Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

አንድነት ፓርቲ በፀረ -ሽብር ሕጉ ላይ ሕዝባዊ ንቅናቄ ሊጀምር ነው

$
0
0

UDJ
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከአራት ዓመት በፊት የፀደቀውን የፀረ-ሽብር ሕጉን ለማሰረዝና ይሄንኑ ሕግ ተላልፈዋል ተብለው በእስር ላይ የሚገኙ የፓርቲውን አመራሮችንና ጋዜጠኞችን ለማስፈታት በአይነቱና በይዘቱ ለየት ያለ ሕዝባዊ ንቅናቄ እንደሚጀምር አስታወቀ።
የፓርቲው የስራ አስፈፃሚ አባልና የሕዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዳንኤል ተፈራ በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት የአንድነት ፓርቲ የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ሰለባ ከሆኑ ፓርቲዎች አንዱና ግንባር ቀደሙ መሆኑን በመጥቀስ አዋጁን ለማሰረዝ በሚሊዮን የሚቆጠር የሕዝብ የድጋፍ ፊርማ በማሰባሰብ አዋጁ ሕገ-መንግስቱን በግልፅ የሚጥስ መሆኑን ማስረጃ በማቅረብ ጭምር ክስ ለመመስረት መታቀዱን ተናግረዋል።
የህዝባዊ ንቅናቄ አተገባበሩን በተመለከተም በነገው ዕለት በፓርቲው ጽ/ቤት የፖለቲካ እስረኞች ቤተሰቦች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ወኪሎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ጋዜጠኞች በተገኙበት ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ንቅናቄው መጀመሩ በይፋ እንደሚበሰር አመልክተዋል።
ሕዝባዊ ንቅናቄው “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል የሚጀመር ሲሆን ለቀጣዮች ሶስት ወራትም በተከታታይነት እንደሚቀጥል ከአቶ ዳንኤል ገለፃ መረዳት ተችሏል።
ፓርቲው ባስቀመጠው የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ መሰረት በአዲስ አበባና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች መዋቅሮቹን ሲያደራጅ መቆየቱን ያስታወሱት አቶ ዳንኤል ሕዝባዊ ንቅናቄውን ትርጉም ባለው ደረጃ ማንቀሳቀስ የሚያስችል በአዲስ አበባ በ23ቱም ወረዳዎች እንዲሁም ከአዲስ አበባ ውጪ በዋና ዋና ከተሞች መዋቅር መመስረቱንም አረጋግጠዋል። የሕዝባዊ ንቅናቄውን ዓላማ ከዳር ሊያደርስ የሚችል ግብረኃይል መደራጀቱን አያይዘው አመልክተዋል።
ሕዝባዊ ንቅናቄው የሚካሄደው የድጋፍ ፊርማ በማዘጋጀት፣ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍና የአደባባይ ላይ ሕዝባዊ ስብሰባዎች በማካሄድ እንደሆነም አቶ ዳንኤል ገልፀዋል።

፦ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ


የሙስና ምርመራ እየተወሳሰበ ነው! “መበላላት እንዳይጀመር ስጋት አለ”

$
0
0

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Sheraton Addis, Addis Ababa, Ethiopia

Sheraton Addis, Addis Ababa, Ethiopia

በጉምሩክና ገቢዎች ባለስልጣን የተጀመረው የጸረ ሙስና ዘመቻ ተከትሎ እየተካሄደ ያለው ምርመራ እየተወሳሰበ መሔዱ ተሰማ። በከፍተኛ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ተከሳሾች የሚሰጡት መረጃ መበላላት ያስነሳል የሚል ፍርሃቻ እያስነሳ ነው። “ሰፈር የለየው” የጸረ ሙስና ዘመቻ የፈጠረው ስጋት የሃይል ሚዛን የያዙትንም ስጋት ውስጥ ከትቷል።

በኢትዮጵያ ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ የታየው የውስን ሰዎች በድንገት በመበልጸግ ከባለስልጣኖችና ከከፍተኛ የስርዓቱ ሰዎች ቤተሰቦች ጋር በሚከናወን መተሳሰር አማካይነት እንደሆነ ከህዝብ የተሰወረ አይደለም። ሰሞኑንን ይፋ የተደረገው የባንክና የንብረት እግድ እንዳመለከተው የዝርፊያው ሰንሰለት በቤተሰብ የታጠረ መሆኑን ነው።

አቶ መለስ ከድነው ያቆዩትና የሳቸውን ሞት ተከትሎ ከፖለቲካው ልዩነት ጋር በተያያዘ እንደተጀመረ የሚነገርለት የጸረ ሙስና ዘመቻ፣ በመንግስት በኩል “ቆራጥ” አቋም የተያዘበት እንደሆነ ቢነገርም አስጊ ሁኔታ እየተፈጠረ ስለመሆኑ የጎልጉል የጸረ ሙስና ኮሚሽን ምንጮች ይናገራሉ።

እየተካሄደ ካለው ምርመራ በተገኙ ጭብጦች መታሰር የሚገባቸው ባለስልጣናት እንዳሉ የሚጠቁሙት እነዚሁ ክፍሎች፣ ምርመራው እየሰፋና እየጠለቀ ሲሄድ ችግር ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት ማሳደሩን አይሸሽጉም።

“የመጨረሻው መጠፋፋት መጀመሪያ ላይ እንዳሉ የሚሰማቸው አሉ” በማለት ለጎልጉል መረጃ የሰጡት ክፍሎች “እየሰፋ የሄደውንና መጨረሻው ወዴት እንደሚያመራ የሚታወቀውን የጸረ ሙስና ዘመቻ የማስቆም ፍላጎት እንዳለ የሚያመላክቱ ሁኔታዎች በቢሮ ደረጃ እየሰማን ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ ዘመቻው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት የሚሉ ክፍሎች ስላሉ በሙስና የሚጠረጠሩ ፕሮጀክቶችና ከፍተኛ ግንባታዎችን አስመልክቶ በስፋት መረጃ የሚደርሰው ኮሚሽኑ፣ ከነገ ዛሬ ይመጣብናል በሚል የተፈጠረው መደናገጥ በህገወጥ ሃብት የሰበሰቡትን በሙሉ ስጋት ላይ ጥሏቸዋል። በባንኮች አካባቢ ገንዘብ የማሸሽ፣ ከዶላር ገበያ ራስን የማግለልና የሃይል ሚዛን በመመልከት የመተጣጠፍ ሩጫ በስፋት እንደሚስተዋል የጎልጉል ሰዎች ተናግረዋል።

በሙስናው ሰለባ የሆኑት ቡድኖች አቅማቸውና ትስስራቸው ቀላል ባለመሆኑ፣ የታጠቁ ሃይሎችም ስላሉበት የርስ በርስ መተላለቅ ሊከተል ይችላል በሚል ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚደረግ ያመለከቱት ምንጮች “አቶ መለስ የዘረጉትን ሰንሰለት ሙሉ በሙሉ የመቆጣጠር ችግር እየታየ ነው። መተላለቁ በዚህ ክፍተት ውስጥ ሊከሰት ይችላል” የሚል ስጋት መንገሱን አመልክተዋል።

የሚታወቁ ባለስልጣናትና የክልል አመራሮች “ልማታዊ” ከሚባሉት ኢህአዴግ ሰራሽ ባለሃብቶች ጀርባ ሆነው ፕሮጀክትና ጨረታ በማጸደቅ ምዝበራውን እንደሚመሩ መረጃ ስለመኖሩ የሚናገሩት ምንጮች፣ “በቅርብ ተመስርተው ከፍተኛ ሃብት በሰበሰቡ ሪል ስቴት፣ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች፣ አስመጪና ላኪዎች፣ ሰፋፊ መሬት ለአረብ አገር ባለሃብቶች በማስማማት አየር በአየር የሚጫወቱ፣ በአገሪቱ ከሚታዩት ታላላቅ ግንባታዎች ጋር በተያያዘ ወዘተ ዋናዎቹ ባለስልጣኖችና ቤተሰቦቻቸው ተዋናይ መሆናቸው ይታወቃል። የህወሃት ሰዎች ግንባር ቀደም ናቸው” በማለት የስጋቱን መጠን ይገልጻሉ።

ከአገር ውስጥ በተጨማሪ በአፍሪካና በተለያዩ አገራት የሽርክና ንግድ የከፈቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዳሉ የሚገልጹት የኢህአዴግ የቅርብ ሰዎች “አሁን አመራር ላይ ያሉት የህወሃት ሰዎች የእነዚህን ባለስልጣናት በቤተሰብና ከፍተኛ አቋም በገነቡ ድርጅቶች አማካይነት የተበተቡት ሰንሰለት በቀላሉ መበጠስ ስለማይችሉ የሙስናው ዘመቻ አደጋ ይገጥመዋል። አለያም እርስ በርስ መበታበት ሊከተል ይችላል” በሚል ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከቀረጥ ነጻ በማስገባት ከፍተኛ የመንግስት ገቢ ለግል ተጠቅመዋል በሚል በተከሰሱት ሰዎች ላይ እየተካሄደ ባለው ምርመራ ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ በከፍተኛ ባለስልጣናት ትዕዛዝ አማካይነት የቀረጥ ነጻ ፈቃድ መስጠታቸውን ለምርመራ መኮንኖች መናገራቸውን የጎልጉል ምንጮች አመልክተዋል።

በዚህም የተነሳ ሸራተንን ተገን ያደረጉት የባለሃብቱ ወኪል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መውደቃቸው ተሰምቷል። በነባር የህወሃት ሰዎች የማይወደዱት እኚሁ የባለሃብቱ ወኪል፣ ወ/ሮ አዜብን፣ አቶ አዲሱ ለገሰና የባለሃብቱ ዋና ሸሪክ የሆኑትን አቶ በረከትን ቢተማመኑም ምርመራው ወደእርሳቸው ሊሄድ እንደሚችል የጎልጉል ምንጮች ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል። አንዳንዶቹ የቀድሞ ሸሪኮቻቸው ስልካቸውን ስለማያነሱላቸው ጭንቀት ውስጥ መግባታቸውና ከወትሮው የተለየ ያለመረጋጋት እንደሚታይባቸው የቅርብ ሰዎቻቸውን ሳይቀር ሰላም እንደነሳ ለማወቅ መቻላቸውንም ተናግረዋል።

አብዛኛውን የንግድ በሮች በስጋ ዘመዶቻቸውና በአገር ልጆች ተብትበው የያዙት የባለሃብቱ የኢትዮጵያ ወኪል ምርመራ ዙሪያ የሚነሱትን ጉዳዮች ከመጥቀስ የተቆጠቡት ምንጮች፣ በቅርቡ አዲስ ነገር እንደሚሰማ መረጃዎች እንዳሏቸው አመልክተዋል። ለሸራተኑ ሰውና ለሸራተኑ ቡድኖች እጅግ ቅርብ ነን የሚሉ በበኩላቸው “ወ/ሮ አዜብ መስፍንና አቶ አዲሱ ለገሰ እስካልተነኩ ድረስ ሸራተን ሰላም ነው። አቶ ጌታቸውም እዛው ናቸው” ሲሉ የለበጣ ቀልድ ቀልደዋል። እነዚሁ ክፍሎች ቢያንስ “የኤች አይ ቪ/ኤድስ እድሜ ማራዘሚያ እናመርታለን፣ ለወገን እንደርሳለን በሚል ሰበብ በከፍተኛ ማጭበርበር የተፈጸመውን ወንጀል ጉዳይ ዝም አይበሉት” ሲሉ ለጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ አደራቸውን አስተላልፈዋል።


Source: በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

ኢትዮጵያ የደቡብ አፍሪካው ጨዋታ ተጨማሪ 3 ነጥብ አይቀነስባትም ሲሉ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ተናገሩ

$
0
0

Ethiopia national team
ከይርጋ አበበ

ኢትዮጵያ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያው ከቦትስዋና ጋር ሎባትሴ ላይ ባደረገችው የመልስ ጨዋታ ላይ ሁለት ቢጫ የማስጠንቀቂያ ካርድ የተመለከተውን ምንያህል ተሾመን አለአግባብ ማሰለፏን ተከትሎ በርካታ የደቡብ አፍሪካ የመገናኛ ብዙኃን « ተጫዋቹ አንድ ጨዋታ መቀጣት ሲገባው ሳይቀጣ ከደቡብ አፍሪካ ጋር በተደረገው ጨዋታ ላይ ተሰልፏልና በጨዋታው የተመዘገበው ውጤት ተሰርዞ ደቡብ አፍሪካ ፎርፌ ማግኘት አለባት » የሚሉ ዘገባዎችን በስፋት አሰራጭተዋል።
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ሳህሉ ገብረወልድ በሰጡት አስተያየት « ኢትዮጵያ ተገቢ ያልሆነ ተጫዋች በማሰለፏ የምትቀጣው ተገቢ ያልሆነው ተጫዋች የተሰለፈበት ጨዋታ ውጤትን ብቻ ነው። በመሆኑም ተጨማሪ ሦስት ነጥብ ፈጽሞ አይቀነስባትም » ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ከዓለም አቀፉ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (ፊፋ) ጋር በስልክ መነጋገራቸውንና ፊፋም በአንድ ጥፋት ሁለት ጊዜ ቅጣት እንደማይጣል እንዳረጋገጠላቸው አብራርተዋል።
የተለያዩ የደቡብ አፍሪካ መገናኛ ብዙኃን ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ ረስተንበርግ፣ ኢትዮጵያና ቦትስዋና አዲስ አበባ ላይ ባደረጉት ጨዋታዎች ላይ ሁለት የማስጠንቀቂያ ቢጫ ካርዶችን የተመለከተውና የሚቀጥለውን ጨዋታ ማረፍ ሲገባው ሎባትሴ ላይ ከቦትስዋና ጋር በተደረገው ጨዋታ የተሰለፈው ምንያህል ተሾመ ዋሊያዎቹ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ባለፈው እሁድ ባደረገችው ጨዋታ ላይ ተሰልፎ መጫወቱ ተገቢ አለመሆኑን በመጥቀስ በስፋት ጽፈዋል።
መገናኛ ብዙኃኑ የአገሪቱ እግር ኳስ ማህበር ጉዳዩን ወደ አወዳዳሪው አካል ፊፋ እንዲወስደውና በጨዋታው የተመዘገበው ውጤት ተሰርዞ ለአገራቸው እንዲሰጥ አቤት እንዲልም ጠይቀዋል። ይህንን ሐሳባቸውን የሚደግፉ «ባለሙያዎችንም» ቃለ መጠይቅ በማድረግ ሃሳቡን ለማጉላት ሞክረዋል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ሳህሉ ገብረወልድ ግን ይህ ሃሳብ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለውና የሕግ ድጋፍ የማይገኝለት መሆኑን ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ አክለውም ፊፋ የምንያህል ተሾመን ጉዳይ እንደሚያጣራ በላከው ደብዳቤ ላይ ተጨማሪ ቅጣት እንደሌለ ማረጋገጡንም አስታውቀዋል።
የፊፋ የዲስፕሊን መመሪያ አንቀጽ 19 ንጹስ አንቀጽ 5 መሠረት አንድ ጊዜ ፎርፌ የተሠጠበት ጨዋታ ለዳግም ቅጣት አይዳርግም እንደሚልም ተናግረዋል። ይህ ማለት ምንያህል ተሾመ በቦትስዋናው የመልስ ጨዋታ ላይ ማረፍ ሲገባው በመጫወቱ ቦትስዋና በፎርፌ ኢትዮጵያን ሦስት ለባዶ እንዳሸነፈች ተደርጎ ስለሚቆጠር ተጫዋቹ በደቡብ አፍሪካ ጨዋታ ላይ በመሰለፉ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ቅጣት አይጣልባትም።
ኢትዮጵያ ሁለት ቢጫ ያለው ተጫዋች በማሰለፏ ከሚቀነስባት ነጥብ በተጨማሪ ስድስት ሺ የስዊዝ ፍራንክ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልባትም ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሜዳው ውጪ ቦትስዋናን በማሸነፍ ያገኘው ሦስት ነጥብና ሦስት ግብ ቢቀነስበትም ምድብ አንድን በአስር ነጥብና በአንድ ንጹሕ ግብ የሚመራ ይሆናል። ጷጉሜ ሁለት ቀን 2005ዓ.ም ከሜዳው ውጪ ከመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ጋር የሚያደርገውን የመጨረሻውን የዓለም ዋንጫ ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ ለቀጣዩ የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ ማለፉን ያረጋግጣል።
የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አቶ ሰውነት ቢሻው ቡድናቸው ጠንካራ ዝግጅት አድርጎ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክን በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ማጣሪያ እንደሚያልፉና ሕዝቡን እንደሚክሱ ከትናንት በስቲያ መግለጻቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
በተያያዘ ዜና እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ ያልተገባ ተጫዋች በማሰለፏ ምርመራ እየተደረገባት የምትገኘው ቶጎ ሎሜ ላይ ከካሜሩን ጋር ባደረገችውና ሁለት ለባዶ ባሸነፈችው ጨዋታ ላይ ያልተገባ ተጫዋች ማሰለፏን አምናለች።
የአገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ቱሳ ኮሚ ጋብርኤል ለቢቢሲ በሰጡት አስተያየት አሌክሲስ ሮማኦ የተባለው ተጫዋች ከካሜሩን ጋር በተደረገው ጨዋታ መሰለፍ እንዳልነበረበት አምነው ጉዳዩን በተመለከተ ለፊፋ ምንም ዓይነት ማስተባበያ እንደማያቀርቡ አሳውቀዋል።

ጅቡን ከነሕይወቱ አጥምዶ በአህያ ጋሪ በመጫን በመቂ ከተማ ሲዘዋወር የነበረው ግለሰብ ታሰረ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) “ወይ ጉድ!” ሊያስብል የሚችል ዜና እንደሆነ ይሰማናል። ይህን ዜና ከነምስሉ የበተነው በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሥር የሚታተመው ‘ፖሊስና እርምጃው” የተሰኘው ጋዜጣ ነው።
Police and Ermejaw
“ይህ የምትመለከቱት ፎቶ ሰሞኑን በምሥራቅ ሸዋ ዞን ቱግጃ ወረዳ መቂ ከተማ ውስጥ የተከሰተ ሲሆን በምስሉ ላይ የሚታየው ተከሳሽ ጅቡን አጥምዶ ከነሕይወቱ በመያዝ በአህያ ጋር ጭኖ መቂ ከተማ ውስጥ ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ በመዘዋወር ላይ ሳለ በህብረተሰቡ ጥቆማ መሠረት በቁጥጥር ስር ውሏል። ተከሳሹ በምን ምክንያት እና ለምን ጅቡን እንደያዘው ለፖሊስ ያልገለጸ ሲሆን እንስሳትን በማንገላታት ክስ ተመስርቶበት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ይገኛል” ይላል ሰሞኑን ታትሞ የወጣው የፖሊስ እና እርምጃው ጋዜጣ ዘገባ።
police and irmejaw“ሰው የሚያስብ እንስሳ” ነው ሲሉ ተመራማሪዎች ይገልጻሉ። የ እንስሳት መብት አይከበር እያልን ሳይሆን፤ የሚያስበውን ሰው በአሸባሪነት በመክሰስ፣ እንደፈለገው እንዳይንቀሳቀስ በማገድ የሚታወቀው መንግስት ደርሶ ለእንስሳት ተቆርቋሪ መስሎ በሚዲያ መቅረቡ የሚያስገርም ነው። ጅቡን አንገላታ የተባለው “እንስሳትን የማንገላታት አንቀጽ” ተጠቅሶበት ታሰረ፤ እነ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ነፃ አሳቢ የፖለቲካና የሃይማኖት መሪዎችን እስር ቤት እያንገላቱ ያሉትስ? ነው ወይስ “መንግስታችን” የቆመው ለማያስቡ እንስሶች ብቻ ነው?

ዘ-ሐበሻ አስተያየትዎን ጨምሩበት ስትል ትጋብዛለች።

የጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች ኢትዮጵያዉያን አይደሉምን ? ታዲያ ለምን?

$
0
0

አበራ ሽፈራው                                                      

 ከጀርመን                                                                                                  

አበራ ሽፈራው

አበራ ሽፈራው

የኢትዮጵያዉያንን ችግር ያባባሰዉ ጉዳይ ህወሐት / ኢህአዴግ እንድንለያይ ከመታወቂያችን ጀምሮ እየጸፈ የስጠን የብሄርህ ማነዉ ጥያቄ አንዱ ነዉ ለማለት ያስደፍራል።የዚህ ጥያቄ ክፋታዊ እቅድ እውስጣችን ሳናዉቀዉ አድጎና ቅርንጫፍ አዉጥቶ በመቀጥሉና ከዉስጣችን ባለመጥፋቱ ጉዳቱ አሁን አሁን ጐልቶ እየታየ ነው ። በዚህም ምክንያት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እራሱን አጥብቦ እንዲያይና  ከጎሳ አልፎ ወደ ጎጥ እንዲወርድ ተደርጓል። ይህም ኢትዮጵያዊነቱን እየጎዳ እንዳለ ይታያል ። ከዚህ የተነሳ ህወሐት እንደፈለገዉ ህዝቡን እንዲጨቁን እድል እንደፈጠረለት ልንገነዘብ ይገባናል ። እዚህ ላይ ግን ኢትዮጵያዊያን ስለጎሳቸዉ ፣ስለባህላቸውና ስለቋንቋቸው እንዲሁም ሌሎች ማንነታቸዉን በሚገልጹ ጉዳዮች ላይ አያስቡ ወይም አይሳተፉ ማለቴ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ።

 

በየትኛውም ጎሳና ክልል ልወለድ ፣የትኛውንም ቋንቋ ልናገር ፣የትኛዉም ባህል ይኑረኝ አንድ ነገር ይገባኛል፤እርሱም ኢትዮጵያዊ መሆኔ።ኢትዮጵያዊ ነኝ ካልኩኝ ደግሞ የተወለድኩበት ወይም ያደኩበት ማህበረሰብና ቦታ ብቻ ሳይሆን ከሰሜን እስከ ደቡብ ፣ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ያለው ሁሉ የኢትዮጵያ የምድር መዳረሻ ሁሉ የእኔም ሃብትና ንብረት መሆኑ፤መኖሪያዬ መሆኑ ፤ህዝቡም ወገኔ መሆኑ፤ የህዝቡም ችግር የእኔም ችግር መሆኑ፤ የህዝቡ ደስታም የእኔም ደስታና ሃዘኑም ሃዘኔ መሆኑም ጭምር ነው ።

 

በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊነቴ ሁሉንም የሚወድ፣የሚቀበል፣ባህላቸዉንና ታሪካቸውን የሚያከብር መሆን ይኖርበታል። ኢትዮጵያዊነቴ የማያዳላና ራሱን ብቻ የማይወድ መሆን ይኖርበታል። ኢትዮጵያዊነቴ አንድነትን በልዩነት ዉስጥ ወይም ልዩነትን በአንድነት ውስጥ ተቀብሎ የሚጓዝ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት። ኢትዮጵያዊነቴ ከጎሳና ከዘር ይልቅ ለሰብአዊ መብት መከበር ቅድሚያ መስጠት አለበት። ኢትዮጵያዊነቴ ሁሉንም የአገሪቷን ህዝቦች በእኩልነት የሚመለከት መሆን አለበት። ኢትዮጵያዊነቴ አገራዊ ፣ ሰፋ ወደ አለና ለትውልም ጭምር ማሰብ አለበት ።

አንድ ነገር ሁሌ ያሳዝነኛል ።እርሱም ህወሐት የአገሪቷን ህዝብ ከፋፍሎ ለመግዛት የተጠቀመበት በማር  ውስጥ  የተቀበረ ሬት የሆነዉ ይህ ተግቶ ለመለያየት የሰራበት ክፋታዊ እቅዱ ምን ያህል ዘልቆ በኢትዮጵያዊያን ላይ ተጽዕኖ እንደፈጠረ ነው ። ለማስረጃነት ያህልም በሃገር ውስጥ ከሚታየዉ ልዩነት ይልቅ በውጭዉ ያለን ኢትዮጵያዊያን በዚህ ችግር ተተብ ትበን ለመቀራረብ ትልቅ ማነቆ ሆኖ መቆየቱ ግልጽ ነዉ ።ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ችግሩ እየተሰበረ መምጣቱና መሻሻል እየታየበት መሆኑ ደስ የሚያሰኝ ጅምር ነው ።ይህም በህወሐት መንደር ትልቅ ድንጋጤ እንደሚፈጥር ይታወቃ ል።የአንድ አገር ህዝቦች ሳለን ላለፉት የህወሐት የገዥነት አመታት ሆድናጀርባ ሆነን የቆየንባቸዉን ችግሮች ለመፍታት እንነሳ። በዚህም ለወደፊቱም የሚፈጠሩ ችግሮችን አሁን እየፈታናቸው እንድንሄድ ያስችሉናል።

ይህንን ጉዳይ ለመቅረፍ ከጸሐፊዎች፣ከጋዜጠኞች፣ከፖለቲከኞችና በዚህ ዘረኛ መንግስት የተጠቁ ሁሉ ሊያስቡበት የሚገባ ጉዳይ ነው ብዬ አምናለሁ ።ትኩረትም ተሰጥቶት መነጋገር ቢቻል ተገቢነዉ እላለሁ ።

ለጽሁፌ መነሻ የሆነኝ ጉዳይ በቅርቡ በአገራችን ኢትዮጵያዊያ ጋምቤላ ክልል በህዝቡና በመሬቱ ላይ እየተፈጸመ ስላለዉ ጉዳይ ወደ ኢንተርኔት ስገባ የተመለከትኳቸው ጽሁፎች ናቸዉ ።የተወሰኑ ኢትዮጵያዉያን በጉዳዩ ላይ ጽፈዋል።በዋናነት ግን የጻፉት የውጭ ሰዎች ወይም ሚዲያዎች ናቸዉ ። የኢትዬጵያ ሳተላይት ቴሌቨዥንና ሬዲዬ /ኢሳት/ ሽፋን ሰጥቶታል።ይህ በጋምቤላ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ህዝብ ባለፉት ዓመታት ከደረሰበት የዘር ማጥፋት ዘመቻ ሳያገግም በተከታታይ የሚደርስበትን የተቀናጀ ጥቃት መስማትና ማየት ሁሉንም ኢትዮጵያዊያንን የሚያም ድርጊት ነዉ ብዬ አምናለሁ ።አሁንም በዚህ ህዝብ ላይ የሚፈፅመዉ ግፍ አላቆመም ቀትሏል።

ሂዪማን ራይት ዎች እንደ ጊርጎርያን አቆጣጠር በማርች 24 /2005 ባወጣዉ ረፓርት ላይ እንደገለጸዉ በዲሴምበር 13/2003 በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት 43ኛ ክፍለ ጦር እና ሌሎች ስቪል ታጣቂዎች በጋምቤላ በአኟኮች ላይ የተፈጸመዉ ግፍ ቀላል እንዳልነበር ገልጻል። ጥቃቱም ዒላማ ያደረገዉም ወንዶችን እንደነበረና ከዚህም በተጨማሪ ሴቶች በወታደሮች ተደፍረዋል።በዚህ ጥቃት 424 ሰዎች መገደላቸዉን ጽፏል።ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ሰዎች ህይወታቸዉን ለማዳን ወደጫካ መሽሻቸዉን፣ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመጠለል መገደዳቸዉን፣ወደከተማ በመሄድ ቅርብ ዘመዶቻቸዉጋ ለመጠለል እንደሞከሩና ሌሎችም ከሃገር መሰደዳቸዉን ገልጻል።ለበለጠ መረጃ www.hrw.or HYPERLINK “http://www.hrw.org/”g መመልከት ይቻላል።

ከዚህ በጨማሪ የአኟክ የፍትህ ካዉንስል /Anuak Justice Council/ ስለዚሁ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲያብራራ በዚሁ ቀን ማለትም በዲሴምበር 13/2003 424 ሰዎች መደብደባቸዉንና ከዚያም መገደላቸዉን ጽፏል።ድርጊቱ የተፈጸመዉ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደሮችና በሌሎች አናሳ ነዋሪዎች በተቀነባበረ የጅምላ ጭፍጨፋ እቅድ እንደሆነ ገለጿል።ከዚህ ጊዜ በኋላም 2,500 ሰዎችም በተጨማሪ መገደላቸዉን ጽፏል።በዚሁ የግድያ ወቅት በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ተቃጥለዋል፣በመቶዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ተደፍረዋል፣የሚመገቡአቸዉ እህሎችና የቤት እንስሳትም ወድመዋል፣አኟክ ፓሊሶች ትጥቅ እንዲፈቱ ተደርጓል፣በመንግስት ስልጣን የነበሩ ተወግደዋል።ከዚህም የተነሳ ከ51,000 በላይ አኟኮች ክልሉን ጥለዉ እንዲሰደዱ ተደርጓል።ለበለጠ መረጃ Anuak Justice Council ዌብ ሳይትን  HYPERLINK “http://www.anuakjustice.org/”www.anuakjustice.org መመልከት ይቻላል።

አሁን ደግሞ በዚሁ በአገራችን ኢትዮጵያዊያ የጋምቤላ ክልል ህዝቡን በግድ በማፈናቀል 42% የሚሆነዉንና በስፋቱ ከኒዘርላንድ አገር ጋር ሊወዳደር የሚችልን መሬት በግፍ ከህዝቡ ነጥቆ በማን አለብኝነት ለውጭ ሰዎችና ለህወሐት ደጋፊዎች በልማት ስም ለመሸጥ የሚደረገዉን እያየን ምነዉ ዝም አልን?። በዚህ ዙሪያ እየሰሩ ያሉና እየታገሉ ያሉትን ሳላመሰግን አላልፍም ።ጉዳዩ የሁላችንም ነዉ፤ ስለሆነም ለምንዝም እንዳልን እራሳችንን በመጠየቅ ዝምታዉ ይሰበር።

 

ትኩረት ያልሰጠነዉ ካለን ቀላል ነገር አይደለምና ትልቅ ትኩረት ልንሰጠዉ ይገባል እላለሁ።ዛሬ ወገኖቼ አንድ ነገር በድፍረት እጠይቃለሁ። ኢትዮጵያዊያዊ ነህ/ሽ ?።አዎ ካልከኝ/ሽኝ ለዚህ ችግር ሌላ ሰዉ የለምና ይህም ችግር አሳሳቢ ነዉና ሌላ ጊዜ ለወገንህ እንደተሰበሰብህ ፣ሰልፍ እንደወጣህ፣እንደተቃወምህ ዛሬም ትልቅ ሊያዉም ተደጋጋሚ ችግር በህዝቡ ላይ እየደረሰ ይገኛል።ይህ የህዝቡ መከራ የሁላንም ችግር ነውና ሁላችንም ኢትዬጵያውያን በችግሩ ላይ እንሰባሰብ፣ሰልፍ ይደረግ ፣እንቃወም ፣መፍትሔም እንፈልግ ፣የፓለቲካ ፓርቲዎችና ስቪክ ማህበራትም ስብሰባቸዉ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥተዉ ይነጋገሩበት መፍትሄም ያስቀምጡለት።ጉዳዩ በሰብዓዊ ፍጡር ላይ የሚፈጸም ትልቅ ግፍ ነዉና ዝምታዉ ይሰበር።

ከዚህ በፊት በዚሁ ክልል የተፈጸመዉን ግፍ ኢትዬጵያዉያን  እንዳናውቀዉ ተደርጎ ነበር።ነገር ግን ጉዳዩ በጥቂት ሰዎች ጥረት በዓለምና በኢትዬጵያውያን ዘንድ እየታወቀ ከመጣ በኋላ እጅግ ብዙ ህዝብን ያስደነገጠ ነበር ። የህወሐትን ጭካኔንም ያሳየና በታሪክም ለዘመናት የማይረሳ ድርጊት ሆኖ ተመዝግቧል ። ዛሬ ደግሞ በማን አለብኝነት በጋምቤላ ህዝብ ላይ ትልቅ ፈተና ተጋርጧል ። ፈተናዉ የሁላችንም ፈተና ነዉና በዚህ መጥፎ የታሪክ አጋጣሚ ለህዝባችን አለኝታነታችንን ልናረጋግጥለት ይገባል። በዚህም የህወሐት የመከፋፈል ሴራ በተግባር ይፈነቃቀል ። ይህንን ትልቅ የሃገር ጉዳይ በዝምታ ማየቱ ተገቢ አይደለምና ዝምታዉ  ይሰበር።እንደኔ  ሁሉም እራሱን እንዲጠይቅ እመክራለሁ ፤ካልሆነ ግን በታሪክ አጋጣሚ እኛም ከመጠየቅ አናመልጥም ።

 

እግዚአብሔር  ኢትዮጵያን  ይባርክ

 

የአባይ ግድብ ዲፕሎማሲ አጀንዳ! (ከግርማ ሞገስ )

$
0
0

 

The Nile River has become a point of contention between Egypt and Ethiopia.

