Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

Breaking News: የቀድሞው የኦነግ መሪ ዶ/ር ዲማ ነገዎ ኢትዮጵያ ገቡ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ዶክተር ዲማ ነገዎ አዲስ አበባ መግባታቸውን የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች አረጋገጡ::

የኦነግ መስራቾችና አንጋፋ መሪዎች፣ እነ ዶ/ር ዲማ ነግዎ፣ አቶ ሌንጮ ለታ የመሳሰሉት፣ የኦሮሞ ጥያቄ የመገንጠል ሳይሆን የዴሞክራሲ ጥያቄ ነዉ በሚል፣ ራሳቸውን ከኦነግ አግልለው፣ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፎረም (ኦዴፍ) የሚባል ድርጅት ማቋቋማቸውን ዘ-ሐበሻ በተደጋጋሚ መግለጹዋ ይታወሳል::

የቀድሞው የኦነግ መሪ ዶ/ር ዲማ ነገዎ

የቀድሞው የኦነግ መሪ ዶ/ር ዲማ ነገዎ


ዘንድሮ በሚደረገው የኢትዮጵያ ምርጫ ላይ ለመሳተፍና ድርጅቱንም በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ለማስመዝገብ ወደ አዲስ አበባ እንዳቀኑ የገለጹት የዘ-ሐበሻ ምንጮች ጉዳዩ ብዙዎችን ማስገረሙን ገልጸዋል::

በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ አማካኝነት በተለይ በሚኒሶታ የቀድሞ የኦነግ መሪዎችን ለማግባባት ከፍተኛ ሥራ ይሰራ እንደነበር ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም በፎቶ ግራፍ በተደገፈ ማስረጃ ስትዘግብ የቆየች ሲሆን በዶ/ር ዲማ ነገዎና በኦቦ ሌንጮ ለታ የሚመራው ኦዴፍ ለኦሮሞ ሕዝብ አዲስ የትግል ራዕይ አለኝ በሚል ሃገር ቤት ገብቶ ለመታገል መወሰኑንና ከዚህ በኋላም የኦሮሞ ሕዝብ ስለመገንጠል ሳይሆን በአንድነት ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር የሚኖርበትን መንገድ ፈጥሮ ለመታገል መወሰኑን መግለጹ ይታወሳል::

በቀጣዩ ዲሴምበር ወር አካባቢ አቶ ሌንጮ ወደ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ በሰፊው ሲወራ የቆየ ቢሆንም ምክትላቸው ዶ/ር ዲማ ነገዎ አዲስ አበባ ቀድመው ገብተው ድርጅቱን በኢትዮጵያ ለማስመዝገብ እየተሯሯጡ ይገኛሉ ያሉት የዘ-ሐበሻ ምንጮች ኦዲኤፍ በቀጣዩ ምርጫ እንደሚወዳደርም ጠቁመዋል::

ዶ/ር ዲማ ነገዎ በሽግግር መንግስት ወቅት በማስታወቂያ ሚ/ርነት ያገለገሉ መሆናቸው ይታወሳል::

ይህን ተከትሎ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች በሚኒሶታ አካባቢ የሚገኙ ፖለቲከኞችን ያነጋገሩ ሲሆን የዶ/ር ዲማ ነገዎ አዲስ አበባ መግባትና የኦዲኤፍ በምርጫ መሳተፍ በገደል አፋፍ ላይ የነበረውን የወያኔ/ኢሕ አዴግ መንግስት ነብስ ይዘራበታል ሲሉ ይህን ውሳኔ ይተቻሉ:: እነዚሁ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉትም ኢሕ አዲኤግን በኃይል ለመጣል የመጨረሻው ሰዓት ላይ የደረሰ ቢሆንም የአቶ ሌንጮና የዶክተር ዲማ ኦዲኤፍ ኢትዮጵያ መግባት ኢሕ አዴግ ለሚፈልገው ና በምርጫ ስም ለሚያገኘው የፕሮፓጋንዳ ጥቅም አንድ አጋዥ ይሆንለታል ሲሉ ትችታቸውን ያስከትላሉ::

በሌላ በኩል የኦዲ ኤፍ ኢትዮጵያ መግባት ለኦሮሞና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ ድል ነው የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች በተለይ እነዚህ የኦነግ መስራቾች የመገንጠል አላማቸውን ትተው በአንድነት ለመታገል መወሰናቸው ለሁሉም የምስራች ነው ይላሉ::

የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች በዚህ ዙሪያ የምትሰጡትን አስተያየት እንጠብቃለን::

የኦዲኤፍን ውሳኔ እንዴት አዩት?


ወያኔ፣ ፍትህ እና እኛ –ያሬድ ኃይለማርያም

$
0
0

ያሬድ ኃይለማርያም
ከብራስልስ፣ ቤልጅየም
ጥቅምት 5፣ 2007 ዓ.ም.

ያሬድ ኃይለማርያም ለ7 ዓመታት ያህል ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ካውንስል ጋር አብሮ የሠራና የኖቬምበር 1 እማ 2ቱን ጭፍጨፋ ተከትሎ ከሃገር ብዙ ምስጢሮችን ይዞ በመውጣት ለአውሮፓ ሕብረት ያቀረበ ነው።

ያሬድ ኃይለማርያም ለ7 ዓመታት ያህል ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ካውንስል ጋር አብሮ የሠራና የኖቬምበር 1 እማ 2ቱን ጭፍጨፋ ተከትሎ ከሃገር ብዙ ምስጢሮችን ይዞ በመውጣት ለአውሮፓ ሕብረት ያቀረበ ነው።

በመጀመሪያ “ወያኔ፣ … እና እኛ” በሚል ርዕስ የማቀርባቸውን ጽሁፎች ዋና ዓላማ ለአንባቢያን ግልጽ ላድርግ። ዛሬ አገራችን ለምትገኝበት አስከፊና ውስብስብ የፖለቲካ ሁኔታም ሆነ በየግላችን ለደረሰብንና ለገጠሙን ቁሳዊና መንፈሳዊ ኪሳራዎች ሁሉ ተጠያቂው ወያኔ ነው ብለን ስለደመደምን እርግማኖቻችን፣ ነቀፌታችን፣ ዝልፊያችን፣ ወቀሳችን፣ ውንጀላችን፣ ዛቻና ማስፈራሪያችን ሁሉ ወያኔ ላይ ያነጣጠሩ ናቸው። እርግማንና ዝልፊያ ግፍንና ግፈኞችን ጠራርገው የሚያጠፋ ቢሆን ኖሮ ባለፉት ሃያ አመታት በወያኔ ላይ ያዘነብነው እርግማንና ውርጅብኞች ወያኔን ብቻ ሳይሆን የተቀሩትንም የአፍሪቃ አምባገነኖች ሁሉ ጎርፍ ሆኖ በወሰዳቸው ነበር። በጸሎታችንም ብዛታ እኛ ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳንሆን ቀሪውም የአፍሪቃ ሕዝብ ከግፈኞች መዳፍ ነጻ በወጣ ነበር። ያ ግን አልሆነም። የሚያሳዝነው ታዲያ በጩኸታችን፣ በጸሎትና በእርግማን ለአሥርት ዓመታት የተሸከምናቸውን ግፈኞች ከጫንቃችን ላይ ማውርድ አለመቻላችን አይደለም። ይልቅስ ዛሬም ከዚሁ ከቆረብንበት የመረጋገም፣ የመጠላለፍና የመጯጯ አባዜ ሳንላቀቅ ከወያኔ ጋር ያሳለፍነውን የሰቆቃ ዘመን እያደስን ማራዘማችን ነው። ወያኔ ሰብዓዊ መብቶችን በገፍ በመጣስ፣ አገርንና ሕዝብን በማዋረድ፣ ዘረኝነትን በማስፋፋት፣ በሙሰኝነት፣ የአገሪቱን ተቋማት በማዳከምና መሁራንን በማሳደድ አለም ያውቀዋል። ቀሪው አለም ታዲያ የሚታዘበው ወያኔን ብቻ ሳይሆን እንዲህ ያለውን ክፉና አፋኝ ሥርዓት ተሸክመን እዚህ ያደረስነውን እኛንም ጭምር ነው። እንደ እኔ እምነት ወያኔ ሕዝብ የፈቀድንለትን ዕድሜ ነው እየኖረ ያለው። ምራኝ በሎ የፖለቲካ ፈቃዱን በነጻነት ሰጥቶታል እያልኩ አይደለም። በተገዥነት ለመኖር ግን ተመቻችቷል።

ሕዝብ በተለያዩ መንግዶች የፖለቲካ ፈቃዱን ይገልጻል። ጤናማ በሆነ የፖለቲካ ማህበረሰብ ውስጥ የሕዝብ የፖለቲካ ፈቃድ በነጻና ፍትሐዊ በሆነ የምርጫ ሥርዓት ወይም በሌሎች ሕጋዊና ሰላማዊ መንገዶች ይገለጻል። እነዚህን እድሎች ሲነፈግ ደግሞ ቁጣውን ባደባባይ ወጥቶ በማሳየት መልዕክቱን ያስተላልፋል። ኃይሉንም ያሳያል። የፖለቲካ መዘውሩን የጨበጡትን ኃይሎች ያርቃል፣ መስመር ያሲዛል፣ ካልሆነም ያስወግዳል። በእንዲህ ያለ ማህበረሰብ ውስጥ እያፈኑ፣ እየገደሉ፣ ሕዝብን እያሸበሩ፣ ንጹሃንን አስረው እያሰቃዩና በሙስና ውስጥ እየዋኙ መቀጠል አይቻልም። ቢሞከርም የሥርዓቱ ዕድሜ አጭር እንጂ እንደኛ በአሥርት አመታት የሚቆጠር አይሆንም። ይህ አይነቱ ማህበረሰብ አፋኝ ሥርዓትን ተሸክሞ ለመዝለቅ እኛ ያለንን ትእግስቱም ሆነ የደነደነ ሰፊ ተከሻ የለውም። እየተራቡና እየደኸዩ ባለሥልጣናትን ማጠብደል፣ ከእወቀትና ከእውነት ጋር ለተጣሉ የሥርአቱ ተከታዮች አገርን ጥሎ መሸሽና እራስን ለውርደት ማመቻቸት፣ በሌሎች ላይ የሚፈጸሙ በደሎችን እንዳላዩና እንዳልሰሙ ሆኖ በራስ ጉዳይ ብቻ መጠመድ፣ ለሐይማኖተኝነት የተሳሳተ ትርጓሜ በመስጠትና የራስን ፍርሃት ለመደበቅ የአገር ጉዳይና ፖለቲካ አይመለከተኝም በሚል የኃይማኖት ተቃማትንና ቅዱስ መጻህፍትን የቀበሮ ምሽግ ማድረግ በተዘዋዋሪ የአገዛዝ ሥርዓቱ እንዲያፈረጥም ድጋፍ እንደ መስጠት ነው የሚቆጠረው። ይህ ደግሞ አገሪቷ ዛሬ ለተዘፈቀችበት አዘቀት፣ በሥርዓቱ ውስጥ ለሚታየው ብልሹነትና ለሚፈጽማቸው ወንጀሎች ሁሉ በአንድ ወይ በሌላ መንገድ እያንዳንዳችን ድርሻ ያለን መሆኑን ያሳያል። ማድረግ የሚገባንን ያህል ባለማድረጋችን ይሁን ወይም ማድረግ የማይገባንን በማድረጋችን የጥፋቱ ተጋሪዎች እንድንሆን ያደርገናል። ስለዚህ የወያኔን ጥፋቶች እያነሳን በተወያየን ቁጥር በጉዳዩ ዙሪያ የሚኖረንን የዜግነት ወይም የተወላጅነት ድርሻ አብረን ልንፈትሽ ራሳችንን ልንጠይቅ የሚገባን በርካታ ነገሮች አሉ። በአገሪቷ ውስጥ ይህ ሁሉ ወንጀልና ግፍ ሲፈጸም፣ ወያኔ ባለፉት ሃያ ዓመታተ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ሰዎችን ሲገድል፣ በመቶ ሺዎችን አስሮ ሲያሰቃይና አፍኖ ሲሰውር፣ ገበሬዎችን ሲያፈናቅልና ሲያሰድድ፣ ወጣቶችን ለአረብ አገራት ባርነት ሲያመቻችና ሲያሰድድ፣ አገሪቱን በዘር ከፋፍሎ ሲያምስና ሲያጫርስ የት ነበርን? ሰምተንስ ምላሻችን ምን ነበር? ምንስ የማደረግ አቅም ነበረን? ድርሻችንን ተወጥተናል ወይ? የበኩላችንን አድርገናል ብለን ካሰብንስ ታዲያ ለምን ሥርዓቱን ማረቅ አቃተን? የሚሉና ሌሎች ተመሳሳይ ጥያቄዎችን አንስተን ራሳችንን መሞገት ይገባናል። ለዚህም ነው ቀደም ሲል “ወያኔ፣ ሽብርና እኛ” በሚለው ጽሁፌ ወያኔ ብቻ ሳይሆን የወያኔን እኩይ ገድል እየዘከዘክንና መፍትሄን በማያመላክቱ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳዎች ላይ ተጠምደን ሕዝብን አብረን አናሸበር ያልኩት።

ወደ ዛሬው ጽሑፌ ልመለስና “ፍትሕ” በሚለው ቃል ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ አለ ብዮ ስለማምን በዙ ማለት አይጠበቅብኝም። ፍትሕን በተመለከተ ከጥንታዊቷ ግሪክ ፈላስፎች አንስቶ የዘመኑ የፍልስፍ እና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን የሚስማሙበት የጋራ ነጥብ አለ። ይሄውም ፍትሕ በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ በግለሰቦች መካከል በእኩልነትና በመከባበር መንፈስ ላይ የተመሰረተ ጤናማ ግንኙነት እንዲፈጠር፣ እንዲሁም ዘላቂነት ያለውና የተረጋጋ የፖለቲካ ማኅበረሰብ እንዲኖር ከሚያስችሉት መሰረታዊ እሴቶች መካከል አንዱና ዋነኛው መሆኑ ላይ ነው። አንድ የፖለቲካ ሥርዓት ምንም አንኳን ጥሩ የሆነ መንግስታዊ አወቃቀር፣ ሕገ-መንግሥትና የዳበረ የኢኮኖሚ መሰረት ቢኖረውም ፍትሕ እስከ ከተጓደለበት ድረስ ሊፈተሽ፣ ሊስተካከልና እንዳስፈላጊነቱም ሊወገድ ይገባዋል። ታዋቂው የፍልስፍና መምህርና ፈላስፋ ጆን ራውልስ “A Theory of Justice” በሚለው መጽሐፉ መግቢያ ላይ በጥሩ አገላለጽ እንዲህ ሲል አስቀምጦታል “A theory however elegant and economic must be rejected or revised if it is untrue; likewise laws and institutions no matter how efficient and well-aranged must be reformed or abolished if they are unjust”።

ፍትሕ ባልሰፈነበት ማኅበረሰብ ውስጥ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማኀበራዊ መረጋጋቶች አይታሰቡም። ፖለቲካው በውጥረትና በቀውስ የተሞላ ነው የሚሆነው። ኢኮኖሚውም ለጥቂቶች መደላደልን ፈጥሮ ብዙሐኑን የሚያቆረቁዝና ለከፋ ድኀነተና ባርነት የሚያመቻች ነው የሚሆነው። ማኅበራዊ ቀውሶች ይፈጠራሉ። ፍትሕ በተጓደለበት ሥፍራ ሁሉ ሰዎች በዘራቸው፣ በጽኦታቸው፣ በቋንቋቸው፣ በፖለቲካ አመለካከታቸውና በሙያቸው የሚገለሉበት፣ የሚዋከቡበትና ለጥቃት የሚመቻቹበት ሥርዓትም ይፈጠራል። መሰረታዊ ሰብዓዊ መብቶቻቸውን እና ነጻነታቸውን የተነፈጉ፣ በባለሥልጣናት የወንጀል አድራጎት የጥቃት ሰለባ የሆኑ ሰዎችና ግፉአን በሞሉበት አገር የሚኖረው ሰላም ሁሌም አንጻራዊ ነው። ተበዳዮች የፍትሕ ጥማታቸውን የሚወጡበት ሕጋዊ መስመር ሰለሚያጡ ቂምና በደልን አንዳረገዙ ነው የሚቆዩት። ኃይልና ጉልበት ያገኙ የመሰላቸውም ቀን ቁጣቸውን የሚገልጹት ፍጹም ቅጥ ባጣ የአመጽ እርምጃ ነው። የፍትሕ ጥማታቸውን እንደማያረካ ቢረዱትም ቁጣቸውን ለመግለጽ በሚወስዱት እርምጃ የመጀመሪያው የጥቃት ሰለባዎች የልማትና የመንግሥት ተቋማት፣ የግል ባለሃብቶች ያፈሯቸው ንብረቶች እና ባለስለጣናት ናቸው። የሩቁን እንተወውና በቅርቡ እንኳን የኦሮሚያ ክልል ተማሪዎችን ቁጣ ተከትሎ በአንቦ ከተማ የተስተዋለው የንብረት ውድመትና የሰው ሕይወት ህልፈትን ልብ ይለዋል። ፍትሕ በሌለበት ሥፍራ የሚኖር ልማትና የኢኮኖሚ እድገት የገዢዎቹ መፎከሪያና መሟሰኛ ከመሆን ባለፈ ሕዝብ እንደ ራሱ ሃብት የሚቆጥረው የለውጥ መሰረት አይሆንም። ሕዝብ በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ እምነት እንዲያጣ በሚደረግበት ሁኔታ ውስጥ በፖለቲካወም ሆነ በልማቱ ዘርፍ ንቁ ተሳታፊ ሊሆን አይችልም።

