለው። ለማንኛውም ….

  1. ድምጻችን ይሰማ ለእንደዚህ መሰል ነገሮች በዬሰከንዱ ለሚፈጠር ግሎባል ግድፈት ጋራንቲ ዋስትና ሊሰጠን ፈጽሞ አይችልም። አይጠበቅበትም-ም። ስለምን የሚለውን እመጣበታለሁ።
  2. በፍጹም ሁኔታ እንዲህ አይነቶች ነጠላዊ ጉዳዩች ወይንም ቀንጣዊ ክስተቶችን ዬሚሊዮን ወላዊ ድምጽ ኃላፊነት ወስደው ከሚሸከሙ እንደ “ድምጻችን ይሰማ” ካለው ጋር ሆነ ከሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ማነካካት አይገባም ባይም ነኝ። ፈጽሞ በዚህ ዕይታ ውስጥ “ድምፃችን ይሰማ” መጠቀስ ሥሙ መነሳት አልበረበትም። ስለምን? የነጠረውን እውነት ፈላጊነታችነን ዳመናማ ያደርገዋልና። ለሰብዕዊ መብት ተሟጋችነታችነንም በአረም ያስውጠዋል። ወያኔ ሃርነት ትግራይ “አሸባሪ” ያላለው ምን አለና። ሳር ቅጠሉ ንፋሱ ሳይቀር ለወያኔ “አሸባሪ” ነው፤
  3. በሌላ በኩል የነፃነት ረሃብተኛነት ቋሚ ፍላጎትን ስንጥር ሊነቀንቅው አይገባም። ሶስት ዓመት እኮ ልጅ ተጸንሶ ተወልዶ በእግሩ የሚሄድበት ብቻም ሳይሆን አፍም የሚፈታበት ወቅት ነው። ንቅናቄው በዚህ ቆይታው ከመምህርነቱ በስተቀር የታዬበት ግድፈት የለም። ፈተናዎቹንም በስልትና በጥበብ በመያዝ ትብትቦቹን እዬረገጠ ወደ ፊት መገስገሱን ነው ያዬነው።

ወጀቡ ሊያል ይችላል። ጦሩም ሊመዘዝ። አውሎም ሊንጥ። እኔ እላለሁ ጋዜጠኝነት የማሰብ ጥበብ ልቅና የሚታይበት የህማማት ሙያ ነው። ጋዜጠኝነት የምቾት፣ የድሎት ወይንም የዕውቅና ፍለጋ፣ ወይንም የቅልጣን ሙያ  አይደለም። ይልቁንም ሁሉንም መከራ ተቀብሎ ለዕውነት ጥንግና ድርብ በመሆን ሚዛን ጠብቆ ዘብ መቆም ነው። ስለሆነም ፈተናውን ሁሉ በመቀበል ሂደት ውስጥ አጋዢ ወይንም ጥግ ወይንም አይዞህ /ሽ/ የሚል ላይኖር ይችላል። ግን ዕውነት በጠባቂነት ስለሚሰለፍ፤ የእውነት አቅም ኃይልን እያመረተ ወደ ውስጥ የማዬትን ጸጋ ያፈልቀዋል – መጎናጸፊያውም ትጋትን አበረታቶ ፊት ለፊት ወጥቶ በማገዶነት መጓዝን ይመርቅለታል። ስለዚህ ለጋዜጠኛ ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል – ይመራዋል። የሙያው ሥነ – ምግባር ሃይማኖቱም ይሄው ነው። ፈጣሪ አምላክ በአምሳሉ ለፈጠረው „ሰው“ ልዩ የአክብሮት አቅምና ጉልበት በውስጡ የመገንባት ጥበብ – ጋዜጠኝነት። ደንበር የለሽ ሙያ – ጋዜጠኝነት። ከተከፉ ጋር የሚሰለፍ መከራን የደፈረ ሙያ – ጋዜጠኝነት።

አብሶ ነፃነት ተጋድሞ እንደ ግንድ በአንባገነኖች በሚፈለጥበት ወቅት „ነፃነትን“ ነፃ ሊያወጡ የሚተጉ ከሌላ ሙያ ያሉ ወገኖች ሳይቀር ወደ ሙያው አዘንብለው የእውነት፣ የሰብዕዊ መብት ጥሰት፣ የህግ ረገጣን በመቃወም ፊት ለፊት ወጥተው አንባገነኖችን ሆነ አንባገነኖችን የሚደግፉትን ዲታ ሀገሮች ሳይቀር ይሟገታሉ። ለዚህ ሩቅ ሳንሄድ መምህርና ጋዜጠኛ ርዕዮትን አለሙን፤ መምህርና ጋዜጠኛ አብርሃም ደስታን እንደ ናሙና መውሰድ እንችላለን። በሌላም በኩል የዞን ዘጠኝ በመባል የሚታወቁትን ወጣት ትንታግ የብሎግ አርበኞች ዕጣ ፈንታ በማስተዋል መመርመር እንችላለን። የጠራቸው፤ ያሰባሰባቸው፣ ያነሳሳቸው አንድ ነገር ብቻ ነው። ማህበራቸውም አንድ ነው። የሰብዕዊ መብት ጥበቃ በአረም መዋጥ። ነፃነትነትን ከነደራጎን መንጋጋ ለማውጣት ከህዝብ ጎን ቆሞ „ሰብዕነትን“ ሁሉን መከራ መቀበል ነፃ ማውጣት። ይህ ነው የጋዜጠኝነት ተልዕኮ። በአጋጣሚ በእሳት ላይ ሁነው በዞን ዘጠኝ ጋዜጠኞች የቀጠሮ ቀን ሳይታክቱ፤ በራስ በመተማመን ፍጹማዊ መንፈስ በፍርድ ሂደቱ ቦታ በመገኘት እራሳቸውን ለመስጠት የተዘጋጁትን ወገኖቼን በማድነቅ – አመሰግናቸዋለሁ። በወራሪ ወታደር ታጅበው ይህን ያህል ጥንካሬ ማሳዬት፤ በመከራ ቀን ለዕንባ ዘብ መቆም የኢትዮጵያን ተስፋ ያሰፋዋል – ኑሩልን። እናንተ እራሳችሁ የጀግንነት ድሪ ናችሁና።

አሁን ወደ ነጥቤ። ሙያውን ከነፍሳቸው ጋር አዋህደው ወደውትም የጀመሩትም ቢሆን፤ መፍቅድ የቻሉት አንድ ነገርን ብቻ ነው። ዝናን አይደለም። ስለ እውነት ጧፍ መሆንን ብቻ ነው። ለዚህም አባ ትርጉም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን፤ አብነቱን በጥልቀት በመስተዋል መመርምር ይቻላል። ታታሪዎችን ጋዜጠኛ ውበሸት ታዬ እና ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝምም ፈለጉን አጠንከረው ራሳቸውን የሰጡበት ሚስጢር የህሊናቸው የማስብ ደረጃ ልቅናው ከፍ ያለ በመሆኑ፤ እነኝህ የዘመን አባ እና እማ ወራዎች ማገዶነቱን በመምረጥ በመከራው ዘመን ቀንዲል መሆን ችለዋል። በርካቶችም ሳይወዱ ተገደው ተሰደዋል። ይህ እንግዲህ በእኛዋ እናት ሀገር ኢትዮጵያ ያዬነው ጭብጥ ንጡር የሙያው ባላቤቶች ተግባር ነው። በውጪውም ቢሆን ከሞቀውና ቅልጥ ካለው ስልጡኑ ሀገራቸው ወጥተው ለሙያው ክብርና ሥነ – ምግባር ሲሉ ባልተወለዱበት ሀገር በጦርነት ውስጥ ያለፉ፤ የሃቅ ፈርጦች፤  ዬእውነት ኮከቦች የሙያው ዘውዶች ዓለማችን በዬዘመኑ በእጅጉ አስተናግዳለች።

