Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ግፍና አፈና ዐመጽን ይወልዳሉ! –ከያሬድ ኃይለማርያም (ብራስልስ፣ ቤልጂየም)

$
0
0

የዐመጸኛ አፍ ጥልቅ ጉድጓድ ነው (መ. ምሳሌ ም. 22፣  ቁ. 14)

ከያሬድ ኃይለማርያም

ብራስልስ፣ ቤልጂየም

ታኅሣሥ 10፣ 2007

ያሬድ ኃይለማርያም ለ7 ዓመታት ያህል ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ካውንስል ጋር አብሮ የሠራና የኖቬምበር 1 እና 2ቱን ጭፍጨፋ ተከትሎ ከሃገር ብዙ ምስጢሮችን ይዞ በመውጣት ለአውሮፓ ሕብረት ያቀረበ ነው።

ያሬድ ኃይለማርያም ለ7 ዓመታት ያህል ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ካውንስል ጋር አብሮ የሠራና የኖቬምበር 1 እማ 2ቱን ጭፍጨፋ ተከትሎ ከሃገር ብዙ ምስጢሮችን ይዞ በመውጣት ለአውሮፓ ሕብረት ያቀረበ ነው።

ሰብአዊ መበቶችን በመጣስ፣ ግፍ በመፈጸምና አፈናን በማጠናከር እደሜ የሚሸምት የአገዛዝ ሥርዓት የእያንዳንዱን ሰው መንፈሳዊና አካላዉ ጥንካሬ የማዳከም፣ ቅስምን የመስበርና ፍርሃትን የማንገስ ከፍተኛ አቅም እንዳለው ሁሉ በብሶት የሚወለዱ፣ እምቢኝ ለግፈኞች፣ እምቢኝ ለአንባገነኖች፣ እምቢኝ ለነጻነቴ የሚሉ መንፈሰ ጠንካራ ጀግኖችንና ታጋዮችንም ይወልዳል:: የአለማችን ስመ ጥርና ዘመን የማይረሳቸው የነጻነት ታጋዮች እነ ማህተመ ጋንዲ፣ ማርቲን ሉተር ኪነግ፣ ማንዴላ፣ ኡንግ ሳን ሱ ኪ እና ሌሎችም ብዙዎች የፈለቁት በብሶት ከተሞላ፣ ጭቆና ካንገሸገሸውና በአፋኝ ሥርዓት ከታመቀ ማኅበረሰቡ ጉያ ነው:: አንድን ማኅበረሰብ በአፈሙዝ፣ በሕግና በገንዘብ ኃይል ጭፍሎቆና አፍኖ ማቆየት የሚቻለውም ለተወሰነ ጊዜ ብቻ መሆኑን የእነዚህ ታጋዮች ገድልና የአለም ታሪክም ይመሰክራል:: አንድ ሕዝብ በላዩ ላይ ገዢዎች እየተፈራረቁበት ረዘም ላለ ጊዜ በአገዛዝ ሥርዓት ሥር ሊቆይ ይችል:: ይሁንና እድሜ ልክ የገዛ አፋኛ ሥርዓት ግን የለም:: ሥርዓቱም እንደ ድርጅት፣ ሹማምንቱም እንደ ሰው የጉብዝና እድሜያቸው የተወሰነ ነው:: የአፈናን ስልት በመለዋወጥና ሸምቀቆውን በማጥበቅም እድሜን ማራዘም የሚቻል ቢመስልም በተቃራኒዉ ውድቀትንም ያፋጥናል:: ግፉ እየበረታና የመብት ጥሰቱም መረን እየለቀቀ በሄደ ቁጥር የሕዝብ ትእግስት ይሟጠጣል:: ሕዝብ መቆጣት ከጀመረና ቁጣውም ወደ አደባባይ አመጽ በተቀየረ ጊዜ የግፍ አገዛዝ ወደ መቃብር፣ ግፈኞቹም ወደ ዘብጥያ እንደሚወርዱ እርቀን ሳንሄድ ባለፉት አምስትና አሥርት አመታት ውስጥ በአለም የታዩ ሕዝባዊ ነውጦችንና ያስከተሉትን መዘዝ ማጤን በቂ ነው::
9783_596573470488802_1311708396556689267_n
ትልቁ ጥያቄ በግፍ አገዛዝ ውስጥ ያለ ሕዝብ መቼ እና ብሶቱስ ምን ደረጃ ላይ ሲደርስ ነው የሚቆጣው? መቼ ነው ቁጣውንስ በየመንደሩ ከማጉረምረም አልፎ ባደባባይ የሚገልጸው? ቁጣውስ ወደ አመጽ ሊያመራው የሚችለው በምን ሁኔታ ነው? የሚለው ነው:: የሕዝብ ቁጣ ወደ አመጽ የሚለወጥበት ጊዜና ደረጃው የሚለካው በተለየ ሳይንሳዊ ቀመር ስላልሆነ መቼና በምን ሁኔታ ሊከሰት እንደሚችል እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቸግራል:: ይህ አይነቱ ሁኔታ በእያንዳንዱ ማኅበረሰቡ ባህላዊ፣ ኃይማኖታዊና ማኅበራዊ አመለካከቶችና የፖለቲካ ንቃተ ህሊና ላይ ይወሰናል:: በትንሽ በትልቁ አደባባ እየወጣና በሚሊዮን የሚገመት የመንግሥትና የሕዝብ ንብረትን እያወደመ ተቃውሞውን የሚገልጽ ሕዝብ አለ:: በሌላ መልኩም አገሩን ቢሸጡበት፣ መሬቱን ቢነጥቁት፣ ሚስቱን ቢያስጥሉት፣ ልጆቹን ቢደፍሩበት፣ ቢገድሉበት፣ ቢያስሩበትና ቢያፍኑበት፣ ቤቱን በላዩ ላይ ቢያፈርሱበት፣ ቀየውን ለቱጃሮች ሰጥተው ቢያፈናቅሉት፣ ግብር እየከፈለ ያስተማራቸውን ልጆቹንና አመራቹን ኃይል እያዋከቡ ከአገር ቢያሰድዱበትና ለባርነት ቢዳርጉት፣ ከሰው ተራ አውርደው በየጎዳናው ቢጥሉትም ‘አዬ ጉድ፣ አዬ ጉድ’ ከማለት ባለፈ ቁጣውን የማያሳይም ሕዝብ አለ:: በከፋ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ታዋቂ የነበሩት ሟቹ ጠ/ሚ መለስ ያረፉ ወቅት አስከሬናቸውን ይሳለሙ ከነበሩ ሰዎች በኑሮው እጅግ የተጎዳና የተጎሳቆለ አንድ የጎዳና ተዳዳሪ በመንግሥት የቴሌቪዥን ማሰራጫ ሃዘኑን የገለጸበት መንገድ ጥሩ ማሳያ ሊሆን ይችላል:: የአዞ እንባውን እያነባ “እኔ እኮ እሳቸውን ተማምኜ ነው ጎዳና ላይ የማድረው” ነበር ያለው::

በሳንቲም ደረጃ የዋጋ ጭማሪ ተደረገብኝ ብሎ ወደ አደባባይ እየደጋገመ የሚወጣውን የኬኒያን ሕዝብ ቁጣ ለማየት በሚያዚያ ወር 2011 (እ.ኤ.አ) የነዳጅ ዋጋ ማሻቀብን ተከትሎ የተከሰተውን የኑሮ ውድነት በመቃወም በናይኖቢ የተካሄደውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ማየት ይቻላል:: እኛ ዘንድ የነዳጅ ዋጋ ስንት ጊዜ አሻቀበ? በእያንዳንዱ የእለት ተዕለት መገልገያ ቁሳቁሶች ላይ በምን ያህል መጠንና ስንት ጊዜ የዋጋ ንረት ታየ? የቤት ኪራይ፣ የትራንስፖርት፣ የጤና አገልግሎት፣ የመድሃኒቶች እና ሌሎች መሰረታዊ አቅርቦቶች ዋጋስ በስንት እጥፍ ናረ? እኛስ ስንት ጊዜ ቁጣችንን ገለጽን? በኑሮ መማረራችንንስ በምን መልኩ ለገዢዎቻችን አሳየን? ከኑሮ ዋስትና ማጣት ባሻግር የሹመኞች ከሕግ በላይ መሆን የዜጎችን በሕገ-መንግሥቱ የተደነገጉ መሰረታዊ የፖለቲካና የሲቪል መብቶችንና ነጻነቶችንም ትርጉም አልባ ሲያደርጋቸው እያየን ምን አደረግን? ለዚህም ነው የሕዝብ ብሶትና ምሬት የት ደረጃ ላይ ሲደርስ ቁጣ ወደተቀላቀለበት ተቃውሞ ሊያመራ እንደሚችል ሳይንሳዊ በሆነ ቀመር ማረጋገጥ ወይም መገመት የማይቻለው:: ምክንያቱም ግፍና በደሉን የተሸከመው ሕዝብ ያለው የታጋሽነት ልክ፣ ሆደ ሰፊነቱ፣ አርቆ አሰተዋይነቱ፣ የተዋጠበት የፍርሃት ጥልቀት ወይም ሌሎች ስነ-ልቦናዊ ሁኔታዎች ናቸው ይህን የሚወስኑት:: በዛሬዎቹም ሆነ በትላንት ገዢዎቹ ጭካኔና የማስተዳደር ብቃት ማነስ የተነሳ ለከፋ ድህነት የተጋለጠውና በልቶ ማደር ፈተና የሆነበት የኢትዮጵያ ሕዝብ ምሬቱንም ሆነ ተማጽኖውን የሚያሰማው ለፈጣሪው ብቻ ነው:: ሲመረውም ‘ምነው ዝም አልክ? ወይ ፍረድ ወይ ውረደ’ እያለ ካምላኩ ጋር መሟገት ይቀለዋል:: ትንሽ ሲደሰትም ‘ተመስጌን ይችን አትንሳኝ’ እያለ የነገን እጣፈንታውን እያሰላሰለ ፈጣሪውን ያመሰግናል:: ስለዚህ መንግሥት በሕዝብ ላይ ያሻውን ቢያደርግም ሕዝብ የልቡን የሚወያየውም ሆነ ይግባኝ የሚለውም ከመንግስት ዘንድ ሳይሆን ከፈጣሪው ጋር ነው:: ይህ አይነቱ የኅብረተሰብ ምላሽ ገዢዎችን ያማግጣል፣ ያሻቸውን እንዲያደርጉም ያበረታታል፣ ሕዝብን እንዲንቁና እራሳቸውንም ከሕግ በላይ አድርገው እንዲያስቡ ያደርጋል::

በዚህ አይነት ማኅበረሰብ ውስጥ ትልቁ ቀውስና ፖለቲካዊ ነውጥ የሚጀምረው የገዢዎቹ መረን መልቀቅ እየበረታ፣ የሕዝቡም ክፌት እየገነፈለ ሕዝብ የሚጠብቀው የፈጣሪው ምላሽ ግን የዘገየ ዕለት ነው:: ያኔ የሕዝብ ትግስት ይሟጠጣል፣ ሰፊውም ሆድም በቂም፣ በክፌትና በጥላቻ ይሞላል፣ አርቆ አሰተዋይነቱም ወደ ግብታዊነትና ንዴት ይለወጣል፣ ፍርሃቱም ተስፋ መቁረጥ ወደሚያሰከትለው ጨለምተኝነትና ጀብደኝነት ይቀየራል:: እዛ ደረጃ ከተደረሰ በኋላ የሚሆነውን መገመት አይከብድም:: በቅርቡ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች በተለይም በቱኒዚያ፣ በግበጽ፣ በሊቢያ፣ በዩክሬንና ሌሎች አገሮች የተከሰቱት የሕዝብ ቁጣዎች ለዚህ ጥሩ ማሳያዎች ናቸው:: ባለፉት አራት አመታት ውስጥ በሕዝብ ቁጣና አመጽ ሲናወጡ የከረሙትን፣ በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመቶችን ያሰተናገዱትንና የመንግሥታትም ለዉጥ የታየባቸውን የአረብ አገራት መለስ ብለን የተመለከትን እንደሆነ አብዛኛዎቹ በቡዙ መልኩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሚገኝበት ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ሁኔታዎች እጅግ በተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኙ ናቸው:: ጥሩ የነፍስ ወከፍ ገቢ ያላቸው፣ ሕዝብ በምግብ አጦት የተነሳ በርሃብ የማይሰቃየባቸውና የማይሞትባቸው፣ እጅግ የተሻለ የእሌክትሪክ፣ የውሃ፣ የነዳጅ፣ የጤና፣ የትምህርት፣ የኢንተርኔትና ልሎችም መሰረታዊ አቀርቦቶች የተሟሉባቸው አገሮች ናቸው:: ከፖለቲካ ነጻነቱም አንጻር ብዙዎቹ ከኢትዮጵያ በተሻለ ሃሳብን የመግለጽ፣ የመደራጀት፣ ባደባባይ የመሰብሰብና ተቃውሞንም የመግለጽ ነጻነትም የሚታይባቸው ናቸው:: ይሁንና በእነዚህ አገራት ውስጥ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ የሥልጣን ባለቤት ባለመሆኑና ብለሹ በሆኑት የፖለቲካ ሥርዓቶች እጅግ ተከፍቶ የቆየ ስለነበር በቀላሉ ወደ አመጽ ሊያመራ ችሏል:: አንዳንዶቹም ዘላቂ ለሆነ ቀውስ መዳረጋቸው ይታወቃል::

በእነዚህ አገራት የሕዝብ የነጻነትና የመብት ጥያቄ የሥርዓት ለውጥን ለማምጣት ወደሚችልበት ሕዝባዊ አመጽና ኃይል ወደታከለበት ግጭት እንዲያመራ የውጪው አለም ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተ አይካድም:: ቢሆንም ዋነኛው ምክንያት ግን የተጠራቀመው የሕዝብ ክፌትና ብሶት ነው:: በእነዚህ አገሮች በተነሱት የሕዝብ አመጾችና በተከሰቱት የፖለቲካ ቀውሶች ማን አተረፈ የሚለው እራሱን የቻለ ሰፊ የመወያያ ርዕስ ነው:: ነገር ግን በግልጽ እንደሚስተዋለው የመጀመሪያዎቹ ተጠቂዎች ሕዝብን ሲያሰቃዩ፣ ሲያፍኑ፣ ሲገደሉና ሲያስገደሉ፣ ሚሊዮኖችን እያደኸዩ ሃብት ሲያካብቱ የነበሩ ሹማምንትና ዙሪያቸውን የከበቡዋቸው ባለሃብቶች ለመሆናቸው በጋዳፊና በሙባረክ እንዲሁም በዙሪያቸው የነበሩ ሰዎችን እጣ ፈንታ ማየት በቂ ነው:: ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሕዝብ ክፌትና ብሶት፣ የአፈናው ደረጃ፣ የኑሮ ውድነት፣ የመሰረታዊ አቅርቦቶች መጓደል፣ የባለሥልጣናቱ ሙሰኝነትና ከሕግ በላይ መሆን፣ የሥራ አጡ ቁጥር፣ የድኅነቱ ደረጃ፣ ተሰፋ ማጣትና ጨለምተኝነት በምንም መልኩ ቢሆን ከሌሎች በአገዛዝ ሥርዓት ውስጥ ከሚገኙ አገሮች ጋር የሚወዳደር አይደለም:: የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ከገጠሙት ክፉና አንባገነናዊ ሥርአቶች ውስጥ የወያኔን አገዛዝ የተለየና የከፋ የሚያደርገው የዘረኝነት ፖሊሲው ብቻ ሳይሆን በአገር ሃብትና ንብረት የከበሩ የንግድ ድርጀቶች ባለቤትና ከታጋይነት ወደ ሚሊየነርነት የተቀየሩ ቱጃር ባለሥልጣናትንና የጦረ አዛዦችን የያዘ ድርጅት መሆኑ ነው:: ብሶት የወለዳቸው የወያኔ ባለሥልጣናት ዛሬ በተራቸው ሕዝብን ሆድ ከማስባስ አልፈው ማቆሚያ ወደማይኖረው የእርስ በርስ ግጭት፣ አመጽ፣ ቀውስና የዘር ቁርሾ ውስጥ እንዲገባ እየጋበዙት ነው::

የኢትዮጵያ ሕዝብ የወያኔ ሥርዓት አራሱን እንዲያርቅና አገሪቱንም ከተንጠለጠለችበት የገደል አፋፍ እንዲታደግ ከሃያ ዓመታት በላይ እድል ሰጥቶታል:: ፍጹም ሰላማዊና ስልጡን በሆነ መልኩም በ1997ቱ ምርጫ የማስጠንቀቂያ ደውሉን አቃጭሏል:: ይሁንና ይህን ማስጠንቀቂያ የወያኔ ባለሥልጣናት የተረጎሙበት መንገድ ሕዝብ ማስተላለፍ ከፈለገው መልዕክት እጅቅ የራቀና በተሳሳተ መልኩ መሆኑን ለመረዳት ምርጫውን ተከትሎ የወሰዱትን የኃይል እርምጃና ከዛም ወዲህ ያሳዩትን አፈናውን በሕጎች አጠናክሮ የመቀጠል ፍላጎት ማጤን በቂ ነው:: ለሕዝብ ያላቸውን ንቀትና እብሪትም በደንብ ያመላክታል:: ከዚህ በመነሳት ከፊታችን የሚጠብቀን ምርጫ ሊኖሩት የሚችሉትን ሁለት ገጽታች መገመት ይቻላል::

  • የመጀመሪያው ወያኔ ከዚህ ቀደም እንደነበሩት ምርጫዎች ብቻውን ተወዳደሮ ወይም አጃቢ ተቃዋሚዎችን አስከትሎ ያለምንም ችግር 99% ወይም ተቀራራቢ በሆን አሃዝ ጠቅልሎ ይቀጥላል:: አለያም የተወሰኑ ግጭቶችን ባስከተሉ ተቃዉሞዎች ውስጥ አልፎ ከ 10% እስከ 20% መቀመጫን ለተወሰኑ ተቃዋሚዎች ለቆ የፖለቲካ መዘውሩን እንደያዘ ተደላድሎ ይቀጥላል::
  • ሁለተኛው ግምት ደግሞ በተቃዋሚዎች አበሮ መስራት ላይ በተመሰረት ጥንካሬና ከሕዝብ በሚገኝ ድጋፍ ምርጫው ለምክር ቤት ወንበር ሽሚያ ሳይሆን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ከአንባገነናዊ ሥርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማላቀቅ፣ ሕዝብንም የሥልጣን ባለቤት ለማድረግና እና አገሪቱንም ካንዣበበባት አደጋ ለመታደግ የሚደረግ የነጻነት ወይም ሞት ትግል ይሆናል::

በመጀመሪያው ሂደት ውስጥ የሚከሰቱት ነገሮች መሰረታዊ ለውጦችን ለማምጣት የታለሙ ሳይሆን የአገዛዝ ሥርዓቱ ያስቀመጠውን የጨዋታ ሕግ በማክበር ተቃዋሚ የሆነው የፖለቲካ ኃይልም ሆነ ሕዝቡ ሥርዓቱን በረዥም ጊዜ ሂደት እንለውጠዋለን ወይም በራሱ ጊዜ ይከስማል ወይም አራሱን በሂደት ያርቃል የሚል ተስፋ ሰንቀው እድሜውን እንዲያራዝም የሚፈቅዱበት ሁኔታ ነው:: ባጭሩ “ያለ ምንም ደም ወያኔ ይቅደም” ነው:: በዚህ አካሄድ አትራፊዎቹ ወያኔ እና በወያኔ መቆየታ ላይ ተማምነው በኢኮኖሚም፣ በጸጥታ ዘርፍም እና ሆነ በአካባቢው የፖለቲካ መረጋጋት ለማትረፍ ከሥርዓቱ ቃር የተወዳጁ የውጪ ኃይሎችና የዘመኑ ባለሃብቶች ብቻ ናቸው:: ሰፊውና ድሃው የኢትዮጵያ ሕዝብ አገሩን ለቀማኞች አስረክቦ የስቃይ ዘመኑን በየአምስት አመቱ በሚደረጉ የማደናገሪያ ምርጫውዎች እያደሰ የግፍ እንቆቆውን መጋቱን ይቀጥላል::

ይህ አይነቱ በምርጫ ስም የሚደረግ ማደናገሪያ ከቀዝቃዛው የአለም ጦርነት ማብቂያ ወዲህ በበርካታ የሦስተኛው አለም አገሮች ተደጋግሞ የሚታይ ክስተት ሆኗል:: ባለፉት አስርት አመታት እንደተስተዋለው ምርጫ አንድ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመገንባትና የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ የሚረዳ መንገድ የመሆኑን ያህል ድሃ ሕዝብን አፍኖ ለመግዛትና የአንባገነኖችንም እድሜ ለማራዘም እያገለገለ መሆኑን ነው:: በዚህ ሂደት ውስጥ ዋነኛ ተዋናዮቹ የአገዛዝ ሥርዓቶቹ ብቻ ሳይሆኑ የምዕራቡ አለም እና የአለም ከበርቴዎችም ናቸው:: የቅኝ ግዛት ታሪክ ካከተመ በርካታ አመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም አገሮችን በቅኝ ለመግዛት የምዕራቡ አለም ቆርጦ የተነሳባቸው ዋነኛ የኢኮኖሚና የፖለቲካ መንስዔዎች ዛርም እጅግ በከፋና ባፈጠጠ መልኩ ይታያሉ::

የምዕራቡ አለምና ከበርቴዎቹ የቅኝ ግዛት ፖሊሲዎቻቸውን ለማስቀጠልና ጥቅሞቻቸውንም በእነዚህ ድሃ አገሮች ላይ፣ በተለይም በአፍሪቃ አገሮች ውስጥ እንደተጠበቀ ለማቆየት እንደ አማራጭ ከወሰዱት መንገድ አንዱ ከትቢያ እያነሱ ወደ ስልጣን እንዲመጡ የረዷቸውን የጫካ ሽፍቶች በስልጣን ለማቆየት በገንዘብና በጦር መሳሪያ ከሚያደርጉላቸው ድጋፍ ባሻገር አንጻራዊ የሆነ የፖለቲካ መረጋጋትም እንዲኖር የእነዚህን አፋኝ ቡድኖች እድሜ በይስሙላ ምርጫ እንዲታጀብ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ማድረግ ነው:: ይህ አካሄድ ሁለት ግቦች አሉት:: አንዱ እነዚህ አንባገነኖች ሙሉ በሙሉ በምዕራቡ አለም ድጋፍ ነው የቆሙት ወደሚል ድምዳሜ ከተደረሰ የዳግም ቅኝ ግዛት እቅዳቸውን ከማጋለጡም በላይ የምዕራቡ አለም ከአንባገነኖችና የሰብአዊ መብቶችን በገፍ ከሚጥሱ ቡድኖች ጎን አብሮ በመቆም የደሃ አገር ሕዝቦችን በማሰቃየትና ሃብታቸውንም በመዝረፍ ተግባር ውስጥ መጠመዳቸው ፈጦ እንዳይታይ ይጋርዳል:: ሌላው ምርጫው የተጭበረበረ ቢሆንም የሕዝብ ተሳትፎ እስከታየበት ድረስ ገዢዎቹ እራሳቸውን ትክክለኛና ተቀባይነት (legitimate) ያላቸው አድርገው እንዲቆጥሩና ሕዝብም ይህን አምኖ እንዲቀበል ለማስገደድ ይረዳል:: በምርጫ ወቅት የሚታዩ ግድፈቶችም ሆኑ ያፈጠቱ ውንብድናዎች በእነዚህ ድሃ አገሮች ውስጥ እስከሆነ ድረስ የተከሰቱትና በሥልጣን ላይ ያሉት ቡድኖችም የምዕራቡ አለም ወዳጆች እስከሆኑ ድረስ ችግሮቹ የዲሞክራሲያዊ ግንባታው ሂደት አካል ተደርገው እንዲወሰዱ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጥረትና የሚዲያዎች ቅስቀሳም ይደረግበታል::

