Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ፍፁም ሰላማዊ! (ይቺን ነው መኮረጅ!) –ከአቤ ቶኪቻው

$
0
0

ከአቤ ቶኪቻው

980132_456214187800412_886270627_oቀጥሎ ስለ ሰላማዊ ሰልፉ ጥቂት ልናወጋ ነው፡፡ በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በትግርኛ እና በጥቅሉ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ስለ ሰላማዊ ትግል ስናወራ ስለ ሙስሊም ኢትዮጵያውን በማውራት ብንጀምር የወጋችንን ደረጃ ከፍ ደርገዋል ሞገስም ይሰጠዋል እና እንቀጥል…

መንግስታችን በዛን ሰሞን በገዛ ቴሌቪዥኑ የሙስሊሙን ህብረተሰብ ተቃውሞ በሌላው ህብረተሰብ ላይ የተቃጣ ትንኮሳ አስመስሎ ኮሳሳ የሆነ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ሲሰራ አይተን ታዝበን ታዝበን ታዝበን አልወጣልንም፡፡

በተደጋጋሚ እንዳየነው ሙስሊም ኢትዮጵያውን ከአመት በላይ በመስጂዳቸው ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ያሳዩን ጨዋነት ገዢዎቻችንን ያሳፈረ ነበር የሚለው ቃል አይገልፀውምና “አፈር ያስበላቸው ነበር” ማለት ይሻላል፡፡ (አረ እንደውም አፈር ደቼ እንበል እንጂ… ሃሃ… “ደቼ” የምትለውን ቃል ትርጓሜ ከሳቴ ብርሃን መዝገበ ቃላትን ላይ ባገላብጥም፤ ደቸር፣ ደቻሪ ደቻራ፣ ደችሮ ብሎ ይዘላታል እንጂ ትርጉሟን አላስኮርጅ አለኝ…) የምር ግን የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጨዋነት የተላበሰ ተቃውሞ ገዢውን እና አሳሪውን መንግስታችንን አፈር ደቼ ያበላ ነበር ከሚለው ውጪ ገላጭ ቃል ከየት ይገኝለታል?

የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጥያቄ የሌላው ኢትዮጵያዊም ጥያቄም ነው፡፡ ኢትዮጵያውን ሙስሊሞች፤ “መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ አይግባ” ይላሉ፡፡ ሌላውም ኢትዮጵያዊ፤ “አዎን እንኳንስ በሀይማኖት እና በታክሲ ወረፋም ጣልቃ መግባት ነውር ነው” ይላል፡፡ ኢትዮጵያውን ሙስሊሞች፤ “መንግስት የምንጠይቀውን ጥያቄ በእስር እና በጠብ መንጃ አይመልስልን” ይላሉ፡፡ ሌላውም ኢትዮጵያዊ “አዎ ሰው ማሰርን በሬ እንደማሰር አታቅልሉት ሰው ለመጥመድም በሬ እንደመጥመድ አትቸኩሉ” ይላል፡፡ በጥቅሉ ኢትዮጵያውን ሙስሊሞች “ድምፃችን ይሰማ” ይላሉ፡፡ ሌላው ኢትዮጵያዊም፤ “ጮክ ብሎ ዜና እናሰማለን ማለት ብቻ ዋጋ የለውም የእኛንም ድምፅ መስማት ልመዱ” ሲል በየአጋጣሚው ሁሉ ይጮሃል፡፡

እስከ አሁን ኢትዮጵውን ሙስሊሞች በአንድ ላይ ሆነው በየሳምንቱ በየ መስጂዳቸው ድምፃችን ይሰማ ሲሉ የቆዩ ሲሆን፤ የተቀረው ኢትዮጵያዊ ደግሞ በጋራ ሆኖ ኡኡ የሚልብት አማካይ ቦታ ተቸግሮ “የት ሄጄ ልፈንዳ” እያለ ይገኛል፡፡

አሁን እድሜ ለሰማያዊ ፓርቲ፤ ሁሉን በጋራ የሚያሰባስብ አንድ መድረክ ተፈጥሯል፡፡ እሁድ ግንቦት 25 ዋቄፈታውም፣ ኦርቶዶክሱም፣ ሙስሊሙም፣ ፕሮቴስታንቱም፣ ካቶሊኩም በአንድ የሚሰባሰቡበት መድረክ ተፈጥሯል፡፡ በጥቅሉ ኢትዮጵያውያን በአንድ ድምፅ ተባብረው “ድምፃችን ይሰማ” ይላሉ፡፡ መንግስት ሊሰማም ላይሰማም ይችላል፡፡ የጋራ የሆነው የሰማዩ አምላክ ግን እንደሚሰማ ግን በጣም ርግጠኛ ነን!

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤

እስከ አሁን በደረሰኝ ወሬ ከቢሸፍቱ (ደዘዎች) እና ከአዳማ (ናዝሬት) በርካቶች በሰልፉ ለመታደም ተነሳሽነት አሳይተዋል፡፡ እንደ ቅንጅት ጊዜው በክልላችሁ ተሰለፉ ካልተባሉ በስተቀር፤

በመጨረሻም

ፖሊስ እና ወታደሩ የተሰላፊው ወገን መሆኑን መርሳት ራስን ከመርሳት ጋር እኩል ነው፡፡ ተሰላፊዎች ሃምሳም ሁኑ ሃምሳ ሺህ አንድ ፀባይ ግን ያስፈልጋል እርሱም ፍፁም ሰላማዊ መሆን! ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በሚሊዮን ሆነው አቤት ሲሉ የአቤቱታው ፀባይ አንድ ነበር ፍፁም ሰላማዊ! (ይቺን ነው መኮረጅ!)

በመጨረሻው መጨረሻ

ለሰላማዊ ተቃዋሚዎች፤ ሰላሙን ያብዛ! ብለን እንመርቃለን!

አሜን!


ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ የፎቶ ዘገባ

$
0
0

ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በአዲስ አበባ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ተገኙ። የፎቶ ዘገባውን ይመልከቱ። (ፎቶዎቹ የጋዜጠና በፍቃዱ ኃይሉ ናቸው)
463787_10200726544579943_1927157516_o

463813_10200726548540042_1752304564_o

737064_10200726533179658_1146948848_o

964050_10200726454377688_1498466_o

964160_10200726506378988_351801364_o

964382_10200726554220184_1320094080_o

964529_10200726535019704_2096094436_o

964989_10200726449297561_2096771415_o

965358_10200726557420264_1775746088_o

965628_10200726516779248_1690226839_o

965836_10200726448057530_536932729_o

965873_10200726551140107_1183655609_o

967118_10200726502298886_1077028948_o

976879_10200726555860225_1504955293_o

977861_10200726226811999_641498735_o

979885_10200726530979603_470373367_o

980342_10200726537499766_444268736_o

981835_10200726504818949_491585949_o

semayawi

በአዲስ አበባ የተደረገውንና የዛሬውን ሰልፍ የሚያሳዩ ቪድዮዎች

$
0
0

ጭቆና ይጥፋ ወኔ የሌለው የሀገር ሸክም ነው

አንድነት ለሃገራችን

ሃገራችን እንደዳዳቦ አንቆራርስም

መማር ያስከብራል ሀገርን ያኮራል

ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ በሰላም ተጠናቀቀ

$
0
0

980132_456214187800412_886270627_o(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ዛሬ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም የተደረገውን የሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ ተቃውሞ የኃይለማርያም ደሳለኝ መንግስት ፍቃድ መስጠቱ የሚያስመሰግነው ቢሆንም የሕወሓት/ኢሕአዴግ ወታደሮች በሌላ በኩል ሰልፉ እንዳይካሄድ ሲያውኩ ነበር የከረሙት። ትናንት በአዲስ አበባ 6 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሾላ የካ ሚካኤል አካባቢ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ወቅት ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው የነበረ ሲሆን ነገር ግን ፍርሃት የሚባለውን ነገር እያስወገደ የመጣው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአካባቢው የሚገኙ ህብረተሰቦች በግምት ወደ 200 የሚጠጉ ልጆቹን ለማስፈታት ባደረጉት ጥረት ከአንድ ሰአት ግርግር በኋላ የታሰሩትን ልጆች ማስፈታት እንደቻሉና፤ ባካባቢው የነበረውም ህብረተሰብ ጭብጨባና ዘፈን በማሰማት ከአካባቢው መበተኑን ሰማያዊ ፓርቲ አስታውቆ ነበር።
981090_456217131133451_659197631_oመንግስት ይህን የተቃውሞ ሰልፍ በአንድ በኩል ፈቃድ ሰጪ በሌላ በኩል አሰናካይ በመሆን ቢቀርብም ለሰላማዊ ሰልፍ የወጣው በበብዙ ሺዎች የሚቆጠረው ህዝብ ግን ጥያቄው አሁንም ሰላማዊ መሆኑን አሳይቶ ድምጹን በሚገባ በማሰማት በሰላም ወደ መጣበት ተመልሷል።
ከምርጫ 97 በኋላ ሟቹ ጠ/ሚ/ር ከቤት ውጭ የሚደረጉ ማናቸውንም የተቃውሞ ሰልፎች ከከለከሉ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በተደረገው በዚህ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተገኘው ህዝብ በተለይ የታሰሩ የፖለቲካ፣ የሃይማኖትና ጋዜጠኛ ህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፤ በአባይ ስም የሚደረገው ማጭበርበር እንዲቆም፣ የተማረ ቤቱ ቃሊቲ እንዳይሆን፣ የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ የመናገርና የመጻፍ መብት እንዲከበርና ሌሎችንም ጥያቄዎችን ማንሳታቸውን የዘ-ሐበሻ የአዲስ አበባ ዘጋቢዎች ገልጸዋል።
“በሃገራችን ሰላም አጣን”
“የኑሮ ውድነት ያጎበጠው ትከሻችን እረፍት ይሻል”
“የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ይፈቱ”
“መማር ያስከብራል ሃገርን ያኮራል”
“ነፃነት የሌላት ሃገር ጨለማ ናት”
“መማር ያሳስራል፤ ቃሊቲ ያስገባል”
“የመንግስትን በኃይማኖት ጣልቃ ገብነት እናወግዛለን”
“ኮሚቲዎቻችንን ይፈቱ”
“ልማት እያሉ ሙስና ሰሩ”
“ፍትህ! ፍትህ! ፍትህ!”
“መብትን መጠየቅ ወንጀል አይደለም፤ መብትን መጠየቅ ስልጣን አይደለም”
“ዜጎችን ማፈናቀል የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው”
“መብትን መጠየቅ አሸባሪነት አይደለም”
“ኢቲቪ ሌባ፤ ውሸት ሰለቸኝ”
“የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄዎች ይመለሱ”
“ህገመንግስቱን የሚጻረሩ ህጎችን እንቃወማለን”
የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮችን ያሰሙት ሰላማዊ ሰልፈኞቹ መንግስት በአስቸኳይ ድምጻቸውን እንዲሰማም ጠይቀዋል።
(ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እስከምንመለስ ከአዲስ አበባ ከተደረገው ሰልፍ በኋላ እዚያው አዲስ አበባ የነበረው ገጣሚ ፋሲል ተካልኝ ስለስልፉ በግጥም የተሰማውን ጽፏል። እናካፍላችሁ)

_ጥቂቶች ስንት ነን?!?___
“ጥቂቶች” አትበሉን..እናንት ብዙኃኑ!
የጊዜ ጉዳይ ነው..እልፍ አዕላፍ መሆኑ::
እናንት ብዙኃኑ!..
ተዉ አታሳንሱን..ተዉ አታንኩዋስሱን..
እናንተም ጥቂቶች..
እንደነበራችሁ.. እኛን አታስታውሱን::
ወር ተራው ደርሷችሁ..
አውነታው ጠፍቷችሁ..
…ዛሬ ስታገሉን
ጥቂት እንኩዋ’ አታፍሩም?!?
…”ጥቂቶች” ስትሉን
እናንተ ብዙኃን..”ጥቂቶች” አትበሉን
ሐቁን ስነግራችሁ..ሐቁን ተቀበሉን::
“…ተባዝቶ..ተባዝቶ..
ዛሬ ምድርን ሞልቶ..
ሰባት ቢሊዮናት..ቁጥሩ የደረሰው
ከጥቂትም..ጥቂት..ከጥቂት እሚያንሰው
የኦሪቱም አዳም..ነበረ’ኮ አንድ ሰው::…”
እናንት ብዙኃኑ!..
ኧረ ለመሆኑ…
እማንታያችሁ..በቁጥራችን ገነን
“ጥቂቶች” ስትሉን..”ጥቂቶች ስንት ነን?!?”
* * *
___ፋሲል ተካልኝ አደሬ___
___________________________________________________
በሌላ በኩል የቀድሞ የኢትኦጵ እና የአዲስ ዜና ዋና አዘጋጅ ወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን በፌስቡክ ገጹ ስለዛሬው ሰልፍ የሚከተለውን ጽፏል።
“አሂምሳ!”
ዝምታው ተሰበረ!!!
ሠማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ሰልፈኞች አደባባይ ወጥተው ስለ ፍትህ ዘመሩ፡፡ እጅግ አስደናቂ፣ እጅግ አስገራሚ፣ ፍፁም ሠላማዊ የሆነ ሰልፍ…!!
በግሌ በሠላማዊ ትግል ላይ ያለኝ ጠንካራ ዕምነት የሚያመረቃ ፍሬ ያፈራበት፣ እጅግ በጣም የተደሰትኩበት፣ በተለይ በወጣተ ትውልድ መነቃቃት የኮራሁበት ቀን ነው፡- ዛሬ፡፡
እንደዛሬ “የፎቶ ካሜራ በኖረኝ” ብዬ የተመኘሁበት ቀን የለም፡፡ እንዲያም ሆኖ በሞባይል ካሜራ አስደናቂውን ሰላማዊ ሰልፍ በምስል ላሳያችሁ ሞክሬአለሁ፡፡ እውነት እውነት እጅግ በጣም የሚያኮራ ቀን ነበር ዛሬ፡፡ የሠላማዊ ትግል ትንሳኤ ነበር ማለት ይቻላል፡፡
ጋንዲ ለሚታወቁበት “የጨው አብዮት” ለሠልፍ የወጡት በ20 ሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ነበሩ፡፡ ዋናው ግብ ቦታ የደረሱት ግን በቁጥር 193 ሰዎች ነበሩ፡- ታሪክ እንደዲነግረን፡፡

“አሂምሳ” እንዲሉ ማህተመ ጋንዲ ጠንካራ ወኔ መንፈስ የተላበሱ ሠልፈኞች በቸርችል ጎዳና ላይ በእምነት ፈሰሱ፡፡…ያኮራሉ! ኮርቻለሁ!

የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ከድጡ ወደ ማጡ

$
0
0

London churchዘመነ ካሳ (ከጀርመን)
በዚህ በትልቁ የአውሮፓ ክፍል የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ለረጅም ዘመናት አገልግሎት የሰጠች እንደመሆንዋ መጠን በሙያ የበሰሉ አገልግሎታቸው የተመሰገኑ አባቶች አገልግሎት የሰጡበት መሆኑ ታሪክ የሚያስታውሳቸው ነው:: ከነዚህም አባቶች መካከል በቀድሞው ስማቸው አባ አረጋዊ በኋላ ብጹእ አቡነ ዮሐንስ እንዲሁም ሊቀ ካህናት ሰሎሞን ገብረ ስላሴና ሌሎችም ይገኙበታል:: ይህቺ ቤተ ክርስቲያን ለተዋህዶ እምነት ተከታዮች ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክተች ቤተ ክርስቲያን ስትሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከኣውሮፓ ቀደምት ተብለው ከሚጠሩት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በቁጥር አንድ የምትቀመጥ ከመሆንዋም በላይ ከሀገራችው ተሰደው ከወገን ከዘመድ ተለይተው ለሚገኙ ምእመናን ከፍተኛ መጽናናት ትንሿ እናት ሀገር ኢትዮጵያ መሆንዋ የማይካድ ነው::
ስለሆነም በካህናቱ መልካም አገልግሎት በምእመናኑ ያልተቆጠበ ጥረት ህንጻ ቤተ ክርስቲያን በመግዛት አርያነቱ ለሌሎች የሚተርፍ ቅርስና ታሪኩ ለትውልድ የሚተላለፍ አስደናቂ ተግባር ፈጽመው በባእድ ሀገር የህንጻ ቤተ ክርስቲያን ባለቤት ለመሆን በቅተዋል::

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ኢሕአዴግ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ሊያስር መሆኑን ፍንጭ ሰጠ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በመወጣት ድምጻቸውን ካሰሙ በኋላ የኢሕአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ “ፓርቲው ህገ መንግስቱን በመጣስ በሃይማኖት እጁን መክተቱና በህግ የበላይነት አምናለሁ እያለ በፍርድ ቤት ጉዳያቸው የተያዘባቸው ሰዎች በሁካታ ይፈቱልን ማሰኘቱ ተጠያቂ ያደርገዋል” አሉ።

964382_10200726554220184_1320094080_oአቶ ሬድዋን በፍርድ ቤት ሽብርተኛ የተባሉ ሰዎችን ሰማያዊ ፓርቲ እንዲፈቱለት መጠየቁ አግባብ አይደለም ካሉ በኋላ “የሃይማኖት አክራሪነትን አጀንዳው አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሰማያዊ የፖለቲካ ፓርቲ ጸረ ህገ መንግስታዊ እንቅስቃሴው ዛሬ በጠራው ሰልፍ ተጋልጧል ብሎ ኢህአዴግ ያምናል።” በማለት የፓርቲው ሰዎችን ለማሰር ያለውን እቅድ ፍንጭ ሰጥቷል።

የኢሕአዴግ መንግስት በተለያዩ ጊዜያት በልምድ እንደታየው ግለሰቦችን ማሰር ሲፈልግ “ሕገመንግስቱን” እንደሚጠቅስ የሚያስታውሱት የፖለቲካ ተንታኞች ኢሕአዴግ ይህን “ሰማያዊ ያዘጋጀውን ሰላማዊ ሰልፍ ላልተፈለገ አላማ አውሎታል” ሲል መግለጹ እንደተለመደው ሰበብ ፈልጎ ለማሰር ያለውን እቅድ ያሳየ ነው ብለውታል።

አቶ ሬድዋን በመግለጫቸው “በሰልፉ በአብዛኛው የተንጸባረቀው የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ይፈቱ እየተባለ መስተጋባቱ፤ ፓርቲው ህገ መንግስቱን በመጣስ በሃይማኖት እጁን መክተቱና በህግ የበላይነት አምናለሁ እያለ በፍርድ ቤት ጉዳያቸው የተያዘባቸው ሰዎች በሁካታ ይፈቱልን ማሰኘቱ ተጠያቂ ያደርገዋል” ሲሉ በግልጽ መናገራቸውን የተመለከቱ የፖለቲካ ተንታኞች ስርዓቱ ይህን አይነት መግለጫ የሚሰጠው ከፍራቻ እንደሆነ ተናግረዋል።

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው ለመንግስታዊ ሚዲያዎች ሰጡት በተባለው አስተያየት በሃይማኖት ውስጥ ችግር አለ እስከተባለ ድረስ እና የታሰሩ ሰዎች እስኪፈቱ ድረስ ፓርቲው ትግሉን ይቀጥላል ብለዋል። በዛሬው በሰልፉ በቅርቡ በቤንሻንጉል ክልል እንግልት የደረሰባቸው የአማራ ክልል አርሶ አደሮች አደሮች ጉዳይ ፣ በ”አሸባሪነት” ተጠርጥረው የታሰሩ የፖለቲካ መሪዎችና የህዝበ ሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም የጋዜጠኝነት ሙያቸውን በአግባቡ በመወጣታቸው የተወነጀሉ ጋዜጠኞች ከእስር ይፈቱ የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ በየትኛውም አካባቢ ተዘዋውረን የመኖር መብታችን ይከበርልን ፣ ህገ መንግስቱን የሚቃወሙ አፋኝ አዋጆች ይሰረዙልን ብለዋል ሰልፈኞቹ ሲሉ የመንግስት መገናኛ ብዙሃንም ዛሬ ጠዋትም ዘ-ሐበሻ መዘገቧ ይታወሳል።

ወርሃ ግንቦት ሲታወስ! – (ኢሮብ መብት ተማጓች ማኅበር የበተነው ጽሑፍ)

