Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

Health: የአረንጓዴ ሻይ የጤና ጥቅሞች

$
0
0

Green Tea

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

የሰዉነት ክብደትን ለመቀነስ
አረንጓዴ ሻይ የሰዉነት ክብደትን እና የተከማቸ ስብን የማስወገድ አቅም አለው።

ለስኳር ህመም
የስኳር መጠንን ባለበት ለመቆጣጠር ይረዳል።

ለልብ ህመም
ተመራማሪዎች እንደሚያስረዱት ከሆነ የደም ስር ግድግዳን እንደተፍታታ እንዲቆይ እና የተከማቸ ደም እንዳይኖር በማድረግ ከድንገተኛ ልብ ህመም ይከላከላል።

ለኮሌስቴሮል
ጠቃሚ ያልሆነውን የስብ አይነት ከደም ውስጥ በመቀነስ ጠቃሚው ስብ እንዲበዛ ይረዳል።

ለደም ግፊት
በመደበኛ ሁኔታ አረንጓዴ ሻይን መውሰድ የደም ግፊት መጨመርን ይከላከላል።

ፀረ ባክቴሪያ እና ፀረ ቫይረስ
ይህ የሻይ አይነት ባክቴሪያ እና ቫይረሶችን ማጥፋት እንደሚችል ተመራማሪዎች ይናገራሉ። ለጉሮሮ ህመም፣ ለጥርስ እና የአፍ ውስጥ ኢንፌክሽኖች ፍቱን መሆኑንም አሳውቋል።

ለቆዳ ጤንነት
የቆዳ መሸብሸብን ይከላከላል በፀሃይ እንዳይጎዳም ይረዳል።

ጤና ይስጥልኝ

The post Health: የአረንጓዴ ሻይ የጤና ጥቅሞች appeared first on Zehabesha Amharic.


በኢትዮጵያ ሰላም የሚያመጣ የአማራ የተራድኦና የዕርቅ ድርጅት ያስፈልጋል- (ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ)

$
0
0

Getachew Haileመነሻዬ የሻለቃ ዮሴፍን ትግል ይቀጥላል የሚል ርእስ የሰጠው ዘንድሮ አዲስ አበባ ላይ የታተመው መጽሐፍ ነው። ያነበብኩት ቁጭትና ንዴት እየተሰማኝ ነበር። ለዚህ ሰውነት የሚጎዳ ስሜቴ ዋናው ምክንያት የመጽሐፉ ደራሲ እንደገለጸው፥ ጀኔራል አማን አንዶም የተሻለ ለውጥ ለማምጣት ዕድሉ እጃቸው ላይ ወድቆ ሳለ፥ የተሳለ ቢላዎ የያዙ አራጆች ወደቄራ እንደሚነዱት የደለበ በሬ ወደሚገደሉበት ሁኔታ ሲመሯቸው፥ ዓይናቸው እያየ እጃቸውን ሰብስበው በጥሞና መሄዳቸው ነው። ደራሲው እንደሚለው ራሳቸው ጀኔራሉ የመረጧቸው ረዳቶቻቸው ወጣት የጦር መኳንንት (አንዱም ደራሲው ነበር) የደረሳቸውን መረጃ እየጠቀሱ ሲያስጠነቅቋቸው ሰልችቷቸው ኖሮ፥ “ስሙ፣ እኔ የምሰራውን አውቃለሁ፡ ዝም ብየ ባልተጣራ መረጃ አልጓዝም፡ እንድታውቁ የምፈልገው፣ አማን ማለት ደርግ ነው፣ ደርግ ማለት አማን ነው፡ ወደፊት በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት ነገር እንድታነሱብኝ አልፈልግም፡ እዚያም ያሉት እኮ ከማንም የሚያንሱ አይደሉም” አሏቸው። እንደ ሰንጠረዥ፥ እንደ ኳስ ጨዋታ፥ በአንድ ስሕተት የተመኘነው ለውጥ ገደል ገባ።

የዚህ ግራ የገባው የጀኔራሉ አቋም ምክንያቱ ምን እንደሆነ ወጣቶቹ ረዳቶቻቸው በደረሳቸው መረጃ ዐውቀውታል፤ ዶክተር በረከተ አብ ሀብተ ሥላሴ ረዳቶቻቸውን ትተው ከደርግ ጋር እንዲተባበሩ ስለመከራቸው ነው። በበረከት አስተያየት ጊዜው ሲደርስና ሲያመች ደርጎችን ማስወገድ ይቻላል፤ እነዚህን ግን አይቻልም። (ባይቻልና ለውጡን እነዚህ የአካዴሚ ምሩቆች ቢመሩት ምን ይሆን ነበር?)

ልጽፍ ያሰብኩት እንኳን በጀኔራል አማን ስሕተት ስለባከነው ዕድል ሳይሆን፥ ጀኔራሉ ለእርዳታ የመለመሏቸው ወጣት የጦር መኳንንት ማንነት ስለሰጠኝ ትዝብት ነው። እነዚህ የጦር መኳንንት የጀኔራል አማንን ችሎታና በጦር ሠራዊቱ ዘንድ ያላቸውን ተወዳጅነት በመተማመን እሳቸውን መሪ አድርገው ንቅናቄ ለማካሄድ ሞክረው ነበረ። የነዚህ ወጣት ሹማምንት ማንነት ሁለት ቁም ነገሮችን አሳይቶኛል። መጀመሪያ ስማቸውን፥ ገጽ 38 ላይ እንደተዘረዘረው ልቅዳው፤ የዚያን ጊዜ ማዕርጋቸው የሁሉም ሻለቅነት ነበር።

አብዱላሂ ዑመር
ሽመልስ መታፈሪያ
አበራ ባንቲዋሉ
ሁሴን አሕመድ
ዮሴ ያዘው
ካህሣ ወልደአብ
ጎሹ ወልዴ
እምቢበል አየለ

እነዚህ ወጣት የጦር መኳንንት ከተለያየ ጎሳ መምጣታቸውን ስማቸው ይመሰክራል። ፍጹም የአማራ ስም ያላቸው በቍጥር በዛ ይላል። ግን ሁሉም አማሮች ናቸው ለማለት ፈጽሞ አይቻልም። ሌላው ቢቀር ጎሹ ወልዴ አማራ እንዳይደለ እናውቃለን። የነዚህ ወጣቶች በአንድ ቡድን ተስማምቶ መሰለፍ ሁለት ቁም ነገሮችን ያስገነዝበናል፤ አንደኛ፥ የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ጎሰኝነት አልነበረበትም፤ ሁሉንም ለሀገራዊ ቁም ነገር በአንድ ዓይነት ሙያ እኩል አሰልጥኖ ለግዳጅ እኩል አስሰልፏቸዋል። ሁለተኛ፥ ወጣቶቹም ለውጥ ለማምጣት አብረው ሲዶልቱ፥ ጎሰኝነት ኢትዮጵያውያንነታቸውን አላሰናከለባቸውም፤ ለአንድ ዓላማ በመተማመን በአንድነት ቆመዋል። ለአንደኛውም ሆነ ለሁለተኛው ቁም ነገር አለቃቸውና መሪያቸው ሊያደርጉት ያሰቡት አማን አንዶም ከማን ጎሳ እነደነበረ እናስታውስ።

ሕዝብ የተመኘውን ለውጥ (ዲሞክራሲን) ትተው የጎሰኝነትን መርዝ የረጩብንና አሁን ደግሞ ሀገሪቷን የወረሷት ጉደኞች እስኪጨፍሩብን ድረስ፥ እኛ የምናውቃት ኢትዮጵያና መንግሥቷ ከጥንት ጀምሮ እንደዚህ ነበሩ። የወረስናት ኢትዮጵያ ይኸን ትመስል ነበር፤ ነበር፡ ነበር!

የጉደኞቹ መርዝ መጀመሪያ ጊዜ የተረጨው በተማሪዎቹ ንቅናቄ ውስጥ እንደነበረ እናስታውሳለን። ደርግ ድጋፍ ያገኘ መስሎት በኋላ እስኪያፈገፍግ ድረስ ኮሚኒዝም የሚባል የማባባሻ ዘዴ ከሶቬት ዩኒየን እያመጣ አፋፋመው። በፍልስፍናው ላይ ያሰበበትም ያላሰበበትም ሁሉም እኩል ሆይ አለለት። የሚያዳላን እንጂ ሁሉን እኩል የሚያይ አስተዳደርን ማን ይጠላል? ግን ፍልስፍናው “ኢትዮጵያ የጎሳዎች እስር ቤት ናት፤ አሳሪዎቹም አማሮች ናቸው” የሚል መሆኑ ቀደም ብሎ በፍልስፍና ደረጃ ቢታወቅም አሁን ሥር እየሰደደና በሥራ ላይ ሲውል አሠጋ። ይኸን ያነሣሁት ያልተሰማ አዲስ ታሪክ ለማሰማት ሳይሆን፥ ቀጥሎ ወደማነሣው ትዝብት እንዲያሸጋግረኝ ነው።

ወጣቶቹ የጦር መኳንንት የጀኔራል አማንን መሪነት ካጡ በኋላ፥ የለውጡን አመራር ከደርግ ቀምቶ ቀና አቅጣጫ ለማስያዝ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ብዙ ጊዜ በሰዋራ ቦታ ላይ እየተገናኙ ተወያይተዋል። በአንዱ ስብሰባቸው ላይ አብዱላሂ (ዑመር) እንዲህ አለ፤

ይህንን በሀገራችን ላይ የተፈጠረውን አሰቃቂ ሁኔታ፣ እኛ አሁን ባለንበት ደረጃ፣ ልንለውጠው እንደማንችል አምናለሁ፡ ሆኖም ደግሞ፣ ይቅርታ አድርጉልኝና፣ እኔ በአደሬነቴ ሳየው፣ በሀገራችን ውስጥ ጭቆና አልነበረም ለማለት አልደፍርም፡ ይኽንንም ስል፣ ለውጡ አሁን በተያዘው መንገድ ፣ በእስራትና በጭፍጨፋ፣ ይቀጥል ማለቴ አይደለም፡ ነገር ግን፣ እኛ ምንም ማድረግ ካልቻልን፣ ምናለበት ለአንድ አመት ያህል፣ አብረን እየሠራን ብናየው፡ ደርግም እኰ፣ ሲረጋጋ፣ ምናልባት፣ ሕዝብ የሚቀበለውን ለውጥ፣ [ሊ]ያመጣ ይችል ይሆናል፡ ያ ካልሆነ ደግሞ፣ የዚያን ጊዜ እንደገና እንሞክራለን፣

ልብ እንበል፤ የጀኔራል መንግሥቱ ንዋይ አመፅ ለውጥ ለማምጣት ነበር። የ“ትግል አይቆምም” ጸሐፊና ጓደኞቹም ያድሙ የነበረውና ትግሉን የቀጠሉት ለውጥ ለማምጣት ነበር። በሀገራችን የፖለቲካ ለውጥ ማስፈለጉን ማንም አይክደውም። ሕልማችን ጥንታዊት አገራችን ዘመናዊ ዲሞክራሲ እንዲሰፍንባትና ሁላችንም በነፃነትና በእኩልነት እንድንኖር ነው። በአጭሩ ዲሚክራሲን እንደምንፈልገው አድርገን እንቀርጸዋለን እንጂ በአሁኑ ዘመን ተወዳዳሪ አይቀርብለትም።

አብዱላሂ ዑመር ግን የለውጡን አስፈላጊነት ያየው ከዲሞክራሲና ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንጻር ሳይሆን፥ ከጎሰኝነት ነው። በእሱ አእምሮ ለውጥ የሚያስፈልጋቸውና የማያስፈልጋቸው ኢትዮጵያውያን አሉ። የኢትዮጵያን ሕዝብ በአእምሮው ውስጥ ለውጥ ከሚያስፈልገውና ከማያስፈልገው ከፍሎታል። ይህ እምነት የአንድ አደሬ ነው ወይስ እንደዚህ የሚያምኑ ሌሎችም አሉ? አጭሩ መልስ የወያኔዎችን የጥርቃሞ ፓርቲ (ኢሕአዴግን) ዘርዝሮ ማየት ነው። “እነዚህ ወያኔ የፈጠራቸው ተቀጽሎዎች ናቸው” ብንልም፥ በፖለቲካው ደስተኞች የሉባቸውም ለማለት አንደፍርም። አሉባቸው። በሕዝብና በመንግሥት ዘንድ ሥር ሰድዶ የነበረው ኢትዮጵያዊነት እንዳይፋፋ፥ መጀመሪያ የተማሪዎቹ ንቅናቄ፥ ቀጥሎ ደርግ፥ አሁን ደግሞ ወያኔዎች ወኻ ከልክለው አጠውልገውታል። በምትኩ ጎሰኝነትን ስለተከሉበት፥ የትግሉ መልክ ተለውጧል። ለዚህ ነው የሀገር ወዳዱ የትግል ሰይፍ ሁለት ስለት ያለው መሆን ያለበት፤ አንዱ ጎሰኝነትን መጒመጃ ሲሆን ሁለተኛው ለጥንቱ (ለዲሞክራሲ) ትግል መንገዱን መጥረጊያ ይሆናል።

በጎሰኞቹ እምነት መሠረት፥ ለውጥ የያስፈልጋቸው (“” አጥብቀን እንያዝ) የተባሉት እነማናቸው? “ኢትዮጵያ የጎሳዎች እስር ቤት ናት፤ አሳሪዎቹም አማሮች ናቸው” ከተባለ፥ ለውጥ የማያስፈልጋቸው አማሮቹ መሆናቸው ነው። ጉዳዩ ለውጥ የማያስፈልጋቸውን ኢትዮጵያውያን ለይቶ ከማወቅ ላይ አላቆመም። የችግሩ ምክንያት (የኢትዮጵያን ጎሳዎች አሳሪዎችና ጨቋኞች) እነሱ ስለሆኑ፥ ለውጥ

ለማምጣት መፍትሔው “ለውጥ የማያስፈልጋቸውን” መምታት ነው ከሚለው ውሳኔ ተደርሷል። ይኼ እኮ ያንን ሁሉ የኢትዮጵያ ጎሳ በአማራው ሕዝብ ላይ በጠላትነት ማስነሣት፥ የአማራው ሕዝብ ሠላሳ ሚሊዮን ከሆነ ሕዝብን እርስ በርስ ማጫረስ ነው!!
መፍትሔው ምንድን ነው? አማራውን ታጠቅ ማለት የባሰውን ማፋጀት ይሆናል። በዘር መደራጀት ደግሞ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የታሪክ ተቺዎች ርእስ አድርጎ መቅረት ይሆናል፤ በተለይ በአማራው ላይ አያምርበትም። ግን በዘር፥ በሃይማኖት፣ በጾታ፥ በቀየ፣ በሙያ መደራጀት ፍጹም አስከፊ ርምጃ ነው ወይ? መልሱ እንደ ድርጅቱ ዓላማ ነው፤ ሰዎች ድርጅት የሚያቋቁሙት ወይ ራሳቸውን ለመጠበቅና ባህላቸውን ለማዳበር፥ ወይም ሌላውን ለማጥቃት፥ የፖለቲካ ፓርቲ ለመሆንና በመንግሥት ንብረት የራስን ወገን ብቻ ለመጥቀም፥ ወይም የሌላውን ዘር፥ የሌላውን ሃይማኖት፣ ባለሌላውን ጾታ፥ የሌላውን ቀየ ነዋሪዎች፥ የሌላውን ሙያ አባላት ለማጥቃት ይሆናል። ይኼኛው ዓይነት ድርጅት በሕግ መከልከል፥ መኰነንም አለበት። ለመረዳዳት፥ ከዚያም አልፎ ሌሎችን ለመርዳት ከሆነ ግን በሕግ መፈቀድ፥ መደገፍም አለበት።

እንዲያውም እኮ፥ የአንድ ሀገር የዲሞክራሲ መሠረት እንደዚህ ያሉ የተራድኦ ሕዝባዊ ድርጅቶች መብዛትና መጠናከር ነው። በአሜሪካን አገር የጥቁሮች ሰብአዊ መብት ሊከበር የቻለው ጥቁሮች ለመብታቸው ማስጠበቂያ ባዘጋጁት ድርጅት ጥረትና መሪነት ነው። የሴቶች ማኅበር የሴቶችን መብት ከማስከበር አልፎ፥ ሴቶች በፖለቲካ እንዲሳተፉ ቀን ከሌት እየሠራ ነው። በምርጫ ጊዜ፥ “የእስፓንኛ ተናጋሪዎች ድምፅ ወዴት ይሄድ ይሆን?” የሚለው ጥያቄና መልሱ የጋዜጦቹን የመጀመሪያ ገጽ ይይዛሉ።

የተጠናከረ የአማርኛ ተናጋሪዎች (የአማሮች) የተራድኦና የዕርቅ ድርጅት ቢኖር፥ ለሀገሪቱ የሚሰጠው ጥቅም ወሰን አይኖረውም። እግረ-መንገዱንም በአማራነታቸው በየቦታው በተናጠል ስለሚጠቁት ድምፃቸውን ማስተጋባትና ለመርዳትም ፈጥኖ ለመድረስ ይችላል። ዋና ዓላማው ግን፥ ዕርቀ ሰላም ማውረድና ለዲሞክራሲ መዳበር አመርቂ አገልግሎት መስጠት ነው። የአማሮች ቊጥር ብዙ ነው ብለናል፤ በዚያ ላይ በደጉም በክፉውም ምክንያት ከሌሎቹ ጎሳዎች ጋር በደም የተሳሰረ ስለሆነ፥ ለአንድነት፥ ለነፃነት፥ ለእኩልነት የቆመን የፖለቲካ ተወዳዳሪ ዘርና ሃይማኖት ሳይለይ ለመደገፍ ዝግጁ ነው። ለቍጥረ-ትንሽ ጎሳዎችም መከታ ይሆናል። ኢትዮጵያን ከዘራፊዎች ነፃ የሚያወጣት ፓርቲ የአማራው የተራድኦና የዕርቅ ድርጅት የሚደግፈው ፓርቲ መሆኑን ወያኔዎች ስለሚያውቁ፥ አማራ እንዲደራጅ አይፈልጉም። በአንድ በኩል፥ “አማራ በዘር አይደራጅም” እያሉ አማራውን የሚያደናግሩትን፥ በሌላው በኩል፥ “አማራ እንደገና ሊገዛችሁ ነው” እያሉ ጎሳዎችን ከሥጋት ላይ የሚጥሉትን የሚሽረው የአማራ የተራድኦና የዕርቅ ድርጅት ነው።

አማርኛ ተናጋሪው እንዳይደራጅ የተጣለበትን የውጪ ተጽእኖና የውስጥ የሕሊና ደንቃራ አንሥቶ ለሦስት ግዴታ መደራጀት አለበት፤

አንደኛ፣ ከጎሳዎችና ከድርጅቶቻቸው ጋር ውይይት (dialogue) ለመክፈት። በውይይቱ ብዙ ነገሮች ይነሣሉ። አለመግባባት ካለ፥ ምክንያቱ ምንድንነው? መቸም ወያኔዎቹ ጎሳዎችን በአማራው ላይ ለማስነሣት የቀናቸው፥ ሻለቃ አብዱላሂ ዑመርም፥ “እኔ በአደሬነቴ ሳየው፣ በሀገራችን ውስጥ ጭቆና አልነበረም ለማለት አልደፍርም” ያለው ያለምክንያት ነው ለማለት አልደፍርም። ምክንያቱ ምንድንነው? መሰማት አለበት። አማራውም ላለበት ክስ ሕዝባዊ ፍርድ ቤት አቋቁመን በሰባት ወይም ዘጠኝ ገለልተኛ ዳኖች ፊት መልስ መስጠት አለበት። ከሳሾችም ተከሳሾቹም የምሁራን ምስክሮች እየጠሩ ስለሚሟገቱ፥ ፍርድ ቤቱ ሕዝብ የሚታዘብብበር ትልቅ የምሁራን ጉባኤ ይሆናል። የተረታ ይክሳል፤ የረታ ይካሳል።

ሁለተኛ፣ በምርጫ ጊዜ ኢትዮጵያ-አቀፍና ለኢትዮጵያውያን ሁሉ የሚጠቅም የኢኮኖሚ እድገት አጀንዳ ያለው ፓርቲ የሚያቀርበውን ተወዳዳሪ ለመደገፍ። ተወዳዳሪው የየትኛውም ጎሳ አባል፥ የማንኛውም ሃይማኖት ተከታይ ሊሆን ይችለል። እንዲህ ያለ ድጋፍ ለመስጠት የድርጅቱ ቃል ኪዳን ይሆናል።

ሦስተኛ፣ ማንም ኢትዮጵያዊ በቋንቋው፥ በጾታው፥ በሃይማኖቱ ምክንያት መንግሥት ሲያጠቃው ፈጥኖ ለመድረስ። ድርጅቱ ሲቋቋም፥ ለምሳሌ ለተፈናቀሉት አማሮችና መሬታቸውን ለከበርቴ ተነጥቀው ለተባረሩት አኝዋኮች አለኝታ ይኖራቸዋል።

አማርኛ ተናጋሪው ኢትዮጵያን ለማዳን ከአባቶቹ የወረሰው የታሪክ ግዴታ አለበት። ግዴታውን ለመወጣት ብዛቱና ታሪኩ ይረዳዋል። ታሪካችንን ስንመረምረው፥ ከአክሱም ዘመነ መንግሥት ጀምሮ የኢትዮጵያን መንግሥታዊ ሥልጣኔ የመሠረተውና ያዳበረው፥ እንደ ግዕዝ ሴማዊ ቋንቋ ከሚናገረው ክፍል የሆነው የአማራው ሕዝብ ነው። ዛጔዎች ሥልጣኑን ለጥቂት ዓመታት ቢወስዱትም ያንኑ የአማራ ሥልጣኔ እያዳበሩ ተጓዙ እንጂ ሌላ ሥልጣኔ አላመጡም። አፄ ይኩኖ አምላክና ወራሲዎቹ ሥልጣኑን አስመልሰው፥ የጥንቱን ሥልጣኔ መጀመሪያ በሸዋ-አምሐራ፥ በኋላ በጎንደር አስፋፉት። አፄ ዮሐንስም የሥልጣኑን ማእከል ወደትግራይ አመጡት እንጂ፥ አክሱም ላይ የተመሠረተውን ሥልጣኔ አልለወጡትም። የዳኝነት ችሎታቸውን የሚያካሂዱት በአማርኛ ነበር። ንጉሡና በሳቸው ዘመን የነበሩ ሌሎቹ የትግራይ ባለሥልጣኖች ከውጭ አገር ጋር ይጻጻፉ የነበረው በአማርኛ ነበር። ደብዳቤዎቹ አሁንም በውጪ ሀገር መዛግብት ተከትተው ይገኛሉ።

አማራው ግዴታውን ለመወጣት የመጀመሪያ እርምጃው የተራድኦና የዕርቅ ድርጅት ማቋቋም ነው። የድርጅቱ መቋቋም ኢትዮጵያውያንን ሁሉ የሚያስደስትና ተስፋ የሚያበሥር (የወያኔን ቡድን ብቻ የሚያሠጋ) መሆኑ በግልጽ ቃላት መቅረብ አለበት። አሁን አገራችን ባለችበት የፖለቲካ ሁኔታ ስናየው፥ “አማራ መጣብህ” የሚለውን የወያኔ ማስፈራሪያ ከአማራ የተራድኦና የዕርቅ ድርጅት ሌላ ሊያሳፍርና ውድቅ አድርጎ ሰላም ሊያወርድ የሚችል ኀይል የለም።

ለዚህ ደርሰት አስፈላጊነቱ ስላልታየኝ፥ “አማራ ማነው?” ከሚል፥ መልሱ ብዙ ገጽ ከሚፈጅ ጥያቄ ውስጥ አልገባሁም። ሁሉም ራሱን ስለሚያውቅ፥ “አማራ ነን” የሚል ሁሉ በሙሉ አባልነት፥ በድርጅቱ የዕርቅና የሰላም ዓላማ የሚያምን ግን “አማራ ነኝ” የማይል ኢትዮጵያዊ ደግሞ በደጋፊ አባልነት መመዝገብ ይችላል።

ሳልረሳው፤ ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆኑት ወጣት የጦር መኳንንት ጀኔራል አማን አንዶምን መሪ አድርገው ደርግን ለመጣል ሳይችሉ ሲቀሩ፥ ከአማን ሞት በኋላ ሌላ ሰፋ ያለ ሙከራ አድርገው ነበር። መሪዎቹ ያድሙ ከነበረብረት ቦታዎች አንዱ ኢንጂኔር ሞገስ ቡሩክ ቤት ሲሆን፥ ባለቤቱ ወይዘሮ ደረጃሽ ወርቅ ቅጣው ብትያዝ የሚደርስባትን እያወቀች ምንም ቅሬታ አላሳየችም። ያም ሲከሽፍ፥ ሞገስ ቡሩክ፥ ተፈሪ ተ/ሃይማኖት፥ ጸሐፊው ዮሴፍ ያዘው ቤተ ሰቦቻቸውን የትም በትነው፥ ኬላ ሰብረው ወጥተው ትግላቸውን እስከመጨረሻው በትጥቅ ትግል ቀጠሉ። የሻለቃ ዮሴፍ ያዘው ባለቤት ወይዘሮ ወይንሸት መኰንን ባሏን የሸኘችው፥” ብቻ እግዚአብሔርን የምለምነውና አንተንም አደራ የምልህ፣ ተይዘህ በዚህ ሳጥን (ጣቷን ወደቲቪው እየጠቆመች) ውስጥ እንዳላይህ ነው” በሚል መሪ ቃል ነበረ፤ የጀግና ሚስቶች!! ተፈሪ ወደቀ፤ ሁለቱ ከዓሥራ ሰባት ዓመት በኋላ ከሚስቶቻቸው ጋር ሊገናኙ ቻሉ። ታሪካቸው የሚያስገርምና የሚመዘገብ የኢትዮጵያ ታሪክ ነው።

የዚህ ጽሑፍ ትኩረት ግን አማራውን ለዕርቅና ለሰላማዊ ለውጥ የማደራጀት ጥሪ ነው። ሞረሽ ወገኔ የሚባል ድርጅት እንዳለ አውቃለሁ። ማሳሰቢያየ በሐሳብ ደረጃ ተደንቆና ተኰንኖ እንዳይቀር፥ አስኳሉ ካለ አስኳሉን ማጎልበት ይቻላል።

– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/5335#sthash.jbZxJjIE.dpuf

The post በኢትዮጵያ ሰላም የሚያመጣ የአማራ የተራድኦና የዕርቅ ድርጅት ያስፈልጋል- (ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ) appeared first on Zehabesha Amharic.

