Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ቀንዲሎቿን የረሳች ሀገር

0
0

ይህ ቁም ነገር መፅሔት 13ኛ ዓመት ቁጥር 190 የሽፋን ርዕስ ነው፡፡
መነሻ
አራት ኪሎ ከዳግማዊ አፄ ምንሊክ ቤተ መንግስት ከፍ ብሎ የተገነባው የቅድስት ስላሴ ካቴድራል በስነ ህንፃ ውበቱም ሆነ በግዙፍነቱ ለአይን ማራኪ የሆነ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ከዚሁ ካቴድራል ጋር ተጎራብቶና ታኮ የሚገኘው የበዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያንም ምንም እንኳ እንደ ካቴድራሉ የገዘፈ ስነ ህንፃዊ ውበት አይኑረው እንጂ የሚያመሳስላቸው ታሪክ አላቸው፡፡ ሁለቱም በጉያቸው የቀደምት ታዋቂ ኢትዮጵያውያን አፅም ይዘዋል፡፡
yofetahe nigussie
በዓለ ወልድ ቤተክርስቲያን ማንም የእምነቱ ተከታይ ከዚህ ዓለም ሲለይ በቤተክርስቲያኗ ቀኖና መሰረት የሚያርፍበት የቀብር ቦታ እስከ 2001 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ነበረው፡፡ በዚህም ሳቢያ ብዙ ታዋቂ የሆኑና ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን በዚሁ ስፍራ ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟል፡፡ በ2001 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ግን በመሀል አራት ኪሎ የሚገኘው የበዓለ ወልድ ቤተክርስቲያን እንደማንኛዎቹም ከተማ መሀል እንዳሉት አብያተ ክርስቲያናት አንድ ጥናት አሰርቶ ‹‹የቀብር ቦታውን ለልማት እፈልገዋለሁ›› አለ፡፡ ይህንኑ ተከትሎም አንድ ማስታወቂያ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ተነገረ፡፡ ቤተሰቦቻችሁን በበዓለ ወልድ ቤተክርስቲያን የቀበራችሁ ምዕመናን ‹አፅሙን በአስቸኳይ እንድታነሱ› የሚል፡፡

ከዓመታት በፊት ወዳጅ ዘመዶቻቸውን አልቅሰው የቀበሩ ቤተሰቦች ዳግመኛ እያለቀሱ የወዳጅ ዘመዶቻቸውን አፅም ቀላል የማይባል ክፍያ በመክፈል ማስወጣት ጀመሩ፡፡ የቻሉ ዳግመኛ ቦታ እየገዙ የቤተሰቦቻቸውን አፅም ሲያሳርፉ አቅም የለንም ያሉ ቤተሰቦች አፅሙ በአንድ ማጠራቀሚያ ውስጥ ከየሐውልት ማስታወሻቸው ጋር እንዲገባ አስደረጉ፡፡ ሁሉም የየራሱንና የሚያውቀውን ግለሰብ አፅም ሲያስነሳና አግባብ ነው ባለው መልኩ እንዲቀመጥ ሲያደርግ ወዳጅ ዘመዶች ያጡ /ወይም የሌላቸው ጥቂት ሐውልቶች አፅማቸውን በሆዳቸው ይዘው ቆመው ይታዩ ነበር፡፡ እነዚህ ወዳጅ ዘመድ አጥተው የተተውትን አፅሞች ቤተክርስቲያኗ በራሷ ግብረ ሀይል አስነስታ ወደ ማጠራቀሚያ የምትከታቸው ሲሆን ‹እዚህ ነው ያረፉት› ወይም እነእከሌ ናቸው› የሚል ማስታወሻ የማግኘት ዕድላቸው ይጠባል፤ ምክንያቱም ጠያቂ ወገን ለሌለው ሰው ቤተክርስቲያኗ የምታደርገው ነገር ስለሌለ፡፡

ከነዚህ ወገን ጠፍቶ አፅማቸውን የሚያወጣላቸው አጥተው ከቆሙ ሐውልቶች መካከል አንዱ የአንድ እውቅ ኢትዮጵያዊ የጥበብ ሰው መቃብር ነበር፡፡ ይህ መቃብር ለምን ሰው አጣ? ለምን አስታወሽ አላገኘም? እኝህ ሰው በኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ውስጥ አሻራቸውን ያኖሩ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ቴአትር አባትና ፋና ወጊ ናቸው – ቀኝ ጌታ ዩፍታሔ ንጉሴ፡፡ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ቴአትር ታሪክ ፈር ቀዳጅ የሆኑት ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ህዝብ መዝሙር ደራሲ ሲሆኑ በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት የህግ መወሰኛ ምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩና ለዛሬዋ ኢትዮጵያ መሰረት የሆኑ ተግባራትን ያከናወኑ ሰው ናቸው፡፡

የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ አፅም የሚያሰነሳው ጠፍቶ ባለበት ሰዓት ታሪክና ስምን ጠንቅቀው በሚያውቁና ኢትዮጵያዊ ወኔና ደም ባልተለያቸው ሶስት ሰዎች አስተባባሪነት አፅማቸው ተቆፍሮ ሲወጣ ይህ ነው የሚባል ተቋም ወይም የኪነ ጥብብ ሰው አብሯቸው አልነበረም፡፡ የዮፍታሔ አፅም እንዲወጣና የተራውን ኢትዮጵዊ ወግ እንዳያጡ ያደረጉት ሶስት ሰዎች አቶ ጀማነህ ወርቁ፤አቶ ጌታቸው ግዛውና ዶ/ር ፍስሃ ገ/አብ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ከዮፍታሔ ጋር የስጋ ዝምድናም ሆነ ቤተሰባዊ ግንኙነት የላቸውም፡፡ ‹ማንም ሰው ከሞት አያመልጥም፤እኝህን ስንት ታሪክ የሰሩ ሰው መዘንጋት ከህሊና ወቀሳ አያድንም፡፡ የዛን ጊዜ ከሞቱ 62 ዓመታቸው ቢሆንም በአዲሱ ትውልድ ትልቅ አርአያ የሆኑ ሰው መሆናቸው ሊረሳ አይገባም›› ይላል ጎልማሳው አቶ ጀማነህ በወቅቱ ሀውልቱን ለማስነሳት ከሀገር ፍቅር እስከ ቤተ ክህነት የተመላለሰበትን ሁኔታ በማስታወስ፡፡ ግለሰቡ በወቅቱ የነበረውን አፅም የማስወጣት ሂደት ለታሪክ እንዲቆይ በፎቶግራፍ ጭምር ቀርፆ ይዟል፡፡ ይህንኑም ለዝግጅት ክፍላችን አቅርቧል፡፡

ዮፍታሔ ንጉሴ ማነው?

በሀገራችን የቴአትር ታሪክ በቀዳሚነት ስሙ የሚነሳው ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ የተወለደው በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በደብረ ኤልያስ ሙዛ በተባለ ቀበሌ ሲሆን ጊዜው ሚያዚያ 23 ቀን 1887 ዓ.ም ነበር፡፡ በዘመኑ እንደነበሩ ሊቃውንት ሁሉ ዮፍታሔም ፊደልን የቆጠረው በቤተክህነት ትምህርት ነው፡፡ በዚያ ጊዜ በጣም ጎበዝ ተማሪና አስተዋይ እንደነበር ባለቅኔው ዮሐንስ አድማሱ በፃፈው የዮፍታሔ ግለ ታሪክ ላይ ሰፍሯል፡፡
‹‹ከህፃንነቱ ጀምሮ ልበ ብሩህ እንደነበረ፣ እንኳን የተነገረው የሰማው ቀለም ቀርቶ፣ አልፎ ሄያጅ ቀለም እንኳ ሳይሻው ሳይፈቅደው ይጠልፈው እንደነበር በተለይ ኤልያስ በነበረበት ጊዜ የሚያውቁት ሁሉ ይናገራሉ፡፡›› በማለት ዮሐንስ ስለ ዮፍታሔ ይነግረናል፡፡

በተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙ ቤተሰቦች የተገኘው ዮፍታሔ የልጅነት ህይወቱን ያሳለፈው በተቀማጠለ ኑሮ ነው፡፡ የቅኔ ተማሪዎች የሚያጋጥማቸው ችግርና መንገላታት በሱ ላይ አልደረሰም ማለት ይቻላል፡፡ የቤተሰቦቹ የኑሮ ደረጃ ጥሩ መሆንና በዚያው በደብረ ኤልያስ በዘመኑ የታወቁት የቅኔ ሊቅ መምህር ገ/ሥላሴ ዘኤልያስ መኖራቸው ከአካባቢው ስላላራቀው ከችግሩ ለማምለጡ ዋና ምክንያቶች ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡
በፅሑፍ የተቀመጡ መረጃዎችን መሠረት አድርገን ዮፍታሔ ቅኔ መዝረፍ የጀመረበት እድሜውን ስንፈልግ 12 ወይም 13 ዓመቱ ላይ ሊሆን እንደሚችል እንገምታለን፡፡ ዮሐንስ አድማሱ እንደፃፈው ዮፍታሔ የቅኔ ትምህርቱን ለማጠናቀቅ የፈጀበት ቢበዛ ሦስት ዓመት ብቻ ነው፡፡

በአጠቃላይ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ወደ አዲስ አበባ ከመምጣቱ በፊት ድጓ፣ ምዕራፍ፣ ቅኔና ዜማ ተምሮ አጠናቆ ተምሯል፡፡ በዮፍታሔ ታሪክ ውስጥ እጅግ የሚያስደንቀው እነዚህን ሁሉ ትምህርቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ መማሩና ማጠናቀቁ ብቻ አይደለም፡፡ ዮሐንስ እንደሚለው አስደናቂው ነገር ገና 20 ዓመት እንኳን ሳይሞላው ‹ቀኝ ጌታ› የሚለው ማዕረግ ማግኘቱ ነው፡፡ ቀኝ ጌትነት የሽማግሌዎች ሹመት ነው ይባላል፡፡ በዕድሜያቸው የገፉና በዕውቀታቸው አንቱታን ያተረፉ ሰዎች የሚያገኙትን ሹመት ገና በለጋ ዕድሜው ማግኘቱ በዘመኑ የነበሩትን ሁሉ ያስደነቀ ነበር፡፡
ዮፍታሔ ደብረ ኤልያስን ለመጨረሻ ጊዜ ተሰናብቶ ወደ አዲስ አበባ የገባው በ1909 ዓ.ም እንደሆነ ይነገራል፡፡ የአባቱን መሞት ተከትሎ እናቱ ወ/ሮ ማዘንጊያ ቁርባናቸውን አፍርሰው ሌላ ባል በማግባታቸው ምክንያት ዮፍታሔ ተቀይሞ የትውልድ ቀየውን እንደሸሸ ተፅፏል፡፡

ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ በኢትዮጵያ የቴአትር ታሪክ አሻራውን ማኖር የጀመረው ከ1920ዎቹ መጀመሪያ አንስቶ እንደሆነ ይገመታል፡፡ በተለይ በዘመኑ የነበረውን ፖለቲካዊ ሽኩቻ ገፀ ባህሪያት በመቀያየር ለማሳየት ጥሯል፡፡ በተምሳሌትና ስም ለበስ ቅኔ ስልት የፃፈው ‹ምስክር›› የሚለው ቴአትሩ ለዚህ ተጠቃሽ ነው፡፡ ቴአትሩ የተፃፈበት ጊዜ 1923 ዓ.ም መሆኑ ይነገራል፡፡ በኢትዮጵያ ቴአትር ውስጥ የነገሰው ዮፍታሔ ንጉሴ ዕርበት ፀሐይ፣ አፋጀሽኝ፣ ዳዲ ቱራ፣ እመት አታላይ ባላቸውን አቶ መታለያን እንዳስታመሙ፣ የሕዝብ ፀፀት የእመት በልዩ ጉዳት፣ መሸ በከንቱ ስራ በፈቱ እና የደንቆሮዎች ቴአትርን ፅፎ፣ መርቶና አዘጋጅቶ አቅርቧል፡፡ ባለቅኔው የሚያዘጋጃቸው ቴአትሮች ሁሉ ማለት ይቻላል በመዝሙር የታጀቡ ናቸው፡፡
ዮፍታሔ በርካታ ዜማዎችን የደረሰ ሲሆን ከነዚህ መካከል የወላድ ኢትዮጵያ ዜማ፣ ጉሳማዬ፣ መድኔ መድኔ፣ አንተ ባላጎዛ፣ የጌታው አቶ ከምሲ ዜማ፣ ሶረቲዮና የኛማ ሙሽራ የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡ የኛማ ሙሽራ የሚለው ዜማ ልዑል አልጋ ወራሽ እና ልዕልት ወለተ እስራኤል ሠርጋቸውን ባደረጉበት ወቅት የተዘጋጀ ሲሆን ይህን ዜማ ዛሬም ድረስ በሰርግ ዘፈኖች ውስጥ እንሰማዋለን፡፡የሀገራችን የመጀመሪያው ብሔራዊ መዝሙር ግጥምና ዜማ የተሰራውም በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ነበር፡፡
የበርካታ ስራዎች ባለቤት የሆነው ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ህይወቱ ያለፈው በድንገት ነው፡፡ ዮሐንስ አድማሱ በመፅሐፉ እንደገለፀው የዮፍታሔ አሟሟት በግልፅ አይታወቅም፡፡ ‹‹ዮፍታሔ ከሞተበት ጊዜ አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ ‹በከሰል ጢስ ነው የሞተ› የሚባለው ተረት ይመስለኛል፡፡ የሞተበትን እውነተኛና ዓይነተኛ ምክንያት ለመሸሸግ ሲባል በረቂቅ ስልት የተፈጠረ ተረት ይመስላል››፡፡

የባለቅኔው ሞት መንስኤው ባይታወቅም ቀኑ ግን ሐምሌ 1 ቀን 1939 ዓ.ም ነበር፡፡ እድሜው ደግሞ 52፡፡ በኪነጥበብና በመንግስት አስተዳደር (የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ም/ፕሬዚዳንት ነበሩ) እንዲሁም በመምህርነት (የሚኒሊክ ት/ቤት አስተማሪ ነበሩ) ሀገራቸውን ያገለገሉት ዮፍታሔ ንጉሴ ሞት ከሚያንገበግባቸው ሰዎች መካከል አንዱ ዮሐንስ አድማሱ አንዱ ነው፡፡ ለዚያም ነው ተወርዋሪ ኮከብ በሚለው ግጥሙ እንዲህ ስለ ዮፍታሔ የተቀኘው፡፡
ብሩህ ነፀብራቁ
ውበትና ድምፁ አንድነት ተሰምተው አንድነት ቢበርቁ
የሚያውቅለት ጠፍቶ
ሚስጥሩን አካቶ
ተወርዋሪ ኮከብ በራሱ ነበልባል በራሱ ነዲድ ተቃጥሎ የጠፋ
ተወርዋሪ ኮከብ በምናውቀው ሰማይ ነበረ በይፋ፡፡
(እስኪ ተጠየቁ፡ 1990)
የዮፍታሔ ንጉሴ ቀን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
ሰሞኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ የቴአትር ፌስቲቫል አዘጋጅቷል፡፡ በዮፍታሔ ንጉሴ ስም የተሰየመው ቴአትር ትምህርት ቤት ከጥቅምት 28 ቀን እስከ ህዳር 6 ቀን 2007 ዓ.ም ለሚያካሂደው የቴአትር ፌስቲቫል እያንዷንዱን ቀን በተለያዩ ለቴአትር እድገት አስተዋፅኦ ባደረጉ የጥበብ ሰዎች ስም መሰየሙን ይፋ ያደረገ ሲሆን በ9 ቀናት ውስጥ 9 ቴአትሮች ለእይታ በቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዚህም መሰረት የፊታችን ጥቅምት 29 ቀን 2007 ዓ.ም የመጀመሪያው ቀን በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ስም የተሰየመ ሲሆን በዕለቱ ዮፍታሔ ለሀገራችን ቴአትር ያደረጉት አስተዋፅኦ ይዘከራል ተብሏል፡፡ በተከታታይ ባሉት ቀናት ደግሞ ተስፋዬ ሳህሉ፣ ፀጋዬ ገ/መድህን፣ ተ/ፐሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ፣ መንግስቱ ለማ፣ አባተ መኩሪያ፣ ረ/ ፐሮፌሰር ሃይማኖት አለሙና ፍስሃ በላይ ይማም ይታሰባሉ፡፡

ዩኒቨርሲቲው የቴአትር ት/ቤቱን በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ስም መሰየሙና በዮሐንስ አድማሱ የተጻፈውን የዮፍታሔን ግለ ታሪክ መጽሐፍ ማሳተሙ ለተማሪዎቹም ሆነ ለሌላው ማህበረሰብ የሀገራችን ቴአትር ፋና ወጊ መሆናቸውን ማስተማሪያነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የዮፍታሔ አፅም የወደቀበትና ቦታ በመለየት ክብሩን ጠብቆ እንዲቀመጥና ለታሪክ እንዲሻገር የማድረግ ሀላፊነቱንም አብሮ ሊወጣ ይገባል፡፡ በፎቶግራፍና በስም ብቻ የሚታወቁ የታሪክና የኪነ ጥበብ ጀግኖቻችንን መቃብር በአግባቡ መጠበቅና ማክበር ነገ አዲስ ታሪክ እንዲሰሩ ለምንጠብቃቸው አፍላ ወጣቶች የታሪክ ስንቅ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ቤት በ2003 ዓ.ም በዮፍታሔ ንጉሤ ስም እንዲጠራ መወሰኑ ታላቁን ሰው ለመዘከርና ለማሰብ ትልቅ ሚና ቢኖረውም የትምህርት ቤቱ ተማሪዎችም ሆኑ ሌላው ማህበረሰብ ስለጉዳዩ መረጃ የላቸውም፡፡ ትምህርት ቤቱ በዮፍታሄ ስም መሰየሙን ለማስተዋወቅ የተሰራ ስራ የለም፡፡ በዚህ ወቅት የዮፍታሔ ቲአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተስፋዬ እሸቱ ከቁምነገር መጽሔት በጉዳዩ ዙሪያ ጥያቄ ቀርቦላቸው ምላሽ ሲሰጡ ትምህርት ቤቱ በዮፍታሔ ስም በአሁኑ ወቅት እንደማይጠራና ምክንያቱንም እንደማያውቁ ነግረውናል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእስክንድር ቦጎስያን የስነጥበብ ኮሌጅ ዲን የሆኑት አቶ ነብዩ ባዬ በአንጻሩ ትምህርት ቤቱ አሁንም በዮፍታሄ ስም እንደሚጠራ ገልጸው ነገር ግን ስሙ የተሰጠው ለማስታወሻነት በመሆኑ በዮፍታሔ ስም የሚጠራው በገደብ መሆኑን ነግረውናል፡፡ ‹ደብዳቤዎች ለተለያዩ አካላት ሲጻፉ ስማቸው ይጠቀሳል› ብለዋል አቶ ነብዩ፡፡ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ቤቱ ሰሞኑን ለሚያከብረው የቴአትር ፌስቲቫል ተብሎ ባዘጋጃቸው ፖስተሮችና ሎጎው ላይ የዮፍታሔን ስም አለመጠቀሙ ቸልተኝነት ይመስለናል፡፡ እየዘነጉ እንደገና ለማስታወስ መሞከር ትዝብት ላይ ይጥላል፡፡

ምናልባትም ዩኒቨርሲቲው ለዮፍታሔ በመደበው ዕለት ዮፍታሔ እንደማንኛውም ታሪክ ሰርቶ እንዳለፈ ኢትዮጵያዊ አፅሙ በክብር እንዲያርፍ እና ሀውልቱ እንዲቆም ቤተክርስቲያኗን መጠየቅ ይገባዋል፡፡ ከአንድ ስንዝር መሬት በላይ ወስደው ላልተቀበሩ ሰዎች ሳይቀር አክሱምና ላሊበላን የሚወዳደር የሚመስል መቃብር ቤትና ሐውልት ለመገንቢያነት ቦታ ከልክላ የማታውቀው ቤተክህነት ለዮፍታሔ አፅም ማረፊያ ቦታ ታጣለች ተብሎ አይጠረጠርም፡፡ አለበለዚያ ግን ዮፍታሔ እንዳለው
‹‹ሀገሬ ተባብራ ካረገጠች እርካብ
ነገራችን ሁሉ የእንቧይ ካብ የእንቧይ ካብ››
ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላለ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ› ይሆናል፡፡ አሁን ያለበትን ሁኔታ ዮፍታሔ ንጉሤ ለአፍታ ቀና ብሎ ቢመለከት
‹‹አይኔን ሰው አማረው
የሰው ያለህ የሰው›› ማለቱ አይቀርም፡፡ ከዚህ ስሜት እንድንወጣ ታድያ አስፈላጊው ነገር መደረግ አለበት እንላለን፡፡
ሌሎች የጥበብ ሰዎች መቃብርስ?