ወያኔና ፍትሕ

በበቀል መንፈስ የተሟሸው የወያኔ የአገዛዝ ዘመን ገና ከጅምሩ ነበር ለፍትሕ ያለውን የወረደና የተዛባ ምልከታ ባደባባይ ማሳየት የጀመረው። በጠራራ ጸሐይ በየአውራ ጎዳናው መግደል የጀመሩት ድንበር ተጋዳላዮች በሺህ የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎችን ሕይወት ባለፉት ሃያ አመታት ቀጥፈዋል። የሥርዓቱን ብልሹነት የሚያጎላው የግድያዎቹ መፈጸም ብቻ ሳይሆን ገዳዮች በሕግ አግባብ ሊጠየቁና ለፈጸሙትም የወንጀል አደራጎት ኃላፊ ሲሆኑ አለመታየቱ ነው። ተበዳዮችንና የሟች ወገኖችን እያስፈራሩና አያሸማቀቁ በያደባባዩ ሲንጎማለሉ፣ ሲሾሙና ሲሞገሱ መታየቱ የተለመደ ነው። በጸጥታ ኃይሉ በኩሉ ይታይ የነበረው ሥርዓት አልበኝነትና ከሕግ በላይ የመሆን አዝማሚያም አያደር ተቋማዊ ቅርጽ የዟል። ሕገ-መንግሥቱን በሚጻረር መልኩ የውጡት እንደ ጸረ-ሽብር አዋጁ አይነት አዳዲስ ሕጎችና በካደሬዎች የተሞላው የሕግ ተርጓሚው አካል የወያኔን የአፈና መዋቅር ሕጋዊ መልክ እንዲይዝ አድርገውታል። ሕግን በመጣስ ይፈጸሙ የነበሩ የሰብዓዊ መብት እረገጣዎች ሁሉ ዛሬ በእነዚህ ሕጎች የተፈቀዱ ተግባራት ሆነዋል። በጠመጃ አፈሙዝ ላይም ተወስኖ የቆየው የአፈናው መዋቅር ከምርጫ 1997 ዓ.ም. በኋላ በሕግና በፍትሕ ተቋማት እንዲጠናከር ተደርጓል። ፖሊሱም፣ ዐቃቤ-ሕጉም ሆነ ዳኞች የባለሥልጣናትን ቀጭን ትዕዛዝ አሰፈጻሚዎች ስለመሆናቸው ሰሞኑን በፍርድ ሂደት ላይ ያሉትን የዞን ዘጠኝ አባላትን፣ የጋዜጠኞቹን፣ የፓርቲዎች አመራር አባላትንና ከኦሮሚያ ክልል ተይዘው የታሰሩ ተማሪዎችን ክስና የፍርድ ቤት ደራማ ማጤኑ ብቻ ይበቃል።
በበርካታ አገራት ደረጃው ይለያይ እንጂ የሕግ አስፈጻሚው አካል ብዙውን ጊዜ የሰዎችን መብት ከመጣስና ፍትሕን ከማጓደል የጸዳ አይደለም። ይሁንና በብዙዎቹ አገራት የዳኝነት ክፍሉ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ከአስፈጻሚው አካል ነጻ ሆኖ የመሥራት ዕድልና አቅምም ስላለው ፍትሕ ቢጓደል የመቃናት እድሉ ሰፊ ነው። እሩቅ ሳንሄድ በጎረቤቶቻችን ኬኒያና ኡጋንዳ እንኳን ፖለቲካ ነክ በሆኑ ጉዳዮች ዳኞች ከመንግስት በተቃርኖ ሲፈርዱ ማየት የተለመደ ነው። የአገራችንን ሁኔታ ከብዙዎቹ አገራት የተለየና የከፋ የሚያደርገው በጊዜ ሂደት የሕግ ተርጓሚውም በዚሁ የጥፋት መስመር እንዲሰለፍ መደረጉ ነው። ‘አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ’ አይነት ግንኙነት አንዲኖራቸው ተደርገው የተዋቀሩት እነዚህ የመንግስት ተቋማት የኢትዮጵያን የፍትሕ ሥርዓት ወደ ከፋ አዘቅት ውስጥ ጨምረውታል።

እኛስ?

እንግዲህ እራሳችንን እንጠይቅ። እኛስ? ሥርዓቱ አገሪቱን ፍትሕ አልባ ሲያደርግና ከገለጽኩትም በከፋ መልኩ ሰብአዊ መብቶችን ሲጥስ እያየን ምን አደረግን? የሚሉና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎችን ማንሳትና መወያየት የግድ ይላል። በተበላሸው የፍትሕ ሥርዓት ቀጥተኛ ተጠቂ የሆነውን ያህል ለሥርዓቱ ፍትሕ አልባ ሆኖ መቀጠል በአንድ ወይ በሌላ መንገድ አስተዋጽኦ ላለማበርከታችን እርግጠኞች ልንሆን ይገባል። ከወያኔ በተቃርኖ በቆመው ኃይልና በቀረው ፍትሕ ናፋቂ የኅብረተሰብ ክፍል ውስጥ ለፍትሕ የተሰጠውን ግምትና ቦታ በመጠኑ መቃኘት ግድ ይላል።

• የፍትሕ ጥያቄን በጎሣ፣ በፖለቲካ ወገንተኝነት፣ በኃይማኖት፣ በአገርም ሆነ ሌሎች መስፈርት ከልሎ ማየት ትክክለኛ አስተሳሰብ አይደለም። በየትም ቦታ ይሁን በሰው ዘር ላይ የሚፈጸም የመብት ጥሰትና የፍትሕ መጓደል ሌላውን ሰው ሊያሳስብና እንቅልፍ ሊነሳው ይገባል። ለዚህም ነው ታዋቂው የሲቪል ነጻነት ታጋይ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ “Injustice anywhere is a threat to justice everywhere.” በማለት ያስተላለፈውም መልዕክት ይህንን ሃሳብ ለማንጸባረቅ ይመስለኛል። ወደ አገራችን መለስ ብለን ሥርዓቱን ለመቀየር በትግል ላይ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የታዘብን እንደሆነ በፍትሕ ጥያቄ ዙሪያ ጎልተውና ተደጋግመው የሚስተዋሉ ችግሮችን እናገኛለን። ስለ ፍትሕ በጥቅሉ ከማውራት ባለፈ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው የሚያሰሙት የድርጀታቸው አባል ወይም ደጋፊ የሆነ ሰው ችግር ሲገጥመውና ሲበደል ብቻ ነው። የተወሰኑ ፓርቲዎች አልፎ አልፎ ከሚያሰሙት እሮሮ ባሻገር አብዛኛዎቹ በሌሎች ሰዎች ላይ ወይም የሌላ ድርጅት አባል በሆኑ ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶችንና የፍትሕ መጓደልን ችላ በለው ሲያልፉ ነው የሚስተዋለው። ይህ ከድርጅት ማዕቀፍ ውጪ ማሰብ ያለመቻል ችግር አባላችን ወይም ደጋፊያችን አይደለም ብለው የሚያስቡትን ሰው በደልና ስቃይ እንዳይጋሩ አድርጓቸዋል። በተለይም በጎሣ በተከለሉ ደርጅቶች ላይ ይህ ችግር ጎልቶ ይስተዋላል። የፍትሕ ጥያቄን በጎሣ ወይም በፓርቲ መነጽር ማየት በድርጅቶቹ ውስጥ ያለውን የግንዛቤ ችግር አጉልቶ ከማሳየቱም በላይ ማንን ነው ከወያኔ የአገዛዝ ቀንበር ነጻ ሊያወጡ የሚታገሉት? ሕዝብን ወይስ …? የሚል ጥያቄን ያጭራል።

• ይህ የሌሎችን በደል ችላ የማለት ልማድ ማኅብረሰባዊ መሠረትም የያዝ ችግር ነው። ኢሰመጉ ውስጥ በመብት ጥሰቶች አጣሪነት በሰራሁበት ወቅትና ከዚያም ወዲህ ለመታዘብ እንደቻልኩት ለተገፉ ሰዎች ድምጽን የማሰማትና ከጎናቸው የመቆም ባህል በቡዙ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ቦታ የተሰጠው አይመስልም። ዘጠና ሚሊዮን ሕዝብ በሚኖርበት እና እጅግ የከፋ የሰብአዊ መብቶች አረገጣ ባለበት አገር ከኢሰመጉም ጎን ሆነ ከፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማህበራት ጎን ቆሞ ለራሱና ለሌሎች ሰዎች መብት መከበር ለመታገል የቆረጠው ሰው ቁጥር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ለምን?

• ሌላው አሳሳቢውና ተደጋግሞ እየተስተዋለ ያለው ችግር ፍትሕን የፖለቲካ ጥቅም መደራደሪያ የማድረግ መጥፎ አካሄድ ነው። “የጠላቴ ጠላት …” በሚል የተሳሳተ የፖለቲካ ስሌት ከአገዛዝ ሥርዓቱ ጋር ለአጭር ጊዜም ቢሆን በማንኛውም የሥልጣን ደረጃ ላይ የቆዩና የወያኔን የወንጀል ተግባራት ሲደግፉና በቀጥታም ተሳትፎ ሲያደርጉ የነበሩ ባለሥልጣናት ሥርዓቱን በከዱ ጊዜ ተቃዋሚዉ ኃይል ተቀበሎ የሚያስተናግድበት መንገድ በቅጡ ሊፈተሽ ይገባዋል። ለዚህም እነ አቶ ስዮን፣ አስመራ የገቡትን የወያኔ የጦር ጀነራሎችን፣ በጋንቤላው እልቂት ሊጠየቁ የሚገባቸው የክልሉ ባለሥልጣናትን፣ በበደላችን ብቻ ሳይሆን በወሬ ጥማታችንም ሊያተርፉ የጥፋት ተሳታፊነት ገድላቸውን ያለ አንዳች ሃፍረት በመጽሐፍ ጠርዘው እየቸበቸቡልን ያሉትን እንደ ተስፋዮ ገብረአብ እና ኤርሚያስ ለገሠን የመሳሰሉ ጮሌ ወያኔዎችን ያስተናገድንበት ሁኔታም በቅጡ ሊፈተሸ ይገባዋል።
Corruption
• ሰብአዊ መብቶችን በመጣስ በማናቸውም መልኩ ተሳትፎ የነበራቸውን የወያኔን ሹማምንትና ደጋፊዎች ሥርዓቱን ስለከዱና ወደ ተቃዋሚው ጎራ ስለተቀላቀሉ ብቻ በሕዝብና በአገር ላይ ሲፈጽሙት የቆዩትን ጥፋቶች ሙሉ በሙሉ ችላ በማለት እንደ ጀግና ማሞካሸትና የሌላቸውንም ስብዕና ማላበስ ላጥፊዎቹ መደበቂያ ጫካ ከመሆን ያለፈ ፋይዳ አይኖረውም። ይህ አይነቱ አካሄድ ዛሬ ከሥርዓቱ ጋር ሆነው ሕዝብን እየበደሉ ላሉትም የወያኔ ሹመኞች የሚሰጠው ትምህርትም ሆን የሚያስተላልፈው መልዕክት እጅግ የተሳሳተ ነው የሚሆነው። ‘በሕዝብ ላይ ያሻችሁን ብትፈጽሙም ወያኔን እስከ ከዳችሁና ወደ እኛ ካምፕ እስከ ተቀላቀላችሁ ድረስ ሃጢያታችሁ ሁሉ ይሰረያል፣ የፈጸማችሁትም ወንጀል ካለ የሚጠይቃችሁ አይኖርም’ የሚል መልክት ነው። ይህ ደግሞ ለጥቅምም ይሁን ከልብ ከወያኔ ጋር የቆሙ የጥፋቱ አጋሮች ዛሬ ላይ ሆነው ለሚፈጽሙት ጥፋት ወደፊት ተጠያቂ እንሆናለን በለው እንዳይሸማቀቁ ና ይልቅስ የተንጠለጠሉበት ዛፍ ያዘመመባቸው ጊዜ እግራቸው አፈር ሳይነካ ተቃዋሚው ወዳዘጋጀላቸው ሌላ ዛፍ እንዲጠላጠሉ አድል እየፈጠረላቸው ነው። እዚህ ላይ ግልጽ ለማድረግ የምፈልገው የሥርዓቱን ብልሹነት በቅርበት ከተረዱ በኋላ ከሕዝብ ጎን በመቆም ለፍትሕና ለነጻነት መታገል ለሚፈለጉ የወያኔ ሹማምንት በሩ የዘጋባቸው እያልኩ አይደለም። ከጥፋታችው ታርመውና በቅጡ ተጸጽተው የበደልነውን ሕዝብ እንካስ ሲሉ መንገዱ ሊዘጋባቸው አይገባም። ጸጸታቸውም ከልብ ስለመሆኑ አንዱ ማሳያው በሥራ አጋጣሚ የሰበሰቡትን ወሬና የሕዝብ መረጃ ሲበድሉት ለቆዩት ሕዝብ በነጻ በመግለጽ የሚሰራበትን ደባ እንዲያውቅ ሲያደርጉ ነው። እነ አቶ ኤርሚያስ ካለቆቻቸው የቃረሙትን ተራ ወሬና በሕዝብ ላይ ሲፈጽሙት የነበረውን በደል በመጽሐፍ መልኩ ካልሆን አንገልጽም በሚል ለሁለተኛ ጊዜ በሕዝብ በደል መነገድና ማትረፍ ለትዝብት ይዳርጋል። ግለሰቡ አስቀድመው በኢሳት ያደረጉትን ቃለ-ምልልስ ላሰተዋለ ሰው የወሬያቸውን ዳርዳሩን እየነካኩ ዝርዝሩን ከመጽሐፌ ታገኙታላችሁ እያሉ አይን ባወጣ መልኩ ነበር ያስተዋውቁ የነበረው። እንደ እነዚህ አይነቶቹ ብልጣብልጥ ወያኔዎች ከሆነ በቅርቡ የአሜሪካን የስለላ ድርጅት ሰራተኛ የነበረው ስኖውደን በሕዝብ ላይ የሚሰራውን ደባ ለማጋለጥ መንግሥትን ከድቶ በስደት የለቀቀውን ከፍ ያለ የሚስጢር መረጃ በፈለገው መልኩ ቢያሳትመው ኖሮ ከአለማችና ሃብታሞች ጎን በተሰለፈ ነበር። ስኖውደን ያደረገው ግን ይህ መረጃ የሕዝብ ሃብት ነው ስለዚህም ሕዝብ በነጻ መረጃውን የማግኘት መብት አለው በሚል ጋዜጠኞች ያረፈበት ሆቴል ድረስ ጠርቶ መረጃው ይፋ እንዲሆን አድርጓል። ለዚህም ቤሳቤስቲ ሳንቲም አላገኘበትም። እኛ ዘነድ ያለው የሥነ-ምግባር ችግርና የሞራል ግሽፈት ስር የሰደደ በመሆኑ በእነ አቶ ተስፋዮ ገብረአብና በአቶ ኤርሚያስ ለገሰ የወሬ ነጋሪ መጽሐፍት የሚታተርፉት እነሱ ብቻ ሳይሆኑ እነሱን ጀግና አድርገው ወደ አደባባይ የወጧቸውና መጽሐፎቻቸውን ያሳተሙላቸው ‘ተቃዋሚ’ ኃይሎች ጭምር ናቸው።

