Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

እስረኞችን ለመጠየቅ ቃሊቲ የሄዱ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ተለቀቁ

$
0
0

በአንድነት ፓርቲ በቃሊቲ እና ቂሊንጦ የሚገኙ የህሊና እስረኞችን ለመየጠቅ ወደስፍራው ያመሩ ወደ 30 የሚገመቱ ሰዎች ቀትር ላይ በቃሊቲ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ መለቀቃቸው ታወቀ፡፡
የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አስራት አብርሃ ከ30 ደቂቃዎች በፊት በስልክ እንደነገሩኝ ከሆነ ‹‹እነእስክንድርንና አንዷለምን መጠየቅ አትችሉም፡፡ ተባልን ከዚያም ‹‹ለምን?›› ብለን ስንጠይቅ በዋናው በር በኩል ኃላፊውን አነጋግሩ የሚል መልስ ተሠጠን፡፡ እኛም ይህንን አምነን ሄድን፡፡ ስንደርስ በቁጥጥር ሥር ውላችኋል ብለውን ወደ 30 የምንገመት ሰዎችን መታወቂያችንን ከመዘገቡ በኋላ በአንድ ክፍል ውስጥ ለጊዜው እንገኛለን›› ብለውኝ ነበር፡፡ አሁን ባገኘሁት መረጃ መሰረት ደግሞ በኮንቴይነር ውስጥ ታግተው የነበሩት እስረኛ ጠያቂዎች ከበድ ያለ ፍተሻ ተደርጎላቸው ከቃሊቲ ግቢ እንዲወጡ ተደርጓል

a3 a1 a2

↧

↧

የፓርቲዎች ትብብር ለአዳሩ ሰልፍ ቦታው መስቀል አደባባይ እንዲሆን ወስኗል

$
0
0

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለአዳሩ ሰልፍ የእውቅና ደብዳቤ አስገባ
የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ከህዳር 27/2007 ዓ.ም እስከ ህዳር 28/2007 ዓ.ም ለሚደረገው የአዳር ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ ህዳር 18/2007 ዓ.ም ለአዲስ አበባ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል የእውቅና ደብዳቤ አስገባ፡፡
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ለሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል የገባው ደብዳቤ በሰማያዊ፣ መኢዴፓ እና ኢብአፓ ተፈርሞ የገባ ሲሆን የእውቅና ደብዳቤውንም ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲና የትብብሩ ሊቀመንበር፣ የከንባታ ህዝቦች ሊቀመንበርና የትብብብሩ ም/ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርጌሎ፣ አቶ ግርማ በቀለ ከኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅትና የትብብሩ ፀኃፊ እና የመኢዴፓ ሊቀመንበርና የትብብሩ ገንዘብ ያዥ አቶ ኑሪ ሙደሲር አስገብተዋል፡፡

የትብብሩ አመራሮች ወደ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍሉ በሄዱበት ወቅት የአቶ ማርቆስ ተወካይ ለሆኑት አቶ ፈለቀ አበበ ደብዳቤውን ለመስጠት ጥረት ቢያደርጉም ተወካዩ ‹‹የከንቲባ ጉዳዮች ጽ/ቤ ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው የለም፡፡ እሱ ካልመራበት መቀበል አንችልም›› በሚል ደብዳቤውን አልቀበልም እንዳሏቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ አመራሮቹ ወደ አቶ አሰግድ ቢሮ ቢያቀኑም እንዳላገኙዋቸው ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ሆኖም የትብብሩ አመራሮች ደብዳቤ መስጠት እንጂ ደብዳቤ ማስመራት የሰራተኞቹ እንጂ የእነሱ ስራ እንዳልሆነ በመግለጽ ደብዳቤውን ዛሬ ህዳር 18/2007 ዓ.ም ታመዋል የተባሉት የአቶ ማርቆስ ተወካይ የሆኑት አቶ ፈለቀ ቢሮ በአራት ምስክሮች ፊት አስቀምጠው መምጣታቸውን አስረድተዋል፡፡ አመራሮቹ የእውቅና ደብዳቤውን አቶ ፈለቀ ቢሮ አስቀምጠው ከመውጣታቸውም ባሻገር በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በፈጣን መልዕክት (ኢ ኤም ኤስ) በሪኮመንዴ ቁጥር eg157416502et መላካቸውን ገልጸዋል፡፡

የአዳር ሰላማዊ ሰልፉ ህዳር 27 ከጠዋቱ 3 ሰዓት ተጀምሮ ህዳር 28 ከቀኑ 6 ሰዓት ላይ እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቅ ሲሆን ቦታውም መስቀል አደባባይ ላይ እንደሚሆን መወሰኑ ታውቋል፡፡

የትብብሩ አመራሮች የእውቅና ደብዳቤውን ለማስገባት በሄዱበት ወቅት በቦታው የትብብሩ አመራሮች የሚያውቋቸው ደህንነቶች ባለ ጉዳይ በመምሰል ይመላለሱ እንደነበርና ፖሊሶችም ይከታተሉ እንደነበር ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

unnamed

↧

በዛሬ ቅዳሜ የሚሊዮኖች ድምፅ የህሊና እስረኞች መርሀ ግብር የዞን 9 ዘጠኝ ጦማሪያንን ታስበው ይውላሉ

$
0
0

10486455_735445756540361_3353896174709564280_n

በዛሬ ቅዳሜ የሚሊዮኖች ድምፅ የህሊና እስረኞች መርሀ ግብር የዞን 9 ዘጠኝ ጦማሪያንን ታስበው ይውላሉ፤ እንደሚታወቀው በቃሊቲ ያሉት እስር ቤቶች በተለያዩ ዞኖች ተከፋፈሉ ሲሆን፤ ከዞን አንድ እስከ ዞን ስምንት ይደርሳሉ፤ እኛ በታሰረችው ሀገር በሰፊው እስር ቤት የምንገኝ ደግሞ የዞን ዘጠኝ ታሳሪዎች ነው የምንባለው፤ ስለዚህ ሁላችንም ያለነው ዞን ዘጠኝ ውስጥ ነው፤ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ይህ እውነት ስለገለጡ ነው የታሰሩት።
የሚሊዮኖች ድምፅ የህሊና እስረኞች መርሀ ግብር ከተጀመረ ጀምሮ ብዙ አስደናቂ ነገሮች እየተስተዋሉ ነው ያሉት፤ በትናንትናው ዕለት የአንድነት አባላት ብቻ ተለይተው እነእስክንድር ነጋንና እነ አንዷለም አራጌን በቃሊቲ እንዳይጠይቁ ተከልክሏል፤ መከልከል ብቻ አይደለም ታግተው ውሏል፤ አብዛኞቹ ከሰዓት ላይ ሲለቀቁ፤ አራቱ ደግሞ ማታ ላይ ተለቋል፤ ትግስት ካሳዬ ምትባል የአንድነት የወረዳ አመራር አባል ደግሞ ስትፈታ እዚያው አሳድሯታል።
10408681_735445646540372_7964344976056987440_nታላቁ የህሊና እስረኛ እስክንድር ነጋም ‹‹በርቱ! እንቅስቃሴያችሁ ህጋዊና ሰላማዊ ይሁን እንጂ ትግላችሁን ቀጥሉ!›› የሚል መልዕክት አስተላልፏል። በተጨማሪም አሳሪዎቹ የማናገር ነፃነቱን እዚያው እስር ቤትም ውስጥ ሊገድቡት በመኮሩበት ሰዓት፤
‹‹መብቴን አሳልፌ አልሰጥም፤ የትም ብሆን ስለመብቴና ሀገሬ ያገባኛል፡፡ እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል!›› በማለት አሁንም ለመብቱ ያለው ቁርጥ አቋም አሳይቷል። እስክንድር ቃሊቲ ውስጥ ሆኖ እንዲህ ካለ፤ እኛ በሰፊው እስር ቤት ያለነው ታሳሪዎች ምን እንጠብቃለን! እምቢ ለመብቴ እምቢ ለነፃነቴ እምቢ ለሀገሬ ማለት አለብኝ!
ሁላችንም የዞን ዘጠኝ ታሳሪዎች ነን!

Millions of voices for freedom – UDJ
↧

Health: ሴቶች ከወንዶች ማግኘት የሚፈልጓቸው 6 ነገሮች (ቢቻል ወንዶች ብቻ የሚያነቡት)

$
0
0

ከሊሊ ሞገስ

ሴቶች በየዕለቱ በህይወታቸው ውስጥ ከወንዶች ጋር ያላቸው ግንኙነት በተለያየ መልኩ ይገለፃል፡፡ ከዚህም አልፎ ከወንዶች ጋር ያላቸው ግንኙነት መልካም እንዲሆን የእነሱንም ፍላጎት የሚመችና የሚያረካቸው እንዲሆንላቸው ይፈልጋሉ፡፡ እስከ ትዳር የሚዘልቁም ሆነ ከትዳር በፊት ከትዳርም ውጪ ቢሆን የራሳቸውን ሰብዕና ጥሩ በሆነ መልኩ እየገነቡ የሚያሳዩዋቸው ባህሪያትንና ፍላጎቶቻቸውን ወንዶች እንዲረዱላቸው ይፈልጋሉ፡፡ በተለይም ሴቶች የውስጣቸውን ፍላጎት የሚረዳላቸው ብቻ ሳይሆን ተቀራርቦ አብሯቸው ካለና ፍላጎታቸውን ከተረዳላቸው ወንድ ጋር ረዥም ጊዜ መቆየትንና ደስ የሚል ህይወትን መምራት ይፈልጋሉ፡፡
women needs
ከዚህም በላይ የእነሱን ፍላጎት በጠበቀ መልኩ የሚንከባከባቸውንና የሚጠነቀቅላቸውን ወንድ አጥብቀው ይፈልጋሉ፡፡ ደስ ብሏቸው ከጥሩ ወንድ ጋር መልካም ህይወት ከጀመሩ በኋላ ፈፅሞ መራቅን አይመርጡም፡፡ አብሯቸው ጥሩ ግንኙነት ጀምሮ ወንዱ ሲርቃቸው ውስጣቸው በጣም ይጎዳል፡፡ ጥሩ ነው ብለው የሚያስቡትን መልካም ግንኙነት እየጠሉትም ከወንዶች ጋር እንደገና ጥሩ ግንኙነት ለመመስረት ይቸገራሉ ጥርጣሬ ውስጥም እንዲገቡ ያደርጋቸዋል፡፡

የጥናቱ አካል ከሆኑት መካከል ታዋቂዋ የጎልፍ ተጨዋች ሀና ራውሰን ስትናገር ‹‹በጣም የሚስብና ቆንጆ ነው ብዬ ካሰብኩት ወንድ ጋር ጥሩ የፍቅር ግንኙነት ጀምሬ ነበር፡፡ የሚያሳዝነው ከእኔ ጋር እየቆየ ሲመጣ እኔን የሚንከባከበኝ በመጥፎ ሁኔታ እየሆነ በመምጣቱ ልንለያይ ችለናል›› ብላለች፡፡ ንግግሯን ስትቀጥልም ‹‹በመለያየታችን ውስጤ ቢጎዳም ለሚቀጥለው ህይወቴ ብዙ ነገር እንድማርበትና ፍላጎቴን የሚጠብቅልኝን የተሻለ ወንድ ለማግኘት ይረዳኛል›› ስትል ነበር አስተያየቷን የገለፀችው፡፡

ራውሰን ቀጥላ ስትናገር ‹‹ወንዶች በጣም እንደማምርና ውብ እንደሆንኩኝ ይነግሩኛል፡፡ ለምን የምጫወተው የጎልፍ ጨዋታዬን እያዩም አያበረታቱኝም ትላለች፡፡ ውበቴን ቢያደንቁ የበለጠ ለውበቴ እንድጨነቅና እንዳምር ያደርገኛል እንጂ የጎልፍ ጨዋታ ውጤቴ ላይ የተሻለ ለውጥ እንዳመጣ አያደርገኝም፡፡ እኔ ሁሉን ፍላጎቴን እያደነቀና እያበረታታ ውስጤን የሚጠብቅልንን ወንድ ነው የምፈልገው፡፡ እነዚህን ፍላጎቶቼን አውቆ የበለጠ የሚጠብቅልን ሳገኝ ውጫዊው ሆነ ውስጣዊ ውበቴ እንዲጎላና የአካላዊም ሆነ የጭንቅላት ዝግጁነቴ ሙሉ ሆኖ ኮንፊደንስ ወይም በራስ መተማመን እንዲኖረኝ የማድረግ ኃይል ይኖረዋል›› ብላለች፡፡ አንፃራዊ በሆነ መልኩ ስለሌሎቹ ስትጠቅስም፡፡

በዚህ ጊዜና ሁኔታ ውስጥ ሁላችንም ሴቶች የበለጠ የምንስብ ውብ መሆንም እንችላለን፡፡ ወንዶች ይህን ከተረዱልንም የውስጣችንም ስሜትና ፍላጎት በቀላሉ ፈንድቶ እንዲወጣና እነሱንም የበለጠ በሚፈልጉት መልኩ ማርካት እንችላለን ትላለች የጎልፍ ተጨዋቿና ሞዴሊስቷ ራውሰን፡፡ ከዚህ በመነሳት የራሷን ልምድ በማካፈሏ በብዙ ሴቶች ላይ ያለውን ነገር ለማንፀባረቅ ችላለች፡፡ ራውሰን ስታክል ‹‹ወንዶች ልክ የምጫወትበትን የጎልፍ መምቻና እንቅስቃሴውን ይመስሉኛል፡፡ የጎልፍ መምቺያ ሁልጊዜ በሴቶችና በወንዶች መካክል መነሻ የሚሆነውን ፍላጎት የሚወክል ሲሆን ከመታውኝና ጥሩ ነጥብ ማስቆጠር የምችልበትን እንቅስቃሴ ሳደርግ ወንዶች የእኔን ፍላጎት ተረድተው አብረን እየተጓዙ ደስ የሚል ህይወት ውስጥ የምገባበት ሁኔታን ወክዬ አየዋለሁ›› ስትል ገልፃለች፡፡ በአጠቃላይ የሴቶችን ፍላጎት በመረዳትና ይህፍላጎታቸው የበለጠ ፈንድቶ እንዲወጣ የማድረግ ስራ የወንዶች ይሆናል እንደ ጥናቱ ገለፃ፡፡ ጥናቱ ወደ መጨረሻ የመደምደሚያ ሃሳብ ላይ ሲመጣም የሴቶችን ፍላጎት በመረዳት ወንዶች እንዴት ለበለጠ ጥሩ ግንኙነት እነሱን ማነሳሳት እንደሚችሉና የራሳቸው ሊያደርጓቸው እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡
እነዚህ የሴቶች ፍላጎት የበለጠ እንዲፈነዳና የራሳቸው እንዲሆኑ ከወንዶች የሚጠበቁና ሴቶቹን ወደ ራሳቸው ለማምጣትና ለመምራት የሚያስችሉ ጥለቅ የሆኑ ተግባሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. ፍላጎቷን እስክታገኘው ደጋግመህ ጠይቅ

ብዙውን ጊዜ ሴቶችንም ሆነ ወንዶችን ከአንድ ጊዜ በላይ ወደሆነ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ እንዲገቡ የሚያደርጋቸው ቶሎ የውስጣቸውን ፍላጎት ለማግኘት ስለሚቸገሩ ነው፡፡ በተለይም የሴቶች የውስጥ ፍላጎት ፈንድቶ እንዲወጣ ለማድረግ አስቸጋሪ ስሆነ ይህንን ለማድረግ ወንዶች በተለያየ አቅጣጫ ሴቶችን ደጋግመው መጠየቅ ይገባቸዋል፡፡ በጥያቄዎችህ ውስጥ መላመድህን እሷ እየወደደችው ስትመጣ ፍላጎቷን አውጥታ ትገልፅልሃለች፡፡ ሴቶች በብዙ ነገር ግንኙነት ውስጥ ስለሚፈሩና ስለሚጠነቀቁ ይህንን ተረዳው፡፡ ነካክቶ መተው ለአንተም ለእሷም ጥሩ አይደለም፡፡ ስለዚህም ጥንቃቄ ባለው መልኩ ሳታሰለቻት ደጋግመህ ለመጠየቅ ሞክር፡፡

2. ሴቶችን ወደተሻለ ደረጃ ለማምጣት ሞክር

ብዙ ሴቶች መልካምና ቀና የሚያስብላቸውን ወንድ ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን እጅግ ሲበዛ ጀንትል ሆኖ የሚረጋጋ ወንድ አይመቻቸውም፡፡ ከዚህ ይልቅ ሴቶች የውስጣቸውን እየተረዳቸው በጣም የሚያነቃቃቸውን እንዲሁም የሚፈልጉትን ቶሎ ተረድቶ እርካታን የሚሰጣቸውን ወንድ ይፈልጋሉ፡፡ ለዚህም ወንዱ የተሻለ ደረጃ ላይ ሆኖ እነሱን የበለጠ የሚቆሰቁሳቸውና ትልቅ የንቃት ኃይል ወደ ውስጣቸው የሚጨምርላቸው እንዲሆን ይፈልጋል፡፡ ለዚህም የተሻለ ሆኖ ተገኘና የእነሱንም ፍላጎት አፈንድተህ ለማውጣትና የተሻለ ቦታ ላይ ለማምጣት ሞክር፡፡