$
0
0

irob ethiopia ከ1990 ዓ.ም ወዲህ ወርሃ ግንቦትን በተለይ ደግሞ ግንቦት 23 ደስታና ሀዘን በተቀላቀለው ስሜት ነው የምናስታውሰው። ሀዘን የሚሆንብን ሻዕቢያ እንደሚወረን እየታወቀ የኢትዮዽያ መንግሥት ምንም ዓይንት ዝግጅት ሳያደርግ በመወረራችን ዳር ድንበራችንን ለማስከበር ከፍተኛ የሆነ የሰውና የንብረት መስዋዕትንት በመክፈላችን፣ ወረራውን ተከትሎ በሻዓቢያ ታግተው የተወሰዱ መቶ-እጥፍ ወገኖቻችን እስከ ዛሬ የደረሱበት ሳይታወቅ ይኸው አስራ ሶስት ዓመታት ማስቆጠራችንና ከሁሉም በላይ ደግሞ ታግተው የተወሰዱ ዜጎችን በሚመለከት የኢህአዴግ አገዛዝ ምንም ዓይነት እርምጃ ባለመውሰዱ፤ ወራሪው የሻዓቢያ ሠራዊት ዳር ድንበራችንን መውረሩና ህዝባችንን ለሁለት ዓመት በባርንት ቀንበር ሥር ማቆየቱ አንሶ ሉዓላዊ የኢትዮጵያ ግዛቶችን ለድርድርና ለግልግል ዳኝነት በማቅረብ ለሻዓቢያ ፍላጎት እንድንንበረከክ በመደረጉ፤ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነትን ማስከበር በሚመለከት፡ በኢህአዴግ አገዛዝ ላይ እምነት እንድናጣ ስለሆን ሻዓቢያ በወረራ ይዟቸው የነበሩ የኢሮብ ህዝብ መኖሪያ አከባቢዎች ዛሬም የጦር ሰፈር በማድረግ በርካታ ወገኖቻችን ለልዩ ልዩ በሽታዎች መዳረግ፣ ለባህላችን ውድቀትና የበርካታ ወገኖቻችን ትዳር መፍረስ፣ እንዲሁም በአከባቢው የነበሩ ዛፎችና ደን፣ ሥሩ እየተነቀለ ለማገዶ እንጨት መዋል ወዘተ. እንጂ አከባቢያችን የልማት ማእከል ሲሆኑ ለማየት ያለመታደላችን፤ ናቸው።
በዚህ ሁሉ አሳዛኝ ሰቆቃና ቊጭት ማኸልም የምንጽናናባቸውና የምንኮራባቸው በዜጎቻችን የተፈጸሙ ጀግንነቶችና ቁምነገሮችም አሉ። ይኸውም፤ እናት ኢትዮጵያ ለሕይወቱ የማይሳሳ፤ ለነፃነቷና ለክብሯ ውድ ሕይወቱን የሚሰጥ ጀግና ህዝብ ያላት ሀገር መሆኗ ነው። እንደ ትናንቱ በሻዕቢያ የእብሪት ወረራ ወቅትም ውድ ልጆቿ ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ ቀፎው እንደተነካ ንብ አንድ ላይ ሆ ብለው በመነሳት ለክብሯ ሲሉ ከፍተኛ መስዋእትነትን ከፍለዋልና እጅግ በጣም እናከብራቸዋለን። እነዚህ ሰማእታት የከፈሉት መስዋዕትነትም እኛ ብቻ ሳንሆን መጪ ትውልዶችም በኵራት የሚመለከቱትና የሚመኩበት ከመሆኑም በላይ ለዘለዓለም ሲዘክሩት የሚኖር ይሆናል። አመራሩ ቢክዳቹህም አገራዊ ግዳጃቹህን ተወጥታችኋልና እናከብራቹሀለን በናንተም እንኮራለን ልንላቸው እንወዳለን።
በሁለተኛ ደረጃ የኢህአዴግ አገዛዝ ህዝባችን ደም ገብሮ ወረራውን የቀለበሰ ማግስት የኢህአዴግ አመራር አልጀርስ ድረስ በመጓዝ ለአቶ ኢሳያስ እጅ ነስቶ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚያስደፍር ሰነድ በመፈራረም የግልግል ፍርድ ቤት እንዲቋቋም መፍቀዳቸው የሚታወስ ነው። በዚህ ውል መሠረት የሚከራከርላት ወኪል ያልነበራት ኢትዮጵያ ሄግ ላይ የተሰየመው “የግልግል ፍርድ ቤት” ሲፈርድባት ተመልክተናል። ሽንፈቱን እንደ ድል የቆጠሩት የኢህአዴግ መሪዎች ብይኑ የተሰጠበት ዕለት ከጠየቅነው በላይ ተፈርዶልናል ብሎ በመዋሸትና በለመዱት የማጭበርበር ተግባር ዜጎችን ለማታለል በመሞከር ህዝብ ደስታውን እንዲገልጽ ጥሪ ማቅረባቸውም የሚዘነጋ አይደለም። እዚህ ላይ ከጠየቅነው በላይ አግኝተናል ሲሉ የጠየቁት ከየት እስከ የት እንደነበረ ግልጽ አለመሆኑ ልብ ሊባል ይገባል። የኢሮብ ርእሰ ከተማ ከዓሊተና ወደ ዳውሃን የተዛወረበት ሁኔታን ግምት ውስጥ በማስገባት ካየነው “ከጠየቅነው በላይ አግኝተናል” የሚለው ሐረግ ምን ማለት ሊሆን እንደሚችል እያንዳንዱ አንባቢ የራሱ ድምዳሜ ላይ እንዲደርሰ መልሱን በባዶ ሙላ ልናልፈው መርጠናል።
ዋናው ቁምነገሩና እጅጉንም የኮራንበትና ቀጣይ ትውልዶችም እጅጉን በኵራት የሚያስታውሱት ታሪካዊ ትምህርት ያገኙበታል ብለንም የምናምነው ህዝባችን የኢህአዴግ መሪዎች ዳር ድንበርን የመስጠት ውዲት ቀድሞ በመገንዘቡ ሴራውን ለማክሸፍ ዝግጁ ሆኖ መጠበቁ ነው። የህወሓት/ኢህአዴግ መሪዎች ሄግ ላይ የገጠማቸው ድል እንበለው ሽንፈት (እንደየአተረጓጕማችን ሊለያይ ይችላል) እንደ ደረሰ ለጭፈራ ካነሳሱት ህዝብና ከነባራዊ ሀቁ ጋር መፋጠጥ ነበረባቸው። በመሆኑም፤ ስለደረሰው ሁኔታ ለማስረዳት ከህዝብ ጀርባ ደባ ለመፈጸም ሰፊ ውስጣዊ ውይይት በማካሄድ ስራ ተጠመዱ። በዚህም፤ ግዛታችንን ለሻዓቢያ አሳልፈው ለመስጠት የነበራቸው ዝግጁነት ተግባራዊ ማድረግ ስለፈለጉ ህዝብን የሚያግባቡበት ሌላ ዘዴ ስላጡ መልካም አማራጭ ሆኖ ያገኙት የደረሰውን ሽንፈት ለኤርትራ በተወሰኑት አከባቢዎች ነዋሪ ለሆነው ህዝብ በየቀበሌው እየለያዩ ለማስረዳት በመወሰን አገባብ የሌለውን የክህደት ሥራውን እንዲያከናውኑ ካድሬዎቻቸውን ማንቀሳቀስ ጀመሩ። ከፍተኛ ካድሬዎቻቸውም በሄግ ብይን መሠረት የምትኖሩበት መሬት ለኤርትራ እንዲሰጥ ስለተወሰነና ኒውዮርክ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታትም ሊቀጣን ስለሆነ እናንተ ትነሳላቹህ መሬቱም ለኤርትራ ይሰጣል በማለት ለማስፈራራትና ተጽእኖ ለመፍጠር ሙከራ አደረጉ። በዛን ወቅት ነበር የኢሮብ ህዝብ ሄግም ሆነ የተባበሩት መንግሥታት የምትሉዋቸው ለኤርትራ የሚሰጡት መሬት ካላቸው ይስጡዋቸው፤ ይህ ግን የኛ መሬት ነውና እንኳን መሬታችንን ተንከባልሎ ወደ ኤርትራ ግዛት የሚወድቅ ድንጋይ ቢኖር እንኳን የሚከፈለውን ከፍለን እንመልሳለን ነበር ያላቸው። ይህ ህዝባችን ለመብቱ መከበር የሰጠው የእምቢተኝነት መልስ እጅጉን የሚያኮራ ነው። በመሆኑም፤ ይህ የህዝብ እምቢተኝነት ሉዓላዊ የኢትዮጵያ ግዛት እስከ ዛሬ ሳይሸራረፍ እንዲቆይ አስገድዷልና እጅጉን አስደስቶናል።
ስለሆነም፤ ትውስታችን በቊጭትና በደስታ በተደበላለቀ ስሜት የሚገለጽ ነው ስንል እነዚህን ከላይ የጠቃቀስናቸውን ጭብጦችና ስሜቶች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ነው። እዚህ ላይ አንድ ልብ ሊባል የሚገባ ቁምነገር መኖሩን አንባቢ እንዲገነዘበው እንፈልጋለን። ይኸውም፤ ለኤርትራ ሊሰጧቸው ባዘጋጁዋቸው አከባብዎች የሚኖሩ ህዝቦችን በተናጠል ከቦታው እንዲነሱ ሲያዋክቧቸው ለሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የተገለጸ ነገር እንዳልነበረ ነው። በአቶ መለስ ዜናዊና በአቶ ሥዩም መስፍን በመገናኛ ብዙኃን ለኢትዮጵያ ህዝብ የተነገረው “የአሸንፈናል” የማጃጃል ሙከራ እንዳይከሽፍ በመስጋት ሀቁን ከኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደበቅ የማድረግ ሙከራ እንደነበረ
መዘንጋት የለበትም። የኢሮብ ህዝብ እሺ ብሎ የህወሓት/ኢህዘዴግና የካድሬዎቹን ፍላጎት ተቀብሎ ቢሆን ኑሮ፤ ጉዳዩ እንዳለ ተሸፋፍኖ ይቀር እንደነበረ የሚያጠራጥር አይደለም። እነሱ ያሰቡት የኢትዮጵያ ህዝብ ሳያውቀው በሎህሳሳ መሬቱን ለኤርትራ በመስጠት የኢትዮጵያ ህዝብ ሳያውቀው ሸፋፍነው በደባ ሊያልፉት ነበር። የኢሮብ ህዝብ ግን እምብየው፤ ይህ የኛ መሬት ነው በማለት ለትውልዶች የሚተርፍ ኩራት አለበሱን። የህወሓት/ኢህአዴግ ፍላጎት ግቡን መትቶ ቢሆንና ህዝቡ እሺ ብሎ መሬቱን ለቆ ወጥቶላቸው ቢሆንና የኢትዮጵያ ህዝብ ጉዳዩን አጣርቶ ቢደርስበት፤ የህወሓት/ኢህአዴግ መሪዎች ያለ ምንም ሓፍረት “የኢሮብ ህዝብ በራሱ ፈቃድ ነው ቦታውን የለቀቀው። ባይሆን ኑሮ እኛ ግዛታችንን አሳልፈን አንሰጥም ነበር” ወይም ደግሞ “የኢትዮጵያ ህዝብ ዳር ድንበሩን ሳያውቀው ስለቆየ ነው እንጂ እንዲያውም የኛ ያልነበረ እነ ዓሊተናን አስመልሰናል” የሚል ራስን የመሸንገል አባዜ ይዘው ብቅ ሊሉ ይችሉ እንደነበር ሳይታለም የተፈታ ነው። ዛሬ ስለባድመ ስያወሩ ስለኢሮብ ግዙፍ መሬት ወደ ኤርትራ መካለል ማንሳት የማይፈልጉበት ምክንያትም ይህ ነው።
ስለዚህ የኢሮብ አባት እናቶች አኵርታቹሁናልና ምስጋና ይድረሳቹህ!
ይህንን እንደመንደርደርያ ካኖርን ዘንዳ፤ ግንቦት 23 ቀን 1990 ዓ.ም እሁድ ሌሊት የሻዓቢያ ሠራዊት ለመጀመሪያ ጊዜ የኢሮብን መሬት እንደወረረ ይታወቃል። የሻዓቢያ ወረራ ያተኵረው ዓይጋ ላይ ነበረ፣ዓላማውም ከኢሮብ መሬት ለጦር እቅድ ምቹ ከሆኑት አንደኛ የሆነውን የዓይጋ ከፍታዎችን በቁጥጥራቸው ሥር ማድረግ ነበር። ይሁን እንጂ ለኢሮብ ጅግኖች ምስጋን ይግባቸውና የሻዕቢያ እኩይ እቅድ በዛ ቀን አልተሳካም። በዚሁ ዕለት ንጋት ላይ መሬቱ መወረሩን የተገነዘበ የአከባቢዉ ህዝብ ከጠላት ትጥቅ እየነጠቀ በመዋጋት ወራሪውን ወደ መጣበት መለሰ። ስለዚህም ”ዕጡቃት-ሰንበት” የሚል ስያሜ አገኘ። በዚህ ምክንያት ግንቦት 23 ወይም በዚሁ ሳምነት ሌላ አብዛኛው የኢሮብ ህዝብ የተሰማማበት ቀን (24፣ 25…) ከዓይጋ ኮረብታዎች ጀምረው ከኢሮብ ዳርቻ በጣም እስክርቁ ድረስ ሻዓቢያን እያሳደዱ በመግረፍ ላይ የወደቁት ሊረሱ የማይገባ ጀግኖቻችን መታሰቢያ ቀን በየዓመቱ በዚሁ ሳምነት እንዲዘከርና እንዲከበር የኢሮብ መብት ተማጓች ማኅበር (ኢ.መ.ተ.ማ) ለኢሮብ ህዝብ ሃሳቡን ያቀርባል።
ዕለተ ሰንበት ግንቦት 23 ቀን 1990 ዓ.ም እብርተኛው የሻዓቢያ ሠራዊት የኢሮብን መሬት ለመቆጣጠር በታንኮችና በከባድ መሣርያ በመታጀብ የዓይጋ ኮረብታዎችን ለመቆጣጠር ዘመተ። በጊዜው በኢትዮጵያ መንግስት በኩል በቦታው ምንም የመከላከያ ኃይል ስላልነበረ፤ ሉዓላዊ የኢትዮዽያ መሬት የመከላከል ዕዳ በኢሮብ ህዝብ ጫንቃ ላይ ወደቀ። በመሆኑም በወቅቱ በኢሮብ ወረዳ ቀላልና ጊዜ ያለፈበት መሳሪያ የታጠቁ በጣት የሚቆጠሩ ምሊሻዎች ህዝባቸውን ከኋላቸው አስከትለው ሻዕቢያን ለመጋፈጥ ወደ ዓይጋ ከፍታዎች ተምዘገዘጉ። ምልሻዎቹ የኢሮብ ልማዳዊ የመልእክት ማስተላለፍ ዘዴን በመጠቀም የወረራውን ዜና ባጭር ጊዜ ውስጥ ህዝብ ጆሮ እንዲደርስ አደረጉ። ዜናውን የሰማ ህዝብም ቀፎው እንደተነካበት ንብ መጥረብያ ያለው መጥረብያውን፤ ገጀራ ያለውም ገጀራውን በማንሳት አገርን ለመከላከል ከየአከባቢው ወደ ዓይጋ ኮረብታዎች መትመም ጀመረ። ምልሻዎቹም ጋራ ሽንተረሩን አብጠርጥረው በሚያውቋቸው የዓይጋ ኮረብታዎችና የዘገብላ በረሃ ላይ የሻዓቢያን ሠራዊት በውግያ ያሽመደምዱት ጀመር። ለእርዳታ የመጣው ህዝብም የቆሰለና የተሰዋ የወገን ምልሻ ትጥቅ በማንሳት ብቻ ሳይሆን ከሻዓቢያ ወታደሮች ጋርም ጉሮሮ ለጉሮሮ እየተናነቀ ነጥቆ በመዋጋት ጦርነቱ ተጧጧፈ። እዚህ ላይ ጦርነቱ የተጀመረ ዕለት በጦርነቱ ጀመርያ ሰዓቶች የተፈጸመ የዕጡቓት-ሰንበት ቆራጥነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ታሪክ በሚገባ መዝግቦ ከትውልድ ወደ ትውልድ ማስተላለፍ ያለበት አንድ ቆራጥነታቸውን የሚመሰክር ገጠመኝን አስታውሰን እንለፍ። ይኸውም ፤ አንድ የተወሰነ ኃይል የያዘች የሻዓቢያ ቡድን በአንድ አከባቢ አድፍጣ ቆይታ አንድ ሁለት የኢሮብ ምልሽያዎችን ትከባለች በዚህ ጊዜ በጠላት የተከበቡ አርበኞች በሳሆ ቋንቋ “ታሃም ኒም ማኪክ ኖያ አዶሳይ ሳባዓየ” የሚል መልእክት ያስተላልፋሉ። ትርጉሙም “እነዚህ የኛ አይደሉምና እኛን ጨምራቹህ ምቷቸው” ማለት ነው። በዚህም፤ ዕጡቓት-ሰንበቶች ወገኖቻቸውን ለይተው በመተው ያ የጠላት ቡድንን እንዳለ እዛ አስቀርተውታል።
አሁን በውጊያው ማኸል ስለታዩ ዘርፈ-ብዙ ገጠመኞችን ማንሳት እዚሁ አቁመን ወደ ተነሳንበት የውጊያው አካሄድ እንመልሳቹህ! ይኸውም በውጊያው ያልጠበቀው ጥቃት የደረሰበት ሻዓቢያ የታጠቀውን መድፍና መትረየስን ማንጣጣት መጀመሩ ነው። ታንኮቹም የተሸከሙትን እሳት መትፋት ጀመሩ። ሆኖም እነዛ ምልሻዎችና በዛች ዕለተሰንበት የብረት ምንነት ያወቁ የዕጡቓት ሰንበት ተርቦች የሻዓቢያን ሠራዊት በታጠቁት ቀላል መሣሪያ ያጣድፉት ጀመር። በሰዓታት ጦርነት ሻዕቢያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ቁስለኛና ሬሳውን መቊጠር ጀመረ። ያን ያህል ከባድ ጥቃት እየደረሰበት ያለው በጣት በሚቆጠሩ ምልሻዎችና የብረት ምንነትና ውጊያ ጠንቅቆ በማያውቅ ህዝብ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት ስላልነበረውም ሽሽቱን ተያያዘው። እነዛ የዕጡቓት ሰንበት ተርቦች ግን ሸሽቷል ብለው አልቆሙም። ሻዓቢያን እየተከታተሉ አጨዱት። ሻዓቢያም የቻለውን ያህል ሬሳና ቁስለኛውን እየጫነ እግሬ አውጭኝ ሽሽቱን ተያያዘው። የኢሮብ ተርቦችም ወደ ሰንዓፈ ከተማ እስኪቃረብ ድረስ እየተከተሉ አጠቁት። በዚህ አኳሀን ከሦሰት ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የኢሮብ ህዝብ በትዕቢት ተወጥሮ የመጣው ሻዓቢያን አስተንፍሶ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ እየተከታተለ ወደ መጣበት መለሰው። ይህንን ታምር የፈጸሙ ጀግኖች “ዕጡቓት ሰንበት” የእሁድ ታጣቂዎች የሚል የቅጽል ስያሜ ተሰጣቸው። ዕጡቓት ሰንበት የሚል ስያሜ ያገኙት ያለምክንያት አይደለም። ከነዚህ በዛች ወቅት ጦርነቱ ውስጥ ተሳትፈው የተሰዋ ወይም የቆሰለ ወገናቸውን ትጥቅ እያነሱ እንዲሁም ከወደቀውና ከሚሸሸው ጠላት መሣርያ እየነጠቁ በጥቂት ቀናት ጦርነት ወደ ተፈለገው ምዕራፍ ካደረሱት ውስጥ የሚበዛው ከዛች ዕለት በፊት ብረት የሚባል ነገር ይዘው የማያውቁ ነበሩ። በዛች ቅጽበት ግን በጦርነቱ ማኸል የብረት አያያዝ የሚያውቁት የማያውቁትን እንዴት እንደሚተኵስ እያሳዩዋቸው ነው ሻዓቢያን ያሽመደመዱት። በዛች ዕለተ ሰንበት ታጥቀው የሻዓቢያን ሠራዊት ገጥመው በማሸነፋቸው ነው ዕጡቓት ሰንበት የሚለውን ስያሜ ያገኙት። በዚህም ኢሮብን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን አኩርተዋልና እንኮራባቸዋለን።
ይህ በግንቦት መጨረሻ ሳምንት 1990 ዓ.ም. በዓይጋ ኮረብቶች የተካሄደው የመከላከል ጦርነት የሻዓቢያን ትዕቢት ያስተነፈሰና የኢሮብ ህዝብ ለዳር ድንበሩ ያለው ቀናኢነት በግልጽ ያስመሰከረ ከመሆኑም በላይ የየዕለቱ ውጊያ የሻዓቢያን ሽንፈት ያበስር ነበር። ሆኖም፤ ያ ድል እንዲሁ ዋጋ ሳያስከፍል የተገኘ አልነበረም። በዓይጋ ከፍታዎች የተንጠፈጠፈው ደም የወራሪ ጠላት ብቻ ሳይሆን የተርቦቹ የዕጡቓት ሰንበት የኢሮብ ጀግኖችንም ጭምር ነው። ጀግኖቻችን ከወራሪ ጠላት ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቀው ወድቋል። እንደነሱ ዓይነት ጀግኖች ባይኖሩን ኖሮ ሻዓቢያ በትእቢት እንደተወጠረ መላዋን ኢሮብ ምንም ጥይት ሳይተኵስ የመቆጣጠር ህልም ይዞ እንደተነሳው ሊሳካለት በቻለ ነበር። ጀግኖቹ ግን መስዋእትነት በመክፈል የሻዓቢያን ህልም ለማክሸፍ በቁ። የመንግስት በቂ እርዳታ ታክሎበት ቢሆን ኖሮ ለሁለት ዓመታት በሻዕቢያ ሥር በባርነት ቀንበር መማቀቅ ይቅርና ሻዕቢያ ዳር ድንበራችን ሊደፍር የሚችልበት ዕድልም አይኖረውም ነበር። ያም ሆነ ይህ እነዚህን ጀግኖቻችንን ልናስታውአቸውና ታሪካቸውም ከትውልድ ትውልድ እየተወራረሰ ለዘላለም ሲታወስ እንዲኖር ሁላችንም በጋራ ታሪካቸውን ማደስ አለብን ብሎ ኢ.መ.ተ.ማ በጽኑ ያምናል። ስለሆነም፤ እነዛን ጀግኖች ለሀገራቸው ሉዓላዊነትና ዳር ድንብር መከበር የወደቁበት ቀንን በየዓመቱ ለመዘከር እንዲቻል የኢሮብ ጀግኖች ያ እኩይ ወረራ ካከሸፉባቸው ቀናት አንደኛውን በመምረጥ የነዚህ ጀግኖች የመታሰብያ ቀን እንዲሆን ማድረግ ለሁላችንም ክብር ሲሉ ለከፈሉት ውድ ዋጋ እውቅና መስጠት ተገቢም፤ አስፈላጊም በመሆኑ የኢሮብ ተወላጆች በያሉበት ሊያስቡበት ይገባል ብሎ ኢ.መ.ተ.ማ ያምናል ጥሪም ያቀርባል።
የሰማዕታቶቻንን ቀን “ዕጡቓት ሰንበት” ድል የመቱበት ቀን እንዲሆን የሚመረጠው ያለምክንያት አይደለም። በግንቦት መጨረሻ ሳምንት 1990 ዓ.ም የኢሮብ ህዝብ በዓይጋ ላይ ያሰመዘገበው ድል በኢትዮዽያ መንግስት ተጠብቆ ቢሆን ኑሮ ሻዕቢያ ራሱን ዳግም በማደራጀት የኢሮብ መሬትን እስከ ዓሊተና ድረስ አይዝም ነበር፣ ከዛ በኋላ የተከፈለው መስዋእትነት አይከፈልም ነበር፣ ከዛም አልፎ የኢትዮጵያ ግዛቶች በአልጀርስ ስምምነት ተሳበው ለኤርትራ አይሰጡም ነበር ብሎ ኢ.መ.ተ.ማ በጽኑ ስለሚያምን ነው። እንዳለመታደል ሆኖ ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ሓላፊነቱን ለመወጣት ባለመቻሉ ተጨማሪ መስዋእትነትና የግዛት መነጠቅን ለማስተናገድ በቅተናል። ያም ሆኖ ለውጤቱ የኢትዮጵያ መንግሥት በሓላፊነት የሚጠየቅበት ጉዳይ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ለናት አገር ሲሉ የወደቁትን በወደቁበት ቀን እናስታውሳቸው።
መ.ኢ.ተ.ማ በዚህ አጭር መግለጫ የጦርነቱን ዝርዝር ታሪክ ለማስፈር የቃጣ አለመሆኑና ለወደፊት በጥልቀት የሚመለስበት መሆኑን እየገለጸ፤ ታሪኩ ታሪካችን በመሆኑና ተሰንዶ ለትውልዶች መተላለፍ አለበት ብሎ ስለሚያምን በዚህ የታሪክ ምዝገባ ውስጥ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት የሚችል ሁሉ ሓላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪውን ያቀርባል።
ክብር ሕይወታቸውን ለከፈሉልን ጀግኖች!!
የመታሰብያው ቀን በአሸናፊነት በተወጡበት ዕለት ይዘከራል!!
ኢመ.ተ.ማ
ግንቦት 2005 ዓ.ም