በዘመነ አዶልፍ ሂትለር ያን ያክል እሳት ውስጥ ገብቶ የተርመጠመጠው አርበኛ ፍራንስ ለሆዱ አላደረም ነበር። ባለቤቱ ወ/ሮ ሶፊ በሚደርስባት ተጽዕኖ ተጨንቃ „ትዳራችን እይ ስትለው „እጃችን ተመልከችው የእኔና የአንቺ አንድ አይደለም አስተሳሰባችንም“ በማለት ነፍሱን ለናዚ በለሃሰብ ወታደሮች ሰጥቷል፤ አጋሩ ወ/ሮ ሶፊም ከልቧ በገባው ዕውነት ተማርካ እስከ መጨረሻው አብራው እንድትሆን አድርጓታል። አዶልፍ ሂትለር ጀርመንን ከሌላው የለዩበት ዶክተሪንና ያን ያህል ነፍስ ያጠፋበት፤ ያቃጠሉበት ኢ-ሰብዕዊነት ድርጊትና የሄሮድስ መለስ ዜናዊ „እንኳንም ከእናንተ ተፈጥርኩ፤“ ጠፍ መንገድ ሚሊዮኖች እንዲከፉ፤ አንዲገለሉ እንዲሞቱ እንዲሰደዱ ያደረገው ሁለቱም አንድ መንገድ ነው የተከተሉት። አዶልፍ ጀርመናዊነት ዝርያን ማንጠራራታቸው፤ ሄሮድስ ደግሞ ትግራዊነት ዝርያን ማንጠራራታቸው ወጥ የናዚዝም ጸረ ሰብዕ ፍላጎት በዬዘመኑ እንድናይ አድርጎናል። ለዚህም አውራንባ ታይምስን ከሁለት በከፈለው ግድግዳ የሰውን ልጅ ተፈጥሮ በቅጡ የመተርጎም አቅም ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ነጥሮ ወጣበት፤ በሌላም በኩል የኢትዮጵያ ቴሊቪዥንና ራዲዮ አገልጋዮችና የኛው ውድ ጋዜጠኛ አብርሃም ደስታ ደምቆ የወጣበት ሃቅ ማገርና ግድግዳው ሆነ ባላና ወጋግረው „ሰብዕዊነትን“ በእኩልነት ከማዬት፤ የተፈጥሮን ሚስጢሩን ከማግኘት ያደገ አስተሳሰብ መንጭቶ ነው። ዛሬም እሳት ከሚተፋው ቦንብ ሥር መስዋዕትነቱን እዬከፈሉ የሚገኙ አሉ።

ጋዜጠኝነት — እውነትን የመግለጽ ብቻ ሳይሆን እውነትን የማመን፤ እውነትን የማመን ብቻ ሳይሆን እውነትን የመቀበል፤ እውነትን የመቀብል ብቻ ሳይሆን ስለ እውነት ውስጥን ገዝቶ የእውነት ብራ መሆን የክቡሩ ጋዜጠኛ ምግባሩም ህይወቱም ነው። ጋዜጠኛ ውስጡ የሚቃጠለው እውነት ተዘቅዝቃ ስትንጠለጠል ነው። ጋዜጠኛ መንፈሱ የሚርመጠመጠው „ሰው“ የሚለው አባወራ / እማወራ ፍጡር ክብሩ ትቢያ ሲለብስ ነው። ተፈጥሮ ሲደፈር ማዬት ለጋዜጠኛ ህመሙ ነው።

በዬትኛውም መስፈርት ቢሆን አንድ ጋዜጠኛ በቋሚ የዕውነት ማገሩ ላይ ጽኑ የሆነ አቋም ሊኖረው ይገባል። ኢትዮጵያ የዓለም አካል ናት። ስለሆነችም ነው እኛ መኖራችን የዓለም አቅምና ጉልበት መሆናችን አትዘንጉ። ስለዚህም በሀገራችን ባለው የመብት ረጋጣና የመብት ድፍጠጣ አንባገነናዊ ጎጣዊ አፓርታይድ ሥርዓት ለማስወገድ በምናደርገው የነፃነት ትግላዊ ሂደት ከጎናችን ልትቆሙ ይገባል፤ በማለት በመላ ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵውያን ሲችሉ በጋራ፤ ሳይችሉ ደግሞ በግል የሚችሉትን ሁሉ በማደረግ ላይ የሚገኙት።

በአንፃሩም እንደ ዓለም አካልነታችን ከዬትኛውም ሃይማኖት ወይንም ማህበራዊ ተቋም በዓለም በሚከሰቱ አሉታዊ ሁነቶችም ሆነ መሰል ጥፋቶች ሊሳተፉ የወደዱና የፈቀዱ መኖራቸው ደግሞ ግድ ነው። ዓለም በሽታን የሚያውቅ መሳሪያ አላት። ነገር ግን የሰውን ልጅ አሉታዊና አዎንታዊ ረቂቅ አስተሳሰቡን የምታይበት ወይንም የምታነብበት ወይንም የምትመዘግብበት መስታውት ዘመን አመጣሽ ዲጂታል መሳሪያ እስካሁን አልፈለሰፈችም። ቢሆንማ ዕድሜ፣ ፆታ፣ ሃይማኖት ሳይለይ ይህ በዬሰከንዱ የሚታዬው እጅግ ዘግናኝ፣ አሰቃቂና አስፈሪ አደጋን መቆጣጠር በቻለች ነበር። ዛሬ በእያንዳንዱ ፍጥረት ዙሪያ ስጋት ገዝፎ አለ። ሰው ወጥቶ ስለመመለሱ ስለማያውቅ የስንብት ደብዳቤ ጽፎ መውጣት እዬተለመደ መጥቷል። እርግጥ አንድ የሚያድን ነገር ነበር። ይህን የሚያድን ነገር እሰከ አሁን ዓለም እራሷ አልተጠቀመችበትም። ሚስጢሩንም የደረሰችበት አይመስለኝም። ብትደረስበትም በአንድ ጀንበር ውጤት የሚታይበት አይደለም። የረጅም ጊዜ የጥረት ውጤት ነውና።

የሆነ ሆኖ ዓለም ያልቻለችውን ኢትዮጵያዊው „ድምጻችን ይሰማ“ ከዬትና በምን አቅሙ ያመጣዋል። ሚሊዮኖች የታደሙበት እንቅስቃሴ ውስጥ በምን ስሌትና በምን ሁኔታ፤ በምንስ አቅሙ ዬእንክርዳድ ከስንዴ የውስጥን ስሜትና አቅጣጫ መመርመር ያስችለዋል? ዳኝነት ለራስ ነው። ፁሑፉ ተጠያቂ እንዳለደረገው አውቃለሁ። ነገር ግን የዝንባሌው መንፈስና ጠረን „ድምፃችን ይሰማ“ አቅጣጫውን እንዳይቀር የሚነካኩ ኩነቶች አሉበት። እንደገናም ከውስጡ አረም ቢበቅል የሚል ቅርጥምጣሚ ስጋትም ሸቶኛል። በማህበራዊ ኑሯችንም ስንለካው „በሬ ካራጁ ጋር“ የሆኑ ገጠመኞች እንዳሉንም መዘንጋት የለብንም። ገጹን ታያላችሁ ይመቻችኋል። አብራችሁ መልካሙንም መልካም ያልሆነውን ትጋራላችሁ። ቀጥሎ ደግሞ አጋጣሚ ቀን የሰጣችሁ ቀን  የምታውቁት ያ ሩህሩህ – አስተዋይ – ደግ – አለኝ ብላችሁ ያስጠጋችሁት እምነት የሰጣችሁት፤ በውስጣችሁ ያነገሳችሁት ገፅ ሌላ የማታውቁት ገፅ ሆኖ ያፋጣችኋል። እንደዚህ መሰሉ ረቂቅ ውስጣዊ መንፈስን የማንበብ ሆነ ቀድሞ የመተንበይ ብልሃት „ድምጻችን ይሰማ“ ከአቅሙ በላይ ስለሆነ ተጠያቂ ሊያደርገው ፈጽሞ አይችልም። የሆነ ሆኖ ….

