Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በምእራብ ኢትዮጵያ ቶንጎ አካባቢ ሌሊቱን ውጊያ ሲደረግ ማደሩ ተሰማ

$
0
0

(ምኒልክ ሳልሳዊ) በምእራብ ኢትዮጵያ በቤንሻንጉል ክልል ደቡባዊ አቅጣጫ ቶንጎ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በታጣቂ ሃይሎች እና በወያኔ ወታደሮች መካከል ለሊቱን ከባድ ውጊያ መደረጉን ለታጣቂ ሃይሎቹ ቅርብ ነን ያሉ ምንጮች ከማላካል አስታውቀዋል::
news
ከደቡብ ሱዳን ማላካል ተብሎ ከሚጠራው አከባቢ ተነስተው በምእራብ የኢትዮጵያ ድንበር ከሚገኙት የወያኔ ሰራዊት ጋር ውጊያ የገጠሙት ታጣቂ ሃይሎች በስርአቱ በደል ደርሶባቸው የሸፈቱ እንደሆነ ምንጮቹ ሲገልጹ ለሊቱን ከባድ ውጊያ ያካሄዱ ሲሆን ከታጣቂ ሃይሎቹ 26 ሰውች መሰዋቱን ምንጮቹ ተናግረዋል::

በጋምቤላ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በስርአቱ ከባድ በደል እየደረሰባቸው ሲሆን ምንም አይነት የልማት መዋቅር ካለመዘርጋቱም በላይ ከየአከባቢያቸው እየተፈናቀሉ መሬታቸው ለውጪ ባለሃብት እንዲሁም ከትግራይ መጥተው ለሰፈሩ አልሚዎች ለተባሉ የትግራይ ተወላጆች እየተሰጣብቸው ለስደት ለስራ አጥነት እና ለድህነት ተዳርገዋል::እነዚህ የስርአቱ በደል አንገሽግሿቸው ደቡብ ሱዳን ጫካ በመግባት ራሳቸውን ያደራጁ ታጣቂ ሃይሎች የወያኔን ወታደሮች መዋጋታቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል::

የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለነጻነቱ እና ለመብቱ በሚያደርገው ትግል በአንድነት መነሳት አለበት አለበት ያሉት ምንጮቹ ራሳችንን ከበደል እና ከብዝበዛ ለማዳን ጠንክረን ልንታገል ይገባል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል::

The post በምእራብ ኢትዮጵያ ቶንጎ አካባቢ ሌሊቱን ውጊያ ሲደረግ ማደሩ ተሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.


በአሜሪካ የሶስት ሙስሊም ተማሪዎች መገደልና ከበስተጀርባዉ ያለዉ መንስኤ ሲቃኝ –ወቅታዊ ጥንቅር በሳዲቅ አህመድ (በድምጽ)

$
0
0

በአሜሪካ የሶስት ሙስሊም ተማሪዎች መገደልና ከበስተጀርባዉ ያለዉ ያለዉን መንስኤ ሲቃኝ
ወቅታዊ እና ጥናታዊ ፕሮግራም በሳዲቅ አህመድ


(ሳዲቅ አህመድ)

(ሳዲቅ አህመድ)

The post በአሜሪካ የሶስት ሙስሊም ተማሪዎች መገደልና ከበስተጀርባዉ ያለዉ መንስኤ ሲቃኝ – ወቅታዊ ጥንቅር በሳዲቅ አህመድ (በድምጽ) appeared first on Zehabesha Amharic.

(ዜና ፎቶ) የባለ 5 ቢሊየን ዶላሯ ሰምሃል መለስ ዜናዊ በመቀሌ

$
0
0

Semhal-Meles-deposit-check
ስንታየሁ ከሚኒሶታ

በአንድ ወቅት በ እንግሊዝ ሃገር የሚኖሩት ዶ/ር ወንድሙ መኮንን የቼኩን ኮፒ አያይዘው ባቀረቡት ማስረጃ በኒውዮርክ ውስጥ በሚገኝ ባንክ በ2011 ዓ.ም 5 ቢሊዮን ዶላር እንዳስገባች ያጋለጧት የአቶ መለስ ዜናዊ ልጅ ወ/ሪት ሰምሃል መለስ ሰሞኑን በሶሻል ሚድያዎች ላይ የሕወሓትን 40ኛ ዓመት በማስመልከት ብቅ ብላ መታየት ጀምራለች:: ዶ/ር ወንድሙ የ5 ቢሊዮን ዶላር ጉዳይ ቼኩን አያይዘው ለ እንግሊዝ ፓርላማ ሃውስ ኦፍ ኮመንስ እንዳቀረቡት የተገለጸ ሲሆን ከዛ በኋላ ጉዳዩ ምን ላይ እንደደረሰ አልታወቀም::

ሰምሃል መለስ ዜናዊ ሰሞኑን እንዲህ በፎቶ እንደምታይዋት በሕወሓት 40ኛ ዓመት ላይ ታይታለች::
semhal meles

The post (ዜና ፎቶ) የባለ 5 ቢሊየን ዶላሯ ሰምሃል መለስ ዜናዊ በመቀሌ appeared first on Zehabesha Amharic.

“የምኖረው ለልጆቼ ነው”–አርቲስት ገነት ንጋቱ

$
0
0

የዛሬዋ እንግዳ በሀገራችን አሉ ከሚባሉ ሁለገብ አርቲስቶች መካከል አንዷ የሆነችው አርቲስትና ጋዜጠኛ ገነት ንጋቱ ነች፡ ፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል የመጀመሪያ ዲግሪዋን ካገኘች በኋላ በጋዜጠኝነት ፣ በትወናና ዝግጅት በርካታ ስራዎችን ሰርታለች፡፡ በይበልጥ ግን በብዙዎች ልብ ውስጥ ለመግባት ያስቻላት ‹ውሳኔ› የተሰኘው ፊልም ሲሆን በ ‹ሰው ለሰው› ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማም ድንቅ ብቃቷን አሳይታለች፡፡ ጋዜጠኛና አርቲስት ገነት ንጋቱ ‹ገነት የኪነጥበብ ፕሮሞሽን› የተሠኘ የማስታወቂያ ድርጅት ያላት ሲሆን በFM 96.3 ሬድዮ ጣቢያ ይተላለፍ የነበረ ‹አሸወይና› የተሠኘ ፕሮግራም ታቀርብ ነበር፡፡ ከቁምነገር መጽሄት ጋር ተጨዋውታለች::
Genet
ቁም ነገር፡- ከተጫወትሻቸው ገጸ-ባህሪያት ውስጥ ውስጥሽ የቀረ ንግግር የቱ ነው?
ገነት፡- ውሳኔ ፊልም ላይ ልጆቼን (የፊልሙን ልጆች ) ለተለያዩ አሳዳጊዎች ለመስጠት የወሰንኩበት ምሽት ላይ የነበረውን ንግግርን ከትወናው በጣም አስታውሰዋለሁ፡፡ ልጆቹ በጋራ ምግብ እየበሉ ሁለቱ ወንዶች ልጆች በአጥንት ሥጋ ይጣላሉ ፤ ያንን ያየችው እናት ‹እኔ በህይወት እያለሁ እንደዚህ የሆናችሁ ሳልኖር ምን ልትሆኑ ነው? › ስትል የት ልትሄድ እነንደሆነ ከልጆቿ ለቀረበላት ጥያቄ ስትመልስ ‹‹ እሩቅ ሀገር ፤ ሁላችሁም አንድ ቤት ትሄዳላችሁ ፤ በጣም የሚወዷችሁ እናትና አባት ፡፡ ጥሩ ቤት ፣ጥሩ ልብስ፣ ጥሩ ተውምህርት…….›› እያለች በእንባ ስርቅርቅ የሚቋረጥበት ቦታ ሁሌም በውስጤ አለ፡፡

ቁም ነገር፡- ወላጆች ለልጆቻቸው ማውረስ አለባቸው የምትይው ትልቁ ነገር ምንድነው?
ገነት፡- በራስ መተማመን ፤ፍቅርና ትምህርት ፡፡ ልጆች ሦስቱን ነገር በሚገባ ከያዙ የራሳቸው ጌቶች ይሆናሉ፡፡ ፍቅር ቤተሰባዊና ማህበራዊ ህይወታቸው ውስጥ ቀስ በቀስ የሚገነባ ነው፡፡ ወንድምና እህቶች እርስ በርሳቸው እንዲዋደዱና እንዲተሳሰቡ ከተደረገ ከማህበረሰቡ ጋርም ሲቀላቀሉ ፍቅር እንጂ ሌላ ተቀጽላ ባህሪ አያሸንፋቸውም ፡፡ ምክንያቱም ፍቅር ከቤት ከጓዳ ይጀምራል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ትምህርት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ትርፉ ብዙ ይሆናል ፡፡ይህ በየትኛውም ቦታና ጊዜ ቢቀርብ ለድርድር የማይቀርብ ነገር ነው፡፡ ብርሃን ፈንጣቂ አማራጭ የሌለው በራስ የመተማመን መሰረት ነው፡፡ ትምህርትና ፍቅር በለጋ ዕድሜያቸው ላይ ከመገብናቸው በስተእርጅናቸውም አይቸገሩም፡፡ ከእግዚያብሔር ጋር ሁሌም አሸናፊ ይሆናሉ፡፡ ቀና ብለው መሄድም ይችላሉ፡፡

ቁም ነገር፡- የሴት ልጅ ዕድሜና የወንድ ልጅ ደሞዝ አይጠየቅም የሚባለው ለምንድን ነው?
ገነት፡- እም…. ምናልባት ስለምንፈራ ይሆን? አንዳንዴ ከእግዜር ጋር ሁላ የሚያጣላ ይመስለኛል፡፡ ‹ይሄን ያህል ዕድሜ ስለሰጠኸኝ አመሠግናለሁ› ማለትን የምንፈራ ሁላ ይመስለኛል፡፡ ዕድሜ ሰጭና ነሺም እሱ እያለ ፣እኛ የሱን ሀብትና ስጦታ ለመናገር አለመፈለግ ሁሌም ነው እንቆቅልሽ የሚሆንብኝ! እንደሚታወቀው በእያንዳንዱ ዓመት አንድ አንድ ዓመት እድሜአችን ላይ መደመራችን እንደሆነ የተፈጥሮ ሕግ ነው፡፡ የወንድ ልጅ ደመወዝ አይጠየቅም ላልሽኝ እኔም “ለምን አይጠየቅም ?” የሚል ጥያቄ ነው የማነሳው፡፡ በነገራችን ላይ ይህን አባባል ማን እንዳለው ባውቅ ኖሮ መልሼ
እሱን /እሷን እጠይቅ ነበር፡፡

ቁም ነገር፡- መጀመሪያ የትወና ሥራ የጀመርሽው የት ነበር?
ገነት፡- በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል የመጀመሪያ ዲግሪዬን በምሰራበት ጊዜ ነው የሰራሁት፡፡

ቁም ነገር፡- ቆጮ እንዴት ይዘጋጃል
ገነት፡- በነገርሽ ላይ የቆጮ አፍቃሪ ናቸው ከሚባሉት ሰዎች መሃል አንዷ ነኝ፡፡ በልጅነቴ አሰላ እያለሁ በግቢያችን ውስጥ ይዘጋጅ ነበር፡፡ እድሜ ጠገብ የሆነ የኮባ ተክል መረጣ ጀምሮ ፣ አቆራረጡን፣ እግር ሰቅሎ በመክተፊያ ላይ የሚደረገውን የአፋፋቅ ሁኔታ ፣ የጉድጓድ አዘገጃጀት እና አቀባበር ፣ የተብላሎት እድሜውን፣ ለመጋገር ሲፈለግ ከጉድጓድ ወጥቶ እንዴት ተከፍቶ እና ቃጫው ወጥቶ ንፁህ ሊጥ የሚገኝበትን ጊዜ በሂደት ልነግርሽ እችል ነበር፡፡ ጊዜ ስለሌለን እንለፈው እንጂ፡፡ ሊጡ ከወጣ በኋላ በሚገባ ውሃ ጠብ እየተደረገ ከታሸ በኋላ በኮባ ወይም በገጠር አካባቢ በራሱ የቆጮ መጋገሪያ ስጋጃ ላይ ተጠፍጥፎ ወይ በኤሌክትሪክ ምጣድ አልያም በብረት ምጣድ የሚጋገርበት ሂደትን በሚገባ ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡

ቁም ነገር፡- ገነትን ምን ያዝናናታል?
ገነት፡- ከልጆቼ ጋር የማሳልፈው ጊዜ ለእኔ ዓለምን የጨበጥኩ እስኪመስለኝ ድረስ በደስታ፣ በእርካታ የምቦርቅበት ጥዑም ጊዜዬ ነው፡፡ ከወላጆቼ፣ ከወንድምና ከእህቶቼ ጋር የማሳልፈውንም ጊዜ እደሰትበታለሁ፡፡ አረንጓዴ የበዛበት ተፈጥሮአዊ ቦታ መኪና ነድቼ በመሄድ ብቻዬን በተመስጦ በሃሳብ የማሳልፈውን ጊዜ ማን ይቀማኛል? . . . . በጣም እወደዋለሁ፡፡ በወረቀት መሀል ተከብቤ መቀመጥም እንዲሁም መዝናኛዬ ነው፡፡ ትወናም እግዜር ለመዝናኛዬ አስቦ የሰጠኝ ሌላው መክሊቴ መሆኑ እግዜርን የማመሰግንበት አጋጣሚ ይፈጥርልኛል፡፡

ቁም ነገር፡- ልጆቼ ባይጠይቁኝ እመርጣለሁ የምትይው ጥያቄ አለ?
ገነት፡- ልጆቼ የፈለጉትን የመጠየቅ መብት እንዳላቸው የማምንና በወቅቱም በደስታ መልስ የምሰጥ እናት ነኝ፡፡ ነገር ግን ከጥያቄ ከምትይኝ እርስ በእርሳቸው እየተጣሉና እየተደባበደቡ ለስሞታ ወደ እኔ የሚመላለሱበት የድግግሞሽ ሰዓት አጥብቄ እጠላዋለሁ፡፡ ልጅ ሆኜ ከወንድሞቼ ጋር እየተደባደብኩኝ እናትና አባቴን ምን ያህል እንዳታከትኳቸው እንዳስብና ለትዕግስታቸውም ክብርና አድናቆትን እንድሰጣቸው ያስገድደኛል፡፡ በተለይ ሐሳቤን በሰበሰብኩበትና በንባብ ወይም በድርሰት ፅሁፍ ላይ እያለሁ ሲሆን፤ ንዴቴ በእጥፍ ይጨምራል፡፡ ግን በቃ እናት አይደለሁ! የመቻል ሞራላዊና ፍቅራዊ ግዴታ ስላለብኝ ለማቻቻል እሞክራለሁ፡፡

ቁም ነገር፡- ስምንተኛው ሺህ ሲገባ ዓለም ትጠፋለች በሚለው ታምኛለሽ?
ገነት፡- እሱ ነገር ልጅ ሆኜ ጀምሮ ስሰማው ነው ያደግኩት! እስካሁን አላለፈም እንዴ? መቼም ያለፈ ይመስለኛል፡፡ በነገራችን ላይ ስምንተኛው ሺህ ማለት የዓለም መጨረሻ ነው፡፡ ለእኔ እንደገባኝ የዓለም መጨረሻ ማለት ደግሞ የምድራዊው ዓለም መጨረሻ ነው፡፡ ከዛ ሰማያዊው ዓለም ይቀጥላል፡፡ እንደሚመስለኝ ሰዎች ስምንተኛው ሺህ የሚሉት የምድራዊ ዓለም መጨረሻን ጊዜ ነው፡፡ የክርስቶስ መምጣትን፡፡ ክርስቶስ ደግሞ ድንገት እንደ ሌባ ነው የምመጣው ስላለ ስምንተኛው ሺህ መቼ እንደሆነ ማወቅም መገመትም አይቻልም፡፡ ያኔ ግን ዓለም ትጠፋለች ማለት ሳይሆን አሁን የምንንኖረው ምድራዊ ህይወት አይኖርም ማለት ነው፡፡ ይሄ የዓለም መጥፋት ከሆነ ትርጉሙን አንቺ እንደዛ በይው፡፡