ሁለተኛው ሂደት ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ማካሄድ የሚቻለው ነጻ የፖለቲካ መድረክ፣ ነጻነት የሚሰማውና የሌሎችንም ነጻነት የሚያከብር መንግሥት፣ በነጻነት ማሰብና ሃሳቡንም በነጻነት መግለጽ የሚችል ሕዝብ፣ በነጻነት መደራጀትና መንቀሳቀስ የሚችሉ ጠንካራና ተፎካካሪ የፖለቲካ ኃይሎች እና ነጻ ተቋማት በተለይም ገለልተኛ የሆኑ ምርጫ አስፈጻሚዎችና የፍትሕ ተቋማት ሲኖሩ ብቻ ነው ከሚል እምነት ይመነጫል:: ይህ ደግሞ በወያኔ ዘመን እስካሁን ያልታየና ወደፊትም እነዚህ ነገሮች በሂደት ሊሟሉ ስለመቻላቸው ምንም አይነት የሚታዩ ምልክቶች፣ ዋስትና ወይም መተማመኛ ሊሆን የሚችል ነገር የለም:: እንዚህ ፖለቲካዊና ተቋማዊ አደረጃጀቶችና መሰረታዊ ነጻነቶች ጭርሱኑ በሌሉበት ሁኔታ ነጻ ምርጫ ሊካሄድ አይችልም:: ያለፉት አይነት ምርጫዎች ቢካሄዱም ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ መገመት ቀላል ነው:: ሰለዚህ ምርጫው ሊሆን የሚገባው በቅድሚያ የሕዝብን ነጻነት ማረጋገጥ ወይም በግዞት ውስጥ ሆነን ወያኔ የመረጠልንን ሕይወት መቀጠል ነው:: የእነሱን ቋንቋ ልጠቀምና ባጭሩ “ሃርነት ወይስ ባርነት”::

ይህ የሁለተኛው ሂደት በሕዝብ እምቢተኝነት ላይ የተመሰረተና ፍጹም ሰላማዊ በሆነ የትግል ሂደት ሊመጣ የሚችል ስኬት ነው:: ብዙዎች በሕዝብ እምቢተኝነት ላይ የተመሰረተን ሰላማዊ ትግል ከምርጫ ውድድር ጋር ሲያምታቱት ይሰታዋል::  በአገሪቱ ውስጥ ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች አለመሟላት ወይም በነጻነት የመደራጀት፣ የመሰብሰብ፣ ሃሳብን የመግለጽና ተቃውሞ የማድረግ መብቶችና ነጻነቶች አለመኖርን ለሰላማዊው ትግል ማክተም እንደ አስረጂነት ያቀርቡታል:: ይህ እጅግ የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው:: የእነዚህ ሁኔታዎች አለመሟላት የሚያሳየው በምርጫ ሂደት ተወዳድሮ ሥልጣን መያዝ የሚቻልበት እድል አለመኖሩን በቻ ነው:: እነዚህ ነጻነቶች በተከበሩበትና ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችሉ የተወሰኑ ነገሮች እንኳን ከተሟሉ ሂደቱ ሰላማዊ ትግል መሆኑ ቀርቶ በፓርቲዎች መካከል የሚደረግ ውድድር ነው የሚሆነው:: በአሜሪካም ሆነ በሌሎች ዲሞከራሲያዊ ሥርዓት በጎለበተባቸው አገሮች ፓርቲዎች ለሥልጣን ይወዳደራሉ እንጂ ሰላማዊ ትግል ውጥስ አይደለም ያሉት:: ብዙዎቹ ይህን የትግል ምዕራፍ ከዘጉ ዘመናቶች ተቆጥረዋል:: ሰላማዊ ትግል የሚካሄደው እነዚህ ነጻነቶች ፈጽሞ በሌሉበት፣ አፈና እና ጭቆና በተንሰራፋበት የአገዛዝ ሥርዓት ውስጥ ነው:: ትግሉም ጠመንጃ ያነገበና በኃይል ሕዝብን በሚደፈጥጥ አካል እና በልበ ሙሉነትና ከፍ ባለ የመንፈስ ልዕልና ተሰባስበው ሕዝብንና አገራዊ ዕራእያቸውን ጋሻ በማድረግ ያለ ነፍጥ ሥርዓቱን በሚያርበደቡዱ የሰላም መልዕክተኞች መካከል ነው:: አንደኛው ወገን ይገድላል፣ ያስራል፣ ያሰቃያል:: ሌላኛው ወገን እየሞተ፣ እየታሰረ፣ እየተደበደበና እየተዋከበም ስለ ነጻነት፣ ስለ ፍትሕ፣ ስለ እኩልነት፣ ስለ ፍቅር፣ ስለ ሰላምና ስለ ሕግ የበላይነት በአደባባይ ይዘምራል፣ ይሰብካል፣ ሕዝብን ያደራጃል፣ ይታገላል::

ከወያኔ የአገዛዝ ሥርዓት ለመላቀቅ በ1997ቱ ምርጫ ወቅት ታይቶ የነበረው የሕዝብ ተነሳሽነትና የተጀመረው ሰላማዊ ትግል ሥርዓቱ በወሰደው የጭቃኔ እርምጃ ቢቀለበስም በአገሪቱ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ትቶት ያለፋቸው በርካታ ነገሮች አሉ:: ከዚህ ሂደት ትምህርት በመውሰድ የተጀመረውን ሰላማዊ ትግል ለመቀጠል በአገር ውስጥ ያሉ የፖለቲካ ባርቲዎች እየከፈሉት ያሉት መስዋትነት ሊበረታታና ሊደገፍ የሚገባው ነው:: በተለይም የሰማያዊ ፓርቲ አባላት፣ ደጋፊዎችና አመራሮች እንዲሁም የዘጠኙ ፓርቲዎች ጥምረት በመባል የሚጠሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያሳዩ ያሉት እንቅስቃሴና ከሥርዓቱ ጋር የገጠሙት የእምቢተኝነት ግብግብ ሰላማዊ ትግልን በኢትዮጵያ ውስጥ ማካሄድ እንደሚቻል ብቻ ሳይሆን መጀመሩንም ያረጋግጣል:: ሕግን ማክበርና በሕግ የበላይነት ማመን ከእያንዳንዱ ዜጋ ይጠበቃል:: ግድታም ነው:: ይሁንና ዜጎች በዚህ ግዴታ የሚወሰኑት እያንዳንዱ ሕግ የሕገ-መንግሥቱን የበላይነት እስካልጣሰና በውስጡም የተደነገጉትን መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ባረጋገጠ መልኩ እስከ ተደነገገና በአግባቡም እስከ ተተገበረ ድረስ ብቻ ነው:: ልክ እንደ ደቡብ አፍሪቃው አፓርታይድ ሕግን የማፈኛ መሳሪያ አድርጎ በሚጠቀም ሥርዓት ውስጥ የሚደረግ ሰላማዊ ትግልና ሕዝባዊ እምቢተኝነት የዜጎችን መሰረታዊ ነጻነቶችን ለሚያጠቡ ወይም ጭርሱኑ ለሚያግዱ ሕጎች፣ ደንቦችንና መመሪያውችን አለመገዛትንም ይጨምራል:: በአገር ውስጥ ያለውም ሆነ ከአግር ውጭ ያለው የአገሩ ጉዳይ የሚያሳስበው ኢትዮጵያዊ ለእነዚህ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ብዙ መከራዎችን እየተቀበሉ አንባገነናዊ ሥርዓትን ታሪክ አድርገው ለማስቀረት ከሚታገሉ መንፈሰ ጠንካራ ኢትዮጰያዊያን ጎን በመቆም ትግሉ እንዳይደናቀፍና አገሪቱም አሰከፊ ወደ ሆነ ደም አፋሳሽ ሁኔታ እንዳታመራ ድጋፍ ሊያደርግላቸው ይገባል::

አንባገነናዊ ሥርዓትን ታሪክ አድርገን ለማስቀረት ከሰላማዊ ታጋዮቹ ጎን እንቁም!

በቸር እንሰንብት!

ያሬድ ኃይለማርያም


በ44 ማዞሪያ ለገዳዲ 4536 ቤቶች ሕገወጥናቸው ተብሎ ሊፈርሱ ነው * የአካባቢው ነዋሪ ‘መሄጃ የሌለን የሃገር ውስጥ ስደተኛ ሆነናል”እያለ ነው

$
0
0

44 mazoria legedadi
(ዘ-ሐበሻ) “በ44 ማዞሪያ ለገዳዲ የሚባል ቦታ ላይ ድንጋይ ፈልጠን ከሠል ተሸክመን ቀን ሥራ ሠርተን ለአንገት ማሥገቢያ የሠራናትን ጎጆ ከስሯ ልትነቀል ታህሳስ 14/2007ን በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች” ሲሉ አባወራዎች ለዘ-ሐበሻ ብሶታቸውን ገለጹ::

“እኛ መሠደጃ የሌለን ኢትዮጵያዊ ሆነን ኢትዮጵያዊ ያልሆነው ከርታታዎች የት መኖር እንደምንችል የማናቅ ጠይቀን መልስ ያጣን ስለሆነ የሚችል ወገን ይርዳን” ሲሉ ጥሪያቸውን ያቀረቡት አባወራዎች መንግስት ካለምንም ምትክ ቤታቸውን ሊያፈርስ በመሆኑ የት እንደሚገቡ እንደጨነቃቸው አስታውቀዋል::

በዚሁ አካባቢ እንዲፈርሱ በቀለም ምልክት የተደረገባቸው ቤቶች ቁጥር 4 ሺህ 536 እንደሆነ ያስታወቁት እነዚሁ የአካባቢው ነዋሪዎች ታህሳስ 14 ቀን 2007 ዓ.ምን እየተጠባበቁ መሆናቸውን አስታወቀዋል:: ከነዚህ 4536 ቤቶች ውስጥ ታህሳስ 13 ቀን 2007 ተጨማሪ 2000 ያህሉ ይፈርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል::

መንግስት ካለምንም ምትክ ቤታቸውን ካፈረሰባቸው መሄጃ የሚያጡት እነዚሁ ወገኖች በቀጣይ ምን ለማድረግ እንዳሰቡ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ አስታውቀዋል:: ዘ-ሐበሻ የአካባቢውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረገችው ጥረት አልተሳካም::

Hiber Radio: ኢሳያስ አፈወርቂ ስለሂሊኮፕተር አብራሪዎቹ ሊናገሩ ነው ስለመባሉ…የሳዑዲ ፖሊሶች ከኢትዮጵያውያን ጋር ስለመታኮሳቸው…እና ሌሎችም

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 19 ቀን 2007 ፕሮግራም

< …የዘንድሮ ምርጫም እንደከዚህ ቀደሙ የገዢው ፓርቲ መጫወቻ ቅርጫ ለመሆን እንኳን ያልቻለ ነው። …የተቃዋሚው ሀይል ለምን አትተባበሩም ሲባል አንዱ አንዱን ቡዳው እሱ ነው ቡዳው እሱ ነው ይባባላል ዛሬም ካለፈው ስህተት ተምሮ መፍትሄ አላገኘም…ከስራ ወጥተሃል የሚለውን ላይ ግን>

ዶ/ር መረራ ጉዲና የወቅቱ የመድረክ የውጭ ጉዳይ ሀላፊ የወቅቱን የተቃዋሚዎች ቁመናና በመጪው ምርጫ ጉዳይ በተመለከተ ከህብር ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ጠቅሰዋል (ሙሉውን ያዳምጡ)

አቶ በላይ ፈቃዱ የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ለመገናኛ ብዙሃን ከሰጡት መግለጫ የተወሰደ ሙሉውን ያዳምጡት)

<<…ኢትዮጵያና ኤርትራ ጋዜጠኞችን በማሰር ከአፍሪካ ግንባር ቀደም የፕሬስ ጠላቶች ናቸው…>>

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

  • ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ አገራቸው ዝምታ ስለመረጠችበት ሔሊኮፕተር ይዘው ኤርትራ ስለገቡት ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጠዊ መግለጫ ይናገራሉ ተብሎ ይጠበቃል
  • አንድነት ትብብሩን ጨምሮ ከሌሎቹም ጋር ለመስራት አጀንዳ ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ ነው
  • ለተቃዋሚዎች ተባብሮ ለመቆም ጊዜው አረፈደም ይላል
  • በባህር ዳይ የተገደለው እንግሊዛዊ አሟሟት ጉዳይ እያነጋገረ ነው
  • የዘጠኙ ፓርቲዎች ትብብር ሁለተኛ ዙር ሕዝባዊ ተቃውሞን ሕዝቡን አስተባብሬ እቀጥላለሁ አለ
  • የሳውዲ ፖሊሶች እጽ አዘዋወሩ ካሏቸ ኢትዮጵያኖች ጋር የተኩስ ልውውጥ አደረጉ
  • ሰሜን ኮሪያ ለአገሯ የኢንተርኔትና ስል መስተጓጎል የአሜሪካ እጅ አለበት አለች

“የባህር ዳር መስዋዕትነት የማይቀረዉ ድል ዋስትና ነዉ”–ግንቦት 7 ንቅናቄ

$
0
0

Ginbot-7-Top-logo_4
ወያኔ በየአመቱ ህዳር ወር መጨረሻ ላይ የኢትዮጵያን ብሄር ብረሰቦች ሰብስቦ ዘፈን የሚያስዘፍንበትን በዐል ሲያከብር በተደጋጋሚ ከሚያሳማቸዉ መፈክሮች አንዱ የብሄር ብሄረሰቦች መብትና እኩልነት በህገመንግስታችን ተከበረ የሚል እጅግ በጣም አሳሳች የሆነ መፈክር ነዉ። በእርግጥም ወያኔ ለይስሙላ ወረቀት ላይ ያሰፈረዉ ህገ መንግስት መግቢያዉ ላይ “እኛ የኢትዮጵያ ብሄሮች፤ ብህረሰቦች፤ ህዝቦች በነጻ ፍላጎታችን የህግ የበላይነትና በራሳችን ፍላጎት ላይ የተመሰረተ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ በጋራ ለመገንባት ቆርጠን ተነስተናል” ይላል። መቼም ይህ ምንም በማያሻማ መልኩ ቁልጭ ብሎ የተቀመጠ ህገ መንግስታዊ አንቀጽ ሌላ ትርጉም ካልሰጡት በቀር የአማራንም ህዝብ ያጠቃልላል የሚል ሙሉ እምነት አለን። በዚህ ደግሞ የአማራን ክልል የማስተዳድረዉ እኔ ነኝ ባዩ ባዕዴንም የሚስማማ ይመስለናል። በተግባር ሲታይ ግን ይህ የወያኔ ህገ መንግስት ላይ ህዝብና መንግስት የሚተዳደሩበት ህግ ቀርቶ ህገ አራዊት እንኳን አይመስልም። ምክንያቱም በህገ አራዊት አሰራር ተመሳሳይ ዝሪያ ያላቸዉና በአ ያላቸዉ የዱር አራዊት ይከባበራሉ እንጂ አንዱ ሌላዉን አያጠፋም። ለምሳሌ አንበሳና አንበሳ ይረዳዳሉ ወይም አብረዉ አደን ይወጣሉ እንጂ እርስ በርስ አይተላለቁም፤ ነብርና አንበሳም ቢሆኑ በተገናኙ ቁጥር ተከባብረዉ ይተላለፋሉ እንጂ አንደ ወያኔ ብጤያቸዉን ባዩ ቁጥር አያጠቁም ወይም አይገድሉም።
ginbot 7
ወረቀት ላይ የሰፈረዉን የወያኔ ህገ መንግስት የተመለከተ ሰዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዜጎች መብታቸዉና ነጻነታቸዉ ተከብሮ የሚኖሩ ሊመስለዉ ይችላል። በእርግጥም ይመስላል። ምክንያቱም የወያኔ ህገ መንግስት ችግሩ አጻጻፉ ላይ ወይም ይዘቱ ላይ ሳይሆን በተግባር አተራጓጎሙ ላይ ነዉ። በ1987 ዓም የፀደቀዉ የወያኔ ህገ መንግስት በተግባር ሲታይ ብሄሮች፤ ብህረሰቦችና ህዝቦች የሚለዉ ቦታ ደብዛዉ ጠፍቶ ሁሉም ነገር ወያኔ ወይም ህወሓት በሚለዉ ቃል ተተክቷል፤ ወይም ሁሉም የአገራችን ብሄር ብሄረሰቦች ተጨፍለቀዉ የትግራይ ልህቃን ወይም የህወሓት ሎሌዎችና ተላላኪዎች ሆነዋል። ለዚህ ነዉ አገራችን ኢትዮጵያ ወያኔ ያሰኘዉን የሚያዝባት የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ አንገቱን ደፍቶ የሚታዘዝባት አገር የሆነችዉ።

ሌላዉ ወያኔ ህገ መንግስቱ ዉስጥ አስፍሮ በየቀኑ እንደቤቱ ዉስጥ ምንጣፍ ከሚረግጣቸዉ ህገ መንግስታዊ አንቀጾች ዉስጥ አንዱ አንቀጽ 30 ንዑስ አንቀጽ አንድ ነዉ። ይህ አንቀጽ ማንኛዉም ሰዉ ከሌሎች ጋር በመሆን መሳሪያ ሳይዝ በሠላም የመሰብሰብና ሠላማዊ ሠልፍ የማድረግ ነጻነትና አቤቱታ የማቅረብ ሙሉ መብት አለዉ ይላል። ሆኖም የዚህን አንቀጽ ሙሉ ቃል ከወያኔ የየቀኑ አረመኔነት ጋር ስናነጻጽር አንቀጹ የተጻፈበትን ወረቀት ያክል እንኳን ክብደት የለዉም። ይህንን ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ሠላማዊ ሠልፍ ባደረገባቸዉ ቦታዎች ሁሉ ወያኔ በተከታታይ በወሰዳቸዉ አረመኔያዊ እርምጃዎችና በፈጸማቸዉ ሰቆቃዎች ተመልክተናል። ለምሳሌ ባለፈዉ አመት አምቦ ዉስጥ አሁን ከሰሞኑ ደግሞ ባህርዳር ዉስጥ ህገ መንግስታዊ መብታቸዉን ተጠቅመዉ ጥያቀያቸዉን ሠላማዊ ሰልፍ በማድረግ ያቀረቡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ህፃናት፤ ወጣቶች፤ አዋቅዎች ወንዶችና ሴቶች በአግዓዚ ነብሰ ገዳዮች ጥይት ተጨፍጭፈዋል።

ወያኔ በተደጋጋሚ ሠላም … ሠላም እያለ በአፉ ይናገር አንጂ ወያኔን ከሰላም ጋር የሚያገናኘዉም ሆነ ወያኔ ስለ ሰለም የሚያዉቀዉ ምንም ነገር የለም። እዉነቱን ለመናገር ኢትዮጵያ ዉስጥ ሠላማዊ ሠልፈኞችን የሚገድል፤ ሠላለማዊ ዜጋን አስሮ የሚደበድብና የሠላም መንገዶችን ሁሉ ቅርቅር አድረጎ የዘጋዉ ወያኔ ብቻ ነዉ። ሌላዉ ቀርቶ ወያኔ የሚያስበዉ፤ የሚያቅደዉና ዕቅዱን ወደ ተግባር የሚለዉጠዉ ከህዝብ ፈቃድና ፍላጎት ዉጭ ስለሆነ ልማት ብሎ የሚጀምራቸዉ ፕሮጀክቶች እንኳን የህዝብን ሠላም የሚያናጉና የሠላማዊ ዜጎችን ህይወት የሚቀጥፉ ጅምሮች ናቸዉ። ከሰሞኑ ደግሞ ባህር ዳር ዉስጥ እየታየ ያለዉ ህዝባዊ ቁጣ የዚሁ ወያኔ ልማት እያለ የቀሰቀሰዉ ህዝባዊ እሳት ዉጤት ነዉ።

ወያኔ እራሱን ልማታዊ መንግስት እያለ እየጠራ በሚወስዳቸዉ እርምጃዎች ሁሉ ከህዝብ ጋር መጋጨት ከጀመረ አመታት ተቆጥረዋል። ደቡብ ኦሞ ዉስጥ ሙርሲዎች በልማት ስም ከመሬታቸዉ ተፈናቅለዋል፤ አንፈናቅለም ብለዉ የተፋጠጡት ደግሞ በግፍ ተጨፍጭፈዋል። ታሪካዊዉ ዋልድባ ገዳም ዉስጥ ገዳም አለም በቃኝ ያሉ ሰዎች መኖሪያ አንጂ የእርሻ ቦታ አይደለም ብለዉ የተናገሩ መነኮሳት ቆባቸዉን አንደደፉ በቆመጥና በሰደፍ ተደብድበዋል። ጋምቤላና አፋር ዉስጥም በልማት ስም ከመሬታችን አታፈናቅሉን ብለዉ አቤቱታ ያቀረቡ ገበሬዎች ታስረዋል፤ ተግዘዋል ተገድለዋል። ለመሆኑ ወያኔ ልማት ብሎ አንድ ፕሮጀክት በጀመረ ቁጥር ህዝብን የሚያግዝና የሚገድል ከሆነ ልማቱ የሚታቀደዉ ለማነዉ? በልማቱስ ተጠቃሚ የሚሆነዉ ማነዉ?