3. ግንኙነትህን አጠንክረው

ወደ ፍቅር የሚሄደው ግንኙነትህ ያማረ እንዲሆን አስቀድመህ የእሷን ፍላጎት አፈንድተህ ለማውጣት ደጋግመህ መገናኘትን እንደ ጥሩ ዘዴ ተጠቀምበት፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ እሷ ለአንተ በጣም እንደምታስፈልግህ እየነገርካት እንደሆነ እሷም ፍላጎቷን እንድታወጣውና እየገፋፋሃትና እያሳወቃት እንደሆነ ትረዳለች፡፡

4. ከሴቶች ጋር ማንኛውም ነገር ለማድረግ ባቀድከው መንገድ ተጓዝ፡፡

ለሴቶች ልታደርግላቸው አንድ ነገር ስታስብ ፕሮግራምህን አትሰርዝባቸው፡፡ ሴቶች በተለይም ወደ ጥሩ ግንኙነት እየመጡ ከሄዱ በኋላ የቀጠሮ ሰዓትም ሆነ ሌሎች ነገሮችን ካሳወቃቸው በኋላ የምትሰርዝ ከሆነ ፍፁም ምቾት አይሰጣቸውም፡፡ ሊበሳጩም ይችላሉ፡፡ አንተም ፍላጎቷን ለማግኘት የነበረክ ሂደት ላይ ውሃ እንደመከለስ ስለሚቆጠር ጥንቃቄ አድርግ፡፡ ፍላጎቷን እየመራህ ለመሄድ ፕሮግራሞችህ ወጥና የማይለወጡ ይሁኑ፡፡

5. በእሷ ላይ ጥሩ አቋም ወይም አስተያየት ይኑርህ

አንተ እንደ ወንድነትህ ሌላ እሷ የምትጠረጥረውን ነገር ባታደርገውም እንኳን ንገራት፡፡ ታማኝ መሆንህ ለእሷ ፍላጎት ጎልቶ መታየት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርግልሃል፡፡ ነገር ግን ጥሩነትህን ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ እየገለፅክ በእሷ ላይ ጥሩ የሆነ አቋም እንዳለህ ንገራት፡፡

6. ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ አስፈላጊ ንክኪዎችን ተጠቀም

ልክ እንደምታወሩትና እንደምትተያዩት ሁሉ ጥሩ የሆኑ የእጅ መነካካትና መጨባበጥ ብሎም በእጅህ ትከሻዋን እቅፍ እያደረክ ጥሩ ጊዜ ማሳለፍን እንደ ትልቅ የፍላጎቷ ማውጫ መንገድ ተጠቀምበት፡፡ ከዚህም በላይ ጥንቃቄ የተሞላባቸው አስፈላጊ ንክኪዎች ሴቶችን በፍቅር የማሞቅ ከፍተኛ ኃይል አለው፡፡
በአጠቃላይ እነዚህን መሰረታዊ የጥናቱ የጨመረሻ ሃሳቦችን በመጠቀም ወንዶች የሴቶችን ፍላጎት በቀላሉ በመረዳትና ፈንድቶ እንዲወጣ በማድረግ ወደራሳቸው በማምጣት የሚፈልጓትንም በቀላሉ የራሳቸው በማድረግ ጥሩ ግንኙነት እንዲመሰረቱ ያደርጋቸዋል፡፡ አንተም ወንዱ ፍላጎቷን ጠብቅ ከዛም የበለጠ ራሷ አፈንድታው ትነግርሃለች፡፡ ያኔም የአንተ ትሆናለች፡፡ አንተም የእሷ ማለት ነው፡፡

↧

(የሳዑዲ ጉዳይ) የማለዳ ወግ …በችግር ፣ ስጋት ለዋለሉት የምስራቹ  !

$
0
0

* የእህት ሰሚራ እንግልት
* የጠፉት ኮንትራት ሰራተኞች ያለ እስር ወደ ሀገር እንዲገቡ የሚያስችለው መመሪያ

* የእህት ሰሚራ እንግልት
===============
Nebiyu Sirak  ትናንት ምሽት ከምስራቃዊው የሳውዲ ግዛት በአርአር ከተማ የኢንተርኔየት ስልክ መልዕክት ደረሰኝ …እህት ሰሚራ ነበረች ፣ ሰሚራ ( ስሙ የተቀየረ)   ከሁለት አመት ከመንፈቅ በፊት ሳውዲ በኮንትራት  ስራ የገባች እህት ናት  ፣ የፊስ ቡክ ጓደኛየ የሆነችው የኢንባሲ ጉዳይ ፈጻሚ መስያት እንደነበር አስታውሳለሁ። በመረጃ መረቡ ተገናኝተን ስንጫወት ግን የኢንባሲም ሆነ የቆንስል መስሪያ ቤቱ ሰራተኛ አለመሆኔን ገልጨላት ያም ሆኖ ከሴት ወንድ ይሻላልና እንመካከለራለን ብያት ጥሩ ጓደኛየ ከሆኑት አንዷ ብርቱ ጓደኛየ እህቴ ናት ።

እህት ሰሚራ ለተከታታይ አንድ አመት እየደወለች ያለባትን ችግር የምታጫውተኝ የምታማክረኝ እህትም ናት ። በእለታት በአንዱ ቀን ግን ሰሚራ እንደተለመደው ከአሰሪዋ ጋር ከፍ ያለ ጸብ ላይ እንደደረሱ በነገረችኝና እንድትረጋጋ ባማከርኳት ማግስት መልሳ ሳትደውልልኝ ቀረችና እንደተለያየን ይህው አመት ነጎደ … ሰሚራ ባላሰብኩት በዚህ አጋጣሚ ጠፋችብኝ ፣ የጸብ ድብደባውን ክብደት ታጫውተኝ ነበርና ለማንም ባልናገረውም የእሷ እጣ ፈንታ ውስጤን ሁሌም ያውከዋል ፣ አሳስቦኛል … የሰሚራ ህይወት በወንጀል አልፎ ሌላ መከራ እሰማለሁ ብየ እሰጋለሁና ” ሀበሻ ገደለ! ” የሚለውም ዜና ስሰማና ሳነበው ሁሌም ሰሚራ ትታየኛለች … ምስኪኗ ሰሚራ ለቤተሰቦችዋ መትረፍ ስላለባት ለመግደል ቀርቶ ለመደባደብ ፍላጎት እንደሌላት አጫውታኝ ነበርና “…ተበድላ ፣ ተገፍታ ማንም ሳይደርስላት የትም ወድቃ ይሆናል!”  የሚለው ከአዕምሮየ የማይጠፋው ስጋቴ ሆኖ ከርሟልና አሁን መኖሯን በማወቄ ደስ አለኝ …ተመስገን ያሰጋኝ ሁሉ ግን በሰሚራ ላይ አልሆነም  …

አመሻሹ ላይ ከሰሞነኛው በኮሚኒቲ የከሸፈ ስብሰባና ነዋሪው በምርጫው ላይ ባሳየው ሽሽት ዙሪያ ረብ የለሽ ውጥንቅጥ ሙግት ላይ እያለሁ ነበር የእህት ሰሚራ ጥሪ ያስናገድኩትና ሰላም መሆኗን የተረዳሁት ፣ የሆነውን ማመን አቃተኝ … መጫወት ያዝን  !

* የተገኘችው ሰሚራ …
============
ሰሚራ የነበረችበን ምስራቃዊ የሳውዲ ግዛት አርአርን ከአሰሪዎቿ ጠፍታ ለቃዋለች ፣ ዛሬም እንደወትሮዋ  እያለቀሰች ያለችበትን ሁኔታ በዝርዝር አጫወተችኝ ፣ አደዋወሏ እንደ ቀድሞው ምሬቷን ልታወራኝ ሳይሆን በመረጃ በኩል የምችለውን እንድረዳት ለመማጸን ነበር …

ሰሚራ ከስደቱ እንግልት ተላቃ ወደ ናፈቋት ቤተሰቦቿዋ ወደ ሀገር ቤት መግባት ፈልጋ አንድ ደላላ  ማነጋገሯንና ከፍተኛ ገንዘብ ጠይቋት ለመክፈል ፈቃደኛ ብትሆንም  ከገንዘብ አልፎ የአንሶ መጋፈፍ ጥያቄ ስላቀረበላት ያንን ለሟሟላት  ፈቃደኛ አለመሆኗን አጫወተችኝ ።  እናም ” እባክህ ወደ ሃገር ቤት የምገባበትን መንገድ ጠቁመኝ !” አለችኝ ከቀናት በፊት ”  ከአሰሪዎቻቸው የጠፉ ወደ ሀገራቸው መግባት ይችላሉ!” የሚለው መረጃ በእጀ ገብቷልና ለሰሚራ የምስራች ስለያዝኩ ደስ ብሎኛል ፣  ለተጨነቀችው ሰሚራ  መንገዱ በእርግጠኝነት እንዳለ ካጫወትኳት በኋላ  ከአሰሪዎቿ ስትጠፋ ወንጀል አለመፈጸሟን ለማረጋገጥ የመኖሪያ ፈቀዷን ቁጥር ተቀበልኳትና መልሸ በዚህው የፊስ ቡክ ኢንተርኔት ስልክ እንደምደውልላት ቃል ገብቸ ተለያየን   !

… እህት ሰሚራ አሰሪዎቿ “ጠፋችብን ” ብለው ሪፖርት ከማድረግ ባለፈ በወንጀል እንደማትፈለግ መረጃ አሰባሰብኩና መልሸ ደወልኩላት ፣ ያም ቢሆን ሰሚራ ከወንጀል ነጻ መሆኗ የሚረጋገጠው አሻራ ስትሰጥ መሆኑን አሳወቅኳት ፣ ሰሚራ ስልኩን ስታነሳ   ” ወይ ፈጣሪየ ነቢዩ ምን ልታሰማኝ ይሆን?  ” ስትለኝ ከወጣው አዲስ መመሪያ ጋር ማሟላት ያለባትንና የሆነውን አጫወትኳት ፣ የተጎዳችው እህት ሰሚራ ደስታዋን የገለጸችው በእንባ ተንሰቅስቃ እያቀሰች ነበርና  ውስጥ ስሜቷ ተረድቸዋለሁ …የእኔም ነፍስ የምትወደውን አገኝታለችና በሃሴት ደመቀች  :)

* ሰሚራ ከአሰሪዎቿ ለምን ጠፋች  ?
=====================
ከሰሚራ ጋር ስለተለያየንበት አጋጣሚና ከአሰሪዋ እንዴት እንደ ጠፋች ስታጫውተኝ  ያስታወስኩት ብዙ ሰሚራዎችን ነበር ። …በኮንትራት ስራ መጥተው  በበርሃው ከተሞችና ገጠሮች አበሳቸው በዝቶ ደራሽ አጥተው፣ ለከፋ የወስጥ ደዌ በሸወታ ፣ ለአዕምሮ መታወክ ፣ለወንጀልና ለተለያየ አደጋ መጋለጣቸውን አስራወሰኝናም ቆዘምኩ!  የሰሚራ አጠፋፍ ከማሳዘን ማስገረም አልፎ ለቀሪዎች ካስተማረን በሰሚራ አንደበት የተነገረኝን እነሆ … ” …አሰሪየ ልትገድለኝ ተደጋጋሚ ሙከራ አድርጋ አልተሳካላትም ፣ ሁሌም በሌለሁበትና በማላውቀው ነገር ትመታኛለች ፣ ትሰድበኛለች …በባሏ እየቀናች ታንገላታኛለች … ለመከላከል በማደርገው ግብግብ ናላየ ዙሮ ነፍስ ከማጠፋ ብየ ጠፍቸ ወጣሁ .. አምልጨ የተጠጋሁት ካልሆነ ቦታ ነበር … ይጨንቃል ፣ ግን ሁሉም አልፏል ! ” ነበር ያለችኝ ምክንታቷን ጨምቄ ሳቀርበው … ይህንን ዘርዝራ ስታጫውተኝ የእንባ ሳግ ይቀድማትም ነበር…

ሰሚራ ብልጥና ትጉህ ሴት በመሆኗ ለዛሬ ደርሳለች ፣ ዛሬ ደግሞ ለሷ ከቤተሰብ የምትገናኝበት ወደ ሃገሯ የምትገባበት ቀን የደረሰበት መልካም ቀን ነው  !  …ሰሚራን  የመሰሉ በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩት እህቶች በሃገራት መካከል የረባ የሁለትዮሽ ውል ባልተደረገበት ሁኔታ  በኮንትራት ስራ ሳውዲና ወደ ተለያዩ አረብ ሃገራት መጥተው መግቢያ መውጫው የጨነቃቸው እህቶች ብዙ ናቸው ፣ በጭንቀት በስሜት ተነሳስተው ራሳቸውን ከፎቅ የጣሉ ፣ ራሳቸውን አንቀው የገደሉ ፣ እስከ ድብደባና ነፍስ እስከ ማጥፋት ወንጀል ህይወታቸው መቀመቅ የወረደባቸውን ቤት ይቁጠረው …

እዚህ ላይ መከራው የከበደባቸውን ድምጽ ደጋግሜ ባቀርበውም በሁሉም የአረብ ቤት ችግር አለ ማለት አይቻልም ። ቀንቷቸው ከደጎች ቤት የገቡ ከራሳቸው አልፎ ወገኖቻቸውን የጠቀሙ በርካታ እህቶች አሉ።  አልፎ አልፎ እዚሁ ነዋሪ በሆኑ ጓደኞቻቸው ፣ ዘመድ አዝማድና ደላላ “ደመወዝሽ ትንሽ ነው! ” በሚል እየተታለሉ ከስራ ይጠፋሉ ፣ ይፈናቀላሉ። አልፎ አልፎን በተለያየ ምክንያት የተሻለ ኑሮ ፍለጋ “ጠግበውም” በሉት ” ተጨንቀው ” ከአሰሪዎቻቸው ይጠፋሉ ። ጠፍተው ከሰሩ በኋላ ወደ ሃገር ቤት ለመግባት ግን የእስከ ዛሬው መንገድ የወት አልነበረም  ፣ ዛሬ ግን ለጊዜውም ቢሆን ያ ሁሉ ተለውጧል ፣  “የጠፉ የኮንትራት ሰራረኞች ያለ እስርና እንግልት ወደ ሀገራቸው ይገባሉ!” ተብሎ ተፈቅዷል ፣ የእህት ሰሚራ እንግልት አክትሟል ፣ እንደ እህት ሰሚራ ሩቅ አስቦ ፣ ስሜትን ተቆጣጥሮ መከራ ሰቆቃውን ላለፈው ደግሞ እንዲህ ይነጋል ….

እዚህ ላይ ማሰሪያ ትሆን ዘንድ ለሰሚራ ደላላ የምለውን ልበል …በነጻ ወደ ሀገር የመግባት ህጉ ወጥቶ እያለ ” ጉዳይሽን ልጨርስልሽ ከ5000 የሳውዲ ሪያል ክፈይኝ ፣ አንሶላም እንጋፈፍ! ” ባዩ የሀገር ልጅ ያዘንኩብህ መሆኑን ልብ በል !  …ያም ሆኖ ስታየኝ እንድትሸማቀቅ አልሻም ፣ ከስህተት መታረም ብትችል ደጋግመህ ላደረስከው ጉዳትና ክብረ ነክ ስራህ ልጆች ካሉት አባት የማይጠበቅ ጥፋት ነውና በእኔ የቀረበልህ ይህ ማስታወሻ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ከሆነህ መልካም ነው ፣ ያለበለዚያ ተበዳዮች በስም ጠርተው የሚያቀርቡትን ስሞታ አሰማ ዘንድ እገደዳለሁ !  …ዛሬ ብዙ አልልም  !

እንደ እህት ሰሚራ የተንገላታችሁ በራሳችሁ ወንድም ደላላ የተጎሳቆለችሁና የተጎዳችሁ ፣ መንገዱ  እንዳይጠልፋችሁ ፣ መንገዱ እንዳያደናቅፋችሁ በሳውዲ መንግስት የወጣውን መመሪያ ከዚህ በታች በዝርዝር አቅርቤዋለሁና ተመልከቱት  !

