Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

Who’s a Terrorist? – TPLF or Ginbot 7?


Unique Panel Discussion on the need for political change in Ethiopia – Washington DC & Addis Ababa (Flyer)

$
0
0
Unique Panel Discussion on the need for political change in Ethiopia – Washington DC & Addis Ababa – Monday Jan 19th @11AM – 7701 16th St NW Washington DC

Egypt rejects Ethiopia dam storage capacity

$
0
0
Egypt’s irrigation ministry says the current capacity of the Renaissance Dam will negatively affect its water share Egypt has objected to the storage capacity of Ethiopia’s Grand Renaissance Dam, currently under construction, which it fears will negatively affect its Nile water share. Alaa Yassin, spokesperson on the Ethiopia dam issue for Egypt’s irrigation ministry, called […]

40 ETHIOPIANS INTERCEPTED FOR ILLEGAL ENTRY IN Malawi

$
0
0
Police officers in central region of Dowa recently intercepted and arrested 40 Ethiopian nationals and a Malawian national for allegedly assisting them to enter into the country illegally. Wise Upambo, a Malawian national aged 21 and the Ethiopian nationals were intercepted by the law enforcers during a sweeping exercise held in the district. Reports reaching […]

California links 26 measles cases to Disneyland outbreak

$
0
0
(Reuters) California has confirmed more cases of measles in people who visited Disneyland or its adjacent California Adventure park last month, health officials said on Monday, raising the number of infected people to 26. A total of 22 cases in California have been linked with visits to the Anaheim parks between Dec. 15 and Dec. […]

ምርጫ ቦርድ ከመኢአድ፤ አንድነትና ሰማያዊ ፓርቲ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብቷል

$
0
0

ተከፋፍለዋል’ ያላቸው የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት – መኢአድና የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ – አንድነት የአመራር አባላት  በሚቀጥሉት ሁለት ሣምንታት ውስጥ በየችግሮቻቸው ላይ ጠቅላላ ጉባዔዎቻቸውን አስወስነው ለቦርዱ ሪፖርት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ለሰማያዊ ፓርቲ ደግሞ “የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥቻለሁ” ብሏል።

ፓርቲዎቹም ምላሽ ሰጥተዋል፤ ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ የያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

VOA 1

 

አንድ ጥያቄ ስለ አንድነት! –አቤ ቶኮቻው

$
0
0

አንድነት ፓርቲ ምርጫ ቦርድ ባስጠነቀቀው መሰረት ጠቅላላ ጉባኤውን አድርጎ ሊቀመንበሩን ድጋሚ መርጧል። ይሄንንም ከምርጫው ቀን ቀደም ብሎ ጀምሮ በፎቶግራፍ እያስደገፉ ያፕርቲው ልጆች ሲያሳዩን እኛም እየተደነቅን ላይክም ሼርም ስናደርገው ሰንብተናል። ልክ የጠቅላላ ጉባኤው እለት ታድያ አቶ ትዕግስቱ የተባሉ ሰውዬ ሌላ ቦታ የአንድነት ሊቀመንበር ተደርገው ተመረጠዋል ተባልን።

ከሁሉ ታድያ ግራ የገባኝ ስለ አቶ ትግስቱ የሚከራከሩላቸው የ ኢህአዴግ ስጋ ዘመዶች እንጂ መራጮቻቸው አይደሉም። ምንደነው ነገሩ የኢህአዴግ የስጋ ዘመዶች ስለ አቶ ትዕግስቱ በጣም አብዘተው የተጨነቁት ለምንደነው… የአቶ ትዕግስቱ መራጮችስ ስለምን አደባባይ ወጥተው ”እኛ ነን ትክክለኛውን ምርጫ ያደረገነው…” ብለው ለምን አይሞግቱንም። እውነት እውነት እላችኋለሁ አስራ አንድ ሰው አልጠራም እስቲ አንድ ሰው ጮክ ብሎ እኔ ከአቶ ትግስቱ ወገን ነኝ ሊቀመንበሬ እርሳቸው ናቸው ይበለን… !

ይሄው ቃለ ማህላ ሲፈጽሙ የተነሱት ፎቶ እንኳ ሳይቀር በስለላ የተገኘ ነው! ለንጽጽር የዋናውን አንድነትም ቃለ ማህላ ፎቶ እንየውማ! (የመጀመሪያው ዋናዎቹ አንድነቶች የመረጡዋቸው አቶ በላይ ሲሆኑ ቀጥሎ ያሉት ደግሞ አቶ ትግስቱ ናቸው…)

tigetu

የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ቃጠሎ ውዝግብ ፈጥሯል

$
0
0

bee392ccb91b968f78a29a035271c5d5_L

‹‹የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች እንደደረሱ ቢያጠፉ ሆቴሉን ማትረፍ ይቻል ነበር›› የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ሥራ አስኪያጅ

‹‹በተደወለልን በሁለት ደቂቃ ውስጥ ደርሰናል›› የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ባለሥልጣን

አዲስ አበባ ከተማ በተቆረቆረች በ19ኛ ዓመቷ በአሁኑ አጠራር በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት ፒያሳ በ1898 ዓ.ም. በተገነባውና 109ኛ ዓመቱን ባስቆጠረው እቴጌ ጣይቱ ሆቴል ላይ፣ ጥር 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ከማለዳው 2፡15 ሰዓት አካባቢ የደረሰው የእሳት ቃጠሎ እያወዛገበ ነው፡፡

ለእሳቱ መነሻ ቦታና ምክንያቱ እስካሁን ያልተደረሰበትና በቃጠሎው ምን ያህል ንብረት እንደወደመ የሆቴሉን ባለቤቶች ጨምሮ መግለጽ የሚችል አካል ባይገኝም፣ ከሆቴሉ ሕንፃ ጋር ተያይዞ በተሠራው ‹‹ጃዝ አምባ ላውንጅ›› መዝናኛ የመጀመሪያው እሳት የታየ ከመሆኑ አንፃር፣ የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን ፈጥኖ ደርሶ ቢሆን፣ እሳቱን እዚያው የታየበት ቦታ ማስቀረት (ማጥፋት) ይቻል እንደነበር በአካባቢው የተገኙ ሰዎች እየገለጹ ነው፡፡

በዕለተ ሰንበት (እሑድ) ጥር 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ከማለዳው 2፡15 ሰዓት አካባቢ የእሳት አደጋው እንደተነሳ እንደሰሙና መኖሪያቸው ከሆቴሉ ብዙም ያልራቀ በመሆኑ፣ በአሥር ደቂቃ ውስጥ መድረሳቸውን የሚናገሩት የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ሥራ አስኪያጅ አቶ አያሌው ታደሰም፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና በቃጠሎው ወቅት በሥፍራው የነበሩ ሰዎች በሚሉት ይስማማሉ፡፡

የስልክ ጥሪ በደረሰው በሁለት ደቂቃ ውስጥ በአደጋው ቦታ መድረሱንና ያለውን ኃይል ሁሉ በመጠቀም፣ አደጋው ወደ ሌላ አካባቢ ሳይዛመት ሊቆጣጠር እንደቻለ እየገለጸ የሚገኘውን የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣንን የሚቃወሙት ሥራ አስኪያጁ፣ የባለሥልጣኑ ሠራተኞች ‹‹በሁለት ደቂቃ ደርሻለሁ›› ማለታቸውን ‹‹በፍፁም አልደረሱም›› በማለት ተቃውመዋል፡፡

እንደ አቶ አያሌው ገለጻ፣ በሁለት ደቂቃ ወይም በሌላ ማለቱን ትተው በደረሱበት ወቅት ማጥፋት ቢጀምሩ ኖሮ፣ እሳቱ ወደ ሆቴሉ ሕንፃ ሳይዛመት ጃዝ አምባ ላውንጅ ላይ እያለ ማጥፋት ይችሉ ነበር፡፡ ስልካቸው አልሠራ በማለቱ በመኪና እዚያው ድረስ ተሄዶ እንደተነገራቸውና ነጋሪው መጥቶ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደደረሱም ይዘውት የመጡት የእሳት ማጥፊያ ተሽከርካሪ ማጥፋት የሚችል ባለመሆኑ እሳቱ ወደ ሆቴሉ ሊዛመት መቻሉን አስረድተው፣ ‹‹ስለ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ፍጥነትና መዘግየት በወቅቱ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ይናገሩ፤›› ብለዋል፡፡

እሳቱ ከማብሰያ ክፍል ስለመነሳቱ የተጠየቁት ሥራ አስኪያጁ፣ ‹‹እሳቱ መቶ በመቶ ከማብሰያ ክፍል (ኪችን) አልተነሳም፡፡ መነሻው የሚሆነው ጃዝ አምባ እንደሚሆንና ምክንያቱ ደግሞ ቀድሞ የተቀጣጠለውና ሙሉ በሙሉ የወደመውም እሱ ነው፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡ ጃዝ አምባ እየነደደ የሆቴሉ ማብሰያ ክፍል በሥራ ላይ እንደነበረና በማብሰያ ክፍል ውስጥ የነበሩትን እሳት አባባሽ ነገሮችን ቀድመው ማስወገድ መቻላቸውንም ገልጸዋል፡፡ በጃዝ አምባ ላውንጅ ውስጥ እሳት ሊያስነሳ የሚችል ነገር ስለመኖሩ ተጠይቀው፣ በጃዝ አምባ ውስጥ ሊቀጣጠል ወይም እሳት ሊያስነሳ የሚችል ነገር እሳቸው እንደማያውቁ ገልጸው፣ በወቅቱ ምን እንደነበርም ማወቅ እንዳልቻሉ አስረድተዋል፡፡ ጃዝ አምባ ላውንጅ አብዛኛውን ጊዜ የሚሠራው በምሽት ከመሆኑ አንፃር እሳቱ በተነሳበት ወቅት ሥራ ስለመኖሩ የተጠየቁት ሥራ አስኪያጁ፣ እሳቸው ጠዋት ባይኖሩም የላውንጁ ሠራተኛ የሆነ አንድ ሰው ከጠዋቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ገብቶ መውጣቱን እንደሰሙ ጠቁመዋል፡፡ ጃዝ አምባ ላውንጅ መሥራት ከጀመረ ከሦስት ዓመታት በላይ እንደሆነውም ተናግረዋል፡፡

እቴጌ ጣይቱ ሆቴል ባለአንድ ፎቅ ሲሆን፣ አሥር የመኝታ ክፍሎች እንዳሉትና በእያንዳንዱ ክፍል ሁለት ሁለት አልጋዎች በመኖራቸው፣ በጠቅላላው 20 አልጋዎች እንዳነበሩ ሆነው ሙሉ በሙሉ መቃጠላቸውንም ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ደንበኞቻቸው የውጭ አገር ዜጐች መሆናቸውንም አክለዋል፡፡ በሆቴሉ ውስጥ የነበሩ ቁም ሳጥኖች ከእነዕቃዎቻቸው፣ የተለያዩ ታሪካዊ ምሥሎች፣ ቅርፃ ቅርፆችና ሌሎች ብዙ ዕቃዎች መውደማቸውንም ሥራ አስኪያጁ አስረድተዋል፡፡

የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን ግን፣ በአካባቢው ነበርን የሚሉትንም ሰዎች ሆነ ሌላ አካል የሚለውን አይቀበልም፡፡ የባለሥልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ደጋፊ የሥራ ሒደት መሪ አቶ ሰለሞን መኰንን ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ እቴጌ ጣይቱ ሆቴል ላይ ቃጠሎ እንደተነሳ መረጃ የደረሳቸው ከማለዳው 3፡08 ሰዓት ነው፡፡ የእሳት አደጋ መከላከል ቡድኑ ወዲያው ተሰማርቶ በሁለት ደቂቃ ውስጥ በቦታው ደርሷል፡፡ ‹‹አደጋው ከባድ ነበር፡፡ የባለሥልጣኑ ሰባት ቅርንጫፍ ጣቢያዎች ከባለሙያዎችና ከማሽኖች ጋር ተሰማርተው በመረባረባቸው እሳቱን መቆጣጠር ተችሏል፤›› በማለት ተናግረዋል፡፡

የባለሥልጣኑ ሠራተኞች ከነማሽኖቻቸው ደርሰው በተለያዩ አቅጣጫዎች እሳቱን እየቆረጡ ማጥፋት ባይችሉ ኖሮ፣ በአካባቢው የሚገኙ መሥሪያ ቤቶችንና መኖሪያ ቤቶችን ሊያዳርስና ሊያጠፋ ይችል እንደነበር የተናገሩት የሥራ ሒደት መሪው፣ ‹‹በስንት ሰዓት እሳቱ ተነሳ? በስንት ሰዓት እናንተ ደረሳችሁ? የሚለው ጥያቄ ለእኛ አይጠቅምም፡፡ እኛ የምንሠራው የእሳት ቃጠሎ ተነሳ ተብሎ የተደወለበትን አስበን ነው፡፡ ወዲያው ስላልተደወለ እሳቱ ሊስፋፋ ችሏል፤›› ብለዋል፡፡

በሆቴሉና በባለሥልጣኑ መካከል ያለው ርቀት አጭር ከመሆኑ አንፃር የደረሱበት ሰዓት መዘግየቱን በተመለከተ ተጠይቀው፣ ጥሪው በደረሳቸው በሁለት ደቂቃ መድረሳቸውን የተናገሩት አቶ ሰለሞን፣ እንደተባለው እቴጌ ጣይቱ ሆቴል ለባለሥልጣኑ ቅርብ ከመሆኑ አንፃር የዘገዩት እነሱ ሳይሆኑ፣ ጥሪው የደረሰበት ጊዜ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ባይዘገይ ኖሮ ብዙ ንብረት ማትረፍ ይቻል እንደነበርም አስረድተዋል፡፡

አቶ አያሌው ማብሰያ ክፍሉ ቆይቶ እንደተቃጠለ የተናገሩ ቢሆንም፣ አቶ ሰለሞን ግን ለእሳቱ መባባስ ምክንያቱ በማብሰያ ቦታ አካባቢ የነበሩ ቁሳቁሶች መሆናቸውንና ቃጠሎውንም ከባድ እንዳደረጉት ገልጸዋል፡፡ 113 የባለሥልጣኑ ሠራተኞች በ12 ተሽከርካሪዎችና በአምስት አምቡላንሶች ታግዘው፣ 236,300 ሊትር ውኃና 500 ሊትር ፎም በመርጨት ቃጠሎውን መቆጣጠር መቻላቸውን አቶ ሰለሞን ገልጸዋል፡፡ አደጋውን ለመቆጣጠርም ከሁለት ሰዓት በላይ መፍጀቱን ጠቁመው፣ ምክንያቱ ደግሞ ሆቴሉ ከጥድ እንጨት የተሠራ በመሆኑ በቀላሉ ማጥፋት ስለማይቻል እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

የጃዝ አምባ ላውንጅ ባለቤቶች ወይም ኃላፊዎችን ለማግኘት ባለመቻሉ በእነሱ በኩል ያለውን መረጃ ማግኘት አልተቻለም፡፡

በእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ግቢ ውስጥ ሕብረት ባንክ፣ የትኬት መሸጫ ቢሮና ሌሎች ድርጅቶች ተከራይተው ይሠራሉ፡፡ የትኬት መሸጫ ቢሮ ኃላፊዎችና የሌሎቹ ድርጅቶች ባለቤቶች ጥር 4 ቀን 2007 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፣ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ባለሥልጣን በወቅቱ ደርሶ ቢሆን ኖሮ እሳቱን መቆጣጠር ይቻል ነበር፡፡

በተመሳሳይ የሕብረት ባንክ አክሲዮን ማኅበር ጥር 4 ቀን 2007 ዓ.ም. በፕሬዚዳንቱ አማካይነት መግለጫ የሰጠ ሲሆን መገናኛ ብዙኃንን፣ ኅብረተሰቡንና ሌሎች የሚመለከታቸው አካሎች እሳቱን ለማጥፋትና የደረሰውን አደጋ ለሕዝብ ለማሳወቅ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቋል፡፡ በሆቴሉ ግቢ ውስጥ በነበረው ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ላይ ምንም ዓይነት የገንዘብም ሆነ የመረጃ ሰነዶች መቃጠል እንዳልደረሰበት አስታውቋል፡፡

ደንበኞቹ በሞባይል፣ በኢንተርኔት፣ በኤቲኤምና በሌሎቹም አገልግሎቱን እያገኙና የሚያገኙ በመሆናቸው ምንም ዓይነት ሥጋት እንደሌለ ገልጿል፡፡ እሳት ያልበገረው ካዝናውን በግራይንደር በመቁረጥ ገንዘቡ ተቆጥሮ ከመዝገቡ ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛነቱ መረጋገጡን አስታውቋል፡፡

እቴጌ ጣይቱ ሆቴል በቀድሞ የኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ለአቶ ፍፁም ዘአብ አስገዶም መሸጡ ይታወሳል፡፡ አሁንም የሆቴሉ ባለቤት አቶ ፍፁም ናቸው፡፡ በአፄ በዳግማዊ ምኒልክ ባለቤት እቴጌ ጣይቱ ብጡል በ1898 ዓ.ም. ነው የተገነባው፡፡ የመንበረ ፀሐይ እንጦጦ ማርያም ቤተ ክርስቲያንን ሊመርቅ የመጣው ሕዝብ ምግብና ማረፊያ አጥቶ ስለነበር፣ አፄ ምኒልክ የሌሎች አገሮች የሆቴል ልምድን ከቀሰሙ በኋላ፣ በ1898 ዓ.ም. ‹‹ሆቴል›› የሚል ስያሜ ሰጥተውት ሥራ መጀመሩን የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል ፀሐፊ የነበሩት ፀሐፌ ገብረሥላሴ ካሰፈሩት መረጃ መገንዘብ ይቻላል፡፡

ሆቴሉ ከተሠራ በኋላ ሕዝብ ሊጠቀምበት ባለመቻሉ አፄ ምኒልክ መኳንንቱን እየሰበሰቡ በተደጋጋሚ በመጋበዛቸው፣ የእሳቸውን ብድር ለመመለስ መኳንንቱ ‹‹እቴጌ ውቴል ሄደን እንብላ›› ማለት ስላበዙ ‹‹እቴጌ ሆቴል›› የሚለውን መጠሪያ እንዳገኘም ይታወቃል፡፡

መጠሪያው እስከ 1967 ዓ.ም. የቆየ ቢሆንም፣ ደርግ የንጉሠ ነገሥት ሥርዓቱን ካስወገደ በኋላ ስያሜውን ‹‹አውራሪስ›› ብሎ ነበር፡፡ እስከ ውድቀቱ ድረስ (1983 ዓ.ም.) ሲጠራበት መቆየቱ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ እቴጌ ሆቴል በይፋ የተመረቀው ከ107 ዓመት በፊት ጥቅምት 25 ቀን 1900 ዓ.ም.ነበር፡፡

Source:: Ethiopian Reporter


በጣና ሐይቅ ውስጥ በሚገኘው የዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም አካባቢ እሳት ተነሳ

$
0
0

ፎቶ ፋይል ደጋ እስጢፋኖስ

ፎቶ ፋይል ደጋ እስጢፋኖስ


(ዘ-ሐበሻ) ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንደዘገበው በጣና ሐይቅ ውስጥ በሚገኘው የዳጋ እስጢፋኖስ እሳት ተነሳ::

እንደ ዘገባው ከሆነ እሳቱ የተነሣው ከደኑ አካባቢ ሲሆን ወደ ገዳሙ ገና አልደረሰም፡፡ የክልሉ ፖሊስ ወደ ቦታው በፍጥነት መድረሱ ተሰምቷል ያለው ዲ/ን ዳንኤል አባቶች እሳቱን ቆርጦ ለመከላከል እየሞከሩ ነው ብሏል::

በደጋ እስጢፋኖስ የተነሳውን እሳት በሰው ኃይል ለመከላከል የማይቻል ከሆነ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ክልሉ ገልጦላቸዋል ሲል ዲ/ን ዳን ኤል ዘገባውን ቋጭቷል::

የፖለቲካ ምኅዳሩ እንዳይጠብ ጥንቃቄ ይደረግ!

$
0
0

የአንድ አገር ሉዓላዊነት ባለቤት ሕዝብ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ከምንም ነገር በላይ የአገር የሥልጣን ባለቤት ሕዝብ ነው ማለት ነው፡፡ እንደ እኛ ባለ አገር መቼም ቢሆን ምርጫ ሲከናወን የሥልጣን ባለቤት ሕዝብ መሆኑ ተክዶ አያውቅም፡፡

9f82c54a890bb560467ea1718ee4a9e5_Lነገር ግን ሕዝብ ወሳኝ ሊሆንባቸው በሚገባ የምርጫ ሒደቶች ውስጥ ከሕዝቡ ይልቅ ጎልተው የሚታዩት የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸው፡፡ ምንም እንኳ የሕዝብ ድጋፍ ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች መሆናቸው ቢታመንም፣ በትንሽ በትልቁ በሚደረጉ ክርክሮችና ውዝግቦች የሕዝቡ ድምፅ ዝቅተኛ ሆኖ በጉልህ የሚሰማው የፓርቲዎች ድምፅ ነው፡፡ ሕዝብ ዳር ቆሞ ተመልካች ሳይሆን ወሳኝ መሆኑ አጽንኦት ሊሰጠው ይገባል፡፡

ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁሌም ወሳኝ የሆነው የፖለቲካ ምኅዳሩ ጉዳይ ነው፡፡ ምኅዳሩ ሲሰፋና ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በነፃነት ሲንቀሳቀሱ ለመራጩ ሕዝብ ይበጃል፡፡ በአንፃሩ ምኅዳሩ ጠቦ አማራጭ ሳይኖር ሲቀር ምርጫ ጣዕም አልባ ይሆናል፡፡ የፖለቲካ ምኅዳሩ ሰፍቶ ፓርቲዎች በነፃነት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ፣ ምርጫ በእውነትም ትክክለኛው የውሳኔ መስጫ ሒደት ይሆናል፡፡ ሕዝብም የፈለገውን ፓርቲ ያለምንም መሸማቀቅ በነፃነት የመምረጥ መብቱ ይከበርለታል፡፡

አገሪቱ ባለፉት ሃያ ዓመታት አራት በውዝግብ የተቋጩ ምርጫዎችን አካሂዳ አሁን ለአምስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በዝግጅት ላይ ናት፡፡ ምርጫ በመጣ ቁጥር የፖለቲካ ፓርቲዎች ከሕዝብ ታዛቢዎች ምርጫ፣ ከዕጩዎች ምዝገባ፣ ከመራጮች ምዝገባ፣ ከምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ እስከ ድምፅ መስጠት ቀንና ውጤት ይፋ መሆን ድረስ ለወራት በተለያዩ ሥራዎች ይጠመዳሉ፡፡ በእነዚህ ሒደቶች ውስጥ በርካታ ጭቅጭቆችና ውዝግቦች ይከሰታሉ፡፡ ግጭቶች ይካሄዳሉ፡፡ የሰው ሕይወትም ይጠፋል፡፡ እነዚህ አሳዛኝ ድርጊቶች በተደጋጋሚ ተከስተዋል፡፡

በአገራችን በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለልተኝነት ላይ ከሚነሱ ጥያቄዎች ጀምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ገዥው ፓርቲ ጭቅጭቃቸው አሁንም እንዳለ ነው፡፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖለቲካ ምኅዳሩ ጠቦ ጠቦ በፍፁም የማይላወሱበት ደረጃ ላይ መሆናቸውን በስፋት እየገለጹ ነው፡፡ በአንድ በኩል ከገዥው ፓርቲ፣ በሌላ በኩል ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጫና እየደረሰብን ነው እያሉ ነው፡፡ ገዥው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ ይህንን አቤቱታ እያጣጣሉ ናቸው፡፡ እንዲህ ዓይነት ፈፅሞ የማይጣጣም ቅራኔ ባለበት ሁኔታ ምርጫ ማካሄድ በጣም ከባድ ነው፡፡ የከበደውን ለማቅለል ከተፈለገ ዴሞክራሲ ሒደቶችን ለመተግበር ምን ያቅታል?

እንደሚታወቀው ከ17ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በሥራ ላይ ያለው ዘመናዊው የውክልና ዲሞክራሲ ገቢራዊ መሆን የጀመረው በምርጫዎች አማካይነት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሒደት ደግሞ የሚሠራው መንግሥት ለመመሥረት ብቻ ሳይሆን ለተለያዩ የግል የቢዝነስ ተቋማት፣ ለተለያዩ ዓላማዎች ለሚመሠረቱ ማኅበራት፣ ለበጎ ፈቃደኞች ስብስቦችና ለትላልቅ ኮርፖሬሽኖች ጭምር ነው፡፡ ለዚህም ነው ምርጫ የብዙኃኑን ሕዝብ ወኪሎች ለመምረጥ እንደ ሁነኛ መሣሪያ የሚታየው፡፡ ምርጫም ነፃ፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒ የሚሆነው በተወዳዳሪዎች መካከል እኩል የመፎካከሪያ ሜዳ ሲኖር ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ምርጫ አለ ለማለት ያስቸግራል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በምርጫ ቦርድና ዋነኛ በሚባሉት የተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል እየታየ ያለው ውጥረት የተሞላበት ግንኙነት መርገብ ይኖርበታል፡፡ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ነፃና ፍትሐዊ አድርጌ አስፈጽማለሁ ሲል ቢያንስ ቢያንስ የፖለቲካ ፓርቲዎቹን በቅርበት ማነጋገር አለበት፡፡ አለ የሚሉትን ችግር መስማት ይኖርበታል፡፡ የገለልተኝነቱ ጥያቄ እንዳለ ሆኖም የምርጫው ተዋናዮች እስከሆኑ ድረስ ሊደመጡ ይገባል፡፡ ከሕጋዊና ከሰላማዊ ጥያቄዎቻቸው በተጨማሪ በምርጫ እንቅስቃሴያቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ መሰናክሎች እንዳይጋረጡባቸው መከላከል አለበት፡፡ ለምርጫው ሰላማዊነት፣ ነፃነት፣ ፍትሐዊነትና ተዓማኒነት የሚጠቅመው ይህ ዓይነቱ መንገድ ነው፡፡ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ሕጎችን አስከብራለሁ ሲል ሁለገብ የሆኑ ጥያቄዎችን በብቃት ሊመልስ የግድ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ‹‹በሆደ ሰፊነት…›› እያለ የሚገልጻቸው አባባሎች ግራ ያጋባሉ፡፡

ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ መንግሥት እንደመምራቱ መጠን ለምርጫው ስኬት ከልቡ ካልተነሳ ለዓመታት የዘለቁ ችግሮች ተባብሰው ይቀጥላሉ፡፡ በምርጫ ተሳታፊነቱ ራሱን እንደ አንድ ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲ ማየት ከተሳነው ችግር አለ፡፡ ሠራዊቱንና የፀጥታ ኃይሎችን በሕገ መንግሥቱ መሠረት ገለልተኝነታቸውን መጠበቅ፣ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት በምንም ዓይነት ሁኔታ ለምርጫ ቅስቀሳ እንዳይውል ማድረግ፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ከመድፈቅ መታቀብና ምርጫው ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን የበኩሉን ሚና መጫወት አለበት፡፡ በርካታ የተለያዩ ፍላጎቶችና ስሜቶች ባሉበት አገር ውስጥ አንድ ፓርቲ ሁሉንም ጠቅልሎ ወሰደ ሲባል ያስነቅፋል፡፡ ምርጫ ትርጉም ከማጣቱም በላይ ባይኖርስ ያስብላል፡፡ ይህ ዓይነቱ መንፈስ ደግሞ በዚህ ዘመን ተፈላጊ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ የኋላ ቀርነት ምልክትም ነው፡፡

የፖለቲካ ምኅዳሩ እንዲሰፋ ሲፈለግ የአገሪቱ ዴሞክራቲክ ተቋማት በሙሉ ከምንም ነገር ነፃ መሆን አለባቸው፡፡ ምንም እንኳ ነፃነት በምሉዕነት ተሟልቶ ሊገኝ ይችላል ተብሎ ባይታመንም፣ ቢያንስ ቢያንስ እነዚህ ተቋማት የገለልተኝነት ሚናቸውን እንዲወጡ መደገፍ ያስፈልጋል፡፡ ሚዲያውም ከወገንተኝነት ነፃ ሆኖ የምርጫውን እንቅስቃሴ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው እንዲዘግብ የማመቻቸት ትልቁ ኃላፊነት የመንግሥት ነው፡፡ ይህ በንድፈ ሐሳብ ደረጃ የሚታመንበት እንደሆነ ተደጋግሞ ቢነገርም፣ በተግባር ባለመረጋገጡ ለምርጫ ሒደት እንቅፋት ሆኗል፡፡ የፖለቲካ ምኅዳሩ መስፋት የሚፈለገውም ለዚህ ነው፡፡

ለምርጫ እንደ ፈተና ከሚታዩ ችግሮች መካከል አንዱ የሕግ የበላይነት ደካማ መሆን ነው፡፡ በብዙ ታዳጊ አገሮች ምርጫዎች ዓለም አቀፍ ደረጃን ያልጠበቁ ናቸው የሚባለው በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ምርጫ ነፃና ፍትሐዊ እንዲሆን ሲፈለግ ከምንም ነገር በላይ የሕግ የበላይነት ክብደት ሊሰጠው ይገባል፡፡ የሕግ የበላይነት ሲኖር የፖለቲካ ምኅዳሩ ይሰፋል፡፡ ምርጫም ነፃና ዴሞክራሲያዊ ይሆናል፡፡ ተወዳዳሪ ፓርቲዎችም ለሕግ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ መንግሥት የአገሪቱ ሕገ መንግሥትና ሌሎች ተያያዥ ሕጎችን ማክበርና ማስከበር አለበት፡፡ ሕጎች ባልተከበሩት ስለዴሞክራሲያዊ ሥርዓትም ሆነ ስለምርጫ መነጋገር ፋይዳ የለውም፡፡ የሕግ የበላይነት መኖር ወሳኝ ነው፡፡

የፖለቲካ ምኅዳሩን በማጥበብ በኩል ከገዥው ፓርቲ በተጨማሪ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም የራሳቸው ድርሻ አላቸው፡፡ ገዥው ፓርቲ ችግሮች አሉበት ሲባል የተገዳዳሪዎቹም መጠቀስ አለበት፡፡ ይህ የሚጠቅመው ደግሞ ጉድለቶቻቸውን አርመው ወደ ምርጫ እንዲገቡ ነው፡፡ ተቃዋሚዎች ከአደረጃጀታቸው፣ ከአቻ ፓርቲዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት፣ ዓላማቸውን በበቂ ሁኔታ ለሕዝብ በማሳወቃቸው፣ ውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲን ተግባራዊ በማድረጋቸው፣ እርስ በርስ በመጠላለፋቸው፣ ወዘተ ያላቸው ይዞታ መመርመር አለበት፡፡ ሕዝቡን ግራ የሚያጋቡ ብዙ ችግሮች አሉባቸውም፡፡ ውጫዊ ችግሮችን ከሚፈቱባቸው ሥልታዊ አካሄዶች ድክመት አንስቶ የተለያዩ ተግዳሮቶች ይታዩባቸዋል፡፡ በመተባበር፣ በመቀናጀት፣ ግንባር በመፍጠርና በመዋሀድ ሒደቶች ውስጥ በሚፈጥሯቸው ችግሮች ምክንያት ሲጠላለፉ ይታያሉ፡፡ ለችግሮች መፍትሔ በማፈላለግ በኩልም አዝጋሚ ናቸው፡፡ የገዥውን ፓርቲ ጫና ብቻ እየተረኩ ሌሎችን ድክመቶች ያድበሰብሳሉ፡፡ የዳያስፖራው ተፅዕኖ እግር ተወርች ሲያስራቸው በፅናት ሲታገሉ አይታዩም፡፡ በእነዚህ ምክንያቶች ለፖለቲካ ምኅዳሩ መስፋት ጥርሳቸውን ነክሰው መታገል ሲችሉ ይብረከረካሉ፡፡ አንዳንድ ወገኖች የተቃዋሚዎች ችግር ለምን ይነሳል ይላሉ፡፡ በዚህ ዓለም ፍፁምነት የለምና ለሰላማዊ ፖለቲካ ትግሉ መሳካት ራሳቸውን በቅጡ ቢያዩ ይበጃቸዋል፡፡ አንድ ነገር ላይ ብቻ በማተኮር ጊዜያቸውን በማጥፋት የፖለቲካውን መንገድ መሳት የለባቸውም፡፡ የፖለቲካ ምኅዳሩ እንዲሰፋ ሲፈልጉ ማንኛውንም ችግር ችለው መልፋት አለባቸው፡፡

የመጪው ግንቦት ምርጫ ከወዲሁ ሲገመገም ካሁኑ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ መፍትሔ ያሻዋል እንላለን፡፡ በተደጋጋሚ ምርጫው ነፃ፣ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ ይሆናል ሲባል በተግባር መረጋገጥ አለበት፡፡ ኢትዮጵያ አገራችን የአብሮ የመኖርና የመቻቻል ተምሳሌት በመሆኗ ወሳኙ ሕዝብ ሊከበር ይገባዋል፡፡ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ከሚያስፈልጉ ግብዓቶች አንዱ ሕጋዊ ምርጫ ሲሆን፣ ይህ ምርጫ የሕዝባችንን ፍላጎት የሚያማክል መሆን አለበት፡፡ ሕዝብ የሥልጣን ምንጭ እስከሆነ ድረስ ድምፁ ሊከበር እንደሚገባ ሁሉ፣ የምርጫ ሒደቱም ከእንከን የፀዳ እንዲሆን የሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ መረባረብ አለባቸው፡፡ ዳር ሆኖ ግለት መፍጠር ሳይሆን እውነተኛ ምርጫ እንዲኖር አስተዋጽኦ ማድረግ የአገር ወዳድ ዜጎች ኃላፊነት ነው፡፡ ለዚህም ነው የፖለቲካ ምኅዳሩ እንዳይጠብ ጥንቃቄ ይደረግ የሚባለው!