ባለፈው ዓመት አጋማሽ ላይ ለጉብኝት ወደ አዲስ አበባ የመጡት የጃፖኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጋር በተያያዘ ስለ አበበ ቢቂላ ሐውልትና የመታሰቢያ ሙዚየም ግንባታ በቁም ነገር መፅሔት በኩል ብዙ ብለናል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ አዲስ አበባ በመጡበት ወቅት የሮምና የቶኪዮ ማራቶኑ ጀግና አበበ ቢቂላን ቤተሰቦች ለመጎብኘት ቀጠሮ ሲይዙ አበበ በስሙ የተመሰረተ ደረጃውን የጠበቀ ሙዚየም ባለመኖሩ ቤተሰቦቹን በአንድ ሆቴል አነስተኛ ክፍል ውስጥ በተጨናነቀ ሁኔታ እንዳነጋገሯቸው ፅፈናል፡፡ ሐውልቱም በቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን በሙታን መንደር እንደዋዛ ቆሞ የሚታይ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወደ አደባባይ ይውጣ ብለን ፅፈናል፡፡ ምንም እንኳ ምላሹ ከመንግስትም ይሁን ከሌሎች አካላት (ከጃፓን ኤምባሲ በስተቀር) ዝምታ ቢሆንም፡፡

ከዚሁ ከአበበ ቢቂላ የመቃብር ቦታ ዙሪያውን ይገኙ የነበሩ የታዋቂ ኢትዮጵያውያንና የጥበብ ሰዎች መቃብሮች ከቦታው ለልማት መፈለግ ጋር በተያያዘ ፈራርሰውና ሐውልታቸውም ተሰባብሮ መመልከት ሀላፊነት ለሚሰማው ሰው ሁሉ ያማል፡፡
የዛሬ ሁለት ዓመት መላ የጥበብ ስራቸውንና ባለ ግርማ ሞገስ መኖሪያ ቤታቸውን ለመንግስት ያወረሱት እጅግ የተከበሩ የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈርቅ ተክሌ መቃብር ቦታም ሃውልት ሳይሰራለት ተረስቶ ይገኛል፡፡ ‹ነብይ ባገሩ አይከበርም› እንዲሉ ፈረንጆቹ በክብር ጨረቃ ላይ ስማቸውን ያኖሩላቸውን ታላቅ ሰዓሊ እኛ ግን ሐውልት እንኳ ልናቆምላቸው አልቻልንም፡፡ የሰጠናቸው ቦታ ከማውራት የዘለለ አልሆነም፡፡ ቢያንስ ቤታቸውን የወረሰው የኢትዮጵያ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት መስጠት ይኖርበት ነበር፡፡

በቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን መካነ መቃብር ውስጥ ድምፀ መረዋዋ ብዙነሽ በቀለንም ታገኟታላችሁ፡፡ ከአበበ ፊት ለፊት የሚገኘው የብዙዬ ሃውልት ፈራርሷል፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ በፍርስራሹ መካከል ስሟን ላልተመለከተ ሰው የሷ መሆኑን ለማወቅ ይቸገራል፡፡ በአደባባይ ላይ በታላቅ ክብር ልንመለከተው የሚገባው የብዙነሽ በቀለ ሃውልት በመካነ መቃብሩ መካከል እንኳ በሚያሳዝን ሁኔታ ተጎሳቁሏል፡፡ የወደቀውና የፈራረሰው ሲሚንቶ ላይ ግን ይህ ጽሁፍ ይነበባል፡-‹‹ብዙዬ››
በሜክሲኮው ኦሎምፒክ ላይ በማራቶንና በ10 ሺህ ሜትር የተወዳደረው አትሌት ማሞ ወልዴም አስከሬኑ ያረፈው በዮሴፍ ቤተክርስቲን ግቢ ውስጥ ሲሆን የሱም ሃውልት ‹‹የሰው ያለህ›› እያለ ነው፡፡ የጀግናው አትሌት መቃብር ላይ ያለው ሃውልት መሬት ላይ ከወደቀ አመታት አልፈዋል፡፡ ከአበበ መቃብር ጀርባ መገኘቱን የሰማ ሰው ምናልባት በግምት ማሞ ወልዴ መሆኑን ካልጠረጠረ በቀር የሜክሲኮውን ጀግና መቃብር ይህ ነው ብሎ ማግኘት ይቸግራል፡፡ ማሞ ወልዴ ከዚያ መሬት ስር ማረፉን የሚጠቁም አንዳች ልዩ ምልክት እንኳ የለም፡፡

ሰለሞን ተሰማ በኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኞች ታሪክ ፈር ቀዳጅ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ህይወቱ እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ያለመታከት ለሃገሩ የሚዲያ እድገት ሰርቷል፡፡ ለዚህ ታላቅ ሰው ሃገሩ የሰጠችው ቦታ ግን እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ሰለሞን በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው የስፖርት ጋዜጣ አዘጋጅ እንደሆነና ከበርካታ የጥላሁን ገሠሠ ዘፈን ግጥሞች ጀርባ እንዳለ የምናውቅ ስንቶቻችን ነን?
ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ የተገኘ ሰው ደግሞ ይሄን በአይኑ አይቶ ያረጋግጣል፡፡ የታላቁ ጋዜጠኛ መቃብር ላይ የተቀመጠው ሃውልት ፈራርሷል፡፡ እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ሰዎች ድንገት ከመቃብራቸው ተነስተው ሁኔታውን ቢመለከቱ እንዴት ይታዘቡን?

በመጨረሻም

ትውልድ ይፈራረቃል፡፡ ትላንት በዛሬ ይተካል፡፡ ይሁንና ዛሬ በትላንት ውስጥ አለ፤ ወይም ትላንትን በዛሬ ውስጥ እናገኘዋለን፡፡ ህይወት እንደ ዱላ ቅብብሎሽ ነው፡፡ ትላንትን ካላከበርን፣ ላለፈው ትውልድ ቦታ ካልሰጠን፣ መጪው ትውልድም እኛን እንዳልተፈጠርን ሁሉ ይዘነጋናል፡፡ ማንን አርአያ ማድረግ እንዳለበት አያውቅም፤ ተነሳሽነት በውስጡ አይኖርም፡፡ ስለሀገሩ ሳይሆን ስለራሱ ብቻ የሚጨነቅ ትውልድ እየፈጠርን እንሄዳለን፡፡ ራዕዩ ከመብላትና ከመጠጣት፣ ቤት ከመስራትና መኪና ከመግዛት ያላለፈ ይሆናል፡፡
አበበ ቢቂላን ሳናከብር ሌላ አበበ ቢቂላ ልናገኝ አንችልም፤ ጥላሁን ገሠሠን ዘንግተን ሌላ ጥላሁንን መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡ ፈረንጆቹ ከዕድገታቸውና ከስልጣኔያቸው ጀርባ ያለፈው ትውልድ እንዳለ ይገነዘባሉ፡፡ ላለፈው ትውልድ ክብር መስጠታቸው ለአሁኑ ትውልድ ትልቅ መነሳሳትን እንደሚፈጥር ያውቃሉ፡፡


በኢብራሂም መሀመድ መዝገብ ተከሰው ከነበሩት 6 ቱ ላይ የቅጣት ወሳኔ ተላላፈባቸው

0
0

(ቢቢኤን. ሐሙስ ጥቅምት 27/2007) ስኔ 27 አሚሩ ድምፃችን ይሰማ ጠርቶት በነበረው ሰላማዊ ተቃውሞ በግፍ ተይዘው ታስረው ከነበሩት ወንድሞች መካከል 5ቱ ጥቅምት 24 በዋለው ችሎት ያቀረቡት የመከላኬያ ምስክር በቂ ነው በማለት በነፃ ተሰናብተው የነበረ ሲሆን በተቀሩት 6 ት ተከሳሾችን ደሞ ጥፋተኞች ናቸው በማለት ለቅጣት ውሳኔ ለዛሬ መቅጠሩ ይታወሳል።
news
ፍርድ ቤቱም ዛሬ በዋለው ችሎ ፍርደ ገምደልነቱን በግልፅ ያሳየ የፍርድ ቤቱን ካንጋሮነት ያረጋገጠ አሳፋሪ የቅጣት ወሳኔ መስጠቱን ለማወቅ ተችሎዋል።የቅጣት ውሳኔ ከተላለፈባቸው 6ቱ ንፁሀን ሙስሊሞች መካከል 10ኛ ተከሳሽ ሲቀር በሌሎቹ ላይ 1 አመት ከ 3 ወር የፈረድ ሲሆን 10ኛ ተከሳሽ ላይ ግን የ1 አመት ከ5 ወር የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፋን ለቢቢኤን ምንጮች ገልፀዋል።

በሌላ ዜና የህዝበ ሙስሊሙ መፍቴ አፈላላጊ ኮሚቴዎች የመከላኬያ ምስክር በዛሬው እለትም ተደምጦ መዋሉን ታወቀ::

የሚሊዬን ኢትዬዺያውያን ሙስሊሞች ተወካይ የሆኑትና የሚሊዬን ኢትዬዺያውያንን ጥያቄ አንግበው በግፍ ለእስር የተዳረጉት የሳላም አንባሳደሮች የህዝበ ሙስሊሙ መፍቴ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ችሎት ዛሬ ቀጥሎ የዋለ ሲሆን መኪ መሀመድ በጭብጥ 11ና ሐይረዲን ከድር በጭብጥ 7 ለሰላም አንባሳደሮቹ የመከላኬያ ምስክር ሆነው ቀርበዋል።

የችሎቱ ቀዳሚ ምስክር የነበረው ወንድም መኪ መሀመድ በጭብጥ 11 የመሰከረ ሲሆን የመንግስት ታጣቂ ሀይሎች ወረሀ ሐምሌ 8 በአወሊያ ሊደርግ ታስቦ የነበረው የሰደቃና አንድነት ፕሮግራም ለማሰነዳት ሀምሌ 6 ምሽት ለፕሮግራሙ ዝግጅት ሲያደርጉ በነበሩት ንፁሀን ኢትዬዺያውያን ሙስሊሞች ላይ የወሰዱትን አስከፊ እርምጃና የፈፀሙትን መንግስታዊ ሽብር አስመልክቶ ለፍርድ ቤቱ ሰፍ ያለ ማብራሬያ ሰጥተዋል።መንግስት በእለቱ ሊደረግ የነበረው የሰደቃና አንድነት ፕሮግራም ለማደናቀፍ ሆን ብሎ በማሴር ያሰማራቸው የመንግስት ታጣቂ ሀይሎች የተከበረውን የምእመናን መስገጃና ፀሎት ማድረጌያ የሆነውን መስጂድ በመድፍር በንፁሀን ሙስሊሞች ላይ ከባድ የሆነ አካላዊም ስነ ልቦናዊም አደጋ ማድረሳቸውንም ጨምሮ ገልፆዋል በእለቱም በርካቶች የተደበደቡ እንደ ነበሩ በመግለፅ በተለይም በአሁኑ ሳአት ከህዝበ ሙስሊሙ መፍቴ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ጋ በግፍ በሀሰት ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የአወሊያ ተማሪና የካውንስል አባል ወንድም ሙባረክ አደምንና ሌላኛውን ወንድማችንን ሀለዲ ኢብራሂምን ከፍተኛ ድብደባ እንዳደረሱባቸውም ለፍርድ ቤቱ የዛሬው ምስክር የነበረው ወንድም መኪ መሀመድ ገልፆዋልዩ።በአጣቃላይ ሀምሌ 6 ምሽት አወሊያ ላይ የመንግስት ታጣቂ ሀይሎች ሲፈፅሙት የነበረው በደልና ግፍ ከገደብ ያለፈና እጅግ ሰባአዊነት የጎደለው ተግባር ሲፈፅሙ እንደ ነበረ ምስክሩ ጨምሮ ገልፆዋል።

በእለቱ ችሎት ለሰላም አንባሳደሮቹ ሁለተኛ ምስክር ሆኖ የቀረበው ወንድም ሐይረዲን ከድር የነበረ ሲሆን በጭብጥ 7 ላይ መንግስት ሙስሊሙ መሀበረሰብ አንስቶዋቸው በነበሩት 3 ህጋዊና ህገ መንግስታዊ ጥያቄዎች ላይ ምን ያክል ጣልቃ ይገባ እንደነበረና በተለይም መስከረም 27 2004 ሊደረግ በነበረው ምርጫ ላይ መንግስት ሲያደርገው የነበረውን ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት አስመልክቶ ሰፋ ያለ ማብራሬያ ለድርድ ቤቱ ሰጥተዋል።በተለይም የመስከረም ወሩ ምርጫ ከመካሄዱ አስቀድሞ በተለያዩ የአዲስ አበባ ወረዳዎች ላይ ምርጫውን አስነልክቶ ስብሰባዎች ይካሄዱ እንደነበረ የገለፁት ምስክር በስብሰባዎቹ ላይ በሚሊዬን ኢትዬዺያውያን ሙስሊሞች የተመረጡትን የህዝበ ሙስሊሙን መፍቴ አፈለሰላጊ ኮሚቴዎችን ስም የማጥፋት ዘመቻ ማድረግና በተለይም ሙስሊሙ ማሀበረስብ ምርጫው እንዲካሄድ የጠየቀው መስጂድ መሆኑን ተከትሎ መንግስት የራሱን የግል አላማውን ለማሳካት በማሰብ ምርጫው መካሄድ ያለበት በቀበሌ ነው ሲል በተወካዬቹ በወረዳው ስራ አሰፈፃሚዎች በኩል ጫና ያሳድር እንደነበረም ምስክሩ ለፍርድ ቤቱ ጨምሮ ገልፀዋል። የእለቱ ችሎት በዚሁ የተጠናቀቀ ሲሆን የእለቱ ምስክር የነበሩት ወንድሞች ከሁለቱም የህግ ባለሞያዎች ለተነሱላቸው ዋናና መስቀለኛ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ በመስጠት አሰገራሚ የመከላኬያ ምስክርነት ቃለቸውን ሰጥተዋል::

በእለቱ ከነዚ ሁለቱ ምስክሮቻ ጋ ለመመስከር ፍርድ ቤት ቀርበው የመበሩት ሁሴን ጣሂርና ሀይሪያ ሁሴን እነሱ ሊመሰክሩት የነበረው ጭብጥ ቀደም ሲል በመሰከሩት ምስክሮች ተገቢ በሆነ ሆኔታ በመብራራቱ የተከሳሽ ጠበቆች ገልፀው ቀሪዎቹ እንዲሰናበቱላቸው ጠይቀዋል በጠየቁትም መሰረት ሁለቱ ምስክሮቻችን በበቂ እንዲሰናበቱ ተደርጎዋል።
ህዝበ ሙስሊም ዛሬም እንደተለመድው ችሎት በመገኝት በመገኝት ለወካላቸው ንፁሀን መሪዎች ያለውን አጋርነት ገልፆዋል ችሎት በዚሁ የተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪ የሰላም አንባሳደሮ የመከላኬያ ምስከር ለመስማል ለነገ ለአርብ ለጥቅምት 28/2007. ተቀጥሮዋል::
ነገም በሚኖረው ችሎት ህዝበ ሙስሊሙ የተለመደውን አጋርነቱን ይገልፃል ተብሎም ይጠበቃል

ሰሞኑን በጋምቤላ በተከስተው ግጭት 60 የሞቱ ; 36 የተሰደዱ; 4 የደረሱበት ያልታወቀና 23 የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ዝርዝር

0
0

የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች የአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ሰመጉ ባወጣው 132ኛ ልዩ መግለጫ በክልሉ በመንገሽና ጎደሬ ወረዳዎች ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የተገደሉ የ60 ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል። ዝርዝሩን ይመልከቱ
gambela

gambela 2

gambela 3

የማለዳ ወግ …በገዥው ኢ.ህ.አ.ዴ.ን.ግ / ደ.ህ.ዴ. ን ክብረ በዓል ! (ነቢዩ ሲራክ)

0
0
የማለዳ ወግ … በገዥው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ  / ደ.ህ.ዴ.ን ክብረ በዓል  !በገዥው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ክንፍ የደ.ህ.ዴ.ን ፖለቲካ ፖርቲ አባላት ወዳጆቸ ባደረጉልኝ ግብዣ መሰረት በደ.ህ.ዴ.ንን 22ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ተገኝቸ ነበር ።  እንደ ዛሬው የደ.ህ.ዴ.ን በዓል ፍሪዳ ተጥሎ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ድርጅቶች የልደት በዓላቸውን ሲያከብሩ እግር ጥሎኝ ስገኝ በምባረርበት የጅዳ ቆንስል ግቢ በሚገኘው የኮሚኒቲ አዳራሽ ተገኝቸም ኬክ እስኪቆረስና ሙዚቃው እስኪጀመር ያለውን ፕሮግራም ተከታትያለሁ። በልደት ፕሮግራሙ በቀረበው የድርጅቱ የትግልጉዞ “የስምጥ ሸለቆው ታጋዮች ” የሚል ስያሜ የተሰጠውን የደቡብ የነጻነት ታጋዮች ከህወሃት ጋር ተቀዳጅተው በቅድመ ደርግ ያደረጉትን ትግል ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር  የሰማሁት። በትግሉ ሂደት 57 ብሄረሰብን ይወክላሉ የተባሉት 22 ድርጅቶች አንድ ሆነው ደ.ህ.ዴ.ንን ብለው  አንድ ግንባር መስርተው ለልማት ያደረጉትንም ፋና ወጊ የተባለ ሂደት ሃገሬው ባንድ ድምጽ ባንስማማበትም በቀረበው የበዓሉ መግለጫ ተሞካሽቶ ቀርቦም ነበር  ።
unnamed (1)
እንዲህ እያለ የቀጠለው መግለጫ በስደቲ እንፈ አሸን የፈሉት የፖለቲካ ድርጅቶች መኖርና እንቅስቃያቸው በዜጎች መብት ማስከበር ዙሪያ እርባና ያለው ለውጥ ስላላመጣ የተባለውን ዲስኩር በማዳመጡ ባልሳብም  ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ  / ደ.ህ.ዴ.ን የሳውዲውን ስደተኛ መከራ ለመቅረፍ ስላደረገው ጥረት መስማት እንደጓጓሁ በሪፖርቱ የተጠቀሰ  ነገር ባለመኖሩ አልተደሰትኩም። በዚህ ረገድ  ” ለህዝብ ቆምኩ ” የሚለው ድርጅት ለቆመለት ህዝብ አካል ለሆነው  ስደተኛ ዜጋ መብት ማስጠበቅ አልተጋም ብየ ለምሞግተው ዜጋ በስደት በዓሉን የሚያከብረው  ድርጅት ዲስኩር መረጃ አልሰጠኝምና ላወግዝ ፣ ልቃወመው አልልም ። ድርጅቱ በበዓሉ ያሻውን ማለት መብቱ የተጠበቀ እንደመሆኑ እኔም እንደ ዜጋ የሚሰማኝን የመናገር መብቴን ተጠቅሜ የተሰማኝን እንዲህ እጦምራለሁ  ! ፈራጁ ታዳሚው ብቻ ነውና …  !በድግሱ ቁርጡን ጨምሮ ያማረ ምግብ ቀርቦ ፣ በዓሉ በአባላቱ ደምቆ ከሚከበርበት አዳራሹ ሳልወጣ ” ዘንድሮ የአቋም ለውጥ እያመጣህ ነው ፣ ትናንት በአሰራሩ ትኮንነው የነበረውን ቆንስል መስሪያ ቤት የፓስፖርት እድሳት ማስታወቂያ በፊስ ቡክህ መልካም ጅምር ነው በማለት እያሞካሸህ የምትጽፍና የታደሰውን ፖስፖርት ዝርዝር የምታወጣው ጋዜጠኛ ሆነሃል፣ ይባስ ብሎ ዛሬ ደግሞ  ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ  / ደ.ህ.ዴ.ን በዓል ተጋዥ መሆንህ ተገለባባጭ መሆንክን እያሳየን ነው ” ያሉኝ የኮሚኒቲ ሹሞች ሱፍ ባይደርቡበትም ከሸሚዛቸው ላይ ከረባቷን ጣል አድርገዋል፣ አንዳንዶቹ ደግሞ የዘወትር ልብሳቸውን እንደለበሱ በአሉን እንደኔው ለመከታተል ታድመዋል ። የኢህአዴግ ድርጅቶች በስደት ያለውን የነዋሪ ጩኽትና መከራ በቅረብ እተመለከታችሁ መፍትሔ ስለማታመጡ አልደግፋችሁም ፣ በሚል የሰላ ሂስ በማቅረብ የምሞግታቸው በውይይት የሚያምኑት ግን ለውጥ ማምጣት አልቻሉም የምላቸው ስልጡን የድርጅት አባላት ወዳጆቸም በዓሉን ለማድመቅ ያማረ ሱፍና ከረባታቸውን ቦጫ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ  / ደ.ህ.ዴ.ን አርማ ያለበት ቢጫ ኮሪያቸውን ደንቅረው ሲያሰተናግዱና ሲስተናገዱ አምሽተዋል። ” ከምንም በላይ የዜጎችን መብት ማስቀደሙ ይቅደም!”  ለምለውና በግል በዘር ለማላምነው ዜጋ የድርጅቱ አባላት ወዳጆቸ ” በሳውዲ ስደተኛ ህይወት ዙሪያ መሻሻልና መብት መጠበቅ ተግተን እንሰራለን! ” ስለሚሉን ስራ በበዓላቸው ማዘከሪያ በቀረበው ሪፖርት አለመገለጹን እንዴት እንደሚያዩት የምሰማው ግን ነገ ከነገ ወዲያ ይሆናል  …
እዚህ ላይ አንድ አፍታም ቢሆን መንፈሴን ስላወከውና ስላልተቀበልኩት ጉዳይ ልጠቁም … ከ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ  / ደ.ህ.ዴ.ን ድርጅት  የትግል ሂደት ማስተዋወቂያ ሪፖርት ቀጥሎ በመድረኩ አስተዋዋቂ በአቶ ሰመሩ ርቱዕ አንደበት ተቀሽራ በቀረበች አንድ ግጥም በደቡብ ከታቀፉ ብሔረሰቦች መካከል አንዳንዶቹ ተጠቅሰው በቅድመ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ አገዛዝ ” ቀጥቃጭ” እና “ሸማኔ ” እየተባሉ እንደተጨቆኑና እንደተገፉ በአጽንኦት ተገልጿል። ግጥሟ በተስጎድጓጅ ድምጽ በመነበቧ፣ ስንኝ በመምታቷና በተከሸነ ቋንቋ ከመቅረቧ ባሻገር በጥላቻ የታመቀች ጥበብ ነበረችና አልወደድኳትም። ቢያንስ በዚህ የልደት በዓል ባልቀረበች ብያለሁ …ራሴ ለራሴ  !
ከግጥሙ ቀጥሎ በዓሉን ለማድመቅ ሙዚቃና ዳንኪራው ጀመረ ፣ ዲፕሎማቶችን ጨምሮ የድርጅቱ አባላትና ተጋባዦች መድረኩን ተቆጣጠሩት ፣ መድረኩ ሞቅ ሞቅ ሲል ጠሪዎችን አመስግኘ ወደ ቤቴ ስመለስ አንድን ሰሞነኛ ጉዳይ እያውጠነጠንኩ ነበር።  “አቋምህን ትቀያይራለህ ” ስለተባልኩበት ወቀሳ ፣ ከድርጅት አባላቱ ጋር የስደተኛውን ህይወት ታደጉት በሚል ስለማደርገው ሙግት ምክክርና ውይይት ፣ ከልታማውን የጅዳ ኮሚኒቲ “ከማህበረሰቡ ወደ መንግስት ይዞታ ይቀይረዋል ” ተብሎ ስጋት ስለማንዣበቡና በዚያ ዙሪያ ያለኝን ጭብጥ መረጃ በማለዳ ወጌ ለመዳሰስ ነበርሸማሰላሰሌ   ! አዎ የስደተኛው ጉዳይን የሚመለከት ማንኛውኛውም ጉዳይ ያገባኛልና አቅሜ በፈቀደ መጠን እዳስሰዋለሁ ! የስደተኛው ጉዳት ያገባኛልና ዛሬም እጦምራለሁ  !ሰላምነቢዩ ሲራክ

