Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በአዋሽ ለ38 ሰዎች ሕይወት መጥፋት ምክንያት የሆነው የመኪና አደጋ መንስኤ ግመል ናት ተባለ (የአደጋዎቹን ፎቶዎች ይዘናል)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ በአዋሽ አካባቢ በደረሰው የመኪና አደጋ 38 ሰዎች መሞታቸውን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ ይታወሳል:: ይህን ተከትሎ አደጋው በደረሰበት አካባቢ የነበሩ የዘ-ሐበሻ የዓይን ዕማኞች በፎቶ ግራፍ አስደግፈው በላኩልን መረጃ መሰረት ለአደጋው መነሻ የሆነችው ግመል ናት ብለዋል:: የዘ-ሐበሻ እማኞች ከመኪኖቹና ከሞተችው ግመል ፎቶ ግራፉ ጋር አያይዘው በላኩት መግለጫ የመኪና ሾፌሮቹን ጨምሮ የ38 ሰዎች ሕይወት ተቀጥፏል::

በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየደረሱ ያሉ የመኪና አደጋዎች እጅጉን የሚያሳቅቁ እየሆኑ ነው::

ዘጋቢዎቻችን የላኩትን የአደጋውን ፎቶዎች እነሆ
accidenet

accident

accident 3


አሜሪካ ድምጽ ፒተር ሃይንላይንን ከሃላፊነቱ አነሳ

$
0
0

አዲስ ቮይስ) የአሜሪካን ድምጽ ዳይሬክተር ዴቪድ አንሶር የአፍሪካ ቀንድ የበላይ ሃላፊ የነበረው ፒተር ሃይንላይን ከሃላፊነቱ መነሳቱን አሳወቁ። ዳይሬክተሩ ባለፈው አርብ የክፍሉን ሰራተኞች በድንገት  ሰብስብስበው እንዳስታወቁት ሃይንላይን ከሃላፊነቱ ተነስቶ በምትኩ የርሳቸው ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ዊሊያም ማርሽ በግዚያዊነት መሾማቸውን ገልጸዋል።

178763-thumbበቅርቡ  በአሱዛ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲ ለአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ተሰጥቶ የነበረ ክብር መሰረዙ ጋር በተያየዘ ከሄኖክ ሰማእግዜር ጋር በመተባበር የተዛባ ዘጋባ አቅርቧል የሚል ክስ ቀርቦበት የነበረው ፒተር ሃይንላይን የአስተዳደር በደል አቤቱታም በተጨማሪ በስሩ ያስተዳድራቸው ከነበሩ ሰራተኞች ቀርቦበት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

የአሜሪካ ድምጽ የበላይ ሃላፊዎች በሃይንላይን ላይ የቀረቡትን አቤቱታዎች መመርመራቸውንና ከፍተኛ የአሰራር ጉድለቶች እንደነበር ማረጋገጣቸው ታውቋል። በጋዜጠኛና አክቲቪስት አበበ ገላው አቤቱታ የቀረበበትን ዘገባ በተመለከተ የአሜሪካን ድምጽ የበላይ አስተዳደር (Board of Broadcasting Governors) ጉዳዩን በጥልቀት መርምሮ ዘገባው ያለተሟላና ከአሜሪካ ድምጽ ደረጃ በታች የወረደ ነበር ሲል መግለጹ ይታወሳል።

ይሁንና የአሜሪካን ድምጽ የአማርኛ ክፍል ግዜውን በጠበቀ መልኩ አግባብ ያለው እርምትና ማስተካከየ ሳያደርግ መቅረቱና ስህትቱን ከማረም ይልቅ መሸፋፈን በመምረጡ ተጨማሪ አቤቱታ ለቪኦኤ የበላይ ሃላፊዎች ቀርቦ እንደነበር አበበ ገላው ገልጿል።

አበበ በተለይ ፒተር ሃይንላይን እንደ ባለስልጣን ሃላፊነት በተሞላበት መልኩ ማስተካከያ ከማድረግ ይልቅ አደናጋሪና የተዛቡ ዘገባዎችን በተደጋጋሚ እንዲቀርቡ ማድረጉ ለእርምጃው መወሰድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው የውስጥ አዋቂዎችን በመጥቀስ አስረድቷል።

አዲሱ የአፍሪካ ቀንድ ሃላፊ ሆነው የተሾሙት ማርሽ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሃላፊነት ለሶስት አመታት ማገልገላቸው የታወቀ ሲሆን በሰራተኞች የተከበሩና ለሙያቸው ትልቅ ከበሬታ ያላቸው መሆኑን ለማወቅ ተችላሏል። ፒተር ሃይንላይን ከሃልፊነት ቦታው ወርዶ ያልምንም አስተዳደራዊ ሃላፊንት ወደ አፍሪካ ክፍል መዛወሩ ለመረዳት ተችሏል።

ልጅአለም።

$
0
0

17.11.2014 /ሲዊዘርላንድ ዙሪክ/

ኃይለመድህን አበራ

ኃይለመድህን አበራ

አንቀላፍተው ሰነባበቱ። አሁን ግን ጭር ብለዋል። ተያይዝው እቅፍቅፍ ብለው በተመሰጠ ቢጫማ ፍቅር ከደርቡ ቤታቸው ወረድ ብለው ምድር ቤት አሰኛቸውና ተያይዘው ተኙ። ….. ለኦርኬስተሩም ረፍት ስለሰጡት ውዝዋዜያቸው ሆነ ዳንሳቸው ተግ ብሏል። ጊዜያዊ ስንብት ለቋሚ ደንበኛ ኤጀንታቸው ለጌታ ንፋስ ሰጥተዋል። ከመንፈቅ በኋላ ይነቃሉ … ምንአልባት ያን ጊዜ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ይሆን? አዎን የአውሮፓ ዕጽዋት እንቅልፍ ላይ ናቸው … ጸጥ ረጭ ብለው ሰላምን ተጎናጽፈው፣ ነፃነትን ተንትርሰው ይለሸልሻሉ … የታደሉ …

ግን ደህና ናችሁ የኔዎቹ … እኔ አይደለሁም ልጅአለም ስትል እናት ኢትዮጵያ ልዕለተ – ልዕልት ናት ለጀግንነት የጫጉላ ጊዜው ለልጇ የእትብት ልባም የሆነ ሽልማት ሥም የሰጠችው። ልጅ የተስፋ ሀገር – ጥሪት፣ የተስፋ መኖር – ትንፋሽ፣ የተስፋ ማህጸን – ታሪክ፣ የተስፋ ልዕለ – መሰረት፣ የተስፋ ላዕላዬ መዋቅር – እርገት፣ የፍጥረት ፍጹም ልዩ ሥጦታ ነው። ልጅ ፍቅርን በፍቅር ጠልፎ ሥነ ተፈጥሮን አቅልሞ፣ አለምልሞና አሳብቦ ህይወትን የሚፈወስ አንጡራ የሰማይ ጸጋ ነው። የምድርም ገነት። ልጅነት ማግኘት በራሱ ሰማያዊ ጸጋ ሲሆን እናትነት ማግኘትም ሰማያዊ – ሥጦታ።

ዬልጅነት የከበረ ጸጋነት ማረጋገጫው ደግሞ ተግባሩ ነው። ተግባሩም ግልብ ሳይሆን ዬእትብትን ውስጥ ባግባቡ የሚተረጉም ልዩ ክህሎት ነው። ክህሎቱ በሰው ሰራሽ ስልጠና የሚገኝ አይደለም። ይልቁንም ከሰጪው የተበረከተ ፍጹም ረድኤት እንጂ። የእናትና የልጅ ግንኙነት ሁነት ቢሆን ኮርስ የሚወሰድበት፣ ተቋም ተከፍቶ፣ ሰራዊት ተሰማርቶ በገሃዱ አለም ታሪክ የሚንቦለቦል ወይንም የሚጠፈጠፍ አይደለም። የቅድስና መርሃዊ ክንዋኔው ኤዶማዊ ነው። ጠረኑም ሰውኛ አይደለም አምላካዊ

እንሆ ዬታላቅ ሀገር ኢትዮጵያ ልጆች ዘመንና ወቅት ሳይገድባቸው ወይንም ደንበር ሳይወስናቸው የእናታቸውን ዘመነ ህማማታዊ ጥሪ በተግባር አብተው አለሁባይነትን ዘውድ እንዲደፋ እንዲህ ይፈቅዱለታል። በሥርዓተ ንግሥናው ቅብዕ ልጅነት የሚከውኑት ገድል ደግሞ መስዋዕትነትን ፈቅደውና ወደው ደስ ብሏቸው በማጽደቅ ነው።

ዬጡትነት ውለታዊ ኪዳን ፍሬ ነገሩ በመሆን ተራምዶ፣ በውስጡ በመኖር በድል አድራጊነት ያበራል። ዘመኑ ሁኗል የዕዬለቱ የጀግና ፍጥረተ ነገርን የማዬት። ዳር ድንበሩ – ጫካ ዱሩና ገደሉ፤ በወርቃማ ሸንተረራማዋ ባዕት ብቻ ሳይሆን በሰለጠነው ዓለም ሳይቀር ኢትዮጵያዊ ጀግንነት ቦግ ብሎ በርቶ እዬታዬ ነው። የትናንቱ የእነ አብዲሳ አጋ፤ ዘራዕይ ደረስ፣ በላይ ዘለቀ፣ ሞገስ አስገዶምና አብርኃም ደቦጭ፤ የነመንግሥቱ ንዋይ የነሳራ ግዛውና የሌሎችም ገድላት ታሪክን ትውልዱ አንግሦ በውደሳ ብቻ ሳይታቀብ እንሆ በዓለም ሁሉ ያሉ ተተኪዎችን በጀግንነት ክታብ ተግባራቸው አንቱ አስኝቷቸዋል። ዓይናችንም በጀግንነት መስኖ በዬመስኩ እያለሙት ይገኛሉ –  አርበኞቻችን። ኑሩልን። ፈጣሪ አማላካችንም ይጠብቅልን። አሜን!

ኢትዮጵውያን በዬትኛውም ዓለም ከሀገር እርቀውም ሆነ እዛው ይኑሩ ደማቸውን ገላጭ የሆነውን የአርበኝነት ትውፊተ – አደራቸውን ሳያሾልኩ ወይንም ሳይጨፈልቁ በተግባር ያንቆጠቆጡበት ምዕተ ዓመት ማለት ይቻላል – 21ኛው ክፍለ ዘመን። በዬትኛውም ሙያ፤ በዬትኛውም ዕድሜ፤ በዬትኛውም የዕውቀት ደረጃ ይገኙ በተገኘው ክፍተት ሁሉ ስለ አረንጓዴው ቢጫ ቀዩ ዘመን አሻጋሪና ትውልድን ገንቢ እንዲሁም ነገን አሳዳሪና መሪ ሰንደቃቸው ግንባራቸውን ሳያጥፉ፤ ፊት ለፊት ወጥተው የመስዋዕትነትን ጽዋ በሐሴት እዬተቀበሉ ይገኛሉ። ማገዶነታቸውንም – አስመችተውታል። የታደሉ!

ሌት ተቀን ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ባንዳን በማጋለጥ፤ ባዕድ ስሜትን እርቃኑን በማስቀረት፤ መረጃ በማለዋወጥ፤ ወቅታዊ ሁኔታዎችን በማቀባበል፤ በተገኙ አለምአቀፍ መድረኮች ሁሉ የትናንት አርበኝነት ታሪካቸውን በበራ አዲስ ታሪክ እንሆ ያንቆጠቁጡታል። ያሳምሩታል። ያስውቡታል። ከጽንፍ እስከጽንፍ ለሰንደቃቸው “የቤትህ ቅናት በለኝ” ያለውን የልብአምላክ ዳዊት ምስብዕክ ያመሳጥሩታል። እነኝህ የተግባር ቀንዲሎቻችን፣ የአንድምታ ትውፊትነት ከደማቸው ያገኙት ሲሆን የሰውነታቸው ልዩ ህዋሳዊ ንጥረ ነገር ነውና ሁነውበታል።

ጀግኖች የትም ቦታ፤ በዬትም ሁኔታ፤ በማናቸውም ጊዜ ይፈጠራሉ። እንሆ የካቲት 17 ቀን 2014 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በግልጽና በስውር በተገኘው አሳቻ ጊዜ በሽፍታው ወያኔ ለሚታረዱት ወገኖቹ በልበ ሙሉነት ጥቃትን በድል ያወራረደው ቀንበጥ ጀግና ካፒቴን አበራ ሃይለመድህ የተፈጠረውም በዘመናችን ነው። ጀግንነትን ካለግድፈት አዬር ላይ ነፍስ ዘርቶ አብቅሎ ያሰበለ – አባወራ። ልጅአለም ብርሃናማው ሞገዱ ዓለምን አካቶ አነጋነገ። እናቱ አንተ አለሜ፣ ልጄ ለምለሜ ብላ በጠራቸው ጊዜ ቀድሞ ጥቋቷን ከቶውንም ጥበቡን ተማራምሮ ሊደርሱበት በማይችሉት ፍጹም ረቂቅ ብልህ ክንዋኔ በድል አኩርቶ ከወነው። የሰማዕቱ አሰፋ ማሩ የጠራራ ጸሐይ መስዋዕትነት ሆነ የሌሎች ቅን ወገኖች ወጥቶ ቀሪነት ጥቃት ካለ ሠራዊት ሰልፍ፤ ካለ ከባድ መሳሪያ ትርምስ ጸጥ ባለው ባዘቶ ላይ በጣሊያንና በፈረንሳይ አውሮፕላን በክብር ታጅቦ ትልሙን ሲዊዘርላንድ ጄኔባ ላይ ሰፈፉን በድል መና ከተበ። ተባርክ የእኔ ጀግና! አሳዳጊህንም ብርክ – ቅድስ – ጥብቅ! ያድርግ የዕንባ አምላክ …. የምጡን የቀለበት ዘመንም ይፍታህ ይበለው። አሜን።

የልጅአለሙ – የደማሙ

ውሉ ሰማይ ላይ ሆኖ ማማሩ፤

የጉልህ መንበሩ ገበሩ፣

የምርጥ – ዘሩ!

የመድህን ሰፋኒተ – ሥራ

ሃይሉነን ከብብክቦ አፈራ።

ፍቅር ትርጉሙ – ድሩ

የሰማይ ታምር ውቅሩ፤

ድል ሆነለት አዳሩ፣

የጀግና ውሉ ሥሩ

ትሩፋተ – ደንበሩ!

/10.11.2014 ቪንተርቱር – ሲዊዝ /

ውዶቼ ዛሬን እንዳቻላችሁ ጀግናችን አስባችሁ ብትውሉ መልካም ነው። እስኪ በዬአካውንታችሁ ጉብ አድርጉት ጀግናችን። ፍቅር ሰጥቶ ድልን በመሰዋዕትነቱ ዓርማ ለቀለበ ጀግና ሲያንሰው …. ። በተረፈ የጸሐፊ ዮፍታሄ የፅኑ መንፈስ ግንባታ ተግባር … ክፍል አንድን ማዳመጥ ትሻላችሁን? እሺ ከሆነ የፊታችን ሃሙስ በ20.11.2014 ልክ 15 ሰዓት ላይ አዬር ላይ አብረን እናወጋጋ … ናፍቆት እንዲነጋ … በቅኔው ንጉሥ በTsegaye Radio አጋፋሪነት … መሸቢያ ሳምንት – ለእኔዎቹ።

ጀግኖቻችን መንገዶቻችን ናቸው!

ጀግኖቻችን ማተቦቻችን ናቸው!

የጀግና ምንጭ ይተካል ….

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ለስብሰባ ሲቀሰቅሱ የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች 7 ቀን ተቀጠረባቸው • የሽብርተኝነት ክስ ቀርቦባቸዋል

$
0
0

(ነገረ ኢትዮጵያ) የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለህዳር 7/2007 ዓ.ም ጠርቶት ለነበረው የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ አርብ ህዳር 5/2007 ዓ.ም በቅስቀሳ ላይ እንደነበሩ የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች 7 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ሰብሳቢና የምርጫ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል ወጣት ማቲያስ መኩሪያ እና የምርጫ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል ወጣት ሳምሶን ግዛቸው በቅስቀሳ ወቅት ተይዘው አራዳ ፖሊስ መምሪያ የታሰሩ ሲሆን በዛሬው ቀን ችሎት ቀርበው የ7 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ወጣቶቹ ‹‹ሽብር በማነሳሳት›› የሚል ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን ከታሰሩበት ጊዜ ጀምሮ በተለይ ሌሊት ደህንነቶች በተደጋጋሚ በኃይልና በዛቻ እንደሚመረምሯቸው ገልጸዋል፡፡
samson gizachew and matias mekuria
ታሳሪዎቹ ህጋዊ እውቅና ለተሰጠው ስብሰባ የቀሰቀሱ መሆኑን ጠቅሰው መታሰራቸው ህገ ወጥ በመሆኑ እንዲፈለቀቁ ቢከራከሩም፤ ፖሊስ ‹‹ሌሎች ግብረ አበሮቻቸው ስላልተያዙ መያዝ አለብን፡፡ እነሱም ከተለቀቁ መረጃ ያጠፉብናል፡፡›› በሚል የጠየቀው የ7 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተቀባይት አግኝቷል፡፡ በአንጻሩ ታሳዎቹ የቀረቧቸው ቅሬታዎችና መከራከሪያዎች በዳኛዋ ተቀባይነት ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡

አመራሮቹ እስካሁን ታስረው የነበሩት አራዳ ፖሊስ መምሪያ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በርካታ እስረኞች በአንድ ስር ቤት ውስጥ በሚታሰሩበት ወረዳ 9 እስር ቤት መዛወራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሚያዚያ 19/2005 ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ በጠራበት ወቅት ቅስቀሳ ላይ የነበሩ 41 ሰዎች ለ11 ቀን በህገ ወጥ መንገድ መታሰራቸውን ያስታወሱት የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት አቶ ዮናታን ተስፋዬ በአባሎቻቸው ላይ የተፈጸመው እስር የተለመደና የታቀዱት ስራዎችን ለመቀደናቀፍ ሆን ተብሎ የተደረገ እንደሆነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ኃላፊው ጨምረውም ‹‹ገዥው ፓርቲ ወጣቶች ከትግሉ እንዲርቁ ተመሳሳይ እርምጃ የሚወስድ ቢሆንም አባሎቻችን ቆራጥ በመሆናቸው አላማው አይሳካለትም›› ብለዋል፡፡ በተለይ በአሁኑ ወቅት በርካታ ስራዎችን የታቀዱ በመሆኑ ስራዎችን ለማደናቀፍ በርካታ አባላቶቻቸውን ሊያስር እንደሚችልም ግምታቸውን ገልጸዋል፡፡

“ኦሮሞ ስለሆንኩ” እና “ዋጀብሎ”ች (ሰለሞን ስዩም)

$
0
0

Oromo intelectualበእውቀቱ ስዩም በ “እንቅልፍ እና  እድሜ” መፅሀፉ የሳለው የዋና ገጸ-ባህሪዋ  አንድሮሜዳ አፍቃሪ አለ፡፡ እምባ የማይወጣው  ደረቅ፤ ለእናቱ ሞት እንኳ የማይከፈት  የእምባ ከረጢት ያለው፡፡ በእውነቱ ደረቅ  ነበር፡፡ እድሜ ፒተር ቤንሰን ለመራችው የ  “Amnesty International” ጥናት ቢያነብ  ያለወትሮው የእንባ ጎርፍ ያስነሳ ነበር፡፡  “Because I Am Oromo” የሀገር ልጅ  በሀገሩ ልጅ ላይ ቀርቶ በየትኛውም ስጋ ለባሽ  ላይ ማድረጉ ያጠራጥራል፡፡ እምባ አልባው  የበእውቀቱ ገፀ-ባህሪ ይህንን ባየ ጊዜ  በህይወቱ ለሁለተኛ ጊዜ (አንዱ አንድሮሜዳ  ቀብር ላይ ነበር) ፊቱን በመዳፎቹ መሀል  ቀብሮ በተንሰቀሰቀ ነበር፤ እንባውን በዘራ  ነበር፤ ሰው ኦሮሞ በመሆኑ ብቻ የደረሰበትን  መጠን አልባ ጭካኔ ቢያይ፣ ደረቁ ሰው፣  በእውባው ብዛት ፊቱ ቦይ ያበጅ ነበርር፡፡

እኔ እንደዚህ ገጸ ባህሪ የእምባ ድርቅ  የመታኝ ባልሆንም፣ ሆደባሻ ግን አይደለሁም፤  ሆደ ባሻ የደረገኝ የአምንስቲ ሪፖርት  ነው፤ በርግጥ በተግባር የማውቀው የወገኔ  ሰቆቃ፡፡በዚህ ወግ የአምንስቲ ኢንተርናሽል  ሪፖርት ለመዳሰስ አልፈለግሁም፡፡  ሳምንት እና በቀጣዮቹ ጊዜያት መስመር  በመስመር እየተከታተልን እንፅፋለን፡፡ —- [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—-

 

የመኢአድ የቀድሞ ፕሬዚዳንት “መፈንቅለ ሥልጣን ተፈፅሞብኛል” አሉ

$
0
0

“መኢአድ አቶ አበባውን በፕሬዚዳንትነት አያውቃቸውም” አዲሱ ፕሬዚዳንት

0f1e0e4d195bc20c5e6996a13a7566df_Mሰሞኑን ከስልጣን የተነሱት የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሃሪ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ውጪ “መፈንቅለ ስልጣን ተፈፅሞብኛል” ያሉ ሲሆን አዲሱ የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ ማሙሸት አማረ በበኩላቸው፤ መኢአድ አቶ አበባውን በፕሬዚዳንትነት አያውቃቸውም የተመረጡበት ጉባኤም ህገ ወጥ ነው ብለዋል፡፡

ፓርቲው ባለፈው ቅዳሜና እሁድ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ላለፉት 4 አመታት ከፓርቲው አባልነታቸው ታግደው የቆዩትን አቶ ማሙሸት አማረን በፕሬዚዳንትነት የመረጠ ሲሆን እሳቸውና ሌሎች ታግደው የነበሩ የፓርቲው አባላት በድጋሚ የተመለሱት በመኢአድ አማካሪ ቦርድ ለአንድ ወር በተደረገ ጥረት በተፈጠረ እርቅ ነው ተብሏል፡፡

“በፓርቲው አመራር ውስጥ ሳልካተት በተራ አባልነት እቀጥላለሁ” ሲሉ ለፓርቲው ደብዳቤ የፃፉት አቶ አበባው መሃሪ በበኩላቸው፤ ሐምሌ 14 ቀን 2005 ዓ.ም በተደረገው የመኢአድ ጠቅላላ ጉባኤ በፕሬዚዳንትነት የመረጠው እሣቸውን መሆኑን አመልክተው “የትግሉ መስመር በአንዳንድ ብልጣብልጦችና የሴራና የአድማ አካሄድን በሚችሉ ግለሰቦች መጠለፉን ተገንዝቤያለሁ፤ ሆኖም ከንትርክና ከጭቅጭቅ በመውጣት በተራ አባልነት ለመቀጠል ወስኛለሁ” ብለዋል፡፡
አዲሶቹ የፓርቲው አመራሮች ከትናንት በስቲያ በጽ/ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የአቶ አበባው መሃሪን ካቢኔ የተካው ስራ አስፈፃሚ 20 አመራሮች እንዳሉት ጠቁመዋል፡፡

