Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የቴሌቭዥን ድራማዎች በስድስተኛውም የስሜት ህዋሳችንም መቃኘቱን አንርሳ; የትኞቹ ያስተምራሉ? የትኞቹ መታረም ይፈልጋሉ? ”ቤቶች”እና ”ሞጋቾች”ድራማ

0
0

Mogachoch
(የጉዳያችን አጭር ማስታወሻ)

ከጌታቸው በቀለ

በቴሌቭዥን የሚተላለፉ መርሐ ግብሮች አነሰም በዛም በሕዝብ ላይ የሚፈጥሩት የእረጅም ጊዜ ተፅኖ ቀላል አይደለም።በተለይ በታዳጊ ወጣቶች እና ልጆች ላይ ለነገ እነርሱነታቸው የሚጭረው ስሜትም ሆነ አለማቸውን እና አካባቢያቸውን የሚመለከቱበት ዕይታ የጠበበ አልያም የሰፋ ወይንም የተንሸዋረረ የመሆን እድሉ ትልቅ ነው።እዚህ ላይ ወላጆች ለልጆቻቸው ከቴሌቭዥን መርሃ ግብር በኃላ የሚሰጡት የማስተካከያ ሃሳብ ወይንም ልጆችም ሆኑ ወጣቶች ጉዳዩን የሚያዩበትን እይታ ቀላል አይደለም።

የኢትዮጵያ ተለቭዥንን በሀገር ውስጥ የመረጃ ምንጭነት ተአማኒነቱ የወረደበትን ደረጃ ለመግለፅ ህዝቡ ”የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እውነት የምናገረው ሰዓት ብቻ ነው” የሚለውን አባባል መግለፁ ብቻ በቂ ነው።ከግማሽ ክ/ዘመን በላይ በመገናኛ ብዙሃንነት የቆየ የቴሌቭዥን ጣብያ በእዚህ አይነት ደረጃ የወረደ የመረጃ ምንጭ መሆኑ እንደ ኢትዮጵያዊነት በጣም ያሳዝና።ዛሬ ቢልልን ኖሮ ኢቲቪ በመላው ዓለም ባሉ ከተሞች ወኪሎች በኖሩት እና በቀጥታ የሚዘግቡ ዘጋቢዎች በኖሩት ነበር። ይህ ደግሞ ከወጭም አንፃር ብዙ አለነበረም።ምክንያቱም በመላው ዓለም እንደመበተናችን በነፃ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ማግኘት ከባድ አይደለም።ነገር ግን አለመታደል ሆኖ አምባገንነት፣ጎሰኝነት እና ሙስና መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደጠረነፈ ሁሉ የኢትዮጵያ ቴሌቭዝንም አንዱ ሰለባ ነው።ኢትዮጵያውያን ግን በሀገር ቤት የታፈነ ድምፃቸውን በቸልታ አላዩትም።በጥቂቶች አስተባባሪነት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን በመላው ዓለም እና በሀገር ቤት ላሉ ወገኖቻችን ብቸኛው ነፃ የመገናኛ ብዙሃን ለመሆን በቅቷል።

የእዚህ አጭር ማስታወሻ አላማ ስለ ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ታሪክ ለማውራት አይደለም።ስለሚያቀርባቸው ሳምንታዊ ድራማዎች ግን ትንሽ ማለት ፈለኩ።የቴሌቭዥን ድራማዎቹን ምግብ እየበላሁም ሆነ መንገድ ላይ ባለኝ ክፍት ጊዜ እመለከታቸዋለሁ።ይህንን የማደርገው መዝናኛ ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን አሁን ያለውን የሀገር ቤትን ማኅበራዊ፣ስነ-ልቦናዊ፣ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሁኔታ ስለሚያንፀባርቁልኝ ነው።የድራማዎቹን የመሃል እንቡጥ መልእክት ፈልፍላችሁ ለማግኘት ስትሞክሩ (በስድስተኛው የስሜት ህዋስ ማለቴ ነው) ብዙ ጠቃሚ እና ጎጂ ጎኖቹን ለማየት አያስቸግራችሁም።
በስድስተኛው የስሜት ህዋስ የሶስቱ ድራማዎች እይታ

እዚህ ላይ በቴሌቭዥን ከሚቀርቡት ድራማዎች ውስጥ የሁለቱ ማለትም ”ቤቶች” እና ”ሞጋቾች” ላይ የማነሰው የጠለቀ ሂስ አለመሆኑን እና ያንን ለማድረግ የሙያው ክህሎት እንደሌለኝ ለመግለፅ እፈልጋለሁ።ነገር ግን ድራማዎቹ በህብረተሰባችን ላይ ያላቸው አሉታዊ እና በጎ ተፅኖ ላይ ሃሳብ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
1/ ”ቤቶች” ድራማ

ይህ በየሳምንቱ ቅዳሜ ምሽት የሚቀርበው ድራማ በብዙዎች ዘንድ በአስቂኝነቱ የሚጠቀስ እና በርካታ ተመልካች ያለው መሆኑ ይታወቃል።አመታዊ ዝግጅቱን ሲያዘጋጅም የሚመለከቱት ተመልካቾች በርካታ መሆናቸውን ያሳያል።እንደ እኔ አስተያየት ድራማው ከማዝናናት ባለፈ ሊያስተምር የሚገባው በርካታ ነገሮች ይቀሩታል።በመጀመርያ ደረጃ ታሪኩ አንድ በግንብ በታጠረ ቪላ ቤት ውስጥ የሚኖር ቤተሰብ ዙርያ ያጠነጥናል።ቤተሰቡን መካከለኛ ገቢ ያለው ቤተሰብ ለማለት ይከብደኛል።ምክንያቱም መካከለኛ ገቢ የሚባለው ሕብረተሰብ አሁን በራሱ ጠፍቷል።ከሃያ ሶስት አመታት በፊት አንድ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር መሬት ተመርቶ ቤት የመስራት አቅም ነበረው።ዛሬ ቤት ለመስራት ከፍተኛ ገቢ ካላቸው ውስጥ የሚመደብ ካልሆነ አይታሰብም።እናም ድራማው ውስጥ የሚተውኑት ቤተሰብ አባላት ቢያንስ ባለ ሁለት ሰራተኛ እና አንድ የጥበቃ ግለሰብ የሚተዳደሩ ናቸው እና መካከለኛ ከሚለው እናውጣቸው።እዚህ ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከ95% በላይ በእንደዚህ አይነት ኑሮ የሚኖር አይደለም።አዲስ አበባ ብቻ የግል መፀዳጃ የሌለው የሕዝብ ብዛት ከ70% በላይ እንደሆነ ከተገለጠ እሩቅ አይደለም።በመሆኑም ድራማው ተጨባጩን የሀገራችንን ሕዝብ ኑሮ አይወክልም።ይህ ግን ድራማውን ያስወቅሰዋል እያልኩ አይደለም።ጥቂቶችም ብዙሃኑ ግብር በሚከፍልበት ቴሌቭዥን እርስ በርስ ሲጨዋወቱ መመልከት በራሱ ድራማ ነውና።
Tilahun Gugsa
በእዚህ ድራማ ላይ ”ይቤ” ገፀ ባህሪ ይዞ የሚጫወተው ወጣት የዩንቨርስቲ ተማሪ ለወጣቱ ምን ያስተምራል? ብዬ ስጠይቅ በገፀ ባህሩ ላይ ባብዛኛው አሁን በዘመነ ኢህአዲግ/ወያኔ አንድ የዩንቨርስቲ ተማሪ የሚኖረውን መልክ ይዞ ታገኙታላችሁ።ይቤ በድራማው ላይ ይጠጣል፣ይቅማል፣የተለያዩ የሴት ወዳጆች አሉት፣የሚናገረው የተደበላለቀ ማለትም ”ከአራዳ አነጋገር” እስከ እንግሊዝኛ የተደባለቁ፣ኢትዮጵያዊነት በሙሉ የጠፉበት ሆኖ እናገኘዋለን።በነገራችን ላይ ይቤ መሃንዲስ ነው እና የነገ ኢንጅነሮቻችን የሚቅሙ፣የሚያጨሱ ናቸው በመሆኑም መስርያቤቶች ከመሃንድሶች ጋር ሲሰበሰቡ የጫት በጀት መያዝ አለባቸው ማለት ነው።

ቤቶች ድራማ ሶስት መስተካከል ነበረባቸው የምላቸው አቀራረብ አይቼበታለሁ

የመጀመርያው በቅርቡ የታየው ነው ታሪኩ እንዲህ ነው።ሁለቱ የቤት ሰራተኞች ቡና እያፈሉ ሳሉ የቤት ጠባቂው ዘበኛ ያገኘውን ዱቄት መሰል ነገር ፍሙ ላይ ሲጨምሩት እና በቤቱ ውስጥ የነበሩት በሙሉ ሲሰክሩ ያሳያል።እንደ ድራማው አገላለፅ ለካ የጨሰው አደገኛ ዕፅ ነበር።ሙሉ ድራማው በወቅቱ ቀጥሎ ያሳየን ነገር ቢኖር አንድ እፅ የወሰደ ሰው ምን እንደሚታየው፣ለምሳሌ ድመት ዘንዶ እንደሚመስለው፣ሰዎች ትልቅ ሆነው እንደምታዩት በተግባር እያሳየ ትውልዱን አሰለጠነ።የሚገርመው ድራማው የእፅን አስከፊነት ሳይሆን አዝናኝነት ነው እስኪበቃን የነገረን።እፅ ያጨሱት በፖሊስ ሲያዙ እና ሲቀጡ ሳይሆን የአደገኛ እፅን አዝናኝነት ለታዳጊ ወጣት ሁሉ ተነገረው።ይህንን የተመለከተ ወጣት ”አንድ ቀን ልሞክረው” እንዲል አድረገው አቀረቡለት።ይህ ክፍል ከታየ ገና ወራት አልተቆተሩም።በአድዋ በዓል ላይ ሸለላችሁ ብሎ ያገደ ፖሊስ ያለው መንግስት በተለቭዝኑ የእፅ አወሳሰድ ስልጠና ሲሰጥ ማየት ያሳምማል።

ሁለተኛው፣ ቤተሰቡ ለሽርሽር ከሄደባቸው ቦታዎች አንዱ ቅዱስ ላሊበላን ያሳየናል።በቅዱስ ላሊበላ ቅፅር ውስጥ በአካል ቤተሰቡ ቆሞ የሚሰጠውን ገለፃ ያዳምጣል።በእምነት ቦታ በመሰረቱ የቀልድ ድራማ መስራት አስቸጋሪ ነው።ድራማው ላይ ግን ሃይማኖታውም ሆነ ታሪካዊ ገለፃ ሲሰጥ በመሃል የፌዝ እና የቀልድ ንግግሮች ይሰሙ ነበር።ይህ እንግዲህ በመሃል ከሚገባው የሳቅ ጋጋታ ጋር አብሮ ነው።የእምነት ቦታዎች የሚሰጣቸው ቦታ እና በአማኙ ዘንድም ሆነ በታዳጊ እና ወጣቶች ዘንድ የሚያሳድረው ተፅኖ ፈፅሞ አልተጤነም።ቅዱስ ላሊበላ ከመጎብኘቱ ባለፈ የከበረ ቀልድ የማይነገርበት ቦታ መሆኑን ማሰብ ተገቢ ነበር።በሌላ በኩል ግን የድራማው አላማ ሀገርህን እወቅ በሁሉም ቤተሰብ መለመድ አለበት የሚለውን ሃሳብ በማንፀባረቁ የሚደገፍ አይደለም እያልኩ አይደለም።ለእምነት ቦታዎች የማይባሉ ቀልዶች ቀላቀለበት እንጂ።

ሶስተኛው የድራማው አቀራረብ የገጠሩን የሀገራችንን ገበሬ ለከተማው ወጣት የሚስልበት የተሳሳተ አቀራረብ ነው።የቤቱ ዘበኛ ሁል ጊዜ እንቅልፍ በጣም ወዳጅ፣ምግብ የሚወድ፣ሥራ የማይወድ እና ግዴለሽ አድርጎ የሚስልበት ገፀ ባህሪ የኢትዮጵያን ገበሬ ፈፅሞ አይወክልም።የኢትዮጵያ ገበሬ እንቅልፍ የለውም ከማለዳ እስከ ምሽት ሲለፋ ውሎ ማታ የቀረውን ሥራ በመስራት የሚጠመድ፣ንቁ፣በሥራ የሚያምን፣ላመነበት የሚሞት እና ለወዳጁ ሟች ነው።ይህንን የህብረተሰብ ክፍል ነው እንግዲህ ለሕዝቡ ”ሎሽ ማለት ብቻ የሚወድ” ተብሎ የሚቀርበው።ይህ በእራሱ ከቀልድ ባለፈ ብዙ ማህበራዊ ነገሮችን የሚነካ ነው።በኮሜዲ ፊልሞች ላይ ገፀ ባህርያት የተለያዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን እያነሱ ያስተምራሉ እንጂ በኢትዮጵያ ገበሬ ላይ የሚሳለቅ አቀራረብ ይዘው እና ከገበሬው የምንማረው እንቅልፍ ብቻ የመሰለ አቀራረብ ማንንም አይጠቅምም።

እዚህ ላይ የቤቶች ድራማን አንዳንድ ግድፈቶች እና ማስተካከል የሚገባቸውን አቀራረቦች ላይ ሃሳብ ለመስጠት ፍለግሁ እንጂ በደፈናው ድራማውን ለማጣጣል እንዳልተነሳሁ ይታወቅልኝ።ድራማ ከአዝናኝነቱ ባለፈ ወጣቶችን በስነ-ምግባር፣በሀገር ፍቅር ስሜት እና በቅን ለሀገር መስራትን የሚያስተምር ካልሆነ በሳቅ ማንከትከትን ብቻ አላማዬ ብሎ ከተነሳ ስለ እፅ አወሳሰድ የሚያሰለጥነን ከሆነ አደገኛ ነው።ላሰምርበት የምፈልገው ለሕዝብ የሚቀርቡ ድራማዎች በተለያየ ሙያ ላይ ያሉ አማካሪዎች ያስፈልጋቸዋል።ደራሲው ”ህዝብን ካሳቀ እና መንግስትን እስካላሳቀቀ ድረስ መንገዱ ሰላም ነው” በሚል አስተሳሰብ ብቻ አየር ላይ ማዋል የለበትም።

”ሞጋቾች” ድራማ

ከእዚህ በአንፃሩ በ”ኢቢኤስ”ቴሌቭዥን የሚቀርበው ”ሞጋቾች” የተሰኘው ድራማ ጥሩ፣አስተማሪ እና ትውልድን የሚያንፅ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።ሞጋቾች በአንድ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩ የህክምና ዶክተሮች እንዴት ህዝባቸውን በታማኝነት እንደሚያገለግሉ እና በማህበራዊ ኑሮአቸው ውስጥ የሚገጥማቸውን ተግዳሮት ያሳያል።የሞጋቾች ድራማ በፊልም አቀራረፅ እና የድምፅ ጥራቱ ብቻ ሳይሆን የመረጡት ሆስፒታል ተራው ሕዝብ የሚገለገልበትን እና እታች ያለው ሕዝብ የሚላቸውን አባባሎች፣ስሜቶችን ሁሉ የሚያንፀባርቅ አቀራረብ ይታይበታል።እዚህ ላይ ማስታወሻዬ አጭር ከመሆኑ አንፃር ባጭሩ ”ሞጋቾች”ድራማ ሶስት ነገሮችን ለአዲሱ ትውልድ እንደሚያስተምር ጠቅሼ ሃሳቤን ልግታ።

1/ ተምሮ በሀገር መስራትን እና ወገንን ማገልገልን
በድራማው ብዙ ክፍሎች ላይ የሚታዩት አቀራረቦች በዶክተር ደረጃ ያሉ የህክምና ባለሙያዎች ምን ያህል እታች ላለው ሕዝብ እንደሚጨነቁ እና ኃላፊነት እንደሚሰማቸው ያሳያል።

2/ የዩንቨርስቲ ሴት ተማሪዎች ጥንቁቅ እንዲሆኑ ይመክራል
የድራማው ዋና ገፀ ባህሪ በአንድ ወቅት የዩንቨርስቲ ተማሪ ሆና ሳላ አንድ ምሽት በተፈጠረ የምሽት ዳንስ ይመሽባትና ከሰው ቤት ታድራለች።ሆኖም በእዚችው ምሽት ተደፍራ ልጅ ትወልዳለች።ድራማው ባብዛኛው የወለደቻትን ልጅ አባት በመፈለግ ስትደክም ያሳያል።ይህ አሁን ላሉት ወጣቶች እያንዳንዱ ምሽት የምትሰራ ስህተት እና ከዋልጌ ተማሪዎች ጋር መግጠም የሚያስከፍለው ዋጋ ለአመታት የሚተርፍ መሆኑን ያሳያል።ይህም በተለይ ሴት ወጣቶች ጥንቁቅ እንዲሆኑ ይመክራል።

3/ በአንድ ወቅት ችግር ቢያጋጥምም መልሶ መነሳት እንደሚቻል ያስተምራል
የድራማው ዋና ገፀ ባህሪ ባንድ ወቅት ተደፍራ ልጅ ለመውለድ ተገደደች።ሆኖም ተመልሳ ጠንክራ በመማሯ ዛሬ ለህክምና ዶክተርነት በቃች።ይህ በራሱ የሚያስተምረው ትምህርት አለ።ወጣቶች ስህተት ላይ ሊወድቁ ይችላሉ ግን ከስህተታቸው ተመልሰው እንደገና ተነስቶ ለቁም ነገር መብቃት ነው ዋናው ቁም ነገር ይለናል የድራማው መልእክት።

ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ድራማዎች የረቀቀ የፕሮፓጋንዳ መስርያ አውድማ ወይንም የተበላሸ ትውልድ ማፍርያ ማሽን እንዳይሆኑ በስድስተኛውም የስሜት ህዋሳችንም መቃኘቱን አንርሳ።

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
የካቲት 26/2007 ዓም (ማርች 5/2015)

The post የቴሌቭዥን ድራማዎች በስድስተኛውም የስሜት ህዋሳችንም መቃኘቱን አንርሳ; የትኞቹ ያስተምራሉ? የትኞቹ መታረም ይፈልጋሉ? ”ቤቶች” እና ”ሞጋቾች” ድራማ appeared first on Zehabesha Amharic.


የኢሬቻ በዓል በደብረ ዝቋላ እንደሚከበር የተላለፈው ዘገባ ማስተባበያ እንዲሰጥበት ተወሰነ

0
0
  • debra-zeq (1)ለአፈጻጸሙ የወረዳው እና የዞኑ አስተዳደር ባለሥልጣናት ሓላፊነት ወስደዋል
  • ከመጋቢት ፭ ክብረ በዓል በፊት ማስተባበያው እንዲተላለፍ ከስምምነት ተደርሷል
  • ከኹሉም አካላት የተውጣጣ የሽማግሌዎች ኮሚቴ የችግሩን ቆስቋሾች ያጣራል
  • በክብረ በዓሉ ቀን የተጠናከረ ጥበቃ እንዲደረግ መመሪያ ተሰጥቷል
  • ‹‹ለእኛ ዐዲስ ነገር ነው፤ እዚኽ ቦታ ኢሬቻ የለም፤ በአራት ወይም በስምንት ዓመት አንዴ ዝናም እምቢ እንዳይለን ገዳሙን አስፈቅደን ከምንፈጽመው ሥርዐት ውጭ በተነገረው መልኩ የሚከበር በዓል የለም፡፡ ያስተላለፉት መጠየቅ አለባቸው፡፡››

/የአባ ገዳ ተወካዮች/

  • ‹‹ኅብረተሰቡን ከእኛ ጋራ ሊያጣሉ የሚፈልጉ ግለሰብ አመራሮች አሉ፡፡… ለተላለፈው መልእክት ሓላፊነት የሚወስድ አካል ካልተገኘ፣ የመጋቢት ፭ ክብረ በዓል ከመድረሱ በፊት በስሕተት የተላለፈ መኾኑ ይገለጽልን፡፡››

/የገዳሙ አስተዳደር/

  • ‹‹እናንተ ሰላም ፍጠሩ፤ [በክብረ በዓሉ] ከተለመደው ውጭ አንዳችም የሚደረግ አይኖርም፤ ጥበቃውም እንዲጠናከር ይደረጋል፤ የተላለፈውን ዘገባ አጣርተን በኦሮምኛ እና በአማርኛ ማስተባበያ እንዲሰጥበት እናደርጋለን፡፡››

/የዞን የአስተዳደርና ጸጥታ ሓላፊዎች/

Source:: haratewahido

The post የኢሬቻ በዓል በደብረ ዝቋላ እንደሚከበር የተላለፈው ዘገባ ማስተባበያ እንዲሰጥበት ተወሰነ appeared first on Zehabesha Amharic.

ውድ ኮሚቴዎቻችን ለውሳኔ ለዛሬ ወር መጋቢት 30 ተቀጠሩ!

0
0

ሰኞ የካቲት 30/2007

11042677_921194401265250_2791512484073047742_nውድ ኮሚቴዎቻችን የመጨረሻ የመከላከያ ምስክራቸውን ያሰሙ ሲሆን በፍርድ ቤቱ ቀነ ቀጠሮ መሰረት ኡስታዝ በድሩ ሁሴንን ጨምሮ ውድ ኮሚቴዎቻችን በዛሬው ችሎት በልደታው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ታውቋል፡፡ በማዕከላዊ ምርመራ ወቅት በኡስታዝ በድሩ ሁሴን ላይ በኤግዚቢትነት የተያዘው ላፕቶፕ ማስረጃዎች ለፍርድ ቤቱ ቀርበዋል፡፡ ሙያዊ ምስክርነቱን ለመስጠት በችሎቱ የተገኘው የኮምፒውተር ባለሞያ በላፕቶፑ ላይ 5 ሺ ያክል ፎቶዎችን ያየ መሆኑን፣ ነገር ግን አቃቤ ህግ ያቀረበውን ክስ የሚደግፍ ምንም አይነት መረጃ አለመኖሩንም ተናግሯል። ባለሙያው አክሎም የኡስታዝ በድሩ ሁሴን ላፕቶፕ የይለፍ ቃል (ፓስወርድ) የሌለው መሆኑን የገለፀ ሲሆን በዚህም ማንም አካል የሚፈልገውን ሊያደርግ የሚችልበት ክፍተት መኖሩን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ ለመጋቢት 22 ቀጠሮ ከሰጠ በኋላ የኮሚቴዎቻችን ጠበቆች ‹‹ቀን ይጨመርልን›› ሲሉ በጠየቁት መሰረት ለውሳኔ ለዛሬ ወር ለመጋቢት 30 ቀጥሯል።

ፍርድ ቤቱ ከዚህ በፊት ‹‹በሂጃብ ዙሪያና የታራሚዎችን አያያዝ ሁኔታ ያስረዱ› ሲል በቀጠረው መሰረት የማረሚያ ሀላፊው መልሳቸውን በቃል ይዘው የመጡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ‹‹መልሱ በጽሁፍ ይሁን›› በማለት ለመጋቢት 10 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ እንዲሁም ከመጋቢት 30 በፊት አቃቤ ህጉ እና ጠበቆቹ ‹‹የማጠቃለያ ንግግር›› (በከሳሽ እና በተከሳሽ መካከል ከውሳኔ በፊት የሚደረግ ንግግር) በቢሮ በኩልም ሆነ በችሎት እንዲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ ያዘዘ ሲሆን ኡስታዝ በድሩ ሁሴን ችሎት ላይ በህክምና ዙሪያ ባሰማው አቤቱታ መሰረት ‹‹ማረሚያ ቤቱ በቂ ህክምና እንዲደረግለት ያስደርግ›› የሚል ትእዛዝ በማተላለፍ ችሎቱን አጠናቋል፡፡

በዛሬው ችሎት ላይ በርካታ ህዝበ ሙስሊም የተገኘ ሲሆን የፍርድ ቤቱ ጥበቃዎች ‹‹መታወቂያቹን ካላሳያችሁ ከግቢ አትወጡም›› በሚል ትንኮሳ ሲፈጽሙ የነበረ መሆኑ ታውቋል፡፡

ሕዝበ ሙስሊሙ በጀግኖች መሪዎቹ ላይ የሚሰጥን የሐሰት ፖለቲካዊ ብይን በጭራሽ አይቀበልም! በጽኑም ይታገለዋል!!!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

 

The post ውድ ኮሚቴዎቻችን ለውሳኔ ለዛሬ ወር መጋቢት 30 ተቀጠሩ! appeared first on Zehabesha Amharic.

