Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ስምንት ጠቃሚ ነጥቦች ከእስራኤላውያን -ክፍል 3 (ዮፍታሔ)

$
0
0

ዮፍታሔ

  1. የተጋረጠውን ፈተናና መፍትሔውን ዓለምአቀፋዊ ማድረግ።

Jewish+Ethiopians+Reunited+Families+Israel+o1h5oGhsf2Vlበጊዜው ይሆናል ተብሎ ሊታሰብ የማይችለው የእስራኤላውያን ወደ እስራኤል ተመልሶ መሰብሰብና ሕጋዊ የአገር ምስረታ ሊሳካ ከቻለባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱ የነበረባቸውን ችግር፣ ወደ ፍልስጤም የመሰባሰባቸውንና አገር የመመሥረታቸውን እቅድ የነርሱ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሌሎችም ሕዝቦች፣ መንግሥታትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጉዳይና ኃላፊነትም እንዲሆን በማድረጋቸው ነው።

ይህ በተለያየ መንገድ ተከናውኗል። በመጀመሪያ ብዙኀኑ የአውሮፓ አገሮች ቀድሞውንም አይሁዳውያንን ከየከተሞቻቸው በማስወገድ በካምፕ ውስጥ ማስፈር የለመዱትና የሚፈልጉትም ስለነበረ ለአይሁዳውያን መሪዎች ይህንኑ የአውሮፓውያን ፍላጎት በመጠቀም ከየአገሮቻቸው ወጥተው በሌላ አገር ለብቻ ለመኖር እንዲፈቅዱላቸው ማሳመን ነበር። በዚህ አማካኝነት ከአይሁዳውያን ጋራ በተያያዘ በየአገሩ ይከሰት የነበረውን ግጭት፣ ይባክን የነበረውን ወጪ እና የንግድና የሀብት ፉክክር እንደሚያስወግዱ፤ የአይሁድ ነፃነት ለአውሮፓውያንም ነፃነት እንደሆነና አይሁድ በነፃነት ቢኖሩ ለዓለምና ለሰው ዘር በጠቅላላ ሊያበረክቱ የሚችሉትን አስተዋጽዖ በማጉላት እስራኤላውያንን ከየአገሩ አስወግዶ በራሳቸው አንድ አገር መሰብሰብ የሁሉም (በተለይም የሠለጠነው ዓለም) ኃላፊነት እንደሆነ ማሳመንና ሁሉም እንዲተባበር ማድረጋቸው ነው።

ቴዎዶር ሄርዝል ባሰራጨው መጽሐፉ የሚከተለው ይገኛል፦

“I consider the Jews question neither a social nor a religious one, even though it sometimes takes these and other forms. It is a national question, and to solve it we must first of all establish it as an international political problem to be discussed and settled by the civilized nations of the world in council”

ትርጉሙ፦ “ምንም እንኳን የአይሁድ ጥያቄ አንዳንዴ ማኅበራዊ፣ ሀይማኖታዊና ሌሎችንም ቅርጾች ቢወስድም እኔ የማየው እንደዚያ አይደለም። የአይሁድ ጥያቄ ብሔራዊ ጥያቄ ነው። እናም ችግሩን ለመፍታት በዓለም ጉባዔ በሠለጠኑት አገራት ውይይት ተደርጎበት እልባት ማግኘት ያለበት ዓለማቀፋዊ የፖለቲካ ችግር መሆኑን ከሁሉም አስቀድሞ ማረጋገጥ ያስፈልጋል”

የኢትዮጵያውያንም ጥያቄ ዛሬ አገር የማዳን ጥያቄ፤ ይህም ማለት ብሔራዊ ጥያቄ ከሆነ መቆየቱን ልብ ማለት ያስፈልጋል።

በሌላ በኩል ቴዎዶር ሄርዝል በዚህ ጥቅስ “civilized nations/ የሠለጠኑት አገራት” በማለት ለይቶ ኃያላኑን መንግሥታት መጥቀሱን እንመለከታለን። ይህ የሌላው ጠቃሚ ነጥብ አስኳል ስለሆነ በአእምሮአችን ሰሌዳ ይዘነው እንቆያለን።

በመጀመሪያው ጉባኤ ደግሞ ይህን ብሎ ነበር፦

The world will be liberated by our freedom, enriched by our wealth, magnified by our greatness. And whatever we attempt there for our own benefit will rebound mightily and beneficially to the good of all mankind”

ትርጉሙ፡ “በእኛ ነፃነት ዓለም ነፃነቱን ያገኛል፣ በሀብታችን ይበለጽጋል፣ በታላቅነታችን ይጎላል። እናም በዚያ (በእስራኤል) ለራሳችን ጥቅም ብለን የምንጣጣርበት ማንኛውም ነገር በሙሉ ኃይሉና ጠቃሚነቱ ተመልሶ ለመላው የሰው ዘር የሚበጅ ይሆናል።”

 

በሌላ በኩል በአይሁዳውያን ላይ ይደርስ የነበረውን ጭቆናና ጥቃት እየተከታተሉ ማጋለጥና የሁሉም አገሮች ሕዝቦች፣ መንግሥታትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ከሰብዓዊ መብት አኳያ ኃላፊነት እንዳለባቸው ማስገንዘብና ይህ እንዲቆም መላው ዓለም የነርሱን እቅድ እንዲደግፈው ማድረግ ነው።

 

ሦስተኛው ደግሞ ባፈረጠሙት የገንዘብ፣ የድርጅትና የግንኙነት አቅማቸው ተጽእኖ የሚፈጥሩ መንግሥታትን፣ ድርጅቶችንና ግለሰቦችን በማግባባት የነርሱ ችግር ዓለማቀፋዊ ችግር እንደሆነ እንዲያንጸባርቁና የእስራኤልን መመሥረት እንዲደግፉ በማግባባት የተሠራው ሥራ ነው።

 

በዚህ ዓይነት በየደረጃው በመጀመሪያ እንግሊዝ እንድትቀበለው በማድረግ ቅኝ ገዢዋ (ሞግዚቷ) የተቀበለችውን ደግሞ ሌሎች አገሮችና የተባባሩት መንግሥታት ሊቀበሉት ችለዋል።

 

የደቡብ አፍሪካውያን ነፃነት እውን እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካደረጉት ክንውኖች መካከል እነ ኦሊቨር ታምቦን (Oliver Tambo) የመሰሉ ቆራጥ ጀግኖች በውጭ እየተንቀሳቀሱ ትግሉን ከደቡብ አፍሪካ አውጥተው ዓለም አቀፋዊ ማድረግ መቻላቸው እንደሆነ በግልጽ ታይቷል። እነ ኦሊቨር ታምቦ በውጭ ያደረጉት ትግል ዳያስፖራው ምን ያህል አቅም እንዳለው በግልጽ ያሳየም ነበር። የደቡብ አፍሪካ የትግል ታሪክ ራሱን የቻለ አያሌ ትምህርቶች የሚገኝበት ነው። ወደፊት በሌላ ርእስ መመልከት ያስፈልጋል።

 

እኛስ በአገራችንና በወገናችን የተጋረጠውን ፈተና ዓለም-አቀፋዊ ማድረግ የማንችልበት ምክንያት ምንድን ነው? እኛስ በረሀብ፣ በድህነትና በኋላቀርነት ምክንያት ሌላውን ዓለም አላስመረርንም? እኛስ ለባጀታችን በቢሊየኖች የሚቆጠር ገንዘብ ከአደጉት አገሮች እየተደጎምን በመኖር ለጋሽ አገራትን አላስመረርንም? እኛስ አውሮፓን፣ ሰሜን አሜሪካን፣ አውስትራሊያንና እስያን በስደት አላጨናነቅንም? ዛሬ የኢትዮጵያውያን የሰብዓዊ መብት አያያዝ በኢትዮጵያና በአረብ አገራት የማያሳስበው የሰብዓዊ መብት ድርጅትና የዓለም መንግሥት ይገኛልን? በስደት በውኃ የሚወሰዱና በኮንቴይነር ሞተው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ራስ ምታት ያልሆነው የቅርብ ጎረቤትና የሩቅ መንግሥት ይኖራልን? የኢትዮጵያ ጉዳይ በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ደረጃውን ባልጠበቀ የሕፃናት የማደጎ ዝውውር (ሽያጭ) እና በውስጥ አካል ችርቻሮ ከእኛ አልፎ ከሕግና ከሞራል የተነሣ ችግሩ ያላንኳኳው መንግሥት ይኖራልን?

 

እኛስ ዘርን ማዕከል ባደረገ አፓርታይድን በሚያስንቅ አገዛዝ ሥር መሆናችን ለዓለም ይመቸዋልን? ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ፣ ኃያላን መንግሥታትና ጎረቤት አገራት ከአሁኑ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን በመቆም ለጋራ መፍትሔ ካልተባበሩ ሕወኀት በኃይል ተገፍቶ በሚወድቅ ጊዜ ሊፈጥረው የሚችለው ያለመረጋጋት ለሽብርተኝነት ተጨማሪ እድል በመፍጠር ኃያላኑን መንግሥታትና መላውን ሰላም ወዳድ ዓለማቀፍ ማኅበረሰብ አያሳስባቸውምን?

 

ይህ ሁሉ የሚያሳስባቸው እንደሆነ ግልጽ ነው። በየጊዜው ከሚወጡት ሪፖርቶችና ዜናዎች የምንረዳውም ይህንኑ ነውና። ይህ ከሆነ ለኢትዮጵያውያን ትግሉንና መፍትሔውን ዓለማቀፋዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎችም በርካታ መንገዶች እንዳሉ ለመረዳት አያስቸግርም ማለት ነው። መፍትሔ ከተገኘ ዓለማቀፉ ማሕበረሰብ ለመተባበርም ወደኋላ እንደማይል ግልጽ ነው። ነገር ግን ይህ እንዲሆን ችግሩን ሊያስወግድና አስተማማኝ ሥርዓት ለመመሥረት የሚያስችል ተጨባጭ እቅድ ይዞ መቅረብ ይጠበቅብናል፤ ሳንሰለች ደጋግመን በር ማንኳኳት ይጠበቅብናል፤ የዓለማቁፉን ማኅበረሰብ የሚያረጋጋና ለቀጣዩ ጊዜ ዋስትና የሚሰጥ ጠንካራ ድርጅታዊ ብቃት ማሳየት ይጠበቅብናል፤ ገንዘብ እንዲኖረን ሁሉንም ዓይነት ጥረት ማድረግና ሲኖረን ገንዘባችንን በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል። ይህን ማድረግ ስንችል ያለጥርጥር የኢትዮጵያ ጉዳይ ዓለማቀፋዊ ይሆናል። ያን ጊዜ ግፈኛውን አገዛዝ ማስወገድ ብቻ ሳይሆን አስተማማኝና ዘላቂ ሥርዓት በኢትዮጵያ መመሥረት አስቸጋሪ አይሆንም።

 

  1. የዳያስፖራው ወሳኝ ሚና

 

ከእስራኤል ታሪክ የምንማራቸው ብዙ አብይ ቁምነገሮች አሉ። ከነዚህ መካከል በአገር ላይ ለሚደረግ ማንኛውም በጎ ለውጥ ዳያስፖራው ወሳኝ ሚና ያለው መሆኑን በሚገባ መገንዘብ  ዋነኛው ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።

 

እ. ኤ. አ 70 ዓ.ም በኋላ አብዛኛዎቹ አይሁድ (የዛሬዎቹ እስራኤላውያን) በሌሎች አገሮች ቢበተኑም ከዚያ በፊትም ሆነ በኋላ በየትኛውም ዘመን በፍልስጤም የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ አይሁድ እንደነበሩ የሚታወቅ ነው። በውጭ ይኖሩ ከነበሩት አይሁድ ባልተናነሰ ብዙ ግፍ ይፈጸምባቸውም ነበረ። ይህ ሁሉ ሆኖ በፍልስጤም ይኖሩ የነበሩት አይሁድ በቅኝ ገዢዎቹ ላይ በማመጽና በመሳሰሉት አንዳንድ ሙከራዎች ከማድረግ ባለፈ መሠረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ተጨባጭ ነገር ማድረግ አልቻሉም።  በግፍ አገዛዝ አፈናና ተጽእኖ ውስጥ የነበሩ ከመሆኑም በላይ ራሳቸውን ነፃ ለማውጣትና አስተማማኝ ሥርዓት ለመፍጠር የገንዘብ፣ የእውቀት፣ የአስፈላጊ ቁሳቁስና የድርጅት ብቃት ሊኖራቸው አይችልም። በአገራችን ባለፉት 23 ዓመታት የታዘብነው ከዚህ የተለየ አይደለም። ምክንያቱ ግልጽ ነው። ዳያስፖራው አይሁዳዊ ግን የድርጅት፣ የገንዘብ፣ የአስፈላጊው ቁሳቁስ፣ የእውቀትና እንደልቡ ተንቀሳቅሶ ከተለያዩ መንግሥታት፣ ዓለም-አቀፍ ድርጅቶችና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጋር የመገናኘት እድሉና አቅም ነበረው። እነዚህን በመጠቀሙ ፈጽሞ ይሆናል ተብሎ ያልታሰበው በሚሊዮን የሚቆጠረው እስራኤላዊ መሰባሰብና የእስራኤል አገር ምሥረታ እውን ሊሆን መብቃት ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚ፣ በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በሚሊተሪ፣ በመረጃ፣ በሕክምና፣ በእርሻ ወዘተ በዓለም ጠንካራ ከሚባሉት ጥቂት አገሮች መካከል የምትመደብ አገር እንዲኖራቸው ለማድረግ በቅተዋል።

 

ወደራሳችን ስንመለስ የአገራችንን ችግር ያኔ ፍልስጤም በተለያዩ ቅኝ ገዥዎች ትገዛበት ከነበረው ዘመን ጋር የሚያመሳስለው ብዙ ነገር አለ። መልካቸው እኛኑ በሚመስሉ ሰዎች ምናልባትም ከቅኝ ገዢዎች በባሰ ሁኔታ ውስጥ የምንገኝ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ይህ የመጀመሪያው የሚያመሳስለን ነው። አፈናው፣ እመቃው፣ አደንቁሮ መግዛቱ፣ ሕዝቡን ከማንኛውም ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተሳትፎ ማግለሉ ቅኝ ገዢዎችን ያስንቃልና። በሌላ በኩል ግን ከያኔዎቹ የእስራኤላውያን ጠላቶች (በፍልስጤም ሮማውያን፣ ቱርኮችና እንግሊዝ፤ በውጭ አብዛኛው አውሮፓና ይልቁንም ጀርመን) ጋራ ወያኔን ስናነጻጽረው በየትኛውም ማወዳደሪያ እዚህ ግባ የማይባል ደካማ አገዛዝ መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል። ይህ ለነፃነት ናፋቂው ሕዝብና ለተቃዋሚዎች ትልቅ ጥቅም ነው።

 

ሁለተኛው ተመሳሳይነት ልክ እንደያኔው አይሁዳውያን ሁሉ በኢትዮጵያ ያለውን አፈና በመሸሽና የተሻለ ኑሮ ፍለጋ በተለያዩ የዓለማችን አገሮች ተሰዶ የሚኖር በሚሊዮን የሚቆጠር ኢትዮጵያዊ ዳያስፖራ በውጭ የሚገኝ መሆኑ ነው። ልዩነት ከተባለ በእስራኤል ጉዳይ የዳያስፖራው ቁጥር ፍልስጤም ውስጥ ይኖር ከነበረው አይሁዳዊ በቁጥር የሚበልጥ ሲሆን በኢትዮጵያ ጉዳይ በአገር ውስጥ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በዳያስፖራ ከሚኖረው በቁጥር የሚበልጥ መሆኑ ብቻ ነው። ይሁን እንጂ በጊዜው የነበረው አጠቃላይ አይሁዳዊ ዳያስፖራ ከኢትዮጵያዊው ዳያስፖራ በቁጥር ያለው ብልጫ ለውጥ ለማምጣት የሚያስፈልገውን ተጽእኖ በመፍጠር ደረጃ እዚህ ግባ የሚባል የጎላ የቁጥር ልዩነት አልነበረውም። ይልቁንም ኢትዮጵያዊው ዳያስፖራ (ልጆቹንም የትግሉ ተሳታፊ፤ የታሪኩ፣ የባሕሉና የቋንቋው ወራሽ በማድረግ በኩል የጎላ እንቅስቃሴ ማድረግ ያለበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ) በዘመኑ እንደነበረው ዳያስፖራ እስራኤላዊ አገሩን፣ ማንነቱን፣ ባሕሉን፣ ታሪኩን፣ ቋንቋውን ረስቶና በየሄደበት ተዋልዶና ተቀላቅሎ በአካል ብቻ ሳይሆን በመንፈስም ተበታትኖ የሚገኝ ያለመሆኑ የኢትዮጵያዊውን ዳያስፖራ አቅም ከእስራኤላውያኑ ዳያስፖራ ይልቅ የጠነከረና ውጤት ላይ ለመድረስም ትግሉን ከእስራኤላውያን የቀለለ ያደርገዋል። ሦስተኛው የሚያመሳስለን በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ የሁለተኛ ደረጃን ትምህርት ከማጠናቀቅ ጀምሮ እስከከፍተኛው የትምህርት እርከን ድረስ የተማረ፣ ለመረጃ፣ ለግንኙነትና ለቴክኖሎጂ ያኔ እስራኤላውያን ከነበሩበት ጊዜ በብዙ እጥፍ የተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑ ነው። ከፍተኛ የገንዘብም አቅም ያለው ስለመሆኑ ለቤተሰቦቹ ወደአገር ቤት በየዓመቱ የሚልከውን የገንዘብ መጠን (Remittance) ብቻ በማየት መገመት ይበቃል። አራተኛው እንደያኔው እስራኤላዊ ሁሉ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ዳያስፖራ በባእድ አገር መኖር፣ ባይተዋርነት፣ የዘር መድልኦ፣ ልጆቹን በማይቀበለው ባሕልና መጥፎ ልማድ ውስጥ ማሳደግ፣ በአገሩ ድህነትና ኋላቀርነት ምክንያት ዝቅ ተደርጎ መታየት ያንገሸገሸው፣ እልፍ ሲልም እንደያኔው እስራኤላዊ የባርነትን በሚመስል ሁኔታ በየአረብ አገራት በግርድናና ሰብአዊነትን በሚነኩ ሥራዎች የተሰማራና አልፎ ተርፎም በየሄደበት የሚታሰርና የሚገደል ነው። ከዚህ የበለጠ ማን ነፃነት እንዲናፍቀው ይጠበቃል!

 

ለዳያስፖራ አይሁዳውያን በነበረባቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ከምንም ተነሥተው (እንግሊዝን ከመሰለ ቅኝ ገዢ መዳፍ በመፈልቀቅ) አገርን የሚያህል ነገር ለመመሥረትና ብሎም ይህችን ትንሽ አገር በርካታ ጠላቶቿን የምትቋቋም ብቻ ሳትሆን ነፃ፣ ዲሞክራሲያዊትና የበለጸገች ለማድረግ ከቻሉ አገራችን ኢትዮጵያን ካለችበት ሁኔታ አውጥቶ ነፃ፣ ፍትሐዊትና የበለጸገች አገር ማድረግ ለዳያስፖራው ኢትዮጵያዊ በፍጹም አስቸጋሪ ሊሆን አይችልም። ለዚህም ነው በተለምዶ “ዳያስፖራው ነፃ አያወጣህም” የሚባለው አስተያየት ከሕወኀት ፕሮፖጋንዳ ወይም ከየዋሀን ተረት ተረትነት የማያልፈው።

 

ይሁን እንጂ ይህ እንዲሳካ አይሁድ በብቃት ያደረጉትና እኛ ሳንውል ሳናድር ማድረግ የሚጠበቅብን ነፃነት ፈላጊው ኢትዮጵያዊና ድርጅቶች በአንድ ጥላ ሥር የሚሰባሰቡበት ከሁሉም የተውጣጣ አንድ ጠንካራ ዓለም አቀፍ ድርጅት ማቋቋም ነው። በዚህ ድርጅት ጥላ ሥር ደግሞ ለአገር ግንባታ የሚሆኑ በተለያየ ዘርፍ ሥራ የሚሠሩ ከላይ የተጠቀሱትን የተለያዩ ተቋማት ማቋቋም ጊዜ ሳይሰጠው ሊከናወን የሚገባው ተግባር ነው። የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ መሆኑን ደጋግሞ ያስመሰከረው አክቲቪስት ታማኝ በየነ በቅርቡ ያቋቋመው የመረጃ ማዕከል አስፈላጊ ከሆኑት ተቋማት መካከል አንዱ ነው። ዳያስፖራው ይህን ማድረግ ይችላል። ይህን ማድረግ ሲችል ሕወኀትን ማስወገድ ብቻ ሳይሆን ተራራውን ወደጎን ሂድ ቢለው ይሄዳል። ሕወኀትን አስወግዶ በሁሉም የተሟላ አስተማማኝ ሥርዓት መመሥረትና አገራችንን በአጭር ጊዜ ከበለጸጉት አገሮች ተርታ ማሰለፍም ሕልም ብቻ አይሆንም። እውን ይሆናል።

 

በዚህ ወደ 4ኛው ነጥብ እናልፋለን።

 

(ይቀጥላል)

 

ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ ሥራ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!