የሙስና ክተት፤‎ ‎ከታምራት ላይኔ እስከ መላኩ ፈንታ

$
0
0

አቶ ታምራት ላይኔ

አቶ ታምራት ላይኔ

ብዙዎቹ ቱባ የመንግስት ባለስልጣናት ሙሰኞች መሆናቸው ይታወቃል ፡፡ ይቅርታ በፍርድ ቤት ቋንቋ ‹‹ ተጠርጣሪ ›› ፣ በሰልጣኝነት ቋንቋ ‹‹ ዕጩ ›› ለማለት ስነ ምግባሩ ያስገድደናል ፡፡ አማርኛው ይገጣጠም ከተባለ ተጠርጣሪ ወይም ዕጩ ሌቦች ሊባሉ ነው ፡፡ መቼም ለዚህ አባባል ትክክለኛነት የግድ የባንክ ደብተራቸውን መመልከት አይገባም ፡፡ ባለስልጣናቱ በ 4 እና 6 ሺህ ብር ደመወዛቸው ለፈረንጅ እና ለተቋማት ኪራይ የሚበቃ ግዙፍ ህንጻ በየስርጓጎጡ መገንባታቸውን ፣ ብር በየቀኑ እያጨዱ የሚያቀርቡላቸውን ሱቃቸውንና መኪናዎቻቸውን ፣ በራሳቸውም ሆነ በዘመዶቻቸው ከአዲስ አበባ እስከ ሁሉም ጫፎች ያሰባሰቡትን መሬት ማየት ይበቃል ፡፡
የእድል ጉዳይ ሆኖ ግን እጃቸው ለካቴና የሚበቃው የጥቂቶች ነው፡፡ ነገረ ስራቸውን ሲከታተል የሚቆየው ተዘራፊ ህዝብ የሚበሳጨውም የቅጣቱ መንስኤ ፍትሀዊ ይዘትን መሰረት ባለማድረጉ ነው ፡፡ ለበርካታ አመታት ተቆርቋሪ መስለው እንደሚዘርፉ እየታወቀ በሌብነታቸው ብቻ አይጠየቁም ፡፡ በአንዲት ጠማማ ቀን ሌብነቱ ላይ ፖለቲካ ወይም ያልተገባ ‹‹ ነገር ›› ሲጨምሩ ግን ‹‹ ባቡሩ ›› ወህኒ ቤት ያደርሳቸዋል ፡፡
መቼም ይህ ሀሳብ መላምት አይመስልም ፡፡ ምክንያቱም ፤
‹‹ የታምራት ላይኔ ጦር ግባ ተብለሃል ! ›› ሲባል ሰምተናል ፡፡
አቶ ታምራት ‹‹ እለፍ ተብለሃል ›› ሲባሉ የሚጠበቀውን የጀግንነት ፉከራና ቀረርቶ አላሰሙም ፡፡ ስኳር አብዝተው መላሳቸው በቅኔ ተደጋግሞ ሲነገራቸው ልምዳቸውን ተጠቅመው አሪፍ የመልስ ምት ይመልሳሉ ብሎ የሚጠብቀው ብዙ ነበር ፡፡ ለምሳሌ ያህል ‹‹ የኔ ስኳር መቃም ምን ይደንቃል ፣ ሸንኮራ አገዳውን የሚጨረግደው ሞልቶ ›› የሚል አይነት ፡፡ ሆኖም የማይጠበቀውን እንባ ነበር በፍርድ ቤትም ፣ ከእስር በኃላም በስብከት ግዜ ያንቆረቆሩት ፡፡ የፍርድ ቤቱ ምልልስ ሲበዛባቸው ግን በእሳቸው ፣ በልጃቸውና ባለቤታቸው ላይ የተፈጸመውን ደባ በለሆሳስም ቢሆን አስረድተዋል ፡፡
‹‹ የስዬ አብርሃ ሜካናይዝድ ቀጥል ተብለሃል ! ›› ሲባልም ተገርመናል ፡፡
አቶ ስዬ ግን ዝምታ ለበግም አልበጃት በሚል ሀሳብ ገና ከጠዋቱ ነበር ባለፉበት ችሎት ሁሉ ፉከራና ቀረርቶ የተጠቀሙት ፡፡
‹‹ ዘራፍ ! ስዬ አብርሃ !
የድል የጀግንነት ቀለሃ
ማነው ወንዱ ያለ ግብሩ ስም የሰጠው
ላም ባልዋለበት ኩበት የለቀመው ! ››
አቶ ስዬ ለተከሰሱበት አንድም የሙስና ጉዳይ እውቅና አልሰጡም ነበር ፡፡ ‹ እኔ የታሰርኩት በሌብነት ሳይሆን ከአቶ መለስ ጋር በነበረኝ የፖለቲካ ልዩነት ነው ›› ነበር ያሉት ፡፡ አንዳንድ ተረበኞች ግን ያ ሁሉ ተገዛ የተባለው ትላልቅ መኪና የህወሃት ነው ወይስ የኢፈርት ? ማለታቸው አልቀረም ፡፡
‹‹ የአባተ ኪሾ ሻለቃ እለፍ ተብለሃል ! ›› ሲባል ተደምመናል ፡፡
 መላኩ ፈንታ እኚህ ናቸው።

መላኩ ፈንታ እኚህ ናቸው።

ቀስ እያሉ እየጋሉ የመጡት አቶ አባተ አንድ ደፋር ሀሳብ ሰንዝረዋል ይባላል ፡፡ ‹ እኔ በሙስና የምጠየቅ ከሆነ እገሌ / እገሊትም መጠየቅ ይኖርበ / ባታል › የሚል ፡፡ ወሬው በአለ ተባለ ሃዲድ መጥቶ ጆሮአችን የደረሰ በመሆኑ መጠየቅ አለበት የተባለውን ከፍተኛ ባለስልጣን ስም አናነሳም ፡፡
እናም ይህን የመሰለው የክተት ጥሪ ቀላል አልነበረም ፡፡ አቶ ቢተው በላይን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት ባለስልጣናትም ጥሪው ደርሷቸው የደንቡን አድርሰው ተመልሰዋል ፡፡ በርግጥ ሊጠሩ ከሚችሉ ‹‹ አዝማቾች ›› መካከል አንዳንዶቹ ከኑግ ጋር እንደተገኘ ሰሊጥ ላለመወቀጥ ፣ ወይም ምን ያለበት ምን አይችልም እንዲሉ… ብቻ በአንድም ሆነ በብዙ ምክንያቶች ከቻሉ በቦሌ ካልቻሉ በሞያሌ ወጥተዋል ፡፡ በዚህ መልኩ መውጣታቸው እንጂ ኢህአዴግ የብዙዎቹን ስም እየጠራ ብዙ ነጋሪት ለመጎሰም በበቃ ነበር ፡፡ በርግጥ ድርጅቱ ከነበሩበት ከፍተኛ ቦታ አውርዶ መሬት ዘጭ የሚያደርጋቸው የተለያየ ታርጋ በመስጠት ነው ፡፡ በችሎታ ማነስ፣ በእድሜ መግፋት፣ ታማኝነት በማጉደል፣ ኔትወርክ በመፍጠር የሚባሉት የተለመዱ ዓይነቶች ናቸው ፡፡
በእውነተኛ ጨዋታ ህዝብና መንግስት ላይ ተገቢ ያልሆነ ፋውል በመስራትም ይሁን ፣ በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች አይናቸውን በታወሩ ዳኞች ግፍ ቀይ ካርድ በማየት እስር ቤት ተወርውረው የነበሩት ባለስልጣናት / ታምራት፣ ስዬ፣ አሰፋ፣ ቢተው፣ … / ቅጣታቸውን ጨርሰው ዛሬ በራሳቸው መስመር እየተጓዙ ናቸው ፡፡ በያሉበት ሆነው እንደ አዲስ የተነሳውን የመንግስት ጥሪ ወይም ‹‹ እለፍ ተብለሃል ! ›› ን እንደሚሰሙ አይጠረጠርም ፡፡ ጥሪውንም ሆነ ያሳለፉትን መሪር ቆይታ ሲያስታውሱ ቀረርቶና ፉከራ ሳይሆን አሳዛኝነት ያላትን የጦር ሜዳ መዝሙራቸውን ደጋግመው የሚያንጎራጉሩ ይመስለኛል
‹‹ እንዳያልፉት የለ ያ ሁሉ ታለፈ
ታጋይ የህዝብ ልጅ በደሙ በላቡ ታላቅ ታሪክ ጻፈ ››