• ከዚሁ ጋር ተያይዞም የመንግሥት ባለሥለጣናትን ፍርድ አደባባይ ለማቆም ከኢትዮጵያ ውጪ የሚደረጉ ጥረቶችን መፈተሸ ይገባል። ከምርጫ 97 ወዲህ በአውሮፓና በአሜሪካ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ለውጤት ያልበቁ በርካታ ወጥኖች ተጀምረው ከመንገድ ቀርተዋል። ሥርዓቱ በሃያ አመታተ ውስጥ የፈጸማቸው በርካታ በሰው ስብዕና ላይ ያነጣጠሩ ወንጀሎች በአለም አቀፍ የፍትሕ አደባባይ ተጠያቂ ሊያደርጉት እንደሚችሉ የሚያጠራጥር አይደለም። ይሁንና መረን የለቀቀውና አይን ያወጣው የምዕራቡ አለም ኢ-ፍትሐዊነት እንደ ወያኔ ላሉ ታዛዥ አንባገነኖችና ወንጀለኞች ለጊዜውም ቢሆን የማይጠየቁበትን ከለላን ፈጥሮላቸዋል። ይሁንና እድሉ ሙሉ በሙሉ የተሟጠጠ ባለመሆኑ በአንዳንድ አገሮች የፍትሕ ሥርዓት ውስጥ የተፈጠሩትን አመቺ ቀዳዳዎች ለመጠቀም የሚቻልባቸው እድሎች ነበሩ። ሆኖም የተጀመሩት ውጥኖች ከእቅድ ሳይዘሉ እንደተወሩ በመቅረታቸው እነዚህንም እድሎች ባግባቡ ሳንጠቀምባቸው ቀርተናል። ይህም አንዱ የክሽፈታችን መገለጫ ይመስለኛል። ለዚህም እንደ ዋነኛ መክንያት ከሚቆጠሩት ነገሮች አንዱ የፍትሕን ጥያቄዎች ከፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ፍጆታ በዘለለ ለማየት ያለመቻላችን ነው። በባዶ ሜዳ የወያኔ ባለሥልጣናትን ልንከስ ነው፣ ከሰስን፣ ተደራጀን፣ ወዘተ… እየተባሉ ከአንድ ሳምንት ለማይበልጥ የዜና መወያያ የሚውሉ ማሰፈራሪዎች ለፍትሕ ጥያቄዎች ያለንን የወረደ ምልከታና ቁርጠኝነትም ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። በቅርቡ በሲውዲን አገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የአገዛዝ ሥርዓቱን በፍትሕ አደባባይ ለመፈተን ያሳዩት ተነሳሽነት የሚበረታታ ነው። ይሁንና ገና ከጅምሩ ጉዳዩ እንደ ሰበር ዜና ተደርጎ በኢሳት የቀረበበት ሁኔታ ግን እጅግ አሳፋሪና ከእውነት የራቀም ነው። የነገርን ጫፍ ይዞ እያጋነኑ የግምት ትንታቴ መስጠት በኢሳት ዜና አቀራቢዎች ዘንድ የተለመደ ቢሆንም ማንም ሊያረጋግጠው የሚችለውን ሃቅ ሰበር ዜና በሎ አጋኖ ማቀረብ ከሙያ ስነ-ምግባርም ሆነ ለፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ከሚሰጠው ጠቀሜታ ያለፈ ነው። በሲውዲን አገር የተጀመረው ጥረት እውነት ሆኖ ሳለና ያንኑ በአግባቡ መዘገብ ሲቻል በኢሳት ሰበር ዜና ላይ ‘የመንግሥት ባለሥልጣናት ሲውዲን አገር በሚገኘው አለም አቀፍ የጦር ፍርድ ቤት ክስ ተመሰረተባቸው’ በሚል መንደርደሪያ መቅረቡ የኢሳትን ተአማኒነት ብቻ ሳይሆን እየለፉ ያሉትንም ሰዎች ድካም ጥያቄ ውስጥ ይጥለዋል። ማንም ሰው በቀላሉ የሚያነሳው ጥያቄ በሲውዲን አገር እንዲህ አይነት ክስ ሊቀርብለትና ሊያስተናግድ የሚችል ‘አለም አቀፍ’ የሆነ ‘የጦር ፍርድ ቤት’ አለ ወይ? የሚል ነው። መልሱ ቀላል ስለሆነ እያንዳንዱ ሰው ኮመፒዉተሩን ይፈትሽ።

ስለ ፍትሕ ጥያቄዎች ስናወራ በአገዛዝ ሥርዓቱ ስለ ተገደሉ፣ ስለ ታፈኑ፣ ስለ ታሰሩ፣ ስቃይ ሰለተፈ ጸመባቸው፣ የአካል ጉዳት ሰለ ደረሰባቸው፣ ከአገር ስለተሰደዱ፣ ከቄያቸው ስለተፈናቀሉ፣ በዘርና በአስተዳደር መድሎ መሸሻና መጠጊያ ስላጤ ግፉአን ነው የምናወራው። እነዚህ ሰዎች ጊዜው የፈለገውን ያህል ይርዘም እንጂ ፍትሕ የሚያገኙበትን ቀን ይጠብቃሉ፣ ይናፍቃሉ። ለበደላቸውም ካሳም ይሻሉ። በፍትሕ ጉዳይ በቧለትን እና ለፖለቲካ ግብ ማሳለጫነት በተጠቀምንበት ቁጥር ተበዳይ በሆነው ሰው አይን የምንታየው ከዋና በዳዮቹ ጎን የተሰለፍን ያህል ነው። በደልን በመፈጸምና በሰዎች በደል ሌላ አላማን ለማሳካት በመጣር መካከል ያለው የሞራል ክስረት ቡዙም የተራራቀ አይደለም። ለዚህም በዚህ ሳምንት ወደ ቃሊቲ የተወረወረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ “የኮብላዩ ሚኒስትር ወጎች” በሚል ከተበዳይ ወገን ሆኖ አቶ ኤርሚያስ የፈጸሙትን አንዳንድ ነገር እያስታወስ ላቀረበባቸው ትችት እሳቸውን አቅፎ ከያዘው ክፍል ወደ ጋዜጠኛ ደሳለኝ የተወነጨፉት ነቀፌታዎች ጠሩ ማሳያዎች ናቸው። ተመስጌን ለሙያው በጽናት የቆመ መንፈሰ ጠንካራ ሰው ነው። እስርና መከራ ሊገጥመው እንደሚችል ጠንቀቆ እያወቀም እንደ ብዙዎቻችን በርገጎ አገርሩን ጥሎ ለመፈርጠጥም ሆን በፍርሃት አፉን ለጉሞ ለመቀመጥ አልወሰነም። የአቶ ኤርሚያስንና ያለቆቻቸውን ግልምጫና ማስፈራሪያ ሁሉ ችሎ ለአመታት ሲታገል ቆይቷል። ሆኖም አቶ ኤርሚያስ እቅፍ አበባ ተበርክቶላቸው በውጭ የሚገኝውን የተቃዋሚ ኃይል እንዲቀላቀሉና አዲሱ የፖለቲካ ተንታኝ ተደርገው ሰላሳ ጊዜ በኢሳት ብቅ ጥልቅ ሲሉ ጋዜጠኛ ተመስጌን ግን የሕዝብ ልሳን ሆኖ ለእውነትና ለፍትሕ በመታገሉ በወታደሮች ተከቦ ወደ ቃሊቲ ተልኳል። የሥራ ባልደረቦቹም በደረሰባቸው ዛቻና ማስፈራሪያ ተሰደው በጎረቤት አገሮች እየተሰቃዩ ይገኛሉ። ከነዚህም መካከል በዚህ ሳምንት በተሰደደበት ኬኒያ ሕይወቱ ያለፈው ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ አንዱ ነው። አሳዳጆቹ ግን ከአንደኛው ዛፍ ወደ ሌላኛው ዛፍ እየተንጠላጠሉ ኑሮዋቸውን በሕዝብ ብሶትና የወሬ ጥማት አደላድለዋል።

ለፍትሕ በእውነተኝነትና በሙሉ ልብ ልንቆም የገባል። የጥፋትና የወንጀል አድራጎት ተሳታፊ ለሆኑ ሰዎች የመደበቂያ ጫካ ከመሆን ይልቅ የበደሉትን ሕዝብ ከወሬ ነጋሪነት ባለፈ እንዲክሱት እድል ልንሰጣቸው ይገባል።

በቸር እንሰንብት!
ያሬድ ኃይለማርያም

የቀድሞው የኢሕአዴግ ባለስልጣን አቶ ኤርሚያስ ለገሰ “ኢሕአዴግ በምርጫ ስልጣኑን ያስረክባል የሚል እምነት የለኝም”አሉ

$
0
0

የቀድሞው በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ስለ ቀጣዩ የኢትዮጵያ ምርጫ፣ ስለ ምርጫ 97ቱ ግድያ ፣ ስለ አገዛዙ ያልተሳካ የዲያስፖራ ፖሊሲ ፣የሕወሃት ኢትዮጵያን እያተራመሰ ረጅም ጊዜ ስልጣን ላይ ለመቆየት ማሰቡን ከውስ ተመልካች አንጻር ፈትሸውታል። ስለ ቀጣዩ መጽሐፋቸው መጠነኛ ፍንጭ ሰጥተዋል። ከአቶ ኤርሚያስ ለገሰ ጋር በቬጋስ የኢትዮጵያ ራዕይ ማህበር በጠራውና የታሰሩና የተሰደዱ ጋዜጠኞችንና የፖለቲካ እስረኞችን ለመርዳት በተጠራው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ሕብር ራድዮ አግኝቶ አነጋግሯቸዋል። ሙሉውን ቃለ መጠይቅ ተከታተሉ።


ermias copy

የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት በፕሬዚዳንቱ የቀረበለትን ካቢኔ አፀደቀ

$
0
0

10653647_715106701907600_4424009726554435265_n

ጥቅምት 2 ቀን 2007 ዓ.ም የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ከጠዋቱ 3፡00 ሠዓት ጀምሮ በመሰብሰብ በሁለት አጀንዳንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን የብ/ም/ቤቱ ሴክሬታሪያት ለፍኖተ ነፃነት ገለጹ፡፡
የብሔራዊ ም/ቤቱ መወያያ አጀንዳ የነበረው

1- የአዲሱን ፕሬዚዳንት ካቢኔ ማፅደቅ
2- የአማካሪ ሸንጎ መመሪያን ማፅደቅ በሚሉ አጀንዳዎች ላይ ሲሆን
በመጀመሪያው አጀንዳ የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ በላይ ፍቃዱ ለብሔራዊ ም/ቤቱ የካቢኔ አባላቱን ዝርዝር ለብሔራዊ ም/ቤቱ ያቀረቡ ሲሆን በዚሁ መሰረት፡-
1ኛ. አቶ ተክሌ በቀለ ተቀዳሚ ም/ፕሬዚዳንት
2ኛ. አቶ ግርማ ሰይፉ ም/ፕሬዚዳንት
3ኛ. አቶ ሥዩም መንገሻ ዋና ፀሐፊ
4ኛ. አቶ ዘካርያስ የማነብርሃን የድርጅት ጉዳይ
5ኛ. አቶ አስራት አብርሃ ተጠባባቂ የህዝብ ግንኙነት (አቶ ኃብታሙ

አያሌው በእስር ላይ የሚገኝ በመሆኑ)
6ኛ. አቶ ብሩ ቢርመጂ የፖለቲካ ጉዳይ
7ኛ. አቶ አለነ ማፀንቱ የማህበራዊ ጉዳይ
8ኛ. አቶ ደረጀ ኃይሉ የኢኮኖሚ ጉዳይ
9ኛ. አቶ ዳንኤል ተፈራ የውጭ ጉዳይ
10ኛ. አቶ ደምሴ መንግስቱ የህግና ሰብአዊ መብት
11ኛ. አቶ እንግዳ ወልደፃድቅ የወጣቶች ጉዳይ ሲሆኑ ምክር ቤቱም ካቢኔውን ተቀብሎ አጽድቋል፡፡ ተመራጭ የካቢኔ አባላቱም በም/ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሀላ ፈጽመዋል፡፡
ሁለተኛው አጀንዳ የአማካሪ ሸንጎ መመሪያ በንባብ ቀርቦ በምክር ቤቱ የማዳበሪያ ሃሣብ የተሰጠበት ሲሆን በህግና ሰብአዊ መብት ቋሚ ኮሚቴ አማካኝነት ግብአቶቹ ተቀናብረው ለቀጣዩ ስብሰባ እንዲቀርብ በመወሰን ስብሰባው ተጠናቋል ሲሉ የፓርቲው ሴክሬታሪያት ለፍኖተ ነፃነት ዝግጅት ክፍል ገልፀዋል፡፡

10606060_715105301907740_3106963272783930927_n 10003310_715107178574219_2192907481676555384_n

 

መደመጥ ያለበት የአንድነት አመራር አቶ ግርማ ሰይፉ በፓርላማ

$
0
0

መደመጥ ያለበት የአንድነት አመራር አቶ ግርማ ሰይፉ በፓርላማ

በአፋር ክልል በተለያዩ ሞያዎች ሲሰሩ የነበሩ የአማራ ተወላጆች ወደ ክልላቸው እንዲመለሱ ታዘዘ

$
0
0

አኩ ኢብን ከአፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፦

ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የአማራ ተወላጆች ላለፉት 20 አመታት በአፋር ክልል በተለያዩ ሞያዎች ሲያገለግሉ ቆይተዋል። አሁን ከአፋር ክልል ሾልከው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ እነዚህ የአማራ ተወላጆች በአስቸኳይ ወደ ክልላቸው እንዲመለሱ በአማራ ክልላዊ መንግስት ታዘዋል። በጉዳዩ ላይ የአማራ ክልልና የአፋር ክልልን መንግስታት የተስማሙ ሲሆን «ይህ ውሳኔ በህወሓት ሆን ተብሎ በአፋር ክልል ለኢህአዴግ ታማኝ የሆኑ የወያኔ ደጋፊ ትግሬዎች ተወላጆችን ለመተካት የተደረገ ነው» ሲሉም ምንጮቻች ያስረዳሉ።

(አፋር ክልል)

(አፋር ክልል)


ወያኔ በተለይ በሶማሌ ክልልና በአፋር ክልል የሚሰሩ የአማራ ተወላጆችን «ከተቃዋሚዎች ጋር ይተባበራሉ» የሚል ስጋት እንዳለውና ከመጪው ምርጫ በፊት ከአፋር ክልል የአማራ ተወላጆችን አስወግደው በወያኔ ቤተሰብ እንዲተኩ አስቧል። በአፋር ክልል ብዙ በተለያዩ ሞያዎች በመጀመሪያ ዲግሪና በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ ምሁራን ስራ የማያገኙበት ሁኔታ እያለ ክልላችን የህወሓት መጫወቻ መሆኑን የአፋር ወጣቶችን ሞራል የሚነካ ተግባር ነው ሲሉ አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ይናገራሉ። በንግድም ቢሆን የአፋር ክልልን የወያኔ ደጋፊ ትግሬዎች ተወላጆች ብቻ እንዲቆጣጠሩ እየተደረገ ሲሆን በአሁን ወቅት ይሄ ሁሉ ሴራ የሚያሴሩት በተንዳሆ ሱኳር ፋብረካ እያሰሩ የሚገኙት የቀድሞው የህወሓት ታጋይ አቶ ሚካኤል ናቸው።

አቶ ሚካኤል በየእሁድ በአፋር ክልል ለሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በሎግያ ከተማ ስብሰባ የሚያደርጉ መሆኑንና የስብሰባ ቦታቸውም ናዝሬት ሆቴል ቁጥር 1 የሚባለው ሲሆን የናዝሬት ሆቴል ባለቤት በንግድ የአፋር ክልልን የወያኔ ደጋፊ ትግሬዎች ብቻ እንቆጣጠሩ የሚለፉ የትግራይ ሀብታም ናቸው። አሁን ለአቶ ሚካኤል ይህ የመንግስት ሰራተኞችን የማባረር ሴራ ከተሳካላቸው የአፋር ክልል መሉ በሙሉ በወያነ ቤተሰቦች ይያዛል ማለት ነው፣ የአፋር ህዝብም ቢሆን ከከተማ እያስወጡ ወደ ገጠር እየመለሷቸው ነው። ይህ ደግሞ ለወደፊት ከጀቡቲ ታኮሪ ወደ መቀሌ ለሚሰራው የባቡር ሀዲድ ዝርጋታና ወደ ፊትም የትግራይ ክልል የኢንዱስትሪ ዞን የማድረግ አላማ ስላላቸው የአፋር ክልልን በቀላሉ ለመቆጣጠር ነው።