*የወጣው አዲስ መሪያው ዝርዝር …
======================
በኮንትራት ስራ ወደ ሳውዲ አረቢያ መጥተው በተለያየ ምክንያት ከአሰሪዎቻቸው ጠፍተው በግል ይሰሩ የነበሩ በርካታ ኢትዮጵያውያንና የተለያዩ ሀገር ዜጎች ወደ ሀገር የሚገቡበት መንገድ የጠበበ በመሆኑ በርካታዎች ለችግር ተጋልጠው ነበር ።  ከሁለት ቀናት በፊት በሳውዲ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  በኩል ለተለያዩ ሀገሮች የቆንስልና የኢንባሲ መስሪያ ቤቶች በተላለፈ መመሪያ  ከኮንትራት የጠፉ የማናቸውም ዜጎች ያለምንም አይነት እስር ወደ ሀገራቸው ሊገቡ እንደሚችሉ ይፋ ሆኗል። መረጃውን ከዚህ ጋር ባያያዝኩት የአረብ ኒውስ ዘገባ ተብራርቷል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  የሽሜሲ ጊዜያዊ መጠለያ እስር ቤት ተወካይ የሆኑት መሃመድ አብዱልወሃብ ኑጋሊ በኩል የተሰራጨው ይህ መመሪያ የያዘው የጋዜጣው መረጃ ያለ እስር መግባት የተፈቀደላቸው የኮንትራት ሰራተኞች በወንጀል ነጻ የሆኑትንና ከአሰሪዎቻቸው ጋር ክስ ያለባቸውን እንደማይጨምር ያስረዳል።

መመሪያው ከዚሁ ጋር በማያያዝ ሰራተኞች ጉዟቸውን ለማሳካት ማሟላት ያለባቸውን ሶስት ቅድመ ሁኔታዎች አስቀምጧል። ቅድመ ሁኔታዎችም የሚከተሉት ናቸው

1ኛ/  በመንግስት በኩል ያለባቸው ውዝፍ ቅጣት መክፈል
2ኛ/   በኢንባሲና ቆንስሎች በኩል አስፈላጊውን የጉዞ ሰነድ(ሊሴ ፖሴ አለያም ፖስፖርት ) ማቅረብ
3ኛ/  የአውሮፕላን ቲኬት ማቅረብ ቅድመ ሁኔታዎች  እንደሆኑ መመሪያው ጠቁሟል ።

ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ የጠፉ የኮንትራት ሰራተኞች በኢንባሲና ቆንስል መ/ቤቶች በኩል ሰነዶች አሟልቶ ማቅረብ እንዳለባቸው መመሪያው ያሳስባል።  አስፈላጊ መስፈርቶች እንደተጠናቀቁም አሁንም በመንግስታቸው ተወካዮች አማካኝነት ጅዳ አካባቢ ላሉት መካ አጠገብ በሚገኘው የሺሜሲ ጊዜያዊ መጠለያ በመቅረብና የጣት አሸራ በመስጠት ጠቅልሎ መውጫ ቪዛ እንደሚሰጣቸው ታውቋል። ያም ሆኖ የመውጫ ቪዛው እንፈተመታላቸው  በ72 ሰዓታት ውስጥ ሳውዲን ለቀው ወደ ሀገር ቤት መግባት እንዳለባቸው በውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር የተላለፈው ይህው መመሪያ ያስረዳል።

በኮንትራት ስራ መጥተው የሚጠፉ ሰራተኞች ” አስፈላጊውን መስፈርት አሟልተው ወደ መጡበት ሃገር  ያለ እስርና እንግልት ይገባሉ “የሚለው ይህ መመሪያ በአይነቱ የመጀመሪያ ነው።  ከዚህ በፊት በተሰጡት የምህረት አዋጆች እንኳ የጠፉ ሰራተኞችን  አካትቶ አያውቅም። ነገር ግን ኢንባሲና ቆንስሎች የህመም ፣ በስራ ላይ ጉዳትና በደል የደረሰባቸውን የጠፉ የኮንትታት ሰራተኞችን አጥጋቢ ምክንያቶችን በመያዝ ከሳውዲ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የፖስፖርት ፖሊስ ከፍተኛ ሃላፊዎች በልዩ ሁኔታ እያስፈቀዱ ወደ ሃገር ይልኩ እንደነበር ይጠቀሳል።

ይህም በርካታ በችግር ይዋልሉ ለነበሩ ወገኖች መልካም የምስራች ነው !

ነቢዩ ሲራከ
ህዳር 20 ቀን 2007 ዓም

↧
↧

የነዳጅ ዋጋ በዓለም አቀፍ ደረጃ ቢቀንስም የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን የችርቻሮ ዋጋን አልቀነሰም

$
0
0

ለአመት ያህል በበርሜር ወደ 110 ዶላር ንሮ የቆየው የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ፤ ካለፈው ሐምሌ ወዲህ እየወረደ በያዝነው ሳምንት ከ75 ዶላር በታች የደረሰ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ላይ መንግስት እስካሁን ቅናሽ አላደረገም።

በአመት በአማካይ ከሰባት በመቶ በላይ እየጨመረ የመጣው የኢትዮጵያ የነዳጅ ፍጆታ፣ ባለፈው አመት 3.4 ቢሊዮን ዶላር (ከ65 ቢሊዮን ብር በላይ) ወጪ እንዳስከተለ ታውቋል። ሸቀጦች ወደ ተለያዩ አገራት በመላክ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ ባለፉት አራት አመታት እድገት ባለማሳየቱ አመታዊው ገቢ ከሶስት ቢሊዮን ዶላር ገደማ ብዙም ፈቅ ባለማለቱ፣ የነዳጅ ግዢን እንኳ ለመሸፈን የማይበቃ ሆኗል።
news
በአለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ ባለፈው አመት በነበረበት ቢቀጥል ኖሮ፣ በቀጣዩ አመት ኢትዮጵያ ሩብ ቢሊዮን ዶላር (5 ቢሊዮን ብር) ተጨማሪ ገንዘብ ለነዳጅ ግዢ ለማውጣት መገደዷ አይቀርም ነበር። ይሁን እንጂ፣ ያለማቋረጥ እየወረደ የመጣው የነዳጅ አለማቀፍ ዋጋ በስድስት ወራት ውስጥ ሲሶ ያህል ስለቀነሰ፣ ኢትዮጵያ ለነዳጅ ግዢ የምታውለው የውጭ ምንዛሬ ዘንድሮ እንደማያሻቅብ ተገምቷል።

እንዲያውም የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በበርሜል ከ80 ዶላር በታች ሆኖ ከቀጠለ፣ የአንድ ቢሊዮን ዶላር (የ20 ቢሊዮን ብር ወጪ ቅናሽ ያስገኛል፡፡) በርካታ ነዳጅ አምራች አገራትን የሚቆጣጠሩ መንግስታት በአባልነት የተካተቱበት ኦፔክ የተሰኘው ማህበር፣ ሰሞኑን በነዳጅ ዋጋ ዙሪያ የተወያየ ቢሆንም፣ ውይይታቸው በአለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ለውጥ እንደማያስከትል ትናንት ቢቢሲ ዘግቧል። እየወረደ የመጣው የነዳጅ ዋጋ፣ የበርካታዎቹን መንግስታት ገቢ እንደሸረሸረ የገለፀው ቢቢሲ፣ ከፍተኛ የበጀት ጉድለት ያጋጥማቸዋል ብሏል። “ዋጋ እንዲያንሰራራ የነዳጅ ምርት መቀነስ አለብን” የሚል ጥያቄ ከሁለት መንግስታት በኩል እንደቀረበ ዘገባው ጠቅሶ፣ ጥያቄው በአብዛኞቹ መንግስታት ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱን አመልክቷል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የነዳጅ ዋጋ መውረድ የጀመረው፣ በከፊል ከአለም ኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ጋር በተያያዘ ምክንያት ቢሆንም፣ ዋናው ምክንያት ግን የአሜሪካ ኩባንያዎች ከፍተኛ የነዳጅ ምርትን የሚያስገኝ አዲስ ዘዴ በመፍጠራቸውና ተጨማሪ ነዳጅ ማምረት በመጀመራቸው እንደሆነ ፎርብስ መፅሔት ዘግቧል።
ከአለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ ውጣ ውረድ ጋር፣ የኢትዮጵያ መንግስት በንግድ ሚኒስቴር በኩል በየወሩ የነዳጅ ዋጋ ተመን የሚያወጣ ሲሆን፣ ከጥቂት ጊዜያት በስተቀር አብዛኛውን ጊዜ የዋጋ ተመኑ በነበረበት እንዲቀጥል አልያም የአለም ገበያን ተከትሎ እንዲጨምር ሲወስን መቆየቱ ይታወሳል።
ባለፉት ስድስት ወራትም እንዲሁ፣ በአለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ በፍጥነት እየወረደ ቢመጣም፣ በኢትዮጵያ ግን የችርቻሮ ዋጋ በነበረበት ደረጃ እንዲቀጥል አልያም እንዲጨምር የተደረገ ሲሆን፣ በያዝነው ወር መጨረሻ የዋጋ ተመኑ ላይ ምን አይነት ለውጥ እንደሚደረግበት ገና አልታወቀም። በተለመደው የመንግስት አሰራር፣ የዋጋ ተመን ውሳኔው በይፋ እስከሚገለፅበት እለትና ሰዓት ድረስ በሚስጥር ተጠብቆ ነው የሚቆየው።

 

ምንጭ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣ

↧

የህዝብ ነጻነት

$
0
0

ከሃገሩ የወጣ ሃገሩ እስኪመለስ

ቢጭኑት አህያ ቢጋልቡት ፈረስ

ይባል ነበር ድሮ ምንድንነን በሃገርስ

ከእንስሳ አሳንሰው አይደል የሚያዩንስ?

ከሰው ሳይቆጠር በትውልድ በሃገሩ

እነሱ ወርቅ  ዘር እኛ አንሰን ከአፈሩ

መጨፍለቅ  አልቆመ እንዲያ መወገሩ

መታፈን መገረፍ ጨለማ ቤት እስሩ

እንደከብት ቆዳ መሰነታተሩ

ዜጋው በሃገሩ ሞት ሲሆን ቀመሩ

ላይቀናው ሲያማትር ለስደት መብረሩ።

ሃገር የማይናፍቅ ምንድነው ነገሩ?

መሬት ቆርሶ የሚሰጥ ለውጩ አድልቶ፥

ከወራሪ ጠላት ይብሳል አብዝቶ።

ይብቃ መከተሉ እስቲ እንየው ቀርቶ።

ነጩ ፋሺዚምን የጣለው ክንድ ሳይዝል

ዘመን አመጣሹን ሊመክተው ሲችል

ከከገዢዎች ወህኒ አምልጦ ኮብልሎ

በሃገሩ ከመሞት ስንቱ ባህር ዘሎ

በረሃ አቋርጦ አካሉን አጉድሎ

ያገግማል እንጂ አይሄድ ሀገር ብሎ

ይመለሳል እንጂ አይወስን ጠቅልሎ።

Abraham ZTa

juk

↧

ኩማ ደመቅሳ በዋሽንግተን ዲሲ ሆስፒታል ተኝተዋል

$
0
0

(ኢየሩሳሌም አርአያ)

አቶ ኩማ ደመቅሳ በዋሽንግተን ዲሲ ሆስፒታል ተኝተው እንደሚገኙ ታማኝ ምንጮ አስታወቁ።
kuma demekesa
ኩማ በጭንቅላት እጢ (ቲዩመር) በሽታ ምክንያት ለከፍተኛ ህክምና ዲሲ መምጣታቸውን የጠቆሙት ምንጮቹ የመዳን ተሳፋቸው 90 በመቶ የተመናመነ መሆኑን ከሃኪሞች እንደተገለፀላቸው አስታውቀዋል።

ከባለቤታቸው ጋር የመጡት ኩማ ሆስፒታል ከመግባታቸው በፊት ባለፈው ሳምንት ማርዮት ሆቴል አርፈው እንደነበረ ሲታወቅ ሁለት ኢትዮጵያውያንን በሆቴሉ መተላለፊያ ላይ ሲያገኙ ክፉኛ ደንግጠው እንደነበረ ማወቅ ተችሏል። አሜሪካ -ዲሲ መምጣታቸው እንዳይታወቅባቸው የሚጠነቀቁትና ፍርሃት የሚታይባቸው ኩማ የስጋታቸው ምንጭ እንደሌሎች ባለስልጣናት ተቃውሞ ይገጥመኛል በሚል እንደሆነ ሲታወቅ የማያውቁትን ስልክ እንደማያነሱ ማረጋገጥ ተችሏል።

በተለይ የመዳን ተስፋ እንደሌላቸው ከተነገራቸው በኋላ ከኢትዮጵያ የሚደወልላቸውን ስልክ እንደማያነሱ ታውቋል። ኩማ ደመቅሳ ከ1993ዓ.ም በፊት ሙስና ውስጥ እንዳልገቡና ነገር ግን የአዲስ አበባ ከንቲባ ከሆኑ በኋላ በከፍተኛ ሙስና ከተዘፈቁት ባለስልጣናት ተርታ እንደተመደቡ ይታወቃል።

↧

የብሄር ነጻነት እስከ መጨፈር —ክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ) —

$
0
0

ማስታወሻ፡ ይህች ጽሁፍ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከተከሰሰባቸው ሁለት መጣጥፎች አንደኛዋ ናት። በመጭው ወር በአሶሳ የሚደረገውን የብሄር ቀን ድራማ እሳቤ በማድረግ – በርካታ አንባብያን በጠየቁት መሰረት እነሆ በድጋሚ ለንባብ አቅርበናል።
— ክንፉ አሰፋ –
Bahir dar
“እኛ ጭቁን ብሄረሰቦች ከዚህ ቀደም በየሰው ቤት ተቀጥረን የምንሰራ፣ አሽከሮች እየተባልን ነበር የኖርነው። አሁን ግን ይኸውና ህገ-መንግስታችን መብታችንን ሰጥቶናል… ኑሯችንም ተሻሽሎ ዛሬ ዘመናዊ ኑሮ እየኖርን ነው።”
እያለ የሚናገርን አንድ ጎልማሳ የቴሌቪዥኑ መስኮት ያሳያል። የደቡብ ቅላጼና ዘዬ ባለው አማርኛ ከደቡብ የመጣ ጎልማሳ ነው በቴሌቪዥን ቀርቦ መግለጫ እየሰጠ ያለው። ከአነጋገሩ በቀን ሶስቴ የሚበላ፣ የባቡር ሃዲድ እና የኤሌክትሪክ መስመር ገብቶለት፣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚም… ይመስላል።
  የዚህ ምስኪን ሰው ገጽታ እና አለባበሱ የሚነግረን ግን ሌላ ነው። በኢህአዴግ ዘመን መብቱ እንደተከበረና ኑሮው እንደተሻሻለ የሚነግረን ይህ ሰው፣ መሰረታዊ የሆነውን የሰው ልጆችን የኑሮ ፍላጎት እንኳን አላሟላም። ለእግሩ ጫማ የለውም።  በባዶ እግሩ ነው የቆመው። ሃፍረተ ስጋውን ከሸፈነለት ብጣቂ ጨርቅ በስተቀር ሰውነቱም እርቃኑን ነበር።
ለመገናኛ ብዙሃን ፍጆታ አነጋገሩ እንዲያሳምር ተነግሮት ሊሆን ይችላል – ንግግሩ ልክ መካከለኛ ገቢ ካላቸው የምዕራብ አውሮፓ ሃገሮች ተርታ የተሰለፈ ይመስላል። ይህ ደግሞ ገና የ’ትራንስፎርሜሽኑ’ ተስፋ እንጂ፤ ለውጡ በብሄር ብሄረሰቦቹ ላይ እንደማይታይ የቪድዮ ምስሎቹ ፍንትው አድርገው ነው የሚያሳዩት። ኢትዮጵያ በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገሮች ተርታ ላይ እንደምትደርስ ኢህአዴግ ቃል ገብቷል። በአሁኑ ግዜ ሰባት በመቶ ብቻ የሆነው የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ብሄር ብሄረሰብ እና ሕዝብ በአምስት አመቱ እቅድ 80 በመቶ ይደርሳል ብለውናል። በእስር ያለው ጠንቋይ ታምራት ገለቴ ነግሯቸው ካልሆነ በስተቀር መቼም ይህንን ተረት ተረት በማህበራዊውም ሆነ በተፈጥሮ ሳይንስ ሊያረጋግጡልን እንደማይችሉ እርግጥ ነው። ከፈረሱ ጋሪው… እንዲሉ ከተግባሩ ወሬው፣ ከ’ህዳሴው ግድብ’ ስራም ሽልማቱ ቀድሞ መያዣ – መጨበጫው የጠፋ ነው የሚመስለው።
ከገጠር እየታፈሱ ለሚመጡት ለነዚህ ምስኪን ወገኖች የ ‘ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች’ መብት ማለት በአመት አንዴ በጎዳና ላይ እየወጡ መጨፈር እና ያለፈውን ስርዓት ማውገዝ ብቻ ነው የሚመስለው። ጭፈራውና ውግዘቱ እንደ ጥምቀት በዓል ስለተለመደ የግድ መደረግ እንዳለበት ያመኑበትም ይመስላል።

የደርግ ስርዓት ሰዎች በባህላቸውና በቋንቋቸው እንዳይዘፍኑ ከልክሎ እንደነበር የሚጠቁም መረጃ የለም። ደርግ አስራ ሰባት አመት ገዛ፣ 20 አመት ሙሉ በብሄር ጭቆናው ሲወገዝ ኖረ። በባንዲራ ቀን ውግዘት፣ በከተሞች ቀን ውግዘት፣ በብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ውግዘት፣ በግንቦት ሃያ ቀን ውግዘት…. በየሽልማቱ ስነ ስርዓት እና በየበዓላቱ ቀን ውግዘት….። የደርግ ሃጢያት መብዛት የነሱን ግፍ ይሸፍን ይመስል የኢህአዴግ በዓላት እና ውግዘቱ ከለት-ተለት ሲጨምር ብቻ ነው የምናየው – እንደ 11 በመቶው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያ እድገት።

