Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

  **ድንቄም ምርጫ** –ነብሮ

$
0
0

ፍትሕ በተረገጠበትና የዴሞክራሲታዊ ሥርዓት በኃይል በታፈነበት አገር ሕዝብ መሪውን መምረጥ አይችልም።

              EPRDF Election1የምርጫ ጉዳይ ሲነሳ ወደ ኋላ ሄደን የዘመነ ኃይለሥላሴን፤የደርግን የምርጫ ሂደቶች ብናስብ ከዚህ በሰለጠነው ዓለም ከሚካሄደው ምርጫ ጋር በምንም ሁኔታ ሊመሳሰል እንደማይችል ሁላችንም ግልጽ የምንሆን ይመስለኛል።አድሎአዊና ሕዝብን ያላሳተፈ የገዥው መደብ የሚፈልጋቸውን እጩዎች መልምሎ በማቅረብ ሕዝቡን አስገድዶ እንዲመርጣቸው ማድረግ አይነተኛ ባሕሪው መሆኑን መጠራጠር አይኖርብንም።

የባሰ አለ እንዲሉ ከአንድ መንደር የተሰባሰቡና በዘረኝነት በሽታ የተመረዙት (ጎሰኞች) የአሁኖቹ ገዥዎቻችን ከ1997 ምርጫ በፊት ከምርጫው በፊትና በምርጫ ወቅት ሲፈጸም የነበረውን ሤራ በሚገባ የማውቀው ሲሆን የተቃዋሚ ኃይሎች(ድርጅቶች)ውስብስቡን የካድሬ መሰናክል አልፈው በፓርላማው ውስጥ ጥቂት አባሎቻቸውን በፓርላማ ውስጥ እንዲገቡ ያደርጉ ነበር።በፓርላማው ውስጥ ሃሳባቸውን የመግለጽና የማራመድ እድላቸው የጠበበ ቢሆንም የፓርላማውን ውሳኔ የሚነቅፍ የተቃውሞ ድምጽና የተአቅቦ ድምጽ ማስቆጠር ችለው ነበር።ከ1997 ምርጫ በኋላ ግን ዘረኝነት መራሹ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ(ህወሃት)ከኢትዮጵያ ሕዝብ ተነጥሎ እንደቆመ ተንሳፎ የሚገኝ መሆኑን ሕዝብ በምርጫ ካርዱ ፍርዱን ሲሰጥ የበረገገው ገዥ ቡድን ረጅም እጁን የምርጫ ኮሮጆ ዘረፋ ውስጥ አስገባ ያልተመረጠውን ተመርጫለሁ አለ።ሰርቀሃል ድምጻችን መልስ ሲባል ደግሞ ግድያ፤እስራት፤ስብሰባ መከልከል፤ሰላማዊ ሰልፍ የማይደረግ መሆኑን አወጀ በግብርም ውሎ አየነው።ከዚያ በኋላ የዚህን ትውልድ አምክን ዘረኛ አገዛዝ እድሜ ለማስረዘም የደህንነት፤የመከላከያ፤የፖሊስና የልዩ ፖሊስ የክልል ፈጥኖ ደራሽ፤የካድሬው መዋቅር ትኩረት ተሰጥቶ እንዲጠናከር ተደረገ።አፈናው ግድያው ተስፋፍቶ ኢትዮጵያውያን በየጎዳናው ወድቀው የሚገኙበት ሁኔታ ተፈጠረ።

woyaneይህ የምታዩት የህወሃት መለያ ሲሆን ከብጫው ላይ የተቀመጠው ዓርማ የጀርመን ናዚ ልዩ ምልክት የነበረ ሲሆን ዛሬ ኢትዮጵያውያን ህወሃትን ሲያነሱ የጀርመን ናዚን የጀርመን ናዚን ሲያነሱ ህወሃትን የሚያስታውሱበት ምክንያት ህወሃትና የጀርመን ናዚ በቆዳ ቀለም ቢለያዩም በተግባር አንድ ናቸው ብለው ስለሚያምኑ ነው። እኔ የዚህ ጹሑፍ አቅራቢም ህወሃትን ከጣሊያንና ጀርመን ፋሽስቶች ለይቸ አይደለም የምመለከተው።ለዚህ ጹሑፌ መነሻ የሆነኝ የፊታችን ግንቦት ለሚካሄደው ብሔራዊ ምርጫ የህወሃትን ሥርአት በሰላማዊ መንገድ ታግለን በምርጫ አቸንፈን ሥልጣን እንጨብጣለን ብለው በተነሱ ኃይሎች ላይ የህወሃት የምርጫ ቦርድ የፈጸመውን አሳፋሪ ድርጊት ተመልክቸ ሲሆን በምንም አይነት መስፈርያ ይሁን የተቃዋሚ ኃይሎች ለምርጫ ውድድር የሚያቀርቡትን እጩ ራሳቸው ወስነው ያቀርባሉ እንጅ የምርጫ ቦርድ ይህ ይመረጥ ይኸኛው አይመረጥ ብሎ የመወሰን ሞራሉም ሆነ ብቃት የለውም።ለዚያውም በእጣ! የምርጫ ኮሮጆ ገልብጦ ያልተመረጠውንና ሕዝብ አንቅሮ የተፈውን ተመርጠሃል ሕዝብ ይሆነኛል ያለውን በምርጫ ያቸነፈውን አልተመረጥክም ብሎ የሚቀጥፍ የአንድ ሥርአት አገልጋይና ተቋም አምኖ ምን አይነት ምርጫ እንደሚካሄድ ከወዲሁ መተንበዩ ነብይ የሚያሰኝ አይደለም።ለሥርአቱ አስጊ የሆኑ የተቃዋሚ ድርጅቶችን አንድነትና መኢአድን በኃይል አፍርሶ የየድርጅችን ንብረት ዘርፎ በሌሎቹ የተቃዋሚ ኃይሎች ጉያም ለመግባት ረጅሙን ዘራፊ እጁን ለማስገባት እያሴረ ያለው ህወሃትና ጉዳይ አስፈጻሚው የምርጫ ቦርድ ሕገ-መንግሥቱን እየናዱ መሆኑን ሊያጤኑ ይገባቸዋል።

ህወሃት መሠረታዊ ችግሩ ድህነት ከሆነ በትግራይ ሕዝብም ይህ ችግር እንደ ዋነኛ ተደርጎ ከተወሰደ ሌሎችስ ብሎ ማሰብ የሚችል ተፈጥሮ በህወሃት ቤት እንዳማይኖር ቢታወቅም በትግራይ ለተፈጠረው የኢኮኖሚ መዳከምም ሆነ የንዋይ ጥማት የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚጠየቅበት አንዳችም ምክንያት ሊኖር አይገባውም የህወሃት መራሹ ቡድን በፈጠራ ውሸት የቆጥ የባጡን በመቀባጠር የሕዝብ እልቂት እንዲፈጠር በማድረግ በውንድብድና የካሄደው ዘረፋ፤ዜጎችን በተለይም ምሁሩንና አምራቹን ኃይል ከሀገር መንቀልና የመራሹ ቡድን እንባ ጠባቂዎችና ቤተሰቦች አገሪቱን ተስፋፍተው እንዲይዙና ሌላው ዜጋ በዘመናዊ ባርነት መቀጠል ወይም በሌሎች ላይ የደረሰው ጽዋ ሞልቶ እንዲፈስበት ማድረጉ የሚያስከትለውን መዘዝ መገንዘብ ባለመቻል የተፈፀመ ስለሆነ የዛሬው እዩኝ እዩኝ ነገ ሸሽጉኝ ሸሽጉኝን እንደሚያስከትል በድፍረት መናገር ይቻላል።

በአንድ ወቅት የህወሃቱ ፊታውራሪ ስብሃት ነጋ ከጋዜጠኛ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ፡) እንዲህ ብሎ ነበር-ጋዜጠኛ አቶ ስብሃት ድሮ የሃብታምና የባለሥልጣን ልጅ ነበር ስኮላር ሽፕና የውጭ ትምህርት እድል ያገኝ የነበረው ዛሬ ደግሞ የእናንተ ልጆች የሚማሩት ወደ ውጭ አገር ሄደው ነው ሲባል(፡ አቶ ስብሃት ታዲያ እነሱ ያደረጉትን እኛ ብናደርገው ነውሩ ከምኑ ላይ ነው ብሎ ነበር በአራት ነጥብ የዘጋው።እንግዲህ ህወሃት እንዲህ ያሉትን ውዳቂዎችንና ፀረ-ሕዝቦችን አቅፎ ነው ኢትዮጵያን በኃይል አንበርክከን እንገዛታለን ካልሆነልን ደግሞ እናፈራርሳታልን የሚሉን።ከዚህ ወዲያ እብደት የለም እንዲህ ያሉት እብዶች የተሰባሰቡበት ህወሃት ነው ዛሬ በትረ ሥልጣኑን ጨብጦ እየገዛ ያለው።

አንዱ በአንዱ ላይ እምነት እንዳያሳድርና በጥርጣሬ እንዲተያይ ጦርነት ውስጥ እንዲገባ፤አንተ የዚህ አንተኛው ደግሞ የዚህኛው ዘር ነህ በማለት በዘር በማናከስ የሕዝብ ሰላም እንዲደፈርስ ያደረገው ህወሃት ነው። ሰሞኑን ደግሞ አንድ አስገራሚ ድርጊት ተፈፀመ ይህኸውም(ጥቂት ህወሃት የመለመላቸው የቅማንት  ተወላጆች ) በአማራ ገዥ መደብ እስከ ዛሬ ተገዝተናል አሁን በቃን ጐንደር የቅማንት አገር ስለሆነ ራሳችን በራሳችን ለማስተዳደር እንድንችል የራስ ገዝ አስተዳደር ይገባናል በሚል ሲንቀሳቀሱ ቆይተው አሁን የነአቶ በረከትና አዲሱ ለገሠን ይሁንታ አግኝተው ያልተጻፈ የታሪክ ድሪቶ አንግበው በደምና በስጋ የተቀላቀላቸው ወገናቸው ጋር ደም የሚያፋሥስ መንገድ መጀመራቸው ቀልጥፈው ተግባራቸው እኩይ ተግባር መሆኑን አውቀው እንዲያቆሙት ለማስገንዘብ ነው ይህን ጹሑፍ ያዘጋጀሁት። በዚህ ተግባር ግንባር ቀደም ሆነው የሚያራምዱትን በአካል ስለማውቃቸውም ጭምር ወንድማዊ ምክሬን ሊሰሙ እንደሚችሉ በማመን ነው። ህወሃትና የአማራውን ህዝብ ጋንጃ እየመታ የሚገኘውን ብ.አ.ዴ.ንን አምኖ ወደዚህ አጣብቂኝ ጉዳይ መግባት በፍጹም ስህተት ነው።የቅማንት ተወላጅ ለህወሃት የምርጫ ፍጆታ መዋል የለበትም፦የህወሃት ሥርዓትና የሥርአቱ አራማጆች መቀበሪያቸውን ቆፍረው ከመቃብር አፋፍ ላይ በሚገኙበት ወቅት መልካም ታሪክን ማጉደፍ አይገባም።ይህ ስርዓት ወዳቂ ነው በሀገር ጥፋትና እጁን በደም የነከረ ሁሉ በሰፈረው እንደሚሰፈርም ግልጽ ነው።ነገ የዛሬዎቹ ዳኞችና እኛ ፊት ለፊት እንገናኛለን፤ ነገ እኛና ይህወሃት ካድሬ እንገናኛለን፤ነገ የምርጫ ቦርድና እኛ እንገናኛለን፤ነገ የፌደራል ፖሊስና እኛ እንገናኛለን፤ነገ እኛና ፖሊስ እንገናኛለን፤ነገ የአጋዚ ሠራዊትና እኛ እንገናኛለን፤ነገ እኛና የክልል ፈጥኖ ደራሽ እንገናኛለን፤ለዘመናዊ ባርነት ወደ ዐረብ አገር የተላኩ እምቦቃቅላ ሴትና ወንድ ወጣቶችን መዝግበናል፤አገር ጥለው እንዲወጡ የተገደዱ ሙራንና ጋዜጠኞችን ዝርዝር ይዘናል፤ወህኒ ቤት ወርደው ሌትና ቀን እንደ እባብ እየተቀጠቀጡ የሚገኙትን ወጣት ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ድርጅት አመራሮችን እናውቃቸዋለን፤በመላ ኢትዮጵያ የመኖርና ሠርቶ የመብላት መብት የተነፈገው ዘሩ በመድሃኒት እንዲመክን የተደረገውን የአማራ ነገድ ሕዝብ ጉዳይ በሚገባ ተመዝግቦ እንዲቀመጥ ተደርጓል፤ከወሎና ጎንደር ተነጥቆ ወደ ትግራይ የሄደውን መሬት በሚገባ እናውቀዋለን ይህን ሁሉ ህወሃትና መንገድ መሪዎቹ የሚከፍሉት እዳ እንደሆነ ሊያውቁት ይገባል። በዚህ አጋጣሚ አቶ በየነ አስማረና አበበ ንጋቱን አመስግኘ ማለፍ እወዳለሁ።« በወደቀ ግንድ ምሳር ይበዛበታል እንዲሉ » ጣሊያን ጎንደር ሲገባ የተጠቀመበትን ፕሮፓጋንዳ ያነገበው የህወሃት ቡድን ኢትዮጵያን ለመበታተን ሲል የሚያራምደውን የጎሳ ፖለቲካ የተጋቱ አውቆ አጥፊ የቅማንት ተወላጆችንና ሌሎች የተለያዩ በአማራው ነገድ ህዝብ ክልል የሚኖሩ ጎሳዎችን በማነሳሳት በጎሳ መራሹ ቡድን ጣቱን የቀሰረውን ሕዝብ አስተሳሰብና አመለካከት አቅጣጫውን እንዲስት ለማድረግ የሚጠቀምበትን ሕዝብን በሕዝብ የማናከስ ሤራ እያራመዱ ይገኛሉ።

24 ዓመት በመድፈን ላይ የሚገኘው የህወሃት አገዛዝ በሚያካሂዳቸው ምርጫዎች አንድም ቀን ፍትሃዊነት ያልታየበትና የተጭበረበረ መሆኑ እንዳለ ሆኖ በምርጫ ወቅት ለሕዝብ የሚገባቸውን ቃሎች ከመካዱ አልፎ በተቃራኒው እንደሚተገብራቸው ይታወቃል።የዘንድሮ ደግሞ በጣም የለየለትና አውሬነቱን በግልጽ የሳየበት ሁኔታ ላይ ደርሷል ሁላችንም የምግባባበት አንድ መሠረታዊ ጉዳይ ህወሃት ለአፍታም ቢሆን ሥልጣን ከእጁ ካፈተለከ የሚደርስበትንና የሚከፍለውን ዋጋ ስለሚያውቅ በሰላማዊ መንገድ ሥልጣን ያስረክባል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ዋናው አነጋጋሪ ጉዳይ ሕዝብ ካለፈው ተመክሮ የማያገኘውና አልመርጥም የማይልበት ምክንያት ምንድን ነው የሚለው ይሆናል።የሚያሰድድን፤የሚገድልን፤አስሮ የሚያሰቃይን፤ዘር በማጥፋት ላይ የተሰማራን ነብሰ-ገዳይ ቡድንን መርጦ በሥልጣን ላይ ማስቀመጥ አገርን ከመገደል የከፋ ወንጀል ነው።ስለዚህ ሕዝቡ የዘንድሮውን ምርጫ በእምብይታ ሊያስተናግደው ይገባል።

ነብሮ ነኝ ከሰ/አሜሪካ

The post   **ድንቄም ምርጫ** – ነብሮ appeared first on Zehabesha Amharic.


የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ

$
0
0

በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ፤ አሃዱ አምላክ አሜን!!
ባህረ ሐሰቱን የምንሻገርበትን የእውነት መርከብ ማን ይሰጠናል? ወዳጄ ሆይ፡- አትፍራ! እውነት አባትህ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (ዮሐ. 14÷6)፡፡ እርሱ ‹‹ መንገድም ፣ እውነትም ፣ ሕይወትም ›› ነው፡፡ መንገድ ነው፡- ትሰማራበታለህ፣ እውነት ነው ፡-ትይዘዋለህ፣ ሕይወት ነው፡- ትኖረዋለህ !!!

debre-tsion-kidiste-mariam-church-london
የርዕሰ አድራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ።
በእንግሊዝ ሃገር የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ገንዘብና ጉልበቱን አስተባብሮ በእግዚአብሔር ተራዳዒነት የገዛውን ህንፃ ቤተ ክርስቲያን ለወያኔ ሹማምንት አሳልፈው በመስጠት ሥልጣንና ንዋይን የሚያጋብሱ የመሰላቸው የለንደኑ ዳያብሎስ አባ ግርማ ከበደና ተከታዮቻቸው፤ የቤተ ክርስቲያኑን አባላት መብት የሚነፍግ ተግባር ፈጽመው አባላቱ በቤተ ክርስቲያኗ ንብረት እኩል የመገልገል መብታቸው እንዲከበርላቸው ጉዳያቸውን ወደ ፍርድ ቤት ወስደው በ13/02/2013 በዋለው የእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ችሎት ተፈረደላቸው።

More…

The post የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ appeared first on Zehabesha Amharic.

Hiber Radio: ግብጽ የአባይን ግድብ እንቅስቃሴ የሚቃኝ የስለላ ሳተላይት መግጠሟ ታወቀ.. ከ10 ሺ በላይ የቅማንት ማህበረሰብ ከቀያቸው እንዲለቁ ትዕዛዝ ተላለፈ…በካናዳ ለ5 ዓመት የጠፋው ኢትዮጵያዊ አስከሬኑ ከጣራው ስር ተገኘ.. የደብረታቦር ሕዝብ አገዛዙ ስልጣኑን እንዲለቅ በተቃውሞ ሰልፍ ጠየቀ…ኢትዮጵያ ጦሯን ከሶማሊያ ባይዳዎ ግዛት አወጣች…ኢትዮጵያውያን የእግረኛ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በየመን ላሉ ወገኖቻቸው ጠንክረው ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ተጠየቁ…እና ሌሎችም

$
0
0
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ መጋቢት 20 ቀን 2007 ፕሮግራም

< …ዛሬ በደብረ ታቦር ሕዝቡ በተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ወጥቶ ስርኣቱ በቃን ፣ልቀቁን ውረዱ ብሏል…ሕዝቡ ሰልፉን እንዳይቀላቀል መንገድ ዘግተውበታል ። ከፍተና የፖሊስና የደህንነት ሀይል ነበር።..ምርጫው ነጻ ቢኖር ኖሮ ለብአዴን ድምጽ የሚሰጠው አይኖርም …> አቶ ሳሙኤል አበበ በደብረ ታቦር ሰማያዊ ፕርቲን ጨምሮ የዘጠኙ ፓርቲች ትብብር የጠራው ሰልፍ አስተባባሪና የሰማአዊ ዕጩ ተወዳዳሪ ስለሰልፉ ተጠይቆ ከተናገረው የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ )

<…በየመን ያዩ ኢትዮጵያውያን ከወዲሁ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ከዚህ ሳውዲ የተባረሩትም በዚያው ነው የሚመጡት ከአገር ቤትም ወደ የመን የሚሄዱ ይኖራሉ በዚህ የጦርነት ወቅት ግን…>

ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከጂዳ በሳውዲ የሚመራው ጦር በየመን አማጽያን ላይ የከፈተውን የአየር ጥቃት ተከትሎ በኢትዮጵያውያን ላይ ስለጋረጠው ስጋት ካደረግነው ቃለ መጠይቅ(ሙሉውን ያዳምጡት)

<…እዚህ በየመን ያለንበት ሁኔታ እጅግ አስጊ ነው። ስደተኛው በጥሩ መንገድ አይታይም ። የአየር ድብደባውን ተከትሎ የእግረኛ ጦርነት ከተጀመረ ሁኔታዎች አስቸጋሪ ይሆናሉ … አስከፊ ችግር ውስጥ ስንገባ ከመሰለፍ አሁኑኑ አስቀድሞ ሊጮህልን ይገባል…>

ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሀይማኖት በየመን ኢትዮጵያውያን ስላሉበት ሁኔታ ከህብር ተጠይቆ ከሰጠው ምላሽ(ሙሉውን አዳምጡት)

ኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳን በህዳሴው ግድብ ላይ ያደረጉትን ስምምነት መሰረት ያደረገ የግብፅ መገናኛ ብዙሃን እይታ (ልዩ ዘገባ )

ባሻ ይገዙ < ሰይጣን በአገሩ! > (ልዩ ግጥም)

በቬጋስ የፍሪያስ የቀድሞ ታክሲ አሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ ያደረጉበትን ሁለተኛ ዓመት አስመልክቶ ውይይት

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

– ግብፅ የአወዛጋቢውን ህዳሴ ግድብ እንቅስቃሴ የሚቃኝ ዘመናዊ የስለላ ሳተላይት መግጠሟ ታወቀ

– የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎችና የአገዛዙ ወታደሮች ፍጥጫ ውስጥ ገቡ

* ከ10 ሺህ በላይ የቅማንት ነዋሪዎች ከመኖሪያቸው በሁለት ሳምንታት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ መመሪያ ተላለፈባቸው

– ኢትዮጵያ ጦሯን ከሶማሊያ ባይዳዎ ግዛት አወጣች

– የዘጠኙ ፓርቲዎች ትብብር በ15ከተሞች ካቀዱት ሰላማዊ ሰልፍ በጥቂት ከተሞች በከፍተኛ ጫና አካሄዱ

– በደብረ ታቦር በሰልፉ ላይ ህዝቡ አገዛዙ እንዲወርድ ጠየቀ

– ኬኒያ ህገወጥ ያለቻቸውን 65ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በገንዘብ ቀጣች

– በካናዳ ለ5 ዓመት የጠፋው ኢትዮጵያዊ አስከሬኑ ከጣራው ስር ተገኘ

– የየመን የእርስ በእርስ ጦርነት ወደ አካባቢ ጦርነት ማደጉ ስጋት ፈጠረ

– ሱዳን በየመን የተሰማሩ ጄቶቿ ጥቃት እንዳልደረሰባቸው ገለፀች

* ኤርትራ የየመን አማፅያን አላስተናገድኩም አለች

– በየመን የሚገኘው የአገዛዙ ኤምባሲ ዲፕሎማቶቹን ለማስወጣት እየተሯሯጠ ነው

* ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በምዝገባ ስም እየሸነገለ ነው

– ኢትዮጵያውያን የእግረኛ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በየመን ላሉ ወገኖቻቸው ጠንክረው ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ተጠየቁ

– በቬጋስ በፍ/ቤት ታግዶ የነበረው ሁበር በቅርቡ ወደ ገበያው እመለሳለሁ አለ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

The post Hiber Radio: ግብጽ የአባይን ግድብ እንቅስቃሴ የሚቃኝ የስለላ ሳተላይት መግጠሟ ታወቀ.. ከ10 ሺ በላይ የቅማንት ማህበረሰብ ከቀያቸው እንዲለቁ ትዕዛዝ ተላለፈ… በካናዳ ለ5 ዓመት የጠፋው ኢትዮጵያዊ አስከሬኑ ከጣራው ስር ተገኘ.. የደብረታቦር ሕዝብ አገዛዙ ስልጣኑን እንዲለቅ በተቃውሞ ሰልፍ ጠየቀ… ኢትዮጵያ ጦሯን ከሶማሊያ ባይዳዎ ግዛት አወጣች…ኢትዮጵያውያን የእግረኛ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በየመን ላሉ ወገኖቻቸው ጠንክረው ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ተጠየቁ… እና ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.