ደግሞስ ምንስ አዲስ ነገር አለው። ከዬትም ቦታ ከዬትኛውም ሀገር እንዲህ ዓይነት አስተሳሰብ ያላቸው ጋድሞች፣ ሲዖሎች፣ ጸረ ተፈጥሮዎች ይፈጠራሉ። በዬቀኑ አውሮፓ ላይ በግል አባል ሆነው የሚገኙ የሚታሰሩ፤ ሄደው የሚቀላቀሉ እንደ አሉ ዜናዎች ያመልክታሉ። ነገም ከነገም ወዲያ ኢትዮጵያ የዓለም አካል እንደመሆኗ ኢትዮጵያዊ የሆነ ወይንም የሆነች ይህን ጸረ ሰብዕ፤ ጸረ እድገት፤ ጸረ ነፃነት የሆነውን አጥፊ ድርጅት ሊቀላቀሉ የሚችሉ የጥፋት አቀንቃኝ ብቻ ሳይሆን መሪ ሆነው ሊገኙም የሚችሉ ይኖራሉ። ይህን መጠበቅ ይገባል። ለዚህ „ድምጻችን ይሰማ“ ጋራንቲ ወይንም ጥብቅ የዋስትና ኪዳን እንዲሰጥ አይጠበቅበትም – በፍጹም። ክፍል ከፍተው እኮ በይፋ „ጀሃዲስትነትን“ በአደባባይ ሲያውጁ ነበር። ይህን በዛ „ጆኖሳይድ“ በሚባል ክፍል ውስጥ የበቁት ዬኢንተርኔት ባለሙያ ኢትዮጵውያን ወገኖቼ አድራሻቸውን እንደሚይዙት ተስፋ አደርጋለሁ። ያው ኢትዮጵያዊነት ዬይሉኝታ ማርዳ በመሆኑ አሳልፈው ሳይሰጧቸው በመረጃነት አስቀምጠውት ይሆናል ብዬም አስባለሁ።

„ድምፃችን ይሰማ“ እንቅስቃሴ ነው። እንቅስቃሴው አንድ የነፃነት ትግል ፕሮጀክት አለው። ፕሮጀክቱ የዕምነቱን ነፃነት በነበረው አቮዊና ትውፊታዊ መልክ ማስመለስ ነው። ይህ ከተመለሰለት ዬፕሮጀክቱ ተልዕኮው ያበቃል ማለት ነው። በቃ! ግልጽ ጥያቄ ነው። „መሪዎቻችነን በመስጊዳችን እንመርጥ። ምርጫው የሃይማኖታችን ሥርዓት በሚፈቅደው መሰረት ስለመሆኑ ለእኛ ተውልን። መንግሥት በሃይማኖታችን ጣልቃ አይግባብን፤ ካለአግባብ የታሰሩ መሪዎቻችን ይፈቱልን፤ ከታሰሩበት ቦታ ኢ – ሞራላዊ ጭካኔ አይፈጸምባቸው፤ መሪዎቻችን የሃይማኖት መሪ እንጂ አሸባሪዎች አይደሉም፤ በሃይማኖታችን በምታደርሱት በደል ከፍቶናልና ድምፃችን ስሙ“ ይሄ ነው። ከተሳሳትኩኝ ልታረም ዝግጁ ነኝ። ይህን ቀላል ጥያቄ የወያኔ ሃርነት ትግራይ መመለስ አልቻለም። ለምን?

እስትንፋሱ የሚቆዬው በዚህ ዙሪያ በሚሰራቸው የጣልቃ ገብነት ተግባር ስለሆነ ሽፋን አይገኝም – ከዲታ ሀገሮች። በኢትዮጵያም „አሸባሪዎቸ አሉ እነሱን እዬገላገልኩላችሁ ነው። ሰብስቤ አስሬላችሁአለሁ፤ ማለት እንዲችል „ፈጥሮ የአሸባሪ ሥም ለጥፎላቸዋል“ ይህም ብቻ አይደለም። ይህን በማደረጉ „የድምጻችን ይሰማ“ በእልህና በቁጭት ተነሳስቶ ወደ ጥፋት ተግባር እንዲሰማራ፤ የሌሎችን የሃማኖት ተቋማትን በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን ክብር በግብታዊነት እንዲያወድም – እንዲያዋርድ፤  ዬእርስ በእርስ ሃይማኖታዊ ግጭት ጠብ እንዲጭር፤ እሳት እንዲነድ ለማድረግ ብዙ ጥሯል። ግን አልተሳካለትም። „ድምፃችን ይሰማ“ የብልህነት ጥንካሬው ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ ነውና።

„ድምፃችን ይሰማን ፍላጎትና ተልዕኮ“ የቁጣ፣ የእልህ እርምጃ አድርገውት ቢሆን ኖሮ፤ ለወያኔ ሰፊ የሆነ የቅጠፈቱ ቋት ይሆን በነበር። ዓለምም „ትክክል ነህ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በማለት ጎሽ! ደግ አደረከህ ብሎ ይሸልመው በነበር።“ ሌላው ወያኔ የማይተኛበት ነገር በመሃላቸው አስርጎ የማስገባቱ ጉዳይ ነው። ይህም ግምት ውስጥ ሊገባ ይገባዋል። አንድነት ለኢትዮጵያን የመሰለ ብሄራዊና መጠነ ሰፊ ትልም የነበረውን የተስፋ ፓርቲን ያፈረሰው በዚህ በሰለጠነበት የሸር ሙያው ነው። የሆኖ ሆኖ ወያኔ ሃርነት ትግራይ እንዳሰበው አልተሳካለትም የከሸፈ ባዶ ቀላሃ ነው የሆነው።

እንቅስቃሴው ትእግስቱን ዋጥ አድርጎ፤ መከራውን ችሎ በስልትና በጥበብ እርምጃዎችን ሳይመራ ለወያኔ ሴራ ቀለብ ቢሆን ኖሮ፤  እኛም ብዕራችን ሰብሰብ አድርገን፤ መንፈሳችን ቁጥብ አድርገን እንቀመጥ ነበር። ስለምን? ወጥቶ መቅረትን የሚመኝ አንድም ዜጋ ሊኖር አይችልምና። ሰቀቀን የሚደግፍና የሚበረታታ ነፍስ አይኖርምና። ጭካኔን የሚያባብል አንድም መንፈስ አይኖርምና። ከሁሉ በላይ የሃይማኖት ነፃነቱን ለመቀማት ማንም ሊተባበር አይችልምና። ነገር ግን በሁሉንም መሥፈርት የቀደመ፣ ብልህና ሥልጡን አመራሩ ተልዕኮውን በአረም አላስዋጠውም። ይልቁንም በጠራ መስመር መራው እንጂ ….። ከዚህ ጋር ተያይዞ መታዬት ያለበት ቁም ነገር በሰላማዊ ትግል ውስጥ ምላሽ ያለማግኘት ጉዳይ ዕድሜ ጠገብ ሲሆን፤ ከፍ እያሉና እያደጉ የሚሄዱ ማዕቀቦች መኖራቸውን መዘንጋት የለብንም። መብቱን የተቀማ ግን ህግን የጠበቀ፤ ብስጩነትን የተቆጣጠረ ግን ሙት መሬት ላይ ሆኖ ድልን ያለመ ብርቱ ሰላማዊ ተጋድሎ ከዚህ ጠንከር ብሎ ሊሄድ እንደሚችል ልብ ሊባልም ይገባዋል። እኔ በዕድሜዬ እንዲህ ያለ ምራቁን የወጣ ብርቱ፤ ተከታታይነት ያለው፤ ትጉህ፤ ንቁ፤ የመሪና የተመሪ ግንኙነት የሰመረበት ጤናማ ሂደት አይቼ አላወቅም። ከድንቅ በላይ ነው። ለታሪክ ሥጦታ ነው! በራስ የመተማማን ብቃቱ ከተነሳበት የእውነት ማህደር ይቀዳል። ስለዚህም – አይወዛወዝም።

