Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የአዲስ አበባ ነዋሪ ዜግነቱን እንዲያገኝ መፍትሄው “የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል”ብሎ 10ኛ ክልል መጨመር –ያሬድ ጥበቡ (ጌታቸው ጀቤሳ)

0
0

What is Ato Yared Tibebu belching about?
ምን ይሻላል?

የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች በብዙ ጉዳዮች የሚለያዩ ቢሆንም፣ ፊንፊኔ መናገሻችን ናት በሚለው ጉዳይ ግን ይስማማሉ ። ለዚህም ይመስ ላል በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳይ፣ ኦሮሞ ፈርስትና ኦፒዲኦ እጅና ጓንት ሆነው ሃገሩን ያተራመሱት ። ለመሆኑ ፊንፊኔ የኦሮሞ መናገሻ ነበረች? ኦሮሞዎች ከየት መጡ? የኦሮሞን አፈታሪክና መዝሙሮች ፣ የታሪክ ተመራማሪዎችም ከፃፉዋቸው፣ ከሱማሌና ሐረሪ ህዝቦች አፈታሪክ በማጥናት፣ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ይልማ ዴሬሳ “የኢትዮጵያ ታሪክ በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን” የሚል መፅሀፍ በ1959 አም ፅፈዋል ። የታላቁ የኦሮሞ አፈታሪክ ቁንጮ፣ የብላታ ዴሬሳ ልጅ በመሆናቸው ልናዳምጣቸው የግድ ነው ። የመጨረሻው የሌቃ ነቀምቴ ንጉስ የሞቲ ሞረዳ በከሬ የቅርብ ዘመድም ስለሆኑ ( cousin) ታሪካቸውን ልቅም አድርገው ያውቃሉ ። እንዲህ ይሉናል ።

” ይህ ምዕራፍ የተፃፈው፣ የኦሮሞን ወይም አማሮች ጋላ የሚሉትን ነገድ ታሪክ በዝርዝር ለማስረዳት አይደለም ። ስለሆነ በ16ኛው መቶ ዘመን መጀመሪያ ይህ ነገድ ከደቡብ ኢትዮጵያ ወደ ሰሜንና ወደ ምስራቅ ጎርፎ የሚበዛውን ደጋ አገር ይዞ ስለሰፈረበት በዘመኑ ታሪክ ውስጥ የኦሮሞን ነገድ ፈንታ ሳናነሳው ያለፍን እንደሆነ የ16ኛው መቶ የኢትዮጵያ ታሪክ ሙሉ ሆኖ አይገኝም ።…

… ታሪክ ሲነጋጋ የኦሮሞ ህዝብ ከአደን ሰላጤና እስከ ቅርብ የእንግሊዝ ሱማሌ በሚባለው የሱማሌ ሪፐብሊክ አውራጃ መካከል ከሚገኘው የአፍሪካ ቀንድ በተባለው አገር ሲኖሩ ታዩ ። ኦሮሞዎች በየትኛው የታሪክ ዘመን በዚህ ምድር እንደሰፈሩ ግልፅ አይደለም ። … ይሁንና ከ10ኛው መቶ ዘመን በፊት ሱማሌ የተባለው ነገድ ከታጁራ ቤይ አቅጣጫ ተንቀሳቅሶ በኦሮሞዎች ላይ ጦርነት ባደረገ ጊዜ፣ መጀመሪያ የእንግሊዝ ሱማሌ የነበረውን አገር ለቀው ወደ ምስራቅ ደቡብ መጓዝ እንደጀመሩ ታውቋል ። ኋላም የአፍሪካ ቀንድ ከምትባለው ሶስት ማእዘን ወረዳ ተነስተው በዋቢ ሸበሌና በጁባ ወንዞች መካከል ቤናዲር በተባለው አውራጃ ሰፍረው በዚያ ብዙ ዘመን እንደኖሩ በጋሎች አፈታሪክ ሲነገር የኖረ ነው ። …

… ከሰሜን የሱማሌዎች ከደቡብ ባንቱዎች የሚያደርጉባቸው ጦርነት ምንም ጊዜም ሰላም የሰጣቸው አይመስልም ። ስለዚህ ከዚህም ከአዲሱ አገራቸው እንደገና መሰደድ ግዴታ ሆነባቸው ።
…ጋሎች ወላቡ፣ አበያ፣ ባሕርና ሕዲ ዳዲ ከሚባሉት አቅጣጫ የሰፈሩት በአስረኛው መቶ በዛጕዌዎች ዘመነ መንግስት መጀመሪያ ላይ ይመስላል ። … የኦሮሞ ህዝብ በሥጋና በወተት የሚመገብ ዘላን ስለነበር ድርቅ ከሆነው ከቤናዲር አውራጃ ተጉዞ ወላቡ ወይናደጋ በገባ ጊዜ ይህች ምድር ማርና ወተት ታፈሳለች እንደተባለችው እንደ ምድረ ከነአን የምትቆጠር ሁና አገኙዋት ። … በወላቡ ተራራና በአበያ ባህር አጥቢያ በኖሩበት ጊዜያት የሰላምና የጥጋብ የዕድገት ዘመን መሆኑን ሲወርድ ስዋረድ የመጣው የጋሎች አፈታሪክ አጋኖ ይገልፅልናል ። …

ኦሮሞዎች እላይ በተመለከተው አኳኋን በወላቡ ዙሪያ ብዙ ትውልድ ካሳለፉ በኋላ ከልክ ያለፈ ተራብተው ምድር ጠበባቸው ። … ከዚህም ሌላ በጥንት ዘመን ከቀድሞው መኖሪያቸው ከአፍሪካ ቀንድ ወግቶ ያስወጣቸው የሱማሌ ህዝብ፣ አስራ አምስተኛው መቶ ሲጋመስ ወይናደጋው ድረስ እየመጣ አዲሱን አገራቸውን መውረር ጀመረ ። በዚህ አኳኋን የኦሮሞ ህዝብ ለመከላከልና ለግጦሽ የሚፈልገውን መሬት አስፍቶ ለመያዝ ከሰላማዊ አኗኗር ወደ አርበኝነት ሃሳቡን መለሰ ። …ከወላቡ ሳይነሱ በገዳ ድርጅት ውስጥ የጦር ሠራዊትን ማከናወን ዋና ጉዳይ አድርገው ያዙት ። …በዚህ ዘመን ኦሮሞዎች ከረዩ፣ ቱለማ፣ ሜጫና፣ ወሎ በሚባል ባራት ትልልቅ ነገድ ተከፍለው ይገኙ ነበረ ። ስለዚህ ከረዩ የተባለው ነገድ፣ ባሌን ፈጠጋርንና ደዋሮን እንዲወር፣ ቱለማ ወደ ሰሜን ተጉዞ ዛሬ የሸዋ ጋላ ምድር የተባለውን እንዲይዝ፣ ሜጫ በስተ ምእራብና በስተደቡብ የሚገኘውን የእናሪያዎችን አገር እንዲወስድና፣ ወሎ የተባለው ነገድ በሸዋ በስተምስራቅ ተጉዞ ከወሎ አውራጃ እስከ ትግሬ የተዘረጋውን አንጎት የተባለውን አውራጃ እንዲይዝ የተቀየሰው ኦዳ ነቤ በነበሩ ጊዜ ነው ። …
ለጦርነት የተደረገው ድርጅት ከአለቀ በኋላ ኦሮሞዎች ዘመቻውን ፈጥነው አልጀመሩትም ። [ ዛሬ ኢሳያስ ወያኔን ለመበቀል የሚያሳየውን አይነት ትእግስት ይመስላል * የኔ] ይልቁንም በነዚህ ዘመናት ውስጥ ሱማሌዎች ክርስቲያናዊውን ኢትዮጵያ ለመውረር በትልቁ በመዘጋጀት ላይ ስለነበሩ፣ ምቹ ጊዜ ለማግኘት ኦሮሞዎች በትእግስት ጠበቁ ። በ1506 አም አነስተኛ ወረራ ወደሰሜን በሚገኘው ወረዳ ላይ ከአደረጉ በኋላ ጥቂት ገፍተው ቆሙ እንጂ ውጊያውን አልቀጠሉም ። … ስለዚህ በ1520ና በ1532 አም መካከል ግራኝ የኢትዮጵያን ደጋ ወሮ በአማራና በሱማሌዎች መካከል ሃይለኛ የሆነ ትግል ሲደረግ ጋሎች ያሰቡትን ለመፈፀም በፀጥታ ሲጠባበቁ ቆዩ ። …

እስከ 16ኛው መቶ ዘመን በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ድምፁን ሳያሰማ የቆየው የጋላ ነገድ በ1524 አም ከደቡባዊ መኖሪያው መንቀሳቀስ ጀመረ ። የዚህም እንቅስቃሴ አላማ ከዚህ በላይ እንደተመለከተው ሁሉ በደጋው የኢትዮጵያ አወራጃዎች ላይ ለመስፈር ነበር ። ”

እንግዲህ ከላይ በታላቁ ሰው ብእር ያነበብነው፣ ኦሮሞዎች ከየት ተነስተው ዛሬ የሚኖሩባቸውን ግዛቶች እንደያዙ ነው ። ገና 500 አመታት እንኳ ያላደረገ ታሪካዊ ክንዋኔ ነው ። ታዲያ የሶስት ሺህ አመት መንግስታዊ ታሪክ ባላት ሃገር ላይ፣ ታሪክ የሚጀምረው ከምንሊክ መስፋፋት ወዲህ ያለው ብቻ ነው የሚል ክርክር የት ያደርሳል? ፊንፊኔስ ብትሆን ከከብት አርቢዎች ሆራነት ወጥታ የአፍሪካ ዲፕሎማሲያዊ መናገሻ የሆነችው በመላ ኢትዮጵያውያን ትጋትና ድካም መሆኑ እየታወቀ፣ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ውስጥ ናት የሚል ወያኔአዊ ደባ ምን ይጠቅማል? የአምስት ሚሊዮን ነዋሪዎቿስ መብት ለምን ታገደ? ብዙ ጥያቄዎች አሉ ። መፍትሄዎችም እንዲሁ ።

አንዱ የሚታየኝ መፍትሄ ፣ አሁን ባለው ፌዴራላዊ አወቃቀር ውስጥ የአዲስ አበባ ነዋሪ ዜግነቱን የሚያገኝበት መንገድ ማፈላለግ ነው ። ለዚህም፣ ማዘጋጃ ቤቱን እንደ ማእከል ወይም መነሻ በመውሰድ፣ 150 ኪሎ ሜትር ሬዲየስ ያለውን ግዛት “የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል” ብሎ 10ኛ ክልል መጨመርና፣ ይህም ክልል በፌዴራል ምክርቤት ድምፅ እንዲኖረው ማድረግ ። ይህ ክልል የሁሉም ብሄረሰቦች የጋራ ክልል በመሆኑ፣ በምክርቤቱ ውስጥ ያለው ድምፅም ቢያንስ አንድ ሶስተኛውን የያዘ ቢሆን፣ ሃገሪቱን ማረጋገት ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረው ይመስለኛል ።

ይህ እቅድ ሶስት ችግሮች ይገጥሙታል ። አንዱ የሸዋን አማራ ከአማራ ክልል ያወጣዋል ። ሁለተኛው ችግር የኦሮሞን ክልል በምእራብና ምስራቅ ሁለት ቦታ ይከፍለዋል ። ሦስተኛው ችግር ደግሞ ጉራጌው የሚኖርበትን ከደቡብ ክልል ያስወጣዋል ። የአማራና ኦሮሞ ክልሎች ግን በወያኔ የፖለቲካ ፕሮዤ የተወጠኑ እንጂ፣ በታሪካዊ ወይም ውስጣዊ ፍላጎታቸው የተከለሉ አይደሉም ። ኦነግ ውስጥ የፖለቲካ ችግር በተነሳ ቁጥር፣ እስላምና ክርስቲያን፣ አርሲና ወለጋ እየተባባለ እንደሚቧደን ሁሌም የምንታዘበው ነው ። የአማራ ክልል ውስጥ የተካተቱም ህዝቦች፣ ከአማራነት ይልቅ ወሎዬነታቸው፣ ጎጃሜነታቸው፣ ጎንደሬነታቸውን ይበልጥ ያፈቅሩታል፣ ይወዱታልም። የወያኔ የዘር መድልኦ መባባስ ገና ወደፊት ይመስለኛል አማራ የሚባለውን ብሄር ቀጥቅጦ የሚፈጥረው ። ጉራጌው አዲስ አበባን ደክመው ከሰሯት ቀዳሚ በመሆኑ፣ ማእከላዊ ኢትዮጵያ ከልል ውስጥ ግባ ቢባል፣ ያን ቆንጆ ጭፈራውን ሲያቀልጠው በአይነ ህሊና ይታየኛል ። ሸዌው የኢትዮጵያ ማንነቱን አስቀዳሚ ሰለሆነ፣ ከኦሮሞና አማርነቱ በላይ ኢትዮጵያዊነቱን ያስቀድማል ብዬ መከራከር እወዳለሁ ። ስለሆነም ዜግነቱን የሚያሰከብርለት የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቢያገኝ የሚያሰማው እልልታና ሆታ፣ የፈረሱ ኮቴ በእዝነ ህሊናዬ እያደመጥኩት ነው ።

ስለሆነም የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መፈጠር፣ ኦሮሞውን ቢያንስ ወደ ሁለት ክልል፣ አማራውን ደግሞ ወደ ሶስት ሊከፍለው ይችላል ። ይህ ግን ለተሻለ አስተዳደርና ልማት ጥርጊያውን ሰለሚከፍት ጥሩ ሃሳብ መስሎ ይሰማኛል ። አሁን ያለውንም የአዲስ አበባ ማሰተር ፕላን ችግር ከስር መሰረቱ ይፈታዋል ብዬ አስባለሁ ። አዲስ አበባንም ለፖለቲካ ተንኮል ተብሎ ከተጣለባት የአንድ ብሄር ክልል ውስጥ የመወርወር አደጋ ይታደጋታል ። የኢትዮጵያ ብሄርተኝነትም ዙሪያውን በከበቡት የኦሮም፣ የጉራጌ፣ የአማራ ገበሬዎች እየታገዘ፣ ከሸገር በሚፈልቀው የመላ ኢትዮጵያውያን ባህላዊ መስተጋብርና ፍቅር እየተመራ፣ የኢትዮጵያን ቀጣይነት ያረጋግጣል ብዬ አስባለሁ ። ይህ ለብዙ ወራት ተጨንቄ ያቀረብኩት ሃሳብ በመሆኑ ለማውገዝ አትቻኮሉ ። እሰኪ እንደኔ ተጨነቁበት ።

በተለይ አዲስ በቀል የሆናችሁት የትግራይ ከበርቴዎች፣ የሃገር መረጋጋት የሚፈጥረው ጥቅም ተጠቃሚ ስለሆናችሁ ፣ ከመለስ የስልጣን ተንኮሎች ባሻገር፣ ለልጆቻችሁ የምታወርሱት ሃገርና ንብረት እንዲኖራችሁ፣ የሚቀርቧችሁን የወያኔ መሪዎች ከሃገር ማጥፋት እኩይ ተግባርና ከዘረኝነት እንዲርቁ ምከሩ ። ይህን ማድረግ አቅቷችሁ እስካሁን እንደተያዘው ተቃውሞን በጥይት ማጥፋት ይቻላል ብላችሁ ከገፋችሁበት፣ እንኳንስ ሃገር፣ መሰደጃ ስንኳ አታገኙም ። ከቀዬው የነቀላችሁት ስደተኛ “የኒዮ ሊበራሊዝም ጠበቆች” እያላችሁ በምታወግዟቸው አለምአቀፍ መያዶች እየታገዘ ያድናችኋል። ከዚህ ይሰውራችሁ ። ለሃገር የሚበጅ መላ ምቱ። ይህችን ቅድስት ድሃ ሃገር የሁላችን እናድርጋት ። ታላቁ ትግራዋይ ኢትዮጵያዊ ገብረሕይወት ባይከዳኝ ከመቶ አመታት በፊት እንደፃፈው “ጠንካራ መንግስት ከህዝብ ልብ ይቀዳል”

The post የአዲስ አበባ ነዋሪ ዜግነቱን እንዲያገኝ መፍትሄው “የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል” ብሎ 10ኛ ክልል መጨመር – ያሬድ ጥበቡ (ጌታቸው ጀቤሳ) appeared first on Zehabesha Amharic.


Health: የአስም ሕመም ቀስቃሽ 7 ሁኔታዎች

0
0

Dr Honilet
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
የአስም ሕምተኛ ከሆኑ ስለአስም ሕመም ቀስቃሽ ስለሆኑ ሁኔታዎች በሚገባ ሊያውቁት ይገባዎታል፡፡
የአስም ሕመምዎን የሚቀስቅሱ ሁኔታዎችን ማስወገድ ሕመሙ እንዳይነሳብን ይረዳል፡፡
1) ሲጋራ ማጤስ
ሲጋራ ማጤስ ጉዳትን የሚያስከትል እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን ለአስም ሕመምተኞች ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ ሕመሙን ስለሚቀሰቅስ ሲጋራን የምናጤስ ከሆነ ልናቆም ይገባል፡፡
2) በቤት ውስጥ የሚገኙ ተባዮች
በቤትዎ ውስጥ የሚገኙ ተባዮች ለአስም ሕመም መቀስቀስ ምክንያት ሊሆኑ ስለሚችሉ ተባይ ማጥፊያ በመጠቀም ማጥፋት ተገቢ ነው፡፡
3) የቤት እንስሳዎች
በቤትዎ የሚያሳድጓቸው የቤት እንስሳት የፀጉራቸው ብናኝ አስም ቀስቃሽ ስለሚሆን የእንስሳቱን ንፅህና መጠበቅ እና ከተቻለ ከአስም ሕመምተኞች አካባቢ እንዲርቁ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
4) ሻጋታ
በሞቃታማ ጊዜያት በቤትዎ ውስጥ ሻጋታ ሊፈጠር ስለሚችል የአስም ሕመምዎን ይቀሰቅሳል፡፡ ስለዚህም ቤትዎን በሚገባ ማፅዳት ያስፈልጋል፡፡
5) የአካባቢ አየር ብክለት
ከፋብሪካ፣ከመኪና እና ከሌሎች ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታዎች የሚወጡ አየርን የሚበክሉ ሽታዎች የአስም ሕመምን ስለሚቀሰቅሱ አካባቢያችንን በማፅዳት የግላችንን አስታዋፅኦ ማበርከት ይገባናል፡፡
6) ከከሰል ወይንም ከእንጨት ማቃጠል የሚፈጠር ጭስ
እነዚህን ዓይነት ጭሶች በምንተነፍስበት ጊዜ የአስም ሕመምን የመቀስቀስ ሁኔታዎችን እጅግ ይጨምራሉ፡፡
7) ሌሎች ቀስቃሽ ሁኔታዎች እንደ ጉንፋን ሕመም፣አለርጂዎች፣ ከባድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣የአየር ንብረት ለውጦች፣ቅዝቃዜ እና ሽቶዎች የአስም ሕመምን ሊቀሰቅሱብን ይችላሉ፡፡
እባክዎን ለወዳጆችዎ ያካፍሉ
ጤና ይስጥልኝ

The post Health: የአስም ሕመም ቀስቃሽ 7 ሁኔታዎች appeared first on Zehabesha Amharic.

ጄኔራል ፃድቃንና ጤዛዋ ማሌሊት …በ40ኛው –ከአረጋዊ በርሀ

0
0

aregawi berehe
ባለፉት ሳምንታት ህወሓት የተመሰረተበት 40ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የህወሓት መሪዎች ብቻ ሳይሆኑ የኢህኣዴግ ባጠቃላይ መጀመርያ በመቀሌ ቀጥሎ በኣዲስ ኣበባ ተሰባስበው ለኣንድ ወር ሙሉ የሃገሪቱን ሃብት ሲያባክኑና ሲዝናኑበት እንደከረሙ ተገንዝበናል። መቸም የኣምባገነኖች ጭንቀት ማስተንፈሻ ነው መሰለኝ፣ ህዝብ በረሃብና በስራ-ኣጥነት ሲጠቃ፤ ሃገርን በዴሞክራሲያዊ ስርዓት እጦት ስትታፈን ሁሉም ኣምባገነኖች ማስተዳደር ሲያቅታቸው ምክንያት እየፈጠሩ በሃገርና በህዝብ ንብረት እንዲህ መቀለዳቸው የተለመደ ለመሆኑ ሩቅ ሳንሄድ የደርግ ኢሰፓና የነፃድቃንማሌሊት ምስረታ ፌስታ ማስታወሱ በቂ ነው። ኣሁንም ሃገር በቀልና ዓለምኣቀፍ ጥናቶችእንደሚያስረዱት፣ ኢትዮጵያ የተጠመደችበትን ዙርያ-መለስ ቀውስና ህዝቡ እየደረሰበት ያለው ስቃይ መረኑ ኣልፎ ሃገሪቱ ጭራሽ ስርዓት-ኣልባ ወደ እምትሆንበት ደረጃ እያሽቆለቆለች መሆንዋን በጥናት የተደገፈ መረጃ ቢያቀርቡም፣ ግብዞቹ የኢህኣዴግ መሪዎች መራር ሓቁን ከመጋፈጥ ይልቅ፣ ሃገሪቱ የበለፀገች – ህዝቡ የደላው ይመስል፣ ኣሸሼ-ገዳሜ ሲሉ ይገኛሉ።

ህወሓት/ኢህኣዴግ 40ኛ ዓመት-በዓል ብሎ ቅጥ ያጣ ድግስ በጣለበት በኣሁኑ ወቅት፣ የሰቆጣ ህዝብ በከባድ ድርቅ ተጠቅቶ ቀየውን እየለቀቀ ወደ ኣጎራባች ክልሎች በመሰደድ ላይ ይገኛል። በስራ-ኣጥነት የተነሳ ለስደት የተዳረጉት ወገኖቻችን ከተሰደዱባቸው ሃገሮች በገፍና በግፍ እየተባረሩ መሆናቸው የዓረብያው፤ የሱዳኑ፤ የደቡብ ኣፍሪቃው … ይቆይልንና የስሞኑ የኬንያ ክስተት ኣንድ ተጨማሪ ኣሳዛኝ ኣብነት ነው። ለ40ኛው ዓመታቸው ፈንጠዝያ ሲባል ኢህኣዴጎች በመቀሌና ኣዲስ ኣበባ ያባከኑትን ከ100 (ኣንድ መቶ) ሚሊዮን ብር በላይ የህዝብ ሃብት፣ ኣይገባቸውም እንጂ የስንቱን ረሃብተኛና ስራ-ኣጥ ወገን ሕይወት በለወጠ ነበር። በኣሁኑ ወቅት ወገኖቻችን በድርቅ እየተጠቁ መሆናቸውንም የሚያውቁት ኣይመስልም። ቢያውቁስ፣ ፈንጠዚያው ሊያቋርጡ? ዘበት!

ሌላው የሰሞኑ ኣስቀያሚ ድራማ ባለጊዜዎቹ ኣምባገነኖች ለበዓላቸው ማጣፈጫ ብለው ፍፁም በተቆጣጠሩት መገናኛ ብዙሃን (ሚድያ) ሲለቁት የነበረው በውሸትና ማጋነን የተበከለ ኣሳዛኝና ኣስገራሚ ትረካቸው ነው። የሁሉንም ትረካ ዘግበን መተቸት ኣሰልቺ ሊሆን ነው። ስለሆነም ባልጠበቅኩት ሁኔታ ትኩረቴን በሳበው በጄኔራል ፃድቃን ኣስገራሚ ትረካ ላተኩር። ዳንኤል ብርሃኔ የ”ሆርን ኣፈይርስ” (HORN AFFAIRS) ጋዜጠኛ ነበር ቃለ-ምልልስ ኣካሂዶ በ12 የካቲት 2015 ዓ/ም/ፈ/ የፃድቃን ትረካ የለቀቀው።

ፃድቃን ባጠቃላይ በመረጃ ያልተደገፉ ብዙ ነጥቦች ያነሳ ቢሆንም በሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ኣፅንኦት ኣድርጎ እንደተረከ የቃለ-ምልልሱ ዘገባ ያመለክታል፡፡ እኔም በነዚሁ ሁለት ጉዳዮች ላይ በማተኮር እውነታውን ላስረዳ፤ ሁለቱ ነጥቦቹም፣
1ኛ/ “የእርዳታ ገንዘብ ከህዝብ ቀምተን ለመሳርያ ስናውል ኣላውቅም”
2ኛ/ “ማሌሊት (ማርክሳዊ ሌኒናዊ ሊግ ትግራይ) መሰረታዊ ወታደራዊ ለውጥ ኣምጥተዋል” የሚሉ ናቸው። ኣንደኛውን ነጥቡ ዘርዘር ኣድርጎ ሲያስረዳ: “በ77 ዓ/ም በጣም የሚያሳዝን – ሁለመናህን የሚፈትሽ – የድርቅ ሁኔታ ነው የነበረው … በራያ ሃብታም የነበሩ ሰዎች ወደ ታጋዮች ቤዝ እየመጡ ከኛ ምግብ እየተካፈሉ የሚበሉበት ሁኔታ ነበር … ደርግ ካከማቸው እህል ስናመጣ ገበሬው ኣብሮን እንዲወስድ እናደርግ ነበር … ካመጣነውም እናካፍለው ነበር … 90% ስንቃችንም ትጥቁም ከጠላት ነበር የምናመጣው … መቶ ሺ (100ሺ) የሚሆን ህዝብ ከዛ ኣካባቢ ወደ ሱዳን ኣጓጉዘናል …” ይለናል።

የ 77 ዓ/ም ድርቅ በጣም ኣሳዛኝ ለመሆኑ ዓለም ያወቀውና እርዳታም በገፍ የቸረበት ስለነበር ኣከራካሪ ሊሆን ኣይችልም። የሚያከራክረው በድርቅ ለተጠቃው ህዝብ የተሰበሰበው እርዳታ የት ገባ ? የሚለው ከባድ ጥያቄ ነው። ፃድቃን ይህን ጥያቄለመመለስ ላይሳካለት ዙርያ- ጥምጥም ተጉዘዋል። ያልተጠየቀው ጥያቄ ለመመለስ ነበረ ጊዜ ያባከነው። ለብዙዎቻችን ኣሳሳቢ የሆነው ጥያቄ ግን ይኸው የተሰበሰበው እርዳታ የት ደረሰ ነው።
መጀመርያ ደርግ ካከማቸው እህል እየነጠቅን ህዝቡ እንዲወስድ እናደርግ ነበር፣ እናካፍለው ነበር ሲለን፤ ሰጪ (ለጋሽ) እንጂ ወሳጅ (ነጣቂ) እንዳልሆነ ለመምሰል ነው መሰለኝ ጥረቱ፤ ቢሆንም የእርዳታ ገንዘብ የት ገባ? ለሚለው ጥያቄ መልስ ኣይደለም። ከተነጠቀው እህል ህዝቡ ይካፈል ነበር የሚለው ለነገሩ ብንቀበልም፣ ወድያውኑ ኣለፍ ብሎ “100 ሺ ረሃብተኞች ከዛው ወደ ሱዳን ኣጓጉዘናል” ሲለን የተኩራራበት ማካፈሉ ቁምነገር ያለው መፍትሄው እንዳልሆነ ራሱ ይመሰክራል። በእውነት ማካፈል ከነበረ ያን ያህል ህዝብ ድንበር ኣሳልፎ ሱዳን ድረስ ማሻገር ለምን ኣስፈለገ?

ኣለፍ ብሎ ደግሞ “ 90% ስንቁም ትጥቁም ከጠላት ነበር የምናመጣው “ ሲል በስተጀርባ ያለው መልእክቱ ከውጭ እርዳታ ኣያስፈልገንም፤ በጉልበታችን ራሳችንን ችለን ነበር ትግሉንም ለህዝብ ማካፈሉንም ያካሄድነው ለማለት ነው። ይህ ትረካ ደግሞ በህዝቡ ስም ከመጣው የውጭ እርዳታ ለድርጅቱ መሳርያ መግዣ ኣልዋለም ለማለት ንጣፍ መሆኑ ነው። ይህ የንጣፍ መልስ ያነገበው የ90% ኣሃዝ ራሱ ቢመረመርም መረጃ-ኣልባና የተጋነነ መሆኑ እንገነዘባለን። የስንቅና ትጥቅ ምንጭ ትልቁ ድርሻ የያዛው በተለያየ መልክ ከህዝቡ የሚሰበሰበው ድጎማና ዋናው ግን ከለጋሽ ሃገሮችና ድርጅቶች በእርዳታ ስም የሚገባው ለስንቁም ለትጥቁም መግዣ የሚውል ገንዘብ እንደነበረ የማሕበረ-ኢኮኖሚና የውጪ ጉዳይ ሪፖርቶች ከማመላከታቸው ኣልፎ ተጨማሪ መረጃዎቹ የት እንደሚገኙ ለማወቅ እስከዚህ ከባድ አይደለም፣ ኣንዳንዶቹም ወረድ ብዬ እጠቅሳለሁ።
ፃድቃን “90% ስንቁም ትጥቁም ከጠላት ነበር የምናመጣው” በማለት በኣሃዛዊ ኣስደግፎ ነግሮን ሲያበቃ ኣያይዞ ደግሞ “ቺፍ ኦፍ ስታፍ ሆኜ ለሰራዊቱ የሚመደብ ገንዘብ ኣላውቅም ነበር፤ ከውጭም ከውስጥም የሚመጣ ገንዘብ የሚቆጣጠር ማሕበረ-ኢኮኖሚ የሚባለው ክፍል ነበር … ዋናው ነገር ዝርዝሩን ኣላውቅም” በማለት ከወዲሁ ከዋናው ጥያቄ ለመራቅ ይሞክራል።

በነገራችን ላይ ቺፍ ኦፍ ስታፉ ከጠላት የሚገኘው ስንቁም ትጥቁም 90% መሆኑ በኣሃዝ ከነገረን ዘንዳ በራሱ ድርጅት ለወገን ጦር የሚመደበው የስንቅና ትጥቅ መጠን ማወቅ እንዴት ይሳነዋል? “ቺፍ ኦፍ ስታፍ” ባጀቱ ካላወቀ ማን ሊያውቅለት ነው?

ቺፍ ኦፍ ስታፍ ፃድቃን ይህንን ጥያቄ ሲያጠቃልል “ከደርግ የምናገኘው ንብረት ከህዝብ ጋር ስንካፈል ነው እንጂ ከውጭ የሚመጣውን ገንዘብ ከህዝብ ቀምተን ለጦር መሳርያ ስናውል ኣላውቅም” ይላል በኣፅንኦት። ይህ ኣባባል ምንኛ ከሓቁ የራቀ መሆኑ ለመገንዘብ ፃድቃን ራሱ የነበረበት የ77ቱ የማሌሊት ማ/ኮ ስብሰባ ከህዝብ ቀምቶ የወሰነው የባጀት ምደባ ሬኮርድ (ሰነድ) መመልከት ነው። የሚገርመው፣ ስለዚህ ሰነድ/ሬኮርድ በተመለከተ ፃድቃን ብቻ ሳይሆን ሁሉም የኣመራሩ ኣባላት ኣንድ ቃልም መተንፈስ ኣይፈልጉም። ጉዱ ያለው ግን የያዘው በማይለቀው እዚህ ሰነድ ላይ ነው።

ይህን ግፈኛ የባጀት ምደባ ኣስመልክቶ በተለያዩ ኣጋጣሚዎች ገልጨዋለሁ። ወደፊትም መቋጫ እስኪያገኝ ድረስ መግለፄ እቀጥላለሁ፤ ለምን ቢባል በክፉ ቀን ትልቅ የህዝብ ክሕደት የተፈፀመበት ውሳኔ ነውና። በዛ የድርቅ ቀውጢ ወቀት (1977 ዓ/ም) የማሌሊት ምስረታ ለሌላ ጊዜ እንኳን ይተላለፍ ቢባል ሸራቢው ቡድን ኣሻፈረኝ በለዋል። ስለዚህም ቡድናዊ ድርጅት ለመመስረት በሓላፊነት የነበረው የህወሓት ታጋይ ሁሉ ህዝቡን በክፉው ቀን መርዳት እየቻልን ኣንድ ወር ሙሉ ወርዒ በተባለው ሸለቆ እየተደገሰ ተቀምጠናል። ይህ ድርጊት ራሱ የድርቅ ሰለባ ለነበረው ህዝብ ተጨማሪ ቅጣት ነበር።

ማሌሊት ተመስርቶ እዛው ወርዒ የህወሓት/ማሌሊት ማእከላይ ኮሚቴ እቅድ ለማውጣትና ባጀት ለመመደብ ተሰበሰበ። በእቅዱ መሰረት ባጀቱ ለመመደብ የቀረበው ጥሬ ገንዘብ 100 (ኣንድ መቶ) ሚልዮን ብር ነበረ። ይህ ገንዘብ ፃድቃን እንደሚተርከው ከደርግ የተነጠቀ ኣልነበረም፤ ወይም ደግሞ ከህዝቡ የተዋጣ ኣልነበረም – በድርቅ የሚቆላው ህዝብ ስም ከውጪ ረዳቶች የተሰበሰበ ነበር። ይህ ገንዘብ በድርቁ ምክንያት ከግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ከተሰበሰበው ከፊሉ ሆኖ፣ የያኔ የማህበረ-ኢኮኖሚ ሃላፊ ኣውዓሎም ወልዱና የውጪ ጉዳይ ሃላፊ ስዩም መስፍን ለማሌሊት ምስረታ ከሱዳን ሲመጡ እግረመንገዳቸው በጆንያ ጭነዉ ያመጡት እንደነበረ እናውቃለን።

በባጀት ምደባው መለስ ዜናዊ የውሳኔ ሓሳብ ሲያቀርብ ” 50% ለማሌሊት ማጠናከርያ፣ 45% ለህወሓት ስራ ማስኬጃ፣ 5% ለድርቅ ጉዳተኞች” ብሎ ኣረፈው። ለድርቅ ጉዳተኞች 5% ብቻ መመደብ በቂ ኣይደለም፣ ከፍ ማለት ኣለበት የሚል ኣንድ ድምፅ ተሰማ፣ ይሁን እንጂ በማሌሊት ምስረታ የተሳከረው ማ/ኮ ተማፅኖውን ከጉዳይ ኣልቆጠረውም። እንዳውም የማሌሊት ኣፍላ ጀብደኞቹ “ማሌሊት ተጠናክሮ ድል ስንቀዳጅ የህዝቡ ችግር ይፈታል” ሲሉ ይደመጡ ነበር። ፃድቃንም በማሌሊት ምስረታ የምር ተዋናይ እንደነበረ ራሱ ስለገለፀልን በዛ ስካር ተጠምዶ ልመናውን ማዳመጥ እንደሚሳነው ግልፅ ይመስለኛል። የሆነሆኖ ኣሳዛኝና ዋናው ነጥቡ ከእርዳታው ገንዘቡ 95% ለህወሓት/ማሌሊት ለድርጅታዊ ስራ ሲውል 5% ብቻ በድርቅ ለተጎዳው ወገን “ተቸረ” ማለት ነው። ሓቁ ይኸው ነው። 95’ቱ ለራሱ ድርጅት ኣስቀርቶ 5’ቱ ብቻ ለህዝቡ የተወ ድርጊት ከህዝብ ጋር መካፈል ነው ወይስ ከተራበ ህዝብ ኣፍ መንጠቅ? ጄ/ፃድቃን?

