Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በኡጋንዳ 3ለ0 ተሸነፈ * ሰውነት ቢሻው ማረን?

0
0

(ዘ-ሐበሻ) ለወዳጅነት ጨዋታ ወደ ኡጋንዳ አምርቶ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዩጋንዳ አቻው 3ለ0 ተሸነፈ:: በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ዘመን ከ31 ዓመታት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ መድረክ ብቅ ብሎ የነበረው ብሔራዊ ቡድናችን ለዓለም ዋንጫ ለማለፍም ትልቅ ትንቅንቅ አድርጎ እንደነበር ይታወሳል::

(photo File)

(photo File)


የውጭ ሃገር አሰልጣኝ በብዙ ሺ ዶላር በመክፈል ብሔራዊ ቡድኑ እንዲሰለጥን ቢደረግም ውጤቱ ግን እንደ ሰውነት ቢሻው ዘመን ሊሆን አለመቻሉን የስፖርት ተንታኞች ለዘ-ሐበሻ ይናገራሉ::

በሌላ በኩል ኢትዮ ኪክ እንደዘገበው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የለምንም ክፍያ በነፃ የዮጋንዳ እግር ኳስ አፍቃሪ በስታዲየም ገብቶ እንዲከታተለው የአገሪቱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ከአገሪቱ የጤና ቢሮ ጋር በትብብር ያዘጋጁት። በዚሁ እለት የነፃ HIV ምርመራ ማድረግ ለሚፈልጉም ተዘጋጅቷል። ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ዮጋንዳ ተጉዞ ይህን የወዳጅነት ጨዋታ እንዲያደርግ ሙሉ ወጪውን የሸፈነው የዮጋንዳ እ.ፌ ነው።

Ethiopia national team players upon arrival at Entebbe International Airport on Friday.

Ethiopia national team players upon arrival at Entebbe International Airport on Friday.


ዎሊያዎቹ ዛሬ ከዮጋንዳ ጋር አድርገውት የገቡት አረንጓዴ ማሊያ በቀይ ቁምጣ ቁጥሩ ወይም ሳይዙ ለወፍራሙም ለቀጭኑም ተጨዋች ለሁለም አንድ አይነት በመሆኑ አብዛኞቹ ተጨዋቾች ማልያው እና ቁምጣው ሰፍቷቸዋል ቦላሌ ሆኖባቸዋል። አንዳንድ ተጨዋቾቹ ከአዲስ አበባ ከመነሳታቸው በፊት ማላያው እና ቁምጣው ቁጥሩ ትልቅ መሆኑን ቢናገሩም የምትመልሱት ስለሆነ ችግር የለውም ለወዳጅነት ጨዋታ የሰፋ ማሊያ የሰፉ ቁምጣ ችግር የለውም በመባላቸውን ሰምተናል። የሰፋ ማሊያ የሰፋ ጎልና ሽንፈት ይዞ መጣልና ሲል ኢትዮ ኪክ ዘገባውን አጠናቋል::

በአርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ ላይ የቀረበውን የአስገድዶ መድፈር አቤቱታ መንግስት ተድበስብሶ እንዲያልፍ መተባበሩ ተገለጸ

0
0

(ዘ-ሐበሻ) ማክሰኞ ማርች 13 ቀን 2013 ዓ.ም ዘ-ሐበሻ አዲስ አድማስ ጋዜጣን ጠቅሳ “አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ በአስገድዶ መድፈር አቤቱታ ቀረበበት” የሚል ዜና አቅርባ የነበረ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን በዚህ ልማታዊ አርቲስት ላይ የቀረበው ክስ አርቲስቱ ከስርዓቱ ጋር ባለው የጠበቀ ወዳጅነት የተነሳ ተድበስብሶ እንዲያልፍ መደረጉን የቅርብ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገለጹ።

(ሠራዊት ፍቅሬ የቀረበበትን የአስገድዶ መድፈር አቤቱታ በቀጭኑ ሽቦ ተድበስብሶ እንዲያልፍ ካደረጉለት አቶ በረከት ጋር)

(ሠራዊት ፍቅሬ የቀረበበትን የአስገድዶ መድፈር አቤቱታ በቀጭኑ ሽቦ ተድበስብሶ እንዲያልፍ ካደረጉለት አቶ በረከት ጋር)


አንድ ሰው በተለይም ሴት ልጅ በሙያዋ ካለምንም አድልዎ እና ካለምንም የጾታዊ ግንኙነት ሙስና የመሥራት መብቷ የተጠበቀ ቢሆንም አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ ግን ያለውን እውቅና በመጠቀም ሴትን ልጅ ጾታዊ ግንኙነት ለሥራ ማስገኛ መደለያ ተጠቅሟል በሚል በአንዲት ሴት አቤቱታ እንደቀረበበት ይታወሳል። በወቅቱ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ሁኔታውን ሲዘግብ የሠራዊት መልቲ ሚዲያ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ሠራዊት ፍቅሬ ላይ አንዲት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ለፖሊስ አቤቱታ ማቅረቧን የሚናገሩ ምንጮች፣ ባለፈው ቅዳሜ “ለማስታወቂያ ስራ እፈልግሻለሁ” ብሎ ፒያሳ አካባቢ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ ለመሳምና ለማሻሸት ሲሞክር አመለጥኩ” የሚል ነው ብሎ እንደነበር ይታወሳል።

ሠራዊት በወቅቱ ጉዳዩን እንዳልፈጸመ የተናገረ ቢሆንም ልጅቷ ለፖሊስ አቤቱታ ብታቀርብም ጉዳዩ ተድበስብሶ እንዲያልፍ መደረጉን ብዙዎች በትዝብት ተመልክተውታል። በወያኔ ሥርዓት ናፋቂዎች የሚመራው የኢትዮጵያ ሴቶች ጉዳይ የዚህችን ወጣት አቤቱታ ሠራዊት ለስርዓቱ ባለው ተላላኪነት የተነሳ አንዳችም የሆነ ትኩረት ያልሰጠውና ክትትልም ያላደረገበት መሆኑ ያሳዘናቸው የቅርብ ምንጮች የመንግስት ሕግ አስከባሪዎችም ከበላይ በተለይም ከአቶ በረከት ስምዖን በመጣ ትዕዛዝ የሠራዊት የአስገድዶ መድፈር ክስ ተድበስብሶ እንዲያልፍ መደረጉን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀል የሚሰሩ የሥርዓቱ ተላላኪዎች በሕግ የሚጠየቁበት ሁኔታ በጣም አናሳ መሆኑና ለክስ የሚቀርቡትም ከሥርዓቱ ጋር ሲጣሉ መሆኑ ከዚህ በፊት የታዩ በመሆናቸው የሃገሪቱን የሕግ ሥርዓት ዘወትር እንዲወቀስ ያደርገዋል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች በርካታ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በርከት ያሉ የማስታወቂያ ሠራተኞች እና ፊልም እና ድራማ የሚያሰሩ አርቲስቶች ለትወና የሚመርጧቸውን ሴቶች ቅድሚያ ወሲብን እንጅ መንሻ እንደሚጠይቁ፤ ይህን የማያሟሉ ሴቶች ግን ብቃቱ እያላቸውም ቢሆን ለፕሮጀክቱ ብቁ እንደማይሆኑ በተደጋጋሚ መነገሩ አይዘነጋም።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ከፍተኛ የወንጀል ምርመራ ሃላፊ የነበሩት ረዳኢ ገ/አናኒያ ከስልጣናቸው ተነሱ

0
0

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ከፍተኛ የወንጀል ምርመራ ሃላፊ የነበሩት ረዳኢ ገ/አናኒያ ከስልጣን መነሳታቸውን ምንጮች አስታወቁ። የሕወሀት አባል የሆኑት ረዳኢ ከ1985ዓ.ም ጀምሮ የክልል 14 ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ሃላፊ በመሆን በመቶ አለቃ ማዕረግ እስከ 1993ዓ.ም ደረስ ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
news
ፓርቲው ለሁለት ሲሰነጠቅ በመለስ ዜናዊ ታማኝ ሆነው ከተመረጡት አንዱ የሆኑት ረዳኢ በፌዴራል የልዩ ተወርዋሪ ሃይል ሃላፊ ተደርገው መሾማቸውን ምንጮቹ አስታወሰዋል። ቀጥታ ተጠሪነታቸው ለጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ እንደነበር ሲታወቅ በመቀጠል የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ሃላፊ ተደርገው ተሾሙ። በ1997-98 በዜጎች ላይ ለደረሰው የጅምላ ግድያና እስር እንዲሁም ስቃይ ከመለስ ትእዛዝ በመቀበል ሲያስፈፅሙ የነበሩት ረዳኢ መሆናቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል።

በበርካታ ሰላማዊ ወገኖች ላይ ተመሳሳይ ግፍ ያስፈፅሙ እንደነበረ አክለዋል። ረዳኢ በ10 ሚሊየን የሚቆጠር ሃብት በሙስና እንዳከማቹ ምንጮቹ አረጋግጠዋል። ከስልጣን የተነሱት ለመለስ ታማኝ ስለነበሩ ነው ብለዋል ምንጮቹ። ረዳኢ ወደ አሜሪካ ለመምጣት ሃሳብ እንዳላቸው እዚህ ከሚኖሩ የቅርብ ወዳጃቸው የተገኘው ጥቆማ ያመለክታል።

ሌ/ጄነራል አበባው ታደሰ ወደ ውጭ ሊወጡ ሲሉ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በደህንነቶች ተመለሱ

0
0

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)

ጄ/ል አበባው ታደሰ ወደ ውጭ ለመውጣት ሲሉ ከቦሌ አየር ማረፊያ በደህንነቶች እንዳይወጡ መደረጋቸውን ታማኝ ምንጮች ጠቁመዋል።

ከመከላከያ የጦር አዛዥነታቸው በጄ/ል ሳሞራ የኑስ እንዲነሱ የተደረጉት ጄ/ል አበባው ከአገር እንዳይወጡ የተደረገበት ምክንያት ግልፅ እንዳልሆነ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል። በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ የተለያዩ ጥያቄዎች እንዳሉ በመግለፅ ለኢታማጆር ሹሙ ጄ/ል ሳሞራ ከረር ያለ ሪፖርት ያቀረቡት ጄ/ል ሰዓረ፣ ጄ/ል ሞላና ጄ/ል አበባው መሆናቸውን የጠቆሙት ምንጮቹ በሳሞራ የተሰጠው መልስ « የትምህክተኞች ጥያቄ ነው፤ ችግር የለም..» የሚሉና ጥያቄዎቹን የሚያጣጥሉ እንደነበሩ አስታውሰዋል።
abebaw tadese'
ሶስቱ ጄኔራሎች በሳሞራ ምላሽ በመበሳጨት ከስልጣናቸው ለማስነሳት በምስጢር ቢመክሩም መረጃው ባልታወቀ መንገድ አፈትልኰ ጄ/ል ሳሞራ ዘንድ በመድረሱ ጄ/ል ሰዓረ ከሰሜን ዕዝ አዛዥነታቸው፣ ጄ/ል ሞላ ከአየር ሃይል እንዲሁም ጄ/ል አበባው ከያዙት ስልጣን በሳሞራ በአስቸኳይ እንዲነሱ ሲደረግ በተለይ ጄ/ል አበባው ከ2 ወር በፊት ከመከላከያ እንዲባረሩ መደረጉን ምንጮቹ አስረድተዋል። በጄ/ል ሰዓረ ቦታ ጄ/ል ገብራት አየለ ሲተኩ በጄ/ል ሞላ ደግሞ የአግአዚ ክ/ሰራዊት አዛዥ ጄ/ል አደም መሐመድ መተከታቸውን አስታውቀዋል።

ሁለቱ ጄኔራሎች ዝቅ ባለ ደረጃ ተራ የመምሪያ ሃላፊ ተደርገው መሾማቸውን ምንጮቹ ገልፀዋል። ጄኔራል የመሾምና የመሻር ስልጣኑ የጠ/ሚ/ሩ እንደሆነ ህገመንግስቱ ቢደነግግም ነገር ግን የተጠቀሱት ጄኔራሎች የተነሱት በጄ/ል ሳሞራ ትእዛዝ፣ የተተኩትም በሳቸው ውሳኔ እንደሆነና ጠ/ሚ/ር ሃ/ማርያም ከወራቶች በኋላ እንዲያውቁ ተደርጐ ለተሾሙት ጄኔራሎች የማእረግ እድገት እንዲሰጡ መደረጉን ምንጮቹ አስረድተዋል። ጄ/ል አበባውና ጄ/ል ሰዓረ በሙስና ከተዘፈቁ የጦር አዛዦች እንደሚጠቀሱ አክለው ገልፀዋል። ..ይህ በእንዲህ እንዳለ በመከላከያ ከፍተኛ ግመገማ ከሰሞኑ እየተካሄደ ሲሆን ስር የሰደዱ ቀውሶች እየፈነዱ መሆኑ ታውቋል።

“እስሬ፣ ጥሩ ክርስቲያን፣ ሰውና ታጋይ አድርጎኛል”–ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ከቃሊቲ እስር ቤት

0
0

‹‹እስሬ፣ ጥሩ ክርስቲያን፣ ሰውና ታጋይ አድርጎኛል››
‹‹ኢህአዴግ በጭቆና ውስጥ ጸጥ ብሎ የተቀመጠን ሕዝብ እየቆሰቆሰ ነው››
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ከቃሊቲ እስር ቤት

ከኤልያስ ገብሩ

ትናንት፣ በዕለተ ዓርብ እኔ እና የዕንቁ መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ከሆነው ፍቃዱ ማህተመወርቅ (ባሪያው) ጋር ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና ፖለቲከኛን አቶ አንዷለም አራጌን በቃሊቲ ተገኝተን ጠይቀናቸው ነበር፡፡
Eskinder-Nega
ሁለቱም ፍጹም ሰላማዊነት፣ እርጋታ፣ ትህትናና ፈገግታ አብሯቸው ነበር፡፡ ያው ሁለቱንም በአንድ ጊዜ ማናገር ስለማይቻል ተነጣጥለን ማውጋት ግዴታ ነበርና ጥቂት ከአንዷለም ጋር ከተጨዋወትን በኋላ ከእሴው ጋር አወጋን፡፡

እስክንድር የፊታችን ማክሰኞ፣ ሕዳር 2 ቀን 2007 ዓ.ም ፍርድ ቤት ስለምቀርብበት የክስ ጉዳይ አንስቶ የሚሰማውን ነገረኝ፤ ጠንካራ ምክርም ለገሰኝ፡፡ የክሱ እንደምታንም ባላሰብኩት መንገድ አስረዳኝ፡፡ (ይህ ግላዊ ምክር ስለሆነ ልለፈው)

እስክንድርን ከታሰረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ጠይቄዋለሁ፡፡ ስለራሱ መናገር አይፈልግም፡፡ ግን ትናንት ባተለመደ መልኩ ስለራሱ ልቡን ከፍቶ አወጋኝ፡፡ በተለይ ስለፈጠሪው! ሃሳቡን እንዲህ አስቀመጥኩት፡፡

‹‹ኤልያስ፣ እስር ለእንደእኔ አይነት፣ ቤተሰብ ለመሰረተ እና ልጅ ለወለደ ሰው ትንሽ ሊከብድ ይችላል፡፡ ስለባለቤትህ እና ልጅህ ሁሌ ታስባለህ፤ ኃላፊነት አለብህና! ነገር ግን፣ በሌላ መልኩ፣ በመታሰሬ ሎተሪ እንደወጣልኝ አድርጌ እቆጥረዋለሁ፡፡ እስሬ፣ ጥሩ ክርስቲያን፣ ሰውና ታጋይ አድርጎኛል፡፡ አሁን በጣም ሰላም ይሰማኛል፡፡ ክርስቶስን በጣም እንዳውቀው አድርጎኛል፡፡ ፍቅሩ ምን ያህል እንደሆነም ገብቶኛል፡፡ ይህን በመረዳቴ በጣም እድለኛ ነኝ፡፡ መታሰሬ መጽሐፍ ቅዱስን በደንብ እንዳነብ አስችሎኛል፡፡ ባልታሰር ኖሮ እንዲህ የምሆን አይመስለኝም፡፡ ለሌሎች ነገሮች ቅድሚያ እሰጥ ነበር፡፡ ግን ቀዳሚው መሆን ያለበት አምላክህን ማወቅ ነው፡፡ ነገ፣ ይበልጥ የተሻልኩ ሰው እሆናለሁ፡፡ …››

እስክንድር ከላይ ከጠቀስኩላችሁ ሀሳብ አስከትሎ በአሁን ወቅት በሀገሪቷ ላይ ስላለው ጭቆና በጠባቂ ፖሊሶች ፊት ሲናገር ያ ፍጹም የተለመደ ድፍረቱ እና ትህትናው አብሮት ነበር፡፡ እንዲህም አለ፡-

‹‹የስደት፣ የእስርና የክስ መብዛት ሥርዓቱ ያለበትን ከባድ ችግር በግልጽ ያሳያል፡፡ ኢህአዴግ በጭቆና ውስጥ ጸጥ ብሎ የተቀመጠን ሕዝብ እየቆሰቆሰ ነው፡፡ (ከዚህ ጋር በተያያዘ አፈታሪክ ነው ብሎ አንድ ሀገራዊ ምሳሌ ነገረኝ) ይህ ነገ በራሱ ላይ መዘዝ ያመጣበታል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፣ ሥርዓቱ እንዲህ በማድረጉ (የስደት፣ የእስርና የክስ መብዛት) ነገ ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲፈጠር ሳይፈልግ እና ባለማወቅ አበርክቶት እያደረገ ነው፡፡ አለመረጋጋት ይህን ይፈጥራል፡፡ …››
እስክንድር ውስጠ ወይራ ንግግር ተናግሯል፤ ልብ ያለው ልብ ይበል!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

ለአንድ ወር የጠፋችው የኢትዮጵያዊቷ አልማዝ አስከሬን ከነመኪናዋ ጭቃማ ኩሬ ውስጥ ተገኘ

0
0

(ዘ-ሐበሻ) የቴክሳስ ፖሊስ ከኦክቶበር 2 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የጠፋችውን ኢትዮጵያዊት እናት አስከሬን ከሃይቅ ያነሰ ውሃ (ኩሬ) ውስጥ ከነመኪናዋ ገብታ ማግኘቱን አስታወቀ::
almaz
በመዲ ክሬክ የገበሬዎች ከሃይቅ አነስ ያለ ውሃ ውስጥ አንድ ቫን መኪና የተገኘ ሲሆን ፖሊስ ባደረገው ምርመራ የኢትዮጵያዊቷ አልማዝ ገብረመድህንን ሰውነት እንዳገኘ ጠቁሟል:: የወ/ሮ አልማዝ ሰውነት የተገኝበት ጭቃማ ኩሬ የሚገኘው ከምትሰራበት ቦታ በ3 ማይልስ ርቀት ላይ የሚገኝ ነው:: ፖሊስ የአልማዝ ሰውነትን ከነ ሼቭሮሌት መኪናዋ እንዳገኘ ለቤተሰብ ያስታወቀ ሲሆን አሁን እንዴት መኪናው እዚያ ውሃ ውስጥ እንደገባ በምርመራ ላይ ይገኛል::

ተጨማሪ መረጃ ተመልሰን ይዘን እንመጣለን…

Hiber Radio: በጎንደር በተቀሰቀሰ የሕዝብ ተቃውሞ በ4 ወረዳዎች ትምህርት ተቋርጧል * ኢትዮጵያዊቷ በዱባይ ዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደባት

0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ጥቅምት 30 ቀን 2007 ፕሮግራም !