በያዝነዉ ታህሳስ ወር መግቢያ ላይ ባህር ዳር ዉስጥ የአራት ሰላማዊ ዜጎችን ህይወት የቀጠፈዉና አለም በቃኝ ብለዉ ለፈጣሪያቸዉ ያደሩትን መነኩሴ ጨምሮ ለአያሌ ሠላማዊ ዜጎች መቁሰልና መታሰር ምክንያት የሆነዉ ይሄዉ ወያኔ በልማት ስም የጀመረዉና የአካባቢዉን ህዝብ ፍላጎት ያላካተተዉ የወያኔ ፀረ ህዝብና ፀረ አገር እርምጃ ነዉ። በእርግጥም አሁንም ድረስ ያልበረደዉ የባህር ዳሩ ህዝባዊ ተቃዉሞ የተቀሰቀሰዉ ወያኔ የባህር ዳርና የአካባቢዉ ህብረተሰብ የጥምቀት በዐል የሚያከብርበትንና የቤ/ክርስቲያን ንብረት የሆነዉን የቅዱስ ታቦት ማደሪያ ቦታ መንገድና ሱቅ እሰራለሁ ብሎ ማፈራረስ በመጀመሩ ነዉ።

ይህ በልማት ስም ሐይማኖታዊ የማመለኪያ ቦታን የማፈራረስና የቤ/ክርስቲያንን መሬት የመቀማት ሴራ የተዉጠነጠነዉ በወያኔ ቢሆንም የወያኔ ተላላኪ በመሆን ይህንን ከፍተኛ ወንጀል በገዛ ወገኖቹና ለጥቅሙ ቆሜያለሁ በሚለዉ ህብረተሰብ ላይ የሚያሰፈጸመዉ ግን ባዕዴን ነዉ። ባዕዴን ከዚህ ቀደምም በተከታታይ እንደታየዉ አማራዉ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በግፍ ሲባረርና ሲፈናቀል አፉን ዘግቶ የተመለከተና የአማራን ህዝብ ጥቅምና ፍላጎት ለወያኔ አሳልፎ የሰጠ ከሃዲ ድርጅት ነዉ። ባዕዴን ነኝ ብሎ እንደሚናገረዉ በእርግጥም ለአማራ ህዝብ መብትና ነጻነት መከበር የቆመ ድርጅት ቢሆን ኖሮ የለየለት የአማራ ህዝብ ጠላት የሆነዉ ህወሓት አያገባዉ ገብቶ በአማራ ህዝብ ጉዳይ ላይ ሲፈተፍት ዝም ብሎ አይመለከትም ነበር።

ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች የኢትዮጵያን ህዝብ ታሪክና አንድነት ብቻ ሳይሆን ባህሉን ፤ወጉንና ሐይማኖቱን ጭምር እንዳልነበረ ለማድረግ ያላደረጉት ነገር የለም። የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤ/ክኢርሰቲያን ጳጳስ አንስተዉ ቅዱስ መንበራቸዉን እጁ በደም ለተጨማለቀ ካድሬ በመስጠት ጥንታዊት ቤ/ክርስቲያናችንን ለሁለት አንድትከፈል አድርገዋል። ይህ ሁሉ አልበቃ ብሏቸዉ ከሰሞኑ ባህርዳር ዉስጥ ህዝብ ጥምቀተ በዐል የሚያከብርበትንና የቅዱስ ታቦት ማደሪያ የሆነዉን ቦታ ከቤ/ክርስቲያን ቀምተዉ የንግድ ቦታ ለማድረግ ሞክረዋል። የእስልምና እምነት ተከታዮችን በተመለከተም ህጋዊዉን መጂሊስ አፍርሰዉ በእነሱ ፍላጎት ብቻ የሚመራ አሻንጉሊት መጂሊስ በማቋቋማቸዉ ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር የፈጠሩት ግጭት ዛሬም ድረስ እንደተቀጣጠለ ነዉ።

የወያኔ ነብሰ ገዳዮች አዲስ አበባ፤ አምቦ፤ ደቡብ ኦሞ፤ ጋምቤላ፤ አፋርና አሁን በቅርቡ ደግሞ ባ/ህርዳር ዉስጥ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የፈጸሙት አረመኔያዊ ጭፍጨፋ እነዚህ ሰዎች ስራቸዉ አገር መምራት ነዉ ወይስ ህዝበን እያደኑ መግደል ነዉ የሚያሰኝ ነዉ። በእርግጥም ወያኔ እስከዛሬ የገደላቸዉን ሰዎችና ሰዎቹን የገደለበትን ምክንያት ስንመለከት የወያኔ የሙሉ ግዜ ስራ አገር መምራት ሳይሆን ህዝብን ምክንያት እየፈከገ መጨፍጨፍ መሆኑን ያረጋግጥልናል። በተለይ በቅርቡ ባህርዳር ዉስጥ አለም በቃኝ ብለዉ ገዳም የገቡትን መነኩሴ በጥይት መትተዉ ማቁሰላቸዉን ስንመለከት ወያኔዎች የገነቡትን ዘረኛ ስርዐት ዕድሜ ለማራዘም ምንም ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይሉ በግልጽ ያመለክታል።

አለማችን ዛሬም ብዙ ጨቋኝ መሪዎች የሚኖሩባት የአምባገነኖች መድረክ ናት፤ ሆኖም ህዝብ በተቃወማቸዉና በሠላማዊ ሠልፍ ቁጥዉን በገለጸ ቁጥር እንደ ወያኔ ያለ ምንም ማመንታት ሀዝብን በጥይት የሚጨፈጭፍ አረመኔያዊ አገዛዝ የለም። እዚህ ላይ አንድ ፍጹም ግራ የሚያጋባ ነገር አለ፤ እሱም ወያኔ ሠላማዊ ሰለፍኞችን በጥይት የሚጨፈጭፈዉ ሆን ብሎ ህዝብን የሚያስቆጡና የሚያነሳሱ ፀር ህዝብና ፀረ አገር እርምጃዎችን እየወሰደ ነዉ። ለምሳሌ ብዙዎቹን የወያኔ ጭፍጨፋዎች ትተን ሰሞኑን ባህርዳር ላይ የደረሰዉን እልቂት ብቻ ብንመለከት ህዝባዊ ቁጣዉ የተቀሰቀሰዉ ወያኔ ካልጠፋ ቦታ የቅዱስ ታቦት ማደሪያ የሆነዉን ቦታ አፍርሶ የሸቀጣ ሸቀጥ መሸጯ ቦታ ለማድረግ በመሞከሩ ነዉ።

የኢትዮጵያ ህዝብ ሀይማኖቱ ሲነካ ወይም ሀይማኖታዊ ስርዐቱና ልምዱ ጣልቃ ሲገባባቸዉ እጅግ በጣም የሚቆጣና ተኝቶ የማያድር ህዝብ ነዉ። ለምሳሌ የኢትዮጵያ ህዝብ ቤ/ክርስቲያኑ አላግባብ ከፈረሰበትና ጥምቀት፤ ገና፤ ፋሲካ፤ ቡሄ፤ ቅዱስ ዮሐንስና ደመራን የመሳሰሉ ሀይማኖታዊ ስርዐቶቹንና ልምዶቹን በለመደበት ግዜና ቦታ እንዳያከብር ከተከለከለ፤ በከልካዮቹ ላይ መነሳት ብቻ ሳይሆን እነሱን ከማጥፋት የማይመለስ ህዝብ ነዉ። ዛሬ አገር ቤትም ሆነ በዉጭ አገሮች የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ አይኖቹን ወደ ባህር ዳር ያዞረዉና እኛም ዉቧ የባህርዳር ከተማ የወያኔ መጨረሻ የተጀመረባት ከተማ ናት ብለን አፋችንን ሞልተን የምንናገረዉ ይህንን ስለምንረዳ ነዉ።

የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔን ግፍና መከራ ከ23 አመታት በላይ ተሸክሞ ኖሯል። በእነዚህ ሃያ ሦስት አመታት ዉስጥ ሠላማዊ ኢትዮጵያዉያን በየመንገዱና በየአደባባዩ እንደ ዱር እንስሳ እየታደኑ ተገድለዋል። አዲስ አበባ፤ አምቦ፤ አዋሳ፤ደቡብ ኦሞ፤ አፋር፤ ጋምቤላ፤ አርሲ ገደብ አሳሳና ኮፈሌ ዉስጥ አሁን ከሰሞኑ ደግሞ ባህር ዳር ዉስጥ የንጹህ ኢትዮጵያዉያን ደም በግፍ እንደ ጎርፍ ሲፈስ ተመለክተናል። ወያኔንና ዘረኛ ስርዐቱን አስወግደን ኢትዮጵያን የህዝቦቿ አገር ካላደርግናት በቀር ወያኔ ስራዉ መግደል ነዉና እሱ እየገደለ እኛም የእያንዳንዳችን ተራ እስኪደርስ ድረስ ወያኔ የገደለዉን እየቀበርን መኖራችን የማይቀር ነዉ። የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ያለህ አማራጭ አንድ ብቻ ነዉ፤ እሱም ሁሌ እየሞትክና እየቀበርክ ከምትኖር ከወያኔ ጋር ፉት ለፊት ተጋፍጠህ እንዳባቶችህ የክብር ሞት ሙትና ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህ ህይወት ሁንላቸዉ። አንተ በአንድነት ተነስተህ ፊትህን ወደ ወያኔ ካዞርክ ወያኔ እንደ ጉም በንኖ የሚጠፋ ገለባ ነዉ። ወያኔ እየረገጠ የሚገዛህና የሚገድልህ አንተኑ እንደ ሀይል በመጠቀም ነዉና ለወያኔ አልገዛም በል። ከሁሉም በላይ ደግሞ በዚህ በያዝነዉ የሞትና የሽረት አመት ወያኔን ለማስወገድ ከዉጭም ከዉስጥም በሚደረገዉ ትግል ዉስጥ ድርሻህን ተወጣ። ድል ምንግዜም ያንተ ነዉና . . . . አይዞህ፤ በርታ ዝመት!

የህወሃት በዓል ሳሞራ፣ አባዱላ፣ ንዋይ ደበበና ሰራዊት ክፍል1

$
0
0

የህወሃት በዓል ሳሞራ፣ አባዱላ፣ ንዋይ ደበበና ሰራዊት ክፍል 1
ሰሞኑን የ40ኛውን አመት የህውሃት ምስረታን በማስመልከት ብዙ የኪነጥበብ ሰዎች እና ጋዜጠኞች ወደ ትግራይ ክልል በማምራት የወያኔን የትግል ታሪካዊ ስፍራዎችን ሲጎበኙ ከርመዋል:: ከጉብኝቱም በኋላ ብዙ የተለያዩ አስተያየቶችንም ሰጥተዋል ተብሎ አንብቤያለሁ:: እስቲ አንዳንዶቹ ያሉትን እንይ
-“የትግራይ ሕዝብ በፍቅር ሊገድለን ነው” ያለው አርቲስት አበበ ባልቻ ነው፡፡
-የደራሲያን ማኅበር ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው በለጠ በበኩላቸው “ያየነው ነገር ከነገራችሁንና ከጻፋችሁት በላይ ነው፡፡ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሊመለከታቸው የሚገቡ ብርቅዬ ፍፃሜ የያዙ ዋሻዎች ናቸው:: ይኼ ታሪክ የትግራይ ሕዝብ ታሪክ ነው አላችሁት? እንኳን የትግራይ ሕዝብ ታሪክ ማለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ ማለትም ያንሰዋል፡፡ የመላ አፍሪካ ታሪክ ነው፡፡ መቀመጥም ያለበት እዚሁ ተወሽቆ ሳይሆን የአፍሪካ ኅብረት በሚገኝበት ሥፍራ ከኔልሰን ማንዴላ ጎን ነው፡፡ ይኼ ታሪክ ከእሱም በላይ ነው” ብለዋል፡፡
– አርቲስት ታምሩ ብርሃኑ በተሳታፊዎች ከፍተኛ የድጋፍ ጭብጨባ የተደረገለት ይሄን ሲል ነበር “እስካሁን የምንሰማው ትግራይ ለምታለች፣ ተለውጣለች ሲባል ነው፡፡ ስንሰማው የኖርነውና አሁን በዓይናችን ያየነው ግን ለየቅል ነው፡፡ ሰው ሠራሽ ሐይቅ ያየነው ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ሕዝብ የተሠራ ነው፡፡ ተራራ እየፈነቀለ የሚሠራውን ተመልክተናል፡፡ የኑሮው ሁኔታ ግን ድሮ እንደነበረ ነው አልተሻሻለም፡፡ ይህንን በእውነት ልታስቡበት ይገባል፡፡ ይህንን ሁሉ መስዋዕትነት የከፈለ ሕዝብ ልጆቹን ለመስዋዕትነት መርቆ የሸኘ ሕዝብ አልተካሰም፡፡ አሁንም እኔ የምለው አስቡበት ነው” በማለት አላበቃም፡፡ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተዘዋውሮ የተመለከተው የልማት አማራጭ መንገዶች በዚህ ክልል ተግባራዊ የማይሆኑበት ምክንያት “ምንድነው?” ሲል ጠይቋል፡፡ ደጋግሞ ባለሥልጣናቱ እንዲያስቡበትም ተማፅኗል፡፡ የሚወራው ሌላ እየሆነ ያለው ሌላ”
ይህ ሰው ረሳው የትግራይ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ምንም እንዳላገኘ ረሳው እንዴ?
-በመጨረሻም “የወያኔ ህወሃት ታጋዮች ምርጥ የኢትዮጵያ ጀግኖች መሆናቸውን አይተን አረጋግጠናል” በማለት፣ ሰማዕታቱ ትተውት ያለፉት ንፁህ ታሪክ ሳይበረዝና ሳይከለስ ለሕዝብ ለማሳወቅ በየሙያቸው እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል::
ይህንን ሲናገሩና ለተከታታይ ቀናት ጉብኝቱን ሲያደርጉ በነባር የሕውሓት መሥራቾችና ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ታጅበው ነበር:: እነዚህ የኪነጥበብ ሰዎች እና ጋዜጠኞች ኑሮ እጅግ በጣም ተወዶ ህይወት አንገብጋቢና ተስፋ አስቆራጭ በሆነበት በዚህ ጊዜ እንዲህ አይነት አድርባይነትን ከየትኛው የኢትዮጵያዊ ቤተሰብ አስተዳደግ እንደተማሩት ማወቅ ተስኖኛል::
እነዚህ የኪነጥበብ ሰዎች እና ጋዜጠኞች ዋናዎችን ባለስልጣናትን በመፍራትና በመሽቆጥቆጥ እናንተ ምንም አላጠፋችሁም የበታቾቻችሁ ናቸው ያስቸገሩት “እናንተን የማይመስሉ ባለሥልጣናት ሾማችሁብናል፡፡ ሕዝቡን ከታች እስከ ላይ እያማረሩ ነው፡፡ ትናንት የደማችሁለት ቅዱስ ዓላማ ዛሬ እየተበላሸና እየረከሰ ነው፡፡ አርሟቸው፡፡ እኛም ጦር ይዘን ከጎናችሁ እንቆማለን” ማለት እንዴት ነው የቻሉት?
የኢትዮጵያ ህዝብ ባሁኑ ሰአት እንኳን የፈለገውን መናገርና መጻፍ ቀርቶ ህወሃት እና ኢህአዴግን ካማና ስለመንግስት ክፉ ከተናገረ ግፍ እንደሚደርስበት ከነሱ በላይ የሚያውቅ ማን አለ? እውነት ግን የኪነ ጥበብ ሰው እንደዚህ ሞራሉን ገድሎ እና ስብእናውን አሳንሶ መኖር ይችላል? ጥበብ በእንደዚህ ያለ ደረጃ ሃገሬ ላይ መውረዷና መዋረዷ በጣም እጅግ በጣም አሳዝኖኛል:: የጥበብ ሰው እንደዚህ ረክሶ የህዝብን ችግር ከመናገር የመንግስትን ባለስልጣናትን መታዘዝንና ጥቂት ፍርፋሪ ለማግኘት እንደ ውሻ መኖርን እንዴት ይመርጣል? (አንዳንድ ምርጥ የኢትዮጵያ ልጆች እንዳሉ እንዳንረሳው)
የነበሩት ባለስልጣናት እኮ አቦይ ስብሐት ነጋ፣ አቶ ስዩም መስፍን፣ አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ አቶ አዲሱ ለገሠ፣ አቶ በረከት ስምኦን፣ አቶ ካሱ ኢላላ፣ አቶ አባዱላ ገመዳ ታጋይ አቶ ቴድሮስ ሐጎስና ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ናቸው:: እነዚህ ሰዎች በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የሰሯቸውን ግፎች እነዚህ አርቲስት ተብዬዎቹ አያውቁት ይሆን? ጋዜጠኞቹስ?
መንገድ ላይ በጥይት ላለቁ ወገኖች፣ በየወህኒው የሚሰቃዩ ኦሮሞ ወገኖች፣ ከየቦታቸው ሚፈናቀሉ አማሮች፣ በግፍ የታሰሩ ሙስሊም ወገኖች፣ የክርስቲያን አባቶች፣ ጋዜጠኞች… ማን የሚሰራው ግፍ ነው?? እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው ባለስልጣናት አይደሉም እንዴ?
ድሮም ቢሆን ሰው ለሆዱ መኖር ከጀመረ ምን ሰው ነው? ህሊና የሚባል ነገር የሌለው ሰው ምኑን ሰው ይባላል? በጣም ያሳፈርኝና እጅግ በጣም ከባድ የሞራል ዝቅጠት ነው ብዬ ይህን ጽሁፍ እንድጽፍ ያስገደደኝ ደግሞም በጣም ማመን ካለመቻሌ የተነሳ ያሳቀኝ ነገር ሁለት ነው::
– የመጀመሪያው ይህ የሰራዊት ፍቅሬ ፎቶ ነው:: ይህ ሰው የደርግ ወታደር ነበር ብዬ ለማመን ሁላ ከብዶኛል:: የደርግ የሽሬ ሽንፈትን ሲጎበኝ የህወሃት ታንክ ላይ የተነሳው ነው:: የራሱን ሽንፈት ሰላምታ እየሰጠ ያንቆለጳጰሰ ወራዳ ወታደር በአለም ላይ አለ ብዬም አላምንም::

hg

– ሌላው ደግሞ ነዋይ ደበበ አገሬን አልረሳም እያለ ከሳሞራ የኑስ እና ከ አባ ዱላ ገመዳ ጋር እየተቃቀፈ የሚዘፍነውን ሳይ ነው:: የዛሬ አስር አመት 1997 ላይ ይህ ድምጻዊ ከአሜሪካን አገር አንድ ፎቶ ልኮ ነበር በዛ ፎቶ ላይ ጣቶቹን የ‘V’ ቅርጽ ሰርቶ የቅንጅት ደጋፊ መሆኑን እና ወያኔ ነብሰ ገዳይ ነው ብሎ ስንት ሰው እንዳነሳሳ ትዝ ይለኛል:: እሱን ተከትሎ የሞተውን ወጣት እንዲረሸን ካደረገው ከሳሞራ ጋር እየተቃቀፉ መደነሱን ሳይ በጣም ልቤ ተረበሸ:: ንዋይ ደበበ ምንም ቢሆን ይህን ያረጋል ብዬ ስላላሰብኩ
እንግዲህ ይህን ካልኩ በኋላ ሌሎች የኪነጥበብ ሰዎች ደግሞ አላማቸው እና ህልማቸው እስኪሳካ በቻሉት አቅም ትክክለኛ ስነምግባር ለማነጽ ጥበብን ይጠቀሙበታል:: አሸርግዶና ተሞዳምዶ ተዋርዶና ክብርን ሸጦ መኖርን እጅግ ይጠየፉታል ሁልጊዜም ጥበብን እንደ ታላቅ ጸጋ ተቀብለው ከህዝባቸው ጎን እንደተሰለፉ በድህነትና በስደት ይኖራሉ እንጂ ክብራቸውንና ህሊናቸውን ሸጠው መኖር ስለማይመርጡም እንኮራባቸዋለን:: ለዛሬው በዚህ ላብቃና ለመሰነባበቻ

የምዕራብ ጎጃሟ ፍኖተ ሰላም ከተማ ውሃ ጠማት

$
0
0

finote nestanet
(ዘ-ሐበሻ) የምዕራብ ጎጃሟ ፍኖተ ሰላም ከተማ በውሃ እጦት የተነሳ ነዋሪው እየተሰቃየ መሆኑን ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ::

የአካባቢው ነዋሪዎች ለዘ-ሐበሻ እንዳስታወቁት በፍኖተ ሰላም ከተማ ውሃ ከጠፋ አንድ ወር የሆነው ሲሆን በዚህ የተነሳ ነዋሪው በ ዕለት ተ ዕለት ማህበራዊ ሕይወቱ ላይ ችግር አስከትሎበታል::

ነዋሪው ወደ ከተማዋ የውሃ ልማት ቢሮ በመሄድ አቤት ቢልም ምንም አይነት መፍትሄ እንዳላገኘ የጠቆሙት የአካባቢው ነዋሪዎች መንግስት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል:: በውሃ እጦት የተነሳ ሰዎች ራሳቸውን ለመጠበቂያም ሆነ ንጹህ የመጠጥ ውሃ በማጣታቸው ለተለያዩ በሽታዎች እንደሚጋለጡ የህክምና ባለሙያዎች የሚናገሩት ሃቅ ነው::

ዘ-ሐበሻ ወደ አካባቢው የውሃ ልማት ቢሮ በስልክ ቁጥር +251587751386 ደውላ ምላሽ ለማግኘት ያደረገችው ጥረት አልተሳካም::

ደብረማርቆስ፣ ባሶ ሊበንና ሞጣ የመሰናዶ ተማሪዎች የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ላይ ተቃውሙ አሰሙ

$
0
0

• በሶስት ከተሞች ረብሻዎች ተነስተዋል

(ነገረ ኢትዮጵያ) በምስራቅ ጎጃም ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቁመው እንዲወስዱ የተደረገውን የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ላይ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ምንጮን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

(ደብረማርቆስ ከተማ)

(ደብረማርቆስ ከተማ)


በስልጠናው ወቅት የህዝቡ አስተሳሰብ፣ የግል ሚዲያ፣ ተቃዋሚዎች ለኢትዮጵያ እድገት ጠንቅ ተደርገው የቀረቡ ሲሆን ተማሪዎች ይህንን አቀራረብ ተቃውመውታል፡፡ በአንጻሩ ከወራት በፊት ስልጠናውን የወሰዱት መምህራንም ዳግመኛ ስልጠናውን እየወሰዱ ቢሆንም ዝምታን መምረጣቸው ተገልጾአል፡፡
ተማሪዎቹ ‹‹የምርጫ ቅስቀሳ ከሆነ ለተቃዋሚዎችም ይፈቀድ፣ ለምን ለግጭት የሚጋብዙ ቅስቀሳ ትቀሰቅሳላችሁ፣ የኢህአዴግ ፖሊሲ ምሁራንንም ጭምር ለስደት የዳረገ ነው፣ ከቻይና እና ከኮሪያ የሚያስተሳስረን የታሪክም ሆነ የባህል መሰረት የለንም፣ ኢህአዴግ 23 አመት ያልተገበረውን ዴሞክራሲ ሊያስተምረን አይችልም›› የሚሉ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አንስተዋል፡፡

በስልጠናው ወቅት ተቃውሞዎች እየተነሱ ሲሆን በተለይም ደብረማርቆስ፣ ባሶ ሊበንና ሞጣ ላይ ተማሪዎቹ ‹‹ኢህአዴግ ሌላ፣ ኢህአዴግ ሌባ›› የሚል ጩኸት በማሰማታቸው ሲሰለጥኑበት ከነበረው ሰፊ አዳራሽ 20፣ 20 ሆነው በየክፍሉ እንዲሰለጥኑ ተደርገዋል፡፡ በተለይ በደብረማርቆስ ከተማ በሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቹ የካድሬ ስልጠና አንሰለጥንም በማለት መረር ያለ ተቃውሞ እያሰሙ እንደሚገኙ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