 

 


ነፃነት ይቅደም (ባህር ከማል)

$
0
0

Freedomአንዳንዶች እንደሚሉት ሳይሆን በህወሃት የሚመራው  የኢትዮጵያ  ገዢ መደብ  በተናጠልም ሆነ በቡድን ደረጃ ተዳክሟል።በምድር ላይ ያለው እውነታ ይህንን ያመላክታል።ስርአቱ በመርበድበድ (in a state of panic ) ላይ  መሆኑን የሚጠቁሙ  ብዛት ያላቸው ምልክቶ እየታዩ ነው::

  1. ከ 23 አመታት በኋላ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ሰብስቦ ስለአብዮታዊ ዲሞክራሲ መስበክ፤
  2. ከ~95 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ 5% ብቻ የኢንተርኔት ተጠቃሚ በሆነበት “በፌስቡክና ትዊተር ሀዝቡ በተሳሳተ መረጃ እንዳይወናበድ በአግባቡ ለመጠቀም” በሚል ሰበብ ስልጠና መስጠት፤
  3. ባንዲራችንን ጨርቅ (rag ) ነው እንዳላሉ ዛሬ ባንዲራ “ተዋረደ ተረገጠ” ብሎ ያዞ እምባ ማንባት፤
  4. ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ስለነበረች የኤርትሪያ ጥያቄ ከቅኝ ግዛት ነፃ የመውጣት ጥያቄ ነው ሲሉ ቆይተው ዛሬ ከ40 አመት በኋላ ቃላቸውን አጥፈው የኢትዮጵያን ህዝብ ለማጭበርበር “በኤርትራ ጉዳይ የያዝነው አቋም በጉዳዩ ላይ ተገቢ ጥናትና ምርምር ሳይደረግ ነው ” ማለት፤
  5. ትናንት “የአሰብ ወደብ ጉዳይ ከሸቀጥ ተለይቶ አይታይም” እንዳላሉ ዛሬ “ወደብን ገዝቶ ከመጠቀም በዘለለ አኳሃን መነጋገር አስፈላጊ ነው” ብሎ ማውራት፤
  6. እየተጠናከረ የመጣውን የዲያስፖራን ተቃውሞ ” የሚቋቋም ግብረሃይል እንዲመሰረት” ጥሪ ማቅረብ;….ወዘተ ከብዙ የመርበትበት ምልክቶች ጥቂቶቹ ናቸው።

ይህማለት ደግሞ ሥርአቱ መግዛት አቅቶት በራሱ በሚወድቅበት ደረጃ  ላይ ደርሷል ማለትም አይደለም።የግድ የሚገፈትረው የተባበረ ጡንቻ ያስፈልገዋል

የተቃዋሚ/የአማርጭ ሃይሎች ትግሉ በተጠናከረ ሁኔታ እንዲቀጥልና የገዢው ቡድን መግዛት አቅቶት እስኪወድቅ ከመጠበቅና  ሊከሰት ከሚችል ቀውስ አገሪቱን ለማዳንና ህዝቡን ለመታደግ  የተያዘው ትግል ተጠናክሮ መቀጠል የኖርበታል።

መደረግ/መጠናከር ከሚገባቸው ውስጥ ጢቂቶችን መጥቅስ ቢያስፈልግ፤

  1. ከኔ ሌላ አዋቂ የለምና እኔን ብቻ አድምጡኝ/ተከተሉኝን ማቆም።
  2. በፖለቲካ ፓርቲዎችና በሌሉችም ህዝባዊ ድርጅቶች መሃከል አስፈላጊ ያልሆነ ውድድሮችን መግታት፤
  3. አገርውስጥም ሆነ ካገር ውጭ ያሉት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ህዝባዊ ድርጅቶች ህብረተሰቡን ለውይይት ሲጠሩ  ከመድረክ ላይ በሚቀርቡት ገለጻውችና በህወሃት ውንጃላዎች የሰብሰባውን ሰአት ከማባከን እንዴት ስርአራቱን ማስወገድ እንደሚቻል ለታዳሚዎች ሰፊ የውይይት ጊዜ መስጠት።ይህ ደግሞ የህብረተሰቡን ተሳፎ ከመጨመሩም ሌላ የትግሉ በለቤትነትን ያጥናክራል፤
  4. በፖለቲካ ፓቲዎችና በሌሉችም ህዝባዊ ድርጅቶች አባላት መሃከል የመደማመጥ፤የመቻቻል፤ችግሮችን በጊዜ የመፍታት፤በብዙሃን የበላይ ነት የመመራት፥ወዘት ባህልን ማዳበር። ይህ ደግሙ በበኩሉ የድርጅቶችን ዲሞክራሲአዊ አሰራርን፤ጠንካራ ድርጅታዊ ሰነ-ምግባርን፡ ያጠናክራል።አባላት በሆነ ባልሆነ  ባኮረፉ ቁጥር በድርጅቶቻቸው ስሞች  ላይ ዲን D) በመቀጠል ሌላ አዳካሚ ድርጅት እንዳይ መሰርቱ ያደርጋል (በአሁኑ ወቅት አንዳንድ ድርጅቶች ባልጠፋ ስም  የመጀመሪያውን የድርጅታቸውን ስም እንደያዙ እስከሶት እንደተከፈሉ እየሰማን ነው)፤
  5. ከተቻለ ወህደትን አሊያም ግንባር በመፍጠር ጡንቻቸውን ማጠናከር።በጋራ ሊያስማማን በሚችል ላይ በማተኮርና በልዩነት ላይ በመቻቻል ከሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በጋራ ለመስራት ጥረት ማድረግ ያ ካልተቻለ ደግሞ መጠላለፍን መቆም ይበጃል።ወደጎን መጎሻሸም ማብቃት አለበት። ለህወሃት እንጂ ለማንም አይጠቅምምና፤
  6. ትግሉ ያለው አገር ቤት ነው እዚህ ያለው (ዳያስፖራው)ምንም ሊያደርግ አይችልም የሚባለውን በጥሞና ማየት።በዳያስፖራው ያልታገዘ በተለይም በታዳጊ አገሮች አንድም ለውጥ አልተካሄደም። በርግጥ መሪውን (Steering wheels  )ይዞ የለውጥን ባቦር የሚያሽከረክረው አገር ቤት ያለው ህዝብ መሆኑ የሚካድ አይደለም። ሆኖም ዳያስፖራው በነጻነት ሃሳቡን በሚገልጽበትና የተሻለ የምጣኔ ሃብት ባላቸው አገሮች  ስለሚኖር መረጃን  በማቀበልና  የድርጅቶችን አቅም በመገንባት ከፍተኛ አስተውጽኦ አለው።ለዚህም ነው በህወሃት የሚመራው “መንግስት”  ጥቂቶች ናቸው እያለ ነጋ ጠባ ስለ ዳያስፖራው የሚያለቃቅሰው።የፖለቲካ ድርጅቶች ለግባቸው መሳካት በሚያመነጩት አማራጭ ሃስብ ብቻ ሳይሆን በምጣኔ-ሃብትም ጠንካራ መሆን ይኖርባቸዋል። በተለይም  ህወሃት ይህንን ጠንቅቆ ያውቀዋል።በታላቁ የ1984 ዓም ድርቅ ወቅት ቆሜለታለሁ ይል የነበረው ህብረተብ በረሃብ ሲያልቅ ህወሃት የርዳታ ስንዴን ለአቅም መገምቢያ ያደርግ ነበር፤የሃውዜንም እልቂት ያቀነባበሩት ከፖለቲካ ድጋፍ በተጨማሪ የምጣኔ ሃብት  አቅም ግንባታን ከውጭ በእርዳታ መልክ ለማጠንክር ነው።በለስ ቀንቷቸው ቤተ መንግስቱን እንደተቆናጠጡ በ EFFORT ስም የጀመረቱ የኢኮኖምውን ዘርፍ የተቆጣጠሩት በሚያራምዱ ርዕዮታ-አለም ብቻ ያለህዝብ ድጋፍ ስልጣኑን እንደጨበጡ መቆየት የማይችሉ መሆናቸውን ስለሚያውቁ ነው፤
  7. የምዕራባውያን ድጋፍ በተለይም የኢኮኖሚው ድጋፍ ባይኖረው ይህ በህወሃት የሚመራው “መንግስት”  አንድቀንም ውሎ ባላደረ ነበር።ለዝህም በ97 ምርጫ ማግስት በተካሄደው ህዝባዊ ዘመቻ በተወሰነ መልኩ እርዳታ በመቋረጡ ምንያል ህወሃት እነደተደናበረ ማስታወሱ በቂ ነው።ስለዚህ ይህንን የገቢ ምንጭ  (ያለ “መንግስት” ጣልቃገብነት የሚሰጠውን ሰብአዊ እርዳታን ሳይጨምር)እንዲደርቅ በማደረግ ላይ ያለው አመርቂ የሆነ ሥራ መቀጠል አላበት ።በታላቋ ቢሪታኒያ በቆራጥ አክቲቪስቶች እየተደረገ ያለውና ውጤትም ባማሳየት ላይ ያለው በሌሎችም አካባቢዎች መጠናክር ይኖርበታል።ለዚህም የዲፕሎማሲ ሥራ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።ለንደን ወይም ዋሽንግተን ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም የምዕራባዊያ መዲናዎቆች (የመንግታት መቀመጫዎች) ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል፤
  8. ትግሉ ያለው አገር ቤት ነው እዚህ ያለው (ዳያስፖራው)ምንም ሊያደርግ አይችልም የሚባለውን በጥሞና ማየት።በዳያስፖራው ያልታገዘ በተለይም በታዳጊ አገሮች አንድም ለውጥ አልተካሄደም። በርግጥ መሪውን (Steering wheels  )ይዞ የለውጥን ባቦር የሚያሽከረክረው አገር ቤት ያለው ህዝብ መሆኑ የሚካድ አይደለም። ሆኖም ዳያስፖራው በነጻነት ሃሳቡን በሚገልጽበትና የተሻለ የምጣኔ ሃብት ባላቸው አገሮች  ስለሚኖር መረጃን  በማቀበልና  የድርጅቶችን አቅም በመገንባት ከፍተኛ አስተውጽኦ አለው።ለዚህም ነው በህወሃት የሚመራው “መንግስት”  ጥቂቶች ናቸው እያለ ነጋ ጠባ ስለ ዳያስፖራው የሚያለቃቅሰው። የፖለቲካ ድርጅቶች ለግባቸው መሳካት በሚያመነጩት አማራጭ ሃስብ ብቻ ሳይሆን በምጣኔ-ሃብትም ጠንካራ መሆን ይኖርባቸዋል። በተለይም  ህወሃት ይህንን ጠንቅቆ ያውቀዋል።በታላቁ የ1984 ዓም ድርቅ ወቅት ቆሜለታለሁ ይል የነበረው ህብረተብ በረሃብ ሲያልቅ ህወሃት የርዳታ ስንዴን ላቅም መገምቢያ ያደርግ ነበር፤የሃውዜንም እልቂት ያቀነባበሩት ከፖለቲካ ድጋፍ በተጨማሪ የምጣኔ ሃብት  አቅም ግንባታን ከውጭ በእርዳታ መልክ ለማጠንክር ነው፤
  9. የምዕራባውያን ድጋፍ በተለይም የኢኮኖሚው ድጋፍ ባይኖረው ይህ በህወሃት የሚመራው “መንግስት”  አንድ ቀንም ውሎ ባላደረ ነበር።ለዚህም በ97 ምርጫ ማግስት በተካሄደው ህዝባዊ ዘመቻ በተወሰነ መልኩ እርዳታ በመቋረጡ ምንያል ህወሃት እነደተደናበረ ማስታወሱ በቂ ነው።ስለዚህ ይህንን የገቢ ምንጭ  (ያለ “መንግስት” ጣልቃገብነት የሚሰጠውን ሰብአዊ እርዳታን ሳይጨምር) እንዲደርቅ በመደረግ ላይ ያለው አመርቂ የሆነ ሥራ መቀጠል አላበት። በታላቋ ቢሪታኒያ በቆራጥ አክቲቪስቶች እየተደረገ ያለውና ውጤትም ባማሳየት ላይ ያለው በሌሎችም አካባቢዎች መጠናክር ይኖርበታል፤
  10. የዲፕሎማሲ ሥራም ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።ለንደን ወይም ዋሽንግተን ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም የምዕራባዊያን መዲናዎቆች (የመንግታት መቀመጫዎች) ከትኩረቶቹ ውስጥ መጠቃለል አለባቸው። ባልጠበቀው ሁኔታ እየተዳከመበት የመጣ ቢሆንም ህወሃት በምእራባዊአያን ድጋፍ ስልጣን ላይ ለመቆየት በዲፕሎማሲ ስምና ሎቢዎችን በመቅጠር የህዝቡን ገንዘም ሲያፈስ ሰንብቷል።ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው እንደሚባለው አንዳንድ የውጭ ዜጎች ከህወሃት በላይ ለህወሃት ስከራከሩ ለግል ጥቅም (self-interest)ሲባል ሲዋሹ ተደምጠዋል። ህዝቡ ግን የእውነት ባለቤት ነውና ከተሰራበት ውጤቱ ለትግሉ ጠንካራ ድጋፍ ይሆናል፤
  11. ከዚህቀደም የተጀመረውና ከሞላ ጎደል ተግባራዊ እየሆነ ያለው የበህወሃት መራሹ “መንግስት” በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የገቢ ምንጭ የሆኑት ተቋማትና የንግድ ድርጅቶች ማዕቀብ ገንዘብን በቀጥታ ወደ አገር የመላክን ጨመሮ በተጠናከረ መልኩ መቀጠል ይኖርበታል።

አንድ ሰው በትምህርትም ሆነ በልምድ ያካበተውን እውቀት  እንዳለውና ህብረተሰቡን ለማገልገል ፍቃደኝነቱን ማሳየቱ የሚበረታታ መሆን የኖርበታል። አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ከሊላው ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሻለ መሆኑን በርግጠኝነት መሟገቱም እንከን አይኖረውም። ጤናማ ውድድር ለህብረተሰብ እድገትና ለለውጥ አስፈላጊነውና።ይህም ደግሞ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ስላሉ የሚሆን ሳይሆን ባለዕውቀቱም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲውም በተግባር አሳይተው ህብረተሰቡ ሲቀበላቸው ብቻ ነው ።ህብረተስቡ ሊመስክርላቸው የሚችለው ደግሞ በነጻ ሃሳቡን ለመግለጽ ሲችል  ነው ።በሃገራችን ነባራዊ ሆኔታ ሃሳብን በነጻነት ለመግለጽ የታደሉት ጥቂቶች ብቻ ስለሆኑ ከሁሉም ቅድሚያ ሊሰጥ የሚገባው (precondition) ለነጻነት  መሆን አለበት።ነጻነት መቅደም አለበት።ባሁኑ ሰአት ለህዝባችን ከነጻነት ሌላ ሁሉም የቅንጦት ( luxury ) ነው። ህዝቡ በቃኝ ካለ ቆይቷል።አዎ በቅቶሃል አንተን ነጻ ለማውጣት ከጎንህ ነኝ ብሎ በተግባር የሚያሳይ  እንጂ ከላይ ለመጥቀስ የሞከርኩትን የቅንጦት ጊዜ ተግባራት የሚከናወኑትን ማየትም ሆነ መስማት አይሻም።ለህዝቡ ምላሽ ለመስጠት ደግሞ  ከምን ጊዚም የተሻለ ወቅት አሁን ነው የሚል እምነት አለኝ።ስለዚህ እውነት ከልባችን ህዝባችንንና ሃገራችንን ነጻ ለማውጣት ቆርጠኞች ከሆን እላማችን (target) ነጻነት ሆኖ ለዚያ የተቻለን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል።ለተግባራችን መሳካት የፈጣሪያችን እርዳታ አስፈካጊነት ጥርጥር ስለሌለው እንደእእምነታችን ጸሎት/ዱአ ማድረግ ይገባናል።

ፈጣሪያችን ኢትዮጵያን ከነህዝቦቿ ይባርካት። አሚን።

ባህር ከማል

bahirk@hotmail.com

Health: ማንኮራፋትዎን እንዴት ማቆም እንደሚችሉ ያውቁ ኖሯል?