Source:: Ethiopian Reporter

በዞን 9 ጦማርያንና ጋዜጠኞች ላይ የቀረበው ክስ በድጋሜ ‹‹ተሻሻለ››

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ጥር 6 ቀን 2007 ዓ.ም ለ15ኛ ጊዜ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የተሰየመው ቀደም ብሎ በጦማርያኑ እና ጋዜጠኞች ላይ የተመሰረተው ክስ እንዲሻሻል ባዘዘው መሰረት የፌደራል አቃቤ ህግ ክሱን ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ያላሻሻላቸው ነጥቦች ስለነበሩ እነዚህኑ ነጥቦች በድጋሜ አሻሽሎ እንዲቀርብ ባዘዘው መሰረት የተሻሻለውን ክስ ለመስማት ነበር፡፡
36884-zone9-bloggers4
በመሆኑም የፌደራል አቃቤ ህግ አሻሽየዋለሁ ያለውን ክስ ይዞ ቀርቧል፡፡ ክሱ ‹‹ሌሎች ብዙ ‹ኬዞች› ስላሉ›› በሚል ምክንያት በችሎቱ ላይ በንባብ እንዲሰማ አልተደረገም፡፡ ተሻሻለ የተባለው ክስ ለተከሳሾችና ለጠበቆች እንዲደርስ የተደረገውም እዚያው ችሎት ውስጥ ነው፡፡

ክሱ በንባብ ባለመሰማቱና ጠበቆቹና ዳኞቹም ስላላነበቡት በሚል ተሻሻለ በተባለው ክስ ላይ ምንም አስተያየት አልቀረበም፡፡ በመሆኑም ክሱ መሻሻል አለመሻሻሉን ለመመርመርና ብይን ለመስጠት ለጥር 20 ቀን 2007 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

የጦማርያኑ እና ጋዜጠኞች ጠበቃ የሆኑት አቶ አምሃ መኮንን እንዳሉት በቀጣዩ ቀጠሮ ላይ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ተሻሽሎ ካልሆነ ነጥቦቹን ፍርድ ቤቱ ውድቅ ያደርጋል ብለው እንደሚጠብቁ ገልጸዋል፡፡ ‹‹በእኛ በኩል ከዚህ በኋላ የማሻሻያ ሀሳብ አቅርበን ጊዜ አንፈጅም፤ ከሚቀጥለው የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኋላ መደበኛ ክርክራችንን መቀጠል ነው የምንፈልገው›› ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በዛሬው የችሎት ውሎ ላይ በጣም ብዙ እስረኛ (ተከሳሽ) ችሎቱ ውስጥ በመገኘቱ ምክንያት ከፍተኛ የቦታ ጥበት ማጋጠሙ ተስተውሏል፡፡ በአጠቃላይ እስከ 70 የሚደርሱ እስረኞች በችሎቱ ተገኝተዋል፡፡ ስለሆነም ችሎቱን መታደም የቻሉት ጥቂት ጋዜጠኞችና ዲፕሎማቶች ብቻ ሆነዋል፡፡ የተከሳሽ ቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶች ችሎቱን መታደም አልቻሉም፡፡

አንዳርጋቸው ጸጌ በህወሀት የሸፍጥ የምርመራ ወጥመድ ውስጥ

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

አንዳርጋቸው ጽጌ በህወሀት ወንድሞች ቡድናዊ የሸፍጥ ከበባ ስር

ቮልቴር (ፍራንኮይስ ማሬ አሮት) እንዲህ በሚለው ምልከታቸው በስፋት ይታወቃሉ፣ “አንድ ሰው ከሚሰጣቸው ምላሾች ይልቅ በሚያቀርባቸው ጥያቄዎች ምንነቱ ይገመገማል፡፡“
andargachew Tsege
ቮልቴር ብልህነትን በተላበሰ መልኩ እንዲህ የሚል ምልከታም በተጨማሪ አካሂደዋል፣ “ጥሩንባቸውን እየነፉ እጅግ ብዛት ያለውን ህዝብ ካስጨረሱ ገዳዮች በስተቀር ሁሉም ህይወትን ያጠፉ ነብሰ ገዳዮች ይቀጣሉ፡፡“ ይኸ ነገር እንዴት ያለ እውነታ ነው እባካችሁ! አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ እና እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው የወሮበላ ቡድን በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት ወገኖቻችንን በመግደል ከምዕራቡ ዓለም የሚደረግላቸውን እርዳታ በመቀበል ፌሽታ እና ደስታ በማድረግ ከህዝብ እልቂት ሰይጣናዊ ወንጀሎቻቸው ለማምለጥ ላይ ታች በማለት በመንፈራገጥ ላይ ይገኛሉ፡፡

ባለፈው ሳምንት በአንዳርጋቸው ጽጌ ተሰጠ የተባለ የ10 ደቂቃ ከ31 ሰከንዶች ቆይታ ያለውን ሁለተኛ ጊዜ የቀረበ የሙያ ሳይሆን የልምምድ ድራማቸውን በህዝብ ግብር በሚተዳደረው ቴሌቪዥን በማይታዩ ጥያቄ አቅራቢ መርማሪዎች እና ሰዎች የእራሳቸውን የህሊና ዳኝነት እንዲሰጡ በሚጋብዝ መልኩ የተቀነጫጨበ እና በውል ለመረዳት የማይቻለውን ምላሽ የተባለውን ቃለ ተውኔት እንደሰጡ አድርገው አቅርበው ነበር፡፡

በኢትዮጵያ ባለው አገዛዝ የተቃዋሚ ቡድን ከሆነው እራሱን የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ለፍትህ፣ ለነጻነት እና ለዴሞክራሲ እያለ የሚጠራውን ድርጅት ዋና ጸሀፊ የሆኑትን አንዳርጋቸው ጽጌን እ.ኤ.አ ጁላይ 2014 በየመን ካለው ገዥ አካል ጋር የሸፍጥ ዱለታ በማድረግ በተሳካ ሁኔታ ወደር የማይገኝለትን ጠለፋ አካሂደው ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ2009 እና በ2012 አንዳርጋቸው በሌሉበት አሸባሪ በሚል የሸፍጥ ውንጀላ በህወሀት ክስ ተመስርቶባቸው በዝንጆሮው የይስሙላ ፍርድ ቤት የሞት ቅጣት ተበይኖባቸው ነበር፡፡

የአቶ አንዳርጋቸውን አሳፋሪ እና ህገወጥ ጠለፋ በማስመልከት “ኢትዮጵያ፡ ልዩ የሆነ የወንጀል ትወና“ በሚል ርዕስ እኩይ ድርጊት መሆኑን በሳምንታዊ ጦማሬ ላይ አውግዠ ነበር፡፡

አንዳርጋቸው የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው ሲሆኑ በትውልዳቸው ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን በጣም የሚያሳፍረው ነገር የእንግሊዝ ዜግነታቸው ለስም ብቻ የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ አንዳርጋቸው ከእስር ቤት እንዲፈቱ የእንግሊዝ መንግስት ምንም ያደረገው ነገር ወይም ደግሞ በአስከፊነቱ በዓለም ታዋቂ ከሆነው የመለስ ዜናዊ እስር ቤት የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ስቃይ ነጻ እንዲሆኑ የሰራው ስራ የለም፡፡ የህወሀት ወንድሞች ከስድስት ወራት በላይ አንዳርጋቸው ጽጌን ለተደጋጋሚ ጊዜ የብዙሀን መገናኛ የመድረክ የቅጥፈት ተውኔት ማሳያ ሲያደርጓቸው የእንግሊዝ መንግስት አንድም ዓይነት የወሰደው እርምጃ የለም፡፡

እ.ኤ.አ በ1963 በጸደቀው የኮንሱላር ግንኙነት የቬና ስምምነት መሰረት የእንግሊዝ መንግስት ፍጹም በሆነ መልክ ግዴታውን መወጣት አልቻለም፡፡ የእንግሊዝ መንግስት በውጭ የሚኖሩ ዜጎቹን ደህንነት በመጠበቁ እና እገዛ በሚጠይቁ ዜጎቹ ጉዳይ ላይ በሁለት ቢላዋ ምላሱ በማውራት ላይ ይገኛል፡፡ የእንግሊዝ ባለስልጣኖች እንዲህ ይላሉ፣ “በኮንሱላር ባለስጣኖቻችን ወይንም ደግሞ የዲፕሎማሲ ባለስልጣኖቻችን አማካይነት በውጭ ሀገር በችግር ላይ ለሚገኙ ዜጎቻችን የምንሰጠው እገዛ የውጭ ፖሊሲያችን የመሰረት ድንጋይ ነው፡፡“ ከዚህም በተጨማሪ የኮንሱላር እገዛ የእንግሊዝ ዜጎች ማግኘት ያለባቸው የህግ መብት አይደለም በማለት እንዲህ ይላሉ፣ “የእንግሊዝ መንግስት ለዜጎቹ የኮንሱላር እገዛ ለመስጠት ወይም ደግሞ የዲፕሎማሲ ጥበቃ ለማድረግ በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ህጎች ግዴታ የለበትም፡፡“ ከዚህም በላይ በውጭ የሚገኙ ዜጎቻቸው የማሰቃየት ድርጊት እንዳይፈጸምባቸው ወይም ሊፈጸምባቸው እንዳይችል ለማድረግ የዜጎቻቸውን ደህንነት ለመጠበቅ የእንግሊዝ መንግስት የጸረ ማሰቃየት ስትራቴጅ አንዱ እና ዋና ተግባሩ ነው፡፡ የእንግሊዝ ንጉሳዊ ቡድን ጸሀፊ፣ ገጣሚ እና ወታደር የነበሩት ጌታ ዋልተር ራለህ ተገቢ በሆነ መልኩ እንዲህ የሚል ጥቆማ አድርገው ነበር፣ “ኦ፣ የማታለል ተግባራትን ስንፈጽም በነበረበት ጊዜ ምን ዓይነት ድር ማድራት እንደጀመርን!“

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ቢሮ አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ የዝንጀሮው የይስሙላ ፍርድ ቤት ሁለት ጊዜ የሞት ፍርድ የተበየነባቸው መሆኑን እና ከፍተኛ የሆነ ማሰቃየት እንደተፈጸመባቸው ከምንም ጥርጣሬ በላይ አሳምሮ ያውቃል፡፡ እስከ አሁን ድረስ በእንግሊዝ መንግስት የተደረገው ጸጸትን መግለጽ እና ከየመን ባለስልጣኖች ዘንድ ተደጋጋሚ የሆኑ መረጃዎችን መጠየቅ፣ ስለአንዳርጋቸው የእስር ሁኔታ ከቬና ስምምነት በተጻረረ መልኩ መረጃ ማግኘት ያለመቻል ችግር እንዲሁም አንዳርጋቸው ጽጌ በኢትዮጵያ የሞት ብይን ፍርድ እንዳይሰጥባቸው ለማድረግ ግልጽነት የጎዳላቸው አራምባ እና ቆቦ የሆኑ የማስመሰያ መግለጫዎችን ማውጣት እና ጉዳዩ አሳስቦናል የማለት የይስሙላ ጥረት ነበር፡፡ እንደ አንድ ዘገባ ከሆነ ሚስተር ሲሞንድስ የተባሉ አፍሪካዊ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ባለስልጣኖች የኮንሱላር ተደራሽነትን የማይገልጹ በመሆናቸው ሚኒስትሩ የተሰማቸውን ጥልቅ ስሜት ገልጸው ነበር፡፡

አሜሪካኖች እንደሚሉት “ልዩ የሆነ የዳክዬ የደስታ ጩኸት ነው!” ሆድ ሲአቅ ዶሮ ማታ ይላል ያገሬ ሰው። በእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኩል መልካም የሆነ የአዞ እንባ የማንባት የታዕይታ ተውኔት ነው፡፡ የእንግሊዝ ሀገር ዜጎችን ደህንነት በመጠበቅ ሁኔታ ላይ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ዜጋ ይኑር አይኑር እንዲሁ የማሰቃየት ስራ ቢሰራ እና ሁለት ምላስ ንግግር ቢደረግ ኖሮ የሚያስደንቀኝ ነገር አይኖርም ነበር፡፡ አሁን ጊዜ ማጥፋቱን ልተው እና ተገቢውን ጥያቄ ላቅርብ፡፡ በኢትዮጵያ ወሮበሎች እየተሰቃዩ ያሉትን አንዳርጋቸውን የሀገሩ (የንግሊዝ) ሁለተኛ ዜጋ የሆኑትን ግለሰብ መብት ለማስከበር እና ከማጎሪያው እስር ቤት እንዲለቀቁ ለማድረግ የእንግሊዝ መንግስት ምን ያደረገው ነገር አለ? በጭራሽ ምንም ያደረገው ነገር የለም!

ያም ሆነ ይህ ወደ ወያኔ እና ስለአንዳርጋቸው የብዙሀን መገናኛ የመድረክ ላይ ተውኔት እንመለስ፡፡

እውነታውን ተመርኩዘን ስለአንዳርጋቸው ሁኔታ የህሊና ዳኝነት እንድንሰጥ በቪዲዮ ቁራጭ (ክሊፕ) በግልጽ የቀረበውን የወያኔ ግብዣ ተቀብየዋለሁ፡፡ እኔን የገረመኝ እና ከሁሉም በላይ ያስደንቀኝ ነገር በተቃራኒ መልኩ እነዚህ ህሊና የሚባል ነገርጨርሶ ያልፈጠረባቸው ህሊናቢስ የሸፍጥ ስብስቦችለህሊና ዳኝነት በማለት ጥያቄ የማቅረባቸው ጉዳይ ነው፡፡ የሌባ አይነደርቅመልሶ ልብ አድርቅ ይላል ያገሬ ሰው። ሆኖም ግን ላልተገለጹ ጥያቄዎች፣ በማይታወቅ ቦታ እና ጊዜ ለስምየለሽ እና ማንነቱ ላልታወቀ መርማሪ ስለሰጡት ምላሽ እንዴት አድርጌ ነው በአንዳርጋቸው ላይ የህሊና ፍርድ መስጠት የምችለው!?

ፍትሀዊነት በጎደለው እና በአስከፊ የውሸት የተውኔት መድረክ ላይ ለመታየት አንድ ሰው የውንጀላ ክስ የሚመሰረትበት እና በሚሰጣቸው ምላሾች ብቻ የሚዳኘው በእስፓኝ ሀገር በመካከለኛው የዘመን (የዛሬ አምስት መቶ ዓመት በፊት) አቆጣጠር ጊዜ ብቻ ነበር፡፡ (በእርግጥ በሶቪየት ውስጥ በስታሊን የአገዛዝ ዘመን እንደተደረገው ሁሉ የናዚ ወንጀለኞችም በተመሳሳይ መልኩ አንድ ሰው በታዕይታው የፍርድ ሂደታቸው አንድ ሰው በሰጠው ምላሽ ላይ ብቻ በመመርኮዝ ብያኒያቸውን ይሰጡ ነበር፡፡) በእኔ አስተያየት በ10 ደቂቃ ከ31 ሰከንዶች በፈጀው የቪዲዮ እይታ በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ወያኔ ያደረገው የመድረክ ላይ ተውኔት በእርግጥም በመካከለኛው ዘመን የተደረገውን ፍትሀዊነት የጎደለውን እና አስከፊውን የመድረክ ላይ ተውኔት ይመስል ነበር፡፡ ይህ ፍትሀዊነት የጎደለው እና አስከፊ የመድረክ ላይ ትወና ከአንድ ሺህ የተለያዩ ጥያቄዎች ውስጥ አንድ ትክክለኛ መልስ ብቻን ለማግኘት ከተለመደው እምነት እና አስተሳሰብ ውጭ ዓላማ አድርገው የተነሱ ናቸው፡፡ የኸውም “የነበረኝን ጽኑ እምነት ቀይሪያለሁ፣ ተገልብጫለሁ”! የሚል መልስ ብቻ ትክክለኛው እንደሆነ በቅጥፈት ማሳያ የትወና መድረክ ላይ እንዲታይ ማድረግ ነው፡፡

ፍትሀዊነት የጎደለው እና አስከፊው የመድረክ ላይ ተውኔት በሀሰት ውንጀላ የቀረቡ ተጠርጣሪዎች ከተለመደው ባህሪያቸው እምነት ውጭ ለመናገር የሚፈሩ ከሆነ እና ሌሎችም እነርሱ የሚያውቋቸው እንደዚህ ያለ ጸባይ ያላቸው የሚጠረጠሩ ሰዎች ካሉ ይህንን በመተው እራሳቸውን ማውገዝ በሚለው ሂደቱ ይጀመራል፡፡ ያ እንግዲህ ይፋ በሆነ መልኩ እራስን ማውገዝ (እራስን መክሰስ) እና ተጠርጣሪው በመከላከል እስር ቤት ውስጥ በሚቆይባቸው ረዥም ጊዚያት የሚፈጸም ሂደት ነው፡፡ ፍትሀዊነት የጎደለው እና አስከፊው የመድረክ ላይ ተውኔት ሂደቶች በሚስጥር የሚካሄዱ ናቸው፡፡ ክስ የተመሰረተበት ሰው ለበርካታ ዓመታት በእስር ቤት ሲማቅቅ የቆየ ቢሆንም እንኳ ህጋዊ የሆነ የክስ መጥሪያ እንዲደርሰው አይደረግም ወይም ደግሞ የክስ መጥሪያው በማስታወቂያ እንዲለጠፍ አይደርግም፡፡ የተጠረጠሩ ፍትሀዊነት የጎደለው እና አስከፊ የመድረክ ላይ ተውኔት የሚፈጸምባቸው ዜጎች እራሳቸውን እንዲያወግዙ በሚገደዱበት እና ምርመራ በሚካሄድበት ወቅት በአንድ ክፍል ውስጥ ከቤተሰቦቻቸው እና ከጓደኞቻቸው ጋር መገናኘት እንዳይችሉ ሆነው ለብቻቸው እንዲታሰሩ ይደረጋል፡፡ ፍትሀዊነት የጎደለው እና አስከፊ የመድረክ ላይ ተውኔት በሚሰራበት ጊዜ የሂደቱ ስርዓት ልዩ ልዩ የማሰቃያ ዘዴዎችን በመጠቀም እንዲያምን የሚጠበቀው በሀሰት ውንጀላ በእስር ቤት የሚገኘው አማኝ በአሳማኙ ፈቃድ ብቻ እንዲያምን የሚያስገድድ የህግ መርህ አለው፡፡ በሀሰት ውንጀላ ተጠርጥሮ የተያዘው ግለሰብ እራሱ የሚያምነበትን እምነት ክዶ ከአሳማኙ በቀረበለት ሀሳብ መሰረት እራሱን አውግዞ እንዲናገር በማድረግ ይህንን የመድረክ ላይ ትወና ለህዝብ ፍጆታ ግብር እየከፈለ በሚያስተዳድረው ብዙሀን መገናኛ ላይ ፍትሀዊነት የጎደለው እና አስከፊው የመድረክ ላይ ተውኔት ለህዝብ ዕይታ እንዲቀርብ ከተደረገ በኋላ ወዲያውኑ እነርሱ የሚፈልጉትን ፍርድ በመስጠት በሀሰት በተወነጀለው ግለሰብ ላይ ይጭኑበታል፡፡

እውን በእውነት ወያኔ በቪዲዮ ቀርጾ አንዳርጋቸው ጽጌ የእራሳቸውን፣ የጓደኞቻቸውን እና የሌሎችን እምነት በማውገዝ የሰጡት መረጃ ወይም ምላሾች ናቸው ብሎ ያቀረባቸው ተራ ቅጥፈቶች የእርሳቸውን የጽናት አቋም እና እምነት በማንጸባረቅ የእርሳቸውን ምንነት ይገልጻሉን? የቪዲዮ ማስረጃው ወያኔ አንዳርጋቸውን ከሚያወግዝበት ውግዘት ጋር እኩል የውግዘት እንደምታ አላቸውን? የቪዲዮ ቀረጻው የወያኔን ፍትሀዊነት የጎደለውን እና አስከፊውን የመድረክ ላይ ተውኔት መሰረት በማድረግ ለፍርድ አሰጣጥ ሂደቱ በማስረጃነት ለመጠቀም ነውን? በድብቅ ለወያኔ የይስሙላው ፍርድ ቤት የተሰጠውን የአንዳርጋቸውን የቪዲዮ ማስረጃ መሰረት አድርገን የህሊና ፍርድ እንድንሰጥ እየተጋበዝን ነው ያለነው? የቪዲዮ ቀረጻ ማስረጃው አንዳርጋቸው ጽጌ በይፋ በህዝብ ፊት የወያኔን የወሮበላነት መርህ አሜን ብለው ተቀበሉ ብለን እንድናምን ነው የተፈለገው? የቪዲዮ ቀረጻ ማስረጃው በእርግጥ አንዳርጋቸው “ወደ ወያኔ ወሮበልነት ተቀይሪያለሁ” ብለው በእራሳቸው የስብዕና አንደበት አምነው የተናገሩት መሆኑን ያሰየናል? ወይም ደግሞ የቪዲዮ ቀረጻ ማስረጃው ወያኔ በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ከዚህ ቀደም እንደበየነው አሁን ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ የሚያሳልፈውን የሞት ቅጣት የመጨረሻ ውሳኔ እና መግለጫ አስቀድሞ ለማሳየት ነውን?

አንዳርጋቸው ከቤተሰብ እና ከጓደኞቻቸው ጋር ፍጹም መገናኘት እንዳይችሉ የተደረገው ለምንድን ነው? አንዳርጋቸው ምንም ዓይነት ክስ ሳይደርሳቸው በጣም ለተራዘመ ጊዜ በእስር ቤት ውስጥ እንዲቆዩ ከተለመደው እምነት ውጭ የሆነውን እምነታቸውን አብዮታዊ ዴሞክራሲን (ምንም ምን ይሁን) ተቀብለዋል በማለት በድብቅ ይዞ ለማቆየት ወይም ደግሞ ከዚህ በፊት እንደገለጽኩት ሁሉ የመለሳውያንን/ትን የጨለማ መንገድ በማለት ሲያራምዱት የቆዩትን እምነታቸውን እርግፍ አድርገው ጥለውታል ለማለት ነው? የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀጽ 21 (2) የሚከተለውን መብት ያጎናጽፋል፡ “ማንኛውም በህግ ከለላ በቁጥጥር ስር ያለ ሰው ወይም ደግሞ ክስ የተመሰረተበት ሰው ከማንኛውም ሰው ጋር የመገናኘት፣ በትዳር አጋር፣ በቅርብ ዘመዶች፣ በጓደኞች፣ በሀኪም፣ በኃይማኖት አባት እና በህግ አማካሪው የመጎብኘት መብት አለው፡፡“ ታዲያ ለምንድን ነው አንዳርጋቸው ህገመንግስታዊመብታቸውን በወያኔ የተከለከሉት?

አንዳርጋቸው ምንም ዓይነት ግንኙነት እና የህግ ሂደት ሳይኖር አሁን ባሉበት ሁኔታ እንዲቀጥሉ ይደረግ ይሆናል፡፡ እንደ ደኃ ከረጢት ተቆርጦ እና ተቆራርጦ የተለጣጠፈው እና የተደረተው የቪዲዮ ማስረጃ እንደሚያሳየው አንዳርጋቸው በአልታወቁ ጊዚያት ቢያንስ በአምስት የተለያዩ አጋጣሚዎች እንደተጠየቁ ያመላክታል፡፡ ሆኖም ግን የመለማመጃው የጀማሪዎች የቪዲዮ ቀረጻ እየተቆረጡ እና እየተቀጠሉ የተለጠፉ ቢሆንም የተበላሸውን የ10 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ የቪዲዮ ቀረጻ ማስረጃ ለማዘጋጀት ምን ያህል ጊዜ እንደተጠየቁ ለማወቅ አይቻልም፡፡

ሁሉም የአንዳርጋቸው የቪዲዮ ቀረጻ ማስረጃዎች የተዘጋጁት በህገወጥ መልኩ ኃይልን በመጠቀም በማስገደድ መሆኑ ጥያቄ የሚቀርብበት ጉዳይ አይደለም፡፡ ያንን ያህል ብዛት ያላቸውን ጥያቄዎች በአንድ ጀንበር ብቻ ሊመልሱት አይችሉም፡፡ አንድ ተጠርጥሮ በፖሊስ ወይም ደግሞ በፍርድ ቤት ባሉ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ያለ ተጠርጣሪ ወይም ተከላካይ የሚቀርብ ጥያቄ ምርመራ ነው፡፡ ማናቸውም መልሶች በተለይም ደግሞ እራስን በማውገዝ የሚሰጡ መልሶች በፍርድ ሂደቱ ላይ ያሉ ሰዎች ካሏቸው የስብዕና መልሶች በተለየ መልኩ ያለውድ በግድ ቅቡል የሆኑ ወይም ደግሞ እምነት የተሰጠባቸው ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ህገመንግስት አንቀጽ 19 (5) የባለስልጣኖችን የግዳጅ የምርመራ ጥያቄ እንዲህ በማለት ይከለክላል፣ “ማንኛውም ሰው በህግ ስነስርዓት ሂደቱ ጊዜ በጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ በግዳጅ የእምነት ቃል ወይም ደግሞ መረጃ ሊሰጥ አይችልም፡፡“ የአንዳርጋቸው የቪዲዮ ቀረጻ የእምነት ማስረጃዎች በዝንጀሮው የይስሙላ ፍርድ ቤት የሸፍጥ የፍርድ ሂደት ላይ በጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ አይደሉምን?

