Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ኦባንግ ሜቶ ከኢትዮጵያውያን ጋር በሚኒሶታ ሊወያዩ ነው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ታዋቂው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ኦባንግ ሜቶ ወደ ሚኒሶታ በመምጣት የፊታችን ቅዳሜ ዲሴምበር 6 ቀን 2014 ዓ.ም ከኢትዮጵያውያን እና ከትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር እንደሚወያዩ ታወቀ።
Save Ethiopian Meeting with Obang metho in Israel
ቅዳሜ ሴንት ፖል በሚገኘው ኬሊ ኢን ሆቴል ከቀኑ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚደረገው በዚህ ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ኦባንግ ሜቶ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ዙሪያ ከሚኒሶታ ሃገር ወዳዶች ጋር ይየሚነጋገሩ ሲሆን የስብሰባው ዋና ዓላማም በተለይ በተቃዋሚዎች አካባቢ መደረግ ስላለባቸው የጋራ ትብብሮች እንደሚሆን አስተባባሪው አቶ ግርማ ብሩ ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።

“እንደሚታወቀው የኢሕአዴግ መንግስት ላለፉት 23 ዓመታት ካለምንም እፍረት ስልጣኑን በእጁ እንዳስገባ ይገኛል፤ ይህ ሆኖ እያለ ግን በተቃውሚዎች በኩል እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ሁሉም በየፊናው በመሆኑ ትግሉን ወደ አንድ አቅጣጫ ለማምጣትና አንድ ግብ ያለው ትግል ለማካሄድ አቶ ኦባንግ ሜቶን ወደ ሚኒሶታ ጋብዘናል” ያሉት አስተባባሪው አቶ ግርማ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በተጠቀሰው ሆቴል ከቀኑ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በመገኘት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያውያኑ ከኦባንግ ሜቶ ጋር ቅዳሜ ዲሴምበር 3 ቀን 2014 ዓ.ም የሚያደርጉበት የሰብሰባ አድራሻ 161 St Anthony Ave, St Paul, MN 55103 ሲሆን የበለጠ መረጃም በ612-325-8690 ማግኘት እንደሚቻል አቶ ግርማ አስታውቀዋል።

በሌላ ዜና በያዝነው ዲሴምበር ወር በአኝዋክ በአንድ ቀን ከ400 ሰዎች በላይ የተጨፈጨፉበት 11ኛ ዓመት የመታሰቢያ ቀን በዚሁ በሚኒሶታ በጋምቤላ ኮምዩኒቲ አማካኝነት ይዘከራል።


”ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች!”–ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት (የጉዳያችን ማስታወሻ)

$
0
0

እናት አርበኞች

”ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች” ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ሰሞኑን ፓርቲው እና ዘጠኙ አጋር ፓርቲዎች በጋራ በጠሩት በመጪው ቅዳሜ እና ዕሁድ (ህዳር 26 እና 27/2007 ዓም) በአዲስ አበባ የተጠራውን የ 24 ሰዓት የተቃውሞ ሰልፍ አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተናገሩት ንግግር ነው።

ይህ ንግግር አሁን ላለው ትውልድም ሆነ በኢትዮጵያዊነቱ ለሚያምነው ሁሉ ከሰማይ የገዘፈ፣ ሲያስቡት በትንሿ አእምሯችን ልንሸከመው የሚከብድ ግን ከእውነትም በላይ የሆነ እውነት ነው።
arebegnoch
ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ካቆሟት ነገሮች ውስጥ አንዱ ለዘመናት የኖረው ሕግ ነው።ዓለም እንደ ዛሬው ስለ ሕግ ብዙ ሳይናገር በቤተ መንግስቱ እና በሕዝቡ መካከል የሚያገናኙ ሕጎች ነበሩ።የተበደለ ፍትህ የሚያገኝበት፣አቤት የሚልበት ቦታ ነበረው።በዳኝነት የተቀመጠውም ህሊናውን እና አምላኩን የሚፈራበት መመዘኛ ነበረው።ፍፁምነት በእራሱ ከሰው ልጅ ባይጠበቅም እንደ ማህበረሰብ፣እንደ ሕዝብ እና እንደ መንግስት ኢትዮጵያ እና ህዝቧ ለሺህ ዓመታት ሲዳኝ የኖረው ከፈረንሳይ ሀገር በመጣ ወይንም ከእንግሊዝ በመጣ ሕግ አይደለም። ሃይማኖታዊ መሰረቱን በያዘ፣ህሊናን እና ህዝብን ታሳቢ ያደረገ ሕግ እና ፍርድ ለዘመናት አኑረውናል።

ይህንን ሕግ እና በነፃነት የመኖር ፀጋን አባቶቻችን በነፃ አላገኙትም።ወጥተው እና ወርደው ደምተው እና ቆስለው ያቆዩት እኛነታችን ነው።ለእዚህ ነው ዛሬ ላይ ሆነን ለነገ ለማስተካከልም ሆነ የምናወራው ስለ ምን ዓይነቷ ኢትዮጵያ እንደሆነ ለማስታወስ ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት ሀገር መሆኗን ለአፍታም አለመርሳቱ ተገቢ የሚያደርገው።ብዙ የተደከመባት ብቻ አይደለም ብዙ ታላልቅ ሰዎች የተሰዉላት ሀገር ነች።ኢንጅነር ይልቃል ያስታወሱን እኔም በአምሮዬ ሲመላለስ የከረመው አረፍተነገር ይህ ነው።

ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች

ኢትዮጵያ ንግስት ሳባ በሴት አቅሟ በረሃ ለበረሃ ተንከራታ ኢየሩሳሌም ድረስ ሄዳ ታቦተ ፅዮንን ያመጣችላት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ ንጉስ ካሌብ እስከ የመን የሀገሩን ስም ይዞ ሄዶ በባርነት የተያዙትን ናግራውያንን ነፃ ያወጣባት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ የመሐመድ ቤተሰቦች ተሰደው በክብር ተቀብላ መጠለያ ሰጥታ እስልምና ሃይማኖትን ለዛሬ አማኝ የሰው ልጆች በሙሉ ከመጥፋቱ በፊት የታደገች ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ በዘመነ ዮዲት (ጉዲት) ለአርባ ዓመት የመከራ ዶፍ ሲወርድባት ከመከራው ጋር የነደዱ፣በእሳት የተቃጠሉ፣በጦር የተወጉ ለሀገራቸው እና ለህዝባቸው ክብር በሰይፍ የተቀሉ ጀግኖች የሞቱባት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ ክብር ፣ለሌሎች ነፃነት እና ለእምነታቸው ፅናት የተጉ እነ አፄ ዳዊት፣ነገስታቷ ግብፅ ያሉ ህዝቦች ተጨቆኑ ብለው በሱዳን በረሃ ተንከራተው የግብፅን ሕዝብ ከመከራ የታደጉ ሲመለሱም የክርስቶስን መስቀል ይዘው የተመለሱ በመንገዳቸው መከራ ህመምን ታቅፈው ሀገራቸው ድንበር ላይ የሞቱባት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ ባዕዳን እንግሊዞች ሀገራችውን እና ወገናቸውን በከዱ ባንዳዎች እየተመሩ ሲመጡ እጅ አልሰጥም፣ኢትዮጵያን መሳቅያ አላደርግም ብለው የገዛ ሽጉጣቸውን ጠጥተው የሞቱባት አፄ ቴዎድሮስ የተሰዉላት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ ራስ አሉላ ”ፈረሴ የቀይ ባህርን ውሃ ሳይጠጣ አይመለስም” ብለው በባህረ ነጋሽ በረሃዎች ተንከራተው የሀገራቸውን ክብር ያስጠበቁ የተሰዉላት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።
ኢትዮጵያ አፍሪካን በጠረንጴዛ ዙርያ ተሰብስበው ለመቀራመት ከተስማሙ በኃላ ሊወራት የመጣውን ጣልያንን ለመዋጋት ለወራት በእግራቸው እስከ አድዋ ድረስ ተጉዘው መስዋዕት የተቀበሉባት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ ኢጣልያ ዳግም በ1928 ዓም ሲወራት ከሊቅ እስከ ደቂቅ በረሃ ለበርሃ ተንከራተው ከውስጥ አርበኛ እስከ ዓለም አቀፍ ሙግት ገብተው፣ከጳጳሳቷ እስከ ሕፃን ሰማዕት የሆኑባት፣በአዲስ አበባ በየካቲት 12 ቀን ብቻ ከአስር ሺህ በላይ የንፁሃን ደም በአካፋ እና በዶማ ጭምር የፈሰሰባት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ እነ ሞገስ አስገዶም እና አብርሃም ደቦጭ በአርበኝነታቸው ተይዘው ጥፍራቸው እየተነቀለ ተሰቃይተው የሞቱላት ሀገር ነች ኢትዮጵያ።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

Ethiopians on Sunday celebrated the 118th anniversary of the Adowa battle when an untrained Ethiopian army routed a better equipped Italian invasion army. Photo Credit: Turkish Press

Ethiopians on Sunday celebrated the 118th anniversary of the Adowa battle when an untrained Ethiopian army routed a better equipped Italian invasion army.
Photo Credit: Turkish Press


ኢትዮጵያ በሮም ጣልያን አደባባይ ጎራዴ መዘው የጣልያንን ፋሽትትን የቀሉ በመጨረሻም ለሞት ሰማዕት የሆነላት ዘርአይ ድረስን ያበቀለች ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ ከጣልያን እስር ቤት አምልጦ በገዛ የጣልያን በረሃ ሸፍቶ ፋሽትን ያርበደበደ በመጨረሻም በድል የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እያውለበለበ ሮም የገባ እና ከአዲሱ የጣልያን ፕሬዝዳንት የገዛ የእጅ ሰዓታቸውን አውልቀው የሸለሙት ጀግና አብዲሳ አጋን ያፈራች ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ የተሻለ አስተዳደር ያስፈልጋታል።ብለው እራሳቸውን የሰጡ ጀግና የጦር ኃይል አባላት እነ ጀኔራል መንግስቱ ንዋይ እና ገርማሜ ንዋይ በስቅላት አንገታቸውን ለገመድ የሰጡላት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ አሁንም የተሻለ አስተዳደር ያስፈልጋታል፣”ሕዝባዊ መንግስት አሁኑኑ!” ያሉ በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች ለሞት እራሳቸውን የሰጡባት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ የዚያድባሬ ሱማልያ ”ቁርስ ድሬዳዋ፣ምሳ አዲስ አበባ” ብላ በምትፎክርበት ወቅት ከሶስት መቶ ሺህ በላይ ወዶ ዘማች ባጭር ጊዜ ለኢትዮጵያ እሞትላታለሁ ብለው የተሰለፉላት እና ሺዎች በፈንጅ ላይ እየተራመዱ ሞተው ሀገራቸውን ለክብር ያበቁ ዜጎች የወለደች ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ አንድነቷ አይናጋም፣አትቆራረስም፣በጎሳ እና በዘር አትከፋፈልም ብለው ሰማዕት የሆኑላት እንደ ምፅዋ በነበረው የእርስ በርስ ውግያ ሳንጃ በሳንጃ እየተሞሻለቁ ከአፈር የተደባለቁላት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ አሁንም ከአምባገነናዊ አገዛዝ ትላቀቅ ብለው ተነስተው በመጨረሻ ሰንደቅ አላማዋን ተጠቅልለው በመከላከያ ሚኒስትር ቢሮ ውስጥ የተሰዉላት እነ ጀነራል መርድን፣በሰሜን እኔ ብ/ጄነራል ደምሴ ቡልቱን፣ኮለኔል ታሪኩን ያፈራች መሬት ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

አዎን ! ዛሬ በጎሳ እና በከፋፋይ አገዛዝ እጅ ወድቃ ብትቆስልም ኢትዮጵያ ብዙ ደም የፈሰሰላት፣ብዙዎች የደከሙላት ወደፊትም የሚደክሙላት ሀገር ነች።ዛሬ ኢትዮጵያን ስናስብ ይህንን ሁሉ ድካም እና እንደጎርፍ የፈሰሰው ደም ሊታወሰን ይገባል።

ይህንን ሁሉ ነው የኢንጅነር ይልቃል ንግግር ያስታወሰኝ።ይህንን ስናስብ ነው በሀገራችን ምን ያህል እንደቀለድን ሀገራችንን ለአልባሌ እዚህ ግባ ለማይባል ዘረኛ ቡድን ሰጥተን ግማሾቻችን ለስደት የቀረነው ለህሊና እስረኝነት መዳረጋችን የሚያንገበግበው።

አዎ እያወራን ያለነው ስለ ኢትዮጵያ ብዙ ስለተደከመላት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች ስለተሰዉላት ሀገር ነው።አዎን!! ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች! ይህ ትውልድ የሀገሩን ክብር ማስመለስ ያለበት ወሳኝ ጊዜ ላይ ነው።ሁሉ እንጀራ ጋጋሪ አይሆንም።ሁሉም ወጥ አይሰራም።ባለን በችሎታችን ለሀገራችን ካልሰራን ከሞቱት አንሰናል።ብዙዎች የደከሙላት እና የሞቱላት ሀገር ላይ ቸል የማለት መብት የለንም።

ጉዳያችን
ህዳር 24/2007 ዓም (ደሴምበር 3/2014)

ከ5 ሚሊዮን የማያንሰው ዐማራ ዬት ደረሰ?

$
0
0

moreshየትግሬ-ወያኔ ለ17 ዓመታት በሽፍትነት፣ ለ23 ዓመታት ደግሞ በገዢነት ተፈናጦ በዐማራ ሕዝብ ባደረሰው የዘር ማጽዳት እና የዘር ማጥፋት ዘመቻ ምን ያህል ንፁሃን ዐማሮች እንደተጨፈጨፉ የተለያዩ አስተያዬቶች ሲደመጡ ቆይተዋል። ሞረሽ ወገኔ ባደረገው ዝርዝር የሕዝብ ብዛት ቆጠራ ትንተና መሠረት ከ1983ዓ.ም. ወዲህ ደብዛቸው ከምድረ-ገፅ እንዲጠፉ የተደረጉት ዐማሮች ብዛት ከ5 ሚሊዮን እንደማያንስ ይጠቁማል። ይህ ምንን ያመለክታል? ከጥናቱ ውጤት የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ጎልተው ይወጣሉ።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው አገር አቀፍ ብሔራዊ የሕዝብ ቆጠራ የተካሄደው በ1976 ዓ.ም. ነበር። በወቅቱ ኤርትራን እና የአሰብ አስተዳደርን ጨምሮ ጠቅላላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት 42,616,876 ያህል ነበር። በኤርትራ እና በአሰብ አስተዳደር ኗሪ የነበሩት ዜጎች ቁጥር ሲቀነስ በቀሪዋ ኢትዮጵያ ይኖር የነበረው ሕዝብ ብዛት 39,868,572 ይሆናል። በወቅቱ በሕዝብ ብዛት አንደኛ የነበረው የኦሮሞ ነገድ ብዛቱም 12,387,664 ሲሆን፤ እንዲሁም ዐማራ በሁለተኛ ደረጃ12,055,250 ያህል ተወላጆች ነበሯቸው። ስለሆነም በወቅቱ በሁለቱ ነገዶች ተወላጆች ብዛት መካከል የነበረው የቁጥር ልዩነት 332,414 ይሆናል ማለት ነው። የመጀመሪያው የሕዝብ ቆጠራ ከተደረገ ከ23 ዓመታት በኋላ፣ ማለትም በ1999 ዓ.ም. በተደረገው ሦሥተኛው የሕዝብ ቆጠራ ውጤት መሠረት ዐማራው ቁጥሩ በአዝጋሚ ሁኔታ ወደ 19,867,817 ሲጨምር የኦሮሞዎቹ ብዛት ግን ከእጥፍ በላይ አድጎ ወደ 25,488,344 ደርሷል። ስለዚህ በኦሮሞ እና ዐማራ ተወላጆች ብዛት መካከል ያለው የቁጥር ልዩነት 5,620,527 አሻቅቧል ማለት ነው። በዐማራው እና በኦሮሞው መካከል የነበረው የቁጥር ልዩነት ተመጣጣኝነት እንዳለ እንደተጠበቀ ይቀጥል ቢባል እንኳን ከ23 ዓመታት በኋላ ሊኖር የሚችለው ልዩነት ከ664,828 አይበልጥም። በመሆኑም ከ5ሚሊዮን የማያንሰውን ዐማራ ዬት እንዳደረሱት የሚያውቁት የትግሬ-ወያኔዎች እና ሎሌዎቻቸው ናቸው።

ባለፉት 23 ዓመታት ከ4,751,333 በላይ የዐማራ ነገድ ተወላጅ የጠፋው ወያኔ ገና የትጥቅ ትግል ሲጀምር «የትግራይ ሕዝብ ደመኛ ጠላት ዐማራ ነው፤» « ዐማራን፣ የአማርኛ ቋንቋን እና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ማጥፋት አለብን!» ብለው የተሰለፉ በመሆናቸው የዐማራውን ነገድ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በመግደላቸው ነው። በግልፅ እንደሚታወቀው ወያኔ የዐማራውን ነገድ በሚከተሉት ሥልቶች አጥፍቷል። እያጠፋም ነው፥