ቁም ነገር፡- ደስታ እንዴት ይገኛል?
ገነት፡- አንቺ አዕምሮ ውስጥ፡፡ ለኔም አዕምሮዬ ውስጥ ነው፡፡ ለነ እርሱም አዕምሮአቸው ውስጥ ነው ያለው፡ ፡ ደስታን ከገበያ ገዝተሽ አትደሰችበትም፡፡ ሁላችንም ባለን ነገር መደሰት ከቻልን ፣የምንደሰትበትን ቦታና ጊዜ ከመረጥን ደስታ የኛ ነው፡፡ ሁላችንም በመዳፋችን ጨብጠን የምንዞረው የቀና አስተሳሰባችን ውጤት ነው፡፡ ለእንካ ሰላምትያው፣ ለትርኪሚርኪውና፣ ለመንደርተኛው አስተሳሰብ ቦታ ካልሰጠን የደስታችንን አጥር አጥብቀን ከያዝነው ደስታ ከዚያ ነው፡፡

ቁምነገር፡- ምን ያህል ዓመት መኖር ትፈልጊያለሽ?
ገነት፡- የእግዜሩን ለእግዜር ትቼ፤ እኔ መኖር የምሻው ልጆቼን አስተምሬና ለቁም ነገር አብቅቼ ኃላፊነቴን ከትከሻዬ እስከማወርድበት ጊዜ ነው፡፡ እስከዚያ እግዜር ጨክኖ ባይወስደኝ ደስ ይለኛል፡፡ እኔ ለልጆቼ ነው የምኖረው፡ ፡ ከዚያ ለእናትና አባቴ፤ ለምን ብትይኝ እነሱ ቀደም ሲል ለእኔና ለወንድም እህቶቼ ሲሉ ብዙ ዋጋ ከፍለዋል፤ ዕድሜም ለምነዋል፡፡ የእኔ መኖር በእነሱ ዕድሜ ላይ በጎ ተጽእኖ አለው፡፡ አየሽ ልጅ ከመጣ በኋላ መኖር ያጓጓል ፡፡ እነሱ መርጠውኝ ሳይሆን በእኔ ፈቃድ ምድር ላይ ለመጡ ልጆቼ ከእግዜር ቀጥሎ የማኖር ፣የማድረግ ፣ለቁም ነገር የማብቃት የእነዚህ ሁሉ ነገሮች ዋስትና በእኔ እጅ ስላለ ይዤባቸው ቶሎ አልሙትባቸው፡፡

ቁም ነገር፡- በሃገራት ስም የሚጠሩ የሰው ስሞችን የትኞቹን ታውቂያለሽ?
ገነት፡- እ . . . እየሩሳሌም፣ ኢትዮጵያ፣ ኤደን፣ ቻይና፣ አፍሪካ(ይሄ ከአህጉር መሆኑ ነው) አስመራ ወዘተ. . . ይሄ የተናገርኩት አይበቃም? ክፍል ውስጥ ለፈተና የተቀመጥኩኝ አስመሰላችሁኝ እኮ ሆ!
Mogachoch

ቁም ነገር፡- የኔ ድክመቴ ነው የምትይው ነገር ምንድነው ጥንካሬሽስ
ገነት፡- ድክመቴ ለልጆቼ ስል የማላምንበትን ነገር ሁሉ ላደርግ እችላለሁ፡፡ ከወንጀል በስተቀር ማለቴ ነው፡፡ እነሱን የሚያስደስታቸው ነገር ከሆነ እንደሻማም ቀልጬ ባልቅ ህመሙ የሚሰማኝ አይመስለኝም፡፡ ልጆቼ እንደ ልባቸው የሚያዙኝ እናት ነኝ፤ አንዳንዴ ትዕዛዛቸው የግል እምነቴንና አቋሜን ሁሉ ቀስ በቀስ ሲሸረሽርብኝ ይታወቀኛል ፡፡ በራሴ ላይ በግርምት እስቃለሁ፡፡ በቃ ምን አደርጋለሁ እኔ ደግሞ አንዲት ኢትዮጵያዊ እሩህሩህ እናት ነኝ፡፡ ጠንካራ ጎኔ ነገሮችን እንደ አመጣጣቸው በተለያዩ በጎ በጎ ትርጉሞች በመለወጥ የመመለስ ፍጥነቴን እንደ
አንድ ጥንካሬ አየዋለሁ፡፡ ብዙ ሰዎችን የጎዳ፣ ያቆሰለ፣ ያሳዘነ ነገር ገነት ጋር ሲደርስ ተራና ጊዜ ሊሰጠው የማይገባ ጉዳይ ይሆናል፡፡ ቀለል የማድረግ ብቃቴ ከአባቴ የወረስኩት ባህሪ ይመስለኛል፡፡ አባቴ ጠንካራና ብልሃተኛ ነው፡ ፡ ሁሌም ቢሆን ለነገሮች ትኩረትና ጊዜ በሰጠሽ ልክ ነው የምትናደጅውም የምትደሰችውም፡፡ ከአባቴ ይህንን ተምሬያለሁ፡፡

ቁም ነገር፡- የፊልም ስራ አትራፊ ነው አትራፊ አይደለም?
ገነት፡- አትራፊም ነው፡፡ አትራፊም አይደለም፡፡ አገሩን እንደሚወድ ፕሮፌሽናል ባለሙያ ካሰብነው ፊልም የአገር ገጽታን፣ ባህልን፣ ቋንቋና አጠቃላይ የአኗኗር ስርዓትን አሳማኝና አስደማሚ በሆነ መንገድ ደግሞም በቦታና በጊዜ በማይገደብ ደረጃ ለትውልዶች ሁሉ የሚሸጋገር እሴት እንዲኖረው ተደርጎ መሰራት አለበት፡፡ ከዚያ በኋላ ለገበያ ሲቀርብ የአትራፊነቱ ጥያቄ የሚወድቀው ለፕሮሞሽን እንደሚከፈለው ዋጋ ወይም እንደሚሰጠው ጊዜ ይለያይ ይሆናል፡፡ ፕሮሞሽን ላይ የበረታ ፕሮዲውሰር ያተርፋል እንጂ አይከስርም፡፡

ቁም ነገር፡- ባላደርገው ኖሮ ይቆጨኝ ነበር፤ የምትይው ነገር ምንድን ነው?
ገነት፡- ባልወልድ ኖሮ በደንብ ይቆጨኝ ነበር፡፡ በእርግጥ ልጅ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው ለእኔ ደግሞ የልቤን መሻት ሰጥቶኛል፡፡ ዩኒቨርስቲ ባልገባ ኖሮ በጊዜ ነበር የምወልደው፤ የሚገርምሽ ልጆቼ አድገው ለእናት አባታቸው ሲያስቡ፣ ሲጨነቁና እኛን ለማስደሰት ጥረት ሲያደርጉ ሳይ ደጋግሜ “ባልወልዳችሁ ነበር የሚቆጨኝ” ብዬ የልቤን እውነት በቀልድ እያዋዛው እነግራቸዋለሁ፡፡

ቁም ነገር፡- ሐውልትሽ ላይ እንዲጻፍ የምትፈልጊው ነገር ምንድን ነው?
ገነት፡- እንዴ! ሐውልትሽ ስትሉኝ እኮ ሞቴን እያስታወሳችሁኝ ነው፤ ምናለ ትንሽ ብትታገሱኝ?
ቁም ነገር፡- ለማለት የፈለግኩት አልገባሽም ?
ገነት፡- አ….አ… ተይው ገብቶኛል፡፡ ለቀልድ ያህል ነው /ሳቅ…../፡፡ ምን ተብሎ ቢጻፍ እ. . ./እንደማሰብ/ “ለልጆቿ ኖራ፤ ለልጆቿ የሞተች ምርጥ እናት!” ቢባልልኝ አይከፋኝም፡ ፡ ምክንያቱም አሁን ላይ የምኖረው ህይወት በተለይ በእነሱ ፍላጎትና ትዕዛዝ ላይ ያተኮረ በመሆኑ የውስጤን እውነት የሚገልጽልኝ ይመስለኛል፡፡
Mogachoch

ቁም ነገር፡- በአሁኑ ጊዜ የጋብቻውን ያህል ፍቺው በዝቷል፡፡ ለዚህ ምክንያቱ በአንቺ አመለካከት ምን ይመስልሻል?
ገነት፡- በአደባባይና በጓዳ ውስጥ ያለው ማንነታችን እንደ ሳንቲም ግልባጭ
መለያየቱ ብልሽስ ? በፍቅረኝነት ዘመን ብዙ ነገር ግልጽ አይሆንም፤ ፍቅር ፍቅር እንጂ ገበና ለገበና ተገላልጦ መተዋወቅ አይታሰብም፡፡ ፍቅር ደግሞ በአደባባይ ይጣፍጣል፡፡ ያንን ይበልጥ ለማጠናከር በመጓጓት ለመኖር ይወሰናል፤ መኖርም ይጀመራል፡ ፡ ያኔ ታዲያ እርቃን ማንነታችን፣ ድብቅ ባህሪያችን ቀስ በቀስ ሲወጣ አለመግባባት ይፈጠራል፡፡ በመሰረቱ ሁለት በተለያዩ ማህበረሰብ ውስጥ ያደጉ ሰዎች በአንድ ቤት ውስጥ ሲገናኙ መጋጨታቸው አይገርምም ፡፡ የትዳር ምስጢር ያለው እዚህ ጋር ነው፡፡ ፍጹምነት ከጓደኛችን መጠበቃችን ነው ለፍቺ የሚያበቃን እንጂ የትዳር ሚስጢሩ ረቂቅ ነው፡፡ ትዳርን እርስ በእርስ በግልጽነት ላይ ከገነባነው የትዳርን ምስጢር ለሶስተኛ ሰው አሳልፈን ካልሰጠን፣ ቤታችንን ትተን የሌላ ባለትዳሮች አድናቂ ካልሆንንና ሁሌም ማደስ ከቻልን ፍቺ የት ያገኘናል?

ቁም ነገር፡- በህይወትሽ ደግሞ እንዳይመጣ የምትፈልጊው ቀን አለ?
ገነት፡- የመጀመሪያ ልጄን ስወልድ ስቃይ ብቻ ሳይሆን ወደ ሞት አምርቼ ዳግም ነፍስ የዘራሁበት ጊዜ ስለነበር ደግሞ አይምጣብኝ፡ ፡ ደግሞ ቢመጣብኝ ደስ የሚለኝ ቀን ደግሞ፤ በስቃይ የወለድኳት ቆንጅዬዋን ልጄን፤ ከህመምና ስቃይ ጋር ግብ ግብ ፈጥሬ ቀና ብዬ አይቼ ሳም አድርጌ “ስታምር!” ያልኩበትን የእርካታ ጊዜ አቤት ደስታዬ !

ቁም ነገር፡- ሁለገብ አርቲስት መሆን ጥቅሙ ምንድነው? ጉዳቱስ ?
ገነት፡- ጥቅሙ ብዙ ነው፡፡ ሁለገብነት የተለያዩ አማራጭ የስራ መስኮች የመፍጠር አቅምን ያመለክታል፡፡ ለምሳሌ ወደ እኔ ብትመጪ በድርሰቱ ባይሳካልኝ ዝግጅት አለልኝ፡፡ በዝግጅት ውጤታማ ባልሆን፤ ትወናው ይጠብቀኛል፡ ፡ ትወናው ይቅርብኝ ብል ደግሞ ጋዜጠኝነቱ የኔ ነው፡፡ ታዲያ ምን ጉዳት ይኖረዋል ትያለሽ? ከጥቅሙ በቀር ጉዳትስ የለውም፡፡

ቁም ነገር፡- አንድ ሰው ስንት ጊዜ ያፈቅራል? አንቺስ ስንት ጊዜ ፍቅር ያዘሽ?
ገነት፡- ነፍሱ እስከፈቀደችለት ድረስ ቢያፈቅር ምን አለበት? አመንዝራነት እንለዋለን እንጂ ፍቅርን አንገድበውም፡፡ ይህ እኮ የነፍስ ምስጢር ነው፡፡ ካልኩሌሽን የለውም፡፡ ወደ እኔ ከመጣሽ ከልጆቼ አባት ጋር አንድ ሶስት ጊዜ አላፈቀርኩም ብለሽ ነው ፡፡ ፍቅር ስቃዩ ጣፋጭ ነው፤ የኔው ፍቅር ደግሞ ሂደትም ውጤትም አለው፡፡

ቁም ነገር፡- ህይወትሽን የምትመሪበት የራስሽ የሆነ ፍልስፍና አለ?
ገነት፡- የኔ ፍልስፍና በዋናነት ‹‹ሁሉም ነገር ለበጎ ነው ነው›› የሚለው ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ‹‹አንኳኩ ይከፈትላችኋል ፤እሹ ታገኛላችሁ›› ነው፡ ፡ በእያንዳንዱ ቀን ውሎዬና አዳሬ ህይወትን በነዚህ ፍልስፍናዎች መነፅር ውስጥ ማየት ችያለሁ፡፡
ቁም ነገር፡- አመሠግናለሁ፡፡

The post “የምኖረው ለልጆቼ ነው” – አርቲስት ገነት ንጋቱ appeared first on Zehabesha Amharic.

በቬጋስ የህብር ሬዲዮን 5ተኛ ዓመት ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባጎልድኮስት ሆቴል እንዲካሔድ ባለመፈቀዱ ወደ ሐምተን ኢን ሆቴል እንዲዛዋወር ተደረገ

$
0
0

unnamed (1)ዛሬ ከላስቬጋስ አልፎ በመላው አለም ተደማጭ የሆነው የህብር ሬዲዮ፤ 5ተኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ በመጭው ረቡዕ ፊብርዋሪ 25ቀን2015 በቬጋስ ጎልድ ኮስት ሆቴል ያቀደውን ታላቅ ስብሰባ ሆቴሉ  ረቡዕ ማካሄድ አይቻልም ብሎ በመሰረዙ፤ በዚያው በቬጋስ ወደሚገኘውሐምፕተን ኢን ሆቴል በዕለቱ በተመሳሳይ ሰዓት እንደሚያካሂድ የህብር ሬዲዮ ዝግጅት ክፍል ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ ገለፀ።

የአድዋ ድል 119 ዓመት በሚዘከርበት፣ ወቅታዊ የአገር እና የጤና ጉዳይ ዋና መወያያ በሆነበት፣ በዚህ ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ አቶ ኦባንግሜቶ ከካናዳ፣ የዘ-ሐበሻ ድህረ ገፅና ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሄኖክ አለማየሁ ከሚኒሶታ፣ እውቁ ዩሮሎጂስት / ሙሉጌታ ካሳሁን ከቬጋስበሚገኙበት፤ አቶ ኪዳኔ አለማየሁ የዓለም አቀፍ ፍትህ የኢትዮጵያውያን ጉዳይ ዋና ስራ አስኪያጅ የሚሳተፉበትን ይህን ስብሰባ ሐሙስ እንጂረቡዕ ሊካሄድ አይችልም ሲል አስቀድሞ የተገባውን ውለታ አፍርሶ ዝግጅቱን ሰርዟል።በዚህ ከአቅማችን በላይ በሆነ ምክንያት የስብሰባውንቦታ በዕለቱ በሐምተን ኢን ሆቴል ለማድረግ ተገደናል።

ጎልድ ኮስት ሆቴል ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ፌብርዋሪ 12/ 2015 በላከው የስልክ መልእክት የህብርን 5ተኛ ዓመት ዝግጅት የሰረዘ መሆኑንአሳውቀውናል። ከዚያ በኋላ በተደረገው ውይይት ረቡዕ ስብሰባው አለመደረጉ በህብር ላይ ጉዳት ያደርሳል ብለን ገልጸናል። በዚህ ሳቢያዝግጅቱን በመጭው ዕረቡ በቬጋስ ትሮፒካናና ዲን ማርቲን ላይ በሚገኘው ሐምፕተን ኢን ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚካሄድ የህብርዝግጅት ክፍል ገልጿል።

የህብር ሬዲዮ 5ተኛ ዓመት በዋነኛነት የሚመጡ እንግዶች ባሉበት  ስብሰባውን በተሳካ መንገድ ማድረግ ነው የወቅቱ ትኩረታችን የሚለውየህብር ሬዲዮ መግለጫ ባለፈው ዓመት በጎልድ ኮስት ሆቴል 4ተኛ ዓመታችንን ፌብርዋሪ 26/2014 በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን አስታውሷል።

ህብር ሬዲዮ የወቅታዊ መረጃ ምንጭ በመሆን በወቅታዊ አገራዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ፣በኢኮኖሚ፣ በጤና እና በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ላይሰፊ ትኩረት በመስጠት አቅም በቻለው መጠን የአማራጭ የሚዲያ ተግባሩን እያከናወነ መቆየቱን ይሔው መግለጫ ጠቅሶ /ሰቡ በቬጋስናበአካባቢው የሚኖሩ የኢትዮጵያ ወዳጆች በመጭው ረቡዕ ፌብርዋሪ 25 ቀን 2015 5 ፒኤም ትሮፒካናና ዲን ማርቲን ላይ በሚገኘውየሀምፕተን ኢን ሆቴል በሚካሄደው በዚህ ታላቅ ስብሰባ ላይ በመገኘት የተሳካ ዝግጅት እንዲደረግ  የህብር ሬዲዮ አጋር እንዲሆኑ መግለጫውጥሪውን አስተላልፏል።                              

The post በቬጋስ የህብር ሬዲዮን 5ተኛ ዓመት ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባጎልድኮስት ሆቴል እንዲካሔድ ባለመፈቀዱ ወደ ሐምተን ኢን ሆቴል እንዲዛዋወር ተደረገ appeared first on Zehabesha Amharic.