የአቶ አንዳርጋቸው የቪዲዮ ቀረጻ ማስረጃ ምላሾች የተዘጋጁት እርሳቸው በእስር ቤት ውስጥ ባሉበት ሁኔታ፣ ከማንም ጋር እንዳይገናኙ ሆነው (ከቤተሰብ፣ ከጓደኛ፣ ከህግ አማካሪ ፍጹም እንዳይገናኙ ተደርጎ) እና የህግ ጠበቃ በሌለበት ሁኔታ ነው፡፡ ስለሆነም እርሳቸው የሰጧቸው መልሶች በእርግጠኝነት በግዳጅ የተሰጡ መሆናቸው አያጠራጥርም፡፡ ሁሉም ተጠርጣሪዎች በወያኔ የሽብር ወንጀል የሚል ክስ የሚመሰረትባቸው ስለሆነ የህግ የምክር አገልግሎት እንዲያገኙ እና ህገመንግስታዊ መብታቸውን እንዳይጠቀሙ በኃይል ስለሚከለከሉ የአንዳርጋቸው ጽጌም ምርመራ እና ተጨማሪ ማስረጃ ለማግኘት ሲባል የተፈጸመባቸው አካላዊ እና የስነ ልቦና ስቅይት በግዳጅ ህገወጥ ድርጊት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ያመላክታል፡፡ (ቀደም ሲል “ልዩ የሆነ የወንጀል ተውኔት” በሚል ርዕስ ያቀረብኩትን ትችት ልብ ይሏል፡፡)

የአንዳርጋቸውን የቪዲዮ ቀረጻ ምስል ከተመለከትን በኋላ ምን ዓይነት የህሊና ዳኝነት እንድንሰጥ የተፈለገው? ለመሆኑ የመጨረሻው የህሊና ፍርድስአንዳርጋቸውን አንድንሰጥ የተፈለገው ከብረት ምሰሶ ጋር አስሮማቃጠል ነውን!?

10 ደቂቃ ከ31 ሰከንዶች በወሰዱ ጊዚያት ተቆርጠው በተቀጠሉ የአንዳርጋቸው የቪዲዮ ቀረጻ ምላሽ ማስረጃዎች ላይ ብይንመስጠት፣

በአንዳርጋቸው የተሰጡ በ10 ደቂቃ የቪዲዮ ቀረጻ የተቀጠሉ እና የተለጠፉ ምላሾችን ዓላማ ወይም ደግሞ ይህንን በቅጥፈት የተሞላ የመድረክ ላይ ተውኔት ለህዝብ ዕይታ ማቅረብ ምን ፋይዳ ሊያመጣ እንደሚችል ለማወቅ መሞከር ለእኔ አጠቃላይ የሆነ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው፡፡ አንዳርጋቸው የጽናት ተምሳሌት የሆኑ የአረብ ብረት ሳይሆኑ በወያኔ የማሰቃያ ክፍል ውስጥ በሚቀርብ የምርመራ ጥያቄ በቀላሉ የሚቀልጡ እና በነው የሚጠፋ ጥንካሬ የሚጎድላቸው ቀላል ነገር ናቸው ለማለት ተፈልጎ ነውን? የማሰቃያ የእስር ቤት ክፍል ውስጥ እንዲሰቃዩ በማድረግ ከወያኔ ግርፋት እና ስቅይት እንዲያገግሙ እና ትምህርት ወስደው የወሮበላነት ወንድሞቻቸውን እንዲቀላቀሉ ለማድረግ ታስቦ ነውን? ግንቦት ሰባት የተባለው ድርጅት ደካማ የሆነ እና ጠንካራ ወይም ደግሞ ብቁ የሆነ አመራር የሌለው እንዲሁም በቀጣይነት የህዝብ ድጋፍ የማያገኝ አስመስሎ ለማቅረብ የተዘየደ የሞኞች ብልሀት ነውን? አንዳርጋቸው በትጥቅ ትግል በእርግጠኝነት እምነት እንደሌላቸው እና አስመሳይ እንደሆኑ በማስረገጥ ሆኖም ግን በሰላማዊ ትግል እንደሚያምኑ እና ለእርሳቸው እና ለድርጅታቸው እንዲሁም ለጓደኞቻቸው የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ ለመስጠት ታስቦ ነውን? በእራሳቸው ድርጅት ወይም ጓደኞች ዘንድ እምነት የሌላቸው ለዓላማቸው በጽናት ያልቆሙ አስመስለው ለማቅረብ ቋምጠው ነውን? በሌሎች የተቃዋሚ ድርጅቶች አመራሮች እና ድርጅቶች እንዲሁም በግለሰቦች ላይ ንቀትን የሚያሳዩ ናቸው በማለት ለማሳየት ፈልገው ነውን? በተወሰኑ የወያኔ መሪዎች እና በእራሱ የወያኔ ድርጅት ላይ ጥልቅ የሆነ ጥላቻ ወይም ፍቅር አላቸው የሚለውን ለማሳየት ነውን? እርሳቸው መጥፎ እንደሆኑ፣ የሞራል ሰብዕና የሌላቸው እና ሊታመኑ የማይችሉ እምነተቢስ ሰው እንደሆኑ ለማሳየት ተፍልጎ ነውን? በታማኝነት እና እነርሱ በሚፈልጉት መንገድ ላቀረቧቸው ጥያቄዎች ሁሉ ትክክለኛውን መልስ ሰጥተዋል በሚል ምክንያት አንዳርጋቸው ምክንያታዊ ሰው ናቸው ለማለት ተፈልጎ ነውን?

ለወገኖቼ እና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድምጼን ከፍ አድርጌ መጮህ እንድችል የ10 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ የቪዲዮ ቀረጻውንየገሀነምነት ዓላማ ሊነግረኝየሚችል ሰው ሊኖር ይችላልን!?!

የ10 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ ያህል ቆይታ ያለው የቪዲዮ ቀረጻ ማስረጃ በአምስት የተለያዩ አጋጣሚዎች በመምረጥ ከተለያዩ የቪዲዮ ክፍሎች ተቆርጦ እና ተለጥፎ የተዘጋጀ በእውነታ ላይ ሳይሆን በቅጥፈት ድሪቶ ላይ ተመስርቶ የተደረተ የሸፍጠኞች የማስመሰያ እና የማታለያ ቅጥፈት ነው፡፡ ሆኖም ግን ግቡን መታ ሊባል የሚችለው የሚታለል ሞኝ ሲገኝ ብቻ ነው!

በሌላ በኩል ደግሞ ጥቂት የሆኑት የቪዲዮው ክፍሎች ተመርጠው ከአንድ ወይም ከሁለት በላይ ከሆኑ የተንዛዙ መጠይቆች በቆረጣው መቀሳቸው እየተቆረጡ ተለጥፈዋል፡፡ የቪዲዮ ቀረጻው የአርትኦ ስራ እና የቆረጣ እንዲሁም የመለጠፍ ስራዎች በጣም አስቀያሚ እና እጅ እግሩ የማይያዝ ዝብርቅርቁ የወጣ በአንዳርጋቸው ተሰጡ የተባሉት መልሶች የእርሳቸውን የፖለቲከ እምነት እና በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ የሚሰጧቸውን ትንታኔዎች ብስለት ሊያስገነዝቡ ይቅር እና ሰዋስዋዊ ይዘታቸው እንኳ የማይጨበጥ እና የማይዳሰስ ምንም ዓይነት ትርጉም የማይሰጡ ሆነው የተስተዋሉ በመሆኑ ነገሩን የበለጠ እንዲወሳሰብ አድርጎታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በርካታዎቹ የቪዲዮው ክፍሎች የቅጥፍና ስልቱን ለማሳለጥ እና የተዛባ ግንዛቤ ለመፍጠር በሚል እኩይ ምግባር በአንድ ላይ እንዲታጀሉ በማድረግ ማቋረጫ በሌለው መልኩ ቀረጻውን በማካሄድ አንዳርጋቸው በእርግጠኝነት ምን ዓይነት ስብዕና ያላቸው ሰው እንደሆኑ ለማስመሰል ተሞክሯል፡፡

ይህንን የቪዲዮ ቀረጻ አጠናቅቀው እንዲለቀቅ ያደረጉትን ሰዎች ለህዝብ የህሊና ፍርድ ዳኝነት ሲሉ ሙሉውን ጥያቄ ምንም ዓይነት ቆርጦ ቀጥል የቅጥፈት ስልት ሳይጨመርበት መልቀቅ እንዲችሉ እጠይቃቸዋለሁ፡፡

የአንዳርጋቸው የመጀመሪያው የቪዲዮ ቀረጻ ምላሾች 10 ደቂቃ ከ31 ሰከንዶች ከሚወስደው አጠቃላይ ጊዜ ውስጥ 20 ሰከንዶችን በመውሰድ ይጀምራል፡፡ በዚያ ክፍል ውስጥ ሁለት ጎንዮሽ እና በክንዶቻቸው ላይ ነጠላ የሆነ ነጭ ጠቃጠቆ ከአረንጓዴ የውስጥ ሸሚዝ ጋር በነጭ ዚፕ የተዘጋጀ የአትሌት ልብስ ለብሰዋል፡፡ መደቡ ነጭ በሆነ ወንበር ላይ የተቀመጡ ይመስላል፡፡ (መርማሪዎቹ ስለምርመራ አቀራረቡ ቀደም ሲል ካቀረብኩት ትንታኔየ ትምህርትን የቀሰሙ ይመስላል እናም በአንዳርጋቸው የምርመራ ጉዳይ ላይ የምርመራው ቦታ የት እንደሆነ እና በምን ጊዜ እንደተደረገ የሚያሳይ ምንም ዓይነት ፍንጭ አያመላክትም፡፡ ሁሉንም ነገር በድብቅና በስውር ለመፈጸም ጥረት ባደረጉ ቁጥር በእርግጠኝነት ሁሉንም ነገር ይፋ እንደሚያወጡት ሊያውቁት ይገባል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ወረድ ሲል የምመጣበት ይሆናል፡፡) ከአንዳርጋቸው በስተቀኝ በኩል በምርመራ ጠረጴዛው ላይ ያልተከፈተ በፕላስቲክ ውስጥ ያለ ውኃ ይታያል፡፡ ይኸኛው የቪዲዮ ቀረጻ ክፍል በ30፣ 41 እና 55 ሰከንዶች… በድምሩ በ2 ደቂቃ ከ6 ሰከንዶች ተከፋፍሎ የቀረበ ነው፡፡ የመጀመሪያውን ወጥ የሆነውን የቪዲዮ ቀረጻ እንደ ስጋ እየመተሩ በአስከፊ ሁኔታ በጣጥሰውታል፡፡ እናም ማንም የአንዳርጋቸውን መልስ ለመገንዘብ የሚፈልግ ሰው ሁሉ ዲጂታል በሆነ መልኩ የተገጣጠሙትን የአንዳርጋቸውን ምስሎች በአንክሮ በማየት እና በቪዲዮ የምርመራ ስልት አፋቸውን ሲያንቀሳቅሱ በመመልከት አገጣጥሞ ለመተርጎም እና በመጠኑም ቢሆን ምን ለማለት እንደፈለጉ ግንዛቤ ለመውሰድ ይቻላል፡፡

ሁለተኛው የቪዲዮ ቀረጻ ክፍል በ4 ደቂቃ ከ29 ሰከንድ ላይ ይጀምራል፡፡ አንዳርጋቸው ቀደም ሲል በመጀመሪያው የቪዲዮ ቀረጻ ክፍል የምርመራ ወቅት ለብሰውት የነበረውን ጃኬት እና በአንገቱ ዙሪያ ነጭ ቀለም ያለው ፈጋ ያለ ውኃ ሰማያዊ ቀለም ያለው ሸሚዝ ለብሰዋል፡፡ ከአንዳርጋቸው በስተቀኝ በኩል ከምርመራ ጠረጴዛው ላይ በከፊል የሚታይ የኤሌክትሮኒክ መሳሪያ ይታያል፡፡ ይኸኛው የቪዲዮ ቀረጻ ክፍልም እንደዚሁ የተቆራረጠ እና በአስከፊ ሁኔታ ለበርካታ ጊዚያት እንደ ጥሬ ስጋ የተመተረ መሆኑን በግልጽ ያመላክታል፡፡

ሶስተኛው የቪዲዮ ቀረጻ ክፍል ደግሞ በ5 ደቂቃ ከ20 ሰከንዶች ላይ ይጀምራል፡፡ በዚህኛው የቀርጥራጭ ክፍል አንዳርጋቸው በእጅጌው ላይ ነጭ ቀለም ያሰነበረበት ጥቁር አዲዳስ የአትሌት ቱታ ለብሰዋል፡፡ የቪዲዮ ቀረጻው መደቡ ነጭ በሆነ በአንድ ጊዜ የቀረጻ ተኩስ የተወሰደ መሆኑን ይመሰክራል፡፡ የምርመራ ጠረጴዛው ሙሉ በሙሉ በትክክል አይታይም፡፡ እንደዚሁም ደግሞ የቪዲዮ ቀረጻው በረዥም ጊዜ የምርመራ ጥያቄ በመታጀብ ለበርካታ ጊዚያት ተቆርጦ የተቀጠለ ድሪቶ መሆኑን በግልጽ ያመላክታል፡፡

አራተኛው የቪዲዮ ቀረጻ ክፍል በ8 ደቂቃ ከ33 ሰከንድ ላይ ይጀምራል፡፡ አንዳርጋቸው በቪዲዮ ቀረጻው ክፍል 1 እና 2 የለበሱትን ዓይነት ሰማያዊ ጃኬት ለብሰዋል፡፡ ሶስተኛው የቪዲዮ ቀረጻ ክፍል የክፍል 1 እና 2 ቀጣይ መሆኑን የሚያመላክት ግልጽ የሆነ ነገር የሌለ ሲሆን አንዳርጋቸው የሚሰጧቸውን ምላሾች ለመድረክ ትወና አጋንኖ ለማቅረብ ሲባል ቆርጦ የመቀጠሉ ተግባራት በሰፊው ተሰርቷል፡፡ በዚህ ክፍል የቪዲዮ አርታዒዎቹ እና የቪዲዮ ቀረጻ ስራውን የሚያዘጋጁት ሰዎች ምን ለመስራት ና አንዳሰቡ ማወቅ አይቻልም፡፡ (አንደዚህ አይነት አሳፋሪ ስራ ከመስራት በፕሮፓጋንዳ ፊልም ወይም በሌላ ተመሳሳይ ስራ ላይ ስልጠና ቢወስዱ ከትዝብትና መሳቅያ ከመሆን ያድናቸዋል፡፡)

አምስተኛው የቪዲዮ ፊልም ቀረጻ ክፍል በ9 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ ላይ ይጀምራል፡፡ አንዳርጋቸው በቪዲዮ ቀረጻው ክፍል 1 እና 2 የለበሱትን ዓይነት ሰማያዊ ጃኬት ለብሰዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አስስተኛው የቪዲዮ ቀረጻ ክፍል በተለያዩ ነጥቦች ላይ ረዥም የሆነ የመቁረጥ እና የመቀጠል ስራዎች ተከናውነውበታል፡፡

እንደቅርጫ ስጋ እና እንደጥሬ ስጋ በተከፋፈለ እና በተመተረ የሸፍጥ መረጃ ላይ መሰረት በማድረግ እንዲሁም የት እና መቸእንዲሁም ማንነታቸውባልታወቁ የቪዲዮ ቀረጻ ቆርጦ ቀጥሎች በተዘጋጀው የመድረክ ትወና ዝግጅት ላይ ህብረተሰቡ የህሊናፍርድ እንዲሰጥ ተጋብዟል፡፡ የአንዳርጋቸው ምላሾች ጥያቄ አልባዎች ናቸው፡፡ ምላሾቹ በርካታ የሸፍጥ የአርትኦ ስራ ተሰርቶባቸዋል፣ የተወሰኑ የቪዲዮ ቀረጻ ክፍሎችን ብቻ መሰረት በማድረግ በአንዳርጋቸው ላይ ለተመልካች መጥፎ ስዕል እንዲሰጥ በማሰብ በመርማሪዎች እምነት ስራው ግቡን መታ ለማለት እንዲቻል ተቆርጠው እንደገና ከእነርሱ ጋር በማይሄዱ እና በማይስማሙ የቅጥፈት ቁርጥራጮች በአንድነት ተቀጥለዋል፡፡ በአምስቱም የቪዲዮ ቀረጻ ክፍሎች ላይ አንዳርጋቸው ይቅርታ ጠያቂ፣ ጸጸት የተሰማቸው ለማስመሰል፣ እርግጠኛ ያልሆኑ፣ ከጠለፋው በፊት የነበረውን የእራሳቸውን ህይወት የሚያወግዙ፣ በዓላማ ጓደኞቻቸው እና በድርጅታቸው ላይ ጣቶቻቸውን የሚቀስሩ፣ ብልህነት የጎደላቸው፣ የሚያደናግሩ፣ ኃይል የተቀላቀለባቸው፣ ጸጸት እንዲደረግ የሚገፋፉ፣ አሳፋሪ ስብዕናን የተላበሱ፣ የጥፋትኝነት ስሜትን የተከናነቡ፣ አሳዛኝ፣ አዋራጅ፣ ህሊናን የሚያስቱ፣ በቅሌት የሚዘፍቁ፣ እርባናየለሽ የሆኑ፣ ማጭበርበር የተሞላባቸው፣ ወዘተ ምላሾች እንዲሰጡ ጥንቃቄ በተመላበት መልኩ ወያኔ ጥረት አሳይቷል፡፡ እንግዲህ በዚህ ዓይነት ሁኔታ በተቀረጸ የቪዲዮ የቅጥፈት የምላሽ ማስረጃ ነው የወያኔ ዓይን አውጣ የወሮበላ ስብስብ ተመልካች የሆነውን የኢትየጵያ ህዝብ እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአንዳርጋቸው ላይ የህሊና ፍርዳቸውን እንዲሰጡ እየጠየቀ ያለው፡፡

ያም ሆነ ይህ በአንዳርጋቸው ላይ የህሊና ፍርድ እንድንሰጥ የቀረበልንን ግብዣ እቀበላለሁ!

የአንዳርጋቸው ጽጌ የፍርድ ሂደት በእኔ የህሊና ዳኝነት፣

በቪዲዮ ቀረጻው በቀረቡት 10 ደቂቃ ከ31 ሰከንዶች ቆይታ በነበራቸው የወያኔ የቪዲዮ ቀረጻ ወካይ የሚሆኑ ምላሾች ላይ መሰረት በማድረግ በአንዳርጋቸው ጽጌ ተሰጡ በተባሉት ምላሾች ላይ ያለኝን የህሊና ዳኝነት እነሆ፡፡ ከዚህ በታች የቀረቡትን የእኔን ፍርድ አንባቢዎቼ ካነበባችሁ በኋላ የሰጠሁት ፍርድ የዝንጀሮ የይስሙላ ፍርድ ነው ልትሉኝ እንደምትችሉ ጥርጥር የለኝም፡፡ ሆኖም አንድታቁለኝ የምፈለገው እኔ ቢያንስ አውነተኛና ፍትሀዊ የሆንኩ የዝንጀሮ የይስሙላ ፍርድ ቤት ነኝ፡፡

የቪዲዮ ቀረጻውን በተመለከተ በአንዳርጋቸው የምርመራ ጥያቄ ላይ የእኔን የህሊና ፍርድ መግለጫዎች እና ማብራሪያዎች ከዚህ እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡ በአንዳርጋቸው ላይ የቀረበው የቪዲዮ ምስል የዕይታ ጥራቱ በጣም ደካማ የሆነ፣ ምንም ዓይነት እውቀት በሌላቸው ተለማማጅ የቪዲዮ ኦዲዮ ቀራጮች ተቆርጦ፣ ተቀጥሎ፣ ተጥፎ እና ተደርቶ የተዘጋጀ መሆኑን መሰረት በማድረግ የህሊና ፍርዴን እሰጣለሁ፡፡ አንዳርጋቸው ለየትኞቹ ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጡ እንደሆነ በምንም ዓይነት መልኩ ባወጣ ባወርደው ልገነዘበው አልቻልኩም፣ ልገነዘበው ያልቻልኩት ደግሞ የመገንዘብ ችግር ወይም የቋንቋ እጥረት ኖሮብኝ ሳይሆን የቀረበው የልጆች ተረት ተረት ጨዋታ፣ ምንም ዓይነት ግንዛቤን ሊፈጥር የማይችል በቅጥፈት የተሞላ የሸፍጠኞች ድሪቶ እዚህም እዚያም የሚረግጥ አራምባ እና ቆቦ ሆኖ በመገኘቱ ብቻ ነው፡፡ አቶ አንዳርጋቸው የሰጧቸው ምላሾች በቪዲዮ ተቀርጸው እና በቆርጦ ቀጥል የወያኔ ስልት ተጥፈው፣ ተለብደው እና ተሸሞንሙነው ለህዝብ የህሊና ዳኝነት የቀረቡ ከመሆናቸው ውጭ በእርግጥ የሀሰት ውንጀላ ሰለባው ጉዳዩን አውቀው በእራሳቸው አንደበት አምነውበት በተጽዕኖ አንደሰጡ ምንም ጥረጣሬ የለኝም፡፡ እንደዚሁም ደግሞ እነዚህ በቪዲዮ ተቀርጸው ከተጠናቀቁ በኋላ በወያኔ የመቁረጫ መቀስ ተቆርጠው፣ በወያኔ መርፌ ተሰፍተው፣ ተደርተው እና ተለብደው የቀረቡ ለመሆናቸው አንዳርጋቸውን ጥፋተኛ አድርጎ በህዝብ ህሊና ውስጥ የተዛባ አመለካከት ለመፍጠር እና እርሳቸውን ከማጥ ውስጥ ለመጨመር የተፈበረከ የመድረክ ላይ ውኔት መሆኑን አውቃለሁ፡፡ አንዳርጋቸው ቀደም ሲል ተሰጥተዋቸው የነበሩትን በጥያቄ አቅራቢዎቻቸው ለሚሰጡ ጥያቄዎች ተደጋጋሚ ምላሽ እየሰጡ እና እየደገሟቸው መሆኑን አውቃለሁ፡፡

የአንዳርጋቸው አዕምሯዊ እና አካላዊ ደህንነት አስተማማኝ በሆነ መልኩ ሙሉ ጤንነትን የተላበሰ መሆኑን ባላወቅሁበት ሁኔታ እና ምንም ዓይነት መረጃ ወይም ፍንጭ ባላገኘሁበት ሁኔታ ላይ ነው ይህንን የመሰለ የህሊና ዳኝነት አስተያየት በመስጠት ላይ ያለሁት፡፡ አቶ አንዳርጋቸው በግዳጅ ምላሽ እንዲሰጡ ከመደረጋቸው በፊት በጠያቂዎቻቸው አማካይነት አደንዛዥ እና አዕምሮን የሚያስት መድኃኒት ተሰጥቷቸው ይሁን አይሁን ወይም ደግሞ አዕምሯቸውን ሊለውጥ የሚችል ሌላ የማሰናከያ ወጥመድ ተጠምዶላቸው ይሁን አይሁን በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር የለም፡፡ አንዳርጋቸው አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጫና እና ማሰቃየት ወይም ደግሞ ምላሾችን እንዲሰጡ ኃይል የተቀላቀለበት ማስገደጃ የተደረገባቸው ለመሆናቸው እውቀቱ ሳይኖረኝ (ሆኖም ግን ከፍተኛ የሆነ ጥርጣሬ አለኝ) ነው ይህንን የህሊና ፍርድ በመስጠት ላይ ያለሁት፡፡ አንዳርጋቸው ምላሾችን እንዲሰጡ ከመገደዳቸው በፊት ለበርካታ ጊዚያት እንቅልፍ ተከልክለው እንደሆነ ወይም ደግሞ ምግብ ወይም ሁለቱንም እንዳያገኙ ተደርገው እንደሆነ የማውቀው ምንም ዓይነት ፍንጭ የለኝም፡፡ (በመጀመሪያው የቪዲዮ ቀረጻ ክፍል ውስጥ ያልተከፈተ የፕላስቲክ ውኃ በጠረጴዛው ላይ ተቀምጦ ይታያል፡፡ ይህ ውኃ አንዳርጋቸው ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሙሉ ለወያኔው አጥጋቢ የሆነ ምላሽ መስጠት ከቻሉ ከጥያቄ እና መልስ ሂደቱ መጠናቀቅ በኋላ በሽልማት መልክ ሊሰጡ የታቀደ ነውን? ነው ወይስ ደግሞ መድረኩን ለማስዋብ ተብሎ የተቀመጠ ነው? አንዳርጋቸው በቪዲዮ ቀረጻ ምስሎች ላይ ደማቅ ጠቆር ያለ የአትሌት ልብሶችን ለብሰው ከመታየታቸውም በላይ ፊታቸው ብቻ ተነጥሎ እንዲታይ ተደርገዋል፡፡ ይኸ ሁኔታ በዚህ ዓይነት አለባበስ እንዲታዩ መደረጉ ምናልባትም በሰውነታቸው ላይ ጉዳቶችና የማሰቃየት ውጤት የሆኑት ጠባሳዎች እንዳይታዩ ከህዝብ ዕይታ ለመደበቅ ተብሎ በሸፍጥ መሰሪዎቹ የተቀነባበረ ድርጊት ሊሆን ይችል ይሆን?

እኔ አሁን በዚህ መድረክ በአንዳርጋቸው ጉዳይ ላይ የህሊና ፍርዴን እና አስተያየቴን በመስጠት ላይ ያለሁት መሰጠት ያለባቸው ምላሾቹ አስቀድመው በተዘጋጁበት፣ ጥያቄዎቹ ምን እንደሚሉ እና ማንስ እንደሚጠይቅ ባልታወቀበት፣ በአጠቃላይ የተሟላ መረጃ በሌለበት እና አስቀድሞ እቁቡ በተበላበት የቅጥፈት የትወና መድረክ ላይ ሆኘ ነው፡፡ አንዳርጋቸው በሙሉ ቃለ መጠይቁ ወቅት ለጠያቂዎቻቸው ምን እንዳሉ እና ምንስ እንዳላሉ ምንም ዓይነት እውቀት ሳይኖረኝ ነው በቀጥታ ወደ ማጠቃለያ መደምደሚያው እመር በማለት የእኔን የህሊና ፍርድ እና አስተያየት በመስጠት ላይ ያለሁት፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ይህ ጥያቄ የቀረበላቸው በየት ቦታ እና በምንስ ጊዜ እንደሆነ ምንም ዓይነት መረጃ ሳይኖረኝ፣ የጠያቂዎቻቸው ማንነት ባልታወቀበት ሁኔታ፣ ሲቀርቡላቸው የነበሩት ጥያቄዎች ብዛት እና ዓይነት ምን እንደሆነ ባልታወቀበት፣ የሚሰጡት ምላሾች ለተወሰኑ ግልጽ ለሆኑ ጥያቄዎች መሆን አለመሆናቸው እና ይህንን የጥያቄ እና መልስ ሂደት እንዲከናወን ትዕዛዝ የሰጡት ባለስልጣኖች ማንነት እና ከዚህ ቃለ መጠይቅ በኋላ የተገኘውን ምላሽ ለህዝብ በመልቀቅ የህሊና ዳኝነት እንዲሰጥ በመጠየቅ ላይ ያለው እና ከዚህ በመነሳት ምን ዓላማን ለማራመድ እንደሆነ በግልጽ ብቻም ሳይሆን በግርድፉም ቢሆን ባልታወቀበት ሁኔታ ነው ይህንን የህሊና ዳኝነት እና አስተያየት በመስጠት ላይ ያለሁት፡፡ አንዳርጋቸው ለአንድ ወይም ከአንድ በላይ ለሆኑ ጥያቄ አቅራቢዎች ምላሽ የሰጡ መሆን አለመሆናቸውን ባላወቅሁበት ሁኔታ ላይ ነው ይህንን የህሊና ፍርድ እና አስተያየት በመስጠት ላይ ያለሁት፡፡ በበርካታዎቹ የቪዲዮ ቀረጻ ክፍሎች ውስጥ የአቶ አንዳርጋቸው ዓይኖች ምላሽ በሚሰጡበት ክፍል ውስጥ በፍጥነት ከማዕዘን ወደ ማዕዘን ከግድግዳ ወደ ግድግዳ ሲንቀዋለሉ እና ሲያማትሩ የመስተዋላቸው ሁኔታ በጥያቄ እና መልስ የመስጠት ሂደቱ ወቅት በርካታ ጠያቂዎች የነበሩ ለመሆኑ ማስረጃ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳርጋቸው በተናገሯቸው እና በቀረቡት ቁርጥራጭ መረጃዎች ላይ መሰረት በማድረግ ነው እንግዲህ የእኔን የህሊና የዳኝነት እና አስተያየት በመስጠት ላይ ያለሁት፡፡

ስለሆነም በአንዳርጋቸው ጥያቄ አልባ በሆኑ በዚህች ምድር ላይ ለወሮበሎች በተሰጡ ምላሾች ላይ የእራሴን ፍርድእሰጣለሁ፡፡

የአንዳርጋቸው አስረጅነት፡ “ባለፈው ጊዜ የብሩህ አዕምሮ ባለቤት የሆኑት ተማሪዎች ነበር ወደ ፖለቲካው ዓለም ይገቡ የነበሩት፡፡ በሂደት በሞት የተለዩትን (በፖለቲካ የትግል ሂደት ውስጥ) የእነዚህን ተማሪዎች ስም ዝርዝር ባቀርብ እጅግ በጣም ትደነግጣላችሁ፡፡”

ይኸ ትክክለኛ መግለጫ ነው፡፡ በርካታዎቹ የባለብሩህ አዕምሮ ባለቤቶች፣ የመጠቀ ሀሳብ አፍላቂዎች እና አራማጆች፣ እንዲሁም ጀግኖች እና ጀግኒቶች ወጣቶች እ.ኤ.አ በ1970ዎቹ በአምባገነኑ ወታደራዊ አገዛዝ እንዲያልቁ ተደርጓል፡፡ ሌሎች ድርጅቶች ወጣቱን ትውልድ የእራሳቸውን የፖለቲካ ዓላማ ለማራመድ እንደ ዝቅተኛ ማዕረግ እንዳላቸው ወታደሮች በማድረግ ተጠቅመውባቸዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ጥቂቶችን አውቃለሁ፡፡ አንድ ቀን ታሪካ እነዚህን ወጣቶች ከእነርሱ ትውልዶች ምርጦች እና የባለብሩህ አዕምሮ ባለቤቶች በማለት ሊያስታውሳቸው ይችላል፡፡

“አንዳርጋቸው፡ በአሁኑ ጊዜ ያሉ ወጣቶች ዲግሪዎቻቸውን ካገኙ እና ለትንሽ እድል ከበቁ ወደ ውጭ ሀገር ሄደው ነው የሚኖሩት፡፡ እዚያም ከሄዱ በኋላ ስራ ያገኛሉ እናም ኑሯቸውን እዚያው ይቀጥላሉ፡፡ እነዚህ ወጣቶች እንዲያውም በሀገራቸው ውስጥ ለመቆየት እና ለመኖር የሚችሉ አይመስላቸውም፡፡ በዚያ ዓይነት መልኩ አያስቡም…”

ይሄማ የማይካድ እውነታ ነው፡፡ እስቲ እውነተኞች እንሁን፡፡ ማንም ወንድም ሆነ ሴት ወጣት ያለመውን ህልም እውን ለማድረግ እንዲችል ነጻነቱን የሚያጎናጽፍ ሀገር ሲያገኝ ከኢትዮጵያ ወደዚያ ወደ ውጭ ሀገር የማይሄድ ወጣት ማን አለ? ምንም ከማያውቁ የደናቁርት ስብስቦች እና በሙስና እስከ አንገታቸው ድረስ ከተዘፈቁ ወሮበላዎች ጋር እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ መኖርን የሚመርጥ ወጣት ሊኖር ይችላልን?