  • በተለያዩ ሰበቦች በጅምላ በመግደል፦ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በሠቲት፣ በአርማጭሆ፣ በራያ ሕዝብ ላይ የፈፀሙት የግፍ ግድያ፣
  • በአሰቦት ገዳም፣ በአርባ ጉጉ፣ በወተር፣ በበደኖ በሌሎችም የሐረርጌ እና አርሲ አካባቢዎች ይኖሩ በነበሩ ዐማሮች ላይ የፈፀሙት የግፍ ጭፍጨፋ፤
  • በወለጋ፣ በኢሉባቡር፣ በጅማ ያካሄዷቸው ዐማራን በጅምላ የመግደል ዘመቻዎች፤
  • ከ1983 -1987 ዓ.ም. ድረስ በሕወሓት ሠራዊት አማካይነት በሸዋ፣ በወሎ፣ በጎጃም እና በጎንደር ኗሪ በሆኑ ዐማሮች ላይ የ«ሽፍታ ምንጠራ» እና «ብረት ማስፈታት» የሚሉ የሽፋን ዘመቻዎች በማካሄድ በፈፀሟቸው ጭፍጨፋዎች፤
  • ዐማራውን በተለያዩ ተፅዕኖዎች በማስፈራራት ዐማራነቱን ክዶ የሌላ የነገድ ማንነት እንዲቀበል በማስገደዳቸው፤
  • ዐማራውን እየለዩ ከሥራ በማባረር በርሃብ በመጨረሳቸው፤
  • «የመሬት ድልድል» በሚሉት እና ዐማራን «መሬት አልባ የትግሬ-ወያኔ ጭሰኛ» ለማድረግ በቀየሱት ፖሊሲ ዐማራው ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ተለይቶ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል አርሶ እና ሠርቶ እንዳይኖር በማድረጋቸው፤
  • ነባሩን የወባ መከላከያ ድርጅት ዘግቶ ድርጅቱን ወደ ትግራይ በማዛወር የዐማራውን ነገድ ተወላጆች የወባ መከላካያ አገልግሎት በማሳጣት አያሌ ዜጎች እንዲያልቁ በማድረጋቸው፣ በተለይም በጎጃም ሕዝብ ላይ ከ1985-1989 ዓ.ም. ያደረሱት እልቂት በምሣሌነት ይጠቀሣል፤
  • የዐማራውን ነገድ ተወላጆች በዘር ጠላትነት ፈርጀው የኤች.አይ.ቪ./ኤድስ ቫይረስን በመርፌ በማስተላለፍ በገፍ እንዲያልቁ በማድረጋቸው፤
  • የዐማራውን ተወላጆች መሠረታዊ የጤና አገልግሎት በመንፈግ በተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች እንዲያልቁ በማድረጋቸው፤
  • በወሊድ ቁጥጥር ስም የነገዱን አባሎች መካንና ታማሚ በማድረጋቸው፤
  • ከዐማራ የጸዱ ክልሎችን ለመፍጠር በተያያዙት የዘር ማፅዳት ዘመቻ «ኦሮሚያ፣ ደቡብ ብሔር-ብሔረሰቦች፣ ቤንሻንጉል-ጉምዝ፣ ጋምቤላ፣ አፋር እና ሶማሌ» ብለው በከለሏቸው «ባንቱስታን-መሠል» ግዛቶች ይኖሩ የነበሩት ዐማሮችን በግፍ እና በገፍ በማባረር፣ በመግደልና በመደብደብ ለተደራራቢ ችግሮች በማጋለጣቸው፤

ለዐማራው ነገድ ቁጥር መቀነስ ዋና እና ተያያዥ ምክንያቶች ናቸው። ስለሆነም ያለምንም ማወላወል የዐማራው ነገድ በትግሬ-ወያኔ በተከፈተበት የማያባራ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ዘመቻ ሰለባ መሆኑን ትውልዱ ሊገነዘበው ይገባል።

በተለይ ለዐማራው ነገድ ተወላጆች እና ለሃቀኛ ኢትዮጵያውያን የቀረበ ጥሪ፦

ይህን መረጃ በማባዛት ለዓለም ሕዝብ ባሉት የመገናኛ መሣሪያዎች በመጠቀም በማሰራጨት፣ ሆን ተብሎ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለተፈጸመበት የዐማራ ነገድ ድምፅ ልንሆን ይገባል። ለተበደሉ እና የመኖር ሰብአዊ መብት ለተነፈጋቸው ሰብአዊ ፍጡሮች ድምፅ መሆን ዘረኝነት ወይም ጠባብነት አይደለም። በመሆኑም የዐማራው ተወላጆች ብቻ ሣይሆኑ፤ ለሰብአዊነት የቆሙ ሁሉ ለዚህ ነገድ ድምፅ ከመሆን አልፈው፣ በኢትዮጵያውያን ላይ ይህን ዓይነት የከፋ ወንጀል የሚፈፅሙትን ለፍትኅ አደባባይ ለማቅረብ ለተያያዝነው ትግል፥ የመረጃ፣ የምክር፣ የዕውቀት እና የገንዘብ ልገሣ እንድታደርጉልን በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

 

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!

የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት ዳግም ትንሣዔ በቆራጥ ልጆቿ ተጋድሎ ዕውን ይሆናል!

Health: 10ሩ የእንቁላል የጤና በረከቶች

$
0
0

egg and health
(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም)

እንቁላል ሁሌም በገበያ ላይ የሚገኝ እና ለብዙ ምግቦች በአዘገጃጀት ወቅት የምንጠቀምበት እና በውስጡ ለሰውነት ጠቀሜታ ያላቸውን ንጥረ ነገሮችን የያዘ የዘምግብ አይነት ነው፡፡
1. እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ የምግብ አይነት ሲሆን 6 ግራም የሚሆን ፕሮቲኖችን ይዟል፡፡ እነዚህ ፕሮቲኖችም ለሰውነት እድገት ከፍተኛ ጠቀሜታ አላቸው፡፡
2. እንቁላል ኮሊን (choline) የሚባል ለአእምሮ እና ለልብ ተስማሚ እና አስፈላጊ የሆነ ንጥረ ነገርን ይዟል፡፡
3. እንቁላል ዓይናችን በጸሃይ ጨረር እንዳይጎዳ የሚያደርግ ጠቃሚ ንጥረ ነገርም በውስጡ ይገኛል፡፡
4. ጥናቶች እንደሚያሳዩት እንቁላል የተለያዩ የካንሰር አይነቶችን የመከላከል አቅም አለው ፡፡ በተለይም የጡት ካንሰርን ከመከላከል አንጻር አፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡
5. እንቁላል የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅምን በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል፡፡
6. እንቁላል ለሰውነት ጤንነት ተስማሚ እና የተመጣጠነ ክብደት እንዲኖረን የሚያደርግ የቅባት አይነት በወስጡ ይዟል፡፡
7. እንቁላል ከፍተኛ የሃይል ምንጭ ነው
8. እንቁላል በወስጡ ተፈጥሯዊ ቫይታሚን ዲ (vaitamin D) ስላለው ጤናማ እና ጠንካራ የአጥንት ጥርስ እንዲኖረን ያደርጋል፡፡
9. በእንቁላል ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚመለክቱት እንቁላል ከድንገተኛ የልብ ህመም፣ የደም መርጋት እና ድንተኛ ከሆነ የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስን ይከላከላል ፡፡
10. እንቁላል ለጸጉር ተስማሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ስለያዘ ለጸጉር እና ለጥፍር እድገት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

ብሔራዊ ደዌአችን በፈውስ ዋዜማ ላይ ይሆን?

$
0
0

ከሚካኤል ዲኖ

ይህ ፅሁፍ በጥልቅ ጨለማ ውስጥ ከወደቀ መንፈስ የፈለቀ ነው፡፡ በዓለሙ ሁሉ የሚከናወነው ግፍና በደል እንዲሁም የሰብዓዊነት መጣጣል እለት በእለት ወደ ጥልቁ ከሚደቀፅቃት መድረሻ ቢስ ስንኩል ነፍስ በጣር ወደህዋው የተወነጨ በህቅታ የታጀበ እውነት ነው፡፡
hana and sayat

ምስኪኗ ሀና
አንቺ የዓፉዐን ናሙና
ወግቶኛል ህመምሽ
ቆጥቀቁጦኛል እንባሽ
አምናለሁ
ፍርድ ከላይ ነው
ግምድል ነው ከታች ያለው
አምናለሁ
አካልሽ ቢዝልም በርኩሳን ሥራ
ነፍስሽ ግን ታርፋለች በቅዱሳን ስፍራ›

በርትራንድ ረስል «ማኅበረሰብ ያለሴተኛ አዳሪ መኖር አይችልም» ይላል አስቀያሚ እውነት ነው፤ በሌላ መልኩ ሰው ሀጥያት ሳይሰራ ሊኖር አይችልም ማለትም ነው፡፡ የኛ ማህበራዊ ተራክቦም ከዚህ እውነታ አያፈነግጥም፡፡ በአስፈሪ ሁኔታ እየተንኮታኮተ ለሚገኘው የስነ- ምግባር ምሰሷችን አይነተኛ ማሳያ ለመሆኑ ምስክር የሚያሻው አይመስለኝም፡፡ ‹‹ሀይማኖተኛ ነኝ›› እያለ በሚመፃደቀው ሕዝባችን መሃል በስውር ህልውና ይንሳፈፍ የነበረው የዝሙት ተግባር ጨለማን ተተግኖ መሬት ከመርገጥ አልፎ በቀን ብርሃን በተለያየ ሽፋን ቢሮዎችን ከፍቶ፣ ከግዜ ወደግዜ ቁጥራቸው እየናረ የሚሄደውን ደንበኞቹን በትጋት እያገለገለ ይገኛል፡፡ ባሳለፍነው እሁድ ረፋድ በሸገር ካፌ በርቀት ታድሜ በዚህች ታዳጊ ቅጭት ዙሪያ የሬዲዮ ጣቢያው ጭንቅላት የሆነችው መዐዛ ብሩና ዶ/ር ምህረት ደበበ ያደረጉትን ውይይት አዳምጫለሁ፡፡

በውይይት ጠረጴዛው ከውጤቱ ይልቅ ወደፍንጩ ለማተኮር መሞከሩ ተገቢ ነው፡፡ከጭካኔና ከኋላቀርነት ጋር የተላቆጠውን ባህላችንን በርህራሄና በዕውቀት እያነጠሩ መልካሙን አጥልሎ ዝቃጩን በማስወገድ ፈንታ ሌላ ወገን ላይ ለመደፍደፍ ሲሞከር ይታያል፡፡ ከነጮቹ አለም በርካታ በካይ ነገሮች ወደ ውስጣችን መዝለቃቸው አያጠያይቅም፡፡ ይህም ሆኖ በገዛ ድንቁርናችን ያዛነፍነውንና በስንፍና ያስቀጠልነውን ባዕድ ላይ መላከክ አይጠቅምም፡፡ በዚህ መሠሉ የእሮሮ አውድ ከሚቀርቡ ልጠፋዎች አንዱ ሴተኛ አዳሪነትን ያመጣብን ጣልያን ነው የሚለው አንደኛው ነው፡፡ እንደ እውነቱ ግን ከጣልያን ወረራ በፊትም በንፅህና የኖርን ሕዝቦች አይደለንም፤ ከወረራው በፊት በነበረው ባህላችን የሰው ሚስት መወሸም፣ ባለትዳር ቢኮንም ተጨማሪ ሴትን በተጠባባቂነት ማስቀመጥ፣ የጭን ገረድ፣ በተገኘው አጋጣሚ መወስለት እንደነበር አያጠያይቅም፡፡ጣልያን በአምስት አመቱ ያልተረጋጋች ህልውናው ያደረገው ነገር ቢኖር እንዲህ ተበጣጥሶና መልክ አልባ ሆኖ የከረመውን ሀጢያት ተቋማዊነት ማላበስ ብቻ ነው፡፡

አምላኩን ከሰርክ ተግባሩ አባሮ በሃይማኖት ለበስ ድግሱ እንዲሁም በምላሱ ብቻ ቦታ የሰጠ ማህበረሰብ ሀጥያተኛ እንጂ ወንጀለኛ መሆን አልነበረበትም፤ ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ድርብ ውድቀትን ተላብሷል፡፡ አሳዛኙ እውነታም ይኼው ነው፡፡ ከእምነትም፣ ከህሊናም በመለስ ስናስብ ሴተኛ አዳሪዎች ለማህበረሰቡ ደህንነት እጅግ አስፈላጊ ናቸው፡፡ ነውሩ የወጠረውን ክልፍልፍ በተረገመው መንገድ ተደራድረው ሃጥያቱን በማስፈሰስ፤ ይሄ አማራጭ ባይኖርለት ኖሮ በማህበረሰቡ ውስጥ ይፈጥር ከነበረው ትርምስ ራሱንም መንጋውንም ይታደጉታል፡፡ ይሄ ያልተጠና ድንበር፣ በሚያስደነግጥ መልኩ የሌለ ያህል እየተጣሰ ቀሪውም ማህበረሰብ ከማንና መቼ እንደሚከፈትበት የማያውቀውን ጥቃት እያሰበ በፍርሃት ይማቅቃል፡፡ አምላኩን ቸል ያለ ሃጥያተኛ፣ ህሊናውን ያዳፈነ ነውረኛ፣ ሕግን ያልፈራ ወንጀለኛ ….. የዛሬው ማንነታችን እውነተኛ መልክ ነው፡፡ ዛሬ በየትኛው ዝምድና
መተማመን ይቻላል? አባት ልጁን ይተኛል… ወንድም እህቱን ይጎዳኛል…. አያት የልጅ ልጁን ያስረግዛል … ልጅ እናቱን ይቃብዛል… በሰቀቀን እየኖርን ነው፡፡ ሁላችንም ለሰለባነት ታጭተናል፡፡ ወንድ መሆን ከጥቃት እንደማያድን አይተናል፡፡ ዳዴ ማለት በሰይጣን ክንፎች ከሚበረው ንስር እይታ
ውጪ እንዳልሆነ ሰምተናል፡፡ በእርጅና ዝሎ በዱላ ለመራድ መንገታገትም መስፈርት ሆኖ ከመቅሰፍቱ አላዳነም፡፡ በአንድ ማንነት ውስጥ ካለው ሁለትነት ጋር ተስማምቶ ለመተግበር የሚከብደውን ነውር፣ ሁለት ሶስት ሆነን በመመካከር ሰውን በቁሙ ወደ መብላት ተሸጋግረናል፡፡

በዚች ምስኪን ላይ የደረሰው ግፍ ይፋ ከሆነ በኋላ በወንጀለኞቹ ላይ ከማህበረሰቡ ከፍተኛ ውግዘት የፍርድ ሀሳብ ጭምር እየተሰነዘረ ይገኛል፡፡ የአስተያየቶቹ መግፍኤ የድርጊቱ ዘግናኝነት እና የልጅቷ ፍፃሜ አሳዛኝነት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ መረሳት የሌለበት ነገር ግን ሕግ አለ፡፡ የትኛውም ወንጀል፣ ምንም አስከፊ ቢሆን ሕጉ ካስቀመጠው የቅጣት ጣራ በላይ ሊያስቀጣ አይገባም፡፡ በስሜት ለተፈፀመ ጭካኔ የስሜት ቅጣት ለመስጠት መሞከር ለነገ አንዳች ትርፍ አይኖረውም፡፡ ለዚህም በምሳሌነት በቅርቡ ኖርዌይ ውስጥ አንድ አውቶማቲክ መሣሪያ የያዘ ወፈፌ ወደ አውራ መንገድ ብቅ ብሎ ወደሰባ አካባቢ ሰዎች የጨፈጨፈበትን ታሪክ ማንሳት ይቻላል፡፡ የሀገሪቱ ህግ ከፍተኛ የቅጣት ዘመን ሀያ ሁለት አመት በመሆኑ የተፈረደበት ይኸው ነው፡፡ ይህን ተከትሎ ግን ህጉን በመከለስ ቅጣቱን ከፍ አድርገውታል፡፡ በሌላ መልኩ በዚህ የወል ኩነኔ ውስጥ ራስን የማፅደቅ፣ እጅን በ “ከደሙ
ንጹህ ነኝ” ዘይቤ የመታጠብ ውስጣዊ አላማም ይታየኛል፡፡ “ከናንተ መሀል ንፁህ ነኝ ብሎ . . .” የሚል ተጋፋጭ እንደሌለ ተገንዝቦ ለወገራ ማሰፍሰፍም ይስተዋላል፡፡

እኛስ ግን ማን ነን? ወንድን በንጉስነት ሴትን በባርነት የበየነ ባህል ባለቤቶች አይደለንም እንዴ? ሴት ልጅን አናንቀን ወንድን ልጅ አተልቀን የምናሣድግ ቤተሰቦች አይደለንምን? ንቀት እና ጭካኔ መግበን እንዲህ ያሉ አረመኔዎችን አብቅለን ስናበቃ፣ መሠቀያቸውን ለማዋቀር ደፋ ቀና ማለት እኛን ያነፃናልን? ደፍረን መድፈር ባንችል በትዳራችን ላይ አንወሰልትም? በስሜት ተነድተን በጓደኛችን ላይ አንሄድም? ዝምድናን አንሰብርም? “በጨለማ ያደረከውን በብርሃን አወጣዋለሁ” መባሉን ዘንግተን በምሽት ሴተኛ አዳሪ አልጎበኘንም? ሌላው ቢቀር በመንገድ በምኞት ተሞልተን የቆንጆ ሴት ቀሚስን በምናብ ገልጠን አልቃዥንም? ታዲያ እኛ . . . ? ? ? ደፍሮ ከደፈረው፣ ያኮበኮበው እጅግ ይበልጣል፡፡ ዛሬም ሀናዎች እልፍ ናቸው፡፡ በእርግብ ንፅህና ገላጣ ሜዳ ላይ ይርመሰመሣሉ . . . ቁራዎችም አመቺ ወቅት ፍለጋ በላያቸው ያንዣብባሉ፡፡ በብዙ መልኩ እየዘቀጥን ነው፡፡ ይሄ
አንደኛው መልክ ብቻ ነው፡፡ ምናልባትም ለራሱ ክብር የማይሰማው፣ አምላኩ መኖሩንም ከጭርታው ይሻላል በማለት የተቀበለ ሰዋዊነቱንም ከእንስሳዊ እውነታው አሻግሮ መመልከት የማይሻ መንጋን አኗኗር በማሳያ ለማስደገፍ ሲባል ብቻ የሚጠቀስ አይነት ብቻ ነው፡፡

በሚደንቅ ሁኔታ በመገናኛ ብዙሃን ስለዚህ ጉዳይ በተነገረ መጠን ውግዘቱና እርግማኑ ተገልብጦ አንደማስታወቂያ እያገለገለ ይገኛል፡፡ መሻቱ ተዳፍኖ ለሚግለፈለፍበት ያገነፍልለታል፡፡ ጭራሽ ውጥኑ የሌለው ላይ ደግሞ ሃሳብ ያጭርበታል፡፡ በየመስኩ ያለውን የኢትዮጵያውያን ሁኔታ ጠቅለል አድርጌ ስመለከተው እጅግ ተስፋ አስቆራጭ ነው፡፡ በተስፋ ለማፍጠጥ የምሞክረው ድቅድቅ ያለ ጨለማማ ዋሻ ውስጥ ሆኜ ነው፡፡ በጨለማው ከማልቀስ ብዬ የምለኩሳት ሻማም ዙሪዬን በሚርመሰመሱት ዞምቢዎች ትንፋሽ ትጠፋለች፡፡ አንዳንዴ አንደውም በማይገፉት የተንሰራፋ ጨለማ ምስኪን ብርሃን መለኮስ ራስን ኢላማ ውስጥ መክተት ይመስለኛል፡፡ ሰው በመሆን መሰልቸት፣ በኢትዮጵያዊነት ችግር ሃዲድ ላይ ለዘመናት መንኳተት ሳቢያ ሙትትት እያለ ካለው መንፈሴ ውስጥ በልብ ትርታ ምት የምትመሰል ስልምልም ተስፋ ግን አንዲህ ትለኛለች . . . “ግን ምልባት ድቅድቅ ያለው ጨለማ
በንጋት ድንበር ላይ እንደሆነስ? ምናልባት ድንዛዜው ከንቃት ጥቂት ርቀት ላይ እንደሆነስ? ብሔራዊው ደዌ በፈውስ ዋዜማ እንደሆነስ….? ምናልባት …..” ትርታው ወደ ድለቃ ሲያድግ ይሰማኛል፡፡ ማን ያውቃል ለመኖር ያለኝን የፍላጎት እስትንፋስ አፍኖ ሊገድላት የደረሰው ተስፋ መቁረጥ እየተምዘገዘገ ከነበረበት የገደል መሬት ሳይላተም ነጥሮ ዳርቻው ላይ በማረፍ የህይወትን ዙሪያ ገባ በተስፋ አይን ይማትር ይሆናል፡፡ ማን ያውቃል???