ምን ታቅዶ ምን ተፈፀመ?፣ …የቀጣይ የትግል አቅጣጫ ምን ይሁን? (ኤርሚያስ ለገሰ)

$
0
0

( ክፍል አንድ)

daniel ermiasምርጫ 2007 አስመልክቶ ገዥው መደብ “ምን አስቦ ምን ይፈጵማል ” የሚለውን መነጋገር ከጀመርን ግማሽ አመት አለፈው። ባለፋት ወራት በርካታ የተጠበቁም ያልተጠበቁም ድርጊቶች ተፈጵመዋል። ከእነዚህ ድርጊቶች ወሳኝ የሚባሉትን ነቅሶ በማውጣት መመልከት ያስፈልጋል። በመሆኑም ባለፋት ጊዜያቶች ይፈፀማሉ ብለን የገመትናቸውን ግምገማ እና በቀጣይ ወራት ሊፈፀሙ የሚችሉ እቅዶችን ትንበያ አስተሳስሮ ማየት ተገቢ ይሆናል። ባለፋትም ሆነ በቀጣይ ጊዜያት የሚኖሩ ተግባራት በመለየት መከራከር፣ መወያየትና በመሰረታዊ ጉዳዬች ላይ የጋራ መግባባት ፈጥሮ መንቀሳቀስ ወሳኝ ይሆናል።

እያንዳንዱ ባለድርሻ አካል በአጀንዳው ዙሪያ መነጋገር መቻሉ የተለያዩ ጠቀሜታዎች ይኖሩታል። በአንድ በኩል በኢትዬጲያ የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ትግል የደረሰበትን ደረጃ ለመመልከት ያስችላል። በሌላ በኩል እንደ ግለሰብ ” የእኔ አስተዋጵኦ ምን ነበር? ፣ ከዚህ በኃላስ ከእኔ ምን ይጠበቃል?” የሚለውን ወደ ራሱ ውስጥ እንዲመለከት እድል ይከፍትለታል። በመሆኑም እነዚህን ከላይ የተጠቀሱ ጠቀሜታዎች ታሳቢ በመውሰድ እንደ አንድ ኢትዬጲያ ውስጥ የዲሞክራሲ ስርአት እንዲመጣ የሚመኝ ግለሰብ ያለፋትን ለመገምገምና ቀጣዩን ለመተንበይ የሚከተሉትን የመነሻ ሀሳቦች ለማንሳት ወደድኩ። እነዚህ አስተያየቶች የየትኛውንም የፓለቲካ ፓርቲ ሆነ የሚዲያ ተቋም ( “የእኔ የሆነውን ” ኢሳት ጨምሮ) አቋም የሚመለከት አይደለም። ከዚህ በተጨማሪም ግምገማውም ሆነ ትንቢቱ እንደመነሻ ለውይይት የቀረበ በመሆኑ ያገባኛል ባዬች በተሻለ ሁኔታ እንደሚያዳብሩት ታሳቢ ተወስዷል።

በዚህ ክፍል አንድና በቀጣዩ ክፍል ሁለት ” ምን ታቅዶ ምን ተፈፀመ?” የሚለው ላይ ብቻ ለማተኮር እሞክራለሁ። በሶስተኛው ክፍል “በቀጣይ ገዥው መደብ ምን ያስባል፣ የቀጣይ የትግል አቅጣጫው ምን ይሁን?” የሚለው ላይ የመነሻ ሀሳብ ይቀርባል። ” ምን ታቅዶ ምን ተፈፀመ?” በሚለው ክፍል ገዥው መደብ የምርጫው ሂደት ትኩረት እንዲነፈገው ያደረገበት ምክንያት፣ ህብረተሰቡን የሚያነቁ አካላት ላይ የተወሰደ እርምጃ፣ ምርጫ ቦርድን የኢህአዴግ ክንፍ ለማድረግ የተወሰዱ እርምጃዎችን፣ የፓርቲ በአላትን እንደ ቅስቀሳ ስልት የመጠቀም ስትራቴጂን፣ የሀይማኖት ተቋማት እና አመራሮች ላይ ገዥው መደብ አቅዶ የፈፀማቸውን እንመለከታለን።

ሀ• ምን ታቅዶ ምን ተፈፀመ?
1• ለምርጫው ሂደት ትኩረት የመንፈግ ስትራቴጂ

በኢትዬጲያ አዲሱ አመት መጀመሪያ ወር ላይ ከሲሳይ አጌና ጋር በነበረን ቆይታ ቅድሚያ ትኩረት ሰጥተን የተነጋገርነው ህውሀት/ ኢህአዴግ ቀጣዩ ምርጫ በሀገሬው ህዝብና የአለም አቀፍ ተቋማት እንዳይነገር ትኩረት መንፈግ ስትራቴጂ እንደሚከተል ነበር። የዚህ ስትራቴጂ መነሻ በምርጫ ዘጠና ሰባት ኢህአዴግ ለምን ተሸነፍን የሚለውን ሲገመግም የተቀመጠ አቅጣጫ እንደሆነ ለማመላከት ተሞክሯል። በ1997 አ• ም• የምርጫው ሂደት በመስከረም ላይ በይፋ ተጀምሮ ነበር። ካልተሳሳትኩ በትምህርት ፓሊሲው ላይ በፓለቲካ ፓርቲዎች መካከል ክርክር የተደረገው በመስከረም ወር ላይ ነበር። በተከታታይ ወራትም የተጋጋለ የምርጫ ክርክር በመካሄዱ ህዝቡ የፓለቲካ ፓርቲዎችን አላማ መገንዘብ ቻለ። እንደ እኔም ሆነ ኢህአዴግ እምነት የምርጫ 97 የፓለቲካ ድባብ ከግራ ወደ ቀኝ የገለበጠው በወቅቱ የተካሄዱት የምርጫ ክርክሮች ናቸው። ይህን አስመልክቶ የመለስ ትሩፋት ገጵ 301 ላይ የሚከተለውን ድምዳሜ ኢህአዴግ ማስቀመጡን ታመለክታለች፣

” … በምርጫ ክርክር ወቅት ኢህአዴግ ባልተዘጋጀበት ሁኔታ በሩን መበርገድ አልነበረበትም። ግንቦት ለሚካሄድ ምርጫ መስከረም ጀምሮ የሚዲያ ክርክር መካሄዱ ጥፋት ነበር።”
በመሆኑም የምርጫውን ሂደት ትኩረት መንፈግ የማይታለፍ ሆነ። አሁንም ሆነ ህውሀት በስልጣን ላይ እስከቆየ ድረስ ይህ ስትራቴጂ ተጠናክሮ ይቀጥላል። በምርጫ 2007 እያየነው ያለነው ይህንኑ ነው። እስከ ታህሳስ መጨረሻ ድረስ ስለምርጫ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ የሚወራ ነገር በመንግስት ሚዲያም ሆነ በገዥው መደብ ካድሬዎች አልነበረም። የምርጫ ክርክሩ የተጀመረው በዚህ ሳምንት ምርጫው ሊካሄድ ከሁለት ዲጅት በታች ቀናት ሲቀረው ነው። ይህም ቢሆን በሰአት ድልድሉ ገዥው መደብና ተላላኪዎቹ የአንበሳውን ድርሻ ወስደው ” አይኔን ግንባር ያድረገው” ቅስቀሳና ማስፈራሪያ ያደረጉበት ነበር። እንደዛም ሆኖ ከእነእጥረቱም ቢሆን የተቃዋሚ አመራሮች የተሻለ ነጥብ አስመዝግበው የወጡበት ነበር። ለዚህ እማኝ የሚሆነው በማህበራዊ ድረገጶች የተፈጠረውን መነቃቃት መመልከት በቂ ይሆናል። ከማህበራዊ ድረገጶች ወጥቶ በህብረተሰብ ደረጃ መነሳሳት ፈጥሯል ወይ? የሚለው ላይ የተሟላ መረጃ ስለሌለኝ ብዙ ማለት የሚቻል አይደለም። ይሁን እንጂ በምርጫ ለውጥ አይመጣም፣ መድብለ ፓርቲ ወደ መቃብር ከወረደ ቆይቷል ፣ ምርጫ ቦርድ የኢህአዴግ አንድ ክንፍ ነው፣… ወዘተ የሚለው አመለካከት በኢትዬጲያ ህዝብ ገዥ አመለካከት በሆነበት ሁኔታ የተለወጠ ነገር አለ ብሎ መገመት ማሞ ቂሎ ከመሆን የሚዘል አይደለም።

2• ህብረተሰቡን የሚያነቁ አካላትን ልክ የማስገባት ስትራቴጂ

ለዚህ ስትራቴጂ መነሻ የሆነውም የምርጫ 97 ውጤት ግምገማ ነው። በግምገማው የተደረሰበት ድምዳሜ የኢትዬጲያን ህዝብ ለመብቱና ነጳነቱ ለማታገል ወስነው የሚንቀሳቀሱ አካላትና ግለሰቦችን ” ዲሞክራሲያዊ ኢንስትሩመንት” በሚል አቅጣጫ “አብዬታዊና ዲሞክራሲያዊ እርምጃ ” መውሰድ የሚል ነበር። ይህ አብዬታዊ እርምጃ ባለፋት አመታት በሚያስደነግጥ ሁኔታ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ይህ አይን ያወጣ የጭካኔ እርምጃ በኢትዬጲያ ህዝብ እየተለመደ ከመሄዱ የተነሳ ” ቀጣዩ ተረኛ እከሌ ፓርቲ፣ እከሌ ግለሰብ ነው!” የሚል ትንበያ የሚያሰጥበት አስፈሪ ደረጃ ደርሷል። እንደተባለውም ፓርቲዎችና ግለሰቦች እርምጃ ሲወሰድባቸው ” ምን አዲስ ነገር መጣ? ” የሚሉ አባባሎች ህብረተሰባችን ፀረ ዲሞክራሲን የመሸከም መጥፎ አዝማሚያ አሳይቷል። ይህ አስተሳሰብ ከገባንበት ፍጱም የድህነት አረንቋ ጋር መጃመሉ ስለማይቀር በሂደት እንደ ሀገር ብቻ ሳይሆን እንደ ሙሉ ሰው መቀጠላችንን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ወደ መሆን መሸጋገሩ አይቀርም።
ወደ ስትራቴጂው ስንመለስ ከአጭር ጊዜ አኳያ እንደ ቡድን የመጀመሪያ ሰለባ የሆኑት ራሳቸውን ” የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን” የሚል ስያሜ የሰጡት ወጣቶች ናቸው። እነዚህ ወጣቶች ላይ ገዥው መደብ ለምን ልዩ ትኩረት ሰጠ? የሚለውን መልሶ ማለፍ ተገቢ ይሆናል። የመጀመሪያው የቡድኑ አባላት ወጣት መሆናቸው ከሚፈጥርላቸው ጉልበት ባሻገር የተለያየ ፕሮፌሽን ባለቤቶች መሆናቸው ነው። የተለያየ ሙያ ባለቤት በመሆናቸው በሁሉም አቅጣጫ የገዥው መደብ ውሳኔዎች፣ እርምጃዎች፣ ፓሊሲዎችና ኩነቶችን ተከታትለው የመንቀፍ እድል ፈጥሮላቸዋል። በተለይ ራሱ ገዥው መደብ የሚፈጥራቸውን ኩነቶች ተገን አድርገው ( የህገመንግስት ቀን፣ የብሔረሰብ ቀን) የማስተማሪያ ስልት ቀይሰው መንቀሳቀሳቸው የሚያበሳጭ እንደሆነ ይጠበቃል። ይህም የኢትዬጲያ ህዝብ ( በተለይ ወጣቱ) ከድርጊቶቹ በስተጀርባ ያሉትን እውነታ እንዲገነዘብ እድል ፈጥረዋል።

ገዥው መደብ በሁለተኛ ደረጃ ልዩ ትኩረት ሊሰጥ ያስገደደበት ምክንያት ባልተጠበቀ ሁኔታ የምሁርነት ሚናን በመዘንጋትና በምናገባኝነት በመሸፈን ራሳቸውን ከሀገራቸው ጉዳይ ያገለሉ ምሁራንን የማነቃቃት ድርሻ በመጫወታቸው እንደሆነ ይገመታል። ይህ ደግሞ ለደቂቃ በትእግስት ሊታለፍ የሚችል አይደለም። የገዥው መደብ ፍላጐት ምሁራንና ተሰሚነት ያላቸው ግለሰቦች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ባይተዋር እንዲሆኖ፣ አልፎ ተርፎም በተሰማሩበት ቦታ ወጣቱን ” ዲ -ፓለቲሳይዝ” እንዲሆን አድርገው እንዲያፈሩ ነው ( በቅርብ ጊዜ ፓለቲካ ምን ያደርግላችኃል የሚሉ የሀይማኖት ሰባኪያን በአደባባይ መውጣታቸውን ልብ ይሏል)። በመሆኑም ገዥው መደብ “ምሁራን በሁለቱም ወገን የተሳለ ቢላዋ” ብሎ የፈረጃቸው ከመሆኑ አንጳር ጦማሪያኑ በሚያነሱት አጀንዳ ተጐትተው ወደ አብዬቱ በመግባት ግንባራቸውን ለጥይት የሚሰጡበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ማድረግ ጊዜ የሚሰጠው አይደለም።

ሶስተኛው ምክንያት እነዚህ ጦማሪያን በኢትዬጲያ ውስጥ ያልተጠበቀና አዲስ ሁኔታ መፍጠር መቻላቸው ነው። ይህም በአንድ በኩል ወጪ ቆጣቢና እያደር እየሰፋ የሚሄድ ስልት መከተላቸው ሲሆን፣ በሌላ በኩል ገዥው መደብ ባወጣቸው አፋኝ ህጐች ማእቀፍ ውጭ መንቀሳቀሳቸው ነው። ከዚህ አንጳር ጦማሪያኑ በግብር የመንግስታዊ ያልሆኑ ሲቪክ ድርጅቶችና የሚዲያ ሚና እየተጫወቱ በህግ ደግሞ በአዲሱ NGO LOW ሆነ በሚዲያ ህጉ መታቀፍ አለመቻላቸው ትልቅ ራስ ምታት ይሆናል። እስከማውቀው ድረስ በሁለቱም አዋጆች ጦማሪያኑን ለመመዝገብም ሆነ ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችል ምእራፍም ሆነ የአንቀጵ ማእቀፍ የለም። በዚህም ምክንያት ይመስላል ገዥው መደብ በህልሙም አስቦት የማያውቀውን አዲስ የሚዲያ አዋጅ ወደ ማውጣት የተሸጋገረው።

በመሆኑም የገዥው መደብ የቅድሚያ እርምጃ እነዚህ የየትኛውም የፓለቲካ ፓርቲ አባላት ያልሆኑ ወጣቶችን የሽብርተኝነት ካባ በማልበስ ከጨዋታ ውጭ ማውጣት ነበር። ይህም ከሞላ ጐደል የተሳካ እርምጃ ቢሆንም በተቃራኒው የወጣቶቹን ፈለግ የሚከተሉ፣ የቀደምት ተግባራቸውን የሚዘክሩ፣ ከልደት በአላቸው አንስቶ በተለያዪ አጋጣሚዎች የወጣቶቹን ቀንዲልነት የሚዘክሩ አእላፍ ሀይሎች ከመፈጠር ሊያግዱት አልቻሉም።

ህብረተሰቡን እንዳያነቁ ልክ ከማስገባት አንጳር የገዥው መደብ ጡንቻ ቀጥሎ ያረፈው ተጵእኖ የሚያሳርፋ የፓለቲካ ፓርቲዎችና አመራሮች ላይ ነበር። ( ይቀጥላል)

The post ምን ታቅዶ ምን ተፈፀመ?፣ …የቀጣይ የትግል አቅጣጫ ምን ይሁን? (ኤርሚያስ ለገሰ) appeared first on Zehabesha Amharic.

(የሳውዲ ጉዳይ …) ህገ ወጦችን የማጥራት ዘመቻ ከተጀመረ 50,254 ተይዘዋል –ነቢዩ ሲራክ

$
0
0
* የሳውዲ መንግስት ህገ ወጥ ያላቸውን የውጭ ዜጎች የማጥራቱንና የመያዙን ዘመቻ አጠናክሮ የቀጠለበት ሲሆን በእስካሁኑ አሰሳ 50,254 በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል
Nebiyu Sirak* መረጃውን ያስተላለፉት የመዲና ፖሊስ አዛዥ ጀኔራል አብዱል ሃዲ አል ሸሃራኒ መሆናቸውን የጠቆሙት የሳውዲ ጋዜጦች ህገ ወጦች የተያዙት በዋና ከተማዋ በሪያድ በጅዳ ፣ በመካ ፣ በመዲና በተቡክ መሆኑን ጠቁመዋል። ባለስልጣኑ በማከልም የተያዙት ህገ ወጦች ማጣራት እየተደረገ እንደ ተጠረጠሩበት ወንጀል እንደሚከሰሱና ወደ ሃገራቸው እንደሚሸኙ አስታውቀዋል።
* ዘመቻው ከተጀመረ ወዲህ ሁከትና ግርግር ብዙም ባይስተዋልም በርካታ በውጭ ዜጎች የሚተዳደሩ ሱቆች የተዘጉ ሲሆን ሞቅ ደመቅ ያለውን የጅዳና የተለያዩ ከተሞች የገበያ እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ መፍጠሩ ይጠቀሳል። ምሽት ላይም የተለመደው የሞቀ እንቅስቃሴ የተገታ መሆኑ መስተዋሉ ይጠቀሳል ።
* በተለያዩ ምክንያቶች የመኖሪያ ፈቃዳቸው ጊዜ ሳይታደስ ስለወደቀባቸው የውጭ ዜጎች ጉዳይ የተናገሩት ጀዋዛት ተብሎ የሚታወቀው የሳውዲ የፓስፖርት እና ኢሚግሬሽን ዋና ኃላፊ መ.ጀኔራል ሱሌማን የህያ ፖስፖርታቸው በጊዜ ያላደሱት ፣ ስላላሳደሱበት በቂ ምክንያት እስካላቀረቡ ድረስ ከተያዙ ወደ ሀገራቸው እንደሚሸኙ ባሳለፍነው አርብ ማስታወቃቸው አይዘነጋም ።
* ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሰሳው ስጋት ያደረባቸው ኢትዮጵያውያን እጃቸውን በሰላማዊ መንገድ እየሰጡ የሚሄዱበት መንገድ እንዲያመቻቹላቸው የጅዳን ቆንስልና በሪያድ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ከሳውዲ መንግስት ጋር በመነጋገር መንገዱን ያስተከሰክሉ ዘንድ ተማጽኗቸውን እንዳሰማ በተለያየ መንገድ ጠይቀውኛል።
እነሆ መልዕክቱን አድርሻለሁ!
እስኪ ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 7 ቀን 2007 ዓም

The post (የሳውዲ ጉዳይ …) ህገ ወጦችን የማጥራት ዘመቻ ከተጀመረ 50,254 ተይዘዋል – ነቢዩ ሲራክ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከምርጫው በፊት ልናደርገው የሚገባ ሌላ ምርጫ (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና)

$
0
0

Gezahegn Abebeበኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ስርዓት በማስመልከት በተለያዩ ድረገጽ እና የዜና አውታሮች ላይ የህዝብን ንቃተ ህሊና ሊይጎለብቱ የሚችሉ የተለያዩ ዘገባዎች ይቀርባሉ። በተለይም ደግሞ ፍትህ፣ነጻነት፣እኩልነትን አስመልክቶ እንዲሁም ሊጀመር ጥቂት ጊዜያት የቀረውንና የኢትዮጵያዊያንን አዕምሮ በያዘው የሀገራችን ምርጫ ዙሪያ መነጋገሩ፣ መከራከሩ እና  ከምርጫው በፊት  መስተካከል የሚገባችውን ነገር ማውሳቱ የሰሞኑ ዓቢይ ጉዳይ ሆኗል። በርግጥ የ1997ቱ ምርጫ የህዝብ ቅስም የተሰበረበት እና እስከአሁንም ድረስ የኢትጵያ ህዝብ ስብራት ያላገገመበት ሁኔታ በስፋት ይታያል። በመሆኑም እንደ እኔ እምነት ፍትህ ከሌለበት ሀገር ከፊታችን ካለው ምርጫ ምንም ይፈጠራል ብዬ የምጠብቀው ነገር ባይኖርም ግን ጥቂት የሚባሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች  ምርጫውን አስመልክቱ እየሰሩት ያለው ቅስቀሳ እና ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የወያኔን መንግስት ከስልጣኑ በማውረድ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት እየከፈሉት ያለው መስዋትነትና ሊያስመሰግናቸው ይገባል ባይ ነኝ ።  እርግጥ ነው ከሁሉም አቅጣጫ የሚስተጋባው የኢትዮጵያዊ ድምጽ ሀገርን ከመውደድ እና ለሀገር ነጻነት እንዲሁም ሉአላዊነት የሚከፈል መስዋዕትነት እስከሆነ ድረስ ትግሉ ይፋፋም ይቀጥል ያስብላል።

ፍትህ የሰፈነበት ምርጫ ሊካሄድ የተገባ መሆኑን ሁላችንም እንስማማበታለን። የሁላችንም የኢትዮጵያ ልጆች ናፍቆት ሰላም የሰፈነባት ሀገር ላይ ምርጫው የህዝብ እንዲሆን ነው። ይህም ህልም በምድራችን ላይ ተጨባጭ ይዞታ ኖሮት  ተግባራዊ ቢሆን ሀገራችን ምን አይነት ቅርጽ ሊኖራት እንደሚችል ማሰብ ከባድ አይደለም። ስለሆነም በአሁን ወቅት   በምድሪቷ ላይ እየገነነ የመጣው ግፋዊ  አገዛዝ ወደበለጠ ደረጃ ደርሶ እጅግ ከመክፋቱ በፊት የትውልድ ሁሉ ናፍቆት የሆነውን እኩልነት እና  ህዝብ ለብዙ ጥፋት ታልፎ በተሰጠበት እንዲሁም ከሀገሪቷ ፊት ለፊት ታላቅ የሆነ ክስረት ተጋርጦ ባለበት የአምባገነን ስርዐት ዘመን የሰከነና የተረጋጋ ህይወትን በኢትዮጵያ ላይ ለማምጣት ታላቅ የሆነ ርብርቦሽ ያስፈልጋል።

ይህንን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የዘቀጠ የፓለቲካ ስርዐት ወደኋላ ከተጎተተበት ኢፍትሐዊ አሰራሩ ተናጥቆ ለማውጣት እና የሰለጠኑ ሀገራት ወደደረሱበት የነጻነትና እና የእኩልነት ክልል ለማድረስ ከጨዋታ ውጪ የተደረጉት የኢትዮጵያ ምሁራን እና ከማንኛውም የእድገት  እንቅፋቶች የጸዳ አላማ ያላቸው ሀገር ወዳዶች የተዘጋባቸው በር ክፍት ሆኖ  በሁሉም ሀገራዊ አቅጣጫ ጉዳይ ላይ ለምድራቸው የሚቻላቸውን አስተዋጾ እንዲያደርጉ በተለይም ደግሞ ከፊት ለፊታችን በወያኔ ቁጥጥር ስር ያለው ምርጫ በህዝብ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን የኢትዮጵያ ሊሂቃን እድሉ ያለምንም ተጽእኖ በነጻነት ተሰጥቷቸው እንዲሳተፉ ማድረግ ተመራጭነት አለው። ይህን መሰሉ ተግባር በምድሪቷ ላይ የጸና እስከሚሆን ድረስ  እንዲሁም የገዥውን ቡድን እድሜ መቀጠል ፣ የተመዘበሩ ኮሮጆዎች እና የምርጫ ዕቃ ዕቃ ጨዋታ ወቅታቸውን እየጠበቁ ያለፈውን ልማዳቸውን ለመድገም የሚደረጉት እንቅስቃሴዎች ተፈጻሚ ከመሆናቸው በፊት በሁሉም አቅጣጫ መታገል እንደሚገባን እና ከምርጫው በፊት ህዝባዊ አመጽ እንደ አማራጭ ከመውሰድ  በስተቀር በሌላ መንገድ ወያኔን ማክሸፍ እንደማይቻል ሊታወቅ ይገባል።

እውነታውን በመሸፋፈን  ወያኔ በምግብ ራሳችንን ችለናል እያለ  በሚቀልድበት በዚህ የረሀብ ዘመን ዘወትር ሽቅብ እየወጣ ሰማይ ለመንካት እየተመነጠቀ ስላለው የኑሮ ውድነት ህዝቡም ሲያወራ ወያኔም ስለ ‹‹11%›› እድገት ሲደሰኩር፣ ህዝብ ስለ ስራ-አጥነት እና  እርዛት ሲያወራ ወያኔ ‹‹ስለኢንቨስትመንት መስፋፋት›› ሲያብራራ፣ ህዝብ ስለረሃብ ሲያወራ መንግስት ‹‹ስለጥጋብ›› መፈክሩን ሲያሰማ ፤ ህዝብ ስለዳቦ ሲጮህ የወያኔ መንግስት ‹‹ስለመሰረተ ልማት›› እያወሩ እርስ በርስ መግባባት ተስኗ ቸው 23ኛ አመት ዐመት አልፎ ተጋምሷል ። ይህ ያላቻ ጋብቻ ይባላል። በድግሳቸው ቀን  አንዱ የደስታ ሌላኛው የሃዘን ሻማ በማብራት አክብረው አሳልፈዋል፡፡ ከእንደዚህ አይነት ስርዓት አልባ ገዢ ጋር ፍቺ ብቸኛ አማራጭ ነው። ምርጫውም ፍትሀዊ እና የህዝብ ካልሆነ በስተቀር ለኢትዮጵያዊያን የሚያመጣው ምንም አይነት ፈውስ እንደሌለው የታወቀ ይሁን። ይልቁኑም የከዚህ በፊቱን ውሸት እና ማስመሰል ረቀቅ ባለ ማደናገሪያው ለመድገም እየተሯሯጠ መሆኑ ግልጽ በሆነበት በዚህ ወቅት አምባገነኑን ወያኔን ከምርጫው ውጭ ለማድረግ በየትኛው ጎዳና ብንሔድ በትግላችን ግቡን እንደምንመታ  እና የተለያዩ የትግል ልምድ ስልቶች ልውውጥ አድርገን ሀይላችንን በማጠናከር በአንድ የተባበረ ኢትዮጵያዊ ክንድ ከምርጫው በፊት ህዝባዊ አመጽን  የሁላችን ምርጫ ይሁን በማለት መነሳት አለብን።

የኔ የግል ምልከታዬ በአሁን ሰአት ሀገራችን ባለችበት ደረጃ የትግላችን ኢላማ እና መድረሻው መሆን የተገባው አስቀድሞ በሐስት የወያኔ ነቢያቶች ለተነበዩለት   ምርጫ ተባባሪ ሆኖ በመሰለፍ አምባገነኑ አገዛዝ እንዲቀጥል አስተውጽኦ ማበርከት ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚወስነውሀገር የምትተዳደርበት ልማታዊ የሆነ ህግ በምድሪቷ ላይ የበላይ እንዲሆን የዜጎች እኩልነት እና ሰብዓዊነት የሚከበሩባቸው ስርዓት በማስፈን ወያኔ በጭቆና የተቆጣጠርውን ስልጣን በመቀማት የህዝብ የስልጣኑ ባለቤት ሆኖ  ፍጹም የሆነ ብሩህ ተስፋ የሚታየባትን ኢትዮጵያን መፍጠር  ነው።

መቼውንም ቢሆን ወያኔ ለነጻ ፍትሀዊ ምርጫ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ የበላይነት ለምን አልቆመም ተብሎ አይጠየቅም። ምክንያቱም ይህ ቡድን “ከጅብ ጅማት የተሰራ ክራር ምንጊዜም ቅኝቱ እንብላ እንብላ ነው” እንዲሉ ከፅንሰቱም ፀረ ኢትዮጵያዊ መሆኑ የታወቀ ነው። ከዚህ አስከፊ ስርዓት መልካም የሆነ አስተዳደር መጠበቅ የሚታሰብ አይደለምና እንደገና ሌላ ምዝበራ በሀገርችን ላይ ከመፈፀሙ በፊት ምርጫው ጋር ሳንደርስ በፊት የህዝባዊ አመፅ ትግልን በመምረጥ ወደ ውጤት እንጓዝ።  ምርጫው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመርጠው እና የሚወዳደረው እንጂ ለተሳትፎ ብቻ ብቅ ብሎ በወያኔ ሻጥር የሚሸነፍበት ሊሆን አይገባም።
ለውጥ የግድ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ሁሉንም የማይጠቅም ቢሆን እንኳን ለብዙኃኑ ሲባል የግድ መምጣት አለበት፡፡ የለውጥ ፍርሐትን አስወግደን በቂ ዝግጅት በማድረግ በተገቢው መንገድ ወያኔን ማስወገድ  ይቻላል፡፡ ለውጥ የሚመጠበትን መንገድ ፈርቶ እና ህዝባዊ አምፅን  ተቃውሞ  ለውጥን መጨበጥ ዘበት ነው፡፡ ‹‹መፍራት ያለብን ፍርሐትን ራሱን ነው›› እንዲሉ ፍራንክሊን ሩዝቬልት፡ የትኛውንም ወደኋላ የሚጎትተንን ፍርሀት ትተን ድጋሚ በምርጫው ከመጭበርበራችን በፊት አስቀድመን በህዝባዊ አመጽ መታገንልን እንምረጥ። ከምርጫው በፊት የኢትዮጵያውያን ምርጫ  በህዝባዊ አመጽ ትግል ለዘመናት በአንባገነንነት በስልጣን ላይ ተቀምጦ ህዝብን በማሰር ፣ በመግደል ላይ ያለውን አረመናዊ መንግስት ከስልጣን ላይ ማውረድ ይሆን ነው  መልዕክቴ ።
gezapower@gmail.com

የሕዝብ ትግል ያቸንፋል !!!

The post ከምርጫው በፊት ልናደርገው የሚገባ ሌላ ምርጫ (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና) appeared first on Zehabesha Amharic.

የታንዛንያ ፖሊስ ሐገሬ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ ገብተው ሲንቀሳቀሱ አገኘኋቸው ያላቸውን 63 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን መያዙን ገለጸ

$
0
0

77024212ፖሊስ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በትብብር ባደረገው ዘመቻ ስደተኞቹን ለመያዝ እንደቻለና በሂደቱም አንድ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ሕይወቱ እንዳለፈ ተገልጿል. ስደተኞቹ ሊያዙ የበቁት የአካባቢው ማሕበረሰብ ለፖሊስ ባደረሰው ጥቆማ መሆኑም ተዘግቧል.

ዘገባው አክሎም ስደተኞቹ ይጓጓዙበት የነበረው መኪና ተበላሽቶ እንደቆመ. በዚህም ወቅት የመኪናው አሽከርካሪ ስደተኞቹን ጫካ ውስጥ ተጠልለው እንዲጠብቁት ማድረጉና ከዚያም ጥሏቸው መጥፋቱ ተጠቅሷል.

ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች በተያዙበት ወቅት በረሀብ እና በጤና ችግር ተጎሳቁለው እንደነበር; ረሀብ የጠናባቸው አንዳንዶቹም ማሳ ውስጥ በመግባት ረሃባቸውን ለማስታገስ መሞከራቸውን, ሌሎቹም የአካባቢውን ሕዝብ ምግብ ሲለምኑ እንደነበር የዴይሊ ኒውስ ዘገባ ያስረዳል.

source –.diretube

The post የታንዛንያ ፖሊስ ሐገሬ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ ገብተው ሲንቀሳቀሱ አገኘኋቸው ያላቸውን 63 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን መያዙን ገለጸ appeared first on Zehabesha Amharic.

አንድነት ራስ ምታቱ ነበር ፣ አሁን ደግሞ ሰማያዊ ሆድ ቁርጠቱ ሆነ –ግርማ ካሳ

$
0
0

“የአንድነት አመራር በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከተለዬ በኃላ በተሰጠው የሰባት ቀን እጩ የማስመዝገቢያ ጊዜ ውስጥ ለተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤቶች በ80 ምርጫ ክልሎች ተደራሽ በማድረግ 230 እጩዎችን ለማስመዝገብ ችለናል፡፡”
በምርጫ ቦርድ አሰራር፣ ለምርጫ የሚሰጡ የገንዘብ ድጎማዎች ፣ በኢቢሲ/ኢቲቪ የሚቀርቡ የቅስቀሳ ጊዜያቶችን ፣ ፓርቲዎች ባቀረቡት ተመራጮች ቁጥርና አሁን በፓርላማ ባላቸው መቀመጫ ቁጥር እንዲሆን ነው የተደረገው። ይህ አሰራር በእጅጉ ሕወሃትን እንደሚጠቅም የታወቀ ነው።
semayawi
በዚህ መሰረት የሰማያዊ ፓርቲ በሚደረገው ምርጫ 7 ጊዜ ለአሥራ አምስት ደቂቃ መቀስቀስ እንደሚችል ተገልጾለታል። «በቂ ባይሆንም ያን ያህል ኢቢሲ/ኢቲቪ መፍቀዱ ጥሩ ነው» ሊያስብል ይችላል። ሆኖም ሕወሃት በአንድ በኩል ሲከፍት በሌል በኩል እንዴት ለመዘጋት እንደሚሞከር እናሳይ፡:

1) ሰማያዊ የሚያቀርባቸው የቅስቀሳ መልእክቶች ሳንሱር የሚደረጉ ናቸው። ከስድስት ጊዜ በላይ ኢቢሲ « ይሄን ካላስተካከላችሁ አናስተላልፍም» ብሎ መልሷል። እንድ ጊዜ እንደዉም አረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ለም አደረጋችሁ በሚል ነው።
2) ሰማያዊ እንዲያቀርባቸው ከተፈቀደለት ሰባት ፕሮግራሞች አምስቱ እንዲተላለፉ የተወሰኑት ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ( በፈረንጆች ነው። ወላጆች ልጆቻቸዉን ትምህርት ቤት ለመላክ ፣ ወደ እስራም ለመሄድ ደፋ ቀን በሚሉበት፣ ብዙዎች ከእንቅልፋቸው ሊነሱ በማይችሉበት ሰዓት ነው ።
የሕወሃቱ ኢቢሲ/ኢቲቪ ሆን ብሎ ሕዝቡ የሰማያዊ ፓርቲን መልእክት ለማዳመጥ እንዳይችል፣ ሲስተማቲክ በሆነ መንገድ ለማከላከል ለምን ፈለገ ? መልሱ አጭር ነው። ሕወሃት ከመቼዉም ጊዜ በላይ የፈራበትና በራሱ መተማመን ያልቻለበት ጊዜ ነው።
በነገራችን ላይ ለፓርላማ ወደ 480 ፣ ለክልሎች ደግሞ 1200 በላይ እጩዎችን አንድነት ፓርቲ ሊያስመዘግብ ተዘጋጅቶ እንደነበረ ሁላችንም እናዉቃለን። በሶማሌ ክልል በስተቀር ከአምስት መቶ በላይ በሆኑ የምርጫ ወረዳዎች ነበር አንድነት የሚወዳደረው። መረቡን ዘርግቶ በስፋት እየተንቀስቀስ ነበር። ሆኖም ባፈጠጠና ባገጠጠ መልኩ ህወሃት የኃይል እርምጃ ወስዶ፣ የአንድነትን ፓርቲ ጠፍጥፎ ለሰራው የትግስቱ ቡድን ሰጧል። አንድነት ማሸነፍ ብቻ ስይሂኦን ድምጽን የማስከበር አቅም እንዳለው ስላወቀ፣ ለምርጫ ቦርድ ቀጥታ ት እዛዝ በመስጠት አንድነት አገደ።

የአንድነት አባላት ሰማያዊን ተቀላቀሉ። ሰማይዊ የበለጠ ተጠናከረ። ከ400 በላይ የፓርላማ እጩዎች አስመዝገበ። ከ200 በላይ የሚሆኑትን ያለ ምንም ምክንያት ምጫ ቦርድ ሰረዘ።
አይ የወያኔ/ሓወህት አስቂኝ ምርጫ ! ከዚህ በፊት በምርጫው ቀን ነበር የሚያወናብዱት። በዚህ አመትማ ለይቶላቸዋል። ምርጫዉ ከመድረሱ ሶስት ወር በፊት ሰዎቺ እየተደናበሩ ነው !!!!
በከዚህበፊት ምርጫ ሕዝብ መርጦ ፣ ድምጹ ነበር የሚሰረቀው። ሕወሃት የድምጽ ሌባ ሰራቂና አጭበርባሪ ነበር። አሁን ግን ሕወሃት መራጭ የሆነበት ምርጫ ነው። አንዱን ፓርቲ እንዲወዳደር፣ ሌላውም እንዳይወዳደር ያደረገ፣ እጩዎች እየሰረዘ አትወዳደሩም በማለት መራጭ የሆነበት ምርጫ ነው! ሕወሃት ድሮ ያደርግ የነበረዉን ማስመሰል እንኳ ትቶ ፍጹም አምባገነን መሆኑን ያሳየበት ምርጫ ነው።

The post አንድነት ራስ ምታቱ ነበር ፣ አሁን ደግሞ ሰማያዊ ሆድ ቁርጠቱ ሆነ – ግርማ ካሳ appeared first on Zehabesha Amharic.

“ኢንተርኔትና ሚድያውን አጨናንቀዋለሁ ”ጥበቡ ወርቅዬ የቀድሞ ድምፃዊ፣ የአሁኑ ዘማሪና ሰባኪ

$
0
0

አቤንኤዘር ጀምበሩ

ጥበቡ ወርቅዬ አገልግሎት ለመታደም ወደ ቤዛ ቤተ/ክ በ06/07/07 ዓም ተገኝቼ ነበር። ምንም እንኳ ዝግጅቱ 8:00 ይጀመራል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ጥበቡ ቦታው የደረሰው ከዘጠኝ ሰዐት በኃላ ነበር። ጥቤ የቀድሞ አስታይለኛ አለባበሷ አና ፍሪዟ እንዳለች ነው፣ ፊቱ ላይም ላቅ ያለ የደስ ደስ ስሜት እና መመቸት ይታይበታል። ለአድምተኛው ምንም አይነት ቀረፃ ማድረግ አንደማይፈቀድ ከተላለፈ በኋላ ፣ ጥሪ ተደርጎለት ወደ መድረክ ሲወጣ የነበረው ህዝብ ቆሞ እያጨበጨበ እና እየጮኸ ሲቀበለው “አለማዊ” መድረክ ስራዎቹን ሳያስታውሱት የቀሩ አይመስለኝም።

በኋላ ላይ እራሱ እንደገለፀው “እዛ በታለንትና በድፍረት፣ እዚህ ግን በቅባት” ብሏል። ዝማሬን በሚያቀርብበት ወቅት በሙዚቃ ህይወቱ የሚታወቅበት መልካም ቃና ያለውን ድምፁን ወደ መዝሙር ቀይሮታል፣ ምንም እንኳን አልፎ አልፎ ያሉ መሸጋገሪያዎች ላይ የለመዳቸው የሙዚቃ መግቢያዎች ሲጐትቱት ታዝቤያለሁ። ለምሳሌ አንድ ጊዜ “ነይ ነይ” ብሎ ወዲያው “ሃሌሉያ” አድርግዋታል። የመዝሙር አገልግሎቱን ጨርሶ ወደ ቃል ማካፈል ሲያልፍ፣ የትምህርቱን መነሻ ያደረገው ሐዋሪያት ስራ ምእራፍ 2 ላይ ስላለው የበአለ ሀምሳ ክብረ በአል ላይ ነበር። ጥበቡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውቀቱ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን መገንዘብ አያዳግትም፣ እንዲሁም ለእምነቱ ከፍተኛ ቅንአት እንዳለውም ጭምር። ይህም የሚያመለክተው ከፍተኛ ጊዜውም በመፅሐፍ ንባብ ላይ እንደሚያሳልፍ ነው። እራሱም እንደገለፀው ለሶስት አመት ተኩል በር ዘግቼ ጨለማ ቤት ጭምር በንባብና በመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ አሳልፌያለሁ ብሏል ።
tibebu workiye

“አንዳንዶች ይመለሳል ይሉኛል፣ ግን ወዴት ነው የምመለሰው” ሲልም አፅእኖት ሰጥቷል። ምንም እንኳን ጥቤ ጥሩ አንዳነበበ አና መረዳት አንዳለው መገንዘብ ቢቻልም፣ በማስተማሩ ረገድ ግን የአቅም ውስንነትና ድፍረት እንደሚስተዋልበት ደፍሮ መናገር ይቻላል። በተለይ ባሁኑ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታን ፣ ከተጨባጭ ገሃዳዊ ሁኔታዎች እና ከስነ ልቦናዊ ዝግጅት ጋር አያያዙ የሚስቡ ትምህርቶችን ማዘጋጀት በአለም ሁሉ ላይ ባሉ የፕሮቴስታንት ቤተ/ኖች የሚንፀባረቅ ነገር ነው። እንዳየሁት የቃሉ መረዳት ቢኖረውም ከላይ የተጠቀሱት ክህሎቶች ጐድለውት ተመልክቻለሁ። ትምህርቱ ባብዛኛው ረድፍ ያልጠበቀ እና መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱ ነገሮችን መልሶ የመናገር፣ ወይም ትንታኔያዊ አስተምሮ ያለማቅረብ ሁኔታዎች ታዝቤያለሁ። ዘማሪው በትምህርቱ ወቅት የተለያዩ ነገሮችን አንስቷል፣ በአለማዊ ህይወቱ በተለይ በጫት ሱስ እጅጉን እስረኛ አንደነበረ ፣ቄማ ላይ እያሉ ከአርቲስቶች ጋር አብዝቶ ይጋጭ እንደነበር “አይወደኝም፣ ሌላ ሰው ባጠፋው ጭምር እኔ ነበርኩ የምሰደበው፣ ሰይጣን የሱ አንዳልሆንኩ ያውቅ ስለነበር ነው። ” ብሏል።

አርቲስቱ ድሮ በመቃብር አካባቢ እንኳን ሲያልፍ እጅጉን ይሸበር እንደነበርና አሁን ግን በራሱ አገላለፅ “በኮንፊደንስ ነው” ሲል ተደምጧል። ለሱ ከአለም ለመውጣት ምን ያህል አስቸጋሪ እንደነበርና ብዙ የሚይዙ ነገሮች እንደነበሩ ጠቅሰዋል። “የሙዚቃ ዝና፣ ሙዚቃቤት፣ ቁጥሩ የበዛ የሙዚቃ መሳሪያና ሌሎችም ነበሩ” ብሏል። ወደ ጌታ ከመጣ በኋላ መንፈሳዊ ክንውኖቹን ሲናገር፣ 1900 በላይ ሰዎችን ወደ ጌታ አንደመለሰ (የመገናኛ ብዙሃን የተጠቀሙትን ሳይጨምር) ፣ ትልልቅ አርቲስቶችን ሰብስቦ አንደመሰከረ፣ ወደ ጌታ አንደመለሰ እንዲሁም ብዙዎች በመንገድ ላይ እንደሆኑ ገልፅዋል። ሌላው አሁን አሁን በአንዳንድ ድህረ ገፆች ላይም እንደሚታየው ተአምራዊ አገልግሎቱ ነው።

ከንግግሩ መረዳት የሚቻለው እነዚህ እነዚህ አገልግሎቶች ሁሉም ቤት እንዲገቡ ይፈልጋል ፣ በቃሉም “ካሁን በኃላ ኢንተርኔትንና ሚድያውን አጨናንቀዋለሁ” ብሏል። በቅዳሜው አገልግሎት በስራ ማጣት የተፀለየላት ወጣት ፣ ስራ ማጣቷ መንፈሳዊ ተግዳሮት እንደነበር እና በፀሎት ወቅት ጮሆ ሲወጣ በዛው ቅፅበት አቤቷ ስልክ ተደውሎ ለስራ መጠራትዋን እሱ ሲናገር አሷ እጇን በማውለብለብ በእሁዱ ፕሮግራም አረጋግጣለች። እንዲሁም እሱ ፀሎት ያደረገላቸው ሰዎች በእንቅልፍ ወደ መንግሥት ሰማያት ደርሰው እንደተመለሱ ጠቅሷል፣ በስልክ ልውውጥ አጋነንትን እንዳስወጣም ጭምር። ትላልቅ አርቲስቶች ላይ ያለ መሪ መንፈስ ሲመታ መንጋው ይበተናል የሚለው አርቲስቱ፣አሁን ላይ ብዙ አርቲስቶች አንደሚደውሉለት እርሱም አንደሚፀልይላቸው መስክሯል። ሌላው የገረመኝ ነገር በትልልቅ ዘፋኞች ስም የተሰየሙ አርኩሳን መናፍስቶች መኖራቸውን መግለፁ ነው፣ ምድራዊ ህግ ስለማይፈቅድ እንጂ ቢጠራቸው እየጮሁ ወደ አርሱ እንደሚመጡ ገልፅዋል። ድምፃውያኑ አንደ ኮካ በስማቸው የተሰየሙ መናፍስት መኖራቸው አያስገረመኝ፣ ይህችን አረፍተ ነገር በሚናገርበት አፍታ ሁለት አርቲስቶች ወደ አእምሮዬ መጡ።ታደለ አና ሰማኸኝ። በእነዚህ ሙዚቀኞች የተሰየሙ መናፍስት ይኑሩ አይኑሩ ባላውቅም፣ ኖረው ቢጠራቸው ብዬ አሰብኩት። የታደለ “አጋቡዮ” እያለ የሰሜ “አላበድኩም ፣ ጤነኛ ነኝ፣ ያዥኝ” እያሉ ወደ ፊት ሲሮጡ በምናቤ ታየኝ።

ጥቤ ጌታ ይባርክህ። ቸር!

The post “ኢንተርኔትና ሚድያውን አጨናንቀዋለሁ ” ጥበቡ ወርቅዬ የቀድሞ ድምፃዊ፣ የአሁኑ ዘማሪና ሰባኪ appeared first on Zehabesha Amharic.


የብሄር ብሄረሰብ ፖለቲካና የአድዋ ድል –ሚንጋ ነጋሽ

$
0
0

የካቲት 23 2007 (ማርች 2, 2015) የ119ኘዉ የአድዋ ድልና የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ነዉ። አከባበሩ በሃገር ዉስጥ ቢቀዘቀዝም፤ በተዘዋዋሪዉ በአሉን የሚያከብረዉ በዉጭ ሃገር የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ ቁጥር እየጨመረ ይገኛል። በሰሜን አሜሪካ የድል በአሉ ቀን ከአፍሪካ አሜሪካዉያን ታሪክ መዘከሪያ ወር ጋር መያያዙና የየካቲት 12 ሰማእታትን መታሰቢያ ቀን ደግሞ ከሰላሳ በላይ በሆኑ ያለም ከተሞች መዘከሩ፤ በዉጭ  የሚኖሩ ኢትዮጰያዉያን ትኩረት የሰጡት ስለሀገር አቀፍ ድልና ስለአፍሪካዊነት (Pan Africanism) መሆኑ ራሱን የቻለ መልዕክት አለዉ።

በዚህች አጭር ጽሁፍ ለማስገነዘብ የምሞክረዉ አድዋንና መሰል የሃገራችንን እሴቶች በብሄር-ብሄረስብና ወይም በሃይማኖት ዘመም  የፖለቲካ  መነፅር (ethnocentric paradigm) መመልከትና በብዙሃን ዘመም (diverse, multi-ethnic) መነፅር መመልከት የሚየስከትሉትን እደምታዎች ለማሳየት ነዉ። ሁለቱም አመለካከቶች የሚያዩት አንድ ነገር ቢሆንም የሚሰጡት ትርጉም ግን የተለያየ ነዉ። ሃገር አቀፍ ፖሊሲ ሲነደፍ ሁለቱ መነፅሮች የሚያሳዩትን ልዩነትና አንድነትን በቅጡ መረዳት ይጠይቃል። እኔ የታሪክ ወይም የፖለቲካ ስነልቦና ሳይንስ ተማሪ አይደለሁም። ሰለአድዋ ድልም የማዉቀዉ በጣም ዉሱን ነዉ። ቢስማርክ ከጠራዉ እ.ኤአ 1884/85 የበርሊን የአፍሪካ ቅርጫ ኮንፍረንስ (the conference for the scramble of Africa) ጀምሮ እንዴት ኢትዮጵያ እንደሌላዉ የአፍሪካ ክፍል የዚህ ቅርጫ ሰለባ አለመሆንዋ ብዙ የታሪክ ምሁራንን አስረገርሞዋቸዋል። ይህንን ታሪክ አፈወርቅ ገብረየሱስ፡ ገብረ ህይወት ባይከዳኝ፡ ራይመንድ ጆናስ፡ ሪቻርድ ፓንክረስት፡ ዶናልድ ሌቢን፡ ኤድዋርድ ክሬሚ፡ ሃሮልድ ማርከስ፡ ጆን ሰፔንሰር፤ ታደስ ታምራት፡ መርእድ ወልደአረጋይ፤ ብርሃኑ አበበ፤ አለሜ እሽቴ፤ ባህሩ ዘውዴ፡ ሽፍራዉ በቀለ፡ ሹመት ሲሻኝ፡ ዘዉዴ ገብረስላሴ፤ ጌታችዉ ሃይሌ፤ጳዉሎስ ሚለኪያስ፤ ጳዉሎስ ኞኞ መስፍን አርአያ፤ ጌታቸዉ መታፈሪያ በቀጥታና በተዘዋዋሪ የጻፉትንና የተናገሩትን የማንበብ እድል ነበረኝ፡፡

ከፊልም፤ሙዚቃና ግጥም ስራዎች ደግሞ እነ ቦብ ማርሌና ራሰ ተፈሪያኒዝም፤ የሃይሌ ገሪማን፤ የአለምፅሃይ ወዳጆን፤ የፀጋዮ ገብር መደህን፤አዲሰ አለማየሁ እጅጋይሁ ሽባባዉና የቴዎድሮስ ካሳሁንን ስራዎች መስማትና ማየቱ ተጨማሪ ሰሜት  ፈጠሮልኛል።። ከታላላቅ የፖለቲካ መሪዎች ጽሁፎችና ንግግሮች መካከል ደግሞ፡ እነ ማርከስ ጋቢ፡ ማርቲን ሉተር ኪንግን (የኢትዮጵያ ኤምባሲ ግብዣ ጨምሮ)፤ የአፍሪካ የነፃነት መሪዎች ማለትም እነ ሙዋሊሙ ኔሬሬ፡ ኬኔዝ ካዉንዳ፤ጆሞ ኬንያታ፤ ኔልስን ማንዴላ፡ ታቦ እምቤኬ፡ ክዋሚ ንክሩማ፤ በደቡባዊ አፍሪካ በ1880ዎቹ የተፈጠሩትና እስከዛሬ ያሉትን በኢትዮጵያ ስም የሚጠሩትን ቤተ ክርስቲያኖች ታሪክን በተመለክተ የፐ/ር ማሞ ሙጬን የቅርብ ጊዜ ፅሁፎች ሳነብ፤ አሜሪካም በተለይ በሁለተኛዉ እ..ኤ.አ የ1933 የጣሊያን ወረራ ጊዜ ስለነበረዉና ስለአነ መላኩ በያን ሥራና ስለአፍሪካ አሜሪካዉያን ወዶ ዘማቾች ምልመላ ሳነብ፤ የተረዳሁት አድዋ የአድዋዉያንና የኢትዮጵያዉያን የድል ታሪክ ብቻ አለመሆኑን ነዉ። የሃይቲን የነፃነት ትግልና በልጅነቴ እሰማ የነበረዉን የአፄ ምኒልክን የደስታ የተኩስ ሩምታ ምክንያት ያስታዉሰኛል። እነዚህ ምሁራን የነፃነት መሪዎችና አርቲስቶች የተከተሉት በአብዛኛዉ የብሄረሰብና የብሄር መነፅር የታሪክ ትርጉም አልነበረም ብሎ መደምደም ይቻላል።

በአንፃሩ አዲስ ህይወት (የብዕር ሰም): ቦኒ ሆልኮምብና ሲሳይ ኢብሳ፤ ማሩ ቡልቻ፤ በ 1990ዎቹ በ Red Sea Printers ና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በኩራዝ አሳታሚ የታተሙ መጻህፍትና ገድል መሰል ጽሁፎች የፖለቲካ ትንታኔያቸዉ በአንዳንንድ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የሚታየዉን ብሄረ ተኮር ጥናቶች (ethnography and ethnic studies) ተደግፈዉ ማርክሳዊ መሰል ትንታኔና ትርጉም ሊሰጡ ይሞክራሉ። ጎልቶ የሚወጣዉ መልዕክታቸዉ ኢትዮጵያ የሚለዉን የፖለቲካና የሶሺያል መሰረቶች የሚንድ (de-legitimize) ነዉ። የሀገር ዉስጥ ግጭቶችን በብሄር መነጽር ያይዋቸዋል። የአድዋ ጦርነትን ዋና መሪዎችን ከሌሎች ግጭቶች ጋር እያጣቀሱ ሲወቅሱ ይሰማሉ። ብሄር ተኮር ድርጅቶችም ግጭቶቹን የአንድ ወገን በማስመሰል ከዛሬ ፖለቲካ አገናኝተዉ ቢቻል አዲስ ነፃ ሀገር ባይቻል ደግም አሁን ካለዉ የተሻለ የፌዴራል አስተዳደር እንመሰርታለን እያሉ ቃል ይገባሉ። የድሮዋ ኢትዮጵያም ልዩ የብሄረሰቦች እስር ቤት ነበረች የሚል ትረካም አላቸዉ። አዲሲትዋ ኢትዮጵያም የብሄረስቦች (nations, nationalities, peoples, volks) ድምር ነች ወይም ትሆናለች ይላሉ። በዚህም የተነሳ የፖለቲካ የአስተዳደርና የትምህርት ወዋቅሩ ይህንኑ ተከትሎዋል። ይህ አካሄድም ሀገሪቱዋን ከመበተን አድኖዋት በኢኮኖሚም እየተራመደች ነዉ ብለዉ ይከራከራሉ።

የፖለቲካ መሪዎች ይመጣሉ-ይለወጣሉ። ስርአቶቹን የሚመራዉም ርአዮተ አለም እንዲሁ ይቀያየራል። ይህ ደግሞ በብዛት የሚታየዉ አፍሪካ ዉስጥ ባሉ ከቀኝ ግዛት በሁዋላ በተፈጠሩ ሀገሮች (post colony states) ነዉ። አንድ ቲዎሪም ሁሉን ነገር (phenomenon) ሊያብራራ አይችልም። ይህ እንኩዋን በኩዋሊቴቲቭና በፊኖሚኖሎጂ የምርምር መንገድ የሚጠኑ ስራዎችን ቀርቶ በኢምፒሪካል  የምርምር መንገድ ላይም በየጊዜዉ የሚታይ ሁኔታ ነዉ። ታሪክንም በተለያዩ መነፀሮች መመርመር በራሱ ችግር የለዉም። እንዴዉም ይህ አካሄድ በተ;ለይ በፖሊሲ ንድፊያ ጊዜ የተሻለ አካሄድ ሊሆን ይችላል። በእኔ እድሜ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሶስተ ያስተዳደር መርሆዎችን አይቻለሁ። ባለፉት 40 አመታት ዉስጥ ብሄር ዘመምና የግራ ዘመም የታሪክ ትርጉዋሜዎች የመንግስትን ዋና ዋና ፖሊሲዎች ሲመሩ አይተናል። ሁለቱም ህብረተስብን በመደብ በብሄርና ወይም በሃይማኖትና በጾታ መክፈልና ልዩነቶች ላይ ማተኮርን ይወዳሉ። አንድን ህብረተሰብ በዴሞግራፊ መርሆዎች ከፍሎ ማጥናቱ ችግር የለዉም። ልዩነታቸዉ ብዙሃንነት (diversity) እንዴት እንደሚስተናገድ ነዉ። ሰለ ከአንድ በላይ ማንነት (dual & multiple identities) በሃገራችን ብዙ አይነገርም።

ብዙዎቹ የዛሬ የብሄር ንቅናቄ መሪዎች በአንድ ወቅት የማርክሲስት ርአዮተ አለም ተከታዮች እንደነበሩ ይታወቃል። አስተዳደር ላይ የሁለቱ ልዩነት ማርክሲሰቶች ሀገር አቀፍ፡ አህጉር አቀፍ፤ከዚያ አልፎ ኢንተርናሽናሊዘምን ሲያወድሱ፤ በተቃራኒዉ ብሄር ተኮር አካሄድን የሚመርጡ ደግሞ ጭንቀታችዉ ቆመንልሃል ለሚሉት የህብረተሰብ ክፍል ሲሆን ግራ ዘመምነታችዉ ስታሊን በስራ ላይ ያላዋለዉን የመገንጠል መንገድ እንዲያቀነቅኑ አድርጎዋቸዋል። ግራ ዘመም ያልሆኑት ብሄር ተኮር ድርጅቶች ደግሞ ተግባራቸዉ ወደ ፋሽዝምና አፓርታይድ፤በማወቅም ሆነ ባለማወቅ፤ ሲያቀርባቸዉ ይታያል። የሶቪየት ህብረትና የይጎዘላቪያን አፈጣጠር፤ አፈራረስና ዉጤቱን ማጤን ይረሳሉ። ስለሆነም አንድ ብሄር ተኮር የፖለተካ ሃይል የተለያዩ ብሄሮች ባሉበት ሀገር ላይ የበላይነት በያዘበት ቦታ ገዢዉን ብሄር ለመጥቀምና ለማሞገስ ተብለዉ የሚደረጉ ሙከራዎች ትክክለኝነታቸዉና ትረጉዋሜያች በቅጡ ሳይፈተሹ በህገ መንግስት ላይ ይሰፍራሉ። የመንግስትም ስራዎች በብሄር ተኮር ፖሊሲዎች ይመራሉ። የብሄር ድርጅቱ ካናሳ ወግን ከመጣ የአናሳዎችን  ህብረት በመፍጠር የብዙሃኖችን ግፊት ለመቁዋቁም ይሞክራል። ማንነት (identity) የምርጫ አጀንዳ ሆኖ ዜሮና አንድ ወይም እድገትና ድህነት፤ባርነትና ነፃነት፤ እኛና እነሱ፤ ሰይጣንና መልአክ፤ወዘተ ተብሎ ይቀርባል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ይህ አካሄድ በሃይማኖት (bigotry) በመታጅብ ላይ ይገኛል።  ከዚህ ባሻገር ደግሞ ሊበሪቴሪያኒዘምን ማለትም ግለሰብ መብት ላይ የሚያተኩር  የፖለቲካ አስተሳሰብን የሚያራምዱ አሉ። ሁሉም ማለትም የግራዉም ብሄር ተኮሩም ሆነ ሊበሪቴሪያኑ “ዲሞክራሲያዊ” የሚል ታፔላ አላቸዉ።