አንዳርጋቸው፡ “ግንቦት 7 በብዙ መንገዶች በወጣቶች ላይ የሚያተኩር ድርጀት ነው፡፡ ወጣቶች በሰላማዊ ትግል ላይ እምነት አላቸው፣ እናም እንደ ዱሮው የኢህአፓ ወጣት ሁሉ መሞትን አይፈልጉም፡፡ ያ ያለፈበት ጊዜ ነው… ወጣቶች እንዲህ ይላሉ፣ “እራሳችንን መግለጽ እንችላለን፣ በግልጽ በአደባባይ ወጥተን ተቃውሟችንን ማሰማት እንችላለን፡፡ በእኛ ላይ የሚደርስብን አንዳችም ነገር የለ፡፡ የአሁኑ ዘመን ሌላ ጊዜ ነውና””

በዚህ በክፍል 1 የቪዲዮ ቀረጻው ክፍል ላይ የቀረበው ምላሽ አስከፊ በሆነ መልኩ ተቆርጦ ተቀጥሏል፣ እንዲለጠፍም ተደርጓል፡፡ ስለሆነም አንዳርጋቸው የትኛውን ክፍል ለመጥቀስ እንደፈለጉ ለማወቅ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ምላሻቸውን በትክክል ተገንዝቤው ከሆነ እውነት ነው የኢትዮጵያ ወጣቶች ሰላማዊ የሽግግር ለውጥን ይፈልጋሉ፡፡ ለውጥን ከፍቅር እና እውቀት ጋን ውስጥ እንጅ ከድንቁርና እና ከAK-47 የጠብመንጃ አፈሙዝ ፈጽሞ አይፈልጉም፡፡ አንድም ኢትየጵያዊ የሆነ ወጣት በእውቀት እና በጉብዝና ላይ በተመሰረተ መልኩ ከሰላም ይልቅ ጦርነትን፣ ከፍቅር ይልቅ ጥላቻን እና ከወንድማዊነት ጠላትነትን ይመርጣል የሚል የማውቀው አንድም ወጣት የለም፡፡

አንዳርጋቸው፡ “ግንቦት 7 አሳሳቢ የሆኑ ችግሮች አሉበት፡፡ ከዚህ ቀደም ያላየናቸው እና ወደፊት ግን ማየት ያለብን ነገሮች እንዳሉ እንገደዳለን…ዋና ዋና ተግባራት ናቸው ያልናቸውን ተግባራት እስካሁን ድረስ አላከናወንንም…“

ለእኔ ይህ መግለጫ ታማዕኒነት ያለው ይመስለኛል፡፡ ስግንቦት 7 ውሰጣዊ አሰራር እና ሂደት የማውቀው ነገር የለኝም፣ ሆኖም ግን ከአንዳርጋቸው ምላሽ ለመገንዘብ እንደቻልኩት በግንቦት 7 ላይ ያለው ችግር በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ባሉ በሌሎች በእያንዳንዱ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት ላይም የሚንጸባረቅ ይመስላል፡፡ ምን ዓይነት አሰልች ድግግሞሽ ነው!

አንዳርጋቸው፡ “የኢትዮጵያ የተቃዋሚ የፖለቲካ ቡድኖች በፖለቲካ ሂደቱ ላይ እንዴት መንቀሳቀስ እና መስራት እንዳለባቸው ጥያቄ አለኝ፡፡ የተቃዋሚ የፖለቲካ ቡድኖች መንግስት ምን እየሰራ እንዳለ ግልጽነት በተመላበት ሁኔታ የማያውቁ ከሆነ ለመስራት እንዴት ዝግጁ እንደሚሆኑ ወይም ደግሞ የፕሮግራም ሰነዳቸውን/manifesto ወይም ደግሞ የምርጫ ዕቅዶቻቸውን እንዴት እንደሚያዘጋጁ እና እንደሚተገብሩ የማውቀው ነገር የለም፡፡ ግልጽነትን በተመለከተ ኃላፊነቱ ያለው በመንግስት ላይ ነው፡፡ ይህ የእኔ እምነት ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድኖች የተሰባበሩ ናቸው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ይህንን ትልቅ ኃላፊነት ለመቀበል እና አንድ ሆነው በመተባበር ለመስራት ወደ አንድነት መምጣት አለባቸው… በጣም ግለሰባዊ የሆኑ የተወሰኑ እሴቶች አሉ…ለተቃዋሚ የፖለቲካ ቡድኖች አንዱ እና ዋናው ችግር ወደ አንድነት የመምጣት እና በሚያስማሟቸው ጉዳዮች ላይ የጋራ አጀንዳ ቀርጸው ለጋራ ዓላማ መንቀሳቀስ አለመቻላቸው ነው…የኢኮኖሚ ፖሊሲ ሲነድፉ እና ሲያወጡ አይቸ አላውቅም፡፡ የኢኮኖሚ ፖሊሲያቸው ምንድን ነው?…አንድ ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በአንድ ላይ ተሰባስበው የፖለቲካ ፓርቲ ማቋቋም ይችላሉ… ወይም ደግሞ 5 ሰዎች የፖለቲካ ፓርቲ መስርተው ለስልጣን መወዳደር ይችላሉ በሚለው ሀሳብ ላይ እምነት የለኝም…ጥቂት የተቃዋሚ የፖለቲካ ቡድኖች ስብሰባ በሚያካሂዱበት ጊዜ፣ 20 ሰዎች ሊኖሯቸው ይችላል፣ ለምሳሌም የኢህአፓ፣ ሸንጎ፣ ወዘተ…የእኛ ሰዎች ሲጨመሩበት ደግሞ 23 ወይም ደግሞ 24 ሊሆን ይችላል…ምንም ዓይነት የዓላማ አንድነት ሳይኖራቸው እንደ ጥቅምት አክርማ ይሰነጠቃሉ፣ ይሰነጣጠቃሉ…“

ይህ በቪዲዮ ቀረጻ ክፍል 3 በተሰጠው ምላሽ ላይ አስከፊ በሆነ መልኩ ቆርጦ የተቀጠለ እና አንዳርጋቸው ስለተቃዋሚ የፖለቲካ ባህሪያት በትክክል ምን ለማለት እንደፈለጉ ለመገንዘብ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ሆኖም ግን የኢትዮጵያ የተቃዋሚ የፖለቲካ ቡድኖች የተሰባበሩ፣ የተበጣጠሱ፣ ወደ አንድነት ለመምጣት ያልቻሉ እና ህብረት ፈጥረው የህወሀትን ገዥ ፓርቲ ግንባር ለግንባር ለመጋፈጥ ያልቻሉ ናቸው የሚለው ሀሳብ የማይካድ ሀቅ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፖለቲካ ቡድኖች የሀገሪቱን ችግሮች ለማስወገድ የሚያስችሉ የእራሳቸው ግልጽ እና በሚገባ የተቀመሩ ፕሮግራሞች ወይም ደግሞ የፓርቲ የፕሮግራም ሰነዶች/manifestos የሌሏቸው ናቸው፡፡ ከአምስት ዓመታት ገደማ በፊት የአውቀት መርሀግብር/think tank program በማዘጋጀት የተቃዋሚ የፖለቲካ ቡድኖች የተባበረ የፖለቲካ ሀሳቦች/agenda እና መርሀ ግብሮች እንዲኖሯቸው ሀሳብ አቅርቤ ነበር፡፡ (“እውነታውን ለእውነት ፈላጊዎች መናገር” በሚል ርዕስ አቅርቤው የነበረውን የሁፍንግቶን ፖስት ትች ቴን ይመለከቷል፡፡) እኔ በዚህ መልክ ካቀረብኩት ሀሳብ ላይ አንድም የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ወስዶ በስራ ላይ ለማዋል የሞከረ የለም፡!

በቪዲዮ ምስሉ ላይ የአንዳርጋቸው የመጨረሻ ምላሽ፡ አድናቆትን ልሰጣቸው (ስለ እኔ እስራት) የምችልባቸው በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ ወደዚህ በመጣሁበት ጊዜ የለበስኳት ሸሚዝ እና ፓንት ብቻ ነው የነበረኝ፡፡ ከምግብ አንጻር ስኳርነት ከሌላቸው ምግቦች ውጭ እኔ እራሴ የመረጥኩትን የእኔ አሳሪዎች ሲታዘዙ የሚያቅርቡልኝን እጠቀማለሁ፡፡ እዚህ ከመጣሁ በኋላ በጣም ጤናማ ሆኛለሁ፡፡ ፍጹም በሆነ መልኩ በሚስማማ ሁኔታ ላይ እገኛለሁ፣ በምንም ዓይነት ሁኔታ የማይስማማ ነገር አላየሁም፡፡ በግቢው ውስጥ እራመዳለሁ፣ እንሸራሸራለሁ፣ እናም ሁሉንም የስባትነት የውፍረት ሁኔታዎችን ሁሉ አስወግጀ ሙሉ በሙሉ ሸንቃጣ እና ያማረበት ሰው ሆኛለሁ፡፡

በቡርጅ አል መለስ ዜናዊ ሆቴል ለሚደረገው የምግብ አሰራር አስተያየት ለመስጠት አልችልም፡፡ ሆኖም ግን በመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት ውስጥ ለአንዳርጋቸው ጤንነት ተብሎ ከፍተኛ የሆነ ክብካቤ ይኖራል ብሎ ለማመን ጉምን በእጀ በመዳፉ እንደመዝግን የምቆጥረው ስለሆነ ጥርጣሬየ የበረታ ነው፡፡ እንደዚሁም ደግሞ አንዳርጋቸው እስከ አሁን ድረስ ከታዩት አሸባሪዎች ሁሉ በጣም “አደገኛ አሸባሪ” እንደሆኑ ተደርገው በወያኔ የወሮበላ ስብስብ ተነግሮናል፡፡ ለዚህም ነው እ.ኤ.አ በ2009 እና እንደዚሁም በ2012 ሁለት ጊዜ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው፡፡ በእርግጥም ወያኔ በጣም ረዥም ጊዜ ወስዶ ልዩ የሆነ የመድረክ ላይ ተውኔት አዘጋጅቶ ለህዝብ እይታ እና ለህሊና ዳኝነት በሚል አሳፋሪ ዘለፋ ለኢትዮጵያ ህዝብ ማቅረቡ አንዳርጋቸው አደገኛ ሰው ቢሆኑበት መሆኑ አጠራጣሪ አይደለም፡፡ እ.ኤ.አ ጁላይ 2014 አንዳርጋቸው የመን ላይ በወያኔው መጠለፋቸውን ተከትሎ ወያኔ አንዳርጋቸውን ከኦሳማ ቢንላደን ጋር መሳ ለመሳ በሆነ ቋንቋ አቅርቧቸው ነበር።

ለምንድን ነው የወያኔ ወሮበላ ስብስብ የኢትዮጵያ ኦሳማ ቢንላደን ናቸው እያለ ለሚያሰቃያቸው አንዳርጋቸው ጽጌ እንደዚህ ያለየንጉሳዊ ክብካቤ እያደረገሙሽራ አስመስሎ የያዛቸው???

ወያኔ አንዳርጋቸውን እንደዚህ ባለ የንጉሳዊ ቤተሰብ ክብካቤ ዓይነት አያያዝ እያቀማጠላቸው ከሆነ ለምንድን ነው 10 ደቂቃ ከ31ሰከንዶች በወሰደውምላሻቸው አንድ ጊዜ እንኳ ቢሆን የድሎት ፈገግታ ሳያሳዩ የመድረክ ትወናው የተጠናቀቀው? ለማያውቁሽ ታጠኝ! ነው ነገሩ፡፡

የአንዳርጋቸውን የቪዲዮ ቀረጻ ፊልም ቀደም ሲል ተመልክቸዋለሁ፣

የወያኔ የወሮበላ ስብስብ ብዙ ዓይነት ድንቁርናዎችን፣ ሰይጣናዊ እና ከአፍንጫ የማያልፉ አስተሳሰቦችን፣ ውስብስብ የሆኑ የማታለል ድርጊቶችን፣ የሞኝ እና የጅላጅል እኩይ ምግባሮችን ለበርካታ ዓመታት ሲፈጽም ቆይቷል፡፡ የወያኔ የወሮበላ ስብስብ የሸፍጥ ቪዲዮ አስቀርጾ እና አቀነባብሮ ሰላማዊ የሆኑ የሙስሊም ማህበረሰብ ተወካዮችን በሀገሪቱ ቴሌቪዥን በማሳየት አሸባሪ ናቸው በማለት የስም ማጥፋት ዘመቻውን ሲያጧጡፍ በታላቅ አግራሞት ስመለከተው ነበር፡፡ በሁለት አሳዛኝ እና በለማጅ የቪዲዮ ቀራጮች የተዘጋጁ የቪዲዮ ዘገባዎች ወያኔ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ዋና ጽንፈኞች ናቸው በማለት ስም የማጥፋት ሙከራውን ሲያካሂድ ተስተውሏል፡፡ ወያኔው በሁለት የቪዲዮ ዘገባዎች ማለትም የደም መሬት/አኬልዳማ ወይም ደግሞ የሙስና መሬት በሚሉ ከእውነታው ጋር የማይገናኙ ነገሮችን እያገናኘ የስም ማጥፋት ዘመቻውን በስፋት ቀጥሎበት ይገኛል፡፡ እ.ኤ.አ ዴሴምበር 2011 (“ኢትዮጵያ፡ ፍርኃት እና ስም የማጥፋት ዘመቻ” እና እ.ኤ.አ ፌብሯሪ 2013) የኢትዮጵያን ሙስሊሞች መብት በመከላከል የባለስልጣኖች በእምነት ላይ ጣልቃ የመግባት፣ የመፐወዝ እና አግባብ ያልሆነ የቁጥጥር ስርዓት እንዲወገድ ተከራክሪያለሁ፡፡

የወያኔ የወሮበላ ስብስብ አሁን በህይወት የሌለውን የመለስ ዜናዊ የሌለውን እውነተኛ ያልሆነውን ስብዕና በቅጥፈት እና በዘራፊነት ስብዕና ለመተካት ሲባል የዳግማዊ ምኒልክን ሰብዕና ሲቆርጡ እና ሲቀጥሎ ተመልክቻለሁ፡፡ ይህንንም ጉዳይ በማስመልከት “የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት መቀባት” በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችት በምንመጣበት ጊዜ በዓላማ ጽናት (ነገሮችን በጥንቃቄ የመያዝ እና ልዩ የሆነ ውስጣዊ ባህሪ)፣ ያቀዱትን እና ያሰቡትን ከመፈጸም አንጻር (የተግባር ሰው፣ ታማኝ)፣ ክብር ከመስጠት አንጻር (በክብር መሞላት እና እራስን ምሳሌ አድርጎ ሌሎችን የመሳብ ሁኔታ) እና ልዩ ተፈጥሯዊ ባህሪ (አንድን ጉዳይ ለመፈጸም በጦርነት ጊዜ የሚታይ ጅግንነት፣ ጽናት፣ ደፋርነት) በሚታይበት ጊዜ መለስ ከምኒልክ ጋር መወዳደር ቀርቶ የጫማቸው ተረከዝ የማይደርስ በወያኔ የይስሙላ ዲስኩር ታጅቦ ለእኩይ ዓላማ ማራመጃቸው ሲባል ብቻ ፕሮፓጋንዳ የሚነዛለት ቀፎ መሆኑን ለማሳየት ሞክሪያለሁ፡፡ መለስ እና ግብረ አበሮቹ ከምርጡ ከእምዬ ምኒልክ ጋር (ስማቸው በምግባራቸው እና በተግባራቸው በሚወዳቸው ህዝብ ፍላጎት የተሰጠእንጅ እንደ መለስበጉልበት ፕሮፓጋንዳ በህዝብ ላይ ለመጫን ያልተሞከረ መሆኑን ልብ ይሏል) ሊወዳደሩ የማይችሉ ተራዎች መሆናቸውን ለማሳየት ጥረት አድርጊያለሁ፡፡ ምኒልክ በአመራር ጥበባቸው ከፍተኛውን ስኬት የተጎናጸፉ ክብር ያላቸው መሪ ነበሩ የሚለውን ለማረጋገጥ የሚጠበቅብኝ አይሆንም፡፡ (እ.ኤ.አ ኖቬምበር 7/1909 በኒዮርክ ታይምስ ታትሞ የወጣውን መመልከት በቂ ነው፡፡)

እንደዚሁም ሁሉ የወያኔ ወሮበላ ስብስብ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ቡድን አመራሮችን፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን እና ሌሎችን ለሀገር የሚቆረቆሩ ዜጎችን ለማዋረድ ሲሉ ሁሉንም ዓይነት የጅልነት ተግባራት፣ ኃላፊነት የማይሰማው የህጻናት ዓይነት ድርጊቶችን በአደባባይ ስፈጽሙ ይታያሉ፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት ታላቁን የመድረክ ላይ ተውኔት ባለሙያ ቀንዲል የሆነውን ደበበ እሸቱን እንደ አንዳርጋቸው ጽጌ ሁሉ በእስር ቤት ውስጥ አስገብተው የውሸት ድሪቶ የቪዲዮ ፊልም ቀረጻቸውን አዘጋጅተው ግብር በሚከፈልበት በኢትዮጵያ ህዝብ ቴሌቪዥን በማቅረብ ለህዝብ ህሊና ለፍርድ ሲያቀርቡት እርሱን ያዋረድን መስሏቸው እነርሱ እራሳቸው በቅሌት እና በውርደት ጉድጓድ ውስጥ ወደቁ፡፡ ያንን የማይረባ እርባናየለሽ የቪዲዮ ፊልም ዘገባ ከተመለከትሁ በኋላ የእራሴን የህሊና ፍርድ ሰጥቸ ነበር፡፡ ለአርቲስት ደበበ እሸቱ ከፍተኛ የሆነ አድናቆት እንዳለኝ እና ታላቅ ክብርንም በመስጠት የህሊና ፍርድን የበየንኩት ለዓላማው በጽናት የቆመ መንፈሰ ጠንካራ ስለሆነ ብቻ አልነበረም ሆኖም ግን እውነተኛ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ጀግናም ስለሆነ ጭምር እንጅ፡፡ ደበበ እሸቱ ለሰብአዊ መብት ጥበቃ እራሱን መስዋዕት ያደረገ ኢትዮጵያዊ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡

የወያኔ የወሮበላ ስብስብ የኢትዮጵያ የሙስሊም ማህበረሰብ የሰብአዊ መብት ተሟጋች በሆነው በአቡባከር አህመድ ላይ ተመሳሳይ ድርጊትን ፈጽሟል፡፡

የወያኔ ወሮበላ ስብስብ በአንዳርጋቸው ላይ የተለየ ድርጊት አልፈጸመም፡፡ በተለየ ቀን እና በተለየ የሰብአዊ ፍጡር ሰለባ ላይ የተገበረው ከመሆኑ በስተቀር የወያኔው ስብስብ ያው የተለመደውን ‘የሞኝ ዘፈን ሁል ጊዜ አበባዬ’ የሚለውን ዘፈንበመዝፈን እስክስታውን በማስነካት ላይ ይገኛል፡፡ እስክስታው እስከ መቼ ይዘልቃል የሚለው ወደፊት የሚታይ ይሆናል!

በማይታወቅ ጊዜ፣ ቦታው የት እንደሆነ በማይታወቅ አካባቢ ተቆርጦ እና ተቀጥሎ በተዘጋጀው የወያኔ የቪዲዮ ቀረጻ ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ሰምቶ እና ተመልክቶ የእራሱን የህሊና ፍርድ እንዲሰጥ ሲጋበዝ ለጊዜው የሚደረገውን ጉድ ከመመልከት በስተቀር ምንም ዓይነት ነገር ሳልናገር ዝም ብየ ቆይቻለሁ፡፡ ምንድን ነው የሚያስቡት የነበረው? (ያ የደንቆሮ ጥያቄ ነው፡፡ ምንም አያደርጉ! እንደዚህ ያለ እርባናቢስ የሆነ የቪዲዮ ፊልም ተዘጋጅቶ እንዲለቀቅ ያደረገው ማን ነው? (እንደገና ሌላ የደንቆሮ ጥያቄ፡፡) የወያኔ ወሮበላ ስብስብ በእኛ ብልህነት ላይ ያለው ንቀት እኛ በወያኔ ድንቁርና፣የአዕምሮ ዘገምተኝነትእና ድድብና ላይ ያለን ንቀት ብቻ ይበልጠዋል ። አንድ ሰው በሰጠው ምላሽ ብቻ በመመርኮዝ የህሊና ዳኝነት እንድንሰጥ ይጠይቁናል! እንግዲህ ይህ ምን አይነት የደንቆሮና በድን አስተያየት ነው!

አንዳርጋቸውን በቃሎቻቸው ሳይሆን በሰጧቸው ምላሾች መገምገም፣

የአንዳርጋቸው ጠያቂዎች የጠያቂዎቹን ማንነት፣ የት ቦታ እንደሆነ እና የቪዲዮ ፊልሙ መቸ እንደተቀረጸ፣ እንዲሁም አንዳርጋቸውን ለማዋረድ ከፍተኛ የሆነ የመድረክ ላይ የሸፍጥ ትወና በማካሄድ የተዛባ፣ የተዛነፈ፣ የተንሸዋረረ እና የተፐወዘ ውጤት በህዝቡ ላይ ለመፍጠር በሚል እኩይ ድርጊት አጠቃላይ ሁኔታውን ለመደበቅ ጥረት አድርገዋል፡፡ ሆኖም ግን አንዳርጋቸው ሰጧቸው በተባሉት ምላሾች ላይ ታሪኩን በተለየ መልኩ ሊያሳዩ የሚቸሉ ሌሎች ምላሾች ነበሩ፡፡

የቪዲዮ ቀረጻ ወንጀልን በሚያጠኑ እና በሚከላከሉ ባለሙያዎች ትንትና መሰረት ትንሽ ነገር ማለት ይቻላል፡፡ የአንዳርጋቸውን የሰውነት አጠቃላይ እንቅስቃሴ፣ ውሱን የሆኑ የአካላቸውን ንቅናቄ እና በቪዲዮ የቀረጻ ክፍሎች ሂደት ጊዜ የተደረገውን የሰውነታቸውን አቀማመጥ በአንክሮ በመመልከት ብቻ ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎች እንዳሉ ይገልጻሉ፡፡ ያም ሆነ ይህ በወያኔ የወሮበላ ስብስብ ተቀርጾ በተለቀቀው የቪዲዮ ፊልም ምላሾች ላይ በርካታ የሆኑ እርስ በእርስ የማይገናኙ እና የተጣረዙ ውዥንብሮች በገፍ ታጭቀው ይታያሉ፡፡ የወያኔ የወሮበላ ስብስብ የቪዲዮ ቀረጻ እንደሚያሳያው አንዳርጋቸው ከብዙዎቹ በጥቂቶቹ ጣቶቻቸውን ሲያወናጭፉ ይታያሉ፣ አዲስ የሆነ ያልተለመደ የሰውነት እንቅስቃሴ ያሳያሉ፣ እጆቻቸውን በአየር ላይ ከወዲያ ወዲህ ያወናጭፋሉ፣ እራሳቸውን በተደጋጋሚ ያወዛውዛሉ፡፡ አቶ አንዳርጋቸው በወያኔው የማጎሪያ እስር ቤት ከመግባታቸው በፊት በሚታወቁ አጋጣሚዎች እና በህዝብ ፊት ንግግር ሲያደርጉ የተቀረጸውን አጠቃላይ የሰውነታቸውን እንቅስቃሴ አሁን ከተቀረጸው የሸፍጥ የቪዲዮ የመድረክ ላይ ትወና ቀረጻ ጋር ሲነጻጸር በአጠቃላይ በወያኔ ይዞታ ስር ሆኖ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ሁሉ አዲስ እና ያልተለመደ መሆኑን በግልጽ ያመላክታል፡፡

በወያኔ የቪዲዮ ቀረጻ በርካታ ክፍሎች ላይ የአንዳርጋቸውን የሰውነት አቀማመጥ፣ እንቅስቃሴ እና አጠቃላይ ሁኔታ በምንመረምረርበት እንዲሁም ምላሾቻቸውን በሚሰጡበት ጊዜ የሚታይባቸው የመረበሽ ሁኔታ እርሳቸው በከባድ ውጥረት ውስጥ እና በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ መሆናቸውን በግልጽ ያለመላክታል፡፡ የተወሰኑ “ምላሾች” የተለዩ ከፍተኛ የሆኑ ጭንቀቶችን መዝግበው ይታያሉ፡፡ አጠቃላይ የሰውነታቸው ገጽታ በንቀት የሚመለከቷቸውን ጠያቂዎቻቸውን በማየት እንዲሁም በእርሳቸው ላይ የጥላቻ መንፈስን ከሚያሳዩ ጠያቂዎቻቸው ጋር ዓይን ለዓይን ሲተያያዩ መንፋሳቸው እየተረበሸ አስደናቂ በሆነ መልኩ ገጽታቸው ሲለዋወጥ በግልጽ ይታያል፡፡ አንዳርጋቸው በተቀመጡበት ወንበር ላይ ሆነው በርካታ የሆኑ የተጋነኑ የሰውነት ገጽታዎችን እና የሰውነት እንቅስቃሴ ምልክቶችን አንዴ ኮስተር በማለት ሌላ ጊዜ ደግሞ ፈታ በማለት ያልተለመደ እና ከፍተኛ የሆነ የአካል እና የመንፈስ ምቾት የሌላቸው መሆኑን በግልጽ ያመላክታል፡፡

አንዳርጋቸው ምላሾችን በሚሰጡበት ጊዜ የድምጻቸውን መጨቆን እና በተለመደው ሁኔታ መናገር አለመቻላቸው፣ ምላሾችን ብቻ እንዲናገሩ የተሰጧቸው መሆኑን እንዲሁም ድምጻቸው በጣም የደበዘዘ እና የሰነነ መሆኑን ስናጤን ለሚሰጧቸው ምላሾች እና መግለጫዎች ሁሉ በግዳጅ እንዲመልሱ መደረጋቸውን በግልጽ ያመላክታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የአንዳርጋቸው ምላሾች ድንገተኛ እና ወዲያውኑ ከሚቀርቡት ጥያቄዎች በመነሳት የሚሰጡ አይደሉም፣ ሆኖም ግን ቀደም ሲል የተዘጋጀ እና ይህንን ለማድረግ ሲለማመዱት የቆየ ይመስላል፡፡ የአንዳርጋቸው በቡርጅ አል መለስዜናዊሆቴል የንጉሳዊ ቤተሰብን የመሰለ እንክብካቤ እንደሚደረግላቸው ሆኖ የቀረበው የማይታመን መሆኑ ብቻ አይደለም ሆኖም ግን በማያስፈልግ ሁኔታ እጅግ ተጋንኖ የተዘጋጅ የመድረክ ትወና ነው፡፡

የአንዳርጋቸው የድምጻቸው ቅላጼ ከፍ እና ዝቅ የማለት ሁኔታ እንደዚሁም የተወሰኑ ቃላት እና ሀረጎችን በሚናገሩበት ጊዜ የድምጽ መቀያየር ሁኔታ ለጠያቂዎቻቸው ምላሽ በሚሰጡበት ጊዜ ከሚኖርባቸው ጭንቀት የተነሳ የተፈጠሩ ሊሆኑ እንደሚችሉ ለመገመት ይቻላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሲያሳዩትየነበረው የሰውነት እንቅስቃሴ ከአፋቸው ከሚወጣው ድምጽአንጻር ሲታይ በጣም ወደ ኋላ የተጓተተ የመሆኑ ጉዳይ በድምጻቸው እና በአካላዊእንቅስቃሴ መካከል የመጣጣም ሁኔታአለመታየቱን ያመላክታል፡፡

አጠቃላይ በሆነ መልኩ ስናየው አንዳርጋቸው ከሚሰጧቸው እንደ ደኃ ከረጢት ከተጣጣፉት የቪዲዮ ቀረጻ ምላሾች አንጻር በመነሳት ስናየው በጣም ውጥረት የበዛበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው ተገደው የሰጡት መሆናቸውን በግልጽ ያመለክታል፡፡ ውስን ለሆኑ ምላሾች አንዳርጋቸው የሚሰጧቸው ምላሾች ጭንቀት፣ ያለመረጋጋት፣ ተጠራጣሪነት፣ ፍርሀት፣ ንዴት እና እንዲሁም የመሰላቸት ሁኔታ ይታያል፡፡

አንዳርጋቸው በእርግጥ ለወያኔ ቪዲዮ በትክክል ምላሾችን በመስጠት ሀሳባቸውን ለመግለጽ ወይም ደግሞ ለመድረክ ትወና ፍጆታ ሲባል ብቻ ምላሽ ሊሰጡ ይችላሉን? አንዳርጋቸው እንዲናገሯቸው ከቀረቡላቸው ምላሾች ውጭ እራሳቸው የሚያምኑበትን መልስ ሊሰጡ ይችላሉን? ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚሰጡትን መልሶች አውቃለሁ፣ ሆኖም ግን አንባቢዎቼ ሁሉ የእራሳቸውን የህሊና ፍርድ እንዲሰጡ እጠይቃለሁ፡፡

የወያኔ ወሮበላ ስብስብ ለሚቀጥለው ጥያቄ አልባ የቪዲዮ ምላሽ ዝግጅቱ የሚከተሉትን በጣም ቀላላ የሆኑ የቪዲዮ ምስልምርመራ ዘዴዎችን በመጠቀምለህዝብ “የህሊና ፍርድ” ያቀርባል የሚል ተስፋ አለኝ፡፡

አንዳርጋቸው ማራኪዎቻቸውን እንዲወዱ የተገደዱ የስቃይ ሰለባ ናቸውን?