የሰላም ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ ታሰረ

0
0

ነገረ ኢትዮጵያ 

10624743_609169355875393_2834013995865368265_nተቃዋሚ ፓርቲዎችን በማስተባበርና በማቀራረብ እርቅ ለማስፈን እንደሚንቀሳቀስ የሚነገርለት የመግባባት፣ አንድነትና ሰላም (ሰላም) ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ መታሰሩን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ አቶ ፋንታሁን የታሰረው ‹‹የሰላም ጥሪ›› በሚል ነጭ ሰንደቅ አላማ በማውረብለብና የማህበሩን አላማ የሚገልጹ፣ እንዲሁም ማህበሩ በአሁኑ ወቅት ለአገሪቱ ችግር የሚላቸውን ጉዳዮች በዝርዝር የያዘ በራሪ ወረቀት ለህዝብ በመበተን ማህበሩን በማስተዋወቅ ላይ በነበረበት ጊዜ እንደሆነ ታውቋል፡፡

በራሪ ወረቀቱ የህሊና እስረኞች መፈታት እንዳለባቸው፣ መንግስት በሀይማኖቶች ላይ ጣልቃ መግባት እንደሌለበት፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ዜጎችን ማፈናቀሉ እንዲቆምና መንግስት በተቋማት ላይ ከሚያደርገው ጣልቃ ገብነት እንዲቆጠብ የሚመክሩ ሀሳቦች እንዳሉበት ለማወቅ ተችሏል፡፡

ነጭ ሰንደቅ አላማ ሲያውረበልብ፣ የማህበሩን አላማና በህዝብ ላይ አሉ ያላቸውን ችግሮች ለህዝብ ሲያስተዋወቅ የተያዘው አቶ ፋንታሁን ህዝብን ለማነሳሳትና አመጽ ለመቀስቀስ ሙከራ በማድረግ በሚል እንደተከሰሰም ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

አቶ ፋንታሁን እሁድ ጥቅምት 23 ሽሮ ሜዳ አካባቢ በራሪ ወረቀት ሲበትን ተይዞ ላዛሪስት በሚባለው ፖሊስ ጣቢያ ታስ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

አሽካካች …. (ሥርጉተ ሥላሴ)

0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 07.11.2014 (ሲዊዘርላንድ ዙሪክ)

ጨረሯ ብቻ ደረሰኝ። ምን ደረሰኝ ብቻ አዳረሰኝ። እሷ ግን አትታይም። ስብሰባ ትሆንን? ወይንስ ሰማያዊ አልጋዋ ላይ ተኝታ … ወይንስ ጫጉላ ጊዜ ላይ ትሆን ወይንስ ከባዘቶማዋ ፍራሽ ተኮፍሳ? ክብር ሲወድላት — ደግሞም ሲያምርባት የለችም። ብቻ የለችም። ግን አለች ትንፋሿ ሀገር ያዳርሳል። መንፈሷ ይሆን የሌለው?  ይሆናል። ምን ይሆናል ነው እንጂ። ግን ለምን? … እእ … ለምን …. እ … „ለምን …?“

Sirgutጠብቅኳት አልመጣችም። ለእኔ ለእራሱ የላከችው ለብ ያለ ጉድ ነው። ልም ነገር። ስትገርም። ለእናንተስ ይሄው የእኔ ዕጣ ፈንታ ደረሳችሁ ይሆን? … አላውቅም። ቀና ብዬ ፈራ ተባ እያልኩ ተመለከትኳት … ነገ ሌላ ቀን ነው   አሃ! ብላ ጽፋለች።

ቀና ብዬ ስመለከት ደግሞ ይህም ያልፋል  ብላ ጽፋላች? ጎሽ! አልኩና ተረጋጋሁ። ግን ለምን? አላውቅም። ለመሆኑ ያነብበኩትን እርግጠኛ ነውን? ነገ ሌላ ቀን ነው ብላ ስለመጻፏ እንደ ገና አዎን እንደ ገና አሻቅቤና ሻቅዬ*  ሳዬው ተለውጦ …„የማይቻለውንም መከራ ቢሆን በትእግስት ቻይው ብላ ጽፋልኛለች። ወይ ጉዴ ግን … ለምን? አላውቅም። ዝቅ ብዬ እንደ ገና … አዎና እንደ ገና ተመለከትኩኝ።

ከመከራው በስተጀርባ ክብር አለ በማለት ደግማ ጽፋለች። ምን ማለት ነው ይሄ ደግሞ?  እሷን ብሎ ትንቢተኛ፤ እሷን ብሎ ስለነገ ራዕይ ተንታኝ – በታኝ … ከደንቀራው ጋር ስትደልቅ ከርማ ብዬ ላኮራፋት ዳዴ ስልላችሁ በአንድ አቅጣጫ የላከችው ጨረር ተባዛ …ሳቀይንስ ተደመረ …   ተዳምሮ ተባዛና ተነሰራፋ … ሞቅ አንደ ማለት ዳዳኝ። በጨረሮቹ ልክ የተደረደሩ ትዕይንታዊ ስንኞች ኪነን አንግበው ይታዬኛል። ጠጋ ብዬ ልዳስሳቸው ስል በቅጽበት – ቅጽበት ሆነው እርፍ። … ግን እንደ ገና ተፃፈ። መነጠሬን ከኮሮጆዬ አወጣሁና በጥደፊያ ተያያዝኩት …

አንዱ ምን ይል መሰላችሁ … ወይ ጉድድድድድ …!የጨለማ ፀሐይ  ይላል። እ! አልኩኝ … ምን ማለት ይሆን ይሄ? —————ብዬ ሳመናታ እራሱን ቀዬር አድርጎ ፈታልኝ  ህልም ሲል … አህ! ብዬ ልቤን አዳመጥኩት። አሁን ወደ ቀጣዩ መልዕክት        መሄድ እንደለብኝ ህሊናዬ ማስታወሻ ቢጤ ጫር ጫር አድርጎ ላከልኝ። ቀጣዩ … የሰማይ ቤት  ሸንጎ  የሚል መጣልኝ። ሃሃ! አልኩኝ።  ይህ ደግሞ ምን ይሆን? ብዬ ሳመናታ ሌላ አንድ በአንድ ዘርዘር እያለ ጠብታ ከች አለ ሳገጣጥመው

የሞት አደባባይ ብሎ ቁጭ። ውይ? ይሄም ደግሞ አለ? በጣም ፈራሁ። ጨነቀኝ። ተዘንፈዘፍኩ – ስላችሁ።አይጣል? መነጠሬን ለማውለቅ ስታገል … እሱ ደግሞ ለካስ ከዓይኔ ላይ ስበት ተፈጥሮለት አሻም እንዳለ ተሰክቶ ቅርት። ሲያናድድ። ተናዳደዱ እባካችሁ ከእኔው ጋር። ማስቲካ! ….ቀጥይ ማለቱ እንደሆነም ገባኝ። በምልክት ቋንቋ … በቃ አሸከረከረኝ እንደ – ዛቢያ። ገና እኮ ነኝ ወደ ሁለተኛው ጨረር አልሄድኩም። መዳህ ታውቃላችሁ ዝም ብሎ ታቱ …ዥግራ … ከወፌ ቆመች ያልተደረሰ … ብልጭ ድርግም በሐመራዊነት … አንተ ደግሞ ምን ልትል ይሆን ብዬ ዳጥም – ላጥም ይዞ ሊፈጠርቀኝ ግብግብ ስገጥምላችሁ …. አምካላችሁ አለ ሰውነቴ የማለውቀው ሆነብኝ። ዖዬ! እኔ ወይንስ ሌላ .. ህም ተስፋ ይለመልማል  አይልም መሰላችሁ። ወህ! ተመስገን አልኩኝ። ይሄስ ምን ትርጉም ያስፈልገዋል ብዬላችሁ ወደ ሶስተኛው ጨረር ላዘግም ስሰናዳ  ውልብልቢቴን ጨምድዶ ያዝ አደረገና … ተስፋ ይጎድላል  አለኛ! እቴ የምን ጭንጫ ነገር ነው የኳተ …መጀመር እንጂ ፍጻሜ የሌለው ሕይወት … የራስህ ጉዳይ ነው ፈንግጠው! ብዬ ቀጨር መጨሬን ሰባስቤ ስሰናዳ … ያለዬለት የነበረው ቀለም እዬነጠረ እዬነጠረ መውጣት ጀመረ

… አረንጓዴ ~ ቢጫ ~ ቀይ! ዋው፡~! እንኳንም ለሀገሬ አፈር አበቃህኝ ብዬ ጠላታችሁ ድፍት ይበልና ፍግም ብዬ መሬቱን ልስም ስል  አትቸኩይ! የሀገርሽ ጉድ ገና ነው።  የሚል መልእክት በስተጀርባዬ …. ደለቀ። ቁጣም ግልምጫም ድንፋታም ተዘልለው – ህም!… አንኳኳ …. እህ አልኩኝና ደግሞ ምን ቀረ ከማርያም መቀነት ወዲያ ስል አራተኛው ጨረር ፊት ለፊቴ በራልኝ … ሰንደቁ በእግር ብረት ታስሯል   የሚል መልዕክት ፃፈ … ደሜ ሲንተከተክ ተሰማኝና … እኮ እንዴት?! ስል በድፍረት ያነን የተላከልኝን አራተኛ ጨረር አፋጠጥኩት … አሻቅቤ እያዬሁ በድፈርትና – በወመኔ ቁጣ፤ ፈንግጪው እንዳይለኝ ግን ስሜቴ ተክ — ተክ —- ትር —– ትር —- ብን —- ብን ሲል ነጋሪት ይጎስማል … እንቅልፋም“  ተብሎ ተጻፍልኝ።

ይህችን ትወዳላች ኧረ እኔ ነኝን እንጉልቻም? ብዬ ያነኑ አራተኛ ጨረር —– ላጣድፈው ፈራ ተባ ስል …. እኔ ትልቁ ችግሬ እንቅልፍ ማጣት ነው። መቼ ተኝቼ የማውቀውን ነው … ይህቺ ብዕር የሚሏት ቀለማም አድብታ ሳለች ነጋ ጠባ ከእርሷ ጋር ነኝ … እያልኩ ስብተከተክ አምሰተኛው ጨረር ከች አለ።ከዚህስ ወዲያ! … ¡¡¡“  የሚል በቃለ ስላቅ በትዝበት የቆዘመ ስንኝ ብቅ ጥልቅ እያለ አቅሌን መፈናፈኛ ነሳት። ወይ አይጸድቅ ወይ አይነቀል። ወቼ ጉድ አልኩኝ። ማለት ነበረብኝ። ኧረ ባበቃልኝና ግልግል በሆነ ስል ተተካ ተረኛው፤ ትራስሽ ምን ግዴ ነው  ተባለኩኝ። ህም! እሺ ምን ልሁን? ምንስ ላድርግ? ይነገረኝ እያልኩ ወኔዬ ገፍትሮኝ እዬተለማማጥኩኝ ስንተባተብ ስድስተኛው ጨረር አደብበሆደ ሰፊነት- ይመስጠር። ሲል ውሽክ ብሎ ፈታልኝ።

በተፈጥሮዬ ጮኽ ብሎ መነገር አይሆንልኝ። ግጥሜ አይደለም። ፊታውራሪ በር እንኳን ከልጅነት እስከ እውቀት አንድ ቀን  ሰለቀችኝ – ቡጢዋን እልቻልኩትም ብሎ ችሎት ገትሮኝ አያውቅ፤ እንደተመሰጋገን ይሄው አለን። ግን ነገር ግን የአሁን አቤቱታ ቁሮ እንጂ የእኔ ማንነት አይደለም እያልኩ ብቻዬን እያወጋሁ እጄን ከግራ ወደ ቀኝ … ከቀኝ ወደ ግራ ሳወራጭ — ላችሁ … መንፈሴ መሳሪያውን ሲያቀባበል – ልተኩስ — ተሰማኝ … „ዛሬ! ዛሬ! ዛሬ! ቁረጭ – ምረጭ! ለህዝብ ጠቀም ተግባር ሰባራ ሰንጣራን ከባህር ከገደል ጠቅልለሽ ከነዲሪቶው ጣይ … በይ! በይ!“ በማለት ወጥሮ ሰንጎ ለምን አይዘኝም መሰላችሁ።

እሺ ምን ልሁን ? ፈወስምንድን ላድርግ?“ እያልኩ እጅግ በሚያባብል በቁልምጫ ህሊናን ዘና አድርጎ የጫጉላ ሽርሽር በሠረገላ ፈሰስ – ፈርሰስ በሚያደርግ ድምጽ ትህትናን አጋብቼ በክብር አሽሞንሙኜ ቀና አልኩ። አዎን በተጠንቀቅም ጸጥ ረጭ ብዬ ቆምኩኝ። እንደባንዴራው። ከዛ አዎን ከዛማ ሰባተኛውን ጨረር ተላከ። እንዲህም ይላል፤ በጉልህም ኮቢውም ብራናውም ፈቅደውለት ተጥፏል። ይበል …   የተግባር ስንቅና ትጥቅ ይኑርሽ በማለት የጉዳዩን አናት በዕለተ ሰንበት ጸበሉን ትእዛዝ አሳወቀችኝ። ይሁን! እሺ! ብዬ ልሰግድ ጎንበስ ስል እርገት ወረደ … ሰባቱም በአኃቲ ድምጽ … ቁረጪ! ትውልዳዊ ድርሻሽን ለመወጣት   ብለው ሲናገሩ … በእነሱ ቅኔዊ – ቃናዊ ድምጽ መጉላት ጉልበታምነት መሰለኝ … ከዙፋኗ ብቅ አለችና ብርኃኗን በመቁንን ሰደድ አደረገችልኝ። „እንዴት ነው ነገሩ ለብም አለደረገኝ። ከአንጀቴም አልደረሰም የብርኃን እናት ክብርት ልዕልተይ — ስላት …“—በተስተካከለ ሙላት ለመኖር ሆኖ መገኘትበማለት ከልቧ አዎን ክልቧ  …. አ – ሽ – ካ – ካ – ች

በመጨረሻ ትናንት 06.111.2014 ምን አስቦ ምን እንደከወነ በጸጋዬ ራዲዮ ፕሮግራም ማወቅን ትሻላችሁን? እንግዲያውስ www.lora.ch. Aktuelle Sendung Radio Tsegaye ያዳምጡ ዘንድ በአክብሮት አሳስባለሁ። ለውዶቼ – የእኔዎቹ  መሸቢያ ሰንበት።

 

አድርገህልኛልና ለዘላለም አመስግንሃለሁ።”

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

የእስክንድር ውዱ የልደት ቀን ስጦታ!

0
0

ከጌታቸው ሽፈራው

በጠዋት ቂሊንጦ (ሁለት ቦታ ተከፍለን) እነ ኃብታሙን፣ የሽዋስን፣ አብርሃን፣ በፍቄን፣ አጥናፍንና ሌሎችንም ከጠየቅን በኋላ ለ30 ደቂቃ ብቻ እንዲጠየቁ ‹‹የተፈቀደላቸውን›› እነ እስክንድር፣ አንዱ ዓለምና መላኩ ተፈራ (የአንድነት አባል የነበሩ) ለመጠየቅ ወደ ቃቲ አቅንተን ነበር፡፡ በተለይ እስክንድር ወደዚች አለም የመጣባት ቀን ስለሆነች ከእሱ ጋር ትንሽም ጊዜም ቢሆም ማሳለፍ ፈልገን ነው ወደቃሊቲ ያቀናነው፡፡
Eskinder Nega
እስክንድር የተወለደበትን ቀን አስታውሰን ወደ ቃሊቲ መሄዳችንን አመስግኖ ሌላ ቦታ ላይ በእስር ስለሚገኙት፣ ውጭ ስላለው ጉዳይ በአጠቃላይም በአገራዊ ጉዳይ ላይ አስተያየት ወደ መስጠት ገባ፡፡ ከቆይታ በኋላ በአንድ የአፍሪካ ጉዳይ ላይ መረጃ መስማት አለመስማቱን ጠየቅነው፡፡ ዋናው ደግሞ የቡርኪናፋሶ ጉዳይ ነው፡፡
‹‹ቡርኪናፋሶዎች አምባገነናቸውን አስወገዱ፡፡›› ስለው በጣም በደስታ ‹‹እውነት!›› አለኝ፡፡

አዎ! ‹‹ኮምፓወሬን በአንድ ቀን ተቃውሞ ከስልጣን አስወገዱት፡፡ ስለው አላስጨረሰኝም፡፡

‹‹ኮምፓዎሬን?!›› እስክንድር አላመነም!