ሰለዚህ ኤትኖሼንትሪዝም በሃገራች ሲታይ ልዩነትን (diversity) ለማስተናገድ እ.ኤ.እ በ1993 የሰራዉ ህገ መንግስት መፍትሄ እንዳልሆነና ሀገር አቀፍ መግባባት ለመፍጠር አለመቻሉ በቅጡ ተፈትሾአል። የ1991 ዱም ቻርተር ማለትም የህገ መንግሰቱ አዋላጅ የተፃፈዉ ከግጭት በሁዋላ ስለነበር ያመለከተዉ የጊዜዉን የሃይል አሰላለፍ ነበር። ጸሃፊዎቹም እርስ በርሳቸዉ ይጣሉ እንጂ በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ከ25 አመታት በሁዋላም ቢሆን መሰረታዊ ልዩነት አይታይባችዉም። በትምህርት ቤቶችም የሚሰጡ ትምህርቶች የብሄር ተኮር መሰረት ስላላቸዉ ከፍተኘ ትምህርትም በብሄር በመዋቀሩና በክልል አሰተዳደር ስር መሆናቸዉ፤ በምሁሩም ቅን ልቦናዊነት (bona fide, honesty and integrity) ላይ ለመተማመን አስቸጋሪ እየሆነ መጥቶዋል። ሃገሪቱ የተማረ ህዝቡዋን በተለያዩ ምክንያቶች ስታጣና፤ አብዛኛዉ ወጣት የሆነዉ ህዝብ የስራ አጥነት፤የኢኮኖሚና የፖለቲካ ስደት ሰለባ ሲሆን፤ በባህር ላይ ሲሰምጥና በየስደተኛ ካምፖችና እስር ቤቶች ሲታጎር፤ የምርምር ተቁዋሞች መሰረታዊ ምርምር ማደረግ አለመቻላቸዉ፤ ዮኒቨርሲቲዎችም ከጥራት ይልቅ ወደ ብዛት አተኩረዉ በየክልሉ ሲረጩ፤ በብሄር ተኮር ሹማምንት ሲመሩ፤ ዉጥረቶቹንም በፍትሃዊ ምርጫዎች ለማስተንፈስ አለመቻሉ፤ ብሄርና ሃይማኖት የፖለቲካ ማማ (platform) ሆነዉ መቀጠላቸዉ፤ በግጭት ቀጠና ዉስጥ ያለችዉን የሀገራችንን ችግሮች እጅግ ዉስብስብ አድርገዉታል።

ስለዚህም በሀገራችን ዛሬ በስልጣን ላይ ያለዉ ብሄር ተኮር መንግስት እንደ ቀድሞዎቹ የማርክሲሰትና የንጉሳዊ መንግስታት ሁለት ችግሮች ገጥመዉታል። በአንድ በኩል ሌሎች ብሄር ተኮር ተፎካካሪዎቹ የማዕከላዊ መንግስት ስልጣኑን ሊወስዱብትና ለራሳችዉ ብሄር ሊተኩ ይፈልጋሉ፡፡ ይህ ካልሆነላቸዉ ደግም ሃብት ወደ አሽናፊዉ ብሄር ብሄረሰብ እንዳይፈስስ ሲሰተሙን ለማፍረስ ይጥራሉ። ይሀ ጥረት በራሱ በመንግስትና ፓርቲ ዉስጥ፡ በምርጫና በጠመንጃም እየተሞከረ ይገኛል። የብሄር ድርጅቶች መሪዎችም ለሁለተኛ ድል (second breakthrough) እየተዘጋጀን ነዉ ይላሉ። ሁኔታዉ በሶቪየት ህብረትና በዩጎዝላቪያ የኮሚኒስት ፓረቲዎች ዉሰጥ የብሬዥኔቭና የቲቶን ሞት ተከትሎ የተፈጠረዉን ክስተት በገዥዉ የብሄሮች ግምባር ዉስጥ አይከሰትም ብሎ መናገር አይቻልም። እሰከ አሁን በድርጅቱ ዉስጥ የነበረዉ  የሃይል አሰላለፍ ለማስቀጠል ርብርቦሽ ያለም ይመስላል። በሌላ በኩል ደግሞ ከብዙሃኖችና ከዲሞክራሲ ሃይላት ክፉኛ ዉድድር ገጥሞታል። በነፃና ፍትሃዊ ሀገር አቀፍ ምርጫ እንደማያሸንፍ ተረድቶታል። ስለሆነም ተፎካካሪዎቹን ስልጣን ከማካፈል ይልቅ ማፍረስንና አሽባሪዎች ብሉ መሰየሙን መርጦዋል። በ2005ቱ ምርጫ ያኮረፉም ጠመንጃ አንሰተዉ ከቆዩት ጋር የታክቲክ ወዳጅነት የፈጠሩ ይመስላሉ። የሰላም መንገድ መጥበብና መዘጋት አመፅ ተቀባይነት እንዲያገጘ እያደረገ ይገኛል። ከዚህም አልፎ ሰለሰላማዊና የመሳሪያ ትግሎች (armed & peaceful resistance) ተጉዋዳኝነት የሚያሳዩ ፍልስፍናዎች እየቀረቡ ይገኛሉ። ይህንንም ሁኔታ ጎረቤት ሀገሮች ለራሳቸዉ በሚጠቅም መንገድ ሂደቱን ሊቃኙት እንደሚፈልጉ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነዉ። በቀጠናዉ ያለዉን አጠቀላይ በሃገሮች መሃል ያሉትን ዉጥረቶችን ወደጎን አድርገን የሃገሪቱን የዉስጥ ዉጥረት ብናይ የመጪዉ ግንቦት ምርጫ ወይም አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት ጥገናዊ የህገ መንግስት መሻሻል እዚህ ግባ የሚባል ፋይዳ እንደማይኖራችዉ ግልፅ ነዉ።

ሰለዚህ በሀገራችን ያሉትንና እየተፈጠሩ ያሉትን ዉጥረቶች ለመፍታት ወሳኝ እርምጃዎች መዉሰድ ያስፈልጋታል። ለዚህም  ቁልፉዋ የምትገኘዉ በአብዛኛዉ የማእከላዊ መንግስትን ስልጣን በሚቆጣጠረዉ ብሄር ተኮር ድርጅት እጅ ቢሆንም   ድርጅቱ ይህንን ሊሰራ የሚችል መሪ ከዉስጡ ለማዉጣጥ እስካሁን አልቻለም። ብሄራዊ አንድነትንና እኩልነትን የሚገነባ፤እሸናፊና ተሸናፊ የሌለበት የፖለቲካ አስተሳሰብና አስተዳደር መመስረት የዛሬዉ የሃገሪቱ ፈተናዎችዋ ሲሆኑ፤ እነዚህ ፈተናዎች ግን የዛሬ 119 እመት በፊት እነ አፄ ምኒልክን፡ እቴጌ ጣይቱን፡ ራሰ አሉላን፤ ፊታዉራሪ ሃብተ ጊዎርጊስን፤ ራስ ጎበናንና ሌሎቹን በሺህ የሚቆጠሩትን የአድዋን አርበኞች ገጥመዋችዉ ከነበሩት ፈተናዎች ጋር የሚወዳደሩ አይደሉም። እ.ኤ.አ ከ1937ቱ ፈተናዎች ጋርም የሚወዳደሩ አይደሉም። በእነዛ ከባድ ፈተናዎች ጊዜ ብዙ መስዋእትነት ተከፍሎዋል።  እነዛን ፈተናዎችን ስንመረምር የእኛ ትዉልድ ፈተና የኤትኖሴንሪክ የታሪክ መነጽር ወዴት እየወሰደን መሆኑን መገንዘብና በቅን ልቦና ላይ የተመሰረተ ብሄራዊ መግባባት የሚፈጠርበትን መንገዶች መሻት ነዉ። ችግሮችን መካድ ወይም መደበቅ ሳይሆን፤ በእዉቀት በዉይይት በዲሞክራሲና በፍትሃዊ ካሳ (restorative justice) የሚፈቱትን የታሪክ ጠባሳዎች እያጎሉ ጣት መቀስሩ ለማንም ጠቃሚ እንደማይሆን ማወቅ ነዉ። የዛሬ ተሽናፊዎች ነገ አሸናፊዎች ለመሆን እንዳይሰሩ፤ ይህንንም በር በጊዜዉና በቅጡ በብሄራዊ እርቅና መካካስ መዝጋት እንጂ፤ እንዴዉ በደረቁ የርስ በርስ ጦርነት ሂደቶችን እንደ ገድል እየቆጠሩ፤ ከበሮ መምታቱ፤ በግብር ከፋዩ ገንዘብ ስርግና ምላሽ መደገሱ፤ ለአንድነትና ለብሄራዊ መግባባት ጠቀሚ ርምጃዎች ሊሆኑ እንደማይችሉ፤ ከድግሱ በሁዋላ ቢሆንም፤ ግንዛቤ መዉሰድ ያስፈልጋል።

ከዚህም በላይ ኤትኖሴንትሪዝም የማእከላዊ መንግስትን ስልጣን ቢይዝም ሆነ ባይዝ የሚያልመዉ ስለ አንድ ንፁህ የጠራ የተቀባ፤ወርቃማና እግዚአብሄር ስለመረጠዉ ጭቁንና ስለተጎዳ ወዘተ ማህበረሰብ ስለሚኖርባት ቅኖናዊት ሀገር  (utopian state) መሆኑ መረሳት የለበትም። በዚህም የተነሳ የተረጋጋ የብዙሀን ብሄር ብሄረሰቦች ሀገርን ማስተዳደር ከባድ ፈተና ይሆንበታል። በብዙ ክልሎችም በነፃ ምርጫ ማሽነፍ ያስቸግረዋል። ቀልፍ የአስተዳደር የማከላከያ የኢኮኖሚ አዎታሮችን ቃል እንደሚገባዉ ማስተዳደር ይሳነዋል። አዲሲቱ ኢትዮጵያ መሆን ያለባት ከብሄርና ብሄረስቦች (nations, nationalities, ethnic groups, volks) የተዉጣጡ ስብስቦች (የህገ መንግስቱን መግቢያ ይመልከቱ) ተስማምተዉ የሚፈጥሩት ሀገር ናት የሚለዉም ምርጫ መር ከሆነ ዲሞክራሲ ጋር ማጣጣም አስቸግሮታል። ስምምነቱም ካልሰራ ደግሞ አንቀፅ 39ን ተጠቅሞ መሄድ ይቻላል የሚለዉን መፈፅም ቀላል አለመሆኑን ተረድቶታል። የሚሄደዉም ክልል ምንም እንኩዋን በአፍሪካም ሆነ በአወሮፓ ለጊዜዉ የሚታየዉ ብሄረሰብና ሃይማኖት ተኮር የሆነዉ የፖሊቲካ ምህንድስና ዉጤት አሉታዊ ቢሆንም፤ የተሻለ/ች አባት/እናት ሀገር መመስረት ይቻላል የሚሉ አሁንም አልጠፍም። ይህንን አካሄድ መፋትሄ ነዉ ብሎ ሀገሪቱ ባለችበት ሁኔታ ለህዝብ በሬፈርነደም ማቅረብ ግን ሃላፊነት የጎደለዉ አካሄድ ነዉ። የጋራ እሴቶችን፤ ክፉም ይሁኑ ደግ መኖራቸዉን መርሳት፤ ሰዎች ከአንድ በላይ ማንነት (dual or multiple identity) እንደሚኖራቸዉ፤ የሀገራት አመሰራረት ሁል ጌዜ ያለችግር አለመሆኑን በቅጡ አለመመርመርና የወዲፊቱን ጉዞ በቅጡ ማለም አለመቻልን ያመለክታል።

በመጨረሻም በዉጭ የምንኖር ኢትዮጰያዎያን ባንፃራዊ ነፃነት ስለምንገኝና ከጊዜ ወደጊዜ ቀጥራችንም እየበዛ ስለሄደ፤ እንደ አድዋ አይነት ሃገር አቀፍ የሆኑ እሴቶች ከማክበር የሚከለክለን ነገር መኖር የለበትም። በሃገራችንም የሰላም ድምፅ ከፍ ብሎ እንዲሰማ መሞከር ይኖርብናል። በመሬትና በአንዳንድ ጥቅሞች መደለልና የገዛ ጥላችንን ሳይቀር መፍራት የለብንም። ራሳችንን ከፍርሃት ነፃ ማዉጣት ይገባናል። ስለ አሀጉራዊ ስለአፍሪካ ዲየስፖራ፤ ስለአፍሪካ አሜሪካዉያን ሰለሃገር አቀፍ እሴቶች ዉርስና ቅርሶች መናገር መጻፍ፤ ማክበርና መዘክር ይኖርብናል። በተለያዩ ቦታዎች ያሉትን የታሪክ አሻራዎች (historical footprints) በምንችለዉ ዘዴ መረዳት፤ማሰባሰብና የተዘረፉት ቅርሳ ቅርሶች እንዲመለሱ መሞከር ይገባናል። የአክሱም ሃዉልት መመለስ የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ መሆን የለበትም። ከበስተሁዋላም ሆነ ከፊት ሆነዉ የሚሰሩትንና የሚረዱትን ማመስገን ይገባል። ዶ/ር አበራ ሞላና አቶ ኪዳኔ አለማየሁ በመካከላችን መገኘታቸዉና እየሰሩ ያሉትንም ልናዉቅላቸዉና ልናበረታታቸዉ ይገባል። በብሄር ተኮር ፖለቲካ ዉስጥ ራሳችንን አጥረን፤ ታሪካችን የግጭት፤የረሃብ፡ የቸነፈርና የስደት ብቻ እንዳይሆን፤ዛሬ አፍሪካ አሜሪካዉያን የገቡበትን ራስን ያለማወቅ ቀዉስ (identity crisis)፤ ሌሎች አፍሪካዉያን ወገኖቻችን ያለባቸዉን የራስ መተማመን ችግር፤ ልጆቻችን በአዉሮፓ እንዳሉት አናሳ ኮሚኒቲዎች፤ የኢኮኖሚዉ፤የፖለቲካዎና የዕዉቀት ጭራ፤በሁዋላም የአሀገሮቹ ባዐዳን እንዳይሆኑ፤ ከወዲሁ ማስብና ዘዴ ማግኘት የእኛ የመጀመሪያ ትዉልድ ፈላሾች (immigrants) ፈተና ነዉ።

 

[1] አ.ኤ.አ በማርች 15, 2015 በዴንቨር ኮሎራዶ የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ላይ የተደረገ ንግግር;;

comment pic

The post የብሄር ብሄረሰብ ፖለቲካና የአድዋ ድል – ሚንጋ ነጋሽ appeared first on Zehabesha Amharic.

በረከት ስምዖን “የትግራይ ተወላጅ የሆነ መለስን የሚተካ መሪ አይፈጠርም”ካሉ በኋላ ሕወሓቶች በብስጭት “ብአዴን”የሚለውን ቃል እንደ ስድብ እየተጠቀሙበት ነው

$
0
0

Bereket simon
“..አንተ ብኣዴን ….! …” አዲሱ ስድብ – አምዶም ገብረ ስላሴ

በመቐለ ከተማ ኣዲስ ስድብ ተፈጥሯለች። እቺ ስድብ ለማንኛውም በህወሓት መሪዎች ላይ የብቃት ጥያቄ ያነሳ ሰው እየተሰጠች ያለች ቃል ናት።

በትግራይ የተለየ ሃሳብ ያንፀባረቀ፣ ከባድ የህዝብ ጥያቄ አንስቶ ተቀባይነት ያገኘ፣ የልማት ይሁን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ያነሳ ሰው ዓረና እየተባለ እንዲሸማቀቅ ይደረግ ነበር።

ሕወሓት ኣርባዋኛዉን አመት ባሳለፈችበት ወቅት፣ ኣቶ በረከት ስሞን የአቶ መለስን የትግል ድርሻ አስመልክተው ባቀረቡት “..የብኣዴን ኣቋም የሚያንፀባርቅ ..” (እሳቸው ጥናታዊ ፅሁፍ ያሉት) ፅሁፍ ካቀረቡ በኋላ ግን ነገሮች ተቀያይረዋል።
ኣቶ በረከት በፅሑፋቸው ኣቶ መለስ ከእንግዲህ በትግራይ መሬት ከመቶ ኣመት በሗላ ካልሆነ በስተቀር እሳቸው የመሰለ (የሚተካ) መሪ ዳግም የማይፈጠር መሆኑ ተነበዩ። ይቺ ኣገላለፅ ለህወሓት ካሁን በሗላ ኣገሪቱ የመምራት ብቃት ያለው ሰው የላቹምና ለኛ ተውልን የሚል መልእክት ያዘለች ነበረች።

በመድረኩ ነበሩ ያተባሉት ኣቦይ ስብሓት “..በረከት ያለውን ሙሉ በሙሉ ኣልቀበለውም፣ ከፈልግሁ ሺዎች ከመልስ የበለጡ እኔ የማውቃቸው ወጣቶች ማቅረብ እችላለው።..” በማለት በእጃቸው እያቃለሉ የኣት ስሙት መልእክታቸው ኣስተላለፉ።
ኣቶ ኣርከበ ዕቑባይም “..እኛ እዚህ ያደረሰን ህዝብ ነው። ትግሉ የመራን የትግራይ ህዝብ ነው። በግለ ሰው ወይም በቡድን ተመርቶ ለድል የበቃ ትግል ኣላውቅም..” የሚል መልእክት በማስተላለፍ ኣቶ በረከትን “..የት ነበርሽ እኛ ኣይደለም ወይ መንገድ መሪ እንድትሆኚ ያደራጀንሽ ..” ኣይነት መልእክት ኣስተላለፉላቸው።

የመለስ ራእይ የሚል መፎክር የያዙት ግን ብኣዴኖች ብቻ ኣይደሉም። በትግራይም ጭፍራ ያላቸው መሆኑን ይታወቃል።
ወደ ዋናው ሃሳቤ ልመልሳቹና ኣንተ ባዴን …! የሚል ቃል በመቐለ ስድብ ኣድርገው የሚጠቀሙበት ሰዎች እየበረከቱ ናቸው። ለነገሩ በፌስቡክም “…ብኣዴን ሲፏቁ ጉንበት 7 ናቸው..” የሚል ዘመቻ እንደተጀመረ እያነበብን ነው።
የኣማራ “..እንገንጠል..” የሚል ጥያቄም የብኣዴንና ህወሓት ልዩነት የወለደውና “..ብኣዴን ትግሉ የተለየ ኣቅጣጫ ሊያስይዘው ፈልጎ ያነሳው ሃሳብ ነው..” የሚሉ ሰዎች ኣሉ።

በወልቃይት ያለው ኣለመረጋጋትም የብኣዴን እጅ ኣለበት እየተባለ ይወራል። ለማንኛውም በመቐለ ከተማ የህወሓት ኣመራሮች ኣቅመ ቢስነት ያወራ ሰው “…ኣንተ ብኣዴን…” የሚል ስድብ እየወረደበት ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።

ብኣዴን የህወሓት የቦክር ልጅ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በትጥቅ ትግል ከነበረው ሚና በላይ እነ ስየና እነ መለስ ልዩነት በፈጠሩበት ወቅት የመለስ መቺ ሃይል መሳርያ በመሆን የተጫወቱት ተራ ይልቃል።

ለብኣዴኖች የምለግሰው ምክር የነብር ጭራ ኣይያዙ ከያዙም ኣይልቀቁ ነው። ብኣዴኖች በኣቋማቸው ከፀኑ ህወሓት ኣፍርሶ በቦታቸው ሌላ ድርጅት ይተክልላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።
‘…ኣንተ ባዴን …!”
ነፃነታችን በእጃችን ነው..!

The post በረከት ስምዖን “የትግራይ ተወላጅ የሆነ መለስን የሚተካ መሪ አይፈጠርም” ካሉ በኋላ ሕወሓቶች በብስጭት “ብአዴን” የሚለውን ቃል እንደ ስድብ እየተጠቀሙበት ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: 10 ትልልቅ የፊት አስተጣጠብ ስህተቶች

$
0
0

face wash wrong

ይህ ጽሁፍ በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 72 ላይ ታትሞ ወጥቷል

  1. የተሳሳተ ምርት መምረጥ

ፊትን መታጠብ በጣም ቀላል እና የተለመደ የዕለት ተዕለት ተግባር ይመስላል፡፡ ይሁን እንጂ ፊታችንን በምንታጠበብት ወቅት የምንጠቀማቸው አንዳንድ ምረቶች የፊት ቆዳችን ላይ የትየለሌ ችግር ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ከእነዚህ የቆዳችግሮች ውስጥ ድርቀት፣ የማቃጠል ስሜት፣ የወዝ መብዛት እና የቆዳ መሰነጣጠቅ በቀዳሚነት ስማቸው ይነሳል፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመከላከል በዋናነት ስልምንጠቀማቸው የፊት ቆዳ ማፅጃዎች ምንነት እና አዘገጃጀት ማወቅ ጠቃሚ ነው፡፡ በተለይ በተለይ የማፅጃዎቹን ይዘት አውቆ መምረጥ መቻል ያለምንም የጎንዮሽ ጉዳት የምርቶቹ ተጠቃሚ ለመሆን ይረዳል፡፡

 

  1. ከልክ በላይ መታጠብ

አንዳንድ ሰዎች ፊታቸውን አያምኑትም፡፡ በቀን አስሬ መታጠብ ይቀናቸዋል፡፡ በወጡ በገቡ ቁጥር ውሃ ፊታቸውን ማስነካት የዘወትር ተግባራቸው ነው፡፡ የፊት ቆዳን በቀን አንድ ጊዜ አልያም ሁለት ጊዜ መታጠብ ይመከራል፡፡ ከሁለት ጊዜ በላይ ፊትን ሙልጭ አድርጎ መታጠብ በአንፃሩ የተለያየ የፊት ቆ ችግር የስከትላል፡፡ ችግሩ የሚከሰትበት አንዱ ምክንያት በተደጋጋሚ እጥበት ምክንያት የሚከሰትን ድርቀት ለመከላከል ቆዳችን ከልክ በላይ ዘይት መሰል ነገር ለማምረት ግዴታ ውስጥ ስለሚገባ ነው፡፡ ሜክአፕ፣ ሰንስክሪን እና መሰል መዋቢያዎችን የማትጠቀሙ ከሆነ እና ያን ያህል ላብ ፊታችሁ ላይ ከሌለ ምንም አይነት ማፅጃ ሳትጠቀሙ ለብ ባለ ውሃ ብቻ ፊታችሁን ማታ ማታ ታጠቡ፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ቆዳችሁ ምንም አይነት መዋቢያ የማይጠቀምበት እረፍት መስጠትም መልካም ነው፡፡

 

  1. ከልክ በላይ የጋለ ውሃ መጠቀም

ሞቃት ውሃ የፊታችንን ቆዳ ቀዳዳ ክፍት ያደርጋል፣ ቀዝቃዛ በሌላ በኩል ይዘጋል የሚል የተሳሳተ አመለካከት አለ፡፡ እውነታው ግን ፊታችን ላይ የሚገኙ ቆዳዎች ራሳቸውን የመክፈትም ሆነ የመዝጋት አቅም የላቸውም፡፡ እንደውም በሞቃት ውሃ ከልክ በላይ ቆዳችሁን በማጠብ ከፍተኛ ድርቀት ወይም አላስፈላጊ የሆነ ከፍተኛ የ‹ሴበም› ምርትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ የሚመከረው ለብ ያለ ውሃ መጠቀም ነው፡፡

 

  1. ከልክ በላይ ‹ስክራብ› ማድረግ

የፊት ቆዳ ላይ የሚገኙ የሞቱ ህዋሶችን ቀርፎ በተለያየ መንገድ ማንሳት (ስክራብ) ተገቢ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይሄም በልኩ መሆን መቻል አለበት፡፡ እነዚህን ህይወት የሌላቸው ህዋሶች ለማስወገድ ተፈጥሯዊ የሆኑ ነገሮችን መጠቀም ይመከራል፡፡ ከስኳር እና ከፍራፍሬዎች የሚገኝ አሲድ ተመራጭ ቆዳን ‹‹ስክራብ›› ማድረጊያ ናቸው፡፡ ቢበዛ ቢበዛ በሳምንት ሁለት እና ሶስት ጊዜ ብቻ ስክራብ አድርጉ፡፡ ስክራብ በምታደርጉበት ወቅት ቆዳችሁ ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳይደርስ ከመታጠቢያ ፎጣ ይልቅ ጣታችሁን ተጠቀሙ፡፡

 

  1. በበቂ ሁኔታ አለመታጠብ

የፊት ቆዳን በአግባቡ አለመታጠብ የፊት ቆዳ ቀዳዳዎች እንዲደፈኑ እና ድርቀት እንዲከሰት ያደርጋል፡፡ ጠዋት ከእንቅልፋችሁ ተነስታችሁ ስራ ለመጀመር ጥድፊያ ውስጥ ሆናችሁም ይሁን ማታ ድቅቅ ብላችሁ ቤታችሁ ገብታችሁ ከመተኛታችሁ በፊት ፊታችሁን በሚገባ መታጠባችሁን አትዘንጉ፡፡

 

  1. የፊት ቆዳን የሚያቃጥሉ ምርቶች መጠቀም

ፓራቢንን የመሳሰሉ አርቴፊሻል ማቆያዎችን፣ መአዛቸው ደስ የሚያሰኙ ማቅለሚያዎችን ወዘተ በአለመጠቀም ለቆዳችሁ ውለታ ዋሉ፡፡ ሶዲየም ሎውሪል ሰልፌት ሌላኛው ልናስወግደው የሚገባ ንጥረ ነገር ነው፡፡ ምንም እንኳ የፈራረሱ ነገሮችን ለማፅዳት ጠቃሚ ቢሆንም በአመዛኙ ቆዳ እንዲቃጠል ያደርጋል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ለአንዳንድ ሰዎች አለርጂም ጭምር ነው፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን የምትጠቀሙት ምርት ውስጥ ምን ምን አይነት ነገር በምን ያህል መጠን እንደሚገኝ ለመረዳት ሙከራ አድርጉ፡፡

 

  1. በፎጣ ፊትን መወልወል

ፊታችሁን በእጃችሁ አሻሹ እንጂ በፎጣ አትወልውሉ፡፡ በፎጣ ፊትን መወልወል ደስ የሚያሰኝ ነገር ቢሆንም በሌላ መልኩ ግን ቆዳን ሊልጥ እና ጉዳት ላይ ሊጥል ይችላል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በአቅራቢያችሁ የሚገኝ አገልግሎት ላይ የዋለም ይሁን ያልዋለ ፎጣ ዝም ብላችሁ አንስታችሁ አትጠቀሙ፡፡ አንድ ሰው የሚጠቀምበትን ፎጣ ሌላ ባይጠቀምም መልካም ነው፡፡ ንፁህ እና ለስላሳ ፎጣ መርጣችሁ ፊታችሁን ጠራርጉ፡፡

 

  1. ፊት እስከሚደርቅ መጠበቅ

ፊታችሁን ከታጠባችሁ በኋላ ወዲያውኑ እርጥበቱ ሳይጠ ፋፊታችሁን ለማለስለስ የምትጠቀሟቸውን መዋቢያዎች ተቀቡ፡፡ ፊታችሁ ከደረቀ በኋላ መዋቢያዎችን መቀባት የተቀባችሁት ማንኛውም ነገር የቆዳ ቀዳዳዎች ዝግ ስለሚሆኑ ወደ ውስጥ ለመግባት ይቸገራል፡፡ በዚህ ምክንያት ፊታችሁ እንደ አብለጨለጨ ሁሉ ትውሉ ይሆናል፡፡

 

  1. ብዙ ገንዘብ ማውጣት

ለፊት ቆዳ ጤንነት አጠባበቅ አቅም እስካለ ድረስ ምንም ገንዘብ አለማውጣት ትክክለኛ ውሳኔ ላይሆን ይችላል፡፡ ቀላል እና ተፈጥሯዊ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን የያዙ የፊት ቆዳ ማፅጃዎችን ተጠቀሙ፡፡ ከዚህ ውጪ ውድ የሆኑ በአናቱም ተፈጥሯዊ ያልሆኑ የፊት ቆዳ ማፅጃዎችን መጠቀም አይመከርም፡፡ ይህ ተግባር ኪስንም የፊት ቆዳንም አንድ ላይ ይጎዳል፡፡

 

  1. ዘይት ነክ ማፅጃዎችን መፍራት

ረዘም ላለ ጊዜ ዘይት ነክ ማፅዎች እና ቅባቶች የቆዳ ቀዳዳዎችን ይደፍናሉ የሚል የተሳሳተ እምነት ነበር፡፡ ይህ እምነት ግን አሁን እየተቀየረ ነው፡፡ አጥኚዎች አሁን ቆዳን በዘይት ማፅዳት ጠቀሜታ ሊኖረው እንደሚችል በመግለፅ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሌላው ቀርቶ ወዝ የሚበዛባቸው የፊት ቆዎች እንኳ በዚህ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ ዘይት ዘይትን ያሟሟል፡፡ ጥሩ ጥሩ የቆዳ ማፅጃ ዘይቶች ቆዳ ቀዳዳ ውስጥ የሚገኙ ቆሻሻዎችን እንዲሁም ባክቴሪዎችን ያፀዳሉ፡፡ የተጎዳ ቆዳን ለማከም ይረዳሉ፡፡ በመሆኑም ተፈጥሯዊ የሆኑ የአትክልት ዘይት ይዘት ያላቸውን ማፅጃዎች ተጠቀሙ፡፡