ዘመን ሞቷል –ኃይሉ አትበሉ (ወለላዬ ከስዊድን)

$
0
0

hai2

ማስታወሻው ጠፍቶ ምስሉ

ተገርስሶ ወድቆ አካሉ

ተሰርዞ ቃለ ውሉ

ዘመን ሞቷል ኃይሉ አትበሉ።

 

ታሪክ የለም አምልጦናል

ዘመን ቆመን ሞቶብናል

ሁሉም አልቆ ተጠቃሏል

ጋሼ ኃይሉ ይዞት ሄዷል

 

ለዘመን ነው እንባ ማፍሰስ

ለታሪክ ነው ከል መልበስ

ለጊዜ ነው ፊት መከስከስ

ለጋሽ ኃይሉ ይብቃን ማልቀስ

 

የዘመንን በሞት ማምለጥ

የጊዜውን መገላበጥ

ገና በፊት ጋሼ ኃይሉ

ተናግሮታል በአፉ ሙሉ

መጣ ብለን ሚሊኒየም

በክብሩ ላይ ልንታደም

ወዲያ ወዲህ ስንሯሯጥ

ምድር ስንቀድ ሰማይ ስንፈልጥ

ከረምንና አገር ወጥቶ

ተበልቶና ተጠጥቶ

ጋሼ ኃይሉ ብቻ ቀርቶ

ምነው ጠፋህ? በዚህ በዓል

አንተ ብቻ ብሎ ሲባል

ያልኖርኩትን አላከብርም

ይሄ በዓል የኔ አይደለም

መች ኖሬ ነው የማከብረው

የኔ ዘመን ሞቷል ተወው

ብሎ ነበር መልስ የሰጠው

 

ጋሼ ኃይሉ እንዲህ ልቆ

ከዘመኑ ተራርቆ

ከጊዜው ጋር ተናንቆ

አንድ ራሱን ብቻ ችሎ

አንድ ራሱን ብቻ ጥሎ

ቢገላገል ቢሄድ ከፍቶት

አረፈ እንጂ ሞተ አትበሉት

 

ታሪክ የለም አምልጦናል

ዘመን ቆመን ሞቶብናል

ጋሼ ኃይሉ ይሄን አውቋል

ቀደም ብሎ መኖር ትቷል

 

ማስታወሻው ጠፍቶ ምስሉ

ተገርሶ ወድቆ አካሉ

ተሰርዞ ቃለ ውሉ

ዘመን ሞቷል ኃይሉ አትበሉ።

 

ትልቁ ሰው ጋሼ ኃይሉማ

ገና ድሮ ይዞ ዓላማ

ተልኮውን እስኪጨርስ

አጠገቡ ሞት እንዳይደርስ

ብዙ ሮጧል ብዙ ሰርቷል

አሸንፎት ሞትን ኖሯል

አሁን ግና ሰርቶ ደክሞት

ቤቱ ድረስ ሲመጣ ሞት

ተቀብሎ በሩን ከፍቶ

ሳይከፋ ተደስቶ

ስለሄደ ተሰናብቶ

ይበቃናል እንባ ማፍሰስ

በረፍቱ ላይ አንላቀስ

ወዲያ ወዲህ አናዋክበው

በኡኡታ አናጅበው

በዋይታ አንቀስቅሰው

በጥሞና በእርጋታ

እንሸኘው በዝምታ

 

ጋሼ ኃይሉን የምታውቁት

ወዳጆቹ ምታከብሩት

የበፊቱን አታስታውሱት

እባካችሁ እንባ ተዉት

ታሪክ ቆመን የሞተብን

እውነት ፊቱን ያዞረብን

ዘመን ጥሎን ያመለጠን

እሱ ሳይሆን እኛ እኮ ነን

ጋሼ ኃይሉ ሞቱን አውቋል

ቀደም ብሎ ተሰናብቷል

እየኖረም መኖር ትቷል

 hai3

ማስታወሻው ጠፍቶ ምስሉ

ተገርስሶ ወድቆ አካሉ

ተሰርዞ ቃለ ውሉ

ዘመን ሞቷል ኃይሉ አትበሉ።

***

ወለላዬ ከስዊድን (welelaye2@yahoo.com)

ስምንት ጠቃሚ ነጥቦች ከእስራኤላውያን -ክፍል 5 (ዮፍታሔ)

$
0
0

ከዚህ ቀደም በነበሩት 4 ክፍሎች የእስራኤልን ታሪክ በአጭር በመቃኘት ስለአንድ ማዕከላዊ ድርጅትና ስለተቋማት አስፈላጊነት፣ ትግሉን ዓለምአቀፋዊ ስለማድረግ፣ ስለዳያስፖራው ወሳኝ ሚናና የጋራ ቋንቋ ለአንድ አገር ያለውን ጥቅም በሚመለከት ተገልጿል። ክፍል 5 በአገር ጉዳይ የሀይማኖት መሪዎችና አገልጋዮች ሊኖራቸው ስለሚገባው የመሪነትና የማስተባበር ሚና ከእስራኤል ታሪክ በማጣቀስ ያብራራል።

 

  1. የሀይማኖት መሪዎችና አገልጋዮች ሚና

 

Jewish+Ethiopians+Reunited+Families+Israel+o1h5oGhsf2Vlበኢየሩሳሌም የነበረው ቤተመቅደስ በሮማውያን ፈርሶ እስራኤል በየአገሩ ከተበተኑ በኋላ ብዙ የአይሁድ ካህናት አልነበሩም። ምክንያቱም ቤተመቅደስ በሌለበት ካህን ሊኖር ስለማይችል ነው። ሆኖም ይህ ባይቻልም ብዙዎች መምህራን (ረበናት) ሆኑ። በአይሁድ ታሪክ ውስጥ እነዚህ የአይሁድ መምህራን የነበራቸው አስተዋጽኦ ሁሌም ገንቢ ባይሆንም እጅግ ከፍተኛ ነበር። በየሄዱበት ፈጽሞ እምነቱ እንዳይጠፋና አይሁድም የሚሰባሰቡበትና እየተገናኙ በዓላትን የሚያከብሩበት የአምልኮ ስፍራዎች (Synagogues) ከማቋቋም ጀምሮ በማንኛውም አገርን የሚመለከት ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ ሁልጊዜም ከፊት የሚገኙት እነዚህ መምህራን ነበሩ።

 

ያቋቋሟቸው ቤተመቅደሶች እምነቱ ባህሉና የእብራይስጥ ቋንቋ (በንግግርም ባይሆን በጽሑፍ) ፈጽሞ እንዳይጠፋ ዋና ምክንያት ነበሩ። አይሁዳውያን በተጠቁ ጊዜ መጠለያ፣ በትግሉ ጊዜ መሰባሰቢያ ወዘተ ሆነው አገልግለዋል።

 

እነዚህ የሀይማኖት መምህራን በዚህ ብቻ አልተወሰኑም። ጠንካራ ማኅበራትን በማቋቋም በትግሉ ውስጥ የመሪነትና የአስተባባሪነት ሚና ተጫውተዋል። በአንደኛው የዓለም ጦርነት (እ. ኤ. አ በ 1914) በኦቶማን ቱርኮች ጭቆና ሥር የሚማቅቁትን አይሁድ ለመታደግ ሲባል በአስቸኳይ በተፈለገ 50,000 ዶላር መነሻ ከአሜሪካ ግዛቶች ብቻ የተሰባሰቡት አይሁድ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ከ 78 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማዋጣት የቻሉት በእንደዚህ ዓይነት ማኅበራት (ኦርቶዶክስ አይሁድ በአብዛኛው የሚገኙበት American Jewish Distribution Committee ዋናው ነው) የተሰባሰቡ ነበሩ። ይህ ማኅበር ለተፈናቀሉ ርዳታና የመልሶ ማቋቋም አገልግሎት ከማበርከቱም በላይ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ አይሁድ ጀርመንን ለቀው እንዲወጡ በማድረግ ሕይወታቸውን ታድጓል። በ 1943 (እ. ኤ. አ) ከአራት መቶ በላይ ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የተሰባሰቡ የአይሁድ መምህራን በአውሮፓ በአይሁዳውያን ላይ የሚደርሰውን ግፍ በመቃወምና የተባበሩት መንግሥታቱ ኃይል ግፉን ለማስቆም የወሰደውን ርምጃ በመደገፍ በአሜሪካን አገር ያደረጉት ሰልፍ በጊዜው የዓለምን የመገናኛ ብዙሐን ቀልብ በመሳብ  የአይሁድ ሕይወት በስደት ምን እንደሚመስል ለዓለም ሕዝብ ያስገነዘበና በእስራኤል የትግል ታሪክ ሁልጊዜም ሲጠቀስ የሚኖር ነው።

 

በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የቤተክርስቲያንና የመስጊድ አገልጋዮች ከአይሁድ ጋር የሚመሳሰሉት በየሄዱበት ከሕዝቡ ጋር በመተባበር አብያተክርስቲያንንና መስጊዶችን በማቋቋም ያበረከቱትና አሁንም እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ ነው። እነዚህ የሀይማኖት ተቋማት ለሕዝቡ መንፈሳዊ አገልግሎት ከማበርከት በተጨማሪ እንደመሰባሰቢያ በመሆንም ያገለግላሉ።

 

ኢትዮጵያውያን የሀይማኖት መሪዎች በሕዝቡ ዘንድ ከማንም ይልቅ ተቀባይነትና ተሰሚነት ቢኖራቸውም ይህን ተቀባይነትና ተሰሚነት እስካሁን ለአገር ጉዳይ በአብዛኛው ሲጠቀሙበት አልታየም ቢባል እውነት ነው። ይህ ደግሞ የአገርን ጉዳይ ብቻ የሚመለከት ሳይሆን መንፈሳዊ (የተጎዱትን የማጽናናት፣ የተጨነቁትንና የተሸበሩትን የማረጋጋት፣ ርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ፈጥነው ርዳታ እንዲያገኙ የማስተባበር ወዘተ) እና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በሚመለከት ነው። ቋንቋን፣ ባህልንና ታሪክን ጠብቆ ለሚቀጥለው ትውልድ የማስተላለፍ ሥራ የነዚህ የሀይማኖት ተቋማት፣ አገልጋዮችና መምህራን ሥራ ሆኖ ለዘመናት የዘለቀ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ መድረክ ላይ ቆሞ ከማስተማር ባለፈ በተጠናና በተዘጋጀ መንገድ ለቀጣዩ ትውልድ (ለልጆች) በበዓላት መዝሙር ሲዘምሩ ከማሳየት ባለፈ ይህን መሰል እውነተኛ አገልግሎት ሲሰጥ አይታይም። በቋንቋና በሀይማኖት ትምህርት በኩል አንዳንድ ሙከራዎች ቢኖሩም ከወላጆችና ከሰንበት ትምህርት ቤቱ የሚያልፍ አይደለም። ይህም በሚገባ በተደራጀና ተከታታይነት ባለው ሁኔታ የሚፈጸም ባለመሆኑ ውጤት አይታይበትም።

 

በውጭ የሚገኙት አባቶች፣ ካህናት፣ የሀይማኖት መሪዎችና አገልጋዮች በውጭ ያላቸውን ነፃነት ተጠቅመው በመንፈሳዊውም ሆነ ከመንፈሳዊው እጅግ የተሳሰረ በሆነው የሕዝቡ ማኅበራዊና የአገር ደኅንነት ጉዳይ በመሪነትና በማስተባበር ብዙ ሊያደርጉ ሲገባ መክሊታቸውን አልተጠቀሙበትም። በየአረብ አገራት (በቅርቡ በሳውዲ አረቢያ የተፈጸመውን ጨምሮ) በኢትዮጵያውያን ላይ ለሚደርሰው የማያቋርጥ ችግር ተባብረው የውግዘትና የተቃውሞ ድምጻቸውን ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ከማሰማትና ለጥቃቱ ሰለባዎች የመንፈሳዊ ማረጋጋትና ማጽናናት አገልግሎት ከመስጠት ጀምሮ ምእመናንንና ዳያስፖራውን በመሪነት በማስተባበር “ሠርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ” ዓይነት ሳይሆን የደረጁ ቋሚ ማኅበራትን በመፍጠር ችግሩ ለደረሰባቸው ወገኖች አስቸኳይ ርዳታ እንዲደርስ ማድረግና ችግሩን ከምንጩ ጀምሮ በማየት የረጅም ጊዜ ዘላቂ መፍትሔ መስጠት ከማንም በፊት የሀይማኖት አባቶችና አገልጋዮች ሥራ ነው። ይህን አላደረጉም። ልጆች በማደጎ ሰበብ ካገር እየወጡ ብዙ ችግር ሲደርስባቸውና አሁንም የልጆች ሽያጭ ሲቀጥል ይህን ለማስቆምና ሌላ አማራጭ መፍትሔ ለማግኘት አንዳችም ነገር አላደረጉም። ከሕዝቡ ፊት መገኘት ሲኖርባቸው የነርሱ ኃላፊነትና ሥራ በሆነው ሁሉ ሕዝቡና የፖለቲካ ድርጅቶች እየቀደሟቸው እነርሱ ከኋላ ሲጎተቱ ታይተዋል።  አንዳንዴም ሀይማኖታዊ ግዴታቸውን ረስተው በጥቅምና በዘር እየተደለሉ ከሚያልፈው ጋር እየተሰለፉ ሊያገለግሉት የሚገባውን እግዚአብሔርንና የእግዚአብሔርን ሕዝብ ከአምባገነኖች ጋር ተባብረው ሲጎዱት ታይተዋል። በዚህም ሕዝቡ ተስፋ ከእነርሱ መጠበቁን ትቶ ከሌሎች መጠበቅ ከጀመረ ቆይቷል። ሕዝቡንና አገርን የመታደግ፣ የመጠበቅና የሕዝቡን ኑሮ በመንፈሳዊም በቁሳዊም የማበልጸግ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን ግዴታም አለባቸው። ምክንያቱም ቁሳዊው መንፋሳዊውንም ስለሚጎዳው ነው።

 

ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ልጆች ማንነታቸውን፣ ባሕላቸውን፣ እምነታቸውን፣ ታሪካቸውንና ቋንቋቸውን እንዲያውቁ ማድረግ የትግሉ አንድ አካል ነው። ግእዝ አዋቂ የሆነው የኢትዮጵያዊው መሪጌታ፣ ካህንና ዲያቆን ልጅ አማርኛ የማያውቅ ከሆነ ችግር አለ ማለት ነው። በአገራችን ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት ታሪክን፣ ባሕልን፣ እምነትንና የጋራ ቋንቋ እንዳይኖር በማድረግ አገሪቷን የመበተን ዘርፈ ብዙ ስለሆነ ትግሉም እንደዚሁ ሥርዓቱን ከመቀየር ጎን ለጎን ብዙ ዘርፍ እንዲኖረው ያስፈልጋል። ዘረኛው ሥርዓት ኢትዮጵያን አጠፋለሁ ስላለ አትጠፋም። ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ የሚያደርጓት በዋናነት እነዚህ እሴቶቿ ናቸው። እነዚህ ካልጠፉ አትጠፋም። ነገር ግን እኛም ተባባሪ ሆነን እነዚህን እሴቶች በማቃለል ይልቁንም ለሚቀጥለው ትውልድ ማስተላለፍ ካልቻልን ያን ጊዜ በርግጥ የኢትዮጵያ ሕልውና አደጋ ላይ ይወድቃል። ይህ እንዳይሆን የወላጆች ድርሻ ትልቅ ቢሆንም የሀይማኖት መሪዎች እነርሱ አርአያ በመሆን ወላጆችን በማነሳሳትና በመርዳት ባሕሉ፣ ታሪኩ፣ እምነቱና ቋንቋው ተጠብቆ ወደልጆች እንዲተላለፍ ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

 

እነዚህ አቢያተክርስቲያናት ያላቸውን ተቋማዊ አቅምና የያዟቸውን በተግባር በጉልበታቸው፣ በጊዜአቸውና በገንዘባቸው ላመኑበት ነገር (ሀይማኖት) ወደኋላ የማይሉ ምእመናን ችላ እያለ በዳያስፖራው ትብብር ጠንካራ ተቋማትንና ድርጅቶችን እመሠርታለሁ ብሎ የሚያስብ ማንኛውም አካል የተሳሳተ ነው። ሕወኀት አብያተክርስቲያንን እያበጣበጠ በሥሩ አድርጎ ለመቆጣጠር ሙሉ ኃይሉን የሚጠቀመው ለምንድን እንደሆነ በሚገባ ልንረዳ ይገባል። በጠቅላላ አብያተክርስቲያንን ከዚህ ተጽእኖና ቁጥጥር ነፃ ማድረግና በምትኩ ለአገራቸው አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ መንገዱን ሁሉ ማመቻቸት የትግሉ አንድ ዘርፍ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል።

 

(ይቀጥላል)

 

ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ ሥራ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!