ሰነድ የነከሰው ሓቅ ይህ ሆኖ እያለ የተለያየ የህወሓት/ማሌሊት ማ/ኮ ኣባላት (ኣረጋሽ፣ ገብሩ፣ ስብሓት፤ ኣውዓሎም፣ ፃድቃን…) በየወቅቱ በመረጃ ያልተደገፈ የተለያየ ዘገባ ሲሰጡ እንደቆዩ ሳንገነዘብ ኣልቀረንም። ከነዚህ ሁሉ ዘገባ ግን ለሓቁ የቀረበ የኣውዓሎም መሆኑ ባለፈው ፅሁፌ ዋቢ ጠቅሼ ዘግቤኣለሁ። መድገም ካስፈለገ ደግሞ፣ ‘ይህ ነውረኛ የበጀት ምደባ ኣስመልክቶ ኣምባሳደር-ነበር ኣውዓሎም ወልዱ ለኣዲስ ኣድማስ ጋዜጣ 27 ጥቅምት 2003 ዓ\ም ገጽ 21 ላይ ባሰፈረው መረጃ፣ “35% ለህዝቡ፣ 65% ለድርጅቱ ተከፋፍለዋል” ‘ ይላል።

ይህ የበጀት ምደባ በኣብዝሃው ማ\ኮሚቴ ስብሰባ ጸድቆ፣ ቃለ ጉባኤውም በጽሑፍ ሰፍሮ፣ በቴፕ ተቀድቶ በህወሓት ሰነዶች ማእከል ይገኛል። ይህ ሰነድ እያለ ለምን የባጡን የቆጡን መደርደር እንዳስፈለገ ይገርማል፣ ሰነዱን መዞ ማየት እየተቻለ። ከህወሓት ፋይሎች ኣልፎም የዓለምኣቀፍ የረድኤት ማሕበራትና እንደ ቢቢሲ የመሰሉ የሚድያ ተቋማትን ኣሁንም እያተራመሰ ይገኛል። በቴፕ የተቀዳና በፅሁፍ ቃለ-ጉባኤ የተያዘለት ይህ ኣስነዋሪ ክንዋኔ ለምን እንደሚያከራክር መገመት ኣይከብድም፣ ከተጠያቂነት ለመሸሽ ኣይደል? ግራም ነፈሰ ቀኝ መረጃውን መመልከት ስለሚቻል የጊዜ ጉዳይ እንጂ ተጠያቂነቱ ኣይቀርም። በነገራችን ላይ፣ ጋዜጠኛ ዳንኤል የእርዳታው ገንዘብ ጉዳይ ፃድቃንን መጠየቁ ላልቀረ ስለተጠቀሱት ቁልፍ የጽሑፍና የቴፕ ማስረጃዎች ማንሳት ለምን ኣልፈለገም? ሆን ብሎ ወይስ ባለማስተዋል?

2ኛው የፃድቃን ነጥብ “ማሌሊት መሰረታዊ ወታደራዊ ለውጥ ኣምጥተዋል” የሚል ሲሆን ዘርዘር ያለ ትረካው ቀጥሎ እንመልከት።

“ከማሌሊት ምስረታ በፊት ከፍተኛ ችግር ነበር። ትልቅ ሓይል ይዘን የደርግን ትንሽ ሓይል የማናሸንፍበት፣ ብዙ ኪሳራ የምንከፍልበት፣ ወዴት ነው የምንሄደው … ውዥንብር የታየበት ወቅት ነበር። ከማሌሊት ምስረታ በኃላ ዲያለክቲካል ማቲርያሊስት … ሳይንቲፊክ በሆነ መንገድ ነገሮችን ማየት የጀመርንበት፣ ወታደራዊ ስራን እንደ ኣንድ ሶሻል እንቅስቃሴ ማካሄድ እንዳለብን መልስ ያገኘንበት ነው። የታጠቀ ህዝብ ስትራተጂ ከማሌሊት በፊት ኣልነበረንም፣ ኃላ ሰራዊቱን በሶስት ካታጎሪ (ደረጃ) ማለት 1ኛ- ዋና መቺ ሓይል፣ 2ኛ- በዞን የተደራጀ፣ 3ኛ- ከምርት ስራ ያልተላቀቀ ኣድርገን ኣስቀመጥን። ከወርዒና ተከዘ በረሃዎች ወጥተን ወደ ህዝብ ተሰማራን፤ በደጀን ኣመሰራረታችን ፍፁም የተለየ ኣቋም ኣመጣን፤ ራሳቸውን ችለው በማንኛውም ቦታ ሊዋጉ የሚቸሉ ባታልዮኖች ፈጠርን” ይላል።

እንደ ፃድቃን ኣባባል ማሌሊት ከመፈጠሩ ኣስር ዓመታት ቀደም ብሎ የነበረው መሰረታዊው የህወሓት ትግል ዋጋ ኣልነበረውም እንደ ማለት ነው። ባንድ ጀንበር ሰራዊትም ደጀንም ይታነፅ ይመስል፣ ማሌሊት ፈጠረችው ይለናል። ከከባዱ ድርቅ ጋር በ77 ዓ/ም ብቅ ያለው ማሌሊት ብዙም ሳይቆይ በ82 ዓ/ም ደብቁኝ – ሰውሩኝ ማለት ጀምሮ በ83 ዓ/ም እነ ፃድቃን ስልጣን ላይ ሲወጡ ማሌሊት የተባለው ቡድናዊ ስብስብ እንደ ጧት ጤዛ በኖ ጠፋ። ገና 6 ዓመት ሳይሞላው ተቀጨ። ለመሆኑ ለራሱ መቆም ኣቅቶት ስንዝር መቀጠል ያልቻለ ድርጅት እንዴት ነው በከባድ ትግል የታነፀው ህወሓትን ዋጋ ኣሳጥቶ፣ ብዙ ተዓምር ሰሪ ሆኖ የሚቀርበው? ጄ/ ፃድቃን?

“ትልቅ ሓይል ይዘን የደርግን ትንሽ ሓይል የማናሸንፍበት፣ ብዙ ኪሳራ የምንከፍልበት” ችግር ውስጥ ነበርን ይላል ፃድቃን። ሁሉም ታጋይ እንደሚያውቀው የህወሓት ወታደራዊ ፍልሚያ በ3 ደረጃዎች ማለፍ ነበረበት። 1ኛ/ በሽምቅ ውግያ ጀምሮ ከዛ 2ኛ/ ወደ ተንቀሳቋሽ 3ኛ/ና መጨረሻም ቋሚ በመሆን እድገቱንና ተልእኮውን ተከትሎ ተከናውነዋል። ይህ ሂደት ትግሉ “ሀ” ብሎ ሲጀመር የተነደፈና ተግባር ላይ የዋለ እንጂ ማሌሊት ብቅ ሲል ብቅ ያለ፣ ማሌሊት ሲጠፋ ደግሞ ኣብሮ ሊጠፋ የሚችል ኣልነበረም። ኪሳራ በተመለከተ ደግሞ በኣሃዝ የተደገፈ ጭብጥ የለውም። ይሁንና በ 17 ዓመታት ጦርነት የተሰዋው ታጋይ 54 ሺ ሲገመት፣ በባድመና ፆሮና ኣንድ ውግያ ላይ ያለቀው ወጣት ግን 50 ሺ እንደሆነ ይነገራል። ይህ ለማነፃፀሩም የሚከብድ ኪሳራ በብዙ ወታደራዊ ጠበብት ሲተች የመካከለኛው ዘመን (ሜዲቫል) ጦርነት ያስከተለው ኪሳራ ይመስላል እንደሚባል ፃድቃን ሰምቶ ይሆን?። እንግዲህ ጥያቄው “ዲያለክቲካል ማቲርያሊስት … ሳይንቲፊክ” ስትሆን እንዴት ነው ጭራሽ እጥፍ-ድርብርብ፣ ለንፅፅር ኣስቸጋሪ የሆነው ኪሳራ የተፈጠረው?

እንዲያው ጄ/ ፃድቃን ወርዶበት ነው እንጂ እላይ ወታደራዊ ለውጦች ብሎ በኣዲስ መልክ የጠቃቀሳቸው ነጥቦች፣ ድሮ ከማሌሊት ምስረታ በፊት፣ ህወሓት በንድፈ-ሓሳብ ይሁን በተግባር የሚያውቃቸውና ስራ ላይ ያዋላቸው ወታደራዊ ስትራቴጂዎችና ስልቶች ናቸው። ይህ ብቻም ኣይደለም፤ እነዚህ ወታደራዊ ስትራቴጂዎችና ስልቶች ኣያሌ ዘመናት ያስቆጠሩ፤ በቻይና፣ በቬትናም፣ በኣልጄርያ፣ በኣፍጋኒስታን፣ በይጎዝላብያ … ስራ ላይ የዋሉ ናቸው። ለፃድቃን ኣጉል ትረካ ምላሽ ለመስጠት ወደ ሳንዙ (500 ዓመታት ከክርስቶስ ልደት በፊት) ወይም ወደ ክላውስዊዝ (200 ዓመታት ወደ ሁዋላ) መሄድ ኣስፈላጊ ኣልመሰለኝም። እነ ማርክስ እነ ሌኒን ከነዚሁ ተውሰው ነበር የፃፉት። እነ ማኦ በቻይና፣ እነ ጂያፕ በቬትናም፣ ወዘተ. ይህንኑ የታጠቀ ህዝብ ስትራተጂ ከነባሮቹ የወታደራዊ ስትራቴጂ ጠበብት ተቀብለው በየሃገራቸው ተግባር ላይ ያዋሉት። ፅንፋኛ እስላሙ ታሊባን ማርክሰ-ሌኒኑ ሶቤት-ሕብረትን ኣሸንፎ ኣፍጋኒስታንን የተቆጣጠረበት ትግል ፃድቃን ከትረካው ጋር ማጣጣም ይችላልን?

ምናልባት ፃድቃን በማሌሊት ምስረታ ወቅት እንደ ኣዲስ ተገልጦለት ወይም የማሌሊት ፍቅሩ ኣሁንም ኣልለቅ ብሎት ይሆናል እንጂ ህወሓት ከመመስረቱ በፊትም ይኸው የታጠቀ ህዝብ ስትራተጂ በህወሓት መስራቾችና በነባሮቹ ታጋዮች ይታወቅ እንደነበር ላረጋግጥለት እወዳለሁ። ኣንድ ኣብነት ልጥቀስ፡ በ70ዎቹ መጀመርያ “ሓፋሽ ይንቃሕ፣ ይወደብ፣ ይተዓጠቕ” ማለት ሰፊው-ህዝብ ይንቃ፣ ይታጠቅ፣ ይደራጅ” የሚል መመርያ ተነድፎ ህወሓት ተግባር ላይ ያዋለው የዛ ዘመናት ያስቆጠረው የታጠቀ ህዝብ ስትራተጂ ተቀጥያ ነው ። ሰራዊቱም በሶስት ደረጃ ማለት 1ኛ/ በመደበኛ ሓይል 2ኛ/ ‘ከራቢት’ በሚባሉ ኣሃዱዎች የሚመራ ዞባዊ ሓይል 3ኛ/ ከምርት ስራ ያልተላቀቀ ‘ወየንቲ’ በሚበሉ የሚሊሻ ሓይል ተዋቅሮ ሲታገል እንደነበረ በትግሉ ያለፉ ሁሉም ታጋዮች ይቅርና የደርግ ወታደሮችም ሊነግሩ ይችላሉ። “ በ77 ዓ/ም ከወርዒና ተከዘ በረሃዎች ወጥተን ወደ ህዝብ ተሰማራን “ ለሚለው ልቅ ፈጠራው ደግሞ ከ68 ዓ/ም ጀምሮ ህዝቡን በየፈርጁ ሲያደራጁና ሲያታግሉ የነበሩ (በተለይ የክፍለ-ህዝብና የክርቢት) ታጋዮች ይታዘቡ ብል ለጊዜው ይበቃል።

“በደጀን ኣመሰራረታችን ፍፁም የተለየ ኣቋም ኣመጣን” ለሚለው፣ ፃድቃን የሚጨበጥ ነጥብ ኣላቀረበም ብቻ ኣይደለም። እንዳውም ደጀን እንዴት እንደሚመሰረትና ከግንባር ጋር ያለው የተቆራኘ/የተሳሰረ ግኑኝነት በቅጡ የያዘው ኣልመሰለኝም። ግንባር ያለ ደጀን እንደማያድግ ሁሉ፣ ደጀንም ያለ ግንባር ዘላቂ ኣስተዋፅኦ ኣይኖረውም። ይህንን መርህ ከጅምሩ ግንዛቤ ውስጥ ያስገባው ህወሓት ደጀኑና ግንባሩ በተመጣጣኝ ዕድገት እንዲጎለብት ኣድርጎ፣ ፃድቃን እንደሚለው ሳይሆን ከማሌሊት ምስረታ በፊት፣ ባንድ በኩል ህዝቡን በእድሜ፣ በፆታ፣ በሞያ ኣደራጅቶ፣ በብዙ ወረዳዎች ‘ባይቶዎች’ (ማሕበራዊ ኣስተዳደር) መስርቶ፣ በሌላው በኩል ሰራዊቱን ከባታልዮን ኣልፎ በብርጌድም ኣቋቊሟል። በህይወት የሌሉትን እነ ሓየሎም፣ ኢያሱ-ባጋ፣ መንጅር፣ ፀጋብርሃን ወዘተ. እንተወውና፣ በህይወት የሚገኙት ነባሮቹ የባታልዮንና የብርጌድ መሪዎች ይታዘባሉ ኣለማለቱ ምን ይባላል።

እዚህ ላይ ኣንድ መጠቀስ ያለበት ትልቅ ነጥብ ኣለ። በህወሃት ውስጥ ሲያከራክር የቆየው ‘ህዝባዊው’ የደጀን ኣመለካከት፣ በኢትዮጵያ ኣንድነት በሚያምነውና ትግራይን ለመገንጠል ሲያቀነቅን በነበረው ቡድን መካከል ግጭት ፈጥረዋል። ተገንጣዩ ቡድን በትግራይ ብቻ ደጀን እናጠናክር ሲል ተቃዋሚው ደግሞ የምንታገለውን ደርግ ሃገራዊ ሓይል ስለሆነ በኢትዮጵያ ደረጃ ደጀን ማጠናከር ይገባል ባይ ነበር። ይህ ኣቋም ፖለቲካዊ ትርጉም ነበረው፣ እሱም በኣንድ በኩል የኢትዮጵያ ኣንድነት ማጎልበት ሲሆን በተፃራሪው ደግም ኣንድነትን ማቀጨጭ ነበር። ኣስመሳዮቹ የመገንጠሉ ኣቋም ኣሁን ድረስ ሕገ-መንግስት የሚል ስም በሰጡት ፕሮግራማቸው ውስጥ ሸንክረውት ይገኛል። ያቅጣጫ ማጣት ውዥንብር እዚህ ላይ ነበር። ይህ ደግሞ በዋናነት ፖለቲካዊ እንጂ ወታደራዊ ውዥንብር ኣይደለም።

የደጀኑ ጉዳይ ከሻዕብያ ጋርም ለረጂም ጊዜ ኣጋጭቶናል። ሳሕል በረሃ ላይ የመሸገው የሻዕብያ ጦር የሳሕል ተራራዎች ታቅፎ ይኖራታል እንጂ ደርግን ኣያፈርስም። ደርግን ድል ማድረግ ከፈለገ የታጠቀ ህዝብ ስትራተጂ ተከትሎ ለተግባራዊነቱ የደጀን መሰረት ወደ ሆነው ህዝቡ መሰማራት ኣለበት ብሎ ህወሓት የመከተው ድሮ ጤዛዋ ማሌሊት ብቅ ከማለትዋ 5 ዓመታት በፊት ነበር።

ከጤዛዋ ማሌሊት ምስረታ ጀምሮ “ዲያለክቲካል ማቲርያሊስት … ሳይንቲፊክ በሆነ መንገድ ነገሮችን ማየት” እንደጀመረ የሚተርክልን ፃድቃን ከተጨባጭ ሓቁ ጋር ምን ያህል እንደተራራቀ ኣንድ ኣብነት ላክል። የማሌሊት ቡድን ህወሓትን እንደተቆጣጠረ ታጋዩ ብሄራዊ ስሜቱ እያላላ፣ ባንፃሩ ሃገራዊ ስሜቱ እያጎላ ስለሆነ ይህ ኣዝማምያ እንዲቀለበስ ተብሎ መቀስቀሻ ፅሁፍ ተዘጋጅቶ ቅስቀሳው ለወራት ተካሂደዋል። በመሆኑም የደርግ መውደቅያ ተቃርቦ ታጋዩ ወደ ማህል ኢትዮጵያ ዝለቅ ሲባል፣ “ለምን? ያስተማራችሁን በትግራይ ብቻ እንድንወሰን ኣይደል እንዴ?” ማለት ጀምሮ ግንባሩንም እየጣለ ወደየቤቱ መመለስ ቀጠለ። በዚሁ ወቀት ጨካኙ የማሌሊት ቡድን ካድሬዎቹን ኣሰማርቶ በታጋዩ ላይ መረን የለቀቀ ግፍ ፈፅመዋል። ‘ጎሓፍ’ (ውዳቂ) እየተባሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ታጋዮች ተረሽነው የጅምላ መቃብር ውስጥ ተጥለዋል። ከዛ ቁጥር በላይ ደግሞ በእስር ተሰቃይተዋል። የስነ ኣእምሮ ጥቃት የደረሰባቸው ጥቂት ኣይደሉም። ይህና ኣያሌ ተመሳሳይ ድርጊቶች ስናሳ ፃድቃንን የቱ ላይ ነው ሳይንቲፊክ የሆናችሁት ብለን መጠየቅ እንችል ነበር፣ ሆኖም ወደ ተራዘመ ንዝንዝ ከመግበት ይልቅ ከናአካቴው ራስዋ መቆም ያቃታት ማሌሊት የት ገባች ብሎ ባጭሩ መጠየቁ የሚሻል ይመስለኛል። የተመደበላት 50 ሚልዮን ብር ኣልበቃ ብሎ ነው ? ወይስ ቡድናዊ ተልእኮዋ፣ ማለትም ተቃዋሚዎቹን የመምታት ግዳጅዋን ከፈፀመች በቃ ኣታስፈልግም ተብላ ተጥላ ነው።

በማጠቃለል “ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል” ሆነና በቁምነገር ለቁምነገር ያልተፈጠረችው ጤዛዋ ማሌሊት የውሃ ሽታ ከሆነች እነሆ 20 ዓመታት ኣልፏታል። ፃድቃን ደግሞ የህወሓት 40ኛ ዓመት መዘከር ትቶ፣ ለሸር የተጠፈጠፈችውን ቡድናዊ ድርጅቱን ማሌሊት ሲያሞግስ መደመጡ ብዙዎችን ሳያሳስብ ኣልቀረም።ይሁን እንጂ ይቺ ለሸር ብቅ ብላ የከሰመችው ድርጅት የፈጠረችው ምስቅልቅል ግን ኣሁንም ህዝቦቻችንን እያተራመሰ፣ ሃገራችንን እያደማ ይገኛል። ኣቅጣጫ-የለሽ ውዥንብር ይሉታል ይህ ነው። በማህሉ ሃገር ወደብ ኣልባ፣ ህዝብ መብት ኣልባ፣ ወጣት ስራ ኣልባ ያደረገችው ሳይንቲፊክዋ ማሌሊት ለራስዋም ባትሆን ቢያንስ ፈጣሪዎችዋን ግን ለጊዜውም ቢሆን ጌቶች ኣድርጋቸዋለች።

ህዝባዊ ስርዓት ያልተመሰረተበት ሃገር ለጥቂቶቹ ገነት፣ ለብዙዎቹ ሲኦል መሆኑ ኣልቀረም። ኢትዮጵያ ኣንድዋ ኣብነት ነች። ከዚህ መከራ ለመገላገል ጋሬጣው ቢበዛም የጋራ ድርጅት ፈጥሮ ለጋራ ስርዓት መታገል ነው።
ኣረጋዊ በርሀ
11 ማርች 2015

The post ጄኔራል ፃድቃንና ጤዛዋ ማሌሊት …በ40ኛው – ከአረጋዊ በርሀ appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: መጥፎ የአፍ ጠረንን ለመካከል ወይም ለመቀነስ 5 ቀላል ዘዴዎች

0
0

smelly
መጥፎ የአፍጠረንን ለመከላከል ወይንም ለመቀነስ ማድረግ ያለብዎትን ያውቃሉ?
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

1) የአፍዎን ንጽህና በሚገባ ይጠብቁ፡- ጥርስዎን ቢያንስ በቀን ሁለት ጊዜ ማጽዳት እንዳለብዎ ይወቁ ከተቻለ ከምሳ በኋላም ለማጽዳት የጥርስ ብሩሽና የጥርስ ሳሙና በቦርሳዎ በመያዝ ጥርስዎን ያፅዱ፡፡ እንዲሁም የጥርስ ብሩሽዎን በየ3ወሩ መቀየር ተገቢ ነው፡፡

2) ፈሳሽ በብዛት ይውሰዱ፡- ውሃን መጠጣት በአፍ ውስጥ እርጥበትን ሰለሚፈጥር በብዛት እንዲወስዱ ይመከራል፡፡ ከስኳር ነፃ ሆኑ ማስቲካዎችና ከረሜላዎች መውሰድ በአፍ ውስጥ (Saliva) ምራቅ እንዲመነጭ በማድረግ በአፍ ውስጥ የቀሩ ምግብና ባክቴሪያዎችን እንዲያጥብ ያደርጋል፡፡

3) ሲጋራን ማጤስ ማቆም፡- ሲራጋ ማጤስ ለመጥፎ የአፍ ጠረን መኖር ምክንያት ስለሚሆን
ማቆም ይኖርብዎታል፡፡

4) የሚወስዱትን ምግብ ወይንም መድኃኒት መጥፎ የአፍ ጠረን እንደሚያመጣብዎ ካወቁ ወደጥርስ ሐኪምዎ በመሄድ ማሳየት ተገቢ ነው፡፡

5) የጥርስ ሐኪምዎን በዓመት አንዴ እንዲያይዎት ማድረግ እንዲሁም በሕክምና የታገዘ ባለሙያዊ የጥርስ ዕጥበት በዓመት አንድ ጊዜ ማድረግ መጥፎ የአፍ ጠረን እንዳይኖር ያደርጋል፡፡

The post Health: መጥፎ የአፍ ጠረንን ለመካከል ወይም ለመቀነስ 5 ቀላል ዘዴዎች appeared first on Zehabesha Amharic.

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትትህ የድጋፍ ማህበር በስዊድን ባለው መልኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ወስኖል

0
0

ማርች 7ቀን 20015 በተደረገው ስብሰባ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትትህ የድጋፍ ማህበር በስዊድን ባለው መልኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ወስኖል

sweden-mapእኛ በሰዊድን የምንገኝ የአንድነት የድጋፍ ማህበር የአንድነት ፓርቲ አመራር መመሪያ እሰከሚሰጥበት ድረስ አሁን በያዝነው መስመር እንድንቀጥል የታሰሩትንም የአንድነት ፓርቲ አባላት ቤተሰቦች መደጎም ማህበራችን በቀጣይ ከሚያደርገው ተግባር አንዲሆን ማህበራችን አንድነት ፓርቲን መደገፍን ጨምሮ በሃገራችን ፍትህ ዲሞክራሲ እኩልነት እስኪረጋገጥና የሰብአዊ መብቶች እስኪከበሩ የሚታገል ማህበር እንደመሆኑ ምንም አይነት እንቅፋቶች ቢደረደሩ የተነሳንበት አላማ እውን እስኪሆን ድረስ ትግላችንን አጠናክረን እንድንቀጥል የድጋፍ ማሕበራችን በማህበራዊ ኑሩዋችንም ትልቅ ትርጉም ያለውና ለህብረተሰቡም ትልቅ ስራ በመስራት ጠቃሚነቱን ያሳየ ማህበር እንደመሆኑ አሁን ባለው መልኩ ተጠናክሮ እነደሚቀጥል ወስኖአል፡፡

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትትህ የድጋፍ ማህበር በስዊድን

Unity for Democracy and Justice Support organization of Sweden

The post አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትትህ የድጋፍ ማህበር በስዊድን ባለው መልኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ወስኖል appeared first on Zehabesha Amharic.

የምርጫ አስፈፃሚው የደኢህዴን አባል መሆናቸው ተረጋገጠ

0
0

ነገረ ኢትዮጵያ

• ነዋሪዎች ከሁለት በላይ የምርጫ ካርድ እንዲያወጡ እየተደረገ ነው

በደቡብ ክልል በምርጫ አስፈፃሚነት የተመደቡ ግለሰቦች የዴኢህዴን አባላት እንደሆኑ ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ በላኳቸው ሰነዶች አረጋገጡ፡፡ ለአብነት ያህልም አረካ ከተማ የምርጫ ክልል በአስፈጻሚነት እየሰሩ ከሚገኙትን አቶ ግዛው ቴማ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አባል መሆናቸው ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ የተላኩት ሰነዶች ያሳያሉ፡፡ አቶ ግዛው ለፓርቲያቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) በነሃሴ ወር 2006 12 ብር ከ87 ሳንቲም፣ እንዲሁም በ2007 መስከረምና ጥቅምት የሁለት ወር 25 ብር ከ74 ሳንቲም መዋጮ የከፈሉበት ደረሰኝ የደኢህዴን አባልነታቸውን ያረጋግጣል፡፡

በሌላ በኩል በደቡብ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ነዋሪዎች በግዳጅ ከሁለት በላይ የምርጫ ካርድ እንዲያወጡ እየተገደዱ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሕዝቁኤስ ቱጨ ቱፋ ለባለቤታቸውን ለወይዘሮ መሰለች ኬንዳን ጭምር ካርድ እንዲያወጡ የተደረገ ሲሆን፣ በዚሁ ቀን ህዝቡ ካርድ እንዲያወጣ የሚቀሰቅሱ ሌሎች ካድሬዎች ወይዘሮ መሰለች ኬንዳም የባለቤታቸው የአቶ ሕዝቁኤስ ቱጨ ጨምረው ሁለት ካርዶችን እንዲወስዱ ተደርገዋል፡፡ ሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎችም በተለያዩ ካድሬዎች አማካኝነት በርከት ያሉ የምርጫ ካርዶችን እንዲወስዱ መደረጉን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በቀን 07/05/ 2007 ዓ.ም ወ/ሮ መሰለች በ173ኛ እና 147ኛ ቁጥር፣ እንዲሁም ባለቤታቸው አቶ ህዝቁኤል ቱጫ ቱፋ በተመሳሳይ ቀን 172ኛ እና 151ኛ ተራ ቁጥር ላይ ተመዝግበው ሁለት ሁለት የምርጫ ካርዶችን እንዲወስዱ ተደርገዋል፡፡ በተጨማሪም ነዋሪዎች መምረጥ ለማይችሉት የቤተሰብ አባላት ጭምር ‹‹ካርድ ውሰዱላቸው›› እየተባሉ በአንድ ሰው በርከት ያለ ካርድ መውጣቱን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

11045382_678850302240631_7727559560221046908_n 11009130_678850215573973_6496558354382052425_o

The post የምርጫ አስፈፃሚው የደኢህዴን አባል መሆናቸው ተረጋገጠ appeared first on Zehabesha Amharic.

እኔ „እኔን“ ከጠረጠረ –በእኔ ውስጥ „እኔ“ የለም ማለት ነው –ከሥርጉተ ሥላሴ

0
0

TPLFየጹሑፉ ውበት ጠሩኑ ምቹ፣ መካርነቱ ደግሞ ዬዬኔታ ማዕረግን የሰጠሁትን የጸሐፊ አቶ ይሄይስ አእምሮ ጹሑፍ በጣም የወደድኩት መሆኑና ምስጋናውን ዘለግ አድርጌ አክዬ ወደ እኔው አብረን እላለሁ „ሥነ ጹሑፍ ከማህበረሰቡ ጓሮ ይታፈሳል“ የሥነ ጹሑፍ መምህሬ አቶ አበበ ኬሪ።

ዛሬ ከህይወቴ ተነስቼ ሃቅን በሃቅ እንዝርት ፈትዬ ወርቁን ሸማ በሙያተኛ አዘናክቼ ህይወቴን በጥልቀት ከውስጤ ጋር ስምምነቱን መግለጥ አስኝቶኝ እነሆ ብዕሬ ለሽ ብላ ከተኛችበት ማሳዋ ቀስቀስ አድረጌ ከእኔው ጋር አሰለፍኳት።

  • ሰሞናቱ በእስልማና ሃይማኖት መብት መዳጥ ምክንያት በተፈጠረው „የድምፃቻን ይሰማ‘‘ ለግላጋ ተመክሮ ያልተመቻቸው ውርጭ ሃሳቦች – አዬሁ። ባሻጋሪ አይደለም። ቀረብ ብዬ። ውርጩ እኔንም ከውስጤ በመሆኑ ተጋራሁት እናም – አዳመጥኩት። የእኔ ጹሑፍ በዲያቆን ዳንኤል ክብረትና በአቶ ኤርምያስ ለገሰ ዙሪያ አይደለም። መነሻዬ የጸሐፊ ከተማ ዋቅጅራ ጹሁፍ ሲሆን የጸሐፊ መሃመድ ሙፍቲህ ነፃ አስተያየትና ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን ባቀረቡት ዙሪያ ላይ ነው። መንፈሱ ግራ ቀኙን መጎብኘት አሰኝቶታል ካላችሁም መልካም ነው። ከማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚወጡ ጹሑፎች ሚዛን ጠበቂ ዘበኛ ያስፈልጋቸዋልና እኔም የሚሰማኝን እንዲህ።

ጹሑፎች በሁለት ጅረቶች በድጋፍና በተቃውሞ አቅጣጫ ነበሩ። በቅድሚያ ጸሐፍት በግልጽነት ሃሳባቸውን ማብራራታቸው ጌጣችን ነው። አስተናጋጁም ዘሃባሻ መልካም ቤት ነው። እንደ መሬት ሁሉንም ማስተናገዱ። የግራ ቀኙን አይቶ ታዳሚ ዳኛው አይዋ ዕውነት ነውና ይፈርዳል። አንተም ተው! አንተም ተው! ደንበርህ እሰከዚህ ነው በይርጋ ይላል …. ነፃነት የሚመቸውንም – የማይመቸውንም ማስተናገድ ከቻለ ሃሳብን የመግለጽ ጉዞ ርትሃዊ ያደርገዋል።

አሁን ከጋሼ አቤ ትምህርት ልነሳ። ከህይወቴና ከገጠመኞቼ። ለእኔ „የድምጻችን ይሰማ“ እንቅስቃሴ የእኔ ነው። ለእኔ „የድምጻችን ይሰማ እንቅስቃሴ“ ገዢው ሃሳብ በኢትዮጵያዊነት ውስጥ እንጅ ከኢትዮጵያዊነት በላይ ባለመሆኑ ጠረኔ ነው። ለእኔ „የድማጻችን ይሰማ“ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መምህሬ ነው። ለአኔ „የድምጻችን ይሰማ እንቅስቃሴ“ የሃይማኖት ነፃነት ጥያቄ ነው። ለእኔ „የድምጻችን ይሰማ እንቅስቃሴ“ ከእውነተኛ ብሄራዊ ማንነት የተነሳ፤ በኢትዮጵያ ሰንድቅዓላማ ሥር ያለ ውበቴ ነው። አንድም ሳይቀሩ ልቅም ብለው መሬዎቹ በበለኃሳብ እጅ የገቡበት አንድ ሃይማኖታዊ እምነት ሊያደርገው የሚገባ፤ ሊወስደው የሚገባውን እርምጃና መርኽ የተከተለ በመሆኑ እኔም – ታዳሚው ነኝ። እነዛ የተከበሩ የሃይማኖቱ አቨዎ መሪዎቹ እስር ቤት ሊደርስባቸው የሚችለው ሥነ – ሞራልን የጣሰ የበቀል እርምጃ ሲታሰብ ወስጥን – ያቀልጣል። እንደ እራስ፣ እንደ እኔ፣ በእኔ ቢደርስ ብለን እንዬው … ጉዳያችን ነውና፤ አርቅን ሳይሆን ቋያውን አቅርበን እንፈትነው። የቃለ – አዋዲ አፈጻጻም በሰበካ ጉባዔ በአጥቢያ አድባራት መሆኑ ቀርቶ በከተማ ነዋሪዎች ማህበር በቀበሌ ቢሆን የተዋህዶ ልጆች ይመቻቸዋልን፤ ሊቃውንተ ቤተክርስትያናትስ ይደላቸዋልን? አምላካችንስ ቢሆን አይከፋውንም?