Health: በሽታን ተከላካይ የሆኑ አረንጓዴ ተክል ምግቦች

$
0
0

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
የአረንጓዴ ተክሎች ለጤና ጠቃሚ መሆን የማያጠራጥር ሲሆን ለዛሬ በጥቂቱ ስለተክሎቹ አይነትና ጥቅሞቻቸዉ ልነግራችሁ ወደድኩኝ፡፡
healthy food
✔ ብሮኮሊ
ይህ አትክልት በቫይታሚን ሲ እና በፋይበር የበለጸገ ሲሆን በዉስጡ የያዛቸዉ ንጥረ ነገሮች በሽታን የመከላከል አቅማቸዉ ከፍተኛ ነዉ፡፡ የሳንባ እና የካንሰር ህመሞችን የመከላከል አቅም አለዉ፡፡
✔ ጥቅል ጎመን
የተለያዩ አይነት የጎመን ዝርያዎች ያሉ ሲሆን ሁሉም በቫይታሚን ኤ፤ ሲ፤ካልሲየም እና ሌሎች ንጥረ ነገሮች የበለጸጉ ናቸዉ፡፡በአዉስትራሊያ የተሰራ ጥናት እንደሚያመለክተዉ እነዚህን አረንዴ ተክሎች መመገብ ለካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል፡፡
✔ የጀርመን ሰላጣ
የጀርመን ሰላጣ ሠዉነታችንን ካንሰር እንዲዋጋ አቅም የሚሠጥ ሲሆን ከዛም ባለፈ ለብጉር፤የፀጉር መነቀል እና ሌሎችንም ይከላከላል፡፡
✔ ቆስጣ
ቆስጣን መመገብ የጉበት፣ የአንጀት፣ የማህፀን እና የፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ጥናቶች የሚያሳዩ ሲሆን ከነዚህም በተጨማሪ ለጡንቻ መዳበር ጠቃሚነት አለዉ፡፡
✔ የሾርባ ቅጠል
ምግብን ለማጣፈጥ የምንጠቀምበት የሾርባ ቅጠል በዉስጡ ፎሊክ አሲድ፣ቫይታሚን ኤ፣ቢ፣ኬ እና ሌሎች ንጥረ ነገሮችን የያዘ ሲሆን የአጥንት መሳሳትንና የልብ ህመም ተጋላጭነትን እንደሚቀንስም ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
✔ ሠላጣ
ሠላጣን መመገብ ለደም ግፊት ህመምተኞችና ከፍተኛ የሠዉነት ክብደት ላላቸዉ ሠዎች የሚመከር ሲሆን የደም ዉስጥ ስር መጠንንም ይቀንሳል፡፡ ሠላጣ በዉስጡ የያዘዉ ካልሲየምና ፎስፈረስ ለአጥንት ጤናማነት ጠቃሚ ሲሆን ሴሊኒየም የሚባለዉ ንጥረ ነገር ደግሞ የሠዉነታችን ቆዳ ቶሎ እንዳረጅና የአንጀት ካንሠርን የመከላከል አቅም እንዲኖረዉ ያደርጋል፡፡
✔ ጥቁር ጎመን
ጥቁር ጎመን በዉስጡ ቫይታሚን ቢ1፣ቢ2፣ቢ3፣ቢ6 ፣ሲ እና ሌሎች እንደ ፖታሲየም ፣ካልሲየም ፣ፎስፈረስ እና አዮዲንንም ይይዛል፡፡የሠዉነት የበሽታ የመከላከል አቅምን የሚያጠነክርና በሽታንም የሚከላከል የተክል አይነት ነዉ፡፡
ለወዳጅዎ ያካፍሉ
ጤና ይስጥልኝ


ስለ ኢትዮጵያ ብለህ ተነስ!!! –ከ- ሳሙኤል አሊ (ኖርዌይ)

$
0
0

የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን በደል መሸከም ከምንችለው በላይ ሆኗል። ከጫንቃችን በላይ ሸክም፣ ከአእምሮአችን በላይ መከራ የሚደርስብን እየሆነ ከመጣ ዘመናቶች አልፈዋል። አሁን በዚህ በ21 ክፍለ ዘምን ላይ ዓለም በሰለጠነችበት እና እንደ ኔት ዎርክ በቀላሉ የዓለም ህዝብ በሚገናኝበት ዘመን ይህ ሁሉ በደልና አንባ ገነንነት ስርዓት አልበኝነት አገዛዝ በኢትዮጵያ መኖሩ ያሳዝናል። -—[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—–

Download (PDF, Unknown)

 

samuel

በሰላማዊ ትግል የህዝብ ድምፅ የሚረጋገጠው በምርጫ ነው ብለን እናምናለን –የሰማያዊ ም/ሊቀመንበር

$
0
0

1186718_600650739977528_2059123344_nአቶ ስለሺ ፈይሳ የሰያማወኢ ፓርቲ ም/ሊቀመንበር ናቸው። በድርጅቱ ደንብ መሰረት፣  የምርጫ ጉዳይ ሃላፊ ናቸው። በመጪው ምርጫ ዙሪያ ከሚሊዮኖች ድምጽ ጋዜጣ ጋር ቃለ መልልስ አድርገዋል። የሚሊዮኖች ድምጽ ጋዜጣ በአንድነት ፓርቲ ኤዲቶሪያል ቦርድ ታትማ ከሕዝብ የምትሰራጭ ጋዜጣ ናት። ይች ጋዜጣ ከፍኖተ ለነጻነት ጋዜጣ በተጨማሪ ሁለተኛ ጋዜጣ መሆኗ ነው)

 

ሚሊዮሞች ድምጽ – የ2007 ምርጫን እንዴት እየጠበቃችሁት ትገኛላችሁ?

 

አቶ ሰለሺ – ምልክታችንን አሳውቀናል፤ ሰሞኑን እናረጋግጣለን፡፡ በፓርቲያችን ውስጥ ሰፊ ሥራ እየሠራን ነው፡፡ በምርጫ ጉዳይ ላይ የምርጫ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባላቱን አደራጅቶ የአባላቱን ጉልበት፣ ሀብትና ዕውቀትን በመጠቀም ዓመቱን ሙሉ ሰፊ

ሥራዎችን እየሠራን ነው፡፡ የሰማያዊ ፓርቲን ለየት የሚያደርገው፣ የምርጫ ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዩን በምክትል ፕሬዚዳንቱ እንዲመራ በፓርቲው ደንብ ማስቀመጡ ነው፡፡በደንብ እየሰራን ነው፡፡ ንዑሳን ኮሚቴዎችን

 

ምርጫው ቦርድ በጊዜ ሰሌዳው መሠረት እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ ነገር ግን፣ ከምርጫው በፊት ብዙ መሠራት ያለባቸው ጉዳዮች እና መስተካከል ያለባቸው ነገሮች አሉ፡፡ ከጊዜ ሰሌዳው መፅደቅ በፊት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ለመነጋገር ቦርዱ ነገሮችን ማመቻቸት እንዳለበት ገልጾን ነበር፡፡ ነገር ግን ፍቃደኞች አልነበሩም፡፡ በጊዎን ሆቴል ይሄን ተቃውሞ አሰምተን፣ ስብሰባውን ረግጠን ወጥተናል፡፡ ይሄም ሆኖ የምርጫ ምልክት አስገብተናል፡፡ የምርጫ ፓርቲ ነን፡፡

 

በሰላማዊ ትግል የህዝብ ድምፅ የሚረጋገጠው በምርጫ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ለኢትዮጵያ የሚጠቅመው እና ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ለማድረግ የምርጫ ሳጥን ወሳኝ ነው ብለን እናምናለን፡አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ ሲታይ፣ የምርጫ አስፈፃሚው አካልና መንግሥት ሌሎች አማራጮች ለሚያሳዩ ወገኖች በሩን የዘጉ እና ያደፈኑት ይመስላል፡፡

 

በፓርቲያችን አመራሮች እና አባላት ላይ በቅርቡ እንኳን የደረሰውን ድብደባ እና እስር ማየት በቂ ነው፡፡ በምርጫ ወቅት ሰዎች ድምፃቸውንና ተቃውሟቸውን ማሰማት አልቻሉም፡፡ ይሄን ይሄን ስትመለከት፣ ምን ያህል ፍትሃዊ ተዓማኒና ነፃ ምርጫ ይካሄዳል የሚለው በጣም ያሰጋናል፡፡

 

ምርጫ አስፈፃሚው፣ ምርጫ ቦርድ ከላይ እስከታች ድረስ ወገንተኛ የመሆኑ ጉዳይን ሙሉ በሙሉ እናምናለን፡፡ ማስረጃዎችም አሉ፡ ለህዝቡም ገልፀናል፡፡ ‹‹ምርጫ አለ፣ የለም›› የሚለው ያሰጋናል፡፡ የተሻለ የምርጫ ምህዳር የሚከፈት ከሆነ፣ በአዎንታዊ መንገድ ወስደን እንወዳደራለን፡፡ለዚህ ደግሞ በፓርቲው የምርጫ ግብረ ሀይል በኩል እየሠራን እንገኛለን፡፡

 

ሚሊዮኖች ድምጽ – ለምርጫው ምን ዓይነት ዝግጅት በማድረግ ላይ ትገኛላችሁ?

 

አቶ ስለሺ – ምልክታችንን አሳውቀናል፤ ሰሞኑን እናረጋግጣለን፡፡ በፓርቲያችን ውስጥ ሰፊ ሥራ እየሠራን ነው፡፡ በምርጫ ጉዳይ ላይ የምርጫ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባላቱን አደራጅቶ የአባላቱን ጉልበት፣ ሀብትና ዕውቀትን በመጠቀም ዓመቱን ሙሉ ሰፊ ሥራዎችን እየሠራን ነው፡፡ የሰማያዊ ፓርቲን ለየት የሚያደርገው፣ የምርጫ ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዩን በምክትል ፕሬዚዳንቱ እንዲመራ በፓርቲው ደንብ ማስቀመጡ ነው፡፡በደንብ እየሰራን ነው፡፡ ንዑሳን ኮሚቴዎችን አቋቁመናል፡፡ በምርጫ ስንገባ የመጀመሪያችን ሊሆን ስለሚችል የሚያስፈልጉንን የምርጫ ሰነዶች እያዘጋጀን እንገኛለን፡፡

 

ለምሳሌ፣ የፓርቲው ዕጩ የመመልመያ ሰነድ፣ የፓርቲውን የሥነ-ምግባር መመሪያ እንዲሁም የፓርቲውን የታዛቢዎች መመልመያ መመሪያ እና የፓርቲው የምርጫ ወቅት የቅስቀሳ መመሪያ ሰነዶችን እየሠራን ነው፡፡ ትልቁ ሰነዳችን ደግሞ የምርጫ ማኒፌስቶ እያዘጋጀን ወደ መጠናቀቁ ተቃርቧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ‹‹በምርጫው ምን ማግኘት አለብን?››፣ ‹‹የቱ ጋር ደካማ ነን?››፣ ‹‹የቱ ጋር ጠንካራ ነን?››፣ ‹‹የድጋፍ ቦታዎቻችንን (ደካማ እና ጠንካራ) ለመለየት ዳሰሳዊ ጥናት አድርገናል፡፡

 

በዚህ መሠረት በሀገሪቱ 10 የምርጫ ዞኖች በመክፈል እነዚህን የሚያስተባብሩ አምስት አምስት ሰዎች በአጠቃላይ 50 ሰው ያለበት አንድ የምርጫ ግብረ ሀይል በሀገር አቀፍ ደረጃ አቋቁመናል፡፡ ሰሞኑን በተፈጠረው ሁኔታ ነገሮች ስለተበላሻሹብን መጓተት ተፈጠረ እንጂ በቀጣይ እነዚህን የምርጫ ግብረ ሀይላት ከአዲስ አበባ እና ከክልል አምጥተን ለአንድ ሳምንት ያህል ከጥናትና ሥትራቴጂው ጋር ሴሚናር እንሰጣለን፡፡

 

የሚሊዮኖች ድምጽ – ህብረት ወይም ቅንጅት ሳትፈጥሩ፣ በተናጥል ተጉዛችሁ ለመንግስትነት የሚያበቃ ውጤት ማምጣት እና በሰላማዊ መንገድ ከኢህአዴግ ሥልጣን መውሰድ ትችላላችሁ?

 

አቶ ስለሺ –  ምርጫውን ነፃ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ ከስምንት ፓርቲዎች ጋር ትብብርን መመስረት ተችሏል፡፡ ከእነሱ ጋር እየሠራን ነው፡፡ ሌሎችም በዚህ ትብብር ውስጥ የየራሳቸው ተሳትፎ ነበራቸው፡፡ ዋና ዋናዎቹ መኢአድ እና አንድነት በራሳቸው ምክንያት ከትብብሩ ርቀዋል ብለን እናምናለን፡፡አሁንም ጥሪ እያደረግን ነው፡፡ በጋራ የህዝብ ድምፁን ለማግኘት አብረን መስራት አለብን፤ እንሰራለንም፡፡ የምርጫ ቦታን የመሻማትና ያለመሻማት ነገር ሊኖር ይችላል፤ እንደ ችግርም ሆኖ ሊገኝ ይችላል፡፡ ይሄ ችግር እንዲፈታ የቻልነውን ሁሉ እናደርጋለን፡፡

 

ጊዜው ሲደርስ ‹‹ማን የቱ ጋር ጠንካራ ነው?፣ የቱ ጋርስ ደካማ ነው››፣ ‹‹የተሻለ ድጋፍ የቱ ጋር ማን አለው?›› የሚለውን እያየን በትብብርና በቅንጅት ስትራቴጂ ነድፈን ለመስራት ፈቃደኞች ነን፡፡ ሁሉን ነገር በእኛ ብቻ ይሸፈናል ብለን አናምንም፡፡

 

መታወቅ ያለበት፣ 2002 ምርጫን አስመልክቶ ስታትስቲክስ ያወጣው መረጃ፣ መምረጥ ከሚችለውና ከተመዘገበው ህዝብ ኢህአዴግ ያገኘው 33 በመቶ ነበር፡፡ በወቅቱ የተወዳደሩ ተቃዋሚዎች ደግሞ 14 በመቶ፡፡ በድምሩ 48 በመቶውን በጋራ ይዘዋል፡፡ መምረጥ የሚችለው 52 በመቶ ሕዝብ ግን ለኢህአዴግም ሆነ ለተቃዋሚዎች ድምጽ አልሰጠም፡፡ በማንም ላይ ተስፋ እና ዕምነት አልነበረውም፡፡ በዚህ ምክንያት ራሱን ከምርጫው አግልሏል፡፡

 

ተቃዋሚዎች በሰፊው ከሰራን ሰፊው 52 በመቶ ዋነኛ አቅማችን ይሆናል፡፡ በሀገሪቱ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊና በሌሎችም ዘርፎች የዛሬ አምስት ዓመት ከነበረበት የባሰበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ሥርዓቱ እየተጠላ፣ ፖሊሲዎቹ እየተዳከሙ፣ ለኢህአዴግ ድምፅ የሰጠ ሁሉ ከእሱ እየራቀ ሊመጣ ይችላል፡፡ ሰፊ ድጋፍ የሚያደርግ ያልተነካ የመራጭ ሀይል ስላለ፣ እሱ ላይ አትኩረን እንሠራለን፡፡ በመገፋፋት እና በመበላላት ድምፅ እናጣለን ብለን አናስብም፡፡

 

ቢሆን እንኳ አንዱ በአንድ ቦታ ጠንካራ የድጋፍ መሠረት ካለው፣ ለእሱ እንተወዋለን እንጂ የግድ ሰማያዊ ካላመጣው ብለን አንልም፡ ይሄ ጊዜው ሲደርስ አስፈላጊ መዋቅራዊ ሁኔታዎችን በማድረግ ወይም ሥትራቴጂ በመንደፍ በዋናነት የህዝብን ድምጽ እናስጠብቃለን፡፡ ህዝብ ድምጹን እንዲሰጥና እንዲከበርለት በዋነኝነት እንሰራለን፡፡

Health: 10 ከደስታ መንገድ የሚጎትቱህ እንቅፋቶች

$
0
0

ከሊሊ ሞገስ

(ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ላይ ታትሞ ወጥቷል)

የደስታ መንገድህን ለመጥረግ ደስታህ በተሸረሸረበት፣ በጠፋበት፣ በተጨነክ ጊዜ ብታደርጋቸው ፍቱን ናቸው ስለሚባሉ መፍትሄዎች ዛሬ ብንጨዋወትስ?

እስቲ እንደው! ከደስተኛነት ስሜት የሚገቱህን ነገሮች የምትወረወርበት ማጠራቀሚያ እና ማስወገጃ አለ ብለን እናስብና፤ በአሁኑ ሰዓት ‹‹ኧረ በቃ፣ ወደዚያ…!›› ብለህ ወደ ማጠራቀሚያው መወርወር የምትፈልጋቸውን ነገሮች ለጥቂት ጊዜ ንባብህን ገታ አድርግና ለማጤን ሞክር… ሸጋ!

happy ethiopia

በተለያዩ የሕይወት ፍሰቶቻችን ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ከመጨመር፣ ሁሉን አጥብቆ ከመያዝና ብዙ ትርኪ ምርኪ ነገሮችን ከማወቅ ይልቅ መቀነስ፣ ነገሮችና ሁኔታዎች እንዲያልፉ መፍቀድ፣ ያለንበትን ሁኔታ መለስ ብሎ ለማየት መሞከር እጅግ ከሚጠቅሙንና ደስተኛ ከሚያደርጉን ዋና ዋና ምክንያቶች ወይም መፍትሄዎች ውስጥ ጎልተው የሚወጡና የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

አሁን ካሉህ ነገሮችም ሆነ ማንነት ውስጥ ሸክም የሆኑብህና ደስታህን የነጠቁህ ነገሮች (ሁነቶች) አሉ ብለህ ታስባለህ? ከብደውኛል የምትላቸውን አስር ነገሮች ወደ ማጠራቀሚያው ለመወርወር ተዘጋጅ ብትባል ምን ይሰማሃል? ምን ምን ይሆናሉ…? ትንሽ የአስተውሎት/የማሰቢያ ጊዜ ሰጥተህ ማለፍህን አትርሳ፡፡

በሕይወትህ ውስጥ ደስታን እንዳታጣጥም እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮች በዝተውብህ ከሆነ፣ ምናልባትም የህይወት ሹረት አብዝቶ ምቾት ከነሳህ፣ ከዚህ የአሽከርካሪት ጫና ብሎም ሸክማቸው የከበደ የሃሳብ ክምሮች፣ ሲቀጥልም እርስ በእርስ ተተብትበው እየጠለፉ የሚጥሉህን የአስተሳሰብ ሂደቶች ለመቀነስ እጅግ ይረዳሉ ያልኳቸውን አስር ሸጋ የለውጥ መንገዶች አጠር አድርጌ ከዚህ በመቀጠል አብራራለሁ፡፡

በሚገባ ከተተገበሩ ደግሞ ተጭኖ የሸፈነንን ከንቱ አስተሳሰብ ገሸሽ አድርገን፣ የምንሞቃት የደስታ ፀሐይ በእውነት ሁሌም ከጎን እንዳለች፣ ብርሃኗንም ፈንጥቃ ከእቅፏ እንዳስገባችን እናስተውልባቸዋለን፡፡

1. ‹‹አበጀህ! አንተ ባትኖር እኮ…›› መባልን የመፈለግ ፍላጎት በውስጥህ ካለ፤ ይህ ፍላጎት ተንሰራፍቶ የያዘውን ቦታ የመቀነስ ስራ መስራት እንዳለብህ ሁሌም ለማስተዋል ሞክር፡፡

2. ‹‹እኔ ያልኩትን አልተረዱኝም፣… ሊረዱኝ ይገባቸዋል!›› የሚል ሐሳብ በአዕምሮህ የያዘውን ቦታ እንዲያስረክብህ (እንዲለቅ) አድርግ፡፡

3. ዙሪያህ ላሉ ነገሮች ሁሉ ምላሽ የመስጠት ፍላጎትን ብሎም ስሜትህን ቀንስ፡፡ ባለንበት የመረጃ ዘመን በየአቅጣጫው የሚነጉዱትንና፣ የአንተንም ምላሽ ለማግኘት የሚያንኳኩ ጥሪዎችንና መረጃዎችን ሁሉ ለማስተናገድ አለመሞከር፣ አንተን ከማጨናነቃቸው በዘለለ ምላሽ ሰጥተህ ለማትጨርሳቸው ነገሮች፣ ሳታጣጥማቸው የሚያልፉ ብዙ የህይወት እንቅስቃሴዎች እንደሚኖሩ ልብ በል፡፡

4. በሁኔታዎች ወይም በተለያዩ ቦታዎች ላይ ካለፍላጎትህ በሰዎች ወይም በሌላ ተፅዕኖዎች ግፊት ወይም ጫና መገኘትን ወይም ያለመገኘትን ከመወሰን ይልቅ ምርጫውን ወይም ፍቃድህን በፍላጎትህ ለራስህ ስጥ፡፡ አንዳንዴ ጓደኞችህ ሰብሰብ ብለው እንድትቀላቀላቸው ጥሪ ሊያደርጉልህ ይችላሉ፤ አይቀሬ የተባለ ድግስ (ግብዣ) ላይ እንድትገኝ ጥሪ ሊደርስህ ይችላል፤ እዚህ ጥሪ ላይ መገኘት ካልፈለግክ እና የሚያሳጣህ ነገር እንደሌለ ከተገነዘብክ ‹‹ስለጋበዛችሁኝ አመሰግናለሁ፤ ግን አልችልም›› ማለት ከባድ ነገር እንዳልሆነ ስትረዳ፣ የደስታህ ቁልፍ በአንተ እጅ እንዳለ አዕምሮህን የምታስገነዝብበትና የምታጠነክርበት ክስተቶች ናቸው፡፡

5. ‹‹እገሌ/እገሊት ወይም ያ ነገር ለስኬቴ/ ለደስታዬ ወሳኝ ነው/ነች/ናቸው!›› ከሚል የሀሳብ እስር ቤት ራስህን ነፃ ማድረግ እጅግ አትኩሮትህን ሊያገኝ የሚገባ ነጥብ ነው፡፡ ስለምን የደስተኛነቴን ቁልፍ አሳልፌ እሰጣለሁ? ‹‹የደስታዬ ቁልፍ›› በእጄ መሆኑን ሳስተውል ከራሴ አልፌ ለሌሎች ‹‹የደስታ ምንጭ›› መሆን መቻሌ ቀላል መሆኑን ለማለት አልቸገርም፡፡

6. ራስን አጉልቶ የማሳየት ጠንካራ ፍላጎትና ስሜት ከአንተ ውስጥ ማረፊያ እንዳይኖረው ማለፊያ አበጅላቸው፡፡ ያለህ የአንተ ማንነት በራሱ በቂ እንደሆነ ደግመህ ደጋግመህ ለራስህ ማረጋገጫ ስጠው፡፡ ያለህበት ማንነትህ ካንተ ማብራሪያም ሆነ ማረጋገጫ ሳይፈልግ ሳያስፈልገው የሚያዩህና የሚቀበሉህ ሰዎች እንዳሉም አስተውል፡፡

7. በሁሉም ሰው ተቀባይነትን የማግኘትን ሙከራ ራቅ አድርጎ መወርወር፡፡ ሁሉም ሰው ሁሌም በሁሉም ሁኔታ ሊቀበልህ አይችልም፤ ይህ ደግሞ ምንም ማለት አይደለም፤ አንዱ የህይወት ክህሎት ይህን በደስታ መቀበል መቻል ነውና!!

8. እያንዳንዱን የህይወትህን እንቅስቃሴና ክስተት ማወቅ እንደማይጠበቅህ ተገንዘብ! ሁሌም ህይወት የምትፈስበት ቦይና የራሷ የሆነ ምስጢር አሏትና፡፡ ስለዚህ ካለማወቅ ጋር ተመቻችቶ ማለፍ ሌላው ክህሎት እንደሀነም አስተውል፡፡

9. ሁሌም ትክክል ወይም ፍፁም ነኝ ብሎ የማሰብ አባዜና የመሆን ፍላጎት በአስቸኳይ ልታስወግደው የሚገባ ጠባይ ነው፡፡ ይህን ካደረግህ የደስታ መንገድህን በሰፊው ለመቀየስ ያለህን ዝግጁነት ያሳያል፡፡ መሳሳት ያለ፣ የነበረ እና የሚኖር ከመሆኑ ባሻገር የዕድገት መሰላል እንደሆነም መዘንጋት አያስፈልግም፡፡ አንዳንዴ ግራ ተጋብተህ መታየት ራሱ ተአምራዊ ነገር አይደለም፡፡ ይልቅስ ሁላችንም የሚያጋጥመን ክስተት እንጂ!