አረና ትግራይ ኢትዮጵያ ውስጥ በመጪው ግንቦት ለሚካሄደው ምርጫ ያስመዘገባቸው እጩዎቹ ራሳቸውን ከምርጫው ለማግለል እየተገደዱ መሆኑን አስታወቀ።

$
0
0

0,,1589020_4,00አረና ለፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ከ100 በላይ እጩዎቹ ቢመዘገቡም በተለያዩ አካባቢዎች በደረሰባቸው ጫና ምክንያት በርካቶች ከውድድር መውጣታቸውን ፓርቲው አመልክቷል። የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አስራት ሳይቀሩ ካርድ የለም ተብለው እንዲመለሱ መደረጉን የፓርቲው የሕዝብ ግኑኙነት ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

አረና ትግራይ ኢትዮጵያ ውስጥ በመጪው ግንቦት ለሚካሄደው ምርጫ ያስመዘገባቸው እጩዎቹ ራሳቸውን ከምርጫው ለማግለል እየተገደዱ መሆኑን አስታወቀ። አረና ለፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ከ100 በላይ እጩዎቹ ቢመዘገቡም በተለያዩ አካባቢዎች በደረሰባቸው ጫና ምክንያት በርካቶች ከውድድር መውጣታቸውን ፓርቲው አመልክቷል። የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አስራት ሳይቀሩ ካርድ የለም ተብለው እንዲመለሱ መደረጉን የፓርቲው የሕዝብ ግኑኙነት ለዶቼቬለ ተናግረዋል። የክልሉ የምርጫ ቦርድ ሃላፊ ግን የአረናን አቤቱታ መሠረተ ቢስ ሲሉ አጣጥለዋል። ዝርዝሩን ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር አዘጋጅቶታል ።

 
Source- m.dw.de/amharic/

The post አረና ትግራይ ኢትዮጵያ ውስጥ በመጪው ግንቦት ለሚካሄደው ምርጫ ያስመዘገባቸው እጩዎቹ ራሳቸውን ከምርጫው ለማግለል እየተገደዱ መሆኑን አስታወቀ። appeared first on Zehabesha Amharic.

 ህወሃት ምንድን ነው?  –ለታው ዘለቀ

$
0
0

tplfበቅርቡ የህወሃት ኣርባኛ ዓመት ለየት ባለ መንገድ መከበሩ ገርሞኛል። በየዓመቱ እንደሚከበር ሁላችን እናውቃለን። ይሁን እንጂ የዓርባኛ ዓመቱ በዓል እንዲህ ለምን እንደተወራለት ለምን የሌላ ኣገር መሪ ሳይቀር እንደተጋበዘበት ኣልገባኝም። ብዙ ጊዜ እንዲህ ዓይነት ለየት ያለ ድግስ የሚደረገው የኢዮቤልዩ በዓል ሲከበር ነው። የሆነው ሆኖ የመነሻ ኣሳቤ ይሄ ኣይደለም። ህወሃት ኣርባኛ ዓመት በዓሉን ሲያከብር እኔ በህወሃት ተፈጥሮ ስደመም ነበር።

በርግጥ ኢትዮጵያ ኣሁን ላለችበት የተመሰቃቀለ ህይወት ሲንከባለሉ የመጡ ኣንዳንድ ችግሮች ኣስተዋጾ ቢያደርጉም የችግሩ ከፍተኛ ኣስተዋጾ ኣድራጊ ግን ህወሃት ነው። በየክልሉ የህወሃት ተከታዮች ኣስተዋጾኣቸው እንዳለ ሆኖ የህወሃት ድርሻ ግን በጣም ገዝፎ ይታያል። ግን …ግን ለምንድነው በህወሃት መራሹ መንግስት ጊዜ ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነት ኣስከፊ ችግር ውስጥ የገባችው? ብለን መጠየቅ ካማረን የህወሃትን ተፈጥሮና ኣነሳስ በሚገባ መረዳትን ይጠይቀናል። ብዙ ሰው ህወሃትን የሚገልጸው ዘረኛ…… ኣምባገነን በሚል ነው። እውነት ነው ህወሃት ጎጠኛና ኣምባገነን ነው::ከዚህ በተሻለና በጠራ ሁኔታ የህወሃትን ስርና መሰረት መመርመሩ የበለጠ የህወሃትን ተፈጥሮ እንድንረዳው ያደርገናል። ኢትዮጵያ በየጊዜው የሚገጥማት ችግር በርግጥ እንዴት ከዚህ ከህወሃት ተፈጥሮ ጋር እንደሚመጋገብ አብርቶ ያሳየናል። ከዚህም በተጨማሪ የሃገሪቱን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ጉዳይ የበለጠ እንድንረዳው ያደርጋል።

ህወሃት ምንድን ነው?  ምን ዓይነት ጉዳይ ኣንገብግቦት ነው የዛሬ ኣርባ ዓመት ወደ በረሃ የገባው? ብለን ከጠየቅን የህወሃት ኣባላት እንደሚሉት የነጻነት (Liberty) ጥያቄ ጉዳይ ኣይደለም። የነጻነት ጥያቄ ስል ትግራይንም ማለቴ ነው። ህወሃት የታገለው ለትግራይ ነጻነትም ኣይደለም ማለቴ ነው።

ህወሃት ወደ ጫካ ሲገባ በርግጥ በወቅቱ የነበረው የፖለቲካ ድባብ ማለትም “የብሄር ብሄረሰብ ጥያቄ” የሚባለው ነገር ኣስተዋጾ ቢያደርግም ዋናው የዚህ ቡድን ጥያቄ የነጻነት ጥያቄ፣ የእኩልነት ጥያቄ፣ ወይም የዴሞክራሲ ጥያቄ ሳይሆን  በወቅቱ ያበሸቀውና ወደ ጫካ የሰደደው ጉዳይ የኢኮኖሚ ጉዳይ፣ የከፋ ድህነት ጉዳይ ነው። የህወሃት መስራቾች በወቅቱ ስርዓት ኣኩርፈው ወደ ጫካ ሲገቡ በነበራቸው ግምገማ መሰረት ትግራይ በጣም የተጎዳች፣ ረሃብ ያጠቃት ናት። ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ህይወት ከትግራይ የማይለይ፣ የሃብት ክፍፍሉ በኣጠቃላይ ህዝብ ደረጃ ኣብዛኛውን የጎዳ መሆኑን ለማወቅም ሆነ ይህንን ለመመርመር ኣልፈቀዱም። በጠባቡ የትግራይን የኢኮኖሚ ህይወት፣ የገበሬውን ህይወት ኣይተው የትግራይ ሃርነት ትግል ጀመሩ። የዚህ ህዝብ ችግር በሃገር ጥላ ስር ኣብሮ ይፈታል የሚለው ነገር ያበሽቃቸው ነበር። የኣንድነትን ሃይሎች እንደነ ኢህዓፓ ኣይነቶችን እንደጠላት ያዩትም ለዚህ ነው። ትግራይን ነጥለው ሲያዩ ችግሩን ለመረዳት በጣም የቀለላቸው ይመስላል። ለመጡበት ቀየ የራራው ልባቸው ለኦሮሞው ለኣማራው ለሌላው ድሃ ህዝብ ኣልራራም ኣላቸው። እንዴውም ይህንን ስሜት ሳይንሳዊ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ሲጥሩ ታዩ። በመጀምሪያ ኣካባቢህን ከዚያ ሃገር ምናምን… እያሉ  በዚያ ስሜታቸው ከማፈር ይልቅ ለማስተማመን (justify ለማድረግ) ብዙ ጣሩ።

ከፍ ሲል እንዳልነው ህወሃቶች “ትግራይ ሃርነት” ይበሉት እንጂ መራራው ጥያቄ ትግራይን ከሆነ ጨቋኝ ስርዓት ኣላቆ ኣንድ ነጻ ኣገር ለማድረግ ኣልነበረም። ጥያቄው የፖለቲካና የኣስተዳደር ነክ የነጻነት ጥያቄ ስላልሆነ በትግላቸው የመጀመሪያ ወራት ኣንዳንድ ኣባላት የመገንጠል ጥያቄ ኣንስተው የነበረ ቢሆንም ገና በማለዳ ይህ ኣሳብ ተቀጨ። ከፍ ሲል እንዳልኩት መራራው ጥያቄ የኢኮኖሚ ኦፖርቹኒቲ እንዴት ለኛ ሰፈር ይሰፋል? የሚል በመሆኑ ለዚህ ጥያቄ ብዙ መስዋእትነት ተከፈለ። ሌላው ኢትዮጵያዊ በደርግ ስርዓት ተጨቁኖ ስለነበረና ለውጥ ሽቶ ስለነበር የህወሃትን ተፈጥሮ መመራመር ኣልፈለገም። የኣንድ ኣካባቢ ኣርማ ለጥፈው ቢመጡም በኣንድያ የሃገር ስሜት ስር ያደገው ሰፊ ህዝብ ይህ ኣስተዳደጉ ስለ ህወሃት እንዳይመራመር ትኩረቱን ጋረደው። ኣንዳንዱ ሰው ደግሞ ከጅምሩ ብሄርተኞች መሆናቸው ባይዋጥለትም እስቲ ይሁን፣ ወንድሞቻችን ናቸው፣ ማእከላዊውን ስልጣን ሲይዙት፣ ኢትዮጵያ የምትባለውን ኣገር ሲያዩ፣ የሌላውን ህዝብ የከፋ ችግር ጠጋ ብለው ሲያዩ፣ ኣለማቀፋዊ መጋለጥ ሲኖራቸው ይተውታል ብሎ በልበ ሰፊነት ሲጠብቅ እነሆ ህወሃት ኣርባ ኣመቱን ትናንትና ሲያከብር ወይ ፍንክች ኣልተለወጠም።

ወያኔ የዛሬ ሃያ ሶስት ዓመት የኢኮኖሚ ጥያቄ ዋና ጥያቄው ኣድርጎ ስልጣን ላይ ሲወጣ የኦፖርቹኒስቲክ ባህርይ (Opportunistic behavior) በሃጋሪቱ ፖለቲካ ኣካባቢ በሰፊው  ሰፈነ። ይህ ባህርይ የፖለቲካውን ጨዋታ ሁሉ እንዳይሆን እንዳይሆን ኣድርጎ ኣበላሸው:: ማህበራዊ ሃብታችንን በተለይም የመተማመን (የ trust) ሀብታችንን በጣም ጎዳብን።

ህወሃት ትግራይ ትግራይ ይበል እንጂ በትግሉ ጊዜ ለትግራይ የገባውን ቃል መፈጸም ኣልቻለም። ከሁሉ በላይ የትግራይ ህዝብም በወያኔ ጎጠኛ ስሜት ተከፋ። ኣብዛኛውን የትግራይን ህዝብ ወደማይፈልገው ስሜት ውስጥ ከተተው። ስለዚህም ህወሃት ከትግራይም ሌላ ክብ ሰርቶ የዚያን ክብ እርሻ ለወጠ። የዚያን ጠባብ ክብ ኣባላት ነጋዴዎች ኪስ በገንዘብ ጠቀጠቀ።ስልጣኑን ለማቆየት ይረዳኛል በሚል በየክልሉ ጥቂት ጥቂት ክቦችን እየሰራ እነሱን የከፍተኛ የኢኮኖሚ ኦፖርቹኒቲ ተጠቃሚ እያደረገ እልፉን ህዝብ ሜዳ ላይ ጣለው።

ቶሎ እንድናድግ ሃብት በኣንድ ኣካባቢ ይደልብልን በሚል ማታለያ ኣንዳንዴም የልማታዊ መንግስትን ስም ለጠፍ እያደረገ የኢኮኖሚውን ኦፖርቹኒቲ ሁሉ በጣም በጠበበ የህብረተሰብ ክብ ውስጥ ጠቀጠቀው። ይህ ቡድን መነሻው የኢኮኖሚ ችግር በመሆኑና የታገለውም ለዚህ በመሆኑ ነው ይህን የሚያደርገው። ይህ ቡድን ለኢኮኖሚ ጉዳቱ ማገገሚያ ኣድርጎ የወሰደው የፖለቲካ ስልጣንን መሳሪያ በማድረግ በመሆኑ በሃገሪቱ ፍትህ ኣድሮ ሲቀጭጭ ይታይ ጀመር። ያሳዝናል።

ህወሃት ገና ከመነሻው የዚህ የኢኮኖሚ ጥቅም ጉዳይ ኣናዶት ጫካ መግባቱ ብቻ ሳይሆን የጎዳን ይህንን ጠባብ የሆነ የኢኮኖሚ እድል ለማስፋት ኢትዮጵያ የምትከፍለው ዋጋ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ነው። የጥቂት የህወሃት ደጋፊዎችን እርሻ ለመለወጥ፣ የጥቂት የሰርዓቱ ደጋፊ ነጋዴዎችን ኪስ ለመሙላት ኢትዮጵያ የባህር በር እስክታጣ፣ ኢትዮጵያ ድንበሩዋ ተቆርጦ እስክታንስ፣ በዘር ፖለቲካ ማህበራዊ ሃብታችን እስኪፈርስ ድረስ ዋጋ ትከፍላለች።እስከዚህ ጥግ የሄደ መስዋእትነት ይከፈላል። ይሄ ነው እጅግ ኣሳዛኙ ነገር። እነዚህን ኣላፊ ወይም ኣነስተኛ የኢኮኖሚ ድጋፎችን ለማድረግ ስለምን ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቱዋ እስኪደፈር ዋጋ ትከፍላለች? ብለን ስናስብ እስከ ሃቹ ያስደምመናል። ህወሃት ቢገነዘብ ኖሮ ይህን በዙሪያው የኮለኮለውን ጠባብ ቡድን ኣሁን የጠቀመውን ያህል ለመጥቀም ኢትዮጵያ ይሄን ያህል ዋጋ መክፈል ኣልነበረባትም። በኣምባ ገነን ኣገሮች ሙስና እንዳለ ሁሉ በሙስና የተለያዩ ጥቅሞችን ማደረግ ቢቻል የህወሃት ክፋት እስከዚህ ጥግ ይባል ነበር። ይህ ግን ኣልሆነም። ስርዓቱን ለመጠበቅ ሲባል፣ የነዚህን ጠባብ ቡድኖች ጥቅም ለመጠበቅ ሲባል በሱዳን በኩል ተቃዋሚ እንዳይነሳ የጠገበ መሬት ቆርሶ እስከ መስጠት መድረሱ በጣም ያስገርማል። ኢትዮጵያን የሚያህል ትልቅ ኣገር የባህር በር ጥያቄን ኣምርራ ከመጠየቅ ይልቅ ዝምታን መርጣ የነዚህን ጠባብ ጉጅሌዎች ኪስ መሙላት ይሻላል ለወያኔ።