$
0
0

snoring
(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

ማንኮራፋት የምንለው በምንተኛበት ጊዜ በመተንፈሻ አካላችን ላይ በሚፈጠሩ ለውጦች ምክንያት በሚመጣ ድምፅ ነው። ማንኮራፋት አብሮ የሚተኛን ሰው ከመረበሽ ባለፈ አንዳንድ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የጤና እክሎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
Dr Honilet
► ለማንኮራፋት ተጋላጭነት የሚዳርጉ ሁኔታዎች
የሰውንት ክብደት መጨመር:- በተፈጥሮ የሚኖር ጠባብ መተንፈሻ አየር የምናስገባበት አካል መጥበብ የምንስበው አየር ግፊት እንዲጨምር በማድረግ ድምፅን ይፈጥራል
አልኮል መጠጥ ማብዛት፡- የአልኮል መጠጥ የጉሮሮ ጡንቻዎችን በማፍታታት አየር በሚገባበት ወቅት ርግብግቢት በመፍጠር ድምፅ እንዲጨመር ያደርጋል
በአፍንጫ ላይ የሚከሰቱ ችግሮች፡- በአፍንጫ ላይ የሚኖሩ ተፈጥሮአዊ የአቀማመጥ ችግሮች የማንኮራፋት ዕድልን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራሉ
► ማናኮራፋት የሚያስከትላቸው ችግሮች
ቀን ቀን የእንቅልፍ ስሜት መሰማት
ብስጭትና ንዴት
ለነገሮች ትኩረት ማጣት
ለደም ግፊትና ለልብ ሕመም ማጋለጥ
በእንቅልፍ እጦት ምክንያት ለሰው ሠራሽ አደጋዎች መጋለጥ
የትዳር አጋርን እንቅልፍ ማሳጣት ናቸው፡፡
► የሚያንኮራፉ ሰዎች
✔ በእንቅልፍ ጊዜ የሚረብሽ ድምፅ ያሰማሉ
✔ የቀን እንቅልፍ ሊያስቸግራቸው ይችላል
✔ የጉሮሮ መከርከር ይኖርባቸዋል
✔ ሰላም የሌለው እንቅልፍ ያስቸግራቸዋል
✔ በእንቅለፍ ጊዜ ትንታ እና ትንፋሽ ማጠር ያጠቃቸዋል
✔ የደረት መጨምደድና የደም ግፊት ሊኖራቸው ይችላል፡፡
► ማንኮራፋትን የምንከላከልባቸው መንገዶች
✔ አስተኛኘትዎን ያስተካክሉ
በጀርባዎ መተኛት ምክንያት እና ለስላሳ ላንቃዎን ወደ ጉሮሮ እንዲወርዱ ስለሚያደርግ በእንቅልፍ ጊዜ የመርገብገብ ድምፅን እንዳናሰማ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ በጎን መተኛት መፍትሔ ሊሆን ይችላል፡፡
✔ የሰውነት ክብደትዎን ይቀንሱ
የሰውነት ክብደት የሌላቸው ሰዎችም ቢሆኑ ያንኮራፋሉ፡፡ ነገር ግን ማንኮራፋቱ የመጣው የሰውንት ክብደት ከጨመረ በኋላ ከሆነ መንስዔው ሊሆን ስለሚችል ክብደትዎን ይቀንሱ፡፡
✔ የአልኮል መጠጥ አይውሰዱ
የአልኮል መጠጥ የምንወስድ ከሆነ በጉሮሮ አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎችን ስለምናፍታታ ማንኮራፋት እንጀምራለን፡፡ ከመተኛታችን በፊት ባለው ከ4 – 5 ሰዓት ጊዜ ውስጥ አልኮል መጠጥን መውሰድ ማናኮራፋትን ያባብሳል፡፡
✔ የእንቅልፍ ሰዓትዎን ያስተካክሉ
ለረጅም ሰዓታት ያለዕረፍት የሚሠሩ ከሆነ እና በመጨረሻ እጅግ በጣም እራስዎን ካዳከሙ በኋላ የሚተኙ ከሆነ የጉሮሮ ጡንቻዎች ባጣም ስለሚፈታቱ የማንኮራፋት ድምፅ ያሰማሉ፡፡
✔ አፍንጫዎን ከመደፈን ይከላከሉ
አፍንጫዎ በቅዝቃዜም ሆነ በአለርጂ ምክንያት ከተደፈነ የማንኮራፋት ዕድልን ሰለሚጨምር ከመተኛትዎ በፊት በሙቅ ውሃ ገላን መታጠብ በተጨማሪ ውሃ በጨው በማድረግ አፍንጫን ማፅዳት፡፡ ይህ የአፍንጫን ቀዳዳዎች ስለሚከፍት ማንኮራፋትን ይከላከላል፡፡
✔ ትራሰዎን የቀይሩ
በትራስዎ ውስጥ በዓይን የማይታዩ ብናኞች ተከማችተው ሊገኙ ስለሚችሉ መቀየር ተገቢ ነው፡፡
✔ ፈሳሽ በብዛት ይውሰዱ
ፈሳሽን በብዛት መውሰድ ከአፍንጫችን የሚመነጨውን ፈሳሽ ሰለሚያቀጥን ማነኮራፋት እንዳይኖር ይረዳል፡፡
ጤና ይስጥልኝ

ምርጫ 2007ን ለመዝረፍ በሕወሃት/ኢሕአዴግ በከፍተኛ የትምህርት ተቋሞች የተደረጉ ወንጀለኛ ዝግጅቶች – በፓርቲው ውስጣዊ መረጃ ላይ የተመሠረተ ትንታኔ

$
0
0

በከፍያለው ገብረመድኅን Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

“በተለይም በአሁኑ ሰዓት ፈተና ላይ የጣለን የምርጫ ጉዳይ እንደምናሸነፍ ቃል የተያዘበት ቢሆንም [ቃለ ጉባዔ/የፓርቲው ሊቀመንበር መመሪያ?]፤ ፈተናዎች የሚፈጠሩት በሕዝብ እና በራሱ ታማኝ ባልሆኑ ሃይሎች ማለትም በመንግሥት ክንፍ አይቀለበስም ብሎ ማሰብ አይቻልም፡፡ በዚህም ቀድሞ መዘጋጀት ያለበት እና ለሁከት እና ለብጥብጥ መሳሪያ ሊሆን የሚችለው የሕዝብ ክንፍ የተማረው ሃይል ሊሆን ስለሚችል ሊታሰብ ይገባል ብለዋል [የፓርቲው ሊቀመንበር?]፡፡”
“[አደራጃጀታችን] ከምንም በላይ የብጥብጥ እና የሁከት መንስኤ የሆነውን ተማሪ በኢሕአዴግ አመራር አባላት እየታገዘ ለመያዝ የሚያስችል ነው፡፡ በምርጫው ሊፈጠር የሚችለውን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሁከት እና ብጥብጥ፤ ለማሰቆም በማደራጀት፤ መረጃ በመጥለፍ አመችነቱ የላቀ እንደሚሆን ታምኖበታል፡፡”– “በመሆኑም ሁለቱም የሰራዊቱ ክንፍች [የሕዝብና መንግሥታዊ/ፓርቲ] በሙሉ በምርጫው ዘሪያ በቂ ግንዚቤ እንዲጨብጡ ማዴረግ፣ ተገቢውን አደረጃጃትና አሰራር ዘርግቶ መላው መካከለኛ አመራር፤ ዝቅተኛ አመራር፤ መምህራን፤ የምርምር አካላት፤ ድጋፍ ሰጭ ሰራተኛና ተማሪዎች ግልጽ ስምሪት መስጠት፣ ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ በቀጣይነት በማድረግ እያንዲንዱ የሠራዊት ድጋፍ ክንፍ ወደ ሚፈለግበት የጥንካሬ ደረጃ እየደረሰ መሆኑንና የተቋሙ ዕቅድ በውጤታማነት መፈፀሙን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል፡፡”– “… ሁለም የዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንቶች ውጤታቸው የሚሞላላቸው ለምርጫው በሚያዘጋጁት የድጋፍ ኃይል ይወሰናል፡፡”

ምንጭ፡ በትምህርት ሚኒስትሩ ሽፈራው ሽጉጤ አስተባባሪነት የተዘጋጀው:

“የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኢሕአዴግ የምርጫ ድል ልማት ሠራዊት ግንባታ አድረጃጀት ማንዋል – ለምርጫ 2007”

ማጠቃለያ

ራሱ ሕወሃት/ኢሕአዴግም እንዳመነው፡ በከፍተኛ ፍርሃት እየራደ ያለ ባለአራት-ግንባሮችና ሌሎች አናሳ ቡድኖች ስብስብ ዋናው ሥልጣን በሕወሃት እጅ ሆኖ በኃይልና በከፍተኛ ጭቆና ሃገራችንን የሚያስተዳድር የፖለቲካ ድርጅት ነው። ከባህሪው የድርጅቱ ትልቁ ችግርም፡ ሣር ቅጠሉ ሳይቀር፡ ከዛሬ ነገ ሥልጣን ያሳጡኛል ብሎ በሥጋት የሚኖር በመሆኑ፡ ሣሩ፡ ቅጠሉንና ጎመኑም ጠላቶቹ እየመሰሉት፡ በእስር ቤት የሚያጉራቸው ወገኖቻችንን ብዛት ቤቶቻቸው ይቁጠሯቸው ብሎ ማለፉ፡ በቆጠራ ብቻ ጊዜ ከማባከን ያድናል።

ከላይ የተቀመጡት የፖለቲካ ድርጅቱን አስተሳሰብና ማንነት የሚጠቁሙት ጥቅሶች እንደሚያመለክቱት፡ ሌላው ቀርቶ፡ መከላከያውና የስለላው ዘርፍ ሃገር በሚያስተዳድርበት ሁኔታ እንኳ፡ አገዛዙ “በሕዝብ እና በራሱ ታማኝ ባልሆኑ ሃይሎች ማለትም በመንግሥት ክንፍ አይቀለበስም ብሎ ማሰብ አይቻልም” በማለት ስለመጭው ምርጫ ያለውን ሥጋት ያረጋግጥልናል፡፡

በታሪክ እንደታየው፡ አንዳንድ መሪዎችና መንግሥታትም በውናቸውና በእንቅልፋቸው ጠላት ካልፈጠሩ ሥራቸውን መሥራት እንደሚያስቸግራቸው ሁሉ፡ ዛሬ ሕወሃት/ኢሕአዴግም ክፉኛ እየተረበሽ በመሆኑ፡ ኢትዮጵያ ውስጥና ከኢትዮጵያ ባሻገርም እስትንፋስ ያለው ነገር ሁሉ ‘እያሴረብኝ ነው፤ ጠላቴ ነው’ ብሎ የሚያምንበት ደረጃ ላይ ይገኛል።

ይህ ‘መንግሥታዊ’ መሸበር ምን ያህል ሃገራችንንና ሕዝባችንን ይጎዳ ይሆን? ከዚህ በፊት እንዳደረገው ሁሉ፡ ይህ ሁኔታው የሚያስከትለው የሉዓላዊነት ሽያጭና ምንዘራ ይኖር ይሆን? በምርጫ ታኮ፣ ለብዙዎች ሕይወትስ መቀጠፍ እንደገና ሁኔታውን ያመቻች ይሆን? ቀደም ብለው በፖለቲካ ድርጅቱ የተጀመሩት ዝግጅቶች ይህንኑ በገሃድ የሚያመላክቱ ስለሆኑ፡ ለጥያቄዎቹ የኔም መልሴ የእነዚህ ሁኔታዎች ተፈጻሚነት ዕድሎች ካለመሆን ይልቅ ወደ መሆን ያመዝናሉ የሚል ነው!

እነዚህም ድርጊቶቹ በሕግጋት ጥሰት የተሞሉ በመሆናቸው፡-

(ሀ) የምርጫውን ውጤት ከምርጫው በፊት በመተንበይና ውጤቱም በኃይል አጠቃቀም፡ ለሕወሃት/ኢሕአዴግ እንዲመቻች መደረጉን በመረጃነት በመያዝ፤

(ለ) የሀገሪቱን ዜጎች (ወጣቶች፡ ተማሪዎች፡ ምሁራን፡ አብዛኛውን ሕዝብና ቢሮክራሲውን ወዘተ) በመለየት ለጥቃት እያዘጋጀ ሕዝቡንም ወደ እርስ በእርስ ግጭት እየገፋፋ በመሆኑ፤

(ሐ) ከአመራር በማይጠበቅ የማጭበርበርና ሌሎችም ሕገወጥ ተግባሮች፡ ለምሳሌ የሕዝብን የግብር ክፍያለራሱ የፖለቲካ ጥቅም የማዋል ወንጀሎች መፈጸሙን በማስመልከት ዜጎች መረጃውን ለሕዝብ እንዲጋለጥ ማድረጋቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያምም ይህንን ሕገወጥ ድርጊት ሕጋዊ ነው በማለት ባለፈው ጥቅምት፡ ፓርላማ ውስጥ አቋማቸውን ማሳወቃቸው ይታወሳል!

(መ) ወጣት ተማሪዎቻችን በሥነ ሥርዓት ትምህርታቸውን በመከታተል ዕውቀት ቀስመው ሃገራቸውን ወደፊት ለማስገስገስ እንዳይችሉ፡ ትምህርት ቤቶችን ለስለላና ለርዕዮተ ዓለም ማስፋፊያ በመጠቀሙ፣ በቤተስብና በትምህርት ቤቶች ዙሪያ የምሥራቅ ጀርመን የስለላ ድርጅት ስታዚ በተጠቀመበት አንድ ለአምስት የስለላ አሠራር ቤተስቦችንና ሠራተኞችን በየፊናቸው አቆላልፎ (“The Stasi Octopus”) የግለስቦችን ነጻነትና ደህንነት በማናጋቱ፡ ለሰብዓዊ ክብር መዋረድና ለትምህርት ጥራት ጉድለት ሕወሃት/ኢሕአዴግ ተጠያቂ ሊደረግ ይገባል።

On occasion of AAU awarding honorary PHD to Bill Gates; left to right AAU President Dr. Admasu Tsegaye, PM Hailemariam Desalegn, Bill Gates & Tedros Adhanom (Credit: Ethiopian)

የወቅቱ አሳሳቢ ሥዕል

ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ በርከት ያሉ ጸረ-ወጣቶች፣ ጸረ-ተማሪዎችና ጸረ-ምሁራን፣ የትምህርት ጥራትን አዳፋኝ የሆኑ፡ ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን ብቁ የሰው ኃይል እንዳታፈራ የዘለቄታ መንገዷን የሚያደናቅፉ ድርጊቶችና በአመራር አካላት የተዘጋጁ ጽሁፎች – አንዳንዴም እንደ ሕወሃት/ኢሕአዴግ ጥናቶች ሌላ ጊዜ ደግሞ መመሪያዎች እየተባሉ – ገዥው ፓርቲ በቀጥታና በሚስጢር ለአባሎቹ ሲያሠራጭ ከርሟል። ይዘቶቻቸውም ሆነ ተጽዕኖዋቸው (impact) ምን እንደሆነ ለመረዳት ኮሜት ላይ ሮኬት ለማሳረፍ የሚያስችል ዕውቀት አይጠይቅም።

በተጨማሪም አንዳንድ ምንጮች (የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መረጃዎችን ጨምሮ)፣ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የሚካሄዷቸው ጥናቶችና በዚህ ረገድ የውጭ ኤምባሲዎች የሚያስተላልፏቸው መረጃዎች በአንዳንድ አነስ ያሉ ትምህርት ነክ የሆኑ የፖሊሲ ስብሰባዎች አሜሪካና አውሮፓ ውስጥ አልፎ አልፎ ቀርበው፡ ለግንዛቤዎች ሠፊ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። እንዲሁም በየወቅቱና በየደረጃው በመነሻነት ወቅታዊ መረጃዎችንና የአገዛዙን አስተሳሰብ ስለሚያመላክቱ አሠራሮችና እርምጃዎችና ብዙ ጉዳዮች በኢሳት አማካይነትም ተደምጠዋል

አሁን በያዝነው ወር “የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኢሕአዴግ የምርጫ ድል ልማት ሠራዊት ግንባታ አድረጃጀት ማንዋል – ለምርጫ 2007” የተሰኘ ጽሁፍ ቀርቧል – እነርሱ ማንዋል ይሉታል። ‘ማንዋሉ’ በተማሪዎች ሥልጠና ወቅት እንደተፈለገው አልደረሰም። በተደጋጋሚ ታሽቶና ተፈትጎ ቢቀርብም፡ አሁንም ይዘቱ በቀረበበት መልኩ ጥቅም ላይ ሊውል የማይችል በባዶ የካድሬ ቃላት ክምችት የተሞላ ስካር፡ ዓላማው ግን ምርጫውን እንዴት ሕወሃት/ኢሕአዴግ አሸናፊ እንዲሆን ማስቻል በመሆኑ፡ እንደገና እንዲፈተግና ካልጸዳ ሽንፍላነቱ እንዲላቀቅ በሌሎች እንዲሻሻል ተደርጎ እንደገና ጥቅምት 2007 ቢቀርብም፡ ለአባላት እንኳ እንዲበተን ፈቃድ ያገኘው ከብዙ ማመንታት በኋላ ኅዳር 2007 ነው።

A mother grieving the assassination of her son by TPLF Agazi during the rally protesting theft of electoral results by the regime in 2005, where 193 people were mowed down within a few hours in Addis Abeba streets (Credit: BBC)

ያንን የተዘጋጀውን ‘ማንዋል’ ለማንበብ ዕድል በማግኘቴ እንደ አንድ ምሁር፡ በግልጽነት ልለው የምችለውና ካሰመርኩባቸው ጉዳዮች ይዘቶቹ መካከል ለተማሪዎችና ምሁራን ያዘለው ሊገነፍል የደረሰ ጥላቻና ቂም በቀል ግንባር ቀደም ሆነው ታይተውኛል። ከሁሉም የከፋ – ከምርጫ ማጭበርበር ባሻገር – በምርጫው ሰሞን ስለሚሚቀጠቀጡት፡ በአፈሳ ስለሚታሠሩት ወይንም ሊገደሉ ስለሚችሉ ወጣቶች ሚኒስትሩና ግብረ አበሮቻቸው ከወዲሁ ተጠያቂ ሊደረጉበት የሚገባ፡ አፈናና ግድያ እንዲካሄድ መመሪያ የሚሠጥ ሠነድ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

ምንም እንኳ ሃገራችን በዘመነ ሕወሃት/ኢሕአዴግ 31 ያህል ዩኒቨርሲቲዎች እንዲኖራት ቢደረግም፡ ብዛት የጥራት መለኪያ ሊሆን ስለማይችል፥ በ2014 እና በ2013 ጽሁፎቼ፡ እነዚህ የከፍተኛ ትምህርቶች ተቋሞች ከዕውቀት ምንጭነት ይልቅ፡ ለሕወሃት የፕሮፓጋንዳ ማጥመጃ መረቦች መሆናቸውን ከማውቀውና ከሥጋቴ በመነሳት ችግሩን አስመልከቶ ሃሣቤን ለማካፈል ሞክሬያለሁ (http://ethiopiaobservatory.com/2014/08/20/2014-performance-ranking-of-ethiopias-31-universities-an-old-nation-being-reduced-to-beginner/ እናhttp://ethiopiaobservatory.com/2014/01/11/2013-performance-ranking-of-ethiopian-universities-in-both-african-and-global-metrics/)። ከትምህርቴና ከተለያዩ የሥራ መስኮች ከተቀስሙ ልምዶችና ግንዛቤዎች በመነሳት፡ በእነዚህ ጽሁፎችና በተያያዙ በሌሎችም አማክይነት (ለምሳሌም ያህል፡ Improving Education Quality, Equity and Access in EthiopiaEducation under persistent attack in Ethiopia፤ በቅርቡ ደግሞ What a time, when education is openly made instrument for rights violation with TPLF requiring ‘certificate’ of support for its policies for entry to college ወዘተ) ለማሰማት የሞከርኩት ነገር ቢኖር፡ የሃገራችን ዩኒቨርሲቲዎችና የተማረ የሰው ኃይል ምርቶቻቸው በአሁኑ አያያዛቸው፡ ከዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ይቅርና፤ ኋላቀር ነው በሚባለው ሠሃራዊው አፍሪካ ውስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጅች ጋር እንኳ ሃገራችን ተወዳዳሪ መሆን እንደተሳናት ነው።

ሁኔታዎች እንደሚያመላክቱትም ከሆነ፡ ችግሩ ከፖለቲካዊና ከአመራር ድንቁርናና ድህነት የመነጨ በመሆኑ፡ ለወደፊት እየተባባስ እንደሚሄድ ነው የሚተነበየው። ስለሆነም ለተረከበው ሃላፊነቱ ተጠያቂ የሚሆን መንግሥት እስኪመጣ ድረስ፡ ችግሩ ‘በነፕሮፌሰሮች’ ኃይለማርያም ደሳለኝ፡ ሽፈራው ሽጉጤ፡ በረከት ስምኦን፡ አባይ ፀሐዬ፡ ቴድሮስ አድሃኖም ወዘተ፡ የግልና የቡድን ሥልጣን ጥማት በተሳከሩና በጥቅም አሠራር በተመሠረተ አካሄድና አያያዛቸው የሚቀረፍ አይደለም።

በተለይም፡ ዩኒቨርስቲን የሚያህል ነገር፡ ያውም የዩኒቨርሲቲዎቹ ሴኔቶች በሕግ የተሰጣቸውን ሥልጣን በመጠቀም እርምጃ ሊወስዱ ሲገባ፡ (የሌላቸው ዩኒቨርሲቲዎቹም እንዲኖራችው በማድረግ) እንደ ትምህርት ሚኒስቴር ባለ ኋላቀር መሥሪያ ቤት ሥር ለተራ ጉዳዮች እንኳ አራት ኪሎ ማንኳኳትና ደጅ ጥናት የሚያስፈልግበት አስገዳጅ ሁኔታ – ተደርጎ በማይታወቅ አሠራር – በተለይም ስለ አስተዳደሩ፣ ሥራ ካሌንደሩና ካሪኩለሙ ምንም ዐይነት ስሜት፣ ብቃትና ግንዛቤ በሌለው/በሌላቸው ግለሰቦች እንዲመራ መደረጉ አንዱ የችግሩ ምንጭ ነው።፡

መለስ ብለን እንኳ ስንመለከት፡ የአማራ ብሄረስብን አባሎች ሃገራቸው ውስጥ በፈቀዱት አካባቢ የመኖር ሕጋዊ መብት የሌላቸው ዜጎች በማስመሰል በፊርማው ከጉራ ፈርዳ ባባረረ ግለስብ መዳፍ ሥር የሃገሪቱ የትምህርት ፖሊሲ አተገባበርና አፈጻጸም ከመውደቁ በላይ ለዕውቀት ውርደትና ለሃገራችንም ዘለቄታ ከዚህ የከፋ ነገር የለም።

በሌላ በኩል ደግሞ፣ ለማስታወስ ያህል፡ ባለፈው ነሐሴ እንደተነገረው፡ ዩኒቨርሲቲዎች ለፓርቲው ፖለቲካዊና ርዕዮተ ዓለማዊ ተገዥ ያልሆኑትን ተማሪዎች ተቀብለው አንዳያሰተምሩ መከልከሉ፡ ትምህርት ለመስጠትም በራቸውን የሚከፍቱበትን ቀን ሳይቀር ገዥው ፓርቲና ትምህርት ሚኒስቴር የሚወስኑበት ሁኔታ መፈጠሩ፡ የዩኒቨርስቲዎቻችን ራስ ገዝነት ደብዛ ማጥፋትና የሚስጡት ትምህርት መሪዎቹ ራሳቸው በቅጡ ባልሰነቁት ርዕዮተ ዓለም መጨመላለቁ፣ ምን ያህል የትምህርትን ምንነንት ያጎድፈና ዕውቀትን የሚጻረር ድርጊት መሆኑ ሊሠመርበት ይገባል።

Education Minister Shiferaw Shigute (Credit: Addis Fortune)

በአጠቃላይ፡ በተለይም ከሐምሌ 2014 ጀምሮ በከፍተኛ የትምህርት ተቋሞች ሲካሄድ የነበረው እጅግ ተቃውሞ የበዛበት፣ ሕዝብ የተፋውን የገዥውን ፓርቲ ፖለቲካና ርዕዮተ ዓለማዊ አመለካከትና የታሪክ ጥገና በስነጋ ለመጋትና መድረኩም በአብዛኛው ጸረ-ኢትዮጵያ ታሪክና ጸረ-ኢትዮጵያዊነት እንዲሆን በተደጋጋሚ የተደረጉ ጥረቶችን ቀለማቸውን ባልለወጡ የኢትዮጵያ ልጆች በሃገራችን ላይ ስለተቃጣው ደባ ምንነትና ጥልቀት ለወጣቶቻችንና ለኢትዮጵያ ሆኖ ጥሩ ግንዛቤ የሚፈጥር መልካም አጋጣሚ ሆኖላቸዋል።
የትምህርት ልማት ሠራዊት ግንባታ፥ ምንነትና ለምን?

