Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

Sport: በዚህ ወር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊፋ ደረጃ ተሻሻለ: * ከኡጋንዳ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋል

$
0
0

ፊፋ በየወሩ በሚያወጣው የዓለም ሃገራት የ እግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ በዚህ ወር ካለፈው ወር የተሻለ ደረጃን አስመዘገበች:: የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በፊፋ ወርሀዊው የአገሮች ደረጃ ከባለፈው ወር 132ኛ ደረጃውን ወደ 111ኛ አሻሽሏል::
ethiopia
Afcon2015 በማጣሪያ ጨዋታ ማሊን በሜዳው 3- 2 ማሸነፉ ደረጃውን በ21 ከፍ እንዲል እንደረዳው የዘገበው ኢትዮኪክ የማሊ ብሔራዊ ቡድን ከ59ኛ አንድ ነጥብ አሻሽሎ 58ኛ ይዟል::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ ኢትዮ ኪክ እንደዘገበው የዮጋንዳ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ይፉ ያደረገውን መግለጫ ጠቅሶ ሁጋንዳ በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ጋናን በሜዳዋ November 15 ከማስተናገዷ በፊት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ [November -9 ] በማንዴላ ብሔራዊ ስታዲየም ለማድረግ መታሰቡን ተገልፆል።

አፍሪካንፉትቦል ድህረገፅ የዮጋንዳን እግርኳስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ የስራ ኃላፊ ኤጋር ዋትስን ጠቅሶ እንዳስነበበው የወዳጅነት ጨዋታውን ከፌዴሬሽኑ ጎን በተባባሪነት የዮጋንዳ የጤና ሚኒስቴር የተዘጋጀ ሲሆን በተለይም የጤና ቢሮው በወዳጀነት ጨዋታው ወቅት የስፖርት ቤተሰቡ ስለ HIV ስርጭት ትምህርት እና ፍቃደኛ ለሆኑት የነፃ የHIV ምርመራ ለማድረግ የሚችሉበት አጋጣሚ እንደሚኖር ኃላፊው ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ስራቸውን እንደሚቀጥሉ እና የፊታችን እሮብ በፖርቱጋል የነበራቸውን እረፍት ጊዜ ጨርሰው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ ከፌዴሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።


ለ‹‹ዜሮ ድምር››ም ያልበቃው የኢትዮጵያ ፖለቲካ

$
0
0

ጌታቸው ሺፈራው

በአገራችን ከ‹‹ልማታዊ መንግስት›› እስከ ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ››፣ ከ‹‹ኪራይ ሰብሳቢነት›› እስከ ‹‹ሽብርተኝነት››፣ ከ‹‹መሃል መንገድ›› እስከ የ‹‹ጽንፍ ፖለቲካ››፣ ከ‹‹ዘረኝነት›› እስከ ‹‹ወያኔነት››፣ ከ‹‹ብሄር›› እስከ ‹‹ጎሳ›› ያልተተረጎሙ ነገር ግን ማንም እያነሳ የሚጥላቸው፣ ሊተነትናቸው የሚሞክራቸው የፖለቲካ ቃላት አሉ፡፡ እነዚህ አብዛኛዎቹ ማንም አንስቶ የሚለውሳቸው የፖለቲካ ቃላት በአብዛኛው በገዥው በኩል የተለመዱ ሲሆኑ በተቃዋሚው ጎራም ሳይቀር የሚዘወተሩ ነገር ግን ያልተተረጎሙ፣ ረጋ ብለን የማናያቸውም ናቸው፡፡

ከእነዚህ መካከል በተደጋጋሚ የሚሰማው የ‹‹ዜሮ ድምር ፖለቲካ›› የሚባለው ነው፡፡ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ተሳታፊ አሊያም ተመልካች ነን የሚሉ አካላት በተለይም ‹‹ተቀናቃኞች›› የሚሄዱበት መንገድ ትክክል አለመሆኑን ለመግለጽ ‹‹በዜሮ ድምር ፖለቲካ›› ባህላቸው ይወቅሷቸዋል፡፡ በግልጽነት ተናገርን የሚሉ ራሳቸውን አሊያም አጠቃላይ የአገራቸውን ሁኔታ ‹‹የዜሮ ድምር ፖለቲካ ባህል›› እንደተጠናወተው ይተቻሉ፣ ይተነትናሉ፣ ያማርራሉ….፡፡

እኔ እስከ ማውቀው የኢትዮጵያ ፖለቲካ የዜሮ ድምር ፖለቲካ በሚባሉበት አጋጣሚ ‹‹አይደለም›› ያለ አካል አላጋጠመኝም፡፡ ይልቁን ልዩነቱ የሚመጣው ለዚህ ‹‹ባህል›› ተጠያቂው ላይ ነው፡፡ ተቃዋሚዎቹ ገዥውን ፓርቲ አሊያም ሌሎች ተቀናቃኞቹን፣ ገዥው ደግሞ ተቃዋሚዎችን ይወቅሳሉ የፖለቲካ ባህላችን የ‹‹ዜሮ ድምር›› እንደሆነ በማይተማመኑትም መካከል ስምምነት የተደረሰበት ይመስላል፡፡ እኔ ደግሞ ለዚህ ብልሹ የፖለቲካ ባህልም አልደረስንም ባይ ነኝ፡፡

የዜሮ ድምር ፖለቲካ ተብሎ የሚጠራው ‹‹የፖለቲካ ሁኔታ›› ከእንግሊዝኛ የመጣ እንደመሆኑ ከአማርኛው ይልቅ ‹‹zero sume game›› የሚለው የእንግሊዝኛው ሀረግ ይበልጡን ይገልጸዋል፡፡ ይህ የፖለቲካ ሁኔታ የፖለቲካ ጨዋታ ነው፡፡ ጨዋታ ደግሞ ህግ፣ የመጫወቻ ሜዳ፣ ሁለትና ከዚያ በላይ ተጫዋቾች፣ ተመልካች፣ ዳኛ፣ ቢቻል ታዛቢ ያስፈልገዋል፡፡ በተጫዋቾች መካከል የተግባቡበት ግንኙነት ሊኖር የግድ ነው፡፡ ፈረንጆቹ ‹‹political game›› ወይንም እንደ አጠቃላይ ‹‹game theory›› በሚሉት የፖለቲካ ሁኔታም ተጫዋች፣ ህግ፣ ተመልካች፣ ዳኛ ከተቻለም ታዛቢ እንዳለው እናያለን፡፡ በአብዛኛው የዜሮ ድምር ፖለቲካ የሚባለው በየትኛውም የፖለቲካ ‹‹ጨዋታ›› አሸናፊና ተሸናፊ አለ ከሚል አስተሳሰብ በመነሳት ነው፡፡ አሸናፊና ተሸናፊነት በፖለቲካ መድረክ አንዳንዴ አጨቃጫቂ ቢሆንም በግልጽ የሚታዩባቸው እንደ ምርጫ አይነት መድረኮችን መግለጽ ይቻላል፡፡

ፈረንጆቹ ‹‹ጌም ቲዮሪ›› የሚባለውን ‹‹the study of mathematical models of conflict and cooperation between intelligent rational decision-makers›› ብለው ይተረጉሙታል፡፡ ‹‹የዜሮ ድምር ፖለቲካ›› የሚባለው የአማርኛው ፍችም ከመሰል የእንግሊዝኛው ትርጉም የመጣ ነው፡፡ በዚህ ትርጉም ደግሞ ‹‹የዜሮ ድምር ፖለቲካም›› በሂሳብ ስሌት፣ በታሰበበት ውሳኔ እንጂ በማንቦጫረቅና በዘፈቀደ ላይ የተመሰረተ እንዳልሆነ ነው፡፡
police ethiopia
በ‹‹ፈረንጆቹ ትርጉም›› መሰረት የዜሮ ድምር ፖለቲካ አብላጫውን ያገኘው አካልና ያጣው አካል ተደምሮ ዜሮ የሚመጣ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ አንዱ ያገኘውና ሌላኛው ያጣው ተደምሮ ዜሮ ይመጣል እንደማለት ነው፡፡ ይህ በሂሳብ ስሌት አንዱ 2 ሲያገኝ ሌላኛው ሁለትን ያጣል አሊያም ነጋቲቭ ሁለት ያገኛል እንደማለት ነው፡፡ በአገኘውና ያጣው ሲደመር ውጤቱ ዜሮ ይመጣል ማለት ነው፡፡

በአገራችን ‹‹የዜሮ ድምር ፖለቲካ›› ስንል አንዱ ሁሉንም ጠቅልሎ የሚወስድበት አሊያም ሌላኛው ሁሉንም የሚያጣበት የሚለው ትርጉም ይሰጠዋል፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ተወያይቶ ችግርን አለመፍታት፣ ተደራድሮ አለመታረቅ፣ ተነጋግሮ አለመደማመጥ ሁሉ ‹‹ዜሮ ድምር ፖለቲካ›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ሁሉም የሚያጣበት ፖለቲካ ተብሎ ተተረጎመ ማለት ነው፡፡ ዜሮ ሲደመር ዜሮ ያው ዜሮ እንደማለት ነው፡፡

በአብዛኛው የእኛ አገር ፖለቲካ ማንም የማያተርፍበት ፖለቲካ ነው፡፡ በተለይ ተወያይቶ ችግርን አለመፍታት፣ ተደራድሮ አለመታረቅ፣ ተነጋግሮ አለመደማመጥ፣ ተባብሮ አለመስራት፣ ተነጣጥሎም መውደቅ፣ ተባብሮም አለመተባበር ሁሉንም ሲያከስሩ ይታያል፡፡ ይህ ግን ከዋነኛው ትርጉም አንጻር የ‹‹ዜሮ ድምር ፖለቲካ›› ሊሆን አይችልም፡፡ አንዱ ያጣውና ሌላኛው ያገኘው ተደምሮ ሳይሆን ሁለቱም ምንም ያገኙ አይደሉም፡፡ ምን አልባት ‹‹አንችም ዜሮ ዜሮ፣ እኔም ዜሮ ዜሮ›› ለሆነው ለዚህ የፖለቲካ ሁኔታ ሌላ ትርጉም ያስፈልገው ይሆናል፡፡

የእንግሊዝኛው ትርጉም ‹‹አሸናፊው ያገኘው ተሸናፊው ካጣው ከበለጠ (ድምሮ ከዜሮ ይበልጣል) ወይንም አሸናፊው ያገኘው መጠን ተሸናፊው ካገኘው ካነሰ (ሁለቱ ሲደመር ከዜሮ በታች ነው የሚሆነው) ዜሮ ድምር ፖለቲካ አይደለም›› ይላል፡፡ የሁለቱ አካላት ያገኙትና ያጡት ተደምሮ ከዜሮ የሚያንስ ወይንም የሚበልጥ ከሆነ የዜሮ ድምር አይደለም ማለት ነው፡፡ አንዳንዶቹ ይበልጡን አትራፊ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ይበልጡን ከሳሪዎች ይሆናሉ፡፡

በእርግጥ የእኛው አገር የ‹‹ፖለቲካ ጨዋታ›› ከቁጥር ስሌት፣ ከድምር ፖለቲካም የሚገባ አይደለም፡፡ የዜሮ ድምር ፖለቲካ ህግ፣ የመጫወቻ ሜዳ፣ ተጫዋቾች፣ ተመልካቾች፣ ዳኞች፣ ቢቻል ታዛቢዎች ይኖሩታል፡፡ የእኛ አገር የ‹‹ፖለቲካ ጨዋታ›› ህግ፣ ተጫዋች፣ ተመልካች፣ ዳኛ፣ ታዛቢን የሚያሟላ አይደለም፡፡ በእኛ አገር ፖለቲካ በአንድ ‹‹ጨዋታ›› የተለያየ ማሊያ ለብሶ ተጫዋች፣ ዳኛ፣ ተመልካችም፣ ታዛቢም፣ ዳኛም የሚሆነው ራሱ ገዥው ፓርቲ ነው፡፡

በአንድ አካል የበላይ ተዋናይነት የሚመራው የ‹‹ፖለቲካ ጨዋታው›› በቋሚ ህግ የሚመራ ሳይሆን ይህ ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ የሆነ አካል ሲፈልግ ‹‹ጨዋታ ፈረሰ›› የሚልበት፣ ህግ ብሎ ካስቀመጠው ውጭ ጨዋታውን የሚዘውርበት፣ ተቀናቃኝ ተጫዋች ወይንም ቡድን የሚወስንበት፣ የሚያሰለጥንበት፣ የሚቀጣና የሚሸልምበት መድረክ ነው፡፡ በመሆኑም በእኛ አገር የ‹‹ዜሮ ድምር ፖለቲካ›› በሂሳብ ስሌት ማን አገኘ፣ ማን ምን ያህል አጣ፣ ተደምሮስ ስንት ይሆናል ከማለታችን በፊት ‹‹ጨዋታ››ነትን አላሟላም ማለት ነው፡፡

በመሆኑም ዜሮ ድምር ፖለቲካ ሊኖር የሚችለው (በአወንታዊም ሆነ በአሉታዊ መልኩ) ስርዓት ላበጁ፣ ስርዓቱ ምንም ይሁን ምን በዛ ስርዓት ወይንም ህግ ለሚገዙ አካላት ነው፡፡ በእርግጥ ይህ ነው የሚባል ስርዓት የሌላቸው ወይንም ብልሹ የፖለቲካ ስርዓት ላይ የመጫወቻ ሜዳቸውን የመሰረቱ አገራት ላይ በገዥነት ላይ የተቀመጡ ስርዓቶችም ከእኛዎቹ ገዥዎች የተሻሉ ወደ ‹‹ፖለቲካ ጨዋታው›› ይጠጋሉ፡፡

ለአብነት ያህል የምርጫ ቦርድ የሚባል ዳኛ፣ የምርጫ ስነ-ምግባር፣ የምርጫ ቦርድ አዋጅ፣ ህገ መንግስትና ሌሎችንም ህጎች አውጥቶ፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲኖሩ ‹‹ፈቅዶ››፣ ምርጫ የሚባል መወዳደሪያ ሜዳ እንዳለ አሳውቆ፣ ህዝብ (ተመልካች) በነጻነት እንደሚመርጥ ቃል ገብቶና በህግ አጽድቆ ይህን ሁሉ ተግባር በራሱ ከሚወጣው ኢህአዴግ ይልቅ እነዚህን ቀልዳቀልዶች ሁሉ እንደሌሉ ህዝቡ እንዲያውቅ ቁርጡን ተናግሮ ብቸኛ ‹‹ሀቀኛ›› ተጫዋች ነኝ ያለው የኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት ‹‹ለፖለቲካ ተጫዋችነት›› የቀረበ ነው ማለት ይቻላል፡፡

የኢሳያስ መንግስት ራሱ የሚያዘው ምርጫ ቦርድን ‹‹ነጻ ነው!››፣ ራሱ ያሰማራቸውን ካድሬዎች ታዛቢዎች ናቸው፣ መንቀሰቀቀስ የማይችሉትን ተቃዋሚዎች ተቀናቃኞች ናቸው፣ ስርዓቱ የመሰረተውንና በሱ ሳንባ የሚተነፍስ ሚዲያ ነጻ ሚዲያ ነው ብሎ የሌለ ‹‹ጨዋታን›› እንጫወት ብሎ ባለማሞኘቱ ከኢህአዴግን በአንጻራዊነት የተሻለ ያደርገዋል ባይ ነኝ፡፡

እንደ ሙጋቤ ያሉት አምባገነኖች ህግን በቀጥታ ከመጣስ ይልቅ ለእነሱ የሚመች የመጫወቻ ሜዳ ያበጃሉ፡፡ ለዚህም ሲባል የዚምባብዌ ህገ መንግስት በርከት ላለ ጊዜ ተሻሽሏል፡፡ ይህም በቀጥታ የጨዋታውን ህግ ከመጣስ ይልቅ የጨዋታውን ህግ የማስቀየር ጨዋታን ነው የሚጫወተው፡፡ ከዛ በኋላ ግን ላወጣው ህግ ሲገዛ ይታያል፡፡ ይህም ቢሆን ከኢህአዴግ የተሻለ ነው ባይ ነኝ፡፡

እነዚህ አምባገነኖች የገነኑባቸው አገራት ከኢትዮጵያው ሁኔታ ይሻላል በሚል እንጂ ትርጉሙን ያሟላሉ በማለት አይደለም፡፡ የዘሮ ድምር ፖለቲካ በአብዛኛው በተጫዋቾቹ ብቃትና ውሳኔ የሚወሰን ነው፡፡ በእርግጥ ዳኛ፣ ተመልካች፣ ታዛቢም በዜሮ ድምሩ ይቅርና በሌሎች የመዝናኛ ጨዋታዎችም አሸናፊና ተሸናፊን ይወስናሉ፡፡ ሆኖም ግን ተጫዋቾቹ ሚና በመጀመሪያ ደረጃ የሚቀመጥ ይሆናል፡፡ በፖለቲካው ዓለምም ተፎካካሪ በአንድም ሆነ በሌላው ተሳታፊ ተጽዕኖ አግባብ ያልሆነ ውጤት ሊያገኝ ይችላል፡፡

ነገር ግን መጀመሪያ አንደኛው ተጫዋች ሌላኛውን በህጋዊ ሰውነት የሚያይበት፣ እኩልና ተወዳዳሪው መሆኑን የሚያምንበት፣ ህግ ለመጠቀሚያ ሳይሆን ሁለቱን ለመዳኘት የሚውልበት፣ ተመልካቹ በተጫዋቾቹ ብቃት የሚደግፍና የሚመርጥበት፣ ዳኛውና ታዛቢው በገለልተኝነት የሚሰሩበት መድረክ መዘጋጀት አለበት፡፡ በዚህ ሁኔታ በሰዋዊ ስህተትም ሆነ በሌላ መንገድ ማጭበርበር ቢኖርም አንደኛው ተጫዋች ተነስቶ ዳኛ የሚሆንበት፣ ተቃናቃኙን የሚታዘብበት፣ ተመልካቹን አስገድዶ የራሱ የሚያደርግበት መሆን የለበትም፡፡ አሊያም ይህ ስህተት የሚዳኝበት ህጋዊ መሰረት ይኖራል፡፡

ይህ ካልሆነ ግን ልክ እነ ኢሳያስ እንኳን ‹‹እንደ ኢትዮጵያ ከሆነ በአመትም 10 ምርጫ ማድረግ እንችላለን›› እንደሚሉት የኢትዮጵያ አይነት የማሞኛ ምርጫ መሆኑ ነው፡፡ እንዲህ አይነት ‹‹ተጨፈኑ ላሞኛችሁ›› ደግሞ ‹‹ዜሮም ሆነ የሚሊዮን ድምር›› የሚያበቃ የ‹‹ጨዋታ›› ለዛ የለውም፡፡ በዚህ ረገድ ፖለቲካችን ከ‹‹ጨዋታ›› ይልቅ ‹‹መጫወቻ፣ መቀለጃ›› የሆነ ብልሹ ፖለቲካ ነው፡፡

የፖለቲካ ጨዋታ ዜሮም ይሁን ምን ተጫዋች፣ ተመልካች፣ ህግ፣ ተመልካች፣ ታዛቢና ሜዳ የሚኖረው በመሆኑ በእኛ አገር ራሳቸው ህግ አውጥተው፣ ራሳቸው ከሚጥሱት፣ እየተጫወቱ ተመልካችም፣ ዳኛም ታዛቢም ከመሆኑት ብቸኛ ተጫዋችነትን በገሃድ ባወጁት ‹‹ቅን አምባገነኖች›› አለ ቢባል ይቀላል፡፡ በትርጉሙ መሰረት ደግሞ ወጠምሻዎች ከሚመሩት ‹‹ስርዓት›› ይልቅ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በገነቡት አገራት ሊኖር የሚችል የ‹‹ፖለቲካ ጨዋታ›› ነው፡፡

ይህን ሁሉ ስናይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በብልሹነቱ ከምናነሳው የ‹‹ዜሮ ድምር›› ፖለቲካም ደረጃም አልደረሰም ማለት ነው፡፡ የሂዳን ስሌቱ እንዳለ ሆኖ ቢያንስ በዛ ‹‹ብልሹ ፖለቲካ››ም ውስጥ ተጫዋቾች፣ የሚከበር ህግ፣ ተመልካቾች፣ ዳኞች፣ ታዛቢዎች መኖር ይጠበቅባቸዋልና ነው፡፡

[የማለዳ ወግ] –ከሊባኖስ እስከ ሳውዲ፣ ሌላ የደም እንባ እንዳናነባ! * የተዘጋው የአረብ ሀገር ጉዞ ይጀመር ይሆን?

$
0
0


እለተ አርብ ጥቅምት 14 ቀን 2007 ይላል የቀን መቁጠሪያው ። በጠዋቱ ተነስቸ መብተክተክ ይዣለሁ ፣ መነሻየ ከሳምንት በፊት በሃገረ ሊባኖስ መዲና ቤሩት ስሟን ለደህነንነት ስል የማልገልጻት ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ በግድያ ወንጀል ተጠርጥራ ባለችበት ሁኔታ በነፍሰ ገዳይነት ውንጀላ መክሻሸፍ አስመልክቶ አዳዲስ መረጃን ለወዳጆቸ ለእናንተ ለማቀበል ነው ። ብዙም ሳልቆይ ቤሩት የመረጃ ምንጭ ወዳጆቸ ስልክ ደወልኩ … መረጃውን ሰባሰብኩ ፣ የኢትዮጵያ ቆንስል ጀኔራል መስሪያ ቤት ጉዳዩን በቅርብ እየተከታተለው እንደሆነ ሰማሁ ፣ ዘብጥያ ውስጥ ያለችው እህት ስላለችበት ሁኔታ ቤሩት የሚገኘው የኢትዮጵ ቆንስል መ/ቤት ሊባኖስ ላሉ ተቆርቋሪ ዜጎቹ እንኳ መረጃ ለማቀበል ተቆጥቧል። እንደ ምክንያት ያቀረበው ” በፍርድ ቤት ያለ ጉዳይ ስለሆነ ምንም አይነት መረጃ መስጠት አይቻልም! ” የሚል ነው ። እዚህ ላይ ግራ ተጋብቻለሁ… ከሳሽ በመገናኛ ብዙሃን የናኘው ወደ ኋላ የተወላከፈ መረጃ ሆኖ የተገኘው መረጃ ባይሳካለትና ቢከሽፍበትም በፍርድ ቤት ያለ ጉዳይን ዘክዝኮ የወነጀላትን እህት ከሳሽ ህግ መጣሱን በመረጃ አስደግፎ መብቷን ማስጠበቅና መከላከል አይቻል ይሆን? ለፍርድ ቤት አቅርቦ የዋስ መብቷን ማስከበር የማይሞከርበትን መንገድ ምንድን ነው ? ይህን እየተደረገ ነው ወይ ? ብለን ሰውኛ ጥያቄ ብንጠይቅ መልሱ ጉዳዩ በፍርድ ከመያያዙ ጋር ታኮ መመለስ አንችልም የሚል ምላሽ መሰጠቱ ግራ ቢያጋባኝ አትገረሙ … ከዚሁ ጋር አሳሳቢው “ተከሳሽ እህት በምርመራ ተገዳ መግደሏን ልታምን ትችላለች!” የሚለው ስጋት እያንዣበበ መሆኑም ይጠቀሳል። ፍርዱ የሚሰጠው በአረብ ምድር በሊባኖስ ሰማይ ስር በመሆኑ በቆንሰሏ በር ተጎትታ ስትደበደብ የተመለከትናት እና የህሊናችን የማትጠፋ ቁስል የሆነችው የአለም ደቻሳ በአዕምሯችን ለታተመ ዜጎች የዚህች እህት መጨረሻ ያሳስበናል …

ይህንና ያንን ሳስብ ሳሰላስል ደጎስ ያለ መረጃ እስኪገኝ ስደቱን ተከትሎ ለከፋው ስማችን ምንጩን አውጥቸ አወረድኩት …. ከዚያ ሁሉ በፊት ግን “የአረብ ሃገሩ የተዘጋ መንገድ ሊከፈት ነው!” የሚል ሰሞነኛ የሹክሹክታ መረጃና የቱጃር የቪዛ ደላሎች ሳውዲ መድረስን ዜና ሰምቻለሁና እሱን ነካክቸው ላልፍ ፣ ከዚህ በፊት በኮንትራት ሰራተኞች አበሳ ዙሪያ ያጋጠመኝን አወሳስቸ ላልፍ ከራሴ ጋር ተስማማሁና ወጌን ጀመርኩት …

ከያዝነው ወር በፊት ጀምሮ “ወደ አረብ ሃገራት የተዘጋው የኮንትራት ቪዛ ይከፈታል !” የሚል መረጃ በሰፊው በመሰራጨት ላይ ነው ። እኔም የሚሆነው የሚናገሩት ባይሆንም ኢምሬት ላይ በጉዳዩ መግለጫ የሰጡት ፕሬዘደነት ዶር ሙላትና የኢምሬት አምባሳድር የተዘጋውን የአረብ መንገድ ለመክፈት ገና ህግ መመሪያ እየወጣ መሆኑን ፣ ከሃገራት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ከሁሉ አስቀድሞ እንደሚከወን ማሳሰባቸውን እንጅ መንገዱ ይከፈታል የሚል መረጃ አለመኖሩን በመረጃ ማስረጃ ለማስረዳት መሞከሬ ባይቀርም የእኔ መረጃ የከሸፈ መሆኑን ወዳጆች እየነገሩኝ ነው ፣ እነርሱ እውነት ነው ላሉት ማስረጃ ጭብጥ የሚሉትም አላቸው ። ይህም በቪዛው ንግድ ተሰማርተው ከገጠር እስከ ከተማ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰራተኛን ለሳውዲ ” ገበያ” ያቀረቡት ባለ ኤጀንሲ ደላላሉች ጅዳና ሪያድ መምጣት መጀመራቸው ነው ። እርግጥ ነው ከምንም ተነስተው ዛሬ “አንቱ “የተባሉና ጠባቂ የሚያስፈልገው ንብረት አላቸው የሚባሉት ወጣትና ጎልማሳ ኢትዮጵያውያን ደላሎችና የቪዛ ነጋዴዎች በጅዳና ሪያድ ከተሞች በአድርባዮች ታጅበው ሲንሸራሸሩ ተመልክቻለሁ … ሁሉንም መኮነን ባይቻል በአብዛኛው ደላሎቸደና አዘዋዋሪ ነጋዴዎች ለገንዘብ ሲሉ ምንም የማያውቁ እህቶቻችን ከየገጠሩ እየሰበሰቡ በየአረብ ሃገሩ ሲበትኗቸው የት እንዳሉ ያሉበትን ሁኔታ እንኳ ማወቅ የማይፈልጉ መሆናቸውን አውቃለሁ ። ሰራተኞች ተበደልን ብለው ስልክ ሲደውሉላቸው ስልካቸውን አያነሱም ። እኒህ ናቸው ሌላ ዜጋን አሁንም ወደ መከራው አለም ለመላክ በከተማችን ገብተው የመንገዱን መከፈት የሚጠባበቁት …መቸም ባለ ጸጎች ናቸውና ስላካበቱት መዋዕለ ንዋይ ጓጉቸ የቀናሁ እንዳያስመሰል በሚል ብዙ ከማለት መቆጠቡን እመርጣለሁ ። ይህን ስል ስማችን ለመጉደፉ ምክንያቶቸን በአጭሩ ፣ የግፍ በደሉን ቀማሽ እህቶች የሰማሁትን ምስክርነት በጨረፍታ መመልከቱ ግድ ይለኛል።
Cry Ethiopia in Saudi ድሮ ድሮ በማይባል የሩቅ ዘመን ትዝታ ሃበሻ በሚል የምንታወቀው ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንን ጨምሮ በአረቦች ዘንድ እንከበር ፣ እንታመን ፣ እንወደድ ነበር ። ይህን ወቅት ድንጋይ ዳቦ የነበረበት ዘመን አይደለም ። … እኔም “ኩራት ክብር እየቀረ ነው !” በሚባልበት የጊዜ ጫፍ የዛሬ 20 አመት ገደማ ሳውዲ መጥቸ በአረብ ሃገር ተንደላቀው በክብር የኖሩት ጎደለብን ብለው “ቀረ ፣ እየጠፋ ነው! “።ያሉትን የሃበሻ ክብርና ሞገስ ደርሸበታለሁ ። አሁን አሁን ግን እንጃ …አመኔታውና ክብሩ እየሸሸን መሄዱ ይሰማኛል። ሳንታመን ፣ ሳንከበር እንዳንከርምን የባጀነውም ያለ ምክንያት አይደለም ። አዎ በሚሊዮን የሚቆጥር ስደተኛ የህግ ሽፋን በተሰጠውና ህግ በማያውቀው ህገ ወጥ መንገድ ተሽሎክሉከው በቦሌም ፣ በባሌም ፣ በሞያሌም ፣ በጅቡቲና ሶማሊያም ወደ ከፋው የስደት ቀጠና ሲያቀኑ ነገር ተበላሽቷል። ስለማላውቀው የአፍሪካ ሃገር የከፋ ስደት መናገር ባልችልም ስለ አረቡ ሃገር ስደተኛ መናገር አይገደኝም ።