ይህ ስርዓት ከቀደሙት የሚለየው በዚህ ነው። የቀደሙት ስርዓቶች ኣምባገነን ሆነው የሆነ ክብን እየጠቀሙ ብዙውን ኣግልለው ይኖሩ ነበር። እነዚህ መንግስታት ይህን ቡድናቸውን ወይም ጉጅሌዎቻቸውን የሚጠቅሙት ግን የድሃውን ጉልበት እስከመበዝበዝ በሚደርስ ጭካኔ ነው። ህወሃት ግን ድሃውን ከመበዝበዝ ኣልፎ ኢትዮጵያን ራሱዋን ሉዓላዊነቱዋን ታሪካዊ ማንነቷን ሁሉ ሸጦ ነው ቡድኑን የሚጠቅመው።

ደርግ ለዚህ ምሳሌ ነው። ሁሉ እንደሚያስታውሰው ጨካኝ በመሆኑ ኢትዮጵያ ብዙ ዋጋ ከፈለች። ነገር ግን ለስልጣኑ ሲል የሃገሩን ሉዓላዊነት ኣላስደፈረም። ደርግ ለስልጣኑ ሲል በሉዓላዊነት ላይ ቢነሳ ኤርትራን እንድትገነጠል ማድረግ ብቻ ይበቃው ነበር። ኤርትራን በሰላማዊ መንገድ እንድትገነጠል ቢስማማ ወይም ቀደም ብሎ በኮንፌደሬሽን ኣስተዳደር ችግሩን ቢፈታ ሃይሉን ኣሰባስቦ ወያኔን ያጠፋ ነበር። ህወሃት ወደ ስልጣን እንዲመጣ የሻእቢያ ኣስተዋጾ እጅግ የጎላ እንደነበር ይታወቃል። በመሆኑም ያለፉት መንግስታት በስልጣን ለመቆየትና ለግል ጥቅም ልክ የነበራቸው ሲሆን ያሁኑ መንግስት ግን ኢትዮጵያን መስዋእት እያደረገ ኣላፊ የሆነ ጥቅማጥቅም የሚቃርም በመሆኑ በታሪካችን ኣይነተው የማናውቀው ጉደኛ መንግስት ያደረዋል።

በቅርቡ ኣርባ ኣመቱን ያከበረው ህወሃት በኣርባ ኣመት ቆይታው ምንም ኣልተማረም። ከጥፋት ወደ ጥፋት ሲያዘግም ነው የምናየው። መሪዎቹ የዛሬ ሃያ ኣመት ካሳዩት ትህትና ያሁኑ ያንሳል፣ የዛሬ ሃያ ኣመት ካሳዩት የፕሬስ ነጻነት የዛሬው ያንሳል። ወያኔ ኣንዱ እንዳይማር ያደረገው ነገር ከመነሻው ትግሉ የኢኮኖሚ እድልን መጠቀም በመሆኑ እንዲሁ ሃብቱን እንደነከሰ መኖርን ስለሚመርጥ ነው።የህወሃት ተፈጥሮ እንደዚህ ነው። ይህ ስርዓት ካልተለወጠ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ኣጠቃላይ የኣካባቢውን ኣገራት ጂኦ ፖለቲክስ በመቀየር በኣፍሪካ ቀንድ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል መገመት ኣያዳግትም። የዘር ፖለቲካውና የመሬት ነጠቃው የኣካባቢውን ጂዖ ፖለቲክስ ወደ ኣልተፈለገ ኣቅጣጫ ሊወስዱ የሚችሉ እምቅ ችግሮች ናቸው። የመሬት ነጠቃ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚና የኦፖርቹኒቲ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ እንድምታውና ተጽእኖው በሚገባ መታወቅ ኣለበት። እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ በኣፍሪካ ቀንድ ካላት ግዝፈት የተነሳ ኣለመረጋጋት ቢፈጠር በጅቡቲ፣በሶማሊያና በኤርትራ ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖ እጅግ ጉልህ ነው።  የኣፍሪካ ቀንድ ሰላም ሲታሰብ ከኢትዮጵያ ሰላምነት ውጭ ማሰብ ኣይቻልም። ወያኔ ትልቅ ውስጣዊ ችግር በውስጡ ደብቆ ይዞ በኣካባቢው ኣገራት ዘንድና በኣለም ኣቀፍ ተቋማት ዘንድ ሰላም እንደሆነ፣ ሃላፊነት ሊሸከም እንደሚችል ለማሳየት ይሞክራል። ይህ ግን እውነት ሳይሆን በርግጥ ኢትዮጵያ በኣሁኑ ሰዓት ማህበራዊ ሃብቱዋ ያለ ልክ ተጎድቶ በከፍተኛ ውጥረት ላይ ያለች ኣገር ናት። ለኣፍሪካ ቀንድ ዋና ስጋት የሆነው የኣክራሪነት ችግር በህወሃት ኣይፈታም ብቻ ሳይሆን ራሱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድባብ ኣክራሪነት የሚታይበት በመሆኑ እምቅ ኣሸባሪነት በህወሃት ኣገዛዝ ውስጥ ተቀብሮ ይኖራል።ህወሃት በተፈጥሮው የኣሸባሪነት ጠላትም ሊሆን የሚያስችል ነገር የለውም። ኣክራሪነት የሚገለጸው ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ ብቻ ሳይሆን ከማንነት ፖለቲካ ጋር የተያያዘ በመሆኑ ኢትዮጵያ በኣህኑ ሰዓት ይህን ችግር በውስጡዋ ይዛ ያለች ኣገር ናት። በየትኛውም ጊዜ ሊፈነዳ የሚችል የጎሳ ኣመጽን እያፈራች ያለች ኣገር ናት። ከፍ ሲል እንዳልነው የህወሃትን ተፈጥሮ ተከትሎ የመጣው  የኦፖርቹኒስቲክ ጸባይ ብዙዎችን ኣብሽቆ ይታያል። እኛ ኢትዮጵያዊያን የወያኔን ተፈጥሮ ተረድተን የጋራ የሆነችውን ኣገራችንን በጋራ እንደገና ለማነጽ ሳንከፋፈል በጋራ ታግለን ይህን ስርዓት መለወጥ ይኖርብናል። በኣንድም በሌላም መንገድ ለወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ሰለባ ሳንሆን ኣንድነትን ኣጥብቀን ልንይዝ በፍቅር ላይ የተመሰረተ የለውጥ እንቅስቃሴ ልናደርግ ይገባናል።

 

እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ

geletawzeleke@gmail.com

The post  ህወሃት ምንድን ነው?  – ለታው ዘለቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

የዛሬ የቂሊንጦ አጭር ቆይታ አብርሃን መጠየቅ ከጀርባ ሰው ያስከትላል (ከኤልያስ ገብሩ ጎዳና )

$
0
0

‹‹ዕድሜያችንን መቼ ሰራንበት፣ ልደት ማክበርም ያስፈራኛል፡፡
እንኳን ተወለድክ ላላችሁኝ በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ››

ጦማሪ እና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉ

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ

ከዛሬ ከሰዓት በኋላ ከወዳጄ አቤል አለማየሁ ጋር ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት አምርተን ነበር፡፡ አካሄዳችን በዞን ሁለት የሚገኙትን አብርሃ ደስታን፣ ጦማሪ እና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉንና ጦማሪ አጥናፍ ብርሃንን ለመጠየቅ ነው፡፡

የቃሊቲ እና የቂሊንጦ ጸሐይ ከረር ያለች ብትሆንም በቦታው ደርሰን ወደፖሊሶች ለምዝገባ ተጠጋን፡፡ ጠያቂና ተጠያቂ መዝጋቢ የሆነችው ሴት ፖሊስ ‹‹ማንን ነው የምትጠይቀው?›› ብላ አቤልን ጠየቀችው፡፡ በፍቃዱን እና አጥናፍን መሆንኑ ነገራት፡፡ መዘገበችውና ሂድ አለችው፡፡ ‹‹አንተስ ማንን ነው?›› ስትል ጠየቀችኝ፤ ‹‹አብርሃ ደስታን›› አልኳት፡፡ ቀና ብላ አየችኝና ‹‹ቆይ፣ ቁጭ በል›› የሚል መልስ መለሰች፡፡ ሌሎች ሰዎችን መመዝገቧን ቀጠለች፡፡ ‹‹ሰዓት እየሄደ ነው፣ ችግር አለ ወይ?›› አልኳት፡፡ ‹‹አይ ችግር የለም›› ካለች ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ሌላ መዝገብ አምጥታ ፓስፖርቴን መዘገበችው፡፡ (መታወቂያዬ አልታደሰም) ከመዘገበች በኋላም ሌላ የፎርም መሙያ አውጥጣ በድጋሚ መዘገበች፡፡ ይሄንን ስትመዘግብ እኔ እንዳይባት ስላልፈለገች ስትደብቀው አስተውያታለሁ፡፡ …ከሌላ ወንድ ፖሊስ ጋር ከተነጋገረች በኋላ ግባ አለችኝ፡፡

የጸሐይ መነጽር ማውለቅ ግድ ነበር፡፡ ያው ፍተሻውን አልፌ ወደዞን ሁለት አመራሁ፡፡ ከኋላዬ አንድ ሲቪል የለበሰ ወንድ በቅርብ ርቀት እየተከተለኝ ነበር፡፡ አብርሃን አስጠራሁት፡፡ ከኋላዬ የሚከተለኝ ሰው ከጎኔ ሆኖ ሌሎች ጠያቂዎችን ለመጠየቅ ማስመሰል ሞከረ፡፡ በውስጤ ፈገግ መጣ፡፡

አስተናባሪዎቹ ‹‹አብርሃ እዚህ የለም፤ የዞን ሁለት መጠየቂያ ተቀይሯል›› አሉኝ፡፡ በእርግጥም ዞን አንድ ታስሬ በነበረበት ጊዜ የማውቃቸውን እስረኞች ተመለከትኳቸውና ሰላም ተባባልን፡፡ ልወጣ ስል ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ በርቀት አይቶኝ ሰላም አለኝ፡፡ በደስታ ሰላም አልኩት፡፡ ነገር ግን ተመልሼ በእጄ ሰላም እንዳልለው ያ ከጀርባዬ ያለ ሰው ነበር፡፡ ከዚህ ቀደምም ‹‹አቡበከርን ለምን ጠየከው?›› ተብዬ የተፈጠረውን ግርግር አስታወስኩኝ፡፡ አብበከርም ይሄ ስለገባው በርቀት ሰላም ብሎኝ በእጁ ሂድ አለኝ፡፡

የዞን አንድ መጠየቂያ ለዞን ሁለት ታሳሪዎች፤ የዞን ሁለት ደግሞ ለዞን አንድ ታሳሪዎች መጠየቂያ ሆኗል፡፡ አቤል በፍቄንና አጥናፍን አስጠርቷል፡፡ እኔም አብርሃን አስጠራሁ፡፡ በፍቄና አጥናፍ ወዲያው መጡ፡፡
ያ ከጀርባዬ የነበረ ሲቪል ኮፍያ ለባሽ ከጎኔ ቆሟል፡፡ ለአጥነፍ ‹‹በቃ እናንተ ከአቤል ጋር አውሩ፡፡ እኔ አብርሃን ስላጠራሁ ልጠብቀው፡፡ ከአንድ ሰው በላይ መጠየቅ አይቻልም ብለዋል›› አልኩት፡፡ አጥናፍ ከዚህ ቀደም የደረሰብኝን አስታውሶ ‹‹አብርሃ አሁን ጠበቃ ተማንን ሊያገኝ ሄዷል፤ ከጎንህ የቆመው የግቢው ደህንነት ነው፡፡ ይሄን ንገረውና እስከዚያው ከእኛ ጋር ሁን›› አለኝ፡፡ ያን ሰውዬ ትከሻውን ስነካው ደንገጥ ብሎ ዞር አለ፡፡ ስለሁኔታው ነገርኩት፡፡ ‹‹እሱ (አብርሃ) እስኪመጣ ብቻህን ተቀምጠህ ጠብቅ›› አለኝ፡፡ ‹‹እስኪዚያ እነሱን ላናግራቸው›› አልኩት፡፡ ‹‹ብቻህን ብትቀመጥ ይሻልሃል አለኝ›› ተናድጄ ወደውጪ ወጥቼ ሌሎች ፖሊሶችን ስለሁኔታው አስረዳኋቸው፡፡ ኃላፊነት የሚወስድ ጠፋ፡፡ በመጨረሻም አንዱ ፖሊስ ‹‹እሱ አስኪመጣ ውስጥ ጠብቀው›› የሚል ምላሽ ሰጠኝ፡፡ የመጣው ይምጣ በሚል ገብቼ ከበፍቄ ጋር ማውራት ጀመርኩ፡፡

‹‹በፍቄ እንኳን ተወለድክ›› አልኩት፡፡ አሜን ካለኝ በኋላ ‹‹ዕድሜያችንን መቼ ሰራንበት፡፡ ልደት አክብሬ አላውቅም፡፡ ልደት ማክበርም ያስፈራኛል፡፡ ግን እንኳን ተወለድክ ላላችሁኝ በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ›› ሲል እየሳቀ መለሰልኝ፡፡

አቤል እና አጥናፍ ጋር የጦፈ ጨዋታ ይዘዋል፡፡ እኔም ከበፍቄ ጋር ባለችን አጭር ደቂቃ ስለሀገር ጉዳይ፣ ስለዘንድሮ ምርጫ፣ ስለአልጀዚራ ዘስትሪም የሰሞኑ ዘገባ፣ ስለ ክሳቸው እና እስራቸው ጉዳይ፣ ስለእኔ የክስ ሁኔታ፣ በአንድነት ፓርቲ ስለደረሰው ሁነትና አደጋ …በጥቂቱ አወጋን፡፡የመለያያ ደወል ተደወለ፡፡ አብርሃም ሳይመጣ ቀረ፡፡ ያው፣ ቻው ብሎ መለያየት ግድ ነበርና ተለያየን!!!

The post የዛሬ የቂሊንጦ አጭር ቆይታ አብርሃን መጠየቅ ከጀርባ ሰው ያስከትላል (ከኤልያስ ገብሩ ጎዳና ) appeared first on Zehabesha Amharic.