የዚህ ሳምንት ወሬ ደግሞ በመቀሌ ስለተካሄደው ስድስተኛው የ ‘ብሄር – ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን’ ነው። የመከር ወቅት ስራቸውን እንዲያቆሙት ተደርገው፣ ከየክልሉ እየተጫኑ ለጭፈራ መቀሌ የገቡ አርሶአደሮች ቁጥር ቀላል አይደለም። በዲያጎን እየተፈለጉ የተለቀሙ ልማታዊ አርቲስቶች እና የመድረክ አስተዋዋቂዎችም በስፍራው ተገኝተዋል።
የእውቁ ኪነጥበብ ሰው – የኪሮስ አለማየሁ ልጅ ዛፉ ኪሮስ ‘አንበሳ ገዳይ’ በሚለው የትግርኛ ዘፈንዋ መድረኩን ይዛዋለች። በርከት ያለ ሰው መድረኩን ከቦት ይጨፍራል። አዳራሹም በ ‘ብሄር – ብሄረሰቦች እና ህዝቦች’ ተሞልቷል። መቀሌ፣ ኅዳር 27 ቀን 2004 ዓ.ም.።
የእለቱ የመድረክ አስተዋዋቂ ‘አንበሳ ገዳይ’ የሚለው የዛፉ ኪሮስ ዘፈን የተስማማው አይመስልም፤ አልተዋጠለትም። አልያም ዘፈኑን እዚያው መድረክ ላይ እንዲያስተባብል ተነግሮታል። ተራውን ጠብቆ ማይክራፎኑን ያዘ።  
“ህገ መንግስታችን ለብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ብቻ ሳይሆን ለዱር እንስሶችም…”
ብሎ እየተናገረ እያለ እንደተለመደው መብራት ተቋረጠ።
  በዚህ ‘ታላቅ’ ቀን መብራት መቆራረጡ ቢያበሳጭም፣ በእንግድነት ወደ መቀሌ የተጓዙት ‘ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች’ ኤሌክትሪክ ምን እንደሆነ ስለማያውቁ አልደነቃቸውም – የሚያውቁት ደግሞ የለመዱት ስለሆነ – ለእነሱ እንግዳ ነገር አይደለም።  ከቆይታ በኋላ ግን መብራት መጣ። ልማታዊው አርቲስትም ንግግሩን ቀጠለ።
“…ህገ መንግስታችን ለብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ብቻ ሳይሆን የዱር አራዊቶችንም መብት ስላስከበረ አንበሶች አሁን አይገደሉም።…”
በማለት የዘፈኑን መልእክት ለማስተባበል እና ጭብጡን ለብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ለማስረዳት ሞከረ። እዚህ ላይ የመድረክ አስተዋዋቂው እና ዘፋኝዋ እንዳልተግባቡ መገመት ይቻላል። ዛፉ ኪሮስ ዘፈንዋን በዚህ መድረክ ታቅርበው እንጂ መልእክቱ ላሁኑ ትውልድ ሳይሆን ምናልባት ‘ተራራ ላንቀጠቀጠው’ ለዚያኛው ሊሆን ይችላል ብሎ ማሰብ የተሳነው ይመስላል። ያ ቡድን የትኛውን ተራራ እንዳንቀጠቀጠ ባይገለጽልንም አሁን ያጠለለበት የለውጥ ደመና ግን በተራው እያንቀጠቀጠው ለመሆኑ ከሚያደርጋቸው ግራ ገብ ድርጊቶቹ መረዳት ይቻላል።
የሆነው ሆኖ በአሉ ለመቀሌ ህዝብ ልዩ ስሜት እንደሰጠው ይታያል። ይህ ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ተለይቶ፣ በእነ መለስ እና በረከት ካድሬዎች ታጥሮና ታፍኖ የሚገኝ ህዝብ ስለመሆኑ በርካታ መረጃዎች ይመሰክራሉ። ከስፍራው የሚደርሱን መረጃዎች እንደሚተቁሙት ከመንግስት ራዲዮ እና ቴሌቪዥን ውጭ ያሉ የመገናኛ ብዙሃንን በዚያ ክልል መጠቀም ራሱ እስከ ስድስት ወር የሚያሳስር ወንጀል ነው። ለ20 አመታት የታፈነ ህዝብ ከሌላው ወገኑ ጋር ተቀላቅሎ ፣ አብሮ ሲጨፍር የሚፈጥርበትን ስሜት መገመት አያደግትም። የደርግ ስርዓት የአሜሪካ እና የጀርመን ድምጽ ራዲዮን የትግራይ ህዝብ እንዳይሰማ አልከለከለም ነበር። ወያኔ ግን የትግራይ ህዝብን የመናገር ብቻ ሳይሆን የመስማት መብቱንም ጭምር ነው የነፈገው።
የሳተላይት ዲሽ ቴሌቪዥን ክልክል በሆነበት በዚያ ክልል የኢቲቪ አኬልዳማ ድራማ ይደገምልን ብሎ የትግራይ ህዝብ ቢጠይቅ ሊደንቀን አይገባም። ጆሮ ካሰለቸው የ’ህዳሴው ግድብ’ ወሬ እና እጅ እጅ ካሉት ከነ ሰራዊት ፍቅሬ አኬልዳማ ትንሽም ቢሆን ዘና ሳያደርጋቸው አልቀረም። የቴሌቪዥኑ መግቢያ ላይ ታዲያ ‘እንደምን አመሻችሁ ዲሽ የሌላችሁ” ብሎ ነው የሚጀምረው እየተባለም ይቀለዳል። ይህ ህዝብ በስሙ ሲነገድበት እና ከሌላው ወገኑ ጋር እንዲቃቃር ሲደረግ የትግራይ ኢሊቶች ዝም ማለታቸው እጅግ የሚያሳዝን ጉዳይ ነው።
ስለ ዱር አራዊት መብት እና ስለ አንበሳ መግደል ሲነሳ ትዝ ያለኝ የ1983ቱ የአምባሳደር ተስፋዬ ሃቢሶ ንግግር ነበር። ቻርተሩ ሲጸድቅ በነበረበት ጊዜ የከምባታና ሃድያን ጎሳ እወክላለሁ ብለው ወንበር ይዘው የነበሩት አቶ ተስፋዬ ሃቢሶ በወቅቱ ሲናገሩ።
  “እኛ አናሳ ብሄር ብሄረሰቦች ዲሞክራሲ ብቻ ሳይሆን የሚያስፈልገን፣ እንደብርቅዬ እንስሣ እንክብካቤም ይገባናል።” ብለው ነበር።
ኢህዴግም በወቅቱ ለእነኚህ ‘አናሳ ጎሳዎች’ ልዩ እንክብካቤ እንደሚያደርግ ነበር ቃል የገባው።
አቶ ተስፋዬ ይህንን በተናገሩ ከአመታት በኋላ ታዲያ በሃዲያ እና ወላይታ ወገኖቻችን ላይ ጥይት እና ቦምብ እንደዝናብ ወረደባቸው። የ1993ቱ ብሄራዊ ምርጫ ተጭበርብሯል፣ ‘ድምጻችን ይከበር’ ብሎ የጮኸው የደቡብ ወገናችን በመለስ ወታደሮች ያለ ርህራሄ ነበር የተጨፈጨፈው። ልዩ እንክብካቤው እና ዴሞክራሲው ቀርቶ ይልቁንም የቆሙለት፣ በስሙም ስልጣን ያገኙበት፣ የራሳቸው ጎሳ በጥይት ሲቆላ አቶ ተስፋዬ ሃቢሶ ሹመታቸውን ላለማጣት ሲሉ ትንፍሽ አላሉም። እንዲያውም ዛሬም ስለ ‘ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች’ መብት መከበር ከሚነግሩን እና የሌሎችን ጽሁፎች እየሰረቁ ከሚጽፉት ሰዎች አንዱ ናቸው።
  ማሌሊቶቹ የሃገሪቱ የዘመናት ችግር የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች መብት መነፈግ ነው ሲሉ ሰበኩ። የዚህ ችግር መፍቻ ቁልፍም በእጃቸው እንዳለ ነገሩን። በለስ ቀንቷቸው ምኒሊክ ቤተ መንግስት ሲገቡም ጫካ ውስጥ የጻፉትን ያንን የስታሊን ፍልስፍና ወደ ህገ-መንግስትነት ቀየሩት። መፍትሄ ያሉት የጎሳ ፖለቲካም በጥላቻና በበቀል ተተካ።
የማሌሊት ፍልስፍና ሲተገበር ታዲያ የመጀመርያ ሰለባ የሆነው አማራው ወገናችን ነበር። ለፖለቲካ ትርፍ ሲሉ እነ አቶ መለስ ዜናዊ ይዘውት የመጡት የጥላቻና የብቀላ ፖለቲካ እንደስካር ቶሎ በረደ እንጂ አካሄዱ እጅግ ዘግናኝ ነበር። በምስራቅ እና በምእራብ ኢትዮጵያ የአማራ ዘር ጨርሶ እንዲጠፋ ተዘምቶበት ነበር። የአማራን ዘር ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ከተበቀሉት በኋላም ጽዋው ወደ አኙዋክ – ጋምቤላ ሄደ ፣ ከአኙዋክ ጭፍጨፋ በኋላ ደግሞ ዘመቻው በኦሮሞ ወገናችን ላይ ቀጠለ። በወላይታ ተከተለ፣ በኦጋዴን… ተዛመተ። የብሄር መብት እስከመገንጠልን ያስከበረው ህገ-መንግስት ጸድቆ በወረቀት ላይ ተቀምጧል። ይህንን መብት እየጠየቁ ያሉ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችንን ግን በዘራቸው ብቻ እየተመረጡ ማጥፋቱ ዛሬም በሚያሳዝን ሁኔታ እንደቀጠለ ነው።
እነ መለስ እነ በረከት ለዘመናት ተዋልዶና አብሮ ሲኖር የነበረን ህዝብ እንደ እንግሊዝ ከፋፍለህ ግዛው ቅኝ ስርዓት ለአገዛዝ እንዲያመቻቸው ህዝቡን እርስበርስ እያጋጩት ላለፉት 20 አመታት ለመቆየት ችለዋል። የዘር ፖለቲካው ምስጢር ይኸው ነው። ይህንን ባያደርጉ ኖሮ እስካሁን እንደ ጉም ተበትነው በጠፉ ነበር።
  ወደመቀሌው በዓል እንመለስ።
ብሄር ብሄረሰቦቹ በመቀሌ ከተማ በቡድን በቡድን እየዘፈኑና እየጨፈሩ ይጓዛሉ። በተለይ ከደቡብ የመጡት ብሄር ብሄረሰቦች መብታቸው ተከብሮላቸው ወደ እድገት ጎዳና ከተጓዙ ከሃያ አመት በኋላም – ጥንታዊው የጋርዮሽ ስርዓት ከሚመስለው አለባበሳቸው እንኳን አልተቀየሩም።
መር ከሃያ አመት በፊት ቅጠል ለብሶ ይጨፍራል፣ ዛሬም ቅጠሉን አልቀየረም። ዳውሮ ድሮ ለእግሩ ጫማ አያደርግም ነበር አሁንም ጫማ የለውም። ከፊቾ ከ20 አመታት በፊት ከቀንድ የተሰራ የሙዚቃ መሳርያ ነበር የሚጠቀመው፣ አሁንም እሱኑ ይዞ ነው መቀሌ የመጣው…። ሁሉም አንዳች ለውጥ አይታይባቸውም። ታድያ የዚህ ሕዝብ ነጻነቱ፣ ለውጡ እና እድገቱ የቱ ላይ እንደሆነ ማን ይሆን የሚያስረዳን?
ህገ መንግስታዊ መብቴ ይከበርልኝ ባለ ብቻ ምላሹ የጥይት እና ቦንብ የሆነ ሕዝብ ቅጠል ለብሶ መጨፈሩ ምን ትርጉም ይሰጠናል? ይህ ነጻነቱን ያሳየናል እንዴ? ወይንስ ዛሬም የእግር ጫማ እንኳን አለማድረጉ እንደ ባህል ተቆጠረለት?
  ጎንደሬው ሁመራ ላይ ለማረስ ፈቃድ ከመቀሌ መጠየቁ ነው የመብቱ መከበር? ወይንስ መቀሌ ላይ ሄዶ እስክስታ መምታት? አፋርና ኢሳ – ጉርጉራ ላይ ካላረሰ – አማራው ኦሮሞ ምድር ላይ እንዳይሰራ ከታገደ መብቱ ምኑ ላይ ነው?
ተረስቶ ይሆን ይሆናል እንጂ “የአክሱም ሃውልት ለወላይታው ምኑ ነው?…” ብለው ነበር አቶ መለስ። ታዲያ ዛሬ ምን አዲስ ነገር ተገኘ? በመቀሌ እየተደረገ ያለው የወላይታ ጭፈራስ ለአድዋው ምኑ ሊሆን ነው?
‘የኢትዮጵያ ጥንታዊ ስልጣኔ አንተን አይመለከትህም’ ተብሎ የነበረ የወላይታ ህዝብ ዛሬ የመለስን ፎቶ እና ‘ለልማት የተጋ ብቸኛው መሪ’ የሚል መፈክር ይዞ በመቀሌ እንዲሰለፍ ተደርጓል።
ደቡቡ የየራሱን የአፍ መፍቻ ቋንቋ እርግፍ አድርጎ ትቶ ኢህአዴግ በፈጠረለት ‘ወጋ ጎዳ’ እንዲናገር አቶ መለስ፡ ሲያስገድዱት እነሱ ግን ልጆቻቸውን በአለም አቀፍ ቋንቋ ብቻ እንዲማሩ ነው ያደረጉዋቸው። ዛሬ አቶ መለስ የነዚህን ጎሳዎች መብት መከበር ነው በመቀሌ እያበሰሩ ያሉት።
ይህ ህዝብ እንዲሁ ‘ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች እየተባለ ሲቀለድበት እንደዋዛ ሃያ አመታት አለፉ።
በኢህአዴግ ዘመን ተወልዳ፣ ተምራ ዩኒቨርሲቲ የተመረቀች ወጣት አንድ አፍሪካ ሃገር አግኝቼ አወራኋት። ሜሮን ትባላለች። ስለ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች መብት እና ነጻነት ልትነግረኝ ሞከረች። ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባ ውጤት ሳይኖራት ይልቁንም ኢህአዴግ በሰጣት እድል ዩኒቨርሲቲ ገብታ እንደተማረች ስለተነገራት የመለስ ዜናዊ አድናቂ ናት።
በወሬያችን መሃል በድንገት ‘ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ማለት ምን ማለት ነው?’ ብዬ ጠየቅኳት። ጥያቄዬ ዱብዳ ነገር ሆነባት። ለሚለኒየም ግብ ሲባል ከተከፈቱት ዩኒቨርሲቲዎች ለስታስቲክስ ማሟያ የተመረቀች ስለመሆንዋ አመለካከትዋ፣ አስተሳሰብዋ እና ንግግርዋ ይገልጸዋል።
ጥያቄዬን ለመመለስ እንደከበዳት ተረዳሁ። ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የሚለውን ቃል የሜሮን ትውልድ ለሃያ አመታት ያለማቋረጥ ሲሰማው የነበረው ጉዳይ ነው። ለዚህ ትውልድ የብሄር መብት ማለት ግን በየአመቱ በጎዳና ላይ ከሚደረግ ጭፈራ ውጭ የሚሰጠው ሌላ ትርጉም ያለ አይመስለኝም።
ማን ነው ብሄር? ብሄረሰሰቦችስ የትኞቹ ናቸው? ህዝቦች የሚባሉትስ? ለዚህ ጥያቄ እንኳንና ሜሮን – ወያኔም መልሱ እንደሚቸግረው ይገባኛል።
ሜሮን ግን ኮስተር ብላ “ህገ መንግስቱ ነዋ!” አለችኝ።
ከዩኒቨርሲቲ ከተመረቀች ወጣት ቀርቶ ከአንደኛ ደረጃ ተማሪ እንኳን የማልጠብቀውን መልስ በማግኘቴ ባዝንም – በመልስዋ ግን ትንሽ ፈገግ ማለቴ አልቀረም።
ከአፍታ ቆይታ በኋላ – ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ማለት ራሱ መለስ ዜናዊ ይመስለኛል ስትል ቀለደች ሜሮን።
እዚህ ላይ ልብ በሉ! ‘የህዳሴው ግድብ’ ሽልማት ስነ ስርዓት እየተደረገ በነበረበት ግዜ የግድቡ “ወደር የሌለው ተሸላሚ”ን ሰራዊት ፍቅሬ በቴሌቭዥን ሲያስተዋውቅ የሆነው ነገር ታወስውኝ። ነገሩ ጤነኛ አእምሮ ላለው ሰው እንግዳ ነበር።
ሰራዊት እና ሙሉአለም እየተቀባበሉ – እየደጋገሙም ‘የህዳሴው ግድብ ወደር የሌለው ተሸላሚ’ ይላሉ። ከብዙ ደቀቃ በኋላም የህዳሴው ግድብ ወደር የሌለው ተሸላሚ ይፋ ሆነ።
“ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች!” ሲል ሰራዊት ፍቅሬ በሚለኒየም አዳራሽ ለተሰበሰበው ህዝብ አበሰረ።
ሸልማቱን የሚሰጠው አቶ መለስ ዜናዊ ፣ ሽልማቱን የሚቀበለው የኢህዴግ ተወካይ ሲሆን ፣ ይህም በተዘዋዋሪ አቶ መለስ ዜናዊ መሆኑ ነው።
ሜሮን ይህንን ማለትዋ ከሆነ – ጥያቄዬን በትክክል እንደመለሰችልኝ ተረዳሁ።
ሽልማቱ መጣም አልመጣ ለብሄር ብሄረሰቦቹ የሚፈይደው ነገር አይኖርም። በየአመቱ የሚደረገው የጎዳና ላይ ጭፈራ ግን የብሄረሰቦች መብት ብቻ ሳይሆን ግዴታቸውም ሆኗል ብለን እንደምድም።
የብሄር ነጻነት እስከ መጨፈር! ከዛ ካለፈ ግን የህይወት ዋጋም ያስከፍላል። ኦጋዴንን ያስተውሏል?
***