በርግጥ የእስር ቤቱ ሰቆቃ ታልፏል ፡፡ ምን አዲስ ነገር ጻፉ ? የሚል ጥያቄ ግን በአሽሙረኞች ተያይዞ መነሳቱ አይቀርም ፡፡ ‹‹ ከፖለቲካ መሪነት ወደ ሃይማኖት ሰባኪነት ! ›› ይሉናል አቶ ታምራት ‹‹ ፈጣሪን ከመክዳት የፈጣሪ ታላቅነትን ወደ መቀበል ! ›› በማለት አስረግጠው ይነግሩናል ፡፡ ‹‹ ከሰው ገዳይነት ወደ ሰው ተንከባካቢነት ! ›› ቢሉ ማን ይከለክላቸዋል ፡፡ ‹‹ በሃይል ተማምኖና በደመ ነፍስ ተናግሮ ህዝብን ከማስቀየም በመጽሀፍ እያመኑ ፍቅርን ማካፈል ›› ቢሉ ከአንደበታቸው ማር ፈሰሰ አይባልም ? ፡፡ በርግጥም ጉዞው ከአንዱ ዋልታ ወደ ሌላኛው ጫፍ በመሆኑ አዲስ ነገር መሆኑ አያጠራጥርም ፡፡
‹‹ ከኢህአዴግነት ወደ ተቃዋሚነት ! ›› ይሉናል አቶ ስዬ በበኩላቸው ‹‹ ከአብዬታዊ ዴሞክራሲ ወደ ሊበራል ›› በማለትም የፕሮግራሙን መሰረታዊ ልዩነት ሊያብራሩ ይችላሉ ፡፡ ነገሩን ላጡዘው ብለው ካሰቡ ደግሞ ‹‹ ከጎጠኝነት ወደ ህብረ ብሄራዊነት … ከገንጣኝነት ወደ አስመላሽነት… ›› በማለት ምርጫ ሳይደርስ የእንካ ሰላንቲያ መድረክ እንዲከፈት ሊያደርጉ ይችላሉ ፡፡ ምናባቸውን ለማስፋትም የእውቀት ትጥቆችን በውጭ ሀገር እየሸማመቱ መሆኑን ቢጠቃቅሱ አዲሱ ሲቪያቸውን አደለቡ ማለት ነው ፡፡ ይሄ ሁሉ ሆኖ የአቶ ስዬ ለውጥ ከፖለቲካ ምህዋር ባለመውጣቱ መሰረታዊ ለውጥ አይደለም ብሎ ለመከራከር መንገድ ይከፍታል ፡፡ እንደውም አንዳንድ ወገኖች አዲስ ወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ወይስ አሮጌ ወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ የሚል ፈታኝ ጥያቄ ይወረውራሉ ፡፡ በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል ያለውን ልዩነትና ህዝባዊ ጥቅም ፈትፍቶ ማስረዳት የሚችል ፖለቲከኛ ካለ ግን የጎዳናቸውን ‹‹ አዲስነት ›› ማስረዳት ይችላል ፡፡
ለማንኛውም የኢህአዴግ ባለስልጣናት መዝሙሯንና ጥሪዋን እንደ አንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ መመልከት ይኖርባቸዋል ፡፡ ምክንያቱም የተራ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ብዙዎቹ ለጥያቄ ትፈለጋለህ መባላቸው አይቀርም ፡፡ ከእስር በኃላ ደግሞ ‹‹ እንዳያልፉት የለ ! ›› የምትለውን መዝሙር ሊደጋግሟት ግድ ይላቸዋል ፡፡ ምነው ቢሉ – ለመጽናናት ፡፡
እናም ጥሪው ቀጥሏል …
‹‹ የመላኩ ፈንታ ብርጌድ እለፍ ተብለሃል ! ›› ተብሏል ሰሞኑን ፡፡
ይህ ጦር በምክትላቸው በአቶ ገ/ዋህድ ገ/ጊዮርጊስና ልማታዊ በነበሩ ቱጃር ነጋዴዎች የተዋቀረ በመሆኑ የክብደቱን ደረጃ ከፍ ያደርገዋል ፡፡ እንደውም አንዳንድ ነገረኞች በኪሳቸው መደለብ ‹ ቼልሲ › በቅርበታቸው ደግሞ ‹ ፋቲክ ያለበሱ አጋዚዎች › ለማለት እየዳዳቸው ይመስላል ፡፡ ይህ ዜና ከተነገረ በኃላ የተደናገጡ ፣ የተደመሙ ፣ የተደሰቱና እስካሁንም እየሆነ ነገር ባለው ጭፍግ ድራማ እየተዝናኑ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ከኤርትራ ህዝብ ብዛት በሶስት እጥፍ ይበልጣሉ ፡፡
አቶ መላኩ ‹‹ እለፍ ተብለሃል ! ›› ሲባሉ በምላሻቸው የማንን ስልት እንደሚከተሉ ናፋቂ ሁኔታ ፈጥሯል ፡፡ ክሱን አምነው ይቀበላሉ ወይስ በታኮነት ስለሚያገለግለው ፖለቲካና ሌሎች አዳዲስ ጉዳዮች ዘርዘር አድርገው ይነግሩን ይሆን ? አንዳንድ ሚዲያዎች እንደገለጹት በባህርዳሩ ስብሰባ ታክስ የማይከፍሉ በርካታ ‹ ልማታዊ › ካምፓኒዎች መኖራቸውን ጠንከር አድርገው ተችተው ነበር ፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ሾርባው ውስጥ ነጭ ሽንኩርትን የሚወክለው ዝርፊያና ጥቁር አዝሙድን የመሰለው ‹‹ ነገር ›› ተደባልቀው ይገኛሉ ማለት ነው ፡፡
ጸረ ሙስና ኮሚሽን የአቶ መላኩን ብርጌድ አንድ ዓመት ከ 8 ወር በፈጀ ጥናት ነው ገቢ ያደረኳቸው ቢልም ኢኮኖሚስቱ አቶ መላኩም ለመንግስታቸው የማይታመን ገቢ መፍጠራቸውን ልብ ይሏል ፡፡ እንደው ለምሳሌ በሙግታቸው ፣
‹‹ ዘራፍ ! መላኩ !
ስራ ነው አምላኩ
አንድ እንጀራ ልኩ
ሳታውቁት አትንኩ … ›› ብለው ከተነሱ በተያዙበት ጉምሩክ ምን ሰርተው ቆዩ የሚለውን ጥያቄ መመለስ ሊገባን ነው ማለት ነው ፡፡ የኢትዮጽያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በአዲስ መልክ እአአ በ2008 ሲቋቋም በቦታው የተሾሙት በአቶ መለስ ዜናዊ አማካኝነት ነበር ፡፡ መ/ቤቱን በአዲስ አደረጃጀትና አሰራር በአጭር ግዜ በማዋቀር ፣ የታክስ ከፋዩን ቁጥር በማብዛትና አዳዲስ የታክስ ስርዓቶችን ስራ ላይ በማዋል ባስገኙት ለውጥ ተጨብጭቦላቸዋል ፡፡ ሰውየው ቦታውን ከመያዛቸው በፊት የመንግስት ገቢ 19 ቢሊየን ብር ነበር ፡፡ በእሳቸው የስራ ዘመን ማለትም በ2011/12 የፌዴራል መንግስት ገቢ 71 ቢሊየን ብር መድረስ ችሏል ፡፡ አንዳንዶች የቅጣትና የማስገደድ ስርዓትን በመከተላቸው ያገኙት ውጤት ነው እያሉ ቢያሟቸውም የፈጠሩት ለውጥ ግን ትልቅ ሊባል የሚችል ነው ፡፡
የአቶ መላኩ ክስ ሌላ ጦስ ሊያስከትል ይችላል ብለው የሚያስቡ የህብረተሰብም ክፍሎችም ጥቂቶች አይደሉም ፡፡ ምክንያቱም የሃብት ስር በሆነው ቦታ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሲጠቀሙ የነበሩ ባለስልጣናትና ትላልቅ ነጋዴዎች በርካታ በመሆናቸው አንዱ ሌላውን ወደ ጥቁሩ መረብ የማስገባቱ ስራ ሊቀጥል ይችላል በማለት ፡፡ በርግጥ የስነምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን በቅርቡ ከ50 በላይ የሚሆኑ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ነጋዴዎችና ሌሎች ተጠርጣሪ ሰዎችን መያዙን የመግለጹ ጉዳይ እየተነሳ ያለውን ሀሳብ የሚያጠናክር ይመስላል ፡፡
የሰላም፣ ልማትና እድገት ጸር የሆነውን ሙስና በተደራጀ መልኩ መዋጋት ግድ ነው ፡፡ የሚያሳፍረው ግን ባለስልጣናት ለስርዓቱ ታማኝ እስከሆኑ ድረስ ሀገሪቷን ይጋጡ የሚለው ድሃ አስተሳሰብ ነው ፡፡ ብዙዎቹ መንግስትን የሚጠራጠሩትና አብረው ለመስራት ሙሉ ልብ የማይሰጡት ባለስልጣናትን እየቀጣ የሚገኘው በሚያደርሱት በደልና በንጹህ የሌብነት ተግባራቸው አለመሆኑ ነው ፡፡ ከዘራፊነታቸው ይልቅ የፖለቲካ አለመታመናቸው ነው ሚዛን ደፊ ተደርጎ የሚቆጠረው ፡፡
ከ 176 ሀገሮች የ113ኛ ደረጃ በያዘች ሀገር ሙስናን በርካሽ የፖለቲካ ጥቅም ማስታመም ቀስ በቀስ ሀገርን ለመግደል ምቹ ሁኔታ እየፈጠሩ የመጓዝ ያህል የሚያስቆጥር ነው ፡፡ ታዲያስ መጋዚን Global Financial Integrity የተባለ ድርጅትን ጠቅሶ እንደዘገበው ከ 2001 – 2010 ባለው ግዜ ውስጥ በኢትዮጽያ ባለስልጣናትና በተለያዩ ሰዎች ወደ ውጭ የወጣው ገንዘብ 16 . 5 ቢሊየን ዶላር ነው ፡፡ ይህ መረጃ ሊያሳዝነንም ሊያሳፍረንም ይገባል ፡፡ ይህ ሁሉ ሀገራዊ ሀብት ወደ ውጭ የወጣው በላይኞቹ ባለስልጣናት ቀጥተኛ ተሳትፎና የተዘዋወረ ድጋፍ ጭምር መሆኑ መታወቅ አለበት ፡፡
እንግዲህ አደኔን አጠናክሬ እቀጥላለሁ እያለ የሚፎክረው ጸረ ሙስና ኮሚሽን መረቡን በጣም እየተረተረ ባህሩ ውስጥ በጣለ ቁጥር አዞ አይደለም ሻርክን ሊያጠምድ ይችላል ፡፡ ጉዱ የሚፈላው ያኔ ይሆናል ፡፡ ወይ ከሻርኩ ጋር መጋፈጥ አለበት አሊያም መረቡን ለሻርኩ ጥሎ እግሬ አውጪኝ ይላል ፡፡ ይህን የመሰለ አጋጣሚ ከተፈጠረ እንደ ፉከራው በተግባርም ሩቅ ለመጓዝ የሚያስችል መተማመኛ አይገኝም ፡፡
ስለ Back Fire ወይም ተቃራኒ ውጤት ውስን ምሳሌዎችን ልወርውርና ጽሁፌን ልቋጭ ፡፡
. መንግስት አጋጣሚዎችን በመጠቀም ሙሰኞችን የሚሸከምበት ጫንቃ እንደሌለው ለህዝብ ያስረዳል ፡፡ የሙስናው ስር ሄዶ ሄዶ ጭንቅላት ላይ ከደረሰ ግን ክሱ እንዲለዝብ ወይም እንዲሰረዝ ይደረጋል – Back Fire – 1
. ጸረ ሙስና ኮሚሽን አንድ ሰሞን የጀመረው ዘመቻ እንደጋለ እንዲቀጥል ድጋፍ አድርጉልኝ በማለት ለህዝቡ ጥሪ ያቀርባል ፡፡ የጥቆማው ምንጭ ሄዶ ሄዶ ከትልቅ ባለስልጣናት እልፍኝ ዘው ሲል አብሮ መግባት ይከብዳል ፡፡ ውሻው … ፖሊሱ … ንጉስ አይከሰስ የሚለው ብሂሉ… ለቋጥኙ ዘብ ይቆማሉ ፡፡ ጸረ ሙስና በደከመ ትንፋሽ ‹ ጥርስ የሌለኝ አንበሳ ሆኛለሁ › ሲል ይሰማል – Back Fire – 2
. የአቶ መላኩ መ/ቤት ውስጥ ብዙ ሙሰኞች መኖራቸውን ህዝቡ ይጠቁም ነበር ፡፡ ይህን ሃሳብ በመያዝ ይመስላል ሪፖርተር በአንድ ወቅት ከሚ/ሩ ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር ፡፡ ይህ አቤቱታ አውነት ነው ? ሲል ላቀረበው ጥያቄ የሰጡትን ምላሽ እንደወረደ አቅርቤዋለሁ
‹‹ I can not say that our employees do not have problems . For that reason we have put in place special administrative rules . We have applied these rules from hiring to firing . አቶ መላኩም Firing ተደርገዋል … an employee who is unethical and incompetent will have no excuse for coming back . አቶ መላኩም ይቅርታ የማግኘታቸው ጉዳይ የጠበበ ይመስላል … for instance, we have fired fifty employees so far and instituted criminal charges against some of them . አቶ መላኩም ቢያንስ ተጠርጣሪ ወንጀለኛ ተብለዋል … We have managed to have them sentenced up to ten years in prison . አቶ መላኩም በሙግታቸው ካልረቱ በስተቀር ጥቂት የማይባሉ ዓመታትን ወህኒ ቤት ያሳልፋሉ – Back Fire – 3
የተቃራኒው ውጤት / Back Fire / እየበዛ ከሄደስ ? ህዝቡ የነጋሪቱን ጥሪ በሚከተለው መልኩ ለመጎሰም ይገደዳል
‹‹ የኢህአዴግ ፓርቲ ግባ ተብለሃል ! ››