ወደቃሊቲ ስናቀና እስክንድር ሁሌም የሚቀበለን በፈገግታ ነው፡፡ የሚሸኘንም እንዲሁ በፈገግታ! እኛን ለማበረታታት ሲጥር እሱ የታሰረ አይመስልም፡፡ እሱ ሁሌም ደስተኛ ነው፡፡ የዛሬው ደስታው ግን በእጅጉ ይለያል፡፡

‹‹ኮምፓዎሬን?!››

‹‹ብራቮ! ብራቮ! ብራቮ! ብራቮ!….›› ሁለቱንም እጆቹን ጨብጦ ወደ ላይ ዘለለ፡፡ የእስክንድር ነጋ ደስታ እኔንም፣ ከጎኑ ቆሞ የምንለው የሚያዳምጠውን ፖሊስ እስክንድርን በአድናቆት ከማየት ውጭ ምንም ማለት አልቻልንም፡፡

እስክንድርን በልደቱ ቀን ለትንሽ ጊዜም ቢሆን አብረን ከመቆየት ውጭ ምንም አላደረግንለትም፡፡ እሱ ግን ትልቅ ስጦታ ሰጥታችሁኛል አለ፡፡ የኮምፓዎሬን ውድቀት ስላሰማነው፡፡

‹‹በእውነት ይህ ለእኔ ውድ የልደት ቀን ስጦታዬ ነው፡፡ በጣም ትልቁ የልደት ቀን ስጦታዬ!›› እስክንድር ያች አጭር ጊዜ አለቀች ተብሎ ሲመለስም ሁላችንን ያመሰገነው ስላበረከትንለት ትልቁ የልደት ቀን ስጦታው ነው፡፡ ስለ ቡርኪናፋሶው አምባገነን ውድቀት፡፡

“የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ”

0
0

አገሬ (ከስዊድን)፣ 2014-11-05
ይህን ፅሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ ዋናው ምክንያት በድረ-ገጽ ላይ ”ፕሮፌሰር መስፍንን ለቀቅ” በሚል ርዕስ በአቶ አንተነህ መርዕድ የተፃፈው ”አገም ጠቀም” የሆነና ሚዛናዊነት የጎደለው መጣጥፍ ከመቸውም በበለጠ ስለከነከነኝ ነው።
Pro Mesfin
አቶ አንተነህ እንዳሉት አንደኛ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አይደለም ለራሳቸው፣ ለሌላም የሚተርፍ አንደበት አላቸውና ራሳቸው መልስ ይስጡ በማለ፤ ሁለተኛ ትልልቅ አገራዊ ጉዳይ እያለ በዚህ ጠባብ ነገር መጠመድ ለማን ይበጃል በሚል ቢተውት የተመረጠ ነበር። ነገር ግን ያን በማለታቸው ልክ አለመሆናቸውን አምነውበት ለንባብ ያበቁት መጣጥፍ ለፕሮፌሰር መስፍን ለመወገን ሲሉ ብቻ የአማራውን ነገድ «አለ ወይስ የለም?» ማለት እንደማይረባ ጉዳይ ቆጥረውታል። ነገር ግን በተለይ በአሁኑ ሰዓት አማራ እንደሰባዊ ፍጡር ሳይቆጠር ደመከልብ ሆኖ አጥንቱን ከስክሶ ደሙን አፍስሶ ባቆማት አገር እንዳይኖር በሚደረግበት ወቅት ”እንቶ ፈንቶ” ሲሉ ማጣጣል ትልቅ ስህተት ይመስለኛል።

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ባቋቋሙት «የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብት ጉባኤ (ኢሰመጉ)»፣ እርሰዎ እንደሚሉትና የኢትዮጵያም ህዝብ ተረድቶት እንደነበረው በወያኔ አገዛዝ ለሚደርሰው ገፍና በደል አለኝታ ለመሆን አልነበረም። ይልቁንም ከፕሮፌሰር መስፍን ከአንደበታቸው እንደሰማነው ከሆነ ኢሰመጉን ያቋቋሙት ወያኔን ለመርዳት መሆኑን ሰለሰማን የርስዎ የመከራከሪያ ነጥብ ”ከባለቤት ያወቀ ቡዳ ነው” የሚሉት አይነት ይሆንብዎታል። አቶ አንተነህ በውነቱ እርሰዎን ቅር ማሰኘትም ሆነ ፕሮፌሰር መስፍንን የመዝለፍ ሀሰብ በ አይምሮየ የለም ግን ፕሮፌሰር መስፍን የሚነግሩንና የሚሰሩት ነገር ካልተጣጣመ ቃልን ከተግባር በማጣጣም የምናስታርቀው ምን ብንል ነው፧ ፍርዱን ለርስዎ እተዋለሁ።

የአማራን ጉዳይ በተመለከተ አቶ አንተነህ እንደተረዱት ፕሮፌሰር መስፍን የወያኔውን መሪ መለስ ዜናዊን «አማራ የለም» ብለው «ዘረኝነት እንዳይስፋፋ አደረጉ» የሚል አስተያየትዎ እደተጠበቀ ሆኖ፣ እኔ ደግሞ ከአንድ ታዋቂ ግለሰብ መወቀስ ይበልጥ የኢትዮጵያ አገራችንና በህዝቧ ላይ የወደቀው የመከራ ቀንበር እጅጉን ያመኛል። ከወያኔ ወደ ስልጣን መምጣት ትንሽ ቀደም ብሎ ጀምሮ ያደረጓቸውን ድርጊቶች ላስታውስዎ፦

ፕሮፌሰር መስፍን እኤአ 1991ዓ.ም ለንደን ላይ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን በራሳቸው ፈቃድ ወክለው ከነወያኔና ከነኦነግ ጋር ተደራድረው ድጋፍ በመሆን አስገቡዋቸው።

የኢትዮጵያ ህዝብ «መጣብን» ብሎ የፈራውን የዘረኝነት አገዛዝ የተከበሩ ፕሮፌሰር መስፍን በግልፅ በአደባባይ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በተለይም አማራን እንደህዝብ ከሚጠላው የወያኔ መሪ ጋር በማነጋገራቸው ወያኔን እውቅና እንዲያገኝ አደረጉ።
ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ፣ የዘረኝነት አባዜ ይዟቸው ሳይሆን ተገደው፣ ለአማራ ህዝብ የተደገሰለት ድግስ አደገኛ መሆኑን ስለተረዱ ብቻ የኢትዮጵያን ህዝብ ያካተተ የአማራ ድርጅት (ተገደው በግድ በዘር መደራጀት ስለነበረባቸው ያለበለዚያ ግን እውቅና በወያኔ ስለተነፈጉ) ሲመሰርቱ አሁንም ፕሮፌሰር መስፍን በአማራ ላይ የሚፈፀመውን በደል ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው አማራ የሚባል ነገድ የለም በሚል ጎዳና ስለተሰለፉ ህዝቡ በተለይም አማራው በአንድ ልብ እንዳይቆም በደካማ ጎኑ ስለመጡበት ኢትዮጵያን እያለ ከተገንጣይና ካስገንጣይ ጉያ እንዳይወጣና ጠንክሮ እንዳይታገል እውቅናቸውን ተጠቅመው በሚያንፀባርቁት የተዛባ አስተሳሰብ ህዝብም አገራችንም ተጎድተዋል ።

የቅንጅት መሪዎች በፈጠሩት አለመግባባት የኢትዮጵያ ህዝብ ፕሮፌሰር መስፍን አስታራቂ ሀሳብ አምጠተው ቅራኔውን ይፈቱታል ተብለው ሲጠበቁ እሳቸው ለማንም የማይበጅ ምክር በመምከራቸው ህዝብ የሳቸውን ቃል ተከትሎ ቅንጅትን እንዳያንሰራራ አድርጎ አፈረሰ።

«አማራ የለም» ከማለት አልፈው «በአርባ ጉጉ የሞተው ኦሮሞ ነው» ማለታቸው ሟች በሌለበት ገዳይ አይኖርምና የአማራን ደም ደመከልብ እንዲሆን ትብብር አድርገዋል።
ለመሆኑ እኔ እንዲህ ብዬ እንደማስብና የዚህ አይነት ሀሳብ ያለን በሚሊዮን የምንቆጠር አማሮች መሆናችንን ቢረዱ ምን ይላሉ?

አቶ አንተነህ እርሰዎ እንዳሉት ፕሮፌሰር መስፍን «ትልቅ ሰው፣ አዋቂ፣ የተከበሩና የእድሜ ባለፀጋ» በሚለው ቃል እስማማለሁ። ነገር ግን «ደምመላሽ» የሚለው ቃል ሲወጣ አባባሉ ከቅንነት ይሆናል የሚል ግምት ቢኖረኝም የተጠና አልመሰለኝም። «ደምመላሽ» መሆኑ ቀርቶ የአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ አለመሆናቸውን ደሙ ደመ ከልብ ሁኖ አንዲቀር የተወሰነበት «የለህምና አልሞትክም» የሚሉት አማራ ይመሰክራል።

አቶ አንተነህ ስለ አቶ ተክሌና ስለእርስዎ ግንኙነት ሲፅፉ ” ….ብዙ ህዝብ በሚርመሰመስበት የደመቀ በአል መሃል የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት መሪ የሆኑትን አቶ ተክሌ የሻውን አገኘኋቸው። ደስ ብሎኝ ራሴን ካስተዋወቅሁ በኋላ በወጋችን መሃል በቅርቡ ከወጣው መግለጫቸው አምስት ገጽ እውነት ውስጥ ጨዋነት የጎደለው ስድብ ተገቢ እንዳልነበር ነገርኳቸው። የሰማሁት መልስና ለፕሮፌሰሩ ያላቸው ጥላቻ አስደነገጠኝ። ለአማራው ህዝብ መብት ቆሜያለሁ ብለው አደባባይ የወጡ እኒህ ሰው አንዱን ታላቅ ወገናቸውን በሰብዕናቸው ገብተው ሲዘልፉ መመልከት ዓላማቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ሆኖ አገኘሁት። ስልሳዎቹ ውስጥ የሚሆኑ እኒህ አዛውንት ሌላው በእድሜ፣ በእውቀትና በተመክሮ ለሚበልጧቸው ክቡር ሰው የሚሰጠውን የጨዋ አማራ ባህል ከውስጣቸው አላየሁም። ስለሆነም ውይይቴን ብቀጥል የበለጠ ህሊና የሚያቆስል ነገር እንደምሰማ በመገመት ተሰናበትኋቸው። ” ሲሉ አስነብበውናል።

አቶ ተክሌን ሲያገኙ ደስ መሰኘዎትን በዚህ አንቀፅ ቢገልፁም ከላይ በአንቀፅ 4 ላይ ደግሞ ”…የብዙዎችን ላቆየውና በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ካንድ ወገን የሚሰነዘረው ከባህላችን ውጭ የሆነ ዓላማው ግልጽ ያልሆነ ስድ በሚያሰኝ የመንገድ አዳሪ ቋንቋ የስድብ ውርጅብኝ በኒህ አዛውንት አባት ላይ ሲወርድባቸው ዝም ብሎ መመልከቱ ለህሊና ይከብዳል…” ሲሉ ቁጭትዎንና ቁጣዎትን ገልፀው ስለነበር አቶ ተክሌን ሲያገኙ የተደሰቱት ለምን እንደሆነ ለመረዳት አዋቂ መጠየቅ አያስፈልግም።

እንደርስዎ አገላለፅ አቶ ተክሌ በጥላቻ የተሞሉና ስነምግባር የጎደላቸው እንደሆኑ ተርከዋል። ለነገሩ አቶ ተክሌ ራሳቸውን መከላከል ስለሚችሉ አስፈላጊ ሆኖ ከታያቸው መልስ የሚሰጡበት ጉዳይ ይሆናል። ነገር ግን እኔን ያልገባኝ ነገር አቶ ተክሌ ጋር ስትነጋገሩ የተናገሩት ቃል አፀያፊ ከሆነ ቃላቶቹን በፅሁፍዎ ላይ በማስፈር መግለጫውን በተቹበት መልክ ቢያካትቱት የአንባቢውን የግንዛቤ አድማስ ስለሚያሰፉት አንባቢው በራሱ ሚዛን መዝኖ ለፍርድ በበቃ ነበር።
በተረፈ« በጥላቻ የተሞሉና ስነምግባር የጎደላቸው ስለሆኑ ለአማራው ህዝብ መቆማቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ሆኖ አገኘሁት» የሚለው ”ሾላ በደፈና” አባባልዎ፥ «ሞረሽ ወገኔ አላስፈላጊ ድርጅት ነው። አማራ መደራጀት የለበትም» ከማለት ተለይቶ አይታይም። ስድብ ነውር ከሆነ ነውር መሆን ያለበት ከተሳዳቢው አንደበት ሲወጣ እንጅ ተቀባዩ ላይ የሚያደርሰው ጫና ወይም የተሰዳቢው ማንነት ሚዛን ውስጥ እየተቀመጠ አለመሆኑን መዘንጋትዎ አስገርሞኛል። እንዲህ ለማለት ያበቃኝ ደግሞ እርስዎ ”ክደትና መሳት” የሚለውን ቃል በማስረጃነት በማቅረብ ያስነበበውን የሞረሽን መግለጫ ስድብ ካሉ በኋላ በአቶ ተክሌና በሞረሽ ላይ ”ስድ በሚያሰኝ” ”የመንደር አዳሪ ቋንቋ” በማለት አቶ ተክሌን «ስድ» ከማለት አልፎ የሞረሽ ወገኔን አባላትና ደጋፊ ሁሉ «የስድ ስብስብ» እንደማለት የስድብ ውርጅብኝ ሲያዘንቡ ውነቱን ተናገርኩ እንጅ አልተሳደብኩም ሊሉ ይሆን?
ለነገሩ «የወደቀ ግንድ ምሳር ይበዛበታል» ነውና የሚሞተው የሚሳደደው የሚፈናቀለው አማራ እንደ ህዝብ ከ34 ሚሊዮን በላይ ሲሆን፣ ያ ህዝብ ለሚደርስበት በደል ተጠያቂ እንኳዋን እንዳይኖር «የለህም» እያሉ አደባባይ ወጥተው የሚሞግቱት ፕሮፌሰር መስፍን ሳይወቀሱ፣ «የለም ማለት ስህተት ነው በደል የሚደርስበት ወገን ከተካደ በደል ፈፃሚ ነፃ ይሆናል» ያለውን ወገን ለማዳከም ብዕር ማንሳት የሚያሳዝን ክስተት ነው። ለነገሩ እርሰዎ የኢትዮጵያ ጀግኖች ብለው በፅሁፍዎ የደረደሩዋቸው ሁሉም ለኢትዮጵያ አንድነት የተሰለፉ ጀግኖች ናቸው ብየ ስለማላስብ የእርስዎም ሰልፍ ከወዴት እንደሆነ አልገባኝምና ልተወው።

ለማንኛውም እርስዎ ከፐሮፌሰር መስፍን በተለየ «አማራ» የሚባል ነገድ እንዳለና ያም ወገን የተለየ ግፍ እየተፈፀመበት እንደሆነ ውነቱን በመመስከርዎ አድናቆቴን ልቸርዎት እወዳለሁ። ምክንያቱም እርስዎ በፕሮፌሰር መስፍን ማንነትና ፍቅር ስለተሸነፉ፣ የሞረሽ ወገኔን መግለጫ በማጣጣልና «ፕሮፌሰርን በካሀዲነት ወነጀሉ» ብሎ የፕሮፌሰርን ስህተት ማደባበስ ብሎም ያላግባብ ደሙ የሚፈስ ወገን እንዳለ ማመን የተሳነውን ሰው «ደምመላሽ» በማለት ማሞካሸትዎ እንዳለ ሁኖ፣ «በፕሮፌሰር ተፃራሪ አማራ አለ፣ በደልም እየተፈፀመበት ነው፤» ብለው ሲቆሙ ሳይ ታዲያ ምነው የሚያከብሩዋቸውና የሚያደንቋቸው ፕሮፌሰር ሲሳሳቱ በክብር እንዲያስተካክሉ አልጠየቋቸውም ያሰኛል።

እንደእኔ ግንዛቤ ፕሮፌሰር መስፍን በየጊዜው ብዙ ጠቃሚም ጎጅም ፅሁፍ ለንባብ አብቅተዋል። ለዚህም የኢትዮጵያን ህዝብ «ሆዳም» ብለው መዝለፋቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። ለአማራውም «አለሁ» ሲል «የለህም»፣ «እየተገደልኩ ነው» ሲል «የት አለህና?» በማለት 23 አመት ሞግተውታልና ለመግለጫው መልስ የሚያስፈልግ ቢሆን እርስዎም እንደገለፁት እራሳቸው ፕሮፌሰር መልስ መስጠት ስለሚችሉ የእርስዎ ጥብቅና ” የምጣዱ እያለ የንቅቡ ተንጣጣ” እንድል ዳርጎኛል። ፕሮፌሰር መስፍን ነገዱን ሁሉ እየጠሩ እውቅና ሲሰጡ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ «አማራ የሚባል ነገድ የለም» ማለታቸው ግን እንቆቅልሽ ነው በማለት ሀሳቤን እቋጫለሁ።

ፀሀፊዋን agereamanu@yahoo.com ማግኘት ይቻላል።


ወጣትነትና አስትዋጾው

0
0

የአንድ አገር ቀጣይነት ያለው እድገት የሚለካው በአላት ሃብትና ንብረት ብቻ ሳይሆን ያንን ተረክቦ በአደራ ለትውልድ ማስተላለፍ የሚችል ትውልዳዊ ትስስር ሲኖር ነው። ይህንንም እንደ ድልድይ ሆኖ  ከአንዱ ትውልድ ወደቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፈው ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ነው። በማንኛውም አገር፣ ጊዜና ዘመን እያንዳንዱ ተተኪ ትውልድ የአገሩ ወራሽ፣ ተተኪና ተረካቢ፣ ጠባቂና ለሚቀጥለውም ትውልድ የማውረስ፣ የማስተላልፍና የማስረከብ ኃላፊነትና ግደታ  አለበት። አገርን ከእነ ሙሉ ክብራ ለሚቀጥለው ትውልድ ማስተላለፍ ከወጣቱ የዜግነት ግደታ ነው። አገር በአንድና በሁለት ትውልድ ብቻ የሚቆምና የሚያልፍ ሳይሆን የማያቋርጥ ቀጣይነት ያለው ትውልድ ሁሉ የሚቀባበለው፣የሚጠብቀው ያለፈውንና የሚመጣውን ትውልድ ሁሉ የያዘና ያቀፈ የአገርና የሕዝብ የታሪክ ሂደት ነው።ወጣት ለአንድ አገር በሦስቱም ዘርፍ ማለትም በማህበራዊ፣ በሥነ ምጣኔ ሃብታዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያደርጋል። ለዚህም ነው ወጣት ለአንድ አገር የጀርባ አጥንት ነው የሚባለው።

ethio-prisons023ወጣትነት፦ ወጣትነት ማለት በሰው ልጅ ሥነ ሕይወታዊ ምዕራፍ አንድን የእድሜ ክልል የሚወክልና የተለያዩ ምጣኔ ሃብታዊ፣ ሥነ ልቦናዊ፣ ማህበራዊ፣ አካላዊ አቋምና ደረጃ ያለው ነው።  አገራት ከራሳቸው ማህበራዊ፣ ባህላዊና ሌሎች እሴቶችን መሰረት በማድረግ ለወጣትነት የሚሰጡት የእድሜ ክልል ይለያያል። ለምሳሌ፦ አውሮፓ ከ15—30፣ አፍሪካ ከ15_35 ያለውን የሕብረተሰብ ክፍል ይወክላል።በዚህ የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች የወጣትነት መገለጫወች/ምልክቶች ይታዩባቸዋል፤ ለውጦችም በከፍተኛ ደረጃ የሚከሰቱበት ነው። ማለትም አካላዊ/physical፣ ስሜታዊ/emotional፣ አዕምሮአዊ/cognitive፣ እውቀታዊ/ knowledge፣ ጥበባዊ/ skill እና መስተጋብራዊ/relationships። ወጣትነት ከእነዚህ ከፍተኛ ለውጦች ጋር በተያያዘ እራስን ለማወቅ የሚደረገው ጥረት በጣም ከፍ የሚልበት፣ ለችግር ተጋላጭነት የሚጨምርበት፤ አንድን ነገር በማድረግ በሰዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ለማትረፍ የሚሮጥበት እንጂ በሚደረገው ነገር የሚፈጠረው መጥፎ  ነገር በውል የማይጤንበት ጊዜ ነው። በዚህ ወቅት ከፍተኛ ጾታዊ ፍላጎት የሚቀሰቀስበት እና የወጣቶች አዕምሮ የሚባክንበት፤ ለልዩ ልዩ ሱሶች የሚጋለጡበት፤ እኔ ያልኩት ካልሆነ የሚሉበት ወዘተ ጊዜ ነው። በወጣትነት የእድሜ ዘመን ጠቃሚም ጎጅም ምልክቶች ይታዩብናል። ከእነዚህም መካከል የዳበረ አካላዊ ብቃት፣ተለዋዋጭ ስሜት፣ በራስ መተማመን/መመካት፣ ገደብ ማጣት/ገደብን አለመቀበል፣ በልጦ መታየትና ፈጣንነት ናቸው። በተለይ ሁሉንም ነገር ለማየት፣ ለመፈተሽ፣ የመቅመስ ስሜት የሚታይበት ነው። ክፉውንም መልካሙንም፣ የሚጠቅመውንም የማይጠቅመውንም ለመለየት ማየት፣ ማድረግና መሞከር የሚፈለግበት ዘመን ነው። እንዲሁም የወጣትነት ዘመን ከሁሉ በእውቀትም፣ በኃይልም፣ በውበትም፣ በሙያም፣ በችሎታም የምበልጠውና የምሻለው እኔ ነኝ የሚባልበት ጊዜ ነው። የተሻለ ሁኖ ለመገኘት የመፈለግ ስሜት የሚታይበት ነው። ለምሳሌ,፦ ከሌሎች መካከልተውቦ ለመገኘት፣ ተናግሮ ለመደበጥ/ለማሳመን፣  ጽፎ ለማስነበብ፣ አሸንፎ ለመሞገስ በአጠቃላይ አይነ ግቡ ሁኖ ለመገኘት የሚደከምበት ዘመን ስለሆነ ወጣትነት በአግባቡ ከአልተያዘ ጉዳቱ ከፍተኛ ነው።

በአጠቃላይ የዘመኑን ወጣት ለአገሩ በአለው አመለካከት በሦስት መክፈል ይችላል።

  1. ወጣትነትን ተጠቅሞ ለአገሩ የሚያስብ የሚጨነቅ፣ አገራዊ ስሜት ፍቅር ያለው፣ የለውጥ ኃይል የሆነ፣ ለነጻነትም የሚታገል፣ለአገር እድገትና ዲሞክራሲ ግንባታ የሚፋጠኑ
  2. አገሩን የማያውቅ፣ ማንነቱን የረሳ፣ ማዎቅም የማይፈልግ፣ ለጠቅም ብቻ የሚጓዝና ተስፋ የለሽ ወጣት
  3. በስሜት የሚጋዝ፣ አንዴ አገር ወዳድ ይሆናል፣ ወደነፈሰበት የሚጋዝ፣ ዓላማና ግብ የሌለው

አገር እና ዲሞክራሲ ሲባል

አገር በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት አንድ አገር ፣ ሉዓላዊ አገር  ለመባል  ሦስት መሰረታዊ ነገሮች ያስፈልጓታል። ከእነዚህ መሰረታዊ ነገሮች መካከል አንዱ ከተነካ ሉዐላዊት አገር የሚለው ይቀርና ሌላ ስም ይሰጣታል። እነዚህ ሦስቱም ተደጋግፈውና አንዱ የአንዱን ሉዐላዊነት መጠበቅ፣ ማስጠበቅ ይኖርበታል። አንዱ አንዱን ካጣ ምዕሉ ሊሆን አይችልም። የአንድ አገር ሦስቱ መሰረታዊ ነገሮች የሚባሉት ግዛት፣ ህዝብና መንግስት ናቸው። እንዲሁም ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦችን አንድ የሚያደርጋቸውና ከፍ አድርገው የሚያውለበልቡት የአንድ ሀገር መለያ ባንዲራ/ሰንደቃላማ ሲኖራት ነው።

