Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት ድጋፍ ለማሰባሰብ ወደ ሰሜን አሜሪካ ያቀናሉ

$
0
0

የአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበርና የሰማያዊ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበር የተሰጠ የጋራ መግለጫ

በሰሜን አሜሪካ የሰማያዊ እና የአንድነት ፓርቲዎች ድጋፍ አሰባሳቢ ድርጅቶች በትብብር ለመስራት መስማማታቸው ይታወሳል። በስምምነቱ መሰረት የመጀመሪያው የጋራ ስራቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርን የሰሜን አሜሪካ የስራ ጉብኝት በጋራ ማስተባበር አድርገው ጀምረዋል፡፡ በዚህም መሰረት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት በጋራ ኮሚቴው በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት በመጪው ሚያዚያ (ኤፕሪል) ውስጥ በሰሜን አሜሪካ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል፡፡

የጉብኝቱ ዋና ዓላማ፤ በመጪው ግንቦት በሚካሄደው ምርጫ ውስጥ ለሚሳተፉ የሰማያዊ ፓርቲ እጩዎች ገንዘብ ማሰባሰብ ሲሆን፤ በተጨማሪም፤ በኢትዮጵያ የምርጫ ሂደት ምን ይመስላል፣ ምርጫው ውስጥ መቆየት ያለው ፋይዳ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አጠቃላይ ገፅታና እንቅስቃሴ ምን ይመስላል፣ በሚሉት ጥያቄዎች ላይ ውይይት ይደረጋል፡፡ የፓርቲውን የሰላማዊ ትግል ስትራቴጂዎች በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ማስረዳትና በነዚህ ጉዳዮች እንዲሁም ባጠቃላይ የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ከኢትዮጵያዊያን ጋር ዉይይት ማኪያሄድም የዝግጅቱ አካል ነው፡፡

የጉብኝቱ ጊዜያዊ መርሃ ግብር እንደሚከተለው ሲሆን ወደፊት እነደየሁኔታው ሊቀየር፤ ሊጨመር፤ ወይም ሊቀነስ የሚችል መሆኑንም አስቀድመን እናሳስባለን።

የየከተሞቹ ዝርዝር ፕሮግራም በቅርቡ በመገናኛ ብዙኋን ይፋ የሚደረግ ሲሆን፤ በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ባቅራቢያቸው በሚደረጉት የዉይይት መድረኮች ላይ ተሳታፊ በመሆን ስለኢትዮጵያ አገራችን እንዲሁም ስለወገናችን የወደፊት እጣፈንታ ዉይይት እንዲያካሂዱ ኮሚቴዉ ጥሪዉን ያስተላልፋል።

በየከተሞች የምትገኙ የሰማያዊ እና የአንድነት ድጋፍ ሰጪ ማህበራት አባላትም ይህ ፕሮግራም የተሳካ እንዲሆን የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድትለግሱ የጋራ ኮሚቴዉ ጥሪ ያደርጋል።

ከአክብሮት ሰላምታ ጋር

የሰማያዊ እና የአንድነት የሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች የጋራ ኮሚቴ

ለበለጠ መረጃ info@semayawiusa.org ኢሜል በማድረግ ወይም በ (202) 556 – 3078 መልክት በመተው አዘጋጅ ኮሚቴዉን ሊያገኙ ይችላሉ።

semawi

The post የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት ድጋፍ ለማሰባሰብ ወደ ሰሜን አሜሪካ ያቀናሉ appeared first on Zehabesha Amharic.


ሸዋ ረገድ ገድሌ –ዳንኤል ክብረት

$
0
0

የምታስፎክር ሰንጋ ገለሌ

በጦር መካከል ሳይሆኑ አያሌ

በጥይት ገዳይ ነጭ ብርገድሌ

የሴት ወንድ ናት ሸዋረገድ ገድሌ

DSC_0419ተብሎ የተገጠመላቸውን፣ በአምስት ዓመቱ የጠላት ወረራ ጊዜም አኩሪ ጀብዱ የፈጸሙትን የአርበኛዋን የሸዋረገድ ገድሌን ታሪክ የሚተርክ መጽሐፍ ሰሞኑን ቀርቧል፡፡ ‹ሸዋ ረገድ ገድሌ፣ የአኩሪ ገድላት ባለቤት›  ይሰኛል፡፡ ሺበሺ ለማ ጽፎት ዶክተር ክፍሌ ማርቆስ ገድሌ አሳትመውታል፡፡

በአምስት ዓመቱ የፋሽስት ወረራ ጊዜ ለሀገራቸው አኩሪ ገድል በመፈጸምና ለነጻነታችን ዋጋ በመክፈል ስማቸው ከሚነሡ ሴቶች ሸዋረገድ ገድሌ ግንባር ቀደም ናቸው፡፡ በ1878 ዓም የተወለዱት ወ/ሮ ሸዋ ረገድ ገድሌ ሁለገብ እንደነበሩ ታሪካቸው ያሳያል፡፡ የቤተ ክህነቱን ትምህርት ተምረዋል፡፡ ትዳርን አልፈልግም ብለው ምናኔን መርጠው ኢየሩሳሌም ድረስ ተጉዘዋል፡፡ ከመጀመሪያዎቹ የባንክ ተጠቃሚዎች፣ የአክሲዮን ገዥዎች፣ የፋብሪካ ተካዮች መካከል አንዷ ነበሩ፡፡ የጉለሌ ቅዱስ ገብርኤልንም ያስተከሉት እርሳቸው ነበሩ፡፡

 

የሸዋረገድን ስም ይበልጥ ከፍ አድርጎ ያስጠራው አርበኛነታቸው ነው፡፡ የኢጣልያ ጦር ሊጎርሰን ማሰፍሰፉ ሲሰማ በአዲስ አበባ ከተማ በሀገር ተቆርቋሪ ዜጎች በተቋቋመው የሀገር ፍቅር ማኅበር አባልነት መጀመሪያ ከተመዘገቡት ጥቂት ሴቶች መካከል አንዷ እርሳቸው ነበሩ፡፡ ወራሪው ፋሽስት አዲስ አበባ ሲገባና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ወርዶ የኢጣልያ ባንዴራ ሲተካ ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድሌ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ፡፡ በዚህ ምክያትም በኋላ  ‹የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ወርዶ የገናናው የኢጣልያ ሰንደቅ ዓላማ ሲውለበለብ በማየትሽ አልቅሰሻል›› በሚል ተከሰው ነበር፡፡ ሸዋረገድም ያለምንም ፍርሃት ‹አዎ አልቅሻለሁ፤ ያገሬን መወረርና መዋረድ ያወቅሁት የኛ ሰንደቅ ዓላማ ወርዶ የናንተ ሲውለበለብ በመታየቱ ነው፡፡ ሰው ለእናት ሀገሩ ቢያለቅስ ነውሩ የት ላይ ነው?›› ብለው ነበር የመለሱት፡፡

 

ወ/ሮ ሸዋረገድ ለአርበኞች ስንቅ በማቀበል፣ መሣሪያ በመግዛት፣ መረጃ በማሰባሰብ፣ መድኃኒት በመላክና ሞራል በመስጠት አምስቱን ዓመት በተጋድሎ ነው ያሳለፉት፡፡ በዚህ ምክንያት በተከሰሱ ጊዜም ‹‹ለአርበኞች ስንቅ ማቀበሌ እውነት ነው፤ይህንንም ያደረግኩት ለሀገሬ ክብር ብዬ ነው፡፡ ሰው እንኳን ለሀገሩ የእናንተ ወይዛዝርት ሀገራቸው ያልሆነቺው ኢትዮጵያን ለመውረር የጣታቸውን ቀለበት ሳይቀር መስጠታቸውን ትናገራላችሁ፡፡ እኔም ለሀገሬ የሠራሁት ሲያንሰኝ እንጂ አይበዛብኝም›› ነበር ያሉት፡፡

ወ/ሮ ሸዋረገድ ከሚጠቀሱላቸው ሥራዎቻቸው አንዱ ለቀይ መስቀል ማኅበር የነበራቸው ድጋፍ ነው፡፡ በጦርነቱ ዋዜማ ሐምሌ 1 ቀን 1927 ዓም ለተቋቋመው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ንብረታቸውን ሸጠው አስረክበዋል፡፡ እሥር ቤት በገቡ ጊዜ ከተከሰሱበት ወንጀል አንዱም ‹ቀይ መስቀልን ትረጃለሺ› የሚል ነበር፡፡ ሸዋረገድ ቀይ መስቀልን ከመርዳትም ባሻገር ኢትዮጵያውያን ወይዛዝርት እራፊ ጨርቅ እንዲያሰባስቡ በማድረግ ለአርበኞች ቁስል ማሸጊያ ይልኩላቸው ነበር፡፡

 

ሸዋረገድ ከርዳታው ጎን ለጎን ለአርበኞቹ የመረጃ ምንጭም ነበሩ፡፡ በከተማው የሚገኙ የጠላት መረጃዎችን በማሰባሰብና ወደ አርበኞች በምሥጢር በመላክ አርበኞች እንዲጠቀሙባቸው አድርገዋል፡፡ በዚህና በሌሎች ገድሎቻቸው ምክንያትም የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ነበር፡፡ በፈጣሪ ቸርነት ግን ሳይፈጸምባቸው ቀርቷል፡፡ የሞት ፍርዱ ባይፈጸምባቸውም የኢጣልያን እሥር ቤት ከሚያዘወትሩት አንዱ ሸዋረገድ ሆነዋል፡፡ በየጊዜው ይታሠራሉ፤ ይፈታሉ፡፡ በመጨረሻ ግን አዚናራ ወደምትባል ከሰርዲኒያ ሰሜናዊ ምዕራብ ወደምትገኝ ደሴት ታሥረው ተልከዋል፡፡

 

እዚያም ቢሆን ጽናታቸው አልተሰበረም፤ ወኔያቸውም አልተሰለበም፡፡ የሚያደርጉት ቢያጡ በእሥር ቤት የሚቀርብላቸውን የተበላሸ ምግብ በአሣሪዎቻቸው ፊት በመድፋትና ጦማቸውን በመዋል ፋሽስትን ይቃወሙ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታም ለአንድ ዓመት ከመንፈቅ ታሥረው ተፈቱ፡፡ አዲስ አበባ ሲገቡ ግን ትግላቸውን ቀጠሉ እንጂ አላቆሙም፡፡ ሕዝቡም

 

የዘበኛ ሱሪ ካኪና ገምባሌ

እንኳን ደኅና መጣሺ ሸዋረገድ ገድሌ

ብሎ ተቀበላቸው፡፡

 

በተለይም በጅቡቲ የነበረ አንድ ኢትዮጵያዊ የሰጣቸውን ‹የይሁዳ አንበሳ› የሚል ጽሑፍና ዓርማ ያለበትን ወረቀት ከንጉሡ የተላከ የሚመስል መልእክት እየጻፉ ወደ በረሐ በመላክ አርበኞችን አበረታተውበታል፡፡ የአዲስ ዓለም የጣልያን ምሽግ ኅዳር 5 ቀን 1933 ዓም በአርበኞች ሲሰበር ዋናውን መረጃ የሰበሰቡትና ዐቅድ የነደፉት ሸዋረገድ ነበሩ፡፡ ከምሽጉ ሰበራ በኋላም ደጀን መሆኑን ትተው ራሳቸው ወደ ውጊያ ዐውድማ ገቡ፡፡ በተለይም መቂ አካባቢ ከሻለቃ በቀለ ወያ ጦር መካከል ተሰልፈው ተዋግተዋል፡፡ በኋላም ጅማ አካባቢ ከነበረው ከገረሱ ዱኪ ጦር ጋር ለመገናኘት ተጓዙ፡፡ በዚያ እያሉም ጠላት ድንገተኛ አደጋ ጥሎ ገጠማቸው፡፡ ለአራት ሰዓት ያህልም ተዋግተው ተማረኩ፡፡ ወደ እሥር ቤት ተወስደውም የፊጥኝ ታሠሩ፡፡

 

በ1933 ዓም ሀገሪቱ ከፋሽስት ኢጣልያ ወረራ ነጻ ስትወጣ ሸዋረገድ ገድሌ አርበኞችን ወደመርዳትና የበጎ አድራጎት ሥራን ወደ መሥራት ገቡ፡፡ በንግዱም መስክ ተራመዱ፡፡ ሀገራቸውን እስኪበቃቸው አገልግለው፤ ግሼን ማርያም ሄደው ሥጋወደሙን ተቀብለው፤ ከዚያም ወደ ላሊበላ ተጉዘውና ተሳልመው፤ የመጨረሻቸው መሆኑን እየተናገሩ ጥቅምት 22 ቀን 1942 ዓም ዐረፉ፡፡ ሕዝቡም

 

እናንት ወጥ ቤቶች በርበሬ ቀንጥሱ

እናንት ሥጋ ቤቶች ሰንጋውን ምረጡ

ሸዋረገድ ገድሌ ለገና ሲመጡ፡፡

ቤተሰቧ ሰፊ ገናና ጥምቀት

ሸዋረገድ ገድሌ እንደምን ትሙት፡፡ ብሎ ገጠመላቸው፡፡ 

 

ሰፊ ነው ታሪካቸው፡፡ ልብ የሚያሞቅ፤ ወኔ ቀስቃሽ፤ አስደማሚ፤ ከዐለት የበረታ ጽናት፤ ከእቶን የጋለ አርበኝነት፤ ከትንታግ የተንቀለቀለ የሀገር ፍቅር ታገኙበታላችሁ፡፡ ምናለ አደባባዮቻችን በንግድ ኩባንያዎች ስም ከሚጠሩ በነ ሸዋረገድ ገድሌ ስም ቢሰየሙ ብላችሁም ትቆጫላችሁ፡፡

The post ሸዋ ረገድ ገድሌ – ዳንኤል ክብረት appeared first on Zehabesha Amharic.

በመጪዎቹ ሳምንታት በቦይኮት እና ህዝባዊ እምቢተኝነት ላይ ያተኮሩ መርሃ ግብሮች ይኖሩናል!

$
0
0

የህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እምቢተኝነት የተናጠል መስዋእትነትን የሚቀንስ አሳታፊ የትግል ስልት ነው!
ረቡዕ መጋቢት 9/2007

Photo File

Photo File

የኢትዮጵያ ሙስሊም በእምነቱ ላይ የተቃጣውን የአስተሳሰብና የጥቃት ዘመቻ ለመመከት፣ አስተሳሰቡን በኢስላማዊ አስተሳሰብ ለማረቅ፣ በሽፋን የሚደረገውን ጥቃት በህግ እልባት ያገኝ ዘንድ ባደረገው የትግል ሂደት ከላይ ወደታች የሆነ የተመሪነት ስርዓት ብቻ ሳይሆን ከታች ወደላይ ፍሰት ያለው መሪዎችን የመምራት ሥርዐት መፍጠር ችሏል፡፡ ይህም ህዝበ ሙስሊሙን የትግሉ ባለቤትና የመሪዎቹም መሪ አድርጎታል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ አደባባይ የወጣው ‹‹በጊዜ ሂደት ይፈታሉ፣ አልያም ከሀገሪቷ ሁለንተናዊ ዕድገት ጋር አብረው ይቀረፋሉ›› በሚል በሆደ ሰፊነት የተሸከማቸውን ስር የሰደዱ መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ተቋማዊና መሰል ችግሮች ለመጠየቅ ሳይሆን ተገድበው የተሰጡትን መሰረታዊ መብቶች መልሶ የመንጠቁን እኩይ ዘመቻ ለመግታት ነው፡፡ የእነዚህ እኩይ ተግባራት ድምር ውጤት ዘመን ተሻጋሪና በእምነታችን ላይም ሆነ በማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ማንነታችን ላይ የሚያደርሰውን ከፍተኛ አደጋ መረዳቱ ለህዝበ ሙስሊሙ የመንቃት ምንጭ፣ ለትግሉም ገፊ ሀይል ከመሆን ባሻገር ህዝቡን ፅናት ያላበሰና ለመስዋእትነት ያዘጋጀ ነበር፡፡

ከሰው ልጅን የታሪክ ምዕራፍ ሰፊውን ቦታ የሚሸፍነው ትግል ነው፡፡ በተለያዩ ወቅቶች የሰው ልጆች በግልም ይሁን በህብረት ለተለያየ ዓላማና ግብ የተለያዩ ስልትና መርሆዎችን የተከተሉ ትግሎችን አካሂደዋል፡፡ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እምቢተኝነት የትግል ስልት ደግሞ የህዝብን ንቃተ ህሊና መጎልበት የሚያመላክት የሰለጠነ የሰላማዊ የመብት ትግል መገለጫ ነው፤ ምክንያቱም መንግስት የህዝብን ጥያቄ ጆሮ ሰጥቶ ከማድመጥ ይልቅ የህዝብን ድምፅ በኃይል ለማፈን የሚያደረገው ጥረት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ በመጣ ቁጥር ህዝብ የመንግስትን ደጅ ከማንኳኳት ይልቅ መንግስት ላይ ዘርፈ ብዙ ጫና በመፍጠር መንግስት ወደህዝቡ ደጅ እንዲመጣ የሚያስገድዱ ለእምቢተኝነት የተሰጡ የእምቢተኝነት ምላሾችን አማራጭ አድርጎ ይወስዳልና! በተጨማሪም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እምቢተኝነት የተለየ መዋቅር የማይጠይቅ፣ ሁሉም ህብረተሰብ በየአካባቢውና በየዘርፉ የሚታገልበትና የተናጠል መስዋእትነትን የሚቀንስ የትግል ስልት ሲሆን ተጽእኖ ፈጣሪነቱም ዓይነተኛ መሆኑ አሌ የሚባል እንዳልሆነ ታሪክ ይመሰክራል፡፡

ይህ ህዝባዊ የለውጥ ፍላጎት ምክኒያታዊ የለውጥ እርከኖችን ተሻግሮ የመጣ እንደመሆኑ ተግባራዊነቱ ዋስትና ያለው፣ ከጠባቂነት የሚያላቅቅ፣ እስከ ድል ደጃፎች ድረስ የተዘረጋው የመብት ትግል በሰላማዊነት እና ቁርጠኝነት ድልድይ ላይ ተሻግሮ የችግርን ወንዝ እንዲሻገር ያስችላል፡፡ ይህን ህዝባዊ የለውጥ ፍላጎት ማዳመጥ ደግሞ ተገቢ ብቻ ሳይሆን ህዝብ የመሪዎቹ መሪ መሆኑን ማሳያም ጭምር ነው፡፡ በመሆኑም በመጪዎቹ ሳምንታት በቦይኮት እና ህዝባዊ ትብብር መንፈግ (እምቢተኝነት) ላይ ያተኮሩ የተቃውሞ መንገዶችን በመጠቀም የምናካሂዳቸው መርሃ ግብሮች ይኖሩናል፤ በአላህ ፈቃድ! ሁላችንም በዚህ መሰሉ ትግል ላይ ግንዛቤያችንን የሚያዳብሩ ጽሁፎችን በማንበብ እና መንፈሳዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ ዝግጅት በማድረግ ሰላማዊ ትግላችንን እስከድል ደጃፎች ለማድረስ የገባነውን ቃል እናድስ፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

The post በመጪዎቹ ሳምንታት በቦይኮት እና ህዝባዊ እምቢተኝነት ላይ ያተኮሩ መርሃ ግብሮች ይኖሩናል! appeared first on Zehabesha Amharic.