ሸንጎ በአ.አ የተደረገውን ሰልፍ “በሺዎች የተጀመረው እንቅስቃሴ የሚሊዮኖች ይሆናል”አለ

$
0
0

shengo(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) በዛሬው እለት በሰማያዊ ፓርቲ ጠሪነትና በተለያዩ ድርጅቶች ተባባሪነት በአዲስ አበባ ለተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ያለውን አድናቆትና የትግል አጋርነት በድጋሜ እንደሚገልጽ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ። ድርጅቱ ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ “ይህ በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ጎሳ፣ዕድሜ፣ጾታና እምነት ሳይነጥላቸው በአንድ ሆነው የሀገራችንን ህብር በሚያንጸባርቅና በታላቅ ሥነስርዓት የጋለ ስሜታቸውን በይፋ የገለጡበት ህዝባዊ ሠልፍ ፣ በሕዝባችን ላይ የተጫነው የፍርሀት ድባብ እየተሰበረ መምጣቱን የሚያመለከት ታላቅ እርምጃ ነው።” ብሎታል።
“ይህ እጅግ ብዙ ወጣቶችን ያሳተፈ፣ ስሜት ቀስቃሽና ታላቅ ወኔ የታየበት የህዝብ ቁጣ፣ ህዝባችን ለዓመታት የተጫነበትን የግፍ ቀንበር ሊሸከም የሚችልበት ጀርባ እንደሌለው በግልጥ ያሳየበት ቀን ነው።” የሚለው የሸንጎ መግለጫ “ይህ ስላማዊ ሰልፍ የኢትዮጵያ ህዝብ መሰረታዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ እንዲከበር፣ ጎሳ ተኮር የህዝብ ማፈናቀል እንዲያበቃ፣ የኑሮ ውድነት እንዲወገድ፣ በፖለቲካ ጉዳይ በእስር ላይ ያሉ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና ነጻ ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣ የመደራጀት መብት ሙሉ በሙሉ እንዲከበር፣ በየሃይማኖቶች የውስጥ ጉዳይ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት እንዲቆምና የታሰሩት የሙስሊሙ ተወካዮች እንዲፈቱ በመጠየቅ የሀገሪቱን ሕዝብ ብሶት በሚገባ አንፀባርቋል።” ካለ በኋላ “የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) እነዚህና ሌሎች መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎች ባሰቸኳይ እንዲመለሱና ከዚህም አልፎ የአምባገነንነትና የጎጠኛ ስርዓት አክትሞ ህዝብ በምርጫ የራሱን መንግሥት የመመስረት መብቱ እንዲረጋገጥ ለማስቻል ከተለያዩ ኢትዮጵያዊ ሀይሎች ጋር ተባብሮ ትግሉን እንደሚቀጥል አሁንም ያረጋግጣል።” ሲል አቋሙን አስታውቋል።
“በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን፣ ከሀገር ውጭም፣ ዓለምአቀፉ ህብረተሰብ፣ ያለውን ሁኔታ ይበልጥ ተረድቶ፣ በመፍትሄ ፍለጋው አንጻር፣ አወንታዊ ሚና እንዲጫወት፣ ሸንጎው የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል።” ሲል አቋሙን ያጠናከረው ሸንጎ “የተባበረ የህዝብ ትግልን ሊመክት የሚችል ምንም ሀይል የለምና፣ መብታችንን ለማሰከበር ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥል። ዛሬ የተካሄደው ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ፣ ለተከታታይ ሕዝባዊ ንቅናቄዎች በር ከፋች እንጂ መደምደሚያ እንደማይሆን ሸንጎው ይተማመናል።” ብሏል።
ሸንጎው በመግለጫው ማጠናቀቂያ ላይም “ሰላማዊው ትግሉ እንዳይቀጥል የሕወሓት/ኢሕዴግ አሸባሪ አገዛዝ ብዙ ጥረት እንደሚያደርግና ደፍረው በወጡትና ባዘጋጁት ላይም ስበብ እየፈጠረ የሽብር ክንዱን ከመሰንዘር ስለማይመለስ ከወዲሁ ነቅቶ መጠበቅና በጋራ መከላከል የሚቻልበት ዘዴ እንዲፈጠር፣ ተደናግጦና በርግጎም የተጀመረው የነጻነት ጉዞ እንዳይከሽፍና እንዳይቆም ሸንጎ ያሳስባል። ሁሉም ዜጋ የተቻለውን ሁሉ እንዲያደርግም ጥሪ ያደርጋል።” ብሏል።

በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ በገለልተኝነት ያሉ አብያተ ክርስቲያናት እንዲቀላቀሉት ጥሪውን አቀረበ (መግለጫውን ይዘናል)

$
0
0

Holy Sinod Ethiopia
(ዘ-ሐበሻ) በዳላስ ቴክሳስ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ጉባኤውን አድርጎ ያጠናቀቀው በብጹዕ ወ ቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የሚመራው ሕጋዊው ሲኖዶስ ባወጣው ባለ 8 ነጥብ መግለጫው በገለልተኝነት ያሉ አብያተ ክርስቲያናት የቅዱስ ሲኖዶሱን ጥሪ በአንድነት ተቀበለው፤ ለትውልድ የምትተላለፍ አንዲት፣ ቅድስት፣ ሐዋርያዊትና ኩላዊት ቤተክርስቲያንን የሚጠቅም፤ እንዲሁም አገርንና ወገንን የሚጠቅምና የሚያኮራ ሥራ ለመሥራት ቅዱስ ሲኖዶሱን እንዲቀላቀሉ ጥሪውን አቀረበ።

ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የፖለቲካ ኃይል ሽግሽግ ትግል –ቁጥር 01

$
0
0

ግርማ ሞገስ (girmamoges1@gmail.com)
ሰኞ ግንቦት 26 ቀን 2005 ዓ.ም. (Monday, June 3, 2013)

(ግርማ ሞገስ)

(ግርማ ሞገስ)

ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ እሁድ ግንቦት 25 ቀን 2005 ካለምንም እንከን ተጠናቀቀ። አምባገነን መለስ ዜናዊ ከግንቦት 8 ቀን 1997 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በሽብርተኛ ህጎቹ እና ተግባሮቹ የገነባው የፍርሃት ፖለቲካ ህንጻ ፈረሰ። በዚኹ እለት የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኃይሎች ማዕከል በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ መስኮች መፈጸም አለባቸው የሚላቸውን እርማቶች በንግግሮች እና በመፈክሮች በአደባባይ አስታወቀ። እነሱም ከሞላ ጎደል እንደሚከተለው ሊቀርቡ ይችላሉ፥ “መብት መጠየቅ ወንጀል አይደለም፣ ነፃነት እንሻለን፤ ፍትህ እንሻለን፤ አንለያይም፤ የህሊና፣ የሃይማኖት እና ሌሎች ፖለቲከኛ እስረኞች ይፈቱ፤ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄዎች ይመለሱ፤ በአገራችን ሰላም አጣን፤ ልማት እያሉ ሙስና ሰሩ፤ በኑሮ ውድነት የጎበጠው ትከሻችን እረፍት ይሻል፤ ህዝብ ማፈናቀል የዘር ማጥራት ወንጀል ነው፤ ህገ-መንግስት ይከበር፤ የሽብር፣ የነፃ ፕሬስ እና የሲቪክ ድርጅቶች ህጎች ይከለሱ ወይንም ይሰረዙ፤ ኢቲቪ ሌባ፣ ኢቲቪ ውሸት፣ ኢቲቪ ሽብር” የሚሉት ነበሩ።
979885_10200726530979603_470373367_o
መንግስት ለተጠየቀው ጥያቄዎች አዎንታዊ መልሶች መስጠት ይጠበቅበታል። ሁሉም ነገር በእጁ እና በደጁ ስለሆነ አዎንታዊ መልስ ለመስጠት የሚያስቸግረው ምንም ነገር የለም። ዛሬ ብድግ ብሎ “እስከ ዛሬ ድረስ ለፈጸምኩት ጭቆና ይቅርታ ይደረግልኝ። የዜጎችን ነፃነት ከዛሬ ጀምሮ አከብራለሁ። እስረኞችን ነገ እፈታለሁ። በኢትዮጵያ በነፃ ፕሬስ ላይ የጫንኩትን ጭቆና ከዛሬ ጀምሮ አንስቻለሁ። ኢ.ቲቪ እና አዲስ ዘመን ጋዜጣ በአንድ ወር ውስጥ ከመንግስት ፖለቲካ ነፃ ሆነው እንዲደራጁ አደርጋለሁ። ህዝብ ማፈናቀል በኢትዮጵያ ዳግም አልፈጽምም። የተፈናቀሉትም ካሳ ተከፍሏቸው እና ህጋዊ ዋስትና ተስጥቷቸው ወደቀድሞ ኑሮዋቸው እንዲመለሱ በአንድ ወር ውስጥ እፈጽማለሁ። አፈናቃዮችን ፍርድ ቤት አቀርባለሁ። ሁሉም በሙስና የሚታሙ ባለስልጣኖች አዜብ መስፍን ሳትቀር ክትትል እንዲደርግባቸው አደርጋለሁ። አንድን ሙሰኛ ከሌላ ሙሰኛ ሳላበላልጥ ሁሉም ሙሰኞች ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ አደርጋለሁ። በዚህም በዚያም እያልኩ በየውሩ ከደሞዛችሁ እምቆርጠውን ከዚህ ወር ጀምሮ በማቆም የኑሮ ውድነት ያጎበጠው ትከሻችሁ እንዲያገግም አደርጋለሁ። ህገ-መንግስት አከብራለሁ።”

በስልጣን ላይ ያለው አምባገነን መንግስት ከፍ ብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ከፊሉን ያህል በማድረግ እንኳን ከአምባገነንነት ወደ ተሻለ የፖለቲካ ኃይል ሽግሽግ (Political Power Shift) ሊያደርግ ይችላል። ይኽን በማድረግ የነፃነት እና የዲሞክራሲ አድማሶች እንዲሰፋ ያደርጋል። በምላሹ የህዝብ ድጋፍ ሊያገኝ ይችላል። የህዝብ ድጋፍ ማግኘት ማለት ደግሞ የፖለቲካ ድጋፍ ማገኘት ማለት ነው። እነዚህን እርምጃዎች በመውሰድ መንግስት ከተቃዋሚ ዲሞክራሲ ኃይሎች ጋር የፖለቲካ ስልጣን ሽግሽግ ያደርጋል ማለት ነው። ይኽን በማድረግ መንግስት የሚያጣው ነገር ቢኖር አምባገነንነትን ብቻ ነው። ምርጫው የእርሱ ነው። በታሪክ ግን አምባገነኖች ካልተገደዱ በስተቀር በፈቃዳቸው የፖለቲካ ስልጣን ሽግሽግ ያደረጉበት ጊዜ ስለመኖሩ ተጽፎ ያየሁት መረጃ የለኝም።

መንግስት ከፍ ብለው ለተዘረዘሩት ጥያቄዎች አዎንታዊ ምላሽ ካልሰጠ በአምባገነንነት መቀጠል መርጧል ማለት ነው። እሱም ቢሆን ችግር አይሆንም ለዲሞክራሲ ሰራዊት። የዲሞክራሲ ሰራዊት በሰላማዊ ትግሉ የዲሞክራሲ ማዕከሉን መሰረት እና አቅም ያጎለምሳል። ይኽን ማድረግ እንደሚቻል ታሪክ ትመሰክራለች። ይሁን እንጂ መንግስት አምባገነንነትን ከመረጠ ስትራተጂካዊ የፖለቲካ ስህተት መፈጸሙን ልብ ሊል ይገባል። ነፃ ምክር ነው!

ሲጠቃለል፥ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓመተ ምህረት በኢትዮጵያ ሁለት የፖለቲካ ማዕከሎች እንዳሉ እና በመካከላቸው ሰላማዊ ትግል እንደሚካሄድ አሳይታናለች። የዲሞክራሲ ኃይሎች የሚያደርጉት የፖለቲካ ኃይል ሽግሽግ (Political Power Shift) ትግል በስልጣን ላይ ከሚገኘው አምባገነን መንግስት አንፃር የፖለቲካ መሰረታቸውን እና አቅማቸውን ሳያቋርጥ ሽቅብ ማሳደግ አለበት። በውጤቱም የፖለቲካ ኃይል ደረጃቸው ቀስ በቀስ ከበታችነት ወደ አቻነት ከዚያም ወደ በላይነት ደረጃ ይጓዛል። የበላይነት ደረጃ መያዝ ማለት የኢትዮጵያን ህዝብ የመንግስት ስልጣን ባለቤት ማድረግ ማለት ነው። መንገዱ ደግሞ ምርጫ ወይንም ግብጽ ሊሆን ይችላል።

የፖለቲካ ኃይል ሽግሽግ ትግል ሌላ ቁልፍ የሰላማዊ ትግል ጽንሰ አሳብ ነው። አፈጻጸሙን በስፋት ማወቅ ጠቃሚ ነው የተሳካ ሰላማዊ ትግል ለማድረግ። የሽግሽግ ትግልንም ከበካዮች (Contaminants) መጠበቅ ያስፈልጋል።

Golgul/ጎልጉል በፌስ ቡካችሁም (https://www.facebook.com/goolgule) ላይ በማቅረባችሁ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው። አሁንም ቀጥሉበት። ዘሃበሻም እንደዚሁ። የረጅም ጊዜ የሰላማዊ ትግል ጉዋደኛዬ አብርሃ (ኢትዮሚዲያ) ምስጋናዬን ተቀበለኝ። እንዲሁም ቋጠሮ፣ ኢትዮጵያ ዛሬ፣ አቡጊዳ፣ አሲምባ፣ ECADFORM እና ያላየሁዋችሁ ድረገጾች በሙሉ ለምትለግሱኝ ትብብር ምስጋናዬ ገደብ የለውም። ትግሉ የጋራ ቢሆንም!