የምርጫ ክርክር ሶስት- ግብርና እና ገጠር ልማት (ከግርማ ሰይፉ ማሩ)

$
0
0

“በ24 ዓመት አሁንም በአዝማሚያ ላይ ነኝ የሚለው ኢህአዴግ ……”
“የ1997 የምርጫ ክርክር ይደገም ……”
ግርማ ሠይፉ ማሩ
girmaseifu32@yahoo.com; girmaseifu.blogspot.com
ተከራካሪዎች፤
አቶ ተፈራ ደርቤ እና ዶ/ር አብርሃም ተከስተ
አቶ ግርማይ አደራ እና ዐዐዐዐዐ
አቶ ትዕግሰቱ አወሉ እና አቶ ዮሃንስ አሰፋ
አቶ ግዑሽ ገብረሰላሴ እና ትዕግሰቱ ዱባለ
አቶ ጥላሁን እንዳሻው እና ሙላቱ ገመቹ

(ግርማ ሰይፉ)

(ግርማ ሰይፉ)

በመጋቢት 18 እና 19 2007 ለግንቦት ምርጫ የተደረገው “የምረጡኝ ክርክር” የተጀመረው በአቶ ተፈራ ደርበው በተመራው የኢህአዴግ ቡድን በግንባሩ ውስጥ በከባድ ሚዛኑ ህወሃት ተወካዮ ዶክተር አብርሃም ተከሰተ በመታገዝ ነበር የተገኘው፡፡ ተከራካሪዎቹ በኢህአዴግ በተተኪ መስመር የሚገኙ ቢሆኑም እንደ ወትሮ ሁሉ ኢህአዴግ የሚያቀርበው አዲስ ሀሳብ ለሚቀጥለው የስልጣን ዘመን ሊያቀርብ አልቻለም፡፡ እነዚህ የኢህአዴግን ሹሞች ልብ አውልቅ የሆነውን በእውሸት የተሞላውን የቁጥር ጫወታ ይዘው ብቅ ያሉ ሲሆን በዚህ ደረጃ ሊሞግታቸው የሚችል፤ አንድም ተቃዋሚ ነኝ የሚል ለማየት አልቻልንም፡፡ ኢህአዴጎች ከታቃዋሚዎች በላቀ ደረጃ ጎላ ያደረጋቸው የለበሱት ሱፍና የተጫሙት ጫማ ማብቅረቅ ሲሆን ተቃዋሚዎች አሁንም ከጀርባቸው ያስቀመጧቸው አማካሪ ተብዬዎች ምንም ያለመፈየድ ሳይሆን እንቅልፍ ሲያንጎላጃቸው ማየት ኢህአዴግ በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ምን ዓይነት ሰዎችን ወደፊት እያመጣ እና ወደፊትም እንደሚያመጣ አመላካች ነው፡፡ ከተቃዋሚ ጀርባ ለተቀመጡትም ሆነ በፊት መስመር ላሉት ደካማ ተቃዋሚዎች ተጠያቂው ኢህአዴግ እና የዘረጋው ስርዓት መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡
ኢህአደግ ለቀጣይ አምስት ዓምት በስልጣን እንደሚቆይ ቢያውቅም ይህን በትህትና ለገጠሩ ህብረተሰብ ያስተላለፉት ዶክተር አብርሃም ተከሰተ እና ቆጣ ቆጣ ሲሉ የነበሩት አቶ ተፈራ ደርቤ ናቸው፡፡ ለዚህም እንደማስረጃ ያቀረቡልን
· 60 ሺ በላይ የገጠር ልማት ሰራተኞች እና የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች(በተቃዋሚዎች በትክክል ካድሬዎች ተብለው የተፈረጁት)፤
· ድህነትን በ1988 ከነበረበት 48 ከመቶ ወደ 24 ከመቶ ዝቅ ማድረጋቸው፤ (በመቶኛ ቀነሰ ቢባልም በቁጥር ግን በ1988 ከነበረው ጋር ተቀራራቢ ነው፡፡)
· መስኖ እና ሰፈራ በአርብቶ አደሩ አካባቢ ማስፋፋቱ፤
· 2.2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በግል ባለሀብት እየለማ መሆኑ (ይህ መረጃ በቅርቡ እየተነገረ ቢሆንም ኢትዮጵያዊያን በዚህ መስክ የሚያደርጉት ተሳትፎ በግልፅ የሚታይ አይደለም)
· የመሰረተ ትምህርት እና ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት መስፋፋቱ፤ ወዘተ ሲሆን

በዚህ መነሻ አርሶ አደሩ ሀብት እያከባተ በመሆኑ ወደ ማንፋክቸሪንግ ዘርፍ እንሚገባ አሰረድተውናል፡፡ አህአዴጎች በዛሬው ክርክር የቀደሞ ሰርዓት መክስስ ዘዴያቸውን የገቱ ቢሆንም ተቃዋሚዎችን ማጣጣል በተለይ መድረክ ላይ ለመዝመት ተዘጋጅተው እንደመጡ አቀራረባቸው ያሳብቅ ነበር፡፡ አቶ ተፈራ ደርቤ በተደጋጋሚ ተቃዋሚዎች ከላይ የተዘረዘሩትን የኢህአዴግ ሰኬት በመቃወም መሬት ይሸጥ ይለወጥ በማለት አርሶ አደሩን በማፈናቀል ለጥቂት ባለሀብቶ የቆሙ መሆናቸውን ያረጋገጡበት ክርክር ነበር፡፡ አቶ ተፈራ ደርበው ከመድረክ ጋር ተከራከሩ ተብለው መመሪያ እንደተሰጣቸው በሚያሳብቅ ሁኔታ መድረክን መሬት ይሽጥ? ነው የምትሉት ወይስ ሌላ አማራጭ አላችሁ? እያሉ በተደጋጋሚ አንስተውታል፡፡ አቶ ጥላሁን እንሻውም እንዳሻቸው መልሰውላቸዋል፡፡

ከኢህአዴጉ ተወካይ ዶክተር አብርሃም ተከስተ ያነሱት ሀሳብ ግን ወደ 1997 ክርክር መልሶኛል፡፡ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ አቶ አዲሱ “ግብርና ሴክተር የእድገት ፍንጭ” እያሳየ ነው ሲሉ ለሰጡት አሰተያየት “ከ14 ዓመት በኋላ ፍንጭ እየታየ ነው አትበሉን” በሚል የሰጣቸውን ምላሽ አሰታውሶኛል፤ በ2007 ክርክር ዶክተር አብርሃም ተከስተ የግብርና ፖሊሲው “የስራ አጥ ቁጥርን የመቀነስ አዝማሚያ” እያሳየ ነው ብለውን ከ24 ዓመት በኋላ አዝማሚያ ላይ እንደሆኑ ነግረውናል፡፡ በእኔ እምነት የግብርና ዘርፉ ይህን ሁሉ ጉልበት ይዞ መቀመጥ አይጠበቅበትም፡፡ በግብርና ዘርፍ ያለው ትርፍ ጉልበት ሊቀበል የሚችል ግብርና ያልሆነ ዘርፍ መፍጠር ያልቻለው ኢህአዴግ ሊከሰስበት የሚገባው ዋና ነጥብ ነው፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ 24 ዓመት ያልበቃው ኢህአዴግ ምን ሲሰራ ነበር ተብሎ አይጠየቅም፡፡ ብዙዎቹ ሚኒሰትሮች ከሁለተኛ ደረጃ፣ የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም ድህረ ምረቃ ትምህርት ሲከታተሉ እንደነበር ይታወቃል፡፡ አንድ አንዶች ለሶሰተኛ ዲግሪ የሚሆን ጊዜ ነበራቸው፡፡ አበበ ገላው እየገዙ ነው የሚለውን ወደጎን እንተወው ከተባለ ማለት ነው፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ያሉትም ማሰታወስ ያሰፈልጋል “እነዚህ ሰዎች ሀገር እየመሩ/እያሰተዳደሩ ሶሰተኛ ዲግሪ መያዛቸው ወይ ሰራቸውን እየሰሩ አይለም፣ ካልሆነም ትምህርቱ ቀሎዋል ማለት ነው” አሰተያየት ሰምቻለሁ፡፡ ቃል በቃል ባይሆንም፡፡

ለማነኛውም ኢህአዴግ መነሻ ሀሳቡንም፣ ማብራሪያውንም ማጠቃለያውን “በሚመጥነው” ደረጃ አቅርቦ ክርክሩን አጠናቆዋል፡፡ ከዚህ የጠነከረ ክርክር ቢያቀርብ ማን ከቁብ ሊቆጥርለት ነው፡፡ በእኔ ግምት ዶክተር አብርሃም ተከስተ በዚህ ክርክር ላይ ባልመጣው ሳይል የሚቀር አይመስለኝም፡፡ ጠንከር ያለ ቁጥርና ቁጥር ነክ ጥያቄዎች በተለይ ደግሞ የመዋቅራዊ ሽግግር ጥያቄዎች እና ማክሮ ኤኮኖሚክ ነክ የሆኑ ለምሳሌ በውጭ ምንዛሪ ግኝት፣ በግብርና ሴክተር የመሪነት ሚና ላይ ዝርዝር ሀሳቦች ለመመለስ በክርክሩ ላይ የተገኘ ይመስል ነበር፡፡ ዶክተር አብርሃም ተከስተ የክርክር ጊዜውን ለመግደል ዘና ብሎ ሲመልስ ላስተዋለ በእግር ኳስ ጫወታ እየመራ ያለ ቡድን ጎል ጠባቂ ጊዜ ሲያባክን የሚያሳየውን ባህሪ የሚያሰታውስ ነው፡፡

ለማነኛውም አቶ ተፈራ ደርቤ ያቀረቡት የመሬት ጉዳይ በህገ መንግሰት ውስጥ መግባቱ እና አሁን የሚከተሉት የመሬት ፖሊሲ መሰረቱ ኤኮኖሚያዊ ነው ብለው ቢዋሹም፣ ኢህአዴግ መሰረቴ ነው የሚለውን አርሶ አደር ለመቆጣጠር እንዲችል የተቀመጠ ፖለቲካዊ መሰረትነቱ መቼም ክዶት የማያወቅው ታውቆ ያደረ ጉዳይ መሆኑን የሚያስታውሳቸው አላገኙም፡፡ የዶክተር አብርሃም ተከሰተ ትህትና የተሞላበት የምረጡን ጥያቄም አማላይ ነበር፡፡

ኢህአዴግ በአቶ ግርማይ አደራ በሚባሉ ሰው የተወከለ ሲሆን በረዳትነት የተገኘውን ለማወቅ እድል አላገኘንም፡፡ አቶ ግርማይ ጊዜው አይበቃም ቢሉም ሲጀምሩ ቀስ ብለው ተዝናንተው ሲጨርሱም ሁለት ደቂቃ አሰቀርተው ሲያጣቃልሉም ለጊዜ አጠቃቀም ምንም ግድ ሳይሰጣቸው ነው፡፡ እውነቱን ለመናገር ከእኝ ግለሰብ ልይዝላቸው የቻልኩት ነጥብ መሬት ለኢትዮጵያን የዜግነት፣ የሀገር ባለቤትነት፣ የነፃነት መገለጫ ነው የሚሉት እና የማዳበሪያ ዕዳ ለመክፈል አዲስ አባባ ለልመና የሚመጡ አርሶ አደሮች መኖራቸውን ያስታወሱን መሆኑን ነው፡፡ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ መሪ በፅሁፍ የያዘውን በቅጡ የማያነብ፣ በቂ አይደለም ብሎ ካለው ጊዜ ውስጥ በመግቢያና በመውጫ ሠዓት ማባከን ምን ግምት እንደሚያሰጥ ተከራካሪው ያሰቡበት አይመስለም፡፡ ለማነኛውም ኢህአዴግ አቻውን አግኝቶዋል ማለት ይቻላል፡፡ በቃ ኢህአዴግ የሚመጥነው እንደ አቶ ግርማይ አደራ ያሉ ፖለቲከኞች ናቸው፡፡ ምርጫቸው ነው እና ማክበር አለብን፡፡ አቶ ግርማይ አርማው ጋሻና ጦር የሆነ እድር ቢኖራቸው ችግር የለኝም ነገር ግን እርሳቸውም ሆነ የእርሳቸው ፓርቲ በሚሰጡት አመራር በማጠቃለያ እንደነገሩን በምግብ እህል ራሷን የቻለች ኢትዮጵጰያ ሊዚያውም ተርፎዋት ኤክስፖርት የምታደርግ ሀገር አይሰሩልንም፡፡ ለኢትዮጵያዊ የቀረበለት ከዝንጀሮ ቆንጆ መረጣ ነው፡፡

“ድንኩ አንድነት” እንደ ተለመደው በትዕግስቱ አወሉ የተወከለ ሲሆን በረዳትነት የተመደበለት ደግሞ አቶ ዮሐንስ አሰፋ ነው፡፡ አቶ ትዕግሰቱ በቴሌቪዥን በክርክር የሰንብት ክርክሩን አድርጎ ሄዶዋል፡፡ እኛም ተገላገልን፡፡ ባለፈው ድንኩ አንድነት የአንድነት ፓርቲ ውስጥ አባል ያልሆነ ሰው ለክርክር ቀረበ ብለን ትንሽ ተንጫጭተን ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ በረዳትነት የመጣው አቶ ዮሃንስ አሰፋው ለጫጫታ መነሻ የሚሆን አወዛጋቢ ግለሰብ ነው፡፡ ዮሐንስ በወረዳ 24 ውስጥ፣ ገዢውን ፓርቲ ወክሎ ወረዳውን ሲያምሰ የነበረ ነው፡፡ የሴራው ማጠንጠኛም አስራት አብርሃም ነበር፡፡ ፓርቲው አምኖበት በከፍተኛ ሃላፊነት ላይ ያስቀመጠውን ሰው የወያኔ ተላላኪ ነው እያለ ውንጀላ ሲያደርግ፣ በአስራት አብርሃም ደረጃ አሰተዋጽኦ የሚያደርግ ከየትም ቢመጣ ችግር እንደሌለብን አሰርደቼው ነበር፡፡ ለነገሩ ፓርቲውን ለመፍረስ ከሚያሴሩት ጋር በግልፅ እንደሚሰራ እያወቅን በዝምታ ያለፍነው የውስጥ አርበኛ ነው፡፡ አሁን ደግሞ በአሰራት አብርሃም ቦታ ወረዳ 24 ዕጩ ሆኖ የቀረበ ሲሆን ለትዕግሱቱ አወሉ ቡድን በቂ አማካሪ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ከዚህ የተሻለ ከትዕግሱቱ ጎን ማግኘት አጉል ነው የሚሆነው፡፡ ትዕግስቱም የልኩን አማካሪ ኢህአዴግም የሚመጥነውን ተቃዋሚ አግኝተዋል፡፡

ትዕግሰቱ የአንድነትን የፖሊሲ አማራጭም ሆነ ዝርዝር የኢህአዴግን የአፈፃፀም ክፍተት በተሟላ ይዞ ሊቀርብ እንደማይችል ማንም ያውቃል፡፡ በድፍረት ግን “የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ በአሰቸጋሪ ሁኔታም ቢሆን አንድነትን ምረጡ” የሚል ቃል እንዴት ሊወጣው እንደቻለ አልገባኝም፡፡ ከሁሉም ያስገረመኝ ደግሞ “ኢህአዴግ የመሬት ፖሊሲ የምቀይረው በመቃብሬ ላይ ነው” ይላል በሚል የሰጠው አስተያየት ነው፡፡ ኢህአዴግ ለስልጣኑ ዋልታና ማገር ያደረገውን የመሬት ፖሊሲ በመቃብሬ አለ የሚለው ትዕግሰቱ አወሉ እልህ ምላጭ ያስውጣል በሚል መፈክር ከራሱ ሌላ አንድ ሌላ ድምፅ ለማግኘት ያልቻለበትን አንድነት ፓርቲን ከምርጫ ቦርድ እና ከገዢው ፓርቲ ጋር እርሱ በሚያውቀው መስመር ተመሳጥሮ ድንክ ያደረገ ግለሰብ፣ ታንክና ባንክ ለማዘዝ የሚያሰችል ስልጣን የሚያስገኝን የመሬት ፖሊሲ በመቃብሬ ላይ ቢባል ምን እንደሚያስገርም አልገባኝም፡፡ ትዕግሰቱ አወሉ ታንክና ባንክ የሚያዝ መንግስት ቢሆን ብዬ ሳሰበው ዘገነነኝ፡፡

አቶ ትዕግሰቱ አወለ በክርክሮች ሁሉ ቀና ብሎ የቴሌቪዥን ካሜራ ለማየት ማፈሩ ተገቢ ሆኖ ባገኘውም የሚያፍር ከሆነ ለምን ቴሌቪዥን ላይ እንደሚመጣ ነው የማይገባኝ፡፡ አንድነት አማራጭ እንዳለው ሰንድ ማሳየት ይቻላል ያለው ትዕግሰቱ የአንድነትን ፕሮግራመ በቅጡ ማንበብና መዘጋጀት ሳይችል (የምርጫ ማኒፌስቶ እርሱ ሊያገኘው አይችልም፣ ቢሮ ዕቃ በጉልበት ሲዘርፍ በአባላት ጭንቅላት የሚገኝ እውቀት ግን በእርሱ እጅ አልገባም) የዛሬ አምስት ዓመት የተዘጋጀውን ሰትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ለዚያውም በመግቢያ ላይ የተፃፈውን ሰለ ዜጎች ሰደት የሚያወራውን ክፍል ለግብርና ክርክር ይዞ ሲቀርብ፣ “የድንኩ አንድነት” ተወካይ መሪ አቶ ትዕግሰቱ ለመዘጋጀት ፈተና የሆነበት ምን ያህል የውስጥ ሰላም አጥቶ እንደሚገኝ የሚያሳይ ነው፡፡ አንድነት በየትም ቦታ ዜጎች ወደ ከተማ መምጣት ችግር ነው ብሎ አያውቅም፡፡ ይልቁንም ችግር ከሆነ እንደ ችግር የሚያየው ዜጎች ከመሬት ጋር ተጣብቀው በገጠር እንዲኖሩ መደረጋቸወ ነው፡፡

ሌላው ያስገረመኝ የጥርሶቹ ማለቅ ሲሆን (መለስ መላጣ ማለት ይቻላል፣ መንካት ግን አይቻልም ባለው መሰረት)፣ እንዴት ነው አሁን ያለው የገንዘብ ፍሰት ለዚህ የሚሆን እንጥፍጣፊ የለውም ወይ? የሚል ጥያቄ ጭሮብኛል፡፡ ከዚህ በፊት ጥርሳቸውን ያስተከሉ መሪዎች በፓርቲው ገንዘብ ነው እያለ እርሱ ሲያወራ ስለነበር ነው፡፡ ለማነኛውም “ሞያ በልብ ነው አንድነትን ምረጡ” ያለው ትዕግሰቱ በግሌ የወረዳ 8 ነዋሪ ከራሱ በስተቀር አንድም ድምፅ እንዳያገኝ በማድረግ እንዲያዋርደው በማክበር ጥሪ አቀርባለሁ፡፡ በሰፈሩ ያሉት እድሮችና የትዕግሱ የማሪያም ፅዋ ማህበርም ይህን እንዲያስተባብሩ እና ትዕግሰቱ ከራሱ በስተቀር አንድም ድምፅ እንዳያገኝ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን የኢህአዴግ ኮካዎች ማህበራዊ ማግለል ወንጀል ነው ይሉታል፡፡ በትዕግስቱ ላይ ማህበራዊ ማግለል ወንጀል የሚሆንበት ህግ ካለ ለመማር ዝግጁ ነኝ፡፡ መቼም ትዕግሰቱን በመወከል ታዛቢ ይኖራል ብዬም አላምንም፡፡ በተጨማሪ የአንድነት ደጋፊዎችም ትዕግሰቱ ከራሱ ሌላ አንድም ሌላ ድምፅ እንዳያገኝ ጠንክረው መስራት ይኖርባቸኋል፡፡ ይህን ሳናደርግ ብንቀር ሌሎች ትዕግሰቱዎች ለዚህች ሀገር እየጋበዝን መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ አንድነት ዋንጫ የሚያነሳው ትዕግሰቱና የትዕግሰቱ ቡድን ድምፅ ሲያገኝ ሳይሆን እነርሱ ተገቢውን ውርደት ሲከናነቡ ነው፡፡

ኢድአን አቶ ግዑሽ ገ/ሥለሴ እና ትዕግስቱ ዱባለ በተባሉ አባላቱ ተወክሎ ነበር፡፡ በነገራችን ላይ አቶ ግዑሽ ገ/ሰላሴ በ2002 ምርጫ ወቅት መድረክ ሞቅ ያለ የምርጫ ስራ ላይ እያለ “ኢድአን ከምርጫ ወጥቶዋል” በሚል መድረክን ያመሱ ግለሰብ ናቸው፡፡ በምርጫ ወቅት የገዢው ፓርቲ ተቃዋሚዎችን የሚያዳክምበት መሳሪያ ናቸው፡፡ ከምርጫ በኋላ እዚህ ግባ በሚባል ፖለቲካ ውስጥ ጉልዕ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ አይታዩም፡፡ አቶ ግዑሽ ካቀረቡት ክርክር ነጥብ አድርጌ የያዝኩላቸው “ … እሰከ መገንጠል መብት የሰጠ መንግሰት፣ ለአርሶ አደሩ መሬትን እሰከ መሸጥ ለምን መስጠት ፈራ” የሚለው ነው፡፡ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች መብት እሰከ መገንጠል ስለተሰጠ የተገነጠለ የለም በሚል የሚከራከረው ኢህአዴግ አርሶ አደሩ እሰከ መሸጥ የሚደርስ መብት ቢያገኝ በመሬቱ ተጠቃሚ ከሆነ አይሸጠውም የሚል መርዕ እንዴት ሊገባው አልቻለም የሚል ነው፡፡ ተዋዋሚዎች ትንሽ ከሚሏት የክርክር ደቂቃ ሁለት ደቂቃ ያገኘው የአቶ ግዑሽ ረዳት አቶ ትዕግሰቱ ዱባለ ያገኛትን ሁለት ደቂቃ በቅጡ የሚረባ ነገር ሳይናገር ላብ በላብ ሆኖ ወጥቶዋል፡፡ ከእንቅልፉ ድባብ ተቀስቅሶ በመናገሩ የተቸገረ ነው የሚመስለው፡፡ ኢህአዴግ የመጨሻውን ማጠቃለያ መስጠቱን ዘንግቶ ለኢህአዴግ ጥያቄም አቅርቧል፡፡ ለማነኛውም በማጭድ ምልክት ዘመናዊ የግብርና መሳሪያ በድጎማ ማቅረብ አማራጭ አድርጎ ያቀረበልን ኢድአን ከቁም ነገር የሚቆጠር አማራጭ ነው ብለን ልንወሰደው እንቸገራለን፡፡ እንኳን ሌሎች እንዲመርጧቸው ልንደግፋቸው አይደለም የራሳቸው “ከተመረጥን” የሚለው ድምፅ ለመመረጥ እንዳልተዘጋጁ የሚያሳጣ ነው፡፡

መድረክ ተወክሎ የገባው በአቶ ጥላሁን እንዳሻው እና በአቶ ሙላቱ ገመቹ በሚባሉ አባላት ሲሆን፡፡ ኢህአዴግም ቢሆን በዋነኝነት ሊከራከረው የገባው ከላይ እንደገለፅኩት ከመድረክ ጋር ብቻ እንደሆነ ያስታውቅ ነበር፡፡ መድረክ በመጀመሪያ ሰድስት ደቂቃ አንዱን ደቂቃ ጊዜው ትንሽ ነው በሚል ጉንጭ አልፋ ክርክር ጊዜ ያባከነ ሲሆን፤ በተጨማሪ መልስ በሌላቸው ህገመንግሰታዊ ድንጋጌዎችና ትርጉም ጊዜውን እንዳባከኑት ይሰማኛል፡፡ በእኔ ግምት በመሃል የተቆረጠ በሚመስል ሁኔታ አምሰት ደቂቃ የሚሞላ ሀሳብ አልሰማንም፡፡ ኢቲቪ ኢህአዴግን የመከላከል መብቱን ተጠቅሞ የቆረጠው ሃሳብ እንዳለ መገመት ይቻላል፡፡ መድረክ በቀጣዩ በነበረውን ዘጠኝ ደቂቃም ቢሆን ኢህአዴግ ላቀረበለት ጥያቄ መልስ በመስጠት፣ ለምሳሌ በሚል የአቶ ጥላሁን እንዳሻው ትውልድ አቅራቢያ ቦታዎች ላይ የሚገኙ የመሬት መፈናቀልና የመሰረተ ልማት እጥረትን በመዘርዘር ለክርክሩ የሚመጥን ነበር ለማለት የሚያስቸገር ሃሳብ ሲያቀርቡ ነበር፡፡ በ2002 አቶ ጥላሁን እንዳሻው በተመሳሳይ ርዕስ ተከራካሪ የነበሩ ሲሆን ይህን ልምድ ይዘው በተሻለ የመቅረብ እድሉ ቢኖራቸውም ሊጠቀሙበት አልቻሉም፡፡ ከመድረክ ክርክር ነጥብ የሚወሰድ ከሆነ በልማት ሰራተኛ ስም የተሰገሰጉት ካድሬዎች ጉዳይ ሲሆን ኢህአዴጎች ይህን ከሰራተኞቹ ጋር ለማጋጨት ሊጠቀሙበት የሞከሩ ቢሆንም በልማት ሰራተኛ ሰም በገጠር የሚንከራተቱት ሰራተኞች ይህን ተጨማሪ ያለፍላጎታቸው የሚሰጣቸው ሰራ እንደማይወዱት ለሚያውቅ የኢህአዴግ መንገድ የሚሳካ አይመስለኝም፡፡ በክርክሩ የመጨረሻ ተከራካሪ መሆን ያለውን ከፍተኛ የማጥቃት እድል በማያሰፈልግ ሁኔታ ከረዳታቸው ጋር የተካፈሉት አቶ ጥላሁን ረዳታቸውም ምንም አዲስ ነገር ሳይነግሩን ክርክሩም እንዲያበቃ አደርገውታል፡፡

በእኔ እምነት ኢህአዴግ አሁንም ቢሆን መንግሰት ሆኖ ያከናወናቸውን ስራዎች ይህን ማድረግ የማይችሉትን ተቃዋሚዎች መክሰሻ አድርጎ ለማቅረብ ሲሞክር ከመስማት የበለጠ አሳፋሪ ነገር የለም፡፡ ይህ ማለት ግን ተቃዋሚዎች በያዘው ስልጣን ሊያከናውን ያልቻለውን፣ በተለይ ደግሞ ባለፈው አምስት ዓመት በግብርና ዘርፍ አሳካዋለሁ ብሎ ያላሳካቸውን ነጥቦች አንሰተው ደካማ መሆኑን ማሳየት አይችሉም ማለት አይደለም፡፡ ኢህአዴግ አሁን የሚሞግተን የግብርና ፖሊሲና ስትራቴጂ፤

· ባለፉት 24 ዓመታት ይህችን ሀገር በምግብ እራሷን እንድትችል ባለማድረጉ የሚከሰሰበት ዋነኛ ነጥብ ነው፡፡ በሃያ አራት ዓመት አሁንም አዝማሚየ በሚባል ሁኔታ መሆናችን ተቀባይነት የለውም፤

· በኢትዮጵያ ሀገራችን በገጠር የሚኖረው ህዝብ ባለፉት 24 ዓመታት ከነበረበት 85 ከመቶ ወደ 83 በመቶ ብቻ ነው ዝቅ ሊል የቻለው፡፡ ይህ ደግሞ በአፍሪካ ደረጃ ከተሜነት 50 ከመቶ በላይ በደረሰበት ወቅት እጅግ አሳፋሪ ሲሆን፤ ይህን እንደ ነጥብ አንሰቶ የሚሞግት ያለመኖሩ ከዚያ ይልቅ የገጠሩ ህዝብ ወደ ከተማ እየፈለሰ ነው የሚል ቅሬታ የሚያሰሙ ተቃዋሚዎች መኖራቸው የሚያሳዝን ነው፤

· የከተሜነት ያለመስፋፋት፣ ዜጎች በገጠር ከመሬት ጋር ተጣብቀው እንዲኖሩ እያደረገ ያለው ደግሞ፤ ኢህአዴግ በውሸት ኤኮኖሚያዊ ምክንያት የሚለው ነገር ግን ፖለቲካው ምክንያት የሆነው መሬትን ህገመንግሰት ውስጥ መደንቀሩ ነው፤ ይህን ፖለቲካዊ የሆነ ጉዳይ ኤኮኖሚያዊ ነው ብለው ምንአልባት ከፓርቲው አቋም ውጭ የግብርና ሚኒሰትሩ ሃሳብ ሲሰነዝሩ የሚሞግታቸው አላገኙም፤

· ኢህአዴግ መሬት መሸጥ መለወጥ የሚለውን ሃሳብ ሲያነሳ መሬት የሚገዙ ጥቂት የሚላቸው ዜጎች መሬቱን የሚገዙት ምርት ለማምረትና ለማትረፍ በዚህም ሀገራችንን በምግብ እህል ራሰን ከመቻል አልፎ ኤክሰፖርት ለማድረግ መሆኑ ቀርቶ ለቀብራቸው መሬት የሚገዙ ያሰመስለዋል፡፡ መሬቱን ሸጦ የሚፈናቀል አርሶ አደር ደግሞ በሌሎች አገልግሎት ዘርፍ የማይገባ፣ ከመሬት ጋር ብቻ ተጣብቆ እንዲኖር የተፈረደበት ያሰመስልብናል፡፡
ባጠቃላይ በእኔ እምነት የ1997 የግብር እና የገጠር ልማት ስትራቴጂ ክርክር በድጋሚ ይቅረብልን ብዬ ማጠቃለል መርጫለሁ!!!