ጥቅምት 30 ቀን 2007 ዓ.ም በተደረገው የጠቅላላ ጉባኤ ምርጫ፤ አቶ ማሙሸት አማረ ፕሬዚዳንት፣ ዶ/ር ታዲዎስ ቦጋለ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም አቶ እንድሪያስ ኤሮ ም/ፕሬዚዳንትና አቶ ተስፋዬ መላኩ ዋና ፀሐፊ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ በሌላ በኩል የአቶ አበባው ካቢኔ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበሩትና በአዲሱ ፕሬዚዳንት የትምህርትና ስልጠና ጥናትና ምርምር ተጠሪ ሆነው የተመረጡት አቶ ተስፋሁን አለምነህ፤ ከአዲሱ ካቢኔ ራሳቸውን ማግለላቸውን ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡
አዲሱ አመራር ከህዳር 1 ጀምሮ ሥራውን በይፋ የጀመረ መሆኑን ያስታወቁት አዲሱ ፕሬዚዳንት፤ የሰሞኑን ጠቅላላ ጉባኤ ውጤትም ምርጫ ቦርድ ሁለት ታዛቢዎች ልኮ ሲከታተል ስለነበር ጉባኤውን ይቀበለዋል ብለን እናምናለን ብለዋል፡፡
በሐምሌ 2005 የተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ በምርጫ ቦርድ ተቀባይነት ያጣው የጉባኤው አባላት ተሟልተው ባለመገኘታቸው እንደነበር የጠቀሱት አቶ ማሙሸት፤ ሰሞኑን የተጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ግን ቀድሞ የታገዱትንም ሆነ በስራ ላይ የነበሩ አመራሮችን ያካተተ በመሆኑ የተሟላ ነው፤ ምርጫ ቦርድም ይቀበለዋል ብለዋል፡፡

በአዲሱ የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ውስጥ ከተካተቱት አመራሮች አብዛኛው ከእነ አቶ ማሙሸት ጋር ታግደው የነበሩ እንደሆነ ታውቋል፡፡
በፓርቲው የአማካሪ ቦርድ አማካኝነት የፓርቲው የበላይ ጠባቂ ኢ/ር ሃይሉ ሻውል በተገኙበት እርቅ መፈፀሙን የጠቆሙት የፓርቲው አመራሮች፤ በእርቅ ሂደቱም ማንንም ያላገለለ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ በተወሰነው መሠረት ቀድሞ የታገዱትም ሆነ በአመራር ላይ የነበሩት በጋራ በጉባኤው መሰየማቸውን አስታውቀዋል፡፡

“ወደ ጠቅላላ ጉባኤው የገባነው ጉባኤው የሚወስነውን በፀጋ ለመቀበል ተስማምተን ነው” ያሉት አቶ ማሙሸት፤ በጉባኤው ውሣኔ ያኮረፈ ቡድን ስለመኖሩ አናውቅም፤ ጠቅላላ ጉባኤው በመግባባት የተቋጨ ነው ብለዋል፡፡
አቶ ማሙሸት ይህን ይበሉ እንጂ ከአቶ አበባው መሃሪ ጋር በጠቅላላ ጉባኤው ውሣኔ ቅር የተሰኙ የፓርቲው አባላት ሃሙስ ከሰአት በኋላ በኢየሩሣሌም ሆቴል በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ያላቸውን ቅሬታ ለጋዜጠኞች በዝርዝር ገልፀዋል፡፡
ላለፉት 4 ዓመታት ታግደው በእርቅ የተመለሱት እነ አቶ ማሙሸት ወደ አመራርነት ሳይመጡ በአባልነት ለሁለት አመት ቆይተው የባህሪ ለውጥ ማድረጋቸው መገምገም አለበት ተብሎ ቢወሰንም የፓርቲው የበላይ ጠባቂ ኢ/ር ሃይሉ ሻውል በራሳቸው ውሣኔ እኛን ከመድረክ አስወርደው እነሱን ሾመዋል” ያሉት አቶ አበባው፤ ከጠቅላላ ጉባኤው ውሣኔ ውጪ የሆነ መፈንቅለ ስልጣን ተፈጽሟል ብለዋል፡፡

የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ አንድ ፕሬዚዳንት ለሁለት ዓመት ማገልገል እንዳለበት ይደነግጋል ያሉት አቶ አበባው፤ እኛ ግን አንድ አመት ከ3 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ይሄ ደንብ ተጥሶ፣ በኢ/ር ኃይሉ ፈላጭ ቆራጭነት ከስልጣን ተነስተናል ብለዋል፡፡
የእሁዱ ጠቅላላ ጉባኤ የተጠራው የ2005ቱን ጠቅላላ ጉባኤ ምልአተ ጉባኤ አሟልቶ በምርጫ ቦርድ እውቅና ለማሰጠት እንጂ አዲስ ፕሬዚዳንት ለማስመረጥ አልነበረም ሲሉ አቶ አበባው ተናግረዋል፡፡
አዲሱ ተመራጭ አቶ ማሙሸት በበኩላቸው፤ “የፓርቲው ህገ ደንብ በየሁለት ዓመቱ ጠቅላላ ጉባኤ ይካሄዳል እንደሚል ጠቁመው የሰሞኑ ጉባኤ አስቸኳይ እንጂ በደንቡ በየሁለት አመቱ ይካሄዳል የተባለው አይደለም፣ የፕሬዚዳንቱ የስልጣን ዘመን ሁለት አመት ነው የሚልም አልተቀመጠም፤ ምርጫ በየሁለት አመቱ ይካሄዳል ነው የሚለው” ብለዋል፡፡ አቶ አበባው በ2005 ተካሂዷል የሚሉት ጠቅላላ ጉባኤ ህገ ወጥ ነው ያሉት አቶ ማሙሸት፤ “መኢአድ አቶ አበባውን በፕሬዚዳንትነት አያውቃቸውም፤ ጠቅላላ ጉባኤው አልመረጣቸውም፤ ስለዚህ መፈንቅለ ስልጣን ተፈፅሞብኛል ማለት አይችሉም” ሲሉ አጣጥለዋል፡፡

ትክክለኛው ጠቅላላ ጉባኤ ተካሂዶ ፕሬዚዳንት የተመረጠው በዚህኛው ጉባኤ ነው አቶ ማሙሸት፤ “ እነ አቶ ማሙሸት ለሁለት አመታት በተራ አባልነት ይገምገሙ የሚል ሃሳብ በጠቅላላ  ጉባኤው አልቀረበም” ሲሉም አስተባብለዋል፡፡
የፓርቲው ህጋዊ ማህተም በእነ አቶ አበባው መሃሪ እጅ እንደሚገኝ የጠቆሙት አቶ ማሙሸት፤ ማህተሙ ህገወጥ ስራ እንዳይሠራበትና ለህጋዊ ስራ አስፈፃሚው እንዲመለስ ለፖሊስ አመልክተው ምላሽ እየተጠባበቁ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል አዲሶቹ አመራሮች 6 ወር ብቻ ለቀረው ምርጫ ያላቸውን ዝግጅት አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ “ከምርጫው በፊት ያሉት ሂደቶች ዲሞክራሲያዊነትና አሳታፊነት ፓርቲው ወደ ምርጫው ይገባል አይገባም የሚለውን ይወስናሉ” ያሉት አቶ ማሙሸት፤ የሰላማዊ ሰልፍ ጉዳይ፣ የህዝባዊ ስብሰባ፣ የታዛቢዎች ገለልተኛነት፣ የመገናኛ ብዙሃን ፍትሃዊ አጠቃቀም የመሳሰሉት በህገመንግስቱ መሠረት በስራ ላይ መዋላቸውን ከገመገምን በኋላ እንወስናለን” ብለዋል፡፡ከአንድነት ፓርቲ ጋር ተጀምሮ የነበረውን ውህደት በተመለከተም፤ ለውህደቱ የተካሄዱ ውይይቶችን ከሰነዶች ላይ ከመረመርን በኋላ አካሄዱን ፈትሸን፣ በቀጣይ ምን ይሆናል በሚለው ላይ መግለጫ እንሰጥበታለን ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ጽ/ቤት፣ ሰኔ 26 ቀን 2006 ዓ.ም ውህደቱን አስመልክቶ ለመኢአድ በፃፈው ደብዳቤ፤ ከአንድነት ጋር ለሚካሄደው ውህደት ጉድለት አለበት የተባለውን ጠቅላላ ጉባኤ ፓርቲው ማሟላት እንዳለበት አሳስቦ ነበር፡፡

ምንጭ  – አዲስ አድማስ

Hiber Radio: የኢትዮጵያው አገዛዝ አሮጌ 12 ሚግ 23 እና ኤም አይ 24 ሔሎኮፕተሮች ከቡልጋሪያና ከዩክሬን መግዛቱ ተዘገበ

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ህዳር 7 ቀን 2007 ፕሮግራም !

<...>

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የዘጠኙ ፓርቲዎች ትብብር እና የሰማያዊ ሊቀመንበር የአደባባይ ስብሰባው በፖሊስ ጥያቄ መበተኑን አስመልክቶ ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረጉት ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)

> እንቅስቃሴን ፓርቲዎቹ ባቀረቡልን ጥያቄ መሰረት ለማገዝ እየተንቀሳቀስን ነው…>>

አቶ ፋሲል አጥሌ እና አቶ ግርማ ታፈሰ በአገር ቤት ያለውን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ለመደገፍ እየሰሩት ስላለው ላቀረብንላቸው ጥያቄ ከሰጡት ምላሽ

ገጣሚና ባለቅኔ ሀይሉ ገ/ዮሃንስ(ገሞራው) ለአገሩና ለወገኑ ተቆርቋሪ ታላቅ የጥበብ ሰው(ልዩ ዘገባ)

>

ዶ/ር መረራ ጉዲና የወቅቱ የመድረክ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ ለህብቅ ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያደሳምጡ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን:

እንግሊዝ በኢትዮጵያ የሐይማኖት፡ የጎሳና ፖለቲካ ውጥረት አለ ስትል ባለሀብቶቿን አስጠነቀቀች

የኢትዮጵያው አገዛዝ አሮጌ 12 ሚግ 23 እና ኤም አይ 24 ሔሎኮፕተሮች ከቡልጋሪያና ከዩክሬን መግዛቱ ተዘገበ።

በቤኒሻንጉል ጉምዝ በኢቦላ ተጠርጣሪ በሽተኞች ላይ እርምጃ ይወሰድ የሚል ደብዳቤ ሾልኮ ወጣ

ደብዳቤውን አስመልክቶ የአገዛዙ ጤና ጥበቃ የሰጠው ይፋ መግለጫ የለም

ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ የአደባባይ ስብሰባ በፖሊሶች ጫና መበተኑ አላስፈላጊ መስዋእትነትን ለማስቀረት ነው ታማኝነቴን አይቀንሰውም አለ

የሁበር ጉዳይ ነገ በፍርድ ቤት ለጊዜው ይለይለታል ተብሎ ይጠበቃል

ገበርነር ብራያን ሳንዶባል ሁበር በታክሲ ተቆጣጣሪ ወይም በትራንስፖርት ተቆጣጣሪ ስር ሊሰራ ይችል ይሆናል በአዲስ መመሪያ መውጣት ላይ የተጠየቅኩት የለም ብለዋል

በቤኒሻንጉል ጉምዝ በኢቦላ ተጠርጣሪ በሽተኞች የተመድ የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን የመርማሪዎች ቡድን ኢትዮጵያ ገብቶ የመብት ጥሰቶችን ለማጣራት የመንግስትን ፈቃድ እየጠበኩ ነው አለ

በኢትዮጵያ አንዲት ግመል አድናለሁ ያለ አሽከርካሪ ለ38 ሰዎች ሕይወት መጥፋት ምክንያት ሆነ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

የኢትዮጵያ አብዮት አርባኛ ዓመትና ፖለቲካዋ

$
0
0

ከየካቲት 1966 ጀምሮ አንዳዶች የሚድኸዉ መፈንቅለ መንግሥት፤ ሌሎች አዝጋሚዉ አብዮት፤ ሌሎች ደግሞ ግብታዊዉ ለዉጥ የሚሉት አብዮት የወደፊት ሒደት በግልፅ የታየበት፤ደርግ «ያለ ምንም ደም» ከሚለዉ መሪ መፈክሩ በታቃሮኑ መቆሙ የተረጋገጠበት፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዞም በደም «በጨቀየ» ጎዳና መደናበር የጀመረበት ወቅት ነዉ።

ethio
የዛሬ አርባ ዓመት በእዚሕ ሰሞን ለረጅም ዘመን ኢትዮጵያን የገዟት የንጉሠ-ነገሥት አፄ ኃይለ ሥላሴ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በአዲሶቹ ወታደራዊ ገዢዎች የተረሸኑበት፤ በመረሸናቸዉ ኢትዮጵያዉያን በሐዘንና ደስታ ተቃራኒ ስሜት የቆዘሙበት ወር ነበር፤ ኅዳር 1967።
ከየካቲት 1966 ጀምሮ አንዳዶች የሚድኸዉ መፈንቅለ መንግሥት፤ ሌሎች አዝጋሚዉ አብዮት፤ ሌሎች ደግሞ ግብታዊዉ ለዉጥ የሚሉት አብዮት የወደፊት ሒደት በግልፅ የታየበት፤ ደርግ «ያለ ምንም ደም» ከሚለዉ መሪ መፈክሩ በታቃራኒው መቆሙ የተረጋገጠበት፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዞም በደም «በጨቀየ» ጎዳና መደናበር የጀመረበት ወቅት ነዉ።
ለዘወዳዊዉ ሥርዓት መፍረስ በተለያየ መስክ የተሠማራዉ የእዚያ ዘመኑ ኢትዮጵያዊ ትዉልድ በየፊናዉ ያደረገዉ ተቃዉሞ፣ አድማ፣ ሠልፍና አመፅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉ ሐቅ ነዉ።
ግን ያኔ የከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት ተማሪዎችን፤ መምሕራንና ምሁራንን ያክል በግንባር ቀደምትነት ለለዉጥ የታገሉና ሕዝብን ለለዉጥ የቀሰቀሱ ወገኖች ጥቂቶች ናቸዉ። ዘዉዳዊዉን ሥርዓት በመቃወም ለለወጥ ባንድ አብረዉ የታገሉት ኃይላት ግን ከለዉጡ ዋዜማ ጀምረዉ በተለያየ የፖለቲካ ፓርቲ በመደራጀት ጎራ ለይተዉ መሻኮት፤ መወጋገዝ፤ በስተመጨረሻዉም እስከ መገዳደል በደረሰ ቅራኔ ተወጠዋል።
እንዳድ ወገኖች የያኔዎቹ ወጣቶች የገቡበት ቅራኔ ኢትዮጵያን እስከ ዛሬ ለተረፋት ፖለቲካዊ ቀዉስ ዳርጓታል የሚሉ አሉ። ታሪኩ ረጅም፤ ክርክሩ ሠፊ፤ ሰበብ ምክንያቱም ዉስብስብ በመሆኑ በእዚሕ አጭር ዉይይት ገሚሱን እንኳን መዳደስ አንችልም። እንዲያዉ በደምሳሳዉ የእዚያ ትዉልድን ትዉስታ፤ ጉጉት፤ ዉጤት-ዉድቀታቸዉን፤ ተሞክሯቸዉ ላሁኑ ትዉልድ የሚኖረዉን አስተምሕሮ በጨረፍታ ለመቃኘት እንሞክራለን።
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
Source:-dw.de


በኦሮምያ ዜጎችን ማሰሩ እንደቀጠለ ነው

$
0
0

ኀዳር ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ የሚታሰሩ ዜጎች ቁጥር መበራከት የአለምን የመገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን ባገኘ ማግስት፣ አሁንም ዜጎችን በሰበብ አስባቡ እያሰሩ ለፍርድ አቅርቦ ማስፈረድ ቀጥሎአል።
አፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊግ ያወጠው ሪፖርት እንደሚያሳየው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በአምቦ ከተማ እና በሚዳ ቀኒ ወረዳ ከ20 ያላነሱ ተማሪዎች፣ መምህራንና አርሶ አደሮች ታስረዋል። እስራቱ የተፈጸመው መንግስት የአካባቢውን መሬት ለኢንቨስተሮች መስጠቱን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ ነው። ከታሰሩት መካከል
አርሶ አደር ኪጣጣ ረጋሳ፣ ተማሪ ቶሎሳ ተሾመ፣ ድሬ ማሾ፣ ታሪኩ ቡልሾ፣ ያለው ባንቲ፣ ቢንያሳ ኢባ፣ ተስፋይ ቢይነሳ እና ነጋዴ መግስቱ ሞሲሳ ይገኙበታል።
እንዲሁም ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች የጅምላ እስራቶች እየተከናወነ ነው። ብዙዎቹ በህጋዊ መንገድ የሚታገለው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አባላት በመሆናቸው ብቻ መታሰራቸውን የሚገልጸው ሊጉ፣ በጅማ የድርጅቱ አመራሮች የሆኑት አቶ አጀብ ሼክ ሙሃመድ፣ አቶ ሙሃመድ
አሚን ካልፋና አቶ ነቢብ ጀማል ታስረው 2 አመት ከስድስት ወር እንደተፈረደባቸው ጠቅሷል።
ተፈጸመ ስለተባለው እስራት ያነጋገርናቸው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ተጠሪ አቶ በቀለ ነገአ ሰዎቹ በሃሰት እንደተፈረደባቸው አረጋግጠዋል። መሳሪያ የሌላቸውን ህገወጥ መሳሪያ ደብቃችሁዋል በሚል በሃሰት ተመስክሮባቸው መታሰራቸውን አቶ በቀለ አስረድተዋል ከታሳሪዎች መካከል የአቶ አጀብ ሼክ ሙሃመድ
ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ አዳነች ለኢሳት እንደገለጹት ደግሞ ባለቤታቸው በሀሰት ተመስክሮባቸው ከታሰሩ ጀምሮ እርሳቸውም በሚደርስባቸው ማስፈራሪያ ከቤት ለመውጣት መቸገራቸውን ገልዋል። ወደ ጎረቤት ሄደው እሳት እንዳይጭሩ ከመከልከላቸውም ሌላ፣ ቤታቸው በደንጋይ የደበደባል። የባለቤታቸው ወንድም ተመሳሳይ ችግር ስላጋጠመው ስራውን ትቶ ወደ ከተማ መምጣቱንም ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሰሞኑን እስር ቤቶች በኦሮሞ ተወላጆች መሞላቱን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ አለም የመገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን ሰጥተውታል።

Article 2

$
0
0

ቀጥሎ ያለው አጭር መልዕክት ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በእስር በሚገኝበት ቃሊቲ ለተገኘው የነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር የገለጸው መልዕክቱ ነው፤ እንዲህ ቀርቧል፡፡
‹‹ነገሮችን ማወሳሰቡ ለማናችንም አይጠቅምም፡፡ ደግሞ በማናቸውም መልኩ የተወሳሰበ ችግር በመካከላችን ያለ አይመስለኝም፤ የለምም፡፡ እኛ እንደ ሀገር እና ህዝብ ከልዩነታችን ይልቅ አንድነታችን ይልቃል፡፡ ጥልቅ የሆነ ትስስሮሽ በመካከላችን አለ፡፡ በመነጣጠልና የህዝብ ተቆርቋሪዎችን በማሳደድ ስልጣናቸውን ለማስጠበቅ የሚሮጡትን ወደጎን መግፋት ይኖርብናል፡፡ ከምንም በላይ ህዝብ እና ሀገር ይቀድማል፡፡
webshet taye
‹‹አሁን እዚህ እስር ቤት ውስጥ ስላለው ነገር ብነግርህ ብዙ ጊዜ ልወስድብህ እችላለሁ፡፡ ነገር ግን ፈረንሳያውያን አንድ አባባል አላቸው፤ ‹ፊቴን፣ አካባቢየን ካየህ በቂ ነው፣ ነገሮችን ከእኔ እና አካባቢየ ላይ ማንበብ ትችላለህ› የሚል ነው አባባሉ፡፡ እዚህ ግቢ ስትገባ ያለው ሁኔታ ደስ እንደማይል ማንበብ አያቅትህም፡፡ ብዙ ነገሮች አሉ፣ ጊዜ ጠብቀው ይፋ ይሆናሉ፡፡
‹‹እንደ እናንተ ሁሉ ሰዎች መጥተው ሲጠይቁኝ ደስ እሰኛለሁ፡፡ ለምሳሌ በዛሬው የእናንተ መምጣት ምክንያት ለ15 ቀናት ያህል ተረጋግቼ እሰነብታለሁ፡፡ ትልቅ የሞራል ስንቅ አለው፡፡ እንዳልኩህ ግን መሰረታዊው ጉዳይ በሀገር ደረጃ ያለውን ትስስሮሽ ከችግሮቻችን መውጫ መንገድ አድርጎ መጠቀም መቻሉ ላይ ነው፡፡ ይህ ነው የሁላችንንም ተስፋ ወደ እውነታ የሚለውጠው፡፡ ስለ ወደፊቱ ማሰብ ይኖርብናል፡፡ አሁን ያለንበት ሁኔታ ወደ ተሻለ ነገር መለወጥ አለበት፡፡

ምግብ ከተመገቡ በኋላ ማድረግ የሌለብዎትን ያውቃሉ?

$
0
0

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

dr
✔ ገላዎን አይታጠቡ
የተመገቡት ምግብ በሚገባ እንዲፈጭ የደም ዝውውር ወደ ጨጓራዎ እንዳያዘንብል ያስፈልጋል፡፡ ገላዎን በሚታጠቡበት ጊዜ የደም ዝውውሩ በአመዛኙ ወደ እግር እና እጅ ይሄዳል፡፡ይህም የምግብ መፈጨት ሂደትን ያዛባል፡፡ ምግብ ከተመገቡ በኋላ ቢያንስ ለ30 ደቂቃ መጠበቅ ይኖርብዎታል፡፡
✔ እንቅልፍ አይተኙ
ከተመገቡ በኋላ እንቅልፍ ወዲያው መተኛት በጨጓራ ውስጥ ያሉትን ምግብ የሚፈጩ ኤንዛሚዎች ከጨጓራችን ወደ ምግብ ማስገቢያ ጉሮሮ እንዲመጡ ያደርጋል፡፡ ይህም የማቃጠል ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል፡፡
✔ የእግር መንገድ አያድርጉ
ምግብን ከተመገቡ በኋላ የእግር መንገድ ማድረግ የምግብ መፍጨት ሂደትን እንደሚያፋጥን የሚታሰብ ቢሆንም በምግብ መፈጨት ጊዜ ለሰውንት ጠቃሚ የሆኑትን ንጥረ ነገሮች እንዳይወስዱ ያደርጋል፡፡
✔ ሻይን አይጠጡ
ሻይን መጠጣት የልብ ሕመምን ለመከላከል ጠቃሚነት እንዳለው ቢታወቅም ወዲያውኑ ከምግብ በኋላ መጠጣት አይረንና የተለያዩ ፕሮቲኖች በሰውነታችን እንዳይወሰዱ ያደርጋል፡፡
✔ፍራፍሬዎችን አይመገቡ፡
ከምግብ በኋላ ወዲያውኑ ፍራፍሬዎችን መመገብ በሚገባ እንዲፈጩ ስለማያደርግ ፍራፍሬዎችን 1 ሰዓት ከምግብ በፊት ወይንም 2 ሰዓት ከምግብ በኋላ ቆይቶ መመገብ ይቻላል፡፡
✔ ሲጋራን አያጢሱ
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከምግብ በኋላ ሲጋራን ማጤስ ለካንስር ተጋላጭነትን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፡፡ ከምግብ በኃላ ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ ሲጋራ ማጤስ ለጤናዎ ጎጂ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ምግብን በሚመገቡ ጊዜ
• በትክክል ተቀምጦ መመገብ
• በዝግታ መመገብ
• በሚገባ አላምጦ መመገብ
• ከጥጋብ በላይ አለመመገብ ያስፈልጋል
ከምግብ በኃላ ትንሽ ጊዜ ሰጥተው ቁጭ ብለው እረፍት ማድረግም ይችላሉ (መተኛትን አይጨምርም)፣ ቢያንስ ለሰላሳ ደቂቃ ከላይ የተጠቀሱትን ባያደርጉ ይመከራል።
After meals do what you love- sit around with your family and have conversations…this will definitely be good for your health!
ጤና ይስጥልኝ

ለማላገጫ –የወያኔ ምርጫ። (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 20.11.2014 /ሲዊዘርላንድ ዙሪክ/

 

2007 electionሰሞኑን በተከታታይ የማነባቸው ሁሉ በምርጫ ላይ ያተኮሩ ናቸው። ቢሆን መልካም በነበረ። ህልሙ እሱ ስለሆን። ነገር ግን ምርጫ በዬትኛው ነፃነት ነው የሚከወነው? በዬጊዜው ጠንካሮችን እዬገበሩ አዲሶቹ እስኪለማመዱ ጊዜ እዬተገደለ፤ ለተመክሮና ለልምድ አዲስ – ገብ እስኪዋህድ ድረስ ወያኔ ያሻውን እንደ ልቡ እንዲከውን ነውን? ይህ አዟሪታማ ጉዞ የዛሬ አራት ዓመትም ይመጣል። ቀጣዩን አራት ዓመትም መሰሉን ለመከወን አቅዶ እንዳሻው ከባለ ጊዜ ጋር ደልቆ ይነጉዳል። ምርጫ ይመጣል – ይሄዳል። ተጠቃሚውና አትራፊው ግን በውጪ ድጋፍ ለጋሾች ሆነ በፈላጭ ቆራጭነት አገር ቤት – ወመኔው ወያኔ ነው።

አንድ ሰው ወይንም ሁለት ሰው ወይንም አምስት ሰው ከተቃዋሚ ቢመረጥ እንኳን ቋት የማይገፋ ልፊያ እንጂ ለነፃነት ትግሉ የሚፈይደው አንዳችም ነገር የለውም። የምርጫ ሂደትን ማካሄድ ቀርቶ ምርጫ ለማሰብ ንጹህ ነፃነት ያስፈልጋል። መንፈስ ከገዢዎች እስር ቤት በነፃ መለቀቅ አለበት። ህሊና ከሥውር እግርቤት መፈታት አለበት። ቃሊቲ ወይንም ቅሊንጦ ወይንም ጦላይ ወይንም ዝዋይ ያሉት ብቻ አይደሉም እሰረኞች። በኢትዮጵያ ከወያኔ ቀጥተኛ ደጋፊዎች በስተቀር ሁሉም ሰው እስረኛ ነው። ስለነገ፤ ወጥቶ ስለመግባቱ፤ የግል ቤቱ የእርሱ ስለመሆኑ አንድም ሰው እርግጠኛ አይደለም። ቋንቋ ጠፍቶ ጥቅሻ የወልዮሽ መግባቢያ ቋንቋ በሆነበት ሁኔታ ላይ እንዴት ነው በንጹህ አዬር – ባደገው የዴሞክራሲ መንፈስ ሰው ሃሳቡን ፍላጎቱንና ስሜቱን የመግልጽ አቅሙን የሚገለጸው? እንዴት? ይቻላልን? … በገፍ የሚታሰሩት ወገኖቻችን እኮ ሃሳባቸውን ሙሉን ሳይሆን ቅንጣቢ ተነፈሳችሁ ተብለው እኮ ነው ይህ ሁሉ መከራና አሳር እስከነቤተሰቦቻቸው የሚከፍሉት …..