ውዶቼ – መግቢያዬ ላይ እንዳስታወስኩት ዛሬ ከራሴ ኑሮ ነው የምነሳው ብያለሁ። ተማሪ እያለሁ የልብ ጓደኞቼ አህመድ ኪሮስና ሞሚና ነበሩ። አህመድ በስኳር በሽታ ሲሞትብን ጥቁር ለወራት ሁለታችንም ለብሰናል። ሶስታችን አንድ ወንበር ስንቀመጥ አህመድ ማህላችን ሲሆን፤ ኪሮስ ከቀጣዩ ወንበር በኋላችን ይቀመጥ ነበር። ሞሚና የሽንኩርት ነጋዴ ስትሆን እነ አህመድ ደግሞ ሱቅ ነበራቸው። ሞሚና እና እኔ ምሳችን ይዘን ት/ቤት ስለምንሄድ ሁልጊዜ ከሥጋ ውጪ ያሉ ምግቦችን ይዘን እንድናመጣ ተስማምተን፤ አንድ ቀን ሞሚና አንድ ቀን እኔ በፈረቃ ምግብ ይዘን እንሄዳለን። አብረንም እንበላለን። ይህ ማለት ከነሞሚና ቤት ለሽሮ ወጥ ሲሰራ ሽንኩርት መክተፊያው ስጋ የተከተፈበት ሊሆን ይችላል – ብረት ድስቱም ሥጋ የተሠራበት፤ ከእኛም ቤት እንዲሁ። ግን የሁለታችን ፍቅር አላወከውም። ትምህርታችን በዚህ መልክ ጨርሰን እኔ ወደ ሌላ የፖለቲካ ዘርፍ ስጠለፍ እሷ በመምህርነት ቀጠለች። እኔ ከአርሲ ከጢቾ እውራጃ ወደ ጎንደር ስዛወር እሷ ዬአንድ ቀበሌ የሴቶች ድርጀት ተመራጭ ሆና አገኘኋት። ልተዋወቃቸው ስሄድ በሩ ላይ ይጠብቁኝ ነበር። ከመኪና ስወርድ እኔ ነኝ። ሄዳ ከወንበሯ ቁጭ ስትል አብረዋት የነበሩት ተደናገጡ። እኔ ግን ጉዴን አውቀዋለሁ „ ከአብሮ አደግህ ጋር አትሰደድ ነው“ ነገሩ „እኔ ሞሚኒት እሷንማ ቁሜ አልቀበልም ነው።“ ነበር ነገርዬው። ሂጄ ከመቀመጫዋ ተሳሳምን። „ጉድሽን ላይ ነበር።“ አለችኝ ቀጥላም „ ደግሞ ላንቺ ነው አብሬ ሸር ጉድ ስል የቆዬሁት“ አለችኝ ያቺ ድንብልብ የፍቅር ኮረሪሚ …. እህቶቼ ገብያ ሲሄዱ ሽንኩርት ሌላ ቦታ አይገዙም ነበር …

ሁለተኛው – ዬዬካቲትት 66 ፖለቲካ ኢንስቲቲዩት „የኢትዮጵያ ታሪክ“ መምህሬ የአዳሉ ጋሼ አብዲ ነበር። በደሜ ውስጥ፤ በሴሌ ውስጥ፤ በነርቤ ውስጥ ኢትዮጵያዊነትን እንዴት እንደገነባው ቁሜ ልመሰክርበት – ያስችለኛል። ጋሼ አብዲ እምነቱ እስልምና ነው። እንደዛ ፍጹም በሆነ በብሄራዊ የፍቅር ስሜት ስለ እናቱ፣ ስለ ባዕቱ ሲያስተምር የነቁጥ ግድፈት አልነበረበትም። ፍጹም ሰማያዊ ነበር። ልክ ጋዜጠኛ ሳዲቅ „አንቺ እናት ዓለም“ እያለ እንደ ገጠመው የምሽት ማህሌት ነበር … ይህ ሁሉ ጸጋና ክብረት እኔ ቀጥ ብዬ እንድቆም ያደረገ በትምህርት ደረጃ የጋሼ አብዲ ፍሬ ዘለቅ ጥረት ነው። ልመስክረው – ልናገረው … ከአደኩበት ማህበረሰብ ጋር ህትምት ሆኖ እንዲህ ውስጤን የሚገዛው መሠረቱ ባላና ወጋግራው … ወርቁም። አስልማና በኢትዮጵያ የሌላ ተቅጥላ ወይንም አጥፊ ዲቃላ መንፈስ ሊሆን ከቶውንም አይችልም። ካለ ደሙ ካለ ተፈጥሮው። ኢትዮጵያዊው እስልምና እራሱን የቻለ፤ አንገቱን የማያስደፋ፤ ኃላፊነት የሚሰማው፤ በሙሉ ራስ መተማመን ላይ የቆመ የበቀለ – የጸደቀ – የሰበለ ቅዱስ መንፈስና ወጥ ማንነት አለውና። „ለሽብርተኝነትን“ ልመና የሚሄድበት አንድም ቁራጭ ብጣቂ አምክንዮ ሊኖር ፈጽሞ አይችልም። ምን አጥቶ – ከውስጥነቱ?! …. እራሱ እንቅስቃሴው ሲፈጠር በሙሉ ኢትዮጵያዊነት ጨዋነት መንፈስ ነው። እንቅስቃሴው በራስ የመተማመን አምክንዮዊ ጸጋውን ከመፈጠሩ በፊት ከኢትዮጵያዊነቱ የቀዳው ቀድሞ ነው። ሃቅን አንገፍትር ….

ሦስተኛው – አርሲ ጢቾ በነበርኩበት ጊዜ አለቃዬ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው ጓድ ጃርሶ በልዳ የባሌ ጎባ ልጅ ዬእስልማና ሃይማኖት ተከታታይ ነበር። እጅግ ለስላሳ ፍጹም ሰላማዊ፤ ሰብዕዊም ሰው ነበር። ቤታቸው በተደጋጋሚ ሂጃለሁ። መንፈሱ የቤተሰቡ በሙሉ ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነበር። እንደገናም ኮሚቴው ውስጥ የነበሩ አለቆቼ አብዛኞቹ የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ነበሩ። ከዚህም በተጨማሪ የጢቾ አውራጃ ህዝብ ለሥራ ወደ ገጠር ስዘዋወር እንደዛ ግብግብ – ስፍስፍ፤ ይልልኝ የነበረው፤ ወደ ጎንደር ስዛወር ሌትና ቀን ያለቀሰው አብዛኛው እጁ የእስልምና እምነት ተከታይ ነበር። ፍቅርን በገፍ የሸለምኝ። ፍቅሩን ጸንሶ በፍቅር እንድኖር ያደረገኝ፤ ፍጹም ልዩ ክብረት ነበረው። እኔንም – በህብረ ቀለሙ የገነባኝ – ያነጸኝ።

አራተኛው ሥራ ላይ በነበርኩበት ጊዜ የመንደር ምሥረታ የልምድ ልውውጥ እንዳደርግ ከቡድኑ ጋር መላኬም ብቻ ሳይሆን የቡድኑም ጸሐፊ ነበርኩኝ፤ ሽዋ ያዬናቸው የጉራጌ ብሄረሰብ ናሙና መንደሮች አብዛኞቹ የእስልምና ዕምነት ተከታዬች ነበሩ። ኢትዮጵያዊነት ከነክብሩ – ከነፍቅሩ ፈልቆና ደምቆ ነበር መንፈሴን የመገበው …. ፍጹምም ልዩም ነበር ማተቤም ነበር።

አምስተኛው – ከጫካ ስመለስ ምህረት ጠይቄ ገብቼ ግን ወያኔ አሰረኝ። ስፈታም ጎንደርን እንዳለቅ በቁም እስር በ50000.00 ብር ዋስ ነበር። 50000.00 ብሩን ዋስ ያሳያዙት ሐጂ ሲራጅ ነበሩ። የአባቴ የአባባ የምር ጓደኛ ናቸው። አባባ ኢትዮጵያ አልነበሩም። ለደርግ አልገዛም በማለት ሱዳን ነበሩ። ግን ሐጂ ሲራጅ ማተባቸውን ጠብቀው ዋስ ሆነው አስፈቱኝ። ይህም ብቻ ሳይሆን አንድም ቀን በችግራችን ሳይለዩ እንደ ረዱን፤ ፍቅር እንደ ሰጡን፤ ፈተና ሲደርስም የተለዬ ጸሎት ድዋ በማደረግ እናቴን በማጽናናት እስከመጨረሻው በጨለማ ጊዜያችን ያልተለዩ ውድ የኪዳን አባት – የዝምድና አውራ ነበሩ። አሁን ሳውዲ ናቸው። ዕውነቱ ይህ ነው – የአብሮነታችን – እድምታው። ዬት እያመጣችሁ ጎርፍ በንፁህ መንፈሳችን ላይ እንደምትለቁት ፈጽሞ አይገባኝም። መራራ … ወረራ —

ስድስተኛው ወደ ሲዊዝ ስሰደድ መጀመሪያ ለሁለት ሳምንት፤ ከዛም ለ8 ወር በኋላም ለ8ዓመት በአንድ ካንፕ ግን በተለያዬ ክፍል አብሬ የተመደብኳት የእስልማን እምነት ተከታይ እህቴ ክብሬ ሂሩቴ ነበረች። የመጀመሪያው የ8ወር ቆይታችን ዬጋራ ቤታችን ሰው መቆም አያስችልም ነበር። አልጋው ሲደራረብ ይቻላል። ከልተደራረበ ግን መቆሚያ አልነበረውም። በተደረበ አልጋ መተኛት ባለመቻሌ – ነጣጠልነው። ቦታ አልነበረውም።  በአልጋችን ጠርዝ አጠገቡ የበሬ ግንባር የምታክል ታዛ ነበረችን። ከዛች ላይ እኔ ውዳሴ ማርያሜን እሷ ደግሞ ሳላዷን – ትሰግዳለች። 8 ወር ሙሉ የምትሰጠን የሳምንት ስንቅ በጋራ አንድ ላይ ነበረች። 140- ፍራንክ። የግል የሚባል ምንም ነገር አልነበረንም። እሷ ገብያ፤ ልብስ ማጠብ – መተኮስ፤ ማንጠፍ እኔ ደግሞ ምግብ ማብሰል ነበር ተግባራችን። ለ52 ስደተኛ አንድ ክፍል ውስጥ ወደ 12 ምድጃ ነበረን። እኔ የእንሰሳው ኑሮ ስለሚከብደኝ ቢሮ ፈቅዶልኝ አርብ ለቅዳሜ አጥቢያ ሌሊቱን ስሰራ አድራለሁ። ሰርቼ ከሁለታችን ፍሪጅ በቀደም ተከተል አስቀምጣለሁ። ከዛ በኋላ እኔ ወደ ምድር ቤት አልሄድም።

እኔ የሠራሁትን የምታሞቀው እሷ ናት። እኔ ሥሰራው በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብዬ – ስበላው እንዲሁ። እሷ ስታሞቀው ደግሞ ብስሚላሂ ብላ – ስትበላውም እንዲሁ። በአንድ መሥሪያ ነው የምንበላው። የእመቤቴ ወርሃዊ ዝክር እሷ ናት ዳቦ ገዝታ እምታሰናዳ – በአፆማትም እንዲሁ፤ የእሷ ሮመዳን ፆም ደግሞ እኔ ነኝ ማናቸውንም የማሰናዳው።  ዬእሷ ወንድም የሰጠን ቴፕ ነበረን። ሙሉ ቀን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙርን ብቻ ነበር የሚያስተናግደው። ለሰከንድ ቅሬታ ኑሮባት አያውቅም። ይልቁንም ብዙውን በቃሏ ትለውም ነበር። እንደ ገባን የተሳሳተ መዳህኒት ተሰጥቶኝ በድንገተኛ ታመምኩኝ። እግባቴን በቲ – ሸርቷ ነበር የተቀበለችው፤ እብስ – እብስ አድርጋ ከነርጥበቱ ነበር ለብሳ አብራኝ ሆስፒታል የሄደችው። ይህን ከእናት በስተቀር ከቶ ማን ያደርገዋል?! መንፈስ ቅዱስን ጠይቁት ወገኖቼ ሚስጢሩን እንዲገልጽላችሁ – የምር። ለዛውም ጸያፉን እግባት እንደዛ ዝልብ እንዳለ — ለበሰቸው። እፁብ ድንቅ ኢትዮጵያዊነት። ለእሷ የወቅቱ ጥያቄ የእኔ በህይወት መቀጠል ብቻ ነበር። እኔ ኮማ ውስጥ ሁኜ ደጋግሜ እናገር የነበረኩት የሂሩቴን ነገር አዳራ እል እንደ ነበር ነገሩኝ ዬልቤ – ከልቤ እሷ ብቻ ከቤተሰቦቼ ልቃ ነበረችና።

ከዚህም በተጨማሪ ጤናዬ አስተማማኝ ስላልነበረ ታች ወርጄ ስልክ ስደውል ከዘገዬሁ በዛ በረዳማ ሃገር ጫማ ሳታደርግ ነበር መጥታ የምታዬኝ። አንድም የካንፕ ሰው እህትአማች አይደሉም የሚል አልነበረም። ለኬዝ ነው የተለያዩት ነበር የሚሉት። የካንፑ አሰተዳዳሪዎች ሳይቀሩ ብዙ ጊዜ ጠይቀውናል። ለእኛ የነበራቸውም ክብር ልክ አልነበረውም። በፈረንጆች ክሪስማስ ለስደተኛ ስጦታ እንድንሰጥ ያደረጉት እኛኑ ነበር። የቢሮ ቁልፍ አምነው ለእኛ ነበር የሚሰጡን። ይህን ያህል ሚስጢር በኢትዮጵያዊነት ይቀዳል። ምንድነው የሌለ፣ ያልተፈጠረ ተቀጥላ ጉም ነገር የምናወራው? ይህን ቋሚ ምስክር እኔን ሊያኝ የመጣ አንድ ታላቅ ሙህርና ካህን፤ የማህበረ ቅዱሳን መሥራችን ከፍተኛ መሪ አካል ወንድሜ በዓይኑ በብሌኑ ኑሯችን ከሥፍራው ተገኝቶ አይቶታል። እሷ የጋገረችውንም ዳቦ ባርኮ ቆርሶልናል። እኔ „እኔን“ ከጠረጠረ በእኔ ውስጥ „እኔ“ የለም ማለት ነው። ይህን ጹሑፍ  ስፅፈው እራሱ እንደ ወትሮው ሆኜ አይደለም። ስለምን? ቁስሉ – የእሳቱ ላንቃና ሳንቃ እኩል ሊሰማን አለመቻሉ እያርመጠመጠኝ። ፍቅሮቼ ታዳሚዎቼ  እኔ እምጽፈው እራሴን ውስጤን ነው። ለማን ብዬስ – ስለምን ብዬስ እራሴን ሰውሬ አቀርባለሁ?! በግልጽነትና በቀጥተኝነት ስሜቴን ነው የምገልጸው። በወቅቱ እኔን ይቀርቡ የነበሩ የተዋህዶ ልጆችም ለእሷ የነበራቸው ፍቅርና ክብር ልዩ ነበር። እህት – እናት – አስታማሚ – አክባሪ – አዛኝ – የልብ ጓደኛ – ሥራ ወዳድ ያው ኢትዮጵያዊው የጉራጌ ብሄረሰብ መለያ ምልክቱ መዳፍ ነው ሥራ! ሁሉንም – ነበረች። የሁለታችን ባላ፣ ግድግዳና ወጋግራ ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነበር። የአክብሮቷና የፍቅሯ ልክ ዛሬ ላይ ሁኜ ሳስበው ይገርመኛል። ለዛውም እኔን አታወቀኝም ነበር ምን ልሁን ምን?!

ስለዚህ እኔ „እኔን“ የማልጠረጥረውን ያክል፤ እኔ „እኔን“ የማምነውን ያህል ውስጦቼን የኢትዮጵያ የአስልምና እምነት ወንድሞቼንና እህቶቼን ከልጅነት እስከ እውቀት ውስጣቸው አብሮኝ ኖሩ ደስታን የሸለመኝ፤ የረዳኝ፤ ያገዘኝ፤ የተንከባከበኝ፤ በመከራዬ የተገኘ የእኔ ጠረን የሆነ ስለሆነ የዛሬው የወያኔ ሃርነት ትግራይ የመብት ረገጠ በመቃወም የሚያቀርቡት የመብት ትክከለኛ ጥያቄ የእኔም ነው። አብሬ – እስለፋለሁ። ከጎናቸውም – ነኝ። ቁሜ በአደባባይ ስለ ንጽህናቸው ስላላቸው ኢትዮጵያዊነት መንፈስ ስመሰከር ውዬ ባድር አልደክምም – — አላፍርበትምም። ስለ እነሱ ስናገር ስለ ራሴ ነው እምናገረው። ስለዜግነቴ – ስለማንነቴ ነው እምመሰክርው። ኢትዮጵያዊ ነኝ ስል ገድብ የለውም እኔን የፈጠረው ሚስጢር ….. ቅመሙ ጥልቅ እጅግ ጥልቅ ውቅያኖስ ነውና። ሉሲ ድንቅነሽ —- እስኪ ስትችሉ (DNN) መርመር አድርጉና ፈጽሞ ያልጠበቃችሁት ግን ድንቅ የኢትዮጵያዊነትን ግንድነት ውጤትን ታያላችሁ።

ወያኔ ዓለም ዐቀፍ ድጋፉን ለመስቀጠል ትራስ ያደረገው የኢትዮጵያን የእስልምና እምነት ተከታዮችን ካሳ በማቅረብ ነው። ለእርድ ሥጋ በማቅረብ ነው። እራሱ የፈበረከው ችግር እኮ ነው ወያኔ። የከፋፈላቸው – የለያዬቸውም እራሱ ነው። „የሽብር ህግ“ ያለው የወረቀት ነበር ሆኖ ስለቀረበት። „ሽብርተኛው ህጉን ያወጣው ወያኔ ለራሱ ውስጡን ለሚነስተው የሽብር ስውር ተግባሩ ነው“ እኔ ምክንያታዊ በሆነ ጉዳይ የ3 ደቂቃ አጭር ፊልም ሠርቻለሁ። ከፊልሙ ምስል የእስልምና እምነት መሪዎች በሙሉ አሉበት። ወያኔ የሚያላግጥብት ሽፋኑ መጋለጥ ስለነበረበት። በዬትኛውም ሀገር ስደት የሚጠይቁ ኢትዮጵያዊ ሙስሊሞች „የዘመኑ ስጋት“ የማይመለከታቸው ስለመሆኑ ለማጠዬቅ። ፊልሙም ለሚመለከተው አካላት ተልኳል። ሲዊዝም በጋራ ከሌሎች ሀገር ዜጎች ጋር ታይቷል። „ ነብር ጁንጉርጉርነቱን ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊነቱን አይቀይርምና“ በፍጹም ሁኔታ አምጡ ድገሙ ቢባል የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሥነ ምግባር የሚያክል ሰላማዊ መንፈስ የትም ዓለም የለም። እንቅስቃሴው በወላዊ አቋሙ ቁመናው ሲታይ ከማንኛውም እኩይ ተግባር እና ግድፈትም በፍጹም ሁኔታም የተከለከለ ነው። ከዚህ በላይ ትንግርት የለም፤ ከዚህ በላይ ጨዋነት የለም፤ ከዚህ በላይ ትእግስት የለም። ዓለምን ያስተማረ ተጋድሎ ነው ያደረጉት፤ በጸጥታ – በሰላማዊ ሁኔታ፤ በሥልጡን መንገድ። የሰላም ሐዋርያ ናቸው የኛዎቹ የኢትዮጵያ የእስልምና እምነት ተከታዮች። እኛ መተርጎም – ማንበብ – ማመሳጠር እምንችለው ያዬነው የሰማናውን የኖርንበትን እውነት ነው። እርግጥ ነው ነገ ተነገ ወዲያ በተዋህዶ እምነት አደባባዮች፤ ቅዱስ ሥፍራዎች „አክራሪዎች ጥቃት ሰነዘሩ – አቃጠሉ“ የሚጠበቅ ነው የወያኔ ቅይጡ ድራማ …. ግን እኛ እራሳችን እናውቃለን ስንል ወደ ውስጣችን የማዬት አቅማችን የጫካ ተምክሮ በምንም ቀመር ሊቀማን አይገባም። በፍጹም። ወያኔ ዋልድባን በትዕቢት ሲደፍር አላፈረም – አሸባሪስ እሱ።

ሌላው የተነሳው ዬኩርድሽ ጉዳይ ነው። እኔ አንድ ጥንድ፤ ሁለት ኩርድ የራዲዮ ጋዜጠኛ ጓደኞች አሉኝ። ጥንዶቹ ኢራናውያን ናቸው። ሃይማኖት የላቸውም። ሃይማኖታቸን አውነት ነው ባዬች ናቸው። አሊ የጦር መኮነን ባለቤቱ ኤሊ ደግሞ የዋና መምህር ነበረች። የእያንዳንዱን ሀገር የስደት ፖሊሲ ጠንቅቀው ያውቃሉ። ሌላው ቀርቶ ሃያላን መንግሥታት ይፋ የማያደርጉትን ስበስባ ሳይቀር። ቋንቋ የምትማረው እሷ ብቻ ናት። እሷ የተማረችውን ቤት መጥታ እሱን ታስተምረዋለች። ፈተና ላይ እኩል ይቀመጣሉ። ሁለቱም ያልፋሉ። የተሰደዱት ብትን አፈር አጥተው ነው። እውቅና ያገኘ ዜግነት የላቸውም። ስለዚህ ኩርድሽን እንዳለ „በእስልማና አሸባሪነት መመደብ“ አግባብ አይመስለኝም። ሃይማኖት የሌላቸውም አሉና። ሌላው ሁለቱም ጋዜጠኛ ኩርድሾች ጓደኞቼ የቱርኪ ኩርድ ናቸው። እስልማና ሃይማኖታቸውን ማዕከላዊ በሆነ መልኩ የተቀበሉ፤ ጫካ ያሉትን ሴት ታጋዩች የሚደግፉ ናቸው። በነገራችን ላይ የጫካውን ትግል ሴቶች፤ የሎቪውን ተግባር ወንዶች ያካሄዳሉ። ቃል ሊገልጻቸው የማይችሉ በርካታ ሴት ጀግኖች አሏቸው። ልብሳቸውም ፋቲክ ነው። የሚታገሉት ለብሄራዊ ማንነት ነው። ስለዚህ እንዲህ ባለ የሃቅ ማህደር ውስጥ በጅምላ መፈረጅም ወንጀል ይመስለኛል። ምክንያቱም ተጋድሏቸውን የሴቶችን ጥንካሬ ስለምወደው ህይወታቸውን ቅርብ ብዬ ጠረኑ አዬዋለሁ። ንፁህ የነፃነት ትግል ነው። ንፁህ የማንነት ጥያቄ ትግል ነው። ለዛውም ሴት አርበኞች የሚመሩት … ስለዚህ የሚሰነዘሩ ወቀሳዎች አድራጊዎችን ነጥሎና በትኖ ማቅረብ ግድ ይላል። ስለ ኩርድሽ ከተፃፈ ንጹሁ የነፃነት ፍላጎት ሆነ ራዕይ ያላቸውንም አብሮ ማዬት የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ህሊናችን ሚዛን ከኖረው። ይህን መለዬት ስላልተቻለ ብዙዎቹ አንገታቸውን እንዲደፉ ተገደዋል። መሰረታዊ ዕለታዊ የመኖር መብታቸውን እንኳን ለመጠዬቅ አቅም ሲያንሳቸው ይታያል። በወል ስለተፈረጁ። ይህ ደግሞ ለነገ አዲስ ዓለም ሆነ ለቀጣዩ ትውልድ ጠንቅ ይመስለኛል እኔ በግሌ። የስጋትም ጆንያ …  ለምሳሌ በሚሊተሪ አካዳሚክ ሙሩቅ የነበረው የመጀመሪያው ቱርካዊው ፕሬዚዳንት ሙስጦፋ ከማል ዘመናዊቷን ቱርክ የፈጠረ ከቅርቤ ብነሳ ዬሲዊዘርላንድ ሴቶች በፓርላማ እኩል የመሳተፍ መብት ሳይኖራቸው፤ አውሮፓም በብዙ ነገሮች ሥልጡን ሃሳብ የማቅረብ አቅም ሳይኖረው ነበር ቀድሞ የእስልምና እምነት ተከታይ ሴቶችን በድምጽ የመሳተፍን ነፃነት ያወጀው። ሌሎችንም ጉዳዮች እንዲሁ በሚዛናዊነት ያዬው በጣምም ተወዳጅና ሥልጡን የዘማናዊ ቱርክ አባትም እንደሆነ፤ ዘመንን የተከተለ ዕሳቤ የነበረው እንደሆነ፤ የሀገሩ ልጆች የእስልምና ተከታዮች ይናገሩለታል፤ ጥረቱንና ውጤቱን ማንበብ ለምትፈልጉ – ሊንኩ ይሄውና  http://www.bbc.co.uk/history/historic_figures/ataturk_kemal.shtml

http://www.biography.com/people/mustafa-kemal-ataturk-20968109#military-career

http://simple.wikipedia.org/wiki/Mustafa_Kemal_Atat%C3%BCrk እንዲህ ዓይነት ዶክተሪን የሚከተሉም  ዬዕምነቱ ተከታዮች በብዛት አሉ።

በተጨማሪነት –  በአንድ የሰብዕዊ መብት አስከባሪ ማህበር ልምምድ አደርግ ነበር። ተግባሬ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ነበር። ማህበሩ ወይንም ድርጅቶች ወደ 3000 የሚጠጉ የፌስ ቡክ አባላት በመላ ዓለም አሉት። በመላ ዐለም የሚገኙ ከ50% በላይ ጾታ ሳይለይ የእስልምና እምነት ተከታዮች ተሳታፊዎች ናቸው። ሁለት ነገር ደነቀኝ። አንዱ ዘመኑ የፈጠረላቸውን ሥልጣኔ የመጠቀም አቅማቸው ሙሉዕነት ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የሰብዕዊ መብት መረገጥ ያገባናል፣ ይመለከተናል ብለው ንቁና ብቁ ተሳትፎ ማደረጋቸው፤ ይህ እንግዲህ በግሌ ደመና የለበሰውን የዓለምን የተስፋ ጉዞ ብርሃናማ ያደርገዋል የሚል ጉልበታም ተሰፋ በግሌ አሳድሮብኛል።

በሌላ በኩል እንደ ወንጀል የታዬም ተያያዥ ሃሳብ አንብቤያለሁ። አምስቱ አብዬተ ቤተክርስትያን ጋር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ስምምነት አላት። እኔ ከዚህ ሲዊዝ ቀደም ባለው ጊዜ አዲሱን ዓመት ቅዱስ ዮኋንስን እናከብር የነበረው ከእነሱ ጋር በአንድ ላይ ነበር። በተመሳሳይ ቀን፣ በተመሳሳይ ዶግማና ቅኖና ስለሆነ። እና እስልምና እምነት ካለው ጋር መቀራረቡ – መጋባቱ – መወዳጀቱ ምን ክፋት አለው? አፍጋን አግብተው በፍቅርና በሰላም ልጆች ወልደው የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ሙስሊሞች እንዳሉም ሃሳቡን ላቀረቡት ጸሐፍት ወንድሜ ላስታውስ እሻለሁ – በአክብሮት።  በተጨማሪ …. እኔ እራሴ የአርመን ጓደኛ አለችኝ። ስትሄድ – ስትሄድ ወደ ሃገሯ ሜሮን – አድህኖ ስዕላትን ታመጣልኛለች …. በእምነት አንጻር ከሌላው የተዋህዶ ኦርቶዶክስ ኢትዮጵያዊ ወንድማና እህቴ ጋር እኩሌ ናት። ሰው መሆን ብቻ እኮ ነው ተፈጥሮ የሚጠይቀን። እንዴት ያለ ነገር ነው …. ዓይናችን ወደ ፍቅርና ወደ ማስተዋል ብናመራው ምን አለበት …. ? ? !!