↧
↧

ኢትዮጵያ የአንድ ቢሊዮን ዶላር ‹‹ሶቨሪን ቦንድ›› ለዓለም ገበያ አቀረበች

$
0
0

euros_390_1102የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ የ‹‹ሶቨሪን ቦንድ›› ሽያጭ ለዓለም ገበያ ለማቅረብ በወሰነው መሠረት የአንድ ቢሊዮን ዶላር ቦንድ ሽያጭ ረቡዕ ኅዳር 17 ቀን 2007 ዓ.ም. በእንግሊዝ ለንደን ከተማ ለኢንቨስተሮች ይፋ ማድረጉን የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ያቀረበችው ‹‹ሶቨሪን ቦንድ›› ሽያጭ በአሥር ዓመት ተከፍሎ የሚያልቅ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮቻችን የወለድ ምጣኔው ከስድስት እስከ ሰባት በመቶ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ የሚመራው ልዑካን ቡድን ውስጥ የአገሪቱ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ውስጥ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ትብብር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ፍስሃ አበራ፣ የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተሩ አቶ ዋሲሁን አባተና የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲና ማኔጅመንት ዳይሬክተሩ አቶ መዝገቡ አምሃ እንደተካተቱም ተገልጿል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኅዳር 3 ቀን 2007 ዓ.ም. በዝግ ባካሄደው መደበኛ ጉባዔው በሥራ አስፈጻሚው የቀረበለትን የ‹‹ሶቨሪን ቦንድ›› ሽያጭ ተወያይቶ በማፅደቅ፣ ቦንዱን የመሸጥ ኃላፊነት ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ተሰጥቷል፡፡

በዚህም መሠረት ነው የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ የሚመሩት ልዑካን ቡድን ቦንዱን ለመሸጥ ወደ ለንደን ያመራው፡፡ ከለንደን ቆይታው በኋላም በተወሰኑ ሌሎች የአውሮፓ አገሮች ቦንዱን ለሽያጭ የሚያቀርብ ሲሆን፣ በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ ወደ አሜሪካ በመጓዝ የቦንድ ሽያጩን ያከናውናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አህመድ ሸዴ ባለፈው ዓርብ ከዓለም ባንክና ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር የብድር ስምምነት በተፈራረሙበት ወቅት ሪፖርተር በ‹‹ሶቨሪን ቦንድ›› ሽያጩ ዙሪያ ሊያነጋግራቸው ቢሞክርም፣ የቀረበውን መጠን ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡ ይሁን እንጂ ‹‹እጅግ በጣም ጥሩ የሚባል የወለድ ምጣኔ አግኝተናል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ቦንዱን ያቀረብንበት ወቅት ጥሩ ስለሆነ ነው፤›› ብለዋል፡፡

‹‹ሶቨሪን ቦንድ›› በሌላ መጠሪያው ደግሞ ‹‹ዩሮ ቦንድ›› ማለት የኢትዮጵያ መንግሥት የህዳሴውን ግድብ ለመገንባት ለኢትዮጵያውያን በአገር ውስጥ እንዳቀረበው ዓይነት የመንግሥት ሰነድ ሆኖ ይኼኛው የሚለየው ለዓለም አቀፍ ገበያ ወይም ለኢንቨስተሮች በዶላር ወይም የውጭ ምንዛሪ የሚቀርብ መሆኑ ነው፡፡

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የ‹‹ሶቨሪን ቦንድ›› ሽያጩን ለማከናወን በአመቻችነት የአሜሪካውን ጄፒ ሞርጋንና የጀርመኑን ዶች ባንክን የመረጠ ሲሆን፣ ባንኮቹም በአሁኑ ወቅት ቦንዱን መግዛት የሚችሉ ኢንቨስተሮችን በመምረጥ ከኢትዮጵያ ልዑክ ጋር እያገናኙ መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

አጠቃላይ የልዑኩ ቆይታ በሚቀጥለው ሳምንት ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ በማጠናቀቂያው ዕለትም ከቀረበው ቦንድ ምን ያህል መሸጡ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በቦንድ ሽያጩ የሚገኘው ገንዘብ የውጭ ምንዛሪን የሚጠይቁ ፕሮጀክቶችን ብቻ ለመገንባት እንደሚውል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን ባለፈው ኅዳር 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የውጭ ምንዛሪን የግድ ከሚጠይቁት ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል የታላቁ ህዳሴ ግድብና በዕቅድ ተይዘው ያልተጀመሩ አገር አቀፍ የባቡር ትራንስፖርት ፕሮጀክቶች ይጠቀሳሉ፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

↧

የቻይና ኤግዚም ባንክ ለመቐለ ወልዲያ ባቡር ፕሮጀክት ብድር ሊለቅ ነው

$
0
0

የቻይና ኤክስፖርትና ኢምፖርት (ኤግዚም) ባንክ ለመቐለ ወልዲያ የባቡር ፕሮጀክት 1.5 ቢሊዮን ዶላር ብድር ሊለቅ ነው፡፡

f4dd5c1a7bbb150619bc2bac1c3d9648_Lየገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በሚኒስቴሩ ከፍተኛ ኃላፊዎችና የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ጌታቸው በትሩ የተገኙበት ቡድን በቅርቡ ወደ ቻይና ሄዶ ባንኩ ባስጠናው የአዋጭነት ጥናት ላይ ማብራርያ አቅርበዋል፡፡

የፕሮጀክቱ የአዋጭነት ጥናት በኢትዮጵያ በኩል ከዚህ ቀደም የተጠና ቢሆንም፣ የቻይናው ኤግዚም ባንክ በድጋሚ ኩባንያ ቀጥሮ የአዋጭነት ጥናት አስጠንቷል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያትም የቻይና መንግሥት በኢትዮጵያ የፖታሽ ማዕድንን ከማልማት ረገድ ይህ የባቡር ትራንስፖርት መስመር የሚኖረውን ጠቀሜታ አስረግጦ ለመረዳት እንደሆነ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በዚህም መሠረት በጥናቱ ላይ ለተነሱ ውስን ጥያቄዎች ማብራርያ እንደተሰጠና በቅርቡም ገንዘቡ ይለቀቃል ተብሎ እንደሚገመት ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

የመቐለ ወልዲያ ፕሮጀክት 268.2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፣ የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ለፕሮጀክቱ ብድር ለማቅረብ ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር መግባባታቸው ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ባቡር ኮርፖሬሽን በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ እያደረጋቸው የሚገኙ ሦስት የባቡር ፕሮጀክቶች ማለትም የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር፣ የአዲስ አበባ ሜኤሶና የሜኤሶ ድሬዳዋ ደወሌ የባቡር ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ ከቻይና በተገኘ ብድር በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡

ብቸኛው ከቻይና ውጪ በተገኘ ብድር ለመገንባት ዝግጁ የሆነው ፕሮጀክት የአዋሽ ወልዲያ የባቡር መስመር ሲሆን የሚገነባው ከአውሮፓ ባንኮች በተገኘ ብድር ነው፡፡ ይህም መስመር በቻይና ብድር ከሚገነባው የመቐለ ወልዲያ ፕሮጀክት ጋር የሚገናኝ ነው፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

↧

የሶስት ወር ህጻን ልጇን አንቃ የገደለችው በ16 ዓመት እስራት ተቀጣች

$
0
0

ህጻን ልጇን በሻሽ አንቃ በመግደል የጣለችው ተከሳሽ ላይ የእስራት ቅጣት የተወሰነባት መሆኑን የኢትዮጵያ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
crime በአርሲ ዞን የሒጦሳ ወረዳ ፖሊስ እንደገለፀው በተከሳሽ መስታወት ደረጄ ላይ የእስራት ቅጣት ሊወስንባት የቻለው ከወለደችው የሶስት ወር እድሜ ያለውን ልጇን ሐምሌ 14 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ ጎንዴ ፊንጨማ ልዩ ስሙ ሾሪማ ተብሎ ከሚታወቅበት አካባቢ በመውሰድና ከበቆሎ ማሳ ውስጥ በመግባት በያዘችው ሻሽ አንቃ በመግደሏ ነው፡፡ እንደ ሒጦሳ ወረዳ ፖሊስ ገለጻ የተገደለውን ህጻን የተመለከቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መሰረት አስከሬኑ ተነስቶ በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል በተደረገለት የአስከሬን ምርመራ መሠረት ህጻኑ ታንቆ መገደሉ ተረጋግጧል ተብሏል፡፡

ተከሳሿ በቁጥጥር ስር ውላ በሰጠችው የእምነት ቃልም በቡና ቤት አስተናጋጅነት እየሰራች ሳለ ከተዋወቀችው አሽከርካሪ ጋር ፍቅር በመመስረቷና ከወለደችለት በኋላ ሊረዳት ፍቃደኛ ባለመሆኑ ድርጊቱን ልትፈጽም መነሳሳቷን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽ መስታወት ደረጄን በአስራ ስድስት ዓመት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኖባታል፡፡

↧

Health: የሆድ ድርቀት * ምልክቶች * የሚያጋልጡ ነገሮች * ህክምና

$
0
0

አንድ ሰው ለተከታታይ ሳምንታትና ከዚያ በላይ በቂ ጊዜ ሰገራ መዉጣት የሚያስቸግረዉ ከሆነ ወይም በሳምንት ከሶስት ጊዜ በታች ሰገራ የሚወጣ ከሆነ ለረጅም ጊዜ የቆየ የሆድ ድርቀት( Chronic constipation) አለዉ ተብሎ በህክምናው ላይ ይገለፃል፡፡
Chronic constipation
ጊዜያዊ የሆነ የሆድ ድርቀት ብዙ ጊዜ የሚከሰት ነገር ነዉ፡፡ ነገር ግን ለረጅም ጊዜ የቆየ የሆድ ድርቀት በሚከሰትበት ወቅት የታማሚዉን የዕለት ተዕለት የስራ እንቅስቃሴ ከማወኩም በላይ ታማሚዉ ሰገራ በሚወጣበት ወቅት ረዘም ላለ ጊዜ የማስማጥና ሌሎች ምልክቶችም አሉት፡፡

የሆድ ድርቀት ምልክቶች
• በሳምንት ከሶስት ጊዜ በታች ሰገራ መዉጣት • የደረቀ ሰገራ መዉጣት
• ሰገራ በሚቀመጡበት ወቅት ማስማጥ
• ሰገራ በሚቀመጡበት ወቅት አንዳች ነገር ደንዳኔዎትን የዘጋዉ ነገር ያለ ስሜት መሰማት
• ሰገራ ለመዉጣት እርዳታ መፈለግ(በእጅዎ ሆድዎትን መግፋት፣በጣትዎ ሰገራን ለማዉጣት መሞከር)
ለሆድ ድርቀት የሚያጋልጡ ነገሮች
• በእድሜ መግፋት
• ፆታ /በአብዛኛው ሴቶች ላይ ይስተዋላል/
• በቂ ፈሳሽ ያለመዉሰድ
• በፋይበር( fiber) የበለፀጉ ምግቦችን ያለመጠቀም(አነስተኛ የፋይበር መጠን ያላቸዉን ምግቦች ማዘዉተር)
• አነስተኛ ወይም ምንም አይነት የአካል እንቅስቃሴ ያለማድረግ
• ለድርቀት ሊያጋልጡ የሚችሉ መድሃኒቶችን መጠቀም፡-ለምሳሌ የደም ግፊት ለመቀነስ የሚረዱ፣ለስነዓዕምሮ ችግሮች የሚሰጡ (ሴዳቲቭስና ናርኮቲክስ) የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡ የሆድ ድርቀት መንስዔዎች
የሆድ ድርቀት አብዛኛዉን ጊዜ የሚከሰተዉ ከምግብ መፈጨት በኋላ የሚቀረዉ ቆሻሻ ወይም ሰገራ በአንጀት ዉስጥ የሚያደርገዉ እንቅስቃሴ(ጉዞ) በጣም ዘገምተኛ በሚሆንበት ወቅት ሲሆን የሚከተሉት መንስዔዎች አሉት፡-
• በትልቁ አንጀት ወይም በደንዳኔ ዉስጥ መዘጋት በሚኖርበት ወቅት
• የፊንጢጣ መቀደድ( Anal fissure)
• የአንጀት መታጠፍ
• የትልቁ አንጀት ካንሰር
• የትልቁ አንጀት ጥበት
• አንጀት ላይ ጭነት ሊፈጥሩ የሚችሉ ሌሎች የሆድ ዉስጥ ካንሰሮች
• የደንዳኔ ካንሰር
በደንዳኔ ግድግዳ ላይ አድገዉ የሰገራን መተላለፊያ ሊዘጉ የምችሉ ነገሮች(ሬክቶ ሲል)
• በትልቁ አንጀትና በደንዳኔ አካባቢ ባሉ ነርቮች ላይ ችግር በሚከሰትበት ወቅት
የነርቭ ችግር መኖር በደንዳኔና ትልቁ አንጀት ጡንቻዎች ላይ መኮማተርን ስለሚያስከስት የሰገራን እንቅስቃሴ ይገድባል፡፡ ይህን ችግር ሊያስከስቱ ከሚችሉ ነገሮች ዉስጥ፡
• የህብለ ሰረሰር (Spinal cord) ጉዳት መኖር • ስትሮክ( Stroke)
• የፓርኪንሰን ህመም
• አዉቶኖሚክ ንይሮፓቲይ የሚባል የነርቭ
ህመም
• መልቲፕል ስክሌሮሲስ የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡ • ሰገራን ከሰዉነት ለማስወገድ በሚረዱ ጡንቻዎች ላይ ችግር መከሰት
• ሰገራን ለማስወገድ የዳሌ ጡንቻዎች መለጠጥ ያለመቻል(Inability to relax the pelvic muscles)
• የዳሌ ጡንቻዎች በደንብ በተቀናጀ መልኩ ያለመለጠጥና ያለመኮማተር (ዲሲነርጂ)
• የዳሌ ጡንቻዎች መልፈስፈስ
• በሰዉነት ዉስጥ ባሉ ሆርሞኖች ላይ ችግር መከሰት
ሆርሞኖች በሰዉነታችን ዉስጥ ያለዉ ፈሳሽ ተመጣጥኖ እንዲገኝ የሚያደርጉ ሲሆን ይህንን ስርዓት የሚያዛቡ ህመሞች ካሉ ለሆድ ድርቀት ሊያጋልጡ ይችላሉ፡፡ ከነዚህም ዉስጥ፡-
• የስኳር ህመም
• የፓራታይሮይድ ዕጢ ችግር(ሃይፐርፓራታይሮይድዝም)
• እርግዝና
• የታይሮይድ ዕጢ ሆርሞኖች ማነስ(ሃይፓታይሮይድዝም)
የሆድ ድርቀት ህክምና
ለረጅም ጊዜ የቆየ የሆድ ድርቀት በሚኖርበት ወቅት ከሚመከሩ ነገሮች ዉስጥ የአመጋገብና የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥ ማድረግ ሲሆን ይህም ሰገራ በአንጀት ዉስጥ የሚቆይበትን ጊዜ ይቀንሳል፡፡ይህን ማድረግዎ ለዉጥ ካላመጣ የህክምና ባለሙያ ማማከር ይጠበቅብዎታል፡ ፡ የህክምና ባለሙያዎች የሚከተሉትን ነገሮች ሊመክሮት ይችላል፡፡
• የፋይበር አወሳሰዶችን መጨመር እና በቂ ፈሳሽ መዉሰድ፡- ቀስ በቀስ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የጥራጥሬ ዘሮች በብዛት መመገብ
• የአካል እንቅስቃሴ ማዘዉተር፡- ይህ የአንጀትን የጡንቻዎችን እንቅስቃሴ ስለሚጨምር ድርቀትን ይከላከላል
• የሰገራ መምጣት ስሜት ባለዎት ጊዜ ሳያሳልፉ መዉጣት
• የሰገራ ማለስለሻ መጠቀም፡- ፋይበሮች፣ሰገራ ማለስለሻ መድሃኒቶች፣ሰገራን ሊያላሉ የሚችሉ ነገሮችን መጠቀም( Stool softeners)
• የዳሌ ጡንቻዎች ስልጠና፡- በዚህ ረገድ በሰለጠኑ ባለሙያዎች በመታገዝ ሰገራን ከሰዉነት ለማስወገድ የሚረዱትን ጡንቻዎችን በማላላትና በማጠንከር ማሰልጠን ሰገራን በቀላሉ ለመዉጣት ይረዳል፡፡
• የቀዶ ጥገና፡-በቀዶ ጥገና ሊስተካከሉ የሚችሉ የጤና ችግሮችን ለምሳሌ የፊንጢጣ መቀደድ፣ሬክቶሴሌና የአንጀት ጥበት የመሳሰሉት ሲሆኑ እነዚህ ሁኔታዎች ሲኖሩ የቀዶ ጥገና ባለሙያን ማማከር ይመከራል፡ ፡ጤናዎ ይሰመርሎት ዘንድ እየተመኘን ቸር እንሰንብት እንላለን፡፡
ďżźďżź