… ቀን ወጣለት የተባለው ያልሰመረለት የሃገሬ ገበሬ ልጆችን ፣ የኑሮ ውድነት ጣሪያ ነክቶ ፣ የእለት ጉርሱን አግኝቶ መኖር አቅቶት በችጋር የሚደቆሰው ከተሜ ፣ በአንድ ጀንበር የተለወጡት እያማመሉ ያለውን ጥሎ ለተሻለ ኑሮ ፍለጋ የተሰደደው ቀቢጸ ተስፈኛ ፣ በአረብ ሃገር የሚላኩ የተሳሳቱ መረጃዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ አረብ ሃገር ተሰደዋል። “ከገጠር እስከ ከተማ መንገዶች ተሰርተው ፎቆች ተገጥግጠው ፣ በየአመቱ የምታድግ የምትመነደገው ሃገር ” ተብሎ ለእድገቷ ምስክር የሚጣቀስላት ሃገር ዜጎች በግፍ ወደ አረብ ሃገር መሰደድ መጀመራችን ስማችን ማክፋት መጀመሩና ነሩ ሁሉ ሲያበለሻሸው በአይኔ በብሌኑ ተመልክቻለሁ። አምስትና ስድስት አመታት በፊተ በስማችን መክፋት መበለሻሸት ዙሪያ ሲነሳ ከዚህ ቀደም የሚጠቀሱ ምክንያቶች ጥቂት ሃበሾቸ የተሰማሩባች ህገ ወጥ ስራዎች መጠጥ መሸጥ ፣ ዝሙት እና የመሳሰሉት ናቸው ይባል ነበር ። … ይህ ደግሞ የአረቦች ህገ ወጥ ምርት አቅርቦቱን ተጠቃሚ መሆን ፣ በገዥነት ፣ በተባባሪና በድጋፍ ሰጭነት ይሰራ የነበረው ስማችን ካስከፋው ስራ አረቦችን ቂም አስቋጠሮ ስማችን አጉድፎ በአደጋ የጣለን ከኮንተራት ስራው ቅበላው ጋር የመጣው የነፍስ ማጥፋት ውንጀላ ነው ። ይህ በኢትዮጵያውያን የኮንትራት ሰራተኞች ተፈጸመ የተባለው ወንጀል እየሰፋ መጣ ተብሎ በአደባባይ ስማችን እየተነሳ ሲወገዝ ፣ ጉብል እድሜያቸው ከሃያ የማይዘሉ የኮንትራት ሰራተኛ እህቶች “ገዳይ” ተብለው የገደሉበትን ምክንያት በአረብ ታዋቂ መገናኛ ብዙሃን ሲናገሩት ሰምተናል ። ይህም ስማችን ቅስማችን ሰብሮታል … በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች እንደጨው ተበትነዋልና ስማችን አሳፋሪ ሆኖ እስካሁን ቀጥሏል።

ለዚህ ሁሉ ምክንያት ከሃገር ቤት ከወላጅ ጀምሮ እስከ ደላላ ፣ ከደላላ እስከ ሃላፊነታቸውን መወጣት የገደዳቸው የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ናቸው የሚል እምነት አለኝ ። በዋናነት ደግሞ ከኢትዮጵያውያ በህጋዊ መንገድ ወደ ሳውዲና ወደ ቀሩት አረብ ሃገራት መላክ ሲጀመር በሃገራት መካከል በተደረገ ስምምነትን መሰረት ያደረገ አለመሆኑ፣ ከስልጠና ጀምሮ እስከ ስራ ስምሪት በቂ ስልጠናው ቀርቶ በሚደርሱቸው አረብ ሃገራት ያሉ ኢንባሲዎችና ቆንስሎች በሙያው በተካኑ ዲፕሎማቶች አለመመደብና በቂ ዝግጅት ያለመደረጉ አሁን ለተጋረጥንበት ጣጣ አደጋ አብቅቶናል። ይህ በዋንኛነት በእጅጉ እንደጎዳን ፣ እናድስ እንገንባ የምንለውን ስማችን እንዳከፋው ፣ እንደጎዳው አሰረገጦ የመናገር አቅሙ አለኝ …

የዘሃራ ውጋት …

ጊዜው በአዲሱ የፈረንጆች 2012 አሮጌው የፈረንጆች አመት ሊሰናበት ሲያስገመግም አዲሱ አመት 2013 ሊመጣ የቀሩት ሁለት ቀናት ብቻ ናቸው ፡፡ የጅዳ የሰሞኑ አየር ደስ የሚል ሆኗል ፡፡ ሙቀት ወበቅ የሚሉት ነገር ከጠፋ ሰነባብቷል ! አንዳንድ ቀን ግን አመል ሆኖበት ነው መሰል አልፎ አልፎ ሙቀቱ ብቅ ብሎ ጥልቅ ማለቱን ግን አልተወውም . . . ያማታው ብርድ ግን አይጣል ነው . . . ! ጂዳ ቆንስል ግቢ አዲስ በተሰራችው የኮንትራት ሰራተኞች መጠለያ ከታጨቁት እህቶች አንዳንዶቹን ከጎናቸው በርከክ ብየ አዳምጣለሁ፡፡ ሲለኝ ደግሞ ፎቶ ለመረጃ አነሳለሁ. . . ዘሃራ የተባለች እህት ቀልቤን ጨምድዳዋለች ! ይህች ከ15 አመት እድሜዋ የማትዘልለው ጉብል በኮንትራት መጥታና ከአንድ ክፍል ለአራት ቀናት ያለ ምግብና ውሃ በመዘጋቷ በማታውቀው ሃገር ቤቱ ሲከፈትላት ሾልካ ጠፍታለች ፡፡ ያልታደለችው ዘሃራ ግን ሳታስበውና ሳታልመው በሰው አውሬዎች እጅ ወደቀች . . . ሊደፍሩ ለሁለት ሲያንገላቷት የተጎዳው ጀርባዋ አላስቀምጥ አላስተኛ ብሎ እንዳስቸገራት የተረዳሁት ስታናግረኝ ከአንዱ ጎን ወደ ሌላኛው ጎን ለመገላበጥ ስትሞክር ነበር . . ፣ ዘሃራን ደጋግሜ መደፈር አለመደፈሯን ስጠይቃት “አልደፈሩኝም አረ !” ስትል ክብ ፊቷን ከስክሳና እንደ ማፈር እያለች አንገቷን ደፍታ ደጋግማ መለሰችልኝ ! ዘሃራን በኒያ ባለችኝ ጎረምሶች ጡንቻ ተይዛና ተደብድባ ወገቧ ሲሰበር ከመደፈር እንዴት እንደተረፈች ለመገመትና ለማመን አልዋጥልህ አለኝ ! ደግሞ እኮ ጎረምሳ ለምመስለው ለእኔስ ቢሆን እንዴት መደፈሯት ትነግረኛለች? አልኩና በውስጤ ይህንን ጥያቄ ከመደጋገም ራሴን ቆጠብኩ . . . ከትንሿ ልጅ ከዘሃራ ጋር በነበረኝ ቆይታ ስሜቴ ክፉኛ ተጎድቷል !

ዛሬ ዘሃራ ሃገር ቤት ናት ” ብድሬን አልከ ፈልኩምና የወላጆቸን ፊት አላይም !” ማለቷን አስብና ይጨንቀኛል በመንፈስ እታመማናለሁ ፣ አዎ ዘሃራ ህይወቷ እንደ አካሏ መናጋቱን ዘልቆ አውቃለሁና ፣ ብዙ ለጋ ዘሃራዎችን አይቻለሁ ፣ እህ ብየ አድምጫለሁና የውስጥ ህመሜን እኔ ነኝ የማውቀው …ዛሬ ዘሃራ መሰሎችዋ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ግን እንጃ …

የሪያዱ ወዳጀ ልብን የሚሰብር መልዕክት . .

በሪያድ መንፉሃ ተብሎ በሚጠራውና በባህር የመጡ ሃበሾች እርስ በርሳቸው በሰላ ቢላዋ በሚወጋጉበት መንደር በተለያዩ ቀናት በአስገድዶ መድፈር ባሰሪዎቻቸውና በቤተሰቦቻቸው የተጠቁ እህቶችን ተጥለው መገኘታቸውን ሰምቻለሁ፡፡ እህቶችን አግኝተው ያስጠጓቸው ኢትዮጵያውያንን በስልክ አግኝቻቸው ብዙ መረጃን ሰጥተውኛል፡፡ በአብዛኛው እየተደፈሩ የሚመጡ የኮንትራት ሰራተኞች ቁጥር ከፋ ያለ መሆኑ ለመረዳት ችያለሁ፡፡ ከአንድ ወዳጀ ከዚህ በፊት አንድ የደረሰኝ አሳዛኝ መልዕክት የኮንትራት ሰራተኞች ሁኔታ እየከፋ መሄድ ድፍንፍን አድርጎም ቢሆን ያስረዳል ባይ ነኝ! የምሬት መልዕክቱን ዛሬም ደግሜ እንዳለች አውርጃታለሁና ተመልከቷት !

” ወዳጄ ሲራክ ከትላንት ወዲያ ሪያድ ውስጥ ኣንዲት እድሜዋ 19 የሚጠጋት ሴት ልጅ ኣሰሪዎቿ ዑለያ በሚባለው አካባቢ ያለ ምንም ፓስፖርት ወይም ኢቃማ ልብሷን በ ፌስታል አስይዘው ከመኪና አውርደው ጥለዋት ሄዱ። ስታለቅስ አግኝቼ የመጣው ይምጣ ቤቴ ወሰድኳት ። ደሞዝ ተከፍሏት ኣያውቅም ፣ ስራውንም በደምብ ኣለመደችም፣ በጣም ደንግጣለች፣ ዝምታ ወጧታል። የጣሏት ከፊሎቿ እንደሆኑ እና ከመጣች 3 ወሯ እንደሆናት ነገረችኝ።ደቡብ ወሎ ፣ ወግዲ ከሚባል ገጠር ሸህ ሁሴን በሚባል ደላላ ኣማካኝነት ከእህቷ እና ሌሎች 5 ሳዱላዎች ጋር ዕድሜዋን 25 ኣድርገው ወደ ሳውዲ እንዳመጧቸው እና እህቷ የት እንዳለች እንደማታውቅ ነገረችኝ። ዜግነቴን ጠላሁት። የት ልሂድ ከዚህ በላይ ፣እዚህ አገር መኖር አልፈልግም። ዜግነቴን ጠላሁት…” ነበር ያለኝ !

የኮንትራት ሰራተኞችን አበሳ ዘክዝኬ በምስል መረጃ ባቀርበው ደስ ባለኝ ፣ ግን ምስሎቹን ለመለጠፍና ግፉን ለማሳየት ልቤ ቢቆርጥም ፣ ሰብዕናን ላለማሸማቀቅ ስል ብቻ የምስል መረጃውን ልዘለው ግድ ብሎኛል፣ ስማችን ከፍቷል ብሎ በስሱ ስለስም መጨነቅ ለእኔ ቀልድ ነው ፣ የሚሰራው ታስቦና ተጠንቶ ስላልሆነ ፣ መብታችን የሚያስጠበቅልን ስለጠፋ ፣ ከስም በላይ ሰብዕናችን መርከስ ይዟልና ግፍ እየተፈጸብን ነው ፣ ለዚህ ማሳያ በሃገረ ሊባኖስ እየሆነ ያለውን በጥልቀት መመልከቱ ይበቃል፣ ለዚህ ማሳያ በሳውዲ የጅዳ ቆንስልና እና በሪያድ ኢንባሲ መጠለያ ያለፉትንና አሁን ድረስ ያሉትን ግፉዕ ዜጎች በደል ሰምተናል ፣ እየሰማን ነው ! ዜጎች ሰብአዊ መብታቸው ሲደፈጠጥና የተስማሙበት ኮንትራት ውል ተጣሰብን የሚሉ እህቶቸን ድምጽ ማሰማት ለእኔ ነፍሴ የፈቀደው ስራ ነው ፣ የመንግስት ዲፕላማቶች ቀዳሚ ስራ ነጋ ጠባ ለምንጠይቀው የዜጎች መብት ጥበቃ ቆሞ ወገናዊነትን ለህዝብ ለማሳየት መሞከር ነው ! የሚፈለገው የሚያወራ ሳይሆን የሚሰራ ነውና …የመንግስት ተወካዮች በህግና በስርአት የመጡ ዜጎችን መብት ማስከበር አለባቸው ! የቪዛ ውል ማስፈጸሚያ ገንዘብ እየሰበሰቡ ባጸደቁት የኮንትራት የስራ ውል ላይ የተጻፉት ስምምነቶች የመከታተልና የማስፈጸም ሃላፊነት አለባቸው! ፍትህ ሲጎድል ተከራክረው ሊያስከብሩልን ይገባል ! … ከዚህ በፊት መብታቸው ተጥሶ ተሸፋፍኖ እንደተላኩት ጉዳተኞች ወደ ሃገር ቤት ለማሳፈር የሚደረገውን ጥረት ጎን ለጎን የተገፊዎችን በደል ፍትህ ሊፈለግለት ይጋባል ፣ ይህ ግን በአብዛኛው አይደረግም ፣ በዚህ ረገድ እማኝነቱን ከባለቤቶቹ “እህ” ብየ ሰምቻለሁና እነግራችኋለሁ ! የተጎዱት ከተደፋባቸው የመከራ ህይዎትና ከእድሜ አለመብሰል አንጻር ” ወደ ሃገራችን እንግባ ! ከቤተሰቦቻችን ቀላቅሉን !” ማለታቸው ደጋፊ ማጣትና ስጋት እንጅ ያልተበደሉ ሆነው ፍትህን ሽሽት አይደለም !

መንግስት ይህ ሁሉ እየተነገረው የሚሰማ አይመስልም።ከአመት በፊት ወደ አረብ ሃገራት የተዘጋው መንገድ ደላላዎቹን ወደ ሊባኖስ ኩዌትና ኳታር የሚያሸጋግር ስራቸውን እንዳልገደበው አውቃለሁ። ከቀናት በፊት ሊባኖስና ቃጣር በተዘዋዋሪ መንገድ የገቡ ኢትዮጵያውያን አጋጥመውኛል ። ይህም ሁሉ ሆኖ ከኢትዮጵያ መንግስት አስቀድመው የሳውዲ መንግስት ያገደው ከኢትዮጵያን ሰራተኛ የማስማጣት እገዳ በኢትዮጵያ መንግስት ብቻ እገዳው ስለተነሳ ሰራተኛን ወደ ሳውዲ ማስገባቱ ይሰምራል ባልልም የአረብ ሃገሩ መንገድ ምንም ባልተሰራበት ሁኔታ መታሰቡ በራሱ ያማል ። አልተሰራም የምለው በጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት በኩል ያለውን ነባራዊ አቅም አውቃለሁና ነው ፣ ጅዳ ያለ ቋሚ ዲፕሎማት በተጠባባቂው ባለስልጣን መመራት ከጀመረች መንፈቅ ማለፉን ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖም አያውቁም አልልም ፣ ብቻ መንግስት ጀሮ ሰጥቶ ሊሰማን ይገባል ! … አባቶች ” አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ !” እንደሚሉት ሆኖ ሌላ እንባ እንዳናነባ …!

ቸር ያሰማል !

ነቢዩ ሲራክ

በአርባ ጉጉ እና አካባቢው በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል መካድ አይቻልም –ሞረሽ ወገኔ የባህል ማህበር በስዊድን

$
0
0

(24/10/2014)
ሞረሽ ወገኔ የባህል ማህበር በስዊድን

moreshፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ከሸገር ራዴዮ ጣቢያ ጋር በ09/08/2014 ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ምንም እንኳ አማራውን አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ እርስ በራሱ የተምታታ ቢሆንም፣ አማራውን ህዝብ የለም ከማለት አልፈው በአርባ ጉጉ በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ክደዋል። የፕሮፌሰር መስፍን ክህደት ’እስላም ኦሮሞዎች ክርስቲያን ኦሮሞዎችን ነበር የገደሉት’ ለማለት ከሆነ፣ ሀቁና መረጃዎቹ ከፕሮፌሰር መስፍን ክህደት ጋር እንደማይጠጣሙ በተከታታይ መረጃዎችን እየመዘዝን የአርባ ጉጉን እልቂት ለማቅረብ እንሞክራለን። ወይም ጉልበታቸው ለፈረጠመ ወንጀለኞች መውጫ ቀዳዳ በመፈብረክ የተለመደው የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ”የወንድ በር እንስጥ” ፍልስፍናም ከሆነ በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ያልተፈጸመና ያልተደረገ አያደርገውም ልንላቸው እንገደዳለን። ከአባሎቻችንና ከደጋፊዎቻችን ጋር ለመወያየት የግብዣ ወረቀት ከላክን በሗላ፣ ከስብሰባው በፊት በአማራው ህዝብ ላይ በአርባ ጉጉ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ፕሮፌሰሩ መካዳቸው ብዙዎችን እንዳስቆጣቸው መልክት ሲደርሰን፣ እኛም አንድን ሰው ከሀዲ ከማለታችን በፊት መረጃዎችን አቅርቦ ፍርዱን ለአንባቢ ለመተው፣ በጊዜው የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት ለኢህአዴግ፣ ለውጭ መንግስታት ዲፕሎማቶችና ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስ ያወጣውን የአቋም መግለጫ ከሞላ ጎደል ይህን የመስላል።
የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት ’መአህድ’ ኢህአዴግ በካድሬዎቹ አማካኝነት በአማራው ላይ የሚያካሂደውን የእልቂትና የሽብር ዘመቻ እያፋፋመው የአማራ ህዝብም ከፋሽስቶች ዘመን በባሰ ሁኔታ እያለቀ መሆኑን ባወጣው የአቋም መግለጫ አብራርቷል።
የመአህድ ፕሬዜዳንት ለሽግግር መንግስቱ ምክር ቤትና ለልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ባቀረቡት መግለጫ ላይ እንዳብራሩት በአማራው ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍና በደል ”ሰብአዊ አእምሮ ሊሸከመው የማይችል ነው” በተለይ ከግንቦት 26 ቀን 1984 ዓም ጀምሮ ጭፍጨፋው በከፋ መልኩ እንዲቀጥል ተደርጎ የጭፍጨፋው ሰለባ የሆነው አማራ ሬሳው በገደል ውስጥ እንዲጣልና በቤት ውስጥ እንዲቃጠል እየተደረገ ነው። ይላል
Pro Mesfin
”ከግንቦት 26 ቀን 1984 ዓም ጀምሮ በአማራው ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ የተካሄደው በአርሲ ክፍለ ሀገር በአንቦሳ ከተማና በአካባቢው ነው። ኢህአዴግ በዚህ ስፍራ የሚኖሩ ተወላጆችን ሰብስቦ ’በነዚህ መንደሮች የሚኖሩ አማሮች ይገደሉ ብላችሁ ፈርሙ’ በማለት ትእዛዝ ሰጠ።

በማግስቱ ግንቦት 27 ቀን 1984 ዓም አቡሌ የተባለውን መንደር በኦህዴድ (የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራቲክ ድርጅት) የታጠቀ ወታደር ተከቦ ተኩስ ከተከፈተ በሗላ መንደሩ በላውንቸር መደብደብና ማቃጠል ሲጀመር ህዝቡ ህይወቱን ለማዳን ህዝቡ በየአቅጧጫው መሸሽ ጀመረ። ከሚሸሹት መካከል 30 ህጻናት ቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ እንደተጠጉ ከቤተክርስቲያኑና ከካህናቱ ጋር ተቃጥለዋል። አከታትሎም 150 የአማራ ነዋሪ ቤቶች እንዲቃጠሉ ተደርጓል።

የአውራጃው የኢህአዴግ ተወካይ አቶ ዲማ ጎርሜሳ ለወራሪው ሰራዊት ”አማራን መጨረስ ዛሬ ነው” የሚል መፈክር በማሰማት አበሳ የሚባለው የአማሮች መንደር እንዲከበብ አስደርገው ህዝብ ከቤቱ ሳይወጣ መንደሩ እንዲቃጠል ተደርገ። በመንደሩ ከነህይወታቸው በቤት ውስጥ እንዳሉ የሞቱት ቁጥር የማይታወቅ ሲሆን የቤቶቹ ጠቅላላ ብዛት 150 ነው። ከቃጠሎው የተረፉት 50 ሰዎች ተይዘው በጥይት ተረሽነዋል።

በሌላም አሼ በተባለ መንደር በአማራ ተወላጆች በአካባቢው የሚፈጸመውን ሰቆቃ እየተመለከቱ የመንግስት ሃይል ያድነናል ብለው ሲጠብቁ 25 ሰዎች የኢህአዴግ ሰራዊት ፈጅቷቸዋል።

በጉና ወረዳ አዲስ አለም በተባለ ቦታም 150 ቤቶችን ከነነዋሪዎቹ ከማቃጠላቸውም ሌላ ሁለት የአገር ሽማግሌዎች እጅ እግራቸውን አስረው አቃጥለዋቸዋል።

ዋቄንትራ ከተባለው መንደር 100 ቤቶችን ከነነዋሪዎቹ አቃጥለዋቸዋል።

መሶ የተባለውን መንደር በጦር እንዲከበቡና 100 ቤቶች እንዲቃጠሉ ተደርጓ ከቃጠሎው የዳኑት 80 ሰዎች እጃቸው ታስሮ በኦህዴድ (የኢህአዴግ አንዱ ክፍል) ተረሽነው ሬሳቸው ቆሬ ከሚባል ገደል ውስጥ እንዲጣል ተደርጓል። አንድ ሰው በተአምር ከዚህ መአት ተርፏል።

እንደሴ ባዩ የሚባለው መንደር ነዋሪ የሆኑ አማሮች በተመሳሳይ ሁኔታ በኦህዴድ ሰራዊት እነዲከበቡ ከተደረገ በሗላ ከመንደሩ ነዋሪዎች መካከል 80 የሚሆኑት እጅ እግራቸውን ታስረው ተወስደዋል። ወደ ገደል እንደተወረወሩም ይወራል።
ስድስት ቤተ-ክርሲቲያናት በዚህ አካባቢ ተቃጥለዋል። ይህ ሁሉ የተፈጸመው ግንቦት 27 ቀን 1984 ዓም በአንድ ቀን ነው ሲል የመአህድ መግለጫ አብራርቷል።

እንግዲህ ፕሮፌሰር መስፍን በሸገር ራዲዮ ጣቢያ የካዱት ይሄንን በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው።
moweswe@gmail.com

የማለዳ ወግ …ከሊባኖስ እስከ ሳውዲ ፣ ሌላ የደም እንባ እንዳናነባ  !  (ነቢዩ ሲራክ)

$
0
0

* የተዘጋው የአረብ ሀገር ጉዞ ይጀመር ይሆን?