እርግጥ ከዚህ ማዕቀፍ የሚያፈንግጡ የሉም ማለት አንችልም። የእናት ሆድ ጅንጉርጉር ነውና። ግን ሁልጊዜም እውነት ያለበት መንገድ አሸናፊ ነው። ወደ እኛ ይመጣሉ። ደግሞ በአንድ እንቅስቃሴ ወይንም ፓርቲ ውስጥ መታዬት ያለበት የድርጅቱ ሁለንታና ወላዊ መንፈስ እንጂ ነጠላዊ ግለሰባዊ መሆን አይገባውም። እንደ እንቅስቃሴ „ድምጻችን ይሰማ“ እሳከሁን በሳለፈው የተጋድሎ ታሪክ ከግድፈት ነፃ ነው። የ40 ዓመቱ የወያኔ ህልም እንዴት ውሃ በልቶት እንደ ቀረ አያችሁት አይደል። ሁለቱም ሃይማኖቶች በወያኔ ሃርነት ትግራይ የደረሰባቸው ጥቃት የአውሮፓው ኮሚሽን የውሳኔ ንድፍ ሙሉ ዕውቅና ነው የሰጣቸው። የኖርንበት፤ ያደግንበት፤ ያለንበት ሃቅ የእኛ ከእኛ ለእኛ የሆነ ነው። ምንም ዓይነት ሰው ሰራሽ ክትር ውስጣችን ከውስጣችን ነጥሎ ጎርባጣ የማድረግ አቅም የለውም። ኢትዮጵያዊነት ጠበቂ አምላክ አለው። አንድ ኩታ — ፈትሉ ተነጥሎ ወይንም ዘሃው ተነጥሎ ኩታ ሊሆን ከቶውንም አይችልም።

ሌላው ስለታሪክ የተጻፈም አይቻለሁ። ታሪክን ለማጣቀሸነት ማንሳት ከተፈለገ በሌላኛው ሃይማኖት ላይም የጠፋውና የወደመው ጉዳይ እኩል መነሳት አለበት። ዓፄዎቹም ከተነሱ እንዲሁ።  ታሪክ በአንድ የወቅት ማዕቀፍ ውስጥ መልካምም፣ መልካም ያልሆኑ  አዎንታዊና አሉታዊ የህዝብ የተግባር ተሳትፎ ዕድሜ ጠገብ ሲሆን ነውና ታሪክ የሚባለው። ጥቃቱ የዘለለው ሃይማኖት አልነበርም። እኩል መግለጽ ካልተቻለ ሚዛኑ ወልጋዳ ያደርገዋል። በዚህ ዙሪያ መቆፈር ስለማልፈልግ ብቻም ሳይሆን ጠቃሚም ስላልሆነ ወደ ዛ መሄድ አልሻም። ለእኛ ትውልድ የተሰጠው ፈተና አባቶቻችን ተወልደው፤ ተጋብተው፤ ተጎራብተው፤ ጡት ተጣብተው – ተደማምጠው በአንድነት በመከባበር ያቆዮዋቸው ሃይማኖቶች በነበራቸው ትውፊታዊ – ስምረታዊ ጉዞ እንዲቀጥሉ የማደረግ የአደራ ዕዳ አለብን። ለዚህም „የድማጻችን ይሰማ“ ሰላማዊ – ብልህ እንቅስቃሴ አደራ በይ እንደማይሆን ከነሙሉ መንፈሴ ሆኜ መናገር እችላለሁ። እንዲያውም ለእኔ ለዘመነ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ክትምት የበኩሉን ድርሻ የተወጣ፤ ለሰማያዊ ፓርቲ ውጤታም እንቅስቃሴ አቅጣጫ የነደፈ – ፋና፤ ለነፃነት ትግሉ በታማኝነት አቅምን የገነባ፤ አቅምን በአግባቡ ያሰተዳደረ የዘመናችን አብነታዊ የተጋድሎ ታሪካችን ነው። የናሙናነት ሂደቱን አስተምህሮቱን ብንከተል እናተርፋለን። አግዞናልና።

የወያኔ ደጋፊዎች የሚሉትን እኛም የምንደግመው – የምንሰልሰው ከሆነ በባርነት እዬተዘለዘሉ ተደፍሮ ለመኖር ከመፍቀድ ውጪ ሌላ ሊባል ከቶውንም አይችልም። „የድምጻችን ይሰማ“ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያዊነት ከላይ ያደረገ አንቱ የትግል አዝመራ ነው – ለእኔ ለሥርጉተ። በአጋጣሚ በዚህ ጉዳይ እዬፃፍኩኝ ስለሆነ  – አከብራቸዋለሁ – እውዳችዋለሁም መሪዎቹንም  ሆነ ታዳሚዎችንም። እኔ ያደግኩት የሠርጉ ድንኳን እኩል ተሠርቶ አንዳንድ ጊዜም በአንድ ግድግዳ ሁለት ዳስ ግብዣ ሲደረግ ሲሆን ጭፈራው ላይ ደግሞ በጋራ ከትሞ ደስታን ሲኮመኩሙ ነው። ያልተፈጠረ፣ ፈጽሞ የእኛ ያልሆነ ቁጭላ ሃሳብና ቁሮ ጠንቅ እያመጣችሁ ትውልዱን አትበጥብጡት – እባካችሁን።

ሌላው ግርም ያለኝ ጉዳይ ደግሞ „የISIS ቡድን ነፍሰ ገዳዩ ጆን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የቅርብ ጓደኛ አዲስ አበባ ውስጥ ታስሯል መባሉ እያነጋገረ ነው“ የሚለው ነው። እራሱ ኢትዮጵያዊ ቢሆንስ እንኳንስ ጓደኝነት?! ኔት ይፈለጋል – ለውንጀላ። እኔ ለጓደኞቼ ወይንም ጓደኞቼ ለእኔ በሁሉም ነገር ምቾት አይኖረንም። በሚያመሳስለን ጉዳይ ብቻ እንጂ። በጥልቀትም ሲታይ አሁን እናት ቅድስት ትሬዛ በምግባራቸው እንጂ በሀገራቸው አይታወቁም። ኪንግ ማርቲ ሉተርም እንዲሁ። አንድ ያልተመቼ ነገር ሲፈጠር እህ „ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ አማራ፣ እስላም፣ ተዋህዶ፣ አልፎ ተርፎ የትዳር አጋሩ የብሄረሰብ የመንደር ነገር ተነቅሶ ይነሳል“ ዎህ! ልበል። ያደክማል። ለፍቅር ደግሞ ደንበር ተሰራለት። ፈጽሞ የማይገናኙ ነገሮችን በማያያዝ መንፈስን – ማወክ። ለነገሩ አሁን ደግሞ „አይሁዳውያንንም“  በሚመለከትም ያዬሁት ጹሑፍ አለ። ጸሐፌ አቶ ዮፍታሄ ጠላት አናብዛ በማለት ሰፊና ጥልቅ እስከ ክፍል 7 ድረስ የዘለቀ ትንተና … በሌላ በኩል ደግሞ ጠላትነትን ማምረት? የወያኔ መንደርተኝነትን ትርትር አልበቃ ብሎ የኛ መንፈሰም ለዚህ ተጠቂ ሆኖ ቁልቁል። በምን ቋንቋ ልንግባባ እንደምንችል እኔ በግሌ አላውቀውም፤ የባቢሎን ዘመን ዙራአንባ ሁነናል ከቶ ልበልን? አዝናለሁ … በርካታ አይሁድ እምነት ተከታዮች ሆኑ፣ የዘር ሐረግ ያላቸውም በነፃነት ትግሉ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉ እራሳቸውን ለመሰዋትም የተዘጋጁ አሉን። ኢትዮጵያዊነት አኮ ዝንቅ ቅይጥ ግን ቀለማም ውብ ማንነት ነው። ከወጡ ይልቅ ቅልቅሉ ይበልጣል። ድምቀታችንም ይሄው ነው። ማማራችንም! ለማንኛውም እንዲህ ያለው ትንተና ሲመጣ ምን እንደሚሰማቸው እነሱ አላውቅም … ለእኔ ግን ጎርባጣ ነው። ያለብን ችግር አልበቃ ብሎ አዳዲስ ነገር እዬፈጠርን ያን የተዛባ ዕይታ ለማረቅ አቅምን መሻማት። ራዕያችን ማራቅ አቅማችን ማባከን … እንጃ …. ያደክማል።

ምርቃት አስተያዬት „ለድምፃችን ይሰማ“

  1. በተፃራሪ ወገን የሚቀርቡ ሃሳባዎችን ሳያባክኑ ክፍተቶችን መድፈን፤ ድክመት ፈላጊውና ፈብራኪው ወያኔ ተግቶ ይሠራበታልና። ስለዚህ እሱንም መቅደም ብልህነት ይመስለኛል።
  2. ፈንገጥ ብለው የሚወጡ ዝንባሌዎችን ማረቅና – ማሳተካከል። ይህን ሃሳብ ያነሳሁት በፋመ ወቅት ፓል ገብቼ የገጠመኝ ስላለ ነው። „አሜን“ በሚል ሥም ነበር የገባሁት። የኢትዮጵያ ታሪክ ሲነሳ የማድመጥ አቅም የሚነሳቸው የነፃነት ትግሉ ደጋፊዎችን አይቻለሁ። ምክንያቱም ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር በተያያዥነት የሚቀርበው የተዋህዶ እንደሚሆኑ ስለሚያውቁ ጊዜውን ሲቆርጡ ተመልክቻለሁ። ይህን እኮ አውሮፓ ላይ አንቱ ከተባለ ቤተመጸሐፍት ብትሄዱ ይገኛል። ስለምን? አውሮፓን የፈጠረ ሚስጢር ነውና። ሃብትነቱ ግን የጋራ ነው። ኢትዮጵያዊነት የዚህ ድምር ነው። ነጠላዊ ኢትዮጵያዊነት የለም። ፓል ላይ ሰው እዬተናገረ ሰዓት አይወሰንበትም። ከመናገሩ በፊት እንጂ። መመጠን እንዲችል ። ይህን ሳይ እኔ ንግግር ላይ ያለው ይጨርስና በቀጧዩ ተናጋሪ ላይ ብተውስኑ ጥሩ ነው ስላልኩ፤ ባውንስ ተደረኩኙ። ሥሜም የሰጠ ነው „አሜን“ ሆን ብዬ ነበር ይህን ሥም ይዤ የገባሁትም፤ ግራ ቀኙን ማዬት አሰኝቶኝ።  እኔ ስለ እስልምና ሃይማኖት ትምህርት በመደበኛ ቀን  ይሰጥ ነበር። ቁጭ  ብዬ አዳምጣለሁ። ማወቅ ምን ይጎዳኛል። ወደ ዋናው ነጥቤ ስመለስ የቀደመው ኢትዮጵያዊነት ታሪክ ሃብትነቱ የእኔም ነው የማለት መጠነ ሰፊ መንፈስ ኮትኩቶ ማሳደግ ይገባል።  ጭንቅላት አንድ ነው።  ጭንቅላት ውስጥ ከሰው ምርምር በላይ የሆኑ ውስብስብ ተግባሮችን የሚከውኑ ዬተፈጥሮ ጸጋዎች አሉት ግን አንድ  ጭንቅላት ነው። ኢትዮጵዊነት ማለት ጭንቅላት ነው። ብብዙ ሊከሰቱ ሊታዮ በማይችሉ መስተጋብራዊ ጥምረቶች የተዋኻደ። ሰው ሰራሽም አይደለም – ኢትዮጵያዊነት።

ማሰርጊያ ሃሳብን መግለጽ፤ ስጋትን መግለጽ መልካም ቢሆንም አሁን ላለው የዘረኛ አገዛዝ በህይወታቸው ግፍና በደል ለሚሰራባቸው የእስልምና ሃይማኖት አቨው እስረኞቻችን ሆነ ለወላዊ የነፃነት ተጋድሎ የጋራ ትግል አካሄዱ በሉት ጥናታዊ ትንታኔው ኪሳራ እንጂ ትርፍ አይኖረውም። ዘመን – ጊዜ –  ሰዓት – ደቂቃ መደመጥ አለባቸው። ወገናዊነቱ ደግሞ ለሚበልጠው ብሄራዊ ማንነት መደፈርና በባርናት ላለመኖር አሻም! በቃን! ለማለት በሚስችሉ ሁነቶች ላይ ማተኮር አለባቸው።  እስልምና ሲደፈር እኮ ኢትዮጵያዊነትም ተደፍሯል ቀመሩ ይሄ ነው – አሁንም ለእኔ። እንዴት ተደርጎ በደም ውስጥ ያለውን ውሃ ከደሙ መለዬት ይቻላል? ይቻላልን?  —-

እኔ እኔን ሳምነው ኢትዮጵያዊነት እኔን ያምነኛል። ኢትዮጵያዊነት በእኔ ላይ እምነቱ ሲጥልብኝ ደግሞ የምለውን ሆኜ ለመገኘት እንቅፋቱን ሁሉ አሸንፋለሁ። ማሸነፌ ብቻውን በቂ ስለማይሆን በውስጡ – እሰክናለሁ። „ድምፃችን ይሰማም“ እርገቱ ከማህተሙ ከኢትዮጵያዊነት ሥጋና ደም ላይ ነው። የእውነት መጀመሪያውም መጨረሻውም እውነት ነው። የዘመኑ ወጣቶች ካዩት ተጨባጭ ሁኔታ ተነስተው „ለድምጻችን ይሰማ“ ያላቸውን አድናቆትን ክብር በገፍ እንዲሰጡ በትህትና አሳስባለሁ። ዛሬ ያሉት አዲስ ትውልዶች ከእኛ የተሻለ ብልህነት አብዝቼ አይባቸዋለሁና። ለባርነት አልተገዛነም ሲባል እኮ በዬትኛውም የጦርነት አውድ ሁሉ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል ማለት ነው። ይህ ማለት ዬእስልምና ሃይማኖት ልጆች የታሪኩ ባለ ሙሉ ድርሻ ናቸው ማለት ነው። አካላችን – ትንፋሻችን – ጠረናችን – ወዛችን ጸዳላችን – ውበታችን – ጌጣችን ናቸው። ቀለማሙ ማንነታችን ዬድምቀት ሚስጢሩ ይህ ነው። ያደላቸው ሀገሮች ለቀደምት ታሪካቸው ጥንግ ድርብ ማልበስ ብቻ ሳይሆን የእነሱነታቸው መሠረት ስለመሆኑ ተገንዝበው በጣም እርቀው የምርምር ተግባራት ይከውኑበታል። የሚሰጡትም ክብር ከምንገምተው በላይ የሃይል ማመንጫ ማዕከል ነው። ይኼው እምነታቸው በመሆን ስለሆነ ርጥቦቹ ለእኛም በቅተው – አትርፈውናል። እምነቱንም ማንነቱንም ሆነው ስለሚገኙበት። ከረድኤቱም ትውልዱን ያስመርቁበታል። የእኛ ደግሞ – ማክሰል። በመጨረሻ የራዲዮ ድርጅታችን ሰፊ የሆኑ የቴክኒክ ችግሮች ለመፍታት እደሳት ላይ ስለሆነ፤ ለመሥራትም ሰፊ የሆኑ የተክኒክ ዝንቅ ችግሮች ስላሉበት፤ አንዳንድ ጊዜ ለችግርም እረፍት መስጠት ስለሚያስፈልግ ነባሮቹ ብቻ ነው የሚደገሙት እስከ ሚያዚያ መጨረሻ። ስለዚህ ይቅርታችሁን እጠይቃለሁ። በተረፈ የኔዎቹ – ቸር እንሰንብት።

 

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

 

 

 

The post እኔ „እኔን“ ከጠረጠረ – በእኔ ውስጥ „እኔ“ የለም ማለት ነው – ከሥርጉተ ሥላሴ appeared first on Zehabesha Amharic.

የዛሬ የኢሳትን የመጀመሪያ ዜና ሳይ በትዝታ ወደ ኋላ ነጐድኩ፣ ( ቪሽየስ ሰርክል) –ከኤርሚያስ ለገሰ

0
0

ermias copy
” ሀሎ አቶ ሽመልስ ከማል?”
” አዎ! ማን ልበል?”
” ጤና ይስጥልኝ ፣ የብሉንበርግ ጋዜጠኛ ሚስተር እከሌ ነኝ።”
” እሺ ሚስተር እከሌ! ምን ልርዳህ?”
” የእንግሊዝ መንግሥት በጋዜጠኞችና ተቃዋሚዎች ላይ መንግሥትዎ ጫና ያደርሳል በማለት ልትሰጥ የነበረውን ወደ አንድ ቢሊዬን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ አግዳለች የሚል ዜና ደርሶን ነው። በዚህ ላይ የመንግስትዎ ምላሽ ምንድነው?”
ሽመልስ ፣ ” ስብሰባ ላይ ነኝ። ትንሽ ቆይቼ እደውልልሀለው።”
” እሺ ጌታዬ! ምላሾትን እጠብቃለሁ።”
ስልኩ ተዘጋ።
ሽሜ እየሮጠ ወደ ሁለተኛ ፎቅ ሬድዋን ሁሴን ጋር ሄደ። የብሉንበርግ ጋዜጠኛው የጠየቀውን ነገረው። ሁለቱም ለትንሽ ሰአት በአርምሞና ጥልቅ ትካዜ አሳለፋ። ከደቂቃዊች በኃላ ሬድዋን እንደ ሐሳብ አፍላቂ ሆኖ፣
” ሽሜ ለምን ለድርጅቱ አንደውልለትም?” በማለት ጠየቀው።
ሽሜ አንገቱን ከላይ ወደ ታች በመነቅነቅ ተስማማ። ሬድዋን ኢንተርኮሙን በጣቶቹ አንቀጫቀጨ።
” ሀሎ ”
” ሀይ በረከት እንዴት ነህ? ሬድዋን ነኝ። ሽሜም አጠገቤ አለ እየሰማህ ነው።”
” እሺ! እናንተ ሞገደኞች። ምን አዲስ ነገር አለ። ምን ልታዘዝ?” እየሳቀ በታዛዥነት ውስጥ ሆኖ ጠየቃቸው።
ሬድዋን ሽሜ የነገረውን ቃል በቃል ነገረው። አስከትሎም፣
” ጋዜጠኛው እየጠበቀ ስለሆነ ምን ምላሽ እንስጠው? ”
በረከት በቁጣ ውስጥ ሆኖ፣
” አይደለም እርዳታ ኤምባሲያችሁንም ዘግተው ጥርግ ማለት ይችላሉ ብላችሁ ንገሩት።”
ሬድዋን የድል አድራጊነት መንፈስ ተላብሶ፣
” እውነትህን ነው። ለእነሱ እርዳታ ብለን በዴሞክራሲ ጉዟችን ላይ አንደራደርም ። ጥርግ ማለት ይችላሉ።” በማለት በኩራት መለሰለት።
በመሀል ሽሜ ጣልቃ ገብቶና ድምፁን ከፍ አድርጐ ፣
” እነዚህ ኒዬ ሊብራሎች ከሃገራችን ኪራይ ሰብሳቢዎች ጋር በመቀናጀት እንከን የለሹን የምርጫ ሂደት ጭላሸት ለመቀባት እየተሯሯጡ ስለሆነ ልክ ልኩን እነግራቸዋለን። ” በማለት እየተናገረ ሳለ በረከት አቋርጦት ፣
” ሬድዋን ! ሽሜ አንድ ጊዜ አስቸካይ ስልክ መጣብኝ ። ከአስር ደቂቃ በኃላ መልሼ እደውልና እንቋጨዋለን። እዛው ጠብቁኝ።” በማለት ስልኩን ዘጋው ።
ሬድዋን እና ሽሜ ሲጋራቸውን ለኩሰው ቦምብ የሆነ ምላሽ እንዴት እንደሚሰጡ መነጋገር ጀመሩ። ውሻ ከዳገት የማይጐትታቸው የእንግሊዘኛ ቃላት መፈለግ ጀመሩ። አስሯ ደቂቃ ደረሰችና የበረከት ስልክ ተንጫረረች።
” ሀሎ ሬድዋን! ሽሜ! አላችሁ?”
” አለን፣ እየጠበቅንህ ነው” ሬድዋን ፊቱን ወደ ኢንተርኮሙ አዙሮ ምላሽ ሰጠ።
” ጥሩ! አሁን ከጓዶች ጋር አውርተን ነበር። ለእነዚህ ደደቦች ምንም አይነት ምላሽ መስጠት እንደማያስፈልግ ተግባብተናል። ምላሽ ስንነፍጋቸው እንደ ተናቁ ስለሚቆጥሩ ይበልጥ ይንጨረጨራሉ። ስለዚህ ለጋዜጠኛው ምላሽ አትስጡ። ስልኩንም አትመልሱ። ከዛ ይልቅ ” የልማታዊ ዴሞክራሲ ጉዞአችን በጣልቃ ገቦች አይደናቀፍም” የሚሉ የተለያዩ ጱሁፎች አዘጋጁና ለአዲስ ዘመን፣ ለሪፓርተር ፣ ለሰንደቅ፣ ኢትዬ ቻናልና ለሚሚ ስብሀቱ ላኩላቸው። ለአይጋ ፎረም እኔ አዘጋጅቼ ነገ እልክላቸዋለው። በተረፈ ለሁሉም ተቋማት ህዝብ ግንኙነቶች ኦረንቴሽን ስጧቸው።በአስቸኳይ ለዶክተር ቴድሮስ አድሐኖም ደውሉና የትኛውም ኤምባሲ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዳይሰጥ በጥብቅ ይንገራቸው። ይቅርታ ሌላ አስቸኳይ ስልክ መጣብኝ ነገ እደውላለሁ። እንዳልኳችሁ አድርጉ ። ቻው! ቻው!።”
ስልኩ ተዘጋ። ነገም ኡደታዊ እንቅስቃሴው በዚህ መልኩ ይቀጥላል። ስንት አመት እንኖር ይሆን??

The post የዛሬ የኢሳትን የመጀመሪያ ዜና ሳይ በትዝታ ወደ ኋላ ነጐድኩ፣ ( ቪሽየስ ሰርክል) – ከኤርሚያስ ለገሰ appeared first on Zehabesha Amharic.


ሰማያዊ ፓርቲ ቅስቀሳ እንዳያደርግ እንቅፋት እየተፈጠረበት ነው

0
0

• የሶዶ ፖሊስ 8 የሰማያዊ ዕጩዎችን በማሰር ቅስቀሳውን አስተጓጉሏል

• የጅማ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ተዘርፏል

• ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ወደ ህዝብ እንዳይደርስ ሆን ተብሎ የተቀየሰ ስልት ነው›› አቶ ስለሽ ፈይሳ

blue_party_ethiopia101370869814 (1)ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቅስቀሳ እንዳያደርግ በፖሊሶች ክልከላና ወከባ እየደረሰበት እንደሚገኝ የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ጉዳይ ኃላፊና ም/ሊቀመንበሩ አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ዛሬ መጋቢት 5/2007 ዓ.ም ፓርቲው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቅስቀሳ ያደረገ ሲሆን በባህርዳርና ወላይታ ዞን ፖሊስ የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር ቅስቀሰውን ማደናቀፉን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

ዛሬ ሰማያዊ ፓርቲ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ቅስቀሳ በሚያደርግበት ወቅት የከተማው ፖሊስ ‹‹የምርጫ ቅስቀሳ አልተጀመረም›› ብሎ ያዋከበ ሲሆን የፓርቲው አመራሮችና አባላት ቅስቀሳ መጀመሩን ገልጸው ስራቸውን እያከናወኑ በነበሩበት ወቅት ‹‹ህገ ወጥ ሰላማዊ ሰልፍ›› አድርጋችኋል በሚል ሌላ ክስ 8 የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችንና ሌሎች አባላትን በማሰር ቅስቀሳውን እንዳደናቀፈ የወላይታ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ታደመ ፈቃዱ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ በባህርዳር ከተማ ፖሊስ ‹‹በሞንታርቮ ለመቀስቀስ ፈቃድ ስላላመጣችሁ መቀስቀስ አትችሉም፡፡›› በሚል ፓርቲው ሊያደርገው የነበረውን የምርጫ ቅስቀሳ እንዳደናቀፈ የፓርቲው የምዕራብ ጎጃም ዞን ጊዜያዊ አስተባባሪ አቶ አዲሱ ጌታነህ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ‹ለምን ትከለክሏቸዋላችሁ?› በሚል ህዝቡ ፖሊሶቹን በማፋጠጡ በድምፅ መቀስቀስ ባንችልም በህዝቡ ድጋፍ የቅስቀሳ ወረቀቶችን በማሰራጨት የተሳካ ቅስቀሳ አድርገናል›› ሲሉ አቶ አዲሱ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በዚህ ወቅት ቅስቀሳ ለማድረግ ምንም አይነት ፈቃድ እንደማያስፈልግ የገለፁት አቶ ስለሽ ፖሊስ የሚፈጥረው እንቅፋት ሆን ተብሎ ሰማያዊ ወደ ህዝብ እንዳይደርስ የተቀየሰ ስልት ነው ብለዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም ‹‹የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን በመሰረዝ ፓርቲው ምርጫው ላይ የሚፈጥረውን ጫና ለመቀነስ ጥረዋል፡፡ ይህ አልበቃ ሲልም የቅስቀሳ መልዕክቶቻችን በተደጋጋሚ በሚዲያ እንዳይተላለፉ እያደረጉ ነው፡፡ አሁን ደግሞ ወደ ህዝብ እንዳንደርስ በህገ ወጥ መንገድ በፖሊስ ማስቆም ጀምረዋል›› ብለዋል፡፡

በሌላ ዜና የጅማ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ባልታወቁ ግለሰቦች መዘረፉን የምርጫ ጉዳይ ኃላፊው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹በ02/07/07 ሁለት ሰዓት ላይ አራት ግለሰቦች ጽ/ቤቱን በመስበርና የጽ/ቤቱን ጥበቃ አስፈራርተው በማባረር ለቅስቀሳ የተላከ 6 ሺህ ኦሮምኛ በራሪ ወረቀት እንዲሁም 3 ሺህ አማርኛ በራሪ ወረቀት፣ አንድ የፎቶ ካሜራ፣ አንድ ባነር፣ ለሸካ ዞን ሊላክ የተዘጋጀ 5 ሺህ በራሪ ወረቀት፣ 50 ፖስተር፣ አንድ የእጅ ሜጋ ፎን፣ ሁለት ባነር፣ በርካታ ጋዜጦችና መጽሔቶች ሲዘርፉ የጽ/ቤቱን ኮምፒውተርም ሰብረዋል›› ሲሉ ኃላፊው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

The post ሰማያዊ ፓርቲ ቅስቀሳ እንዳያደርግ እንቅፋት እየተፈጠረበት ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

አንድ ሚሊዮን የቴሌቪዥን ባለንብረቶች በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የባለቤትነት ክፍያ መፈጸም ሊጀምሩ ነው

0
0

tv_guideየኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ኤጀንሲ ከዚህ ቀደም ሲሰበስብ የነበረውን የቴሌቪዥን ባለቤትነት ምዘገባና ፈቃድ ክፍያዎችን እንዲሰብስብ፣ ከክፍያ ለሁሉ ኩባንያ ጋር ስምምነት አደረገ፡፡

በዚህ ዓመት ብቻ ከአንድ ሚሊዮን ባለንብረቶች 60 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ እንደሚሰበስብ ይጠበቃል፡፡

መጋቢት 2 ቀን 2007 ዓ.ም. በተደረገው ስምምነት መሠረት ሁለቱን ተቋማት ጨምሮ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሦስትዮሽ ስምምነት ፈጽመዋል፡፡ ከመጋቢት 8 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው የቴሌቪዥን ባለቤትነት ፈቃድና ምዝገባና ዕድሳት ክፍያዎችን በክፍያ ለሁሉ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በኩል ሲሰበሰብ፣ ዓመታዊ የክፍያ መጠኑ በእያንዳንዱ ቴሌቪዥን 60 ብር ሲሆን ክፍያ ለሁሉ ኩባንያ ከእያንዳንዱ ቴሌቪዥን ክፍያ ላይ ለአገልግሎቱ አሥር ብር እንደሚከፈለው፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስጂያጅ አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም ገልጸዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ የግብይትና የማስታወቂያ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰናይት ኃይሌ እንዳስታወቁት፣ በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲና በኮርፖሬሽኑ መረጃ መሠረት በአዲስ አበባ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ቴሌቪዥን እንዳላቸው ይገመታል፡፡ በመሆኑም ከእነዚህ ባለንብረቶች በዚህ ዓመት በሚደረግ የዲጂታል ምዝገባ የታሰበው ገቢ ሊገኝ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ባለፈው ዓመት ከቴሌቪዥን ባለቤትነት ፈቃድና ምዝገባ 13 ሚሊዮን ብር የሚገመት ገንዘብ መሰብሰቡም ታውቋል፡፡ በዚህ ዓመት 60 ሚሊዮን ብር እንደሚሰበስብ ይጠበቃል፡፡

የቴሌቪዥን ባለንብረትነት ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ ሒደቱን ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለማምጣት የአንድ ዓመት ጊዜ መፍጀቱን የገለጹት ዳይሬክተሯ፣ የቴሌቪዥን ባለንብረትነት ክፍያዎችን በማይከፍሉት ላይ ከገንዘብ ቅጣት ባሻገር እስከመውረስ የሚደርሱ ዕርምጃዎች እንደሚወሰዱ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከ40 ዓመታት በፊት በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ከባለንብረቶች ዓመታዊ ክፍያ እየሰበሰበ ሲሆን፣ ወደፊት የግል የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሚመጡበት ወቅት ይህ ሁኔታ ሊለወጥ እንደሚችል አቶ ብርሃነ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ በአንዳንድ አገሮች እንዲህ ያለው የባለንብረትንት ክፍያ የሚጠየቀው የመንግሥት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሌሎች የገቢ ምንጮች የሌሏቸው መሆኑን ታሳቢ በማድረግ እንደሆነ፣ እንደ ቢቢሲ ያሉ የእንግሊዝ የመንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ዋቢ ይደረጋሉ፡፡ በአንፃሩ በኢትዮጵያ ብቸኛው የአገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ከማስታወቂያ ከፍተኛውን ገቢ የሚያስገባ ከመሆኑ ባሻገር፣ የባለቤትነት ዓመታዊ ክፍያዎችን በመሰብሰብም አርባ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡

ክፍያ ለሁሉ ኩባንያ በአዲስ አበባ በከፈታቸው 34 የክፍያ ጣቢያዎች የውኃ፣ የኤሌክትሪክ ኃይልና የቴሌኮም አገልግሎት ክፍያዎችን ለመንግሥት በመሰብሰብ ሥራውን የጀመረ ሲሆን፣ በወር 600 ሺሕ ደንበኞችን በማስተናገድ 1.2 ሚሊዮን የአገልግሎት ክፍያዎችን እያስተናበረ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት በአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም አማካይነት ለ20 ሺሕ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች ቴክኖሎጂ አገዝ ቅርንጫፍ አልባ የባንክ አገልግሎት በሙከራ ደረጃ እየሰጠ ይገኛል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

The post አንድ ሚሊዮን የቴሌቪዥን ባለንብረቶች በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የባለቤትነት ክፍያ መፈጸም ሊጀምሩ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

የዲያቆን ዳንኤል ስሜታዊ ትንተናና መሬት ላይ ያለው እዉነታ ! ክፍል 2 –ከአብዱላህ

0
0
daniel-kibret-300x207

ዲያቆን ዳንኤል

ዲያቆን ዳንኤል በዚህ በታሪክ ላይ ባተኮረው ንግግራቸው ያስተላለፉት መልእክት ኢትዮጵያዊያን ሙስልሞችን  የእስልምና ሃይማኖትን የተቀበሉ አገር በቀል ህዝቦች ሳይሆኑ ከውጭ በመምጣት ቀደም ሲል ኢትዮጵያ ተብላ ትጠራ የነበረችን ሃገር ድንበር ደፍረው እንደ ሰፈሩ የባእድ ህዝቦች አድርገው ነው ።  በመሆኑም እነዝህ ህዝቦች ዘመሰረቷቸውን ሱልጣነቶችን ድንበር መውረርን ተቀምቶ የነበረን ድንበር እንደ ማስመለስ ካልሆነም አገር እንደ ማቅናት በማድረግ ሃሳባቸውን አስቀምጠዋል።   በሱልጣነቶቹ ስር ያሉትን ህዝቦች መጨፍጨፍን ጠላትን እንደ መግደል ፣ የሱልጣኔቶቹ ራሳቸዉን ለመከላከልም ሆነ እንደ ዘመኑ መንግስታት ግዛት ለማስፋት ከዉጭ ሃሎች እርዳታ መጠየቅን ከታሪካዊ ጠላት ጋር በማበር አገር የማድማት ሴራ የሚል ፍቺ ሰጥተዋል።  በሌላ በኩል ግን የዛረዉን የሰሜኑን የአገራችንን ክፍል ይገዙ የነበሩ የክርስትና እምነት ተከታይ ነገስታቶቻችን ለተመሳሳይ ዓላማ  ከዉጭ ሃሎች እርዳታ ሲጠይቁ ድርጊታቸውን አገርን ከታሪካዊ ጠላት ለማዳን የተወሰደ እርምጃ እያሉ ሲያወድሱ ህሊናቸውን አልኮሰኮሳቸዉም ።                         ያቆን ዳንኤል በንግግራቸው ትኩረት ያደረጉት የዛጉየን ስረዎ- መንግስት በ 1270 በሃይል ገርስሶ እራሱን ሰለሞናዊ ብሎ  በመሰየም መንግስት የሆነው ሃይል ላይ ነበር ።  ይህ እራሱን ሰለሞናዊ ብሎ የጠራው የመንግስት ሃይል በዛሬው  የሃገራችን ሰሜናዊ ክልል ብቻ ተወስኖ የነበረውን ግዛቱን የመስፋፋት ህልም የነበረው ነበር።   የዛጉይ ስረዎ- መንግስት ግዛቱን ዝርያው በሰፈረበት ስፍራ ላይ ብቻ ከልሎ ከዚያ ርቆ ለመውጣት ምንም ፍላጎት ያላሳየ  ግዛትን የማስፋፋት እቅድ ያልነበረው ሃይማኖቱንም በሌሎች ላይ የመጫን ፍላጎት ያላደረበት በመሆኑ ከድንበሩ አጎራባች ከነበሩ ሙስሊም ሱልጣኔቶች በጋራ ተከባብሮ በሰላም ይኖር የነበረ ስርዓት እንደነበር ታሪክ ያወሳል።  በወቅቱ የነበሩት ሱልጣኔቶች በዝያን ዘመን እስልምናን በተቀበሉ በዛሬው መካከለኛ  ፣ ምስራቅ እና ደቡብዊ የአገራችን ክፍሎች ይኖሩ የነበሩ ሃገር በቀል ህዝቦች የተመሰረቷቸው ነበሩ።  እነዚህ ሱልጣኔቶች የራሳቸው ስልጣኔ ፣ የአስተዳደር ስርአት ፣ ገንዘብ ወዘተ የነበራቸው እና በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል እንደ ነበሩት ነገስታቶቻትን ነጻ እና ራሳቸዉን የቻሉ ግዛቶች ነበሩ ።  ነገር ግን ዲያቆን ዳንኤል ሃገራችን ኢትዮጵያ ከዚያ ዘመን በፊት የሃገር ምስረታ  nation building ሂደት አጠናቃ የነበረች እና ልክ የዛሬውን ድንበር ይዞታ እና ቅርፅ የነበራት በማስመሰል  ሱልጣነኔቶቹን ከባእድ አገር በመጡ ወራሪ ህዝቦች የተመሰረቱ አድርገው ለማቅረብ ሞክረዋል ።

ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ ከአረብ አገሮች  ወደ ሃገራችን ገብተው የነበሩ ጥቂት የእስልምና ሃይማኖት አባቶችን  እስልምናን ሳይሆን አረባዊነትን ለማስፋፋት ጥረት ያደርጉ እንደነበር ገልፀዋል።  ነገርግን  ከአራተኛው ክፍለ ዘመን እስከ 1950 ዎቹ  ድረስ ለ1500 ዓመታት ገደማ ከግብጽ በሚላኩ ጳጳሳት ትተዳደር የነበረችዋን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ይመሩ የነበሩ የግብጽ ክርስትያኖችን ግን ኢትዮጵያዊነትን እንዳስ ተማሩ አድርገው ተርከዋል።   ይህ አድሏዊ እና ሚዛናዊነት የጎደለው አቀራረባቸዉ በምያሳዝን መልኩ እውነታን ከማየት ይልቅ ስሜታቸዉን የተከተለ ጽሁፍ እንዲያቀርቡ አድርጔቸዋል ።

በተመሳሳይ የተዛባ እይታቸው የክርስትና እምነት ተከታይ የነበሩት በርካት የአገራችን ነገስታት ሙስልሞች ክርስትናን በግድ እንዲቀበሉ ለማድረግ ለረዥም ዘመናት የፈጸሙትን ጭፍጨፋ ሲያስተባብሉ በኢማም አህመድ የግዛት ዘመን የተደረገዉን የተለየ በደል አስመስለው አቅርበዋል።   እንደ ሌሎች ነጥቦቻቸው ሁሉ ይህ የዜጎችን እኩልነት ያለመቀበል ስሜት የፈጠረባቸው የአድሏዊነት መንፈስ መሆኑን በ 21 ኛ ክፍለ ዘመን መገንዘብ ያለመቻላቸውን አሳዛኝ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።

 