10. በአካባቢህ ላሉ ሰዎች ሁሉ ኃላፊነት አለብኝ በሚል ስሜት የሚመጣ ጭንቀት ወይም የሐሳብ ሸክም እንዲጫንህ አትፍቀድ፡፡ በእርግጥ ሌሎችን ማገዝና መርዳት በጎ ነገር ነው፤ ሆኖም ግን የሐሳብ ጫና በሚኖርበት ጊዜ ነገሮች እንዲያልፉ ፍቃድ መስጠት እንዳለብህ ተረዳ፡፡ ሁሌም አንተን የሚረዳህና የሚያግዝህ የህይወት ኃይል እነርሱንም እንደማይጥላቸው እመን፡፡

የተሸከምካቸውንና የከበዱህን የሐሳብ ጫናዎች ለማራገፍ ቀላሉ ነገር ‹‹ራስን ነጻ›› ማድረግ ነው፡፡ በዚህ ነፃነት ውስጥም አዲስ ጥንካሬ፣ አዲስ ተነሳሽነትና አዲስ አቅም በህይወት እንቅስቃሴህ ውስጥ አዳዲስ ተጋባዦች መሆናቸው አይቀሬ ነው፡፡ በዚህ ውስጥም በግል ህይወትና በስራ ወደላቀ ደረጃ ማለፍ በጣሙን እየቀለለህ መሄዱን ካንተ አልፎ አንተን የሚያዩህ ሰዎች የሚያስተውሉት ይሆናል፡፡ በዙሪያህ ላሉ ሰዎችም የሚኖርህ የእገዛ መጠን በብዛትም ሆነ በአይነት ያድጋል፡፡

ደስተኛው ማንነትህ በአንተ፣ በቤተሰብህ፣ በአካባቢህና በዓለም ላይ የተሻሉ ተፅዕኖዎችን የመፍጠር አቅሙ ታላቅ ነው፡፡ እናም የሆነች ያክል ጊዜ ወስደህ ከ5-10 የሚሆኑ ደስተኛነቴን ሸፍነዋል፤ ልወረውራቸው ይገባኛል፤ ለዚህም ዝግጁ ነኝ የምትላቸውን ነገሮች ለመዘርዘር ለራስህ ቃል ግባ፡፡ የዘረዘርካቸውንም አንድ በአንድ ከማንነት እንዲለዩ ቆራጥነትህና ፍቃድህ በአንተው እጅ እንደሆኑ ሁሌም አስታውስ፡፡

እውነትም ዘይደሃል!! ደስተኛነት?!… ይገባሃል! ደስታ ለሁላችንም ይገባናል! ሸጋ እንሰንብት በደስታ፡፡

ምክር እስከመቃብር  – (ከኣልፎ ሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ) –በእውቀቱ ሥዩም

$
0
0

እንደምነሽ ሸገር
እንደምነሽ ሸገር

Bewketu Seyoum – Hagere Mariam (Maryland) USA [Must Listen)
የቤት ኣከራየ የጋሽ ጣሰው ኣገር እየመጣሁ ነው፡፡ ወደ ኣዲስ ኣበባ እየመጣሁ ነው፡፡እናቶች ኣባቶች ልጆች ኦርጅናሎች ሰልቫጆች! እኔ ሳልመጣ ውጊያውን እንዳትጀምሩት ኣደራ፡፡ ኣጭርና ጣፋጭ ይሁን እንጂ በማንኛውም ትግል ላይ ለመሳተፍ ዝገጁ ነኝ፡፡የጥይት መከላከያ ቆብ ሹራብና ሱሪ እንዲሁም ፈንጅ የማይበትነው ጫማ ከተሰጠኝ ኣንድ ሻለቃ እመራለሁ፡፡ኣነሰ ከተባለ ኣንዲት ኮረብታ እቆጣጠራለሁ፡፡ በጦር ምህንድስና ላይ እሳተፋለሁ፡፡ ባሩድ ኣገነፋለሁ፡፡ የታንክ ጎማ እነፋለሁ፡፡በሰላሙ ቀን ለሞባይል፤ በቀውጢው ቀን ለሽጉጥ ማስቀመጫ የሚሆን ሰገባ እሰፋለሁ፡፡
ይሄም ኣላዋጣ ካለ የኤፍሬም ይሳቅን ቡድን የሚፎካከር ኣስታራቂ ቡድን ኣቋቁሜ” ኣንተም ተው ኣንተም ተው፤ ያስታረቅሁበትን ኪሴ ውስጥ ክተተው” የሚል ኣገልግሎት እሰጣለሁ፡፡ቃሌ ነው፡፡የተናገርኩት ከሚጠፋ በቅርቡ የገዛሁት ጋላክሲ ሙባይል ይጥፋ(በዝች ንግግር ውስጥ የተደበቀ ጉራ እንዳለ እናንተ ሳትሉኝ ኣውቀዋለሁ)
ገና ለገና ካሜሪካ ሊመጣነው በማለት ማጅራቴን ለመመታት እያሟሟቃችሁ ያላችሁ ዱርየዎች እንዲሁም ከዱላ የተረፈች ማጅራቴን በማሸት ትርፍ ለማጋበስ የተሰናዳችሁ ወጌሻዎች ተስፋ ቁረጡ ፡፡ ቤሳቢስትን የለኝም፡፡(ማጅራት መምታት ሲነሳ ፋሲል ደመወዝ ትዝ ኣለኝ፡፡እንኳን እግዜር ማረህ ልለው ብደውል ከዲሲ በርሮ ኣትላንታ እንደገባ ነገረኝ፡፡ለኮንሰርት ይሁን ለስልታዊ ማፈግፈግ ኣልነገረኝም፡፡ ወይ ኣበሳ!እኛ ኢትዮጵያውያንኮ ምስኪን ነን ፤ ኣገር በቀል- ዱላ ሸሽተን ስንሄድ የውጭ ኣገር ዱላ ይጠብቀናል፡፡
ኣሜሪካ ሁለት ወር ስቆይ ያተረፍኩት ነገር ቢኖር ግብዣና ምክር ነው፡፡ዲታው ቢራ ጋብዞ ወደ ኣገርቤት ይዣት የምመለስ ቦርጭ ያወጣልኛል፡፡ቺስታው ቦርጬ እንዴት እንደምቀንስ ይመክረኛል፡፡ኣሜሪካ ፍሪሽ የሆነ ሰው ኑሮው ምክር እስከመቃብር ነው፡፡

ከኢትዮጵያ ወደ ኣሜሪካ ገንዘብ የተላከለት የመጀመርያው ሰው ሳልሆን እቀራለሁ?
ለምሳሌ ጺም ለመቆረጥ ኣስር ዶላር መከስከስ ነበረብኝ፡፡ ፈርዶብኝ ኣሜሪካ ስገባ ጺሜ ያለወትሮው ቶሎቶሎ ማደግ ጀመረ፡፡ኣዲኣበባ እያለሁ ጺም ኣልነበረኝም፡፡እንዲያውም” ይሄ ልጅ ጺሚ የሚባል ነገር የለውም ስልብ ነው እንዴ?” የሚል ኣሜት በመንደራችን ይናፈስ ነበር፡፡ስልብ ኣለመሆኔን ለማሳየት ኣንድ ሁለት ቀን መንገድ ዳር ሸንቻለሁ፡፡

እንደልማዴ ከቀናኝ የሚጋብዘኝ ከፈረደብኝ የሚመክረኝ ኣላጣም በማለት Fenton መንገድ ላይ ወደሚገኝ ያበሻ ምግብ ቤት ጎራ ኣልኩ፡፡ ኣንዱ መድረክ ላይ የሱዳን ዘፈን ይዘፍናል፡፡ከተስተናጋጆች ውስጥ ኣንድም የሚያዳምጠው የለም፡፡ሁሉም ሙባይሉ ላይ ኣቀርቅሯል፡፡የታደለው ከፍቅረኛው በቫይበር የተላከለትን የክንፈር ምስል እያየ በደስታ ይዋኛል ፡፡ያልታደለው”የትምርት ቤት ክፍያ እየደረሰብኝ ስለሆነ ቶሎ ላክልኝ እንጅ”የሚል ካገር ቤት የተላከ መልክት እያነበበ ተክዟል፡፡ ሌላው ግድግዳው ላይ በተንጠለጠለው ቲቪ ላይ የሚተላለፈውን ያሜሪካ እግርኳስ እየተመለከተ ምድር ጠቦታል፡፡ ያሜሪካ እግርኳስ ቢሏችሁ እንደ ዋናው እግርኳስ እንዳይ መስላችሁ፡፡ ኣንዱ ጠብደል ጥቁር ሙልሙል ኳስ ይዞ ይሮጣል፡፡ሌላው ኣሳድዶ ይደርስበትና ዘርጥጦ ይጥለዋል፡፡ ለኔ ይህ ጨዋታ ሳይሆን ህጋዊ እውቅና ያለው ኣምባጓሮ ነው፡፡በዚህ መሃል ዘፋኙ “ከ እኔ ጋ ናችሁ?” እያለ ኣስሬ ቢጣራም ማንም ተጉዳይ ኣልጣፈውም፡፡ ልምምድ ላይ ያለ ይመስል ለራሱ ዘፍኖ ወረደ ፡፡ስላሳዘነኝ ባንኮኒውን እንደመቋሚያ ተደግፌ በጥሞና ኣዳመጥሁት፡፡ድምጹ ከዛፍ ላይ ኣምፖል ያረግፋል፡፡ቢሆንም ዘፈኑን ኣለቅጥ ያስረዝመዋል፡፡የሱን የሱዳን ዘፈን ታግሶ መጨረስ ሱዳንን በእግር እንደማቋረጥ ነው፡፡

ጥግ ላይ ክበበው ገዳ ተቀምጧል፡፡ ወንበር ስቤ ኣጠገቡ ተሰየምሁ፡፡ ራት ይጋብዘኛል ብየ ስጠብቅ ከራት ጋር የተያያዘ ገጠመኝ ጋበዘኝ፡፡
ክበበው ገዳ ጎረምሳ እያለ የለቅሶ ቤት እራት ኣያመልጠው ነበር፡፡ እንድያውም እንዲያባላኝ እያለ ቃሪያ በኪሱ ይዞ መዞር ጀምሮ ነበር፡፡ ኣንድ ለቅሶ ላይ ታድያ እራት ሲቀርብ ክበበው ከቤቱ ይዞት የመጣውን ቃርያ ከኪሱ ኣውጥቶ ኮርሸም ሲያደርግ የተመለከተ የሰፈር ልጅ ወደ ኣስተናጋጆች እያጨበጨበ “እዚህ ጋ ቃርያ ኣልደረሰኝም” ብሎ ጮከ፡፡

ኣለፍ ብሎ፤ የጃንሆይ ኣምባሳደር ዘውዴ ረታና ያሬድ ጥበቡ ቁጭ ብለዋል፡፡ያሬድ ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ ሲሆን ዘውዴ የተንቀጠቀጠው ተራራ ነው፡፡ኣሁን ዲማሚቱና ተራራውም ባንድ ጠረጴዛ ዙርያ ተቀምው ሳያቸው ገረመኝ፡፡

ከማጅራቴ ኣካባቢ “ልትጽፍ ነው የመጣህ ኣይደል”የሚል ሹክሽክታ ሰማሁ፡፡ወይንሸት ናት፡፡ ባለፈው ኣመት ከባህል ቡድናችን ጋር ስትመጣ ኮከብ ድምጻዊ ነበረች፡፡ኣሁን እዚሁ ቀርታ ኮከብ ኣስተናጋጅ ሆናለች፡፡ኣፍንጫዋ ላይ የወርቅ ቡግር የመሰለ ሎቲ ለጥፋለች፡፡እዚህ ኣገር ሴቶች ሎቲ የሚያንጠለጥሉት ጆሮኣቸው ላይ ሳይሆን ኣፍንጫቸው ላይ ነው፡፡ ስለወይንሸት በሌላ ምእራፍ እተርካለሁ፡፡

በሩ ኣጠገብ ተኬን ኣየሁት፡፡ ተኬ በደርግ ዘመን ካይሮ ላይ ከጠፋው የብሄራዊ ቡድናችን ገንዘብ- ያዥ ነበር፡፡ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር ባደረገችው በግጥምያ ዋዜማ ላይ በረኛውን ጨምሮ ብዙ ተጫዋቾች ስለኮበለሉ እሱ የበረኛውን ቦታ ተክቶ ተሰልፏል፡፡ ከተቃራኒ ቡድን የተለጋች ኳስ ወደእሱ ኣቅጣጫ ስትመጣ በገንዘብ ቆጠራው ለምዶበት ጣቱን በምላሱ እያጣቀሰ ሲርበደበድ ፤ ኣስራ ሰባት ጎል ገበቶበታል፡፡ (ምንጭ፡ የይድነቃቸው ተሰማ ሪፖርት)ተኬ ጉዳዩ ሲነሳበት ያማርራል፤“ይሄ ውለታ ቢስ ህዝብ የገባብኝን ኣስራ ሰባት ጎል እንጂ ያዳንሁትን ሰባት መቶ ጎል ኣላሰበልኝም” ይላል፡፡ካገሩ ወጥቶ መቅረት ኣሳብ ፈጽሞ ኣልነበረውም፡፡ይሁን እንጅ ይህን ሽንፈት ይዞ ጓድ መንግስቱ ፊት መቆም የሚያመጣውን ነገር ኣስቦ በዛው” ነካው“፡፡

ኣሁን በሩ ኣጠገብ ቁጭ ብሎ ”ብሉ ሙን“ ቢራ ይጠጣል፡፡ የቢራ ጠርሙሱን በጥርሱ ከፍቶ ቆርኪውን ጠረጴዛ ልይ ተፋው፡፡ቢራ መክፈቻ ቢቀርብለትም ተጠቅሞበት ኣያውቅም፡፡እግዜር መንጋጋን የፈጠረው ሲርብህ ኣጥንት እንድትቆረጥምበት ሲጠማህ የቢራ ጠርሙስ እንድትከፍትበት ነው ይላል፡፡

ፖሊስ የደብረማርቆስ ተማሪዎችን እያፈሰ እያሰረ ነው • ‹‹ኢህአዴግ አይገዛንም!›› ተማሪዎቹ

$
0
0

ፖሊስ የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን የተቃወሙ የደብረማርቆስ የመለስተኛ ሁለተኛ እና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ (መሰናዶ) ተማሪዎችን እያፈሰ እያሰረ እንደሚገኝ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ ተማሪዎቹ በትናንትናው ዕለት ኢህአዴግን የሚተቹ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን በማንሳታቸው ይሰለጥኑበት ከነበረው ሰፊ አዳራሽ ወጥተው 20፣ 20 ሆነው በጠባብ ክፍል እንዲሰለጥኑ ከመደረጉም ባሻገር ጥያቄ የሚያነሱት ላይ ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

newsዛሬ ጠዋት ጥያቄ ያነሳሉ የተባሉት ተማሪዎች ስልጠና ወደሚሰጡባቸው ትምህርት ቤቶች ግቢ እንዳይገቡ ከመደረጉም ባሻገር የድብዛ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ስልጠናውን መቃወማቸውን ተከትሎ ፖሊስ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የሰሙ የተክለሀይማኖት መልስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እርምጃውን በመቃወም ለድብዛ ተማሪዎች ድጋፍ መስጠታቸው ተገልጾአል፡፡

የሁለቱም ትምህርት ቤት ተማሪዎች በጋር በመሆን ከተማው አደባባይ ላይ በመውጣት ‹‹አህአዴግ አይገዛንም፣ ኢህአዴግ ሌባ፣…›› የመሳሰሉ መፈክሮችን በማሰማት ተቃውሟቸውን መግለጻቸውን ተከትሎም ፖሊስ ተማሪዎቹን እያፈሰ ወዳልታወቀ ቦታ መውሰዱ ተሰምቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር ጥያቄ የሚጠይቁና ፖሊስ ተቃውሞውን አደራጅተዋል ብሎ የሚጠረጥራቸውን ተማሪዎች እየፈለገ እያሰረ መሆኑን ተማሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በምስራቅ ጎጃም ዞን በ17ቱም ወረዳዎች የሚገኙ ተማሪዎች ስልጠናውን ካልወሰዱ ከትምህርት ቤት እንደሚባረሩና ፈተና ላይ እንደማይቀመጡ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ስልጠናውን መቃወማቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

ነባር ተመዝጋቢዎች በቅርቡ ይተላለፋሉ በተባሉ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ተደናግጠዋል

$
0
0

‹‹በተከታታይ ስድስት ወራት ያልቆጠቡና ቆጥበው ያቆሙ አይካተቱም›› የቤቶችና ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ

መንግሥት በ2007 ዓ.ም. በመጋቢት ወር 75,000 ቤቶችን ለነባር ተመዝጋቢዎች እንደሚያስተላልፍ የገለጸ ቢሆንም፣ ተመዝጋቢዎች ግን ከቁጠባ ጋር በተያያዘ ዕጣ ውስጥ አይገቡም በመባሉ ሥጋት ውስጥ መውደቃቸውን እየተናገሩ ነው፡፡

ነባር ተመዝጋቢዎች ሥጋት ውስጥ የወደቁት በኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ ሰሞኑን ባስተላለፈው ማስታወቂያ ምክንያት መሆኑን ሪፖርተር ከተመዝጋቢዎቹ ለመረዳት ችሏል፡፡ ኤጀንሲው በቅርቡ ግንባታቸው ሙሉ ለሙሉና 80 በመቶ የተጠናቀቁ 75,000 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን (ኮንዶሚኒየም) በዕጣ ለባለድለኞች እንደሚያስተላልፍ ገልጿል፡፡ የዕጣው ተጋሪ ወይም ባለዕድል የሚሆኑት፣ ከዳግም ምዝገባው ጊዜ ጀምሮ በተከታታዩ ስድስት ወራት ለቆጠቡ መሆኑን አክሏል፡፡

2e499ffff526548702f96c6f5ce36153_L

እንደ ኤጀንሲው ገለጻ፣ በተከታታይ ለስድስት ወራትና ከዚህም ቀጥሎ እንደየሁኔታው ጨምሮም ይሁን አጠቃሎ የሚከፍል ያለምንም ችግር የዕጣው ተጋሪ ሲሆን፣ ለተከታታይ ስድስት ወራት ያልቆጠበና ለስድስት ወራት ቆጥቦ ያቆመ ተመዝጋቢ፣ ሁለቱም ከዕጣው ውጪ እንደሚሆኑ አስታውቋል፡፡ ተመዝጋቢው የከተማ ቤቶች፣ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ባወጣው መመርያና በገባው ውል መሠረት መቆጠቡን ከባንክ ደብተሩ ማረጋገጥ እንደሚቻል የጠቆመው ኤጀንሲው፣ ተመዝጋቢው ስለመቆጠቡ የባንክ ሥራ በመሆኑ ምንም እንደማይል አስታውቋል፡፡

አንዳንድ ነባር ተመዝጋቢዎች ግን በተከታታይ ለስድስት ወራት መቆጠብ ያለባቸው አዲስ የተመዘገቡት ስለመሰላቸው፣ በሁለት ወራትና በሦስት ወራት እየቆጠቡ መሆናቸውን በመግለጽ፣ በድንገት ‹‹በተከታታይ ያልቆጠበ ከዕጣ ውጪ ይሆናል›› መባሉን ተቃውመዋል፡፡

ኤጀንሲው ቤቶቹን ለማስተላለፍ ወራት ሲቀሩት በተከታታይ መቆጠብ አስገዳጅ መሆኑን መናገሩ አግባብ አለመሆኑን የገለጹት ተመዝጋዎቹ፣ ሁሉም ተመዝጋቢ በደንብ ገብቶትና እየተቸገረም ቢሆን ሳያቆራርጥ እንዲቆጥብ ተደጋጋሚ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች መሥራት ይገባው እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ወ/ሮ ትዕግሥት ሰለሞን የተባሉ ነዋሪ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ የጋራ መኖሪያ ቤት ለማግኘት የተመዘገቡት በመጀመሪያው ዙር ነው፡፡ በሁለተኛ ምዝገባ ሲመዘገቡ ልብ ያሉት ነገር የመጀመርያዎቹ ተመዝጋቢዎች አግኝተው ሳይጠናቀቁ አዲስ ተመዝጋቢዎች ዕጣ ውስጥ አይገቡም የሚለውን ነው፡፡ በመሆኑም ከሚያገኙት ትንሽ ገቢ የተወሰነችውን አልፎ አልፎ የሚቆጥቡ ቢሆንም፣ ኤጀንሲው እንደሚለው በተከታታይ ለስድስት ወራትና ከዚያም ቀጥሎ ባሉት ጊዜያት እየቆጠቡ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከነገ ዛሬ ዕጣ ይወጣና ከኪራይ እላቀቃለሁ የሚል ጉጉት እንዳላቸው የሚናገሩት ወ/ሮ ትዕግሥት፣ ኤጀንሲው ያወጣውን ማስታወቂያ ሲሰሙ ከመደንገጥም አልፈው ተስፋ እስከ መቁረጥ መድረሳቸውን አስረድተዋል፡፡ በቀጥታ ካልቆጠባችሁ በማለት ተስፋቸውን ከማሳጣት ይልቅ፣ ያላቸውን ቤት የማግኘት ጉጉትና አልፎ አልፎም ቢሆን እየቆጠቡ ያሉበትን ሁኔታ ተመልክቶ በዜግነታቸው ማግኘት የሚገባቸውን የመኖሪያ ቤት እንዲያገኙ የሚመለከተው አካልና የመንግሥት ኃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

እንደ ወ/ሮ ትዕግሥት ሁሉ፣ በርካታ ተመዝጋቢዎች የመጀመርያዎቹን ሁለትና ሦስት ወራት በተከታታይ ከቆጠቡ በኋላ አልፎ አልፎ ከሁለትና ከሦስት ወራትበኋላም ቢሆን እየቆጠቡ መሆኑን ተናግረው፣ በድንገተኛ ማስታወቂያ በተከታታይ ያልቆጠበ ከዕጣ እንደሚወጣ ማወጅ ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ መንግሥት ዜጎቹን የማኖር፣ የመንከባከብና መጠለያ እንዲያገኙ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለበት የተናገሩት ተመዝጋቢዎቹ ከዕጣ እንደሚወገዱ ተናግሮ ዜጎችን ከማሳቀቅ ይልቅ፣ የዕጣው ተሳታፊ ሆነው ቅድሚያ ክፍያ መፈጸም ካቃታቸው ወይም ቤቱን ተረክበው በተከታታይ መክፈል ካልቻሉ፣ ዕርምጃውን ቢወስድ የተሻለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የቤቶች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በምክትል ዋና ሥራ አስኪያጇ ወ/ሮ ሐሊማ ባድገባ አማካይነት በቅርቡ በዕጣ ለነባር ተመዝጋቢዎች ይተላለፋሉ ስለተባሉት 75,000 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተሰጥቷል ስለተባለው ማስጠንቀቂያና ማስታወቂያ፣ ማብራሪያ ለማግኘት፣ ሪፖርተር በተደጋጋሚ እሳቸውን ለማግኘት ባደረገው ጥረት ‹‹ስብሰባ ላይ ነኝ›› በማለታቸው አልተሳካም፡፡ ኮንዶሚኒየም ቤቶቹ የተገነቡትና በመገንባት ላይ ያሉት አራት ኪሎ ባሻ ወልዴ ችሎት፣ የካ ጨፌ፣ ቦሌ አራብሳ፣ ቂሊንጦ፣ ቱሉ ዲምቱና የካ አባዶ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