እርግጥ ነው የተቃዋሚ ፓርቲዎች በአቅምና በመንፈስ ጠንክረው መደራጀታቸው ተፈላጊ ነገር ነው። አመራሩ ጥራት ባለው ሁኔታ ከህሊና ግንባታ ጀምሮ መሰናዶ ማደረጉም – ወሸኔ ነው። ነገ ኢትዮጵያ ሀገራችን የህብር ብሄር ፓርቲ ቀለማም ሥልጡን እስቤ፣ በነፃ የድምጽ ውድድርና ፉክክር የሚመራት እንደትሆን እንፈልጋለን። ይህ ማለት ግን በዬአራት አመቱ ወያኔ በሚነድፈው የማላጋጫ ትልሙ ማሟቂያነት መሆን ማለት አይደለም። የመመሥረታቸው አመክንዮን እኮ ወያኔ በትእቢት ገድሎታል። ምሥረታቸው እኮ ወያኔን በምርጫ ተወዳድሮ ለማሸነፍ ነበር። ግን ሁኔታው አለን? ትንሽ ብጣቂ የመተንፈሻ ቧንቧ እንኳን አላቸውን? መሪዎቻቸው ሃሳብን በሃሳብ አታግለው አሸናፊውን ሃሳብ ህዝብ እንዲደግፈው ማደረግ ይችላሉን? የኛ የነፃነት ትግሉ አካል ፓርቲያት እኮ ልክ ባዕድ ሀገር የመኖር ያህል ነው ያለባቸው ፍዳ። በሀገራቸው መሬት እኩልነታቸው ተረግጦ የመሰብሰቢያ ቦታና አደባባይ ተክልክለው በባይታዋርነት የሚቀቀሉበት ሁኔታ ነው ያለው፤ እንኳንስ ሥልጣንን ለመጋራት – እውነቱ ይሄ ነው።

አሁን ለምርጫው ስንት ወር ቀርቶታል? መሃል ሃገር የአፍሪካ ዋና ከተማ በሆነው አዲስ አበባ እንኳን ህዝብን መሰብሰብ አልተቻለም። እንኳንስ ሌላ ክ/ሀገራት ሆነ ወረዳ። ወደ ታች በተወረደ ቁጥር ደግሞ በቃ! ካራ / ቢላዋ / ተስሎ፣ ገመድ ተዘጋጅቶ፣ ተሰቅሎ ለመታረድ የመዘጋጀት ያህል ነው። እኛ ከምንሰማው ሆነ ከምናስበው በላይ እጅግ የከፋ ነው …. የባለጊዜ ጊዜኞች ዬራሳቸውን ጉልት ገንብተው አጋድመው ነፃነትን – ሰብዕዊነትን የሚርዱበት ለወሬ ነጋሪ ፍርፋሪ መረጃ በማይገኝበት ሁኔታ የታፈነና የተዘጋ ነው። ስለዚህ በዚህ በአለቀ ጊዜ በዬትኛው የኢኮኖሚ አቅም፤ በዬትኛው የማበረታቻ ድጋፍና፤ በዬትኛው የወያኔ ቅን መንፈስ ነው ተቃዋሚዎች ለውድድራቸው የሚያስፈልጋቸውን ማናቸውም ተግባር ሊከውኑ የሚችሉት። ሰው መተንፈስ ካልቻለ ይሞታል። እኔ እንደማስበው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሙት አዬር ነው።

ማገዶነቱ ሆን ግብርነቱ በተናጠል ከሆነ ጥቃቱ ሰፊ ነው። በወል ከሆነ ግን ጥቃቱም ሆነ ግብርነቱ ይቀንሳል። በሌላ በኩል የጥንካሬና የኃይል ምንጩ ደግሞ አቅምን ማድመጥ መቻል ነው። አቅምን አድምጦ በአቅም ልክ መንቀሳቀስ ለውጤት ያበቃል። አሁንም እኔ እንደማስበው ተቃዋሚ ፓርቲዎች አቅም የላቸውም። ስለምን? አቅማቸውን ሆነ ሃይልና ጉልበታቸው ጠብንጃና ካቴና በማናለኝበት ስላፈኑት። ስለዚህ ተቃዋሚዎች መጀመሪያ ማድረግ የሚኖርባቸው አቅማቸውን የቀማቸውን ሁኔቴ ማስለወጥ ነው።አቅማቸው ውጤታማ እንደሚሆን ስለሚያውቅ ነው ወያኔ በቀጥታ ጥቃቱን በአቅም ላይ የሚሰነዝረው።

አንደ እኔ ወደ ሁለተኛው ደረጃ ከመሄድ በፊት የመጀመሪያ ደረጃውን በድል አድራጊነት መወጣትን ይጠይቃል። ንቦችን እያቀበሉ በምርጫ ተወዳድረን እናሸንፋለን ማለት ግራ ነገር ነው። ምክንያቱም ከአርት ዓመት በኋላም ይሄው አሁን የሚታዬው ነገር ይደገማል። ተቃዋሚዎች የማያዳግም ተግባራትን በከወኑ ቁጥር ማለት የህዝብን መንፈስ እልምተው በአንድ አቅጣጫ ግፊት ፈጥሮ ሃይሉን መጠቀም በቻሉ ጊዜ ግን ነገን አብርተው ወደ ቀጣዩ ሂደት መሸጋገር ይችላሉ። በስተቀር ….. ግን ኢትዮጵያ በአረም ተውጣ ተክሎቿ በመጫጫት እንደ ጨለመባት ትቀጥላለች …. በጎሳ አገዛዝ ሥር – ተጎሳቁላ፤

ብዙኃኑ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ቁጭ ብለው መምከር ያለባቸው የተቀሙትን ነፃነት ለማስመለስ ህሊናዊ ሥራዎች ላይ በእጅጉ ማተኮር አለባቸው፤ በማደራጀት ተግባራት ላይ ተግተው መሥራት ይኖርባቸዋል። ይህም ቢሆን ቀላል አይደለም። ፈተናቸው ስቃያቸው –  ግብርነታቸው መጠነ ሰፊ ነው። ነገር ግን ሳይሰለቹ ነገን ለማልማት ዛሬን አድምጠው በረጅሙ አስበው ግን ከትንሿ ነጥብ ተነሰተው ግዙፉን ትውልዳዊ ድርሻ ለመወጣት መተለም ይኖርባቸዋል።

መሰናዷቸው ብቃት ካለው ወያኔ ብቻውን ተወዳድሮ የሚያደርገው የምርጫ ማሸነፍ በሁለት እግሩ ሳይቆም አፍረክርከው የህዝብን ሥርዓት መገንባት ይችላሉ። ይህን ለማድረግ ግን ለማያገኙት ፍሬ፣ ለማያፍሱት ምርት ጊዜ አለማባከኑን፤ ጉልበት አለማፍሰሱን፣ በቅጡ ሊያምኑበትና ጠንከር ካለ ውሳኔ ላይ ሊደርሱበት ይገባል። ፍላጎታቸው በምርጫ ላይ ሳይሆን የወያኔ ዬዬአራት ዓመት ዬማላገጫ ዬምርጫ ዘመኑ እንዴት ሊያከትም እንደሚችል፤ በዚህ ላይ ጠንከረው ቢሰሩበት ወያኔ ምርጫውን አሸነፍኩ ባለበት ማግስት ፎቁ ተደርምሶ ከነቅል ቋንቋራው አመድ ሊሆን ይችላል።

…. ወይንም የምርጫ መሰናዶ ላይ እያለ ነገ ምርጫ ሊካሄድ በዋዜማው እሱ ባሰናዳውና ባማቻቸው ላይ የብዙኃኑ ነፃነት ቁብ ሊል ይችላል … ማን ያውቃል? ተቃዋሚ ፓርቲዎች የበለሃሰብ አላጋጩን ዬምርጫ መንፈስን ለወያኔ ሸልመው፤ እነሱ ግን ለዘለቄታ ፍትህና ርትህ ተከታታይነት ያለው፣ ከመሬት የተነሳ፣ መሬትም የያዘ፣ የህዝብ ተደማጭነትና አክብሮት ያልተነፈገው የተረጋጋ ተግባር መከወን አለባቸው። የነቶሎ ቶሎ ቤት ለዘላቂ ነፃነት ግጥሙ አይደለም። ተቃዋሚዎች በሌላ ጉዳይ ሳይወጠሩ፣ በተቀጥላ ፍላጎት ላይ ብክነት ሳያመጡ ስክን ያለ ተግባር ከከወኑ ሚሊዮኖች ያሸንፋሉ።

የኛ የነፃነት ታጋይ ፓርቲዎች ጥድፊያውን ለወያኔ ይሸልሙት። እነሱ ግን ነፍስን ለሚታደግ፣ የእናት ልጆችን በመሬታቸው ላይ የሚያሰባስብ፣ ውብ ጠረን ያለው መርሃ ግብር ነድፈው ይንቀሳቀሱ። እርሃብ እራሱ ወያኔን ከሥሩ ይፈነቅለዋል። እራህቡን ማናገር፣ ቁሞ እራሱ እራህብ – እራህቡን እንዲገልጽ ማበረታታ፤ ለዘለአለም ከራህብ ፍውሰት ዬማስገኘት አስፈላጊነትን መተርጎም እራሱ እራህብ እንዲችል ማደረግ ከቻሉ መስዋዕትነታቸው ከግቡ ይደርሳል።

አብዛኛው የብዙ ነገር ራህብተኛ ነው። ለምሳሌ በአንድ ትልቅ ድርጅት ውስጥ በኃላፊነት የሚሰራ ሰው … የእህል ራህብ ላይኖርበት ይችላል። ግን የነፃነት ራህብ ይኖርበታል። ድብን እያለ ነው የሚኖረው። በዘሩ፣ በእምነቱ፣ በብቃቱ፣ በፈጠራ ሥራው፣ በተስፋው፤ በሁሉም ላይ በወያኔ ቁጥጥር ሥር መሆኑን ያውቀዋል። ሳይወድና ሳይፈልግ በቦታው ብቻ በቀጥታ የፓርቲ አባል እንዲሆን መገደድ ብቻም ሳይሆን ግዴታውን እንዲያሟላም ይጫነዋል – ወያኔ። … በዬትም ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ ከምርጥ ዘር በስተቀር ነፃነት ያለው ሰው አይኖርም። ከምርጥ ዘርነት ያፈነገጡትም ቢሆኑ ህሊናቸውም መንፈሳቸውም በሁለት ወገን የተወጠረ – ንጹህ አዬር ያጠረው ህይወት ነው የሚኖራቸው። … ስለዚህ በሁሉም ዘርፍ ያለውን ራህብ ቀስቅሶና አደራጅቶ ሃይል መፍጠር፤ ሃይሉ አቅም ሆኖ ነፃነትን አምጦ እንዲወልድ የማድረጉ ጉዳይ ነው አጀንዳ ሊሆን የሚገባው።

በሌላ በኩል ልብ ብሎ እያንዳንዱን ስንኝ ላነበበው የጸሐፊ ዮፍታሄ ግሩም ድንቅ የነገ መንገድ መሪ ጹሑፍ ሀገር ቤትም ሆነ ውጪ ሀገር በተግባር መተርጎም ከተቻለ፤ ማለት አድማጭ መሆን ከቻልን ቁልፉ ይገኛል። የወያኔ ሃይል እኛው ነን። ከእኛ የሚጠበቀው ትንሹ መስዋዕትነት ወያኔ ከእኛ የሚየገኘውን ሃይል ማሳጣት የምንችለባቸውን ተግባራት ላይ ዓይናችንም ሆነ መንፈሳችን ማረፍ አለበት። ሰው ከራሱ ጋር፤ ሰው ከመንፈሱ ጋር፤ ሰው ከአካሉ ጋር መምክርና መደማመጥ – መስማማት ከቻለ ወላዊ ጉዳይን በአንድ አማክሎ ጌጥ ማደረግ ብዙም አይቸግርም። እራስን ማሸነፍ ነው ወያኔን ሊገድለው የሚችለው ጉለበታም ውሳኔ። ማሸነፍ እራስን የሀገር ገዳይ ጠላትን ለመግደል ቀላሉ መፍትሄ።

አቅል አቅምን መርቶ ለድል እንዲበቃ የጎደለንን ቦታ እንፈትሸው።

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

 

 

ባለፈው ወር ብቻ 5,000 ኤርትራውያን ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል ተባለ

$
0
0

4da4c0c59ba52ecd40d2cc0712906e69_L

አገራቸውን ለቀው ወደ ጎረቤት አገሮችና ወደ አውሮፓ የሚፈልሱት ኤርትራውያን ስደተኞች በፍጥነት መጨመሩን ቀጥሎ ባለፈው የጥቅምት ወር ብቻ ከ5,000 በላይ የሚሆኑ ኤርትራውያን ድንበር አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኅዳር 8 ቀን 2007 ዓ.ም. ከወደ ጄኔቫ የወጣው የኮሚሽኑ ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ ባለፈው ወር በኢትዮጵያ መጠለያ ፈልገው የመጡት 5,000 ስደተኞች ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ከነበረው አጠቃላይ ቁጥር በ3,000 ጭማሪ አለው፡፡

እንደ ኮሚሽኑ ሪፖርት፣ ከአጠቃላይ ስደተኞቹ 90 ከመቶ የሚሆኑት ወጣቶች ሲሆኑ፣ በ18 እና 20 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ እንደሆኑም አትቷል፡፡ በተጨማሪም 78 ከመቶ የሚሆኑት ሕፃናትና ታዳጊ ኤርትራውያን ብቻቸውን ያለምንም አጋዥ ብዙ ርቀት ተጉዘው ድንበር በማቋረጥ ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ መሆኑንም ሪፖርቱ አካቷል፡፡

የኮሚሽኑ ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ በዓመቱ ወደ አውሮፓ የሚፈልሱ ኤርትራውያን ቁጥር በፍጥነት እያሻቀበና አሳሳቢነቱ እየተጠናከረ መጥቷል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2014 የመጀመሪያ አሥር ወራቶች ብቻ የኤርትራውያን ስደተኞች ቁጥር በሁለት እጥፍ ያደገ ሲሆን፣ 37,000 ኤርትራውያን ወደ አውሮፓ መጉረፍቸውንና ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው 13,000 በሁለት እጥፍ መመንደጉን ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

እንደ ኮሚሽኑ ሪፖርት፣ በአሁኑ ወቅት 216,000 ኤርትራውያን ስደተኞች በኢትዮጵያና በሱዳን ተጠልለዋል፡፡

በተለይ እ.ኤ.አ. ከ2002 ጀምሮ ኤርትራውያን ወደ ኢትዮጵያ መጉረፍ የጀመሩ ሲሆን፣ አገሪቷ ውስጥ ያለው አገዛዝን በተለይ የአስገዳጅ የውትድርና አገልግሎትን ሸሽተው የሚጓዙበት ዋነኛ ምክንያት እንደሆነም የመንግሥታቱ ድርጅት ሪፖርት ጠቁሟል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

አባ ሳሙኤልን በ16 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የማደስ ሥራ ተጀመረ

$
0
0

88655e67be4c9b67db1e1569bdaaa045_Lበኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የአባ ሳሙኤል የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫን ከቻይና መንግሥት በተገኘ የ16 ማሊዮን ዶላር ወጪ ማደስ ተጀመረ፡፡

የአባ ሳሙኤል የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ በአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት በ1904 ዓ.ም. አቃቂ ወንዝ አካባቢ ተገንብቶ ሥራ መጀመሩን ሰነዶች ይጠቁማሉ፡፡

ኃይል ማመንጫው ሲያመነጭ የነበረውን 3.3 ሜጋ ዋት ኃይል ከዓመታት በፊት አቋርጦ የነበረ ቢሆንም፣ ከቻይና መንግሥት በተገኘው ዕርዳታ ታድሶ ኅዳር 8 ቀን 2007 ዓ.ም. የውኃ ሀብት፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ወንድሙ ተክሌና የኢትዮጵያ አሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ በተገኙበት ሥራው ተጀምሯል፡፡

አባ ሳሙኤል የኃይል ማመንጫ ጣቢያን የሚያድሰው ኃይድሮ ቻይና ኋዶንግ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የተባለው የቻይና ኩባንያ ሲሆን፣ እድሳቱ እንደተጠናቀቀ ኃይል የማመንጨት አቅሙ በእጥፍ አድጐ 6.6 ሜጋ ዋት እንደሚደርስም ተነግሯል፡፡

ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ በተፋጠነ ሁኔታ በራሷ ወጪ በመገንባት ላይ መሆኗን ያስታወሱት ወ/ሮ አዜብ፣ ለረጅም ዓመታት ማለትም ከ100 ዓመታት በላይ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶ በብልሽት ምክንያት አገልግሎት መስጠት ያቋረጠውን አባ ሳሙኤል የኃይል ማመንጫ መታደሱ አጠቃላይ የኃይል ማመንጨት መጠንን ከፍ የሚያደርግ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ሽመልስ ከማልና ፈትያ የሱፍ በፕሬስ ድርጅት እየተወዛገቡ ነው

$
0
0

ነገረ ኢትዮጵያ

‹‹ችግሮች በአስቸኳይ ካልተፈቱ ለበላይ አካል እናሳውቃለን›› ፈትያ የሱፍ
‹‹ችግሮቹ ውጫዊ ናቸው›› አቶ ሽመልስ ከማል

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል እና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባህልና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፈትያ የሱፍ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዙሪያ እየተወዛገቡ እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

10387606_615182605274068_5367734512981320506_nአቶ ሽመልስ ከማል የፕሬስ ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ ሲሆኑ፣ ላለፉት አራት አመታት ድርጅቱ በተለያዩ ችግሮች ተዘፍቆ እያለ በቦርድ ሰብሳቢነታቸው ችግሮቹን መፍታት የነበረባቸው ቢሆንም ተደጋጋሚ ማሳሰቢያዎችን ችላ በማለት ድርጅቱ ከእነ ችግሮቹ እንዲዘልቅ አድርገዋል በማለት የባህልና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፈትያ የሱፍ ተናግረዋል፡፡ ሰሞኑን የ2007 የበጀት እቅድን ለመገምገም በተገናኙበት ወቅት የፕሬስ ድርጅት ቦርድ እና አስተዳደር በበርካታ ችግሮች ዙሪያ ወቀሳ እንደደረሰበትና ችግሮቹ እንዲፈቱም ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠ በራሱ ድርጅት እየታተመ የሚወጣው ኢትዮጵያን ሄራልድ ጋዜጣ በቅዳሜ እትሙ አስነብቧል፡፡

በድርጅቱ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የአስተዳደር ብልሹነት መኖሩን የተናገሩት ፈትያ የሱፍ፣ ‹‹በራሱ ድርጅት በችግር የተተበተበ ጋዜጠኛ እንደምን የሌሎችን ድርጅቶችና ግለሰቦች የአሰራር ችግሮች ሊያጋልጥ ይችላል?›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ አክለውም በተደጋጋሚ ችግሮቹ ለድርጅቱ አስተዳደር በሰራተኞች ሲቀርቡለት የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ እያለ ማለፉን የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ አውስተዋል፡፡

ፈትያ የሱፍ እንደሚሉት የፕሬስ ድርጅት ቦርድ እና አስተዳደር ችግሮቹን በአስቸኳይ የማይፈታ ከሆነ ወደሚመለከተው ከፍተኛ አካል ለማስተላለፍ ከውሳኔ ላይ መደረሱን አስረድተዋል፡፡

የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል በበኩላቸው የድርጅቱ ችግሮች ውጫዊ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ ድርጅቱ የበጀት ችግሮች እንዳለበት ያወሱት አቶ ሽመልስ፣ በተጨማሪ ግን በድርጅቱ ላይ መጥፎ እይታ ያላቸው እና መጠቀሚያ ለማድረግ የሚፈልጉ አካላት በሰራተኞች ስም አላማቸውን ለማስፈጸም የሚሯሯጡ ወገኖች አሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

‹‹የግል እና የመንግስት ሚዲያ ይለያያሉ፤ በአመለካከት፣ በአሰራርና በጥራት ልዩነት አላቸው›› በማለትም ሰራተኞቹ ፕሬስ ድርጅት እንደ ግል ሚዲያ ሊሰራ እንደማይችል ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰብስቤ ከበደ እና አቶ ሽመልስ ከማል ከፍተኛ የሆነ የጥቅም ትስስሮሽ እንዳላቸው የሚገልጹት የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች፣ በዚህ ትስስራቸው የተነሳም የአቶ ሽመልስ ከማል ባለቤት ያለምንም ውድድር በድርጅቱ በጋዜጠኝነት ተቀጥራ ምንም ስራ ሳትሰራ ደመወዝ ትወስድ እንደነበር፣ በኋላ ግን ‹ስራውን አልቻልኩትም› በሚል ከድርጅቱ እንደወረጣች ይናገራሉ፡፡

አቶ ሰብስቤ ከበደ በሰራተኞች ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸው እና በተለያዩ ስብሰባዎች በይፋ ‹አልቻልክም ድርጅቱን ልቀቅ› ተብለው በሰራተኞች እንደተነገራቸው ምንጮች ይናገራሉ፡፡ ሆኖም ግን ከአቶ ሽመልስ ከማል ጋር ባለቸው የጥቅም ትስስር በስልጣናቸው እስካሁን እንደሚገኙ፣ ይህም ድርጅቱን እና ሰራተኞችን እየጎዳ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡


እንግሊዝ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በተመለከተ ደብዳቤ መጻፏን ወያኔ አረጋገጠ

$
0
0

G7የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በተመለከተ ለወያኔዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ደብዳቤ መጻፋቸውንና ወያኔም አቋሙን ግልጽ ማድረጓን የወያኔዉ ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ሚኒስትሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን ተናገረ። ሬድዋን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባለፈዉ ማክሰኞ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ዴቪድ ካሜሩን ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደብዳቤ መጻፋቸውን የተለያዩ የውጭ ሚዲያዎች መዘገባቸውን ሰምቻለሁ ካለ በኋለ “ለምን ጻፉ ማለት አይቻልም፤ ጥያቄዉ መሆን ያለበት ምን መለሳችሁ ነው፤” በማለት የተለመደ የማጭበርበሪያ ቃላት ደርድሯል።

የተለያዩ የእንግሊዝ ሚዲያዎች ኢትዮጵያ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ላይ ቀደም ሲል የተፈረደውን የሞት ቅጣት እንዳትተገብር እንዲሁም ኢትዮጵያ ለሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ አቶ አንዳርጋቸውን የመጐብኘት ቋሚ ፈቃድ እንዲሰጥ በደብዳቤያቸው መጠየቃቸውንም ሬድዋን ሁሴን ተናግሯል።

ለዴቪድ ካሜሮን ደብዳቤ መልስ መሰጠቱን ያረጋገጠዉ ሬድዋን፣ “በተጨባጭ የተፈረደበትን ግለሰብ ነው የያዝነው፤ እንዲህ ብታደርጉት ባታደርጉት ብሎ ማንሳት ይቻላል። ምክንያቱም እነሱም የሚመለከታቸው በመሆኑ። በዚህ ምክንያት ግን የእኛ መልስ በራሳችን ሕግ መሠረት ዓለም አቀፍ ሕጉም በሚለው መሠረት የምናደርገውን እናደርጋለን፤” ብሏል። ኢትዮጵያ የምትተገብረው የራሷን ሕግ መሆኑን የገለጹት አቶ ሬድዋን፣ “ከነጭም ከጥቁርም የሚመጣን ደብዳቤ ተንተርሰን ምንም አንተገብርም፤” ብሏል። ከዚህ በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን ደብዳቤ ጽፈው፣ በኢትዮጵያ በኩልም መልስ ተስጥቷል ያለዉ ሬድዋን ሁሴን በደብዳቤው የቀረቡ ጥያቄዎች ቅሬታ እንዳላስነሱ ሁሉ መልሱም ቅሬታ አያስነሳም የሚል ተስፋ በኢትዮጵያ በኩል መኖሩን ተናግረዋል።

“እነሱ ዜጋዬ ነው ብለዋል፤ የእነሱ ዜጋ እንደ ቼ ጉቬራ ነፃ አውጣ ተብሎ ኢትዮጵያ ውስጥ አልተላከም። የእነሱ ዜጋ ከነበረ የእንግሊዝን ዴሞክራሲ ይበልጥ ለመጨመር መታገል ይችል ነበር። ነገር ግን በኢትዮጵያ በቅጥር ነብሰ ገዳይነት ካልተሰማራ በስተቀር ሌላ ሚና አልነበረውም፤” ብለዋል።

አርቲስት ተሾመ አሰግድ…የፍኖተ ጥበብ የዓመቱ ታላቅ ሰው!