ለዚህ ጉዳይ አስፈላጊነት መንስዔ የሆነው፡ ባለፈው ሐምሌ ወር፡ ከዚያ በፊትም በተበታተነ መልኩ – ክምርጫው መቃረብና ሕወሃት/ኢሕአዴግም በሕዝቡ በአብዛኛው ከመተፋቱ አኳያ – የመለስ ዜናዊ ተክል የሆኑት የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አዲሱ ለገሠ፣ በፓርቲው የሥልጠና ኃላፊነታቸው – “የልማት ሠራዊትን” አቋቁሞ የፓርቲውን የበላይነት በቀበሌ፡ በገበሬ ማኅበር፡ በትምህርት ቤቶች፡ በዩኒቨርስቲዎች፡ በፋብሪካዎች ስለማፋፋም አስፈላጊነት “የኢሕአዴግን ተቃዋሚ ኃይላት ማንኮላሻ አቅም ግንባታ እና የአመራር ግንባታና የትራንስፎርሜሺን ጉዞ” በሚል ጽሁፍ አማካይነት አመራሩን ለማሳመን በመቻላቸው ነው።

የጥናቱ መግቢያ ላይ የመጀመሪያውን አንቀጽ ያነበበ ሰው ጭንቅላት ውስጥ መጀመሪያ የሚከሰተው፡ ሕወሃት እንደዛተው፡ ኢትዮጵያን ማፈራረስና መበታተን ሊችል ነውን የሚለውን ቁጭት የተመላውን ጥያቄ ነው። ይህም አንቀጽ እንዲህ ይላል፦

“አገራችንን በፈጣን ቀጣይነት ያለውና ሕዝቡ በየደረጃው ተጠቃሚ የሚሆንበት የዕዴገት ጉዞ ከዴህነት አላቆ በተራዘመ ሂደት ከበለጸጉት ሃገሮች ጎራ ለማሰለፍ፣ ይህንን ለማድረግ የሚያስችል ዓላማ፣ ስትራተጂ ስሌቶችና ፖሊሲዎችን መቀየስ ይጠይቃል፡፡ በሌላ አነጋገር አቅጣጫውን በትክክል የሚያመለክት መስመር መቀየስ የትራንስፎርሜሺን ስኬት የመጀመሪያ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ መስመሩን ለመቀየስ ይህንኑ ማድረግ የሚችል ብቃት ያለው አመራር ይጠይቃል፡፡ ኢሕአዴግ በዚህ ፈተና ውስጥ ነው፡፡ ለአብነትም እነ አቶ መላኩ ፈንታን ማንሳት ይበቃል፡፡ ይህን ተከትሎል በአገሪቱ ያሉ አመራሮች ለመቀበል አለመቻላቸው እና የኡመድ ኡቦንግ ሃገር መክዳት፤ በጋምቤላ ክልል አመራር ያለው ታማኝነት አስተማማኝ አለመሆኑ፤ የአማራ ክልል አመራሮች ከግንቦት ሰባት ጋር የተያያዘ አመራር መገኝት ፤ የኦህዴድ አመራር ከኦነግ ጋር ማበር እና በአማራ ላይ የደረሰውን በደል በቸልታ መመልከት፤ በአሁኑ ስዓት በትግራይ፤ በቢንሻንጉል ጉምዝ (የአመራሩ ቸልተኝነት እንደተጠበቀ ሆኖ)፤ በአፋር፤ በሶማሌ እና በሐረሬ ምርጫውን ማሸነፍ የሚችል አመራር ዴምፅ የማግኝት ዕዴል አለው፡፡ መስመሩ ከተቀየሰ በኋላ የትራንስፎርሜሺን ትግል በውል ይመራል እንጂ አይጠናቀቅም ቢባልም፣ በስጋት በተቀመጡ ክልሎች አሁንም አፋጣኝ ሥራ ካልተሠራ ኪሳራ ሉያመጡ ይችላል፡፡ ዓላማውን ለማሳካት የስትራተጂውን ኃይሎች ለማብቃትና በአግባቡ ለማሰለፍ የሚችል ብቃትና ቀጣይነት ያለው አመራር ይጠይቃል፡፡”

ይህ ጥናትም በኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ ላለው አስፈሪ ሁኔታ እንደመውጫ ቀዳዳ በመታየቱ፡ እያንዳንዱ የሕወሃት/ኢሕአዴግ ባለሥልጣንና የሕዝብ መገናኛ፡ የአቶ አዲሱ ጥናትን ባለፈው ነሐሴና መስከረም ውስጥ ሕዝቡ ቋቅ እስኪለው ድረስ ሁሉም አንድ ዐይነት ነገር ደግመው ደጋግመው በመጥቀስ፡ እንደ ጀማሪ ቫዮሊኒስቶች ኮንሠርት ወይንም የቁራዎች ጩኸት ለፖለቲከኞች ፍሬ ከርስኪ ማደናቆራቸው፡ የሥልጠናዎቹ ታዳሚዎች፡ በተለይም ተማሪዎች፡ ከመሰላቸትና ትዕግስታቸው በመሟጠጡ፡ የድፍረት ቃላት ልውውጦች በየሥልጠናው ስለመካሄዳቸው – ብዙዎችም በሰበብ አስባቡ ስለመታሠራቸው – ኢሳት በንቃት በመከታተል ‘ሙድና’ ሙቀቱን ሲያስጨበጠን እንደከረመ ይታወሳል።

ከላይ የተጠቀሰውን የአቶ አዲሱን ጥናት አስተከትሎ፡ ሕወሃት/ኢሕአዴግ ለመላው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ተቋሞች፡ ምርጫውን ለማሸነፍ የሚያስችለው ዝግጅትና ስትራቴጂ ቀይሰው ዝግጅታቸውን እንዲያቀርቡ፣ ሥልጠና እንዲያካሄዱ እንዲሁም የተቻላቸውን ያህል በመደራጀትና የአባላት ምልመላ ላይ ርብርብ እንዲጀምሩ ጥብቅ መመሪያ በማዕከላዊ ደረጃ ተላለፈ።

በዚህም መሠረት፡ የሴክተር የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችና ድርጅቶችም በየዘርፋቸው የፓርቲ አባሎቻቸውን አስተባብረው በሚያዝያ 2007 ምርጫ፡ ብሎም ለዘለቄታው ድል – መለስ ዜናዊ እንዳለመው – ሕወሃት/ኢሕአዴግን በትንሹ ለ50 ዓመታ አገዛዝ ለማብቃት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ በዜና ማሠራጫዎች ጭምር ሲናፈስ ከርሟል።

ይህንን የሥራ ድርሻ በሚኒስትር ሽፈራው አማካይነት ትምህርት ሚኒስቴር እንዲያከናውን ከበላይ አካል ለአፍታ ሊዘነጋ የማይችል መመሪያ ደርሶታል። ሚኒስትሩም ብዙ የደክሙበትንና እየታሸ ሲመለስላችው ክርሞ አልጸዳ ያለውን የጥረታቸውን ውጤት – “የትምህርት ሠራዊት” – ሲያቀብጣቸው ሽፋኑና አርዕስቱ ላይ ‘ማንዋል’ብለውት ብዙ እንዲጠብቅበት አድርገው፡ ዓላማውን በሚገባ ቢገልጹም፤ የሚፈለገውን ማበርከት ሳይችኩ ቀርተዋል።

እንደ ሚኒስትሩ አባባል ከሆነ፡ አቶ ሽፈራውና የሚመሩት ኮሚቴ ከፓርቲው አመራር አካል፡ ማለትም ከፓርቲው ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ስለምርጫ ድል አንድ መተማመኛ ተሰጥቷቸዋል። በአቶ ሽፈራው አገላለጽ፡ ምንም እንኳ በተለይም በአሁኑ ሰዓት የምርጫ ጉዳይ “ፈተና ላይ የጣለን ቢሆንም…እንደምናሸነፍ ቃል የተያዘበት” በመሆኑ፤ ዝግጅት ማድረግ ያለብን “ለሁከት እና ለብጥብጥ መሣሪያ ሊሆን የሚችለው የሕዝብ ክንፍ የተማረው ኃይል ሊሆን ስለሚችል” በጥብቅ ሊታሰብበት እንደሚገባ መመሪያ እንደተሰጣቸው ነው፡፡

በካቢኔ አባልነታቸው እንዲህ ማድረግ፡ ዛሬም ባይሆን ነገ በሕግ ያሰጠይቃል ለማለት ስብዕናውም ሆነ ድፍረቱ ወይንም ዕውቀቱ ስለሌላቸው፡ ሚኒስትሩ ያተኮሩት ገና ምርጫው ሳይደርስ ተማሪዎችን ቀድም አድርጎ መምታት ላይ ነው። ለምን ሲባሉ፡ የራሳቸው የሆነ ስለተማሪዎች አንድ ምክንያታዊ አመለካከት አላቸው። የእርምጃቸውን ትክክለኛነት ለማስጨበጥም – የራሳቸውን ግብ ፊታቸው ደቅነው – ከወጣቱ፡ ከተማሪውና ምሁሩ ባህሪ ተነስተው የደመደሙ ይመስል፡ እንዲህ ይላሉ፦

“የዩኒቨርስቲው/የተቋሙ/ የመማር ማስተማር፤ ምርምር፤ የአገልግሎት አሰጣጥና የዱሞክራሲ ሥርዓት መጎልበትን የተማሪዎች ውጤትና የባህሪ መሻሻልን አጀንዳ አንግበው እንደ አንድ ሠራዊት ለስኬቱ የሚረባረብ የጋራ ተልዕኮና ዓላማ ያለው ኃይል በማፍራት አቅም መፌጠርን ይጠይቃል፡፡ [ነገር ግን ወጣቶቹ] በኢሕአዴግ ላይ ያላቸው አቋም የወረደ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በማንኛውም ተቃውሞ ድምፅ ከተጠሩ፤ ሰልፍ የሚያደምቁ፤ ተቃውሞን ከግብ ለማድረስ ሁነኛ መሣሪያ ናቸው፡፡ ተማሪዎች በየትኛውም ሃገር እንደታየው አደባባይን የመያዝ ሕዝብን አሰተባብረው ለተቃውሞ የማሳደም ዕድላቸው የሠፋ በመሆኑ፡ ከዚህም ሲያልፍ፤ የኢሕአዴግ ምከታን በመቃወም ለጠላት ጎራ ተሰልፌው የመታጠቅ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡ በዩኒቨርስቲው/በተቋሙ/ማኅበረሰብ የትምህርት ልማት ሠራዊቱ የሚፈጠርበትና ሚናውን በመጫወት የትምህርት ሴክተሩን የትራንስፍርሜሽን ዕቅድ ማሳካትና በፖለቲካ ስብዕናቸው የተገነቡ ኢሕአዴግን የሚቀበሉ አድርጎ ማውጣት የትምህርት ልማት ሠራዊት ግንባታውን አስፈላጊነትና አማራጭ የሌለው ስልት መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡”

ስለዚህ ሚኒስትሩ በከፍተኛ ትምህርት ተቋሞች ውስጥ ከስለላ ድርጅቱ ጋር በመተባበር የተደራጁትና የሚደራጁት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት “የትምህርት ልማት ሠራዊት”(የመንግሥትና የሕዝብ ክንፎች)” የብጥብጥ እና የሁከት መንስኤ የሆነውን ተማሪ በኢሕአዴግ አመራር አባላት እየታገዙ…በምርጫው ሊፈጠር የሚችለውን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሁከት እና ብጥብጥ ለማሰቆም” ያስችላል ይላሉ።

ሕጻናት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች (photo FOVC Shanto)

ነገር ግን ከአሁን ጀምሮ እስከ ግንቦት 2015 መፈጸም የሚገባቸው ነገሮች፡ ከረዥም ጊዜ ግቦች ጋር ተቀላቅለው አንባብያንን ብቻ ሳይሆን፡ እራሳቸውንም ግራ እንዳጋቡ ማየት ይቻላል። ለምሳሌም ያህል ጥናቱ ከተሰጠው ስያሜ በመነሳት፡ ትኩረቱ ድርጅታዊ፡ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሆኖ ሳለ፡ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ስለትምህርት ጥራት አስፈላጊነት ለመፖትለክ ዳድቷቸው በዚህ ‘ማንዋል’ ውስጥ ብዙ ሲውተረተሩ ይታያሉ።

በዚህም ምክንያት፣ 23-ገጽ በሆነው ማኑዋላቸው ውስጥ የትምህርት ጥራት 17 ጊዜ ተጥቅሷል። ብዙ ለሕዝብ የሚቀርቡ የሕወሃት/ኢሕአዴግ ሠነዶች ውስጥ፡ የዚህ ዐይነቱ አቀራረብ ዓላማ፡ ሥውር የሆኑ እነርሱ የሚያተኩሩባቸው ነገሮች በአንባብያን እንዳይታዩ የሚደረግ ጥረት ነው። ዓላማቸው ያ ካልሆነ፡ ለምንድነው በዚህ ማንዋል ውስጥ የትምህርት ጥራት ጉዳዮች የተካተቱት? ከብዙዎቹ ዕጦቶች መካከል – ለምሳሌ ያህል – መጻሕፍት፡ ብቁ አስተማሪዎች፡ ላቦራቶሪዎች፡ በነጻነት የመማርና ማሰብ ሁኔታዎች በሌሉባቸው ትምህርት ቤቶችና ኮሌጆች ውስጥ፡ የልማት ሠራዊት ምንደነው የሚፈይደው? ለትምህርት ሚኒስትሩ ግን እነዚህ ቅንጦት መስለዋቸው እንደሆን አይታውቅም፡ ሰለ ትምህርት ልማት ሠራዊት እጅግ አስፈላጊነት እንዲህ በማለት ይቀጥላሉ፦

በሃገራችንም የተለያዩ የለውጥ መሣሪያዎችን በመጠቀም የተገኙ ልምድችን በመቀመርና በማስፋፋት አበረታች ውጤቶች የተገኙ ሲሆን፣ ከዚህም ውስጥ የትምህርት ሽፋንን ተደራሽነትንና ፍትሃዊነትን እንደ አንድ አብይ ውጤት መውሰድ ይቻላል፡፡ ነገር ግን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ገና ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅብን ይታመናል፡፡ ይህንን እውን ለማዴረግ መከናወን ከሚገባቸው ነገሮች አንዱ በትምህርት ሴክተሩ መዋቅር ውስጥ የተሟሟቀና የተደራጀ የትምህርት ልማት ሠራዊት በማቀጣጠልና በማስቀጠል የሠራዊት ግንባታ ሂደቱን በአስተማማኝ መሠረት ላይ መጣል ቁልፍ ተግባር ነው፡፡

ከዚህ በላይ ከተጠቀስው ሃሣብ ብዙም በገጾች ሳንርቅ፡ በተመሳሳይ መንገድ፡ በአቶ ሽፈራው ሽጉጤ የሚመራው ኮሚቴ የትምህርት ጥራት እንዴት ከምርጫው ጋር እንደተያያዘ ሳይገለጽ፡ የሚከተለውን ለአንባቢ ካድሬዎቹ ለማስጨበጥ ይሞክራል፦

“በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የትምህርት ልማት ሠራዊት ግንባታ ዝርዝር የአፈጻጸም ሂደትን በሚመለከት የተሟላ ግልጽነትን በመፍጠር ወጥነት ያለው የከፍተኛ ትምህርት የትምህርት የልማት ሠራዊት ግንባታን ወይም የፖለቲካ ሠራዊት ግንባታ በሁለም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተደራጀና በተቀናጀ ሁኔታ በማቀጣጠልና በማስቀጠል ተቋማዊ ለውጡን እውን በማዴረግ የትምህርት ጥራትና አግባብነትን፤ ምርጫ 2007 ውጤታማ ለማድረግና የኢሕአዴግን አሸናፊነት ለማረጋገጥ ነው፡፡”

የትምህርት ሚኒስትሩ ዋናው ችግራቸው፡ የሚያደራጁት የኢሕአዴግ የምርጫ የድል ልማት ሠራዊት ግልጽነት የጎደለው መሆኑን በግልጽ ተጣራሽነት ይናገራሉ። እንዲሁም፡ ተልዕኮውን ተግባራዊ ለማዴረግ የሚያስችለው የአመለካከትና የክህሎት ትጥቅ ያልያዘ ስለመሆኑ በገሃድ ማመናቸውም አንድ ቁም ነገር ነው፡፡ ሆኖም፡ የምርጫ ድል ሠራዊቱን “ወደ ሚፈለገው አቅጣጫ” ለማምራት “የሚያስችለው ቁርጠኝነት” የለውም የሚል ምስክርነት እየሰጡ፡ ይህንን በእርሳቸው ኃላፊነት ሥር የሚደራጀውን ድል አስረካቢ እንዴት ከምርጫው በፊት በቀሩት ስባት ወራት ሊለውጡት እንደሚችሉ ግን የሚሰጡት ሃሣብ የለም፡፡

ስለሆነም፡ ይህ ተጨማሪ ምክንያት ሆኖ፡ እርሳቸውን ምርጫው ከባድ “ፈተና” ውስጥ እንደጣላቸው ቢናገሩና ቢማረሩ፡ እምብዛም አያስገርምም! በልባቸውም፡ አቶ አዲሱ ለገሠን መለስ ዜናዊ በሕይወት ሳለ በጡረታ ተገልለው፡ ሞቱን ተከትሎ ክተሰናበቱበት ሕይወት በባህር ዳሩ ዘጠነኛ ጉባዔ ወቅት ወደ ሥራ ዓለም፣ ኃላፊነትና ሙሉ ደሞዝና የፓርቲ/የመንግሥት የሥልጠና ባለሥልጣንነት የመጡበትን ቀን ሳይረግሙ አይቀሩም!
የቻይና ባህላዊ አብዮት ለሕውሃት/ኢሕአዴግ ከረመጥ መውጫ ሲሆን

አቶ አዲሱ ለገሠ በጥናታችው ወስጥ የቻይናን ባህላዊ አብዮት (Cultural Revolution) ታሪክ ሕውሃት/ኢሕአዴግን ላጋጠሙት ችግሮች እንደ መፍትሄ መጠቀማቸው የአደባባይ ሚሥጢር ነው – በአባባልም፡ በዓላማም፡፡ በዚያ ፈታኝ የኤኮኖሚና የሕልውና ችግሮች ውስጥ ማኦን ላጋጠሙት ክሥልጣን የመገፋት አደጋ የልማት ሠራዊት፡ የተለያሉ ብርጌዶች፡ የወጣት አብዮታውያን ማኅበራትና ሌሎችንም በማቋቋም ጠላቶቹን መምታት ግድ ሆኖአል- የኤኮኖሚ ችግሮቹን ለመፍታት ባይረዱም።

ዛሬ ሕወሃት ለደረሰበት መተፋትና ፈተና እንደ መፍትሄ እነዚህን ዘዴዎች መጠቀማቸው፡ እምብዛም አያስገርምም። ይህንን የምልበትም ምክንያት፡ የፓርቲው የሥልጠና ጉዳይ ኃላፊው – ከላይ ከተጠቀሰው ጥናታቸው ለመገንዘብ እንደሚቻለው – በይዘቱ ቻይና ውስጥ ከ1966-1976 ተካሂዶ በአሥር ዓመታት ውስጥ ለብዙ ምሁራን መታሠርና መደምሰስ፡ ለብዙ ሚሊዮኖች መሰደድ መንስዔ የሆነው “ባህላዊ አብዮት” በሃገራችን በአንድ መልክ ለመጀመር የታቀደ ይመስላል።

የሚያስገርመው ነገር፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ ይህ ነውጥ ያስፈለገበት ምክንያት ከ48 ዓመታት በፊት ቻይና ውስጥ የማኦ ዜቱንግ ሥልጣን የሃገሪቱ የኤኮኖሚ ድቀት፡ በተለይም ፖሊሲው ከተመሠረተበት The Great Leap Forward አለመሳካትና ውድቀት ጋር የተያያዘና በዚያ ትልቅ ሃገር ውስጥ ድህነት፡ ርሃብና እርዛት ተስፋፍቶ ቻይኖች ምንም ዐይነት ነገር የማይጸየፏና እንደ ምግብ እንዲመለከቱ አስገድዷል!