ዬወያኔ ሃርነት ትግራይ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ለቃቅሞ መሪዎችን ከማሰሩ በፊት ጉዝጓዝ ሰርቶለት ነበር። የክርስትና እምነትን ለማስነሳት። ይህን በድንገት የመሠረተው ጉዳይ አልነበረም። የረጅም ጊዜ ዕቅዱ ነበር። ባዶ ቦታ ላይ፤ ምንም ሰው በሌለበት ቦታ ላይ፤ መስጊድ ሲያሰራ ሲያበረታታ የነበረው – ለስውር ፍላጎት ማመሳከሪያነት ነበር። ስለምን? እሱ ለፈጠረው – ለፈበረከው ክስ ቅድሚያ ቬሎ ያስፈልገው ስለነበር። ይሄው ቀድሞውንም ኢትዮጵያን የእስልምና እምነት ተከታይ ሀገር ለማደረግ የታሰበ እርምጃ ሲወሰድ ነበር ለማለት። ግን ወያኔ የሠራው የድቡሽት ትዕይንት ሁሉ አሞራው በረረ ቅሉም ተሰበረ ነው የሆነበት።

ሥነ ጥበብ የመንፈስ ሃብትነቱ እያዋዛ ወደሚፈልገው በጎ አቅጣጫ የመግራት ረቂቅ ልዩ ክህሎቱ ነው። እኔ የማዬው „የድምጻችን ይሰማ“ የሶስት ዓመት ታሪካዊ መምህር አንቅስቃሴም የዚህን ያህል ለእኔ ከልቤ የገባ መሆኑን በድፍረት እናገረዋለሁ። እኔን ኮትኩቶ ከጎኑ ያሰለፈ፤ የአቅም ጥሪትን በአግባቡ የመምራትና የማስተዳደር ልቅና ያለው ሆኖ ነው ያገኘሁት። አንድ እንቅስቃሴ እኮ በተግባሩ ነው የሌላውን ቀልብ መግዛት የሚችለው። የሚወደደውም በተግባሩ ነው። እንዲህ ዓይነት በጨዋነት – የሰከነ፤ ዘመኑን – ያዳመጠ፤ የአብሮነት ሥነ ምግባርን – ያልጣሰ፤ የኢትዮጵያዊነት ረቂቅ ብልጹግ ቀለማም መንፈስን ያልተፃረረ፤ ልዑቅ – በተግባር የከበረ፤ በእድገት የጎለመሰ ረጅም ቆይታ ያለው ሰላማዊ እንቅስቃሴ በታሪኳ ኢትዮጵያ ኖሯት አያውቅም። የታደለ!

ስለሆነም መለኪያችን ሆነ መመተሪያችን እንዳአለ የአካሉን አጠቃላይ እንቅስቃሴና ወላዊ ትልም ተግባራዊነት ላይ ሊሆን ይገባዋል የግድፈት መለኪያችንም እንጂ በእስልምና ዕምንት ዙሪያ በዬሰከንዱ አንድ ሁለት ከዚህም የበረከቱ ቀንጣና ተናጠላዊ የግለሰቦች ከመስመር የወጣ ግድፈት በተፈጸመ ቁጥር፤ ዜናዎችን ባደመጥን ቁጥር ያን እዬመዘዙ ከዚህ ግዙፍ የነፃነት እንቅስቃሴ ጋር ስጋትን መቋጨት ወይንም ጥቂትም ቢሆን ማነካካት የተገባ አይደለም። ዛሬ እናቴ እንኳን ይህን መሰል መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ ያለው አካል የአንድ ማህጸን ልጆችንም አወቀዋለሁ ለማለት ገደብ አለው። ስለዚህ ከሚጠበቀው በላይ የሠራና ያለዬነውን ደመ ግቡ ሥነ ምግባር ያሳዬን ውድ ብሩኽ የነፃነት ተጋድሎ  እንቅስቃሴ አካላችን ስለሆነ ክብሩን ልንጠብቅለት፤ ለመንፈሱ ልንጠነቀቅለት ይገባል ባይ ነኝ። ዕሴቱ ከፍ ያለ ነውና። በሚመለከተው ጉዳይ ብቻ እንጥቀሰው … በሚያይዘው ኩሁነት ብቻ እንጥራው …

ፍላጎታችና ድጋፋችን መሰረት ይኑረው! ተጎድተዋል ወይ!? ጥያቄያቸው ትክክለኛ ነው ወይ? ይህን የነፃነት ትግሉ አካል ነኝ የሚል ወገን መመለስ ይኖርበታል። መልሱ አዎን ተጉድተዋል ነው። እንዲያውም የወያኔ ሃርነት ትግራይ በስውር በሚሰራው ሴራ ሀገርና ህዝብ የመበደሉ ገመና እንዳይጋለጥበት ካሳ ነው ያደረጋቸው። ይህን ልብ ልንለው ይገባል። ዬብዙ ሀገር ዲክታተሮች እዬተጠቀሙበት ያለውም በዚህ ስበብ ነው። ሁሉም እጣቱን የሚጠነቁለው ወደ አንድ አቅጣጫ ብቻ ነው። የበለጸጉ ሀገሮች የሰብዕዊ መብት ረገጣ ለዛውም በ21ኛው ምዕተ ዓመት እዬተመለኩቱ ዓይናቸውን በዓይነ እርግብ ሸፍነው ዲክታተሮችን ከጎናቸው ቁጭ አድርገው የሚያበረታቷቸውም በዚህ ምክንያት ነው። በተለይም ጋዜጠኞች የነፃነት ፍለጋ ጉዞና ሌላውን ደባል አጥፊ ፍላጎት መቀላቀል አይገባቸውም። ስለምን? ጋዜጠኝነት የማሰብ ጥበብ ልቅና ነውና። ማለት የሰው ልጅ የማሰብ ልቅናው መለኪያ አፍቅሮተ ሰው ነውና። አፍቅሮተ ሰው ደግሞ የሰውን ልጅ ተፈጥሮ ከማክበር ይነሳል።

ፍላጎታች ሥር አለው። ሥሩ አንድ ግንድን ፈጥሯል። ነፃነት የመፈለግ ጉዞና ራዕይ። ነፃነት የመፈልግ ጉዞ ዬሥሩ ሴል የሴቶች እኩልነትን፤ የህፃናት ጥበቃና ፍትህን፤ የሙያ ክብራዊ ዕውቅና፤ የአዛውንታት ክብርና ሞገስነት፤ የወጣቶች የተተኪነት መብት፤ የዘመኑ ሥልጣኔ እኩል ነፃነታዊ ማህበራዊ ተጠቃሚነት፤ የቤተሰብ አክብሮትና ጥበቃ፤ ሙያን የመምረጥና በፈለጉት ሙያ የመሰማራት ያልተሸራረፈ ነፃነት፤ በፈለጉት አካባቢ ሰርቶ የመኖር ነፃነት፤ ሃብት የማፍራትና የማስተዳደር እንዲሁም ባፈሩት ሃብት የመጠቀም ነፃነት፤ የመንፈስ ሃብት የማስፋፋት፤ የማሰራጨትና የማሳደግ ነፃነት፤ የዕምነት እኩልነት ነፃነት፤ ዕምነትን በዕምነቱ ዶግማና ቀኖና የማስተዳደር ነፃነት፤ ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ ብቻ ሳይሆን በሃሳቡ ዙሪያ የመወያዬት፣ የመምከር የመተቸት ነፃነት፤ በሀገር ጉዳይ ላይ የመወስን ነፃነት፤  የመደራጀት – የመሰብሰብ – መሪዎችን የመመረጥና እራስም የመመረጥ የማስተዳደር ነፃነት፤ ድጋፍና ተቃውሞ የማቅረብ ነፃነት፤ ብሄራዊ ሰንድቅዓላማን የፈለጉትን ያህል ያልተገደበ የመውደድ ነፃነት፤ የሀገርና የክ/ሀገራት የወሰን ድንበር ውርሳዊና ተፈጥሯዊነት የመጠበቅ ነፃነት፤ በሀገር ንብረትና ሀብት እኩል ተጠቃሚ የመሆን ነፃነት፤ ትክክለኛ መረጃ የማግኘት ነፃነት፤ የሃብት ድልድና ሥርጭት የእኩልነት ነፃነት፤ የባህል ነፃነት፤ የፍልስፍና የሳይንስና የምርምር ነፃነት፤ የህግ የበላይነት ነጻነት ወዘተ ወዘተ …. ወዘተ …