 

የሕወሓት አስተዳደር በዓለም ባንክ ስልጤ ሰፈር በርካታ ቤቶችን ሲያፈርስ ዋለ (ፎቶዎች ይዘናል)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ ሐሙስ በአዲስ አበባ ዓለም ባንክ ስልጤ ሰፈር በርካታ ቤቶች መፍረሳቸውን የዓይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ በፎቶ ግራፍ አስደግፈው ገለጹ::
fire brokes

fire brokes addis ababa
እንደ ዘጋቢዎቻችን ገለጻ ከሆነ ቤታቸው የፈረሰባቸው ወገኖች መሄጃ አጥተው ሸራ ወጥረው የተቀመጡት እነዚሁ ወገኖች በድጋሚ ቤታቸው ፈርሶባቸዋል::

ቤታችን ለምን ይፈርሳል በሚል ጥያቄ የሚያቀርቡትን የመንግስት ደህንነቶች እያስፈራሩ መሆኑን የገለጹት ዘጋቢዎቻችን ቤቶቹ እየፈረሱ ያለው ካርታ የላቸውም በሚል ምክንያት ነው ተብሏል:: እንደዘጋቢዎቻችን ገለጻ ከሆነ መንግስት ከ2003 በፊት የተሰሩ ቤቶች አይፈርሱም በሚል ቃል የገባ ቢሆንም ቃሉን ሳይጠብቅ ከዛ በፊት የተሰሩ ቤቶችም ፈርሰዋል::

በአሁኑ ወቅት ቤታቸው የፈረሰባቸው ወገኖች በችግር ላይ እንደሚገኙም የደረሰን መረጃ ያመለክታል::


ስለ ቅዳሜው አዳር ተቃውሞ የሳዲቅ አህመድ መሳጭ ዜና ትንታኔ (ያድምጡ)

$
0
0

ዘጠኙ ጥምር ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለቅዳሜዉ የ24 ሰዓት ተቃውሞ ከፍተኛ ዝግጅት ላይ ይገኛሉ:: ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ በዚህ ዙሪያ ሰፋ ያለ መሳጭ ዘገባ ያስደምጠናል – ጆሮዎን ይስጡት::


semayawi 24

የወያኔ ምርጫ –ጭንጫ። (ሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 05.12.2014 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

እንደላበዛባችሁ እዬሰጋሁ ግን የገጠመኝን መልካም ነገር ቀድሜ ላወጋችሁ ወደድኩኝ። እባክቻሁ ውዶቼ ፍቀዱልኝ? መቼም ዘንድሮ አውጊ አደራ ሁኛለሁ። …. የማንነት ጽጌረዳ ነውና አትቆርጡም ብዬም አስባለሁ።

2007 electionእንደ – በር። አልኳችሁ ትንሽዬ ቀጠሮ ኖራኝ ወደ አንድ የማላውቀው ሰፈር ተጓዝኩኝ – ዕለተ – እሮብ። የምሄድበት ቦታ አዲስ ስለነበረም ከቀጠሮዬ ሰዓት በፊት ሁለት ሰዓት ቀድሜ ነበር የደረስኩት። ከዚህ በኋላ ትንሽ ሻይም ቡናም ከተገኘ ብዬላችሁ ላይ ብል ታች ብል ፈጽሞ ምንም የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአድባሩ የለም። እንዲህ ደግሞ ገጥሞኝ አያውቅም። ወደ ላይ ሲኬድ ቀጥ ያለ አስፓልት ወደ ታች ሲወረድም ቀጥ ያለ አስፓልት።

በዛ እንደ ባንዴራ በማተቡ በፀና ሎጋና ዠርጋዳ አስፓልት ዳር ለዳር አንዲት ሩጫ የምትለማመድ ደማም ውብ ጸዳላማ ወጣት አገኘሁና „ሻይ ወዴት ላገኝ እችላለሁ?“ ብዬ ጠዬቅኳት። „በዚህ አቅጣጫ ሁለት ሰዓት ብትጓዢ አንዲት ትንሽዬ ኪወስክ ታገኛለሽ። ቡናዋ ግን አይጣፍጥም። በስተቀር ግን ወደ ከተማ ተመልስሼ ካለሆነ በስተቀር እምታገኚው ነገር ዬለም“ ብላ ቁርጤን ነገረችኝ። አመናታሁና ለምን ከዛው ከተቀጠርኩበት አካባቢ ሰማይና መሬት ያገናኘ ዬሚመስለውን የተንጣለለ ሃይቅ እያዬሁ አልቆይም ብዬ ወደዛው አቀናሁ። ብርዱ ደግሞ አይጣል ነበር። አሳቻ ቦታ ላይ  በጣም ወደ ውስጥ ገባ ባለ የወንዝ የመንገድ ግድግዳ አንድ በር ሲከፈትና ሲዘጋ ስላዬሁ ሰዎች በሚገቡበት አቅጣጫ እኔም ዘው ማለት ….

ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? ቦታው ባር ነገር ነው። በውጪ ምንም የተፃፈበት ነገር የለም። ሙዚቃው ደግሞ ምን ሊሆን ይችላል ብላችሁ እስኪ ገምቱ – በሥርጉተ ሞት? ገመታችሁ? ይግርማችኋል ለ1.30 ሰዓት ያህል ቀጠሮዬ እስኪደርስ ተቀመጥኩኝ። ሳይቋረጥ የኢትዮጵያ የመሳሪያ ቅንብር ሙዚቃ ነበር አድባሩን የተቆጣጠረው። ሻዬን ከያዝኩኝ በኋላ ጠጋ ብዬ አስተናጋጁን „ዬዬት ሀገር ሙዚቃ ነው ስል በትህትና ጠዬቅኳቸው?“ ቀጥዬም „አድራሻውን ሊሰጡኝ ይችላሉን?“ አልኳቸው፤ ቀልጠፍ ብለው። „የመሳሪያ ቅንብሩ ሙዚቃ  የኢትዮጵያ በህላዊ ሙዚቃ ነው። ከፈለጉ ደግሞ ሥሙን እሰጠወታለሁ“ አሉኝ። ግርም ብሎኝ ሌላ ጥያቄ ደግሞ ቀጥልኩ „ከዚህ ከእናንተ ባር ኢትዮጵያውያን ሠርተው ያውቃሉን? ወይንም የሚሠራ ኢትዮጵያዊ አለን?“ ስል ጠዬቅኩኝ ….

መቼም ኢትዮጵውያን የጠረናችን ነገር አይሆንልንምና። „ኢትዮጵያዊ ተቀጣሪ የለንም“ አሉኝ። „ኖሮንም አያውቅም።“ በማለትም አከሉልኝ። ቀጥለው ትንሽ እንደማሰብ ብለው „ ነገር ግን እዚህ የጃፓን፣ የቲቤት፤ የቻይናና የኢትዮጵያ የመሳሪያ ሙዚቃዎች የተለመዱ ናቸው። እንግዶቻችን በፍቅር ይወዷቸዋል“ አሉኝ። እኔም ለካንስ የነዚህ ሀገሮች የመሳሪያ ቅንብር ሙዚቃ ለእኔም በግሌ የሚስቡኝ ተመሳሳይ ዬቃና ቅኝት ስላላቸው ይሆን ብዬ ራሴን ጠዬኩኝ። አዎን የአንገቴን ጌጥ በስንድድ የተሠራውን አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ገለጥ አድርጌ „እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ“ ብዬ ነገርኳቸው። ደፍረው የሚናገሩት፤ አንገትን የማያስደፋ – ባርነት ያልጎበኘው፤ የነጠረ ማንነቴ ኢትዮጵያዊነት አለልኝና። ቀጥዬም … „ይህ አክብሮታችሁ የሰማይ ነው እንጂ የምድርም አይደለም። እግዚአብሄር ይስጥልን አልኳቸው።“ ትክ ብለው በመገረም አይተው „እኔም አመሰግናለሁ“ አሉኝ።

እስከ አሁን ይገርመኛል። ደስታውም አልቀቀኝም። እኛ ያልሠራንበትን ጥበበኛው አምላክ እንዲህ አሳምሮ ይሠራልናል። ያግዘናል – የቃል ኪዳን ሃገሩ ናትና – ኢትዮጵያ! የሚደንቀው ነገር የመሳሪያ ቅንብሩ የእነማን እንደ ሆነ፤ ባንዶችን ሳይቀር በዝርዝር ነበር የነገሩኝ። በተጨማሪም ኢትዮጵውያንና ሆላንዳውያንም የጋራ ባንድ እንዳላቸው መረጃውን ሰጡኝ። እንግዶቻቸውም በጣም የሚወዱት ስለሆነ ሙሉ ጊዜውን ሲያዳምጡት ቢውሉ እንደማይሰለቻቸው ገለጹልኝ። እንዲህ ያልተወለደን በፍቅር የሚገዛ ውስጣችሁን ባላሰባችሁበት ቦታና ጊዜ ሲገጥም ከቶ ምን ትላላችሁ? እጅግ ደስ ያለኝና የወደድኩት ጊዜ ነበር። በጋ ላይም ሥራዬ ብዬ እሄዳለሁ። …. ክብራችን – ፍቅራችን ለመጎብኘት …። እንዲህ እንደ ተፈለገ የማይንዘገዘግ ማንነት ያለው ነው ኢትዮጵያዊነት ማለት። ”ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች!” – ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት (የጉዳያችን ማስታወሻ) http://www.zehabesha.com/amharic/archives/36814 እኔም እላለሁ ኢትዮጵያዊነት ረቂቅ ቅዱስ መንፈስ ነው።

እጅግ የሚገርም ነበር። ውስጤን አብዝቶ ፈተሸኝ። ባህላዊ ምግብ ቤት ገብቼ አዳምጬ ስለማላውቅ ማለት ከሀገሬ ከወጣሁኝ፤ ሀገሬ የገባሁ ያህል ነበር የተሰማኝ ለዛውም በነጮች ባር። ወግ አበዛሁ አይደል ክብሮቼ? ተፈርዶብኝ ነው። ደስ ስላለኝ ነው። ይቅርታ … እኔም ቋጥሬ የሄድኩት የእምዬን ዕንባ ስለነበረ … አገጣጠመችው …. ወፊቱ …

የወያኔ ምርጫ – ጭንጫ።

አሁን ወደ ተነሳሁበት ግን አጠር፣ ደንበል አድርጌ – ጭንጫና ቁም-ነገር መንገድ ላይ እንኳን ተገናኝተው አያውቁም። ጭንጫና ፍቅር ሆነ ጭንጫና አብሮነትም እንዲሁ። ጭንጫና ፍትህ ሆነ ርትህም አይጥና ድመት ናቸው። ውዶቼ እስኪ በርከት ያሉ ጭንጫዎችን ከመዳፋችሁ ላይ ኮልኮል አድርጋችሁ እዮዋቸው። ምን ይመስላሉ? ኮልኩሏቸውም፤ – ይስቃሉን? ለመሆኑ ነፍስ ቢጤ አላቸውን? ይተነፍሳሉን? አባብሏቸው – አቆለማምጧቸው? የሚረዱት የሚገባቸው ነገርስ – ይኖራልን?

ቀጥላችሁ ደግሞ ጭንጫውን ውሃ ውስጥ ጨምሩት። ከቶ ሟሟን? ተቀላቀሉን? እንዲያው ምንስ መልክ ኖረው ከቶ? እ … ቡላማ …. አመዳም? ወይንስ የንፁሁን ውሃ ተፈጥሮ ብክል አደረገው ይሆን? አወና! …. መልከ ጥፉ ስለ ሆነ ደህናውን የውሃንም ተፈጥሮ አጎሽቶ አይሆኑ አደረገው አይደል? አንዷን ጭንጫ አፈፍ አድርጋችሁ ደግሞ በጥርሳችሁ እስኪ ሞካክሯት? ታዲያ እንደ እኔ ፈንጠርጣራ ካልሆነ ነው። ደግሞ በህግ እንዳልጠዬቅ …. ባለ ጠንካራ ጥርሶች ፍንክች አለላችሁ ይሆን ሞገደኛው – ጭንጫ?

ጭንጫ ቀዳዳም አልሰራለትም፤ መተንፈሻ ቧንቧም የለውም። ውስጡንም ከፍቶ ማዬትም አይቻልም። ለግሞ  – ሎግሞ የሚይዘው የራሱን ኩረት ተፈጥሮውን ብቻ ነው። ከራሱ ኩረት ተፈጥሮ ውጪ የሚያስጠጋውም አንዳችም ነገር የለም። ውስጡ በልዞ – አሮ ጠንዝሎ – ቢከስልም ያችኑ እሮውን ተሸከሞ እንደ ኳረት ዘመኑን ይሸኛል።

ጭንጫውን አስተካክላችሁ ወደ አንድ ሰው ዓይን ብትወረውሩት ግን …. አደጋ ያመጣል። አደራ እንዳትሞክሩት። ጭንጫ ለመጉዳት ብቻ የተፈጠረ.፣ ቃና የለሽ፤ ወዝ የለሽ፤ ለዛ ቢስ፤ ምንም የማይገባው፤ ለምንምና ለማንም የማይሆን ብቻ ከብለል እያለ እያሾፈ ዘመኑን በተፋቀ ተፈጥሮው እንደ ከብት የበላውን መልሶ እያወጣ ሲያመንዥክ የሚኖር …. መንቻካ  – ጥጥር ያለ የጓጓለ ተፈጥሮ አለው። በጭንጫ ውስጥ አዲስ ተስፋን ማብቀል ሆነ ማጽደቅ የተከለከለ መንገድ ነው። ፍርፋሪ ወይንም ኦፋ ሊወረውር ይችል ይሆናል። ይህም ቢሆን ከሥጋ በይ እንሰሳ ጥርስ ውስጥ ሥጋን የማስለቀቅ ያህል ጣር ነው —– ጣጣውም ምጥ፤

የአቶ ወያኔ ዬምርጫም ማንፌስቶም ጭንጫማ ነው። አይገመስ፤ አይጋጥ፤ አይጣጣም፤ ብጥቅ የምትል ነገር አተወጣውም። አስልቶ ለማጥቃት ብቻ የተሠራ ወይንም የተድቦለቦለ ቅርጽ – ቀለም – ፎርም – ያልፈጠረለት፤ ስድና መደዴ ነገር ነው። በዚህ እንድርቺ – እንድርቺ ጨዋታው ግን ስልቦ ወይንም ሰንጎ* ፍላጎቱን ያስፈጽማል። ጭንጫ የሚመቸው – ለጭንጫ ብቻ ነው። ጭንጫ ግጥሙ አምሳዬው ጭንጫ ነው። ጭንጫ መልኩ ጭንጫ ነው። ጭንጫ ደምና ሥጋው ጭንጫ ነው። ጭንጫ – ቅልቅሉም ሆነ ግጥግጡ ከጭንጫ ከመሰሉ ጋር ነው – ጋብቻውም። ከአምሳያው ውጪ የሚመጣ ቀናዊ ሂደት እንደ ጸጉረ ልውጥ ያዬዋል። እንደ ጠፍርም እስኪበቃው በቂም በቀል ያሸዋል። ይደቃዋል። ይሰልቀዋል። ይፈጨዋል … እንጂ ብጣቂ ርህራሄ አያጎራርሰውም። ጭንጫ ይሉኝታ የለውም – ፈጽሞ።

ጭንጫ ህግ የለውም። ህግ አልባ ነው። ጭንጫ መርህ የለውም – ዳሪ አዳሪ ነው። ጭንጫ የመንፈስ ጥግ አልፈጠረለትም – ሜዳ በቀል ነው። ህግ አልባነቱ በጥሰት መሄዱ ብቻ ሳይሆን፤ ተፈጥሮው በሆነው ብቀላ ተቀናቃኙን እዬዳጠና እዬዳመጠ ነው የሚጓዘው። ይህ የጭንጫ ውስጥ ደግሞ በበቀልና በቁርሾ ኩረት የተሞላ ነው። ህልሙ ማጥቃትን አስልቶ፤ ማቁሰልን አልሞ በመሆኑ ከእሱ በተቃራኒ ያሉ ማናቸውም ሰዋዊ በጉ ሕይወታዊ ዝንባሌዎች ሆኑ አስተሳሰቦች ሁሉ ካለይግባኝ የጥቃቱ ሰለባ ይሆናሉ። አይምሬ ነውና።

በጎጠኝነት ዶክተሪን ሰብዕዊነት የሚባል ነገር የለም – ፈጽሞ። ደረጃው አይፈቅድለትምና። ጎሰኝነት ወይንም ዞገኝነት እኮ ታች ያለ የአስተሳሰብ የታቆረ ድህነት ነው። በአንዲት ምድጃ ዙሪያ ብቻ የተከለለ፣ በተወሰነ ጉዳይ የታጠረ ወይንም የተከተረ ስለሆነ ስለ ሰፊው ዓለምና ስለ ሥልጡኑ ዓለም ዕይታው ሆነ ነገረ ሥራው ጭንጫማ ነው። ዕድገትም አያውቀውም። ዕድገቱ የምድር እንቧይ* ነው። በዚህ የግንዛቤ ደረጃ ላይ የሚገኝ ቡድን ሌላውን የሚሰማበት ወይንም የሚያዳምጥበት ወይንም የሚያስተውልበት ጸጋውን ላልተመጣጠነ ዕድገት ላለው ለኋለቀር አስተሳሰቡ ገብሮታልና።

ይህ ባህሬው ደግሞ ነጭናጫና ቁጡነትን፤ ተጣራጣሪነትን፣ አድብቶና አነጣጥሮ ማጥቃትን፤ ጥላቻና ክፋትን አብቅሎ …. ዘመንን ጠቀራ ያለብሳል። አልብሷልም። ስለሆነም ጠቀራማውን ዘመን ለመቀዬር የመብት ግዴታው ከጭንጫ ጋር አለመዶለትን፤ ማዕደኛ አለመሆንን በእጅጉ ይጠይቃል። መስሪያው* የተለዬ ነውና። እንዴትና እንዴት … ተብሎ? የማይገናኝ መንገድ የወል አድራሻ የለውም። የማይገናኝ ተስፋም የወል እርገት የለውም። አምሳያ ከአምሳያው ጋር ቢወዳደር ቢፎካከር – ወሸኔ ነው። ማለፊያ! …. ከጭንጫ ጋር ግን ….. ምርቱ ሆምጣጤ ብቻ ነው። ከቶ የጭንጫ ማኒፌስቶ በዬትኛው ተፈጥሮው ነው መርህን አክብሮ በመርህ የሚዳኘው?!