$
0
0

ከሱራፌል ወንድሙ

ተሼ … አንተን የዓመቱ ታላቅ ሰው ብለን ስንሰይም ስናከብርህ፤ ክበሩ የእኛ ነው። ፍኖተ ጥበብ የጥበብ ሰውነትህን ከፍ ከፍ ሲያደርግ፣ ላንተ ደርሶ አዲስ ከፍታ ለመስጠት ሳይሆን መጪውም ትውልድ ስምህን ሲዘክር እንዲኖር ጥቁምታ ለመስጠት ነው። የግማሽ ምዕት የሙዚቃ ስራህን አስበን፣ ለዘመናት የትዝታዎቻችን አካል መሆንህን በአንክሮ ተመለክተን፣ እንደሁላችን በስደት እየኖርክ የስደት ቀናቶቻችንን በሙዚቃ ስራዎችህ ማዋዛትህን አድንቀን፣ ዓይናማዎች ነን የምንለው እኛ የሚችሉ አካል ጉዳተኞችን እንዳይችሉ በምናንጉዋጥጥበት፣ በምናደናቅፍበት ዓለም ውጣ ውረዶችን አልፈህ ለዓይነ ስውራን ወገኖቻችን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የፅናት ተምሳሌት መሆንህን ተረድተን፣ ለወጣት የኪነ ጥበብ ሰዎች መነቃቂያ መሆንህን መስክረን ነው ዛሬ በዚህች በመጥን ትንሽ በሃሳቡዋ ግን ትልቅ በሆነችው የማህብረሰባችን መድረክ ልናነግስህ የወደድነው። በብዙ የሙዚቃ መሳሪያዎች ተጫዋችነት፣ በሙዚቃ ደራሲነት፣ አቀናባሪነት እና ድምፃዊነት ገና ከ1950ዎቹ መጨረሻ ጀምረህ እስከአሁን ድረስ በጥበብህ ህይወታችንን በማድመቅህ እንዲህ በደማቁ እናደንቅሃለን።

…//…
teshome asegid
ተሾመ አሰግድ በ1942 ዓ.ም ነው በድሮዋ ወለጋ ጠቅላይ ግዛት የተወለደው። አሁን 63ኛ ዓመቱን ይዙዋል። ገና የአምስት ወር ልጅ እያለ የአይኑን ብርሃን ያጣው ተሾመ እናት ሆነው ያሳደጉት በዝምድና ቁዋጠሮ አክስት በወል ግን እናቱ የሆኑት ወይዘሮ አማካለች ይመር ናቸው። ስድስት ወንድ እና ስምንት ሴት በተወለደበት ቤተሰብ ውስጥ ተሾመ ለአቶ አሰግድ ይመር አራተኛው ልጅ ነው። ቨምንም እንኩዋን በአክስቱ ወ/ሮ አማከልች ጥረት፣ የመንደሩን ልጆች የኔም ናቸው ብሎ በሚያሳድገው ጎረቤት ክብካቤ ቢያድግም ተሾመ ራስን መቻል ይሉትን ጥበብ፣ በገዛ እግር መቆም ይሉትን ብልሃት ገና ብላቴና ሳለ ነው የሚያውቀው። በደምቢዶሎ ቡና በረንዳ ከትላልቆቹ ነጋዴዎች ጆንያ ሾልኮ የሚፈስ ቡና እየለቀመ በመሸጥ ትምህርት ቤት ሲሄድ የሚያጌጥበትን ሸራ ጫማ መግዛት ችሎ ነበር። ተሰጥኦ የሚሉት መክሊት ገና በጠዋቱ እድል ፈንታውን ያሰመረለት ተሾመ በመንደሩ ሰርግ ቤቶች አይታጣም ነበር።

“የኔን የህይወት መስመር እግዚአብሔር በመልካም ሲያበጅልኝ ነው የኖረው” ብሎ የሚያምነው ተሾመ አሰግድ፤ ሚስተር ራሰል ከሚባሉ ኦሮሚኛን አቀላጥፈው ከሚናገሩ ካናዳዊ የወንጌል መምህር ጋር የተገናኘባትን ጀምበር የዛሬ ማንነቴ መሰረት የተጣለባት ነች ይላል። እኚህ ሰው ተሾመን ገና በስድስት ዓመቱ መንገድ አግኝተውት ይህ ህፃን ትምህርት ማግኘት አለበት ብለው ጂፕ መኪናቸው ውስጥ አስገብተው ይዘውት ተፈተለኩ። አዲስ ነገርን የመከተል የልጅነት ጉጉት የሁዋሊት ወደቤተሰቦቹ ጎትቶ ያላስቀረው ተሾመም ሚስተር ራሰልን በፈቃደኝነት ተከተላቸው።

በሃገሩ ወግ ባህል ወደ ሰውነቱ ይዘልቅ የጀመረው የጥበብ እርሾ ከፈርንጁ ዘመናዊ የሙዚቃ ዕውቀት ጋር ተዋህዶ የወደፊት የሙያ እንጀራው ይጋገር ዘንድ ተሾመ ገና በልጅነቱ ከታች በእግር እየተረገጠ ከሚሰራው የድሮ ፒያኖ ጋር ተዋወቀ። ይህ የሆነው የሚስተር ራሰል ባለቤት ቤቱዋ ይህንን የሙዚቃ መሳሪያ ትጫወት ስለነበር ነው። ፒያኖውን ስትጫወት እስሩዋ ሆኖ በአርምሞ ያዳምጣት የነበረው ይህ ልጅ እሱዋ ዘወር ስትል ተደብቆ የልጅ ጣቶቹን ፒያኖው

ቁልፎች ላይ ያሩዋሩጣቸው ጀመር። ገና በአስራ ሶስት ዓመቱ ጥሩ ሙዚቃ መጫወት የመቻሉ ሚስጥር ቁዋጠሮ እንዲህ ባሉ የትላንት ወዲያ ታሪኮቹ ውስጥ ነው የሚገኙት።

ቁምጣ፣ ጥበቆና ሸሚዝ ተገዝቶለት በትምህርት ቤት ገበታ ሊቀመጥ የቻለው ተሾመ ማየት ለሚችሉት ብዙ ቦታዎችን ለአይነ ስውራን ደግሞ ጥቂት ቦታዎችን አሰናድቶ ያስተምር በነበረው የአሜሪካን ሚሽን ትምህርት ቤት ውስጥ ነበር። እናም እስከ አስር ዓመት እድሜው ድረስ እዚያው ተማረ።

አንድ ቀን በአጋጣሚ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ተሾመ የሚማርበትን ትምህርት ቤት ለመጎብኘት ደምቢዶሎ ይሄዳሉ። ህፃናቱን እየዞሩ እያናገሩ ነበርና ለታዳጊው ተሾመም ጥያቄዎችን አቀረቡለት። በኦሮምኛ ነበር ያናገሩት። “ኦሮምኛ ትችላለህ?” የሚለውን ጥያቄ አስቀድመው “እኛ ማን ነን?” ብለው ጠየቁት። እሱም ምን ልጅ ቢሆን ወቅቱ የሚፈልገውን ቁዋንቁዋ ያውቅ ነበርና “የኢትዮጵያ ብርሃን ግርማዊ ጃንሆይ” አላቸው። “ምን እንድናደረግልህ ትፈልጋለህ?” ጠየቁት። በወቅቱ ከፍተኛ የመሰለውን ነገር እንዲፈፅሙለት ነገራቸው። ንጉስ ነበሩና አልክብዳቸውም። ሸራ ጫማው ተገዛለት።

የሚማርበት ትምህርት ቤት ተማሪዎቹን ይዞ ይጉዋዝበት የገንዘብ አቅም ስላለነበረው ጥያቄውን ለቀዳማዊ ሃይለስላሴ አቅርቦ ከስምንት ተማሪዎች ገሚሶቹ ወደ ባኮ ሲሄዱ ገሚሶቹ ደግሞ ወደ ሰበታ ተሸኙ። ተሾመ ለሶስት ዓመታት ባኮ ቢመቀመጥም ለጆሮ ህክምና ስዊድን ደርሶ ከመጣ በሁዋላ ወደ ሰበታ ተዛወረ።

በወቅቱ አጠራር “መርሃ ዕውራን” ተብሎ በሚታወቀው ትምህርት ቤት ዛሬ በካናዳ ከሚኖረው አብዱቄ ከፈኔ እና ከሌሎች ባልንጀሮቹ ጋር ሙዚቃን በቅጡ መለማመድ ጀመረ። የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተርን ጨምሮ እነ ፕሮፍሰር አሸናፊ ከበደ፣ ተስፋዬ ለማ፣ ዓለማየሁ ፋንታ እና መላኩ ገላውን የመሰሉ ሰዎች ተሾመን በማበረታቱ እና የሙያ ፈር በማስያዙ ረገድ በኩል ጉልህ ሚና ተጫውተዋል።

እናም ገና በወጣትነቱ ፍሬውን ማየት ማሳየት ጀመረ። ከስድስት የሰበታ አይነ ስውራን ትምህርት ቤት ጉዋደኞቹ ጋር ሆኖ “ሬንቦው” የተባለ ቡድን አቁዋቁመው ለረዥም ጊዜ ሰርተዋል። “ይህች አጋጣሚ” የተሰኘው የጥላሁን ገሰሰ ዜማ አስቀድሞ ተሾመ አሰግድ ገና በለግላጋነቱ ሊጫወተው የነበረ ዜማ ነው። በአሁኑ ሰዓት ዊስኮነሰን የሚኖረው የህግ ባለሙያ ዶክተር በቀለ ሃይለየሱስ የደረሰው ይህ ስራ በመጀመሪያ ሊቀነቀን የነበረው በተሾመ አሰግድ ቢሆንም የፊሊፕስ ኩባንያ ባለቤት በተፅዕኖ ዜማው ለጥላሁን ገሰሰ እንዲሰጥ ቢያደርጉም ጥላሁን የተሾመን ያማረ አጨዋወት አይቶ የገበያው መሪ ባለሃብት የወሰኑትን መቀልበሱ ባይቻለው እንባውን አፍስሶ ከሙዚቃ ሽያጩ ያገኘውን ሙሉ ገቢ በወቅቱ እሱን ላጀቡት ለእነ ተሾመ አሰግድ – ለሬንቦ ባንድ ስጥቱዋል።

ተሾመ “ውጋጋን” በተባለው የኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን ማህበር የሙዚቃ ቡድን ውስጥም አገልግሉዋል። ተሾመ ከውጭ የትምህርት ቆይታው በሁዋላ ሙያዊ አበርክቶውን ከለገሰባቸው ተቁዋማት መካከል የዓይነ ስውራን ማህበር አንዱ ሲሆን አመራር በመስጠትም ሙያዊና ወገናዊ ሃላፊነቱን ተወጥቱዋል።

ተሾመ እንደአብዛኛው የወቅቱ ወጣት በእድገት በህበረት ዘመቻ ተሰልፎ ነበር። ያንን የወቅቱን ግዴታ ከተወጣም በሁዋላ ነበር ጀርመን አገር ሄዶ የፒያኖ ቅኝት እና ፒያኖ አሰራር ትምህርቱን የተከታተለው። አሁን ኬምኔትስ ተብላ በምትጠራው፤ በቀዝቃዛው ጦርነት የበርሊን ግንብ ዘመን ካርልማረክሽታት ትባል በነበረችው ከተማ በብሎንደን ሴነትሩም ወይም የዓይነ ስውራን ትምህርት ማዕከል ነበር እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1980 ዓ.ም ወደ ከፍትኛ ትምህርት ምዕራፍ የተቀላቀለው። የጀርመንኛ ቁቃንቁዋን ያጠናበትን ስድስት ወር ጨምሮ በአጠቃላይ ለሁለት ዓመት ከመንፈቅ ነበር ተሾመ ትምህርቱን በጀርመን ሃገር ተከታትሎ በዲፕሎም የተመረቀው።

ተሾመ ትምህርቱን በብቃት ጨርሶ ሃገሩን ለማገልገል ወደ ኢትዮጵያ በመንፈሰ ሙሉነት ተመልሶ በቅድሚያ ወደ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ነበር ያቀናው። ተቁዋሙ ግን በልምድ ከሌላ መምህር የተማሩትንና በዘልማድ የሚሰሩትን ዓይናማ ሰው በፒያኖ ቃኚነት ቀጥሮ እያሰራ በጀርመን ሃገር ትምህርት ቤት ገብቶ ሙያውን በብቃት ቀስሞ የመጣውን ተሾመ አሰግድን አልፈልግህም አለው። ለነገሩ ይህ የሙዚቃ ትምህርት ቤት እንደ ፐሮፌሰር አሸናፊ ከበደ አይነት በእኩልነት የሚያምኑ ሰዎች የነበሩበት መሆኑ ባይታበልም አይነ ስውራን ሙዚቃን መማርም ሆነ ማስተማር አይችሉም በሚል እና እነሱን ተቀብለን ለማስተናገድ በበቂ አልተዘጋጀንም በሚል አስባብ እስከዘንድሮ አይነ ስውራንን ከሙዚቃ ትምህርት ገበታ ነጥሎ ኖሩዋል።

ተሾመ ግን በዚያ መገፋት ተስፋ ሳይቆርጥ የባህል ሚኒሰቴርን እና ቴአትር ቤቶችን በር ደጋግሞ አንኩዋኩዋ። የእነዚህ ተቁዋማት በሮች በዋናነት ለዓይናማዎቹ ብቻ የተከፈቱ ነበሩና ማንኩዋኩዋቱ ተሰምቶ በሮቹ አልተክፈቱለትም። ተሾመ ግን “አንኩዋኩቻለሁ፤ በሮቹ ግን አለትከፈቱም” ብሎ መቆዘምን፣ ቀያጅ የሆነው የማህረሰቡ አስተሳሰብ የሚፅፍለትን ዕጣ መቀበልን ምርጫው አላደረገም። የማይከፈቱ በሮችን ከማነኩዋኩዋት ይልቅ ሌሎች በሮችን ወደ መሰራት ሄደ። በተለያዩ ባንዶች ውስጥ ማገልገሉን፣ ከእውቅ ሙዚቀኞች ጋር ተባብሮ መስራቱን ቀጠለ። በሁዋላም ጎረቤት ሃገር ጅቡቲን መኖሪያው አደረገ። ለነገሩ ወደዚያም ሄዶ መስራት ዋዛ አልነበረም። ከሃገር እንዳይወጣ በሮችን ሊቆልፉበት የታገሉም ነበሩ። ማመልከቻው በአንድ ባለስልጣን ጠረጴዛ ላይ ልታርፍ በመቻሉዋ ነበር የጅቡቲ ጉዞውም በመጨረሻ የተሳካው።

በጅቡቲ የአምስት ዓመት ቆይታው “የኩባያ ወተት” የተሰኘ ስራው ገንኖ ቢወጣም ተሾመ የተለያየ ሃገር ዜጎችን ለማዝናናት በተለያዩ ቁዋንቁዋዎች ያዜም ነበር። እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ አፋርኛ፣ ሶማልኛ እና ሌሎችም።

ተሾመ በሙዚቃ ቅንብር በኩል ከኦርኬስትራ ኢትዮጵያ ጋር ስራዎችን አበርክቱዋል። ከነዚህም ውስጥ ለጥላሁን ገሰሰ ያቀናበራቸው “አልማዝን አይቼ”፣ “ያለቀሰ ሲስቅ” እና “ውቢት ህይወቴ ነሽ” የሚሉት ተጠቃሾች ናቸው። በተጨማሪም በኦርኬስትራ ኢትዮጵያ ቆይታው የፀሐይ እንዳለን ዜማም አቀናብሩዋል። ይህም ሆኖ ግን ተሾመ ቅንብርን በሙሉ መንፈስ ስራዬ ብሎ የያዘው በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ የራሱን የድምፅ አሻራ ካተመው ከኢትዮ ስታር ባንድ ጋር ሲሰራ እንድሆነ ይናገራል።

ተወዳጁ አርቲስት ቴዎድሮስ ታደሰ ከህዝብ ጋር በሰፊው ያስተዋወቀው ስራው የሉባንጃዬ ካሴቱ እንደሆነ ይታወቃል። ከዚያ ካሴት ውስጥ በዜማም ሆነ በግጥም እንዲሁም በቅንብር የሚገደፍ አንድም ስራ የለም ብንል ማጋነን አይሆንም። እንደ ሉባንጃዬ እና ቀን ሳይመሽ ሳይጨልም በጊዜን የመሳሰሉት ምርጥ ስራዎች የተካተቱበትን ይህንን ሙሉ ስራ ያቀናበረው ተሾመ አሰግድ ነው።

በሁዋላም የሂሩት በቀለን ልጅ የመስፍን ኤልያስን እና ጥላሁንን ይተካል በሚል ማሞካሻ ይሞገስ የነበረውን ነገር ግን በልጅነቱ በሞት የተቀጨውን የደሳለኝ ቢሻውን ካሴቶችም አቀናብሩዋል። ኪቦርድ ወይም ሲንተሳይዘር የሚባለውን መሳሪያ በመጫወትም ድምፃውያንን አጅቡዋል።

የሙዚቃ መሳሪያዎች ጨዋታ ከተነሳ የተሾመ ችሎታ ሊወሳ ግድ ነው። ተሾመ ክራር፣ መሰንቆ፣ ዋሽንት፣ አኮርዲዮን፣ ፒያኖ- ኪቦርድ የመሳሰሉትን መሳሪያዎች ይጫወታል።

አርቲስት ተሾመ አሰግድ በግልና በጋራ በአጠቃላይ ስድስት አልበሞችን ለህዝብ አበርክቱዋል።

1. “ትዝታ”፡ ከሬንቦው ባንድ ጋር በመሪ ድምፃዊነት ፊሊፕስ ባስቀረፀው ሸክላ 2. “በላሽው”፡ የካሴት ስራ ከሬንቦው ባንድ ጋር
3. “የኩባያ ወተት”፡ ከሮሃ ባንድ ጋር
4. “ደርባባዬ”፡ ከሮሃ ባንድ ጋር

5. በቡድን ከኬኔዴ መንገሻ እና ራሄል ዮሐንስ ጋር
6. በቡድን ከነበዛወርቅ አስፋው፣ ኤሊያስ ተባባልና ማርታ አሻጋሪ ጋር

ተሾመ በተናጥል ተወዳጅ ከሆኑለት እና ዛሬ ድረስ ወጣቶችን እያነቃቁ ከሚገኙት ዜማዎች መካከል “የኔ አካል የኔው ነሽ”፣ “አገሬ ነገር የዛው ሙዳይ”፣ “እንዲያው ዘራፌዋ”፣ “ያዘልቃል ያልሽው ፈጣን መኪና” እና ሌሎችም ተጠቃሾች ናቸው።

ተሾመ አሰግድ በግሪክ፣ ጣልያን፣ ጀርመን፣ ሆላንድ፣ ስዊድን፣ ጅቡቲ፣ ካናዳ እና እንግሊዝ ሃገራት የሚኖሩ አድናቂዎቹን በሙዚቃ ስራዎቹ የደረሰ ሲሆን፤ በሰሜን አሜሪካ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባቸው ከተሞች ሁሉ ማለት በሚባል ደረጃ ተፈጥሮ በለገሰችውና በዘመናት ልምድና ችሎታው ሲያገለግለን ኖሩዋል።

እናመሰግንሃለን! እናከብርሃለን!