136 መምህራን የሥራ ማቆም አድማ መቱ • ‹‹ከአሁን በኋላ ለመምህራን ማህበርና ለአልማ አንከፍልም!››

Next: የነአብርሃ ደስታ, ሃብታሙ አያሌውና ሌሎችም የፍርድ ቤት ውሎ:- ‹‹እኔ አሸባሪ አይደለሁም፡፡ ኢህአዴግ አሸባሪ ነው፡፡ ለሽብር ሀሳቡም ፍላጎቱም የለኝም›› ዳንኤል ሺበሺ ‹‹የተባለውን ለነገር አለማድረጌን ከእኔ በላይ የከሰሰኝ መንግሥት ጠንቅቆ ያውቃል›› ሀብታሙ አያሌው ‹‹ለእኔ ብቸኛው አሸባሪ ህወሃት/ኢህአዴግ ነው፡፡ እኔ የህወሃት/ኢህአዴግ ተቃዋሚ ነኝ›› አብርሃ ደስታ ‹‹ይሄ 19ኛ ችሎት የጦር ፍርድ ቤት ችሎት እየመሰለ ነው›› የሺዋስ አሰፋ ‹‹ሃይማኖቱንና ማኅበረሰቡን ከሚፈራ ህዝብ ወጥቼ እንዲህ አይነት ተግባር አልፈጽምም›› ባህሩ ታዬ
$
0
0

(ነገረ ኢትዮጵያ) በምስራቅ ጎጃም ዞን የደብረወርቅ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 136 መምህራን ዛሬ መጋቢት 10/2007 ዓ.ም የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፁ፡፡ መምህራን ላይ እየተፈፀመ ያለውን የአስተዳደር በደል ተከትሎ 92 መምህራን ‹‹እኛ በደል እየደረሰብን ቢሆን መምህራን ማህበር ችግራችን እየፈታልን ባለመሆኑ ከአሁን በኋላ አባል እንዳልሆንን እንዲታወቅ፣ በየወሩ ከደመወዛችን እንዳይቆረጥብን›› በሚል ፊርማ አስገብተዋል፡፡ ከመምህራን ማህበር በተጨማሪ በየወሩ ከደመወዛቸው ለአልማ የሚቆረጠው ገንዘብም እንዲቆም መምህራኑ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
news
ባለፉት የመምህራን ስልጠናዎች የምስራቅ ጎጃም መምህራን ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራበት ማሳሰቢያ ተሰጥቶ እንደነበር የገለጹት መምህራኑ በተለይ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የሆነው አቶ ዘላለም ጌታነህ የወረዳው መምህራን ማህበር ፀኃፊ ከሆኑ በኋላ ጫናዎች እንደበዙባቸው ገልጸዋል፡፡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና መምህራን ማህበር ፅ/ቤት የሚሰራው አቶ ዘላለም ዕጩ መሆኑ ከታወቀ በኋላ መምህራኑ አራት ጊዜ እንዲፈርሙ የተጠየቁ ሲሆን ይህም አቶ ዘላለም ለመምህራን ማህበሩ እያደረገ ባለው አስተዋጽኦና በፖለቲካ አቋሙ ምክንያት እየተፈፀመ ያለ በደል ነው ብለዋል፡፡

የመምህራኑን ፊርማ ተከትሎም መጋቢት 9/2007 ዓ.ም የወረዳው ምክር ቤት 18 ያህል መምህራንን ብቻ ጠርቶ ‹‹እንወያይ›› ባለበት ወቅት መምህራኑ ‹‹ካወያያችሁ ሁላችንም አወያዩን እንጅ እኛን ብቻ ነጥላችሁ ልታወያዩን አይገባም፡፡›› በማለታቸው ምክር ቤቱና መምህራኑ ሳይግባቡ ተለያይተዋል፡፡ መምህራኑ በትናንትናው ዕለት ስራ ገበታቸው ላይ እያሉ ተጠርተው ‹‹እንወያይ›› ቢባሉም በዝምታ ተቃውሟቸውን በመግለፃቸው የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ በለጠ ገሰሰ ‹‹አንወያይም ብላችሁ አምጻችኋል፡፡ ስለዚህ ነገ ስራ እንዳትገቡ፡፡ ስራ ገብታችሁ ትምህርት ቤቱ ውስጥ የሰው ነፍስ ቢጠፋ ተጠያቂዎቹ እናንተ ናችሁ፡፡›› በሚል እንደዛቱባቸው መምህራኑ ገልጸዋል፡፡ የወረዳው የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅረአዲስ ሙሉሰው በበኩላቸው ‹‹ለአንድ ቀን ብቻ ሳይሆን ለአንድ ወርም መግባት የለባቸውም›› በሚል መምህራኑ ላይ ቅጣት እንዲወሰን መጠየቃቸው ተገልጾአል፡፡

መምህራኑም ለምክር ቤቱ ‹‹በቃል የነገራችሁንን ውሳኔ በጽሁፍ ስጡን›› የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም ውሳኔው በጸሁፍ ሊሰጣቸው እንዳልቻለና የወረዳውን ባለስልጣናት ውሳኔ የሰሙት 136 መምህራን ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የስራ ማቆም አድማው ዛሬ ጠዋት ከተጀመረ በኋላ ተማሪዎች 3፡20 ላይ ክፍል ጥለው በመውጣት መምህራኑን መደገፋቸው ተገልጾአል፡፡
ደብረወርቅ የሰማያዊ ፓር ሊቀመንበር የኢ/ር ይልቃል ጌትነት የትውልድ ቦታ መሆኑን ተከትሎ የብአዴን ካድሬዎች በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደሩ እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

The post 136 መምህራን የሥራ ማቆም አድማ መቱ • ‹‹ከአሁን በኋላ ለመምህራን ማህበርና ለአልማ አንከፍልም!›› appeared first on Zehabesha Amharic.

የነአብርሃ ደስታ, ሃብታሙ አያሌውና ሌሎችም የፍርድ ቤት ውሎ:- ‹‹እኔ አሸባሪ አይደለሁም፡፡ ኢህአዴግ አሸባሪ ነው፡፡ ለሽብር ሀሳቡም ፍላጎቱም የለኝም›› ዳንኤል ሺበሺ ‹‹የተባለውን ለነገር አለማድረጌን ከእኔ በላይ የከሰሰኝ መንግሥት ጠንቅቆ ያውቃል›› ሀብታሙ አያሌው ‹‹ለእኔ ብቸኛው አሸባሪ ህወሃት/ኢህአዴግ ነው፡፡ እኔ የህወሃት/ኢህአዴግ ተቃዋሚ ነኝ›› አብርሃ ደስታ ‹‹ይሄ 19ኛ ችሎት የጦር ፍርድ ቤት ችሎት እየመሰለ ነው›› የሺዋስ አሰፋ ‹‹ሃይማኖቱንና ማኅበረሰቡን ከሚፈራ ህዝብ ወጥቼ እንዲህ አይነት ተግባር አልፈጽምም›› ባህሩ ታዬ

$
0
0

ኤልያስ ገብሩ በፌስቡክ ገጹ እንደዘገበው:-:-

ዛሬ መጋቢት 10 ቀን 2007 ዓ.ም፣ በከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙት እና በእነዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ ያሉ 10 ሰዎች ቀርበው ነበር፡፡ መዝገቡ ለዛሬ የተቀጠረው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመቀበል እና ከ1-5ኛ ተራ ቁጥር ያሉ ተከሳሾች በእስር ቤቱ ደረሰብን ብለው ባቀረቡት አቤቱታ ላይ አስተያየት ካላቸው ለመቀበል መሆኑን የችሎቱ የግራ ዳኛ ገልጸዋል፡፡
Abrha-Desta-Yeshiwas-Assefa-Daneil-Shibeshi-Habtamu-Ayalew
የተከሰሾቹን የጽሑፍ አስተያየት በጠበቃ ተማም አባቡልጉ በኩል ቀርቦ ከመዝገብ ጋር ከተያያዘ በኋላ ተከሳሾቹ በየተራ የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ የግራ ዳኛው በመናገር 1ኛ ተከሳሽን ‹‹በክሱ ላይ እንደቀረበው ወንጀሉን ፈጽመሃል ወይስ አልፈጸምክም?›› ሲሉ ጠየቁት፡፡
ዘላለምም ‹‹አቃቤ ሕግ ባላደረኩት ነገር ህጉን መደገፍ ስለሚሆንብኝ ምንም መልስ አልሰጥም›› ሲል ዳኛው ‹‹በሥነ ሥርዓት ሕጉ ክሱን ክደው ተከራክራል› በሚል መዝግበነዋል›› በማለት መዝገብ ላይ አሰፈሩ፡፡

2ኛ ተከሳሽ አቶ ሃብታሙ አያሌው በበኩሉ ‹‹የተባለውን ለነገር (ሽብር) አለማድረጌን ከእኔ በላይ የከሰሰኝ መንግሥት ጠንቅቆ ያውቃል፤ እረዳለሁም፡፡ አቃቤ ሕግ ለምን እንደከሰሰኝም አውቃለሁ፡፡ የቆምኩለትን ሕጋዊ ፓርቲንም አፍርሶታል፡፡›› ብሏል፡፡

3ኛ ተከሳሽ አቶ ዳንኤል ሺበሺም ‹‹ሽብር የሚባለውን ነገር የሰማሁት ከሟቹ ኦሳማ ቢንላዳንና ከዘቶ መለስ ዜናዊ ነው፡፡ አደረክ ለተባልኩት ነገር ሃይማኖቴ፣ ዓላማዬ …አይፈቅድም፡፡ በዚህ ምክንያት ቤቴ እንዲወሰድ ተደርጓል፡፡ እኔ አሸባሪ አይደለሁም፡፡ ኢህአዴግ አሸባሪ ነው፡፡ ለሽብር ሀሳቡም ፍላጎቱም የለኝም፡፡ መንግሥት ፓርቲዬን ለማፍረስ የፈነቀለው …›› ብሎ ሳይጨርስ ፍርድ ቤቱ ንግግሩን እንዲያቋርጥ አስገድዶታል፡፡
4ኛ ተከሰሽ አብርሃ ደስታ መናገር ከመጀመሩ በፊት ‹‹ድርጊቱን መፈጸም አለመፈጸምህን ብቻ ተናገር›› ተብሎ ከችሎቱ ተነግሮት ነበር፡፡

አብርሃም በተረጋጋ መንፈስ ‹‹መልሱ እሱ አይደለም፤ የፈለኩትን እናገራለሁ፡፡ ሀሳቤን ልግለጽ›› ሲል ተናገረ፡፡ ዳኞች ሳይዋጥላቸው እንዲናገር ፈቀዱ፡፡ ‹‹ክሴ ከአሸባሪ ጋር በመገናኘት …የሚል ነው፡፡ አሸባሪ ለሚፈልገው ዓላማ ሰላማዊ ያልሆነ /ሰውን የሚጎዳ ድርጊት የሚያስፈጽም ነው፡፡ ለእኔ ብቸኛው አሸባሪ ህወሃት/ኢህአዴግ ነው፡፡ እኔ ህወሃት/ኢህአዴግ ተቃዋሚ ነኝ …›› የግራ ዳኛው የአብርሃን ንግግር አቋረጡትና ‹‹ክሱ ላይ ህወሃት/ኢህአዴግ የሚል የለም፡፡ ክሱን መቃወም አለመቃወምህን ብቻ ተናገር›› አሉት፡፡ አብርሃም ‹‹ሕወሃት /ኢህአዴግ፣ ደህንነቱ ማፊያ ነው … ›› ዳኞቹ በድጋሚ አቋረጡት፡፡ አብርሃ ‹‹አልጨረስኩም›› ቢልም ዳኞቹ ከዚህ በላይ ሊሰሙት አልፈቀዱም፡፡

5ኛ ተከሳሽ የሺዋስ አሰፋም ‹‹ዛሬ ለመጨረሻ ጊዜ ነው የምናገረው፣ ስሙኝ›› ሲል ለችሎት ገለጸ፡፡ ዳኞቹ ክሱን መቃወም አለመቃወሙን ብቻ እንዲናገር ገለጹለት፡፡፡ የሺዋስ ‹‹ትንሽ ሁለት ደቂቃ የምትሞላ ንግግር ነች፡፡›› አላቸውና ቀጠለ፡፡ ‹‹ሕገ-መንግሥቱ በአንቀጽ 75/4 ላይ ልዩ ፍርድ ቤት ስለማቋቋም ይደነግጋል፡፡ ይሄ 19ኛ ችሎት የጦር ፍርድ ቤት ችሎት እየመሰለ ነው፡፡ ሕገ-መንግሥቱ ዳኞች ነጻ ስለመሆናቸው ይደነግጋል፡፡ የእኔ ችግር ችሎቱ ላይ ነው፡፡…›› ዳኞች የየሺዋስን ንግግር አቋረጡት፡፡ የሺዋስም ‹‹ዛሬ ብቻ ነው የምናገረው›› በማለት እንዲህ አለ፡- ‹‹በሕገ-መንግሥቱ ላይ ዳኞች ነጻ መሆን እንዳለባቸው ቢቀመጥም የመርማሪ እና ዐቃቤ ሕጎችን ሀሳብ ብቻ የሚሰማው፤ እኛን አይሰማ አሻንጉሊት ፍርድ ቤት ነው፡፡…›› የሺዋስም መናገር የቻለው ይሄን ብቻ ነው፤ ዳኞች ድጋሚ አስቁመውታል፡፡

6ኛ ተከሳሽ፣ ዮናታን ደግሞ ‹‹ያለፈቃድ እንድትናገሩን እየተገደድን ነው›› ብሏል፡፡ 7ኛ ተከሳሽ (ስሙን የዘነጋሁት) ‹‹የተቀነባበረ ክስ ስለሆነ ምንም ማለት አልችልም፡፡›› ሲል 8ኛ ተከሻሽ ባህሩ ታዬም ‹‹ሃይማኖቱንና ማኅበረሰቡን ከሚፈራ ህዝብ ውስጥ ወጥቼ እንዲህ አይነት ተግባር አልፈጽምም፣ አለፈጸምኩምም፡፡ …ጊዜ እውነቱን ይፈርዳል›› ሲል ቃሉን ሰጥቷል፡፡ 9ኛ እና 10ኛ ተከሳሾችም ‹‹ድርጊቱን አልፈጸምንም›› ብለዋል፡፡

ችሎቱም ‹‹ለአንድ ወር የለንም›› ካሉ በኋላ 15 የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ለግንቦት 13፣ 14 እና 17 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡

The post የነአብርሃ ደስታ, ሃብታሙ አያሌውና ሌሎችም የፍርድ ቤት ውሎ:- ‹‹እኔ አሸባሪ አይደለሁም፡፡ ኢህአዴግ አሸባሪ ነው፡፡ ለሽብር ሀሳቡም ፍላጎቱም የለኝም›› ዳንኤል ሺበሺ ‹‹የተባለውን ለነገር አለማድረጌን ከእኔ በላይ የከሰሰኝ መንግሥት ጠንቅቆ ያውቃል›› ሀብታሙ አያሌው ‹‹ለእኔ ብቸኛው አሸባሪ ህወሃት/ኢህአዴግ ነው፡፡ እኔ የህወሃት/ኢህአዴግ ተቃዋሚ ነኝ›› አብርሃ ደስታ ‹‹ይሄ 19ኛ ችሎት የጦር ፍርድ ቤት ችሎት እየመሰለ ነው›› የሺዋስ አሰፋ ‹‹ሃይማኖቱንና ማኅበረሰቡን ከሚፈራ ህዝብ ወጥቼ እንዲህ አይነት ተግባር አልፈጽምም›› ባህሩ ታዬ appeared first on Zehabesha Amharic.