ተወዳድሮ ማሸነፍ የሚችለው ሰማያዊ ብቻ መሆኑ ተረጋገጠ

$
0
0

ነገረ ኢትዮጵያ

መድረክ 218 ኢዴፓ 127 መቀመጫዎች ብቻ ነው ያሰመዘገቡት

ethiopia-blue-party-300x164የምዝገባ ጊዜ ሳይጀምር፣ የአንድነት ፓርቲ ከሶማሌ ክልል በስተቀር በሁሉም የአገሪቷ ክፍሎች ለፓርላማና ለክልል ምክር ቤቶች ተወዳዳሪዎች አዘጋጅቶ እንደነበረ ይታወቃል። የአንድነት ጥንካሬ ከወዲሁ የተረዳሁ የሕወሃት ፖሊት ቢሮ ለምርጫ ቢርድ መመሪያ በመስጠት፣ ተለጣፊ ቡድን በማደራጀት አንድነት ላይ የኃይል እርምጃ ወስዷል።

የአንድነት አባላታ ለድርጅት ሳይሆን ለነጻነት የሚታገሉ እንደመሆናቸው ማሊያ ቀይረው በሰማያዊ ፓርቲ ሥር ለመንቀሳቀስ ተነሱ። የሰማያዊውች እና የአንድነቶች መያያዝ ትግሉን የበለጠ አጠናከረው። ሳምንታ ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ አንድነቶ ተነቃነቁ። ወደ ሰማያዎ ጎረፉ። በፊትም ጠንካራ የሆነው የሰማያዊ ፓርቲ አንድነቶች ሲመጡ የበለጠ ተጠናክሮ ከአራት በላይ ለፓርላማ፣ ከሰባት መቶ በላይ ለክልልተወዳዳሪዎች አስመዘገበ። ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎች በምርጫ ቦርድ የሌላ ፓርቲ አባል ናችሁ በሚል ተሰረዙ።

እንደዚያም ሆኖ ከኢሕአዴግ ቀጥሎ ብዙ ተወዳዳሪዎችን ሰማያዊ ፓርቲ እንዳሰለፈ ለማወቅ ተችሏል። ኢሕአዴግ ከ547 የፓርላማ መቀመጫዎች 457 ላይ ተወዳዳሪዎች ያስመዘገበ ሲሆን፣ ሰማያዊ የተሰረዙትን ሳይጨመር ለፓርላማ 345 (63%) ተወዳዳሪዎችን አስመዝግቧል። ኢሕአዴግ የሚወዳደረው በትግራይ፣ ደቡብ፣ አማራና ኦሮሚያ ክልልም በአዲስ አበባ ብቻ ነው። በአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤኔሻንጉልና ጋምቤላ የሚወዳደሩ ኢሕአዴግ አጋር ድርጅቶች የሚላቸው ናቸው።፡

የብዙ ድርጅቶች ስብስብ የሆነ መድረክ 218 ( 39%) መቀመጫ ብቻ ሲሆን ለፓርላማ ያሰለፈው በትግራይ ከ38 መቀመጫዎች ከሰላሳ በላይ፣ በኦሮሚያ ከ175 መቀመጫዎች በ160ው ተወዳዳሪዎችን አሰልፏል። በደቡም ክልል ወደ ሃያ ብቻ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎችን ያሰለፈ ሲሆን በአማራዉ ፣ በጋምቤላ፣ በአፋር፣ በቤኔሻንጉልና በሶማሌ ክልል ምንም ተወዳዳሪዎችን አላስመዘገበም።
ከመድረክ ቀጥሎ ብዙ ቁጥር ያስመዘገበው ኢዴፓ ሲሆንም ፣ ለ127 መቀመጫዎች (23%) ተወዳዳሪዎችን አስመዝግቧል።

በዚህ መሰረት ገዢው ፓርቲ ድምጽ መስረቁ አይቀርም እንጂ፣ ካሰመዘገባቸው 345 የፓርላማ አባላት 274 ቱን ( 80% ) ማሸነፍ ከቻለ ስልጠና የመያዝ እድል ይኖረዋል። እንድ እመድረክ፣ ኢዴፓና ሌሎች ያሰለፏቸውን በሙሉ መቶ በመቶ ቢያሸንፉም ስልጣን መያዝ አይችሉም።

The post ተወዳድሮ ማሸነፍ የሚችለው ሰማያዊ ብቻ መሆኑ ተረጋገጠ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በዕጩነት እንዳይቀርቡ ተደረገ

$
0
0

• ‹‹ምርጫ በህዝብ ፍላጎት ሳይሆን በሎተሪ ሆኗል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

አዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 5 ለመጭው ምርጫ ለተወካዮች ምክር ቤት ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ሊቀርቡ የነበሩት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ከቀረቡት 17 ዕጩዎች መካከል በተጣለ ዕጣ ወድቀዋል›› በመባላቸው ለመጭው ምርጫ በዕጩነት እንዳይቀርቡ መደረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል በዕጩነት በቀረቡበት ወረዳ 5 የምርጫ ጣቢያ ኢህአዴግ፣ የትግስቱ አንድነት፣ ቅንጅትን ጨምሮ ሌሎች ስድስት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ያለ ምንም ዕጣ አልፈዋል የተባለ ሲሆን ‹‹የሚያልፉት በዕጣ ነው›› የተባሉት ሰማያዊን ጨምሮ 11 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መካከል ሰማያዊና ሌሎች አራት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ‹‹ዕጣ አልወጣላቸውም፡፡›› ተብሏል፡፡
Hiber Radio Interview with Eng Yilkal Getnet
ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ሰማያዊ ህዝብ ውስጥ በሰፊው እየገባና እያንቀሳቀሰ ያለ ግንባር ቀደም ፓርቲ ነው፡፡ እንደ ኢህአዴግ ያሉን ጨምሮ ዕጣ ውስጥ አይገቡም፡፡ ሰማያዊ ደግሞ ይህ ነው የሚባል እንቅስቃሴ ከማያደርጉት ፓርቲዎች ጋር ዕጣ ውስጥ ገብቶ ወደቀ መባሉ ዴሞክራሲ ከጅምሩ ጀምሮ የህዝብ ድምጽ ሆኖ እያለ በእኛ አገር ሎተሪ ሆኗል ማለት ነው፡፡›› ብለዋል::

ሊቀመንበሩ አክለውም ‹‹ሂደቱ ምንም ይሁን ምን አንድን ፓርቲ ወይንም ተወካይን ህዝብ ነው መምረጥ ያለበት፡፡ ህዝብ የሚፈልገውና የሚመረጥ ፓርቲ ነው ለምርጫ መቅረብ ያለበት፡፡ አሁን ግን እየተባለ ያለው በአንድ በኩል ህዝብ የማይፈልገው ያለ ዕጣ ሲገባ፣ በሌላ በኩል ህዝብ የሚፈልገው ሰማያዊን የመሰለ ፓርቲ ዕጣ ውስጥ ገብቶ አላለፈም እየተባለ ነው፡፡ በአንድ በኩል ህዝብ የተማረረባቸው ያለ ቅድመ ሁኔታ ህዝብን እንደሚያንቀሳቅስ የሚታወቀው ሰማያዊ ደግሞ ህዝብ ስፈለገው አሊያም በጥንካሬው ሳይሆን በሎተሪ ወድቀሃል ተብሏል›› ሂደቱ የተሳሳተ ነው ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

The post የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በዕጩነት እንዳይቀርቡ ተደረገ appeared first on Zehabesha Amharic.

በስልጢ ለሳምንት የዘለቀው ቃጠሎ በደን ላይ ውድመት አደረሰ

$
0
0

አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደዘገበው
በደቡብ ክልል ስልጢ ዞን ስልጢ ወረዳ ውስጥ በተፈጥሮ ደን ላይ የእሳት ቃጠሎ ውድመት እየደረሰ መሆኑን ምንጮቻችን የጠቆሙ ሲሆን የወረዳው ግብርና ላይ በበኩሉ እሣቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን ጠቅሶ የአደጋው መንስኤ በፖሊስ እየተጣራ ነው ብሏል፡፡
news
ከሳምንት በፊት የጀመረው የእሳት ቃጠሎ እስካለፈው ሐሙስ ድረስ አለመቆሙን የተናገሩት ምንጮች፤ ከወረዳው ዋና ከተማ ቂቢት በስተምዕራብ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በዘቢዳር ሰንሰለታማ ተራራ ላይ የሚገኘው ይሄው ደን፤ በአራት አቅጣጫዎች በእሳት እየወደመ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

እስካሁን እሳቱን ለማጥፋት ከአካባቢው መስተዳድር የተደረገ ጥረት አለመኖሩን የጠቆሙት ምንጮቻችን፤ በግምት ከ20 ሄክታር በላይ ደን ሳይቃጠል እንደማይቀር ተናግረዋል፡፡ ወሌ 26 እና ቦሌ በሚባሉ ቀበሌዎች ውስጥ የሚገኘው ደኑ፣ የአካባቢው የተፈጥሮ ሃብት መሆኑን የጠቀሱት ምንጮች፤ ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ ቃጠሎ እንደደረሰበትና ግለሰቦች ለማገዶ ፍጆታ ሲሉ እሳት ለቀውበት ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ገልፀዋል፡፡

የወረዳው የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ መሃመድ ከድር ስለጉዳዩ ተጠይቀው ሲመልሱ፤ ከግብርና ቢሮና ከፖሊስ የተውጣጣ ግብረ ሃይል መሰማራቱንና እሳቱን በትናንትናው እለት መቆጣጠር መቻሉን ጠቅሰው ቃጠሎው በሰውና በንብረት ላይ ያደረሰው ጉዳት ባይኖረውም በደኑ ላይ ያደረሰው ውድመት መጠን እንዲሁም ፖሊስ የእሳቱን መንስኤ ፖሊስ እየመረመረ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

The post በስልጢ ለሳምንት የዘለቀው ቃጠሎ በደን ላይ ውድመት አደረሰ appeared first on Zehabesha Amharic.

ይድረስ ለጎንደር ሕዝብ –ልዩ መልዕክት ቁ. 5

$
0
0

(ጎንደር ፋሲል ግምብ - ፎቶ ፋይል)

(ጎንደር ፋሲል ግምብ – ፎቶ ፋይል)


የጎንደር ክፍለ ሃገር በዚህ በያዝነዉ ዘመን የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር በተባለ ቡድን የጥቃት ሰለባ መሆኑን በተደጋጋሚ ተጽፏል፣ ነገር ግን ግፍ እና በደሉ ሰሚ ካጣ ብዙ ዓመታትን አስቆጥሯል። አሁንም መከራዉ እና ሰቆቃዉ ያላቆመዉ የጎንደር፤ የወልቃይት እና ጠገዴ፤ እንዲሁም የጠለምት ህዝብ በቁሙ እዬተቀበረ ነዉ። የዛሬዉ መግለጫችን የሚያተኩረዉ ለሚመለከታቸው የማህበረሰብ አካላት ሁሉ መልዕክታችን በማስተላፍ ነዉ።

Read Full Story in PDF

The post ይድረስ ለጎንደር ሕዝብ – ልዩ መልዕክት ቁ. 5 appeared first on Zehabesha Amharic.

አማራውና “የብሔራዊ”ሕዝብ ቆጠራውና ትንበያ ትርኢት –ለምን የአዲስ አበባ ሕዝብ ቁጥር ተቀነሰ?

$
0
0

AbyssiniaPeople
ከበሻህ ውረድ
መግቢያ

ከ2006 እስከ 2009 ዓ.ም የሕዝብ ቁጥር ትንበያዎቹ በክልልና ወረዳዎች ደረጃ በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ድርጅት የተዘጋጀውን (Population projection of Ethiopia for all Regions at Werreda Level from 2014-2017) በጥልቀት ሲመረመር በተለይ የዓማራውን ሕዝብ ቁጥር በተመለከተ ረገድ ፍጹም የውሸት ዝባዝንኬ የፈጠራ አሃዝ መሆኑ ይታወቃል:: የሕዝብ ብዛት ትንበያው በአሁኑ ጊዜ ይፋ መደረግም ለመጭው ግንቦት ወር የወያኔ ትግሬ የባንቱስታን የጎሳ ተወካዮች ፓርላማ ተብዬው የምርጫ ማጀቢያ መሆኑ ግልጽ ነው::

ሙሉውን እዚህ ተጭነው ያንብቡት

The post አማራውና “የብሔራዊ” ሕዝብ ቆጠራውና ትንበያ ትርኢት – ለምን የአዲስ አበባ ሕዝብ ቁጥር ተቀነሰ? appeared first on Zehabesha Amharic.

አቡነ ማትያስ የእሬቻ በዓል በዝቋላ ገዳም ሊከበር ነው የሚለውን ዜና ኢቢሲ እንዲያስተካክል ጠየቁ

$
0
0

abune-matyas
ማህበረ ቅዱሳን እንዘገበው: በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ላይ በመጋቢት ወር መጨረሻ የኢሬቻ በዓል እንደሚከበር መስከረም 15 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኦሮምኛና በአማርኛ ቋንቋ መተላለፉ ተገቢ እንዳልሆነና ችግር ሊፈጥር የሚችል መሆኑን በመግለጽ የተላለፈው መረጃ እርማት እንዲደረግበት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ለአቶ ሙክታር ከድር በጻፉት ደብዳቤ ጠየቁ፡፡

የሃይማኖቶች እኩልነት በታወጀበት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕግ መንግሥት አንዱ ቤተ እምነት የሌላውን እምነት መንቀፍም ሆነ መንካት እንደሌለበት ተደንግጓል” ያሉት ፓትርያርኩ በሚዲያ ሽፋን የተሰጠው ጉዳይ ሕገ መንግሥቱን የሚተላለፍ፤ የገዳሙን መናንያን መነኮሳትና በአካባቢው የሚኖሩ ሕዝበ ክርስቲያኖችን የሚያስቆጣ በመሆኑ የክልሉ መንግሥት ለተዘገበው ጉዳይ እርማት እንዲሰጥበት ለኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ለአቶ ሙክታር ከድር በጻፉት ደብዳቤ አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል ጉዳያችን የጡመራ መድረክ የሚከተለውን ዘገባ አሰራጭቷል:-
ባለፈው መስከረም 15/2007 ዓም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (በቀድሞ ስሙ ኢቲቪ) በአማርኛ እና በኦሮምኛ እንደተለቀው ዜና ከሆነ ”በመጪው መጋቢት ወር መጨረሻ ላይ የእሬቻ በዓል በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ውስጥ ይከበራል ”ይላል።ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከተከበሩት እና ከታፈሩት ገዳማት ውስጥ አንዱ ነው።ገዳሙ ፃድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ለኢትዮጵያ እና ለመላው የሰው ዘር የፀለዩበት ቅዱስ ስፍራ ነው።

ይህንን ከ800 ዓመታት በላይ ፀንቶ የኖረ ገዳም ”እሬቻ” እንዲከበርበት የተደረገበት ዋና ምክንያት እምነትን ከእምነት ለማጋጨት በስርዓቱ የተሸረበ ተንኮል ነው የሚሉ ብዙዎች ናቸው።ከእዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መሰረተ እምነትን የጣሱ ተግባራት ሲፈፀሙ እና ሙስና የሚፈፅሙ የስርዓቱ አጎብዳጆች (በቤተ ክህነቱ ዙርያ ‘የጨለማው ቡድን አባላት’ በመባል የሚታወቁት) የቤተ ክርስቲያኒቱን ንብረት እና ገንዘብ መተዳደርያቸው ሲያደርጉት አመታት መቆጠራቸው ይታወሳል።

በቅርቡም በርዕሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሙዚየም የወርቅ መስቀልን ጨምሮ ሌሎች በቅርስነት የተመዘገቡ ንብረቶች መጥፋታቸው ይታወሳል።ከእዚሁ ጋር ተያይዞ የደብሩ አስተዳዳሪ ቀደም ብለው ሰራተኞችን ሰብስበው ”በሙዚየሙ የሚገኙ ቅርሶች ተሸጠው ለአባይ ቦንድ መግዣ ይዋሉ” የሚል ሃሳብ አቅርበው በደብሩ አገልጋዮች እና ሰረተኞች ”ታሪክ አጥፍተን ታሪክ አንሰራም” የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው የገለፀው የሪፖርተር ጋዜጣ ባለፈው ሮብ የካቲት11/2007 ዓም በዘገባው ”የቤተ ክርስቲያኗ ካህናት፣ ሠራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች የደብሩን አስተዳዳሪና ሌሎች ኃላፊዎች ተባብረው ወርቆቹን ማጥፋታቸውን፣ በቤተ ክርስቲያኗ ሠራተኞች ላይ በደልና ብልሹ አሠራር እንዲደርስ ማድረጋቸውን በመግለጽ ተቃውሟቸውን በፊርማ በተደገፈ አቤቱታ ለሚመለከታቸው ሁሉ መላካቸውን” ይገልጣል።