አርቲስቶቹ የህወሐት 40ኛ ዓመት ይደገም ቢሉስ?

0
0

serawit fikere
ኤልያስ ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደጻፈው:
.
ሁሌም ምርጫ ሲደርስ ብቅ ብቅ የሚሉ (በኢቢሲ ማለቴ ነው!) ፊታቸው “የቁጣ አስተማሪ” የሚመስል አንዳንድ ግለሰቦች አላጋጠማችሁም? ፖለቲከኞች ወይም ባለሥልጣናት እንዳይመስሏችሁ። (እነሱ አይቆጡም አልወጣኝም!) እነዚህኞቹን “የምርጫ ዬኔታ” ይሏቸዋል፡፡ ይሄ ስያሜ ለምን እንደተሰጣቸው አላውቅም፡፡ ምናልባት ቁጣ ቁጣ ስለሚላቸው ይሆን? የሚገርመው ደግሞ እየተቆጡ የሚያስተምሩን እንዴት ምርጫውን ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ—እንደምናደርገው ነው፡፡ (ሰላማዊ ምርጫ — በቁጣ?!)

እኔ የምለው ግን — አንዳንድ ግለሰቦች “የቁጣ ፈቃድ” አላቸው እንዴ? ወይስ ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል? ከምሬ እኮ ነው—መቼም አንድ ግለሰብ (ለብቻው) 90 ሚሊዮን ህዝብን ለመቆጣት የግድ ፈቃድ ያስፈልገዋል፡፡ ፈቃድ ካለው ህግ አክባሪ ስለሆንን እንታገሰው ይሆናል፡፡ ያለዚያ ግን —- (ምንም!!)
በነገራችን ላይ —- የህወሓትን 40ኛ ዓመት በዓል እንዴት አያችሁት? እንግዲህ በዓሉ ለአንድ ወር ያህል በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ቆይቶ ባለፈው እሁድ ተጠናቋል፡፡(አንድ ወር አላነሰችም?) የሸገር 125ኛ ዓመት የተከበረው እኮ ዓመቱን ሙሉ ነው (ዓመትም ተንዛዛ!) አንድ ነገር ልንገራችሁ— የዘንድሮን ምርጫ ልዩ የሚያደርገው፣ የህወሐት 40ኛ ዓመት በተከበረ ማግስት በመዋሉ ነው፡፡ (የEBCን ዜና ቀማሁት አይደል!) አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ… የዘንድሮን የህወሐት በዓል ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው ብትባሉስ? (ከ40ኛ ዓመቱ ውጭ ማለቴ ነው!) ቀላል እኮ ናት! (ሮኬት ሳይንስ አደረጋችሁት እኮ!) ልዩ የሚያደርገዋ—የህወሐት የቀድሞ ታጋዮች (አሁንማ ባለ ስልጣን ሆነዋል!) ከአርቲስቶች ጋር የሆድ የሆዳቸውን ማውራታቸው ነው!! (መሞዳሞድ ሌላ ነው!)

ተቃዋሚዎች በዓሉን አስመልክቶ የሰነዘሩት ትችት ግን አልገባኝም፤ “ኢህአዴግ በዓሉን ለምርጫ ቅስቀሳ ተጠቅሞበታል” ሲሉ ሰማሁ፡፡ (So what?) …ገና ለገና በግንቦት ምርጫ ይካሄዳል ተብሎ በየካቲት በዓል ላይከበር ነው? (“ማን ላይ ቁጭ ብለሽ ማንን ታምያለሽ” አሉ!) ከዚህም የባሰውን ደግሞ ልንገራችሁ፡፡ “የህወሐት በዓል አድዋን አደበዘዘው” አሉና አረፉት! (በጉዴ ወጣ! ማለት አሁን ነው!)
በጣም ግርም ያለኝ ምን መሰላችሁ? ህወሐትም ሆነ በአጠቃላይ ኢህአዴግ እስከዛሬ ሲተቹበት የነበረው ዋና ጉዳይ —– ምስጢረኞች ናቸው፤ ሆዳቸው አይታወቅም እየተባሉ ነበር፡፡ እናም የህወሐት የቀድሞ ታጋዮች፣ 40ኛ ዓመቱን በማስመልከት ምድረ አርቲስትን ሰብስበው ደደቢት ድረስ ወሰዱ፡፡ ዋና ዋና የትግል ቦታዎችን አስጐበኙ። የትግሉን ገድል ተረኩ፡፡ ከ20 ዓመት በላይ ከርችመውት የቆዩትን ገበና ወለል አድርገው ከፈቱ። (ልብን ከፍቶ እንደ መስጠት እኮ ነው!) እና ይሄ ጥፋቱ ምንድነው? (የምርጫ ቅስቀሳ ያስብላል!?)
ዝም ብዬ ሳስበው ግን በህወሐት ላይ ለተሰነዘረው ትችት ተጠያቂዎቹ አንዳንድ ስሜታዊ አርቲስቶች ይመስሉኛል፡፡ ደደቢትን ከጐበኙ በኋላ አንዳንዶቹ በEBC ሲሰጡት የነበረውን አስተያየት ሰምታችኋል? አብዛኞቹ ባዩት ነገር የምር መደነቃቸውን ከገፅታቸውም ከአንደበታቸውም ተገንዝቤአለሁ። ጥቂቶቹ ግን ትወና ቢጤ ሳይሞካክሩ አልቀሩም (ተሰጥኦ ለመቼ ነው!) ግን እኮ ገና መጀመሪያውኑ ተነግሯቸው ነበር፡፡ “ለጉብኝቱ የመጣችሁት እንድትዘምሩልን አይደለም፤ ሁሉም ሰው ያሻውን ሃሳብ ሊይዝ ይችላል” በሚል፡፡ አንዳንድ አርቲስቶች ግን ማሳሰቢያው የገባቸው አልመሰለኝም (ቀላል ዘመሩ እንዴ!)
በነገራችን ላይ ከበረሃ ትግል ሳይሆን ከዩኒቨርሲቲ ግቢ ወደ ቤተመንግስት ግቢ የመግባት ዕድል ያገኙት ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ በዚህ የህወሐት 40ኛ ዓመት በዓል ላይ “የታጋይነት ማዕረግ” ተሰጥቷቸዋል፡፡ (“ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም” አሉ!) ማዕረጉ የክብር ይሁን የምር ግን አልተነገረንም፡፡ የምር ከሆነ እኮ “ታጋይ ኃይለማርያም” ይባሉበታል ማለት ነው፡፡ የክብር ከሆነ ግን “የክብር ታጋይ” ነው የሚባሉት (የክብር ዶክትሬት እንደማለት!)
አያችሁ—የክብር ዶክትሬት የሚሰጠው ዩኒቨርስቲ ተገብቶ—-ትምህርት ተከታትሎ…ጥናትና ምርምር ሰርቶ — አይደለም፡፡ በተሰማሩበት ሙያ ለአገር ያበረከቱት ታላቅ አስተዋጽኦ ተመዝኖ ብቻ ነው የሚሰጠው፡፡ ይሄም ተመሳሳይ ይመስለኛል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ታጋይ የተባሉት ለ17 ዓመት ጠብመንጃ አንግተው ስለታገሉ አይደለም፡፡ (እሳቸው ከብዕርና ከጠመኔ ውጭ ምንም አያውቁም!) እዚህ ጋ መረሳት የሌለበት ቁምነገር ምን መሰላችሁ? እርግጥ ነው አቶ ኃይለማርያም ከትግል ጋር አይተዋወቁም። እርግጥ ነው ጥይት አልተኮሱም፤ እርግጥ ነው ፈንጂም አላፈነዱም፡፡ ግን የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን (መሬት ይቅለላቸውና!) ተክተው ሌጋሲያቸውን ለማስቀጠል ቃል የገቡት፣ ኃላፊነት የተሰጣቸውም ለእሳቸው ነው፡፡ (ታጋይ መባል አይበዛባቸውም!)
ለነገሩ በኢህአዴግኛ፤ ሥልጣንና ሹመትም እንደ ትግል ወይም መስዋእትነት ነው የሚቆጠረው፡፡ አቶ ኃይለማርያም፤ በጠ/ሚኒስትርነት የተሾሙ ሰሞን አዲሱን ስልጣናቸውን እንደ ትግል እንደሚያዩት መናገራቸው ትዝ ይለኛል፡፡ (አገር መምራትን እንደ ትግል ማሰብ አይገርምም?) ኢህአዴግ እኮ ልማት ማካሄዱንም፣ መልካም አስተዳደር ማስፈኑንም፣ የህግ የበላይነትን ማስጠበቁንም፣ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ማጐልበቱንም፣ የብሔር ብሔረሰቦች መብት ማስከበሩንም…ወዘተ (ከሀ-ፐ በሉት) እንደ ትግል ነው የሚቆጥረው፡፡ (የትጥቅ ትግል አልወጣኝም!)
አንዳንዴ ሳስበው ግን እውነቱን ነው እላለሁ፡፡ ከምሬ ነው…እነዚህ የተጠቀሱትን ጨምሮ…ኪራይ ሰብሳቢዎችን መጋፈጥ… ድህነትን ታሪክ ማድረግ… ፍትሃዊ የሃብት ሥርጭትን ማስፈን…(ሁሉንም እኩል ማደህየት እንደማይሆን ተስፋ እናደርጋለን!) የመድብለ ፓርቲ ሥርዓትን ማጠናከር (“ማን ነበር አክትሞለታል” ያለው?!) ወዘተ… ቀላል ትግል እኮ አይደለም፡፡ እንዴ…ደርግን የሚያህል ግዙፍ ኃይል በትጥቅ ትግል ለመጣል እኮ 17 ዓመት ብቻ ነው የፈጀው (ትንሽ ናት አልወጣኝም!) ቀደም ብዬ ያነሳኋቸው የአገር ችግሮች ግን ይኸው ከ20 ዓመት በኋላም “መች ተነካና!” እያስባሉ ናቸው፡፡ ከዚህ አንፃር ካያችሁት .. የኢህአዴግ ሥልጣን እውነትም መስዋዕትነት የሚከፈልበት ትግል ነው ሊባል ይችላል፡፡ (ተቃዋሚዎች አልገባቸውም!)
ከህወሐት 40ኛ ዓመት በዓል ጋር በተያያዘ የጀመርኩትን ወግ ሳልቋጭ ነው ወደ ትግል ትንተና የገባሁት፡፡ እናም የቀረችኝን ልጨርስላችሁ። አሁንም ጉዳዩ አርቲስቶችን ይመለከታል፡፡ (የህወሐትና የአርቲስቶችን ፍቅር ያዝልቅላቸው!?)
filfilu
በነገራችሁ ላይ ይኸኛውንም በEBC መስኮት ነው የታደምኩት (ከአንዴም ሦስቴ!) ምን መሰላችሁ? የህወሐትን 40ኛ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ ለአርቲስቶች የተዘጋጀ የጥያቄና መልስ ውድድር ነው፡፡ ቦታው አዳማ ይመስለኛል፡፡ ወይም እርግጠኛ ለመሆን በEBC መስኮት!!
የጥያቄና መልስ ውድድሩ “11በ11” የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ነበር፡፡ ለምን? አንደኛ፤ ህወኃት የተመሰረተበት ቀን የካቲት 11 ነው፡፡ ሁለተኛ፤ ጠያቂውን ጨምሮ በውድድሩ የተካፈሉት አርቲስቶች 11 ነበሩ፡፡ እናም 11 በ11 ተባለ፡፡ ምክንያቱ አላጠገባችሁም? (ደግሞ ለምክንያት!) የአሸናፊው ቡድን 5 አርቲስቶች በነፍስ ወከፍ 11ሺ ብር ነው የተሸለሙት፡፡ (የፓርቲ “ሞጃ” ይመቸኛል!) በእነዚህ ሁሉ በቂ ምክንያቶች የጥያቄና መልስ ውድድሩ “11 በ 11” ተብሏል፤ አለ – ውድድሩን የመራው አርቲስት ሸዋፈራሁ፡፡
shewaferaw
ጥያቄና መልሱ ተጀመረ፡፡ በነገራችሁ ላይ ጥያቄዎቹ በህወኃት ትግል ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ናቸው፡፡ (በትንሹ የ30 ዓመት ታሪክ ማለት ነው) እኔ የምለው… የእነ ህወሐት ገድል በታሪክ ትምህርት ውስጥ ተካተተ እንዴ? (እነ ፍልፍሉ እሳት ሲሆኑብኝ እኮ ነው!) ይታያችሁ… የታጋዮች የበረሃ ስም… ህወሐት ደርግን ድባቅ የመታባቸው ዘመቻዎች፤ ቦታዎች፣ ዓመተ ምህረቶች ወዘተ ሲጠየቁ ነበር፡፡ መጠየቃቸው አይደለም የሚገርመው። መመለሳቸው ነው፡፡ ያውም እኮ ከአፍ እየነጠቁ ነበር የሚመልሱት፡፡ ቆይ… የአዲስ አበባ አርቲስትና ኮሜዲያን የህወሐትን ትግል እንዲህ የሸመደዱት መቼ ነው? ይሄውላችሁ… በመልሳቸው ፍጥነት የተገረምኩት እኔ ብቻ ብሆን ኖሮ ችግሩ ከእኔ ነው ብዬ ግለ-ሂስ አወርድ ነበር፡፡ ግን እኔ ብቻ አይደለሁም፡፡

ራሱ የፕሮግራሙ አጋፋሪ፤ አርቲስቶቹ መልሱን እንደ እሳት ሲተፉበት ደንግጦ “አብራችሁ ታግላችኋል እንዴ?” አይል መሰላችሁ፡፡ (ደንግጦ አስደነገጠን!) እኔማ አውጥቼ አውርጄ ተውኩት እንጂ “ጥያቄና መልሱ …ተጭበርብሯል” ብዬ ለህወሐት ልጠቁም ዳድቶኝ ነበር (“ሃብታም በሰጠ …” እንዳልባል ፈርቼ ጭጭ አልኩ!)
ይልቅስ ምኑ ደስ አለኝ መሰላችሁ? ያሸነፈም የተሸነፈም መሸለሙ!! አሸናፊዎቹ (ቅሬታዬ እንዳለ ነው!) እያንዳንዳቸው 11ሺ ብር፤ በጠቅላላ 55ሺ ብር ሲሸለሙ፣ ተሸፊናዎቹ በነፍስ ወከፍ 5ሺ ብር፣ በድምሩ 25ሺ ብር አግኝተዋል፡፡ እኔ የምለው…አርቲስቶቹ ሽልማቱ ጥሟቸው የህወሓት 40ኛ ዓመት ይደገም ቢሉስ? (ምርጫ መሰላቸው?!)

እኛም እንግዲህ ግልጽ ማመልከቻ ለሚመለከተው ወገን አቅርበን ወጋችንን እንቋጭ … የግንቦቱ አገራዊ ምርጫ እንደ ጥያቄና መልስ ውድድሩ እንዲሆን እንፈልጋለን፤ አሸናፊም ተሸናፊም የሚሸለምበት!! ያሸነፈ ደረቱን የማያሳብጥበት፤ የተሸነፈ አንገቱን የማይሰበርበት ምርጫ ያስፈልገናል። (“ታስፈልገኛለህ” አለች ዘፋኟ!)
እንኳን ለአዲስ አድማስ 15ኛ ዓመት በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን!!

The post አርቲስቶቹ የህወሐት 40ኛ ዓመት ይደገም ቢሉስ? appeared first on Zehabesha Amharic.

እስረኞቹ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች በችሎት መድፈር እስር ተቀጡ • ‹‹እኛ የደፈርነው ችሎት አሻንጉሊት ችሎት ነው›› አብርሃ ደስታ

0
0

Habtamu abrhayeshiwas daniel

የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ቅጣት ተላለፈባቸው

᎐ተጨማሪ ቅጣትም ይጠብቃቸዋል

• ‹‹እኛ የደፈርነው ችሎት አሻንጉሊት ችሎት ነው›› አብርሃ ደስታ
• ‹‹ችሎቱ ላይ ያጨበጨብነው በማፌዝ ሳይሆን በምሬት ነው›› የሺዋስ አሰፋ
• ‹‹ፍትህ ተጠምተናል፣ ፍትህ ለኢትዮጵያ ህዝብ!›› ዳንኤል ሺበሽ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ከስምንት ወራት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ፣ የአንድነት እንዲሁም የዓረና ትግራይ ፓርቲዎች አመራሮች ‹ችሎት በመድፈር ወንጀል› ጥፋተኛ በመባላቸው ዛሬ መጋቢት 1/2007 ዓ.ም በልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት በሦስቱ አመራሮች ላይ እያንዳንዳቸው በሰባት ወራት እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል፡፡

የካቲት 26/2007 ዓ.ም ተከሳሾች በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደተፈጸመባቸውና ንብረትም እንደተወሰደባቸው በመግለጽ አቅርበውት ለነበረው አቤቱታ ፍርድ ቤቱ የማረሚያ ቤቱን ምላሽ ሙሉ ለሙሉ በመቀበል አቤቱታቸውን ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ 5ኛ ተከሳሽ አቶ የሺዋስ አሰፋ በማጨብጨቡና 3ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታና 4ኛ ተከሳሽ አቶ ዳንኤል ሺበሽ ሳይፈቀድላቸው ‹‹ጥሩ ፍርድ፣ ጥሩ ብይን›› በማለት አቶ የሺዋስን በመደገፍ ችሎት ደፍረዋል ተብለው ጥፋተኛ መሰኘታቸው ይታወሳል፡፡

በዚህ መሰረት ፍርድ ቤቱ ለዛሬ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ተሰይሞ በአብርሃ ደስታ፣ በየሺዋስ አሰፋ እና ዳንኤል ሺበሽ ላይ የሰባት ወራት እስራት በእያንዳንዳቸው ላይ ወስኗል፡፡ ሦስቱም ተከሳሾች ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ድጋሜ ችሎት ውስጥ አጨብጭበዋል፡፡ በዚህም ድጋሜ ጥፋተኛ ተብለዋል፤ ከሁለት ቀናት በኋላም የቅጣት ውሳኔ ይወሰንባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ሦስቱ ተከሳሾች ‹‹እድል ስጡን እንናገር፣ አቤቱታም አለን ተቀበሉን›› ቢሉም ፍርድ ቤቱ ሊሰማቸው አልፈለገም፡፡ በተለይ ዳንኤል ሺበሺ ‹‹ሌላ አቤቱታ አለኝ፣ ፍርድ ቤቱ ያዳምጠኝ›› ብሏል፡፡ ፍርድ ቤቱ አሁንም ችሎቱ ላይ እያፌዛችሁ ነው በሚል ጥፋተኛ ሲላቸው ሦስቱም አመራሮች ፍርድ ቤቱን ማስፈቀድ ሳያስፈልጋቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

‹‹እኛ የደፈርነው ችሎት አሻንጉሊት ችሎት ነው፡፡ ‹Already› የተደፈረ ችሎት ነው›› ሲል አብርሃ ደስታ ተናግሯል፡፡ በዚህ ጊዜ ዳኞቹ ጣልቃ በመግባት፣ ‹‹የምትናገረው ነገር እንደገና ወደ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ የሚወስድህ ጉዳይ ነው፤ ምርመራ ይደረግበታል›› ሲሉ አብርሃ በበኩሉ ‹‹አሁንስ ቢሆን የምናገረውን ፖሊስ እየሰማ አይደለምን?›› ሲል መልሷል፡፡

አቶ የሺዋስ አሰፋ በበኩሉ ‹‹ከስምንት ወር በላይ ታፍነናል፡፡ በህግ አይደለም የተያዝነው፡፡ ደግሞ ማጨብጨባችን በችሎቱ ከማፌዝ ሳይሆን ከምሬት በመነጨ ነው፡፡ ህገ-መንግስታዊ መብታችን ተጥሷል፡፡ እኔ ለምሳሌ የሰማያዊ ፓርቲ አባል በመሆኔ ነው የታሰርኩት፡፡›› ብሏል፡፡

አቶ ዳንኤል ሺበሽ ድግሞ ‹‹አሁንም ችሎት ደፍራችኋል ካላችሁ ቅጣቱን ጨምሩብንና ሸኙን፡፡ በእርግጥ ዳኞች ላይ ያለውን ጫና እንረዳለን፡፡›› ሲል ችሎት ውስጥ ተናግሯል፡፡

በዚህ ሁኔታ በተከሳሾችና በችሎቱ መካከል ያለው አለመግባባት ሲጨምር ዳኞቹ መጋቢት 3/2007 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ የቅጣት ውሳኔ እንደሚሰጥ በመጥቀስ ሦስቱ ተከሳሾች ከችሎት በፖሊስ እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡ ከችሎት እየወጡ እያሉም አቶ ዳንኤል ሺበሽ ‹‹ፍትህ ተጠምተናል፤ ፍትህ ለኢትዮጵያ ህዝብ!›› እያለ ችሎቱን ለቅቆ ወጥቷል፡፡

በሌላ በኩል ሦስቱ ተከሳሾች ከችሎት መውጣታቸውን ተከትሎ፣ ከዚህ ቀደም በማረሚያ ቤቱ ላይ በቀረበው አቤቱታ ዳኞች በሰጡት አስተያየት ላይ አቤቱታ አቅርቦ እንደነበር በማስታወስ አቤቱታው እንዲመዘገብለት የጠየቀው አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ ‹‹በበኩሌ ያሉኝን መረጃዎች እያቀረብኩ ስነ-ስርዓቱን አክብሬ ክርክሩን አቀጥላለሁ›› ሲል ተናግሯል፡፡

The post እስረኞቹ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች በችሎት መድፈር እስር ተቀጡ • ‹‹እኛ የደፈርነው ችሎት አሻንጉሊት ችሎት ነው›› አብርሃ ደስታ appeared first on Zehabesha Amharic.

ብሄር እንዴት ተፈጠረ?