በአጭሩ የጥንቶቹን ሙስልሞች ታሪካዊ ጠላት ከሚሏቸው የሙስሊም ሃገሮች ማለትም ከቱርክ ፣ ከግብጽ ፣ ከሱዳን ፣ የመንና ሰኡዲ አረቢያ ጋር በተለያዩ የታሪክ ዘመናት አብረው አገር ያደሙ ፣ እስልምናን በግድ ሰዎች ላይ ይጭኑ የነበሩ እያሉ ሲያወግዙ በዘመኑ ያሉትን ደግሞ ታሪካዊ ጠላት ከሚሏቸው ጋር በማበር አገር ሊያጠፉ የተነሳሱ አክራሪዎች በማለት  በምሬት ከሰዋል ።  የዚህ ሁሉ የታሪክ ብረዛ አላማ  ህዝበ ሙስልሙን  በቀደምት አባቶቹ ታሪክ እና በዛሬው ንቃቱ ሊያሸማቅቁት የሚያስችሉ የስነ- ልቦና ጫናዎች በማድረግ በሃገሩ ከጀመረው የእኩል ባለቤትነት የመብት ጥየቃው እንዲታቀብ ለማድረግ መሆኑንን መገመት አያዳግትም።

የሚያስተዛዝበው ጉዳይ ፣ ዲያቆን ዳንኤል የጥንቶቹን ሙስልሞች ከጠላት ጋር አብረው አገር ያደሙ ፣ ወገኖቻችንን በሃይል ወደ እስልምና እንዲገቡ ያደረጉ የነበሩ  አስመስለው ሲወነጅሉ ከቆዩ በኌላ የዛሬዎቹን ሙስሊሞች  ደግሞ ለማሸማቀቅ እንዲመቻቸው የጥንቶቹን ሲያወግዙ መቆየታቸዉን የዘነጉ ይመስል የጥንቶቹ በጋራ መኗኗርን ገንብተው የነበሩ  ለአገር በጎ አሳቢዎች እንደ ነበሩ ለማስመሰል ጥረት ማድረጋቸው ቀደም ሲል ካቀረቡት የውንጀላ ሃሳቦቻቸው ጋር የተጣረዙ ሃሳቦችን አቅርበዋል።  እንደ ሃይማኖት አባት ሰዎች እውነትን እንዲመሰክሩ የሚያበረታቱ  መሆን ሲገባቸው እርሳቸው ግን በሃሰት የሌላ እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸውን ከክርስትና እምነት ተከታይ  ወገኖቻቸው ጋር የሚያጋጭን ጽሁፍ በማቅረብ  በሃገራችን ላይ ከፍተኛ የደም መፋሰስን ሊያስከትል የምችሉ የሃይማኖት ግጭቶችን መለኮስ የሚችሉ ቅስቀሳ ማድረጋቸው ያለባቸዉን የሃይማኖት አባት ሃላፊነት የዘነጉ መሆናቸዉን አጋልጧል።

በአክራሪ ሙስልሞች የተፈጸሙ ወንጀሎች ብለው ዲ/ን ዳንኤል  የዘረዘሯቸውን አስከፊ የጥፋት ድርጊቶች ስንሰማ በቅድሚያ የምናስበው በሃገራችን ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ የሆነ ወደ ከፍተኛ የደም መፋሰስ እያመራ ያለ ውጥረት በክርስትና እና በእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን መካከል እንደተፈጠረ ነው።  በአንድ ሃገር ይህን መሰል ወንጀል ሊፈጸም የሚችለው  ሃገርን የሚመራው መንግስት ይህን መሰል ወንጀል ለመቆጣጠር በቂ የጸጥታ አስከባሪ ሃይል የሌለው ከሆነ አልያም መንግስት ድብቅ አላማዉን ለማሳካት ሆን ብሎ በወኪሎቹ ሲያስፈጽም ብቻ ነው ።

የጸጥታ ሃይልን ጥንካሬ በተመለከተ በይፋ የሚታወቀው ጉዳይ መንግስት ያደራጀው የጸጥታ አስከባሪ ሃይል ከአገራችን ተርፎ በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የተ/መ ድርጅት የሰላም አስከባሪነት አገልግሎት የሚሰጥ ፣ በሶማሊያ በውጊያ የተሰማራ እና በአፍሪካን ቀንድ በጠንካራነቱ የሚታወቅ ነዉ ።  ስለዚህ ሃገራችን እርሳቸው የዘረዘሯቸውን ወንጀሎች ሁሉ  ሊያስቆም የሚችል ብቃት ያለው የጸጥታ አስከባሪ ሃይል ያለው  መሆኑ የተረጋገጠ እስከሆነ ድረስ መሰል ብቃት ያለው መንግስት ባለበት ሃገር ውስጥ የወንጀሎቹን መፈጠር ያለማስቀረቱ ጉዳይ አንድም መንግስት የውንጀሎቹን ፈጻሚዎች እያዬ የሚያልፍ መሆኑን አልያም ደግሞ በጀሌዎቹ ማስፈጸሙን የሚያመላክቱ  ናቸው ።  ሌላው የዚህን እይታ አሳማኝነት የሚያጠናከረው ነጥብ ህወሃት በቀዳሚነት የኦርተዶክስ ቤ/ክርስቲያንን ለማዳከም በትጋት መስራቱን ያለመሸሸጉ እና  እቅዱንም ስለ ማሳካቱ በማን አለብኝነት ስሜት የቤ/ክርስቲያንቷን አከርካሪ መሰበሩን ማሳወቁ ነው (አቦይ ስብሃት የቀድሞ የህውሃት መሪ እንደተናገሩት “አማራን እና ኦርቶዶክስን አከርካሪያቸውን ሰብረናል” ማለታቸው ነው) ።  ታድያ ይህን ግልጽ የሆነ ጉዳይ ዲ/ን ዳንኤል  እንዴት ሳይጠረጥሩ ቀሩ ?  ለዚህ ያለኝ ምላሽ  በእርግጥ እርሳቸው መጠርጠር የለባቸዉም ነው። ምነው ቢባል እርሳቸው የህወሃትን አላማ በእርግጠኝነት ያውቃሉና።

የሙስልም አክራሪዎች በሚሏቸው እንደተፈጸሙ ከጠቀሷቸው ወንጀሎች አንዱ በጅማ ከተማ አቅራቢያ በክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ወንጀል ነው።  ይህ ወንጀል እንደ ተፈጸመ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን የወንጀሉ ሰለባ የነበሩትን ክርስቲያን ወገኖቻችንን ቃለ-መጠይቅ አድርገው የቀረጹትን ቪዲዮ አዘጋጅተው  ለቀው ነበር ።  በቃለ ምልልሱ የተሳተፉት የወንጀሉ ሰለባ የነበሩት ክርስቲያን ወገኖቻችንን በዘመዶቻቸዉ እና  በእነርሱ ላይ የተፈጸመውን ግፍ በተመለከተ ወንጀሉን የፈጸሙትን ቡድኖች ቆመው ሲከላከሉላቸው የነበሩት የመንግስት ታጣቂዎች ናቸዉ የሚል ምስክርነት በወቅቱ ሰጥተዋል።    የቪዲዮው አዘጋጆች በወቅቱ ተጠያቂ አድርገው የከሰሱት ህወሃትን ነበር  በዚህም ምክንያት በቪዲዮው መጀመርያ ላይ የቀረበው የሟቹ ጠ/ሚንስትር ምስል ነበር።   በአሳዛኝ መልኩ ከተወሰነ ግዝያት በኌላ ዲ/ን ዳንኤል  ይህንኑ ህወሃት ተወንጅሎበት የነበረዉን የወንጀል ድርጊት ዛሬ በህዝበ ሙስልሙ ላይ መለተጠፍ ለምን አስፈለጋቸው?

ዲ/ን ዳንኤል  በእርሶ አስተሳሰብ በአንድ ወንጀል ስንት አካሎች ይጠየቃሉ ብለው ያምናሉ? ዲ ዳንኤል ወንጀሉን በሙስሊሙ ላይ ያላከኩበት ምክንያት

1ኛ/ የህወሃት አለቆቹን ከፈጸሙት ወንጀል ነጻ ለማድረግ

2ኛ/ ህወሃት የእስልምና እና የክርስትና እምነት ተከታይ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ለማጋጨት የሚሸርበዉን ሴራ እንዲያሳኩ የተሰጣቸውን ተልእኮ ከግብ ለማድረስ ።

ለዚህም ነው የሃይማኖት አባት ካባቸዉን ተጠቅመው  ለህወሃት የሚሰሩ  የውስጥ አርበኛ ናቸዉ የምለው። ይህን ነጥብ በተመለከተ የተጠቀሰኩትን የቪዲዮ መረጃዎች ከዚህ በታች ይመልከቱ

Ethiopian Government incited killing in Jimma, Ethiopia : https://youtu.be/SwSYIHlQ5ZI

ሌላው እሳቸው እና መሰሎቻቸው በተደጋጋሚ ሙስሊሙን የሚወነጅሉበት ክስ በበደኖ ህወሃት ከአማራ ብሄር ተወላጅ በሆኑ ክርስቲያን ወገኖቻችን ላይ የፈጸመው  ወንጀል ነው።  የወንጀሉ ሰለባ ከነበሩት የክርስትና እምነት ተከታይ የአካባቢው ነዋሪ ሙስልም ወገኖቻቸው እንዴት ከሞት እንዳዳኗቸው መረጃ ያቀረቡበትንና የቃለ-ምልልስ ሙሉ ዘገባ ከዚህ በታች ይመልከቱ።

ዲያቆን ዳንኤል ጽሁፋቸዉን ካቀረቡ ከጥቂት ግዝያት በኌላ  በ2011 አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በውቅቱ በሃገራችን ስለ ነበረው የሃይማኖት መቻቻል እና በዚያም ረገድ የአሜሪካ ፖሊሲ ምን መምሰል አለበት በሚል ጉዳይ ላይ ዘጠኝ ወራት የፈጀ ጥናት አካሄዶ ነበር ። የጥናቱም ውጤት በዊኪሊክዊ ይፋ ሾልኮ ወጥቷል።  ይህም የዊኪሊክ መረጃ ጥናቱ በየክልሎች ያሉ በርካታ የክርስትና እና የእስልምና እምነት አባቶችን አስተያየት ፣ የመጅሊስ እና ሲኖዶስ አባላትን ግምገማ ያካተተ መሆኑን አሳዉቋል።   ተሳታፊዎቹ ስለ ሁለቱ እምነት ተከታዮች አብሮ መኗኗርም ሲገልጹ በጥቅሉ በሃገራችን ያለው የሃይማኖት ግንኙነት ሁኔታ ሁልግዜ ፍቅር በፍቅር ነው ባይባልም የሁለቱ እምነት ተከታዮች  በጋብቻ የተሳሰሩ መሆንና በአንድ ቤተሰብ ዉስጥ የሁለቱ እምነት ተከታዮች መኖር tolerate የምደረግ መሆኑ በዘር የመቆራኘትን  ስላስከተለ ይህን ግንኙነት ለመጠበቅ ማህበረሰባችን ችግሮችን የሚፈታበትን ለየት ያለ ዘዴ mechanism እንዲያበጅ አስችሎታል የሚል አስተያየት ሰጥቷል።  አጥኚዉ ቡድን ይህኑኑ ሃሳብ ለቀድሞ ፓትርያርክ አቅርቦ  እርሳቸውም በጥናቱ ውጤት የተስማሙ መሆናቸዉን በመግለጽ አንድ ተዘነጋ ያሉትን ነጥብ አክለዋል ። ይህም በዋናይቷ ከተማ የሚደረገው የሃይማኖት እሽቅድምድም ሲሆን በእርሳቸው አመለካከት ጥቂት የሁለቱም እምነት ተከታዮች አክራሪነት ታይቶባቸዋል የሚል እንደ ነበር ጥናቱ ያስረዳል።

ከዚህ በተጨማሪ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ ስለ አክራሪነት ስጋት በጥናት ቡድኑ ተጠይቀው ስመልሱ የአክራሪነት ስጋት እንደሌለ የገልጹ ቢሆንም ጥቂት  የሚያሰጋቸው ጉዳይ ቢኖር የሶማልያ ክልል በድርቅ በተጠቃበት ወቅት ከፈደራል መንግስት አፋጣኝ እርዳታ እንዲደርስ ባለመደረጉ  በወቅቱ  አል-ኢታሃድ በመባል የሚጠራው አክራሪ ድርጅት ለተጎጂዎች እርዳታ እያደረገ ስለነበር የአካባቢው ህዝብ ወደ አል-ኢታሃድ እና  ወደ ኦጋዴን ነጻ አውጪ ሊሳብ የመቻል አደጋ ነበር ።  ከዚህ ባሻገር ፓርቲያቸው የሚተገብረው ፖሊሲ  የሙስሊሙን ህብረተሰብ መብት ቀደም ሲል ከነበሩት ስርአቶች በተሻለ መልክ እንዲከበር ስላስቻለ የሙስሊሙ ህብረተሰብ የፓርቲያቸው ደጋፊ በመሆኑ ለአክራሪ አስተሳሰቦች ጆሮ አይሰጥም በማለት የሽብር ስጋት በአገሪቱ እንደሌለ ገልጸው ነበር።

ታዲያ እውነታው ይህ ሆኖ እያለ ዲ /ዳኒኤል ህዝባችንን ሊተላለቅ የተቃረበ የሚያስመስል ጽሁፍ ያቀረቡት ለምን ይሆን ? ይህን የህዝባችንን የመኗኗር ብቃት የሚሸረሽር እና ለአመታት ልቆይ  የሚችል የማይበርድ የደም መፋሰስ ሊያስከትል   መርዛም የሃሰት ዘገባ ማቅረባቸው ለምን ይሆን ? ለዚህ ዋነኛው ምክኒያት ጽሁፋቸው ክፉ ስሜታቸዉን የተከተለ እንጂ መሬት ላይ ያለዉን ሁኔታ ያላገናዘበ መሆኑን እና  ልቦናቸው በእስልምና እምነት ላይ ባለቸው ጭፍን ጥላቻ ተደፍኖ ለህዝባችንና ለሃገራችን ደህንነት ደንታ ቢስ እንዲሆኑ ማድረጉን ነው ። ለነገሩ እንደ ሃይማኖት አባት ይጠበቅባቸው የነበረው የተጣላን በማስታረቅ በህዝባችን መካከል ሰላም ማስፈን ነበር። ያለመታደል ሆኖ እሳቸው ግን በትጋት እየሰሩ ያሉት ህዝባችንን ለማፋጀት ነው። ለህሊናቸው አቤቱታ ማቅረብ እወድ ነበር  ፣  ዳሩ ግን ….. ለክፍል ሶስትላቆየው መሰለኝ

ከአብዱላህ

 

 

The post የዲያቆን ዳንኤል ስሜታዊ ትንተናና መሬት ላይ ያለው እዉነታ ! ክፍል 2 – ከአብዱላህ appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: የጀርባ ሕመም ለምን ይከሰታል?

0
0

back pain
የጀርባ ሕመም
(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
የጀርባ ሕመም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የኅብረተሰባችን ክፍል እያጠቃ የሚገኝ የሕመም ዓይነት ነው፡፡ በአብዛኛው ይህ ሕመም በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ የተለመደ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ግን በወጣትነት የዕድሜ ክልል ባሉ ሰዎች ላይም እየተበራከተ ይገኛል፡፡

► የጀርባ ሕመም ለምን ይከሰታል?
የጀርባ ሕመም ከማንኛቸውም የሰው ጀርባን ከሚሰሩ የሰውንት ክፍሎች ሊነሳ ይችላል፡፡
እነዚህም፤
✔ የጀርባ ጡንቻዎች መሳሳብ (መሸማቀቅ)
✔ ከባድ ዕቃን ያለአግባብ ለማንሳት መሞከር
✔ ድንገተኛ የሆነ ከፍተኛ እንቅስቃሴ
✔ የዲስክ መንሸራተት
✔ የመገጣጠሚያ ላይ ኢንፌክሽን
✔ የአጥንት መሳሳት

► የጀርባ ሕመም ከዕለት ተዕለት የኑሮ ሁኔታችን ጋር ይያያዛል፡፡
✔ ከባድ ዕቃን በመግፋት ወይንም በመጎተት
✔ ከባድ ዕቃን በመሸከም ወይም በማንሳት
✔ ለብዙ ሰዓት በመቆም
✔ ለብዙ ሰዓታት አጎንብሶ መቀመጥ
✔ ያለ ዕረፍት ለብዙ ሰዓታት መኪና ማሽከርከር

► የጀርባ ሕመምን እንዴት መከላከል ይቻላል?
✔ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፡- ኤሮቢክስ የሚባለውን የስፖርት ዓይነት መሥራት የሰውነታችንን አቅም ከመጨመር ባለፈ ክብደታችንን በመቀነስ የጀርባ ሕመም ይከላከላል፡፡
✔ ሲጋራ ማጤስን ማቆም፡- ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ሲጋራን የሚያጤሱ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ ለጀርባ ሕመም ተጋላጭ ናቸው፡፡
✔ የሰውንት ክብደት መቀነስ፡- የሰውነት ክብደታቸው የጨመረ ሰዎች የጀርባ ሕመም ይኖርባቸዋል፡፡
✔ የተስተካከለ አቀማመጥ፡- በምንቀመጥበት ጊዜ ጀርባችንን የሚደግፍ እና እጃችንን የምናሳርፍበት ቀጥ ያለ አቀማመጥ መያዝ፡፡
✔ የተስተካከለ አቋቋም፡- በምንቆምበት ጊዜ የሰውነት ክብደታችን በሁለቱም እግሮቻችን በእኩል መጠን እንዲያርፍ ማድርግ እና ቀጥ ብለን ሳንቆለመም መቆም፡፡
✔ ክብደት ያላቸውን ዕቃዎች በአግባቡ ማንሳት፡- ክብደት ያላቸውን በምናነሳበት ጊዜ ክብደቱን ከወገባችን/ከጀርባችን ይልቅ በእግሮቻችን ላይ እንዲያርፍ ማድርግ ተገቢ ነው፡፡ ዕቃዎችን በምናንቀሳቅስበት ጊዜ ከመጎተት ይልቅ መግፋትተመራጭ ነው፡፡
✔ ጫማ፡- የጀርባ ሕመም እንዳይሰማን የምንጫማቸው ጫማዎች ምቹ ሊሆኑ ይገባል፡፡
✔ መኪና በምንሽከረክርበት ወቅት ጀርባችንን መደገፍ፡፡ ለረጅም ሰዓት የምናሽከረክር ከሆነ በየማሃሉ ከመኪና በመውረድ ሰውነትን ማንሳሰቀስና ዕረፍት መውሰድ ተገቢ ነው፡፡

✔ የአልጋ ፍራሽ ምቾት፡- የምንተኛበት የአልጋ ፍራሽ ቀጥ ያለ መሆን አለበት፡፡
የጀርባ ሕመም ከባድ የሆኑ የጤና ችግሮች ምልክት ሊሆን ስለሚችል በቀላሉ ሊመለከቱት አይገባም፡፡በመሆኑም ከዚህ በታች የሚጠቀሱት ተጫማሪ ምልክቶች ካሉ ወደ ሕክምና ማዕከል በመሄድ መመርመር ያስፈልጋል፡፡እነዚህም፤
✔ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ወይንም መውደቅን ተከትሎ የመጣ የጀርባ ሕመም
✔ ከወር በላይ የቆየ እና እየባሰ የመጣ የጀርባ ሕመም
✔ በሕመም ማስታገሻ እና ዕረፍት በመውሰድ ለውጥ የማያመጣ የጀርባ ሕመም
✔ ከወገብ በታች የመደንዘዝ ስሜት
✔ ደም የቀላቀለ ሽንት መኖር
✔ ከፍተኛ ትኩሳት መኖር እና ሆድ ሕመም መሰማት ናቸው፡፡
በቤቶ ሆነው ሊያከናውኑት የሚችሉትን ይህን ቀላል የ አካል ብቃት እንቅስቃሴ በዚህ አድራሻ ማግኘት ይችላል፡፡

ጤና ይስጥልኝ

The post Health: የጀርባ ሕመም ለምን ይከሰታል? appeared first on Zehabesha Amharic.

‹‹ተወይኖብኛል›› … “በዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ ተልእኮ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተባርሬአለኹ”–ዶ.ር ዳኛቸው አሰፋ/

0
0

dr dagnachew Assefa
ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ከሦስት ዐሥርት ዓመታት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ በሚሌኒየሙ መባቻ ወደ አገራቸው ተመልሰው ላለፉት ሰባት ዓመታት በማስተማር ሥራ ላይ ቆይተዋል፡፡ ምሁሩ በዋናነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና መምህር ቢኾኑም በሕግ ፋክልቲ፣ በሴንተር ፎር ሂዩማን ራይትስ፣ በኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም፣ በአምስት ኪሎ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፋክልቲ፣ በቴአትሪካል አርትስና በያሬድ የሙዚቃ ት/ቤትም አስተምረዋል፡፡ ለሰባት ተከታታይ ዓመታት በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች በተለያየ ጊዜ ሲያስተምሩ ቢቆዩም ከጠየቁት የዓመት ዕረፍት(sabbatical leave) ጋር ተያይዞ ከዩኒቨርስቲው መሰናበታቸው ተሰምቷል፡፡ በዚኽ ዙሪያ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ከዶ/ር ዳኛቸው ጋራ ተከታዩን አጭር ቆይታ አድርጓል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና በእርስዎ መካከል ምንድን የተፈጠረው?

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስተዳደር ጋራ በኹለት ጥያቄዎች ዙሪያ የማይታረቅ ልዩነት ተፈጥሯል፡፡ በመጀመሪያ የዩኒቨርስቲው የሴኔት ሕግና የቅጥር ውሌ ላይ በግልጽ እንደሰፈረው÷ አንድ መምህር ለስድስት ዓመት በተከታታይ ከአስተማረ፣ ለአገለገለበት ዘመን የአንድ ዓመት የጥናትና ምርምር ዕረፍት (sabbatical leave) እንደሚሰጠው ተደንግጓል፡፡ ኾኖም ግን ዩኒቨርስቲው ‹‹የጡረታ ሥርዓተ – ሒደቱን አላሟላኽም›› በሚል በሕጉ ፊት የማይጸና ሰበብ ፈጥረው ይገባኻል ብለው ከፈቀዱልኝ በኋላ መልሰው ነጥቀውኛል፡፡ ለማንኛውም መምህር ሥርዓተ ሒደቱን የማስፈጸም ሓላፊነት የሰው ሀብት አስተዳደሩ ድርሻ ኾኖ ሳለ እኔን ተጠያቂ ማድረጋቸው ብዙዎችን አስገርሟል::

በነገራችን ላይ የጥናት ዕረፍት ፈቃዴን የጠየቅኹት ከሦስት ዓመት በፊት፣ ስድሳ ዓመት ሳይሞላኝ ነበር፡፡ በየሰበቡ ሲጓተት ስለቆየ ወደ ስድሳ ዓመቱ ገደብ ደረስኹ፡፡ ጉዳዩ ወደ ማኅበራዊ ፍርድ ቤት ከመሔዱ አስቀድሞ ውስጣዊ ተቋማዊ መፍትሔ ለማበጀት ወደ ዩኒቨርስቲው የቦርድ ሰብሳቢ ቀርቦ ምላሽ ስጠባበቅ ከሦስት ወራት በላይ ተቆጥረዋል፡፡

የሥራ ውሌን በተመለከተ፣ የፍልስፍና ትምህርት ክፍል የእኔን የአገልግሎት ቆይታ እንደሚፈልግና በተለይም በቅርቡ ለሚጀምረው የሦስተኛ ዲግሪ መርሐ ግብር ተሳትፎዬ እንደሚጠቅም በሙሉ ድምፅ ተስማምቶ በመወሰኑ ውሌ እንዲራዘም ለማኅበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ አካዳሚክ ኮሚሽን ጽፎልኝ ነበር፡፡ የማኅበራዊ ሳይንስ ትምህርት ክፍል ሓላፊዎች በተሰበሰቡበት፣ ኮሚሽኑ ጉዳዩን በአጀንዳ ይዞ ከተወያየበት በኋላ የፍልስፍና ትምህርት ክፍሉን ጥያቄ ዳግመኛ በሙሉ ድምፅ ተስማምቶበት፣ ውሳኔው በማኅበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ዲኑ በፕ/ር ወልደ አምላክ በዕውቀት በኩል የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ይኹንታቸውን እንዲሰጡበት(እንዲያጸድቁት) ተጠይቆ ነበር፡፡ ፕሬዝዳንቱ ግን ከአራት ወራት ያኽል ቸልተኝነት በኋላ ‹‹ወረቀቱ ይመጣለታል›› በሚል ለተከታዩ ሴሚስተር እንዳልደለደል በአዲሱ ዲን በኩል ለትምህርት ክፍሉ ሊቀ መንበር መመሪያ አስተላለፉ፡፡ መመሪያው የእኔን መሰል ጥያቄ ባቀረቡ ሌሎች መምህራን ላይም የተላለፈ ነበር፡፡ ከሦስት ወራት በላይ ደመወዜን ይዘው መክፈል ከአቆሙ በኋላ ‹‹ለሚመጣው ሴሚስተር አትመድቡት›› ማለት በአካዳሚያ ቋንቋ ግለሰቡ ተሰናብቷል ማለት ነው፡፡

በመሠረቱ፣ የትምህርት ክፍሌና አካዳሚክ ኮሚሽኑ የሥራ ውሌን መራዘም ተስማምተው ላቀረቡት ጥያቄ ሲኾን እንደወጉ ማጽደቅ አልያም በአስቸኳይ ውሳኔን ማሳወቅ ሲገባ ፕሬዝዳንቱ ከሦስት ወራት በላይ ማቆየታቸው ኢ-ሕጋዊ ነው፤ ሕጉን ጠብቆ በወጉ ለቀረበ ጥያቄ ከሦስት ወራት በላይ ምላሽ አለመስጠት እብሪት፣ ትዕቢትና ማናለብኝነት እንጂ ሌላ ሊኾን አይችልም፤ በተመሳሳይ ወቅት አንድ ዐይነት ጥያቄ በደብዳቤ ከአቀረብነው መምህራን መካከል፣ ለምሳሌ ከኛው ትምህርት ክፍል ዶ/ር በቀለ ጉተማ በሥራው እንዲቀጥል በቃል ትእዛዝ ፈቅደው፣ ለእኔ በአግባቡ ውሳኔ ሳይሰጡ ‹በሚቀጥለው ሴሚስተር እንዳትመድቡት ማለት የአድልዎ አቀራረብ ብቻ ሳይኾን በዘፈቀደና በግፊት የሚካሔድ አመራር መኾኑን ያረጋግጣል፡፡ በሌላ በኩል፣ ፕሬዝዳንቱ ዶ/ር አድማሱ ዩኒቨርስቲውን ለመምራት ያላቸውን ብቃት ከዝህ ቀደም በአደባባይ ስለጠየቅኹ በቂም በቀልና ኹን ብለው እኔን ለመጉዳት የደረሱበት ውሳኔ ነው፡፡

የጥናትና ምርምር ዕረፍት(sabbatical leave) በተመለከተ በጊዜው የካሌጁ ዲን የነበሩት ዶ/ር ገብሬ ይንቴሶ የፕሬዝዳንቱን ፍላጎት ተከትለው ከላይ እንደጠቀስኹት የሰጡኝን ፈቃድ መልሰው ነጥቀውኛል፡፡ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን ወዳለው ፍርድ ቤት ከማምራቴ በፊት፣ የፕሬዝዳንቱን ምላሽ ከወዲኹ ባውቀውም አቤቱታዬን የግድ ለእርሳቸው ማቅረብ ነበረብኝ፡፡

በኮሌጁ የቀድሞ ዲን ውሳኔ ላይ ከዐሥር ገጽ ያላነሰ አባሪ ሰነዶች አያይዤ ጠዋት ላቀረብኹት አቤቱታ፣ ከቀትር በኋላ ‹‹በጥልቅ መርምረን›› በሚል በአንድ መሥመር የኮሌጁ ውሳኔ እንደማይሻር የሚገልጽ ፌዝና የቀልድ ምላሽ ነው የተሰጠኝ፡፡ ይህ የሚያሳየው ፕሬዝዳንቱ ለዩኒቨርስቲው መምህራን ከበሬታ የሌላቸውና አመራራቸውም ከሞራላዊነት የተራቆተ መኾኑን ነው፡፡ እኔ ግን ታዋቂው አርበኛ አበበ አረጋይ በአንድ ወቅት በፋሽስት ጣልያንና በባንዳ ለተከቡበት የተራቡ ጭፍሮቻቸው ‹‹ሞተን አንጠብቃቸውም፤ ተረጋግታችኹ ብሉ›› እንዳሉት፣ ከማባረር ያልተናነሰ የዘገየ አንድ ብጣሽ ወረቀት ገና ለገና ይመጣል ብዬ ሞቼ አልጠብቃቸውም፡፡
የጡረታ ጊዜያቸው ደርሶ ለማራዘም የተፈቀደላቸው መምህራን አሉ ወይ? ማለትም በዩኒቨርስቲው አሠራር

የጡረታ ጊዜያቸው የደረሰ መምህራን ውላቸውን ማራዘም ይችላሉ ወይ?

በተለምዶ ስድሳ ዓመት የሞላቸው መምህራን የውል ማራዘሚያ ጊዜ ይጠይቃሉ፡፡ እኔ የማውቃቸውና በተደጋጋሚ የተጨመረላቸው መምህራንም አሉ፡፡ በጣም አስገራሚና በግቢው አነጋጋሪ የኾነው የእኔና የዶ/ር መረራ ጉዲና የውል ማራዘሚያ ጊዜ መከልከሉ ነው፡፡

የዚኽ ኹሉ መነሻ ምንድን ነው ብለው ይገምታሉ?
ከኹሉ በፊት የእኔ መከልከልና መሰናበት ከፖሊቲካ እይታ አኳያ የመነጨ መኾኑ ማንም አይስተውም፡፡
ማለት…
በዩኒቨርስቲው በማስተማር ሥራ በቆየኹባቸው ባለፉት ሰባት ዓመታት፣ በጽሑፍና በተለያዩ መድረኮች የማደርጋቸው የዐደባባይ አእምሯዊ እንቅስቃሴዎች አልተወደደዱም፡፡ እንዲያውም ለሹመኞች ቅርበት ያላቸው አንዳንድ ወዳጆቼ እንዳጫወቱኝ፣ ‹‹ዳኛቸው፣ ዩኒቨርስቲውን እንደ ደጀንና ገዥ መሬት ተጠቅሞ መድፍ ሲተኩስብን ቆይቷል›› ተብዬአለኹ፡፡ በርግጥ ይህ ዓይነቱ አቋም ከተወሰደ በኋላ በሥራ ገበታዬ እንድቀጥል አለመደረጉ አይገርመኝም፡፡

ለሰባት ዓመት ካስተማሩበት ዩኒቨርስቲ በዚኽ መልኩ ሲሰናበቱ ምን ተሰማዎ?

እንደ እውነቱ ከኾነ የተደበላለቀ ስሜት ነው በውስጤ የተፈጠረው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ፣ ይህ ነገር ከሰባት ዓመት በኋላ መኾኑ አስደስቶኛል፡፡ ይኸውም የመጣኹበትን የማስተማር ዓላማ ከሌሎች ባልደረቦቼ ጋር በመኾን ለመስኩ ተተኪና ምሉዕ የኾኑ ተማሪዎች ለማፍራት በመብቃታችን አስደስቶኛል፡፡ ይህ ክልከላና ስንብት በቂ ምሩቃን ባላፈራንበት ከሦስትና ከአራት ዓመት በፊት ቢከሠት ኖሮ አዝን ነበር፡፡

በኹለተኛ ደረጃ፣ ‹የዓመት ዕረፍት(ሳባቲካል) አይሰጥኽም፤ ከእንግዲኽ ማስተማርም አትችልም› ስባል ለራሴ በጥልቀት ተሰምቶኝ ያልኹት፣ ‹‹አኹን ገና ኢትዮጵያዊ ኾንኩ፤ ኢትዮጵያዊ ማለት መብቱ የሚረገጥ ማለት ነው›› የሚል ነበር፡፡ በዚኽ ሰባት ዓመት ቆይታዬ ከአሜሪካ ሳልፈታ ይዠው የመጣኹት የነፃነትና የመብት አቅዋም፣ ከአገራችን ፖሊቲካዊ ነባራዊ ዕቀባ በተፃራሪው እንደ ልቤ እንድተችና ያለገደብ እንድናገር አስችሎኝ ነበር፡፡ አኹን ግን ሥርዓቱ ‹ይኼ አሜሪካ አይደለም፤ እንደ ጎረቤትኽ ሳይኾን እንደቤትኽ እደር› ተብዬአለኹ፡፡
ይህን ስል ግን፣ እኔ በዕድሜዬ የምወልዳቸው ልጆች በኾነ ባልኾነ ክሥ ወኅኒ ቤት ተወርውረው ባሉበት ኹኔታ ከሥራ አባረሩኝ ብዬ የማለቅስ ሰው አይደለኹም፡፡ በእኒኽ ብሩህ ተስፋ ባላቸው ወጣቶች ላይ ከደረሰው አንጻር ሲታይ መብቴ መረገጡ እውነት ቢኾንም፣ የአገራችን ተረት ‹‹እናቱ ውኃ ልትቀዳ የወረደች ልጅና እናቱ የሞተችበት ልጅ አንድ ጋር ቆመው ያለቅሳሉ›› እንደሚባለው ይመስልብኛል፡፡

በመጨረሻም በአንድ በኩል፣ በውጭ ለብዙ ዓመት ቆይቼ ስመጣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የት ከረምክ ሳይለኝ ችሎታዬ በሚፈቅድልኝ ቦታ ሥራ ሰጠኝ፡፡ ለዚኽ ትልቅ ምስጋና ነው የማቀርበው፡፡ ኾኖም በሌላ በኩል የውስጥ አስተዳደሩና የውጭ የፖሊቲካ ኃይሎች በመተባበር መክረው ከሕዝብ ባገኘኹት ቸርነት ላይ ወይነውብኛል!