ክብረቶቼ – እርገት ይሁን፤ ከሚጠበቅ ራዕይ ተስፋን መጠበቅ – መልክ አለው። ከማይጠበቅ ምክነት ግን ማለም ተስፋን ማራቆት ወይንም የብዙኃንን ምኞት እርቃኑን እንዲቀር መመቸት ወይንም ዬዕንባን ፍላት ፈቅዶ እራስ ማፈን ይመስለኛል።

የትናንት 04.12.2014 ጸጋዬ ራዲዮ Tsegaye Radio ዝግጅት ሲጀመር ችግር ነበረው – የቴክኒክ። በኋላም 33 ደቂቃ ብቻ ነበር አዬር ላይ የቆዬው። ስለሆነም ታላቅ ይቅርታ በትሁት መንፈስ እጠይቃለሁ፤ ችግሩ እኔ የፈጠርኩት ባይሆንም። የቴክኒክ ችግር ስለ ገጠመ ነበር። በኋላ ግን ከ16 – 17 ቀጣዩን የራዲዮ ዝግጅት ሰርዘው ራዲዮ ጸጋዬ እንደ አዲስ ተጀመረ። ለፈጣኑ እርማትና ለአክብሮቱ ራዲዮ ሎራ እያመሰግነኩኝ ዓይናማዋን፣ ደመ ግቡውን የጋዜጠኛ ተመስገን ወንድም ዬአቶ ታሪኩን እናታችን ፋናዬና ተመስገን በዝዋይ’” መንፈስ ጋር ጸጋዬ ራዲዮ ቆይታውን አድርጓል። ከፈቀዳችሁ አርኬቡ ላይ ማድመጥ ትችላለችሁ።  ኑሩልኝ!

መሸቢያ ሰንበት – ለእኔዎቹ።

መፍቻ።

  • ሰንጎ … በኃይል – በጎልበት – በጡንቻ – በብረት ድጋፍ – አስገድዶ፣ ደም አስፍቶ፣ አንቆ ይዞ ፍላጎትን ማስፈጸም – ለወመኔዎች በትክክል የተፈጠረ ቃል ነው።
  • መስሪያ … በጋራ – በሌማት፤ በሞሰብ – በወልዮሽ፤ በጥራር – በአንድነት፤ ወይንም በትሪ – በአኃታዊነት የጋራ ማዕዶት
  • ጥራር … ከሰንበሌጥ በእጅ የሚሰራ መመገቢያ ባህላዊ ዕቃ … ተወዳጅም።
  • የምድር እንቧይ … እንቧይ ሁለት ዓይነት ተክል አለው። አንዱ በትክክል በቅሎ እንደ አጋም እንደ ቃጋ የሚያድግ እድገቱ የሚታይ ፍሬውም እንደ እንኮይና ኮሽም ዓይነት ሲሆን። ሌላው የምድር ዕንቧዩ ግን እንደ ሥሙ ዕድገቱ መሬት ላይ ነው የሚቀረው። ሀረጉም ብዙ አይጓዝም – ድካም ያሸነፈው ተፈጥሮ ነው ያለው። ፍሬው ቀለሙ ያልበሰለ ወይራ መሰል ቆባ ዱባ ወይንም ዝኩኒ ነገር ነው። ከመሬት በቅሎ ጫጭቶ እዛው ተሰክቶ – አሮም ይቀራል።

ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ኢትዮጵያዊነት!

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ – ኑሩልኝ!

ከመተባበርና አንድ ከመሆን በላይ ታላቅነት የለም –የሰማያዊ ከፍተኛ አመራር

$
0
0

ፍኖተ ነፃነት

“አምናለሁ። አንድ ሆኖ ለአንድ ሀገር መቆም ብንችል እውነት ይሄ ታላቅነት ነው። ከዚህ በላይ ታላቅነት አለ ብዬ አላስብጭ፡፡”

“በፍቅር በሰላማዊ መንገድ በመነጋገር የማንንም ሰው ሀሳብ ማሸነፍ ይቻላል ብዬ አምናለሁ።”

ወ/ሮ ሃና ዋልለልኝ ይባላሉ። የሰማያዊ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ ናቸው። ፍኖተ ነጻነት ባወጣው 86ኛ እትሙ ቃለ መጠይቃ ካደረገላቸው የተወሰደ ነበር። ከቅአለ መጠይቅቁ የተወሰነዉን እንደሚከተለው አቅርበናል።

ፍኖተ ነፃነት፡- በመጪው ምርጫ ላይ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ምንድን ነው የሚጠበቀው?

10344785_738568506228086_275256779448546603_nወይዘሮ ሀና፡ – ከተቃዋሚዎች የሚጠበቀው እርስበርሳችን በመስማማትና ትንንሽ ልዩነቶቻችንን በማስተካከል ባለችው ቀዳዳ፣ ጠባብ ቀዳዳ ማለት እችላለሁ ሾልከን ለውጥ ለማምጣት መትጋት ነው፡፡ የረጅም ጊዜ ልምድ አለ፤ ከዛ ውስጥ ደግሞ ነጥረው የሚወጡ ሰዎች ይኖራሉ፤ የሚታዩም አሉ። ጥሩ ጥሩ ወጣቶችም እያደጉና እያበቡ ነው። እነዚህን ነገሮች ወደ ተግባር ወይም ወደ ውጤት በመቀየር ለምርጫ ራስን ማዘጋጀት ያስፈልጋል። ምክንያቱም ሀገሪቷ ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በምርጫ የሚመጣ ስልጣን ብናገኝ በእውነት ይህቺ ሀገር ታላቅ ትሆናለች። ጥሩ ነገርም ይታይባታል፡፡ስለዚህም እርስ በእርሳችን በብዙ ፍትጊያ ውስጥ አልፈን በብዙ ዘረኝነት ውስጥ አልፈን እዚህ ደረጃ መድረስ ራሱ ትልቅነት ስለሆነ ይሄን ብናደርግ ደግሞ የተሻለ ትልቅ ሰው እንሆናለን ብዬ አምናለሁ። እርስ በርሳችንም እንከባበራለን፤ እንቻቻላለን፤ መቻቻሉ ግን በመተማመን ውስጥ መሆን አለበት ብዬም አምናለሁ።

ፍኖተ ነፃነት፡- በፖለቲካ ፓርቲዎች አብሮ በመስራት ላይ ሁለት አይነት አስተሳሰቦች በአደባባይ ሲራመዱ እናስተውላለን። ፓርቲዎች አንድ ላይ ተባብረው መስራት አለባቸው የሚል ወገን አለ፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ብቻቸውን ነጥረው መውጣት አለባቸው ይላል፡፡ባንቺ አመለካከት አሁን ካለው የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ አውድ አንጻር የትኛው ያዋጣል

ወይዘሮ ሀና፡- ፓርቲዎች ነጥረው ይወጣሉ የሚለው ነገር የእኔም ሀሳብ ነበረ። ጥረቱ ጥሩ ነው። ባልተሄደበት መንገድ መሄድ የአስተዋይነት ምልክት ነው። ባለንበት እንቁምና ባለንበት እንርገጥ የሚል አስተሳሰብ መኖር የለበትም። ሁልጊዜ የሰው ልጅ አዲስ ነገርን ይፈልጋል። አዳዲስ ነገሮችን ማምጣት ይፈልጋል። ስለዚህ ያልተደረጉ ነገሮችን መሞከርና ማድረግ ጤናማነት ነው። ያ ደግሞ የማይሳካበትን ሁኔታ ካወቅን ወይም ደግሞ በፊት አብሮ መስራቱ አይጠቅምም ብለን ከነበረ አሁን ይጠቅማል ወደሚለው ነገር ላይ አስተሳሰባችን ከመጣ ደግሞ ያንን ተቀብሎ ማራመድ ምንም የሚጎዳ ነገር አይደለም።

ሁለቱም ሀገርን ለመጥቀም ለውጥን ለማየት ከመፈለግ የመነጨ እስከሆነ ድረስ ጤናማ ናቸው፡፡ ለየብቻ መስራት የሚያዋጣ ነው ብለን እርግጠኛ ስንሆን ብቻችንን መስራት ይኖርብናል። እኔ አሁን ያለኝ እምነት አብሮ መስራት ታላቅ ያደርጋል ነው። ሁለተኛው ነገር ደግሞ ከአንድ ብርቱ ሁለት መድሃኒቱ የሚለው ተረት ቀላል አይደለም። በሶስት የተገመደ ገመድም ምን ያህል ጠንካራ እንደሆነ እናውቃለን። ከዚህ በፊት ለብቻችን ነጥረን እንውጣ የሚለውን ሀሳብ ከሚያራምዱት ውስጥ ነበርኩኝ። ያም የተደረገበት ምክንያትም ከመገፋት ወይም ደግሞ አቅምንና ያለንን እውቀት ለማውጣትእንዳንችል ከመደረግ አንፃር ነው።ሆኖም ግን ያንን ነገር ለውጠን የአብሮመስራታችንን ብቃታችንን ክህሎታችንን አሳድገን አብሮ በመስራት ለውጥ ማምጣት፣ ራሱን የቻለ ስኬት ነው ብዬ አምናለሁ። አንድ ሆኖ ለአንድ ሀገር መቆም ብንችል እውነት ይሄ ታላቅነት ነው። ከዚህ በላይ ታላቅነት አለ ብዬ አላስብም፡፡ ራስን ለሀገር መሰዋት ማድረግ ያስፈልጋል። በነገራችን ላይ እኔ መስዋዕት የምለው የመሞት የመታሰርን ብቻ አይደለም፡፡ ትልቁ መስዋዕትነት ማለት ፍላጎትን ሁላ ማሸነፍ መቻልን ራስ ወዳድነትን ማሸነፍ መቻልንና ለሌሎች መኖር መቻልን ነው፡፡ ለሌሎች መኖርን መልመድ መቻል አለብን። በአፍ ሳይሆን በተግባር ይሄን ካደረግን የማይፈነቅል ድንጋይ አይኖርም።

ፍኖተ ነፃነት፡- የፓርቲዎች የውስጥ ዴሞክራሲ ምን መሆን አለበት ትያለሽ? በየፓርቲዎቹ ውስጥ ያሉ አስቸጋሪ ባህርያቶችስ ምንድን ናቸው?

ወይዘሮ ሀና፡- ብዙ ጊዜ ችግራችን መደማመጥ አለመቻል ነው ብዬ አስባለሁ። እንደገና ደግሞ እኔ አውቃለሁ የሚሉ ሰዎች ካሉ የሌላውን ሀሳብ የሚገፉ ከሆነ የመናገር መብትን የሚገድቡ ከሆነ ሁልጊዜ ችግር መፈጠሩ አይቀርም፡፡ ከዛ ይልቅ ግን መደማመጥ ቢኖር በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገር ቢኖር ስህተት ያለበትም ሰው ስህተቱን እንዲያምን በሀይል በጠብና በቁጣ ሳይሆን በፍቅር በሰላማዊ መንገድ በመነጋገር የማንንም ሰው ሀሳብ ማሸነፍ ይቻላል ብዬ አምናለሁ።

በሀሳብ ላይ መፋጨት በጣም ጠቃሚ ነው። የተሻለና የነጠረ ሀሳብ እንድናመጣም ያደርጋል። ያ ሰው ምንም ቢሆን ሀሳቡንም ማዳመጥ ማክበር ያስፈልጋል። እንደዚህ አይነት ነገሮችን አዳብረን ብንሄድ አሁንም ደግመዋለሁ የማንፈነቅለው ድንጋይ ይኖራል ብዬ አላምንም።

ፍኖተ ነፃነት፡- በመጨረሻ ማስተላለፍ የምትፈልጊው መልዕክት ካለ

ወይዘሮ ሀና፡- ማስተላለፍ የምፈልገው አንደኛ ለፓርቲዬ ማለትም ለሰማያዊ ፓርቲ ነው። ሰማያዊ ፓርቲ በውስጡ ምርጥ ምርጥ ወጣቶች አሉ፡፡ ብዛትም ባይሆን አንድ ሰው ለውጥ ያመጣል ብዬ አስባለሁ። ያንን ሰው ግን በአግባቡ መጠቀም መቻል አለብን ጓደኞቼን በጣም አከብራቸዋለሁ እወዳቸዋለሁ የአስተሳሰብ ልዩነታችንን በጣም አደንቃለሁ፤ በአስተሳሰብ ልዮነታችን ውስጥ ብዙ የተደበቁ ነገሮች ይወጣሉ ብዬ ስለማምን ስላየሁም ማለት ነው። ጥሩ ነገሮች ብቻ ሳይሆን የተደበቁ ስህተቶችም ይወጣሉ። ይህንን በደንብ አይቻለሁ፡፡ ይሄንን ነገር በደንብ አከብራለሁ። በውስጥ የሚሰራውንም ስራ በርቱ ግፉበት እላለሁ፡፡በተለይ በማንም ፓርቲ ውስጥ ያላየነውን የኦዲትና የኢንስፔክሽን ስራ አከብራለሁ ለዚህም በእውነት አድናቆቴን
ማስተላለፍ እፈልጋለሁ። ጥሩ እየሰራ ነው። ፓርቲ ውስጥ ላሉ ችግሮች እስከ ቅጣት ድረስ በመሄድ ለማስተካከል የተሞከረውን ነገር ሳላደንቅ አላልፍም።

በሁለተኛ ደረጃ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎችንም አከብራለሁ አደንቃለሁ ብዙ ትምህርቶችን እንድማር አድርገውኛል አሁን ለደረስኩበት ብስለት እንድደርስ የእነዚህ ፓርቲዎች መፈጠር ጥሩ አጋጣሚና እድል ፈጥሮልኛል። ሀቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የጭቆናውን አመት
ለመቀነስና በጭንቅ ላይ ያለችን ሀገር ለመታደግ መፍጠን አለባቸው። አሁን የዕንቅልፍ ጊዜ አይደለም፡፡የምንፈጥንበትን የሩጫ ሂደትና ቀስ የምንልበትን እንደገና ደግሞ አሯሯጭ የምንሆንበትን መለየት መቻል አለብን።

የኢትዮጲያ ህዝብንም የምለው ነገር ይኖራል፡፡ የኢትዮጲያ ህዝብ ሆይ! ተስፋ አትቁረጥ፤ ተስፋ የሚቆርጥ የሞተ ብቻ ነው። በቁም ያለ ሰው የሚፈልገውን ነገር እጁ ውስጥ እስካላስገባ ድረስ ተስፋ አይቆርጥም። እስከ መጨረሻ ህልፈተ ህይወቱ ድረስ ማድረግ ያለበትን በሙላ ያደርጋል። ሰው እንሁን፤ ስብእናችንን እንጠብቅ፤ እርስ በእርሳችን እንከባበር፤ እንተማመን፤ መተማመን አንድነትን ያመጣል፤ አንድ ከሆንን ደግሞ የማንሰራው ነገር አይኖርም። ከዓለም በታች ጭራ የሆነችውን ሀገር ከፍ እናደርጋታለን፡፡ለዚህ ደግሞ እግዚአብሔር
ይርዳን ማለት እፈልጋለሁ። አመሰግናለሁ።

የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ በፖሊስ ተከብቦ አደረ

$
0
0

• ምንነቱ የማይታወቅ ወረቀት ሲበተን አድሯል

1507105_623118397813822_166123240512263774_nየሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በፖሊስ ተከብቦ ማደሩንና አባላት ከውጭ እንዳይገቡ መደረጋቸውን ለአዳር ሰልፉ ቅስቀሳ ዝግጅት ቢሮ ያደሩ የፓርቲው አመራሮችና አባላት ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ አመራሮችና አባላቱ እራት በልተው ወደ ፓርቲው ጽ/ቤት ሲመለሱ ቢሮው በፖሊስ ተከብቦ እንዳገኙትና ወደ ውስጥ እንዳይገቡ እንደተከለከሉ በቦታው የነበሩት የፓርቲው አመራሮችና አባላት ገልጸዋል፡፡

አመራሮችና አባላቱ ፖሊስ ከ200 ሜትር ርቀት ውጭ ወደ ፖለቲካ ፓርቲ ጽ/ቤት መጠጋት እንደማይችል ቢከራከሩም ፖሊሶቹ ‹‹መመሪያ ተሰጥቶናል፤ አንሄድም!›› ማለታቸው ገልጸዋል፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ከፖሊስ ጋር ሲከራከሩ የአካባቢው ህዝብ በመውጣቱ ፖሊሶቹ ፓርቲው ጽ/ቤት እንደራቁ ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል ከውጭ ወደ ቢሮ ከሚመጡበት ወቅት የፓርቲው ቢሮ አካባቢ ምንነቱ ያልታወቀ ወረቀት ተበትኖ እንዳገኙና እነሱ ሲደርሱ ፖሊሶቹ እንዳነሱት የፓርቲው የምክር ቤት አባል ወጣት እየሩስ ተስፋው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia

ተስፋዬ ተስፋ ሲቆርጥ –ክፍል 3

$
0
0

ከሠናይ ገብረመድህን (ጋዜጠኛ)