የቪዲዮ ምስል ምርመራ ትንታኔ ባለሙያዎች እንደሚሉት አንዳርጋቸው ‘ማራኪን በመገደድ መውደድ’ (አስቶክሆልም ስንድሮም) እየተባለ ለሚጠራው የምርኮ ሰለባ የሆነው ወይም ደግሞ ምርኮኛው ማራኪውን እንዲወድ የሚዳረግበት የስነልቦና ክስተት ሰለባ ውስጥ ወድቀው ሊሆን ይችላል፡፡ የዚህ ዓይነት ክስተት ሰለባ የሆኑ ሰዎች ብዙውን ጊዜ የሌሎችን ስሜቶች እና ፍላጎቶች በማወቅ እና በአሳሪው/ዋ ላይ ፍቅርን በማሳየት አሳሪውን/ዋን ከመጥፎ ነገር ለመከላከል በማሰብ የተወሰኑ አዎንታዊ የሆኑ እና ሞቅ ያሉ ስሜቶችን ግልጽ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ ሰለባዎቹ አንደ ደግ እና ጨዋ ሰው ሆኖ ምንም ዓይነት የሰብአዊ መብት ረገጣ ያልተፈጸመበት ለምመሰል ከሰውነት እንቅስቃሴዎቹ ጋር እኩል ትርጉም የሚሰጥ መስሎ ሊቀርብ ይችላል፡፡ በቪዲዮው የቀረበው የአንዳርጋቸው የመጨረሻው ምላሽ ተገዶ ማራኪን በመወደድ ደረጃ የስነልቦና ክስተት ውስጥ መግባታቸውን የሚያመላክት ሊሆን እንደሚችል ጠንከር ያለ ጥርጣሬን ይሰጣል፡፡

የህዝብ መገናኛ የመድረክ ተውኔቱ ይቀጥል…

የወያኔ ወንድሞች የባለ ሶስት ቀለበት መድረክ ላይ ተውኔት ይቀጥል፡፡ ቀለበት አንድን በእስክንድር ነጋ፣ በርዕዮት ዓለሙ እና በውብሸት ታዬ፣ ቀለበት ሁለትን ደግሞ በአንዷለም አራጌ እንዲሁም ደግሞ ቀለበት ሶስትን በበቀለ ገርባ እና በአቡባከር አህመድ ላይ ይተወኑበት፡፡

በአንዳርጋቸው ጽጌ ላይ በቀረበው አስከፊ እና ፍትሀዊነት የጎደለው የእስር ቤት አያያዝ እና የቪዲዮ ቀረጻ የመድረክ ላይ ተውኔት ያለኝን የህሊና ፍርድ ሰጥቻለሁ፡፡ ሁሉም አንባቢዎቼ ይህንኑ ተመሳሳይ ድርጊት እንዲፈጽሙ በአክብሮት እጠይቃላሁ፡፡ ፍርድ ከመስጠት በፊት እንዲህ የሚለውን አንድ ጥያቄ አንባቢዎቼ እንዲመልሱልኝ እጠይቃለሁ፡ በአንዳርጋቸው የተሰቃዩ ቃላት ወይስ ደግሞ በአንዳርጋቸው የተሰቃዩ የሰውነት እንቅስቃሴዎች ላይ ነው እምነት የሚኖራችሁ?-

በቪዲዮ ቀረጻ ምስል ትንተና ለዲጂታል የብዙ መገናኛ መሳሪያ ቴክኖሎጂ የስራ መስክ ድጋፍ ለሚያደርጉ የስራ ባልደረቦች ምስጋና ይሁን!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ጥር 5 ቀን 2007 ዓ.ም

ከሆቴሉ ጀርባ…በወላፈኑ ውስጥ የሚታየው –ፍጹምዘአብ አስገዶም ማን ይሆን?

$
0
0

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርስ የነበረው ጣይቱ ሆቴል በእሳት ወደመ:: ከዚሁ ጋር ተያይዞ ታዲያ “አቃጠሉት” እና “አቃጠሉበት” የሚሉት ድምጾች በርክተዋል:: “አቃጠሉበት” የሚለውን የጨዋታ ክር መምዘዝ ከጀመርን; የቤቱ ባለቤት ፍጹምዘአብ ጋር ያደርሰናል:: ፍጹምዘአብ የትግራይ ተወላጅ ነው:: ግን ደግሞ የትግራይ ተወላጅ ስለሆነ ከስልጣን ዙፋን ላይ አልተቀመጠም:: ይልቁንም በዘመነ ኢህአዴግ ከ6 አመታት በላይ የወያኔን እስር ቤትን ቀምሶ የወጣ ሰው ነው::
አሁን በተቃጠለው የጣይቱ ሆቴል ምክንያት ስለቃጠሎውም ሆነ ስለእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ብዙ እየተባለ ነው:: ከዚህም በላይ ብዙ ሊባል ይችላል:: ምንም ተወራ ምን – ቢያንስ መሰረቱን እውነት ያደረገ ወሬ ይመረጣል:: ፍጹምዘአብ የትግራይ ተወላጅ ሆኖ የህወሃት ደጋፊም ተቃዋሚም ስላልሆነ እንደማንፈርድበት ሁሉ – የነጻ ፕሬስ ተጋድሎውን ብዙ በመታሰር እና ባለመታሰሩ ኢትዮጵያዊነቱን ልንለካው አንችልም:: እንደ’ውነቱ ከሆነ; ዘ ሞኒተር ጋዜጣን በሳምንት ሶስቴ ከመታተም አልፎ በየቀኑ የሚታተም የመጀመሪያ እንግሊዘኛ ጋዜጣ እንዲሆን አድርጓል:: ጋዜጣው ከዘመኑ ጋር እንዲሄድ ብቻ ሳይሆን የራሱ ማተሚያ ቤት እንዲኖረው ማድረጉ በራሱ፤ መጋነን ባይገባውም በነጻው ፕሬስ ታሪክ ውስጥ ስፍራ ሊሰጠው ይገባል::

bee392ccb91b968f78a29a035271c5d5_L

(ዳዊት ከበደ ወየሳ)

ፍጹምዘአብን የምናውቀው ከመጀመሪያዎቹ የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጦች አንዱ የሆነውን “ዘ ሞኒተር” ጋዜጣ አሳታሚ ሆኖ ሲሰራ ነው:: እኛ የነጻው ፕሬስን የነጻነት ብዕር ይዘን ባማርኛ ስንውተረተር – ፍጹምዘአብ በእንግሊዘኛ የሚታተም ዘሞኒተር ጋዜጣን ተረጋግቶ ያሳትም ነበር:: የነበረውን መንግስት የሚቃወም ወይም ያለፈውን የደርግ ስርአት የሚያወግዝ ጽሁፍ እምብዛም በጋዜጣው ላይ አይነበብም:: ሁሉንም ነገር በጥንቃቄ ለመያዝ ይሞክራል:: ከዚህም ከዚያም ጋር እየሄደ አይላተምም:: እኛ ኢህአዴግ ያጠመደውን የፕሬስ ነጻነት አልፈን፤ ፈንጂ ወረዳውን እየረገጥን ስንረጋገጥ – ፍጹምዘአብ ግን በጩኸት እና በትርምሱ መሃል በጥንቃቄ መራመድን ያዘወትር ነበር:: እንደዛም ሆኖ ግን ከህወሃት ሰዎች የጥላቻ አይን ሊወጣ አልቻለም::

የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች ከየቢሯቸው እየተለቀሙ ከታሰሩባቸው ጊዜያት መሃል፤ የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ እና አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተነሳው አመጽ ጉዳይ ይጠቀሳሉ:: (እ.ኢ.አ. 1984 እና 1985)

በዩኒቨርስቲው ዘገባ ጉዳይ እኔም ተከስሼ ጉዳያችን ከነሙሉጌታ ሉሌ እና ከነመጽሃፈ ሲራክ መዝገብ ጋር በጠቅላይ ፍርድ ቤት ችሎት ይታይ ነበር:: ይሄ የአንድ ሰሞን ወሬ እንዳለፈ ደግሞ ሌላ ዙር ወሬ መጣ – በዙምባብዌ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ላይ የተደረገው የመግደል ሙከራ የፕሬሱን ገጾች አጣበበ::

በዚህ አዲስ የወሬ ዙር የነፍጹምዘአብ ዘ ሞኒተር ጋዜጣ የፕሬሱን የፈንጂ ወረዳ ረገጠ:: እናም ለሁሉም ጋዜጠኛ የተዘጋጀውን እስር ቤት አብሮን ለመጋራት በቃ – 1988::

ይህ እስር በጥንቃቄ መራመድ ለሚያዘወትረው ፍጹምዘአብ አስገዶም የማንቂያ ደወል ነበር:: እዚህ ላይ ዝርዝሩ ጥቅም የለውም እንጂ አስቀድማ የታሰረችው የጋዜጣው አዘጋጅ ሉሊት ነበረች:: እሷ ወሬውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኢቲቪ እና ሬድዮ ጭምር መዘገቡን ለመርማሪው ታስረዳለች::

መርማሪው መልሶ ይጠይቃታል “እኮ አንቺ ዜናውን ከየት አገኘሽው?”
“ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ካገኘበት ነዋ”
“ማነው ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት?”

ሉሊት ማስረዳቷን ቀጠለች፤ “የመንግስት ዜና አገልግሎት ነው:: እነሱ ዜናውን ከፓን አፍሪካ ኒውስ እና አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ነው ያገኙት:: እኛም እንደነሱ ወርሃዊ ክፍያችንን ስለምንፈጽም የፓናፍሪካ እና የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዜናዎች ይደርሱናል” …ሉሊት እና መርማሪው ሊግባቡ አልቻሉም:: እንዲያውም መርማሪው ከአቅሙ በላይ ስለሆነበት ጉዳዩን ለበላይ ሃላፊዎቹ አስተላለፈ:: የበላይ ሃላፊዎች ደግሞ የጋዜጣው አሳታሚ ፍጹምዘአብ ተጨምሮ እንዲታሰር አደረጉ – ያን ግዜ እሱ እና እኛ በእስር ቤት እኩል ሆንነ :)

ያኔ የፍጹምዘአብ እድሜ ገና በሰላሳዎቹ መጀመሪያ ላይ ስለነበር እድሜያችን ሃያ + ለነበርነው እንደታላቅ የሚታይ ነው:: ለነገሩ በሁኔታው የራዕይ ገንቦ ተሸክሞ የሚሄድ ይመስላል። በዚያን ኢንተርኔት እና ማህበራዊ ድረ ገጾች በኢትዮጵያ ቀርቶ በአፍሪቃ ባልተስፋፋበት ዘመን እሱ ከዘመኑ ጋር ለመራመድ ዳዴ ማለቱን ጨርሷል:: እኛ በሳምንት አንድ ጊዜ የምናሳትማት ጋዜጣ በአፈና ጫና ስር ሆና ስትንፈራፈር – እሱ ወደፊት በኢትዮጵያ የህትመት ብቻ ሳይሆን፤ የግል ኤሌክትሮኒክስ መገናኛዎች መስፋፋት እንዳለባቸው ጥልቅ ትንታኔ ይሰጥ ነበር:: ሆኖም ያቺ አጭር የእስር ዘመን ፍጹምዘአብ አይኑን ገልጦ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የህወሃት አምባገነን ስርአት እንዲመለክት የረዳው ይመስላል::

ታሪኩን ለማሳጠር ያህል ሉሊትም ሆነች ፍጹምዘአብ በኋላ ላይ በአስር ሺህ ብር ዋስ ሲወጡ ጋዜጣቸው ለአንድ ወር ያህል ከህትመት ታግዶ ነበር:: በቀጣይ ግዜያቶች… ዘ ሞኒተር ጋዜጣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳዮችን እንደጾመ ቀጠለ:: ሆኖም በሚገርም ሁኔታ የነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች ሲታሰሩ ጉዳያቸው በውጭ ቋንቋ ተመንዝሮ የሚጻፍበት ብቸኛው እንግሊዘኛ ጋዜጣ ዘ ሞኒተር እንደነበር በፕሬስ ጉዳይ ታስረን የወጣን ሰዎች ሁሌም የምናስታውሰው ነው:: በኋላ ላይ እንደሰማሁት… ሌሎች ጋዜጠኞች ዲ አፍሪክ ጋር በነበረው አርቲክራፍት በተባለ ማተሚያ ቤቱ ያውቁታል – ያመሰግኑታል::

ጋዜጣም ሆነ መጽሄት ለማሳተም ወደዚህ ማተሚያ ቤት የሄድንበት አጋጣሚ የለም:: ሆኖም የኋላ ኋላ የመንግስት ማተሚያ ቤቶች ሲያስቸግሩ የነጻው ፕሬስ ልጆች ወደዚህ ማተሚያ ቤት ሄደው ያሳትሙ እንደነበር – በቅርቡ ከወጡት ጋዜጠኞች መካከል ሰርካለም ፋሲል አስታውሳኛለች::

ፍጹምዘአብ አስገዶም ብዙ የማያወራ ብቻ ሳይሆን በአደባባይ ልታይ ልታይ ማለትን የሚያዘወትር አይደለም:: ውስጡ ሁልጊዜም በዝምታ የተወጠረ እና መቼ እንደሚፈነዳ በማይታወቅ እሳተ ጎመራ የታመቀ ነው:: በዚህ የሰከነ ስሜት ውስጥ ያለ ሰው በፖለቲካ ምህዋር ዙሪያ ሊሽከረከር ቀርቶ – በዚያ ዙሪያ የሚሽከረከሩትንም በሩቁ ከማየት ውጪ እምብዛም ተሳትፎ አያደርግም:: ነገር ግን ምንም ቢጠነቀቅ የፖለቲካው በትር አናቱን ሳይመታው አያልፍም። ምንም ስሙን እና ማንነቱን ቢደብቅ – ማን እንደለኮሰው በማይታወቅ የእሳት ወላፈን መሃል በጭላንጭልም ቢሆን እናየዋለን – ፍጹምዘአብ አስገዶምን::

እንግዲህ ነገሮች በዚህ አይነት አለፉና መታሰር አይቀርም – በ5ኛ አመቱ እንደገና የሚታሰርበት ጊዜ መጣ። በነስዬ አብርሃ ላይ ጥርስ የነከሰው ህወሃት – የነሱ ተባባሪ ያላቸውን ሰዎች በሙስና ሰበብ ማሰር ጀመረ። የሙስናው ምንጭ የተባለው ደግሞ የአቶ ስዬ አብርሃ ታናሽ ወንድም “አሰፋ አብርሃ” መሆኑ ነገሩን ከፍ አደርገው። እኛ በጋዜጣችን ላይ የአቶ አሰፋ አብርሃን የሙስና ጉዳይ ስናነሳ፤ “የክቡር አቶ አሰፋ አብርሃን ስም በማጥፋት…” ተብሎ፤ አንቀጽ ተጠቅሶ፤ እውነት መናገር ወንጀል ሆኖ፤ መንግስት በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ችሎት ከሰሰን። በሚገርም ሁኔታ ግን… የኛ ፋይል ሳይዘጋ አቶ አሰፋ አብርሃን መንግስት ራሱ ከሰሳቸው። ይህን እንደምሳሌ ማንሳት ያስፈለገው – ሰው የኢህአዴግ መንግስት ደጋፊ እስከሆነ ድረስ በሙስና ጭቃ ውስጥ ተዘፍቆ መኖር ይችላል። ከመንግስት ጋር የሚያጣላውን ነገር ከሰራ ግን፤ ስሙ በጥቁር መዝገብ ላይ ሰፍሮ ወደ እስር ቤት ይወረወራል።

ፍጹምዘአብ አስገዶም በፕሬሱ ውስጥ ያደረገው አስተዋጽኦ እንዳለ ሆኖ የትዳር እና የንግድ ህይወቱን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ከነአሰፋ አብርሃ ጋር አቆራኝቶታል። በአንድ በኩል የፍጹምዘአብ ባለቤት የአሰፋ አብርሃ ታናሽ እህት ናት። በሌላ በኩል ደግሞ ጨረታ እያሸነፈ ያገኛቸው የንግድ ቦታዎች በአሰፋ አብርሃ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የተሸጡ የቀድሞ መንግስት ንብረቶች ናቸው። እነዚህም የጉለሌ ሳሙና ፋብሪካ፣ የሃረር ማተሚያ ቤት እና የጣይቱ ሆቴል ናቸው። ከሁሉም ግን የጣይቱ ሆቴል ጉዳይ ጎልቶ በነጻው ፕሬስ ላይ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ሰንብቶ እንደነበር ብዙዎች እናስታውሳለን።

ፍጹምዘአብ አስገዶም ጣይቱ ሆቴልን የገዛው በ425 ሺህ ብር ሲሆን፤ በወቅቱ ብቸኛው ተጫራች ሆኖ ነበር ጨረታውን ያሸነፈው። የተገዛበት ዋጋ ዛሬም ድረስ እንደአስደናቂ ታሪክ መወራቱ ቀጥሏል። ምክንያቱም እንኳንስ ጣይቱ ሆቴል ከነግቢው ቀርቶ፤ በሆቴሉ የላይኛው ክፍል ውስጥ ያለው በ19ኛው ክፍለዘመን ዝነኛ የነበረው የ1889 ስቴንዌይ ፒያኖ ግማሽ ሚሊዮን ብር ያወጣልና። ይህም ሆቴሉ ከተገዛበት ዋጋ ጭምር ያነሰ ነው። እናም ይህ ለማመን የሚያስቸግር ዋጋ – ለፍጹምዘአብ እንደሎተሪ ማሸነፍ የሚቆጠር ነበር። በወቅቱ ነጻው ፕሬስ ውስጥ ያለነውም ሆንን ባህል ሚንስቴር ውስጥ ያሉ አንዳንድ ሰዎች፤ “ጣይቱ ሆቴል በቅርስነት መጠበቅ ያለበት እንጂ፤ ሊሸጥ የሚገባው ንብረት አይደለም።” ብለው እና ብለን ድምጻችንን አሰማን። ሆኖም የሚሰማን ጠፍቶ ጣይቱ ሆቴል ተሸጦ እ.ኢ.አ. ሰኔ 21 1991 ዓ.ም. ርክክቡ ተፈጸመ – የኛም ጩኸት የአንድ ሰሞን ጫጫታ ሆነና ሁሉም ነገር ከግዜው ጋር ተረሳ።

ይሄ ጩኸት ሌላ ትርጉም እስካልተሰጠው ድረስ የቅናት እና የምቀኝነት አልነበረም። ሰሚ ጠፋ እንጂ… ጩኸታችን የኢትዮጵያን ቅርስ ከመጠበቅ አንጻር የሚታይ ነው። ጣይቱ ሆቴል ጥንታዊነቱን ጠብቆ በቅርስነት መጠበቅ ሲገባው እንደሸቀጥ መሸጥ አይገባውም ነበር – የኛ ክርክር። እርግጥ ነው – ጉለሌ ሳሙና ፋብሪካን ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ ጨረታ አሸንፎ፤ ከአንድ አመት በፊት ለገዛው ፍጹምዘአብ የጣይቱ ሆቴል ዋጋ አነስተኛ መሆኑ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም። ሌላው ቀርቶ አሁን ጣይቱ ሆቴል ሲቃጠል የጃዝ-አምባ የሳውንድ ሲስተም እና የሙዚቃ መሳሪያ አብሮ ወድሟል። ስራ አስኪያጁ ኤርሚያስ ፋንቱ እንዳለው ከሆነ፤ “በትንሹ የ4 ሚሊዮን መሳሪያ በቃጠሎው ጠፍቶብናል” ብሏል። ጣይቱ ሆቴል የተገዛበትና የጠፋውን ንብረት ስናነጻጽረው… “የስሙኒ ዶሮ የአንድ ብር ገመድ ይዛ ጠፋች” የሚባለውን ተረት ያስታውሰን ጀምሯል።
ነገርን ነገር እየመዘዘ ወደ ታሪኩ ማጠቃለያ ልንቃረብ ሆነ። ወደኋላ እንመልሳችሁ እና አንዳንድ ነጥቦችን እናንሳ። በዛው ከላይ የጀመርነውን ጨዋታ መስመር እናስይዘው።
…ከዛ በኋላ… ስዬ አብርሃ ከነመለስ ዜናዊ ጋር ስለተጣላ በሙስና ሰበብ ታሰረ። ታናሽ ወንድሙ አሰፋ አብርሃ – በጠቅላይ ሚንስትርነት ማዕረግ – የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ሃላፊ እና የንግድ ባንክ ቦርድ ሰብሳቢ ሆኖ ሲሰራ፤ የፈጸመው ሙስና አለ ተብሎ እሱም ታሰረ። ፍጹምዘአብም “ከአሰፋ አብርሃ ጋር ያለውን ግንኙነት በመጠቀም ጉለሌ ሳሙናን፣ ሃረር ማተሚያ ቤት እና ጣይቱ ሆቴልን ገዝቷቸዋል” የሚል ክስ ተመሰረተበት።

እርግጥ ነው። ፍጹምዘአብ ከመታሰሩ በፊት… ጣይቱ ሆቴልን እያደሰው ነበር። ከታች ለደንበኞች አገልግሎት ይሰጥ የነበረው ቦታ እንዳለ ነው። ከሱ በላይ የነበረው ፎቅ ደግሞ የቀድሞ ሰራተኞች ያድሩበት የነበረ ስፍራ ነው። በኋላ ላይ… እድሳት አድርጎ፤ የፎቁን ቦታ ለእስዕል ጋለሪ እንደሚጠቀምበት ስንሰማ “ይሁን” አልነ። ፍጹምዘአብም ቢሆን ቢሮውን እዚሁ ጣይቱ ሆቴል አድርጎ፤ በየእለቱ የሚወጣውን የዴይሊ ሞኒተርን ጉዳይ የሚከታተለው ከዚሁ ከጣይቱ ሆቴል ሆነ። ሆኖም ሆቴሉንም በገዛው በ2ኛው፤ ጋዜጣውም በተመሰረተ በ10ኛ አመት ታሰረ።

በሚገርም ሁኔታ… ፍጹምዘአብ የታሰረው ከአሰፋ አብርሃ ጋር በነበረው ግንኙነት የሙስና ክስ ተመስርቶበት ቢሆንም፤ ሰዎቹ ግን አጋጣሚውን በመጠቀም The Daily Monitor ጋዜጣን ዘጉ። በኋላ ላይ ፍጹምዘአብ “የጋዜጣው መዘጋት ከተከሰስኩበት ጉዳይ ጋር ግንኙነት ስለሌው፤ ጋዜጣው ስራውን እንዲቀጥል፡” ብሎ ለፍርድ ቤቱ ስሞታ ቢያቀርብም የሚሰማው አጥቶ ጋዜጣው እና የጋዜጣው ቢሮ ተዘግተው ቀሩ።

በኋላ ላይ ፍጹምዘአብ ለአምስት አመታት እድሜውን በእስር ቤት አሳለፈ። መጨዋወታችን ካልቀረ “የባከነው ግዜ” ብለን አጭር ርዕስ እንስጠውና… ከእስር የተፈታበትን አጋጣሚ እናውጋ። ዋናው አጨቃጫቂ ጉዳይ የሆነው የጉለሌ ሳሙና ፋብሪካ ጉዳይ ነበር። በእርግጥ ሃረር ማተሚያ ቤት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ንብረት ሆኖ ሳለ፤ በደርግ ዘመን ተወርሶ የመንግስት ንብረት ሆነ። በኋላ ላይ… በኢህአዴግ ዘመን ቤተ ክርስቲያኗ ማተሚያ ቤቱ እንዲመለስላት አመልክታ ሳለ፤ ሃረር ማተሚያ ቤት ለጨረታ ቀርቦ… ፍጹምዘአብ የወሰደው።

አወዛጋቢው የጨረታ ድራማ የተፈጸመው ግን በጉለሌ ሳሙና ፋብሪካ ላይ ነው። ዱጉማ ሁንዴ እና ጌቱ ገለቱ የተባሉ ትላልቅ ባለሃብቶች ፋብሪካውን ሙሉ ለሙሉ ለመግዛት 21 + ሚሊዮን ብር ይጫረቱና እ.ኢ.አ በ1989 ጨረታውን ያሸንፋሉ። ማሸነፋቸውም ይነገራቸዋል።

ሆኖም ዱጉማ ሁንዴ እና ጌቱ ገለቱ የአሸናፊነት ጽዋቸውን አንስተው ደስታቸውን ከማጣጣማቸው በፊት ደስ የማይል ወሬ ይሰማሉ። ቦርዱ ውሳኔውን ቀይሮ ‘22 ሚሊዮን ብር እና ፋብሪካውን በከፊል ባለቤት ለመሆን የተጫረተው ፍጹምዘአብ የሳሙና ፋብሪካውን እንደሚወስድ ሰምተው አዘኑ። (ከከፊል ባለቤትነት ወደ ሙሉ ይዞታንነትም ተቀየረ) ሆኖም እነዱጉማ ሁንዴ ሌላ በሚሊዮን እና በቢሊዮን የሚቆጠር ቢዝነስ ውስጥ ስለነበሩ፤ “ፋብሪካው ለፍጹምዘአብ አስገዶም ለምን ተሰጠ?” የሚል የመጨቃጨቂያ ርዕስ ከፍተው ለመካሰስ ግዜ አልነበራቸውም። በአጭሩ ጥር 5ቀን፣ 1989 ፋብሪካው ለፍጹምዘአብ ተሸጠ። አራት አመታትም ተቆጠሩ። ከዚያም በህወሃት ውስጥ የርስ በርስ ጦርነት ሲከፈት የተጠመዱት ፈንጂዎች… ከዚህም ከዚያም ይፈነዳዱ ጀመር። በዚህ አጋጣሚ የአገራችንን የፍትህ ጉድለት ያሳያልና የሳሙና ፋብሪካውን ጉዳይ ብቻ እዚህ ላይ ጠቅሰን፤ ስለጣይቱ ሆቴል ትንሽ አውግተን ማሳረጊያ እናደርጋለን።

ላለፉት አራት አመታት ምንም ኮሽ ሳይል… ሳሙናው እየተመረተ ህዝቡ በጉለሌ ሳሙና ልብሱን ማጠቡን ቀጥሏል። ዘ ሞኒተር ጋዜጣም አዲስ በተገዛው ማተሚያ ቤት በየቀኑ እየታተመች ስሟን ቀይራ The Daily Monitor ተብላለች። አዲሱ እስር ሲመጣ ሳሙናው እየተመረተ ልብሳችንን እንጠብ እንጂ፤ ውስጣችንን የሚያጥበው የእንግሊዘኛ ፕሬስ ውጤት ግን እንደተዘጋ ቀረ።

ከርዕሳችን ላለመውጣት ያህል ወደ ሳሙና ፋብሪካው እንመለስ። እናም ጉለሌ ሳሙና በስራ ላይ ሳእ፤ በአራተኛ አመቱ አቃቤ ህጉ “ግዢው ህገ-ወጥ ነው” በማለት ክስ መሰረተ። የከሳሹ አቃቤ ህግ ጭብጥ የነበረው፤ “ፍጹምዘአብ ሳሙና ፋብሪካውን በ22 ሚሊዮን ብር ሲገዛው፤ በህጉ መሰረት 40 ፐርሰንት ለባንኩ ተቀማጭ ማድረግ ነበረበት። እሱ ግን ዜሮ ተቀማጭ በማድረግ ሳሙና ፋብሪካውን ወሰደ።” የሚል ሲሆን፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ ከአሜሪካ አገር ኒው ዮርክ ከተማ መጥቶ የመንግስት ፋይናንስ አማካሪ ሆኖ ከቆየ በኋላ የብሄራዊ ባንክ ስራ አስኪያጅ የነበረው አላዛር ደሴ ጭምር እስር ቤት ገባ። ለነገሩ አላዛር ደሴ በዚህ ምክንያት ይታሰር እንጂ፤ የእስሩ ዋና ምክንያት ወዲህ ነው።