0
0

ጌታቸው ሺፈራው

የብሄርን አፈጣጠር አስመልክቶ ሶስት ዋና ዋና አስተሳሰቦች የየራሳቸውን መልስ ይሰጣሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል ተፈጥሯዊ (Primordial)፣ በማህበራዊ ሂደቶች የተፈጠረ (constructed) እና ልሂቃን ለስልጣን መሳሪያነት የፈጠሩት (instrumental) የሚሉት ይገኙበታል፡፡ የመጨረሻዎቹ ሁለቱ ለብሄር መፈጠር የተሳታፊ ሀይሎችንና ወቅት ላይ ልዩነት ያላቸው ቢሆንም ከመጀመሪያው በተቃራኒ ብሄር የሠው ልጆች የፈጠሩት እንጂ ተፈጥሯዊ አይደለም ብለው ያምናሉ፡፡ በመሆኑም  ክርክሩ ተፈጥሯዊ እና ሰዎች የፈጠሩት በሚል ሁለት ጎራ ጠበብ ብሎ መቅረብ ይቻላል፡፡

የመጀመሪያው አስተሳሰብ  ብሄር ድሮ ሰው ከተፈጠረበት ወቅት ጀምሮ የኖረና ሰዎች እርስ በእርሳቸው ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር ጥቅማቸውን ያስጠብቁበት የነበረ ተፈጥሯዊ (ሲወረድ ሲዋረድ የመጣ) ቡድናዊ መገለጫ ነው የሚል ነው፡፡  ሆኖም ይህ አስተሳሰብ  ከጊዜ ወደጊዜ  ከአንድ ብሄር እየተሰነጠቁ ወይንም በሌላ ምክንያት የሚወጡ ብሄሮችን ጥያቄ ሊመልስ  አልቻለም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ  በአንዳንድ አገራት ጠንካራ የአገር ግንባታ ምክንያት የተለያዩ የነበሩ ህዝቦች አንድነት ስለማድረጋቸውም መለስ የለውም፡፡ ከምንም በላይ የዘመኑ ኢኮኖሚና አገራዊ ብሄርተኝነት ብሄር የሚባልንም ሆነ ሌላ ማህበራዊ ስብስብን እያፈረሰ መገኘቱ ለዚህ አስተሳሰብ  ድክመት ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

ብሄር በሂደት የተፈጠረ ነው የሚለው አስተሳሰብ  ብሄር የተፈጠረው  በተለያዩ  ምክንያቶች  በጊዜ ሂደት በተለይም በማህበራዊ ግንኙነት  የተፈጠረ እና  ትርጉሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀየረ የመጣ ነው  የሚል ነው፡፡ ብሄር ተፈጥሯዊ ነው ከሚሉት በተቃራኒ ብሄር ማህበራዊ ፈጠራ ነው የሚለው የባህል ለውጥ፣ ድንበር፣ ታሪካዊ ወቅት፣ የግለሰቦች ሚና፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ምክንያቶች ለብሄር መፈጠር እንደ ምክንያትነት ይጠቅሳል፡፡

ሶስተኛው አስተሳሰብ ለብሄር መፈጠር ተጠያቂ የሚያደርጋቸው ልሂቃንን ነው፡፡ ይህ አስተሳሰብ ብሄር የተፈጠረው ለልሂቃን መሳሪያነት (instrument) ነው ይላል፡፡ በዚህ አስተሳሰብ ስር የሚገኙ ምሁራን ብሄርን የፈጠሩት በብሄር ስም የሚነግዱ ልሂቃን ወይንም ‹‹የብሄር ኢንተርፕርነሮች›› (ethnic entrepreneurs) ይሏቸዋል፡፡ ይህንም የሚያደርጉት  በአንድ አገር መንግስት ውስጥ ይገባናል የሚሉትን ጥቅም ለማሳደግ፣  ለዚህምና ለሌሎቹ ለሚደረጉ ትግሎች  በዚህ በፈጠሩት ማንነት ስም  በርከት ያሉ ምልምሎችን ለማግኘትና ይህንንም ተጠቅመው የራሳቸውን  ግለሰባዊ ስልጣን ለማጠናከር ነው፡፡

ሁለተኛውና ሶስተኛም አስተሳሰቦች ከልዩነታቸው ይልቅ ተመሳሳይነታቸው የጎላ ነው፡፡ ልዩነታቸው ብሄር በሂደት የመጣ ነው የሚሉት ለብሄር መፈጠር የፖለቲከኞቹን ሚና አጉልተው አለማሳየታቸው ሲሆን በአንጻሩ ብሄር የልሂቃን ፈጠራ ነው የሚሉት ትልቅ ትኩረት የሚሰጡት  ለልሂቃን ብቻ መሆኑ ነው፡፡ በእርግጥ ብሄር ቀስ በቀስ የተፈጠረ ነው የሚሉትም ስለልሂቃን በስፋት ባያነሱም ለብሄር መፈጠር ጠባብ ብሄርተኝነትን እንደምሳሌ ሲጠቅሱ የሚነሳው ብሄር ለልሂቃን መሳሪያ መሆኑ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአንድ ወቅት በልሂቃን የበላይነት የተፈጠረው ብሄርተኝነት ቀስ በቀስ በህዝብ ዘንድ ሲዘወተር ለብሄር መፈጠር ድርሻቸው ከፍተኛ ስለሚሆን ሁለቱ አስተሳሰቦችን የሚመሳሰሉባቸው ነጥቦች ይበዛሉ፡፡ ሁሉቱ አስተሳሰቦች በየራሳቸው ያለባቸው መጠነኛ ክፍተትም ሁለቱን አስተሳሰቦች በጥምረት በመጠቀም  ለብሄር መፈጠር ሙሉ እይታ መፍጠር እንደሚቻል ብዙዎቹ ምሁራን ያምኑበታል፡፡ ሁለቱን የጋራ የሚያደርጋቸው ደግሞ የልሂቃን ሚና ነው፡፡

ethiopia ppl

    ኢትዮጵያና ‹‹ብሄር›› 

ኢትዮጵያ የተለያየ ባህል፣ ወግ፣ ታሪክና ቋንቋ ያላቸው ህዝቦች መኖሪያ ብትሆንም ብሄር በፖለቲካ ቃናው ትኩረት እየተሰጠው የመጣው ከጣሊያን ወረራ በኋላ ነው፡፡ በእርግጥ ከዚያ በፊትም ቢሆን የኢትዮጵያ የተለያዩ ገዥዎች ህዝብን በቋንቋ፣ ከባቢና በመሳሰሉት አንቀሳቅሰው ከሌሎች ጋር ያላቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልዩነት ለማጠናከር አልጣሩም ለማለት አይቻልም፡፡ በተለይ ህዝቦች በመንገድና በመሳሰሉት መሰረተ ልማት ባለመገናኘታቸው ባህል፣ቋንቋና ሌሎችም ባህላዊ እሴቶቻቸው በመለያየታቸው በሂደት ከሌሎች ለሚለዩባቸው አጋጣሚዎች ክፍተት ይፈጠራሉ፡፡ ይህን ልሂቃን በመሳሪያነት ሲጠቀሙበት ደግሞ ብሄር መፈጠሩ የግድ ነው፡፡

አንድ ተመሳሳይ ቋንቋ፣ ባህልና ሌሎች ማህበራዊ እሴቶችን ይከተላል የምንለው ህዝብ በውስጡ መጠነኛ ልዩነቶች ይኖሩታል፡፡ ህዝቦች በተለያዩ ምክንያች ግንኙነታቸው ከተዳከመ እያደር እነዚህ ልዩነቶች እየተጠናከሩም በእነዚህ ህዝቦች መካከል ሰፋ ያለ ልዩነት ይፈጠራል፡፡ በተለይ እነዚህን ልዩነቶች የሚያስታርቅና የበላይ የተባለ ገዥ ማህበራዊ እሴት ከሌለ ህዝቦቹ ቀስ በቀስ  ልዩነታቸው ሊሰፋ ይችላል፡፡ በየትኛውም አንድ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝብ መካከል ዘየና ሌሎች ልዩነቶች በሂደት የቋንቋ መሰረታዊ ልዩነቶችን ይፈጥራሉ፡፡ ለአብነት ያህል አማርኛ እና ትግርኛ ከግዕዝ የመጡ መሆናቸው የሚነገርላቸው ቢሆንም የህዝቦች አሰፋፈር ልዩነት፣ መንገድና ሌሎችን የመሳሰሉ መሰረተ ልማት አውታሮች አለመኖር እንዲለያዩ አድርጓቸዋል፡፡ የልሂቃን ሚና ሲጨመርበት ደግሞ የአሁኑን ፖለቲካ ፈጥሯል፡፡

በአሁኑ ወቅት በትምህርት ደረጃ የሚሰጠው አማርኛ ሸዋ፣ ጎንደር፣ ጎጃምና ወሎ አካባቢ የሚነገሩ ዘየና ሌሎች የቋንቋው ልዩነቶችን ማስታረቅ ባይችል፣ በመሰረተ ልማት መገናኘት ባይችሉ እነዚህ ከጅኦግራፊያዊ አቀማመጥ ውጭ የማይለያዩ አማርኛ ተናጋሪ ህዝቦች ትግርኛ እና አማርኛ እንደተለያዩት የተለያዩ ቋንቋዎች መሆን ይችሉ እንደነበር አያጠራጥርም፡፡

ኢትዮጵያ አገውኛ ተናጋሪ ህዝቦች ይኖሩባት እንደነበር ታሪክ ያስረዳል፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ ይኖሩ የነበሩት ህዝቦች አገዎች እንደነበሩ በኢዛናና ካሌብ ዘመን የነበሩ ቅሬቶች ፍንጭ ሰጥተውል፡፡ እነዚህ ህዝቦች በአማርኛና ትግርኛ ተናጋሪው ህዝብ ተውጠው በአሁኑ ወቅት በተወሰኑ አካባቢዎች ብቻ ይገኛሉ፡፡ ለአብነት ያህል በወሎና ጎጃም አገው በሚል፣ በጎንደር ቅማንት፣ በባህር ዳር አካባቢ ወይጦ እና የመሳሰሉ ስሞች ተሰጥቷቸው ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ህዝቦች ትግራይና ኤርትራ ውስጥም ተበታትነው ይኖራሉ፡፡  ከከረን ጀምሮ በቋራ፣ ዳንግላ፣ ሰቆጣ፣ ጣና ዳር….ተበታትነው ከሚገኙት ውጭ ሌሎቹ በትግርኛ እና አማርኛ ተናጋሪ ሆነዋል፡፡ ይህኛው ክስተት የሚያሳየው ብሄር ተፈጥሯዊ ማንነት ሳይሆን የሚዋጥ፣ የሚቀየር መሆኑን ነው፡፡ እነዚህ በአንድ ወቅት ‹‹አገው›› ተብለው የነበሩ ህዝቦች በሂደት በመጣ ማግበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ‹‹ኤርትራዊ››፣ ‹‹ትግሬ››ና ‹‹አማራ›› ተብለዋል፡፡ ልሂቃንም በተለያዩት እነዚህ ማንነቶች በአንድ ወቅት አንድ የነበሩትን ህዝቦች አንቀሳቅሰዋቸዋል፡፡ ሌላው ይቅርና ግዕዝ ከቤተክርስቲያን አልፎ በተወሰነ ህዝብ የሚነገር ቢሆኑ ኖሮ ኢህአዴግ አንድ ተጨማሪ ብሄር ሊያቋቁም ነበር ማለት ነው፡፡

የአክሱም ስርወ መንግስት በተለያዩ ምክንያቶች ተዳክሞ የዛጉየ ስርወ መንግስት ሲተካ  ከድልነአድ እስከ ይኩኑ አምላክ ያሉት 8 የአክሱም ስርወ መንግስት ነገስታት በሸዋ እየሸሹና ተደብቅው ኖረዋል፡፡ የአሁኑ ወቅት ልሂቅ መር የብሄር ፖለቲካ አክሱም ውስጥ የነበሩትን ነገስታት ‹‹የትግሬ ቅድመ አያቶች›› አድርገው ይወስዷቸዋል፡፡ ከአክሱም መጥተው ሸዋ ነገስትነትን የመሩትን ደግሞ ‹‹አማራ›› ይሏቸዋል፡፡ ታሪክ ደግሞ የአክሱም ስርወ መንግስት ወቅት በሰሜን ኢትዮጵያ ይነገር የነበረው ቋንቋ አገውኛ እንደነበር ያስረዳናል፡፡

ብሄር ተፈጥሯዊ ቢሆን ኖሮ አገውኛ የሚናገሩት አብዛኛዎቹ ኢትዮጰያ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ህዝቦች ሌሎች ቋንቋዎችን በሚናገሩ ህዝቦች ሳይዋጡ ‹‹አገው›› ሆነው በቆዩ ነበር፡፡ ትግሬ ከአክሱማውያን የመጣ ብሄር ቢሆን ኖሮ መነሻቸው ከአክሱማውያን የሆኑት የሸዋ ነገስታትም  እስከ አሁን ‹‹ትግሬ›› ሆነው በቀጠሉ ነበር፡፡ ይሁንና ብሄር በሂደት በተለይም የልሂቃን ሚና ተጨምሮበት የሚፈጠር አዲስና የፈጠራ ማንነት በመሆኑ እነዚህ ህዝቦች የተለያዩ ማንነቶች እንዳላቸው እየተቆጠረ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ኢህአዴግ አራት ያህል የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችን ‹‹ወጋጎዳ›› በሚል አዲስ የብሄር ማንነት ለመመስረጥ ጥረት አድርጎ ነበር፡፡ ይህ አዲስ ማንነት ቢሳካ ኖሮ ሀይለማሪያም ደሳለኝ የወላይታ ሳይሆን በልሂቃን መሳሪያነት ከሌሎች ሶስት (ጋሞ፣ ጎፋና ዳዋሮ) ጋር የተለነቀጠው ‹‹ወጋጎዳ›› ብሄር ተደርገው ሊወሰዱ ነበር፡፡ ምንም እንኳ በተለያዩ ምክንያቶች ባይሳካም ‹‹የወጋጎዳ›› ፕሮጀክት ብሄርን የሚፈጥሩት ልሂቃን መሆናቸውን ቁልጭ አድርጎ አሳይቷል፡፡

ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ በኋላ ብሄር በግልጽ ተፈጥሯዊ እንደሆነ ተደርጎ ተግባራ ሊሆን ችሏል፡፡ ብሄር ተፈጥሯዊ ነው የሚለውን አስተሳሰብ የሚከተሉ አካላት አንድ ግለሰብ በብሄሩ እንጂ በግለሰባዊነቱ መቆም አይችልም የሚል አስተሳሰብ ያራምዳሉ፡፡ ይህም በእኛው ህገመንግስት ‹‹እኛ የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› በሚል ተቀምጧል፡፡ በመሳሪያነት የሚጠቀሙ ፖለቲከኞች ብሄር ተፈጥሯዊ ነው የሚሉ አካላት አስተሳሰብ የሚጠቀሙ ናቸው፡፡ በመሆኑም በአስተሳሰብ ደረጃ ብሄር ተፈጥሯዊ ነው የሚለውን በመጠቀም ኢህአዴግ የብሄር ‹‹ኢንተርፕርነር›› ሆኖ  እናገኘዋለን፡፡  ብሄር ተፈጥሯዊ ከሆነ የትኛውም ፖለቲከኛ ወይንም ፓርቲ ሊመሰርተው የሚችለው መንግስትም ሆነ ስርዓት  ብሄር  ተመሳሳይ የብሄር ማንነት ላይ ያተኮረ መሆን አለበት፡፡ ይሁንና የኢትዮጵያ ህዝቦች በአጼ ሀይለስላሴ፣ ደርግ፣ ኢህአዴግ ስር የያዙት የብሄር ማንነት በየ ስርዓቱ የተለያየና በየ ጊዜው እንደ ልሂቃኑ ጥበትና ኢትዮጵያዊ አላማ የሚወናበድ ነው፡፡

ወደ ኢህአዴግ ወረድ ብልን እንኳ በአቶ መለስ አመራርና በሌሎቹ አመራር ኢትዮጵያንም ሆነ በየ የኢትዮጵያን ብሄሮች የሚያንቀሳቀሱበት አጋጣሚ የተለየ ነው፡፡ አንድ ህዝብ ሊከተለው የሚችለው በጊዜው በኢኮኖሚ፣ ሚዲያም ሆነ ወታደራዊ ሁኔታ ጊዜው ስልጣን የሰጠውን አካል ነው፡፡ ህውሃትና አረና የትግራይን ህዝብ የብሄር ማንነት የሚቀርጹበት ሁኔታ ተመሳሳይ አይሆንም፡፡ ብአዴንና የድሮው መአአድ፣ ኦነግና ኦህዴድ፣ የደቡብ ህብረትና ደኢህአዴን፣ ሶዴፓና ኦብነግ፣ ሻቢያና ጀብሃ እንወክለዋነን የሚሉትን ህዝብ ብሄራዊ ማንነት የሚመሩበትና የሚፈጥሩት በተለያየ መልኩ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከ20 አመት በፊት የነበሩትና አሁን ያሉት እነዚህ ፓርቲዎች ህዝብን የሚቀሰቅሱበት አጋጣሚ የተለያየ ነው፡፡ በቅርቡ ኦነግ የመገንጠል ጥያቄውን አንስቻለሁ ሲል ከ20 አመት በፊት ከነበረው የኦነግ የብሄር ማንነት መለየቱን ለመገንዘብ ይቻላል፡፡

ብሄርና ደም

ብሄር ተፈጥሯዊ ካልሆነ ከደም ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም ማለት ነው፡፡ ሳይንስ  በራሱ  ዘር፣ ብሄርና ሌሎችን የሰው ልጅ ማህበራዊ ትስስሮች ለማመሳሰል ቢሞክርም ሊሳካለት አልቻለም፡፡ በተለይ ምዕራባዊያን ከሌሎች የተለዩ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ሙከራ ያደረጉ ‹‹ሳይንቲስቶች› ዘንድ የሰዎች ዘረመል የሰውን ዘርቁልጭ አድርጎ ያሳያል የሚል መላ ምት የነበራቸው ቢሆንም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ እስካሁን አንድ ሰው ከየትኛው አገር እንደመጣ  የሚያሳይ አስተማማኝ መረጃ እንኳን ማግኘት አልተቻለም፡፡

በእነዚህ ጥናቶችን ተንተርስ ለአብነት ያህል ኢትዮጵያን እንደምሳሌ ብንወስድ የሚያሳየው የአንድ አገር ሰው በዘረመልም ሆነ በደም ከሌሎች አገራት ጋርም የሚመሳሰል ነው፡፡ እንደ ጥናቶቹ  ኢትዮጵያዊያን ከቻይና፣ አብዛኛው የአረብና የኤሲያ አገራት፣ አንዳንድ የደቡብ አሜሪካና ሜክሲኮ ህዝቦች  መካከል ከ10-15 የሚሆኑት በተመሳሳይ የኤ የደም ዘር ባለቤቶች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያውያን፣ አብዛኛዎቹ የአፍሪካዊያን፣ የደቡብ አሜሪካ ኤሲያ ከ5-10 እና ከ10-15 የሚሆነው ህዝባቸው ቢ የደም አይነት ያለው ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያን ጨምሮ አፍሪካ፣ የመንና ሳውዲ የመሳሰሉ የአረብ አገራት፣ የተወሰነ የቻይና ከፍል፣ ጥቂት የምስራቅ አውሮፓ አገራት፣ ከደቡብ አሜሪካ አገራት መካከል አንዳንድ አካባቢዎች፣ የአውስትራሊያ ጠረፋማ ክፍሎች  ከሚኖሩት ህዝቦች መካከል ከ40-70 ኦ የደም አይነት ባለቤቶች ናቸው፡፡  በብሄሮች መካከል ይህን ያህል የሚመሳሰል የዘረመልና  የደም አይነት ለማግኘት አልተቻለም፡፡ በዓለም ህዝቦች ሁሉ ኤ፣ ቤ፣ ኤቤና ኦ የተባሉት የደም አይነቶች የትም የሚገኙ ሲሆን ከአንድ ቤተሰብ ይልቅ በተለያዩ አገራት ያሉ ህዝቦች ለሌላኛው ደም መስጠት ይችላሉ፡፡ በመሆኑም አንድ ኦሮሞ ከብሄሩ ያላገኘውን ተመሳሳይ የደም አይነት ወይንም ልብ፣ ኩላሊትና ሌሎች ተመሳሳይ የአካል ክፍሎች ከትግሬ፣ ከአማራ፣ ከጉራጌና ከሌሎች ብሄሮች አልፎ ደቡብ አሜሪካ፣ ኤሲያ፣ አውሮፓና አውስትራሊያ ከሚገኝ ነጭ ማግኘት ይችላል፡፡

አንድ ቋንቋ የሚናገሩና በተለያየ የአየር ንብረት ከሚኖሩ ህዝቦች በተሻለ የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩና በተመሳሳይ የአየር ንብረት የሚኖሩ ህዝቦች ተመሳሳይ የሰውነት ገጽታ ይኖራቸዋል፡፡ ለአብነት ያህል በመተማና ሁመራ አካባቢ የሚኖሩ ትግርኛ እና አማርኛ ተናጋሪዎች በቆላማው ሶማሊና አፋር ክልሎች ከሚኖሩት የሶማልኛና አፋርኛ ተናጋሪ ህዝቦች ተመሳሳይ የሰውነት ገጽታ፣ አለባበስና አመጋገብ ባህል አላቸው፡፡ ከምንም በላይ በአገራችን ብሄር የፈጠራ ማንነት መሆኑን የሚያሳየው ሁለት የተለያየ ማንነት አላቸው ከተባሉ ቤተሰቦች የተገኘ ልጅ የእናቱን ማንነት ትቶ የአባቱን ማንነት በግድ እንዲቀበል የመመደቡ ጉዳይ ነው፡፡ አንድ ግለሰብ በተለያዩ ምክንያቶች የእናቱን አሊያም ግለሰባዊ ማንነቱን መቀበል ቢፈልግ የወቅቱ የአገራችን ስርዓት በግድ የአባቱን ብሄር አባል ያደርገዋል፡፡ ሰው የፖለቲካ እንሰሳ እንደመሆኑ ብሄርን ሲፈጥር እንሰሳት ከሰው የተሻለ ቁርጥ ያለ ዘር  ያላቸው ማንነታውን በሂደት በሚፈጠር ማህበራዊ ማንነት አሊያም የልሂቃን ፈጠራ የሚያወናብደው ፖለቲካዊና ማህበራዊ ምክንያት ባለመጠቀማቸው ብቻ  ነው፡፡

ሶቬት ወዲያ ኢትዮጵያ…..