ለ8 ዓመታት አነጋጋሪ ሆኖ የቆየው በኢትዮጵያዊቷ ላይ የተፈጸመው ግድያ በዴንቨር – (እውነተኛ ታሪክ)

$
0
0

(ከአዘጋጁ፡ ወ/ሮ አልጋነሽ በርሔ መገደላቸው የተሰማው ዴሴምበር 2 ቀን 2006 ዓ.ም ነው። የወ/ሮዋ ሞት 8 ዓመት ሊሞላው የቀሩት ጥቂት ጊዜያት ነው፤ እስካሁንም አሟሟቷ አነጋጋሪ ከመሆኑ አንጻር ሌሎም እንዲማሩበት፣ ልክ እንደመታሰቢያም በማሰብ ኢሳያስ ከበደ ታሪኩን አቀነባብሮ አቅርቦታል።)

‹‹…አሜሪካን በአስራ አምስተኛው ክፍለ ዘመን ላይ ነው በኮሎምቦስ የተገኘችው፡፡ በወቅቱ የሚኖሩት ቀይ ህንዶች ቢሆኑም ዛሬ ግን ከመላው ዓለም የተሰባሰቡ ሰዎች ኃይል አድርገዋታል፡፡

‹‹መጀመሪያ ኮሎምቦስ ያገኘው ኩባንና በዛሬዋ አሜሪካን ዙሪያ ያሉትን ደሴቶች ነበር፡፡ ከአራት ዓመት በኋላ ግን ቩስፑሲ የተባለ ጣልያናዊ በ1496 ዋናዋን አሜሪካንን አገኘ፡፡ ወደ አውሮፓም ተመልሶ አዲስ ዓለም አገኘሁ ሲል ተናገረ፡፡ የእሱን እግር ተከትለው እንግሊዞች ወደ ቦታው ደርሰው እስከ 1776 ዓ.ም ድረስ አሜሪካንን ቅኝ ገዟት፡፡
alganesh denver
‹‹የዛሬዋ ኃያል ሀገር ከሁለት ክፍለ ዘመን ባለፈ በእንግሊዝ ተገዝታለች፡፡ በ1776 ዓ.ም ነፃ ስትወጣ ጆርጅ ዋሽንግተን የተባለ ሰው የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት ሆነ፡፡ ዛሬ የሀገሪቱ ዜጎች ከመላው ዓለም የተሰባሰቡ ዜጎች ናቸው፡፡ በአያቱና በቅድመ አያቱ አውሮፓዊና አፍሪካዊ ያልሆነ የለም፡፡ ሆኖም ሁሉም አሜሪካውያን ናቸው፡፡ በአንድ መንፈስ ለሀገራቸው ዕድገት በመጣራቸው አሁን ካሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡ እንዲሁም ትላንት ከገዛቻቸው ሀገር፣ ከእንግሊዝም በላይ ለመሆን በቅተዋል፡፡

(ከሰላዮች ትንቅንቅ የተወሰደ)

አሜሪካ ለብዙዎች የምትናፈቅ ሀገር ናት፡፡ ‹‹የማያውቁት አገር አይናፍቅም›› የሚለው የሀገራችን ተረት ለሀገረ አሜሪካን አይሰራም፡፡ ምክንያቱም የማያውቁት ሁሉ ይናፍቋታል፡፡ በተለይ በታዳጊ ሀገር ለሚገኙ ሰዎች የምድር ገነት መስላ ነው የምትታየው፡፡ እና ሁሉም አመቺ ባለው መንገድ አሜሪካን ሄዶ መኖርን ይመርጣል፡፡ በየዓመቱ እድሉን ለመሞከር ዲቪ የሚሞላው ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም፡፡

ወደ አሜሪካን ለመሄድ ከሚመኙት ጥቂቶቹ ተሳክቶላቸዋል፣ ያሰቡት ሞልቶላቸዋል፡፡ እንዳለሟት የምድር ገነት ሆና ያልጠበቀቻቸውም አሉ፡፡ ከሀገር፣ ከወገን ርቆ መኖሩ እንደ መርግ ቢከብድም የግል ጥረታቸው የስደትን ኑሮ ውጣ ውረድ ተጋፍጠው ራሳቸውን የቻሉ፣ ከራሳቸውም አልፈው እዚህ ሀገር ቤት ላሉ ወገኖቻቸው መትረፍ የቻሉም አሉ፡፡ የተሻለ እውቀት የገበዩም ጥቂት የሚባሉ አይደሉም፡፡

በተቃራኒው የስደት ህይወት ያልተመቻቸው፣ ያሰቡት ቀርቶ ያላለሙት የገጠማቸውም አሉ፡፡ ያም ሆነ ይህ ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ነፃ ከወጣች ሁለት መቶ ሰላሳ አንድ ዓመታትን ያስቆጠረችው የዓለማችን ሃያሏ ሀገር አሜሪካን ዛሬም የብዙዎች ምኞት የሆነችና የምድር ገነት መስላ የምትታይ ሀገር ናት፡፡
አሜሪካን ሀገር የስደትን ኑሮ ተጋፍጠው የህይወትን ፈተና በአሸናፊነት ለመወጣት ከቻሉ ጠንካራ ኢትዮጵያውያን መካከል አንዷ አልጋነሽ በርሄ መሸሻ ነበረች፡፡ አምስት የእሷን ድጋፍ የሚሹ ልጆችን ይዛ በሰው ሀገር ሰው ለመሆን የበቃች፣ ከራሷም አልፎ የስደት ህይወት ለጨለመባቸው የሀገሯ ልጆች መከታና አለኝታ ለመሆንም የቻለች ነበረች፡፡ በአሜሪካን ዴንቨር ኮሎራዶ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ በሙሉ አልጋነሽን ያውቃታል፡፡ በግፍ እስከተገደለችበት ቀን ድረስም የብዙዎች አለኝታ ነበረች፡፡ በሰው ሀገር፣ በስደት ህይወት የራሷን ድርጅት ለመክፈትም በቅታለች፡፡ የአምስት ልጆችን የነገ ህይወት የተሻለ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት አድርጋለች፡፡

በግፍ መገደሏ ልጆቿን ብቻ ሳይሆን የሚያውቋትን በሙሉ ያሳዝን ነበር፡፡ ደግነቷ ሁሉንም አስለቅሷል፡፡ በግፍ መገደሏም የሁሉን አንጀት አላውሷል፡፡ ‹‹አልጋነሽ የብዙዎች እናት ነበረች›› ይላሉ በቅርብ የሚያውቋት በሙሉ፡፡ ኑሮዋን ለማሸነፍ፣ የእሷን እርዳታ ለሚሹትም ለመትረፍ ደፋ ቀና ስትል ነበር ይገድለኛል ብላ በማታስበው ግን በምትረዳው ሰው እጅ በ36 ዓመቷ በሞት የተቀጨችው፡፡

(ሺሞንዲ ገብረሥላሴ)

(ሺሞንዲ ገብረሥላሴ)


ከአባቷ ከአቶ በርሄ መሸሻና ከእናቷ ከወ/ሮ ዘርትሁን ገሰሰ በትግራይ አክሱም ከተማ ግንቦት 21 ቀን 1962 ዓ.ም ነበር አልጋነሽ የተወለደችው፡፡ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ከተከታተለች በኋላ በትውልድ ከተማዋ በአክሱምና በመቀሌ ፍርድ ቤት በፀሐፊነት አገልግላለች፡፡ በዕድገት ወደ አዲስ አበባ የመጣችው በ1980 ዓ.ም ነበር፡፡

እዚህ አዲስ አበባ ተዘዋውራ በምትሰራበት ወቅት ከሰዎች ጋር በነበራት መልካም ቅርርብ ዛሬ ድረስ የሚያስታውሷት በርካቶች ናቸው፡፡ ደግ ነበረች፡፡ ያላትን በሙሉ እስኪያልቅ ድረስ ለተቸገረ ሰው የምትሰጥም ነበረች፡፡ አንዴ ከቢሮዋ ስትወጣ ከፍርድ ቤት በራፍ የተሰባሰቡ ሰዎች ታያለች፡፡ እነዛ ሰዎችንም ችሎት ክርክር ላይ አይታቸው ነበር፡፡ ሁኔታቸውን ስትመለከት አሳዝነዋታል፡፡ እያዘኑ መሄድ የእሷ ባህርይ አልነበረምና ለመርዳት ራቅ ካለ ስፍራ የመጡትን ሰዎች ቀርባ ታነጋግራቸዋለች፡፡ ወደ ቤታቸው ለመመለስ ለትራንስፖርት የሚከፍሉት ገንዘብ አልነበራቸውም፡፡ ይህንን ችግራቸውን ነገሯት፡፡ የሰው ችግር ሰምቶ ለማለፍ የሚችል የደነደነ አንጀት አልነበራትምና ከቦርሳዋ ውስጥ የነበረውን ገንዘብ በሙሉ ትሰጣቸዋለች፡፡ ፊታቸው ላይ ያየችው ፈገግታ ለእሷ ከምንም በላይ ዋጋ ነበረው፡፡ ደግ ሰው የሌሎችን ደስታ ከማየት የበለጠ የሚያረካው ነገር የለም፡፡ እና በደስታቸው ተደስታ፣ በፈገግታቸው ረክታ ስታበቃ ከሰው አንድ በር ተበድራ ነበር ያን ዕለት ወደ ቤቷ የገባችው፡፡

ነሐሴ 1993 ዓ.ም 16 ዓመት የቆችበትን ስራ ለቃ ወደ አሜሪካን ተጓዘች፡፡ የሚወዷት፣ በደግነቷ የሚያደንቋት፣ በመልካም ሰውነቷ የሚያከብሯት፣ የስራ ባልደረቦቿ፣ ጓደኞቿ፣ ዳኞች፣ ጠበቆችና ዐቃቤ ህጎች እንዲሁም ወዳጅ ዘመዶቿ በሰው ሀገር መልካሙ ሁሉ ይገጥማት ዘንድ መልካም ተመኝተውላት ወደ አሜሪካን ተጓዘች፡፡

በስደት ህይወት ያጋጠማትን ፈተና በቆራጥነት ተወጣችው፡፡ ኑሮን አሸንፋ በድል ተወጣች፡፡ አምስት ልጆቿን የማሳደግ ኃላፊነቱን ለመወጣት ጠንክራ ሰርታ ራሷን ለመቻል በቃች፡፡ ቤተሰቦቿንም ወደ አሜሪካን ወሰደች፡፡ እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዘመዶቿንም ትረዳለች፡፡
በስደት ዴንቨር የደረሱ ወገኖቿ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ከሆነ የእርዳታ እጇ አይታጠፍም፡፡ በሰው ሀገር ያገኘቻቸውን ወገኖቿን በግል ድርጅቷም ሆነ በመስሪያ ቤቷ የምታስተናግድ፣ በዴንቨር ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን የሚያውቋት፣ የሚያደንቋት ደግ ሰው ነበረች፡፡
አንድ ቀን በዴንቨር ጎዳና ላይ አንድ ሰው ታያለች፡፡ ቀርባ ስታናግረውም ግራ የገባው የሀገሯ ሰው እንደሆነ ትገምታለች፡፡ እናም አልፋው ለመሄድ አልፈለገችም፡፡ መልኩ የሚመስላትን፣ የሀገሯ፣ የወንዟ ልጅ እንደሆነ የገመተችውን ሰው ግራ እንደገባው እያየችው እንዴት ትለፍ? ለተቸገሩ የሚያዝነው አንጀቷ ተገለባበጠባት፡፡ የሀገሯ ልጅ በሰው ሀገር የሚሆነውን አጥቶ ሲጨነቅ ስታየው ሀዘኑ ውስጧን ረበሻት፡፡ እናም ጠጋ ብላ አነጋገረች- አቶ ሸሞንዴ ገ/ሥላሴን፡፡

ሸሞንዴ ዴንቨር ከገባ አጭር ቀኑ ነረብ፡፡ በእዚያ ሀገር የሚያውቀው ሰው አልነበረም፡፡ ከሚያያቸውና ጎዳናው ላይ ከሞሉት ነጮች መካከል ቀልቡ ለፈቀደው ችግሩን እንዳይናገር የቋንቋ ችግርም ነበረበት፡፡ እንዲህ ግራ ሲገባው ነበር አልጋነሽ የደረሰችለት፡፡ ደማቸውና የቆዳ ቀለማቸው አንድ፣ የሚግባቡበትም ቋንቋ ተመሳሳይ፣ የአንድ ወንዝ ልጆች፣ እናም ሸሞንዴ ደስ አለው፡፡ የቸገረውን መርዳት፣ የተከፋውንና ያዘነውን ማፅናናት፣ የጎደለበትን መሙላት ባህርይዋ የሆነው አልጋነሽ አቶ ሸሞንዴን ከወደቀበት የዴንቨር ጎዳና ላይ አነሳችው፡፡ ጨለማ መስሎ የታየው የስደት ህይወት ላይ ብርሃን ፈነጠቀችለት፡፡ የእርዳታ እጇንም ዘረጋችለት፡፡ ውሎ ሲያድር ለሌሎች ባይተርፍም ለራሱ ግን የማያንስ ሰው እንዲሆን አደረገችው፡፡

እያደር መቀራረቡ ቀጠለ፡፡ ቢቀራረቡም መርዳቷን አላቋረጠችም ነበር፡፡ ለእሱ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ከመርዳት የሚታጠፍ እጅ አልበራትም፡፡ ለሰዎች መልካም የምትመኝ፣ ጥሩ የምታስብ፣ ሀይማኖቷን የምታከብር፣ የአምስት ልጆች ብቻ ሳይሆን የሌሎችም እናት ነበረች፡፡

(እ.ኤ.አ) ዲሴምበር 2/2006) ምሽት ላይ፡፡ ዴንቨር ጀምበር ጠልቃለች፡፡ የከተማይቱ እንቅስቃሴ ግን እንደዛው ነበር፡፡ ኑሮን ለማሸነፍ የሚጣደፈው ወደ ምሽት ስራው ይከንፋል፡፡ ሲደክም የሚውለው ደግሞ ጎኑን ለማሳረፍ ወደ ቤቱ ለመሄድ ይጣደፋል፡፡

አልጋነሽ የግል ድርጅቷን ዘጋች፡፡ የናፈቋትን አምስት ልጆቿን ለማየት፣ ጎኗንም ለማሳረፍ ወደ ቤቷ መድረስ ብቻ ነበር የምትፈልገው፡፡ ቀኗን በሰላም እንደዋለች ሁሉ ምሽቱም ሆነ ሌሊቱ የሰላም እንደሚሆንላት ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ አልነበራትም፡፡ ለሰው ደግ ነበረችና ማን በክፉ ያስበኛል ብላ ትጠራጠር? ለሰው የምታዝን ነበረችና የትኛው ሰው ይጨክንብኛል ብላ ትገምት? የሁሉ እናት ማን ጨካኝ እጁን ይዘረጋብኛል ብላ ትጠራጠር?