የዞን 9 ጦማሪያኑ እና ጋዜጠኞቹ በድጋሚ ተቀጠሩ

Previous: የነአብርሃ ደስታ, ሃብታሙ አያሌውና ሌሎችም የፍርድ ቤት ውሎ:- ‹‹እኔ አሸባሪ አይደለሁም፡፡ ኢህአዴግ አሸባሪ ነው፡፡ ለሽብር ሀሳቡም ፍላጎቱም የለኝም›› ዳንኤል ሺበሺ ‹‹የተባለውን ለነገር አለማድረጌን ከእኔ በላይ የከሰሰኝ መንግሥት ጠንቅቆ ያውቃል›› ሀብታሙ አያሌው ‹‹ለእኔ ብቸኛው አሸባሪ ህወሃት/ኢህአዴግ ነው፡፡ እኔ የህወሃት/ኢህአዴግ ተቃዋሚ ነኝ›› አብርሃ ደስታ ‹‹ይሄ 19ኛ ችሎት የጦር ፍርድ ቤት ችሎት እየመሰለ ነው›› የሺዋስ አሰፋ ‹‹ሃይማኖቱንና ማኅበረሰቡን ከሚፈራ ህዝብ ወጥቼ እንዲህ አይነት ተግባር አልፈጽምም›› ባህሩ ታዬ
$
0
0

zone9-e1398747809895
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በፌስቡክ ገጹ እንደዘገበው በእነ ሶሊያና ሽመልስ የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙት የዞን 9 ጦማሪያና ጋዜጠኞች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ቀርበው ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጣቸው፡፡

አቃቤ ሕግ በተከሻሾች ላይ ያቀረበው የኦዲዮ ሲዲ ማስረጃ እንዲደርሳቸው ባቀረቡት ጥያቄ ላይ ችሎቱ ብይኑን ስላልጨረሰ ለመጋቢት 15 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ጋዜጠኛው እንዳለው ሁሉም ተከሳሾች ከችሎት መጀመር በፊት እስር በእርስ ተቀራርበው እያወጉ እና ፈገግ ሲሉ ተስተውለዋል

The post የዞን 9 ጦማሪያኑ እና ጋዜጠኞቹ በድጋሚ ተቀጠሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

(የሳዑዲ ጉዳይ)…ለሃጅ ጸሎት መጥቶ ሳውዲ የቀረው ገበሬ እንግልት … (ነብዩ ሲራክ)

$
0
0

(ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ)
የማለዳ ወግ

ወንድም ራያ ጀማ የ5 ወንድ እና የ3 ሴት ልጆች ጎልማሳ አባት ነው። ወደ ሳውዲ የመጣው ድህነት ፣ የኑሮ ውድነት ፣ የፖለቲካው ሙቀት አለያም የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ገፍቶት አይደለም ። ሳውዲ የመጣው ፣ በእስልምና እምነቱ በሚያዘው መሰረት በህይወት ዘመኑ የሚጠበቅበትን ለማድረግ ከብቶቹን ሽጦ የሃጅ ጸሎት ለማድረግ ነበር … ዳሩ ግና የጅማው ገበሬ ራያው ጀማል እንደ ቀሩት ጓደኞቹ ጸሎቱን አድርጎ ለመመለስ አልቀናውም! ከሀጃጅ ጓደኞቹ ተለይቶ ከቤተሰብ እንደራቀ እዚህ ላለፉት ሁለት አመት ከመንፈቅ ገደማ ሳውዲ በእንግልት ጊዜውን ሊገፋ ግድ ብሎታል ። ምክንያቱም የሃጅ ጸሎቱን ከውኖ መካ ውስጥ መኪና አደጋ ደረሰበትና ነው !
raya jema
የራያ ጀማል ጉዳት …

ራያ ጀማል በደረሰበት የመኪና ግጭት የተለያየ የአካሉ ክፍል በጠና ስለተጎዳ በከፍተኛ ህክምና መካ ውስጥ ለሁለት አመት ተኩል ገደማ በሳውዲ የመንግስት ሆስፒታል ሲረዳ ቆይቷል። የመጓጓዣ የማረፊያና የኢንሹራንስ እስከ 55 ሽህ ብር የሚደርስ ገንዘብ ከፍሏቸው ለጸሎት ያማጡት የሃጅ ኮሚቴዎችም ሆኑ የጅዳ ቆንስል ራያ ጀማልን ሊረዱት ቀርቶ ሊያዩት አልቻሉም! ይህ የሆነው ስለ ራያ ጀማል መረጃ ስላልነበራቸው አይመስለኝም ፣ ይህን ስል መረጃው እንደነበራቸው እኔም መረጃ አለኝና ነው!

ለሃጅ ጸሎት መጥቶ ስለደረሰበት የመኪና አደጋ በያዝነው ሳምንት የ50 ኢዩቬልዩ በአሉን ባከበረው የጀርመን ራዲዮ ዜናውን አቅርበነው ነበርና የቆንስሉ ም የሃጅ ኮሚቴ ኃላፊዎች ያውቃሉ ! ከዚህ ሁሉ በኋላም ልክ የዛሬ አንድ አመት ገደማ የጅዳ ቆንስል ተወካይ ራያ ጀማል በነበረበት የሽሻ ሆስፒታል ለሌላ ጉዳይ ሄደው አግኝተውትም እንደነበር ተገፊው ወንድም አጫውቶኛል ። ተወካዩ ስለ ራያ ጀማልን ስላጋጠመው የመኪና አደጋ በዝርዝር ጠይቀውት መመለሳቸውን ከተጎጅው ጋር በያዝነው ሳምንት ባንድ ምሽት ከወደቀበት የጅዳ ቆንስል አካባቢ በሚገኘው የአንድ አረብ ሃብታም አጥር ኩርትም ብሎ ባገኘሁት አጋጣሚ አጫውቶኛል። ይህ ሁሉ ሆኖ የዜጎች ጉዳይ የሚለመከታቸው የቆንስል ኃላፊዎች ራያ ጀማልም ሆነ ጉዳዩ የት ደረሰ ? ብለው አልጠየቁም !

ራያ ጀማልን ሳገኘው …

የወንድም ራያ ጀማልን ወደ ጅዳ መምጣትና አቤቱታ የማቅረቡ መረጃ ደረሰኝ ። ፈልጌ አጣሁት ። አንድ ምሽት ወደ ኮሚኒቲ ካፍቴሪያው ሳዘግም ከግቢው ውጭ ባለ አጥር ታዛ ተኝቶ አየሁት ። ራያ ጀማል ነው ግን አላልኩም። ተጠግቸ ለማነጋገር ብሞክርም መተኛቱን ተረዳሁና ትቸው ሄድኩ። በካፍቴሪያ አካባቢ ስለወደቀው ወንድም ጠየቅኩ ፣ ጀማል ለመሆኑ በቂ ምልክቱ በምርኩዝ “ክራንች ” እየታገዘ እንደሚመላለስ ሲነገረኝ አገግሞ ከመካ ሽሻ ሆስፒታል የወጣው ራያ ጀማል መሆኑን ተረዳሁ።

ራያ ጀማልን በቀጣዩ ቀን አግኝቸው አወጋን ። ከሁለት አመት በላይ በሳውዲ የመንግስት ሃኪም ቤት በህክምና ሲረዳ የቆየው ኢትዮጵያዊ በቀኝ ጎኑ ደገፍ በሚልባት ምርኩዝ “ክራንች” እየታገዘ ፣ አያነከስ ጉዳዩን ለማስፈጸም ላይ ታች ይላል። ፍትህ ሊያገኝና ወደ ሀገሩ ሊሸኝ ፣ የሞት መርዶውን ሰምተው ያለቀሱ ቤተሰቡን ተሰናክሎም ቢሆን ይቀላቀል ዘንድ ተስፋ ሰንቆ ከመጣበት ቤቱ የሚደግፈውም ሆነ ፣ ለጎኑ ማሳረፊያ መጠለያ የሚሰጠው አጥቷል ። የገዛ ሃገሩ ሰዎች ክብር አልሰጠነውምና በዚህ ሙቀት ከቆንስሉ ርቆ ባለው የአረብ ግንብ ጠጋ ብሎ ውሎ ያድራል …

ራያ ጀማልን ከፍ ሲል ኢትዮጵያዊነቱ ፣ ዝቅ ሲል ቋንቋውን የሚናገሩት የቀየው ልጆች ሞልተው ተርፈዋል ፣ ሁላችንም ግን ጉዳቱን እንኳ ጠጋ ብለን መጠየቅ ገዶናል ። አቅም የለሾቹ በጥድፊያው ብንወጠር ጧትና ማታ የሚያዩት የቆንስል ዲፕሎማቶችና የልማት ማህበር አባላት ብሶቱን ሰምተው ለምን ጨከኑበት ? ማለቴ አልቀረም …መልስ የለኝምና አዘንኩ !

የወንድም ጀማልን ጉዳይ በቅርብ ርቀት ላለፉት ሁለት ሳምንታት ላላነሰ ጊዜ ስከታተል ቆየሁ ። ጉዳዩ ለጉዳይ ፈጻሚው ተላልፎ ሲንከባለል ቢሰነብትም ወደ መጨረሻ ራያ ጀማል ወደ ሀገሩ ለመላክ መወሰኑና ቲኬት ኮሚኒቲው እንዲያቀርብ ትብብር በቆንስል ሸሪፍ የመጠየቁ መረጃ ከአንድ የኮሚኒቲ የምክር ቤት አባል መረጃው ደረሰኝ ።
( በዚህ ዙሪያ ትናንት ባቀረብኩት ተመሳሳይ መረጃ ቅሬታ ያቀረቡልኝ አንድ ጠቋሚ ሃሳብ በመቀበል ሳጣራ ግን ቆንድል ሸሪፍ ኬሩ ራያ የ ጀማል የቲኬት ጥያቄውን ለኮሚኒቲ እንዲያቀርብ በስሙ ደበዳቤ ጽፈው ማዘጋጀታቸውንና ለኮሚኒቲው ምክትል በስልክ “ተባበሩት “ማለታቸውን ማረጋገጥ ችያለሁ)

ከቆንስሉ ግቢ ለቀን ወደ ኮሚኒቲ ጉዳዩን ለማጣራት ራያና እኔ ተያይዘን ስንወጣ ከቆንስሉ ባለጉዳዮች መግቢያ በር በር ነጻ ግልጋሎት የሚሰጡትን የድርጅትና የኦሮሞ ልማት ማህበር አባል ጋር ተገናኘን ። ሳያቸው በስጨት አልኩና ስማቸውን ጠርቸ ” የዚህ ወንድም ጉዳይ ወደ ሃገሩ ለመላክ ሲወሰን አንድም እንደ ዜጋ አለያም እንደ ተወላጅ ለምን መብቱን ማስከበር ተሳናችሁ? ” ስል ጠየቅኳቸው ። ግራ ተጋብተው …” ይህ ወንድም እንደ ተገልጋይ ሲወጣ ሲገባ ከማየት ውጭ ታሪኩን አላውቅም! ” ብለው ሲመልሱልኝ ራያን እንዲ ጠይቁት አድርጌ በኦሮምኛ አውርተው ጨረሱ ፣ ” እውነት እልሃለሁ ፣ ምንም አይነት መረጃ የለኝም!” በማለት በአግርሞት መልሰውልኝ ስናወጋ ሌላው የጅዳ ኮሚኒቲና የኦሮምያ ድርብ ስልጣን ያላቸው እድሜ ጠገብ ወዳጀን አገኘኋቸው …ኮሚኒቲውም ቲኬት እንዲያቀርብ መጠየቁን በማውሳት “ራያው ጀማል ጉዳዩን ሳይጨርስ ለምን ቲኬት ለመስጠት ተስማማችሁ? ” አንስቸ ጠየቅኳቸው ። ኃላፊውም ስለ ቲኬቱ ጥያቄው መቅረቡን ከማመን ባለፈ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ አለመሰጠቱን ጠቁመው ጉዳዪን ከቆንስል ሸሪፍ ጋር እየተነጋገሩበት እንደሆነ ጠቁመውኛል ። ከዚያኒህ ወዳጀ ጋር ውይይታችን እንደቀጠልን ወደ ካፍቴርያው አመራን። በድጋሜ ከራያው ጀማል ማግኘት አለባቸው የምለውን መረጃ ጠይቀው እንዲረዱ አደረግኩ ። መጠለያን በሚመለከትም ሃላፊነቱን ቆንስሉ ከወሰደ መጠጊያ እንደማይጠፋ በመጠቆም ፈቃድ ያመጡልኝ ዘንድ አሳሰብኳቸው ። ከሰነበተበት ሜዳ ወደ የግል መጠለያ ለመውሰድ ፍቃዱን እንደሚጠይቁልኝ አጫወቱኝ ። ኃላፊው የሰጡኝን ምላሽ ሁሉንም ለማመን ሞከሬ እንዲከታተሉት ጭምር ተመካክረን ተለያየን !

ይህ ከሆነ ከአንድ ቀን የኦሮሞ ተወላጆች አመታዊ በአላቸውን ሊያከብሩ ስለ አከባበሩ ዝግጅት መክረው ሲወጡ የኦሮሞው ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ራያ ጀማል ጉዳይ በተሰብሳቢዎች ተነሳነ ራያ ጀማልን ማነጋገራቸውን ሰማሁ ። ሁሉም በሆነው አዝነው በተለይም የድርጅት አባላቱ በቁጭት ለመፍትሄው ከቆንስሉ ጋር እንደሚመክሩ ጠቁመው ፣ ማረፊያ እስኪ ያዘጋጁለት በቆንስሉ ግቢ እንዲያድር አድረገው ተለያዩ ።

መሽቶ ነጋ ፣ የተባለው ደረሰ ፣ ቃል የገቡት የውሃ ሽታ ሆነው ቀሩ ! ባዩት ያዘኑት ሰብዕና አስገድዷቸ ው ለወንድም ራያ ጀማል ጎኑን የሚያሳርፍባት ፍራሽና መላብስ እንባቸውን እያዘሩ አቀብለውት ብቻ አልሄዱም ። እስከ ዛሬ ደረስ አደየመጡ ይጠይ ቁታል ! ራያ ጀማል ከዚያች ቀን በኋላ በማህበር አባላት የዚያች ምሽት ተማጽኖ ከኮሚኒቲው ግቢ ማደር ቢችልም በቀጣዩ ቀናት ከቆንስሉና ከኮሚኒ ቲው ግቢ እንዳያድር ግን ተከለከለ ! ወንድም ራያ ጀማል ያገገመው ስብራቱ በእንግልቱ እየተቀሰቀሰ እየወጋው እየተሰቃየ ነው ። ከሃገሩ ባንዴራ የቅርብ ርቀት ባሉት የአረብ ሃብታሞች አጥር ታዛ ኑሮን በመከራ በመግፋት ላይ ነው !

“ጉዳዩ ተሸፋፍኖ ሊሄድ ነው!” ብለን የሰጋነው የራያ ጀማል ጉዳይ ብዙዎቻችን ያስቆጨ ቢሆንም ዛሬ ነገሮች ተቀያይረዋል ብየ ነበር ከቀናት በፊት ። ይህንንም ያልኩት የቆንስሉ ጉዳይ ፈጻሚ አቶ መሃዲና ወንድም ራያ ጀማል ወደ መካ በማቅናት ከመካ ፖሊስ ጋር የመነጋገራቸውን ሰናይ መረጃ ሰምቸ ነበርና ነው … እቀጥልበታለሁ ብየ ጉዳዩን በእንጥልጥል የተውኩት ጉዳይ ፈጻሚውና ወንድም ራያ ጀማል ከመካው ጉዞ ያገኙትን ውጤት ይዠ ለማምጣት ይቻለኛልና ነበር ። አነሆ ጉዳዩ የተያዘበትን የመካ ፖሊስ ያነጋገሩት ጉዳይ ፈጻሚ የራያን መዝገብ አስቀርበው የገጨውን መኪና ባለቤት በስልክ ማነጋገራቸውን ተገፊው ወንድም አጫውቶኛል። ከዚህ ቀደም ራያ በሆስፒታል እያለ 10 ሽህ የሳውዲ ሪያል ሊሰጡት ፈቃደኛ ሆነው የነበሩት ሳውዲ ዛሬ 3 ሽህ ሪያል ካሳ ሊከፍሉ ፍቃደኛ መሆናቸውን መግለጻቸው ይህም ካልተቀበሉ ወደ ፍርድ ቤት መሄድ እንደሚችሉ መነገራቸውን ራያ ጀማልገልጾልኛል። ወንድም ራያ ከአመት በፊት የሆነውን እያስታወሰ ይህው ሳውዲ የገጨው መኪና ባለቤት ወደ ሆስፒታል መጥተው “10 ሽህ ሪያል ካሳ ልክፈልህ እና ሹፊሬ ከእስር ይፈታ !” ብለው የሆስፒታሉ ዶክተሮች መቃወማቸውን ይናገራል። ምክንያታቸው ደግሞ “ጉዳቱ ከፍተኛ በመሆኑ በክፍያው ማነስ የተነሳ ኢንባሲ ቢጠይቀን አደጋ እንወድቃለን” በማለት ዶክተሮች ፈቃደኛ ባለመሆናቸውን ጉዳዩ መጨናገፉን ራያ ጀማል ከኦሮምኛና አረብኛውን ከአማርኛ ጋር እየቀላቀለ በቁጭት አጫውቶኛል።

ትናንት ምሽት ወንድም ራያ ጀማልን ደጋግሞ ስልክ ደውሎ እንድጎበኘው ጠይቆኝ ላነጋግረው ሄድኩ …ጉዳዩን ሰምቶ ብዙዎች ተስፋ ሰጥተነው የነበረው ተስፋ ተሟጦበት አገኘሁት ። ዛሬስ ምን አዲስ ነገር አለ ምን ሆንል አልኩት!

” አይይ አቶ ነቢዩ ትናንትና ዛሬ ሙቀቱም ነው መሰል ወገቤን መላ የተጎዳ አካሌን ይጠዘጥዘኛል፣ ያመኛል፣ ማረፊያ የለኝም ፣ ሜዳ ላይ ለ18 ቀናት ስሰቃይ ማረፊያ ያልሰጡኝ የሚረዱኝ ፣ 8 ልጅ ፣ አይመስለኝም ፣ ጉዳየን አሁን አንደዚህ በሜዳ ላይ ሆኘ ጉዳየን በፍርድ ቤት ለመከታተል አልችልም!

እዚህ ላይ ራያ ጀማል አደጋ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ አይተውት የማያውቁት የሃጅ ኮሚቴ ሃላፊዎችም ሆኑ የጅዳ ቆንስል የት ነበሩ? አልልም ። የጅዳን ኮሚኒቲ ቲኬት ከመጠየቁ በፊት መደረግ የነበረበት ጉዳይ ለምን ክትትል አልተደረገም ? አንልም ! የራያ ጀማል ጉዳይ አይነት እና ከዚያም የከፉ የመብት ጥሰቶች ተፈጽመው ቆንስል መስሪያ ቤቱ እያሸማገለ የጨረሳቸው ጉዳዮች በርካታ ናቸው። ያም ሆኖ ጉዳትን ከግምት ያሰረገባ ሽምግልና ነበር ብሎ ለማናገር እንቸገራለን። ይህ ካልሆነ ደግሞ ቢቀር ይሻላል። የመብት ጥሰትን በተልካሻ ካሳ ከማሸማገል ወደ ተገቢ ህጋዊ ፍርድ ቤት ማድረስ ይቀላልና ቢታሰብበት መልካም ነው ። ይህ ከማድግ ባለፈ እያሸማገሉ ጉዳዩን ሸፋፍኖ ተበዳይን ወደ ሀገር መሸኘት ሊቆም ይገባል ! ትናንት በቆንስል መስሪያ ቤቱ ዙሪያ የምናውቀው ፣ ጩኸን ማስቆም ያልቻልነው ጉዳይ በሽፍንፍንና በግዴለሽነት ዛሬም ሲያልፍ ማየት ግን ነፍሴ አትፈቅድም !