እንደዚህ አይነት ማፅጃዎችን በቀላሉ ማግኘት የማትችሉ ከሆነ እንኳ ጥራት ያላቸውን የአልሞንድ እና ሱፍ ዘይቶችን እንድትጠቀሙ ይመከራል፡፡ ኮኮናት እና ወይራ ዘይት ለአንዳንዶች በጥሩ ሁኔታ እንደሚሰሩ ቢታወቅም ለአንዳንዶች ግን ራሱን የቻለ ችግር ያስከትላሉ፡፡ በቀስታ ዘይቱን ፊታችሁ ላይ በጣታችሁ ከቀባችሁ በኋላ ለብ ያለ ውሃ ውስጥ በተነከረ ለስላሳ ጨርቅ መልሳችሁ ጥረጉ፡፡ የፊት ቆዳችሁ ቀዳዳዎች በየጊዜው ፊታችሁ ላይ ቀርቶ በሚጠራም ዘይት እንዳይደፈን ሙልጭ አድርጋችሁ በጥንቃቄ የፊት ቆዳችሁን አፅዱ፡፡

The post Health: 10 ትልልቅ የፊት አስተጣጠብ ስህተቶች appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: የኢትዮጵያ ሉሲዎች ከካሜሮን አቻቸው ጋር ይፋለማሉ

$
0
0

Lucy Ethiopia
ኢትዮ ኪክ ኦፍ እንደዘገበው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ለማለፍ ከካሜሩን አቻው ጋር የሚያደርገው ጨዋታ መጋቢት 12 ከቀኑ በ10 ሰአት በአዲስ አበባ ስቴዲየም ይደረጋል። ብሔራዊ ቡድኑ ለዚህ ጨዋታው ዝግጅቱን ከሶስት ሳምንት በፊት ቁጥራቸው 40 የሚደርሱ ተጨዋቾችን ይዞ መጀመሩ ይታወሳል። በአሰልጣኞቹ ምርጫ ከ40ዎቹ 26 ተጨዋቾች ተመርጠው ለካሜሩን ጨዋታ ዝግጅታቸውን ቀጥለዋል።

የሉሲዎቹ ተጋጣሚ የካሜሩን ብሔራዊ ቡድን በዛሬው እለት አዲስ አበባ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ጨዋታውን ግብፃውያን ዳኞች እና ኬንያዊ ኮሚሸነር ይመሩታል።

The post Sport: የኢትዮጵያ ሉሲዎች ከካሜሮን አቻቸው ጋር ይፋለማሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

የደብረ ሊባኖሱ እልቂት –ከዲ/ን ዳንኤል ክብረት

$
0
0

dr. asfea wossen asserate

daniel-kibret-300x207ኢያን ካምፕቤል ፋሽስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በወረረች ጊዜ በደብረ ሊባኖስ ገዳም ላይ ስለ ፈጸመቺው አሰቃቂ እልቂት የሚተርክ The Massacre of Debre Libanos, Ethiopia 1937› የተሰኘ መጽሐፍ አሳትመዋል፡፡ ይኼ ብዙ ጊዜ የማይነገርለት ነገር ግን እርሳቸው ‹ፋሽዝም ከፈጸማቸው ጆሮ ጭው የሚያደርጉ የጭካኔ ሥራዎች አንዱ ነው› ብለው የገለጡት ዘግናኝ የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ሰብአዊ አረመኔነት በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በጥናት ተመሥርቶ በዝርዝር ቀርቧል፡፡

 

ጣልያኖች የኢትዮጵያውያንን የጀግንነት መንፈስ ለመስበር ከመጀመሪያው ተዘጋጅተው ነበር የመጡት፡፡ ለዚህ ደግሞ እንደ አንድ ርምጃ የወሰዱት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ማንበርከክ ነው፡፡ ምንም እንኳን የተወሰኑ ጳጳሳት ከእነርሱ ጋር ለመሥራት ባያንገራግሩም እንደ አቡነ ጴጥሮስ ያለ ቆራጥ አባት መፈጠሩ፤ ብዙዎች ገዳማትና አድባራት አርበኞችን መርዳታቸው፤ ካህናቱም

ወግጅልኝ ድጓ ወግጅልኝ ቅኔ

ወንዶች ከዋሉበት እውላለሁ እኔ

እያሉ ሀገራቸውን ለመከላከል በረሐ መውረዳቸው ጣልያኖችን ዕረፍት ነሥቷቸው ነበር፡፡ በተለይም ደግሞ የካቲት 12 ቀን 1929 ዓም በግራዝያኒ ላይ በተቃጣው የመግደል ሙከራ ዋነኞቹ ተሳታፊዎች አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ጋር ግንኙነት አላቸው መባሉ፡፡ አርበኛው ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስ የፍቼ ተወላጅ በመሆናቸው ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ በመታሰቡ፡፡ ታዋቂው አርበኛ  ኃይለ ማርያም ማሞ  ከገዳሙ መነኮሳት ጋር ይገናኛል መባሉ ጣልያኖች በደብረ ሊባኖስ ላይ የዘንዶ ዓይናቸውን እንዲጥሉ አደረጋቸው፡፡

ይበልጥም ደብረ ሊባኖስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ያለው ቦታ የጣልያኖችን የጥፋት ትኩረት ስቦታል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱን፣ በእርሷም በኩል የጀግንነቱን መንፈስ አከርካሪውን ለመስበር ያሰቡት ፋሽስቶች የታላቁ ጻድቅ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ምዕራፍ፣ የእጨጌው መቀመጫና ለአያሌ ገዳማት መመሥረት ምክንያት የሆነውን ገዳም ለማጥፋት፣ ሲያጠፉትም ሌላውን ሊያስደነግጥ በሚችል መልኩ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲሆን ወሰኑ፡፡

በዚህም መሠረት ግራዝያኒ ያቀናበረውና ጄኔራል ማለቲ የመራው ጦር ግንቦት 10 ቀን 1929 ዓም ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ወረደ፡፡ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ፍልሰተ ዐጽም የተከናወነበትን በዓል ለማክበር የተሰበሰቡትን ምእመናንንና መነኮሳትን መጨፍጨፍም ጀመረ፡፡ በጫጋል፣ በውሻ ገደል፣ በሥጋ ወደሙ ሸለቆና በደብረ ብርሃን አጠገብ በእንግጫ በተከናወነው ጭፍጨፋ ገና ነፍስ ያላወቁ ሕጻናት የቆሎ ተማሪዎችን ጨምሮ ከ1801 እስከ 2201 የሚደርሱ ምእመናንና መነኮሳት በግፍ ተረሸኑ፡፡ አውሬ እንዲበላቸውም የትም ተወረወሩ፡፡

በዚህም አላበቃም፡፡ በገዳሙ የነበሩ መጻሕፍት፣ የከበሩ ዕቃዎች፣ ንዋያተ ቅድሳት፣ ገንዘብና ሌሎች ንረቶች ተዘረፉ፡፡ ገዳሙም ነጻነት እስኪመለስ ድረስ በመከራ ውስጥ ኖረ፡፡

አስገራሚው ነገር ከ500 ዓመታት በፊት ግራኝ አሕመድ ገዳሙን ሲያቃጥል የሞቱት መነኮሳት ቁጥር 450 ነበር፡፡ ፋሽስት ኢጣልያ የጨፈጨፈቺው ከእርሱ አምስት ጊዜ እጥፍ የሚበልጥ መሆኑን ስናስበው የጭካኔውን መጠን ያመለክተናል፡፡

መጽሐፉን ስታነቡት ኀዘን፣ ቁጭትና ግርምት ይፈራረቁባችኋል፡፡ ሕጻናት፣ ወጣቶች፣ ጎልማሶችና አረጋውያን በሃይማኖታቸውና በኢትዮጵያዊነታቸው ምክንያት ብቻ የደረሰባቸውን ግፍ ስናስበው ልባችን በኀዘን ፍላጻ ይወጋል፡፡ ማንበብ እስኪያቅተን ድረስ በሰቆቃወ ደብረ ሊባኖስ እንዋጣለን፡፡ ለደረሰባቸው ግፍ ተመጣጣኝ ካሣ አለማግኘታቸውን፣ ኢጣልያ የፈረመቺውን ውል እንኳን ሳታከብረው 74 ዓመታት ማለፋቸው ስትመለከቱ፡፡ ግራዝያኒ ወስዷቸው ዛሬ እንደ አቤል ደም እየተካሰሱ በሮም የሚገኙትን የገዳሙን ንብረቶች ስታስታውሱ አባቶቻችን ልጅ አለመውለዳውን ዐውቃችሁ ይቆጫችኋል፡፡

ልጅ የለንም እንጂ ልጅማ ቢኖር

ተሟግቶም ተዋግቶም ያስመልስ ነበር፤

ብለው ያንጎራጎሩ ሲመስላችሁ ትቆጫላችሁ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ይኼ እኛ ዛሬ የምንቀልድበት ነጻነት ምን ያህል ዋጋ እንደተከፈለበት ስታስቡ፣ ዋጋ ከፋዮቹንም በዓይነ ኅናችሁ ስትቃኙ ትገረማላችሁ፡፡ ግርምታችሁ በዚህ ብቻ አያበቃም፡፡ በዚያ የመከራ ዘመን የሰማዕታቱን ዐጽም ለመሰብሰብ፣ ቦታቸውም ለማወቅ በመንፈሳዊና ሀገራዊ ወኔ ታጥቀው የከወኑትም፤ ለታሪክም አስረጅ ሆነው የቆሙትን የክፉ ቀን ጀግኖች ስታስቡም ትደነቃላችሁ፡፡ እግረ መንገዳችሁን እንዲህ ያሉት የዓይን ምስክር ጀግኖች በዐረፍተ ሞት ከመገታታቸው በፊት ሌላውም ታሪካችን እንዲጻፍ ትማጸናላችሁ፡፡ አብዛኛው ሕዝብ አንብቦ እንዲጠቀምበትም በአማርኛ ታሪኩ ቢቀርብ መልካም መሆኑንም ሐሳብ ትሠነዝራላችሁ፡፡

ከዚህም በላይ ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሁለት ሥራዎች እንደቀሩትም ትገነዘባላችሁ፡፡ ለእነዚህ ለእምነታቸውና ለሀገራቸው ሲሉ ለተሠዉ ሰማዕታት ተገቢውን ቦታ መስጠት፣ ታሪካቸውንም በስንክሳር ውስጥ በተገቢው ሁኔታ እንዲሠፍር ማድረግ፤ አያይዞም ደግሞ በዓላቸው በኦርዶክሳዊ ሥነ ሥርዓት እንዲከበርና ትውልድ ሀገራዊም መንፈሳዊም በረከት እንዲያገኝባቸው ማድረግ ይገባዋል፡፡ ለዚህም ደራሲው ኢያን ካምፕቤል አጥልቀው አጥንተው፣ ተንትነው ጽፈውታልና ምስጋና እየቸርን መጽሐፉን እናንብበው፡፡

መልካም ንባብ፡፡

The post የደብረ ሊባኖሱ እልቂት – ከዲ/ን ዳንኤል ክብረት appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: የማንጎ የጤና በረከቶች

$
0
0

Mango
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

1. ካንሰርን ይከላከላል
ጥናቶች እንደሚሳዩት ከሆነ ማንጎን መመገብ የአንጀት፣ የጡት፣የደም እና የፕሮስቴት ካንሰርን የመከላከል አቅም አለው።

2. የኮሌስቴሮል መጠንን ይቀንሳል
የኮሌስቴሮል መጠንን መቀነስ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችን በውስጡ ይዟል።

3. ለቆዳ ጤንነት
ማንጎን በመመገብም ሆነ ፊትን በመቅባት የቆዳዎን ጤንነት ማሻሻል ይችላሉ።

4. ለአይንዎ ጤንነት
ማንጎ ቫይታሚን ኤ በውስጡ ስለሚይዝ የአይን የማየት ጥራትን ይጨምራል።

5.የምግብ መፈጨትን ያፋጥናል
እንደ ፓፓዬ ሁሉ ማንጎም የምግብ መፈጨትን ስርአት ያፋጥናል።

6. በሽታን የመከላከያ አቅማችንን ይጨምራል
ቫይታሚን እና ቫይታሚን በተጨማሪ ሌሎች የተለያዩ ንጥረ ነገሮች በሽታን የመከላከል አቅማችንን ያዳብራሉ።

ጤና ይስጥልኝ

The post Health: የማንጎ የጤና በረከቶች appeared first on Zehabesha Amharic.

በፊንጫ ስኳር ቃጠሎ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉ ታወቀ

$
0
0

(ሰንደቅ ጋዜጣ) ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ መጋቢት 5 ቀን 2007 ዓ.ም. ከቀኑ 5 ሰዓት ገደማ የሸንኮራ አገዳ ገለባ (ባጋስ) ማቀጣጠያ ክፍል በተነሳ ቃጠሎ የአንድ ሠራተኛ ሕይወት ሲያልፍ በአስራ ስድስት ሠራተኞች ላይ ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ማድረሱን የኮርፖሬሽኑ የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የሚዲያ ግንኙነት የቡድን መሪ ለሰንደቅ ጋዜጣ አረጋገጡ።
news
የሚዲያ ግንኙነት ቡድን መሪው አቶ ጋሻው አይችሉም ስለቃጠሎው ከሰንደቅ ጋዜጣ ተጠይቀው ሲያስረዱ፣ “የሸንኮራ አገዳ ገለባ (ባጋስ) ማቀጣጠያ ክፍል ለፋብሪካው አማራጭ የኃይል አቅርቦት የሚሰናዳበት ክፍል ሲሆን ለማቀጣጠያ ግብአትነት የሚውለው የአገዳ ገለባ ደረቅ በመሆኑ በቀላሉ ቃጠሎ ሊነሳበት የሚችልበት እድል ሰፊ ነው። የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ ለማጥፋት በተደረገው ርብርብ የአንድ ሰራተኛ ሕይወት ሲያልፍ፣ በአስራ ስድስት ሠራተኞች ላይ ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። ቀላል አደጋ ከደረሰባቸው ሠራተኞች መካከል አምስቱ በፋብሪካው የሕክምና ማዕከል ተገቢውን እርዳታ ተደርጎላቸው በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ አስራ አንዱ ግን በቤቴል ሆስፒታል ተኝተው እየታከሙ ናቸው” ብለዋል።

በፋብሪካው የተነሳው የእሳት ቃጠሎ በዕለቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን የቡድን መሪው ጠቁመው፤ የፋብሪካው ሰራተኞች፣ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ መከላከያ ሰራዊት፣ ፌደራል ፖሊስ፣ እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እሳቱን በማጥፋት ከፍተኛ ድርሻ ነበራቸው። እንዲሁም ሁለት ሂሊኮፕተሮችም ተሳታፊ እንደነበሩ ጠቅሰዋል።

ለቃጠሎው መነሳት ትክክለኛ ምክንያቱን እየተጣራ መሆኑ የገለፁት አቶ ጋሻው፣ የደረሰውም ውድመት ምን ያህል እንደሆነ ግምቱ እየተሰራ ነው ብለዋል። ለጊዜው ግን ለቃጠሎው መነሻ ምክንያት ያለው ግምት የአካባቢው ሙቀት ሳይሆን አይቀርም ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ቃጠሎው ከደረሰበት ቅዳሜ መጋቢት 5 እስከ መጋቢት 7 ቀን 2007 ዓ.ም ድረስ ስራ ለማቆም የተገደደ ሲሆን፤ ከማክሰኞ መጋቢት 8 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ አገዳ መፍጨት በመጀመሩ ከ16 ሰዓታት በኋላ ስኳር ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል።
የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ በተደረገለት አዲስ የፋብሪካ ማስፋፊያ ግንባታ የመፍጨት አቅሙን በቀን ወደ 10ሺ ኩንታል ማሳደጉ ይታወቃል። በሙሉ አቅሙ መስራት ሲጀምር በቀን 12ሺ ኩንታል ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል።3⁄4

The post በፊንጫ ስኳር ቃጠሎ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉ ታወቀ appeared first on Zehabesha Amharic.


Health: ከብጉር ነፃ የሆነ ቆዳ እንዲኖሮ መመገብ ያለቦዎት 7 ምግቦች

$
0
0

banana
(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም)

1. በኦሜጋ ፍሬ የበለፀጉ ምግቦች
ተልባ፣ አሳ፣ ዘይት የመሳሰሉት
2. በአንቲ ኦክሲደንት የተሞሉ ምግቦች
ኢንጆሪ፣ ቦሎቄ፣ የመሳሰሉት
3. ሴሊኒየም የበለፀጉ ምግቦች
አሳ፣ ስጋ፣ ዶሮ፣ እንቁላል፣ ወይም እንጉዳይ
4. በፋይታሚን ኢ የበለፀጉ ምግቦች
አቦካዶ፣ ጎመን፣ አሳ፣ ወይራዘይት፣ ብሮክሊ
5. ብዙ የውሀ መጠን በውስጣቸው የያዙ ምግቦች
ሀብሀብ፣ ኢንጆሪ፣ አናናስ፣ ዝኩኒ፣ ቲማንቲም የመሳሰሉት
6. በፋይታሚን ኤ የበለፀጉ ምግቦች
ካሮት፣ ስኳር ዲኒች፣ አሳ፣ ማንጎ
7. ማግኒዢየም ያላቸው የምግብ አይነቶች
አሳ፣ አቦካዶ፣ ባቄላ፣ ሙዝ
ጣፋጭ የሆኑ ምግቦችን ባይመገቡ ይመከራል
ጤና ይስጥል

The post Health: ከብጉር ነፃ የሆነ ቆዳ እንዲኖሮ መመገብ ያለቦዎት 7 ምግቦች appeared first on Zehabesha Amharic.

“በመጪዎቹ ሳምንታት በቦይኮት እና ህዝባዊ እምቢተኝነት ላይ ያተኮሩ መርሃ ግብሮች ይኖሩናል”–ድምጻችን ይሰማ

$
0
0

(ፎቶ ፋይል)

(ፎቶ ፋይል)


የህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እምቢተኝነት የተናጠል መስዋእትነትን የሚቀንስ አሳታፊ የትግል ስልት ነው!

ረቡዕ መጋቢት 9/2007

የኢትዮጵያ ሙስሊም በእምነቱ ላይ የተቃጣውን የአስተሳሰብና የጥቃት ዘመቻ ለመመከት፣ አስተሳሰቡን በኢስላማዊ አስተሳሰብ ለማረቅ፣ በሽፋን የሚደረገውን ጥቃት በህግ እልባት ያገኝ ዘንድ ባደረገው የትግል ሂደት ከላይ ወደታች የሆነ የተመሪነት ስርዓት ብቻ ሳይሆን ከታች ወደላይ ፍሰት ያለው መሪዎችን የመምራት ሥርዐት መፍጠር ችሏል፡፡ ይህም ህዝበ ሙስሊሙን የትግሉ ባለቤትና የመሪዎቹም መሪ አድርጎታል፡፡
ህዝበ ሙስሊሙ አደባባይ የወጣው ‹‹በጊዜ ሂደት ይፈታሉ፣ አልያም ከሀገሪቷ ሁለንተናዊ ዕድገት ጋር አብረው ይቀረፋሉ›› በሚል በሆደ ሰፊነት የተሸከማቸውን ስር የሰደዱ መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ተቋማዊና መሰል ችግሮች ለመጠየቅ ሳይሆን ተገድበው የተሰጡትን መሰረታዊ መብቶች መልሶ የመንጠቁን እኩይ ዘመቻ ለመግታት ነው፡፡ የእነዚህ እኩይ ተግባራት ድምር ውጤት ዘመን ተሻጋሪና በእምነታችን ላይም ሆነ በማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ማንነታችን ላይ የሚያደርሰውን ከፍተኛ አደጋ መረዳቱ ለህዝበ ሙስሊሙ የመንቃት ምንጭ፣ ለትግሉም ገፊ ሀይል ከመሆን ባሻገር ህዝቡን ፅናት ያላበሰና ለመስዋእትነት ያዘጋጀ ነበር፡፡

ከሰው ልጅን የታሪክ ምዕራፍ ሰፊውን ቦታ የሚሸፍነው ትግል ነው፡፡ በተለያዩ ወቅቶች የሰው ልጆች በግልም ይሁን በህብረት ለተለያየ ዓላማና ግብ የተለያዩ ስልትና መርሆዎችን የተከተሉ ትግሎችን አካሂደዋል፡፡ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እምቢተኝነት የትግል ስልት ደግሞ የህዝብን ንቃተ ህሊና መጎልበት የሚያመላክት የሰለጠነ የሰላማዊ የመብት ትግል መገለጫ ነው፤ ምክንያቱም መንግስት የህዝብን ጥያቄ ጆሮ ሰጥቶ ከማድመጥ ይልቅ የህዝብን ድምፅ በኃይል ለማፈን የሚያደረገው ጥረት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ በመጣ ቁጥር ህዝብ የመንግስትን ደጅ ከማንኳኳት ይልቅ መንግስት ላይ ዘርፈ ብዙ ጫና በመፍጠር መንግስት ወደህዝቡ ደጅ እንዲመጣ የሚያስገድዱ ለእምቢተኝነት የተሰጡ የእምቢተኝነት ምላሾችን አማራጭ አድርጎ ይወስዳልና! በተጨማሪም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እምቢተኝነት የተለየ መዋቅር የማይጠይቅ፣ ሁሉም ህብረተሰብ በየአካባቢውና በየዘርፉ የሚታገልበትና የተናጠል መስዋእትነትን የሚቀንስ የትግል ስልት ሲሆን ተጽእኖ ፈጣሪነቱም ዓይነተኛ መሆኑ አሌ የሚባል እንዳልሆነ ታሪክ ይመሰክራል፡፡

ይህ ህዝባዊ የለውጥ ፍላጎት ምክኒያታዊ የለውጥ እርከኖችን ተሻግሮ የመጣ እንደመሆኑ ተግባራዊነቱ ዋስትና ያለው፣ ከጠባቂነት የሚያላቅቅ፣ እስከ ድል ደጃፎች ድረስ የተዘረጋው የመብት ትግል በሰላማዊነት እና ቁርጠኝነት ድልድይ ላይ ተሻግሮ የችግርን ወንዝ እንዲሻገር ያስችላል፡፡ ይህን ህዝባዊ የለውጥ ፍላጎት ማዳመጥ ደግሞ ተገቢ ብቻ ሳይሆን ህዝብ የመሪዎቹ መሪ መሆኑን ማሳያም ጭምር ነው፡፡ በመሆኑም በመጪዎቹ ሳምንታት በቦይኮት እና ህዝባዊ ትብብር መንፈግ (እምቢተኝነት) ላይ ያተኮሩ የተቃውሞ መንገዶችን በመጠቀም የምናካሂዳቸው መርሃ ግብሮች ይኖሩናል፤ በአላህ ፈቃድ! ሁላችንም በዚህ መሰሉ ትግል ላይ ግንዛቤያችንን የሚያዳብሩ ጽሁፎችን በማንበብ እና መንፈሳዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ ዝግጅት በማድረግ ሰላማዊ ትግላችንን እስከድል ደጃፎች ለማድረስ የገባነውን ቃል እናድስ፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

The post “በመጪዎቹ ሳምንታት በቦይኮት እና ህዝባዊ እምቢተኝነት ላይ ያተኮሩ መርሃ ግብሮች ይኖሩናል” – ድምጻችን ይሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

በሀሰት አልመሰክርም በማለት አውነቱን በፍርድ ቤት የተናገረው ሙጂብ አሚኑ ለሚያዚያ 7 ተቀጠረ

$
0
0

mujib
ቢቢኤን መጋቢት 9/2007
በነ ኤልያስ ከድር መዝገብ በተከከሰሱ ሙስሊሞች ላይ በሀሰት እንዲመሰክር ታፍኖ ማእከላዊ የተወሰደው ሙጂብ አሚኑ በሀሰት እንዲሰክር አቅርበውት አስገራሚ ታሪክ ሰርትዋል፡፡ በወንድሞቼ ላይ በሀሰት አልመሰክርም በማለት እውነቱን በፍርድ ቤት አስረድትዋል፡፡
ለዚህ እኩይ አላማቸው ማስፈጸሚያ አልሆንም ያለው ሙጂብ አሚኑ በሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶበት በማእከላዊ ይገኛል፡፡ በዛሬው እለት ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረ ሲሆን ለሚያዚያ 7 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶታል፡፡
መንግስት የሰራው አይን ያወጣ ሸፍጥ ሁሉንም ያስገረመ ሲሆን ወጣት ሙጂብ አሚኑ የሚመጣውን ሁሉ ዋጋ ለመክፍል በመቁረጡ፤ እውነትን በመጋፈጡ በበርካቶች አድናቆትን ተችሮታል፡፡ ሙስሊሞች ለሱ ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት በዛሬው እለት በፍርድ ቤት በርካቶች ተገኝተዋል፡፡

The post በሀሰት አልመሰክርም በማለት አውነቱን በፍርድ ቤት የተናገረው ሙጂብ አሚኑ ለሚያዚያ 7 ተቀጠረ appeared first on Zehabesha Amharic.

የኢትዮጵያ የ“ዲፕሎማቶች ቁንጮ” መሳለቅያ ቅጥፈት፣ –ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

$
0
0

tew adha
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
 
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
 
የወባ ትንኝ ተመራማሪ የሆነ ሰው ስለዲፕሎማሲ ጥበብ እና ሳይንስ ምንድን ሊያውቅ ይችላል? ወይም ደግሞ እውነትን በመናገር እና ውሸትን በመናገር መካከል ያለው ልዩነት ምን ያውቃል? ወይም ደግሞ የለየለት ቅጥፈትን አምኖ በመቀበል እና ቅጥፈትን  በማውገዝ መካከል ያለውን  ልዩነት ምን ያውቃል? እነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ያለምክንያት አላነሰዋቸሁም፡፡ 
 
ቴዎድሮስ አድኃኖም በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ውስጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር new፡፡ ይፋ በሆነው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሕይወት ታሪክ አድኃኖም “ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያላው የወባ ትንኝ ተመራማሪ” መሆኑን ተገልጿል፡፡ አድኃኖም ከለንደን የጤና አጠባበቅ እና ትሮፒካል ህክምና ትምህርት ቤት/London School of Hygiene & Tropical Medicine የሰው ልጅ ሰውነት በሽታዎችን በመቋቋም ችሎታዎች/immunology ላይ ጥናት በሚያደርገው የተላላፊ በሽታዎች የህክምና ሙያ ላይ የማስተርስ ዲግሪ እንዲሁም ለንደን ከሚገኘው ከኖቲንግሀም ዩኒቨርስቲ እ.ኤ.አ በ2000 በህብረተሰብ ጤና/community health የዶክትሪት ዲግሪ ተቀብለዋል እየተባለ ይነገርለታል ፡፡ እ.ኤ.አ በ2005 አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አድርገው ሾመው፡፡ እ.ኤ.አ በ2012 የመለስ ዜናዊን ህልፈት ተከትሎ አድኃኖም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነ ተሾመ፡፡ የወባ ትንኝ ተመራማሪ በአንድ ጊዜ ባንድ ሌሊት የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በማግስቱ ጀንበር ሳይጠልቅ የሀገሪቱ ታላቅ የተባለውን የዲፕሎማትነት የስልጣን ቦታ መቆጣጠር የሚቻልበት የፖለቲካ ሂደት ሌላ የትም ሀገር ሳይሆን አች በወሮበላ ተቀሰፋ የተያዘቸው  የውሸቷ ሪፐብሊክ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው!
 