The Nile River has become a point of contention between Egypt and Ethiopia.

በአለም አቀፍ ደረጃ እንደ አባይ ግድብ አወዛጋቢ የሆኑ ጉዳዮች ተፈጻሚነት የሚያገኙት አለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ትግል በማድረግ አለም አቀፍ ደጋፊ ማብዛት ሲቻል ነው። የዲፕሎማሲ ትግል ደግሞ ሰላማዊ ትግል ትግል በመሆኑ ብስለት እንጂ ክፉ ቃል አይሻም። ቀረርቶ ደጋፊን አስበርግጎ እንደሚያርቅ እና ለባላንጣ የማጥቂያ ቀዳዳ እንደሚከፍት ግልጽ ነው። የሆነው ሆኖ ይኽን ጽሁፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ የህውሃት ውጭ ጉዳይ ቴዎድሮስ እና አቻው የግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰኔ 11 ግድም ዲፕሎማሲያዊ ውይይት አደረጉ ከተባለ በኋላ ቴዎድሮስ “አብረን እንዋኛለን ወይንም እንሰምጣለን” ማለቱን ካነበብኩ በኋላ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ኃይሎች ጋር ውይይት መክፈት ያስፈልጋል የሚል እምነት ስላደረብኝ ነው።

 

“አብረን እንዋኛለን ወይንም እንሰምጣለን” የሚለው የቴዎድሮስ አባባል “ግብጽ እና ኢትዮጵያ ላይፋቱ ተጋብተዋል” ከሚለው የአምባገነን መሰል አባባል ብዙም የራቀ አይደለም። ሁለቱም ህውሃታዊ አነጋገሮች ናቸው። ስሜት በመቀስቀስ ኢትዮጵያውያንን ለማስከተል እና ስልጣን ለማጠናከር። የቀድሞው የህውሃት ውጭ ጉዳይ ስዩም መስፍን በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ምን ሲል እንደነበር፣ በመጨረሻ ግን ጦርነቱ እና የባድመ ጉዳይ እንዴት እንዳከተመ እናስታውሳለን። ቴዎድሮስም ከስዩም መስፍን የተለየ አደለም። ትናንት ኤርትራን አስገነጠሉ። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትም አብረው ነበሩ። ዛሬም አብረው ናቸው። የሆነው ሆኖ የዲፕሎማሲ ትግል ‘አብረን እንዋኛለን ወይንም እንሰምጣለን” ከሚለው  አባባል ባሻገር እጅግ ሰፋ ያለ ነው። የዲፕሎማሲ ትግል ህግ፣ ፍትህ፣ ታሪክ፣ ሳይንስ፣ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ ሰበዓዊ እና ግብረገባዊ አድማሶች ያሉት የትንታኔ፣ የክርክር፣ የማግባባት፣ የማሳመን ትግል ነው። በተጨማሪ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ከልብ መደረግም አለበት።

 

ከ1938 እስከ 1945 ዓ.ም.  በነበረው በዚያ በጨለማ ዘመን እንኳን እነ ሎሬንዞ እና አክሊሉ ኃብተ ወልድ ከአለም አቀፍ ህግ አማካሪያቸው ከስፔንሰር ጋር ሆነው ኤርትራን ከኢትዮጵያ ለመቀላቀል ባደረጉት ዲፕሎማሲያዊ ትግል የእነ ካናዳን፣ ህንድን፣ ኖርዌይን፣ ግሪክን እና ሌሎች በርካታ አገሮችን ድጋፍ ሊያገኙ የቻሉት ዲፕሎማሲያዊ ትግላቸው በሳል በመሆኑ ነበር። ከልባቸው ያደረጉትም ትግል ስለነበር ነው። በቅድሚያ በምርምር እና በጥናት የተመሰረተ በሳል የዲፕሎማሲ ትግል አጀንዳዎች በመቅረጻቸው ነበር። ዛሬ ጊዜውም እንደያኔ ጨለማ አይደለም። የኃያላን መንግስታት አስተሳሰብ ከቅኝ ገዥነት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ተለወጧል። ዛሬ አፍሪካውያን በተባበሩት መንግስታት ከ50 በላይ መቀመጫ አላቸው። ያኔ እነ ሎሬንዞ እና አክሊሉ ኃብተ ወልድ በተባበሩት መንግስታት መድረክ ለኢትዮጵያ ከልባቸው ሲታገሉ መቀመጫ የነበራቸው እና የድጋፍ ድምጽ የሚሰጡዋቸው ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ ብቻ ነበሩ። ለፍትህ የሚደረግ የዲፕሎማሲ ትግል ከዚያ ከጨለማ ዘመን ይልቅ ዛሬ የማሸነፍ እድሉ ከፍተኛ ነው። ሆኖም ግን በሳል የዲፕሎማሲ ትግል አጀንዳዎች መቀመር እና ከልብ መታገል ያስፈልጋል።

 

ኢትዮጵያ የምታካሂደው የዲፕሎማሲ ትግል ከግብጽ ሳይንትስቶች፣ መሃንዲሶች፣ የህግ አዋቂዎች እና የዴሞክራሲ ኃይሎች ጋር ውይይት መክፈት ቢችል እና በአለም አቀፍ መድረክ ደግሞ የአፍሪካ ህብረትን፣ የተባበሩት መንግስታትን፣ የአሜሪካን፣ የአውሮፓን፣ የአለም ባንክን፣ የአይ.ኤም.ኤፍን ድጋፍ ማግኘት ቢችል ግንባታው ቀላል ይሆናል። ስለዚህ የዲፕሎማሲ ትግሉ ጥናት ላይ የተመሰረቱ አጀንዳዎች ሊኖሩት ይገባል።  የቀድሞ አባቶቻችንን ድሎች እየጠቀሱ እኛም እንደግመዋለን አይነት አኪያሄድ አይጠቅምም። የሚከተሉት የዲፕሎማሲ አጀንዳዎች ለኢትዮጵያ አባይ ግድብ ግንባታ ዲፕሎማሲ ትግል ሊያገለግሉ ይችላሉ የሚል እምነት አለኝ፥

 

አጀንዳ አንድ (1)፥ ግድቡ በሸለቋማ ቦታ ላይ በመገንባቱ በትነት የሚባክነውን ውሃ ዝቅተኛ ያደርጋል።

 

አጀንዳ ሁለት (2) በግድቡ የሚሰበሰበው ውሃ ቁልቁል ሲለቀቅ መዘውሮችን (Turbines) በመምታት ያመቀውን ኃይል (Energy) ወደ መዘውሮቹ ካስተላለፈ (እንዲሽከረከሩ በማድረግ) በኋላ የሚስፈነጠረው ውሃ ወደ ኢትዮጵያ ሳይሆን ወደ ሱዳን ስለሚፈስ ወደ ግብጽ የሚሄደው የአባይ ውሃ አይቀንስም።

 

አጀንዳ ሶስት (3)፥ ግድቡን ለመሙላት የሚያስፈልገው ውሃ በግብጽ ላይ ስጋት መፍጠር የለበትም። በበጋም ሆነ በክረምት ወደ ግብጽ የሚፈሰው የአባይ ውሃ ግብጽን አልፎ ሜድትራኒያን ባህር ስለሚገባ የኢትዮጵያ፣ የሱዳን እና የግብጽ ሳይንትስቶች እና መሃንዲሶች ከአለም እክስፐርቶች ጋር ሆነው ምን ያህል ውሃ ግድቡ ውስጥ እንዲቀር ማድረግ እንደሚቻል ማስላት ይችላሉ። ግድቡን ለመሙላት ከበጋ ይልቅ በክረምት ከፍ ያለ የውሃ ማስቀረት እንደሚቻል ግልጽ ነው።

 

አጀንዳ አራት (4)፥ ከአባይ ወንዝ ውሃ በተጨማሪ ከሱዳን የኤሌክትሪክ መስመሮች ጋር በመተሳሰር ግብጽ የምታገኘው ተጨማሪ ጠቀሜታ እንዳለም የግብጽ እና የአለም ህዝብ እንዲያውቅ ዲፕሎማሲያዊ ቅስቀሳ መደረግ አለበት። ለምሳሌ ግብጽ እና ጆርዳን የኤሊክትሪክ መስመራቸውን አስተሳስረዋል። የኤሌክትሪክ መስመሮቻቸውን ለማስተሳሰር በየብስ ከግብጽ ወደ ጆርዳን በመማዎች ማጓጓዝ ስላልቻሉ ከፍተኛ ወጪ አውጥተው መስመሩን በቀይ ባህር ወለል ስር ቀብረው የሁለቱን አገሮች የኤሌክትሪክ መስመሮች አስተሳስረው የኤሊክትሪክ ኃይል ይነጋገዳሉ። በቅርቡ ደግሞ ግብጽ ከሳውዲ ጋር ለማስተሳሰር ስምምነት ጨርሳለች። ግብጽ ለጆርዳን ከምተሸጠው የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ የተወሰነው የኤሊክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ የሚፈሰው አባይ አስዋን ግድብ ላይ ከሚፈጥረው 2 ሺ አንድ መቶ ሜጋ ዋት መሆኑን አንባቢ ልብ ይበል።

 

አጀንዳ አምስት (5) 09 JUNE 2013 ሪፖርተር ጋዜጣ ከቀድሞ ዲፕሎማት አምባሳደር ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገችው  ቆይታ የውሃ አጠቃቀምን አለም አቀፍ ህግ አስመልክታ ላቀረበችላቸው ጥያቄ አምባሳደሩ መልስ “በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስብሰባ ላይ 101 የድምፅ ድጋፍ፣ በሦስት ተቃውሞና 27 ድምፀ ተአቅቦ ያለፈው የውኃ ኮንቬንሽን የኢትዮጵያን አቋም የሚደግፍ ነው፡፡” ይህን ሁሉ የግብጽ ህዝብ እንዲያውቅ ይደረግ።

 

አጀንዳ ስድስት (6)፥ ግብጽ ከመቶ አመቶች በኋላ የህዝቤ ብዛት 3 መቶ ሚሊዮን ወይንም ከዚያ በላይ ሊሆን ይችላል ከሚል የተደበቀ ስሌት አባይ ይለቀቅልኝ ማለት እንደማትችል ግልጽ መሆን አለበት። 

 

አጀንዳ ሰባት (7)፥ የቅኝ አገዛዝ ዘመንን ውል ኢትዮጵያ እንደማትቀበል በጠዋት ግልጽ መደረግ አለበት። የአባይ ውሃ ባለቤትነት እና የመጠቀም መብታችንን ለድርድር እንደማናቃረብ ህግን፣ ታሪክን፣ ፖለቲካን፣ ኢኮኖሚን እና ግብረገብነትን መሰረት ያደረጉ ትንታኔዎች ማቅረብ።

 

አጀንዳ ስምንት (8)፥ ግብጽ የሚገባው ነጭ አባይ 85% ያህሉን ውሃ የሚያገኘው ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን ከሚፈሱት ጥቁር አባይ (70%)፣ ተከዜ (5%) እና ባሮ (10%) ወንዞች ነው። እነዚህ ሶስት አውራ ወንዞች የሚፈጠሩት በኢትዮጵያ ከተለያዩ ቦታዎች ከሚነሱ በርካታ ገባር ወንዞች ነው። ግብጽ በጸበኛነት የምትቀጥል ከሆነ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ከየአካባቢው የሚነሱትን ትናንሽ ገባር ወንዞች አቅጣጫ ይቀይራል። ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን የሚፈሰው ውሃ መጠን እጅግ ዝቅ ይላል። ግብጽ በወታደራዊ ኃይል የባሮ ወንዝ ከሚገኝበት ደቡብ ምዕራብ ጀምሮ እስከ ሰሜን ምዕራብ ድረስ ሁልጊዜ መዋጋት አትችልም። ይኽን ሃቅ ግብጾች፣ አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ የአለም ባንክ፣ አይ.ኤም.ኤፍ. ሁሉ እንዲገነዘቡት እና የግብጽ ጸበኛነት የማያዋጣ መሆኑ ወለል ብሎ እንዲታያቸው ማድረግ።

 

አጀንዳ ዘጠኝ (9)፥ ግብጽ ጦርነት ከመረጠችም ከምታገኘው ጥቅም ይልቅ የሚደርስባት ኪሳራ ብዙ ነው። ጦርነት ለማኪያሄድ የምታወጣው እና በጦርነት ጀማሪነት እንዲሁም ለደረሰችው ጉዳት የተባበሩት መንግስታት ይቀጣታል።  

 

አጀንዳ አስር (10)፥ ኢትዮጵያ እራስዋን የመከላከል መብቷ የተከበረ መሆኑንም የዲፕሎማሲው ትግል ጨምሮ ይገልጻ።     

 

እነኚህ አስር (10) አጀንዳዎች ቢተነተኑ ትልቅ ሰነድ እንደሚወጣቸው ግልጽ ነው። እነዚኽን አሳቦች ካለቀረርቶ ለግብጻውያንም ሆነ ለአለም ህዝብ ወዝ እና ቁርጣኛነት በግልጽ በሚታይበት አነጋገር በማቅረብ ቢያንስ የግብጽን የተወሰነውን የዴሞክራሲ ኃይል ድጋፍ ማግኘት እና አለም አቀፍ ደጋፊዎችን ብዛት ማሳደግ እንደሚቻልም ግልጽ ነው።

 

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኃይሎች ዲፕሎማሲያዊ ትግላቸውን እንዴት ማኪያሄድ ይችላሉ? በብዙ መንገዶች ማኪያሄድ ይችላሉ። በአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ምሁራን የሚዘጋጁ የበሰሉ የምርምር ጽሑፎችን እና የዲፕሎማሲ ትግሉን ሂደት ደረጃዎች እየተከታተሉ እነ አንድነት ፓርቲ፣ ሰማያዊዎች እና ሌሎች የዴሞክራሲ ኃይሎች የሚያወጧቸውን መግለጫዎች በየድረገጹ በማቅረብ። ድረገጾቹ ለግብጽ ዴሞክራሲ ኃይሎች፣ ለአሜሪካ፣ ለአውሮፓ ዲፕሎማቶች እና የቀድሞው የዓለም አቀፍ አቶሚክ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ለነበረው ለነ መሐመድ አልባራዳይ አይነቱ የግብጽ ዴሞክራሲ ኃይሎች ተደራሽነት ቢኖራቸው ጥሩ ነው። የቀድሞው የዓለም አቀፍ አቶሚክ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የነበረውን መሐመድ አልባራዳይ እና ሌሎች ግብጻውያንን በመጋበዝ ህዝብ ለህዝብ የሚሉ ጉባኤዎች በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ አዘጋጅቶ መነጋገርም ይቻላል። ተደጋጋሚ ቢሆን ጥሩ ነው። በአለም ውስጥ የተሰራጩት ኢምባሲዎች ይኽን አይነቱን ዲፕሎማሲያዊ ቅስቀሳ ቀደም ብለው ማድረግ ነበረባቸው። ችግሩ ህውሃት (ቴዎድሮስ አድሃኖም እና ገብረ ክርስቶስ ) ያላዘዛዋቸውን አያደርጉም።

 

ስለዚህ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኃይሎች በአባይ እና በአገራቸው ጉዳይ የዲፕሎማሲ ትግሉ ባለቤት መሆን አለባቸው። አንድ ነገር በግልጽ መታወቅ አለበት። የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ኃይሎች በራሳቸው አነሳሽነት መራመድ ካልጀመሩ ህውሃት የዲፕሎማሲ ትግል አጋር እንዲሆኑም ሆነ ወደፊት በሚደረጉ ምርጫዎች በነፃ ተፎካክረው ስልጣን እንዲጋሩት ወይንም አሸንፈውት አገር እንዲያስተዳድሩ ፍጹም አይፈልግም። የዴሞክራሲ ኃይሎች ከዳር ቆሞ ተመልካችነትን ከመረጡ የኢትዮጵያ ህዝብም በአባይ ጉዳይ ሆነ በሌሎች ጉዳዮች ያለኝ ጠበቃ እና ጠባቂ ህውሃት ብቻ ነው የሚል አደገኛ እምነት ሊፈጠር ይችላል። የህውሃትም ፍላጎት የኢትዮጵያ ህዝብ በህውሃት ላይ እንዲያመልክ ማድረግ ነው። ስለዚኽ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኃይሎች የአባይም ሆነ የኢትዮጵያ ባለቤትነታቸውን እና ሌሎች የሚጠበቁባቸውን ህዝብ የመምራት ግዴታዎች ለመወጣት ህውሃት የዘጋባቸውን በር እስኪከፍትላቸው መጠበቅ የለባቸውም። የመግለጫ ጋጋታም ህውሃት የዘጋውን በር አይከፍትልህም። የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ሰራዊት ህውሃት የዘጋውን በር እራስህ ከፍተህ በአገርህ ጉዳይ በአቻነት መሳተፍ መጀመር አለብህ! በህዝብህም ዘንድ ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ መታወቅን እና ክብርን የሚያስገኝልህ ብሎም ፕሮግራምህን ተፈጻሚ ማድረግ የምትችለው እንደነዚህ አይነት ስራዎች ስትሰራ ብቻ ነው!

«ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ግንባር» የሚል ስም ይኖረናል –ሌንጮ ባቲ

$
0
0

የቀድሞ የኦነግ መስራችና አመራር አባላት በብዛት ያሉበት፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፎረም በሚል ስም፣ አንድ ድርጅት መቋቋሙ ይታወቃል።  ድርጅቱ የመገንጠል ጥያቄ ጎጂና ጠቃሚ እንዳልሆነ በማተት የኢትዮጵያን አንድነትና ሉአላዊነት በጠበቀ መልኩ የሁሉም መብት የሚከበርባትን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ለመገንባት እንደሚታገልም ገልጾ ነበር። «ለኦሮሞዎች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የኢትዮጵያዉያን መብት እንታገላለን» ያለዉ ኦዴፍ ፣ የአመራር አባላቱ በተለያዩ ፎረሞች በመገኘት ፕሮፖዛሎቻቸውን እያቀረቡ ሲሆን፣ ከተለያዩ ድርጅቶችም ጋር እየተናገገሩ መሆናቸውንም ይናገራሉ።

 

ከጥቂት ቀናት በፊት፣ ሺሆች በሚያዳምጡት የሲቪሊቲ ፓልቶክ ክፍል ቀርበው አስተያየት የሰጡት፣  የኦዴፍ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ፣ አቶ ሌንጮ ባቲ፣  የሚለያየንን ሳይሆን የሚያቀራርበንን ገመድ የበለጠ  ማጠናከር አለብን ብለዋል። ገዢው ፓርቲ በተለይም በአማራዉና በኦሮሞዉ መካከል የመጠራጠርና የመፈራረት ስመንፈስ እንዲኖር በማድረግ ለሃያ አመት በስልጣን ላይ ሊቆይ እንደቻለ የገልጸኡት አቶ ሌንጮ፣ አማራዉም ሆነ ኦሮሞው በመንቃት ፣ ሌሎች ብሄረሰቦችን በማቀፍ አምባገነንነትንና ጭቆናን መታገል እንዳለበት አሳስበዋል።

 

ኢትዮጵያዊ ፣ እንደ ኦሮሞ፣  አቶ ሌንጮ ይሰጡት በነበረዉ  ልብ የሚስብና የሚያረካ አስተያየት አስተያየት ደስ የተሰኙ አንድ አድምጫ  «ኦሮሞ ያልሆኑ  እናንተን እንዴት ሊቀላቀሉ ይችላሉ ? » በሚል  ላቀረቡላቸው ጥያቄ  አቶ ሌንጮ ሲመልሱ ፣ አሁን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ቢባሉም ከሌሎች ጋር ተመካክረን ወደ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲአይዊ ግንባር እንደሚለወጡም አሳዉቀዋል። «እየሰራንበት ነዉ ፣ ትንሽ ታገሱን » ነበር አቶ ሌንጮ ያሉት።

 

ይሄንን ኦዲዮ ላቀረበልን የሲቪሊቲ ፓልቶክ ክፍል ምስጋናችንን እያቀረብን፣  ባለ 2 ክፍል የአቶ ሌንጮን ቃለ ምልልስን አቅርበንላቹሃል።

 

ክፍል 1

ክፍል 2

ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በሕዝባዊ ንቅናቄ እንዲረጋገጡ ጫና እናደርጋለን!!!

$
0
0

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

      ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ለኢትዮጵያ የሚገባትን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ሳይሸራረፍ በሰላማዊ የትግል መስመር ለማረጋገጥ ትግል ከጀመረ አራት ዓመታት አሳልፏል፡፡ በነዚህ ዓመታትም ፓርቲያችን ወደ ፍፁም አምባገንነት እየነጎደ ያለውን ገዥ ፓርቲ የፖለቲካ አካሄድ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የዴሞክራሲያዊ መብቶች ነጠቃ እንዲቆም አጥብቆ ታግሏል፡፡ በትግሉ ሂደትም ስርዓቱ በግልፅና በስውር ፓርቲያችን ላይ ጥቃት ፈፅሟል፤ እየፈፀመም ይገኛል፡፡ አመራሮቻችንና አባሎቻችንም ስለ ቁርጠኛ ዓላማቸው ያለምንም ማፈግፈግ የሚከፈለውን መስዋእትነት ከፍለዋል፣ እየከፈሉም ይገኛሉ፡፡ ስለ ዴሞክራሲና ነፃነት ሲሉ ጨለማ ክፍል ውስጥ የተጣሉትን ወጣት አመራሮች አንዷለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን እና ሌሎችንም፤ ሃሳባቸውን በነፃነት ስለገለፁ እስር ቤት የተጣሉ ጉምቱ ጋዜጠኞችና የዕምነት ጣልቃ ገብነትን ስለተቃወሙ ለእስር የተዳረጉ ኢትዮጵያውያንን መጥቀስ ይቻላል፡፡

አንድነት በሆደ ሰፊነት የፖለቲካ ለውጦች እንዲደረጉ፣ ዜጎች በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ እንዳይታሰሩ፣ እንዳይገረፉ፣ እንዳይሳደዱ፣ መንግስት በኃይማኖት ጣልቃ እንዳይገባና የኃይማኖት ነፃነት እንዲረጋገጥ ስለጠየቁ በጅምላ የድራማ ክስ እየተመሰረተ ወደ እስር ቤት እንዳይጋዙ፣ ጋዜጠኞች ሃሳባቸውን በነፃነት ስለገለፁ እንደ መደበኛ ጠላት ተቆጥረው ሰብዓዊ መብታቸው ተገፍፎ እንዳይታሰሩና ለስደት እንዳይዳረጉ በተደጋጋሚ ገዥውን አካል ያለመታከት መጠየቁ የሚታወስ ነው፡፡ የሀገሪቱ ችግሮች በገዥው ፓርቲ ብቻ የሚፈቱ አለመሆናቸውን በመገንዘብ በሃገራዊ ጉዳዮችና የፖለቲካ መፍትሄዎች ላይ ከተቃውሞ ኃይሎች ጋር ድርድር እንዲያደርግ፣ የዘጋውን በር ለውይይት ክፍት እንዲያደርግ፣ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ያሳተፈ ሀገራዊ መግባባት እንዲፈጠር በተደጋጋሚ ጠይቀናል፡፡ ለነዚህ ዓብይ ጥያቄዎቻችን የተሰጠን መልስ እስራት፣ መፈረጅና ማዋከብ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ገዥው ፓርቲ ለጭቆናው ሕጋዊ ከለላ ለመስጠት ጨቋኝና አፋኝ ህጎችን በማውጣት፤ የረጅም ዓመት የስልጣን ቆይታን በመናፈቅ ዜጎችን በየማጎሪያ ቤቱ እያሰቃየ ይገኛል፡፡ እኛም ይሄንን ዓብይ ችግር ለመፍታት ሰላማዊ በሆነ የትግል ስልት ህዝባዊ ንቅናቄ መፍጠር አስፈላጊ እንደሆነ አምነናል፡፡

ስርኣቱ ዜጎች ካላግባብ ከየመኖሪያ ቀያቸው በገጠርም ሆነ በከተማ በግፍ እንዲፈናቀሉ እያደረገ ይገኛል፡፡ ይሄው ሀገራዊ ይዘት ያለው ማፈናቀል ሦስት አይነት መልክ ያለው ሲሆን በዘር ላይ ተመሰረተ ማፈናቀል፣ በልማት ስም ማፈናቀልና ለመሬት ወረራ ማፈናቀል ናቸው፡፡ ዘርን መሰረት ያደረገው ማፈናቀል በቅርቡ ብቻ በደቡብ ክልል ጉራፈርዳ፣ በቤኒሻንጉል ክልልና ሌሎችም አካባቢዎች የተከሰተው ነው፡፡ በልማት ስም የሚከናወነው ማፈናቀል በአብዛኛው በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች በስፋት የሚታይ ነው፡፡ ዋናው መሰረቱ የገዥው ፓርቲ የመሬት ፖሊሲ ነው፡፡ መሬት በባለቤቱ ፈቃድ የሚሸጥና የሚለወጥ ባለመሆኑ ያለበቂ ካሳና ማስጠንቀቂያ ለማህበራዊ ትስስር ቁብ ሳይኖረው ልማት በሚል ስም ብቻ በማንሳት ዜጎች የሚፈናቀሉበት ነው፡፡ ሌላው የማፈናቀል አይነት ደግሞ ከመሬት ወረራ ጋር በእጅጉ የተቆራኘና በእርሻ መሬት ሰበብ ዜጎች እየተፈናቀሉ ለውጭና ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች በጥቂት ሳንቲም የሚሰጥ ነው፡፡ ይሄም በጋምቤላና በሌሎች አካባቢዎች በስፋት የታየና እየታየ ያለ ነው፡፡ ፓርቲያችን ይህንን ጉልህ ሀገራዊ አደጋ ለማስቆምም የሚጠበቅበትን ትግል ለማድረግ ህዝባዊ ንቅናቄ አስፈላጊ መሆኑን ያምናል፡፡

ከመፈናቀሉ በተጨማሪም ቅጥ ያጣ የኑሮ ውድነትና ስራ አጥነት በሰፊው ተንሰራፍቷል፡፡ የኑሮ ውድነቱን ጣሪያ ያስነካው የዋጋ ግሽበት ዋና መንስኤው ስርዓቱ የሚከተለው የተሳሳተ ፖሊሲ ነው፡፡ የኑሮ ውድነቱ የወለደው ነገር ቢኖር ሀገራችን በታሪኳ አይታ የማታውቀው ስደት ነው፡፡ ዜጎች ከፊት ለፊት ሞት እንደሚጠብቃቸው እያወቁ ተጋፍጠው ለስደት የመነሳታቸው መንስኤ ስራ አጥነትና የኑሮ ውድነት ነው፡፡ ከዚህ ጋር የነፃነት እጦት ሲታከልበት የችግሩን መልክ ውስብስብ አድርጎታል፡፡

የንግዱን ማህበረሰብም ስንመለከት ከመቼውም በባሰ ሁኔታ ነጋዴ መሆን ወንጀለኛ መሆን የሚል ትርጉም ይዟል፡፡ በተጨማሪም ገዥው ፓርቲ በአንድ በኩል ህግ አውጪና አስፈጻሚ፣ በሌላ በኩል ነጋዴ በሆነበት ሁኔታ ፍትሀዊ የንግድ ውድድር የሚታሰብ አይደለም፡፡ ይህም የግሉ ሴክተር በሀገሪቱ ዕድገት ውስጥ ሊኖረው የሚገባውን ሚና እጅግ አቀጭጮታል፡፡ ካላግባብና በግምት የሚጣል ታክስ መክፈል ሃገራዊ ግዴታ የመሆኑን ለዛ አሳጥቶታል፡፡ አንዳንዱ በብልጣብልጥነት ስርዓቱን እንደመታወቂያና ከለላ በመጠቀምና ከባለስልጣናት ጋር በመሻረክ በጥቂት ቀናት ውስጥ የሀብት ማማ ላይ ሲወጣ እንመለከታለን፡፡ ይሄም በንፁህ ንግድ ላይ ለተመሰረቱ በርካታ ዜጎች አደጋ እየሆነ መጥቷል፡፡ ከዚያም ልቆ ኢ-ፍትሃዊነት ነው፡፡ ስለዚህ ፍትሃዊ የንግድ አሰራር እንዲኖርና የግሉ ሴክተር በኢኮኖሚ ውስጥ የሚገባውን ቦታ እንዲኖረው እንጠይቃለን፡፡

በዚህም መሰረት ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ እንዲሳተፍ ለማድረግ በአዲስ አበባና በመላ ኢትዮጵያ ህዝባዊ ውይይትና ሰላማዊ ሰልፍ እናደርጋለን፡፡ ህዝቡንና የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚያሳትፍ፣ አባሎቻችንንና ደጋፊዎቻችንን ያሚያቅፍ፣ አፋኝና ጨቋኝ ህጎችና አዋጆች እንዲሰረዙ ጫና የሚያደርጉ፣ በመሰረታዊ የፖለቲካ ጥያቄዎች ላይ ውይይት ለማካሄድ የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች በፍጥነት መደረግ እዳለባቸው እናምናለን፡፡ በዚህም መሰረት የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት (MILLIONS OF VOICES FOR FREEDOM) በሚል መሪ ቃል ተከታታይነት ያለው የሕዝባዊ ንቅናቄ ዕቅድ ይፋ አድርገናል፡፡

የዕቅዳችን ዋና አላማ ከጊዜ ወደ ጊዜ አምባገነንነትን ማስፉት፤ በአንፃሩ ደግሞ ዴሞክራሲዊና ሰብዓዊ መብትን እየገፈፈ፣ ዜጎችን በፍርሃት ተዘፍቀው በምንደኛነት እንዲኖሩ ያደረገውን ስርዓት መቃወም፤ መሰረታዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ ስልጣን የህዝብ እንዲሆን፣ ግለሰቦች በፖለቲካ አመለካከታቸው፣ በዕምነታቸውና ሃሳባቸውን በነፃነት በመግለፃቸው የማይታሰሩባት ሃገር መፍጠርና ፍትሃዊነትን ማስፈን ነው፡፡ ይህ እውን እንዲሆን ደግሞ የሚሊዮኖችን ድምፅ በመሰብሰብ ከህገ-መንግስቱ ጋር የሚጋጨውንና ፍፁም ነፃነት ነጣቂ የሆነውንና ማሰብ እንኳን የሚከለክለውን የፀረ ሽብርተኝነት ህግ እንዲሰረዝ ማድረግ ነው፡፡ ሚሊዮኖች የፀረ ሽብር አዋጁን በመቃወም የሚፈርሙበት ሰነድም እነሆ ይፋ አድርገናል፡፡ ሚሊዮኖችም የተቃውሞ ፊርማቸውን እንደሚያኖሩ ሙሉ እምነት አለን፡፡ ይንንም መሰረት በማድረግ ለእስር የተዳረጉ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና የሃይማኖት ነፃነት ጠያቂዎች እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡

ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የተቀየሰው የሠላማዊ ስልት በአዲስ አበባና በተለያዩ የክልል ከተሞች ህዝባዊ የአዳራሽ ስብሰባዎችን፤ የአደባባይ ስብሰባዎችንና የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን ያካትታል፡፡ በአዲስ አበባ ስድስት ህዝባዊ ስብሰባዎችን፣ በክልል ደግሞ ለመጀመሪያ ዙር ብቻ አስር ስብሰባዎችን እናደርጋለን፡፡ በሚሊዮኖች ድምፅ ነፃነትን ለማረጋገጥ የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሚሳተፉበት ይሆናል፡

የህዝባዊ ንቅናቄው ዓላማ

  1. የፀረ-ሽብር ህጉ የኢትዮጵያውያንን በርካታ መብቶች የሚገፍ በመሆኑና ከሕገ-መንግስቱ ጋር የሚፃረር በመሆኑ በሚሊዮኖች የሚቆጠር የተቃውሞ ድምፅ በማሰባሰብ በአስቸኳይ እንዲሰረዝ ጥያቄ እናቀርባለን፡፡ የድጋፍ ፊርማ (ፔቲሽን) እናስፈርማለን፡፡ ይህንንም በሰላማዊ ሰልፍ እንጠይቃለን፡፡ የሚሊዮኖችን ድምፅ በመያዝ ወደ ክስ እንሄዳለን፡፡
  2. በሀገር ዓቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለው በገጠርና በከተማ የዜጎች መፈናቀልና የመሬት ቅርምት እንዲቆምና መፍትሄ እንዲያገኝ እንጠይቃለን፤
  3. የስራ አጥነትና የኑሮ ውድነት እንዲቀረፍ፤ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ርምጃዎች እንዲወሰዱ እንጠይቃለን፤
  4. የንግዱ ማህበረሰብ ውስጥ ፍትሃዊ ውድድር እንዲኖር፤ ማጥላላትና ማዋከብ እንዲቆም፤ ገዥው ፓርቲ ህግ አውጭና ነጋዴ የሚሆንበት ስርዓት እንዲያበቃና የግሉ ሴክር በልማቱ ውስጥ ከፍተኛ ሚና እንዲኖረው እንጠይቃለን፡፡

ለዚህ ትልቅ ሀገራዊ ንቅናቄ መሳካት ሕዝቡ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ ሚዲያው፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ለሀገር ተቆርቋሪ ኢትዮጵያውያንና የሀገርን ጥቅም ለማስቀደም የሚፈልጉ የኢህአዴግ አባላት እንዲሳተፉ ሀገራዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

 

የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት!!!