በራያ ጀማል ጉዳይ እሱ እንዳለው ወራት የሚጨርሰውን ጉዳዩን እዚህ ሆኖ ለመከታተል ይከብዳል። ማረፊያ የለውምና ለከፋ ችግር ላይ ነው ። ራያ ጀማል አንድም መሄድና ወክልና መላክ አለያም መጠላያ አግኝቶ ጉዳዩን መከታተል ፣ ይህ ካልሆነም የሚሰጡትን ተቀብሎ ወደ ቀየው መቀላቀል ብቻ ነው። በእኒህ ውስብስብ አማራጮች ላይ ብቻውን ይወስን ለማለት የሚከብደው የሚሰጠው ሀሳብ ከችግር ጭንቀቱ አንጻር ይሆናልነሰ ይጎዳል። የቆንስል ሃላፊዎችና የሚመለከታቸው በዚህ ረገድ አማራጮችን ከህግ አንጻር ተመልክተውና አዋቂ አመካክረው አስፈላጊውን ድጋፍ ቢያደርጉለት ቤተሰቡን በትኖ ለከፋ አደጋ በተዳረገው ወንድም ነፍስ በምድርም በሰማይ ጽድቁ ለራስ ነው! ስለ ራያ ጀማል የማጠቃለው መብቱ እናስከብርለት ፣ የቻልን እንደ አቅማችን እንርዳው በማለት ነው ፣ የምለው ከዚህ ያለፈ አይደለም !

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 10 ቀን 2007 ዓም

The post (የሳዑዲ ጉዳይ)… ለሃጅ ጸሎት መጥቶ ሳውዲ የቀረው ገበሬ እንግልት … (ነብዩ ሲራክ) appeared first on Zehabesha Amharic.

(ዜና ፎቶ) 3 ቃጠሎ ሲደርስ ሹፌር የለም ተብላ ቁጭ ያለችው የእሳት አደጋ መኪና ዛሬ ከቆመ መኪና ጋር ተላተመች

$
0
0

Hosaena 2

hosaena ethiopia 1

ይህ “እኔም የዘ-ሐበሻ ሪፖርተር ነኝ” ያሉ የዘ-ሐበሻ ወዳጆች በፎቶ ግራፍ አስደግፈው የላኩት መረጃ ነው:: በቅርቡ ዘ-ሐበሻ ላይ በሆሳዕና ከተማ በተከታታይ ሶስት የ እሳት አደጋዎች መድረሳቸውን መዘገቧ ይታወሳል:: በጎፈር ሜዳ; በአራዳ እና በሆሳዕና ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የደረሱት አደጋዎችን ዘ-ሐበሻ በወቅቱ ዘግባለች:: እንግዲህ እነዚህ ሶስት የ እሳት አደጋዎች ሲደርሱ በከተማዋ የሚገኘው እሳት አደጋ ቶሎ አልደረሰም ነበር:: በተለይ የሆሳዕና ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ቃጠሎ ሲደርስባት የ እሳት አደጋው ለምን ቶሎ አልመጣም?’ ተብሎ ሲጠየቅ መኪናው ሾፌር ስለሌለው ነው የሚል ቀሽም ምክንያት ተሰጥቶ ነበር:: “እኔም የዘ-ሐበሻ ሪፖርተር ነኝ” ያሉት ዘጋቢያችን በፎቶ ግራፍ አስደግፈው እንደላኩት ዜና ባለፈው ወር ብቻ 3 የቃጠሎ አደጋ በሆሳ ዕና ከተማ ሲደርስ “ሹፌር የላትም” የተባለችው የ እሳት አደጋ ዛሬ ከቆመ መኪና ጋር ተላትማ በንብረት ላይ ከፍተኛ አደጋ አድርሳለች:: በራሷ ላይም በፎቶ ግራፉ ላይ የምትመለከቱትን ውድመት አስተናግዳለች::

በነገራችን ላይ በቅርቡ በሆሳዕና ማርያም ቤ/ክ የደረሰውን ቃጠሎ ተከትሎ ቤተክርስቲያኒቱን እንደገና ለማቋቋም የፕሮቴስታንትና የ እስልምና እምነት ተከታዮች ሳይቀሩ ከፍተኛ ድጋፍ እንዳደረጉ ዲያቆን ዘመድኩን በቀለ መዘገቡ ይታወሳል:: ኢትዮጵያዊነት እንዲህ ነው::

The post (ዜና ፎቶ) 3 ቃጠሎ ሲደርስ ሹፌር የለም ተብላ ቁጭ ያለችው የእሳት አደጋ መኪና ዛሬ ከቆመ መኪና ጋር ተላተመች appeared first on Zehabesha Amharic.


ኢሕአዴግ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቱን ለምን ይፈራዋል?

$
0
0

ከአንደኛው የዓለም ጦርነት መባቻ ጀምሮ ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት የማቋቋም ጥረት አንዳንዴ ተፋፍሞ ሲግም በሌላ ጊዜ ደግሞ ሲሟሽሽ ቆይቶ ከሰባ ዓመት ያልተቋረጠ ጥረት በኋላ እ.አ.አ በ1998 ዓ.ም ጀሮም ስምምነት በፈረሙ አራት ሀገራት እ.አ.አ በ2ዐዐዐ ዓ.ም በሄግ ከተማ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍ/ቤት ተመሰረተ::
Dr_Yacob
የዚህ ፍርድ ቤት መቋቋም የሰው ልጅ የህግ የበላይነት ለማስፈን ከወሰዳቸው እርምጃዎች እንደዋነኛ ስኬት ተቆጥሮአል:: ይህ ፍርድ ቤት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገራት ተንሰራፍቶ ያለው ባለስልጣናት ለሰሩት ወንጀል ተጠያቂ ያለ መሆን ባህል (Culture of impunity) ይሰብራል በሚል እምነት በህግ ምሁራን፤ ለፍትሕ ከበሬታ ባላቸው ህብረተሰብና መንግስታት ዘንድ በትልቅ ደስታ ተቀባይነት አገኝቶአል:: በአንጻሩ ደግሞ ለሰው ልጅ ሕይወትና መብቶች ደንታ የሌላቸው መንግስታት ይህንን ፍርድ ቤት በመደበኛ ጠላትነት ፈርጀውት ለውድቀቱ ሌት ተቀን ይኳትናሉ:: ለዚህ ፍርድ ቤት ምስጋና ይግባውና የአንድ አገር መሪ እንደቀድሞው በማን አለብኝነት ሰውን እንዳሰኘው ጨፍጭፎ የአንድ ዘመን ወጣት ጭዳ አድርጎ ዙምባቡዌ ጐዳና ላይ መንሸርሸር ቀርቶአል:: ዛሬ እንደ መንግስቱ ኃይለማርያም ያሉ ጨፍጫፊዎችና ሌሎችም ይህንን ሰይጣናዊ ድርጊታቸው ከመፈጸማቸው በፊት ከጀርባቸው ይህ ፍርድ ቤት መኖሩና ለወንጀል ድርጊታቸው አንድ ቀን ተጎትተው በዚሁ ፍርድ ቤት ፊት ቀርበው ከፍትህ ጋር እንደሚፋጠጡ ስለሚያውቁ ከእርኩስ ድርጊታቸው ይታቀባሉ::

አምባገነን መሪዎች ይህንን ፍርድ ቤት ምን ያህል እንደሚፈሩት በአንድ ወቀት በሱዳኑ መሪ በአልበሽር የደረሰው ጥሩ አመላካች ነው:: በዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦበት መጥሪያ የሚያሳድደው አልበሽር ኢትዮጵያን ጎብኝቶ ወደ አገሩ ሲመለስ እግረ መንገዱን መቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ ያርፋል:: የተሳፈረበት አይሮፕላን መጠነኛ ችግር ስለገጠመው ጥገና እስኪደረግለት ትንሽ ይዘገያል:: አልበሽር አይሮፕላኑ ውስጥ እየጠበቀ ሳለ አንድ የአሜሪካን አይሮፕላን ቀስ ብሎ የአልበሽርን አይሮፕላን ይጠጋል:: አልበሽር ይህንን የአሜሪካን አይሮፕላን ባየ ጊዜ እኔን ለመያዝ የመጣ ነው በሚል በፍርሃት ይርድ እንደነበር ሁኔታውን የታዘቡ ሰዎች ገልጸዋል:: የአንድ አገር መንግስት የዚህ ፍርድ ቤት ሥልጣን መቀበልና አለመቀበል በአገሪቱ የዴሞክራሲ ስርዓት መኖር አለመኖር ልኬት ነው:: ስለሆነም ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚከተሉ አገራት አፍሪቃንም ጨምሮ የዚህ ፍርድ ቤት አባል ሲሆኑ በአምባገነኖች ደግሞ የፍርድ ቤቱ አባላት ካለመሆናቸው በላይ ፍርድ ቤቱን በማውገዝ ግምባር ቀዳሚዎች ናቸው:: ይህንን ፍርድ ቤት የሚያወግዙ መሪዎች እንዲህ የሚሆኑት በፈጸሙት በወንጀል አንድ ቀን እዚሁ ፍርድ ቤት እንቀርብ ይሆናል ከሚል ፍርሃታቸው የመነጨ መሆን አለበት እንጂ ይህንን ለሰው ልጆች መብት ዘብ የቆመ ፍርድ ቤት የማያወግዙበት ሌላ ምን ምክንያት ሊኖር ይችላል?

ይህንን ፍርድ ቤት ከማንኛቸውም መሪዎች በላይ የሚያወግዙት የብቸኛዋ የተባበሩት መንግስታት መመስረቻ ቻርተር የፈረመችው አፍሪቃዊት አገር፣ የዓለም አቀፍ ህግጋት በመቀበል በቀዳሚነት ትታወቅ የነበረችዋ ኢትዮጵያ፣ የዛሬዎቹ መሪዎች ናቸው:: እነዚሁ የኢትዮጵያ መሪዎች ከማንም በላይ ይህንን ፍርድ ቤት ለመዝለፍ በተለያዩ መድረኮች ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ ምን ፈርተው ነው ከሚለው ጥያቄ መሸሽ አይቻልም:: የኢትዮጵያ መሪዎች ከማንም በላይ ይህንን ፍ/ቤት በማብጠልጠል በፍርድ ቤቱ የጥላቻ ዘመቻ ለመክፈታቸው ማስረጃዎቹ እነሆ:-

1.በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በኒውዮርክ በተባበሩት መነግስታት ጉባዔ ተገኝተው ኢትዮጵያውያንን ባሸማቀቀ መልኩ ይህንን ፍርድ ቤት ሲዘልፉ፣ ሱያንኳስሱ ሰሚ ሁሉ እኚህ ሰውዬ ምንን ፈርተው ነው ይህንን ፍርድ ቤት እንዲህ የሚያብጠለጥሉት ብሎ መየጠቁ አይቀርም:: ፍርድ ቤቶች በነጻነት የፍትህ ስርዓቱን የሚያስተናግዱበት ዴሞክራሲ ሰፍኖ ሕዝብ የስልጣን ባለቤት የሆነበት አገር መሪ አቶ ኃይለማሪያም በፍርድ ቤቱ ላይ ያዘኑበት ዓይነት ነቀፌታ ቢሰነዘር ምናልባት ሰሚ ያገኝ ይሆናል:: እንደ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲ የውሃ ሽታ የሆነበት አገር በፍርድ ቤቱ ላይ የሚሰነዝረው ነቀፌታና እሮሮ የቁራ ጩኸት ከመሆን አይዘልም::

2.የኢትዮጵያ መሪዎች በፍርድ ቤቱ ላይ የቋጠሩት ቂም በዚህ ብቻ አላበቃም:: አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከኒው ዮርክ ጠቅላላ ጉባዔ መልስ በአዲስ አበባ በተደረገው የአፍሪቃ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ይህንን ፍርድ ቤት ሲያወግዙ በሃፍረት እየተሸማቀቅን አድምጠናል:: ቂሙና ጥላቻው የከረረ በመሆኑ እነዚህ ውርጅብኞችም በቂ ሆነው አልተገኙም::

3.በጥር 25 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም አዲስ አበባ በተደረገው የአፍሪቃ የመሪዎች ጉባዔ በፍርድ ቤቱ ክስ ቀርቦባቸው በቂ መረጃዎች እያሉ እነዚህ ማስረጃዎች ባለመገኘታቸው ክሱ ከተነሣላቸው ከኬኒያው ፕሬዚዳንትና የፍርድ ቤት መጥሪያ ከሚያሳድዳቸው ከሱዳን መሪ አልበሺር ቀድመው የኢትየጵያ ተወካዮች ፍርድ ቤቱን ለማውገዝ አጀንዳ አስያዙ:: ኢትዮጵያ የፍርድ ቤቱን ስልጣን ካልተቀበሉ ጥቂት የአፍሪቃ አገራት አንድዋ መሆንዋ አንሶ የኢትዮጵያ ተወካዮች በምንም መልኩ ሳይነኩ በማያገባቸው ገብተው ሲፈተፍቱ ማየት ከማስገረሙም በላይ ያሳፍራል:: ለፍትህ ከበሬታው በላቸው የአፍሪቃ መሪዎችም ትዝብት ላይ መውደቃቸውም አያጠራጥርም:: ሌላም አስገራሚና የውድቀት ምልክት መሆኑ የሚያረጋግጠው የኢትዮጵያን ውግዘብ ደግፎ በተራው ፍርድ ቤቱ ያብጠለጠለው ማን መሆኑ ታውቃላችሁ? ሙጋቤ:: ባልተለመደ መልኩ በወቅቱ ሙጋቤ እንደልማዱ አላሸለበም ነበር:: የኢትዮጵያ መሪዎች የሙጋቤ ድጋፍና አቋም የአይጥ ምስክር ድምቢጥ አይነት ነው:: ፈረንጆች ወዳጅህ ማን እንደሆነ ብትነግረኝ አንተን ማን እንደሆን እነግርሃለሁ (tell me who your friends are and will tell you who you are) የሚለው ብሂል የኢትዮጵያና የዚምባቡዌ መዎች ማንነት ይገልጻል::

በጉባዔው ላይ ኢትዮጵያ መሪዎች ያቀረቡዋቸው ሃሣቦች ፣ጉባዔው በፍርድ ቤቱ ላይ የፀና አቋም እንዲወስድ፣ ፍርድ ቤቱ በተለይ በአፍሪቃ መሪዎች ላይ ማተኮሩ የዓለም ሕብረተሰብ እንዲያወግግ፣ ወንጀለኛ መሪዎችን የሚዳኝ አፍሪቃዊ ፍርድ ቤት ይቋቋም የሚሉ ነበሩ:: ከእነዚህ ጥያቄዎች አንዱም ውሃ የሚቋጥር አይደለም:: በመጀመሪያ የትኛው የአውሮፓ መሪ ነው መሣሪያ ሳይዙ ለሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ዜጐች ላይ ጥይት የሚያርከፈክፈው? አሜሪካን ውስጥ ነው ወይስ ኢትዮጵያ አንተ የዚህ ዘር አባል አይደለህም ከዚህ ጥፋ፣ አንተ የዚህ ሃይማኖት ተከታይ ስለሆንክ የሃይማኖት ነጻነት የለህም የሚባለው?

በፍርድ ቤት የተከሰሱት እኮ በነጻ ምርጫ ለስልጣን የበቁት የታንዛኒያ ወይም የደቡብ አፍሪቃ ወይንም የጋና ፕሬዝዳንቶች ሳይሆኑ ሕፃናት ለጦርነት አሳልፎ ያስፈጀው ቻርለስ ቴለር፣ በዳርፉር ጭፍጨፋ ተጠርጥረው ሕይወታቸው የቆጥ ላይ እንቅልፍ የሆነባቸው የሱዳኑ አልበሽር፣ በኃይማኖት ስም ህዝብን ያፈናቀለውና የጨፈጨፈው ዩጋንዳዊው ኮኒ ሲሆኑ እንዲሁም ሌሎች ተመሳሳይ ወንጀል የፈጸሙ ወንበዴዎች ናቸው:: ፍርድ ቤት ከቀረቡት ከአስር በላይ አፍሪቃውያን ፕሬዝዳንት አልበሽር ብቻ ክስ እንዲቀርብባቸው ጉዳያቸው ዐቃቤ ህጉ እንዲያጣራ ጥያቄ ያቀረበው የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ሲሆን፣ ሌሎች በሙሉ ምርመራው እንዲካሄድባቸውና ክስ እንዲቀርብባቸው ጠያቂዎቹ ኃያላን መንግስታት ሳይሆኑ የየአገራቸው መንግስታት ናቸው:: እንዲያውም ፍርድ ቤቱ በአፍሪቃውያን ወንጀለኞች ላይ ብቻ ቢያነጣጥር እንኳን ለአፍሪቃውያን ፍትሕ እስከቆመ ድረስ ይህ በራሱ ለአፍሪቃውያን ትልቅ ቁም ነገር አይደለም ወይ? ካምቦድያ ውስጥ ወንጀለኞች ስላልተከሰሱ የአፍሪቃ ወንጀለኞች በነጻ ይሂዱ ማለት በዓለም አቀፍ ሕግ ቀርቶ በየአገራቱ ሕግ የተፈቀደ አይደለም:: በነገራችን ላይ በአሁኑ ወቅት የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቱ ዐቃቢ ህግ አፍሪቃዊ ያለልሆኑ ጉዳዮች ይከሰሱ አይከሰሱ የሚለውን ለመወሰን ከአስር መዝገቦች በላይ በመመርመር ላይ ይገኛል::

ፍርድ ቤቱን የመሰረተው የሮማ ህግ በሚዘጋጅበት ጊዜ የአፍሪቃውያን ተሳትፎ ከየትኛውም አህጉር የበለጠ ነበር:: ከየትኛውም አህጉር በላይ አፍሪቃ አገራት የፍርድ ቤቱ አባል ሆነዋል:: ነገር የተበላሸውና መሪዎቿ ከአቋማቸው ሽብርክ ያሉት አንዳንድ የአፍሪቃ መሪዎች ከዚህ በፊት ልማዳዊ ህግ ሆኖ የቆየውና በሰፊው ሲሰመራበት የነበረው የአንድ አገር መሪ በስልጣን እስካለ ድረስ አይከሰስም የሚለው ሕግ ተለውጦ አሁን ግን በህጉ በተጠቀሱት ወንጀሎች የተጠረጠረ መሪ ከተጠያቁነት አይድንም የሚለው በወንጀል ህጉ ላይ ከሰፈረ ወዲህ ነው::