ውሸት በተንሰራፋባት ሀገር የቴዎድሮስ አድኃኖም በ14 ዓመት ልጃገረድ መታለል፣
 
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በትውልድ ኢትዮጵያዊት በዜግነት አውስትራሊያዊት የሆነች እና ከየት ቦታ እንደመጣች የማትታወቅ የ14 ዓመት ልጃገረድ ከአድኃኖም ግን በመቀመጥ ቃለ መጠይቅ በማካሄድ እና በአውስትራሊያ አሸናፊ ሆና በሽልማት ያገኘችውን 20 ሚሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ለትምህርት ቤቶች ግንባታ አገልግሎት እንዲውል የለገሰች መሆኑን በገለጸችበት በዚያ የመድረክ ላይ ተውኔት አድኃኖም ዋና የገጸ ባህሪነት ድርሻን ይዘው ተውኔቱን ዋና ተጭዋች ነበር፡፡ አንድያው ለነገሩ ማንም የመታዘብ ቺሎታ ያለው ሰው እንደዚህ ያለ በህጻን ልጅ የሚደረግ  የሃያ ሚልዮን ዶላር ትረካ አውነት ብሎ ያምናል፡፡ በእርግጥ ባለፈው ህዳር worldnewsdailyreport.com የተሰኘ የቀልደኛ ድረ ገጽ አስርቱ ትዕዛዛት የተጻፉበት ጽላት በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ኃላፊዎች የተሰረቀ መሆኑን በመግለጽ ብዙ ኢትዮጵያውያኖች አስደንግጦና አሸብሮ ነበር።  
 
በስደት ላይ የሚገኘው እና ሙሰኝነትን፣ አጭበርባሪነትን፣ የሀሰት ዲግሪዎችን እና በህወሀት ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ውስጥ ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ የሚጠቀሙትን በማጋለጥ ታዋቂ የሆነው ወጣቱ የምርመራ ጋዜጠኛ አበበ ገላው እ.ኤ.አ መጋቢት 2/2015 አድኃኖም በአንዲት የትምህርት ቤት ልጅ የተታለሉ መሆናቸውን ምርመራ በማድረግ አንድ ዘገባ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ [ማስታወሻ፡ በአድኃኖም የቅሌት ተውኔት ውስጥ የተሳተፈችውን የትምህርት ቤት ልጅ ሆን ብዬ ስሟን ይፋ ማድረግ አልፈልግም ምክንያቱም የልጅቷ ስም በመገናኛ ብዙሀን እንዲወጣ፣ እንድትወገዝ እና የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዲፈጸምባት አልፈልግም፡፡ እንደዚሁም ደግሞ የ14 ዓመት የሆነች ልጅ ሙሉ በሙሉ በእራሷ ስብዕና የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ዝርዝር የማጭበርበር ድርጊት በማውጣት ታታልላለች የሚል እምነት የለኝም፡፡ ከዚህ በኋላ ይህችን ልጅ ወጣቷ ወይዘሪት ወይም ደግሞ ልጅቷ እያልኩ እጠራታለሁ ምክንያቱም እርሷ እራሷ በአድኃኖም እና በግብረ አበሮቹ  አማካይነት ለርካሽ ፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሲባል እንድትዋሽ የተደረገች የማጨበርበሩ ሰለባ ናትና ፡፡]
 
ከአድኃኖም ጋር ሲካሄድ በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ወጣቷ እንዲህ ብላ ነበር፣ “በውድድር አሸናፊ ሆኘ 20 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር በሽልማት አግኝቸ ነበር፡፡ እናም አሁን እዚህ የተገኘሁት ከኢትዮጵያ እና ከአውስትራሊያ መንግስታት ጋር በመሆን በሀገሬ የግንባታ ፕሮጀክት ለመጀመር ነው፡፡“ ቀሪውን የልጅቷን ትረካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ጉዳይ አስፈጻሚ የሆነው ሰው እንዲህ በማለት ተናግሮላታል፡

“መታወቅ ያለበት አንድ ዋና ነገር ልጅቷ በአውስትራሊያ በሚገኙ ክለቦች ውስጥ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የምትገኝ ልጅ ናት፡፡ እርሷ ከምትመራቸው ክለቦች ውስጥ አንደኛው የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ጥበቃ ክለብ ነው፡፡ በዚያ ክለብ ውስጥ እርሷ እና ሌሎች የክለቡ አባላት ሌሎችን ሰዎች እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ሀሳብ ይለዋወጣሉ፣ ውይይትም ያካሂዳሉ፡፡ እርሷ ያነሳቸው ዋነኛው ሀሳብ ሌሎቹ ትምህርት የማግኘት ዕድል እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ከማሰቡ ላይ ነው፡፡ በአውስትራሊያ ያሉ ህዝቦች ይህንን በሚሰሙበት ጊዜ ይህንን ሀሳቧን የደገፉ ሰዎች ገንዘብ አሰባስበው 20 ሚሊዮን ዶላር ለእርሷ ሰጧት፡፡ ይህ ድርጊት የተፈጸመው እ.ኤ.አ በ2014 ነው፡፡ ለጉብኝት ወደ ትውልድ ሀገሯ በመጣች ጊዜ ከእራሷ አንደበት እንደሰማችሁት በሽልማት ባገኘችው በ20 ሚሊዮን ዶላር በሀረር በጋራሙለታ አካባቢ ትምህርት ቤት ለመገንባት እንደምትፈልግ ሀሳቧን ገልጻለች፡፡ እንግዲህ ኃላፊነቱ ካላቸው ባለስልጣኖች ጋር በመተባበር በቅርብ ጊዜ ውስጥ ስራውን ትጀምራለች፡፡”  
 
አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አንዲትን የ20 ሚሊዮን ዶላር ተሸላሚ የሆነች ልጅ እንዴት አድርጎ ሊያውቅ እና ሊያገኛት ቻለ? ለዚህ ጥያቄ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንዲህ የሚል ገለጻ ሰጥቷል፡
ወጣቷ ልጅ በመጣች ጊዜ ስለእርሷ ማንነት የሚገልጹትን ሰነዶች ተመለከትን፡፡ ልጅቷ ወደ እኛ ቢሮ የመጣችው በቤተሰቦቿ አማካይነት ነው፡፡ የተከበሩት የእኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስለልጅቷ ጉዳይ አወቁ እናም ይኸ ጉዳይ ለሌሎች ወጣቶችም መልካም አርዓያ ስለሆነ ልጅቷን ማበረታታት እና ስለዚህ ጉዳይ መናገር አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ አንጻር ሚኒስትሩ ጠንካራ በሆነ መልኩ ልጅቷን አበረታትተዋታል፡፡ ስለሆነም ልጅቷ ወደ እርሳቸው እንድትመጣ ጥሪ በማድረግ አነጋግረዋታል፡፡ መንግስት ማድረግ ያለበትን አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ለማድረግ እና ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን እንዲሁም ልጅቷ የምትፈልገውን እርዳታ ሁሉ እንደሚያደርግላት አረጋግጠውላታል፡፡  
 
ይኸ የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ዋናው ችግር ገንዘቡ ፍጹም የሌለ እና ያልተገኘ የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ ልጅቷ እንደዚህ ያለ ሽልማት በፍጹም አልተቀበለችም፡፡ ይህ ድርጊት ሙሉ በሙሉ ሸፍጥ ነው፡፡ አንድ የተከበረ ሚኒስትር የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነች ልጅ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ከአውስትራሊያ 20 ሚሊዮን የእርዳታ ዶላር በመያዝ ወደ ኢትዮጵያ ትጓዛለች ብሎ ማመን አንደ ማሞ ቂሎ አይነት ተረት ይመስላል ወይም ህዝብን አንዴ ሞኝ ከማየት የመጣ ይመስላል። 

ይህንን አባባል በሌላ መልኩ ለማስቀመጥ የ20 ሚሊዮን ሽልማት ተብየው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ባለፉት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ በየዓመቱ በአማካይ 11 በመቶ የምጣኔ ሀብት ዕድገት አስመዘገብኩ (በነገራችን ላይ ይህ አሀዝ የለየለት ሀሰት፣ ተራ ቅጥፈት እና የቁጥር ጨዋታ መሆኑን ከጥርጣሬ በላይ በማስረጃ አስደግፌ ያረጋገጥኩት ጉዳይ መሆኑን ልብ ይሏል) ከሚለው ማጭበርበሪያ ጋር አንድ አይነት እና ተመሳሳይ ነው፡፡ ሁለቱም ማጨበርበሮች በነባራዊ እውነታ ላይ የሌሉትን እንዳሉ አድርገው የሚያቀርቡ ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ የሆኑ የሸፍጥ አካሄዶች ናቸውና፡፡  
 
የአበበ ገላው የምርመራ ዘገባ በአሰራር ስልት የአድኃኖምን የ20 ሚሊዮን አጠያያቂ ሽልማት ውድቅ አድርጎታል፡፡ አበበ የ20 ሚሊዮን ሽልማት በትምህርት ቤታችሁ ለምትማር ልጅ ሰጥታችኋል ወይ በማለት ልጅቷ ለምትማርበት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር  የስልክ ጥያቄ አቅርቦ ነበር፡፡ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር እንዲህ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፣ “ይኸ እንቆቅልሽ የሆነ ነገር ነው፣ ትምህርት ቤታችን እንደዚህ ያለ የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ሰጥቶም፣ ውድድር አድርጎም አያውቅ፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ልጅቷ ለ20 ሚሊዮን ዶላር የሚያበቃ እውቀትም የላትም፡፡“ አበበ በአውስትራሊያ በሜልቦርን የገንዘብ ማሰባሰቡን የማስተባበር ስራ አከናውኗል ከተባለው ባደን ፓወል ኮሌጅ ጋርም ግንኙነት አድርጓል፡፡ ኮሌጁ እንዲህ በማለት የማስተባበያ ቃሉን ሰጥቷል፣ “እንደዚህ ባለ አስገራሚ ጉዳይ ላይ መሳተፍ ይቅርና ኮሌጁ እራሱን የሚያንቀሳቅሰው 12 ሚሊዮን ዶላር በሆነው አመታዊ በጀቱ ነው፡፡“  በአውስትራሊያ የሮታሪ ዓለም አቀፍ ማናጀር የሆኑት ይህ ድርጀት ሽልማት ለመስጠቱ በአበበ ጥያቄ በቀረበላቸው ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉት ሁሉም ቅርንጫፎች በበጀት ዓመቱ ውስጥ 5.6 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር ብቻ መሰብሰባቸውን እና በምንም ዓይነት መልኩ እንደዚህ ላለች የ14 ዓመት የትምህርት ቤት ልጅ 20 ሚሊዮን ዶላር መሸለምም ሆነ መስጠት አስደንጋጭ እና አሳፋሪ ነገር መሆኑን ግልጽ አድርገው ተናግረዋል፡፡  
 
የአውስትራሊያ መንግስት ስለ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ እና ለኢትዮጵያ መንግስት ለትምህርት ተብሎ የተሰጠ ገንዘብ እንደሌለ ግልጽ አድርጓል፡፡ እንግዲህ ነገሮች ሁሉ እንደዚህ የሚሆኑ ከሆነ የ20 ሚሊዮን ዶላር ቅጥፈት ከየት መጣ?
እንደ አበበ ገለጻ ከሆነ ወጣቷ ልጅ ከአድኃኖም ጋር በካሜራ ተቀርጻ ለቴሌቪዥን የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ከመቅረቧ ከሰዓታት በፊት በአድኃኖም እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቡድን እና በአማካሪዎች አማካይነት ውሸት እንድትናገር በመቅረጽ በቴሌቪዥን እንዲቀርብ እንዲደረግ የማግባባት ስራ ተደርጎላታል የሚል ግምት አለ፡፡ የተባለው ገንዘብ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የጭቆና አገዛዝ ተቀናቃኝ የሆነ ተቃዋሚ በሚንቀሳቀስበት በምስራቅ ኢትዮጵያ በጋራ ሙለታ አካባቢ ለትምህርት ቤቶች ግንባታ ይውላል መባሉ ለህዝብ ግንኙነት ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚውል እንደሆነ ዘግቧል፡፡ እንደ አበበ አስተያየት ከሆነ ሚኒስትሩ [አድኃኖም]፣ በተወልደ ሙሉጌታ የሚመራው የህዝብ ግንኙነት ቡድናቸው፣ በአውስትራሊያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዲሁም የኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ባለስልጣኖች የኦሮሚያን ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አብዱላዚዝ መሀመድን ጨምሮ በዚህ አደገኛ የሆነ ቀውስን ሊያመጣ በሚችል የሸፍጥ ዕኩይ ድርጊት ውስጥ ተሳትፎ አድርገዋል፡፡  
 
አበበ አንድ ጊዜ ታሪኩን ይፋ ማድረግ ከጀመረ በኋላ አድኃኖም ይህንን ድርጊት ለማስተባበል እ.ኤ.አ መጋቢት 7/2015 የማህበራዊ ድረ ገጻቸውን በመጠቀም በለቀቁት ጽሁፍ እርሳቸው በይፋ የዋሹትን ውሸት ልጅቷ አሳስታኝ ነው በማለት ውንጀላውን ሙሉ በሙሉ በልጅቷ ላይ ደፍድፈውታል፡፡ የአድኃኖም የማህበራዊ ድረ ገጽ ገለጻ በእውነታ ላይ ያልተመሰረተ ስለሆነ በጣም የሚያሸማቅቅ እና አሳፋሪ ጉዳይ ነው፡፡ ያቀረቡት አመክንዮ ውጤቱ እርባና የለውም በሚል ህግ ወይም መርህ ላይ በተመሰረተ የመጽሐፍ ምሳሌ እንዲህ በማለት ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ አድኃኖም በአጠቃላይ ልጆች ትናንሽ ልጆችን ጨምሮ ጨዋዎች ናቸው የሚል አመክንዮ ለማቅረብ ጥረት አድርገዋል፡፡ ልጆች ይዋሻሉ፡፡ ልጆች የሚዋሹት ግን ከመጥፎ ድርጊት አስተሳሰብ በመነሳት ለክፋት ሳይሆን ከተራ ስህተት ነው፡፡ የልጆች የተሳሳቱ ውሸቶች ጨዋነት ያላቸው ውሸቶች ናቸው፡፡ ልጆችን አምናቸዋለሁ፣ ምክንያቱም የልጆች ውሸቶች ጨዋነትን የተላበሱ ውሸቶች ናቸው፡፡ እነርሱን ለማመን እመርጣለሁ፡፡ የልጆችን ጨዋነት የተሞላባቸውን ውሸቶች ማመን ስህተት ከሆነ ያንን ስህተት መፈጸምን እመርጣለሁ ብለዋል፡፡
 
አድኃኖም በማህበራዊ ድረ ገጻቸው እንዲህ የሚል የበከተ እና የበሰበሰ ሆኖም ግን በእርሳቸው አባባል ቅዱስነትን በተላበሰ መልኩ ለመጻፍ ሞክረዋል፡
“እንደምታውቁት ወጣቷ ልጅ ታዳጊ ልጅ ናት፡፡ ልጆች ምንም ዓይነት መጥፎ ነገርን የማይቀላቅሉ ጨዋዎች ናቸው በሚለው አባባል ላይ ከእኔ ሀሳብ ጋር ትስማማላችሁ የሚል እምነት አለኝ፡፡ ልጆች ስህተቶችን የሚሰሩ ከሆነ እነዚህ ስህተቶቻቸው ከመጥፎ ነገሮች የሚመነጩ ሳይሆን ከተራ ስህተቶች የሚመሰረቱ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ልጆች የሚነግሩኝን ነገር ሁሉ ለማመን እመርጣለሁ፡፡ ልጆችን ማመን ጥፋት ከሆነ ያንን ስህተት መስራቱን እመርጣለሁ፡፡ ስለሆነም አሁንም ቢሆን ይህችን ወጣት ልጅ ማመን እመርጣለሁ፡፡ ተገቢነት ያልሆኑ ነገሮችን በመጻፍ የልጅቷን ስሜት መጉዳት የለብንም፡፡  የእርሷ የፕሮጀክት ዕቅድ የተቀደሰ ነው፡፡ የእርሷ ፕሮጀክት ስኬታማ እንደሚሆን ጠንካራ የሆነ እምነት አለኝ፡፡ አሁን ዋናው ጉዳይ ይህችን ወጣት ልጅ ማበረታታት እና መደገፍ መቻል ነው፡፡ 
 
በእርግጥ የ20 ሚሊዮን ዶላር የሚባል ምንም ዓይነት ፕሮጅክት የለም፡፡ ሁሉም ነገር እውነት ሳይሆን ሸፍጥ ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለበርካታ አስርት ዓመታት ሲያደርግ እንደቆየው የ11 በመቶ የምጣኔ ሀብት ዕድገት የቅጥፈት የህዝብ ግንኙነት የፕሮፓጋንዳ ስራ ሲካሄድ እንደቆየው ሁሉ ነው፡፡ አድኃኖም በማህበራዊ ድረ ገጻቸው እንኳ ይኸ የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት በተባለው በአንዲት የትምህርት ቤት ልጅ ፍጹም በሆነ መልኩ ተታልያለሁ፣ ተሞኝቻለሁ ወይም ደግሞ ተጭበርብሪያለሁ በማለት ለማመን የሞራል ድፍረቱ አልነበረዉም (በእርግጥ ይህንን መድረክ ላይ ተውኔት እራsu ያቀነባበሩት ካልሆነ በስተቀር)፡፡ ምናልባትም  በዚህ ጉዳይ ላይ ልንደነቅ አንችልም፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ባለፉት አስርት ዓመታት ሀገሪቱ በየዓመቱ በአማካይ በ11 በመቶ የምጣኔ ሀብት ዕድገት ስታስመዘግብ ቆይታለች ያለውን ተራ ወሸት፣ ቅጠፈት እና የቁጥር ጨዋታ ለመሆኑ እውቅና በመስጠት እንዲያምን እስከ አሁንም ድረስ ተስፋ ሳልቆርጥ በመጠበቅ ላይ እገኛለሁ፡፡     
 

ወይ ጉድ! ወይ ጉድ!  

ከዚህ በላይ የተጠቀሰው አባባል ከህጻን ላይ ከረሜላ ነጥቆ እንደመውሰድ የቀለለ ተግባር ነው፡፡ አንድን የዲፕሎማሲ ቁንጮ የሆነን ታላቅ ባለስልጣን እና በቀጣይነትም የጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅን ባለስልጣን አንዲት ህጻን የ20 ሚሊዮን ዶላር የሚከፋፈል ከረሜላ አለ በማለት የማታለል ወንጀል ተፈጽምበታለች ተብሎ ተሰምቶ አያውቅም፡፡ በፍጹም ሊሆን የሚችል ጉዳይ አይደለም! በጣም አስፈሪ የሆነው እውነታ ግን አድኃኖም በ14 ዓመት ልጅ የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ታሪክ ትረካ በማቅረብ የሚታለል ከሆነ አስቸጋሪው እና ትልቁ ነገር ይህ ባለስልጣን ቀንድ ያለው ነገረኛ፣ ካገጩ ላይ ጺሙን ያንጨበረረ መሰሪ፣ ቀጣፊ ምላስ ያለው፣ ተናግሮ ማሳመን የሚችል አንደበተ ርትኡ የሆነ የዲፕሎማሲ ሰው፣ እምነተ ቢስ እና አጭበርባሪ የሆነ ሰው፣ ሁለት ምላስ ያለው፣ ሆን ብሎ ጓደኝነትን ክዶ የሚያጭበረብር፣ አንድን ነገር በማስመሰል የሚደብቅ፣ ጭልፊት የሆነ አታላይ የዲፕሎማሲ ሰው በሚያጋጥመው ጊዜ ምን ሊያደርግ ነው? እንዲያው ሁሉም ነገር በአንክሮ ሲታይ አሳዛኝ እና የሀገሪቱን መጥፎ ዕጣ ፈንታ በጉልህ የሚያመላክት ነገር ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ወኔን አጠንክሮ ቀበቶን ጠበቅ በማድረግ ትግሉን ማጧጧፍ የእያንዳንዱ ዜጋ በተለይም ተማርን ለሚለው ወገን ታላቅ ኃላፊነት ነው፡፡ የትግሉን ቀጣይነት እንዲህ በሚሉ የተቋጠሩ የግጥም ስንኞች ስንቅነት እድንይዘው ጀባ ልበላችሁ፡፡ 
 
በክቦቹ ዙሪያ እሩጡ ዘምሩ፣
ጽጌረዳ ያዙ ማንንም ሳትፈሩ፡፡
በኪስ ሙሉ አበባ በመያዝ እሩጡ፣
ከጫፍ እስከ ጫፉ ሳትበጣበጡ፡፡

ያ መጣ ብላችሁ ሀሳብ ሳይገባችሁ፣
ያ ሄደ ብላችሁ ጭንቀት ሳይዛችሁ፣
ሁላችሁም ለድል ለስኬት ብላችሁ፣
ጉዞውን ፈጽሙት ወገን እባካችሁ፡፡
 
ሩጫው በርትቶ ድካሙ ሳይዘው፣
እስትንፋስ ሳያጥረው ነጭ ላብ ሳይወርደው፣
ጉልበቱ በመራድ ሳይዛነፍ ወኔው፣
ሸሚዙን አውልቆ ሳይዝ በትከሻው፣
ትግሉን አጧጡፉት ለመልካም ፍጻሜው፡፡
 
የአድሃኖም ጋር የሚሰሩ የዲፕሎማሲ ሰዎች አሱን ለማታለል አጃቸዉን አየፈተጉ ለሀጭቻቸዉን አያንጠባጠቡ ከልጅ ከረሜላ አንደመወስድ ያህል አየጠበቁ ነው። 
 
የኢትዮጵያ ቁንጮ የዲፕሎማሲ ሰው የሆነዉን አድኃኖም እንደዚህ ያለ ምንም ዓይነት ማገናዘብ የማይል የዋህ፣ በቀላሉ የሚታለሉ ወይም ደግሞ ብልህነት ያነሳቸው እና ነገሮችን ሰፋ አድርጎ የመመልከት ችሎታ የሌለው በመሆን አንዲት ልጅ ከቢሯቸው ድረስ ሰተት ብላ በመሄድ የ20 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ልገሳ በመስጠት ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚል የተዛባ እና እውነትነት የሌለው ትረካ በማቅረብ ልታታልለው ትችላለች? አድኃኖም እንዴት እንደዚህ በቀላሉ ሊታለል  ቻለ? የሀገር የዲፕሎማሲ ሰው መሆን ማለት ስለሀገር ሲባል በመሰረታዊ ጭብጡ ውሸትን እውነት አድርጎ የማቅረብ ሙያዊ ክህሎት መሆኑን እንዴት ማወቅ ተሳነው? ዲፕሎማሲ ለስልታዊ እና ዘለቄታዊ ጥቅም ሲባል እውነቱን ያለመናገር ክህሎት መሆኑን አልተገነዘቡምን? በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ይህንን ጉዳይ ወደ ኋላ እመልሰዋለሁ፡፡ ውሸት በሚነገርባት በኢትዮጵያ ላይ ውሸት መዋሸት የኑሮ ስልት ነው፡፡
 
በእርግጥ አድኃኖም በእውነታው እና ባቀረቧቸው የክርክር አመክንዮዎች በእጥፍ ስህተት የሰራ ሰው ነው ፡ ህጻናት እንደ ማስመሰያ ጸጉር/ዊግ አይዋሹም፡፡ (ይህ ማለት ወጣቷ ልጅ በምንም ዓይነት መንገድ በዚህ የቅሌት ዕኩይ ተግባር ላይ ትዋሻለች ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም ይህንን የመሰለውን የማታለል ድርጊት መፈጻም እንድትችል የተቀነባበረ እና እንድትፈጽመው ስልጠና የተሰጣት ለመሆኑ ፍንጭ ሊሰጡ የሚችሉ ነገሮች ተንጸባርቀዋል፡፡)
 
ውሸትን ከእውነት ለመለየት ለምንሰራ ሰዎች ቢያንስ ከህግ ምርመራ ሁኔታዎች አንጻር ልጆች እንደ እርካሾቹ የቻይና ሰዓቶች የሚዋሹ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ እድሚያቸው ከሶስት ዓመታት በታች የሆኑ ህጻናት እውነትን ከውሸት ለመለየት አይችሉም፡፡ እስከ ሰባት ዓመታት ድረስ ጥቂት ልጆች በእውነታ እና በማገናዘብ ኃይል መካከል ያለውን ልዩነት የመገንዘብ   ይችላል፡፡ ጥቂት የሆኑ ነጭ ውሸቶችን መዋሸት ይጀምራሉ፡፡ በ10 ዓመታቸው እውነትን መናገር እና ውሸትን መናገር ምን ማለት እንደሆነ አሳምረው ያውቃሉ፡፡ እናም ውሸት በሚዋሹበት ጊዜ ፒኖክዮ እንደሚባለው እውነተኛውን ተናግሮ እንደ እውነተኛ ልጅ ለመሆን እንደሚሞክረው አሻንጉሊት የእንጨት ተክል ናቸው፡፡ በ10 ዓመታቸው በእርግጠኝነት ሲዋሹ እና እውነታውን ለጥጠው ሲናገሩ እንዲሁም ለስለስ ያሉ ውሸቶችን  እና ግማሽ የሆኑ እውነቶችን የመፈብረክ ችሎታን ያዳብራሉ፡፡ እንደዚሁም እውነትን አሳምሮ እና አጣፍጦ ከመናገርም በላይ በዝርዝር የቀረቡ እውነታዎችን እና ረዣዥም ትረካዎችንም ማቅረብ ይችላሉ፡፡
 
በ10 ዓመታቸው ልጆች ሙሉ ለሙሉ በሚዋሹበት ጊዜ ብቻ አይደለም የሚያውቁት እናም የ20 ሚሊዮን ዶላር ማጭበርበር በወጣቷ ልጅ ተፈጽሟል የሚለው ሁኔታ እ.ኤ.አ በ1979 የቀረበውን ተንቀሳቃሽ ህይወት አልባ አስቂኝ ፍጡር በዚህች ውሸት በሚነገርባት ምድር ላይ በመኖር ቶሎ ቶሎ የሚተነፍሰውን የውኃ ተርብ አስታወሰኝ፡፡ በዚያ የህይወት አልባ የምስል እንቅስቃሴ ላይ የሚተውነው ተርብ ሳንዲ የምትባለውን ትንሿን ልጃገረድ በኃይል አስገድዶ ወደ የውሸት ዓለም ወደሆነችው ምድር ላይ በመውሰድ ፒኖክዮ ከሚባለው ታዋቂ ተክል እና እንደ በሬ ወለደ ከሚለው ልጅ ዘንድ በመውሰድ እንድትገናኝ በማድረግ እንዲህ የሚል ቃለ ምልልስ ያደርጋሉ፡

ሳንዲ፡ ፑፍ፣ ተመልከት!
ፑፍ፡ እስከ አሀን ድረስ ማንም አይቷት የማያውቅ ቀይ እና ሰማያዊ ቀለም ያላት ላም ናት፡፡
ሳንዲ፡ እንደዚሁም ቀይ ቀለም ያለው ዝሆን
ፑፍ፡ ጥቂቶች ሁልጊዜ ያያሉ
ሳንዲ፡ ያ ማን ነው?
ፑፍ፡ ኪልሮይ፡፡ ሁልጊዜ እዚያ ነበር እናም የትም አልነበረም፡፡
ፑፍ፡ እኔ የውኃ ተርቡ የትምህርት ቤት የቤት ስራየን ምሳ አድርጌ መብላት እንደምችል ማሰብ አዲስ ነገር አይደለምን? በእርግጥም ከዚህ ቀደም ተደርጎ የማያውቅ አዲስ ነገር ነው፡፡ ውሸት ነገር ነበር፡፡ ቅሌት ነገር ነው፣ ትክክለኛ እና ታማዕኒነት ያለው መልስ መስጠት ያለመቻል ነበር፡፡ ኦ፣  ይኸ ነገር ሳንዲ በምትባል በትንሿ ልጃገረድ የተነገረ ቀላል የሆነ ውሸት ነበር፡፡
ሳንዲ፡ ፑፍ፣ ተመልከት!
ሳንዲ፡ የለም፣ እነዚህ ምዕናባዊ ውሸቶች ናቸው፡፡ እናም ጎጅ ያልሆኑ ምናባዊ ግንዛቤዎች ናቸው፣ እሺ፡፡ እናም ይኸ ነገር አስቂኝም ጭምር ነው፡፡ 
ለቴ እኔም ግማሽ የምናብ ግንዛቤ ነኝ፡፡
 
ወጣቷ ልጃገረድ ከአውስትራሊያ ውሸት ወደሚኖርባት ምድር ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከአድኃኖም እና ከሸፍጡ ግብረ አበሮች ጋር የማታለል ድርጊት ጋር እንድትገኛኝ የተደረገች ይመስለኛል፡፡ ምንም በተጨባጭ የሌለውን እና ማንም ያላየውን ሽልማት 20 ሚሊዮን ዶላር ምዕናባዊ የሆነ ውሸት እንድትዋሽ ተነግሯታል፡፡ በ20 ሚሊዮን ዶላር የትምህርት ቤት ግንባታ የአስራአራት ዓመት ልጅ ታረጋለች ብሎ ማመን ቀይ ዝሆን አለ ብሎ ማመን ያህል ነው። 
  
ሆኖም ግን በውኃ ተርቡ እንደተበላው የቤት ስራ ሁሉ 20 ሚሊዮኑ የአሸናፊነት የሽልማት ዶላር አይን ያወጣ ቅጥፈት ነው፣ ታላቅ ቅሌትም ነው፣ ቀጥተኛ እና እውነተኛ ያልሆነ መልስን በመስጠት እውነትን ለመቅበር የሚደረግ ደባ ነው፡፡ አድኃኖም እና ግብረ አበሮቹ ሽልማቱ ሙሉ በሙሉ ፈጠራ የነበረ መሆኑን አሳምረው ያውቁታል፡፡ ሆኖም ግን ወጣቷ ልጅ ስለዚህ ጉዳይ እንድትናገር አድርገዋል፡፡ አያውቁትም ሊባል የሚችለው እንዴት ነው? እንዴት? አንዲት ትንሽ የሆነች ልጅ ከመንገድ ገብታ  20 ሚሊዮን ዶላር ለትምህርት ቤት ግንባታ የሚውል ገንዘብ አለኝ በማለት የሀገሪቱ ቁንጮ ለሆነ የዲፕሎማሲ ሰው ስትናገር አንድ ምክንያታዊ የሆነ በዓለም ላይ የሚኖር ሰው ማድረግ ያለበት ምንድን ነው? ይህችን ህጻን ልጅ በቴሌቪዥን መስኮት እንድትቀርብ በማድረግ ህዝቡ ከእርሷ ለጋስነት ትምህርት እንዲወስድ መለፍለፍ ነው? ይህንን ፍጹም የተሳሳተ እና ምዕናባዊ የሆነ የገንዘብ ሽልማት ጉዳይ በማስመልከት ለአውስትራሊያ ኤምባሲ፣ ለአንደኛ ደረጃው ትምህርት ቤት፣ ለሮታሪ ክለብ እና ለባደን ፓወል ኮሌጅ በመደወል ለማረጋገጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቢሮ ማድረግ የለበትም ?  በአንድ በስደት ላይ ያለ ጋዜጠኛ ይህንን የመሰለ ቅሌት ጥቂት የሆኑ የስልክ ጥሪዎችን በማድረግ ካጣራ እና ውሸት መሆኑን ካረጋገጠ የአድኃኖም ቢሮስ በተመሳሳይ መልኩ እንደዚህ ማድረግ ያልቻለው ለምንድን ነው? አንዲት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነች ህጻን ልጅ በመንገድ ሰተት ብላ በመሄድ አድኃኖምን ማታለል የምትችል መሆኑ ሲታይ ዝም ብሎ እንደ ተራ ነገር የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም፡፡ የምርመራ ጋዜጠኛ አበበ ገላው እንዳቀረበው ዘገባ ይህ ጉዳይ ታላቅ የሆነ የውስጥ ተግባር ነው፡፡
 