 

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

ሰኔ 12 ቀን 2005 ዓ.ም

አዲስ አበባ

Sign the Petition- MILLIONS OF VOICE FOR FREEDOM !

 

 


የኛ ነገር፡ የአባይ ችግር፡ የአያልሰው ምክር፡ ከልጅ ተክሌ፤ ተረንቶ

$
0
0

Tekeleከልጅ ተክሌ፤ ከተረንቶ

ክፍል 4 (ክፍል ሁለትና ሶስት ይመጣሉ)

  1. ብዜ ግዜ የአቶ አያልሰው ደሴ ጽሁፎች ረዣዥሞች ስለሆኑ፤ እንዲሁም ክፍል ስለሚበዛቸው (1፣ 2፣ 3፣ 4፣ … )፤ ርእሳቸውን ብቻ እያየሁ አልፋቸው ነበር። በዚህ በአባይ ጉዳይ ግን የጻፉት አነበብኩት። ጽሁፉ በርስ በርስ ቅራኔ የሚንተከተክና በኢህአዴግ የአባይ ግድብ ማጭበርበሪያ ዘመቻ ዙሪያ ያለውን ተቃውሞ በቅጡ ያልዳሰሰ፡ ይልቅስ ሌሎችን ተቺዎች በሚከስበት ደዌ ክፉኛ የታመመ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። በተጨማሪም ጽሁፉ የአካባቢውን ፖለቲካ በቅጡ የቃኘ ቢሆንም፤ የደረሰባቸው ድምዳሜዎች ግን የተሳሳቱ ናቸው።
  2. እንደምንም በርትቶ እዚያ ለደረሰ ሰው፤ የአቶ አያልሰው ደሱ ጽሁፍ ዋና ሀሳብ በክፍል ሁለት፤ በአምስተኛው ገጽ፤ በሁለተኛ አንቀጽ ላይ ይገኛል።

“እንደ አንድ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ በሚከተሉት ምክንያቶች ይሄ የህዳሴ ግድብ መደገፍ እንደሚኖርበት እምነቴ ነው። በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክ ውስጥ በአባይ ላይ ግድብ ለመስራት ለኢትዮጵያ ከዚህ ጊዜ የተሻለ የአካባቢና የአለም አቀፍ ሁኔታ ኖሮ አያውቅም ማለት ይቻላል። … ኢትዮጵያ አባይ ላይ ትርጉም ያለው ግድብ መስራት ከፈለገች፡ …ወቅቱ አሁን ነው።”

  1. እንደተረዳሁት ከሆነ፤ አቶ አያልሰው የሚሉት፡ የአባይን ግድብ ሊያሳኩ የሚችሉ ሶስቱም ነገሮች፤ አለማቀፋዊ፤ አካባቢያዊ (ምስራቅ አፍሪካን ማለታቸው ይመስለኛል) እንዲሁም በግልጽ ባይሉትም አገር አቀፋዊ ሁኔታዎች (አገር ወዳድ መንግስት ማለታቸው መሰለኝ) ገጥመዋል። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንደኢህአዴግ ያለ የኢትዮጵያን ራእይ ሊያሳካ የሚችል መንግስት ከአለማቀፋዊ ሁኔታዎች ጋር ስለገጠመ፡ በሳቸው አነጋገር፤ እኛና እሳቸው እዚህ ምን እንደምንሰራም አልገባኝም። አንድ ሁለት ግሬደሮች ይዘን ጉምዝ ብንገባ ሳይሻል አይቀርም።
  2. የአቶ አያልሰው ደሴ ጽሁፍ የተገነባው ፈረንጆቹ “ስትሮው ማን ፋላሲ” በሚሉት፤ የሌላውን ሀሳብ አስቀድሞ በማኮሰስ፤ የኮሰሰውንም በሚተቸው አመንክዮ ላይ ነው። አቶ አያልሰው መጀመሪያ የአባይን የማጭበርበሪያ ግድብ የሚቃወሙ ሰዎችን ሀሳብ፡ ደህና ደህናው እየተዉ፡ በሁዋላ ለማጥቃት በሚመቻቸው መልኩ ደካማ ደካማውን መርጠው፡ እሱንም ፍንክትክት አድርገው አስቀመጡት። ከዚያ በሁዋላ ዋናውን የተቃውሞ ወይንም የጠያቂ ሀሳብ መሞገት ትተው፤ እሳቸው የፈጠሩትን የተፈነካከትና የተጋጋጠ የተቃዋሚዎች ሀሳብ መደብደብ ያዙ። እግዜር አይወደውም።
  3. የአቶ አያልሰው ደሴ ጽሁፍ፤ ከመነሻውም በአያሌ ህጸጾች የተከበበ ነው። መጀመሪያ በአሁኑ ግዜ የአባይን መገደብ የሚቃወሙ ወገኖች ለተቃውሟቸው የሚያቀርቧቸው የሚሏቸውን ደካማ ደካማ ምክንያቶች ብቻ መምረጣቸው ስህተት ነው። ክፍል ሁለት ገጽ አንድን ይመልከቱ። ከዚያ ሲደመድሙ አብዛኛዎቹ የተቃዋሚዎች ወይም ሁሉም ሀሳቦች ቀድሞ በኢህአዴግ ላይ ባለን ጥርጣሬና ጥላቻ የተጋረዱ፤ አብላጫዎቹ ደግሞ “በትክክለኛ መረጃና እውቀት ላይ ያልተመሰረቱ በግልብ ስሜት ላይ የተንጠለጠሉ በአጭሩ የአባይ ግድብ ለኢትዮጵያ ያለውን ፈርጀ-ብዙ ትርጉምና እርባና በቅጡ ካለመገንዘብ የመነጩ ናቸው፡” ሲሉ ፈረጇቸው።
  4. አንደኛ ነገር፤ ለግንዛቤ ይረዳን ዘንድ፤ አቶ አያልሰው ደሴ፡ የነማንን ሀሳብ የት ቦታ ተጽፈው አይተው ይሄንን አቋም እንደያዙ በጽሁፋቸው ላይ አልገለጡልንም። የሚተቹት ፓልቶክ ላይ ያደመጡትን ይሁን ፌስቡክ ላይ የታዘቡትን ሀሳብ አላሳወቁንም። ከሁሉም በላይ ግን የከነከነኝ፡ በግልብ ስሜት ላይ የተንጠለጠሉ ሀሳቦችን ይዘው ሙግት የመግባታቸው ብልሀት ነው። በመሰረቱ፡ በግልብ ስሜት ላይ የተመሰረቱ ተቃውሞዎች ሊታለፉ እንጂ፡ በአቶ አያልሰው ደሴ ጽሁፍ ሊያልፍላቸው አይገባም ነበር። የምናጠቃውን ሀሳብ መምረጥ አለብን።
  5. ሁለተኛ ነገር፡ የሌሎችን ሀሳብ በስሜታዊነት ላይ የተመሰረቱ ብሎ መፈረጅ፡ ተመሳሳይ ፍረጃን በራስ ላይ የመጋበዝ ያህል ነው። የአባይን ግድብ በተመለከተ ጥርጣሌ ያላቸው፤ ወይንም ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች ሀሳብ፤ አባይ ለኢትዮጵያ ያለውን ፈርጀ-ብዙ ትርጉም ካለመረዳት የመነጨ ከሆነ፤ የአቶ አያልሰው አይነት የአባይ ግድብ ድጋፍም፡ ምናልባት የኢህአዴግን ባህርይ ካለመረዳት ወይንም ከመርሳት የመነጨ ነው ወደሚል መደምደሚያ ይመራል። ይመስላልም። ጽሁፋቸው በርግጥም አቶ አያልሰው ደሴ ኢህአዴግን ረሱት እንዴ የሚል ጥያቄ ይፈጥራል። እመለስበታለሁ።
  6. ሶስተኛ ነገር፡ ሶስተኛውን ነገር ረሳሁት።
  7. አራተኛ ነገር፤ ከአባይ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ክርክሮች ላይ፤ አንዱን ቡድን የግድቡን ተቃዋሚ ሌላኛውን ጎራ የግድቡ ደጋፊ አድርጎ የመሳሉ አካሄድ ስህተት ነው። ይሄ ኢህአዴጎችና ደጋፊዎቻቸው ሆን ብለው እኛን ለመከፋፈልና ለማሳሳት የቀየሱት ቀሽም የክርክር መስመር ነው። የአባይን መገደብና ጥቅም ላይ መዋል የሚቃወም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ይኖራል ብየ አላስብም። የአብዛኞቻችን ተቃውሞ፡ ገና ለገና ኢህአዴግ በስስ ብልታችን ስለመጣ፤ የ22 አመቱንና አሁንም የቀጠለውን ጭቆና ችላ ብለን፡ በስመ አባይ ግድብ ኢህአዴግን በጭፍን መርዳት የለብንም ነው።
  8. አቶ አያልሰው ደሴ ሰብአዊ መብትና ዴሞክራሲ የሚሉትን ቃላት ጽሁፋቸው ውስጥ ጣል ጣል ቢያደርጉም፡ ደግመው ደጋግመው የሚያነሱት፤ “ግድቡ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መደገፍ አለበት” የሚለውን ሀሳብ ነው። በሌላ አነጋገር አቶ አያልሰው ደሴ ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ህዝብ ለአመታት እዳ ውስጥ ሊከት የሚችል፤ ወደአለማቀፋዊ ህጋዊ ግዴታ የሚዶል ውል መግባት የሚችል የህዝብ ውክልና ያለው ህጋዊ መንግስት ነው እያሉ ነው። ኤልያስ ክፍሌ ያስቀመጠውን፡ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለዚህ ኢትዮጵያዊያንን ለደፈረ፡ ለገደለ፡ ላሰረ፡ ላዋረደ መንግስት የምንሰጠው እርዳታ፤ በተዘዋዋሪ ኢህአዴግን ህጋዊነት የሚያላብስ፡ ኢህአዴግ የሚፈጽውንም አፋናና የመብት ጥሰት የሚደጉም ነው የሚለውን ስጋት ወይም ክርክር አልዳሰሱትም።
  9. ከዚያ አቶ አያልሰው የግድቡን ተቃዋሚዎች የሚሏቸው ሰዎች የሚያነሷቸውን መከራከሪያ አሳቦቦች በጥልቀት ለመዳሰስና ለመመለስ ይሞክራሉ። ለምሳሌ አቶ አያልሰው  ደሴ “የአባይ ጉዳይ ከባድና ውስብስብ ነው” ይላሉ።

አባይ የኢትዮጵያ ስስ ብልት ነው ማለት ይቻላል። በጣም ጥንቃቄና በእንክብካቤ የሚያዝ ጠቃሚ የአገር አካል ነው። በመሆኑም በእሱ ላይ የሚወሰድ ውሰኔ በተራ የፖለቲካ ስሌት ላይ ተመርኩዞም ሆነ ብድግ ብሎ በዘፈቀደና በስሜታዊነት አዋጅ በማስነገር የሚደረግ አይደለም።

ከዚያ በሁዋላ፤ አቶ አያልሰው፤ አሁንም ለነማን እንደሆነ እንጃ፤ የኢህአዴግ ፕሮጀክቶች ላይ ተቃውሞ ሲደረግ እንዴት መደረግ እንዳለበት ትምህርት ይሰጣሉ። አቶ አያልሰው ደሴ፤ በስም ባይጠቅሷቸውም፤ እሳቸው “ግድቡን የሚቃወሙ” የሚሏቸውን በተራ ፖለቲካ ላይ ተመርኩዘው የሚቃወሙ አድርገው ይስሏቸውና፤ ኢህአዴግ ግን የአባይን ግድብ ከማወጁ በፊት ቢያንስ ለአስር አመታት ያደረገውን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ላይ የሰለቸንን የኢህአዴግ የዲፕሎማሲ ትግል ያወሳሉ።

  1. በመሰረቱ የአባይ ጉዳይ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ነው ካሉ፤ ጥንቃቄው ለመቃወም ብቻ ሳይሆን ለመደገፍም ጭምር ነው። “አባይ አባይ” እየተባለ ሲዘመርልን ስለኖርን ብቻ ኢህአዴግ ማጣፊያው ሲያጥርበት ድንገት ተነስቶ አባይን ልገድብ ነው ሲል፤ “ከቀበሌ ጥይት ፈጥነን” ከኢህአዴግ ጎን መሰለፍ አለብን ማለት አይደለም። ጥንቃቄው ባለሁለት ዘርፍ ነው። አቶ አያልሰው እንደመከሩት ለመቃወምም። እሳቸውን ለማስታወስም ያህል ለመደገፍም ጭምር ጥንቃቄ ያስፈልጋል። አባይን ገነባን ብለን ለኢህአዴግ ገንዘብና ቁስ ወደማቅረብ መሮጥ የለብንም። ቀድሞ ነገር መቼ የአገራችን ባለቤት ሆንነና ነው የአባይን ግድብ ስለመርዳት የምናነሳው? አገርስ አለን እንዴ? አገራችንን ተነጥቀን አባይን ስለመገንባት ስናወራ ትንሽ ግራ ያጋባል።
  2. አቶ አያልሰው፤ የተቃዋሚውን አተያይ በጣም አድርገው ተችተዋል። እሳቸውንም የምናቀውቃቸው በተቃዋሚነት እንደመሆኑ መጠን፤ ራሳቸውን ከየትኛው ወገን አስቀምጠው ተቃዋሚውን እንደተቹ ከጽሁፋቸው ለማወቅ አልቻልኩም። “ከተቃዋሚው በኩል ምንም ይሁን ምን ነገሮችን አገዛዙን ከሚያዩበት መነጽር አኳያ” ነው ማለት ምን ማለት ነው አሁን?
  3. አቶ አያልሰው ደሴ አባይን ስለመገድብ ስልጣን ያስቀመጡትም ሀሳብ ምንጩና መሰረቱ ምን እንደሆነ አልተረዳኝም። አቶ አያልሰው እንዲህ ይላሉ፤

ዞሮ ዞሮ ለማንም በተገቢ ግልጥ መሆን ያለበት ጉዳይ ዓባይን በኢትዮጵያ ምድር ላይ የመገደብና ያለመገደብ ውሳኔ የኢትዮጵያዊያን ብቻ እንጂ በምንም መንገድ ለሱዳን፡ ለግብጽም ሆነ ለሌላ የውጭ ሀይል አሳልፎ የሚሰጥ አለመሆኑን ነው።

ይሄ ሀሳብ አንደኛ ከኮመን ሴንስም ከህግም አንጻር ስህተት የበዛበት ነው። ሁለተኛ አቶ አያልሰው ደሴ ከሚያራምዱት የጥንቃቄ ጉዞና የዲፕሎማሲ ትግል ጋር ይቃረናል።

  1. ጋሼ፤ ኢትዮጵያ ደሴት አይደለችም። አባይም ድንበር ዘለል ወንዝ ነው። ደርግም፤ አጼ ሀይለስላሴም አባይን በእኩልነትና በፍትሀዊነት ሰለመጠቀም ሲናገሩ እንጂ፤ ለብቻችን እንዳሻን የመገደብም ያለመገደብም መብት የኛ ነው ብለው ሲናገሩ የተጻፈበት ቦታ አላያሁም። አባይ ከኢትዮጵያ ይመነጫል እንጂ የኢትዮጵያ ብቻ አይደለም። ልክ ኮሎራዶ ወንዝ ከአሜሪካ ቢነሳም የአሜሪካ ብቻ እንዳልሆነው። ኢትዮጵያ የአባይ ብቸኛ ባለቤት ተደርጋ አልተፈጠረችም። ስለዚህም፤ የአባይን እጣ ፈንታ ለብቻዋ ልትወስን አትችልም። ያለበለዚያ ሰላማችን ይደፈርሳል። በውሀ ጥም ከመሞት ሲታገሉ መሞትን የሚመርጡ ይወሩናል። ተያይዘን እንጠፋለን። ለዚህም ነው ዲፕሎማሲው ያስፈለገው። አቶ አያልሰው ሌሎቻችንን ስሜታዊ እንዳንሆን እየመከሩ እሳቸው ራሳቸው ስሜታዊ ሆነው፤ የተሳሳተ ሀሳብ ነው ያራመዱት። አባይን መገደብ አለመገደብ የኢትዮጵያ ብቻ ጉዳይ አይደለም። አገር ወዳድነት አንድ ነገር ነው። ብሄራዊ ስሜትም አንድ ነገር ነው። ህግና አለማቀፍ ጉዳይ ደግሞ ሌላ ነገር ነው።
  2. በገጽ አምስት ላይ አቶ አያልሰው ደሴ የኢህአዴግ የዲፕሎማሲ ትግል ስላስገኘው ትርፍ ይተነትናሉ። በመሰረቱ እሳቸው እንዳሉት አባይን የመገንባት ጉዳይ የኢትዮጵያ ብቻ ከሆነ፤ የሌሎች አገሮችን ድጋፍ ማግኘት አስፈላጊነቱ አይታየኝም። ይሄ 9 የምስራቅ አፍሪካ አገሮችን ማሰለፍ መቻል ባንድ በኩል የዲፕሎማሲ ትርፍና ድል ቢመስልም፤ በሌላ በኩል አደጋም አለው። አቶ አያልሰው ደሴ ከሚሉት በተቃራኒ፤ 85 ከመቶ የአባይን ውሀ የምታመርት ኢትዮጵያ፤ ይሄንን የአባይ ጉዳይ በዚህ የአባይ ተፋሰስ አገሮች ማእቀፍ ማህበር ስር ለዘጠኝ አገሮች አሳልፋ መስጠቷ፤ ኢትዮጵያን ለነዚህ ዘጠኝ አገሮች ድምጽ እስረኛ ያደርጋታል። ለምሳሌ፡ የአስሩ አገሮች ስምምነት ተፈሳሱን የሚያስተዳዳር ኮሚሽን እንደሚቋቋም ይደነግጋል። ኢትዮጵያ በቀጣይነት በአባይ ላይ ልትገነባ የምታስባቸውን ግንባታዎች ሁሉ ለነዚህ የምስራቅ አፍሪካ አገራት ድምጽ አሳልፋ ልትሰጥ ነው ማለት ነው። ከድጡ ወደማጡ ነው ብሎ መከራከርም ይቻልል።
  3. የአቶ አያልሰው አስገራሚ መከራከሪያ ነጥቦች አያልቁም። ከሁሉም የገረመኝ ግን፡ በገጽ ስድስት ላይ፤ ግብጽና ሱዳን የኢትዮጵያን ሰላም ለማሳጣት ስለተጫወቱት ሚናና አሁን ያ ሚናቸው ስለመቀነሱ የተናገሩት ነው። የነሱ ሚና የቀነሰው አሁን ሳይሆን፡ ያኔ የዛሬ 22 አመት አሁን አራት ኪሎ ያሉትን ሰዎች አስታጥቀው ስንቅ ቋጥረው ስልጣን ላይ ካወጧቸው በሁዋላ ነው። ዛሬ እነሱዳንና ግብጽ ያስታጠቋቸው ቅጥረኞች አራት ኪሎ ቁጭ ብለው፤ አቶ አያልሰው በሱዳንና ግብጽ የጡት ልጆች ላይ ተማምነው ስለነሱዳን ሚና መመንመን ሲሰብኩና ስለ አባይ ግድብ ግንባታ ሲያወሱ እንቆቅልሽ ሆኖብኛል። እንዴት ያለው ሀሳብ ነው ባካችሁ?
  4. ከላይ የዘረዘርኳቸው አይነት ትንታኔዎች ላይ ተመስረተው ነው “ኢትዮጵያዊያን እንደ ህዝብ ይሄንን መሰል የሌለው ሁኔታ” እንዳገኘንና በወቅቱ ካልተጠቀምንበት፡ የመጪው ዘመን ኢትዮጵያዊያንን ምህረትና ይቅርታ የለሽ ምሬት እናተርፋለን ሲሉ የጻፉት። መቼም እውነተኛ ስሜቴን ለመደበቅ ብሞክርም፡ ይሄ ከአያ አያልሰው አምባ ሲመጣ ትንሽ ግራ እንደገባኝ ሳልናገር አላልፍም። አቶ አያልሰው ደሴ ክርክራቸው አንዳንድ ቦታ ላይ ለአንባቢያን ሀሁን የማስተማር ያህል ሆኖ ነው ያገኘሁት። አሁን በማዬ ሞት የአባይ ግድብ ተገንብቶ ሲያልቅ መብራት እንደሚያመነጭ፡ መብራቱ ለአገሬው ህዝብ እንደሚጠቅም፤ መብራቱም ከተሸጠ የውጭ ምንዛሪ እንደሚያስገኝ፡ ከጎረቤት አገሮች ጋር ያለንን ግንኙነትና ትስስር እንደሚያጠናክረው የማያውቅ አለ? አበሳጭተውኛል።
  5. እዚህ ጋር ካላቆምኩ፡ የኔም ጽሁፍ ሊንዛዛ ነው። ተንዛዛ እንጂ። ተንቀዋለለ።
  6. ባጠቃላይ የአቶ አያልሰው ደሴ ጽሁፍ አርቆ አሳቢ፡ ስትራቴጂካዊ፡ ሳይንሳዊና የበሰለ ለመምሰል ጥረት አድርጓል። በርግጥም አንዳንድ ጠቃሚ ሀሳቦችን ለመፈንጠቅ ሞክሯል። ነግር ግን፡ በአብዛኛው፡ ጽሁፉ በርስ በርስ ቅራኔ የሚሰቃይ፤ በኢህአዴግ የአባይ ግድብ ማጭበርበሪያ ዘመቻ ዙሪያ ያለውን ተቃውሞ  በቅጡ ያልዳሰሰ፤ ይልቅስ ሌሎችን በሚከስበት የስሜታዊነት ደዌ ክፉኛ የታመመ ሆኖ አግንቼዋለሁ። በመሰረቱ የአባይን የማጭበርበሪያ ግድብ የምንቃወመው ሰዎች ካለን፤ ተቃውሟችን አቶ አያልሰው ደሴ እንዳሉት ሳይሆን ….

ይቀጥላል …..

እኛው ነን። አያ ተክሌ፤ ከተረንቶ። ሰኔ፡ 2005/2013

በዚህ ይመይሉልን፡ lijtekle@gmail.com

ዓባይና የአሜሪካ ጨዋታ –ከፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

$
0
0

Pro Mesfinከመስፍን ወልደ ማርያም (ፕ/ር)

ሰኔ 2005

በአሥራ ዘጠነኛው ምዕተ-ዓመት አስተሳሰብ ከዚህ ቀጥሎ የተጠቀሰው ዓላማ ለአውሮፓ ቄሣራውያን ዋና ግባቸው ሆኖ እስከሃያኛው ምዕተ-ዓመት ዘልቆአል፤ አሀን ፈጽሞ በተለየ ዘመን አሜሪካ ይህንን አስተሳሰብ ይዞ የተነሣ ይመስላል።

ኢትዮጵያን የተቆጣጠረ ዓባይን ይቆጣጠራል፤ ዓባይን የተቆጣጠረ ግብጽን ይቆጣጠራል፤ ግብጽን የተቆጣጠረ ኃይልቀይ ባሕርን ከመግቢያና መውጫው ጋር ይቆጣጠራል፤ ቀይ ባሕርን ከመግቢያና መውጫው ጋር የተቆጣጠረ ኃይልዓለምን ይቆጣጠራል።

አሜሪካ በግብጽ ላይ የተከለው ጥፍሩ ሲነቃነቅ መነቀሉ አለመቅረቱን ስላወቀው ሌላ የሚተክልበት አገር ይፈልጋል፤ በአካባቢው የግብጽን ነፍስ የሚነካ ከኢትዮጵያ የተሻለ አገር የለም፤ ለአሜሪካ ዓለም-አቀፍ ዓላማ ኢትዮጵያ ስትመረጥ የአሁኑ የመጀመሪያው አይደለም፤ በመሀከለኛው ምሥራቅ የአረቦችን የተባበረ ኃይል ለመቋቋም የተመረጡ ሦስት አረብ ያልሆኑ አገሮች — ቱርክ፣ ኢትዮጵያና ፋርስ (ኢራን) — ነበሩ፤ በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የአሜሪካ ዓለም-አቀፍ ኃይል መሰማት በጀመረበት ጊዜ ኢትዮጵያን ከከበቡአት የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ጋር የነበርዋትን የቆዩ ውዝግቦች ለመቋቋም የአሜሪካ ድጋፍ በጣም አስፈላጊ ነበር፤ አሜሪካን ከአውሮፓ አገሮች ጋር እየመዘኑና እያመዛዘኑ የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስከበር የተደረገው ዲፕሎማሲ (ዓለም-አቀፍ የሰላም ትግል) የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን መንግሥት በእውነት ከሚያኮሩት ተግባሮች አንዱ ነው፤ ይህንን ትግል አምባሳደር ዘውዴ ረታ ምስጋና ይድረሰውና የኤርትራ ጉዳይ በሚለው መጽሐፉ ግሩም አድርጎ አሳይቶናል።

ምናልባት ገና ያልተጠና ጉዳይ በዘመኑ ኢትዮጵያ የነበራት ታሪካዊ ክብር ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ታሪክና ዝና ጋር ተዳምሮ በአፍሪካ ተደማጭነት ነበራት፤ ይህንን ኢትዮጵያ በአፍሪካ አገሮች ላይ የነበራትን ጫና (የዛሬውን አያርገውና) በመጠቀም አሜሪካ አፍሪካን በሙሉ ለዓላማዋ ለማሰለፍ ኢትዮጵያን መሣሪያዋ ለማድረግ ትሞክር ነበር።

እየቆየ የኢትዮጵያ መንግሥት የነጻነት መንፈስን በማሳየት ለአሽከርነት አልመች በማለቱና ለአሜሪካም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች (የእውቀት ጥበቦች) በመፈጠራቸው ኢትዮጵያ ለአሜሪካ ዓለም-አቀፍ ዓላማ አስፈላጊነትዋ በመቀነሱ አሜሪካ ኢትዮጵያን ችላ ማለት ጀመረ፤ የ1966 ግርግር ከዚህ ጋር ተያይዞ የመጣ መሆኑን ጠለቅ ብሎ ማጥናት ያስፈልጋል፤ በዚህ መሀልም የሶቭየት ኅብረት ዓለም-አቀፋዊ ጉልበት እየተሰማ በመሄዱ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የነበረውን ዓላማ ቀስ በቀስ እየለወጠ ሄደ፤ ከዚህም ጋር የሶቭየት ኅብረት ተጽእኖ እያደገ ሄደ፤ የአሜሪካ አያያዝ እየላላ ሲሄድ የሶቭየት ኅብረት አያያዝ እየጠበቀ ሄደ፤ 1966 የአሜሪካ መውጫና የሶቭየት መግቢያ ሆነ ለማለት ይቻል ይሆናል፤ ከዚሁ ጋር አብሮ የሚታየው በኢትዮጵያ የባህላዊው ሥርዓት መሰነጣጠቅና የቆየው ትውልድ መዳከም ነው፤ የአሜሪካ መዳከም ሶቭየት ኅብረትን ሲያጠነክር፣ የአሮጌው ትውልድ መዳከም አዲሱን ትውልድ አጠነከረ፤ ይህ ማለት አሮጌው ትውልድ ከአሜሪካ ጋር የተያያዘውን ያህል አዲሱ ትውልድ ከሶቭየት ኅብረት ጋር ተያያዘ፤ የኢትዮጵያ የውስጥ ሁኔታ ብቻውን ለውጥ እንዳላመጣና ዓለም-አቀፍ ሁኔታዎችና የልዕለ ኃያላኑ ተጽእኖም ምን ያህል እንደነበረ አመላካች ነው።

የአጼ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት መውደቅና የአሜሪካ ተጽእኖ መዳከም በአንድ በኩል፣ የደርግ መፈጠርና የእነኢሕአፓና መኢሶን በአጋፋሪነት መውጣት ከሶቭየት ኅብረት ተጽእኖ መጠናከር ጋር በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ ሁኔታን ፈጠሩ፤ የአዲሱን ሁኔታ አዲስነት በግልጽና በትክክል መገንዘብ ያስፈልጋል፤ በኢትዮጵያ ለብዙ ሺህ ዓመታት ተከብሮና ታፍሮ የቆየው የዘውድ ሥርዓት ተናደ፤ ተዋረደ፤ በኢትዮጵያ ስር እየሰደዱ የነበሩ መሳፍንትና መኳንንት ከስራቸው ተመነገሉ፤ አዲስ የመሬት አዋጅ ወጣና የመሬት ከበርቴዎችን ሙልጭ አውጥቶ ገበሬውን በሙሉ እኩል ባለመሬት አደረገው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻ ወጣ ባይባልም የኢትዮጵያ መሬት ነጻ ወጣ፤ ወታደር፣ ገዢ ሰላማዊው ሕዝብ ተገዢ ሆነ፤ ትርፍ መሬትና ትርፍ ቤት ሁሉ ተወረሰ፤ ቤትን የሚያከራዩ የኪራይ ቤቶችና ቀበሌዎች ብቻ ሆኑ፤ ደሀዎችንና መሀከለኛ ገቢ ያላቸውን ሰዎች ኑሮ ለማቃለል ከሦስት መቶ ብር በታች የነበረው የቤት ኪራይ ሁሉ ተቀነሰ፤ ደርግ በሁለት ዓመታት ውስጥ የአብዛኛውን ገበሬ ኑሮና የአብዛኛውን የከተማ ነዋሪ ኑሮ የሚነኩ መሠረታዊ ለውጦችን አወጀ፤ እያደር ደርግ አስከፊ እየሆነና እየተጠላ ቢሄድም እነዚህ ሁለት አዋጆች ብዙ ኢትዮጵያውያንን እስከዛሬ ድረስ ለደርግ ባለውለታ አድርገዋል፤ እነዚህ አዋጆች ወያኔ ገና አፍርሶ ያልጨረሳቸው የደርግ ሐውልቶች ናቸው።