ስለዚህ አንዱን ሥር ስንነካው ሌላው ላይ ተጽዕኖ ማሳደር ብቻ ሳይሆን፤ ያሰምመዋል፤ ያቆስለዋል፤ ያጠወልገዋል። በተዘዋዋሪ አይደለም በቀጥታ – በእያንዳንዱ የፍላጎታችን ሥር ሴል ላይ ጥቃት ይፈጽማል።

ህም! „ለሚያራግቡት ደህና አጋጣሚ አገኙ“ ለሚባለው ከእውነት ያልተነሳ ቀልብ ሳቢያ ፍለጋ እንደማሰነ ነው ኑሮው የሚጠናቀቀው። ሳቢያ ደግሞ መንገዱ አጭር ነው። ወርዱም – ጥብቆ። በራሱ ጊዜ ይከሽፋል። በራሱ ጊዜ አጀንዳው ይሟሟል። ሳቢያ ቆይታው ለቅጽበት ነው። ለማደግ – ድፍረት የለውም። በዬትኛው አደባባይ ነው የሚታዩት?!  አንገታቸውን ደፍተው ውስጥ – ለውስጥ አዩኝ – አላዩኝ ብለው ተሽሎክሉከው ነው እንደ እባብ መሬት ለመሬት ሲሄዱ የሚታዩት። ስለምን? የሚያቀርቡት አንዲት ሽራፊ የሃቅ ብናኝ የላቸውም። 30 ሺህ ፍትህ ጋዜጣ ሲቃጠልና ቁርሾው አገርሽቶ ለእስር የበቃባት ተሜ አፈር በሆኑት ሄሮድሳቸው ነው። ይህ እውነት አይደለም ለእነሱ። እሬሳ ታቅፈው ዜናውን ኢሳት ሲያቀርብ የተሳሰተ ማሰረጃ ሰጠ ብለው ሲከሱ ነበር። ከዚህ የበለጠ የተገለበ ጉዳይ ምን አለና?! በአደባባይ „ከአዲስ ዓመት በፊት ሥራ ይጀምራል መሪያችን“ አይደለም ያሉት? ግን ሆነ? አፈር ነው የጋጠው ቅጥፈታቸው። እነሱ በአስተሳሰብ ድህነት የተሸፈኑ ናቸው – ሠረገላቸውም ድንብስ። በጎጠኞች የህሊና ሰሌዳ ላይ ያለው ባዶ ቀለሃ … በቻ —–

ነገር ግን ምክንያታዊ የሆኑ አምክንዮች ጭብጣቸው ሆነ ዘላለማዊነታቸው ታሪክን በማብቀል – ነገን አሳምሮ በመስመቸት የበለጸገና የዳበረ ተመክሮን አዝምረው እውነትን በዓምድነት ያበራሉ። እውነት ቀጥ ያለ ደፋር ጧፍ ነው። ስለዚህ የአንድ ሰሞን አታሞ ዘላቂ ፍላጎትን ሊነቀንቀው አይገባም። እንዲያውም እንደ አሮጌ ቆርቆሮ ሲጮሑ ገዢ መሬት ላይ ያለው አሸናፊው ሥነ ልቦና ይደላደላል። ማንነት አለውና! ኢትዮጵያዊነት!

ለማንኛውም „የድምጻችን ይሰማ“ ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት አንድ የነፃነት ማሰከበሪያ ፕሮጀክት ነው። ወያኔ ሃርነት ትግራይ አቅም ኑሮት ለጥያቄው መልስ ቢሰጥ፤ ከጀርባ ሆኖ የሚጎትተው አንዳችም ስውር ፍላጎት ስሌለው ታሪክን በተግባር አቅልሞ በምስራች ይሰናበታል። ይህ ማለት ግን ነፃነት በመከነባት ሀገር የሚኖሩ ዜጎች ለነፃነታቸው በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ከሚፈልጉት የፖለቲካ ድርጅት ጋር ሆነው ትግላቸውን አያደርጉም ማለት አይደለም። የራህቡ – የመገለሉ – የመታረዙ – የሞቱ ሲሳይነታቸው እንደ ዜጋ የእስልምና እምነት ተከታዮችንም ታዳሚ የደርጋቸዋልና። ከዚህም ባለፈ የእስልምና እምነት አባላት የሆኑ ሴቶች – በፆታቸው፤ ወጣቶች – በዕድሚያቸው፤ የሙያ ሰዎች – በሙያቸው፤ የሥነ- ጥበብ ሰዎች – በጸጋቸው፤ የከተማ ነዋሪዎች በከተማ – የገጠር ነዋሪዎች በገጠር ነዋሪዎች ተደራጅተው እንደ ማንኛውም ዜጋ የቡኩላቸውን ድርሻ ይወጣሉ። ይህ ቀጣይ ነው። ከዚህም ባለፈ በተለምዶ በሚታወቁት በወበራ በሥራ ህብረት ወይንም በደቦ፤ በእድር፤ በቁቤ መሰሉን ተግባር በማህበራዊ ኑሯቸው ይከውናሉ። ነገም ቢሆን በማናቸውም የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊ የተሳትፎ ጎራዎች ሁሉ እኩል የመሳተፍ መብትም ግዴታም ይኖርባቸዋል። ይህን ኃላፊነት በብቃት የመወጣት አቅማቸው ሆነ ሥልጡኑ ሥነ ምግባራቸው  በአደባባይ ታይቷል -ምስክር ነው። ያደርጉታል። ያኮራሉና።

መጠነ ሰፊውን የነፃነት ጥያቄ የእኔነት አቅም እንስጠው። በቅንነት ወደ ውስጥ እንዬው። በስጋት ቅንጥብጣቢ ጉዳዮች ፍሬያማ ተልዕኮው እንዳይጎዳ እንጠንቀቅለት። ወያኔ ሃርነት ትግራይ መጫሪያ መለማማጃ ማድረጉ ላይበቃ፤ እኛም ጥግ ከነሳናቸው ሁለት ያጣ የሁለት ሀገር ስደተኛ ይሆናሉ። በወያኔ ሃርነት ትግራይ ጥቃት የሚፈጸምበት ተቋም ወገን ትንፋሻችን ሊሆን ይገባል። እናስጠጋው! ጠረኑ እኛን – እኛን ስለሚል። አቅምም ነው በቅጡ መያዝም ማስተዳደርም ከቻልን።