ከዚኽ በኋላስ ምን ዓይነት ሥራ ላይ ለማተኮር ያስባሉ?
ይህን ጥያቄ ዴሞክራሲና የሕግ የበላይነት ባለበት አገር ብትጠይቀኝ ኖሮ፣ ጉዳዩ በራሴ የሚወሰን በመኾኑ አኹኑኑ እመልስልኽ ነበር፤ ነገር ግን እንደ ቤትኽ እደር ተብዬአለኹና የጥያቄው ምላሽ በእኔ ብቻ የሚወሰን አይደለም፡፡ እንዲያውም ጥያቄው በአንድ ወቅት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ አሉ የተባለውን ያስታውሰኛል፡፡ አንድ ሹም ጃንሆይ ፊት ቀርበው የንጉሡ ትችትና ተግሣጽ ሲገጥማቸው፣ ‹‹እንዲያውም ግርማዊ ሆይ፣ የሰጡኝ ሹመት ይቅርብኝ፤ የአባቴን ርስት እያረስኩ እኖራለኹ›› አላቸው፡፡ ጃንሆይም ወዲያው ‹‹እርሱንም እኛ ስንፈቅድ ነው…›› ብለው አሉ ይባላል፡፡ እኔም እንደ አቅሜ ለመሥራት ፍላጎት ቢኖረኝም በቀጣይ ምን መሥራት እንደምችልና እንደማልችል ብያኔው በመሠረቱ ከእኔ ውጭ ነው፡፡ በተቻለኝ መጠን ግን በአለችኝ ቀሪ ዕድሜ አገሬን ለማገልገል ዝግጁ ነኝ፡፡ በዚኹ አጋጣሚ በቅርቡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሚገኝበትን ተቋማዊ ኹኔታ በተመለከተ አንድ ጽሑፍ እንደማስነብብ ከወዲኹ ለማሳወቅ እወዳለኹ፡፡

The post ‹‹ተወይኖብኛል›› … “በዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ ተልእኮ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተባርሬአለኹ” – ዶ.ር ዳኛቸው አሰፋ/ appeared first on Zehabesha Amharic.

መረብህን ጥለህ አዞ አወጣህ – (ለአቤቱ ኤርሚያስ ለገሰ) –ከመኳንንት ታዬ (ጸሃፊ)

0
0

daniel ermias

ሰሞኑን   ድህረ ገፅ አንዲት  ቁመት የሌላት ግን ሆዷ ሰፋ ያለ የምትመስል አብዛኛውን  የሆዷን ክፍል ከፊል ገለባ ከፊል ፍሬ የሞላባት እንደው ክንብል ክንብል  ስትል  እንደ ዘበት ተመለከትኳትና ፡አዬ ጉድ የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል” ምነው ኤርሚዬ ስል  እንደው እንደዘበት ቆየሁ።አፍታም አልከረመ ከወደ ዳንኤል አንዲት  መልክት መጣች ።”የለም  እንደገና ይታይልኝ “ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ ነው” ነገሩ ስትል።መለሰና  አልተሳሳትኩም ያለው አቶ ኤርሚያስ  ስምህ ዳንኤል ስለነበር አለመተንበይህ  አስገርሞኝ ነው  የማለት ያህል መልስ ሰጠ።እንዴት  እሱስ ኤርሚያስ አልነበረም  ወይ  ቢሉ አንድም  ከወያኔ ጋር ስለነበረ በድርጅቱ መሰረት  መተንበይ አይቻልም።አንድም መተንበይ ቢቻል አስቀድሞ የወያኔ አባል አይሆንም ነበር ሲል።አንድም  ብቃቱ የተገለጠለት አሜሪካን ከመጣ ነው ሲል  ብቻ አንድም እያለ ይቀጥልና  መጨራሻው የመለስ ቱርፋት ላይ ቆመ ወይም  ይቀጥላል። ማለፊያ  ነው ።ለትንቢቱ ዳንኤል ይቀርብ ነበር  አደል  መፆም መፀለዩን  ያበዛ  ቢሉ፤ የለም ኢሃዲግ በሚያስተዳድረው ሃገር  መተንበይ ጨርሶ  ሐገሩን  ለቆ ወጥቶአልና ።ዳ/ን ዳኤንልም  መተንበያ  አለፈው።

በዚህ ምክንያት  እንዲህ  ሲል መልስ ሰጠ። ኩቡር የ አቶ ኤርሚያስ ፍርድ ቤት ሆይ” ጽሑፉ የቀረበው ነሐሴ 25 ቀን 1999 ዓም አሜሪካ፣ ዴንቨር ኮሎራዶ ከተማ ተደርጎ በነበረው ሰባተኛው የአሜሪካ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ ነው፡፡ የተለቀቀው ደግሞ ከአንድ ወይም ከሁለት ቀን በኋላ www.tewahedo.org በተሰኘ ገጸ ድር ነው፡፡ –  በማለት ለኤርሚያስ    ለማስረዳት  እና ለመረዳት እየሞከረ ሳለ አቶ ኤርሚያስ  አንዴም ዳቆኑነቱን እያከበ ሌላም ግዜ ወጣ እያለ ብቻ ዘመቻውን ቀጥሎ ዋለ። እርግጥ ነው  ፖለቲካው በግዜውና በስፍራው መፍትሄ ይኖረዋል።  እርሱ ሁሉም በቦታውና በባለቤቱ ያምራልና  ፍራሹ  ከተመቸህ እንደፈለገህ የመሆን መብቱ የተጠበቀ ነው።የአቶ ኤርሚያስ ለገሰ። ግን እሰቲ በእይታ እንቀሳቀስ;፤ጥያቄ አንድ ።አቶ ኤርሚያስ  ስለምን የ1999 ዓ.ም ን ጥናታዊ  ፅሁፍ  ዛሬ ላይ  ቦታና ቀን ለውጦ አድማጭና  አስተያየት  ሰጪ ሆነ?አቶ ኤርሚያስ  በቤተክርስቲያንና በልጆቿ ስራ ዛሬም ያላለቀ  የቤት ስራ እንዳለውስ።ለምንስ ዳንኤል ላይ ማተኮር አስፈለገ።እንዴትስ  አንተ የምትመገበውን ያላገሳ ሁሉ ስሙን አተኩረህ ታየው የነበረው  የወያኔ አባል ሊሆን ቻለ።እኔ አንድ የቤተክርስቲያኒቱ ልጅ ነኝ ።በብዙ አውደ ምህረት ላይ በመገኘት ተምሬአለሁ።
daniel
ጥናታዊ ፅሁፎቹንም  ተካፍያለሁ;  የሚያቀውንና  መናገር  ያለበትን  እኔም የማውቀውን  የደበቀበት ወይም የአስተባበለበት ግዜ የለም ። ስለዚህ  በዛን ግዜ ተፈፅሞ ያልጠቀሰው  ነገር እንኳን  ቢኖር  ወይ ያላወቀው አልያም የዘነጋው ካልሆነ በስተቀር  ለማደር የሞከረበትን ግዜ አላየሁም። እውነት ነው  አሁን እየሞገትኩህ ያለሁት  ስለዳንኤል ክብረት  መስሎህ  ከሆነ  አሁንም  ችግር አለ ማለት ነው ።ከሱ በስተጀርባ ስላለችው ስለ ቤ/ክ ነው ።ይህ ማለት እሱ ባይኖር  ቤ/ክ  ችግር ይገጥማታል  እያልኩህ አደልም። እእ  ደረጃውን ለማፍረስ  መጀመሪያ ጠጠሮቹን  መፈንቀል የሚል  መመሪያ   ካለ ብዬ ነው ።ግን እንደመጠቅልል  አንተም ታስፈልገኛለህ ።ዳንኤልም  እንዲሁ ለኔ በግሌ ሁለታችሁም  አንድ ናችሁ።ታዲያሳ  ይህን  ፅሁፍ ለመፃፍ ምን አነሳሳህ አትለኝም?። ግን መልሱ አንተን  ተከትሎ እየመጡ ያሉ ሲያዩአቸው  አንበሳ  የሚመስሉ ግን አበላላቸው እንደ ጅብ የሆነ  እያረፉ የሚያስቡ  ስም የለሾች ናቸው ። አስቲ አንተ የምታውቀውን  ግን አንተ ካልከውም ሆነ ለዳ/ን ዳንኤል ክብረት ከፃፍከው ፅሁፍ ጋር ምንም ተዛማጅነት የሌላቸውን  ከዚህ በታች  ያለውን  ጥቂት ነጥቦች ላስነብብህና  የቆምክበትን ቦታ ለካ።ከዛ እንቀጥላለን። አንተ መረቡን ጥለህ አሳ ልታወጣ የኃሊት ዞረህ  ስትስብ በቅርብ ከነበሩት  አዞዎች  ውስጥ የፈጠኑት ወጡ።ለዚህ ማስረጃ ደግሞ ይህን ከዚህ በታች ያለውን ፅሁፍ ማንበብ ብቻ በቂ ነው ።

1.ምነው የትናንቱን የነአባ ማትያስን የማኅበረ ቅዱሳን ክስ አልነገርከንም ?
2.ትናንት በታቦት መውረጃ ምክንያት የባሕር
ዳርን ምእመናን ደማቸውን ያፈሰሱት ወሀቢያ ናቸው አንዳትለን እደራ እላለሁ ።
3.ገና በመጀምሪያው ምእተ ዓመት እመቤታችን የጎበኘቻት አገር ፥
ስለ እመቤታችን አማላጅነት እንደ ትልቅ አጀንዳ አዲስ አድርጎ ማቅረብ ምን ይሉታል ?
ቅዳሴ ማርያም የሚቀደስባት ቤተ ክርስቲያን ትለናለህ ፥ ይህ ነገር እንዴት ሊመጣ ቻለ ? ።
4.የወር አበባ ትምህርትስ ከየት መጣ ?
በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እልባት አግኝቶ ያለፈውን የሚበሉና የማይበሉ የምግብ
ጥያቄ በዚህ ዘመን ለምን ተነሣ ? ።
5. የወር አበባ ትምህርትስ ከየት መጣ ?
በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እልባት አግኝቶ ያለፈውን የሚበሉና የማይበሉ የምግብ
ጥያቄ በዚህ ዘመን ለምን ተነሣ ? ።

 
እንግዲህ  እነኚህ ነጥቦች ስታይ ነው  የመቼት ጥያቄውን እያሰብክ  ምናልባት መረብህን ጥለህ አዞ ማጥመድህ የሚገባህ።ዳ/ን ዳንኤል  አንድ ሰው ነው ።ነገር ግን ከሱ በስተጀርባ  ማን አለ ነው ።እርገጠኛ ነኝ  ማለት የምፈልገው ይገባሃል።ዘመኑ በአህያ ተከልልኦ ጅብን የመግደል ዘመቻ ያላበቃበት ነውና ጥንቃቄና አውቀትህን እንድትጠቀም  የግድ ይላል።እርግጥ ነው  ይህን ፅሁፍ  ለፃፈው ስም የሌሽ የምለው  ቢኖር “”የማታውቅበትን የሰው ጃኖ ለብሳ ተመለሺ ቢሏት በየት  ተመልሳ”” በቂ ነው ።ለቦና ጥጃ ውስ መች አነሰው” ብለዋልና አለቃ ገብርሃና።

አንተ ግን የእውቀት ሰውም ሰለሆንክ እራስን መጥቀም ተፈጥሮን ማየትና ለሌላው መኖር እእምሮአዊ ብቃት  ገንዘብ ከማድረግም በላይ በብልፅግና ውስጥ መኖር ያልተሰወረ ሚስጥር ማለት ሳይሆን ቋጠሮን ለመፍታት  መፍትሄ አልባ ችግርን ማስወገድና ቀዳሚነትን ታሳቢ አድረጎ ለነገ የሚያኖሩትን  ፍለጋ  የህሊናን ቋጥኝ  በጠራራ ሃሳብ  አዝልቆ ከመቆፈር ብሂል ጋር  የማገናኘትን እውነትን የራስ ከማድረግ  እኔነት ጋር የተዛመደ ነው። ግና ሽፍታ ሰፈር  ጎጆህን  ቀልሰህ  ከሆነ መለስ መለስ ብለህ ማየት ተፈጥሮ የምትነግር ህግ ስለሆነ የድርሻህን አለመስራትህን ትዝ የሚልህ  ሌሎች ድርሻ እንደሌለህ ሲነግሩህ ሳይሆን  አንተ ድርሻ የሌኝም ስትል  ብቻ ነው።በጥቅሉ እንደማሰሪያ  አቶ ኤርሚያስ ዳንኤል ባቀረበው ጥናታዊ ፅሁፍ ምክንያት ተተርሰህ  ስለ አማራ አተኩረህ  አልፈሃል። ።አንተም ካማራና ከኦሮሞ ተወልደህ እንደማትሳደብ በሁለተኛዋ ግዜ ጠቆም ጠቆም አድርገሃል። ማለፊያ  ነው።ግን አትርሳ  ታምራት ላይኔ  ሃረር ሔዶ ሰርቶ አዳሪ የሆኑትን  ሆዳም አማራ ብሎ ወደ ገደል ሲያስወረወር እሱ አማራ ነበር። ተፈራ ዋልዋ አዲሱ ለገሰ ተመሳሳይ ጥፋት ሲፈፅሙ አማራ ናቸው።በቅርቡ አቶ አለምነህ  ፤”በባዶ እግሩ እየሔደ የሚናገረው መርዝ ነው” እያሉ ሲያንቋሽሸው እሱም አማራ ነው;”ስለዚህ  አካሔድ(በ ኢሃድግኛ) ችግር አለና ይስተካከል።በተረፈው  ምርጥ የኢትዮጲያ ልጅ ነህ እንደ አቤሚልክ ከ66 አመት በኋላም ብትነቃም።ዋናው በነቁ ግዜ ጥሩ እቃ መሆኑ ነው ቁም ነገሩ።ምነው  ወያኔዎች  ዛሬ ነቅተው  አለን ባሉን  መታደል ነበር ። ግን ምን ያደርጋል ከተኙ 40 አመት አከበሩ። ህዝቡ ደግሞ ከነቃ80 አመቱን አከበረና  ሳይተዋወቁ እየኖሩ ናቸው።

በትንሳኤ ውስጥ ጀግንንት ትርጉም ያገኛል።ሞራል የፍርሃትን ጉም ጥሶ ከፀሃይ ሙቀት ጋር ደባልቆ ጠል  ሆኖ ሁሉን ያረሰርሳል ።ዝናብ አደለምና አያበሰብስም ።ብርድ የለውምና አያንቀጠቅጥም።ህብረት  እንዲህ  ምቾት አለው።ትላንት ብቻህን ዛሬ ከእኛ ጋር ነህና  በርታ ለክተህ ቁረጥ።
 
ቸር እንሰንብት

The post መረብህን ጥለህ አዞ አወጣህ – (ለአቤቱ ኤርሚያስ ለገሰ) – ከመኳንንት ታዬ (ጸሃፊ) appeared first on Zehabesha Amharic.

ከዲሲ ግብረሃይል የተሰጠ መግለጫ: የነጻነት ትግሉን በየፈርጁ

0
0

የኢትዮጵያ የአንድነትና የዲሞክራሲ ሃይሎች በጠላት ጥቃት ደርሶባቸው ተጎድተው ተሸማቀው አንገታቸውን እንዲቀብሩ ሲገደዱ አድርባይ ሃይሎች በመድረኩ መቧረቃቸው የሚጠበቅ ነው፤ይህንን ጊዜያዊ ክስተት እንደ ዘላለማዊ ሃቅ የሚወስዱ ካሉ እጣ ክፍላቸው ተስፋ መቁረጥና ጨለምተኝነት ይሆናል። ከጨለማው ባሻገር የኮከቢቱን ብርሃን የሚያዩ ግን ለወያኔ ግፍ የማይበገሩ የሃቅን አሸናፊነት እና የኢትዮጵያን ትንሳኤ አይጠራጠሩም።
Tensaye
ሊነጋጋ ሲል ይጨልማል እንደሚባለው ዛሬ ወያኔ የተባለው መርገምት የጣር በትሩን በዘጠና ሚሊዮን ህዝብ ላይ እያሳረፈ ይገኛል፤ይህን የግፍ አገዛዝ ለመቋቋም ዜጋው ሁሉ እምቢኝ አልገዛም እያለ በሁሉም አቅጣጫ ሁሉንም የትግል አይነት ያልጀመረው ለመጀመር የጀመረው ለመቀጠል እየተሟሟቀ በሚገኝበት በአሁኑ ሰዓት ይህን ሃቅ እያዩ እንዳላዩ እየሰሙ እንዳልሰሙ የሚሆኑት ፍጥሮች ያለመንቃት መብታቸው የተጠበቀ ቢሆንም እኛ ግን ከተስፋው መቁረጥ አለም የሌለንበት ሁሉንም ጸረ ወያኔ ሃይላት የማበረታቻ ቃል ብቻ ሳይሆን አቅማችን የፈቀደውን ሁሉ ለመለገስ በያለንበት ዝግጁ መሆናችንን እንገልጻለን፤ዛሬ በሃገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች፣ የመብት ጠያቂዎች፣ የድምጻችን ይሰማ ሚሊዮን ሙስሊሞች ሌሎችም ተጠቂ ዜጎች በሙሉ እያስገመገሙት ያለው ህዝባዊ እምቢተኝነት፤ በሌላው ፈርጅ ደግሞ ተምቹን የወያኔ ስርአት በብረት ለመፋለም ስልታቸው ያደረጉ የነጻነት ታጋዮች በሙሉ በየፈርጃቸው ይበርቱ እያልን እኛም በውጪው አለም በስደት ያለነው የዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል አባሎች ከኢትዮጵያ ውጪ ብንሆንም ኢትዮጵያ ግን ከኛ ውጪ አይደለችምና የበለጠ ለመትጋት ያለንን አቋም በኢትዮጵያ ስም ነው የምናረጋግጠው።

እኛ በተለያዩ የትግል ስልት በሚታገሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ስር ያለንና እንዲሁም በአገር ወዳድነት ስም በግልም የምንቀሳቀስ ከሌሎች የመብትና የፍትሕ ተቋሞች ጋር በጋራ እየሰራን ያለን ስንሆን በመጨረሻው ሰዓት ባለው ግፈኛ የወያኔ ስርዓት ላይ ትግሉን በማጧጧፍ ለእምቢተኝነቱ ትግል የአቅማችንን ሁሉ እያደረግን እንዳለን ስንገልጽ አበክረን የምንለው ነገር አለ፤ ለጋራ ሃገራችን ኢትዮጵያ፣ ለሁላችን ጠላት ከሆነው የወያኔ ስርዓት ለመገላገል ዋናው አብነቱ የታጋዮች ህብረት ነውና በማንኛውም አይነት የጸረ ወያኔው የትግል አምባ የተሰለፉት ሁሉ በየፈርጃቸው እንዲተባበሩ እና በጋራ እንዲሰሩ ስንል በትሕትና እንጠይቃለን።

ይህ በሆነበት በትንንሽ ነገሮችና በትግል አካሄዶች የሃሳብ ልዩነት ቢኖርንም ልዩነቱን በውይይት እየፈታን በዋናው ጠላት ላይ እያበርን ትግላችንን እስከድል ደጃፍ እንቀጥል እንላለን፤ ነገር ግን ይሄንን እየተቀጣጠለ የሚገኘውን የህዝብ ትግል በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በማንኛውም መልኩ ለመጉዳት ወይም ለመከፋፈል የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲያቆሙ እየጠየቅን ነገር ግን በአፍራሽ ድርጊታቸው የሚቀጥሉበት ከሆነ በዝምታ እንደማንመለከታቸው እንገልጻለን።

ኢትዮጵያ በአንድነት እና በነጻነት ለዘላለም በክብር ትኖራለች!!!

The post ከዲሲ ግብረሃይል የተሰጠ መግለጫ: የነጻነት ትግሉን በየፈርጁ appeared first on Zehabesha Amharic.


የምርጫ ክርክር አንድ፡ መድበለ ፓርቲ ሰርዓት እና ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብት- በእኔ ዕይታ

0
0

ግርማ ሠይፉ ማሩ
girmaseifu32@yahoo.com; www.girmaseifu.blogspot.com
ተከራካሪ “ፓርቲዎች”
ኢህአዴግ፤ አቶ አሰመላሽ ገ/ስላሴ እና አቶ ሬድዋን ሁሴን (ዋና ተከራካሪ ማን እንደሆነ ባይነገርም ይታወቃል)
አትፓ፤ አቶ አሰፋው ጌታቸው
መድረክ፤ ዶር መረራ ጉዲና
ሰማያዊ፤ አቶ ይልቃል ጌትነት እና አቶ ዮናታን ተሰፋዬ
“አንድነት”፤ አቶ ትዕግሰቱ አወሉ

redwon Husseinከዚህ በታች የማቀርበው አስተያየት የግል ምልከታዬን ሲሆን፤ ሰዎች በተለያየ አረዳድ ሊኖራቸው እንደሚችል መታወቅ ይኖርበታል፡፡ በዘንድሮ ክርክር አንድ ጥሩ ነገር የውይይት ቅደም ተከተል በተራ እንዲሆን መደረጉ ሲሆን ይህ ኢህአዴግ የተሳሳተ መረጃና መደምደሚያ ሰጥቶ አድማጭ እንዳያደናገር ቢያንስ እድል ፊቷን አዙራበታለች፡፡ የመጨረሻውን መልካም እድል ያገኘው “የድንኩ አንድነት” ተወካይ አቶ ትዕግሰቱ አወሉ ቢሆንም በሙሉ ልብ የሚያከራክር ልዕልና ባለመያዙ ይህን ዕድል አልተጠቀመበትም፡፡ ሁለም ፓርቲዎች ከዋና ተከራካሪ በተጨማሪ አንድ አማካሪ ይዘው የገቡ ሲሆን ከሰማያዊ ፓርቲ በስተቀር ሌሎቹ ዕድል ሳያገኙ ወጥተዋል፡፡ ምክር ስለመስጠታቸውም ተመልካቾች እርግጠኞች አይደለም፡፡ አቶ ትዕግሰቱ አወሉ ይዞት የመጣው ግለሰብ ግን ሊመክረው እንደማይችል እርግጠኛ ነኝ፡፡ አንድነትን ድንክ በማድረግ ለዋለው ውለታ በቴሌቪዥን እንዲታይ ብቻ ይመሰለኛል፡፡ የዚህን ያህል እንደ መግቢያ ካልኩ ይበቃኛል፡፡
Dr.-Merara-Gudina
ኢህአዴግ ለ2007 ምርጫ ክርክር አዲስ ሀሳብ ሆነ አዲስ ሰው እንደሌለው ያረጋገጠበት መድረክ ነበር፡፡ ኢህአዴግ አብዮታዊ ወይም ልማታዊ ዲሞክራሲ እያለ በተለያየ ስም የሚጠራውን መስመር (ርዕዮተዓለም ሊባል ስለማይቻል) የሚያስረዱለት ዋነኛውን ሰው አቶ አስመላሽ ገብረስላሴን፤ እንደ አሰፈላጊነቱ ያለምንም ይሉኝታ ሊሳደቡ የሚችሉትን የስድብ አባት የሆኑትን አቶ ሬድዋን ሁሴንን ይዞ በክርክር መድረኩ ላይ ተሰይሞዋል፡፡ ኢህአዴግ የተሰጠውን የመጀመሪያ 15 ደቂቃ አሁንም ደርግን በጣለበት ጀግንነት ሰሜት ውስጥ ሆኖ አውቀው ይሆን ሳያውቁ 24 ዓመትን እንደ 24 ስዓት እንድንቆጥር እያደረጉ (በዕለቱ 24 ዓመት ለማለት 24 ሰዓት ይሉ ነበር፡፡) የለመድነውን በመንግሰትነት የሰሩትን ሰራ በፍፁም ከተቃዋሚዎች ጋር ሊወዳደሩበት የማይገባቸውን ተግባር እያነሱ ሲጥሉ ጨርሰውታል፡፡ ለተቃዋሚዎች ምንም እውቅና ለመስጠት ሳይዘጋጁ እውቅና በመሻት ሰሜት ውስጥ ሆነው ኦሮጌ የሆነውን የመነሻ ሀሳባቸውን አቅርበዋል፡፡ የ2002 ክርክር በድጋሚ ቢቀርብ ለውጡ አቶ አሰመላሽ የተኳቸው ተከራካሪ ያለመኖር ብቻ ነው፡፡

ቀጣዩን መድረክ በቅድሚያ የተረከበው አዲስ ትውልድ ፓርቲ በመባል የሚታወቀው የአቶ አስፋው ጌታቸው የግል ፓርቲ ነው፡፡ የግላቸው መሆኑን መጠራጠር አያስፈልግም፡፡ የቅስቀሳ ፅሁፍ ከማንበብ ጀምሮ በማንኛውም ስብሰባ ላይ ብቸኛው ተወካይ የሆኑት እኚህ ሰው በእርግጥ ሰማቸው እንደሚለው ይህን ትውልድ አይወክሉም እንጂ፤በመጀመሪያው ዙር ለትውልድ ማፈሪያ በሚሆን ደረጃ ለክርክር ቀርበው አግኝተናቸዋል፡፡ እንደ ዕድል ሆኖ ከተቃዋሚ ተብዬዎቹ የመጀመሪያ በመሆናቸው ደግሞ በቀጣይ ለሚከራከሩት ሰዎች ማፈሪያ በሚሆን አጀማመር የጀመሩትን ከፍ ለማድረግ አስቸጋሪ ሁኔታ እንደፈጠሩባቸው መረዳት ቀላል ነበር፡፡ በግልፅ ለታዘበ አቶ ይልቃል ጌትነት ከጎናቸው ሆነው ሲሸማቀቁ ላየ ሰው የአቶ አስፋው ጌታቸው የመከራከሪያ ነጥብም ሆነ መንገድ በሌሎች ተከራካሪዎች ላይ ጉዳት አላደረሰም ሊባል አይችልም፡፡ ከጎን ላሉት አይደለም ቤታችን ለተቀመጥን ለእኛም ማፈሪያ የነበረ ክርክር አጀማመር ነው፡፡
Hiber Radio Interview with Eng Yilkal Getnet
አቶ አስፋው ጌታቸው ለክርክር ስለተመረጠው አጀንዳ “የመድበለ ፓርቲ ስርዓትና ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች” ጉዳይ አንድ ቃል ሳይተነፍሱ ስለ አረንጓዴ ቀለም ትርጉም ከረባታቸውን እና በኪሳቸው የሸጎጡትን ብጣሽ ጨርቅ እያሳዩ የተሰጣቸውን ውድ ጊዜ አጠናቀውታል፡፡ ከአረንጓዴ ትንታኔ በተጨማሪ የነገሩን ነገር ቢኖር ከኢህአዴግ ጋር ግብ ግብ ለመግጠም እንደማይፈልጉ ምለው መገዘታቸው ብቻ ነው፡፡ በእኔ እምነት አቶ አስፋው ጌታቸውም ሆኑ ፓርቲያቸው እንደ ሰማቸው ይህን ትውልድ ሊወክሉ አይችሉም፡፡ አቶ አስፋው ጌታቸው በዚህ ውድ ጊዜ ውስጥ ስለ ግል የትምህርት ዝግጅትና ግላዊ ጉዳይ ለማውራት የወሰዱት ጊዜ በኢትዮጵያ ስለ አለው አስከፊ የሰብዓዊ መብታ ሁኔታ ለመናገር ድፍረት ማጣታቸው አሳዝኖኛል፡፡ ይህን አዲስ ትውልድ እወክላለሁ የሚል ፓርቲ የዞን ዘጠኝ በመባል እስር ቤት ያሉት ብሎገሮች እና ጋዜጠኞች እንዲሁም እነ ሀብታሙ አያሌው እና ሌሎች ትንታግ የዚህ ትውልድ ወኪሎች ማንሳት ነበረበት፡፡ ይህ ትውልድ ወኪል አጥቶ ሳይሆን ሁነኛ ወካዮቹ ቤታቸው በገዢው ፓርቲ ውሳኔ ወህኒ መሆኑ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን ይህ ትውልድ በምንም ሁኔታ በአዲስ ትውልድ ፓርቲ እና በአቶ አስፋው ጌታቸው አይወከልም፡፡

አቶ ሬድዋን እና አቶ አሰመላሽ በሁለተኛው ክፍለ ጊዜ ባገኙት 20 ደቂቃ በጅምላ ተቃዋሚዎችን በተለይ ሰመያዊና መድረክ ላይ ያደረጉት ውረፋ አቶ አሰፋው ጌታቸውንም ያስቆጣቸው ይመሰላል፡፡ በመጀመሪያ ካቀረቡት የመነሻ ኃሳብ በእጅጉ በተሻለ ሁኔታ የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነት የሌለው መሆኑ፣ ኢህአዴግ ርዕዮት ዓለም የሚባል ነገር የሌለው ብቻ ሳይሆን ከኮሚኒዝም እሰከ ነጭ ካፒታሊዝም የሚረግጥ በግለሰቦች ትርጉም የሚመራ ግንባር እንደሆነ አሰቀምጠዋል፡፡ በተለይ ድፍረት አጥተው በግልፅ አይናገሩት እንጂ በተቃዋሚዎች ውስጥ ካለው ክፍፍል በከፋ በኢህአዴግ ውስጥ ያለው የሃሳብ ልዮነት ለከፋ ክፍፍል የሚባቃ እንደሆነ ነገር ግን ስልጣን ላይ በመሆናቸው ግልፅ የሆነ መከፋፈል እንዳላሰዩ ገልፀዋል፡፡ በእኔ እምነት በኢህአዴግ ሰፈር ለመከፋፈል የሚሰጠው ምላሽ በጠብምንጃ የታገዘ እና ወደ ወህኒ የሚያስወረውር እንደሆነ መቀመጥ ነበረበት፡፡ ከዚህ ካመለጡ ደግሞ ሰደት ይሆናል፡፡

ዶክተር መረራ ጉዲና እሰከ ዛሬ ያለቸውን አውቀት ተጠቅመው እንደ ሁልጊዜ በተረጋጋ ሁኔታ በግልፅ በኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት የሌለ መሆኑ በማሰቀመጥ ከርዕሱ ጋር ተዛማጅ የሆነ ጉዳይ አንስተዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ዶክተር መረራ በእኔ እምነት ከፖለቲካው ግንባር ቢለቁ የምመርጥ ቢሆንም ከቀረቡ ወዲህ ግን አዲስ ነገር ይዘው መመጣት አለባቸው የሚል እምነት አለኝ /ዛሬም የጥብቆ እና የሚኒሊክ አልጋ ምሳሌ ቢቀር እመርጣሁ/፡፡ ኢህአዴግ አብዮታዊም ወይም ዲሞክራሲያዊም ያለመሆኑን ያስረዱበት መንገድ ተመችቶኛል፡፡ ዶክተር መረራ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ጉዳይ ሲነሳ አበክረው ሊያነሱት የሚገባ የነበረ ነገር ግን የዘነጉት ከጎናቸው ተወስደው በእስር የሚማቅቁትን አባላቶቻቸውን ነው፡፡ እነ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ሌሊሳ እና ሌሎች የኦሮሞ ልጆችን በሰም ጠርተው የሚደርሰብቻውን ግፍ ለህዝብ ማሳየት አልቻሉም፡፡ የኦሮሞ ልጆች ከምንጊዜውም በላይ እየደረሰባቸው ያለውን የሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት ሊያሳዩን ሙከራ አላደረጉም፡፡ በኢትዮጵያችን በአሁኑ ጊዜ ከኦሮሞ ልጆች እኩል በደል የደረሰበት ያለ አይመስለኝም፡፡ ዶክተር መረራ ለፓርቲዎች ውህደት ጥያቄ ሲቀርብ ኦሮሞነታቸውን የሚያጎሉትን ያህል በሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት ብሔረተኝነታቸውን ሊጠቀሙበት አለመቻላቸው ተገቢ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡ ለመራጮቻቸው በዚህ ርዕስ ጉዳይ ከዚህ የተሻለ ማሰረጃ ሊሰጥዋቸው የሚችሉበት አጋጣሚ ሊያገኙ የሚችሉ አይመስለኝም፡፡ ለምሳሌ ህገ መንግሰታዊ መብታቸውን ተጠቅመው ሰልፍ የወጡ የአምቦ ዮኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ነዋሪዎች በጥይት የተሰጣቸው መልስ ትክክል ያለመሆኑን ለማስረዳት ከዚህ የተሻለ ጊዜ የሚያገኙ አይመስለኝም፡፡ መብቶችን ለመጠቀም ሁል ጊዜ የሚነሳው ጉዳይ ልክ መሆን አይኖርበትም፡፡
ኢህአዴግ በሁለተኛ ክፍለ ጊዜ ባደረገው ጉንተላ እጅጉን ተበሳጭተው መስመር ከሳቱት በዋነኝነት የሚጠቀሱት ዶክተር መረራ ናቸው፡፡ ተማሪያቸው የነበረው አወያይ ጋዜጠኛ እስኪያቋርጣቸው ድረስ መስመር ጥሰው ሄደዋል፡፡ ርዕሱ “መድበለ ፓርቲ፣ የሰብዓዊና ዲሞክራሲያ መብቶች” ሆኖ እያለ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ ጉዳዮችን አንሰተው ጊዜያቸውን ጨርሰውታል፡፡ ከውይይት ርዕሱ ጋር የማይሄዱ ነጥቦችን ኢህአዴግ አማራጭ የላቸውም አለን ብለው አድማጭ ሊይዘው በማይችለው ደረጃ ዝርዝሩን ዘርግፈውት በተገቢው ሁኔታ የወከሉትን ግንባር ምልክት እንኳን ሳያስተዋውቁ አጠናቀዋል፡፡ ለሌላ ጊዜ ለክርክር የሚቀርቡ ተከራካሪዎች በወረቀት ላይ የታተመ የምርጫ ምልክት ይዘው መግባት የሚጠቅማቸው ይመስለኛል፡፡