The post አቡነ ማትያስ የእሬቻ በዓል በዝቋላ ገዳም ሊከበር ነው የሚለውን ዜና ኢቢሲ እንዲያስተካክል ጠየቁ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአዲስ አበባ የታክሲ ሹፌሩ መኪናውን አቁሞ ራሱን ወደድልድዩ ወርውሮ ሕይወቱን አጠፋ (ፎቶዎች ይዘናል)

$
0
0

አዲስ አበባ ያሉ የዘ-ሐበሻ ተከታታዮች “እኔም የዘ-ሐበሻ ሪፖርተር ነኝ” ካሉን ቆይተዋል:: በሶሻል ሚዲያ ለዘ-ሐበሻ መረጃዎችን በፎቶ አስደግፈው መላካቸውን ቀጥለዋል:: አሁንም ለሌሎች ኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በሌሎች ሃገራት የሚገኙ የዘ-ሐበሻ ወዳጆች ‘እኔም የዘ-ሐበሻ ሪፖርተር ነኝ’ በማለት መረጃዎችን በቶሎ በሶሻል ሚዲያዎቻችን በፌስቡክ, ዋትሳፕ, ቫይበር, ስካይፕ, ትዊተር እና ሌሎችም መንገዶች ሊያደርሱን ይችላሉ::

ዛሬ የአዲስ አበባ የዘ-ሐበሻ “ሪፖርተር” 6 ፎቶ ግራፎችን ከመረጃ ጋር አድርጎ ልኮልናል:: እንደመረጃ ምንጫችን ገለጻ ድርጊቱ የተፈጸመው በአዲስ አበባ በተለምዶ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን አካባቢ ነው:: ትናንት ከቀኑ 8:45 አካባቢ እስጢፋኖስ ቤ/ክ አካባቢ የሚገኝ ድልድይ ጋር የሚነዳትን ታክሲ በማቆም ወደ ወንዙ ራሱን በመወርወር ራሱን አጥፍቷል:: በፎቶዎቹ እንደምታዩት ፖሊስ ጉዳዩን ሲከታትልና የወደቀውን ታክሲ ሾፌር ነው:: የታክሲ ሹፌሩ ለምን ራሱን እንዳጠፋ በምርመራ ላይ ሲሆን ለጊዜው የተገኘው መረጃ ራሱን ማጥፋቱ ብቻ ነው::

ፎቶዎችን ይመልከቱ:: እርስዎም የዘ-ሐበሻ ሪፖርተር ይሁኑ::
addis ababa suside

addis ababa suside1

addis ababa suside2

The post በአዲስ አበባ የታክሲ ሹፌሩ መኪናውን አቁሞ ራሱን ወደድልድዩ ወርውሮ ሕይወቱን አጠፋ (ፎቶዎች ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.


የISIS ሁኔታ አቅሎ ማየት እና መደባበስ ሳይሆን ትክክለኛውን ነገር በመናገር በአገር ላይ የተቃጣውን ጥፋት ማስቆም ያስፈልጋል

$
0
0

ISIS Ethiopia
ከ-ከተማ ዋቅጅራ

የISIS ሁኔታ አቅሎ ማየት እና መደባበስ ሳይሆን ትክክለኛውን ነገር በመናገር በአገር ላይ የተቃጣውን ጥፋት ማስቆም ያስፈልጋል!!!
ልናውቀው የሚገባው ነገር ቢሮር ነገሮችን በመደባበስ አልያም በፍራቻ ልናልፋቸው የምንሞክረው ነገር ካለ አደገኛነቱን ከመጨመር ውጪ የምንቀንሰው ነገር እንደሌለ ልናውቀው ይገባል። ዛሬ ልናገር የምፈልገው የISIS እንቅስቃሴ ከአገራችን ሁኔታ ጋር በማያያዝ ነው። ለዚህ ቀውስ ዋና አቀጣጣይ እና ይሄ እንቅስቃሴ እንዲከሰት የሚፈልገው የተቀናጁ እና የተደራጀ ሃይል ያላቸው ነው። ወያኔ ከስልጣን የማውረዱ እንቅስቃሴ በቅርብ በከፍተኛ ሁኔታ እንቅስቃሴ ስለሚኖር እናም በህዝብ ሃይል እንደሚደመሰስ ቢታወቅም በዚህ መሃል ሊመጡ የሚችሉትን አደጋ ለመቆጣጠር ፖለቲከኞችም ሆኑ ህዝቡም የISIS እንቅስቃሴን በንቃት እና በጥንቃቄ ሊከታተለው ይገባል።

ISIS ማን ነው? አላማውስ ምንድን ነው ብለን ስናይ ISIS ማለት Islamic State of Iraq and Sorya ማለት ሲሆን መጀመሪያ አነሳሱ ኩርዲሽ የራሳቸውን ይዞታ ለመፍጠር የተለያየ እንቅስቃሴ በማድረግ ይታገሉ ነበር። ኩርዲሾች በአምስት ሃገር ውስጥ የሚሮሩ ሲሆን እንዚህ በአምስት አገር መሃል ያሉት ኩርዶች የራሳቸው ግዛት እንዲኖራቸው የመፈለግ እንቅስቃሴን ያካሂዱ ነበረ። ለአምስቱም አገር ኩርድ የራሳቸው አገር እንዲመሰርቱ ጥያቄዎችን አቅርበው የነበረ ሲሆን። ከእነዚህ አገራት የተሰጣቸው መልስ ይህ አገር የናንተ አገር ነው እንደዜጋ በሃገራችን ያለምንም አድሎ መኖር ትችላላላቹ አይ አንፈልግም ካላችሁ ግን ለቃችሁ መሄድ ትችላላላችሁ ከአገራችን ቁራሽ መሬት አታገኑም የሚል ነበረ። በተለይ ቱርክ ውስጥ ሰፊ መሬት ላይ የሚኖሩት ኩርዶች ቱርክ ጠንከር ያለ ነገር እንደተናገረች ይታወቃል። እነዚህ አምስቱ አገር ቱርክ፣ ሶሪያ፣ ኢራቅ፣ ኢራን እና አርመን ሲሆኑ በአምስቱ አገር የሚኖሩት ኩርዶችን የራሳቸው ግዛት እንዲኖራቸው በመፈለግ እንቅስቃሴ ያደርጉ ነበር። በኃላም ይሄ ትግል አዋጪ አለመሆኑን ሲያውቁ እንቅስቃሴውን በመቀየር ISI Islamic State of Iraq በማለት እንቅስቃሴአቸውን ማድረግ ጀመሩ። በዚህም ቀላል የማይባል የሰው ኃይል አላማቸውን በመደገፍ ተቀላቅለዋቸዋል። ISI ከ2006-2013 ድረስ ከቀጠለ በኋላ ለሶስተኛ ግዜ ሃሳቡን በመቀየር ከፍ በማድረግ ISIS Islamic State of Iraq and Sorya በሚል የበለጠ የሰው ኃይል በማግኘት ለሙስሊሙ የሚታገሉ በማስመሰል ሃሳባቸውን ከፍ አድርገውታል።June 2014 ላይ Islamic State በማለት በካርታ በተደገፈ በማውጣት ካርታው ላይ ያሉት አገራት በሙሉ እስልምናን በግድ እንዲቀበሉ አዋጅ አውጀው መንቀሳቀስ ጀመሩ።የዚህን ግዜ በርካታ ሙስሊም ሱኒ(suuni) በመቀላቀል ኃይላቸውን እያጠናከሩ ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው ሙስሊሞች ከተለያየ አለማት ተቀላቀሏቸው። ለዚህም ማስረጃ የሚሆን የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ሱማሌዎች።የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው እንዲሁም በኖርዌይ ውስጥም የኖርዌይ ፓስፖርት ያላቸው የሱማሌ እና የኤርትራ ትውልድ ያላቸው ሙስሊሞች መሳተፋቸው እንቅስቃሴው ምን ያህል እንደሰፋ ማየት ይቻላል።

ISIS በአሁኑ ሰአት አላማውን ግልጽ አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ያለ በእስልምና ስም አላዋ ክበር በማለት ሁሉንም ክርስቲያንን ብቻ ለማጥፋት ሳይሆን በሌላ እምነት ያለውም በሙሉ የሚያጠፋ ኃይል ነው። ሌላው ቀርቶ እስላምም ሆነው ሱኒ(Sunni) ካልሆኑ ኢሻ(Shia) የሆኑት ምስሊሞች ሁሉ የሚያጠፋ ምንም ሰባዊነት የማይታይበት የዘመኑ አረመኔ እና አደገኛ ቡድን ነው። ቃስ በቃስ እንቁላል በግሯ ትሄዳለች ይላሉ አበው። ይህ ቡድን መጀመሪያ ስለ ድንበሩ መታገል ጀመረ ቀጥሎም ኢራቅን ሱኒ ሙስሊም ለማድረግ ተንቀሳቀሰ ከዛም ሶሪያ ጨምሮ መንቀሳቀስ ቀጠለ በኋላም አላማው ፍጹም ተቀይሮ ኢስላም ስቴት ለመመስረት ካርታ በማስቀመጥ በግድ ሊሰልሙ የሚገቡትን አገራትን ይፋ አድርጓል። እንቢ ያሉትን እንደ በግ ሊያርድ አልያም መሬት ላይ አጋድሞ በጥይት መረሸን የ አልያም በጥይት አናት አናት እየመቱ ወደ ባህር መወርወር የምናየው ሃቅ ነው።
ታዲያ ይህ አደገኛ ኃይል ከፊለፊቱ ያሉትን በሙሉ እያረደ እና እያጠፋ አረመኔአዊ ተግባር የሚሰራ ሴጣናዊ ተግባር የሚያራምድ ቡድን ነው። ISIS አለም እያወገዘው ቢገኝም የተለያዩ ደግሞ የማለባበስ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ። እውን የማለባበስ ስራ የሚሰሩት በራፋቸው ሲመጣ በማለባበሳችን ሊያልፈን ይችላል ብሎ መገመት አልያም እኛ መንደር አይገባም ብሎ ማሰብ በጣም የዋኅነት ነው። ብልጥ ከሰው ይማራል ሞኝ ግን በራሱ ይማራል የሚባለው ነገር ተፈጻሚነት እንዳይሆንብን ነገሮችን ቀድሞ ማሰብ ተገቢ ነው።

ታዲያ ISIS ኢትዮጵያን ሊያሰጋት እንዴት ይችላል? ኢትዮጵያ ሙስሊምና ክርስቲያኑ እንዲሁም ዋቄ ፈናም አልያም የአይሁድ እምነት ከእምነቱም የሌለበት ጥምር ተዋደው ያሉባት አገር ላይ ነው ያለነው ብለን እናስብ ይሆናል። ማሰባችን መልካም ነበረ ግን ሃሳባችን ትክክል ነው ወይ? ግምታችንስ ምን ያህል ወደ እውነቱ የቀረበ ነው? ካልን አከራካሪ ነጥቦችን እናስተናግዳለን። ለመከራከር ሳይሆን የሌላው እምነት ማለትም ከእስልምናው ውጪ ብቻ ሳይሆን ሙስሊም ወንድሞችና እህቶች በአንክሮት ሊያስቡበት እና ሊታገሉት በገኃድም ሊቃወሙት የሚገባ ሴጣናዊ አካሄድ ስለሆነ ስለዚህ አደገኛ ቡድን ትንሽ ልጠቋቁምና ሁሉም ተወያይቶበት የራሱን አስተያየት እንዲሰጥበት እፈልጋለው።

የአለማችን ስጋት የሆነው ISIS የሚያደርገውን እንቅስቃሴ መቃወም እስልምናን መቃወም መስሎ የሚታያቸው ሙስሊም ወገኖቻችን አሉ። እንደ እኔ አመለካከት ከእውነት የራቀ ነው። ለምን ቢባል ሁሉም ሙስሊም ISIS ደጋፊ አይደሉምና። እንደውም ISIS ሺአ(Shia) ሙስሊሞች በነዚህ ቡድኖች ማለትም በሱኒንዎች(Sunni) መስኪዳቸውን በማቃጠል ጭምር የሚያጠፉ ኃይል መሆኑን አይተነዋል።

የISIS እንቅስቃሴ የሚጀምረው በየትኛውም አገር የውስጥን ችግር መነሻ በማድረግ ነው። የውስጡ ፖለቲካ ሲጦዝ መረጋጋት ሲያቅተው በየአካባቢው ችግር ሲነሳ እነዚህ ሃይሎች ይነሳሉ። ችግሮችም እንዲባባሱ ፖለቲካውስጥ ገብተው የማጦዝ ስራንም በከፍተኛ ይንቀሳቀሳሉ። ለዚህም እንደአስረጅ ብንወስድ ኢራቅ ሳዳም ከወደቀ በኃላ የውስጥ መረጋጋቱ እንዳይመጣ ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርገው የአሁናን ኢራቅ የሰው ደም እንደ ጎርፍ የሚወርድባት አገር አድርገው ፈጠሯት። ቀጥለውም በሶሪያ በተፈጠረው አለመረጋጋት የኢራቁ አክራሪ እስላሙ ወደ ሶሪያ በመዝለቅ የኢራቅ እና የሶሪያ እስላማዊ እንቅስቃሴ ብሎ ሶሪያንም የደም ጎርፍ እንድታስተናግድ አድርገዋታል። የመንም እንደዚሁ እንቅስቃሴ አለ። ሊቢያም ከጋዳፊ ውድቀት በኃላ መረጋጋት ባለመቻሏ በዚህ አጋጣሚ እነዚህ አይሎች አንድ ትልቅ ከተማን በመቆጣጠር በከተማዋ የሚኖሩትን ክርስቲያኖችን ባህር እስከሚቀላ ድረስ ደማቸውን አፍሰው አረመኔአዊ ተግባራቸውን ለአለም ህዝብ አሳይተዋል። እንግዲህ ልብ በሉ በምን ያህል ፍጥነት እየተዛመተ እንዳለ። እንቅስቃሴአቸው በሙሉ የአገር የፖለቲካ ሰላም እንዲናጋ በማድረግ በዚህ መሃል የራሳቸውን ስር በፍጥነት መትከልና ህዝብን መፍጀት ነው።

በአለማችን ላይ የISIS ደጋፊ ቁጥር ከፍተኛ የሆኑት አገራት ሳውዲአረቢያ 28.8% ኢራቅ 15.7% ግብጽ 7.8% ሶሪያ 7.0% አፍጋኒስታን 7.0% ሊቢያ 5.4% ሲሆኑ ከግብጽ እና ከሳውዲ አረብያ ውጪ የተቀሩት አገራት ላይ በሰፊው እንቅስቃሴውን ጀምሯል። ግብጽ እና ሳውዲአረቢያ ጠንካራ መንግስት ስላላቸው ነው እንጂ እነዚህ አገር ውስጥ አለመረጋጋት ከመጣ እና የውስጥ ሰላም ከተናጋ አቅጣጫቸው ወደት እንደሚያመራ ግልጽ ነው።