የግል ድርጅቷ በር መዘጋቱን አረጋገጠች፡፡ ከራሷና ከቤተሰቧ አልፎ ሌሎችንም እንድትረዳ ያስቻላትን ድርጅቷን ትወደዋለች፡፡ ድርጅቱን ለማስፋፋትና የተሻለ ለመስራት፣ ውጥኗን ወደ ተግባር ለመለወጥ የመጨረሻ የመሰናዶዋ ወቅት ነበር ያ ጊዜ፡፡ የዴንቨር ከተማ ባለስልጣናት ፈቅደውላታል፡፡ የሰሞኑን ሀሳቧ ይህ ነበር፡፡ እቅዷን ወደ ተግባር ለመለወጥ ነበር ምኞቷ፡፡

የመኪናዋን በር ከፍታ ገባች፡፡ የመኪናውን ሞተር እንዳስነሳች አንድ ሰው ወደ እሷ ተጠጋ፡፡ ቀና ብላም አየችው፡፡ የምታውቀው ሰው ነበር፡፡ አቶ ሸሞንዴን ገ/ሥላሴ፡፡ በድንገት መምጣቱ ቢያስገርማትም ስለት ያለው ቢላ እስኪያወጣባት ድረስ ግን የመጣው ለክፉ ነው ብላ አልተጠራጠረችም፡፡
የሞባይል ካርድ፣ የተለያዩ ቅመማ ቅመሞችንና የኢትዮጵያ ዕቃዎችን ከምትሸጥበት የግል ሱቅ በራፍ ላይ በራሷ መኪና ውስጥ፣ እየረዳች ሰው ባደረገችው ሰው በቢላ አንገቷን ያረዳት ሸሞንዴ ደሟ ከውስጧ ተንጠፍጥፎ ነፍሷ ከስጋዋ እስክትለይ ድረስ አጠገቧ ነበር፡፡ የዴንቨር ፖሊስ የሟቿን አስክሬን በዕለተ ቅዳሜ ምሽት በህንፃ ቁጥር 1400 በIVY ስትሪት እንዳገኘው በምርመራ ውጤቱ ላይ አስፍሮታል፡፡

የወ/ሮ አልጋነሽ ሞት እንደተሰማ የማያውቋትን ሁሉ ነበር ያሳዘነው፡፡ የገዳይዋ በፖሊስ ያለመያዝ ደግሞ ሀዘኑን እጅግ በጣም ነበር ያባባሰው፡፡ ይሁን እንጂ የዴንቨር ፖሊስ ይህንን ወንጀል የፈፀመውን ሰው ደርሰንበታል፣ አቶ ሸሞንዴ ገ/ሥላሴ ይባላል፡፡ ይህ ሰው አንደኛ ተጠርጣሪ ሆኖ በፖሊስ እየተፈገለ ነው፡፡ ግለሰቡ አራት በር ያለውና የ1995 ዓ.ም ስሪት የሆነ ፓንቲያክ ግራንድ (pantiac Grand) የሰሌዳ ቁጥር 493 N.P.B የሆነ መኪና ያሽከረክር እንደነበር ገልፆ ያየው ሰው ለዴንቨር ፖሊስ እንዲጠቁም መግለጫ ያወጣል፡፡
በዴንቨር ያሉ ኢትዮጵያውን በመልካም ተግባሯ፤ በደግነቷ የሚያደንቋት፣ ኢትዮጵያውያን ወዳጆቿ፣ በሰው ሀገር የምታሳድጋቸው ልጆቿና የምትረዳቸው ዘመዶቿ የተገኙበት ቀብሯ ተፈፀመ፡፡ ከቀብር መልስ የሁሉም መነጋገሪያ የነፍሰ ገዳዩ ጉዳይ ነበር፡፡ ለምን እንደገደላትም አልታወቀም፡፡ በተቻላት ትረዳው ነበር እንጂ በመሀከላቸው ለግድያ የሚያበቃ ምክንያት አልነበረም፡፡ የ12 ዓመቱ የወ/ሮ አልጋነሽ በርሄ ልጅ ሳሙኤል ካሳዬ ‹‹እናቴ በጣም ግሩም ነበረች፡፡ በጣም ጥሩ ነበረች፡፡ ይህንን ሁላችሁም ታውቁት ነበር›› ሲል ነበር ስለ እናቱ መልካም ሰውነት የተናገረው፡፡
ለቀሪ ወገኖቿ ዘላለም የማይረሳ የሀዘን ጠባሳ ጥላ ያለፈችው አልጋነሽ ከተገደለች ቀናት ተቆጠሩ፡፡ የዴንቨር ፖሊስ በአንደኛ ደረጃ በነፈስ ግድያ የጠረጠረውን ግለሰብ ለመያዝ ክትትሉን ቀጥሏል፡፡ ይህ በነፍስ ግድያ የተጠረጠረው ግለሰብ ሎስ አንጀለስ ከተማ ውስጥ መታየቱ ለፖሊስ ጥቆማ ይደርሰዋል፡፡ ሰውዬውን እንዳዩ ለፖሊስ የጠቆሙት ደግሞ ሀይማኖታዊ አገልግሎት የሚሰጡ አንድ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ ፖሊስ ከግለሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተጠርጠሪውን ለመያዝ የተጠናከረ ክትትል ማድረጉን ቀጠለ፡፡ ወ/ሮ አልጋነሽ ከተገለደች ከአስር ቀናት በኋላ ግለሰቡ ከሎስ አንጀለስ ወደ ሜክሲኮ ለመሻገር ሲሞክር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ለመዋል በቃ፡፡

የተጀመረውን የፍርድ ሂደት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነበር የሚከታተለው፡፡ ጃንዋሪ 14/2007 ደግሞ በሀመረ ኖህ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን የ40 ቀን የመታሰቢያና የፀሎት ስነ ስርዓት ተደርጎ ነበር፡፡

ወ/ሮ አልጋነሽን ገድሏል ተብሎ ተጠርጥሮ ታስሮ የነበረው ሻሙዲ ገብረስላሤ

ወ/ሮ አልጋነሽን ገድሏል ተብሎ ተጠርጥሮ ታስሮ የነበረው ሻሙዲ ገብረስላሤ

በነፍስ ግድያ ተጠርጥሮ የተያዘው አቶ ሸሞንዴ ገ/ሥላሴ ያደረገችለት እርዳታ በሰው ለመገደል የሚያበቃት ሳይሆን ሰው ሆኖ ራሱን እንዲችል በማብቃቷ ልትመሰገን እንደሚገባት ነው በደንብ የሚያውቋት ሰዎች የሚናገሩት፡፡ ‹‹ሰው ማለት ሰው በጠፋ ጊዜ ሰው የሚያደርግ ነው›› የሚል ብሂል በዚህ ዘመን አይሰራም ይላሉ የነፍስ ገዳዩን ጭካኔ የሚገልፁ ሰዎች፡፡ መልካም ማድረግ ለሞት የሚያበቃ ነው ወይ? የብዙዎች ጥያቄ ነው፡፡ ለምን በቢላ አርዶ እንደገደላትም በግልፅ የሚታወቅ ምክንያት የለም፡፡ የዴንቨር ፖሊስም በዚህ ዙሪያ የገለፀው ነገር የለም፡፡

የነፍስ ግድያው ወንጀል ለፍርድ ቤት ቀርቦ ጉዳዩን ሁሉም እየተከታተለው ነበር፡፡ ግን ጉዳዩ ከወራት በፊት በእንጥልጥል ቀረ፡፡ በዴንቨር ፍርድ ቤት የተከፈተው ፋይል ውሳኔ ሳይሰጥበት ተዘጋ፡፡ በነፍስ ግድያ የተከሰሰው ሸሞንዴ ገ/ሥላሴ በእስር ቤት እያለ በኤሌክትሪክ የራሱን ህይወት ማጥፋቱ ነበር ለፋይሉ መዘጋት ምክንያት የሆነው፡፡ አንዳንዶች ተከሳሽ የራሱን ህይወት ያጠፋው በፈፀመው የጭካኔ ግድያ ተፅእኖ ነው ብለው ይገምታሉ፡፡ ግምቱ እውነት ቢሆን እንኳን ወ/ሮ አልጋነሽ የእሷን እገዛ የሚሹ ያለ አባት የምታሳድጋቸውን አምስት ልጆቿን በሰው ሀገር በትና በጭካኔ ተገድላ ይህችን ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡

አትሌት ቤተልሄም ሞገስ የአምስተርዳምን ማራቶን አሸነፈች

$
0
0


(ዘ-ሐበሻ) በሆላንድ አምስተርዳም በተደረገው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ቤተልሄም ሞገስ ድል ቀናት።
Betelhem Moges zehabesha
በዚሁ ተመሳሳይ ዓመት በዱባይ ማራቶን ድል ቀንቷት የነበረችው አትሌት ቤተልሄም ሞገስ የአምስተርዳሙን ማራቶን ለማጠናቀቅ የፈጀባት ጊዜ 2:28:35 ሲሆን ኬንያዊቷን አትሌት ኦልጋ ኪማዮን አስከትላ ገብታለች ያሉት የዘ-ሐበሻ የአምስተርዳም ዘጋቢዎች ቤተልሄም ኦልጋን በ40 ሰከንዶች ቀድማ የገባች ሲሆን ያስመዘግበችው ውጤትም በአመርቂነቱ ተመዝግቧል ብለዋል።

ወጣቷ አትሌት ቤተልሄም 2:28:35 ከሮጠች በኋላ አንዳችም የድካም ስሜት ያልታየባት ሲሆን ይህም ኢትዮጵያ ወደፊት ኦሎምፒክን ጨምሮ በዓለም ዋንጫና በሌሎች መድኮች ለሚጠብቃት የማራቶን ውድድሮች ትልቅ ተስፋን ጥሏል።

ቤተልሄም እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ሜይ 3 ቀን 1991 ነው የተወለደችው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በ34ኛው የቤንጂንግ ኢንተርናሽናል ማራቶን ላይ የተካፈለው ኢትዮጵያዊው አትሌት ግርማይ ብርሃኑ ገብሩ በአሸናፊነት አጠናቀቀ።
Girmay Birhanu gebru
ከ55 ሃገራት በላይ የመጡ አትሌቶችና 30 ሺህ የሚጠጉ ራጮች በተካፈሉበት በዚሁ የማራቶን ውድድር ግርማይ ውድድሩን ለማጠናቀቅ የፈጀበት 2 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ከ42 ሰከንድ ነው።


የማለዳ ወግ …የጅዳው ት/ቤታችን እንደ አረቡ አብዮት ከድጡ ወደ ማጡ! –ነብዩ ሲራክ (ከሳዑዲ አረቢያ)

$
0
0

* ታዳጊዎች የተሟላ ትምህርት አያገኙም
* ወላጅም ዝምታን መርጧል

nebyu sirakየጅዳ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት በተወሳሰበ የአሰራር ፣ አመራር ሂደት ውስጥ በማለፍም ቢሆን የመማር ማስተማር ሒደቱን ከጀመረ ሁለት ወር ደፍኗል። በሁለት ወራት ልጆቻችን ተምረው ተመለሱ ብሎ ለጠየቀ ምላሹ ቆሽት ያሳርራል ። በእስካሁኑ የትምህርት ቅበላ ባለው ከስድስት ያላነሰ ክፍለ ጊዜ የሚማሩት ከሁለትና ሶስት ከፍለ ጊዜ ሲሆን አልፎ አልፎ አራት ክፍለ ጊዜ ብቻ ብቻ ተመረው ይመለሳሉ ። ይህን እውነታ ልጆቹን እንደማዋያ ጥሎ ዘወር የሚለው ባይተዋር ወላጅ ከልጆቹ ይሰማዋል። የልጆቹን ደብተር አገላብጦ የሚመለከት የእኔ ቢጤ ብስጩ አባት ደግሞ ከልጆቹ ከመስማት አልፎ በማስረጃ ደብተሩን ሲያገላብጥ የሚታዘበው እውነታ ነው ።

በአንዳንድ ክፍሎች ዘመናዊውን ትምህርት ትምህርት የሚያሰኙት የእንግሊዝኛና የሒሳብን ጨምሮ ከፍ ሲል የኬሚስትሪ፣ የፊዚክስና የኮምፒውተር ትምህርቶች መሰጠት የተጀመረው በያዝነው ሳምንት ነው ። የሚያም እውነት ነው … ልጆች በተወለዱበት ሃገር ዜግነት ቀርቶ ፣ ቅንጣት ልዩ መብት አይሰጣቸውም ። ይህ በሆነበት የአረብ ሀገሩን ስደት መከራና የኑሮ ውጣ ውረድ ላገናዘበው ፣ ማህበረሰቡ በራሱ ጥረት ት/ቤት መስርቶ አስፈላጊ ክፍያ ፈጽሞና ልጅን ትምህርት ቤት ሰዶ ያልተማረ ልጅን መቀበል ግፍ ነው ፣ አመቱን ሙሉ ወደ ትምህት ገበታ ሳይሆን ወደ ማዋያው ማመላለስ የለየለት ዝቅጠት ነውና ከዚህ መከራ ይሰውረን !
saudi arabia
ዛሬ ማለዳ አንድ የፊስ ቡክ ወዳጀ ስለትምህርት ቤቱ መረጃ ያቀበሉኝ አዝነው ነው፣ ማምሻውን ደግሞ ብርቱ ውስጥ አዋቂ ወዳጀ ስልክ ደውሎ “ምነው የትምህት ቤቱን ጉዳይ ረሳህውሳ ? ቢያንስ ይጻፍ የሚሰማ ቢገኝ! ” ሲል የውስጥ የውጩን የተተረማመሰ አሰራርና በየደቂቃው የምሰማውን የወላጁን ሮሮ አስተጋባልኝ …ገፋፍቶኝ ወደ ከሸፈው የኮሚኒቲ የአመታት የለውጥ መንፈስ ነጎድኩ … ተመለስኩና ሌላ የከሸፈ ታሪክ የአረቦች የጸደይ አብዮት አቀናሁ … ከምናቡ ቅኝት ተመልሸ የጅዳው ት/ቤታችን እንደ አረቡ አብዮት ከድጡ ወደ ማጡ .. . ብየ ጀመርኩት ፣ ህመሜን ልተንፍስ በሚል … ከቀደመው ልጀምር …
የተሻለ ይመጣ መስሎን በድክመቱ ላይ አተኩረን ሳናመሰግነው ያለፍነው የቀድሞው ኮሚኒቲ ትልቅ ስራ ሰርቶ ማለፉን ማሰታወስ ግድ ይላል ። የዛሬን አያድርገውና የጅዳ ኮሚኒቲ የውስጥ ችግሩ እንዳለ ሆኖ በትምህርት ቤቱ ዙሪያ ያደርግ የነበረው ትልቅ ድጋፍ የሚዘነጋ አይደለም ። የቀድሞው አሁን ካለውና በድርጅት ሰዎች ጫና ውሳኔ እንደ ሚያሳልፍ ከሚነገረን ኮሚኒቲ የተሻለ ነው የምንለው በርካታ መምህራንን አስመጥቶ ስለነበርና በመማር ማስተማሩ ጠንካራ አቋም ነበረውና ነው ።

የቀድሞው ኮሚኒቲ ከአስር ያላነሱ መምህ ራንን ከሃገር ቤት አስመጥቶ ነበር … ግን አልበረከቱም ። አለመበርከታቸው ፈርጀ ምክንያት አለው። ድንቅ ድንቅ የሚባሉ መምህራን በትምህርት ቤቱ አስተዳደር፣ በሚኒቲ ጣልቃ ገብነትና በራሳቸው የግል ጉዳይ ሃገር ቤት ሄደው እዚያው ቀርተዋል … የትምህርት ቤቱን ዳይሬክተርን ጨምሮ ፣ ከሃገር ቤት መጥተው ከእኛ ጋር የከረሙትም ባለሙያ መምህራን ዛሬም አሉ ፣ ከማስተማሩ ክልል ግን በሹመት ሰበብ ገለል እያሉ ነው ። “በምርጫ ” የትምህርት ቤቱን ዋና ዋና ኋላፊነት ቦታወች ተቀዳጅተዋል፣ በውጭ ህይወታቸው ዲሞክታሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው በዲሞክታሲያዊ ፖለቲካ አባልነት ሲመለመሉና ሲጠመቁ አሁንም ” በምርጫ” የገዠው መደብ የኢህአዴግ የፖለቲካ ድርጅት ቁንጮ ባለስልጣናት ሆነዋል ፣ በስራና ስብሰባም ተወጥረዋል። ጥቂት ወደ ውስጥ ገባ ካልን የምናገኘው ደስ አይልም። በዚህ ሁኔታ መምህር እያለ መምህር ፣ የማጣታችን ያማል …

የቀድሞው ኮሚኒቲው ከሃገር ቤት የኬሚስትሪ መምህር ቢያስመጣም መምህሩ የአስተዳደር ሹመት እና ሌላም በድርጅት ስልጣን ተንበሽብሸዋል። “መሽ አላህ ብያለሁ ፣ ሹመት ያዳብር ” የማልለው ታዳጊዎች እየተጎዱ ስለ ለመሆኑ ዋቢ ጠቅሸ ማስረዳት እችላለሁና ነው ። …

በቀድሞው ኮሚኒቲ ትምህርት ቤቱ በአንድ ወቅት አስመጥቷቸው የነበሩት የሒሳብ መምህር በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቁ ወጣት ምሁርን ነበሩ ፣ አለመታደል ሆኖ ንቃት ትጋት ተቆርቋሪነታቸው ለትምህርት ቤቱ የበላይ ሃላፊነት መመጠናቸው አልተፈለገምና በረቀቀ መንገድ ተወገዱ …

የኮምፒውተር መምህርም በቀድሞው ኮሚኒቲ ትጋት ከሃገር ቤት አስመጥተን ነበር ፣ ባለ ሙያውን በአግባቡ መያዝ ባለመቻሉ መምህሩ ሃገር ቤት ሄደው ቀሩ …

ቀጠለና ከአመታት በፊት የኮምፒውተር አስተማሪ እዚሁ በወጣ ማስታወቂያ ተገኘና ቅጥሩ ተፈጸመ። ከጥቂት አመታት በኋላ ግን ማለትም ካሳከፍነው አመት ጀመሮ በሙሉ ሃይላቸው ከማስተማሩ የሚገታቸው የትምህርት ቤቱ ዩኒት ሊደርነት ሃላፊነት ተሰጣቸው ። እነሆ ዛሬ የኮምፒተሩ መምህር በተሰጣቸው ሹመት መሰረት ማስታማሩን ትተው መምህር የሌላቸው ተማሪዎችን ሲያሯሩጡ ይውላሉ ! ይህስ አያም ፣ አያሳዝንም ?