ብርጋዴር ጄኔራል ከማል ገልቹ ወታደሮቻቸዉን በህግደፍ የተዘረፉበት ኩነት ብዙዎቻችንን በታሪካችን አንድ አስገራሚ ሆኖ ያለፈ ዜናን ማስታወሱ አልቀረም፡፡ “ኮ/ል መንግስቱ ሀይለማርያም በሱዳን አስተባባሪነት ዜጎቼን በእስራኤል ተዘረፍኩ አሉ” በሚል የተዘገበዉን የአሜሪካ ድምፅ የአማርኛ ፕሮግራም
ዜና ፡፡ ኢትዮጵያዉያኖቹ ቤተእስራኤሎች በድብቅ ወደ እስራኤል የተጉዋጉዋዙበት የሞሰስ ኦፕሬሽን ይሄዉ ሶስት አሰርት ደፈነ፡፡ የቤተእስራኤሎቹን ጉዳይ በተመለከተ ዘረፋ ወይንም የማጉዋጉዋዝ ኦፐሬሽን ተብሎ በዜና ተወርቶላቸዋል፡፡ በህግደፍ ስለተዘረፉት ኢትዮጵያዉያኖች ግን ምንም አልተወራላቸዉም፡፡ ያዉም በዘመነ ኢንፎርሜሽን፡፡ (እኔ እሆን ገና አሁን ስለመዘረፋቸዉ እያወራሁ ያለሁት ?) ከሆነም እኮራለሁ፡፡ ስለወገኖቼ በግፍ መዘረፍና ታጋችነት የሰሚ ያለህ በመናገሬ ፡፡ እነሱ ብቻም አይደሉ ህግደፍን አምነዉ ተጠልለዉ ግና ባልገመቱት ሁኔታ በህግደፍ የታፈኑ ያታገቱና የተዘረፉት፡፡ ጊዜና ሁኔታ እንደፈቀደልን የምናዉቀዉን ያለፍንበትን የእማኝነታችንን አቤት እንላለን፡፡ የነበርን ሰዎች፡፡ ፍርዱንም ለሁለቱም ህዝቦች በጎ አሳቢና አላሚዎች እንተዋለን፡፡ ላሁኑ ይህን እንቀጥል!
የኒያላ ሆቴል ሰፋፊ ሳሎኖች ቀኑን ፀጥታ ስለሚነግስባቸዉ እንደልብ እየተደማመጡ ወግ ለመኮምኮም ይመቻሉ፡፡ ተስፋየ ገ/አብም ፡ ሌ ኮ/ል አበበ ገረሱና ሌ/ኮል አለበል አማረን በጋራም ሆነ በተናጥል እያገኛቸዉ ብዙ ቀናቶችን ወግ የተቀባብሉት እዚያ ነዉ፡፡ ተቀባይ ተስፋየ ሰጪ ሌ ኮ/ሎቹ ፡፡፡ ተስፋየ ደግሞ በቢራ ጀምሮ ለጥቆም በጂን እያቀባበለ ጨዋታቸዉን አወራርዱዋል፡፡ ጨዋታን ጨዋታ ካነሳዉ በአለኮል አጃቢነት የሚወርዱ ጨዋታዎች ጡጦዋ በጨመረች ቁጥር በግነት በስሜታዊነት በቅብዥርዥርነት አይበረዙም ትላላችሁ? ተስፋየ ራሱ እንደነገረኝ እንዲህ ባሉ የጠረጴዛ ምሽቶች የሚመሰጥባቸዉን ጨዋታዎች በዉስጡ ሲያከማች ያመሽና ሌሊት ይፅፋቸዋል፡፡ ወደ አንጎሉ እንደአወጣጣቸዉ ሁሉ እንደወረዱ ስለመፃፋቸዉ ግን እንጃ! የጂን ነገር! (የኒያላ ሆቴልን ነገር ካነሳን ይቺን እንበል ፡፡ አስመራን የረገጡ አያሌ ኢትዮጵያዊያን በኒያላ ሆቴል የትግል ጎራ ተስተናግደዋል፡፡ እኔም አንዳንዴ “እስኪ ኒያላ ሆቴል ግምባር ጎራ ልበል!” እያልኩ ቀልድ ቢጤ ጣል አደርግ ነበር፡፡ የምቀልደዉ በኢትዮጵያዉያን ወገኖቼ አልነበረም፣ በህግደፍ የአጋች ታጋች ተግባር እንጂ፡፡ ኒያላ ሆቴል አፍ ቢኖረዉ … !! ከብ/ጄ ከማል ጦር ጋር ኤርትራ የገባዉ ሌኮ/ል አበበም የአስመራዉ ኦነግ ለሁለት ሲከፈል ከብ/ጄ ከማል ጋር ወገነ፡፡ ብዙም ሳይቆይ በጤና ሳቢያ ከነከማል ቡድን ተሰናበተ፡፡ ህግደፍም ኒያላ ሆቴል እንዲመሽግ ፈቀደለት፡፡ ሰንበትብት ብሎም የራሴን የፖለቲካ ድርጅት መስርቻለሁና በሚዲያችሁ ይለቀቅልኝ አለ፡፡ የማይታሰብ ነበር፡፡ ለህይወቱ ስለሰጋሁ “እረ
ባክህ እዚህ ሆነህ ድርጅት መስርቻለሁ የምትለዉ ነገር ይቅርብህ፡፡ በሰላም ከዚህ አገር መዉጫህን ፈልግ” የወንድምነቴ ተማፀኖ ነበር፡፡ አልሰማኝም፡፡ በኢንተርኔት ለቀቀዉ፡፡ ሌኮ/ል አለበል ደግሞ በከፍተኛ አመራርነት የአማራ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ መመስረቱን ከእኔ ጋር ባካሄደዉ የቴሌቭዥን ቃለመጥይቅ ይፋ አድርጉዋል፡፡ ከኤርትራ እስከወጣሁ ድረስ ይህ ሁኔታ ነበር፡፡ ከተስፋየ ጋር በሚገናኙበት ወቅትም በዚህ ሁኔታ ላይ ነበሩ፡፡ የኒያላ ሆቴል ወጎች ልንለዉ እንችላለን (ጎበዝ ትዝታየ የጎንዮሽ ይዞኝ ሲነጉድ ራሴን ታዘብኩት)፡፡

Author Tesfaye Gebreab

Author Tesfaye Gebreab


ተስፋየ ከሌ/ኮ አበበ ገረሱና ከሌ/ኮ አለበል ጋር ሲገናኝ አንድ ነገር አዉቁዋል፡፡ ሌ/ኮ አበበ ከብ/ጄ ከማል ጋር መቆራረጡንና በህግደፍ ይሁንታ ኒያላ ሆቴል መመሸጉን ፡ ሌ/ኮ አለበል አማረ የአማራ ድርጅት ምስረታ ላይ መሆኑን ፡፡ እንዴት አያዉቅ ጎበዝ ! ኢትዮጵያን እንደ ቅርጫ ተካፍለዉ በቅዠት በሪሞት ኮንትሮል የሚገዙዋት ኮ/ል ፍፁም(ሌኒን) ኮ/ል ጠዐመ (መቀለ) ኮ/ል ጋይም፣ ኮ/ል ዮናስ እኮ ወዳጅና መሃንዲሶቹ ናቸዉ፡፡ ዋናዉ የህግደፍ ቢሮ ቤቱ ነዉ፡፡ እነ ብ/ጄ ከማልና ብ/ጄል ሀይሉ ጎነፋ ደግሞ ከህግደፍ ጋር ስለተፋቱ አላስፈለጉትም፡፡ ለህግደፍ አይመቹም ፡፡ (የህግደፍን ፊት መንሳት ካነሳን በኤርትራዊያን ላይ የሚወርደዉን ግፍ ትተን በእንግድነት የገቡትን ኢትዮጵያዉያንን ብንነቅስ፡ አነጋፋዉ የኦነግ አመራር አቶ ገላሳ ዲልቦ ከኦነግ አመራርነት ተወግደዉ አቶ ዳዉድ ከህግደፍ ጋር ሲወዳጁ አቶ ገላሳ አስመራ ላይ እንዴት እንዴት በህግደፍ ፊት እንደተነሱና በከባድ ህመም ሲሰቃዩ ችላ ተብለዉ ህይወታቸዉ በኤርትራዊዉ የቀድሞ የአ/አ ዩኒቨርሰቲ ጉዋደኛቸዉ አቶ ምህረቱ በእምነት እርዳታ መትረፉን መዘከር ይበጃል፡፡ በአስመራዉ የስደተኞች ኮሚሽን የስደት አገር ተገኝቶላቸዉ ከኤርትራ ሚግሬሽን የመዉጫ ቪዛ ስለተከለከሉት ወገኖችስ ቢሆን ማን ይሆን ያገታቸዉ ማን ይሆን ያሳገታቸዉ ? ( የታሪክ ማጣቀሻ መፅሃፍ ይወጣዋል ) እነዚህን መሰል ህግደፍ በኢትዮጵያዊያን ላይ ስለፈፀማቸዉ ወንጀሎች ፊት መንሳት…መንቀስ ይቻላል ፡፡ ግን እንዲህ ነበር የሆነዉ እየሆነ ያለዉም ፡፡ በቃ! አሁን ግን ይሄን ገታ አርገን ወደ ጀመርነዉ እንለፍ፡፡

የነተስፍሽን የአመሻሽ ማዕድ እየተጋራሁ ከጨዋታቸዉ ስጋራ ሰነበትኩ፡፡ሌ/ኮል አበበና ሌ/ኮል አለበል የቀጣዩ መፅሃፍ ባለታሪኮች መሆናቸዉን አወቅሁ፡፡በዚያዉ ሰሞን ምሽት ሌላ አንድ እንግዳ አብሮ ተገኘ፡፡በአምሳዎቹ የሚገኝ፡፡ አምቼ ኤርትራዊ ኢኒጂነር መሆኑን በትዉዉቅ ተረዳሁ፡፡ጥርት ባለ አማርኛዉ፡፡ ከጠረጴዛዉ ጨዋታ ገለል ብለን ከኢነጂነሩ ጋር ወግ ጀመርን፡፡ ወሎ ደሴ ማደጉን ከገለጠልኝ በሁዋላ ስለዝነኛዉ የወይዘሮ ስህን ት/ቤት የቀድሞ ትዝታዉ እያነሳ ጨዋታን ጨዋታ እየመዘዘዉ ነጎድን፡፡ እኔም የወሎ ልጅ [ከወረሴህና ጃንጥራሮች የምወለድ] ነኝና ጨዋታዉን በፍስሃ ስሜት ተሞለቼ አጣጣምኩት፡፡ በጥያቄ በትዉስታዎች ያቅሜን እየተሳተፍኩ፡፡በጨዋታ መሀል አስመራ ከሚገኙት የቀድሞ የስህን ት/ቤት ተማሪ ከነበሩት ከአቶ ጠሐ ሱዋሊህ ጋር ያደረግኩትን የትዉስታ ዝግጅት እንደወደደዉ ገለጠልኝ፡፡ ኢትዮጵያ ዉስጥ ተወልደዉ ያደጉና ረዥም የህይወት ዘመናቸዉን በተለያዩ ሙያ ያሰለፉና በአማርኛ ሀሳባቸዉን መግለፅ የሚችሉ ታጋዮች ኤርትራዊያንን ወደ ፕሮግራማችን በመጋበዝ የምናካሂደዉ የጨዋታ ጊዜ በበኩሌ በጣም ነበር የምወደዉ፡፡ በዉስጤ የሁለቱን ህዝቦች በፍቅር የተሞላ ግንኙነት ያንፀባርቃል ብየ ስለማምን፡፡ ከጥላቻ ፖለቲካ የራቀ በመሆኑም፡፡ “ሠናይ ከኢነጂነር ጋር የምታደርገዉን የግል ጨዋታ አቁዋርጥ” ተስፋየ በጨዋታችን መሃል አንባርቆ ገባ፡፡ “እንዴ ለምን? እንዲያዉም የፕሮግራማችን የጨዋታ እንግዳ አደርገዋለሁ፡፡ ስለ የወሎ ጣፋጭ ጨዋታዎችና በቀደምት ተማሪዎች ትግል ታሪክ አዉራ የሆነዉ የስህን ት/ቤት ትዝታዎች ባለቤት ነዉና ባስተናግደዉ እኔንም ፕሮግራማችንንም ያኮራናል” ስል መለስኩለት፡፡ “ኢነጂነርም ፈቃደኛ ነዉ” አከልኩ፡፡ ተስፈየ ተወራጨ ፡፡ ሞቅታም አለ፡፡ ከዚያም ወደኔ ቀረብ አለና በልመና መልክ “እኔ ታሪኩን በቀጣዩ መፅሃፌ ላካትተዉ ስለሆነ እባክህ ተዉ፡፡” ሲል ተማፀነ፡፡ “ያንተ በመፅሃፍ ስለሆነ ረዘም ልታደረገዉ ትችላለህ እኛ ግን በዉስን የአየር ሰዓት ነዉ የምናስተናግደዉ፡፡

አቀራረቡ ደግሞ የተለያየ መሆኑን ከኔ በላይ ታዉቃለህ፡፡” ተስፋሽ አልተዋጠለትም፡፡ “በእናነተ መጀመሪያ ከቀረበ ለኔ ጥሩ አይመችም” ሌላ ሰበብ አከለ፡፡ “አሁን የመፅሀፍህ አካል የሚሆኑት ኮ/ል አበበና ኮ/ል አለበልም እኮ በእኛ ፕሮግራም ተስተናግደዋል፡፡ አሁን የኢነጂነር ልዩነቱ ምንድን ነዉ?” ጥያቄየ ነበር፡፡ አልመለሰልኝም፡፡ የንትርካችን ምክንያት አልታይህ አልዋጥልህ አለኝ፡፡ በመሀል አጣብቂኝ የገባዉ ኢነጀር “ሠናይ ግድ የለም፤ መጀመሪያ ከተስፋየ ጋር እንስራና ከእናንተ ጋር በቀጣይ አደርጋለሁ፡፡ እዚሁ ስለሆነ ያለሁት ችግር የለም” ሲል የሽምግልና ሀሳብ አቀረበ፡፡ እየሳቅሁ ጣጣ የለዉም አልኩ፡፡ የኢነጂነርን ሁኔታ በመረዳት፡፡ ተስፍሽ ፊቱ ፈካ አለና “በእሪኩም ዘመዳ.. አባብለህ ባለታሪኬን ልትማርክ” ቀለደ፡፡ እኔም ትዝብቴ ጦዘ፡፡ ይሄዉ ጥቂት ወራት ቆጥሮ የስደተኛዉ ማስታወሻ ወጣ፡፡ ተስፍሽና ህግደፍ መፅሃፉን አሰራጩት ቸበቸቡት፡፡ እኔም ባለታሪኮቹም አነበብነዉ፡፡ አንድ ምሽት ኒያላ ሆቴል ጎራ ስል ሌ/ኮ/ል አለበልና አበበን አገኘሁዋቸዉና “እህሳ አማን ነዉ? እንዴት እንዴት ተነበበ መፃፉ?” መፅሃፉ ዉስጥ እንዳገኘሁዋቸዉ በሚያመላከት ወንድማዊ ሰላምታ ወግ ከፈትኩ፡፡ በአንዳች ስሜት ተያዩና “ሆድ ይፍጀዉ አለ ጥላሁን” አቤ ተነፈሰ ከቀጭን ፈገግታ ጋር ፡፡ “እዚሁ በህይወት እያለን ያልተባለ ነገር መፃፍ በጣም ነዉር ነዉ” አለበል ተከተለዉ በትንታግ ስሜት፡፡ ከሁለቱም ኮሎኔሎች ጋር ደረግነዉ ቆይታ ለተሰፋየ ያጫወቱትን በተዛባ መልኩ ማቅረቡንና ከቶወኑም ያላሉትን ጨማምሮ መፃፉ እጅግ እንዳሳዘናቸዉ በሚገልፅ ምሬት የተሞላ ነበር፡፡ “ከብዙ ወዳጆቼ ትችት ደረሰበኝ፡፡ የኦሮሞን ህዝብ ክብር አዋረድክ አሉኝ ፡፡ እኔ ያላለኩትን ጨማምሮበታል ብልም ሰሚ አጣሁ። ስለዚህ ከመፅሃፉ ታሪክ በታሪክ እየጠቀስኩ በዉጭ በሚዲያ አጋልጠዋለሁ” የሚለዉን የተሰበረ የሌኮ/ል አበበን ስሜት አስታዉሳለሁ፡፡ “አሁን ባለህበት ሁኔታ በዉጭ ሚዲያ ተስፋየን መተቸቱ ላንተ ህይወት ጥሩ ስለማይሆን እስኪ ታገስ” ከማለት በቀር በበኩሌ የምለዉ አልነበረም ፡፡ ነዉርነቱን በማጠናከር ፡፡ “ያልሰማ ጆሮ ከጎረቤት ያጣላል” ብለዋል አበዉ ፡፡ ጆሮ ዳዋ ልበስ ከሆነ ግን ሆን ተብሎ ለነገር እንጂ ለሌላ ምን ይሉታል፡፡ የሆነ ሆኖ ኮ/ሌኖሎቹ ተስፋየ ላይ
ንዴታቸዉን በግል እንዳይተነፍሱ በከተማዉ ፈልገዉ አጡት ፡፡ ከኤርትራ ወደ ዉጭ በመሄዱ፡፡ እንዲሁ እየተብሰከሰኩ ወር ሁለት ወር ካሳለፉ በሁዋላ ታዲያ ከተስፋየ የተዘዋዋሪ መልዕክት ደረሳቸዉ፡፡ ለእያንዳንዳቸዉ 5 ሺህ ናቅፋ ጠቅላላ 10ሺህ ናቅፋ(200 ዶላር) ፡፡ በተግባሩ ማዘናቸዉን ሰምቶ አፍ መዝጊያ ከባህር ማዶ ብር እንደላከላቸዉ እየቀለዱ አወጉኝ ፡፡ ይበልጥም አዘኑበት ፡፡ ጉርሻዉንም አልተቀበሉትም፡፡ ገንዝብ እንደሚያስፈልጋቸዉ ባያጠያይቅም ክብረ ነክ በሆነ መልኩ መቀበልን አልመረጡም፡፡ በዉነት ከኩሩወቹ ወገኖቼ በመሆናቸዉ ኮራሁባቸዉ ፡፡