↧
↧

እናታችን ፋናዬና ተመስገን በዝዋይ…. (የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም እንደፃፈው)

$
0
0

ከታሪኩ ደሳለኝ
(የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም)

ያቺ የስምጥ ሽለቆ ከተማ ይበልጥ መንደድ ከጀማመራት አንድ ወር አልፏታል:: በፍትህ መዛባት ስሜቱ የተጎዳ፣ በወገኖቹ ስቃይ መንፈሱ የታመመ፣ ሀገራቸውን ከስቃይ መታደግ በሚችሉበት እድሜያቸው በታሰሩ፣ በተሰደዱና በተገደሉ ወገኖቹ ልቡ ያዘነ፣ ለሀገሩና ለባንዲራው ያለው ፍቅር ጥልቅ የሆነ አንድ ወጣት ጋዜጠኛ በውስጧ ይዛለች፡፡ ዝዋይ፡፡
ከዚህች ከተማ ሦስት ኪሎ ሜትር ገደማ ወደሚርቀው የዝዋይ እስር ቤት ለመሄድ የአስፓልት ዱካ እንዳረፈበት በሚያሳብቀው ኮሮኮንቻማ መንገድ ማለፍ የግድ ይላል፡፡ ከረጅም ዓመታት በፊት ተሰርቶ ዛሬ አስታዋሽ ያጣው ይህ ጎዳና እስረኞችን የመጠየቁን ጉዞ አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡ ከፀሐዩ ግለት ትይዩ ያለው የመሬቱ አቧራ በእግሩ ቆሞ ይሄዳል ብል አይበዛበበትም፡፡ ይህን አልፈን ግዞት ቤቱን እናገኛለን፡፡ የእስር ቤቱን መግቢያ ያለበሰው አቧራ ደግሞ ቅጥሩን በቁፋሮ የተገኘ ጥንታዊ ከተማ አስመስሎታል፡፡ የግቢው ገፅታ ለዕይታ በማይስቡ ነገሮች ቢከበብም፣ ተናፋቂውን ብዕረኛ ግን ደጋግሜ እንድጠይቀው ከወንድምነት የሚዘለው ጥንካሬው ይስበኛል፡፡
በአቧራውና በንዳዱ መካከል ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከቀድሞ ይልቅ በጠነከረ ፅናቱ ስለመኖሩ ሳስብ ደስተኛ እሆናለሁ፡፡ እናታችንስ ምን ታስብ ይሆን? የማይበርድ፣ የማይዳፈንና የማይጠፋ የሀገር ፍቅር ስሜቱ ከአቧራውና ከንዳዱ በላይ መሆኑ ለእርሷ ምን ስሜት ያጋባባታል?
yetemesgen enat
እናታችንና ተሜን ሲገናኙ…

ዛሬ ቅዳሜ ህዳር 20/07 ዓ.ም ነው፡፡ እናቴ አብረዋት ከኖሩ ጎረቤቶቿ ጋር በመሆን፣ ዝዋይ እስር ቤት ከከተመ አንድ ወር ያለፈውን ተመስገንን ልታየው ተሰናድታለች፡፡ ዝዋይ ከሄደ ወዲህ አይታው አታውቅም፡፡ እንደናፈቃት ግን የፊቷ ገፅታ ይመሰክራል፡፡ እንደ ልጅነቱ ፀጉሩን ባትደባብሰውም፤ እጁን ልትነካውና በዕርጅና አንደበቷ ‹እንዴት ነህ?› ልትለው ወደዚያው እያቀናች ነው፡፡ ጠዋት ወጥተው ማታ እንደሚገቡት፣ ክፍለ-ሀገር ሰንብተው እንደሚመለሱት እንደ ጓደኞቿ ልጆች ተመስገን እንደማይመለስ የተረዳችው እናታችን ልጇ ጋር እየሄደሰች ነው፡፡

ለሊት 11፡30 ከጀሞ ኮንዶሚኒየም የተነሳችው መኪና ዝዋይ የደረሰችው ከጠዋቱ 2፡20 ላይ ነበር፡፡ አስፋልት መሰል ፍርስራሽ መንገዱን ስለለመድኩት ነው መሰለኝ ዛሬ አልሰጠኝም፡፡ ፍተሻውን አልፈን እስረኛና ጠያቂ የሚገናኘበት ቦታ ላይ ደረስን፡፡ ከነበርነው ሰዎች ይልቅ እናታችን ጉጉት እንዳደረባት ለመናገር ሁኔታዋን ማየት ብቻ በቂ ነው፡፡

እናታችን ተመስገን በልጅነቱ ከዕኩዮቹ ጋር ተጫውቶ ሲመጣ ጠብቃዋለች፣ ትምህርት ቤት ውሎ ሲመጣ ጠብቃዋለች፣ ስራ ውሎ ሲመጣ ጠብቃዋለች፤ አንዳንዴም ሲያመሽ ደውላ ‹‹አልመሸም፤ የቀረው ለነገ ይቆይህ›› ትለዋለች፤ እርሱም ሁሌ እንደሰማት ነበር፡፡ ዛሬ ግን ልጇን የምትጠብቀው ከትምህርት ቤት አልያም ከጨዋታ ወይም ከስራ አይደለም፡፡ ከእስር ቤት ውስጥ እንጂ!

እናታችን እስረኞች ከሚወጡበት በር ላይ ከተቀመጠችበት ደቂቃ ጀምሮ አይኗን አላነሳችም፡፡ በሩ ሲከፈት የወታደር ልብስ የለበሰ ወጣት ወጣ፡፡ ከወታደሩ በኋላ ተሜ እስካርፉን እንዳደረገ ተከተለ፡፡ እናቴ ከመቀመጫዋ ተነሳች፤ ዐይኗቿ እንባ አዘሉ፡፡ በዕስረኛና በጠያቂ መሀል ያለውን አጥር ተደገፈች፡፡ ሌላ ጊዜ አጥሩን መደገፍ የሚከለክሉት ወታደሮች እናታችንን ግን ጥቂት ታገሷት፡፡ ምን ያድርጉ? እነሱም እኮ እናት አላቸው፡፡ ከተመስገን ኋላ ሌላ ወታደር አለ፡፡ በሁለት ወታደሮች መካከል ሆኖ ተሜ እናቱን አያት፤ ፈገግ አለ፡፡ እየቀረበ ሲመጣ ግን ፈገግታው ከፊቱ ላይ ጠፍቶ በሀሳብ ተተካ፡፡ እናቴን በዚህ እድሜዋ አንከራተትኳት ብሎ እንዳላሰበ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ከዚህ ይልቅ ስንትና ስንት እናቶች በየቦታው እየተንከራተቱና እየተሰቃዩ ስለመሆናቸው እያሰበ የተጨነቀ ይመስላል፡፡ እናትና ልጅ አንገት ለአንገት ተቃቅፈው ቆዩ፡፡ ምን አለ ባይለያዩ? እንዲሁ እንዳሉ ወደ ቤት ቢሄዱስ ምን ነበረበት?

ይሄ ግን አይሆንም፤ ይሄ ቦታ ተሜ ለሀገሩ የከፈለውን፣ እየከፈለ ያለውንና የሚከፍለውን መስዋዕትነት ማቅረቢያው ቦታ ነው፡፡ ተሜ ወደ ቤት አይሄድም፡፡

ተሜና እናቴ የተጫወቱት ብዙ ነው ፡፡ ሲገናኙ የነበረው ድባብ ጠፍቶ ሁለቱም ደስ ብሏቸዋል፡፡ ተሜ ትንሽ አይቷት ‹‹ከስተሻል›› ሲላት ፈገግ እንዳለች ‹‹አረ አልከሳሁም፤ አንተ ግን ጤናህ እንዴት ነው?››፤ ‹‹ደህና ነኝ››… እናቴ በየመሀሉ ጨዋታቸውን ገታ እያደረገች በስስት ታየዋለች፡፡ እናትና ልጅ የሆድ የሆዳቸውን እንዲያወሩ የፈቀዱት ወታደሮችም ሁለቱን በስስት የሚያዩ ይመስላሉ፡፡

ሳይታወቀን 6፡00 ሆነ፡፡ የመሰነባበቻ ጊዜ ደረሰ፡፡ እናቴ እየሳቀች አቀፈችው፤ ተሜም እየሳቀ ተሰናበታት፡፡ እንደ አመጣጡ በሁለቱ ወታደሮች መካከል ሲሄድ ከጀርባው ትክ ብላ አየችው፡፡ የሆነ ነገር ልትል የፈለገች ትመስላላች፡፡ ‹‹ተመስገን›› አለች፤ አልሰማትም፡፡ በሩን አልፎ ገባ፡፡ እሱ ፊት የደበቀችውን እንባ ማቆም አልቻለችም፡፡ በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ከፈገግታዋ ጋር አለቀሰች፡፡

እሁድ ህዳር 21/07 ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት፡፡ እናቴ ልጇ እስኪፈታ አልጋ ላይ አልተኛም ብላ መሬት መተኛት ከጀመረች 1 ወር ከ17 ቀኗ ነው፡፡ የዛሬውን ለሌት እንዳለፉት ጊዜ አንዴም ተነስታ ‹አይ ልጄ› ወይም ‹እህህ….እህህ….› ሳትል በሰላም ተኝታ በማደሯ ሳልተኛ እያየኋት አደርኩ፡፡ ልክ 12፡10 ሲል ነቃች፡፡ ስታየኝ እያየኋት ነው፡፡ ‹‹ስንት ሰዓት ሆነ?›› ነገርኳት፡፡ አላመነችም፡፡ ተሜ ከታሰረ ጀምሮ እንደ ዛሬ ተኝታ አታውቅም፡፡ ተነሳች፡፡ ‹‹እስከዚህ ሰዓት ስተኛ ዝም ትላለህ?›› አለችኝ፡፡ ‹‹እንዴት ዝም አልልም?›› አልኳት፡፡ ‹ዛሬ የዓመቷ ማሪያም ነች› አለችኝ፡፡ ፊቷ ላይ ድካም አይታይባትም፡፡ … ከደቂቃዎች በኋላ የሀገር ባህል ጥበብ ቀሚስ ለብሳ አየኋት፤ አምሮባታል፡፡ የደስታ ሲቃ ይዞኝ ‹ትላንት እንዴት ነበር?› አልኳት፡፡ በፈገግታ እያየችኝ ‹‹ልጄ ጀግና ነው፤ ጀግና›› ስትል መለሰችልኝ፡፡ እኔም በመስማማት ራሴን ነቀነኩ፡፡ እናቴ በንጋት ፀሐይ ታጅባ የሀገር ባህል ልብሷን እንደለበሰች ስትሄድ በዐይኔ ተከተልኳት፡፡ ይሄ ብርታቷ እስከመቼ እንደሚቆይ እያሰብኩ ነበር፡፡

ተሜ ለሀገሩ ሲልና ሀገሩ እንድትሆን የሚመኝላትን በመፃፉ በግዞት እስር ቤት በአቧራና በንዳድ መሀል እንዲሰነብት ተፈርዶበታል፡፡ ፍትህ የነገሰባት፣ ልጆቿ የማይገደሉባትና የማይሰደዱባት ኢትዮጵያ እንደምትመጣ በተቃጠለ ስሜት እያሰበ፣ በማለዳ የወጣችውን የንጋት ፀሐይ በፈገግታ እያያት እንደሆነ ሳስብ እኔም በደስታ ተሞላው፡፡

↧

የተወዳጁ ድምፃዊ ፀሐዬ ዮሃንስ “የኔታ” በቅርብ ይወጣል

$
0
0

ከኢየሩሳሌም አረአያ’

ተወዳጁ ድምፃዊ ፀሐዬ ዮሃንስ “የኔታ” የሚል ርእስ የሰጠው አዲስ አልበም በቅርቡ እንደሚለቅ ታወቀ። ከአንድ አመት ለበለጠ ጊዜ የፈጀው ይህ አልበም የሙዚቃ አድማጩ ሊወደው እንደሚችል ፀሐዬ ተናግሯል። ስለእናት አገሩ ኢትዮጵያ በየአልበሙ የሚያቀነቅነው ፀሐዬ በዚህኛው “የኔታ” አልበም እንዲሁ ማዜሙን ገልፆዋል። አቋም ካላቸውና አገርና ህዝባቸውን በማክበር ከሚወዱ ድንቅ አርቲስቶች አንዱ ፀሐዬ ዮሃንስ ነው። የፀሐዬን ዘፈኖች በፍቅር ከመውደዴ በተጨማሪ ከህይወቴ ገጠመኞች ጋር የተቆራኙ ናቸው! ከፀሐዬ ጋር ባለፈው አመት ቨርጂኒያ ተገናኝተን የተናገረውን በዚህ አጋጣሚ መጥቀስ (መድገም) ወደድኩ። « ህዝብ በጭራሽ አይሳሳትም! ሁሌም ህዝብ ትክክል ነው!» ነበር ያለው።
(በፎቶው አዲሱ የፀሐዬ ዮሃንስ አዲስ አልበም ፖስተር)
yenita

↧

ምርጫ መሳተፍ በመርዕ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ወይስ ኢህአዴግን ማጀብ? –ከግርማ ሰይፉ ማሩ

$
0
0

ሰዎች በማንኛውም መንገድ ሸብረክ ሸብረክ የሚሉ ከሆነ መርህ አልባ መሆናቸውን ከማሳየት ውጭ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም፡፡ ባለፈው ሳምነት ፍኖተ ነፃነት ላይ ወጣቱ ፀሃፊ ኢዮኤል ፍስሃ ዳምጤ ለምን እንደምንፈራ ቁልጭ አድርጎ አሳይቶን ነበር፡፡ የገዢዎቻችን በትር የበረታብን በእነርሱ ጥንካሬ ሳይሆን ከፍርሃት በመጣ ዝምታችን እንደሆነ አስምሮበታል፡፡ መፍትሔውም ከፍርሃት መላቀቅና ዝምታውን ማፍረስ ነው፡፡ በዛሬው ፅሁፌ ማንሳት የፈለኩት ደግሞ ለምን ሸብረክ ሸብረክ እንደምንል ነው፡፡
ለምንድነው ኮሽ ሲል ደንግጠን ከቆምንበት “መርዕ” ከምንለው አስተሳሰብ የምንሸራተት? እንዲህ ከሆነ ቀድሞውንም መርዕ አልነበረንም ማለት ነው፡፡ መርዕ ብለን የምንይዘው አሰተሳሰብ በእኔ እምነት ለምናደርገው እንቅስቃሴ የማዕዘን ድንጋይ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ መርዕ ሸርተት ስንል ቀጥሎ የምናገኝው ሌላ የተሻለ ማዕዘን የሚሆን ድንጋይ ሳይሆን ድጥ ወይመ ማጥ ነው የሚሆነው፡፡ ብዙዎች መርዕ የሚመስላቸው በአቋራጭ የሚፈልጉትን ግብ የሚያሳካ አጭር መንገድ አድርገው ይወስዱታል፡፡ ይህ አቋራጭ መንገድ ግን ብዙን ጊዜ ወደ ሌላ ውጥንቅጥ ከመውሰድ አልፎ ለስኬት ሲያበቃ አይታይም፡፡
Girma Siefu
ግልፅ ያልሆነ የህይወት ግብ ያለን ሰዎች የምንሄድበትን ስለማናውቅ ሌሎች በሄዱበት ተከትለን እንነጉዳለን፣ ሌሎች ግባቸውን ሲያሳኩ እኛ የበይ ተመልካች መሆናችን አይቀርም፡፡ ግባችን ግልፅ ያለመሆኑ መድረሻችንን ብቻ ሳይሆን መነሻችንንም ስሚያዛባው ከየት ተነስተን የት እንደምንደርስ፣ እንዴት እንደምንደርስ እንዳናውቅ ያደርገናል፡፡ መርዕ ማለት አሁን ካለንብት ቦታ ተነስተን ወደምንፈልገው ቦታ ለመድረስ የምንጓዝበት ፍኖተ ካርታ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በአሰተሳሰብ ብቻ ሳይሆን በተግባርም ልክ መሆን ያለበት ነው፡፡ አንድ አንድ ሰዎች የምንፈልገውን ግብ ለማሳካት ማነኛውንም መንገድ መጠቀም ችግር የለውም ይላሉ፡፡ ይህ የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጭው /the end justify the means/ የሚባለው ዓይነት መሆኑ ሲሆን፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ ሌሎች የምንሄድበት መንገድ እንደ ወጤቱ ሁሉ መርዕ ላይ መመስረት አለበት የሚሉ ናቸው /The means is equally important as the end/:: በግሌ የማምነውም የምከተለውም የኋለኛውን አማራጭ ነው፡፡ የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጭው የስግብግቦች መንገድ ነው ብዬ በፅኑ ስለማምን፡፡