‹‹የግብፅ የውኃ ድርሻ እንደማይጐዳ ኢትዮጵያ በሰነድ እንድታረጋግጥ እንፈልጋለን›› የግብፅ ፕሬዚዳንት አልሲሲ

$
0
0

የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ኢትዮጵያ የግብፅ የውኃ ድርሻ እንደማይጐዳ በሰነድ እንድታረጋግጥ እንፈልጋለን አሉ፡፡ ፕሬዚዳንቱ እ.ኤ.አ. በጃንዋሪ ወር መጨረሻ ላይ ኢትዮጵያን ይጐበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

fad1600bf474567af7ce16118055d7d2_Lፕሬዚዳንቱ ባለፈው ሰኞ ከሦስት የግብፅ መንግሥት ጋዜጦች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል በአሁኑ ወቅት መልካም ግንኙነት መኖሩን አስረድተዋል፡፡

እ.ኤ.አ. በጃንዋሪ 2015 ፕሬዚዳንቱ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ከሚያደርጉባቸው አገሮች መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ገልጸዋል፡፡ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ፕሬዚዳንቱ ኩዌትን፣ ባህሬንና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስን እንደሚጐበኙ አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ኢትዮጵያን በሚጐበኙበት ወቅትም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግ በሰጡት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል፡፡ ‹‹እኛ የምንጠይቀውና የምንፈልገው ኢትዮጵያ ግድቡ የግብፅን የውኃ ድርሻ እንደማይጐዳ በቃል የሰጠችውን ዋስትና በሰነድ እንድታረጋግጥ ነው፤›› ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ከሳምንት በፊት ግብፅን ሲጎበኝ፣ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ መጠቀምንና የህዳሴው ግድብ በግብፅ ላይ ጉዳት እንደማያደርስ መግለጹ ይታወሳል፡፡ ፕሬዚዳንቱም አገራቸው ግብፅ የኢትዮጵያን ከድህነት መላቀቅና መልማት እንደምትፈልግ ገልጸው፣ ግብፅ በውኃ እጥረት እንዳትጎዳ ጥንቃቄ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያን ግድብ መገንባት እንደማይቃወሙም መናገራቸው አይዘነጋም፡፡

የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድኑ መሪ አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ የግብፅ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያን እንዲጐበኙና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ንግግር እንዲያደርጉ በድጋሚ ጋብዘዋቸዋል፡፡ ፕሬዚዳንት አልሲሲ ኢትዮጵያን እንዲጐበኙ ጥሪ የቀረበላቸው በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አማካይነት ባለፈው መስከረም ወር መሆኑ ይታወሳል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በቃለ ምልልሳቸው፣ ‹‹ኢትዮጵያ የግብፅን የውኃ ድርሻ እንደማትጐዳ በቃል የሰጠችውን ዋስትና በሰነድ እንድታረጋግጥ እንፈልጋለን፤›› ቢሉም፣ ኢትዮጵያ ግን የግብፅ የውኃ ድርሻን በተመለከተ የሰጠችው የሰነድ ዋስትና አለመኖሩን ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

የዓባይ ተፋሰስ አገሮች በኡጋንዳ የተፈራረሙትና ኢትዮጵያና ሩዋንዳ በፓርላማቸው ያፀደቁት የዓባይ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት (CFA)፣ የተፋሰሱ አገሮች ውኃውን በሚጠቀሙበት ጊዜ በሌላው የተፋሰስ አገር ላይ ጉልህ ጉዳት ማድረስ የሌለባቸው መሆኑንና ኢትዮጵያ የምትከተለውም ይህንኑ መሆኑን ባለሙያዎቹ ጠቁመዋል፡፡

የግብፅ ፕሬዚዳንት በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ የሩሲያው ፕሬዚዳንትና የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር በዚሁ በጃንዋሪ ወር ግብፅን የሚጐበኙ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ፕሬዚዳንት አልሲሲ መንግሥታቸው ከኳታር ጋር ዕርቅ ማውረዱንና ለዚህም የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት የተጫወተውን ሚና አድንቀዋል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter


‹‹ከአንድ ሊቅ በሚጠበቅ መልኩ በተጠያቂነት ደረጃ ሙሉ አገልግሎት በመስጠት መላ ዘመናቸውን አሳልፈዋል›› – የሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ ዜና ሕይወት እና ዕረፍት

$
0
0
(ሚያዝያ ፲፱ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ.ም. – ታኅሣሥ ፲፱ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.)

(ሚያዝያ ፲፱ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ.ም. – ታኅሣሥ ፲፱ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.)

  • ከትምህርት ቤትና ከመጻሕፍት ያገኙት ዕውቀት አራት ዓይና ያደረጋቸው ሊቁ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ በተጠያቂነት ደረጃ የሚገኙና አገልግሎታቸውም ሙሉ ነበር፡- ቀዳሽና መዘምር፤ ጋዜጠኛና ሰባኬ ወንጌል፤ ጸሐፊና ተርጓሚ፤ አስተዳዳሪና መምህር፤ የአውራጃ አብያተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ፤ ኤርትራን ጨምሮ የአህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስምንት መምሪያዎች ምክትልና ዋና ሓላፊ፡፡
  • ሊቁ በሓላፊነት በተመደቡባቸው ቦታዎች ኹሉ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጡት÷ ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን ለማስተማር፤ ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት፤ ሰበካ ጉባኤያትንና ሰንበት ት/ቤቶችን ለማቋቋም፣ ለማደራጀትና ለማጠናከር፤ አገልጋዮች ካህናትን በትምህርትና ሥልጠና በማብቃት አስተዳደርን ለማሻሻልና ተጠቃሚ ለማድረግ፣ የቤተ ክርስቲያንን የውስጥ ድርጅት በንዋያተ ቅድሳትና በጽ/ቤት መገልገያዎች ለማሟላት እንደነበር ዜና ሕይወታቸው በስፋት አትቷል፡፡
  • የአብነት ት/ቤቶችን፣ የካህናት ማሠልጠኛዎችንና ኮሌጆችን በበላይነት በሚያስተባብረው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነትየትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ለሦስት ጊዜያት በዋና ሓላፊነት ተመድበው የላቁ ተግባራትን አከናውነዋል፡፡ ከእኒኽም በመንግሥት የተወረሱ 27 መንፈሳውያንና ዘመናውያን ት/ቤቶችን በተለይም የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲመለስ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሐሳብ በማቅረብና በቅ/ሲኖዶስ ከተወሰነም በኋላ የበኩላቸውን ክትትል በማድረግ መንፈሳዊ ኮሌጁ ለቤተ ክርስቲያናችን ተመልሷል፡፡
  • በመምሪያ ደረጃ የሊቃውንት ጉባኤ አባል ኾነው ከተመደቡበት ጥቅምት ወር ፲፱፻፹፰ ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው መዳረሻ ከሌሎች ሊቃውንት ጋራ በመኾን ካከናወኗቸው ተግባራት መካከል÷ ቤተ ክርስቲያናችን የራስዋ የተጣራ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲኖራት 81 ቅዱሳት መጻሕፍትን በግእዝ ቋንቋ መሠረትነት አርመውና አስተካክለው ለኅትመት አብቅተዋል፡፡ ለካህናትና ምእመናን በሴሚናር ሲያሰለጥኑበት የቆዩት የቃለ ዐዋዲ ደንብ ለሦስተኛ ጊዜ ሲሻሻል የበኩላቸውን ተሳትፎ አድርገዋል፡፡‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ ሥርዐተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነት›› መጽሐፍ ከሊቃውንት ጉባኤ አባላት ጋራ በአንድነት አዘጋጅተው ለምእመናን እንዲዳረስ አድርገዋል፡፡ በርካታ የቅዱሳን ገድላትና የመላእክት ድርሳናት ከግእዝ ወደ አማርኛ ቋንቋ መልሰዋል፡፡
  • የቤተ ክህነት ሥነ ጽሕፈት ኮሚቴ አባል በመኾን በዐበይት የቤተ ክርስቲያን በዓላት በሚወጡ ኅትመቶችና በሚሠራጩ የሬዲዮ መግለጫዎች በቅዱሳት መጻሕፍት ማስረጃዎችና በምርምር የተደገፉ፤ አንባቢንና አድማጭን የሚያረኩ በርካታ ጽሑፎችን በማቅረብ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፉ ታላቅ ምሁር ነበሩ፡፡ በግል አዘጋጅተው ካሳተሟቸው መጻሕፍት መካከል ‹‹ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን››፤ ‹‹ሳታዩት የምትወዱት›› በሚል ለትምህርትና ለተግሣጽ ባሰራጯቸው ሥራዎቻቸው ለሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንና ለነገረ ሃይማኖት መጠበቅ ተከራክረዋል፤ ተሟግተዋል፡፡ በተለይም ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን በኮሌጅ ደረጃ እንደ አንድ የትምህርት ዘርፍ ራሱን ችሎ የቆመ የትምህርት ክፍል ኾኖ እንዲሰጥ ግንባር ቀደም አስተዋፅኦ አድርገዋል፤ መጽሐፉም በኮሌጆችና በካህናት ማሠልጠኛዎች ለመምህራንና ለተማሪዎች መመሪያና ማጣቀሻ ኾኖ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡
  • የሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አገልግሎት ዓለም አቀፋዊም ነበር፡፡ ከግንቦት ፲፬ – ፴ ቀን ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. የያሬዳዊ ማሕሌትን ዐውደ ትርኢት በምዕራብ ጀርመን ለማሳየት ከተመረጡት ሊቃውንት አንዱ በመኾን የማሕሌታችንን ሥርዐት አሳይተው ተመልሰዋል፡፡ እ.አ.አ ከሐምሌ ፱ – ፲፭ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ‹‹ክርስቶስን ዛሬ መስበክ›› በሚል ርእስ በእስክንድርያ በተደረገው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ የቤተ ክርስቲያናችን መልእክተኛ በመኾን ጥንታዊ እምነቷንና ሥርዐቷን በቃልም በጽሑፍም በመግለጥ ተሳትፈዋል፡፡ በየመንና በጅቡቲ ለሚኖሩ ምእመናን ለበርካታ ጊዜ እየተመላለሱ መንፈሳዊና ሐዋርያዊ አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡፡

*           *           *

  • ከደግ ቤተሰብ ተገኝተው በመልካም አስተዳደግ የወጡት ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ በትዳራቸውም የጋብቻ ጽናት ምሳሌነታቸውን በተግባር ያረጋገጡ ናቸው፡፡ ጥር ፲፪ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. በተክሊልና በሥርዐተ ቁርባን ካገቧቸው የሕግ ባለቤታቸው ወ/ሮ ድጋፍ ወርቅ ፈቄ ጋራ የ፶ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ የጋብቻ በዓላቸውን ከኹለት ዓመት በፊት አክብረው ነበር፡፡ ስምንት ልጆችንና ዐሥር የልጅ ልጆችን አፍርተውም ለወግ ለማዕርግ አብቅተዋል፡፡
  • ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል በሢመተ ክህነት÷ በ፲፱፻፵፩ ዓ.ም. ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማዕርገ ዲቁና፤ ሰኔ ፲፩ ቀን ፲፱፻፶፱ ዓ.ም. ከብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ሢመተ ቅስና ተቀብለዋል፡፡ የትምህርት ዝግጅታቸው በዜማ፣ በአቋቋም፣ በቅኔና በነገረ ሃይማኖት ላይ ያተኮረ ኾኖ ትርጓሜ መጻሕፍትንና የቤተ ክርስቲያን ታሪክን ከተለያዩ ሊቃውንት በመማር ምስጢር አደላድለዋል፡፡ በ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በከፍተኛ የነገረ መለኰት ትምህርት የቴዎሎጂ ዲፕሎማ ተቀብለዋል፡፡ በቅድስት ሥላሴ ት/ቤት እና በዳግማዊ ምኒልክ የአንደኛና የኹለተኛ ደረጃ ት/ቤት ትምህርታቸውን ተምረው አጠናቀዋል፡፡

*           *           *

  • ‹‹በዕለተ ሰንበትና በዐበይት በዓላት እየቀደሱና እያወደሱ፣ በሥራ ቀናት በቢሮ እየሠሩ፣ ለምእመናን ወንጌል እየሰበኩ፣ በመንፈሳዊ ኮሌጆችና በካህናት ማሠልጠኛዎች እያስተማሩና እያሠለጠኑ ከአንድ ሊቅ በሚጠበቅ መልኩ በተጠያቂነት ደረጃ በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ከግማሽ ምእት ዓመት በላይ ሙሉ አገልግሎት ሲያበረክቱ ኑረዋል፡፡

Lique Kahinat Kinfe Gabriel Funeral

  • በቀድሞው የሸዋ ክፍለ ሀገር በይፋት አውራጃ በማፉድ ወረዳ በደብረ ምሥራቅ ሾተል ዓምባ በኣታ ለማርያም አጥቢያ ሚያዝያ ፲፱ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ ስማቸው ክንፈ ገብርኤል፤ ያረፉትም የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ዋናው በዓል በሚከበርበት በታኅሣሥ ገብርኤል፤ ኹሉን ማድረግ የሚችል አምላክ ለነፍሳቸው ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያትን ያድልልን፤ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጆቻቸው መጽናናትን ይስጥልን፤ በእርሳቸው እግር ምሁራንን እንዲተካልን ፈጣሪን በጸሎት እንለምነዋለን፡፡››

ዜና ሕይወቱ ወዕረፍቱ ለሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ
፩. ልደትና ልህቀት

ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ ሚያዝያ 19 ቀን 1929 ዓ.ም. ከአባታቸው ከአቶ አልታዬ ናደውና ከእናታቸው ከወ/ሮ በለጥሻቸው እርዳቸው በቀድሞው ሸዋ ክፍለ ሀገር በይፋት አውራጃ በማፉድ ወረዳ በደብረ ምሥራቅ ሾተል ዓምባ በኣታ ለማርያም አጥቢያ ተወለዱ፡፡ የሕፃንነት ጊዜአቸውን በቤተሰቦቻቸው በመልካም አስተዳደግ ካሳለፉና የሕፃንነት ደረጃ ካለፉ በኋላ እንደ አገሩ ልማድ ቤተሰቦቻቸውን በመርዳት ለአባትና እናታቸው እየታዘዙና እያገለገሉ አደጉ፡፡

፪. ትምህርትና መዋዕለ ውርዝውና

ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ ዕድሜአቸው ለትምህርት እንደ ደረሰ ለመንፈሳዊ ትምህርት ባላቸው ዝንባሌ በትውልድ ሀገራቸው በደብረ ምሥራቅ ሾተል ዓምባ በኣታ ለማርያም፡- ከመምሬ መሸሻ ካሳዬ ፊደል፣ ንባብና ጽሕፈት፤ ከአለቃ ተሰማ ወልደ ጊዮርጊስ ዜማና አቋቋም በሚገባ ተምረው አጠናቀዋል፡፡

ከዚኽ በኋላ በ1948 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ ከተማ መጥተው በዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ገዳም መንፈሳዊ ት/ቤት ገብተው፡- ከሊቀ ጠበብት አክሊለ ብርሃን ወልደ ኪሮስ የአማርኛ ሰዋስው፤ ከመጋቤ ምስጢር ጌራ ወርቅ ጥበቡና ከመልአከ አርያም ይትባረክ መርሻ ቅኔና የግእዝ ቋንቋ ከነአገባቡ በሚገባ ተምረውና አደላድለው በመምህርነት ተመርቀዋል፡፡ በተጨማሪም በዚኹ ት/ቤት ከቀኝ ጌታ ሞገስ ሥዩምና ከሊቀ ጠበብት ሐረገ ወይን ደምሴ የአቋቋም ትምህርታቸውን አስፋፍተው ተምረዋል፡፡

ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ ለትምህርት የነበራቸው ፍላጎት ከፍተኛ የነበረ በመኾኑ በተማሯቸው ልዩ ልዩ ትምህርቶች ሳይወሰኑ፡- ከአለቃ አዘዘ መጻሕፍተ ብሉያት፤ ከመ/ር ሙሉጌታ መጻሕፍተ ሐዲሳት፤ ከመልአከ ሰላም ሳሙኤል ተረፈና ከሊቀ ሥልጣናት ኤልያስ (በኋላ ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ) ነገረ ሃይማኖት(ዶግማ)፤ ከመ/ር ወንድም አገኘኹ እና ከአለቃ ይኩኖ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ፤ ከዶክተር አበበ እና ከረዳት ፕሮፌሰር ሉሌ መልአኩ እንዲኹም ከአለቃ ወልደ ኢየሱስ የዓለም ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በሚገባ ተምረዋል፡፡

በ1951 ዓ.ም. በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብተው በኮሌጁ የሚሰጠውን ከፍተኛ የነገረ መለኰት ትምህርት ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ተምረው በ1953 ዓ.ም. ከግርማዊ ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ እጅ የቴዎሎጂ ዲፕሎማ ተቀብለው የግእዝ የአማርኛ ቋንቋና የነገረ ሃይማኖት መምህር ኾነው ተመርቀዋል፡፡

የዘመናዊ ትምህርትን በሚመለከትም በዚኹ በቅድስት ሥላሴ ት/ቤትና በዳግማዊ ምኒልክ ት/ቤት የአንደኛና የኹለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተምረው አጠናቀዋል፡፡

ሊቁ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ በጉባኤ ያልሰሟቸውና በግል ያላነበቧቸው መጻሕፍት የሉም ብንል ማጋነን አይኾንም፡፡ በዚኽም መሠረት ከትምህርት ቤትና ከመጻሕፍት ያገኙት ዕውቀት ሙሉዕ በኩለሄ፣ አራት ዓይና ስለአደረጋቸው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንበተጠያቂነት ደረጃ ሙሉ አገልግሎት በመስጠት መላ ዘመናቸውን እንዲያሳልፉ አድርጓቸዋል፡፡

፫. ሢመተ ክህነትና አገልግሎት

በ1941 ዓ.ም. ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የዲቁና ማዕርግ ተቀብለው የተወለዱባትን የሾተል ዓምባ በኣታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን፤ የተማሩባትን የታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ገዳም በቅዳሴ፣ በመዘምርነትና በስብከተ ወንጌል ዘርፍ አገልግለዋል፡፡

በ1954 ዓ.ም. የመንዝና ይፋት አውራጃ ቤተ ክህነት ሰባኬ ወንጌል ኾነው እየተዘዋወሩ በማስተማር ሐዋርያዊ አገልግሎት አበርክተዋል፡፡ በዚኹ ጊዜም በደብረ ሲና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤት አቋቁመዋል፡፡

በዚያው በ1954 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሬዲዮ ትምህርት እንድትሰጥ መንግሥት ሲፈቅድ፣ ቀደም ሲል ተመርቀው ለወንጌል አገልግሎት ከተሰማሩት ሊቃውንት መካከል ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ አንዱ በመኾን ተመርጠው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የታሪክና ድርሰት ክፍል ባልደረባ ኾነው ለዐሥር ዓመታት ያኽል የወንጌልን ቃል በምሥራች ሬዲዮ፣ በጋዜጣና በመጽሔት በማሰራጨት ለቤተ ክርስቲያን፣ ለሀገርና ለወገን ሰፊ አገልግሎት አበርክተዋል፡፡

በ1956 ዓ.ም. በሬዲዮ ሲተላለፍ የነበረው ያሬዳዊ ዜማና መዝሙር ሓላፊ፤ በ1958 ዓ.ም. የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ምክትል አዘጋጅ፤ በ1960 ዓ.ም. የጠይቆ መረዳት መርሐ ግብር አዘጋጅ፤ በ1961 ዓ.ም. የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅየድርሰትና ሥነ ጽሑፍ ክፍል ሓላፊ በመኾን መንፈሳዊ አገልግሎት በስፋትና በብቃት ሰጥተዋል፡፡ የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በነበሩበት ጊዜም የጋዜጣውን ሥነ ጽሕፈትና ቴክኒክ በማሻሻል ዘመናዊ ውበት እንዲኖረው፣ የጋዜጣ መልእክና ቅርፅ እንዲይዝ በማድረጋቸው የጋዜጣው 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓል በተከበረበት በ1962 ዓ.ም. በወቅቱ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ከነበሩት ከክቡር ንቡረ እድ ድሜጥሮስ እጅ ሽልማትና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጥቶአቸዋል፡፡

ሊቁ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ ለቤተ ክርስቲያን የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት ፍጹም ሐሳብና ዕቅድ ስለነበራቸው ሰኔ 11 ቀን 1959 ዓ.ም. ከብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ሊቀ ጳጳስ ሢመተ ቅስና ተቀብለው በዕለተ ሰንበትና በዐበይት በዓላት እየቀደሱና እያወደሱ፣ በሥራ ቀናት በቢሮ እየሠሩ፣ ለምእመናን ወንጌል እየሰበኩ፣ በመንፈሳዊ ኮሌጆችና በካህናት ማሠልጠኛዎች እያስተማሩና እያሠለጠኑ ከአንድ ሊቅ በሚጠበቅ መልኩ የድርሻቸውን ከግማሽ ምእት ዓመት በላይ በአዲስ አበባና በመላ ኢትዮጵያ እየተዛወሩ ሲያበረክቱ ኑረዋል፡፡

በ1966 ዓ.ም. በሸዋ ሀገረ ስብከት የየረርና ከረዩ አውራጃ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ በመኾን ተሹመው በነበረበት ወቅት የናዝሬት ካህናት ማሠልጠኛን በራስ አገዝ መርሐ ግብር ከፍተው ካህናትን በማሠልጠን ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን በማስተማር ተዳክሞ የነበረውን ሰበካ ጉባኤ እንደገና በማቋቋምና በማጠናከር በየአብያተ ክርስቲያናቱ የሰንበት ት/ቤቶችን በማቋቋም በፈጸሙት ሐዋርያዊ ተግባር የአውራጃው ካህናትና ምእመናን ምን ጊዜም ሲያስታውሷቸው ይኖራሉ፡፡

በ1967 ዓ.ም. የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ዋና ጸሐፊ ኾነው እንዲሠሩ ተመድበው የነበሩ ሲኾን ከዚኹ ሓላፊነታቸው በተጨማሪ የቀበና መካነ ሕይወት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ኾነው እንዲሠሩ በታኅሣሥ ወር 1967 ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ተሹመዋል፡፡ በዚኹ ሓላፊነታቸው የሰበካውን ምእመናን በማስተባበር ፈርሶ የነበረውን ሰበካ ጉባኤ በማቋቋምና በማደራጀት፣ የቤተ ክርስቲያኑን አስተዳደር በማሻሻል በነፃ ያገለግሉ ለነበሩት የደብሩ ካህናት በጀት በማስፈቀድ የወር ደመወዝተኞች እንዲኾኑ አድርገዋል፤ የቤተ ክርስቲያኑን የውስጥ ድርጅት፣ የጎደሉ ንዋያተ ቅድሳትን፣ አልባሳትንና መጻሕፍትን በማሟላት እንዲኹም ጽ/ቤቱን በማቋቋምና በማደራጀት ለቤተ ክርስቲያን የዕድገት መሠረት ጥለዋል፡፡

ይህንኑ የአስተዳደር ሓላፊነት እንደያዙ በጥር ወር 1968 ዓ.ም. የካህናት አስተዳደር መምሪያ ሓላፊ (መጋቤ ካህናት) ተብለው ተሹመው አገልግለዋል፡፡