<...>

ዶ/ር አክሎግ ቢራራ የኢኮኖሚ ተመራማሪና የቀድሞ የዓለም ባንክ ኤክስፐርት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለጻፉት ደብዳቤ የሰጣቸውን ምላሽ አስመልክቶ ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረጉት ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)

በደላሎች ከወላጆቻቸው ጉያ እየተነጠቁ ለአሜሪካና ሌሎች አገራት ለማደጉ የሚሰጡ ልጆች ዕጣ ፈንታ እና የማደጎው ሳምንት በአሜሪካ(ልዩ ጥንቅር)

አልማዝን እንርዳ ለወገን የቀረበ ጥሪ በመኪና አደጋ በአረብ አገር ጉዳት ደርሶባት በቅርቡ አገሯ የገባችውን ኢትዮጵያዊት ለመታደግ የተጀመረ ዘመቻ (ልዩ ዝግጅት)

ኡበር ወደፊት አሽከርካሪውስ? (ውይይት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በጎንደር በተቀሰቀሰ የሕዝብ ተቃውሞ በአራት ወረዳዎች ትምህርት ተቋርጣል

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ኢህአዴግ በጭቆና ውስጥ ጸጥ ያለውን ሕዝብ መቆስቆሱ ለውጡን ያግዛል ለስርዓቱ መዘዝ ያመጣል አለ

ኢትዮጵያዊቷ በዱባይ የቀጣሪዎቿን ሶስት ልጆች ልትገድል ሞከረች ተብላ ዕድሜ ልክ ተፈረደባት

የተመድ የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን የመርማሪዎች ቡድን ኢትዮጵያ ገብቶ የመብት ጥሰቶችን ለማጣራት የመንግስትን ፈቃድ እየጠበኩ ነው አለ

አንድነት በተጽዕኖ ከመድረክ ተገፍቼ ወጣሁ አለ

የፓርቲው ም/ቤት ከመድረክ ጋር ያለው ግንኙነት ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ሰጠ

ተቋርጣ የቆየችው ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ታትማ ወጣች

ከዳላስ የጠፋችው ኢትዮጵአዊት ወይዘሮ አስከሬንና ታሽከረክረው የነበረችው መኪና ተገኘ

ኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ከኤርትራ ምንም ድጋፍ አላገኝም ሲል የተመድን ሪፖርት ተቃወመ

የመን 12 አሳ አስጋሪዎቼ በኤርትራ የባህር ጠባቂዎች ተይዘዋል ስትል ወቀሳ አቀረበች

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

በ‹‹ዴሞክራሲ›› ያጌጡት አምባገነኖች

0
0

ጌታቸው ሺፈራው

የማይገባውን ማንነት ለመላበስ የሚደረግ ጥረት ከሰዎች ተፈጥሯዊ የመታወቅ አሊያም የመከበር ተፈጥሮ የመነጨ ይመስላል፡፡ ከጸባያቸው በተቃራኒ ደግ፣ ሩህሩህ፣ ለስው አሳቢ መስለው ለመታየት የሚጥሩ አሊያም የእንደዚህ አይነት ሰዎችን ማንነት የሚገለጽበት ስም ሳይገባቸው የሚይዙ አሊያም የሚሰጣቸው በርካቶች ናቸው፡፡ ከፍ ሲል ደግሞ በወታደራዊ፣ ፖለቱካ፣ ኃይማኖራዊ፣ አካዳሚያዊ ጉዳዮች ከሚገባቸው በላይ ማዕረግ የሚያገኙትም የትየለሌ ናቸው፡፡ መንግስትም የእነዚህ ግለሰቦች ስብስብ ነውና የማይገባው ማዕረግ ወይንም ማንነት ይሰጠዋል ወይንም ይላበሳል፡፡
eprdf_meeting
እነዚህ ከማንነታቸው ውጭ አጓጊዎቹን ማንነቶች በአጋጣሚ የስልጣን ባለቤት ሲሆኑ አሊያም ተጽዕኖ ሲኖራቸው ደግሞ አገራት፣ መንግስት፣ ፓርቲ፣ መሪዎች የሚኖራቸው ስብዕና የተጋነነና ከነባራዊ ሁኔታው ጋር የማይመሳሰል ይሆናል፡፡ መንግስት ወይንም አገር ከሚጠሩበት የተገናነ ማንነት መካከል ሪፖብሊክ፣ ጭራሹን ሲጋነን ደግሞ ዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ አንዱ ነው፡፡ ከእነዚህ አገራት መካከል ደግሞ የኢህአዴጓ ‹‹ኢትዮጵያ›› አንዷ ነች፡፡ ይች የኢህአዴግ ‹‹ኢትዮጵያ›› ከሪፖብሊክም በላይ ዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ተብላ ትጠራለች፡፡

የዓለም ‹‹ሪፖብሊኮች››

በዓለም ከሚገኙት 206 እውቅና ያላቸው አገራትና እንዲሁም ግዛቶች መካከል 154 በሪፖብሊክ ነው የሚጠሩት፡፡ አፍሪካ ውስጥ ካሉት ጥቂት ግዛቶችና 55 አገራት መካከል አራት ያህል እውቅና ያላገኙ ግዛችና ከ44 አራት በላይ አገራት ራሳቸውን የሚጠሩበት በሪፖብሊክነት ነው፡፡ ከእነዚህ ራሳቸውን በሪፖብሊክነት የሚጠሩ መንግስታት የየራሳቸው መግለጫዎች አሏቸው፡፡ አንዳንዶቹ እስላማዊ፣ ሌሎቹ ፌደራላዊ፣ ቀሪዎቹ ህዝባዊ፣ ሌላኛዎቹ ደግሞ ሶሻሊስት፣ አረባዊ እንዲሁም ዴሞክራሲያዊ መሆናቸውን በመግለጽ የመንግስታቸውን ማንነት ለመግለጽ ይጥራሉ፡፡ እንደ አሜሪካ፣ ካናዳና ቦትስዋና ያሉ አገራትና ግዛቶችን ጨምሮ 15 ያህሉ ብቻ ምንም መግለጫ ሳያስፈልጋቸው መንግስታቸውን በአገራቸው ስም ይጠራሉ፡፡ እንደ እስራኤል፣ ሊቢያና ኤርትራ ያሉ አገራት ደግሞ ዴሞክራሲያዊ፣ ሪፖብሊካዊ……የተባሉ መግለጫዎችን ሳይጨምሩ ‹‹የእስራኤል መንግስት፣ የኤርትራ መንግስት …›› ብለው ራሳቸውን በእንቅጩ ይገልጻሉ፡፡

በዓለም ከሚገኙት አገራት መካከል አብዛኛዎቹ ሪፖብሊክነትን ሲጠቅሱ ‹‹ሪፖብሊክ›› የሚለው አንዳች ተወዳጅ ነገር መያዙን ለመረዳት አያዳግትም፡፡ ሪፖብሊክ እንደ መንግስት ስም እንደ ፈረንሳይና ጀርመን ከመሳሰሉት ዴሞክራሲያዊ አገራት እንደ ቻይና፣ ሰሜን ኮሪያ፣ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያና ጅቡቲ የመሳሰሉ አገራት መጠቀሚያ ሲሆን ደግሞ እነዚህ በምንም አይነት መንግስት ስርዓታቸው የማይመሳሰሉ አገራት ቃሉን አወላግደው እየተጠቀሙበት ስለመሆኑ ያስጠረጥራል፡፡ አፍሪካ ውስጥ ካሉት ጥቂት ግዛቶችና 55 አገራት መካከል አራት ያህል እውቅና ያላገኙ ግዛችና ከ44 በላይ አገራት ራሳቸውን የሚጠሩበት በሪፖብሊክነት ነው፡፡

ዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ፣ ፌደራል ዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ የሚባሉት ደግሞ ጭራሹን የመንግስታትን ማንነት ለማጋነን የሚደረጉ ስሞች ስለመሆናቸው እንደ በአገራችን ያለው ተጨባጭ ሁኔታ መውሰድ ይቻላል፡፡ በዓለም ከሚገኙት 154 ሪፖብሊኮች መካከል 10ሩ ብቻ ራሳቸውን ዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ይጠራሉ፡፡ ከአስሩ መካከል ደግሞ 5ቱ (አልጀሪያ፣ ኮንጎ፣ ኢትዮጵያ፣ የሳኦ ቶሚና ፕሪንሲፒ፣ ምዕራብ ሰሃራ (ሳሃራዊ ሪፖብሊክ) አፍሪካ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ቀሪዎቹ 5ቱ (ሰሜን ኮሪያ፣ ላኦስ፣ ሲሪላንካ፣ ምስራቅ ቲሞርና ኔፓል) ከአፍሪካ ቀጥሎ አምባገነኖች በሚገኝበት ኤስያ ውስጥ የሚገኙ አገራት ናቸው፡፡

‹‹ሪፖብሊክ›› ለምን?

ሪፖብሊክ በእነ አርስቶትል ጀምሮ ረዘም ያለ ታሪክ ያለው የመንግስት አይነት ነው፡፡ አንድ መንግስት ሪፖብሊክ ለመባል ለፖለቲከኞች አሊያም ለተወሰኑ ቡድኖች ሳይሆን ለህዝብ መስራት አለበት፡፡ እንዲያውም አንዳንዶች የህዝብ መንግስት የሚሉት ይህን አይነስ ስርዓት ነው፡፡ አሁንም ቢሆን ‹‹ሪፖብሊክ›› ሲባል የመንግስት የስልጣን ምንጭ ህዝብ ሲሆንና ይህ መንግስትም የሚሰራው ለህዝብ ነው ሲባል ነው፡፡

በድሮ ዘመን ልዓላዊ ስልጣን ያለው ንጉስ ወይንም ሌላ አካል ነበር፡፡ የመንግስት ስርዓትም ቢሆን ከአሁኑ ይለያል፡፡ በአሁኑ ዘመን ህዝብ የራሱን መንግስት ሊመሰርት የሚችለው ተወካዮቹን በነጻነት በመምረጥ ነው፡፡ ሆኖም በዚህ ምርጫ ላይ የራሳቸውን ተመራጭ በመምረጥ ሂደት ልኡላዊ ሰልጣን ሊኖራቸው የግድ ነው፡፡ ስለሆነም ‹‹ሪፖብሊክ›› ምርጫ በግድ፣ በንጉሳዊ ቤተሰብ አሊያም ፓርቲ ወይንም ሌላ ባስቀመጠው ሳይሆን በህዝብ፣ ለህዝብና የህዝብ ስርዓት መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡

በእርግጥ ድሮም ቢሆን እንደ ሮማ ያሉት በርካታ ህዝቦችን በግድ እየወረሩ፣ እያፈናቀሉ፣ ባሪያ እየፈገሉ፣ ቅኝ እየገዙም ስሙን ተጠቅመውበታል፡፡ በአንድ አገር ሳይቀር አንዱ ‹‹ሪፖብሊክ›› ብሎ የሰየመውን መንግስት አይነት ሌላኛው ‹‹የህዝብ መንግስት አይደለም›› ብሎ አፍርሶ የራሱን ‹‹ሪፖብሊክ›› ለመምስረት ስለመጣሩ ታሪክ ያትታል፡፡ ለዚህ በምሳሌነት የምትጠቀሰው ፈረንሳይ ናት፡፡ ከታዋቂ እ.ኤ.አ ከ1792 የፈረንሳይ አብዮት ጀምሮ እስከ 1958 ድረስ ፈረንሳይ አምስት የተለያዩ ‹‹ሪፖብሊኮች›› ስም ተጠርታባቸዋለች፡፡

የዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊኮች እንቆቅልሽ

ሪፖብሊክ የመንግስት የህዝብ መንግስት ቢሆንም በብዙሃን ወይንም በሌላ ምክንያት የሚያጣ ህዝብ የለም፡፡ ዴሞክራሲ (የብዙሃን ዴሞክራሲ) የሚባለው ግን ብዙሃን ጥቂቶች በምርጫና በመሳሰሉት ድምጽ በተሻለ የሚገዛበት ነው፡፡ በሪፖብሊካን መንግስት ውስጥ ሁሉም የአገር ንብረት የህዝብ ንብረት ነው፡፡ በዘመናዊው ትርጉም ተቋማትና መንግስት ከፓርቲ የተለዩና ለህዝብ የቆሙ ናቸው፡፡

ዴሞክራሲም ሆነ ሪፖብሊክ ‹‹ዴሞክራሲያዊ›› ስርዓቶች መገለጫ ቢሆኑም በአንጻራዊነት ‹‹ሪፖብሊክ›› የህዝብ መንግስት መገለጫ ነው፡፡ ሪፖብሊካ ከህዝቦች ልዓላዊ ስልጣን (Sovereign power›› ጋር የተገናኘ በመሆኑ በምርጫና በሌሎች ዴሞክራሲያዊ እሴቶች ጋር በቀላሉ የማይነጻጸር ‹‹በህዝብ፣ ለህዝብ፣ የህዝብ›› የመንግስት አይነት ነው፡፡ በአንጻሩ ከሪፖብሊክነት ጋር ሲነጻጸር ዴሞክራሲ የብዙሃን ጨቋኝነት ይታይበታል ተብሎ ይተቻል፡፡ በሪፖብሊክነት ተጨቋኝም ጨቋኝም የለም፡፡ ለአብነት ያህል የአሜሪካ ሁለት ፓርቲዎች ከሚለያዩበት መካከል ነጻነት ላይ ያላቸው አመለካከት ነው፡፡ ዴሞክራቶቹ ህዝብን በሀብትና በመሳሰሉት ለማመጣጠን ክትትል፣ መጠነኛ የመንግስት ጣልቃ ገብነት (እርዳታ) ያስፈልጋል ብለው ያምናሉ፡፡ ይህ መርሃቸው ከሪፖብሊካኞቹ በአንጻራዊነት ሲታይ አምባገነኖች ያስብላቸዋል፡፡

በተቃራኒው ሪፖብሊካኖቹ ህዝብ ብቁ የሚሆነው ነጻ ሲሆን በመሆኑ በነጻነት ሲንቀሳቀስ ነው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሊደርስ የሚችለው ብለው ያምናሉ፡፡ በመሆኑም መንግስትም፣ አገርም፣ ግለሰቦችም ሊለወጡ የሚችሉት በህዝብ ነጻነት ጣልቃ ካልተገባበት ነው ብለው ያምናሉ፡፡ የእያንዳንዱን ግለሰብ በነጻነት የተገኘ ውጤት ለአገሪቱም ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል፡፡ ግለሰቦች በነጻነት የሚመርጡት ማንኛውም ነገር በአገሪቱ ከፍተኛ ጥቅም ይኖረዋል ባይ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ሪፖብሊካኖቹ ለመንግስት መሰረቱ የዜጎች ነጻነት ነው ሲሉ ዴሞክራቶቹ መንግስት ለዜጎች ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለው ያምናል፡፡ ሶሻሊዝም ደግሞ ከመንግስትም ወደ ፓርቲ ይመጣል፡፡ ከአሜሪካዎቹ ፓርቲዎች መካከል የትኛው ወደ ሶሻሊዝም ይቀርባል ብንል የምናገኘው ዴሞክራቶቹን ነው፡፡ ሆኖም ከዚህ የራቁት እነ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ይሉታል፡፡ ኢትዮጵያ የምትገኝበትና የሶሻሊዝም አንድ ውላጅ የሆነው አምባገነንነትና ጠቅላይነት ፓርቲዎች ስልጣንን ዴሞክራሲም ሆነ ሪፖብሊክ ከሚከተለው የህዝብ ስልጣን ይልቅ ወደ ማዕከላዊ ኮሚቴው ጥቂት ሰዎች ከዛም ወደ አንድ ግለሰብ ያወርደዋል፡፡

የአምባገነኖቹ ተቃርኖ

በዓለም ከዴሞክራሲም ጥቂት የዴሞክራሲያዊ እሴቶችን የማይተገብሩት ራሳቸውን በዴሞክራሲያውነት ከዚህም አልፈው በሪፖብሊክነት ይጠራሉ፡፡ ይህ አልበቃቸው ሲል ደግሞ ከዴሞክራሲም እንደሚበልጥ የሚነገርለትን ‹‹ሪፖብሊክ›› ስርዓት በዴሞክራሲ ለማሳመር ይጥራሉ፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ 10 የአለማችን ሪፖብሊኮች ከዚህ ፍጹም ነጻነት ጋር ከሚያያዘው የመንግስት ስርዓት ስያሜ ላይ ‹‹ዴሞክራሲያዊ›› የሚል ቅጥያ የጨመሩበት ‹‹ይበልጥ ዴሞክራሲያዊ›› መሆናቸውን ለመግለጽ ነው፡፡ እንደ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ጋና፣ ያሉ አገራት የሪፖብሊክነትን በቅጥያ ቢወስዱም ‹‹ዴሞክራሲያዊ›› የሚል አልወሰዱም፡፡ እንደ ቻይና ያሉት አምባገነን መንግስታትም ቢሆን ልክ እንደ ጀርመንና ሌሎች ዴሞክራቶች ጋር በእኩል ‹‹ ሪፖብሊክ››ን ብቻ ነው የወሰዱት፡፡ ቢያንስ ዴሞክራሲና ሪፖብሊክ ምን ማለት እንደሆነ የገባቸው ይመስላል፡፡

አብዛኛዎቹ ስርዓቶች በእውነተኛ ማንነት መገለጽ ከነበረባቸው በዴሞክራሲያውም ሆነ በሪፖብሊክነት መጠራት አልነበረባቸውም፡፡ እንዲያው ይጋነን ከተባለ እንኳ የብዙሃን አምባገነንነት እንደ ህጸጽ የሚጠቀስበትን ‹‹ዴሞክራሲያዊ›› ስርዓት መጠሪያ ማድረግ አንድ ነገር ነበር፡፡ ከዚህ በላይ እናጋንን ቢሉም ልክ እንደ ቻይና የህዝብ መንግስት የመሰረትን ‹‹ሪፖብሊኮች›› ነን ማለት ይችሉ ነበር፡፡ እነ ኢትዮጵያና ሰሜን ኮሪያ ግን ፍጹም ነጻነት አለው የሚባለውን ‹‹ሪፖብሊክ›› ከዚህ የመንግስት ስርዓት ባነሰው ‹‹ዴሞክራሲያዊ›› ለማጋነን ሲሉ ነው የተሳሳቱት፡፡ ነጭን ነገር ይበልጡን ለማንጻት ከሌላ ቀለም ጋር እንደመለወስ ማለት ነው፡፡

ከምንም በላይ እነዚህ ሪፖብሊካንን ከዴሞክራሲ ጋር የሚያጣርሱ አገራት በዓለም ካሉት አምባገነኖች መካከል ቀዳሚ መሆናቸው ነው፡፡ ከ10 አገራት መካከል የተሻሉ የሚባሉት ብቸኛዋ ሳኦቶሚና ፕሪንሲፒ ተባለችው ሁለተኛዋ የአፍሪካ ትንሽ አገር ነች፡፡ በእርግጥ ይች ሀገር ከአፍሪካ አገራት መካከል አስከ 10 ካሉት ዴሞክራቶች የምትመደብ ነች፡፡ ከዚች አገር ቀጥሎ አልጀሪያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት ተስፋ ያላት ብትሆንም አሁንም ቢሆን በምርጫ ማጭበርበር፣ በሙስና፣ ሰብአዊ መብት ጥሰትና በሌሎች ኢ-ዴሞክራሲያዊነት እንደታጀበ ነው፡፡ ግራ የተጋባው የዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊክና ሪፖብሊክ ቀርቶ ዴሞክራሲያዊ የሚለው ይበዛባታል፡፡

ላኦስ ከአምባገነኗ ቻይና ጥግ የምትገኝ አገር ናት፡፤ ከኩባ፣ ቻይና እና ቬትናም ቀጥሎ አራተኛዋ የሶሻሊስት ቅሬት የምትከተል አገር ናት፡ ገዥ ፓርቲዋም የላኦስ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ ይባላል፡፡ ምንም እንኳ ከ1983 ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ የተባለ ህገ መንግስት ቢጸድቅም የራሳቸውን ህዝቦች ከሚያሳቃዩ መንግስታት መካከል በቀዳሚነት እየተወቀሰ ነው፡፡ ደቡብ ምስራቅ ኤሲያዋ ትንሽና ድሃዋ ምስራቅ ቲሞርም ‹‹ዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊክን›› የምትጠቀም የኢህአዴግ ኢትዮጵያ አይነት አገር ነች፡፡
ሌላኛዋ ዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ነኝ የሚለው አምባገነኑ የሰሜን ኮሪያ መንግስት ነው፡፡ በሰሜን ኮሪያ ለስሙ ብዙሃ ፓርቲ ስርዓት እንዳለ ተደርጎ ነው የሚቆጠረው፡፡ ሆኖም ግን በአንድ ቤተሰብ በመጣ አንድ ፓርቲ የምትደዳደር አገር ከሆነች ከርማለች፡፡ ሪፖብሊክ ትርጉሙ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በውርስ፣ በቤተሰብ መሆን እንደሌለበት የሚያስረዳ ቢሆንም የሰሜን ኮሪያ አምባገነን መንግስት ግን ፊውዳሊዝምና ሶሻሊዝምን ያጣረሰ አዲስ ስርዓት ነው፡፡ ምን አልባትም በዓለም ላይ ለሪፖብሊክ እንደሱ የሚርቅ የለም ማለት ይቻላል፡፡ ከኢህአዴግ ከሰሜን ኮሪያው የሚለየው የሰሜን ኮሪያው ቀጥታ የቤተሰብ ስርዓት በመሆኑ ነው፡፡ ‹‹ዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊክን›› ከሚጠቀሙት ሌሎች ግራ የተጋቡ መንግስታት መካከል ኮንጎ በእርስ በእርስ ጦርነት እየተናጠች ነው፡፡ እ.ኤ.አ በንጉሳዊ ስርዓት ስትመራ የነበረችው ኔፓል በአሁኑ ወቅትም ቢሆን በማኦኢስት ፓርቲ ነው የምትታመሰው፡፡ ስሪላንካ በሶሻሊስት ፓርቲ የምትመራ አገር ነች፡፡

የ‹‹ብሄር›› ቁርሾና ከፋፍለህ ግዛም የእነዚህ ‹‹ዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊኮች›› ዋነኛ መገለጫዎች ናቸው፡፡ በሁሉም አገራት ለስም መድብለ ፓርቲ፣ ህገ መንገግስት፣ ፍርድ ቤት……. የሚባሉ የዴሞክራሲያዊ እሴቶች የመንግስታቱን ስም ጣራ ለማድረስ ተብሎ እንደተጨመረው ‹‹ዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊክነት›› በስም የይስሙላህ ብቻ ነው፡፡ ሰብአዊ መብት ረገጣም፣ የምርጫ ማጭበርበር፣ አፈና እና ሌሎች የአምባገነን እሴቶች ዋነኛዎቹ መገለጫዎቻቸው ቢሆኑም ዴሞክራሲንም ሆነ ሪፖብሊክን ግን ሳይገባቸው ለሌላቸው ማንነት ማስጌጫነት ይጠቀሙበታል፡፡


ከሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የወጣ መግለጫ

0
0

Legal ethiopian sinodosበስደት ላይ የሚገኘውና በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የሚመራው ሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ 40ኛውን መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 26-28 /2007 ዓ/ም በኮሎምበስ ኦሐዮ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ካቴድራል አካሄዷል።

[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

ግልጽ ደብዳቤ ”ለጠቅላይ ሚኒስትር” ኃይለማርያም ደሳለኝ : ከታሳሪ ዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች

0
0

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሕገ መንግስታችንን ያክብሩ!