ታቦተ ጽዮንን በተመለከተ የተሠራጨው ዘገባ ሃሰት መሆኑን የፓትሪያርኩ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ (መግለጫውን ይዘናል)

$
0
0
ንቡረእድ ኤልያስ አብርሃ

ንቡረእድ ኤልያስ አብርሃ

ታቦተ ጽዮንን አስመልክቶ በቅዱስ ፓትርያርኩ መግለጫ እንደተሰጠበት አስመስሎ በሰሞኑ ሲናፈስ የነበረው ወሬ ፍጹም የፈጠራ ወሬና አሉባልታ መሆኑን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት ህዳር 6 ቀን 2007 ዓ.ም በወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡ የሐሰት ወሬው ምንጭ ዘመኑ በወለደው ኢንተርኔት አማካኝነት የተናፈሰ ሲሆን ጽሑፉ ሙሉ በሙሉ ሐሰትና እርስበርስ የሚጋጭ አንድም እውነታ የሌለው ከመሆኑም በላይ የቤተ ክርስቲያንንና የሀገርን ሰላም ለማወክ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ሴራ መሆኑን መግለጫው አስታውቆአል፡፡ በተጨማሪም ይህንን የፈጠራ ሐሰተኛ ወሬ ወደ ጎን በመተው ምዕመኑ የተለመደውን ታሪካዊ የኅዳር ጽዮን በዓል በቅድስት ከተማ በአክሱም ጽዮን በመገኘት እንዲያከብሩም ጥሪውን አስተላልፎአል፡፡ የተከበራችሁ አንባቢዎች ከቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት የተሰጠውን ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ፣ – ገጣሚዋ የኪነ ጥበብ ባለሙያ “ከማይበገረው የመንፈስ ጽናቷ ጋር”

$
0
0

Meron Getenet
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
 
 
እጅግ በጣም የተለዬ ችሎታ ያላት ወጣት ኢትዮጵያዊት የኪነ ጥበብ ባለሙያ የሆነችው ሜሮን ጌትነት ባለፈው ሳምንት “ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጠንካራ የሆነ የአማርኛ ግጥም በዩቱቢ ድረ ገጽ በመልቀቅ እንዲነበብ አድርጋለች፡፡ ሜሮንን ለመጨረሻ ጊዜ “ያየኋት” በዚህ አሁን በያዝነው ዓመት መስከረም ወር በአንዲት ኢትዮጵያዊት ልጃገረድ ላይ በተደረገው የጠለፋ ጋብቻ ወንጀል ላይ ተመስርቶ የተሰራውን ተውኔት (ፊልም) በማስታወቂያነት እንዲያገለግል በቪዲዮ ተቀርጾ  የቀረበውን ምስል ባየሁበት ጊዜ ነበር፡፡ በሀገሪቱ በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ የሚገኘው ገዥ አካል ለዚህ ጉዳይ ጆሮ ዳባ ልበስ ስላለ ያ አስቀያሚ የጠለፋ ጋብቻ ወንጀል ድርጊት አሁንም ቢሆን እንደቀጠለ ይገኛል፡፡ ድፍረት በሚለው ተውኔት ላይ ሜሮን የማትበገር የህግ ባለሙያ ገጸ ባህሪን በመላበስ ወሳኝ ሚናን በመጫወት የጥቃቱ ሰለባ ለሆነችው ልጃገረድ ነጻነት ብቻ ሳይሆን እርሷ እንደሴትነቷ የራሷን እና የሌሎችን ሴቶች ክብር ለማስጠበቅ ስኬታማ የሆነ ተውኔት ሰርታለች፡፡
 
ታላቅ ዕውቅናን ያገኘው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የአሸናፊነት ቦታን የያዘው “ድፍረት” የተሰኘው ተውኔት ባለፈው መስከረም ወር በአዲስ አበባ በአንድ ትያትር ቤት ውስጥ ለህዝብ ዕይታ ለመቅረብ የሰከንዶች ያህል ጊዜ ሲቀረው የተያዘው ዕቅድ እንዲሰረዝ በማድረግ ተውኔቱም እንዳይታይ እገዳ ተጥሎበታል፡፡ በዚያ አስደንጋጭ ድርጊት ላይ የተውኔቱ ዳይሬክተር የሆነው ዘረሰናይ ብርሀኔ ከመድረኩ ላይ በመውጣት ታላቅ ይቅርታን በመጠየቅ ለተመልካቾች እንዲህ የሚል አስደንጋጭ ማሳሰቢያ ሰጠ፣ “ይህንን ተውኔት ለተመልካች ማሳየት እንደማንችል በፖሊስ ተነግሮናል፡፡ የፍርድ ቤት ማገጃ ታዟል ተብለናል… በእውነቱ ይህ በእኛ ላይ የተሰነዘረ ግልጽ ጥቃት ነው…“ 
 
በሰንዳንስ እና በበርሊን ዓለም አቀፍ የፊልም በዓል ውድድር ላይ ቀርቦ የ2014ን የዓለም አቀፍ “የተመልካቾች ሽልማት” አሸናፊ በሆነው ተውኔት ላይ ለተሳተፉት ሁሉ ግልጽ የሆነ የውርደት ጊዜ ነበር፡፡ በተለይም ደግሞ የእርሷን የተከበረ ሙያ እና ኪናዊ ውበት ለህዝብ ለማሳየት ጠንካራ ፍላጎትን ሰንቃ በቀረበችበት ጊዜ እና በሀገሯ ክብር እና በስራዋ እንዲሁም በጓደኞቿ ላይ የደረሰውን ውርደት በማየት ሜሮን ጌትነት የተለዬ ሀዘን ደርሶባታል፡፡ እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ወያኔ) እያለ የሚጠራው በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል እንዲህ ያለውን ቆንጆ አጋጣሚ በመጠቀም ተመልካችን ከሚያስደስቱት ወጣት ከያኒያን ነጥቀው ለምን ለእራሳቸው ለማድረግ ግዴለሽነትን ለማሳየት እና ጨለምተኛ ለመሆን እንደፈለጉ ገርሞኛል (ለረዥም ጊዜ ባይሆንም እንኳ)፡፡ ወያኔን  “በሰዎች ስቃይ እና መከራ የሚረካ ገዥ አካል” ማለትም የገዥው አካል አመራሮች በሰዎች ስቃይ፣ መከራ እና ሌሎች ሰዎች መጥፎ ዕድል ሲያጋጥማቸው የሚረኩ እና የሚደሰቱ አርኩሳን ፍጡሮች የሚል ስያሜ ሰጥቻቸዋለሁ፡፡
 
በመስከረሙ የቪዲዮ ምስል ላይ ሜሮንን በተመለከትሁ ጊዜ ለእርሷ ሀዘን እና ለህዝቡ መዋረድ ጥልቅ የሆነ ስሜት ተሰማኝ፡፡ ያ ታዋቂ እና አሸናፊነትን የተቀዳጀው ምርጥ ተውኔት ለተመልካች ዕይታ ቢቀርብ ኖሮ ለሀገሯ፣ ለህዝቧ እና ለእራሷም ክብር ምርጥ የሆነ አጋጣሚ ሊሆን ይችል የነበረውን በመጨረሻዎቹ ሰከንዶች እንዲታገድ መደረጉን ከገለጸችበት ጊዜ በኋላ ተውኔቱን የማየት ጽናቴ ሟሾ ከሰመ፡፡ በዚያ የቪዲዮ የማስተዋወቂያ ምስል ላይ የነበራትን ውጫዊ ባህሪ እንደዚህ ነበር የገለጽኩት፡

…ቆንጆዋ ወጣት የፊልም ተዋንያን ሜሮን ጌትነት ምንም ነገር ትንፍሽ ሳትል በድን ሆና ተቀምጣለች፡፡ በግልጽ እንደምትታየው በጣም የማዘን እና ግራ የመጋባት ሁኔታ ይነበብባት ነበር፡፡ ከመድረኩ የሰማችው ነገር እውነት ሊሆን አይችልም በሚል የተደበላለቀ ስሜት እና እምነት ስለዚሁ ጉዳይ የተሰማትን ስሜት እና እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ሀሳቧን ለማካፈል የምትፈልገው ሰው ለማግኘት በዓይኖቿ በአካባቢው ላይ በማማተር ላይ ነበረች፡፡ ማንንም አላገኘችም እናም ከመጥፎ የሌሊት ቅዠቷ ጋር እንዳለች ያህል ቆጠረችው፡፡ ሜሮን ከተቀመጠችበት ቦታ ሆና በልማዳዊው የጸሎት አቀራረብ ዓይነት የማይሳነው አምላክ በዚህ አስደንጋጭ እና በሀገር ላይም ታላቅ ውርደትን ሊያስከትል በሚችል ሰይጣናዊ ድርጊት ላይ እጁን እንዲያስገባ እና ፍትህን በመስጠት ህዝቡን ከብስጭት ሀገሪቱን ከውርደት እንዲታደግ በሚማጸን መልኩ የእጅ መዳፎቿን ጠበቅ አድርጋ በመያዝ ወደ ላይ አንጋጠጠች፡፡ አንድ ማንንቱ በውል ያልታወቀ ሰው በዚህ አስደንጋጭ ሁኔታ ላይ ምን እንደሚሰማት ጥያቄ አቀረበላት፡፡ (አንድ ሰው ልቡ ከዓለም እይታ ላይ ተነቅሎ እንዲወገድ ከተደረገ በኋላ እንዴት ያለ ስሜት ሊሰማው ይችላል?) ሜሮን በግልጽ በሚታይ መልኩ በተሰበረ ልብ ውስጥ ናት፡፡ ሆኖም ግን ጸጥታን የተጎናጸፈ እና ጀግንነትን የሚያንጸባርቅ ዓይነት ገጽታዋን ታሳያለች፡፡ ንዴቷን እና ድንጋጤዋን ለመደበቅ ትግል ስታደርግ በግልጽ ትታያለች፡፡ ከእንባዎቿ ጋር እፈሳለሁ አትፈሱም ትንቅንቅ ገጥመዋል፡፡ ሆኖም ግን በተሰበረ ልብ ውስጥ ያለች ብትመስልም እርሷ ግን በፍጹም የተሰበረ መንፈስ እና ልብ ውስጥ አይደለችም…
 
ክብር ማጣት፣ ክብርን ማግኘት፣
 
ባለፈው መስከረም ወር ድፍረት በተባለው የማስታዋቂያ ፊልም ላይ የሀዘን እና የውርደት ስሜት ያጠላባትን ሜሮንን ከተመለከትሁ በኋላ ወንጀለኛው የህወሀት ገዥ አካል የሜሮንን ኪናዊ ውበት የተላበሰውን ተውኔት ለእይታ እንዳይቀርብ በማገድ እና እርሷንም በስነልቦና እንድትጎዳ የተቻለውን ሁሉ በማድረግ ተሳክቶለታል የሚለውን እውነታ በግርድፉ ተቀብየው ነበር ፡፡ ሆኖም ግን በቅርቡ “ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ” በሚል ርዕስ ያወጣችውን ግጥም ካዳመጥኩ በኋላ መንፈሷ አንድቺም አንዳልተነካ ተገነዘብኩ፡፡ ሜሮን የደረሰባትን ስቃይና መከራ ለማስታገስ ስትል በግጥሞቿ እራሷን ለመከላከል እና ለማጽናነት እንዲሁም ለመሞገት ጥረት አድርጋለች፡፡ የእርሷን ኪናዊ ውበት ለመጨፍለቅ ጥረት ያደረጉትን ኃይሎች ጽናትን እና ድፍረትን በተላበሰ መልኩ እስከ አፍንጫቸው ድረስ ነግራቸዋለች፡፡ ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በሚለው ግጥሟ የሜሮንን እራስ በእብሪተኞች ተመትቶ አየሁት; ሆኖም ግን ጭንቅላቷ በምንም ዓይነት መልኩ አላጎነበሰም፣ ዘንበልም አላለም፡፡ የመንፈስ ጽናቷ ተጎድቶ አየሁት ሆኖም ግን አይበገሬነት እና የአሸናፊነት ጽናቷ በጉልህ ታየኝ ፡፡ በፊቷ ላይ የአምባገነኖችን አደጋ አነበብኩ ሆኖም ግን የማትፈራ እና የማትበገር እንደምትሆን ሆና አገኘኋት፡፡ ዕውቅ ገጣሚ የሆኑትን የዊሊያም ኢርነስት ሄንለይ  ሀረጎች በመዋስ በሀገሬ፣ ህዝቤ እና ክብሬ ሜሮን የማትበገር! (ሜሮን ፍጹም የማትሸነፍ! የማትበገር ) ሆና አገኘኋት፡፡  ሜሮን አትበገሬ !!! 
 
ቃላት የሰውን ባህሪያት የሚገልጹ ከሆኑ “ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ” የሜሮን ግጥም የስብዕና መገለጫ ከሆኑት ልዩ የመሳብ ኃይል፣ ብሩህ ህሊና እና ክብር እና ሞገስ የካርቦን ክሮች ጋር በጽኑ የተሰሩ እና ከአረብ ብረት 10 ጊዜ እጥፍ የጠነከሩ ባህሪያት ሜሮን አንዳላት ያሳያሉ፡፡ ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ የሚሉት የእርሷ ግጥም ቃላት እንደ ቁጡው የሳሙራይ ጎራዴ የሚከትፉ፣ እንደ አለት መፈርከሻ ደማሚት በኃይል የሚመቱ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ቃል የህወሀትን የፖለቲካ የማታለያ ሸፍጥ ነቅሶ የሚያወጣ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሀረግ የህወሀትን የአስመሳይነት ባህሪ አፍረጥርጦ የሚያጋልጥ ነው፡፡ እያንዳንዱ የግጥም ስንኝ የህወሀትን አሳፋሪ ከሀዲነት ፈልፍሎ የሚያወጣ ነው፡፡ ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ የህወሀትን ቀጣፊነት፣ የህወሀትን በሙስና ባህር ውስጥ እየዋኘ ያለ የበከተ ድርጅት መሆኑን እና ህወሀት የሰብአዊ መብቶችን እንደ ገና/ታህሳስ በርበሬ እየደቆሰ ያለ የወንጀለኛ ወሮበላ ቡድን ስብስብ መሆኑን በግልጽ ያመላክታል፡፡
 
ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ የተሰኘው ግጥም እንደ ድህረ ጸረ-አፓርታይድ/የጸረ-ዘረኝነት የተቃውሞ ትግል፣
 
የግጥም ዋና እና ልዩ የውበት መገለጫው ለአንባቢው እና ለአድማጩ የሚቀርቡት ቃላት እና ሀረጎች ጥልቀት ላለው ትርጉም እና ለአጠቃላይ ግንዛቤ በመጋበዝ ብዙ ምርምር እንዲደግ የመፍቀድ ችሎታቸው ነው፡፡ ግጥሙ አንድ ጊዜ በገጣሚው ከተወለደ እና ለተጠቃሚው ከደረሰ በኋላ ወዲያውኑ ህይወት ከሰጠው አካል በመለየት ነጻ በመሆን የእራሱን ህይወት ይጀምራል፡፡ ግጥም በእያንዳንዱ/ዷ አንባቢ እና አድማጭ አዕምሮ ውስጥ የእራሱን መኖሪያ ያዘጋጃል፡፡ ግጥሙ የእራሱን ድብቅ መልዕከት ለመግለጽ እና ሚስጥራዊነቱ እንዲታወቅ እንዲሁም እንቆቅልሹን ለመፍታት እንዲቻል በግጥም አፍቃሪው የቀዶ ጥገና ማካሄጃ ጠረጴዛ አዕምሮ ላይ ይዘረጋል፡፡ ድብቁን ትርጉም ፈልጎ ማግኘት፣ ከሸፍጡ እና ለትርጉም ክፍት ከሆኑ ቃላት ሀረጎች መካከል ለይቶ በማውጣት ግጥሙ ለማስተላለፍ የፈለገውን ዓላማ እና የግጥሙን እውነተኛ ትርጉም ሚስጥር ማጋለጥ፣ መፍታት እና ግልጽ ማድረግ የአንባቢው እና የአድማጩ ተግባር ነው፡፡    
 
በተለያዩ የስነጽሁፍ የጥበብ ስራዎች እና በአሜሪካ የባህላዊ ይዘት ያላቸው ትምህርቶች እና ጽሁፎች እራሱን እንዳስተማረ ሰው የትርጉም ገላጭነት እና ትንታኔን የመስጠት ባህሪ ባላቸው የስነጽሁፍ መስኮች ላይ ጥቅም ሊያስገኙ የሚያስችሉ ጥቂት የማይባሉ እውቀቶችን ሸምቻለሁ፡፡ ለእኔ ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ግጥም ግላዊ ትንታኔ በዋናነት የድህረ የጸረ-አፓርታይድ/የጸረ-ዘረኝነት የተቃውሞ ትግል ግጥም ነው፡፡   
 
ዘረኝነት በደቡብ አፍሪካ የጥቂት አፍሪካውያን/ት የነጭ ዘሮች የፖለቲካ የበላይነቱን በመቆጣጠር በአብዛኞቹ በጥቁር አፍሪካውያን/ት ዘንድ ፍጹም የሆነ የፖለቲካ ጫናን በማሳደር ሲገዙ የነበረበት፣ እንዲሁም የምጣኔ ሀብቱን ሙሉ በሙሉ በእነዚህ ጥቂት ዘረኛ ነጮች የበላይነት ተይዞ የሚመራበት ስርዓት ነበር፡፡ የደቡብ አፍሪካ የዘርኝነት ስርዓት የተመሰረተው ባንቱስታንስ (በትክክል ትርጉሙ የትውልድ “ክልል”) ተብሎ ተለይቶ የተቀመጠ አስተዳደር በሚጠራ እና ፍጹም የሆነ የዘረኝነት አድልኦ የሚፈጽመው የጥቂት የነጮች የበላይነት በሚል የህዝቦች አመዳደብ ሁኔታ ነበር፡፡ ጥቂቶቹ አፍሪካውያን/ት የነጮች የበላይነት በዘረኝነት ዕኩይ ምግባር በመታበይ የበላይነት ስሜት ይሰማቸዋል ምክንያቱም በወታደራዊ ኃይል አሸንፈው የመጡ ስለሆነ ምንም ዓይነት የጊዜ ገደብ ሳይኖር እንደፈለጉ ህዝቡን እንደብረት ቀጥቅጠው እንደ ሰም አቅልጠው የመግዛት እና በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለመኖር እንዲሁም እነርሱን የሚቃወም ማናቸውም ዓይነት ኃይል ቢመጣ ርህራሄ የሌለው የሰብአዊ መብት ረገጣ ከማካሄድ የማይታገሱ አምባገነኖች ነበሩ፡፡ በአፍሪካ የጥቂት ነጮች የዘረኝነት አገዛዝ ጊዜ አምስት ዓይነት የዜጎች ምድቦች ነበሩ፡፡ የመጀመሪያው መደብ የሀገሪቱን የፓርቲ አመራሮች፣ የእነርሱ ደጋፊ ሀብታሞችን እና የእነርሱን ግብረ አበሮች ያካትታል፡፡ ሁለተኛው የዜጎች መደብ አፍሪካን የሚባል ቋንቋ የሚናገሩ እና በ17ኛው ክፍለ ዘመን ከሆላንድ አገር መጥተው የሰፈሩ እና የሆላንድ ዝርያ ያላቸው ተራ አፍሪካውያንን/ትን ያጠቃልላል፡፡ የነጭ እና የጥቁር ድብልቅ ዝርያ ያላቸው ዜጎች ደግሞ በሶስተኛ ደረጃ ምድብ ይካተታሉ፡፡ የህንድ እና የኤስያ ዝርያ ያላቸው ዜጎች ደግሞ በአራተኛ ደረጃ መደብ ይጠቃለላሉ፡፡ አብዛኞቹ የአፍሪካ ዜጎች በጥቂት የነጮች የበላይነት የሚመራው ገዥ አካል ለምንም የማይጠቅሙ እና ዋጋ ቢስ ዜጎች ብሎ የፈረጃቸው ደግሞ በአምስተኛ ምድብ ላይ ተካተዋል፡፡
 
እንደ ደቡብ አፍሪካው የጥቂት የነጮች የዘረኛ የፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ሁሉ በኢትዮጵያ የፖለቲካ አመራሩ፣ መንግስታዊ ቢሮክራሲው፣ የፖሊስ ኃይሉ፣ የደህንነት እና የወታደራዊ ተቋማት በሙሉ በህወሀት የገዥ አካል በብቸኝነት ተይዘዋል፡፡ 

እንደ ደቡብ አፍሪካው የጥቂት የነጮች የዘረኛ የፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ሁሉ ደም መጣጩ የህወሀት ገዥ አካል እና ደጋፊዎቹ ሁሉንም የኢኮኖሚ ዘርፎች ማለትም የባንክ ኢንዱስትሪውን፣ የግንባታ እና የስሚንቶ ምርቶችን፣ የማዕድን ስራውን፣ የትራንስፖርት ዘርፉን፣ የኢንሹራንስ እና የአስመጭ እና ላኪ ዘርፉን በብቸኝነት አጠቃልሎ ይዟል፡፡ 

እንደ ደቡብ አፍሪካው የጥቂት የነጮች የዘረኛ የፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ሁሉ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃ ዜጋ መደቦች የህወሀት ገዥዎች ናቸው፡፡ የሁለተኛ ዜጋ ቡድን ደግሞ የህዝብን ሀብት እየዘረፉ እና ከህግ አግባብ ውጭ በሆነ መልኩ የሀገሪቱን ጥሪት በብቸኝነት እየተቀራመቱ የሚገኙት ያለአግባብ በሀብት የደለቡት የህወሀት አሽከሮች እና ደጋፊዎቻቸው ናቸው፡፡ ዛሬ በአዲስ አበባ እና በሌሎች የክፍለ ሀገር ከተሞች እየተገነቡ ያሉት ትላልቅ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች በባለቤቶቹ የድካም እና የላብ ውጤት የተገነቡ ሳይሆኑ በአንጡራ የአትዮጵያ ህዝብ ገንዘብ እና ንብረት የተሰሩ መሆናቸው አገር ያወቀው እና ጸሐይ የሞቀው ቢሆንም ጊዜው ሲደርስ የሚጠየቁበት እና ለባለቤቱ ህዝብ የሚመለሱ መሆናቸውን በውል ሊያጠኑት ይገባል፡፡ ገዥው የወያኔ ቡድን አባላትም አይን ባወጣ መልኩ በሌሎች ዘመዶቻቸው እና በአቃጣሪ ሎሌዎቻቸው ስም በማስመሰያነት ይዘዋቸው ያሉት ህንጻዎች እንዲሁም በውጭ አገሮች በተለያዩ ዓለም አቀፍ ባንኮች የባንክ ደብተር እየከፈቱ የሚያጭቁት የዶላር ሀብት በተራ ዘራፋ ከኢትዮጵያ ደኃ ህዝብ በጠመንጃ አፈሙዝ እያስፈራሩ የነጠቁት እንጅ የላባቸው ዋጋ ስላልሆነ በህግ አግባብ ለባለንብረቱ የሚመለስ እንደሆነ እና ያ ሀብት ለዘራፊው የወሮበላ ቡድን ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ እንደሆነ እንዲገነዘቡት ያስፈልጋል፡፡

በሶስተኛ ዜግነት መደብ  የሚመደቡት ዜጎች ደግሞ ለግል ጥቅማቸው እና ሌሎች ገዥው አካል የውጭ ኢንቨስተሮች እያለ የሚጠራቸው ከከርሳቸው ውጭ ሌላ ስለምንም ጉዳይ የማያስቡት “ሆዳሞች” እየተባሉ የሚጠሩት ሆድ አደሮች ይካተታሉ፡፡ እነዚህ ሆድ አደሮች መዋዕለ ነዋይን በሀገር ውስጥ ማፍሰስ በሚል ስልት ከገዥው አካል ጋር በመሞዳሞድ እና ሌላ የፖለቲካ ሸፍጥን ለመስራት እንዲችል በማስመሰያነት የሚጠቀምባቸው ስመ ዲያስፖራ ኢትዮያውያን/ት በጭንቅላታቸው ሳይሆን በቦርጫቸው የሚያስቡ እኩይ ምግባር ያላቸው በኢትዮጵያ ህዝብ መከራ እና ስቃይ ላይ ቁማር የሚጫወቱ የገዥው አካል ሎሌዎች እና ሆድ አደሮች ናቸው፡፡ 

አራተኛው የዜግነት መደብ እራሱን ኢህአዴግ እያለ የሚጠራው እና በኢትዮጵያ ውስጥ እውነተኛ የብዙሀን ፓርቲ ስርዓት እንዳለ ለማስመሰል በሎሌነት እና አሽከርነት እንዲሁም በተራ ጥቅም እየተደለሉ በውስጥ ግን እውነተኛውን ፈላጭ ቆራጭ ገዥ አካል ህወሀትን ለማስመሰያነት የሚደብቁ ሆዳሞችን ያካትታል፡፡ እነዚህ ሆዳሞች ከየብሄረሰቡ ለይስሙላ ስልጣን እየተወከሉ ለህወሀት እኩይ ተልዕኮ በአስፈጻሚነት የቆሙ በእራሳቸው ስብዕና መመራት የማይችሉ በአዕምሯቸው ሳይሆን በቦርጫቸው የሚያስቡ ሆድ አደሮች ናቸው፡፡ እነዚህ ፍጡሮች በህገወጥ መልክ የዜጎችን መሬት እየተቀራመቱ በመሸጥ ኪሳቸውን እስካደለቡ ድረስ፣ በሙስና እና በምልጃ የተዘረጠጠውን ቦርጫቸውን እና ቀፈታቸውን እስከሞሉ ድረስ ነጻ ሆነው በእራሳቸው አስበው ሊሰሩበት በማይችሉት የስልጣን ወንበር ላይ እንደ አሻንጉሊት ፊጥ ብለው ርካሽ የከርስ ጥቅሞቻቸውን ከማግበስበስ ውጭ ለኢትዮጵያ ህዝብ ፋይዳ ያለው ስራ የማይሰሩ ሆድ አምላኩ ናቸው፡፡ 