ሌላው በፍርድ ቤቱ ላይ የሚሰነዘረው ስሞታ ፍርድ ቤቱ የኃያላን መሳሪያ ሆኖአል የሚል ሲሆን ሀቁ ግን ይህንን አያረጋግጥም:: የፍርድ ቤቱ ዋና አቃቢ ህግ የጋምቢያ ተወላጅ ሴት ወይዘሮ ሲሆኑ በፍርድ ቤቱ መዋቅር ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የያዙ አፍሪቃውያን በብዛት ይገኛሉ:: የኢትዮጵያ መሪዎች ፍርድ ቤቱን ከመዝለፋቸውም በላይ እግረ መንገዳቸው ለአፍሪቃ የወንጀል ፍርድ ቤት በአፍሪቃውያን ይቋቋም ያሉት የምራቸው እንዳልሆነ ማንም ይገነዘበዋል:: በእውነት አሁን የአፍሪቃ መሪዎች ከጥቂቶቹ በስተቀር የዚህ የሚቋቋመው ፍርድ ቤት መጥሪያ አክብረው ፍርድ ቤት ቀርበው ለቀረበባቸው ክስ መልስ ይሰጣሉ? የተባበሩት መነግስታት የጸጥታው ምክር ቤትና መላው የሰለጠነው ዓለም ከጀርባው ያሳለፈው ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንኳን የመያዝ ትዕዛዝ የወጣበትን አልበሺር በአፍሪቃ በኩራት እንደልቡ ሲንሸራሸር የፍርድ ቤቱ አባል የሆኑ አገራት ይዘው ማስረከብ ሲገባቸው አንዳቸውም ለመያዝ አልሞከሩም::

ይህ አለም አቀፍ ፍርድ ቤት አባል ለሆኑ አገራት ህዝቦች ከጨቋኝ መሪዎቻቸው የሚጠብቃቸው ከለላ ሲሆን የኢትዮጵያ መሪዎች በኢትየጵያውያን ላይ ለሚፈጽሙ ወንጀሎች ግን ለዓለም አቀፍ ሰላም ጠንቅ እስካልሆኑ ድረስ ኢትዮጵያውያን ምንም አይነት ከለላ የላቸውም:: በህግ ያለተገደበ ስልጣን አደገኛነቱ የተረጋገጠ ነው:: አንድ አምባገነን መሪ ከኋላዬ ህግ አለ እጠየቅበቃለሁ ካላለ ማንን ፈርቶ ከድርጊቱ ይታቀባል? ስለሆነም እንደ ማንኛውም የዓለም ህዝብ ኢትዮጵያውያን የህግ ከለላ ያስፈልገናል:: የዚህ ፍርድ ቤት አባል መሆን ይገባናል:: የጠበቆች ማህበር፣ የህግ ምሁራን፣ የሴቶች ማህበርና የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ኢትዮጵያ የዚህ ፍርድ ቤት አባል እንድትሆን በመንሥስት ላይ የሚችሉትን ያህል ግፊት ማድረግ ይኖርባቸዋል::

The post ኢሕአዴግ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቱን ለምን ይፈራዋል? appeared first on Zehabesha Amharic.

የወያኔ በሬ ላም ወለደ። ከ-ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

Ketemaበተለያዩ ጽሑፎቼ ለመዳሰስ በተወሰኑ ነጥቦች ሲሆኑ የማብራራት እና ሃሳብን በማሳደግ ዙሪያ እንዲሁም አስተያየትን በመስጠቱ ጉዳይ እንዲሁም የምታውቁትን የማሳወቁ ጉዳይ የአንባቢያን ይሆናል።

አፈ ዲሞክራሲ አፍነህ ግዛሲ የሆነው በኢሕአዲግ ስም የሚንቀሳቀሰው TPLF አውራ አውራ የሚባሉትን የኦሮሞ ህዝብን የሚወክሉ የአማራን ህዝብ የሚወክሉ የደቡብን ህዝብ የሚወክሉ እና የትግራይን ህዝብ  የሚወክሉ ጥምር ስም እንደሆነ እላይ እላዩን ሁሉም ህዝብ የሚያውቀው ጉዳይ ነው። እላይ እላዩን ያልኩበት ምክንያት ከላይ በጠቀስኳቸው ስም ምክንያት ማሊያ ለብሰው የሚጫወቱ የTPLF ሰዎች ስለሆኑ ኢሕአዲግ የሚለው ስም ከስምነት ያለፈ  እንደሌለው ለማደናገሪያነት ከመዋል ውጪ ምንም ፋይዳ እንደሌለው ስለሚታወቅ የላይ የላዩን የውጪ መንግስታትን እና ህዝብን ለማደናገር በጭቃ ቤት ላይ የአሸዋ ግርፍ ተገርፎ የድንጋይ ቤት ነው ብሎ እንደመዋሸት ያህል ወያኔ ኢሕአዲግ የሁሉ ብሔር ብሔረሰቦች የእኩልነት ድርጅት ነው ብሎ መደስኮር ከጀመረ ሃያ አራት አመት አስቆጠረ።

ልብ በሉ ወያኔ ሃያ አራት አመት ሙሉ የጭቃ ቤትን በአሸዋ ስለተገረፈ ብቻ የድንጋይ ቤት ነው ብሎ እየዋሸ እና እየሰበከን ያለው። አንዱ ነው አሉ ከሚስቱ ጋር ወደ ውጪ ለስራ ጉዳይ ይሄዳሉ ከዛም ይሄ ፓስታ ፒዛ የሰለቸው ባል  እንጀራ አማረኝ ጋግሪና  እንብላ ይላታል። ሚስትም እሺ ትልና ብዙ አመት ውጪ የኖሩትን ጎረቤታቸውን እንዴት እንደሚጋገር ጠይቃ ሁሉን ነገር ገዛዝታ ትመጣለች በኃላም ዛሬ እራት እንጀራ ነው ስትለው ደስ ብሎት የናፈቀውን እንጀራ ለመብላት የራት ሰአትን ይጠባበቅ ጀመረ። እናም እንጀራው ተጋግሮ የራት ሰአትም ደርሶ እራት ይቀርባል። እንጎቻ እንጎቻ የምታክል ነገር ከጠረጴዛው ላይ ተቀምጧል ዝም ብሎ ሲመለከተው ብላ የውጪ አገር እንጀራ እንደዚ ነው ብላ ኮስተር ስትልበት ባልም ሚስቱን በጣም ይፈራት ስለነበረ ከማነሷ አይን የሚባል የለውም እናም ትኩር ብሎ እያየው ቂጣ ነው ይሄ ነገር ብሎ ሚስቱን ሲጠይቃት አይደለም እንጀራ ነው ብላ ኮስተር አለች አጋገሩን ስላልቻለችበት አይን የሌለው ቂጣ የመሰለ ነገር ነበረ የጋገረችው። እሱም ሁለቱን ሳብ አድርጎ ሰሃኑ ላይ ካስቀመጠ እና ወጥ ካረገበት በኋላ ትኩር ብሎ የምግብ ሰሃኑን  እያየው እንጀራ ነህ እንጀራ ነህ ተብለሃል ብሎ መመገብ ጀመረ ይባላል። ወያኔም እያደረገ ያለው እንዲህ ነው። አሸዋ ግርፍ ቤት የድንጋይ ቤት ነው ብሎ ይናገራል ህዝቡም የድንጋይ ቤት ነህ ድንጋይ ነህ ብሎ መኖር ከጀመረ አመታቶች ነጉደዋል።

እውነትን እንጂ ውሸትን የማይቀበሉ ለህሊናቸው እንጂ ለሆዳቸው ያላደሩ የአሸዋን ግርፍ ቤት የአሸዋ ግርፍ ነው እንጂ  የድንጋይ ቤት አይደለም ብለው የሚናገሩ በእውቀትም በእውነትም የሚሄዱትን ወይ ከአገር በግድ እንዲወጡ ይደረጋሉ አልያም የእውቀት ሃብታም የገንዘብ ደሃ ሆነው ይኖራሉ፣ ወይም ደግሞ ምክንያት ተፈልጎባቸው ወደ እስር ቤት ይወርዳሉ። እነዚህ ሶስት መንገዶች ሲጠቃለሉ ስለእውነት ብለው ባላቸው እውቀት ትክክለኛ ነገር ስለሚናገሩ የሚታሰሩ ናቸው። ዛሬ ይሄ ሰውዬ ይሄ ሰውዬ ይህቺ ሴትዮ ይህቺ ሴትዮ ተብለው በሃብት ሚዛን ላይ የተቀመጡት የኧሸዋን ግርፍ የድንጋይ ቤት ነው ብለው የተቀበሉት እንደሆኑ ይታወቃል ከጥቂት ባለሃብቶች በስተቀር ያለው ሃቅ ይሄው ነው።ስር ሳይኖራቸው መሰረት ሳይጥሉ በአጭር ግዜ እንደ ሸንበቆ ተመዘው የሃብት  አናት ላይ ደርሰው የምናያቸው የኢሕአዴግ ካባ ለብሰው የTPLF ፖሊሲ የሚያራምዱ ናቸው።

ወያኔ ባለእውቀቶችን እና ባለእውነተኞችን የማይፈልግበት ዋናው ምክንያት የወያኔ አሰራርን የአሸዋ ግርፉን ፈልፈል ፈልፈል ቆፈር ቆፈር አድርገው ይሄ እኮ የጭቃ ቤት ነው ከስር መሰረትም የለውም ምሶሶዎችንም ምስጥ በልቶአቸው በስብሰዋል ስለዚህ ይሄ የግርፉን ቤት አፍርሰን በትክክለኛው መሰረት በጠበቀ ብረት ሁሉም ያለስጋት የሚኖርበት የድንጋይ ቤት እንሰራለን ለዚህም ብቃትም እውቀትን እውነትም አገር ወዳድነትም አለን ህዝብን የሚጠቅም አገርን የሚለውጥ እና የሚያሳድግ ችሎታ እንዳላቸው  እና ህዝቡም እንደሚከተላቸው ስለሚያውቁ ባለ  እውቀተኞችን እና ባለ እውነቶችን አየፈልጉም ወይ ያስራሉ ወይ ከአገር እንዲሰደዱ ያደርጋሉ።

ወደፊት አገር ነጻ በምትሆንበት ሰአት ብቁ መምህራን የሚገኙት ከዩንቨርስቲ ሳይሆን ከእስር ቤት ነው። እስር ቤት ስንል አንድም ከነእውቀታጨው ወይኒ የገቡት አንድም እውቀት ኖሯቸው እንዳያስተምሩ የታገዱት አንድም እውቀት ኖሯቸው ከአገር የተሰደዱት ነው። ህዝቡም በእውቀትም በእውነትም በሰላም እጦትም ታስሮ እንዳይኖር የእስር ቤትን ኑሮ አሸንፈው እንዲወጡ ግፈኝነትን ሰብረው ነጻነትን ለብሰው እውቀትና እውነትን ያስተምራሉ። እዚህ ጋር ግን ከዩንቨርስቲ መምህራን አይወጡም እያልኩኝ አይደለም። እውቀት እና እውነት ያላቸው የድንጋይ መሰረቶች እየተባረሩ እና እየታሰሩ የአሸዋ ግርፎች የሆኑት ግን በማስተማሩም በማደናበሩም ለወያኔ ተመራጭ ሆነው የወያኔ ስራ አስፈጻሚ ሆነው ይሾማሉ የሚለውን ሃረግ እንድትመዙልኝ እፈልጋለው።

ስለዚህ የተማረን የሚጠላ እና የሚፈራ እውነትን የማይቀበል እና የማያውቅ ለህዝብና ለአገር ይጠቅማል ተብሎ መጠበቅ በጠራራ ጸሐይ ዝናብ ይዘንባል ብሎ  እንደመጠበቅ ነው። ወያኔን የኢትዮጵያን ህዝብ ንቀውታል ጠልተውታል፣ ገፍተውታል ጥለውታል፣ ዘርፈውታል በልጽገውበታል፣ ሰልጥነውብናል ሰይጥነውብናል፣ ቂም በቀል አብቅለው  ቂም በቀል ዘርተውብናል። የሃያ አራት አመት ፍሬአቸውን የአሸዋ ግርፍ የማስመሰል ስራዎችን አስቃኝተውናል። ታዲያ ዛሬ ግዜው የሰሩትን የክፋት እና የግፍ ስራ ይቀበላሉ። የዘሩትን ማጨጃቸው የሰበሰቡትን መውቂያቸው የወቁትን ማከማቻቸው ግዜው ደርሷል። የአሸዋ ግርፍ ስራችሁ ተገልጦ ሲታይ መሰረት የሌለው ውስጡ ምስጥ የበላው የበሰበሰ ምሶሶዎች ተገልጠው የሚታዩበት የእውነት ግዜው ደርሷል አስመስሎ እና አስፈራርቶ መኖር ከአሁን በኋላ ተቀባይነት የለውም በአሸዋ ገርፋችሁ የውስጥ ማንነታችሁን ደብቃችሁ የተንኮል ስራችሁን ህዝብ ስለተረዳው የበሰበሱት ምሶሶዎችን መሰረት የሌሌው የአሸዋ ግርፍ ቤታችሁን ገፍቶ የሚጥልበት ግዜ እና እውነትን ከባለ እውቀቶች የምንሰማበት ግዜ ቅርብ ነው።

ሃሰት የእውነት ጠላት ነው። አላዋቂ የባለ እውቀት ጠላት ነው። ወንጀለኛ እውነትን ይፈራል። እውቀት የሌለለውም ባለ እውቀቶችን ይሸሻል። ወንጀለኛ ቢደበቅ ለጥቂት ግዜ መሃይምም ቢያዝ ለተወሰነ ግዜ ነውና ፡- እውነት እና እውቀት አሸናፊነታቸው ለሁል ግዜ ነው ነዋሪነታቸው ለዘለቄታ ስለሆነ ይሄንን እንከተላለን ።

ከ-ከተማ ዋቅጅራ

19.03.2015

Email-waqjirak@yahoo.com

 

The post የወያኔ በሬ ላም ወለደ። ከ-ከተማ ዋቅጅራ appeared first on Zehabesha Amharic.

ለብአዴን አባላት ……ከሰማችሁ …….ከሞግዚት አስተዳደር ተፋቱ! –አንበርብር ከአማራ ሳይንት

$
0
0

tplfአፄ ዮሃንስ ንጉስ ተከለ ጊዮርጊስን ድል ነስተዉ ጎጃም ሲገቡ ራስ አዳል አልተደሰቱባቸዉም ነበርና ራስ አዳል ሸሽተዉ በርሃ ገቡ፡፡ አፄዉ ለራስ ደስታ ተድላ ዘመዳቸዉን ድረዉ በጎጃም ላይ ይሾሟቸዋል፡፡ ሆኖም ግን አፄ ዮሃንስ በራስ ደስታ ተድላ ላይ ሙሉ እምነት አልነበራቸዉምና በስራቸዉ ሐጎስ የሚባል አስተዳዳሪ ሾመዋል፡፡ ራስ አዳል ግብር በዛብን ያለዉን ህዝብ አስተባብረዉ የአፄ ዮሃንስ ሰራዊት ሲያጠቁ በዉጊያዉ አፄዉ የሾሟቸዉ ራስ ደስታ እና ሞግዚቱ ሐጎስ ይገደላሉ፡፡

የሟቾችን አስክሬን ወደቀብር ሲወጣ የራስ ደስታን በእንጨት አልጋ፤ የሐጎስን በአጎበር በተከለለ አልጋ ሲወሰዱ ባለቅኔዉ የጎጃም ህዝብ

“እኔስ ምን ቸገረኝ ካንተ አልዋጋ
እስራኤሉን በእንጨት ወታደሩን ባልጋ”

እያለ ሲቀኝ እንደነበር እና የሞግዚት አስተዳደር መጨረሻዉ ዉርድት እንደሆነ ታሪክ ይነግረናል፡፡(ምንጭ፡- የንግስና ሥርዓት እና የነገስታት የዘር ሃረግ፤በጥላሁን ብርሃነ ስላሴ)

የሞግዚትነት አስተዳደር ሙሉ አስተዳደር አይደለም፡፡ የይስሙላ አስተዳደር ነዉ፡፡ ሲፈለግ የሚፀና ሳይፈለግ የሚነሳ፣ ያልፀና እና መልካም ፈቃድን ያልተከተለ አሰራር ነዉ፡፡ የሞግዚትነት አስተዳደር ህዝብን ካለማመን የሚነሳ ቢሆንም ዋና ዓላማዉ የራስን የበላይነት ጠብቆ ማቆያ ነዉ፡፡

አፄ ዮሃንስ ጎጃሜዉንና ሆነ ራስ ደስታን ስላላመኗቸዉ፣ የሐጎስ ሞግዚትነት አስፈልጓቸዋል፡፡ የሞግዚት አስተዳዳሪነት ህዝብን ካለማመን እና ከመጠራጠር መጥቶ በመጨረሻዉ ሰዓት ክብር የሚሰጠዉ ለሞግዚቱ ነዉ፡፡

ሕወሓት-ኢህአዴግ በየቦታዉ ከሚሾማቸዉ አስተዳደሪዎች ጀርባ አንድ ሞግዚት እንደሚያስቀምጥ ትንሽ እልፍ ወይም ገባ ብሎ ለመመረመረ ከነደስታ ጀርባ ሺህ ሐጎሶችን መመልከት ይችላል፡፡ በሞግዚት አስተዳደር ስር መዉደቅ ሁለት ጊዜ መሞት ነዉ፡፡ አንድ ጊዜ ተንቆ እየተደገፉ መኖር እና ነፃነትን ማጣት ሲሆን ሁለተኛዉ በህዝቡም ሆነ በገዥወቻችሁ ፊት ታማኝነት ማጣት እና በስተመጨረሻ የራስ ደስታን ዕጣ መጋራት ነዉ፡፡