ሰሞነኛ ወደ ሆነው የምርጫ አጀንዳ እና በመርዕ ላይ የተመሰረተው የአንድነት ፓርቲ ምርጫ እሳተፋለሁ ውሳኔ እንዴት መታየት እንዳለበት በአጭሩ ይህን አቋም ለደገፉም ሆነ ለተቃወሙ ማሰረዳት ተገቢ ይመስለኛል፡፡ አንድነት ፓርቲ ስልጣን የሚገኘው በህዝብ ድምፅ ነው የሚል መርዕ አለው፡፡ የህዝብ ድምፅ የሚገኘው ደግሞ በምርጫ ወቅት መራጩ ህዝብ በሚሰጠው ካርድ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ በምርጫ የህዝብ ድምፅ ይገኛል ማለት ነው፡፡ ብዙዎች ምርጫ ለመሳተፍ እኩል ሜዳ ያሰፈልጋል ይላሉ፡፡ ትክክል ነው እኔም አምንበታለሁ፡፡ ሜዳውን ትክክል ከሚያደርገው አንዱ ጉዳይ የምርጫ ቦርድ ገለልተኝነት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ካልሆነ ማለትም ሜዳው ትክክል ካልሆነ ስልጣን በሌላም መንገድ መያዝ ተቀባይነት አለው የሚል መከራከሪያ ለማቅረብም ሰበብ ይሆናል፡፡

ስልጣን በተለያየ መንገድ ለመያዝ እንደሚቻል አማራጭ ማሳየት አንድ ጉዳይ ሆኖ እኛ የመረጥነው ብቻ ልክ ነው ማለትም ተገቢ አይደለም፡፡ በተገኘው መንገድ ለመያዝ መሞከር ግን መርዕ አልባ ያደርገናል፡፡ ሰላማዊ ትግል እከተላለሁ ብሎ በሰላማዊ ትግል መርዕዎች አምናለሁ የሚል ማታ-ማታ ወይም ቅዳሜና-እሁድ በሌላ መንገድ ልሞክር የሚል ከሆነ መርዕ አልባነት ነው፡፡ በእኔ እምነት ችግር ያለው የምርጫ ሜዳ ላይ ከሆነ የምርጫው ሜዳው ለማስተካከል ምን አድርገናል? ከሚለው መነሳት አለበት፡፡ ስልጣን የመያዣው መንግድ ኮሮኮንች በዝቶበታል ማለት ኮሮኮንቹን እንዴት እናሻሽል ወደሚል ሊገፋን ይገባል፡፡

ሁሉም ሰው መረዳት ያለበት ገዢው ፓርቲ የምርጫ ሜዳውን ያጠበበው ወይም ኮሮኮንች እንዲበዛበት ያደረገው አውቆ ነው፡፡ ሜዳው ደግሞ የጠበበን ደግሞ አማራጭ አለን የምንል ፓርቲዎች ነን፡፡ አማርጭ ለማቅረብ እድል ስንነፈግ መጠየቅ ያለብን አንድ መስረታዊ ጥያቄ አማራጭ የተከለከለው ህዝብ ምንም ማድረግ አለበት የሚለው ነው? አማራጭ የሚፈልግ ህዝብ ድንጋይ ወይም ጠብመንጃ ይዞ አማራጭ አትከልክሉን ቢል ነው የሚሻለው ወይስ የምርጫ ካርድ ይዞ? አንድነት የመረጠው መስመር የምርጫ ካርድ ይዞ ቢሆን ይሻላል የሚለውን ነው፡፡ ይህ በምንም ዓይነት ሌሎች የመረጡት መስመር አይሰራም ማለት አይደለም፡፡ የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጭውን እንደ መርዕ የተቀበለ ብዙ ሌላ አማራጭ ሊያስብ፣ ሊተገብር ይችላል፡፡ ችግሩ የእኛ ካልሆነ ብሎ የሌሎችን ምርጫ ለማክበር አለመፈለጉ ላይ ነው፡፡

ETHIOPIA ELECTIONSበሀገራችን ኢትዮጵያ በ1997 ከተደረገው ምርጫ ውጭ ህዝቡ በምርጫ እንዲሳተፍ የምርጫ ካርድ እንዲወስድ በተቃዋሚ ፓርቲዎች በተገቢው መልኩና ደረጃ ተቀስቅሶዋል የሚል እምነት የለኝ፡፡ ከ1997 በፊት ምርጫ መወዳድር ወያኔን ማጀብ ነው እያልን ምርጫ የሚወዳደሩትን ብቻ ሳይሆን መራጩንም ተሰፋ እያስቆረጥን ኖረናል፡፡ ይህን ምርጫ የማጣጣል ስትራቴጂያችንን በደንብ የተረዳው ገዢው ፓርቲ የራሱን መራጮችና ተመራጮች እያዘጋጀ ውድድር ሲያድርግ ነበር፡፡ እንደዚያም ሆኖ ህዝቡ በምርጫ ካርዱ ቅሬታውን ሲገልፅ እንደ ነበር የገዢው ፓርቲ የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዴእታ የነበሩት አቶ ኤርሚያስ ለገሠ “የመለስ ትሩፋቶች” በሚለው መፅሃፍ አስነብቦናል፡፡ ስለዚህ የአንድነት ቤተሰቦች ምርጫ እንሳተፋለን ስንል መራጮቻችን እንዲመዘገቡ እናደርጋለን ማለት ነው፡፡ የእኛ መራጮች ሲመዘገቡ፣ ገዢው ፓርቲ የእኔ ብሎ ያስመዘገባቸውም ቢሆኑ እኛን ለመምረጥ እንዲችሉ መሸሸጊያ እንሰጣቸዋለን፡፡
ብዙ ሰው መረዳት ያለበት የምርጫ ቅስቀሳ የሚጀመርበት ወቅት መራጮች ምዝገባ ሊጠናቀቅ ሳምንት ሲቀረው ነው (በ1997 ቀድሞ የምርጫ ቅስቀሳ ተጀምሮ ነበር)፡፡ ለዚህ ነው ገዢው ፓርቲ ሁል ጊዜ የሚጮሁት ካርድ ያልያዙ ናቸው የሚለው፡፡ ያስመዘገባቸውን ስለሚያውቅ ነው፡፡ የእኛ መራጮች ካርድ ባልያዙበት ሁኔታ የፈለገ አማላይ የሆነ ለሀገር የሚጠቅም አማራጭ ብናቀርብ ለማሸነፍ ያለን እድል አነስተኛ ነው፡፡
ማስተላለፍ የፈለኩት ነጥብ ምርጫ እገባለሁ-አልገባም በሚል ዥዋዝዌ ስንጫወት ደጋፊዎቻችን በመራጭነት ሳይመዘገቡ እንዳይቀሩ በአንድነት በኩል የተወሰደው እርምጃ ትልቅ ፖለቲካ ውሳኔ ነው፡፡ የምርጫ ፓርቲ መሆናችን የሚታወቅ ቢሆንም እስከ አሁን በተቃዋሚ ፓርቲዎች መስመር ምርጫ መግባትና አለመግባት በቁርጥ ቀድሞ ስለማይወሰን መራጮች ሁለት ልብ እየሆኑ ከጫወታ ውጭ ሲደረጉ ከርመዋል፡፡ ይህ እንዳይደግም መራጮች እንዲመዘገቡ እና በምርጫው ሙሉ ሂደት በንቃት እንዲሳተፉ ይህን አቋም መያዝ እጅግ አስፈላጊ እና ጠቃሚ ነበር፡፡ ሁሉም እንደሚረዳው ያልተመዘገበ ደግሞ አይመርጥም፣ ያልመረጠ ደግሞ ድምፁ እንዲከበር ዘብ ሊቆም አይችለም፡፡ ድምፃችን ይከበር የሚለው እንቅስቃሴ የሚጀምረው ከህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ እሰከ ድምፅ ቆጠራ ድረስ ይዘልቃል፡፡
ጎበዝ ሰላማዊና ህጋዊ ትግል እናደርጋልን ስንል የሰላማዊና ህጋዊ ትግል መርዖዎችን ጠንቅቀን መረዳት የግድ ይለናል፡፡ በስላማዊ ትግል ዋናው ግብ የህዝብን የስልጣን ባለቤትነት ማረጋገጥ ሲሆን፣ ስልጣን መያዝ የሚፈልግ ፓርቲ የህዝብ ይሁንታ ማግኘት የግድ ይለዋል፡፡ ይህ ደግሞ በምርጫ የሚገኝ ነው፡፡ ምርጫውን የህዝብ ፖለቲካ ተሳትፎ መለኪያ አድርገን ለመውስድ ቁርጠኞች መሆን የግድ ይለናል፡፡

ቸር ይግጠመን

↧

Hiber Radio: የ9ኙ ተቃዋሚዎች ትብብር የመስቀል አደባባይ አዳር ተቃውሞ ዕውቅና ደብዳቤውን ተቀበለ፤ ሁበር በኔቫዳ ታገደ

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ህዳር 21 ቀን 2007 ፕሮግራም !

<... ...>

አቶ ወረታው ዋሴ የሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ሀላፊ በመስቀል አደባባይ የተጠራውን ተቃውሞ አስመልክቶ ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረጉት ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)

በጥቁሩ ወጣት ላይ የተፈጸመው ግድያ እና ጥቁርነት እና የአሜሪካ የሕግ አስከባሪዎች እርምጃ ተቃውሞውና ይዟቸው የመጣው የዘር መድልዎ እርምጃ እርምጃዎች (ልዩ ዝግጅት)

የኦባማ ኬር ዳግም ምዝገባና የአይ ኤር .ኤስ ቅታት ባልተመዘገቡት ላይ (ልዩ ቃለ መጠይቅ ከአቶ ተካ ከለለ በአትላንታ የቲኬ ሾው አዘጋጅ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ ሁለተኛ ክፍል))

ዜናዎቻችን
በመስቀል አደባባይ ለተጠራው የአዳር የተቃውሞ ሰልፍ ከነገ ጀምሮ የአደባባይ ቅስቀሳ ይጀመራል

ሕዝቡ ከወዲሁ በተለያዩ መንገዶች የተቃውሞውን ጥሪ እንደሚደግፍ እየተገለፀ ነው

ኢትዮጵያና ግብፅ በአካባቢው የበላይነት ፉክክር ውስጥ መግባታቸው ተዘገበ

የሙባረክ በፍርድ ቤት ነፃ መባል ግብፃዊያንን ለሁለት ከፈለ

ደቡብ አፍሪካ ህገወጥ ያለቻቸውን ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አሰረች

ታንዛኒያ ከዓመት በላይ ያሰረቻቸውን ከ250 በላይ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደ አገራቸው ላከች

የኬኒያ ፍርድ ቤት አገሪቱን ከኢትዮጵያና ከሱዳን ጋር ያገናኛል የተባለውን ግዙፍ የወደብ ፕሮጀክት አገደ

የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች የአንድ ሳምንት ዘመቻ ዛሬ ተጠናቀቀ

በአንድነት ፓርቲ ፅ/ቤት ከህሊና እስረኛ ቤተሰቦች በተገኙበት የዘመቻ መዝጊያ ተካሔደ

የታገደችው የፍትህ ጋዜጣ ባልደረባ ስርዓቱን ልንገዳደረውና በአገር ጉዳይ ላይ ሁላችንም ሊያገባን ይገባል ሲል ጥሪ አስተላለፈ

ሁበር ለጊዜያዊው እግድ በዘላቂነት መፍትሔ ለመፈለግ የጀመረውን ትግል በህግ ሰጭዎቹ ወይም በፍ/ቤት በኩል እንደሚቀጥል አስታወቀ

ኔቫዳ በአሜሪካ ሁበርን በማገድ የመጀመሪያ ግዛት መሆኑ ተዘገበ

በሎስ አንጀለስ አንድ የሁበር አሽከርካሪ በደንበኞቻቸው ድብደባ ተፈጸመባቸው

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

↧
↧

የሐበሻ ሬስቶራንት ሥራ አስኪያጅ ድምፃዊት ኢየሩሳሌም አስፋው (ጄሪን) ለምን ውስጥ እግሯን እና ታፋዋን በቢለዋ ወጋቻት? (ያንብቡ)

$
0
0

ድምፃዊት ኢየሩሳሌም አስፋው (ጄሪ) በሙዚቃ አፍቃሪያን ዘንድ ‹ሀሎ አዲስ አበባ› በተሠኘ ተወዳጅ ዘፈኗ ትታወቃለች፡፡ እስካሁን ድረስ ሁለት የሙዚቃ አልበሞች የሠራች ሲሆን ስድስት ያህል ነጠላ ዜማዎችም አሏት፡፡ ከልጅነቷ ጀምሮ ባደረባት የሙዚቃ ፍቅር የተለያዩ ድምፃዊያንን ዘፈኖች ትጫወት የነበረ ሲሆን ታዋቂው ኮሜዲያን አለባቸው ተካ በችሎታዋ ተደንቆ በተወዳጁ ‹‹አለቤ ሾው›› የቴሌቪዥን ፕሮግራሙ ላይ እንግዳ አድርጓት ነበር፡፡ የተለያዩ ነጠላ ዜማዎች ከማውጣቷ ጎን ለጎን ሶስተኛ የሙዚቃ አልበሟን እየሠራች ባለበት በዚህ ወቅት ከሠዎች በተሠነዘረባት ጥቃት ያልተጠበቀ ጉዳት ደርሶባት ህክምና እየተከታተለች ትገኛለች፡፡ የቁምነገር መጽሔት ድምፃዊቷን ያለችበትን ሁኔታ አነጋግሯል፤ መልካም ንባብ
1425440_1379530885635493_1774138377_o
ቁም ነገር፡- ሙዚቃ መጫወት የጀመርሽው መቼ ነበር?
ኢየሩሳሌም፡- ወደ ሙዚቃ ህይወት የገባሁት በልጅነቴ ነው፡፡ ወላጅ አባቴ ከመሞቱ በፊት ‹‹ልጄ ዘፍና ትጦረኛለች›› ይል ነበር፡፡ አያቴ ግን አይፈቅድልኝም ነበር፡፡ ቀበሌ እሠለጥን በነበረበት ጊዜ ከሠባ አምስት ተወዳዳሪዎች መካከል አንደኛ ወጥቼያለሁ፡፡ በውድድሩ ላይ እኔ የምዘፍነው የንዋይን ነው ስላቸው ሳቁብኝ፡፡ ከዚያም የማርታ አሻጋሪን፣ የበዛወርቅ አስፋውንና የአስቴር ከበደን ዘፈኖች ዘፍኜ አሸነፍኩና እዚያ ጀመርኩ፡፡
ቁም ነገር፡-ከዚያ በኋላስ የት የት ሠርተሻል?
ኢየሩሳሌም፡- ሴሌክት የምሽት ክለብ ለሠባትና ስምንት ዓመት ያህል የሠራሁ ሲሆን ‹ሀሎ አዲስ አበባ›› የሚለው የመጀመሪያ የሙዚቃ አልበሜ ከወጣ በኋላ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ የራሴን ምሽት ክለብ ከፍቼ መስራት ጀምሬ ነበር፡፡ ግን አላዋጣኝም፡፡ ከዚያ ደግሞ ‹‹ከሚሚ መጋሎ››፣ ሐሊማ አብዱረህማን እና ከዝናሽ (ሀቢቢ) ጋር በጋራ የምሽት ክለብ ከፍተን ለመስራት ሞክረን ነበር፡፡ በመሀል ልጅ ወለድኩና አቋረጥኩኝ፡፡
ቁም ነገር፡- ወደ ሐበሻ ሬስቶራንት ገብተሽ መዝፈን የጀመርሽው መቼ ነበር?
ኢየሩሳሌም፡- ከአምስት ከስድስት ዓመት ምናምን በፊት ነው፡፡ በ2005 ዓ.ም ሮዛ ግዛው በተባለች ማናጀሬ በኩል ወደ ዱባይ ሄጄ ከታንዛንያ፣ ከናይጄሪያና ከኮንጎ የሙዚቃ ባለሙያዎች ጋር እየሠራሁ ሙሉውን ዓመት አሣልፌያለሁ፡፡ ገራጅ የሚባል የምሽት ክበብ ነበር የምንሠራው፡፡ እንዲያውም ሌሎቹ ባለሙያዎች በየሶስት ወሩ ሲቀያየሩ እኔ ምንም ቪዛ ሳልቀይር እዚያው መቆየት ችያአለሁ፡፡ ክለቡ ከሠባት መቶ እስከ ስምንት መቶ የሚደርሡ ሰዎች ይይዛል፡፡
የጊኒ፣ የታንዛኒያ፣ የናይጄሪያ፣ የኬንያ ዜጎች እንዲሁም አረቦችና ህንዶች የሚዝናኑበት ሲሆን አንዳንድ አበሾችም አልፎ አልፎ ይመጡ ነበር፡፡ ሽልማታቸው፣ ፍቅራቸው ሁሉ ልዩ ነው፡፡ የእነሡን ሙዚቃ የምሠራላቸው ያህል በተለያየ ሁኔታ ነው የሚያዩኝ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ዘፋኝ አይተን አናውቅም ብለው ነበር ገንዘብ የሚሸልሙኝ፡፡
ቁም ነገር፡- ሐብታም ሆነሽ ነበራ ከውጪ የመጣሽው? (ሣቅ)
ኢየሩሳሌም፡- ብዙ ቤተሠብ ነው ያለኝ፡፡ ቤት ተከራይቼ ነው የምኖረው፡፡ ዱባይና አቡዳቢ እየተመላለስኩ ቤተሠቦቼን ነበር የምረዳው፡፡ ያስተማርኳቸው፣ የዳርኳቸው አሉ፡፡ ለእኔ ብዬ ያደረኩት ነገር የለም፡፡
ቁም ነገር፡ እስካሁን ድረስ ምን ያህል የሙዚቃ አልበሞች ሠርተሻል?
ኢየሩሳሌም፡- የመጀመሪያ አልበሜ ‹ሀሎ አዲስ አበባ› የሚለው ነው፡፡ በ1997 ዓ.ም በህዳር ወር ነበር የወጣው፡፡ ‹ይጠራኛል› የሚል ሌላ አልበምም አሣትሜ ነበር፡፡ በአጋጣሚ የክቡር ዶክተር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ ህይወት ያለፈበት ቀን ላይ ነበር ሣይታሠብ የወጣው፡፡ በዚህ ምክንያት ሣይደመጥ ቀረ፡፡ በ2006 ዓ.ም ከዱባይ የመጣሁት ለአልበም ሥራ ነው፡፡ የአልበም ሥራ መስራት ጀምሬያለሁ፡፡ የሁለት ዓመት ቪዛ እያለኝ ነው የአልበም ሥራዬን ለመጨረስ የመጣሁት፡፡ ጥሩ ጥሩ ግጥምና ዜማዎች ሠብስቤያለሁ፡፡ ከአለማየሁ ይለፍ ጋር ነው የምሠራው፡፡
ቁም ነገር፡- የተለያዩ ነጠላ ዜማዎችም አሉሽ አይደል?
ኢየሩሳሌም፡- አዎ! ከ‹ሀሎ አዲስ አበባ› አልበሜ በኋላ ያወጣሁት ‹ጀነናው› የሚል ነጠላ ዜማ አለ፡፡ የሄለን በርሄ ‹‹ኦዛዛ አሌና›› የተሠኘው ዘፈን ያለበትና የሌሎች ዘፋኞችንም ሥራዎች የያዘ ፣‹ድሪም ኮሌክሽን› የሚል አልበም ላይ የተካተተ ነበር፡፡ ‹አግባ አግቢ› የሚል ነጠላ ዜማም ሠርቼያለሁ፡፡ ‹ደቅ ላይ› የሚል የባህል ዘፈን፣ ‹ዞማ ዞማ› የሚል በኮንሶ ስልት (ሪትም) የተሠራ ነጠላ ዜማም አለኝ፡፡ የተለያዩ ቪዲዮ ክሊፖችንም እሠራለሁ፡፡ አላረፍኩም፡፡ እለፋለሁ፡፡ በጣም እለፋለሁ፡፡ የተቀመጥኩበት ጊዜ የለም፡፡ እንደኔ የሚለፋ ሠው ያለ አይመስለኝም፡፡ ለምን እግዚአብሔር ይህን እንዳደረገ አላውቅም፡፡
ቁም ነገር፡- ቅድም ልጅ እንዳለሽ ነግረሽኛል፡፡ የትዳር ሁኔታ ግን አላነሣንም?
ኢየሩሳሌም፡- ልጅ ወልጄያለሁ፡፡ አባቱ ከእኔ ጋር አይኖርም፡፡ ተለያይተናል፡፡
ቁም ነገር፡- ስንት ዓመቱ ነው?
ኢየሩሳሌም፡- እግዚአብሔር የተመሠገነ ይሁን ስምንተኛ ዓመቱን ይዟል፡፡ ልደቱን ለማክበር ሶስት ቀን ሲቀረው ነው የታረድኩት፡፡