በአሳር በመከራ ወላጅ ስብሰባ ተጠርቶ ሲሰበሰብ ትውልድ በማነጹ ስራ ስለመጓተቱ ፣ ስለ መምህራን እጥረት ፣ ስለ ማስተማሪያ ቁሳቁስ እና ስለትምህርት ጥራት ፣ ስለ ደመወዝ ማነስ ፣ ስለ አጠቃላይ አሰራር መጓተት ሂደት መረጃ አጣቅሰው ትምህርት ቤቱ ያለበትን አደጋ ሲናገሩት መስማቱን ለምደነዋል ። በዚህ ደረጃ እየተመራ ያለውና እየመሩን ያሉት የትምህርት ቤቱ ሹማምንት የሚሰሩት ጠጋ ብለን ስንጠይቃቸው ” ጎደለ” የሚሉትን ለማሟላት ስላለመስራታቸው አጥጋቢ የምለው ምክንያት አለኝ …

ትምህርት ቤቱ ከጀመረ ጀምሮ እንግሊዝኛ በማስተማር ትልቁን ክፍተት ይሸፍኑ የነበሩት ህንዳዊ መምህር ሚ/ር ሳንቱሽ ሲጓተት የተበለሻሸ የመኖሪያ ፈቃድ ማዛወር ሒደት አልተሳካም። ይህም ለጎደለው ትምህርት ፣ ለማስተማሩ ክፍተት መሆኑ ብዙዎች መናገር የምንፈራው እውነት ነው ። ኮሚኒቲው ሃላፊዎች የእውቁና ባለ ውለታ መምህሩን የሚ/ር ሳንቶሽ ፈቃድ ቅየራ ባጓተቱበት እጃቸው የትምህርት ቤቱ ስም በሚሰጠው ፈቃድ የካፍቴሪያው ሰራተኞችን እንደ ባለሙያ አድርጎ ፈቃድ ማስተካከሉ ተሳልጦላቸዋል። ዛሬ ብትቱው መምህር ሁለመናው ከሽፎባቸው ፣ ከቤት ውለዋል አሉ ። እኛም ትጉህ መምህር አጥተናል ! በትምህርት ቤቱ ዙሪያ በዘመድ አዝማድ በተሳሰረው አሰራር የሚታየውና የሚሰማውን ሁሉ ፍትሃዊ የአለመሆን ሂደት ውስጥን ያደማል ፣ ቢያብከነክንም አይጠቅምምና ወደ ውስጥ ዘልቄ አልነካካውም። … ሁሉን ተናግሬ ሆዴ ባዶ እንዳይቀር ቢስተካከል በሚል እሳቤ ከተጨበጠው መረጃ ግን ጥቂት ጥቂት ብቻ እየቆነጠርኩ መናገሬን ልብ በሉ …

የከሸፈው የጸደዩ አብዮት …

ዛሬ ዛሬ የእኛ ትምህርት ቤት ነገር እንደ አረብ ሃገሩ ” የጸደይ አብዮት” ሆኖብናል ። የጸደዩ የአረቦች አብዮት ማዕበል ሃይለኛ ነበር ። የቱኒዝያ ንጉስ ፕሬዚደንት ቢን አሊ ገርስሶ ፣ ሶስት ክፍለ ዘመን የተሻገረውን የግብጽን ፕሬዚደንት የሁስኒን አንባገነን መንግስት ደረማምሶታል። የማይመስል ፣ አይሆንም ተብሎ የሚገመተው በአብዮቱ ማዕበል ተንጦና ተደረማምሶ አይተናል። የአብዮት ማዕበሉ ሊቢያ ላይ ሲያርፍ “የአፍሪካ ንጉሰ ነገስት ነኝ ” ባዩን ፕሬዚደንት ጋዳፊን ከነምናምናቸው ደብዛቸውን አጥፍቷቸዋል። የየመኑን ፕሬዚደንት ሳላህን አላስቀራቸውም ። ከተረጋጋውና በሳውዲ የሚደገፈውን ወንበራቸው በማዕበሉ ተጠቅቶ ፣ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኛ መሆናቸውን በሹክሹክታም ቢሆን ሰምተናል። የመን ግን ከአንድ ሃገርነት ልትወጣ መከራዋን እያየች ነው … የቀድሞዋ ጥንታዊ አረብ ሃገር የሻሟ የአረቦች ቅምጥል ሃገረ ሶርያ የአብዮቱ ማዕበል ጎድቷት ከሃገር ተራ ወጥታለች … ሶርያ የሃያላኑ ምዕራባውያን የእነ አሜሪካና አጋሮቿ ፣ የራሻና ፣ ቻይናና የኢራን ጉልበት መፈተሻ የጦርነት ቀጠና ፣ የለየላቸው ጨካኝ አክራሪ ጽንፈኞች መፈንጫ የደም ሆናለች ….ሶርያ !
ተጠልፏልና ያልጠቀመው አብዮት …

እነሆ አብዮቱ ለሁሉም አልበጃቸው ፣ ይህን የምለው ሃገራት ከሃገርነት ተርታ በሚያወጣ እሰጣ ገባ ቋፍ የመገኘታቸው እውነታን ማየታችን ነው ። ብቻ አየሆነ ያለው በአብዮቱ የተገኘው የመልካም ለውጥ ትንሳኤ ምሳሌ ሳይሆን መልካሙ የለውጥ ጀምር በእኩዮች ተጠልፎ ለውጡ ውድቀት ዘመም መሆኑን ነው ። አብዮቱ ድሉን መትቷል እንዳንል አብዮቱ የተካሔደባቸው ሃገራት የገቡበት ከማጥ ወደ ማጥ የመሆኑን ሃቅ ስናጤነው ብቻ ነው … ይህ በመሆኑ ከአብዮቱ መባቻም የነዋሪው መከራ ካለፈው የከፋ ሆኗል! የሆነው የተፈለገው ሳይሆን ያልተጠበቀው ነውና … !

የተመሳሰለብኝ የእኛው ጉዳይ …

የማይገናኘውን ታላቅ የታሪክ ሂደት ከደቃቃው የእኛ ገጠመኝ ጋር ማመሳሰሉ አይገጥምምና ይገርማችሁ ይሆናል … ትልቁን ከትንሹ ማዛመዴ የለውጡን ፍላጎት ፣ በለውጡ መባቻ በጀርባ የተጠለፈውን የለውጥ መንፈስ ተመሳሳይ ሂደት ለማጣቀስ ይረዳኝ እንደሁ ብየ ነው …ቢጨነቀኝ ! በጅዳና አካባቢዋ ለማህበረሰቡ ጥቅም መከበር በማሰብ የተሻለ ይመጣ መስሎን በቀድሞው ኮሚኒቲ ድክመት ላይ አተኩረን ለለውጡ መረባረባችን እውነት ነው ። ለውጥም መጥቶ ነበር ፣ ለውጡ ግን በጉልበተኞች ተጠለፈ ! የተረባረብንበት የደከምንበት ሁሉ ለዛሬው ፍዳ አደረሰን ….ምርጫው ተጠልፎ ለውጥ ሊመጣ ቀርቶ እያዘገምን ያለው መንገድ በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል … መፍትሔ ጠቁም እንዳትሉኝ ፣ ለመፍትሔው ከሁላችንም ምክክር መምጣት ይገባዋል ፣ ከሁሉም በላይ የ3000 ተማሪዎች የትምህርት ቅበላ በዋናነት የሚያገባቸው የመንግስት አካላት አደባባይ በሚታየው የገዘፈ የትውልድ ግንባታ አደጋ ላይ ወድቋልና “ያገባናል ” ብለው ስላልመከሩ ቂም ይዘን አንወቅሳቸውም ፣ አሁንም ለተቀመጡበት ወንበር ፣ ለቆሙለት ዜጋ ፣ ለሚከፈላቸው ክፍያ ሁሉ ቀርቶ ላስተማረቻቸው ሃገር ትንሳኤ ለተተኪው ትውልድ ሲሉ የ3000 ተማሪዎችንና የትምህር ማዕከሉን ሊታደጉት ይገባል። በዚህ ዙሪያ ገብ የጉዳዩ ባለቤቶችን ዜጎችን ማወያየት ከሹሞቻችነወ ይጠበቅባቸዋል ! ….. እኛ የሚያገባን ግን ፣ ይህ ሆነ አልሆነ ትናንትም ዛሬም እንደምናደርገው የሃገር ተረካቢ ልጆች ጉዳይ ” ያገባናል” ፣ ወላጅ በፍርሃት ተሸብቦ እንኳ ዝምታን ቢመርጥ እንመክር እንጦምርበት ዘንድ ግድ ብሎናል ! ጆሮ ያለው ይሰማል ፣ ሰምቶ የዝሆን ጀሮን የተመኘ ጥቁር የታሪክ አሻራን መጣሉን ልብ ቢል መልካም ነው !
ቸር ያሰማን
ነቢዩ ሲራክ

በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ ጫናው በርትቷል “ሰላማዊ ትግል የሚባል ነገር አይሰራም፤ ጫካ ገብታችሁ ሞክሩን›› -የብአዴን አመራሮች

$
0
0

• ‹‹ሰላማዊ ትግል የሚባል ነገር አይሰራም፤ ጫካ ገብታችሁ ሞክሩን፡፡››
የብአዴን አመራሮች

በምስራቅ ጎጃም ዞን የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ከገዥው ፓርቲ ባለስልጣናት የሚደርስባቸው ጫና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ የምስራቅ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ጸሃፊ የሆነው ጠበቃ ሳሙኤል አወቀ በእሱና በሌሎች የፓርቲው አመራሮችና አባላት ላይ ዛቻ እንደሚፈጸምባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
blue party

የምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ ቢሮ በ2006 ዓ.ም የእቅድ ግምገማ እና የ2007 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም እቅድ በተወያየበት እና የሁሉም ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የስራ ሂደት ባለቤቶች በተገኙበት፣ ‹‹ሳሙኤል አወቀ የሚባል በጥብቅና ሽፋን የመሬት ፖሊሲውን የሚታገል፣ ለተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ደጋፊ አርሶ አደሮች ጥብቅና የሚቆም፣ ከአሸባሪ ጋር ግንኙነት ባለው ድርጅት አመራር የሆነን ግለሰብ በህግ ሽፋን እስር ቤት እንዲወርድ ያላደረገ አቃቤ ህግ አቃቤ ህግ አይደለም›› ተብሎ በህግ ስም እርምጃ እንዲወሰድበት ትዕዛዝ መተላለፉን ጠበቃው ገልጾአል፡፡

በተለይ የደብረማርቆስ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት አቃቤ ህጎች ዋነኛ ችግራቸው ጠበቃ ሳሙኤልን በህግ ስም ማስቀጣት አለመቻላቸው እንደሆነ ተገምግመዋል ተብሏል፡፡ ጠበቃው ወዲያውኑ የፈጠራ ክስ እንደተመሰረተበት፣ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ‹‹ለፍትህ ስርዓቱ አጋዥ ባለመሆኑ›› በሚል መከሰሱንና ባልተከራከረበት ፍርድ ሂደትም 8000 ብር ቅጣት እንዲከፍል እንደተወሰነበት ገልጾአል፡፡

ጠበቃው በ28/1 እናርጅ እናውጋ ለቀጠሮ ባቀናበት ወቅትም የእናርጅ እናውጋ አስተዳደርና ጸጥታ ኃላፊ አቶ ስራው በረኩ እና የብአዴን የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ መኳንንት አበበ እና ሌሎችም ከፖሊስና ከጸጥታ የመጡ አመራሮች ‹‹ምን ልታደርግ ነው? ልትቀሰቅስ ነው?›› በሚል እንዳዋከቡትና አቶ ስራው በረኩ ‹‹አንጠልጥዬ ነው እስር ቤት የማስገባህ፡፡ ማንም ሊያድንህ አይችልም›› ብለው እንደዛቱበት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

‹‹የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሆነህ በፍትህ ስርዓቱ መገልገል አትችልም፣ ጥብቅናህን መልቀቅ አለብህ፣ ነገረ ኢትዮጵያ ላይ ትጽፋለህ፣ የፍትህ መምሪያ ሃላፊውን (ጸጋየ መንግስቴ) ችግር እንደሚፈጽምብህ በነገረ ኢትዮጵያና በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ ጽፈህበታል፣ እንዲህ እያደረክ መኖር አትችልም፣ አንተን ገሎ መጣል ቀላል ነው፣ ለነፍስህ የምታዝን ከሆነ አገር ልቅቅ›› ብለው እንደዛቱበት ገልጾአል፡፡

ሌሎች ጠበቃ ጓደኞቹ ከእሱ ጋር እንዳይሄዱ ‹‹እሱ ማለት ሰማያዊ ነው፡፡ ሰማያዊ ደግሞ የአክራሪ ሙስሊም ፓርቲ ነው፡፡ እናንተ ለምን ከእሱ ጋር ትሄዳላችሁ?›› ብለው እንደሚያስፈራሯቸውና ደንበኞቹ ከእሱ ጋር እንዳይሰሩ ማስጠንቀቂያ እንደሚደርሳቸው ጠበቃው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

ጠበቃውን ጨምሮ ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት የሰማያዊ ፓርቲ አመራርና አባል ሆነው ማደራጀት መብታቸው መሆኑን ሲገልጹ የብአዴን አመራሮች ‹‹እናንተ እኛን ስለማትረዱን ነው፡፡ እኛ ጋር ሰላማዊ ትግል የሚባል አይሰራም፡፡ ወንድ ከሆናችሁ ጫካ ገብታችሁ ሞክሩን›› በሚል ለህግ የማይገዙና ለሰላማዊ ትግል ቁርጠኝነት እንደሌላቸው አሳይተውናል ብለዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የሰማያዊ ፓርቲና አመራር የሆኑ ነጋዴዎች ከፓርቲው እንዲለቁ ለማድረግ የንግድ ድርጅታቸውን እንደሚዘጉ እያስፈራሩ እንደሆነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ለአብነት ያህልም አቶ ይኸይስ ቀጸላ የተባሉ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ‹‹ሻይ ቤት ከፍተው እያደራጁ ነው፡፡ የንግድ ድርጅቱን እንደ ጽ/ቤት ይጠቀሙበታል፡፡ በመሆኑም ካላረፉ ሻይ ቤቱን እንዘጋዋለን›› እያሉ እንደሚያስፈራሩ ታውቋል፡፡

የዞኑ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት የገዥው ፓርቲ ዛቻና ማስፈራሪያ እንዲሁም እርምጃዎች እየተጠናከሩ ቢሆንም እርምጃው እነሱ ተጽዕኖ በመፍጠራቸው የመጣ በመሆኑ ይበልጡን እንደሚያበረታታቸውና የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

አቶ መኳንንት አበበን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችን የእጅ ስልካቸው ላይ በመወደል ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፡፡

የአዲሱ ወጣት የአንድነት መሪ፣ በላይ ፍቃዱ ቃለ ምልልስ

$
0
0
Belay Fekadu

አቶ በላይ ፍቃዱ የአንድነት ፓርቲ ፕሬዘዳንት

“ማር እንኳን 23 አመትት ቢላስ ይመራል ። 23 አመት እንደ ኢሕአዴግ ላለ ፓርቲ እጅግ በጣም ረጅም አመት ነው”
“ሕዝቡ ለዉጥ ይፈልጋል። በዚህ ላይ ምንም አነት ጥርጣሬ የለም፡፡በመላው ኢትዮጵያ ሲኬድ ይሄን አይነትት ስሜት አለ”
“ትልቁ ነገር አማራጭ ሆኖ ሕብረተ ሰቡ ተስፋ ሊይደርገው የሚችል ፓርቲ ሆኖ መዉጣት የውወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ ይመስልኛል”