የብአዴን ሰዎች እኔ ከማዉቃችሁ ሰዎች ጨምሮ ኑሯችሁ የቀንድ አዉጣ፣ አስተዳደራችሁ የሞግዚት አስተዳደር እና ከሁለት ያጣ ወገን የሆናችሁ ናችሁ፡፡ በቅርብ እየሰማነዉ እንዳለሁ ጀርባችሁ ሲፋቅ ግንቦት 7 እየተባላችሁ፣ ታማኝነታችሁን አጥታችኋል፡፡ በእነ ሓዱሽ እየገፋችሁት ያለዉ የሞግዚት አስተዳደራችሁ ወደ ሞት የሚወስዳችሁ ከመሆኑ በላይ እናንተን በእንጨት ሞግዚታችሁን በወርቅ ሲጭኗችሁ ሁለተኘዉ ሞት ነዉ፡፡

ጊዜዉ ወደ ወገን የመጠቅለያ ነዉ፡፡ ያረጁትን የብአዴን መሪዎቻችሁን እርሷቸዉ እና ከአዲሱ የአማራዉ ክልል ትዉልድ ጋር ስለህዝባችሁ ተነጋሩ፡፡ በመንግስት ላይ አሻጥር እየሰሩ ስልጣን የያዘዉን አካል ማንኮታኮት እና ማዉረድ ከእናንተ ይጠበቃል፡፡ እኔ የማምናቸዉ ብአዴን ዉስጥ ሰርገዉ የገቡ የቅርብ ሰዎች አሉኝ፡፡ ድርጅቱን በብዙ ነገር እየበከሉት ቀፎዉን ሲያስቀሩትእያየሁ ብዙ ጊዜ አብረን የድርጅቱን መፍረሻ ቀን ቆጥረናል፡፡ አሁንም አስተሳሰብ ለዉጥ ላይ እያተኮርን በየመስሪያ ቤቱ ብአዴን በሚያካሂደዉ አደረጃጀት እና ስብሰባ እየገባን ሌሎችን በአስተሳሰብ ነፃ እያወጣን ጎድጓዱን አርቀን መቆፈር እንችላለን፡፡

እንደ መዉጫ የሞግዚት አስተዳደርነት መነሻዉ ህዝብን መናቅ እና አለማመን ስለሆነ እንደ ራስ ደስታ ሁለተኛ ሞት ሳንሞት ራሳችን ከሞግዚትና ከአሳዳሪዎቻችን ነፃ እናድርግ፡፡ የብአዴን አባሎች ሕወሓት በተደጋጋሚ ጀርባቸዉን ሲፍቀዉ ግንቦት 7 ናቸዉ እያላችሁ ሳትታመኑ አብራችሁ ልትኖሩ አይገባም፡፡ ከድርጅቱ በአስተሳሰብ በልጣችሁ ሄዳችሁም አልሄዳችሁም ከመጠርጠር እና ካለመታመን ስለማትድኑ ዛሬዉን ከሞግዚት አስተዳደር ራሳችሁን አላቃችሁ ተከተሉን፡፡

 

The post ለብአዴን አባላት ……ከሰማችሁ …….ከሞግዚት አስተዳደር ተፋቱ! – አንበርብር ከአማራ ሳይንት appeared first on Zehabesha Amharic.

በመስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ህወሃት የዘረጋውን የጥላቻና የበቀል ዘመቻ ለመከላከል የወጣ የአቋም መግለጫ

$
0
0

MUslimHኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የተጣሰውን ህገመንግስታዊ መብት በህግ ለማስከበር የጀመሩት ሰላማዊ ትግል ድፍን ሶስት ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ይህ ትግል በመላው አለም ሰላማዊ ትግልን መታገል ለሚሹ አርአያ ከመሆኑም ባሻገር በተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት እውቅናን ያገኘም ነው፡፡ በነዚህ መራራ ሶስት የትግል አመታት ህዝቡ በፊርማው የመረጣቸው የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች የእስር ብቻ ሳይሆን የድብደባ፣ የግርፋት፣ የማዋረድ፣ የሰብዓዊ መብትም መገፈፍ ሰለባ ሆነዋል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ሲታሰሩ፣ ሲገረፉ፣ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ደግሞ ለመሰደድ በቅተዋል፡፡ሰላማዊ ዜጎች በግፍ ጥይት እየተደበደቡ ለሞት መዳረጋቸው ሊካድ የማይችል የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡[ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—–

The post በመስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ህወሃት የዘረጋውን የጥላቻና የበቀል ዘመቻ ለመከላከል የወጣ የአቋም መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.

ማርች 8’ትን ስናስታውስ –በላይ ገሠሠ

$
0
0

Birtu & Aregashበሕብረተሰባዊ የዕድገት ታሪክ ውስጥ ሴቶች ለነፃነት፣ እኩልነት፣ ለሰብኣዊ መብትና ፍትሕ መረጋገጥ የከፈሉትን መስዋእትነት ትልቅ ስፍራ ይዞ ይገኛል:: ይህ በመሆኑም ዘንድሮም እንደ ተለመደው በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በሀገራችን መከበሩ የሚያሳየን የማርች 8 በዓል ታላቅነት ነው:: በሀገራችን የትግል ታሪክም በተመሳሳይ መልኩ ሴቶች ያልተሳተፉበት የነፃነት ትግል አልነበረም ቢባል የተጋነነ አይደለም:: የባዕዳን ሐይሎች ሀገራችንን በወረሩበት ጊዜም እቴጌ ጣይቱን ጨምሮ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ሴቶች ዘማችና አዝማች በመሆንና ከወንዶች እኩል በመሰለፍ ለኢትዮያችን ህልውና ኩቡር መስዋእትነትን ከፈለው አልፏል:: በዘመናችንም የስርዓት ለውጥ ለማምጣት የተካሄደው ሁለ ገብ መራራ ትግልም የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል:: በዚሁ መራራ ትግልም እነ ማርታን ጨምሮ በሽዎች የሚቆጠሩ ጀግኖች ሴቶች አኩሪ መስዋእትነትን ከፍለው አልፏል:: —[ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—

 

Download (PDF, 1.22MB)

 

The post ማርች 8’ትን ስናስታውስ – በላይ ገሠሠ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሃገሪቱን ሃብት የወያኔ ባለስልጣናት ከጉምሩክ መጋዘኖች ሲዘርፉ አደሩ

$
0
0

Samora (2)
በሃገሪቱ አንጡረ ሃብት ላይ ከፍተኛ ዘረፋ እና በሕዝብ ላይ ከፍተኛ ጭቆና በማድረግ ላይ የሚገኙት የወያኔ ከፍተኛ ባለስልጣናት በጄኔራሎች እና በደህንነት ባለስልጣናት እየተመሩ ለሊቱት ከጉምሩክ መጋዘኖች በውርስ የገቡ እቃዎችን ሲጭኑ ያደሩ መሆኑን ምንጮች ከአዲስ አበባ ገልጸዋል::

ለሊቱን በአዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ የጉምሩክ መጋዘኖች የተወረሱ የመኪና መለዋወጫዎች የኤሌክትሮኒስ እቃዎች የሞባይል ቀፎዎች ውድ ጌጣጌጦች የቤት እቃዎች የመሳሰሉት በባለተሳቢ መኪናዎች አስጭነው መውሰዳቸው ሲታውቅ እቃዎቹ በሃገሪት በተለያየ አከባቢ ተበትነው እንደሚሸጡ ምንጮቹ ገልጸው ለሊቱ የጄነራል ሳሞራ የኑስ የሜ/ጄነራል ተክለብርሃን እና የአርከበ እቁባይ መኪኖች እና ጠባቂዎቻቸው እና ተላላኪዎቻቸው በየመጋዘኖቹ ሲዘዋወሩ እንደነበር እና ለዚህ ዘረፋ ተሳታፊዎቹ እነማን እንደሆኑ በግልጽ ያሳያል ሲሉ ምንጮቹ ገልጸዋል::

የወያኔ ባለስልጣናት ሕዝብን እየጨቆኑ እየዘረፉ እስከመቼ እንደሚቀጥሉ የሚያሳስብ ጉዳይ መሆንን አውቀን ህዝብን እና ሃገርን ከዘረፋ እና ከጭቆና ለማዳን ከለውጥ ሃዮች ጎን በመቆም በሃገር ውስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በአስተባበር እና ሕዝብን በመቀሰቀስ ከአስከፊው ስርአት ነጻ ለመውጣት በጋራ መንቀሳቀስ አለብን:: ነጻነታችንን ማራጋገጥ የምንችለው እኛው ታግለን መሆኑን ማውቅ ያለብን ወስኝ ወቅት ላይ ስለሆንን በአንድነት በመቆም ይህንን የሌቦች መንግስት ስርአተ ቀብር እናጣድፈው ዘንድ ጠንክረን መስራት አለብን::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

The post የሃገሪቱን ሃብት የወያኔ ባለስልጣናት ከጉምሩክ መጋዘኖች ሲዘርፉ አደሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኦቦ ሌንጮና ያልተወራረደው ሂሳብ

$
0
0

lencho leta
By Dawit Solomon

የኦነግ ከፍተኛ አመራር የነበሩት ሌንጮ ለታ የስደት ህይወታቸውን ቋጭተው አገር ቤት ስለመግባታቸው እያደመጥን ነው፡፡በዚህ መቼም ደስ የማይሰኝ የአገሬ ልጅ ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡ደስታውን ሙሉ የማያደርገው በፖለቲካ አመለካከታቸው የተነሳ ብዙዎች አሁንም ከቀያቸው ተፈናቅለው፣አልያም ለእስር ተዳርገው በመገኘታቸው ብቻ ነው፡፡
በዚህች አገር ሁሉም አመለካከቱን እያራመደ መኖር የሚችልበት የፖለቲካ ሰርዓት ባለመፈጠሩ የሌንጮን ወደ አገር ቤት መመለስ እንደ ትንግርት እየቆጠርነው ነው፡፡
ምናልባት የሌንጮ የፖለቲካ ቁመና እንደ ቀድሞው ላይሆን ይችላል፣ጦር መዝዞ የነበረው ኦነግም የተቃዋሚዎች ዕጣ ደርሶት ተሰነጣጥቆ ይሆናል፡፡ሌንጮ ግን ድርጅቱን ለረዥም አመታት በመምራት ትልቅ ስም ገንብቷል፡፡እናም ኦነግ ሲባል ሌንጮ ሌንጮ ሲሰኝ ኦነግ ብቅ ይልብናል፡፡

የሌንጮ ኦነግ በዘመነ የሽግግር መንግስት በአሩሲ፣በአርባ ጉጉና በበደኖ ዘር ተኮር የሆነ ጥቃት በማድረስ ብዙዎችን ለህልፈተ ህይወት ስለመዳረጉ በህወሓት ቁጥጥር ስር የሚገኘው የቀድሞው ኢቴቪ መዘገቡ አይዘነጋም፡፡የኦነግ አመራር በበኩሉ ከአገር ከወጣ በኋላ ባወጣቸው መግለጫዎች ለጭፍጨፋው ተጠያቂ መሆን የሚገባው የህወሓት ኦህዴድ ስለ መሆኑ ተናግሯል፡፡

የተፈጸመው ጭፍጨፋ አለም አቀፍ ወንጀል በመሆኑና በጊዜ ይርጋ ስለማይታገድ ዛሬም ለመናገር አልረፈደም፡፡በጭፍጨፋው ወላጆቻቸውን፣የትዳር አጋሮቸቸውን፣ልጆቻቸውን በግፍ የተነጠቁ ዜጎች በመኖራቸው ሌንጮ የሚሰጡት የእምነት ክህደት ቃል ትርጉም እንደሚኖረው ይሰማኛል፡፡

ምናልባት ከመስኮት በስተጀርባ በተደረገ ድርድር ይህ ጉዳይ እንደማይነሳ ስምምነት ተደርሶ ወደ አገር እንዲገቡ መደረጋቸውን መጠርጠር ባይከፋም ክቡር የሆነውን የሰውን ህይወት ስላጠፋ ክስተት አለመነጋገር የዜጎችን ፍትህ የማግኘት መብት ከመርገጥ አይተናነስም ፡፡

ሌንጮ ይመሩት የነበረው ድርጅት ድርጊቱን አለመፈጸሙን እንደ ቀድሞው መመስከር ቢችሉ ይህንን የማስረዳት ሸክም በህወሓትና ኦህዴድ ላይ ይወድቃል፡፡ኦነግ በእርግጥ ድርጊቱን ፈጽሞ ከነበረም የድርጅቱ ሊቀ መንበር ኦቦ ሌንጮ የእጁን ማግኘት ይኖርበታል፡፡

The post ኦቦ ሌንጮና ያልተወራረደው ሂሳብ appeared first on Zehabesha Amharic.


ቋሚ ሲኖዶስ የፓትርያርኩን መመሪያ ተፈጻሚነት አግዷል * ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ፓትርያርኩን አሳሰቡ

$
0
0

abune-matyas
Source: ሐራ ዘተዋሕዶ

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ: ፓትርያርኩ ለቤተ ክርስቲያን ሰላም ሲሉ መዋቅራዊ አሠራርን በእጅጉ የሚፃረረውን አካሔዳቸውን እንዲያጤኑ አሳሰቧቸው፤ ቋሚ ሲኖዶስ የፓትርያርኩን መመሪያ ተፈጻሚነት አግዷል::

•የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ ፓትርያርኩ ከሕግ አግባብ ውጭ ለሾሟቸው ዋና እና ምክትል ሥራ አስኪያጆች የምደባ ደብዳቤ እንደማይጽፉ በዛሬው የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ አስታውቀዋል፡፡ ቋሚ ሲኖዶሱ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አስተያየታቸውን በጽሑፍ እንዲያቀርቡ አዝዟቸዋል፡፡
•አሠራሩ፣ ምርጫው እና መመሪያው ተቀባይነት የሚኖረው ሥራ አስኪያጆቹ ‹‹በሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ተመርጠው ቀርበው ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የጋራ ስምምነት ተደርሶበት በፓትርያርኩ ሲሾሙ ነው፡፡››

* * *

•‹‹ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ምክትል ሥራ አስኪያጅ ለፓትርያርክ ተጠሪ ኾኖ አያውቅም፤ ሊኾንም አይችልም፤ የሕግ ድጋፍ ስለሌለው፡፡ ይህ ያልተለመደ የሥራ ሒደት ብቻ ሳይኾን ከሕገ ቤተ ክርስቲያን፣ ከቃለ ዐዋዲው እና ከአገሪቱ የሕግ አሠራር ጭምር ውጭ ኾኖ ተመልክቸዋለኹ፡፡››
•‹‹የሥራ አስኪያጅ ምርጫው እና የተሰጠው መመሪያ ከትዝብት ላይ የሚጥል መኾኑን ተረድተውልን ለቤተ ክርስቲያን ሰላማዊ አሠራርና ለኹላችንም ሰላም ሲባል ውሳኔዎን እንደገና እንዲያጤኑት እያሳሰብኹ በተሰጠው መመሪያ እንዲኹም በሥራ አስኪያጅ ምርጫ የማልስማማና ለማስተናገድ የምቸገር መኾኔን ለቅዱስነትዎ ሳቀርብ በታላቅ ትሕትና ነው፡፡››

/ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ፤ የከምባታ ሐዲያና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት ለፓትርያርኩ ከጻፉትና ለቅዱስ ሲኖዶስ በግልባጭ ከአሳወቁት ደብዳቤ/

The post ቋሚ ሲኖዶስ የፓትርያርኩን መመሪያ ተፈጻሚነት አግዷል * ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ፓትርያርኩን አሳሰቡ appeared first on Zehabesha Amharic.

በጎንደር ከተማ አንድ የሚሊሺያ አዛዥ ተገደለ በርካታ ሰዎችም ታሰሩ

$
0
0

ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የጎንደር ከተማ የሚሊያሻዎች ሃላፊ ኮማንደር መጋቢት 11 ቀን 2015 ዓም ቀበሌ 15 ወይም ፋሲለደስ ትምህርት ቤት አካባቢ ከምሽቱ 2 ሰአት አካባቢ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድሏል። ገዳዮቹም መሳሪያውን ማርከው ከእነ ትጥቃቸው ወደ አርማጭሆ ጫካ መግባታቸው ታውቋል። የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው ግንባሩ አካባቢ በጥይት የተመታ ሲሆን ወዲያውኑ ህይወቱ አልፏል።

ድርጊቱን ተከትሎ የጸጥታ ሃይሎች አከታትለው በመተኮሳቸው ህዝቡ ሁኔታውን ለማየት ወደ አደባባይ ሲወጣ ወደያውኑ መብራት እንዲጠፋ ተድርጓል።
newss
አዣዡ በህዝቡ ላይ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ይፈጽም እንደነበር የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት አሁንም በአካባቢው እያንዣበቡ መሆኑን የአይን ምስክሮች ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ሰሞኑን ታጣቂዎች ገብተዋል በሚል መንግስት ከፍተኛ ቁጥር ሰራዊት በአብርሃ ጅራ፣ አብድራፊና አጎራባች ከተሞች አሰማርቶ ፍተሻ እያካሄደ ሲሆን፣ የአካባቢው ባለስልጣናትም ሳይቀር ተቃዋሚዎችን ትደግፋላችሁ ተብለው ተይዘዋል።
በመተማ አካባቢ በቅርቡ ለመከላከያ ሰራዊት ደሞዝ ሊከፍሉ በመንገድ ላይ የነበሩ አንድ ኮሎኔል፣ አንድ መቶ አለቃ፣ አንድ ተራ ወታደርና ሹፎራቸው ተገድለው ገንዘቡ በታጣቂዎች ከተወሰደ በሁዋላ ፣ ድርጊቱን የፈጸሙት ወደ አብርሃ ጅራ የገቡ የአርበኞች
ግንቦት7 አባላት ናቸው በሚል ፍተሻ ሲካሄድ ሰንብቷል። ምንጮች እንደሚሉት ታጣቂዎቹ 3 ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች፣3 ሽጉጦችንና 250 ሺ ብር የያዘ የገንዘብ መያዢያ ቀረጢት ይዘው ተሰውረዋል።

ታጣቂዎቹ ምእራብ አርማጭሆ ገብተው ምሳ መብላታቸውን፣ የአካባቢውን ነዋሪዎች በሬ ግዝተው መጋበዛቸውንና ስለ አለማቸው ማስረዳታቸውን የሚገልጹት የአይን እማኞች፣ የአካባቢው ነዋሪም ድጋፉን እንደሰጣቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በአብድራፊና አብርሃጅራ ከተማዎች መምህራን፣ አንድ ሴቶች ጉዳይ ውስጥ በሃላፊነት የሚሰራ የመንግስት ሰራተኛ፣ የአካባቢው የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ሃላፊ ፣ የመንግስት ታጣቂ ሚሊሺያ ተይዘው ታስረዋል። በአካባቢው የታሰሩት ሰዎች ቁጥር ከ20
በላይ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ።