በአገራችን የብሄር ማንነት የሚጣረሰው ገና ከትርጉሙ ነው፡፡ ብሄር በግዕዝ አገር ማለት ቢሆንም ከ1960ው ጥራዝ ነጠቅ ትውልድ ትርጉም በኋላ አገሪቱ የተሰራችባቸው ማንነቶች ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ በእነ ስታሊኑ ትርጉም እንኳ ብንሄድ ብሄር የሚለውን ‹‹ተመሳሳይ ወይንም ተቀራራቢ ቋንቋ፣ ባህል፣ ታሪክ፣…..›› ለሚጋሩ ህዝቦች የሚሰጥ ነው፡፡ እንግዲህ እነዚህ ህዝቦች ከሌሎች የተለዩ፣ ማንነቱ ተፈጥራዊና ከሌሎች በፍጹም የተለየ በመሆኑ መቼም ቢሆን ይህን ባህላቸውን፣ ማንነታቸውን አይቀይሩም እንደማለት ነው፡፡ ‹‹የጋራ ታሪክ ያላቸው›› ብሎ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ወላይታ፣ (ቢሳካ ኖሮ ደግሞ ‹‹ወጋጎዳ)፣ ሲዳማ…ሲልም የአድዋና ማይጨውን ጨምሮ የሚጋሩት ታሪክ የላቸውም እያሉን ነው፡፡

በሶቬት ህብረትና በኢትዮጵያ መካከል ከፍተኛ ልዩነት ነው ያለው፡፡ ሌኒን 15 አገራት አንድ ከማድረጉ በፊት ኢትዮጵያውያን በጋራ አገር ለመመስረት ለረዥም አመት ሰርተዋል፡፡ በአንጻሩ የሶቬት ክፍሎች አንድ እስኪሆኑ ድረስ ያላቸው ታሪክ የተለየ ነው፡፡ የሶቬት ህብረት አባላት ህብረቱን ከመራችው ሩሲያም ሆነ ከሶቬት ህቭረት የተለየ የአገር ምስረታ ታሪክ አከናውነው የተቀላቀሉ ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ የሩሲያ መንግስት ከመስፋፋቱ በፊት በኦቶማን ቱርክና በሌሎች ቀኝ ገዥዎች ስርም የነበሩ ናቸው፡፡ የሶቬት ህብረት ፌደራል አወቃቀር በአገራት እንጅ አገር ውስጥ ባሉ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝቦች የተመራ አልነበረም፡፡ ኢህአዴግም የነ ስታሊንን ስርዓት ሲገለብጥ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ፣ አፋር፣ ሀረሪ…..እያንዳንዳቸው ‹‹አገር›› ሆነው ፌደራሊዝሙን እንደተቀላቀሉ እየነገረን ነው፡፡ በተቃራኒው ኢትዮጵያ ውስጥ በየ አካባቢው የነበሩ ነገስታት ኢትዮጵያን በራሳቸው መልክ ለመገንባት እንጅ የያዙትን አካባቢ ገንጥለው አገር ለመመስረት አልነበረም፡፡  የየራሳቸውን ግዛት ለመመስረት ነበር የሚል የፈጠራ መረጃ እንኳን ቢቀርብ ‹‹አገር›› ለመሆን የሚያስችል ቅርጽ ሳይዙ ማዕከላዊ መንግስት ውስጥ መጠቃለላቸው ከሶቬት አባላት በእጅጉ የተለዩ ያደርጋቸዋል፡፡

እንዲያው የስታሊኑን ትርጉም ብንወስድ እንኳን የእኛው የብሄር ትርጉም የተሳሳተ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ኢትዮጵያውያን ቋንቋ ሳይገድባቸው እንጀራና ጥሬ ስጋ ይመገባሉ፡፡ ጠላና ጠጅ ይጠጣሉ፡፡ ተዋልደውና በጉድፍቻ አብረው ይኖራሉ፡፡ አተራረሳቸው፣ አመራረታቸውና ምርቶቻቸው በአየር ንብረት ካልሆነ በስተቀር ልዩነቱ ጎልቶ የሚተይ አይደለም፡፡ በጋራ አላማ ቅኝ ገዥዎችን ተዋግተዋል፡፡ አገር ገንብተዋል፡፡ በመሆኑም በስታሊኑ ቋንቋ ‹‹ተመሳሳይ ወይንም ተቀራራቢ ባህል፣ ታሪክ፣ አላማ….›› መሰረት አንድ ብሄር (አገር›› ውስጥ የሚካተቱበት እንጅ የሚነጣጠሉበት አልነበረም፡፡

በነገራችን ላይ ህዝቦች የተለያዩ ናቸው ተብሎ ‹‹ብሄር›› የተለያዩ ቋንቋ ተናገሪ ህዝቦች መጠሪያ በዋለበት እንደገና ‹‹ብሄር›› ማለት አገር ማለት መሆኑን ይነገረናል፡፡ ለአብነት ያህል ብሄራዊ ቡድን ሲባል የኦሮሞ፣ የአማራ፣ ትግሬ፣ ወላይታ ተጫዋቾች ብቻ የተሰባሰቡበት ሳይሆን የአገሪቱ ቡድን መሆኑ ነው፡፡ ብሄራዊ ባንክ ሲባልም ቢሆን የአገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ እንጅ በሂደት ሲቀየር፣ ሲዋጥ፣ ሲያንሰራራ በኖሩት ቋንቋን መሰረት ያደረጉ ማንነቶች ላይ የተመሰረተ አይደለም፡፡

ከማርክሲስቱ ትርጉም ይልቅ የምዕራባዊያን ትርጓሜ ‹‹ብሄር›› የተወናበደ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል፡፡ ብሄር (አገር) በእንግሊዘኛው (በምዕራባዊያኑ አስተሳሰብም) ‹‹Nation›› በሚለው ቃል ይገለጻል፡፡ ‹‹Nationality›› የሚለው ደግሞ አንድ ግለሰብ ከአገሩ ጋር ያለው ግንኙነት የሚገለጽበት ነው፡፡ ነዋሪ፣ ተወላጅ፣ ዜጋ በሚለው ልንወክለው እንችላለን፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥም ቢሆን በፓስፖርትና በመሳሰሉት ‹‹Nationality›› ቋንቋ ሳይገድበው የሚገልጸው ዜግነትን ነው፡፡ ለፖለቲካው ዘርፍ ደግሞ ‹‹ከትልልቆቹ ብሄሮች ያነሱ›› የሚሏቸውን ማንነቶች ለመግለጽ ይውላል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ብሄር የሚባለው ‹‹Nation›› (አገርን) ሳይሆን ‹‹ethnicity›› የሚለውን ‹‹ማንነት›› እንዲወክል ተደርጓል፡፡ ‹‹ethnicity›› ደግሞ በወጉ ይተርጎም ከተባለ ከጎሳ ያለፈ ቃል ሊገኝለት አይችልም፡፡

ህዝብ ማለት ደግሞ በአንድ አገር ውስጥ የሚኖር እያንዳንዱ ዜጋ በድምር ሲገለጽ ነው፡፡ ኢህአዴግ ከህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴን ተወጣጥቶ  የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ብሎ ሲጠራ የሚያወራው ስለ ኢትዮጵያ ህዝቦች ነው፡፡ እንደ ፖለቲካ ትርጉማቸው ቢሆን ኖሮ ፓርቲው ‹‹የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር›› ነበር መባል የነበረበት፡፡ ይህ ሆኖ እያለ ግን ብሄር ማለት እንደ ኦሮሞ፣አማራ፣ ትግሬ፣ አፋር ያሉትን ህዝቦች እንደሆነ ይገለጻል፡፡ ብሄረሰቦች ደግሞ ከእነዚህ ያነሰ ቁጥር ያላቸው እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡ ህዝቦች ማለት ደግሞ ከዚህ ያነሱ ብዛትም ሆነ ሌሎች የማንነት መግለጫ ያላቸው እንደሆኑ ይነግሩናል፡፡ በተለያዩ ወቅቶች የወቅቱ የኢህአዴግ መሪዎች ህዝብን ሲቀሰቅሱ ‹‹የኢትዮጵያ ህዝብ›› የሚል መጠቀማቸው የተለመደ ነው፡፡ በሌላ ጊዜ ደግሞ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ይሉናል፡፡ ይህ የሚያሳየው መሰረታቸውን ካደረጉበት የስታሊኑ ትርጉም ጋር እንኳ አብረው መሄድ አለመቻላቸውን ነው፡፡ ይህ ተቃርኖ የሚመነጨው ብሄር ከሂደቱም ይልቅ ፖለቲካ ፈጠራው ማመዘኑ ነው፡፡ በአገራችን ደግሞ ከሁለቱም ትርጉሞች ሳይሆን ጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ላይ ማተኮሩ ተቃርኖውን ውስብስብ አድርጎታል፡፡

The post ብሄር እንዴት ተፈጠረ? appeared first on Zehabesha Amharic.

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከመጪው ምርጫ በኃላ የአዲስ ካቢኔ ምስረታ በተመለከተ እስማኤል አሊ ሲሮ እና ሱዩም አወል ያቀዱት እቅድ ተጋለጠ

0
0

(አፋር ክልልን ፍልሥሥ ብሎ የሚመራው ኢስማኤል አሊስሮ ይህ ነው)

(አፋር ክልልን ፍልሥሥ ብሎ የሚመራው ኢስማኤል አሊስሮ ይህ ነው)


አኩ ኢብን ከአፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው:-
 ሁላችንም እንደምናውቀው እስማዕል አሊ ሲሮ እና ሱዩም አወል ህወሀትን በመወከል ላለፉት 20 አመታት በአፋር ህዝብ ላይ አስከፊ የሆነ ግፍ እና ግዲያ፣ እንዲሁም ህዝብን በማፈናቀል በክልሉ ጎሰኝነትና ህዝብን በዞንና በወረደ ጎራ በመለየት ህዝብን እርስ በእርስ እንዲጋጭ እያደረጉ፣ ሙስና እና ዝርፊያን በማስፋፋት ክልሉን ወደ አስከፊ ደረጃ እየወሰዱት ይገኛሉ። እነዚህ ባለስልጣናት የራሳቸውን ስልጣን ላለማጣት የአፋርን ህዝብ ሊወጡት ወደማይችሉበት አዘቅት ውስጥ እያስገቡት ይገኛሉ። በአፋር ክልል ከቀበሌ እሰከ ክልል ያሉት ባለስልጣናት አብዛኛቸው ፊደል ያልቆጠሩ ማሃይሞችና በራሳቸው የማይተማመኑ የህወሀት ሹመኞች ሲሆኑ በህወሀት በተሰጣቸው የከፋፍለህ ግዛው መሰረት በአፋር ህዝብ ውስጥ አለመግባባት እንዲያስፋፉ በህወሀት የተሰጠቸው መርህ እየተገበሩ መምጣታቸው ብቻ ሳይሆን አሁንም የአፋርን ህዝብ ለማጥፋት አዳድስ ሴራዎችን በማሴር እያስተገበሩ ይገኛሉ። እስማኤል ሲሮና ሱዩም እንደዚህ ሲያድረጉ ምንድነው ጥቅማቸው? በመጀመሪያ እስማኤልና ሱዩም አወል ወያኔ ከ 30 ዓመታት በፊት ያቀደውን የትግራይ ሪፖብሊክ ምሰረታን ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህንን ረጂም ስትራቴጂ አንድ አካል የሆነውን አፋርን ወደ አዲስቷ የትግራይ ሪፖብሊክ ለማካለል ካላቸው እቅድና ፈላጎት አንፃር እነዚህ ባለስልጣኖች በስልጣንና በጥቅም በመደለል በአፋር ህዝብ አናት ላይ በግዴታ የተሾሙ ካድሬዎች ናቸው ። ጎሰኝነትን በማስፋፋት አፋርን እያከፋፈሉ እንዲገዙዋቸው በ1985 እ.ኤ.አ በህወሀት የተሰጣቸውን እቅድ እነሆ ዛሬ በጣም አስከፊ ደረጃ ላይ አድርሰውት ይገኛሉ። አሁንም ቢሆን የተማሩ ወጣቶች ወደ አመለካከታቸው እያስገቡ ወጣት ምሁራን እርስ በእርስ እንዳይተማመኑ እና እንዳይስማሙ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ለምሳሌ፣ አሊ ሁሴንና አምባሳደር ሀሳን ዓብዱልቃዲር፣ ጣሃ አህመድና አ/ር ሀሳን አብዱልቃዲር፣ አ/ር ሀሰንና መሀመድ ኡስማን፣ አህመድ ሱልጣንና ሀሰን አብዱልቃዲር፣አወል ወግሪስና መሀመድ ኡስማን፣ መሀመድ በልኮዓ እና ሌሎችም እነዚህ ምሁራን የሚባሉትን እርስ በእርስ እንዲጋጩ የተለያዩ ዜዴዎች እየፈጠሩ ይገኛሉ። እንዲሁም እነዚህ ምሁራን ወጣቶች የስልጣን ሱስ እንዲይዛቸውና እርስ በእርስ በጎሳና በአከባቢ ጎራ በመለየት እንዲጣሉ ፣እንዲከፋፈሉና አንድነት እንዳይኖራቸው ተደረገዋል። እስማዕል ዓሊ ሲሮና ሱዩም የአፋርን አንድነት ለመበታተን የሚጠቀሙበትን ጎሳኝነትን እነዚህ ምሁራን ወጣቶች መረዳት ነበረባቸው ለምሳሌ በመሀመድ ኡስማንና አወል ወግሪስ ማሃል የነበረው አለመግባባት መነሻው ፈጣሪዎች እኚህ ባለስልጣናት ናቸው። አሁንም በጣሃ አህመድና አ/ር ሀሰን ማሃል ያለው አለመግባባት ፈጣሪዎቹ እነርሱ ናቸው። እስማኤል ሲሮና ሱዩም ማለቴ ነው! በእቅዳቸው መሰረት እነዚህ ምሁራን ወጣቶች በተለያዩ መንገዶች አርስ በእርሳቸው እየተወቃቀሱ ይገኛሉ።

ይህ ደግሞ ለወደፊት ለአፋር ከልል ( ህዝብ ) በጣም አሰቸጋሪ ከመሆኑም በላይ ህወሀቶችና እነዚህ ሁለት የወያነ ካድሬዎች ለስልጣናቸው ዕድሜ መራዘሚያ የሚጠቀሙበትን የማከፋፈል እና የመጋጨት ልምዳቸው ሰለሆነ ወጣቶቹ ቆም ብለው ለአፋር ህዝብ እንዲያስቡ እጠይቃለሁ። በነገራችን ላይ በዘንደሮው ምርጫ አቶ እስማእል ሲሮ ለክልል ካቢኔ አይወዳደሩም። ምክንያቱም አቶ ሲሮ ለፈደራል ፓርላማ እንዲወዳሩ ሰለተደረገ አሁን የክልል ፕረዜደንት መሆን ያለበት ማን እንደሆነ ራሱ ወጣቶችን እልክ ውስጥ ከከተቱት ጉዳዩች አንድና ዋነኛው ነጥብ ነው ። ልብ በሉ ባለፉት አራት ወራት አምሳደር ሀሰንን የክልል ፕረዜዳንት እናድረጋሀለን እያሉ ለጣሃ አህመድ ደግሞ በክልሉ ሁለት ትላልቅ የስልጣን ቦታዎች በመስጠት ወጣቶችን መለያየት ጀመሩ። እዚህ ላይ ሁል ጊዜ እስማእልና ሱዩም ተንኮላቸውን ለማሳካት ሲሉ ወይም ወጣቶችን ጎራ ለማስለየት ሲሉ ሁለቱንም እንደተጣሉ በማስመሰል የሱዩም ቡዱንና የእስማእል ቡዱን እያደራጁ የወጣቶችን አንደነት ይሰብራሉ። ለምሳሌ፥ በቅርብ ጊዜ ሱዩም ከእስማእል ጋር እንደተጣላ አስመስሎ የራሱን ቡዱን መስርቶ ነበረ፣ እስማእልም እንደዚሁ።

አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃዲር በሴነጋል የአፍሪካ አምባሳደሮች ማህበር ሊቀመንበር ሲሆን የአፋር ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የማሃል ኮሚቴ አባል ሰለሆነ አንድንድ ግዜ ሰብሰባ ሲኖር ይመጣ ነበረ። አምሳደሩ የተማረና የፖለቲካ ብቃት ስላለው ከወጣቶቹ ጋር እንዳይስማማ ከሁለቱም ቡዱኖች ወደ አንድ ማስገባት ነበረባቸው። ሰለዚህ ስዩም አወል ወደራሱ ቡዱን በማስገባት ከቀሪዎቹ ወጣቶች ጋር እልክ ውስጥ ካስገቡት በኃላ በምርጫ ለክልል ካቢኔ እንዳይወዳደር አደረጉት። ሌላው ደግሞ በእስማእል የሚመራው ቡዱን ሲሆን አንዱና ዋነኛው ጣሃ አህመድ ነው። ጣሃ አህመድም ለጊዜውም ብሆን በክልሉ ከፍተኛ የስልጣን ቦታዎችን በማስጨበጥ ከሌሎች ምሁራን ጋር እንዳይስማማ በማድረግ ዞሮ ዞሮ የምሁራን ወጣቶችን አንድነት ማደፈረስ ከጅምሩ ለሱዩምና ለእስማእል ከህወሀት የተሰጣቸው ተልዕኮ ሰለሆነ እየገፉበት ይገኛሉ፣ አሁንስ እስማእል ከሄደ የአፋር ክልል አዲስ ርዕሰ መስተዳደር የሚሆነው ማን ይመስላቹሃል? አወል ዓርባ ነው ? ጣሃ ነው ? መ/ድ አንበጣ ነው ? ሱዩም ነው? ማሀመድ ኡስማን ነው ? አይደለም አይደለም! ማን ነው ? ቢታምኑም ባታምኑም የአሁኑ የጤና ቢሮ ኃላፊ የሆነው አሊ ሁሴን ወዒሳና አሊ መ/ድ ጋርቦኢስ የክልሉ ፕሬዜዳንት፣ ምክትል ፕሬዜዳንትና የፓርቲው ለቀመንበር ይሆናሉ። እስማእልና ሱዩም አ/ ር ሀሰንን ና ጣሃ አህመድን የሚያጣላሉ ሆነዋል። በመጨረሻም ጣሃም ሆነ አምባሳደሩ የተከፈላቸው ውለታ ወይም የወጣላቸው ዕጣ አንድ አይይነት ሆነዋል። ባለፈው ፈብርዋሪ 12/ ከምሽቱ 12:00 am አስከ 11:00 pm ድረስ እስማእል ሲሮና ሱዩም አወል በእስማእል መኖሪያ ቤት በአምባሳደር ሀሰን ላይ የተጫወቱትን ድራማ ላይ እየሳቁ አሁንም ጣሃ አህመድን ከስልጣኑ ሊያባረሩት የሚችሉበትን መንግድ መንደፋቸው ተረጋገጠ።

ጣሃ አህመድ እንዴት እንደሚያባርሩ ካማየታችን በፊት አሊ ሁሴንና አሊ ጋርቦእስ ለምን ተመረጡ ?

1/ በሙስና በሰበሰቡት ሃብትና ህዝብ ላይ ላደረሱት ወንጀሎች ላለመጠየቅ መከላክያ እንዲሆኑላቸው ለእነሱ ካላቸው እምነት አንፃር፣ ለምሳሌ እስማእል በዱብቲ በፈደራሎች እጅ ባስገደላቸው ሰዎች መጠየቁ ሰለማይቀርለት ካለው ፊራቻ በተነሳ አሊ ሁሴን ወዒሳ የክልል መሪ ቢሆን ሊከላከልልኝ ይችላል የሚል እምነት አላቸው።

2/ ባለስልጣናትን በጎሳኝነትና በአከባቢ በመከፋፈል ከላቸው ፖሊሲ አንድ አካል በመሆኑ!

3 / የህወሀት ምስጢር ሳይጋለጥ ሊረከቡት፣ ሊጠብቁትና ሊትገበሩት ሰለሚቺሉ ( የሚችሉት እነርሱ ብቻ ሰለሆነ)፣

4/ የለመዱትን ሙስና እና ዝርፊያ ላለማስቆም ከእነሱ ሌላ ምረጫ ባለመኖሩ፣

5/በፌደራል ላይ ላሉት አንዳንድ የወያኔ ሚኒስቴሮች ለብዙ አመታት ጉቦ ሲሰጡት በነበሩት ገንዘብ መሰረት ከነዚህ አንዳንድ ሚኒስቲሮች ባላቸው ድጋፍ ምክንያት፣

6/ በአፋር ህዝብ ውስጥ ጎሳኝነትና እንዲሁም በአፋር ከልል ህዝብን በማፈናቀል እየተሰራ ያለው የመንግስት እርሻዎች እንዲቀጥሉ ከሁለት አሊዎች ሌላ አማራጭ ባለመኖሩ። የትምህርት ቢሮ ኃላፊ እና የአብዴፓ ፓርቲ ለቀመንበር የሆነው ጣሃ አህመድን ለማባረር ያቀዱት እቅዶች… ጣሃ አህመድ ከፓርቲ ሊቀመንበረነት አዲስ የክልል መንግስት ከማቋቋሙ በፊት እንዲወርድ ታቀደዋል።

ጣሃን ለማባረር የታቀዱት እቅዶች ከዚህ በታች እናያለን።

በመጀመሪያ የዚህ ስተራቴጂ ዋናው መነሻ የሆነው ከተቻለ እስማእል ዳግም ስልጣን ላይ እንዲቆይ የሚደረግና በአለቃ ፀጋይና በአቦይ ፀሀዬ የሚደገፍ ሴራ ነው። እንዴት? እሰማእል ከክልል ፕረዘደንትነት የሚነሳ ከሆነ ለሱዩምና ለራሱ ለእስማእል ብቻ ሳይሆን ለአለቃ ፀጋይና ለአቦይ ፀሐዬም ጭምር ጥሩ አይደለም። ሰለዚህ ከምረጫ ውሳኔ በፊት የፓርቲው አመታዊ ጉባኤ በመጥራት በሱዩም እና በአወል ሚዔ፣ አወል ዓርባና ሌሎች ካቢነዎች መሃል አለመግባባት የተፈጠረ በማሰመሰል የውሸት አለመግባባት ማስነሳት ፣ ቀደም ሲል በአ/ር ሀሳን እና በጣሃ መሃል የለኮስትን እሳት ማረገብና ጣሃን መሸኘት፣ በአጣቃላይ ከእስማእል በሰተቀር ክልልን ማሰተዳደር የሚችል አካል እንደሌለ ማሰመሰል። ሰላም እና መግባባት ብቻ በእስማእል እጅ እንዳለ፣ እስማእል ከሄደ ክልል ይፈረሳል የሚል ኘሮፓጋንዳ ማናፈስ፣ በአቶ እስማእልና በአቶ ሱዩም ለራሳቸው ስልጣን ሲሉ የአፋር ክልልን ለማዳከም ያቀዱት እቅዶች ይህን ይመስላሉ::

The post የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከመጪው ምርጫ በኃላ የአዲስ ካቢኔ ምስረታ በተመለከተ እስማኤል አሊ ሲሮ እና ሱዩም አወል ያቀዱት እቅድ ተጋለጠ appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: 6 ነጥቦች ስለ ማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን (Vaginal Candidiasis)

0
0

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

Dr Honiletየማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን እጅግ በጣም የተለመደ እና ከ4 ሴቶች በ3ቱ ላይ በዕድሜ ዘመናቸው ቢያንስ አንዴ የሚከሰት የሕመም ዓይነት ነው፡፡
የማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን ከአባለዘር በሽታዎች ውስጥ የማይመደብ ሲሆን ቀላል በሚባል ሕክምና ሊድን የሚችል ነው፡፡ በዓመት ውስጥ ከ4 እና ከዛ በላይ የሚከሰት ከሆነ ግን ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ሕክምና ያስፈልገዋል፡፡

የማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን የሚከሰተው ካንዲዲያ (Candidia) በሚባል ፈንገስ ምክንያት ነው፡፡
በሴቶች ማህፀን በተፈጥሮ የሚገኙ የፈንገስ እና የባክቴሪያ ሕዋሳት አሉ፡፡ ሁለቱም በተመጣጠነ ሁኔታ የሚገኙ ሲሆን ባክቴሪያው አሲድን በማመንጨት የፈንገስ መብዛትን ይከላከላል፡፡ ማንኛውም ዓይነት ይህን ተፈጥሮአዊ መመጣጠን የሚያዛባ ሁኔታ ለፈንገስ መባዛት (yeast overgrowth) ስለሚዳርግ የማህፀን ማሳከክ፣ማቃጠል እና ሌሎች ምልክቶችን ያስከትላል፡፡

6. የማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን በምን ምክንያት ይከሰታል?
– ፀረ ባክቴሪያ(Antibiotic)መውሰድ በማህፀን ውስጥ የሚገኘውን የባክቴሪያ መጠን ስለሚቀንስ ለማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን ምክንያት ይሆናል
– እርግዝና
– በሕክምና ያልተስተካከለ የስኳር ሕመም ካለብን
– በሽታ የመከላከል አቅማችን የተዳከመ ከሆነ
– በማንኛውም ዓይነት ሁኔታ የማህፀን ውስጥ ባክቴሪያ መጠን ሲቀንስ ለማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን ሊያጋልጥ ይችላል፡፡

5. ለማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን ተጋላጭነት የሚጨምሩ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
– ፀረባክቴሪያ በመውሰድ ላይ ያለች ሴት
– የኤስትሮጂን ሆርሞን መጠን መጨመር፣ እርጉዝ (ነፍሰጡር) ሴቶች እና የኤስትሮጂን መጠኑ ከፍተኛ የሆነ የወሊድ መቆጣጠሪያ የሚወስዱ ሴቶች
– በሕክምና ክትትል ያልተስተካከለ የስኳር ሕመም ያላቸው ሴቶች
– በሽታን የመከላከል አቅማቸው የተዳከሙ ሴቶች
– ግብረስጋ ግንኙነት፡- የማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን ከአባለዘር በሽታ ባይመደብም በተለያዩ የግብረስጋ ግንኙነት አይነቶች ምክንያት ግን ሊተላልፍ ይችላል፡፡

4. የማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን ምልክቶች ምንድን ናቸው?
– በማህፀን አካባቢ ማሳከክ
– የውሃሽንት በማስወጣትና በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ የማቃጠል ስሜት
– የማህፀን አካባቢ መቅላትና ማበጥ
– የማህፀን ሕመም
– ነጭ፣ወፍራም እና ሽታ አልባ የማህፀን ፈሳሽ መኖር ናቸው፡፡

3. ከባድ የሆነ የማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን መኖሩን የሚያመለክቱ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
– ከፍተኛ የሆነ የማህፀን ማሳከክ፣ማበጥ እና መቅላት መኖር
– በዓመት ውስጥ 4 ጊዜ እና ከዛ በላይ የሚከሰት የማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን
– ነፍሰጡር ሴት ላይ የሚከሰት የማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን
– በሕክምና ያልተስተካከለ የስኳር ሕመም መኖር
– ከተለመደው የፈንገስ ዓይነት በተለዬ የፈንገስ ዓይነቶች የሚከሰት ኢንፌክሽን
– በሕክምና ወይንም በሕመም ምክንያት የተዳከመ በሽታን የመከላከል አቅም መኖር ናቸው፡፡

2. የማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽንን እንዴት መከላከል ይቻላል?
– የማያጠብቁ (ዘና የሚያደርጉ) ሱሪዎችን መልበስ
– ከጥጥ የተሠሩ የውስጥ ሱሪዎችን መልበስ
– ዕርጥበት ያላቸውን የውስጥ ሱሪዎች ለብሰው አለመቆየት ለምሳሌ የዋና ልብስ
– በጣም በሚሞቅ ውሃ አለመታጠብ ወይንም አለመዘፍዘፍ
– የግል ንጽህናን በሚገባ መጠበቅ

1. ሐኪምዎን ማማከር ያለብዎት መቼ ነው?
– በሕመሙ ሲጠቁ የመጀመሪያዎ ከሆነ
– በማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን መያዝዎን እርግጠኛ መሆን ካልቻሉ
– የሕመሙ ምልክቶች ሐኪምዎ በሚሰጥዎት መድኃኒት ማይጠፋ ከሆነ
– ሌሎች ተጨማሪ ምልክቶችን ካስተዋሉ ናቸው፡፡
የሕመሙን ምልክቶች እንዳስተዋሉ ወደሕክምና ቦታ በመሄድ ለሕክምና የሚሆን መድኃኒት በመውሰድና በሚገባ በመጠቀም ከሕመሙ ነፃ መሆን ይችላሉ፡፡
ጤና ይስጥልኝ

The post Health: 6 ነጥቦች ስለ ማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን (Vaginal Candidiasis) appeared first on Zehabesha Amharic.


የአውሮፓ ሕብረት ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ተወያየ • ‹‹ኢህአዴግ እያታለላችሁ ነው፡፡ እናንተም ለመታለል ዝግጁ ሆናችኋል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

0
0

Hiber Radio Interview with Eng Yilkal Getnet
(ነገረ ኢትዮጵያ) የአውሮፓ ህብረት ዛሬ መጋቢት 1/2007 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው ጽ/ቤቱ ባደረገው ስብሰባ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በተጋባዥ እንግዳነት ተገኝተው ከህብረቱ ተወካዮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ኤምባሲ ያላቸው 20 ያህል የህብረቱ አባል አገራት በተገኙበት ስብሰባ ላይ አብዛኛዎቹ በአምባሳደሮቻቸው እንዲሁም ቀሪዎቹ በምክትል አምባሳደሮቻቸው ተወክለው የተገኙ ሲሆን ተወካዮቹ ወቅታዊ የምርጫ ሂደት እንቅስቃሴና የሰማያዊን የምርጫ እንቅስቃሴ፣ በምርጫው ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች፣ የፓርቲው አማራጭ ፖሊሲዎች፣ የድርጅቱን ጥንካሬ፣ የአንድነት አባላት ወደሰማያዊ መምጣታቸው ለትግሉ የሚኖረው ትርጉምና ሌሎችም ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለኢ/ር ይልቃል ጌትነት ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው ሰማያዊ ፓርቲ ከ200 በላይ ዕጩዎች በህገ ወጥ መንገድ እንደተሰረዙበት፣ የፓርቲው የቅስቀሳ መልዕክቶቹ ከ6 ጊዜ በላይ በሚዲያ እንዳይተላለፍ መከልከሉን፣ የተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ድብደባ፣ እስራትና ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ጠቅሰው በምርጫ ሂደት ኢህአዴግ አፋኝነቱን አጠናክሮ መቀጠሉን ገለጸዋል፡፡

በሌላ በኩል የአንድነት አባላት ሰማያዊን መቀላቀላቸው ትግሉን እንደሚያጠናክረው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአንድነትና መኢአድ ላይ የተፈፀመው ህገ ወጥ ተግባር መሆኑን እንዲሁም ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን በኃይል እያጠፋ ‹‹ከእኔ ውጭ አማራጭ የለም›› የሚል አቋሙን ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ማሳየት እንደሚፈልግ ለህብረቱ ተወካዮች አስረድተዋል፡፡
‹‹የአውሮፓ ህብረት ችግር የኢትዮጵያን ችግር በአውሮፓውያን ተቋማትና የስነ ልቦና ልክ ማየቱ ነው›› ያሉት ኢ/ር ይልቃል የአውሮፓ ህብረት ‹‹የተቃዋሚዎች አማራጭ ፖሊሲያቸው ምንድን ነው?›› በሚል የሚያነሱትን ተደጋጋሚ ጥያቄ አስታውሰው መደረጀትና መናገር ያልቻለውን የኢትዮጵያን ህዝብ በአውሮፓ ተቋም አይን አይቶ እንዲህ አይነት ጥያቄዎችን ማንሳቱ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ብዙም እርባና እንደሌለው ገልጸዋል፡፡ ‹‹በእኛ አገር የፖለሲ አማራጭ ለማቅረብ አይቻልም፡፡ ሚዲያው በገዥው ፓርቲ የተያዘና የተቃዋሚዎችን ሀሳብ የማያስተናግድ ዝግ ሆኗል፡፡ እናንተ እንደምትገምቱት የፖሊሲ አማራጭ ለማቅረብ አመች ሁኔታዎች ቢኖሩ ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ የተሻለ ምሁርራንና ሀሳብ ስላላቸው ዝርዝር ፖሊሲያቸውን ለማቅረብ አይቸገሩም ነበር፡፡›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ኢህአዴግ ‹‹ተቃዋሚዎች የተበታተኑና የተዳከሙ በመሆናቸው ለቀጠናው ሰላም አማራጩ እኔ ብቻ ነኝ›› ብሎ የአውሮፓ ህብረትን እንደሚያታልል የገለጹት ኢ/ር ይልቃል ‹‹ኢትዮጵያውያን ካላቸው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ማየት ስላልቻላችሁ ኢህአዴግ እያታለላችሁ ነው፡፡ እናንተም ለመታለል ዝግጁ ሆናችኋል፡፡›› ሲሉ የአውሮፓ ህብረትን ወቅሰዋል፡፡

The post የአውሮፓ ሕብረት ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ተወያየ • ‹‹ኢህአዴግ እያታለላችሁ ነው፡፡ እናንተም ለመታለል ዝግጁ ሆናችኋል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተመራጩ ሰውነት ቢሻው ወይስ ማሪያኖ ባሬቶ?

0
0

ታምራት አበራ

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከ1982ዓ.ም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለ2013ቱ አፍሪካ ዋንጫ ስታልፍ መላው ኢትዮጵያዊ ደስታውን በየአደባባዩ ሲገልጽ ላስተዋለ «ከበስተጀርባ ማን አለ?» ሲባል ሰውነት ቢሻውን የሚዘነጋ የለም፡፡የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለኚህ ባለውለታ ለሰሩት ሥራ ምስጋና በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል አዘጋጅቶ ልዩ ሽልማት ማበርከቱም ይህንኑ ያጠናክራል፡፡
sewenet
እ.ኤ.አ ጥቅምት 2011 ከቀድሞው ቤልጂየማዊው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቶም ሴንትፊልት ተረክበው ብሄራዊ ቡድኑን ለሁለት ዓመት ያህል ያሰለጠኑት የ62 ዓመቱ ሰውነት ቢሻው በሁለት ዓመት የብሄራዊ ቡድን ቆይታቸው 32 ዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን አድርገዋል።ከዚህም በ11 ሲያሸንፉ፣ በ12 ተሸንፈው እንዲሁም በ9 ጨዋታ አቻ ወጥተው ዋልያዎቹን ለ2013ቱ የደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ በማሰለፍ የሰሩት ውለታ መቼም አይዘነጋም፡፡በአብዛኛው የኢትዮጵያ እግር ኳስ አፍቃሪያን ዘንድ ዋልያዎቹ ከ31 ዓመት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፉ፣ በ1962 የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን የሆነው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሌላ ታሪክ ተተኪ ትውልድ አገኘ ብሎ ያልጓጓ አልነበረም፡፡ ሆኖም ግን ያልተጠበቀው ሆነና ተስፋ የተጣለባቸው ዋልያዎቹ ሁሉንም የምድብ ጨዋታዎች ተሸንፈው ከመጀመሪያው ዙር ተባረሩ፡፡

እጅግ አጓጊ በሆነና ምርጥ ሁለተኛ በሚል ናይጄሪያን ተከትለው ወደ 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወደ ደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድናቸውን ይዘው የከተሙት የ62 ዓመቱ ሰውነት ቢሻው፣ በመጀመሪያው ዙር ከምድቡ ማለፍ ተስኗቸው ቢባረሩም በየጨዋታው ላይ ያሳዩት የጨዋታ ፍሰት ከየሀገራቱ ተውጣጥተው ደቡብ አፍሪካ የከተሙ የስፖርት አፍቃሪያንን በማስገረም ‹‹አዲሱ ብራዚል›› የሚል ስያሜ እስከ ማግኘት መድረሳቸው አይዘነጋም፡፡በምድብ ድልድሉ ከቡርኪናፋሶና ናይጄሪያ ጋር የተደለደለችው ኢትዮጵያ በሁሉም ጨዋታ ብትሸነፍም በፍጻሜው ጨዋታ ቡርኪናፋሶና ናይጄሪያ መገናኘታቸውን ያየ ሁሉ ምድቡ የሞት ምድብ መሆኑን ለመረዳት ቀላል ነበር፡፡

አሰልጣኝ ሰውነት በተለይ ደግሞ ዋልያዎቹ በደቡብ አፍሪካ አዘጋጅነት ለተካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፉ በጥሎ ማለፍ ጨዋታ ከዘወትር ተቀናቃኛችን ሱዳን ጋር በደርሶ መልስ ጨዋታ 5ለ5 በመውጣት ከሜዳ ውጪ ባገባ በሚለው ህግ ታግዘው ወደ ምድብ ድልድሉ መግባታቸው ይታወሳል፡፡ የዋልያዎቹ ወደ አፍሪካ ዋንጫ መመለስ ለረጅም ዓመታት ተቀዛቅዞ ለነበረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ የማነቃቂያ ደወል የሆኑት ሰውነት ቢሻው መላ የኢትዮጵያ ህዝብ ላለፉት 31 ዓመታት የበይ ተመልካች ከሆነበት የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ እንዲሆን ያበቁ አሰልጣኝ ናቸው፡፡

mariano bareto ethiopia coachበሌላ መልኩ ሰውነት ከሰሯቸው ጥሩ ሥራዎች በተጨማሪ ደካማ ጎናቸውን ስንመለከት ምንም እንኳን ከሌሎች አሰልጣኞች በተሻለ መልካም የሚባል ጨዋታን የማሸነፍ ሪከርድ ቢኖራቸውም ከሜዳቸው ውጪ ባደረጓቸው አስራ ስድስት ጨዋታዎች 1 ብቻ ሲያሸንፉ 6 አቻ እንዲሁም በ9 ጨዋታ ሽንፈትን መቅመሳቸው ከሜዳቸው ውጪ ያላቸውን ክፍተት ጠቋሚ ሆኗል።በብሄራዊ ቡድን ውስጥ የሚጠቅሟቸው ተጫዋቾች በእድሜ የገፉ መሆን እና በውጭ ሀገር ክለብ ውስጥ የሚጫወቱ ኢትዮጵያዊ ተጫዋቾች ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ እድል አለመስጠታቸው ሌላው እንደ ክፍተት የሚታይ ነው፡፡

ከሰውነት ቢሻው ሥራ መልቀቅ በኋላ በተደረገው ውድድር ከሰርቢያዊው ጎራን ስቴቫኖቪች ተሽለው ዋልያዎቹን የተቀበሉት በትውልድ ህንዳዊ በዜግነት ፖርቹጋላዊው የ57 ዓመቱ ማሪያኖ ባሬቶ ከሚያዝያ 2014 ጀምሮ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ኮንትራት በወር 18ሺ ዶላር እየተከፈላቸው ብሄራዊ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛሉ፡፡ባሬቶ ሚያዝያ ወር ላይ ሥራቸውን ሲረከቡ ከገቡት ቃል ውስጥ ዋልያዎቹን ለ2015ቱ ሞሮኮ ዋንጫ ማሰለፍና እድሜያቸው የገፉ ተጫዋቾችን በወጣት መተካት ዋነኛ ዓላማቸው እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ፖርቹጋላዊው ማሪያኖ ባሬቶ የአሰልጣኝነት ታሪካቸው እ.አ.አ ከ2003 የሚጀምር ሲሆን ዳይናሞ ሞስኮን ጨምሮ ስድስት ክለቦችን እንዲሁም ለ9 ወር ያህል የጋናን ብሄራዊ ቡድንምም አሰልጥነዋል። ይህም ይበልጥ ተመራጭ አድርጓቸዋል፡፡በወር 378 ሺ ብር ወደ ካዝናቸው የሚያስገቡት ባሬቶ ዋልያዎቹን ከተቀበሉ ሚያዝያ 2014 ጀምሮ አስር ጨዋታዎችን አድርገዋል።በዚህም 1 ጨዋታ አሸንፈው በ8ቱ ተሸንፈው እንዲሁም በአንድ ጨዋታ አቻ ወጥተው በንጽጽር 80በመቶውን ተሸንፈው ቃል ከገቡትም የአፍሪካ ዋንጫ ውጪ መሆናቸው አሰልጣኙ ይህ ነው የሚባል ሥራ አለመስራታቸውን ይጠቁማል፡፡ ባሬቶ ዋልያዎቹ ለረጅም ጊዜ ያላስደፈሩትን የሱዳን ተፎካካሪነት በቅርቡ በድሬዳዋ ስታድየም 2ለ1 እንዲሁም ባለፈው ዓርብ ለመልስ ጨዋታ ወደ ሱዳን አቅንተው 2ለ0 መሸነፋቸው በሱዳን ብልጫ እንዲወሰድብን ምክንያት ሆነዋል፡፡

በተቃራኒው ከባሬቶ ጥሩ ጎኖች ውስጥ በውጭ ሀገር ክለብ የሚጫወቱ ኢትዮጵያዊ ተጫዋቾችን ለብሄራዊ ቡድን በመጥራት ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ ማድረጋቸውና ለወጣት ተጫዋቾች ዕድል መስጠታቸው ይጠቀሳሉ፡፡ ባሬቶ በትውልድ ስዊድናዊ በዜግነት ኢትዮጵያዊ የሆኑትን ዋሊድ አታንና የሱፍ ሳላን እንዲሁም አሚን ኦስካርን ከኖርዌይ ለብሄራዊ ቡድኑ መጥራታቸው ተጫዋቾቹ በአውሮፓ ያካበቱትን ልምድ እንዲያካፍሉ ዕድሉን ቢያመቻቹም ይህ ነው የሚባል ውጤት ማስመዝገብ አልቻሉም፡፡

ሌላው ማሪያኖ ባሬቶ በተተኪ ትውልድ ላይ የሰሩት ሥራ ይበል የሚያስብል ነው፡፡ ባሬቶ ብሄራዊ ቡድኑን ሲረከቡ ቃል ከገቡት ውስጥ አዳዲስ ወጣት ተጫዋቾችን በቡድኑ ውስጥ ታያላችሁ ያሉት ይገኝበታል፡፡ እውነትም ባሪያቶ እንደተናገሩት ለወጣት ተጫዋቾች ዕድል በመስጠት ናትናኤል ዘለቀን የመሰለ የማይታክት ተጫዋች ማፍራት መቻላቸው እንደ ጥሩ ጎን ይወሰዳል፡፡

በአጠቃላይ «ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተመራጩ በዝቅተኛ ደመወዝ ብሄራዊ ቡድኑን ለአፍሪካ ዋንጫ ያበቁት ሰውነት ቢሻው ወይስ በወር 378ሺ ብር የሚከፈላቸው ማሪያኖ ባሬቶ?» የሚለው የሁሉንም እግር ኳስ ወዳድ ህዝብ ምላሽ የሚጠብቅ ጥያቄ ነው፡፡እስከ ዛው ግን ባሬቶ በሽንፈት የሚቀጥሉ ይሆን? ወይስ ተጨማሪ ጊዜ ቢሰጣቸው(የሰውነት ቢሻውን ያህል ቆይታ ቢኖራቸው) የተሻለ ውጤት ያስመዘግቡ ይሆን? ጊዜ የሚፈታው እንቆቅልሽ፡፡

The post Sport: ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተመራጩ ሰውነት ቢሻው ወይስ ማሪያኖ ባሬቶ? appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: በርናንድ ላጋት የኃይሌን ክብረወሰን ለማሻሻል ብዙ መስራት እንደሚጠበቅበት ተናግሯል

0
0

ከዳንኤል ዘነበ
lagat

የአምስት ጊዜው የቤት ውስጥ ና ከቤት ውጪ የዓለም ሻምፒዮኑ በርናርድ ላጋት በማንቸስተር ከተማ በሚካሄደው የ10ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር አዲስ ክብረወሰን ለማስመዘገብ እንደሚሮጥ አስታውቋል።

ትውልደ ኬንያዊው የአርባ ዓመት አሜሪካዊው ሯጭ ላጋት በቤት ውስጥ ውድድር ከአርባ ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸው አትሌቶች ያስመዘገቡትን ክብረወሰን ለማሻሻል በአውሮፓ ታላቅ በሚባለው የማንቸስተር ከተማ ሩጫ ለመወዳደር እቅዷል። ይህ ክብረወሰን የተያዘው በጀግናው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ሲሆን፣ ሰዓቱም 28 ደቂቃ ከ00 ሰከንድ ነው።

በፍላግ ስታፍና አሪዞና ጠንካራ የሆነ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው ላጋት « ነገሮች ቀላል ላይሆኑ ይችላሉ፤ ይህን ክብረወሰን ለማሻሻል አምስት ኪሎ ሜትርን በአስራ አራት ደቂቃ መሮጥ ይጠበቅብኛል፤ ይህን ፈጣን ሰዓት ማሻሻል ቀላል ባይሆንም የተቻለኝን ጥረት አደርጋለሁ» በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል።
ላጋት እ.ኤ.አ 2007 በተካሄደው የዓለም ሻምፒዮና ላይ 1500ና 5000 ሜትር ከማሸነፉ ባሻገር የዓለም የቤት ውስጥ 3000 ሜትር ሩጫንም ለሦስት ጊዜ አሸንፏል። የ5ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ሁለት ጊዜ ተካፍሎ ጥሩ ተፎካካሪ የነበረው ላጋት በአንድ የግማሽ ማራቶን ውድድር ተካፍሎም 10ኪሎ ሜትሩን በ29ደቂቃ ከ40 ሰከንድ ማገባደድ ችሏል።

በ1500ሜትር የክብረወሰን ባለቤት ከሆነው ከሞሮኳዊው ሂችሃም ኤልግሩዥ ቀጥሎ በርቀቱ ፈጣን ሰዓት ያለው ትውልደ ኬንያዊው ላጋት እንደ ማንቸስተር ዓይነት ባሉት ታላላቅ የጎዳና ላይ ውድድሮች ተሳትፎ አያውቅም።በዚህ የተነሳም ክብረወሰኑን በእርግጠኛነት እንደሚያሻሽለው ለመናገር አልደፈረም። ነገር ግን በዩኒቨርሲቲ ደረጃ እያለ በአስር ኪሎ ሜትር አገር አቋራጭ ውድድር ተሳትፎ ጥሩ የሚባል ሰዓት እንደነበረው አስረድቷል።

ባለፈው ህዳር 40ኛ ዓመቱን ያከበረው የዓለማችን ምርጡ የረጅምና የመካከለኛ ርቀት ሯጭ ላጋት ባለፈው ዓመት በ300 ሜትር የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ላይ ተካፍሎ የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ሆኗል። በአምስት የኦሊምፒክ መድረኮች ላይ በመካፈልም ጥሩ ልምድ በማካበቱ በሚቀጥለው ዓመት በሪዮ ዲጄኔሮ በሚካሄደውና በመጪው ክረምት በቤጂንግ የዓለም ሻምፒዮና በ5000ሜትር ተካፋይ እንደሚሆንም ይጠበቃል።
ላጋት የሦስት ሺ ሜትር የቤት ውስጥ ክብረወሰንን ለሦስተኛ ጊዜ ያሻሻለው ባለፈው ሳምንት በፈረንሳይ ሜዝ ከተማ በተካሄደው ውድድር ላይ ነው።በውድድሩ ያስመዘገበው አዲስ ሰዓትም 7፡37፡71 ነው። ላጋት በኒውዮርክ ሚልሮዝ ጨዋታዎች ላይ ተካፍሎ በኢሞን ኮግላን ተይዞ የነበረውን ከአርባ ዓመት በላይ የማይል ክብረወሰን በ3፡54፡91 ማሻሻል ችሏል።
HAMBURG MARATHON 2014..DUEL OF GIANTS…HAILE GEBRESILASSIE vs MARTIN LEL

ላጋት ባለፉት አስራ ስምንት ቀናት ውስጥ ስድስት ያህል የዕድሜ ክብረወሰኖችን በማሻሻል አስደናቂ ብቃቱን ማሳየት ችሏል። « ማኔጀሬ ስለ ማንቸስተር አስር ኪሎ ሜትር ውድድር ኃይሌገብረስላሴና ቀነኒሳ በቀለን የመሳሰሉ አትሌቶች እንዳሸነፉበት አጫውቶኛል» ያለው ላጋት የእነዚህን ታላላቅ አትሌቶች ፋና መከተል እንዳለበት እምነቱን ገልጿል።

ላጋት ኃይሌ ገብረስላሴን ክብረወሰን ለማሻሻል ጠንካራ ዝግጅት ማድረግ እንዳለበትም አምኗል። « ግማሽ ማራቶንን በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሆኜ ሮጫለሁ፤ አሁንም ጥሩ ዝግጅት ካደረኩኝ የተሻለ እሰራለሁ ብዬ አምናለሁ» በማለት ላጋት አስተያየቱን ሰጥቷል።

The post Sport: በርናንድ ላጋት የኃይሌን ክብረወሰን ለማሻሻል ብዙ መስራት እንደሚጠበቅበት ተናግሯል appeared first on Zehabesha Amharic.