በውጭ አመራር ደግሞ የአሜሪካ ተጽእኖ ክፉኛ ተበጠሰ፤ አሜሪካ ማለት ስድብና ውርደት ሆነ፤ አሜሪካ ማለት በዝባዥነትና የቄሣራዊ ተልእኮ አራማጅ ማለት ሆነ፤ የአሜሪካ ማስታወቂያ ቢሮ ተዘጋ፤ ብዙ የአሜሪካ እንደወባ መከላከያ ያሉ የተራድኦ ድርጅቶች ተዘጉ፤ አሜሪካ ለዩኒቨርሲቲዎች ሲያደርግ የነበረውን እርዳታ አቋረጠ፤ በዚህ በተለይም የዓለማያ ዩኒቨርሲቲ በጣም ተጎዳ፤ የወባ ቢምቢም ከ‹‹ኢምፒሪያሊዝም›› ጭቆና ነጻ ወጣችና  አዲስ አበባ ደረሰች! ይባስ ብሎም አለማያ ዩኒቨርሲቲ ያፈራቸው አሉ የተባሉት በተለያዩ የእርሻ ሙያዎች የተካኑት አብዛኞች ሙልጭ ብለው ከአገር ወጡ።

አሜሪካ ከደርግ ጋር እየተጋገዘ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ክፉኛ አዳከመው፤ አያይዞም በኢትዮጵያ ዳር ዳር የሚነደውን እሳት አቀጣጠለው፤ በአንድ በኩል የውስጥ ተገንጣይ ቡድኖችን — የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት፣ የኤርትራ ነጻ አውጪ ድርጅት፤ የኦሮሞ ነጻ አውጪ ድርጅት — በሌላ በኩል በድንበርም ሆነ በሌላ ምክንያት ከኢትዮጵያ ጋር የሚፋለሙትን አገሮች ሶማልያንና ሱዳንን በግልጽ መርዳት ጀመረ፤ እንዲያውም ከግብጹ ፕሬዚደንት ሳዳት ጋር እየተመካከረ ኢትዮጵያን ለማዳከም ሞከረ፤ ከመሞከርም አልፎ ኤርትራን አስገነጠለ፤ የኢትዮጵያን ዙፋን ለወያኔ አመቻቸ፤ አሜሪካ ኮሚዩኒስት ነኝ የሚለውን ወያኔን በጎሣ ፖሊቲካ አስታጥቆ ቀለቡን እየሰፈረ በኢትዮጵያ ላይ ሠራው፤ ደርግ በሰይፍ ብቻ አንድነትን ለማምጣት መሞከሩና ሕዝቡን ለጦርነት ማነሣሣቱ አሜሪካንን አስደንግጦታል፤ ለአሜሪካ ደርግ የቀሰቀሰው የአንድነት ብሔራዊ ስሜት የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ የሚፈስስ መስሎ ታየው፤ በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያን የአንድነት ብሔራዊ ስሜት የማፈራረስ እቅዱን አወጣ፤ የሚያሳካለትንም ቡድን አገኘ።

 

ጣህሪር አደባባይና ዓባይ

ስንት ሰዎች በካይሮ ያለው አደባባይ ከዓባይ ጋር ግንኙነት አለው ብለው ያምናሉ? እስቲ ጠጋ ብለን እንመርምረው፤ ጣህሪር አደባባይ የግብጽ ሕዝብ የነጻነት ጥሪ ነበር፤ በአሜሪካ አጋዥነት ተጭኖት የነበረውን አገዛዝ ለማውረድ ቆርጦ መነሣቱን የገለጸበት አደባባይ ነው፤ የጣህሪር አደባባይን ማእከል ባደረገ ቆራጥ ትግል አገዛዙን አንኮታኩቶ አወረደው፤ በሰላማዊና ሕጋዊ ምርጫ የግብጽ ሕዝብ አዲስ መንግሥትን መሠረተ፤  የእስልምና ወንድማማቾች የሚባለው ቡድን አሸናፊ ሆኖ መውጣቱን አሜሪካም ሆነ እሥራኤል በጸጋ የተቀበሉት አይመስልም፤ ስጋት አላቸው፤ ለግብጻውያን ከአገዛዙ ጋር የሚወርድ ሌላ ጭነት አለባቸው፤ አሜሪካ ለራስዋም ዓላማ ሆነ ለእሥራኤል ዓላማ በግብጽ ላይ የምታደርገውን ከባድ ጫና ማንሣት ከትግሉ ዓላማዎች አንዱ ነበር፤ አሜሪካንና እሥራኤልን ያሰጋው የለውጡ ዓላማ አገዛዙን መጣሉ ሳይሆን በእነሱ ጥቅም ላይ ያነጣጠረውን ክፍል ነበር፤ በጦር መሣሪያ በኩል ግብጽ የአሜሪካ ጥገኛ ነች፤ ቀደም ሲል የሶቭየት ኅብረት ጥገኛ ነበረች፤ በአሁን በአለው የጊዜው ትርምስ አሜሪካ ግብጽ አንዳታመልጠው ይፈልጋል፤ ስለዚህም ስጋት አለው።

ግብጽን ሰንጎ ለመያዝና ለማስጨነቅ ከዓባይ የበለጠ ኃይል የለም፤ ዓባይን ሰንጎ  ግብጽን ለማስጨነቅ ከኢትዮጵያ  የበለጠ  ምቹ  አገር  የለም፤ በተጨማሪም ኡጋንዳን፣  ኬንያንና ደቡብ ሱዳንን ከአሰለፈ ለአሜሪካ ሁኔታው ይበልጥ ይመቻቻል፤ ጫናው በግብጽ ላይ የጠነከረ ሊመስል ይችላል፤ አሜሪካ የግብጽን ወዳጅነት ለዘለቄታው ለማጣት ይፈልጋል? ለእኔ አይመስለኝም፤ አሜሪካ የአረቦችን ሁሉ ጠላትነት ይፈልጋል? ለእኔ አይመስለኝም፤ ታዲያ እስከምን ድረስ ነው አሜሪካ ግብጽን ለማስጨነቅ የሚፈልገው? ዋናው ጥያቄ ይህ ነው

ትልቁ የአስዋን ግድብ ሲሠራ የነበረውን ውዝግብና መካካድ ለማንሣት ይዳዳኛል፤ ግን ሰፊ በመሆኑ አልገባበትም፤ አንዳንድ ሁነቶችን ብቻ ልጥቀስ፡– የምዕራብ ኃይሎች በተለይም አሜሪካና ብሪታንያ ለግድቡ ሥራ አስተዋጽኦ ለማድረግ ቃላቸውን ከሰጡ በኋላ ሀሳባቸውን ለወጡ፤ የሶቭየት ኅብረት አንድ ቢልዮን ተሩብ ያህል ዶላር ለማበደር ዝግጁ ሆነ፤ ግብጽም ብድሩን ለመክፈል እንድትችል በዓለም-አቀፍ ኩባንያ ይተዳደር የነበረውን የስዌዝ ቦይ ብሔራዊ ሀብትዋ አድርጋ አወጀች፤ ይህንን በመቃወም ብሪታንያ፣ ፈረንሳይና እሥራኤል ግብጽን ወረሩ፤ በተባበሩት መንግሥታት ግፊት (አሜሪካና የሶቭየት ኅብረት በተባበሩት መንግሥታት መድረክ ላይ በአንድ ላይ የቆሙበት ብርቅ ሁኔታ ነበር፤) ወረራቸውን አቁመው ከግብጽ ወጡ፤ በኋላ ነገሩ ሁሉ ተገለባብጦ ግብጽ ሶቭየት ኅብረትን ትታ የአሜሪካ ወዳጅ ሆነች!

አሜሪካ የሶርያን ሳይጨርስ፣ የኢራንን ሳይጀምር ከግብጽ ጋር ውዝግብ ቢጀምር ምን ጥቅም ያገኛል? ደግሞስ በዓባይ ጉዳይ በኢትዮጵያና በግብጽ ውዝግብ የሚያሸንፈው አሜሪካ መሆኑ ያጠራራል ወይ? አሜሪካ ሲያሸንፍ ግን ከኢትዮጵያና ከግብጽ አንዳቸው ይወድቃሉ፤ ወይም ይቆስላሉ፤ ሁለቱንም እኩል አያቅፋቸውም፤ ደርግ አሜሪካንን በማስቀየሙ በአለፉት ሃያ ዓመታት በኢትዮጵያ መሬትና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ያስከተለው መዘዝ እያሰቃየን መሆኑን ልንረሳው አይገባንም

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያና በግብጽ መሀከል ያለው ጉዳይ አህያ ላህያ ቢራገጥ ዓይነት አይመስለኝም።

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. እና ኢትዮጵያ –ከገብረመድህን አረአያ (አዳዲስ መረጃዎች)

$
0
0

ወደ ግንቦት 20ቀን, 1983 .ከመግባታችን በፊት ትንሽ ወደ ኋላ መለስ በማለት የደርግ ስርዓትን በትንሹ እንቃኘው::

ደርግ

samoraየካቲት ወር 1966 ዓ.ም. የዘውድ አገዛዙን ስርዓት በመቃወም በአርሶ አደሩ ፣ በተማሪው ፣ በአስተማሪው ፣ በመንግስት ሰራተኛው ፣ በወዛደሩ ፣ በነጋዴው እና በመለዮ ለባሹ ወዘተ ፣ ወዘተ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ ጊዜ ሳይወስድበት በ6 ወራት ውስጥ የተነሳው ህዝባዊ አመጽ ግቡን መታ::

ህዝባዊ አመጹን የሚመራው የተደረጀ ፓርቲ ባለመኖሩ በር የተከፈተለት መለዮ ለባሽ አመቺ ሁኔታ በማግኘቱ በፍጥነት ተደራጅቶ ከተራ ወታደር ጀምሮ የተለያዩ ማእረግ ያላቸው አባላቱን አስመርጦ ወደ 120 የሚጠጉ ተወካዮቹን አዲስ አበባ በሚገኘው አራተኛ ክፍለጦር አሰባሰበ::

ከጦር ሃይሎች ፣ ከክቡር ዘበኛ እና ከፖሊስ የተውጣጡት እንኚሁ መለዮ ለባሾች በሰኔ ወር 1966 ዓ.ም. ተሰብስበው ብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ መስርተው “ኢትዮጵያ ትቅደም ፣ አቆርቋዥ ይውደም” በሚል መርህ ስር ሰፊ ሊባል የሚችል የህዝብ ድጋፍም አግኝተው ነበር::

መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም. የተመሰረተው አስተባባሪ ኮሚቴ ንጉሱን ከስልጣን አውርዶ “ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ” የሚል ስም በመያዝ ኢትዮጵያን ማስተዳደር ጀመረ:: ቀስ በቀስም ደርግ የስልጣን ወንበሩን በማመቻቸት የሃገሪቷ መንግስት ለመሆን ቻለ::

በወቅቱ በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች ሃገራት ሶሻሊዝም ወይም ህብረተሰባዊነት በሚባል ርዕዮተ አለም እድገት እና ብልጽግና የማይገኝበት “ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ” ስርዓት በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት እና ቻይና ፕሮፖጋንዳ አለምን እንደማዕበል ሲወዘውዛት የነበረበው ሁኔታ ሆኖ በደርግ የተመሰረተው መንግስት ግራና ቀኙን ሳይመለከት ሶሻሊዝም በኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈጥረውን ቀውስ እና ችግር ሳያጤን እና ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትን ሳያማክር በ1972 ዓ.ም. ኢሰፓአኮን(የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ አደራጅ ኮሚሽን) መሰረተ:: ይህንን ምስረታ ተከትሎም ደርግ አንድ እግሩን ገደል ከተተው::

በዚህ ጽሁፍ ሁለት ነገሮችን ለያይቼ በማሳየት ለማለፍ እሞክራለሁኝ፤

1.      ደርግ እንደ ፖለቲካ ተቋም እና ስርዓት

2.     መለዮ ለባሹ እንደ አገር መከላከያ ሰራዊት

ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያዊ የሆነ እና በዘመናዊነቱ በአፍሪካ ጭምር ተወዳዳሪ ያልነበረው እንደነበር ነው:: የደርግ ስርዓት ከወታደሩ በወጡ ሰዎች ቢመሰረትም ሰራዊቱ ግን በየትኛውም መለኪያ የኢትዮጵያ ሰራዊት ለመሆኑ ከጥያቄ ውስጥ ሊያስግባው የሚችል አንዳችም መከራከሪያ ሊቀርብ አይችልም:: አገራችን ዘመናዊ ጦር ማደረጀት ከጀመረችበት ከሃያኛው ክፍለዘመን መባቻ ጀምሮ በስንት ወጪ እና ጥረት የገነባችውን ጦር የ “ደርግ ጦር” የሚል ቅጽል በመስጠት ከፍተኛ የሆነ የስም እና የሞራል ማጥፋት ዘመቻ የፈጸሙበት ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑት ወያኔ እና ሻዕቢያ ናቸው::

ይህ ጦር ደሙን አፍስሶ ፣ አጥንቱን ከስክሶ ፤ ራበኝ ፣ ደክመኝ ሳይል ወያኔ እና ሻዕቢያን እግር እግራቸውን እየተከታተለ ሲደመሥሳቸው እና ሲያጠፋቸው የነበረ የኢትዮጵያ ብርቅ ልጅ ነው:: የዛሬው የወያኔ ዘረኛ ሰራዊት ግን እንኳን ስለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ሊከላከል ይቅርና ራሱ የወያኔ ሰራዊት ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ ህዝብ የአንድ ጎጠኛና ዘረኛ ታጣቂ ቡድን ነው:: አሁን ያለው በዘር የተደራጀው ቅጥረኛ እና ባንዳ ሰራዊት በየትኛውም መለኪያ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ተብሎ ሊወሰድ የሚችልበት ሁኔታ የለም::

የደርግ መንግስት በስልጣን በቆየበት 17 አመት ውስጥ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ቀይ ባህርን የጠበቀ ፤ ከገንጣይ እና አስገንጣዮች አገሪቷን እየተከላከለ ሉዓላዊነትን የጠበቀ የኢትዮጵያ ስርዓት ነበር::

በሚከተለው ርዕዮተ አለም ቀስ በቀስ እየተዳከመ በመሄድ እንደነበረው አገርና ህዝብ ለማዳን አልቻለም:: ደርግ በተዳከመ ጊዜም ሰራዊቱ ይዳከማል:: አንድ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ከመንግስት የሚቀርብለት ነገሮች ብዙ ናቸው:: ይህ አልሆነም:: ሰራዊቱም መንግስት በመዳከሙ ምክንያት የነበረው አልበገር ባይነት ስሜቱ እና ጀግንነቱ የውጊያ ብቃቱ ተስፋ በመቁረጡ ችግር እየፈጠረለት ሄደ ቢሆንም ግን ወያኔም ሆነ ሻዕቢያ አሁንም ፈቀቅ ሊሉ አልቻሉም:: የማይበገር የኢትዮጵያ ሰራዊት መሆኑን ያውቁታል እና::

seyoum_mesfinይህ በዚሁ እንዳለ የሃገሪቱ ፕሬዚደንት መንግስቱ ሃይለማሪያም ግንቦት 13 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያን ለቀው ዚምባብዌ ሃራሬ ገቡ:: እዛም ጥገኝነት ጠየቁ:: መሆን የማይገባውን ስራ ሰሩ:: በኢትዮጵያ ሃገራቸው ሰርተው ሂወታቸው ቢያልፍ ታላቅ ስምና ክብር ያገኙ ነበር:: ግን አላደረጉትም:: ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ ሰራዊት ተበተነ::

ግንቦት 15 ቀን 1983 ዓ.ም. በፕሬዚደንት መንግስቱ እግር የተተኩት ጀነራል ተስፋዬ ገብረኪዳን በዜና እወጃ የኢትዮጵያ ሰራዊት የነበርከው በያለህበት ቦታ መሳሪያህን ለህወሃት(ኢህአዴግ) እና ለሻዕቢያ እያስረከብክ ወደ ምትፈልግበት ሂድ፤ ሻዕቢያም ኤርትራን ህወሃትም ኢትዮጵያን እንዲቆጣጠሩ ፈቅደናል በማለት ፍጹም ክህደት በሆነ መንገድ ኢትዮጵያ እና ህዝብዋን ለደመኛ ጠላቶች አሳልፈው ሰጡ::

ያን በወታደራዊ ሳይንስ እና የጦር ውጊያ የተከማቸ እውቀት እና ችሎታ የነበረውን የኢትዮጵያ የሃገር መከላከያ ሰራዊት እልም ባለ ገደል ወረወሩት:: ለስንት አመታት የሃገሩን ዳር ድንበር ያስከበረ እና የጠበቀ ጦር ግንቦት 15 ቀን 1983 ዓ.ም. ካልምንም መተዳደሪያ እና የአገልግሎት ክፍያ በየበረሃው ተበተነ:: በስንት ሚሊዮን የሚቆጠሩ የምድር ጦር ፣ አየር ሃይል ፣ ባህር ሃይል ፣ አየር ወለድ እና አየር መቃወሚያ አባላት እና ቤተሰቦች ለመከራ እና ለችግር ተዳረጉ::

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ወያኔና ሻዕቢያ:: ሻዕቢያ ኤርትራን ሲቆጣጠር ወያኔ ህወሃት ደግሞ ግንቦት 15 ቀን 1983 ዓ.ም. በፈንደቀለት ጸሃይ አዲስ አበባን ግንቦት 20 ቀን 1983 ተቆጣጠረ:: ኢትዮጵያም ለፋሺስት መሪዎች ተዳረገች:: ሰራዊቱ እየጫነ ካለምንም ችግር ካለ ምንም ውጊያ ወያኔ ኢትዮጵያን ተቆጣጠረ:: ከግንቦት 20 ቀን ጀምሮ ወያኔ በከፊል የተቆጣጠረው ወሎ ፣ ጎንደር እና ጎጃም ብቻ ነበር:: ቀሪው የኢትዮጵያ ግዛቶች በተለይ ደቡብ ምስራቅ-ምዕራብ ወያኔ የገባው ከሶስት ወር በኋላ ነበር እንጂ:: ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ አልተቆጣጠረም:: ወደ አዳዲስ ክፍለ ሃገራት ሲሄድ ብዙ ገንዘብ በመክፈል በነዋሪዎች እየተመራ ነው:: ምክንያቱም ወያኔ ህወሃት ከትግራይ አይወጣም ነበር::

ስለሆነም ለኢትዮጵያ ነጻነትና ዲሞክራሲ ስል ብዙ መስዋትነት ከፍያለሁ የሚለው ከንቱ ውሃ የማይቋጥር መፈክሩ ይህ ትልቅ ምስክርነት የሚያሳየው ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን እንደማያውቃት ነው::

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ለኢትዮጵያ እና ህዝብዋ ምን ይዛ መጣች? በግንቦት 20 ኢትዮጵያ አገራችን በጨለማ ጉም ተሸፈነች:: አገርና ህዝብ ጥቁር የሃዘን ልብስ ለበሱ:: ሲጠሏት እና ታሪኳን እና ህዝቧን ሲያዋርዱን ሲያንቋሽሹ በነበሩት ወያኔ ህወሃት ለእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ተዳረገች:: ዘረኛው እና ጎጠኛው ወያኔ ህወሃት በመለስ ዜናዊ የሚመራው የማፍያ ፋሺስት ግልገል እና ግብረ አበሮቹ ጸረ ሀገር እና ጸረ ህዝብ የሆኑትን ለዘመናት የተከበረው የምኒሊክ ቤተ መንግስት ተቆጣጥረው የግልገል ፋሺስቶች መንደላቀቂያ ሆነ:: እነሱም ስልጣን እንደጨበጡ ኤርትራን አስገንጥለው የቀይ ባህር ንግስት የነበረችው ኢትዮጵያ ወደብ ወይም የባህር በርዋን አጥታ አንገትዋ የተቆረጠ ዝግ አገር አደረጉዋት::

ወያኔ ህወሃት ከደደቢት ይዞት የመጣውን ህገ ደንቡን የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አደረገው:: ኢትዮጵያን በዘር ፣ በቋንቋ እና በሃይማኖት ከፋፍሎ የህዝቡን አንድነት እና ኢትዮጵያዊነት አጠፋዋለሁ ብሎ ያመጣውን የዘረኝነት ህጉን በኢትዮጵያ ዘረጋ::

ይህ በዚህ እንዳለ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያ እና ግንቦት 20 ምን ይዞለት መጣ? የኢትዮጵያ ህዝብስ ከግንቦት ሃያ ቀን ምን ተጠቀመ? ምን እድገት አገኘ? ፍትህና ነጻነቱ እንዲሁም ሰብዓዊ መብቱስ እንዴት ሆነ? የሃገሪቷ ሃብትስ በትክክል ለህዝብ ጥቅም ዋለ ወይስ ምን ሆነ? የትምህርት እድገቱስ? የዘመናዊ ቴክኖሎጂስ ለህዝብ ተስፋፋ ወይ? ሌላም ጥያቄዎችን ማንሳት ይቻላል:: ለሰው ልጅ አደገኛ ጠንቅ ዕጽ መስፋፋት ለምን? ሽርሙጥና መስፋፋት ለምን? ስራ አጥነት ፣ የወንጀል ድርጊት መስፋፋት እንዴት እና ለምን? የህዝብ መፈናቀል ለምን? የዘር ማጥፋት በኢትዮጵያ ስለምን ተደረገ? ወዘተ ::

ወደ ግንቦት 20 1983 ዓ.ም. ከመግባታችን በፊት ከ17 አመታት በፊት ወያኔ ህወሃት እንደተፈጠረ የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም. የትግራይ ህዝብ የአደረበትን ስሜት ባጭሩ ልዳሥ::

ወያኔ ህወሃት በዚሁ ቀንና ወር ደደቢት በረሃ ሲወጣ የትግራይ ህዝብ የዚሁ እኩይ ድርጅት ማንነቱን አያውቅም ነበር:: ቀስ በቀስም በየቦታው ብቅ ጥልቅ ሲል የትግራይ ህዝብ አልተቀበለውም::በህዝቡ ወያኔ ህወዋት ተቀባይነት በማጣቱ የተነሳ ምክንያት ጭንቀትን ንዴት የተነሳ በሰላማዊ የትግራይ ተወላጆች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመረ:: አስገድዶ ንብረቱን መውረስ እና አስገድዶ እርዳታ እንዲሰጥ ተደረገ:: ምክንያቱም የሚከላከልለት ረዳት የሌለው ህዝብ ሻዕቢያ፣ ወያኔ እና ጀብሃ ሶስቱ በየፊናቸው አስቸገሩት:: የትግራይ ህዝብ ከየቦታው እየተለቀመ ተገደለ::

ከዚህም ቀጠል በማድረግ ወያኔ ህወሃት በሃይማኖት ጣልቃ በመግባት ክርስቲያን ጸረ ክርስትና እስላሙ ጸረ እስልምና ሃይማኖታቸውን እንዲያወግዙ የተቻለውን ቢሰራም አልሆነለትም::

ጸረ ህወሃት እና ጸረ ሻዕቢያ እየተባሉ ያልሆነ ያላሰቡት ብዙ ፣  ብዙ የትግራይ ሰላማዊ ዜጎች ሃለዋ ወያኔ (06) እየገቡ እሱም/እርሳውም ተገድለው ቤት ያፈራው ሃብታቸው ተወርሰው ህጻናት አልባሌ ቦታ ወድቀው ቀርተዋል::

በየከተማው ወያኔ ህወሃት ሽብርተኞች () በማሰማራት በጠራራ ጸሃይ ብዙ ሰው ገድለዋል:: ህወሃት የትግራይን ህዝብ እንደግሉ መሳሪያ አድርጎ የሚናገረው የትግራይ ህዝብ ከመጀመሪያ ትግሉ ጀምሮ እስከ 2005 ዓ.ም. ለወደፊትም አልተቀበለውም:: አይቀበለውምም:: ህወሃት የሚቀልደው ያለ ጉልበቱ ተማምኖ ነው:: ለዚሁም ዋና ምስክር ምርጫ 97 ዓ.ም. ትግራይ ወያኔ አልመረጠውም:: ለወደፊቱም ወያኔን አይመርጥም:: ሁለቱ ሊታረቅ የማይችል ቂም አላቸውና::

ወያኔ ህወሃት የትግራይ ወጣት ሴት ፣ ወንድ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ለሻዕቢያ አሳልፎ በመስጠት በማያውቁት የኤርትራ በረሃዎች ሞተዋል:: እዛው አጥንታቸው ተበታትኖ መቅረቱ የትግራይ ህዝብ እስከ አሁን ደም እያለቀሰ ያለበት ጊዜ ነው::

በአጠቃላይ በትግሉ ወቅት በትግራይ ህዝብ ወያኔ ህወሃት የፈጸመው ግፍ በከፍተኛ ወንጀል የሚይስጠይቀው ነው:: የትግራይ ህዝብ ወያኔ የተፈጠረባት የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም. በሚከበርበት ጊዜ በየቦታው የሚጠራበት ስም አለው:: በተምቤን አካባቢ “የተረገመች ቀን” ሲላት በአድዋና አክሱም አካባቢ “የጨለማ ቀን”" ሲለው በሽሬ አካባቢ ደግሞ “የእልቂት ዘመን” ይለዋል::

ወያኔ ህወሃት በለስ ቀንቶት አዲስ አበባን የተቆጣጠረበት ቀን ግንቦት 20,1983  ኢትዮጵያ እና ህዝቧ በደመኛ ጠላታቸው የወደቁበት እና በእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ የመጣበት ቀን ነው::

ከዚሁ ቀን መነሻ በማድረግ ወያኔ በኢትዮጵያ ህዝብ የነበረው ቂም በቀል በማያቋርጥ ሁኔታ በ22 አመት የወያኔ ህወሃት አገዛዝ የወረደበት ግፍና ሰቆቃ ቀጥለን ባጭር ባጭሩ እንመልከት::

ግንቦት 21 ቀን 1983 ዓ.ም. ወያኔ ኤርትራን አስገነጠለ:: ኢትዮጵያንም ካለ ባህር በር አስቀራት::

ወያኔ ህወሃት የኢትዮጵያ ዝነኛው ምድር ጦር ፣ አየር ሃይል ፣ ባህር ሃይል ፣ ፖሊስ ወዘተ የጠላይ ጦር በማለት ይደርግ ስርዓት በራሱ ሂደት ተመናምኖ በወደቀበት ለብዙ አመታት የሃገሩ ዳር ድንበር ሲያስከብር ከጠላት ሲከላከል የነበረው ካለምንም ጡረታና መተዳደሪያ የ”ጠላት ጦር” በማለት ለልመና እና ለችግር ዳረገው:: የሚይስተዳድራቸው ቤተሰቡ በሚልዮኖች የሚቆጠር ለረሃብ እና ችግር ተዳርገው ተበታትነው ቀሩ:: ከትግራይ ይዟቸው የመጣ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች የሃገር መከላከያ ሰራዊት አደረገ:: ቀሪዎቹን ታጋዮች ደግሞ ፖሊስ ፣ ደህንነት በማለት ዘረኛ ሰራዊት በኢትዮጵያ አቋቋመ:: ይህም በምንም አይነት ኢትዮጵያን የማይወክሉ ሁሉም ከላይ እስከ ታች ለነዚህ ተሰጠ:: እነዚህም በፊናቸው በኢትዮጵያ ህዝብ አስከፊ ሰቆቃና ግድያ በህዝቡ እየፈጸሙ ይገኛሉ::

ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ በዘር ማጥፋት ወንጀል ተሰማራ:: ዘር ማጥፋቱን ገና ከ1969 ዓ.ም. የጀመረው ሲሆን በበለጠ ደግሞ ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ አማራው ከያለበት እየተፈለገ ዘሩን ማጥፋት ተጧጧፈ ቀጥሎም ኦሮሞ ፣ ጋምቤላ ፣ አፋር ፣ ቤኑሻንጉል ወዘተ :: በትግራይ ውስጥም አደገኛ ጠላት ናቸው የሚላቸውን በዘዴ አጠፋቸው::

ወያኔ ህወሃት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ የአማራው ቋንቋ ስለሆነ ይህ ቋንቋ የትምህክተኛና የነፍጠኛው ቋንቋ በየትኛውም ክልል እንድይነገር በማለት የኢትዮጵያ ህዝብ መገናኛው እና ሃሳብ ለሃሳብ የሚለዋወጥበት ለስንት ሺህ አመታት ሲጠቀምበት የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔ ህወሃት እያጠፋው ይገኛል:: በየትኛውም ክልል አማርኛ መናገር በህጉ ከለከለው::

ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን በዘር በቋንቋ ከፋፍሎ ሲያበቃ ለዘመናት ኢትዮጵያዊው ህዝብ በፈለገው ቦታ ሲኖርና በጋብቻ በደም የተዋሃደው ህዝብ ከየክልላችሁ ከሌላ ቦታ የመጣውን ተስፋፊ ህዝብ አስወጡ በማለት እርስ በርሱ በማጋጨት ብዙ ሂወት ጠፍቶ ንብረቱም ተዘርፎ በየበረሃው ተበትኖ ግንቦት 20 ቀን 1983 ይዞት የመጣውን መከራ ገፈት ቀማሽ ሆነ:: በተለይ አማራው::

ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ማድረጉ አልበቃ ብሎት በ19ኛው ክፍለ ዘመን ሱዳን በእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ በምትደዳርበት ገዳሪፍ በተባለው የሱዳን ግዛት አስተዳዳሪ በነበረው ሻለቃ ጉዌን የወሰን መስመር ለጣልያኖች ይጠቅማል በማለት በ1903 እ.ኤ.አ በህገወጥ መንገድ የነደፈው የመስመር ክልል በአጼ ምኒልክ ኋላም በአጼ ሃይለስላሴ እና በደርግ መንግስት ውድቅ የተደረገው እና ተቀባይነት ያጣውን ወያኔ ህወሃት ከየት እንዳገኘው ሳይታወቅ የኢትዮጵያን የወሰን ድምበር በመጻረር ለወዳጁ ሱዳን ከሰቲት ሁመራ እስከ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ድረስ ወደውስጥ ከ40 እስከ 60 ኪ.ሜ. የሚዘልቅ እና 1,600ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው ለሱዳን መንግስት የአንዲት ኢትዮጵያን ሰፊና ለም መሬት የሸጠ ወያኔ የሱዳን መንግስት ለውለታው ከገዳሪፍ እስከ መቀሌ የባቡር መንገድ እንደሚዘረጋ የሃገራችንን ሉአላዊነት በመድፈር ለግል ጥቅሙ ሃገራችን እያወደመ ያለ ስርዓት ነው:: የግንቦት 20 ቀን 1983 መዘዝ::

ወያኔ ህወሃት በተፈጥሮ ባህሪው አምባገነን እና ሽብርተኛ ድርጅት እሱን የሚቃወም እና የሚፈጽመው ግፍ እንዲነሳበት አይፈልግም:: ፍላጎቱ ተሳስተሃል አትበሉኝ:: ስለኔ አትናገሩ ከሚለው ፋሺስታዊ ባህሪው በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ እንዲኖር አይፈልግም:: የህዝቡ በነጻነት መናገር እና ሃሳቡን መግለጽ ለወያኔ እንደ እሳት የሚለበልበው ለመሆን የፕሬስ ነጻነት ያገደው:: ይህም እንደ ገዢ ፓርቲ ህወሃት የታገደ ነው:: በዚሁ ፖለቲካዊ ውሳኔ የነጻ ፕሬስ በማደን ፣ በማሰር ፣ በማንገላታት ሳያበቃ ብዙ የፕሬስ ጋዜጠኞች ሃገራቸውና ቤተሰቦቻቸው ለመከራን ስደት ተዳረጉ:: ነጻ ፕሬስ በኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ተዘጋ::