ቸር ይግጠመን!!!!!!!

The post የምርጫ ክርክር ሶስት- ግብርና እና ገጠር ልማት (ከግርማ ሰይፉ ማሩ) appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: የስነ ምግብ ባለሙያውን ያማክሩ

$
0
0

ጥያቄ፡- በስራ ፀባዬና ማህበራዊ መስተጋብሮቼ ምክንያት የፈለኩትን አማርጬና እንደፈለኩ ተረጋግቼ መመገብ አልችልም፡፡ በመሆኑም አትክልቶችን የምመገብበት ጊዜ እጅግ ውስን ነው፡፡ ስለዚህ ለአመጋገብ በጣም ቀላል የሆነና የሚያስፈልጉኝን ንጥረ ነገሮች ሁሉ የማገኝበት አንድ አትክልት ምንድን ነው?
ደረጄ
best food for men
መልስ፡-
በእርግጥ እያንዳንዱ አትክልት የራሱ ባህሪ ያለውና በተለያዩ ንጥረ ነገሮች የበለፀገ ነው፡፡ በመሆኑም አንዱ አትክልት ሁሉንም አትክልቶች ይተካል ማለት አይችልም፡፡ ነገር ግን ለመብላት ቀላል በመሆኑ፣ በሀገራችን ውስጥ ከዓመት ዓመት ከመገኘቱ አንጻር እና ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚሰጥ በመሆኑም ጭምር ካሮት ተመራጭ ነው፡፡
በየቀኑ ሁለት በመጠኑ የተቀቀሉ ወይም ጥሬ ካሮቶች ብትመገብ በቀን የሚያስፈልግህን ያህል 2 ግራም ፋይበር፣ 4960 ሚሊ ግራም ቤታካሮቲን፣ 127 ሚሊ ግራም ፖታሲየም፣ 6 ግራም ቫይታሚን ሲ እና ሌሎችም ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ይሰጥሃል፡፡ በተጨማሪም ሁለቱ ካሮቶች ወደ 50 ካሎሪ ኃይል የመስጠት አቅም አላቸው፡፡

ጥያቄ፡- ምሳ ወይም እራት ከበላሁ በኋላ የምግብ አለመፈጨት ያስቸግረኛል፡፡ በዚህም ምክንያት የምግብ አለመፈጨት እና አለመመቻቸት ስሜት በሆዴ እና አካባቢው ይሰማኛል፡፡ የተመገብኩት ምግብ በመጠኑ ከፍ ያለ ከሆነ ደግሞ ያለመመቻቸት ስሜቱ በጣም ከፍ ይላል፡፡ አመጋገቤን እንዴት እና በምን መልኩ ባደርገው ነው ከዚህ ችግር ልላቀቅ የምችለው?
አቤኔዘር
መልስ፡-
የምግብ አለመፈጨት ችግር በአሁኑ ወቅት ብዙ ሰዎችን የሚያጠቃ ችግር ነው፡፡ ይህ ችግር በአብዛኛው ትክክለኛ የአመጋገብ ልማድን ባለመከተል የሚከሰት ሲሆን ምግብ ለመፍጨት የሚጠቅሙ ፈሳሾች በአግባቡ አለመፈጨት የችግሩ ዋናው መነሻ ነው፡፡ አንተ እንደጠቀስከው ምግብ አብዝቶ መመገብ ጨጓራን ከመጠን በላይ በማጨናነቅ እና አተነፋፈሳችን ላይም ችግር በመፍጠር ምቾት እንዳይሰማን ያደርጋል፡፡ እንዲሁም ልባችንንም ቢሆን በተወሰነ ደረጃ ሊጫነው ይችላል፡፡
ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩልህ ከመጠን በላይ መብላት፣ በፍጥነት መብላት፣ በአግባቡ አኝኮ አለመዋጥ እና ሌሎችም ችግሮች በጨጓራ ላይ የመጨናነቅ እና ያለመመቻቸት ስሜት ይፈጥራሉ፡፡ እነዚህ ልማዶች በጨጓራ ውስጥ ከመጠን በላይ አሲድ እንዲመነጭ በማድረግ በብዙ አጋጣሚ ሀይፐር አሲዲቲ እንዲከሰት ምክንያት ሲሆኑ ይስተዋላል፡፡ በተለይ በፍጥነት በምንመገበብበት ወቅት አየር ከምግብ ጋር ተቀላቅሎ ስለሚገባ እና የተወሰነውን አሲድ ወደ ኤሶፋገስ እና ጉሮሮ እንዲመጣ ስለሚያስገድድ ከጨጓራ በላይ ባለው የምግብ ቱቦ የማቃጠል ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል፡፡
ከዚህም በላይ አንዳንድ ምግቦች በተለያዩ ምክንያቶች ያለመፈጨት እና ያለመስማማት ስሜት የሚያስከትሉ ሲሆን በተለይ ቅመም የበዛባቸው እና በዘይት የተጠበሱ ምግቦች የሆድ ዕቃ አለመመቻቸትን እና መረበሽን ያስከትላሉ፡፡ በተለጨማሪም እነዚህ የተጠበሱ እና ቅመም የሚበዛባቸው ምግቦች በሆድ ዕቃችን ውስጥ አየር እንዲፈጠር በማድረግ ሆዳችን እንዲነፋ የማድረግ ተፅዕኖም አላቸው፡፡ ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮል መጠጣት እና የሆድ ድርቀትም ተመሳሳይ የሆነ የምግብ አለመመቻቸት ሲያስከትሉ ይታያል፡፡ ምግብን በመመገብ ወቅት ውሃን አብዝቶ በላይ በላይ መጠጣት፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ንዴት፣ ፍርሃት እና አካላዊ እንቅስቃሴ አለማድረግ የምግብ አለመፈጨትን ከሚያባብሱ ነገሮች ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡
ስለዚህ ለዚህ ችግር መፍትሄው ምንድን ነው? በአብዛኛው ያለመፈጨት ችግርን ለመከላከል ፍራፍሬዎችን መመገብ ተመራጭ ነው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ሎሚን መጠቀም በጨጓራችን ውስጥ ያሉ አለመመቻቸቶችን ሲያስወግድ ጥሩ የምግብ ፍላጎትንም የመፍጠር አቅም አለው፡፡ ቡርትኳን፣ የወይን ፍሬ እና የአናናስ ጁስም ተመሳሳይ ውጤት ይሰጣሉ፡፡ በመጨረሻም አቢኔዘር የሚከተሉትን አራት ነገሮች ተከትለህ ብትመገብ የተሻለ ውጤት ልታይ ትችላለህ፡፡
ሀ. ምግብ እየበላህ ውሃ አትጠጣ፡፡ ውሃ መጠጣት ያለብህ ምግብ ከመብላትህ ከ30 ደቂቃ በፊት ወይም ከበላህ በ30 ደቂቃ በኋላ መሆን አለበት፡፡ ወተት ወይም የአትክልት ሾርባ ግን የምግብ አካል በመሆናቸው ከምግብ ጋር አብረህ ብትወስዳቸው ለክፉ አይሰጡም፡፡
ለ. በቻልከው መጠን ቀስ ብለህ ለመመገብ ሞክር፡፡ አንድ ጊዜ ወደ አፍህ ያደረከውን ምግብ ሙሉ በሙሉ እስኪልም ድረስ እና የበላኸው ምግብ እንጀራ ከሆነ እንጀራ መሆኑን ፓስታ ከሆነ ፓስታ መሆኑን መለየት እንስኪያቅትህ ድረስ በማኘክ ለመዋጥ ሞክር፡፡
ሐ. ሁሌም ከመጠን በላይ ሳትጠግብ መብላትህን አቁም፡፡ ምግብ መብላትህን ስታቆም በተወሰነ ደረጃ ተጨማሪ መብላት መብላት እንደምትችል እየተሰማህ ቢሆን ይመረጣል፡፡
መ. ምግብ ለመብላት ስትቀመጥ ተጨንቀህ፤ በጣም ደክመህ ወይም ተናደህ ባይሆን ይመረጣል፡፡ ምክንያቱም በእነዚህ ስሜቶች ውስጥ ሆነህ በምትመገብበት ወቅት ምግቡን ለመፍጨት የሚያስፈልጉ ፈሳሾች ለተወሰነ ጊዜ ስለማይመነጩ ነው፡፡
ሠ. የምግብ ፍላጎት ሳይኖርህ ወይም የረሃብ ስሜት ሳይሰማህ ለመብላት አትሞክር፡፡ መብላት ሰውነትህ ምግብ ባስፈለገው ሰዓት ብቻ መሆን አለበት፡፡
ረ. እንደ አንተ ያሉ በምግብ አለመፈጨት የሚቸገሩ ሰዎች በአንድ ጊዜ የተለያዩ ምግቦችን ባይበሉ ይመከራል፡፡ ለምሳሌ ስጋና አትክልቶች በተለያየ አይነት ፈሳሾች አማካኝነት ከመፈጨታቸው አንፃር በተለያዩ ጊዜ ብትመገባቸው በቀላሉ ለመፍጨት አትቸገርም ማለት ነው፡፡
በመጨረሻም አቤኔዘር እነዚህ ነገሮችን እያደረክ የምግብ አለመፈጨት ችግሩ ከቀጠለ ወደ ሐኪም ዘንድ ሄደህ ሌላ መሰረታዊ ችግር እንዳለ ማረጋገጥ ይኖርብሃል፡፡

ጥያቄ፡- የሥራ ጸባዬ ቀኑን ሙሉ ተቀምጬ እንድውል ስለሚያስገድደኝ ሳላስበው ከመጠን በላይ ጨመርኩኝ፡፡ ቢሆንም ባለፉት ጥቂት ወራቶች ውስጥ አመጋገቤን በማስተካከል ወደ 8 ኪሎ ገደማ ቀንሻለሁ፡፡ አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ ብገኝም ከዚህ በላይ መቀነስ እንጂ እንደገና የመጨመር ፍላጎት የለኝም፡፡ ስለዚህ በስንት መከራ ከቀነስኩ በኋላ ተመልሼ ላለመወፈር ምን ማድረግ አለብኝ፡፡
ሊዲያ

መልስ፡-
በመጀመሪያ ሊዲያ ከመጠን በላይ መወፈር ለጤና ጠንቅ እንደሆነ በመገንዘብ ለመቀነስ መሞከርሽ እጅግ የሚያስመሰግንሽ ነው፡፡ ነገር ግን ሰውነት ለመቀነስ በሚደረግ ጥረት ውስጥ ብዙ አይነት ሳይንሳዊ አካሄዶች ያሉ ሲሆን በሙሉ ጤንነት ላይ ችግር የማያስከትል አይነት የመቀነሻ መንገድ መጠቀም የሚመረጥ ነው፡፡ የተከተልሽው የሰውነት ክብደት መቀነሻ መንገድ ሳይንሳዊ እና ጤናማ ነው በሚል አስቤ ልነሳና ከሁሉም በላይ ከባዱን ሥራ በመወጣትሽ እና ወደ 8 ኪሎ ገደማ መቀነስ በመቻልሽ እንኳን ደስ ያለሽ፡፡ ነገር ግን ወደ ጤናማ የሰውነት አቋም በሚደረገው ጉዞ ውስጥ ይህ ግማሹ መንገድ እንደሆነ ልንገርሽ እወዳለሁ፡፡
ስለዚህ በየጊዜው የሰውነት ክብደትሽ በመመዘን ምን ደረጃ ላይ እንዳለሽ መከታተል ብልህነት ነው፡፡ ሁሌም በጠዋት ተነስተሽ ወደ ሥራ ከመሄድሽ በፊት እጅግ በጣም ጥሩ የሆነ ቁርስ መመገብሽን እርግጠኛ ሁኚ፡፡ ሆድሽን በማይከበድሽ መልኩ የተለያዩ አይነት ምግቦችን መመገብ ሰውነትሽን ከማወፈር ይልቅ እስከ ምሳ ሰዓት ድረስ ለሚኖርሽ እንቅስቃሴ ጥሩ ስንቅ ይሆንሻል፡፡
በቀን ውስጥ በሚኖርሽ የአመጋገብ ሂደት ውስጥ ጤናማ ያልሆኑ እና ከእንስሳት የሚገኙ የስብ ዝርያዎችን መቀነስ ይኖርብሻል፡፡ እንደ ክብደትሽ መጠንም በሳምንት ለተወሰነ ጊዜ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግሽም አትዘንጊ፡፡ በተለይ በስራ ፀባይሽ ምክንያት መቀመጥን ስለምታበዢ በየቀኑ መጠነኛ የሆነ የእግር ጉዞ ማድረግ አለብሽ፡፡ ለምሳሌ በቀን የ30 ደቂቃ ፈጣን የእግር ጉዞ ወደ 400 ካሎሪ ገደማ እንድታቃጥይ ይረዳል፡፡ ከዚህም በላይ በገበያ ቦታዎችም ሆነ በቢሮ አካባቢ ስትንቀሳቀሽ ከሊፍት ይልቅ ደረጃን መጠቀም በብዙ ልፋት የቀነሽውን የሰውነት ክብደት በነበረበት እንዲቆይ ያግዝሻል ማለት ነው፡፡

The post Health: የስነ ምግብ ባለሙያውን ያማክሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢትዮጵያ አንድነት ፈተናዎች –ከአበበ ከበደ

$
0
0

የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ሃገር ኢትዮጵያ በቀደሙት ዘመናት ክፉ ነገሮችን የምትከላከል፣ የደጋጎችና የቅን ሰዎች መኖርያ እንደነበረች ታሪክ ያስረዳናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃገሬን አትንኩ” ይል እንደሆን እንጂ ከማንም ጋር በልቶ፣ ጠጥቶ ከመሸበት የሚያድር የዋህ ፈሪሃ አምላክን የተላበሰ ሕዝብ ነው። ኢትዮጵያ ሕዝቡን በፍትህና በጥበብ የሚያስተዳድር ጀግና መሪንም የምታገኘው ከእግዚአብሄር ነበር። ኢትዮጵያ ሃገሯና ሊወር የመጣን ጠላት ድባቅ የምትመታው እግዚአብሄር ከፊት ቀድሞ ስለሚዋጋላት እንጂ ከሌሎች የበለጠ የፈረጠመ ጡንቻ ኖሯትም አልነበረም። ይህ ሁሉ ታሪክ ምስቅልቅሉ የወጣው ኢጣልያ ዳግም ኢትዮጵያን ከወረረች በኋላ ነው። ራሷ ኢጣልያ በኤርትራ የቆየችበት ዓመታትም ዋናውን የአንድነቱን ማብከኝያ መርዝ በቅርብ ሆና ለመቀመም የቻለችበት ኢትዮጵያን የጎዳ ዘመን ነበር። የኤርትራ ጉዳይ እንደመዥገር ሆኖ ከኢትዮጵያ ገላ ላይ አልላቀቅ ያለውም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነው። የኤርትራ ከእናት ሀገሯ ጋር የተደበላቀችበት ጥበባዊ ሥራ በምእራብያውያኖች፣ በመካከለኝው ምሥራቅ ፖለቲካ መዘዝ፣ በግራ ክንፉ የሥልጣን ትንቅንቅ ሳብያና በፖለቲካ መሪዎቹ አናሳ ብስለት ምክንያት ተጨናገፈ። የግራው ክንፍ ፖለቲካም ከኢጣልያ መሠሪ አሰራር ልምዱን ባገኙ ኤርትራዉያን ፖለቲከኞች ሲመራ ቆይቷል። ሻዕቢያ የፊትና የኋላውን መመርመር ያልቻሉትን ግለሰቦች በመደለል፣ የነቁትን በማግለል፣ ላንዳንዱ ደግሞ ሥልጣን መዳረሻ የሚሏቸውን የሃሰት ሥልቶች አስታቅፈው፣ ሲቻል እያፋጇቸው ሳይቻል እያነታረኳቸው፣ ዓላማቸውን ከንቱ ለሆነውና እርባና ቢሱ የኤርትራ ግንጠላ አዋሉት። ኤርትራም በከንቱ ተገንጥላ ለመከራና ስደት ስትዳረግ ኢትዮጵያና የዋህ ሕዝቧ በቆሸሸው ፖለቲካ ውስጥ ተነከሩ።

የኢትዮጵያ ችግር በአብዛኛው መንፈሳዊ ነው። ፀሎት ሥጋዊ ሆኗል፣ ፖለቲካው አስመሳይ ሆኗል። ድህነቱ አዋራጅ ሆኗል። አብዛኛው ሰው ከደረሰበት ችግር ለመላቀቅ የእግዚአብሄርን መንገድ ትቶ ለምእራቡ ዓለም ሰግዷል። ለንዋይ መምበርከኩ ታቦትና ጽላት እስከመሸጥ ድረስ ደፋር አድርጓል። ስደቱ ማንነቱን ከመለወጡ አንስቶ ወደ ሌላ አሳፋሪ ድርጊት ተሸጋግሯል። አሁን ግን አምላክ በቃ እንዲለን ከዚህ በታች የምዘረዝራቸውን የመፍትሄ ሃሳቦች ሳላንዛዛ ባጭሩ ለማቅረብ እሞክራለሁ። ይህ ከዚህ ቀደም ብዙ ቢባልለትም እኔ ለማስታወስ ያህል እንደገና እንዲህ አድርጌ አቀርበዋለሁና በጥሞና አስተውሉት።

ኢትዮጵያ ማነችኢትዮጵያዊስ

ኢትዮጵያ ከሰባት ሺህ አምስት መቶ ዓመታት በኅልውና የቆየች እግዚአብሄር አላማውን ለመፈጸም ሲል ከሚታይና ከማይታይ መከራ እየከለለ ያቆያት የዋህና ጀግኖች ሕዝቦችን ያቀፈች በአፍሪካ ቀንድ አሕጉር የምትገኝ ሃገር ነች። ኢትዮጵያ የጽላቱና የታቦቱ ምስጢር የተገለጠባት፣ ጥንታዊ የሆነ የራሷ ጽሑፍ ያላት፣ ከእግዚአብሄር ምልክቷ ይሆን ዘንድ ልዩ ባንዲራን የለበሰች በአምላክ ልዩ ጸጋ የምትደዳደር ሃገር ነች። ነብር ዥንጉርጉርነቱን ኢትዮጵያዊ መልኩን መቀየር አይቻለውም። ኢትዮጵያዊ ድህነት፣ ችግርና መከራ ተንበርካኪ የማያደርጉት ጀግና ነው።

ቅናት ምንድነው?