አድኃኖም ምክንያታዊ ባልሆነ እና በተሳሳተ መልኩ በማህበራዊ ድረ ገጽ ያካሄደው ጫካውን የመደብደብ ከንቱ ጥረት በቁስል ላይ እንጨት መስደድ እንዲሉ ከመሆን ሌላ የሚፈይደው ነገር የለም፡፡ ፈላስፋነትን የተላበሰ በሚመስል ሆኖም ግን በቅጥፈት በተላበሰ አንደበት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ልጆች በስህተት ይዋሻሉ፡፡ የልጆች ውሸቶች ጎጅዎች አይደሉም፡፡ ወጣቷ ልጅ ስህተት አትሰራም ወይም ደግሞ ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ ልትዋሽ ካልሆነ በስተቀር ጎጅ ውሸት አትዋሽም፡፡ ቁንጮ በሆኑት የዲፕሎማት ሰው እና በግብረ አበሮቿ በተነገራት መሰረት ታላቅ የውሸት ትረካ ፈጽማለች፡፡ ውሸትን እንደ ጨዋነት አድርጎ አስመስሎ የሚያቀርበው እና ታዕማኒነትን ባጓደለ መልኩ ቅዱስ ሀሳብ እንደሆነ አድርጎ የሚያቀርበው የአድኃኖም እምነተቢስ የማህበራዊ ድረ ገጽ መልዕክት ጥረት የተንሻፈፈ እና  የግንዛቤ አድማሳችንን የሚፈታተን ከንቱ ስሌት ከመሆን ያለፈ ፋይዳ የለውም፡፡ ዋልተር ስኮት “በመጀመሪያ ደረጃ መዋሸት ስንጀምር ምን ዓይነት ድር ነው እያደራን ያለነው” በማለት ተናግረው ነበር፡፡
 
አድኃኖም 20 ሚሊዮን ዶላር ስለተባለው የሀሰት የተጭበረበረ ገንዘብ ሁኔታ በእርግጠኝነት ምንም ዓይነት ነገር ሊነግረን አልደፈረም፡፡ ስለዚያ ጉዳይ የሚያውቁት ነገር ከሌለ ሆን ብለው እራሱን ደንቆሮ አድርጎ ነውን? ሰውየው በገዥው አካል በብቸኝነት በተያዘው በህዝብ መገናኛ ብዙሀን ለኢትዮጵያ ህዝብ ስላስተላለፉት ስለ20 ሚሊዮኑ ዶላር ቅጥፈት ኃላፊነቱን አልወሰደም፡፡ አድኃኖም እንደዚህ ባለ መልኩ ስለተፈጸመው ታላቅ ቅሌት ምርመራ እንዲደረግበትም እንኳ ትዕዛዝ አላስተላለፈም ፡፡ መግለጫዎችን አዘጋጅቶ በማቅረብ ሁኔታውን ለማረም እና በብዙሀን መገናኛ እንዲተላለፍ ምንም ዓይነት ጥረት አላደረገም፡፡  
 
የበለጠ አስደንጋጩ እውነታ ደግሞ ህጻኗን ልጅ በሰይጣን እና በጥልቅ ሰማያዊ ባህር መካከል ጥለው ምንም ዓይነት ኃላፊነት ያለመውሰዱ ጉዳይ ነው፡፡ ይህች ህጻን ልጅ በጓደኞቿ እና አታላዩዋ ልጅ፣ አሳዛኟ ወንጀለኛ እና አጭበርባሪዋ ልጅ እየተባለች በመጥፎነት ስትታወስ  የምትኖር ስለመሆኗ አድኃኖም ጉዳዩ አይደለም፡፡ አድኃኖም ልጅቷን ከፈጣን አውቶብስ ስር በመጣል በጠቅላላ በ20 ሚሊዮን ዶላር ቅሌት ጋር በተያያዘ ለተፈጠረው ቸግር ሁሉ ሙሉ ኃላፊነቱን እንድትወስድ አድርገዋል፡፡ ልጅቷን ከመረጃ የትችት ማዕበል ውስጥ ጥለዋት ሄደዋል፡፡ እንደዚህ ያለ የጫካ ቅሌትን በማደራጃት እና በመምራት ለሰሩት ግፍ ይህችን ወጣት ልጅም ሆነ የኢትዮያን ህዝብ ይቅርታ አልጠየቀ ም፡፡ ወጣቷ ልጅ ጨዋነትን የተላበሰ እና ምንም ዓይነት ጉዳትን ሊያስከትል የማይችል ውሸት እንደዋሸች አድርጎ በመፈረጅ ይህንን ታላቅ ቅሌት እንደ ቀላል ነገር ለበስ ለበስ አድርጎ ለማለፍ ጥረት ተደርጓል፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ሰዎችን ሆን ብሎ ለመጉዳት ዕኩይ ምግባር ለሚያራምድ ሰው፣ ቁንጮ ዲፕሎማት፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ከመቅጽበት ለይስሙላ ተቀምጦ ያለውን ጠቅላይ ሚኒስትር በማስወገድ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቢሮን ለመውሰድ ዙፋኑን እያሟሟቀ ላለ ባለስልጣን ምን ይባላል?
 
የሞራል ተቀባይነት በሌለው በአድኃኖም ባህሪ እጅጉን ደንግጫለሁ እናም አዝኛለሁ፡፡ ይህ የአድኃኖም ድርጊት ለኢትዮጵያ ህጻናት እና ለወጣቱ ትውልድ የሚያስተላልፈው መልዕክት ምንድን ነው? ለእነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች ምን ዓይነት ምሳሌነት ነው እያስቀመጡ ያሉት? ልጆች፣ እሺ ይሁን ይዋሹ ምክንያቱም በምትዋሽበት ጊዜ ስህተት እየሰራህ ነው፡፡ ውሸቶች ጨዋነትን የተላበሱ እስከሆኑ ድረስ ተገቢ ናቸው በማለት ለልጆች እየተናገሩ ነውን? የ20 ሚሊዮን ዶላር ጨዋ ውሸቶች የሞራል ዝቅጠት እና ስህተት የለባቸውም ምክንያቱም ልጆች መታመን አለባቸው በማለት እያስተማሩ ነውን? ለኢትዮጵያ ወጣቶች ምን ዓይነት አርዓያነትን ነው በማስተማር ላይ ያሉት? አድኃኖም የዚህን አዋራጅ ቅሌት ጉዳይ ከኢትዮጵያ ህጻናት ልጆች እና ወጣቶች አመለካከት አንጻር ተመልክቶታልን? ወጣቷ ልጅ ለኢትዮጵያ ወጣቶች ተምሳሌት ቀንዲል እንድትሆን አድኃኖም ጽኑ ፍላጎት አድሮበታል፡፡ የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ጉዳይ ቅሌት መሆኑ በአደባባይ እየታየ እና በህዝብ ዘንድ እየታወቀ በአድኃኖም በኩል ወጣቷ ልጅ ምን ዓይነት የተምሳሌትነት ቀንዲል እንድትሆን ነው የተፈለገው? አድኃኖም የፈጠሩት የተምሳሌትነት ቀንዲል በአሁኑ ጊዜ የተዋረደ እና በቅሌት የተዘፈቀ አጭበርባሪነት ተብሎ የተወገዘ ስለመሆኑ ደንታ አላቸው እንዴ?
 
አድኃኖም ስለሞራል ስብዕና አመክንዮ ችሎታ አላቸውን? ልጆች እንደልጅነታቸው መዋሸታቸው ስህተት የለውም ብለን ብናምንም እንኳ እንደ አዋቂ ሰው መዋሸት ስህተት የሚሆነው ለምንድን ነው? በእርግጥ ውሸት እና ሸፍጥ በተንሰራፋበት ምድር መዋሸትም ፍጹም ተገቢ ነው የሚለው አባባል ትክክል ነው፡፡ ይቅርታ ሊደረግለት የማይችለው እና በምንም ዓይነት መልኩ ተቀባይነት የሌለው ነገር ግን አሁን በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የዲፕሎማሲ ሰው ከህዝብ ነቀፌታ፣ ከቅሌት እና ውግዘት እራሳቸውን ለመከላከል በማሰብ ውሸት ጨዋነትን የተላበሰ ስህተት ነው በማለት ጉንጭ አልፋ እና አመክንዮ የሌለው ክርክራቸውን የመቀጠላቸው ጉዳይ ነው፡፡ ካፈርኩ አይመልሰኝ መሆኑ ነው እንጅ በምንም ዓይነት መንገድ ቢሆን ውሸት ውሸት እንጅ መቸውንም ጊዜ ቢሆን ውሸት ጨዋ ሊሆን አይችልም፡፡ ኢትዮጵያዊ ባህላችንም አይደለም አድኃኖም ሊበርዝብን ካልሆነ በስተቀር፡፡ ስህተት በነጠረ እውነት እንጅ በእራሱ በስህተት አይታረምም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ጨዋ ውሸት ያው ውሸት እንጅ በፍጹም ጨዋነትን ሊላበስ አይችልም፡፡ ስለሆነም በሀገር ላይ እየተሰራ ያለው ደባ እና ሸፍጥ በምንም ዓይነት መልኩ ይቅርታ ሊደረግለት የማይገባ የሞራል ስብዕና ወንጀል ነው፡፡
የሞራል ሰብዕና መሪዎች ወጣቶች እንዲዋሹ በፍጹም አያደፋፍሩም ወይም ደግሞ ውሸትን ታላቅ ቅሌት እንጅ የደግ ነገር ተምሳሌት ነው ብለው አቃልለው አይመለከቱም፡፡ የሞራል ሰብዕና መሪዎች ወጣት ውሸታሞች ውሸትን እንዲፈበርኩ ትዕግስቱ የላቸውም ወይም ደግሞ ጨዋ ዋሾች በማለት ይቅርታ አያደርጉላቸውም፡፡ የሞራል ሰብዕና መሪዎች በስህተት ነው ውሸት የተነገረው ለሚለው ምንም ዓይነት ይቅርታ የላቸውም፡፡ አንድ ህጻን የቤት ስራውን ወይም ስራዋን ባለማከናወኑ/ኗ ምክንያት የቤት ስራውን ውሻው በላው በማለት መዋሸት የለበትም/የለባትም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ አንድ መንግስታዊ የሆነ ተቋም በእርግጠኝነት ውሸት፣ ተራ ቅጥፈት እና የቁጥር ጨዋታ መሆኑን አስረግጦ እያወቀ ባለሁለት አሀዝ የምጣኔ ሀብት ዕድገት አስመዝግበናል በማለት መዋሸት በምንም ዓይነት መልኩ ትክክል አይደለም፡፡ ልጆቻችን ሀቀኞች፣ የተከበሩ፣ ሞገስን የተላበሱ፣ ላመኑበት ዓላማ ጽኑዎች እና ግልጾች እንዲሁም ታማኞች እንዲሆኑ እነዚህን መሰረታዊ እሴቶች በቤት እና በትምህርት ቤቶች እንዲማሩ እናደርጋለን፡፡ እንደዚህ ዓይነቶቹ የሞራል ስብዕና እሴቶች በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምድር ውስጥ ቦታ የላቸውም፡፡
 
በተደጋጋሚ ስናገረው እንደቆየሁት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች የሬክ/የጀርመን የፕሮፓጋንዳ ሚኒስትር የነበሩትን የጆሴፍ ጎቤልስን እንዲህ የሚለውን መርህ አበርትተው ይከተላሉ፣ “ታላቅ ውሸት ከዋሸህ እና ይህንኑ ውሸት ደግመህ ደጋግመህ ከፈጸምከው በመጨረሻው ጊዜ ህዝቦች ማመን ይጀምራሉ፡፡ ውሸቱ ተደጋግሞ የሚነገረው መንግስት በህዝቡ ላይ ከተነሳበት የፖለቲካ፣ የምጣኔ ሀብት እና/ወይም ወታደራዊ የውሸት ውጤቶች በህዝብ ከሚወሰዱ እርምጃዎች እራሱን ለመደበቅ ሲል ብቻ በዚያን ጊዜ የሚፈጽመው ድርጊት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት መንግስት ያለውን ኃይል ሁሉ በመጠቀም ሰላማዊ አመጸኞችን ለመጨቆን፣ እውነት ዋና የውሸት ጠላት በመሆኗ እና ከዚህም በመነሳት እውነት ዋነኛ የመንግስት ቀንደኛ ጠላት ስለሆነች ውሸትን እንደ በቀቀን መድገም እና መደጋገም አስፈላጊው ነገር ነው፡፡“
 
አድኃኖም እና የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሆን ብሎ እንደ በቀቀን ደግሞ እና ደጋግሞ የመዋሸትን የጎቤልን ትምህርት ወደ ላቀ እና ከፍ ወዳለ ደረጃ አሸጋግረውታል፡፡ የ20 ሚሊዮን ዶላር ውሸትን በመፈብረክ ውርርድ ገብተው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይህንን ውርርድ በጽናት በሚታገለው መርማሪ ጋዤጠኛ አበበ ገላው ሙያዊ ክህሎት ተራ ቅጥፈት ሆኖ በመገኘቱ ውርርዳቸውን አጥተዋል፡፡ ውርርዱን ማጣት ብቻም ሳይሆን በቅሌት ባህር ውስጥም ተዘፍቀው በመንቦጫረቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ ላለፉት አስርት ዓመታት ስለኢትዮጵያ ባለሁለት አሀዝ የምጣኔ ሀብት ዓመታዊ ዕድገት ታላቅ ቅጥፈትን ፈጽመዋል፣ ሆኖም ግን የለየለት ውሸት መሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ ተይዘዋል፡፡ ስለሆነም እነርሱ ሊቃወሙት የማይፈልጉት እንዲህ የሚል ስጦታ ልሰጣቸው እፈልጋለሁ፡ ስለባለሁለት አሀዝ የምጣኔ ሀብት ዕድገት፣ ስለ 20 ሚሊዮን ሽልማት፣ ምርጫዎች የሚዋሹትን ታላቅ ውሸት የሚያቆሙ ከሆነ እና ሌሎች በየሳምንቱ አዳዲስ ተራኪ ቅጥፈቶችን ከመፈብረክ የሚታቀቡ ከሆነ እኔም እንደዚሁ በየሳምንቱ ሰኞ እውነታውን በማውጣት ስለእነርሱ ቅጥፈት የምዘግበውን አቆማለሁ!
 tewedros
የወያኔ የቅጥፈት ዲፕሎማሲ እና ዋና የዲፕሎማት ሰው፣
 
የአድኃኖምን ድፍረት የተቀላቀለበት የዲፕሎማሲ አካሄድ እስከ አሁን ድረስ ተከታትያለሁ፡፡ በቪዲዮ የተቀረጸውን እና ለህዝብ የቀረበውን ተመልክቻለሁ፡፡ እናም እሱም ያደረገዉን ንግግር በማነብበት ጊዜ ማመን ተስኖኝ እራሴን በመያዝ አግራሞቴን ገልጫለሁ፡፡ የሀሳብ ምጥቀት ዳህራቸው ቅርብነት አስደንጋጭ ነው፡፡ የሚያደርጓቸው ንግግሮች ምንም ዓይነት ጥቅም እና ፋይዳ የሌላቸው በመሆናቸው ጥራት ይጎድላቸዋል፣ እንደዚሁም ደግሞ የነገሮች ተያያዥነት የላቸውም፡፡ እጅግ በጣም ውስብስብ የሆኑ ጉዳዮችን መልክ ለማስያዝ  በተማሪዎች እንቅስቃሴ ወቅት ሲነገሩ የነበሩ አሁን ጊዜ ያለፈባቸውን እና የቀሩትን ቃላት እና ሀረጎችን በመጠቀም አሁን በህይወት የሌሉትን አለቃቸውን ለመምሰል ይታትራሉ፡፡ ዓለምአቀፍ ዲፕሎማሲን በማወቅ በኩል በጣም አናሳ የሆነ ግንዛቤ አላቸው፡፡ አጅግ በጣም መሰረታዊ የሆኑ የዓለም አቀፍ ህጎች፣ ውሎች እና ስምምነቶች እውቀት ግንዛቤ እና መጠነኛ የሆነ ዕውቀት አንኳ ያላቸው ለመሆናቸው ምንም ዓይነት ማረጋገጫ አያሳዩም፡፡ ያቀረብኳቸውን ነጥቦች ተጨባጭ ለማድረግ አስረጅ ምሳሌዎችን እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡  
 
1ኛ)  የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት/ICC በኡሩ ኬንያታ እና በዊሊያም ሩቶ ላይ መስርቶት ከነበረው ክስ ጋር በተያያዘ መልኩ፣
 
የኬንያ ፕሬዚዳንት በሆኑት በኡሁሩ ኬንያታ እና በእርሳቸው ምክትል በሆኑት በዊሊያም ሩቶ ላይ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ክስ መስርቶባቸው እ.ኤ.አ ለጥቅምት 2013 ተይዞ ለነበረው ቀጠሮ ቅድመ ዝግት ለማድረግ እና ክሱ እንዲቋረጥ ወይም እንዲራዘም ለማድረግ በማሰብ የአፍሪካ ህብረት አዲስ አበባ ላይ አድርጎት በነበረው ጉባኤ ላይ አድኃኖም ቀንደኛ አስተባባሪ በመሆን በሁለቱ ተጠርጣሪዎች ላይ የተመሰረተው ክስ ካልተቋረጥ የአፍሪካ ሀገሮች በሙሉ የሮማን ስምምነትን በመርገጥ በጅምላ ጥለው እንዲወጡ ሲያስተባብር ነበር፡፡ በአፍሪካ ህብረት ልዩ ጉባኤ የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ በመገኘት አድኃኖም እንዲህ የሚል ንግግር አሰምቶ ነበር፡
 
 የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አፍሪካን እና አፍሪካውያንን ኢላማ በማድረግ እራሱን ወደ ፖለቲካ መሳሪያነት አሸጋግሯል፡፡ ይህ ዓይነቱ ትክክል እና ፍትሀዊ ያልሆነ አያያዝ ፍጹም ተቀባይነት የለውም፣ እናም ለዚህ ነው በICC ላይ ያለንን ስጋት ስንገልጽ የቆየነው…የኬንያን ፕሬዚዳንት እና ምክትላቸው ህገ መንግስታዊ ግዴታዎችን እና ኃላፊነቶችን ለመወጣት እንዲችሉ የራሳቸውን ስብሰባ እንዲመርጡ ፍርድ ቤቱ እንዲፈቀድላቸው ያቀረብነውን ጥያቄ አዎንታዊ ምልሽ አላገኘም…ኬንያን እና አህጉራችንን የሚበጠብጥ እንደዚህ ያለ የተጠርጣሪ/ሰለባ ዓይነት አቀራረብ አንፈልግም…የመንግስታት ርዕሰ ብሄሮች ሊከሰሱ አይችሉም እና ያለመከሰስ ከለላ አላቸው በሚሉ ጉዳዮች ላይ ግልጽ የሆኑ ውሳኔዎችን ይዘን መውጣት ይኖርብናል…ይኸ ጉዳይ በኬንያ እና በአጠቃላይ በአፍሪካ ላይ ትልቅ የሆነ መዘዝ ሊያመጣ የሚችል ለመሆኑ የሚያጠራጥር ነገር አይደለም… ምናልባትም ይህ ጉዳይ በICC እንዴት መያዝ እንዳለበት ወደፊት አፍሪካ ከICC ጋር በሚኖራት ግኙነት ላይ ጠንከር ያለ እንደምታ ይኖረዋል… ICC በእንደዚህ ያለ ሁኔታ በአፍሪካ እና በአፍሪካውያን ላይ የበላይነቱን እያሳዬ መኖር እዲቀጥል መፍቀድ የለብንም፡፡  
 
በጉባኤው የመዝጊያ ስነስርዓት ንግግር ላይ አድኃኖም በባዶው የድል አድራጊነት መንፈስን በተላበሰ መልኩ ተኩፍሰው ታይቷል፡፡ በሮም ስምምነት መሰረት ሁሉንም የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገሮች አሳድመው ከICC አባልነት በጅምላ እንዲወጡ ሊያደርጉት የነበረው ዕቅዳቸው ሙሉ በሙሉ ከሸፈበት፡፡ ሆኖም ግን እንዲህ በማለት ንግግሩን ቀጥሎ ነበር፡
 
ICC ዓለም አቀፍ የፍትህ አገልግሎቱን ለመስጠት ሲል የሚጠቀማቸውን የአድልኦ አሰራሮች ውድቅ አድርገናል፡፡ እንደዚሁም ICC በአፍሪካ በተመረጠ መልኩ በአድልኦ የሚፈጽማቸውን ተግባራት ግልጽ በሆነ እና በማያሻማ መልኩ የተሰማንን ቅሬታ ግልጽ አድርገናል፡፡ በተለይም ለመጀመሪያ ጊዜ በመንግስት ርዕሰ ብሄር እና በምክትላቸው ላይ በተመሰረተው የICC ክስ በጣም የተጎዳንበት እውነታ መፈጠሩን እና ይህም ሁኔታ የኬንያን ሉዓላዊነት የተዳፈረ መሆኑን ያመላክታል…
 
የኬንያታን እና የሩቶን በICC ከመከሰስ ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ አድኃኖም በሰጠው ትንታኔ ላይ የፍሬ ነገር ጭብጥ፣ የሕግ እና የአመክንዮ ግድፈት ይስተዋላል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አፍሪካን እና አፍሪካውያንን ኢላማ በማድረግ እራሱን ወደ ፖለቲካ መሳሪያነት አሸጋግሯል የሚለው የአድኃኖም ፍረጃ ይህ ድርጊት እውነት ስለመሆኑ ቅንጣት ያህል ማስረጃ ማቅረብ አይችልም፡ ICC በአፍሪካ እና አፍሪካውያን ላይ የበላይነትን በማሳየት አድሎአዊ አሰራርን ያራምዳል ለሚለው ውንጀላ ተራ አሉባልታ ካልሆነ በስተቀር በተጨባጭ ምንም ዓይነት የቀረበ ማስረጃ የለም፡፡ ምንም!
 
አድኃኖም ተጨባጭነት ያለው እና በማስረጃ እና በሕግ በተደገፈ አሰራር ሳይሆን ማሸነፍ የፈለገው የICCን ስም በማጥፋት እና ጥላሸት በመቀባት ነው፡፡ አድኃኖም በአፍሪካ እና በአፍሪካውያን ላይ አስቀድመው ያለምንም ማስረጃ የእራሱን ሀሳብ በመጫን እና የእርሳቸውን ሀሳብ እንዲቀበሉ ጥረት በማድረግ የሌሎች ሰዎች ስሜቶች እንዲጎዱ አድርገዋል፡፡ እንዲሁም በአድኃኖም እምነት መሰረት የነጮቹ የICC ዳኞች እና አቃብያነ ሕጎች የእነርሱን የዱሮውን የቅኝ አገዛዝ ስርዓት በICC አማካይነት በአፍሪካ እና በአፍሪካውያን ላይ ለመጫን ጥረት እያደረገ ነው በማለት ሌሎችም በስሜታዊነት የእርሱን በማስረጃ ያልተደገፈ ውንጀላ በመከተል ተንጋግተው እንዲወጡ ለማድረግ ጥረት አድርግዋል፡፡ እውነታው ግልጥልጥ እና ፍርጥርጥ ብሎ ሲታይ ግን በሚገዟት ሀገር በአሁኑ ጊዜ እየተገበሩት እንዳሉት ሁሉ ልምዳቸውን ከፍ በማድረግ በአፍሪካ በአሁጉር ደረጃ የዘር ካርድን ነቅሶ በማውጣት ነጮቹን የICC ሰዎች አሳፍረው እና አሸማቅቀው ለማባረር ያደረጉት የህጻን ዓይነት ጨዋታ እራስን ከትዝብት ላይ ከመጣል በስተቀር አንድም የፈየደው ነገር አልነበረም፣ ሊኖርም አይችልም፡፡
ዘረኝነትን አህጉር አቀፍ ለማድረግ ያደረጉት ያልተሳካ ሙከራ በአጫፋሪዎቻቸው ዘንድ ሊደገፍ ካልሆነ በስተቀር በሌላ በማንም የሚያስብ አዕምሮ ባለው ሰው ዘንድ የሚታሰብ ጉዳይ አይደለም፡፡ እውነታው ግን ICC እንደ እራሱ በጎጥ እና በመንደር የጠባብነት የዘር ስሜት የሚነዳ ሳይሆን በዘር፣ በመልክዓ ምድር እና በጾታ ህብረ ውህድ ያለው ለሰው ልጆች ሁሉ ሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ ፍትህ በዓለም ላይ ሁሉ እንዲሰፍን የሚታገል ዓለም አቀፋዊ ድርጅት ነው፡፡ በእርግጥ የእርሱ የይስሙላ አለቃ የሆነው ኃይለማርያም ደሳለኝ ICC ዘር አዳኝ ነው በማለት በይፋ በአደባባይ ተናግሮ ነበር፡፡ በዚያ ንግግር እኔ በግሌ በጣም ነው ያፈርኩት እና ውርደት የተሰማኝ፡፡ ከድፍን 60 ዓመታት የነጻነት ህይወት በኋላ የአፍሪካ መሪዎች የዘር ካርድን እየመዘዙ ማውጣቱን ስራዬ ብለው ተያይዘውታል፡፡ ምን ዓይነት የወረደ አሳፋሪ ድርጊት ነው!
 
እንደዚሁም ደግሞ ICC በማንኛውም የአፍሪካ ተጠርጣሪ ላይ አግባብነት የሌለው ድርጊት ለመፈጸሙ እና ፍትሀዊነት የጎደለው አሰራር ለመስራቱ ከመወንጀል በስተቀር ምንም ዓይነት ማስረጃ የለም፡፡ የአድኃኖም ድብቁ የክርክር ጭብጥ ግን ICC አፍሪካን እና አፍሪካውያንን በሰብአዊ መብት ወንጀሎች ይከሳቸዋል ምክንያቱም ጥቁር ስለሆኑ ነው የሚል አራምባ እና ቆቦ ሆኖ ይገኛል፡፡ የተከበሩ አድኃኖም ለመሆኑ አፍሪካውያን በዘር በICC ክስ ይመስረትባቸዋል ከተባለ በዘር ተከሰሱ እንዳይባሉ ንጹሀን ህዝቦችን ይፍጁ፣ ዕልቂት ይፍጠሩ፣ ያውድሙ እንደፈለጋቸው ይሁኑ እንዲባል ነው ፍላጎቱ? ወይስ ደግሞ ይህ የአምባገነንነት ሰይጣናዊ አስተሳሰብ የተጠናወተው የአፍሪካ ጥቁር ወሮበላ ዘራፊ በጠብመንጃ አፈሙዝ ስልጣንን እየጠቆጣጠረ እንደፈለገው በህዝቦች ላይ እልቂትን እየፈፀመ ሀብት እና ንብረታቸውን እየቀማ ባለበት ሁኔታ በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት ላጠፋው ጥፋት ተጠያቂ ይሁን መባሉ ለአፍሪካ ሲሆን እንዴት በዘር ነው ሊባል ይችላል?
 