በመጨረሻ እና በአምስተኛ ደረጃ የዜግነት መደብ ላይ የተቀመጡት ደግሞ ምንም ነገር የሌላቸው ሆኖም ግን በስርዓቱ ጎስቋላ አመራር እየተደቆሱ፣ እንደ በግ እየታሰሩ፣ እንደ እባብ እየተቀጠቀጡ የሚገደሉ፣ እንደ ፈረስ የሚጋለቡ፣ ሲያስፈልግም ከገዛ ሀገራቸው በማን አለብኝነት ውጡ እየተባሉ ለስደት የሚዳረጉ፣ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እናንተ የሌላ ብሄረሰብ አባል ናችሁ ውጡ እየተባሉ የሚባረሩ፣ በዘመናት ያፈሯቸውን ንብረቶቻቸውን የሚቀሙ፣  የሚገደሉ እና ሁሉም ዓይነት በምድር ላይ ያለ የጭቆና ዓይነት የሚተገበርባቸው ንጹህ ኢትዮጵያውያን/ት ናቸው፡፡  
 
እንደ ደቡብ አፍሪካው የጥቂት የነጮች የፈላጭ ቆራጭነት አገዛዝ የአፍሪካ ብሄራዊ ፓርቲ ሁሉ የወያኔ አመራሮች እና አባላትም ለዘላለም ኢትዮጵያን ለመግዛት የትውልድ መብት ያላቸው እና እራሳቸውን የተቀቡ የዘር ቅብአቶች አድርገው ይቆጥራሉ፣ ምክንያቱም አሁን እየዘረፉ ያሉበትን ከንቱ ስልጣን ያገኙት በወታደራዊ ኃይል አሸንፈው እና የማቋርጥ ኃይልን በመጠቀም በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለመኖር ፍላጎት ስላላቸው ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ እንዳለው የዘረኛው ጥቂት ነጮች የፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ሁሉ ኢትዮጵያም ክልል (በመሰረታዊ ፍልስፍናው እና በፖሊሲ ደረጃም ከአፓርታይድ የዘረኛ መንግስት ጋር አንድ ዓይነት የሆነ) እየተባሉ በሚጠሩ ለከብቶች እንደሚከለሉ የግጦሽ መሬቶች ሁሉ በዘር የአንድ አካባቢ ህዝቦችን በዚያው ተወስነው ስለሌላው የሀገሪቱ ክፍሎች የማይመለከታቸው እና ተዘዋውረው የመስራት መብታቸውን ገደቦ በካድሬዎቹ አማካይነት የጠብ አጫሪነት ድርጊቶችን እየፈጸሙ ብሄር ከብሄረሰቦች እያጋጩ ዜጎቻችንን በማስጨረስ ላይ ይገኛሉ፡፡ እንደ ደቡብ አፍሪካው የጥቂት የነጮች የዘረኛ የፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ እና አብዛኛው የደቡብ አፍሪካ ህዝቦች መሬት አልባ እንደተደረጉት ሁሉ በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ኢትዮያውያን/ት መሬት አልባ እንዲሆኑ ተደርገዋል (መሬቶቻቸውም በርካሽ ቁርጥራጭ ገንዘብ በጨረታ ለወያኔ እና ለዓለም አቀፍ የመሬት ተቀራማቾች ተቸብችበዋል፣ በመቸብቸብም ላይ ይገኛሉ)፣ ምክንያቱም መንግስት አጠቃሎ በእራሱ ቁጥጥር ስር አውሏል፡፡ የነጻ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ከምዕራባውያን አበዳሪ እና እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ማታለያነት ያለፈ ፋይዳ የሌለው ጉዳይ በመሆኑ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው መንግስት ማን ነው? ወያኔ/ህወሀት!
 
የደቡብ ጥቁር አፍሪካውያን/ት ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት እና በአሁኑ ጊዜ ደግሞ አብዛኛው  የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ የሆነ አንድ ዓይነት ነገር አላቸው፡ አጠቃላይ የሆነ አገር አልባነት፣ ዜግነት አልባነት እና ከሀዲነት፡፡ ስለሆነም ሜሮን ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በማለት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲሰማው ድምጿን ከፍ አድርጋ ትጮሀለች፡፡
 
የፖለቲካ ተቃዋሚ ግጥም እንደመሆኑ መጠን ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ እንደዚህ ያለውን ዜጎችን በስነጽሁፋዊ ይዘት መመደብን ይቃወማል፡፡ ልዩ በሆነ መልኩ የተለያዩ የግጥም ዓይነቶችን በውስጡ ሊያቅፍ ይችላል፡፡ የምልክትነት ስብስቦች ሊኖሩት ይችላል፣ ሆኖም ግን ሊያጠራጥር በማይችል መልኩ እውነተኛ እና ተገቢ የሆነውን መልዕክት ሊያስተላልፍ የሚችል መሆን አለበት፡፡
 
ግጥሙ ስሜትን የሚኮረኩሩ እና ለየት ያለ ትርጉም ያለው ይመስላል፣ ቢሆንም ግን በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለሚገኙት ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ ለሚጠቀሙት እውነታውን እስከ አፍንጫቸው ድረስ ይነግራቸዋል፡፡ ይህ ግጥም የነገሮች ተመሳስሎን፣ የተዘዋዋሪ ገላጭነትን፣ ተመሳሳይነት ያላቸውን አናባቢዎች የመጠቀም ስልትን፣ የቃላት ጨዋታ አጠቃቀምን፣ አንድን ነገር በሌላ አስመስሎ መግለጽን እና ትክክለኛ ምሳሌ መስጠትን ይጠቀማል፡፡ ሆኖም ግን ተራኪ እና ኪናዊ ውበትን የተላበሰ የማያቋርጥ፣ መሳጭ እና ቀልብን የሚማርክ  የግጥም ዓይነት ነው፡፡ ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ የሚለው ግጥም በቴክኒካዊ አቀራረቡ የሚማርክ እና መሳጭ መሆኑ እንዳለ ሆኖ በእያንዳንዱ ቃላት እና ሀረጎች ላይ የተካተቱት የፖለቲካ ተቃውሞዎች ከምንም በላይ ስሜቴን ነክተውታል፡፡ 

(ማስታዋሻ፡ በዚህ ጽሁፍ የቀረቡት ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ የሚሉት ስንኞች የእንግሊዝኛ ትርጉሞች የእራሴ ናቸው ሆኖም ግን ሌሎችም ጠቃሚ የሆኑ ነገሮችን የሚያበረክቱ መሆኑ እንዳለ ሆኖ፡ የተመሳስሎ፣ የስነጽሁፍ ውበት እና የባህል ውስብስብነት ያላቸውን የአማርኛ ግጥሞችን መተርጎም እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው፡፡ ከዚህ በታች በእንግሊዝኛ ተርጉሜ ያቀረብኩት የሜሮንን ግጥሞች ውስጣዊ ይዘት ሙሉ ትርጉም ይወክላል ብዬ እገምታለሁ፡፡)
 
ገና ከመጀመሪያ በዩቱቤ ኦዲዪዮ ሲደመጥ ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ወያኔን እና የወያኔ የክርስትና አባት የሆነውን አሁን በህይወት የሌለውን መለስ ዜናዊን ለመክስስ ተዘጋጅቶ የቀረበ የወንጀለኞች የክስ መጥሪያ እንደሆነ አድርጌ ነው ያሰብኩት፡፡ በሀገሪቱ ላይ ደባ እና ሸፍጥ በመስራት ላይ የሚገኙት የወሮበላ እና የወንጀለኛ ቡድኖች ሁሉንም የሀገሪቱን ሀብት በመዝረፍ፣ ሁሉንም ህዝብ ዜግነት አልባ በማድረግ እና የሁሉንም ህዝብ ክብር በማዋረድ በሚል አቃቤ ህጉ የክስ ጭብጡን ሲያነብ የሚጠቀምባቸው ቃላት እንደ ገደል ማሚቶ በእራሳቸው ያስተጋባሉ፡፡ በእርግጥ ግጥሙ በስም ህወሀት/ወያኔ እነማን እንደሆኑ አይገልጽም፣ ሆኖም ግን በተዘዋዋሪ መንገድ በጣም ከፍተኛ ወንጀሎችን የፈጸሙ እና መለስተኛ ወንጀሎችን የፈጸሙ በሚል የቀረበው አገላለጽ የወንጀለኞችን ማንነት በተጨባጭ የሚያመላክት ነው፡፡
 
ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ የሚለው የግጥም መድብል የተመሰረተው እና የሚያጠነጥነው የዜግነት መብቶች እጦት፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ፣  ሰብአዊ ክብርን ማጣት እና መዋረድ፣ ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ መጠቀም፣ ሙስና፣ የተምኔታዊ የሀሰት የምጣኔ ሀብት ልማት፣ እና በኢትዮጵያ የገቢ ኢፍትኃዊነት በሚሉ ርዕሶች ስር ነው፡፡ የግጥም መድበሉ አገራዊ የሆኑ በርካታ ጉዳዮችን የዳሰሰ፣ በጣም ጠልቆ በመግባት ስሜትን የሚቀሰቅስ እና የዚህ ግጥም አድማጮች የወያኔን ገዥ አካል የጭቆና አገዛዝ እና የኢትዮጵያውያንን/ትን ከሰብአዊነት በወረደ መልኩ ግፍ እየተፈጸመባቸው ያሉ መሆኑን ስዕላዊ የሆነ መግለጫ በመስጠት ኃይላቸውን አስተባብረው ይህንን ያገጠጠ እና ያፈጠጠ የዕውር ድንብር ስርዓት በመራራው ትግላቸው አሽቀንጥረው በመጣል የእራሳቸውን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መመስረት እንዲችሉ የሚያነሳሳ ጠንካራ የግጥም መድብል ነው፡፡  
 
በእኔ የትንታኔ አተረጓጎም ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ጸጥ ያለውን የኢትዮጵያውያንን/ትን ድምጽ እንደ ገደል ማሚቶ እንዲያስተጋባ የሚያደርግ እና በሚሊየኖች የሚቆጠሩትን በእራሳቸው ሀገር የተገፉትን እና ባይተዋር የሆኑትን እንዲሁም እነርሱ እንዳይታዩ እና ተረስተው እንዲቀመጡ የተደረጉትን ብቻ ሳይሆን እንደ ሰው ያልተቆጠሩትን፣ ከምንም ያልተቆጠሩትን ኢትዮጵያውያን/ት የተስፋ መቁረጥ ጸጥታ የሚመልስ እና ለአዲስ የትግል ምዕራፍ በአዲስ ወኔ ባማነሳሳት እውነተኛ የሀገሩ ባለቤት እና አድራጊ ፈጣሪ በመሆን የወያኔን የጅብ መንጋ ስብስብ ከምድረ ገጽ ኢትዮጵያ በማስወገድ ሰላም፣ ዴሞክራሲ፣ ሰብአዊ መብት እና የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት አዲሲቱን ኢትዮጵያ በአምባገነኖች ከርሰ መቃብር ላይ ይገነባል የሚል ትርጉምን ይሰጠኛል፡፡ በፍቅር የተሞላው እና ለተገፉት ምንም ለሌላቸው ኢትዮጵያውያን/ት የሚጮኸው የሜሮን ግጥም እንዲህ የሚለውን የኢዱአርዶ ጋሊያኖን የግጥም ስንኞች አስታወሰኝ፣ “ምንም የሌላቸው ያጡ የነጡ”፡…/ ምንም የሌላቸው ያጡ የነጡ፣ የማንም ያልሆኑ ልጆች፣ ንብረት አልባ የሆኑ/ ምንም የሌላቸው ያጡ የነጡ፡ ማንም ያልሆኑ፣ ማንም ያልነበሩ፣ እንደ ጥንቸል የሚሮጡ/በህይወት የሚሞቱ፣ በየመንገዱ የሚጠመዘዙ…ምንም የሌላቸው ያጡ የነጡ፣ የተገደሉበትን ጥይት ያህል ዋጋ የማያወጡ/…/ “     
 
በእኔ የትንታኔ አተረጓጎም ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ መደቦች የተለያዩ ትርጉሞችን ይዞ ይገኛል፡፡ የወያኔ አባላት ለሆኑት ለመጀመሪያዎች የዜግነት መደቦች የውግዝ መልዕክትን ያስተላልፋል፡፡ የህወሀት ሀብታም ሎሌዎች እና ደጋፊዎች ከወያኔ ጋር ቁርኝት በመፍጠር ያልተገባ ጥቅም በማግበስበስ ላይ ለሚገኙት ለሁለተኛ ደረጃ የዜግነት መደብ ለተሰጣቸው ደግሞ እንዲጠነቀቁ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡ በአጠቃላይ መልኩ ለግል ጥቅማቸው ብቻ እንጅ ለምንም ነገር ለማያስቡ እንዲሁም የወያኔ አቃጣሪ በመሆን በስመ ኢቨስተርነት ወደ ሀገር ቤት በመምጣት የሚሞዳሞዱ እና ከሆዳቸው እና ከከርሳቸው በስተቀር ለህዝባቸው እና ለሀገራቸው ምንም ነገር ትዝ የማይላቸው ሆዳም/ከርሳም እየተባሉ ለሚጠሩት በሶስተኛ ደረጃ የዜግነት ምድብ ላይ ለሚገኙት ደግሞ ግጥሙ የቅሌት ዘለፋ ያቀርብላቸዋል፡፡ እንደዚሁም ኢህአዴግ በሚል የማተለያ ሽፋን ስር እራሳቸውን ወሽቀው ህወሀት የሚያሽከረክራቸው በስም ሰው መሳይ በተግባር ግን የሚፐወዙ ሮቦቶች ለሆኑት እና በብዙህን መድብለ ፓርቲ ስም የተፈጠሩባትን የእናት አገራቸውን ጡት አስቆራጭ ከንቱዎች እና ለአራተኛ የዜግነት ምድብ ላላቸው የባዶ አዕምሮ እና የተነፋ ቦርጭ ባለቤቶች ያልተቀደሰውን የሸፍጥ የፓርቲ መሳይ ዱለታ ያጋልጣል፡፡ ኢህአዴግ የሚባለው የከንቱዎች እና የሴረኞች ስብስብ ቡድን ባለራዕይው መሪያቸው በጫት እና በሀሽሽ ምርቃና ሲፈላሰፍ እንደተነበየው ሁሉ ሲፋቅ ህወሀት ሆኖ ይገኛልና፡፡ ምንም የሌላቸው ቀሪዎቹ ኢትዮጵያውየን/ት የሚመደቡበት አምስተኛው እና የመጨረሻው የዜግነት ምድብ ደግሞ ከእንቅልፋችሁ ንቁ፣ በአንድነት እና በጽናት ቁሙ እና ለመብታችሁና ለምንም ለማንም ድርድር ለማይቀርበው ነጻነታችሁ አሁኑኑ ተነሱ በማለት የጥሩንባ ድምጹን በጉልህ ያሰማል፡፡
 
ሜሮን በተውኔቱ ላይ በግልጽ ቀደም ሲል የሀገሯ ልጅ ሀገሩን ህዝቡን ጥሎ ወደ ውጭ እንዳይሰደድ በማለት የተማጽኖ ጥያቄ በማቅረብ እንደተረከችው የእርሷ ጥልቅ የሆነ ጸጸትን በማቅረብ ይጀምራል፡፡ ክብር እና ሙሉ የዜግነት መብት እዚሁ ለሚቆዩ እና ሀገራቸውን ለሚገነቡ አይደለም የሚሰጠው ሆኖም ግን ሀገራቸውን ጥለው ሄደው ለነበሩ እና አሁን ሀብታም ሆነው ለሚመጡት ሆድ አደሮች የሚሰጥ መሆኑን ሜሮን በጣም ዘግይታ ነው የተረዳችው፡፡ አንድ ሰው ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ  ለበርካታ ዓመታት እዚያው በመቆየት ገንዘብ ይዞ ወደ ሀገሩ በመመለስ ዜግነቱ እውቅና እንዲሰጠው እና ክብሩ እንዲከበርለት ያደርጋል፡፡ እዚሁ ሀገራቸውን ለመገንባት በሀገራቸው ውስጥ ያሉ ዜጎች ግን ከዜግነት ውጭ እየተደረጉ ይረሳሉ ይወገዛሉ፡፡ በግጥሟ የመጀመሪያው መስመር ላይ ሀዘኔታ በተቀላቀለበት መልኩ የተጸጸተች መሆኗን እንዲህ በማለት ገልጻለች፣ “እንዳትሄዱ! እንዳትሄዱ!፡፡ ብዕሬን መዝዠ በእናንተ ላይ ጩኸት አሰምቸ ነበር/ከሀገራችሁ እና ከህዝባችሁ ፍቅር ውጭ ጥላችሁ እንዳትሄዱ/ከእኛ ላብ ውጭ የሀገራችን ህልውና ሊረጋገጥ አይችልም/…/ሀገራችሁን ጥላችሁ እንዳትሄዱ ለማስቆም የምችለውን ሁሉ አድርጊያለሁ/…/ሙሉ በሙሉ በእሾህ በታጠሩ መንገዶች ላይ እየተጓዝን ቢሆንም/ ’እንዲሆን እፈቅዳለሁ፣ እኔ እለቅቃለሁ‘ በፍጹም እንዳትሉ/አብረን ሆነን እናጽዳው፡፡/ በመቆጣት ዓይነት እዚሁ አገር ውስጥ እንድትቆዩ ብየ ስህተት እንድተሰሩ ሳደርግ ስሀተት ሰርቸ ነበር…/እነዚያን ቃላት የጻፍኩበት ብዕር አሁን እኔን ይመለከተኛል/እኔን በሀፍረት ይይዘኛል/…/
 
የሜሮን የሀገሯ ልጅ ለእራሱም ሳይሆን እራሱንም ሳይሆን  ይኸው እስከ አሁን ድረስ በሀገሩ ውስጥ አለ፡፡ የእርሱን መጥፎ ዕድል እንዲህ በማለት ትገልጸዋለች፣ “…በሀገርህ አፈር ለመኖር ትግል ስታደርግ/የአንተን መከራ እና ስቃይ የሚያይልህ የለም…/የአንተ እርባናየለሽ ላብ በዶላር ይተካል/… ለሀገርህ በምትጭህበት ጊዜ የአንተን ታማኝነት በምን ያህል ማትረፍ እንደቻልክ ይገመግሙሀል…/ህዝቡ የውጭ እሴቶችን አምላኪ ሆኗል/ ልቦቻቸው ተንበርክከዋል/…    
 
የሜሮን የሀገር ልጅ ሀገርም የለውም፣ ክብር እና መብትም የለውም፡፡ እዚሁ መቆየት ይችላል ወይስ መሄድ፣ መሄድ ሲባል ክብሩን ሊያስመልስ ወደሚችል በጣም ሩቅ ሀገር፣ ዜግነት ሊያገኝበት ወደሚችል ሀገር እና መብቱን ሊያስከብር ወደሚችልበት ሀገር እናም ተመልሶ ሲመጣ ተመሳሳይ ሁኔታ የሚገኝባትን ሀገሩን በመናፈቅ፡፡
 
ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ አጠቃላይ የሆነ የዜግነት አልባነት ስሜት፣ ለበርካታ አስርት ዓመታት በውጭ ሀገር የሚኖሩ ዓለም አቀፋዊ ባለሙያዎች እንደ አጋጣሚ በጣም ባልተጠበቀ መልኩ የሚሰማቸው ዓይነት ስሜት ያለው መልዕክት ያስተላልፋል፡፡
 
ግጥሙ አድማጮቹን በኢትዮጵያ ሀገርየለሽ፣ ንብረትየለሽ፣ አቅመቢስ ኃይልየለሽ፣ እረዳትየለሽ እና ተከላካይየለሽ ምን ማለት እንደሆኑ በውል እንዲሰማቸው ያስገድዳቸዋል፡፡ በእኔ የትርጉም ትንታኔ ግጥሙ በአጠቃላይ መልኩ ስለንብረት አልባነት፣ ጭቆና እና በቅኝ ግዛት አገዛዝ ስር እንደመበዝበዝ ያህል ነው፡፡ በሀገር ውስጥ ወያኔ እየተባለ በሚጠራው የጠባብ ጎሳዊ ቡድን አማካይነት ኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት እየተገዛች እንዳለች ሊገልጽ የሚችል ግጥም ነውን?
 
ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በእብሪት የተወጠሩ አጉል ጀብደኛ መሪዎችን እና በውርደት፣ ክብራቸው ዝቅ ተደርጎ እና ዜግነታቸውን ተነፍገው እየተጭበረበሩ ስለሚኖሩ ተገዥዎች ይናገራል፡፡ ግጥሙ የሀገር ባለቤትነታቸውን ለተነጠቁት፣ ቤታቸውን እና መሬታቸውን ላጡት እንዲሁም ክብራቸውን እና ሙገሳቸውን ለተቀሙት ዜጎች የሀዘን ጩኸቱን ያሰማል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ግጥሙ ሀገራቸው ለተዘረፈችባቸው እና ለተሰረቀችባቸው ዜጎች ይጮሀል፡፡ ግጥሙ እንዲህ የሚለውን የነብዩ ኤርምያስን ትንቢት ያስታውሰኛል፣ “የእኛ ውርሶች ለእንግዶች ተሰጡ፣ ቤቶቻችን ለውጭ ባዕዳን ተሰጡ፡፡ እኛ አባቶች የሌሉን ወላጅ አልባዎች ነን፣ እናቶቻችን ጋለሞታዎች ናቸው፡፡ ለገንዘብ ስንል ውኃዎቻችንን በአልኮል በከልናቸው፣ እንጨቶቻችን ለእራሳችን ተሸጡ፣ አንገቶቻችን በታላቅ ስቃይ ውስጥ ናቸው፡ እንሰራለን፣ እናም እረፍት የለንም…“
 
ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ላጡ ለነጡ፣ ከጭቃ ጎጆዎቻቸው ተነቅለው በግፍ መሬቶቻቸውን ተነጥቀው ለተባረሩት በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት እና በርካታ ፎቆች ያሏቸው ህንጻዎችን ለሚገነቡ የገዥው አካል አቃጣሪዎች እና አደግዳጊዎች ለሚሰጡት በሀዘን እጮሀለሁ፡፡ ግጥሙ የከተማ ተሀድሶ እና ልማት በሚል ሰበብ ከቀያቸው እየተነቀሉ ለሚባረሩ ወገኖች ይናገራል፡፡ 
 
ግጥሙ ስለወያኔ ጉልበተኞች እና የእነርሱ የውጭ አገር ግብረ አበሮች የድሆችን መሬቶች በገፍ እየተጠቀሙ ህዝቡን ቤትየለሽ፣ የረኃብ ሰለባ እና ድህነት እንዲበላቸው ስለማድረጉ ይናገርላቸዋል፡፡ የከተማ እና የገጠር መሬት በጣም አስደንጋጭ በሆነ ፍጥነት እየተበላ መሆኑን እና ለድሆች ወደፊት ምንም ዓይነት ኪስ የሆነ ትንሽ መሬት እና ከዚያም አልፎ ለንብረት የለሾች እና ለድሆች ለቀብር የሚሆን ቦታ እንኳ ማግኘት እንደማይቻል ግጥሙ ይናገራል፡፡
 
በቤት እጦት ችግር ምክንያት ለረዥም ጊዜ ሲሰቃዩ እና የመንግስት አፓርትመንቶችን (ኮንዶምንዩም) ለማግኘት ቃል ተገብቶላቸው ከቆዩ በኋላ በአቋራጭ ከመጠባበቂያ የስም ዝርዝሩ እያወጣ ወፍራም ጉቦ ለሚሰጡት ሙሰኞች እንዲሰጡ ይደረጋል፡፡ “ደስታ፣ ደስታ፣ ደስታ ለሁሉም እዚህ ለሚኖሩ ድሆች/ ሀገራቸውን ከነውድቀቷ ለሚወዱ ወገኖች/ ለድሆች እና ለተጨቆኑ/ባለብዙ ፎቅ ህንጻዎች ለእናንተ ይገነባሉ/ቤት ለማግኘት የሎተሪ ቲኬቱን በመያዝ ጸሎት ማድረግ ይገባል/ቆይ እና ቆይ፣ እና ለዓመታት ቆይ/ ከዚያም የእራስን ቤት ለማግኘት ዝግጁ ስትሆን/ጉቦውን ለመክፈል ሳትችል ትቀራለህ/እንደገና ደግሞ ሌላ ለውጥ እስኪመጣ ድረስ እና ጎረቤትን እስኪያስወጣልህ/…ለሁሉም ነገር ማመስገን ጥሩ ነገር ነው/ማቃሰት ዋጋ የለውም/በሀገሪቱ ውስጥ ለመቀበሪያ የሚሆን መሬት እንኳ አይኖርም/…/   “ 
 
ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በኢትዮጵያ መሰረታዊ የሰዎችን ክብር እና የሰብአዊ መብቶችን ጥበቃ በመከልከሉ እረገድ እንዲህ የሚሉ የተወሰኑ ጥያቄዎችን ያነሳል፡፡ ዜጋ የመሆን ዋጋው ምንድን ነው?/ብዙ መሬት ተትረፍርፎ ይገኛል/ግን መሬቱን በነጻ ለማግኘት የምትችለው በውጭ አገር ያገኘኸውን ገንዘብ ይዘህ ስትመጣ ነው/ያንተ ዋጋ የዚህን ያህል ነው/…/እንዴት ያለ ተጻራሪ ነገር ነው፣ ሀብታቸውን ከውጭ አገር ያገኙ ሰዎች፣ የሀገሪቱ ዜጋ ያልሆኑ በህገወጥ መልክ በድህነት ከደቀቁ ኢትዮጵያውያን/ት ያገኙትን ገንዘብ ሁሉንም ነገር ማግኘት ይችላሉ፣ ሆኖም ግን ድሆቹ ዜጎች መከራቸውን የሚያዩት እና ሀገራቸውን ለመገንባት ስቃይ እያዩ ያሉት ከምንም ሳይቆጠሩ ይተዋሉ፣ ይረሳሉ እናም ከዜግነት ውጭ ይደረጋሉ!    
 
ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ መናገር እና መስማት ለተሳነው ህዝብ ነው፡፡ በኢፍትሀዊነት ላይ ተቃውመው ለቆሙ እና ስለኢፍትሀዊነት፣ ስልጣናቸውን አለአግባብ ለሚጠቀሙ እና ሙስና ለሚፈጽሙ ማህበረሰቡ ምንም ደንታ በሌለው መልኩ በጸጥታ ይለመከታል፡፡ ማንም የሚሰማ የለም፡፡ ሁሉም ተኝቷል፡፡ በኢትዮጵያ ስላለው ኢፍትሀዊነት የሚደረገው ጩኸት ጀሮ ዳባ ልበስ ተብሏል፡፡ ሆኖም ግን በውጭ አገር የሚገኙት ዲያስፖራዎች ለውጥ መደረግ አለበት በማለት ሲንሾካሾኩ ይደመጣሉ፡፡ “በሀገሪቱ መሀከል ላይ ቆመሀል/በሀገሪቱ መሀከል ላይ ቆመሀል/እናም ለሀገርህ ለሀገርህ ጩህ/እዚያ የሚሰማ ምንም የለም/በውጭ አገር ስትሆን ብቻ ነው የአንተ ሽክሽክታ ነገሮችን ሊለውጥ የሚችለው/…/
 
ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ስለትምህርት ጥራት መዝቀጥ እና ዋጋየለሽ መሆን እና ባልተማሩ ደናቁርት እየተመራ መሆኑን (የገዥው አካል በሆኑ ሰዎች እና ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ ባላቸው እና እንዲሁም ዲግሪን ከኢንተርኔት የዲፕሎማ መፈልፈያ ወፍጮዎች እየተገዛ ያለበት ሁኔታ) መቃወም አስፋላጊ ነገር ነው፡፡ “እድሜ ልክህን ለትምህርት በማዋል ከፍተኛ ዲግሪ ማግኘት ትችላለህ/የማስተር ወይም የፒኤች ዲግሪ ዲግሪ ማግኘት ትችላለህ/እውነታውን ልንገርህ/በእኔ ሀገር የትምህርት የእውቀት ደረጃውን የሚያመዛዝነው የሶስት ወራት (የካድሬ) ስልጠና ሰርቲፊኬት ነው/…/
 
ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ስለባለስልጣኖች የአቅም ማነስ ድሁርነት እና ሀላፊነትን በአግባቡ መወጣት አለመቻል ቅሬታ ያቀርባል፡፡ የዕለት ከዕለት ስራዎችን የሚያከናውነው የቀበሌ ባለስልጣን (የአካባቢ አስተዳዳሪ) በቢሮው ውስጥ በፍጹም አይገኝም፡፡ የእራሱ ስራ ህዝቡን ማገልገል አይደለም ሆኖም ግን ጊዜውን በከንቱ ማጥፋት እና በየዕለቱ ስብሰባ እና ዲስኩር ሲያሰማ የሚውል አለቃውን በድብቅ ሲከታተል ይውላል፡፡ “ከቀበሌ አገልግሎት ለማግኘት ተገኝታችሁ ነበርን?/ በቢሮ ውስጥ ምንም ዓይነት ሰው አይገኝም፣ ባዶ ወንበር ብቻ/ለሻይ ወጥቷል ተብሎ ይነገራችኋል/ከሻይ እስከሚመለስ ድረስ ለሁለት ወይም ለሶስት ሰዓታት ያህል ጠብቁ ትባላላችሁ/ዝም በሉ፣ ተቀመጡ እና ጠብቁ/ነገ ከቢሮ አይኖርም ምክንያቱም ይድከመዋል/ለእረፍት ይወጣል/አንድ ቀን ይታመማል/ሌላውን ይረሳዋል/በማስፈረሚያ ወረቀቱ ላይ ሳይፈርም ወጥቶ ሄዷል/በስብሰባ ላይ ነው/ስራ ላይ ነው/በእርግጠኝነት ምንድን ነው የሚሰራው?…/ዛሬ በስብሰባ ላይ ነው/ነገ ከአለቆቹ ጋር ነው/…/
 
የሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ግጥም አንድ ሰው በገዛ ሀገሩ ከመኖር ይልቅ ከሀገሩ ተሰዶ በሰው ሀገር እንግዳ ሆኖ መኖሩ የተሻለ ስለመሆኑ ይናገራል፡፡ አንድ ሰው በገዛ ሀገሩ አምስተኛ ደረጃ ዜጋ ሆኖ እንዲኖር የሚገደድ ከሆነ ለምንድን ነው በትውልድ ሀገራቸው ለመቆየት የሚፈልጉት? “እንደፈለጉ ይሁኑ/ልንገርህ/ብትለቅ የተሻለ ነው (ሀገርህን)/የአንተን መኖር የሚያውቅልህ ምንም ዓይነት ሰው ከሌለ/ሀገርህን የማትለቀው ለምንድን ነው?/…/“
 
ግጥሙ ሀገራቸው የተሰረቀችባቸው ዜጎች ወደ ውጭ ሀገር እንዲሄዱ እና ጥቂት ዓመታትን እዚያ ከቆዩ በኋላ በአዲስ ዓይነት የጸጉር አቆራረጥ እና ገንዘብ ይዞ ወደ ሀገር እንዲመለሱ ይመክራል፡፡ ከዚያም ገንዘብ ይዘው የሚመጡ ዲያስፖራዎች በመንግስት ስራ የበዛበት ሚኒስትር እጆቻቸውን ዘርግተው እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ይቀበሏቸዋል፡፡ ሀገራቸውን ለመገንባት እዚሁ ሀገራቸው ውስጥ የሚቆዩ እታች ያሉትን የቀበሌ መሪዎችን እንኳ ማየት አይችሉም፡፡ “እተወሰኑ ጥቂት ሀገሮች ለሶስት ዓመታት ብትሄዱ/እና በአዲስ የጸጉር አቆራረጥ/ምንም ዓይነት ችግር አይገጥምህም/ምንም ዓይነት ጭራቃዊ ዓይን አያይህም/…/በምትመለስበት ጊዜ የአንተን ችግሮች የሚሰማው የተከበረ ሚኒስትር ይሆናል…/በአደባባይ ለአንተ ምን ዓይነት ሀውልት ሊነባልህ እንደሚገባ ይነግርሀል/ስለዚህም መጭው ትውልድ የአንተን ፈለግ ተከትሎ ይሄዳል/ለአንተ ያላቸው ዘመቻ የዚያ ዓይነት ነው…/
 
ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ጋብቻ መፈጸም የግል የጋብቻ ስርዓት ተቋም ውጤት መሆኑን ይናገራል፡፡ ወጣቷ ልጃገረድ ባለፈው ጊዜ በባህላዊ ሽማግሌዎች አማካይነት እጇ ለሌላ ሳይሰጥ አምልጣ ከቆየች በአሁኑ ጊዜ በደኃዋ እናቷ ገንዘብ ላለው ለሀብታም ትሰጣለች፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው መልካም አጋጣሚዎች ያለመኖር እና አስደንጋጭ የሆነ የድህነት መንሰራፋት ምክንያት የተከበሩ ወላጆች ልጃገረዶቻቸውን ወደ ውጭ አገር ለመሄድ አቅሙ ላላቸው ለመኖር ለሚችሉ ሰዎች እንዲሰጡ ይገደዳሉ፡፡ “ቆንጆዋን ልጃገረድ ሽማግሌዎችን በመላክ ልታገኛት አትችልም/በልጆች እና በአዋቂዎች ተፈቃሪ የሆነች ታገኛለህ/አሁን ከእናቷ እቅፍ መንጭቀህ ልትወስድ ትችላለህ/ውጭ ሀገር በመሄድህ እና ሀብታም በመሆንህ አይደለምን?/
 
ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ነገሮችን እንዳሉ ባለመገንዘብ ምክንያት እና በዘፈቀደ አንድን ሀገር እና ህዝብ በማፍቀሬ ምክንያት ይቅርታ ባለማድረጌ እና ግለሂስ ባለመውሰዴ ይናገራል፡፡ ግጥሙ የገዥው አካል ዋናው የፖሊሲ ማጠንጠኛ ዜጎችን ከሀገራቸው እንዲሰደዱ በማድረግ ተቃዋሚ ይሆናሉ ተብለው የሚጠረጠሩትን ዜጎች መቀነስ ይቻላል፣ እንደዚሁም ሁሉ ከውጨ ሀገር ወደ ሀገር ውስጥ በሚልኩት ገንዘብ የረሚታንስ ገቢን ማግኘት ይችላል፡፡ ገንዘብ ያላቸው እና ገንዘባቸውን ወደ ሀገር ወስጥ በመምጣት መዋዕለ ንዋያቸውን የሚያፈስሱ የዲያስፖራ ሰዎች ይከበራሉ፣ እናም አንበሳ ሆነው ይቆጠራሉ፣ ሆኖም ግን እዚህ በሀገር ውስጥ ትንሽ ገንዘብ ይዘው ያሉ ዜጎች ግን ፍጹም ይተዋሉ፡፡ “ እራሴን ተመልክቻለሁ/በእራሴ አፍሪያለሁ/እንዲህ ያለውን ርካሽ የሆነ ሀሳብ/…/ምስጋና የሌላት ሀገር መኖር ለአንተ ምን ጥሩ ነገር አለው/የለቀቁ ሰዎች እንዲቆዩ ይፈቀድላቸዋል/እዚህ የቆዩት ግን እንዲጠፉ ይደረጋል/ምስጋና የሌላት ሀገር ለአንተ ምን ጥሩ ነገር ይኖረዋል?/…
 
ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ስለብልህ እና የተማሩ ሰዎች መጥፋት ጉዳይ ነው፡፡ ግጥሙ አንድን ትልቅ የቴምር ዛፍ በሰው በመመሰል የሞራል መሪዎች እና የህብረተሰቡ ምሰሶ የሆኑት፣ የህዝቡ የሀሳብ አመራሮች እና የህብረተሰቡን ንቃተ ህሊና የሚያጎብቱ እንደቴምር ዛፉ ቀስ በቀስ እየደከመ እንደመጣ ይገልጻል፡፡ እነዚህ መሪዎች ለጥላነት የሚያገለግሉትን ቅጠሎቹን እንደሚያረግፍ  የቴምር ዛፍ ሁሉ ተቆርጠው ይወድቃሉ፡፡ በማህበረሰቡ ዘንድ የቴምር ዛፎች ስማቸውን በትክክል መጻፍ የማይችሉ የደናቁርት የደንደኑ ቅርንጫፎች ናቸው፡፡ “ብልህ ሰዎች በማይኖሩህ ጊዜ/ሀገር ናት እየተሰቃየች ያለች/ህዝቡ ነው በመሰቃየት ላይ ያለው/ባንዲራዋ ናት እየደበዘዘች ያለችው/መዝሙሩ ነው ትክክለኛ ትርጉሙን እያጣ ያለው/እንድትመለስ ነግሬህ የነበረው እንግዲህ ያ ነው/ስለሆነም ሀገርህን አትለቅም/ምንም የቀረ ሀገር የለም/ምንም የቀረ መንፈስ የለም/የብልህ እጥረት አለ/ትልቁ ዛፍ (ዋርካ) ምንም ዓይነት ጥላነት አይሰጥም/ማዕረግ ክብሩን አጥቷል/ምን ዓይነት ትልቅ ዛፍ?/ጥሩ መጥረቢያ በዛፉ ቅርንጫፍ ላይ መጠቀም የተመረጠ ነገር ነው/መሬቱን እና እንጨቱን ቤቶቻቸውን ለሚሰሩት ባለሀገሮች ስጣቸው/ለለውጥ መጓዝ/ልበስ እና ወደ ከተማ ሂድ/እወቀት ምን ያህል ጥሩ ነገር ነው በስልጣን ላይ ያሉ ባለስልጣኖች የማሰብ ችሎታ ዜሮ ሲሆን?/በአሀኑ ጊዜ ያለው ፋሽን ድንጋይን በድንጋይ ላይ መቆለል እና ባለብዙ ፎቅ ህን  ጻዎችን መገንባት/ስለሆነም መልሸ እወስደዋለሁ/ስላለመልቀቅ ቀደም ብየ እንደነገርሁህ መልሸ ወስጀዋለሁ/ሰርዠዋለሁ/ደውልልኝ ስለሆነም ከአንተ ጋር እለቅቃለሁ/ሀኖም ግን አልጠራጠርም/የኢትዮጵያን ውኃ የጠጣሁ ስለሆነ ተመልሸ እመጣለሁ/ስሜን ከለወጥኩ በኋላ ተመልሸ እመጣለሁ/ከዚያ በኋላ ህዝቦቸ እኔን ይቀበሉኛል እናም በፍቅር እንድሞላ ያደርጋሉ/ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ/
 
በሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ የግጥም ኃይል አማካይነት ተስፋየለሽነትን እና ተስፋ ማጣትን ባዶ ስለማድረግ ጉዳይ ነው፡፡ በግጥም ተስፋቢስነትን፣ ውሸትን በመታሪ እና በከታፊ ቃላት የመዋጋት ጉዳይ ነው፡፡ ግጥም ብቻ ነው አዳማጮቹን በእራሳቸው ቅዠት ውስጥ ተዘፍቀው ከሚደናበሩ፣ እራሳቸውን ከሚጠራጠሩ እና እራሳቸውን ከሚያታልሉ አምባገነኖች ነጻ የሚያወጣው፡፡ 
 
“ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ አገር አልባነት፣ ንብረትየለሽነት፣ ኃይልየለሽነት፣ እረዳትየለሽነት እና ተከላካይነት ስሜት ስለሚሰማቸው ኢትዮጵያውያን/ት ጉዳይ ነው፡፡ ግጥም ነው ስለእውነታው ጩኸቱን የሚያሰማው፣ “ከዚህ በኋላ የትም ድረስ ልሸከመው አልችልም! ከዚህ በኋላ በድሀረ አፓርታይድ የዘረኞች አገዛዝ ስርዓት ውስጥ ለመኖር አልችልም!”
 
ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ግጥም ለድርጊት የሚያነሳሳ ጥሩንባ ለመጨረሻ ጊዜ እየነፋ ነው፡፡ ይህ ጥሪ ዜግነት አልባ ድፍረትን በመላበስ ሀገሩን መልሶ የሀገሩ ባለቤት ለሆነው ህዝብ የቀረበ ጥሪ ነው፡፡ ለእኔ ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ የተባለው ግጥም ማለት የፈለገው ከሀገር ውጭ ምንም ዓይነት ክብር እንደሌለ፣ ከህዝብ ውጭ ሀገር እንደሌለ፣ ከሀገር እና ከህዝብ ውጭ ክብር እንደሌለ በግልጽ ያስተምራል፡፡ ግጥሙ ለሰው ልጅ ትዕግስት የእራሱ ወሰን ያለው ሲሆን ከዚያ ካለፈ በኋላ ግን ተቀባይነት እንደማይኖረው ወይም ደግሞ ትዕግስት እንደማይኖር ያስገነዝባል፡፡ “ቀስ በቀስ የሚንጠባጠብ ውኃ ጠንካራውን አለት ይፈረካክሳል/ሁላችንም ህዝቡ ከተኛበት እስኪነቃ ድረስ በህብረት አብረን እንጩህ/ሀገሪቱ እስከምትነሳ ድረስ/ከዚያ በኋላ እንደነገርኩህ ተመለስ/ምን ያህል ትንሽ ነገር ነው የማውቀው/ወርቁን እርግፍ አድርገው በመተው መዳቡን ለማግኘት ይስገበገባሉ/
ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ኃያሉን አምላክ ስለማመስገን ነው፣ የእራሱ ቁጣ እና የበቀል እርምጃ እስከሚነሳ ድረስ ጭራቃዊነትን ድርጊትን ሲፈጽሙ ያለምንም ማስጠንቀቂያ በትዕግስት ስለሚመለከተው አምላክ ጉዳይ ነው፡፡ 
 
ህይወትን የሚያመሳስል ኪነ ጥበብ፣
 
ሜሮን ጌትነት ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በሚሉት ቃላት ሁላችንንም በሚገባ ደስሳናለች፡፡ ስለሜሮን ግጥም ለቁጥር የሚያዳግቱ የአድናቆት አስተያየቶችን ተቀብያለሁ፡፡ ግጥሙን የሰሙ ሰዎች ሜሮን ከሀገር፣ ከህዝብ እና ከክብር ውጭ የሚኖረውን ስሜት ምን እንደሚመስል የነገራቻቸው መሆናቸውን፣ በአምስተኛ የዜግነት ምድብ ደራጃ መኖር ምን ማለት እንደሆነ፣ የእብሪተኛ ደናቁርት ሰለባ መሆን፣ በጭቆና እና ከህግ አግባብ ውጭ መኖር እንዲሁም ምንም የለሽነት፣ ኃይልየለሽነት፣ እረዳትየለሽነት፣ እና ተከላካይየለሽነት በወሮበላ ዘራፊ አምባገነን የአዙሪት አገዛዝ መዳፍ ስር መኖር ምን ማለት እንደሆነ እና ከዚህ ጭራቃዊ ስርዓት እንዴት መውጣት እንደሚቻል የሚያመላክት ነው፡፡ እኔም የዚህ ዓይነት ስሜት ተሰምቶኛል፡፡
 
የ19ኛው ክፍለ ዘመን የአየርላንድ ደራሲ እና ገጣሚ የነበሩት ኦስካር ዊልዴ በጽሁፋቸው እንዲህ ብለው ነበር፣ “ህይወት ኪነጥበብን የመመሰሉ ሁኔታ ኪነጥበብ ህይወትን ከሚመስለው የበለጠ ይመስላል፡፡ ይህ ህይወት በዘፈቀደ ከሚመስለው ውጤት የሚመነጭ አይደለም ሆኖም ግን የህይወትን የእራስ ንቃት ህሊና ዓላማ ለመግለጽ እና ያ ኪነጥበብ የተወሰኑ ቆንጆ ዓይነት ሁኔታዎችን ህይሉን ወደተግባር ለመተግበር የሚያስችለው ነው፡፡“
 
ድፍረት በተባለው ተውኔት ላይ በነበራት ሚና እና ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በሚለው ግጥሟ  የሜሮንን ስራ በጥንቃቄ ስመለከት ባለሁበት ሁኔታ የእርሷ ህይወት እንዴት ወደ ኪነጥበብነት ማመሳሰል እንደቻለ ተደንቂያለሁ፡፡ ድፍረት በሚለው ተውኔት ላይ ሜሮን የማትበገር የኢትዮጵያዊነት የህግ ባለሙያ ገጸ ባህሪን በመያዝ ለአንዲት የጠለፋ ጋብቻ እና የአስገድዶ መደፈር በአንድ በኋላ ቀር እና ጎጅ ባህል የተጠመደ ሰው ሰለባ ለሆነች ልጃገረድ ተከላካይ ጠበቃ ሆና ስትሰራ ተመልክቻለሁ፡፡  
 
ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በሚለው ግጥሟ ኢትዮጵያ የምትባል ሌላ ሴት ምህረት በሌላቸው የወሮበላ እና የዘረፋ ስብስቦች ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ተጠልፋ እና የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈጽሞባት እውነተኛ ተከላካይ ጠበቃ ሆና ደግማዋለች፡፡ ድፍረት በሚለው ተውኔት ሜሮን የጠለፋ ጋብቻ እና የአስገድዶ መደፈር ሰለባ የሆነችውን የአንዲት ወጣት ልጃገረድ ክብር እና ሞገስ አስጠብቃለች፡፡ ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በሚለው ግጥሟ ደግሞ የሐገሯን ክብር፣ የህዝቦቿን እና የእራሷን ክብር ታስከብራለች፡፡ ሜሮን በተውኔቱ ላይ ባላት ትክክለኛ የስራ ድርሻ እና በምትጫወተው ሚና መሰረት በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በሚል ርዕስ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ባቀረበችው ግጥሟ ልዩ የሆነ ድፍረትን አሳይታለች፡፡ 
 
ሜሬሮን በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት በተለይለም በዝምታ በተቀመጡ ሁልጊዜ ለሚወገዘው እና በተስፋ መቁረጥ ህይወትን ይገፋል ለሚባለው ለእርሷ ትውልድ እና በእራሳቸው ላይ ዘግናኝ የሆኑ ወንጀሎች እየተፈጸሙባቸው ዓይኖቻቸውን ሰፋ አድርገው ከፍተው እንቅልፍ ለወሰዳቸው ወገኖች ሜሮን ከልብ ተናግራላቸዋለች፡፡ የእርሷ ድፍረት በግጥሞቿ ላይ በመናገር እና በመጮህ ኢትዮጵያውያንን/ትን ሁሉ በተለይም ወጣቱን ትውልድ በአዲስ መንፈስ ነጻነቱን ለማስከበር እና በጽናት ለመታገል እንዲነሳሳ ትርጉም ያለው መልዕክት አስተላልፋለች፡፡ ሜሮን ትክክል ናት፣ በጣም ትክክል ናት፡ “ሁላችንም ህዝቦች ከእንቅልፋቸው እስኪነቁ ድረስ እስቲ ሁላችንም በአንድነት እንጩህ/ሀገሪቷ ለነጻነቷ እስከምታምጽ/…
 
ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ለእኔ የተለዬ ግጥም ነው፡፡ በስልጣን ወንበር ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለመኖር ህልማቸው አድርገው የተነሱት የደናቁርት ወሮበላ ገዥዎች የኢትዮጵያን ወጣት መስዋዕት አድርገው እነርሱ በደስታ እና በፈንጠዝያ ዓለማቸውን ሲቀጩ ሳይ የእራሴ ንዴት እንደ ገደል ማሚቶ እያቃጨለ እንቅልፍ ይነሳለኛል፡፡ ሆኖም ግን ሁልጊዜም ቢሆን ከኢትዮጵያ ወጣቶች ጋር በጽናት እቆማለሁ፡፡
 
የሜሮን ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በሚለው ግጥሟ ላይ ያሉት እነዚህ ቃላት በአዕምሮዬ ላይ ያቃጭላሉ፡፡ “በሀገሪቱ እምብርት ላይ ቆመሻል/በሀገሪቱ እምብርት ላይ ቆመሻል/እናም ለሀገርሽ እሪ ብለሽ ጩሂ/እዚያ አንድም የሚሰማ የለም/ውጭ ሀገር ስትሆን ብቻ ነው የአንተ ሽክሹክታ ነገሮችን ሊለውጥ የሚችለው/…/
 
ሜሮን ድምጿን ከፍ አድርጋ እና በግልጽ መጮኋን የሰማን መሆናችንን ልትገነዘብ ይገባል፡፡ አንችን  ለመስማት እዚህ ነን፡፡ አንንሾካሾክም፣ እንጮሀለን፣ እናለቅሳለን እናም ከእርሷ ጋር እሪ እንላለን፡፡
 
ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ” “ኢትዮጵያ የሚለውን ግጥም” አስታወሰኝ፡፡ ታላቁ የሙዚቃ ንጉስ ጥላሁን ገሰሰ ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ የሚለውን ትርጉም ለእኔ ትውልድ ያስተማረ የመጀመሪያው የኪነ ጥበብ ሰው ነበር፡፡ ሁልጊዜ “ኢትዮጵያ! ኢትዮጵያ!” እያልኩ እዘምራለሁ…
 
ኢትዮጵያ! ኢትዮጵያ!
ኢትዮጵያ! የእኛ መመኪያ (ጋሻ)
የእኛ እናት ሀገር፣ ኢትዮጵያ
የእኛ እናት ሀገር፣ ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ! የእኛ መመኪያ (ጋሻ)

 
            የእኛ እናት ሀገር፣ ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ ምድረ ገነት ሀገር…
 
ኢትዮጵያ ከተዘፈቀችበት የሲኦል ማጥ ውስጥ ትነሳለች፣ እናም እንደገና ምድረ ገነት ትሆናለች!
 