አቶ ይልቃል ጌትነት በአቶ አሰፋው ጌታቸው የክርክር ሂደት በግልፅ በሚታይ መልኩ የደረሰባቸውን መሸማቀቅ በዶክተር መረራ ዘና ያላ አቀራረብ ዱካኩ የተገፈፈላቸው ቢሆንም በቅድመ ክርክር ወቅት የነበረውን ነጥብ አምጥቶ ካለቸው ውድ ጊዜ ለመጠቀም መወሰናቸው እንደ ሁልጊዜውም አጋጣሚውን ለህዝብ ግንኙነት ስራ መጠቀም የፈለጉ ያስመስለዋል፡፡ ክርክሩ ላይ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት የለም ብሎ በግልፅ ያስቀመጡት አቶ ይልቃል የሰብዓዊ መብትን ለማቅረብ የሄዱበት መስመር ሰብዓዊና ዲሞክራሲያ መብቶችን ለህዝብ በሚገባው ግልፅ ምሳሌ ከማቅረብ ይልቅ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያው መብቶችን በመቀላቀል ማቅረባቸው የዝግጅት እጥረት እንደነበረባቸው ለመረዳት አያስቸግርም፡፡ በሰው ፊት ለንግግር ሰንቀርብ ሀምሳ ከመቶ ዝግጅት መሆኑን አቶ ይልቃል የዘነጉት ይመስላል፡፡ ከዝግጅት አንፃር ተዝረክርከው ማስታወሻውን ወደፊት ወደኋላ ሲገልፁ የነበሩትን አቶ አስፋው ጌታቸውን ማንሳት ሳያስፈልግ ነው፡፡

አቶ ይልቃል በሁለተኛውም ዙር የተሰጣቸውን ጊዜ በአግባቡ ከመጠቀም ይልቅ የተሰጠው ጊዜ አንሰተኛ መሆኑን በሚገልፅ ቅሬታ ጊዜ ሲያባክኑ ነበር፡፡ በሁለተኛው ዙር አቶ ይልቃል ያስቆጠሩት ዋነኛ ነጥብ አቶ አስመላሽ ሰለ ሰመያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉበዔ አጠራር አሰመልክቶ ያነሱት ነጥብ ነው፡፡ ይህ ነጥብ ኦቶ ይልቃል ከመረጃ እጥረት በሚል እወሰደዋለሁ ቢሉም ይህ የጠቅላላ ጉባዔ ጉዳይ ህወሃት/ኢህአዴግ ከምርጫ ቦርድ ጋር ለሰማያዊ ፓርቲ ከተቀመሙት መርዞች አንዱ እንደሆነ ሁሉም ማወቅ አለበት፡፡ አቶ አስመላሽ የሰማያዊ ፓርቲ ደንብ ጊዜ አግኝተው ሊያነበትም ሆነ ሊያስነብቡ አይችሉም፡፡ አንብበው ፓርቲ ማፍረሻ ቀዳዳ የሚያቀብሉ በምርጫ ቦርድ የተቀመጡ ወኪሎቸ አሉ፡፡ ለዚህ ቅብብል የሚሆን ደግሞ የተዘረጋ ህጋዊ የሚመስል መስመር እንዳለ ሁላችንም እናውቃለን፡፡ ለማነኛውም አቶ ይልቃል የነበረውን ጊዜ በርዕስ ጉዳዩ ላይ ብቻ አተኩረው በምድር ላይ ባለ የሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት አሰደግፈው መከራከር አልቻሉም፡፡ እንደ ዶክተር መረራ በኢህአደግ ትንኮሳ መበሳጨታቸው ቢታወቅም ለመረጋጋት ያሰዩት ጥረት ጥሩ ነበር፡፡ ኢህአዴግ ዘመኑን የዋጀ ፓርቲ አይደለም እራሱን የሚያወዳድረው ከንጉሶች ወይመ ከደርግ ጋር ነው፣ መሻሻል የማይፈልግ ፓርቲ ነው፡፡ በሚል ያነሱት ነጥብ በኢትዮጵያ ህዝብ ሊያዝ የሚችል አንኳር ጉዳይ ነው – በምርጫ ካርድ ይሁን በህዝባዊ አመፅ ግልፅ ሆኖ አልተቀመጠም፡፡

የመጨረሻውን እድል ያገኘው የድንኩ “አንድነት” መሪ የሆነው አቶ ትዕግሰቱ አወሉ ነው፡፡ አቶ ትዕግሰቱ ከሌሎቹ በተሻለ የሰብዓዊ መብት ለመርገጥ ገዢው ፓርቲ እየተጠቀመበት ያለውን “የፀረ ሽብር ህግ” አንስቶ ለመሞገት ሞክሮዋል፡፡ በምንም መልኩ ግን አስተያየት ሊሰጥበት ያልቻለው ግን የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ጉዳይ ነው፡፡ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ትዕግሰቱ በትክክል ያውቀዋል፡፡ በኢህአዴግ ኢትዮጵያ ይህች ያገኛትን ቦታ በአባላት ይሁንታ ሳይሆን በተደራጀ ሾኬ እንዳገኛት ስለሚያውቅ መድበለ ፓርቲ ስርዓት የለም ሊል አልደፈረም፤ ቢያንስ በመግቢያው ንግግር፡፡ የሚገርመው ግን አሁንም “አንድነትን” ሲጠራ አፉ ይተሳሰራል፡፡ “እንደ አንድነት ማለትም እንደ እኛ አመለካከት” ሲል ውስጡ ያለው የአንድነት መንፈስ እንዳልሆነ ያሳብቃል፡፡ ትዕግሰቱ የአንድነትን አቋም በሙሉ ልቡ ሊናገር የሚችልበት የሞራል ልዕልና ላይ እንደሌለ በሚያሳብቅበት ሁኔታ ላይ ነው የሚገኘው ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም፡፡

አቶ ትዕግሰቱ አወሉ ስለሚያቀርበው ሃሳብ ያለኝን የግል ንቀት ለመተው እየሞከርኩ ቢሆንም ለመያዝ የሞከርኩት ነጥብ የዲሞክራሲ ተቋማት የይስሙላ መሆናቸውን ገልፆ በተለይ ምርጫ ቦርድን ጠቅሶ መለወጥ እንዳለበት ሲናገር የበላበትን ወጨት ሰባሪ ቢያደርገውም እውነት መናገሩን ግን መካድ አይቻለም፡፡ ኢህአዴግ ህዝቡን አፍንጫህን ላስ የሚል ፓርቲ መሆኑን መግለፁም ትክክል ነው፡፡ በዚህ አስተያየቱ ኢህአዴግ ተጨማሪ እድል ባለማግኘቱ ምን እንደሚከተለው ማወቅ አይቻልም፡፡ ለማነኛውም ጌቶቹን በተለይ ምርጫ ቦርድ ታዛዥነቱን አይቶ በሰጠው ወንበር ሰሙን ጠርቶ መዝለፉ ሽርክናቻው አንድነትን ድንክ እሰከማድረግ ብቻ አስመስሎባቸዋል፡፡

የኢህአዴግ የምላሽ ወቅት ሰለባዎች እንደሚጠበቀውም ሰመያዊና መድረክ ነበሩ፡፡ የፈለገ ጠንካራ ተቃውሞ ቢያቀርቡም “አትፓ እና ድንኩ አንድነት” በኢህአዴግ አፍ ለዘለፋ አይፈለጉም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ድንኮች ምንም በማያመጣ መልኩ ተሰርተዋል ተብሎ ስለሚታመን ነው፡፡ አንድነትን ድንክ በማድረግ ሂደት ዋነኛዎቹ ተዋናዮች የነበሩት ሁለቱም የኢህአዴግ ወኪሎች አንድ ጊዜ እንኳን አንድነትን ሳይዘልፉ ይልቁንም ጅምሩ ጥሩ ነው በሚል ማለፋቸው ሰራቸው ማጠናቀቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ የኢህአዴግ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት መገለጫ ተብለው የቀረቡልን ምሳሌዎች ግን ተጨፈኑ ላሞኛችሁ ነገር ነው፡፡ እነርሱም፤

አሁን 75 ፓርቲዎች በሀገራችን መኖራቸው የመድበለ ፓርቲ መገለጫ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም አሁን ለክርክር የቀረቡት ፓርቲዎች መኖር ዋናኛ ማሳያ ነው፡፡ እንደ ኢህአዴግ በፓርቲ ምዝገባና ቁጥር የመድበለ ፓርቲ ቢለካ እውነት ነበር፡፡ በወረቀት የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዳለ ሳይካድ በተግባር ገን የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዲኖር የማይፈቅደው ኢህአዴግ ጉንጭ አልፋ ክርክር ያቀርባል፡፡ እምነታቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኪራይ ሰብሳቢዎች ናቸው ብለው እንዲጠፉ እየሰሩ ለእርዳታ ሰጪዎች ፍጆታ የፓርቲነት ሰርተፊኬት በማደል የመድበለ ፓርቲ ስርዓት አለ ብለን እንድናምን ይፈልጋሉ፡፡ በአሜሪካን ሀገር በዋነኝነት ሁለት ፓርቲዎች መኖራቸው ዲሞክራሲ ያለመኖሩ ማሳያ ነው እንደማለት ነው፡፡ የኢህአዴግ ጉንጭ አልፋ ክርክር፡፡

ለምርጫ ውድድ የቀረቡ ዕጩዎች ሌላኛው የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ማሳያ አድርገው ኢህአዴጎች አቅርበዋል፡፡ ማንም እድሉን ሊሞክር ለምርጫ ዕጩ ሆኖ እራሱን ማቅረብ ለመድበለ ፓርቲ ስርዓት ማሳያ እንዴት ሊታይ እንደሚችል አቶ አሰመላሽ እና አቶ ሬድዋን ብቻ ናቸው የሚያውቁት፡፡ ይህ በቅርቡ የመጣ የመድበለ ፓርቲ ስኬት መገለጫ ነው፡፡

ለምርጫ ማስፈፀሚያ የተመደበው በጀት ደግሞ ሌላው የመድበለ ስርዓት ስለመኖሩ ማሳያ ተድረጎ ነው የተብራራልን፡፡ አስገራሚው ነገር ከተመደበው ገንዘብ አብዛኛውን የሚወሰደው ገዢው ፓርቲ መሆኑ እየታወቀ፤ ፓርቲዎች በምርጫ ሰሞን በሚያገኙት በዚህ ገንዘብ የመድበለ ፓርቲ ስርዓትን ለማጠናከር ምን ሊያደርጉበት እንደሚችሉ ማሰረዳት አይችሉም፡፡ ተመደበ የተባለው ገንዘብ ዋነኛው ወጪ ከ45 ሺ በላይ ለሚሆኑ ምርጫ አስፈፃሚዎች አበል ሲሆን፤ ለአንድ ዕጩ ተወዳዳሪ ብር 500 በማይደርሰበት ሁኔታ ይህ ገንዘብ እንዴት እንደሚጠቅም ኢህዴጎች ሊያስረዱን አይችሉም፡፡

በጣም ያስገረመኝ አንዱ መከራከሪያ “የመድበለ ፓርቲ በሊብራል ዲሞክራሲ በሚያራምዱ ሀገሮች ለብሔር ብሔረሰቦች የማይፈቅድ ነው” የሚልው ነው፡፡ ኢትዮጵያን የተለየች የብሔር ብሔረሰቦች መኖሪያ አድርጎ ለማሳየት የሚደረገው የተሳሳተ ነገር አሁንም ቅጥ ያጣ ይመስላል፡፡ በዓለም ላይ አሉ የሚባሉ ብሔሮችና ብሔረሰቦች በሙሉ የሚኖሩባት ሀገር አሜሪካ ውስጥ በፈለጉት ቡድን ለመደረጃት አንድም ጥያቄ እንደማይቀርብ የምናውቅ አይመስላቸውም፡፡ ሊብራል ዲሞክራሲን ያለ ስሙ ሰም እየሰጡ የራሳቸውን የፖለቲካ መስመር አንዴ አብዮታዊ ሌላ ጊዜ ልማታዊ ዲሞክራሲ እያሉ ሊያደናብሩን ይፈልጋሉ፡፡ ይህ የብሔርና ብሔረሰብ ፖለቲካ ጉዳይ ሲነገር የሚያስታውሰን አንድ ነገር “ለምለሚቱ ሀገሬ” የሚለው ነገር ነው፡፡ በሌሎች ሀገራት ሳር የማይበቅል፣ ወተት ማር የማይገኝበት፣ ወዘተ ይመስለን የነበረው ዓይነት አሳሳች ምሳሌ ነው፡፡

በመጨረሻም በክርክሩ የነበሩ ተቃዋሚ እና “ተቃዋሚ ተብዬ” ፓርቲዎች በኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ግንባት ውይይት ሲደረግ በቅርብ ርቀት በአንድነት ላይ የተፈፀመውን የመንግስታና ለመድበለ ፓርቲ ስርዓት ግንባት ለማጠናከር መቆም ያለበትን ምርጫ ቦርድ ሴራ በምሳሌ አንስተው ለመሞገት ያለመሞከራቸው፤ በተለይ መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ የአንድነት ድንክ መሆን እነሱን ከፍ ማድረጉን በግልፅም ባይሆን በውስጣቸው የፈጠረላቸውን ደስታ የሚያሳይ ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ አንድነትን ድንክ በማድረጉ ብቻውን እንዳልተጠቀመም ማሳያ ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ የሚችለውን በመምረጥ አንፃር በጣም ተሳክቶለታል፡፡ በዚህ ፅሁፍ ለአንድነት ፓርቲ አመራሮች እግረ መንገዴን የማስታውሳቸው ዘወትር በነበሩን ስብሰባዎች ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ለማስተባበር ስንደክም ከእኛ ይቅር ስንል የነበረው ለእነዚህ ፓርቲዎች መሆኑን ማስታወስ ይኖርብኛል፡፡ በተለይ ሰማያዊ ፓርቲን አስመልክቶ አንድነት ፓርቲ ውስጥ የነበረንን ልበ ሰፊነት ሳስበው በጣም ነው ያዘንኩት፡፡ ለምን አደረግነው የሚል ቁጭት የለብኝም፡፡

አንድነት ፓርቲ በዚህ ክርክር ውስጥ ቢኖር ኖሮ በመጀመሪያ ከኢህአዴግ እኩል ሁሉንም ለመከራከር እድል ነበረው ፓርቲ ይሆን ነበር፡፡ ምክንያቱም 450 ዕጩዎች ለፌዴራል ምክር ቤት እና 1200 የማያንሱ የክልል ምክር ቤት ዕጮዎች ስለሚያቀርብ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ለመከራከር ሊመጡ የሚችሉትን ትንታግ የአንድነት ወጣቶች ሳሰብ እንባ እየተናነቀኝ ነው፡፡ የዛሬ አምሰት ዓመት የዚህን ተመሳሳይ ክርክር አንድነትን ወክሎ የተከራከረው ምን አልባትም በዚህ ክርክር መነሻ ቂም ተይዞበት የነበረው፣ ዛሬ በወህኒ የሚገኘው አንዱዓለም አራጌ ነው፡፡ አንድነት ፓርቲ ክርክሩ ከመደረጉ በፊት በዚህ ጉዳይ ላይ በሚኖረው 6 ደቂቃ የመነሻ ኃሳብ ልናነሳ የምንችለውን ቢያንስ 12 ነጥብ ይዘን እንገባ ነበር፡፡ ወይም 10 ነጥብ እና በቀሪው ሁለት ደቂቃ ለህዝብ ውይይት ሊጭር የሚችል ሃሳብ የሚነሳበት ይሆን ነበር፡፡ ሁለተኛው ዙር ዘጠኝ ደቂቃ በዝርዝር ህገ መንግሰታዊ ድንጋጌዎችን አሰመልክቶ ኢህዴግ የሚሰራቸውን የክርክር ፋውሎች ለህዝብ የምናጋልጥበት ይሆን ነበር፡፡ ለዚህ ነው በ2007 ኢህአዴግ የሚችለውን መርጦዋል የምንለው፡፡

ለማጠቃለል ተቃዋሚዎች በኢህአዴግ ትንኮሳ ተገፍተው በመድበለ ፓርቲ እና በሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ዙሪያ ትኩረት ሰጥተው ለመከራከር አልቻሉም፡፡ ክርክሩን በኢህአዴግ ሜዳ ላይ ለማድረግ ማተኮር የነበረባቸው “ህገ መንግሰት” ላይ የተዘረዘሩትን መብቶች እያነበቡ በተግባር የገጠመውን ፈተና በማቅረብ ህዝቡ እነዚህን ጉዳዮች ገዢው ፓርቲ የአፈፃፀም ችግር ናቸው ቢልም በመርዕ የማያምንባቸው መሆኑን እራሱ ኢህአዴግ ከፃፋቸው የፖሊሲ፣ሰትራቴጂና የርዕዮታለም ትንተና መፅሃፉች ጋር እያጣቀሱ ማስረዳት ነበረባቸው፡፡ የህገ መንግሰቱ ምዕራፍ ሶሰት ክፍል አንድ ከአንቀፅ 14 -28 የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን በማየት በተግባር የገጠሙትን ፈተናዎች፤ ምዕራፍ ሶሰት ክፍል ሁለት ከአንቀፅ 29-44 ዲሞክራሲያዊ መብቶቸን በማየት የገጠሙትን ፈተናዎች በዝርዝር መተንተን ይቻል ነበር፡፡ በዚህ መስመር ክርክሩ ቢደረግ ኢህአዴግ ሊከራከር የሚችለው ህገመንግሰቱን ለማዘጋጀት ህይወትና ደም ተከፍሎበታል ከሚል ፉከራ ውጭ ለምን በተግባር ላይ እንደማያውላቸው ሊያስረዳ አይችልም ነበር፡፡ ምንም በቂ ምክንያት ሊኖር አይችልም የሚል እምነት አለኝ፡፡
ቸር ይግጠመን!!!!

The post የምርጫ ክርክር አንድ፡ መድበለ ፓርቲ ሰርዓት እና ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብት- በእኔ ዕይታ appeared first on Zehabesha Amharic.

የህብር ሬዲዮ መጋቢት 6 ቀን 2007 ፕሮግራም –የኢህአዴግ የደህንነት ሹም ደገሃቡር ውስጥ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ሰሞኑን ተገደሉ ከኢትዮጵያ የተነሳ የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን የአልሸባቡን መሪ መግደሉ ተነገረ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ኢህአዴግ ስልጣኑን ማጣት እንደማይፈልግና የዘንድሮው ምርጫ ግራ የሚያጋባ መሆኑን ገለፁ አሰብ የኢትዮጵያ ናት ልትመለስ ይገባል ብለዋል ኢትዮጵአያ፣ግብጽና ሱዳን ካርቱም ላይ በአባይ ጉዳይ ሊፈራረሙ ነው

0
0

Habitamu<…የኢትዮጵያ ሕዝብ የአገዛዙን ዘረኛ ቅስቀሳ ቦታ መስጠት የለበትም እውነተኛ የሀይማኖት መሪዎችም በሀይማኖት ስም ስርዓቱ አንዱን ከሌላው የሚያደርገውን ማጋጨት ሊያወግዙ ይገባል ።ይህን ስል ግን በሀይማኖት ስም የተሸሸጉ የአገዛዙ ካድሬዎች…> ጋዜጠኛና አክቲቪሰት አበበ ገላው የኢትዮጵያው አገዛዝ በይስሙላው ምርቻ ቅስቀሳ ላይ ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት ስለሚፈጽመው ቅስቀሳ አስመልክቶ ተጠይቆ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡ)

<…የኢትዮጵያ ሕዝብ ተቻችሎ የኖረ የዘመናት ታሪክ ባለቤት ያለው በመሆኑ ህወሃቶች እድሜያቸውን ለማራዘም በሀይማኖትና በብሄር ለማጋጨት የሚያደርጉትን ሴራ ጠንቅቆ ያውቃል…በሀይማኖት ስም የተሸሸጉ ሀሰተኛ ካድሬ የሀይማኖት ወኪሎችን ሴራ ማወቅ ያስፈልጋል ዱርዬዎችን አንስተው የሙስሊሙ ወኪሎች ሲሉ በቅርቡ አይተናል…> ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ በይስሙላው ምርጫ ወቅት ስለሚደረጉ የአገዛዙ ዘርን ከዘር ሀይማኖትን ከሀይማኖት የማጋጨት ሴራዎች ላይ አስቀድሞ ሊወሰድ ስለሚገባው ጥንቃቄ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ (ሙሉውን ያዳምጡ)

<…የዘንድሮው ምርጫ ቅርጫ ለመሆንም አልቻለም…ኢህአዴግ ሁለቱን ምርኩዞቹን ጠመንጃውንና ምርጫ ቦርድን ይጣልና በአንድ ወር እኛ እናሸንፈዋለን…ፕ/ት ግርማ እንኳን ቤተ መንግስት ከመግባታቸው በፊት የእኛ ወዳጅ ነበሩ…> ዶ/ር መረራ ጉዲና ስለወቅታዊው የምርቻ ቅስቀሳ፣ ስለ ቀድሞው ፕ/ት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ወቅተቀዊ አስተያየት ጠይቀናቸው ከሰጡን ቃለ ምልልስ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

ዶ/ር ቴዎድሮስን ጨምሮ እነ አዶልፍ ሒትለርም እንደሳቸው ከሚዋሹ ፖለቲከኞች መካከል ይጠቀሳል። ሌሎቹስ(ልዩ ጥንቅር ስለ ውሸታም ፖለቲከኞች)

ሌሎችም ዜናዎቻችን

የኢህአዴግ የደህንነት ሹም ደገሃቡር ውስጥ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ሰሞኑን ተገደሉ

ከኢትዮጵያ የተነሳ የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን የአልሸባቡን መሪ መግደሉ ተነገረ

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ኢህአዴግ ስልጣኑን ማጣት እንደማይፈልግና የዘንድሮው ምርጫ ግራ የሚያጋባ መሆኑን ገለፁ

አሰብ የኢትዮጵያ ናት ልትመለስ ይገባል ብለዋል

ኢትዮጵአያ፣ግብጽና ሱዳን ካርቱም ላይ በአባይ ጉዳይ ሊፈራረሙ ነው

ግብፅ ከወዲሁ ኢትዮጵያ ከመጠን ያለፈ ውሃ ካከ

ማቸች ስጋቴ ዘላለማዊ ነው ስትል አስጠነቀቀች

በደቡብ ኦሞ አጠገብ የሚገኙ አርብቶ አደሮች በልማት ስም እየሞትን ነው አሉ

በኢትዮጵያ 2.9 ሚሊዮን ህዝብ በአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይፈልጋል ተባለ

ዶ/ር መራራ ጉዲና በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለመኖሩ ማስረጃ አምጡ በሚል ከአገዛዙ የኦሮምኛ ቋንቋ ቴሌቪዥን የምርጫ ክርክራቸው መታገዱን ገለጹ

ለውጥ ፈላጊው ለኢህአዴግ የከፋፍለህ ግዛ ትኩረት ሳይሰጥ በጋራ እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል

አንድ የእንግሊዝ የፓርላማ አባል ኢትዮጵያ አወዛጋቢውን የባድመን አካባቢ ለኤርትራ እንድትሰጥ ጠየቁ

ኤርትራ በብሔራዊ ውትድርና ስልጣኖች ላይ የምታደርገው ጫና ለመቀነስ ማቀዷን ገለፀች

በፈርጉሰን ሁለቱን ፖሊሶች ገሏል የተባለው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

ሚሼል ኦባማን ዘረኛ ስድብ የተሳደበው ጋዜጠኛ ከስራ ተባረረ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

(ህብርን ከዘሐበሻ፣አፍሮ አዲስ ድህረ ገጾችእና በሌሎችም ያዳምጡ። በተጨማሪ በማንኛውም ቀን በስልክ ለማዳመጥ 2139924347 ይደውሉ)ነ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በ1340 ኤ.ኤም የአየር ሞገድ ያዳምጡ። በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው።

The post የህብር ሬዲዮ መጋቢት 6 ቀን 2007 ፕሮግራም – የኢህአዴግ የደህንነት ሹም ደገሃቡር ውስጥ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ሰሞኑን ተገደሉ ከኢትዮጵያ የተነሳ የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን የአልሸባቡን መሪ መግደሉ ተነገረ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ኢህአዴግ ስልጣኑን ማጣት እንደማይፈልግና የዘንድሮው ምርጫ ግራ የሚያጋባ መሆኑን ገለፁ አሰብ የኢትዮጵያ ናት ልትመለስ ይገባል ብለዋል ኢትዮጵአያ፣ግብጽና ሱዳን ካርቱም ላይ በአባይ ጉዳይ ሊፈራረሙ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

የምርጫ ክርክር አንድ፡ መድበለ ፓርቲ ሰርዓት እና ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብት- በእኔ ዕይታ (ግርማ ሠይፉ ማሩ)

0
0

ግርማ ሠይፉ ማሩ / girmaseifu32@yahoo.com;

ተከራካሪ  “ፓርቲዎች”

ኢህአዴግ፤   አቶ አሰመላሽ ገ/ስላሴ እና አቶ ሬድዋን ሁሴን (ዋና ተከራካሪ ማን እንደሆነ ባይነገርም ይታወቃል)

አትፓ፤      አቶ አሰፋው ጌታቸው

መድረክ፤    ዶር መረራ ጉዲና

ሰማያዊ፤    አቶ ይልቃል ጌትነት እና አቶ ዮናታን ተሰፋዬ

“አንድነት”፤  አቶ ትዕግሰቱ አወሉ

(ግርማ ሰይፉ)

(ግርማ ሰይፉ)

ከዚህ በታች የማቀርበው አስተያየት የግል ምልከታዬን ሲሆን፤ ሰዎች በተለያየ አረዳድ ሊኖራቸው እንደሚችል መታወቅ ይኖርበታል፡፡ በዘንድሮ ክርክር አንድ ጥሩ ነገር የውይይት ቅደም ተከተል በተራ እንዲሆን መደረጉ ሲሆን ይህ ኢህአዴግ የተሳሳተ መረጃና መደምደሚያ ሰጥቶ አድማጭ እንዳያደናገር ቢያንስ እድል ፊቷን አዙራበታለች፡፡ የመጨረሻውን መልካም እድል ያገኘው “የድንኩ አንድነት” ተወካይ አቶ ትዕግሰቱ አወሉ ቢሆንም በሙሉ ልብ የሚያከራክር ልዕልና ባለመያዙ ይህን ዕድል አልተጠቀመበትም፡፡ ሁለም ፓርቲዎች ከዋና ተከራካሪ በተጨማሪ አንድ አማካሪ ይዘው የገቡ ሲሆን ከሰማያዊ ፓርቲ በስተቀር ሌሎቹ ዕድል ሳያገኙ ወጥተዋል፡፡ ምክር ስለመስጠታቸውም ተመልካቾች እርግጠኞች አይደለም፡፡ አቶ ትዕግሰቱ አወሉ ይዞት የመጣው ግለሰብ ግን ሊመክረው እንደማይችል እርግጠኛ ነኝ፡፡ አንድነትን ድንክ በማድረግ ለዋለው ውለታ በቴሌቪዥን እንዲታይ ብቻ ይመሰለኛል፡፡ የዚህን ያህል እንደ መግቢያ ካልኩ ይበቃኛል፡፡

ኢህአዴግ ለ2007 ምርጫ ክርክር አዲስ ሀሳብ ሆነ አዲስ ሰው እንደሌለው ያረጋገጠበት መድረክ ነበር፡፡ ኢህአዴግ አብዮታዊ ወይም ልማታዊ ዲሞክራሲ እያለ በተለያየ ስም የሚጠራውን መስመር (ርዕዮተዓለም ሊባል ስለማይቻል) የሚያስረዱለት ዋነኛውን ሰው አቶ አስመላሽ ገብረስላሴን፤ እንደ አሰፈላጊነቱ ያለምንም ይሉኝታ ሊሳደቡ የሚችሉትን የስድብ አባት የሆኑትን አቶ ሬድዋን ሁሴንን ይዞ በክርክር መድረኩ ላይ ተሰይሞዋል፡፡ ኢህአዴግ የተሰጠውን የመጀመሪያ 15 ደቂቃ አሁንም ደርግን በጣለበት ጀግንነት ሰሜት ውስጥ ሆኖ አውቀው ይሆን ሳያውቁ 24 ዓመትን እንደ 24 ስዓት እንድንቆጥር እያደረጉ (በዕለቱ 24 ዓመት ለማለት 24 ሰዓት ይሉ ነበር፡፡) የለመድነውን በመንግሰትነት የሰሩትን ሰራ በፍፁም ከተቃዋሚዎች ጋር ሊወዳደሩበት የማይገባቸውን ተግባር እያነሱ ሲጥሉ ጨርሰውታል፡፡ ለተቃዋሚዎች ምንም እውቅና ለመስጠት ሳይዘጋጁ እውቅና በመሻት ሰሜት ውስጥ ሆነው ኦሮጌ የሆነውን የመነሻ ሀሳባቸውን አቅርበዋል፡፡ የ2002 ክርክር በድጋሚ ቢቀርብ ለውጡ አቶ አሰመላሽ የተኳቸው ተከራካሪ ያለመኖር ብቻ ነው፡፡

ቀጣዩን መድረክ በቅድሚያ የተረከበው አዲስ ትውልድ ፓርቲ በመባል የሚታወቀው የአቶ አስፋው ጌታቸው የግል ፓርቲ ነው፡፡ የግላቸው መሆኑን መጠራጠር አያስፈልግም፡፡ የቅስቀሳ ፅሁፍ ከማንበብ ጀምሮ በማንኛውም ስብሰባ ላይ ብቸኛው ተወካይ የሆኑት እኚህ ሰው በእርግጥ ሰማቸው እንደሚለው ይህን ትውልድ አይወክሉም እንጂ፤በመጀመሪያው ዙር ለትውልድ ማፈሪያ በሚሆን ደረጃ ለክርክር ቀርበው አግኝተናቸዋል፡፡ እንደ ዕድል ሆኖ ከተቃዋሚ ተብዬዎቹ የመጀመሪያ በመሆናቸው ደግሞ በቀጣይ ለሚከራከሩት ሰዎች ማፈሪያ በሚሆን አጀማመር የጀመሩትን ከፍ ለማድረግ አስቸጋሪ ሁኔታ እንደፈጠሩባቸው መረዳት ቀላል ነበር፡፡ በግልፅ ለታዘበ አቶ ይልቃል ጌትነት ከጎናቸው ሆነው ሲሸማቀቁ ላየ ሰው የአቶ አስፋው ጌታቸው የመከራከሪያ ነጥብም ሆነ መንገድ በሌሎች ተከራካሪዎች ላይ ጉዳት አላደረሰም ሊባል አይችልም፡፡ ከጎን ላሉት አይደለም ቤታችን ለተቀመጥን ለእኛም ማፈሪያ የነበረ ክርክር አጀማመር ነው፡፡

አቶ አስፋው ጌታቸው ለክርክር ስለተመረጠው አጀንዳ “የመድበለ ፓርቲ ስርዓትና ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች” ጉዳይ አንድ ቃል ሳይተነፍሱ ስለ አረንጓዴ ቀለም ትርጉም ከረባታቸውን እና በኪሳቸው የሸጎጡትን ብጣሽ ጨርቅ እያሳዩ የተሰጣቸውን ውድ ጊዜ አጠናቀውታል፡፡ ከአረንጓዴ ትንታኔ በተጨማሪ የነገሩን ነገር ቢኖር ከኢህአዴግ ጋር ግብ ግብ ለመግጠም እንደማይፈልጉ ምለው መገዘታቸው ብቻ ነው፡፡ በእኔ እምነት አቶ አስፋው ጌታቸውም ሆኑ ፓርቲያቸው እንደ ሰማቸው ይህን ትውልድ ሊወክሉ አይችሉም፡፡ አቶ አስፋው ጌታቸው በዚህ ውድ ጊዜ ውስጥ ስለ ግል የትምህርት ዝግጅትና ግላዊ ጉዳይ ለማውራት የወሰዱት ጊዜ በኢትዮጵያ ስለ አለው አስከፊ የሰብዓዊ መብታ ሁኔታ ለመናገር ድፍረት ማጣታቸው አሳዝኖኛል፡፡ ይህን አዲስ ትውልድ እወክላለሁ የሚል ፓርቲ የዞን ዘጠኝ በመባል እስር ቤት ያሉት ብሎገሮች እና ጋዜጠኞች እንዲሁም እነ ሀብታሙ አያሌው እና ሌሎች ትንታግ የዚህ ትውልድ ወኪሎች ማንሳት ነበረበት፡፡ ይህ ትውልድ ወኪል አጥቶ ሳይሆን ሁነኛ ወካዮቹ ቤታቸው በገዢው ፓርቲ ውሳኔ ወህኒ መሆኑ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን ይህ ትውልድ በምንም ሁኔታ በአዲስ ትውልድ ፓርቲ እና በአቶ አስፋው ጌታቸው አይወከልም፡፡