ኢትዮጵውያን እጅግ ታላቅ ግዙፍ የወል ኪዳናዊ አምክንዮ አለን። „ሰው የመሆን፣ ኢትዮጵያዊነታችን ከጎጣዊ የበታችነት ወረራ የማስመለስ ፣ ነፃነትን – የመናፈቅ፣ ባለሀገር የመሆን፣ ዬወጥ ሰንድቅዓላማችን ብሄራዊ ክብር የማስመለስ፤ የጋራ የሆነ የሚያስማማ ብሄራዊ መዝመሩ ባለቤት የመሆን፤ በህዝብ በጸደቀ ህገ መንግሥት ድምጽ የሚመራት የእኩልነት የተስፋ ሀገር የማግኘት፤ ተናፋቂዋን ሀገራችን የርትህ ባዕት የማደረግ፣ የተጣሱ ደንበሮችን ተፈጣሯዊነት የማስጠበቅ፤ ፍቅር ወተታችን ምህረት ማራችን፣ አብሮነት ተክሊላችን የማደረግ ራዕይ የወልዮሽ አቅጣጫችን ነው። ግን እንዲህ ዓይነትን ችግሮች ሲያፋጥጡን በጋራ የመቀበል አቅም፤ መራራውን ዘመን አብሮ የመሆን ውስጣዊ ፈቃድ ከኖረን ብቻ። የማይናወጽ ዘላቂ ፍላጎት ከኖርን ብቻ። በመሰረታዊ የችግሩ ምንጭ መስማማት ከቻልን – ብቻ። ለተጎዳ – ለተገለለ ውስጣችን መገበር እስከፈቀድን ድረስ ብቻ።

እጅግ የማከብራችሁ ወገኖቼ  ቆዳችን የውስጥ አካላችን መሸፈኛ ብቻ ነው። ጸጉራችንም የአንጎላችን መሸፈኛ። የውስጡ ልባችን፣ ኩላሊታችን፣ ደማችን፣ ሳንባችን፣ ትንፋሻችን ጠረኑ ሰውኛና ወጥ ነው። ሰውኛነት ደግሞ ሰብዕነትን ያዳምጣል። „የድምጻችን ይሰማ“ መሪዎች ኢ – ሞራላዊ ግፍ ከውስጣችን እናስገባው። የውስጣችን ማተብ እናድርገው። ከሂደቱ፤ ከተግባሩ፤ ከስልቱ፤ ከሥልጣኔው፤ ከብልህነቱ፤ ከስተዋይነቱም ለመማርም እንፍቀድ። ግምገማችን፣ እድምታችን ሆነ ዕይታችን በወላዊ ፍላጎቱና ግብዕቱ ላይ እንጂ በተነጠላዊ ግለሰባዊ ቅንጣቶች አይሁን እላለሁ – እኔ። …. በምንም ሁኔታ የትም ሀገር ቀርቶ ኢትዮጵያው ውስጥም በግልሰብ ደረጃ ይህ ነገር ቢከሰት ከጽኑው አቋማችን ፈቅ አንበል።

ናይጀሪያ ላይ እኮ የቦኮ ሃራም ቡድን የተወሰነው ክፍል ተቆጣጥሮ እዬጨፈረ ነው ያለው። ነገር ግን የናይጀሪያ ተወላጆች የእስልማና እምነት ተከታዮች የሆኑት በዚህ አልተፈረጁም። የሚደግፉት ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት ቢቻልም ማንኛውም ናይጀሪያዊ የእምነቱ ተከታይን ግን በጎሪጥ አይታይም። …. እንኳንስ አንዲት ጋት መሬት ኢትዮጵያ ውስጥ የሌለው። እንዲያውም ጋት መሬት እንዲኖረው ይህ አሸባሪ ቡድን ወያኔ ይፈልጋል።  ለወያኔ ሃርነት ትግራይ የሚቀርበው እኮ የህዝብ ኃላፊነት አይደለም እእ! ቅዠቱን ማስፈጽም ነው “ የታላቋ ትግራይ ህልመኛነት“ አሽዋ ሞልቶ እህል ያለ፤ ዬሃውዚን ህፃናትን – ነፍሱጥር – እናቶችን፤ አዛውንታትን አስደብድቦ ድጋፍ ያፈሰ አረመኔ እኮ ነው ወያኔ ማለት። ወያኔና አሸባሪነት፤ ወያኔና ስጋትን መፈብርክ መቼ ተፋተው ሲውቁ ነውና። ኢትዮጵያዊ እስልምና እምነት ተከታዮችን ሰላም የነሳቸውና ሰላማቸውን ያሳጣቸው እሱ እራሱ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ነው። የወያኔ ሃርነት ትግራይ አንድ የአልሸባብ ጉድብ ቢደረምስ „የድምጻችን ይሰማ“ አካላዊ ቅስም አይሰበረም። ስለምን? ግንኙነት – ስሌለው።  ይልቁንም እንደ ሰው ዬዓለምን ሰላም የነሳው፣ መኖርን በስጋት ያስዋጠው፤ ሃይማኖታቸውን ተገን አድርጎ ዬትውልድን ተስፋ ጥቁር ለማልበስ በሚተጋው፤ የሃይማኖታቸውን ክብር በማጥቆር በጥርጣሬ በጠቀለለው „የአሸባሪ ቡድን“ ክንፉ ሲሰበር፤ ሲደመሰስ ደስታውና የምሥራቹ  ከእኛ ጋራ ነው የሚሆነው። እምነት ተወዶና ተፈቅዶ የሚቀበሉት የመልካም ነገሮች ሁሉ የነፃነት ፍሬ ነው። ሃይማኖት ሰብዕዊነት የፈጠረ ነው፤ ተፈጥሯዊነትን ያረቀቀ – ያጸደቀ ነው ነው እንጂ፤ የሰው እርድ ናፋቂ አይደለምና።

ክወና „ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም“ ይላሉ አቨው ቀደምቶች። ገና ዓለምን በሽብርተኛ ተግባሩ እዬናጠው ያለው ISIS  ዬእስልማና እምነት ጽንፈኝትን የዓለም የስጋት ምንጭ ነው ተብሎ፤  የእምነት ነፃነታቸውን በግፍና በማንአለብኝነት የተቀሙት የነፃነት ራህብተኛ ወገኖቻችን የጠራ ጥያቄያ ቀጣይ እንቅስቃሴ ላይ እኛ እራሳችን ስጋት ማከል አይገባንም። እነሱም  ከዚህ ጋር ሊያያዝ ይችላል ብለው፤ ወይንም የዚህ ድርጅት ኢትዮጵያዊ አባላት ተገኙ ወደፊትም ሊኖሩ ይችላሉ ብለው “ድምጻችን ይሰማ” አንድ ጋት ወደ ኋላ ከተልዕኮው ሊያፈግፍግ አይገባውም ባይ ነኝ። አይደለም ይሄ የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና ዛሬ “ድምፃችን ይሰማ” ከሚመሩት መሃከል የዚህ ድርጅት አባል አለ ብሎ ዓለም ዓቀፍ የስለላ ድርጅት ቢያረጋግጥ እንኳን “የድምጻችን ይሰማ” የሚልዮኖች ድምጽ ለእምነት ነፃነት ትግል ሊቋረጥ አይገባም። በዬደቂቃው እስር ሳይሆን ያን መራራ ስቃይ የተቀበሉ፤ የተደፈሩም መሪዎችን ማሰብ በአጽህኖት ይገባዋል። ንቅናቄው በህይወቱ እኮ የተከሰቱ በርካታ ፈታኝ ነገሮች አሉ። ጽንፈኛ መንፈሶች ነበሩ “ድምጻችን ይሰማ” ግን ክብር ነስቶ ጥሏቸው ነው የተጓዘው። ለደቂቃም ቀልቡን አልሰጣቸውም። ዞር ብሎም አላያቸውም። ቂጡ እንደ ወለቀ እንሰራ አውልቆ ሲያስቀራቸው ተመልክተናል። ትቢያ ነው ያለበሳቸው። ይህ ጥንካሬው በቀጣዩ ተስፋ ላይ ማዕቀብ እንዳይኖር ያደርገዋል።