ከአምስት አመታት በኋላ…

አቃቤ ህጉ በፍጹምዘአብ ላይ ምስክር አቀረበ። አንደኛው እና ዋነኛው ምስክር የባንኩ ኦዲተር ነበር። እናም ፍጹምዘአብ ማስቀመጥ ሲገባው ስላላስቀመጠው 40 ፐርሰንት ተቀማጭ ጉዳይ ተጠየቀ። ኦዲተሩ ግራ በመጋባት፤ “አረ አስቀምጧል።” አለ።
“አርባ ፐርሰንቱን ለባንክ ከፍሏል?” ዳኛው በመገረም ጠየቁ።
“አዎ ተከፍሏል። ይኸው መረጃው!” ፍጹምዘአብን የሚረዱ፤ 8.9 ሚሊዮን ብር የከፈለበት መረጃ ቀረበ።
አቃቤ ህጉ ገና ከመጀመሪያው መከራከሪያ ያደረገው “አርባ ፐርሰንት አልከፈለም” የሚለው ጉዳይ እዚህ ላይ አበቃ። መንግስትን በመወከል የሚከራከሩት አቃብያነ ህጎች ‘ኩም’ አሉ – አፈሩ። ፍርድ ቤቱም በፍጹምዘአብ ጉዳይ የዚያኑ ቀን ውሳኔ ሰጠ። “ፍጹምዘአብ ከዛሬ ጀምሮ በዚህ ጉዳይ ነጻ ነው” ሲል አሰናበተው። ይህ የሆነው በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጥር 11 ቀን፣ 1998 (የዛሬ ዘጠኝ አመት ነው)

ፍጹምዘአብ ሲታሰር እንጂ ሲፈታ አገር ውስጥ ስላልነበርኩ ዝርዝር ታሪኩን እንዘለዋለን። በዚያው ዝላይ ወደድሮ ታሪክ እንሸጋገራለን።

የጣይቱ ሆቴል ነገር ሲነሳ ትንሽ ወደ ኋላ ተመልሰን በዘመኑ ዘመነኛ ስለነበረው ሆቴል ማሰባችን አይቀርም። ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ አገር ሰዎች የሚያርፉበት ሆቴል አለመኖሩ፤ ሌላው ቀርቶ ከፍለው እንኳን የሚበሉበት ምግብ ቤት አለመኖሩ ያሳሰባቸው አጼ ምኒልክ ናቸው – ሆቴሉ እንዲሰራ ያደረጉት። ሆኖም ከቤት ውጪ – ሊያውም ገንዘብ ከፍሎ መብላት ስላልተለመደ ወደ ጣይቱ ሆቴል መሄድ አይዘወተርም ነበር። በኋላ ግን እንዲህ ሆነ።

አንድ እሁድ ቀን ከቤተ ክርስቲያን መልስ አራዳ ጊዮርጊስ ከሚገኘው (አሁን የአጼው ሃውልት ካለበት ስፍራ) ዋርካው ስር ችሎት ቆይተው ሲጨርሱ፤ እዚያ የነበሩትን ባላባት እና መኳንንት፤ “በሉ ከጣይቱ ሆቴል ሄደን ምሳችንን እንብላ” አሏቸው።
መኳንንቱ በፈረስ እና በበቅሎ ተከታትለው አዲስ ከተሰራው ጣይቱ ሆቴል አመሩ።

ምግብ ከመብላታቸው በፊት፤ አጼ ምኒልክ አሉ፤ “በውጭ አገር እንዲህ ያሉ ሆቴሎች ይሰሩና ሰዎች ይመገባሉ” አሏቸው። አሉና እየተበላ እና እየተጠጣ ጨዋታው ደራ።

በመጨረሻ… ከተመገቡ በኋላ የበሉት እና የጠጡት ተሰልቶ ሂሳብ ቀረበላቸው። መኳንቱ ባልጠበቁት ነገር ተገርመው ሊቆጡ የቃጣቸውም ነበሩ። ምኒልክ ግን አሉ፤ “አያቹህ… በውጭ አገር ሰው ሆቴል ከተመገበ በኋላ ሂሳብ ይከፍላል” አሉና ገንዘብ አወጡ።

ነገሩ የምር እንደሆነ ያወቁት መኳንንት፤ “የለም። መክፈል ካለብንም እኛ እንከፍላለን እንጂ፤ እርስዎ አይከፍሉም።” አሏቸው። ሂሳቡን መክፈል የሚፈልጉት ሰዎች ብዛት ሲጠየቅ ይሄም ያም እየተነሳ፤ “ዘራፍ ደሞ ለ’ቴጌ” እያለ ለመክፈል ይጋበዝ ጀመር። አጼ ምኒልክም ለመክፈል የሚጋበዙትን መኳንንት ካዩ በኋላ፤ “እንግዲህ በውጭ አገር…” ብለው ጀመሩ፤ ሁሉም ዝም ብሎ ይሰማ ጀመር።

“እንግዲህ በውጭ አገር እንዲህ በልተው፤ አንድ ሰው ሂሳብ ከከፈለ፤ ሌላው ደግሞ በተራው በሚቀጥለው ሳምንት ይከፍላል” አሏቸው። ከዚያን በኋላ በየሳምንቱ እንደ እቁብ ጣይቱ ሆቴል እየተገኙ ምሳ መገባበዝ ተለመደ። ፈረንጆችም ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የሚያርፉበት እና የሚመገቡበት የመጀመሪያው ዘመናዊ ሆቴል ሆነ።

አጋጣሚውን በመጠቀም ስለ ጣይቱ ሆቴል ይቺን እንመርቅ። በሁለተኛው የኢትዮጵያ ጣልያን ጦርነት ወቅት – በጄነራል ፔትሮ ባዲዮ (በኋላ ላይ ማርሻል ሆኗል) የሚመራው ጦር ወደ አዲስ አበባ ሲገሰግስ፤ የጣይቱ ሆቴል የላይኛው ክፍል የጥቁር አንበሳ ጦር መገናኛ ሬድዮ ተሰድሮበት የሚስጥር እና ግልጽ ግንኙነት ይደረግበት ነበር። ጃንሆይ ሚያዝያ 25 ቀን፣ 1928 የአዲስ አበባ ከተማን ለቀው ሲወጡ፤ ከተማውን ራስ አበበ አረጋይ በከንቲባነት ይቆጣጠሩት በነበረበትም ወቅት ጣይቱ ሆቴል ጊዜያዊ መገናኛቸው ነበር። ጃንሆይ አዲስ አበባን ለቀው እንደወጡ አመጽ ተቀሰቀሰ፤ ዘረፋም በረከተ። የክብር ዘበኞችም በንዴት ተነሳስተው አዲስ አበባ የሚገኙ አውሮፓውያንን ማሳደድ ጀመሩ። በዚህም ግዜ ጭምር… የብዙዎቹ መሸሻ ጣይቱ ሆቴል ነበር።

ጄነራል ፔድሮ ባዲዮ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ፤ ከሰራዊቱ ጋር አብረው የመጡት የጣልያን ጋዜጠኞች እንዲያርፉ የተደረገው ጣይቱ ሆቴል ስለነበር፤ በተለይ አንደኛ ፎቅ ላይ የነበረው፤ ድሮ ሰራተኞች የሚተኙበት አሁን ጃዝ አምባ የተሰኘው ላውንጅ የሚገኝበት ቦታ… ጣልያኖቹ ጋዜጠኞች ለጋዜጣ ህትመት የሚሆኑ ፎቶ የሚያነሱበትና የሚያትሙበት ስፍራ ነበር። እንዲህ እንዲህ እያልን የጣይቱ ሆቴል ጥንታዊ ታሪኮችን መምዘዝ ከጀመርን ቦታ እና ግዜ አይበቃንም።

ሰዎች በጣይቱ ሆቴል የየራራሳቸው ትዝታ ይኖራቸዋል። ለምሳሌ እኔ ጣይቱ ሆቴልን ሳስብ፤ ቶሎ ወደ ህሊናዬ የሚመጣው የሙያ ወንድሜ እስክንድር ነጋ ነው። መጀመሪያ Habesha የተባለ እንግሊዛኛ ጋዜጣውን፤ ከዚያም ምኒልክ ጋዜጣን ማሳተም ከመጀመሩ በፊት ጣይቱ ሆቴል እየተገናኘን ሰፊ ውይይት እናደርግ ነበር። በተለይ ምኒልክ ጋዜጣን ከመጀመሩ በፊት ጣይቱ ሆቴል ከፊል ቢሯችን ሊሆን ምንም አልቀረውም። ምሽት ላይ ፒያሳ ከመሸብንም የጣይቱ ሆቴል መኝታ ቤቶች ቤቶቻችን ነበሩ። ይህ ሁሉ ታዲያ ሆቴሉ ተሽጦ ወደ ፍጹምዘአብ ከመዛወሩ በፊት ነው። ፍጹምዘአብ ጣይቱ ሆቴልን ከገዛው በኋላ ብዙም ወደዛ መሄዳችንን አላስታውስም። ስለዚህ “ድሮ እና ዘንድሮ” በማለት ለማወዳደር እንቸገራለን። ሆኖም በቅርቡ ብዙዎችን ያነጋገረው “አትሂድ” የሚለው የሜሮን ጌትነት ግጥም እና ሌሎች ስራዎች የተቀረጹት እዚሁ ጣይቱ ሆቴል፤ ጃዝ አምባ አዳራሽ ውስጥ ነበር። (ወጋችንን እናሳርግ)
በቅርቡ አገር ቤት ደርሶ ከተመለሰ ጓደኛዬ ጋር ስንጨዋወት ጣይቱ ሆቴል ሄዶ እንደነበር አወራኝ። በዚያው ስለሆቴሉ አያያዝ ጠየቅኩት። “ኢትዮጵያ ውስጥ የአጼ ምኒልክ፣ የእቴጌ ጣይቱ እና ሌሎች ታላላቅ ኢትዮጵያውያን ፎቶ በትልልቁ ተሰቅሎ ያየሁት ጣይቱ ሆቴል ውስጥ ብቻ ነው” አለኝ።

ስለጣይቱ ሆቴል ከናንተ ጋር ያወራነውን አወራን። ፍጹምዘአብ ብቸኛ ተጫራች ሆኖ ሆቴሉን እንዴት እንደገዛው፤ ታስሮ በነበረበት ወቅት ስለነበረው ሂደት… ብዙዎች ስለማያውቁት የፍጹምዘአብ የፕሬስ አስተዋጽኦ አወራን። ከዚህ ጨዋታችን በኋላ ግን ደጋግሜ የማስብ የነበረው … ‘በሙስናም ሆነ በጉብዝና ሆቴል አንድ ግዜ በፍጹምዘአብ ስር ወድቋል። ሌላ… ምኒልክን የሚጠላ፣ የኢትዮጵያ ታሪክን የሚያጥላላ ሰው ያንን ጥንታዊ ሆቴል ገዝቶት ቢሆን ኖሮ… ምናልባት ሆቴሉን አፍርሶ ወይም፣ ስሙን ቀይሮ ሌላ ነገር ቢያደርገው ማን ጠያቂ ነበረበት? ደግሞ ባለበትም ቢሆን ጥንታዊነቱን የለቀቀ ናይት ክለብ ወይም ልብስ ቤት ወይም ስጋ ቤት ወይም ሌላ ነገር ሊሆን ይችል አልነበረምን?’ እያልኩ ደጋግሜ እያሰብኩ፤ ፍጹምዘአብንም ከነጉድለቱ መልካም ስራውን እያሞገስኩ ሳለ የጣይቱ ሆቴልን መቃጠል እንደመርዶ እሁድ ማለዳ ላይ ሰማነ።

እናም ከዚህ ቃጠሎ ጀርባ፣ በወጋገኑ ውስጥ የምናየው ፍጹምዘአብ አስገዶም ወልደሚካኤልን በቁንጽል አስተዋወቅናቹህ። ጣይቱ ሆቴልን በብላሽም ይሁን በርካሽ ገዝቶት፤ ለግዜው የግል ንብረቱ ሆኗል። ከቃጠሎው በኋላ ከማንም ባላነሰ ሳይሆን በባሰ ሁኔታ ሊያዝን ይችላል… የሚል እምነት አለን። የሱም ሆነ የሁላችንም እንባ ሊደርቅ የሚችለው ግን… ጣይቱ ሆቴል ጥንታዊ መሰረቱን ሳይለቅ እንደገና ከገነባልን ነው። እናም ሁሌም በዝምታ ውስጥ ሆኖ ትልቅ ነገር ለሚያስበው ፍጹምዘአብም እንዲህ በሉልን። “የእያሪኮ ግንብ ስለሃጢያታቸው ብዛት በእሳት ወድሞ ቀረ። የምኒልክ እልፍኝ፣ የጣይቱ ማጀት ግን እንደገና አምሮ ይሰራ። እነሆ ዘንድ መሰረቱን ጣል – ምሰሶውንም ከፍ አድርግ። እነሆ ፀሃይቱም እንደወርቅ ጠልሰም ዳግም ትድመቅ! ”
አሜን! (አሳርገናል)

የአንድነትን ፓርቲና የምርጫ ቦርድ –ግርማ ሠይፉ ማሩ

$
0
0

ደብዳቤ ልውውጦች ዝርዝር ሁኔታ በማሰረጃ የተመሰረተ

ታህሳስ 19-20፡
*********

(ግርማ ሰይፉ)

ግርማ ሠይፉ ማሩ

አንድነት ፓርቲ ታህሳስ 19-20/2006 ዓ.ም ልዩ ጠቅላላ ጉባዔ አካሄድ፡፡ ይህ ጠቅላላ ጉባዔ ልዩ የተባለበት ምክንያት የአንድነት አምስት ዓመት ስትራቴክ ዕቅድ ላይ በተቀመጠው መሰረት ፓርቲ ከ2007 ዓ.ም ምርጫ ቀደም ብሎ የአመራር ሽግሽግ በማድረግ ፓርቲውን በአዲሰ አመራር ወደ ምርጫ ይዞ ለመግባት በተቀመጠ ግብ መሰረት ነው፡፡ በዚህ ጠቅላላ ጉባዔ ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው የፓርቲው ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጠዋል፡፡ ይህ ጠቅላላ ጉበዔውም የተለያዩ ውሳኔዎች አሳልፎዋል ከዚህ ውስጥ መሰረታዊ ሊባል የሚችለው ጉባዔው በሌለበት ወቅት ፕሬዝዳንቱን ማንሳት የሚያስችል ስልጣን ለብሔራዊ ምክር ቤቱ መስጠቱ ሲሆን ሌሎችም ለምሳሌ የወጣቶች፣ የሴቶች ጉዳይ ኃላፊዎች በስራ አስፈፃሚ ውስጥ እንዲካተቱ ያደረገ ሲሆን የተቀደሚ ፕሬዝዳንት ቦታም እንዲኖረው አድርጎዋል፡፡
አንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔውን ባካሄደ በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ አመራሩ በሚጠበቅበት ፍጥነት አልሄደም በሚል አለመስማማት የተፈጠረ ሲሆን በአጋጣሚ አንድነት ከመኢህአድ ጋር የሚያደርገው ውህደት ጉዳይ ውይይት በመጀመሩና ለመጠናቀቅ አፋፍ ላይ የደረሰ ሲሆን ይህንንም አጋጣሚ በመጠቀም የውህዱን ፓርቲ የሚመራ የአንድነት ተወካይ ዕጩ ፕሬዝዳንት በብሔራዊ ምክር ቤት ተሰይሞ ውሕደት ይጠናቀቃል ሲባል ውህደቱ እንደማይቻል በምርጫ ቦርድ በኩል ይፋ ተደረገ፡፡ ኢ/ር ግዛቸው ሸፈራው በዚህ አጋጣሚ ተጠቅመው ለወጣት አመራር ቦታ ይለቃሉ ሲባል ይህን ከማድረግ ይልቅ ለውህደት በሚጠራው ጉባዔ በዕጩነት ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን ይፋ አደረጉ፡፡
ሐምሌ 14-30፡
*********
በኢንጅነር ግዛቸው የሚመራው ስራ አስፈፃሚ በታህሳስ 19-20 የተካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ ሪፖርት ገቢ ያደረገው 7 ወር ዘግይቶ ሐምሌ 14 ቀን 2006 ዓ.ም ነበር፡፡ ብዙ ሰዎች ይህ ሪፖርት እንዲዘገይ የተደረገው በአዲሱ አመራር ስለሚመስላቸው ነው ይህን ነጥብ መግለፅ የፈለኩት፡፡ ይህን ሪፖርት መሰረት አድርጎ ምርጫ ቦርድ ሐምሌ 25 ቀን ዘጠኝ ነጥቦችን አንስቶ ማብራሪያ እንዲሰጠው ጠይቆዋል እነዚህም፤

በጉባኤው ዕለት በቀረበው ሪፖርት የገቡት አላሰፈላጊ ቃላት እንዲወጡ፤
የፓርቲው ባንዲራ እንዲቀርብ፤
ፓርቲው አሻሽሎ ባቀረበው አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 2 ሰር የተዘረዘረው ሃሳብ ግልፅ አለመሆኑ፤
የጉባዔተኛው ቁጥር አለመገለፁ፤
የፕሬዝዳንቱን በብሔራዊ ምክር ቤት መመረጥ ከህግ አንፃር ያለው ጉዳይ በሚመለከት፤
የፓርቲው የገቢ ምንጭ በአዋጅ ቁጥር 573/2000 መሰረት ያለመቀመጡ፤
የፓርቲ መፍረስ በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 573/2000 መሰረት ያለመቀመጡ
የፓርቲው አባልነት በውርስ እንደማይተላለፍ አለመገለፁ፤ እና
ፓርቲው ያቀረባቸው የፓርቲ አካላት ውስጥ የሚሳተፉ አባላት አድራሻና በኃላፊነት ለመስራ የተሰማሙበት ሰነድ ያለመቅረቡ፤

የሚሉት ናቸው፡፡ ለእነዚህ ለቀረቡት ጥያቄዎች ሐምሌ 30 ቀን 18 ገፅ ያለው ማብራሪያ ተሰጧዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የመኢህአድና የአንድነት ውህደት አሰመልክቶ ከምርጫ ቦርድ ጋር በሚደረግ ውይይት በአንድነት በኩል ምንም ችግር እንደሌለ ነገር ግን ቦርዱ ሲሰበሰብ ውሰኔ እንደሚሰጥ በተደጋጋሚ ሲነገር ቆይቶ የመኢህአድ ጠቅላላ ጉባዔ ኮረም ሳይሞላ የተካሄደ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም በሚል ሰበብ ውህደቱ እንደማይሳካ በምርጫ ቦርድ ተገለጠ፡፡ ይህንንም ተከትሎ የአንድነት ስራ አሰፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የነበሩ አምሰት ከፍተኛ አመራሮች በሰራ አሰረፃሚነት ላለማገልገል መወሰናቸውን ገልፀው መልቀቂያ ደብደቤ አሰገቡ፡፡ ኢንጂነር ግዛቸውም በምትካቸው ሌሎች አመራሮቸን በመሰየም ስራቸውን ለመቀጠል ሞከሩ፡፡
ጥቅምት 3፤
********
ኢንጂነር ግዛቸው ሸፈራው የብሔራዊ ምክር ቤቱን ጠርተው በጥቅምት ሁለት ካቢኔያቸውን ማሰናበታቸውን በመግለፅ ከውስጥና ከውጭ በደረሰባቸው ጫና ለፓርቲው እልውና ሲሉ ጠቅላላ ጉባዔ የሰጣቸውን ኃላፊነታቸውን ለመልቀቅ እንደወሰኑ ለምክር ቤት አቀረቡ፡፡ ምክር ቤቱም ኃላፊነት ለመልቀቅ መወሰናቸው ተቀብሎ ፓርቲው አመራር በቀጣይ እንዴት መሆን አለበት በሚል ባደረገው ከፍተኛ ውይይት ፓርቲው ለአንድ ቀንም ያለ አመራር ማድር እንደማያስፈልግ ታምኖበት ከዚህ በፊት የመኢህአድና አንድነት ውሕደት አስመልክቶ ለዕጩነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን ጨምሮ ሌሎች ተጨማሪ ዕጩዎች በፈቃደኝነት ቀርበው ውድድር ተደርጎ በሚስጥር ደምፅ አስጣጥ በተደረገ ምርጫ አቶ በላይ ፍቃዱን በፕሬዝዳንትነት ሰየመ፡፡ በሳምንቱ ጥቅምት 10 ደግሞ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴውን ሰይሞ ስራውን በይፋ ጀመረ፡፡
ጥቅምት 19-21፤ የምርጫ ቦርድ ፅ/ቤት ምክትል ኃለፊ ጥቅምት 19 በተፃፈ ደብዳቤ አንድነት ፓርቲ ያደረገው የፕሬዝዳንት ምርጫ በታሕሳስ 19-20 በተደረገው ጉባዔ የተሻሻላው ደንብ በቦርዱ ባለፀደቀበት ሁኔታ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም የሚል ስሜት ያለው ደብዳቤ ሲፃፍልን፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር ጥቅምት 20 የቦርዱ ፅ/ቤት ኃላፊ ጋር ለመነጋገር የፓርቲ ወኪሎች ስንሄድ የቦርዱን ጥቅምት 19 ያደረገውን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ውሳኔ ደረሰን፡፡ ፓርቲያችን ሁለቱን ደብዳቤዎች መሰረት አድርገን ከቦርዱ ፅ/ቤት ኃላፊ ጋር ባደረግነው ውይይት ቦርዱ በጥቅምት 20 ላቀረባቸው ጥያቄዎች መልስ ስጡ ዋናውም የቦርዱ ጥያቄ ነው ተብለን በመግባባት መንፈስ ተለያየን፡፡ ቦርዱ ጥቅምት 19 ተሰብስቦ ለፓርቲያችን ያቀረበልን ጥያቄዎች፤
1. ሪፖርቱ ለምን 7 ወር ዘገየ፤
2. የጠቅላላ ጉበዔ አባላት ቁጥር በደንቡ ውስጥ የለም እና
3. የፕሬዝዳንት መረጣ ለማድረግ ጠቅላላ ጉባዔ ለብሔራዊ ምክር ቤት ውክልና የሰጠበት አግባብ ከዲሞክራሲያዊነት እና ከአባላት ተሳትፎ አንፃር ማብራሪያ ይፈልጋል፤
የሚሉት ናቸው፡፡
ለእነዚህ የቦርዱ ጥየቄዎች እና ጥቅምት 19 በቦርዱ ምክትል ኃላፊ ለቀረቡት ህገወጥ ጥያቄዎች መልስ አዘጋጅተን ጥቅምት 21 2007 ዓ.ም ለቦርዱ ፅ/ቤት ገቢ አደረገን፡፡
ህዳር 10 -19/2007፤
*************
የምርጫ ቦርድ በጥቅምት 20 ላቀረባቸው ጥያቄዎች በጥቅምት 21 ለሰጠነው መልስ ገምግሞ የሚከተሉትን ውሳኔዎች የያዘ ደብዳቤ ህዳር 10 2007 ዓ. ም ለፓርቲያችን እንዲደርስ አደረገ፡፡ እነርሱም
1. ሪፖርት መዘግየቱ አግባብ ያለመሆኑን ጠቅሶ ለወደፊት ሪፖርቶች በወቅቱ ገቢ እንዲደረግ፤
2. የጠቅላላ ጉባዔ አባላት ቁጥር ተወስኖ በደንብ ውስጥ መግባት እንደሚያስፈልግ እና
3. የፕሬዝዳንቱን ምርጫ አስመልክቶ ጠቅላላ ጉባዔው ለብሔራዊ ምክር ቤት ውክልና የሰጠበትን አግባብ በቅንንት እንደሚያየው ገልፆ፤
በተራ ቁጥር 2 ለተጠየቀው ጥያቄ መልስ ሲቀርብ ውሳኔ እንደሚሰጥ የሚጠቅስ ነበር፡፡
ህዳር 11 ቀን 2007 ዓ.ም የጠቅላላ ጉባዔ አባላት ቁጥር 320 እንደሆነ እና ከዚህ ውስጥ 161 ሲገኝ (ሃምሳ ከመቶ በላይ)ምልዓተ ጉባዔ እንደሆነ ገልፀን ለቦርዱ አስገባን፡፡ በዚሁ መሰረት መልስ ይሰጡናል ብለን ስንጠብቅ፣ በቦርዱ በኩል ደግሞ ዝምተው ስበረታብን የቦርዱን ፅ/ቤት ኃላፊ እንዲሁም የቦርዱን ሰብሳቢ ሰናነጋግር ደንብ የሚሻሻላው በደብዳቤ ሳይሆን ይህን ማድረግ በሚችለው በጠቅላላ ጉባዔው መሆኑን በተዘዋዋሪ ገለፁልን፡፡ በዚህ ውይይት ዘወትር የሚሰጠን ምክር አርፋችሁ ለምርጫ ዝግጅት አድርጉ እኛ በቅንንት ነው የምናየው የሚሉ የማግባቢያ ንግግሮች ነበሩት፡፡ ይህንን ግን በፅሁፍ እንዲያደርጉት ባደረግነው ጉትጎታ ህዳር 19 ቀን ቦረዱ ያለውን የመጨረሻ ጥያቄ በፅሁፍ ሰጠን፡፡ ይኽውም የጠቅላላ ጉባዔ አባላትን ቁጥር በደንብ ውስጥ አካቱና አምጡ የሚል ነው፡፡ ቦርዱ ከዚህ በኋላ ባደረገው የደብደቤ ልውውጥ የህዳር 10 እና ህዳር 19 ደብዳቤ ሆን ተብሎ አይጠቅስም፡፡ የቦርዱን ቅንነትና ሆደ ሰፊነት የሚለውን አባባል ያልተመቻቸው አባላት ጠቅላላ ጉባዔ አባላት ተጠርተው ለጉዳዩ መቋጫ ለመስጠት በመወሰን ጉባዔ እንዲጠራ ተወሰነ፡፡
ታህሳስ 3-4፤
*********
የአንድነት ፓርቲ በቦርዱ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት የጠቅላላ ጉባዔ ኮረም በደንብ ውስጥ ለማስገባት ብቻ መጥራት ተገቢ አይደለም በሚል እምነት ከጉባዔ አባላት ቁጥር ከማካተት በተጨማሪ ያሉ የዞን አመራሮችን ጨምሮ በምርጫ ጉዳይ ላይ ሰፊ ውይይት የሚያደርግበት በፓርቲያችን ላይ በምርጫ ቦርድ በኩል በሚዲያ እየተፈጠረ ያለውን ብዥታ ለማጥራት የሚያሰችል ደማቅ ጉባዔ ተካሄደ፡፡ መፈክራችንም “ምርጫ 2007 ለለውጥ” የሚል ነበር፡፡ በኢትዮጵያ የተቃዋሚዎች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሸበረቀ ጉበዔ አካሄደን የሚከተሉትን ውሳኔዎች ጉባዔ አሳለፈ፤
1. የጠቅላላ ጉባዔ አባላት ቁጥር 320 እንዲሆን እና ኮረም 50 ከመቶ ሲደመር አንድ እንዲሆን፤
2. የብሔራዊ ምክር ቤቱ የፓርቲውን ፕሬዝዳንት ለመምረጥ የሄደበት መንገድ ህገ ደንባዊ መሆኑን፤
3. በቀጣይ ምርጫ ቦርድ በጠቅላላ ጉባዔው ውሳኔ ላይ ጥያቄ የሚያነሳ ቢሆን ብሔራዊ ምክር ቤቱ የጠቅላላ ገባዔውን ወክሎ ምላሽ እንዲሰጥ የሚሉት፤
ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
ታህሳስ 10፤
**********
የጠቅላላ ጉበዔውን ሪፖርት ታህሳስ 10 ቀን 2007 ዓ.ም ለቦርዱ ፅ/ቤት ገቢ የተደረገ ሲሆን ቦርዱ ይህንን ችላ በማለት ፍፁም ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ በዕለቱ ምሽት የቦርዱ ኃላፊዎች በሚዲያ ቀርበው በአንድነት ፓርቲ ውስጥ ችግር እንዳለ የሚገልፅ መግለጫ ይሰጣሉ፡፡ በማግስቱ ቅዳሜ ደውለው ደብዳቤ እንድንወስድ ይነግሩናል፡፡ በታህሳስ 10 ቦርዱ ተሰብስቦ በወሰነው መሰረት የጠቅላላ ጉባዔ ሪፖርት በ7 ቀን ውስጥ እንድታስገቡ የሚል ነበር፡፡ ይህን ደብዳቤ አስመልክቶ እና በሚዲያ የሰጡትን መግለጫ አስመልክቶ ከቦርዱ ስብሳቢ ጋር ባደረግነው ውይይት ያቀረብነውን ሪፖርቱን በአጭር ጊዜ ተሰብሰበው ውሳኔ እንደሚሰጡት መግለጫ በክፋት ሳይሆን በቅንንት እንደሆነ ይገልፁልናል፡፡ ይህ እንደማይሆን ግን ምልክቶች እያየን ነበር፡፡ የቦርዱ ፅ/ቤት ኃላፊና ምክትላቸው በተለያየ መልኩ ከፓርቲያችን ውስጥ ቅሬታ ተሰምቶናል የሚሉ ህገወጦች ጋር በቢሮዋቸው እንደሚዶልቱ እየሰማን ነበር፡፡ በግንባርም በኃላፊው ቢሮ ከግለሰቦቹ ጋር ሲመክሩ አግኝተናቸዋል፡፡
ታህሳስ 27 -30፡
***********
ቦርዱ ተሰብሰቦ ያቀረብነውን ሪፖርት መርምሮ መልስ ይሰጣል ብለን በቅንንት ስንጠብቅ ታህሳስ 26 እሁድ በስልክ ተደውሎ የቦርዱ ኃላፊዎች ለውይይት እንደሚፈልጉን ይነገረናል፡፡ የዚያኑ እለት እሁድ በፓርቲያችን ለሆዳቸው ያደሩ ባንዳዎች አራት ኪሎ በሚገኝ ካፍቴሪያ ተሰብሰበው ፊርማ ተፈራርመው ለቦርዱ ገቢ አድርገዋል፡፡ በእሁድ ቀን ማለት ነው፡፡ ታታሪው ምርጫ ቦርድ አንድነትን ለማናጋት እሁድን ጨምሮ ሌት ከቀን ይሰራል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2007 ዓ.ም ቦርዱ ፅ/ቤት ስንገኝ ካሜራ ደቅነው ከአቶ የማነአብ አሰፋ እና ከአቶ አየለ ሰሜነህ ጋር “ውይይት” እንድናደርግ ግብዣ ያደርጉልናል፡፡ ዓላማው በምሽት ቦርዱ ሊሰጠው ላሰበው ውዥንብር መፍጠሪያ መግለጫ የቪዲዮ ግብዓት ለማግኘት የነበረ ሲሆን መኢህአዶች በየዋህነት በቪዲዮ ተቀርፀው ሲቀርቡ እኛ ከእነዚህ ሰዎች ጋር በምርጫ ቦርድ መድረክ የምናደርገው ውይይት እንደሌለ፤ ቦርዱ ያሰገባነውን ሪፖርትና ግለሰቦች ያቀረቡትን ሪፖርት መርምሮ ውሳኔውን እንዲያሳውቅ ብቻ መሆኑን ገልፀን ተመለስን፡፡ በምሽቱ የቦርዱ ምክትል ሰብሰቢ የውስጥ ችግራቸውን እንዲፈቱ ልናስማማቸው ሞክረን አልተሳካም፤ የታህሳስ 19-20 ሪፖርት 7 ወር አዘግይተው አስገብተዋል፤ የፕሬዝዳንቱ ምርጫ ህገወጥ ነው፤ የሚሉ መግለጫዎችን በመስጠት ህዝቡን ብዥታ ውስጥ ለመክተት ሞከሩ፡፡ ይህን ሲያደርጉ ቦርዱ ስብሰባ የተጠራው ለታህሳስ 28 ሲሆን ቦርዱ ከመሰብሰቡ በፊት በቅድሚያ በማን አለብኝነት የቦርዱ ምክትል ሰብሰቢ የግል ውሳኔያቸውን አስታውቀው ለቀሪዎቹ የቦርድ አባላት ዋጋ ቢስነት በህዝብ ፊት አረጋገጡ፡፡
በታህሳስ 28 በምሳ ሰዓት ተደውሎ የቦረዱን ውሳኔ ለመስማት በ9፡00 ሰዓት እንድንገኝ ጥሪ ተደርጎልን ስንሄድ ገዛኽኝ አዱኛ የሚባል የወረዳ ስድሰት አባል እና እራሱን የወረዳ ሰድስት ዕጩ አድርጎ ያቀረበ 10+1 ያጠናቀቀ እና ሰፊው የሚባል የወረዳ 7 አባልና አራሱን ለ2007 ምርጫ የወረዳ 7 ዕጩ አድርጎ አቅርቦ ያልተሳካለት አኩራፊ አኩራፊ የአንድነት አባላትን ወክለው እንዲገኙ በአኩራፊዎች ተወክለው ነበር፡፡ ይህ ቡድን ምርጫ ቦርድ ከመምጣቱ በፊት በአምባሳደር መናፈሻ ድራፍት ቢራ እየተጎነጩ በአቶ ትዕግሰቱ አውሎም መመሪያ ሲሰጣቸው ነበር፡፡
ቦርዱ ፅ/ቤት ያለውን ሁኔታ ስንረዳው አሁንም ለኢቲቪ የቪዲዮ ግብዓት ለማግኝት ካልሆነ ትርጉም እንደሌለው በመረዳታችን የቦርዱ ውሳኔ በፅሁፍ እንዲሰጠን ጠይቀን ወደ ቢሮዋችን ተመለስን፡፡ በምሽት ዜና እና በቅርቡ በከፍተኛ ወኔ ገዢውን ፓርቲ ለመከላከል የቆመው የኢህአዴግ ሚዲያ የሆነው ሬዲዮ ፋና የቦርዱ ውሳኔ ነው ያሉትን ነገር ግን ቦርዱ ከመሰብሰቡ በፊት በቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ በሚዲያ የተነገረውን ውሳኔ በትንተና አቀረቡት፡፡ የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጊያም ከንፈራች እስኪደርቅ ድረስ አንድነት ላይ አለ የሚሉትን ክስ ሁሉ አዘነቡት፡፡ ታህሳስ 29 የገና በዓል በመሆኑ ታህሳስ 30/ 2007 ዓ.ም ጠዋት ማልደን ምርጫ ቦርድ ተገኘተን በሚዲያ የነዙትን ክስ በፅሁፍ እንዲሰጡን ስንጠይቅ ደብዳቤ እየተዘጋጀ እንደሆነ ገልፀውልን በ5፡00 ሠዓት ደብዳቤ ሰጡን፡፡ አባላቶቻችን ቁጭ ብሎ ተረቆ የተፃፈ ደብዳቤ አስገራሚው በሆነ ሁኔታ በታህሳስ 28 ተደርጎ ወጭ እንዲሆን ተደርጎ ቀን ተፃፈበት፡፡ እዚህ ጋ የቦርድ ኃላፊዎች የበታች ሰራተኞችን ምን ያህል ከህግ ውጭ እንደሚያሰሩ ነው፡፡ የቦርዱ ፅ/ቤት ምን ያህል ለመዋረድ እንደተዘጋጀ የሚያሳይ ነው፡፡ ለማነኛውም ታህሳስ 30 የደረሰን ደብዳቤ አራት ነጥቦች ያሉት ለማስመስል ቢሞክርም ሁለት ጥያቄዎች ናቸው ያሉት፡፡ እነርሱም
1. የታህሳስ 19-20 ሪፖርት ለምን ዘገየ የሚል እና
2. የፕሬዝዳንቱ ምርጫ የፓርቲውን ህገ ደንብ የተከተለ አይደለም የሚል ነው፡፡
የሚያሳዝነው ነገር ቦርዱ የታህሳስ 3 ቀን 2007 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባዔ ሪፖርት ለመመርመር ተሰብሰቦ የታህሳስ 19-20/2006 ዓ.ም ሪፖርት ለምን ዘገየ ማለቱ ብቻ ሳይሆን በቅንንት ተቀብዬዋለሁ ያለውን የፕሬዝደንት ምርጫ በድጋሚ ማንሳቱ ነው፡፡ በግልፅም ቦርዱ የአንድነትን ሪፖርት በጥልቀት ገመገምኩ ይበል እንጂ እንዳልገመገመው ማሳያ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ቦርዱ ወሰነ የተባለው እና የቦርዱ ምክትል ሰብሰቢ ከቦርዱ ስብሰባ በፊት በሚዲያ የሰጡት መግለጫ መመሳሰል ብቻ ሳይሆን ቦርዱ ሊመረምረው ከተቀመጠው ሪፖርት ይዘት የወጣ ውሳኔ አሳለፈ መባሉ ነው፡፡
ስለዚህ የታህሳስ 19-20/2006 ዓ.ም ሪፖርት ለምን ዘገየ ከአሁን በፊት በቂ መልስ ተሰጥቶታ ቦርዱ እንደተቀበለው ማስታወስ እና አንድነትም በተከታይ ባደረገው ጠቅላላ ጉባዔ በሰባት ቀን ሪፖርት ማስገባቱ ነው፡፡
ጥር 1-3፤
********
አንድነት ፓርቲ ለመጨረሻ የደረሰው ደብደቤ ጥር 1 ቀን 2007 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 11፡45 (ከሰራ ሰዓት ውጭ) የደረስን ህገወጥ ደብዳቤ በጥር 3/2007 ዓ.ም ለሚደረገው ጠቅላላ ጉባዔ የምርጫ ቦርድ ታዛቢ መላክ እንደማይችሉ ገልፀው ለዚህም የሰጡት ሰበብ በእነ አየለ ሰሜነህ የሚመሩ አባላት ሌላ ጠቅላላ ጉባዔ በሳሬም ሆቴል በመጠራቱ ሁለት ቦታ ጉባዔ ታዛቢ መላክ አልችልም የሚል ነው፡፡ በመሰረቱ የምርጫ ቦርድ በእጁ በሚገኝው የፓርቲያችን ደንብ አባላት ጠቅላላ ጉባዔ ሊጠሩበት የሚችሉበት ስርዓት በግልፅ ተቀምጦ እያለ ከዚህ ውጭ የፓርቲውን ጉባዔ ለማደናቀፍ ምን ያህል እየተሰራ እንደሆነ ግልፅ ማሳያ ነው፡፡ አንድነት በማግስቱ መገኘት ባይፈልጉም ጉባዔው በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት እንደሚቀጥል ጥር 2/2007 ዓ.ም እንዲያውቁት ተደርጎዋል፡፡ በዚሁ መስረት አድነት ጥር 3/2007 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ይህን መስመር የፃፍኩት ጉባዔዬው አመስራጭ ኮሚቴ ሰይሞ ሲያጠናቅቅ ነው፡፡ ትግሉ ይቀጥላል……….. የደብዳቤው ልውውጥም ይቀጥላል፡፡ ይህ ታሪካዊ ዘገባ ይሆናል፡፡