Cry Ethiopia in Saudi እለተ አርብ ጥቅምት 14 ቀን 2007 ይላል የቀን መቁጠሪያው ። በጠዋቱ ተነስቸ መብተክተክ ይዣለሁ ፣ መነሻየ ከሳምንት በፊት በሃገረ ሊባኖስ መዲና ቤሩት ስሟን ለደህነንነት ስል የማልገልጻት ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ በግድያ ወንጀል ተጠርጥራ ባለችበት ሁኔታ በነፍሰ ገዳይነት ውንጀላ መክሻሸፍ አስመልክቶ አዳዲስ መረጃን ለወዳጆቸ ለእናንተ ለማቀበል ነው ። ብዙም ሳልቆይ ቤሩት የመረጃ ምንጭ ወዳጆቸ ስልክ ደወልኩ … መረጃውን ሰባሰብኩ ፣ የኢትዮጵያ ቆንስል ጀኔራል መስሪያ ቤት ጉዳዩን በቅርብ እየተከታተለው እንደሆነ ሰማሁ ፣ ዘብጥያ ውስጥ ያለችው  እህት ስላለችበት ሁኔታ ቤሩት የሚገኘው የኢትዮጵ ቆንስል መ/ቤት ሊባኖስ ላሉ ተቆርቋሪ ዜጎቹ እንኳ መረጃ ለማቀበል  ተቆጥቧል። እንደ ምክንያት ያቀረበው ”  በፍርድ ቤት ያለ ጉዳይ ስለሆነ ምንም አይነት መረጃ መስጠት አይቻልም! ” የሚል ነው ። እዚህ ላይ ግራ ተጋብቻለሁ… ከሳሽ በመገናኛ ብዙሃን የናኘው ወደ ኋላ የተወላከፈ መረጃ ሆኖ የተገኘው መረጃ ባይሳካለትና ቢከሽፍበትም በፍርድ ቤት ያለ ጉዳይን ዘክዝኮ የወነጀላትን እህት ከሳሽ ህግ መጣሱን በመረጃ አስደግፎ  መብቷን ማስጠበቅና መከላከል አይቻል ይሆን?  ለፍርድ ቤት አቅርቦ የዋስ መብቷን ማስከበር የማይሞከርበትን መንገድ ምንድን ነው ? ይህን እየተደረገ ነው ወይ ? ብለን ሰውኛ ጥያቄ ብንጠይቅ መልሱ ጉዳዩ በፍርድ ከመያያዙ ጋር ታኮ መመለስ አንችልም የሚል ምላሽ መሰጠቱ ግራ ቢያጋባኝ አትገረሙ … ከዚሁ ጋር አሳሳቢው “ተከሳሽ እህት በምርመራ ተገዳ መግደሏን ልታምን ትችላለች!”  የሚለው ስጋት እያንዣበበ መሆኑም ይጠቀሳል። ፍርዱ የሚሰጠው በአረብ ምድር በሊባኖስ ሰማይ ስር በመሆኑ በቆንሰሏ በር ተጎትታ ስትደበደብ የተመለከትናት እና የህሊናችን የማትጠፋ ቁስል የሆነችው የአለም ደቻሳ በአዕምሯችን ለታተመ ዜጎች የዚህች እህት መጨረሻ ያሳስበናል …

ይህንና ያንን ሳስብ ሳሰላስል ደጎስ ያለ መረጃ እስኪገኝ ስደቱን ተከትሎ ለከፋው ስማችን ምንጩን አውጥቸ አወረድኩት  …. ከዚያ ሁሉ በፊት ግን “የአረብ ሃገሩ የተዘጋ መንገድ ሊከፈት ነው!” የሚል ሰሞነኛ የሹክሹክታ መረጃና የቱጃር የቪዛ ደላሎች ሳውዲ መድረስን ዜና ሰምቻለሁና እሱን ነካክቸው ላልፍ ፣ ከዚህ በፊት በኮንትራት ሰራተኞች አበሳ ዙሪያ  ያጋጠመኝን አወሳስቸ ላልፍ ከራሴ ጋር ተስማማሁና ወጌን ጀመርኩት …

ከያዝነው ወር በፊት ጀምሮ “ወደ አረብ ሃገራት የተዘጋው የኮንትራት ቪዛ ይከፈታል !” የሚል መረጃ በሰፊው በመሰራጨት ላይ ነው ። እኔም የሚሆነው የሚናገሩት ባይሆንም ኢምሬት ላይ በጉዳዩ መግለጫ የሰጡት ፕሬዘደነት ዶር ሙላትና የኢምሬት አምባሳድር  የተዘጋውን የአረብ መንገድ ለመክፈት ገና ህግ መመሪያ እየወጣ መሆኑን ፣ ከሃገራት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ከሁሉ አስቀድሞ እንደሚከወን ማሳሰባቸውን እንጅ መንገዱ ይከፈታል የሚል መረጃ አለመኖሩን በመረጃ ማስረጃ ለማስረዳት መሞከሬ ባይቀርም የእኔ መረጃ የከሸፈ መሆኑን ወዳጆች እየነገሩኝ ነው ፣ እነርሱ እውነት ነው ላሉት ማስረጃ ጭብጥ የሚሉትም አላቸው ። ይህም በቪዛው ንግድ ተሰማርተው ከገጠር እስከ ከተማ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰራተኛን ለሳውዲ ” ገበያ”  ያቀረቡት ባለ ኤጀንሲ ደላላሉች ጅዳና ሪያድ መምጣት መጀመራቸው ነው ። እርግጥ ነው ከምንም ተነስተው ዛሬ “አንቱ “የተባሉና  ጠባቂ የሚያስፈልገው ንብረት አላቸው የሚባሉት ወጣትና ጎልማሳ ኢትዮጵያውያን ደላሎችና የቪዛ ነጋዴዎች በጅዳና ሪያድ ከተሞች በአድርባዮች ታጅበው ሲንሸራሸሩ ተመልክቻለሁ … ሁሉንም መኮነን ባይቻል በአብዛኛው ደላሎቸደና አዘዋዋሪ ነጋዴዎች ለገንዘብ ሲሉ ምንም የማያውቁ እህቶቻችን ከየገጠሩ እየሰበሰቡ በየአረብ ሃገሩ ሲበትኗቸው የት እንዳሉ ያሉበትን ሁኔታ እንኳ ማወቅ የማይፈልጉ መሆናቸውን አውቃለሁ ። ሰራተኞች ተበደልን ብለው ስልክ ሲደውሉላቸው ስልካቸውን አያነሱም ። እኒህ ናቸው ሌላ ዜጋን አሁንም ወደ መከራው አለም ለመላክ በከተማችን ገብተው የመንገዱን መከፈት የሚጠባበቁት …መቸም ባለ ጸጎች ናቸውና ስላካበቱት መዋዕለ ንዋይ ጓጉቸ የቀናሁ እንዳያስመሰል በሚል ብዙ ከማለት መቆጠቡን እመርጣለሁ ። ይህን ስል ስማችን ለመጉደፉ ምክንያቶቸን በአጭሩ ፣ የግፍ በደሉን ቀማሽ እህቶች የሰማሁትን ምስክርነት በጨረፍታ መመልከቱ ግድ ይለኛል።

ድሮ ድሮ በማይባል የሩቅ ዘመን ትዝታ ሃበሻ በሚል የምንታወቀው ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንን ጨምሮ በአረቦች ዘንድ እንከበር ፣  እንታመን ፣ እንወደድ ነበር ። ይህን ወቅት ድንጋይ ዳቦ የነበረበት ዘመን አይደለም ።  … እኔም “ኩራት ክብር እየቀረ ነው !” በሚባልበት የጊዜ ጫፍ የዛሬ 20 አመት ገደማ ሳውዲ መጥቸ በአረብ ሃገር ተንደላቀው በክብር የኖሩት ጎደለብን ብለው “ቀረ ፣ እየጠፋ ነው! “።ያሉትን የሃበሻ ክብርና ሞገስ ደርሸበታለሁ ። አሁን አሁን ግን እንጃ …አመኔታውና ክብሩ እየሸሸን መሄዱ ይሰማኛል። ሳንታመን ፣ ሳንከበር እንዳንከርምን የባጀነውም ያለ ምክንያት አይደለም ። አዎ በሚሊዮን የሚቆጥር ስደተኛ የህግ ሽፋን በተሰጠውና ህግ በማያውቀው ህገ ወጥ  መንገድ ተሽሎክሉከው በቦሌም ፣ በባሌም ፣ በሞያሌም ፣ በጅቡቲና ሶማሊያም ወደ ከፋው የስደት ቀጠና ሲያቀኑ ነገር ተበላሽቷል። ስለማላውቀው የአፍሪካ ሃገር የከፋ ስደት መናገር ባልችልም ስለ አረቡ ሃገር ስደተኛ መናገር አይገደኝም ።

…  ቀን ወጣለት የተባለው ያልሰመረለት የሃገሬ ገበሬ ልጆችን ፣ የኑሮ ውድነት ጣሪያ ነክቶ ፣ የእለት ጉርሱን አግኝቶ መኖር አቅቶት በችጋር የሚደቆሰው ከተሜ ፣ በአንድ ጀንበር የተለወጡት እያማመሉ ያለውን ጥሎ ለተሻለ ኑሮ ፍለጋ የተሰደደው ቀቢጸ ተስፈኛ ፣ በአረብ ሃገር የሚላኩ የተሳሳቱ መረጃዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ አረብ ሃገር ተሰደዋል።  “ከገጠር እስከ ከተማ መንገዶች ተሰርተው ፎቆች ተገጥግጠው ፣ በየአመቱ የምታድግ የምትመነደገው ሃገር ” ተብሎ ለእድገቷ ምስክር የሚጣቀስላት ሃገር ዜጎች  በግፍ ወደ አረብ ሃገር መሰደድ መጀመራችን ስማችን ማክፋት መጀመሩና ነሩ ሁሉ ሲያበለሻሸው በአይኔ በብሌኑ ተመልክቻለሁ። አምስትና ስድስት አመታት በፊተ በስማችን መክፋት መበለሻሸት ዙሪያ  ሲነሳ ከዚህ ቀደም የሚጠቀሱ ምክንያቶች  ጥቂት ሃበሾቸ የተሰማሩባች ህገ ወጥ ስራዎች  መጠጥ መሸጥ ፣ ዝሙት እና የመሳሰሉት ናቸው ይባል ነበር ። … ይህ ደግሞ የአረቦች ህገ ወጥ ምርት አቅርቦቱን ተጠቃሚ መሆን ፣ በገዥነት ፣ በተባባሪና በድጋፍ ሰጭነት ይሰራ የነበረው ስማችን ካስከፋው ስራ አረቦችን ቂም አስቋጠሮ ስማችን አጉድፎ በአደጋ የጣለን ከኮንተራት ስራው ቅበላው ጋር የመጣው የነፍስ ማጥፋት ውንጀላ ነው ። ይህ በኢትዮጵያውያን የኮንትራት ሰራተኞች ተፈጸመ የተባለው ወንጀል እየሰፋ መጣ ተብሎ በአደባባይ ስማችን እየተነሳ ሲወገዝ ፣ ጉብል እድሜያቸው ከሃያ የማይዘሉ የኮንትራት ሰራተኛ እህቶች “ገዳይ”  ተብለው የገደሉበትን ምክንያት በአረብ ታዋቂ መገናኛ ብዙሃን ሲናገሩት ሰምተናል ።  ይህም ስማችን ቅስማችን ሰብሮታል … በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች እንደጨው ተበትነዋልና ስማችን አሳፋሪ ሆኖ እስካሁን ቀጥሏል።

ለዚህ ሁሉ ምክንያት ከሃገር ቤት ከወላጅ ጀምሮ እስከ ደላላ ፣ ከደላላ እስከ ሃላፊነታቸውን መወጣት የገደዳቸው የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ናቸው የሚል እምነት አለኝ ። በዋናነት ደግሞ ከኢትዮጵያውያ በህጋዊ መንገድ ወደ ሳውዲና ወደ ቀሩት አረብ ሃገራት መላክ ሲጀመር በሃገራት መካከል በተደረገ ስምምነትን መሰረት ያደረገ አለመሆኑ፣ ከስልጠና ጀምሮ እስከ ስራ ስምሪት በቂ ስልጠናው ቀርቶ በሚደርሱቸው አረብ ሃገራት ያሉ ኢንባሲዎችና ቆንስሎች በሙያው በተካኑ ዲፕሎማቶች  አለመመደብና  በቂ ዝግጅት ያለመደረጉ አሁን ለተጋረጥንበት ጣጣ አደጋ አብቅቶናል። ይህ በዋንኛነት በእጅጉ እንደጎዳን ፣ እናድስ እንገንባ የምንለውን ስማችን እንዳከፋው ፣ እንደጎዳው  አሰረገጦ የመናገር አቅሙ አለኝ …

የዘሃራ ውጋት …

ጊዜው በአዲሱ የፈረንጆች 2012 አሮጌው የፈረንጆች አመት ሊሰናበት ሲያስገመግም አዲሱ አመት 2013 ሊመጣ የቀሩት ሁለት ቀናት ብቻ ናቸው ፡፡ የጅዳ የሰሞኑ አየር ደስ የሚል ሆኗል ፡፡ ሙቀት ወበቅ የሚሉት ነገር ከጠፋ ሰነባብቷል ! አንዳንድ ቀን ግን አመል ሆኖበት ነው መሰል አልፎ አልፎ ሙቀቱ ብቅ ብሎ ጥልቅ ማለቱን ግን አልተወውም . . . ያማታው ብርድ ግን አይጣል ነው . . . ! ጂዳ ቆንስል ግቢ አዲስ በተሰራችው የኮንትራት ሰራተኞች መጠለያ ከታጨቁት እህቶች አንዳንዶቹን ከጎናቸው በርከክ ብየ አዳምጣለሁ፡፡ ሲለኝ ደግሞ ፎቶ ለመረጃ አነሳለሁ. . . ዘሃራ የተባለች እህት ቀልቤን ጨምድዳዋለች ! ይህች ከ15 አመት እድሜዋ የማትዘልለው ጉብል በኮንትራት መጥታና ከአንድ ክፍል ለአራት ቀናት ያለ ምግብና ውሃ በመዘጋቷ በማታውቀው ሃገር ቤቱ ሲከፈትላት ሾልካ ጠፍታለች ፡፡ ያልታደለችው ዘሃራ ግን ሳታስበውና ሳታልመው በሰው አውሬዎች እጅ ወደቀች . . . ሊደፍሩ ለሁለት ሲያንገላቷት የተጎዳው ጀርባዋ አላስቀምጥ አላስተኛ ብሎ እንዳስቸገራት የተረዳሁት ስታናግረኝ ከአንዱ ጎን ወደ ሌላኛው ጎን ለመገላበጥ ስትሞክር ነበር . . ፣ ዘሃራን ደጋግሜ መደፈር አለመደፈሯን ስጠይቃት “አልደፈሩኝም አረ !” ስትል ክብ ፊቷን ከስክሳና እንደ ማፈር እያለች አንገቷን ደፍታ ደጋግማ መለሰችልኝ ! ዘሃራን በኒያ ባለችኝ ጎረምሶች ጡንቻ ተይዛና ተደብድባ ወገቧ ሲሰበር ከመደፈር እንዴት እንደተረፈች ለመገመትና ለማመን አልዋጥልህ አለኝ ! ደግሞ እኮ ጎረምሳ ለምመስለው ለእኔስ ቢሆን እንዴት መደፈሯት ትነግረኛለች? አልኩና በውስጤ ይህንን ጥያቄ ከመደጋገም ራሴን ቆጠብኩ . . .  ከትንሿ ልጅ ከዘሃራ ጋር በነበረኝ ቆይታ ስሜቴ ክፉኛ ተጎድቷል  !

ዛሬ ዘሃራ ሃገር ቤት ናት ” ብድሬን አልከ ፈልኩምና የወላጆቸን ፊት አላይም !” ማለቷን አስብና ይጨንቀኛል በመንፈስ እታመማናለሁ ፣ አዎ ዘሃራ ህይወቷ እንደ አካሏ መናጋቱን ዘልቆ አውቃለሁና ፣ ብዙ ለጋ ዘሃራዎችን አይቻለሁ ፣ እህ ብየ አድምጫለሁና የውስጥ ህመሜን እኔ ነኝ  የማውቀው …ዛሬ ዘሃራ መሰሎችዋ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ግን እንጃ …

የሪያዱ ወዳጀ ልብን የሚሰብር መልዕክት  . .

በሪያድ መንፉሃ ተብሎ በሚጠራውና በባህር የመጡ ሃበሾች እርስ በርሳቸው በሰላ ቢላዋ በሚወጋጉበት መንደር  በተለያዩ ቀናት  በአስገድዶ መድፈር ባሰሪዎቻቸውና በቤተሰቦቻቸው የተጠቁ እህቶችን ተጥለው መገኘታቸውን ሰምቻለሁ፡፡ እህቶችን አግኝተው ያስጠጓቸው ኢትዮጵያውያንን በስልክ አግኝቻቸው ብዙ መረጃን ሰጥተውኛል፡፡  በአብዛኛው እየተደፈሩ የሚመጡ የኮንትራት ሰራተኞች ቁጥር ከፋ ያለ መሆኑ ለመረዳት ችያለሁ፡፡ ከአንድ ወዳጀ ከዚህ በፊት አንድ የደረሰኝ አሳዛኝ መልዕክት የኮንትራት ሰራተኞች ሁኔታ እየከፋ መሄድ ድፍንፍን አድርጎም ቢሆን ያስረዳል ባይ ነኝ!   የምሬት መልዕክቱን ዛሬም ደግሜ እንዳለች አውርጃታለሁና ተመልከቷት !

” ወዳጄ ሲራክ ከትላንት ወዲያ ሪያድ ውስጥ ኣንዲት እድሜዋ 19 የሚጠጋት ሴት ልጅ ኣሰሪዎቿ ዑለያ በሚባለው አካባቢ ያለ ምንም ፓስፖርት ወይም ኢቃማ ልብሷን በ ፌስታል አስይዘው ከመኪና አውርደው ጥለዋት ሄዱ። ስታለቅስ አግኝቼ የመጣው ይምጣ ቤቴ ወሰድኳት ። ደሞዝ ተከፍሏት ኣያውቅም ፣ ስራውንም በደምብ ኣለመደችም፣ በጣም ደንግጣለች፣ ዝምታ ወጧታል። የጣሏት ከፊሎቿ እንደሆኑ እና ከመጣች 3 ወሯ እንደሆናት ነገረችኝ።ደቡብ ወሎ ፣ ወግዲ ከሚባል ገጠር ሸህ ሁሴን በሚባል ደላላ ኣማካኝነት ከእህቷ እና ሌሎች 5 ሳዱላዎች ጋር ዕድሜዋን 25 ኣድርገው ወደ ሳውዲ እንዳመጧቸው እና እህቷ የት እንዳለች እንደማታውቅ ነገረችኝ። ዜግነቴን ጠላሁት። የት ልሂድ ከዚህ በላይ ፣እዚህ አገር መኖር አልፈልግም። ዜግነቴን ጠላሁት…” ነበር ያለኝ  !

የኮንትራት ሰራተኞችን አበሳ ዘክዝኬ በምስል መረጃ ባቀርበው ደስ ባለኝ ፣ ግን ምስሎቹን ለመለጠፍና ግፉን ለማሳየት ልቤ ቢቆርጥም ፣ ሰብዕናን ላለማሸማቀቅ ስል ብቻ የምስል መረጃውን ልዘለው ግድ ብሎኛል፣ ስማችን ከፍቷል ብሎ በስሱ ስለስም መጨነቅ ለእኔ ቀልድ ነው ፣  የሚሰራው ታስቦና ተጠንቶ ስላልሆነ ፣ መብታችን የሚያስጠበቅልን ስለጠፋ  ፣ ከስም በላይ ሰብዕናችን መርከስ ይዟልና ግፍ እየተፈጸብን ነው ፣ ለዚህ ማሳያ በሃገረ ሊባኖስ  እየሆነ ያለውን በጥልቀት መመልከቱ ይበቃል፣ ለዚህ ማሳያ በሳውዲ የጅዳ ቆንስልና እና በሪያድ ኢንባሲ መጠለያ ያለፉትንና አሁን ድረስ  ያሉትን ግፉዕ ዜጎች በደል ሰምተናል ፣ እየሰማን ነው ! ዜጎች ሰብአዊ መብታቸው ሲደፈጠጥና የተስማሙበት ኮንትራት ውል ተጣሰብን የሚሉ እህቶቸን ድምጽ ማሰማት ለእኔ ነፍሴ የፈቀደው ስራ ነው ፣  የመንግስት ዲፕላማቶች ቀዳሚ ስራ  ነጋ ጠባ ለምንጠይቀው የዜጎች መብት ጥበቃ ቆሞ ወገናዊነትን ለህዝብ ለማሳየት መሞከር  ነው ! የሚፈለገው የሚያወራ ሳይሆን የሚሰራ ነውና …የመንግስት ተወካዮች በህግና በስርአት የመጡ ዜጎችን  መብት ማስከበር አለባቸው ! የቪዛ ውል ማስፈጸሚያ ገንዘብ እየሰበሰቡ ባጸደቁት የኮንትራት የስራ ውል ላይ የተጻፉት ስምምነቶች የመከታተልና የማስፈጸም ሃላፊነት አለባቸው! ፍትህ ሲጎድል ተከራክረው ሊያስከብሩልን ይገባል ! … ከዚህ በፊት መብታቸው ተጥሶ ተሸፋፍኖ እንደተላኩት ጉዳተኞች ወደ ሃገር ቤት ለማሳፈር የሚደረገውን ጥረት ጎን ለጎን የተገፊዎችን በደል ፍትህ ሊፈለግለት ይጋባል ፣ ይህ ግን በአብዛኛው አይደረግም ፣ በዚህ ረገድ እማኝነቱን ከባለቤቶቹ “እህ” ብየ ሰምቻለሁና እነግራችኋለሁ ! የተጎዱት ከተደፋባቸው የመከራ ህይዎትና ከእድሜ አለመብሰል አንጻር ” ወደ ሃገራችን እንግባ ! ከቤተሰቦቻችን ቀላቅሉን !” ማለታቸው ደጋፊ ማጣትና ስጋት እንጅ ያልተበደሉ ሆነው  ፍትህን ሽሽት አይደለም !

መንግስት ይህ ሁሉ እየተነገረው የሚሰማ አይመስልም።ከአመት በፊት ወደ አረብ ሃገራት የተዘጋው መንገድ ደላላዎቹን ወደ ሊባኖስ ኩዌትና ኳታር የሚያሸጋግር ስራቸውን እንዳልገደበው አውቃለሁ። ከቀናት በፊት ሊባኖስና ቃጣር በተዘዋዋሪ መንገድ የገቡ ኢትዮጵያውያን አጋጥመውኛል ።  ይህም ሁሉ ሆኖ ከኢትዮጵያ መንግስት አስቀድመው የሳውዲ መንግስት ያገደው ከኢትዮጵያን ሰራተኛ የማስማጣት እገዳ በኢትዮጵያ መንግስት ብቻ እገዳው ስለተነሳ ሰራተኛን ወደ ሳውዲ ማስገባቱ ይሰምራል ባልልም የአረብ ሃገሩ መንገድ ምንም ባልተሰራበት ሁኔታ መታሰቡ በራሱ ያማል ። አልተሰራም የምለው በጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት በኩል ያለውን ነባራዊ አቅም አውቃለሁና ነው ፣ ጅዳ ያለ ቋሚ ዲፕሎማት በተጠባባቂው ባለስልጣን መመራት ከጀመረች መንፈቅ ማለፉን ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖም አያውቁም አልልም ፣ ብቻ መንግስት ጀሮ ሰጥቶ ሊሰማን ይገባል ! … አባቶች ”  አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ !” እንደሚሉት ሆኖ ሌላ እንባ እንዳናነባ  …!

ቸር ያሰማል  !

ነቢዩ ሲራክ

“ጥሬ ሥጋ መብላት ካቆምኩ በኋላ ውፍረቴ ቀንሷል…”ድምፃዊ ታምራት ደስታ (ቃለምልልስ)

$
0
0

ከቁምነገር መጽሔት ጋር የተደረገ

ታምራት ደስታ ከዚህ ቀደም ለአድናቂዎቹ ባደረሳቸው የሙዚቃ አልበሞቹ ይታወቃል፡፡ በተለይ አንለያይም የተሰኘ አልበሙ በብዙ አድናቂዎቹ ተወዶለታል፡፡ ከዚህ ቀደም ከሰራኋቸው ዘፈኖች በተሻለ የተዘጋጀሁበት ነው ያለውን ‹ከዛ ሰፈር› የተሰኘ አዲስ አልበም በያዝነው 2007 ዓ.ም ለገበያ ባቀረበበት ማግስት የመሿለኪያ አምዳችን እንግዳ አድርገነዋል፡፡
Tamrat Desta
ቁም ነገር፡- ሰሞኑን ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳልነበርክ ሰምተናል፡ ፡ የት ነበርክ?
ታምራት፡- በስራ ጉዳይ እና በግል ምክንያት አውሮፓ ነበርኩኝ፡፡
ቁም ነገር፡- ምን ያህል ጊዜ ቆየህ?
ታምራት፡- ብዙ አይደለም፡፡ አንድ ሶስት ወር ነው፡፡
ቁም ነገር፡- ከዛ ሰፈር የሚለው አዲሱ አልበምህ የወጣው እዛው ሆነህ ነው ማለት ነው?
ታምራት፡-አዎ
ቁም ነገር፡- አልበሙ ከወጣ በኋላ እዚያ የነበረው ስሜት ምን ይመስል ነበር?
ታምራት፡- በጣም ጥሩ ነው፡፡ ምክንያቱም እዚያ ካሴቶች ቶሎ ይደርሳሉ፡፡ ሲጀመር አሳታሚውም ናሆም ሪከርድስ ስለሆነ ናሆም ብዙ ቅርንጫፎች አሉት፡፡ በአውሮፓም በአሜሪካም በተለያዩ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራትም ብዙ ማከፋፈያዎች ስላሉት አቀባበሉ በጣም አሪፍ ነው፡፡ ስዊዘርላንድ ጀርመን ጣልያን አካባቢ ነበርኩኝ፡፡
ቁም ነገር፡- እዚህ ኢትዮጵያ ከመጣህ በኋላስ አልበምህ ያለበትን ደረጃ እንዴት አገኘኸው? እየተደመጠ ነው?
ታምራት፡- አውሮፓ ሆኜ እዚህ የአልበሙ ፕሮሞሽን ስላልተሰራ ብዙ ሰዎች ጋ እንዳልደረሰ ሰምቼ ነበር፤ አሁን ከመጣሁ በኋላ ግን ያው ቪዲዮዎ ክሊፖችን አዘጋጃሁኝ ነው፡፡ እ…የተለያዩ ሬዲዮ ጣቢያዎች ጋር አንዳንድ ማስታወቂያዎችን ሰራን፤ ከዛም ባለፈ ግን ራሴ ቃለመጠይቅ እየተደረግኩኝ ስለ አልበሙ ተናግሬያለሁኝ፡፡ በሙዚቃ ቤቱም በኩል ያለው ነገር በጣም አሪፍ ነው፡፡ ወደ ህዝቡ እየደረሰ ነው፡፡ ስራዎቹ ሲሰሙ ያምራሉ፡፡ የሚያምርና ቆንጆ የሆነ ስራ ባልሰራ ወደ ህዝቡ አልመጣም፡፡ ያልሰሙትም ሰዎች ካሉ ሰምተው ወደዉት አስተያየታቸውን እንደሚሰጡኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ቁም ነገር፡- አልበምህን ለማዘጋጀት ምን ያህል ጊዜ ወሰደብህ?
ታምራት፡- ዝግጅት ሳደርግ እንግዲህ ብዙ ጊዜ ቆይቼአለሁ፡፡ ለነገሩ የቆየሁት ዜማዎችና ግጥሞችን በመምረጥ ብቻ አይደለም፡፡ ሌሎች ስራዎች ስለነበሩኝ፤ እንደገና በዚህ በቅጂ መብት በኮፒ ራይት ዙሪያ ደስ የሚል ነገር ስላልነበረ ያ ነገር ከዛሬ ነገ ይሻሻላል ለውጥ ይመጣል በሚል ጊዜዬን ተሸሻምቶብኛል፡፡
ቁም ነገር፡- ሁለተኛ አልበምህ ከወጣ ስንት ዓመት ሆነህ?
ታምራት፡-ሁለት ሺህ ላይ ነው ያኛውን አልበም ያወጣሁት፤ በመሃል ግን ዘፈኖች አሉ፡፡ አዳዲስ ዘፈኖች ክሊፖች ምናምን ሰርቼያለሁ፡፡በዚያኛውና በዚህኛው አልበም መካከል የሰባት ዓመት ልዩነት አለ፡፡ የዚያኔ የምሰራቸው አልበሞች ደግሞ የዚያን ዘመን አሻራ ጥለው እንዳለፉ ሁሉ ይሄም ደግሞ የራሱ ዘመን አለው፤ የምትሰራበትም ስሜት ደግሞ እንደዛሬ እንጂ እንደትናንት አትኖርም.. (ሳቅ…) ምን ለማለት ፈልጌ ነው ያመንኩበትን ስራ ነው ወደ ህዝቡ ያመጣሁት፡፡ እርግጠኛ ነኝ ደግሞ አሪፍ አልበም ነው፡፡
ቁም ነገር፡- በቀደሙ አልበሞችህ ውስጥ ለፍቅር ዘፈኖች የምትሰጠው ትኩረት ከፍ ያለ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በአሁኑ አልበምህስ ለፍቅር የሰጠኸው ቦታ ምን ይመስላል?
ታምራት፡-ከፍቅር በላይ ምን አለ ብለህ ነው (ሣቅ…) ፍቅር ማለት በእኔ እይታ ራስን ለሌላው አሳልፎ መስጠት ማለት ነው፡፡ በመጽሐፍም እንደምናውቀው የፍቅር ጥጉን አይተነዋል፡፡ ስለዚህ ማህበራዊ ሕይወትና ፍቅር ላይ ትኩረት አደርጋለሁ፡፡ እነሱን መስበክ ያስደስተኛል፡፡ ምክንያቱም ሰው መጀመሪያ አስተሳሰቡን ነው መቀየር ያለበት፡፡ ከጥላቻ ይልቅ ወደ ፍቅር መምጣት አለበት፡ ፡ አንድ ድርጊት እንኳን ከማድረጋችን በፊት መጀመሪያ አዕምሮአችን ለክፋትም ይሁን ለቅንነት ለጥላቻም ይሁን ለፍቅርም አዕምሮአችን ውስጥ ነው የሚታሰበው፡ ፡ ስለዚህ ሁልጊዜ አስተሳሰባችንን ሊለውጥ የሚችል እ…በዘፈንም ይሁን በተለያዩ ጥበብ ነክ ነገሮች ማህበረሰቡን መደገፍና ምናልባት ተናግረው ማሳመን የማይችሉ ብዙ ሰዎች ይኖራሉ ፤አንደበታቸው ቢዘጋ ያው እንግዲህ በዘፈን ስታቸውን ይገልፃሉ፡፡ …የተለያየ ይህን ፊልም እይልኝ ይህን ዘፈን አዳምጪልኝ የሚባሉ ነገሮች አሉ፡፡ ፍቅር የማያረጅ ነገር ነው፤ አያረጅም፡፡ ከፍቅር ውጪ ሁሉ ነገር ከንቱ ይመስለኛል፡፡ ለዛነው እኔም እዚህ ላይ ትኩረት አድርጌ የምዘፍነው፡፡ ይህንን ስል ደግሞ ሌሎች ነገሮችን አላነሳም ማለት አይደለም፡፡ ብዙ የተነሱ ጉዳዮች አሉ፡፡ አዲስ አበባ ሌላ ጉዳይ ነው፤ የጎጃም የባህል ዘፈን አለ(የፍቅር ቢሆንም)፤ ማማዬ የሚለውም ስለእናት ይሆንና ከሴትና የወንድ ግንኙነት ወጣ ይላል፡፡እናት ላይ ያተኮረ ዘፈን ነው፡፡ ትራክ(ቁጥር) አስራ አራት ላይ ብታይ ደግሞ ለምኔ የሚል ዘፈን አለ፡፡ እዚያ ላይ የአንት ፍልስፍና አንተን አመለካከት ነገሮችን ሁሉ እንዴት ወደ ቅንነት እንዴት ወደ በጎ ምግባር ማምጣት እንደሚቻል የሚያሳይ ዘፈን ነው፡፡
ቁም ነገር፡- አንድ አልበም ሲዘጋጅ ከፍተኛውን ተጽእኖ መውሰድ ያለበት ማን ነው ድምጻዊው ነው ወይስ የግጥምና ዜማ ደራሲው?
ታምራት፡-ዘፈን ማለት የጋራ ስራ ነው እንደ እግር ኳስ በጋራ የሚሰራ ስራ ነው፡፡ ስለዚህ የግጥምና የዜማ ደራሲዎቹ መኖር አስፈላጊ ነው፤ቅንብሩ የድምጽ ጥራቱ እነዚህ ሁሉ መጉደል የለባቸውም፡፡ የሁሉም አስተዋጽኦ አለበት ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የጋራ ስራ እንደመሆኑ ተስማምተን ነው የምናደርገው፡፡ ወደ ድምጻዊው ስትመጣ ዜማና ግጥሙን የመምረጥ መብቱ የድምጻዊው ነው፡፡ የማይፈልጋቸው ዜማና ግጥሞች ከሆኑ አይመርጣቸውም፡፡ አቀናባሪም ደግሞ አንተ የሚመችህን አይነት ነገር ትንሽ ፍንጭ ከሰጠኸው አሪፍ አድርጎ ሊሰራልኽ ይችላል፡፡ ስለዚህ የብዙ ሰው እጅ ይጠይቃል፡፡