ወያኔ ህወሃት የሽግግር መንግስት ብሎ ከሰኔ ወር 1983 ዓ.ም. እስከ ግንቦት ወር 1985 ዓ.ም.  በስልጣን በቆየበት ምርጫ በማለት በጸረ ዲሞክራሲያዊ መንገድ በ1987 ዓ.ም. , በ1992 ዓ.ም. , በ1997 ዓ.ም. እና በ2002 ዓ.ም. በማካሄድ በተለይ በ1997ዓ.ም. ቅንጅት በተለያዩ ፓርቲዎች ቀስተ ደመና ፣ መኢአድ ፣ ኢዴሊ ፣ ኢዴአፓ-መድህን ወዘተ በተጠናከረ ማዕከላዊ ፓርቲ “ቅንጅት” ተብሎ እንደተመሰረተ እምነቱ መሰረታዊ ኢትዮጵያዊ ዲሞክራሲና እድገት ፣ ብልጽግና ፣ ፍትህ ፣ ነጻነት ፣ ከዘረኝነት የጸዳ በምርጫው ለመወዳደር በቀረበበት ምርጫም ተካሂዶ መሉ በሙሉ አሽንፎ ሲወጣ በአንጻሩ ወያኔ -ህወሃት/ኢህአዴግ በዜሮ ተሸንፎ ከምርጫ የወጣው በጉልበቱ ምርጫውን በመንጠቅ ድምጻችን አይነጠቅም ብለው የወጣውን ሰላማዊ ዜጎች በአግአዚ ቅልብ የመለስ ዜናዊ ጦሮች ግደሉት ብሎ ትዕዛዝ በመስጠት ብዙ ኢትዮጵያውያንን ሲገደሉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ በየወህኒ ቤት በማሰር ወያኔ ህዝብ ያጠፋበት ቀን የሌባው አይነ ደርቁ ወያኔ በ2002 ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ እንደልማዱ ኮረጆውን በመገልበጥ 99.6% አሸነፍኩ ብሎ ኢትዮጵያና ህዝብዋን ማውደሙን ቀጠለ:: ይህ ሁሉ ችግርን ግድያ ሰቆቃ የግንቦት 20ቀን 1983 ዓ.ም. ውጤት ነው::

ወያኔ ህወሃት በፕሮግራም እንዳስቀመጠው የኤርትራ ጥያቄ ያላንዳች ጥርጥር ሃቀኛና ታሪካዊ መሰረት ያለወ ጸረ ቅኝ አገዛዝ ትግል ነው በማለት ወያኔ ያመነበት ነገር ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የማያምንበት የኤርትራ ህዝብም ያላመነበት በኢትዮጳዊነታቸእው የማያምኑ መሆናቸው አንዳች ጥርጣሬ የለውም:: ድርጊቱ የወያኔ ብቻ ነው:: ይህ በዚህ እንዳለ አሰብ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የኤርትራ ግዛት አልነበረችም ሁሉ ተከታታይ ዘመናት በወሎ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ ሆና ስትተዳደር እንደነበረች ሁሉ ኢትዮጵያ በትክክል የሚያውቀው ሃቅ ነው:: አሰብን በኤርትራ ካርታ ጨምሮ በ1967 ዓ.ም. ያወጣው ወያኔ ብቻ መሆኑን በግልጽ የሚታወቅ ሃቅ ነው:: ወያኔ ህወሃት ይህን የታሪክ እና የሃገር ክህደት የፈጸመው ሆን ተብሎ ኢትዮጵያ የባህር በር እንዳይኖራት ያደረጉት ኢትዮጵያና ህዝብዋ ጠላት ብለው ስለአስቀመጡት የፈጸሙት ጥቃት ነው:: ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን ወሮ እንደተቆጣጠረ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያ የባህር በሯን አጣች::

ይህን በተመለከተ ወያኔ/ህወሃት እና ሻዕቢያ እንግሊዝ አገር ለንደን ከተማ ከግንቦት 5 ቀን እስከ ግንቦት 9 ቀን 1983 ዓ.ም. የቀድሞው የአሜሪካ  ፕሬዚደንት ጂሚ ካርተር የሻዕቢያ መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ እና የወያኔው መሪ መልስ ዜናዊ ባሉበት ስብሰባ ኢትዮጵያ 85 ሚሊዮን ህዝብ ስላለባት የባህር በር ያስፈልጋታል:: አሰብም ከኤርትራ ያልተካለለ በመሆኑ በአጼ ኃይለስላሴም ሆነ በደርግ ስርዓትም ከኤርትራ ውጭ ሆኖ በወሎ አፋር የተካለለ ስለነበር ቀደም ሲልም አሰብ ከኤርትራ ውጪ ሆኖ በጣሊያንም ብዙ ያልተደፈረች የኢትዮጵያ የባህር በር እንደነበረች ይታወቃል:: አሰብ የኢትዮጵያ የባርህ በር መሆን አለበት ብለው ሃሳባቸውን ሲያቀርቡ የወያኔው መሪ መለስ ዜናዊ በጣም ተናዶ ኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ አገዛዝ የወደቀች ሃገር የነበሩ አመራር አጼ ኃይለስላሴ ሆኑ ደርግ ያስቀመጡት ካርታ ህወሃት አይቀበልም:: አሰብ የኤርትራ መሬት ነው:: እኛ አሁን በኢትዮጵያ ስልጣን የምንቆጣጠረው የወደብ ችግር አይኖረንም:: ችግር አይፈጠርብንም:: ብንፈልግ ጂቡቲን አሊያም የሶማሊያ እና የኬኒያን ወደቦች እንጠቀማለን:: አሰብ የኤርትራ ስለሆነ እምነታችንም ይህ በመሆኑ አሰብ የኤርትራ እንጂ የኢትዮጵያ አይደለም::

ፕሬዚደንት ጂሚ ካርተር እና ሌሎች አደረዳሪዎች አቶ መለስ ዜናዊ አሰብን የኤርትራ ነው ፤ የወደብ ችግር የለብንም ብለው እኛንም ስለአሳመኑን አሰብ በኤርትራ ውስጥ መካተቱን ተቀብለናል በመለት ሲዘጉት ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን ታሪካዊና ጥንታዊው የባህር በርዎችዋን አሳጥቶ ግንቦት 20 ቀን 1983ዓ.ም. አገራችን ኢትዮጵያን በጠላቶችዋ እጅ የወደቀችበት የኢትዮጵያ ህዝብም በድቅድቅ ጨለማ እና ጭቆና ፋሽስት ስርዓት ይዛ የመጣች ይህች ግንቦት የተረገመች ቀን ናት:: በምስራቅ-ምዕራብ-ሰሜን-ደቡብ የሚገኙ ኢትይጵያውያንም እየተረገመች ነው:: 

ወያኔ ህወሃት በግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያን በለስ ቀንቶት ወሮ በተቆጣጠረበት ወቅት የኢትዮጵያን ሃብት-ንብረት ወያኔና ሻዕቢያ ተባብረው ዘረፉት:: የወላድ መሃን የሆነችው ኢትዮጵያ ተከላካይ የሌላት ሁለት ከደደቢትን ከሳህል በረሃ የመጡት ሙሉ ሰራዊታቸውን በማሰማራት ሃብትዋን ንብረትዋን ዘርፈውታል:: የተለያዩ ተቋማት ተዘርፈዋል:: ጠቅላላ ጥሬ ገንዘብዋ ተዘርፏል:: ጥሬ ህብቶቿ ተዘርፏል:: የቀራት ነገር የለም:: ለውጪ ገበያ ለሺያጭ የሚመረት ቡና ፣ ሰሊጥ ፣ አደንጓሬ ወዘተ አይን ባወጣው ዝርፊያ ቀን እና ሌሊት ተፈጽሞባታል:: ዝርፊያው በግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የጀመረው እስከ አሁን ቀጥለውበታል:: ኤርትራ የቡናና የቅባት ምግብ አምራች በመሆን በአለም ገበያ አቅራቢ ሆና ከዓለም 3ኛውን ደረጃ ያዘች:: ከኢትዮጵያ በተዘረፈው ጥሬ ሃብት ዋና ገንዘብ ወያኔ ህወሃት መሪዎች 1. መለስ ዜናዊ እና ባለቤቱ አዜብ መስፍን 2.ስብሃት ነጋ 3.አባይ ጸሃዬ 4.ስዩም መስፍን 5.አርከበ እቁባይ 6.አዲስ አለም ባሌማ 7. አባዲ ዘሙ 8.ጸጋይ በርሄ እና ባለቤቱ ቅዱሳን ነጋ 9.ተክለወይኒ አሰፍ 10.ብርሃነ ገብረክርስቶስ ወዘተ ሆነው ኢፈርተን አቋቁመው ስልጣኑንም ተቆጣጥረው የናጠጡ ባለብዙ ፋብሪካዎች ትልልቅ ተቋማት መስርተው ቱጃር በለሃብቶች ሆነዋል:: ወያኔ ህወሃት ወደ ስልጣን ባልበቃበት ጊዜ በአጼ ኃይለስላሴና በደርግ ስርዓት ነጻ ተቋም በመሆን የኢትዮጵያን ህዝብ ሲያገለግሉ የነበሩትን ብሄራዊ ባንክን ፣ ንግድ ባንክን ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ፣ እርሻ ትራንስፖርት ፣ መአድናት ወዘተ ወያኔን ስልጣን እንደጨበጠ ሁሉን ከህዝብ በጉልበቱ ነጥቆ በመቆጣጠር የሃገርና የህዝብ ሃብት የህወሃት ተቋማት ሆኑ:: ይህም ወያኔ ህወሃት በከፍተኛ ወንጀል የሚጠየቅበት ከዋናዎቹ አንዱ ነው:: 

effortወያኔ ከኢትዮጵያ የዘረፈው ገንዝብ እና ጥሬ ሃብት ኢፈርት በትግርኛ ት.እ.ም.ት የሚል ስያሜ በመስጠት በትግራይ ህዝብ ስም ሲያጭበረብር የትግራይ ህዝብ መነገጃ ማድረጉም ህወሃት በዚሁ ሌብነቱ በወንጀል የሚያስጠይቀው ነው:: በትግራይ ህዝብ ስም የወያኔ መሪዎች ነገዱበት እንጂ የትግራይ ህዝብ ከት.እ.ም.ት ተጠቃሚ አይደለም:: ህዝቡም ራሱ የሚናገረው ሃቅ ይህ ነው::

ወያኔ ህወሃት ድርጅት ነው ስንልም ህወሃት የተመሰረተውና እስከ አሁንም ያለው ህወሃት ግለሰቦች ተደራጅተው የፈጠሩት የማፍያ ስብስብ እንጂ በምንም ተአምር የትግራይ ህዝብን የማይወክል ነው:: በድርጅቱ የተሰባሰቡ ግለሰቦችን ያቀፈ:: ህዝብ ሌላ፤ ህወሃት ሌላ:: ህወሃትን የመሰረቱት ሰዎችም ጸረ ህዝብ እና ጸረኢትዮጵያ ናቸው:: ይህ ህወሃት ተብሎ የሚጠራ በሻዕቢያ የተመሰረተ ኤርትራን ነጻ ለማውጣትና ትግራይም የአማራው ቅኝ ግዛት በማለት የተነሳ ከጥዋቱ ኢትዮጵያዊነቱን የካደ የከሃዲዎች ስብስብ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ሰላማዊ ዜጎች የገደለ ጸረ ህዝብ ነው:: በመሆኑም የትግራይ ህዝብ ገና ከትግሉ መነሻ ጀምሮ ህወሃትን በእውቅና አልተቀበለውም::

ወያኔ ህወሃት ገና በ1968 ዓ.ም. በኢትዮጵያ መሬት እጠቀማለሁ በማለቱ ከባድሜ እስከ አፋር ቡሬ የመሬት ቆዳ ስፋት 1.ታች አዲያቦ 2. ላይ አዲያቦ 3.ጭላ ወይም አንከረ ባሩካ 4. አሕሰኣ 5.እገላ 6.ዛላምበሳ  በዚሁ ውስጥ የሚጠቃለሉ ኢሮብ ፣ ጻልገዳ ፣ ዓውዳ ፣ አይጋ ፣ ሶቦያ ፣ ወዘተ 7.የአፋር መሬት  እስከ ቡሬ 8. አሰብ የኤርትራ መሆንዋን በዚሁ ፊርማቸው በ1969 ዓ.ም. አረጋግጠዋል:: 1. መለስ ዜናዊ 2.አባይ ጸሃዬ 3.ስብሃት ነጋ በዋናነት የሚጠቀሱ በትክክል የኤርትራን መሬት ነው በማለት ፈርመው የሰጡት ህዳር ወር 1969 ዓ.ም. ነው:: በዚሁ መሰረት የትግራይ ህዝብ 1.በሻዕቢያ 2.በጀብሃ 3.በህወሃት  በእነኚህ ሶስት ድርጅቶች ትተዳደራለህ ብለው በመወሰን ህዝቡም በእነኚህ ሶስት ድርጅቶች ቁም ስቃዩን በማየት ተገደለ:: ንብረት ሃብቱ ተዘረፈ:: አቤት የሚባልበት በማጣት በየስደቱ ተበታተነ:: ወያኔ ይህን ወንጀል እንደፈጸመ በአንጻሩ ከሰሜን ጎንደር እና ሰሜን ወሎ ለም ወሬት ነጥቆ ወሰደ::

የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ዋና ጦሱ ከላይ እንደተጠቀሰው ነው:: የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት መንስኤ   ው በግልጽ የሚታወቅ ነው:: ወያኔ ህወሃት አመራር የሚያላክኩት በኢኮኖሚ ችግር የተፈጠረነው ሲሉ በተደጋጋሚ በተለይ የወያኔው መሪ ነበር መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማሳመን ለከት በሌለው ውሸቱ ሲለፋደድ ሃገር ሙሉ ያውቃል:: ቀሪዎቹ የሱ የአመራር አባላቱ ስብሃት ነጋ ፣ አባይ ጸሃየ ፣ ስዩም መስፍን ፣ አርከበ እቁባይ ወዘተ የመለስ ዜናዊን ሃሳብ በማስተጋባት በየውጪ ሃገሩ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለማሳመን ብዙ ውጣ ውረድ ቢያደርጉም እስከ ዛሬ ተቀባይነት አላገኙም::

የጦርነቱ መንስዔ በኢኮኖሚ ሳይሆን በትክክለኛው አነጋገር በተጨባጭ ሁኔታው የመሬት ይገባኛል ነው:: ሻዕቢያ የኔ ግዛት ነው:: ከዚህ ቀደምም በ1969 ዓ.ም. ተስማምተን እናንተም የኤርትራ መሬት ነው በማለት ያመናችሁበትን አስረክቡን በማለት ወደ ጦርነቱ ሻዕቢያ እና ወያኔ ገቡ:: እውነቱ ይህ ነው:: ይህ በዚሁ እንዳለም የኢኮኖሚው ጉዳይም አስተዋስኦ ያደረገበት አለ:: ሁሉ ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው ከ1983 ዓ.ም. ግንቦት ወር ጀምሮ እስከ 1990ዓ.ም.  የሻዕቢያው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራ የግላችን የኢትዮጵያ ሃብት ደግሞ የጋራችን ተባብለው በህወሃት መሪዎች መጠነ ሰፊ ድጋፍ ሁለቱ ማለት ሻዕቢያና ወያኔ የሃገራችን ኢትዮጵያን ጥሬ ሃብትዋን መዓድኗን እና ሃገሪቱ ያፈራችውን የተለያዩ ፋብሪካዎቸ እና ባንኮችን አብረው ተባብረው ዘርፈዋል:: ኢትዮጵያ እና ህዝብዋ ለረሃብ እና ችግር ተዳርገው ኤርትራውያን ጤፍ በየአይነቱ ዳጉሳ ፣ ስንዴ ፣ ገብስ ወዘተ በርካሽ ዋጋ ኤርትራ ሲሸጥ የኢትዮጵያ ገበያ ባዶ ቀረ:: ስለዚህ ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሲነሳ ያ የለመዱት በሰው ሃገር ሃብት ሲንደላቀቁ የቆዩት አሁን ሲያጡት ለጦርነቱ አስተዋጽኦ ያደረገም ነበር:: በጣም ከሚገርሙ ነገሮች እና አሳዛኝ የሆነው ሁለቱ መለስ ዜናዊ እና ኢሳያስ አፈወርቂ በስልክ ጥብቅ ግንኙነት እንደነበራቸው ብዙ ሰዎች ተናግረዋል:: ስብሃት ነጋ ፣ አባይ ጸሃዬ እና ሌሎቹ የወያኔ መሪዎች በጣም የደመቀ ግንኙነት ከጦርነቱ ዋዜማ አንስቶ የወያኔ መሪዎች ይገናኙ እንደነበር ምስጢሩም የሚያውቁ ሰዎች ተናግረውታል::  

ኢሳያስ አፈወርቂ ላቀረበው የአንድ ቢሊዮን ብር ላክልን መለስ ዜናዊ ሳያቅማማ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ተፈቅዶ ገንዘቡ አስመራ እንደገባ በቀናት የኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ መቀሌ ውስጥ(ሃይደር) የሚገኘው የመዋዕለ ህጻናት ትምህርት ቤት በሚግ አውሮፕላን ደበደበው:: ከተዋጊ አውሮፕላኖቹ የተጣለው ክላስተር ቦምብ ወድያውኑ 53 ህጻናትና አስተማሪዎች ሲሞቱ 185 ደግሞ ከባዱ ቁስል ደረሰባቸው:: ለዚሁም ተጠያቂው መለስ ዜናዊ እና ስብሃት ነጋ ናቸው::

የሻዕቢያ ተዋጊ ጀቶች እንደገና ተመልሰው ቦምብ ጭነው 48 ሰላማዊ ሰዎችን 10 ህጻናትን ሲገድሉ 150 ሰዎች አቆሰሉ:: በማለት ቢ.ቢ.ሲ. እና ሲ.ኤን.ኤን. የዘገቡት ዋቢ ነው:: ይህ ጥቃት የደረሰው በግንቦት ወር መጨረሻ 1990 ዓ.ም. ሆኖ አስራት አብርሃም በአሳማኝ ሁኔታ ከ’ሃገር በስተጀርባ’ በሚል መጽሃፉ እንደገለጸው መለስ ዜናዊን ኢሳያስ አፈወርቂ እስከ ታህሳስ ወር 1991 ዓ.ም. ይገናኙ እንደነበሩም ያስረዳል:: መለስ ዜናዊን ግብረአበሮቹ እነ ስብሃት ነጋ ወዘተ ኢትዮጵያዊ ሳይሆኑ የባዕዳን ቅኝ ገዢዎች መሆናቸው በግልጽ የሚያሳይ እውነታ ነው::

የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትም ሆን ብሎ ያሰናከለው መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ እና አባይ ጸሃዬ መሆናቸው ሲታወቅ ምክንያቱም በ1969 ዓ.ም. ከላይ የተጠቀሰ መሬት የኤርትራ ነው ብሎ ወያኔ የፈረመበት በመሆኑ ይህም በአልጀርሱ ስምምነት ወያኔ መሪ መለስ ዜናዊ አሳልፎ ለኤርትራ መስጠቱ የ1969 ዓ.ም. ትልቁ ማሳያ ነው:: የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት እነማን መሩት? ይህን እንመልከት::

 

1. መለስ ዜናዊ የጦሩ ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስቴር …………………………………………ኤርትራዊ

2. ጻድቃን ገብረተንሳኤ የጦሩ ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ……………………………………………..ኤርትራዊ

3. ሳሞራ የኑስ…ከፍተኛ ጀነራል…………………………………………………………………………………….ኤርትራዊ(በናቱ ከርከበት በአባቱ ሱዳናዊ)

 

እነዚህ ሶስቱ አመራር በምንም ተአምር ለኢትዮጵያ ይሰራሉ?? ጦርነቱን በትክክል ይመራሉ ብሎ ማሰብ “ላም አለችኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ” አይነት ነው:: እነዚህ ትልቁ ምኞታቸው የኤርትራ ሰራዊትና ህዝብ እንዳይጎዳ ኢትዮጵያዊው ሰራዊት ቢያልቅ ምንም የማይሰማቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ሁሉም የውጊያና ጦርነት አመራር ብቃት የሌላቸው በአጋጣሚ የተገኘው ጠ/ሚኒስቴርነት እና ጀነራልነት ከንቱ ነው:: ጠቅላላ የወያኔ ህወሃት መሪዎች ጀነራሎች እና ወታደሮች ከወታደራዊ ሳይንስ ያላቸው ርቀት ሰማይና መሬት ነው:: በ1991 ዓ.ም. ያለቀው ሰራዊት ተጠያቂም ናቸው::

2ኛው በዚሁ ኢትዮ ኤርትራ ውጊያ ሲመሩ የነበሩ የመለስ ዜናዊ እና የስብሃት ነጋ ታዛዦች ናቸው:: አታድርጉ ከተባሉ አያደርጉም:: በዋናነት ጎልተው የሚጠቀሱም::

 

1. ሰዓረ መኮንን

2.ዮሃንስ ገ/መስቀል (ቦጅቦጅ)

3.ታደሰ ወረደ

4.አብርሃ ወ/ማሪያም(ኳርተር)

5.ብርሃነ ነጋሽ ወዘተ ሲሆኑ ሌሎችም አሉ::

 

ስለሆነም በ1991ዓ.ም የደረሰው ውድመት ከ100,000ሺ ሰራዊት የሞተበት ወደ 200,000 የሚጠጋ ሰራዊት አካለ ጎዶሎ የሆነበት ግምቱ አስቸጋሪ የሆነው የኢትዮጵያ ሃብት ንብረት የወደመበት ተጠያቂው ማነው??

 

የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የተፈጠረበት ምክንያት እና ሰበቡ ምንድነው?? እነዚህ ሁልቱ ጥያቄዎች መልስ በግልጽ ለማስቀመጥ እፈልጋለሁኝ::

 

1. በኢትዮ-ኤርትራ ለደረሰው ግድያና በጦርነት የወደመው ሃብትና ንብረት ተጠያቂዎች::

 

1. መለስ ዜናዊ

2. ስብሃት ነጋ

3.አባይ ጸሃዬ

4. አርከበ እቁባይ

5. ጻድቃን ገ/ተንሳኤ

6. ሳሞራ የኑስ

7. ስዩም መስፍን

እነዚህ በሰው ህይወት ለደረሰው እልቂትና ጉዳት በሃገሪቱ የደረሰው ከፍተኛ ውድመት ግንባር ቀደም ተጠያቂ ናቸው::

በጦርነቱ የወደመው ሃብት እና ንብረት ተጠያቂውስ ማነው? ለሚለው::

1. መለስ ዜናዊ

2.ስብሃት ነጋ

3.ጻድቃን ገ/ተንሳኤ

4.አበበ ተክለሃይማኖት

5.ገዛኢ አበራ

6.ጀነራሉ በባለ ሌላ ማእረግ

7.ስዩም መስፍን

8.ብአዴን, ኦህዴድ እና የደቡብ ህዝብ ንቅናቄ

9. በወቅቱ የነበሩ የፓርላማ አባላት በሙሉ

10. የህወሃት ካድሬና ደጋፊዎች በሙሉ::

እነዚህም ግንባር ቀደም ተጠያቂዎች ሲሆኑ፤

 

3. የጦርነቱ መንስኤ ለሚለው ጥያቄ የህወሃት አመራር በ1969 ዓ.ም. ሻዕቢያ ላቀረበው የመሬት ይገባኛል በወቅቱ አምነት ተቀብለው በፊርማቸው ባረጋገጡት መሰረት በትግራይ ህዝብ ተቀባይነት የሌለው የህወሃት ጥቂት የማፍያ ስብስብ በፈጸሙት ነገር ከሃዲዎች ከሻዕቢያ ጥቅም እናገኛለን ብለው የፈጸሙት ሚያዝያ ወር 1991 ዓ.ም. የፈነዳ ጦርነት ነው:: ተጠያቂዎቹም ህወሃቶች ናቸው::

 

በብዙ በርካታ ወንጀሎች የትግራይ ህዝብ ሊከሳቸው ዝግጅቱን አጠናቅቆ ቀኑን በመጠባበቅ ላይ ነው:: ህወሃት እና መሪዎቹ ይከሰሳሉ:: አዎን ለፍርድም ይቀርባሉ::

የአይደ መዋእለ ህጻናት የአየር ጥቃትም የትግራይ ህዝብ ካቀረባቸው ክሾች ውስጥ አንዱ ስለሆነ በዚሁም በዋናነት የሚጠቀሱ መለስ ዜናዊ እና ስብሃት ነጋ መሆናቸው ነው::

 

ግንቦት 20 ቀን1983 ዓ.ም. ይህን አይነት አሰቃቂ ድርጊቶችን አስከትላ ነው ብቅ ያለችው:: የተረገመችው ይህቺ ቀን ኢትዮጵያ ለምለም አገራችንን ለከሃዲ ባንዳዎች አሳልፋ የሰጠች::

 

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ይዛው የመጣችው ሰቆቃ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በፈለገው የሃገሩ ግዛት የመኖር ለዘመናት ተጠብቆ የቆየውን መብቱን በህወሃት ከፋፍለህ ግዛ በሚመቸው ሃገራችን በዘር በቋንቋ ከፋፍሎ ጠባብ ብሄረተኛ በሆነው መንገድ የዘር ፌደራሊዝም መሰረት ይህ የእቅድ ሃሳቡም አማራውን ለማጥፋት እና ለማክሰም የተቀነባበረ ሴራ ነው:: ይባስ ብሎም ሸዋ ጠ/ግዛት ለሌሎች ብሄራት በመስጠት ጎጃም በጌምድር ጠ/ግዛት ወሎ ጠ/ግዛት በታትነው አማራው መኖሪያ አልባ ተደረገ:: በተለያዩ ጠ/ግዛት ይኖር የነበረው አማራ ውጣ እየተባለ በወያኔ ህወሃት ከህጻን እስክ ሽማግሌ እየተገደለ በየበረሃው ወድቆ የዘሩን ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል:: ቀስ በቀስም ኦሮሞ ጋምቤላ አፋር ወዘተ ተመሳሳይ እጣ ደረሰባቸው:: በጠቅላላው ከተወለደበት ካደገበት ኢትዮጵያዊ ከመሬቱ የተፈናቀለ 24 ሚሊዮን ሲሆን በወያኔ ህወሃት የተገደሉ ኢትዮጵያውያን አንዳንድ ጥናቶች የሚያመለክቱተ 7.9ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ ወያኔ ህወሃት እንደገደላቸው ያሳያሉ::

ግንቦት 20ቀን 1983 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሁለቱ ሃይማኖቶች እስልምናእና ክርስትና በእጁ አስገብቶ ለመቆጣጠር እና ቀስ በቀስም ሃይማኖቶቹን ለማክሰም ተነሳ::

 

1. የኢትዮጵያ እስልምና ሃይማኖት ለብዙ ዘመናት ወግና ህግጋቱን ጠብቆ የመጣ በብዙ ሚሊዮን እስልምና ተከታይ ያለው የኢትዮጵያ ቅርስና የምንኮራበት ሃይማኖት ዛሬ በወያኔ ህወሃት ተደፍሮ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ሙሉ መብታቸውን ተነጥቀው በእስራት መከራ እየተሰቃዩ በገዛ ሃገራቸው ለክፉ ችግር ተዳርገዋል::

2.የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም በክፉ አደጋ ወድቃለች ቤተ ክርስቲያና እየተቃጠሉ ታሪካዊ ቅርሶችዋን በወያኔ ተዘረፉ::ወያኔ የሚቃወሙ ብጹአን አባቶች ለስደት ተዳርገዋል:: ብዙም ተገድለዋል:: ይህን ሁሉ የፈጸመው የወያኔ አባል የነበረው አባ ገብረመድህን ወይም አባ ጳውሎስ የሚባል በወያኔው መሪ መለስ ዜናዊ አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ፓትሪያርክ ካደረገው ብዙ ወንጀል በቤተ ክርስቲያናችን ፈጽመዋል::

ለመሆኑ አቡነ ጳውሎስ ማነው??

 

abune gerimaአቡነ ጳውሎስ ትውልዳቸው ትግራይ አድዋ ያደጉትም እንዳባገሪማ ገጠር ነው:: እንዳባገሪማ የተባለበት ምክንያት በአክሱም ዘመነ መንግስት በንጉስ አልአሜዳ ብ470ዓ.ም. ከመጡት ተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ አባ ገሪማ ሲሆኑ ከአድዋ በስተምስራቅ የ18 ኪሎ ሜትር ርቀት የምተገኘው ተራራማ ቦታ አባ ገሪማ በጣም አስደናቂ ሆኖ የተሰራው ቤተ ክርስቲያናቸው በማነጽ እዛው ሞተው እዛው ስለተቀበሩ በዚሁ ምክንያት እንዳባገሪማ ተብላ ትጠራለች::የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ያዋረዱን የቤተ ክርስቲያኗን ህገ ደንብ እና ቀኖናውን የለወጡ እና ያፈረሱ ፣ ለስጋቸው ያደሩ: አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያን ጥንታዊ ሃይማኖት ለማጥፋት ጸረ ክርስትና የሆኑት ጳውሎስ የአድዋ ልጅ በመሆናቸው በኢትዮጵያ ህጋዊ ሊቀ ቅዱሳን ፓትሪያርክ በቤተ ክርስቲያኑ ህግና ደንብ የተሾሙት ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትሪያርክ ዘኢትዮጵያ ወያኔ በሃይል አስወግዶ አባ ጳውሎስን ሾመ:: ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሀይማኖት ወግና ስርዓቱን ለማጥፋት የታቀደ ነው:: የቤተ ክርስቲያኑን ህግና ደንብ የሚጻረርም ነው::

አቡነ ጳውሎስ የወያኔ ህወሃት በአባልነት የመለለመሉት በ1976 ዓ.ም. ነበር:: በወቅቱ የሚነገረው ዶ/ር አባ ገብረመድህን የተባሉ የኛ አባል ስለሆኑ ትግራይ ሃገራችን ከአማራው ቅኝ አገዛዝ ነጻ በምትወጣበት እኚሁ የትግራይ ፓትሪያርክ ይሆናሉ በማለት ስብሃት ነጋ በለመደው ወሬ ማዛመት በታጋይ ውስጥ ተሰራጨ:: ቢሆንም ግን ታጋዩ ብዙ ስሜት አልሰጠውም:: ምክንያቱም ሃይማኖት የለሽ የወያኔ አመራር በትግሉ ወቅት እግዚያብሄር የሚባል አማልክት የሚባሉ በፍጹም የሉም:: ይህ ለአማራው አገዛዝ እንዲመችለት የፈጠረው ከንቱ ሃሳብ ነው:: በማለት ስለአስተማሩን የአባ ገብረመድህንም ይህን ድባብ የሸፈነው ነበር::

ንገሩ እንደገና በ1980 ዓ.ም. መጀመሪያ ታድሶ መጣ የህወሃት አባል አባ ገ/መድህን ከአሜሪካ ሱዳን ድርስ መጥተው ስብሃት ነጋ የወቅቱ የህወሃት ሊቀ መንበርና መለስ ዜናዊ ሱዳን ድረስ በመሄድ እንደተገናኙ በድጋፍ መልክም $15,000 የአሜሪካን ዶላር መስጠታቸውን የሄዱት ሁልቱ የወያኔ አመራሮች በድብቅ ሳይሆን በግልጽ የተናገሩት ነበር:: ከዚሁም በተጨማሪ ሱዳን ካርቱም ውስጥ የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን አስቀድሰው በውስጡ የሚገኙ ቀሳውስት ካህናት ወደ ህወሃት አባልነት መልምለው በሶስተኛው ቀን ወደ መጡበት መመለሳቸም ተነገረ::ስብሃት ነጋ አቡነ ጳውሎስ የህወሃት መሪህ ባህታ(vanguard) ናቸው በማለት ይጠራቸዋል::

እንግዲህ የአቡነ ጳውሎስ ነገር ይህ ሆኖ ትግሬ በመሆናቸው ብቻም በደርግ መታሰራቸውን ብዙ ግፍ ተፈጸመብኝ የሚሉት አቡነ ጳውሎስ የኢትዮፕያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን አባላት እውነት ይሁን አይሁን ለነሱ ልተው:: ከሆነም አባ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያንዋ ላይ በቂም በቀል ማወካቸው ከአንድ መናኝ አባት መፈጸም የሌለበት ፈጽመዋል:: ነብሳቸውም ለሲዖል ተዳርጋለች::

አቡነ ጳውሎስ የፓትርያርኩ ስልጣን አግባብ በሌለው መንገድ የተረከቡት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያናት በምርጥ ካድሬነታቸው በዋልድባና በተለያዩ ቤተ ክርስቲያናት ብዙ ግፍ ከመፈጸማቸው በላይ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች ከየቤተ ክርስቲያኑ በማስወጣት ሸጠዋል::

ይህ ሁሉ በእስልምና ሃይማኖትና በክርስትና መዘዙ ይዞት የመጣው ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የተረገመች ቀን ናት::

ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያውያን እንደተቆጣጠረ ብዙ የዝርፊያ ተቋማት አመቻችቶ ነበር:: አገራችንን የተቆጣጠረው 1. ዋና ኢፈርት 2. ለም የኢትዮጵያ መሬት ለባዕዳን መሸጥ 3. ኢትዮጵያውያን ከተወለዱበትና ካደጉበት መሬት ማፈናቀል 4. ገዢ የሆኑት የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ተቋማት በህወሃት ቁጥጥር ውስጥ መዋል 5. ኢትዮጵያዊው የሃገሩ ዳር ድንበር ጠባቂ አማራው ማጥፋት ከዚህም ጎን ለጎን አማርኛ ቋንቋ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ ማጥፋት እና ማክሰም:: 6.የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሀ.አየር ኃይል ለ. ምድር ጦር ሐ.ባህር ሃይል መ.ፖሊስ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ አስወግዶ የራሱን የህወሃትን ታጋዮች ከትግራይ የመጡ ሁሉ የኢትዮፕያ ምድር ጦርና አየር ኃይል ለማድረግ ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ በራኡ መዳፍ ውስጥ ለማስገባትና ለመቆጣጠር ደህንነቱም ከላይ እስከ ታች በትግሬዎች ማዋቅር አላማው ነበር::

ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ የወያኔ አመራር መለስና ስብሃት ነጋ ባወጡት እቅድ ተግባራዊ ተደርገዋል::

የኢትዮጵያ ህዝብ በእርሻ የሚተዳደረው መሬቱን ተቀምቶ ለባዕዳን ሳውዲ አረቢያ ፣ ህንድ ፣ እና ለቻይና ወዘተ ህወሃቶች ሸጡት:: በሽያጭ የተገኘው ገንዘብም ሆነ በነ መለስ ዜንዊና ባለቤቱ ወ/ሮ አዜብ እጅ ሲገባ ከመሬቱ የተፈናቀለ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በየበረሃው ወድቆ ለክፉ ችግርና መከራ ተዳርገዋል::

ወያኔ ህወሃት በዘር ማጥፋት ወንጀል ተሰማርቶ ህዝበ ኢትዮጵያዊ እያለቀ ነው:: አማርኛ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ ጠላት ነው ብለው ወያኔዎቹ ፈረጁት:: ለመሆኑ የቋንቋ ጠላት አለን?? ይህ ሁሉ በግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የመጣ የኢትዮጵያ ህልውና አጠያያቂም ሆነ:: ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያን ያፈረሰ ህዝብዋንም ለችግር እና ለመከራ የዳረገ በጥቁር ታሪክ የሚመዘገብ የፋሺስት ወያኔ ህወሃት አገዛዝ ስርዓትና የጨለማ ዘመን በማለት ታሪ ዘግቦታል::

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. አንቺ ጥቁር የታሪክ አተላ ቀን የስንቱን ኢትዮጵያዊያን ህይወት በላሽ?! ስንቱን ኢትዮጵያዊ ምሁራን የነጻ ፕሬስ እውቅ ጋዜጠኞች ለስደት ለመከራ ዳረግሽ?! ስንቱን ወጣት ሴት እና ወንድ ከሃገሩ ጠፍቶ የባህር ቀለብ ሆነ:: ስንቱስ በስደት ሂወቱ እየማቀቀ ለክፉ መከራ ተዳረገ:: ስንቱ ቤተ ሰብ አፈናቅለሽ የስንቱን ቤት አፈረሽው:: ወጣት የሴት ህጻናት ሽርሙጥና ዳረግሽ:: አደንዛዥ እጽ እና አሺሽ ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ተራ የንግድ ገቢ ሆኖ ወጣቱ ትምህርት ተከልክሎ እቅቀት እና ስልጣኔ በኢትዮጵያ የጠፋበት ዛሬ በኢትዮጵያ ስራ አጥነት የተስፋፋበት የወንጀል ድርጊት በስፋት የሚፈጸምበት ህጻናት በየቆሻሻው የተጣሉ ምግብ አይነት ነክ እየለቀሙ የሚበሉበት የጎዳና ተዳዳሪ ጠዋሪ ማደሪትይ ያጡ ህጻናት ለአቀመ አዳም ያልደረሱ ልጆች ወንድ ሴት ማደሪያቸው በየመንገዱ ሆነ:: ህጻናት በርሃብ በየመንገዱ በየትምህርት ቤቱ አእምሮዋቸውን እየሳቱ የሚወድቁበ እርጉዝ ሴት መኖሪያ አልባ ሆና በየዱር ገደሉ እየወለደች ከተወለዱ ህጻናት ከ10 ህጻናት 6 በ3 እና በ 4 ወራቸው እየሞቱ ህክምና ጠፋ:: ውሃ ጠፋ:: መብራት ጠፋ:: አረ ስንት ጉድ ነው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የወረደው ግፍ::

የወያኔ ህወሃት አባል ድርጅቶች ህወሃት ራሱ የነዚህ ቤተሰብ ልጆች ውጭ አገር እየተንደላቀቁ ሲማሩ ሃገር ውስጥ ያሉ አመራሩ ደጋፊዎች በኑሮ ተንደላቀው በሙስና ተዘፍቀው የሃገር እና የህዝብ ሃብት እየዘረፉ ቀኑ ለነሱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ የችግር ጨለማ መብቱ የተረገጠ ባሪያ ጥዋት ማታ በወያኔ ስርዓት የሚሰቃይ ግዞተኛ ባዕድ ሆኖ ያለበት ዘመን ነው::

ይህ ክፉ አረመኔያዊ የህወሃት አገዛዝ በዚሁ መንገድ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይቀጥል ሁሉ ኢትዮጵያዊ በአንድነት ይነሳ በህዝባዊ ትግል ወያኔን ከስረ መሰረቱ ነቅለን እንጣለው::

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

ገብረመድህን አርአያ

አውስትራሊያ

ከትናንቱ ሰልፍ በኋላ ዛሬ በአ.አ 40 ወንድና 2 ሴት የአንድነት አባላት ታሰሩ (ስም ዝርዝራቸውን ይዘናል)

$
0
0

8611_669727903043674_1400680652_n(ዘ-ሐበሻ) አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ትናንት በደሴና በግንደር ሰላማዊ ሰልፉን አድርጎ በሰላም ካጠናቀቀ በኋላ ዛሬ ሐምሌ 8 ቀን 2005 (ጁላይ 15 ቀን 2013) ዓ.ም መንግስት የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን የወረዳ አመራሮችንና አባላትን በዘመቻ ማሰር መጀመሩ ተዘገበ፡፡
አንድነት ፓርቲ በድርጅቱ ፌስቡክ ላይ እንዳስታወቀው ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሰዓትም 42 የሚሆኑ የአንድነት ፓርቲ አባላት በፖሊስ ታስረዋል። የአንድነት ፓርቲ በአዲስ አበባ እያሰራጨ ያለውን ህጋዊ በራሪ ወረቀት ለህዝብ እያደሉና በማደልም ላይ በመሆናቸው የተያዙት አባላት ከአዲስ ከተማ 15፣ ከጉለሌ7 ፣ ከየካ 9 እንዲሁም ከንፋስ ስልክ ላፍቶ እንደሆኑ ፓርቲው ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ አረጋግጧል።
“የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል አንድነት የጀመረው እንቅስቃሴ ለዴሞክራሲና ለሰላም ቆሚያለው የሚለው በጠመንጃ ሃገሪቷን በማስፈራራት ላይ የሚገኘው የኢሕ አዴግ መንግስት የአንድነት አባላትን ማሰሩ ከድንጋጤ የመጣ ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ተደምጠዋል።
ዛሬ ከታሰሩት 42 የአንድነት ፓርቲ አባላት መካከልባ ለፈው ሳምንት ቄራ አካባቢ ተመሳሳይ ወረቀት ሲበትኑ በህገወጥ መንገድ በፖሊስ ታስረው የነበሩት ስንታየሁ ቸኮልና ዳንኤል ፈይሳ ዛሬም በድጋሚ እንደታሰሩ ፓርቲው አጋልጧል።
ዛሬ የታሰሩት የተፈፀመባቸው የአንድነት አባላት ዝርዝር፦
1ኛ. ስንታየሁ ቸኮል
2ኛ. ዳንኤል ፈይሳ
3ኛ. ኤፍሬም ሰለሞን
4ኛ. ታሪኬ ከፋ
5ኛ. ዘገዬ እሸቴ
6ኛ. ተፈሪ ተሾመ
7ኛ. ሀብታመ አድነው
8ኛ. ፍቃዱ በቀለ
9ኛ. ብስራት ተሰማ
10ኛ. መኳንንት ብርሀኑ
11ኛ. ፋና ወልደጎርጊስ
12ኛ. ሽፈራው ተሰማ
13ኛ. ፋንቱ ዳኜ
14ኛ. ገነት ሰለሞን
15ኛ. አላዛር አርአያ
16ኛ. ሳሙኤል ኢሳያስ
17ኛ. ደመላሽ ሙሉነህ
18ኛ. አማኑኤል መንግስቱ
19ኛ. ታሪኩ ጉዲሳ
20ኛ. አስማረ ንጉሴ
21ኛ. ፍቃደስላሴ ግርማ
22ኛ. አሸናፊ አስማረ
23ኛ. ዳንኤል
24ኛ. ለሚ ስሜ
25ኛ. ሰይፈ
26ኛ. ባዩ ተስፋዬ
27ኛ. ሰለሞን አክሊሉ
28ኛ. ወርቁ አንድሮ
29ኛ. ኃይሉ ግዛው
30ኛ. ሸዋአገኘው ማሞ
31ኛ. ቴዎድሮስ ገብሬ
32ኛ. አክሊሉ ሰይፉ
33ኛ. ንጉሴ ቀነኒ
34ኛ.ደረጀ ጣሰው
35ኛ. ገዛኸኝ አዱኛ
36ኛ. ሰፊው መኮንን
37ኛ. ታደለ ድሪባ
38ኛ. ሀብታሙ ሺበሺ
39ኛ. ሽመልስ ድንቁ
40ኛ. በየነ አበበ
በተጨማሪም 2 ስማቸውን ለጊዜው ማግኘት ያልተቻለ ሰዎች ታሰረዋል።
አንድነት በጀመረው የሰላማዊ ትግል የኢሕ አዴግ መንግስት አባላቱን ጠራርጎ አንድ ሰው እስከሚቀር ድረስ እንደሚታገል መግለጹን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ ይታወሳል።

ትንሽ ስለጃዋራዊያን –ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)

$
0
0

jawar
የጃዋር ንግግር ያበሳጫቸው ብዙ የፌስ ቡክ ወዳጆቻችን ቁጣቸውን በቻሉት መንገድ ሁሉ እየገለጹ ነው። ነገሩ ከቁጣ ወይም ከውግዘት ወይም ከይቅርታ መጠየቅ ወይም አቋምን ከመግለጽ ባለፈ በደንብ ተብላልቶ መታየት ያለበት ይመስለኛል። በመጀመሪያ ፣ ጃዋር የዚህ ትውልድ ( የህወሀት ዘመን ልጅ ነው)። እርሱ ቢክደውም ፣ የአብዮታዊ ዲሞክራሲን የብሄር ፖለቲካ ጡጦ እየተጋተ ያደገ ልጅ ነው። የብሄር ፖለቲካን ለመጋት የግድ የህወሀት አባል መሆን አይጠይቅም፤ በማርክስ አስተምህሮ መሰረት የገዢው ፓርቲ ርእዮትዓለም የተገዢዎች ርእዮትዓለም ሆኖ የሚያገለግልበት እድል ሰፊ ነው። በተለይ ነጻ አስተሳሰቦች እንደልባቸው በማይንሸራሸሩበት ወይም ፕሮፓጋንዳው ሁሉ ከአንድ ኩሬ በሚፈልቅበት አገር የገዢው ፓርቲ ርእዮትዓለም በተለይ በወጣቶች አስተሳሰብ ላይ ተጽእኖ ማሳደሩ አይቀሬ ነው። ወጣቶች እያወቁ ወይም ሳያውቁ የገዢው ፓርቲ አይዲዮሎጂ ሰለባዎች ይሆናሉ። እንዲህ አይነቱ አስተሳሰብ በአእምሮ ውስጥ አንዴ ከበቀለ ደግሞ በቀላሉ መንቀል አይቻልም፤ አንዳንድ ምሁራን ሀይማኖት እና ብሄር primordial value ናቸው ይላሉ። እነዚህ አስተሳሰቦች በአእምሮ ውስጥ አንዴ ከበቀሉ በሁዋላ መንቀል አይደለም በቀላሉ አይለወጡም፣ ልለወጥ ቢሉ እንኳ ረጅም ጊዜ ይወስድባቸዋል፤ በጣም የሚገርመው ደግሞ እንዲህ አይነት አስተሳሰቦች አብዛኛውን ጊዜ የሚቀረጹት በወጣትነት እድሜ መሆኑ ነው ።

በኢህአዴግ ዘመን የተማርን ወጣቶች የብሄር ፖለቲካን ስንጋት አድገናል፤ አንዳንዶቻችን ተቀብለነው ጃዋራውያን ሆነናል፣ ሌሎቻችን ሳንቀበለው ቀርተናል። በተለይ ታሪክ በድሎናል በማለት አቤቱታ ከሚያሰሙ አካባቢዎች የመጡ ወገኖች የብሄር ፖለቲካው አስተሳሰብ ተመችቶአቸዋል። እንግዲህ ዋናው ጥያቄ በአገራችን ስንት ጃዋርያውያን አሉ የሚለው ነው። በአገራችን የጃዋርያውያን ቁጥር 50 +1 ከሆነ እንደ አገር አክትሞልናል፤ ህወሀት ያሰበው ሆኖለታል ማለት ነው። ቁጥሩ ከ51 በመቶ የሚያንስ ከሆነ ግን እንደ አገር የመቀጠሉ ተስፋ አለን። አገራችንን ለማዳን መበሳጨት ወይም መፎከር ብቻውን በቂ አይደለም፣ ከእነ ጃዋር የተሻለ አስተሳሰብ ይዞ መገኘት፣ የተሻለው አስተሳሰብም ገዢ አስተሳሰብ እንዲሆን መታገል ይገባል። እነጃዋር አስተሳሰባቸውን እንዲለውጡ ከማስገደድ፣ የእነሱ አስተሳሰብ ወደ ሌሎች ወጣቶች እንዳይሰራጭ ወይም ምርኮኞቻቸውን እንዳያበዙ መታገል ያስፈልጋል። ጃዋራውያንን በሜንጫ ወይም መድረክ በመንፈግ ማሸነፍ አይቻልም፣ በግልጽ መድረክ በመከራከር አስተሳሰባቸውን በአስተሳሰብ ማሸነፍ ሲቻል ብቻ ነው ዘላቂ መፍትሄ ሊመጣ የሚችለው። ጃዋርን በግልጽ በመሞገት እና እጸጾቹን በማሳየት ሌሎች ወጣቶች እንዳይቀበሉት ማድረግ ያስፈልጋል። ሌላው ደግሞ ወጣቶቻችን ታሪክን እንዲያዉቁ፣ የፖለቲካ ግንዛቢያቸው እንዲሰፋ ማድረግ የአንድነትን ሀይል ከሚሰብኩ ወገኖች ይጠበቃል፡፡

ጃዋር ለፕሮፓጋንዳው እንዲጠቅመው አድርጎ ያነበበው ታሪክ ወንዝ የማያሻግር መሆኑን ለማየት ይቻላል። በብዙ ብሄርተኞች ላይ እንደሚታየው ጃዋር በታሪክ ላይ ተሳልቋል፣ ታሪክም በጃዋር ላይ ተሳልቋል። እንዳለመታደል ሆኖ የጥንትኦሮሞዎች የጽሁፍ ባህል አልነበራቸውም፣ ታሪካቸውንም ጽፈው አላስቀመጡም፤ ጃዋር የእነሱን ታሪክ ለማንበብ የግድ በግእዝ ወይም በአማርኛ የተጻፉ መጽሀፍትን ማገላበጥ ሊኖርበት ነው፤ አማርኛን ደግሞ ይጠላል፣ አማርኛ ማንበብ በአማራ ባህል መወረር ነው ብሎ ያምናል፣ ስለዚህ ለጃዋር ያለው ምርጫ በአፈ ታሪክ ላይ ተመስርቶ ተረቱን ታሪክ እያደረገ ጆሮ ለሰጠው ሁሉ ማቅረብ ነው፤ አፈ ታሪክ ደግሞ ረጅም ርቀት አይወስድም፣ ይኸው አሁን እንደምናየው መያዣ መጨበጫ የሌለው ነገር ያናግራል። ስለኦሮሞ ጥንተ-ታሪክ የተጻፉ የፈረንጅ መጽሀፍትም ቢሆኑ ብዙዎቹ በአባ ባህሬን መጽሀፍ ላይ ተንተርሰው ወይም በአፈ ታሪክ ላይ ተመስርተው የተጻፉ ናቸው። አንዳንዶቹ የፈረንጅ መጽሀፍትም ለጃዋርያውያን የሚመቹ አይደሉም፤ ለምሳሌ በጅ የተባለ የታሪክ ጸሀፊ ስለኦሮሞች ማንነት የጻፈው ጽሁፍ ብዙ ኦሮሞችን እንዳበሳጨ ለመመልከት የሚሻ ሰው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መጽሀፍት ቤት ገብቶ መጽሀፉን ተውሶ ማየት ይበቃዋል፤ መጽሀፉ በኦሮሞ ተማሪዎች ተሰርዞ ተደልዞ ታዩታላችሁ። እንደያውም በዩኒቨርስቲው የሚገኙ አብዛኞቹ የታሪክ መጽሀፎች ስርዝ ድልዝ አላቸው በተለይ ኦሮሞን የሚመለከቱ ክፍሎች። በጥንቶቹ የታሪክ መጽሀፍት ውስጥ The Oromo Migration ( ስደት) የሚለው ሀረግ The Oromo Expansion በሚለው እየተሰረዘ እንዲተካ ተድርጓል። ታሪክ አስተማሪዎችም ኦሮሞ ተስፋፋ እንጅ ተሰደደ ብለው እንዳያስተምሩ ታዘው ተግባራዊ እያደረጉት ነው። አንድ ጊዜ ፕ/ር መርእድ ወ/አረጋይን “ለምን?” ብየ ጠይቄአቸው ነበር። “ታሪክ ሰዎችን አብረው እንዲኖሩ እንጅ እንዲለያዩ አያበረታታም” ብለው መለሱልኝ። ልክ ነበሩ። ኦሮሞ ተስፋፋሁ እንጅ አልተሰደድኩም ቢል ኢትዮጵያዊነቱን ይበልጥ የሚያረጋግጥ በመሆኑ እቀበለዋለሁ። የእኔም ክርክር ኦሮሞ መጤ ሳይሆን ተወላጅ ነው የሚል ነው። እነጀዋር ግን ሳያውቁት አንዴ ራሳቸውን መጤ ያደርጋሉ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ተወላጆች ነን ይላሉ። ታሪክን ማዛባት እንዲህ ያወናብዳል።

ከጃዋር የታሪክ ግድፈት አንዱን እንመልከት። “ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ከፕሮቱጋሎች እርዳታ በመቀበል ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን ወግተዋል” ይለናል። ጃዋር ታሪኩን አዛብቶ ለራሱ በሚመች መልኩ አቅርቦታል። ክርስቲያኖች ፖርቱጋሎችን እርዳታ ከመጠየቃቸው በፊት ፣ ኦቶማን ቱርኮች ለግራኝ ሙሀመድ እርዳታ በመስጠት ልብነድንግልን እንዲወጋ አድርገውታል፣ ለዚህም ነው ግራኝ ያሸነፈው። ፖርቱጋሎች ገላውዲዮስን ለመርዳት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ክርስትናን ለማስፋፋት አስበው አልነበረም፤ (ፖርቱጋሎች ካቶሊኮች የኢትዮጵያ ንጉስ ደግሞ ኦርቶዶክስ እንደነበሩ አንርሳ)። ኦቶማን ቱርኮችም ግራኝን ሲደግፉ እስልምናን ያስፋፋልናል ብለው በማሰብ አልነበረም። ሁለቱም የዘመኑ ሀያሎች በኢትዮጵያ ውስጥ ክርስትናን ወይም እስልምናን የማስፋፋት አላማ አልነበራቸውም፤ የሁለቱም አላማ ቀይ ባህርን በመቆጣጠር ንግዳቸውን ማስፋፋት፣ ግዛታቸውን ማስፋፋት ነው። ለሁለቱም አገሮች ሀይማኖት እንደ መሳሪያ እንጅ እንደግብ ሆኖ አላገለገለም።

በአለም የግዛት አመሰራረት ታሪክ ኦቶማን ቱርኮች በአንድ ነገር ይለያሉ። እነሱ አንድን ግዛት ሲቆጣጠሩ በቁጥጥር ስር ያዋሉትን ህዝብ ሀይማኖቱን አስገድደው አያስቀይሩትም። ኦቶማን ቱርኮች ኢየሩሳሌምን በያዙበት ወቅት የዴር ሱልጣን ገዳምን ኢትዮጵያኖች እንደያዙ እንዲቆዩ፣ በእየሩሳሌም የሚገኙ ክርስቲያኖችም ሀይማኖታቸውን እንደያዙ እንዲቀጥሉ ፈቅደውላቸዋል። ቱርኮች በኢትዮጵያ ጉዳይም የተለየ አቋም የሚይዙበት ነገር አልነበራቸውም። ግራኝ እስልምናን በሀይል ለማስፋፋት መሞከሩ እውነት ነው፤ ቱርኮች ለግራኝ ድጋፍ ማድረጋቸውም እንዲሁ እውነት ነው፣ ነገር ግን ቱርኮች ግራኝን የረዱት እስልምናን እንዲያስፋፋላቸው ነው የሚለውን ለመቀበል እቸገራለሁ። ቱርኮች በጊዜው ለእነሱ የሚገብር መንግስት በኢትዮጵያ ይፈልጉ ነበር፣ ያ መንግስት ክርስቲያንም ይሁን ሙስሊም አሜን ብሎ እስከገበረ ድረስ ግድ አልነበራቸውም። ግራኝን የደገፉት ሙስሊም ስለሆነ አይወጋንም፣ ለእኛም ይገዛል ብለው ነው። ልብነድንግል ከቱርክ ጋር ቢስማማ ኖሮ ግራኝ መሳሪያ ባለገኘ ስልጣኑንም ባላጣ ነበር። ማወቅ ያለብን ግን ግራኝም ልብነድንግልም ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን ነው። የሁለቱም ታሪክ ታሪካችን ነው። ግራኝ ብዙ ቤተክርስቲያኖችን አውድሟል፤ ክርስቲያኖችም ብዙ መስጊዶችን አጥፍተዋል፤ ታሪኩ ግን ሁለት እምነት የሚከተሉ የአንድ አገር ልጆች ወይም የወንድማማቾች ታሪክ ነው።

ደፋሩ ጃዋር ” ኦሮሞች በሀረር የሚገኙ ሙስሊሞችን ከክርስቲያኖች ጥቃት አድነዋቸዋል” ይለናል ። በየትኛው መጽሀፍ ተጽፎ እንዳገኘው አላውቅም። እኔ እስከማውቀው ድረስ በምስራቅ ዝቅተኛ ቦታዎች የሚገኙ የሶማሊ ተወላጆች ( አብዛኞቹ ሙስሊሞች) ፣ ከጥንት እስከዛሬ ከኦሮሞች ጋር በግጦሽ መሬት እንደሚዋጉ ነው ( በቦረናና በባሌ አካባቢዎች ያለውን ይመለከቷል) ። ለመሆኑ ኦሮሞ ጥንት ግዛቱን ሲያስፋፋ የዋቄ ፈታን እምነት ለምን አብሮ ሳያስፋፋ ቀረ? የኦሮሞ ባላባቶች “ንጉስ ሿሚ እና ሻሪ” በነበሩበት የእነራስ አሊ አንደኛ እና ሁለተኛ ዘመን ለምን የዋቄ ፈታን እምነት ትተው ክርስትናና እስልምናን ተቀበሉ? የትኛው የሙስሊም ንጉስ ነው ኦሮሞችን በሀይል አስገድዶ እስልምናን እንዲቀበሉ ያደረጋቸው? ጃዋር ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ የሚያገኝ አይመስለኝም።

በኢትዮጵያ ውስጥ ከግራኝ በፊትና በሁዋላ እስልምና በአብዛኛው የተስፋፋው ከንግድ ጋር በተያያዘ እንጅ በሀይል አይደለም፣ ኦሮሞችም ሁለቱን ሀይማኖቶች የተቀበሉት ተገደው ሳይሆን የግዛት ማስፋፋት ፖሊሲያቸው አንዱ አካል ስለነበር ነው። ኦሮሞዎች ወደ መሀል ፣ ሰሜን እና ደቡብ ኢትዮጵያ ሲስፋፉ በሄዱበት አካባቢ ያለውን ባህል እና እምነት ያከብራሉ ወይም የራሳቸውን በማዳቀል አዲስ እምነት ይፈጥራሉ። ጎጃም፣ ጎንደር ፣ ወሎና ከፊል ሸዋ ብትሄዱ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆነ ሰው ለአባይ ወንዝ ስለት ሲያስገባ ወይም ወርካውን ቅቤ ሲቀባ ታዩታላችሁ። ሙስሊሞችም ዶሮአቸውን አርደው አካባቢውን ይረጩታል፣ ቆሎም ይበትናሉ። በእነዚህ አካባቢዎች የዋቄ ፈታ እምነት ከክርስትና ወይም እስልምና ሀይማኖት አስተምሮዎች ጋር ተደባልቋል። ይሄ ስህተት አይደለም፣ እምነትም ባህልም በዚህ መንገድ ነው የሚስፋፋው፤ የኦሮሞ የመስፋፋት ፖሊሲ እንደ ኦቶማን ቱርኮች በባህል ላይ ጫና አያደርግም፣ የእኔን እምነት ካልተቀበልክ ብሎ ሰው አይገድልም። እንዲህ ባያደርግ ኖሮ ኦሮሞ ዛሬ የያዘውን የመሬት ስፋት ባልያዘ ነበር። ኢትዮጵያም ተረጋግታ እንዳገር ባልቀጠለች ነበር። ለጥንት የኦሮሞ ፖለቲከኞች ያለኝ አድናቆት የሚመነጨውን ከዚህ አንጻር ነው። በነገራችን ላይ እኔ ባደኩበት አካባቢ (ጎጃም) ኦሮሞ መባል፣ እነጃዋር እንደሚሉት የሚያሳፍር ሳይሆን፣ የሚያኮራ ነው። አንድ ጊዜ እናቴን እንች እኮ የኦሮሞ ደም አለሽ፣ ይህ አካባቢ እኮ በኦሮሞዎች የተያዘ ነበር አልኳት። ” እንዴ ልጄ ምን ማለትህ ነው፣ እኔ እናትህ እኮ የባላባት ዘር ነኝ፤ ኦሮሞ እኮ ባላባት ነው፣ የእነ እከሌ ዘር ነኝ፣ ከዚህ በመለስ እኮ ያለው የዘመዶቼ …ግዛት ነበር” አለችኝ። ኦሮሞ ማለት በጎጃሞች ዘንድ የባላባትነት መገለጫ መሆኑን የአሁኑ ዘመን የኦሮሞ ተወላጆች ሊሰሙትም አይፈልጉም።

በአንድ ወቅት መለስ ዜናዊ ትግራይ ላሉ ወጣቶች ሲናገር ” የእኛ ስጋት ምን ያክል የትግራይ ወጣቶች ርእዮተአለማችንን እስከመጨረሻው ይዘው ይዘልቃሉ፣ እኛ ብናልፍ ለምን ያክል ጊዜ አላማውን ይዘው ይጓዛሉ? ” የሚለው ነው በማለት ተናግሮ ነበር። መለስ ዛሬ ከመቃብር ወጥቶ ጃዋር የሚለውን ቢሰማ በደስታ በተፍነከነከ ነበር።

በአለም ላይ የተከሰቱ የብሄር ግጭቶች ታሪክን ከማጣመም ወይም ታሪክን ከመጠምዘዝ ጋር የተሳሰሩ ናቸው፡፤ ፖለቲከኞች ስልጣን ሲያምራቸው ታሪክን አጣመው ደጋፊዎችን ለማሰባሰብ ይሻሉ፤ ለስልጣን በሚያደርጉት እሩጫ የዘላለም ጠባሳ ጥለው ያልፋሉ። ለምሳሌ በዩጎዝላቪያ የእርስ በርስ ግጭት ከመጀመሩ ጥቂት ቀደም ብሎ ( እኤአ 1989) ሚሎሶቪች ከ600 አመት በፊት ሰርቦች በቱርኮች መሬታቸውን መቀማታቸውን የተመለከተ ንግግር በማድረግ ህዝቡን ለጦርነት አነሳስቶ ነበር። የእነጃዋር አካሄድም ግቡ ከዚህ የተለየ አይደለም። የብሄር ፖለቲካ የዜሮ ድምር ፖለቲካ ነው። ሁሉንም በእኩል አያስተናግድም።

አንድነትን የሚሰብኩት ወገኖች ጃዋርያውያንን በመሳደብ ፣ በማውገዝ ፣ በማግለል ወይም ፎቶአቸውን በማበላሸት ማሸነፍ እንደማይቻል ልብ ሊሉት ይገባል። እንዲህ አይነቱን አስተሳሰብ ማሸነፍ የሚቻለው የተሻለ አስተሳሰብ በማምጣትና በመሞገት ነው። ለምሳሌ ጃዋር ኦሮሞ ቁጥሩ ብዙ ስለሆነ ስልጣን መያዝ ይገባዋል ይላል። በጉልበት ማለቱ ከሆነ ተሳስቷል፤ ቁጥር ብቻውን ጉልበት እንደማይሆን እናውቃለን፤ እንዲያ ቢሆን ህወሀት 22 አመታት ባልገዛን ነበር። በምርጫ ማለቱ ከሆነም እንደ ሁኔታው ይወሰናል። ኦሮሞ ከእያንዳንዱ ብሄረሰብ ጋር ሲወዳደር በእርግጥም ቁጥሩ ብዙ ነው። ነገር ግን ኦሮሞ ከሌሎች ብሄሮች ድምር ጋር ሲወዳደር ቁጥሩ 50+1 አይሞላም። ለምሳሌ በኦሮሞ ፓርቲና በአንድ ህብረ-ብሄራዊ ፓርቲ መካከል የምርጫ ፉክክል ይደረግ እንበል። ሁሉም ኦሮሞዎች የኦሮሞውን ፓርቲ ቢመርጡና ከኦሮሞ ውጭ ያለው ህዝብ ደግሞ ህብረ-ብሄራዊ የሆነውን ፓርቲ ቢመርጥ የኦሮሞው ፓርቲ 51 በመቶ ድምጽ ስለማያገኝ መሸነፉ አይቀርም። ኦሮሞ ብዙ ቁጥር አለኝ ቢልም በምርጫ ለያሸንፍ የሚችለው፣ ሌሎች ህዝቦችን በመያዝ ብቻ ይሆናል ማለት ነው።

የእነ ጃዋር የቁጥርም ሆነ የታሪክ ጨዋታ እሩቅ እንደማይሰድ ለማሳየት ብዙ ማለት በተቻለ። ለአሁን በዚህ ለብቃ፣ ሙግቱን የምናሰፋው ከሆነ ከተጨናነቀው ጊዜየ እየቆጠብቁ አንዳንድ መስመር ለመወርወር ዝግጁ ነኝ።

ጃዋር እና ኢስላማዊት ኦሮሚያ – (ከያሬድ አይቼህ)

$
0
0

ከያሬድ አይቼህ – ጁላይ 15፥2013

አቶ ጃዋር መሃመድ የኢስላምና የኦሮሞ ትግል አይነጣጠሉም የሚል ሃሳብ ያቀረበበትን ቪዲዮ ተመለከትኩ። ሀጂ ነጂብም “80% የኢትዮጵያ ሙስሊም ኦሮሞ ነው” ማለታቸውንም ሰምቻለሁ። እነዚህ ወገኖቻችን ሃሳባቸውን የመግጽና የእምነት መብታቸውን አከብራለሁ። ያሳሰበኝ ጉዳይ ግን የዲያስፓራው ኢትዮጵያውያን ፓለቲካ ሊሂቃን ለኦሮሚያዊነት ተገቢውን እውቅናና ክብር ባለመስጠቱ ፡ የኦሮሞን ጥያቄ ፅንፈኛ ሙስሊሞች ሊጠቀሙበት መዘጋጀታቸው ነው።

የዲያስፓራ ሊሂቃን በተደጋጋሚ የኦሮሞን ጥያቄ በማንጓጠጥ ፡ በማሽሟጠጥ ፡ በመናቅና ችላ በማለታቸው የተነሳ የኦሮሚያዊነት ማንነትን እንጀ ጭንብል ተጠቅመው በኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት ውጥረትን መፍጠር የሚፈልጉ ፅንፈኛ ሙስሊሞች ብቅ ማለት ከጀመሩ ቆይቷል። ይሄንን ስል ጃዋርም ሆነ ሀጂ ነጂብ ፅንፈኛ ናቸው ማለቴ አይደለም። የነገሩ ዝንባሌ ግን ወደፅንፈኝነት የሚንደረደር ይመስላል።
jawar
የአገራችን ሊሂቃን ፡ በተለይ የአማራ ሊሂቃን ፡ አሁን አገራችን ላለችበት የፓለቲካ ቅርጽና ይዘት ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። የተጫወቱት ሚና ግን ሁሉ የሚያስመሰግን ብቻ ሳይሆን የሚያስወግዝም ጭምር ነው። ለምሳሌ ለኤርትራ መገንጠል ዋናው ተጠያቂ የአማራ ሊሂቃን ናቸው። ኤርትራን በኮንፌደሬሽን ከመያዝ ይልቅ በጉልበት እና በሞኝነት ኤርትራን ከ’እናት አገሯ ጋር ትቀላቀል’ ብለው አሁን የኤርትራ ህዝብ ለገባበት ስቃይ እና መከራ የዳረጉት የአማራ ሊሂቃን ናቸው።

ከዛ ትልቅ ስህተት ያልተመረው የዲያስፓራ ሊሂቃን (አማራና ሌሎች ብሄሮችን ያካትታል) ኦሮሚያዊነትን በመናቅ የኦሮሞን ጥያቄ በፅንፈኛ ሙስሊሞች እንዲጠለፍ አሳልፈው እየሰጡት ነው። የኤርትራዊነትንና እና የኢትዮጵያዊነትን ማንነቶች አብሮ የመኖር አቅም ያልተገነዘቡት የአጼው ሊሂቃን ፡ ኤርትራን አስገነጠሉ። አሁን ደግሞ የአጼው ሊሂቃን ልጆች እና የልጅ ልጆች ለኦሮሚያዊነት እና ለኢትዮጵያዊነት በቂ የማንነት ምህዳር ከመፍጠር ይልቅ ፡ “ኦሮሚያ የሚባል አገር የለም” በሚል የሞኝ ዘፈን ኦሮሚያን ለፅንፈኞች እየዳረጓት ይመስላል።

ኦሮሞን መናቅ የኤርትራውን አይነት ሁኔታ እየፈጠረ ነው። ኤርትራውያንን በመርዳት ኢትዮጵያን ማዳከም የፈለጉ ባዕዳን ሃይሎች አጋጣሚውን ተጠቅመው ወገናችን የሆነውን የኤርትራን ህዝብ ከኢትዮጵያዊው ወገኑ ለይተው ለፋሽስት ስርዓት ዳርገውታል። ኦሮሚያውያን ወገኖቻችንንም ካላከበርናቸው ፡ ለማንነታችው ሙሉ እውቅና ካልሰጠን ፡ ጥቂት ኢስላሚስት ኦሮሚያውያን በባዕዳን ተደግፈው ወደ አስከፊ ነውጥ እና ቀውስ አገራችንን መዳረጋቸው አይቀሬ ነው።

ለኦሮሚያዊነት እውቅና መስጠት የኦሮሞን ህዝብ ማክበር ነው። እውቅና መስጠቱ የተከፈተውን ቀዳዳ ይደፍነዋል። ካልሆነ ግን ቀዳዳው እየሰፋ ፡ ኢስላሚስት ኦሮሚያ መመስረቷ አይቀሬ ነው። ከታሪክ እንማር ፡ ከስህተታችን እንማር።

- – - –
ጸሃፊውን ለማግኘት፦ yared_to_the_point@yahoo.com

30ኛው የኢትዮጵያውያን ባህልና ስፖርት ፌዴሬሽን ዝግጅት እንዴት አለፈ?