 

ሠላም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር!? እንዴት ነዎት? ያስታውሱ ከሆነ የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢከፊሉ የዚህ ማስታወሻ ፀሃፊዎች  ‘ግልፅ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ’

“ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እባክዎትን የተለያዩ የመንግስት አካላት የሕገ መንግስታችንን ድንጋጌዎች እየጣሱ ነውና እርስዎም በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 74/13/ መሠረት ሕገ መንስቱን የማስከበርና የማክበር ግዴታ ስላለብዎት ሕገ መንግስቱን ያክብሩ” በማለት አንዲት አጭር ደብዳቤ ፅፈንልዎት ነበር፡፡

zone9ድንገት በተለያዩ ምክንያቶች የጻፍንልዎትን ደብዳቤ ካላነበቡት ወይም ማስታወስ ካልቻሉ ዛሬ ይሄን ማስታወሻ ስለምንፅፍልዎት ግለሰቦች አንድ ሌላ ማስታወሻ እንስጥዎ፡ ከ6ወራት በፊት /በሚያዚያ 2006 ዓ.ም/ ሶስት  ጋዜጠኞችንና ስድስት ጦማሪያንን ‘ሕገ መንግስቱንና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ በመሞከር ወንጀል ጠርጥሬያችኋለሁ’ በማለት መንግስትዎ ልማታዊ ርምጃ (አብዮታዊ ርምጃ እንደሚባለው) ወስዶ ነበር፡፡

እኛም የዚህ ማስታወሻ ፀሃፊዎች የዚህ ‘ልማታዊ ርምጃ’ ሰለባ የሆንን ግለሰቦች ነን፡፡በርግጥ ከሁለት ዓመታት በፊት ‘ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሕገ መንግስቱን’ ያስከብሩልን በማለት ጥያቄ ያቀረብንልዎት ግለሰቦች ‘ከ6 ወራትበፊት ሕገ መንግስቱን ለመናድ  ሞክራችኋል’ በማለት መንግስትዎ ሲያስረን ሕገ መንግስቱ እንዲከበር ጠይቀን ሕገ መንግስቱን ለመናድ በመሞከር ወንጀል ተጠርጥረን ስንታሰር እስሩ በጣም ግራ አጋብቶን ነበር፡፡በዚህ ያልቆመው መንግስትዎ ክሱን ‘ሕብረተሰቡንና ሀገሪቱን ለማሸበር አቅዳችኋል ሞክራችኋል አሲራችኋል…’ በማለት ወደ ‘ሽብርተኝነት’ያሳደገው ሲሆን እርስዎም ከዚህ ጋር በተያያዘ ሃሳብዎትን ሲሰጡ ስለተመለከትንዎ ትንሽ ቅሬታ ይዘን መጣን፡፡

በቅድሚያ አሁን ያለንበትን ሁኔታ በትንሹ ብናስረዳዎት ቅሬታችንን ለመረዳት ያስችልዎታልና አንዳንድ ጉዳዮችን እንንገርዎት፡፡

ይሄን ማስታወሻ በምንፅፍልዎት ወቅት ከታሰርን ከ 200 ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን፣ነገር ግንጉዳያችን ገና በቅድመ ክስ (Pre Trial) የክርክር ሂደት ላይ ይገኛል፡፡ ይሄ የሆነበት ዋነኛ ምክንያትም መንግስትዎ እንኳን ለእኛ ለተከሳሾች ለከሳሽ አካልም ግልፅ ያልሆነ ክስ በማቅረቡ ነው፡፡ ይሄንንም ስንል ልትፈፅሙት ነበር የተባለው ‘የሽብርተኝነት ድርጊት’ ሳይጠቀስ ‘በቃ የሽብርተኝነት ድርጊት ልትፈፅሙ ነበር’ በማለት በጨበጣ ስለመጣብን ነው፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እንግዲህ የብዙ ድብደባ፣ ዛቻ እና ስድብ ሰለባዎች ከሆንን በኋላምየቀረበው ይሄ  ክስ ነው ከ6 ወራት በኋላም ተከሳሾች ከሳሾቻችንምሳንረዳው በየቀጠሮው እየታሸ ነው የሚገኘው፡፡ ‘የተፋጠነ ፍትህ’ ሕገ መንግስትዊ መብት ነውና የተፋጠነ ፍትህ ይሰጠን፣ እርስዎምይሄን ሕገ መንግስታዊ መብት ያክብሩ እያልንዎት አይደለም ‘ሕገ መንግስቱ ተከብሮ እያለ ሕገ መንግስቱ ይከበር በማለቴ ጥፋተኛ ነኝ’በማለት ‘ጥፋት የሚያሳምን’ ( አንዱ የዚህ ደብዳቤ ጸሃፌ ጦማሪ ጥፋት ብሎ አንዲፈርም የተገደደው ህገ መንግስቱ ተከብሮ እያለህገመንግስቱ ይከበር ማለቴ ጥፋት ነው ብሎ መሆኑ መንግስትዎን መልክ ግልጽ አድርጎ ያሳያል) መንግስት አለዎትና ይህ ጥያቄ አንደሚበዛብዎትእናውቃለን፡፡

ይልቁንም ቀላልና ግልፅ ቅሬታን ነው ይዘን የመጣነው፡፡ ይሄውም የኢፌድሪ ሕገ መንግስትበአንቀፅ 20/3/ ላይ

‘የተከሠሡ ሰዎች[…]  በፍርድ ሂደት ባሉበት ጊዜ በተከሰሱበት ወንጀል እንደ ጥፋተኛ ያለመቆጠር[…]መብት አላቸው::’

በማለት የደነገገ ሲሆን፣ ይሄንን ሕገ መንግስታዊ መብትም ማንኛውም የመንግስት አካል እንዲሁም ግለሰብ የማክበር ግዴታ አለበት፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር እርስዎና መንግስትዎም በተደጋጋሚ ‘ሕገ መንግስቱ ሳይሸራረፍ እናስከብራለን’ ይላሉና ይሄን ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌ የምታውቁት ይመስለናል፡፡ ነገር ግን ከታሰርን ወዲህ ስለእኛ የእስር ጉዳይ በተጠየቁባቸውጊዜያት ይሄን ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌ በመጣስ ‘ፍርድዎትን’ በተደጋጋሚ ሲሰጡ ታዝበናል፡፡ እናስረዳዎ፡- ሐምሌ 12/2006 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣሚ መግለጫ ላይ ስለእኛ እስር ጉዳይ ለቀረበልዎት ጥያቄ ሲመልሱ፡-

 

‘ከአስመራ እስከ ሞቃዲሾ የተዘረጋው የሽብር ሰንሰለት ውስጥ አንዴከገቡ በኋላ ብሎገር ነኝ፣ ጋዜጠኛ ነኝ ማለት ዋጋ የለውም’

በማለት ብዙ ነገሮችን ተናገሩ፡፡ ይሔውልዎት ስህተትዎ፡-

1.     የክሳችን ዋነኛ ጭብጥ በሃገርውስጥ ‘የሽብርተኛ ድርጅት በማቋቋም ‘የሽብርተኝነት’ ተግባራትን ለመፈጸም አሲረዋል፡ አቅደዋል… የሚል እንጂ፣ እርስዎም እንደሚሉት ‘ሰንሰለት’ ምናምን አይደለም፣

2.    እሺ አሸባሪዎችም ይበሉን፣ነገር ግን ሕገ መንግስቱ እንደሚደነግገው በፍርድ ቤት ‘ጥፋተኝነታችን’ እስሚረጋገጥ ቢጠብቁስ ምናለበት? ይህ የሚያመለክተው እርስዎም እንደ ማእከላዊ መርማሪዎች ነፃ ሆኖ የመገመት (presumption of innocence) መብታችንን እያከበሩልን እንዳይደለ ነው፡፡

ይሄ ነገር የሆነው በድንገት ሊሆን ይችላል ብለንዝም ብንልም እርስዎ ግን በድጋሚ ጥቅምት 6/2007 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ከምክር ቤቱ አባል ለቀረበልዎ ጥያቄሲመልሱ፡-

 

“የብሎገር ጭምብልአጥልቆና በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ ተሸሽጎ ከተከሳሽነት ማምለጥ አይቻልም፡፡ ሽብርተኝነትን መዋጋታችን ይቀጥላል…” እያሉ እርስዎ ያሉትን የብሎገር ጭምብል አውልቀውና ተሸሸጉበት ያሉትን የጋዜጠኝነት ሙያመሸሸጊያ አፍርሰው ባንዴ ‘የአሸባሪነት’ ካባ ደረቡልን፡፡

ክቡር ጥቅላይ ሚኒስቴር፣ እያልን ያለነው የአንድ ሰው ‘አሸባሪነት/ወንጀለኝነት’ የሚረጋገጠው በፍርድ ቤት እንደሆነ ሕገ መንግስቱ ደንግጎ እያለ፣ እርስዎ ግን ነፃ ሆኖ የመገመት መብታችን ወደ ጎን ብለው እንደ ከሳሽም እንደፈራጅም በመሆን ‘አሸባሪዎች’… እያሉን ይገኛሉ ነው፡፡

ምናልባት ‘ስራ አስፈጻሚው ከሳሽ ነውና እኔም የስራ አስፈጻሚው አካል መሪ ስለሆንኩ የፈለኩትን አስተያየት የመስጠት መብት አለኝ’ ብለው ከሆነ፣ ሕገ መንግስቱን የማክበር ጉዳይ ‘ርስዎን ጨምሮ ሁሉም ዜጎች ላይ የተጣለ ግዴታነው፡፡ እርስዎ ‘L’e’tat, c’est moi’ ይሉት አይነት የራስ ግምት ውስጥዎ ከሌለ በስተቀር እንዲህ በግልፅ እየጠየቅንዎት ‘ሕገ መንግስትቱን  አላከብርም’ በማለት ገና ዋነኛ ክርክሩ እንኳንያ ልተጀመረ ክስን (ዋነኛ ክርክር ካለው) መሠረት በማድረግ ከዚህ በኋላ እኛን ‘አሸባሪዎች’ አይሉንም ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ይህን ተመሳሳይ ምላሽ “በእርግጠኝነት አሸባሪ ናቸው” በሚል ቃና ለቢቢሲ ለኢንቢሲ ለመሳሰሉት አለም አቀፍ ሚዲያ  ተቋማትም መስጠትዎን ሰምተናል፡፡

ሌላው ልናስታውስዎ የምንፈልገው ጉዳይ እንደኛ አይነት የተራገበ( በሰፊው በታወቀ የአደባባይ)የፍርድ ጉዳይ ([un] popular case) ላይ የመንግስት አካላት አስተያየት (say) ያለውን ተፅእኖ እንዲያስቡት ነው፡፡እርስዎ በምክር ቤት ቀርበው የአሸባሪነት ፍርድ ከበየኑብን (አሁን እያደረጉት እንዳሉት) ፍርድ ቤትም ሆነ ሌሎች የመንግስትዎ አካላትምን ሊያስቡ እንደሚችሉ አስተውለውታልን?!

ይሄን ሁሉ ስንልዎ እንዲያው ሕጉን ያክብሩልን ለማለት ያክል ነው እንጅ፣ ከሽብርተኝነትጋር የሚያገናኘን ቅንጣት ያክል እውነት /A segment of fact/ እንደሌለና የሰው ልጆች መልካምና ደስተኛ ሕይወት እንዲኖራቸውከመመኘትና ለአገራችን ያገባናል ከማለት ያለፈ ሕይወትም ፍላጎትም እንደሌለን እኛም እናውቀዋለን እርስዎና መንግስትዎም ያውቁታል፡፡ነገር ግን ካለፉት ስድስት ወራት አንስቶ ጨዋታውን በግድ ካልተጫወታችሁ ተብለናልና እየተጫወትን ነው፡፡ የአሁኑ ጥያቄያችን ግን በጣም ቀላል ነው፣ ጨዋታው ገና በደንብ እንኳን ሳይጀመር ውጤቱን እይወስኑት ነው፡፡

እርስዎ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት የስልጣን ደረጃ በወጡ ሰሞን አብዛኞች የዚህ ማስታወሻፀሃፊዎች መጠነኛ ለውጥና ማሻሻዎች ያደርጋሉ የሚል ተስፋ ሰንቀን “The First 100 Days” ወዘተ እያልን ብዙ ጠብቀንዎት ነበር፡፡ ከሁለት ዓመት በሚበልጥ ግዜ እንደተመለከትንዎ ግን ተስፋችን ፍሬ ሊያፈራልን አልቻለም፡፡ አሁንም አዲስ ተስፋ ሰንቀን ግን ፡- “ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር እባክዎትን ሕገ መንግስቱን ያክብሩ! የእኛንም መብት ያክብሩልን” እንላለን፡፡

 

‘’የብሎገር ካልሲ አድርጎ፣ የጋዜጠኝነት ጫማ ተጫምቶ የሽብረተኝነት ሰንሰለት ውስጥ ከገቡ በኋላ ሕገ መንግስቱን ያክብሩልኝ ማለት ዋጋ የለውም!’’በማለት ተስፋችን ዋጋ እንደማያሳጡት ተስፋ አለን፡፡

 

ከአክብሮት ጋር

 

 ጦማርያን                    ጋዜጠኞች

ዘላለም ክብረት                 ኤዶም ካሳዬ

ናትናኤል ፈለቀ                ተስፋለው ወ/የስ

በፍቃዱ ሃይሉ                አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ

አጥናፍ ብርሃኔ

አቤል ዋበላ

ማህሌት ፋንታሁን

 

 

 

ሌ/ጄነራል አበባው ታደሰ ወደ ውጭ ሊወጡ ሲሉ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በደህንነቶች ተመለሱ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

0
0

ጄ/ል አበባው ታደሰ ወደ ውጭ ለመውጣት ሲሉ ከቦሌ አየር ማረፊያ በደህንነቶች እንዳይወጡ መደረጋቸውን ታማኝ ምንጮች ጠቁመዋል።

ከመከላከያ የጦር አዛዥነታቸው በጄ/ል ሳሞራ የኑስ እንዲነሱ የተደረጉት ጄ/ል አበባው ከአገር እንዳይወጡ የተደረገበት ምክንያት ግልፅ እንዳልሆነ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል። በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ የተለያዩ ጥያቄዎች እንዳሉ በመግለፅ ለኢታማጆር ሹሙ ጄ/ል ሳሞራ ከረር ያለ ሪፖርት ያቀረቡት ጄ/ል ሰዓረ፣ ጄ/ል ሞላና ጄ/ል አበባው መሆናቸውን የጠቆሙት ምንጮቹ በሳሞራ የተሰጠው መልስ « የትምህክተኞች ጥያቄ ነው፤ ችግር የለም..» የሚሉና ጥያቄዎቹን የሚያጣጥሉ እንደነበሩ አስታውሰዋል።
Tadesse
ሶስቱ ጄኔራሎች በሳሞራ ምላሽ በመበሳጨት ከስልጣናቸው ለማስነሳት በምስጢር ቢመክሩም መረጃው ባልታወቀ መንገድ አፈትልኰ ጄ/ል ሳሞራ ዘንድ በመድረሱ ጄ/ል ሰዓረ ከሰሜን ዕዝ አዛዥነታቸው፣ ጄ/ል ሞላ ከአየር ሃይል እንዲሁም ጄ/ል አበባው ከያዙት ስልጣን በሳሞራ በአስቸኳይ እንዲነሱ ሲደረግ በተለይ ጄ/ል አበባው ከ2 ወር በፊት ከመከላከያ እንዲባረሩ መደረጉን ምንጮቹ አስረድተዋል። በጄ/ል ሰዓረ ቦታ ጄ/ል ገብራት አየለ ሲተኩ በጄ/ል ሞላ ደግሞ የአግአዚ ክ/ሰራዊት አዛዥ ጄ/ል አደም መሐመድ መተከታቸውን አስታውቀዋል።

ሁለቱ ጄኔራሎች ዝቅ ባለ ደረጃ ተራ የመምሪያ ሃላፊ ተደርገው መሾማቸውን ምንጮቹ ገልፀዋል። ጄኔራል የመሾምና የመሻር ስልጣኑ የጠ/ሚ/ሩ እንደሆነ ህገመንግስቱ ቢደነግግም ነገር ግን የተጠቀሱት ጄኔራሎች የተነሱት በጄ/ል ሳሞራ ትእዛዝ፣ የተተኩትም በሳቸው ውሳኔ እንደሆነና ጠ/ሚ/ር ሃ/ማርያም ከወራቶች በኋላ እንዲያውቁ ተደርጐ ለተሾሙት ጄኔራሎች የማእረግ እድገት እንዲሰጡ መደረጉን ምንጮቹ አስረድተዋል። ጄ/ል አበባውና ጄ/ል ሰዓረ በሙስና ከተዘፈቁ የጦር አዛዦች እንደሚጠቀሱ አክለው ገልፀዋል። ..ይህ በእንዲህ እንዳለ በመከላከያ ከፍተኛ ግመገማ ከሰሞኑ እየተካሄደ ሲሆን ስር የሰደዱ ቀውሶች እየፈነዱ መሆኑ ታውቋል

የመኢአድ ጠቅላላ ጉባኤው ተጠናቀቀ –እነ አቶ አባበው ለቀው ወጡ

0
0

ግርማ በለጠ

aeup

ነሐሴ ወር 2006 ዓ.ም መኢአድ እና አንድነት ዉህደት ይፈጽማሉ ተብሎ ተጠብቆ እንደነበረና የሕወሃት ምርጫ ቦርድ ለመኢአድ አመራር እውቅና አልሰጥም በሚል ዉህደቱን ማጨናገፉ ይታወቃል። ከሁለት አመታት በላይ በአቶ አበባው መሐሪ ከሚመራው መኢአድ ጋር ደብዳቤዎች ሲጻጻፍ የነበረው ምርጫ ቦርድ ፣ አንድም ጊዜ በአመራሩ ላይ ጥያቄ አንስቶ ሳያውቅ፣ ዉህደት ሊደረግ ሲል፣ ሸንካላ ምክንያት በመፍጠር ሆን ብሎ ዉህደቱን ማጨናገፉ፣  ምርጫ ቦርዱ በሕወሃት አመራር ታዞ ያደረገዉ እና ምንም አይነት ገለልተኝነት እንደሌለው ያሳየበት እንደሆነ ብዙዎች ያናግራሉ።

የምርጫ ቦርድን ሕገ ወጥ ጥይቄ ለማሟላት መኢአድ ቅዳሜ ጥቅምት  29 እና እሁድ  ጥቅምት 30  ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ የነበረ ሲሆን፣ ጠቅላላ ጉባኤው ባለመስማማት እንደተጠናቀቀ ለማወቅ ችለናል።

አርብ ጥቅምት  28 ቀን፣  የመኢአድ ላእላይ ምክር ቤት ተሰብስቦ የመኢአድ አመራር የነበሩና በተለያዩ ችግር የተገለሉ ፣ አቶ ማሙሸት አማረን ያካተተ ፣ 14 ሰዎችን ጉዳይ፣  ጠቅላላ ጉባኤው በነገታው ዉሳኔ እንዲያሳልፍ ስምምነት የተደረሰ ሲሆን፣  ምንም እንኳን ከአንድንት ጋር ሊደረግ የነበረዉን ዉህደቱ ምርጫ ቦርድ ቢያጨናግፈውም፣ የምርጫ ዘመቻውን ከአንድነት ጋር በተቀናጀ መልኩ ለማድረግ በጠቅላላ ጉባኤው ዉሳኔ ለማስወሰን ታስቦም እንደነበረ ለማወቅ ችለናል።

ቅዳሜ ጥቅምት 29 ቀን ጠቅላላ ጉባኤው በአቶ ሃይሉ ሻዉል መሪነት የተከፈተ ሲሆን፣  ከ335 በላይ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ተገኝተዉም ነበር።  እነ አቶ ማሙሸት በርካታ ሰዎች በስብሰባው እንዲገኙ ማድረጋቸዉንም ለማረጋገጥ ችለናል።

በስብሰባው ወቅት በአቶ ኃይሉ ሻዉልና በአቶ አበባው መሐሪ መካከል ጠንካራ ልዩነቶችና አለመስማማቶች የነበሩ ሲሆን ስብሰባው በጥሩ ሁኔታ እንዳልተጠናቀቀም ለማውቅ ችለናል። አቶ አበባው፣ ከሁለቱ በስተቀር የሥራ አስፈጻሚ አባላት በሙሉ ለደህንነታቸው ፈርተናል በሚል  ስብሰባዉ ጥለው እንደወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከስብሰባው ከወጡት መካከል የመኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊው አቶ ተስፋሁን አለምነህም ይገኙበታል።

ስብሰባው እሁድ ጥቅምት 30 በቀሩት በአብዛኛው እነ አቶ ማሙሸት የሰበሰቧቸው ተወካዮች ባሉበት አቶ ማሙሸት አማረን የመኢአድ ፕሬዘዳንት አድርገው መርጠዋል።

ጠቅላላ ጉባኤው  ቅዳሜ ጥቅምት 29 ቀን የተደረገ  እለት የምርጫ ቦርድ ተወካይ እንዳልነበረም የደረሰን ዘገባ ሲያመለክት፣ የምርጫ ቦርድ ተወካይ በሌለበት፣ አብዛኛው የጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች አልተገኙም በተባለበት የተደረገ ምርጫ ምን ያህል ሕጋዊ ሊሆን እንደሚችል ግልጽ የሆነ ነገር እንደሌለ ከመኢአድ አባላት የሚደርሱ ዘገባዎች ይገልጻሉ።

ከአራት አመታት በላይ ያልታዩት ኢንጂነር ኃይሉ ሻዉል፣ በዚህ መልኩ ስብሰባው በሰላም እንዲጠናቀቅ አለማድረጋቸው እንዳልተደሰቱ የሚገልጹት አንድ ያነጋገርናቸው የመኢአድ አባል ለመኢአድ አሁን ያለበት ደረጃ በዋናነት ተጠያቂው አቶ ኃይሉ ሻወል እንደሆኑ ይናገራሉ።

በመኢአድ እና በአንድነት መካከል ሊደረግ ታስቦ የነበረ አብሮ የመስራት ዉሳኔ በነበረው አለመስማምምት  አልመሳካቱ ጥሩ እንዳልነበረ የተናገሩት እኝሁ የመኢ፤አድ አባል፣  “አብዛኛው የመኢአድ አባል ከአንድነቶች ጋር እየታሰረ፣ እየተደበደበ፣ እየተገደለ ነው። በተግባር የመኢአድ እና የአንድነት አባላት አንድ ናቸው” ሲሉ በአመራሮች ዘንድ አለመስማማቶች ቢፈጠሩም በሜዳ በየዞኑና በየወረዳው ያለው የመኢአድ ታግይ እንኳን እርስ በርሱ እንደ አንድነቶ ካሉ ሌሎች የትግል አጋሮቹ ጋር አንድ ሆነ እየሰራ እንደሆነም ይገልጻሉ።

በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው ከበርካታ ተወካዮች ጋር ስብሰባዉን ለቀው የወጡት አንድ የመኢአድ ከፍተኛ አመራርር አባል፣  በማንም ድርጅት አለመስማማቶች እንደሚፈጠሩ ገልጸው፣ ብሶት ለመናገር ወደ ኢቲቪ እንደማይሮጡ ገልጸዋል።

በአቶ አማረ ማሙሽት የሚመራው መኢአድ ጽ/ቤቱን ተቆጣጥሮ አዲስ ካቢኔም እንዳዋቀረ ለማወቅ ችለናል። በዚሁ መሰረት አዲስ ካቢኔ የሚከተሉት  አባላትን አካቷል፡
1: አቶ ማሙሸት አማረ (ፕሬዝዳንት)
2: ዶ/ር ታዲዎስ ቦጋለ (ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት)
3: አቶ እንድርያስ ኤሮ (ምክትል ፕሬዝዳንት)
4: አቶ ተስፋየ መላኩ (ዋና ፅሃፊ)
5: አቶ ሰማሀኝ አብርሃም (የድርጂት ጉዳይ)
6: ኮኔሌር ትርሶት ጉልላት(የህዝብ ግንኙነት)
ገ: ወ/ሮ አለማየሁ ሞገድ (የሴቶች ጉዳይ)
8: አቶ አብርሀም ጌጡ (የውጭ ጉዳይ)
9: አቶ ሀብተማርያም ያንተ(ፋይናንስና አስተዳድር)
10: አቶ ታጠቅ አሰፋ (የወጣቶች ጉዳይ)
11:አቶ ሀይለየሱስ ሚናስ (የምርጫ ጉዳይ)
13:አቶ ተስፋሁን አለምነህ (ትምህርትና ስልጠና አላፊ)
14 : መ/አ አየለ አለ(የህግና ዲስፕሊን አላፊ)
15: አቶ ወርቁ ከበደ (የምሃል ቀጠና ሃላፊ)
16: አቶ አዳነ ጥላሁን(የሰሜን ቀጠና ሃላፊ)
17: አቶ ብሩ ደሲሳ( የምራብ ቀጠና ሃላፊ)
18: አቶ ገለቱ ደጀርሳ (የደቡብ ቀጠና ሃላፊ)
19: አቶ ተፈራ መንግስቴ (የምስራቅ ቀጠና ሃላፊ)\

 

 

የዶክተር ቴዎድሮስ ውሎ በኦስሎ (ከ-እምሻውጫኔ/ኖርዌይ)

0
0

2እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከኦክቶበር 16 ቀን 2014 ጀምሮ ለሶስት ቀናት ፣ Invest in Ethiopia በሚል መሪ ቃል አዲስ  አበባ የሚገኘውን የኖርዌጅያን አምባሳደር ጭምር አጀብ አስከትለው ወደ ኖርዌይ የመጡት ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ፣ሶስቱንም  ቀን ሳይመቻቸው ስፍራና ቦታ በመቀያየር፣ የመጡበትን ርጥባን ልመናና ፥ በተጨማሪም የቤተሰብ ጥየቃ ሥራቸውን ጨርሰው  ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል==  ሙሉውን ጋዜጣ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ=== 

 

 

ከ- እምሻው ጫኔ/ኖርዌይ

ወያኔ/ኢሕአድግ እና ምርጫ 2007

0
0

Dagnachew Tegegne

November.11.2014

Norway,oslo

2007 electionበያዝነው 2007 ዓ.ም በግንቦት ወር ለሚካሄደው አገራዊ ምርጫ በገዢው ፓርቲ እንዲሁም በተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ ሲሆን ምርጫ ቦርድም ምርጫውን በበላይነት ለመምራት ቁሳዊና ቴክኒካል ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑን ከገዢው ፓርቲ ልሳን ከሆነው EBC በተደጋጋሚ እየተሰማ ነው፡፡ ይህን ተከትሎ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል መከፋፈሎች እንዲሁም አለመረጋጋቶች እየተስተዋሉ ሲሆን ለዚህም ምክንያቶቹን በእርግጠኝነት መግለጽ አዳጋች ቢሆንም ካለፉት የምርጫ ተሞክሮዎች በመነሳት የገዢው ፓርቲ ረጃጅም እጆች እንዳለበት መተንበይ አዳጋች አይሆንም፡፡

በዚህ በያዝነው አመት የሚካሄደውን አገራዊ ምርጫን ለመተንበይ በቅድሚያ ከዚህ ቀደም የተካሄዱትን አገራዊ ምርጫዎች በወፍ በረር ቅኝት ማየቱ የግምቱን ይዘት ጠንካራ ያደርገዋል፡፡ በዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ እምነት እንዲሁም በተለያዩ ጊዜያቶች ከሚወጡ ጥናታዊ ጽሁፎች ለመረዳት እንደሚቻለው በአገራችን ተስፋ ሰጪ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ተካሂዷል ተብሎ የሚታሰበው በ1997ዓ.ም በተካሄደው አገራዊ ምርጫ ነው፡፡ ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩትም በዋነኛነት ገዢው ፓርቲ በወቅቱ ለነበሩት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የነበረው ዝቅተኛ አመለካከት (በወቅቱ ቅንጅት የምርጫው ምዝገባ ሊጠናቀቅ ጥቂት ጊዜያት በቀሩበት ወቅት ቅንጅት መፍጠሩን ልብ ይለዋል) እንዲሁም የምዕራባዊያኑን ቀልብ በመሳብ አገሪቷ ለዴሞክራሲያዊ ግንባታ እየተጋች መሆኗን ለማሳየትና ከፍተኛ ፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞም በወቅቱ በመንግስት ይዞታ ስር የነበሩትን የንግድ ተቋማት ወደ ግል ይዞታነት በማዞር (privatization) መንግስት ቀደም ሲል ይተችበት የነበረውን ሶሻሊስምን ወደ ጎን በመተው ዘመኑን መምሰሉን በማሳየት ምዕራባዊያንን ለማሳመን የሚተጋበት ወቅት ስለነበረም ጭምር ነው፡፡ ስለሆነም ያለፉትን የምርጫ ሂደቶችን ለመገምገም ምርጫ 97 እንደመነሻ (base year) በመውሰድ ገዢው ፓርቲ እንዲሁም ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫው ላይ የነበራቸውን ሚና በሚከተለው መልኩ ለመዳሰስ ወደድኩኝ፡

ምርጫ 97

ኢሕአድግ 1997ቱ ምርጫ ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ለተቃዋሚዎች በነበረው ዝቅተኛ ግምት ፤ ምርጫውን በበላይነት አሸንፋለው ከሚል የተሳሳተ ግምት እንዲሁም የምዕራባዊያኑን ቀልብ ለመግዛት የዲሞክራሲ በሩን ገርበብ አድርጎ በመክፈቱና ለምርጫው ቅስቀሳ ከዛ በፊት ይሰጡ ከነበሩት የመከራከሪያ ሰዓት በአንጻራዊነት ሰፊ ጊዜ ለተቃዋሚዮች በመስጠቱ ህዝቡ የሁሉንም ፓርቲዎች ፕሮግራም የሚሰማበት እድል ፈጥሯል፡፡ በወቅቱ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች አንጻር ኢሕአድግ በፖለቲካ ልምድ እንዲሁም በህብረተሰቡ ተሰሚም ታዋቂም ስለነበር ገዚው ፓርቲ ምርጫውን በበላይነት ለማጠናቀቅ ሙሉ ዕምነት ነበረው ሆኖም ግን ወደ ምርጫው ቅስቀሳ ሲገባ እየታየ የመጣው ፈጽሞ ያልተጠበቀና ገዚው ፓርቲ የከፈተውን የዶሞክራሲ በር ለመዝጋት አስቸጋሪ የነበረበት እንዲሁም ወደ ኋላ ማፈግፈግ የማይችልበት ወቅት ነበር፡፡

በተቃዋሚዎች በኩል በወቅቱ የምሁሮች ስብስብ ተብሎ ሲሞካሽ የነበረው ቅንጅት የገዢው ፓርቲ ጠንካራ ተፎካካሪ ነበር ለዚህም ምክንያቶቹ በርካታ ቢሆኑም ድርጅቱ በውስጡ ጉምቱ የፖለቲካ አዋቂዎችን ማካተቱ ፤ ድርጅቱ በመረጃ የተደገፈ ጠንካራ ክርክር ማካሄዱ፤በምርጫ  ክርክሮች ወቅት ሚያቀርባቸው ተከራካሪዎች ኢሕአዴግ ከሚያቀርባቸው የተሻሉ መሆናቸው፤ የማህበረሰቡን የልብ ትርታን መሰረት ያደረጉ ጠንካራ ትችቶችን  በገዢው ፓርቲ ላይ በማቅረባቸው (የዘር ፓለቲካን  ፊትለፊት  በመተቸታቸው ፤ ሙስናን በመረጃ አስደግፈው በማጋለጣቸው፤ በገዢው ፓርቲ  የተንቋሸሸውን  ስራ አጥ ወጣቱን ስራ ፈጣሪ ለማድረግ ንድፈ ሃሳብ ማቅረቡ ከብዙ በጥቂቱ ሚጠቀሱ ናቸው) ፤ ዘርን መሰረት ያላደረገ  የፖለቲካ አቅጣጫ (political ideology) ይዞ መቅረቡ ፤ ድርጅቱ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችን ያቀናጀ መሆኑና ሌሎች ምክንያቶች ተደማምረው የምርጫውን ግምት አፋልሰውታል፡፡

ኢሕአዴግን ለውድቀት የዳረጉ ውስጣዊ ምክንያቶች

ከላይ በጠቅላላው ለማሳየት እንደተሞከረው የምርጫ 97 ለተቃዋሚዎች የፈጠረውን እድልና ገዢው ፓርቲ ላይ ያስከተለውን አሉታዊ ተጽዕኖ ሲሆን ከዚህ በታች የምንመለከተው በድርጅቱ ውስጥ የነበረውን ውስጣዊ ችግሮችን ይሆናል፡

1.ከመጠን ያለፈ በራስ መተማመን

ኢሕአዴግ ከ1997 በፊት በነበሩት ምርጫዎች ተቀናቃኝ የነበሩትን በቀጥታ እንዲሁም በተዘዋዋሪ ካዳከማቸው ከፊሎችንም ከበታተነ በኋላ አስጊ የፖለቲካ ተቃዋሚ ስላልነበረ በምርጫ 97 ፍጹም የበላይነትን ለመቀናጀት እምነት ነበረው ለዚህም ማሳይው ከሌሎች የምርጫ ጊዜያቶች በተለየ ሁኔታ ለተቃዋሚዎች ሰፊ የአየር ሽፋን መስጠቱ ፤ የተለያዩ በርካታ የመከራከሪያ መድረኮችን ማዘጋጀቱ ፤ ክርክሮቹ ቀጥታ የአየር ሽፋን ማግኘታቸው ሲሆኑ ባልተጠበቀ መልኩ ጠንካራ ሆኖ የቀረበው ቅንጅት እንዲሁም ሌሎች ተቃዋሚዎች እድሉን በሚገባ ስለመጠቀማቸው በወቅቱ የነበረው የምርጫ ውጤት አመላካች ነው፡፡

2.ጠንካራ ተከራካሪ ያለማዘጋጀት

በተለያዩ የክርክር መድረኮች ኢሕዴግን ወክለው የሚቀርቡ ተከራካሪዎች ከተቃዋሚዎች ተሸለው ባለመገኘታችው እንዲሁም የሚያቀርቧቸው መከራከሪያዎች በመረጃ የተደገፉ አለመሆናቸውና  በተደጋጋሚ በተለያዩ የመንግስት ሚዲያዎች ሲሰሙ የቆዩ በመሆናቸው አሰልቺ ነበሩ፡፡ በወቅቱ በተቃዋሚዎች የሚቀርቡትን ፈታኝ ጥያቄዎች በበቂ ሁኔታ የሚመልስ ባለመኖሩ ኢሕአዴግ እየኮሰሰ ሌላው እየገነነ የመጣበት ሁኔታ እንደነበር የሁላችንም የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፤፤

3.የአባላት ታማኝ አለመሆን

የተለያዩ መረጃዎች እንደሚያመለክተው ኢሕዴግ በ1997 ምርጫ ወቅት ጠቅላላ ከ6 ሚሊዬን በላይ አባላት የነበሩት ሲሆን ይህንን አባላት በማሰብ ገዢው ፓርቲ በቀላሉ እንደሚያሸንፍ መገመቱ ስህተት ላይመስል ይችል ይሆናል ነገር ግን ከምርጫው ማግስት ለመረዳት እንደተቻለው አብዛኛው አባላት የድርጅቱን የፖለቲካ ፕሮግራምን በመረዳት ሳይሆን የስራ ዕድል ለማግኘትና የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን በመፈለግ ፓርቲውን መቀላቀላቸው ነው፡፡ በአዲስ አበባ ድርጅቱ ድምጽ አገኝባቸዋለው ብሎ ባሰበባቸው በተክለሃይማኖት ፤ ቦሌ እና ሌሎች አካባቢዎች መሸነፉ አንዱ ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡

4.ሙስና

ኢሕአዴግ በዋነኛነት ከሚታወቅባቸው እኩይ ባህሪያቶቹ አንዱ ሙስና ሲሆን ይህም የሚከናወነው ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ሳይሆን በተወሰኑ ቡድኖች ፤ ነባር ታጋዮች እንዲሁም ዘርን መአከል ያደረገ ስለነበር ሌሎች አጋር ድርጅቶች ውስጥ ውስጡን መከፋታቸው የነበረ ሲሆን ይህም መከፋት አባላቱ ሌሎች አማራጫ ፓርቲዎችን  እንዲመለከቱ ወይም ድርጅቱ ላይ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ከማነሳሳቱም በላይ ድርጅቱን የግላቸው አድርጎ ለማሰብ አዳጋች ነበር፡፡

ምርጫ 2002:- በዚህ ምርጫ ላይ ኢሕአዴግ ከ1997ቱ ምርጫ ብዙ የተማረበት እና በቂ ዝግጅት ያደረገበት ስለነበር ውጤቱን ለመቀልበት ችሎ ነበር፡፡ በዚህ ምርጫ ወቅት ድርጅቱ በአብዛኛ የፖለቲካ ተንታኞች ሲገለጽ እንደነበረው ብቻውን ሮጦ ብቻውን ያሸነፈበት ምርጫ ነበር፡፡ ለዚህም ምክንያቶቹ፡-

  • በምርጫ 97 ላይ ጠንካራ የነበረውን ቅንጅትን አከርካሪውን በመስበር የበላይ አመራሮቹን በማሰር እንዲሁም ከሀገር እንዲሰደዱ በማድረግ ፤ ህዝቡን ይቅርታ እንዲጠይቁ በማስገደድ በህዝቡ ውስጥ እምነት እንዳይኖራቸው በማድረግና በሌሎችም እኩይ የፖለቲካ ስራዎቹ ድርጅቱን በማዳከሙ /በማፈራረሱ
  • በራሱ በኢሕአዴግ የተፈጠሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በመፍጠር እንዲሁም ሌሎች ተቃዋሚዎች በኢሕአዴግ ሴራ እንዲሁም በግላቸው ምክንያት ከምርጫ እራሳቸውን ማግለላቸው
  • አጭር የክርክር መድረኮችን በማዛጋጀት እንዲሁም ለተቃዋሚዎች አጭር ጊዜ በመስጠት በተቃራኒው ለራሱ ሰፊ የአየር ሽፋን በመስጠት የድርጅቱን ፕሮግራሞች ማስተዋወቁ
  • በ1997 በቅንጅትና በሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ይቀርቡ የነበሩ አማራጭ የልማት እስትራተጂዎችን በመውሰድና ከፊሎችንም በመተግበር ከተሰራው ስራ በላይ ፕሮፖጋንዳ በመስራት (ጥቃቅንና አነስተኛ ፤ ማህበራትን ማደራጀት ፤ ወጣቱን አደገኛ ቦዘኔ ከማለት ወደ ወጣት የልማት ሀይል መቀየር ፤ የጋራ የመኖሪያ ቤቶችን መገንባትና የመሳሰሉት ከምርጫ 1997 በፊት በገዢው ፓርቲ ተሰምተው የማይታወቁ ሲሆን ከምርጫ 97 በኋላ ጽንሰ ሀሳቡ ከተቃዋሚዎች ስለመሰረቁ ማሳይዎች ናቸው)
  • ቀደም ሲል ገጠርን ማዕከል ያደረገውን ልማት ወደ ከተማ በማምጣት የሚታዩ ለውጦችን በማቅረብ እነሱንም በመንግስት ሚዲያዎች አግንኖ ማቅረቡ (መንገድ ፤ ውሃ ፤ ኤሌክትሪክ ወዘተ)
  • የህዝቡ ተስፋ መቁረጥ፡ – በምርጫ 97 ወቅት በህዝቡ ተስፋ የተጣለባቸው ፓርቲዎች ከነአካቴው መጥፋታቸውና እነሱን ሊተካ የሚችል ጠንካራ ተፎካካሪ ፓርቲ መጥፋቱ
  • ጠንካራ የፖለቲካ ቅስቀሳ መደረጉ ፡ – መንግስት የተለያዩ መድረኮችን በማዘጋጀት የተሰሩ የልማት ስራዎችን በማቅረብ ፤ ህብረተሰቡን በማወያየት እንዲሁም ትልልቅ ካፒታል የሚጠይቁ ፕሮጀክቶችን በማስፋፋቱና የረጅም ጊዜ ዕቅዶችን በማቅረቡ
  • ምርጫ ቦርድ ላይ ያለውን ስውር እጅ በማስፋፋት ጠንካራ ክትትል ማድረግና የድርጅቱ የቀኝ ክንፍ መሆኑ በዚህና በሌሎች ምክንያቶች ገዢው ፓርቲ ሙሉ ለሙሉ የምርጫው አሸናፊ ሊሆን ችሏል፡፡ ከሁለቱ ተከታታይ ምርጫዎች የምንማራቸው አበይት ጉዳዮች ቢኖሩ፡
  • ኢህአዴግ በቢሊዮን የሚቆጠር የፋይናንስ አቅም እንዳለውና ለፖለቲካ ቅስቀሳ በቂ አቅም እንዳለው በተቃራኒው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያላቸው የፋይናንስ አቅም እጅግ አናሳ በመሆኑ በራካታ አባላትን ለማፍራት እንዲሁም ቅስቀሳዎችን ለማድረግ የአቅም ውሱንነት እንዳላቸው
  • ኢሕአዴግ የ1997ቱ ምርጫ ብዙ ልምዶችን የቀሰመበትና በወቅቱ አሳይቶት የነበረው የዲሞክራሲ ጭላንጭል በማጥፋት ፍፁም አምባገነን እየሆነ መምጣቱን
  • ኢሕአዴግ የተቃዋሚዎችን ደካማ ጎን በመጠቀም እንዲሁም የስለላ መረቦቹን በመጠቀም ተቃዋሚዎችን የማዳከምና የማፈረካከስ ልምዱን ያካበተ መሆኑን እና ፓርቲዎች ለምርጫ ከመድረሳቸው አስቀድሞ ከምርጫው እራሳቸውን እንዲያገሉ ጫና ማሳደሩን
  • የምርጫ ቦርድ መመሪያዎችንና ደንቦችን ኢሕአዴግ በፈለገው መልኩ ማሻሻሉንና ህጉ ለሁሉም በእኩል ደረጃ ተጠቃሚ የማያደርግ መሆኑንና እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች ናቸው፡፡እነዚህን እንደ መነሻነት በመጠቀም በምርጫ 2007 ሊገጥሙ የሚችሉትን ከወዲሁ ለመገመት ያህል፡ -

ኢሕአዴግ

በገዢው ፓርቲ በኩል ለምርጫው እየተደረጉ ያሉ ቅድመ ዝግጅቶች ከዚህ ቀደም ሲደረጉ ከነበሩት በእጅጉ የላቁ ናቸው፡፡ ይህም ነፃ የግል ፕሬሶችን ያለምንም በቂ ማስረጃ  በማሰር ፤ በመክሰስ ፤ በማስፈራራት ፤ እንዲሁም አገር ለቀው እንዲሰደዱ በማድረግ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ፕሮግራማቸውን  የሚያስተዋውቁበትን  መንገድ መዝጋቱ፡፡ ከዚህም  በተጨማሪ  ህዝቡ አማራጭ የመረጃ ምንጮች እንዳይኖሩት በማድረግ ህዝቡ በሚያገኘው አንድ አገራዊ የቴሌቪዝን ጣቢያ የገዢውን ልማታዊ ስራዎች ብቻ እንዲያይ ማድረጉ ነው፡፡

የተለያዩ የማህበረሰብ ድህረ ገፆች ላይ ፤ የደህንነት ሀይሎችን በማሰማራት እና ድንገተኛ ፍተሸዎችን በማድረግ ህዝቡን በማሸማቀቅ ፤ ሀይማኖትን ከሀይማት በማጋጨት ፤ የዘር ግጭቶችን በማቀነባበር ፤ ህዝቡ ላይ ሽብር በመንዛት ህዝቡ ከኢሕአዴግ ውጭ አማራጭ እንዳያስብ በማድረግ ህዝቡ እንዲመርጠው ብሎም ደግሞ የደህንነቱን ጡንቻ በማሳየት ለማስፈራራት በመሞከር ላይ ነው ለዚህም ማሳይው የተለያዩ የፖለተካ ስደተኞችን እና እንዲሁም በተለያዩ አገራት ይኖሩ የነበሩ የተቃዋሚ ድርጅት ቁልፍ ሰዎችን  አፍኖ በማምጣት ህዝቡ ላይ ፍራቻን ሲዘራ ይስተዋላል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ እንደ ምርጫ 2002 ሁሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን  በመከፋፈል ፤ በመታተን እንዲሁም በተለይዩ ምክንያቶች አመራሮቻቸውን በማሰር ተሳትፏቸውን ማዳከምን ተያይዞታል እንደ ማሳይም በአንድነት ለዲሞክራሲና ለልማት ፤ በአረና ፓርቲ እንዲሁም በሰማያዊ ፓርቲ ላይ እያደረሰ ያለው የማፈራረስ ፤ የማሸማቀቅ እንዲሁም እስራቶችን ማየት በቂ ማስረጃ ነው፡፡