ከዚህም በላይ፡ ኅብረተስቡ ውስጥ ምሬትና ቁጣ ተበራክቶ፡ አንዳንድ የኮሚኒስት ፓርቲውና የወታደሩ ክንፍ ማኦ ላይ ዘመቻ መጀመራቸው ስለተደረስበት፡ ማኦ የነበረው ምርጫ ሳይቀደም መቅደም በመሆኑ፡ ባህላዊ አብዮት ጠላቶቹን ለመምታት የተጠቀመበት መሣሪያ ነበር።

አቶ አዲሱ ከዚህ – ቋንቋው እንኳ ሳይቀር (“ማፋፋም”፡ “ማቀጣጠል” “ፖለቲካዊ ትግል”፡ “ባህላዊ ለውጥ”፡ “መላውን ሕዝብ ከዳር ዳር ማነቃነቅ” ወዘተ) ከቻይና የባህል አብዮት የተዋሱት ሃሣብ፣ ዋና ዓላማው ሕወሃት የተነሳበትን ሕዝብና የሚወጉትን ኃይሎች ከበር ለመመለስ ያላቸው ምርጫ ሆኖ በመታየቱ ይመስላል።

ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል: "ስልጠናው በመላ ሀገሪቱ በመተግበር ላይ ባሉ ስኬታማ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ዙሪያ ጥልቅ የሆነ ግንዛቤ መፍጠር ያስቻለ ነው" (Credit: EBC)

 

መደምደሚያ

የወደፊቱን አስተካክሎ ማየት ለብዙ የሕወሃት/ኢሕአዴግ ባልሥልጣኖች ከባድ ቢሆንም፡ እንደ “እንደብድብ”፡ “እንሠር”፡ “እንምታ”፡ እንደ “እንግደል” ግን የሚቀላቸው ነገር ያለ አይመስልም።

የትምህርት ሚኒስቴር ባለሥልጣኖችም፡ አብዮታዊ ዴሞክራሲን ለመጠበቅና ምርጫውን በአሸናፊነት ለመወጣት ሕጋዊ የሃሳብ፣ የዓላማና ድርጅታዊ ፉክክር አልከሰትላቸው ብሎ፡ ከሚኒስትር ሽፈራው ሽጉጤ ጥናት እንደተመለከትነው፡ አስፈላጊው ቀዳሚ ዒላማቸው፣ ወጣቱንና ምሁሩን የመምታትና የመደምሰስ ስምምነት ያደረጉ ይመስላል።

በመሆኑም፡ አቶ ሽፈራው ከዚህም ሆነ ከሌሎች ንግግሮቻቸው ለመረዳት እንደተቻለው፡ ወቅቱን የሚያቆይላቸው (safeguarding the status quo) ማናቸውም እርምጃ ትክክለኛ ነው ብለው ያምናሉ። የ2007 ምርጫን አስመልክቶም፡ ግቡም ተጨባጭና በእጅ ሊያዝ የቀረበ አድርገው ይመለከቱታል።

በሌላ በኩል ደግሞ፡ አቶ አዲሱ ጥናታችው ውስጥ አንድ ቁም ነገር ይመሰክራሉ። ይኸውም፡ ኢትዮጵያን ወደ በለጸገች ሃገር ለመለወጥ ብቃት ያለው አመራር ብቻ ሳይሆን፡ ቀጣይነትም ያስፈልገዋል ይላሉ። በሌላ አባባል፡ የገዥው ፓርቲ ችግር፡ አሁን ሁለቱም የሉትም ነው የሚሉት፡፡ ይህንን ሁኔታ ቆጠብ ብለው እንዲህ ሲሉ ያብራሩታል፦

“በከተማም ያለው አባላችን ከትምህርት ዝግጅቱ ወዘተ አኳያ ሲታይ ሙያተኛ አመራር የመሆን ዕዴሉ ከአርሶ አደሩ የሰፋ ሆኖም፣ ከጥቂቱ በስተቀር በየሥራ መስኩ የሚቀጥል እንጂ ሙያተኛ የፖለቲካ መሪ ሆኖ የመሰለፍ ዕድል የሌለው ነው፡፡”

ለምን ለሚለው ጥያቄ መልስ ባይሰጡም፡ ኅብረተስቡን በነፃነትና ያላንዳች ማስገደድ ምን እንደሚፈልግ ያለመጠየቁን ጉዳይ አያነሱትም። እስከምናውቀው ድረስ፡ ሕዝቡ የሚለው አትርገጡኝ፡ አትናቁኝ፡ ራሴ በምፈልገው መንገድ ልደራጅ፡ አጭበርባሪዎችና ዘራፊዎች አልወድም ነው። ይህ ደግሞ ለሕወሃት/ኢሕአዴግ የሚያስኬድ መንገድ አልሆነም። በመሆኑም፡ ዛሬም እንደትላንቱ፡ ይህ ሁኔታ በአብዛኛው ኢትዮጵያውያንንና ሥልጣኑን በያዙት ሰዎች መካከል ትልቁ የልዩነት ምንጭ ሆኖ ይቀጥላል – መጭውን ምርጫ በሚመለከት።

ሌላው ቀርቶ፡ የገዥው ፓርቲ ሰዎች (think tanks) የሚጽፏቸውን ጥናቶች ስመለከት፡ ግርም የሚለኝ፡ በዚህ ዕጦትና ጽልመት ውስጥ የሕወሃት/ኢሕአዴግ ለልማት ሠራዊት አባላት አመራርና አደራጅነት ያሠለጠናቸውንም የፓርቲውን አባላትም አስመልክቶ – እንደ ትምህርት ሚኒስትሩ ሁሉ – አቶ አዲሱም ሠፋ ስላለውና ትልቁ “የልማት ሠራዊት” ግንባታ ያጋጠመውን ችግር በመገምገም፡ ተስፋቸው ዝቅተኛ መሆኑን ለመሸፋፈን ቢሞክሩም፡ ከሞላው የተረፈው አምልጧቸው፡ እርሳቸውም ግምታቸው ዝቅተኛ መሆኑን ጥናታቸው ውስጥ አሥፍረውታል።

ይህ የትናንቱና የዛሬይቱ ኢትዮጵያ አብዮት ሪአልቲ ነው! ለመሆኑ የት ይሆን አብዮት የምኞታቸውንና የታገሉለትን ያ ክቡር ዓላማ ፍሬ አፍርቶ ሰዎች በዕድሜያቸው ለማየት የበቁት? ፈረንሣይ? አሜሪካ? ሩስያ? ቻይና? ኩባ? አብዮታዊ ዴሞክራሲ? አልመስለኝም! ከሌሎቹ ለመማር ችሎታ የተነፈግን ይመስል፡ ታዲያ ለምን ይሆን ዛሬም የአብዮት አስፈላጊነት ለኢትዮጵያውያን የሚስበክልን?

ስለአቶ ሽፈራው ሽጉጤ የሥራ ድርሻ ስናስብ ለቁጥር ድርሻ – ትምህርት – ትርጉሙ ሕንጻ ገንብቶ ሕጻናት ራስ በራስ ከማፈጋፈግ ውጭ – የዛሬይቱ ኢትዮጵያ “እነዚህ ልጆች ምን ተማሩ?”፥ “ካለፈው ዓመትስ ወዲህ ትምህርት ምን ያህል አሳደጋቸው?” ወዘተ ብላ ለመጠየቅ ጊዜው፣ ፍላጎቱም የሌላት “ዲሞክራሲያዊት ሃገር” መሆኗ፣ የሕፃናቱን የወደፊት ተስፋ ሥልጣን ሲገፋው፤ ከላይ ባነሳኋዋቸውና ተመሳሳይ የፖለቲካና የአስተሳሰብ ድህነቶች ምክንያት፡ ሃገራችን ብትሮጥም ቆማ መቅረቷን ሳስብ ሁለንተናዪ በፍርሃት ይርዳል!።

ኢህአዴግ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ለማሰር መዘጋጀቱ ታወቀ • የኢህአዴግ አመራሮች መካከል ልዩነት ተፈጥሯል

$
0
0

(ነገረ ኢትዮጵያ) ገዥው ፓርቲ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን ለማሰር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ታማኝ ምንጮች ገለጹ፡፡ ሰሞኑን የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ባደረጉት ስብሰባ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃልን ወይንስ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችን ማሰር ያዋጣል በሚል ልዩነት እንደተፈጠረ የገለጹት ምንጮቻችን በስተመጨረሻም የኢንጅነር ይልቃል መታሰር ትኩረት የሚስብ በመሆኑ ንቁ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችን ማሰር አዋጭ ነው የሚለው ቡድን ተደማጭነት እንዳገኘ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
blue party 2
በተመሳሳይ የሰማያዊና ሌሎች ፓርቲዎች አመራሮችን ‹‹ከኢሳት ጋር ግንኙነት ያደርጋሉ›› በሚል በሽብር ስም ለመክሰስ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችንም ሆነ ሌሎችን ‹‹ከኢሳት ጋር ግንኙነት አላቸው›› በሚል ይከሰሳሉ የተባሉት እስከህዳር ወር መጨረሻ ሊታሰሩ ይችላሉ ሲሉ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል በዚሁ ስብሰባ ኢንጅነር ይልቃል ወይንም ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችን በማሰር ከተፈጠረው ልዩነት በተጨማሪ አመራሮችን በተለያዩ ሰበቦች ለማሰር በተዘጋጀውና ‹‹በዚህ መንገድ መሄዱ እስከመቼ ያዋጣናል?›› የሚሉ ጥያቄ በሚያነሱ ከፍተኛ የኢህአዴግ አመራሮች ልዩነት መፈጠሩንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህም ባሻገር በሌሎች የፓርቲው አካሄዶች ላይ ልዩነት በመፈጠሩ ፓርቲው ውስጥ አደጋ ተፈጥሯል ያሉት የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች በአቶ አባይ ፀሐዬ የሚመራ ቡድን ‹‹ልዩነታችን ቢያንስ እስከ ምርጫው ድረስ ማቻቻል አለብን›› በሚል በሁለቱ ቡድን መካከል ያለውን ልዩነት ለመፍታት እየጣረ ነው ብለዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ከሌሎች 8 ፓርቲዎች ጋር በመተባበር የአዳር ሰልፍን ጨምሮ የአንድ ወር መርሃ ግብር ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ሲሆን የወሩ የመጀመሪያ መርሃ ግብር የሆነው የአደባባይ ስብሰባ ለማድረግ ሲቀሰቅሱ የተገኙ የፓርቲው አራት አመራሮች መታሰራቸው ይታወቃል፡፡

በአብርሃ ደስታ ላይ የቀረበው ክስ ዝርዝር (እንደወረደ)

$
0
0

Abrha Desta
(ዘ-ሐበሻ) የአረና አመራር አባልና በማህበራዊ ሚድያዎች የተለያዩ መረጃዎችንና አስተያየቶችን ያቀርብ የነበረው የመቀሌ ዩኒቨርሲቲው መምህር አብርሃ ደስታ በመንግስት የቀረበበት ክስ ዝርዝር እንደሚከተለው እንደወረደ አቅርበናል::

abreha desta 1

abreha desta 2

abreha desta 3
abreha desta 4
abreha desta 5
abreha desta 6
abreha desta 8
abreha desta 9
abreha desta 10
abreha desta 11

እነ ሀብታሙ አያሌው ዋስትና ተከለከሉ

$
0
0

አቃቤ ህግ ማስረጃ አሟልቶ እንዲቀርብ ታዝዟል

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

Habtamu abrhayeshiwas danielበእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ በፌደራል አቃቤ ህግ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው አራቱ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች እና በተመሳሳይ መዝገብ የተከሰሱት ሌሎች ስድስት ተከሳሾች ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡

ሀብታሙ አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ እና ዳንኤል ሺበሽ በሚገኙበት የክስ መዝገብ የተከሰሱት አስሩም ተከሳሾች ዛሬ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት፣ ተከሳሾቹ ህገ መንግስቱን በመጥቀስ ያቀረቡትን የዋስትና መብት ጥያቄ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ የጸረ ሽብር አዋጁን በመጥቀስ ዋስትናው እንዳይፈቀድ ያቀረበውን መከራከሪያ በመቀበል የዋስትና ጥያቄውን አልተቀበለውም፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች ፍርድ ቤቱ ክሱን መርምሮ በሂደት ውሳኔ እስኪያሳልፍ ድረስ በእስር ላይ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ወስኗል፡፡

በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ጠበቆች የቀረበውን ማስረጃ አለመሟላት በመመርመር አቃቤ ህግ ለህዳር 17 ቀን 2007 ዓ.ም ማስረጃዎችን አሟልቶ እንዲቀርብ በሚል አጭር ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በዛሬው ዕለት ተከሳሾች ከላይ ሙሉ ነጭ ሸሚዝ ለብሰው ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ነጭ ማድረጋቸውም ‹ሰላማዊ ነን› የሚለውን መልዕክት ለማስተላለፍ በማለም እንደሆነ መረዳት ተችሏል፡፡

በዳንኤል ሺበሺ ላይ የቀረበው ክስ ዝርዝር (እንደወረደ)

$
0
0

Habtamu abrhayeshiwas daniel
(ዘ-ሐበሻ) ከነአብርሃ ደስታ ጋር አብሮ እስር ላይ የሚገኘው የአንድነት ፓርቲ አመራር አቶ ዳንኤል ሺበሺ ላይ የቀረበው የክስ ዝርዝርን ዘ-ሐበሻ ለአንባቢዎቿ እንደወረደ እንደሚከተለው አቅርባዋለች::

daniel shibeshi 1

daniel shibeshi

daniel shibeshi 3

daniel shibeshi 4
daniel shibeshi 5
daniel shibeshi 6
daniel shibeshi 7
daniel shibeshi 8


በሃብታሙ አያሌው ላይ የቀረበው ክስ ዝርዝር (እንደወረደ)

$
0
0

habtamu ayalew
(ዘ-ሐበሻ) በእስር ላይ የሚገኘው ታዋቂው ወጣት ፖለቲከኛ ሃብታሙ አያሌው በመንግስት አቃቤ ሕግ የቀረበበት የክስ ቻርጅ በፍርድ ቤት ተሰምቷል:: ሙሉው የክስ ቻርጅ ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ግንዛቤ ይረዳል በሚል እንደወረደ ቀርቧል::
habtamu ayalew
habtamu sp


habtamu ayalew2habt 1
habtamu ayalew 1habt1
hab 7habt8habt9habtamu ayalew 4
habt 12habt13habtamu ayalew 5
habt15habtamu ayalew 6
habtamu ayalew 7
habtamu 19

በመርጫ “ለመሳተፍ” ጋዜጣዊ መግለጫ ለምን ? (ከይድነቃቸው ከበደ)

$
0
0
ይድነቃቸው ከበደ

ይድነቃቸው ከበደ

“አንደነት ፓርቲ” እንዲሁም ሌሎች የጉዳዩ ባለቤት የሆኑት አብዛኛው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከዚህ ቀደም ‹‹የፖለቲካ ምህዳሩ ጠቧል›› ከሚለው አልፈው ‹‹ ተዘግቷል›› ወደሚል ድምዳሜ መሸጋገራቸውን በተጨባጭ ማስረጃ ሲያጋልጡ እና ሲያረጋግጡ ከርመዋል፡፡እዚህ ደረጃ ላይ መድረሳችሁንም በተለያየ ወቅት በጋዜጣዊ መግለጫቸው ለሕዝብ አሳውቀዋል፡፡ “የፖለቲካ ምህዳር” ምርጫንም የሚያካትት ነው፡፡
ደካማ የመንግስት አስተዳደር ለመለወጥ ምርጫ ያስፈልጋል፡፡ይሁን እንጂ ነጻነት በሌለበት ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ አይቻልም፡፡ የገዢው የወያኔ መንግስት ጉዳይ ፈጻሚው በሆነው፣ በምርጫ ቦርድ በኩል በተለመደው መንገድ፣ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ምርጫ ቢካሄድ የወያኔ መንግስት አሸናፊ ሆኖ የሚወጣበት እድሉ የሰፋ ነው፡፡ እንዲህ መሆኑን የተረዱ እውነተኛ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫ ሥም ማጭበርበር ይበቃ !በማለት ትብብር መስርተው፣ ዘጠኝ ፓርቲዎች “ ነፃነት ለፍትሃዊ ምርጫ” የሕዝባዊ ትግል ፕሮግራም ይፋ አድርገዋል፡፡ ለነጻ፣ፍትሃዊ፣ ተኣማኒና አሳታፊ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ፣ እንዲካሄድ በሠላማዊ ትግል አዎንታዊ ተጽዕኖ ለማሳረፍ ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ፡፡
ሆኖም ግን በምርጫ ቦርድ እና በመንግሰት ላይ በሰላማዊ ትግል አዎንታዊ ግፊት ለማድረግ፣ በተጀመረው ህዝባዊ እንቅስቃሴ አጋር እና ደጋፊ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ፓርቲ “እኔ በምርጫ እሳተፋለው” በማለት የይወቁልኝ እና የይድረሱልኝ ጥሪ ሳይገደድ በፍቃደኝነት ከወዲኹ ማስተላለፉ ምን የሚሉት ነገር ነው፡፡ወይስ የሚባለው ነገር እውነት ይሆን እንዴ ?
ለማንኛውም ነገሩን ግልፅ ለማድረግ ያህል ፤አንድ ፓርቲ በሕጋዊ መንገድ ሲቋቋም ስልጣን ሊይዝ የሚችለው በመርጫ እንደሆነ ይታወቃል፣ ይህ ማለት በምርጫ መሳተፍ የአንድ ፓርቲ መደበኛ ተግባሩ ነው፡፡ መደበኛ ተግባርን ለማከናወን የተለየ መግለጫ አያስፈልግም፡፡ከዚህ ይልቅ በምርጫ አልሳተፍም ማለተ የተሸለ የተለየ መግለጫ ያስፈልገዋል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የተሰጠ ተግባር ከማከናወን ይልቅ አለማከናወን በቂ ምክንያት የሚያስፈልገው በመሆኑ፡፡ለማንኛውም ይሄ በወፍ በረር ስለ ጉዳዮ ለምግለፅ ያህል ነው፣ወደፊት በሰፊው እመለስበታለው፡፡ እስከዚያው ቸር ወሬ ያሰማን !
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!