ቁም ነገር፡- ምናልባት ይህንን ያነሳሁት የአሁኑ አልበምህ በተለመደው የዜማና ግጥም ደራሲ የተሰራ ስላልሆነ ነው፡፡ ከዚህ በፊት በነበራችሁ ግንኙነት ታምራት ደስታ ሲነሳ የብዙ ግጥምና ዜማዎቹ ደራሲ የሆነው ሀብታሙ ቦጋለ ይነሳል፡፡ የእርሱ ስራዎች ለምን አልተካተቱም? ከዚህ ጎነን ለጎንም ከእርሱ ጋር ያላችሁ ግንኙነት ሰላማዊ ነው?
ታምራት፡-አይ… ያው ሀብታሙም አለ ዳግማዊ አሊ አለ፡፡ እነዚህ ሰዎች ማለት ለኔ እዚህ ጋ መድረስ ትልቁን ሚና የተጫወቱ ናቸው፡፡ እ… ምንድነው እርሱ አሁን ወደዚህ አልበም ስመጣ አንደኛ ሳውንድ ለመቀየርም ነው፡፡ ማለት በተለመደ ነገር ከመሄድ ውጪ የሰው ጆሮ አዲስ ነገር መስማት ይፈልጋል፡፡ የሰው ዓይን ደግሞ ሁሌም አዲስ ነገር ማየት ይፈልጋል፡፡ ከዚህ አንጻር የራሴን ምልከታ ዓይቼ ይሄን ነገር እንዲህ ባደርግ ይሻላል በሚል እንጂ ከእነርሱ ጋር እንደቀድሞው ሳልገናኝ ወይም በሌላ ምክንያት አይደለም፡፡ በአዲሱ አልበም ውስጥ የተካተቱት ሰዎችም ቢሆኑ ለተለያዩ ሰዎች ግጥምና ዜማ የሰሩ ናቸው፡፡ ጌትሽ ማሞ አለ፤ አማኑኤል ይልማ አለ፤ መሰለ ጌታሁን አለ፤ ኤፍሬም ዳምጠው አዲስ ልጅ ነው፡፡ እዮቤል ብርሃኑ …እነዚህ እነዚህ ጎበዝ ልጆች ናቸው፡፡ እድሉንም ደግሞ አንዳንድ ጊዜ ለእነርሱም መስጠት ጥሩ ነው፡፡ ሁል ጊዜ አንድ አቅጣጫ ብቻ የምናይ ከሆነ መልካም አይደለም፡ ፡ ሌሎች አቅጣጫዎችን መመልከት አለብን፡፡ እኔ ደግሞ የዜማም ደራሲ ነኝ፡፡ እኔ ራሴ አልተሳተፍኩም፤ ሀሳቤን ብቻ አክያለሁኝ እና አንዳንድ የዜማ ማጠፊያዎችን፤ አዝማች፤ አንዳንድ የመሃል ዜማዎችን የማስተካከል፤ ወደ መሃል የማምጣት… እንጂ ከዚያ ውጪ ሁሉንም ስራ ሌሎች ሰዎች ናቸው የሰሩት፡፡ ትልቁን ቦታ የሚወስደው ጌትሽ ማሞ ነው፡፡ ከዚያ አማኑኤል አለ፤ መሰለ ጌታሁን አለ፤ እዮቤል ብርሃኑ አለ በግጥም፡፡ እና ኤፍሬም ዳምጠው፡፡ እነዚህ ሁሉ ልጆች ጎበዞች ናቸው፡፡ ከእነርሱም ጋር በመስራቴ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡

ቁም ነገር፡- በዚህ አልበምህ ላይ አዲስ አበባን አንስተሃል፡፡ ከዚህ በፊት ደግሞ በጋራ በተሰራ ነጠላ ዜማ ወላይታን አንስተሃል፡፡ እ… የጎጃምና የወሎ ዜማዎችን እንዲሁም ስለ ድሬዳዋም ዘፍነሃል፡፡ ከዚህ በኋላስ የሚዘፈንለት ተረኛው ከተማ ማን ይሆን?
ታምራት፡-አሁን ለምሳሌ ስለዚህ ከተማ እዘፍናለሁ ብለህ አይደለም የምትዘፍነው፡፡ በወቅቱ እዛ ከተማ ላይ ሄደህ ሊሆን ይችላል፡፡ ወይ ደግሞ ኖረህ ሊሆን ይችላል፡፡ እ…እንደገና ደግሞ የተለያዩ ገጠመኞች ይኖሩሃል፡፡ እንግዲህ ከምታነበውም ከምታየውም ነገር የተነሳ ማለት ነው፡፡ ሀዋሳን ብትል ሀዋሳ እና ሻሸመኔ የትውልድ አካባቢዎቼ ናቸው፡፡ ድሬዳዋ ደግሞ የኖርኩበት በልጅነቴ ሄጄ ሙዚቃም የጀመርኩበት ሃገር ነው፡፡ የተለየም ፍቅር አለኝ፡ ፡ አዲስ አበባ ብትል ደግሞ ሰርቼ የተለወጥኩበት፤ ከህዝቡ ጋር ተስማምቼ የኖርኩበት፤እ..ብዙ ፈተናም የተፈተንኩበት ፤በፍቅርም ህይወቴ ይሁን በተለያዩ ነገሮች ብዙ ነገር ያየሁበት ከተማ ነው፡፡ ስለዚህ የዚህ ከተማ ትዝታው እና አሻራው በውስጤ አለ፡ ፡ ከተማውን ስታስብ ህዝብ አለ፡፡ ህዝብ ደግሞ ተቀብሎ እዚህ አድርሶኛል፡፡ ነገም እንግዲህ በተለያዩ አጋጣሚዎቸች ማንሳት የምፈልጋቸው ጉዳዮች ካሉ እ… በዘፈን መልክ አንስቼ ለሰዉ ላቀርብ እችላለሁ፡፡
ቁም ነገር፡- በዕድል ታምናለህ ታምራት?
ታምራት፡-እ.. አስራ አምስት በመቶ ምናምን፤ እንጂ እኔ ሰማኒያ አምስት በመቶ በስራ ነው ብዬ ነው የማምነው፤ ከመሬት ተነስቶ የሚፈጠር ነገር የለም፡፡ እጅህን አጣጥፈህ ቁጭ ብለህ ከሰማይ መና እንዲወርድልህ የምትጠብቅ ከሆነ ምናልባት ሌላኛውን ዓለም መምረጥ አለብህ፡ ፡ ምክንያቱም ሰው ጥሮ ግሮ እንዲበላ ነው ከአዳም ጀምሮ የምናውቀው እና በመስራት አምናለሁኝ፡ ፡ እ… በመስራት የማመኔ ትልቁ ምክንያት ደግሞ ያለፍኩትን ጎዳና ስለማውቅ ነው፡፡ ስለዚህ ለዕድል ከሃያ እና ከሰላሳ በመቶ የበለጠ አልሰጠውም፡፡
ቁም ነገር፡- ስመ ሞክሼህ ከሆኑ ታዋቂ ሰዎች መካከል እነማንን ታውቃለህ?
ታምራት፡-ዘፋኞች
ቁም ነገር፡- ማንኛውም ሙያ ውስጥ ያሉ?
ታምራት፡- ለምሳሌ ራሱ የዚህ መጽሔት አዘጋጅ ታምራት ነው፡፡እ..ከአንጋፋ አርቲስቶች ደግሞ ታምራት ሞላ፤ ታምራት አበበ አለ የድሮ ዘፋኝ ነው፡፡ እንደገና ደግሞ ሌላ ጋዜጠኛም አለ መሰለኝ፡፡

ቁም ነገር፡- በዘንድሮ አልበምህ ውስጥ ከተካተቱት ዘፈኖች መካከል የአንተ ስሜት የበለጠ የሚያደላው ለየትኛው ነው?
ታምራት፡- ዘፈኖቼን ስሰራ አንዱን ከአንዱ 35 አበላልጬ የማይበት መንገድ ብዙም የለም፡፡ ግን ያው ጣቶቻችንም አንዱ ከአንዱ ይበላለጣሉ፤ቢሆንም አንዱ ያለ አንዱ አይኖርም፡ ፡ የአንዱ መጉደል አንዱን ያጎድለዋል፡፡ ዘፈኖቼ ውስጥ እንግዲህ እንደ ቴስት የምወዳቸው ዘፈኖች አሉ፡፡ከዛ ሰፈር አሪፍ ነው፤ ራሱ ፍፁም ሰላም፤ ማማዬ የተለየ ነገር አለው፤ተአምር ያስፈልጋል የሚል ዘፈንም አለ፡፡ ጌትሽ ማሞ ግጥሙን የጻፈበት እይታው ያስገርመኛል፡ ፡ እና በጣም ደስ ይለኛል፡፡ ብቻ አንድ ነው ሁለት ነው ሶስት ነው አልልህም፡፡ ሁሉንም ነው እኔ የምወድደው፡፡

ቁም ነገር፡- ከሌሎች ድምጻውያን ጋር በጋራ በሰራኸው አንድ የወላይትኛ ዘፈን የሙዚቃ ቪዲዮ ላይ ልጆችህ የሚታዩ ይመስለኛል፡፡ በቅርቡ ደግሞ አብነት አጎናፍር ባወጣው አዲስ አልበም በአንድ ዘፈኑ ላይ ልጆቹን አሳትፏል፡፡ ልጆችህን በሙዚቃ ስራዎችህ ላይ የማሳተፍ ሃሳብ አለህ?
ታምራት፡- ከልጆቼ መካከል እኔን የሚመስሉ አሉ፡፡ ድምጽም ያላቸው አሉ፡፡ በተለይ አንዱ ልጅ በጣም ጎበዝ ነው፡፡ ግን እስካሁን በአልበምም ሆነ በሙዚቃ ደረጃ አሳትፌያቸው አላውቅም፡ ፡ራሳቸው በግል የሚያደርጉትን ነገር ግን ቤት ውስጥ እሰማቸዋለሁ፤ እቀርፃቸዋለሁ አንዳንድ ጊዜ፡፡ አሁን ለጊዜው ትምህርታቸው ላይ ትኩረት ቢያደርጉ እመርጣለሁኝ፡፡
ቁም ነገር፡- ከአልበምህ መውጣት በኋላ ኮንሰርት ለማዘጋጀት አላሰብክም?
ታምራት፡- በእርግጥ አልበም ሰርተህ ቶሎ ብለህ ኮንሰርት አታቀርብም፡፡ ዘፈኖቹ በሰዉ አዕምሮ ውስጥ በደንብ ገብተው ቦታ መያዝ አለባቸው፡፡ ሰዉ አጣጥሟቸው አብሮህ ማለት እስከሚጀምር ድረስ መጠበቅ አለብህ፡፡ የዚያን ጊዜ እንደ ማንኛውም ሰው ኮንሰርት ልሰራ እችል ይሆናል፡፡
ቁም ነገር፡- ሰሞኑን በሀገራችን የተለያዩ ሰዎች ሀብታቸው እየተመዘገበ ነው፡፡ ተራው ወደ አንተ ደርሶ ሀብትህን አስመዝግብ ብትባል የምታስመዘግባቸው ሶስት ነገሮች ምንድን ናቸው?
ታምራት፡- እ… አንደኛው ሕዝብ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ ሀብቴ ልጆቼ ናቸው፡፡ (ሣቅ…) እንግዲህ ሌላ እኔ የማስመዘግበው ነገር የለኝም(ሣቅ…)፡፡
ቁም ነገር፡- እስካሁን ድረስ በህይወትህ ውስጥ ተመኝተኸው ያላገኘኸው ነገርስ ምንድን ነው?
ታምራት፡-እንደዛ እንኳን የለም፡፡እንግዲህ መፈልጋቸው የምመኛቸውን ነገሮች ሁሉ አግኝቼያቸዋለሁ፡፡ ምን አልባት ከዚህ በኋላ አገኘዋለሁ ብዬ የማስበው ነገር ይኖር ይሆናል፡፡ ነገር ግን እንደሌሎቹ እርሱም ይሆናል የሚል ግምት አለኝ፡፡ እስካሁን የሚያጓጓ፤ እንቁልልጭ የሚያስብለኝ ምንም ነገር የለም፡፡
ቁም ነገር፡- በአንድ መድረክ ላይ ያገኘኸው ከፍተኛ ሽልማት ስንት ነው?
ታምራት፡- በሽልማት ደረጃ የተለያዩ ሽልማቶች ይኖራሉ ፤ ሰዎች ሲደሰቱ የሚሰጡህ ስጦታዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ አንድ ጊዜ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የተባበሩት አረብ ኤምሬት ሀገር ውስጥ አንድ ጊዜ ለስራ ሄጄ ከፍተኛ የሆነ ስጦታ ተሰጥቶኛል፡፡ ሽልማቱ ሰዓት ነበር፡፡ ሰዓቱ ውድ ሰዓት ነው፡፡ ትልቁ ችግር ሠዓቱን መሸጥ አትችልም፡፡ ልሽጠው ብትል እንኳን ሰዓቱ በአንተ ስም አይደለም የተገዛው፡፡ እና እስከ ስልሳ ስምንት ሺህ ብር የሚደርስ ነበር ግን ምንታደርገዋለህ (ሣቅ…) እጅህ ላይ አድርገኸው ስትሄድ ራሱ የመክበድ ስሜት አለው፡፡ እኔ በተፈጥሮዬ ከባድ ነገር ብዙም አይመስጠኝም፡፡ ህይወቴ ራሱ ቀለል ያለ ነው፡፡ እንደ ማንኛውም ሰው የሚያስፈልገኝን ነገር አደርጋለሁ፡፡
ቁም ነገር፡- ሕይወቴ ቀለል ያለ ነው ስትል… ታምራት ለምሳሌ በቀላሉ ተፈልጎ ይገኛል? ስልኩንስ በስንተኛው ጥሪ ነው የሚያነሳው?
ታምራት፡- እ…(ሣቅ…) አዎ! እኔ እ… ውጪ ካልሄድኩኝ ወይም ደግሞ ስራ ላይ ካልሆንኩኝ በስተቀር አካባቢዬም ሆነ ከአካባቢዬ ውጪ ከድሮም ጀምሮ ከማውቃቸው ሰዎች ጋር ግንኙነት አለኝ፡፡ እገናኛለሁኝ፡፡ ማድረግ ያለብኝን ነገር ሁሉ ከጎረቤቶቼም ይሁን ከዘመዶቼም ከጓደኞቼም ጋር እገናኛለሁኝ፡፡ እንደዚህ ወጣ ብዬ ራሴን አግልዬ ምናምን አልኖርም፡ ፡ያው ከሰው ውጪ የሚሆን ነገር ስለሌለ ማለት ነው፡፡ ብትደምቅ ያለ ሰው አያምርም፡ ፡ ሁሉ ነገር ከሰው ጋር ሲሆን ነው ደስ የሚለው፡፡ እና ስለዚህ እንደ አርቲስት ታዋቂ ነኝ ብዬ ራሴን በጣም አግልዬ የምኖርበት ላይፍ ስታይል የለኝም፡፡ ምናልባት አንዳንድ ጊዜ በፊት በጣም የምታደረጋቸውን ነገሮች ላትጠቀም ትችላለህ፡፡ ከዛ ውጪ ግን ከሰዎች ጋር በስራም ሆነ በተለያየ መልክ እየተገናኘሁ ከእያንዳንዱ የማህበረሰብ ክፍል ጋር ለምሳሌ ፊልም ቤቶች ሄጄ ፊልም አያለሁ፡ ፡እንደገና ደግሞ መጽሔትም ጋዜጣም ገዝቼ አነብባለሁ፡፡ ሻይ መጠጣት ካለብኝ የሆነ ቦታ ገብቼ ሻይ እጠጣለሁ፡፡ እኛ ሀገር ደግሞ ህዝቡ መልካም ነው፡፡ ወጥተህ ተጫውተህ ትገባለህ፡፡
ቁም ነገር፡- ደም ሰጥተህ ታውቃለህ?
ታምራት፡- የሚገርምህ ነገር ሁልጊዜ አስባለሁ፡፡ ግን የኔ ደም ራሱ ደም ያስፈልገዋል(ሣቅ…)፡፡ የደም አይነቴ ምን አይነት የሚሆን ይመስልሃል ስታስበው?
ቁም ነገር፡- ኦ ይሆን?
ታምራት፡- ኦ ፕላስ ነኝ፡፡ እንዲያውም ነጌቲቭ ሳልሆን አልቀርም… ቆይቷል ቼክ ካረግኩት፡፡ አንድ ነገር ቢያጋጥምህ የደም አይነትህ ኦ ከሆነ ብዙ ሰዎችን ያለማግኘት ችግር አለ ይባላል፡፡ እና ስልክ ቁጥር ራሱ መዝግቤ የያዝኩበት ጊዜ አለ፡፡ እንግዲህ እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ነገር ስላልገጠመኝ ያው ቅድመ ዝግጅት አድርጌያለሁ፡፡ ለሌሎች ግን ደም አልሰጠሁም፡፡ ብሰጥ ግን ደስ ይለኛል፡፡
ቁም ነገር፡- እንቅልፍ ላይስ እንዴት ነህ? በጣም እንቅልፋም ነህ ወይስ መደበኛ የመኝታ ልምድ ነው ያለህ?
ታምራት፡- በፊት የተዛባ የእንቅልፍ ስርዓት ነው የነበረኝ፡፡ ምክንያቱም ማታ ሠርቼ ጠዋት ነው የምተኛው፡፡ አስፈላጊ ከሆነ አንዳንድ ጊዜ የምቀሰቀስበት ጉዳይ አለ፡ ፡ የኤምባሲ ጉዳይ ሲሆን እና ሌላም ሌላም ነገር ሲኖር ተቀስቅሼ እነሣለሁ፤ በዚህ ሁኔታ ይዛባል፡፡ የአመጋገብ ሰዓቴ ራሱ የተዛባ ነበረ፡፡ ቁርስ ምናምን ላይ ብዙ አላተኩርም፡ ፡ ምሣና እራት ነው የምበላው፡፡ ይሄ ሁሉ ከስራዬ አኳያ የመጡ ችግሮች ናቸው፡ ፡ አሁን ግን የምሽት ሥራ ካቆምኩኝ ወደ አራት አምስት ዓመት ስለሆነኝ የእንቅልፍ መዛባት የለም፤ ቁርሴንም በሰዓቱ እበላለሁ፡ ፡ እንደማኝኛውም ሠው ጠዋት ተነስቼ፤ የጠዋት ፀሐይ ሞቄ፤ ሻይ ጠጥቼ፤ ከዚያ በፊት ስፖርቴን ሰርቼ… ያው አሁን እንደምታየኝ ኪሎዬ ጨምሯል (ሣቅ…)
ቁም ነገር፡- በነገራችን ላይ ኪሎህ ስንት ደረሠ?
ታምራት፡- አሁነ አንዳየህ ጥሬ ስጋ (መብላት) ካቆምኩ በኋላ ቀንሷል ኪሎዬ (ሣቅ!)፡፡ ጥሬ ሥጋ ምናምን፤ አንዳንድ ነገሮችን ክትፎ ነገር እወድ ነበር፡፡ አለርጂ እየሆነብኝ ስለተቸገርኩ ባልወስደው ይመረጥ ነበር፡፡ አሁን ጥሬ ስጋ ከተውኩ ረጅም ጊዜ ሆኖኛል፡፡ እ…. ስፖርት ዱቡ ዱብ ማለት ጀምሬያለሁኝ አሁን፡፡ በፊት ሠማንያ ሁለት ኪሎ ሆኜ ነበር፡፡ እንግዲህ ከየት ተነስቼ ሠማንያ ሁለት እንደደረስኩ አንተ መገመት ትችላለህ (ሣቅ!)
ቁም ነገር፡- አዎን ቀጭኑን ታምራት እናውቀው ነበር (ሣቅ…)
ታምራት፡- እንግዲህ የበፊቱ ቀጭኑ ታምራት ነው ይሄኛውን ታምራት የወለደው የዛኔ የነበረው አስተሣሠብህ፤ ለምሣሌ በወቅቱ ከፍተኛ የሆነ ጉልበት ባይኖር ኖሮ የመለወጥ… አሠርቶ የማደግ ጉልበት በቀጭኑ ታምራት ውስጥ ባይኖ ኖሮ ይሄኛውን ታምራት ማግኘት ይከብዳል፡፡ ለማንኛውም በጣም ወደ ቀጭኑ ታምራት መመለስ እንኳን ባልችልም… አሁን ወደ ሠባ አምስት ኪሎ ሆኜያለሁ፡፡ ቀስ ብዬ ደግሞ ሠባ ኪሎግራም ለመግባት ነው ሀሣቤ፡፡ ቁመቴ አንድ ሜትር ከሠባ ሶስት በመሆኑ በእኔ ቁመት በሀኪም የሚመክረው ከስልሣ ስምንት እስከ ሰባ ኪሎ ግራም ክብደት እንዲኖረው ነው፡፡
ቁም ነገር፡- የሌሎችም ድምፃውያንን ዘፈን የመጫወት ሀሣብ ቢኖርህ ለየትኛው ዘፈን ነው ስሜትህ የሚያደላው፡፡ በጣም ስሜትህን የሚገዛው ዘፈን የትኛው ነው?
ታምራት፡- ከወጣትም ከአንጋፋም ድምፃውያን መካከል በጣም ደስ የሚሉኝ ብዙ ድምፃውያን አሉ፡፡ ስለዚህ እኔ ከድምፄ ጋር ሊሄድ የሚችል መርጩ የምዘፍንበት ብዙ ጊዜ አለ፡፡ ከእነዛም መካከል ለምሳሌ የኤፍሬም፣ አሊቢራ፣ የነዋይም… ከዚያ ውጪ ደግሞ በራሴ መንገድ የጋሽ ጥላሁን ዘፈኖችም እሠራለሁ፡፡
ቁም ነገር፡- ቆይታችንን እያጠናቀቅን ነው በምን እንሠነባበት?
ታምራት፡- እንግዲህ እንደከዚህ ቀደሙ የቀደሙት አልበሞቼን ሰምታችሁ አስተያየት እንደሠጣችሁኝ ሁሉ ይህንንም አልበም ሠምታችሁ እንድታጣጥሙት በዚህ አጋጣሚ እጋብዛለሁ፡፡ ዘፈኖቹ መልዕክታቸውም ሆነ ውስጡ ያለው የዜማው፣ የሙዚቃው፣ የድምፁ ጥራት ሁሉ ከአሁኑ በፊት ካወጣኋቸው አልበሞች በተሻለ መልኩ የመጣሁበት ነው፡፡ የእኔ ሀሳብ ይህ ነው የእናንተን ሀሳብ ደግሞ እንድታጋሩኝ እጠብቃለሁ፡፡
ቁም ነገር፡- አመሠግናለሁ፡፡

“አድርገህልኛልና ለዘላለም አመሰግንሃለሁ (ሥርጉተ ሥላሴ )

$
0
0

(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 51 ቁጥር 9)

ከሥርጉተ ሥላሴ 24.10.2014 (ሲዊዘርላንድ ዙሪክ)

“እርግብ በር” 7ኛው አዲሱ መጸሐፌ ነው። የትውልዱ ነገር ከልጅነቴ ጀምሮ ይጨንቀኛል። በተለይ ወላጆቻቸው ተለያይተው ስለሚያድጉ ልጆች፤ ከጋብቻ ውጪ ስለሚወለዱ ልጆች በእጅጉ አስባለሁ።

trtአንድ ሰው ልጅ መውለድ ያለበት በተለይ ትዳር ላይ ከሆነ አብሮ ለማሰደግ ሲወስንና ሲቆርጥ ብቻ መሆን አለበት። ይህን ሳያጓድሉ መከራውንና ፈተናውን ታግሰው ልጆቻቸውን በጋራ የሚያሳድጉ የቤተሰብ አባ ወራና እማ ወራዎች የትውልዱ ልዩ ጌጦች ናቸው። ከዚህ በላይም ትውልዳዊ ድርሻ የለምና ለዚህ የታደሉትን ከልብ  በአክብሮት ላመስግን አውዳለሁ። የ አዲሱ ትውልድ ግርማ ሞገሶች ናቸውና።

ምክንያቱም ወላጆቻቸው የተለያዩባቸው ልጆች እስከ ህይወታቸው ፍጻሜ ድረስ መንፈሳቸው በተከደነ ቁስለት ይፈናቀላል። አባት የእናትን፤ እናትም የአባትን ድርሻ፣ ጉርሻ፣ ተፈጥሮዊ ክህሎት፣ ሊያተካኩ አይችሉም። ለልጆች ወላጆቻቸው አብረው ሲሆኑ የመኖር ንጹህ አዬራቸው ነው። ተስፋቸውም ለምለም ይሆናል። ሙሉ  እንደሆኑ ይሰማቸዋል።