የፖለቲካ ቅስቀሳዎችን በተመለከተም በአሁኑ ወቅት በሲቪል ሰርቫንቱ እና በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንዲሁም በነዋሪው ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ስልጠናዎችን እያካሄደ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ  ተቃዋሚ ፓርቲዎች የመሰብሰቢያ አዳራሾችን የመከራይት አቅም ማሳጣት  አቅም ያላቸውንም  ደግሞ የአዳራሽ፣ ቢሮ፣እንዲሁም  ኪራይ ቤቶች እንዳያገኙ ተጽዕኖ በመፍጠር  ላይ ነው፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲዎች

በያዝነው ዓመት ማገባደጃ ላይ ለሚከናወነው አገራዊ ምርጫ ተቃሚ ፓርቲዎች እያደረጉ ያለው ቅድመ ዝግጅት በገዢው ፓርቲ ጥብቅ ክትትል ስር ሲሆን ፓርቲዎቹ የሚደርስባቸውን ጫና ለመቋቋም እንዲሁም ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን እንዲያስችላቸው ውህደት ለመፈፀም በሂደት ላይ ሲሆኑ በገዢው ፓርቲ ስውር እጆች ምክንያት በሚፈለገው ፍጥነት እየተጓዘ እንዳልሆነ እያየን ነው፡፡ በዚህ ምርጫ በሃገር ውስጥ ትልቅ  ግምት ከሚሰጣቸው እንደ አንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲ  በገዢው ፓርቲ ተደጋጋሚ ትንኮሳ እየደረሰባቸው ሲሆን ይህም የምርጫው ዋዜማ ላይ ሊበረታ እንደሚችል ይገመታል፡፡

ህብረተሰቡ

ካለፉት የምርጫ ጊዜያቶች በተለየ ሁኔታ ማሕበረሰቡ የፓለቲካ አድማሱ የሰፋበት ሆኔታ ሲሆን ለዚህም አበይት ምክንያቶቹ በማሕበራዊ ድህረ ገፆች የሚለቀቁ የተለያዩ አክቲቪስቶችን  ንግግር ፤ ክርክሮች ፤ በግል ፕሬሱ ይታተሙ የነበሩ የፖለቲካ ትንታኔዎች ፤ ከገዢው ፓርቲ እየሾለኩ የሚወጡ የተለያዩ መረጃዎች እንዲሁም ህብረተሰቡ አማራጭ የመረጃ ምንጭ በማግኘቱ ነው፡፡ በመሆኑም ማሕበረሰቡ ምርጫው በገዢው ፓርቲ የተለመደ ማጨበርበሮች ሊጠናቀቅ እንደሚችል ግምቱ ቢኖረውም እንደ ባለፉት የምርጫ ጊዜያቶች በቸልታ ያልፈዋል ተብሎ አይታሰብም ምክንያቱም ህዝቡ መንግስት የሚያደርገውን የመብት ረገጣ ፤ አድሎአዊ አገዛዝ ፤ ሙስና ፤ እንዲሁም በእስልምና ሀይማኖት እና በኦርቶዶክስ የዕምነት ተከታዮች ላይ እጁን በማስገባት እየፈፀመ ያለውን በደል በሚገባ ስለሚያውቅ ድርጅቱ ጉልበት ያለው ቢመስልም ውስጡ ግን ባዶ ፤ ደጋፊ ያለው ቢመስልም አባላቱ በጥቅም ፤ በዘር እንዲሁም በመልካም አስተዳደር እጦት ያኮረፉ የሚበዙበት ሲሆን ገዚው ፓርቲ ከሕወሓት ውጨ ያሉ ፓርቲዎችን በአይነ ቁራኛ መመልከቱና አብዛኛውን ስልጣን ጠቅልሎ መያዙ በአጋር ድርጅቶች ጥርስ ውስጥ እንዲገባ ምክንያት ሆነዋል፡፡

ማጠቃለያ

የምርጫውን ውጤት ከወዲሁ መተንበይ ባይቻልም በገዢው ፓርቲ ውስጥ ያሉ አባላት   በወያኔ ሕወሓት ላይ በተለይዩ ምክንያቶች ውስጣቸው የሻከረ በመሆኑ (ብአዴን በግንቦት 7 ፤ ኦሕዴድ በወጣት ተተኪዎቹ የስልጣን ይገባናል ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ፤ እንዲሁም በሌሎች አጋር ፓርቲዎች) የምርጫውን ውጤት ወዳልተገመተ አቅጣጫ ሊመሩት እንደሚችል ይገመታል፡፡ የማሕበረሰቡ ንቃተ ህሊና መጨመር ፤ ገዢውን ፓርቲ በተጨባጭ መረጃዎች መወንጀል መጀመሩ ፤ መንግስት በተደጋጋሚ የሚፈፅማቸው የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች ፤ የአገሪቱን ከፍተኛ ቁጥር የሚሸፍኑትን አንጋፋ የሀይማኖት ተቋማትን ማስኮረፉ ከሀይማኖቱ ተከታዮች የምርጫ ካርድ ሊነፈግ እንደሚችልም  ይገመታል ይሁንና ገዢው ፓርቲ በምርጫ ቢሸነፍም ስልጣኑን ለመልቀቅ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ድምፁ የተሰረቀበት ማሕበረሰብ አልመረጥኩም ብሎ በጥያቄ  ተቃውሞ ቢነሳ  ተቃውሞውን በበቂ ሁኔታ የሚያስተባብርና ሀላፊነቱን የሚወስድ ፓርቲ ባለመኖሩ አገሪቷን ወደ አላስፈላጊ ዕልቂት እንዳይጥላት ያሰጋል፡፡ ገዢው የወያኔፓርቲ የምርጫውን ውጤት በጸጋ ተቀብሎ ለመጪዋ ኢትዮጵያ ዘላለማዊነት በቅን ልቦና ምርጫውን ለግል ጥቅም ሳይሆን የህዝቡን ድምፅ እንዲያከብር ልባዊ  ምኞቴ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!

ፍርድ ቤቱ በሽዋስ አሰፋ፣ በሀብታሙ አያሌው፣ በአብርሃ ደስታና በዳንኤል ሺበሽ በዋስትና ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ለህዳር 11 ቀጠሮ ሰጠ

0
0

(ነገረ ኢትዮጵያ) የሽዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታ፣ ዳንኤል ሺበሽን ጨምሮ በአቶ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የተከፈተባቸውን የ10ሩን ተከሳሾች የዋስት ጉዳይ ለማየት ለዛሬ ህዳር 2/2007 ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት በዋስትና ጉዳይ ብይን ለመስጠት ለህዳር 11/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጠ፡፡
Habtamu abrhayeshiwas daniel
በሌላ በኩል የደንበኞቹና የእሱም መብት እየተከበረ ባለመሆኑ ላልተወሰነ ጊዜ ችሎት እንደማይቆም ያሳወቀው ጠበቃ ተማም አባ ቡልጉ ተከሳሾቹ ዋስትና እንዲፈቀድላቸው የሚጠይቅ 13 ገጽ ጽሁፍ ለፍርድ ቤቱ ማስገባቱን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

10ሩ ተከሳሾች ህዳር 11/2007 ዓ.ም ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ላይ ዋስትና ይሰጣቸው አይሰጣቸው ለሚለውን ውሳኔ ልደታ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡


የታፈኑት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ወደ ማዕከላዊ መዛወራቸው ተሰማ

0
0

Tensaye ከአንድ ሳምንት በፊት በየ ክፍለ ሀገሩ በገዥው ፓርቲ የደህንነት ኃይሎች የታፈኑት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ወደ ማዕከላዊ መዛወራቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ በሰሜን ጎንደር ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ሰብሳቢ የሆነው አቶ አግባው ሰጠኝ እንዲሁም፤ በዚሁ በሰሜን ጎንደር ዞን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራር አቶ አንጋው ተገኝ በትናንትናው ዕለት ወደ ማዕከላዊ መዛወራቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ጠቅሰዋል፡፡

ሰሞኑን በየ ክፍለ ሀገሩ በገዥው ፓርቲ የደህንነት ኃይሎች የታፈኑት የሰማያዊ፣ የአንድነት፣ የመኢአድና የአረና አመራሮችና አባላት የደረሱበት ሳይታወቅ የቆየ ሲሆን ከትናንትና ጀምሮ ወደ ማዕከላዊ እየተዛወሩ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ

አስተዳደሩ ትብብሩ እሁድ ለሚያደርገውን የአደባባይ ስብሰባ የእውቅና ደብዳቤ ተቀበለ

0
0

blue party
(ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ እንደዘገበው) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለሚያደርገው የመጀመሪያ ዙር መርሃ ግብር የአደባባይ ስብሰባ የተላከውን ደብዳቤ ተቀበለ፡፡ የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር በአንድ ወር ውስጥ ከሚያደርጋቸው መርሃ ግብሮች መካከል እሁድ ህዳር 72007 ዓ.ም አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ሜዳ ወይንም ቤልኤር ሜዳ ላይ የሚደረገውን የመጀመሪያውን የአደባባይ ስብሰባ ሰማያዊ ፓርቲ እንዲያስተባብር ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን የማሳወቂያ ክፍሉ ደብዳቤውን በዛሬው ዕለት ተቀብሏል፡፡

ትብብሩ እሁድ ህዳር 7 የሚያደርገው የአደባባይ ስብሰባ ፍትሃዊ ምርጫ ስለሚደረግበት ሁኔታ አባላቱንና ደጋፊዎቹን የሚያስተምርበት መሆኑን ለአስተዳደሩ ያስገባው ደብዳቤ ላይ ጠቅሷል፡፡ በስብሰባውም ከ3000 በላይ ህዝብ እንደሚገኝ የስብሰባው አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡

የአደባባይ ስብሰባው አስተባባሪዎች ከአሁን ቀደም በተደጋጋሚ ወደ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍሉ ያቀኑ ቢሆንም የክፍሉ ሰራተኞች በተደጋጋሚ ‹‹የሉም›› እየተባሉ ሳያገኟቸው ይመለሱ እንደነበር ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ትብብሩ በአንድ ወር ውስጥ የሚያደርጋቸውን ሌሎች መርሃ ግብሮች ሰማያዊና ሌሎቹም ፓርቲዎች በየተራ እንደሚያስተባብሯቸው ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያ በ2014፡ ሁልጊዜ በህዳር አስታውሳለሁ

0
0

ጭራቁ ህዳር 2005!

እ.ኤ.አ በ2005 ኢትጵያውያን/ት ለመናገር የሚዘገንን እጅግ በጣም የሚያስፈራ ድርጊትን አስተናግደዋል፡፡ በዚያኑ ዓመት በግንቦት ወር የተካሄደውን ፓርላሜንታዊ ምርጫ ተከትሎ የህዝብ ድምጽ በአደባባይ በጠራራ ጸሐይ በመዘረፉ ምክንያት ታቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመግለጽ ወደ አደባባይ የወጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት አሁን በህይወት በሌለው የገዥው አካል ቁንጮ ፈላጭ ቆራጭ መሪ በነበረው በመለስ ዜናዊ ልዩ ትዕዛዝ እና ቁጥጥር በግፍ በጥይት ተደብድበው እንዲያልቁ ተደርገዋል ወይም ደግሞ በፖሊስ እና በደህንነት ኃይሎች በጥይት ተደብድበው በከፍተኛ ደረጃ ቁስለኛ ሆነዋል፡፡ በመለስ ዜናዊ ልዩ ትዕዛዝ በተቋቋመ አጣሪ ኮሚሽን የምርመራ ውጤት መሰረት ተቃውሟቸውን ለመግለጽ በሰላማዊ መንገድ በአውራ መንገዶች ተሰልፈው የነበሩትን 193 ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች እንዲሁም በከፍተኛ ደረጃ ጥብቅ ክትትል እየተደረገባቸው በእስር ቤት ይገኙ የነበሩ የህግ እስረኞችን ጨምሮ ሆን ተብሎ ታስቦበት እና ተመክሮበት በወሮበላ ፖሊሶች እና የደህንነት ኃይሎች ጭንቅላቸውን እና ደረታቸውን በጥይት እየተደበደቡ እንዲገደሉ ተደርገዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ 763 ወገኖቻችን ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል**፡፡ 

eth cryእ.ኤ.አ ከ2007 ጀምሮ ሁልጊዜ በየዓመቱ ህዳር በመለስ ልዩ ትዕዛዝ እና ቁጥጥር  የዕልቂቱ ሰለባ የሆኑትን በመቶዎች የሚቀጠሩ ንጹሀን ዜጎች ሰማዕት ለመዘከር እና ለማስታወስ የዝክረ ሰማዕት ጸሁፍ እያዘጋጀሁ ለአንባቢዎቼ ጀባ እላለሁ፡፡ እነዚህ ጀግኖች ሰማዕታት ለዴሞክራሲ እና ለነጻነት ሲሉ መተኪያ የሌላትን ውድ ህይወታቸውን ገብረው አልፈዋል፡፡ እነዚህን ጀግኖች የነጻነት ሰማዕቶቻችንን መርሳት ነጻነትን እና ሰብአዊ መብትን መካድ እና መርሳት ማለት ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2007 “የሰኔ እና የህዳር 2005 የኢትዮጵያን ሰማዕታት ለዘላለም እናስታውስ!“ በሚል ርዕስ ባዘጋጀሁት የመጀመሪያ የሰማዕታቱ መታሰቢያ ጽሁፍ በአንድ ወቅት ከእልቂት በታምር የተረፈውን የኤሊ ዊሰልን አባባል በመዋስ በኢትዮጵያ “ለሞቱት እና በህይወት ላሉት ምስክር የመሆን የሞራል ግዴታ አለብን” በማለት አንባቢዎቼን አሳስቤ ነበር፡፡

የመለስ የእልቂት ሰለባ የሆኑትን ወገኖቻችንን ማስታወስ አለብን ምክንያቱም ኤሊ ዊሰል እንዲህ ብሎ ነበርና፣ “ያለፈውን የእኛ የጋራ ትውስታ የሆነውን ታሪክ እና ድርጊት ቀጣዩ ትውልድ እንዳያውቀው የመከልከል እንዲረሳ የማድረግ መብት የለንም፡፡ ያለፈውን እልቂት እና ሰቆቃ አለማስታወስ ወይም ደግሞ መርሳት አደገኛ ብቻ አይደለም፣ ሆኖም ግን በህዝብ ላይ የሚደረግ ዘለፋም ነው፡፡ የሞቱትን እና ሰማዕት የሆኑትን መርሳት እነዚህን የክብር ሰማዕቶች እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ መግደል ማለት ነው፡፡“

ህዳር አረመኔ ወር ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ የማድረግ አቅሙ ቢኖረኝ እና የምችል ቢሆን ኖሮ በቀጥታ ህዳርን በመዝለል ከጥቅምት ወደ ታህሳስ ተወርውሬ እጓዝ ነበር፡፡ ስልጣን እና ኃይል ቢኖረኝ ኖሮ ህዳርን ወንጀለኛ ዘራፊ አድርጌ ለህግ አቀርበው ነበር፡፡ ህዳር የሚባል ወር ባይኖር ኖሮ የማስታውሰው ምንም ዓይነት ነገር አይኖርም ነበር፡፡ ማርክ ዋይን ይህንን ጉዳይ በማስመልከት እንዲህ ብለው ነበር፣ “እውነቱን እስከተናገርህ ድረስ ምንም ዓይነት የምታስታውሰው ነገር አይኖርም፡፡“ በእውነቱ ማርክ ዋይን ይህንን ሲሉ ተሳስተዋል፡፡ እውነታውን በተናገርህ ጊዜ ሁሉንም ነገር ታስታውሳለህ በተለይም ውሸቶችን፣ ጩኸቶችን፣ ወንጀሎችን፣ እልቂቶችን እና ፍጅቶችን፡፡

አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ እና የእርሱ የወንጀል ፈጻሚ እና ተባባሪ የሆነው የወሮበላ ድርጅት ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሰሩትን ግፍ እና ሰቆቃ ማስታወስ እና እውነታውን ፍርጥርጥ አድርጌ ለወገኖቼ እና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳወቅ ለእኔ በጣም አስፈላጊ ጉዳዬ ነው፡፡ መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በሰኔ እና በህዳር 2005 በመቶዎች የሚቆጠሩ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ሳይታጠቁ ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመግለጽ ወደ አደባባይ የወጡ ንጹሀን ዜጎችን በእርሱ የማን አህሎኝ የድፍረት እና የእብሪት ትዕዛዝ በጥይት እየተደበደቡ እንዲያልቁ ሲያደርግ ያለምንም ስህተት እና ግልጽ በሆነ መልኩ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሊያስተላልፍ የፈለገው መልዕክት ነበረው፡፡ ይኸውም እርሱን እና ህወሀት የሚበለውን የጉግ ማንጉግ ደርጅት ለዘላለም በስልጣን ኮርቻ ላይ አጣብቆ ለማኖር ሲል በአውሬያዊ እና በአረመኒያዊ ምግባሩ ለሰላማዊ ተቃውሞ የሚነሳውን ንጹሀን ዜጋ ሁሉ ያለምንም ርህራሄ በገፍ መግደል፣ መምታት እና ማቃጠል እንደሚችል በተግባር ለማሳየት ነው፡፡ መለስ ዜናዊ የሬይችፉህረር ሄንሪክ ሂምለር (የጀርማን አረመኔ ናዚው ) ጎበዝ ተማሪ ነበር፡፡ የሄንሪክ ሂምለር አስተምህሮ በጎበዙ እና በባለራዕይው መሪ በመለስ ዜናዊ ጭንቅላት አድሮ እንዳለ ምንም ጠብ ሳትለው ኮርጆ እንዲህ የሚለውን የዕኩዮች ስነምግባር በስራ ላይ አውሎታል፣ “በጣም ተመራጭ የሆነው የፖለቲካ መሳሪያ ሽብርን መንዛት እና ማስፋፋት ነው፡፡ ጨካኝነት ክብርን ያዝዛል፡፡ ሰዎች ሊጠሉን ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን ስለእነርሱ ፍቅር ማግኘት አንጠይቅም፣ የምንጠይቀው ነገር ቢኖር ፍርሀት እንዲፈሩ ማድረግ ብቻ ነው፡፡“

መለስ እና የእርሱ ህወሀት ወሮበላ ቡድን ገና ከጫካ ከነበሩበት ጊዜ ጅምሮ ሁልጊዜ ሽብርን በመሳሪያነት ይጠቀሙ ነበር፡፡ እናም በአሁኑ ጊዜም የጸረ ሽብር ህግ እየተባለ የሚጠራ ቀያጅ ህግ በማውጣት እራሱ ሽብርተኝነትን በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ መለስ በንጹሀን ዜጎች ላይ ሊነገር የማይችል ጭካኔ እና ክልከላን በማድረግ ሰብአዊ መብትን ሲደፈጥጥ እና ክብርን ሲያዋርድ ቆይቷል፡፡ ምንም ዓይነት ክብር አልነበረውም፡፡ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ክፍል ውስጥ ውርደት እና ንቀትን የሚቸረው ሰው ነበር፡፡ መለስ እና የእርሱ ወሮበላ ግብረ አበሮች ሁልጊዜ እንዲፈሩ ይፈልጋሉ፡፡ እነርሱ ግን በህዝቡ ዘንድ ተፈሪነት የላቸውም፣ ይልቁንም በኢትዮጵያ ህዝብ ይጠሉ እና ይናቃሉ፡፡ ይኸ ነው እንግዲህ እውነታው!