አቶ ሬድዋን እና አቶ አሰመላሽ በሁለተኛው ክፍለ ጊዜ ባገኙት 20 ደቂቃ በጅምላ ተቃዋሚዎችን በተለይ ሰመያዊና መድረክ ላይ ያደረጉት ውረፋ አቶ አሰፋው ጌታቸውንም ያስቆጣቸው ይመሰላል፡፡ በመጀመሪያ ካቀረቡት የመነሻ ኃሳብ በእጅጉ በተሻለ ሁኔታ የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነት የሌለው መሆኑ፣ ኢህአዴግ ርዕዮት ዓለም የሚባል ነገር የሌለው ብቻ ሳይሆን ከኮሚኒዝም እሰከ ነጭ ካፒታሊዝም የሚረግጥ በግለሰቦች ትርጉም የሚመራ ግንባር እንደሆነ አሰቀምጠዋል፡፡ በተለይ ድፍረት አጥተው በግልፅ አይናገሩት እንጂ በተቃዋሚዎች ውስጥ ካለው ክፍፍል በከፋ በኢህአዴግ ውስጥ ያለው የሃሳብ ልዮነት ለከፋ ክፍፍል የሚባቃ እንደሆነ ነገር ግን ስልጣን ላይ በመሆናቸው ግልፅ የሆነ መከፋፈል እንዳላሰዩ ገልፀዋል፡፡ በእኔ እምነት በኢህአዴግ ሰፈር ለመከፋፈል የሚሰጠው ምላሽ በጠብምንጃ የታገዘ እና ወደ ወህኒ የሚያስወረውር እንደሆነ መቀመጥ ነበረበት፡፡ ከዚህ ካመለጡ ደግሞ ሰደት ይሆናል፡፡

ዶክተር መረራ ጉዲና እሰከ ዛሬ ያለቸውን አውቀት ተጠቅመው እንደ ሁልጊዜ በተረጋጋ ሁኔታ በግልፅ በኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት የሌለ መሆኑ በማሰቀመጥ ከርዕሱ ጋር ተዛማጅ የሆነ ጉዳይ አንስተዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ዶክተር መረራ በእኔ እምነት ከፖለቲካው ግንባር ቢለቁ የምመርጥ ቢሆንም ከቀረቡ ወዲህ ግን አዲስ ነገር ይዘው መመጣት አለባቸው የሚል እምነት አለኝ /ዛሬም የጥብቆ እና የሚኒሊክ አልጋ ምሳሌ ቢቀር እመርጣሁ/፡፡ ኢህአዴግ አብዮታዊም ወይም ዲሞክራሲያዊም ያለመሆኑን ያስረዱበት መንገድ ተመችቶኛል፡፡ ዶክተር መረራ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ጉዳይ ሲነሳ አበክረው ሊያነሱት የሚገባ የነበረ ነገር ግን የዘነጉት ከጎናቸው ተወስደው በእስር የሚማቅቁትን አባላቶቻቸውን ነው፡፡ እነ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ሌሊሳ እና ሌሎች የኦሮሞ ልጆችን በሰም ጠርተው የሚደርሰብቻውን ግፍ ለህዝብ ማሳየት አልቻሉም፡፡ የኦሮሞ ልጆች ከምንጊዜውም በላይ እየደረሰባቸው ያለውን የሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት ሊያሳዩን ሙከራ አላደረጉም፡፡ በኢትዮጵያችን በአሁኑ ጊዜ ከኦሮሞ ልጆች እኩል በደል የደረሰበት ያለ አይመስለኝም፡፡ ዶክተር መረራ ለፓርቲዎች ውህደት ጥያቄ ሲቀርብ ኦሮሞነታቸውን የሚያጎሉትን ያህል በሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት ብሔረተኝነታቸውን ሊጠቀሙበት አለመቻላቸው ተገቢ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡ ለመራጮቻቸው በዚህ ርዕስ ጉዳይ ከዚህ የተሻለ ማሰረጃ ሊሰጥዋቸው የሚችሉበት አጋጣሚ ሊያገኙ የሚችሉ አይመስለኝም፡፡ ለምሳሌ ህገ መንግሰታዊ መብታቸውን ተጠቅመው ሰልፍ የወጡ የአምቦ ዮኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ነዋሪዎች በጥይት የተሰጣቸው መልስ ትክክል ያለመሆኑን ለማስረዳት ከዚህ የተሻለ ጊዜ የሚያገኙ አይመስለኝም፡፡ መብቶችን ለመጠቀም ሁል ጊዜ የሚነሳው ጉዳይ ልክ መሆን አይኖርበትም፡፡

ኢህአዴግ በሁለተኛ ክፍለ ጊዜ ባደረገው ጉንተላ እጅጉን ተበሳጭተው መስመር ከሳቱት በዋነኝነት የሚጠቀሱት ዶክተር መረራ ናቸው፡፡ ተማሪያቸው የነበረው አወያይ ጋዜጠኛ እስኪያቋርጣቸው ድረስ መስመር ጥሰው ሄደዋል፡፡ ርዕሱ “መድበለ ፓርቲ፣ የሰብዓዊና ዲሞክራሲያ መብቶች” ሆኖ እያለ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ ጉዳዮችን አንሰተው ጊዜያቸውን ጨርሰውታል፡፡ ከውይይት ርዕሱ ጋር የማይሄዱ ነጥቦችን ኢህአዴግ አማራጭ የላቸውም አለን ብለው አድማጭ ሊይዘው በማይችለው ደረጃ ዝርዝሩን ዘርግፈውት በተገቢው ሁኔታ የወከሉትን ግንባር ምልክት እንኳን ሳያስተዋውቁ አጠናቀዋል፡፡ ለሌላ ጊዜ ለክርክር የሚቀርቡ ተከራካሪዎች በወረቀት ላይ የታተመ የምርጫ ምልክት ይዘው መግባት የሚጠቅማቸው ይመስለኛል፡፡

አቶ ይልቃል ጌትነት በአቶ አሰፋው ጌታቸው የክርክር ሂደት በግልፅ በሚታይ መልኩ የደረሰባቸውን መሸማቀቅ በዶክተር መረራ ዘና ያላ አቀራረብ ዱካኩ የተገፈፈላቸው ቢሆንም በቅድመ ክርክር ወቅት የነበረውን ነጥብ አምጥቶ ካለቸው ውድ ጊዜ ለመጠቀም መወሰናቸው እንደ ሁልጊዜውም አጋጣሚውን ለህዝብ ግንኙነት ስራ መጠቀም የፈለጉ ያስመስለዋል፡፡ ክርክሩ ላይ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት የለም ብሎ በግልፅ ያስቀመጡት አቶ ይልቃል የሰብዓዊ መብትን ለማቅረብ የሄዱበት መስመር ሰብዓዊና ዲሞክራሲያ መብቶችን  ለህዝብ በሚገባው ግልፅ ምሳሌ ከማቅረብ ይልቅ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያው መብቶችን በመቀላቀል ማቅረባቸው የዝግጅት እጥረት እንደነበረባቸው ለመረዳት አያስቸግርም፡፡ በሰው ፊት ለንግግር ሰንቀርብ ሀምሳ ከመቶ ዝግጅት መሆኑን አቶ ይልቃል የዘነጉት ይመስላል፡፡ ከዝግጅት አንፃር ተዝረክርከው ማስታወሻውን ወደፊት ወደኋላ ሲገልፁ የነበሩትን አቶ አስፋው ጌታቸውን ማንሳት ሳያስፈልግ ነው፡፡

አቶ ይልቃል በሁለተኛውም ዙር የተሰጣቸውን ጊዜ በአግባቡ ከመጠቀም ይልቅ የተሰጠው ጊዜ አንሰተኛ መሆኑን በሚገልፅ ቅሬታ ጊዜ ሲያባክኑ ነበር፡፡ በሁለተኛው ዙር አቶ ይልቃል ያስቆጠሩት ዋነኛ ነጥብ አቶ አስመላሽ ሰለ ሰመያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉበዔ አጠራር አሰመልክቶ ያነሱት ነጥብ ነው፡፡ ይህ ነጥብ ኦቶ ይልቃል ከመረጃ እጥረት በሚል እወሰደዋለሁ ቢሉም ይህ የጠቅላላ ጉባዔ ጉዳይ ህወሃት/ኢህአዴግ ከምርጫ ቦርድ ጋር ለሰማያዊ ፓርቲ ከተቀመሙት መርዞች አንዱ እንደሆነ ሁሉም ማወቅ አለበት፡፡አቶ አስመላሽ የሰማያዊ ፓርቲ ደንብ ጊዜ አግኝተው ሊያነበትም ሆነ ሊያስነብቡ አይችሉም፡፡ አንብበው ፓርቲ ማፍረሻ ቀዳዳ የሚያቀብሉ በምርጫ ቦርድ የተቀመጡ ወኪሎቸ አሉ፡፡ ለዚህ ቅብብል የሚሆን ደግሞ የተዘረጋ ህጋዊ የሚመስል መስመር እንዳለ ሁላችንም እናውቃለን፡፡  ለማነኛውም አቶ ይልቃል የነበረውን ጊዜ በርዕስ ጉዳዩ ላይ ብቻ አተኩረው በምድር ላይ ባለ የሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት አሰደግፈው መከራከር አልቻሉም፡፡ እንደ ዶክተር መረራ በኢህአደግ ትንኮሳ መበሳጨታቸው ቢታወቅም ለመረጋጋት ያሰዩት ጥረት ጥሩ ነበር፡፡ ኢህአዴግ ዘመኑን የዋጀ ፓርቲ አይደለም እራሱን የሚያወዳድረው ከንጉሶች ወይመ ከደርግ ጋር ነው፣ መሻሻል የማይፈልግ ፓርቲ ነው፡፡ በሚል ያነሱት ነጥብ በኢትዮጵያ ህዝብ ሊያዝ የሚችል አንኳር ጉዳይ ነው – በምርጫ ካርድ ይሁን በህዝባዊ አመፅ ግልፅ ሆኖ አልተቀመጠም፡፡

የመጨረሻውን እድል ያገኘው የድንኩ “አንድነት” መሪ የሆነው አቶ ትዕግሰቱ አወሉ ነው፡፡ አቶ ትዕግሰቱ ከሌሎቹ በተሻለ የሰብዓዊ መብት ለመርገጥ ገዢው ፓርቲ እየተጠቀመበት ያለውን “የፀረ ሽብር ህግ” አንስቶ ለመሞገት ሞክሮዋል፡፡ በምንም መልኩ ግን አስተያየት ሊሰጥበት ያልቻለው ግን የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ጉዳይ ነው፡፡ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ትዕግሰቱ በትክክል ያውቀዋል፡፡ በኢህአዴግ ኢትዮጵያ ይህች ያገኛትን ቦታ በአባላት ይሁንታ ሳይሆን በተደራጀ ሾኬ እንዳገኛት ስለሚያውቅ መድበለ ፓርቲ ስርዓት የለም ሊል አልደፈረም፤ ቢያንስ በመግቢያው ንግግር፡፡ የሚገርመው ግን አሁንም “አንድነትን” ሲጠራ አፉ ይተሳሰራል፡፡ “እንደ አንድነት ማለትም እንደ እኛ አመለካከት” ሲል ውስጡ ያለው የአንድነት መንፈስ እንዳልሆነ ያሳብቃል፡፡ ትዕግሰቱ የአንድነትን አቋም በሙሉ ልቡ ሊናገር የሚችልበት የሞራል ልዕልና ላይ እንደሌለ በሚያሳብቅበት ሁኔታ ላይ ነው የሚገኘው ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም፡፡

አቶ ትዕግሰቱ አወሉ ስለሚያቀርበው ሃሳብ ያለኝን የግል ንቀት ለመተው እየሞከርኩ ቢሆንም ለመያዝ የሞከርኩት ነጥብ የዲሞክራሲ ተቋማት የይስሙላ መሆናቸውን ገልፆ በተለይ ምርጫ ቦርድን ጠቅሶ መለወጥ እንዳለበት ሲናገር የበላበትን ወጨት ሰባሪ ቢያደርገውም እውነት መናገሩን ግን መካድ አይቻለም፡፡ ኢህአዴግ ህዝቡን አፍንጫህን ላስ የሚል ፓርቲ መሆኑን መግለፁም ትክክል ነው፡፡ በዚህ አስተያየቱ ኢህአዴግ ተጨማሪ እድል ባለማግኘቱ ምን እንደሚከተለው ማወቅ አይቻልም፡፡ ለማነኛውም ጌቶቹን በተለይ ምርጫ ቦርድ ታዛዥነቱን አይቶ በሰጠው ወንበር ሰሙን ጠርቶ መዝለፉ ሽርክናቻው አንድነትን ድንክ እሰከማድረግ ብቻ አስመስሎባቸዋል፡፡

የኢህአዴግ የምላሽ ወቅት ሰለባዎች እንደሚጠበቀውም ሰመያዊና መድረክ ነበሩ፡፡  የፈለገ ጠንካራ ተቃውሞ ቢያቀርቡም “አትፓ እና ድንኩ አንድነት” በኢህአዴግ አፍ ለዘለፋ አይፈለጉም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ድንኮች ምንም በማያመጣ መልኩ ተሰርተዋል ተብሎ ስለሚታመን ነው፡፡ አንድነትን ድንክ በማድረግ ሂደት ዋነኛዎቹ ተዋናዮች የነበሩት ሁለቱም የኢህአዴግ ወኪሎች አንድ ጊዜ እንኳን አንድነትን ሳይዘልፉ ይልቁንም ጅምሩ ጥሩ ነው በሚል ማለፋቸው ሰራቸው ማጠናቀቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ የኢህአዴግ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት መገለጫ ተብለው የቀረቡልን ምሳሌዎች ግን ተጨፈኑ ላሞኛችሁ ነገር ነው፡፡ እነርሱም፤

  • አሁን 75 ፓርቲዎች በሀገራችን መኖራቸው የመድበለ ፓርቲ መገለጫ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም አሁን ለክርክር የቀረቡት ፓርቲዎች መኖር ዋናኛ ማሳያ ነው፡፡ እንደ ኢህአዴግ በፓርቲ ምዝገባና ቁጥር የመድበለ ፓርቲ ቢለካ እውነት ነበር፡፡ በወረቀት የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዳለ ሳይካድ በተግባር ገን የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዲኖር የማይፈቅደው ኢህአዴግ ጉንጭ አልፋ ክርክር ያቀርባል፡፡ እምነታቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኪራይ ሰብሳቢዎች ናቸው ብለው እንዲጠፉ እየሰሩ ለእርዳታ ሰጪዎች ፍጆታ የፓርቲነት ሰርተፊኬት በማደል የመድበለ ፓርቲ ስርዓት አለ ብለን እንድናምን ይፈልጋሉ፡፡ በአሜሪካን ሀገር በዋነኝነት ሁለት ፓርቲዎች መኖራቸው ዲሞክራሲ ያለመኖሩ ማሳያ ነው እንደማለት ነው፡፡ የኢህአዴግ ጉንጭ አልፋ ክርክር፡፡
  • ለምርጫ ውድድ የቀረቡ ዕጩዎች ሌላኛው የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ማሳያ አድርገው ኢህአዴጎች አቅርበዋል፡፡ ማንም እድሉን ሊሞክር ለምርጫ ዕጩ ሆኖ እራሱን ማቅረብ ለመድበለ ፓርቲ ስርዓት ማሳያ እንዴት ሊታይ እንደሚችል አቶ አሰመላሽ እና አቶ ሬድዋን ብቻ ናቸው የሚያውቁት፡፡ ይህ በቅርቡ የመጣ የመድበለ ፓርቲ ስኬት መገለጫ ነው፡፡
  • ለምርጫ ማስፈፀሚያ የተመደበው በጀት ደግሞ ሌላው የመድበለ ስርዓት ስለመኖሩ ማሳያ ተድረጎ ነው የተብራራልን፡፡ አስገራሚው ነገር ከተመደበው ገንዘብ አብዛኛውን የሚወሰደው ገዢው ፓርቲ መሆኑ እየታወቀ፤ ፓርቲዎች በምርጫ ሰሞን በሚያገኙት በዚህ ገንዘብ የመድበለ ፓርቲ ስርዓትን ለማጠናከር ምን ሊያደርጉበት እንደሚችሉ ማሰረዳት አይችሉም፡፡ ተመደበ የተባለው ገንዘብ ዋነኛው ወጪ ከ45 ሺ በላይ ለሚሆኑ ምርጫ አስፈፃሚዎች አበል ሲሆን፤ ለአንድ ዕጩ ተወዳዳሪ ብር 500 በማይደርሰበት ሁኔታ ይህ ገንዘብ እንዴት እንደሚጠቅም ኢህዴጎች ሊያስረዱን አይችሉም፡፡
  • በጣም ያስገረመኝ አንዱ መከራከሪያ “የመድበለ ፓርቲ በሊብራል ዲሞክራሲ በሚያራምዱ ሀገሮች ለብሔር ብሔረሰቦች የማይፈቅድ ነው” የሚልው ነው፡፡ ኢትዮጵያን የተለየች የብሔር ብሔረሰቦች መኖሪያ አድርጎ ለማሳየት የሚደረገው የተሳሳተ ነገር አሁንም ቅጥ ያጣ ይመስላል፡፡ በዓለም ላይ አሉ የሚባሉ ብሔሮችና ብሔረሰቦች በሙሉ የሚኖሩባት ሀገር አሜሪካ ውስጥ በፈለጉት ቡድን ለመደረጃት አንድም ጥያቄ እንደማይቀርብ የምናውቅ አይመስላቸውም፡፡ ሊብራል ዲሞክራሲን ያለ ስሙ ሰም እየሰጡ የራሳቸውን የፖለቲካ መስመር አንዴ አብዮታዊ ሌላ ጊዜ ልማታዊ ዲሞክራሲ እያሉ ሊያደናብሩን ይፈልጋሉ፡፡ ይህ የብሔርና ብሔረሰብ ፖለቲካ ጉዳይ ሲነገር የሚያስታውሰን አንድ ነገር “ለምለሚቱ ሀገሬ” የሚለው ነገር ነው፡፡ በሌሎች ሀገራት ሳር የማይበቅል፣ ወተት ማር የማይገኝበት፣ ወዘተ ይመስለን የነበረው ዓይነት አሳሳች ምሳሌ ነው፡፡

በመጨረሻም በክርክሩ የነበሩ ተቃዋሚ እና “ተቃዋሚ ተብዬ” ፓርቲዎች በኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ግንባት ውይይት ሲደረግ በቅርብ ርቀት በአንድነት ላይ የተፈፀመውን የመንግስታና ለመድበለ ፓርቲ ስርዓት ግንባት ለማጠናከር መቆም ያለበትን ምርጫ ቦርድ ሴራ በምሳሌ አንስተው ለመሞገት ያለመሞከራቸው፤ በተለይ መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ የአንድነት ድንክ መሆን እነሱን ከፍ ማድረጉን በግልፅም ባይሆን በውስጣቸው የፈጠረላቸውን ደስታ የሚያሳይ ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ አንድነትን ድንክ በማድረጉ ብቻውን እንዳልተጠቀመም ማሳያ ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ የሚችለውን በመምረጥ አንፃር በጣም ተሳክቶለታል፡፡ በዚህ ፅሁፍ ለአንድነት ፓርቲ አመራሮች እግረ መንገዴን የማስታውሳቸው ዘወትር በነበሩን ስብሰባዎች ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ለማስተባበር ስንደክም ከእኛ ይቅር ስንል የነበረው ለእነዚህ ፓርቲዎች መሆኑን ማስታወስ ይኖርብኛል፡፡ በተለይ ሰማያዊ ፓርቲን አስመልክቶ አንድነት ፓርቲ ውስጥ የነበረንን ልበ ሰፊነት ሳስበው በጣም ነው ያዘንኩት፡፡ ለምን አደረግነው የሚል ቁጭት የለብኝም፡፡

አንድነት ፓርቲ በዚህ ክርክር ውስጥ ቢኖር ኖሮ በመጀመሪያ ከኢህአዴግ እኩል ሁሉንም ለመከራከር እድል ነበረው ፓርቲ ይሆን ነበር፡፡ ምክንያቱም 450 ዕጩዎች ለፌዴራል ምክር ቤት እና 1200 የማያንሱ የክልል ምክር ቤት ዕጮዎች ስለሚያቀርብ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ለመከራከር ሊመጡ የሚችሉትን ትንታግ የአንድነት ወጣቶች ሳሰብ እንባ እየተናነቀኝ ነው፡፡ የዛሬ አምሰት ዓመት የዚህን ተመሳሳይ ክርክር አንድነትን ወክሎ  የተከራከረው ምን አልባትም በዚህ ክርክር መነሻ ቂም ተይዞበት የነበረው፣ ዛሬ በወህኒ የሚገኘው አንዱዓለም አራጌ ነው፡፡ አንድነት ፓርቲ ክርክሩ ከመደረጉ በፊት በዚህ ጉዳይ ላይ በሚኖረው 6 ደቂቃ የመነሻ ኃሳብ ልናነሳ የምንችለውን ቢያንስ 12 ነጥብ ይዘን እንገባ ነበር፡፡ ወይም 10 ነጥብ እና በቀሪው ሁለት ደቂቃ ለህዝብ ውይይት ሊጭር የሚችል ሃሳብ የሚነሳበት ይሆን ነበር፡፡ ሁለተኛው ዙር ዘጠኝ ደቂቃ በዝርዝር ህገ መንግሰታዊ ድንጋጌዎችን አሰመልክቶ ኢህዴግ የሚሰራቸውን የክርክር ፋውሎች ለህዝብ የምናጋልጥበት ይሆን ነበር፡፡ ለዚህ ነው በ2007 ኢህአዴግ የሚችለውን መርጦዋል የምንለው፡፡

ለማጠቃለል ተቃዋሚዎች በኢህአዴግ ትንኮሳ ተገፍተው በመድበለ ፓርቲ እና በሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ዙሪያ ትኩረት ሰጥተው ለመከራከር አልቻሉም፡፡ ክርክሩን በኢህአዴግ ሜዳ ላይ ለማድረግ ማተኮር የነበረባቸው “ህገ መንግሰት” ላይ የተዘረዘሩትን መብቶች እያነበቡ በተግባር የገጠመውን ፈተና በማቅረብ ህዝቡ እነዚህን ጉዳዮች ገዢው ፓርቲ የአፈፃፀም ችግር ናቸው ቢልም በመርዕ የማያምንባቸው መሆኑን እራሱ ኢህአዴግ ከፃፋቸው የፖሊሲ፣ሰትራቴጂና የርዕዮታለም ትንተና መፅሃፉች ጋር እያጣቀሱ ማስረዳት ነበረባቸው፡፡ የህገ መንግሰቱ ምዕራፍ ሶሰት ክፍል አንድ ከአንቀፅ 14 -28 የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን በማየት በተግባር የገጠሙትን ፈተናዎች፤ ምዕራፍ ሶሰት ክፍል ሁለት ከአንቀፅ 29-44 ዲሞክራሲያዊ መብቶቸን በማየት የገጠሙትን ፈተናዎች በዝርዝር መተንተን ይቻል ነበር፡፡ በዚህ መስመር ክርክሩ ቢደረግ ኢህአዴግ ሊከራከር የሚችለው ህገመንግሰቱን ለማዘጋጀት ህይወትና ደም ተከፍሎበታል ከሚል ፉከራ ውጭ ለምን በተግባር ላይ እንደማያውላቸው ሊያስረዳ አይችልም ነበር፡፡ ምንም በቂ ምክንያት ሊኖር አይችልም የሚል እምነት አለኝ፡፡

ቸር ይግጠመን!!!!

 

The post የምርጫ ክርክር አንድ፡ መድበለ ፓርቲ ሰርዓት እና ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብት- በእኔ ዕይታ (ግርማ ሠይፉ ማሩ) appeared first on Zehabesha Amharic.

ተደናቁሮ ለማደናቆር የመረጠ ሰርአት ማነው? – ሊቁ እጅጉ

0
0

በ 21ኛ ክፍለ ዘመንሰ ድንቁርና የተፈረደባት አገር ማነች ? (ሎሚ-ተራ ተራ)

በ እርግጠኝነት በቅርቡ በዚህ በአሜሪካን አገር ተወዳጀ በሆነው ጀፐርዲ (Jeopardy!, ) ተብሎ በሚታወቀው እርሦም ይሞክሩት የጥያቄና መልሰ ውድድር በጥያቄነት መቀረቡ አይቀሬ ነው ተብሎ የሚገመተውን የጥያቄ አርእሰት ነው ይዤላችሁ የቀረብኩት፡፡

አዎ በ እርግጥ ይዞታው አሰቂኝ ቢመሰልም እውነታውን በአንክሮ ለተመለከተው ማንኛውም ዜጋ ግን ከልብ ያሳዝናል ያሰቆጫልም። ተደናቁሮ ለማደናቆር የመረጠው የወያኔ ሰርአት ግን ማንም ከልካይ በሌለው ሁኔታ ትውልዱን ለ24 አመት በማፈንና አዕምሮውን እንኳን በእወቀት እንዳየሰፋ ታዋቂና አዋቂ ናቸው ትውልዱን ሀብት ባይሰጡትም እውቀት ያሰገበዩታል ተብለው የሚታመንባቸውን የ ዩንቨርሲቲ አሰተማሪ ፐሮፌሰሮችን ያለምንም አፈረት እውቀትን ለምን አሰፋፋችሁ ? አደናቁሩ አልናችሁ እንጂ ህዘቡ አይኑ ተገልጦ የእኛን አፍራሽነትና የዘረኝነት ፖሎቲካ አራማጅነት እንዲረዳ በእውቀት አጥምቁ መች አልናችሁ ? የሚሉ ይመሰል ባደባባይ አይናቸውን በጨው አጥበው ማባረሩን ተያይዘውታል ። ይሔ ታዲያ ምን ሰም ሊሰጠው እና ምን ሊባል እንደሚችል በ እውነቱ አሰቸጋሪ ነው ? እርግማን አይመሰላችሁም ? አሁን ዶ/ር ጌታቸውን ማባረር ምን ይባላል?

“እርሳቸው ግን አሁን ገና ኢትዮጵያዊ ሆንኩ ፣ምከንያቱም ኢትዮጵያዊ መሆን ማለት መብቴ የሚረገጥ ማለት ነውና ” በሚል የወያኔ ሰርአት ኢትዬጲያዊነትን ምን አክል እንደሚጠላና አላማውና እቅዱ ሁሉ አገር ማፈረሰና ማጥፋት እንደሆነ እንደፍልሰፍና መሁርነታችው በፍልሰፍና ቃል በጥሩ ሁኔታ ገልጸውታል። ጥያቄው ግን ያፈጠጠ ሰርአት አልበኝነት እሰከመቼ በዚህ እብሪተኝነት መቀጠል ይችላል ተብሎ ይታመናል ነው ? ሕዝብሰ ይኸንን አይነት አይን ያፈጠጠ ማን አለብኝነት ሰርአት እሰከመቼ ተሸክሞ ይዘልቃል ? በቃኝ ! በቃኝ አሁንሰ መረረኝ ብሎ አሸቀንጥሮ ለመጣል አቅም ያጣበት ምክነያት ምን ይሆን ? በእርግጥ ወያኔ በጥናቱ ባሰላው የማደናቆር እቅድ ሕዝቡ ተደናቁሯል ማለት ነው? ከሆነሰ የእኛ በ ውጭ የምንኖረው አልተደናቆርንም የምንለው ወያኔ አደናቁሮታል ያልነውን ሕዘባችንን የመታደግ ግዴታችንን እንዴት መወጣት እንችላለን ትላላችሁ ? እር ይታሰብበት ጎበዝ እኛንም አደናቆሩን እንበል እንዴ ? አይገባም እንንቃ ሕዘባችንንም እንታደገው ።
አልታይህ አለኝ አይኔን ጉም ሸፍኖት
አልገለጥ አለኝ እሰትራፖ ይዞት
አይን የሚሸፍን አይን የሚጋርድ
አዲሰ በሸታ ነው “ወያኔ” መሆኑን ሕዘቤ ሆይ ተረዱት
*
ምንድነው ብላችሁ ጥያቄም አቅርቡ
ምላሹን የሚሰጥ ባይኖርም በቅርቡ
ጥያቄም ጠይቁ ለ አቦይ ሰብሀት
ፊት መሪ ለሆነው ለድንቁርና እሳት
ጥያቄም አቅርቡ ለ አቦይ ጸሀይ
ጮቤ ለሚረግጠው በ ሕዘቡ ሰቃይ

*
ዳይሰፖራም ጠይቅ አንተም ተጋርደሀል መደናቆር ይብቃ
በ አንደነት እንቁም የወያኔ ጭፍራ ሴራው እንዲያበቃ።
እንቢኝ በይ ሴቲቱ እንቢኝ በል ወጣቱ እንቢኝ በል ወገኔ
በርቀት መልሰው አጠገብህ ሳይደርሰ የወያኔን ኩነኔ።

በቸር ይግተምን ። አሰተያየት ቢኖሮት በዚህ መላክ ይችላሉ ኢሜል ፤- mwl200825@yahoo.com
ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኖራለች !!

 

comment_stage_5

The post ተደናቁሮ ለማደናቆር የመረጠ ሰርአት ማነው? – ሊቁ እጅጉ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሕዝበ ሙስሊሙ ትግል ወደ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ማደጉን ድምጻችን ይሰማ አስታወቀ

0
0

Muslim in ethiopia
ለ 3 አመታት በተለያዩ የሰላማዊ ትግል ዘዴዎች መብቴን አክብሩ ሲል የቆየው ህዝበ ሙስሊም የህዝብን ድምፅ ለመስማት ፈቃደኛ ያልሆነው የሃገራችን መንግስት በቀጣይ የህዝብን ድምፅ ይሰማ ዘንድ ወደሚያስገድዱ ህዝባዊ እንቢተኝነት ትግሉ መሸጋገሩን ድምፃችን ይሰማ አስታውቋል፡፡

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል፡-

ሕዝብ የአንድ አገር መሠረት ነው፡፡ የአገር ምሰሶዎች የሚተከሉትም በህዝብ ላይ ነው፡፡ ስለዚህ ‹‹ሕዝብ ለአንድ አገር ሕልውና ዋነኛው ምንጭ ነው›› ብንል በእርግጥም አንሳሳትም፡፡ የመንግስት ተቋማትም ሆነ መንግስት ራሱ የመቋቋሚያ ዓላማው ህዝብን ማገልገል፣ የህዝብን ፍላጎት ማስፈጸም ነው፡፡ ይህ ሳይሆንለት ሲቀር ህዝብ ይቀየማል፤ ይቆጣልም፡፡ መብቱን በተለያዩ መንገዶች መጠየቅ ይጀምራል፡፡ ኢትዮጵያዊው ሙስሊምም ላለፉት ሶስት ዓመታት ሲያደርግ የቆየው ይህንኑ ነው
ትግል የራሱ ደረጃዎች ያሉት ሂደት ነው፡፡ በለዘብተኛ አቤቱታ ይጀምራል፡፡ ድርድሮችን ያልፋል፡፡ ጠንከር ያሉ የመብት ጥየቃ ሂደቶችን ያሳልፋል፡፡ ጥያቄውም ወደትግል ይቀየራል፡፡ መስዋእትነቶች ይከፈሉበታል፡፡ እያዳንዷ መስዋእትነት በራሷ ለትግሉ የሚኖረውን ቁርጠኝነት እና ወኔ እየጨመረች ትሄዳለች፡፡ አሁንም ችግሩ ካልተፈታ ህዝብ ያገለግለው ዘንድ ራሱ በሾመው አካል ላይ ተስፋ መቁረጥ ይጀምራል፡፡ የአገሪቱ ተቋማት ዋነኛ ባህሪያቸውን ለውጠው በደልን የማገልገል ሚና መወጣት በቀጠሉ ቁጥር የህዝቡም ቁርጠኝነት በዚያው ልክ እያደገ ይመጣል፡፡
የአንድ መንግስት ህልውና በእሺተኛ ህዝብ ፍቃደኝነት ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡ ሕዝብ ሲመረውም ‹‹መብቴ ይከበርልኝ›› ከሚል ጩኸት ‹‹መብቴን ካላከበርክ እኔም….. !›› ወደሚል ዛቻ መሄዱ አይቀሬ ነው፡፡ ይህን ጊዜ ሕዝቡ ‹‹ትብብር የመንፈግ ትግል ውስጥ ገባ›› ይባላል፡፡ ይህ ዓይነቱ ትግል ውጤታማ መሆኑ አይቀሬ እንደሆነ የዘርፉ ምሁራን አጽንኦት ሰጥተው ያስተምራሉ፡፡

አዎን! በጨዋ ደንብ እና በአንጸባራቂ ሰላማዊ ስነ ምግባር ለሶስት ዓመታት መብቱን ሲጠይቅ እና ሲታገል የቆየው ኢትዮጵያዊው ሙስሊም ‹‹መብቴ ይከበርልኝ›› ከሚል ያልተሰማ ጥያቄው ‹‹መብቴን ካላከበርክ እኔም….. !›› ወደሚልበት የትግል ምዕራፍ ላይ እነሆ ደርሰናል! ሰሞኑን ይህንኑ አስመልክቶ የምንለው ይኖራልና ሁላችንም ቃል የገባንበትን ትግል እስከድል ደጃፎች ለማድረስ ወገባችንን እናጥብቅ፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!

ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

The post የሕዝበ ሙስሊሙ ትግል ወደ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ማደጉን ድምጻችን ይሰማ አስታወቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live