እነ ሌኮ/ል አበበና አለበል ይህን ቅያሜያቸዉን ካካፈሉኝ በሁዋላ ወሎ አደጉን ኢነጂነር አግኝቼ የሚለዉን መስማት ፈለግሁ፡፡ “ኢኒጂነር የነ ኮ/ሎኔልን ታሪክ አነበብኩት ያንተን ታሪክ ግን አጣሁት፡፡ ስለ ወሎ የአንድ ሰዉ ታሪክ ትዝታ ግን አንብቢያለሁ፡፡ አንደ ልጅ በኢንተርኔት በብዙ ድርድር ያደረሰኝ የወሎ አባት ታሪክ ነዉ በሚል ያቀረበዉን ፡፡ ያንተስ የታለ?” እንዳገኘሁት ያቀረብኩት ጥያቄ ነበር፡፡ “እሱ እኮ ነዉ እኔ ያካፈልኩት ታሪክ ፡፡ በዚህ መልኩ እንደሚቀርብ አልገመትኩም፡፡ ስሜ ይጠቀሳል እንጂ አይጠቀስም ብየ አልጠበቅኩም” ሲል ኢነጂነር ያልጠበቅኩትን ገልፆ ቅሬታዉን አዘነበዉ፡፡ “የታሪኩ ባለቤት አንተ እዚሁ እያለህ ከሌላ በደጅ ጥናት እንደደረሰዉ አስመስሎ በሌላ ስም አቀረበዉ ነዉ የምትለኝ ?” የሰማሁትን ማመን አልቻልኩም፡፡ ዕዉቁ የብዕር ሰዉ በዓሉ ግርማ ጋሼ ስብሃትና ሌሎችም ደራሲዎች ከሰዎች እዉነተኛ ታሪክና እዉኑ አለም ሰዎች ባህሪያት ተመስርተዉ ልቦለድ የመፃፍ ክህሎታቸዉን አዉቃለሁ አንብቢያለሁ፡፡ የጋሼ ስብሃት ትኩሳት ሌቱም አይነጋልኝ አጋፋሪ እንደሻዉ የበአሉ የቀይ ኮኮብ ጥሪ መፅሃፉ ላይ ያሉት እነ እምአእላፍና ደርቤ በቅርብ ከሚያዉቃቸዉ መሆኑን፡፡ ደራሲዉ ከፊል የደራሲ ስብሃት ገ/እግዚአብሄር ታሪክ ስለመሆኑ፡፡ ጋሼ ስብሃት ስለ በአሉ ሲናገርም ይህንኑ ማብራራቱን ሰምቻለሁ፡፡ በሌሎችም በልቦለድ ዉስጥ የእዉኑ አለም ሰዎች ገፀባህሪያት ተላብሰዉ መቅረባቸዉ የተለመደ አፃፃፍ ነዉ፡፡ ግለታሪክ ከሆነ ግን እንደወረደ መቅረብ የሚኖርበት ይመስለኛል፡፡ ባለታሪኩ በዘመኑና በቦታዉ ጀልባ ዉስጥ አሳፈሮ በትዝታ ባህሩ ዉስጥ እየተመላለስን እንድንሳፈፍ ከማድረጉም ባሻገር ዘመኑንና ቦታዉን እንደነበረ ለማየት እንድናጣጥም ይረዳል እላለሁ፡፡እናምነዋለንም፡፡ ለባለ ግለታሪኩም እዉቅናን ሰጥተን እናከብራልን፡፡ የደራሲ ሀዲስ አለማየሁ ግለታሪክ የደራሲና ገጣሚ መንግስቱ ለማ ታሪክ የዘነበ ወላ የስብሃት ማስታዎሻ የፍቅሩ ኪዳኔ የአራዳ ልጆች …… ; የመሳሰሉት ግለታሪክ መፃህፍት ባለታሪኮቹ በራሳቸዉ ስለሚተርኩልን መሳጭነታቸዉ አያጠያይቅም፡፡ ተስፋየ እንዳደረገዉ ግለ ታሪክ ብለን ያነበብነዉ ልብወለድ ሆኖ ስናገኘዉ እንዴት እናምነዋለን? “አይነጋ መስሉዋት ….. “ አበዉ ያሉት ነገር ፡፡ እንጃ እንግዲህ ከብሂሉ ባሻገር ሌላዉ የስነፅሁፍ ባለሙያዎችን ይመለከታል፡፡

ከህይወት ዘመኑ የወሎ ትዝታዉን ለተስፋየ ያካፈለዉ ኢነጂነር እነሆ እዉቅናና አክብሮቱ ቀርቶ ስሙን እነኩዋን ከደራሲዉ ማስታወሻ ላይ ማግኝት ሳይችል ቀረ፡፡ “በጣም ያሳዝናል፡፡ ተስፋየ በእኛ የቴሌቭዥን ፐሮግራም ላይ የጨዋታ እንግዳ ሆነህ እንዳትቀርብና ስለወሎ ደሴ ወ/ሮ ስህን ት/ቤት መልካም ትዝታህን ቀድመህ እንዳታካፍል የፈለገዉ ከሌላ የደረሰዉ አስመስሎ ለማቅረብ ስለፈለገ መሆኑ ነዉ ፡፡ ለነገሩ እሱ መች ሆነና …..” ንግሬን አልጨረስኩትም፡፡ ስሜቴን መቆጣጠር ተገቢ መሆኑን ዉስጤ ነገረኝ፡፡ “ይሄዉ ተስፋየ ታሪኬን በአደባባይ ዘረፈዉ “ ኢነጂነር መራራ ቀልድ ቀለደ ፡፡ በክህደት የተሞላዉ ህግደፍ ያመኑትን ኢትዮጵያዉያን ወታደሮችን ዘረፈ ፡፡ መዝረፉንም ቀጠለ ፡፡ ተስፋየ ገ/አብም ግለ ታሪክ ዘረፈ ፡፡ ‹የአባት ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ› መሆኑ ይሆ ? ለዛሬ በዚሁ ይብቃን፡፡ ለቀጣዩ የዚያ ሰዉ ይበለን !
ቸር እንሰንብት፡፡

ሠናይ ገብረመድህን (ጋዜጠኛ)
አዉስትራሊያ ሜልበርን
ለግል አስተያየታችሁ ከአክበሮት ጋር ፡ Wosenmarta_2010@yahoo.com

(ሰበር ዜና) ቴዲ አፍሮ ከሃገር እንዳይወጣ ታገደ

$
0
0

teddy afro

(ዘ-ሐበሻ) በአውሮፓና የተለያዩ የሩቅ ምስራቅ አገራት የሙዚቃ ኮንሰርቶቹን ለማቅረብ ወደ ውጭ ሃገር ሊወጣ የነበረው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከሐገር እንዳይወጣ መታገዱን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው የታማኝ ምንጮች መረጃ አመለከተ። ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርቱን በፊንላንድ ሄልሲንኪ በነገው እለት ይጀምራል ተብሎ የነበረ ሲሆን የሙዚቃ ባንዶቹ አባላትና ማናጀሩ እዛው ፊላንድ ቢገቡም ቴዲ በደህንነቶች ከሃገር እንዳይወጣ በመታገዱ የተነሳ የነገው የፊንላንድ ኮንሰርት መሰረዙን አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

ከጥቂት ወራት በፊትም ቴዲ አፍሮ ወደ አሜሪካ ሊመጣ ሲል እንዲሁ በደህነንቶች ተይዞ በኤርፖርት ሲጉላላ እንደቆየና በኋላም ወደ ውጭ እንዲወጣ እንደለቀቁት ያስታወሱት የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች፤ በአሁኑ ጭራሹኑ እንዳይወጣ ፓስፖርቱን ውስደውበታል ብለዋል። ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የቴዲ አፍሮ ፓስፖርት ያልተመለሰለት ሲሆን ወደፊት እንዲወጣ ይፍቀዱለት አይፈቀዱለት የታወቀ ነገር የለም ብለዋል።

የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት ቴዲ ለምን ከሃገር እንዳይወጣ እንደታገደ የተገለጸለት ነገር የለም:።

በሄልሰንኪ ፊላንድ የቴዲን መምጣት በጉጉት የሚጠባበቁ የነበሩ ኢትዮጵያውያን በርካታ ሲሆኑ አዘጋጆቹም ቴዲ ይመጣል በሚል በርካታ ትኬቶችን ሸጠው ነበር። ሆኖም ግን ኮንሰርቱ በመሰረዙ የተነሳ ትኬቱን የገዙ ሰዎች ገንዘባቸው እንደሚመለስላቸው አዘጋጆቹ በቪድዮ ለዘ-ሐበሻ በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል። ቪድዮውን ይመልከቱት።

በዚህ ዙሪያ የቴዲ አፍሮ ማናጀር የሆነውን አቶ ዘካሪያስ ጌታቸውን ዘ-ሐበሻ ለማነጋገር እየሞከረች ሲሆን ማናጀሩን እንደገኘነው ሃሳቡን ለአንባቢዎቻችን እናካፍላለን።

(ሰበር ዜና) መስቀል አደባባይን በርከት ያሉ ፖሊሶችን የጫኑ የፌደራል መኪኖች አጣበዋታል; ለሰልፍ የሚወጣውን እያፈኑ ነው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ሰማያዊ ፓርቲን ጨምሮ 9ኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዛሬ በመስቀል አደባባይ የጠሩት የ24 ሰዓት የተቃውሞ ሰልፍን ለማስቆም መንግስት መስቀል አደባባይ ላይ የፌደራል ፖሊስ በጫኑ መኪናዎችን ማስፈሩን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ::
semayawi
9ኙ ፓርቲዎች መንግስት ተቃውሞውን ለማፈን ከመንገድ ላይ እያስቀረ በመሆኑ በአንድ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ከመሄድ ይልቅ በተለያያ አቅጣጫ እንዲሄድ ከደቂቃዎች በፊት ባወጡት መግለጫ ጥሪ አቅርበዋል::

በመስቀል አደባባይ የተገኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እየታፈኑ ወደ ኤግዚቢሽን ማዕከል እየተወሰዱ መሆኑን የገለጹልን የአይን እማኞች ሂጃብ የለበሱ የሙስሊም ሴቶች; የኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ህብረት ሊቀመንበርና የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፀሃፊ አቶ ግርማ በቀለ; አህመድ ሞሃመድ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል እና ሌሎችም ታፍነው ተወስደዋል::

በአሁኑ ወቅት መስቀል አደባባይ የሚገኘው ፌደራል ፖሊስ ለተቃውሞ የወጣውን ሕዝብ እየበተነ; እያሰረ ይገኛል::

ተጨማሪ መረጃ ይዘን እንመለሳለን::


ቴዲ አፍሮን ቦሌ ላይ ለምን አገቱት? –ክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)

$
0
0

teddy afro
ክንፉ አሰፋ
ወደ አውሮፓ የሚያስገባውን ቪዛ እና ትኬት ይዞ ከወዳጆቹ ጋር ጉዞውን ለመጀመር ወደ ቦሌ አለም-ዓቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ አቀና። እዚያው እንደደረሰ የተለመደው የፓስፖርትና ትኬት ቁጥጥር ተደረገ። ሁሉም የተሟላ ነበር። ቴዲ ሸኚዎቹን ተሰናብቶ ወደ ውስጥ ገባ። እለተ ሐሙስ፣ ህዳር 28 ቀን 2007 ዓ.ም.።

የአውሮፓው ኮንሰርት በፊንላንድ፣ ሄልሲንኪ ቅዳሜ፤ ህዳር 28 ቀን ይጀምራል። ፊንላንድና አካባቢው ያሉ የቴዲ አድናቂዎች ትኬት ቆርጠው አርቲስቱን በጉጉት እየተጠባበቁት ነው። የቴዲ አፍሮ ማናጀርም አቡጊዳ ባንድን ይዞ ሄልሲንኪ ላይ ለቅዳሜው ስራ በልምምድ ላይ ይገኛል።

ቴዲን ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተሰናብተው የተመለሱ ወዳጆቹ አውሮፓ ደውለው አርቲስቱን ሄልሲንኪ ላይ እንዲቀበሉት ተናግረው ነበር። ነገሩ እነሱ እንዳሰቡት ግን አልነበረም። ዘግየት ብሎ ሌላ ነገር መጣ። ሰዎቹ ቦሌ ላይ አገቱት። በውድቅት ሌሊት ፓስፖርቱን ነጥቀው ወደ ቤቱ አሰናበቱትም። ይህንን ያደረጉበትን ምክንያትም አልነገሩትም። አስቀድመው ገና ከበሩ ላይ መከልከል ይችሉ ነበር።… ግን ማንገላታት ነበረባቸው። ስሜቱን ለመጉዳት መሞከር ነበረባቸው። ጉልበት እንዳላቸው ማሳየት ነበረባቸው። ፈላጭ፤ ቆራጭ መሆናቸውን ማሳወቅ ነበረባቸው። ቂመኞችና ተበቃዮችም መሆናቸውን መናገር ነበረባቸው። ….

ነገሩ ያልተጠበቀ ባይሆንም፤ ለቴዲ ጠበቆች ግራ ማጋባቱ አልቀረም። በነጋታው ጠበቆቹ ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ፍርድ ቤት መሄድ ነበረባቸው። ከፍርድ ቤት ያገኙት ምላሽ በቴዲ አፍሮ ላይ ምንም አይነት የማገጃ ትዕዛዝ ያለመኖሩን ነው። ከዚያም ወደ ኢሚግሬሽን ጉምሩክ እና ሌሎች ጉዳዩን የሚመለከቱ ቢሮዎች ሁሉ አመሩ። እዚያም የጉዞ ማገጃ አልተገኘም። ታዲያ ማን ይሆን ያዘዘው? የካዛንችዙ ስውር መንግስት ስራውን እንደገና ጀምሮ ይሆን?

ጉዳዩ ግራ ያጋባል። እርግጥ ነው። የዛሬይቱ ኢትዮጵያ አንድ ተራ ካድሬ እንዲህ አይነት ተራ ወንጀል የሚፈጽምባት ሃገር ሆናለች። አንዳንድ ቦታዎች ላይ “መንግስት የለም እንዴ?” የሚያስብሉ ወንጀሎች እንደሚፈጽሙ ይሰማል። የቀድሞው የኮሚኒኬሽን ሚንስትር ዴዔታ የነበረው ኤርምያስ ለገሰ፤ በቅርቡ ባሳተመው “የመለስ ትሩፋቶች” የተሰኘ መጽሃፉ አዲስ አበባን ባለቤት አልባ ከተማ ብሏታል።
በልማታዊ አርቲስቶች እለት-ተለት የሚወደሰው ጸሃዩ መንግስት፤ ለልማት የተጋው መንግስት፣ ጭቆናን ያቆመው መንግስት፤ ለዜጎች መብትና ነጻነት የቆመ መንግስት፣ ሃገሪቱን ወደ እድገት እና ትራንስፎርሜሽን ጎዳና ላይ ያስኬደ መንግስት፣ የመቻቻል ባህልን ያመጣ መንግስት…. እንዴት ሆኖ የጥላቻ፣ የቂም እና የበቀል እርምጃ ሊወስድ ቻለ?

ልማታዊ አርቲስቶቻችን ይቅርታ አድርጉልኝና የአስተሳሰብና የአመለካከት ለውጥ ሳይኖር ቁሳዊ ለውጥ ይመጣል ብሎ የነገራችሁ ማን ይሆን? አመለካከታችን ካላደገ፣ እድገት ይታሰብ ይሆን?

ወደ ጉዳዩ ስንመለስ፣ ከፊንላንድ በኋላ ሌሎች ስድስት የአውሮፓ ከተሞች ላይ ኮንሰርቶች ተዘጋጅተዋል። ፕሮሞተሮች ለመሰናዶው ብዙ ወጪ አውጥተዋል። የአርቲስቱ አድናቂዎችም አስቀድመው ትኬት ቆርጠዋል። ይህንን ካድሬዎቹ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ሁሉንም ማጉላላቱ፤ ከተቻለም ማደናቀፉ ደስታን ይሰጣቸዋል። እንዲህ አይነት የድፍረት ስሜት የሚመነጨው አርቲስቱን ሳይሆን ይልቁንም ሕዝብን በጅምላ ከማናቅ ነው። ሕዝብን ከመጥላት። እየገዙት ያሉትን ህዝብ መናቅና መጥላት የት ድረስ ሊያደርሳቸው እንደሚችል የምናየው ይሆናል። እንደ ሰብአዊ ፍጡር ሳይሆን እንደ እንስሳ የሚያስቡ እነዚህ የዘመናችን ጉዶች ሕዝብ የሚወደውን ነገር በሙሉ በመጥላት፤ የህዝብ አካል እንዳልሆኑ እይረጋገጡልን ነው። ከጫካ ከወጡ 21 አመታትን አስቆጥረዋል። አካላቸው ከጫካ ወጣ እንጂ አመለካከታቸው ግን እዛው እንደሆነ ድርጊታቸው ይነግረናል። ከሁለት ዓስርተ-ዓመት በኋላም ጥንት ከሚያስቡበት ከጫካው ህግ አልተላቀቁም።

ይህንን ትልቅ ሃገር እና ይህንን ትልቅ ሕዝብ እየመሩ ለምን እንደመንገስት ሊያስቡ እንደማይችሉ አይገባኝም። መንግስት ሆነው እንደግለሰብ ቂም ይይዛሉ። ቂም ይዘው እንደ ክፉ ሰው ይበቀላሉ። ሀገር ደግሞ በጥበብ እና በማስተዋል እንጂ፤ ከቶውንም በቂም እና በበቀል አትመራም። ይህንን የሚያደርጉ ሁሉ መጨረሻቸው ውድቀት፤ አወዳደቃቸውም የውርደት እንደሆነ ለደቂቃ አስተውለውት የሚያውቁ አይመስለኝም።

እንግዲህ ይህ ተራ ወንጀል በዚህ ድንቅ አርቲስት ላይ ሲፈጸም የመጀመርያ አይደለም። ከወራት በፊትም ወደ አሜሪካ ሊጓዝ ሲል የአየር መንገዱ ካድሬዎች ይዘው ብዙ አጉላልተውት ነበር። እርግጥ ነው ቴዲ አፍሮ ላይ ጥርሳቸውን ነክሰውበታል። ኤርምያስ ለገሰ፤ በ”መለስ ትሩፋቶች” መጽሃፉ ላይ የቴዲን ጉዳይ አንስቶ የገዢው ፓርቲ ሰዎች ይህንን አርቲስት እንዴት በክፉ አይን እንደሚመለከቱት ዳስሷል። ይህ አርቲስት ምናልባት በአንዲት ዜማ ተችቷቸው ይሆናል። እነሱም አላለፉትም። በፍትህ ስም የበቀል ዱላቸውን አሳርፈውበታል። ወህኒ ወርዷል። እስኪበቃቸውም ቀጥተውታል።

ቴዲ አፍሮ ግን ቂም አልቋጠረባቸውም። አሁንም የሚያቀነቅነው ስለ ፍቅር ነው። አሁንም የሚለው እንዲህ ነው። “ፍቅር ያሸንፋል!”