ዶ/ር በያን አሶባ ለግልጽ ደብዳቤዬ ለሰጡት ምላሽ መልስ –ከዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ

$
0
0

ዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ

ዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ

ውድ ዶ/ር በያን አሶባ

በቅርቡ ለጻፍኩልዎት ግልጽ ደብዳቤ የከተቡልኝን አጻፋ በኢትዮሚዲያ ድህረ ገጽ አስፍረው ዐየሁት። የደብዳቤዎን ርዕስ እንደአጤንኩት “እኚህ ሰው በጣም ትልቅ ናቸው፤ ቢዘገዩም መልስ ሰጡኝ። እንግዲህ ስለሕዝባችን እጣ ፈንታ በቁምነገር ሊያነጋግሩኝ ነው” በማለት አክብሬዎት ነበር። ወደ ውስጥ ዘልቄ ሳስተውለው ግን ለካስ እርስዎ የሕዝባችንን ሕይወት የሚነካውን አንገብጋቢ ቁምነገር ወደ ጎን ትተው የእርስዎን እና የእኔን ስሞች አንስተው እየሰነጣጠቁ ኖሯል የከተቡልኝ።

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Hiber Redio: ግብጽ እውን በአባይ ጉዳይ በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ታነሳለች? (ወቅታዊ ዘገባ)

$
0
0

የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ግንቦት 25 ቀን 2005 ፕሮግራም

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

> አቶ ተካበ ዘውዴ
- የፌዴሬሽኑ የውድድር አስተባባሪና የቀድሞ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ
- በቬጋስ ከስራ ማቆም አድማ እስከ እስር የኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ታክሲ አሽከርካሪዎች መብት ትግል
- ግብጽ እውን በአባይ ጉዳይ በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ታነሳለች? (ወቅታዊ ዘገባ)
- ሙስናው ምነው ገቢዎች ላይ ብቻ ቆመ? ዋናዎቹስ? (ትንታኔ አለን)
ሌሎች ቃለ መጠይቆችም አሉን

ዜናዎቻችን:-
- ሕዝቡ ፍርሃትን አሸንፎ ለሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ ምሬቱን መግለጹ ብዙዎችን አስገርሟል
* ሰማያዊ ፓርቲ ከሁለት ወር በፊት ለግራዚያኒ ሰልፍ ሲጠራ አመራሮቹ መታሰራቸው ይታወሳል
- የኢትዮጵያውያን ሰሜን አሜሪካ ፌዴሬሽን አመራሮች በቬጋስ ተጫዋቾች ሊከሰሱ ነው
- ፌዴሬሽኑ ተጫዋቾች አይወክለንም ባሉት ግለሰብ ስር ተመዝግበው እንዲመጡ ውሳኔ ወስኗል
- ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ብትፈጽም የከፋ ኪሳራ እንደሚጠበቃት የእገሪቱ ከፍተኛ ጄነራል አስጠነቀቁ
- በኢትዮጵያ ውስጥ መሬት የተቀራመቱ ባእዳን ባለሃብቶች ከአገዛዙ ጋር ሆድ እና ጀርባ እየሆኑ ናቸው ተባለ ኢሃዲግ እርምጃ እስውዳለሁ ሲል ዝቷል
- ሟቹ መለስ ዜናዊ የ3ቢሌዮን ዶላር ባለቤት መሆናቸው ዛሬም እያነጋገረ ነው

ሌሎችም ዜናዎች አሉን:-

Sport: ብራዚላዊው አጥቂ ኔማር ባርሴሎና ገባ

$
0
0

Neymar-Barcelona

Neymar: Barcelona complete £49m signing of Brazil striker

ብራዜላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኔማር ለስፔኑ ሃያሉ ክለብ ባርሴሎና ለመጫወት በ48.6ሚሊዮን ኢሮ ከቀድሞው ክለቡ ሳንቶስ ተዘዋውሯል፡፡
የ21 ዓመቱ ብራዚላዊው ኔማር በባርሴሎና ለ5ዓመት ለመቆየት ተስማምቷል፡፡ ኔማር በሳኦ ፖሎ ቆይታው 229 ጭዋታ አድርጎ 138 ጎሎችን አስቆጥሯል፡፡ ለሀገሩ ብራዚልም በተሰለፈባቸው 33 ጭዋታዎች 20 ጎሎችን በስሙ አስቆጥሯል፡፡
ኔማር በአምስት ዓመት የባርሴሎና ቆይታ 190 ሚሊዮን ዩሮ ያገኛል፡፡ ኔማር ኑካንብ እስከሚደርስ ድረስ ለሳንቶስና የባለቤትነት መብት ላላቸው ሶስት ካንፓኒዎች 57ሚሊዮን ዩሮ ወጥቶበታል፡፡
ኔማርን ለማስፈረም የወጣው ወጪ ውድ መሆኑ ሌሎች ክለቦች የኔማር ፈላጊ ሆነው በመገኘታቸው ነው ብለዋል የባሴሎና ምክትል ፐሬዘዳንት ጆሴፕ ባርቶሚዩ፡፡
በተመሳሳይ ዜና ማንችስተር ሲቲ በሲቪያ የክንፍ ተጨዋች የሆነውን ጀሰስ ናባስን በ17 ሚሊዮን ዩሮ ለማዘዋወር ሁለቱ ክለቦች መስማማታቸውን የሲቪያ ድረ -ገፅ አረጋግጧል፡፡ የ27 ዓመቱ ናቫስ እ.ኤ.አ በ2010 በተካሄደው የአለም ዋንጫ የውጤታማው የስፔን የእግር ኳስ ቡድን አባል መሆኑ ይታወሳል፡፡

ሁመራን የብሄር ግጭትና የኤርትራ ታጣቂዎች አመሷት

$
0
0

(ሁመራ ከተማ)

(ሁመራ ከተማ)


(ፍኖተ ነፃነት) በምዕራብ ሁመራ ማይካራ መቻች በተከሰተ የብሔር ግጭት የሰዎች ህይወት ጠፋ፤ መንግስት ግጭቱን ለማስቆም የወሰደው እርምጃ አለመኖሩ በአካባቢው ተከታታይ ግጭቶች ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት መፍጠሩን የአካባቢው ምንጮች ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡
ሱዳን ጠረፍ ላይ ቅዳሜ ግንቦት24 ቀን 2005 ዓ.ም በብሄር ምክንያት የተቀሰቀሰው ይኸው ግጭት በሁለት ቀናት ውስጥ የ12 ሰዎችን ህይወት መቅጠፉንፉን የፍኖተ ነጻነት ምንጮች ጨምረው ገለፀዋል፡፡ በኢትዮጵያና ሱዳን ጠረፍ አካባቢ በምትገኘው መቻች በረሃ በቀን ራያ የተሰማሩ ሰዎች በብሄር እየተቧደኑ መገዳደል ከጀመሩ ሶስት አመታት ማስቆጠራቸውን ያስታወሱት ምንጮቻችን መንግስት ችግሩን መፍታት ምንም አይነት ሚና ለመጫወት አለመፍቀዱ የሟቾቹንና የተጎጂዎቹን ቁጥር እንዲያሻቅብ አድርጓል፡፡
ሰራተኞቹ በወሎ፣በጎጃም፣በጎንደርና በራያ ተወላጅነት ተቧድነው በካራ፣በዱላና በእሳት በፈጠሩት ግጭት የሰው ህይወት ተቀጥፏል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው አካባቢውን ጠሚያውቁ አስተያየት ሰጪዎች “መንግስት በኢትዮጵያ የብሄር ጥያቄ ተመልሷል በማለት የብሄር ብሄረሰቦችን በዓል በሚያከብርበት ወቅት በጎሳ ፖለቲካ እንዲህ አይነት ዘግኛኝ ድርጊቶች እየተፈጠሩ የሰው ህይወት መብላታቸው ጥያቄዎቹ በተገቢው መንገድ ላለመመለሳቸው ማሳያ ይሆናል” ብለዋል፡፡
በተያያዘ ዜና በዚሁ በሁመራ በረከት ወረዳ ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ለመዝረፍ የሚሞክሩ ሽምቅ ተዋጊዎች በተለያዩ ጊዜያት ድንገተኛ ወረራ በማድረግ የአካባቢውን ነዋሪዎች ሲያስጨንቁ እንደነበር የጠቀሱት ምንጮቻችን በቅርቡ ታጣቂዎቹ አካባቢውን ከሚጠብቁ ሚልሺያዎች ጋር ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ በሁለቱም ወገን ህይወት መጥፋቱን አጋልጠዋል፡፡ በተደጋሚ የማያባራ የተኩስ ልውውጥ መስማት በአካባቢው የተለመደ እንደሆነም የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጨምረው ገልፀዋል፡፡
በሁመራ ስለተከሰተው የግጭት ለማጣራት የአካባቢውን ባለስልጣናትና የፖሊስ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡


ለአርቲስት አበበ መለሰ ገቢ ማሰባሰቢያ 9 ዘፋኞች በአ.አ የሙዚቃ ኮንሰርት አዘጋጁ፤ ኤፍሬም ታምሩ?

$
0
0

abebe melese(ዘ-ሐበሻ) ለዜማና ግጥም ደራሲው አበበ መለስ መርጃ የሚውል ታላቅ የሙዚቃ ድግስ በአዲስ አበባ እንደተዘጋጀ ታወቀ። በዚህ ሰኔ 8 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይደረጋል በተባለው ኮንሰርት ላይ 9 ዘፋኞች ለአርቲስቱ መርጃ በሚውለው ኮንሰርት ላይ በነፃ ለመሥራት ቃል ሲገቡ ኤፍሬም ታምሩ ግን ተጠይቆ ፈቃደኛ ሳይሆን መቅረቱን ከአስተባባሪዎቹ አካባቢ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመልክቷል።
እንደ ደረሰን መረጃ ከሆነ ለአርቲስት አበበ መለሰ መረጃ፦
1ኛ. ቴዎድሮስ ካሳሆን (ቴዲ አፍሮ)
2ኛ. ግርማ ተፈራ
3ኛ. ሀመልማል አባተ
4ኛ. ፀሐዬ ዮሐንስ
5ኛ. ማዲንጎ አፈወርቅ
6ኛ. ጸጋዬ እሸቱ
7ኛ. ሃይልዬ ታደሰ
8ኛ. ዳዊት መለስ ሥራዎቻቸውን ለማቅረብ ፈቃደኛ ሲሆኑ ድምጻዊ ኤፍሬም ታምሩ ግን በኮንሰርቱ ላይ እንደማይገኝ ተናግሯል። ለኤፍሬም ታምሩ በርከት ያሉ ዜማዎችን መስጠቱን የሚያስታውሱት አስተያየት ሰጪዎች አሁን ይህ ዝነኛ ሰው የሰው እጅ ለማየት በተገደደት ወቅት ኤፍሬም ፊቱን ማዞሩ ብዙዎችን እያነጋገረ መሆኑን ከአዲስ አበባ የመጣው መረጃ ያመለክታል። በዚህ ጉዳይ ድምጻዊ ኤፍሬም ታምሩን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

አበበ መለሰ እስራኤል ሃገር ከሚገኝ አንድ ቲቪ ጋር በቅርቡ ያደረገውን ቃለ ምልልስ ይመልከቱ።

ቆስቁሱት ይጋጋም የአብዮቱን እሳት (ወቅታዊ ግጥም ለግንቦት 25ቱ ሰልፍ)

$
0
0

Breaking News: ሲኖዶሱ አቡነ ፊልጶስን በአቡነ ማቴዎስ፤ አቡነ ሕዝቅኤልን በአቡነ ሉቃስ ተካ

$
0
0
አቡነ ሉቃስ

አቡነ ሉቃስ

(ዘ-ሐበሻ) አዲስ አበባ የሚገኘው ሲኖዶስ በዛሬው የ5ኛ ቀን ጉባኤው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅን እና የቅዱስ ሲኖዶሱን ዋናጸሐፊዎች ምርጫ አካሄደ።  

ሲኖዶሱ በዛሬው የ5ኛ ቀን ጉባኤው ከዚህ ቀደም ለ3 ዓመታት አቡነ ሕዝቅኤል ይዘውት የነበረውን ሥልጣን የሰቲት ሁመራው ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሉቃስ ተክተው እንዲሰሩ እንደመረጣቸው የዘ-ሐበሻ ምንጮች አረጋግጠዋል። በሌላ በኩልም አቡነ ፊሊጶስ ይዘውት የነበረውን መንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅነቱን ሥልጣን ደግሞ  የወላይታ ዳውሮ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ እንዲይዙት መርጧል።

አቡነ ማቴዎስ

አቡነ ማቴዎስ

አቡነ ማቴዎስ ለ6ኛው የፓትርያርክነት ተወዳድረው ‘ተሸንፈዋል’ በሚል ቢነገርም መንግስት አቡነ ማትያስን ከ እየሩሳሌም አምጥቶ መሾሙን የሚያምኑ አስተያየት ሰጪዎች አቡነ ማቴዎስ በምርጫ ተሸንፈዋል ብለው እንደማያምኑ በተለያየ አጋጣሚ አስተያየታቸውን መስጠታቸው ይታወሳል።

አቡነ ፊሊጶስ

አቡነ ፊሊጶስ

ለፓትርያርክነት ምርጫ ተወዳድረው እንደነበር የሚታወሱት  አቡነ ሉቃስ ጋራ ለቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊነት በዕጩነት የቀረቡት ጳጳሳት አቡነ ሔኖክ እና አቡነ ዲዮስቆሮስ መሆናቸውን የሚናገሩት የዘ-ሐበሻ ምንጮች  አቡነ ሉቃስ ከፍተኛ ድምፅ አግኝተው በመመረጣቸው ለቀጣዩ ሦስት ዓመታት ቅ/ሲኖዶሱን በዋና ጸሐፊነት እንዲያገለግሉ መመረጣቸውን አስታወዋል።