እኔ በግሌ ሁልጊዜም ከድምጻችን ይሰማ መንፈስ ጋር መንፈሴ ውል አስሯል። ጥያቄያቸው በአግባቡ መልስ ሊያገኝ ይገባዋል ባይ ነኝ። ስጋትም የለብኝም። ነገም ከነገ ወዲያም ዘለግ አድርጌ በግለሰብ ደረጃ የሚፈጠሩ ግድፈቶች እንደሚኖሩ አስባለሁ፤  ነገር ግን ከ„ድምፃችን ይሰማ“ ተልዕኮ ጋር ግን አይደባለቅብኝም። ግልጽ ጥያቄ ነው ጥያቄው። ለዛውም በአንድ ስብሰባ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባ የነበረ፤ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ግን ያሾለከው ብርቅዬ ዕድል። „ድምጻችን ይሰማ“ ድምጹ ሊደመጥ የሚገባው ብቁና የነፃነት ትግሉ በኸረ ጉልበታችን ነው! የዕምነት ነፃነት የራበው ማስታገሻው ጥያቄው መልስ ሲያገኝ ብቻ ሲሆን „ድምፃችን ይሰማ“ ትግሉን አጠንክሮ በሚያደርገው ጉዞ እኛም በአጋርነት መሰለፍ ይገባናል። በተለይም ጋዜጠኞች፣ የጥበብ ሰዎች፣ የሰብዕዊ መብት ረገጣ የሚጎረበጥው ዜጋ ከጎናቸው ሊቆም ይገባል። ኢትዮጵያዊነትን የሚጠይቀው በኽረ ጥያቄ የመመለስ አቅም „ሰው“ መሆንን ብቻ ነው። ቅመሙ የተሠራው ከእኔም ከእርሰዎ ነውና – ኢትዮጵያዊነት!

ለነበረን ውብ ጊዜ አመስግኜ መሸቢያ ህልም ተመኝቼ ልሰናበት። ደህና ሁኑልኝ – የኔዎቹ።

ዓራት ዓይናማው መንገዳችን ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

 

 

 

The post ጋዜጠኝነት የማሰብ ጥበብ ልቅና ነው! – ሥርጉተ – ሥላሴ appeared first on Zehabesha Amharic.

ታሪክ ይፋረደናል! –አንዱዓለም ተፈራ –የእስከመቼ አዘጋጅ

$
0
0

ቅዳሜ፤ መጋቢት ፳፮ ቀን ፳፻፯ ዓመተ ምህረት  – 04/04/2015

እንደ እውነቱ ከሆነ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ገዥ ቡድን በእብሪት ተወጥሮ ሀገራችንን ሲጫወትባት፤ “እኛ የኔ ድርጅት! የለም የኔ ድርጅት!” “እኔ ልምራ እናንተ ተከተሉኝ! የለም እኔ ልምራ እናንተ ተከተሉኝ!” “እኔ እበልጣለሁ! የለም እኔ እበልጣለሁ!” እየተባባልን፤ በሌለ ሥልጣን ሽሚያ ልባችን ተወጥሮ፤ ዛሬ ትናንት፤ ነገ ደግሞ ዛሬ እየሆነ ዓመታትን አስቆጠርን። ለምን? የሀገር ጉዳይ እያንዳንዳችንን የሀገሯ ተወላጆች እኩል አይሸነቅጠንም? ምን እንስኪሆን ድረስ ነው የምንጠብቀው? በየድረገጹ የማነበው፣ በየፓልቶኩ ክፍል የማዳምጠው፣ በየሬዲዮኖች የሚተላለፈው፤ በአንድነት እስካልተነሳን ድረስ፤ ትግሉ አይሳካም! የነገውም ሂደት አያስተማምንም! ነው። ለምን በዚህ አውቶቡስ ሁላችን አንሳፈርም? ኧረ ተው! ታሪክ ይፋረደናል!

አሜሪካ ፈልጌውና ጓጉቼለት የመጣሁበት ሀገር አይደለም። የዴሞክራሲ ሥርዓቱ ናፍቆኝም አይደለም የመጣሁት። የተሰማራሁበት ትግል ሂደት ተሰናክሎ፣ ቀኑ ጨልሞብኝ፣ በሰደት ከነበርኩበት የኑሮ ዝግመት ማምለጫ ስለሆነልኝ ነበር። መጥቼ ደግሞ በአድናቆት ተውጬ ማንነቴን ረስቼ አልቧረቅሁበትም። በርግጥ ያገኘሁትን ዕድል በመጠቀም ኑሮዬን ገፍቻለሁ። ይኼው ከመጣሁ ሰላሳ ዓመታት አልፈዉኛል። የአሜሪካን የዴሞክራሲ ሥርዓት አካሄድ ስገነዘብ፤ ያላቸውን ድክመት ደግሞ በዚያው ጎን ለጎን አጢኛለሁ። ለሀገሬ ከማደርገው መሯሯጥ ጋር፤ በአሜሪካ ሀገር ያለሁበትን ሀገር የፖለቲካ ሀቅ ለማስተካከል፤ እንዲህ መሆን ሲገባው ለምን አልሆነም? እያልኩ ከማማረር አልቦዘንኩም። አሜሪካኖች የራሳቸውን የዴሞክራሲ አካሄድ “ፍጹም ወደ መሆን እያዘገምን ነው።” ብለው ነው የሚያምኑት። “ፍጹም ነው!” አይሉም። በምችለውና ባጋጠመኝ መንገድ ሁሉ፤ ይኼን ፍጹም ወደመሆን የሚጓዘውን ሂደታቸውን፤ በንቃት በመሳተፍ እየረዳሁ ነው።

አሁን በሀገራችን የኑሮ ሀቅ፤ የወሃ ጥማት፣ የምግብ ማጣት፣ በሰላም የገበያ አገልግሎት፣ የመንገድ አለመሠራት፣ የትምህርትና ሕክምና አለመስፋፋት፣ የመናገርና የመጻፍ፣ የመሰባሰብና ተቃውሞን የመግለጽ፣ የአድልዕና ሙስና መንገሥ፤ መሠረታዊ የኅብረተሰቡ ጥያቄዎች፤ የፖለቲካውን መድረክ ማዕከላዊ ቦታ አልያዙም። ለዚህ ተጠያቂ የሆነውን መንግሥት በመወንጀል ባንድነት የመነሳት ግዴታችንን በውል አልጨበጥነውም። በርግጥ ከአሜሪካ ጋር የኛን ሀገርና የኛን ሁኔታ እያወዳደርኩ አይደለም። አዎ እንደነሱ በሀብት የበለጸግን አይደለንም። ግን ይኼ ላለንበት ሁኔታ ወሳኝነት የለውም።

የሀብት ጉዳይ ከተነሳ፤ በሀብት ያልበለጸግን መሆናችን አዲስ አይደለም። ከሕዝቡ ጥቅምና ከሀገሪቱ ዕድገት ይልቅ የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም ቅድሚያ የሠጡ ገዥዎች በነበሩበት ዘመን፤ አጠቃላይ የሀገሪቱን እውነታ ፈትሸው፤ ለረጅሙ የወደፊት ብልጽግና በማቀድ እርምጃ ስላልወሰዱ፤ ድኅነቱ አብሮን ኖሯል። እዚህ ላይ አንዳንዶቹ ያደረጉትን የልብ አስተዋፅዖ በምንም መንገድ ልስት አልችልም። ከነዚህ መካከል ባገኘሁት ዕድል ሁሉ፤ መጽሐፍትን በማገላበጥ ለማወቅ ጥረት ከማደርጋቸው መሪዎች መካከል፤ አፄ ዘርዓ ያዕቆብንና አፄ ቴዎድሮስን እጠቅሳለሁ። በአፄ ቴዎድሮስ ዘመን ምን ነበር? ያሁኑስ ዘመን ከዚያ ዘመን በምን ይለያል?