(የሳዑዲ ጉዳይ) …ለተሃድሶ ጀማሪዎች ለጅዳ ቆንሰል ተማጽኖየ –ነብዩ ሲራክ

0
0

saudi
* ፖለቲካውን እንደርስበታለን መብት በማስከበሩ ላይ በርቱ

ሰሞነኛ ወጋችን ፍተሻ ፣ አሰሳ ፣ ማጣራት ሆነና ልብን በሃዘን የሚሰብሩት ጩኸት እንዳይረሳ ሰጋሁ ። ለነገሩ የሳውዲ መገናኛ ብዙሃን በሚለቋቸው መረጃዎች ልክ መረጃ ተለዋውጠናል ባይባልም ፣ ያለፈውን አመትና የቆየውን ሁከት የሚያሳይ የቆየ ተንቀሳቃሽ ምስል እየለጠፉ የቆየነው አዲስ ነው ሳይሉና ሳያሳውቁን መረጃውን የሚለቁ የራሳቸን ሰዎች ተበራክተዋል። በዚህም ፍተሻ አለ የለም ወደሚለው አተካራ እየተዶልን ይመስላል። ተወደደም ተጠላ የሰው ሃገር የሰው ነው ፣ ሳውዲዎች በሃገራቸው ሰማይ ስር እንኳንስ በአደባባይ በተናገሩት ጊዜ ባሻቸው ጊዜ ህገ ወጥ ያሉትን ይዘው የማባረር መብት አላቸው ። አለመቀደም ነው እንጅ ሲላቸው ም የጠራረጉትን ጠራርገው ሲያበቁ ሁሉ ትተው የምህረት አዋጅ ሲሉ እናውቃለን ። ይህ ሲወርድ ሲዋረድ የምናውቀው አሰራራቸው ነው ። የዘንድሮውን ለየት የሚያፈርገው ” የምህረት አዋጅ የሚባል ነገር አይታሰብም “ማለቱ አይደለም ። ይልቁንም ስራቸውን በጣም በተረጋጋ ሁኔታ የመብት ጥሰት እንዳይኖርና ማህበራዊ ገጾች ጥሰቱን እየተቀባበሉ እንዳያወግዟቸው በጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑን ልብ ብለን የግንባር ስጋ ከመሆን ካመለጥን መልካም ነው !

ከሰሞነኛው መረጃ ቅበላ ጎን ለጎን በተለያዪ አላባቢዎች ያሉ ወዳጆቸ ከሚያደርሱኝ መረጃዎች መካከል ሰሞነኛው የአፈሳ ፣ እስራት ፣ ማጣራቱ መረጃ ከአዕምሮየ አላዳፍን ያላቸውን የሚያሙ ግን ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባ ጉዳዮችን ማንሳት ወደድኩ ! ለዚህ የማለዳ ወግ መነሻ የሆነኝ ባሳለፍነው ሳምንት የዲያስፖራ ምክር ቤት የሚሉትን ለማቋቋም ከተሰበሰቡት የድርጅት ሰዎች አጠራርና የህዝብ ውክልና ጉዳይ ነው። ከአንድ አፍቃሬ ህወሃት ወዳጀ ጋር በዚህ ዙሪያ ስናወጋ ” ያን ሰሞን ተሃድሶ አድራጊውን ቆንስል እንዳላመሰገንክ ዛሬ በዲያስፖራው ጉዳይ ነካከህው! ” ነበር … ቀድሞውንም አሁንም በማይረባውና በማንግባባበትን የፖለቲካ ጉዳይ እንደርስበታለን መብት በማስከበሩ ላይ ግን ኢህአዴግ ምንቴስ ሳንል እንትጋ ፣ በርቱ እንበርታ ስል ባደረግነው ማሳረጊያ ተገወባባን … እናም ሰሞነኛ የመረጃ ግብአቱ ቦታውን ሳያጣብበው ለተገፋት የወገኖቻችን መብት እንደጋገፍ እንበርታ ስል የደረሰኝን መረጃ ተከትሎ በውስጤ ከሚጉላሉት ብዙ አሳዛኝ ታሪኮችን በጨረፍታ ዳስሸ መብት በማስከበሩ ረገድ መስማት የጀመሩት የጅዳ ቆንስል ተወካዮቻችንን ለመብታችን መከበር ጽኑልን ስለ መማጸን ፈለግኩ …

የሰሚራ ጉዳት …

ባሳለፍነው አንድ ቀር ገደማ በጥይት ተመታ በቢሻ ሆስፒታል በጥይት ተመታ ቆስላ በሆስፒታል ስለምትገኘው እህት ጉዳይ በማህበራዊ መረጃ መረቡ በኩል መረጃው ሲሰራጭ እኔም እጅ ገባ ። ብዙም ሳይቆይ በየድህረ ገጾች ተለቀቀ ። እኔም መረጃውን ለማጣራት ያፈረግኩት ሙከራ በተሳካ ማግስት በጅዳ የጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ወደ ቦታው በማቅናት ተጎጅዋን ማግኘታቸውን፣ ማነጋገራቸውንና ጉዳዩን እየተከታተሉት የመሆኑን የምስራች አበሰሩን ፣ ደስም አለን! ምስጋናም አቀረብን !
ይህ ከሆነ ከሳምንት በኋላ የሰሚራን ጉዳይ ለመከታተል ስሞክር በመረጃ አሰባሰቡ ዙሪያ ያልጠበቅኩት ችግር መከሰቱን ሰማሁ ፣ ረፋዱ ላይ ወደ ጅዳ ቆብስል ጎራ በማለት ጉዳዩን ከያዙት ዲፕሎማት የደረሰኝን መረጃ መሰረት በማድረግ ለማጣራት ብሞክርም ሃላፊው ለስራ ስለወጡ ማግኘት አልቻልኩም ። ያም ሆኖ በቦታው ላገኘኋቸው መልዕክቴን አስተላልፊ ተመለስኩ ! ይህ በእንዲህ እንዳለ በጉዳዩ ዙሪያ ያናከርኩት አንድ ወዳጀ በደረሰኝ መረጃ ዙሪያ አንድ ወንድም ዘርዘር ያለ መረጃ ያለው መልዕክት ከነ ተንቀሳቃሽ ፊልም ጭምር የያዘ መረጃ ማስተላለፉን ጠቆመኝ ። መረጃውን ከያዘው ወንድም መረጃ ትመለከቱት ዘንድ ከዚህ ገሰር አያይዠዋለሁ !
ሩቅያ …

ከወራት በፊት እዚህ ጅዳ ውስጥ በአንድ ት/ቤት የቅርብ ርቀት በተከሰተ የመኪና አደጋ የአሰሪዎቿን ልጆች ለማዳን ስትል ለከባድ አደጋ የተጋለጠች ሩቅያ የተባከች እህት አሳዛኝ ታሪክ አውቃለሁ። የሩቅያ ታሪክ በአረብ መገናኛ ብዙሃን ሳይቀር ቀርቧል። ከአደጋው በኋላ ራሷን የማታውቀው ሩቅያ በአንድ ሆስፒታል ለወራት ስትታከም ቆይታ ” ከህመሟ አገግማለች !” ተብሎ ከሆስፒታል ወጥታለች ። ያለ ወገን ደገሰፊ አምስት እህት ወንድሞችዋን የምታስተምር ትጉህ ክጅ አግር ናት ሰሚራ። ለህክምና ብትወጣም እርዳታ በማድረግ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች ግን አልረሷትም ። አደጋ ያደረሰባት ደግሞ ከእስር ወጥቷል ። እንዴት ወጣ አይታወቅም ። በውል ቋሚ የሆነ የሚደግፍ የሚረዳት ግን የለም ። ጉዳዩን በፊት ገጼ ካቀረብኩት በኋላ ለጅዳ ቆንስል አሳውቄ ነበር ። በወቅቱ ሄደው ጠይቀዋታል።እየተመላለሱም ጉዳዩን የተከታተሉ መሆኑን የገለጹልኝ የጅዳ ቆንስል ባለደረባ የሩቅያን ጉዳይ እንዳልረሱት ከቀናት በፊት አጫውተውኛል ። ይሁን … ብዙዎች ግን የሩቅያ ጉዳይ ተድበስብሶ እንዳይቀር እንማጸናለን !

መሃመድ …

መሃመድ ይባላል ፣ በ3 አመት የብላቴና እድሜው ድክ ድክ እያለ ለቀላል ቀዶ ህክምና ወደ ሃኪም ቤት ገባ ፣ ከቀዶ ጥገናው ክፍል ከገባ ከሰአታት በኋላ ከቀዶ ህክምናው ቢወጣም አልነቃ አለ። ሰአታት ተቆጠሩ ፣ ቀኖች ሲከተሉ ጉዳይ አስደንጋጭ እየሆነ መጣ ! ወላጅና የቤተሰብ አባላት የሚይዙ የሚጨብጡት ጠፋባቸው። ህክምናውን ያከናወኑት የሚሰጡት የተስፋ መልስ ጭብጥ እውንት ጠፋበት … ቀናት በቀናት ተተክተው ሳምታት ወርን ሲወልዱ የብላቴናው አለመንቃት በሆስፒታሉ ሃኪሞች ስህተት እንደሆነ ይፋ ተነገረ ! ይህ ሲሆን ታዲያ ከሆስፒታሉ የተሰጠው ምላሽ አስደንጋጭ ነበር ። የሶስት አምት ልጃቸው መሃመድ በህክምና ስህተት ማደንዘዣ በዝቶበት እንዳልነቃነና ይህን ስህተት የፈጸመው ዶር ከስራው መባረሩ ተገልጾላቸው መሃመድ እስኪነቃ አስፈላጊ ህክምናና ክፍል ተሰጥቶት ህክምናውን በነጻ እንደሚቀጥል ለወላጆች መርዶ ተነገራቸው ! ይህንን በደል ለማሰማት ወላጆቹ ከጅዳ ቆንሰል ከፍ እስካሉ የመንግስት መ/ቤቶች ቢደርሱም ሰሚ አላገኙም። እንዲያ ሆኖ ብላቴናው ከሰመመንና ከተኛበት አልጋ ሳይነቃ 11 ኛ አመቱን ዘንድሮ ይዟል …
ጉዳዩ አሳዛኝ ነው ከማለት በላይ ነው … ይህ በደል ወደ ሳውዲ ከፍተኛ የመንግስት አካላት ስለመታወቁ ግን አሁንም እጠራጠራለሁ ፣ ይህንኑ ለማጣራት አምድ ወዳጀ ከቤተሰብ አባላቱ ጋር ሊያገናኘኝ ቃል ገብቶልኛል። ያ ሙሉ አሳዛኙን መረጃ በዝርዝር እናወጋዋለን ! .. ባሳለፋቸው የብላቴናውና የወላጆቹ አስከፊ የጨለማ የመከራ አመታት ብላቴናውን የአልጋ ቁራኛ ህክምና በሚሰጠው ክፍል ሄጀ ለማየት ካንድም ሁለት ሶስቴ በሩ ላይ ደረስ ደርሸ ህመሙን መቋቋም ሳልችል ቀርቸ ሳላየው ተመልሻለሁ ! መውለድ ከባድ መሆኑንም የተረዳሁት ያኔ ነበር … የመሃመድ ጉዳይ በአንባሳደር ተክለአብ በአንባሳደር መርዋን እና በቆንስል ጀኔራል ዘነበ እየታወቀ እልባት የሚሰጥ የሚከታተለው ጠፍቶ ጉዳዩ ተድበስብሶ እዚህ ደርሷል ። ይህም ያማል ! ዘንድሮ ግን በቆንስሉ ትጉህ የተሃድሶው መሪዎች መፍትሔ ያገኙለት ዘንድ እንማጸናለን !

ስላለፈው ወቃሹ ታሪክ እንጅ እኛ አይደለንም፣ አንወቃቀስም …
የጀዛኑን ካልድ ለሶስት አመታት የቀጠለ አበሳ ሰሞኑን እልባት ሊያገኝ መሆኑን ሰምቻለሁ ፣ በካልድም ጉዳይም ሆነ በስም አይጠሬውን የአንድ እህት ሬሳ ታሪክ የምናወራው ዛሬ አይደለም ፣ አልነካካውም ! ስላለፈው መብት ጥሰትና የመብት ጥበቃ ጉድለት መረጃዎችን ከመሰብሰብ አልፈን ፣ ያለፈውን ጉዳይ እያነሳን መወቃቀሱ አይጠቅምም !

ዛሬ ሌላ ቀን ነው ፣ ላለፉት 11 ዓመታት እልባት ካልተሰጠው ከመሃመድ ጉዳይ ጀምሮ እስከ ጀዛኑን ካልድ ፣ በአሰሪዋ የፈላ ውሃ የተደፋባትና ላለፉት አንድ አመት ጉዳዩዋን በጅዳ ቆንስል ሆና የምትከታተለው የሄለን ጉዳይ ፣ በቅርብ በጥይት ከተመታችው የሰሚራ ጉዳይ እና መኪና ተገጭታ አካሏ እስከ ጎደለው ሩቅያ የዜጎችን መብት ለማስከበር የመንግስት ተወካዮች የተከፈተው በር እንዳይዘጋ ስንማጸን ፣ መረጃዎችን በማሰባሰቡ ረገድ ግልጽ መረጃ በመለዋዎጥ የመንግስት ተወካዮች መብታችም ያስከብሩልን ዘንድ ደጋግሜ እንማጸናችኋለሁ !
እስኪ ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 1 ቀን 2007 ዓም

The post (የሳዑዲ ጉዳይ) …ለተሃድሶ ጀማሪዎች ለጅዳ ቆንሰል ተማጽኖየ – ነብዩ ሲራክ appeared first on Zehabesha Amharic.

ለ3 ቀናት ከቤኒን ወደ ናይጄሪያ በአውቶቡስ የተጓዙት ደደቢቶች ከብዙ እንግልት በኋላ ነገ ዎልቭዝን ይገጥማሉ

0
0

449221-thumb-250x200ኢትዮኪክ ኦፍ እንደዘገበው የኢትዮጵያው ደደቢት ከረጅም የጉዞ ድካም እና እንግልት በኃላ ትላንት ናይጄሪያ ደርሷል። የቡድኑ አባላት ወደ ናይጄሪያ ለመጓዝ በረራቸው ሌጎስ የነበረ ቢሆንም በረራው ቤኒን ከደረሰ በኃላ የቡድኑ አባላት ከቤኒን ብዙ ኪሎ ሜትሮችን በአውቶቡስ የሶስት ቀን መንገድ ተጉዘው ጨዋታው የሚደርጉበት ከተማ በሰላም ትላንት ከሰአት ደርሰዋል።

ደደቢቶች እንደዚህ አይነት የእንግልት ጉዞ ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም፤ እንደሚታወሰው በመጀመሪያው የማጣሪያ ዙር ጨዋታቸው ወደ ሲሸልስ ሲጓዙ በኬንያ አድርገው ጨዋታ የሚደረግባት ሲሸልስ ሲደርሱ በድካም ተንገላተው እንደነበር ይታወሳል ። ጨዋታውን ሲሸልስ ላይ ካደረጉም በኃላም ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ በበረራ ችግር በሚል አንድ ሳምንት ጉዞው ፈጅቶባቸዋል።

ይሁንና ደደቢቶች በመጀመሪያው ዙር ያጋጠማቸውን የጉዞ መንገላታት ተቌቁመው ተጋጣሚያቸውን ከማጣሪያው ውጪ አድርገዋል።

በሀሉተኛው ዙር የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን የማጣሪያ ጨዋታ ነገ የናይጄሪያው ዋሪ ዎልቭስ በዋሪ ሲቲ ስታዴየም ደደቢትን ያስተናግዳል።

ዋሪ ዎልቭስ ለኢትዮጵያው ደደቢት ትልቅ ግምት ሰጥተዋል ፤ ጨዋታውን ደጋፊዎቹ በስታዲየም ተገኝተው ተጨዋቾቹን እንዲያበረታቱ ጥሪ አቅርበዋል።

በተለይም የክለቡ ቃል አቀባይ ለSL10.ng ድህረ ገፅ እንደተናገሩት የኢትዮጵያው ደደቢት ጨዋታውን አገሩ ላይ ሲያደርግ ከ35 ሺ ያላነስ ተመልካቾች ይኖሩታል ፤ እኛ ደግሞ ከ20ሺ ያላነሰ ደጋፊ ጨዋታውን ተገኝቶ ተጨዋቾቹን ቢያበረታታ የተሻለ ውጤት እንዲኖረን ያችላል ብለዋል።

የጨዋታው ኮሚሺነር ጋናዊው ሲሆኑ ጨዋታውን የሚመሩት ሁሉም ሶማሊያውያን አልቢተሮች መሆናው ነው የድህረ ገፁ መረጃ የሚያመለክተው።

 

The post ለ3 ቀናት ከቤኒን ወደ ናይጄሪያ በአውቶቡስ የተጓዙት ደደቢቶች ከብዙ እንግልት በኋላ ነገ ዎልቭዝን ይገጥማሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከአዲስ አበባ ወደ ደምቢዶሎ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ ተገልብጦ የ12 ሰዎችን ህይዎት ቀጠፈ

0
0

ዛሬ ማለዳ ከአዲስ አበባ ደንቢዶሎ 68 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ተገልብጦ 12 ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ ቀሪዎቹ 56 ተሳፋሪዎች ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለጸ። በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች አምቦ እና አዲስ አበባ በሚገኙ ሆስፒታሎች ለህክምና እንደተላኩም ፖሊስ አስታወቋል። አውቶቡሱ 194 ኪሎ ሜትር እንደተጓዘ ረፋድ 4 ሰአት ላይ ምዕራብ ሸዋ ጨሊያ ወረዳ ራቾ ገጠር ቀበሌ ልዩ ስሙ መሳለሚያ አካባቢ ሲደርስ ነበር አደጋው የደረሰው። የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ከበደ ደቢርሳ ተናግረዋል።

10420270_936584116374429_3710191187454730855_n

 

 

The post ከአዲስ አበባ ወደ ደምቢዶሎ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ ተገልብጦ የ12 ሰዎችን ህይዎት ቀጠፈ appeared first on Zehabesha Amharic.

(የሳውዲ ጉዳይ …) በሳውዲ መንግስት የተጀመረው ህገዎጦችን የማጥራት ዘመቻ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተይዘዋል

0
0

saudi arabia

ነቢዩ ሲራክ

* ዘመቻውን ተከትሎ መንግስት ያወጣው መረጃ እንደሚጠቁምው በሃገር አቀፍ ደረጃ በቀን በአማካኝ 1200 ህገ ወጦችን እንደሚያዙ አረብ ኒውስ ከቀ ት በፊት ተትቁሞ ነበር ። ያም ሆኑ በትናንትው እለት በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ የሰጠሀት” ጀዋዛት ” ተብሎ የሚጠራው የፖስፖርትና ኢምግሬሽን ባለስልጣበን ተቀዳሚ ኃላፊ ሜጀረ ጀኔራል ጃማን አል ጋምዲን የጠቀሰው ሳውዲ ጋዜጣ March 8 ,2015 ሁለተኛው የማጽዳት ዘመቻ ከተጀመረ ወዲህ ባሉት ቀናት በአማካኝ 4000 አራት ሽህ ህገ ወጥ እንደሚያዝ ባለስልጣኑን የጠቀሰው የሳውዲ ጋዜጣ ዘገባ አስታውቋል::

* በሪያድና አካባቢው ከተለያዩ የሚመለከታቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከፖሊስ ጋር በመሆን ባደረጉት አሰሳ 20 ሴቶችና ጨምሮ 866 ወንድ ህገ ወጦች መያዛቸውን ዛሬ የወጣው አረብ ኒውስ አስታውቋል::

* የተያዙት የውጭ ዜጎች መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ፣ ከመኖሪያ ፈቃዳቸው ከተመለከተው ስራ ውጭ ሲሰሩ የተገኙና ከአሰሪያ ጨው ውጭ ለሌላ አሰሪ ሲሰሩ የተገኙት መሆናቸው ታጠቅሷል::

* በሪያድ የተያዙት አብዛኛው የመንና ኢትዮጵያውያን ዜጎች መሆናቸው የጠቆመው የዛሬው አረብ ኒውስ ከተያዙት 20 ሴቶች መካከል ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞች መሆናቸውን የጋዜጣው ዘገባ ጠቁሟል

* በመገናኛ ብዙሃን በከፍተኛ ሁኔታ ዘመቻው ቢራገብም እስከዛሬዋ ቀን ድረስ እዚህ ጅዳም ሆነ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ኑሮው ነዋሪው በስጋት ተወጥሮ ኑሮን በመግባት ላይ ነው ። ቀን ላይ የተጠናከረና የተወጣጠረ ፍተሻ ባይስተዋልም በአንዳንድ የኮንስትራክሽን የስራ ቦታዎችና በሱቆች ድንገተኛ ያልተጠበቀ ፍተሻ እና ሌሊት ሌሊትም በጥቆማ በሚደረጉ ፍተሻዎች ዘመቻው ተጠናክሮ መቀጠሉ ይነገራል ።

saudi arabia 1

* በማጣራቱ ዘመቻ ስጋት ያደረባቸው በርካታ የውጭ ሃገር ዜጎች ምግብ ቤቶችና ሱቆቻቸውን እስከመዝጋት መድረሳቸውን በፎቶ ሳይቀር መረጃው ይፋ ያደረገው የአረብ ኒውስ የዛሬ ዜና ዘገባ ይጠቁማል

* ይህ በእንዲህ እንዳለ በሽሜሲ እስር ቤት ያለው ታሳሪዎችን የመሸኘት ሂደት በመሳለጥ ላይ መሆኑ ሲጠቀስ የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ጉዳይ ግን እስኪጣራ ጊዜ መፍጀቱ መረጃዎች ደርሰውኛል
እስኪ ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 4 ቀን 2007 ዓም

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/39693#sthash.az1N8J8e.dpuf

The post (የሳውዲ ጉዳይ …) በሳውዲ መንግስት የተጀመረው ህገዎጦችን የማጥራት ዘመቻ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተይዘዋል appeared first on Zehabesha Amharic.