መለስ እ.ኤ.አ በ2005 ያልታጠቁ ሰላማዊ አመጸኞችን በጥይት ተደብድበው እንዲያልቁ በሚያደርግበት ጊዜ ከአዲስ አበባ በ9 ሺ ማይል ርቀት ላይ የሚገኝ እና ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ምድር ላይ ያልነበረ የእርሱ የማይበገር እና ሰላማዊ ተቃዋሚ እንዲሁም እረፍትየለሽ ትችትን የሚያቀርብበት ከኢትዮጵያ ተገንጥሎ ያለ የአካዳሚ እና የህግ ባለሙያ ያለ አልመሰለውም ነበር፡፡ የመለስ እልቂቶች በህይወቴ አንድ ጥቁር ጠባሳ ጥለው ያለፉ እና የማልረሳቸው ሰቆቃዎች ሆነው ይኖራሉ፡፡ እኔ ኢትዮጵያን በለጅነቴ ጥዬ ስወጣ ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ ሃሳብ ፈፅሞ አልነበረኝም። መለስ አነዚያን ንፁሃንን ሲያስጨፈጭፍ ምንያህል ኢትዮጵያ ከኔ ልብ አንዳልወጣች ተገነዘብኩ።

አንደሚባለው አስቸጋሪ ሁኔታ በሚፈጠርበት ጊዜ እኛ እራሳችን ድርጊቱን እነወስነዋለን ወይም ደግሞ ድርጊቱ እራሱ እኛን ይወስናል፡፡ በእኔ ላይ ሁለቱም ነበሩ፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ለመሆን አልመረጥኩም ነበር፡፡ ሆኖም ግን መለስ ዜናዊ የእብሪት ትዕዛዝ በመስጠት ያልታጠቁ ንጹሀን ወገኖቻችንን በጥይት ባስፈጀበት ወቅት እራሱ መረጠኝ፡፡ መለስ ላስፈጃቸው ንጸሀን ዜጎች ምስክርነት ለመሆን አልመረጥኩም ነበር፡፡ ሆኖም ግን የመለስ የእልቂት ሰለባ የሆኑት ንጹሀን ዜጎች እራሳቸው ምስክር እንድሆናቸው መረጡኝ፡፡ ለዚህም ነው በእያንዳንዷ የሰኞ ዕለት አንዷንም ሳምንት ሳላስተጓጉል ለስምንት ዓመታት በሰማዕታቱ ጎን ቆሜ ምስክርነቴን ለዓለም የህሊና ፍርድ ቤት ማስረጃ ሳቀርብ የኖርኩት።

እ.ኤ.አ ከ2005 በፊት አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ ለእኔ ፍሬከርስኪ ዋጋቢስ ጨካኝ የአፍሪካ ሸፍጠኛ አምባገነን ነበር፡፡ የ2005ን የሞት እልቂት ካዘዘ በኋላ ግን በእኔ አዕምሮ ውስጥ የጭራቃዊነት፣ የአውሬነት ዋና ባለስልጣን ካቦ ሆነ፡፡ ጭራቃዊነትን መዋጋት አለብኝ ምክንያቱም ጭራቃዊነት አይሞትምና፡፡ ከሁሉም በላይ ጭራቃዊነትን መዋጋት አለብኝ ምክንያቱም በመጨረሻ ምንም ይሁን ምን መልካም ነገር በጭራቃዊነት ላይ ድል መቀዳጀቱ የማይቀር መሆኑ አጠራጣሪ አይደለምና፡፡

ለዚህም ነው ሁልጊዜ ህዳርን ማስታወስ ያለብኝ፡፡ የህዳርን፣ የታህሳስን፣ የመስከረምን፣ የጥቅምትን፣ ጭራቃዊነት ማስታወስ አለብኝ…

meles zenawiጭራቁ መለስ ዜናዊ እና የእኩይ ምግባሩ ተባባሪ የሆነው ህወሀት የሚባለው የማፊያ ቡድን በኢትዮጵያ ላይ የሰሩትን ግፍ እና ሰቆቃ ማስታወስ አለብኝ፡፡ ኢትዮጵያን ለመገንጠል እና ለመገነጣጠል ያደረጉትን እኩይ ምግባር እና ጭራቃዊ ሁነት ሁልጊዜ ማስታወስ አለብኝ፡፡ በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለመኖር ሲሉ ብቻ የኢትዮጵያን ህዝብ እንዴት አድርገው መከፋፈል እንደቀጠሉ ማስታወስ አለብኝ፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በረኃብ አለንጋ እየተገረፈ እና በድህነት አዘቅት ውስጥ እየማቀቀ ባለበት ሁኔታ እነዚህ ግፈኞች የሀገሪቱን ሀብት እየዘረፉ በውጭ ባንኮች የእራሳቸውን ሂሳብ እየከፈቱ በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የሚያጭቁበትን እኩይ ምግባር ማስታወስ አለብኝ፡፡

የመለስ ዜናዊ እና የህወሀት የአፈና እና ጭራቃዊ አገዛዝ የህያወት ሰለባ የሆኑትን ማስታወስ አለብኝ፡፡ ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና እና ዝና ያለውን እና ከዋናው ከተማ በስተደቡብ በኩል በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ወጣ ብሎ በሚገኘው በመለስ የማጎሪያ እስር ቤት ውስጥ ለብቻው ከሰው ተነጥሎ ታስሮ በመማቀቅ ላይ የሚገኘውን ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ወንድሜን እስክንድር ነጋን አስታውሳለሁ፡፡ ስለእርሱ የውሸት ፐሮጀክቶች እውነታውን በማፍረጥ ደፍራ በመጠየቋ እና በመጻፏ ምክንያት ብቻ በጨካኙ በመለስ ዜናዊ እስር ቤት ተወርውራ በመማቀቅ ላይ የምትገኘውን ወጣት እህቴን ርዕዮት ዓለሙን አስታውሳለሁ፡፡ ወንድሞቼን አንዷለም አራጌን፣ በቀለ ገርባን፣ አቡባከር አህመድን፣ ውብሸት ታዬን፣ ወጣቶቹን የዞን 9 ጦማሪያንን፣ ተመስገን ደሳለኝን እና ሌሎች በርካታዎቹን ሁሉ አስታውሳለሁ፡፡

ለምንድን ነው የማስታውሰው?

ማስታወስ ካልቻልኩ እነርሱን ሊያስታውስ የሚችል እዚያ ያለ ማን ነው? አስታውሳቸዋለሁ ምክንያቱም የምረሳቸው ከሆነ ተንሰራፍተው የቆዩት ወንጀሎች እና አረመኔ እና እብሪተኞቹ ወንጀለኞች ይረሳሉ፡፡ እኔ ከረሳኋቸው እንዴት አድርጎ ነው ታሪክ ሊያስታውሳቸው የሚችለው? ታሪክ ሊያስታውስ የሚችለው የሚያስታውስ ሰው ሲያገኝ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም ማስታወስ አለብኝ፡፡ የምስክርነት ቃሌን ሁልጊዜ ሰኞ እየሰጠሁ በህዳር፣ በታህሳስ እና በጥር… ውስጥ ማስታወስ አለብኝ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ላሉ ወጣቶች እና ወደፊትም በኢትዮጵያ ለሚወለዱ ልጆች ማስታወስ አለብኝ፡፡ የኤሊ ውሰልን አባባል በመዋስ “ያለፈው ጊዜ የወደፊት ህይወታቸው እንዲሆን አልፈልግም፡፡”

በህዳር ውስጥ ለእኔ ምንም ዓይነት ደስታ ነገር የለኝም፡፡ እውነት ነው ህዳር ጨካኝ ወር ነው፡፡ የቶማስ ሁድ የሀዘን እንጉርጉሮ እንዲህ ይገልጸዋል፡

ምንም ሙቀት የለም፣ ምንም ደስታ የለም፣ ምንም ጤናማ ህይወት የለም፣

ማንም አባል የሚሰማው ምቹ ሁኔታ የለም፣

ምንም ጥላ የለም፣ ምንም ብርሀን የለም፣ ቢራቢሮዎች የሉም፣ ንቦች የሉም፣

ፍራፍሬዎች የሉም፣ አበባዎች የሉም፣ ቅጠሎች የሉም፣ ወፎች የሉም፣

ህዳር!

በእራሴ ነጻ ስንኝ ደግሞ “የመለስ የእልቂት ሰለባ ለሆኑ ወገኖቻችን ፍትህ የለም“

መለስ ላሰፈጃቸው በመቶዎች ለሚቆጠሩ ወገኖቻችን ፍትህ የለም፣

ቁጥር ስፍር ለሌላቸው ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች ካሳ የለም፣

ከሞት ለተረፉት ወይም የጉዳት ሰለባ ለሆኑት ቤተሰቦች የሚሰጥ የጉዳት ከፍያ የለም፣

በህገወጥ መልክ ለእስር ለተዳረጉ በአስር ሺዎች ለሚሆኑ ዜጎች የፍርድ ማቅለያ ምህረት የለም፣

በህገወጥ አፈና የተሰወሩትን ዱካ የሚፈልግ የለም፣

በመስከረም፣ በጥቅምት እና በህዳር ለተፈጸሙት ወንጀሎች የተሰጠ ካሳ ወይም የተደረገ የኃጢአት ኑዛዜ የለም፣

የመለስ የህዳር እልቂትን አስመልክቶ የተጠየቀ ይቅርታ የለም፣

ህዳርን መድገም የለም፣

ህዳር መታወስ ያለበት ነው፡፡

እ.ኤ.አ የ2005 የወሮበላ ቡድኑ የእልቂት ሰለባ የሆኑትን ንጹሀን ዜጎች መርሳት በእነዚህ ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ዘግናኝ እልቂት እና እነዚያን ኋላቀር አውሬ ወንጀለኞች የሰሩትን ወንጀል ይቅርታ እንደማድረግ ያህል ነው፡፡ እልቂቶችን መርሳት ለወንጀለኞች ምንጊዜም ተጠያቂ እንደማይሆኑ እና ደረታቸውን ነፍተው እየገደሉ፣ እያሰቃዩ እና ሰብአዊ ክብርን እያዋረዱ እንዲኖሩ ዋስትና የመስጠት ያህል ነው ምክንያቱም ወንጀሎቹ ተረስተዋል የሚል ትረጉም ስለሚያሰጠው፡፡ በመጨረሻ መርሳት ማለት በስልጣን ወንበር ላይ ተፈናጠው ለሚገኙ ወንጀለኞች ደግመው እና ደጋግመው ወንጀል እንዲሰሩ የግብዣ ወረቀት በመስጠት እብሪተኞቹ ያለምንም የወንጀል ተጠያቂነት እንዲኖሩ እንዲያውም ቀደም ከነበረው እልቂት በበለጠ መልኩ እንዲፈጽሙ ማደፋፈር ማለት ነው፡፡

አስታውሳለሁ ምክንያቱም ልረሳ አልችልም እናም አልረሳም! በፍጹም!

የ2005ን የእልቂት ሰላበዎች አስታውሳለሁ፡፡ እያንዳንዱን/ዷን እና እያንዳንዳቸውን አስታውሳለሁ፡፡ ለእኔ ቁጥር አይደሉም ይልቁንም ከዚያ በላይ በአዕምሮዬ ጓዳ ውስጥ አሉ፡፡ አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ እና የእርሱ የህወሀት ወሮበላ ቡድን የእነርሱን የግፍ ሰለባ የሆኑ ንጹሀን ዜጎች ስምየለሾች፣ መልከየለሾች፣ ሰውነት አልባዎች፣ ጓደኛ የለሾች እና ቤተሰብ የለሾች እንዲሁም ወገን አልባዎች ሊያደርጓቸው ይፈልጋሉ፡፡ መለስ የእልቂት ሰለባ እና አካለ ስንኩል ሽባ ያደረገው እያንዳንዱ/ዷ ዜጋ ለእኔ ልዩ ነው/ናት፡፡ እናት ለመሆን እንዳይችሉ የተደረጉትን ወጣት ሴቶች የተገደሉትን አስታውሳለሁ፡፡ አባት እንዳይሆኑ የተደረጉትን ወጣት ወንዶች የተገደሉትን አስታውሳለሁ፡፡ ወላጆቻቸው የእልቂት ሰለባ እንዲሆኑ የተደረጉባቸውን ወላጅ ያጡ ህጻናትየተገደሉትን አስታውሳለሁ፡፡ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ልጆቻቸውን ማየት ላልቻሉ አባቶች እና እናቶች እንዲሁም የልጅ ልጆቻቸውን ለማየት ያልቻሉትን አስታውሳለሁ ምክንያቱም ሁሉንም መለስ እንዲያልቁ እና እንዲፈጁ አደርጎባቸዋልና፡፡

እነዚህን ጭራቅ ወሮበላ ወንጀለኞች አልረሳቸውም፡፡ በወገኖቻችን ላይ ጭፍጨፋውን ሲያካሂዱ የነበሩ 237 የድሁር አስተሳሰብ ባለቤት የሆኑትን ነፍሰ ገዳይ ቅጥረኛ ፖሊስ ተብዮዎች፣ እንዲሁም ዋነኛ የወንጀሉ አቀናባባሪ መሀንዲሶች እና አውራ ወንጀለኞች አንድ በአንድ በስም አስታውሳቸዋለሁ፡፡ ምንጊዜም ቢሆን በህዳር ውስጥ አስታውሳለሁ፣ እንዲሁም በታህሳስ እና በጥርም፣ እንደዚሁም ደግሞ በየካቲት እና በሚያዚያም…

አስታውሳለሁ

ሬቡና እርገጤ፣ የ34 ዓመት እድሜ እና ግንበኛ፣ መልሳቸው አለምነው፣ የ16 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ ሀድራ ኡስማን፣ የ22 ዓመት እድሜ እና ስራዋ የማይታወቅ፣ ጃፋር ኢብራሂም የ28 ዓመት እድሜ እና የንግድ ባለሙያ፣ መኮንን፣ የ17 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ወልደሰማያት፣ የ27 ዓመት አድሜ እና ስራ የሌለው፣ ባህሩ ደምለው፣ እድሜው እና ስራው የማይታወቅ፣ ፈቃደ ነጋሽ፣ የ25 ዓመት እድሜ እና መካኒክ፣ አብረሀም ይልማ የ17 ዓመት እድሜ እና የታክሲ ሾፌር፣ ያሬድ እሸቴ የ23 ዓመት እድሜ እና የንግድ ባለሙያ፣ ከበደ ገብረ ህይወት፣ የ17 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ ማቴዎስ ፍልፍሉ የ14 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ ጌትነት ወዳጆ፣ የ48 ዓመት እድሜ እና የንግድ ባለሙያ፣ እንዳልካቸው ሁንዴ፣ የ18 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ቃሲም ረሺድ፣ የ21 ዓመት እድሜ እና መካኒክ፣ ኢማም ሸውሞሊ፣ የ22 ዓመት እድሜ እና የንግድ ባለሙያ፣ አልዬ ኢሳ፣ የ20 ዓመት እድሜ እና የቀን ሰራተኛ፣ ሳምሶን ያዕቆብ፣ የ23 ዓመት እድሜ እና የህዝብ ማመላለሻ ሰራተኛ፣ አለበለው አበበ፣ የ18 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ በልዩ ቢ. የ18 ዓመት እድሜ እና የትራንስፖርት ረዳት፣ ዩሱፍ ጀማል፣ የ23 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ አብረሀም አገኘሁ፣ የ23 ዓመት እድሜ እና የትራንሰፖርት ረዳት፣ መሀመድ በቃ፣ የ45 ዓመት እድሜ እና አርሶ አደር፣ ረደላ አወል፣ የ19 ዓመት እድሜ እና የታክሲ ሾፌር፣ ሀብታሙ ኡርጋ፣ የ30 ዓመት እድሜ እና የንግድ ባለሙያ፣ ዳዊት ጸጋዬ፣ የ19 ዓመት እድሜ እና መካኒክ፣ ገዛኸኝ ገረመው፣ የ15 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ ዮናስ አበራ፣ የ24 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ግርማ ወልዴ፣ የ38 ዓመት እድሜ እና ሾፌር፣ ወ/ሮ ደስታ ብሩ፣ የ37 ዓመት እድሜ እና የንግድ ባለሙያ፣ ለገሰ ፈይሳ፣ የ60 ዓመት አዛውንት እና ግንበኛ፣ ተስፋዬ ቡሽራ፣ የ19 ዓመት እድሜ እና ጫማ ሰፊ፣ ቢኒያም ደገፋ፣ የ18 ዓመት እድሜ እና ስራ የሌለው፣ ሚሊዮን ሮቢ፣ የ32 ዓመት እድሜ እና የትራንስፖርት ረዳት፣ ደረጀ ደኔ፣ የ24 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ ነብዩ ኃይሌ፣ የ16 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ ምትኩ ዋለንዳ፣ የ24 ዓመት እድሜ እና የአገልግሎት ሰራተኛ፣ አንዋር ሱሩር፣ የ22 ዓመት እድሜ እና የንግድ ባለሙያ፣ ንጉሴ ዋበኝ፣ የ36 ዓመት እድሜ እና የአገልግሎት ሰራተኛ፣ ዙልፋ ሀሰን፣ የ50 ዓመት እድሜ እና የቤት እመቤት፣ ዋስሁን ከበደ፣ የ16 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ ኤርሚያስ ከተማ፣ የ20 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ መለያ ቁጥሩ 00428 የሆነ፣ የ25 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ መለያ ቁጥሩ 00429 የሆነ፣ የ26 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ መለያ ቁጥሩ 00430 የሆነ፣ የ30 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ አዲሱ በላቸው፣ የ25 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ደመቀ አበበ፣ እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ መለያ ቁጥሩ 00432 የሆነ፣ የ22 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ መለያ ቁጥሩ 0045 የሆነ፣ የ20 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ መለያ ቁጥሩ 13903 የሆነ፣ የ25 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ መለያ ቁጥሩ 00435 የሆነ የ30 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ መለያ ቁጥሩ 13906 የሆነ፣ የ25 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ተማም ሙክታር፣ የ25 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ በየነ በዛ፣ የ25 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ወሰን አሰፋ፣ የ25 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ አበበ አንተነህ፣ የ30 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ፈቃዱ ኃይሌ፣ የ25 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ኤሊያስ ጎልቴ፣ እድሜው እና ስራው የማይታው፣ ብርሀኑ ወርካ፣ እድሜው እና ስራው የማይታወቅ፣

አስታውሳለሁ

አሸብር መኩሪያ እድሜው እና ስራው የማይታወቅ፣ ዳዊት ሰማ፣ እድሜው እና ስራው የማይታወቅ፣ መርሀጽድቅ ሲራክ፣ 22 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ በለጠ ጋሻው ጠና፣ እድሜው እና ስራው የማይታወቅ፣ በሀይሉ ተስፋዬ፣ የ20 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ መለያ ቁጥሩ 21760 የሆነ፣ የ18 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ መለያ ቁጥሩ 21523 የሆነ፣ የ25 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ መለያ ቁጥሩ 11657 የሆነ፣ የ24 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ መለያ ቁጥሩ 21520 የሆነ፣ የ25 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ መለያ ቁጥሩ 21781 የሆነ፣ እድሜው እና ስራው የማይታወቅ፣ ጌታቸው አዘዘ፣ የ45 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ መለያ ቁጥሩ 21762 የሆነ፣ የ75 ዓመት አዛውንት እና ስራቸው የማይታወቅ፣ መለያ ቁጥሩ 11662 የሆነ የ45 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ መለያ ቁጥሩ 21763 የሆነ፣ የ25 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ መለያ ቁጥሩ 13087 የሆነ የ30 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ መለያ ቁጥሩ 21574 የሆነ የ25 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ መለያ ቁጥሩ 21761 የሆነ፣ እድሜው እና ስራው የማይታወቅ፣ መለያ ቁጥሩ 21569 የሆነ፣ የ25 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ መለያ ቁጥሩ13088 የሆነ፣ የ30 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ እንዳልካቸው ገብርኤል፣ የ27 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣

አስታውሳለሁ

ኃይለማርያም አምባዬ፣ የ20 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ መብራቱ ዘውዱ፣ የ27 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ስንታየሁ በየነ፣ የ14 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ታምሩ ኃይለሚካኤል፣ እድሜው እና ስራው የማይታወቅ፣ አድማሱ አበበ፣ የ45 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ እቴነሽ ይማም፣ የ50 ዓመት እድሜ እና ስራዋ የማይታወቅ፣ ወርቄ አበበ፣ የ19 ዓመት እድሜ እና ስራዋ የማይታወቅ፣ ፈቃዱ ደግፌ፣ የ27 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ሸምሱ ካሊድ፣ የ25 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ አብዱዋሂብ አህመዲን፣ የ30 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ተክሌ ደበሌ፣ የ20 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ታደሰ ፈይሳ፣ የ38 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ሰለሞን ተስፋዬ፣ የ25 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ቅጣው ወርቁ፣ የ25 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ እንዳልካቸው ወርቁ፣ የ25 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ደስታ ነጋሽ፣ የ30 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ይለፍ ነጋ፣ የ15 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ዮሃንስ ኃይሌ፣ የ20 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ በኃይሉ ብርሀኑ፣ የ30 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ሙሉ ሶሬሳ፣ የ50 ዓመት እድሜ እና የቤት እመቤት፣ ቴዎድሮስ ግደይ ኃይሉ፣ የ23 ዓመት እድሜ እና ጫማ ሻጭ፣ ደጀኔ ይልማ፣ የ18 ዓመት እድሜ እና  የመጋዘን ሰራተኛ፣ ኡጋሁን ወልደገብርኤል፣ የ18 ዓመት ተማሪ፣ ደረጀ ማሞ ሀሰን፣ የ27 ዓመት እድሜ እና አናጺ፣ 

አስታውሳለሁ

ረጋሳ ፈይሳ፣ የ55 ዓመት እድሜ እና የልብስ ንጽኅና መስጫ ሰራተኛ፣ ቴዎድሮስ ገብረዎልድ የ28 ዓመት እድሜ እና የግል ንግድ፣ መኮንን ገብረእግዚአብሄር፣ የ20 ዓመት እድሜ እና መካኒክ፣ አሊያስ ግብረጊዮርጊስ፣ የ23 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ አብርሀም መኮንን፣ የ21 ዓመት እድሜ እና የቀን ሰራተኛ፣ ጥሩወርቅ ገብረጻድቅ፣ የ41 ዓመት እድሜ እና የቤት እመቤት፣ ሄኖክ መኮንን፣ የ28 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ጌቱ መረሳ፣ የ24 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ወ/ሮ ክብነሽ መኬ ታደሰ፣ የ52 ዓመት እድሜ እና ስራዋ የማይታወቅ፣ መሳይ ስጦታው፣ የ29 ዓመት አድሜ እና የግል ንግድ፣ ሙሉዓለም ወይሳ፣ የ15 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ አያልሰው ማሞ፣ የ23 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ስንታዬሁ መለሰ፣ የ24 ዓመት እድሜ እና የቀን ሰራተኛ፣ ወ/ሮ ጸዳለ ቢራ፣ የ50 ዓመት እድሜ እና የቤት እመቤት፣ አባይነህ ሳራ ሰዴ፣ የ35 ዓመት እድሜ እና ልብስ ሰፊ፣ ፍቅረማሬም ተሊላ፣ የ18 ዓመት እድሜ እና ሾፌር፣ አለማየሁ ገርባ፣ የ26 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ጆርጅ አበበ፣ የ36 ዓመት እድሜ እና የግል ማመላለሻ፣ ሀብታሙ ዘገዬ ቶላ፣የ16 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ ምትኩ ገብረስላሴ፣ የ24 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ ትዕዛዙ መኩሪያ፣ የ24 ዓመት እድሜ እና የግል ንግድ፣ ፍቃዱ ዳልጌ፣ የ36 ዓመት እና ልብስ ሰፊ፣ ሸዋጋ ወልደጊዮርጊስ፣ የ38 ዓመት እድሜ እና የቀን ሰራተኛ፣ አለማየሁ ዘውዴ፣ የ32 ዓመት እድሜ እና የጨርቃጨርቅ ሰራተኛ፣ ዘላለም ገብረጻዲቅ፣ የ31 ዓመት እድሜ እና የታክሲ ሾፌር፣ መቆያ ታደሰ፣ የ19 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ ኃይልዬ ሁሴን፣ የ19 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ ወ/ሮ ፍስኃ ግብረጻዲቅ፣ የ23 ዓመት እድሜ እና የፖሊስ ተቀጣሪ፣ ወጋየሁ አርጋው፣ የ36 ዓመት እድሜ እና ስራ የሌለው፣