የ28 ዓመትዋ ወጣት ጋዜጠኛ ፣ ገጣሚ እና አርቲስት ትዕግስት ምትኩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች፡፡

$
0
0

ከአንዷለም አስፋው

በምስራቅ ሸዋ ሎሚ ወረዳ (ሞጆ) ታህሳስ 19 ቀን 1979 ዓ/ም ተወልዳ በናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት ከጀማሪ እስከ 12ተኛ ክፍል የተከታተለች ሲሆን በናዝሬት የጥበቡን ኢንዱስትሪ ለማሳደግ ተፍ ተፍ ከሚሉት ወጣት ገጣሚያን መካከል አንዱዋ ነበረች፡፡ ይሄን እንቅስቃሴዋን ያዩት ኮሜዲያን እንግዳዘር ነጋ እና ገጣሚ ፊርማዬ ዓለሙ ወደ አዲስ አበባ መጥታ ስራዎችዋን እንድትገፋበት ከፍተኛውን ሚና ተጫውተዋል፡፡
ልፋታቸውም ባዶ ሜዳ ላይ አልቀረም በጋዜጠኝነት አጫጭር ስልጠናዎችን በመውሰድ በኤፍ.ኤም 96.3 እና በኢቲቪ 2 (ኢቢሲ 2) ላይ ከ10 ዓመት በላይ በማገልገል ላይ ትገኝ ነበር፡፡
በዚህም አላበቃችም በ1999 ዓ.ም የመጀመሪያ ግጥም መድብል የሆነውን ‹‹የጠፈር አበባ›› የተሰኘውን መፅሐፍ ስታሳትም በ2003 ዓ/ም በሴት ገጣሚያን ማህበር ውስጥ የተለያዩ ግጥሞችን ለንባብ አብቅታለች ከነዚህ ውስጥ ‹‹የእኛ›› የተባለው የግጥም መድብል በአንባቢያን ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፎላታል፡፡
tigist mitiku
ጋዜጠኛ ፣ ገጣሚ እና አርቲስት ትዕግስት ምትኩ ወደ ትወናውም እንድትመጣ እንደ አብዛኞቹ አርቲስቶች ሁሉ የክቡር ደ/ር ተስፋዬ አበበ (ፋዘር) እጅ አርፎበታል፡፡ በዚህም ለቁጥር የሚከብዱ የሬዲዮ ድራማዎች ላይ የተሳተፈች ሲሆን በቴሌቭዥን አጫጭር ድራማዎችን በመስራት ላይ ትገኝ ነበረ፡፡
በፊልሙ ዘርፍ ከአምስት ያላነሱ ፊልሞችን የሰራች ሲሆን ከዚህ ውስጥ በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈችበት ‹‹እሾአማ አጥር›› ይጠቀሳል፡፡

በእነዚህ ፊልሞች ልምድ እና ተሞክሮ የወሰደችው ትዕግሰት በ2006 ዓ/ም ለስክሪን የበቃው ‹‹ኤመን›› የተሰኘው የሙሉ ጊዜ ፊልም ላይ በድርሰት እና በአዘጋጅነት እንዲሁም ፕሮዲዩስ አድርጋለች፡፡

በጋዜጠኝነቱ ከኤፍ.ኤም 96.3 እና ከኢቲቪ 2 (ኢቢሲ 2) በተጫማሪ በቃል ኪዳን ፣ በሮዳስ እና በሮያል መፅሔቶች ላይ የተለያዩ ፅሁፎችን ለንባብ ታቀርብ ነበር፡፡
ጋዜጠኛ ፣ ገጣሚ እና አርቲስት ትዕግስት ምትኩ በቅርቡም አዲስ ነጠላ ዜማ ሰርታ ለማሳተም በእንቅስቃሴ ላይ ትገኝ ነበር፡፡
የ28 ዓመትዋ ወጣት ጋዜጠኛ ፣ ገጣሚ እና አርቲስት ትዕግስት ምትኩ በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ህክምናዋን በመከታተል ላይም ነበረች፡፡

ጋዜጠኛ ፣ ገጣሚ እና አርቲስት ትዕግስት ምትኩ የቀብር ስነ-ስርዓት ሐርብ 12/03/07 ከቀኑ 6፡00 ሰዓት በቀራኒዮ ቅዱስ ገብርሔል ቤተ ክርስቲያን ይፈፀማል፡፡
……..እሱ የወደደውን አደረገ የወደደውንም ወሰደ….. ቲጂዬ ነብስሽን በገነት ያኑረው አዘኔ ከባድ ነው፡፡

ምርጫ ሲባል አማራጭ ሳያሳጡ መሆን ይኖርበታል!!! (ከአንድነት ፓርቲ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ)

$
0
0

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

un3በሀገራችን ኢትዮጵያ ለአምስተኛ ጊዜ ሀገራዊ ምርጫ እንደሚደረግ በመንግስት በኩል በከፍተኛ ደረጃ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ከዚህ በፊት የተከናወኑት አራት ምርጫዎች ያየን እንደሆነ በሀገራችን የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ ወደፊት ሊወስዱ እንዳልቻሉ እሙን ነው፡፡ ይህም ሆኖ የኢትዮጵያ ህዝብ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያለውን ፍላጎት በተለያየ መንገድ ሲገልፅ ቆይቷል፡፡ በተቃራኒው መንግስትና ገዢው ፓርቲ በፍፁም መለየት በሚያስቸግር ሁኔታ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ሆነው ተቀናጅተው ለአንድ ለአውራ ፓርቲ ግንባታ እየሰሩ እንደሆነ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ይህ የመንግሥትና የገዢው ፓርቲ ተግባር ምርጫን ያለ አማራጭ እንዲሆነ እያደረገው እንደሆነ ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም፡፡

በቅርቡ የአንድነት ፓርቲ አባላት ላይ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ዘመቻ በሚባል ደረጃ እየተካሄደ ያለው አፈናና እስር፤ ከዚህም ባሻገር ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከህዝብ ጋር እንዳይገናኙ ክልከላውና ወከባው ተጠናከሮ መቀጠሉ፤ ገዥው ቡድን የምር ተቃዋሚ ፓርቲ ናቸው ብሎ የሚያስባቸው ፓርቲዎች ለማዳከምና ከምርጫው ውድድር ውጪ ለማድረግ ያለው ቁርጥ አቋም የሚያሳይ ነው። ይህ የገዢው ቡድን አካሄድ በሀገራችን ዴሞክራሲያዊ የሆነ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዲመሰረት ፍላጎት እንደሌለው በደንብ የሚያረጋግጥ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃና ፍትሐዊ በሆነ ምርጫ የሚፈልገውን ፓርቲ እንዲመርጥ እድል ሊጠሰው ሲገባ በሥርዓቱ በእኩል ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ እንዳያካሄድ የተለያዩ ጫናዎች እየተደረጉበት የሚካሄዱት ምርጫዎች ሁሉ ትርጉም አልባ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ ይህ የገዢው ቡድን ሀላፊነት የጎደለው እንቅስቃሴ በተግባር የሚደግፈው ከሠላማዊ ትግል ይልቅ የኃይልና የአመፅ መንገድ እንደሚሆን የተረዳ አይመስልም፤ ይልቁንም በሠላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ያሉትን ፓርቲዎች ወደ አላስፈላጊ መስመር በመግፋት ሀገራችን ወደ ብጥብጥና ወደ እርስ በእርስ ጦርነት እንድትገባ የሚያደርግ ሁኔታ እየተከተለ ነው የሚገኘው። በሥልጣን ላይ ያሉት ወገኖች ይህ አሳሳቢ ሁኔታ በትክክል እንዳያዩ ጭፍን የሥልጣን ጥም ጋርዷቸዋል፡፡

በቀጣይ ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. የሚደረገው ምርጫም በመንግስት በኩል የመድበለ ፓርቲን ስርዓት ለማጎልበት ምንም ዓይነት ምቹ ሁኔታ እንዳይፈጠር ከአሁኑ የተለያዩ እንቅፋቶችን በመደርደር ላይ ነው። የአንድነት አመራሮችና አባላት በግፍ በማሰር ፓርቲው በምርጫው እንዳይሳተፍ ከፍተኛ የሆነ ጫና እየተደረገ ቢሆንም አንድነት ፓርቲ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሆኖ ህዝቡ እንዲሳተፍ በመቀስቀስና በማበረታታት የተዘጋውን የዴሞክራሲ በር በምርጫ ካርዱ ሊያስከፍት እንደሚችል ከፍተኛ እምነት አለው፡፡

ከሁሉም በላይ ደግሞ እንደከዚህ ቀደሙ ኢህአዴግ ደጋፊዎቼ የሚላቸውን ብቻ በመራጭነት አስመዝግቦ ምርጫ የሚያደርግበት ሁኔታ ማብቃት ይኖርበታል ብለን እናምናለን፡፡ ይህ ተግባራዊ እንዲሆን በእኛ በኩል ደጋፊዎቻችን በመራጭነት እንዲመዘገቡ ከማበረታት ጀምሮ የህዝብና የፓርቲ ታዛቢ በመሆን የምርጫ ሂደቱን በሙሉ በንቃት እንዲከታተል እንዲሳተፍ የበኩላችንን ጥረት በማድረግ የ2007 ሀገራዊ ምርጫ ከጅማሮው ህዝባዊ እንዲሆን ትግላችንን እንቀጥላለን፡፡ ይህ እርምጃም ህዝቡን የስልጣን ባለቤት ለማድረግ ወሳኝ እርምጃ ነው የሚል እምነት አለን፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ በገዥው ቡድን መልካም ፍቃድ ወይም በማንኛውም ውጫዊ ተፅዕኖ የፖለቲካ ምህዳሩን እንደማይሰፋ ሊገነዘብ ይገባል። ምህዳሩ የሚሰፋውና ትክክለኛ የሆነ ዴሞክራሲያዊ ለውጥ የሚኖረው ህዝቡ በጠቅላላ ከፍርሀት ቆፈን ተላቆ በሙሉ ልብ ለመብቱ ሲቆም፣ ለፓርቲዎች ተገቢው ድጋፍ ሲሰጥ፤ ከፍ ሲልም ወደ ትግሉ ሲቀላቀል መሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል።

በዚህ አጋጣሚ አንድነት ፓርቲ ከህዳር 14 እስከ 20 ቀን 2007 ዓ.ም. የሚቆይ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች” የሚል የሶሻል ሚዲያ ዘመቻ አዘጋጅቷል። በዚህ ዘመቻ ለመንግስት ባለስልጣናት፣ ለታዋቂ ግለሰቦች፣ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማትና ለልዩ ልዩ የሚዲያ ድርጅቶች በኢንተርኔትና በሶሻል ሚዲያ በእኩል መልዕክት በመላክ በሀገራችን ያሉት የፖለቲካ እስረኞች ሁኔታና አያያዝ በተመለከተ መረጃ በመስጠት ተገቢ የሆነ አያያዝ እንዲኖራቸው፤ ከእስር እንዲፈቱ፣ በሰላማዊ መንገድ የሚታሉትን ማሰርና ማዋከብ እንዲቆም በመንግስት ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ለመፍጠር ያለመ ነው። በዚህ ዘመቻ ላይ ሚሊዮኖች ለሚያውቁትና ተፅዕኖ ማሳደር ይችላል ለሚሉት ሰው ሁሉ መልዕክት በኢተርኔትና በሶሻል ሚዲያ በመላክ ድምፃቸውን ያሰሙ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)
ህዳር 11 ቀን 2007 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

ከ400 በላይ ህዝብ የተፈናቀለበት መሬት በሙስና ተቸበቸበ

$
0
0

ኢሳት ዜና

49127291በደቡብ ወሎ ዞን በኮምቦልቻ ወረዳ ቀበሌ 11 በተለምዶ ጋሪሳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ይኖሩ የነበሩ 470 ሰዎች ቦታው ለኢንቨስትመንት ይፈለጋል ተብሎ ሰብአዊ መብታቸው ተጥሶ እንዲፈናቀሉ ከተደረገ በሁዋላ፣ በካሬ ሜትር 1 ብር ከ46 ሳንቲም መሬታቸው እንዲጨጥ ተደርጓል።

ጉዳዩ የህዝብ መነጋገሪያ ሆኖ ከቆየ በሁዋላ ሰሞኑን ከህዝቡ እየጨመረ የመጣውን ግፊት ተከትሎ በተደረገ ህዝባዊ ስብሰባና የካቢኔ አባላት ስብሰባ፣ የወረዳው አዛዦች ከተፈናቃዩ ደሃ ህዝብ የወሰዱትን መሬት በሙስና መቸብቸባቸውን እርስ በርስ እየተገላለጡ ይፋ አድርገዋል።

የወረዳው ላይዘን ኦፊሰር አቶ ሃብቶም የተባሉ ግለሰብ፣ አስተዳዳሪውን አቶ አበራ አበረን በአዲስ አበባና በባህርዳር መሬት ገዝተው ቤት መስራታቸውንና ቡልዶዘሮችን ገዝተው እያከራዩ መሆኑን ሲያጋልጡ፣ ምክትል ከንቲባው ደግሞ በባንክ ሂሳባቸው 8 ሚሊዮን ብር እንደተገኘባቸው እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች ቤቶችን መገንባታቸውን አጋልጠዋል። አጋላጩ አቶ ሀብቶምም በከተማዋ ሁለት ቦታ ገዝተው ቤት መስራታቸውን መቀሌ ላይ ተጨማሪ ቦታ መግዛታቸው በሌሎች ባልደረቦቻቸው ተጋልጧል።

ሶስቱም ባለስልጣኖች ለጊዜው ከስራቸው ቢታገዱም እስካሁን የተወሰደባቸው እርምጃ የለም።

አንዳንድ ተፈናቃይ አርሶደአሮች ለኢሳት እንደገለጹት አቤቱታ ቢያቀርቡም ሰሚ በማጣታቸው ለስደትና ለረሃብ መዳረጋቸውን ለኢሳት ገልጸዋል ።

ሰዎቹ ከስራ ቢሰናበቱም ወደ ሌላ ቦታ ተዛውረው መስራታቸው አይቀርም ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በደቡብ ክልል በጉራፈርዳ ወረዳ ከ100 በላይ አርሶደሮች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። አርሶ አደሮቹ የመሬት ዋስትና ወረቀት እንዲሰጣችሁ በነፍስ ወከፍ 4 ሺ 500 ብር ክፈሉ ተብለው የተጠየቁ ቢሆንም፣ አርሶአደሮች ግን እስከዛሬ ግብር እየከፈልን ኖረናል፣ አሁን ተጨማሪ አንከፍልም በማለት ተቃውመዋል። ይህ ተከትሎ መሬታቸውን እየተቀሙ መሬቱ ለኢንቨስተር እየተባለ እየተቸበቸበ ነው።

አብዛኞቹ ባለስልጣኖች ከኢንቨስተሮች ጋር አክሲዎን እንዳላቸው መንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። በአካባቢው የሚታየው ተደጋጋሚ ግጭት ከዚሁ ጋር የተያያዘ መሆኑን ምንጮች ይናገራሉ።

ብርሃንና ሰላም ይሸጣል መባሉ ሰራተኛውን አስደንግጧል

$
0
0

ኢሳት ዜና

berhanena-selam-printing-pressቀድሞ የአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት ስራ አስኪያጅ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተው ከሰራተኛው ጋር በተፈጠረ ውዝግብ ስማቸው በተደጋጋሚ ሲነሳ የነበሩት የኢህአዴግ አባሉ አቶ አባዲ ተካ ከተሾሙ ካለፈው አመት ጀምሮ ብርሃንና ሰላም መረጋጋት ተስኖት ከቆየ በሁዋላ በቅርቡ ደግሞ ድርጅቱ በኪሳራ ምክንያት ይሸጣል መባሉ ሰራተኛውን አስደንግጧል።

በተለያዩ የሙስና ወንጀሎች የሚከሰሱት አቶ ተካ “ድርጅቱ እየከሰረ መቀጠል የለበትም፣ መሸጡም አይቀርም” በማለት ለሰራተኞች ከተናገሩ በሁዋላ ለረጅም ጊዜ ሲያገለግሉ የቆዩት ሰራተኞች በጭንቀት ውስጥ ይገኛሉ። የውስጥ ምንጮች እንደሚሉት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ አንድም ቀን ኪሳራ አጋጥሞት ባያውቅም፣ አቶ ተካ ከተሾሙበት ጊዜ አንስቶ በሚወሰዱ የተበላሹ አሰራሮች የድርጅቱ ህልውና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።

አቶ ተካ ለብርሃንና ሰላም 800 ሰራተኞች አያስፈልጉም በማለት እድሜያቸው ከ50 በላይ የሆኑትን ወደ 400 የሚጠጉ ሰራተኞችን ለማባረር የተዘጋጁ ሲሆን፣ ሰራተኞች እንደሚሉት ልምድ ያላቸውን በማባረር አዳዲስ የኢህአዴግ ወጣት አባላት ለመቅጠር አቅደዋል። በድርጅቱ ውስጥ ከሚሰሩት ሰራተኞች መካከል 100 ያክሉ የኢህአዴግ አባላት ናቸው።

በሰራተኞች ላይ የሚወሰደውን እርምጃ በመቃወማቸው ላለፉት 18 አመታት የሰራተኛውን ማህበር የመሩት አቶ ተስፋየ መላኩ ከስራ እና ከደሞዝ ክፍያ ታግደዋል። ሰራተኞች እንደሚሉት ድርጅቱ ስራ እንዳጣ ተደርጎ ሪፖርት የሚደረገው በኪሳራ ስም የህወሃት ንብረት ለሆነው ሜጋ የህትመት ድርጅት ለመሸጥ በመታቀዱ ነው።

በጉዳዩ ዙሪያ የድርጅቱን ስራ አስኪያጅ ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

በጂቡቲ ታጎሪ ከተማ የኢትዮ-ጂቡቲ የሁለትዮሽ የድምበር ሰላም በሚል ሰብሰባ ይካሄዳል ተባለ

$
0
0

አኩ ኢብን ከአፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው:-

በአቶ እስማእል አሊ ሲሮ የሚመራው ቡዱን ዛሬ ጧት በጋላፊ አቆረጠው ወደ ጀቡቲ ገበተዋል።

የኢትዮጲያ መንግስት ከጀቡቲ እስከ መቀሌ እየገነባ የሚገኘው የባቡር ሃዲድ መንገድ የሰላም ሁኔታ በተመለከተ ከጅቡቲ መንግስት ጋር አብሮ ለመሰራት ተሰስማምተዋል።
et-map300
በዚያ አከባቢ የሚገኙ የጅቡቲ መንግስት ተቀዋሚዎች በእንግለዘኛ ምህጻረ ቃል FRUD እንዲሁም የኢትዮጲያ መንግስትን የሚቃወሙ የኢትዮጲያ አፋሮች ኡጉጉሞና የአፋር ጋዲሌ የሚንቀሳቀሱበትን አከባቢዎች ላይ የሁለት አገራት ደህንነቶች አብረው ለመስራት እንደሆነ መረጀው ያሳያል።
ይሁን እንጂ ካሁን በፊት በአፋር ክልል በኤሊ ዳዓር ወረዳ በማንዳ ከተማ የጅቡቲና የኢትዮጲያ
የመከላኪያ ጀነራሎች በሰላም ዙሪያ ባደረጉት ስምምነት የአቶ እስማእል ኡመር ግሌ መንግስት የኢትዮጲያ መንግስት የፉሩድ ተጣቂዎችን እንዲዋጋ ቢጠይቁም የኢትዮጲያ መንግስት የፉሩድ አባላት ወደ ኢትዮጲያ ገብተው እሰካለተገኙ ድረስ የኢትዮጲያ መንግስት ሊዋጋው እንደማይችል ግን ወደ ኢትዮጲያ ገብተው ከተገኙ አሳልፈን እንሰጣቹሁለን በማለት ነበረ የተስማሙት።
ወያኔ በፉሩድም ሆነ በአፋር ኡጉጉሞ እንዲሁም ጋዲሌ ላይ አንድም የሃይል እርምጃ እወሰዳለሁ ቢል የሚያስከፊለውን ዋጋ ጠንቅቆ ያውቃል።
ይህ በእንደህ እያለ የጀቡቲ መንግስት በዚህ ከታጎሪ እሰከ መቀሌ የሚገነባው የባቡር መንገድ እስኪጠናቀቅ የጀቡቲ ተወላጆች ብቻ በጉልበት ስራ እንድሳተፉ ቢጠይቅም ህወሀቶች አልተስማሙም። ይህ ከ1800 ኪሎ ሚቴር በላይ የባቡር ሃዲድ መንገድ
በኢትዮጲያ የአፋር ክልል ነወሪዎች በብዙ መልክ የሚጎዳ ነው።
እንደሚታወቀው አበዛኛው የአፋር ህዝብ አርቢቶ አደር በመሆኑ በዚህ መንገድ ዳር የሚኖሩ ነወሪዎች ለእንስሶቻቸው አደጋ ሰለሚሆንባቸው ሊፈነናቀሉ ይገደዳሉ።
ይሄ ደግሞ ካሁን በፊት በሱኳር ፋብሪካ ምክንያት ተፈናቅለው በበረሃ ለሚኖሩ ነዋሪዎች በጣም አስቸጋሪ ነው።
ባለ ቤት አልባው የአፋር ክልል መሬት ህወሀቶች በፈለጉት መልክ ስጠቀሙበት ያአፋር ህዝብ ግን በራሃብና በውኃ ጥም እየተሰቃየ ይገኛል።

ያላህ ፈትህ ስጠን!!!!
ምንጭ አኩ አብን አፋር


ሽምግልና የህወሃት የጥቃት ደመና – ከሳዲቅ አህመድ

$
0
0

“የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ህገ መንግስታዊ ጥያቄ በአንባገነናዊ ዙፋን ላይ ለመቀመጥ በሽምግልና ስም ለሚፈጸም ዉንብድና የሚቀርብ አይደለም። ግን ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች በዚያ ዙፋን ላይ የሚቀመጠዉን የፖለቲካ ሐይል አወዳድሮ የማጫረት ብቃት ብቻ ሳይሆን፤በዙፋኑ ላይ የሚፈልጉትን የማስቀመጥም የማንሳትም ሐይልም አላቸዉ!”