ከእግዚአብሄር ልዩ ጸጋን የታደለ ሃገርም ይሁን ግለሰብ አርፎ አይተኛም። ቀናተኛው ዲያቢሎስ ይግደራደራቸዋል። የቃል ኪዳኑ ታቦት ቤት የሆነችው ኢትዮጵያም ከቀናተኞች ዓይነጥላ አትሰወርም። የእግዚአብሄር ቃል ኪዳን መፈጸምያዋ እስራዔልም ብትሆን ችግሮች ተፈራርቀውባታል። ዲያቢሎስ እስራኤልንም ኢትዮጵያንም ፋታ አይሰጣቸውም። እናንተ እሥራኤሎች ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ አይደላችሁም” የሚለው የእግዚአብሄር ቃልም እሥራኤል በኢትዮጵያ ላይ ፊቷን እንድታዞር ያደርጋታል። መንፈሳዊ ቅናት ተፈጥሯዊ ነው፣ መጠኑ የበዛ ሥጋዊ ቅናት ግን የሰይጣን ነው። ያእቆብ በልጆቹ መካከል ያደረገው ልዩነት ነው ቅናትን አሳድጎ ታናሽ ወንድማቸውን ዮሴፍን ወደ ጉድጓድ እንዲወረውሩ የገፋፋቸው። ኢትዮጵያውያኖች ቀድሞ በግዕዝ ቋንቋ ይጠቀሙ ነበር። የኋላ ኋላ እስከዛሬ ድረስ የመንግሥቱ መጠቀምያ የሆነው ቃንቋ አማርኛ ግዕዙን ተካ። በአማርኛ ቋንቋ ላይም ቅናት ተበራከተ። ኢትዮጵያ ሁሉንም ታላላቅ ኃይማኖቶች ማለትም ክርስትናን፣ እስልምናንና የአይሁድ ኃይማኖትን አካታለች። ሶስቱ ኃይማኖቶች በመሃላቸው የቀኖና ልዩነት አላቸው። ልዩነት ውበት መሆኑ ቀርቶ ውዝግብ የሚያደርገው ቅናት ነው። ዮዲት ጉዲት በአይሁድ ኃይማኖት ሥር ለማካተት እልቂትን ስታመጣ ግራኝ መሃመድም ወደ እስልምናው ለመጠቅለል ለአስራ ሰባት ዓመታት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን ላይ አውዳሚ ዘመቻ አወጀባት። ቅናት ከብልሹ ስሜት ይመነጫል። አንዳንድ ጊዜ ከፍርሃት አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የፍላጎት መጠን መንዛዛት የቅናትን ስሜቶች ያሳድጋሉ። ኢትዮጵያ ዙርያዋን በከበቧት ቅናቶች ሳብያ ዘወትር ትመሰቃቀላለች፣ ትቦረቦራለች፣ ትከሳለች። ከእጇ የጎረሱት፣ ውሃዋን የተጎነጩት እንኳን ተረከዛቸውን ያነሱባታል። በገዳማቱ ባሉ እውነተኞች አባቶችና እናቶች ጸሎት ይኸው በኅልውና አለች።

ቅናት በዘመናዊ ፖለቲካ ሲቀመም

ከኢጣልያ ዳግም ወረራ በኋላ ኢትዮጵያን የሚያጠፋው መርዘኛው ፖለቲካ በቅኝ ግዛት በተያዘችው በኤርትራ ውስጥ ይቀመም ጀመር። ኢትዮጵያ ብሄረሰቦች የሚጨቆኑባት ሃገር ነች አሉ። አማርኛ ቋንቋን መጨቆና መሣርያ አድርጎ ለማሳየት ከቅኝ ግዛት አስተዳደሩ ውክልናን ያገኙ ሰዎች ከማርክሲዝም ሌኒኒዝም ቀኖና ጋር ለውሰው የቀድሞ ቅናታቸውን አነባብረው አማራው ሌሎች ብሔረሰቦችን በጭቆና ይገዛል” የሚል አጥፊ ሃሳብ ፈበረኩ። ተከታታይ የነበረውን የኢትዮጵያ መልካም አስተዳደር ላንዴና ለመጨረሻ ለመናድ ከ ሀ እስከ ፐ ያለውን አማርኛ ፊደልንና አማራ ሕዝብን ጨቋን ጭራቅ አድርጎ የመሳሉ ተልዕኮ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ማህበራዊ አኗኗርንና የዋህነቱን በሚገባ ለሚረዱት ሠርጎ ገብ አጥፊዎች የቤት ሥራ ተደርጎ ተሰጠ። በዚሁ መሠረት የሻዕቢያ ተላላኪዎች በተማሪው እንቅስቃሴ ኋላም በተለያዩ ጊዜዓት በተመሰረቱት የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በደርግም ጭምር፣ ሠርገው በመግባት ሌሎች ኢትዮጵያ በሚጠሉ ሃገሮች እየታገዙ ለኤርትራ ግንጠላና አዋሉት። ስለዚህ ጉዳይ ብዙ ስለተባለ ይህን ብቻ ባጭሩ አስቀምታለሁኝ። ሻዕቢያ በዲያቢሎስ ቅናት ተገፋፍቶ አማራን ጭራቅ አድርጎ ስሎ ሲያበቃ ጥቂት ግለሰቦችን በማሰባሰን ፀረ አማራውን ኦነግን መሠረተ። ይህ ትልቁ መሠርያዊ ተግባር ለጊዜው ተሳክቶለት ራሱ ሻዕቢያ ኤርትራን ሲያስገነጥል፣ ማለሊት ኋላም ሕወሃት ለስልጣን በቅቶ ሻዕቢያ ሠራሹን ኦነግን እንደ ጉም በተነ። እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ስለሚጠብቅ ቋንቋቸውን አደበላልቆ በሻዕቢያና ሕወሃት መካከል ያለውን ስምምነት በብረት መጋረጃ ጋረደው። ሆኖም ግን ሕወሃት ከወንድሙ ሻዕቢያ በተማረው መሠረት አማራን ይበልጥ ጭራቅ አድርጎ ስሎ በርካታ ዘርን ማዕከል ያደረጉ ድርጅቶችን ፈጠረ። አማራ ሊመጣባችሁ ነው ራሳችሁን ጠብቁ” እያለ እያሞኛቸው በስልጣን ወንበሩ ላይ ለረዥም ዓመታት ተቀመጠ።

መፍትሄ ያመጣሉ ብዬ የገመትኳቸው ሃሳቦች

አንደኛ፣ እኛ ኢትዮጵያውያኖች ዘመናዊው ዘመነ መሳፍንት ውስጥ ሳናውቀው ድንገት ተዘፍቀናል። በመሆኑም በአጼ ቴዎድሮስ፣ አጼ ዮሃንስና አጼ ሚኒልክ ዘመን የነበረውን የቀደመውን ፍቅርና አንድነትና ጀግንነት ዳግም መመለስ ይገባቸዋል። ሶስቱም ነገሥታት አማርኛ ቋንቋን የመንግሥት ቋንቋ አድርገው ይጠቀሙበት ነበር እንጂ አማራን ጨቋኝ አድርገው አልሳሉም። ራዕያቸውም ሆነ የነጋ ጠባ ምኞታቸው ኢትዮጵያን አንድ ማድረግና ከውጭ ጠላቶቿ መጠበቅ ነበር። አጼ ቴዎድሮስ ራዕያቸው አንድነት በመሆኑ ነው ሃሳባቸውን የተቃወሟዋቸውን የራሳቸውን ዘመዶች ሳይቀር ያስወገዱት። አጼ ዮሃንስ አማራን ቢጠሉ ኖሮ አማርኛን አስወግደው በትግሬኛ ቋንቋ ለመተካት ሙከራ ያደርጉ ነበር። አጼ ሚኒልክ በዘር ቢያስቡ ኖሮ ራስ ጎበናን፣ ፊታውራሪ ኃብተጊዮርጊስ ወይም ደጃዝማች ባልቻን ለትልቅ ሥልጣን አያበቋቸውም ነበር። እኛ ኢትዮጵያውያኖች ይህን መልካም መንፈስ ዳግም እንድንላበስ ማስተዋላችንን ዳግም ማደስና ለመሆኑ ወዴት እየተጓዝን ነው?” ስንል መጠየቅ እንዲሁም መፍትሄ ማፈላለግ ይኖርብናል።

ሁለተኛ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን አባቶች በቤተ ክርስትያኗ መሃከል የተፈጠረውን ክፍፍል ለመቅረፍ መንፈሳዊ መላ ማፈላለግ የሚኖርባቸው ይመስለኛል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ኃያል የነበረውን የቅኝ ግዛት ወረራርን ለመቋቋም ከጀግኖች አባቶቻችን ጋር አብራ መዝመቷን ከታሪክ ተምረናል። በግራኝም ሆነ በኢጣልያ ፋሺስት ወረራ ዘመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በዱር በገደሉ ተሰዳ እየጸለየች እስከዛሬ ገድላቸው ምሳሌና ጥንካሬ የሆነልንን እንደነ አቡነ ተክለሃይማኖትንና አቡነ ጴጥሮስን የመሳሰሉ መስዋዕቶችን አፍርታለች። ዛሬ በስደት የሚኖሩት ወገኖች ለሁለት ተከፈለው ከፖለቲካ ጉዳይ በባሰ ሁኔተ የሚነታረኩትና አንዱ ባንደኛው ላይ እጁን የሚቀስረው በሃገር ቤትና በውጭ ሁለት ሲኖዶሶች በመኖራቸው ሳብያ ነው። ተሳስቼ ከሆነ እርማቱን ለመቀበልና ለመማር ዝግጁ ነኝ። ቤተ ክርስትያኗ ለሁለት መከፈሏ ለጠላት እንዲሁም ኢትዮጵያን ለሚጠሉት ሁሉ አመቺ ሆኗል። እውነትን ደፍሮ የሚናገር ራሱን በንሥሃ አድሶ በቅዱስ ቁርባን አጽድቆ የሚተጋ፣ ለሌሎች ምስክርነቱን በተግባር የሚያሳይ፣ ግዳጁ በሥራ የሚታይ ጠፋ። ስነምግባር ተወላግዶ ግብረገብነት ተሰውሮ፣ ኃይማኖት ተንቃ፣ የሚፈራ የሚከበር ተዉ የሚል ዳኛ ጠፍቶ ሁሉም አንደኛውን ተገን አድርጎ እንዳሻው ይናገራል። ዲያቆኑ ቄስ፣ አስመሳዩ ዳኛ፣ ጉልበተኛው አገልጋይ፣ አዝማሪው ዘማሪ፣ ባለገንዘቡ ፈላጭ ቆራጭ ሆነው እስኪቀርቡ ድረስ ታሪካዊዋ ቤተክርስትያናችን ህልውናዋ ደበዘዘ። ስለዚህ ጉዳይ በጥልቀት ለመናገር በቂ እውቀት የለኝም ነገር ግን የቤተክርስትያኗ ዋናው ሲኖዶስ መንበረ ፓትርያርክ ሃገር ውስጥ እግዚአብሄር እመረጣት ቅድስት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲቆይ በሃገርም በውጭም የሚገኙ መንፈሳዊ አባቶች እርቀ ሠላምን ፈጥረው፣ እግዚአብሄርን በጽኑ ተመርኩዘው በመጾም፣ በመጸለይና በእምነተ ተግባር በመንደርደር መንፈሳዊው ትግሉን በማጎልበት ኅያውን ቅርስ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲያስተላልፉ ስል ተንበርክኬ ልመናዬን አቀርባለሁ። ማንም ለእግዚአብሄር ሲል ቢሸነፍ በሰማዩ አባታችን እግዚአብሄር ዘንድ ትልቅ ሥፍራን ይጎናጸፋል። የምድር ነገሥታት ወይም ተጻራሪ አቋም ያላቸው ድርጅቶች እንኳን በዲፕልማሲው ስልት እየተግባቡ ጦርነትንና መናቆርን ያስቀራሉ እንኳንስ የእግዚአብሄርን አደራ የተሸከሙ ታላላቆቹ አባቶች ይቅርና። ቤተክርስትያናችን አንድነቷ ሲመለስ የሃገሪቱ መንፈሳው ችግር ይቀረፋል።

ሶስተኛ፣ ቢቻል የተማረው፣ የተመራመረው በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ወደ ሃገሩ መመለስ ይገባዋል። ለሃገሪቱ ሙያዊ አስተዋጾ ማቅረብ የሚችሉት ሃኪሞች፣ ማምህራን፣ መተርጉማን፣ ደራስያን፣ መሃንዲሶች፣ የተግባረ ዕድ ባለሙያዎችና የማህበራዊ ሣይንስና ወታደራዊ ጠበብት ባጠቃላይም በችግሯ ጊዜ አብረዋት ሆነው አይዞሽ ሊሏት የሚገባቸውና በሰላማዊ ትግሉ የሚሳተፉ ደፋሮች ሁሉ ቢመለሱ ሃገሪቱ አሁን ከተዘፈቀችበት መከራ ትገላገላለች የሚል እምነት አለኝ። የተማረው ሁሉ ከተሰደደ የሥራ ዕድል እንዴት ይፈጠርሠብሎችንና ንጥረነገሮች ተቀምመው ለምርት ውጤት እንዴት ይብቁሃገሪቱን ከውጭ ጠላት ማን ይጠብቅበአሜሪካና አውሮፓ ላሉት ስደት ትልቅ የገቢ ምንጭ ወይም የድሎት ቤት መሆኑ ቢታወቅም እንኳን በሌላ በኩል ደግሞ ስደት የቅድስቲቱ ኢትዮጵያን ስም ማጉደፉን ልንገነዘብ ይገባናል። ስደት ኢትዮጵያዊና እስራኤላዊ ላይ አያምርም። ዜግነት በመለወጡ ከኢትዮጵያዊነት ቀለም ማምለጥ አይቻልም። ሠበባ ሠበብን ከምረው ራሳቸውን በማታለሉ ስልት የሚኖሩ ሁሉ እርካታ በሌለበት ሕይወት የሰባውን፣ የላመውን፣ የጣመውን እየበሉ መኖር ብቻ ነው ትርፋቸው። ኢትዮጵያዊነትን ለመለወጥ የሚያበቃ ኅሊና የማይታዘበው እውነተኛ ሠበብ ከቶም የለም።

አራተኛ፣ አማራው ጭራቅ አለመሆኑን የሚያሳይ አዲስ በቅን መንፈስ ላይ የተመሠረተ የቃል ኪዳን ማህበር ሊመሰረት ይገባል። የዚህ ማህበር አባል ሊሆኑ የሚገባቸው እውነተኞችና ራሳቸውን ለሃገሪቱ ሲሉ መሰዋዕት ለማድረግ የተዘጋጁ ከበቀልና ጥላቻ የራቁ ማስተዋልን የተላበሱ እንዲሁም ራስን በንሥሃ አንጸው ለኢትዮጵያዊነት የሚበቁ ደጋጎች ሊሆኑ ይገባል። አባላቱ ኢትዮጵያዊ የሆኑ፣ በውጭ ሲኖሩ ዜግነታቸውን ያለወጡ፣ በማንነቱ ቀውስ (identity crisis) ያልተበከሉ ወይም የለወጡትን ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን ሊያስመልሱ የተዘጋጁ ሊሆኑ ይገባል። አታክልትን ውሃ እንጂ ማር ቢያጠጡት አይበቅልም። ሃቀኛና ለመስዋትነት ያልተዘጋጁ ሰዎችን አባል ማድረግ ድርጅትን በቁጥር ብዛት ማሳደግ እንጂ በዓላማ፣ ተግባርና ጥራት አያጸናም። እውነተኞችና ደፋሮች ጥቂት ሊሆኑ ይችላሉ። ጥቂት እውነተኞች ግን ኃይላቸው ጠንካራ ነው። ቆራጥ ዓላማ የጽናት ድምር እንጂ የሰዎች ብዛት ብቻውን ቁጥር ነው። ዛሬ በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ምክንያት በዘፈቀድ ወደ ቤተክርስትያን የሚመላለሱትንም ሆነ ለማህበራዊ ጥቅም ሲሉ ልዩ ልዩ ድርጅቶችን የተቀላቀሉትን ወገኖች በማስተማር ወደ ትክክለኛ አስተሳሰብና እውነት እንዲመለሱ ለማድረግ የተማሩት፣ የተመራመሩት ሁሉ የማስተማር ግዴታ ቢኖርባቸውም የኃይማኖት አባቶች ደግሞ ከእግዚአብሄር የተቀበሉት ልዩ አደራ አለባቸው። 

አምስተኛ፣ እንደ ግንቦት ሰባት ያሉት የፖለቲካ ድርጅቶች ከሻዕቢያ ጋር ያሰሩትን የቃል ኪዳን ቀለበት እንዲያወልቁ በቅጡ መገሰጽ ያስፈልጋል። ሻዕቢያ እንኳንስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅርና አቅፈው ደግፈው፣ ገንዘብ አዋጥተው ሰልለውና አሰልለው ለስልጣን ላበቁት ወገኖቹም እንኳን በጎ አልሆነም። ሻዕቢያን መፍትሄ ያመጣልናል” ብለው ያሰቡት ትላልቆቹ ሰዎች ቀድሞ በትምህርት ቤት ሲማሩ አይጥ ሞቷን ስትሻ ስታበዛ ሩጫ፣ ሄዳ ታሸታለች የድመት አፍንጫ” የተባለውን የታሪክና ምሳሌ መጽሔትን ምሳሌያዊ አነጋገር አላነበቡም አይባልም። ህወሐትን ለመጣል ሻዕቢያን የመጠጋቱ ስልት እማዬ፣ ድመት የኛን የመሰለ ለስላሳ ቆዳ አለው የቀይ ስጋ ቁንጮ ራሱ ላይ ያለው ዶሮ ነው የሚያስጠላው” በማለት እናቷን ልታደናግር እንደሞከረችው የትንሽቱ አይጥን ተላላ ሃሳብ የመከተል ዓይነት ስልት ነው። ሻዕቢያን የጋረደው ራሱ እግዚአብሄር ነው። ይህ ሊገባን እንዲችል አድርጎ አምላክ ብዙ ቅድመ ሁኔታዎችን ፈጽሟል። መገንጠሉ ባዶ ፖለቲካ ከመሆኑ አንስቶ ኢትዮጵያን መጠበቁ ራሱ ዋነኛ ምልክቶች ናቸው። አቶ ኢሳያስ ይህን እውነት አልተረዱም አይባልም ግን ሕዝቡን ይቅርታ ለመጠየቅ ባህርያቸው ገና አልፈቀደላቸውም። ኢሳት ባቀረበላቸው ቃለ መጠይቅ ላይ በግራው ፖለቲካ ላይ ያካበቱት ችሎታቸውን በእብሪት መልክ እንደገና ሊያስረዱን ሞክረዋል። አቶ ኢሳያስ ብዙ ምልክቶችን አይተዋል፣ ኢትዮጵያ የእግዚአብሄር የቃል ኪዳን ሃገር መሆኗንም ተረድተዋል ነገር ግን የኢትዮጵያን ቅድስትነትና የታሪኳን ገናናነት ገና አልተቀበሉም። ሻዕቢያ ቀድሞውንም ቢሆን እንደነ ፕሮፌሰር ጌታቸው፣ዶክተር ታዬ ወልደሠማያት፣ ዶክተር አሰፋ ነጋሽ የመሳሰሉት ደፋሮቹንና ሃቀኞችን የፖለቲካና ታሪክ አዋቂዎች እንዲገለሉ የሚያስደርገው ኢትዮጵያን የማዳከሙ ዓላማ እንዲመቻችለት ነው። ሻዕቢያ እውነተኛ ኢትዮጵያዉያን ድርጅቶችንና ማህበሮችን እንዳይጠጉ ለማድረግ እንደ ፈረስ በሚጋልብባቸው ተላሎች፣ ወረተኞችና ጥቅመኞች ይታገዛል።

ስድስተኛ፣ ቀድሞ እሽቅድምድሙ የኢትዮጵያ አንድነትን ማጎልበትና ልዕልናዋን ማስጠበቁ ላይ እንጂ ለስልጣን መራወጡ እንዲህ እንዳሁኑ አሳፋሪ አልነበረም። የቀደመውን እንኳን ትተን የቅርቡን አንስተን ብንወያይ በንጉሡም በድርግም ዘመንችሎታ” እንጂ ዘር” ለስልጣን ክህሎቱ የሚያበቃ መስፈርት አልነበረም። ይህ የተበላሸው በግራው ፖለቲካ አስተሳሰብ ከአልቤንያ ኮሙኒስቶች ካባ የለበሰው ህወሐት ስልጣኑን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ነው። ሥልጣን የአንድነቱ ማስጠበቅያ መሳርያ መሆኑ ቀረ። ህወሐት በአናሳ ብሄረሰቦች ስም ሳይቀር የዘር ድርጅት መስርቶ መሳለቅያ አደረጋቸው። በመሆኑም ይህን የተሳሳተ ምግባር ለመቀየር ሁሉም ዘሩ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ማስረዳት ያስፈልጋል። ኢትዮጵያዊነት ኃይማኖት፣ ጀግንነትና አንድነት ነው። ዛሬ አስፈሪ ሆኖ የሚታየውን በሻዕቢያ የሚታገዙትን የአልሻባብንና ኦነግን የሽብር ዛቻ ለመቋቋም ኢትዮጵያዊነትን ይበልጥ ማጎልበት ያስፈልጋል። ኢትዮጵያ የታላላቆቹ ኃይማኖቶች እስልምናና ክርስትና የጋራ መሰባሰብያ ቤት ነች። ይህ ሃገራዊ ጉዳይ ልል እንዲሆን የሚያደናግሩትን እውስጣችን የተሸሸጉትን የሻዕቢያ ጉዳይ ፈጻሚ ተላላኪዎችን ልንነቃባቸው ይገባል። ሌላው ቀርቶ ትግራይዋን ወገኖችን በማስጠላትና በማስገለል ድርጊቶቻቸውና ቅስቀሳቸው ላይም ቢሆን መተባበር የለብንም። ትግራይ የሚኖረው ወገናችንም ቢሆን እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በደሎች የሚፈራረቁበት ሕዝብ ነው።

ሰባተኛ፣ ባዶ ስሜት ሊወገድ ይገባል። ባዶ ስሜት ሙያን ገደል። ባዶ ስሜት ጋዜጠኛ ሆነ። ባዶ ስሜት ፖለቲከኛ ሆነ። ባዶ ስሜት ጦረኛ ሆነ። ባዶ ስሜት ፓስተር፣ ቄስ ሼህ ሆነ። ከንቱ ስሜት እንደስካር ነው፣ እመስዋትነቱ መንደር ጫፍ ላይ ሳያደርስ ድንገት ይበናል። ልበ ደንዳናነት፤ ለጥቅመ ጥቅሞች ማነፍነፍ ወይም ፍርሃት ባዶ ስሜትን ያመነጫል። ልባቸው ያልተለወጠውን፣ ድፍረት ያለበሱትን፣ ሃቅን ያልተመረኮዙትንና ያልተማሩትን ያልተመራመሩትን ማሰለፉ ሽንፈትን ይጋብዛል። ለጥቅም በተሰለፉ ሰዎች ብዛት ድርጅት ቢፈላ ጠብ የሚላ ነገር የለም። ባዶ ስሜተኞች በዝተው እውነተኞች ካህናት የተናቁባትና ኃይማኖታዊ ምግባርን የማይተገብሩ ሰዎች የበዙባት ቤተክርስትያን መንፈሳዊነቷ ደካማ ነው፣ አታስተምርም፣ በቅዱስ ኪዳኑ ኃይማኖት አታፀናም፣ ፍቅር አታላብስም፣ ይቅር ባይ ልብ አትፈጥርም፣ ፍሪ አታፈራም፣ ቅንነት አታጎለብትም፣ ምዕመናን ያልተንዛዛ የኑሮ ሥርዓት እንዲከተሉ ወይም ሕይወትን በመልካምነት እንዲመሩ አታደርግም። ባዶ ስሜተኞች የበዙባት የፖለቲካ ድርጅትም መካን ነች። ለሥጋዊ ጥቅሙ የሚያደላና ለዕለት ኑሮው የሚጨነቅ ግለሰብ ለኃይማኖቱ፣ ለኢትዮጵያዊነቱም ሆነ ለወገኑ ደንታም የለውም። ደንታ ያለው እንዲመስል በባዶ ስሜት ይወራጫል፣ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል። ሲለቁት ደግሞ ተግባር የለም።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቃል።

Comment

The post ኢትዮጵያ አንድነት ፈተናዎች – ከአበበ ከበደ appeared first on Zehabesha Amharic.

የመረጃ ግብአት …በ5 ኛው ቀን ዘመቻ …–ነቢዩ ሲራክ

$
0
0

የዘመቻ ” ወሳኙ ማዕበል ” አበይት ክንውኖች ዳሰሳ  !
===========

Nebiyu Sirak*  በሳውዲ የሚመራው የአረብ ሀገራት ህብረት ጦር የአየር ድብደባው ተጠናክሮ ቀጥሏል

* የየመን ባህርና አየር በሳውዲ አየር ሃይል ቁጥጥር ስር  መዋላቸው ሲጠቆም ኢራንን ጨምሮ ለሁቲ አማጽያን ስንቅና  ትጥቅ ማቀበያ በሮች መዘጋጋታቸውን የህብረቱ ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ አስታውቀዋል

* ከዘመቻው መምሪያ ጋር በተደረገ ቅንጅት የመን የገባው የፖኪስታን ጃምቦ ጀት 482 ፖኪስታናውያንን ከመንን አውጥቷል

* በጦርነቱ መካከል ያሉ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ አሳሳቢ ሆኗል ። በጥብቅ በታጠረው የሳውዲ ድንበር ወዲህና ወዲያ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በጦረነቱ እሳት መካከል  በአጣብቂኝ ውስጥ ስለ መሆናቸው በግል የሚደርሱኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ

*  በሳውዲ የመን ድንበር በባህር ጠረፎች ከፍተኛ የእግረኛና የባህር ኃይል ሰራዊትና የሜካናይዝድ ጦር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተመልክቷል

* በሳውዲ ድንበር ፣ በጀዛን እና በኤደን የባህር ወሽመጥ በባብ አልመንደብ አካባቢ የባህር ኃይልና የምድር ጦር ዝግጅቱን አስመልክቶ የተጠየቁት ብርጋዴር ጀኔራል አህመድ አሲሪ ” በጦርነት ውስጥ እያለህ ይህ መሰሉ ዝግጅት የተለመደ ነው! ” ብለው መልሰዋል

* የምድር ጦር በሚመለከት በአንድ ታዋቂ የአሜሪካ ቴሌቪዠን የተጠየቁት በአሜሪካ የሳውዲ አምባሳደር አድል አል ጃብሪ በሳውዲ በኩል የምድር ጦር ለማዝመት እስካሁን ውሳኔ አለመደረሱን ጠቁመዋል

* የየመን ፕሬ አብድልረብ መንሱር በሳውዲ ስደት ላይ ሆነው በኢምሬት የየመን አንባሳደር አድርገዋቸው  የነበሩትን አህመድ አሊ አብደላ ሳላህን ከስልጣን አባረሩ ። አህመድ አሊ በአባታቸው የአገዛዝ ዘመን ከፍተኛ የጦር መኮነን ነበሩ ። በኢምሬት አምባሳደር የተሰጣቸው በፕሬ አብድልረቡ ሲሆን ከነበሩበት ቁልፍ የጦር መሪነት ተጽዕኖ ፈጣሪ ቦታ ለማሸሸት ታስቦ ነበር ።  አህመድ የፕሬ አብድልረቡ ወዳጅና የአሁን ሁነኛ ባላንጣቸው የሆኑት  የቀድሞው ፕሬ የአሊ አብደላ ሳላህ የብኸር ልጅ ናቸው ፣ ከቅርብ ወራት ጀምሮ አህመድ ከአባታቸው ጋር ሆነው ፕሬ አብድልረቡን ለማውረድ የሁቲ አማጽያንን በመደገፍ መሪውን አሽቀንጥረው የመንን ለዛሬ መከራ እንደዳረጓት ይወነጀላሉ

* ባሳለፍነው ቅዳሜ  መጋቢት 19 ቀን 2007 በግብጽ ሻርማ ሸክ የተደረገው የአረብ ሊግ ስብሰባና ውጤቱ የአረብ መገናኛ ብዙሀን በሰፊው እየተዘገበበት ይገኛል

* እዚህም እዚያም የቃላት ጦርነቱ ተጋግሟል …
===========================

* የሁቲ አማጽያን የሳውዲ መራሹን የጦር አውሮፕላን ጣልን ይላሉ ፣ የሳውዲ መራሹን ጦር ቃል አቀባይ በአንጻሩ የሁቲ አማጽያን ከዚያ የሚያደርሰውን አቅም በመጀመሪያ ቀን የአየር ድብደባ ብቻ አክሽፈነዋል በማለት በተዋጊ ጀቶቻቸው ላይ ጥቃት አለመድረሱን በመግለጫቸው በአጽንኦት ተናግረዋል

* በየመን የሁቲ አማጽያንን በሳውዲ መራሽነት የተጀመረው የአየር ድብደባ እንዲያቆም ከሚፈልጉት ሀገራት መካከል ቀዳሚ የሆነችው የራሻው ፕሬ ፑቲን ለአረብ ሊግ ስብሰባ በላኩት ደብዳቤ አረብ ሀገራት በመካከለኛው ምስራቅ የወደፊት ሰላምን ለማምጣት ከጦርነት ውጭ ያለውን የሰላማዊ መንገድ አማራጭ ይጠቀሙ ዘንድ መክረዋል

* የሳውዲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዑድ አል ፈይሰል ግን የፑቲንን መልዕክቱን ተቃውመዋል ።  በኢራን የሚደገፈውን በሶርያ የአሳድን መንግስት የገዛ ዜጎቹን እየፈጀ በራሽያ ስንቅና ትጥቅ ይደገፋል ሲሉ የራሻን ተቃርኖ መንገድ ላይ የሰላ ሂስ ያቀረቡት ልዑሉ የራሻው ፕሬ ፑቲን ከአረብ ሀገራት ጋር የቆየ ግንኙነታቸውን ለማስቀጠል ንግግራቸውን አርመው አቋማቸውን ይፈትሹ ዘንድ አሳስበዋል።

* ከኢራን እርዳታ በማግኘት የሚታሙት የሽምቅ ተዋጊው የሀማስ መሪዎች ሳውዲን ጭምሮ የ10 አረብ ሀገራትን ዘመቻ ሲደግፉ የኢራንና የሶርያ መንግስት ደጋፊ የሊባኖሱ የሂዝቦላህ መሪ ሸህ ሀሰን ነስርአላህ የሳውዲ መራሹን ዘመቻ በማውገዝ በተለይ በሳውዲ መንግስትን መወረፋቸው የሳውዲን መንግስት አስቆጥቷል

* በሊባኖስ የሳውዲ አምባሳደር አሊ አዎድ አሲሪ ጭብጥ የሌለው ሀሰት ነው ያሉት የሂዝቦላሁ ሀሰን ነስርአላህ ንግግር ሂዝቦላህ የሚወክለውን የኢራን አቋም የተንጸባረቀበት አሳሳች መልዕክት እንደሆነ ለአረብ ኒውስ አስረድተዋል

ቸር ያሰማን  !

ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 21 ቀን 2007 ዓም

The post የመረጃ ግብአት … በ5 ኛው ቀን ዘመቻ … – ነቢዩ ሲራክ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኦቦ በቀለ ገርባ ዛሬ ተፈተው እንደገና ዛሬ ታስረው ሞጆ ላይ ተለቀቁ

$
0
0

Bekele Gerba

(ዘ-ሐበሻ) አቶ በቀለ ገርባ የ እስር ጊዜያቸውን ጨርሰው መፈታታቸው ተሰማ:: ለዘ-ሐበሻ የደረሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት አቶ በቀለ ዛሬ ተፈተው እቤታቸው ከገቡ በኋላም እንደገና ደህንነቶች “ያልተጣራ ነገር” አለ ብለው እንደገና ወስደው ለሰዓታት ካሰሯቸው በኋላ መልሰው ሞጆ ላይ ለቀዋቸዋል::

አቶ በቀለ ገርባ 26 ዓመት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ልሳን መምህር የነበረሱ ሲሆን የሰውነት አቋማቸው ግን ገና 26 ዓመታትን የሚሰሩ ያስመስላቸዋል።

የኢሳት ራድዮ ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ “የአቶ በቀለ አፈታት ድራማ” በሚል በዘገበው ዘገባው ላይ የሚከተለውን ጽፏል::
Bekele Gerba

*ዛሬ መጋቢት 21 2007 ዓም አቶ በቀለ የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው የሚፈቱበት ቀን ነው።
*ጠዋት ላይ ባለቤታቸው ወይዘሮ ሀናን ጨምሮ የአቶ በቀለ መፈታትን ለማየት ወደ ዝዋይ እስር ቤት አቀኑ
*አቶ በቀለ ተፈቱ:: ቤተሰባቸውን በእቅፋቸው አድርገው በደስታ እንባ ታጅበው መነፋፈቃቸውን ገለጹ። ከዚያ ጉዞ ወደ ቤት…
*በድንገት የህወሓት ፖሊሶች ወደ አቶ በቀለ መጡና “መጣራት ያለበት ጉዳይ ስላለ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ይወሰዳሉ” አሉ:: ቤተሰብም አቶ በቀለም ቀልባቸው ተገፈፈ:: ደስታቸው ብን ብሎ ጠፋ!
*በደንጋጤ የተዋጡት ወይዘሮ ሀና ይህንን ጉዳይ ለኦፌኮ አመራሮች አሳወቁ። የኦፌኮ አመራሮች በፍጥነት አቶ በቀለ ይሄዳሉ ወደተባሉበት ቃሊቲ እስር ቤት ተጓዙ።
*ሆኖም ቢጠበቅ-ቢጠበቅ አቶ በቀለ ብቅ ሳይሉ ቀሩ
*አቶ በቀለን ይዘው የነበሩት ጠባቂዎች ታሳሪውን ይዘው ሞጆ አካባቢ ለቀቋቸው።
ውዥንብሩ ለምን እንደተፈጠረ ባይታወቅም ዋናው ደስታው ነውናን ቤተሰባቸው አቶ በቀለ ገርባን ይዞ ወደ አዳማ ናዝሬት ይዞ ሄደ። አቶ በቀለና ሴት ልጃቸ ቦንቱን ኢሳት በስልክ አግኝቶ አነጋግሯቸዋል::

በካንጋሮው የሕወሓት ፍርድ ቤት “በሽብርተኝነት” ክስ ጥፋተኛ ተብለው 3 ዓመት ከ7 ወር የተፈረደባቸው አቶ በቀለ በመጀመሪያ ስምንት ዓመት ቢፈረድባቸውም ተከራክረው ወደ 5 ዓመት ማስደረጋቸው ይታወቃል:: በየኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ም/ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ የ3 ዓመት ከ7 ወር የእስር ጊዜያቸውን እንደጨረሱ በኣመክሮ መለቀቅ የነበረባቸው ቢሆንም መከልከላቸው ይታወሳል:: እስር ቤትም ህክምናም ሳያገኙ ብዙ ተሰቃይተዋል:: አቶ በቀለ ገርባ የ 3 ዓመት ከ 7 ወር የእስር ጊዜያቸውን ኣጠናቀው መለቀቅ የነበረባቸው ባለፈው ጥር 11 ቀን ነበር::

The post ኦቦ በቀለ ገርባ ዛሬ ተፈተው እንደገና ዛሬ ታስረው ሞጆ ላይ ተለቀቁ appeared first on Zehabesha Amharic.


በቀልድ የታጀበው ምስክሮችን የመስማት ውሎ -የዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች ላይ

$
0
0

ከዞን 9 ብሎግ የተገኘ የፍርድ ቤት ውሎ ዘገባ

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆየው የማስረጃ መስማት ውሎ ዛሬ ምስክሮችን በማስማት ተጀምሯል፡፡ በዚህም መሰረት አቃቤ ህግ ጉዳዬን ያስረዱልኛል ያላቸውን 17 ምስክሮች ያስመዘገበ ሲሆን 15ቱ በፍርድ ቤቱ ተገኝተው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ አቃቤ ህግ ችሎቱ በዝግ ችሎት አንዲሆን የጠየቀ ሲሆን ምስክሮቼ እና የቤተሰቦቻቸውን ደህንነት ለመጠበቅ ችሎቱ በዝግ ሊሆን ይገባል የሚለውን አቤቱታውን ጠበቆች በከፍተኛ ደረጃ ተቃውመውታል፡፡ ምስክሮቹ የጭብጥ ምስክሮች ሳይሆኑ ፍተሻን የታዘቡ የደረጃ ምስክሮች በመሆናቸው እና ስማቸውም በግልጽ ተከሳሾች ጋር ስለደረሰ ምንም አይነት የደህንነተ ስጋት የለባቸውም ከሚለው የጠበቆች ክርክር በኋላ ፍርድ ቤቱ በጉዳዬ ላይ ተወያይቶ ለመወሰን ረፍት ወስዷል፡፡ በዚህም መሰረት የአቃቤህግን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ችሎቱ በግልጽ ሆኖ መስክሮች ምስክርነታቸውን እነዲያሰሙ ታዟል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አቃቤ ህግ ያቀረባቸው ምስክሮች አነማን ላይ አንደሚመሰክሩ እና ምን አንደሚመሰክሩ በተጠየቀው መሰረት ፍርድ ቤቱም በጠበቆቹ ስለተነሱት ነጥቦች የአቃቤ ህግን ምላሽ ጠይቋል፡፡ አቃቤ ህግም በዛሬው ዕለት የቀረቡት ምስክሮች በ2ኛ፣ በ3ኛ፣ በ5ኛ፣ በ6ኛ፣ በ7ኛ እና 8ኛ ተከሳሾች ( በስድስቱ የዞን9 ጦማርያን ላይ እና በጋዜጠኛ አስማማው ላይ ) ላይ እንደሚመሰክሩ ገልጾ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቡድን በብርበራ ያገኛቸው ማስረጃዎች ከተከሳሾች የተገኙ ስለመሆናቸው ያስረዱልኛል ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
zone 9 bloggers
በምላሹም መሰረት የአቃቤ ህግ ምስክሮች ምስክርነታቸው ሰጥተዋል፡፡ ምስክርነታቸው ሲሰጡ በነበረበት ወቅት የተከሳሾችን ስም አለማወቅ አንዲሁም የተከሳሾችን መልክ አለመለየት የመሳሰሉት ጉዳዬች የተስተዋሉ ሲሆን ምስክርነታቸውን የሰጡት ሰዎች ስም ዝርዝር እና የምስክርነታቸው ጭብጥ በአጭሩ አንደሚከተለው ነው ፡፡

1.ሙሉጌታ መዝገቡ ለማ – ናዝሬት ነዋሪ ነኝ መአከላዊ ምርመራ ለግል ጉዳይ ሄጄ ፓሊስ ታዛቢ ምስክር አንድሆን ጠይቆኝ በዚያ መሰረት ምስክር ሆኜ ተገኝቻለሁ፡፡ ከአቤል ከኮምፒውተሩ ላይ ጽሁፍ ሲወጣ እና ሲፈርም አይቼ እኔም ፈርሜያለሁ ፡፡ የጽሁፉን ይዘት አላነበብኩም አንዳንድ ቦታ አፍሪካ ሪቪው ኬንያ የሚል ቃል አይቻለሁ የሚል ምስክርነት ሰጥተዋል፡፡

2.በለጡ አበበ ዮሴፍ ይባላሉ፡፡ እድሜያቸው 32 ሲሆን ከፍተኛው ፍርድ ቤት የካ ምድብ ሰራተኛ ናቸው፡፡ አዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆኑ በማን ላይ ለመመስከር እንደመጡ ሲጠየቁ በስም እንደማያስታውሱት ገልጸው በአካል ግን ለይተው አሳይተዋል፡፡ መስካሪዋ በ6ኛ ተከሳሽ ዘላለም ክብረት ላይ የሚመሰክሩ ሲሆን በተለየ ስም ሲጠሩት ተስተውለዋል:-
“የሽብርተኝነት ጉዳይ የሚያመለክት ይመስለኛል፡፡ ወደ 70 ገጽ አማርኛና 10 ገጽ እንግሊዝኛ ጽሁፍ ተገኝቷል፡፡ ያየሁትን አይቼ ፈርሜያለሁ፡፡” ካሉ በኋላ ተከሳሹስ ፈርሟል ተብለው ሲጠየቁ መጀመሪያ አላስታውስም ቢሉም እንደገና ሲጠየቁ ግን አዎ ፈርሟል ብለዋል፡፡

3.እታፈራሁ ጌታቸው ወልዴ የሚባሉ ሲሆን እድሜያቸው 36 ነው፡፡ በመንግስት ት/ቤት በአስተዳደር ሰራተኛነት የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ ማን ላይ እንደሚመሰክሩ ሲጠየቁ ፍቃዱ እና…..(ስሙ ጠፍቶባቸው ቆይተው) እ…አጥናፉ ብለዋል፡፡ በአካል ደግሞ በፍቃዱን አሳዩ ሲባሉ አጥናፍን አሳይተዋል፡፡ የምስክርነት ቃላቸውም ማእከላዊ ምርመራ ለግል ጉዳይ ሄደው ጽሁፎች ሲታተሙ ማየታቸውንና በፍቃዱ በፍቃደኛነት ሲፈርም ማየታቸውን ተናግረዋል፡፡ ስለጽሁፎቹ ሲጠየቁ “የአማርኛ ጽሑፎች ናቸው፡፡ 60 ገጽ የሚሆን ‹ወያኔ ይውደም› ምናምን የሚል ጽሑፍ አይቻለሁ፡፡ እንግሊዝኛም አለው 10 ገጽ ይሆናል፡፡ በምስል ከውጭ ሰው ጋር ሆነው የሚነጋገሩትም አይቻለሁ፡፡ ይዘቱ ግን ግር ይለኛል፡፡” ብለዋል፡፡ አጥናፍን አስመልክቶ ደግሞ ‹‹የእሱንም በዚያው መልኩ ነው ያየነው፡፡ ዕለቱም ግንቦት 16/2006 ነው፡፡ ኮምፒውተሩ ላይ የነበሩትን ጽሁፎች እዚያ ለነበሩት ሲያሳይ ነበር፡፡ ጽሑፎችን አይቻቸዋለሁ….‹የጨለማው ቀን….የጨለማው ንጉስ› የሚል አይቻለሁ፡፡ ‹ኢትዮጵያ አንድ ናት› የሚልም አይቻለሁ፡፡ ወደ 30 ገጽ ይሆናል፡፡ ሁሉም ፕሪንት ተደርጎ ሁላችንም ፈርመንበታል፡፡››ብለዋል::
zone 9 ethioia1
ሶስቱ ምስክሮች ከተሰሙ በኋላ ጠበቆች በሂደቱ ላይ አስተያየት አለን በማለት፣ ዶክመንቶቹ ፕብሊክ ዶክመንት ናቸው በአደባባይ የተጻፉ ጽሁፎቻቸው እና በማንኛውም ቦታ የሚገኙ ስለሆኑ ዶክመንቶቹን ክደን አልተከራከርንም የእኛ ክርክር ዶክመንቶቹ ለወንጀል ስራ የሚበቁ አይደሉም ነውና በዚህ ጭብጥ ዙሪያ ምስክር መስማቱ ያብቃልን የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡አቃቤ ህግ በበኩሉ ሁሉም ምስክሮች አንዲሰሙልኝ እፈልጋለሁ በማለቱ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ያስረዱልኛል ካለ ይቀጥል በማለቱ ምስክሮቹ ቀጥለዋል፡፡ ጠበቆች መስቀለኛ ጥያቄ ሳይጠይቁ ተከታዬቹ ምስክሮች መሰማታቸው ቀጥሏል፡፡

4.አራተኛው ምስክር አፈወርቅ ካሳ ይባላሉ፡፡ የግል ሰራተኛ ሲሆኑ እድሜያቸው 46 ነው፡፡‹‹ቀኑ ሚያዝያ 18/2006 ነው፡፡ የተከሳሹ አስማማው ቤት ጠዋት 3፡00 አካባቢ ሲፈተሸ ታዛቢ ነበርኩ፡፡ ጋዜጦች፣ መጽሔቶች፣ ፓስፖርት…ብዙ ወረቀቶች ላይ ‹‹አዎ የእኔ ናቸው›› እያለ ሲፈርም አይቻለሁ፡፡ እኔም ፈርሜያለሁ፡፡ ቤተሰቦቹም ቤት ውስጥ ነበሩ፡፡ አብዛኛው ያየሁት የግል መጽሄቶችን ነው፡፡ ማህተምም አይቻለሁ፡፡ ደሞ ቢሮው ሄደን ላፕቶፕ፣ ፍላሽ፣ ሲዲ፣ መጽሔቶች አይቻለሁ፡፡ ፖሊስ የሚፈልገውን እየለየ ፈርመናል፡፡ ወደቢሮው የሄድነው በመኪና ነበር፡፡ ከዛ ደግሞ አድራሻችንን ይዘው ስለነበር ሰኔ 4….አይ 14/2006 ነው መሰለኝ ከማዕከላዊ ተጠርተን ላፕቶፕ ላይ የነበረውን ስዕሎችና የእንግሊዝኛ ንግግሮች ሲወጡ አይቻለሁ፡፡ የእኔ ነው ብሎ ሲፈርም እኛ ታዛቢዎችም ፈርመናል፡፡›› ብለው ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

5.አምስተኛ ምስክር አጌና አንከና ይባላሉ፡፡ እድሜያቸው 48 ሲሆን ነዋሪነታቸው አ.አ ነው፡፡ የሚመሰክሩት ደግሞ በ3ኛ ተከሳሽ ናትናኤል ላይ ነው፡፡ የምስክርነት ቃላቸው፣ ‹‹ሰኔ 17/2006 ለግል ጉዳይ ማዕከላዊ ነበርኩ፡፡ ከቀኑ 8፡00 ታዛቢ ሁነኝ ብሎ ፖሊስ ጠይቆኝ ታዝቤያለሁ፡፡ ላፕቶፑ ላይ አማርኛ ጽሑፎች አይቻለሁ፡፡ ጽሑፎቹ የተከሳሹ ስለመሆናቸው አምኖ ሲፈርምባቸው ታዛቢዎችም ፈርመናል፡፡ ይዘቱን ግን አላነበብኩትም፤ አልተረዳሁትም፡፡ የገጹን ብዛትም አላስታውስም፡፡›› የሚል የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡
36884-zone9-bloggers4
6.ስድስተኛ ምስክር ገብረጨርቆስ ገብረመስቀል ይባላሉ፡፡ የ50 ዓመት የመንግስት ሰራተኛ ናቸው፡፡ ምስክሩ በአስማማው ላይ ለመመስከር እንደመጡ ቢናገሩም በአካል ግን ለይተው አላወቁትም፡፡ እንዲያውም አስማማውን አሳዩ ሲባሉ አቤልን አሳይተዋል፡፡

ከፍርድ ቤቱ ውሎ በኋላ አስተያየታቸው የሰጡት የተከሳሾች ጠበቆች አቃቤ ሀግ ያቀረባቸው ምስክሮች ወረቀት ሲፈረም አየን ከማለት ውጪ ምንም አይነት ለሂደቱ ቁም ነገር ያለው ምስክርነት የሚሰጡ አይደሉም ፡፡ ተከሳሾች ተገኘባቸው የተባለው ጽሁፍ የአደባባይ ዶክመንት ከመሆኑም በላይ አልተገኘብንም ብለን ክደን አልተከራከርንም በይዘቱ ላይ ክርክር ስላልተደረገ መስቀለኛ ጥያቄ ለማቅረብም ብዙ አልጨነቅንም ብለዋል፡፡አቃቤ ሀግ የወንጀሉን የመጀመሪያ ደረጃ ጭብጥ የሚያሳዬ ምስክሮችን ያቅርብ አይቅርብ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ የማስረጃ ማሰማት ሂደቱ ነገ ይቀጥላል፡፡

በተቃራኒው ምሳቸውን ችሎት ውስጥ የተመገቡት ሁሉም እስረኞች በጠንካራ መንፈስ ሆነው ሲጨዋወቱ እና ሲነጋገሩ ተስተውለዋል፡፡ የችሎቱ ተሳታፌዎች በምስክሮች መደናበር እየሳቁ ነበረ ሲሆን የዞን9 ወዳጆች አጋሮች ቤተሰብና ጋዜጠኞች ተገኝተዋል፡፡

የዞን 9 ማስታወሻ

የዛሬውን አስቂኝ የፍርድ ቤት ውሎ ባልተካደ ነገር ላይ ወርቃማውን የተከሳሾች ሰአትም ሆነ የፍርድ ቤቱን የስራ ሰአት ማባከኑ የሚገርም ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ችሎቱ በግልጽ አንዲካሄድ መፍቀዱን በበጉ መልኩ ተመልክተነዋል፡፡ አቃቤ ህግ ለምስክሮቹ ደህንነት ሳይሆን የራሱን መዋረድ ለመቀነስ ሲል ችሎቱን በዝግ ለማድረግ መሞከሩ ተከትሎ የመጣውም የምስክሮች መወዛገብ ግልጽ የሚያደርገው ነው ፡፡ የዞን9 ጦማርያን አና ጋዜጠኞች ላይ የቀረበባቸው ማስረጃ በተለያየ ቦታ የጻፏቸው የራሳቸው እና የሎሎች የአደባባይ ምሁራን ጽሁፎች በመሆናቸው ጽሁፉ የእኛ መሆኑ ምስክር አያሻውም ፡፡ በተደጋጋሚ እንዳልነው ሃሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው የታሰሩት ወጣቶች ክስ የጸፉት ጽሁፍ ይዘት ላይ ነው፡፡ የታሰሩ ወዳጆቻችንን ለመፍታት አሁንም አልረፈደም ፡፡

በዚህ አጋጣሚ ፍርድ ቤት ተገኝተው አጋርነታቸውን ለሚያሳዬ የዞን9 ወዳጆች ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ህገ-መንግስታዊ መብት ይከበር ፡፡

Source: ዞን9

The post በቀልድ የታጀበው ምስክሮችን የመስማት ውሎ -የዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች ላይ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሳዑዲ አረቢያ ድብደባ እና የኢትዮጵያውያኑ ሁኔታ –ነብዩ ሲራክ ቃለምልልስ (የሚደመጥ)

$
0
0

ሕብር ራድዮ በየመን እና በሳዑዲ አረቢያ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ኑሮውን በሳዑዲ ካደረገው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ጋር ቆይታ አድርጓል:: ነብዩ የሳዑዲን ድብደባ ከኢትዮጵያውያን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር አያይዞ ይተነትናል:: ያድምጡት::

saudi

The post የሳዑዲ አረቢያ ድብደባ እና የኢትዮጵያውያኑ ሁኔታ – ነብዩ ሲራክ ቃለምልልስ (የሚደመጥ) appeared first on Zehabesha Amharic.

(የየመን ጩኸት) የሳዑዲ የቦምብ ድብደባና በየመን የሚኖሩ ከ200 ሺህ የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ (ቃለምልልስ ከጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት ጋር) –ያድምጡት

$
0
0

በስደት የመን የሚገኘው የቀድሞው የገመና እንዲሁም የአስኳል ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት ሰሞኑን ሳዑዲ አረቢያ በየመን ላይ እየወሰደችው ያለችውን የቦምብ ድብደባና እንዲሁም በየመን ያለውን አለመረጋጋት ተከትሎ እዚያው የሚኖሩ ከ200ሺህ የማያንሱ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ በማስመልከት ከተወዳጇ ሕብር ራድዮ ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ ጋር ቃለምልልስ አድርጓል:: ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት የውጭ ሚዲያዎች ያላሳዩንን በቃለምልልሱ ይዳስ ሳል:: ያድምጡት::

Girum Teklehimanot

The post (የየመን ጩኸት) የሳዑዲ የቦምብ ድብደባና በየመን የሚኖሩ ከ200 ሺህ የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ (ቃለምልልስ ከጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት ጋር) – ያድምጡት appeared first on Zehabesha Amharic.

” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ” አንጀሊና * ዘሐራ ጥቁር አልማዝ ሆና ነጯን እናት ስታደምቅ

$
0
0

-ነቢዩ ሲራክ

ለማፍቀር መፈቀር ፣ ሰው ለመርዳት ሰው መሆን ግድ ይላል ! ይህ ተፈጥሯዊ ህግ ሆኖ በሁላችንም ላይ ባይሰረጽም የታደሉት ሲሆኑትና ሲታደርጉት ከማየት አልፎ የድካማቸው ፍሬ አፍርቶ ሲያዩት ምስክር እማኝ መሆን መታደል ነው ። መልካም መስራት ለራስ ነው እንዲሉ ውስጥን ከሚሰጠው እርካታ ባሻገር የታደሉት የዘሩት አሽቶ መልካም ስራቸው በስኬት ጎዳና ሲታይና በውጤት ስኬቱ ሲደምቁ ማየት ከምንም በላይ ያስደስታል ። በአንጻሩ መልካም ሰርተው እጃቸው ” አመድ አፋሽ ” የሆኑንም አለማችን ከማስተናገድ አልቦዘነችም ። የአማድ አፋሽነቱ ህመም ጥልቆ ቢያመም የሰሩት ለውስጥ እርካታ ነውና ሁሉምም የሚያየው አንድ ፈጣሪ ፍርድ ይሰጣልና ህመሙ ህመም አይባልም ። አድርጎ “አመድ አፋሽ ” መሆን ክሽፈት ነው ከተባለ ምድራዊ ጊዜያዊ ክሽፈትነት ፈቀቅ አይልም ፣ የመልካምነት ሰማያዊ ጸጋቸው ሰፊ ነውና እኒህም የታደሉ ናቸው !
angelina jolie
የዛሬዋን አጠር ያለች የማለዳ ወጌን እንድሞነጫጭር ምክንያት የሆነኝ ትናንት መጋቢት 20 ቀን 2007 የልጆች ምርጫ Nickelodeon’s 28th Annual Kids’ Choice የተሰኘውን አመታዊ የሽልማት ስነ ስርአት አዋርድ በማሸነፍ ተሸላሚ የሆነችው የኦስካር አሸናፊዋ ድንቅ ተዋናይት አንጀሊና ጆሊ ሽልማት አይደለም። ሰብዕናዋ ፈቅዶ የዘራችው አጎምርቶ ለደስታዋ ድርብ ደስታ መሆኑን በማየቴ እንጅ …ቅዱስ መጽሐፉ ” የዘራቸውን ታጭዳላችሁ! ” እንዳለው ከመከራው ኑሮ አቅፋ ደግፋ ያሳደገቻቸው ልጆቿ በአሳዳጊ እናታቸው አንጀሊና ጆሊ ማሸነፍ እየፈነደቁ ሲያቅፉና ሲስሟት የተሰማኝ የደስታ ስሜት ለመግለጽ ያህል ነበር ብዕሩን መጨበጤ …

የተጨበጨበላት ድንቋ የፊልም ተዋናኝ ፣ ደራሲና በጎ አድራጊዋ አንጀሊና ጆሊ ሽልማቷን ስትቀበል ባሰማችው ንግግር ” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ” ነበር ያለችው … አዎ ልዪነተ መልካም ነገር ነው ! አንጀሊና እንዳለችው ልዩነት መልካም ነገር ነው ፣ ልዩነት ጌጥ መሆኑን አምኖ በሚያስማማው ነገር ተስማምቶ መኖር ይቻላል ።
angelina_jolie_zhara
አንጀሊና እንደ ፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር በ2005 ወደ ኢትዮጵያ መጥታ በጉዲፈቻ ወስዳ ያሳደገቻት ዘሐራ ተለውጣለች ። እነሆ አሳዳጊ እናቷ ስትሸለም ከእቅፍ ወርዳ ከጎኗ ተቀምጣ ደስታዋን የምትጋራ የጥቁር አልማዝ ሆና ነጯን እናት አድምቃታለች ” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ” እኔም እላለሁ በፍቅር እንድትዋጅ ፍቅርን ስጥ … ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው ” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ”

ደስ ሲል: )

ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 21 ቀን 2007 ዓም

The post ” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ” አንጀሊና * ዘሐራ ጥቁር አልማዝ ሆና ነጯን እናት ስታደምቅ appeared first on Zehabesha Amharic.

የቴድሮስ አድሃኖም ዋና አማካሪ የሃሰት ፕሮፌሰር መሆናቸውን አበበ ገላው አጋለጠ

$
0
0

አዲስ ቮይስ– የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤትና የሚኒስትሩ ዋና አማካሪ እንዲሁም የፖሊሲ ጥናትና ትንተና የበላይ ሃላፊ የሆኑት “ፕሮፌሰር” መኮንን ሃዲስ የሃሰት ፕሮፌሰር እደሆኑ አዲስ ቮይስ ባካሄደው እረዘም ያለ ምርመራ ማረጋገጥ ችሏል።። ግለሰቡ ለ15 አመታት በፕሮፌሰርነት አገልግየዋለሁ የሚሉት አንድ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ እንደማያውቃቸው የገለጸ ሲሆን የዶክትሬት ዲግሪ ያገኙበት ተቋምም በአሜሪካ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት “የዲፕሎማ ወፍጮ” (diploma mill) ተብሎ የተፈረጀ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
Mekonnen Haddis
“ፕሮፌሰር” መኮንን ሃዲስ ከኦክቶበር 2010 ጀምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋና አማካሪ ሆነው በመንግስት የተሾሙ ሲሆን አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩ ወቅት ዋና አማካሪያቸው ሆነው ያገለገሉት እኚሁ ግለሰብ በአሁኑ ግዜ የዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ዋና አማካሪ እንዲሁም የፖሊሲ ጥናትና ትንተና ክፍል የበላይ ሃላፈ ሆነው በመስራት ላይ ይገኛሉ።

“ፕሮፌሰር” መኮንን ለረጅም አመታት በአሜሪካን አገር ሜሪላንድ ውስጥ የኖሩ ሲሆን በዚሁ ግዛት ውስጥ በሚገኘው ባዊ ስቴት ዩኒቨርሲቲ (Bowie State University) ለ15 አመታት ያህል በፕሮፌሰርነት ማገልገላቸውን በይፋ ሲናገሩ ቆይተዋል። ከዚህም በተጨማሪ በካሊፎርኒያ ፓስፊክ ዌስተርን ዩኒቨርሲቲ በሚል ስም ይንቀሳቀስ ከነበረ ተቋም የዶክትሬት ዲግሪ ማገኘታቸውን በተለያየ ግዚያት ሲገልጹ የነበረ ቢሆንም ዩኒቨሲቲው ዲግሪ ያለ ምንም ትምህርት እንደሚሸጥ በአሜሪካ ሴነት ትእዛዝ በተካሄደ ስምንት ወራት በፈጀ ምርመራ ከተረጋገጠበትና “የዲፕሎማ ወፍጮ” በሚል ስያሜ ከተፈረጀ በሁዋላ እአአ 2005 መዘጋቱን ለማወቅ ተችሏል። ምርመራው በተጨማሪም ኬኔዲ ዌስተርን ዩኒቨርሲቲ፣ ሃሚልተን ዩኒቨርሲቲ እና ካሊፎርንያ ኮስት ዩኒቨርሲቲዎች ዲግሪ ያለ ትምህርት የሚቸበችቡ ወፍጮ ቤቶች መሆናቸውን ይፋ አድርጎ እንደነበር እጃችን የገቡ መረጃዎች አረጋግጠዋል።

ይሄው በካሊፎኒያ ግዛት ይንቀሳቀስ የነበረውና የተዘጋው ዩኒቨርሲቲ የባችለር ዲግሪ በ $2295፣ የማስተርስ ዲግሪ $2395፣ እንዲሁም የዶክትሬት ዲግሪ 2595 ዶላር ይሸጥ እንደነበር ለህግ መወሰኛው ም/ቤት በልዩ ምርመራ ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር በነበሩት ሮበርት ክሬመር የቀረበው ሪፖርት አረጋግጧል።

ለአስራ አምስት አመታት በፕሮፈሰርነት አገለገልኩት የሚሉት ባዊ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የግለሰቡን ፕሮፌሰርነትም ይሁን ቅጥር ጉዳይ እንደማያውቅ ለአዲስ ቮይስ ገልጿል። አዲስ ቮይስ በጉዳዩ ላይ መረጃ ከዩኒቨርሲቲው ለማግኝት በጠየቀው መሰረት የዩኒቨርሲቲው የሰው ሃይል አስተዳደር ከፍተኛ ዳይሬክተር የሆኑት ሼይላ ሆብሰን በሰጡት ምላሽ ዩኒቨሲቲው በአሁኑ ወቅትም ይሁን ቀደም ባሉ አመታት መኮንን ሃዲስ የሚባል የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር እንደማያውቅ አስታውቀዋል።

አዲስ ቮይስ በጉዳዩ ላይ መረጃ ከዩኒቨርሲቲው ለማግኝት በጽሁፍና በስልክ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት የዩኒቨርሲቲው የሰው ሃይል አስተዳደር ከፍተኛ ዳይሬክተር የሆኑት ሼይላ ሆብሰን በሰጡት ምላሽ ዩኒቨሲቲው አሁንም ይሁን ባለፉ አመታት በፕሮፌሰርነት ይሁን በሌላ ደረጃ መቀጠራቸውን የሚያሳይ ምንም መረጃ መግኘት አለመቻሉን በኢሜይል በላኩት ምላሽ አሳውቀዋል። ዳይረክተሯ የዩኒቨርሲቲው የሰው ሃይል አስተዳደር ክፍል ከኮምፒውተር ሰነዶች በተጨማሪ በወረቀት የያዛቸውን የመረጃ ክምችቶች ፈትሸው መኮንን ሃዲስ የሚባል ሰው የፕሮፌሰርነት ሹመትም ይሁን የቅጥር ማስረጃ ማግኘት አለመቻላቸውን አስረድተዋል።

አዲስ ቮይስ ባቀረበረበው ተጨማሪ የስልክ ጥያቄ መሰረት ፕሮፌሰሩ የተለያዩ ኮርሶችን አስተምርበት ነበር ያሉትን የታሪክና የስነ መንግስት የትምህርት ክፍል ሊቀመንበር የሆኑትን ፕሮፌሰር ሳሚ ሚለርን ዳይሬክተሯ ጠይቀው የተሩዱት መኮንን ሃዲስ አንድ ወይንም ሁለት ሴሜስተር ለሚሆን ግዜ ከረጅም አመታት በፊት በረዳትነት ማስተማራቸውን ብቻ እንደሚያውቁ አረጋግጠውላቸዋል። ዳይሬክተሯ ዩኒቨርሲቲው ውስጥ በተለያዩ ግዚያት ለአጭር ግዚያት በረዳትነት የሚያስተምር ማንኛውንም ግለሰብ እንደ ዩኒቨርሲቲው ተቀጣሪ እንደማይቆጥር ገልጸዋል። በትምህርት ክፍሉ እንደ ፕሮፌሰር ሚለር ከሰላሳ አመታት በላይ ያገለገሉት ፕሮፌሰር ዊሊያም ሌውስ በበኩላቸው መኮንን በዩኒቨርሲቲው የማስተርስ ዲግሪ ተማሪ እንደነበር አስታውሰው ትምህርቱን ካጠናቀቀ በሁዋላ ለጥቂት ግዚያት ብቻ የተወሰኑ ኮርሶችን በረዳትነት ማስተማሩን አስታውሳለሁ በማለት የመኮንን ሃዲስን ለአስራ አምስት አመታት የዘለቀ የፕሮፌሰርነት አገልግሎት ትክክል አለመሆኑን አረጋግጠዋል።
ፕሮፈሰሩ ለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጡ ያደረግነው ሙከራ ሳይሳካ የቀረ ሲሆን በስራ ላይ መጠመዳቸውን ካስረዱ በሁዋላ “Leave me alone!” በማለት ስልኩን ዘግተዋል። ወደ ኢትዮጵያ በኤክስፐርት ደረጃ ግብረገብ፣ ዴሞክራሲ፣ የግጭት ማስወደድና ተዛማጅ ጉዳዮችን በተመለከተ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና፣ መንግስታዊ ድርጅቶች እየተዘዋወሩ እውቀት ለማካፈል በ2007 ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት መኮንንን ሃዲስ አለም አቀፍ የገጣሚያን ማህበር በአለፉት መቶ አመታት ውስጥ በአለማችን ከተገኘኑ ምርጥ አንድ መቶ ገጣሚዎች አንዱ ነህ ብሎ አክብሮኛል በማለት በይፋ ተናግረው እንደነበር በጋዜጦች ተዘግቦ ነበር። በ ኦክቶበር 2007 የወጣው “ዴይሊ ሞኒተር” ጋዜጣ ፕሮፌሰሩ በበርካታ መቶዎች በሚቆጠሩ ግጥሞቻቸው እንደሚታወቁ መናገራቸውን ከመጥቀስ አልፎ በአለፉት መቶ አመታት ውስጥ ከተከሰቱ ”100 ምርጥ የአለማችን ገጣሚያን አንዱ” በማለት የአለም አቀፍ የገጣሚያን ማህበር የሚባል ድርጅት እንደሰየማቸው ዘግቧል።

ይሁንና ጉዳዩን ለማጣራት ባደረግነው ጥረት በአሁኑ ግዜ የተዘጋው ይህ ድርጅት ሃሰተኛ የሆኑ የግጥም ውድድሮችን በማኪያሄድ አብዛኛውን ተወዳዳሪ በማጭበርበር በርካታ አቤቱታ ቀርቦበት የነበረ ሲሆነ ድርጅቱም ሌላ የንግድ ተቋም መሸጡ ታውቋል።
—-
ጥቆማና ጠቃሚ መረጃ ለመላክ ይህን ኢሜይል ይጠቀሙ editor@addisvoice.com

ተያያዥ መረጃዎች
Related links
Professor Mekonnen Haddis: Chief Advisor of the Ministry (MoFA biography)

http://www.mfa.gov.et/abtMnstrMore.php?pg=20

Biography: Screenshot

http://addisvoice.com/wp-content/uploads/2015/03/bio.png

Ethiopia: Media Behavior During Election 2005 ‘Shameful’ U.S. Scholar (Copy)

http://addisvoice.com/wp-content/uploads/2015/03/All-africa-monitor.pdf

Report on Degree Mills, U.S. Senate, Robert J. Cramer, Director Office of Special Investigations

http://addisvoice.com/wp-content/uploads/2015/03/Pacific-Western-Univesity.pdf

The Contester: Poetry.com Struggles for Legitimacy

http://www.pw.org/content/contester_poetrycom_struggles_legitimacy

Political Snapshots (Mekonnen Haddis’ blog)

http://addisvoice.com/wp-content/uploads/2015/03/Mekonnen-Haddis-Blog-screenshot.pdf

The post የቴድሮስ አድሃኖም ዋና አማካሪ የሃሰት ፕሮፌሰር መሆናቸውን አበበ ገላው አጋለጠ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከፍትፍቱ አጉሩሱኝ ከመረቁ ፃመኛ ነኝ –ቢንያም ግዛው (ከኖርዌይ ኦስሎ)

$
0
0

Biniamየብዙሀኑ  የጣት ሽታ  እንደገደፈ ያሳብቃል። በጥቂትም ሆነ በብዙ ያልተነካካ ቢፈለግ በግራም ሆነ በቀኝ ቢነፍስ ፃሙን ያላፈረሰ ማግኘት አልተቻለም።ከፍትፍቱ አጉሩሡኝ ከመረቁ ፃመኛ ነኝ ብሎ እንክት አድርጎ ከሰለቀጠ ወዲያ ምንም  እንዳልገደፈ አፉን ጠረግ ጠረግ አድርጎ ባላየ ባልሰማ የሚጓዘው ተበራክቷል።  በዕንዶድም የማይነፃ ጣት! ከምን አይነት መረቅ ውስጥ ቢዘፈቅ ይሆን ? . . . ጠቢቡ ሠሎሞን በምሳሌው . . .  ስጦታ በስውር ቍጣን ታጠፋለች፥ የብብትም ውስጥ ጉቦ ጽኑ ቍጣን ታበርዳለች ያለው ትዝ አለኝ በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያን የባለስልጣን ቢሮዎችን ሳስባቸው ምን ቢያምራቸው እንኳን  ምራቃቸውን ገርገጭ አርገው ውጥው ስርዓቱ እና ህጉን በማክበር ቢፃሙ ምን አለ?  ሁሉም ቢሮ ስጋ ስጋ ደም ደም ነው የሚሸተው። በፃሙ!

 

ትምህርት ሚኒስቴር፣ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ ፍትህ ሚኒስቴር፣ ፌዴራል ፖሊስ ፣ ወህኒ ቤት፣ ሆስፒታል፣ ባንክ ቤቶች፣ ወ ዘ ተ . . . መጥቀስ እስኪታክት ድረስ ሁሉም በዋና ዋና  የሀጢያት አበጋዞች ተዘፍቀዋል። በተለይም በወያኔ ዘመን ያለቅጥ ተንሰራፍቶ የሚገኘው  ብዙ በደለኞችን ፃድቅ አድርጎ ፍርድን እና ፍትህን በማጣመም አይን የሚያስውረው በሽታ   ምድሪቷን ጠፍንጎ ከመግቢያው የግሙሩክ መስሪያቤት ጀምሮ እስከመውጫው ኢሚግሬሽን ድረስ በጉቦኝነት ጠፍንጓታል። በኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔ እስካለ ድረስ ሀቀኛ ነኝ አልነካካም  ብትል እንኳን ብዙም ሳትሔድ በቀላሉ በጥንቃቄ እያሽከረከርክ በምትነዳበት መንገድህ ላይ የሸሚዙ ቁልፍ እስኪፈናጠር በላይ በላይ የሚበላው ትራፊክ ፖሊሱ እቁብ ስለደረሰበት ብቻ ፊሽካውን ነፍቶ ሲያስቆምህ ከመንጃ ፈቃድህ ይልቅ የመቶ ብር ኖቶችን ማዘጋጀቱ ብቻ ነው መገላገያ መንገዱ።በቃ ፃምህን ያስገድፉሐል።  በዚህ ውስጥ ያልተነከረ እና ያልተዘፈቀ  እጁን ያሳይ? . . . የተነከረበት ከሩቅ የሚሰነፍጠው መረቁ ምስክር ነው ። በጉቦ መረቅና  በሙስና የተዋዛ ጣት !

 

እጅ የሚስቆረጥም የፍትፍት ጉርሻ ፅኑ ቁጣን እንደምታበርድ ፥ የንፁሐንን ቃል እና ፍርድ በጉቦ ተጣሞ  ለማይገባቸው ሲፈረድላቸው ማየት አዲስ ነገር አይደለም። በተለይም ድንገት አዲስ እንደተወለደ ህፃን ከዚህ በፊት ሳይታዩ ከባዶ ካፒታል ላይ ተንደርድረው ከናጠጠ ሀብት ጋር ብቅ የሚሉት ቱጃሮች የሀብታቸው ምንጭ ከየት እንደፈለቀ ለማወቅ ግልፅ ሆኖ ሳለ ከባለስልጣናቱ ጋር በመሞሳመስ የሚያደራጁያቸው የተለያዩ የንግድ ሂደቶችም በፌደራሉ ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምንም አይነት ክትትል  ሊደረግባቸው የማይችልበት  ዋናው ምክንያት ባለስልጣናቱ ከላይ እስከታች እያንዳንዱን ተጠያቂ ስለሚያደርጋቸው እና ክትትል አድራጊውም ሆነ ድርጊቱን ፈፃሚው ከአንድ ወንዝ የተቀዱ ስለሆኑ ነው። ቢሆንም የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣኑ ባለቤት ሆኖ ይህ አገዛዝ ለፍርድ እስከሚቀርብበት ጊዜ  ድረስ  አንድነትን በመጠበቅ በፅናት እና  በትዕግስት ለሐገሪቷ ነፃነት እየታገሉ መቆየት የእያንዳዳችን ድርሻ ሊሆን የተገባ ግዳጃችም ነው።

 

እያልኩ ያለሁት ለምን ሰው ባለጠጋ ሆነ አይደለም። ይልቁንም የፖለቲካን የበላይነት እና ባለስልጣን መሆንን ተገን አድርጎ የሚደረግ  የሀገርን  ሀብት የመዝረፍ ወንጀል ከአውራነቱ የተነሳ  በምድሩም ሆነ በሰማይ  በሚሰየመው ችሎት እንደሚያስጠይቅም ለማሳሰብ ጭምር እንጂ። በተጨማሪም በኢትዮጵያ ከተከሰቱት ታላላቅ መፍትሔያቸው የራቁ የኑሮ ቀውሶች መካከል ለሰው ልጅ መኖር መሰረታዊ  የሆኑትን ብቻ    ለመገብየት ከዋጋው ግሽበት የተነሳ የሀገሪቱ የገንዘብ ጉልበት  እጅግ ደቃቃ  ሆኖ አቅም የለሽ በሆነበት፣ ስራ አጥነት ተበራክቶ ብዙሀን የወጣቱ ክፍል ህይወቱን ያጣበት የበረሀ ጉዞ እና በባህር ሰጥሞ አስከመቅረት  ዋጋ የሚይስከፍሉ የስደት አይነቶች ህዝብ እንዲጋለጥ፣ ወላጅ እየተጦረ እፎይ ብሎ በሚያርፍበት የሽምግልና ዘመኑ ለልመና ሰው ፊት የቆመበት እንዲሁም በብዙ ምሬት ውስጥ በመሆን ለተጎነበሰበት እና በምድሪቷ ላይ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሙስና ባህል እስኪመስል ድረስ በእጅጉ ተንሰራፍቶ ጥላውን እንዲያጠላ እና እንዲባባስ ገዢው ብድን ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። እየተጫወተም ይገኛል። አምባገነናዊነት፤ እብሪት፤

ግትረኛነትና ትምክህተኛነት በከባድ የተጠናወተው ቡድንተኛ መሪ የሃገሪቱንም ሆነ የህብረተሰቡን አንጋፋ ችግሮች በጋራ ተመካክሮ፤ የፖለቲካ ስልጣንን በመካፈል ፤ የሕዝቡን ድምጽ አክብሮ፤ በተለይ ሀገር ተረካቢውን ወጣቱን ትውልድ ፍላጎት ለማሟላት በሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫ  በእኩልነት ለመስራት የተዘጋጀ አይደለም። አቅሙም ልቡም የለውም። ይልቁንም የአብዛኛው ህብረተሰብ የኑሮ ሁኔታ ወደ ማጡ አባብሶታል። ይህ የአንድ ብሔር ብቻ ወገንተኛ  የፖለቲካ ብድን ፤ የኢትዮጵያን ህብረተሰብ እና የተለያዩ ብሔሮችን ግልፅ በሆነ አሰራር ሳያካትት የሀገሪቷን አንድነት  ባልጠበቀ ዘመቻው በአደገኛ ሁኔታ በሙስና እና በተለያዩ ጤናማ ባልሆኑ አካሄዶቹ የህዝቡን ኑሮ ከስሩ አናግቶታል። የጉቦኛነት ተስቦ ሳያንሰው ከሁሉም በላይ አዲሱ ትውልድ በኢትዮጵያዊነት ሳይሆን በጠባብ ጎሰኛነት  እንዲያምን በሚያደርገው ርብርብ ኢትዮጵያዊነት ከቶውንም ተሽሮ ብሔርተኝነት እንዲያብብ  የማያቋርጥ ተጋድሎ እያደረገም ጭምር ነው።

 

የሙስናው እንቅስቃሴ እና  ተግዳሮት  ለሀገርና ለህዝብ ጠንቅ መሆኑ አለም ሁሉ የሚስማማበት ስለሆነም በተለይም ደግሞ ሰላም በሰፈነባቸው  ሀገሮች ይህ ድርጊት እንደ ትልቅ ውርደት የሚታይ እና በአንዳንዶች ዘንድ ፈፅሞ የማይታወቅ ተልካሻ ስርዓት ነው። ዛሬ የስቃይ ኑሮ ገፈት ቀማሽ ያደረገን ወያኔ ከፅንሰቱ ጀምሮ እጁ ከሙስና ሳይፆም የረከሰ በመሆኑ ምክንያት አባላቱን እንኳን ሲመለምል ቀድሞውንም ስለ ኢትዮጵያ በመቆም ለትግሉ በእውነተኛነት አሳምኖ ሳይሆን በፍቅረ ንዋይ የተቃጠሉትን በማማለል ከድል ማግስት የሚገኘውን ሀብት በማለም ብቻ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ለዚህም ነው ዛሬ በሀገራችን የተማረው  ክፍል በሙያቸው፣ በዲግሪያቸውም ሆነ በልምድ እውቀታቸው ሰርተው ሀገር የሚያለሙበት  መንገዱ ሁሉ ቢዘጋጋባቸው ለመኖር ሲሉ የግዳቸውን ከባለስልጣናቱ ጋር የተለያየ አይነት የሙስና መንገዶችን ለማጠቀም የሚገደዱት።

 

በኢትዮጵያ ከኖርክ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ለመኖር ስትል ጉቦ ትሰጣለ ወይም ታበላለህ። በዕጅ ማለት ብርቅ አይደለም። ከዘበኛው ጀምረህ ባለስልጣኑን እስክታገኘው ድረስ ሁሉን እያጉረስክ ማለፍ የግድ ነው። ለምሳሌ የገንዘብ ተመን ከወጣላቸው ጉቦኝነት መሀከል የመኪና መንጃ ፈቃድ ለማውጣት የሚከፈለው ክፍያ ነው። ካልሰጠህ መንጃፍቃድ የምይታሰብ ጉዳይ ነው ፥ ሊያውም ዳጎስ ያለ እንደሆነ ደግሞ ያሉበት ድረስ ይመጣልዎታል። ይህም ሂደት ሀገሪቷን ለከፍተኛ የመኪና አደጋ አጋልጦ ሰጥቷታል። በመሬት ንግዱ ዙሪያ እና የፃድቁን ውሳኔ ለማጣመም በፍርድ ቤቶች   የሚከፈሉት የዳጎሱ ጉርሻዎች ሐገር ሁሉ የሚያውቀው ራቁትነት ነው። የተማረው፥ፊደል የቆጠረው በደጅ ሆና ተስፋ ቆርጦ ሲማረር እና ፀሀይ ሲበላው ሌላው ዘሩን ጠርቶ የግንባሩን ምልክት አሳይቶ ለምሁሩ የተዘጋበትን በር አስከፍቶ ዘው ይልበታል። ለዚህ ሁሉ ውድቀት ዋናው  ምክንያቱ  ባለቤት እና እውነተኛ መሪ በሌላት ሀገር ላይ  የመንግስት ተቋማት ከፍትፍቱ አጉሩሱኝ ከመረቁ ፃመኛ ነኝ በማለት ሳይነክሱ መኖር አቅቷቸው ለሙስና በመዘፈቃቸው ብቻ ነው፡፡

 

ጉቦኝነት ሁሉን ዳሶታል ። ፈተናውን ሁሉ ለመለፍ ወይ ገንዘብ አሊያም እንደ ባለስልጣናቱ  ጥያቄ መሰረት ፍላጎታቸውን ማርካት የተለመደ ቢሆንም ይህን ሀገርን ወደኋላ የሚጎትት አሰራር ከስሩ ለማድረቅ ኢትዮጵያውያን የሆንን ሁሉ ለሀገራችን ነፃ መውጣት የምንከፍለው ሌላ ክፍያ አለ። በሁሉ አቅጣጫ አንድነታችንን በማጉልበት ለወያኔ አገዛዝ በእንቢተኛነት መጋፈጥ! ብሔር ከሀገር አይበልጥምና  የጎሰኝነትን እና የብሔርተኝነትን የመለያየት መርዝ አርክሰን በአንድነት መቆም!