አስታውሳለሁ

መላኩ ከበደ የ19 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ አባይነህ ኦራ፣ የ25 ዓመት እድሜ እና ልብስ ሰፊ፣ ወ/ሮ አበበች ሆለቱ፣ የ50 ዓመት እድሜ እና የቤት እመቤት፣ ደመቀ ጀንበሬ፣ የ30 ዓመት እድሜ እና አርሶ አደር፣ ክንዴ ወረሱ፣ የ22 ዓመት እድሜ እና ስራ የሌለው፣ እንዳለ ገብረመድህን፣ የ23 ዓመት እድሜ እና የግል ንግድ፣ አለማየሁ ወልዴ፣ የ24 ዓመት እድሜ እና መምህር፣ ብስራት ደምሴ፣ የ24 ዓመት እድሜ እና መኪና አስመጭ፣ መስፍን ኃይለጊዮርጊስ፣ የ23 ዓመት እድሜ እና የግል ንግድ፣ ወሊዮ ዳሪ፣ የ18 ዓመት እድሜ እና የግል ንግድ፣ በኃይሉ ገብረመድህን፣ የ20 ዓመት እድሜ እና የግል ንግድ፣ ሲራጅ ኑርሰይድ፣ የ18 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ እዮብ ገብረመድህን፣ የ25 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ ዳንኤል ሜሉጌታ፣ የ25 ዓመት እድሜ እና የቀን ሰራተኛ፣ ቴዎድሮስ ደገፋ፣ የ25 ዓመት እድሜ እና በጫማ ፋብሪካ ውስጥ የሚሰራ ሰራተኛ፣ ጋሻው ሙሉጌታ፣ የ24 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ ከበደ ኦርኬ የ22 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ ሌችሳ ፋታሳ፣ የ21 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ ጀጋማ በሻ፣ የ20 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ ደበላ ጉታ፣ የ15 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ መላኩ ፈይሳ፣ የ16 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ ወ/ሮ እልፍነሽ ተክሌ፣ የ45 ዓመት እድሜ እና ስራዋ የማይታወቅ፣ ሀሰን ዱላ፣ የ64 ዓመት እድሜ እና ስራቸው የማይታወቅ፣ ሁሴን ሀሰን ዱላ፣ የ25 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ደጀኔ ደምሴ፣ የ15 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ሌላ ስሙ የማይታወቅ፣ አሁንም ሌላ ስሙ የማይታወቅ፣ አሁንም ሌላ ስሙ የማይታወቅ፣ ዘመድኩን አግደው፣ የ18 ዓመት እድሜ እና ስራው የማያታወቅ፣ ጌታቸው ተረፈ፣ የ16 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ደለለኝ አለሙ፣ የ20 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ዩሱፍ ኡመር፣ የ20 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ

አስታውሳለሁ

መኩሪያ ተበጀ የ22 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ባደመ ተሻማሁ፣ የ20 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ አምባው ጌታሁን፣ የ38 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ተሾመ ኪዳኔ፣ የ65 ዓመት እድሜ እና የጤና ሰራተኛ፣ ዮሴፍ ረጋሳ፣ እድሜው እና ስራው የማይታወቅ፣ አብዩ ንጉሴ፣ እድሜው እና ስራው የማይታወቅ፣ ታደለ በሀጋ እድሜው እና ስራው የማይታወቅ፣ ኤፍሬም ሻፊ እድሜው እና ስራው የማይታወቅ፣ አበበ ሀማ፣ እድሜው እና ስራው የማይታወቅ፣ ገብሬ ሞላ፣ እድሜው እና ስራው የማይታወቅ፣ ሰይዲን ኑሩዲን፣ እድሜው እና ስራው የማይታወቅ፣ እነዬው ጸጋዬ፣ የ32 ዓመት እድሜ እና የህዝብ ማመላለሻ ረዳት፣ አብዱራህማን ፈረጅ፣ የ32 ዓመት እድሜ እና የእንጨት ስራ ሰራተኛ፣ አምባው ብጡል፣ የ60 ዓመት እድሜ አዛውንት እና በቆዳ ፋብሪካ ውስጥ የሚሰራ ሰራተኛ፣ አብዱልመናን ሁሴን፣ የ28 ዓመት እድሜ እና የግል ንግድ፣ ጅግሳ ሰጠኝ፣ የ18 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ አሰፋ ነጋሳ፣ የ33 ዓመት እድሜ እና አናጺ፣ ከተማ ኡንኮ፣ የ23 ዓመት እድሜ እና ልብስ ሰፊ፣ ክብረት እልፍነህ፣ የ48 ዓመት እድሜ እና የግል የጥበቃ አባል፣ እዮብ ዘመደኩን፣ የ24 ዓመት እድሜ እና የግል ንግድ፣ ተስፋዬ መንገሻ፣ የ15 ዓመት እድሜ እና የግል ንግድ፣ ካፒቴን ደበሳ ቶሎሳ፣ የ58 ዓመት እድሜ እና የግል ንግድ፣ ትንሳኤ ዘገዬ፣ የ14 ዓመት እድሜ እና ልበስ ሰፊ፣ ኪዳና ሽኩሮው፣ የ25 ዓመት እድሜ እና የቀን ሰራተኛ፣  አንዷለም ሺ በለው፣ የ16 ዓመት እድሜ እና ተማሪ፣ አዲሱ ተስፋሁን፣ የ19 ዓመት እድሜ እና የግል ንግድ፣ ከሳ በየነ፣ የ28 ዓመት እድሜ እና ልብስ ሻጭ፣ ይታገሱ ሲሳይ፣ የ22 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፣ ሌላ ስሙ የማይታወቅ የ22 ዓመት እድሜ እና ስራው የማይታወቅ፡፡

አስታውሳለሁ

የፖሊስ እና የደህንነት ኃላፊዎች የእርስ በእርስ በተደረገ የመሳሪያ ተኩስ የተገደሉ የሚከተሉት ናቸው፡ ነጋ ገብሬ፣ ጀበና ደሳለኝ፣ ሙሊታ ኢርቆ፣ ዮሀንስ ሰለሞን፣ አሸናፊ ደሳለኝ እና ፈይሳ ገብረመንፈስ ናቸው፡፡ 

.. ኖቬምበር 2/2005 በቃሊቲ እስር ቤት ግቢ በእስር ቤቶቻቸው ውስጥ እያሉበጥይትተደብድበው እንዲያልቁ የተደረጉ እስረኞች ስም ዝርዝር፣

አስታውሳለሁ

ጠይብ ሸምሱ መሀመድ፣ እድሜው አይታወቅም፣ ጾታ ወንድ፣ የጦር መሳሪያ ደብቀሀል ተብሎ ክስ የተመሰረተበት፣ ሳሊ ከበደ፣ እድሜው አይታወቅም፣ ጾታ ወንድ፣ ምንም ዓይነት የተመሰረተበት ክስ የለም፡፡ ሰፊው እንድሪስ ታፈሰ ወረደ፣ እድሜው አይታወቅም፣ ጾታው ወንድ፣ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሰ፣ ዘገዬ ተንኮሉ በላይ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ በዘረፋ ወንጀል የተከሰሰ፣ ቢያድግልኝ ታመነ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ የክሱ ምክንያት ያልታወቀ፣ ገብሬ መስፍን ዳኘ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ ስራው የማይታወቅ፣ በቀለ አብርሀም ታዬ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ ሁከት በመፍጠር ወንጀል የተከሰሰ፣ አበሻ ጉታ ሞላ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ የክሱ ምክንያት የማይታወቅ፣ ኩርፋ መልካ ተሊላ፣ በማስፈራራት ወንጀል የተከሰሰ፣ በጋሻው ተረፈ ጉደታ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ ሰላም በማደፍረስ የተከሰሰ፣  በዱልወሀብ አህመዲን፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ በዘረፋ ወንጀል የተከሰሰ፣ ተስፋዬ አብይ ሙሉጌታ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ የጦር መሳሪያ ደብቀሀል ተብሎ የተከሰሰ፣ አዳነ ቢረዳ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ በነፍስ ግድያ ወንጀል የተከሰሰ፣ ይርዳው ከርስማ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ የክሱ ምክንያት ያልተገለጸ፣

አስታውሳለሁ

ባልቻ ዓለሙ ረጋሳ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ በዘረፋ ወንጀል የተከሰሰ፣ አቡሽ በለው ወዳጆ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ የክሱ ምክንያት ያልተገለጸ፣ ዋለልኝ ታምር በላይ፣ እድሜው ያልታወቀ፣ ጾታ ወንድ፣ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሰ፣ ቸርነት ኃይሌ ቶላ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ በዘረፋ ወንጀል የተከሰሰ፣ ተማም ሸምሱ ጎሌ፣  እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ የክሱ ምክንያት ያልታወቀ፣ ገበየሁ በቀለ አለነ፣ አድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ የክሱ ምክንያት ያልታወቀ፣ ዳንኤል ታዬ ልኩ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ የክሱ ምክንያት የማይታወቅ፣ መሀመድ ቱጂ ቀኔ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ የክሱ ምክንያት ያልተገለጸ፣ አብዱ ነጅብ ኑር፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ የክሱ ምክንያት ያልተገለጸ፣ የማታው ሰርቤሎ፣ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሰ፣ ፍቅሩ ናትናኤል ሰውነህ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ በማስፈራራት ወንጀል የተከሰሰ፣ ሙኒር ከሊል አደም እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ሁከት በመፍጠር የተከሰሰ፣ ኃይማኖት በድሉ ተሾመ፣ አድሜው የማይታወቅ፣ ህግ በመጣስ ወንጀል የተከሰሰ፣ ተስፋዬ ክብሮም ተክኔ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ በዘረፋ ወንጀል የተከሰሰ፣ ወርቅነህ ተፈራ ሁንዴ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ የክሱ ወንጀል ያልተገለጸ፣

አስታውሳለሁ

ሲሳ ምትኩ ሁነኝ፣ በማጭበርበር ወንጀል የተከሰሰ፣ ሙሉነህ ዓይንዓለም ማሞ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ የክሱ ምክንያት ያልተገለጸ፣ ታደሰ ሩፌ የኔነህ፣ በማስፈራራት ወንጀል የተከሰሰ፣ አንተነህ በየቻ ቀበታ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ የጦር መሳሪያ ደብቀሀል በሚል ወንጀል የተከሰሰ፣ ዘሪሁን መረሳ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ በንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ ወንጀል የተከሰሰ፣ ወጋዬሁ ዘሪሁን አርጋው፣ በዘረፋ ወንጀል የተከሰሰ፣ በከልካይ ታምሩ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ የክሱ ምክንያት ያልተገለጸ፣ የራስወርቅ አንተነህ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ በማጭበርበር ወንጀል የተከሰሰ፣ ባዝዘው ብርሀኑ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ በግብረሰዶማዊነት የድርጊት ወንጀል የተከሰሰ፣ ሰለሞን እዮብ ጉታ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሰ፣ አሳዩ ምትኩ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ በማስፈራራት ወንጀል የተከሰሰ፣ ጋሜ ኃይሉ ዘገዬ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ሁከት በመፍጠር እና ጸጥታ በማደፍረስ የተከሰሰ፣ ማሩ እናውጋው ድንበሬ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሰ፣ እጅጉ ምናለ፣ አድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ በግድያ ሙከራ የተከሰሰ፣ ኃይሉ ቦስኔ ሀቢብ፣ አድሜው የማይታወቅ፣ ለወንጀለኛ መጠለያ በመስጠት ወንጀል የተከሰሰ፣ ጥላሁን መሰረት፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ የክሱ ምክንያት ያልተገለጸ፣ ንጉሴ በላይነህ እድሜው ያልታወቀ፣ በዘረፋ ወንጀል የተከሰሰ፣ አሸናፊ አበባው፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ የክሱ ምክንያት ያልተገለጸ፣ ፈለቀ ድንቄ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ የክሱ ምክንያት ያልተገለጸ፣ ጀንበሬ ድንቅነህ ቢለው፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ ጸጥታ በማደፍረስ ወንጀል የተከሰሰ፣ ቶሎሳ ወርቁ፣ አድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ በዘረፋ ወንጀል የተከሰሰ፣ መካሻ በላይነህ ታምሩ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ ሁከት በመፍጠር ወንጀል የተከሰሰ፣ ይፍሩ አደራው፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ የክሱ ምክንያት ያልተገለጸ፣ ፋንታሁን ዳኘ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ የክሱ ምክንያት ያልተገለጸ፣ ጥበበ ዋከኔ ቱፋ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ ሰለሞን ገብረ አምላክ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ ሁከት በመፍጠር ወንጀል የተከሰሰ፣ ባንጃው ቹቹ ካሳሁን፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ በዘረፋ ወንጀል የተከሰሰ፣ ደመቀ አበጀ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ እድሜ 58፣ የመግደል ሙከራ በማድረግ ወንጀል የተከሰሰ፣ እንዳለ እውነቱ መንግስቴ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ የክሱ ምክንያት ያልተገለጸ፣ አለማየሁ ገርባ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ እ.ኤ.አ በ2004 የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ካደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የታሰረ፣ መርኮታ ኢዶሳ፣ እድሜው የማይታወቅ፣ ጾታ ወንድ፣ የክሱ ምክንያት ያልተገለጸ፣

ለታሪክ ምዘገባ፡ በእነዚህ ከላይ በተዘረዘሩት የግድያ እልቂቶች ሙሉ በሙሉ እና በቀጥታ የተሳተፉ እጃቸው በደም የተጨማለቀ ቢያንስ 237 ስማቸው እና ማንነታቸው በውል የተረጋገጠ የፖሊስ እና የደህንነት ኃላፊዎች ስምዝርዘር አለ፡፡

የኔሰው ገብሬን አስታውሳለሁ፡፡

yenesew gebre

እ.ኤ.አ በ11/11/11 የኔሰው ገብሬ የሚባል የ29 ዓመት እድሜ የነበረው ኢትዮጵያዊ የትምህርት ቤት መምህር እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች በደቡብ ኢትዮጵያ ዳውሮ ዞን በተርጫ ከተማ ከህዝብ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ወጣ ብሎ በሚገኝ በአንድ ቦታ ላይ በእራሱ ላይ እሳት በመለኮስ እራሱን አቃጠለ፡፡ ለሶስት ቀናት ቁስለኛ ሆኖ ከቆዬ በኋላ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡ በእራሱ ላይ ያንን የመሰለ አሰቃቂ እርምጃ ከመውሰዱ በፊት የኔሰው ከመሰብሰቢያ አዳራሹ ውጭ ተሰብስቦ ለነበረው የአካባቢው ህዝብ እንዲህ የሚል ንግግር አድርጎ ነበር፣ “ፍትህ እና ፍትሀዊ አስተዳደር በሌለባት ሀገር፣ ሰብአዊ መብቶች በሚደፈጠጡባት እና በማይከበሩባት ሀገር እራሴን መስዋዕት በማድረግ እነዚህን ወጣቶች ነጻ አወጣለሁ፡፡“

  2005 ምርጫ ሁከትን ተከትሎ ያለቁ ሰላማዊ ዜጎች    

ህወሀት እና አመራሮቹ በስልጣን እርካብ ላይ ተቆናጥጠው ለመቆየት ሲሉ እልቂት ከማድረስ፣ ከመምታት እና ከማቃጠል ወደኋላ እንደማይሉ ለጥያቄ የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም፡፡ እ.ኤ.አ በ2015 ይካሄዳል እየተባለ የሚደሰኮርለትን ምርጫ ተብዮ ቢያንስ 99.6 በመቶ እንደሚያሸንፉ አስቀድመው ያውቃሉ፣ ሆኖም ግን በፍርሀት እና በጭንቀት ውስጥ ተዘፍቀው በመራድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ነጻ ጋዜጠኞችን ሰላማዊ አመጸኞችን ያስራሉ፣ የነጻው ፕሬስ ጋዜጦችን በሙሉ ዘግተዋል፡፡ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን ያስራሉ፡፡ ለምንድን ነው እንደዚህ በፍርሀት እየራዱ በነጭ ላብ ተዘፍቀው የሚገኙት?

እነዚህ ግፈኞች ይፈራሉ ምክንያቱም ከኢትዮጵያ ህዝብ ምንም ዓይነት ድጋፍ እንደሌላቸው ያውቃሉ፡፡ የያዙት ስልጣን መሰረት የሌለው እና ትንሽ የሚገዳደር ነገር ቢያጋጥመው እንደ እንቧይ ካብ በቀላሉ እንደሚፈራርስ ያውቃሉ፡፡ በአንድ ወቅት ህዝቡ ፊቱን እንደሚያዞርባቸው እና ከስልጣናቸው ላይ እንደ መጥፎ አረም እየነቀለ እንደሚጥላቸው ያውቃሉ፡፡ በስልጣናቸው ላይ እንደመዥገር ተጣብቀው ለመቆየት ብቸኛው አማራጭ አደገኛ የሽብር ሁኔታዎችን በመፍጠር የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን (ተቃዋሚ ፓርቲዎችን እና ሰላማዊ አመጸኞችን) ማጥፋት፣ በመንግስት ላይ የሚደረግን ትችት (ነጻውን ፕሬስ) መዝጋት እና ነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫ እንዳይካሄድ ማድረግ እንደሆነ ጽኑ እምነት አላቸው፡፡ በፍርሀት፣ በሽብርተኝነት ተዘፍቀው እና ኃይልን እንደብቸኛ አማራጭ በመጠቀም መግዛት ይፈልጋሉ፡፡ ህወሀት አሁንም በስልጣን ላይ ተጣብቆ ለመቆየት እልቂትን መፈጸም፣ መምታት እና ማቃጠልን እንደተለመደው እንደ ስልት ሊጠቀም ይችላልን? የለመደች ጦጣ ሁልጊዜ ሽምጠጣ አይደል ነገሩ! ሲኦል ውስጥ የሚያስገባ እና አጠራጣሪ ጉዳይ ነው! እ.ኤ.አ በ2005 በመቶዎች የሚቆጠር እና ያን ይህል ብዛት ያለው ህዝብ ሲገድሉ እና በሺዎች የሚቆጠሩትን ደግሞ ሲቆስሉ እና ወደ እስር ቤትም በመውሰድ ሲያጉሩ ምንም ዓይነት መጥፎ ነገር ያልገጠማቸው ስለነበር አሁን በ2015 ይደረጋል እየተባለ የሚደሰኮርለትን የይስሙላ ምርጫ በማስታከክ ደግሞ ያንን ሰይጣናዊ ልምዳቸውን ከፍ ወዳለ ደረጃ በማድረስ በሺዎች የሚቆጠሩትን ሊገድሉ፣ ሊያቆስሉ፣ ሊያስሩ እና ሊያሰቃዩ ይችላሉ፡፡ እንደዚህ ያለውን ነገር ነው እንግዲህ ወሮበሎች እና ዘራፊዎች ደጋግመው የሚሰሩ!november (1)

እ.ኤ.አ በ2005 የተፈጸሙት ጭራቃዊ ወንጀሎች በ2015 እንዳይደገሙ ከፈለግን በአንድነት ተነስተን በአንድ ላይ ቆመን ለኢትዮጵያውያን/ት ወንድሞች እና እህቶች መብት መከበር መታገል አለብን፡፡ በዲያስፖራ የሚገኘው እና የምትገኘው እያንዳንዱ/ዷ እና ማንኛውም/ዋም ኢትዮጵያዊ/ት የወያኔን የሸፍጥ ወንጀሎች ለማምከን በአንድ ላይ መቆም፣ በአንድነት መናገር፣ ፈትለፊት መጋጠም፣ መደጋገፍ፣ መተባበር፣ በአንድ ላይ መናገር መቻል አለባቸው፡፡  

አጠቃላይ የመርሳት ችግራችንን እናስወግድ፣ የመለስን የእልቂት ሰለባዎች እናስታውስ 

የእልቂቱን ሰለባዎች እንደማልረሳ፣ የእልቂቱ ፈጻሚዎችን እና ቅጥር ነፍሰ ገዳዮችን እንደማልረሳ እያደረግሁት ላለው ጥረት ወደ ትግሉ ተቀላቀሉ፡፡ በትግሌ ውስጥ ለድል እንደምንበቃ አንድ ሺህ አንድ ያህል ምክንያቶችን በመደርደር ተስፋዎቼን ሰንቂያለሁ፡፡ ምክንያቱም አስታውሳለሁ፡፡ ተስፋቢስ አልሆንም:: ምክንያቱም አስታውሳለሁ፡፡ ተስፋቢሰነትን ለማስወገድ የሞራል ግዴታ አለብኝ፡፡ ከተስፋ ማጣት በኋላ ተስፋን ማለምለም ይቻላል”፡፡ ኤሊ ዊሰል 

የመለስ ዜናዊን የህዳርን እና የታህሳስን እንዲሁም . እናስታውስ!