ግዛት፦ የአንድ አገር ግዛት ማለት ወሰኗ፣ ድንበሯ፣ የቆዷ ስፋቷ፣ በውስጧ የየያዘዛቸው ወንዝ፣ ተራራ፣ሸለቆ፣ ባጠቃላይ ሙሉ ካርታዋ ማለት ነው። የኢትዮጵያ ግዛት ስንል በምስራቅ፣ በሰሜን፣ በደቡብና በምዕራብ ከሚያዋስኗት ግዛቶች የምትለይበት ቦታ፣ ድንበር ወይም ክልል ጀምሮ በውስጧ የየያዘዛቸው ወንዝ፣ ተራራ፣ሸለቆ ወዘተ ሙሉ የቆዳ ስፋቷን ያዋስናል። ከዚህ የቆዷ ስፋቷ ትንሽ ከተነካ ግን የነበራት ሙሉ ግዛት አይኖራትም። መንግሥት ለግዛቷ ሲጨነቅ አናይም። እንደ ጥሬ እቃ ግዛቷን ሲሸጥም፣ ሲደራደርባትም እናያለን። ይህን ግዛቷን ለማስጠበቅ ወጣቱ  በመተባበርና በመጠበቅ ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት።

ለሕዝብ፦ ከሁሉም በላይ ክብርና ሥልጣን ሊሰጠው የሚገባ ነው። ሕዝብ ከሌለ የምንላቸው ነገሮች የሉም። ህዝብ ከሌለ ለግዛት ስም ጠርቶ፣ ወሰን ወስኖ ሊያስቀምጥ የሚችል አካል የለም። ስለዚህ ሕዝም ውድ ዋጋ ያለው ነው። በሌላም በኩል ፈጣሪ አክብሮና ባለ አዕይምሮ አድርጎ የፈጠረው መተኪያ የለለው ፍጡር ነው። ስለዚህ ግዛት በሕዝም ይከበራል፤ መንግሥት ደግሞ በሕዝብ ይከብራል/ይነግሣል። ላከበረው፣ ላነገሠው ሕዝብ መንግሥት ዋጋ ሊከፍልለት ይገባል። ከዚያ ውጭ ግን(የዜግነት ክብር በኢትዮጵያችን ፀንቶ፣ ታየ ህዝባዊነት ዳር እስከዳር በርቶ)እያልን የአገር መለያ፣ የማንነታችን መገለጫ የሆነውን ባንዲራ እያውለበለብን የምንዘምረው የህዝብ መዝሙር ከንቱና ዋጋ አልባ ሆኗል ማለት ነው። ባንዲራ ደግሞ ጨርቅ አይደለም ልዩ መለያ ማንነታችን ነው። ይህን የማንነት ጉዳይ ሊያስከብረው የሚችል ደግሞ ህዝብ ነው። ሕዝብ ማለት ደግሞ እያንዳንዳችን ስብስብ/ድምር ውጤት ነው። ስለዝህ ለህዝብ የሚያስፈልገውን ነጻነት፣ እድገት፣ብልጽግና እንዲያገኝ እኛ ወጣቶች የበኩላችንን ድርሻ መወጣት አለብን፤ ግዴታችንም ነው።

መንግሥት፦ መንግሥት ማለት በጥሬ ትርጉሙ በአንድ አገር  ውስጥ ሕጎችን ለማውጣትና ለማስፈጸም፣ ሕዝብን ለማስተባበርና ደኅንነቱን ለማስጠበቅ፣ አገርን ለማስከበር  ስልጣንና ኃላፊነት ያለው አካል ማለት ነው። እንዲሁም በምርጫም ይሁን በሌላ መንገድ በሕዝብ ድጋፍ ስልጣን ላይ የወጣ አካል ነው። ስለዚህ ይህ በሕዝብ ድጋፍ ሥልጣንን የያዘ አካል ከስሙና ከትክክለኛ ትርጉሙ አንፃር ለህዝብና ለአገሪቱ ግዛት ከማንም በላይ የሚጨነቅ፣ የሚያስብና የሚቆረቆር አካል መሆን ይኖርበታል። ምክንያቱም ሕዝብ ከሌለ መንግሥት የለም፤ ግዛትም ከሌለ እንዲሁ። ከምንም በላይ ለመንግሥት መኖር ሁለቱም ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው። የየትኛም አገር መንግሥት ይህን ተገንዝቦ ለሁለቱም የሚገባውን እንክብካቤና ክብር መስጠት ካልቻለ የመኖር ዋስትናው ጥያቄ ውስጥ ይገባል። አወዳደቁም በእጅጉ የከፋ ይሆናል።

ዲሞክራሲ፦ ማለት የዲሞክራሲ ጥንታዊ ትርጉም “ የህዝብ ሃይል” ወይም “ የህዝብ አስተዳደር” ሲሆን መሰረቱም ሁለት የግሪክ ቃላቶች ዴሞስ(demos)“ህዝብ” እና ክራቶስ (kratos)“ሃይል” ውህደት ነው:: የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት በነበሩት አብረሃም ሊንከን አተረጓጐምም መሰረት ደግሞ ዲሞክራሲ ማለት በህዝብ የተመረጠና ለህዝብ የቆመ የህዝብ መንግስት ማለት ነው:: በዚህ ዓይነት ስርዓት ውስጥ የተመረጡ መሪዎች ቀጥተኛ ተጠሪነታቸው (accountability) ለህዝቡ ሲሆን የሚሰጡት አገልግሎትም በህዝቡ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ብቻ እንደሆነ ይገለጻል:: ዘመናዊው የዲሞክራሲ ምንነት በቀደምቶቹ ትርጉሞች ላይ የዳበረ ሲሆን የሰው ልጅ መሰረታዊና ፖለቲካዊ መብቶች የማክበር፣ በህዝቦች መካከል የሰፈነ እኩልነት፣ ነጻና ፍትሃዊ የመምረጥና የመመረጥ መብት ያለው፣ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ የሚፈቅድ፣ እንዲሁም ከማንኛውም ተጽዕኖ ነጻ የሆነ የፍትህ ሥርዓትንና ነጻ ፕሬስን ያካተ ተቋም መሆን እንዳለበት ይታወቃል።

ኢትዮጵያ አገራችን ብዙ  መንግሥታትን ያስተናገደች አገር ናት። ሆኖም ግን ለዘመናት ታሪኳን፣ ባህሏን፣ እምነቷን፣ አንድነቷን፣ ድል አድራጊነትን እና ዳር ድንበሯን ጠብቃ አስጠብቃ  የኖረች እና መተሳሰብን፣ መከባበርን፣ እንግዳ ተቀባይነትን፣ ዘርንና ጎሳን መሰረት ሳታደርግ ለዘመናት የቆየች የጀግኖች አገር ናት።

ዛሬ መንግሥት ነይ ባዩ የወያኔ/ሕወሓት ቡድን ግን፦

  • ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንዳትኖር የሚፈልግ፣  አገራዊ ስሜት ፈጽሞ የማይታይበት፣ ህዝቧና አገሪቱን የድህነት ሰለባ አድርጎ ከመኖር ወደ አለመኖር ዳርጎናል።
  • ትውልድ ገዳይ/ ወጣት አልባ /አገራዊ ስሜት እንዳይኖረን/ከሥርዓተ ት/ቱ ጀምሮ
  • የሰባዊ መብት ጥሰትና ረገጣ በግንባር ቀደም የሚጠቀስ፣ ከራሱ ቡድን ውጭ ሰው እንደሰው የማይቆጠርበት አገር አድርጓታል።
  • ተፈጥሮአዊና መሰረታዊ መብት የማምለክ፣ የመንቀሳቀስ፣ የመሥራት፣ የመኖር ነጻነታችንን ነፍጎናል፤
  • ዲሞክራሲያዊ መብታችን የመደራጀት፣ የመቃወም፣ የመወያየት፣ የመምረጥ  ወዘተ በዲሞክራሲ ስም ፀረ ሰላም፣ ፀረ ልማት፣ ፀረ ዲሞክራሲ፣ ፀረ ህግ ተብሎ በፀረ ሽብር ህግ አማካኝነት አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የሚገደሉበት፣ የሚታሰሩበት፣ የሚንገላቱበት፣ የሚደበደቡበት፣ የሚሰደዱባት (አንዳርጋቸው ጽጌ፣ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታየ፣ አንዷለም አራጌ፣ ርዮት ዓለሙ፣ ጦማርያን፣ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሳይቀሩ)
  • ልማት ለወያኔ በተግባር ሳይሆን በቃል ብቻ 11% ማደግ፣ አገርን መሸጥ እና ሰባዊ መብትን ከመገንባት ይልቅ ህንጻና መንገድ መገንባት ማለት ነው።

ይህን ጨቋኝና አፋኝ ሥርዓት አሶግዶ አገራዊ ስሜት ለመላበስ እንዲሁም ለአገር እድገትና ዲሞክራሲ ግንባታ የወጣቱ አስትዋጾ ከፍተኛ መሆኑን ተረድቶ ለነጻነት መታገል የእያንዳንዱ ወጣት አገራዊ ግዴታም ኃላፊነትም ነው።

አገራዊ ስሜት መላበስ ሲባል አገርን በሚገባ ማወቅና በማነኛውም መልኩ ለችግሯ ደራሽና ተቆርቋሪ መሆን ማለት ነው። ለባንዲራዋ ክብር መስጠት ነው። ኢትዮጵያዊነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ማወቅ መገንዘብ ነው። ወያኔ ወጣቱን ስለአካባቢው እንጂ እንደ አገር ማውራት እንዲያቆም አድርጎናል። ስለ ኢትዮጵያ ሲወራ እንደ ሁለተኛ ሦስተኛ ዜጋ ሁነን ቁመን የምንሰማ በርካቶች ሁነናል። ትርጉሙም ስሜቱም ጠፍቶብናል። ወጣቱም ብሔርን፣ ቋንቋን ይሰብካል። የፖለቲካ ድርጅቶችም ይህንኑ ያስተጋባሉ። ለአገር ሳይሆን ለብሔር ብቻ የቆሙ ናቸው። ይህን ከባድ ችግር አሶግደን አገራዊ ስሜት ሰንቀን ኢትዮጵያዊነት ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳን የወያኔ ቡድን አሁን በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን ችግር ማስቆም እንችላለን። አገራዊ ስሜት በውስጣችን ከነገሰ ለአገር፣ ለወገንና ለክብራችን ዘብ እንቆማለን።

አገራዊ ስሜት ያለው ወጣት ከሌሎች የሚለዩበት፦

  • ፍቅር …ሰባዊና አገራዊ ፍቅር፣ ለሰው ልጅ ሰው በመሆኑ ብቻ ክብርና ፍቅር መስጠት።
  • ተስፋ …ለተተኪ ትውልድ አርቆ ያስባል፣ መልካም ነገሮችን በተስፋ መነጸር መመልከት ይችላል፣ ተስፋ ኃይልና ብርታት ይሆናል፣ በተስፋ የነጻነት፣ የፍትህና የዲሞክራሲ ብርሃን ማየት ይቻላልና።
  • ግልጽነትና ተጠያቂነትን ገንዘብ ያደርጋል, የሚሰራውን ተግባር በግልጽና በተጠያቂነት ያከናውናል፣ ለሥራው ሁሉ ለራሱ፣ ለአገሩና ለወገኑ ተጠያቂ ይሆናል።
  • ሙስናን ፈጽሞ ይጠላል፣ ያጋልጣል/ይቃዎማል።
  • መልካም ሥነ ምግባር የተላበሰ/ ከማይጠቅም ነገር እራስን ያርቃል።
  • የአገርን ግዛቷን፣ ታሪኳን፣ ባህሏን መጠበቅ መመስከር፤ ለአገሩ ደራሽና ተቆርቋሪ ነው።
  • እራስን ሁኖ መኖር ይችላል፣ ማንነቱን ጥንቅቆ ያውቃል፣ በማንነቱም ይኮራል።
  • ለነጻነት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ እየታገሉ ምሳሌና አርያ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን ይከተላል።

አገራዊ እድገትና ዲሞክራሲ ለማስፈን ወጣቱ ሊከተላቸው የሚገቡ ነገሮች

  1. ዓላማ፦ በመጀመሪያ ከስሜት ወጠን ዓላማና ግብ ሊኖረን ይገባል።  ምን እንደምንሰራ እና የት ለመድረስ የሚሉትን ነገሮች ከመጀመራችን በፊት በሚገባ ማዎቅና መገንዘብ፣
  2. ቆራጥነት፦ ዓላማችንን ከግብ ለማድረስ ቆርጦ መነሳት ያስፈልጋል። ፈራ ተባ ማለት ለውጠት አያበቃም። ወጣትነት ኃይል፣ጉልበት አለንና።
  3. እውቀት መገብየት፡ በቆራጥነት ለተነሳንበት ዓላማ በቂ እውቀት ያስፈልገናል። ስለ ታሪካችን፣ ባህላችን፣ማንነታችን እውቀት ያስፈልጋል። በቅኝ ግዛት በተገዛን ኑሮ  የሚል ወጣት ይሰማል ከእውቀት ማነስ የተነሳ፣ የቅኝ ግዛት ምንነትና አስከፊነት ባለመረዳትና አባቶቻችን ለምን ሰማዕትነትን እንደተቀበሉ ካለመረዳት።.ስለዚህ ለሁሉም ነገር እውቀት አስፈላጊ ነው። እውቀትን ከህይወት ተሞክሮ፣ ከት/ት፣ ከመልካም ጋደኛ፣ ከቤተሰብ፣ ከታላላቅ ሰዎች እንቀስማለን።
  4. ስልታዊ ዕቅድ መንደፍ፦ በአገኘነው እውቀት ተጠቅመን ሊያዋጣና ሊያስኬድ የሚችል ስልት፣ ሁለገብ የትግል ስልት መንደፍና መከተል። ከዓላማችን ሊያደርሰን የሚችል ወቅታዊና ዘላቂ እድገትን፣ መብትን፣ ሰላምን፣ ሊያጎናጽፍ የሚችል ስልት መከተልና ውጤታማ ለመሆን መታገል እንደሚያስፈልግ ልንገነዘብ ይገባል።
  5. ነጻነትን ማዎጅ፦ ነጻነት የሚለውን ቃል ሰዎች የተለያየ አተረጓጎም ሊሰጡት ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን ነጻነት ማለት ከግዞት መውጣት፤ ከሌሎች ተጽኖዎች መውጣት፤ በራስ መወሰን ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ማንም ሌላ ሰው ሳያስገድደን እና የማንንም መብት ሳንነፍግ በነገሮች ላይ በራስ ወይም በጋራ መወሰን መቻል ነው፡፡ ደሞክራሲ ሊባልም ይችላል፡፡ ነጻነት አለ ካልን ሃሳባችን ወይም ተሳትፏችን ተሰሚነትና ተቀባይነት አለው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ነጻነትን አውጀን  ለሰላም፣ ለፍትህና ለዲሞክራስ ቆርጦ  መነሳት ያስፈልጋል።
  6. አንድነታችን መጠበቅ፦  ወጣቱ ሊያከናውን ከሚገባው ነገር አንዱና ትልቆ ጉዳይ አንድነትን ብሄራዊነትን፣ አገራዊነትን ማምጣት ነው።ችግር ለመፍታትም ሆነ መፍትሔ ለመፈለግ እኛ አንድ መሆን ይኖርብናል። መግባባት፣ መነጋገር፣ መወያየት በምንችልባቸው ነገሮች ላይ አንድ መሆን አለብን። በአንድ አገር ውስጥ የተለያየ ቋንቋ፣ ባህል፣እምነት ያለው ህዝብ በአገሪቱ ግዛት አንድ መሆን መቻል አለብን። ይህንን ሊያስተባብርና ሊመራ እንዲሁም አንድ ሊያደርገን የሚችል መንግሥት ሊኖረን ይገባል። ከዚያ ውጭ በቋንቋ፣ በባህል፣ በእምነት እንደተለያየን ሁሉ አንድ ሊያደርገን የሚችል የጋራ የሆነ ነገር ከለሌን ችግሩን በህብረት መቅረፍም ሆነ መቀነስ አንችልም። ወያኔ/ህወሓት ብሔር፣ ጎሳ፣ ቋንቋ፣ እምነት እያለ ሊከፋፍለን፣ ሊለያየን አይገባም። ይህን ድርጊት የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሀይማኖት ተቋማት፣ የግል/ሰባዊ መብት ድርጅቶችና ሕዝብ ሁላችንም  ማውገዝና ማስቆም ይኖርብናል። በተለይ ወጣቱ ትውልድ ትልቅ ኃላፊነት አለበት።

በአጠቃላይ የወጣቱ አስትዋጾ ዘርፈ ብዙ ነው፤ በዚህ ወይም በዚያ ብሎ መወሰን ከባድና አስቸጋሪ ነው። የለውጥ ኃይል እስከሆነ ድረስ በሁሉም ዘርፍ መገኘት እና አገርን ወደተሻለ ደረጃ ማድረስ የዜግነት ግዴታ አድርጎ  መውሰድ ይኖርብናል።

በማነኛውም መልኩ አገራችንን ለማገልገል እራሳችንን ብቁና ዝግጁ ማድረግ ይገባል።ለአገር እድገት፣ ለነጻነት፣ ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲ ግንባታ የወጣቱ አስትዋጾ ከፍተኛ መሆኑን ተረድተን በምንችለው ሁሉ የበኩላችንን ኃላፊነትና ግዴታ መወጣት አለብን። መንግሥት ነኝ ባዩን የህወሓትን ቡድን በቃህ መብትና ህግ ይከበር ብለን በአንድነት መነሳት አለብን።

 

አቶ መለስ የሕይወታቸው ፍፃሜ የሆነባት የቤልጅየም ዋና ከተማ ብራስልስ ከመላው አውሮፓ በመጡ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ ተናጠች (ቪድዮ)

0
0

አቶ መለስ የሕይወታቸው ፍፃሜ የሆነባት የቤልጅየም ዋና ከተማ ብራስልስ ከመላው አውሮፓ በመጡ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ ተናጠች

ከሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ የተላለፈ ጥሪ

0
0

የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ በአቡነ ዳንኤል አማካኝነት አዲስ ታቦት ዛሬ አግኝቷል:: አቡነ ዳን ኤል የኪዳነምህረትን ታቦት ይዘው ሚኒያፖሊስ ሴንት ፖል ኤርፖርት ሲደርሱ ታላቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል:: ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ እንደላከው መግለጫ ከሆነ የፊታችን እሁድ የዓመቱ መድሃኔዓለም በዓል አከባበር አቡነ ዳንኤል በተገኙበት ይደረጋል:: ፍላየሩን ይመልከቱት
aba daniel

ለሕዝብ የተላከን ምግብ ሊሸጡ ሲሉ የተያዙ የተባሉ 4 ባለስልጣናት ታሰሩ

0
0

አኩ ኢብን ከአፋር

ባለፈው ወር በአፋር ክልል በአሚባራ አካባቢ ህዝብ ላይ የደረሰው የጎረፍ አደጋን ተከትሎ ከ30ሺ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ከአካባቢው መፈናቀላቸው ይታወሳል። ለእነዚህ ወገኖች ከተለያዩ የእርዳታ ድርጅቶች እና ከመንግስት የተላከው እርዳታ በመንግስት ኃላፊዎች ለሙስና መዳረጉን ምንጮቻችን ከቦታው ዘግበዋል።
afar
ባለፈው ሰኞ ከአዋሽ ፋንቲ አሌ ወረዳ ወደ መትሃራ በመንግሥት ኃላፊዎች ተዘርፎ ሊሸጥ የነበረና ብዛቱ በውል ያልታወቀ ብዙ ኩንታሎች የእርዳታ እህል በመኪና ተጭኖ ሲንቀሳቀስ ከሌሊቱ 6:00 ላይ በህዝብ ተቆማ በቁጥጥር ስር ውሏል።

እነዚህ ባለስልጣናት ለጊዜው የታሰሩ ሲሆን ስማቸው ከዚህ በታች በዝርዝር ይቀመጣል፦
1 – አቶ አደም መሀመድ የአዋሽ ፋንቲዓሌ ወረዳ ምክትል አስተዳደር
2 – አቶ አባህ አባ የግብርና የገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ
3 – አቶ ሙስጣፋ ሀሳን የአዋሽ ወረዳ የአብዴፓ ፓርቲ ቢሮ ኃላፊ፤
4 – ወ/ሮ ፋጡማ እብራሂም የንብረት ክፍል ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ እነዚህ ባለስልጣናት በጊዜው ለፖሊስ በሰጡት ቃል «የተያዝነው ጊዜ ባለፈበት እህልና እቃ ሲሆን ለመንግስትም ለመመለስ እየተንቀሳቀስን በነበረበት ሰአት ነው» ብለዋል ሲሉ ምንጮች ፓሊስን ጠቅሰው ዘግበዋል።

ይህን የህዝብ እርዳታ እንዲሸጡ ያስገደዳቸው የአፋር ክልል አፈጉባኤ የሆኑት አቶ መሀመድ አንበጣ ወደ አዋሽ በመሄድ ለወረዳው ካቢኔዎች ገንዘብ አምጡ ብለው 20,000 ብር ቢሰጧቸውም ጨምሩ ሰላሏቸው የህዝብ እርዳታ እንዲሸጡ መገደዳቸው አንድ ስሙ ሊገለፅ ያልፈለገ ሊንደብቅለት የመንግስት ሰራተኛ የላክለን መረጃ ያስረዳል።

እስላማዊ መንግስት ለማቋቋም ሲንቀሳቀሱ ነበር የተባሉት ክሣቸው ተሰማ

0
0

ከአልሸባብና ደቡብ አፍሪካ ከሚገኝ የሽብር ቡድን ጋር ግንኙነት ነበራቸው ተብሏል
መቃወሚያቸውን እንዲያቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል

(ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንዘገበው) በጅሃድ ጦርነት እስላማዊ መንግስት ለማቋቋም በጅማ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ ነበር የተባሉ ተጠርጣሪዎች፤ ሰሞኑን ፍ/ቤት ቀርበው ክሣቸው ከተሰማ በኋላ የክስ መቃወሚያቸውን እንዲያቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡

Photo File

Photo File


በፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ባለፈው ረቡዕ ክሣቸው በንባብ የተሰማው 7 ተጠርጣሪዎች፡- ጃፋር መሃመድ መሃሙድ ኑር፣ መሃመድ ሣኒ፣ መህዲን ጀማል፣ መሃሙድ አባቢያ፣ አንዋር ትጃኔ እና ሼክ ከማል አባጪብሳ ሲሆኑ በዋና ወንጀል ፈፃሚነት መሠረታቸውን ጅማ አካባቢ አድርገው፣ እስላማዊ መንግስት ለመመስረት ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተጠቁሟል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ደቡብ አፍሪካ ከሚገኝ የሽብር ቡድንና በሶማሊያ ከሚንቀሳቀሰው አልሸባብ ጋር ግንኙነት ነበራቸውም ብሏል – የአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ፡፡ 1ኛ ተከሣሽ ጃፋር መሃመድ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ሃይማኖታዊ ጦርነት ለማወጅና እስላማዊ መንግስት ለማቋቋም የሚያስችለውን ስልጠና ከደቡብ አፍሪካ ወስዶ በመምጣት፣ ጅማ አካባቢ ለአላማው ማስፈፀሚያ ቦታ በመምረጥ አባላትን በመመልመል ሲንቀሳቀስ ነበር ተብሏል፡፡

ተከሳሹ በደቡብ አፍሪካ ይገኛል ከተባለው አሸባሪ ቡድን የተላከለትን 80ሺህ የደቡብ አፍሪካ ራንድ ተቀብሎ ለመሣሪያ መግዣ እንደተጠቀመበት የክስ መዝገቡ አመልክቷል፡፡ በጅማ አካባቢ ኮዳ በተባለ ጫካ ውስጥ የመለመላቸው ግለሰቦች ለ6 ቀናት ስልጠና እንደወሰዱና እንቅስቃሴው በፀጥታ ኃይሎች እንደተደረሰበት ሲረዳ፣ ወደ ሶማሊያ ሄዶ ከአልሻባብ ጋር ለመቀላቀል ሙከራ ሲያደርግ በግንቦት 2006 ዓ.ም በቁጥጥር ስር መዋሉን የአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ያስረዳል፡፡
በመዝገቡ የተካተቱት ቀሪዎቹ 6 ተጠርጣሪዎች አባል በመሆን፣ የሽብር ተልዕኮ በመቀበልና እስላማዊ መንግስት የመመስረት አላማቸውን ለማሳካት ሲንቀሳቀሱ በፈፀሙት በሽብር ቡድን ውስጥ የመሳተፍ ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ ባለፈው ረቡዕ ፍ/ቤቱ ክሱን በንባብ ካሰማ በኋላ፣ የተከሳሾች ጠበቃ በክሱ ላይ መቃወሚያ ካላቸው እንዲያቀርቡ ለህዳር 10 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Sport: በ60ኛዋ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ፕሪሚዬር ሊግ ፤ ከቦንደስ ሊጋና ላሊጋ ይተናነቃል

0
0

የ7.3 ቢሊዮን ዩሮ ተጨዋቾች፤ ከ2.09 ቢሊዮን ዩሮ በላይ ወጭ ፤ እስከ 57.4 ሚሊዮን ዩሮ ሽልማት
5 ክለቦች ታጭተዋል ፤ ሪያል ማድሪድ፣ ባየር ሙኒክ፣ ባርሴሎና፣ ቼልሲና ማን. ሲቲ
ፕሪሚዬር ሊግ ፤ ከቦንደስ ሊጋና ላሊጋ ይተናነቃል

የ2014-15 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሰሞኑን በአራተኛ ዙር የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ቀጥሏል፡፡ በምድብ ማጣሪያው ቀሪ የሁለት ዙር ጨዋታዎች ቢኖሩም 5 ክለቦች ሪያል ማድሪድ፤ ቦርስያ ዶርቱመንድ፤ ፒኤስጂ፤ ባርሴሎና እና ፖርቶ ወደ ጥሎ ማለፍ መሸጋገራቸውን አረጋግጠዋል፡፡
chmapions league
አትሌቲኮ ማድሪድ፤ አያክስን ጨምሮ አምስት ክለቦች ከውድድሩ ተሰናብተዋል፡፡ የአውሮፓ እግር ኳስ በየውድድር ዘመኑ እስከ 30 ቢሊዮን ይንቀሳቀስበታል፡፡ በተለይ ደግሞ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ በትርፋማነቱ የሚስተካከለው የለም፡፡ በትራንስፈርማርኬት ድረገፅ የቀረበ መረጃ እንደሚያመለክተው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ፤ በየውድድር ዘመኑ ከቅድመ ማጣሪያ አንስቶ እስከ ዋንጫ ጨዋታ እንዲሁም የውስጥ የሊግ ውድድሮችን ጨምሮ 853 ተጨዋቾችን የያዙ 155 ክለቦችን በማሳተፍ ይካሄዳል፡፡ በዝውውር ገበያው የዋጋ ግምታቸው እስከ 7.3 ቢሊዮን ዩሮ የሚተመኑ ተጨዋቾች በየክለቡ ተሰልፈው የሚፋለሙበት መድረክ ነው፡፡ ለዘንድሮው ሻምፒዮንስ ሊግ በአምስቱ የአውሮፓ ሊጎች የሚወዳደሩት ክለቦች ከፍተኛ ትኩረት መስጠታቸው የተረጋገጠው በተጨዋቾች የዝውውር ገበያው 2.09 ቢሊዮን ዩሮ በላይ ወጭ ማድረጋቸው ነው፡፡ ከተጠቀሰው የዝውውር ገበያ ወጭ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ 45 በመቶ ድርሻ ይዟል፡፡

25 በመቶውን የስፔን 10 በመቶውን የጀርመን ክለቦች አውጥተዋል፡፡ የጣሊያን እና የፈረንሳይ ሊጎች ዝቅተኛውን የወጭ ድርሻ አስመዝግበዋል፡፡ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በ2014 /15 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግና ዩሮፓ ሊግ ውድድሮች ለሽልማትና ሌሎች ገቢዎች ድርሻ 1.34 ቢሊዮን ዩሮ መቅረቡን አስታውቋል፡፡ ካለፈው የውድድር ዘመን በ30 በመቶ ጭማሪ አለው፡፡ የእግር ኳስ ማህበሩ እንዳመለከተው ሌሎች የገቢ ድርሻዎችን ሳይጨምር 60ኛዋን ዋንጫ ለማንሳት የሚበቃው ክለብ እስከ 57.4 ሚሊዮን ዩሮ የሽልማት ገንዘብ ይከፈለዋል፡፡ በምድብ ማጣርያው ላይ የሚገኙት 32 ክለቦች ደግሞ ቢያንስ 8.6 ሚሊዮን ዩሮ የገቢ ድርሻ አላቸው፡፡ በእያንዳንዱ የምድብ ጨዋታ በሚመዘገብ ውጤት መሰረትም የሽልማት ገንዘብ ይከፈላል፡፡ ለድል 1 ሚሊዮን ዩሮ እና ለአቻ ውጤቶች ደግሞ 500ሺ ዩሮ ይታሰባል፡፡ የምድብ ማጣርያውን አልፈው ጥሎ ማለፍ የሚገቡ 16 ክለቦች 3.5 ሚሊዮን ዩሮ ገቢ ሲኖራቸው፤ የሩብ ፍፃሜ 8 ክለቦች እያንዳንዳቸው 3.9 ሚሊዮን ዩሮ፤ የግማሽ ፍፃሜ አራት ክለቦች እያንዳንዳቸው 4.9 ሚሊዮን ዩሮ ፤ በዋንጫ ጨዋታ ተሰልፎ ሁለተኛ ደረጃ የሚያገኘው ክለብ 6.5 ሚሊዮን ዩሮ እንዲሁም ዋንጫውን የሚያሸንፈው ክለብ 10.5 ሚሊዮን ዩሮ ከሽልማት ገንዘብ ብቻ ይከፈላቸዋል፡፡ ባለፈው የውድድር ዘመን በሻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ ለነበሩ 32 ክለቦች የተከፋፈለውገቢ 904.6 ሚሊዮን ዩሮ ነበር፡፡ 57.4 ሚሊዮን ዩሮ በማግኘት 10ኛውን የሻምፒዮንስ ሊግ ያስመዘገበው ሪያል ማድሪድ መርቷል፡፡ በሩብ ፍፃሜ የተሰናበተው ፓሪስ ሴንትዥርመን በ54.4፤ ሁለተኛ ደረጃ አግኝቶ የጨረሰው አትሌቲኮ ማድሪድ በ50፤ ዘንድሮ የማይሳተፈው እና አምና በሩብ ፍፃሜ የተሰናበተው ማንችስትር ዩናይትድ በ44.8፤ ለግማሽ ፍፃሜ የደረሱት ባየር ሙኒክ በ44.6 እንዲሁም ቼልሲ በ43.4 ሚሊዮን ዩሮ የገቢ ድርሻ ተከታታይ ደረጃ ነበራቸው፡፡ ፕሪሚዬር ሊግ በጥሎ ማለፍ ከቦንደስ ሊጋና ላሊጋ ጋር ይተናነቃል በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ወደ ጥሎ ማለፉ የሚሸጋገሩበት ክለቦች ዘንድሮም ከ5ቱ ታላላቅ ሊጐች መገኘታቸው የማይቀር ይመስላል፡፡

17 ክለቦች በየሊጋቸው ያለፈው የውድድር ዘመን ሻምፒዮን ሆነው የሚሳተፉበት ውድድር ቢሆንም ማለት ነው፡፡ በአውሮፓ እግር ኳስ በገቢው ከፍተኛነት የሚታወቀው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ፤ በተረጋጋአስተዳደርና አትራፊነቱ እንደተምሳሌት የሚቆጠረው የጀርመን ቦንደስ ሊጋ እንዲሁም በተወዳጅነት እና በክዋክብት ስብስቡ የደመቀው የስፔን ላሊጋ ለሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ቋሚ ተፎካካሪ ሊጎች ከሆኑ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ተቆጥረዋል፡፡ በተለይ ከሻምፒዮንስ ሊጉ የዋንጫ ፉክክር ከራቁ ሶስት የውድድር ዘመናት ያለፋቸው የእንግሊዝ ክለቦች ጥሎ ማለፍ ብቻ ሳይሆን ግማሽ ፍፃሜ መድረሳቸው እየተጠበቀ ነው፡፡ ቼልሲ፤ ማንችስተር ሲቲ ፤ ሊቨርፑልና አርሰናል እንግ ለዋንጫ እንደሚያበቁ በየአቅጣጫው ሰፊ ትንታኔዎችን ተሰጥተዋል፡፡ ይሁንና ባለፉት ስምንት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚዎች ሰባቱ የስፔንና የጀርመን ክለቦች መሆናቸው ከባድ ክፍተት ነው፡፡ ባለፈው የውድድር ዘመን የሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ተፋላሚዎች ሁለቱም ከስፔን ነበሩ ፡፡ ባለፉት አራት የውድድር ዘመናት ደግሞ በግማሽ ፍፃሜ ሁለት የላሊጋው ክለቦች ቋሚ ተሰላፊዎች ሆነው አሳልፈዋል፡፡ በ2011 ባርሴሎና እንዲሁም በ2014 ሪያል ማድሪድ ዋንጫን መውሰዳቸውም የስፔኑ ላሊጋ ከቦንደስ ሊጋው በላቀ ግምት እንዲታይ ያደርገዋል፡፡ በሌላ በኩል የጀርመኑን ቦንደስ ሊጋ የሚወክለው ባየር ሙኒክ ባለፉት አራት የውድድር ዘመናት ለ3 ጊዜ ፍፃሜ መድረሱ እና በ2013 ዋንጫውን መውሰዱና ከፍተኛ ግምት አሰጥቶታል፡፡ ዘንድሮ ፍፃሜው በበርሊን ከተማ መዘጋጀቱ ደግሞ የአሸናፊነት ግምቱን ለጀርመኑ ክለብ ያበዛለታል፡፡ በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር የስታትስቲክስ ሰነድ የአምስቱ ታላላቅ ሊጎች በሻምፒዮንስ ሊግ መድረክ ስላላቸው የውጤት የበላይነት በርካታ ማስረጃዎች አሉ፡፡

ከ1993 እስከ 2014 እኤአ በሻምፒዮንስ ሊጉ 27 የዋንጫ ጨዋታዎች ተካሂደው ዋንጫዎቹን 13 ክለቦች ሰብስበዋል፡፡ 7 ጊዜ የስፔን፤ 5 ጊዜ የጣሊያን፤ አራት ጊዜ የእንግሊዝ፤ 3 ጊዜ የጀርመን እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ የፈረንሳይ፤ የሆላንድ እና የፖርቱጋል ክለቦች ዋንጫዎቹን ወስደዋል፡፡ አራቱን ዋንጫ በመውሰድ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ ነው፡፡ እያንዳንዳቸው እኩል ሶስት ጊዜ የሻምፒዮናነት ክብር ያገኙት ደግሞ የጣሊያኑ ኤሲ ሚላን እና የስፔኑ ባርሴሎና ናቸው፡፡ እኩል ሁለት ጊዜ ዋንጫውን በማንሳት የእንግሊዙ ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ እና የጀርመኑ ባየር ሙኒክ ሲጠቀሱ፤ እያንዳንዳቸው አንድ ጊዜ ዋንጫ በማግኘት የተሳካላቸው ክለቦች የፈረንሳዩ ኦሎምፒክ ማርሴይ፤ የሆላንዱ አያክስ፤ የጣሊያኑ ጁቬንትስ፤ የጀርመኑ ቦርስያ ዶርትመንድ፤ የፖርቱጋሉ ኤፍሲ ፖርቶ፤ የእንግሊዙ ሊቨርፑል፤ የጣሊያኑ ኢንተርሚላንና የእንግሊዙ ቼልሲ ናቸው፡፡ ባለፉት 27 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የውድድር ዘመናት ስፔን 22 ጊዜ በግማሽ ፍፃሜ በመወከል ትቀድማለች፡፡ 19 ጊዜ እንግሊዝ፤ 13 ጊዜ ጣሊያን፤ 12 ጊዜ ጀርመን እንዲሁም 6 ጊዜ ፈረንሳይ በክለቦቻቸው የግማሽ ፍፃሜ ውክልናን አግኝተዋል፡፡ ስፔን በ4 ክለቦች ለ11 ጊዜያት ለዋንጫ ጨዋታ በመቅረብ አሁንም ግንባር ቀደም ነች፡፡ ጣሊያን በ3 ክለቦች ለ11 ፤ እንግሊዝ በ4 ክለቦች ለ9፤ ጀርመን በሶስት ክለቦች ለ8 እንዲሁም ፈረንሳይ በ2 ክለቦች ለ2 ጊዜያት ለዋንጫ ተጫውተዋል፡፡ በሌላ በኩል ከ1955 እሰከ 2014 እኤአ በተደረጉት 59 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ የውድድር ዘመኖች 14 ጊዜ የሻምዮናነት ክብሩን በመውሰድ የስፔን ክለቦች ይመራሉ፡፡

በክለቦቻቸው እያንዳንዳቸው 12 ዋንጫዎች ወሰዱት የእንግሊዝ እና ጣሊያን ናቸው፡፡ ሌሎች የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎች 7 በጀርመን ፤ 6 በሆላንድ፤ 4 በፖርቱጋልክለቦች የተወሰዱ ሲሆን፤ እያንዳንዳቸው አንድ ጊዜ በክለቦቻቸው የአውሮፓን ክብር ያገኙ አራት አገራት ፈረንሳይ፤ሮማንያ፤ ስኮትላንድ እና ሰርቢያ ናቸው፡ 5ቱ የዋንጫ ተፎካካሪዎች የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ገና በምድብ ማጣርያ 4ኛ ዙር ጨዋታዎች ላይ ቢገኝም ለዋንጫው አሸናፊነት 5 ክለቦች እንደታጩ በተለያዩ ዘገባዎች እየተገለፀ ነው፡፡ ለዋንጫው ከታጩትዋናዎቹ ሪያል ማድሪድና ባርሴሎና ከስፔን ፤ባየር ሙኒክ ከጀርመን እንዲሁም ቼልሲና ማንችስተር ሲቲ ከእንግሊዝ ናቸው፡፡የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ በየዓመቱ በአማካይ እስከ 300 ሚሊዮን ተመልካች በመላው ዓለም የሚያገኝ ነው፡፡ ዘንድሮ ለ60ኛዋ ዋንጫ የሚደረገው ፍልሚያ ከ7 ወራት በኋላ በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ውስጥ በሚገኘው ኦሎምፒያ ስታድዮን ይስተናገዳል፡፡ ባለፈው የውድድር ዘመን 10ኛውን የሻምፒዮናነት ክብር በመቀዳጀት የተሳካለት የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ በተለያዩ ትንተናዎች፤ ቅድመ ትንበያዎች እና ውርርዶች ዘንድሮም ለሻምፒዮንነት በመጠበቅ የላቀ ግምት ወስዷል፡፡ ስለሆነም ሪያል ማድሪድ ምናልባትም ለ11ኛ ጊዜ ዋንጫውን በማንሳት የውድድሩን የከፍተኛ ውጤት ክብረወሰን በማሻሻል አዲስ ታሪክ ሊሰራ እንደሚችል በብዛት ተገምቷል፡፡ ይሁንና ባለፉት 24 ዓመታት በተከታታይ ሁለት የውድድር ዘመናት በማሸነፍ የሻምፒዮንነት ክብሩን ሊያስጠብቅ የቻለ ክለብ ግን የለም፡፡ በሻምፒዮንስ ሊግ የቅርብ ታሪክ ዋንጫዋን በተከታታይ ሁለት የውድድር ዘመናት ለማሸነፍ የበቃ ክለብ በ1990 እኤአ ላይ የጣሊያኑ ኤሲ ሚላን ብቻ ነው፡፡ ከዚያን በኋላ በተካሄዱት 24 የሻምፒዮንስ ሊግ የውድድር ዘመናት በሻምፒዮንነት ክብሩ የቀጠለ አልነበረም፡፡ በውድድሩ የቅርብ ጊዜ ታሪክ በቀደመው ዓመት ዋንጫውን አሸንፈው የሻምፒዮናነት ክብራቸውን ለማስጠበቅ እስከ ፍፃሜ ደርሰው ያልሆነላቸው 4 ክለቦች ነበሩ፡፡ ኤሲ ሚላን፤ አያክስ፤ ጁቬንትስ እና ማንችስተር ዩናይትድ ናቸው፡፡ በዓለም የእግር ኳስ ስፖርት የሚንቀሳቀሱ እውቅ አቋማሪ ድርጅቶች ለዋንጫው ድል ከፍተኛ ግምት በመስጠት አነስተኛ የውርርድ ገንዘብ ያቀረቡት ለስፔኑ ክለብ ለሪያል ማድሪድ ነው፡፡ ባየር ሙኒክ፤ ባርሴሎና፤ ቼልሲ እና ማንችስተር ሲቲ እንደቅደምተከተላቸው በአቋማሪዎች በየደረጃው የውርርድ ሂሳብ ወጥቶላቸው ለሻምፒዮንነት ክብሩ ተጠብቀዋል፡፡

ለናሙና ያህል ቢስፖርትስ የተባለ አቋማሪ ድርጅት ያወጣውን የውርርድ ስሌት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ቢስስፖርትስ 32 ክለቦች በሚፎካከሩበት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የዋንጫ ፉክክር ሪያል ማድሪድ 19.03 በመቶ የአሸናፊነት ግምት እንደሚሰጠው አመልክቶ፤ ባየር ሙኒክ 16.69፤ ባርሴሎና 15.51 ፤ ቼልሲ 11.87 እንዲሁም ሲቲ 6.7 በመቶ የማሸነፍ እድል እንደሚኖራቸው በመጥቀስ የውርርድ ሂሳቡን አስታውቋል፡፡ በሌላ በኩል ታዋቂው የእግር ኳስ ዘጋቢ ድረ ገፅ ጎል የአንባቢዎቹን ድምፅ በመሰብሰብ በሰራው የሻምፒዮንነት ትንበያ ላይ ዋንጫው የባርሴሎና ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል፡፡ እንደጎል ድረገፅ አንባቢዎች ግምት 60ኛው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ለማሸነፍ 25.6 በመቶ እድል በመያዝ ባርሴሎና ቀዳሚ ነው፡፡ ቼልሲ በ25.5፤ ሪያል ማድሪድ በ13.2 እንዲሁም ባየር ሙኒክ በ11 በመቶ ድምፅ አግኝተው በተከታታይ ደረጃ ለዋንጫው ግምት ተሰጥቷቸዋል፡፡ ከአሰልጣኞች መካከልም ለዋንጫው አሸናፊነትና ለታሪካዊ ስኬትም የተጠበቁ አሉ፡፡ ጆሴ ሞውሪንሆ ከፖርቶና ከኢንተር ሚላን በኋላ ከቼልሲ ጋር በሶስተኛ ክለብ ጋር ዋንጫ በማንሳት ታሪክ መስራታቸው ግምት ተሰጥቶታል፡፡ ለሪያል ማድሪዱ አንቸሎቲ እና ለባየር ሙኒኩ ፔፔ ጋርዲዮላ ተመሳሳይ ታሪኮች ይጠበቃሉ፡፡ ክለባቸው አርሰናል ዘንድሮ ለመጀመርያ ጊዜ ሻምፒዮንስ ሊግን ማሸነፍ እንደሚችል በይፋ የተናገሩት ደግሞ አርሴን ቬንገር ናቸው፡፡ ቬንገር 90 በመቶ የዋንጫ ግምቱ ለሪያል ማድሪድ፤ ባርሴሎናና ባየርሙኒክ ቢያጋድልም፣ በሻምፒዮንስ ሊግ ልምድ ያለው አርሰናልም ለመጀመርያ ጊዜ ሻምፒዮን ለመሆን ተስፋ የሚኖረው ዘንድሮ ነው ብለዋል ፡፡