ግርማ ሠይፉ ማሩ (ጥር 3/ 2007)

 

በዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ጫካ የተነሳው እሳት በገዳሙ ላይ ጉዳት ከማድረሱ በፊት በቁጥጥር ስር ውሏል

$
0
0

ዘ-ሐበሻ ዛሬ በቀዳሚ ዜናዋ ከቀኑ ሰባት ሰዓት አካባቢ በታላቁ እና በጥንታዊው የዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም አካባቢ ተነስቶ ስለነበረው ድንገተኛ የእሳት አደጋ መዘግቧ ይታወሳል:: አሁን በደረሰን መረጃ መሠረት ይህ እሳት ወደ ገዳሙ ሳይዛመትና ብዙ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ፎቶ ፋይል ደጋ እስጢፋኖስ

ፎቶ ፋይል ደጋ እስጢፋኖስ


በገዳሙ ጫካ ውስጥ የተነሳው የዚህ እሳት መንስኤ በይፋ ባይረጋገጥም፣ መሬቱን ለጌሾ ልማት ዝግጁ ለማድረግ በአንድ የገዳሙ መነኰስ የተለኰሰው እሳት በአቅራቢያው በብዛት በሚገኙት የሐረግ ተክሎችና ሸምበቆዎች መቀጣጠሉ እንደኾነ ማኅበረ መነኰሳቱን ያነጋገሩ የዐይን እማኞች ገልጸዋል ሲል ሃራ ተዋህዶ ዘግቧል::

እሳቱ ወደ ሰማይ 100 ሜትር ከፍታ መያዙና ጭሱ በቅርብና በርቀት ላይ በሚገኙ ደሴቶች ውስጥ በሚኖሩ ነዋሪዎች በመታየቱ በተለይ በደቅ ደሴት ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች በጀልባ ወዲያው በመድረስ ከገዳሙ አባቶች ጋር በመሆን እሳቱ እንዳይዛመት ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በስፍራው ከሚታየው ጢስና የተዳፈነ እሳት ጨርሶ መጥፋቱን ለማረጋገጥ ከሚደረግ እንቅስቃሴ በቀር የእሳት ቃጠሎው ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል::

እሳቱ ባይጠፋና ተዛምቶ ወደ ገዳሙ ቢዘልቅ ኑሮ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ታሪክና ቅርሶች ሊወድሙ ይችሉ ነበርና ወደፊትም እንዲህ ያለው አደጋ እንዳይከሰት አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ ዘ-ሐበሻ ሃሳቧን ታካፍላለች::


ወያኔን ሁለት ግዜ እንገድለዋለን!!! -ከ-ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

ወያኔና ንብ ከአፋቸው ማር  ከሆዳቸው መርዛማነት አላቸው።

rtምርጫ ሊደርስ በወራቶች የሚቆጠር ግዜ ቀርቶታል ልዩ ምልክቱ ንብ ስሙ TPLF ስራው ጥፋት። ንብ የመረጡት ሰራተኛ ነኝ ለማስባል በሆዳቸው ያለውን መርዝ መናገር የማይወዱ ግን መርዘኝነታቸውን ህብረተሰቡ የተረዳቸው በዲሞክራሲ ስም አደናቋሪ የግን ሞት (ግንቦት) ምርጫ እየደረሰ ነው።በግን-ሞት (በግንቦት) ምርጫ ንብ ይዘው ማሯን ሳያሳዩ መርዟን ታቅፈው ሳይመረጡ ተመረጥን ሳይሾሙ ተሾምን ሳይፈለጉ ተፈለግን የሚሉበት ግዜ እየተቃረበ ነው። ወያኔ ከህዝቡ ልቦና ከወጣ ህዝቡም አንቅሮ  ከተፋው ቆይቷል። በመርዝ የተለወሰ የጣፈጠ የሚመስል ወሬ ለአለም መንግስታት በተቆጣጠረው  ሚዲያ እና በተለያዩ አገራት በሚጋበዘው መድረክ ላይ ዲሞክራሲ፣ ልማት፣ የህዝቦች እኩልነት፣ እያለ በሚደሰኩረው ዲስኩር ካደጉ አገራት እርዳታን በመለመን እና ብድራትም በመሰበሰብ እራሱን በማደለብ አገሪቷን እና  ህዝቧን ደሃ በማድረግ ሊቆይ የሚችልበትን የጥፋት ስራውን ሽር ጉድ ማለት ከጀመረ  ውሎ አድሯል። ወያኔ  በመርዝ የተለወሰ  ማር በየግዜው በማቅረብ በሆዱ ያለውን መርዝ መሸፈኛ አድርጎ  በምርጫ ሸፍኖ ቆይቷል። እስቲ ንብና ወያኔን እንዴት እንደተስማሙ እናያለን።

ንብ፡- በአንድ የንብ ቀፎ ውስጥ ሶስት የተለያዩ  ንቦች አሉ

  1. ንግስቲቷ(አውራ) ንብ
  2.  ድንጉላ ንብ
  3. ሰራተኛ ንብ

ንግስቲቷ  ንብ በይዘቷ ረዘም ብላ ሽንጥ ያላት ስትሆን በቀፎ ውስጥ አንድ ብቸኛ ንግስት ሆና የምትኖር ናት። የሁሉ መሪ ሁሉን አስተዳዳሪ በቀፎ ውስጥ ያሉት ንቦች የሚታዘዙላት የንግስቲቷ  መኖር የቀፎው ንብ መኖር የንግስቲቷ መጥፋት የንቦቹ መጥፋት ሆና በቀፎ ውስጥ ተከብራ እና ነግሳ የምትኖር ንግስት ናት።

ድንጉላ ንብ በይዘቱ ከሰራተኛው ንብ ከፍ ያለ ሲሆን በቀፎ ውስጥ በጣም ትንሽ ቁጥር ያለው ሆኖ የሚኖር ሲሆን ሁል ግዜ ሳይሆን ዘር ለመተካት ከመጣ በኃላ ለተወሰነ  ግዜ ታይቶ  የሚጠፋ ነው።

ሰራተኛ ንብ በይዘታቸው ከንግስቲቱ እና  ከድንጉላው ያነሱ ሲሆኑ በብዛት እና በቀፎ ውስጥ ያለውን ስራ በመሰራት ድርሻ ያላቸው ንግስቲቷንም እንደወታደር ሆኖ በመጠበቅ የሚያገለግሉ ሆነው የሚኖሩ ናቸው።

በወያኔ፡- መንግስት ሶስት የተለያዩ  አካል አሉ

1.ንጉስ

2.ሚንስተሮች

3.ካድሬዎች

ወያኔ በአንድ ንጉስ የሚመራ ሁሉም በንጉሱ የሚስተዳደሩ ሁሉን ፈላጭ ሁሉን ቆራጭ ሁሉን አድራጊ ሁሉን ሰሪ ለወያኔ ጠቢብ የሆነ ንጉስ የነበረ።

ሚንስተሮች በንጉሱ የሚመሩ ያለንጉሱ ፈቃድ መስራት የማይችሉ የንጉሱ ትዛዝ ተቀባዮች እና ትዛዝ አስፈጻሚዎች ያለንጉሱ ህይወት የሌላቸው ያለንጉሱ መስራት የማይችሉ ንጉሱ ሲፈልግ የሚሾማቸው ሲፈልግ የሚሽራቸው ያለ ንጉሱ ህይወት የሌላቸው ሲሆኑ በቁጥርም ብዙ ጥቂት ናቸው።

ካድሬዎች በቁጥራቸው  የበዙ ሲሆኑ ንጉሱ የፈለፈላቸው በየስርቻው ያሰማራቸው ንጉሱ አድርጉ ያላቸውን የሚያደርጉ አታድርጉ ያላቸውን የማያደረጉ የንጉሱን ንግግር እንደ ጸሎት መጽሐፍ እየደጋገሙ የሚጠቀሙ እንደ መድኃኔዓለም ምስል የንጉሳቸውን ፎቶ በኪሳቸው ይዘው  የሚዞሩ በቢሮአቸው በትልቁ ግድግዳ ላይ ሰቅለው ሲገቡና  ሲወጡ የሚሳለሙት የንጉሱን አላማ የሚያራምዱ የንጉሱን ቃል የሚጠብቁ ናቸው።

ወያኔዎች ንጉሳቸውን  አርቀው ነው የሾሙት አርቀው ነው የካቡት ሊደርሱበት በማይችሉት አኳሃን። ንጉሳቸው ለእነርሱ ሁሉን አዋቂ እርሱ ህግ አርቃቂ እርሱ ህግ ተርጓሚ እርሱ ጥበባቸው እርሱ ፈላስፋቸው እርሱ መመሪያቸው እርሱ መሪያቸው እርሱ ሁሉ ነገራቸው ነው። እንደዚህ የካቡት መሪያቸው ምን አይነት ስራ  ይሰራ  እንደነበረ ታሪክ እራሱን ሲደግም ስራው ሁሉ  የሚነበብበት ግዜ እሩቅ አይደለምና  ያኔ የስራው ስራ በግልጽ የምናየው ጉዳይ ነው።

ወያኔዎች ንጉሳቸው ሁሉን ነገር የሚሰራላቸው ትግሉን ሁላ  ሳይቀር የሱ ድል አድርገው የሚያምኑ በንጉሳቸው መልክ የሚደሰቱ በስራው የሚያምኑበት ሁሉ ነገር ለንጉሳቸው የሰጡት የተናገረውን ንግግር እንደ አየር መልሰው መልሰው ወደ ውስጥና ውጪ በማውጣትና በማስገባት እንደ እስትንፋስ ንጉሱ የተናገሩትን ንግግራቸውን የሚደጋግሙት መሪያቸው የነበሩ ነበረ።

ወያኔዎች ንጉሳቸውን  እሳት ብለው የሚጠሯቸው ካድሬዎቹ ደግሞ ብረት የሆኑላቸው የብረት ጫፏን እሳታዊው ንጉሳቸው ሲነኳት በሙሉ የሚግሉላቸው  ከዛም ንጉሱ በሚፈልጉት ቅርጽ ቀጥቅጧቸው የሚሰሯቸው እና  የሰሯቸው ናቸው። ንጉሱ በራሱ ሞዴል ቀርጾ የሰራቸው ካድሬዎች የአስተዋዩን ህዝብ ጆሮ የንጉሳቸውን ንጉስነት ማህበረሰቡ ሳይቀበላቸው ሳይፈልጋቸው የሁሉም ንጉስ እንደሆነ ሲያደናቁሩ ይከርማሉ። ምን ያድርጉ ወያኔዎች ከንጉሳቸው ውጪ ህይወት የሌላቸው እንደሆነና  ስራም መስራት እንደማይችሉ የንጉሱ የስራ ውጤቶች እንደሆኑ ይታወቃል።

የወያኔ ንጉሳቸው ሁሉንም የሚያዝ ነው ልክ እንደ ንግስቲቷ ንብ። በቀፎ  ውስጥ ያሉት ንቦች መኖር የሚችሉት ንግስቲቷ  እስካለች ድረስ ነው። ንግስቲቷ  የለችም ማለት በቀፎ ውስጥ ያሉት ንቦች ሁሉ ቃስ በቃስ እየሞቱ እና  እየተፉ በኋላ  ቀፎው ባዶ ይሆናል። ወያኔም ንጉሳቸው ስለሞቱ ቃስ በቃስ እየሞቱ እና  እየጠፉ ይመጣሉ። አጠፋፋቸው ግን በሁለት መንገድ ነው።

1ኛ. ንጉሳቸው ስለሌለ የሚሰበስባቸው ባለመኖሩ ሁሉን አጠቃሎ የሚሰራላቸው ስለሞተ ወያኔዋች እርስ በራሳቸው መደማመጥ ስለማይችሉ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ በመሃላቸው ስላለ እኔ ትክክል ነኝ እኔ አዋቂ ነኝ እኔ ቀዳሚ መስራች ነኝ በሚል ስለማይግባቡ ለኔ  ይህ ይድረሰኝ ለኔ  ይሄኛው ይገባኛል እያሉ ያገሪቷን ንብረት የግል ለማድረግ ስለሚፈልጉ ሃሳባቸው ሁሉ ስለግል ጥቅማቸው እና የሰሩትን ወንጀል ለመደበቅ በሚያደርጉት ፍትጊያ እርስ በራሳቸው ይጠፋፋሉ።

2ኛ. ንብን መርዝ እንዳላት ያወቀ  ሰው መከላከያ  አድርጎ ሄዶ የፈለገውን ነገር ማድርጎ ጣፋጥ ምግቧን እንደሚወስድ ከፈለገም ማጥፋት እንደሚችለው ሁሉ ወያኔንም መርዛማ  እንደሆነ  ስለተረዳነው መከላከያን ተጫምተን በመሄድ መርዙን ሳይተፋው ሆድ ውስጥ እንዳለ እስከመርዙ በቀላሉ ማጥፋት የምንችልበት ግዜ  ነው። ከአሁን በኋላ በወያኔ መርዝነት ተወግቶ በቀላሉ የሚሞት የለም ያለፉት ግዜያቶች ህዝባችንን ገድሎ የፎከረበት ዘምን አይደገምም ለመርዛማው ወያኔ መርዙን የሚያስተፋ አልያም ከነመርዙ የሚያጠፋ ሙሉ ትጥቅ ታጥቀን ቀርበናል። ይሄ አይደለ ሁለት ሞት የሚባለው ላይመለስ የሚጠፋበት አንድም በቀመመው መርዝ እርስ በራስ በመወጋጋት ሲጠፋፉ ሁለተኛውና ዋንኛው ደግሞ መርዘኛነታቸውን የተረዳው ሰፊው ህዝብ የሚያጠፋቸው ነው።

ወያኔ አዲስ አበባ ተንደርድራችሁ  ስትገቡ ሰፊው ህዝብ በሩን ከፍቶ ምግብ እየመገበ ውሃ እያጠጣ የቆሰለ እያከመ በጉያው እየደበቀ አስገብቶአችሁ ነበረ ። ያንን ግን ረስተውታል ወይም ማውራት አይፈልጉም። አሁን ግን ከአዲስ አበባ በህዝቡ እንቢተኝነት ስትወጡ  በሩን ዘግቶ መርዘኛነትህን ሁሉም ስለተረዳችሁ  በሩን ዘግቶ ሊያጠፋችሁ ወደ ውጪ ይወጣል። ያኔ ከደደቢት ተንደርድራችሁ አዲስ አበባ እንደገባችሁ ከአዲስ አበባ ተንደርድሮ ደደቢት መግባት የለም። በየት በኩል ሊኬድ በየት በኩልስ ሊታለፍ አሁን በግፍ የጋገራችሁት እንጀራ  የምትመገብበት ግዜ መጥቷል የሳቃችሁበት ጥርሶቻችሁም መራገፊያቸው ደርሷል የተደሰቱ ልቦናችሁ ማዘኛችሁ ደርሷል በግፍ የዘራችሁት ስለሆነ በመከራ  ታጭዱታላችሁ፣ ስትቀዱት  የነበረውን የደም ጽዋ ያኔ ትጎነጩታላችሁ። ድንፋታችሁ ከንቱ ድንፋታ  ቀረርቶአችሁ ከንቱ ቀረርቶ እንደሆነ በማሳወቅ ወያኔዎችን ሁለት ግዜ በመግደል የሰፊው ህዝብ የበላይነት ይረጋገጣል። የኛ ምርጫ ይሄ ነው። ሁሌም ህዝብ አቸናፊ ነው።

ከ-ከተማ ዋቅጅራ

14.01.2014

 

 

 

 

ወያኔ ኢትዮጵያን አፍርሶ ወደ ጉሬው ለመግባት የመጨረሻ መሠናዶውን እያደረገ ነው

$
0
0
  • የትግሬ-ወያኔዎች ከተለያዩ ጎሣዎች እና ነገዶች ሰዎችን መልምለው እና አደራጅተው፣ እንዲሁም የወታደራዊ፣ የደህንነት፣ የአደረጃጀት፣ የአመራር እና የቁጥጥር ሥራ የሚሠሩ የትግሬ-ወያኔዎች መድበው በከፍተኛ ሚሥጢር ኢትዮጵያን የማፈራረስ ሤራ እየተዶለቱ መሆኑን በተጨባጭ መረጃዎች አረጋግጠናል።

የትግሬ-ወያኔ የመጨረሻ ግብ ኢትዮጵያን በመበታተን፣ የትግራይ ረፑብሊክ መመሥረት መሆኑን በ1968 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው ፕሮግራሙ መሠረት ላለፉት ፵(አርባ) ዓመታት ያደረገው ጉዞ ያሣያል። በጉዞው የኢትዮጵያን የረጅም ዘመን ታሪክ ክዶ በመቶ ዓመት መገደቡን፣ የትግሬ-ወያኔ መሪዎች እና አባሎች በተደጋጋሚ በጻፉዋቸው መጻሕፍት እና በየአጋጣሚው ባደረጉዋቸው ንግግሮች ለሕዝብ ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል። «ኤርትራ በኢትዮጵያ በቅኝ ግዛትነት የተያዘች ናት፤ ስለሆነም ሻዕቢያ የሚያካሂደው የመገንጠል እና የነፃነት ጥያቄ ተገቢ እና ትክክል ነው።» ብለው፣ ከሻዕቢያ በላይ ሻቢያ ሆነው፣ የትግራይን ልጆች የጦር ማገዶ በማድረግ ኤርትራን ማስገንጠላቸው ማንም ሊያስተባብለው የማይችለው ሃቅ ነው። ኢትዮጵያውያንን እንደ አንድ ሕዝብ ያስተሳሰሩ የወል ዕሴቶችን፥ «የኢትዮጵያዊነት አገራዊ እና ብሔራዊ ስሜት የሁሉም በኢትዮጵያ የሚኖሩ ነገዶች እና ጎሣዎች ሳይሆኑ፣ የዐማራው ብቻ የማንነት መገለጫዎች ናቸው፤ ዐማራው ጨቋኝ እና በዝባዥ ነገድ ነው፤ እርሱን ሁሉም ነገዶች እና ጎሣዎች በወያኔ መሪነት ተባብረው ማጥፋት አለባቸው።» በማለት በከፈቱት የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ጦርነት፣ የኢትዮጵያዊነት የወል ዕሴቶችን፣ ተቋሞችን፣ ግንኙነቶችን፣ አሠራሮችን ወዘተርፈ በማጥፋታቸው ዛሬ አገሪቱ እና ሕዝቧ የሚገኙበት ሁኔታ በግልጽ ያሣያል። የአገሪቱ ዘመን-ጠገብ መልከዐ-ምድራዊ መለያ ስሞች እና ወሰኖች ተሽረው በተወሰኑ ነገዶች ማንነት ብቻ ላይ የተመሠረቱ ስሞች በመስጠት፣ የኢትዮጵያውያንን ተዘዋውሮ በፈለጉት ቦታ እና አካባቢ የመኖር እና የመሥራት ተፈጥሮአዊ፣ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ሰብአዊ መብቶቻቸውን ገፍፈው፣ አንድነታቸውን አሣጥተው፣ አብሮነታቸውን ክደው፣ በጠላትነት እንዲተያዩ አድርገዋቸዋል። ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ከሕዝቡ ስሜት ፈጽሞ እንዲጠፉ መጠነ ሠፊ የሆነ የሥነልቦና ጦርነት ከፍተው አገሪቱን ከመጨረሻው የጥፋት ጠርዝ ላይ አድርሰዋት ይገኛሉ።

የትግሬ-ወያኔ እና ተከታዮቹ በኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና ብሔራዊ ጥቅም፣ እንዲሁም በሕዝቧ ኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ ታሪክ፣ ትውልድ፣ ሕግ እና ማናቸውም ዓይነት ሥነ-ምግባር ይቅር ሊለው የማይችል የክህደት ተግባሮችን የፈጸሙ መሆኑን ከማንም ይበልጥ ራሣቸውም አይክዱም። ይህም በመሆኑ የኢትዮጵያ አንድነት ተጠብቆ ከዘለቀ በየትኛውም ጊዜ በአገር ክህደት ወንጀል ተጠያቂ እንደሚሆኑ ያውቃሉ። ከዚህ ተጠያቂነት ለመዳን እንችላለን ብለው የሚምኑት ሁለት ነገሮችን ጎን ለጎን ማከናወን ሲችሉ ብቻ  ነው። እነዚህም፦ አንደኛ የወያኔ ትውልድ ለሚቀጥሉት መቶ ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሕይዎት ላይ የወሳኝነቱን ሚና ይዞ የሚቀጥልበት አስተማማኝ ሁኔታ  ሲረጋገጥ፤ ይህ የመጀመሪያው ዕቅድ በተለያዩ ምክንያቶች ባይሣካ ሁለተኛው አማራጭ ዕቅድ ትግራይን ከኢትዮጵያ በመገንጠል የትግራይ ረፑብሊክ በመመሥረት ጎጆ መውጣት፤ የሚሉ ናቸው።