ወደኤርትራበርሃየሚሻገሩኢትዮጵያውንቁጥርመበራከቱንተከትሎ፣በሱዳንጠረፍዙሪያመከላከያሰራዊትየመውጫበር የተባሉትን ቦታዎች ሁሉ ዘግቶ ጥበቃውን አጠናክሯል።

የአካባቢው ሰዎች እንደሚናገሩት ከተቃዋሚዎች ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል በተለያዩ ወራቶች ከተገደሉት መካከል ዓስናቀውታፈረ፣ ሙሉጸሓይ፣ አቡሃይ ተክሌ ፣ ፣ ፈንታ አዛናው ፣ ድግሴ አድየ፣ ታደሰ ድረስ፣ ተስፋው አለሙ፣ ሙሉጌታ ማሞ፣ ደጀን
በይፋ፣ አለነ ተገኘ ፣ ሙላው አለሙ፣ ጋራ ጉርባ፣ ተስፋ፣ ዳርጌ አወቀ፣ ደጉ፣ ጨምር፣ ጥላሁን ፣ ሃብቴ አለምኔና ጸጋው ዘመነ የተባሉት ይገኙበታል።

ምህረት አባይ የተባለው ባለስልጣን ደግሞ እነ ሙላው አለሙን ማስገደሉን ነዋሪዎች ሲናገሩ፣ ሹመት የሚባለው የጎንደር የጸጥታ ሹም ደግሞ ከሳንጃ እስር ቤት በማስወጣት በእነ ደጉ፣ ጨምርና ጥላሁን ላይ እርምጃ ወስዷል።
በጉዳዩ ዙሪያ የወረዳዎችን አመራሮች አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም።

The post በጎንደር ከተማ አንድ የሚሊሺያ አዛዥ ተገደለ በርካታ ሰዎችም ታሰሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢትዮጵያውያኑ በጄኔቫ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

$
0
0

Geneva ethiopia

Geneva
የጀርመን ድምጽ ራድዮ ዘገባ:-
በተለያዩ ሃገራት በስደት የተበተኑ ኢትዮጵያዉያን ስለሚገጥማቸዉ ችግር ለተመ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን እንደሚያሳዉቁ የገለፁት የሰልፉ አስተባባሪዎች፤ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ፖለቲካ እና የሰብዓዊ መብቶች ይዞታ ለዓለም ዓቀፍ ተቋማት ለማሳወቅ መሰብሰባቸዉንም አመልክተዋል። ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ መሆናቸዉን የገለፁልትን አቶ ዉሂብ የሺጥላን ስለሰልፉ ዓላማ ለጀርመን ድምጽ ራድዮ እንደሚከተለው አስረድተዋል:: ያድምጡት:-

The post ኢትዮጵያውያኑ በጄኔቫ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ appeared first on Zehabesha Amharic.

(ሰበር ዘገባ) የአፍሪካ ሰብአዊና የህዝቦች መብት ኮሚሽን በሕዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴዎች ላይ ለተፈጸሙት ኢሰብአዊ የመብት ጥሰቶች ምላሽ እንዲሰጡ ማሳሰቢያ ደብዳቤ ላከ

$
0
0

Muslim in ethiopia
ሰበር ዜና BBN ሁሉም መስማት ያለበት ሰበር ዘገባ
የአፍሪካ ሰብአዊና የህዝቦች መብት ኮሚሽን የህዝበ ሙስሊሙን ኮሚቴዎች በማስመልከት ለኢትዪጲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ለተፈጸሙት ኢሰብአዊ የመብት ጥሰቶች ምላሽ እንዲሰጡ ማሳሰቢያ ደብዳቤ ላከ:: ኮሚሽኑ የጻፈውን ደብዳቤ አስመልክቶ ዶክተር አባድር ኢብራሂምን በማነጋገር ሰበር ዘገባ አሰናድተናል:-

The post (ሰበር ዘገባ) የአፍሪካ ሰብአዊና የህዝቦች መብት ኮሚሽን በሕዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴዎች ላይ ለተፈጸሙት ኢሰብአዊ የመብት ጥሰቶች ምላሽ እንዲሰጡ ማሳሰቢያ ደብዳቤ ላከ appeared first on Zehabesha Amharic.

ትርትር …. –ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

 

ከሥርጉተ ሥላሴ 21.03.2015 /ሲወዘርላንድ – ዙሪክ/

እኔ እላላሁ እንዲህ —- ዓለም „ሰው“ ለሚለው ቃል የሚመጥን፣ አቅም ያለው ድርጊትም ትርጉምም የላትም። ፍቅር ግን አለው።

ጠፋብኝ – መንደሩ

የብትንድር  – ግብሩ፤

ንክንኩ – ዛለእግሩ

ንክንፋስ – ምግባሩ

ትርትር ሆነ – በትሩ።

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

እኮ ስለምን ይለፍ እንሰጠዋለን?! እኮ ለምን ይፈቅድለታል? ምን ለማትረፍ? እያዘንኩ ልጀምረው። እኛ በእኛ ላይ ወይነናል። እኛ በእኛ ላይ ሸፍተናል። እኛ በእኛ ላይ ጥቃት እዬፈጸምን – ይመስለኛል። እኮ ለምን? ምን ለማትረፍ? ሃዘኑ እያርመጠመጠኝ ልቀጥለው – እስቲ። ዘሃ ግራው የጠፋበት ዘመን ….

ወያኔ አሸንፎናል ወይንስ አላሸነፈንም? ወያኔ በመንፈሳችን ላይ ጫና መፍጠር ችሏል ወይንስ አልቻለም? እኛስ የመንፈሳችን ስደት ወደ ወያኔያዊ ማንፌስቱ አድርገነዋልን ወይንስ ነፃ ወጥተናል? ዳኛው ህሊናችን ይበይንበት።

አሁን ለእኔ የዲ/ዳንኤል „የአገው ብሄረሰብ አባልነት ወይንም የትዳር አጋሩ ‚ትግሬነት‘“ ምን ይፈይድልኛል ለእኔ ጉዳዬ ነውን?“ በነገራችን ላይ የአገው ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ሥልጣኔ ጉልህና ደማቅ ድርሻ የነበረው፤ ግን አቅም ያለው ዕውቅና ያልተሰጠው፤ ብዙም ያልተባለለት ነው። ሌላው የማንዲጎ ጎንደር ተወልዶ ማደግ ምንስ ዕሴት አለው? እራፊ የቀረች መሬት አንድ አረም በቀለባት ተብሎ መከራ ማዬት። የመጣው ሁሉ እንደ ጥንቸል ቤተ – ሙከራ መሆኑ መፈጸሚያ አልበቃ ብሎ ብተውት ምን አለ ጎንደርን ባዕቱ እኮ ህማማት ላይ ነው። ስለምንስ ብሩኩ ቡቃያ የበቀለበት ዬባለቅኔው! ዬቴዲ እትብት የተቀበረበት አልተጠቀሰም። አስፈላጊ ከሆነ ለንጽጽርም ይረዳ ነበር – አረም አብቃዩና ፍሬ ዘለቁ። ይገርም ነው። የአቶ ኤርምያስ ግማሽ ኦሮሞነትና አማራነት ምን ጠቃሚ ጠረን አለው?“ ወይንም የትናንት በሥርዓትና በሀገር ደረጃ የተከወነ ዛሬም ያለ ኢትዮጵያን የማጥቃት የውጭ ዝንቅ – ገብ ሂደት ከእኛ ጋር ተዋልደው፣ ተጋብተው፣ ተዛምድው ያሉ ወገኖች እዬነቀሱ „የዚህኛው የዛኛው ብሄረሰብ ሃይማኖት ነገድ አባል አይሁድ ምንትስ ማለትስ ምን አመጣው?“ ለዛሬ ወይንስ ለነገ በረከት ይሆናልን? ዛሬም እዬተሰደድን፤ ዛሬም ጥገኝነት እዬጠዬቅን፤ ዛሬም እርዳታ እዬጠዬቅን፤ ዛሬም ከውጭ ሀገር ዜጎች ጋር እዬተጋባን፤ ልጆች እዬወለድን ትናንት እንዲህና እንዲህ ነበሩ በስተጀርባ እከሌ የሚባል ሀገር ነበር ማለቱ ይገባልን? ነገም እኮ ኢትዮጵያ ተለይታ ደሴት ሀገር ልትሆን አትችልም። አስፈላጊው የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከመላው ዓለም ጋር ጠንክሮ ቀጣይ ነው።

ህም! ለነገ ደግሞ ስደተኞችን ለይቶ መተንተኑስ … ክቡሩን የሥጋ – ወደሙ ጋብቻ ከማፈናቀል አንፃርስ ይህ ዝንባሌ  ሃይማኖታዊ ነውን? „ትግሬ“ የትዳር አጋሩ የሆነ ሁሉ በሚፈጽመው የራሱ አሉታዊ ሆነ አዎንታዊ ተግባር ባለቤቱ እያለ ሌላ መንጠላጠያ ሳቢያ መፈለጉ ምን አስፈለገ? ስለምን በምክንያቱ ላይ አናተኩርም? ለዚህም ነው መፍትሄ አመንጭነታችን ታቱ የሚለው። የሚነካካ ነገር ይፈለጋል። የሚወገዝ ነገር ይፈለጋል። ነገ ደግሞ በዚህ ጎሳዊ ማንፌስቶ ተገደው በጠበንጃ ታፍነው የዕለት ኑራቸውን የሚገፉት እዬተነጠሉ ስደት ይታጭላቸዋል። መልካም ነገሮችም አብረው ይናዳሉ – ጥናት አልባ በሆነ ሁኔታ። የሀገር ሃብትነቱ ይዘላል። ለዚህ ከሆነ የነፃነት ራህቡ … ቁርጭምምጭሚቱ ውልቅ ይሆናል። ዛሬም እኮ መስዋዕት የሚከፍሉ ወገኖቻችን አሉበት። በእግር ብረት ሥር ሆነው ስለነፃነት ግንባራቸውን የሚሰጡ – ማገዶዎች አሉበት። በሌላ በኩልም ዬአካላቸውን ካቴና ችለው ኃላፊነት ወስደውም ቤተሰቦቻቸውን የሚያስተዳደሩ፤ ዱላውንም – መፈንከቱንም ግልምጫውንም የወያኔን የቻሉ። ዓይን እያዬ ጆሮም እዬሰማ …. ህ!

ብቻ ለእኔ ዜሮ ሲደምር ዜሮ ወይንም ዜሮ ሲባዛ በዜሮ ሆኖ ነው ያገኘሁት። የሚጠቅመው ለምሳሌ፤  ሥርጉተ በተሰማራችበት፤ ወይንም ኃላፊነት ወስዳ በምታራምደው – እምነት ወይንም የፖለቲካ መስመር፤ ያጠፋቸውን ነገር ነቅሶ በማውጣት፤ በትኖ በመተንተን እሷኑ እራሷን ሞግቶ ማሸነፍ፤ ወይንም እድትታረም ማደረግ ነው እንጂ ሥርጉተ ያደገችበት ማህበረሰብ ወይንም ነገድ አብሮ መወቃት – መታጨድ የተገባ አይደለም። እኔ ላጠፋሁት – ለበደልኩት – ላባከንኩት – ለተሻማሁት ጊዜ ተወቃሿ እኔ ብቻ እንጂ ሌላ ቦታ ስደት መሄድ አያስፈልግም።  „ትግሬነት፤ ኦሮሞነት፤ አገውነት፤ አማራነት፤ ጎጃሜነት፤ ጉራጌነት፤ ሃድያነት፣ እስራኤላዊነት ወዘተ – ወዘተ“ የወል መጠሪያ ነው። በዛ ብሄረሰብ ስንት መልካም ሰዎች፤ ስንት ደጎች፤ ስንት አብነቶች ስንትስ የአደራ ናሙና ዜጎች አሉን? እልፍ ናቸው …

በዛ የማህበረሰብ ማዕቀፍ ስንት አንቱዎች፤ ስንት ሊቀ – ሊቃናት፣ ስንት ቅዱሳን አሉ? እልፎች። …. የተጸዎዖ ስም እኮ የወጣበት ምክንያት እኔን እንዲገልጽ ሆኖ ነው። የወል ሥምም እንዲሁ። ….. የወሉን ሥነ – ሞራል፣ ሥነ – ምግባር ሥነ —- ኑሮ፤ ሥነ – ታሪክ እንዲገልጽ ነው። በአንድ ማሳ አረም ይበቅላል። ፍሬ የሚሰጥም እጽዋትም ይበቅላል። አረሙ ከማደጉ በፊት ዘር እንዳያበላሽ ተነጥሎል ይነቀላል። ፍሬ ዘለቁ ደግሞ እድገቱ እንዳይደናቀፍ ተመጣጣኝ አዬርና ህልው የሚያድርጉ ነገሮች ይሟሉለታል። አሁን እኛ እያደረግን ያለው ግን እንደዛ አይደለም። ሁሉንም አረም እያደረግነው ነው። ትውልድን ለማተካካት ድርሻን በዚህ መልክ መከወን ሰባራ መንገድ ነው። ማንዘርዘሪያ ዬት ይገዛ ይሆን?! ይህ ማለት ግን በዳይም – ተባዳይም፤ የበለጠ እጁን ተጠቃሚ የለም ማለት አይደለም። ከጎሳ ፓሊሲ የሚጠበቁት አሳሮች ሁሉ እስከፈለጋቸው ድረስ፤ በረዶው ሁሉ እስኪበቃው አድቅቆናል ወረራውም – ደቁሶናል። ህልማችን በመሰሉ አይጓዝ ነው ብልሃቱ። ተሽሎ መገኘት የሚባል ብሂል አለ ….

የሆነ ሆኖ „ዛሬ የአማራ ወጣቶች እራሳችን መቻል እንችላለን። ስለዚህ እንገንጠል“ የሚል ጥያቄ እንዳነሱ አንብቤያለሁ። ብዕሯ መከፋቷንም አብራ ጨምራ ግልጻለች። እኔም በተደሞ ነበር ያነበብኩት። እንዲሁም በዚህ ዙሪያ ልንሠራበት የሚገባውን ተግባር እያወጣሁ እያወረድኩ እያለ፤ ቀጣይ ጹሑፍ በተከታታይ ወጣ። ዘር ቆጠራው ቀጠለ። ዝንቅንቅ ያለ- ጭብጡም የተቦጫጨረ – ጉድ። „አይሁድ፣ አገው ወዘተ ወዘተ .. ምንትሶ ቅብጥርሶ“ ምን ያድርጉ እነዚህ ወጣቶች!? ወያኔ በፓሊሲ ደረጃ ጎሳዊ ሶሻሊስትን ንድፈ ሃሳብ ፀንሶ – ወልዶ – አሳድጎ – እዬበተነ እኛ ደግሞ በራሳችን መንፈስ የወያኔ ሃርነት ትግራይን ማንፌስቶ ፍለጋ ስደት ፈቃጅ እንሆንለታለን። እያንዳንዷ የዚህ መሰል ስንጥርና ስንጠቅ ሂደት በኢትዮጵያዊነት ላይ ጫና እዬፈጠረ ስለመሆኑ ከልብ ማሰብ ያስፈልጋል። አንዳንድ ወገኖችን ስታወያዩ ተቆርቋሪነታቸው በሁለመናነት ታያላችሁ። ከዛ – ከዛማ ደስ ብሏችሁ አብራችሁ ስትወያዩ መጨረሻ ላይ መዳራሻቸው ከጎሳቸው ላይ ይሆናል። ስለምን? እኛም አብረን በጎጥ፣ በመንደር ዶክተሪን እንዲህ ብልዩነት መስመር ተመስጠን እዬሠራንበት ስለሆነ። ማርክ ቢሰጥ … ውስጣችን ስለ መውደቁ ማወቅ ቀላል ነው። ለዚህም ነው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ጥቃት በሰነዘረባቸው ላይ ተባደግ ዕይታ የሚኖረን፤ አርበኛ በላይነሽን የሚያደንቅ ርዕዮትን አይጨምርም፤ ርዕዮትን የሚል ኦልባና ሊሊሳን አያክልም፤ ኦልባና የሚል አንዱአለምን አያካትም፤ አንዱአለም የሚል አቡበከርን ይዘላል፤ አቡበከር የሚለው አብርሃምን ይተዋል፤ አብርሃም የሚለው አንዳርጋቸውን ይሰርዛል ወዘተ .. ወዘተ ። ቃል የማውጣት አቅም ያንሳል። መርምሩት – ወገኖቼ በትህትህና፤ አቅማችን ዋጥ የሚያደርገውን አሳማውን ዝንባሌ ….