ከተጨዋቾች ለዋንጫው ያለውን እድል በተመለከተ ከተናገሩት ዋንኛው ተጠቃሽ የባርሴሎናው ሊዮኔል ሜሲ ነው፡፡ የካታላኑ ክለብ ከ3 የውድድር ዘመናት መራቅ በኋላ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ሊወስድ የሚበቃው በሊውስ ስዋሬዝ ምክንያት እንደሚሆን ሊዮኔል ሜሲ ተናግሯል፡፡ የሮናልዶ የወርቅ ኳስ ሃትሪክ እና ትንቅንቁ በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) እና በታዋቂው የፍራንስ ፉትቦል መፅሄት ትብብር ለሚከናወነው የ2014 የዓለም ኮከብ እግር ኳሰኞች ምርጫ የቀረቡ እጩዎች ከሁለት ሳምንት በፊት ታውቀዋል፡፡ መላው ዓለም በጉጉት በሚጠባበቀውና ዋናው ሽልማት የሆነው የወርቅ ኳስ ነው፡፡ 23 ተጨዋቾች የመጨረሻ ዕጩዎች ሆነው ቀርበውበታል፡፡ አሸናፊው ከዓለም ዋንጫ ወይንስ ከሻምፒዮንስ ሊግ ይገኛል የሚለው ጉዳይ እያነጋገረ ነው፡፡ የኮከብ ተጨዋች ምርጫው በስፖርታዊ ብቃትና ዲሲፕሊን ተለክቶ ይበረከታል፡፡ በድምጽ አሰጣጡ ላይ በታዋቂው ፍራንስ ፉትቦል መጽሔት አማካኝነት ከመላው ዓለም የተውጣጡ ጋዜጠኞች እንዲሁም በፊፋ ስር ደግሞ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር አባል የሆኑ አገራት የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞችና አምበሎች ይሳተፋሉ፡፡ ዘንድሮ ለወርቅ ኳስ ሽልማት ተፎካካሪ ከሆኑት 23 እጩዎች መካከል የስፔኑ ላሊጋ 10 ተጨዋቾች በማስመረጥ ይመራል፡፡

የጀርመን ቦንደስ ሊጋ 6 እንዲሁም የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ 5 ተጨዋቾች ከእጩዎቹ ተርታ በማካተት ተሳክቶላቸዋል፡፡ ለ2014 ወርቅ ኳስ ሽልማት ዋና ተፎካካሪዎች የሆኑት የሪያል ማድሪዱ ክርስትያኖ ሮናልዶና እና የባርሴሎናው ሊዮኔል ሜሲ መሆናቸው በተለምዶ ቢነገርም የዓለም ዋንጫን ያሸነፉት የጀርመን ተጨዋቾች ዋና ተቀናቃዐኞቻቸው ናቸው፡፡ ጀርመናዊያኑ ፊሊፕ ለሃም፣ ቶምስ ሙለር፣ ማኑዌል ኑዌር እና ማርዬ ጐትዜ ፊፋ ለራሱ ውድድሮች በሚሰጠው ግምት ከመጨረሻዎቹ 3 እጩዎች ተርታ የመግባትና የማሸነፍ ዕድል እንዳላቸው እየተገለፀ ነው፡፡ ከጀርመናውያኑ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዎች ከባድ ፉክክር ባሻገር በ2014 የዓለም ኮከብ ተጨዋቾች ምርጫው ከፍተኛ የማሸነፍ ዕድል እንዳለው የሚነገርለት ፖርቱጋላዊው የሪያል ማድሪድ ተጨዋች ክርስትያኖ ሮናልዶ ነው፡፡ ሌላ የቅርብ ተፎካካሪው ሊዮኔል ሜሲ ነው፡፡

ክርስትያኖ ሮናልዶ በ2014 ብዙ ስኬቶች ነበሩት፡፡ በአውሮፓ ትልልቅ ሊጎች ኮከብ ግብ አግቢነት የወርቅ ጫማ ለሶስተኛ ጊዜ መሸለሙ ተጠቃሽ ነው፡፡ ባለፈው የውድድር ዘመን ከሪያል ማድሪድ ጋር 10ኛውን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ድል በማግኘቱ፣ በ17 ጐሎች የውድድሩ ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ መጨረሱ፣ በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ምርጫ የዓመቱ ኮከብ ተጨዋች ሆኖ መመረጡና ከሁለት ሳምንት በፊት የላሊጋው ኮከብ ሆኖ አራት ልዩ የክብር ሽልማቶችን ማግኘቱ ለወርቅ ኳሱ ሽልማት የሚባቀበትን ሁኔታ አስፍቶለታል፡፡ ሮናልዶ ምንም እንኳን በዓለም ዋንጫ ከአገሩ ብሔራዊ ቡድን ጋር ስኬታማ ባለመሆኑ በምርጫው በፊፋ አባል አገራት ሊያገኛቸው የሚችላቸውን ድጋፎች ቢያወርድበትም 2014 ከገባ በክለብ ደረጃ በ44 ጨዋታዎች 45 ጐሎች ማስመዝገቡ የውድድር ዘመኑ ምርጥ ተጨዋች ያደርገዋል፡፡ ብራዚል ባዘጋጀችው 20ኛው የዓለም ዋንጫ አገሩን አርጀንቲና ለፍፃሜ ያደረሰው እና የዓለም ዋንጫው ኮከብ ተጨዋች ሆኖ የተመረጠው አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ ምናልባትም ከሮናልዶ ጋር ብዙ ተፎካካሪ የሚሆንበት ስኬት የለውም፡፡ ይሁንና ሊዮኔል ሜሲ በሻምፒዮንስ ሊጉ የ4ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ክለቡ ባርሴሎና የሆላንዱን አያክስ 2ለ0 ሲያሸንፍ ሁለቱንም ጎሎች በማግባት በውድድሩ ታሪክ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አግቢነትን በ71 ጎሎች ከቀድሞው ስፔናዊ ራውል ጋር በመጋራት ከሮናልዶ የቀደመ ስኬት ማግኘቱ ትኩረት እየሳበለት መጥቷል፡፡ ራውል 71 ጎሎች ያስመዘገበው በ144 ጨዋታዎች ሲሆን ሜሲ በ90 ጨዋታዎች ክብረወሰኑን ተጋርቶታል፡፡ ሮናልዶ በ107 ጨዋታዎች 70 ጎሎች አስመዝግቧል፡፡

ሊዩኔል ሜሲ የወርቅ ኳስ ሽልማትን ለ4 ጊዜያት ያሸነፈ ሲሆን ክርስቲያኖ ሮናልዶ ያሸነፈው ደግሞ ሁለቴ ነው፡፡ በ2013 የዓለም ኮከብ ተጨዋች ምርጫ ላይ ኢትዮጵያውያን በነበራቸው ተሳትፎ የብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የነበሩት ሰውነት ቢሻው ሮናልዶ፣ ኢንዬስታ እና ኔይማር በማለት ኮከባቸውን በደረጃ አከታትለው ሲመርጡ ፤ የብሔራዊ ቡድን አምበል የነበረው ደጉ ደበበ ዣቪ፤አንድሬ ፒርሎና ቶሞስ ሙለርን ብሎ ነበር፡፡ በጋዜጠኞች ዘርፍ ደግሞ ታዋቂው መንሱር አብዱልቀኒ ፍራንክ ሪበሪ፤ ክርስትያኖ ሮናልዶ እና ሽዋንስታይገር ብሎ ድምፅ ሰጥቶ ነበር፡፡ በነገራችን ላይ ሰሞኑን ፎርብስ ለዓለም ስፖርተኞች ለዓመቱ ከፍተኛ ገቢ ባወጣው ደረጃ ሮናልዶ በ64 ሚሊዮን ዩሮ ከእግር ኳስ ተጨዋቾች አንደኛ ከሁሉም ስፖርተኞች ሁለተኛ ደረጃ አለዐው፡፡ የሮናልዶ ገቢ 41.6 ሚሊዮን ዩሮው ከደሞዝ ሲሆን 22.4 ሚሊዮን ዩሮ ደግሞ ከተለያዩ የንግድ ውሊች እና የስፖንሰርሺፕ ክፍያዎች ያገኘው ነው፡፡ ሜሲ በ52፤ ዝላታን ኢብራሞቪች በ32.32፤ ጋሬዝ ቤል በ29.12፤ ፋልካኦ በ28.32 እንዲሁም ኔይማር በ26.88 ሚሊዮን ዩሮ ገቢያቸው ተከታታይ ደረጃ ወስደዋል፡፡ ፡

Source: addis adamass newspaper

በአፋር ክልል በኤሊ ዳኣር ወረዳ በኩፍኝ በሽታ የ9 ሰዎች ህይዎት አለፈ

0
0

አኩ ኢብን ከአፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው

ከአንድ ሳምንት በፊት በኤሊ ዳኣር ወረዳ በጌራ ከተማ የታየው የኩፍኝ በሽታ እሰካሁን ወደ ሌላ ከአከባቢዎች እየተስፋፋ ስሆን እሰካሁን 9 በተለያዩ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ሰዎች ሞተዋል።
news
አሁንም ሞት አልቆመም በኤሊ ዳኣር ወረዳ የሚገኘው ጤና ጣቢያ 24 የሚሆኑ በሸተኞች እየታከሙ ቢሆንም አሁንም አስፈላጊውን መድኃኒት ባለሞያ እየገኙ እንዳልሆነ የቦታው ምንጮች አያይዘው ዘገበዋል።


ከሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ የተላለፈ ጥሪ

0
0

ከሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ የተላለፈ ጥሪ
unnamed (2)

ዝምታው ለምን ነው? (አንተነህ መርዕድ)

0
0

ዝምታው ለምን ነው?

ኢትዮጵያ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለችው።

  • መንግስት እንደድሮው መግዛት ተስኖታል
  • ህዝቡም እንደድሮው መገዛት ታክቶታል
  • የተቃዋሚው ቋንቋም እንደባቢሎኖች የተከፋፈለበት ወቅት ላይ ነን
  • ከዚያም ብሶ ሚድያው ታፍኗል።

ትግሉን በተደራጀ መልክ ዳር የሚያደርስ ጠርቶ ባልወጣበት ሁኔታ ህዝባዊ ዓመጽ ሊፈነዳ ጫፍ ላይ መድረሱን ለማወቅ ሊቅነት የሚጠይቅ አልሆነም። በዚህ ሁኔታ ዐመጽ ከተነሳም የሚከተለው ትርምስና እልቂት ቀላል ስላይደለ ንፁህ ህሊና ያለው ሁሉ በግልፅ ታይቶት መፍራት አለበት። ይህ ፍርሃት በጎ ፍርሃት ሊሆን የሚችለው ወደ መፍትሄው መሄድ ካስቻለን ነው።

በእንደዚህ ዓይነት ፈታኝ ወቅት ነፃ ሚድያ ግዙፍ ሚና አለው።

  • ህዝብ ተገቢ መረጃ እንዲኖረውና እርምጃው በእውቀት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን በማድረግ
  • በእንደዚህ ዓይነት ቀውጢ ወቅት ብቅ የሚሉ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች ህዝባዊ ትግሉን ወደ ተለየ አቅጣጫ እንዳይመሩትና ለሌላ ተስፋ አስቆራጭ ክስተት እንዳይዳርጉት በማጋለጥ (ይህ ለታሪካችን አዲስ አይደለም)
  • የህዝቡን የጋራ ብሶትና የጋራ ተስፋውን አጉልቶ በማውጣት ወደ ብሄራዊ መግባባት ለመድረስ መገናኛ ብዙሃን ከባድ ሃላፊነት አለባቸው።

ስለሆነም አምባገነን ስርዓቱ ሚድያውን ለማዳከም ያሰደደንና በሁሉም የዓለም ክፍል ተበትነንና ተደላድለን የምንኖር ሆንነ አሁንም በወከባው ውስጥ ያለነው ተረጋግተን የምንነጋገርበት ወቅት አሁን ነው። የሃሳብ ልዩነቶች ሊኖሩን ይችላሉ። እንዲያውም “የሃሳብ ልዩነቶች ለዘለዓለም ይኑሩ”የሚለውን መፈክር ልናነግበው የሚገባ ነው። ነገር ግን የሃሳብ ልዩነት መኖሩ የሃሳብ ግብይትን ያቆመው እለት የሃገር ውድቀት እሙን ነው። የሃሳብ ልዩነት የሃሳብን ግብይትና መቀራረብን ሊያቆመው አይገባም። (ኮሙኒኬት የማያደርጉ ኮሙኒኬተርስ) ከመሆን እንውጣ።

ሀገርን የማዳን ቃል ኪዳን በሁላችንም ዘንድ እንዳለ ይታወቃል። ችግሩ ማን ይጀምረውና እንዴት ይጀመር የሚለው ነው።

  • የታሰሩ ወንድሞቻችን የሚከፍሉትን መስዋዕትነት በፀጋ ቢቀበሉትም የቤተሰቦቻቸውን ጫና የማቃለል የሞራል ሃላፊነት አለብን።
  • በጎረቤት አገሮች በስደት የሚሰቃዩ የሙያ ባልደረቦቻችን ያሉበትን ሁኔታ ያለፍንበት ሁሉ እናውቀዋለን። በችግሮቻቸው መድረስ ይኖርብናል።
  • ከሁሉም በላይ ግን ማንም ሳያስገድደን ለራሳችን ቃልኪዳን የገባነው ህዝብን ተመጣጣኝ መረጃ የመስጠት ሥራ እዚህ ደርሶ አላበቃም። እንዲያውም ተፈላጊነቱ እየጎላ ነው።

“ተባበሩ ወይም ተሰባበሩ” የሚለው የህዝብ መፈክር ለተቃዋሚዎች ብቻ ሳይሆን ለጋዜጠኞችም ጭምር ነው። በነጠላ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ የማይናቅ ቢሆንም በጋራና በተቀናጀ እንደሚደረገው ፈጣንና አመርቂ ውጤት አያመጣም። አገሪቱ ያለችበት ፈታኝ ሁኔታ ፋታ የሚሰጥ ባለመሆኑ በተገኘው መንገድ ሁሉ ግንኙነቱ ይቀጥልና በህብረት ወደ አንድ አቅጣጫ እንንቀሳቀስ። ስለዚህም መነጋገር እንጀምር። “ባለቤት ካልጮኸ ጎረቤት አይደርስም” ነው ተረቱ። ህዝቡን እንዲረዳን የምንጠራው መጀመርያ ራሳችን ችግሩን አውቀን ስንንቀሳቀስ ነው። ለችግራችን እኛው መፍትሄ እንፈልግለትና በአገር ጉዳይም የማንናቅ የመፍትሄ አካል እንሁን። ዝምታው ለምን ነው?

ቸር እንሰንብት

አንተነህ መርዕድ

Comment

 

የቁርሾ ቋሳ –አለቅት ዝቅጠት። (ሥርጉተ ሥላሴ)

0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 09.11.2014 /ዙሪክ – ሲዊዘርላንድ።/

በቅድሚያ ዬጸሐፊ አቶ ጌታቸው ሽፈራው “ጥቁሩ አብዮት›› እንዲሁም ዬጸሐፊ ዮፍታሔ „ስምንት ዋና ነጥቦች ከእስራኤላውያን“ ጭብጦቹ በሚሉ እርእሰ ጉዳዮች የተጻፉት የፍላጎታችን ፍሬ ነገር፤ የመንፈስ መርህና መሪ ከመሆናቸውም በላይ መንገድ ጠራጊም ናቸው። አስፈላጊነታቸውም የዓይን ያህል ናቸው። እንደዚህ መስል ጹሑፎች ናቸው „የአሻም ፈሎች“ ሆነው በቃኝን አምርተው ድምጽ የሚመራት የርትህ ሀገር የሚፈጥሩት። ስለሆነም አመሰግናለሁ ከልብ – ጸሐፍትን። ለነገሩ የጸሐፊ ጌታቸው ሽፍራውን ጹሁፍ ሌላ መጻፍ ሳያስፈልግኝ በ07.11.2014 በነበረኝ የቅኔው ልዑል የጸጋዬ ራዲዮ ፕሮግራም /Radio Tesgaye/ ሙሉን ተጠቅሜበታለሁ። የጸሐፊ ዮፍታሄም ለቀጣዩ ዝግጅት ታጭቷል። በተያያዘ ሁኔታ ስለ ኢቦላ ባይረስና ስለ ህዝብ ጉዳይ ግድ ስለማይሰጠው የወያኔ አስተዳደር „ጀብደኝት ..“ የተጻፈውም ወርቅ ነበር – እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

ሰሞኑን አዲስ ዜግነት ደግሞ ተስጥቶናል ሰምታችኋል አይደል የእኔ ውዶች  „የአፍሪካ ቀንድ ዜጎች“ ወይ ማላገጥ። እንዴት ተቀለደ …  ከአፍሪቃ ቀንድ ዜጎች ጋር በአካባቢያችን የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ፣ እንዲሁም በስነፅሁፍ ነክ ርእሰ ጉዳዮች፣ ካደረግሁዋቸው ውይይቶች እጅግ ብዙ ትምህርት ቀስሜያለሁ።”

የዛሬው ጸሐፊ  ገዳ ገብራብ ነገ ደግሞ ተሰፋዬ አክራም በመባል ወደ ሳውዲ ወይንም ተስፋዬ ሮቬርቶ በመባል ወደ ጣሊያን እንደ ሽንብራ ቂጣ መገላበጡን እንጠብቃለን። እንዲህ በሚጸዬፈውና ግማሽ ዕድሜውን በጨረሰበት የጥላቻ መግል ውስጥ ሆኖ ስለምን በተገፋውና በተረገጠው፤ በተገለለውና በተናቀው አማርኛ ቋንቋ መጻፍ እንዳስፈለገውም ፈጽሞ አልገባኝም። ለነገሩ እኔ ለወደቀ እንጨት ብዙም ቁብ ስለማይሰጠኝ ሰው ከፍቅር ሃፍትነቱ ወደ መፏከት ሲያሰኘው እምለው አልነበረኝም። ለቡጀሌ ለምን ጊዜ ይቃጠል?! ነገረ ግን ዛሬ የተጠላውና አጥብቆ በጥርሱ በያዘው – በተፀዬፈውም የኢትዮጵያዊነትን ሰንደቅን ከፍ ባደረገው ዬምልዕተ ቤት በዘሃበሻ  የካህዲ ጹሑፍ አቅም አግኝቶ ገልባጤን እንዲህ ሲያቀናጣ በማዬቴ ዝም ብዬው ማለፍን መንፈሴ አላስቻለውም።

በቅድሚያ እጅግ የማከብራችሁ የፁሁፌ ታዳሚዎች እና እንዲሁም ልጅነቱን ፈቅደው ለተቀበሉት „አባወራ ኦቦ ሉቤ“ የቤት ሥራ መስጠቱን ወሰንኩ። እናንተም ውዶቼ ብታነቡት አይከፋም። እርእሱ ብቻ ይበቃል። አንዲት የትውልድ ዕንቁ ብቻ አይደለም ብልህ ወጣት መሪ ክብርት ዳኛ ብርቱካንን „ከባህር የወጣች አሳ“ ሲል ቅብጥ ሲል ያዛላጠውን ጨቀጨቅ እሳቤ ለኩት … እንሆ በትሁት ቅናዊ መንፈስ ሊንኩን https://www.facebook.com/ethiopiazare/posts/535876466438109

http://www.ethiopiazare.com/art-56/short-story/2565-birtukan-mideksa-by-tesfaye-gebreab ጹሑፉን ከማንበባቸሁ በፊት ግን የክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዲቅሳ ዬለጠፈውን ፎቶውን እንዴት አበልቆ እንዳወጣው ተመልከቱት። በወቅቱ እኔ እንዲነሳ እጅግ ለማከብረው ወንድሜ ጽፌለት ነበር። ከዚህ በኋላም ነበር በአንድ ቀን ሌሊቱን አክዬ በጉጉት አንብቤ የጨረስኩት „ዬጋዜጠኛው ማስታወሻ“ ክፍል አንድ መጸሐፉ ብዕርና የእኔ ፍቅር ተምሶ የተቀበረው። ለማንኛው ውስጡን በሚገባ ጎብኘት አድርጋችሁ ከእነብልቱ – ፈትሹት። ጠረኑም ጠጋ አድርጋችሁ አሽቱት። በተረፈ ቀጣዩ የህሊና ፍርዱን ለክብረቶቼ ለአንባብያን ትቼ ልጅነቱን የተቀበሉለትን „አባወራ ኦቦ ሉቤ“ ከክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዲቅሳ እና ከጸሐፊ ገዳ ገብረመድህን የትኛው ለደማቸው እንደሚቀርብ እራሳቸውን ይለኩት ዘንድ በአጽህኖት አሳስባለሁ። እንዲህ የተረገጠ – የተጠቀጠቀ – የተወቀጠ – የተናቀ – የተጣለ – የተቃለለ – የተሳለቀበት አካላዊ እትብትና ሥጋ እንደ ገና ደጅ ጥናት ተሄዶለት እውቅና ሰጠኝ አስብሎ በአታሞ ያሳዳከረው ይሄው ገማና ነው። ብልሃት የሌለው ቅላት።

„ከአሜሪካ መልስ እነሆ! በህግ ኦሮሞ ሆኛለሁ። ኦሮሞ መሆን “ኢትዮጵያዊ መሆን” ማለት ግን አይደለም። ወደፊት የኦሮሞ ህዝብ ስለማንነቱ በነፃነት ሲወስን ያን ጊዜ የሚታይ ይሆናል። ኢትዮጵያዊነትን በመተው ኦሮሞ ብቻ ሆኖ መቆየት እንደሚቻል ግን ቀደም ሲል በሞጋሳ ባህል ኦሮሞነትን ከወሰዱ ግለሰቦች ተረድቻለሁ።“

ጸሐፊ ተስፋዬ ጥሩ አብሾ ተጎንጭቶ ብቻ ሳይሆን አብሾው መሥራቱን ያመለከተው መሰረታዊ ነገር የኢትዮጵያ ጠላትነቱን ዝርግፍግፍ አድርጎ ቄጤማ ማድረጉ ነው። እንዲህ ይልናል በግልጽና በስውር ሴራ በገደል ለተወረወሩ፤ ለተገደሉ፤ በስለት ለታረዱ፤ አድራሻቸው ሳይታወቅ ለቀሩ ለተፈናቀሉ ሚሊዮኖች ሥቃይ፤ ለጥላቻ አምራችነቱ፤ ተጠያቂነቱን ብዕሩ ቁማ እንሆ መሰከረች። የተከደነው ተዘሎ እንዲህ አለን ግማሽ የህይወቱን ክፍል የታገለለት አላማ በመጨረሻ በኦሮሞ ህዝብ ፊት ዋጋና ሞገስ ማግኘቱ በትክክለኛው መስመር ላይ ሲጓዝ እንደቆየ ማረጋገጫ ሆኖለታል።” የስለላ ተግባሩ፤ በ6ቢላዋ መብላቱ፤ ደም እዬተጎነጨ በደም ሰብቶ መኖሩን፤ ፍንትው አድርጎ ከነመግሉ አሳይቶናል። „ኢትዮጵያዊነት“ ሲገፋ እንዲህ ያንደፈድፋል። እንዲህ ያስቃዣል። እንዲህ ቅብጥብጥ ያደርጋል። ኢትዮጵያዊነት የመንፈስ ሥነ ህይወት ነው። ኢትዮጵያዊነት ልዕቅናው ሆነ ልዕልናው ዕውቅናው ጥበቡ የመረቀው የአባቱ የአደኖይ ነው። አሁን እንኳን ከሃብቱ ለመውጣት ጋዳ ሆኖ አማርኛ ቋንቋ አስጎንብሶ ያስደገድጋል። ተመስገን!