(ሳዲቅ አህመድ)

(ሳዲቅ አህመድ)

ከሳዲቅ አህመድ
የኢትዮጵያዉያንን ሰላማዊ ትግል በሐይል መቀልበስ ያልቻለዉ ህወሃት መራሹ መንግስት፤ ትግሉ ወደ ድል ደጃፎች የሚያደርገዉን ጉዞ ለማፋለስ የተለያዩ ሴራዎችን ያሴራል። ከነዚህም የተንኮል መንገዶች ዋነኛዉ በሰላማዊ ትግል ላይ የተሰማራዉን ሙስሊሙን ማህበረስብ ማከፋፈል፣የሰላም አምባሳደር የሆኑትን ኮሚቴዎችን ባደባባይ ባሸባሪነት እየፈረጀ…በምስጢር በጣም ድንቅ የሆኑ የኢትዮጵያ ልጆች መሆናቸዉን በመግለጽ በመንግስት ላይ የሚደረጉ ተቃዉሞዎች ቢረግቡ ሊፈታቸዉ እንደሚችልና ነገሮች ሁሉ ወደነበሩበት እንደሚመለሱ የዉሽት ቃልኪዳን ይገባል። ህወሃት በልማት ስም የሚቀርባቸዉ ወይም ከዲያስፖራ አገር በመግባት ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት ያላቸዉን ሰዎች በመደለል በአንድነት የሚታገለዉን ሙስሊሙን ማህበረሰብ እንዲሸረሽሩ ስዉር የማታለል ተልእኮም ይሰጣል።

አንባገነናዉያን እርቅና ሽምግልናን ከሚገቡበት አጣብቂኝ ለማምለጥ ከሚጠቀሙባቸዉ የማሳሳቻ መሳሪያዎች ዋነኛዎቹ ናቸዉ።ሐይልን ለህዝብ መስጠት የማይፈልግ አንባገነናዊ መንግስት በሽምግልና እና በእደራደራለሁ ማታለያ የአዞ እንባዉን እያፈሰሰ የሰላማዊ ትግል ትሩፋቶችን እንክት አርጎ እንደሚበላ ለማወቅ ብዙ ምርምር ባያሻዉም የአለማችንን ወቅታዊ ሁናቴዎችን ማጤን ብቻ ይበቃዋል። አወቀዉትም ይሁን ሳያዉቁት፣ መልካም ይመጣል ብለዉ በመታለል፣ በሰላማዊ ትግሉ በመዛል (በመዳከም) ነገሮች ወደነበሩበት እንዲመለሱ በመሻት፣ የተጀመሩ ኢንቨስትመቶች እንዲያልቁ ካልያም አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን ለመጀመር መዉጫ ቀዳዳን ለሚፈልገዉ ህወሃት መራሹ መንግስት መዉጫን በነጻ ለመቸር (መዉጫን ጀባ ለማለት) የሚንደፋደፉ ወገኖች በየቦታዉ እየተታዩ ነዉ።

ትላንት በኢህአዴግ የተንገፈገፉ ዛሬ ከኢህአዴግ ጋር መሞዳመዱን ዲሞክራሲያዊ መብት እንደሆነ በድፍረት መግለጽ የጀመሩም አሉ። ኢትዮጵያዉያንን በጅምላ እያገላታ ያለዉን፣ ሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን አስሮ በምድራዊ ቸነፈር ያሰቃየዉን፣ቁርዓንና ሒጃብን ያቀጠለዉን፣ መስጊዶቻችንን የሚያፈርሰዉን፣መስጊዶቻችንን ወርሶ ካድሬ ሚሾመዉን፣ መጽሄት ጋዜጦቻችንን የዘጋዉን፤…ኡለሞች፣ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች ካገር እንዲሰደዱ ያደረገዉን ፣እምነትን ነጥቆ በአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ለማጥመቅ የሚዳክረዉን፣ በደም የተበከሉ እጆቹን በእምነት ተቋም ዉስጥ በማስገባት የአገርን ሉአላዊነት ለማናጋት ሌት ተቀን የሚሰራዉ ህወሃት መራሹ መንግስት ጋር መሞዳመዱ እንደመብት ከታየ…ከሐይማኖት በላይ የመንግስትን አጀንዳ ለማራመድ የሚቅበዘበዙ ጥቂቶች አንገዋሎ መለየቱና መቃወሙ መብት ብቻ ሳይሆን ግዴታ የሆነበት ወሳኝ አጋጣሚ ከፊት ለፊታችን ላይ ተጋርዷል።

“በረዶ አዘል የህወሃት የጥቃት ዶፍ ከመዉረዱ በፊት የአዞእንባ አልቃሹን ህወሃት እንጠንቀቀዉ!”

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች የሚደረገዉን ሰላማዊ ትግል ሙሉ ለሙሉ ቢደግፉም በጣት የሚቆጠሩ ጥቂቶች ግን ለህወሃት መራሹ መንግስት መዉጫ ቀዳዳን ይፈልጉለታል።የህወሃት መራሹን የማታለልና የማዘናጋት ሴራ ወደ መሬት ለማዉረድ የሚንቀሳቀሱ እነማን ናቸዉ?

· ከዲያስፖራ ወደ ኢትዮጵያ የሚመላለሱ የይስሙላ የኢንቨስትመንት ቀረቤታ ያለቸዉ ወይም ኢንቨስት ማረግ የሚፈልጉ ጥቂቶች
· ከባለስልጣናት ጋር ቀረቤታ ያላቸዉ ወይም ባለስልጣን ዘመድ የቤተሰብ አባል ያላቸዉ።ባሉበት የምቾት አለም ዉስጥ በሰላም መቀጠል የሚፈልጉ
· ከመንግስት ባለስልጣናት ሁሉም ነገር ወደነበረበት ይመለሳል ተብለዉ የዉሸት ቃል የተገባላቸዉ
· ዲያስፖራ በሚገኙ ኤምባሲዎች በልማት ስም በብሔር ብሔረሰቦች ጉዳይ ወጣ ገባ የሚሉ
· ከዲያስፖራ ወደ አገር ቤት ባጋጣሚ የሔዱና መሬት ላይ ያለዉን ተቃዉሞ እና የመንግስት በደል በሚገባ ያላጤኑ
· አገር ቤት ሆነው ያንባገነናዊዉ ስርዓት ተጠቃሚ የሆኑ፤ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች የሚያደርጉት ሰላማዊ ትግል ያላቸዉን መረጋጋት እና ከስርዓቱ የሚያገኙትን ጥቅም የነካባቸዉ
· ከአንባገነናዊዉ ስርዓት ጋር ቁርኝት ያላቸዉና ከስርዓቱ የሚጠቀሙ፤ የሙስሊሞች ቅዋሜ ከገፋ ስርዓቱን ሊንደዉ ይችላል የሚል ፍራቻ ያለቸዉና ስርዓቱን ለማዳን የሚሯሯጡ
· ከሐማኖት በፊት የብሔር ጉዳይ የሚያስቀድሙና ብሔርተኛዉን መንግስት ማዳን የሚፈልጉ
· ህወሃት መራሹ መንግስት ከጥፋቱ ተምሮ እራሱን አሻሽሎ ይስተካከላል ብለዉ የሚያምኑ። ከተስተካከልም በተስተካከለዉ መንግስት ዉስጥ እራሳችንንም ጠቅመን ወገናችንን እንረዳለን ብለዉ በየዋህነት የሚያስቡ
· በማህበረሰቡ ዉስጥ ቦታ የነበራቸዉ ግን ከሰላማዊ ትግሉ ፍጥነት ጋር አበረዉ መጓዝ ያልቻሉ።በድምጻችን ይሰማ በህቡእ የሚደረገው ስኬታማ ትግል ተሰሚነትን የነጠቃቸዉ…የተሰሚነትን ቦታ ፈላጊዎች
· አፈንጋጮች፦ ከብዙሗን አመለካከት ዉጪ የራስቸዉን በጣም አናሳ ንኡስ ክፍል ለመስረት የሚጠሩ። ተምረናል፣አንብበናል በማለት የነርሱ አስተሳሰብ የላቀና የመጠቀ እነደሆነ በማሳየት፤ ብዙሃኑ የሚያደርገው ትግል የመንጋ(mob) ጥረት ነዉ ብለዉ የሚያጣጥሉ። ተግባር የለሽን (theory) ትግል በሞላቀቅና በፍልስፍና ለማስረጽ የሚሞክሩ ናቸዉ።
· አደገኞቹ፦ መንግስትን መቃመም፤ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ክልክል ነዉ የሚል ዲሞክራሲ ከሌለባቸዉ የአረብ አገራት የመጣ አመለካከትን (Dogma) ለመተግበር የሚሹ። እነዚህ አካላቶች ከጠላት ጋር ማበርን ተገቢ ነዉ የሚሉበት አጋጣሚ ስለሚኖር አደገኛነታቸዉን ከግምት ዉስጥ ማስገባቱ ግድ ይላል።
· የሚፈሩ፦ በመላዉ አለም በሙስሊሞች ላይ የሚደረሰዉን ጥቃት በማየት ‘የባሰዉን አታምጣዉ!’ በሚል እሳቤ ‘እስኪያልፍ ያለፋል!’ እያሉ በጭቆና ዉስጥ መኖር የሚፈልጉ።
· ግራ የተጋቡ፦ የሙስሊሙን ህገመንግስታዊ መብት መከበር ቢደግፉም፤ ህወሃት መራሹ መግስት በአወሊያ ያቋቋመዉ የስሙላ ቦርድና መጅሊስን አስመልክቶ ያደረገዉ የሐስት ምርጫ ለዉጥ ነዉ ብለዉ ማመካኛ(excuse) የሚሰጡ። በድንበር የለሹ የህወሃት ፕሮፓጋንዳ ግራ የተጋቡ።
· ጀዝባ እና ስራ ፈቶች፦ በሱስ የተጠመዱ፣ የኔ የሚሉት ስራ የለላቸዉ ማንኛዉንም መግስታዊ ሴራ በርካሽ ክፍያ ከመፈጽም ወደ ሗላ የማይሉ ናቸዉ። እነዚህ ግለሰቦች ዛሬን በልቶ ማደር እንጂ ነገን አርቀዉ መመልከት የማይችሉም ናቸዉ። በህገወጡ መጅሊስም ይሁን በመስጊድ ነጠቃ ወቅት የመንግስትን ሴራ ለማስፈጽም ያለ እፍረትና ፍርሃት ይንቀሳቀሳሉ።

የሌላ እምነት ተከታዮችን መላክ፦

መፍትሔዉ ያለዉ ህወሃት በቂሊንጦ እስር ቤት አስሮ በሚያሰቃያቸዉ የሰላም አምባሳደሮችና የሚሊዮኖች ወኪሎች ዘንድ መሆኑንን እያወቀ፤ ቀደም ሲል ህወሃት ከተቃዋሚዎች ጋር በነበረዉ ችግር አመርቂ የፖለቲካ ስራ ያሰራቸዉን ሰዎች ዛሬም የሙስሊሙን ሰላማዊ ትግል ለማሰናከል ሲጠቀምባቸዉ ይስተዋላል።ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ካለፉት የፖለቲካ ስተቶች የተማሩ በመሆናቸዉ ህወሃትን ያልተበላበትን እቁብ እንዲፈልግ እያሳፈሩት ነዉ።

‘ድመትን በር ዘግተህ አትደብድባት’ የሚለዉ አባባል በራሱ አንባገነናዊ የዞረ ድምር ለናወዘዉ ህወሃት መልስ ሰጪ ነው። የህወሃት መዉጫ ቀዳዳ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የጠየቀውን ጥያቄ ባግባቡ መመለስና መመለስ ብቻ ነዉ። ባቋራጭ የሚፈለጉ መዉጫ ቀዳዳዎች ሽንቁር (ክፍተት) ለመፈጠር ከሚደረጉ የጨቋኝ ፈላጭ-ቆራጮች ሴራ ቢሆኑ እንጂ ምንም ሊሆኑ አይችሉም። በርግጥ ህወሃት መራሹ መንግስት መፍትሔን የሚሻ ከሆነ እራሱ ወደ አዘጋጀዉ የማጎሪያ እና የማሰቃያ ቀዬ ወደሆነዉ ቂሊንጦ እስር ቤት ዝቅ ቢል መፍትሔን ያገኛል። ካልያ የድመቲቱ ተረት እዉን መሆኑ አይቀሬ ነዉ።

በርግጥ ድመቲቱ መዉጫ ቀዳዳ ስታጣ ልትቧጥጥ ልትቧጭር ትችላለች፤ በስተመጨረሻ ግን ያካባቢዉ ሰዉ ተሰባስቦ ያቺን መረን የለቀቀች ድመት በቁጥጥር ስር ያዉላታል። እነሆ የድመቲቱን መቧጨርና መቧጠጥ የቻለዉ ትዉልድ ትግላችን እስከድል ደጃፎች ድረስ በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል እያለ ወደፊት እየገሰገሰ ነዉ።
ከልብ የሰረጸ ህዝባዊ እንቅስቃሴ አይቀለበስም።ተወልዶ፣ አድጎ፣ ጎርምሶ፣ ወጣትን የተላበሰዉ ሰላማዊ ንቅናቄ ጎልማሳ ሲሆን ብልሃትና ዘዴን ይቀዳጃል። ብልሃትና ዘዴን የተቀዳጀዉ ሰላማዊ ንቅናቄ ወሳኝ ለዉጥን ለማምጣት ስልታዊ ዝምታን፣ስልታዊ ማፈግፈግን እና ስልታዊ ቅኝትን ይጠቀማል። ጉዞዉ ረጅም መሆኑንን የተረዱት ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች የትግል ሐይልን ለመቀዳጀት ስልታዊ አካሔድን ሲመርጡ ስጋት የገባዉ ማፍያዉ ህወሃት ኮንደሚኒየም፣ መሬት እሰጣችሗለሁ በማለት የድለላ ተገባር ወደ ማህበረሰቡ የሚልካቸዉ የፖለቲካ ቤተ-ሙከራ የዋሃን ሰራተኞች መሰማራታቸዉ እየታየ ነዉ። እፈኝ የማይሞሉ የዋሃን ከህወሃት በላይ እምነታቸዉን በህዝበ ሙስሊሙ የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ እና በድምጻችን ይሰማ ላይ ጥለዉ ቢረጋጉ መልካም ነዉ የሚልም ትችት ይሰነዘራል።

“ዝምታ ወርቅ ነዉ!” በኢንቨስትመንትም ይሁን በኮንዶሚኒየም ስጦታ ወይም በሌላ ጥቅም የተሸበቡ ሰዎች በዝምታ ልማታዊ ዜጎች መሆን ይችላሉ። ግን ድንበርን አልፈዉ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ደሙን ያፈሰሰበት ትግል ላይ በደም የተጨማለቀዉን የህወሃት እጅ ለማጠብ ደፋ ቀና የሚሉ ከሆነ…ከጨቋኝ ጋር በማበር ለሚመጣ ተጠያቂነት እራሳቸዉን ለምን ያጋልጻሉ የሚልም ጥያቄ ይነሳል።

ህዝብ በሰላማዊ ትግል የሚቀዳጀዉ ዉጤት ዘገምተኛ እና ዘለቄታዊ ነዉ። በዚህ እልህ አስጨራሽ የትግል ሒደት ዉስጥ ግዜ ዋነኛ መሳሪያ ነዉ። የግዜን መዝለግ ለራስ ጠቀሜታ እንዲዘነበል ለማደርግ አንባገነናዉያን የግዜን ስርቆት ይፈጽማሉ። ቀደም ሲል ግዜን ለመስረቅ ያደባዉ ህወሃት ህዝብን ያልማከለ የሽምግልና ሴራዉን ፈጽሞ አይደለም ሽምግልናዉ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ለማሰባሰብ በሰሜን አሜሪካ የሚገኝ እደዣንጥላ የተዘረጋ ድርጅት መክኗል። አሁንም ዳግም ህወሃት በመደራደር ስም ያደመነዉ የጥቃት ደመና በረዶ አዘል ዶፉን ሊያዘንበዉ እየጠቋቆረ በመሆኑ ጥንቃቄ በሚያሻበት ወስኝ ወቅት ላይ እንገኛለን።

በጽናት መታገል እንጂ መለሳለስ አንባገነናዉያንን አያረግባቸዉም። ጫናዉ ግፊቱ ሊቀጥል ይገባል፤ ህወሃት መዳራደር ከፈለገ ከዲያስፖራ በልማትና በኢንቨስትመንት ስም ወይም በካንዳሚኒየምና መሬት ታገኛላቹ ድለለላ በመለመላቸዉ ግለሰቦች ሳይሆን፤ በሚሊዮን በሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ዘንድ ተመርጠዉ ዛሬ ቂሊንጦ እስር ቤት ከሚገኙ ጀግኖች ጋር ነዉና ልብ ያለዉ ልብ ይበል።

“በረዶ አዘል የህወሃት የጥቃት ዶፍ ከመዉረዱ በፊት የአዞእንባ አልቃሹን ህወሃት እንጠንቀቀዉ!”