“አንድነት የሁሉም ኢትዮጵያዊያኖች ቤትና ፓርቲ እንዲሆን ለመስራት ከፍተኛ ትጋት እናደርጋለን። በፕሮግራም በደንብ ደረጃያአንድነት ከሁሉም ፓርቲ በሚለይ መንግድ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያኖች በሚያቅፍ ሁኔታ የተዋቀረ ነው። በአሰራርና ቶበአካሄድ አንዳንድ ክፍተቶች አሉብን ፣ ስለዚህ እነዚህ ክፍተቶችን የመሙላትና፣ በቀን ተቀን ስራዉ ሁሉም ኢትዮጵያዉያኖችን ማቅቀፍ የሚችል መሆኑን ማሳየት አለብን።”
ከላይ የተጠቀሱት ፣ አቶ በላይ ፍቃደ፣ አዲሱ ወጣት የአንድነት ፓርቲ ፕሬዘዳንት፣ ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን ለአንድነት ራዲዮ ከተናገሩት የተወስደ ነው።
አቶ በላይ ለመረጧቸዉና ለደገፏቸው ምስጋናቸውን አቅርበው፣ ከርሳቸው የተሻለ ሌሎች አሉ ብለው ሌሎችን ለደገፉ
ከፍተኛ ክብርርና አድናቆት እንዳላቸው የገለጹት ሲሆን፣ አሁን ግን የመሰባሰብና የስራ ጊዜ እንደሆነም አስረድተዋል።
የተቃዋሚዎች መዳከምና አማራጭ ሆኖ አለመገኘት ለኢሕአዴግ መቆየት ምክንያት እንደሆነ የሚናገሩት አቶ በላይ
ከሌሎች ድርጅቶች ጋር አብረዉ እንደሚሰሩ፣ ከወዲሁ ንግግሮች እንደትጀመረና ሁኔታው በሂደት እንደሚገለጽ ሳይጠቁሙ አላለፉም።
“ኑና አብረን እንስራ” ሲሉ፣ በአገር ውስጥና ከአገር ዉጭ ላሉ ኢትዮጵያዉያን መልእክታቸውን ያጠናቀቁት አቶ በላይ፣ ትግሉ የጥቁቶች ሳይሆን የሚሊዮኖች እንደመሆኑ፣ ሁሉም ዜጋ ትግሉን እንንዲሳተፍና እንዲተባበር ተማጽኖ አቅርበዋል።

Hiber Radio: ኢትዮጵያ የኢቦላ ተጠርጣሪዎችን ናሙና ወደ ኬኒያ እንደምትልክ አንድ የአገሪቱ ባለስልጣን ገለጹ; * ካራቱሪ በኪሳራ ሳቢያ መሬቱን አሳልፎ እየሸጠ መሆኑ ተጋለጠ

$
0
0

የህብር ሬዲዮ ጥቅምት 9 ቀን 2007 ፕሮግራም !

<...>>

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


ጋዜጠኛ ኤልያስ ጉዲሳ የቃል ኪዳን መጽሔት ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር በስደት ካለበት ኬኒያ የአገዛዙ ሰዎች እንዴት በሞት የተለየውን የሙያ አጋሩን እንኳን መሰናበት እንደከለከሉት ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ምላሽ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)

<...>

አቶ ኤርሚያስ ለገሰ የቀድሞ በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረጉት ቃለ ምልልስ(ሙሉውን ያዳምጡት)

ኢቦላ እና ዛሬም ያልተቀረፈው ስጋት በአሜሪካ (ልዩ ዘገባ)

ዜናዎቻችን

ኢትዮጵያ የኢቦላ ተጠርጣሪዎችን ናሙና ወደ ኬኒያ እንደምትልክ አንድ የአገሪቱ ባለስልጣን ገለጹ

ሰፊ መሬት በኢትዮጵያ ያለው ካራቱሪ በኪሳራ ሳቢያ መሬቱን አሳልፎ እየሸጠ መሆኑ ተጋለጠ

በኢትዮጵአ በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ በምርጫ ማውረድ እንደማይቻል የስርዓቱ የቀድሞ ሚኒስትር አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ገለጹ

አቶ ሌኒጮ ለታ ምክትላቸውን ተከትለው አዲስ አበባ በቅርብ ቀን እንደሚገቡ ድርጅታቸው አስታወቀ

የዶ/ር ዲማ ነጎ ኢትዮጵአ መግባት አነጋጋሪ ሆኗል

ኤርትራ ውስጥ የመንግስት ለውጥ ያስፈልጋል ያሉ አንድ የተባበሩት መንግስታት ኤክስፐርት ስልጣናቸውን ለቀቁ

ኤርትራ አልሸባብን ሳይሆን የኢትዮጵያን ትጥቅ ያነሱ ተቃዋሚዎች እንደምትረዳ ተገለጸ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Sport:አሰልጣኝ ስቲቨን ኬሺ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ሊረከቡ ነው

$
0
0

new ethiopia coach zehabesha
ለናይጄሪያ የ2013 የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊነት እና ለ2014 የአለም ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ማለፍ ምክንያት የነበሩትና በቅርቡ ከስራቸው የተነሱት አሰልጣኝ ስቲቨን ኬሺ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን የማሰልጠን ስራ ከአሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ በመረከብ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ለመነጋገር በዚህ ሳምንት አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፣ ሲል አንድ የፌዴሬሽኑን ምንጭ ዋቢ አድርጎ AfricanFootball.com የተባለው ድረ ገጽ ዘገበ።

Health: “ሬድ ቡል”ን የመሳሰሉ ሃይል ሰጪ መጠጦች የጤና ችግር ያስከትላሉ ተባለ 

$
0
0

“ሬድ ቡል”ን የመሳሰሉ ሃይል ሰጪ መጠጦች በተለይ ከአልኮል መጠጥ ጋር ተደባልቀው ሲጠጡ የጤና ችግር ሊያስከትሉ እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት ተመራማሪዎች አስጠነቀቁ፡፡

RedBullበአውሮፓ የተደረገ ጥናት እንዳረጋገጠው፣ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑ እድሜያቸው ከ18-29 ዓመት የሚደርሱ ወጣቶች፣ እንደ “ሬድ ቡል” ያሉ ሃይል ሰጪ መጠጦችን (Energy drinks) ከአልኮል መጠጥ ጋር እየደባለቁ ይጠጣሉ፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ጥናት እንደሚለው፤ ዋነኛው የስጋት ምንጭ በመጠጦቹ ውስጥ ያለው ከፍተኛ የካፌይን መጠን ሲሆን ይሄም ፈጣን ወይም ያልተመጣጠነ የልብ ምት፣ ከፍተኛ የደም ግፊት፣ ማስመለስ፣ ከፍተኛ የሰውነት መንቀጥቀጥና ባስ ሲልም ለሞት የሚዳርግ የልብ በሽታ… የመሳሰሉ የጤና ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል፡፡

ካፌይን በህፃናት ላይ በጥናት የተረጋገጠ አሉታዊ ተፅአኖ እንዳለው ተመራማሪዎቹ በጥናት ሪፖርታቸው ላይ ጠቁመዋል፡፡

“የሃይል ሰጪ መጠጦች ተወዳጅነት መጨመር ያደረሰው ሙሉ ተፅእኖ ገና በቁጥር አልተቀመጠም፤ ነገር ግን ወጣቶችን ዒላማ ያደረገው የሃይል ሰጪ መጠጦች ጠንካራ የገበያ ስልት በምርቶቹ ላይ ከሚደረግ ውስንና ተለዋዋጭ ቁጥጥር ጋር ሲዳመር እነዚህ መጠጦች ለህብረተሰቡ ጉልህ የጤና ስጋት የሚሆኑበትን ድባብ ፈጥሯል” ብለዋል – ተመራማሪዎቹ፡፡

ዩሮሞኒተር ባሰፈረው መረጃ መሰረት፣ የሃይል ሰጪ መጠጦች ዓለም አቀፋዊ ሽያጭ እ.ኤ.አ በ1991 ዓ.ም ከነበረው 2.4 ቢሊዮን ፓውንድ በ2013 ዓ.ም ወደ 17.3 ቢሊዮን ፓውንድ አሻቅቧል፡፡ “ሬድ ቡል” የተባለው ሃይል ሰጪ መጠጥ በእንግሊዝ በከፍተኛ ሽያጫቸው ከሚታወቁ ለስላሳ መጠጦች በሦስተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

አንዳንድ የቡና ዘሮች ተመሳሳይ የካፌይን መጠን ያላቸው ቢሆንም ሃይል ሰጪ መጠጦች ቀዝቃዛውን የሚጠጡ በመሆናቸው በከፍተኛ ፍጥነት የሚወሰዱ ናቸው ብሏል – ጥናቱ፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት የጥናት ቅኝት እንደሚለው፤ እስካሁን የሚታወቁት ሃይል ሰጪ መጠጦች ካላቸው የካፌይን መጠን በእጅጉ የላቀ ካፌይን የያዙ አዳዲስ ምርቶች እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡

ሃይል ሰጪ መጠጦች ከካፌይን በተጨማሪ ጉዋራና፣ ታውሪንና ቢ ቪታሚንስ የተባሉ ንጥረነገሮችን እንደያዙ የሚናገሩት ተመራማሪዎቹ፤ ስለምንነታቸውና ከካፌይን ጋር ስላላቸው መስተጋብር ለማወቅ ተጨማሪ ምርምር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት ፖሊሲን አይወክልም በተባለ የጥናት ፅሁፍ ላይ እንደተጠቆመው፣ ሃይል ሰጪ መጠጦችን ከአልኮል መጠጥ ጋር ደባልቆ በመጠጣት ጉዳት እንደሚደርስ የሚያሳዩ ማስረጃዎች እየጨመሩ መጥተዋል፡፡ የአውሮፓ የምግብ ደህንነት ባለስልጣን ጥናት፤ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑ እድሜያቸው ከ18-29 የሚደርሱ ወጣቶች ሃይል ሰጪ መጠጦችን ከአልኮል ጋር ደባልቀው እንደሚጠጡ አረጋግጧል፡፡  አጥኚዎቹ እንደሚሉት፤ አልኮል ብቻውን ከመጠጣት የበለጠ ይሄኛው በጣም አደገኛ ነው፤ ምክንያቱም የስካሩ መጠን ባይቀንስም ሰዎች መስከራቸውን ለማወቅ እንዲቸገሩ ያደርጋቸዋል፡፡

ሃይል ሰጪ መጠጦች በአብዛኛው የስፖርት ብቃትን እንደሚጨምሩ እየተነገረ ቢተዋወቁም ከአካል እንቅስቃሴ ጋር ሲጣመሩ ለአደጋ ሊያጋልጡ እንደሚችሉ ጥናቱ አክሎ ገልጿል፡፡

በእነዚህ መጠጦች ውስጥ መካተት ያለበት የካፌይን መጠን ምን ያህል እንደሆነ ተመራማሪዎቹ በቁጥር ባይገልፁም በጥናት ላይ የተመሰረተ መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

በእንግሊዝ የምግብ ጥራት መመዘኛ አጀንሲ፣ ከታህሳስ ወር ጀምሮ ከፍተኛ የካፌይን መጠን የያዙ ሃይል ሰጪ መጠጦች፣ ይሄንኑ በምርቶቻቸው ላይ እንዲጠቁሙና “ለህፃናት ወይም ለነፍሰጡር ወይም ጡት ለሚያጠቡ ሴቶች አይመከርም” የሚል ማስጠንቀቂያ እንዲያሰፍሩ ያስገድዳል ተብሏል፡፡ በግንቦር ወር ደግሞ ሉቱዋኒያ እንዲህ ያሉ መጠጦች እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት እንዳይሸጥ የሚያግድ ህግ በማውጣት የመጀመሪያዋ የአውሮፓ አገር ትሆናለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በቤተ ክህነት ውስጥ ሆነው የሚያምሱት እና ማኅበረ ቅዱሳን ላይ እጃቸውን የሚቀስሩቱ ለሃይማኖቱ ክብር ባለው በትግራይ ሕዝብ ታንቅረው የተተፉ ለመሆናቸው እማኝ የሆንኩባቸው አጋጣሚዎች (ከማስታወሻ ደብተሬ)

$
0
0

የዛሬ ስድስት ዓመት ገደማ ይመስለኛል በቀድሞ መስርያ ቤቴ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አብሮኝ ይሰራ የነበረ እና የመንፈሳዊ ወንድሜ የሆነ ወዳጄ ሰርጉ መቀሌ ላይ  ነበር።ሙሽሪት አባት እና እናቷ የመቀሌ ከተማ ነዋሪ ነበሩ።መቀሌን ከእዚህ በፊት ወደ አክሱም ፅዮን መንፈሳዊ ጉዞ  ስንሄድ መቀሌ ጊዮርጊስ ስናርፍ በማደር እንጂ በውል አላውቃትም ነበር።ከተማዋን ለእዚህ ወዳጀ ሰርግ በሄድኩበት ወቅት በቆየሁባቸው ሁለት ቀናት ውስጥ ግን  የአፄ ዮሐንስ ቤተ መንግስትን እና በመቀሌ የማኅበረ ቅዱሳን ማዕከል ፅህፈት ቤት ለማየት ዕድሉ ገጥሞች ነበር።መቀሌ የሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን ፅህፈት ቤት የነበሩት እና መቀሌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ያሉ  ወንድሞች እና እህቶች ትሕትና እስከመቼም አይረሳኝም።

Aksum 1

በተለይ ወደ አክሱም ፅዮን በሁለት የተለያዩ ጊዜያት ከመንፈሳውያን ሰራተኞች ጋር ጉዞ በሄድንበት ወቅት አዳራችን መቀሌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ ነበር። የመቀሌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰንበት ትምሕርት ቤት አባላት  ትህትና ከአዕምሮዬ አይጠፋም። በመንፈሳዊ ጉዞው የነበሩትን ከአንድ መቶ ሃያ የማያንሱትን መንገደኞች በሙሉ እግር አጥበው፣ለእያንዳንዳችን ነጠላ ጫማ እና ፍራሽ  ከቤታቸው ሰብስበው አምጥተው፣እራት አብልተው እና ለሚቀጥለው ቀን ጉዞ ስንቅ የሚሆነን እኛ ተኝተን እነርሱ ሌሊቱን ሲሰሩ አድረው የሚሸኙን እነኝሁ የመቀሌ መንፈሳውያን ወጣቶች ነበሩ።

ወደሰርጉ አጋጣሚ ልመልሳችሁ 
እድምተኞች በታደሙበት ሆቴል፣በሰርጉ ምሽት እራት ላይ ከአዲስ አበባ ድረስ አብረውን የሄዱት አባት ለሃያ ደቂቃዎች ያህል ትምህርት አስተምረው ሲጨርሱ ከታዳሚው አንድ ሰው ተነሱ እና በትግሪኛ መናገር ጀመሩ።እጅግ መቆጣታቸው በንግግራቸው መሃል እንባ እና ሳግ ሲተናነቃቸው ያስታውቃል።በመሃል ትግርኛውን ገታ አድርገው በሚጣፍጥ አማርኛ ቀጠሉ ከንግግራቸው መሃከል የማስታውሰው  ”ወንድሞቻችን እንደገባኝ  ከአዲስ አበባ ነው የመጣችሁት። የመቀሌ ህዝብም ተቸግሯል።አሰሙልን! ንገሩልን! ቤተ ክህነት ያሉት ሰዎች ምን እየሰሩ ነው? እየሾሙ የሚልኩት ላይ ጥያቄ አለን።ቅሬታ አለን ስንል ስም ይለጥፉብናል ።መናፍቅ እና ተሃድሶ ከቤተ ክህነት ይውጣልን!አያምታቱን! ንገሩልን! ሃይማኖታችን እየተዋረደች ነው” እጃቸውን እያወራጩ ነበር የሚናገሩት። የሰርጉ ታዳሚ በሃዘን ከንፈሩን መጠጠ።ሙሽራው እና አብረውን የሄዱት አባት ከአዲስ አበባ መምጣታቸው ብቻ ቤተ ክህነት የሚሰማቸው መስሏቸዋል።እኛ ከአዲስ አበባ መምጣታችን ብቻ ለቤተ ክህነት የቀረብን አድርገውናል።ቆይቶ የሙሽሪት ወላጅ እንዳስረዱን የተናገሩት አዛውንት የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ሰብሳቢ በከተማዋም ውስጥ ከቀድሞ መንግስት ጀምሮ የታወቁ እና የተከበሩ አዛውንት መሆናቸው ነገሩን።