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።

ቢንያም ግዛው (ከኖርዌይ ኦስሎ)

 

 

 

 

The post ከፍትፍቱ አጉሩሱኝ ከመረቁ ፃመኛ ነኝ – ቢንያም ግዛው (ከኖርዌይ ኦስሎ) appeared first on Zehabesha Amharic.

በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በተከሰሱት ጦማሪያንና ጋዜጠኞች ላይ ምስክሮች መሰማት ጀመሩ

$
0
0

zone 9 bloggersየፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የሽብርተኝነት ክስ በመሠረተባቸው ጦማሪያንና ጋዜጠኞች ላይ ምስክሮቹን ከመጋቢት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ማሰማት ጀመረ፡፡

ዓቃቤ ሕግ መጋቢት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ባስያዘው ጭብጥ፣ በዕለቱ ያቀረባቸው ምስክሮች የደረጃ ወይም ታዛቢ ምስክሮች መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድቶ፣ የሚመሰክሩትም ፖሊስ በተከሳሾቹ ቤት፣ በቢሮአቸውና በማዕከላዊ ምርመራ ቢሮ፣ ከተከሳሾቹ ላይ የተገኙ ማስረጃዎች የእነሱ መሆናቸውን አምነው ሲፈርሙ ማየታቸውንና እነሱም መፈረማቸውን መሆኑን ገልጿል፡፡

ታዛቢ ምስክሮቹ አንዳንዶቹ ለግል ጉዳያቸው በፌዴራል ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) ሄደው ፖሊስ ታዛቢ እንዲሆኑለት ሲጠይቃቸው፣ በፈቃደኝነት የታዘቡ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ተከሳሾቹ ከራሳቸው ላፕቶፕ ላይ (አንዳንዶቹ) የአማርኛና እንግሊዝኛ ጽሑፎችን ማየታቸውንና ርዕስ ርዕሱን ማንበባቸውን ገልጸዋል፡፡ አቤል ዋበላ የተባለው ጦማሪ በራሱ የይለፍ ቃል (Pass Word) ላፕቶፑ ተከፍቶ የታተመ ‹‹አፍሪካን ሪቪው›› የሚል በእንግሊዝኛ የተጻፈ ነገር ማየታቸውን መስክረዋል፡፡ ‹‹ወያኔ ወይኔ ጉዱ›› የሚል ርዕስ ያለው ጽሑፍ ደግሞ የበፈቃዱ ኃይሉ ላፕቶፕ ተከፍቶ ሲታተም ማየታቸውን መስክረዋል፡፡

አንድ ታዛቢ የታዘቡትና ምስክር የፈረሙት በጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ ላይ መሆኑን ቢገልጹም፣ አስማማውን ከስም በስተቀር በአካል መለየት አቅቷቸዋል፡፡

ቀረብ ብለው እንዲለዩት ቢደረግም ጦማሪ አቤል ዋበላን ‹‹እሱ ነው›› ብለው ደጋግመው ከመናገር ያለፈ አስማማውን መለየት ባለመቻላቸው የችሎት ታዳሚውን አስፈግገዋል፡፡ ሌሎቹም ምስክሮች ተመሳሳይ ምስክርነት በመስጠት ተከሳሾቹ ከፈረሙ በኋላ እነሱም በሰነዱ ላይ መፈረማቸውን ገልጸዋል፡፡

ስድስት ምስክሮችን መጋቢት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ያሳማው ዓቃቤ ሕግ፣ መጋቢት 22 ደግሞ ስምንት ምስክሮችን አቅርቦ ሰባቱን አሰምቷል፡፡ ሁሉም ተመሳሳይነት ያለው ቃል መስክረዋል፡፡ ቀሪዎቹ ምስክሮች መጥሪያ ደርሷቸው ባለመቅረባቸው ታስረው እንዲቀርቡለት፣ ሌሎች ምስክሮችን ፖሊስ ፈልጎ ሊያገኛቸው ባለመቻሉ፣ ተጨማሪ ጊዜ ተሰጥቶት አፈላልጎ እንዲያቀርብ ጠይቋል፡፡

የተከሳሾች ጠበቆች የዓቃቤ ሕግን ጥያቄ ተቃውመዋል፡፡ ፖሊስ አፈላልጎ ስለማጣቱ ዓቃቤ ሕግ ምንም ማስረጃ ባላቀረበበት፣ ተለዋጭ ቀጠሮ መጠየቁ አግባብ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ መጥሪያ ደርሷቸው ያልቀረቡትም ቢሆኑ በአዳር እንዲቀርቡ እንዲታዘዝላቸው ጠይቀዋል፡፡ በአጠቃላይ ተከሳሾቹ የሰነድን ማስረጃ በሚመለከት ስላልካዱ እነሱን በእስር አቆይቶ እንዲንገላቱ ከማድረግ ያለፈ ፋይዳ ስለሌለው፣ ዓቃቤ ሕግ ተመሳሳይነት ያላቸው ምስክሮቹን ማሰማቱን አቋርጦ ወደ ቀጣይ ማስረጃ መስማት እንዲጀመር ጠይቀዋል፡፡

ዓቃቤ ሕግ መጋቢት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ምስክሮቹን ከማሰማቱ በፊት አቤቱታ እንዳለው አመልክቶ ፍርድ ቤቱ ሲቀበለው፣ በምስክሮች ጥበቃ አዋጅና በፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652 2001 አንቀጽ 32 መሠረት ‹‹ምስክሮቼ ለደኅንነታቸው ስለሚሰጉ ምስክርነቱ በዝግ ይታይልኝ፤›› ብሎ አመልክቷል፡፡

ዳኞቹ ተመካክረው በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 20 መሠረት በዝግ የሚታዩ ጉዳዮች ተዘርዝረው ከመቀመጣቸው አንፃር፣ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው አቤቱታ አሳማኝ አለመሆኑን በመንገር አቤቱታውን ወድቅ አድርገውበታል፡፡

በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ መጋቢት 22 ቀን 2007 ዓ.ም. በሰጠው ትዕዛዝ ፖሊስ ያላገኛቸውን ምስክሮች ፈልጎ እንዲያቀርብና መጥሪያ ደርሷቸው ያልቀረቡት ምስክሮች ታስረው ለመጋቢት 30 ቀን 2007 ዓ.ም. እንዲቀርቡ ቀጥሯል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

The post በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በተከሰሱት ጦማሪያንና ጋዜጠኞች ላይ ምስክሮች መሰማት ጀመሩ appeared first on Zehabesha Amharic.


ለሆቴሎች ደረጃ ለመስጠት የምዘና ሥራ ሊጀመር ነው

$
0
0

hiltonየባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ በአገሪቱ ለሚገኙ ሆቴሎች በአዘጋጀው መሥፈርት በመለካት፣ የኮከብ ደረጃ ለመስጠት የግምገማና ምዘና ሥራ እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ ቱሪዝም ፈቃድ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ታደሰ እንዳይላሉ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የአገሪቱን ሆቴሎች የሚመጥናቸውን የኮከብ ደረጃ ለመለካት በተመድ የዓለም ቱሪዝም ድርጅት ተዘጋጅቶ በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ በቅርቡ በፀደቀው በመሥፈርት መሠረት ሚያዝያ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ይጀመራል፡፡

ለሆቴሎች ደረጃ የመስጠት ኃላፊነት የተሰጠው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ነው፡፡ ሚኒስቴሩ በተለያዩ ጊዜያት ደረጃ ለማውጣት እየሞከረ ከሽፎበታል፡፡ ባለፈው ዓመት ይህን ሥራ ለዓለም ቱሪዝም ድርጅት መስጠቱ ይታወሳል፡፡

ዳይሬክተሩ እንደገለጹት፣ አሰጣጡ የዘገየበት ምክንያት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጨረታዎች አፈጻጸም ምክንያት ነው፡፡ የጨረታ ሒደቱ ሁሉ አልቆ ደረጃ የማውጣቱ ሥራ ለዓለም ቱሪዝም ድርጅት መሰጠቱን ያስታወሱት አቶ ታደሰ፣ በዚህ ድርጅት መሥፈርት መሠረት አገር በቀሎቹም ሆነ ዓለም አቀፍ ሆቴሎች ይገዛሉ ብለዋል፡፡

በመላው አገሪቱ የሚገኙ 600 ሆቴሎች እንደሚያሟሏቸው መሥፈርቶችና እንደ አገልግሎት ብቃታቸው ተመዝነው በሚያገኙት ውጤት መሠረት፣ ደረጃዎቻቸውን እንደሚያገኙ ይጠበቃል ሲሉ አቶ ታደሰ ገልጸዋል፡፡ በዚህም መሠረት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት በአዲስ አበባ የሚገኙ 400 ሆቴሎችን እስከ ግንቦት 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ባሉት 45 ቀናት ውስጥ እንደሚያጠናቅቅ ለሪፖርተር የገለጹት አቶ ታደሰ፣ በክልል ከተሞች የሚገኙት 200 ሆቴሎች ደግሞ በሚኒስቴሩና በክልል ቢሮዎች በጋራ እንደሚከናወን ጨምረው አስረድተዋል።

ለሆቴሎቹ የደረጃ ምደባ መሥፈርቶችን የመገምገም ሥራ ለሚያከናውኑ ባለሙያዎች ተገቢውን ሥልጠና በአሁን ወቅት እየተሰጠ መሆኑን የሚገልጹት አቶ ታደሰ፣ የሁሉም ሆቴሎች የግምገማና የምዘና ውጤት ሙሉ በሙሉ ተሰብስቦ ሳያልቅ የየትኛውም ሆቴል ደረጃ ይፋ እንደማይደረግ አስታውቀዋል።

ከወራት በፊት ሚኒስቴሩ ከሆቴል ባለቤቶችና ከመስተንግዶ ኢንዱስትሪው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በሆቴሎች ደረጃ መለኪያና የመመዘኛ መሥፈርቶችን አስመልክቶ፣ የዓለም ቱሪዝም ድርጅት ባቀረበው ረቂቅ ሰነድ ላይ መወያየታቸው ይታወሳል፡፡

በወቅቱ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ታደለች ዳለቾ፣ ለሆቴሎች ደረጃ መስጠት ያስፈለገው ለተጠቃሚዎች ሆቴሎች ያሟላቸውን አስፈላጊ ግብዓቶችና የሚሰጡትን አገልግሎት በተመለከተ ግልጽ ምሥል ለመስጠት ነው፡፡ በተጨማሪም በዘልማድ በኢንዱስትሪው ውስጥ የሚሰጠውን ደረጃ በተሻለ መሥፈርት መዝኖ ለመስጠት ታስቦ መሆኑን ተናግረው እንደነበር ይታወሳል፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የሆቴሎችን የደረጃ አሰጣጥ መሥፈርት የሚያትተው መረጃ እንደሚገልጸው፣ እያንዳንዱ ሆቴል ለደረጃ ምደባው ብቁ መሆን የሚችለው ቢያንስ እስከ አሥር የመኝታ ክፍሎች ሲኖሩት፣ የጤና ጥበቃ አስፈላጊ ሕጎችንና ደንቦችን ሲያከብር፣ ከእሳት አደጋ አስተማማኝና ደኅንነቱ የተጠበቀ ሲሆን፣ አካባቢያዊ መሥፈርቶችን፣ የቆሻሻ አወጋገድና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች ማሟላት ሲችል እንደሆነ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሆቴሉ ያሉት የተማረ ሰው ኃይልና በሥልጠናና በክህሎት መሥፈርቱ ውስጥ የተካተቱ ጉዳዮች ናቸው።

ላለፉት በርካታ ዓመታት ሁሉም ሆቴሎች ለራሳቸው በሰጡት ደረጃ ሲተዳደሩ የቆዩ ሲሆን፣ ይህም የተለያዩ ችግሮችን ሲፈጥር መቆየቱን የሚኒስቴሩ ኃላፊዎች ሲገልጹ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይህ ሁኔታ በገጽታ ግንባታ በኩል የራሱ የሆነ እክል ሊፈጥር እንደሚችል መረዳት እንደሚገባ የሚገልጹም አሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በብራንድ ሆቴልነት የሚተዳደሩት ሸራተን አዲስ፣ ሒልተንና ራዲሰን ብሉ ሆቴሎች ብቻ ናቸው፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

The post ለሆቴሎች ደረጃ ለመስጠት የምዘና ሥራ ሊጀመር ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

የኮሜዲያን አለባቸው ተካ አልባሳትና የግል ቁሳቁስ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙዚየም ተሰጠ

$
0
0

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የቶክ ሾው አዘጋጅና አቅራቢ የነበረው የኮሜዲያን አለባቸው ተካ የግል የመድረክ አልባሳትና የግል ቁሳቁሶች ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ሙዚየም ተበረከተ፡፡
alebachew teka
ለሙዚየሙ የተሰጡት የአለባቸው ተካ የግል ቁሳቁሶች መሃከል የመድረክ ልብሶቹ፤ፎቶግራፎች፤ዋንጫዎች፤መፅሔቶችና የአለባቸውን ተካን ስራና የግል ሕይወት የተካተተበት ዶክመንተሪ ፊልም እንደሚገኝበት የአለባቸው ባለቤት ወ/ሮ ሳባ ሀይሌ ለቁም ነገር መፅሔት ተናግራለች፡፡
አለባቸውን ከዚህ ዓለም የተለየበትን 10 ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የግል መጠቀሚያ ንብረቶቹን ጠብቃ በማቆየት ለሙዚየሙ ያስረከበችው በተለያየ ጊዜ ስለ አለባቸው ጥናትና ምርምር ለማድረግ የሚፈልጉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስለ ስራውና ማንነቱ በተደራጀ መልኩ መረጃዎች በአንድ ቦታ እንዲያገኙ በማሰብ እንደሆነ አስድታለች፡፡

አለባቸው በህይወት በነበረበት ጊዜ የሰራቸውን ስራዎች ከግምት በማስገባት ከታላላቅ ኢትዮጵያውያን ባለታሪኮ ጎን ሆኖ ሥራው ለትውልድ እንዲተላለፍ ዪኒቨርቲው በመፍቀዱ ከፍ ያለ ምስጋናዋን አቅርባለች፡፡

የዛሬ አስር ዓመት ለስራ ወደ ጅማ ከተማ ሲያመራ በደረሰበት የመኪና አደጋ ሕይወቱን ያጣው አለባቸው ተካ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይቀርብ በነበረው ፕሮግራሙ አማካይነት የተረሱ ቀደምት የጥበብ ሰዎችን ከማስታወሱም በላይ የተቸገሩ ወገኖቹን እንዲረዱ በማድረግ ‹የድሃ አባት› የሚል የክብር ስም ማግኘቱ ይታወሳል፡፡ የአለባቸውን ተካን ስራና ህይወት ከሚያሳየው ዶክመንተሪ ፊልም በተጨማሪ የአለቤ ማስታወሻ የተሰኘ ልዩ ፕሮግራም በቅርቡ ለማቅረብ እየተሰራእንደሆነ ወ/ሮ ሳባ አስታውቃለች፡፡

Source: ቁም ነገር መፅሔት 14ኛ ዓመት ቅፅ 14 ቁጥር 200 ልዩ ዕትም\

The post የኮሜዲያን አለባቸው ተካ አልባሳትና የግል ቁሳቁስ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙዚየም ተሰጠ appeared first on Zehabesha Amharic.

‹የማሞኛ ቀን› ወይስ ‹የሞኞች ቀን› / April the fool/

$
0
0

ከቁምነገር መጽሔት

ጓደኛዎ ቢሮ እንደ ገቡ ስልክ ደውሎ ትምህርት ቤት ለመግባት በጠዋት የወጣው ልጅዎ የመኪና አደጋ ደርሶበት ወደ ሆስፒታል መወሰዱን ይነግርዎታል፡፡ ተደናግጠው ጉዳዩን ለአለቃዎ አሳውቀው ወደ ሆስፒታል ሊያመሩ ሲሉ ሌላ ስልክ ይፈልግዎታል ይባላሉ፡፡ የልጅዎ ሳያንስ ሌላ አስደንጋጭ መልዕክት ይደርስዎታል፡፡
april-fool-day
ንዝህላሏ የቤት ሰራተኛዎ በለኮሰችው እሳት ‹‹ቤትዎ እየነደደ ነው›› ይባላሉ፡፡ መኪና ተመድብዎሎት ወደ ቤትዎ ለማምራት ሲዘጋጁ ይኸው ጓደኛዎ ሞባይል ላይ ደውሎ ዕድሜ የጠገቡት ወላጅ እናትዎ ማረፋቸውን ያረዳዎታል፡፡ በድንጋጤ በንዴትና በብስጭት ውስጥ ሆነው ወደ ልጅዎ ት/ቤት ሲሄዱ ልጅዎ በሰላም እየተማረ ነው፡፡ እቤትዎ ሲደርሱ ቤትዎ ሰላም ነው፡፡ እናትዎ ቤት ሲያመሩም እናትዎ በረንዳ ላይ ቁጭ ብለው ፀሐይ ሲሞቁ ያገኘዋቸዋል፡፡

‹‹እንዴት እንዲህ አይነት የጅል ቀልድ ይቀልድብኛል?›› በማለት ወደ ጓደኛዎ መ/ቤት በፍጥነት ይገሰግሳሉ፡፡ ጓደኛዎን ገና ሲመለከቱት በሳቅ ይፈርሳል፡፡ ሁኔታው ግራ አጋብቶዎት ‹‹ምንድነው የምትሰራው?›› ብለው ሲጠይቁት ሳቁን እንደምንም ችሎ ‹‹ዛሬ እኮ ኤፕሪል ዘ ፉል ነው›› ይሎታል በዚህ ጊዜ የሚያዝኑት በማነው? በእርስዎ ጭንቅ በተሳለቀ ጓደኛዎ ወይስ…. የማሞኛ ቀን / April the fool/ በየዓቱ በፈረንጆች ሚዚያ 1 ቀን የሚውል የአውሮፓውያን የቀልድ ልማድ ቀን ነው፡፡ በዚህ ዕለት አውሮፓውያን ወዳጅ ዘመድ ጓደኛን በማሞኘት ነው የሚያሳልፉት፡፡ ለመሆኑ የዚህን ዕለት ታሪካዊ አመጣጥ ያውቃሉ?

እ.ኤ.አ በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ የኖርዌይ ወላጅ የሆነው ሉፍ ሊርፓ /Loof Lirpa/ የተባለ ሳይንቲስት የበረራ ምስጥርን ለማወቅ ጥረት ያደርግ ነበር፡፡ አንድ ቀን ሙከራው ስለተሳካለት በወቅቱ የሀገሪቱ ንጉሥ ለነበረው ለንጉሥ ሄነሪ ስምንተኛ ደብዳቤ ይፅፍለታል፡፡ የደብዳቤ ፍሬ ሃሳብ የበረራ ምስጢርን ተመራምሮ ማግኘቱንና አውሮፕላን ሰርቶ መጨረሱን የሚገልፅ ነበር፡፡ የሙከራውን ድንቅ ውጤት ለህዝብ በትርኢት መልክ ለማሳየት ስለፈለገም በዚሁ ዕትም ንጉሱ የክብር እንግዳ በመሆን የልፋቱን ውጤት እንዲመለከትለት ይጋብዘዋል፡፡ ትርኢቱም የሚቀርብበት ዕለት እ.ኤ.አ ሚያዚያ 1 ቀን 1545 ነበር፡፡

ንጉሱ የሊርፓን ደብዳቤ ካነበበ በኋላ በሳይንቲስቱ የምርምር ችሎታ በመደሰት ታላላቅ ሹማምንቱን አስከትሎ ወደ ትርኢቱ ሥፍራ ይሄዳል፡፡ ለክብሩ በተዘጋጀው ሰገነት ላይ በአካባቢው ከተሰበሰበው ህዝብ ጋር ሆኖ ሳይንቲስቱን መጠባበቅ ጀመረ፡፡ ይሁን እንጂ ሊርፓ በወቅቱ ሳይመጣ ቀረ፡፡ የንጉሱ ባለሟሎች ተጨነቁ ተጠበቡ፡፡ በመጨረሻም ንጉሱም ተናዶ ወደ ቤተመንግሥቱ ተመለሰ፡፡ ለጊዜው የሊርፓ ጉዳይ ምስጢር ሆኖ ቆየ፡፡

ድርጊቱ ሊርፓ ንጉሱን ለማሞኘት ሆን ብሎ ያደረገው አልነበረም፡፡ ሙከራው ሳይሳካለት ቀርቶም አይደለም፡፡ ከጊዜ በኋላ እንደተረጋገጠው ሉፍ ሊርፓ የበረራውን ትርኢት ሳያሳይ የቀረው እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ነበር፡፡ ሊርፓ የክብር እንግዳውና ህዝቡ ወደተሰበሰቡበት ቦታ አውሮፐላኑን እያበረረ ለመድረስ ገና ጉዞ እንደጀመረ ከአንድ ትልቅ ዛፍ ጋር ተላትሞ ህይወቱ ያልፏል፡፡ በዚህ የተነሳም ከሚያዚያ 1 ቀን 1545 እ.ኤ.አ ጀምሮ የሀገሩ ህዝብና አውሮፓውያን አሜሪካውያንም ጭምር የደረሰውን አጋጣሚ መሠረት በማድረግ ልክ እንደ አንድ ልማድ በመውሰድ ዘመድ ወዳጅና ጓደኞቻቸውን በማሞኘት በተሞኙት ላይም በመሳቅ ቀኑን ማክበር ጀመሩ፡፡ በሊርፓ ስምም ከአሣ ከሙዝ ከማርማላታና ከቼኮላት ልዩ ልዩ ኬኮችን በመስራት በመመገብ ያከብሩታል፡፡ አብዛኛዎቹ ግን ቀኑን የሚያከብሩት ሰዎችን በሚያስቅና በሚያዝናና ሁኔታ በማሞኘት ነው፡፡

ይህ ልማድ ከግለሰቦች የእርስ በእርስ ማሞኘት ሌላ በዜና ማሰራጫዎችም አልፎ አልፎ ይደረጋል፡፡ ግን በማይጎዳ መልኩ ነው፡፡ በአንድ ወቅት የቢቢሲ ቴሌቪዥን ጣቢያ በዚያን ዕለት ያቀረበው ዜና ከመሞኘትም አልፎ የሚያጃጅል ነበር፡፡ ጣቢያው እንዳለው ከሜዲትራንያን የባህር ዳርቻ የነፈሰው ነፋስ በዛፍ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሱና የፖስታ ምርት ስለቀነሰ ከፍተኛ የዋጋ ንረት እንዳስከተለ የሚገልፅ ዜና አስተላለፈ፡፡
ይህንን አሰከፊ ዜና የሰማው ህዝብም ከየመደብሮቹ የቀሩትን ፖስታ ለመግዛት ሰልፍ ያዘ፡፡ ህዝቡ በወቅቱ ፖስታ ከዱቄት እንጂ ከዛፍ እንደማይመረት ለማገናዘብ አልቻለም ነበር፡፡ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ጣቢያው ዕለቱ ኤፕሪል ዘፉል መሆኑነ ሲገልፅ ህዝቡ በራሱ ላይ ስቋል፡፡ይህ ልማድ በሰፊው በሀገራችን አይሰፋፋ እንጂ በከተሞች አካባቢ አለ፡፡ ያተደረጉ ያልተከሰቱና አስደንጋጭ ወሬዎችን በስልክም ሆነ በሌላ መንገድ በመንገር ማሞኘት እየተለመደ ነው፡፡ ለማንኛውም በሞኞች ቀን ሞኝ ከመሆን ይሰውረን፡፡ ለመሆኑ የሉፍ ሊርፓ /Loof Lirpa/ ስም ከቀኝ ወደ ግራ ሲነበብ / April fool/ መሆኑን ልብ ብለዋል?