በጥቅምት ወር 1969 ዓ.ም. የኤርትራ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ በሰኔ ወር 1969 ዓ.ም. የካፋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው በመሾም በየአብያተ ክርስቲያናቱ ተዳክሞ የነበረውን ሰበካ ጉባኤ በማቋቋምና በማደራጀት አስተዳደሩን በማሻሻል ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን በማስተማርና በተለይም ሥርዐተ ቅዳሴው በልዩ ሥርዐት እንዲመራ በማድረግ ከፍተኛ አገልግሎት አበርክተዋል፡፡

በ1971 ዓ.ም. የጠቅላይ ቤተ ክህነት ትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ምክትል ሓላፊ፤ በ1972 ዓ.ም. ሊቀ ካህናት ተብለው በመሾም የአዲስ አበባ ደቡብ አውራጃ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ኾነው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ተሹመው ቃለ ዐዋዲውን ለካህናትና ምእመናን በሴሚናር በማስጠናትና የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደር በማስተማር ሰበካ ጉባኤን በሚገባ አደራጅተው ለአኹኑ ውጤት ያበቁ የቤተ ክርስቲያናችን ባለውለታ አባት ነበሩ፡፡

በ1976 ዓ.ም. የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር መምሪያ ምክትል ሓላፊ፤ በ1978 ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት የገንዘብና ንብረት አስተዳደር መምሪያ ምክትል ሓላፊ፤ በ1979 ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት የቁጥጥር አገልግሎት ተ/መምሪያ ሓላፊ፤ በ1980 ዓ.ም. የበጀትና ንብረት አስተዳደር መምሪያ ሓላፊ፤ በ1983 ዓ.ም. የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሓላፊ፤ በ1987 ዓ.ም. የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ምክትል ዲን በመኾን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት አበርክተዋል፡፡

ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል፣ ሐምሌ 1983 ዓ.ም. ለሦስተኛ ጊዜ የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ሓላፊ ኾነው በተመደቡበት ወቅት በደርግ መንግሥት የተወረሱና የቤተ ክርስቲያን ንብረት የኾኑ 27 መንፈሳውያንና ዘመናውያን ት/ቤቶች ለቤተ ክርስቲያን እንዲመለሱ አድርገዋል፤ እንዲኹም የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲመለስ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስና ለቅዱስ ሲኖዶስ ሐሳብ በማቅረብና በመከታተል ጉዳዩ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወስኖ ጥያቄው ለመንግሥት እንዲቀርብ የበኩላቸውን ጥረት አድርገዋል፤ መንፈሳዊ ኮሌጁም በቅዱስነታቸው ያላሰለሰ ክትትል ለቤተ ክርስቲያናችን ተመልሷል፡፡

የሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አገልግሎት ዓለም አቀፋዊም ነበር፡፡ ከግንቦት ፲፬ – ፴ ቀን ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. የያሬዳዊ ማሕሌትን ዐውደ ትርኢትበምዕራብ ጀርመን ለማሳየት ከተመረጡት ሊቃውንት አንዱ በመኾን የማሕሌታችንን ሥርዐት አሳይተው ተመልሰዋል፡፡ እ.አ.አ ከሐምሌ ፱ – ፲፭ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ‹‹ክርስቶስን ዛሬ መስበክ›› በሚል ርእስ በእስክንድርያ በተደረገው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ የቤተ ክርስቲያናችን መልእክተኛ በመኾን ጥንታዊ እምነቷንና ሥርዐቷን በቃልም በጽሑፍም በመግለጥ ተሳትፈዋል፡፡ በየመንና በጅቡቲ ለሚኖሩ ምእመናን ለበርካታ ጊዜ እየተመላለሱ መንፈሳዊና ሐዋርያዊ አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡

በነሐሴ 1987 ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ መልካም ፈቃድ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች÷ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ነገረ መለኰት አስተምረዋል፤ ሰብከዋል፡፡ በዚኽም አገልግሎታቸው ፑና ከሚገኘው የቅዱስ ቶማስ ቤተ ክርስቲያን ስጦታና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በጥቅምት 1988 ዓ.ም. የሊቃውንት ጉባኤ አባል ኾነው በመመደብ ከሌሎች ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጋራ በመኾን የቃለ ዐዋዲ ደንብአሻሽለዋል፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ ሥርዐተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነት›› በሚል ርእስ መጽሐፍ አዘጋጅተው ለኅትመት አብቅተዋል፡፡ ‹‹በዐድዋ ጦርነትና ድል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ድርሻ›› በሚል ርእስ ለዐድዋ ድል ፻ኛ ዓመት መታሰቢያ መጽሐፍ አዘጋጅተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የራስዋ የተጣራ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲኖራት ከሌሎች የሊቃውንት ጉባኤ ባልደረቦቻቸው ጋር በጋራ በመኾን 81 ቅዱሳት መጻሕፍትን በግእዝ ቋንቋ መሠረትነት አርመውና አስተካክለው ለኅትመት አብቅተዋል፡፡ በተጨማሪም ‹‹ሥርዐተ አምልኮ››የተሰኘውን መጽሐፍ ከሊቃውንት ጉባኤ አባላት ጋራ በአንድነት በማዘጋጀት ለምእመናን እንዲዳረስ አድርገዋል፡፡

የቤተ ክህነት ሥነ ጽሕፈት ኮሚቴ አባል በመኾን በዐበይት የቤተ ክርስቲያን በዓላት በሚወጡ ኅትመቶችና በሚሠራጩ የሬዲዮ መግለጫዎች በቅዱሳት መጻሕፍት ማስረጃዎችና በምርምር የተደገፉ፤ አንባቢንና አድማጭን የሚያረኩ በርካታ ጽሑፎችን በማቅረብ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፉ ታላቅ ምሁር ነበሩ፡፡

ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል በግል አዘጋጅተው ካሳተሟቸው መጻሕፍት መካከል ‹‹ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን››፤ ‹‹ሳታዩት የምትወዱት››የተሰኙና በዚኽ ጽሑፍ ያልተጠቀሱ ለትምህርትና ተግሣጽ በሚጠቅሙ እጅግ በርካታ ሥራዎቻቸው ለሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንና ለነገረ ሃይማኖት መጠበቅ ተከራክረዋል፤ ተሟግተዋል፡፡ በተለይም ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን በኮሌጅ ደረጃ እንደ አንድ የትምህርት ዘርፍ ራሱን ችሎ የቆመ የትምህርት ክፍል ኾኖ እንዲሰጥ ግንባር ቀደም አስተዋፅኦ አድርገዋል፤ መጽሐፋቸውም በኮሌጆችና በካህናት ማሠልጠኛዎች ለመምህራንና ለተማሪዎች መመሪያና ማጣቀሻ ኾኖ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

Lique Kahinat Kinfe Gabrial's finest book00

ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን በመጽሐፈ ሲኖዶስ፣ በፍትሐ ነገሥት በሌሎችም የሥርዓት መጻሕፍት በሰፊው ተወስኖ ተጽፎዋል፡፡ ይኹን እንጂ ምእመናን ጥልቅና ምጡቅ የኾነውን የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት በመጠኑም ቢኾን ለመማርና ለማስተማር፣ ለማወቅና ሥርዓቱን ለመፈጸም እንዲችሉ በማሰብ ይህ ‹‹ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን›› መጽሐፍ በአስተዋፅኦ መልክ (በማውጣጣት) ተዘጋጅቷል፡፡

መጽሐፉ የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓትና ምስጢር በቅድሚያ አመሠራረቱን መነሻውን፣ ከዚያም አመጣጡንና ታሪኩን፣ አሠራሩንና አፈጻጸሙን ይገልጣል፡፡ በአጠቃላይ አነጋገር መጽሐፉ የገለጠው ሰባቱ ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን እንዲኹም ሥርዐተ ቤተ መቅደስ እና ሥርዐተ ጸሎት ኹሉ በመጻሕፍተ ብሉያት፣ በመጻሕፍተ ሐዲሳት፣ በመጽሐፈ ሲኖዶስ እና በፍትሐ ነገሥት የተሠራውንና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን የተወሰነውን እንጂ ከዚያ ምንጭነት የማያልፍ የማይወጣ ስለኾነ ‹‹ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን›› ተብሎ ተሰይሟል፡፡ /ከመጽሐፉ መግቢያ የተወሰደ/


በትርጉም ደረጃ በርካታ የቅዱሳን ገድላትና የመላእክት ድርሳናት ከግእዝ ወደ አማርኛ ቋንቋ መልሰዋል፡፡ በተጨማሪም በግራ ጌታ ኃይለ ጊዮርጊስ በግእዝ የተዘጋጀ የልዑል ራስ መኰንን እና የዐፄ ኃይለ ሥላሴ ዜና መዋዕል በልዕልት ተናኘ ወርቅ አሳሳቢነት ከግእዝ ወደ አማርኛ ቋንቋ መልሰዋል፡፡

ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ የሕግ ባለቤታቸው የኾኑትን ወ/ሮ ድጋፍ ወርቅ ፈቄን በተክሊልና በሥርዐተ ቁርባን ጥር 12 ቀን 1955 ዓ.ም. አግብተው አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ልጆች እንዲኹም 10 የልጅ ልጆችን አፍርተውና አስተምረው ለማዕርግ አብቅተዋል፡፡ የ50ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ የጋብቻ በዓላቸውን ከኹለት ዓመታት በፊት አክብረው የጋብቻ ጽናት ምሳሌነታቸውን በተግባር አረጋግጠዋል፡፡

ዜና ዕረፍት

ከጥቂት ዓመታት ወዲኽ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ78 ዓመታቸው ከሚወዱት ቤተሰባቸውና የመንፈስ ልጆቻቸው ተለይተው ታኅሣሥ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ከዚኽ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለይተዋል፡፡

ሥርዓተ ቀብራቸውም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የቤተ ክርስቲያን ሓላፊዎች፣ የሥራ ባልደረቦቻቸው፣ ልጆቻቸውና ዘመዶቻቸው በተገኙበት ታኅሣሥ 20 ቀን 2007 ዓ.ም. ከቀኑ በ9፡00 በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በክብር ተፈጽሟል፡፡

ኹሉን ማድረግ የሚችል አምላክ ለነፍሳቸው ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያትን እንዲያድልልንና ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን እንዲሰጥልን በእርሳቸውም እግር ምሁር እንዲተካልን ፈጣሪን በጸሎት እንለምነዋለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እንኳን አደረሰን ! –ይድነቃቸው ከበደ

$
0
0

ከምንም በላይ ግን ያኔ ከመነሻው ለአገር እና ለህዝብ የሚጠቅም ፓርቲ እንመስርት ብለን፣ገንዘባችን፣ ጊዜያችን፣ እውቀታችን ሳንሰስት በመስጠት፤በወቅቱ ፓርቲ እንመስርት ማለታችን ትክክል እንደነበር የዛሬ ውጤታችን ምስክር ነው ! 

—————————–

ሰማያዊ ፓርቲ ከተመሰረተ አሁን ሦስተኛ ዓመቱ ነው፣የአገራችን አሉታዊ እና አዎንታዊ ፖሊቲካ ድርጊቶችና ክስተቶችን በመመርመር የመፍትሔ አካል ለመሆን በአገር ወዳድ ኢትየጵያዊያን ታህሳስ 22/2004 ዓ.ም በይፋ ተመሰረተ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በእውነት እና በእውቀት ላይ የተመሠረተ ሰላማዊ ትግል በማድረግ ፣የዜጎች የሥልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ አባላቱ እና ደጋፊዎችሁ እያሣየነው ያለው ቁርጠኝነት እና ታማኝነት ለፓርቲያችን ጥንካሪ ዋንኛ መሠረት ነው፡፡
9783_596573470488802_1311708396556689267_n
ሰማያዊ ፓርቲ ከምስረታው ጀምሮ ያስመዘገባቸው አኩሪ ድሎች፣ በአገራችን እየተንቀሳቀሱ ከሚገኙ ቁጥራቸው ከበዛ ፓርቲዎች ተርታ፣ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠሩ አንዱ ለመሆነ ችሎአል፡፡ፓርቲያችን ከተመሠተር እና ወደ እንቅስቃሴ ከገባ አጭር ጊዜ ቢሆነውም ፣በኢትዮጵያዊያን ካለው ተቀባይነት እና በገዥው መንግስት ላይ እያሣደረ ያለው አስጨናቂ ተፅኖ በመመልከት አንዳንድ ታዛቢዎች ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ ? በማለት ይጠይቃሉ፣ መልሱ ግን አጭር ነው፡፡ እሱም ጠንከራ ጓዳዊ ትስስር ፣ጥልቅ የሆነ የአገር ፍቅር ስሜት፣ለዓላማ መሞት፣ በእውቀት እና በእውነት ላይ የተመሰረት ሰላማዊ ትግል ተግባሪዊ ማድረግ ፣ለፓርቲያችን ውጤት የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል፡፡

ይህ ማለት ግን  ፓርቲያችን  ሊደርስበት ካሰበው  ደረጃ እጅግ በጣም ትንሽ መሆኑ ሁላችንም የምንረዳው ሃቅ ነው፡፡ የሁላችንም የጋራ ዓላማ፣ ህዝብ የአገሩና የሥልጣን ባለቤትነቱ  እንዲረጋገጥ ማድረገግ ነው ! ይህን ለማሳካት አሁን ላይ ፓርቲያችን ያስመዘገበው ድል የዋናው ትግላችን ውጤት ማሣያ መለኪያ እንጂ ፍፃሜ አይደለም፡፡ እርግጥ ነው ከትግሉ ጅምሮ አንስቶ የጠልፎ መጣል የተለመደው አዙሪት ፓለቲካ፣ ፓርቲያችን ፈተና ውስጥ የከተተው ቢሆንም በአመራሩ ጠንካራ ውሳኔ ከገጠመው ፈተና በብቃት ለመወጣት የተቻለው ሲሆን፣ወደፊትም እንዲኸ ዓይነቱ ክስተት እንዴት መወጣት እንዳለበት ት/ት ያገኘበትም መልካም አጋጣሚ ጭምር ነው፡፡

ፓርቲያችን ከሌሎች በአገር ውስጥ ከሚንቀሣቀሱ የዲሞክራሲ ኃይሎች ጋር በመተባበር መጪው አገር አቀፍ ምርጫ 2007፣ ፍታሓዊ እና ዲሞክራሳዊ እንዲሆን ጠንክሮ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን፣በ2005 ዓ.ም ሊካሄድ ታስቦ የነበረ የአካባቢ ምርጫ፣ ገዥው መንግስት በቻውን ተወዳድሮ ብቻውን ያሸነፈበት የይስሙላ ምርጫ መሆኑን የ33 ፓርቲዎች ጠንካራ ትብብር ያስገኘው ውጤት ነው ! የዚህም ውጤት ባለቤት ከሆኑ ፓርቲዎች ውስጥ ሰማያዊ ከዋናዎቹ አንዱ ነው፡፡አሁንም ወደፊትም ለአገር እና ለህዝብ ጥቅም ሲባል ፓርቲያችን በጥናት ላይ የተደገፈ ከእውነተኛ የዲሞክራሲ ኃይሎች ጋር የሚያደርጋቸው ማናቸውም ዓይነት ግንኙነት በፓርቲያችን ደንብ መሠረት ገደብ የተጣለበት አይደለም፡፡

ገዥው መንግስት የፓርቲያችንን ጥንካሪ በአግባቡ በመረዳት፣በምናደርጋቸው ሰላማዊ ትግል ምክንያት በመፍጠር በተደጋጋሚ ከሚወስዳቸው የእስራት እና ደብዳባ እርምጃ ባለፈ ፓርቲያችንን ለማፍረስ በግልፅ እና በስውር እየተነቀሣቀሰ ይገኛል፡፡ከዚህም በላይ የፓርቲያችን ሰላማዊ ተጋይ አቶ የሺዋስ አሰፋ ከአ/አ፣ አቶ በፍቃዱ አበበ ከአርባምንጭ እና አቶ አግባው ሰጠኝ ከሰሜን ጎንደር በሽብርተኝነት ከሱ  እያሰቃያቸው ይገኛሉ፡፡ይሁን እንጂ የጀመረነው ሰላማዊ ትግል ከዚህም በላይ ዋጋ እንደሚያስከፍል ቀድመን የተረዳነው ስለሆነ ወደፊት እንጂ ወደ-ኋላ ማለት በእኛ ዘንድ ነውር መሆኑ ጠንቅቀን እናውቃለን  !

ፓርቲያችን ባሣለፈው ሦስት ዓመታ ውስጥ የገጠመው ውስጣዊ እና ውጫዊ ችግሮች ማንኛወም ጠንካራ ፓርቲ ሊገጥመው ከሚችለው የተለይ ነገር አይደለም ፡፡ሆኖም ግን ያጋጠሙት ችግሮች ለመፍታት የተሄደበት መንግድ ማንኛውም ፓርቲ እና የፓርቲ አባላት ከሚሄዱበት በአንፃራዊ እጅግ በጣም የተሻለ ነበር ፡፡አሁንም ወደፊትም ችግሮች መኖራቸው የማይቀር መሆኑ ታሣቢ በማድረግ፣ የፓርቲው አባል የሆን ጥልቅና ዝርዝር ውይይት በግልፅ በማካሄድ ክፍተቶቻችን እንደምንሞላ ተስፋ አድርጋለው፡፡

ከምንም በላይ ግን ያኔ ገና ከመነሻው ለአገር እና ለህዝብ የሚጠቅም ፓርቲ እንመስርት ብለን፣ገንዘባችን፣ ጊዜያችን፣ እውቀታችን ሳንሰስት በመስጠት፤በወቅቱ ፓርቲ እንመስርት ማለታችን ትክክል እንደነበር የዛሬ ውጤታችን ምስክር ነው !ለዚህም በመብቃታችን መስራች አባላት ለሆን እንኳን ደስ አለን፣አላችሁ! ለማለት እወዳለው፡፡

የጀመራችሁት አገር የማዳን ትግል የእናተ የመስራቾች ብቻ ሳይሆን የእኛም ጭምር ነው !በማለት ከፓርቲው ምስረታ ጀምሮ እስካሁን ሰማያዊን በመቀላቀል በአመራርነት እና በአባልነት በማገልገል ፣አኩሪ የትግል መሰዋትነት እየከፈላችሁ ለምትገኙ ለገዥው ለወያኔ መንግስት የእግር እሳት ለሆናችሁ የእኔ ትውልድ ጓዶች እንኳን አደረሳችሁ !

ፓርቲያችን አሁን ላይ ያለበት ደረጃ እንዲደርስ በአሳብ እና በገንዘብ እየረዳችሁ ለምትገኙ በአገር ውስጥ እና በውጪ የምትገኙ ድጋፍ ሰጪዎቻችን ፣ድካማችሁ ፍሬ እያፈረ በመሆኑ የሚሰማችሁ ደስታ ለተጫማሪ ድጋፍ እንደሚነሳሳችሁ ተስፋዬ የበዛ ነው !ከምንም በላይ ግን ሁሌም ለማይለይን የሃሳብ እና የገንዘብ ድጋፋችሁ አገራዊ ግዴታችሁ ቢሆንም፣  በቀናነት እና በአገር ወዳድነት ለምታደርጉት ድጋፍ ምስጋና ተገቢ ነው፡፡ምስጋናውን ከአክብሮት ጋር እንድትቀበሉ በመጠየቅ ፣ለዚህ በመብቃታችን እንኳን አደረስን በማላት የ3ኛ ዓመት የእንኳን አደረስን የግል መልእክቴን በዚህ አጠቃልላለው፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !

አርማጮ በአማራ ንቅናቄ ሰራዊት እና በወያኔ ሰራዊት በውጊያ ተወጥራለች

$
0
0

(ምንሊክ ሳልሳዊ)

በአርማጮ አከባቢ በአማራ ንቅናቄ ሰራዊት እና በወያኔ ሰራዊት መካከል ከባድ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን የንቅናቄው ምንጮች ከአከባቢው አስታወቁ::የህዝቡ ተሳትፎ በከፍተኛ ደረጃ እየታየ ባለበት እና ህዝቡ እና የንቅናቄው ወታደሮች በመቀናጀት ዱር ቤቴ ብለው ወደ ጫካ መግባታቸው ሲታወቅ በመተማ ሸዲ አከባቢ በትላንትናው እለት በወያኔው ጦር ላይ ጥቃት አድርሶ ወደቦታው የተመለሰው የአማራ ንቅናቄ ሰራዊት ከሕዝቡ ጋር በመተባበር እጅግ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን እንደማረከ ምንጮቹ ተናግረዋል::

(ፎቶ ከፋይል)

(ፎቶ ከፋይል)


ካለፈው አርብ ጀምሮ የተነሳው ውጊያ በአሁን ወቅት ቀጥሎ ያለ ሲሆን በዛሬው ለሊት ከፍተኛ የቶክስ እሩምታዎች እና የከባድ መሳሪያ ድምጾች በአከባቢው እየተሰሙ መሆኑ ታውቋል::በአብድራፊ አብሃጂራ ሶረቃ ግጨው ማርዘነብ ማይጸማር ሃሙስ ገበያ ዳንሻ ማይካድራ እና አከባቢው ጦርነቱ ይስፋፋባቸዋል የሚል ከፍተኛ ስጋት ስላደረ በአከባቢው የወያኔ ሰራዊቶች በብዛት መስፈራቸው ሲታወቅ አዳዲስ ታንኮችን የጫኑ ከባባድ መኪኖች በቦታው ደርሰዋል::

እንዲሁን ወደ ሱዳን ክልል ዘልቀው የገቡ እና ከሱዳን ወታደሮች ጋር አሰሳ የሚያደርጉ ወያኔዎችን እንዳጠቁ የአማራው ንቅናቄ ወታደሮች ተናግረዋል::
በአርማጮ እና አከባቢው የተከሰተውን ግጭት በተመለከተ የአማራ ንቅናቄ ሰራዊት መግለጫ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል::

አቶ በረከት እሱን መች ጠየቅንህ?