ስለነገው ቀለበጡሊ ትረካ ደግሞ „አዳማ ላይ ከብቶችን አርብቶ ለመኖር መቋመጡን“ አንብበናል። ሲያምርህ ይቀራል እንላለን። ወንዱ ቀበቶ ከሌለው አንስቶች እምናደርገውን እናውቃለን። በተረገጠና በተናቀ መሬት መልሶ መፈንጨት አይፈቀድም። „ኢትዮጵያዊነቴን ማንም ሊሰጠኝ ወይንም ሊነሳኝ አይችልም“ ባልክበት አንደበት ደግሞ ዛሬ „በህግ ኦረሞ ሆኛለሁ“ ትለናለህ። ያልሆንከውን ልትሆን እንደማትችል ታውቃዋለህ – ጌታው። እንግዲህ በሞጋሳ ስርአት መሰረት ኦሮሞነትን በኩራት የተቀበልኩ በመሆኑ በኦሮሚያና በአካባቢያችን ጉዳዮች ላይ የመፃፍ ብቻ ሳይሆን፣ የመሳተፍ ጭምር ግዴታ አለብኝ።„ አባ አዋጉ ያው ለማንኮር። ያው ለማተራመስ – ዬአረም አጥሚት። ኦሮሞ ሲከበር ልጁንም ነው። ሲወዱ እስከ ንፍጥ ልጋጉ …  ብርቴ ከዬት የመጣች መሰለችህ? የቅኔው ልዑል ጸጋዬ ገ/መድህን ምንጩ ማን መሰለህ? ለልዑሉ አክብሮት ካለህ ለእትብቱም …. „ትንሽ ሥጋ በመርፌ ትውጋ“ ይህን ለአቶ በረከት ንገራቸው – ከኑዛዜያቸው በፊት__ ያው በመስመራችሁ እዬተገናኛችሁ የሰብዕና ዘረፋችሁን አና ብላችሁት የለ። ለማንኛውም አራባና ቆቦ እዬረገጡ አምታቶ መኖር – አላጋጦ መኖር፤ በደም ቋንጣ ንግድ እንዲሁም መዘባነን ህልም ነው።

ሌላው የተነሳው ነገር የእኛን ልቦና ፈታሽና ነገር አዋቂ ሆነህ መገኘትህ ደግሞ የሚገርም ገደል ነገር ነው። ኢትዮ አማሮች ደግሞ ከወያኔ በከፋ ደረጃ የኦሮሞን ህዝብ መብቶች ለማፈን ጊዜ የሚጠብቁ መሆናቸውን የኦሮሞ ህዝብ ጠንቅቆ ሊረዳው ይገባል። በመሆኑም ከወያኔ መውደቅ ቀጥሎ የኦሮሞ ህዝብ ከባድ ፈተና የሚገጥመው ከእነዚሁ እላዩ ላይ መጥተው ቁጭ ካሉበት ሰፋሪዎች ነው።” ቃሬዛ የዋኘበት ዝልቦ ትንተና …..

እንዲህ ለዛቀጠ ለወረደ ሰብዕና፤ ተፈጥሮ ለሚያረግርግ እንዳንተ ላለ ሊሆን ይችላል። ይህ ስንጥቅና ትርትር ፈት ግልቢያ። ለጥንቁቁ የኢትዮጵያ ህዝብ አካል ለሆነው አማራ ግን የሚበልጥበት እናት ሀገሩና ሰንደቅዓላማዋ ነው። በእኔ ውስጥ ያለው ነገር እኔን እንጂ ሌላውን ሊወክል አይችልም። ትናንትም ዛሬም ማንነት ችግር ያለበት በወደቀ በተነሳ – በፈረጠ በዘለለ ቁጥር ማተባችን አንበጥስም። ተግባባን?! መስመራችን አፈራችን መሆኑን ስለምናወቅ እንደማተባችን ኖረን እንደ ማተባችን እናልፋለን። እኔን ለመተርጎም ኢትዮጵያዊነትን የማንበብ ሆነ የመተርጎምና የማመሳጠር አቅም የተሰጠው ብቻ ይሆናል ስለ እኔ ስለ ሥርጉተ ስሜት ፍላጎት ራዕይ የውስጥ አዋቂ ሊሆን የሚችለው። …. ስለዚህ የእኛን ለእኛ ተወው። አንተ የተፈጠርክበትን በደም አላባ ተዘፍቆ ውሎ ማደር፤ በሴራና በተንኮል በክቶ ቁርሾን ታቅፎ ለቂም ሰግዶ በቋሳ ዘልቦ መኖሩን ለመረጠከው ስለራስህ እንዲህ ዘርግፍ …. ዝርግፍ —-

ግን ክብሮቼ የእኔዎቹ የሀገሬ ልጆች ደሞቼ „አለቀት“ ታውቃላችሁን? አለቀት ውሃን ተግን አድርጎ ውሃን መስሎ የሚኖር ተውሳክ ነው። ከብቶች ውሃ ሲጠጡ ሰለል ብሎ ውሃን ተመሳስሎ ገብቶ ወይ አይወጣ ወይ ወደታች አይወርድ ጉሮሮ ላይ ተሰንቅሮ ከብቶችን አሰቃይቶ ይገድላል። ለዚህ ሙያ የተካኑ ሀገረሰብ ሃኪሞች አሉ። ከብቱ ከመሞቱ በፊት የባህል ሃኪሞች ከደረሱ አለቅቱ ሲወጣ ደም ጎርሶ ነው የሚወጣው። ከወጣ በኋላ ደግሞ እንደ ቅል ተነፍቶ በደም ተቀብሮ ይገኛል። የዘመናችን አለቅት ለዛውም የቁርሾና የቋሳ ቀንዳሙ ደግሞ ፀሐፊ ገብረ ጉንዳን ነው።

ሌላው ደግሞ ምንድን ነው የተባለነው? „ጉዳይ ሳይኖረኝ ወደ ምጽዋ ሄድኩ። ሰላምታ ላቀርብ“ አዬ ትዕቢት። ትናንት ወደ ምፅዋ ሄጄ ነበር። ምፅዋ የሚያስኬድ ምንም ጉዳይ አልነበረኝም። የተጓዝኩት ለቀይባህር ደረት የሞቀ ሰላምታ ለማቅረብ ብቻ ነበር። የቀይባህር የምሽት ማእበል ናፍቆኝ ነበር። የምፅዋ ሙቀት በጣም ናፍቆኝ ነበር። የጀበና ቡና እና ፈንዲሻ – ባህሩ ዳርቻ ናፍቆኝ ነበር።” …. ድንቄም ቡና “ወደሽን ቆማጤ ንጉሥ ትመርቂ” አሉ …

አላስችልህ አለህ? ግን ለመሆኑ የጤፍ ጠላ ጠጥተህን ታውቃለህ? ታቅፈው ወይንም አሽኮኮ አድርገኸው ዙር። አባቶቻችንና ወንድሞቻችን እንደ ክረምት እንጨት አካላቸው ተደርድሮ በበቀል – ታጭደው – የተቃጠሉበት – የነደዱበት – አመድ የሆኑበት ነው። የሰው ልጅ የማገዶ መሬት ነው። የአካላችን ጢሱ ከመንፈሳችን ውስጥ አለ። ለአንተ ግን እንኳን ለዚህ አበቃህ ክክክክክክክከ —- ከውስጡ ገብተህ ብትጠመቅ ምን አልባት መላ አሳጥቶ የሚያስለፈልፍ ጉድህ ይለቅህ ይሆን? እስኪ ሞክረው?

ሌላ ምን ነበር የተደስኮረልን ደጎስ ያለውን ልበወለድ ትልም „የአሜሪካ ቆይታዬን በተሳካ ሁኔታ አጠናቅቄ ቀጣዩን ዳጎስ ያለ ታሪክ ቀመስ ልቦለድ ድርሰት ለመፃፍ ወደ ኤርትራ ተመልሻለሁ።” ሪፖርቱ ለዬትኛው ታዳሚህ ነው? ጉብራህን የተረገጠኽ ከቶ ይኖር ይሆን? ማን ጠዬቀኽ?! ከተሳካልህ ለአማርኛ ተነጋሪዎች ሳይሆን ለመረጥከው ቋንቋ አወራርደው … አይመስልህም? ይመስለህ።  …. „ስለክብርት ዳኛ ብርቱካን የጻፍከው እርእስ ለአንተ ነበር እኮ የተነበይከው? „ከባህር የወጣ አሳ“ ይህ የሚስማማው እንደ አንተ ላሉ ማንነታቸው ጠፍቶባቸው በበታችንት ስሜት ለሚወዛወዙ ዝልቦች ይመስለኛል። የችግርህ ቁንጮው በለው ጅራቱ ማንነትህን የሚመልስልህ መንፈስ አላገኘህም ምን አልባት ብትተረተር ልታገኘው ትችል ይሆናል። ተሰንጠቅ እና እስኪ የቀረህ ይኸው ነውና እዬው —–

„ኢትዮጵያዊ ነኝ“ ያልከን አንተው። እኛ የትኛውን አማላጅ ይሆን ዬላክንልህ? ናልን እባክህ ብለን ደጅ አልጠናነኽ? ዛሬ ደግሞ ከረፋኝ የምትለን አንተው ነህ። ትዋዥቃለህ ማህለቋ እንደተሰበረ መርከብ። ቀድሞ ነገር ለጥበብ ሰው „ሰው መሆኑ ብቻ ይበቃው በነበር“ ጥበብ የሰማይ ሥጦታ ስለሆነ ድንግልናው ቅድስናው ቤተ መቅደስ ነው። ጥበብ ታቦት ነው። የሚወደድ የሚከበር ለሥነምግባሩ በፍቅር ፈቅደው የሚገዘሉት ድንበር ወሰን ያልተሰራለት ፍጥረት ለተባለ ቀርቶ ለድንጋይ ቅሬቶች ለግዑዛን ሳይቀር እንደ ተፈጥሯቸው ብርቱ ጥንቃቄ የሚያድርግ የሰብዕና ልዩ መለያ ሰማያዊ ጸጋ ነበር። አዳካርከው … አንቦጨራቅከው …. ይብላኝላት አንተን አግብታ ለምትኖር ብዕርና ብርና …. መጥኔ! ….. ፈርዶባት … ያተረፈቸውን ፍቅር በቤንዚን አርክፍክፎ ከሚያቃጥል ግልብ ተጠግታ መለመላዋን ቀረች ….

አንተ በገዢው ፓርቲ ውስጥ ሆነህ የሰራኸው ደባ፤ ዛሬም አንተን አምነው የተጠጉትን የበላህ የቀን ጅብ ነህ። ስለላና ጥበብን እንዴት አድርገህ አጋብታሃቸው ኖርክ ከቶ … ?! ይገርማል አካልህን መክሊትህ ተሸክሞት መኖሩ … እራሱ አንድ የጨለማ መጸሐፍ ያጽፋል። ዳፍንት ነህና —

ሌላው ድሉም ቅርብ እንደሆነ ተንብዬሃል። ዘለልክ …. የፈጣሪንም ሥልጣን ቀማኸው። ልክ ይኑርህ። በእጅህ ምን እንዳለ እናውቃለን። ግን እሳቱ ከዚህም አለ። የምትፎክርበት ይህ ከንቱ ዓለም በሰው ሰራሽ ጥበብ ሰክኖ አያውቅም። የፈጣሪ ታምር ብቻ ነው ደምን አርግቶ ሰውን አቁሞ የሚያስኬደው፤ መሬትን ካለ ካስማ ሰማይን ካለባላ ያቆመ አምላክ አላት … ክብርት ልዕልት ኢትዮጵያ ….  አይመስለህ ወድቃ የማትወድቅ ደክማ የማትደክም አላዛር ናት።

አሁን ግራ ቀኙ እሳት ነው። የአባ ገብርህይወትና የእማማ ብሬ ልጅ ጠ/ሚሩ እሱ ነው ያው እትብትህ። … ጽጌ መልስ ይኖራታል ብዬ ነበር …  አቮይም ተዛው ናቸው ዘሃ ግራው ተጀምሮ እስኪጨርስ ድረስ በጠላት የታጠረች ሀገር ናት ጥንታዊቷ ቀደምት ሀገር ንግሥት ኢትዮጵያ። … ግን አምላክ አላት። የማያንቀላፋ – የማይተኛ … ከቶውንም የማይረሳት …. 90 ሚሊዮን ህዝብ ከተነሳ ደግሞ የግራ ቀኙን ትዕቢቱን ሁሉ ያስተነፍሳል። የቆመ የሚመስለው ሁሉ በቁሙ ነቅዞ … ከንቱነት ይጨፍርበታል ….

ሽልማት ደግሞ ሰጠህ። ተቀናጣህ – ካለልክህ ተወጣጠርክ – ተወራጨህም። እራስህ በምናብህ በምትፈጥረው ጥያቄ ተጠይቀህ መልስ እንደሰጠኽበት ታወራለህ። „ወሎ …. ምን?“ መብቱ ያለን ሰዎች ነው የመናገር መብት ያለን። ሰባራ ገል ለምን ነበር አገልግሎት የሚውለው? እቴ አምጡልኝ እባካችሁ? ኣህ መጣልኝ  … ለእሳት መጫሪያነት … አዎን የአግልግሎት ጊዜህ መጠናቀቁን እወቀው …. ደሙ አስክሮ እራሱ ይደፋሃል … መጣፊያ – መለበጃ የድሪቶህ ማግኘትህ እያወሩ ብቻን ከመሄድ ይታደግኽ ይሆን?!

መቋጫ ለዳርቻ —- ከገለባ ጋር። እንደራስህ ኖረህ አፈር ለመሆን ያብቃህ ልበልህ ወይንስ ማንነትህን ሳታገኝ እንደባዘንክ ስንብት ይሁንልህ? የተሻለህን ውስድ። ከዜሮ በታች —

ውዶቼ የሞተ ውይብ መንፈስ ሊንክ ካስፈለጋችሁ ይኼው ነው። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35970

ለእኔዎቹ ብቻ … አብረን በመቆዬታችን ደስ አለኝ። መለዬቴ ደግሞ ጊዜያዊም ቢሆን ከፋኝ። በሌላ ጉዳይ እስንገናኝ ድረስ ሁሉንም ውስጤን በልግስና ሸልሜ ልሰናበት። መሸቢያ ሳምንት።

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል።

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

እርም (ሐራም) 1 (ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ)

0
0
ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ጥቅምት ፳፻፯ ዓ.ም.
በባህላችን የሰው ስም በትርጉም አልባነት እንደማይለጠፍ፤ ከሰውነታችን ጋራ የሚገናኙ ነገሮችም ስማቸው ከመነሻቸው ጋራ የተያያዘ ነው። “እንጀራ” ከምድራዊ ህይወታችን ጋራ ከተገናኙት መሠረታውያን ነገሮች አንዱ ነው። እንጀራ እስካሁን ድረስ የተነሳበትን የታሪክ ትዝታ ተሸክሞ ብዙ ዘመን ተጉዟል። እንጀራ ከወላጅ እናቱ ከጤፍ ጋራ በመተባበር ከኢትዮጵያና ከህዝቧ ጋራ ያላቸው ግንኙነት ሩቅና ጥልቅ ትስስር እንዳለው ሁሉ፤ ከመብላት ስሜትና ሱስ ጋራ ተዋህዶ በሰውነታችን ስለጋባ፤ ዝንት ዓለም የኖረ ይህን ጥብቅ ግንኙነት የሚያስለቅቅ፤ ጥብቅ ምክንያት መቅረብ ያለበት ይመስለኛል። ከኢትዮጵያ እየተጫነ የሚመጣውን እንጀራ አትብሉ ወደሚለው ሀሳብ ምን እንደወሰደን በግልጽ ለማቅረብና፤ እንዴትስ እናቁም ወደ ሚለው ውይይት ለመግባት፤ ከጉባዔ ትምህርት ቤት መምህራን የሰማሁትን ለውይይታችን መንደርደሪያ ብናድርገው የሚጠቅም ይመስለኛል። –-  [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]——

አቶ በረከት ስምዖን ያስገቡትን የስልጣን ጥያቄ ሕወሓቶች እንዳልተቀበሉት ተነገረ; “እለቃለሁ የሚል ከሆነ ሃብቱ መመርመር አለበት”ተብሏል

0
0

ምንሊክ ሳልሳዊ

-በውሳኔው የማይስማማ ከሆነ በሱና በቤተሰቡ በወዳጆቹ ስም የተመዘገበው ሃብት እንዲጣራ ተብሏል::
-ሳያገግሙ ስብሰባ እንዲመራ እና ሚዲያ ላይ እንዲቀርብ ታዟል::

የብአዲን/ኢሕአዲግ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ያቀረቡት የስልጣን መልቀቂያ ለጊዜው በሚል ውድቅ መደረጉን ሆኖም በቅርቡ መልስ ይሰጥበታል ሲሉ የሕወሓት ባለስልጣናት መመለሳቸውን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::
Bereket Simon weeping with his wife over Meles Zenawi's death
አብዛኛውን ጊዜ ራሳቸውን ከቤት በማስቀመጥ እና በማዝናናት ያሳልፋሉ የተባሉት አቶ በረከት ስምኦን በልባቸው ላይ በተገጠመላቸው አርቴፊሻል መሳሪያ በጤንነታቸው ላይ ከባድ እክል እንደፈጠረባቸው እና ከወራት በፊት ሳኡድ አረቢያ ታክመው ቢመጡም ሊሻላቸው እንዳልቻለ እንዲሁም ባለፈው ሳምንት በድጋሚ ቢሄዱም ሆስፒታሉ ተስፋ እንዳስቆረጣቸው ሲታወቅ ከሕክምና መልስ ወደ ቢሯቸው የገቡት በጣት የሚቆጠር ቀናት እንደሆነ ታውቋል::

ይህን ሰሞን ስብሰባ መምራት አለብህ በሚዲያ መታየት አለብህ የሚል ግዳጅ ከሕወሓት ባለስልጣናት ወርዶላቸው የተደናበሩት አቶ በረከት ማገገም እንኳን ሳይችሉ በስራ መደራረብ እንዲሞቱ እየተደረገ ነው ሲሉ ከቤተሰባቸው አንዱ የሆኑት ሲናገሩ ተሰምቷል::አቶ በረከት በከፍተኛ ህመም ውስጥ እንዳሉ ሲታወቅ የሕወሓት ባለስልጣኖች የአዜብን ቡድን እንደመቱት ወዲያው በረከትንም ከጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ አሽቀንጥረው ካሳንቺስ አዲስ ቢሮ እንደሰጡት ሲታወቅ መገፋቱ እያንገበገበው በሽታውን እንዳባባሰበት ታውቋል::

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live