ይህም ብቻ አይደለም በተገኘው አጋጣሚ ክፍተት የሚፈጥሩ ነገሮች መደፈን ሲጋባቸው – ይሰፋሉ።  „ሊቃውንተ ቤተክርስትያን እኔን ሲያስተምሩ „ነብዬ መሃመድ“ ብሎ መጥራት ወንጀል ነው ብለው አልነበረም። ይልቁንም ማዕድ ላይ እያሉ „‘አላህ አክብር‘ ሲታወጅ፤ እኛ ማዕድ ላይ ሆነን አነሱ ግን ፈጣሪያችን ያመሰግናሉ ይሉ ነበር – በአድናቆት፤ ዝናብ ሲኮርፍ እባካችሁ ለእነሱ ንገሩ ድዋ – ያድርጉ፤ እኛም ምህላ ለሁለት ሰባት እናደርጋለን ሲሉ‘ የዓለም ሊቃውንት 100 ድንቅ ካሏቸው የሥነጹሑፍ ምርቶች ውስጥ ነብዬ መሐመድ አንዱ ናቸው ሲሉ ነበር ያነበብነው“ እንዲህ ሁሉም ነገር መጫሪያ ፈላጊ ሆኖ ቋፍ ላይ ባለበት፤ ሆድ በባሳው ወቅት፤ በግልም በጋራ ዕንባን አምጦ፤ አልቅሶ ውሎ በሚያድርበት የጨለመ – ምዕራፍ ላይ ሆነን እንዲህ ባሉ ጠመዝማዛ የአረም ቅንጦቶች መጓዙ ዛሬንም አያበረክትም። ነገንም አያሰመርቅም። የትናንት አደራንም አያሰነበትም። ተከታይም – አያገኝም። አንድ መምህር ለትምህርቱ አጋዢ ማነጻጸሪያ ወይንም መንተራሻ ቢያስፈልገው መንቀሳቀስ እንዳይችል እስር እኮ እዬተበዬነበት ነው – ህም! ሥምም ማዕቀብ – ድንበር ተጣለበት። ወዮ ነፃነት! በለስ ቢቀናሽ ሥንት የቤት ሥራ እንዳለብሽ እስኪ መትሪው —-

እኛም እኮ መሃመድ የሚባሉ ብዙ ደሞች አሉን እኮ። መሃመድ በሚል ሥያሜ የሚጠሩ የነገ ሀገር ተረካቢ ልጆች አሉን። ወገኖቼ „መሃመድ“ የሚባል ጓደኛ፤ የሥራ ባልደረባ፤ ባለ ሱቅ፤ ጎረቤት ወዳጅ ቢኖራችሁ ሥሙን ስትጠሩ በጥቅሻ ሊሆን ይሆን?! ምን አይነት አሲዳዊ ፍሰት እንደሆነ ለእኔ ግራና ወልጋዳ ነው። ግብጽ ላይ እኮ የቅዱስ አባታችን የአቡነ ተ/ሃይማኖት በክብርና በሞገስ መታሰቢያ አለ። http://en.wikipedia.org/wiki/Tekle_Haymanot። በሀገረ ግብጽ በገዳማት ያሉ ደናግል ሆኑ ማህበረ ምዕመናኑ መጠሪያም እንደ ሀገራቸው የአጠራር ዘይቤ ሲሆንም ቋንቋውም እንዲሁ። ዘልቀን ብንገባበት ያነንም እንወነጅል ይሆን? የትኛውም ዓለም ቅዱስ ጊዮርጊስ መታሰቢያ ብቻ ሳይሆን እልፎች ይጠሩበታል። … እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ስለምን ሃጢያተኛ በዛ? ለሚለው ዲያቢሎስ ስለሚያስታቸው ነውና ስለምን ከዲያቢሎስ ጋር እርቅ አታደርግም ብላ አምላኳን ፈጣሪያዋን ስለመጠዬቋ ከታምሯ ላይ አለ። የእሷ ጭንቀት ለኢትዮጵውያን ብቻ አልነበረም፤ ለዓለም እንጂ። … ቅዱሳን ሀገር የላቸውም፤ የትም ቦታ በዬትኛውም ሁኔታ ሊፈጠሩ ሊላኩ ይቻላሉ።

እንዲህ መላ ተቋማት ኢትዮጵያዊነትን የሚያውጁ በመንፈስም በአካልም ጦር በተመዘዘባቸው ወቅት „ወደ ማንነት ማዬት“ አምራጭ የለሽ መፍትሄ ሆኖ ሳለ፤ የቁርሾ ጉድፍ መበተን በፍጹም ሁኔታ ከትውልዱ ድርሻ ውጪ ነው – ለእኔ። እርግጥ የበለጠውን ጉዳት የሚያውቁት የዬአካባቢው ተወላጆች ስለሆኑ፤ ለመረጃ ልውውጥ ካልሆነ በስተቀር ለነገ የኢትዮጵያዊነት አቅም መቅኖ ግን የግልሰቡን ጎሳ ወይንም ባዕት እዬነጠሉ ማቅረብ፤ ተጠያቂም ለማደረግ ማስላት እጥፍ ድርብርብርብ ኪሳራ ነው። የዚህን የእኛ ትውልድ ዋንኛ የተልዕኮም ዕጣም ሆነ አቅጣጫም ቅርጭጭታም፤ ቀጫጫም ያደርገዋል – ባይ ናት ሥርጉተ – ሥላሴ።

ሰው በማንነቱ፣ በእሱነቱ፣ ከውስጡ ነፃነት እንዲሰማው ያስፈልጋል። ሲተችም፣ ሲጽፍም ነፃ ሆኖ መፃፍ የሚችለው በዚህ መንፈስ ሲሆን ብቻ እንጂ ገና ከዚህ አካባቢ እትብቴ ስለተቀበረ፤ ወይንም ሃይማኖቴ ይህ ስለሆነ ወይንም ነገዴ ይህ ስለሆነ፤ ወይንም የትዳር አጋሬ እንዲህ ስለሆነች ብሎ ስጋት ሊኖርበት አይገባም። ቀጥ ብሎ ለመቆም በራሱ የተማመነ፤ ማንነት ካለ እራሱን ገልጦ ውስጡን ማሳዬት ይቻላል። ውስጡን ማዬት ከተቻለ የጎሸውን ለማጥራት፤ እንክርዳድና ግርዱን መለዬት ብቻም ሳይሆን ጤናማና አዎንታዊ መንገድ ለመደልደልም ያስችላል። የተጎዳውንም አይዞህ ከጎንህ ነን ለማለት ይረዳል። ይህን እኛው ከነፈግነው ግን የድብብቆሽ ጨዋታ ይሆናል። የድብብቆሽ ጨዋታ ደግሞ ራዕዩን የድቡሽት ቤት ያደርገዋል፤ ርህራሄ – የለውምና። ከሁሉ በላይ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ በፈቃድ እጃችን ሰጥተናል ማለት ነው። ተወረናል። አቅምም አይኖርም የጎሳ ማንፌስቶን የመተቸት፤ የማውገዝና የመታገል። ነገም ወጮፎው ያዬለበት ዳመናማ ነው።

በአንድ ሥርዓት ውስጥ እልፎች ሠርቶ በማደር መኖር ግድ ይላቸዋል። ሌላም ሃላፊነት አለባቸው። እኛ ትተነው የመጣነውን ትውልድን የመተካት። ከዚህ ውጪ አማራጭ የለም። ስደቱም ቢሆን የአንድ ሀገር ህዝብ እንዳለ ሊሰደድ ከቶውን አይችልም። ጫካ ልግባ ቢልም እንደዚሁ። እኛ ደግሞ አንድ የነፃነት አርበኛ እስረኛ ቤተሰብ አብልተን ለማሳደር የምንችል አይደለንም። እንኳንስ ለእልፍ አለንልህ በማለት ለኑሮው መደጎም። ቀላሏን በወር አንድ ብር በዓመት በነፍስ ወከፍ 12 ብር እንደዬአለንበት ሀገር ማዋጣት እንኳን የምንፈቅድ አይደለንም። በእጃችን አለን የምንላት ቤሳ ሳንቲም የለንም። አቅም ያለው እራሱን በራሱ የሚያስተዳደር ተቋም ለዘር – የለንም። እንኳንስ ከዚህ የላቁ ነገሮችን ለመከወን። ፕሮጀክቱን ለመዘርጋት ቢታሰብም እንኳን፤ ፕሮጀክቱ ከመፈጠሩ በፊት ለራዕዩ ቀብረ – ሥርዓት ይታወጃል። /እራሴ ሞክሬ አይቸዋለሁ/  10 ሺህ ወገን በወር አንድ ብር ቢያወጣ 10 ሺህ ይሆናል በዓመት ደግሞ 120ሺህ …. ይሆን ነበር። ከሁሉ በላይ መንፈስን ወጥ አድርጎ የመግራት፤ አቅሙም አንቱ ነበር ተጨማሪ የኃይል አምንጭነቱም ጉልላት ይሆን ነበር። ሌሎችም ዕምቅ ትርፎች አሉበት ምህረት እርቅ ተስፋ ፍቅር ወዘተ … ለማንኛውም መድረስ አለመቻል ነው መጠነ ሰፊው ህዝብ ተጎጂ ሆኖ ግን ሰጥ ለጥ ብሎ እዬተገዛ ያለው። መድረስ አንችልማ? ቅልብጭ ያለው እውነት ቁምነገርም ይሄው ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ ቁልጭ ያለ ባርነት ነው ያለው። ዴሞክራሲ ከባርነት ነፃ ለወጡ ሀገሮች ነው። „ እዬዬም ሲደላ ነው።“ የኛው ግን ከጎጥ አገዛዝ ባርነት ገና አልወጣነም። በዚህ ሁለመናው እራስ ከእግር በሆነ ሁኔታ ላይ ሁነን ተጨማሪ ችግር ለዛውም ጥላቻ- ንቀት – ዘር በጣሽ መስመር ስንቀጣጥል ወይንም ስናመርት ውልን እናድራለን። — ምግለት!

ለመሆኑ አዲስ ሥርዓት ተሳክቶ ቢመሠረት ከሥራአቱ ጋር የሠራህ እዬተባለ ደግሞ ሌላ የስደት መንገድ፣ የመከራ ዘመን ልናጭለት ይሆን – ለዚህ መከረኛ ህዝብ? ህ! ዛሬ ሥልጣን ላይ ያለው የትግራይ ወያኔ ሃርነት ማንፌስቶ ነው። ነገ ይህ ማንፌስቶ አመድ ቢሆን፤ በዚህ ሥያሜ ሥር የነበሩ በሥርዓቱ ውስጥ ሠርተው ለማደር እንደ ሌሎች ይገደዱ የነበሩ የነገዱ አባሎች ወገኖቻችን ከእነሱ ጋር የተገባ፤ የተዋለደ ወገን አብሮ በነቂስ የበቀል መሻሪያ ሊሆን ነውን?! ሃራም ጋብቻ፤ ሃራም ጉርብትና፤ ሃራም አበልጅነት ሊባል ነውን? የጋራችን ልጆች ደግሞ እኮ አሉ። ለማን ነው ድካሙ?! ለቀጣዩ ትውልድ አይደለንም? ልጅነት እኮ የአንድ ነጠላ ቤተሰብ ብቻ አይደለም። ኃላፊነቱ የማህበረስብ ነው። እርክክብ አለ – የትውልድ። እንዲህ ያለ የተጋጋጠ ወይንም ጠረኑ የተነነ – ብዕር ለእኔ አረም የዘራ፣ አረም የሚያመርት፤ አረም የሆነ መንፈስ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነቱን ወዶ ስደት የላከ ነው። እራሱን አጥቷል በፈቃዱ። „ተቆርቋሪነት“ ትልቅ ተልዕኮ አለው። እጅ – ለእጅ፤ ደም – ለደም፤ ሥጋ – ለሥጋ፤ የሚያያዝባቸው ሊቃናተ – ሁነቶች እረቂቃን ናቸው።

እንጃ! እንዴትና እንዴት ይሆን እምናስበው? ከቱግታ ወጥተን ተግ ላይ እንስከን፤ ኢትዮጵያዊነት በዕውን በውስጣችን ካለ፤ እንዲሁም ያ ክቡር ሰንደቅዓላማ በወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ህግ ስለታሰረበት ወገን፤ — የለበሰው፣ ሰንደቁን ያፈቀረ ምክንያት ተፈልጎ ግዞት መላኩ እያገላበጠ መንፈሳችን – ከቀቀለው። እባካችሁን እራሳችን ‚እራሳችን‘ እንዲቀማው አንፍቀድለት?!!!

ወደ ራሳችን እንመለስ – በአክብሮት። ወደ ክብራችን እንመለስ – በዘንካታ ትህትና፤ ወደ ውስጣችን እንይ – በጀርጋዳ ቅንነት፤ ወደ ሥነ – ትውፊታዊ ህይወታችን እናስተውል – ከልባችን። የውበታችን ረቂቅነት ከልባችን ይግባ፣ ከደማችን ጋር ይመሳጠር – ያውጋም። ግልቢያ – ለፈረስ ነው፤ ስግረትም – ለወንዝ፤ በረራም – ለወፍ፤ የሰው ልጅ አላምጦ መዋጥ አለበት። „አደራ ለዛውም – የሀገር አደራ፤ አደራ ለዛውም – የዜግነት አደራ፤ አደራ ለዛውም የአኩሪ ታሪክ ባላቤትነት መለያነት – የነፃነት አደራ አለብን፤ አደራ ትውልድን ገንብቶ የመተካት ውድ አደራ አለብን። አደራ በመሆን የከበረ የፍቅር ልዑቅ አደራ አለብን“ ለዚህ እንማስን። የጠላትን ጥቃትን የሚቋቋም ሙሉ አኃታዊ ሥነ ምግባርን አምጠን እንውለደው። የጥቃታችን መሠረተ ፍሬ ነገር የጎጥ ዶክተሪን ነውና።

የትም ሀገር የተሰደደ ወይንም ሊሰደድ ያሰበ፤ ወይንም በትምህርት – በጋብቻ፤ ውጪ የሚወጣ ሁሉ መጀመሪያ ፎርሙን የሚሞላው „ኢትዮጵያዊ“ ብሎ ነው። ወያኔ የፈጠረውም ይሁን እኛ እያመጣን ያለው ልጥፍ ልሙጥ ጉድ ለውጭ ሀገር ዜጎች እራሱ ባዕድ ነው። የሚገርመው በዚህ ማንነት ውስጥ ኑሮ ከተደላደለ በኋላ የተገለበጠ እራስን ያልሰጠ መሽሎክ ይታያል። እሱን ህሊና ይዳኘው። ነገም ቢሆን ኢትዮጵያ የሚለው ሥያሜ ይጠፋል ብሎ ማሰብ መሽቶ አይነጋም ማለት ነው። ወይንም አህጉራት ሁሉም ሰባቱ ውቅያኖስ ይሆናሉ ብሎ ማለም ነው። የዕውነት ፍልቀቱ ዳርቻ የለውም። ኢትዮጵያዊነት ዕድሜውን መገደብ አይቻልም። ዘላቂ ነውና … ። የጎሳ ራዕይ በራሱ ጊዜ በመዳህኒዓለም ጥበብ ከስሟል። በዬትም ዓለም ከእንግዲህ እንደበፊቱ ቁልምጫ የለም።

ለማንኛውም መለመድ ያለበት መንገድ ለዛሬም ለነገም፤ የትኛውም ወገኔ እኔ ባጠፋሁት፣ በፈጸምኩት ስህተት ብቻ ሳይሆን፤ ስህተት ነው ብሎ ባሰበው ወይንም በሚመስለው ወይንም ስህተት ነው በሚለው ቢፈልግ ይክተፈኝ፤ ይተርትረኝ፤ ይፍለጠኝ፤ በመዶሻ ይቀጥቅጠኝ። ከቻልኩ ሙግቴን አቀርባለሁ፤ ከናቅሁት ደግሞ እተወዋለሁ፤ ነገር ግን ዕትብቴ የተቀበረበት ክ/ሀገር ሆነ ነገዴ ወይንም የሃይማኖቴን ዶግማ ግን መንካት የለበትም። በፍጹም። ትዳሬና አካሌም። ደግሞ ነፃነት የዘር ሀረግ ቆጠራ ቀመር አይደለም። ነፃነት ያደገና የሰለጠነ – ሰው የመሆን፤ እንደ ሰው ለመኖር ፈቃዱን ሰው የመስጠትም ሆነ የመንሳት መብት እንዴለለው የሚገልጽ ልዩ ክስተታዊ የእኩልነት አምክንዮ ነው። ነፃነት በጭነት አይተረጎምም። ጓዘ ቀላል ነው።  ….

በመጨረሻ እምለው ኢትዮጵያ ሀገራችን የአድምታ ሚስጢር ልዑላን ዲታ ናት – ተርፎም ይናኛል። ንባቡን፣ ትርጉሙን፤ ማመሳጠሩን ዓራት ዓይናማዎች አሉበት። ክህነተ ሥልጣን የመስጠትም የመነሳትም አቅም ያለው ሃይማኖታዊ ዶግማ በማስፈጸም ከአቨው ነው። ለነገሩ ሥልጣነ ክህነት ሰውኛም አይደለም። „ካልተሠራበት እሳት ሆኖ ያቃጥላል“ ይላሉ – አቨው። ጠያቂውም መዳህኒተአለም ነው፤ እንደ ሥራው ይላል መጸሐፉም። ባለቤቱ „ቅብዕ – ሥልጣኑን“ ቢያረክሰው እንኳን „ተመሥጥሮ ክብሩ አለ“ ይላሉ – አቨው። ስለዚህም „አትዳፈሩት!“ ብለው በአፅኽኖት ይመክራሉ። ለነገሩ እኔ „እኔን“ ሳከብረው ሌላውም እኔን ያከብረኛል። እኔ ሌላውን ሳከብረው ከሌላው ጋር ያሉ መንፈሶች ሁሉ እኔን ያከብሩኛል። ስጥለው ክብሬን የትም ደግሞ ሁሉም የክብረት መንፈስ ይሸሸኛል።

እህ! ሌላስ ያደግነበት ማህበረሰብ እኮ ታላቆችን ወንዶች ጋሼ፣ አይዋ፤ እያያ፤ ጥላዬ፣ ጋሻዬ ብለን አክብርን አቆላምጠን አልበረንም የምንጠራው፤ ሴቶችን እትዬ፣ አቫዬ፣ እቴ-ወለላዬ፣ እታታ፣ እታለም፤ እቴዋ፤ እቴ-አባባ፤ እቴ-አንጀቴ፤ እቴ-ማሬ አልነበረም? ብልህ አዋቂዎችን፤ ማር፣ ቀኝ ጌታ፤ የኔታ፣ ብላቴ፣ ጌታ፣ አለቃ አልነበርንም፤ እንኳንስ ዬሥርዓተ – ቤተክርስትያናት ዓዕማዳተ – ሃውልተ – ሚስጢራት ያለበት „ዲቁና“ ወይንም „ነብይነት“። እንደ ወርዳችን እና ቁመታችን ልክ ቢኖረን መልካም ነው። ልቅነት የእኛ አልነበረም። ጎንደሬም ሲተርት „ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል“ ይላል። ልብ ይስጠን አምላካችን። ከእኛ በመንፈስ በላቀ ጥንካሬና ጽናት ሆነ፤ በማገዶነት የተሻለውን የሚያደርጉት ግን ያልበሉትን ዕዳ እንዲከፍሉ የተገደዱትን አዲስ የትውልዱ – የዘመኑ ባለቤቶች /ግርድ – ድቃቂ – እንክርዳድ/ እዬዛራን አናምሳቸው – እባካችሁን /// //////  መሸቢያ ሳምንት – ለእኔዎቹ። ውዶቼ ዘሃበሻ! እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል።

ኢትዮጵያዊነት አሸናፊ ቀለማም ማንነት!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

The post ትርትር …. – ከሥርጉተ ሥላሴ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live