$
0
0

kinfu4(ቴዲ – አትላንታ)
ከተመሰረተ 30 ዓመት ያስቆጠረው የባህልና ስፖርት ፌዴሬሽኑ ሠላሳኛ ዓመቱን ከጁን 29 እስከ ጁላይ 6 በሜሪላንድ ዋሽንግተን አክብሯል። በዚህ ዝግጅት ላይ ምን ያህል ሰው እንደተገኘ ከፌዴሬሽኑ በይፋ የተነገረ ነገር እስካሁን ባይኖርም ፣ ከ30ሺ ያላነሰ ሰው እንደነበር መገመት ግን ይቻላል። ስቴዲየሙ በጠቅላላ 54ሺ ሰው የሚይዝ ሲሆን፣ ቢያንስ ግማሽ ያሉ ቦታ ሞልቶ ታይቷል፡፡ በዚህ ውድድር በማሸነፍ ዋንጫ ለወሰደው የቨርጂኒያ ቡድን እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን።

(ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ)


Hiber Radio: እስራኤል ከአገሯ በሚባረሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ምትክ ለኢህአዴግ መንግስት የጦር መሳሪያ ለመስጠት እየተደራደረች መሆኑ ታወቀ

$
0
0

የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ፕሮግራም

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የሚሉ መፈክሮችን ሕዝቡ ራሱ ሲያሰማ ነበር …>>

አቶ ሀብታሙ አያሌው የአንድነት፣ለፍትህና ለዴሞክራሲ የብሔራዊ ም/ቤት አባልና የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ዘመቻ አስተባባሪዎች አንዱ ከጎንደር ለህብር ከሰጡት ቃለ ምልልስ (ሙሉውን ያዳምጡ)


ሀይሌና ፖለቲካ አብረው መነሳት ከጀመሩ ቆይተዋል። ሀይሌ በሩጫው ጀግና ቢሆንም ምርጫ 97 ተከትሎ ያ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም ነገር አበርዳለሁ ብሎ የወያኔ መሳሪያ የሆነው ዕውነት መናገር የፈራው የሽማግሌ ቡድን አባል ነው። ቢያንስ የእሱና የሌሎች ሽማግሌዎች ዝምታ የፕ/ር ይስሃቅ ውሸትና ዝምታ ለብርቱካን ዳግም እስር ለእነ አቶ መለስ ጉልበት ሰጥቷል የሚል አግባብ ያለው ቅሬታ ይቀርባል።በዚህ ሁሉ ግን ሀይሌ ገ/ስላሴ ፕሬዝዳንት ለመሆን በፖለቲካው ዓለም ለመሮጥ ዘንድሬ የቆረጠ ይመስላል ። የሀይሌን ውሳኔና ተከትሎት የመጣውን የሰዎች አስተያየት ቃኝተኛል

> በስራ ማቆም አድማ ላይ ከሶስት ወር ተኩል በላይ ያለ አንዳች ክፍያ ከቆዩና ለስራ አጥ ኢንሹራንስ ይግባኝ ካሉ አሽከርካሪዎች አንዱ ለህብር ከሰጠው ቃለ ምልልስ የተወሰደ

(ዝርዝሩን ከወቅታዊው ዘገባ ያዳምጡ)

ሌሎችም ቃለ መጠይቆች አሉን

ዜናዎቻችን
- በፍሎሪዳ የ17 ዓመቱን ታዳጊ ተኩሶ የገደለው ራሱን ለመከላከል ተብሎ ነጻ መሆኑ በአሜሪካ ሕዝባዊ ተቃውሞ አስነሳ

- ሟች ጥቁር ስለሆነ የተፈጸመበት በደል ነው የሚል ቁጣ ቀስቅሷል

- እስራኤል ከአገሯ በሚባረሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ምትክ ለኢህአዴግ መንግስት የጦር መሳሪያ ለመስጠት እየተደራደረች መሆኑ ታወቀ

- አንድነት ፓርቲ በጎንደርና በደሴ ደማቅ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄደ

- የጸጥታ ሀይሎች በጎንደር ከ15 በላይ በደሴ ከ6 በላይ ካሜራ ይዘው ፍርሃት ለመፍጠር ሲቀርጹ ነበር

- የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲሱ ቦይንግ አውሮፕላን ለንደን ላይ የመጨስ አደጋ ቢገጥመውም መብረሬን አላቆምም አለ

- በጎንደር ከ40 ሺህ በደሴ ከ50 ሺህ በላይ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ ተቃወመ

- በአዲስ አበባ ሌቦችን “ለመርዳት ሞክርዋል” የተባሉ አቃቤ ህግ እና የፖሊስ አባል ተያዙ

- በአገር ቤት የሙስሊሙ ህ/ሰብ በአገር አቀፍ ተቃውሞ > አለ

- የአርቡን ተቃውሞ ተከትሎ ከ24 በላይ ወጣቶች በአዲስ አበባ ታስረዋል

– ይግባኛቸው የተደመጠው በስራ ማቆም አድማ ላይ ያሉት የቬጋስ አሽከርካሪዎች በሕግ እኛሸንፋለን የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገለጹ

ሌሎችም ዜናዎች አሉን

በዋልድባ ገዳም የሚገኘው የስኳር ፕሮጀክት ነዳጅ ማራገፊያ የመሬት መንሸራተት አጋጠመው

$
0
0

የዋልድባ ገዳም አባቶች የድረሱልኝ ጥሪያቸውን ያሰማሉ

የዋልድባ ገዳም አባቶች የድረሱልኝ ጥሪያቸውን ያሰማሉ

“በዋልድባ ገዳም የሚገኘው የስኳር ፕሮጀክት ነዳጅ ማራገፊያ የመሬት መንሸራተት አጋጠመው” አንድአድርገን የተሰኘው ሃይማኖታዊ ድረ-ገጽ ዘገበ።
ድረ ገጹ ዛሬ ባሰራጨው ዜና “መንግስት እገነባቸዋለሁ ካላቸው የስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ ብዙ ውዝግብ ያስነሳው ፤ ብዙ ዋጋ ያስከፈለው አሁንም እያስከፈለ ካለው የሥኳር ፋብሪካ ውስጥ በዋልድባ ገዳም የሚገነባው አንዱ ነው፡፡ እነዚህን ፕሮጀክቶች በበላይነት የሚመራው መቀመጫው መሀል ካሳንቺስ ያደረገው በአቶ አባይ ጸሀዬ የሚመራው የስኳር ኮርፖሬሽን መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከፕሮጀክቶቹ አንዱ እና ዋንኛው የሆነውን የዋልድባን የስኳር ፋብሪካ ግንባታን በመቃወም ብዙ መነኮሳት ከበአታቸው በመሰደድ በያሉበት ሆነው ስራውን እየተቃወሙ ይገኛሉ ፤ ፕሮጀክቱን ለመስራት በየጊዜው የሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የመጡ ኮንትራክተሮች ውል በመቋጠር እንደገና በመፍታት አሁን ላይ ሶስተኛው ስራ ተቋራጭ ስራው እያካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡” ብሏል።

አንድ አድርገን ዘገባውን በመቀጠል መንግሥት በትላልቅ ፕሮጀክቶች ስራቸው እንዳይተጓጎል ለማድረግ ከየትኛውም ፕሮጀክቶች በተለየ መልኩ ከብሔራዊ ነዳጅ ማከማቻ ጋር የተለየ ውል መያዙን የውስጥ ሰዎች ይገልጻሉ ፤ ለአንድም ቀን ይሁን እነዚህ ፕሮጀክቶች ላይ የሚሰሩ መኪናዎችና የተለያዩ በነዳጅ የሚሰሩ መሳሪያዎች ስራቸው እንዳይስተጓጎል በመጀመሪያ ደረጃ በተለየ ምልከታ የነዳጅ ፍላጎታቸው በየጊዜው እንደሚቀርብላቸው ምንጮች ያስረዳሉ፡፡ ብሏል።

“ከሳምንታት በፊት በዋልድባ ገዳም እየተሰራ ለሚገኝው የሥኳር ልማት ፕሮጀክት አንድ ከነተሳቢው ነዳጅ የጫነ መኪና ከአዲስ አበባ ወደ ዋልድባ የጫነውን ነዳጅ ለማራገፍ ወደ ቦታው ያመራል ፤ ቦታው ላይም ነዳጅ የጫነው መኪና በጊዜው መድረስ ችሎ ነበር ፤ ነገር ግን ነዳጅ የጫነው መኪና በጊዜው ቢደርስም ነዳጁን ለማራገፍ በሚሞክርበት ጊዜ ከመሬት ስር የተቀበረው ነዳጅ ማራገፊያ በመሬት መንሸራተት ምክንያት ከዋናው ቦታ መሸሹን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህ ምክንያትም ነዳጁን የያዘው መኪና በመሬት መንሸራተት ምክንያት ቦታውን ያጣውን ነዳጅ ማከማቻ ወደ ቦታው የመመለስ ስራ እስኪሰራ እና ለመገልበጥ ሁኔታዎች እስኪመቻቹ ድረስ ለ21 ቀናት በቦታው ላይ መቆሙን ለማወቅ ተችሏል፡፡” ያለው ድረገጹ እግዚአብሔር በአንድም በሌላም መንገድ ይናገራል ፤ በዋልድባ ከፕሮጀክቶቹ ጋር ተያይዙ ብዙ ምልክቶች እየታዩ ይገኛሉ ፤ ላስተዋለ አንድም ምልክት በቂ ነበር ላላስተዋለ እንደ ፈርኦን አስራ አንድ ምልክት ቢከታተል ልቡ ደንድኗልና የመጨረሻውን ምልክት እስከሚያይ ድረስ ፤ ባሕረ ኤርትራ ተከፍቶ እስኪውጠው ድረስ ከጥፋት ስራው ሊመለስ አይችልም ፤ መጽሀፉ ‹‹ ማንም የቆመ ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ›› ይላል” ሲል ምክሩን አጠናቋል።

Sport: ዋሊያዎቹ ኡጋንዳን ቢያሸንፉም ለቻን ዋንጫ ትኩረት ይስጡት

$
0
0

ከቦጋለ አበበ
Ethiopia national team
ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች የማይሳተፉበት የአፍሪካ ዋንጫ (የቻን ) ጨዋታ ላይ ለመሳተፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጨረሻው የጥሎ ማለፍ ድልድል ከሩዋንዳ አቻው ጋር ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም የመጀመሪያውን ጨዋታ አካሂዷል፡፡
ዋልያዎቹ ጨዋታውን በአስራት መገርሳ ብቸኛ ግብ አንድ ለባዶ ማሸነፍ ቢችሉም ለጨዋታው ብዙ ትኩረት እንዳልሰጡ መመልከት ተችሏል፡፡ በጨዋታው የተሻለ እንቅስቃሴ ቢያደርጉም በርካታ ግቦችን አስቆጥረው ወደ ሻምፒዮናው የሚያልፉበትን ሰፊ እድል ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል፡፡
በጨዋታው ዋልያዎቹ ከደቡብ አፍሪካው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በተሻለ ማራኪ እንቅስቃሴ ማሳየት ችለዋል፡፡ ኳስን መሠረት ያደረገ አጨዋወት መከተላቸውም ውበት ያለው ጨዋታ እንዲያሳዩ አስችሏቸዋል፡፡
ዋልያዎቹ በጨዋታው የመጀመሪያ አርባ አምስት ደቂቃ በተሻለ የኳስ ፍሰት በተቃራኒያቸው ላይ ጫና ፈጥረው ተጫውተዋል፡፡ ለግብ የቀረቡ በርካታ ሙከራዎችን በማድረግም ከተቃራኒያቸው የተሻሉ ነበሩ፡፡ ይሁን እንጂ ያገኟቸውን መልካም አጋጣሚዎች ወደ ግብ መቀየር ባለመቻላቸው ካለምንም ግብዕረፍት ለመውጣት ተገደዋል፡፡
በመጀመሪያው አርባ አምስት ደቂቃ የጨዋታ ጊዜ በተለይም ተከላካዩ ዓይናለም ኃይሉና ሽመልስ በቀለ ያደረጉት ለግብ የቀረበ ሙከራ የሚያስቆጭ ነበር፡፡ በዚሁ የጨዋታ ጊዜ በግራ ክንፍ በኩል ምንያህል ተሾመ፣ በቀኝ ክንፍ ደግሞ ስዩም ተስፋዬ ያሻገሯቸው ጥሩ ኳሶችን ወደ ግብ የሚቀይር አጥቂ አለመኖሩ የሚያስቆጭ ሆኗል፡፡
በተከላካዮች በኩል የመዘናጋትና የጥንቃቄ ጉድለት ቢስተዋልም በአማካይ ስፍራ አስራት መገርሳና ሽመልስ በቀለ ማራኪ እንቅስቃሴ አድርገዋል፡፡ አጥቂው ዳዊት ፍቃዱም ጥሩ ተንቀሳቅሶ ኳስን ከመረብ ማገናኘት ሳይችል ቀርቷል፡፡
በሁለተኛው አርባ አምስት የጨዋታ ጊዜ ዋልያዎቹ በኳስ ቁጥጥር የተሻሉ ቢሆኑም በኃይሉ አሰፋ ሃምሳ ሰባተኛው ደቂቃ ላይ ያሻገራትን ኳስ አስራት መገርሳ በግንባሩ ገጭቶ በግሩም ሁኔታ ካስቆጠራት ግብ ውጪ ተጨማሪ ግብ ከመረብ ማሳረፍ አልቻሉም፡፡
ዋልያዎቹ በጨዋታው እንደነበራቸው የበላይነት በርካታ ግቦችን አስቆጥረው የመልስ ጨዋታው ላይ የሚኖርባቸውን ጫና ማስወገድ ይችሉ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ያገኟቸውን መልካም አጋጣሚዎች ባለመጠቀማቸው በመልሱ ጨዋታ ጫና ውስጥ ገብተዋል፡፡
ዋልያዎቹ ከዝግጅት ጀምሮ ለሻምፒዮናው ብዙ ትኩረት እንዳልሰጡ በጨዋታው መመልከት ይቻላል፡፡ በርካታ ግቦች አስቆጥረው በቀጣዩ ጨዋታ ቢያንስ በጠባብ ግብ ተሸንፈው በቀጥታ የሻምፒዮናው ተሳታፊ ከመሆን ይልቅ በአንድ ግብ ብቻ በራስ መተማመን ታይቶባቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ በቀጣዩ ጨዋታ አደጋ ውስጥ እንዲገቡ ከማድረጉ በተጨማሪ ከሻምፒዮናው ከወዲሁ የሚሰናበቱበትን አጋጣሚ ሊፈጥር ይችላል፡፡
ሻምፒዮናው በፊፋ እውቅና ያለው እንደመሆኑ መጠን የአገራችንን የእግር ኳስ ደረጃ የት እንደደረሰ የምናሳይበት ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር በአህጉር ደረጃ የተዘጋጀውን ዋንጫ ማንሳት ባይቻል ጥሩ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቅ እግር ኳሳችንን በማነቃቃት ረገድ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡
የመልሱ ጨዋታ ከሜዳችን ውጪ ከሁለት ሳምንት በኋላ በሩዋንዳ አማሃሮ ስታዲየም ይካሄዳል፡፡ ዋልያዎቹ በሻምፒዮናው ለመሳተፍ በዚያ ጨዋታ የአቻ ውጤት በቂያቸው ነው፡፡ ይሁን እንጂ አሙቫቢ ወይንም ተርቦቹ በመባል የሚታወቁት ሩዋንዳዎች ቀላል ይሆናሉ ብሎ መገመት ከባድ ስለሆነ ከወዲሁ ትኩረት ልንሰጠው ይገባል፡፡
የቻን ሻምፒዮና በመጪው ዓመት በደቡብ አፍሪካ አዘጋጅነት ይካሄዳል፡፡ ከምስራቅ አፍሪካ ሦስት አገሮች የተሳትፎ ኮታ አላቸው፡፡ ከዋልያዎቹና ከተርቦቹ አሸናፊ በተጨማሪ ከቡሩንዲና ከሱዳን እንዲሁም ከታንዛኒያና ኡጋንዳ አሸናፊ የሚሆኑ አገራት የሻምፒዮናው ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡
በቅድመ ማጣሪያው ጨዋታ ዋልያዎቹ ከኤርትራ ጋር ተደልድለው ኤርትራ ከሻምፒዮናው ራሷን በማግለሏ በፎርፌ በቀጥታ ወደ መጨረሻው ማጣሪያ ማለፋቸው ይታወሳል፡፡
በአሰልጣኝ ኤሪክ ኒሺሚያማ የሚሰለጥኑት ተርቦቹ በዚህ ሻምፒዮና ከሁለት ዓመት በፊት በመሳተፍ ከዋልያዎቹ የተሻለ ታሪክ አላቸው፡፡
ሻምፒዮናው ለመጀመሪያ ጊዜ እ.ኤ.አ በ2009 በኮትዲቯር አዘጋጅነት ተካሂዶ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ጋናን ሁለት ለባዶ በማሸነፍ ዋንጫ አንስታለች፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደውን ሻምፒዮና ደግሞ ሱዳን አዘጋጅታ ቱኒዚያ አንጎላን ሦስት ለባዶ በማሸነፍ ሻምፒዮን እንደነበረች ይታወሳል፡፡

Sport: በአርሴናል የማይፈለጉ 11 ተጫዋቾች

$
0
0

sagnaከይርጋ አበበ

የሰሜን ለንደኑ አርሴናል ባለፉት ዓመታት ወደ ክለቡ ያዘዋወራቸውና የተጠበቀውን ያህል መጥቀም ያልቻሉትን ተጫዋቾች የመውጫ በሩን የከፈተላቸው ሲሆን ከእነዚህ በርካታ ተጫዋቾች መካከል የተለያዩ ምንጮች የዘረዘሯቸው አስራ አንድ ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው።

1

ግብ ጠባቂ
ማኖኒ
ጣሊያናዊው የ25 ዓመት ወጣት ነው። በግብ ጠባቂነቱ የንስ ሌህማንንና ዴቪድ ሲማንን እንደሚተካ ተስፋ ተጥሎበት ከጣሊያኑ ናፖሊ ወደ ሰሜን ለንደን አርሴናል የደረሰው ከሰባት ዓመት በፊት ነበር። ልምድ እንዲያገኝ በማሰብ በውሰት ወደተለያዩ ክለቦች ቢዘዋወርም ከመንከራተት በቀር የታሰበውን ያህል ሆኖ ባለመገኘቱ የ2013/14 የውድድር ዘመን ሳይጀመር ቦታህን ፈልግ ተብሏል። ወደ ምሥራቅ እንግሊዝ በማምራትም ጥቋቁር ድመቶቹ ለሚባሉት ለሰንደርላንድ በሁለት ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳበ ዝውውር አድርጓል።

2

ተከላካዮች
ባካሪ ሳኛ
የቀድሞው የኦግዜር ተጫዋች በሰሜን ለንደኑ ክለብ ከፍተኛ ግልጋሎትን መስጠት ቢችልም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ያሳየው የወረደ አቋም ቬንገር ፊታቸውን እንዲያጠቁሩበት አድርጓል። በዚህም በቀጣዩ የውድድር ዘመን ለፈረንሳዮቹ ፒ.ኤስ.ጂ ወይም ሞናኮ ሊፈርም እንደሚችል ይገመታል።

3

አንድሬ ሳንቶስ
የአርሴናል ደጋፊዎች የዚህን ብራዚላዊ ስም መስማት አጥብቀው ይጠሉታል። ለዚህ ያበቃቸው ደግሞ ሜዳ ላይ ከሚሰራቸው ተደጋጋሚ ስህተቶቹ በተጨማሪ ባለፈው ዓመት ክለቡን ለቆ ለማንቸስተር ዩናይትድ የፈረመውን ሮቢን ቫንፐርሲን ማሊያ እንዲቀይረው መልበሻ ክፍል ድረስ ሂዶ መለመኑ ነበር። ካለበት የአቋም መዋዠቅ ጋር ተደማምሮ በቀጣዩ የውድድር ዓመት የአርሴናልን ማሊያ ከማይለብሱ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ሊሆን እንደሚችል ሰፊ ግምት ተሰጥቶታል።

4

ሴባስቲያን ስኩላቺ
ፈረንሳዊ ነው። የቀድሞው የሲቪያ ተከላካይ ተጫዋች የነበረ ሲሆን፣ አምስት ሚሊዮን ፓውንድ ተከፍሎበት ነበር በ2010 ኢምሬትስ የደረሰው። ነገር ግን አንጋፋው ተከላካይ ለስህተት በእጅጉ የቀረበ መሆኑ የኢምሬትስ መውጫ በሮች ተከፍተውለት በነጻ ወደ ፈለገው ክለብ እንዲዛወር ፍቃድ ተሰጥቶታል።

5

ዩሃን ዡሩ
ትውልደ ኮትዲቯራዊ የሲዊትዘርላንድ ተከላካይ ነው። ወደ አርሴናል ሲዘዋወር አዲሱ ሶል ካምቤል ይሆናል ተብሎ ነበር። ከጉዳት ጋር ያለው ዝምድና በእጅጉ የቀረበው ይህ ተከላካይ ዓመታት በተፈራረቁ መጠን ብቃቱም ያንኑ ያህል እየቀነሰ መሄዱ ለ2013/14 የውድድር ዘመን ወደ ጀርመን ተጉዞ ለሃምቡርግ እንዲጫወት ቬንገር የአንድ ዓመት የውሰት ውል ፈቅደውለት ወደዚያው አምርቷል።

6

አማካዮች
ጄርቪንሆ
ለአስተያየት ሰጨዎች ግራ ያጋባው ይህ ተጫዋች በቀጣዩ ዓመት የአርሴናል ደጋፊዎች የክለባቸውን ማሊያ እንዲለብሱ ከማይፈልጓቸው መካከል አንዱ ነው። ፈጣን እና ጥሩ የኳስ ችሎታ ቢኖረውም የመጨረሻ ኳሶቹ ማረፊያ ማለትም ዒላማ የሚስት መሆኑ ነበር የክለቡን ደጋፊዎችና የአሠልጣኞች ቡድን ያበሳጫቸው። ወደ ቱርኩ ጋላታሳራይ ወይም ወደ ፈረንሳዮቹ ሊልና ሊዮን ዝውውር ሊያደርግ እንደሚችል ይገመታል።

7

ዴኒልሰን
ብራዚላዊው አማካይ ተጫዋች በ2006 ሃይበሪ ሲደርስ የጂልቤርቶ ሲልቫ ትክክለኛ ተተኪ እንደሚሆን ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶት ነበር። በመጀመሪያዎቹ ሦስት ዓመታት የክለቡ ደጋፊዎች ስሙን እየጠሩ የሚዘምሩለት ኮከብ ቢሆንም ከጉዳት በኋላ ብቃቱ ወርዶ ታይቷል። የቀድሞ ብቃቱን እንዲያገኝ በማሰብ ለብራዚሉ ሳኦፖሎ በውሰት እንዲጫወት ወደ ብራዚል ቢያቀናም እርሱና ብቃቱ ላይገናኙ የተለያዩ መስለው የታያቸው አርሴን ቬንገር በቀጣዩ ዓመት ከክለባቸው ጋር እንደማይቆይ በይፋ ነግረውታል።

8

ኢማኑኤል ፍሪምፖንግ
በትውልድ እንግሊዛዊ የሆነው የጋና ዜግነት ያለው የአማካይ ተከላካይ ተጫዋች ሜዳ ላይ በሚቆይበት እያንዳንዱ ደቂቃ ለውዝግብና ለፀብ የተጋለጠ መሆኑ ክለቡን በተደጋጋሚ ጊዜ አደጋ ላይ ሲጥል ተስተውሏል። በዚህም ተስፋ የቆረጡት አንጋፋው ፈረንሳዊው የክለቡ አሠልጣኝ ወደ ሌላ ክለብ ተዘዋውሮ እንዲጫወት ነግረውታል።

9

አንድሪ አርሻቪን
ታታሪ እንዳልሆነ የሚነገርለት የቀድሞው የሩሲያ ብሔራዊ ቡድን አምበል አርሻቪን፣ አርሴናልን ከተሰናበተ ቀናት ተቆጥረዋል። እስካሁን ለአርሴናል ሪከርድ በሆነ የዝውውር ሂሳብ በ2009 ጥር ላይ ከሩሲያው ዜኒት ሴንት ፒተርስበርግ ነበር የተዘዋወረው። ተቀያሪ ወንበር ላይ መቀመጤ ለአዕምሮ ጭንቀት ዳርጎኝ ነበር ብሎ ለሀገሩ ቴሌቪዥን የተናገረው አርሻቪን በአርሴናል በነበረው ቆይታ የመጨረሻ ዓመታት የተጠበቀውን ያህል መጥቀም አለመቻሉ ነበር በነጻ ዝውውር ኢምሬትስን እንዲሰናበት ያደረገው።

10

አጥቂዎች
ኒኮላስ ቤትነር
ራሱን የዓለም ኮከብ ነኝ እያለ የሚመጻደቅ ዴንማርካዊ ቁመተ መለሎ አጥቂ ነው። ከአርሴናል ጋር ያለው እህል ውሃ የሚያበቃው በዚህ በተከፈተው የዝውውር መስኮት ነው። በተደጋጋሚ ጊዜ ወደ ተለያዩ ክለቦች በውሰት እየተዘዋወረ ራሱን እንዲመለከት ቢደረገም፣ ብቃቱን ማሻሻል አለመቻሉ ሌላው የክለቡ ተሰናባች ሊሆን ችሏል። እርሱም በቀጣዩ ዓመት ወደ ጀርመን ተጉዞ ለሃምቡርግ ወይም ለቱርኩ ግዙፍ ክለብ ጋላታሳራይ ሊፈርም ይችላል።

11

ማሩዋን ሻማክ

መለሎው ሰሜን አፍሪካዊ ማሩዋን ሻማክ ከቦርዶ ወደ አርሴናል በተዘዋወረበት የመጀመሪያ ዓመት ቆይታው አጃኢብ ያስባለ አቋም ነበር ያሳየው። ነገር ግን የሮቢን ቫንፐርሲ ከጉዳት ማገገም ተከትሎ ወደ ተቀያሪ ወንበር መውረዱ የራስ መተማመኑም አብሮ ወርዷል እየተባለ ይታማል። የአካውንቲንግ ምሩቁ ይህ ሞሮኳዊ አጥቂ በቀጣዩ ዓመት ወደ ፈረንሳይ ተመልሶ መጫወት እንደሚፈልግ መናገሩን ተከትሎ ለቀድሞ ክለቡ ቦርዶ ይፈርማል ተብሎ ይጠበቃል።

በረከት ስሞዖን “መርጋ አድማሱ”በሚል የብዕር ስም አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ስለ ግንቦት 7ና ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጻፉ

$
0
0

ኤርትራዊው አቶ በረከት ስምዖን መርጋ አድማሱ በሚል የብዕር ሥም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ “«ግንቦት ሰባት» ያመነው ተላላኪነቱና አንድምታው” በሚል ርዕስ ጽሁፍ ማስፈራቸው ተጋለጠ። ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ቅርብ የሆኑ ሰዎች እንዳጋለጡት ከዚህ ቀደምም አቶ መለስ ዜናዊ እንዲሁ በብእር ስም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከመፃፍ በተጨማሪ “አዲስ ራዕይ” የተባለው የኢሕ አዴግ ጋዜጣ አዘጋጅ እንደነበሩ ከሞቱ በኋላ መገለጹን ጠቅሰዋል። አቶ መለስም ሆነ አቶ በረከት ስምዖን በብዕር ስም ስለአንድ ድርጅት በአዲስ ዘመን ከፃፉ የዛ ድርጅት እንቅስቃሴ አስፈርቷቸዋል ማለት ነው የሚሉት ይህን ያጋለጡት የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ምንጮች ግንቦት 7 አሁንም የኢሕ አዴግ ራስ ምታት እንደሆነ ቀጥሏል ብለዋል።፡ኤርትራዊው አቶ በረከት ግንቦት ሰባትን እና ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን በኤርትራ ተላላኪነት የከሰሱበት ጽሁፍ መርጋ አድማሱ በሚል በአዲስ ዘመን ጋዜጣ “አጀንዳ” በሚል አምድ ስር የጻፉት ጽሁፍ ደርሶናል ለግንዛቤዎ አቅርበነዋል።
ከመርጋ አድማሱ (በረከት ስምዖን)