ሱኒን(Sunni) ISISNን የሚያራምዱ ሙስሊም በአገራችን የሉም ለማለት አይቻልም። የሉም የሚል ካለ ይህ ሰው ከእውነት የራቀ አልያም ነገሮችን መደባበስ የሚፈልግ ከእውነት የራቀ ሰው መሆን አለበት። ባገራችን የተደረጉትን እንቅስቃሴ በጥቂቱ እንመልከት…. ጅማ ላይ ሌሊት ማህሌት ቆመው ምስጋና የሚያቀርቡትን ካህናትን እና ምዕመናንን በቤተ መቅደስ ውስጥ ማረዳቸው። በአርሲ ውስጥ የክርስቲያን ቤቶችን እና የህህል ጎተራቸውን እና ክምር ሰብላቸውን ማቃጠላቸው። በስልጤ ውስጥ የክርስቲያን እና የውሻ ድምጽ መስማት አንፈልግም ብለው ቤተክርስቲያንን ማቃጠላቸው እና አሁንም በውስጣችን ቁጭ ብለው አጋጣሚዎችን የሚጠብቁ እንዳሉ ልናውቅ ይገባናል። የጅማን ክርስቲያኖች በታረዱ ሰሞን የነበረው የቃላት ጦርነት ምን ያህል እንደነበረ ልንረሳው አይገባም። እንደውም አጠገባችን ካለ ክርስቲያን አፍጋኒስታን ያለ ሙስሊም ለኛ ቅርብ ነው ብለው አፍጋኒስታኑን አብሮ ከኖረው ከአገሩ ህዝብ አስበልጠው እንደሚወዱ የተናገሩበትም ግዜ ነበረ። ሌላው ቀርቶ በኢትዮጵያ ውስጥ ብረት ያነሱ ሙስሊሞች እናዳሉና የትጥቅ ትግልም እንደጀመሩ ልናውቅ ይገባል። ይህንን እውነት ማናችንም ልንሸፍነው አይገባም።መሸፈን ዋጋ የለውም ወደፊት ገጦ የሚመጣ ሃቅ ስለሆነ። ዋናው ነገር ነገርን በእንጭጩ የሚለውን አባባል መጠቀሙ ነው አዋጩ።

በአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ወያኔ እየሰራ ያለውን የዘቀጠ እና የTPLF የበላይነት እንቅስቃሴ ህዝቡ አልቀበልም በማለቱ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው። ወያኔ ክስልጣን የማስወገድ ሁኔታ በሁሉም አቅጣጫ በጎላ መልኩ ተቃውሞዎች እየበረቱ እና እየጠነከሩ ነው። በዚህም ምክንያት ለህዝብ ያላቸውን ጥላቻ እና ንቀት ገሃድ እያወጡት ነው። ሰሞኑን በOMN ኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ በለቀቀው ዜና አቦይ ጸሃዬ ለኦሮሞ ህዝብ ያላቸውን በውስጣቸው የነበረውን ንቀት እና ጥላቻ አውጥተውት መስማታችን ቀድሞ ወያኔን አንቅሮ የተፋው ህዝብ ትግሉን እንዲያጠናክር ሃይል ሆኖታል።

ወያኔን ከስልጣን የማስወገዱ ጉዳይ ከሁሉም አቅጣጫ በተቀጣጠለ መልኩ እየተካሄደ ነው። እዚህ ጋር ግን ከፍተኛ ጥንቃቄ መወሰድ ያለበት ነገር ስለ ወያኔ መውደቅ ወይም መጥፋት አይደለም የሚያሳስበው። በወያኔ መደምሰስ ጉዳይ እራሳቸው ወያኔዎችን ሊያሳስባቸው ይገባል።ምክንያቱም የሰሩት ግፍ የትም ቢሄዱ ሊደበቁ ስለሚያስችላቸው። ሊያሳስበን እና በጥንቃቄ ሊታይ የሚገባው ጉዳይ ወያኔ የማጥፋት ስራ በሚሰራበት ግዜ በመሃል አቅጣጫውን ሊያስቱ የሚችሉት የISIS ግሩፕ እንዳይገቡ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ሊያስቡበት እና ኃላፊነትን እንዳለባቸው ሊያውቁት ይገባል። የውሻ እና የክርስቲያን ድምጽ መስማት የማይፈልገው አክራሪው ቡድን ለክርስቲያኑ፣ ለሺአው ሙስሊም፣ ለዋቄ ፈናው፣ ለይሁዲው፣ እምነት ተከታዮችን ለማጥፋት የተነሳ ኃይል ሰለሆነ በህብረት እንቅስቃሴውን በነቃ ሁኔታ ልንጠብቀ ይገባል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በመሸፋፈን አደጋውን ልናስቆመው አንችልም።

ከላይ ካርታው ላይ እንዳየነው ኢትዮጵያ እስላም እስቴት የሚለው ላይ የተካተተች አገር በመሆኗ ለአደጋው ከታለሙላት አገር ተርታ ተሰልፋለች ማለት ነው። ISIS በከፍተኛ ፍጥነት እየተጓዘ ብዙ አገራትን በመያዝ እና በመንቀሳቀስ የንጹኃኑን ደም በከንቱ በአረመኔአዊ እና ሴጣናዊ ሁኔታ እያፈሰሰ ይገኛል። ይህ ቡድን የአገራትን የፖለቲካ አለመረጋጋትን አይቶ ሰርጎ በመግባት ለከፍተኛ ብጥብጥ እና ጥፋት የሚዳርግ ስለሆነ ለውጡ በሚመጣበት ሰአት የፖለቲካ ታጋዮች ግምት ውስጥ በማስገባት የISISን እንቅስቃሴ በአገራችን ሰርጎ እንዳይገባ በጥንቃቄ መራመድ አለብን።
ከ-ከተማ ዋቅጅራ 25.02.2015 Email- waqjirak@yahoo.com

The post የISIS ሁኔታ አቅሎ ማየት እና መደባበስ ሳይሆን ትክክለኛውን ነገር በመናገር በአገር ላይ የተቃጣውን ጥፋት ማስቆም ያስፈልጋል appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: እንቁዋ አትሌታችን ገንዘቤ ዲባባ ፉክክሯ ከሰዓት ጋር እየሆነ መጥቷል

$
0
0

ከቦጋለ አበበ

ልክ የዛሬ ዓመት ነው ገንዘቤ ዲባባ በሦስት ሺ ሜትር የቤት ውስጥ የዓለም ክብረወሰንን በማሻሻል ዓለምን ማስደመም የጀመረችው። ዘንድሮም ልክ በዓመቱ ገንዘቤ የውድድር ዓመቱን በክብረወሰን ታጅባ ታሪክ በመሥራቷ ቀጥላለች።
የታላላቅ እህቶቿን ፈለግ ተከትላ በአትሌቲክሱ ዓለም አዲስ ታሪክ እየሠራች የምትገኘው ገንዘቤ ባለፈው ዓመት በስዊድን ስቶክሆልም ኤሪክሰን ግሎብ አሬና የቤት ውስጥ ውድድር በሦስት ሺ ሜትር የዓለምን ክብረወሰን አስመዝግባ ዘንድሮ በተመሳሳይ ውድድር በአምስት ሺ ሜትር ያንኑ ታሪክ መድገም ችላለች።
genzebe 2

ገንዘቤ ወደ ውድድሩ እንደምትመለስ ከታወቀበት ጊዜ አንስቶ ያለፈውን የሦስት ሺ ሜትር ታሪክ በአምስት ሺ ሜትር እንደምትደግም በርካታ ወገኖች ተስፋ አሳድረው ነበር። እርሷም በስቴዲየም የታደሙትን አሥር ሺ ደጋፊዎቿን አላሳፈረችም። የስፖርቱ ተንታኞች የሰጧትን ግምትም አሳክታለች። አሁን አሁን ገንዘቤ ውድድሯ ከአትሌቶች ጋር ሳይሆን ከሰዓት ጋር እየሆነ ነው። በቤት ውስጥ ውድድሮች ገንዘቤ ውድ ገንዘብ መሆኗን በርካታ የስፖርቱ ቤተሰቦች አፋቸውን ሞልተው ይናገሩላታል።

ገንዘቤ ይህን ታሪክ ያስመዘገበችበት ሰዓት 14፡18፡86 ሲሆን፤ ከቀድሞው ክብረወሰን በአምስት ሰከንድ የተሻለ ነው። የርቀቱ ክብረወሰን ከስድስት ዓመት በፊት እዚያው ስቶክሆልም በመሠረት ደፋር የተያዘ ነው። ገንዘቤ የዛሬ ዓመት በሦስት ሺ ሜትር ያስመዘገበችው የዓለም ክብረወሰንም ቀደም ሲል በመሠረት ደፋር ተይዞ የነበረ ነው።
genzebe 1

ገንዘቤ የውድድሩን የዓለም ክብረወሰን ለማሻሻል አሯሯጩ ቢያንስ እስከ ውድድሩ ግማሽ ድረስ ሊያሯሩጣት ይገባ ነበር። ይሁን እንጂ ገንዘቤ አሯሯጭ ያስፈለጋት እስከ ሁለት ኪሎ ሜትር ድረስ ብቻ ሆኗል። ከአሥራ ሁለት ወራት በፊት ገንዘቤ ዲባባ አዲስ ታሪክ መሥራት እንደምትችል ያሳየችበት ወቅት ነበር። ከሦስት ሺ ሜትር የዓለም ክብረወሰኗ በኋላ በሁለት ሳምንታት ውስጥ የአንድ ሺ አምስት መቶ ሜትርና የሁለት ማይል የቤት ውስጥ የዓለምን ክብረወሰን በእጇ ማስገባቷ አይዘነጋም። በዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናም ከሁለት ዓመት በፊት በአንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር ያስመዘገበችውን የወርቅ ሜዳሊያ በሦስት ሺ ሜትር መድገም ችላለች።

ገንዘቤ የቤት ውስጥ ውድድሮች እንቁ መሆኗን ቀጥላለች። የዘንድሮው የውድድር ዓመት የመጀመሪያ የውድድር ምዕራፏ ብሩህ ሆኗል። ከእዚህ በኋላ በሚኖራት ውድድርም ገንዘቤ ሌላ ታሪክ አትሠራም ብሎ መገመት አይቻልም። አሁን ያስመዘገበችው ክብረወሰንና አስደናቂ ብቃት የአትሌቲክስ አፍቃሪው ብዙ እንዲጠብቅባት አድርጓል።
genzebe dibaba
ገንዘቤ ከትናንት በስቲያ ያሳየችው ድንቅ ብቃት ኢትዮጵያ በመጪው ክረምት ቤጂንግ ላይ በሚካሄደው የዓለም ሻምፒዮና ተስፋ እንድትጥልባት አድርጓል። በተለይም ታሪካዊቷ የረጅም ርቀት ንግስት ጥሩነሽ ዲባባ በእርግዝና ምክንያት በዘንድሮው የዓለም ሻምፒዮና አለመካፈሏ ለኢትዮጵያ ስጋት ቢሆንም ታናሽ እህቷ ገንዘቤ ዲባባ በምትኩ የወርቅ ሜዳሊያ እንደምታመጣ ተስፋ ሆናለች።

The post Sport: እንቁዋ አትሌታችን ገንዘቤ ዲባባ ፉክክሯ ከሰዓት ጋር እየሆነ መጥቷል appeared first on Zehabesha Amharic.

ታሪካዊ የአድዋን መታሰቢያ በአል ማስታወቂያ

“ሰማንያ አንድ ዜሮዜሮ –ኤ” (ክንፉ አሰፋ)

$
0
0

ወቅታዊው የቴሌቭዥናችን አዝማች፤

.. ሰማንያ አንድ ዜሮዜሮ- ኤ ብለሽ መላዕክት ከላልሽ፣

አባይን ገድበሽ ሽልማት በሽበሽ። …. 8100 …. 8100 …. 8100-A A A

Fake-Indian-degrees-aboundየምትለው ዜማ በብዛት ትለቀቃለች። ኮሜዲያን ተሰብሰበው የሰሩዋት ዜማ ናት። ቀልደኞቹን ማኖ ለማስነካት ተብላ የተቀነባባረች ነገር ናት የሚሉም አሉ። የቴሌቭዥኑን ጣብያ ከፍቶ የሚመለከተው ሰው እጅግ ጥቂት ቢሆንም መልእክቱ በማህበራዊ ድረ-ገጾች መደመጡ አልቀረም። የዚህ ማስታወቅያ አላማ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የእጣው ዝርዝር ግን ለብዙዎች እንግዳ ሳይሆን አልቀረም።

አንዲት አዛውንት የልጃቸውን ተንቀሳቃሽ ስልክ እያነሱ ይቀጠቅጣሉ።  በሳምንት ሶስቴ 8100 እየደወሉ ‘A’ ፊደልን ይጫናሉ። ከብዙ ግዜ በኋላ ታዲያ ልጃቸው አወቀባቸው። በመገረምም ለምን ይህንን ሁሉ ግዜ መደወል እንደፈለጉ ጠየቃቸው።  እናት መለሱ “ሁሉም ነገር አለኝ። ዲግሪ ግን የለኝም። በዚህ እድሜየም  በአቋራጭ ካልሆነ ላገኘው አልችልም።” ሲሉ የማስትሬት ዲግሪው እጣ እንዳጓጓቸው ነገሩት።

ሶስት ብር ከፍሎ ‘8100-A’ አጭር መልዕክት የላከ ሰው ሁሉ እጣ ይወጣለታል። እነሱ እንደሚሉት ከሆነ እድሉ የቀናው ሰው የመኖርያ ቤት፣ መኪና፣… እንዲሁም ዶክትሬትና ማስትሬት ዲግሪ ይደርሰዋል።

ማስትሬት እና ዶክትሬት ዲግሪ በእጣ እንዴት ነው ለህዝብ ሊቀርብ የሚችለው? መሰረታዊ ትምህርት የሌለው  አንድ አርሶ-አደር አልያም አንዲት የቤት እመቤት የዶክትሬት ዲግሪ እጣ ቢደርሳቸው ዩኒቨርሲቲ ገብተው ዲግሪያቸውን ሊጭኑ ነው? ብቻ  ምን ችግር አለ?  ለመዕተ-ዓመቱ እቅድ ማሟያ ተብለው የተሰሩት ፴ ዩኒቨርሲቲዎች አሉ። ምሁራንን ሳይሆን ‘ድንጋይ ማምረቻ’ እየተባሉ የሚተቹ ዩኒቨርሲቲዎች። የኮሌጅን መስፈርት በአምስት በመቶ እንኳን የማያሟሉ ባዶ ህንጻዎች። ከነዚህ ኮሌጆች እየተመረቁ የሚወጡት ተማሪዋች ስማቸውን እንኳን በቅጡ መጻፍ አይችሉም የሚባሉበት ኮሌጆች።

ለነገሩ በስልጣን ላይ ያሉትም ሁሉ ዛሬ የማስትሬት እና የዶክትሬት ዲግሪ ባለቤቶች ሆነዋል። ሴንቸሪ ዩኒቨርሲቲ ምስጋና ይግባውና እነ አባዱላ ገመዳም ማስትሬት ዲግሪ ገዝተዋል። ጀነራል ባጫ ደበሌም ሁለት ዲግሪ ጭነዋል።

ያልተጠና እና ግብታዊ በመሆኑ ይመስላል የ 8100-A ዘመቻ መቀለጃ እየሆነ መምጣቱ። ኢሳያስ አፈወርቂም የዚህ እጣ እድል ደርሷቸዋል አሉ። ባለፈው ሰሞን የኢትዮጵያ አየር ሃይል ባልደረባ የነበረው ካፒቴን የህወሃትን ስርዓት በመቃወም ይዞት የጠፋውን ሚግ 23 አውሮፕላን ለአስመራው መንግስት እንዳስረከበ ነበር ይህ ቀልድ የተነገረው።

የዚህ ጽሁፍ ዋናው ጉዳይ የትምህርት ማሽቆልቆል ነገር አይደለም። የ 8100-A ዜማ እንዳበቃ  ባናቱ ላይ የሚነገር አንድ መልእክት ላይ እንጂ። የሰማንያ አንድ ዜሮ-ዜሮ ቁልፍ በእዚህ መልእክት ላይ ይገኛል።

“እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን?”