አቡነ እሕዝቄል

አቡነ ሕዝቅኤል

አቡነ ማቴዎስ የተወለዱት ምንጃር፣ አቡነ ሉቃስ ደግሞ ትግራይ ተምቤን የተወለዱ አባቶች ናቸው።

እየተካሄደ ባለው የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ አስተያየት እንዲሰጡን የጠየቅናቸው አንድ የሃይማኖት አባት “ሲኖዶሱ ከዚህ ቀደም የትግራይ አርቲስቶች በመኪና አደጋ ሲሞቱ ታቦት ተሸክመው በመሄድ ለአርቲስቶቹ ፍትሃት እንዳደረጉት ሁሉ፤ በባህርዳር ከተማ ይህ ሁሉ ሰው በጥይትና በተፈጥሮ አደጋ ሲሞት ተመሳሳይ ነገር አልተደረገም። ይልቁንም አንዳችም  መግለጫ አለማውጣቱና አለመወያየቱ፤ የዋልድባ ጉዳይን አልማንሳቱ በጣም የሚያስተዛዝብ ነው” ብለውናል።  እኚሁ አባት ጨምረውም “አዲስ አበባ ያሉት አባቶች ስለሙስና ትኩረት ሰጥተው መወያየታቸው የሚያሳየው ቤተክርስቲያን ምን ያህል እየተመዘበረች እንዳለች ነው። አሁንም እነዚህ አባቶች በሙስና ጉዳይ ላይ የሚነጋገሩት እከሌ ከኔ የተሻለ ሰርቋልና እኔም እንዴት ልሰርቅ እችላለሁ በሚል ነው እንጂ እውነት ሙስናን ከቤተክርስቲያኒቱ ለማጠፋት ቁርጠኝነት ኖሮ አይደለም” ሲሉ አሰታየታቸውን አጠናቀዋል።

የጎሕ መንፈስ (በየነ ሞገስ)

$
0
0

የጎሕ መንፈስ
(በየነ ሞገስ)
Rainbow-Spiritየዕለቱ ውሎዬ አድካሚ ሆኖ ነው ያለፈው፡፡ ጉዳይ ለመከታተል በየመስሪያ ቤቱ መሄድ፤ የማኅበራዊ
ግዴታዎችን መወጣት፤ እንዲሁም ለማተሚያ ቤት የሰጠሁትን ኅትመት የመጨረሻ ይዘቱን ተመልክቶ
ማረምን የሚያካትት ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ተዳምሮ ወደ ምሽት ላይ እቤቴ እንደገባሁ ወደ መኝታዬ ለመሄድ
ብዙ ጊዜ አልወሰደብኝም፡፡ ትንሽ የማጋነን ስሜት ቢኖርበትም እንቅልፍ የወሰደኝ አንገቴ ትራሱን ሳይነካ
ነበር፡፡ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ – - -ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ለአንዳንድ ጥያቄዎች መልስ (ከፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)

$
0
0

ከፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

ግንቦት 2005

Pro Mesfinበጽሑፎቹ ላይ የቀረቡት አስተያየቶች በመሠረቱ ሁለት ዓይነት ናቸው፤ አንዳንዶቹ እንደምክር ያለ ነገር፣ አንዳንዶቹ ጽሑፎቹን መውደዳቸውን ወይም አለመውደዳቸውን በመግለጽ ጽፈዋል፤ በነዚህ ላይ ምንም አስተያየት የለኝም፤ መውደድም ሆነ መጥላት፣ መንቀፍም ሆነ ለወደፊት የምሻሻልበትን ምክር መስጠት መብታቸው ነው፤ በግድ እኛ የምንልህን ተቀበል ሲሉኝ ከመብታቸው ያልፋሉ፤ ቢሆንም መልስ አያስፈልጋቸውም።

ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች ወደፍሬ-ነገሩ ውስጥ ገብተው ለመሞገት ይሞክራሉ፤ ግልጽ የሆነ የሁነት ግድፈት ሲያገኙ ቢያመለክቱኝ በደስታና በምስጋና እቀበላቸዋለሁ፤ ሁነቱ ለእነሱ በሚጥም መንገድ ባለመገለጹ ወይም ሁነቱን እነሱ የሚወዱት ባለመሆኑ ሙግት ውስጥ የሚገቡ ሲሆን የማይጠቅም መሆኑን ስለተረዳሁ አንድ ዘዴ አቀረብሁ፤ ሁነቱ እኔ ከገለጽሁት ውጭ ሆኖ ከተገኘ አምስት መቶ ብር እከፍላለሁ ብዬ ጻፍሁ፤ እስከዛሬ ብሩን የጠየቀኝ የለም፤ ሊሞግተኝ የሞከረውም አዋቂ ነኝ-ባይ ከዝምታ አልወጣም፤ ፍሬ-ነገሩ ሙግት የሚያቀርቡ ሰዎች ሁለት ዓይነት ይመስሉኛል፤ በቅን መንፈስ በውይይቱ ላይ አስተዋጽኦ ለማድረግ የሚፈልጉ አሉ፤ ሌሎች ደግሞ ሌላ ሰው ሲጽፍ እየጠበቁ ‹‹እኛ የተሻለ አለን›› እያሉ የሚጮሁ አሉ፤ ዓላማቸው ውይይቱን ለማዳበር ሳይሆን ራሳቸውን አብጧል ከሚሉት ሰው እኩል ማሳበጥ ቢቻልም መብለጥ ነው፤ በራሳቸውም ሆነ በሀሳባቸው እምነት ስለሌላቸው የሚናገሩት ራሳቸውን በመቃብር ውስጥ ከትተው ነው፤ በመቃብር ቤት ውስጥ ማበጥ ለምስጦች እንደሆን እንጂ ለሌሎች ‹‹የጭቃ እሾህ›› የሚል ስያሜን ከማትረፍ አያልፍም።

በተከታታይ በቀረቡት ጽሑፎች ላይ ሁለት አንባቢዎች በተቸገሩባቸው ሀሳቦች ላይ አስተያየቴን ልስጥ፤ በመጀመሪያ አርበኛና ባንዳ የሚባሉትን ቃላት የማይወዳቸው አንባቢ ችግሩ አልገባኝም፤ ስገምተው ከቅን መንፈስና ከኢትዮጵያዊ ይሉኝታ ጋር የተያያዘ ይመስለኛል፤ አርበኞችና ባንዶች መኖራቸውን የካደ አይመስለኝም፤ አርበኞች ነበሩ፤ አሁንም አሉ፤ ባንዶችም ነበሩ፤ አሁንም አሉ፤ አርበኛም የለም፤ ባንዳም የለም ለማለት አልችልም፤ ባንዳነት ሲነሣ ኅሊናቸውን የሚቆረቁራቸውና የሚያፍሩ ባንዳዎችና የባንዳ ልጆች ከአሉ፣ ይቆርቁራቸው፤ ይፈሩ፤ የሚያሳፍር ሥራ ውጤት ነው፤ አርበኝነት ሲነሣ ልባቸው የሚያብጥና የሚኮሩ ካሉ፣ ይበጡ፤ ይኩሩ፤ የሚያኮራ ሥራ ውጤት ነው፤  ምንድን ነው ስሕተቱ? የታሪካችን መክሸፍ አንዱ ምክንያት በይሉኝታ ዓይኖችን ሸፍኖ ፍሬውንና አንክርዳዱን ለመለየት አለመፈለግ ነው፤ (በአሥራ ዘጠኝ መቶ አርባዎቹ አጋማሽ ላይ በጾም ጊዜ በምግብ ቤቶች የሚቀርብ የፍስክ ወጥ ነበረ፤ ሽፍንፍን ይባል ነበር፤ ሳይጾሙ የሚጾሙ መስሎ ለመታየት፤) እንክርዳዱንና ፍሬውን እኩል አድርጎ ለማየትና ለማሳየት መፈለግ ነው፤ የኢትዮጵያ አርበኞች ታሪክ ተዳፍኖ የቀረው በአጼ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ውስጥ ባንዶች ተሰግስገውበት ስለነበረ ነው፤ በዚህም ምክንያት ፍሬና እንክርዳዱ ሳይለይ አንዱ ትውልድ ለሚቀጥለው ትውልድ እያስተላለፈ መማርና መሻሻል ያቅተናል፤ አንባቢው ይህንን ይመኛል ብዬ አልገምትም፤ እውነትን የሚገፋ፣ እውነትን የሚያደበዝዝ፣ እውነትን የሚያጨልም ነገር ሁሉ በአገርም ሆነ በግለሰብ ደረጃ መጨረሻው ገደል ነው።

ሁለተኛው ምንም አንኳን በጎ ፈቃድ ከሌለው ሰው የተሰነዘረ ቢሆንም ሌሎችን ሰዎች ሆን ተብሎ ከሚረጨው መርዝ ለመጠበቅ ባጭሩ በአንድ ሀሳብ ላይ ብቻ የሰውዬውን ጤናማ ያልሆነ ዓላማ ላሳይለት፤— እኔ የሚከተለውን ጻፍሁ፤–

የኢሳት መክሸፍ የኢትዮጵያውያንን ተስፋ ያጨልማል፤ አንፈራጥጠው ከላይ ቤት እታች ቤት እየቀላወጡአካላቸውን፣ አእምሮአቸውንና መንፈሳቸውን የሚያባልጉ ሰዎችን ያበራክታል፤ የድብቅብቆሽ ዓለምን እየፈጠሩየጠራውን ከደፈረሰው፣ የጸዳውን ከአደፈው፣ ሳይለዩ ለሚያወሩት ደካሞች ሜዳውን ያሰፋላቸዋል፤የወያኔ/ኢሕአዴግን ፍርሃት ወደመርበድበድ ይለውጠዋል፤ የጦርነት ጥሩምባ ለሚነፉትም ሜዳውን እያሳየ  የቀረርቶበር ይከፍትላቸዋል፤ ይህ ሁሉ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላምንና ስምምነትን፣ እድገትንና ብልጽግናን፣ ኩራትንና ክብርንአያስገኝም።

በነዚህ አምስት መስመሮች ላይ የሰፈረው ሀሳብ አስቸጋሪ አይደለም፤ ማንበብና መጻፍ እችላለሁ ለሚል ሰው ቀላል ነው፤ ዋናውና መሪው ሀሳብ የኢሳት መክሸፍ የኢትዮጵያውያንን ተስፋ ያጨልማል፤ የሚለው ነው፤ አራት የሚሆኑ አጫፋሪ ሀሳቦች ተከታትለው ቀርበዋል፤ የኔን ጽሑፍ ሲያነብ አንጎሉ እያጠናገረ የሚመዘግብለት ሰው ሲጽፍም አንጎሉ አጠናግሮ የመዘገበለትን ስለሚያቀርብለት የተወላገደ መደምደሚያ ላይ ይደርስና ያንኑ ለሌሎች አዋቂ መስሎ ያስተላልፋል፤ ላንዳንዶች ሰዎች ይህ አገላለጼ የከረረ ይመስላቸው ይሆናል፤ በአውነት ይህ አገላለጽ ከበጎ መንፈስ የመነጨ ነው፤ በጎ መንፈስ የሌለበት አገላለጽ ብመርጥ የበለጠ የሚያስከፋ ይሆን ነበር፤ የእውነት ውበት የሚታየው ጨለማውን ሲገልጠው ነው፤ አንዱ አስተያየት ሰጪ እንዳለው ‹‹የጭቃ እሾሁን›› ማየት መቻል ነው፤ እንግዲህ ከላይ የተጻፈውን ሰውዬው እንዴት አወላግዶ እንደተገነዘበውና እንዴት አወላግዶ እንዳወጣው እዩት፤ –

“የኢሳት መክሸፍ የኢትዮጵያውያንን ተስፋ ያጨልማል፤ ………………………………የጦርነት ጥሩምባ ለሚነፉትም ሜዳውን እያሳየ የቀረርቶ በር ይከፍትላቸዋል፤ ይህ ሁሉ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላምንና ስምምነትን፣ እድገትንና ብልጽግናን፣ ኩራትንና ክብርን አያስገኝም። ”እኔም ‹ለሃገራችን ችግር መፍትሄው አንድ መንገድ (የእርሶ መንገድ) ብቻ አይደለም› ያልኩት ኢሳት ነጻ ሚዲያ እንዲሆን የምንሻ ከሆነ ከመርህ አኳያ ሁሉንም በእኩል መድረክ መስጠት እንዳለበት ለመግለጽ ፈልጌ ነው፡፡ ከተሳሳትኩ ለመታረም ዝግጁ ነኝ።››

እግዚአብሔር ያሳያችሁ! ከላይ በትክክል የጠቀስሁትና ይህ ተቆራርጦና ተወላግዶ የቀረበው አንድ ናቸው? እኔ ከጻፍሁትስ እንዴት ብሎ ከውልግድግዱ የተሰጠው መደምደሚያ ሊወጣ ይችላል? ‹‹የጭቃ እሾህ›› ለምን ይጠቅማል? ለማን ይጠቅማል? በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ለኢትዮጵያ ችግር መፍትሔው አንድ መንገድ ብቻ ነው (የኔ ብቻ) ያልሁት የት ነው? ተከታታይ ጽሑፎቹን ሁሉ ያነበበ ሁሉ የተለያዩ አመለካከቶች በእኩልነት ይስተናገዱ የሚል እንደሆነ ከዚህ ሰው በቀር የተረዳው ይመስለኛል።

‹‹ከተሳሳትሁ ለመታረም ዝግጁ ነኝ›› የምትለዋ አስቂኝ ነች!  የተሞከረው ማታለል አልሠራ ሲል ወደሌላ ማታለል! አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት መች ይሰማል!

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live