ነዋሪዎች ከሁለት በላይ የምርጫ ካርድ እንዲያወጡ እየተደረገ ነው

0
0

(ነገረ ኢትዮጵያ) በደቡብ ክልል በምርጫ አስፈፃሚነት የተመደቡ ግለሰቦች የዴኢህዴን አባላት እንደሆኑ ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ በላኳቸው ሰነዶች አረጋገጡ፡፡ ለአብነት ያህልም አረካ ከተማ የምርጫ ክልል በአስፈጻሚነት እየሰሩ ከሚገኙትን አቶ ግዛው ቴማ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አባል መሆናቸው ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ የተላኩት ሰነዶች ያሳያሉ፡፡ አቶ ግዛው ለፓርቲያቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) በነሃሴ ወር 2006 12 ብር ከ87 ሳንቲም፣ እንዲሁም በ2007 መስከረምና ጥቅምት የሁለት ወር 25 ብር ከ74 ሳንቲም መዋጮ የከፈሉበት ደረሰኝ የደኢህዴን አባልነታቸውን ያረጋግጣል፡፡

electionበሌላ በኩል በደቡብ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ነዋሪዎች በግዳጅ ከሁለት በላይ የምርጫ ካርድ እንዲያወጡ እየተገደዱ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሕዝቁኤስ ቱጨ ቱፋ ለባለቤታቸውን ለወይዘሮ መሰለች ኬንዳን ጭምር ካርድ እንዲያወጡ የተደረገ ሲሆን፣ በዚሁ ቀን ህዝቡ ካርድ እንዲያወጣ የሚቀሰቅሱ ሌሎች ካድሬዎች ወይዘሮ መሰለች ኬንዳም የባለቤታቸው የአቶ ሕዝቁኤስ ቱጨ ጨምረው ሁለት ካርዶችን እንዲወስዱ ተደርገዋል፡፡ ሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎችም በተለያዩ ካድሬዎች አማካኝነት በርከት ያሉ የምርጫ ካርዶችን እንዲወስዱ መደረጉን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በቀን 07/05/ 2007 ዓ.ም ወ/ሮ መሰለች በ173ኛ እና 147ኛ ቁጥር፣ እንዲሁም ባለቤታቸው አቶ ህዝቁኤል ቱጫ ቱፋ በተመሳሳይ ቀን 172ኛ እና 151ኛ ተራ ቁጥር ላይ ተመዝግበው ሁለት ሁለት የምርጫ ካርዶችን እንዲወስዱ ተደርገዋል፡፡ በተጨማሪም ነዋሪዎች መምረጥ ለማይችሉት የቤተሰብ አባላት ጭምር ‹‹ካርድ ውሰዱላቸው›› እየተባሉ በአንድ ሰው በርከት ያለ ካርድ መውጣቱን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

The post ነዋሪዎች ከሁለት በላይ የምርጫ ካርድ እንዲያወጡ እየተደረገ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

በዲ/ን ዳንኤል ክብረትና በኤርሚያስ ለገሰ ዙሪያ እኔም የምለው አለኝ:- “እኛ ጋር ካልሆናችሁ እነሱ ጋር ናችሁ”

0
0

ermias copy
ሰሞኑን አቶ ኤርሚያስ ለገሰ “ግልጽ ደብዳቤ ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት” ብሎ የጻፈውን፤ ከዚያም ዲያቆን ዳንኤል ለዚህ ደብዳቤ የሰጠውን ምላሽ (ታላቅነቱን በሚያሳይ ትህትና)፤ እንዲሁም አቶ ኤርሚያስ “የመጨረሻ ደብዳቤ” (በሃሳብ መሸነፍ የወለደው የስድብና አሉባልታ ጥርቅም) ብሎ የሰጠውን መልስ ብዙዎቻችን አንብበነዋል፡፡

“አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት የባሏን መጽሃፍ አጠበች” እንደተባለው አቶ ኤርሚያስ ራሱም ተዋናይ ሆኖ ሲተውነው የኖረውን ስለተረከ ብቻ “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው” በሚለው የተሳሳተ ብሂል ጆሮ ሲሰጠው ጊዜ ራሱን ሊያስገምት በሚችል ሁኔታ ያኛውን ትረካ ሲጨርስ ወደዚህም መጣ፡፡ በነገራችን ላይ “የመለስ ትሩፋቶች ደራሲ” የምትለዋ ሁልጊዜ የእሱ ስም ሲነሳ ከፊት ትቀድማለች፡፡ ይቺ ነገር ከፊት ካልቀደመች እሱ አይታወቅም ማለት ነው? ወይስ “እንዴ! እንዲህ ያደረገ ሰው እኮ ነው!” ለማለት ነው? (በጣም ገርሞኝ ነው)
በኢትዮጵያ ፖለቲካ አንድ አስቂኝ ጨዋታ አለ፤ በገዢው ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ዘንድ አንድ የፖለቲካ ንቃተ-ህሊና (ግንዛቤ) ያለው ሰው የእነሱ ፓርቲ አባል ወይም ደጋፊ ካልሆነ “እንዴ! እሱማ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ወይም ደጋፊ ነው” የሚል ጭፍን ፍረጃ ይሰጡታል፡፡ ተቃዋሚዎቹ ደግሞ ያ ሰው ጨዋታውን እነሱ በሚፈልጉት መንገድ የሚጫወት ሰው ካልሆነ “እሱማ ወያኔ ነው፣ ካድሬ ነው፣ ከእነ እንትና ጋር ግንኙነት አለው” (የልደቱ አያሌውን መጽሃፍ ማንበብ ትችላላችሁ) ብለው ሃላፊነት በጎደለው አኳኋን ይፈርጁታል፡፡ ነገር ግን የሁለቱም ጨዋታ ያልተመቸውና ከአስተሳሰቡም ጋር ያልሄደለት ሰው መሃል ላይ ራሱን ሆኖ እንደሚኖር አይረዱትም፡፡ በተግባርም ብዙዎቹ ገዢውም ሆነ ተቃዋሚዎቹ ፓርቲዎች የሚያራምዱት አልጥማቸው እያለ በንጽህናና በነፃ ህሊና ራሳቸውን ሆነው የራሳቸውን አስተሳሰብ እየተከተሉ ይኖራሉ፡፡ ይህን ደግሞ ሃጢያት አድርገውት ቁጭ ይላሉ፡፡ ምን እንሁን ታዲያ? “እኛ ጋር ካለሆናችሁ እነሱ ጋር ናችሁ” ብለው በጭፍን ይፈርጃሉ፡፡ ታዲያ ይሄን የሚሉት “ዜጎች የፈለጉትን ሃሳብ በነፃነት ማራመድ እንዲችሉ እንዲሁም የሀሳብ ብዝህነትና ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ በኢትዮጵያ እንዲመጣ ጠንክረን እየሰራን ነው ወዘተ . . . ” እያሉ የሚምሉትና የሚገዘቱት ሲሆኑ ነገሩ ያስገርማልም፣ ያሳፍራልም፡፡

ዲያቆን ዳንኤልን በተመለከተ ልክ እንደ ኤርሚያስ ሁሉ ብዙዎች ብዙ ብለዋል፤ እሱ ግን የሚወራበትን ሳይሆን በተግባር እሱ የሆነውን (የታላቁን አባት የብፁዕ አቡነ ጎርጎሪዎስ ካልዕን መርህ በመከተል (“ሥራህን ሥራ፤ አንበሳው ሲያጓራ ፍንክች አትበል፤ የሰይጣንን ውሾች ለመውገር አትቁም . . . ”)) በሚለው መሰረት ከእነዚህ ከሚያወሩት ሰዎች በላይ ትርጉም ያለው ስራ ለሀገሩ እየሰራና ትውልድን በተሻለ አስተሳሰብ ለመቅረጽ፣ የሀገር ታሪክ፣ ባህልና ትዉፊት በዚህ ትውልድም ታውቆና ተጠብቆ እንዲኖር እየሰራ ያለ ሰው ነው፡፡ በተለያዩ ቦታዎች ሄዳችሁ ከምታገኟቸው አምስት ሰዎች ውስጥ ቢያንስ አንዱ ስለ ዳንኤል በሚገባ ብዙ ነገሮችን ሊነግራችሁ ይችላል፡፡ ይሄ በቅንነትና በትጋት ከመስራት የመጣ መሆኑ በነፃ ህሊና ለሚያስብ ሰው ግልጽ ነው፡፡ ታዲያ እነ ኤርሚያስ ይህን ሰው ፈልገውት ኖሮ “እናንተ ጋርም አልሄድም፣ እነዚያ ጋርም እየሄድኩ አይደለም፣ እንደ እስካሁኑ ሁሉ አሁንም በራሴ መንገድ ነው መሄድ የምፈልገው ሲላቸው” “አይ አንተማ እነሱ ጋር ነህ” ብለው ፈረጁት፡፡

ዳንኤልን በአካል አንድ ቀን ብቻ አግኝቼው ለተወሰኑ ደቂቃዎች አውርተናል፡፡ ከዚያ ውጪ ግን በተለያዩ መድረኮች አስተምሮኛል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሁኑ ብዙ ሰዎች የራሳቸው ብሎግ ሳይኖራቸው (በኢትዮጵያ እየኖረ የራሱ ብሎግ የነበረው የመጀመሪያው ወይም ከመጀመሪያዎቹ አንዱ የሆነ ሰው ነው) በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩና ከህይወታችን፣ ከባህላችንና ከሀገራችን ታሪክ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን እጅግ መሳጭና ነገሮችን በተለየ መንገድ እንዲናይ የሚያደርጉ ጽሑፎቹን በማንበብ፤ እንዲሁም በሚያሳትማቸው መጽሃፍቶቹ በደንብ አውቀዋለሁ፡፡ ጽሑፎቹን በተመስጦ ሳነብ ኖሬያለሁ፤ ብዙ እውቀቶችንም አግኝቻለሁ፤ ወደፊትም እንደ አምላክ ፈቃድ እንዲሁ ይቀጥላል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
daniel kibret
ስለ አንድ ሰው ይህን ያህል ራሱን ሊገልጹ የሚችሉ የአዕምሮው ውጤቶች የሚነግሩንን ትተን ወደ ተራ አሉባልታ የምንወርድበት ሁኔታ ግን ከምቀኝነትና እርሱም በአንድ ወቅት ከአንድ እንግሊዛዊ ጋር አፄ ኃ/ስላሴን በተመለከተ ሲወያዩ ሰውየው ያለውን “አይከንን መግደል” (ሃሳቡን እንጂ ርዕሱ በትክክል ይሄ መሆኑን ርግጠኛ አይደለሁም) በሚል ጽሑፉ እንዳሰፈረው ኢትዮጵያን ሁልጊዜም ልጅ እያላት የልጅ ደሃ የሆነች ሀገር ያደርጋታል፡፡ ይሄ ሰው ለብዙ ወጣቶች አርዓያ መሆን የሚችልና እውነት ለመናገር ከብዙዎቻችን በላይ ለሀገርም ትልቅ ዋጋ ያለው ሥራ እየሰራ ያለ ወደፊትም ትልቅ ነገር ማድረግ የሚችል በመሆኑ በተራ አሉባልታ ስም ማጥፋቱ ጉዳቱ ለሀገር ነው፡፡ እንደ ሀገር ያሉንን እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ቁጥራቸውን ማብዛት እንጂ ያሉትን ሁልጊዜ ማጥፋቱና መግደሉ አይጠቅመንም፡፡

በ“ግልጽ ደብዳቤው” “የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል” እንደሚባለው አቶ ኤርሚያስ ብዙ ስህተቶችን ጭምር ተሳስቷል፡፡ ዳንኤል ጥናታዊ ጽሑፉን ሲያቀርብ የነበረውን እውነታ ወደ ጎን ትቶ ሃሳቡ አሁን ካለው ሁኔታ ጋር አገናኝቶ ብቻ ከስሶ ለከሳሽ ለመስጠትም ሞከረ፡፡ በነገራችን ላይ “እንዲህ ነው” “እንዲያ ነው” የሚለውን አሉባልታውን ትተን በጥናታዊ ጽሑፉ ከተነሱት ጉዳዮች ውስጥ እነዚህ እውነት አይደሉም ብሎ ማስረጃ በማቅረብ ብንወያይ ጥሩ ነበር፡፡ ዳንኤል በወቅቱ የሆነውንና እየሆነ የነበረውን በማስረጃ አቅርቧል፤ በጊዜው የሆነውን ነገር መግለፁ ጥፋት ከሆነ ጥያቄው ለምን ተናገረ የሚለው ይሆናል ማለት ነው፡፡ አየህ ወንድም ኤርሚያስ! እውነትን መናገርና ዝም አለማለት የተለያዩ ናቸው፡፡

አቶ ኤርሚያስ “የመጨረሻ…” ባለው ጽሑፉ ውስጥ ደግሞ “እኔን ከአማራዎች ጋር ልታጋጨኝ ነው” ብሎ ሲናደድ አስገርሞኛል፡፡ እሱ ዳንኤልን ከሙስሊሞች ጋር ለማጋጨት መሞከሩ ትክክል ነው፤ ነገር ግን አማራን በተመለከተ ኤርሚያስ ሲያደርግ የኖረውን ሲነግረው ጮቤ ረገጠ፡፡ አይ ኢትዮጵያ! እንዲህ ዓይነቱ ሰው ነው እንግዲህ ሲገዛን የኖረው እንዲሁም ወደ ፊት ሊገዛን የሚቋምጠው፡፡

ብዙ ጊዜ እንደምናየው ሰዎች በሀሳብ ሲሸነፉ ሃሳቡን በሌላ አሸናፊ ሃሳብ ከመሞገት ይልቅ ወደ ስድብና ተራ ነገር እያነሱ ስም ወደ ማጥፋት ይሄዳሉ፡፡ አቶ ኤርሚያስም ይህንኑ ሲያደርግ እናየዋለን፡፡

“ሰዎች ፊት ቆመህ የምትሰብከው እንደዚህ ዓይነት የከረፋ አመለካከትና ውሸት ተሸክመህ…” ይሄን ማለት ያለባቸው በተመስጦ ቁጭ ብለው ትምህርቱን የሚያዳምጡትና የሚከታተሉት ምዕመናን ናቸው እንጂ አንተ አይደለህም ወንድም ኤርሚያስ፤ አንተ ያነሳኸውን ጉዳይ በተሻለ ሀሳብ (ካለህ) ብትሞግት ይሻላል፡፡ ሲያስተምር አንተ መቼ አይተኸው ታውቅና ስለዚያ ታወራለህ? ብታየውማ ለዚህ ስህተት አትዳረግም ነበር፡፡

“እኔን በፀረ-አማራ ፈርጀህ (የኦርቶዶክሱን እንዴት አለፍከው ወይስ ተቀብለኸዋል ማለት ነው?) ብትጽፍ ሚዛን እንደሚደፋልህ የተቀመረች…” እሱ ካየውና ከታዘበው በመነሳት የሆንከውን ነገረህ፤ ላለመሆንህና ላለማድረግህ የራስህን ሃሳብ ማቅረብ ትችላለህ፡፡ እዚህ ላይ ግን አንተም በተለመደው ፖለቲካዊ ቀመር የሆነች ትርፍ ለማግኘት ብለህ ነው ይህን ጽሑፍ ለመፃፍ የተነሳኸው እንጂ ያነሳኸው ጉዳይ የምር አሳስቦህ አይደለም ማለት ነው፡፡

“አቦይ የላከው… እንድልህም…” ዝም ብሎ የመጣልህን ከማለት ለእኛም ሊያሳምነን የሚችል ማስረጃህን ብታቀርብ እንዴት ጥሩ ነበር መሰለህ፤ እስካሁን ሲያስነብበን የኖረው የአዕምሮው ውጤቶች ከብዙሃኑ የተሻለ የአስተሳሰብ ልዕልና ላይ ያለ ሰው መሆኑን ነው የሚመሰክሩት፡፡ (እባክህ ሌላውን ተወውና ሰሞኑን በብሎጉም ሆነ በፌስቡክ ገፁ የፃፋቸውን አንብባቸው)

ሌላው ደግሞ መገንዘብ ያለብህ አስተማሪ ማስተማር እንጂ መሳደብ የለበትም፤ ስላልተሳደበ ደግሞ ወዳጃቸው ነው ማለቱ ከንቱ ፍረጃ ነው፡፡ ክርስቲያን በ“ቢላዋው” ስርም ሆኖ ያስተምራል፣ ይፀልያል እንጂ አይሳደብም፡፡
በጣም ያስገረመኝ የአንተ “ማተማቲክስ” “ሙስሊሞች ሁሉ ቅዱሳን ናቸው እንደማልለው ሁሉ ክርስቲያኖች ሁሉ አክራሪዎች ናቸው ብዬ አላውቅም በል” ትለዋለህ፤ እንዲህ የምትለው ዲያቆን ዳንኤል እኮ የክርስትና ሃይማኖት መምህር እንጂ የስነ-ዜጋ መምህር አይደለም፡፡ አንተ እንዲታከብረው ከእምነቱ ውጪ የሆነን ነገር ይንገርህ? ይሄን ማለትስ ለምን አስፈለገ?

እንደው እነዚህን ነጥቦች አነሳሁ እንጂ ብዙ ያስገረሙኝና ያሳዘኑኝ ሃሳቦችም ነበሩ፤ “የመጨረሻ ደብዳቤ” ብለህ ቋጨሃት፤ ዓላማህን አሳካህ ማለት ነው? ለኩሶ ዘወር . . . ለነገሩ ከዚህ በላይ መሄዱ እንደማያዋጣህ አስልተሃታል (ቀመረኛው)፡፡

ንትርክና ክስ ህዝቡ እንዴት እንደሰለቸው ባወቅክ፤ በእንደዚህ ያለው አስተሳሰብ አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ከማስቀጠል ባለፈ ምንም የተሻለ ነገር አናመጣም፡፡ ባለፉት 40 እና 50 ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ሲካሄድ ኖረ፤ ምን አተረፍን? የት አደረሰን? ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም “የፓርቲ ፖለቲካ በቃኝ” ብለው ሲሰናበቱ “ሁላችንም የኢትዮጵያን ህዝብ አልቅሰን ይቅርታ መጠየቅ አለብን” ብለው ነበር፡፡ ወደምንመኘው መድረስ ከፈለግን ንስሃው የግድ ለሁላችንም አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡ አዲስና ከእስካሁኑ የተሻለ የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ግዴታ ነው፡፡
እስካድማስ አየነው ፣ አዲስ አበባ

The post በዲ/ን ዳንኤል ክብረትና በኤርሚያስ ለገሰ ዙሪያ እኔም የምለው አለኝ:- “እኛ ጋር ካልሆናችሁ እነሱ ጋር ናችሁ” appeared first on Zehabesha Amharic.

“ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ ይቀጥል…ገንዘባችሁን ከሕወሓት ባንኮች ከወጋገንና አንበሳ ባንኮች አውጡ”–አርበኞች ግንቦት 7

0
0

የግንቦት 7 ወቅታዊ ጽሑፍ

የኢትዮጵያ ሕዝብ በአለፉት 23 ዓመታት በህወሓት ዘረኛ አገዛዝ የደረሰበት ስቃይ እንዲቀንስ፤ ገዢዎቹ ከጫንቃው እንዲወዱ፤ ህወሓትን አውርዶ የሚፈልጋቸው መሪዎችን በነፃነት እንዲመርጥ ሲጠይቅና አቤቱታ ሲያሰማ ቆይቷል። በ1997 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሕዝብ ምኞት የሚሳካ መስሎ የታየ የነበረ ቢሆንም በአገዛዙ አረመኔዓዊ እርምጃ ተሰናክሏል። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ “ድምፃችን ይሰማ” የሚሉ አቤታዎች ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መምጣት ጀምሯል – “ድምፃችን ይሰማ ሙስሊሞች”፣ “ድምፃችን ይሰማ ኦርቶዶክሶች”፣ “ድምፃችን ይሰማ መምህራን”፣ “ድምፃችን ይሰማ ተማሪዎች”፣ … ወዘተ። በተለይ ሙስሊም ወገኖቻችን በተደራጀ መንገድ “ድምፃችን ይሰማ” እያሉ ሲወተውቱ ሦስት ተከታታይ ዓመታት አልፈዋል። ወገኖቻችን “ድምፃችን ይሰማ” በማለታቸው ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ ተገድለዋል።
wegagen bank
አቤቱታ የሚሰማ ጆሮ የሌለው አገዛዝ ሲገጥም ምን ይደረጋል? ለአቤቱታ አቅራቢው ያለው ምርጫ ከሁለት አንድ ነው። ወይ አቤቱታን እርግፍ አድርጎ ጥሎ በደልን ተቀብሎ “እህህ !” እያሉ መኖር፤ አሊያም “በቃኝ፣ እንቢ አልገዛም” ማለት፤ ሦስተኛ ምርጫ የለም።

አቤቱታ ሰሚ ሲያጣ እና ሕዝብ መሮት “እንቢኝ፣ አልገዛም” ሲል ነው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተቀሰቀሰ የሚባለው። ሕዝባዊ እምቢተኝነት ብዙ መልኮችና ቅርጾች ቢኖሩትም ዋነኛዎቹ መገለጫዎች ሁለት ናቸው። አገዛዙ ሕዝብ እንዲያደርግ የሚፈልገውን አለማድረግ እና/ወይም አገዛዙ ሕዝብ እንዲያደርግ የማይፈልገውን ማድረግ።

ለምሳሌ፣ አገዛዙ ሹማምንቱ እንዲከበሩ፣ ሕዝብ እንዲታዘዝላቸው ይፈልጋል፤ እንቢ ያለ ሕዝብ ግን የአገዛዙን ሹማምንት ይንቃል፣ በየደረሱት ያዋርዳቸዋል፣ “አልታዘዛችሁም” ይላቸዋል። ማንኛውም መንግስት የዳኝነት ሥርዓቱ እንዲከበርለት ይፈልጋል፤ በደል የመረረው ሕዝብ ግን የአምባገነኖች ችሎት ውሳኔ አይቀበልም፤ ዳኞችንም ዳኝነትንም አያከብርም። ሕዝብ የመንግሥትን ግብር በወቅቱ እንዲከፍል የማንኛውም መንግሥት ፍላጎት ነው። በመንግሥት ያመረረ ሕዝብ ግን ግብር አይከፍልም፤ መክፈል ግድ ከሆነበትም አዘግይቶ፣ አስለፍቶ ነው። የመረረው ሕዝብ ምሬቱን መፃፍ በሌለበት ቦታ ይጽፋል። በደል የበዛበት ሕዝብ “ዝም በል” ሲሉት ይናገራል፤ “ተናገር” ሲሉት ዝም ይላል።

አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የሕዝባዊ እምቢተኝተኝነት እርምጃዎች ጅምሮች እየታዩ ነው። በአማራ ክልል፣ ሕዝብ በሹማምንት ላይ የራሱን እርምጃ መውሰድ ጀምሯል። ሕዝብ ራሱ የፓሊስንም የፍርድ ቤትንም ሥራ ተክቶ እየሠራ ነው። ይህ መበረታታት ያለበት ትልቅ እርምጃ ነው። እንደዚሁም ሁሉ በተለይ ወጣቶች ብሶቶቻቸውን በብር ኖቶች ላይ ጽፈው ገበያው እንዲያዘዋውራቸው እያደረጉ ነው። ይህም “የወረቀት ገንዘብን ለተሠራበት ዓላማ ብቻ ተጠቀሙ” የሚለውን ህግ በመጣስ ለቅስቀሳ ሥራ መጠቀም በመሆኑ የሕዝባዊ እምቢተኝነት አካል ነው። በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ በርካታ የወረቀት ገንዘቦች በምሬት መግለጫነት ይውላሉ ተብሎ ይገመታል።

በተጓዳኝ በርካታ አማራጭ ስልቶች ሥራ ላይ መዋል ይኖርባቸዋል። ለምሳሌ፣ ተቀማጭ ገንዘብን ከህወሓት ባንኮች ማውጣት በቀላሉ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል ስልት ነው። በውጋጋን ባንክ ተጀምሮ ወደ አንበሳ ኢንተርናሽናል ከዚያም ወደ ንግድ ባንክ ማሸጋገር ይቻላል።

በወገኖቻችን ላይ የግፍ ፍርድ የሚያስፈርዱ አቃቢያነ ህግ እና የግፍ ብይኖችን የሚሰጡ ዳኞች በቸልታ ሊታለፉ አይገባም። በእስር ቤቶችም በወገኖቻችን ላይ ሰቆቃ እየፈፀሙ ያሉ ጨካኞች ከሰላማዊ ሕዝብ ጋር ተደባልቀው ሰላማዊ ሕይወት እንዲመሩ ሊፈቀድላቸው አይገባም። እነዚህ ሁሉ ሊወገዙ፣ ሊገለሉ፣ በየደረሱበት ሊዋረዱ ይገባል።

በአገዛዙ መንግሥታዊ መዋቅር ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችን በሥራቸው ላይ መለገም ተቀባይነት ያለው በጎ ተግባር እንደሆነ ሰፊ ግንዛቤ ሊያገኝ ይገባል። ከአምባገነን ሥርዓት ጋር መተባበር እኩይ ተግባር ሲሆን አምባገነን ሥርዓትን ከውስጥ መቦርቦር ደግሞ የሚበረታታ ሰናይ ሥራ ነው።

ለወያኔ አገዛዝ ግብር መክፈል የምናቆምበት ሰዓትም ተቃርቧል። በራሳችን ገንዘብ ገዳዮቻችን እንዲሰለጥኑብን መፍቀድ የለብንም። ስለሆነም “ግብር አንከፍልም”፤ “መዋጮዎቻችሁ አይመለከቱንም” የምንልበት ቀን ቀርቧል።

በፋይዳ የለሽ ምርጫ የሀገር ሀብት ሲመዘበር ማየት አንሻም። በአግባቡ ለማይቆጠር ድምፃችን አንድም ደቂቃ የምናባክንበት ምክንያት የለምና ሁላችንም የምርጫ ካርዶቻችንን ቀዳደን ቁርጭራጮቹን በየመንገዱ ልንበትናቸው ይገባል።

እነዚህን እነዚህን የመሳሰሉ ናቸው የሕዝባዊ እምቢተኝነት የመጀመሪያ ደረጃዎች። እነዚህን እያደረግን በምስጢር መደራጀታችንን እንቀጥል። ከጥቂት በኋላ አምባገነኑን ሥርዓት የሚያንበረክክ ኃይል እንፈጥራለን። ጥቃት ቢደርስ የሚመክት ኃይል የተደራጀ በመሆኑም ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ሕዝባዊ አመጽ ተቀናጅተው እንዲሄዱ ይደረጋል።

አርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሕዝባዊ እምቢተኝነትንና ሕዝባዊ አመጽን አቀናጅቶ ለመምራት የተዘጋጀ፤ ለዚህ የሚያበቃው ድርጅታዊ አቅም እየገነባ ያለ ድርጅት ነው። አርበኞች ግንቦት 7 “እንሰባሰብ በወያኔ ላይ የምናቀርባቸው ተቃውሞዎች በሙሉ ወደ እምቢተኝነት ከፍ እናድርጋቸው” ይላል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

The post “ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ ይቀጥል… ገንዘባችሁን ከሕወሓት ባንኮች ከወጋገንና አንበሳ ባንኮች አውጡ” – አርበኞች ግንቦት 7 appeared first on Zehabesha Amharic.