======================

በመለስ እልቂቶች ላይ ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ የሰብአዊ መብት ተሟጋች የነበረው ያሬድ ኃይለማርያም ለአውሮፓ ህብረት ድንገተኛ የጋራ ጉባኤ የልማት እና የውጭ ጉዳይ እና የሰብአዊ መብት ንኡስ ኮሚቴ የፓርላማ አባላት ፊት በግንባር ቀርቦ “በኢትዮጵያ በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል፡ የሰኔ እና የህዳር 2005 የአዲስ አበባ ህዝብ እልቂት/CRIMES AGAINST HUMANITY IN ETHIOPIA: THE ADDIS ABABA MASSACRES OF JUNE AND NOVEMBER 2005“ በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ ሜይ 15/2006 የሰጠውን ምስክርነት መመልከት ይቻላል፡፡

**አጣሪ ኪሚሽኑ የእልቂቱ ሰለባ የሆኑትን ዜጎች ሙሉ በሙሉ ነጻ በማውጣት ወንጀሉን ሙሉበሙሉበፖሊስ እና በምልምል የፖሊስ ኃይሎች ላይ ደፍድፎታል፡፡ ኮሚሽኑ እንዲህ የሚልመደምደሚያ ሰጥቷል፣በሰላማዊ አመኞች የተፈጸመ የንብረት ውድመት የለም፣  ጥቂት አመጸኞችጠብመንጃ እና ቦምብ የታተቁነበሩ በማለት በመንግስት ቀጥጥር ስር ባሉት መገናኛ ብዙሀንእንደተዘገበው ሳይሆን አንድም ጠብመንጃያነገተ ወይም ደግሞ የእጅ ቦምብ የያዘ ሰላማዊ አመጸኛአልነበረም፡፡ በመንግስት ታጣቂ ኃይሎች ሲደረጉየነበሩት የጥይት ተኩሶች የሰላማዊ አመጸኞችንስብስብ በመበተን ዓላማ ላይ ያነጣጠሩ አልነበሩም፡፡ ሆኖምግን የሰላማዊ አመጸኞችን ጭንቅላትእና ደረቶች እያነጣጠሩ በመበርቀስ ህይወት አልባ ማድረግ ነበር“  

የኮሚሽኑ 193 የእልቂት ሰለባዎች ስም ዝርዝር .. ከሰኔ 6 እስከ 8 እና ከህዳር 1 እስከ4/2005ኮሚሽኑ በእነዚህ ውሱን በሆኑ ቀናት ብቻ እንዲያጣራ በታዘዘው መሰረት አጣርቶያቀረባቸው የተገደሉንጹሀን ዜጎችን ብቻ ያካተተ ነው፡፡ ኮሚሽኑ ከዚህ በተጨማሪም በገዥውአካል የፖሊስ እና የደህንነትኃይሎች ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ የተገደሉ ንጹሀን ዜጎች ስምዝርዝር አለው፡፡ ሆኖም ግን ኮሚሽኑአጣርቶ እንዲያቀርብ የታዘዘው ከላይ በግልጽእንደተቀመጠው የሌሎች ቀናትን ብቻ ሰለነበር በዚህምክንያት እነዚህን ከህግ አግባብ ውጭበዘፈቀደ የተገደሉትን ዜጎች በዘገባው ይፋ ማድረግ ሳይችልቀርቷል፡፡ 

የወገኖቻችን ሬሳ የውሻ ሬሳ ሆኖ ደመከልብ ሆነው አይቀሩም!

ፍትህ አንድ ቀን የርትዕ ሰይፏን በመምዘዝ በግፈኞች ላይ ታሳርፋለች!

የማይሳነው ቸሩ አምላክ ያለቁትን ወገኖቻችንን ነፍስ በገነት ያኑርልንአሜን! 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ህዳር 2 ቀን 2007 .

ለአስራ አራት ቀን አራስ ጥይት? – (እውነተኛ የወንጀል ታሪክ)

0
0

crime
አቶ አስጨናቂ ደስታ፤ ተሬ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ በእርሻ የሚተዳደሩ አርሶ አደር ናቸው፡፡ ትዳር መስርተው መኖር ከጀመሩ ደግሞ አስራ ሶስት ዓመታትን አስቆጥረዋል፡፡ ባለቤታቸው ወ/ሮ ኮከብ ወርቁ ከአቶ አስጨናቂ አራት ልጆችን አፍርተዋል፡፡ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን በቀወት ወረዳ ለረጅም ዓመታት በትዳር አብረው የኖሩት ሁለቱ ጥንዶች ትዳራቸው እንዲሁም ቤተሰባቸውን እንከን ገጥሞታል፡፡ አቶ አስጨናቂ ደስታ ታታሪ ገበሬ በመሆናቸው ነው በአካባቢው የሚታወቁት፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን አቶ አስጨናቂ ደስታ ርቋቸዋል፡፡ እርሳቸው እና ቤተሰባቸው በመጥፎ የስሜት ድባብ ውስጥ ሆነው ጊዜው እየነጎደ ነው፡፡ ይመሻል ይነጋል፡፡ ይህ የሆነበት ደግሞ ምክንያት አለው፡፡ አቶ አስጨናቂ በአጭር ጊዜ ውስጥ አራት በሬዎቻቸውን አጡ፡፡ የሚመኩባቸው የእርሻ በሬዎቻቸው ሳይታሰብ እየታመሙ ሞተው አለቁባቸው፡፡
የሀገራችን ገበሬዎች በበሬዎቻቸው በጣም ነው የሚመኩት፡፡ ዘር ዘርተው… አርመው… ጎልጉለው… አጭደውና ወቅተው ምርት የሚያገኙት የበሬዎቻቸውን ጉልበት በመጠቀም ነው፡፡ በሬ ለሀገራችን ገበሬዎች ከምንም በላይ እንደሆነ በአርሶ አደሮች አንደበት ጭምር ይነገራል… ይዘመራል፡፡

‹በሬ እረስልኝ…
በሬ ዙርልኝ
አጋዥ ባልደረባ
አራሽም የለኝ
በጥቋቁር በሬ…
መሬት ካላረሱ
ገንዘብ የት ይገኛል…
ቦርሳ ቢዳብሱ›
ከአርሶ አደሮች አንደበት የሚደመጡ የማሞካሻ ስነ-ቃሎች ናቸው፡፡ ለበሬ ማሞካሻ… ማሞገሻ… ውለታ መግለጫ የሚሆኑ ስነ-ቃሎች እነዚህ ብቻ አይደሉም፡፡
አቶ አስጨናቂ አራት ልጆቻቸውን አርሰው የሚመግቡባቸው የአራት በሬዎቻቸው ሞት ትልቅ ሀዘን እንዲሰማቸው አድርጓቸዋል፡፡ የበሬዎቻቸው ሞት ራቁታቸውን ስላስቀራቸው የኑሮ ምስቅልቅልን ፈጥሮባቸዋል፡፡

‹መሬት ያለ በሬ
ምርት ያለገበሬ› አይታሰብም የሚለው የሀገራችን ብሂል በአርሶ አደር አስጨናቂ ደርሶባቸው ዘወትር ጭንቀት ሆኖባቸዋል፡፡ በእነዚህ መጥፎ አጋጣሚዎች ውስጥ ቤተሰባቸውን እንዴት እየመሩ ነበር? ከባለቤታቸው ወ/ሮ ኮከብ ጋር ምንምን ነገሮችን ያወሩ እንደነበር ለማወቅም ወ/ሮ ኮከብን ማግኘት አልተቻለም… ለምን? ቢሉ… ምክንያቱ ወዲህ ነው፡፡
የወርሀ ሐምሌ ክረምት ወቅት ነው፡፡ ሐምሌ 4 ቀን 2001 ዓ.ም በግምት ከረፋዱ አምስት ሰዓት ላይ አቶ አስጨናቂን ‹‹ምን አስጨከናቸው?›› ያስባለ ትእይንት በመኖሪያ ቤታቸው ተከሰተ፡፡ ጎረቤትን… ዘመድ አዝማድን… የአካባቢውን ነዋሪ ያስደመመ በእጅጉ ያሳዘነ ትእይንት ነበር የተከሰተው፡፡

ወ/ሮ ኮከብ ወርቁ በትዳር ሕይወታቸው አራተኛ ልጃቸውን ከወለዱ ገና አስራ አራተኛ ቀናቸው ነው፡፡ ወገባቸው ያልጠነከረ አራስ ናቸው፡፡ በአራስ ቤት ውስጥ ሁለተኛ ሳምንታቸውን ገና አልደፈኑም፡፡ በመጫቷ ወ/ሮ ኮከብ ላይ የተፈፀመው ግን ‹‹መታረስ ነው የሚገባቸው ወይንስ ሌላ?›› የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ …ጥያቄው ደግሞ የሁሉም ሰው ነው፡፡ አቶ አስጨናቂ የአራት ልጆቻቸውን እናትና ባለቤታቸውን ‹‹…እንደ ቤታችን ምን ላቅርብልሽ?›› ብለው አልጠየቁም፡፡ በእዚህ ምትክ የሰጧቸው ጥይት ነበር፡፡ የአራት ልጆቻቸው እናት እና አራሷ ወ/ሮ ከባለቤታቸው በተተኮሰባቸው ጥይት ተመተው እስከ ወዲያኛው አሸለቡ፡፡

ለጥፋት የተዘረጋው የአቶ አስጨናቂ የጭካኔ እጅ በእዚሁ አላበቃም፡፡ ጭካኔያቸው ቀጥሏል፡፡ የሰባት ዓመት ሴት ልጃቸውንም እናቷን እንድትከተል አድረጓት፡፡ አባወራው ባለቤታቸውንና የሰባት ዓመት ሴት ልጃቸውን ጨክነው በጥይት መትተው የህይወት እስትንፋሳቸው እንዲቆም አደረጉ፡፡

ተግባራቸውን ያየ… የሰማ ሁሉ ‹‹ምንድን ነው ይህንን ያህል ጭካኔ?›› ብሎ እንዲጠይቅና እንዲወያይ አደረገው፡፡ እውነት በሬዎቻቸው ስለሞቱባቸው ተስፋ ቆርጠው ይሆን? ይህ የእኛ ጥያቄ ነው፡፡ ጎረቤቶች ግን የሚሉት አራት በሬዎችን በአንድ ጊዜ በሞት በማጣታቸው ተስፋ ቆርጠው ነው ብለዋል፡፡ ፖሊስ ጉዳዩን በማጣራት ላይ ነው፡፡ በእንስሳት ሞት የቤተሰብን ህይወት ማጥፋት ለምን አሰፈለገ? የሚለው የፖሊስም ጥያቄ በመሆኑ ምርመራው እንደተጠናቀቀ የሚታወቅ ነው የሚሆነው፡፡
አሁን አቶ አስጨናቂም በህይወት የሉም፡፡ ምክንያቱም በዕለቱ በባለቤታቸውና በሰባት ዓመት ሴት ልጃቸው ላይ ግድያውን ከፈፀሙ በኋላ በራሳቸው ላይ ፈረዱ፡፡ ራሳቸውን አጠፉ፡፡ በአራት በሬዎች ሞት የሦስት ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ሁሉንም ያሳዘነ እንደሆነ የአካባቢው ሰዎች ይናገራሉ፡፡

ቤት ባዶ ቀረ፡፡ ሦስት ልጆችም ያለ አሳዳጊ ቀሩ፡፡ እናታቸውን፣ አባታቸውንና እህታቸውን አጡ፡፡ የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ መሐመድ እንደገለፁት የልጆቹን ህይወት ለመታደግ በአራስ ቤት ያለው ህፃን ወደ ሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር የህፃናት እንክብካቤ ተቋም በመወሰድ ተገቢውን እንክብካቤ እንዲደረግለት ተደርጓል፡፡ ቀሪዎቹ ሁለት ልጆች ደግሞ ያለ አሳዳጊ እንዳይቀሩ አሳዳጊ እንዲያገኙ ፖሊስ በጥረት ላይ ነው፡፡ የፖሊስ ጥረት ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ ሁለቱን ህጻናት ለመታደግ ግለሰቦች፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች፣ መንግስትና ሌሎችም እጃቸውን ማስገባት ቢችሉ በጎ ተግባር ነውና ሁላችሁም የበኩላችሁን አበርክቱ የሚለው የዝግጅት ክፍላችን መልእክት ነው፡፡

Health: የስኳር ህመምና ስንፈተ ወሲብ

0
0

ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር አህመድ ረጃ እንደፃፉት ስለ ስንፈተ ወሲብ መፃፍም ሆነ መነጋገር አስቸጋሪ ጉዳይ መሆኑ ይሰማኛል፡፡ ይህም የሚሆነው ባህላችንና ሃይማኖታችን በሚያሳድርብን ተፅዕኖ ነው፡፡ ነገር ግን ችግሩ አሳሳቢና የትዳር ሁኔታንም የሚፈታተን በመሆኑ ለስኳር ህሙማንም የሚፈታተን በመሆኑ ለስኳር ህሙማንም ሆነ የትዳር ጓደኞቻቸው ግልፅ እንዲሆኑ ይህን ፅሑፍ አቅርበናል፡፡ በዚህ በስንፈተ ወሲብ ችግር በፍርሃት ዝሙትን መርጠው ውስጥ ውስጡን ለአካላዊና ስነ-አዕምሯዊ ችግር የሚዳረጉት ስኳር ህሙማን ስለ ችግሩ ከህክምናቸውና ከትዳር ጓደኞቻቸው በግልፅ ለመወያየት ይህ ፅሑፍ ይጠቅማቸዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ አንባቢያን እንዲረዱልኝ የምፈልገውን አንድ ነገር በቅድሚያ ላስቀምጥ፡፡ ስለ ስንፈተ ወሲብ በምንፅፍበት ጊዜ ከባህላችንና ከልምዳችን ውጭ አንዳንድ ቃላቶች ብንጠቀም ስለ ጉዳዩ በግልፅ ለማስረዳት ሲባል ብቻ ታስቦ መሆኑን ከይቅርታ ጋር እንድትረዱልን እንጠይቃለን፡፡

sex and diabtics

ስንፈተ ወሲብ ማለት ምን ማለት ነው?

ስንፈ ወሲብ ስንል አንድ ወንድ ወሲባዊ ግንኙነት ለማድረግ ብልቱ መነሳት ሲያቅተው ወይም ተነስቶ ግንኙነት ሳይፈፅም ሲተኛበት ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ለወሲብ ግንኙነት ፍላጎት ከማጣት ጋር ወይም አስቀድሞ የዘር ፍሬ ፈሳሽን ከማውጣት ጋር ለይተን ማየት ይኖርብናል፡፡

በጣም አብዛኛዎቹ ስኳር ህሙማን የሚያጋጥማቸው ችግር ለወሲባዊ ግንኙነት ከፍተኛ የሆነ ውስጣዊ ፍላጎት እያላቸው ነገር ግን ግንኙነት ለማድረግ ሲያስቡ ብልቱ አልሰራ ሲላቸው ነው፡፡

የስንፈተ ወሲብ ስርጭት ምን ይመስላል?

አንዳንድ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት 35 ከመቶ እስከ 50 ከመቶ የሚሆኑት ስኳር ህሙማን ስንፈተ ወሲብ ችግር እንደሚያጋጥማቸው ይጠቁማሉ፡፡

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ስለ ችግሩ የሚያወሩት ግን በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ ብዙዎቹ በፍርሃትና በመሸማቀቅ ውስጥ ውስጡን በመቃጠል ለብዙ ችግር ይዳረጋሉ፡፡ ብዙዎቹ ወንዶች ለትዳር ጓደኞቻቸው በግልፅ ስለማይናገሩ ትዳራቸው የሚፈርስባቸው ብዙ ናቸው፡፡ ችግሩ ስር ሳይሰድ ከባለሙያ ጋር ቢመካከሩበት ደግሞ መፍትሄ ሊገኝለት ስለሚችል፣ ስኳር ህሙማን ከዝሙት ወጥተው ሐኪሞቻቸውን መጠየቅና መረዳት ይኖርባቸዋል፡፡

አንዳንድ ጊዜ ወንዶች ጊዜያዊ በሆነ መልኩ ስንፈተ ወሲብ ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡ ይህም የሚሆነው ለምሳሌ ያህል ከመጠን ያለፈ አልኮል ሲጠጡ ወይም በስራ ብዛት ከልክ ያለፈ ድካም ሲያጋጥማቸው ነው፡፡ ይህ ቋሚ ስላልሆነ መደናገጥ ወይም መረበሽ አያስፈልግም፡፡ ነገር ግን በተከታታይ ስንፈተ ወሲብ ካጋጠመ ባለሙያን ማማከሩ አስፈላጊ ነው፡፡

ለመሆኑ ስንፈተ ወሲብ በምን ምክንያት ይከሰታል?

ወሲባዊ ግንኙነት ለማድረግ የወንድ ብልት መነሳትና መጠንከር ይኖርበታል፡፡ ብልቱ እንዲጠነክርና እንዲነሳ ሶስት ሁኔታዎች መሟላት አለባቸው፡፡

- ወደ ብልቱ የሚሄድና የሚያንቀሳቅሱት ነርቮች ስራቸውን በአግባቡ መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡ 

- ወደ ብልቱ የሚሄዱት የደም ቧንቧዎች ጤናማ መሆንና የደም ዑደቱ በቂ መሆን አለበት፡፡

- ከአንጎል የመነሳሳት ስሜት መኖር አለበት፡፡

ከነዚህ ሶስት ሁኔታዎች አንዱ ላይ እንኳን ችግር ቢገጥም ስንፈተ ወሲብ ይከሰታል፡፡ ለረጅም ጊዜ በቁጥጥር ስር ያልዋለ የስኳር ህመምና በስኳሩ መብዛት የተነሳ ወደ ብልት የሚሄዱት ነርቮች የደም ቧንቧዎች ስለሚጎዱ ስኳር ህሙማን ወንዶች ስንፈተ ወሲብ ያጋጥማቸዋል፡፡ ከስኳር ህመም በተጨማሪ የደም ግፊትና ደም ውስጥ የስብ መጠን መጨመር በሚታይባቸውና ሲጋራ የሚያጨሱ ህሙማን ችግሩ እጥፍ ድርብ ይሆንባቸዋል፡፡

ስንፈተ ወሲብን የሚያባብሱ ሁኔታዎች 

- ከመጠን ያለፈ ክብደትና ውፋሬ

- ሲጋራ ማጨስ 

- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ

- ከመጠን በላይ አልኮል መጠጣት

- ጫት መቃም

- አደንዛዥ እፆችን መጠቀም

- ለሌላ በሽታ የሚዋጡ አንዳንድ መድኃኒቶች

- የመንፈስ ጭንቀትና ውጥረት (Anxiety, Stress) 

- ድብርት (Depression)

የስንፈተ ወሲብ ፈርጀ ብዙ ችግር

ወንዶች ስኳር ህሙማን ስንፈተ ወሲብ ችግር ሲያጋጥማቸው የተለያዩ አካላዊና ስነ-አዕምሯዊ ችግሮች ያጋጥማቸዋል፡፡ ከነዚህም በጥቂቱ፡-

- የመንፈስ ጭንቀት፣ ድብርት፡፡

- ገና ለገና እምቢ ይሉኝ ይሆናል በማለት የወሲብ ፍርሃት፡፡

- የትዳር ጓደኛ ጋር በየጊዜው መጨቃጨቅና መጣላት፡፡ ብሎም የትዳር መፍረስ፡፡

- ቁጭትና ፀፀት፡- የትዳር ጓደኛን ባለማርካት የሚፈጠር ስሜት፡፡

- ለራስ ያለን ስሜት ማሳነስ፡፡ ቀደም ሲል ስንፈተ ወሲብ ካጋጠመ የሚፈጠር ስሜት ነው፡፡

- የስንፈተ ወሲብ ያለባቸው ሰዎች የልብ ችግርም ሊኖርባቸው ይችላል ተብሎ ስለሚታምን ህሙማን ልባቸውን በሚገባ መመርመር ይኖርባቸዋል፡፡

የወንድ ብልት ለወሲባዊ ግንኙነት ዝግጁ የሚሆነውና የሚጠነክረው እንዴት ነው?

የብልት መነሳት የሚጀምረው ከአንጎል ነው፡፡ አካላዊ ሆነ አዕምሯዊ መነቃቃት ሲኖር በአንጎል ውስጥ ያሉ ነርቮች በተለያዩ ኬሚካሎች አማካይነት ወደ ብልት ለሚሄዱ ነርቮች መልዕክት ያስተላልፋሉ፡፡

በዚህም የተነሳ ወደ ብልት የሚሔዱት የደም ቧንቧዎች መስፋት ይጀምሩና ብልቱ በደም በተሞሉ ቧንቧዎች አማካይነት ይወጠርና ይጠነክራል፡፡ ወደ ብልት የሚሄደው የደም ዝውውር ሲቀንስና የገባው ደም ተመልሶ ወደ ሌላ አካላት በሚሄድበት ጊዜ ብልቱ መጠኑ ቀንሶ ለስላሳ ይሆናል፡፡
አንድ የስኳር ህመምተኛ የስንፈተ ወሲብ ችግር ሲያጋጥመው መደረግ ያለበት ነገር ይህ ችግር ሲያጋጥም መጀመሪያ ከስኳሩ ውጭ ሌላ ህመም መኖር አለመኖሩ መረጋገጥ አለበት፡፡ ሌላው መረጋገጥ ያለበት ነገር ስንፈተ ወሲብ ሊያስከትሉ የሚችሉ መድኃኒቶች ይወስድ እንደሆነ መለየት አለበት፡፡ ቀደም ሲል የተገለፁት ስንፈተ ወሲብን የሚያባብሱ ነገሮች ይኑሩ አይኑሩ መታወቅ አለበት፡፡

ከዚህ ተጨማሪ የሆርሞኖች መዛባት መኖር በመመርመር ተለይቶ መታወቅ ይኖርበታል፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ተጠንተው ስንፈተ ወሲብ ከስኳር ህመም ጋር በቀጥታ ተያያዥነት አለው ተብሎ ከታመነ የሚከተሉት የሕክምና ዘዴዎችን መጠቀም ያሻል፡፡

የስንፈተ ወሲብ የህክምና ዘዴዎች

- ስለ ችግሩ በግልጽ መወያየት፡፡ ከህክምና ባለሙያ ጋርና ከትዳር ጓደኛ ጋር

- ስኳሩን በቁጥጥር ስር ማዋል

- የደም ግፊትና የኮሌስትሮል መጠንን መቆጣጠር

- ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ማቆም አልኮልም፣ ጫትና አደንዛዥ ዕጾችን አለመጠቀም

- ውፋሬን ማስወገድና አዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

- ጭንቀትና ውጥረትን ለማስወገድ የምክር አገልግሎት ከባለሙያ ማግኘት

- በአፍ የሚዋጡና በህክምና ትዕዛዝ የሚሰጡ እንክብሎች፡- ከነዚህም መድኃኒቶች በሀገራችን በአሁኑ ሰዓት አንድ አይነት በስራ ላይ ውሏል፡፡ ሲልዲናፈል ይባላል፡፡

- በብልት ቀዳዳ ውስጥ የሚጨመሩ መድኃኒቶች

- በብልት ላይ የሚወጉ በመርፌ የሚሰጡ መድኃኒቶች ያሉ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን አይገኙም፡፡

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live