አቶ በረከት

አቶ በረከት

«…100 ሺ ዶላሩን ሀገር ውስጥ ለሚካሄደው ሰላማዊ ትግልና ለዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ፣ 200 ሺ ዶላሩን ለኢሳት እንዲሁም 200 ሺ ዶላሩን ደግሞ ለወታደራዊና ለደህንነት ስራዎች አውሉት ተብለናል…» ይላል- ሰሞኑን ራሱን «ግንቦት ሰባት» እያለ የሚጠራውን የሽብር ቡድን የሚመሩት ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ከኤርትራ ባለስልጣናት ጋር ያካሄዱት ምስጢራዊ የቴሌኮንፍረንስ ውይይት።«የዶክተር ኢኮኖሚስቱ» በራስ አንደበት የተነገረው የተላላኪነት ምስክርነት በዚህ ብቻ አያበቃም። ቀጥሎም ያለ አንዳች ሃፍረት «…እናመሰግናለን እግዚአብሔር ይስጥልን ስንላቸው፣ ‘ለምን ታመሰግኑናላችሁ? እኛ ለራሳችን ብለን እኮ ነው የምንሰጣችሁ አሉን!’…»ይላል።
ይህን የዶክተር ተብዬውን ‘ተላላኪዎች ነን’ የሚል አሳፋሪ አባባል በቦታው ተገኝቼ የሰማሁት እኔ የዚህ ፅሑፍ አቅራቢ አይደለሁም። ሰሞኑን አይጋ ፎረም የተሰኘው ድረ-ገፅ ምንጮቹን በመጥቀስ ካሰማን ትክክለኛው የዶክተሩ ድምፅ ያዳመጥኩት እንጂ። እርግጥ አሸባሪው ቡድን በየስድስት ወሩ ግማሽ ሚሊዮን ዶላር ከሻዕቢያ እንደሚሰጠው ያመነበት ይህ አባባል፤ የሀገራችን ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስትና ታላቁ መሪያችን አቶ መለስ ዜናዊ የሽብር ቡድኑን አስመልክተው «…ግንቦት ሰባት በሻዕቢያ ነጭ ለባሽነት የሚንቀሳቀስ የሽብር ቡድን ነው…» በማለት ደጋግመው የተናገሩትን ዕውነታ የሚያረጋግጥ ነው- «ጉድና ጅራት ከበስተኋላ ነው» እንዲል የሀገራችን አርሶ አደር።
ታዲያ በእኔ እምነት በራስ ማንነታዊ ተግባር ላይ የተሰጠው ይህ የተላላኪነት ምስክርነት የአሸባሪው «የዶክተር ኢኮኖሚስቱ » ቡድን ሀገሩን የካደ እንዲሁም ለገንዘብና ለባዕዳን ጥቅም ሲል በፖስተኝነት ተቀጥሮ የሚሰራ ባንዳ መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ የሚያስረዳ ብቻ አይደለም። ከዚህ ባለፈም ምንም እንኳን ከላይ ላዩ አዛዡና ፋይናንስ አድራጊው የአስመራው ቡድን ይሁን እንጂ፣ በኤርትራ መንግስት ትከሻ ላይ ዶላሩን በመያዝ ያለ ከልካይ እግሩን አንፈራጥጦ በመቀመጥ (የሽማግሌው የአቶ ኢሳያስ ትከሻ ምን ያህል እንደሚችለው ባላውቅም)፣ ሀገራችን ታላቁን የህዳሴ ግድብ እንዳትገነባ ለማደናቀፍ ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎችን መደገፍ ጨምሮ «…ሁሉም አማራጮች ክፍት ናቸው»ያሉትና በአሮጌው ዘመን አስተሳሰብ የሚዳክሩት የግብፅ ገዥ መደቦች እጅም ከበስተጀርባው ያለበት ይመስለኛል። ምክንያቱም ይህ እሳቤ በቀጥታ በካይሮ መንግስት ሚዲያዎች ሲስተጋባ የነበረ በመሆኑ ነው።
እርግጥ የተላላኪው ዶክተርም ይሁን የሽብር ቡድናቸው የትናንት ዳራ ሲፈተሽ ስብዕናቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገቡ ሃቆች ይገኛሉ፡፡ በትረ ስልጣን የሚያስገኝልኝ ከሆነ ከዲያቢሎስ ጋርም በሽርክና የመስራት ችግር የለብኝም ብለው ነበር አሜሪካ ቁጭ ብለው ስልጣን እንደ እህል ውሃ የሚርባቸውና የሚጠማቸው ዶክተር ብርሃኑ ነጋ። ይሁንና ሰውዬውም ሆነ ድርጅታቸው ከትናንት እስከ ዛሬ ድረስ የኤርትራ መንግስት ተላላኪና ተወርዋሪ ድንጋይ በመሆን ተንቀሳቅሰውና ለመንቀሳቀስ ሞክረው አንዳችም ፋይዳ አላስገኙም። ወትሮም ቢሆን «ሊቁ ዶክተር» ሀገርን አጫርቶ ለባዕዳን የመሸጥ እንጂ የዲፕሎማሲ ዕውቀት ስለሌላቸው ሃሞታቸው ሁሌም እንደፈሰሰ ነው።
ያለ አንዳች ሰራዊት «ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው» የሚል አሮጌ ብሂልን ይዘው ኢሳትን በኤርትራ ዳረጎት ሰጪነት ያቋቋሙት የአሸባሪው ቡድን መሪ፤ ልክ እንደ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ይካሄድ እንደነበረው ግብረ-መልስ በሌለው ባለ አንድ መንገድ የተግባቦት ስራ ታጥሮ በአሉባልታ የሚመራ ህዝብ ያለ የሚመስላቸው የሞኝ አዝማች ናቸው። በአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ሳንባ የሚተነፍሱት አሸባሪው ዶክተር ከተራ ጉራ እና አሉባልታ በስተቀር ስለ ዴሞክራሲ የሚያውቁት አንዳችም ነገር የለም፡፡ ዴሞክራሲን እንደ ተላጠ የኤሌክትሪክ ሽቦ በመፍራት ራሳቸውን ለሽብርተኝነትና ለአመጽ ያዘጋጁና ኢትዮጵያን መበታተን ከሚሹ ወገኖች ጋር «ጎሮ ወሸባዬ»የሚሉ ግለሰብ ናቸው፡፡
አስመራ ውስጥ አቶ ኢሳያስ ሲያሰነጥሳቸው፤ መሃረብ አስይዘው እንዲያብሱ ወደዚያች ትንሽዬ ሀገር ምክትል አሸባሪያቸውን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን የመደቡት እኚህ ፀረ – ሠላም፣ ፀረ-ልማትና ፀረ – ዴሞክራሲ ግለሰብ፤ ምን ያህል የሀገራችን ደመኛ ጠላት መሆናቸውን የእዚህ ጽሑፍ አንባቢ እንደሚገነዘበው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ምንም እንኳን ሰውዬው በአሜሪካ ፔልሲቪኒያ ግዛት ውስጥ ፀንሰውት አስመራ በሚገኘው የሽብር ማህፀን ውስጥ የተገላገሉትን ባንዳ ቡድን ቢመሰርቱም፤ ይህን የሁከት ስብስብ በአግባቡ መምራት ያልቻሉ ናቸው አሸባሪ ቡድናቸው ሁለትና ሶስት ቦታዎች ላይ ተሰነጣጥቋልና።
ታዲያ ከሽብር ቡድኑ ያፈነገጡት ቡድኖች እንደሚገልጹት፤ አቶ አንዳርጋቸው በአቶ ኢሳያስ ትዕዛዝ ለ«ጓል አስመራ» (ለአስመራ ሴት) ተድረዋል ምናልባትም በዓላማም ይሁን በግብር ከማይገናኟቸው«እሳትና ውሃ» ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ጋር ተስማምተው ለመስራት ካላቸው ፍላጎት አኳያ ተመዝነው ሊሆን ይችላል። እንዲያውም የኢትዮጵያን ጉዳይ በተመለከተ የአስመራው የሽብር አዝማች ዋና ምስጢረኛ ሆነው የአቶ ኢሳያስ አማካሪ የሆኑትን የአቶ የማነ ገብረአብን (መንኪ) ስልጣንን ሳይጋሩ የቀሩ እንደማይመስልም እኚሁ ተሰንጣቂዎች ይናገራሉ። እርግጥም አንድ ሀገሩን ለገንዘብ ሲል የሸጠ ግለሰብና ቡድን ከዚህ መሰሉ የመላላክ ተግባር የተለየ ምንም ዓይነት ቁም ነገር ሊሰራ አይችልም፡፡
ለነገሩ የእነ «ሊቁ ዶክተር» ፍላጎት ስልጣንን አቶ ኢሳያስ ጫንቃ ላይ ቁጭ ብሎ ለማግኘት የራስን ትከሻ ለአቶ ኢሳያስና ከጀርባቸው ላሉት የግብፅ ገዥ መደቦች ማከራየት ነው። ይሁንና ስልጣን በዴሞክራሲያዊ የምርጫ ፉክክር እንጂ፤ የራሱ ስልጣን በቫይረስ ተጠቅቶ አንድ ሐሙስ የቀረውን የአስመራው የሁከት ቡድን አጋፋሪን «የጡት አባት» በማድረግ ሊገኝ አይችልም- የኢትዮጵያ ህዝብ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤት ሆኖ ላለፉት አራት ተከታታይ ምርጫዎች የሚበጀውን ኃይል እየመረጠ መጥቷልና- እነ «ዶክተራችንን» እና መሰል ፀረ-ህገ-መንግስት ኃይሎችን እያንጓለለ በመጣል። እናም ሚዛናዊውና ሁሌም እውነትን ፈራጅ የሆነው የሀገራችን ህዝብ ሰውዬውንና ጀሌዎቻቸውን አንቅሮ ከተፋቸው ስምንተኛ ዓመቱን ይዟል፡፡ የተተፋ ነገር ደግሞ ተመልሶ ስለማይላስ በሀገራችን ህዝብ ስም ባይነግዱ በጄ ነው። ስለሆነም ተላላኪው ዶክተርና ባንዳው ቡድናቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ህዝብ ይሁንታ ስልጣን ማግኘት «እንቁልልጭ» መሆኑን ማወቅ ያለባቸው ይመስለኛል፡፡
ውድ አንባቢዎቼ ስለ «ሊቁ ዶክተር» እና ስለ ሽብር ቡድናቸው ባንዳዊ ማንነት በመጠኑም ቢሆን ይህን ያህል ከተገነዘባችሁ ዘንዳ፤ አሁን ደግሞ «በአዲስ መልክ የሽብር ስራ ጀምረናል» በማለት በቀቢፀ-ተስፋ ሀገራችንን ለማተራመስ ከሻዕቢያ በዳረጎት መልክ የተቀበሉትን የ500 ሺ ዶላር ክፍፍል እና ቡድኑ እንዲያውለው ስለታዘዘው ስራ ብሎም ከበስተጀርባው ሊኖር ስለሚችለው የግብፅ ቡድን ጥቂት እናውጋ።…እስቲ በቅድሚያ ስብዕናቸውን መሬት ላይ አፈር ድሜ እስኪበላ ድረስ ፈጥፍጠው ተላላኪ የሆኑት «ዶክተር ኢኮኖሚስት» አንድ መቶ ሺህ ዶላሩን «ሀገር ውስጥ ለሚካሄደው ሰላማዊ ትግልና ለዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች» እንዲያውሉ ከታዘዙበት ጉዳይ እንነሳ። ማንም የዚህ ፅሑፍ አንባቢ እንደሚያውቀው የአሸባሪው ሰውዬ ቡድን ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በወሬም ቢሆን በኃይል ለመናድ የተነሳ ተላላኪ እንጂ፣ ሀገራችን ውስጥ ሰላማዊ ትግልን የሚያካሂድ አይደለም። በሻዕቢያ የአሸባሪነት ባህር መዝገብ ውስጥ እንጂ፣ ሰላማዊ ትግል ለማካሄድ በምርጫ ቦርድ ሰነድ ላይ ተመዝግቦም አይገኝም። ስለሆነም ‘እናስ ለየትኛው ሰላማዊ ትግሉ ነው በሀገር ቤት አማካይ ስሌት የሁለት ሚሊዮን ብር በጀት የመደበው?’ የሚል ጥያቄን ማንሳት በእጅጉ ያስፈልጋል።
የጽንፈኛው ፖለቲካ መንገድ በሀገር ውስጥ ያሉ ፓርቲዎችንም ይበክል ይሆን እንድል የሚያደርገኝ አንድሪው ሚለር የተባሉ ግለሰብ ‘ትራንፔት ዶት ኮም’ በተሰኘው ድረ-ገፅ ላይ እ.ኤ.አ. ጁላይ 13 ቀን 2013 ዓ.ም የሰማያዊ ፓርቲን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክተው እንደፃፉት፤ በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ፀረ-መንግስት ሰልፎች በግብፅ የሚደገፉ ናቸው ማለታቸው ነው። ለዚህ ደግሞ በምክንያትነት የሚጠቅሱት የካይሮውን መንግስት የሚመራው የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ (ዛሬ ችግር ላይ ነው ያለው) ዴሞክራሲያዊ አብዮቶችን ወደ እስልምና ጉዳዮች የመቀልበስ ልምድ ስላለው ነው ባይ ናቸው። ፀሐፊው አክለውም ‘የኢትዮጵያ ህዝብ ቀጣዩ የዚህ አጀንዳ ሊሆን ይችላልን?’ ሲሉም ይጠይቃሉ።
እርግጥም በእኔ እምነት በሰላማዊ ፓርቲነት ስም ተመዝግቦና ከመንግስት ፈቃድ ወስዶ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣው ሰማያዊ ፓርቲ በቅድመ-ሰልፍ ሂደቱ የሀገራችንን ገፅታ ጥላሸት ለመቀባት በማሰብ ማቅ ለብሼና ማቅ መስዬ የአፍሪካ መሪዎች ካላዮኝ ማለቱ እንዲሁም ፓርቲው ያዘጋጀው ሰልፍ በአብዛኛው በሃይማኖት ስም የሚነግዱ ፅንፈኛ ግለሰቦች አሊያም የዶክተር ብርሃኑ ዓይነት አቋም ያላቸው እንደ ዶክተር ያዕቆብ ኃ/ማርያም የመሳሰሉ የከሰሩ ፖለቲከኞች ተፅዕኖ ስር መውደቁ የሚስተር ሚለርን ምክንያታዊ አመክንዩ ጥያቄን ሚዛን እንዲደፉ ያደርገዋል። አዎ! የግብፅ መንግስት ዶላሩን ለሻዕቢያ፣ ሻዕቢያ ደግሞ የራሱን የድለላ «ኮሚሽን» በመውሰድ ትራፊውን ለ«ግንቦት ሰባት» ይሰጠውና ከዚያም የዶክተሩ ቡድን ደግሞ እንዲሁ የራሱን ኪራይ መሰብሰቢያ ኮሮጆ ከሞላ በኋላ ሽርፍራፊውን ለሀገር ውስጥ «ጉዳይ ፈፃሚዎቹ» ይልካል ማለት ነው። እናም ይህ ትስስር ቀደም ሲል የተጠቀሰው የ100 ሺህ ዶላር የሁከት ማስፈፀሚያና ገፅታን የማጠልሺያ በጀት እንዴት እንደሚውል የሚያሳይ ይመስለኛል።
ተጨማሪ አስረጅ እንካችሁ ልበል-በአንድ ወቅት የመድረክ አመራር አባል የሆኑት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ሳት ብሏቸው ያሉትን አባባል። ፕሮፌሰሩ እንዲህ ብለው ነበር-«በውጭ የሚገኙ ዲያስፖራዎች 50 ዶላር እየሰጡ መንግስት እንድንገለብጥ ይፈልጋሉ።» …ታዲያ ይህ የመድረክ አባባል ሀገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን አክብረን እንንቀሳቀሳለን እያለ፤ በሌላ መልኩ ደግሞ ህገ-መንግሰቱን በሚፃረር አግባብ መንግስት እንዲገለበጥ ከሚሹ ሃይሎች ጋር በመሞዳሞድና 50 ዶላር በነፍስ ወከፍ ከአክራሪ ዲያስፖራዎች በመቀበል ሲሰሩ እንደነበር የሚያረጋግጥ ነው። ምክንያቱም ራሳቸው እማኝነት የሰጡበት ጉዳይ ነውና።
ያም ሆነ ይህ ግን ከአሸባሪው ዶክተር ምፅዋት በመቀበል በአንድ በኩል ህጋዊነትን እየተከተሉ በሌላ በኩል ደግሞ ህገ-ወጥነትን የሚያጣቅሱና በሰላማዊ መንገድ እንንቀሳቀሳለን የሚሉ የሀገራችን ተቃዋሚዎች ካሉ፤ ይህ ድርጊት ሽብርን መደገፍ ብቻ ሳይሆን በኤርትራ ነጭ ለባሽነትና በግብፅ ገንዘብ ሰጪነት በሀገራችን ላይ ለማካሄድ እየታሰበ ያለውን ታላቁን የህዳሴ ግድብ የማደናቀፍ የማይሳካ ሴራ አካል መሆናቸውን የሚዘነጉት አይመስለኝም። ይህ ደግሞ ሀገር ውስጥ ቁጭ ብሎ (ለዚያውም በሰላማዊ መንገድ በመታገል ስልጣን እይዛለሁ የሚል ፓርቲ) የባዕዳንን ጥቅምና አጀንዳን ማስጠበቅ በመሆኑ በኢትዮጵያ ህዝብ ይቅር የማይባል ነውር መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። እናም ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ እንደማይወጣው ሁሉ፤ የሀገራችን ተቃዋሚዎች እንዲህ ያለውን ጅልኛ አካሄድን ለገንዘብ ብለው የሚመርጡ ከሆነ አደጋው ከአንዴም ሁለቴ መሰባበር ሊሆን እንደሚችል መገመት ያለባቸው ይመስለኛል። ለምን ቢሉ፤ የሀገራችን ህገ-መንግስታዊ ስርዓት ህጋዊና ህገ-ወጥ አካሄዶችን እያጣቀሱ በህዝብ ሀብትና ንብረት ላይ እንዲቀለድ የሚፈቅድ አንዳችም ዓይነት ቀዳዳ የሌለው በመሆኑ ነው።
የዚህን ፅሑፍ አቅራቢ በጣም ያስግረመኝ ሌላኛው ነገር «ግንቦት ሰባት» ከ100 ሺህ ዶላሩ ቀንሼ ለዲፕሎማሲያዊ ተግባሬ አውለዋለሁ ያለው አስገራሚ ልቦለድ ነው። ኧረ ለመሆኑ አሸባሪው ቡድን ምን ዓይነት ዲፕሎማሲ ነው የሚያካሂደው?- መቼም የዶክተሩ ቡድን ይህን ያህል ታዋቂ ባለመሆኑ የዲፕሎማሲያዊ ስራ ልሰራ እችላለሁ ማለቱ የቀልዶች ሁሉ ቀልድ ሳይሆን የሚቀር አይመስለኝም።
እርግጥ የሽብር ቡድኑ ዲፕሎማሲ ያካሂዳል ብለን ብናስብ እንኳን፤ ምናልባትም ተግባሩን ሊከውን የሚችለው አስመራ ውስጥ ቁጭ ብለው የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂን ትዕዛዝ ከሚጠባበቁ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ጋር ብቻ ነው-እንዴት አድርገው ኢትዮጵያን ሊያሸብሩ እንደሚችሉ በወሬ ደረጃ ብቻ ለመመካከር። ግና እርሱም ቢሆን ጠብ ያለ ነገር ለሁሉም አላስገኘላቸውም፤ ከአሜሪካ በግብፅ በኩል አድርገው አስመራ እንደ ውሃ ቀጂ በየጊዜው እየተመላለሱ ቢማስኑም። ለነገሩ አሸባሪው ዶክተር ባይቀናቸውም ሀገርን እያስማሙ ለመሸጥ ላይ ታች ከማለት በስተቀር የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል የዲፕሎማሲ ዕውቀት የላቸውም። እናም ‘ዲፕሎማሲ ምንትስ’ የሚሉት ነገር ወግ ወጉ መያዙ መሆኑ ነው። መቼም ‘ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ’ የሚለውን ብሂል እዚህ ላይ ሳልጠቅሰው ባልፍ ራሳቸው ጋሼ ብርሃኑ የሚታዘቡኝ ይመስለኛል። ምክንያቱም ሰውዬው ለገንዘብ ሲሉ የማያስማመሙት ነገር ስለማይኖር ሊቀየሙኝ ስለሚችሉ ነው-ህሊናውን ለጥቅም ሲል የሸጠ ግለሰብ በትንሹ ሆድ ይብሰዋልና።
ዶክተር ብርሃኑ ከሻዕቢያ«አየር ተይዞባቸው» ከተቀበሉት 500 ሺህ ዶላር ውስጥ 200 ሺ ዶላሩን ‘ኢሳት’ ለተሰኘው የሽብር ማቀጣጠያ ጣቢያቸው እንዲያውሉት ታዘዋል። አንዳንድ ሰዎች ይህ የውሸት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ 22 ዓመት ሙሉ በእንቶ ፈንቶ ወሬ መኖር ባልሰለቻቸው በእነ ታማኝ በየነ አማካኝነት ከዲያስፖራው በሚሰበሰብ መዋጮ የሚንቀሳቀስ ይመስላቸዋል። አሁን ግን አሸባሪው ሰውዬ እውነቱን ግልጥልጥ አድርገው ነግረውናል-በራሳቸው አንደበት። አዎ! ዘር ከዘር እየከፋፈለ ህዝቦችን ለማባላት ቆርጦ የተነሳው እሳትና ኢሳት ባለቤትነቱ ‘የግንቦት ሰባት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት’ ነው። ‘ኢሳት’ የሻዕቢያዊያን ነው-በግብፆች የእጅ አዙር ዶላር የሚንቀሳቀስ ተላላኪ የሬድዮና የቴሌቪዥን ጣቢያ። እናም ‘ኢሳት’ አንድም ሶስትም ነው ማለት ይቻላል። በቅርብ ርቀት ተላላኪው ዶክተር የሚቆጣጠሩት፣ ራቅ ብሎ ደግሞ አጀንዳው እንዲተላለፍለት የሚሻው የኤርትራ መንግስት ከአስመራ የሚመራው እንዲሁም ግብፅ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ በውጭ ያለው የሀገራችን ዲያስፖራ ቦንድ እንዳይገዛ ቅስቀሳ እንዲካሄድለት ገንዘብ እየከፈለው የሚያንቀሳቅሰው ባንዳ ጣቢያ።
ለዚህ አባባሌ ዶክተር ብርሃኑ ከሰጡን ተጨባጭ ማስረጃ ባሻገር ሌሎች አብነቶችንም መጥቀስ እችላለሁ። በቅርቡ የኤርትራ መንግስት በራሱ ወታደሮች የመፈንቅለ መንግስት ዓይነት ሙከራ ሲካሄድበትና ዓለም አቀፍ ታላላቅ ሚዲያዎች ሰፊ ሽፋን ሰጥተው ሲዘግቡት ‘ኢሳት’ የተሰኘው በኤርትራ ዶላር መዳቢነት የሚሰራው የሽብር ጣቢያ ግን ዓለም ላይ የሌለ ይመስል አሊያም ነገሩን እንዳልሰማ በመቁጠር እርሱም በፊናው ልክ እንደ ሻዕቢያ መገናኛ ብዙሃን ትንፍሽ አለማለቱ የመጀመሪያው ተጠቃሽ አስረጅ ነው። ይኸውም ኢሳትም ይሁን የአስመራ በሬ ወለደ ሚዲያዎች በኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር አጀንዳ እየተሰጣቸው የሚንቀሳቀሱ መሆናቸውን ነው። እርግጥም አንድ ገንዘቡን የከፈለ አካል ተላላኪውን እንዳሻው መቆጣጠሩ አግባበነት አለው። ተላላኪውም የተባለውን መፈፀም እንጂ ‘ለምን?’ ብሎ ሊጠይቅ አይችልም። አዎ! ዓለም የሰማውንና በአቶ ኢሳያስ ላይ የተካሄደውን መፈንቅለ-መንግስት ዓይነት ነገር፣ ሽብር መቀመሪያ ፋብሪካው ‘ኢሳት’ አይቶ እንዳላየ፣ ሰምቶ እንዳልሰማ የሆነው ለዚሁ ነው።
እጅግ በሚያስገርም ሁኔታ ግንቦት ሰባትና የሁከት ልሳኑ ታላቁን የህዳሴ ግድብ እንደሚቃወሙት መግለፃቸው እንዲሁም ሰሚ ባያገኙም ኢትዮጵያዊያን ለግድቡ ግንባታ የሚውል የቦንድ ግዥን እንዳይፈፅሙ መወትወታቸው፤ እነዚህ ተላላኪዎች በተዘዋዋሪ መንገድ በግብፅ ለተከፈላቸው ዳራጎት ውለታ እየከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ነው። ይህ ሃቅም አሸባሪው ሰውዬና የሽብር ጣቢያቸው ህሊና የሚባለውን ነገርዬአቸውን አሽቀንጥረው በመጣል ለከፈላቸው ባዕድ ሁሉ የሚሰሩ ግዑዞች እንደሆኑ የሚያስረዳ ነው።
ግና ታላቁ ህዳሴ ግድብ የመላው ኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሐብት ነው። አዎ! የዘመን ቁጭታችንን ያረገበው ይህ ታላቅ ፕሮጀክት እውን እንዲሆን መላው ኢትዮጵያዊ በአንድ ድምፅ የተቀበለው እንዲሁ ዝም ብሎ አይደለም-ከልብ ከመነጨ ስሜት እንጂ፡፡ የምንናገረው ነጭና ጥቁር ሃቅ መሆኑን ለማመልከት የግድ ዋስ መጥራት አሊያም ቃላት መደረት የሚያስፈልግ አይመስለኝም፡፡ ሁሉም እንደየ አቅሙ፣ በጉልበቱ፣ በዕውቀቱ፣ በገንዘቡ የሚጠበቅበትንና ከሚጠበቅበትም በላይ የዜግነቱን ለማበርከት ቃል ገብቶ፤ ቃሉንም በተግባር መለወጥ መቻሉን ማስታወስ ብቻ በቂ ነው- ከምግባር የቀደመ ታማኝ እማኝ የለምና። ኢትዮጵያዊ ሁሉ ለግድቡ ግንባታ የሰጠው ምላሽ እርግጥም በታሪክ ድርሳን ተከትቦ መቀመጥ ያለበት ይመስለኛል፡፡ የግድቡ ግንባታ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠሩም ክስተቱ የታሪካችን ልዮ ሁኔታ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው- ኢትዮጵያዊ እንደ አንድም እንደ ሰማንያ ሚሊዮንም ሆነው ዘብ የቆሙለት በመሆኑ። እናም የተላላኪዎቹ የአሸባሪው ዶክተርና የሽብር ልሳናቸው የቁራ ጩኸት እዚህ ግባ የማይባል መሆኑን ላኪውም ይሁን የላኪ ላኪው መገንዘብ ያለባቸው ይመስለኛል። ከግድቡም ይሁን ከሌሎች ጉዳዮች አኳያ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያዊያን ዘንድ የተፈጠረው የብሔራዊ መግባባት ቋጠሮ እንኳንስ በአሉባልታ ቀርቶ በሌላም ፈታኝ ድርጊት ቢሆን የሚፈታ አይደለምና።
እስቲ አሁን ደግሞ ተላላኪው ዶክተር 200 ሺ ዶላሩን ለወታደራዊና ለደህንነት ስራዎች እንዲያውሉት መታዘዛቸውን ወደ ጠቀሱት አባባላቸው እንሸጋገር። እርግጥ ሰውዬው በሌለ ማንነታቸው በጀት የሚመድቡት ለማን እንደሆነ ባይታወቅም፤ አባባሉ ግን በአስቂኝነቱ ከ«ኮሜዲ ድራማ» ተለይቶ የሚታይ አይደለም። ምክንያቱም የሽብር ቡድኑ አንድም ወታደር ስለሌለው የሚመድበው በጀት ለሌለ ነገር ስለሆነ ነው። እኔ እስከሚገባኝ ድረስ አንድ «ድርጅት» ገንዘብ የሚመድበው በገሃዱ ዓለም ላለ፣ ለሚጨበጥና ለሚዳሰስ አካል ነው። ለምናባዊ ኃይል የሚመደብ በጀት ሊኖር አይችልም። እናም የኤርትራ መንግስት ገንዘቡን በቀጥታ እየሰጠ ያለው ለዶክተር ብርሃኑ ተላላኪነት ወረታ መሆኑ ነው። ለምን ቢባል፤ ለእርሱም ይሁን የገንዘቡ ባለቤት ለሆነው የግብፅ መንግስት «ሰራዊት» ማለት ሀገራቸውን የካዱት እነ «ጋሼ ሽብሩ» እና እፍኝ የማይሞሉት ግብረ-አበሮቻቸው ናቸውና።
ያም ሆነ ይህ ግን ስለ ተላላኪው ዶክተር በሻዕቢያውያን ስለደረሰባቸው አሳፋሪ ውርደት ጥቂት ልበልና ፅሑፌን ልቋጭ። ሰውዬው ገንዘብ ስላገኙ ብቻ እየቀላመዱ የአስመራውን ቡድን አመራሮች ‘እናመሰግናለን፣ እግዚሐብሔር ይስጥልን’ ሲሏቸው፤ ሻዕቢያውያኑ ‘አንተ አታመስግነን፣ ተላላኪያችን እኮ ነህ፣ ዋናው ጥቅም የእኛ ስለሆነ ምስጋና ምን ይሰራል?’ በማለት አዋርደዋቸዋል። እንግዲህ ይታያችሁ!-አንድ የተማረ፣ ለዚያውም አሜሪካ ሀገር ውስጥ የሚያስተምር «ዶክተር ኢኮኖሚስት» እዚህ ግቡ በማይባሉ የሻዕቢያ አሽቃባጮች ‘ሀገርህን በመሸጥ ራስህን ያዋረድክ፣ ሞራልህንም ጫማህ ስር የከተትክ በመሆንህ ያንተ ምስጋና ከቁብ አይቆጠርም’ ሲባል!…አዬ ቅሌት! መቼም «የቅሌት ቀን አይመሽም» የሚባለው በእንዲህ ዓይነቱ ወቅት ሳይሆን አይቀርም።
እርግጥም አሸባሪውን ዶክተር ከዚህ በላይ የሐፍረት ካባን የሚያከናንባቸው ነገር ያለ አይመስለኝም-አንተ ከመላላክ ውጪ ስለ ምስጋና የማውራት መብት የለህም መባል። ለነገሩ ሰውዬው ለገንዘብ ሲሉ ራሳቸውን ዛሬም ይሁን ነገ እያዋረዱ በባዶ ሜዳ ላይ መንጎዳቸው አይቀርም-«ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይተውም» እንዲሉ አበው። ግና እርሳቸውና ቡድናቸው «መሸጥ የለመደ እናቱን ያስማማል» እንደሚባለው የባዕዳን ተላላኪ ሆነው ያለ አንዳች ውጤት በውርደት ላይ ውርደትን እየደራረቡ ቢቀጥሉም፤ ሀገራችንን እና ህዝቦቿ ግን የተያያዙትን የዕድገት ትልም አጠናክረው ይቀጥላሉ-የወሬ ሽብርተኞችና ላኪዎቻቸው ለሰኮንድም ያህል የልማት ዕቅዶቻቸውን የማደናቀፍ አቅሙም ይሁን ብቃቱ የሌላቸው መሆናቸውን አሳምረው ያውቃሉና።

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live