ነጭ የቆዳ ቀለም ያለው ሰውም ቢሆን ሰብአዊ መብትን እስከደፈጠጠ ድረስ ከተጠያቂነት አያመልጥም፡፡ ይኸ ነገር የዘር እና የቆዳ ጉዳይ አይደለም፡፡ በርካታ መብት ደፍጣጮች በአፍሪካ ውስጥ የመገኘታቸው ሁኔታ እውነት ነው፣ ስለዚህም በርካታዎቹ ወይም ደግሞ ሙሉ በሙሉም ቢባል ወንጀለኞች እስከሆኑ ድረስ የአፍሪካው አምባገነኖች በህግ መጠየቃቸው ከዘር ጋር የሚያገናኘው አንድም ነገር የለም፡፡ አድኃኖም ወይም ደግሞ በዚህች መከራዋ ባላለቀላት ሀገር መሰረትሁት እንዳሉት የዘር የፖለቲካ ዥዋዥዌ ጨዋታ ሁሉ እንደ ብሄር ብሄረሰቦች የይስሙላ በዓል አከባበር እንደምታደርጉት ሌሎች ወንጀል ያልሰሩትን አህጉሮች ሁሉ በመጨመር በኮታ ከአፍሪካ፣ ከአሜሪካ፣ ከኢስያ፣ ከአውሮፓ፣ ከላቲን አሜሪካ፣ ከአውስትራሊያ….ይህን ያህል ሰብአዊ መብት ደፍጠጮች በICC ክስ ተመሰረተባቸው እንዲባል ይፈለጋል? የይስሙላ የመንደር እና የቀበሌ ኮታዎን እንደለመደው እዚሁ በመንደር እና በቀበሌዎ ያድርገው፡፡ እውነተኛውን ዓለም አቀፋዊ የፍትህ አካሉን ስም ማብጠልጠሉን እና ጥለሸት መቀባቱን ግን ፋይዳ አላስገኘለትምና፡፡ 
 
ቀደም ሲል እንደነበረው ቅኝ ገዥዎች ሁሉ የነጮቹ የICC ዳኞች እና ዓቃብያነ ሕጎች በፍርድ ቤት እያስቀረቡ የአፍሪካን መሪዎች ይገድላሉ፡፡ በእርግጥ ይህን አባባል ማራመድ የለየለት ድድብና ነው! ICC በአፍሪካ ላይ ሰብአዊ መብቶችን የደፈጠጡትን ወንጀለኞች ለሕግ በማቅረብ ፍትህን ይሰጣል፡፡ ከዚህ አንጻር ዊሊያም ሱቶን ለተባለ አንድ የአሜሪካ የታወቀ ባንክ ዘራፊ ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠው እንዲህ የሚለው መልስ ትዝ አለኝ፣ “አንተ ባንኮችን ሁልጊዜ የምትዘርፈው ለምንድን ነው?“ ተብሎ ሲጠየቅ እንዲህ የሚል ቆምጫጫ መልስ ሰጠ፣ “ምክንያቱም ገንዘቡ የሚገኘው እዚያ መሆኑን ስለማውቅ ነው፡፡“ እንደዚሁም ሁሉ ICC የፍርድ ሂደቱን ቀጥሎ ያለው በአፍሪካ ተጠርጣሪዎች ላይ ነው ምክንያቱም አብዛኞቹ ተጥርጣሪ ወንጀለኞች የሚገኙት በአፍሪካ በመሆኑ ነው፡፡ በእርግጥ የሮም ስምምነት መሰረት ያደረገው እ.ኤ.አ ከ2002 ወዲህ ለተፈጸሙት የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ወንጀሎች ብቻ ነው፡፡
 
አድኃኖም ስለICC ያላው የሕግ ሂደት ግንዛቤ ከእርሱ የፍትህ ስርዓት ጋር በጣም የሚመሳሰል መስሎ ታይቶታል፡፡ እንደ ወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ሁሉ ለአባላት፣ ለተባባሪዎች እና ለደጋፊዎች አንድ ዓይነት ሕግ ለሌሎች ኢትዮጵያውያን/ት ደግሞ ሌላ ሕግ እንደሚያወጡ ሁሉ አድኃኖም ለICCም በተመሳሳይ መልኩ እንደዚህ ያለ ሕግ መውጣት እንዳለበት ያምናል፡፡ ICC በሰብአዊ መብት ወንጀል ድፍጠጣ ለሚጠየቁ ተጥርጣሪዎች ሁለት ዓይነት ሕግ አያወጣም፡፡ ለሀገር መሪ ወንጀለኞች ለሌሎች የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ተብሎ የሚወጣ ሕግ የለም፡፡ በአድኃኖም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ውስጥ ዋናዎቹ የፓርቲው አባሎች ክስ ሊመሰረትባቸው የሚችሉት ከፓርቲያቸው ውጭ ለየት ያለ ሀሳብ ማሰብ ሲጀምሩ ነው፡፡ በዚህን ጊዜ በሙስና ስም ክስ ይመሰረትባቸዋል፡፡ አንግዲህ ወያኔ በእንደዚህ ያለ የሕግ ሂደት ነው ገና ከጫካ ጀምሮ እስከ ወታደራዊው ደርግ ድረስ ሲካሄድ በነበረው የትጥቅ ትግል ዋና ዋና የሚባሉትን ወታደራዊ አዛዦቻቸውን በመግደል ስልጣናቸውን እያመቻቹ እዚህ የደረሱት፡፡  
 
2ኛ) አድኃኖም ለአፍሪካ ህብረት ያቀረቡት የክርክር ጭብጥ የኡሁሩ እና ሩቶ ህገመንግስታዊ ግዴታዎቻቸውን እና ኃላፊነቶቻቸውን እየተወጡ ነው ወደ ICC የፍርድ ሂደት ችሎት መቅረብ ያለባቸው፣
 
አድኃኖም ኬንያታ እና ሩቶ በሰው ልጆች ላይ ስለፈጸሙት በጣም ከፍተኛ የዕልቂት ወንጀል፡ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ የዘር ማጥፋት፣ እና የጦር ወንጀለኝነት ጉዳይ ከምንም አልቆጠረዉም፡፡ ይህ ድርጊት የሚያሳየው ገዳዮች፣ የዘር ማጥፋት ወንጀለኞች፣ እና ሌሎችም አሰቃቂ የሆኑ የሰው ልጅ መብቶችን የሚደፈጥጡ ወንጀለኞች እንደ ወንጀላቸው ሕጉ በሚፈቅደው ሳይሆን እነርሱን እንደተመቻቸው ወደ ICC ብቅ እያሉ የፍርድ ሂደታቸውን ጉዳይ ይከታተሉ ማለት አድኃኖም በሕጉ ላይ ምንም ዓይነት እውቀት እንደሌላቸው ከማሳየቱም በላይ ለሰው ልጅ ህይወት ምን ያህል የቀለለ አመለካከት እንዳላቸው በተጨባጭ ያመላክታል፡፡ ያ ቢደረግ ኖሮ ICC ማን ተብሎ ሊጠራ ነበር? ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት/International Crimininals Court መባሉ ቀርቶ ዓለም አቀፉ የዝንጀሮዎች ፍርድ ቤት/International Kangaroo Court ነው ሊባል የሚችለው፡፡ ሆኖም ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ያለኝን አቋም ለመቀየር እምነት አድሮብኛል፡፡ ይህም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምንም ዓይነት የፍትህ አካል ሳይጎበኛቸው በ10ሺዎች እና ከዚያ በላይ የሚቆጠሩ በየእስር ቤቱ ያጎራቸውን ተጠርጣሪ ወገኖቻችንን የፍርድ ሂደት ተጠርጣሪዎቹ በሚመቻቸው መንገድ እያመቻቸ እየተዝናኑ የፍርድ ሂደታቸውን እንዲከታተሉ የሚያደርግ ከሆነ የማቀርበውን ተቃውሞ በሙሉ ውድቅ በማድረግ በነጻ እሰናበታለሁ፡፡  
 
3ኛ) አድኃኖም ICC ይህንን ቀላል የሆኑ የተጠርጣሪ/ሰለባ አቀራረብን በማራመድ በኬንያ እና በአህጉራችን ብጥብጥ ሊያስነሳ የሚችለውን ነገር ህብረቱ ውድቅ ሊያደርገው ይገባል… የሚል ተማጽዕኖ ለጉባኤው አባላት ማቅረባቸው፣
 
በእርግጥ ይኸ አባባል ፍየሌን ያስገኝልኛል፡! አድኃኖም በኬንያታ እና በሩቶ የተፈጸሙት ወንጀሎች ቀላሎች እና ብዙም እርባና የሌላቸው አድርገው ለማቅረብ ሞክረዋል፡፡ እነዚያ ተጠርጣሪዎች በአንቀጽ 25 (3) (a) ስር በዝርዝር በቀረቡት በሮም ስምምነት በሰው ልጆች ላይ በተፈጸሙ በአምስት ዓይነት ወንጀሎች ነው ክስ የተመሰረተባቸው፡፡ ዝርዝር የህግ ጨብጦችም ሀ) ግድያ መፈጸም፡ በአንቀጽ 7 (1) (a) ስር የተጠቀሰው፣ ለ) ማጋዝ ወይም ደግሞ በግዳጅ ማፈናቀል፡ በአንቀጽ 7 (1) (d) ስር የተጠቀሰው፣ ሐ) አስገድዶ መድፈር፡ በአንቀጽ 7 (1) (g) ስር የተጠቀሰው፣ መ) ማሰቃየት፡ በአንቀጽ 7 (1) (h) ስር የተጠቀሰው፣ ሠ) ሌሎች ሰብአዊ ወንጀሎች፡ በአንቀጽ 7 (1) (k) ስር ተጠቅሶ የተጠቃለሉት ናቸው፡፡
 
ውንጀላዎቹ 155 ገጽ በያዘ ሰነድ በማስረጃ ተሟልተው እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ምስክሮችን ቃል አካትተው በመያዝ የቀረቡ ሲሆን ለህሊና የሚሰቀጥጡ እና ዝርዝር ነበሩ፡፡ በ59 ቀናት ውስጥ ወደ 1,400 የሚሆኑ ሰዎች እንዲያልቁ የተደረጉ ሲሆን ሌሎች 600,000 የሚሆኑት ደግሞ ኬንያ አደገኛ በሆነ መልኩ ወደ የእርስ በእርስ ጦርነት ወደሚመስል ደረጃ በተንሸራተተች ጊዜ ከቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2007 በኬንያ የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ ተከስቶ በነበረው ውዝግብ በህዝቦች ላይ የደረሰው እልቂት እና ውድመት አድኃኖም እንዳቀረቡት ቀላል የሚባል ነገር አልነበረም፡፡
 
ምናልባትም እንደዚህ ያሉት ዕልቂቶች እና ስቃዮች ለአድኃኖም ምንም ማለት ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ ምናልባትም ለአድኃኖም እንደ እስታሊን ሁሉ የአንድ ሰው ሞት አሰቃቂ ነው፣ የ30 ሚሊዮን ህዝቦች ዕልቂት ግን የቁጥር ጉዳይ ነው፡፡ አሁን በህይወት የሌለው የእርሱ አለቃ እ.ኤ.አ በ2005 በኢትዮጵያ የተካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ ተከስቶ በነበረው ውዝግብ በእራሳቸው ስልጣን የጦር እና የደህንነት ኃይሉን በቁጥጥራቸው ስር በማድረግ ትዕዛዝ በመስጠት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች እንዲገደሉ አድርጎ ነበር፡፡ ምንም ዓይነት የሕግ ተጠያቂነት አልደረሰቤትም ነበር፡፡ ተጨባጭ የሆኑ መረጃዎችን በመያዝ ኬንያታ እና ሩቶም የመለስን የህዝብ እልቂት በማየት እና ቢያንስ 182 ነፍሰ ገዳዮች እና ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ የግድያ ሙከራ አድራጊዎች በሕግ ሳይጠየቁ ምንም እንዳልሆኑ ግንዛቤ በመውሰድ ይህንን የፈሪዎች እና የደናቁርት ዕኩይ ድርጊት ከእነርሱ በመኮረጅ እነኬንያታ እና ሩቶ በኬንያ ህዝብ ላይ ፈጽመውታል የሚል የእራሴ እምነት አለኝ፡፡
 
4ኛ) በሀገር መሪዎች ላይ ምርመራ ማካሄድ እና በሕግ እንዲዳኙ ማድረግ ለኬንያ እና ለአፍሪካ በአጠቃላይ ውስብስብ የሆነ ችግርን ያስከትላል በማለት በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ ክርክር ማቅረባቸው፣
 
አድኃኖም ይህንን የመሰል የክርክር ጭብጥ ማቅረቡ ፍጹም በሆነ መልኩ ትክክል ናቸው፡፡ ሟቹ መለስ እ.ኤ.አ በ2005 የተደረገውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ በተከሰተው ውዝግብ በርካታ ንጹሀን ዜጎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ በመስጠቱ  ምክንያት በICC ክስ ቢመሰረትበት እና ለሕግ ቢቀርቡ ኖሮ በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ እ.ኤ.አ በ2007 በኬንያ የተደረግውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ በተከሰተው ውዝግብ ሰበብ የኬንያ ህዘቦች እልቂት አይፈጸምም ነበር፡፡   
 
ሆኖም ግን አድኃኖም የሮም ስምምነትን አጠቃላይ ሀሳብ ዘለውታል፡፡ ICC የተቋቋመው እያንዳንዱ ነፍሰ ገዳይ ዘራፊ ከቢሮው በምቹ ተሸከርካሪ ወንበር ተቀምጦ ነገ ደግሞ እነማንን ልግደል፣ ልድፈር፣ ላፈናቅል እያለ በሰው ልጆች ስቃይ ላይ ዳግም ስቃይ እየደገሰ ተዝናንቶ በተቀመጠበት ሁኔታ አይደለም የሕግ ጉዳዩ የሚታየው፡፡ ድርጅቱ ዓላማ አድርጎ የያዘው እጅግ በጣም ጨካኝ የሆኑ የወንጀል ተጠርጣሪዎችን ለፍትህ በማቅረብ ለወንጀል ሰለባዎቹ ፍትህን ለመስጠት እና እንደዚሁም ሁሉ በእብሪት በመነሳሳት ወደፊትም በሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ተመሳሳይ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ወንጀሎች እንዳይፈጸሙ ለመማሪያ እንዲሆኑ ማስቻል ጭምር ነው፡፡ ዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በአፍሪካ ውስጥ ያለምንም ተጠያቂነት በሰው ልጆች ላይ ወንጀል በሚፈጽሙ አምባገነኖች፣ የጦር ወንጀለኞች እና የዘር ማጥፋት ወንጀልን በሚፈጽሙ ተጠርጣሪ  ወንጀለኞች ላይ ICC ፍትህን የሚያጎናጽፍ እርምጃ የሚወስድ በመሆኑ በአፍሪካ መሪዎች፣ አምባገነኖች እና ጦረኞች ላይ አስፈሪ እና አስደንጋጭ ሁኔታ መፍጠሩ ከጥያቄ ሊገባ የሚችል ጉዳይ አይደለም፡፡ በሰው ልጆች ላይ ሰብአዊ ወንጀልን በሚፈጽሙ የአፍሪካ አምባገነኖች ላይ ICC ተገቢ የሆነውን እርምጃ የሚወስድ ከሆነ ይህንን እንደ ትምህርት በመውሰድ በአሁኑ ጊዜ በስልጣን ላይ ያሉት አምባገነኖች ከህግ አግባብ ውጭ የእራሳቸውን ዜጎች መብት ከመደፍጠጥ እንደዚሁም ሁሉ በጫካ ውስጥ ተደብቀው ያሉ ጦረኞች ከተደበቁበት ጫካ ውስጥ በመውጣት በዜጎች ላይ አሰቃቂ እና ጭካኔን የተሞለባት ዕልቂት ከመፈጸም ይታቀባሉ፡፡
 
አድኃኖም የሀገር መሪዎች በህግ መጠየቅ የለባቸውም ምክንያቱም እነርሱ የሕግ ተጠያቂ የሚሀኑ ከሆነ የአፍሪካ ሉዓላዊነት ይጣሳል ይላሉ፡፡ እንደ ወንጀለኛ አቀራረብ ስነስርዓት ኡሁሩ እና ሩቶ በፈቃደኝነት ለICC ቀረቡ፡፡ ስለዚህ ምንም ዓይነት የሉዓላዊነት ጥያቄ የለም፡፡ አድኃኖም ምን ለማለት ፈልጎ ነው!? እንደ እርሱ አባባል ሉዓላዊነት ማለት ሀገሪቱ፣ ድንበሯ እና ጠቅላላ ህዝቧ መሆናቸው ቀርቶ ሉዓላዊነት ማለት አንዱ ፈላጭ ቆራጭ የሀገር መሪ ተብዬው ነው፣ ስለዚህ እርሱ የሰብአዊ መብት ደፍጥጦ ለICC የፍትህ አካል የሚቀርብ ከሆነ ሉዓላዊነት ተደፈረ ነው ነው እያሉን ያሉት! ለማሰብ ቀርቶ ለመስማትም ያሳፍራል!
 
የአፍሪካ መሪዎች በሰው ልጆች ላይ ሰብአዊ ወንጀልን ሲፈጽሙ፣ የጦር ወንጀል ሲፈጽሙ እና የዘር ማጥፋት ወንጀልን ሲፈጽሙ ምርመራ እና ለፍትሀ አካል ቀርበው እንዲዳኙ የማይደረገው ለምንድን ነው? አድኃኖም ለዚህ ጥያቄ ምንም ዓይነት መልስ የለዉም፣ ዝም ብሎ ምንም ዓይነት አመክንዮ ሳይኖር በደፈናው ያለምንም ማስረጃ በቀኖናዊነት የሚቀመጥ ካልሆነ በስተቀር ይህ ነው የሚሉት ምሁራዊ አንደበት የላቸውም፡፡ አድሃኃኖም ስለዚህ መሪዎቹ ያለመከሰሳቸው ትክክል ነው ብቻ ነው የሚለው ከዚህ ያለፈ የሚለው ነገር የለም፡፡
 
አድኃኖም ሆን ብሎ በድንቁርና በሰው ልጆች ላይ የተሻሉ እና መጥፎ የሰብአዊ መብት ወንጀሎችን፣ የጦር ወንጀለኞች እና የዘር ማጥፋት ወንጀለኞችን  የሚፈጽሙ የሚባል ነገር የለም፡፡ እንደዚህ ያሉትን ሰብአዊ ወንጀሎች በሚፈጽሙ በአንድ የሀገር መሪ እና በአንድ የጦር ወንጀለኛ መካከል ምንም ዓይነት የሞራል እና የሕግ ልዩነት የለም፡፡ እንደ አድኃኖም ባለ የተንሻፈፈ እና አመክንዮየለሽ ሀሳብ ከሆነ ከአፍሪካ በቋፍ ላይ ካለ የፖለቲካ ሁኔታ አንጻር ምንም ዓይነት የሰብአዊ መብት ወንጀል የሚፈጽም የሀገር መሪ ፍጹም ሊከሰስ አይችልም፡፡ ከፍተኛ የሆነ እልቂት እና ውድመት ፈጽመው ስልጣንን በኃይል የሚቆጣጠሩ አማጺ መሪዎች እና የጦር አበጋዞች ወይም ደግሞ ምርጫን አጭበርብረው ከህዝብ ፈቃድ ውጭ በስልጣን ማማ ላይ ፊጥ የሚሉ ወንጀለኞች እንደ አድኃኖም ባለ ለእራስ አገልግሎት የቆመ እና አስደንጋጭ መርህ የሚከተል እቡይ ካልሆነ በስተቀር እንደ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ለህግ ይቀርባሉ፡፡  
 
እነዚህ የአፍሪካ አምባገነኖች “ርዕሰ ብሄር እና የሀገር መሪ በቢሮ ውስጥ እስካሉ ድረስ በሕግ አይጠየቁም” ይላሉ፡፡ በእርግጥ በስልጣን ላይ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች እንደ ሱዳኑ ኦማር አልባሽር ያሉት ስልጣናቸውን በመጠቀም ለበርካታ አስርት ዓመታት የሰብአዊ መብት እልቂትን እየፈጸሙ የሀገር መሪ በመሆናቸው ምክንያት በሕግ አግባብ የማይሞከሩ አይነኬ፣ ከማንኛውም ዓይነት ተጠያቂነት እና ከሕግ በላይ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የአማጺ፣  ወታደራዊ እና የጦር አበጋዝ መሪዎች እነርሱ እራሳቸውን ብቻ ለዚያች ሀገር መድህን እና ጥሩ መሪዎች አድርገው በማቅረባቸው ምክንያት ያለመከሰስ እና ከሕግ ፊት ያለመቅረብ መብት እንዳላቸው ከመጠየቅ ማን ያግዳቸዋል?
 tewedros adhanom with returnees

በሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያውን/ት ሠራተኞች ስቃይ፣
 
እ.ኤ.አ ሕዳር 2013 በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በሳውዲ አረቢያ ጭካኔ በተመላበት ሁኔታ ሲደበደቡ፣ ሲሰቃዩ፣ እና በሳውዲ አረቢያ አገዛዝ፣ በፖሊስ እና በተራው ህዝብ የውርደት ድርጊት ሲፈጸምባቸው ነበር፡፡ በዚያን ወቅት አድኃኖም በታዛዥነት እና እራስን ባዋረደ መልኩ በኢትዮጵያውያን ላይ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ያካሄደውን አገዛዝ ተጻራሪ በሆነ መልኩ ይቅርታ ጠየቁ፡፡
 
ይኸ ድርጊት ሌላ ሳይሆን በሽታ ነበር፡፡ በወገኖቻችን ላይ ሲደረግ የነበረው የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ወንጀል ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ጊዜ አድኃኖም እንዲህ ብለው ነበር፣ “የሳውዲ ባለስልጣኖች ህገ ወጥ የሆኑ ስደተኞችን መልሶ ወደ ሀገራቸው ለማጋዝ ያወጣውን ፖሊሲ እና ስላስተላለፉት ውሳኔ ኢትዮጵያ ያላትን ክብር ትገልጻለች፡፡“ ይኸ ንግግር በዲፕሎማሲ ቋንቋ አሳዛኝ የሆነ ደንታቢስነት፣ ብቃየለሽነት እና ለተያዘው ቦታ ሊመጥን የማይችል እርባናየለሽነት ነው፡፡ አድኃኖም ኢትዮጵያውያን/ት በሳውዲ አረቢያ በደረሰባቸው ህገወጥ አያያዝ ስሜታቸው የተጎዳ መሆኑን አምነው በመግለጽ ለሳውዲ አረቢያው አምባሳደር ይኸ ተቀባይነት የሌለው ነው በማለት ተናግረው ነበር፡፡ እርሳቸው እና መንግስታቸው ነገሮችን እንዴት ተቆጣጥረው እንዳለ ለማሳየት በሚመስል መልኩ አድኃኖም እንዲህ ብለው ነበር፣ “ወገኖቻችንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እና ለመቀበል ዝግጅታችንን ሁሉ ያጠናቀቅን መሆናችንን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ“    
 
አንድ የእራሱን ዜጎች ሰብአዊ መብት በመርገጥ የሚያዋርድን ሌላ ሀገር ፖሊሲ እንዴት ነው ሊያከብር የሚችለው? አንድ ጤናማ አዕምሮ ያለው ሰው  ዜጎቹ ለተደፈሩበት፣ ለተገደሉበት፣ አካለ ጎደሎ ለሆኑበት፣ለተሰቃዩበት እና በውጭ ሀገር እህት እና ወንድሞቻቸው ለተገደሉባቸው ዜጎቹ እንዴት “ተቀባይነት የለውም” የሚለውን ትርጉመቢስ እና እርባናየለሽ ቃል ምርጫው ያደርጋል? በሳውዲ አረቢያ ሲያልቁ የነበሩትን ወገኖቻችንን ህይወት ለመታደግ እና ግድያውን ለማስቆም አድኃኖም ለሳውዲ አረቢያ አምባሳደር መጮህ ነበረባቸው፡፡ እንዴት አንድ ወገኖቹ የግድያ ሰለባ ሲሆኑ እና ሰብአዊ መብታቸው ተደፍጥጦ እየተሰቃዩ ባሉበት ሁኔታ ግላዊ ጭንቀት እና ሀዘን ይሰማኛል ሊል ይችላል? አንድ ሰው እንዴት የዜጎቹ መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶች በአምባገነኖች ሲጣሱ እና ሲደፈጠጡ እንዴት ምንም ነገር ባለማድረግ ቀዝቅዞ እና የሰብአዊነት ርህራሄ ሳይኖረው ዝም ብሎ ይመለከታል?  እንዴት አንድ ሰው ዜጎቹ ስቃያቸውን እየተቀበሉ እያየ በመበሳጨት ዲፕሎማሲያዊ ቁጣውን እና ንዴቱን መግለጽ ይሳነዋል? በሺዎች ለሚቆጠሩ ስለእህቶቻችን እና ወንድሞቻችን በሞት እና በሽረት መካከል መኖር እየተነጋገርን ነው፡፡ ደህና ይኸ ነው እንግዲህ አሁን በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁ ባለስልጣን እየሰራው ያለው ስራ!
 
እ.ኤ.አ ጥቅምት 2014 የአድኃኖም አንዱ ደጋፊ በሆነው ዘራፊ የዲፕሎማት ከለላ አለው ተብሎ በዋሽንግተን ዲ.ሲ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ጥይት ስለተኮሰው እና ያልተጠበቀ የዲፕሎማሲያዊ ቀውስ እንዲከተል ስላደረገው ሁከት ፈጣሪ ስለነበረው እብሪተኛ መናገር እችላለሁ፡፡ በዋሽንግተን ዲ.ሲ የዲፕሎማቶች መዝገብ ላይ ተቀርጾ የሚገኘው ሰነድ እንደሚያሳየው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብሰብ ሌባ ዲፕሎማት ተብዬ ሰላማዊ አመጸኞችን ከኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ለማባረር በኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ጥይት በመተኮስ ከዓለም የመጀመሪያ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
 
አድኃኖም በዓለም ዋናዋ እና የመጀመሪያዋ የዲፕሎማት ማዕከል በሆነችው በዋሽንግተን ዲ.ሲ ያንን የመሰለ ወሮበላ ምንም ዓይነት የዲፕሎማሲ ልምድ፣ ስልጠና ወይም ደግሞ እንደ ከደህንነት አታሸ ሙያ ጋር ምንም ዓይነት ክህሎት የሌለውን ተራ ማይም ልከው ነበር፡፡ ደህና እስከ አሁን ድረስ ስለወሮበላ ዲፕሎማሲ እና ስለዘራፊ ዲፕሎማት ብዙ ብለናል፡፡
 
በእውነት የብሩክሊንን ድልድይ እጅግ በጣም ርካሽ በሆነ ዋጋ ለሽያጭ ለማቅረብ ዕድሉን አግኝቻለሁ፡፡ የማዲሰን እስኩዌር ጋርደን ህንፃን እንደ ጉርሻ በተጨማሪነት አባሪ በማድረግ እሰጣለሁ፡፡
 
አድኃኖም ፍላጎት ሊኖረህ ይችላል ?
 
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
መጋቢት 8 ቀን 2007 ዓ.ም

The post የኢትዮጵያ የ“ዲፕሎማቶች ቁንጮ” መሳለቅያ ቅጥፈት፣ – ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም appeared first on Zehabesha Amharic.

ሜሮን ጌትነት ከዳና ድራማ ተሰናበተች

$
0
0

Meron Getenet

ከኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ጋር በውዝግብ ውስጥ ሆኖ የሰነበተው ዳና ድራማ አንዴ ሲቆም አንዴ ሲጀመር እዚህ ደርሷል:: ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ድራማውን እናንተ የማትጨርሱት ከሆነ እኔ እጨርሰዋለሁ በሚል እስከማገድም ደርሶ ነበር:: ሆኖም ግን ድራማው ከተወሰኑ ሳምንታት መቋረጥ በኋላ እንደገና የተጀመረ ሲሆን ሊጠናቀቅም ከ7 ክፍል የማይበልጥ እድሜ እንደቀረው ይነገራል::

የድራማው አዘጋጆች በዳና ድራማ ላይ ወሳኝ ገጸባህርይ የነበራትን አርቲስት ሜሮን ጌትነትን ያሰናበቱ ሲሆን እርሷን ተክታ ወጣቷ አርቲስት ዕጸሕይወት አበበ የህሊናን ቦታ እንደምትጫወት የደረሰን መረጃ ያመለክታል::

ከወራት በፊት በአዲስ አበባ በተዘጋጀ የግጥም መድረክ ላይ ባቀረበችው ግጥም በስርዓቱ ባለስልጣናት ጥርስ እንደተነከሰባት ሲገለጽ የነበረችው አርቲስት ሜሮን ጌትነት በአሁኑ ወቅት በሰሜን አሜሪካ እንደምትገኝ ዘ-ሐበሻ ያላት መረጃ ያመለክታል::

ሜሮን አሜሪካ የመጣችው ቀለበት ያሰረችለት ሰው ጋር አብራ ለመኖር ነው የሚሉ የቅርብ ወገኖች ለዘ-ሐበሻ ቢገልጹም ከአርቲስቷ በኩል የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም::

የዳና ድራማዋ ሕሊና ካለ ሜሮን በ ዕጸህይወት እንዴት ይተወን ይሆን? – በቀጣይ ሳምንት የምናየው ይሆናል::
Estehiwot abebe

The post ሜሮን ጌትነት ከዳና ድራማ ተሰናበተች appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live