$
0
0

January 1, 2015

Bereket በረከትህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) የተመሠረተበትን አርባኛ ዓመት ለማክበር ሽር ጉድ እየተባለ ባለበትና በመጠኑ ከፍተኛ የሆነ የሀገሪቱ የገንዘብ ወጭ ተደርጎBereket-Simon አስረሽ ምችው የሚደለቅበት ሰአት ላይ ያለን ሲሆን የዘድሮው በዓል አከባበር ደግሞ የተለየ ሆኗል አስቀድመው ነው የጀመሩት ያም ሆነ ይህ በዓሉ ለምን ይከበራል? የሚያከብረውስ ማን ነው? ብለን ስንጠይቅ ድርጅቱ በጫካ አሥራ ሰባት ዓመት በትረ ሥልጣኑን ከጨበጠ በኋላ በከተሞች ለሃያ ሦሥት ዓመታት ያህል የምሥረታ በዓሉን በከፍተ የገንዘብ ወጭ እያከበረ ዘልቋል።በዓሉ የሚከበርበት ምክንያት፦ ህወሃት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተነሳበት ዓላማ ግቡን እየመታ በመምጣቱ፤ ከዚህ ግቡ የማይባሉ ሰዎችን ለሀገር ሥልጣን በማብቃቱ፤ጥቂቶቹን ሚሊየነር በማድረጉ፤የድርጅቱን ዓላማ የሚቃወሙትን እያወደመና እየበላ በመምጣቱ፤ ከሀገር እንዲሰደዱ በማድረጉ እንዲሁም አሰቃቂና ጭካኔ በተሞላበት ድብደባና እንግልት በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ ድርጅት አመራሮች ፤ጋዜጠኞች፤ ጦማርያን፤ የሃይማኖት መሪዎች፤ ተማሪዎች፤አስተማሪዎች፤ ነጋዴዎች፤አርሶ አደሮች ወህኒ ቤት ወርደው እንደ ብረት እየተቀጠቀጡ የሚገኙበት፤የሀገር ሀብት ተንጠፍጥፎ ካዝናው ባዶ እስኪሆን ድረስ ተጠርጎ ወደ ውጭ አገር ተልኮ በጥቂት ባለሥልጣናትና ቤተሰቦቻቸው የግል ባንክ አካውንት በመቀመጡ፤ ከአጎራባች አገሮች ጋር የሚዋሰነው የኢትዮጵያ ለም መሬት በገፀ-በረከትነት የኢትዮጵያ ጠላት ለሆኑ አገሮች በመሰጠቱ፤በኢንቭስት-መንት ስም ነዋሪው ኢትዮጵያዊ ዜጋ እየተፈናቀለ መሬት ለውጭ ባለሀብት ያለምንም ክፍያ በመሰጠቱ፤ የንግዱም ሆነ የግብርናው ዘርፍ ሕዝብ የማይሳተፍበትና በባለሥልጣናት እጅ የገባበት፤አገሪቱ ወደብ አልባ የሆነችበት፤ አንድነት የጠፋበትና ለዘመናት አብረው በሰላምና በፍቅር በአንድነት የኖሩ ነገደ ኢትዮጵያውያን በጥርጣሬና በጥላቻ የሚተያዩበት ሁኔታ በመፈጠሩ፤ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷ የተረገጠበት ላይ በመድረሱ ህወሃትና ጋሻ ጃጌዎችን የሚያስደስት ተግባር ከዚህ በላይ ስለማይኖር በዓሉ ይከበራል።

ይህን የህወሃት በዓል የሚያከብረው ማን ነው? የህወሃት አባላት፤ አመራርና ጋሻ-ጃግሬዎች ምስኪኑን ሕዝብ በቀጭን ትዕዛዝ በኃይል ተገዶ እንዲወጣ በማድረግ ሲሆን እምብኝ አልወጣም በዓሉ የኔ በዓል አይደለም ያለውን ደግሞ በታጠቀ ኃይል በመሣሪያ ጀርባውን፤ ግንባሩን በጠመንጃ አፈሙዝ እየተገጨ እንዲወጣ በማስገደድ ነው በዓሉን የሚያከብሩት። ከህወሃት አምባገነናዊ ባህርይ መልካም ነገር የማይታሰብ ቢሆንም ህወሃት ለተነሳበት እኩይ ዓላማ ፀንቶ የቆመ በመሆኑ በዓሉን አታክብር ማለት የዋህ የሚያስብል ይሆናል።ነገር ግን ይህን ጠባብና ዘረኛ ሥርዓት ማስወገድ አለብኝ የሚሉ ኃይሎች በዓላማቸው ፀንተው አንድነት ፈጥረው ትግል አለማካሄዳቸው ህወሃትን ለዚህ ያበቃው መሆኑን ግልጽ አድርጌ ማለፍ እወዳለሁ።ሕዝቡ በቃኝ ካለ ሰንብቷል፤ አመጽ ያረገዘ ሕዝብ ከየአቅጣጫው እየሰነዘረ ያለው ርምጃ የተቃዋሚ ኃይሎችን የሕዝቡ ትግልና አመጽ ጭራ አድርጓቸው እየታየ ነው።ስለዚህ የተቃዋሚ ኃይሎች (ድርጅቶች)ሕዝብ እየሄደበት ባለው ፍጥነት በመሄድ የማደራጀት ተግባር መቅደም አለበት ብየ አምናለሁ ወይም ይጠበቅባቸዋል።ይህ የሚያግባባን ከሆነ መነሻ ወደ አደረኩት ርእሴ ተመልሸ ከበረከት ህብረ-ብሄራዊ ድርጅት መቆም አልቻለም።ውሎ አድሮ ደግሞ ኢህአዲግ በሚል የጋራ ግንባር ሥር ገብቶ ወደቀ መጥፎ ቀን የኢህዲን ታጋይ ባመናቸው መሮዎቹ ሊወጣ ከማይችልበት እሥር ቤት ገብቶ የህወሃት ጥቅም አስጠባቂ ሆነ።እነዚህ ከላይ ስማቸውን የጠቀስኳቸው ግለሰቦች የታገሉት የአማራው ነገድ ሕዝብ በሚኖርበት አካባቢ ሲሆን አማራ ስለአልሆኑ ኃላፊነት በጎደለው መንፈስ የአማራውን ነገድ ሕዝብና አብሯቸው ይታገል የነበረውን ትውልደ አማራ እየበሉና እያስበሉ የመጡ የእናት ጡት ነካሾች ናቸው። ይህ አይነት የግድያ ተግባር በደርግ ጊዜ የተጀመረ ብቻ ሳይሆን ደርግ ከወደቀ በኋላም ተጠናክሮ ቀጥሏል። የመጀመርያው ዘመቻ አማራውን ማስወገድ ሲሆን ሁለተኛው ዙር ደግሞ በኦሮሞው ላይ ይሆናል። የዚህን ጅማሮ እየተመለከትነው ነው።

4ኛ/ ህወሃት አንድ የሚመፃደቅበት አንድ ትራጀዲ አለ እሱም የብሄር ብሄረስቦችን መብት አረጋግጫለሁ የብሄር ብሄረሰቦች ምክር ቤት አቋቁሜ ያለሁ የሚለው ፈሊጥ ነው።እያንዳንዱ ብሄር ብሄረሰብና ጐሣ ወይም ነገድ ሕዝብ በሰላም ውሎ እንዳያድር የዲሞክራሲና የፍትህ፤የእድገት፤ የእምነት ጥያቄዎችን እንዳያነሳ እርስ በርስ እያናከሳቸው ይገኛል።በአጭሩ ለማሳየትም ሁለት ምሳሌዎችን ልጥቀስ በኢትዮጵያ ሶማሌና አፋር ክልል ግጭት ተፈጠረ የግጭቱ ፈጣሪ ራሱ ህወሃት ሲሆን የተሰጠው መፍትሄ ደግሞ በጣሙን የሚገርምና በሁለቱ ሕዝቦች መሀከል ያለውን ግንኙነት ለማሻከርና ተባብሶ እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው። ሶሞኑን በአማራና በትግራይ አጎራባች ክልሎች የተፈጥረው ግጭት ሆነ ተብሎ በህወሃት የተፈበረከ ሲሆን ከሁለቱም ወገኖች ደም እንዲፈስ ንብረት እንዲወድም እስከወዲያኛው የማያገናኝ ተግባር እየተፈፀመ ይገኛል። ድርጊቱን የሚያስፈጽሙት እንደ እባብ ገላ ማንነታቸውን አውልቀው የጣሉ የለየላቸው ሆዳም የህወሃት ጀሌዎች አማራዎችና የወረራው ፊታውራሪ ህወሃት መሆናቸው ቢታወቅም ሰፊው የትግራይና የአማራ ነገድ ሕዝብ እንደ ድሮው እንደ ጥንቱ በአገራችን ባህል መሠረት የተጫረውን እሳት ሊያበርዱት ይገባል።በተለይ የትግራይ ሕዝብ ህወሃት ለአርባ ዓመታት ያህል መጠቀሚያ አድርጐ የተጠቀመበት ሲሆ ዛሬም ባድማው ባዶ እንዲሆን ከኤርትራ ሕዝብና ከአማራ ሕዝብ ጋር በማጋጨት ሰላምህን እያደፈረሱ ስለሆነ በቃችሁ በላቸው።

በመጨረሻም አቶ በረከት እሱን መች ጠየቅንህ በሚል የጀመርኩት ብእዴንም ወያኔዎች (ወየንቲ) ነን ብሎ የተናገረውን ሰምቼ ነው። ህወሃትን ከሚገባው በላይ ሲያወድስ ብእዴን እንዴት ይንከባከቡት እንደነበር ሲደርት ብእዴን የመጣ አሁን በዚያ ወቅት የነበረው ኢህዲን ይህንም መለየት ከማይችልበት የደረሰ ይመስለኛል ታናንት **ህወሃት የታገለው የአክሱማዊ ዳይናስቲን ለመመለስ አይደለም ** ያለው ጀግና ዛሬ ድመት እጅ እንደገባች አይጥ በጣም አንሶና አድርባይነቱን ሊሸፍን በማይችል መልኩ ሲዘላብድ ደደቢት ላይ ሆኖ የተወራ ወሬ ወይም ድስኩር አይሰማም ብሎ አስቦ ወይንስ አንዳች ነገር ወርዶበት? ህወሃት በዓሉን የሚያከብረው በየካቲት ነው ዘንድሮ አስቀድሞ ወደ ደደቢት ሄዶ ያን ያህል ውሽከታ ሲደረግ ግርምት ጥሎብኝ ነበር።

በረከት፦ ላንተ የሚቀርብህ ሻእብያ እንጅ ህወሃት አይደለም ብአዴን ልትሆንም አትችልም ምክንያቱም አንተ የሞቱት እማ ብሬና የአባ ገብረእግዚአብሔር ልጅ ነህ እነሱ ደግሞ ጥርት ያሉ ጨዋ ኤርትራዊ ናቸው ታዲያ አንተ ብሔረ አማራ ሆነህ እንዴት ነው አማራውን የምትወክለው? ይህን ነው መመለስ የሚገባህና የምንጠይቅህ ስለህወሃት ጀግንነት ስለደርግ ጨቋኝነት አንተ አትነግረንም ይልቁንስ አንተን ጨምሮ ከጌቶችህ ጋር የምታራምዱት ሥርዓት ምን እንደሚመስል ለማሰብ ሞክር። ወጣት ሴቶችና ወንዶች በዘመናዊ ባርነት ሥር እንዲወድቁ የሚያደርግ ህጋዊ የደላላ ጽ/ቤት ከፍቶ ስደትን የሚጠራ መንግሥት፤ በተለያየ ሱስ ተለክፈው መደበኛ ተግባራቸውን እንዳይፈጽሙ የሚያደርግ መንግሥት፤ በዓረብ አገር ያሁሉ ግፍ ሲፈጸም፤ ወደ ዓረብ አገር ለመሄድ በሽዎች የሚቆጠሩ ባህር ላይ ሰምጠው የአሳ ቀለብ ሲሆኑ ከየአቅጣጫው በኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃት ሲደርስ ያንተ መንግሥት አንድም የደረሰ ጉዳት የለም፤ የሞተ፤የታሰረ የለም ብሎ ሞግቶናል የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎችን ጋዜጠኞችን፤ ጦማርያንን፤ ተማሪዎች አስተማሪዎችን ነጋዴውን፤አርሶ አደሩን የሃይማኖት መሪዎችን ማሰር መግደል አስሮ ማሰቃየት የሚል መርህ የሚያራምድና የዘረጋ ጭፍን አስተሳሰብ ከሚያስቡትና በቀልተኝነትን ከሚገፉት አንዱ አንተ ነህ ምናልባት ባንተ አመለካከት እንደ ኤርትራዊነትህ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ጥቃትም ሆነ ጉዳት ላይሰማህ ይችል ይሆናል ደግሞም ትክክል ነው። እኛ ግን እንጠይቅሃለን ማተብህን ከፈታህ ወዲህ በአስፈጃቸው አማራዎች ሁሉ እንጠይቅሃለን፤የመንግሥት ሥልጣንን መከታ በማድረግ በአባቶቻችን ደምና አጥንት ተከብሮ የኖረውን ዳር ድንበራችን በማስደፈርህ እንጠይቅሃለን፤አንዱን ጐሣ ከሌላኛው ጐሣ ጋር በማጋጨት ደም በማፋሰስህ እንጠይቅሃለን፤ ምስኪን አብሮ አደጐችህን የትግል ጓዶችህን ጊዜ ጠብቀህ ስለበላሃቸው እንጠይቅሃለን። ብአዴን እንዲፈርስ አንተም ከአማራ ሕዝብ ትካሻ እንድትወርድ ሌሎችንም እንዲወርዱ እንጠይቃችኋለን ፤የአማራ ዘር እንዲመክን በማድረግህ እንጠይቅሃለን።ለዛሬው ይህ ይበቃሃል ደጋግመህ አንብበው አያ በረከት።

ነብሮ ነኝ ከሰ/አሜሪካ

 የግቢዬ ዛፎች –ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

አንድ በእድሜ ባለጸጋ የሆኑ አባት በግቢያቸው 14ት አይነት ዛፍ እየተንከባከቡ ያሳድጉ ነበረ። እነዚህ ዛፎችን አባዝተው ግቢያቸውን ሞልተውታል። የግቢያቸው ስፋት የዛፎቹ ልምላሜና የከለር ድምቀት ላየ ልብን ይማርካሉ። ህይወት ማለት እጽዋት እጽዋት ማለት ህይወት እንድሆነ በግቢው ያሉት ዛፎች ይናገራሉ። የዛፎቹ ልምላሜ ንጹ አየር የሚተነፍሱበት ከፀሐይ የሚጠለሉበት ከፍሬአቸው ምግብ የሚመገቡበት ባጠቃላይ ህይወታቸው ናቸው። በማለዳ  ጠዋት ተነስተው ከዘራቸውን  ይዘው ግቢውን ቃኘት ቃኘት እያደረጉ የደረቁ ቅጠሎችን በከዘራቸው እያራገፉ መሬት የወደቁትን እየሰበሰቡ ግቢያቸውን ከቃኑ በኃላ ነው ወደ ጉዳያቸው የሚሄዱት።

ለመሆኑ አልኳቸው አሁን ግቢዎትን እንደዚ የሞሉት 14ት የዛፍ ፍሬዎት ናቸው ? አልኳቸው።

አዎ አሉኝ ልባቸውን ሞልተው …ወዲያው ግን ክፍት ብሎአቸው ከ14ቱ አንዷ  በለሊት የመጣ ሽፍታ ቆረጣት በእጃቸው እያመለከቱኝ ያችትልህ ስር አላት ግንድና  ፍሬዎቻ ግን የሉም። የቀሩት 13ት ነበሩ በግቢየ የገባው ሽፍታ 9ኝ አስቀርቶ 4ቱን አጠፋው። ይሁን 9ኙ ዋና ዋና ናቸው ብዬም ዝም ብለው የ9ኙን ዛፍ ያለኔ ፈቃድ ማንም እንዳይነካ ፍሬአቸውንም ያለኔ ፈቃድ ማንም እንዳይመገብ ብሎ የሽፍታ ህግ አውጥቶ  ግቢዬን  በመሳሪያ  አጠረው። ግቢዬም በሽፍታ ተወረረ ፍሬዎችንም ያለግዜው ሳይደረሱ በላቸው የዛፎቼን ውበት አጠፋቸው በፊት እንደ ልቤ ተዘዋውሬ የምንከባከባቸው እንደልቤ ከፍሬአቸው የምመገብባቸው በፍቅር የማያቸው ተክሎቼን ድንበር አበጅቶላቸው እንዳልጎበኛቸው አጠራቸው። ድንበሩም ባልከፋ ግን ሽፍታን ማን ያምናል? የሽፍታ  በኅሪ ያው ሽፍታነት ነው ዘረፎ መብላት ገድሎ መኖር። ለዛፎቹ 1,2,3,4,5,6,7,8,9 ቁጥር ሰጣቸው አንድ ላይ አንድ ይኑር ሁለት ለይ ሁለት ይኑር እያለ ለዘጠኙም ተናገረ። የአንድን ሁለት እስከ ዘጠኝ ያሉት እንዲነኩ አይፈቀድላቸውም የሁለትንም እንደዚሁ እያለ እስከ ዘጠኝ ይቀጥላል ለምን ሲባል ሁሉም በራሱ  እንዲኖር ነው ይላል። አንድ ለአንድ ሁለትም ለሁለት ሶስት ለሶስት አራትም ለአራት እያለ ዘጠኙም ስለራሳቸው የመብት ጥያቄ ሲያነሱ ሽፍታነቱ ይመጣና ብረቱን አንስቶ መፍጀት ይጀምራል ምን አገባችሁ ከ1-9 ያሉት የዛፎቹ ባለቤት እኔ ነኝ በኔ ስር እስካላችሁ ድረስ ከኔ ሃሳብ ውጪ ማሰብም መጠየቅም አትችሉም ሃሳባችሁን በኔ ሃሳብ ልክ ስፉት እያለ  ሽፍታነቱን ያሳያል። አንድ በሁለት ለይ ሁለት በሶስት ላይ ሶስት በአራት ለይ ሲነሱ ግን ቁጭ ብሎ  ይስቃል የእርስ በራስ ፍጭቱ ሽፍታው የሚኖርበትን ዘመን ስለሚያራዝመው እንደዚህ አይነቱን ግጭት ይናፍቀዋል የናፈቀው ነገር አልሰራ  አለው እንጂ። ዛሬ 9 ያደረጋቸውን ነገ 19 ሊያደረጋቸው ይችላላ 9ኙ በ9ኝነታቸው እንዲቆዩ አልያም ወደሚፈልጉት ኃሳብ መድረስ እንዲችሉ ሽፍታን ከስሩ ነቅሎ ዳግም እንዳይመጣ ማድረግ ያስፈልጋል። ሽፍታ  በራሱ ህግ በየግዜው አንድ ነገር ብልጭ ስትል ለብልጭታ አዲስ ህግ እያወጣ ግቢውን አመሰው ወይ ግቢውን መምራት አልቻለ ወይ ፍሬውን በአግባቡ መመገብ አልቻለ ብቻ ዘይት እና  ውሃን ለመቀላቀል ይሞክራል  ደግሞም ይላል በኔ ዘመን(በሽፍታው ዘመን) ዘይት እና  ውሃ ሲቀላቀል ታያላችሁ በግቢው ለሚኖረው ነዋሪ በሙሉ የኔን ቃል የመቀበል ግዴታ አለበት የማይቀበል ቢኖር ግን ዘይት እና  ውያ መቀላቀላቸውን ሳያይ ይወገዳል። የሚል የሽፍታ ህግ አጽንቶ ግቢውን አምሶታል። እኔም መልእክቴን ላስተላልፍና  ወደ ተከለለው ግቢዬ ልግባ። በግቢ ውስጥ አንቱ የተባሉ የተከበሩ ሽማግሌዎች አሉ። እግዚአብሔርን ሲያመልኩ በእድሜ የሸመገሉ፣ አላህን ሲያመልኩ በእድሜ የሸመገሉ፣ ዋቄፈናን ሲያመልኩ በእድሜ የሸመገሉ እናንተ በእውቀት የበሰላችሁ ብዙ ፍሬ  ያፈራችሁ አባቶች ስለ  ግቢያችሁ የምታስቡ ስለ ዛፎቻችሁ የምትጨነቁ ስለ ፍሬዎቻችሁ የምትጓጉ አባቶች ስለ  ግቢያችሁ አስቡ ስለ ዛፎቻችሁ አስቡ ስለ  ፍሬዎቻችሁ አስቡ። ግቢ የተባለችው አገር ናት። ስትደሰቱ የምትደሰቱባት ስታዝኑ የምታዝኑባት አርሳችሁ የምታበቅሉባት ነግዳችሁ የምታተረፉባት ተምራችሁ የምታስተምሩባት ደምቃችሁ የምትታዩባት ከደምና ከአጥንታችሁ የተሳሰረች ይህቺ ናት አገርህ።  ዛፎች የተባሉት 9ኙ ክልሎች ናቸው። በእድሜ ከፍ ከፍ የምትሉበት ከራሳቸው ሽበት ከአእምሮአቸውም በሳል እውቀት ከአንደበታቸውም ጠጋኝ ቃላት የሚናገሩባት የሚኖሩበት። አባት.. አባት እናት.. እናት ብለን የምንጠራቸው መኖሪያ፣ ቄዬ.. ቄዬ አድባር.. አድባር የምልበት፣ ሰፈር.. ሰፈር መንደር.. መንደር የምንልበት፣ ጎሳ ..ጎሳ ብሔር.. ብሔር የምንልበት፣ እሷ ናት ክልልህ። ፍሬ የተባሉት ደግሞ ሮጠው ያልጠገቡ፣ ቁልቁለት ዳገቱን ሜዳው ላይ የሚቧርቁ፣ ነገ አባት እናት የሚሆኑ፣ ነገ የሰፈር መሪ፣ የመንደር መሪ፣ የጎሳ መሪ፣ የክልል መሪ፣ የአገር መሪ የሚሆኑ፣ ነገ  ጳጳስ፣ ሼህ፣ አባ ገዳ፣ የሚሆኑ እነሱ ናቸው ፍሬዎች።

ሽፍታ  ግቢህን ወሮታልና የፈለከውን ላማድረግ የፈለከውንም ለመስራት አትችልም። ምክንያቱም የሽፍታ  ባህሪ ከራሱ ውጪ የሚሰማው ነገር ስለሌለ። ትላንትና 14 ዛፍ የነበርክ የአገሬ ዛፍ ሆይ ዛሬ 9ኝ ሆነኻል ይህ ጥሩ ባልከፋ ነገር ግን ሽፍታ  ነግሶ ባለበት ግቢ ውስጥ ነገ ምን እንደሚልና ምን እንደሚሰራ አይታወቅም እና የግቢ ነዋሪዎች ግቢ ማለት አገር እንደሆነ ጠቅሻለው የማን ግቤ ያልተደፈረ የማን ፍሬ ሳይደርስ ካለግዜው ያልተቀጠፈ የማን ዛፍ ያልተለመለመ የለም ከአንድ እስከ ዘጠኝ ብንሄድ ዘጠኙም ዛፍች  ሃዘን ላይ ናቸው። እህህ…. የማይል የለም። ሽፍታ እስካለ ሃዘን ለቅሶ ችግር ስደት ድህነት ፍቅር ማጣት የደስታ ህይወት ባጠቃላይ ሰላም በግቢህ ውስጥ አይኖርም። ደስታ ሰላም ፍቅር ነጻነት እድገት የምንፈልግ ከሆነ ሽፍታን መጣልና  ማጥፋት አለብን። ሽፍታ  የሚጠፋው በልመና ሳይሆን በሽፍታነት ነው። ሽፍታ  የሚፈራው ሽፍታን ብቻ ነው። እናንተ  ዘጠኙ ዛፎች የናንተ  ሽፍታነት ሽፍታን እስከሚጠፋ  ብቻ  ነው እንጂ ነገ ሽፍታው ከጠፋ  በኃላ እናንተም ሌላ ሽፍታ  እዳትሆኑ አጥብቄ እነግራችኃለው።

 

በዚህ አባባል መልእክቴን ልጨርስ <<<የማትረባ  ፍየል ዘጠኝ ትወልድና

እርሷም ትሞታለች ልጆቿም ያልቁና>>>

እንዳይሆንብን ስለ አገርህ ስትል፣ ስለ አባት እናትህ ስትል፣ ስለ ባል ሚስት ስትል፣ ስለ ልጆችህ ስትል፣ ሽፍታውን በማስወገድ ከፊታችን የተጋረጠውን ጨለማ ገፈን ሰላም የነገሰበት አገር እንመስርት።

 

rtከ-ከተማ ዋቅጅራ 31.12.2014

Email-waqjirak@yahoo.com

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live