ከአፄ ቴዎድሮስ ዘመን የአሁኑ ዘመን የሚለየው፤ ያኔ ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያ፤ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ትልቅ ክብር የነበራቸው ሲሆን፤ አፈሩ እንኳ ሳይቀር የተከበረበት ዘመን ነበር። አፄ ቴዎድሮስ፤ ከሕዝቡ በመጠቀ ደረጃ፤ ከራሳቸው የወቅቱ ክብር ይልቅ፤ የሀገራቸው እድገትና በአካባቢያቸው የተኮለኮሉት የውጭ ጠላቶች እንቅስቃሴ፤ የዕለት ተዕለት ጭንቀታቸው ነበር። የተበታተነች ኢትዮጵያን ለመመለስና የቀድሞ ቦታዋን ለማስያዝ የሕይወታቸው ዋና ማዕከላዊ ትርጉም አድርገው ጣሩ። ለራሳቸው የስም ማስጠሪያ ግንብ ወይንም ቤተክርስትያን ከማሠራት ይልቅ፤ ለሀገራቸው መጠበቂያ የጦር መሣሪያ እንዲያበጁላቸው ነበር የውጭ ሀገር ሰዎችን የጠየቋቸው። ምንም እንኳ አሁን ምሁር ነን ባዮች፤ የአፄ ቴዎድሮስ ጠላቶች በውጭም ሆነ በውስጥ የነበሩት የጻፉትንና ያሉትን ተሸክመው ቢይጥላሏቸውም፤ እኒህ መሪ በተወለዱበት ዘመንና በቦታው የነበራቸውን የፖለቲካ ድርሻ አጢነው ቢመረምሩ፤ ከማንም መሪ የበለጠ ሊያደንቋቸው በተገባ ነበር።

የበዕደ ማርያም መምህሬ ዶክተር ገብሩ አስራት ለቀረበላቸው ጥያቄ የሠጡት መልስ እጅግ በጣም አርክቶኛል። ከነበሩት መሪዎች ሁሉ አንደኛ አድርገው የሚያደንቁትን ቃለ መጠይቅ አቅራቢዋ እንድትነግራቸው ስትጠይቃቸው፤ ያለምንም ማመናታት “ፄ ቴዎድሮስ ናቸው!” በማለት በኩራት አስቀምጠውላታል። ልክ ድሮ ሲያስተምሩኝ እንዳደነቅኋቸው ሁሉ፤ አሁንም መምሬ ሆነው አገኘኋቸው። ከመሬት ተነስተው፤ ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት ሀገራዊ ሕልውና፤ የመሠረቱን ደንጋይ ያስቀመጡ አፄ ቴዎድሮስ ናቸው። ከግለሰብ ማንነታቸው ይልቅ፤ የሀገራቸው መሪነታቸው ነበር ልባቸውን የሞላው። ያኔ በሕዝቡም መካከል፤ ከግለሰብ ምንነታችን ይልቅ የስብስብ ማንነታችን ማዕከላዊ ቦታውን የያዘ ነበር። ዛሬ በኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያዊነት አፈር የተንከባለለበት፤ ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ኢትዮጵያዊ አለመሆን የተወደደበት፣ ከኢትዮጵያዊያን ስም ይልቅ የውጪ ሀገር ስሞች የተመረጡበት፣ ከራሳችን ቋንቋ ይልቅ የውጪ ቋንቋ፣ ከራሳችን እምነት ይልቅ የውጪ እምነት፣ ከራሳችን ምግብ ይልቅ የውጪ፤ ባጠቃላይም ከራሳችን ማንነት ይልቅ የውጪውን መቅዳትና መስሎ መገኘት የጎላበት ክስተት፤ ሀቅ ሆኖ ይታያል። ለምን? ዋናውን ማዕከላዊ ቦታ ይዞ በተጠያቂነት የቆመው ያለው ገዥ ቡድን ነው። ዋና ሥራዬ ብሎ የያዘው፤ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ማጥፋት ነው። ይኼንንም በትውልድ ማንነት ተክቶታል። እናም ከራሱ የገማን አሣ . . . እንደሚባለው ቆርጦ መጣል ያለበት ገዥው ክፍል ነው።

አሁንም ያኔም ኢትዮጵያዊነት፤ ኢትዮጵያዊነት ነው። አሁን ግንዛቤያችን ፈሩን ለቋል። የብሔር ብሔረሰብ ጥያቄ የፖለቲካውን ማኅደር አጥለቅልቆታል። ምኑም ሆነ ምኑ የሀገራችን ሀቅ፤ ከዚህና ከዚህ ብቻ እንዲታይ ተደርጓል። ይህ ደግሞ በገዥው ክፍል ብቻ ሳይሆን በታጋዩም ወገን ያለ እውነታ ነው። በዚህ ተለጉመን፤ መሠረታዊ የመኖርና ያለመኖር የሕልውና አምዶች፤ ቦታ ተነፍገዋል። የፍትኅ መጓደል፣ የትምህርት ጥራትና ዕድገት ወደ ታች ማሽቆልቆል፣ የሕክምና አለመሟላት፣ የምግብ እጥረትና ረሃብን የመቋቋም ዕቅዶች አለመኖር፣ የሴቶችን እኩልነት አለመቀበልና ተሳትፏቸውን አለማሳደግ፣ አድልዕና ሙስና፤ እነዚህ መሠረታዊ የሕልውና ጥያቄ ናቸው። መስመሩ የተዘጋበት የውሃ ፈሰስ፤ ዙሪያውን ይዳስሳል። የተገደበበትን መዝጊያ መጋፋቱን፤ በጎን መፋሰሻ ከመፈለግ ጋር በእኩል ይዳስሳል። ተገድቤያለሁ ብሎ ተስፋ በመቁረጥ አይረጋም። ከግድቡ ጋር ብቻም አይታገልም። ዙሪያውን በሙሉ ነው ጥረት የሚያደርገው። በግድቡ አናት፣ በግድቡ ሥር፣ ከታቆረበት ዙሪያ ይውዘገዘጋል። የታፈነ በመሆኑ ቦርቅቆ ለመውጣት ይፍጨረጨራል።

ወገኖቻችን በየበረሃው መንገላታታቸው፣ እህቶቻችን በአረብ ሀገሮች መጎሳቆላቸው፣ በገዛ ሀገራቸው ወገኖቻችን መፈናቀላቸው፣ በገዛ ሀገራቸው ወንድምና እህቶቻችን በረሃብ ተጠምደው ለማኝና ሀገሪቱ በሞላ የውጭ ሀገር ምጽዋተኛ መሆናቸው፤ አእምሯችንን በማስጨነቅ የፖለቲካ ምኅዳሩን ሊያናጉት ይገባል። በርግጥ በአሁኑ ሰዓት የፖለቲካ ውይይቱ ተጧጡፏል። ይህ በምን ዓይነት ውጥረት ላይ መሆናችንን አመልካች ነው። ነገር ግን መፍትሔ አፈላለጉ ላይ ለየብቻ እየሮጥን ነው። ለየብቻ ሮጦ የግብ መሰመሩ ላይ ለየብቻ ነው የሚደረሰው። ታዲያ ምን ዋጋ አለው? ግቡ የማንም ግለሰብ ወይንም ቡድን የግል መኖሪያ አይደለም። የሁላችንም ነው። ባንድ ላይ መሯሯጥ አለብን። የተጎተቱ ካሉ፤ አብረን መሳብና መሳሳብ እንጂ፤ እኔ ቀድሜ ሄጄ እሸለማለሁ ወይንም ሌሎችን እጎትታለሁ የሚባልበት አይደለም። አብረን ስንነሳ፤ ቀዳሚ ሆነው የቆሙት ሲመሩ፤ የተጎተቱት ደግሞ ሲከተሉ፤ ባንድነት ከግባችን እንደርሳለን። ታሪክ ደግሞ ከኛ ጋር አብሮ ይኖራል። ተወቃሽ አያደርገንም። ከታሪክ ተወቃሽነት መዳን አለብን። በሕይወት እስካለን ድረስ፤ ሆዳችን መሙላቱን ሳይሆን፤ በሕይወት የኖርንበትን ወቅት ትርጉም መሥጠቱ ላይ ማተኮር አለብን። ቆመን እንቆጠር። አብረን እንሰለፍ።

eske.meche@yahoo.com

eskemeche

 

 

 

The post ታሪክ ይፋረደናል! – አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live