የግዲቾ ብሄረሰብ አባላት ያነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ ፖሊሶች አንድ ሰው ገድለው 8 አቆሰሉ

0
0

ኢሳት ዜና :-የግዲቾ ብሄረሰብ አባላት ተቃውሞውን ያስነሱት መሬታቸው ለትምባሆ ተክል እርሻ ለአንድ ባለሀብት መሰጠቱን ተከትሎ ነው።
ESAT Radio November 26, 2013
በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን በምእራብ አባያ ወረዳ የሚኖሩት ቁጥራቸው እስከ 5 ሺ የሚደርሱ የብሄረሰቡ አባላት፣ ቀደም ብሎ በአባያ ሃይቅ መካከል በሚገኘው ደሴት ይኖሩ ነበር። ደሴቱ በሃይቁ ሙሉ በሙሉ መሸፈኑን ተከትሎ የብሄረሰቡ አባላት ሃንቲ ወደ ሚባል አጎራባች ቀበሌ በመሄድ ኑሮአቸውን ሲገፉ ቆይተዋል።
ይሁን እንጅ የዞኑ ምክር ቤት የእርሻ መሬታቸውን ለ4 ኢንቨስተሮች በመስጠቱ፣ ነዋሪዎቹ በእርሻ መሬት እጦት ሲሰቃዩ ቆይተዋል። ባለፉት ጥቂት ወራት ደግሞ የብሄረሰቡን አባላት ሙሉ በሙሉ በሚያፈናቅልና መድረሻ በሚያሳጣ ሁኔታ ፣ መሬታቸው ለአንድ ትምባሆ አምራች ኢንቨስተር ተሰጥቷል።

ነዋሪዎቹ በተወካይ ሽማግሌዎች አማካኝነት አቤቱታቸውን ለዞኑና ለክልል ምክር ቤት አባላት ሲያቀርቡ ቢቆዩም፣ በየደረጃው ካሉ ባለስልጣናት ያገኙት መልስ ግን ስድብ ብቻ ነው።
ባለፈው ማክሰኞ አዲሱ ባለሃብት ወደ አካባቢው በመሄድ ደኖችን መመንጠር ሲጀምር በአካባቢው የነበሩት ሴቶችና ህጻናት በመጮህ ተቃውመዋል። የአካባቢው ፖሊሶች ፈጥነው በመድረስ በጩኸት ሲቃወሙ ከነበሩት መካከል አንዷን አሮጊት ክፉኛ መደብደባቸውን፣ ጨኸቱን ሰምተው የተሰባሰቡት ወንዶችም ተቃውሞአቸውን መግለጻቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።

ፖሊሶች ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ያገኙትን ሁሉ ከመደብደብ አልፈው ጥይቶችን በመተኮስ አንዱን የብሄረሰቡ አባል በ4 ጥይቶች አናቱን መትተው ሲበታትኑት፣ 8ቱን ደግሞ ክፉኛ አቁሰለዋቸዋል። አንደኛው ሰው አንጀቱ አካባቢ ተመትቶ የህክምና እርዳታ እያገኘ ቢሆንም፣ ላይተርፍ ይችላል ተብሎአል። ሌሎች ደግሞ እጅና እግራቸው መሰባበሩን የአይን እማኖች ለኢሳት ተናግረዋል።
“በጣም የሚያሳዝነው” ይላሉ ነዋሪዎች፣ “ሟቹ ለ6 ሰአታት ያክል መንገድ ላይ ወድቆ አስከሬኑ እንዳይነሳ መደረጉ ነው”።
የብሄረሰቡ አባላት በከፍተኛ ድህነት ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣ መሬታቸው በጉልበት ለባላሀብቱ ከተሰጠ፣ ወደ ከተሞች ተሰደው የጎዳና ተዳዳሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይናገራሉ።
በጉዳዩ ዙሪያ የጋሞጎፋ ዞን ፖሊስ ጽ/ቤትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል።

The post የግዲቾ ብሄረሰብ አባላት ያነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ ፖሊሶች አንድ ሰው ገድለው 8 አቆሰሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአዲስ አበባ ነዋሪ ዜግነቱን እንዲያገኝ መፍትሄው “የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል”ብሎ 10ኛ ክልል መጨመር –ያሬድ ጥበቡ (ጌታቸው ጀቤሳ)

0
0

What is Ato Yared Tibebu belching about?
ምን ይሻላል?

የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች በብዙ ጉዳዮች የሚለያዩ ቢሆንም፣ ፊንፊኔ መናገሻችን ናት በሚለው ጉዳይ ግን ይስማማሉ ። ለዚህም ይመስ ላል በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳይ፣ ኦሮሞ ፈርስትና ኦፒዲኦ እጅና ጓንት ሆነው ሃገሩን ያተራመሱት ። ለመሆኑ ፊንፊኔ የኦሮሞ መናገሻ ነበረች? ኦሮሞዎች ከየት መጡ? የኦሮሞን አፈታሪክና መዝሙሮች ፣ የታሪክ ተመራማሪዎችም ከፃፉዋቸው፣ ከሱማሌና ሐረሪ ህዝቦች አፈታሪክ በማጥናት፣ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ይልማ ዴሬሳ “የኢትዮጵያ ታሪክ በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን” የሚል መፅሀፍ በ1959 አም ፅፈዋል ። የታላቁ የኦሮሞ አፈታሪክ ቁንጮ፣ የብላታ ዴሬሳ ልጅ በመሆናቸው ልናዳምጣቸው የግድ ነው ። የመጨረሻው የሌቃ ነቀምቴ ንጉስ የሞቲ ሞረዳ በከሬ የቅርብ ዘመድም ስለሆኑ ( cousin) ታሪካቸውን ልቅም አድርገው ያውቃሉ ። እንዲህ ይሉናል ።

” ይህ ምዕራፍ የተፃፈው፣ የኦሮሞን ወይም አማሮች ጋላ የሚሉትን ነገድ ታሪክ በዝርዝር ለማስረዳት አይደለም ። ስለሆነ በ16ኛው መቶ ዘመን መጀመሪያ ይህ ነገድ ከደቡብ ኢትዮጵያ ወደ ሰሜንና ወደ ምስራቅ ጎርፎ የሚበዛውን ደጋ አገር ይዞ ስለሰፈረበት በዘመኑ ታሪክ ውስጥ የኦሮሞን ነገድ ፈንታ ሳናነሳው ያለፍን እንደሆነ የ16ኛው መቶ የኢትዮጵያ ታሪክ ሙሉ ሆኖ አይገኝም ።…

… ታሪክ ሲነጋጋ የኦሮሞ ህዝብ ከአደን ሰላጤና እስከ ቅርብ የእንግሊዝ ሱማሌ በሚባለው የሱማሌ ሪፐብሊክ አውራጃ መካከል ከሚገኘው የአፍሪካ ቀንድ በተባለው አገር ሲኖሩ ታዩ ። ኦሮሞዎች በየትኛው የታሪክ ዘመን በዚህ ምድር እንደሰፈሩ ግልፅ አይደለም ። … ይሁንና ከ10ኛው መቶ ዘመን በፊት ሱማሌ የተባለው ነገድ ከታጁራ ቤይ አቅጣጫ ተንቀሳቅሶ በኦሮሞዎች ላይ ጦርነት ባደረገ ጊዜ፣ መጀመሪያ የእንግሊዝ ሱማሌ የነበረውን አገር ለቀው ወደ ምስራቅ ደቡብ መጓዝ እንደጀመሩ ታውቋል ። ኋላም የአፍሪካ ቀንድ ከምትባለው ሶስት ማእዘን ወረዳ ተነስተው በዋቢ ሸበሌና በጁባ ወንዞች መካከል ቤናዲር በተባለው አውራጃ ሰፍረው በዚያ ብዙ ዘመን እንደኖሩ በጋሎች አፈታሪክ ሲነገር የኖረ ነው ። …

… ከሰሜን የሱማሌዎች ከደቡብ ባንቱዎች የሚያደርጉባቸው ጦርነት ምንም ጊዜም ሰላም የሰጣቸው አይመስልም ። ስለዚህ ከዚህም ከአዲሱ አገራቸው እንደገና መሰደድ ግዴታ ሆነባቸው ።
…ጋሎች ወላቡ፣ አበያ፣ ባሕርና ሕዲ ዳዲ ከሚባሉት አቅጣጫ የሰፈሩት በአስረኛው መቶ በዛጕዌዎች ዘመነ መንግስት መጀመሪያ ላይ ይመስላል ። … የኦሮሞ ህዝብ በሥጋና በወተት የሚመገብ ዘላን ስለነበር ድርቅ ከሆነው ከቤናዲር አውራጃ ተጉዞ ወላቡ ወይናደጋ በገባ ጊዜ ይህች ምድር ማርና ወተት ታፈሳለች እንደተባለችው እንደ ምድረ ከነአን የምትቆጠር ሁና አገኙዋት ። … በወላቡ ተራራና በአበያ ባህር አጥቢያ በኖሩበት ጊዜያት የሰላምና የጥጋብ የዕድገት ዘመን መሆኑን ሲወርድ ስዋረድ የመጣው የጋሎች አፈታሪክ አጋኖ ይገልፅልናል ። …

ኦሮሞዎች እላይ በተመለከተው አኳኋን በወላቡ ዙሪያ ብዙ ትውልድ ካሳለፉ በኋላ ከልክ ያለፈ ተራብተው ምድር ጠበባቸው ። … ከዚህም ሌላ በጥንት ዘመን ከቀድሞው መኖሪያቸው ከአፍሪካ ቀንድ ወግቶ ያስወጣቸው የሱማሌ ህዝብ፣ አስራ አምስተኛው መቶ ሲጋመስ ወይናደጋው ድረስ እየመጣ አዲሱን አገራቸውን መውረር ጀመረ ። በዚህ አኳኋን የኦሮሞ ህዝብ ለመከላከልና ለግጦሽ የሚፈልገውን መሬት አስፍቶ ለመያዝ ከሰላማዊ አኗኗር ወደ አርበኝነት ሃሳቡን መለሰ ። …ከወላቡ ሳይነሱ በገዳ ድርጅት ውስጥ የጦር ሠራዊትን ማከናወን ዋና ጉዳይ አድርገው ያዙት ። …በዚህ ዘመን ኦሮሞዎች ከረዩ፣ ቱለማ፣ ሜጫና፣ ወሎ በሚባል ባራት ትልልቅ ነገድ ተከፍለው ይገኙ ነበረ ። ስለዚህ ከረዩ የተባለው ነገድ፣ ባሌን ፈጠጋርንና ደዋሮን እንዲወር፣ ቱለማ ወደ ሰሜን ተጉዞ ዛሬ የሸዋ ጋላ ምድር የተባለውን እንዲይዝ፣ ሜጫ በስተ ምእራብና በስተደቡብ የሚገኘውን የእናሪያዎችን አገር እንዲወስድና፣ ወሎ የተባለው ነገድ በሸዋ በስተምስራቅ ተጉዞ ከወሎ አውራጃ እስከ ትግሬ የተዘረጋውን አንጎት የተባለውን አውራጃ እንዲይዝ የተቀየሰው ኦዳ ነቤ በነበሩ ጊዜ ነው ። …
ለጦርነት የተደረገው ድርጅት ከአለቀ በኋላ ኦሮሞዎች ዘመቻውን ፈጥነው አልጀመሩትም ። [ ዛሬ ኢሳያስ ወያኔን ለመበቀል የሚያሳየውን አይነት ትእግስት ይመስላል * የኔ] ይልቁንም በነዚህ ዘመናት ውስጥ ሱማሌዎች ክርስቲያናዊውን ኢትዮጵያ ለመውረር በትልቁ በመዘጋጀት ላይ ስለነበሩ፣ ምቹ ጊዜ ለማግኘት ኦሮሞዎች በትእግስት ጠበቁ ። በ1506 አም አነስተኛ ወረራ ወደሰሜን በሚገኘው ወረዳ ላይ ከአደረጉ በኋላ ጥቂት ገፍተው ቆሙ እንጂ ውጊያውን አልቀጠሉም ። … ስለዚህ በ1520ና በ1532 አም መካከል ግራኝ የኢትዮጵያን ደጋ ወሮ በአማራና በሱማሌዎች መካከል ሃይለኛ የሆነ ትግል ሲደረግ ጋሎች ያሰቡትን ለመፈፀም በፀጥታ ሲጠባበቁ ቆዩ ። …

እስከ 16ኛው መቶ ዘመን በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ድምፁን ሳያሰማ የቆየው የጋላ ነገድ በ1524 አም ከደቡባዊ መኖሪያው መንቀሳቀስ ጀመረ ። የዚህም እንቅስቃሴ አላማ ከዚህ በላይ እንደተመለከተው ሁሉ በደጋው የኢትዮጵያ አወራጃዎች ላይ ለመስፈር ነበር ። ”

እንግዲህ ከላይ በታላቁ ሰው ብእር ያነበብነው፣ ኦሮሞዎች ከየት ተነስተው ዛሬ የሚኖሩባቸውን ግዛቶች እንደያዙ ነው ። ገና 500 አመታት እንኳ ያላደረገ ታሪካዊ ክንዋኔ ነው ። ታዲያ የሶስት ሺህ አመት መንግስታዊ ታሪክ ባላት ሃገር ላይ፣ ታሪክ የሚጀምረው ከምንሊክ መስፋፋት ወዲህ ያለው ብቻ ነው የሚል ክርክር የት ያደርሳል? ፊንፊኔስ ብትሆን ከከብት አርቢዎች ሆራነት ወጥታ የአፍሪካ ዲፕሎማሲያዊ መናገሻ የሆነችው በመላ ኢትዮጵያውያን ትጋትና ድካም መሆኑ እየታወቀ፣ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ውስጥ ናት የሚል ወያኔአዊ ደባ ምን ይጠቅማል? የአምስት ሚሊዮን ነዋሪዎቿስ መብት ለምን ታገደ? ብዙ ጥያቄዎች አሉ ። መፍትሄዎችም እንዲሁ ።

አንዱ የሚታየኝ መፍትሄ ፣ አሁን ባለው ፌዴራላዊ አወቃቀር ውስጥ የአዲስ አበባ ነዋሪ ዜግነቱን የሚያገኝበት መንገድ ማፈላለግ ነው ። ለዚህም፣ ማዘጋጃ ቤቱን እንደ ማእከል ወይም መነሻ በመውሰድ፣ 150 ኪሎ ሜትር ሬዲየስ ያለውን ግዛት “የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል” ብሎ 10ኛ ክልል መጨመርና፣ ይህም ክልል በፌዴራል ምክርቤት ድምፅ እንዲኖረው ማድረግ ። ይህ ክልል የሁሉም ብሄረሰቦች የጋራ ክልል በመሆኑ፣ በምክርቤቱ ውስጥ ያለው ድምፅም ቢያንስ አንድ ሶስተኛውን የያዘ ቢሆን፣ ሃገሪቱን ማረጋገት ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረው ይመስለኛል ።

ይህ እቅድ ሶስት ችግሮች ይገጥሙታል ። አንዱ የሸዋን አማራ ከአማራ ክልል ያወጣዋል ። ሁለተኛው ችግር የኦሮሞን ክልል በምእራብና ምስራቅ ሁለት ቦታ ይከፍለዋል ። ሦስተኛው ችግር ደግሞ ጉራጌው የሚኖርበትን ከደቡብ ክልል ያስወጣዋል ። የአማራና ኦሮሞ ክልሎች ግን በወያኔ የፖለቲካ ፕሮዤ የተወጠኑ እንጂ፣ በታሪካዊ ወይም ውስጣዊ ፍላጎታቸው የተከለሉ አይደሉም ። ኦነግ ውስጥ የፖለቲካ ችግር በተነሳ ቁጥር፣ እስላምና ክርስቲያን፣ አርሲና ወለጋ እየተባባለ እንደሚቧደን ሁሌም የምንታዘበው ነው ። የአማራ ክልል ውስጥ የተካተቱም ህዝቦች፣ ከአማራነት ይልቅ ወሎዬነታቸው፣ ጎጃሜነታቸው፣ ጎንደሬነታቸውን ይበልጥ ያፈቅሩታል፣ ይወዱታልም። የወያኔ የዘር መድልኦ መባባስ ገና ወደፊት ይመስለኛል አማራ የሚባለውን ብሄር ቀጥቅጦ የሚፈጥረው ። ጉራጌው አዲስ አበባን ደክመው ከሰሯት ቀዳሚ በመሆኑ፣ ማእከላዊ ኢትዮጵያ ከልል ውስጥ ግባ ቢባል፣ ያን ቆንጆ ጭፈራውን ሲያቀልጠው በአይነ ህሊና ይታየኛል ። ሸዌው የኢትዮጵያ ማንነቱን አስቀዳሚ ሰለሆነ፣ ከኦሮሞና አማርነቱ በላይ ኢትዮጵያዊነቱን ያስቀድማል ብዬ መከራከር እወዳለሁ ። ስለሆነም ዜግነቱን የሚያሰከብርለት የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቢያገኝ የሚያሰማው እልልታና ሆታ፣ የፈረሱ ኮቴ በእዝነ ህሊናዬ እያደመጥኩት ነው ።

ስለሆነም የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መፈጠር፣ ኦሮሞውን ቢያንስ ወደ ሁለት ክልል፣ አማራውን ደግሞ ወደ ሶስት ሊከፍለው ይችላል ። ይህ ግን ለተሻለ አስተዳደርና ልማት ጥርጊያውን ሰለሚከፍት ጥሩ ሃሳብ መስሎ ይሰማኛል ። አሁን ያለውንም የአዲስ አበባ ማሰተር ፕላን ችግር ከስር መሰረቱ ይፈታዋል ብዬ አስባለሁ ። አዲስ አበባንም ለፖለቲካ ተንኮል ተብሎ ከተጣለባት የአንድ ብሄር ክልል ውስጥ የመወርወር አደጋ ይታደጋታል ። የኢትዮጵያ ብሄርተኝነትም ዙሪያውን በከበቡት የኦሮም፣ የጉራጌ፣ የአማራ ገበሬዎች እየታገዘ፣ ከሸገር በሚፈልቀው የመላ ኢትዮጵያውያን ባህላዊ መስተጋብርና ፍቅር እየተመራ፣ የኢትዮጵያን ቀጣይነት ያረጋግጣል ብዬ አስባለሁ ። ይህ ለብዙ ወራት ተጨንቄ ያቀረብኩት ሃሳብ በመሆኑ ለማውገዝ አትቻኮሉ ። እሰኪ እንደኔ ተጨነቁበት ።

በተለይ አዲስ በቀል የሆናችሁት የትግራይ ከበርቴዎች፣ የሃገር መረጋጋት የሚፈጥረው ጥቅም ተጠቃሚ ስለሆናችሁ ፣ ከመለስ የስልጣን ተንኮሎች ባሻገር፣ ለልጆቻችሁ የምታወርሱት ሃገርና ንብረት እንዲኖራችሁ፣ የሚቀርቧችሁን የወያኔ መሪዎች ከሃገር ማጥፋት እኩይ ተግባርና ከዘረኝነት እንዲርቁ ምከሩ ። ይህን ማድረግ አቅቷችሁ እስካሁን እንደተያዘው ተቃውሞን በጥይት ማጥፋት ይቻላል ብላችሁ ከገፋችሁበት፣ እንኳንስ ሃገር፣ መሰደጃ ስንኳ አታገኙም ። ከቀዬው የነቀላችሁት ስደተኛ “የኒዮ ሊበራሊዝም ጠበቆች” እያላችሁ በምታወግዟቸው አለምአቀፍ መያዶች እየታገዘ ያድናችኋል። ከዚህ ይሰውራችሁ ። ለሃገር የሚበጅ መላ ምቱ። ይህችን ቅድስት ድሃ ሃገር የሁላችን እናድርጋት ። ታላቁ ትግራዋይ ኢትዮጵያዊ ገብረሕይወት ባይከዳኝ ከመቶ አመታት በፊት እንደፃፈው “ጠንካራ መንግስት ከህዝብ ልብ ይቀዳል”

The post የአዲስ አበባ ነዋሪ ዜግነቱን እንዲያገኝ መፍትሄው “የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል” ብሎ 10ኛ ክልል መጨመር – ያሬድ ጥበቡ (ጌታቸው ጀቤሳ) appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live