ከዚህ ማዕቀፍ ወላጆች ልጆችን ሲያወጧቸው ግን የቀንበጦች ጠቅላላ ሰብዕናቸው ጥላሽት ይለብሳል። በፈለገው ዓይነት ቀመር ቢሆን ደስታቸውን ሙሉዑ ሊያደርገው አንዳችም ነገር አይኖርም። መኖርን እንደ ፈሩት፤ መኖርን እንደ ሸሹት መኖርን ሳይተረጎሙት ሳይኖሩበትም ባልተመለስ ጥያቄ መንፈሳቸው እንደናወዘ መዋዕለ ዕድሜያቸው በጠቆረ ግን በተመሰጠረ ዬመከራ ዘመን ይከወናል። በህይወታቸው እንደ ጦር የሚፈሩት ነገርም ጋብቻን ይሆናል። በጋብቻ ጉዳይ ደፋሮች አይሆኑም – በፍጹም። በልጅነት ጊዜያቸውም የፈለገ ብቃት፤ ችሎታ፤ ክህሎት፤ ጸጋና ሥጦታ ቢኖር ወይ ተቀብሮ ወይ አንክሶ ወይ ተጋድሞ ይቀራል። ይህን እኔ በስማበለው ሳይሆን በራሴ የደረሰ ስለሆነ ወገኖቼ ዕውነቱን ነው የምነግራችሁ። ስለሆነም “እርግብ በር” መጸሐፌን የፃፍኩበት አብይ ጉዳይ በዚህ ምክንያት ነው። የልጆች የነገ ንድፍ ተጨናግፎ – አሮ – ተቀጭቶ እንዳይቀር።

“እርግብ በር” ረቂቁ በ2006 ተሰርቶ ጹሑፉ ደግሞ በ2013ና 2014 እስኪበቃኝ ለሁለት ዓመት አሽቶኝ ተጠናቀቀ። ወላጆች ለልጆቻቸው የሚያወርሷቸው ትልቁ ነገር የቤተሰብ ምስረታ – ማገሩ ፍቅር መሆን ስለአለበት አትኩሮቱ ይኼው ነው። ይህን ደግሞ ወላጆች መሆን ሲችሉበት ነው። ልጆች ከሚሰሙት ይልቅ በሚያዩት ነገር ይማራሉ። ልጆች የዕውነተኛው ዓለም ጭብጦች ናቸውና።

“ፍቅር” ጥሩ አስተዳዳሪን ከገኘ ፈተናን የማሸነፍ አቅሙ ልክ የለውም። የሰውን ልጆችን የፈጠረው ፍቅር እንደ ተፈጥሮው ሊያዝና  በአግባበቡ ጸጋው ሳይጓደል ድርጊትን ማዬት አብዝቶ ይሻል። ፍቅር ሊተርኩት ሳይሆን ሊኖሩበት የተፈጠረ፤ በራሱ በፈጣሪው በመዳህኒትዓለም ደም የጸደቀ የመኖር ብቸኛው ሃይማኖት ነው። ስለሆነም የሰው ልጅ ሥጦታውን ያጌጥበት ዘንድ ሳይታክት ተግቶ በዕለት ተግባሩ ውስጥ ሊሆንበት ይገባል። “የእርግብ በር” መጸሐፍ መሰረታዊ ዓላማ ይሄው ነው።

ትልቁን የሰማይ የደስታ ጸጋ፤ የሰናይ ሃብት፤ ጥቃቅን ተውሳኮች እንዳያሳምሙት ወይንም እንዳያምሱት ጥንቃቄ እንዴት ሊደረግ ይገባል ነው የመጸሐፉ ተልዕኮ። ትዳር ሲጸና ልጆች ካለስጋት ነገን ያልማሉ። ስለሆነም ነገ ለትውልዱ ቀጥ ያለ ፍቅርን እንዲጠብቅ ወሳኙ ድርሻ ያለው ከተጋቢዎች ዘንድ ነው። ውርርሱም በአግባቡ ይሆናል።

የመጸሐፌ እርእስ ከላይም እንደጠቀስኩት “እርግብ በር” ነው። ደጉ ንጉሥ ዓፄ ፋሲል ካሰሩት ቤተ መንግስት ከ12ቱ በሮች የአንዱ በር መጠሪያ ነው። ስለሆነም መግቢያው ላይ ታሪክ ቀመስ ነገሮችን መጸሐፉ አነሳስቷል። ይህን በማድረጌ አዘውትራ እናቴ ክብዬ ታሪክ ቀመስ መጸሐፍቶች ላይ እንዳተኩር ስታሳስበኝ ስለነበር እንሆ ፍላጎቷን ስለፈጸምኩኝ ዝቀሽ ምርቃን አገኛለሁ ብዬም አስባለሁ። በሌላ በኩል በወላጆቼ መለያዬት ምክንያት ያጣኋቸው ለጋ ዕድሎቼ፤ ተጨናግፎ የቀረው የመማር በኽረ ህልሜ በነገ ትውልዱ ላይ ላይ እንዳይደገም ትንሽ ነገር በማድረጌም ደስተኛ ነኝ። ስለዚህ ሐሤቴ እጥፍ ድርብ ነው።

በተረፈ በህይወት ወስጥ እኩል በሆነ ግንዛቤ ህይወትን መተርጎም ስለማይቻል፤ እኔም ያለኝን እርሰዎም ያለወትን አክለን ነገን ለማንጋት በወልዮሽ የምንችላትን ከከወን፤ ትውልዱ ከሚነቀስበት ጉዳይም እንድናለን – ለጋራችን። መቼም ይህ ትውልድ መከረኛ ነው። ሁልጊዜም እንደ ተረገመ ነው …..

በተረፈ መጸሐፉ የዘመን ግጭት እንዳይፈጠር እንደ ተፈጥሯችን አሳምረን በፍቅር ተጠቃሚ እንሆን ዘንድ በስድና በግጥም መልክ የተቀነባበረ ጫሪ ጉዳዮችን ነካክቷል። አንዳንድ ሰዎች ዕድሎኞች ናቸው  ከሰጡት በላይ ያገኛሉ። የእኔ ቢጤዎች ደግሞ የሚመጥን ቀርቶ የነበረውን ያጣሉ። በፍቅር ህይወት ውስጥ መሆን የሚገባውን በትንሽ ምሳሌ ብገልጸው መልካም ይሆናል።

ምርቃተ – ምሳሌ።

ሁለት ተመሳሳይ ብርጭቆ በተመሳሳይ መጠን ውሃ ጨምሩ። ውሃውን ወደ አንዱ ብርጭቆ ጭልጥ አድርጋችሁ ሙሉት – ጠብ ሳይል። ፍቅር ፈዋሽ ጠበል ነው። የሥጋም የነፍስም። አንዱ ባዶ ሌላው ሙሉ ይሆናል። አንደኛው ስለሞላም፤ ሁለተኛው ባዶ ስለሆነ ሁለቱም ሥራ የለቸውም። ማለት ሥራ ፈት ሆነዋል ማለት ነው። ስለዚህ ከአንድ ቦታ ላይ ግንኙነቱ ተበጥሷል ማለት ነው። ባዶው – ባዶውን ነው በቃ የነጠፈ ጉድ። …. አልተመለሰለትም። የሞላለት ግን ጨልጧል። ነገር ግን ስስታምና ቆጥቋጣ ስለሆነ ተመጣጣኙን አልመለሰም። … ስለዚህ ይህ ንጡሕ ፍቅር አይደለም።

ለእኔ ሲገባኝ ፍቅር ማለት በተመሳሳይ ብርጭቆ እኩል መጠን ያለው ውሃ ሳይቋረጥ አንዱ ሌላው ሲቀዳለት ሌላው ተቀብሎ መልሶ ሲቀዳለት ሳይቋረጥ ሌትና ቀን በመስጠትና በመቀበል ሁለቱም ባተሌ ሲሆኑ ነው። አልፎ አልፎ የጥራት ሳይሆን የመጠን ከፍ ወይንም ዝቅ ሊል ይችላል። በውስጣዊና ውጪያዊ ተጽዕኖች ወይንም በመሬትና በአዬር ለውጥ፤ ወይንም በጨረቃ ሙሉነትና ግማሽነት ወይንም በዝንቁ ጎድጓዳ ዓለም ትርምስ። የሆነ ሆኖ ዝቅ ያለው መልሶ በዛው መጠን ይመጣለታል – ይቀበላል – ይሰጣል … ሳይተጓጎል አይቋረጥም። ፍቅር አይደክመውምና። ልክ በዚህ መልክ የሚኖር ፍቅር ነው የሰው ልጅ የሚያሰፈልገው ….  ይሄነን ሁለት ብርጭቆ አዘጋጅታችሁ ሁለቱንም እኩል መጠን ያለው ውሃ ጨምራችሁ ሞክሩት … አቃዱት እራሱ ሂደቱ ጥበብ አለበት ውህደቱ አይታይም ስሜት ብቻ ነው ጠረኑን ማወቅም መተርጎም የሚችለው።  …. የተሰጠው ነውና ….

“እርግብ በር” መጸሐፌ በ333 ገጽ እጅግ በርካታ ርእሰ ጉዳዮችን አነሳስቷል። መፋቻም በመጠኑ አለው። ከድካሙ ጋር ጥረቱና ፍሬው ሳዬው ግን እሱ ራሱ ፍቅር ነውና ፍቅርን ለግሶኛል። አታሚው ድርጅት እራሱ በጣም በጥንቃቄና በአክብሮት ነበር የሠራልኝ። እያንዳንዱን ጥቃቅን ነገር እያማከረኝ። ምክንያቱም ፋሲል ግንብ ቅርስነቱ – ውርስነቱ ሆነ ትውፊትነቱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለዓለምም በመሆኑ። ለሽፋኑ ሆነ ለህትምቱ ወረቀት ምርጫ ሰፊ ጊዜ ነበር የወሰድነው። ክብረቶቼ – ዋና መማር ትፈልጋላችሁን.? ከፈለጋችሁ ፍቅርን ይዛችሁ ወንዝ ውረዱ። ፍቅር ጥሩ የዋና መምህር ነውና ….

የኔዎቹ ጌጦቼ – “እርግብ በር” ከመጨረሻ ሽፋኑ  …. እርገቱ በእሱ ይሁን ….

“ፈጽሞ

ማንነት ያለው ተስፋ ስላለኝ የመንፈስን እስር የመፍታት አቅሙ ፈተና ላይ አይወድቅም። ይልቁንም ማንነት ያለው መፍትሄ የመፍጠር ዕሴቱ ሆነ አቅሙ ጉልበታማ ነው። ጉልበታሙ ማንነቴ ወደ ፊት የሚፈጥረው ግፊትና የሚጨበጥ ራዕዩ ደግሞ ትጥቅና ስንቄም ነው። በተሟላ ስንቅና ትጥቅ  የተሰናዳ ማንነት ደግሞ ጉልህና – አሸናፊ ነው። ከዚህ በኋላ ወይንም ከእንግዲህ ወዲህ በቃኝ ብሎ ለስንፍናና ለፍርኃት እጁን አይሰጥምና እና …. ፈጽሞ” …. ከረዳቴ ከፈጣሪ አምላኬ ጋርምበጣም በእርግጠኝነት የመንፈስ ሃብታት ፍሰት በተመሳሳይ ሙቀት ተጠናክሮ ይቀጥላል።

በመጨረሻ ትናንት 23.10.2014 ምን አስቦ ምን እንደከወነ በጸጋዬ ራዲዮ ፕሮግራም ማወቅን ትሻላችሁን? እንግዲያውስ www.lora.ch. Aktuelle Sendung Radio Tsegaye ያዳምጡ ዘንድ በአክብሮት አሳስባለሁ። መሸቢያ ሰንበት።

 

“አድርገህልኛልና ለዘላለም አመስግንሃለሁ።”

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

ለቅድስት ቤተ-ክርስቲያን መልካም ሥራ የሚሠሩ ማኅበራትን ለማፍረስ መሞከር ቅድስት ቤተ-ክርስቲያንን ለማፍረስ እንደመሞከር ይቆጠራል

$
0
0

መግለጫ ፎቶ
ጥቅምት 10 ቀን 2007 ዓ.ም.

ቁጥር : 10102014/0038

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ለቅድስት ቤተ-ክርስቲያን መልካም ሥራ የሚሠሩ ማኅበራትን ለማፍረስ መሞከር ቅድስት ቤተ-ክርስቲያንን ለማፍረስ እንደመሞከር  ይቆጠራል::

ለቅድስት ቤተ-ክርስቲያናችን ሕልውና ዘወትር በትጋት በማገልገል ላይ የሚገኘውን ማኅበረ-ቅዱሳንን ለማፍረስ እየተካሔደ ያለውን እንቅስቃሴ በመቃወም ከዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት የወጣ መግለጫ

“ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ:: እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሏቸዋል:: በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል:: ገንዘብንም በመመኘት በተፈጠረ ነገር ይረቡባችኋል ፍርዳቸውም ከጥንት ጀምሮ አይዘገይም ጥፋታቸውም አይዘገይም::” ፪ኛ ጴጥሮስ  ፪ ፥ ፩ – ፫

 

ጥንታዊት ታሪካዊትና ሐዋርያዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከተመሰረተችበት ጊዜ አንስቶ ፈተና ርቋት አያውቅም:: ለዘመናት በተለያዩ ኃይሎች የተለያዩ ፈተናዎችን ስታስተናግድ የቆየች ሲሆን ሁሉንም በጠባቂዋ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተቋቁማ ካለንበት ጊዜ ደርሳለች:: አሁንም በውስጥና በውጪ ጠላቶቿ ፈተና እየተፈራረቀባት ትገኛለች:: በተለይም ኢሕአዴግ በትረ ሥልጣኑን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ በመንግሥት የሚደርስባት ጫናና ተጽእኖ እጅግ እየበረታ የመጣ ሲሆን በአማኞቿ ላይ የሚፈጸመው ስቃይና እንግልት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው:: ጉዳዩን በጥልቀት ለሚመረምር ሰው የቤተ ክርስቲያኒቱ የውጪና የውስጥ ጠላቶች ከረጅም ጊዜ ጀምሮ የሚደክሙበትን ቤተ ክርስቲያኒቱን የማሽመድመድና ከተቻለም የማፍረስ ሕልም ተግባራዊ ለማድረግ የሚሰራ ይመስላል:: ሆኖም እዚህ ላይ መረዳት የሚያስፈልገው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተመሰረተችው በክርስቶስ ደም በመሆኑ ማንም ሊያፈርሳት አይችልም:: ይህንንም ለማወቅ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፮ ፥ ፲፰ ማንበብ ያስፈልጋል:: ከታሪክም እንደምንረዳው በግራኝ መሐመድና ዮዲት ጉዲትም ብዙ ደክመው ቤተ_ክርስቲያኒቱን ማጥፋት እንዳልቻሉ ወደኋላ ሄዶ ታሪክን መመርመር ይገባል:: ይህንንም በማየት በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የጥፋት በትሮቻቸውን ያነሱት ኃይሎች በሙሉ እጆቻቸውን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ማንሳት ጠቃሚ ነው እንመክራለን፥ ምክንያቱም ትግሉ ሲጥል እንጂ ሲታገል ከማይታየው ኃያል የምድርንና የሰማይ ፈጣሪ አምላክ ጋር ነውና::

በተደጋጋሚ እንደሚታየውና እንደሚሰማው የመንግስት ባለሥልጣናት ከእነርሱ በላይ የሁሉ ፈጣሪ ልዑል እግዚአብሔር መኖሩን ባለማመን ይሁን ባለማወቅ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንና በተከታዮቿ ላይ ብዙ በደልና ግፍ ሲፈጽሙ ቅንጣት ያህል ሃፍረትና ፍርሃት አይሰማቸውም:: በሥልጣን ወንበሩ ላይ ያስቀመጣቸው ሁሉን ማድረግ የሚችል ኤልሻዳይ እግዚአብሔር መሆኑን ባለመገንዘብም ዘወትር በእብሪትና በትዕቢት የተሞሉ በርካታ ነገሮችን ሲናገሩ ይሰማሉ::

ለምሳሌ ያህል “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአማራ ዋሻ ናት”፤ “የአማራንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን አከርካሪ ሰብረናል” ፤ “አደረጃጀታችንን ስንጨርስ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኞችም ማዕተብ እናስወልቃለን”፤ የሚሉትና የመሳሰሉት ይገኙባቸዋል:: ከሚፈጽሙት በደሎች መካከልም በልማት ሰበብ አብያተ ክርስቲያናትን ማፍረስ፤ ገዳማትን መዳፈር፤ ይዞታዎችን መንጠቅ ፤ በዘርና በጎሣ በማጋጨት ክርስቲያኖችን ማፈናቀል፣ ማስገደል፣ ማሰቃየት፣ ማንገላታት ወዘተ በጉልሕ የሚጠቀሱ ናቸው::

በ፪ኛ ጴጥሮስ  ፫ ፥ ፱ ላይ ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለተስፋ ቃሉ አይዘገይም፤ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሳል:: ተብሎ እንደተጻፈው የሰውን ጥፋት ሳይሆን መመለስ የሚፈልገው አምላክ ለእነዚህ በሕዝብና በሃይማኖታችን ላይ በደል ለሚፈጽሙ ባለሥልጣናት የንስሐ ጊዜ ቢሰጣቸውና ምልክትም ቢያሳያቸው ከክፉ ሥራቸው ከመመለስ ይልቅ ልባቸውን በማደንደንና ማን አለብን በማለት በጥፋት ላይ ጥፋት እየጨመሩ እንደ ፈርዖን ፈጣሪን በመገዳደር ላይ ይገኛሉ::

ሰሞኑንም በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ በፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ሰብሳቢነት በተካሔደው ጉባዔ ላይ በተቀናጀ ሁኔታ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ሲሰነዘር የነበረው ውንጀላ በገሃድ የመንግሥትን ተልዕኮ ለማስፈጸም ታቅዶ የተጠራ ፖለቲካዊ ስብሰባ መሆኑን በስብሰባው ላይ የተንጸባረቁት ሃሳቦችና አስተያየቶች የሚያሳብቁ ነበሩ:: ለማስረጃም ያህል በስብሰባው ላይ ወቀሳ ሲያቀርቡ የሚሰሙት ካህናት ተብዬ ካድሬዎች በአብዛኛው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ይልቅ የፖለቲከኞቹን የአቶ መለስ ዜናዊንና የኢንጅነር ኃይሉ ሻውልን ንግግር እየጠቀሱና በዓለማችን ላይ በአሸባሪነታቸው የሚታወቁ ጽንፈኛ ድርጅቶችን ስም እያነሱ መናገራቸው አንዱ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ጉባዔው የተጠራው መዋቅር ሳይጠበቅና ጽሕፈት ቤታቸው ሳያውቀው መሆኑን የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ መግለጻቸው ተጨማሪ ማስረጃ ነው::

ማኅበረ ቅዱሳን በእኛ ተቋምም ሆነ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ የሚታወቀው፦

፩/ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ ድረስ ዘልቆ በመግባት በችግር ምክንያት የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን ችግራቸውን አስወግዶ በማስከፈት፤

፪/ የቤተ ክርስቲያኒቱ የዕውቀት ምንጭ የሆኑትን የአብነት ት/ቤቶችን በመርዳት፤

፫/ የቤተ-ክርስቲያኒቱ ዕንቊ የሆኑ የአብነት መምህራንንና የአብነት ተማሪዎችን የሚያስፈልጋቸውን በማሟላት፤

፬/ በቤተ-ክርስቲያኒቱ ላይ የቅሰጣ ሥራ የሚሰሩ የመናፍቃን ተላላኪዎችንና የቤተ-ክርስቲያኒቱን ሀብት የሚመዘብሩ አማሳኞችን በማጋለጥ፤

፭/ ለሀገርና ለወገን በተለይም ለቤተ-ክርስቲያን ተቆርቋሪ የሆነ መንፈሳዊነትን የተላበሰ ትውልድ በማፍራት፤

፮/ በሀገራችን የሚገኙ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳማትን በመንከባከብና ምዕመናን የማያውቋቸውን እንዲያውቋቸው በማድረግ፤

፯/ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃንና በሕትመት ሥርጭቶች ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት ሲሆን እነዚህን ዋና ዋናዎቹን ለአብነት ጠቀስን እንጂ ማኅበሩ ቀን ከሌሊት የሚተጋባቸው ብዙ በጎ ሥራዎች እንዳሉት ለማንም የተሰወረ አይደለም::

ታዲያ ይህ ሁሉ በጎ ሥራው እየታወቀ ፍጹም ፖለቲካዊ በሆነና ማመዛዘን በጎደለው መልኩ በእውነት ላይ ያልተመረኮዘ ትችት በማቅረብ ማህበሩን ለማፍረስ መሞከሩ ብዙ ምዕመናንን ያሳዘነና ያስቆጣ ከመሆኑም በላይ ከፓትርያርኩ ጀምሮ እስከ ካህናቱ ድረስ ለያዙት ሰማያዊ ሥልጣንና ኃላፊነት የማይታመኑ አድርጓቸዋል:: ከዚህ በተጨማሪ ፓትርያሪኩም ሆኑ ካህናቱ ሊረዱት የሚገባው ዋነኛው ነገር፣ ማኅበረ ቅዱሳንን እናፈርሳለን ሲሉ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋውን አባላቱን እና የማኅበሩ ደጋፊ የሆኑትን ምዕመናን ከቅድስት ቤተ-ቤተክርስቲያናችን እንደመግፋት እና እንደማባረር እንደሚቆጠር ሊገነዘቡት ይገባል። መንግሥትም በተደጋጋሚ እንደሚያደርገው እራሱ ያዘጋጀውን ሕገ-መንግሥት በመጣስ በሃይማኖታችን ውስጥ ገብቶ ለማተራመስ እየዳከረ በመሆኑ ሕዝበ ክርስቲያኑን ወደ አልተፈለገ አመፅ እና እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲገባ እየገፋው እንደሆነ ሊረዱት ይገባል::

ስለዚህ የኢሕአዴግ መንግሥት ይህንን ተገንዝቦ ለቤተ-ክርስቲያኒቱ በጎ ሥራ የሚሰራውንና ከፖለቲካ ነጻ የሆነውን ማኅበር በቤተ-ክርስቲያኒቱ ውስጥ በሰገሰጋቸው ካድሬዎቹ ተጠቅሞ በእጅ አዙር ለማፍረስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲያቆም እያሳሰብን፤ በማንኛውም መንገድ ማኅበሩን ለማፍረስ የሚካሔደው ስውር ደባ ቤተ-ክርስቲያኒቱን ለማፍረስ የሚካሔድ ተግባር አድርገን ስለምንቆጥረው በጽኑ የምናወግዘውና የምንቃወመው መሆኑን እንገልጻለን::

በመጨረሻም የቤተ-ክርስቲያኒቱ የበላይ ጠባቂ ቅዱስ ሲኖዶስም ሆነ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ክፍሎች ሁሉ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በማኅበሩ ላይ የሚካሔደውን ሤራ እንዲያስቆሙ ስንጠይቅ ሕዝበ ክርስቲያንም በሙሉ በኃይማኖታችን ላይ የሚሸረበውን ስውር ደባ በአጽንዖት እንዲቃወሙና ሁላችንም አንድ ሆነን ቅድስት ቤተ-ክርስቲያናችንን እንድንጠብቅ ጥሪያችንን እናቀርባለን::

ዓለም አቀፍ የኢ/ኦ/ተ/ቤተ- ክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት

ግልባጭ

  • ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
  • ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
  • ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ
  • ለብፁዕ አቡነ ማቴዎስ
  • ለብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ
  • ለብፁዓን አባቶች በሙሉ
  • ለማኅበረ ቅዱሳን ጽ/ቤት

ሙሉውን መግለጫ ለማየት እዚህ ይጫኑ


ቴዲ አፍሮ በአውሮፓ 6 ከተሞች የሙዚቃ ኮንሰርቶቹን እንደሚያቀርብ ተገለጸ

$
0
0

teddy afro
(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ግዮን ሆቴል ከዛም በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የተሳካ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን ያቀረበው ቴዲ አፍሮ “70 ደረጃ” የተሰኘውን ነጠላ ዜማ ከለቀቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ 7 የተለያዩ ከተሞች የሙዚቃ ኮንሰርቶቹን እንደሚያቀርብ ከድምጻዊው ሥራ አስኪያጅ ያገኘነው መረጃ አመለከተ::

ቴዲ ዲሴምበር 6 በፊላንድ ሄልሲንኪ
ዲሴምበር 13 በፈረንሳይ ፓሪስ
ዲሴምበር 20 በኖርዌይ ኦስሎ
ዲሴምበር 27 በስዊድን ስቶክሆልም
ለፈረንጆች አዲስ ዓመት ዋዜማ ዲሴምበር 31 በጀርመን ፍራንክፈርት
ለፈረንጆች አዲስ ዓመት ጃንዋሪ 3 በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ሥራዎቹን ያቀርባል::

በአውሮፓ ቴዲ ኮንሰርቶቹን እንደሚያቀርብ ከተሠማ በኋላ ብዙዎች ቀኖቹን በጉጉት እየጠበቁት እንደሆነ ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች ያገኘናቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ::

70 ደረጃ ለተሰኘው ነጠላ ዜማ አዲስ የሙዚቃ ክሊፕ እየተሠራለት እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ብዙዎች ይህን በጉጉት እንደሚጠብቁት ይታወቃል::