በባህርዳር ከተማ እየተለጠፉ ያሉ የተቃውሞ ወረቀቶች (ዜና ፎቶ)

“ፍጹም ነው እምነቴ” ጸሀፊ አቶ ነሲቡ ስብሀት

$
0
0

ሰለሞን ከተማ ቦሩ፣ ታዛቢ

photo“ፍጹም ነው እምነቴ” ይናገራል ይህን የአቶ ነሲቡ ስብሐት መጽሐፍ ሳነብ፣ ወደሁዋላ ሄጄ ብዙ ነገር እንዳሰላስልና እንዳይ ብቻ ሳይሆን ገፈቱንና ህመሙን፣ ጭንቀቱንና ብሶቱን፣ የተሸናፊነት መሪር ቁጭቱን እንድነከርበት አድርጎኛል። ያለፉትን፣ የወደቁትን፣ የቆሰሉትን፣ የጨለመባቸውን፣ ተስፋቸው የተቆረጠውን፣ በተሰናከለ ህይወት ውስጥ የሚጉዋዙትን የዛን ዘመን ጀግና ወጣቶች ሁሉ በሚንከራተት አይነ ህሊናዬ እንድዳሥሳቸው፣ እንድባባላቸው አድርጎኛል። ካቻምና አንድ ልጆቻቸው በቀይ ሽብር የተገደሉባቸው አዛውንት “ኢህአፓ ይመጣል፣ ከምላሴ ፀጉር ይነቀል ይህ ባይሆን” እያሉ በምሬት ሲነግሩኝ፤ በህብረተሰባችን ውስጥ የተተከለውን ቁስል እና የነፃነት ተስፋ ከዚህ መጽሀፍ ጋር እንዳቆራኘው አድርጎኛል። –[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—–

 

እውነት እንነጋገር! (ማስረሻ ባዴጋ)

$
0
0

በማስረሻ ባዴጋ

 

በአገራችን ከሚካሄዱ ማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች( ትርምሶች) ገለል ብሎ ከዳር መቃኘት ለሞከረ ብዙ ነገሮችን መታዘብ ይቻለዋል፡፡ ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ችግሮች ተባብሰው መቀጠል፤ የተቃዋሚ ድርጅቶች(ሓይሎች) የውስጥ ችግር፤ አንዳንድ ድርጅቶች(ሃይሎች) የመረጡት ቅጡ ያልታወቀ መደዴ የትግል መንገድ፤ የአንዳንዶቹ በተለይም የዲያስፖራው መለያ እየሆነ የማጣው ዓላማው ግልፅ ያልሆነ ጭፍን ግብግብ፤ በቀደምት እንስቃሴያቸው አንቱ የተባሉ አንዳንድ ግለሰቦች ባልተጠበቁበት ቦታ መገኘት፤ ግለሰቦችና ድርጅቶች ውስጥ ያለ ፅንፈኝነት፤ ጥላቻ፤ መፈራረጅ፤ ተጠራጣሪነት፤ አለመደማመጥ፤ ፍፁም ዘረኝነት፤ ወ.ዘ.ተ የወቅቱ ፖለቲካ ባህላችን ልዩ ባህሪያቶች ናቸው፡፡ ከላይ ለመጥቀስ የሞከርኳቸውና ሌሎች ምክንያቶች ተዳምረው ሲታዩ አንዲት የተሸለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሚደረግ ትግል ሳይሆን በዝና የምናውቀውን የባቢሎን ታሪክ ለመድገም የሚደረግ ግብግብን መልክ የያዘ ነው፡፡

ልብ ብለን ከሆነ በየግዜው እንደ አዲስ የሚጀመሩና ብዙ የተባለላቸው እንቅስቃስዎችም ቢሆኑ ለውጥ ያመጣሉ ተብለው ሲጠበቁ ብዙም ሳይራመዱ ቆመው አሊያም የዚያ የእብድ ሰፈራችን ፖለቲካ ማድመቂያ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ቀደም ብለው የነበሩ ትልልቅ ችግሮችን እንደ ችግር ቆጥሮ ለእርሱ መፍተሄ ለማምጣት መስራት ለእኛ አገር ፖለቲካ ባዳ ነው፡፡ የተሞከሩ ቢኖሩም ትርምስንና ለእንዲህ አይነት ነገር የሚሰጠውን ስምና ዘለፋ መቛቛም አቅቷቸው ብዙ ያልተጓዙ ናቸው፡፡ ለጥራዝ ነጠቅ የፖለቲካ ባህላችን መፍትሄ ከመሻት ይልቅ ልምድና እውቀት የማይጠይቀው ግርግር ውስጥ ገብቶ የችግሩ ተዋናይ መሆን የወቅቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፋሽን ነው፡፡ ችግር ፈቺ ናቸው ተብለው የተጀመሩ የፖለቲካ ትግሎች የተነሱበትን ዓላማ ትተውና ይባስ ብለው ችግር ሆነው ሲመጡ እያየን ነው፡፡
አብዛኞች የተቃዋሚ ድርጅቶች(ሃይሎች) የመጨረሻ ግባቸው ወያኔን መጣል ብቻ ሆኖ እናየዋለን፡፡ ይህ አካሄድ ራሱን የቻለ ትልቅ ችግር ነው፤ በምንም መመዘኛ ስልጣን ላይ ያለን አምባገነን ለመጣል ብቻ መስራት ያለብንን ችግር የሚፈታ ስርዐትን ይዞ ይመጣል ማለት አይደለም፡፡ምክንያቱም አሁን እኛ አለብን የምለው ችግር አምባገነን መንግስትን ከመጣልና አዲስ መንግስት ስልጣን ላይ ከመተካት ያለፈ ነውና፡፡ በየቦታው በተበታተነ መልኩ የሚካሄድ የተቃውሞ እንስቃሴ የራሱን ችግሮች ሳይፈታ የመንግስት ስልጣንን በሌላ ተክቶ ሰላምና ዲሞክራሲን ያመጣል ብሎ ማሰቡ ፌዝ ነው የሚሆነው፡፡
የዚህ ውጤት አልባ የተቃውሞ ፖለቲካችን በተለያዩ ችግሮቹ የምንመኘውን ፍትህ እና ዲሞክራሲ ሲያቀዳጀን ካለመቻሉ ባለፈ ብዙ ዋጋ እያስከፈለን መሆኑንም ልብ ልንለውይገባል፡፡ የኔም የዚህ ሁሉ መንደርደሪያዬ ማሰሪያው ይሄነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በገዢው ፓርቲ ዕይታ አብዛኞቹ በሃገርም ውስጥም ሆነ በውጪ ያሉ ድርጅቶች(ሃይሎች) እንደፖለቲካ ድርጅት መቆጠራቸው ካበቃ የቆዩ ይመስላል፡፡ ከዚህ የፖለቲካ ምህዳር መጥበብ ጋር ተያይዞ የተቃዋሚ ድርጅቶች አመራሮች፤ ደጋፊዎቻቸው፤አክቲቪስቶች፤ ጋዜጠኞችና በሌሎች ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን መታሰር፤ መዋከብ፤ሃገርን ጥሎ መሸሽና ሌሎች ጫናዎች በተደጋጋሚ መፈፀማቸው የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡
ይህንን ተከትለው ሰላማዊ ትግልን ትተው በሌላ አማራጭ የትግል መንገድ እንታገላለን ያሉ ድርጅቶች( ሃይሎች) የተፈጠሩበት ሁኔታ የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው፡፡ አንዳንዶቹ ከምርጫ 97 በኋላ የመጣውን የመንግስት ጫናና እርምጃ ለዚህ ውሳኔ ያበቃቸው ቢሆንም ይህ ነው የሚባል እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ያለየናቸው አንዳንድ ሃይሎች ከዚያ ቀድመው በትጥቅ ትግል ስም እንስቃሴ ላይ መሆናቸው የሚታወቅ ነው፡፡
በሃገራችን በፖለቲካው ሜዳ የብዙ ነገሮች መቀየርና መፈጠር ምክንያት የሆነው ከ97 ምርጫ በኋላ ሰላማዊ ትግልን ትቶ ሁለገብ የትጥቅ ትግል አማራጭ የሌለው ነው ብሎ የጀመረው ግንቦት ሰባትም ከ97 በኋላ ተፈጠሩ ለሚባሉ ነገሮች የአንበሳውን ድርሻ የሚይዝ ነው፡፡ ከሌሎች በተለየ ግንቦት7ን ላለንበት ፖለቲካ ማሳያና እንደምሳሌ ማንሳቴም ያለምክንያት አይደለም፡፡
በዚህ ፅሁፌ የሃሳቤን መሃከል ግንቦት7ን ያደረግሁበትን ተያያዥ ጉዳዮች ለመጥቀስ እሞክራለሁ፤
በመጀመሪያ የብዙ ሰዎች ተስፋ የነበረው የቅንጅትን ወራሽነት ይዞና በመንግስት የተገታውን ትግል በሌላ መንገድ አስቀጥለዋለሁ ብሎ በመነሳቱና ከዚያ ጋር ተያይዞ በሚመጡ ነገሮች ስሙ ስለማይጠፋ፤
ሁለተኛው በዚህ የግንቦት7 ስብስብ ውስጥ ህዝቡ ከሚያውቀው እውነታ ጋር ፍፁም ተቃራኒ የሆኑ እውነታዎችን በቅርበት ለመመልከት በመቻሌና ይህም ዛሬ ላለንበት ችግር ሰበብም ነው ብዬ ስለማምን እንዲሁም ከዚህ ስብስብ የመነጩ ናቸው በተባሉ ጉዳዮች በተለያዩ ግለሰቦች፤ ድርጅቶችና በአጠቃላይ በተቃውሞ ፖለቲካ እንቅስቃሴያችን ላይ እየደረሰ ያለው አሉታዊ ጫና እየተባባሰ መምጣቱ ዋነኘ ምክንያቶቼ ናቸው፡፡
ግንቦት7 ሁለገብ የሚለውን የትግል መንገድ ይዤ እታገላለሁ ባለ ጥቂት ግዜ ውስጥ ነገሮችን ለመዘጋጋትና እርምጃ ለመውሰድ ወደኋላ የማይለው የኢህአዴግ መንግስት ይህን ይመክትልኛል ያለውንና አስደንጋጭ የሆነውን የፀረ ሽብር ህግ ይዞ ከተፍ አለ፡፡ ይህን አፋኝ ህግ ለማስፈፀም ይረዱኛል ያላቸውን ነገሮች ተንትኖ አስቀመጠ በዚህም አላበቃም አሸባሪ ያላቸውን ድርጅቶችና ስብስቦችን ስም ዝርዝር ይፋ አወጣ፡፡ በዚህም ዝርዝር ውስጥ ዋና ተጠቃሽ የነበረው ግንቦት7ም የቻለውን ያህል በተለያዩ የአለም ክፍሎች ያሉትን አባለትና ደጋፊዎች ሊያሰባስብ የሚችልባቸውን መዋቅሮች ፈጥሮ መንቀሳቀስ ጀመረ፤ ቀድሞም ህዝብ ጋር የነበረው የ97 ምርጫ ቁጭት ለግንቦት7 ቶሎ መታወቅና የአባላትና የደጋፊውን ቁጥር ለማብዛት እጅጉን ረዳው፡፡ በዚያው ሰሞን ከሃገር ውስጥም ከሶማሌ ክልል ውጪ በተቀሩት ሁሉም ክልሎች የተደረጃ መዋቅር እንዳለው የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ደጋሞ ሲናገር ተሰማ፡፡ ይህን የሰጋው የወያኔ መንግስት በግንቦት7ና በሌሎች ሃይሎች ይመጣብኛል ያለውን ኪሳራ አስልቶ የሚከላከልባቸውን የተለያዩ መንገዶች ሲያበጃጅ ተመልክተናል፡፡
በዚህ አይነት ሂደት ውስጥ ስንጓዝ ስድስትና ሰባት አመታት አለፈ፡፡ ግንቦት7ም ሆነ ሌሎች  ሃይሎች እዚህ ግባ የሚባል ስራ ሰርተው ሳያሳዩን እንሱ የነኩትም እዲሁም የማያውቁትም የዚህ ፀረ-ሽብር ህግ ሰለባ መሆን ችለዋል፡፡ መንግስትም ለስርአቱ ስጋት የመሰሉትን በሙሉ በሽብርተኝነት መነፅር በመመልከት ብዙ ግለሰቦችን፤ ፖለቲከኞችን፤ ጋዜጠኞችንና በሃገሬ ጉዳይ ያገባኛል ያሉ ዜጎች ወደ እስር ቤት ሲወረወሩ ቆይቷል፡፡ ከዚህም ባለፈ በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማህበራት በተለያየ መንገድ ሲያሸመደምድ አስተውለናል፡፡
ይህ ሲባል ግን ገና ከመነሻው ከሃገር ውስጥና ከሃገር ውጪ ብዙ ወቀሳዎች የበዙበት የፀረ- ሽብር ህጉ ሰለባ የሆኑት ግለሰቦችና ተቛማት በሙሉ ከግንቦት7ና ከሌሎች በሽብር የተፈረጁ ሃይሎች ጋር ግንኙነት አልነበራቸውም ማለት አይቻልም፡፡ ግንቦት7 በዘረጋላቸው ዝርክርክ መስመር ሄደው የማዕከላዊና የቂሊንጦ ሲሳይ የሆኑትን ግለሰቦች ቤቱ ይቁጠረው፡፡
ከግንቦት7 ጋር ንክኪ አላቸው ተብለው ለእስራት፤ለእንግልትና ከሃገር መሰደድ የበቁ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን ጉዳይ ስንመለከት አንዲት ነገር ሳይፈጠር ሁልግዜ ግንቦት7 በጠራቸው ቦታዎች በሙሉ ገንዘብና ግዜውን የሚለግስ ዲያስፖራ ባየን ቁጥር “ምንም አልሰራችሁም ” የሚለውን የአባላትና ደጋፊዎች ወቀሳ ብቻ በመፍራት ያልተጠናና ጭራሽ አዋጭ ያልሆነ የኤርትራ ውስጥ ትግል ተቀላቅለው የሻእቢያን ድብቅ አጀንዳ ማስፈፀሚያና መቀለጃ የሆኑ ወጣቶችን ባሰብን ቁጥር፤ የተቃውሞ ሜዳን የብቻ ለማድረግ በሚደረግ ግብግብ ውስጥ ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶችንና ሲቪክ ማህበራትን ለማፍረስ አልያም ለመቆጠር የሚካሄደውን የፖለቲካ ብልግና ልብ ባልን ቁጥር፤ ያላደረጉትን አደረግን፤ ያልደረሱበትን ደረስንበት ተብሎ የሚነገር የውሸት ፕሮፓጋንዳቸውን ዘወትር በሰማን ቁጥር “ጎመን በጤና” ከማለት ባለፈ በግንቦት7 ላይ ተስፋ ማድረግ ካቆምን ሰንበት ብለናል፡፡
አሁንም ቢሆን  ሃገርቤት ውስጥ ያለው ከግንት7 ጋር በተያያዘ በወገን ላይ የሚደርሰው እስራትና እንግልት እየበዛ የመጣበትን ሁኔታ እያየን ነው፡፡ ብዙ ወጣት ፖለቲከኞች፤ አመራሮ፤ አክቲቪስቶች፤ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች ለእስራትና ለስደት ተዳርገዋል፡፡ የብዙዎቹ ጉዳይ ከመንግስት ስጋት የመነጨ ተራ ክስ ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ በግንት7 መዋቅር ስር ወድቀው የተገኙ እንዳሉም ነው፡፡ ለዚህ ጉዳት ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም በተጠያቂነት የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው ግንቦት7 በዚህ ጉዳይ ላይ አንዳች ነገር ሲል አልተስተዋለም፡፡
ከግንቦት7 ጋር ንክኪ አላችሁ ተብለው በስህተት የተከሰሱ ግለሰቦችን በተመለከተ አንዳች ነገር ለማለት ፍቃደኛ ሆኖ አያውቅም፤ በየግዜው ከዲያስፖራው ከሚሰበሰበው ገንዘብ ለእስራት በመዳረጋቸው ለከፍተኛ ችግር የተዳረጉ ቤተሰቦቻቸውን ሲረዳ አላየንም፤ የሚረዱበትን መንገድ ፈልጎም አያውቅም፤ ሌላው ቢቀር ሃገር ጥለው የወጡትን እንኳን ባሉበት ቦታ ለማገዝ ሲሞክሩ አልታዩም፡፡
ይህን እውነት ብዙዎች የሚያውቁትንና የሚረዱት ቢሆንም የሚያውቁትን ያህል ግንቦት7ን በተመለከተ ጨከን ብለው ለመናገር ብዙ አልደፈሩም፡፡ የግንቦት7ን  በአደባባይ መናገር ትግልን የሚጎዳና ዞሮዞሮ ጥቅሙ ለኢህአዴግ ነው ብለው የሚያስቡም ይኖራሉ “ለምጣዱ ሲባል አይጧ ትለፍ” የሚለው የትግርኛ ብሂል ለዚህ አይሰራም፡፡ ተስፋ የማይጣልበት ተስፋ ማድረግ ነው ትግል የሚጎዳ፤ ከወያኔ ብቻ ሳይሆን የብዙዎች እስራትና እንግልት ከመሆን ባለፈ ፋይዳ ከሌላቸው ግንቦት7ና መሰሎቹ ይሰውረን አሜን፡፡
Comment

የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል የትብብሩን ደብዳቤ አልቀበልም አለ

$
0
0

ነገረ ኢትዮጵያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ህዳር 21/2007 ለሚያደርገው ስብሰባ የጻፈውን ማሳወቂያ ደብዳቤ አልቀበልም ማለቱን የትብብሩ ጸኃፊ አቶ ግርማ በቀለ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡

addisdemo3የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ህዳር 21 ለሚያደርጉትና መኢዴፓ ለሚያስተባብረው ስብሰባ ረቡዕ ህዳር 10 የፓርቲው ዋና ጸሃፊ አቶ ዘመኑ ሞላ፣ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ አይችሉም አያል እንዲሁም የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ መሰለ እውኔ ደብዳቤ ይዘው ሄደው የነበር ሲሆን አቶ ማርቆስ ብዙነህ እና እሳቸውን ተክተው ሲሰሩ የነበሩት አቶ ፈለቀ ታመዋል በሚል የከንቲባ ጉዳይ የካቢኔዎች ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው ማሳወቂያ ደብዳቤውን አንቀበልም ማለታቸው ታውቋል፡፡

የመኢዴፓ አመራሮች ህዳር 10 ደብዳቤውን ለመስጠት በሄዱበት ወቅት ‹‹ዛሬ ደብዳቤውን አንቀበላችሁም›› ተብለው የነበር ቢሆንም ለህዳር 12 እንደሚቀበሏቸው እንደገለጹላቸው ይታወሳል፡፡ ይሁንና በትናንትናው ዕለት የመኢዴፓ ፕሬዝደንትና የትብብሩ ገንዘብ ያዥ አቶ ኑሪ ሙደሲር እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ ደብዳቤውን ይዘው ቢሄዱም የከንቲባ ጉዳይ የካቢኔዎች ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው የእናንተን ደብዳቤ አንቀበልም እንዳሏቸው ታውቋል፡፡

የትብብሩ አመራሮች ደብዳቤውን የሚቀበላቸው ሲያጡ ጠረጴዛ ላይ ጥለውት የመጡ ሲሆን በፖስታ ቤት በሪኮመንዴ eg156846735et እንደላኩ አቶ ግርማ ገልጸዋል፡፡ የትብብሩ ፀኃፊ አክለውም ‹‹ይህ የሚያሳየው ስርዓቱ ሁሉንም ነገር ጠርቅሞ እንደዘጋና ለህዝባዊ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ያለውን ፍርሃት ነው፡፡ በመንግስት ገንዘብ የሚተዳደር መስሪያ ቤት በገዥው ፓርቲ መሳሪያ መሆኑን ያሳየ ነው፡፡ ሆኖም ግን ትግሉን ከመቀጠልም ሆነ ደብዳቤውን ከመድረስ አያግደውም›› ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህዳር 11/2007 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ህዳር 7/2007 ዓ.ም ሰማያዊ ፓርቲ በማስባበር ሊያካሂደው የነበረው የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፀረ ህገ መንግስታዊ ነው በሚል እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቁን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live