Eth

ሁለተኛውን ግብ ለማሣካት በኢትዮጵያ ላይ ሥልጣን ከተቆጣጠሩ ጊዜ ጀምሮ ለምትገነጠለው ትግራይ ቁሣዊ፣ ቴክኒካዊ እና ኅሊናዊ ሁኔታዎች እንዲሟሉ የሚያስችሉ ተግባሮችን ማከናወን እንዳለባቸው ታሣቢ አድርገው መንቀሣቀሣቸው ባለፉት ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት የሥልጣን ዘመናቸው  ትግራይ ውስጥ አያሌ የመሠረተ ልማት ሥራዎች መሥራታቸው ይታወቃል። በዚህም መሠረት የትግራይ ክልል ከጎንደር እና ከወሎ ክፍለ ሀገሮች መሬት ነጥቀው በታሪክ የትግራይ አካል ሆነው የማያውቁ አካባቢዎችን አጠቃልለው ጥንተ-ነዋሪውን የዐማራ ነገድ አባላት የሚገድሉትን በመግደል፣ ቀሪውን በማሠር እና በማሰደድ ትግሬን አስፍረውበታል። ይህ የያዙት ግዛት ወደፊት ለምትገነጠለው ትግራይ ይጠብባል በማለት ከሰቲት ወደ ደቡብ ምዕራባዊ የጎንደር እና የጎጃምን የሱዳን አዋሳኝ ወረዳዎችን ከቤንሻጉል ጉምዝ እና ጋምቤላ ክልሎች ጋር በማገናኘት የታላቋ ትግራይን የመሥፋፋት ዓላማ ዕውን በማድረግ ላይ ይገኛሉ (አባሪ ካርታውን ይመልከቱ)።

በዚህም መሠረት ለወደፊቷ ትግራይ ለምትጠቀልለው ሠፊ ግዛት፣ ከውጭው ዓለም ጋር የሚያገናኙ የመገናኛ መሥመሮችን ዘርግተዋል፣ ተጨማሪ መሥመሮችንም በፍጥነትም በመገንባት ላይ ይገኛሉ። የትግራይን ምርት ወደ ውጭ ለመላክ እና ከውጭ የሚፈለጉ ሸቀጦችን ወደ ውስጥ ለማስገባት፣ ከጅቡቲ እስከ መቀሌ፣ ከሱዳን ጠረፍ እስከ መቀሌ የሚያገኛኙ የባቡር ሐዲድ ግንባታዎች በመፋጠን ላይ ናቸው። ሁለት ታላላቅ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ጣቢያዎች መቀሌ እና አክሱም ላይ ገንብተዋል። ቀበሌዎችን ከወረዳ ከተሞች፣ ወረዳዎችን ከአውራጃዎች (ዞኖች)፣ አውራጃዎችን ከዋና ከተማዋ ከመቀሌ ጋር የሚያገናኙ፣ ክረምት ከበጋ ያለምንም እንከን አገልግሎት የሚሠጡ መረብ-መሰል አውራ መንገዶች ተገንብተዋል። ድርቅን  ለመቋቋም የክረምት ዝናብን ለማቆር የሚያስችሉ በርካታ ግድቦችን ሠርተው አገልግሎት ላይ አውለዋል። የትግራይን አዲሱን ትውልድ ከኢትዮጵያዊነት ስሜት አውጥቶ የትግራዊነት ስሜት እንዲገነባ የሚያስችሉ፣ በተቀነባበረ ሁኔታ ቅስቀሣ እና ትምህርት በማያቋርጥ መልኩ የሚሰጡ ተቋሞች ተገንብተዋል። በርካታ ትምህርት ቤቶች፣ ኮሌጆች፣ የቴክኒክ እና የሙያ ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርስቲዎች ተከፍተዋል። በኢንዱስትሪ ግንባታ ረገድ የነባሮቹን የኢትዮጵያ ፋብሪካዎች ሕልውና የሚያጠፉ የመድኃኒት፣ የጨርቃጨርቅ፣ የስሚንቶ፣ የመጠጥ እና የብረታ ብረት ፋብሪካዎች በሁሉም የትግራይ አውራጃዎች ተቋቁመዋል። ከእነዚህ መካከል፦ የአዲግራት መድኃኒት ፋብሪካ፣ እንዲሁም መቀሌ የተገነቡት የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ፣ የአልሜዳ የጨርቃጨር ፋብሪካ፤ የመሥፍን ኢንጂነሪንግ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ፣ ወዘተርፈ ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው። አሽጎዳ አካባቢ በአፍሪቃ በግዙፍነቱ ቀዳሚ የሆነ እና በነፋስ ኃይል ኤሌክትሪክ የሚያመነጩ ተርባይኖች በብዛት ተገንብተዋል።

የአገሪቱ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መዋቅሮች ያላአንዳች ይሉኝታ በወያኔች የተያዙ ናቸው። የአገሪቱን የአየር እና የምድር ኃይል መከላከያ የማዘዣ ማዕከሎች ከአዲስ አበባ እና ከደብረዘይት በማስወጣት ማዕከላዊ ዕዛቸውን ትግራይ ላይ እንዲሆን በማድረግ ወሣኝ የሆኑት የመከላከያ መሣሪያዎች ትግራይ ውስጥ እንዲከማቹ ተደርጓል። የከባድ ሮኬቶች መተኮሻ መንኮራኩሮች ትግራይ ውስጥ ተገንብተዋል። የአገሪቱ የመከላከያ ኃይል ከጓድ እስከ ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ድረስ ያሉት ቁልፍ የአዛዥነት፣ የመገናኛ፣ የድርጅት፣ የሎጂስቲክ ኃላፊነቶችን በሙሉ በትግሬዎች በማስያዝ የወታደራዊ ተቋሙ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴው የትግራይን መገንጠል ዕውን በሚያደርግ መልኩ ወደፊት እየተባለ ይገኛል።

በአጠቃላይ የትግራይን ግንጠላ ዕውን መሆን ሂደቱ የተመቻቸ እንዲሆን፣ በ«ሽግግር ዘመን» ተብየው «ልማት ቅድሚያ በጦርነት ለተጎዱ ክልሎች» በሚል ስም የአገሪቱ  አጠቃላይ በጀት ለትግራይ ልማት ተመድቦ ለአምስት ዓመታት ከላይ ለተጠቀሱት ተግባሮች እንዲውል መደረጉ ይታወቃል። ከሽግግር መንግሥቱ ፍጻሜ በኋላም የተዘጋጀው «ሕገመንግሥት» ተብየው የሽግግር መንግሥቱ ቻርተር ተከታይ ሆኖ በመዘጋጀቱ፣ አጠቃላይ ያለፉት ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት ሲሠራ የኖረው ከፍ ሲል የተጠቀሱትን ሁለት ግቦች ለማሟላት፣ ማለትም፦ የትግሬ-ወያኔ ትውልድ ለመቶ ዓመታት በኢትዮጵያ ሥልጣን ላይ የሚቆይበትን ሁኔታ እያረጋገጡ መጓዝ፣ ይህ የማይሆን ከሆነ ለምትገነጠለው ትግራይ ቁሣዊ፣ ቴክኒካዊ እና ኅሊናዊ መሠረት ሊሆኑ የሚችሉ የሁለንተናዊ ግንባታ ተግባሮችን በተጓዳኝ ማከናወን የሚለው በተደጋጋፊ መልኩ ሲሠራ መቆየቱ ይታወቃል።

ይህ ሁሉ ሤራ ቢጎነጎንም፣ የትግሬ-ወያኔ ባልጠበቀው መልኩ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ከሕዝቡ ኅሊና ውስጥ ከመፋቅ እና ከመደብዘዝ በተቃራኒ፣ የበለጠ እየጠነከረ መሄዱ የአደባባይ ምሥጢር ነው። ለዚህ ማረጋገጫዎች በተከታታይ በሚነሱ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች እና በተቃዋሚ ኃይሎች መበራከት ናቸው። ስለዚህ የትግሬ-ወያኔ ቡድን «ለመቶ ዓመታት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥልጣን ላይ እቆያለሁ» የሚለው ዓላማው ሊሣካ የማይችል እንደሆነ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ በ፲፱፻፺፯ (1997) ዓ.ም. ብሔራዊ ምርጫ በማረጋገጡ፣ አጠቃላይ እንቅስቃሴውን «ትግራይን ከቀሪዋ ኢትዮጵያ መገንጠል» በሚለው ሁለተኛ ግቡ ላይ እንዲያተኩር ሁኔታዎች እንዳስገደዱት ይታያል። ለዚህ የግንጠላ ዓላማው ያጸደቀው «ሕገመንግሥት» ተብየው ዋናው መሣሪያው መሆኑ ይታወቃል። አንቀፅ ፴፱(ሰላሣ ዘጠኝ) ለማንም ጥቅም ተብሎ ሣይሆን፣ የትግራይን ግንጠላ ለማሣሳካት የተቀረጸ አንቀፅ እንደሆነ ማንም ይስተዋል አይባልም። ዛሬም ቢሆን የትግሬ-ወያኔ የተመሠረተበትን ዋናውን ስሙን (ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ) ያለመቀየሩ የሚያረጋግጠው ሃቅ ትግራይን ከቀሪዋ ኢትዮጵያ መገነጠል በይደር የቆየ የማይቀር አጀንዳው መሆኑን ነው። ይህ ዕውነት እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ አንቀፅ ብቻ ትግራይን ገንጥሎ በሰላም መኖር እንደማይችል የትግሬ-ወያኔ ጠንቅቆ ያውቃል። የትግሬ-ወያኔ መሪዎች ከተጠያቂነት መዳን የሚችሉት፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የዘረፉትን ንብረት መጠቀም የሚችሉት፣ የትግራይ መገንጠል ለጊዜውም ቢሆን ዕውን ሊሆን የሚመችለው፣ በቀሪዋ ኢትዮጵያ ነገዶች መካከል መበታተን ሲፈጠር፣ ከሁሉም በላይ ዐማራ የተሰኘውን ነገድ ሌሎች ነገዶች በጠላትነት ፈርጀው እርሱን ማዳከም ሲችሉ፣ እንዲሁም «ዐማራ» ሲል የከለለውን ክልል ከውጭ አገር ጋር እንዳይገናኝ ዝግ በማድረግ ብቻውን አቁሞ ኅልውናውን ማጥፋት ሲቻል እንደሆነ ብቻ መሆኑን ይህ ቡድን አቅዶ በተግባር ሲንቀሣቀስ ቆይቷል። ለዚህም ባለፉት ዓመታት ሁሉም በሚባልበት ደረጃ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙት ነገዶች ዐማራውን በአውራ ጠላትነት ፈርጀው የጥፋት እጃቸውን እንዲያነሱበት አድርጓል።

የትግሬ-ወያኔ ምዕራባዊውን «የዐማራውን ክልል» ለም እና ድንግል መሬቶች ለሱዳን በገጸበረከት ሰጥቷል። በቀረው ምዕራባዊ ዳርቻ የትግራይን ግዛት በማስፋት ከቦ፣ ከቤንሻጉል ጉምዝ እናከጋምቤላ ክልሎች ጋር አገናኝቷል (አባሪ ካርታውን ይመልከቱ)። ከ5 ሚሊዮን የማያንስ ዐማራ ከምድረ ኢትዮጵያ አጥፍቷል። አያሌ ዐማሮች በአገር ውስጥ ሠርቶ የመኖር መብታቸውን በመገፈፋቸው ለስደት ሕይዎት ተዳርገዋል። በስደት በዓለም ዙሪያ ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ መካከል ከመቶ ፷(ስድሣ) እጁ በላይ ዐማራ መሆኑ የሚያመለክተው፣ ዐማራው በገዛ አገሩ ሠርቶ የመኖር መብቱን የተገፈፈ መሆኑን ብቻ ሣይሆን፣ ዐማራው በመጥፋት ሂደት ላይ መሆኑን የሚያሣይ ነው።

ሰሞኑን ለሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ከደረሱት እጅግ አስተማማኝ መረጃዎች መካከል፣ ወያኔ በኢትዮጵያ ፖለቲካ አናት ላይ የመቆየት ዓላማው የማይሣካ መሆኑን ተገንዝቦ፣ ወደ ሁለተኛው እና የመጨረሻ ግቡ፣ ማለትም፦ ትግራይን ለመገንጠል በከፍተኛ ሚስጢር እየሠራ መሆኑን የሚያረጋግጡ ናቸው። ይህም የትግራይ ግንጠላ ዕቅድ ለማሣካት እንዲቻል፣ ከአገር ውስጥ ተቃዋሚ ኃይል እንዳይነሣ፣ ኢትዮጵያን በሽግግር ዘመኑ ከፋፍለዋት በነበረው ፲፬(አሥራ አራት) እና ከዚያም በላይ የሆኑ የክልል ወሰኖችን የሚያመለክቱ ካርታዎችን አዘጋጅተው፣ ከየጎሣው ሰዎችን መልምለውና አደራጅተው፣ ለነዚህ ሰዎች የወታደራዊ፣ የደህንነት፣ የአደረጃጀት፣ የአመራር እና የቁጥጥር ሥራ የሚሠሩ የትግሬ-ወያኔዎች ተመድበው በከፍተኛ ሚሥጢር ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ እየተዶለተ መሆኑን አረጋግጠናል። ይህም ከ1997 የምርጫ ሽንፈታቸው ማግሥት ጀምሮ በመከናወን ላይ ያለ ተግባር እንደሆነ የመረጃ ምንጮቻን ገልፀውልናል። «ይህ አይሆንም፣ አይደረግም፣ አይታሰብም» ሊባል የማይችል እንደሆነ የወያኔ ጉዞ እና ተግባር ከጥርጣሬ ውጭ በሆነ መንገድ ያስረዳናል። ለዚህ ሤራቸው ማረጋገጫዎቹ በነባር ኢትዮጵያዊ እምነቶች መካከል እየሰራ ያለው የማጥፋት ሥራ፤ በጎጃም፣ በጎንደር፣ በአዲስ አበባ፣ በሶማሌ፣ እየተካሄዱ ያሉት የጥፋት እርምጃዎች የዚህ ዕቅድ አካሎች መሆናቸውን ልብ ሊባል ይገባዋል።

ሌላው የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን የማፈራረስ ተልዕኮው የማይቀር እና የፍጻሜው የመጨረሻ ደረጃ ላይ መድረሱን ማሣያው፣ የምዕራቡ ዓለም የመረጃ እና የስትራቴጂክ ጥናቶች ተቋም ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት አጋማሽ ላይ በ2030 እ.አ.አ. ከዓለም ካርታ ላይ ከሚጠፉ አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ይፋ ማድረጉን እናስታውሳለን። በተመሣሣይ ሁኔታ በኅዳር ወር ፪ሺህ፯ ዓ.ም. ሞስኮ ውስጥ የተካሄደ የዓለም አቀፍ ቀውሶች ጥናት ተቋም ባዘጋጀው ስብሰባ፣ በምሥራቅ አፍሪካ የሚታየውን ብጥብጥ ለዘለቄታው ለማስወገድ የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ኮንፌደሬሽን መመሥረት እንዳለበት ግፊት የሚያደርግ ጥናት ቀርቧል። የኮንፈደሬስሽኑ አባል አገሮች ጥንት እንግሊዝ «ከኢትትዮጵያ ተቆርሶ ወደ ሱዳን ይካተት» ትለው የነበረው የኤርትራ ምዕራባዊ ክፍል ወደ ሱዳን ተካልሎ ሱዳን ከሦስት እንድትከፈል፣ የኤርትራ ደጋማው ክፍል ከትግራይ ጋር ተቀላቅሎ ትግራይ ትግርኝ የተሰኘ ግዛት እንዲፈጠር፣ የአፋርኛ ተናጋሪዎች በአንድ ግዛት ተጠቃለው አንድ ግዛት እንዲሆኑ፣ በአምስቱ ዓመት የአርበኛነት ዘመን ፋሽስት ጣሊያን «ዐማራ» ብሎ ሰይሞት የነበረው ክልል አንድ የዐማራ ግዛት እንዲሆን፣ የቀሩት አካባቢዎች የፋሽስት ጣሊያንን ክፍፍል መሠረት አድርገው የየራሳቸውን ግዛቶች እንዲመሠረቱ እና በነዚህ አገሮች መካከል ኮንፌደሬሽን ይመሥረት የሚል ነው። የእነዚህ ጥናቶች ግብም ከወዲሁ ኢትዮጵያዊው የኢትዮጵያን መፍረስ አይቀሬነት እንዲለማመደውና «ድሮም ተብሎ ነበር» በማለት የአገሩን መፍረስ በፀጋ እንዲቀበል የሥነ- ልቦና ሰለባ ከወዲሁ መሠራቱን የሚያመለክቱ ናቸው።

ካርታ፦ ለወደፊቱ «የትግራይ ሪፑብሊክ» ተብሎ በትግሬ-ወያኔ የሚገነጠለው የኢትዮጵያ አካል በአረንጓዴ ቀለም የተቀለመው ነው።

የትግሬ-ወያኔ እና ዕኩይ ዓላማው ኅልው ሆነው የሚዘልቁት ኢትዮጵያውያን ሠፊውን ለቀን ጠባቡን፣ ኢትዮጵያዊነትን ትተን ጎሣዊ ማንነትን ስንላበስ፣ ዕውነትን ከድተን ከውሸት ጎራ ስንሰለፍ፣ ዘላቂውን ትተን አላቂውን እና ጠፊውን ስንይዝ፣ አኩሪውን ትተን  ነገ የሚያሳፍረውን ስንከተል፣ ለኅሊና ሳይሆን ለጥቅም ስንገዛ ነው። እስካሁን የትግሬ-ወያኔ ያለ ልጓም የጋለበን በነዚህ ምክንያቶች ብቻ ነው። አሁን ግን የትግሬ-ወያኔ አጥፍቶን ሊጠፋ ከመጨረሻው ጠርዝ ላይ ቆሟል። የመጥፋቱም ያለመጥፋቱም ጉዳይ የሚወሰነው በእኛ ብቸኛ ምርጫ ነው። ምርጫችን በኢትዮጵያዊነታችን መቀጠል ከሆነ፣ ወያኔ ያጠመደልንን የመነጣጠል መንገድ ትተን በአንድነት በመቆም ኢትዮጵያን ከመጥፋት ለመታደግ ቁርጠኛ አቋም ልንይዝ ይገባል። ቢመሽም፣ እጅግ ብንዘገይም፣ ፈጽሞ ከመቅረት ይሻላል እና እጅ ለጅ ተያይዘን አገራችን እንድናድን ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ጥሪውን ያቀርባል።

ከሁሉም በላይ የትግሬ-ወያኔ ወደ መጨረሻ እርምጃው ሲያመራ አጥፍቶ የሚጓዘው፣ ከጽንሱ ጀምሮ በአውራ ጠላትነት ፈርጆ ላለፉት ፵(አርባ) ዓመታት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሲገድለው፣ ሲያስረው፣ ሲያሰቃየው እና ሲያሳድደው የኖረውን ዐማራ እስትንፋስ ሳያቋርቋጥ ከጉሬው እንደማይገባ አውቀን፣ ከተደገሰልን ጥፋት እራሳችን መከላከል እንድንችል ከምንጊዜውም በላይ ነቅተንና ተደራጅተን ኅልውናችን ለማስጠበቅ ቁርጠኛ ሆነን እንድንቆም ሞረሽ-ወገኔ አደራ ይላል።

 

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!

ኢትዮጵያ በጀግና እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ታፍራ እና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!

የአማራ ክልል አስተዳደር ምርጫውን ተከትሎ አመጽ ይነሳል በሚል የ‹‹ፀጥታ ኃይሎችን›› እያሰለጠነ መሆኑ ተሰማ

$
0
0

• ፖሊሶች የደረጃ እድገት እንደሚደረግላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል

ethiopia_detail_mapየአማራ ክልል መስተዳደር በግንቦት 2007 ዓ.ም ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀውን አምስተኛው አገራዊ ምርጫ ተከትሎ አመጽ ከተከሰተ ለመቆጣጠር ያስችላል ያለውን ስልጠና ለክልሉ ፖሊስ፣ ለማረሚያ ቤት ፖሊስ፣ ለሚሊሻና ለመከላከያ ሰራዊት አባላት እየሰጠ መሆኑን ሰልጣኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ስልጠናውም፤ ለፖሊሶች በዞን እንዲሁም ለሚሊሻና ለፀጥታ ጉዳይ በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች እየተሰጠ መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

የስልጠናው ዋና አላማ በቀጣዩ ምርጫ ሊከሰት ይችላል ተብሎ የሚፈራውን አመጽ መቆጣጠር እንደሆነ የገለጹት የፖሊስ ምንጮች በተለይ ፖሊስና ፀጥታ ጉዳይ ከ‹‹ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ›› ጋር በመተባበር የደፈጣ ውጊያን ለመከላከል ‹‹የደፈጣ ውጊያ ስምሪት›› በሚል አጭር ስልጣና እየወሰዱ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ ይህም አገር ውስጥ አመጽ ያነሳል ተብሎ ከሚፈራው ህዝብ በተጨማሪ መሳሪያ ያነሱ ተቃዋሚዎች በምርጫው ወቅት ጦርነት ይከፍታሉ የሚል ስጋት በመኖሩ ነው ሲሉ ሰልጣኞቹ ገልጸዋል፡፡ በደብረማርቆስ ውስጥ ስልጠናውን የሚወስዱት ሰልጣኞች ማታ ማታ የተኩስ ልምምድ እንደሚያደርጉ አንድ የደብረማርቆስ ከተማ ነዋሪ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ምርጫውን ተከትሎ ይከሰታል ከተባለው አመጽና ታጣቂ ቡድኖች ያደርሱታል ተብሎ ከሚፈራው ጥቃት በተጨማሪ የጥምቀት በዓል ላይ አመጽ እንዳይነሳ መከላከል፣ ከተነሳም መቆጠጠር የስልጠናው የአጭር ጊዜ ግብ ነው ተብሏል፡፡

በስልጠናው ወቅት በተለይ ፖሊሶች ‹‹ልዩ ኃይልና ፌደራል ፖሊስ በስራችን ጣልቃ ስለሚገቡ ነጻነት የለንም፣ ፖሊስ የህዝብ ነው እየተባለ ህዝብ ግን ይጠላናል፣ በህገ መንግስቱ መሰረት የህዝብን ሰላም ማስጠበቅ ሲገባን እርምጃ እንድንወስድ ከበላይ አካል እንታዘዛለን፣ ከፖለቲካው ገለልተኛ አይደለንም›› የሚሉና ሌሎች ቅሬታዎችንና ጥያቄዎችንም አንስተዋል ተብሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ፖሊሶች በቂ ደመወዝና ዩኒፎርም አይቀርብልንም የሚል ቅሬታ እንዳቀረቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በስልጠናው ወቅትም በተለይ ፖሊሶች ጠንካራ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን መሰንዘራቸው ተከትሎ ሁሉም የክልሉ የፖሊስ አባላት አንድ የደረጃ እድገት እንደሚሰጣቸው ቃል ተገብቶላቸዋል ተብሏል፡፡ ጥር 12007 ዓ.ም የጀመረው የ‹‹ፀጥታ ኃይሎች›› ስልጠና ቅዳሜ ጥር 9/2007 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከጥር 7/- ጥር 11/2007 ዓ.ም ለሚሊሻዎች አመራሮች ተጨማሪ ስልጠና እንደሚሰጥ ተገልጾአል፡፡

በታህሳስ ወር የታቦት ማደሪያው ለባለሀብት መሰጠት የለበትም በሚል የባህርዳር ከተማ የክርስትና እምነት ተከታዮች አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ ማሰማታቸው እንዲሁም በደብረማርቆስና በሌሎች የክልሉ ከተሞች ስልጠና ላይ የነበሩ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ስልጠናውን በመቃወም ሰልፍ መውጣታቸው በ‹‹ፀጥታ ኃይሎች› ስልጠና ወቅት መወያያ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን ሁለቱ ክስተቶች የአማራ ክልል አስተዳደር በዚህ አመት አመጽ ይነሳል የሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዲገባ ምክንያት ሆነዋል ተብሏል፡፡

Election2007‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

በተከሳሽ የፓርቲ አመራሮችና በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት መካከል ያለው አቤቱታ አልተፈታም

$
0
0

Habtamu abrhayeshiwas daniel

∙በቃል የቀረበው አቤቱታ ከድምጽ ክምችት ክፍል ጠፍቷል ተብሏል

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች እና ሌሎች በተመሳሳይ መዝገብ ያሉ የሽብር ተከሳሾች በቂሊንጦ እስር ቤት አስተዳደር መካከል ያለው አቤቱታ እስካሁን እልባት ሊያገኝ አልቻለም፡፡

ዛሬ ጥር 7 ቀን 2007 ዓ.ም ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና አቶ አብርሃ ደስታ እንዲሁም አንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቅአገኘሁን ጨምሮ ሌሎች ተከሳሾች ማረሚያ ቤቱ የመብት ጥሰት እየፈጸመባቸው እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ አቤት ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በዛሬ ዕለት በጉዳዩ ላይ የማረሚያ ቤቱ አስተዳዳሪ ችሎት ቀርበው መልስ ይሰጣሉ ተብሎ ቢጠበቅም ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ቀደም ባለው ቀጠሮ ወቅት አቤቱታው በቃል ተሰምቶ በመቅረጸ ድምጽ ተቀድቶ እንደገና በጽሑፍ ተገልብጦ ከመልስ ጋር እንዲቀርብ ታዝዞ የነበር ቢሆንም ድምጹ ከፍርድ በቱ ድምጽ ክምችት ክፍል ሊገኝ ስላልቻለ በወረቀት ተገልብጦ መልስ እንዲሰጥበት ለማረሚያ ቤቱ አለመድረሱ ተገልጹዋል፡፡

በዚህ የተነሳም ፍርድ ቤቱ ለጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ችሎት ቀርቦ መልስ እንዲሰጥ ለማስቻል፣ በቀጣዩቹ ቀናት ውስጥ አቤቱታው እንደገና በጽሑፍ ለፍርድ ቤቱ እንዲቀርብ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

በተመሳሳይ በቀድሞው የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦኬሎ አኳይ የክስ መዝገብ በተከሰሱ ሰዎች ላይ የአቃቤ ህግ ምስክሮች የሰጡት ምስክርነት ከድምጽ ክምችት ክፍል ስለጠፋ እንደገና በሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ ድጋሜ ምስክሮቹ እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡

ሰማያዊ ቲሸርት የለበሱ ወጣቶች ከስላሴ በዓል ላይ ተባረሩ

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ

• ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ‹የፈራ ይመለስ› የሚል ቲሸርት አስለብሶ ሲበጠብጠኝ ሰንብቷል፡፡›› የየካ ክፍለ ከተማ ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ

• ‹‹ገዥው ፓርቲ ጥላውን የማያምንበት ደረጃ ላይ ደርሷል!›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ

semayawiዛሬ ጥር 7/2007 ዓ.ም የዓመቱን የስላሴ በዓል ለማክበር አራት ኪሎ የሚገኘው ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን የተገኙ ወጣቶች ሰማያዊ ቲሸርት በመልበሳቸው በፖሊስ እንደተባረሩ የአይን እማኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ ‹‹ያመነ፣ የተጠመቀ ይድናል!›› የሚል ሰማያዊ ቲሸርት የለበሱትን ወጣቶች ቲሸርቱን እንዲያወልቁ ሲጠይቅ ወጣቶቹ አናወልቅም በማለታቸው ከበዓሉ ማባረሩን እማኞቹ ገልጸዋል፡፡ ከተባረሩት ወጣቶች መካከል አብዛኛዎቹ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚገቡትንና የሚወጡትን አማኞች በማስተባበር ላይ እንደነበሩ የተገለጸ ሲሆን የተባረሩት ወጣቶች ይታሰሩ አይታሰሩ የታወቀ ነገር የለም፡፡

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የመጡ ከፍተኛ ኃላፊዎች ለጥምቀት በዓል ሰማያዊ ቲሸርት ያዘጋጁትን የጃንሜዳ አካባቢው የጥምቀት በዓል አስተባባሪዎች፣ ያዘጋጁት ሰማያዊ ቲሸርት በዓሉ ላይ እንዳይለበስ በተደጋጋሚ እያስጠነቀቁ እንደሚገኙ ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በፖሊሶችና በደህንነቶች ተደጋጋሚ ጫናም ለጃንሜዳ አካባቢ ወጣቶች የተዘጋጀው ሰማያዊ ቲሸርትና ‹‹ያመነ፤ የተጠመቀ ይድናል›› የሚለውን ጥቅስ በነጭ ቲሸርት እና በሌላ ጥቅስ እንድንቀይር ተገደናል ብለዋል፡፡ በአንጻሩ የፈረንሳይና ቤላ አካባቢ ወጣቶች ሰማያዊ ቲሸርቱን እንዲቀይሩ ጫና ቢደርስባቸው አንቀይርም በሚል አቋማቸው መጽናታቸው ታውቋል፡፡

በተመሳሳይ ጥር 6 የአዲስ አበባ መስሪያ ቤቶችና ወረዳዎች ኮሚኒኬሽን ኃላፊዎች አዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት ባደረጉት ስብሰባ የየካ ክፍለ ከተማ ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ፈረንሳይ ሌጋሲዮን አካባቢ ‹የፈራ ይመለስ› የሚል ሰማያዊ ቲሸርት አስለብሶ ሲበጠብጠኝ ሰንብቷል፡፡›› ሲል ሪፖርት ማቅረቡን የስብሰባው ተሳታፊዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ‹‹ደህንነት፣ ፖሊሶችና ካድሬዎች እያንዳንዱን የህዝብ እንቅስቃሴ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በማገናኘት ወቀሳ የሚያቀርቡት ህዝብ ውስጥ ብሶት እንዳለ፣ ሰማያዊም የህዝብን ብሶት እንደሚያሳማ ስለሚያውቁ፣ ከምንም በላይ ገዥው ፓርቲ የራሱን ጥላ የማያምንበት ደረጃ ላይ ስለደረሰ ነው›› ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ባነሱባቸው ጊዜያት ሁሉ ገዥው ፓርቲ ሰማያዊ ፓርቲን ‹‹የሙስሊም ፓርቲ ነው›› በሚል ሀሰተኛ ወሬ ሲያሰራጭ እንደነበርና ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በሰጠው የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ሰማያዊ ፓርቲን ሲወቅስ እንደከረመ ያስታወሱት ኃላፊው አሁንም ፓርቲውን ከእያንዳንዱ የህዝብ እንቅስቃሴ ጋር እያገናኘ ቢበረግግ አያስገርምም ብለዋል፡፡

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live