የይለፍ ሚስጥር ቁልፍ ሰብሮ መረጃ የሰረቀው ግለሰብ ጥፋተኛ ተባለ

$
0
0

አቶ ዮናስ ካሳሁን የተባለ ግለሰብ የወ/ሮ አኪኮ ስዩምን ኢ-ሜይል አድራሻ የይለፍ ቃል (ፓስወርድ) ያለ ግለሰቧ ፈቃድ ባልታወቀ መንገድ በመጠቀም ግለሰቧ ከተለያዩ ሰዎችና ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን የመረጃ ልውውጥ ወደራሱ አድራሻ በመላክ፣ በማጥፋትና ለ3ኛ ወገን አሳልፎ በመስጠት ወንጀል ጥፋተኛ ተባለ፡፡ ግለሰቡ በአሁኑ ሰዓት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኝ ሲሆን የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ፍ/ቤቱ ለሰኞ ጠዋት ቀጠሮ ይዟል፡፡
newsየኦርኪድ ቢዝነስ ግሩፕ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ የሆነችው የግል ተበዳይ ወ/ሮ አኪኮ ስዩምን የኤሌክትሮኒክ አድራሻ ባልታወቀ መንገድ አልፎ የግል የመረጃ ልውውጦቿን ወደራሱ አድራሻ መላኩና ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠቱ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ መረጋገጡም ታውቋል፡፡
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ዘርፍ የፎረንሲክ ምርመራ ዳይሬክቶሬት ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ከኤሌክትሮኒክስ አድራሻ (ኢ.ሜል) መረጃ የመስረቅና የማጥፋት ወንጀል ዙሪያ ሙያዊ ድጋፍ እንዲያደርግለት በጠየቀው መሰረት፤ ተጠርጣሪው ወንጀሉን ለመፈፀም በህገ-ወጥ መንገድ የተበዳይዋን የወ/ሮ አኪኮ ስዩምን የኤሌክትሮኒክ አድራሻና የይለፍ ቃል (ፓስወርድ) ባልታወቀ መንገድ በመጠቀም ግለሰቧ ከተለያዩ ሰዎች እና ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን የመረጃ ልውውጥ ወደ ራሱ ከመላኩም በተጨማሪ ኢ/ር ግርማ ገላው ለተባለ ሶስተኛ ወገን መላኩን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ያረጋገጠ ሲሆን ግለሰቧ በተለያዩ ወቅቶች ለተለያዩ የንግድ ስራዎች ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር መልእክት የተላላከችበትን ቀናት በአገራችንና በአውሮፓውያን ዘመን ቀመር በግልፅ አስቀምጦ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ዘርፍ የፎረንሲክ ምርመራ ዳይሬክቶሬት ልኳል፡
ከኦርኪድ ቢዝነስ ግሩፕ ሦስት ጠበቆች አንዱ የሆኑትን አቶ ወገኔ ካሳሁንን አነጋግረን በሰጡን ምላሽ፤ ተከሳሽና ተበዳይ ቀደም ሲል የፍቅር ግንኙነት እንደነበራቸውና ግንኙነታቸው መቋረጡን፣ ከዚያ በኋላ የተበዳይዋን የኢሜል ሳጥን በመስበር በርካታ መረጃዎችን እንደሰረቀ በመታወቁ መረጃዎቹን እንዲመልስላት ራሷም በአማላጅም ጠይቃው እንደነበር ጠበቃው ተናግረዋል፡፡
“ተጠርጣሪው መረጃዎቹን እንድመልስልሽ 40 ሚሊዮን ብር ክፈይኝ፤ ያለበለዚያ መረጃውን አልመልስም” ማለቱን የጠቆሙት ጠበቃው፤ ከዚያም ወመረጃዎችን በመያዝ ክስ መመስረቱን ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡
“ምስክሮች እንድናቀርብ ፍ/ቤቱ ጠየቀን፤ በምስክርነትም ራሷ ተበዳይና የሰረቃቸውን የኢ-ሜይል መረጃዎች እንዲመልስላት አማላጅነት የላከቻቸው ሰዎች ቀርበው የሚያውቁትን አስረዱ” ያሉት ጠበቃው፣ ከዚህ ሁሉ ሂደት በኋላ ተጠርጣሪው በበቂ ሁኔታ መከላከል ባለመቻሉና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲም ሆነ ምስክሮች በበቂ ሁኔታ ጥፋተኝነቱን በማረጋገጣቸው ባለፈው ረቡዕ ፍ/ቤቱ ጥፋተኛ ብሎታል ብለዋል፡፡
ፍ/ቤቱ የቅጣት ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ተጠርጣሪው ማረሚያ ቤት እንዲቆይ ያዘዘ ሲሆን የቅጣት ውሳኔውን ለመስጠት ለሰኞ ጠዋት 3፡30 ሰዓት ቀጠሮ ይዟል፡፡
“በአገራችን የግለሰቦችን የመረጃ ሳጥን በህገ-ወጥ መንገድ በመስበር ጥፋተኛ የተባለ ሰው ስሰማ የመጀመሪያዬ ነው” ያሉት የኦርኪድ ቢዝነስ ግሩፕ ጠበቃ፤ እነዚህ ወንጀሎች በአገራችን አዲስ ናቸው፤ በ1949 የወጣው የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ላይ አልተካተቱም፤ በአዲሱ ላይ ግን ተካተው ይሄው እየሰሩ ነው ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
ኦርኪድ ቢዝነስ ግሩፕ በኮንስትራክሽን ዘርፍ፣ በውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ፣ በአስጐብኚ ድርጅትና ማሽነሪዎችን በማከራየት እንዲሁም በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማራ ኩባንያ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Source : Addis Admas

በአርባ ጉጉ እና አካባቢው በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል መካድ አይቻልም – ሞረሽ ወገኔ የባህል ማህበር በስዊድን

$
0
0

Moreshፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ከሸገር ራዴዮ ጣቢያ ጋር በ09/08/2014 ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ምንም እንኳ አማራውን አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ እርስ በራሱ የተምታታ ቢሆንም፣ አማራውን ህዝብ የለም ከማለት አልፈው በአርባ ጉጉ በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ክደዋል። የፕሮፌሰር መስፍን ክህደት “እስላም ኦሮሞዎች ክርስቲያን ኦሮሞዎችን ነበር የገደሉት” ለማለት ከሆነ፣ ሀቁና መረጃዎቹ ከፕሮፌሰር መስፍን ክህደት ጋር እንደማይጠጣሙ በተከታታይ መረጃዎችን እየመዘዝን የአርባ ጉጉን እልቂት ለማቅረብ እንሞክራለን። ወይም ጉልበታቸው ለፈረጠመ ወንጀለኞች መውጫ ቀዳዳ በመፈብረክ የተለመደው የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም “የወንድ በር እንስጥ” ፍልስፍናም ከሆነ በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ያልተፈጸመና ያልተደረገ አያደርገውም ልንላቸው እንገደዳለን። ከአባሎቻችንና ከደጋፊዎቻችን ጋር ለመወያየት የግብዣ ወረቀት ከላክን በሗላ፣ ከስብሰባው በፊት በአማራው ህዝብ ላይ በአርባ ጉጉ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ፕሮፌሰሩ መካዳቸው ብዙዎችን እንዳስቆጣቸው መልክት ሲደርሰን፣ እኛም አንድን ሰው ከሀዲ ከማለታችን በፊት መረጃዎችን አቅርቦ ፍርዱን ለአንባቢ ለመተው፣ በጊዜው የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት ለኢህአዴግ፣ ለውጭ መንግስታት ዲፕሎማቶችና ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስ ያወጣውን የአቋም መግለጫ ከሞላ ጎደል ይህን ይመስላል።

Pro-Mesfin
“የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት ‘መአህድ’ ኢህአዴግ በካድሬዎቹ አማካኝነት በአማራው ላይ የሚያካሂደውን የእልቂትና የሽብር ዘመቻ እያፋፋመው የአማራ ህዝብም ከፋሽስቶች ዘመን በባሰ ሁኔታ እያለቀ መሆኑን ባወጣው የአቋም መግለጫ አብራርቷል።

የመአህድ ፕሬዜዳንት ለሽግግር መንግስቱ ምክር ቤትና ለልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ባቀረቡት መግለጫ ላይ እንዳብራሩት በአማራው ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍና በደል “ሰብአዊ አእምሮ ሊሸከመው የማይችል ነው” በተለይ ከግንቦት 26 ቀን 1984 ዓ.ም ጀምሮ ጭፍጨፋው በከፋ መልኩ እንዲቀጥል ተደርጎ የጭፍጨፋው ሰለባ የሆነው አማራ ሬሳው በገደል ውስጥ እንዲጣልና በቤት ውስጥ እንዲቃጠል እየተደረገ ነው።” ይላል።

“ከግንቦት 26 ቀን 1984 ዓ.ም ጀምሮ በአማራው ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ የተካሄደው በአርሲ ክፍለ ሀገር በአንቦሳ ከተማና በአካባቢው ነው። ኢህአዴግ በዚህ ስፍራ የሚኖሩ ተወላጆችን ሰብስቦ “በነዚህ መንደሮች የሚኖሩ አማሮች ይገደሉ ብላችሁ ፈርሙ” በማለት ትእዛዝ ሰጠ።

በማግስቱ ግንቦት 27 ቀን 1984 ዓ.ም አቡሌ የተባለውን መንደር በኦህዴድ (የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራቲክ ድርጅት) የታጠቀ ወታደር ተከቦ ተኩስ ከተከፈተ በሗላ መንደሩ በላውንቸር መደብደብና ማቃጠል ሲጀመር ህዝቡ ህይወቱን ለማዳን ህዝቡ በየአቅጧጫው መሸሽ ጀመረ። ከሚሸሹት መካከል 30 ህጻናት ቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ እንደተጠጉ ከቤተክርስቲያኑና ከካህናቱ ጋር ተቃጥለዋል። አከታትሎም 150 የአማራ ነዋሪ ቤቶች እንዲቃጠሉ ተደርጓል።

የአውራጃው የኢህአዴግ ተወካይ አቶ ዲማ ጎርሜሳ ለወራሪው ሰራዊት ”አማራን መጨረስ ዛሬ ነው” የሚል መፈክር በማሰማት አበሳ የሚባለው የአማሮች መንደር እንዲከበብ አስደርገው ህዝብ ከቤቱ ሳይወጣ መንደሩ እንዲቃጠል ተደርገ። በመንደሩ ከነህይወታቸው በቤት ውስጥ እንዳሉ የሞቱት ቁጥር የማይታወቅ ሲሆን የቤቶቹ ጠቅላላ ብዛት 150 ነው። ከቃጠሎው የተረፉት 50 ሰዎች ተይዘው በጥይት ተረሽነዋል።

በሌላም አሼ በተባለ መንደር በአማራ ተወላጆች በአካባቢው የሚፈጸመውን ሰቆቃ እየተመለከቱ የመንግስት ሃይል ያድነናል ብለው ሲጠብቁ 25 ሰዎች የኢህአዴግ ሰራዊት ፈጅቷቸዋል።

በጉና ወረዳ አዲስ አለም በተባለ ቦታም 150 ቤቶችን ከነነዋሪዎቹ ከማቃጠላቸውም ሌላ ሁለት የአገር ሽማግሌዎች እጅ እግራቸውን አስረው አቃጥለዋቸዋል።

ዋቄንትራ ከተባለው መንደር 100 ቤቶችን ከነነዋሪዎቹ አቃጥለዋቸዋል።

መሶ የተባለውን መንደር በጦር እንዲከበቡና 100 ቤቶች እንዲቃጠሉ ተደርጓ ከቃጠሎው የዳኑት 80 ሰዎች እጃቸው ታስሮ በኦህዴድ (የኢህአዴግ አንዱ ክፍል) ተረሽነው ሬሳቸው ቆሬ ከሚባል ገደል ውስጥ እንዲጣል ተደርጓል። አንድ ሰው በተአምር ከዚህ መአት ተርፏል።

እንደሴ ባዩ የሚባለው መንደር ነዋሪ የሆኑ አማሮች በተመሳሳይ ሁኔታ በኦህዴድ ሰራዊት እነዲከበቡ ከተደረገ በሗላ ከመንደሩ ነዋሪዎች መካከል 80 የሚሆኑት እጅ እግራቸውን ታስረው ተወስደዋል። ወደ ገደል እንደተወረወሩም ይወራል።

ስድስት ቤተ-ክርሲቲያናት በዚህ አካባቢ ተቃጥለዋል። ይህ ሁሉ የተፈጸመው ግንቦት 27 ቀን 1984 ዓም በአንድ ቀን ነው ሲል የመአህድ መግለጫ አብራርቷል።

እንግዲህ ፕሮፌሰር መስፍን በሸገር ራዲዮ ጣቢያ የካዱት ይሄንን በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው።

በወለጋ እና አካባቢ ስለተጨፈጨፉት የአማራው ሕዝብ እልቂት ተጨመሪ መረጃ ከዚህ ላይ ያንብቡ – ምስራቅ ወለጋ 1993 ዓ.ም.

ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ ኾነው ተመደቡ

$
0
0

ሐራ ዘተዋሕዶ

 

ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም

ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም

ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬ፣ ጥቅምት ፲፭ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. አራተኛ ቀን ውሎው የድሬዳዋና ምዕራብ ሐረርጌ ሊቀ ጳጳስ የኾኑት ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም፣ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ኾነው እንዲሠሩ የምደባ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ምልአተ ጉባኤው ውሳኔውን ያሳለፈው፣ ከግንቦት ፳፻፭ ዓ.ም. ጀምሮ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ ኾነው በነበሩት ብፁዕ አቡነ ዳንኤልና በማኅበሩ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ዙሪያ ከመከረ በኋላ ነው፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ አለመግባባቱን ለመፍታት ፈቃደኛነታቸው ተረጋግጦ በተነሡት ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ቦታ ለመመደብ ያመለከቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ጥያቄ መርምሮ ለውሳኔ የሚያቀርብ አምስት ብፁዓን ሊቃ ጳጳሳት የሚገኙበት ኮሚቴ በትላንትናው ውሎው ሠይሞ ነበር፡፡

የኮሚቴው አባላት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ገሪማ፣ አቡነ ቀውስጦስ፣ አቡነ እስጢፋኖስ፣ አቡነ ጎርጎርዮስ እና አቡነ ዲዮስቆሮስ÷ ለምልአተ ጉባኤው ምክረ ሐሳባቸውን ካቀረቡ በኋላ ከፍተኛውን ድምፅ ያገኙት ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም እንዲመደቡ መወሰኑ ታውቋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም ከጥቅምት ፳፻፭ ዓ.ም. ጀምሮ የድሬዳዋና ምዕራብ ሐረርጌ አህጉረ ስብከትን ሲመሩ ቆይተዋል፡፡

በተለይም ሥራው ለስድስት ዓመታት የተጓተተው የሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ግንባታ ጥራትና ሒሳብ በውጭ ኦዲተር እንዲመረመር ቋሚ ሲኖዶስ ያሳለፈውን ውሳኔ ከደብሩ አስተዳደር ጋራ ኾነው በማስፈጸማቸው ከፓትርያርኩ ጋራ ቅራኔ ውስጥ ገብተው ቆይተዋል፡፡

እስከ ልዩ ጽ/ቤት በተዘረጋ የሙስና ሰንሰለት ከስምንት ሚልዮን ብር በላይ የምእመናን ገንዘብ መመዝበሩ የተረጋገጠበት የኦዲት ሪፖርት፣ በደብሩ ጽ/ቤት ለምእመኑ ይፋ መኾኑን ተከትሎ ‹‹የደብሩ ሰላም ይታወካል›› በሚል ሰበብ የደብሩ አለቃ ያለብፁዕነታቸው ዕውቅና በፓትርያርኩ ቀጥተኛ ትእዛዝ ተነሥተው ያለሥራ እየተንገላቱ ይገኛሉ፡፡

ፓትርያርኩ ለአማሳኞች የምዝበራ ሰንሰለት ሽፋን የሚሰጠው የጣልቃ ገብነት ርምጃቸው ስሕተት መኾኑን አምነው ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱን ይቅርታ ቢጠይቁም በኦዲት ሪፖርቱ ግኝቶች ዙሪያ የፀረ አማሳኞች ትብብሩን ያጠናከረው የከተማው አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን አገልጋይና ምእመን፣ ምዝበራን ያጋለጡት አለቃ ወደ ቦታቸው እንዲመለሱና ከዚኽ ውጭ የሚደረግ ምደባን ላለመቀበል በመወሰኑ ደብሩ ያለአስተዳዳሪ እንደሚገኝ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

በአህጉረ ስብከቱ በብፁዕነታቸው ቦታ የሚመደቡትን ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ በተመለከተ ምልአተ ጉባኤው ለጊዜው ባይወስንም አህጉረ ስብከቱ በተለይም የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የተወላጅነት መቧደንንና አስተዳደራዊ ችግሮችን ከለላ ባደረጉ የኑፋቄ ርዝራዦች የሚታመስበት ችግር ከፍተኛ ትኩረትና አፋጣኝ መፍትሔ እንደሚሻ ተመልክቷል፡፡

የእንግሊዙ ጠ/ሚ የአቶ አንዳርጋቸው የሞት ፍርድ እንዳይፈጸም ጠየቁ

$
0
0

“ክቡር ጠ/ሚ አባታችንን ከሞት ያድኑልን”  የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ልጆች

Andargachew Tsige.jpg2የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን በእስር ላይ በሚገኙት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ከአምስት አመታት በፊት የተጣለው የሞት ፍርድ ተፈጻሚ እንዳይሆንና በቆንስላ ሰራተኞች መጎብኘት እንዲችሉ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በግላቸው በላኩት ደብዳቤ መጠየቃቸውን ዘ ኢንዲፔንደንት ከትናንት በስቲያ ዘገበ የአቶ አንዳርጋቸው ልጆች አባታቸውን ከሞት እንዲታደጉላቸውና ከእስር ተፈትተው ዳግም የሚገናኙበትን መንገድ በማመቻቸት በኩል ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው የሚጠይቅ ልብ የሚነካ ደብዳቤ እንደላኩላቸው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን፣ የልጆቹን ጥያቄ መነሻ በማድረግ ለጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደብዳቤ መላካቸውን አስታውቀዋል፡፡

የእንግሊዝ የስራ ሃላፊዎች በእስር ላይ የሚገኙትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በቋሚነት መጎብኘት እንዲችሉ ግፊት ቢያደርጉም፣ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በጎ ምላሽ እንዳልሰጡ ለልጆቹና ለእናታቸው በሰጡት ምላሽ የገለጹት ዴቪድ ካሜሩን፣ ከዚህ በፊት የተደረገው ጥረት ውጤታማ አለመሆኑን በማጤን በግላቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ደብዳቤ መላካቸውን አመልክተዋል፡፡የእንግሊዝ መንግስት የቆንስላ አባላት አንዳርጋቸው ጽጌን በቋሚነት መጠየቅና ማማከር የሚችሉበት ሁኔታ እንዲመቻችና መንግስታቸው ሲቃወመው የቆየው የሞት ፍርድ ተፈጻሚ እንደማይሆን ማረጋገጫ እንዲሰጥ በላኩት ደብዳቤ መጠየቃቸውን የገለጹት ዴቪድ ካሜሩን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለ ማርያም ለደብዳቤያቸው በጎ ምላሽ እንደሚሰጧቸው ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡
የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ልጅ የሆነችው የ7 አመቷ ምናበ እና መንታ ወንድሟ ይላቅ፣ ለጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ካሜሩን በላኩት ደብዳቤ፣ “አባታችን ልጆቹን የሚወድና የሚንከባከብ መልካም አባት ነው፡፡ አባታችንን ከእስር ለማስፈታት ምንድን ነው የሚያደርጉልን?” በማለት መጠየቃቸውን ያስታወሰው ዘገባው፤ የመጀመሪያ ል©cW የ15 አመቷ ህላዊት በበኩሏ፣ “አባታችን በጣም ናፍቆናል፡፡ እባክዎት በቅርብ ጊዜ መልሰው ወደ ቤታችን ያምጡልን” በማለት ስሜቷን እንደገለፀች ዘገባው ጠቁሟል፡፡

Source : Addis Admas

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

$
0
0

የመንግሥት ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ብሏል
የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለምን ወጣ መባሉ ተገቢ አይደለም – ምርጫ ቦርድ

37c0d11e857ac49890fe06ddbb0e9d2f_Mምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ተፅዕኖ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥና የምርጫ አፈፃፀም ችግሮች ሳይወገዱ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለማወጅ መዘጋጀቱ ተገቢ አይደለም ሲል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩት ኢማዴ-ደህአፓ ተቃወመ፡፡ መንግስት፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ ያለው ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ሲልም ፓርቲው ኮንኗል፡፡
የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ ሰሞኑን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገባው ግልፅ ደብዳቤ፤ ያለፉት አገር አቀፍና የአካባቢ ምርጫዎች ከመካሄዳቸው በፊት በምርጫ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር የሚወያይበት መድረክ እንዲዘጋጅ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም እስካሁን ከቦርዱ የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ የለም ብሏል፡፡
ሃገሪቱ “በአንድ አውራ ፓርቲ” ብቸኛ ቁጥጥር ስር መውደቋ አደገኛና አሳሳቢ ነው ያለው ፓርቲው፤ የመድብለ ፓርቲ ስርአት የመገንባት ተስፋችን ጨርሶ እንዳይከስም ቦርዱ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለመፍጠር ገዥው ፓርቲና ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወያዩበት መድረክ እንዲያመቻች በህግ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ የገባውን ቃል በማጠፍ መድረኩን ሳያመቻች የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀቱ ፋይዳ የለውም ብሏል – ፓርቲው፡፡
ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በተሻሻለው የምርጫ ህግ፣ ለቦርዱ የተሰጠውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ የማስተባበር ስልጣን ለመቀማት ታማኝ ፓርቲዎችን በተቃዋሚ ስም አሰባስቦ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ” በመፍጠር የምርጫ ውድድር አሯሯጭ አሰልፏል ሲል ፓርቲው ተችቷል፡፡ገዥው ፓርቲ ያልተገደበ መንግስታዊ ስልጣኑን በመጠቀም የተለያዩ ጫናዎችን እያሳረፈ፣ ተቃዋሚ በሌለበት በአፈናና በጉልበት ሃገሪቱን በአምባገነንነት እየገዛ ነው ያለው ፓርቲው፤ በአሁኑ ወቅት መንግስት ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ ያለው ስልጠና የምርጫ ህግን የጣሰ የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ብሏል፡፡ ለስልጠናው በሚሊዮን የሚቆጠር ሃብት ማባከኑም አግባብ አይደለም ሲል ፓርቲው ተቃውሟል፡፡ ምርጫ ቦርድ ከስነምግባር ደንቡ ውጪ የሆነውን የኢህአዴግን አካሄድ ማስቆም ሲገባው እርምጃ አለመውሰዱ ቦርዱ በፓርቲው ተፅዕኖ ስር መውደቁን ያሳያል ብሏል – ፓርቲው፡፡
የኢማዴ-ደህአፓ ሊቀመንበር ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ለአዲስ አድማስ በሰጡት ማብራሪያ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጠናው በመንግስት ፖሊሲዎች ዙሪያ ግንዛቤ የማስጨበጥና መንግስታዊ ኃላፊነትን የመወጣት ስራ ነው ቢሉም ለስልጠና በተሰራጩ ሰነዶች ላይ “ፓርቲያችን ኢህአዴግ” የሚሉ አገላለፆች መስፈራቸውን ጠቁመው ይሄም በቀጥታ የመንግስት መዋቅርንና ሃብትን በመጠቀም የፓርቲን አጀንዳ የማስረፅ (ኢንዶክትሪኔሽን) ስራ ነው ብለዋል፡፡
በስልጠናው ወቅት የተበተነው ሰነድ ስለኢህአዴግ መስመር የሚተነትን ነው ያሉት ሊቀመንበሩ፤ ሰነዱ የፓርቲ እንደሆነ እየታወቀ ስልጠናው የመንግስት ነው ማለት ተቀባይነት እንደሌለው ተናግረዋል፡፡
“መንግስት ፖሊሲውን ለማስገንዘብና የፈፀማቸውን ተግባራት ለማሳወቅ ስልጠና ማዘጋጀት አይጠበቅበትም፤ በሴሚናርና በዎርክሾፕ መልክ መድረኮችን ማዘጋጀት ይችላል” ብለዋል ፕ/ር በየነ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ፤ “በምርጫ አሸንፎ ስልጣን የያዘ ፓርቲ የመንግስትን ፖሊሲ የማስረፅ ኃላፊነት እንዳለበት ገልፀው ለምን ይሄን አደረጋችሁ ብሎ መጠየቅ ህዝቡ ለምን መረጣችሁ እንደማለት ነው ብለዋል፡፡ የኢማዴ-ደህአፓ ደብዳቤ ለምርጫ ቦርድ ፅ/ቤት መድረሱን ያረጋገጡት የፅ/ቤቱ ም/ዋና ኃላፊ አቶ ወንድሙ ጎላ፤ ሁሉም ፓርቲዎች በምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ያላቸውን አስተያየት በፅሁፍ እንዲያቀርቡ በተጠየቀው መሰረት የቀረበ ደብዳቤ ነው፤ ቦርዱ ተሰብስቦ የሚያየው ይሆናል ብለዋል፡፡
ፓርቲው ለፅ/ቤታቸው ባስገባው ደብዳቤ፤ ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ ጋር የሚወያዩበት መድረክ እንዲዘጋጅ ተጠይቆ ምላሽ ሳይሰጥ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለማውጣት መጣደፍ አግባብ አይደለም ማለቱን የጠቀስንላቸው አቶ ወንድሙ፤ ለምርጫ ቦርድ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ጠቁመው፤ የጊዜ ሰሌዳ ለምን ይወጣል መባሉ ተገቢ አግባብ አይደለም ሲሉ ተችተዋል፡፡ ምክትል ዋና ኃላፊው፤ የውይይት መድረክ የተባለውን በተመለከተ ምርጫ ቦርድ በቀጣይ የሚያዘጋጀው ይሆናል ብለዋል፡፡ በጊዜያዊነት በወጣው የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ የፓርቲዎች አስተያየት ከተሰበሰበ በኋላ በቦርዱ ውይይት ተደርጎበት ሲፀድቅ፣ ለህዝቡ ይፋ እንደሚደረግም አቶ ወንድሙ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡

የኖርዌይ ኦስሎ ወጣቶች ስለአገራቸው ውይይት አካሄዱ

$
0
0

የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የወጣቶች ክፍል ቅዳሜ ጥቅምት 10/2007 ዓም(ኦክቶበር 25/2014) “ለአገር እድገትና ለድሞክራሲ ግንባታ የወጣቶች አስትዋጾ” በሚል ሰፊ ውይይት ከ15:00 እስከ 18:00 ስዓት ተካሄደ።

የመግቢያ ንግግሩ በድርጅቱ ህዝብ ግንኙነት በአቶ አቢ  አማረ የውይይቱን ዓላማና አስፈላጊነት ለተሳታፊው በመግለጽ ወጣቶች ውይይቱ ውጤት ሊያመጣ በሚችል መልኩ እንዲካሄድ አጽንኦት ሰጠው ውይይቱ ቀጥሏል።

norwa

በመቀጠልም የአንድ አገር ቀጣይነት ያለው እድገት የሚለካው በአላት ሃብትና ንብረት ብቻ ሳይሆን ያንን ተረክቦ በአደራ ለትውልድ ማስተላለፍ የሚችል ትውልዳዊ ትስስር መኖርና ይህንንም እንደ ድልድይ ሆኖ  ከአንዱ ትውልድ ወደቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፈው ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል እንደሆነ፤ በማንኛውም አገር፣ ጊዜና ዘመን እያንዳንዱ ተተኪ ትውልድ የአገሩ ወራሽ፣ ተተኪና ተረካቢ፣ ጠባቂና ለሚቀጥለውም ትውልድ የማውረስ፣ የማስተላልፍና የማስረከብ ኃላፊነትና ግደታ እንዳለበት፤ ወጣት ለአንድ አገር በሦስቱም ዘርፍ ማለትም በማህበራዊ፣  በምጣኔ ሃብታዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማድረግ እንደሚችል ተረድቶ ወጣቱ ትውልድ በዓላማ፣ በቁርጠኝነት፣ በዕቅድና በመደራጀት  ለአገር እድገት፣ ነጻነት፣ፍትህና ዲሞክራሲ መታገልና ለውጥ ማምጣት እንዳለበት በክፍሉ ተወካይ በወጣት ይበልጣል ጋሹ ለውይይት እንደ መነሻ ባቀረበው ሃሳብ ላይ ገልጿል። እንዲሁም የወያኔን አስከፊ፣ ዘረኛና አምባገነናዊ ሥርዓት ለማስገወገድ  ወጣቱ ትውልድ የበኩሉን ሃላፊነት ወስዶ ይህን  ለአገርና ለህዝብ መቆም እንዳለበት በመግለጽ የውይይት ሃሳቦችን አስቀምጦ ስዓቱን ለውይይት ክፍት አድርጓል።