ምን ማለት ነው? ላይጨርሱት ኖሯል እንዴ የጀመሩት? አባባሉ የጀመሩትን የመጨረስ ጥርጣሬ ውስጥ እንዳሉ ፍንጭ ይሰጠናል። ፍጹም በግብታዊ በሆነ፣ በዕውቀት እና ዕቅድ ላይ ያልተመረኮዘ፣  የባለሙያ ክህሎት ያልነበረው ጅምር መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳየናል።

“እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን!” መፈክር ሆነ። እድገት የሚመጣው በመፈክር ሳይሆን በስራ ነው። ስራ ደግሞ በእውቀትና በእቅድ እንጂ በስሜት አይከወንም።

ሃይለማርያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱ ስልጣን ላይ ጉብ ያሉ ሰሞን ደጋግመው የሚሉት ነገር ነበር። “እዚህ የተቀመጥቁት መለስ የጀመረውን እቅድ ሁሉ ለመጨረስ ነው።”

ይህን ካሉን ሶስት አመታት አለፉ። ሃይለማርያም ደሳለኝ የጨረሷቸውን ፕሮጀክቶች ስንፈትሽ አንድ ነገር ብቻ አገኘን። እሱም የጸረ-ሽብር አዋጁን ተግባራዊ በማድረግ የህሊና እስረኞችን ቁጥር መጨመር ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ በገዢው ፓርቲ ተጀምረው የተጨረሱ ነገሮች የሉም። ሌሎቹን ለግዜው ተወት አድርገን የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶችን ብቻ እንቃኝ።  አስራ አንድ ግድቦች ተጀምረዋል። ግን ሁሉም አላለቁም። ለምን? በዚህ ላይ ወደ ኋላ እመለስበታለሁ።

ባለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት የተጀመሩት የመስኖ እርሻ እና የሃይድሮ-ኤሌክትሪክ ልማት ፕሮጀክቶች በርካታ ናቸው። የተንዳሆ ግድብ፣ የከሰም ግድብ፣ የርብ ግድብ፣ የጊዳቦ ግድብ፣ የአርጆ ደዴሣ ግድብ፣ የራያ አዘቦ ግድብ፣ የቆቦ ጌራ ግድብ፣  አድአ በቾጠ ግድብ፣ የቆጋ ግድብ፣ የመገጭ ግድብ፣ እንዲሁም የጉደር እና ዳቡስ ግድቦች ናቸው። በ፩፱፱፯ ዓ.ም  በአፋር የተጀመረው የከሰምና የተንዳሆ ግድብና መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ  አመታት አለፉት። የታቀደለት ጊዜ ከ ፭ አመት በፊት ቢያልፍም ስራው ገና አልጀመረም። በ፪፻፪ ዓ.ም የተጀመረው የርብ ግድብ ግንባታ፣  የጊዳቦ ግድብ ግንባታ፣ የአርጆ ደዴሣ ግድብና መስኖ ልማት፣ የራያ አዘቦ  መስኖ ልማት፣ የቆቦ ጊራ መስኖ ልማት፣ አድአ በቾጠ መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ሁሉ ግዚያቸውን በልተው የኤሊ ጉዞ ላይ ናቸው።  ግንባታው በ፪፻፬ የተጀመረው የቆጋ መስኖ ልማት፣ የመገጭ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት፣ ላይኛው ጉደር መስኖ ልማት፣ ዳቡስ መስኖ ልማት … ተጀምረው ቆመዋል።…እነዚህ እንግዲህ “እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን!”  ያልተባሉ ፕሮጀክቶች ናችው። ምክንያቱም የፖለቲካ ጠቀሜታቸው ይህን ያህል ስላልሆነ።

እርግጥ ነው። በመጀመሪያው “የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ” ውስጥ የአባይ ግድብ ፕሮጀክት አልነበረም። ከበጀቱም ውጭ ነው። ስለሆነም አጀማመሩ ድንገት ነበር። ጥናት ሳይጠና፣ ሳይመከር፣  በጀት ሳይያዝ የተጀመረ ፕሮጀክት ነው።  አባይ በባዶ ተጀመረ። የቦንድ ሽያጭ ተሞከረ።…እንዲህ እያለ ሎተሪ ላይ ደረሰ… ይህ ብዙ እንዳላስኬደ በግልጽ ይታያል። በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ሁሉም ነገር በስሜት እና በግብታዊነት ስለሚሰራ የአጭር ጊዜን እንጅ ረጅሙን አያዩትም። በመጨረሻ ግን ግዜው ደርሶ ማጠፊያው ሲያጥራቸው ይታያሉ።  የዚህ ፕሮጀክት አጀማመር በእርግጠኝነት አባይን ገድቦ ልማት ላይ ለማዋል ተብሎ ሳይሆን ከወቅታዊው የስልጣን ችግር ለማምለጥ የተወጠነ  እቅድ ነበር።  ለግዚያዊ ጥቅም ተብሎ እንደቀልድ የተጀመረው ነገር አሁን የህዝብ እምሮ ውስጥ ስለገባ ይመስላል ቅኝቱን ያስተካከሉት። … እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን!

የአባይ ጉዳይ ለገዥው ፓርቲ  ህልውና ወሳኝ ነገር ተደርጎ ተወስዷል። ከኢኮኖሚው ይልቅ የፖለቲካ ጠቀሜታው ቀላል አይደለምና።  የኢኮኖሚውን ጠቀሜታ ቢመለከቱ ኖሮ አባይን መገደብ እንደሚያወሩት ከባድ አልነበረም። ገዥው ፓርቲ ለሃገር ካሰበ ገንዘቡም ቅርብ ነው። የዜጎች ደሞዝ ሳይቆረጥ፣ ቦንድ ሳይሸጥ፣  ህዝብ ሳይቸገር፣ ቀረርቶ ሳይነፋ… አባይን መገደብ ይቻላል። የኤፈርት ገንዘብ ብቻ አንድ ሳይሆን ሃምሳ አባይን ይገድበዋል። በግል ከተዘረፈው 16ቱ ቢሊየን ዶላር ሳይነካ ማለት ነው።

አባይ ተገድቦ አገልግሎት ቢሰጥ መልካም ነገር ነው። ይህ ጎስቋላ ህዝባችንም ከድህነት አረንቆ ሲወጣ ብናይ ሁላችንም ደስታችን ነው።ዲያስፖራውም አባይ ተገድቦ ማየት ይፈልጋል።  ችግሩ ያለው ግልጽነት እና ቅንነት በጎደለው በዚህ መልኩ ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል ብቻ በመከናወኑ ነው። ችግሩ ያለው በልማት ስም በሚደረገው የሰብአዊ መብት ጥሰት ላይ ነው። አባይን ከመገደቡ በፊት የመብት ረገጣው ቢገደብ ዲያስፖራውም በዚህ ላይ በተረባረበ ነበር።

“እድገትና ትራንስፎርሜሽን” የተባለው “ቅኝት” አምስቱን አመት እንደዋዛ ዘልቆታል። የተባለው ለውጥ ግን አልታየም። ሃይለማፘም ደሳለኝ ፓርላማ ላይ ጉብ ብለው በእቅዱ አፈፃፀም የነበሩ ተግዳሮቶችን ዘርዝረውልናል። አፈጻጸም አሉን እንጂ ነገሩ ሌላ ነው። ከ85 በመቶ በላይ የሚሆነው የአገሪቱ ህዝብ የሚተዳደርበትን የግብርናውን ዘርፍ  ለማሻሻል የታቀዱ የመስኖ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ አልሆኑም። የገጠር መንገዶች ሰባ በመቶ እንደሚሰሩ ቅኝቱ ላይ ነበር። ይህም ፈጽሞ ሊሆን አልቻለም። አሁን ያለውን አስር በመቶ የኤሌትርክ ሃይል ተጠቃሚ በሰማንያ አምስት በመቶ ለማሳደግ ቃል ገብተው ነበር። ወጤቱን ስናየው ግን የነበረው አስር በመቶም ወደ ፈረቃ አሽቆልቁሎ መሄዱን ነው።

በደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ታምቦ ምቤኪ የሚመራው የጥናት ቡድን ባለፈው ወር ከሂልተን ሆቴል የለቀቀው ዘገባ በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው ስለዘረፋው አስደንጋጭም አስረጋጭም ነበር። ከኢትዮጵያ ተዘርፎ የወጣው ገንዘብ 16.5 ቢሊየን ዶላር መድረሱን አረጋግጦልናል።  ይህ አስደንጋጭ ዘገባ ከዚህ ቀደም Global Financial Integrity (GFI)  አለማቀፍ የገንዘብ ግልጸኝነት ተቋም ዘገባ ላይም ወጥቷል።  የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽባል ዘገባ እንደሚለው ከሆነ ከተዘረፈው ገንዘብ ግማሽ ያህሉ ከሃገር የወጣው በእድገት እና ትራንስፎርሜሽኑ ዘመን ነው።

ሌላም አስደንጋጭ ነገር አለ። ኢትዮጵያ በዘመነ ህወሃት በዋስትናም ሆነ ያለዋስትና የተበደረችው እዳ 40 ቢሊየን ዩ..ኤስ. ዶላር ደርሷል። ይህን የዘገበው ላሙዲ የተባለው አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ነው። ይህ እዳ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሲሰላ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የግማሽ ሚሊዮን ዶላር ባለ እዳ እንደሆነ ይጠቁመናል። ይህ ገንዘብ ለልማት መዋል ሲኖርበት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ከሀገር እየወጣ መሆኑን ነው እንዚህ አለም አቀፍ ተቋማት እየነገሩን ያለው።

በዚህ በኩል የ”ሰማንያ አንድ ዜሮዜሮ” ዘመቻ፣ በዚያ በኩል ደግሞ ዘረፋው ሊጣጣሙ አልቻሉም። የሚወጣው ከገቢው አልተስተካከለም። ዘረፋው ግዙፍ ነው። በዚህ ሁኔታ ነው መፈክር እየተሰማ ያለው። “እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን!”

በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ከሆኑት ከኬን ኦሃሺ ስለ መፈክሩ ቅኝት የተናገሩት የሚያስደምም ነው።

“ኢትዮጵያ … ተዓምራዊ በሆነ መልኩ የነዳጅ ክምችት ጉድጓድ ካላገኘች ወይንም ያልተጠበቀ – ነፋስ አመጣሽ የሆነ ገንዘብ ከሰማይ እንደ መና ካልወረደ በስተቀር (እድገት እና ትራንስፎርሜሽኑ) በምንም ዓይነት መልኩ ቀጣይነት ያለው መሆኑ አይታየኝም… እንደዚህ ያለውን በኃይል እና በመፈክር የተሞላ እና የውስጥ ችግሩን በጥልቅ ያልተመለከተ ዕቅድ እንዴት ሊያስቀጥሉት እንደሚችሉ የሚታየኝ ነገር የለም።  እንደ ሀገር በቂ የሆነ ጥሪት መቆጠብ እስካልተቻለ ድረስ ምንጊዜም ቢሆን ጥገኛ የሚሆነው በውጭ መዋዕለ ንዋይ፤ አልያም ደግሞ ጤናማ እና ቀጣይነት በሌለው የመዋዕለ ንዋይ መሰብሰቢያ መንገድ ነው… እንደዚህ ያለ ወጥመድ ውስጥ ነው ተወጥረው ያሉት…

“ዕዳ ካለ አደጋ አለ… ይህ የመንግስት-መራሹ ኢንቨስትመንት ዕድገት አንድ ቦታ ላይ ቢቆም ወይም ለጥቂት ጊዜ መንቀሳቀስ ባይችል እና ቢንገዳገድ እነዚህ ሁሉ የብድር ዕዳዎች ይመሰቃቀላሉ…የግል ዘርፉን ባላሳተፈ እና ጠንካራ ሆኖ ባልተስፋፋበት መልኩ የሚመጣ ፈጣን የምጣኔ ሀብት ዕድገት ዘለቄታ እንደማይኖረው እና፤  ይህ ከሆነ እነዚህ በጊዜ ሂደት የሚደረጉ የብድር ዕዳዎች ሁሉ ከቁጥጥር ውጭ ሊሆኑ የሚችሉ መሆናቸው እጅጉን ያሳስበኛል።”

ሲሉ ለገዥው ፓርቲ ዱብዳ የሆነ ይህን እውነታ አፍረጥርጠውታል። እውነታው ይህ ነው። ሳይጨመርና ሳይቀነስ የቀረበ የገለልተኛ አካል ምልከታ።

ሁላችንም በአንድነት እንዲህ እንበል። አባይ ይገደባል። ከአባይ በፊት ግን የመብት ረገጣው ይገደብ!

በሰሞኑ ቀልድ ልሰናበት። ጎተራ አካባቢ ነው። መብራት ፈረቃውን ተከትሎ ጠፍቷል። የሰፈሩ ማጅራት መቺ ምሽቱን ተገን በማድረግ ፍተሻ ጀምሯል። ጸዳ ያለ መኪና አቁሞ ወደ ቅምጥ ቤቱ እየነካ ያለውን ስውዬ አስቆመው።

“ቁም! ሳተበላሽ ገንዘብህን በሙሉ አስረክብ!”

“ምን ነካህ!  እኔ’ኮ ባለስልጣን ነኝ።  ምንስቴር!” ባለስልጣኑ መለሰ።

“አሃ!  ክቡር ሚኒስቴር እንግዲያውስ ገንዘቤን ሃምጣ!”

***

 

ለዛሬ በዚህ እነሰነባበት። በሚቀጥለው ጽሁፌ ስለ ኢሳያስ አፈወርቂ የምለው አለኝ። የነገ ሰው ይበለን።

 

 

The post “ሰማንያ አንድ ዜሮዜሮ – ኤ” (ክንፉ አሰፋ) appeared first on Zehabesha Amharic.

119ኛው የአድዋ ድል በዓል ቀን በዳላስና አካባቢዋ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ

$
0
0

እንደሚታወቀው አሁን የያዝናት ወር ለኛ ለኢትዮጵያውያን ብሎም ለመላው ለጥቁር ህዝብ ትልቅ ድል የተከናወነበት ወር ነው። መላው አለም ነጭ የበላይ አድርጎ በሚቆጥርበትና ሁሉም የአፍሪካ አገሮች በቀኝ ግዛት በወደቁበት ወቅት ኢትዮጵያን ለመውረር የመጣውን የጣልያን ጦር በጀግናው በአፄ ምኒሊክ ብልህ መሪነት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ኢትዮጵያን ከቀኝ ግዛት ያዳኑበት ወር ሲሆን በአለማችን የሚገኙ ጥቁሮችና በቅኝ ግዛት የነበሩት የአፍሪካ አገሮች ለነፃነታቸው እንዲታገሉ ተስፋ የሆናቸው ድል ነው። ይህ የሆነው March 1, 1896 ነበር። እነሆ ታሪክና ትውፊት መጠበቅ ለአንድ አገርና ሕዝብ ህልውና መሆኑን በመገንዘብ 119ኛው የአድዋ ድል በዓል ቀን በዳላስ በግራንድ ሆቴል (Grand Hotel) ለማክበር ተዘጋጅተናል። በዳላስና አካባቢ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያ March 1, 2015 በግራንድ ሆቴል (Grand Hotel) በመገኘት የበዓሉ ተካፋይ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል።

Guest Speakers:-
1. Mr. Obang Metho
Executive Director of SMNE
2. Prof. Solomon A. Getahun
Associate Proffesor of History Department at CMU
3. Journalist Kifle Mulat
Former President of EFJA

Place:- Grand Hotel Located @ 7815 LBJ Frwy, BLDG B Dallas, Tx 75251
Date:- March 1, 2015
Time:- 4 PM – 8 PM

For more info:- 1(214) 404 4737
#ኢትዮጵያውያን #አድዋ #ጥቁር

 

unnamed

The post 119ኛው የአድዋ ድል በዓል ቀን በዳላስና አካባቢዋ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live