እነዚህ ሰዎች ሃያ ሁለት አመታት ሙሉ ከጥፋት አለመማራቸው ብቻ አይደለም የሚደንቀው። በአንድ ግለሰብ ምክንያት ከሚሊዮኖች ጋር እንደሚላተሙ አለማሰተዋላቸውም የሚገርም ነው። ለሟቹ ፓትሪያርክ ሲሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኦርቶዶክስ ምዕመናን ጋር ተቃርነው ነበር። አንድ የሙስሊም መጅሊስ መሪን ለመያዝ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሙስሊም ምዕመናን ጋር ጠፋጥተዋል።

ዛሬ አንድ ቴዲን ቢያንገላትቱት፣ ቢያግቱትም ሆነ ፓስፖርቱን ቢነጥቁት ለግዜውም ቢሆን የአድናቂዎቹን ስሜት ሊጎዱት ይችሉ ይሆናል። ይህ ድርጊታቸው ቴዲ አፍሮን ቅንጣት ያህል አይጎዳውም። ይልቁንም የበለጠ ተወዳጅ እና የበለጠ ጀግና ያደርገዋል። ከዚህ የፖለቲካ ንግድ እነሱ የሚያተርፉት ነገር ቢኖር የህዝብ ጥላቻን ነው። የቴዲን መታገት የሰሙ የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ሳይቀሩ እንዲህ ሲሉ ተደመጡ፤ “አሁንስ አበዙት… ሃገራችንን እንድንጠላ አደረጉን….” ካድሬዎቹ ማህበራዊ ድረ-ገጾችን ቢጎበኙ የህዝቡን ስሜት ያነብቡ ነበር።

በሕዝብ አመኔታ ሳይሆን ይልቁንም በጆሮ ጠቢዎችና በመሳርያ በመተማመን እስካሁን ስልጣን ላይ ላላችሁት ገዢዎች ግን አንድ የምለው አለኝ። የፈረንሳዩ አንባገነን ናፖሊዮን ቦናፓርት የነበረውን ሰራዊት እስተውሉ። ይህ ግዙፍ እና የሰለጠነ ሰራዊት በህዝብ እንደ አሸዋ ተበተነ። የግብጹ ሆስኒ ሙባረክ ያልታሰበ እና ያልታለመ ውድቀት የመጣው እንዲሁ በመሳርያ ከመተማመን እና ህዝብን ከመናቅ ነበር። ይህ አስደንጋጭ ትዕይንት ለእናንተ ትምህርት ካልሰጣቸሁ የሱ እጣ ፈንታ ይጠብቃችኋል። መቶ አመት የቆየ አንባገነን ገዢ በታሪክ አላየንም።

(አሁን የደረሰን ዜና) ፖሊስ ለሰልፍ የሚወጣውን መደብደብ ጀመረ; ሰልፉን አስቁሞ መንገድ እየዘጋ ነው

$
0
0

addis ababa semayawi

addis ababa semayawi party

addis ababa semayawi party 1
(ዘ-ሐበሻ) በከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ እንደወደቀ የሚነገርለት የሕወሓት/ኢሕአዴግ አስተዳደር ፖሊሶችን በማስመራት ከሰማያዊ ፓርቲ ተነስተው ወደ መስቀል አደባባይ የሚያመሩትን ሰልፈኞች በመደብደብና መንገድ በመዝጋት ላይ እንደሚገኝ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታወቁ:: በሌላ በኩል በደረሰን መረጃ ሰላማዊ ሰልፉ ከሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ጀምሮ መፈክር እያሰማ ወደ አብዮት አደባባይ እየሄደ ቢገኝም የጀመረመው ሰልፍ እንደራሴ ሆቴል ላይ ፖሊስ አስቆሞታል::

ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በደህንነቶች እና በፖሊስ መከበቡን ያስታወቁት ዘጋቢዎቻችን ፖሊስ የሃይል እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ገልጸዋል::

በሌላ በኩል ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ከአዲስ አበባ አሁን ባደረሰን መረጃ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት፣ አለሳ መንገሻ የጌዴኦ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር፣ የከንባታ ህዝቦች ኮንግረንስ ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ፣ ወሮታው ዋሴ፣ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ እየሩስ ተስፋው፣ ጋዜጠኛ በላይ ማናየ፣ ወይንሸት ሞላ፣ ሳሙኤል አበበ፣ እያስፔድ ተስፋዬ፣ሜሮን አለማየሁ፣ ንግስት ወንዲፍራው፣ ወይንሸት ንጉሴ፣ ምኞት መኮንን፣ አቤል ኤፍሬም፣ ኤፍሬም ደግፌ፣ ኃይለማሪያም፣ ሜሮን፣ ኢብራሂም አብዱልሰላም፣ እና ሌሎችም የትብብሩ አመራሮችና አባላት ከፍተኛ ቁጥር ባለው ፌደራል ፖሊስ ተይዘዋል፡፡ ነዋሪውን ወደየቤቱ እንዲገባ በማድረግና መኪና መንገድ በመዝጋትሜዳ ላይ እየደበደቧቸው ነው፡፡ የትብብሩን አመራሮች፣ አባላትና የሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊ ለመደብደብ ወደየ ቤታቸው እንዲገቡ ሲታዘዙ አልገባም ያሉ፣ መንገድ ላይ የተገኙና ሌሎችም የአካባቢው ነዋሪዎች፣ አልፎ ሂያጆች በፖሊስ እየተደበደቡ ነው፡፡

40 ያህል አመራሮችን ፌደራል ፖሊስ በጭካኔ ደብድቧል፡፡ ሰላማዊ ሰልፉን ከሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ጀምረው ወደ አብዮት አደባባይ በማቅናት ላይ ከነበሩት መካከል 40 ያህሉ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸዋል፡፡ አቤል ኤፍሬምን ጨምሮ በርካታ የሰልፉ አስተባባሪዎች እራሳቸውን እስኪስቱ ተደብድበዋል፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ

አሁንም ዘ-ሐበሻ አዳዲስ መረጃዎችን እንዳገኘች ትመለሳለች

BBN Radio: 9ኙ ፓርቲዎች የጠሩት የአዳር ሰልፍ በፖሊስ ጭካኔ የተሞላበት ድብደባና አፈሳ ተቋረጠ (ቃለምልልሶች ይዘናል)

$
0
0

ቢቢኤን ሰበር ዜና ዘገባ (በድምጽ)
የዘጠኙ ጥምር የትብብር ፓርቲዎች የጠሩት ሰልፍ በፌድራል ፖሊሶች ጭካኔ የተሞላበት ድብደባና አፈሳ ተቋረጠ
ወደ ቦታው በመደወል ሰበር ዜና አጠናቅረናል ዳውንሎድ በማድረግ ያድምጡ

addis ababa semayawi party

ኢትዮጵያ ፋናዬን ትመስላለች –ሀገርና ልጆቿ እንዲህ በመከራ ሰጠሙ። (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 06.12.2014 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

እሜቴ ነፃነት እንደምን ከርመሻል?!

ከአምናው ሸክማሸክምሽ ዘንድሮ ብሶሻል ።

ዕንባነን አቅንተሽ ዘመን ሸኝተሻል ….

እትብትን ገብረሽ መከራ ወሮሻል። …

ያልፋልም ሳይመጣ እንዲህ ጠቋቁረሻል፤

የፋሽስቱ ኑሮ እንዲህ አሳሮሻል

ያገተው ተፈጥሮሽ – ራሄልን ሆኗል።

Teme & momየሀገሬ ልጆች እንዴት ናችሁልኝ? የዛሬን „የወያኔን የዱላ ቀን“ ሰበር ዜና ከዘሃበሻ እዬተከታተልኩ – እያነበብኩ የጻፍኩት ነው። ይህ ፎቶ ሀገራችን ከነውስጧ ይናገራልስለማያልቀው አሳሯ ይመስክራል። እያደር ስለሚጎላው የበቀል ዱላ ያብራራል። ኢትዮጵያ ለእኔ ፋናዬን ትመስላለች። አዛውንቷ እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ እንዲህ በግራጫ ዘመኗ ክልትምትም ትላለች። ልጇ እንደ ናፈቃት፣ እንደሳሳት፣ ወጥቶ ሳይመለስ ይቀርባታል። በሰው እጅ ወድቆ በመከራ ስንቅነት ይቀጠቀጣል። ለንዳድ ወይ ለባሩድ ገጸ በረከት ይሰጣል። አዎን እናት ኢትዮጵያ ፋናዬን ትመስላለች ….

ዕድሜ ጠገቧ እመቤት ሀገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ አልጋ አያስፈልጋትም – መሬት እንጂ። …. መቀነት አላስፈለጋትም ገመድ እንጂ፣ እህል አለስፈለጋትም – ፆም እንጂ፤ ደስታን አታቅድም ልጇቿ አሳራቸው ጠንቷልና፤ ሠርግ አያምራትም ልጃቿ ተስፋቸውን ተቀምተው ወጣትነታቸው ካቴና እንዲሆን  በአረመኔዎችና በጨካኞች ተገምድሎባቸዋልና *። ግን አቅሟ ያለው ከብሌኗ ስለሆነ ታነባለች – ሌትና ቀን። አዎን ልዕልተ ኢትዮጵያ እንዲህ ፋናዬን ትመስላለች ..

ልጇ ስጋቱ መንፈሱን ሲወጥረው ተንፍሶ ሃሳቡን ቢገልጽ  – ዱላ ነው፤ ወስፋቱ ሲንጫጫ፤ መጋኛው ሲተራመስ እራበኝ ብሎ ቢናገር – እርግጫ ነው፤ ጉሮሮው ድርቆ ሊያረጥብ ጠብታ ለምኖ ጠማኝ ለማለትም – ቅጥቀጣ ነው፤ ሌማቱ ድሆኖ* በባዶነቱ ሲያቅትቱ ኑሮን አልቻልኩም ቢል – መከትከት ነው፤ የተጣፈችው፣ ዘመን በልቷት አፍረተ ሥጋውን ለመከወን አቅም ያነሳትን ጥብቆ እያያት ከበላዩ ስታልቅ ታርዝኩኝ ቢልም –  ወንጀል ነው፤ የዘመን አራጣ ከፋይ ሆኗልና።

ሀገሬ፣ እናቴ ኢትዮጵያ ብሎ ደፍሮ ለመናገርም አሸባሪ“ ተብሎ ከርቸሌ ወይንም የባሩድ እራት ይሆናል፤ የማንነቴ መግለጫ ባርነትን ያለሳህኝ ባለውለታዬ ዓርማዬ ሰንደቄ እራቡንም ጥማቱንም በአንተው ልቻለው ብሎ ፈተናውን ለመተጋስ ሰንደቁን ቢለብስም የከፋ ጦር ይታዘዝበታል – ማረጃ ይሰናዳለታል።  ብሄርተኛ አክራሪ“ ነህ ተብሎ የፊጥኝ ታስሮ መፈጠሩን እስኪረግም ድረስ በዱላ ይቀጠቀጣል፤  ስለሆነም ዬልጇቻ ፍዳ እዬጠና መሄድ ያሳሰባት እናት ታወርደዋለች ዕንባዋን። …. እዬረጨችም በመማጸን … አዎ ኢትዮጵያ እንዲህ ናት ውስጧ ፋናዬን ትመስላለች።

መጣህልኝ ልጄ? ምን ይሻልህ? ደከመህ ወይ? አመመህን? የት አመሸህ? ቀረ … እንደ ራበ … ጠጋ ብሎ ጠረንን – ለጠረን እዬጣጣሙ በፍቅር እናታዊ ዓይን ልጅን መዳበስ – መዳሰስ – ማሻሸት- የፆም ውሃ ሆነ፤ ልጅና እናት የሆድ የሆድን ጧት ማታ ማውጋጋት ቀረ፤ የወጣነውም ብንሆን ቢታመሙ አንደርስ፤ ቢሞቱ አንቀብር እንደ ወጣን ቀረን፤  ሀገር ቤት ያለውም እንደ ወጣ ቀረ ጅቦቹ ኑሮውን ነጠቁት አራዊቶች ባዕቱን ቀሙት። ለፍዳው ዞን ተበጀለት። አዎ ኢትዮጵያ ዛሬ ያረረባት ፋናዬን ትመስላለች ….

እሷ የሚያስፈልጋት የፋካ የልጇ ጠረን ብቻ ነበር። ወጥታ ገብታ፣ አግኝታው፣ ቅርብ ብላ ጠረኑን መጠጣት። ድራ ኩላ ከጎረቤቱ፣ ከቤተዘመዱ ጋር ሐሤታን ተጋራታ ዓይኗን በዓይኗ ማዬት፤ የልጅ ልጅ መሳም፤ አዲስ የጋብቻ ዝምድና ፈጥራ ዝክሩን ማህበሩን ሞቅ ደመቅ አድርጋ በፈግጋታ ፍሬዋን መዬት ነበር፤ ለፍታ – ደክማ – ጠቁራ – ከስላ ያሳደገችው ለዚህ እንጂ ለበቀል ቁርስ ምሳና እራት አልነበረም። ግን ሆነ … እንዲህ ተስፋዋን አተነነው ዞገኛው ወያኔ።

ፍላጎቷን እንደ ህልሟ ማዬት እናት ሀገር ኢትዮጵያ አልቻለችም። ልጇ ለተለያዩ የቋሳ መፈተኛ እዬዋለ ነው። …. እያለ ሰውነቱ ዝሎ የራሴ የሚለው አካሉ ሸሽቶት ሞትን ናፈቀ። ይህን ታያለች አናት። የፈዘዘውን የልጇን አካል ታስተውላላች – እናት። ዬልጇ ክብሩ አካል ለአራዊት ፈንጠዝያ፤ ለባህር ሲሳይ፤ ይሄው ነው ኑሮዋ ኑሮ ከተባለ። …. ስለሆነም እንቅልፍ እልባዋ ቀንም ሌትም  በአሳር – ትፈተላለች። በጥቃት – ትባዘታለች። በሰቀቀን – ትወጋላች። ነገር ግን ሩቅ ታሰባለች። ቢሆንም እያች ግን የለችም። ሁለመናዋን መንፈሷን ሳይቀር ተነጥቃለች።  … አዎን እናት ሀገር ኢትዮጵያ ፋናዬን ትመስላለች ..

የፋናዬ ዕንባ ጅረት ነው፤ የአባይ ፏፏቴ ነው። …  ይነጉዳል ዘመንን እዬወቀሰ። ይሄዳል … ዘመንን እዬነቀሰ፤ ፈጣሪን ግን ተማጽኖ – መጪውን ዘመኑን በርኮ ከበለኃሰቦች እንዲታደግ እያሳሰበ … ጠብታዋ ጉዞውን አሁንም ቀጥሏል – እዬተከዘ። አያልቅበት ይፈሳል … መከራው የሚያልቅበትን ቀን ያልማል፤ ፍዳው የሚቋጭበትን ሁኔታ ያሰላል …. ዋናው በዕንባ ወንዝነት …. ይሠግራል ….

ተፋሰሱ አልፎ ደረቷን እራስ ሲያደርገው፤ ተፋሰሱ ቀጥሎ ዕንብረቷን ሲጎበኘው። ያን ጊዜ እትብቱና መከራው ተገናኝተው ያወጋሉ፤ ማለፊያውን ቀን ያልማሉ። እንደ ገና በህቅታ ቃና እና ሲቃ የፈላ አዲስ ፋፋቴ ይተካል። እኔ እቀድም እኔ እቀድም በአዲስ ጉልበት ይሯሯጣሉ። ገደቡን ጥሶ ይለቀቃል …. አዎን ኢትዮጵያ ፋናዬን ትመስላላች ….

ዱላው ቀጥላሏ፤ ዛሬም የዱላ ቀን ነው። ነገም እንዲሁ … ግን ሲከር ይበጣሳል ሲሞላም ይፈሳል። እግዚአብሄር ይስጥልኝ – ኑሩልኝ  የእኔዎቹ። የራሄልን ዕንባ የታደገ ዕንባ የፋናዬንም ይታደግ! አሜን! አዛውንቷ ፋናዬ ልዕልት ኢትዮጵያ ናትና ….

መፍቻ * መገምደል …  ኢ – ፍታህዊነት፤ ኢ – ህጋዊነት የወረረው ጋድም ዳኝነት።

* ድሆኖ ከጭቃ የተሠራ የእንጀራ መያዣ፤ ነገር ግን ጉዝጓዝ ጥሬ ሽንብራ ወይንም የቁንዶ በርበሬ ዛላ ቅጠል ወይንም  ባህርዛፍ ቅጠል ወይንም እንሰት /ኮባ/ ቅጠል ከሥር ያስፈልገዋል። በዘመነ ደረቁ ለምለም ስለመኖሩ ግን አላውቅም።                

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ከታሰሩት መካከል አብዛኛዎቹ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል * ማዕከላዊ አጠገብ የሚገኝ እስር ቤት ተወስደዋል

$
0
0

(ነገረ ኢትዮጵያ) በሰልፉ ሰልፉ ወቅት ታፍሰው ከታሰሩት መካከል አብዛኛዎቹ እጅና እግራቸውን እንደተሰበረ እማኞች ገልጸዋል፡፡ ታሳዎቹ መጀመሪያ ከነበሩበት ጨርቆስ አካባቢ የሚገኝ እስር ቤት ምሽት ሶስት ሰዓት ላይ ሶስተኛ ወደተባለው እስር ቤት ሲዘዋወሩ እያነከሱና በሌሎች ታሳሪዎች ደግፈዋቸው ታይተዋል፡፡ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት እጁን እንደተሰበረ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህም ባሻገር ብርሃኑ ተክለያሬድና ሌሎች በርካታ ታሳሪዎች በሌሎች ታሳሪዎች ተደግፈው ታይተዋል፡፡
semayawi
በሌላ ዜና በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት የታፈሱት አመራሮች ማዕከላዊ አጠገብ ወደሚገኘው እስር ቤት ተዛወሩ::

9ኙ ፓርቲዎች በጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ የታፈሱትና ጨርቆስ ፖፖላሬ እስር ቤት ታስረው የነበሩት የፓርቲ አመራሮች፣ አባላትና የሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎች ማዕካለዊ ጥግ ወደሚገኘውና በተለምዶ ሶስተኛ ተብሎ ወደሚጠራው እስር ቤት መዛወራቸው ታወቀ፡፡

ታሳሪዎቹ ከጨርቆስ ፖሊስ ጣቢያ ወደ ሶስተኛ የተዛወሩት ከምሽቱ አንድ ሰዓት በኋላ ሲሆን ሶስት ሰዓት ተኩል አካባቢ በሶስትትልልቅ አውቶቡሶች የታጨቁ ታሳሪዎች ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መድረሳቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ በሌላ አውቶቡስ የተጫኑ እስረኞች ወደ ሌላ እስር ቤት መዛወራቸው ታውቋል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ለታሳሪዎች እራትና ልብስ ሊያድሱ ወደ እስር ቤት ያቀኑት ቤተሰቦችና የትግል አጋሮች ምግብ እንዳያስገቡ መከልከላቸውን ገልጸዋል፡፡ በሌላ ካሳንቺስ አካባቢ የሚገኘውና ስድስኛ ተብሎ በሚጠራው እስር ቤት አካባቢ ሌሎች ታሳሪዎች እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ ጨርቆስ እስር ቤት ታስረው የነበሩት ሁሉም አመራሮች፣ አባላትና የሰልፉ ተሳታፊዎች ወደ ሶስተኛ ወይንም ሌላ እስር ቤት ይዛወሩ አይዛወሩ እርግጠኛ መሆን አልተቻለም፡፡

የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ አባላትና ተሳታፊዎች ከታፈሱበት ጊዜ ጀምሮ ሶስት ያህል እስር ቤቶች እንደተዛወሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live