በውይይቱም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ወጣቱ ለክፉም ለመልካምም የራሱ የሆነ ትልቅ አገራዊ ታሪክ እንዳለው በመግለፅ  ወጣቱ እንዴት መታገልና ለውጥ ማምጣት እንደሚችል ገንቢ አስትያየቶች፣ ምክሮችና አቅጣጫ ተሰጠዋል። ከተነሱትት ሃሳቦች መካከልም በበቂ ሁኔታ መደራጀት፣ በእውቀት እራስን ማብቃት፣ አገራዊ ስሜት መላበስ፣ታሪክን ጠንቅቆ ማዎቅ፣ አንድነት መፍጠር፣ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ስልታዊ እቅድ መከተል፣ አቀራረባችንን እና ትኩረታችን መለየት፣ ቀጣይነት ያላቸው የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀት እና ክፍሉን ማደራጀት ከተነሱት አበይት ሃሳቦች መካከል ነበሩ። በተጨማሪም ክፍሉ ከሌሎች የወጣት ህብረት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ልምድና ተሞክሮ  በመለዋወጥ ወጣቱን ይበልጥ ማንቃትና ፖለቲካዊ አድማሱን ማስፋትና የወያኔን ጨቋን መንግሥት ሊታገል የሚችልበትን አቅጣጫ ማሳየትና መንደፍ ተገቢ መሆኑን አጽንኦት ተሰጦበታል።


የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት ተሰብስቦ ውሳኔዎችን አሳለፈ

$
0
0

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ብሔራዊ ምክር ቤት ዛሬ ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ በመሰብሰብ የስራ አስፈጻሚውን የ10 ወር ዕቅድ መርምሮ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁንና በተጓደሉ የኤዲቶሪያል ቦርድ አባላት ምትክ ምርጫ ማካሄዱን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ለፍኖተ ነፃነት ገለጹ፡፡
እንደ አፈ ጉባኤው ገለጻ የዲሲፕሊን ጥሰት የፈጸሙ የፓርቲው የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት ጉዳይ ላይ ምክር ቤቱ ሰፊ ውይይት ካካሄደ በኋላ በሥራ አስፈጻሚ በኩል ወደ ዲሲፕሊን ኮሚቴ እንዲመራ በመወሰን ስብሰባው መጠናቀቁን አፈ ጉባኤው ለፍኖተ ነፃነት ዝግጅት ክፍል ገፀዋል፡፡

1546209_718191084932495_4741612790237882908_n

10702104_718191194932484_28106377305738686_n

 

1505243_718191134932490_6358908736255763742_n

ዘውደ ወይ ጎፈረ ብሎ መመዳደብም መፍትሄ ነው።

$
0
0

ዳዊት ዳባ

Sunday, October 19, 2014

dawitdaba@yahoo.com

 “ይምርጡን ሳናዳላ፤ ሳንገል፤ ሳናስር፤ሳንዋሽና ሳንሰርቅ ፍፁም በሆነ አገራዊ ፍቅር አክብረንህ እናስተዳድራለን ”። የምርጫ መሪ ቃል ብትሆን ያልኳት።

2007 electionጎሽ እንዲህ ነው መቅደም። አገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ዘጠኝ ድርጅቶች በጋራ ለመታገል መስማማታቻውን ስሰማ ሀሴት ነው ያደረኩት።  መጀመርያ ዜናውን ስሰማ ጥሩ ነው አልኩ። አንድነትና መድረክ ስይካተቱ የሚፈለገውን ውጤት አያመጣም በሚል አላካበድኩትም ነበር። ደስታዬን ሙሉ ያደረገው  ከሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በኢሳት ላይ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እነዚህ ድርጅቶች  ሀይላቸውን ተጨማሪ ጉለበት የማድረግቸው እድሉ የሰፋ መሆኑን መስማቴ ነው። ፅሁፌን ብዴና እጄ ላይ ቢያስረጀውም ለማንኛውም ብዬ  ለቅቄዋለው።

ቀጣዩ  ምርጫ ሊደረግ ሰድስት ወር ነው የቀረው።  ምርጫው የሚካሄደው በከፋ አፈናና በበዛ ፖለቲካል ውጥንቅጥ ውስጥ ነው።  መንግስታዊ ሽብር ጣሪያ ነክቷል።   ከየድርጅቶቹ ትግሉ ላይ ወደፊት የመጡት ወጣቶች ተለቅመው ታስረዋል። በአገሪቷ ውስጥ ያሉ ነፃ ጋዜጠኞች በሙሉ ማለት በሚችል እንዲሁ  ታስረዋል ወይ ተሳደዋል። ይህ ቀጣይም ነው። በተናጠል ቀደም ብለው  አማሮች፤ ሙስሊሞች ኦሮሞዎች እያሉ ሆን ብለው ህዝብን ተንኩሰው  ሀሞቱ ያላቸውን ዜጎች ለቅመው ገድለዋቸዋል። ብዙዎችን በየእስር ቤቱ አጉረዋል። የቀሩትን  መዝገበው በአይነ ቁራኛ እየተከታተሏቸው ተራ እየጠበቁ እንዳሉ መገመት ይቻላል።   ጋንቤላ፤ አንድ አድርጋቸው ፅጌ። ማህበረ ቅዱሳን ቴዲ አፍሮ። አፋር፤ተመስገን ደስአለኝ። ኦጋዴን ይቀጥላል  እያሉ ገና ለገና በፍራቻ ለምርጫው ሲባል ወንጀላቸው ቀጥሏል።  ልዩነቱ  በከረባት መሆኑ ነው እንጂ ልክ እንደቦኩ ሀራሙ ሰውዬ በተራ እየወጡ የሚያሰሙትን ቀረርቶ መስማቱ ካሁኑ አላኖረን ብሏል። በተጓዳኝ ደግሞ ሁሉን  ተቆጣጥረው ስላሉ ያለ ጠያቂ የሚያዝበትን ገንዘብ፤ ሜዲያና መንግስታዊ መዋቅር  እየተጠቀሙ የቅጥፈት  የምርጫ ዝግጅትና ቅስቀሳ  ብቻቸውን  አበርትተው ተያይዘዋል። ይህ እንግዲህ የወያኔ የቀጣዩ የምርጫ  እቅድ  ነው።  ለእቅዱ ተፈፃሚነት ሲባል ጭካኒያዊ በሆነ ሁኔታ እየጎዷቸው ያሉትን ወገኖቻችንን ማሰባችን ስለማይቀር የዘንድሮውም እቅዳቸው እንደሁሌው አህያነት እንዳለበት ማንችንም ብንሆን የምንስማማ ይመስለኛል።  ዞሮ ዞሮ እቅድ ያሉት ሁሉም መራገጥ ነው።  ይህ ሁሉ እርግጫና ወንጀል በመጨረሻ ኮሮጆ መገልበጣቸው ላይቀር  ለምን? ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ከጣርን ብቻ ነው የፍራቻቸውን ምክንያታዊነት፤ እንዴት ምርጫውን ሊያልፉት እንዳሰቡ እቅዱ በመጠኑም ቢሆን የሚገባን።  እኛ ደግሞ ምን ማድረግ እንዳለብን እንድናስብ የሚያደርገን።

አገዛዙ ይህን ሁሉ ሽብር ፈፅሞና ከተንደፋደፈ በሗላም አካሄዱ የማያዋጣው ከመሰለው  ምርጫ የሚባል ነገር እስከጭራሹ ቀርቷል ማለት ድረስ ሊሄድ ይችላል። እስካላለ ግን ይህን በመሰለ አስቸጋሪና አስፈሪ ሁኔታ ውስጥም ቢሆን ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ምርጫውን መጠቀም  በእርግጥም  አለባቸው። በግሌ  መጠቀማቸው ትክክል ነው ብዬ አጥብቄ አምናለው። ስለማምን ብቻ ሳይሆን ምርጫው ውስጥ መግባታቸው ስለማይቀርም  ደግሞ ነው። ስለዚህም መነሻ የማደርገው በምርጫው ላይ የለውጥ ፈላጊው ድርሻ ከሚለው ነው።

ትኩረት መሆንና በቶሎ ሊሰራበት የሚገባው በየምርጫ ጣቢያው ከሁለትና ሶስት ተቃዋሚ መሀል እንዴት ነው አንድኛውን የተቃዋሚ እጩ  ለይቶ  አሸናፊ የሚያደርገውን ድምፅ ሳይበታተን እንዲያገኝ ማድረግ የሚቻለን?። ከጊዜና ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ተለያይተው ባሉበት ሁኔታ እንዴት ነው ሁለንተናዊ አቅማቸውን ተረባርበን ማጠንከር የሚቻለን?። ምርጫው ሙሉ በሙሉ ሊሰኝ በሚችል የሚገባውን ትኩረት በዜጎች ገና አላገኘም።  ይህን በቶሎ መቀየር የሚቻለው እንዴት ነው?። የመሳሰሉት ጥያቄዎች ናቸው።

ምርጫው በዜጎች ዘንድ ትኩረት ያልተሰጠው አገዛዙ እቅድ አደርጎ ተግባራዊ እያደረጋቸው ካሉና  የእብደት ሊሰኙ ከሚችሉ   ተግባራትና ከቀደሙ ምርጫዎች የመጨረሻ ውጤት አኳያ ብቻ ስለታየ ይመስለኛል። ሌላው ምርጫ የሚባለው ጉዳይ ላይ ያለ  ግንዛቤ ነው። ላብዛኞች ምርጫ ትግል አይደለም።  እውነታው ግን አይደለም ከወያኔዎች ጋር ህግና ስርአት በአለበት ዲሞክራሲያዊ በሆኑ አገሮች የሚደረገውም ምርጫ ይዘቱ ይለያያል እንጂ  ትግል ነው።  አንባገነኖች ኖረው ደፍረው ምርጫ አለ ካሉ በፈለገው አይነት እርግጫና ህገ አልባ በሆነ እቅዳቸው ውስጥ፤ በከፋ አፈናና መሰዋትነት  ውስጥ ሆኖም በደስታ ልንለው የሚገባ የተከፈተ የትግል አውድማ  ነው። ትግልም ብቻም አይደለም። መታገያ ሜዳ ብቻም አይደለም። ለሌዋም አይነት የትግል አይነት መሰረትና ማጎልበቻ ነው።

ለማንኛውም ለሁላችንም ለአገርም ደህንነትና ጥቅም ሲባል ቀጣዩ ምርጫ በጭራሽ እነሱ እንዳሰቡትና እንዳቀዱበት አልጋ በአልጋ መሆን የለበትም።  ከምርጫ97ቱ ያነሰ ነብስ ግቢ ነብስ ውጪ ውስጥ የማይከታቸው መሆንም የለበትም። ከጥቂቶች በቀር የበዛው ዜጋ ይህ ዘረኛና አድሏዊ አገዛዝ እንዲያበቃ ይፈልጋል።  ይህ እስከሆነ ደደብ ወይ ተስፈኛ ወይም ሌላም በሉኝ አሁን በአላው ጠቅላላ የአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ምርጫውን አስቸጋሪ ጠንካራ ህዝባዊ ቡጢ የምናቀምስብት ማድረግ ይቻላል። ከዘም አልፎ ኮሮጆ መገልበጡንም አስቸጋሪ ማድረግ እርግጠኛ ሆኜ ይቻላል እላለው።

እነሱ መንግስታቸውን በምርጫ አይደለም። ብዙ ሆነን አይደለም። አንድ ስው ዘፍኖ ወይ ፅፎ አፈር ድሜ እንደሚያስገባው ነው የሚያምኑት። በጣምም ትክክል ናቸው። እኛ ደግሞ ተመስገን “ተግዳድሮት” ነው የሚለው ብቻ አሉብን የምንላቸውን ችግሮች መፍትሄ አልባና ተራራ አሳክለን ነው ሁሌም የምናያው። በዛ ላይ የነሱን እጅግ ብዙ የሆኑ ስስ ብልት አሳንሰን ነው የምናየው።  ሲጀመር በዚህ አለም ላይ ምንም መፍትሄ የሌለው ችግር የለም። አባባሉን የበለጠ እውነት የደረገልኝ ከዚህ አድሏዊ ዘረኛ ስርአት ጋር እየተደረገ ባለው ትግል በገጠሙን  ችግሮች ካገዛዙ ይምነጩ ወይ ለለውጥ በቆመው አካል ስህተት ይፈጠሩ  ሁሌም መፍትሄ እንደነበራቸው በእርግጥ አይቻለው። ይህ ወደፊትም ትግሉ ላይ አሉ የምንላቸው ችግሮች ሁሉ መፍትሄ የሌላቸው እንዳልሆኑ አሳምኖኛል። ሁሌ ግን መፍትሄዎቹ ሁኔታዎች ግድ ያሉት እንጂ ተመራጭ ላይሆኑ ይችላሉ።

የዚህ ፅሁፍ አላማ ከለው ጊዜና ከተደጋጋሚ የብዙ ዜጎች አድማጭ ያጣ ውትወታ በሗላ በአስራ አንደኛው ሰአት ላይም በምርጫ ለሚሳተፉ እውነተኛ ተቃዋሚዎች በስም መ. ኢ. አ ድ፤ አንድነት፤ ሰማያዊና መድረክ እያለ ሰላሳ ሶስት ሆነው መነጋገር የጀመሩ ድርጅቶችን መጎትጎት ነው። በየምርጫ ጣቢያው አንድ ብቻ እውነተኛ ተቃዋሚ እጩ መራጮች  ማግኘት አለብን። ይህን እንዴትም አድርጋችሁ ስሩት ግድ የሚል ጉዳይ መሆኑን በድጋሚ ለማሳሰብ ነው። ከውያኔ ጋር የሚሞዳሞዱት ተቃዋሚዎች የፈለገውን አይነት ፕሮግራም ነድፈው ቢመጡ ወይ ዋው የተሰኘለት የቅስቀሳ ስራ ቢሰሩም በየምርጫው ጣቢያው መራጩ ላይ የሚኖራቸው ተመራጭነት ከቤተሰብና ከትውውቅ አልፎ  እንቅፋት ሊሆን የሚችል ወይ ውጤቱን የማያዛባ ስላልሆነ ነው።

እነዚህ እውነተኛ ተቃዋሚዎች አሁን ላይ ምን ቢያደርጉ በየምርጫ ጣቢያው አንድ አንድ እጩ ተቀናቃኝ ብቻ ያቅርቡ የሚለው ችግር መፍትሄ ካላበጁለት ሁላችንንም ተሸናፊ ስለሚያደርግ አሳሳቢ ነው።  ይህን ጉዳይ የት ድረስ ወስጄ እንደማየው ለማሳየት ተቃዋሚዎቹ በየምርጫ ጣቢያው አንዳንድ ተቃዋሚ እጩ ብቻ ማቅረቡን ሳይስማሙ ቀርተው ወድ ምርጫ የሚገቡ ከሆነ ዜጎችም ብንሆን ቀድምን በሆነ መንገድ መላ አበጅተንለት ልንመርጥ መሄድ ይኖርብናል።  መላ ደግሞ ይኖራል። አንዱ መንገድ ውጫዊ በሆነ አካል  ለየድርጅቶቹ  ሚዛናዊ በሆነ መንገድ የምርጫ ጣቢያዎቹን ማከፋፈል ነው። ማከፋፈሉ ላይ የሚቀርቡ እጩዎችን ተመራጭነትና የመራጩን ህዘብ ፖለቲካዊ  ዝንባሌ ግምት ውስጥ ባስገባ ማደላደል ይቻልል።   ይህን ማድረግ እኔም እናኳ ይዳዳኛል።

ተቃዋሚዎች እዚህ ሳይደርስ መላ ልትሉበት ትችላላችሁ። አግባብ የሚኖረውና በእርግጥ የሚቀለውም በናንተ ሲሰራ ነው። የተሰባሰባችሁበትን መድረክ መጠቀም ትችላላችሁ። ሰማያዊ ፓርቲዎች ተመለሱ። ይኑሩበት።  ሁላችሁም የእጩዎቻቸሁን ስም ዝርዝርና የምትወዳደሩበትን ምርጫ ጣቢያ ዝርዝር አቅርቡ። በዚሁ ቁም ነገር ላይ ብቻ በቀናነት መነጋገር ጀምሩ። መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ መንገዶችን አጥኑ። በየድርጅቱ የቀረቡትን እጩዎች አጥኑ። ምን አልባት መደራደር፤መደላደል፤ መቀያያር  ይፈለግ ይሆናል እንጂ ይቻላል። ብቻ ሳንቲብ ወደሰማይ አጡዞ ዘውድ ወይ ጎፈረ ማለት ድረስ መፍትሄ ተደርጎ መሞከር ግን አለበት።

ሁሉን ወገን የሚያስማማ አገራዊ መፍትሄ መቅረፁና በዛ ስር ተሰባስቦ ባንድ ሆኖ መግጠሙ ጉልበታም ነበር። ካለው ጊዜ አኳያ አሁን ስለማይቻል ይቆይ።  በተቃዋሚነት ደረጃ ተሆኖ በዛ ላይ ዜጎች በከፋ አፈና ውስጥ ስላለን ልንዳኛችሁ የማይቻለን ሆኖም ነው ያስቸገረው።  ተችሎም ቢሆን መሰረት ለመጣልና ሂደቱን ለማስጀመር ነበር። አሉ የምንላቸው ዋናዎቹ ልዩነቶች  የትኛውንም አይነት ስምምነት ቢደረግ፤ እኔነኝ ያለ ዲሞክረሲያዊ መንግስት ቢፈጠርና ፈጣን በሆነ ሁለንተናዊ እድገት ማድረግ ብንችልም። ከልዩነቶቹ ባህሪ የተነሳ መፍትሄያቸው ረጅም በጣም ረጅም ጊዜ የሚፈልጉና የሂደት ያላሰለሰ ስራንና ትኩረትን የሚፈልጉ ናቸው። መተጋገሉ ገና ለመቶ አመት ይቀጥላል። ይህን ታሳቢ አድርጋችሁ   እስካለው ልዩንት በጋራ ስልጣኑን ከወያኔ ለመረከብ መስራት አንድና አንድ  ትኩረት ይሁን። አንድም ልዩነቱን ህግና ስርአት ባለበት፤ ከከበደ ሀላፊነትና ተጠያቂነት ጋር ፓርላማ ውስጥ ማስገባት ስለሚሆን አገር ከዚህ ሊጠቀም ይችላል። ያኔ የሚመች ሶፋ ላይ ፈልሰስ ብሎ  ውስኪ እየተቀዳ ዘና ባለ ሁኔታ ውስጥ የሚሰራ ስለሚሆን ይቀላል። ባዛ ላይ  ልዩነት  እየለዘበ ይሄዳል። ቢበዛ ፓርላማ ውስጥ ቡጢ ስትወራወሩ ደግሞ እያየን ፈን እንይዛለን።

ኮሮጆ መገልበጡንም የማይቻል ማድረግ ይቻላል ብያለው። መጀመርያ እናንተ እንድትመቹ ባግባቡ ሁኑ እንጂ  ይቻላላ።

“ይምርጡን ሳናዳላ፤ ሳንገል፤ ሳንዋሽና ሳንሰርቅ ፍፁም በሆነ አገራዊ ፍቅር አክብረንህ እናገለግላለን ”።

ምን ማድረግ እንዳለብን ሁሉን ነግሮናል። ይሄን ልጅ ፍቱ ብያለው።

በአገር ላይ የሚመጣ አደጋን አቅልሎ የማየት ያልሰለጠነ አስተሳሰብ

$
0
0

(ኤፍሬም እሸቴ)

ታዳጊ አገሮችን በሙሉ የሚያመሳስላቸው አንድ ግርም የሚለኝ ነገር ከገደል አፋፍ ቆሞ ገደሉን መናቅ፣ ከአደጋ ጫፍ ቆሞ አደጋን ማቃለል፤ ከዚያም ከገደሉ ወድቆ መሰበር፣ በአደጋው ተጠራርጎ መወሰድ። ይህ ሐሳብ በርግጥ ፍንትው ብሎ የታየኝ የማሌዢያ አውሮፕላን በዩክሬይን ሰማይ ላይ በሚሳኤል በጋየበት ጊዜ ነበር። ሁላችሁም እንደምታስታውሱት የሰው አካል ቁርጥራጭ ከሰማይ ይዘንብ እንደነበር እማኞች ሲናገሩ መልክተናል።
-
ታላላቆቹ የዜና አውታሮች ራሺያ ላይ አተኩረው ነገሩን በዚያ ፈፀሙት አንጂ “አውሮፕላኑ በጦርነት ሰማይ ላይ ለምን ሄደ?” የሚለውን የሚያነሱ ሰዎችም ተደምጠዋል። ብዙ አየር መንገዶች አቅጣጫቸውን ቀይረው በሌላ መስመር መሔድ ከጀመሩ ቆይተው ነበር። የሳንቲም ስባሪ ለማትረፍ አንድም በማሌዢያኛ “አቦ አታካብዱ” ብለው ሳይሆን አይቀርም በዚያ በታዳጊ አገር አስተሳሰብ መንገዳቸው ሳይቀይሩ ቀሩ።

“የእባብ ጉድጓድ በጅል ክንድ ይለካል” እንደሚባለው የዩክሬይን አየር በማሌዢያ አውሮፕላን ክንድ ሲለካ ጅልም እጁ አይተርፍ፣ አውሮፕላኑም አልተረፈ። ተመሳሳይ ነገር እነሆ ሊከሰት ነው። ኢትዮጵያ በበኩሏ 200 ነርሶች ወደ ኢቦላ ዞን (Ebola ZOne) ልትልክ ጀብደኛ ውሳኔ ወስናለች። የማሌዢያ ውሳኔ።

ኢቦላ ምዕራብ አፍሪካን ምን እያደረገ ነው? ከበሽተኛው በሚወጣ ፈሳሽ በሚተላለፈው በዚህ በሽታ የአገራች ኢኮኖሚ እንዴት እንዴት እየሆነ ነው? የዚያ አገር ዜጋ የሆኑ በማለው ዓለም የሚኖሩ ሰዎች እንዴት እየታዩ ነው? ምን ዓይነት ችግር እየገጠማቸው ነው? አይበለውና በሽታው አገራችን ቢገባ ዘመዶቹን በማስታመም የሚታወቅ የአገራችን ሰው እንዴት ባለ አደጋ ላይ ይወድቃል? የትኛው ሆስፒታል በርግጥ ብቁ ነው? መቸም በፌዴራል ፖሊስ ዱላ አታስቆሙት ነገር።“የሕዳር በሽታን” በአገራችን በ21ኛው ክ/ዘመን ልታመጡብን ካልሆነ በእውነቱ ምን ሌላ ምክንያት ይኖራችኋል?
በዓለም ላይ በሕክምና አያያዛቸው ጥራት የተመሰገነላቸው ብዙ አገሮች አሉ። ኢቦላን በረዓድ እያዩት ነው። ሕዝቡ ገና ስሙን ሲሰማ ሽብር ይይዘዋል። አንድ ሰው ቴክሳስ ግዛት በበሽታው በመሞቱ መላው አሜሪካ ከሥሩ ነው የተነቃነቀው። በርግጥ እነርሱ ፈሪዎች ስለሆኑ እኛ ጀግንነት ይዞን ይሆን? የሚመጣውን ጉድ ስለሚረዱት ነው።

ይህንን ያልሰለጠነ አስተሳብ እንዴት ማስለቀቅ ይቻል ይሆን? አለመሰልጠን ወንጀል አይደለም ነገር ግን አገር ላይ ሊያመጣ የሚችለውን አደጋ እያወቁ ለጋ ወጣቶችን ወደ እሳት መላክ ግን ሌላ ዓላማ እንዳለው ነው የሚረዳኝ። ምናልባት በበሽታው የሚገኝ ትርፍ እንዳለ እንጃ። ፈጣሪ ሕዝቡን ይታደገዋል። ለእናንተ ግን እንጃ!!!

መክሸፍ እንደ እኔ ጉብኝት (በዓለማየሁ ገላጋይ) –ስለ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