(ይቀጥላል ….) 
 
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
 ህዳር 9 ቀን 2007 ዓ.ም

ተስፋዬ ገ/አብ –በጋዜጠኛ ሰናይ ገ/መድህን እይታ * ተስፋዬ ተስፋ ሲቆርጥ – 2

$
0
0

ክፍል 2

የጋዜጠኛዉ ማስታወሻ እየተተረከ በነበረበት ሰሞን ከአንድ አሁን ስሙን መጥቀስ ከማልችለው የኤርትራ የደህንነት ባልደረባ ኮ/ል ጋር አንድ ምሽት ቁጭ አልንና መሎቲ ቢራ እየተጎነጭን ወግ ጀመርን፡፡ ጭዉዉታችን ወደ ጋዜጠኛዉ ማስታወሻ ይዘት ላይ ገባ፡፡ ስለ ሥነፅሁፋዊ ዉበቱ ወይንም ክህሎቱ መነጋገር አላሻንም፡፡ አልቃጣንምም፡፡ አቅማችን ስላይደለ ብቻም ሳይሆን ዋናዉ ሊያነጋግረን የሚገባዉ ጉዳይ ይዘቱ ስለሆነ ፡፡ በተለይ ደህንነቱ ወዳጄ ኢትዮጵያ ዉስጥ በከፍተኛ ልኡክነት የሰራና የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አካሂያድና የወቅቱ የኢትዮጵያ ነገሮች የገባዉ በመሆኑ ጭዉዉቱ ይመቸኛል። በኢትዮጵያ ጉዳይ ሚዛናዊ አስተያየት ያለዉ ከመሆኑ ባሻገር የእኛ ፕሮግራሞችን በተመለከተ በትኩረት ከሚከታተሉና አስተያየታቸዉን ከሚለግሱን ነዉ፡፡
“መፅሃፍን አንብበኸዋል እንዴት አገኘኸዉ?” የኔ ጥያቄ ነበር።

“ክላዕ ሀለዉ ለዉ እዩ ዝብል ዘሎ!” “ዝም ብሎ ነዉ የሚቀባጥረዉ” ሲል በንቀት አይነት መለሰልኝ።

የእኔን አስተያየት ቆጥቤ የእሱን ሙሉ ሃሳብ መስማት ስለመረጥኩ ጥያቄየን ቀጠልኩ፡፡ “ማለት .. አላመንከዉም”

(ተስፋዬ ገብረአብ)

(ተስፋዬ ገብረአብ)

“እንዴት ነዉ የሚታመነዉ፡፡ መለስና ሰዬ ሲነጋገሩ፣ የአቦይ ስብሃት የአባዱላን ..እንትና እንዲህ አለዉ እንዲህ አሉት፡፡ በአጠቃላይ ስለ ወያኔ ባለስልጣኖች የቢሮ ጨዋታ የት ሆኖ ሰማና ነዉ ሊነግረን የሚሞክረዉ፡፡ ተፈራ ዋልዋ የትግል አጋሮቹን እነደዚያ ወርዶ ይናገራል ፍፁም፡፡ቢያንስ እኮ እነዚህ ሰዎች የኢትጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸዉ፡፡ የተስፋየ ጉዋደኞች አይደሉም፡፡ ከመፅሃፉ አብዛኛዉ ታሪክ ያልነበረበት ቦታ እንደነበረ ሆኖ ነዉ የሚያወራዉ። ድርሰት ከሆነ ጥሩ፤ ያለበለዚያ ለኔ አሉባለታ ነዉ። ለኔ የሚሰማኝ ስለ ከፍተኛዎቹ ባለስልጣናት የቢሮ ጨዋታ ከሆነ ቦታ ከተነገረዉ በሁዋላ ያንተ ገጠመኝ አድርገህ ፃፈዉ ያለዉ አካል አለ። አሁን ከወያኔ ጋር ስለተጋጨን ልቅቃሚ የማይታመን ወሬ ሁሉ በእኛ ሚዲያ ማስተጋባቱ ደግሞ በዉነት ለኤርትራ ህዝብ ሀፍረት ዉርደት ነዉ፡፡ ለሱ መተዳደሪያዉ ይሆናል፡፡ ለኛ ግን ዘላቂ ጥቅም የለዉም፡፡ በተስፋየ ወሬ የኢትዮጵያ ህዝብ ህወሓት ከኢህዴን አማራ ከኦሮሞ እርስ በርስ ይጋጫል ተብሎ ከሆነ ትርፉ ትዝብት ነዉ፡፡ ለነገሩ ምን ተስፋየ ብቻ፤ እናንተስ ወሬ እየተነገራችሁ ታማኝ ምነጮች እንደጠቀሱት እያለችሁ ወሬ ታራግቡ የለ” አለና ከት ብሎ ሳቀ፡፡ ( መቼም ኮ/ሉ ወዳጂ ተስፋየ ኤርትራ ከገባ ጀምሮ ከህግደፍ ባለስልጣናትና ከወታደራዊ የስለላ ኮ/ሎች ጋር የተልእኮ ቅንጅት መፍጠሩን ኣያዉቅም አልልም፡፡ እንዲያዉ ያረረ ቆሽቱን በጨዋ ወግ እኔ ላይ መተንፈስ ቢከጅል እንጂ፡፡ እንዲያዉም ግምገማዉ የሱ ብቻ ነዉ ሳልል በኢሳያስ አምባገነንነትና በሁለቱም ህዝቦች ዘላቂ ጥቅም ላይ እጅግ ጎጂ የሆነ አሻራ እያሳረፈ ባለዉ በኢትዮጵያ ፖለቲካ አያያዝ የተበሳጩ በሳል ኤርትራዊያንን አቁዋም ያንፀባርቃል ብየ ገመትኩ ) የሆኖ ሆኖ ስለተግባባንና አባባሉ በጣም ስለተመቸኝ እኔም በሳቅ አጀብኩት፡፡ እረ የልቤንም ስለዘረገፈዉ ነዉ ፡፡ እነ ኮ/ል ፍፁም(ሌኒን)ና ኮ/ል ጠዐመ (መቀለ) እያመጡልንና ታማኝ ምንጮች እንዳሉት እያልን ያራገብናቸዉ አያሌ ወሬዎች ዓይነ ህሊናዬ ላዬ ሲመላለሱ ይታወሰኛል፡፡ በሀፍረት እያሸማቀቁኝ፡፡ አቦ ዋሽቶ ከሚያስዋሽ ይሰዉራችሁ ይባል የለ! ትልቅ ምርቃት ነዉ ወገኖቼ፡፡ ላሁኑ የወሬዎቹን ነገር ትተን ወደ ተስፋየ እናተኩር ፡፡

ከኮ/ል ወዳጄ የተሰነዘሩት ትችቶች ዓይነት እየተበራከቱ ይደርሱን ገባ፡፡ በተለይም ከአምቼዎች፡፡ ( ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ በፈቃዳቸዉ የገቡና እኔን መሰል ከተባረሩ አምቼዎች ) በሳልና ጠንከር ያሉ ትችቶች፡፡ እኔ ላገኛቸዉ ከቻልኩዋቸዉ ማለቴ ነዉ፡፡ ከሁሉም አላልኩም፡፡ እንዴትስ እላለሁ፡፡ ተስፋየ እኔ ብ/ጄል ከማል ገልቹ እና አሁን ስሙን ከማልጠቅሰዉ (ጎበዝ ስማቸዉን የማትጠቅሳቸዉ በዙሳ እንደማትሉኝ አምናለሁ፡፡ የኤርትራን አኗኗር ማን የማያዉቅ አለና !) ወዳጃችን ጋር ሆነን ያደረግነዉ የተሲያት በሁዋላ ጨዋታ ከረር ያለ እንደነበረ አስታዉሳለሁ፡፡ ያስታዉሳሉ፡፡ ቦታዉ ሳቫና ሆቴል፡፡ የጨዋታችን ጉዳይ ያዉ የጋዜጠኛዉ ማስታወሻ መፅሃፍ ነበር፡፡

እንግዲህ እንዲህ ነዉ ፡፡ ተስፋየ የጋዜጠኛዉ ማስታዎሻን አስመራ ሆኖ ገና እየፃፈ እያለ በኦነግ አመራር መካከል ልዩነቱ ይፋ ሆኖ የብ/ጄ ከማልና የአቶ ዳዉድ ኢብሳ ቡድን ጎራ ለዩ፡፡ ቪላና ማዕዳቸዉንም ከፈሉ፡፡ ይህንን ተከትሎ (በወቅቱ በአስመራ ኦነጎች መካከል ዱላ ያማዘዘዉና በኤርታራዊያን ጎረቤቶቻቸዉ ሆስፒታልና ፖሊስ ጣቢያ .. ትዝብት ላይ የጣላቸዉን ነገር አሁን አናነሳዉም ፡፡) የተፈጠረዉን ክፍፍል በተመለከተ እኛ ትንፍሽ እንዳንል ጥብቅ መመሪያ ከህግድፍ ፖለቲካ ቢሮ ሃላፊ ከአቶ የማነ ገብረአብ ተሰጠን ፡፡ የነ ብ/ጄል ከማል ስም እንዳይነሳ ምስላቸዉም በቴሌቭዥን እንዳይታይ ጭምር ፡፡ (በነገራችን ላይ በኦነግ ዜና ጉዳይ ከዚህ በፊትም ከአቶ የማነ ገ/አብ ለእኛ ክፍል ጥብቅ መመሪያ ስለመሰጠቱ እማኝ ነኝ፡፡) ምክንያት የህግደፍ ወዳጅነት ከአቶ ዳዉድ ኢብሳ ቡድን ጋር በመሆኑ፡፡ በእኛ ስር በሚገኘዉ የኦሮሚኛ ክፍል የሚሰሩት የኦነግ አባላት ግን ሁሉም የዳዉድ ቡድን ደጋፊ ስለነበሩ መመሪያዉ ተመችቱዋቸዋል ማለት ይቻላል፡፡ ለጊዜዉም ቢሆን ገበናን ላለማዉጣት፡፡ ለኦነግ አባላቶች በርግጥ ድብቅ አልነበረም፡፡ ለዉጩ እንጂ። ይሁንና ጉዳዩን በቅርብ የተከታተልነዉ ሳንተነፍስ የሩቆቹ ሚዲያዎች ወዲያዉኑ ይፋ አወጡት፡፡ እንደ ሙያተኛ እኛን አስቆጭቶናል፡፡ያሳዝናልም ፡፡

የአቶ ዳዉድ ቡድን ሁለት ራዲዮ ጣቢያዎች አንዱ በኤርትራ ማስታዎቂያ ስር የሚገኘዉና ሌላኛዉ ከመኖሪያ ቪላቸዉ የሚሰራጭ ሲኖረዉ የቴሌቭዥን ፐሮግራም ደግሞ ከኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ስቱዲዮ ያሰራጫል፡፡ የዚያኛዉ የእነ ብ/ጄ ከማል ቡድን ግን ከኤርትራ የሚያሰራጨዉና አቁዋሙን የሚገልፅበት ሚዲያ ስለሌለዉና የኤርትራን ማስታወቂያ ሚኒሰቴር ሚዲያ በእኩልነት እንዳይጠቀምበት ከህግደፍ በመነፈጉ የራሱን ሚዲያ መፈለጉ ግድ ነበር ፡፡ በግሌ በሁኔታዉ እጅግ በማዘኔ የፖለቲካ ልዩነቶቻቸዉን ለነሱ በመተዉና ገለልተኛ በመሆን (ሁሉም ለኔ ወገኖቼ ናቸዉና) በሙያዬ በትንሹ ለነከማል ቡድን ድጋፌን አበርከተኩ፤ ራዲዮ ጣቢያቸዉን በማቋቋሙ ረገድ፡፡ ብሎም ከአስመራዉ የጀርመን ድምፅ ወኪል ከወዳጄ ጎይቶም ቢሆን ጋር በማገናኘትና ድምፃቸዉን እንዲያሰሙ በማድረግ በመሳሰሉት ሙያነክ ነገሮች፡፡

የነ ብ/ጄ ከማል ቡድን ከህግደፍ ፊት እየተነሳዉ መሄዱ መታወቅ ጀመረ፡፡ ቀለብና ቤት ካለሆነ በቀር እንቅስቃሴያቸዉ ተገደበ፡፡ የብ/ጄ ከማል ቡድን አመራሮች ከአስመራ ዉጭና ከኤርትራም እንዳይወጡ ታገዱ ( የሁዋላ ሁዋላ ደብዛዉን እንዳጠፉት እንደ ኮ/ሌ ታደሰ ሙሉነህ ማለት ነዉ) ብዙም ሳይቆይ ብ/ጄ ከማል ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ይዘዋቸዉ የመጡትን 400 አካባቢ ሌ/ኮ እና ሻለቆች የሚገኙባቸዉን ወታደሮቻቸዉን በጠራራ ፀሀይ ተዘረፉ፡፡ ዘራፊዉ ደግሞ ያመኑት ህግደፍ ሆነ ፡፡

ይህ ታሪካዊ የኦነግ ክፍፍል፣ የህግደፍ አድልዎ፣ የአደባባይ ዝርፊያ ሲከናወን እዚያዉ በቅርብ ሆነዉ ለማየትም ለመስማትም ከበቁትና ለኦሮሞ ህዝብ ቅርብ ከሆኑት ወገኖች አንዱ ተስፋየ ገ/አብ ነዉ፡፡ ታዲያ በዚያ በሳቫና ሆቴል ቆይታችን በጋዜጠኛዉ ማስታዎሻ መፅሃፍ ዙሪያ እያነሳን ከጣልናቸዉ ግምገማ ቢጤዎች መሃል ድነገት ብ/ጄ ከማል “የኦሮሞ ህዝብ ወዳጅ ነኝ ትላለህ፣ በኦሮሞ ህዝብ ታሪክ ላይም ትፅፋለህ። ግን በኦነግ ላይ ይሄ ሀሉ ፍፃሜ ሲከናወን እዚሁ ሆነህ አንድም ቀን ሁኔታዉን ለማወቅም ሆነ ብትፅፈዉም ባትፅፈዉም በገለልተኛነት እኛን አላነጋገርክም፡፡ ምክንያቱም እነሱም ለኦሮሞ ህዝብ ነዉ የሚታገሉት እኛም እንዲሁ፡፡ አንተ ግን የነ አቶ ዳዉድ ቤተኛ ሆነህ እኛን ከነመፈጠራችን ረሳኽን፡፡ ግን ለምን?” ሲል የሂስ ዶፉን አወረደበት፡፡ ከኦነግ ክፍፍል በሁዋላ ተስፋዬ ለሰላምታም እንኩዋን ቢሆን ከነ ብ/ጄ ከማል እየራቀ መሄዱን ታዝበነዉ ነበር፡፡ ቀጠለ ዶፉ “እንዲያዉም ስለ ኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ስትፅፍ የጠቀስከዉ ሌ/ኮ ገመቹ አያና እኔ ይዣቸዉ ከመጣሁዋቸዉ አንዱ መሆኑን ታዉቃለህ፡፡ መፅሃፍህ ዉስጥ አካተትከዉ ምክንያቱም ገመቹ ብቸኛዉ ኮ/ል የነ ዳዉድ ቡድንን የወገነ ስለሆነ፡፡ እኔንና ብ/ጄ ሀይሉ ጎንፋን ማነጋገር አልፈለግክም፡፡ ላንተ መፅሃፍ የሚበቃ ታሪክ ስለሌለን ይሆን? የእኔነት ጉዳይ አይደለም የሚያናግረኝ፣ ስለ ኦሮሞ ስለ ኢትዮጵያ ስታስብ ገለልተኛ ለምን አትሆንም ለምን ትወግናለህ ነዉ ትችቴ፡፡(ከልጅ ልጅ ቢለዩ…) ምክንያቱን ግን አንተም እኔም ሁላችንም እናዉቀዋለን ፡፡” ብ/ጄ ከማል እኔም ሌላኛዉ የዉዉይቱ ማዕድ ታዳሚም እንደወረደ ወረድንበት ነዉ የሚባለዉ፡፡

ተስፍሽ ለምን ከነ አቶ ዳዉድ ቡድን ጋር እንደተቆራኘ እንዲያብራራልን አልጠበቅነዉም፡፡ ሆድ ሲያዉቅ ዶሮ ማታ እንዲሉ.፡፡ ከመፅሃፉ ዉስጥ እየነቀስን ለሰነዘርንበት ትችትም ምላሽ አልነበረዉም፡፡ በድምድሙ በሌላ ገጠመኝ ሊነሱ የሚችሉ ህፀፆችን የቻልነዉን ያህል ነቀስንለት፡፡ እባክህ እባክህ ሚዛናዊ ለመሆን ሞክር ተማፅኖአችን ነበር ፡፡ ቆዳዉ ወፍራም ቢሆንም ያኔ በበቃኝ ሲዘረር አየነዉ፡፡ ከአፍታ ፀጥታ በሁዋላ ተስፍሽ በደመ ነፍስ በሚመስል ስሜት ሀሳብ አመጣ ፡፡ “ቀጣዩ መፅሃፌ የደራሲዉ ማስታወሻ ነዉ፡፡ በዚህ መፅሃፍ ላይ የነ ብ/ጄ ከማል ጦር ድንበር ተሸግሮ የወጣበትና የዮናታን ዲቢሳ ከኦህዴድ – ኦነግ ታሪክን አካትታለሁ፡፡ ሊፃፉ ስለሚገባቸዉ የትዉልዳችን የትግል ታሪኮች አንስተን እንወያያለን በአጋጣሚ ሁላችሁም በኢህዴንና ኦህዴድ የትጥቅ ትግል ዘመን ያለፋችሁ ስለሆነ የምታስታዉሱት የታሪክ አላባ ይኖራል” ሲል ግብዣዉን አቀረበ፡፡

በነገራችን ላይ ዮናታን ዲቢሳ ነባር የኢህዴን ታጋይ በሁዋላም የኦህዴድን መስራች ጉባኤ የመራ ኤርትራ ነፃነትዋን ስታዉጅ ከአቶ ሌንጮ ለታ ጋር ኢትዮጵያን ወክለዉ ከመጡት ሁለት የክብር እንግዶች አንዱ ሆኖ የተገኘ አሁን ደግሞ በስደተኛነት የተጠለለ ነዉ፡፡ ኤርትራን ሁለቴ ታይቶባታል ማለት ነዉ፡፡ በክብር እንግድነትና በስደተኝነት፡፡ በህይወቱ ዙሪያ የቴሌቭዥን ቃለመጠይቅና ዶክመንታሪ ፕሮግራም ሰርቸበታለሁ፡፡ ሁላችንም በታሪክ ዉስጥ ለለዉጥ ሲሉ ለተሰዉ ለታገሉ ለሚታገሉ ለሁሉም አክብሮት ያለን መሆናችንን ገልጠን የሁሉም ህዝቦች ታሪክ ያለአድልዎ ሊወሳ ይገባል በሚል በይሁንታ ተሰነባበትን ፡
ተስፍሽ በቅርቡ እየተገናኘን ገጠመኞቻችሁን አሰባስባለሁ ብሎ ከተለያየን በሁዋላ ብ/ጄል ከማልንም ብ/ጄ ሀይሉ ጎንፋን ሆነ ዮናታንን አላገኘም፡፡ አልፎ አልፎ ከኔ ጋር በአጋጣሚ ኒያላ ሆቴል እንገናኛለን። ከሰላምታ በቀር ቁምነገር ሳናወራ እንለያያለን፡፡ ከዚያ ሰንበትበት ብሎ ከሌ/ኮ አለበል አማረ እና ሌ/ኮ አበበ ገረሱ ጋር በተደጋጋሚ የቢራና ጂን ወግ ላይ አየሁዋቸዉ፡፡ ከሌላ ኤርትራዊ አምቼ ጋርም እንዲሁ፡፡ አንድ ቀን እንደዘበት “የመፅሃፉ ዝግጅት እንዴት ነዉ?” ስል ጠየቅሁት ፡፡ “ጥሩ እየሄደ ነዉ” መለሰልኝ ፡፡

በዚያኑ ሰሞን ደዉሎልኝ ተገናኘን፡፡ እነ ከማልን የፈለገ ነበር የመሰለኝ፡፡ ግን “የጋዜጠኛዉ ማስታወሻን በሲዲ እንድትተርክልኝ እፈልጋለሁ፡፡ ዉጪ አገር በሲዲ ቢሆን ብዙ ተደራሽነት ይኖረዋል ብለዉኛልና እንቅረፀዉ” ሲል ጠየቀኝ፡፡ “ደስ ይለኛል ግን ትከፍለኛለህ፡፡ በነፃ አታስበዉ አልኩት” ቢዘነስ ስለሆነ፡፡ “ከናንተ ቢሮ እኮ በነፃ መዉሰድ እችላለሁ” “ከቻልክ ሞክር ግን አይመስለኝም” አልኩት። “እሺ ስቱዲዮ ፈልግና ንገረኝ” አለና በዚሁ ተለያየን፡፡ የሙዚቃ አቀናባሪና የግሉ ስቱዲዮ ያለዉ ጉዋደኛየን የማነ ኪዳኔን (አብዛኛዉን የሄለን መለስ ሙዚቃ የሰራ ባለሙያ ነዉ) ጠየቅኩት። “እሺ አንተ እንድትጠቀም ስል በመጠነኛ ክፍያ እሰራላችሁዋለሁ” አለና ፕሮግራም አስያዘኝ፡፡ ለተስፋየ ነገርኩት፡፡ አልተስማማዉም፡፡ ምክንያት ደረደረና አያዋጣም አለ፡፡ 5ሺህ ናቅፍ (100 ዶላር) ነበር ለስቱዲዮ የተጠየቀዉ። ቢዝነሱን አንተ ታዉቃለህ አልኩና ለሱ ተዉኩት፡፡

እነሆ የደራሲዉ ማስታወሻ እዚያዉ አስመራ ታትሞ ወጣ ፡፡ ለባለታሪክነት የተመለመሉት እነ ብ/ጄ ከማልና ሌሎች አልተካተቱበትም፡፡ ይሄዉ መፅሃፍ ለትረካ ወደ እኛ ፐሮግራም መምጣቱ ፡ከመፅሃፉ ባለታሪኮች ጋር ያደረግሁት ጭዉዉት ለቀጣይ ወግ ይሁነን፡፡ የዚያ ሰዉ ይበለን!

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live