ድምፃዊት እየሩሳሌም እግሯን እና ታፋዋን ከተሰፋች በኋላ

ድምፃዊት እየሩሳሌም እግሯን እና ታፋዋን ከተሰፋች በኋላ

ቁም ነገር፡- በቅርቡ አንድ አደጋ ደርሶብሽ እንደነበር ሠምተናል፡፡ ምን ነበር ምክንያቱ? ሁኔታው እንዴት ተፈጠረ?
ኢየሩሳሌም፡- ‹እስማማለሁ አልስማማም› በተሠኘው የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ እንግዳ ሆኜ ቀርቤ ነበር፡፡ እና ፕሮግራሙ በሚለቀቅበት ምሽት ቀድሜ ነው ወደ ሐበሻ ሬስቶራንት የገባሁት፡፡ ለምሽት ስራዬ ዝግጁ ሆኜ ሚኒስከርት ለብሼና ሂል ጫማ አድርጌ ነው ወደ ሬስቶራንቱ የገባሁት፡፡ ሰው ገብቷል ሙዚቃ ግን አልተጀመረም፡፡ ለባለቤቱ ደውዬ የሙዚቃ ስራ እስከሚጀመር ቴሌቪዥን እንዲያስከፍትልኝ ስነግረው እርሡ ለማናጀሯ ደውሎ ‹‹ሙዚቃ አልተጀመረም›› ሲላት ከእኔ ጋር መነጋገር ትጀምራለች፡፡ ከእሷ ጋር ስንነጋገር ሁለቱ የሬስቶራንቱ አስተናጋጆችሙዚቃ እንዳልጀመረ ለምን ነገርሽው በማለት መጥተው አንዷ ገፍታ ጥላኝ ላዬ ላይ ወጣች፤ ሌላኛዋ ደግሞ ፀጉሬን ያዘችኝ፡፡ በዚህ መሀል ማናጀሯ ቢላ ይዛ መጥታ የግራ እግሬ መሀል ታፋዬ ላይ፣ ቀኝ እግሬ መቀመጫዬ ላይ እና የቀኝ ውስጥ እግሬን ትወጋኛለች፡፡ የሠውነቴ መጋጋጥ የሚነገር አይደለም፡፡ በወቅቱ ራሴን ስቼ ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ፍርድ ይስጠኝ፡፡ የደረሠብኝን ጉዳት እንደዚያ ተቀድጄ ሠውነቴ እየደማ ለሆቴሉ ባለቤት ሄጄ አሣየሁት፡፡ እሡ ሀሌሉያ ክሊኒክ ወስዶ ህክምና እንዳገኝ አደረገ፡፡ ከዚያም ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄጄ አስመዝግቤ ሁለቱ ሴቶች በቁጥጥር ስር ሲውሉ የሬስቶራንቱ ማናጀር ትጠፋለች፡፡ በቢላ የወጋችኝ የሬስቶራንቱ ማናጀር ለአሥራ ሁለት ቀናት ጠፍታ የእነርሡን መታሠር ስትመለከት ለፖሊስ እጇን ሰጠች፡፡ አሁን ሶስቱም በሦስት ሺህ ብር ዋስ ተፈትተው የፍርድ ቤት ቀጠሮ እየተጠባበቅን ነው፡፡
ቁም ነገር፡- አድናቂዎችሽስ የደረሠብሽን ነገር ሲመለከቱ ምን ተሠማቸው?
ኢየሩሳሌም፡- ማመን ከምችለው በላይ ነው የሠው ምላሽ፡፡ ‹ስንት ዓመት ጠፍተሽብን የመጣሽ ልጅ ምን ብታደርጊያቸው ነው ይህን ያደረሡብሽ› ብለውኛል፡፡ ያላዘነ፤ የማያለቅስ የለም፡፡ ከሱዳንና ከዱባይ እየደወሉ ሲያለቅሱ እኔንም ያስለቅሡኛል፡፡ ብዙ ቦታዎች ላይ መወጋቴ ነው ትልቁ አደጋ፡፡ ደም በብዛት ነበር የፈሠሠኝ፡፡
ቁም ነገር፡- አደጋውን ካደረሱብሽ ሠዎች ጋር የቆየ ቂም ነበራችሁ?
ኢየሩሳሌም፡- ማናጀርዋ ወደ ሬስቶራንቱ ከመጣች ዘጠኝ ወሯ ነው፡ ፡ ሁለቱ ደግሞ ከአስር ዓመት በላይ የቆዩ አስተናጋጆች ናቸው፡፡ መሀል ላይ ማናጀሯ ደሞዝ ስትቆርጥ፣ ሠራተኛ ስታባርር ለምንድነው ይህን የምታደርጊው እያልኩ እናገር ነበር፡፡ ያ ነገር ነው እዚህ ደረጃ ያደረሰን፡፡ ለሠሚም፣ ለተመልካችም፣ ለራሴም ነው (የደረሠብኝ ጉዳት) ትንግርት የሆነብኝ፡፡ እንደተገረዘ ህፃንነበር ቆሜ የምሸናው፡፡ ለሥራ ወጥቼ ያልሆነ ነገር ሆንኩኝ፡፡ ወይ እንደ ጓደኞቼ እንደሚካያ እና እንደ ኢዮብ መኮንን ታምሜ ሰው ሠምቶ ብሞት የተሻለ ነበር፡፡
ቁም ነገር፡- አሁን ያለሽበት ሁኔታ እንዴት ነው? ጤንነትሽ?
ኢየሩሳሌም፡- ከሠባት ቀን ህክምና በኋላ የቤቱ ባለቤት እኔን ማሣከም አቁሟል፡፡ የጭንቅላቴን ውጤት መስማት አልተቻለም፡፡ ህክምና ላይ ያለው ነገር በሙሉ ቆሟል፡፡ የሁለት ወር ደመወዝም አልተሠጠኝም፡፡ ቤተሰቦቼ፣ ጓደኞቼና እኔ ራሴ ነኝ እየተሯሯጥን ያለነው፡፡ አሁን ቤት ውስጥ ነው ያለሁት፡፡ መጥቶም፣ ጠይቆኝም አያውቅም፡፡ የውስጥ እግሬና ጭንቅላቴ አሁንም ያመኛል፡፡ አንደኛው ስካን ማድረጊያ መሣሪያ በሀገር ውስጥ የለም ተብሎ እየፈለግኩኝ ነው፡፡ እግሬ በጣም ነው የተጎዳው፡፡ ውስጥ እግሬ ድረስ ነ በር የተወጋሁት፡፡ ሌላውን የልጄ አምላክ አትርፎኛል፡፡
ቁም ነገር፡- ከዚህ በኋላ አበሻ ሬስቶራንት ተመልሠሽ የምትሠሪ ይመስልሻል?
ኢየሩሳሌም፡- በፍፁም፡ ፡ አሁን ለሦስተኛ ስራዬ ‹‹ውብ አዲስ አበባ›› የሚል ትልቅ ፖስተር (አበሻ ሬስቶራንት) ለጥፌያለሁ፡፡ ሰው እኔን ብሎ ነው የሚመጣው፡፡ ማናጀሯ ግን አርቲስትነቴን እንኳን አላየችውም፡፡
ቁም ነገር፡- ከዚህ ቀደም ‹‹ሐሎ አዲስ አበባ›› የሚል የሙዚቃ አልበም አሣትመሻል፡፡ አሁን ደግሞ ‹‹ውብ አዲስ አበባ›› የሚል አልበም ነው እየሠራሽ ያለሽው፡፡ አዲስ አበባ ላይ የተለየ ትኩረት የሰጠሽበት ምክንያት ምንድን ነው?
ኢየሩሳሌም፡- ጨርቆስ ነው ተወልጄ ያደግኩት፡፡ ከወላጅ አባቴ ቤተሰቦች ጋር ነው ያደግኩት፡፡ አዲስ አበባ አገርህ ናት፤ መለያህ ናት፡፡ ውጪ ሀገር በምሔድበት ወቅት ይከፋኛል፡፡ እዚህ ደግሞ አየሩ ያምራል፡፡ ባህል አለኝ፡፡ ያለው ለሌለው ያበድራል፡፡ እዚያ ናፍቆት አለ … ብዙ ነገር አለው፡፡
አሁን የምሠራው ‹‹ውብ አዲስ አበባ›› የሚል አልበም ደግሞ የአሁኗ አዲስ አበባ መጀመርያ ከነበረችው የተለየች መሆኗን የሚያሳይ ነው፡፡
↧

የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እሰረኞች የመዝጊያ መርሀ ግብር በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ!

$
0
0

ከህዳር 14 ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ያህል በማህበራዊ ሚዲያ ሲካሄድ የሰነበተው የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እሰረኞች መርሀ ግብር ዛሬ እሁድ ህዳር 21 የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች በክብር የተጋበዙ እንግዶች በተገኙበት ቀበና በሚገኘው የአንድነት ዋና ጽ/ቤት በደማቅ ስነርዓት ተካሄዷል። በዚህ ዕለት ጋዜጠኛ ሃይለመስቀል ሸዋምየለህ ጋዜጠኝነትና የእስር ፖለቲካ በሚል ርዕስ ፅሁፍ ያቀረበ ሲሆን ስርዓቱ በደንብ ልንገዳደረውና ሀገር ጉዳይ ላይ እኛም እንደሚያገባን ልናሳየው ይገባል የሚል መልዕክት አስተላልፏል። ከዚህም በተጨማሪ በዚሁ የመዝጊያው ስነስርዓት ላይ የህሊና እስረኞች ቤተሰቦችም ተገኝተው ንግግር አድርጓል።

10801908_736236639794606_9187664140258709230_n 10250308_736236993127904_6572687959640040337_n 10734030_736237036461233_491920497824514999_n10801820_736236813127922_2029697978365008761_n

↧

Hiber Radio: በመስቀል አደባባይ ለተጠራው የአዳር የተቃውሞ ሰልፍ የአደባባይ ቅስቀሳ ይጀመራል፤ ሁበር በኔቫዳ ታገደ

$
0
0
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ህዳር 21 ቀን 2007 ፕሮግራም !

 

አቶ ወረታው ዋሴ የሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ሀላፊ በመስቀል አደባባይ የተጠራውን ተቃውሞ አስመልክቶ ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረጉት ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)

በጥቁሩ ወጣት ላይ የተፈጸመው ግድያ እና ጥቁርነት እና የአሜሪካ የሕግ አስከባሪዎች እርምጃ ተቃውሞውና ይዟቸው የመጣው የዘር መድልዎ እርምጃ እርምጃዎች (ልዩ ዝግጅት)

የኦባማ ኬር ዳግም ምዝገባና የአይ ኤር .ኤስ ቅታት ባልተመዘገቡት ላይ (ልዩ ቃለ መጠይቅ ከአቶ ተካ ከለለ በአትላንታ የቲኬ ሾው አዘጋጅ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ ሁለተኛ ክፍል))

ዜናዎቻችን
በመስቀል አደባባይ ለተጠራው የአዳር የተቃውሞ ሰልፍ ከነገ ጀምሮ የአደባባይ ቅስቀሳ ይጀመራል

ሕዝቡ ከወዲሁ በተለያዩ መንገዶች የተቃውሞውን ጥሪ እንደሚደግፍ እየተገለፀ ነው

ኢትዮጵያና ግብፅ በአካባቢው የበላይነት ፉክክር ውስጥ መግባታቸው ተዘገበ

የሙባረክ በፍርድ ቤት ነፃ መባል ግብፃዊያንን ለሁለት ከፈለ

ደቡብ አፍሪካ ህገወጥ ያለቻቸውን ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አሰረች

ታንዛኒያ ከዓመት በላይ ያሰረቻቸውን ከ250 በላይ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደ አገራቸው ላከች

የኬኒያ ፍርድ ቤት አገሪቱን ከኢትዮጵያና ከሱዳን ጋር ያገናኛል የተባለውን ግዙፍ የወደብ ፕሮጀክት አገደ

የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች የአንድ ሳምንት ዘመቻ ዛሬ ተጠናቀቀ

በአንድነት ፓርቲ ፅ/ቤት ከህሊና እስረኛ ቤተሰቦች በተገኙበት የዘመቻ መዝጊያ ተካሔደ

የታገደችው የፍትህ ጋዜጣ ባልደረባ ስርዓቱን ልንገዳደረውና በአገር ጉዳይ ላይ ሁላችንም ሊያገባን ይገባል ሲል ጥሪ አስተላለፈ

ሁበር ለጊዜያዊው እግድ በዘላቂነት መፍትሔ ለመፈለግ የጀመረውን ትግል በህግ ሰጭዎቹ ወይም በፍ/ቤት በኩል እንደሚቀጥል አስታወቀ

ኔቫዳ በአሜሪካ ሁበርን በማገድ የመጀመሪያ ግዛት መሆኑ ተዘገበ

በሎስ አንጀለስ አንድ የሁበር አሽከርካሪ በደንበኞቻቸው ድብደባ ተፈጸመባቸው

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live