The post ‹የማሞኛ ቀን› ወይስ ‹የሞኞች ቀን› / April the fool/ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ከአገር እንዳይወጡ ታገዱ

$
0
0

Yilkal

ሐብታሙ አሰፋ

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ከተሞች ፓርቲው ሊያደርገው ላቀደው ስብሰባ ለመገኘትና ከኢትዮጵያውያን ጋር ለመወያየት ዛሬ አዲስ አበባ ኤርፖርት ላይ ከአገር እንዳይወጡ ተከልክለው መመለሳቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

ኢ/ር ይልቃልን ከኤርፖርት የደህነቱ ሰራተኞች ፓስፖርታቸውን ተቀብለው የመለሷቸው ሲሆን ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ከአገር ሊወጡ ሲሉ ፓስፖርታቸውን ቀምተው ከውስጡ ገጽ ቀደው እንደመለሱላቸው ይታወሳል።

የሰማያዊ እና እውነተኛው የአንድነት ፓርቲ የሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ሰጪ ማህበራት አማካይነት የተጠራው ስብሰባ በሰሜን አሜሪካ በተለያዩ ከተሞች ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሀን ከነዚህም በዲሲ፣በቺካጎ፣በቦስተን፣በሲያትል፣በቬጋስና በሌሎች የሚጠቀሱ ሲሆን ኢ/ር ይልቃል በነዚህ ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት ነበር ከአገር ሊወጡ የነበረው።

ኢ/ር ይልቃል አስፈላጊውን የጉዞ ሰነድ ያሟሉ ቢሆንም የስርኣቱ የደህንነት ሰራተኞች ፓስፖርታቸውን ከተቀበሉ በሁዋላ ኢሚግሬሺን መጥተህ ጠይቅ በማለት መልሰዋቸዋል።

The post ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ከአገር እንዳይወጡ ታገዱ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሳኦል ፍሬዎች ፊልም የምረቃ ስነስርዓት –ዳዊት ኢያዩ

$
0
0

sauelበመጀመሪያ ጥሪያችንን አክብራችሁ የተገኛችሁ የክብር እንግዶች ፣ የፊልም ባለሙያዎች  እንዲሁም ለዚህ ፊልም መሰካት ትልቁን አስተዋጽዎ በማድረግ ከአምስተርዳም የኢሳት ስቱዲዮ ጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን ፣ አድካሚውንና ከባዱን ትግል በመታገል ለፍሬ እንዲበቃ በፊልሙ ላይ የተሰተፋችሁ ተዋንያን ፡ እንዲሁም አዘጋጅና የፊልም ባለሙያ  በበርገን ቅርጫፍ  ኢሳት ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ አባላት ስም ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ፡፡

የሳኦል ፍሬዎች ፊልም በዚህ በውጪው አለም በዲያስፖራው ያልተሞከረ በአይነቱ የመጀመሪያው ፈር ቀዳጅ የሆነ ወቅታዊውውን የሃገራችንን ሁኔታ የሚያሳይ የተዋንያኑን የደራሲውን የአዘጋጁን አቅም የፈተነ ፡ ይህን ሃላፊነት ወስዶ ለመስራት ጀግንነትን የሚጠይቅ ስራ ነው በፊልሙ ስራ ላይ የተሳተፍት በሙሉ  በብቃትና በመስዋዕትነት ከግዜአቸውን ፣ ከቤተሰባቸውን ፣ ከስራቸው እና  ከንብረታቸው ሳየሰስቱ ፡ እውቀታቸውን እና ጉልበታቸውን ያፈሰሱበት ቀን ከሌሊት ሳይሉ በፍቅር በመከባበር ፊልሙን ለዚህ ላበቁት ይህን ያህል መስዋዕትነት ለከፈሉ  ሁሉ ሞቅ ያለ ጭብጨባ ፡፡ ያንሳቸዋል

ከዚህ በመቀጠል የሳኦል ፍሬዎች ፊልሙ ላይ ወደ በርገን አመጣጡን ፣ የተዋንያኑን መረጣ ፣ ከጥናቱ ጀምሮ እስከ እሰከ ፊልም ቀረጻው ስላከናወናቸው ውጣ ውረዶች ቀረጻው የፈጀውን የግዜ ርዝመት ፣ የሰው ሃይል ብዛት እና ፊልሙን እስኪጠናቀቅ ድረስ የወጣውን የገንዘብ መጠን ጠቅለለው አድርገው ገለጻ የሚአደርጉልን የበርገን ቅርጫፍ ኢሳት ድጋፍ ሰጪ ሊቀመንበር አቶ ሰለሞን አሸናፊ ይሆናሉ ፡ በጭበጨባ ተቀበሉልን ፡፡ አቶ ሰለሞን አሸናፊ ወደ መድረኩ

 

በኢኮኖሚ በሰው ሃይል እንዲሁም የፈጀውን ግዜ  ለቀረበልን ሰፊ የሆነ ማብራሪያ የበርገን ቅርጫፍ ኢሳት ድጋፍ ሰጪ ሊቀመንበር አቶ ሰለሞን አሸናፊ እናመሰግናለን ፡፡

በቀጣይ በፊልሙ ላይ ተዋናይ እና ስክሪፕት ጸሀፊ ፣ ለፊልሙ ሙያዊ እገዛ በማድረግ ፊልሙ ተጀምሮ እስኪያበቃ ድረስ ከጎናችን በመሆን ፣ እዚህ ከኛ ጋር ሆና ዋናው ስራዋ ሳይበደል በስራዋ  ውሳኔ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች ከአመስተርዳም ስቱዲዮ ጋር እየተነጋገረች ስብሰባዎችን በስልክ እያካሄደች በፊልሙ ስራ ላይ አብላጫውን ቦታ ይዛ የምትገኘው ፡ ሙሉ የፊልሙን ቀረጻ በመውሰድ አሰልቺውን እና አድካሚውን የኤዲቲንግ ስራ ከባለሙያቹ ጎን ሳትለይ ፣ ለመጀመሪያ ግዜ ፊልሙ መመረቅ ያለበት በተሰራበት ቦታ በኖርዌይ በርገን ከተማ ነው በማለት ይህን እድል የሰጠችን ጋዜጠኛ እና ተዋንያን ገሊላ መኮንን ከ አመስተርዳም በመሃከላችን ትገኛለች ፡፡

ጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን ሙሉ በሙሉ ወጪዋን በመሸፈን በዚህ በሳኦል ፍሬዎች የምረቃ ስነስርዓት ላይ እንድትገኘን ያደረጉልንን ኢሳት አመስተርዳም ሰቱዲዮን ከልባችን እናመሰግናልን ፡፡ እስቲ ለነሱም አንድ ሞቅ ያለ ጭብጨባ

በፊልሙ ላይ የተሰማትን ስሜት ያሳለፈችውን ውጣ ውረድ ከተዋንያኑ ከደራሲው ከፊልም ቀረጻው እና የቦታ አመረራረጥ  ጋር የነበራትን ተሳትፎ ድካሙ እንዴት እንደነበረበ አይነ ህሊናችን ስላ  ታሳየናለች ፡፡ ጋዜጠኛ እና ተዋንያን ገሊላ መኮንን ወደ መድረክ ፡፡ በጭብጨባ ተቀበሉልልን ሞቅ ያለ ፡፡

ከንግግር በሃላ

ጋዜጠኛና ተዋንያን ገሊላ መኮንን ዝግጅታችንን አክብረሽ ለዛሬዋ እለት በመካከላችን በመገኘትሽ በበርገን ቅርጫፍ ኢሳት ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ ስም  በጣም እናመሰግለን ፡፡

 

የሳኦል ፍሬዎች ደራሲና ተዋንያን አይንሸት ገበየሁ ካሳ ምንም በዛሬው እለት በመካከላችን ባይገኝም  በዚህ ቦታ እንድንሰባሰብ ምክንየት የሆነን ጸሐፊ ነው ፡፡ በዚህ ፊልም ላይም ነዋሪነቱ በ ክርስቲያንሳንድ የሆነው ወንድማችን በዚህ ቦታ ላይ ተገኝቶ የሳኦል ፍሬዎችን ድርሰት እንዴት እነደጻፈው ፣ ለምን እንደጻፈው ማብራሪያውን ቢሰጠን በወደድን ነበር ግን አልሆንም ፡፡ ለደራሲና ተዋንያን አይንሸት ገበየሁ ሞቅ ያለ ጭብጨባ   ፡፡ እናመሰግናልን

 

ፕሮግራማችን ይቀጥላል

ከዚህ በመቀጠል የሳኦል ፍሬዎች የመጀመሪያ እይታውን ያደርጋል ፡፡ ሁላችሁንም ስለፊልሙ አስተያየት ስለምትጠየቁ በደንብ ተከታተሉት ወደ ሳኦል ፍሬዎች ፊልም ጋር መልካም ቆይታ ታደርጉ ዘንድ የበ.ቅ.ኢ.ድ.ሰ.ኮ ይጋብዛችሃል  አመሰግናለሁ ፡፡

 

፡-   ወደ የሳኦል ፍሬዎች ፊልም

ከፊልሙ በሃላ

ፊልሙ ይህን ይመስላል በጣም እንደተደሰታችሁ ከሁላችሁም ፊት መማንበበ ይቻላል የ እኛም የበርገን ቅርጫፍ ኢሳት ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ ከዛሬ 4 ወር በፊት ባሳወቀው ኢሳት ይቀጥላል መርህ መሰረት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍላችን ከሚያደርግው ድጋ ጎን ለጎን እኛም የ አቅማችንን ለመወጣት በተሰራው በዚህ በሳኦል ፍሬዎች ፊልም በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ መተንበታል ፡፡

  1. ይህ ፊልም ከምረቃው በሃላ ኢሳት በሚደርስባቸው ቦታዎች ሁሉ በኖርዌይ የተለያዩ ከተሞች ፣ በ አውሮፓ እንዲሁም በ አሜሪካ በሁሉም ግዛቶች ሁሉ በተያዘለት የግዜ ሰሌዳ መሰረት ለ እይታ ይቀርባል ከዚህ ከሚያገኘው ገቢ በሃገራችን ላይ በመረጃ እጥረት በወያኔ የሃሰት ማታለያ እየተጨብረበረ ላለው ወገናችን ኢሳት የህዝባችን አይንና ጆሮ ሆኖ እንዲቀጥል የኢኮኖሚ ድጋፍ በመሆን ያገለግላል በተጨማሪም ከ እይታ ሲወርድ በቪሲዲና በዲቪዲ ተባዝቶ ለህዝቡ ለሽያጭ ይቀርባል
  2. በወያኔ እየደረሰብን የሚገኘውን አፈና ግድያ ስደት የህዝባችንን በደል አሳይተንበታል ይህ ፊልም የመጀመሪው በመሆን ብዙ የተደበቁ እውነተኛ ታሪኮችን መሰረት ያደረጉ ሌሎች ፊልሞችም እንዲሰሩ ምክነያት ይሆናል

በ አጠቃላይ በዚህ ደረጃውን ጠብቆ በተሰራው ፊልም ላይ ለተሳተፋችሁ የውዲቷ ሃገራችን ታጋይ ልጆች አርቲሰቶች እንኳን ደስ አላችሁ እያልን ፡ ከኢሳት አመስተርዳም ስቱዲዮ እና ከበርገን ቅርጫፍ የኢሳት ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ ያዘጋጀላችሁ የምስክር ወረቀት እና የምስጋና ደብዳቤ ይሰጣችሃል

 

በአንደኛ መደብ ተሸላሚዎች

የመጀመሪያዎቹን 3 ተሸላሚዎች  ስጦታ የሚሰጡልን የክብር እንግዳ በዚህ በበርገን ከተማ ውስጥ ነዋሪ የሆኑት አቶ—— ናቸው ፡፡

  • ደራሲና የፊልም ተዋንያን የፊልሙ መሰረት መነሻ የሆነን አሁን ምንም እንኳ በመሃከላችን ባይገኝም ከዛሬ አራት ወር በፊት ፊልሙ ሲሰራ በእስር ቤት የሚደርስብንን መከራ ለማሳየት (በፊልሙ ላይ ) ያያችሁትን ወጣት እና ደራሲ አይንሸት ገበየው ካሳ ( ተፈሪ) የመጀመሪያው ተሽላሚያችን ነው ፡፡

በዚህ ቦታ ላይ በመገኘት ዛሬ ፊልሙ ለዚህ መብቃቱን ቢያየውን የራሱን አስተያየት ቢሰጠን በጣም ደስ ይለነ ነበር ፡፡ ፊልሙ ላይ ሲሰራ በደረሰበት አደጋ እስካሁን ድረስ የሃኪም ክትትል እያደረገ ይገኛል ፡፡

የደራሲ እና ተዋንያን አይንሸትን የምስክር ወረቀት የሚቀበሉልን ተወካይ ——— ይሆናሉ ወደ መድረኩ  ይመጡ ዘንድ በጭበጨባ ተቀበሉልን ፡፡

  • ፊልሙ ደረጃውን ጠብቆ እንዲህ ባመረ ደረጃ እንዲሰራ ጥረት ስታደርግ የነበረቸው እንዲሁም የፊልሙን ድርሰት ሪ ራይት በማድረግ ሙያዊ እግዛ በማድረግ ፣ እሷን ባናገኝ ኖሮ እንጀምረው ነበር እንጂ አንጨርሰው ፡፡
  • ሪ ራይተር እና ተዋንያንያን እንዲሁም ጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን ከአመስተርዳም የኢሳት ስቱዲዮ ወደ መድረኩ ፡፡ እባካችሁ በጭብጨባ ተቀበሉልን ፡፡
  • ታሪክ የሚሰራው ከታሪክ ነው በጣም ታዋቂና ባለሙያ ይህንን ፊልም ለታሪክ እንዲተላለፍ ከንብረቱ ከሙያውያው ሳይሰስት ለዚህ እንዲበቃ በትህትና በታዛዥነት አድካሚውን የፊልም ቀረጻ ያደረገ ፣ ከሳኦል ፍሬዎች ደራሲ ጋር በመነጋገር ሃሳቡን ይዞልን የመጣው በተዋንያን መረጣ ላይ ሙሉውን ሃላፊነት በመውሰድ ስራውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ተግቶ ሲሰራ የነበረ  የቶም ስቱዲዮ ባለቤት ፣ የፊልም ቀረጻ ስራ ቀላል አይደለም አንድ ሲን ከ 20 ግዜ በላይ ሊቀረጽ ይችላል
  • አዘጋጅና // ካሜራ ማን አቶ ቶማስ አለባቸው ወደ መድረኩ ቢመጡል ፡፡ እባካችሁ በጭብጨባ ተቀበሉልን

ጥያቄ ፡- 1 የሳኦል ፍሬዎች ፊልም አልቆ ለምረቃው በዓል ላይ እንገኛለን ዛሬ ምን

ተሰማችሁ ?

2 ሶስታችሁ በፊልሙ ላይ ሰፊውን ድርሻ ወስዳችሁ ዛሬ ለመመረቅ የበቃውን

ፊልም ለማየት በቅተናል  ፡፡ ለህዝቡ ምታስተላልፍት መልክት ምንድነው

ጋዜጠኛ እና ተዋንያን ሪ  ራይተር ገሊላ መኮንን

አቶ ቶማስ አለባቸው

ደራሲና ጸሐፊ አቶ አይንሸት

ከልብ  እናመሰግናልን እግዚአብሔር ይስጥልን

 

 

 

 

በሁለተኛ መደብ ተሸላሚዎች

 

በሁለተኛ መደብ 4 ተሸላሚዎች መሪ ተዋንያን ይሆናሉ

ስጦታውን  የሚሰጡልን የክብር እንግዳ በዚህ በበርገን ከተማ ውስጥ ነዋሪ የሆኑት በ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ሁሌም ከጎናችን የማይለዩ አቶ—— ናቸው ፡፡

 

  1. በሳኦል ፍሬዎች ላይ ዋናውን ገጸ ባህርይ ወክሎ የተጫወተው ለፊልሙ ትክክበብቃትና
  • ተዋንያንያን መክብብ ሙሉጌታ / ሃይሉ / ወደ መድረክ
  1. በሳኦል ፍሬዎች ላይ በመሪ ተዋናይነት ተሳታፊ የነበረው ለፊልሙ ማማር የራሱን ድርሻ የተወጣ፣ እንደ መሃሪ በመሆን የተወነው አንዴም ሲያናድደን አንዴም ሲያስቀን ሁለቱንም ገጸ ባህሪ አጠቃሎ የያዘ ፣ ይህ ብቻ አይደለም አዲስ ትዳሩን በመተው ሆሊውድ ጠቅሎሎ በመግባት ተዋንያኑን  በስራ የደከመው መንፈሳቸውን በጫወታው የሚአያዝናና ፊልሙ እስኪያልቅ ድረስ ትልቅ መስዋዕትነት የከፈለው ፡፡
  • ተዋንያን ሳሙኤል ተወልደ / መሃሪ/ ወደ መድረክ
  1. በሃገራችን ውስጥ የሚደርስብብን በደል የማይነገረውን መከራ ግፍ ወክሎ ከራሱ ጋር በመታገል ተውኖ የጨረሰው ማድረግ አይደለም ማሰብ በሚከበድ መልኩ ከባድ ገጸ ባህሪ በብቃት የተጫወተው ፣ ቤተሰቡን ልጆቹን ትቶ ፊልሙ ወደሚሰራበት ቦታ በሄደ ቁጥር ለተዋንያንኑ ባዶ እጁን የማይመጣው
  • ተዋንያን አንተነህ አማረ / ወዲ ጠቆ / ወደ መድረኩ መጥተው ስጦታዎን ቢቀበሉልን
  1. የሴት ተዋንያን በመብራት ተፍሎጎ በማይገኝበት ቦታ የተገኘች ፡፡ ከፊልሙ ቀረጻ ቀን ጀምራ እስከ ፍጻሜው ተዋንያኑን በመንከባከብ የሴቶችን ተሳትፎ በማሳደግ ላይ የምትገኘው የጀግናዋ የጣይቱ ልጅ
  • ጋዜጠኛ እና መሪ ተዋንያን ሜሮን አድማሱ ገ/ሃና /ማስተዋል / ወደ መድረኩ መጥተው ስጦታዎን ቢቀበሉልን

በዚህ መድረክ ላይ የምታይዋቸው በሳኦል ፍሬዎች ፊልም ላይ የመሪ ተዋንያኑ ገጸ ባህሪ ወክለው በብቃት የተወኑ ናቸው ፡፡ እባካችሁ ሞቅ ባለ ጭብጨባ ወደ ወንበራቸው ትሽኙልን ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን ፡፡

ጥያቄ ፡- 1

2

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

በሦስተኛ መደብ ተሸላሚዎች  

 

በሁለተኛ መደብ 4 ተሸላሚዎች ተዋንያን ይሆናሉ

ስጦታውን  የሚሰጡልን የክብር እንግዳ በዚህ በበርገን ከተማ ውስጥ ነዋሪ የሆኑት በ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ሁሌም ከጎናችን የማይለዩ አቶ—— ናቸው ፡፡

 

  1. በወገናቸው ላይ ሆዳቸውን በመውደድ ለገንዘብ የሚገዙ፣ ራስ ወዳዶችን የምናይበት ፣ ወንድማቸውን ሳይቀር አሳልፈው የሚሰጡ የወያኔ ደህንነቶችን ወክሎ የሰራ የተሰጠው ገጸ ባህሪ እነሱን አስመስሎ የተወነ ፡፡ ፊልሙ ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ ቤቱን ለእንግዶች በመልቀቀ ታላቅ መስዋዕትነትን የከፈለ ተዋንያን ነው
  • ተዋንያን ብሩክ ጌታነህ ጥሩነህ / ዋሴ/
  1. ሁሉም ተዋንያን እቤቱ ነበር ቁርስ የሚበሉት ግማሹ ተዋንያን ቀን ሰርተው ማታ እሱ ቤት ነው የሚያርፍት ፡፡ ፊልሙ እየሰፋ ሲመጣ ወሳኝ ቦታ ላይ ክፍተቱን የሞላ ፣ የተሰጠውን ገጸ ባህርህይ በ አጭር ግዜ ውስጥ በመዘጋጀት የተዋጣለት ስራ የሰራ ፣ በበርገን ቅርጫፍ የ ኢሳት ድጋፍ ሰጪ ሊቀ መንበር
  • ተዋንያን አቶ ሰለሞን አሸናፊ ሙሉጌታ / ቦጋለ/
  • በሳኦል ፍሬዎች ፊልም ላይ ብቸኛ ከነቤተሰቧ የተሳተፈች ልጆቿን ጭምር በፊልሙ ላይ ያሳተፈች ፣ ገሊላ ገና ስታያት ለተዋንያነት የመረጠቻት ፡፡ ግዜ ገንዘብ በሆነበት ሃገር ላይ ሃገራዊ ጉዳይ ይበልጣል በማለት ሌሊቱን ሙሉ ቤቷን ለቀረጻ በመፍቀድ ትብብር ያደገችው ፡፡
  • ተዋንያን ሰላም በጋሻው ከነቤተቧ / የመሰረት ጓደኛ በመሆን የተወነች /
  1. ግደሉ ሲባሉ የሚገድሉ እሰሩ ሲባሉ የሚያስሩ ግረፉ ሲባሉ የሚገርፍ ለምን ብለው እንኳ ጥያቄ የማይጠይቁ የወያኔ መጫወቻ አሸከር የሆኑ ሆዳቸው ብቻ ከሞላ ሌላ የማያስቡ የወያኔ ደህንነት አባል የሆኑ ያልተማሩ ወክሎ የሰራው በፊታችሁ ቆሞ የሚያስተዋውቀው
  • ተዋንያን ዳዊት እያዩ / ደህንነት/ ጭብጨባ ፡፡ አመስግናለሁ
  1. ቀን በስራ ደክሞ ማታ ለቀረፃ በሚጠራበት ቦታ ሁሉ እየተገኘ የተፈለገብትን የስራ ድርሻ እየተወጣ ፣ ለስራው ቅልጥፍና መኪናውን ጭምር ተዋንያኑ እንዲጠቀሙበት የሰጠ በስራችን ሁሉ ተባባሪ የነበረው
  • ተዋንያን አቶ ማንደፍሮ መንግስቱ / የደህንነት ሹፌር / በመሆን የሰራ
  1. የዌብ እና ፖሰተር ዲዛይነር ነው ፣ የማስታወቂያ ስራዎችን ፖስተሮችን በጥራትና በብቃት የሚሰራው ፣ የሳኦል ፍሬዎችን ፖስተር በሦስት በተለያዩ ዲዛይኖች በመስራት ለምርጫ ሁሉ አስከምንቸገር ድረስ ፊልሙን በፖስትር ላይ ማስቀመጥ የሚችል ብቃት ያለው ፡፡ በፊልሙ ላይም ተዋንያን በመሆን የተወነ
  • ተዋንያን እና ፖስተር ዲዛይነር አቶ ሺበሺ ጌታቸው መታፈሪያ

በሳኦል ፍሬዎች ላይ በተዋናይነት የተወኑ ናቸው

ጥያቄ ፡-

 

የበርገን ቅርጫፍ የኢሳት ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ ከሳኦል ፍሬዎች ፊልም የማዘጋጀት ሂደት ከፍተኛ ልምድ እና ትምህርት አግኝቶበታል ፡፡ በቀጣይም ኢህን ልምድ በመውሰድ የተሻለ ስራ ይዞ ለመቅረብ በ እቅዱ ውስጥ አስገብቶ እየሰራበት ይገኛል ፡፡

ይህን ፊልም በሚታየበት ቦታ ሁሉ ከዚህ ፊልም መነሻነት ደፍረው ያልተነገሩ የወያኔ የ አደባባይ ሚስጢር አውነተኛ ማንነታቸውን ለህዝብ አቅርቦ ህዝቡ ፍርድ እንዲሰጠበት ማድረግ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግዴታም ነው ፡፡ይህ ፊልም የፍርሃታችንን ድባብ አስወግዶ በሌላም ቦታ እነደዚህ የመሰሉ ስራዎች እንዲሰሩ ፈር ቀዳጅ ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን  ፡ የሳኦል ፍሬዎች ቧልትና ቀልድ በበዛበት ዘመን ደፍሮ የተሰራ ኮስታራ ፊልመ ነው ፣ የማይነካውን ነክቶ ያሳየ መንገዱን ያመላከተ የተዋጣለትፊልም ነው

 

The post የሳኦል ፍሬዎች ፊልም የምረቃ ስነስርዓት – ዳዊት ኢያዩ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live