$
0
0

temesgen
ፍቱን መጽሔት ጥቅምት 15 ቀን 2007 ዓ.ም)
የጉብኝት ጉዞው በማለት ተጀምሯል፤ ያለንበት መኪና ወደ አዲስ አበባ ደቡብ አፍንጫውን ቀስሯል፤ በመካከላችን ጸጥታ ረብቧል…
ዕጣ ፈንታህ በዘመን እጅ ነው ዘመንት ሲፈቅድ የዘመንህ ‹‹ ጉዱ ካሳ›› ትሆናለህ፤ ስውር እስር ቤት ትገባለህ፤ እንደ እብድ ትታያለህ፤ በመገለል ዘብጥያ ባመደመጥ ዋርድያ ስር ትሆናለህ፡፡ እውነትህ እንደቅራቅንቦ ይቆጠራ ይናቃል…
… ወይም ….
ዘመንህ ሲፈቀድ ካሳ (ዩሐንስ) ትሆናለህ፡፡ ወደ መብት ድንበርህ ትገሰግሳለህ፡፡ አንገትህን ለክብርህ ትሰጣለህ፡፡ ከማንቁርትህ በታች ትመለሳለህ፡፡ ከአገጭህ በላይ ጠላት እጅ ትወድቃለህ …. የራስህ ‹‹መተማ-ዩሐንስ››ትመሰርታለህ… ጠላት የማይሻረው የደም ድንበር ትሆናለህ…
… ወይም …
ዘመንህ ግድ ሲል ካሳ (ቴዎድሮስ) ትሆናለህ፡፡ መቅደላ ላይ ትቆማለህ፡፡ እስህ ትጮሃለህ፣ መድፍህን ታጮሃለህ፣ ጥይትህን ትጠጣለህ፡፡ አሸናፊህን ተሸናፊ ታደርጋለህ፣ አማራኪህን ትማርካለህ…
…የዚህ ዘመን ‹‹ካሳነት›› ምንድን ነው …. ከዲማው ጉዱ ካሳ፣ ከመተማው ዩሐንስ ካሳ፣ ከመቅማላው ቴዎድሮስ ካሳ… የማይገጥመው፣ ዘመን የፈቀደው ካሳነት የቱ ነው ….
… እያልኩ አስባለሁ …
ጉብኝት ጉዞው ወደ ቂሊንጦ ነው፡፡ መኪናዋ ትርገፈገፋለች፡፡ መንገድ ሳይዘጋጋ አዲስ አበባን ለመልቀቅ ትነጫነጫለች፡፡ ጎተራን፣ ንፍስ ስልክን፣ ሳሪስን… እየጠቀለለች ትጎርሳለች፡፡ ቃሊቲ ስትደርስ፣ ሰበታን ወደ ቀኝ ትታ፣ በአሮጌው ድልድይ ስር አፍንጫዋን ወደ ምስራቅ ቀሰረች፡፡ ቃሊቲ ስትደርስ፣ ሰበታን ወደ ቀኝ ትታ፣ በአሮጌው ድልድይ ስር አፍንጫዋን ወደ ምስራቅ ቀሰረች፡፡ እዚያ ቂሊንጦ አለች፡፡ እውስጧ አንድ ‹‹ አዲስ እንግዳ›› ይዛለች….
… የቂሊንጦ አዲሱ እንግዳ ተመስገን ደሳለኝ ነው፡፡ ጥቅምት ሶስት‹‹ ጥፋተኛ›› ተብሏ፣ ጥቅምት አስራ ሰባት ፍርድ ይቀበላል፡፡ እስከዚያ እዚህ ይቆያል፡፡ እሱን ለሚያውቁ ቅር ቢያሰኝም ለእርሱ ግን ለውጥ አያመጣም፡፡ ከእነርሱ በላይ እርሱ ተዘጋጅቷ፡፡ እንግዳው ማነው እነርሱ ወይስ እሱ …. እንድል አድርጓል ተዘጋጅቷል፡፡
ሁለት ልጆች አሉት የሚያሳድጋቸው ከስጋ አብራክ በላይ በተስፋ አብራ ያወዳቸው ብርሃን የሆናቸው ከረሃብ ወደ ጥጋብ ያመጣቸው፡፡ ሚኪ እና ማሪያሟ፡፡
‹‹እንዲያ ብሆን እንዲህ ይደረግላቸው›› የሚልላቸው፡፡ ከእርሱ እንዲያ መሆን በላይ የእነርሱ ‹‹እንዲህ›› መሆን ሐሳብ ላይ ይጥለዋል፡፡ ደጋግሞ አደራ ይላል፡፡ እንዳንድ ጊዜ እንዲህ ነው፤ ፍትህ እየተባለ የሚቆላመጠው ‹‹ፍርድ›› ዱላነቱ ምንም ለማያውቁ ንጹሃን ጭምር ነው፡፡ ስጋ ሳይሆን ፍቅር የተጠለሉት ሚኪ እና ማሪያሟ ‹‹የዱላው›› ተጋሪዎች ናቸው፡፡ ያለጥጥ ተመቺዎች ናቸው፤ ከመጣል ያነሳቸው እጅ ሲታሰር ወደመጣል መመለስ አፋን ከፍቶ ይጠብቃቸዋል፡፡ ያሞት የሚያስመርጥ ህይወት …
… የመጀመሪ ቀን ያየኃቸው ፍትህ ጋዜጣ የነበረበት ግቢ ውስጥ ነው፡፡ ሁለት አመት ያልደፈኑ መንታዎች፡፡ ወንዱ በአካል ትልቅ ይመስላል፤ ሴቷ በአስተሳሰብ ብኩርና ይዛለች፡፡ የራስ መኮንን ወንዝ ንጭንጭ ግቢው ላይ የተንጠረበበ ድብርት ፈጥሯል፡፡ ይህም አልበቃ ብሎ አከራይዋ የልጆቹ አባት ላይ ይነጨነጫሉ፡፡ የሚላስ የሚቀመስ ካሳ ሆድ በላይ የግቢዋ ባለቤት ቁርጠት ሆነዋል፡፡
‹‹ምንድነው›› አለ ተሜ፡፡
‹‹ወር በመጣ ቁጥር በቤት ኪራይ ክፈል አትከፈል ንትርክ፤ ሰለቸኝ ቤቴን ይልቀቅልን፡፡›› አሉ፡፡
ያኔ ፍትህ ጋዜጣ እንኳን ሌላ ዕዳ ልትጨምር እራሷንም አልቻለችም ነበር፡፡ ተሜ ዝም ብሎ የልጆቹን አባት ተመለከተው ፡፡ የልጆቹ አባት የህሊና ጸሎት አድራሻ መስሎ ከመሸማቀቅ ጋር ቆሟል፡፡ ልጆቹ የተነፋፈቀ ፊታቸውን እንደያዙ እግሩ ስር ተኮልኩለዋል፡፡
‹‹ስንት ነው እኔ እከፍላለሁ አለ፡፡ ከዚያች ቀን በኃላ ልጆቹ ‹‹ የፍትህ ጋዜጣ›› ቤተኛ ሆነ፡፡ እነዚህን ልጆች አሁን በቅርብ አይቻቸዋለሁ፡፡ ከትምህርት ቤታቸው አውጥቷው ካፊጤሪያ እያጋበዛቸው ነበር፡፡ በጣም ገረመኝ፡፡ እነሱ አይመስሉም፤፤ የቀረበላቸውን ከ ክ እና ጭማቂ ንቀው ለጨዋታ አድልተደው ነበር፡፡ ተሜ ላይ ነገር ባንዣበበ ቁጥ ነጭናጫው የራስ ሞንን ወንዝና ንዝናዛዋ አከራይ የልጆቹ አዙሪታም ጭጣ ፈንታ ሆነው ይታዩኛል፡፡ ያ ሞት የሚያስመርጥ ህይወት …
… ቂሊቂንጦ ሶስት ሜትር ከፍታ ያለው ግንብ የታጠቀ ጸጥታ ነው፡፡ ከግዝፈቱ ጋር የማይነጻጸር ሽንቁር በር አለው፡ ግንቡን ተገን ያደረገው የጠያቂዎች ማረፊያ የአጠና ድርድር ነው፡፡ በተቀማጮች ሟልጯል፡፡ የአጥሩ አናት ላይ የጽሑፍ ማስጠንቀቂ ተለጥፏ፡፡ ወደ ማረሚያ ቤቱ የማይገቡ ነገሮ ዝርዝር ነው፡፡ ከሞባይልና ከታሸጉ ምግቦች ጋር ስለት ነገር እንደማይገባ ተገልጻል – ገረመኝ፡፡ ስለት ይዤ ልግባ የሚል ይኖር ይሆን ባህል ካልሆነ በስተቀር፤ መቼም የዘንድሮ ባህል ቅጥ አጥቷል፡፡
… ቂሊንጦ ለጥ ያለ ሜዳ ነው፡፡ ጉትያ የመሳሰሉ ዕጽዋት ሞልተውታል፡፡ በርቀት አዳዲስ ሰፋሪዎች አዳዲስ ሰቀላ በመገንባት ላይ ናቸው፡፡ ከመንገድ ወዲያ ማዶ አንድ የኮንዶሚኒየም ሳይት አለ፡፡ ጥቂት ከፍ ብሎ ደግቦ ‹‹ሔኒክን›› ያስገነባው አዲስ ቢራ ፋብሪካ ተገሽሯል፡፡
ለሶስት ሰዓት አስ አምስት ደቂቃ ሲቀረው ደርበብ ያለች የፌደራ ፖሊስ አባ መዝገብ ይዛ ብቅ አለች፡፡ የፖሊስ ደርባባ ግንጥል ጌጥነት ሳይሆን አይቀርም፡፡ በመደዳ መታወቂያ እያየቸች የተጠያቂውን ስም ትመዘግብ ጀመር፡፡ እኛም ተመዝግበን ለመግባ ስንጠባበቅ ሌላ አጣሪ ፖሊስ መጥቶ ዳግም መታወቂያ ይመረምር ጀምር፡፡ ላለማስገባት ሰበብ ያሚፈልግ ይመስላል፡፡
‹‹ይሄ መታወቂያ አይሆንም››
‹‹ለምን››
‹‹የግል ድርት እዚያው ለድርጅቱ ነው››
‹‹ምን ማለት ይሆን››
‹‹ለምን››
‹‹አልታደም››
ያም ሆነ ይህ አኔ ከማይገቡት ወገን ተመደብኩ፡፡ ይሁን! መጠየቅ የመንፈስ ጉዳይ ነው፡፡ ከግንብ ወዲያ እና ከግብ ወዲህ በሚል ድንበር አያበጅም ስሜ ገብቷል፤ መልጭክት ይደርሰዋል፡፡ እነሆ አለማየሁ የመጠየቅ ተልዖኮውን ዘጠና ከመቶ ተወጥቷል፤ አስር ከመቶ ሲቀረው ተሰረናክሏል ይሉታል፡፡ ተሜን አውቀዋለሁ ፈገግ ይላል፤ ይቀልዳል፡፡ ሊጠይቅ፤ የሄደን ያዝናናል ያጽናናል ይጠይቃል፡፡ በእርግጥም ልንዝናና፤ ልንጽናናና ልንጠይቅ የሚገባ እኛ ነን፡፡ እሱማ…፡፡

‹‹የነ እንትና ታቦት›› :ዳንኤል ክብረት

$
0
0

ዳንኤል ክብረት

St. E and St. Tዓርብ ዕለት የተከበረውን የአቡነ አረጋዊ በዓል ለማክበር አውስትራልያ አደላይድ ነበርኩ፡፡ እዚያ ከተማ የሚገኝ አንድ የድሮ ወዳጄ በፌስ ቡክ አገኘኝና አደላይድ መሆኔን ነገርኩት፡፡ ‹‹የት እንገናኝ›› ሲለኝ ‹‹ነገ (ቅዳሜ) የአቡነ አረጋዊን በዓል ለማክበር ስለምሄድ እዚያ እንገናኝ›› አልኩት፡፡ ‹‹አንተም እርሱን በዓል ታከብራለህ?›› አለኝ፡፡ በዓይነ ኅሊናየ ራሱን እየነቀነቀ ታየኝ፡፡ ‹‹እንዴት?›› አልኩት፡፡ ‹‹የእነ እንትና ታቦት አይደል እንዴ›› አለኝ የሆነ የኢትዮጵያ አካባቢ ጠርቶ፡፡ ‹‹ማን እንደዚያ አለ?›› ስል ጠየቅኩት፡፡ ‹‹ምን፣ የታወቀኮ ነው›› አለኝ፡፡ እየገረመኝ ተለያየን፡፡
በማግሥቱ በዓሉ ላይ ተገኘሁ፡፡ በዓሉን እኩለ ቀን ላይ ጨርሼ ስወጣ ሌላ የጥንት ዘመዴን አገኘሁት፡፡ ያ ትናንት ማታው ጓደኛዬ እዚህ ከተማ እንዳለ የማላውቅ መስሎት ይኼኛው ነገረኝ፡፡ እኔም ሰው ላለማጋጨት ብዬ ያለኝን ሳልዘረዝር እንዴው በደፈናው ደውዬለት መምጣት አልችልም እንዳለኝ ነገርኩት፡፡ ይኼኛውም እኔ እንዳልነግረው የደበቅኩትን እርሱ ገልብጦ ነገረኝ ‹‹የኛ ታቦት ሲሆንኮ እነ እንትና አይመጡም›› አለኝ ፈገግ እያለ፡፡ ‹‹ማን ነው የእናንተ ታቦት ያደረገው›› አልኩ በአግራሞት›› ‹‹ያው አቡነ አረጋዊ የኛ ሀገር ሰው አይደሉ›› አለኝ የሠፈሩ ሰው ያህል ርግጠኛ ሆኖ፡፡ ወይ ግሩም፣ ይኼ በሽታ ለካ ማናችንንም ሳይለይ በደንብ ይዞናል አልኩ በልቤ፡፡

ጋሽ ግርማ ከበደ ‹‹ሰው የሚጠላውን ኃጢአት ደጋግሞ ይሠራዋል›› ይል ነበር፡፡ ብዙዎቻችን የሌላውን ሰው ዘረኛነት ለመግለጥ የምንጠቀምበት መንገድ ራሱ ዘረኛ ነው፡፡ አሁን እየተጓዝንበት ያለው አቅጣጫ በመካከላችን ምንም ዓይነት የጋራ ነገር እንዳይኖረን የሚያደርግ ነው፡፡ የጋራ ሆነው የቆዩትን ነገሮች እንኳን አሁን አሁን ወደ ራስ መውሰድ፣ አለበለዚያም ደግሞ የሌላው ብቻ አድርጎ ከራስ ክልል ማስወጣት ጀምረናል፡፡ ምንም እንኳን የኔታ እሸቱ ‹‹የጎጥ ጀግና የለም፤ ጀግና ከሆነ የሁላችንም ነው፤ ያለበለዚያ ደግሞ ጀግና አይደለም›› ቢሉም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ምንኖርባትንና የቆምንባትን ኢትዮጵያ ያወቅናት አልመሰለኝም፡፡ ከሰሜን የጀመረ መስቀል ደቡብ፣ ከደቡብ የጀመረ ቆጮ ሰሜን በዘለቀባት ሀገር፤ የኮንሶ የእርከን ሥራ የትግሬ ገበሬ ገንዘብ፣ የትግራይ አምባሻ የደቡብ የቅንጦት ምግብ በሆነባት ሀገር፣ የኦሮሞ ጉዲፊቻ የሁሉም ባህል በሆነባት ምድር፣ ይኼ የእነ እገሌ ብቻ ነው፣ እኛን አይመለከትም ብሎ ለመናገር እንደመድፈር ያለ የአላዋቂ ድፍረት የለም፡፡

ማንኛውም ነገር መነሻ ይኖረዋል፡፡ ዓባይ ከግሼ ዓባይ እንደሚመነጨው፡፡ ነገር ግን መነሻው መድረሻው አይደለም፡፡ ዓባይ ከግሼ ዓባይ ስለመነጨ የጎጃም ቀርቶ የኢትዮጵያ ብቻ ሊሆን አልቻለም፡፡ አዋሳኙ ሁሉ የእኔም ነው ብሎ ሲመክርበት ይኖራል፡፡ በመካከለኛው ምሥራቅ የተጀመሩትን ኦሪትን፣ ክርስትናንና እስልምናን የኛ አድርገን እየኖርንባቸው አይደል እንዴ ? ከአውሮፓ የወረስነውን ኮትና ሱሪ ቂቅ ብለንበት እየተዳርንበት አይደለም እንዴ? በፖርቹጋሎች በኩል ከሜክሲኮ የደረሰን በርበሬ ይኼው የአበሻ መለያ ሆኖ የለም እንዴ፤ የአውስትራልያ ባሕር ዛፍ ኢትዮጵያዊ ሆኖ የለም እንዴ፤ እንዴት ነው ጎበዝ፡፡ ጤፍ ለምግብነት ዋለ የሚባለው ከክርስቶስ ልደት በፊት 5000 ዓመት ቀደም ብሎ በሰሜን ደጋማ ቦታዎች ነው፡፡ ዛሬ ግን ይኼው ድፍን ሐበሻ ባሕሉ አድርጎት፤ ዘልቆም ድፍን ዓለም ሊበላው እየተሻማ ይገኛል፡፡ የሰሜን ነው ብሎ ማን ተወው፡፡

መልካም ነገር ከአንድ ቦታ ይነሣል፡፡ ከዚያም ሌላውም ከባሕሉና እምነቱ ጋር እያዛመደ ይዋረሰዋል፤ ወይም ገንዘብ ያደርገዋል፡፡ ከዚያም የእርሱም ጭምር ይሆናል፡፡ በተለይ በታሪካችን ውስጥ ከአንዱ የተነሣ ነገር ሰፍቶና መልቶ የሌላውም ገንዘብ የሆነበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ እንዲያውም በሚያስደንቅ መልኩ ከመነሻው ጠፍቶ ከመድረሻው የተገኘ ብዙ ነገር አለ፡፡

ከላይ መነሻዬ ከሆነው የአቡነ አረጋዊ ነገር ልጀምር፡፡ አቡነ አረጋዊ ሀገራቸው ኢትዮጵያ አይደለም፡፡ ሮማዊ ናቸው፡፡ በ5ኛው መክዘ ከተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ ሆነው ወደ ኢትዮጵያ መጡ፡፡ አቡነ አረጋዊ መጨረሻቸውን በደብረ ዳሞ፣ ትግራይ ቢያደርጉትም በወሎ፣ በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋና በደቡብ ታሪክ ውስጥ ግን አሉ፡፡ ደቡብ ጎንደር ውስጥ ጥንታዊው ገዳማቸውና የዝማሬ መዋሥዕት ማስመስከሪያው ዙር አባ አረጋዊ አለ፡፡ ጣና ቂርቆስ፣ አዲስ አበባ አጠገብ የሚገኘው የረር፣ እንዲያውም ከዚያ ተሻግሮ ጋሞጎፋ የምትገኘው ብርብር ማርያም ታሪካቸውን ከእርሳቸው ጋር ያገናኛሉ፡፡ የመጨረሻውና ታላቁ ገዳማቸው ደብረ ዳሞ ስለሆነ የኛ አይደሉም ብለው አያውቁም፡፡ የጎንደር ሊቃውንት በ17ኛውና በ18ኛው መክዘ ለዓመት የሚቆመውን ዚቅ ሲያዘጋጁ ቦታ ከሰጧቸው ቅዱሳን አንዱ አቡነ አረጋዊ ናቸው፡፡ የአቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን የሀገሪቱ ድንበር ጠባቂ ሆኖ ሞያሌ ላይ ይገኛል፡፡ ለሁለቱ ኢትዮጵያውያን የምንኩስና መሠረቶች ለአቡነ ተክለ ሃይማኖትና አቡነ ኢየሱስ ሞአ ምንኩስናን የሰጠው ደብረ ዳሞ ነው፡፡ ዋርካው ሲሰፋ እዩት፡፡

እንግዲህ እኒህን ከሁሉም በላይ ሆነው፣ የሁሉም የሆኑትን አባት ነው አንዳች ጎጥ ውስጥ ልንከታቸው መከራ የምናየው፡፡ ልክ አንዳንዶቹ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ከሸዋ ብሎም ከአማራ ጋር ለማያያዝ እንደሚሞክሩት፡፡ እንዲያውም በሚገርም ሁኔታ ገድላቸው የአያቶቻቸውን ጥንተ መሠረት ከትግራይ፣ በኋላም ከዋድላ ጋር ነው የሚያያይዘው፡፡ በኋላም ሥርዓተ ምንኩስናን የፈጸሙት በአምሐራና በሐይቅ እስጢፋኖስ(ወሎ)፣ በስተ መጨረሻም በደብረ ዳሞ(ትግራይ) ነው፡፡ በውስጣቸውም የትግራይ ገዳማትን የመጎብኘት ልዩ ፍላጎት ስለነበራቸው ለብዙ ዓመታት በዚያው በትግራይ እየተዘዋወሩ አገልግለዋል፣ ተሳልመዋልም፡፡ ታላቁንና የሰሜን ኢትዮጵያ የምንኩስና መሠረት ከሆኑት አንዱ የሆኑትን አቡነ መድኃኒነ እግዚእንም አመንኩሰዋል፡፡ እንዲያውም እዚያው ትግራይ ውስጥ ቀንጦራር በተባለ ቦታ(በደቡብ ምሥራቅ ትግራይ?) ለመቅረትና ገዳም ለመመሥረት ፈልገው ነበር፡፡

አያሌ የኤርትራና የትግራይ ገዳማት የምንኩስና ሐረጋቸውን ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት የሚጀምሩትም በዚህ ምክንያት ነው፡፡ እንደ አጭር ማሳያ የዋልድባውን አቡነ ሳሙኤልና የቆየጻውን አቡነ ሳሙኤል መጥራቱ ብቻ ይበቃል፡፡ በጣና ገዳማት የሚገኙት የግድግዳ ላይ ሥዕሎች ሁለቱን አባቶች – አቡነ ተክለ ሃይማኖትንና አቡነ ኤዎስጣቴዎስን ጎን ለጎን ነው የሚሥሏቸው፡፡

ከሰሜን ተነሥቶ ደቡብ መምጣት፣ ከደቡብ ተነሥቶም ሰሜን መሄድ እንዲህ እንዳሁኑ ከባድ አልነበረም፡፡ እነ አቡነ ፊልጶስና አቡነ አኖሬዎስ ነገሥታቱ ሲያሳድዷቸው የተጠለሉት በትግራይ ገዳማት ነበር፡፡ የተጋዙትም ወደ ዝዋይና አርሲ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሠራዔው አቡነ ኤዎስጣቴዎስ እስከ ሸዋ ምድር ድረስ ደርሰው አስተምረዋል፡፡ የአኩስም ጽዮን ካህናት ከዮዲት መዓት ለማምለጥ ወደ ዝዋይ ነበር የመጡት፡፡ ያለ ሀገራችሁ፣ ያለ ክልላችሁ ያላቸው አልነበረም፡፡ በ14ኛው መክዘ በነበረው የሰንበት ክርክር ጊዜ የሞረቱ ዜና ማርቆስ ገዳም መነኮሳት በቦታ ከሚቀርባቸው ደብረ ሊባኖስ ገዳም ይልቅ የኤርትራ ገዳማት የያዙትን አቋም ደግፈው ነበር፡፡ የሙገርን ቅዱሳን ያስተማረው ሐራንኪስ የአኩስም ተወላጅ ሲሆን የቡልጋን ቅዱሳን ያስተማረው ሕይወት ብን በጽዮን ደግሞ የተማረውና የማስተማሪያ መጽሐፉን ያገኘው ከትግራይ ገዳማት ነው፡፡ እንዲያውም ለብዙ ዓመታት በትግራይ ገዳማት ቆይቶ ተምሮ ሲመለስ የተወለደባትን ዞረሬን ባያት ጊዜ ‹‹እንደ ሀገሬ እንደ አኩስም መሰለችኝ›› ነበር ያላት፡፡

በኤርትራ ታላቅ ቦታ ያላቸው አቡነ አብራንዮስ የጎጃም ሁለት እጁ እነሴ ተወላጅ ሲሆኑ፣ በምሥራቅ ጎጃምና በደቡብ ጎንደር ታላቅ ቦታ ያላቸው አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ደግሞ የኤርትራ ተወላጅ ናቸው፡፡ የምሥራቅ ጎጃም ገበሬ በኤዎስጣቴዎስ ከማለ መላሽ የለውም፡፡ የሙገሩ አቡነ አኖሬዎስ በሸዋ የነበረው ገዳማቸው ሲጠፋ በላስታና በደቡብ ወሎ ግን  ገዳማቸው አሁንም በክብር አለ፡፡ እንዲያውም ልብሳቸው፣ መስቀላቸው፣ የጸሎት መጽሐፋቸው የሚገኘው ላስታ፣ ዋናው ገድላቸው የሚገኘው ተንቤን ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ አኩስም ቢወለድም ድጓው የሚገኘው ደቡብ ጎንደር ቤተልሔም፣ ዝማሬ መዋሥዕቱ የሚገኘው ደቡብ ጎንደር ዙር አምባ ነው፡፡ አሁን በያሬድ ዜማ ሲዘም ማን አኩስምነቱ ትዝ ይለዋል፡፡ የላስታው ላሊበላ በላስታ ካለው ደብር በላይ በምዕራብ ጎጃም ያለው ይልጣል፡፡ በዚያ ከአምስት በላይ በስሙ የሚጠሩ አድባራት አለው፡፡ በጉራጌ ትልቁን ሐዋርያነት የሠሩት የሰሜን ሸዋው አቡነ ዜና ማርቆስ ናቸው፡፡ በጎንደር ደግሞ ትልቁን ሥራ የሠሩት የጉራጌ ሊቃውንት ናቸው፡፡

በግራኝ አሕመድ ዘመን ከሆነው ጥፋት በኋላ ጎንደርን ሊያቀና የተነሣው ዐፄ ሠርፀ ድንግል ትልቅ ችግር የሆነበት ለጎንደር አድባራት የሚሆኑ ሊቃውንትን ማግኘት ነበር፡፡ በኋላ ግን እነዚህ ሊቃውንት ከጉራጌ ምሑር ኢየሱስ ገዳም ተገኙ፡፡ እነዚህ ‹‹አርባዕቱ ሊቃውንተ ምሑር›› በመባል የሚታወቁት አባ መሰንቆ ድንግል ዘቤተ ልሔም፣ አባ ለባዌ ክርስቶስ ዘዙር አምባ፣ አባ ብእሴ እግዚአብሔር እና መምህር ተክለ ወልድ ዘለገደባ ማርያም ናቸው፡፡ በላይ ጋይንት ደብረ ማርያም የሚገኘው ሃይማኖተ አበው ‹‹ዐርባዕቲሆሙ ኅቡረ፣ ቃላቲሆሙ ሥሙረ – አራቱም አንድ ነበሩ፣ ቃላቸውም የሠመረ ነበረ›› ይላቸዋል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት ነበሩ እየተማከሩ ጎንደርን እንደገና አቅንተው የሊቃውንት መፍለቂያ ያደረጓት፡፡ በጎንደር ከተማ የዘር ነገር የማይነሳው ለዚያ ይሆን?

ከጎንደር ሳንወጣ ዛሬ አደባባይ ኢየሱስ የሚባለው ቤተ ክርስቲያን ታቦት ጥንት የነበረው ከምባታ ነበር፡፡ (በገድለ ተክለ ሃይማኖት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ አካባቢው ባደረጉት ጉዞ መጀመሪያ የተከሉት ታቦተ ኢየሱስን መሆኑ ይናገራል፤ ምናልባት እርሱ ሊሆን ይችላል) በግራኝ ጊዜ በተፈጠረው ስደት ካህናቱ ተሰደዱ፡፡ ታቦቱንም በአንድ ቦታ ሠረወሩት፡፡ የመከራው ጊዜ ሲያልፍ ደብሩን እንደገና ቢደብሩትም ታቦቱን ግን ማግኘት አልቻሉም፡፡ በዐፄ ሠርፀ ድንግል ዘመን አባ ንዋይ የተባሉ አባት ወደ ከምባታ ወርደው ታቦቱ ያለበትን ቦታ ለ47 ዓመት ሲፈልጉ ቆይተው በ1570 ዓም አካባቢ አገኙት፡፡ ወደ ንጉሡም ይዘውት መጡ፡፡ ዐፄ ሠርፀ ድንግልም ያመፀውን ባሕረ ነጋሽ ይስሐቅንና ቱርኮችን ለመውጋት በዝግጅት ላይ ስለነበሩ በ1572 ዓም ደንቢያ ላይ እያሉ ከአባ ንዋይ ጋር ተገናኙ፡፡ በዚህ ጊዜ የባሕረ ነጋሽ የትዕቢት መልእክት ከሁለት ጥይት ጋር መጥቶላቸው ነበርና አንዱን በታቦተ ኢየሱስ፣ ሌላውን በግምጃ ቤት ማርያም ላይ አድርገው እንዲጸልዩበት አዘዙ፡፡

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ታቦተ ኢየሱስ ከንጉሡ አልተለየም፡፡ በ1572 ረዳዒ የተባለውን የቤተ እሥራኤል መሪ፣ በ1579 ጎሼን ለመውጋት ሲዘምቱ አብሮ ነበረ፡፡ በኋላ በዐፄ ፋሲል ዘመን አደባባይ ኢየሱስን ሠርተው ታቦቱን በዚያ አኖሩት፡፡ ይኼው ከከምባታ መጥቶ ጎንደር ላይ ተተክሎ ይኖራል፡፡ ልክ ወሎ መካነ ሥላሴ የነበረውና በግራኝ ተቃጥሎ ፍራሹ የሚታየው የመካነ ሥላሴ ታቦት አሁን አራት ኪሎ ሥላሴ ካቴድራል እንደሚገኝው ማለት ነው፡፡ የቁልቢ ገብርኤል ታሪክ ከአኩስምና ከቡልጋ ጋር እንደተያያዘው፡፡

መርጡለ ማርያምን ቤተ ክርስቲያንን ከግራኝ ዘመን ትንሽ ቀደም ብሎ ባመረ ሁኔታ እንደገና አሠርተዋት የነበሩት እቴጌ ዕሌኒ የሐድያ ተወላጅ ነበሩ፡፡ ሕዝቡ በደግነታቸው ስለሚወዳቸው በሞቱ ጊዜ ከሩቅ ሀገር ሳይቀር እየሄደ መርጡለ ማርያም ከመቃብራቸው ላይ ያለቅስ ነበር ይላል አልቫሬዝ፡፡

እንዴው ባጠቃላይ እንደ ዘሐ ዘጊ ወዲህና ወዲያ እንዲህና እንዲያ በተዋረሰውና በተወራረሰው ሕዝብ መካከል ‹‹የዚያ ብቻ›› ወይም ‹‹የእኔ ብቻ›› የሚል ነገር ማምጣት ካለ ማምጣቱ ይልቅ የሚከብድ ይመስለኛል፡፡ እንኳን ደጉ ነገር ክፉው ነገራችን እንኳን ተዋርሶ ተዋርሶ የሁላችን ሆኗል፡፡ ምንም እንኳን የራሳችን ቋንቋ፣ ባሕልና ማንነት ቢኖረንም፣ የበለጠ የሚያዋጣን የኛንም ሸጠን፣ የሌላውንም ገዝተን የተዋርሶና የተገናዝቦ ማንነት ብንፈጥር ነው፡፡ ከአጥሩ ይልቅ ድልድዩ ያተርፈናል፡፡ ሀገር እንደ ገና ዳቦ ስትያያዝ እንጂ እንደ ቡሄ ዳቦ ስትነጣጠል ዘላቂ አትሆንም፡፡

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live