ተመሳሳይ ጉዳይ አክሱም ፅዮን አጋጥሞኛል። አክሱም ፅዮን ለመጀመርያ ጊዜ መንፈሳዊ ጉዞ ስሄድ ወደ ስልሳ የምንጠጋ  መንገደኞች በአንድ አውቶብስ ተሳፍረን ነበር  ከአዲስ አበባ የተነሳነው። አክሱም ፅዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያንን፣የአክሱም ሃውልት፣የቅዱስ ያሬድ ቃለ ሙራድ? የተቀበለበት ቦታ እና የንግሥት ሳባ ቤተ መንግስትን ያየሁበት አጋጣሚ ነበር።በአንድ መኪና የመጣው መንገደኛ በሙሉ የሚያድረው ከቤተክርስቲያኑ አጠገብ ከሚገኝ የእንግዶች ማረፍያ ጠበብ ያለ አዳራሽ ነበር።

በምሳ፣በእራት እና በቁርስ ሰዓት ለመንገደኞች ውሃ ማምጣት ኃላፊነት ከተሰጣቸው ውስጥ ነበርኩ። በመሆኑም በቀን ጊዜ ወደ አስር ደቂቃ የሚያስኬድ ሬስቱራንት መሄድ እና ውሃውን በባሊ ማምጣት ነበረብን። በእዚህ መሃል ነበር  ውሃ በነፃ እንድንወስድ የፈቀደልን የሬስቱራንት ባለቤት ጋር መግባባት የቻልነው።ግለሰቡ አዲስ አበባ የኖረ የአክሱም ሰው ነበር።በንግግራችን መሃል ታድያ ባብዛኛው የምናተኩረው በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ዙርያ ነበር።ግለሰቡ ከንግግሮቹ ሁሉ ጎልቶ የሚወጣው  የቤተ ክህነቱ  በሙሰኞች እና ከሃይማኖታዊ ምግባር እና ቀኖና በወጡ አገልጋዮች የበላይነት መመራቱ እንደሚያሳዝነው ነበር።ሁሉን ማውራቱ እዚህ ላይ ባይጠቅምም ከነገረን ውስጥ የሚገረመው ግን የአክሱም ከተማ ምዕመናን በቅርሳቸው ጥበቃ ላይ የሚፈሩት ከባዕዳን እኩል ቤተ ክህነቱ ውስጥ ያሉ እንደ እርሱ አጠራር ”ዘራፊ እና ቀማኛዎችን” መሆኑን ሲነግረን ሁላችንም በድንጋጤ የተያየንበት ወቅት ነበር።

እነኝህ ሁለት አጋጣሚዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በቤተ ክህነት ውስጥ ሆነው የሚያምሱት እና ማኅበረ ቅዱሳን ላይ እጃቸውን የሚቀስሩቱ ለሃይማኖቱ ክብር ባለው  በትግራይ ሕዝብ ታንቅረው የተተፉ ለመሆናቸው እማኝ የሆንኩባቸው አጋጣሚዎች ሆነው አልፈዋል።ዛሬ የማስታወሻ ደብተሬን እንዳነሳ ያደረገኝ ሰሞኑን የተያዘው አዲሱ የቤተ ክህነት አማሳኞች እና የማኅበረ ቅዱሳንን አገልግሎት ቦታ የለየ አስመስሎ የሚያቀርብ ፅሁፍ በማየቴ ነው።በዛሬው እለት በወጣው ፅሁፍ ላይ ”የአባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ገዳምን ስም ማኅበረ ቅዱሳን ለማንሳት ይፀየፋል” የሚል ሙሉ በሙሉ በውሸት የተለወሱ አረፍተ ነገሮች ይነበባሉ።የሚገርመው ነገር ገዳሙ ተረስቶ እና  የሚያስበው አጥቶ በብዙ ድካም እና መንገላታት ከቦታው ደርሶ ለገዳሙ የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት ቀርፆ ለገዳሙ ያስረከበ  ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑን ፀሐፌው አለማወቃቸው ምን ያህል በመረጃ ዘመን ከመረጃ የራቁ መሆናቸውን አመላክቶኛል።አልያም ሃይማኖትን ለማመስ ከአማሾች ጋር የተባበሩም  መሰሉኝ። ለሁሉም ማኅበረ ቅዱሳን በምን አይነት ፈተና ወደ አባ ሰላማ ገዳም  ተጉዞ ፕሮጀክት እንደቀረፀ እና እንደተገበረ ይህንን  ማያይዣ በመክፈት  ፊልሙን ይመልከቱ እና ይታዘቡ።

ጉዳያችን
ጥቅምት 11/2007 ዓም (ኦክቶበር 21/2014)


የመዠንገሩ ግጭት ታሪክ

$
0
0

50C090C9-C7C5-473C-912C-E2DDE0F1CE4C_w640_r1_s_cx0_cy11_cw0ከጳጉሜን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ጋምቤላ ክልል፣ መዠንገር ዞን፤ ጎደሬ ወረዳ በተለይ ሜቲ ከተማ ውስጥ ግድያና በአካባቢውም ግጭቶች መካሄዳቸውን የተለያዩ ዌብ ሳይቶችና መገናኛ አውታሮች እየዘገቡ ናቸው።

እንደዘገባዎቹ ከሆነ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፣ ብዛታቸው በውል ያልታወቀ ደግሞ ለከባድ የመቁሰል አደጋ ተጋልጠዋል።

«ግጭቱ የሚካሄደው በአማሮች ላይ ነው» የሚለው መኢአድ ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ የመንግሥት ካድሬዎችና ፌዴራል ወታደሮች እጃቸው እንዳለበት አመልክቷል።

ለመሆኑ ግጭቱ እንዴትና ለምን ተቀሰቀሰ? መንግሥትም ሆነ የክልሉ አስተዳደር ምን እያደረጉ ናቸው?

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ትንሹ መለስ በሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ

$
0
0

ተሻለ መንግሥቱ (ከአዲስ አበባ)

mocis_tig_homeኢትዮጵያ እጅግ ድሃና ኋላ ቀር ከሚባሉ የዓለም ሀገሮች ተርታ የምትሰለፍ መሆንዋን የተለያዩ ዓለም አቀፍ ጥናቶች ያረዳሉ – እኛም በዘግናኙ ኑሯችን ይህንኑ መራራ እውነት እያረጋገጥነው እንገኛለን፡፡ በሰብኣዊ መብት አያያዝ፣ በኢኮኖሚ፣ በሥልጣኔና በመሳሰሉ የሀገርና የሕዝብ ጤናማ ዕድገት መለኪያዎች ከሁሉም ሀገሮች ግርጌ ሆኖ መገኘት ለገዢዎቻችን ምን ያህል የደስታ ስሜት እንደሚፈጥርላቸው ማወቅ ባንችልም እኛ ዜጎቿ ግን በየምንሄድባቸው ሀገራት ሁሉ በዚህ የ“ፊተኞች ኋለኞች ይሆናሉ” እውናዊ ክስተት በግልጽ የሚንጸባረቅበት ውራነታችን እያፈርንና እየተሳቀቅን በዚህ ዘመን ኢትዮጵያዊ ሆኖ መፈጠር የሚያሸክመው ቀምበር ምን ያህል ከባድ እንደሆነም ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ እየተረዳን መጥተናል፡፡ በልማድ “ሳታጣ ያጣች” እያልን የምናንቆለጳጵሳት ሀገራችን በወያኔ ትግሬ የራሷ መዥገሮች ተወርራ ላሚቷ በመክሳቷ ለጥቂቶች ታልባ የማትነጥፍ ጥገት ስትሆን ለሚሊዮኖች ግን ድርቅ መትቷት ይሄውና ብዙዎቻችን የምንልሰውንና የምንቀምሰውን እያጣን በርሀብ አለንጋ እየተገረፍን እንገኛለን፡፡ ብልጭልጩ የአስፋልት መንገድና እዚያና እዚህ ሕይወት አልባ ሆነው የተገተሩት የሙሰኛ ዜጎች ቤቶችና ሕንፃዎች እንዲሁም ኢንዱስትሪና ፋብሪካዎች በሚሰጡን የተንሻፈፈ ምስል ሕዝቡ እንዳለፈለት በተለይ በገዢው የትግሬ ዘረኛ መንግሥት ሚዲያዎች ነጋ ጠባ ቢለፈፍም እውነቱ ግን በእጅጉ ተቃራኒና ለመግለጽም አስቸጋሪ ሆኗል፤ ብናነገር የማንታመን መሆናችን በራሱ የሚያስከትለው ጭንቀት ደግሞ ከበደሎች ሁሉ የከፋ በደል ሆኖብናል፡፡ የፍትህ ዕጦት የሚያሰቃየውን በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንደተምበሸበሸ፣ የራበውን በልቶ እንደጠገበ፣ የተጠማውን ጠጥቶ እንደረካ፣ የታረዘውን ሡፍና ሀር ለብሶ እንዳማረበትና እንደሞቀው … ተደርጎ እንዲታይ በተለይ በዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ የውሸት ምስል ለመፍጠር የሚጥር መንግሥታዊ የፕሮፓጋንዳ ማሽን በመኖሩ የምሥኪኖች ዋይታና ልቅሶ እስካሁን ሰሚ ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ሰውና እግዜር ተባብረው የጨከኑባት ሀገር – ኢትዮጵያ!

ድህነታችን አጥንትን ዘልቆ የገባና ሀገሪቱንና ሕዝቧን ጥልቅ ገደል ውስጥ የከተተ ሆኖ ሳለ የመንግሥት ሥልጣን የተቆጣጠሩት ወያኔዎች እየዘረፉት ያለው የሀገሪቱ ውሱን ሀብት እንዲህ በቀላሉ ሊገለጽ የማይችል መሆኑን አንድ አብነት ጠቅሰን በዚች ጽሑፍ ውስጥ ወረድ ብለን እንመለከታለን፡፡ እንዲህ የምናደርገው ለታሪክ መዝገብ ፍጆታ እንዲሆን እንጂ በአሁኑ ወቅት አድማጭ ተገኝቶ መፍትሔ ይኖራል ብለን እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል – ያን ያህል ሞኝነት በአሁኑ ወቅት የለም፡፡ እንናገራለን – ሰሚ ቢጠፋ የኢትዮጵያ ዐፈርና ዛፍ ቅጠል ሰምቶ በታሪካዊ መዝገብነት ቀረፆ ያኖረዋል፤ መጪው ትውልድም ይፋረዳል፤ ይማርበታልም፡፡ እንጂ አፄ ቴዎድሮስ ካህናት አናደውት ሲገስጽ “አንድሽ አንባቢ አንድሽ ተርጓሚ” እንዳለው እነዚህ በሙስና የበከቱ ወያኔዎች አንዳቸው ሌላኛቸውን አደብ ለማስገዛትና ሥርዓት ለማስያዝ የሚያስችል የሞራል ብቃት አላቸው ተብሎ አይታሰብምና ከነሱ ምንም አንጠብቅም –  በዚያ ላይ “አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ” ወይም “የመጥረቢያ ልጅ መዘለፊያ” እንዲሉ በመሆናቸውና ለሀገርም ሆነ ለወገን የሚቆረቆር አንዳችም ስሜት የሌላቸው ግዑዝ ፍጡሮች በመሆናቸው ከነሱ አንዲት ቅንጣት በጎ ነገር መጠበቅ በሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ራስን ማቂያቂያል ይመስለኛል፡፡ በሙስና ስም ሲካሰሱና ሲተሳሰሩ የምናያቸው ለሽፋን እንጂ እውነተኛ ምክንያቱ የሥልጣን ሽኩቻ ወይም ከጥቅም ጋር የተያያዘ የግል ጠብ ነው፡፡ በሙስና የተዘፈቀ ሰው በሙስና የተዘፈቀን ሰው እንዴት በፍትህ አደባባይ ሊያቆም ይችላል? ብዔል ዘቡል ብዔል ዘቡልን ሊያወጣስ ይቻለዋልን? ፈጽሞ የሚታሰብ አይደለም፡፡

ባለታሪካችን የወያኔ ጎምቱ ካድሬ የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ የዕድሜ ይፍታህ ፕሬዚደንት የሆነው ዶክተር ኃይለ ሚካኤል ማንትስ ይባላል፡፡ ኢትዮጵያ በዘመነ መሣፍንት የአገዛዝ ቅኝት ሥር እንደምትገኝ አንዱ ተጨባጭ ማስረጃ የሚሆነን የዚህ ሰውዬ ሃይ ባይ የሌለው ጋጠወጥ አድራጎት ሲታይና በእግረ መንገድም ሀገራችን የገባችበት አዘቅት ምን ያህል ጥልቀት እንዳለው ስንረዳ ነው፡፡ በዚህ ላይ መማር አለመማር በወያኔ መንደር ምንም ማለት እንዳልሆነ እንገነዘባለን፡፡ አንድ ሰው ዶክተርም ሆነ ማስተርስም ኖረው ዘረኝነቱና ሆዱ ከዕውቀት እንደሚበልጥበት በነዚህ ዶክተር ተብዬ የወያኔ አንጋፋ ካድሬዎች አስነዋሪ ተግባራት እንረዳለን፡፡ እነዶክተር ቴዎድሮስ፣ እነዶክተር ገ/አብ ባርናባስ፣ እነ“ፕሮፌሰር” ክንፈ፣ እነዶክተር ሶሎሞን ዕንቋይ፣ እነዶክተር ሐጎስ፣ እነዶክተር አርከበ ዕቁባይ፣ እነዶክተር አብረኸት፣ እነዶክተር አምለሰት፣ እነዶክተር ፍትዊ፣ እነዶክተር ዘርዑ፣ እነዶክተር መዓሾ፣ ያሉትም የሞቱትም … የሚሠሩትን የዘረኝነትና የምዝበራ ወንጀል ሁሉ ተመልክተን “መማር ባፍንጫችን ይውጣ!” ብንል ሊፈረድብን አይገባም፡፡ አዲዮስ ትምህርት! (በአንድ ሆቴል ውስጥ አንዱ ጣሊያን አንዱ ሀበሻ የቀረበለትን ፓስታ በግሩም ሁኔታ በሹካ እየጠቀለለ ሲያወራርደው ባጠገቡ ተቀምጦ ይመለከታል አሉ፡፡ አበላሉ ሥልጡንና አንዲትም የፓስታ ክር ወደጠረጴዛው ወይም ደረቱ ላይ ወዳንጠለጠላት የገበታ ናፕኪን ጠብ ሳትልበት ጥንቅቅ አድርጎ ስለጨረሰ ፈረንጁ ታዛቢ ደስ ይለዋል፡፡  ግን ምን ዋጋ አለው – ያ ሀበሻ ሲያቀብጠው አንድ አቦሬ ውኃ አንስቶ ግጥም አድርጎ ይጠጣና ፓስታውን ያወራርድበታል፡፡ ያኔ ነው “አዲዮስ ፓስታ!” በማለት ጣሊያኑ የፓስታዋን በጎርፍ መወሰድ በጩኸት የገለጸው – እነሱ ወይን ነዋ የሚጠጡት፡፡ የኛም “ምሁራን” ዶክትሬታቸውን በዕውቀት ሣይሆን በዘረኝነት ለወሱት፤ በሙስና አጨቀዩት፤ ብኩርናቸውንም ለግል ጥቅምና ብልጽግና ሲሉ በርካሹ ሸጡት፡፡)

እያንዳንዱን የመንግሥት መሥሪያ ቤት ስናይ የሙስናው ነገር ያስደነግጣል፡፡ የወያኔ ነገረ ሥራ ሁሉ ሱቅ ውስጥ የገባ ሕጻን ነው፡፡ ሕጻኑ ሕጻን ስለሆነ ያንንም ይህንንም ግዙልኝ ቢልና ዐይን ዐዋጅ ቢሆንበት ሕጻን ስለሆነ አንፈርድበትም፡፡ ወያኔዎች ግን ሀፍረታቸውን ባወጣ ሸጠው የሀገሪቱን ሀብት በግላጭና ካለንዳች ይሉኝታ እየተቃረጡት ናቸው፡፡ የሌላውን ነገድ ባይተዋር አባላት በመጠኑ ስኳር እያስላሱ እነሱ ዋናውን ማር በአካፋና በጎላ ይዝቁታል፡፡ እነሱ ባለመብቶች ሌሎች መፃተኛ እንደሆኑ ስለሚቆጥሩም ከነሱ ፈቃድና ይሁንታ ውጪ የተፈጸመች ማንኛዋም የሌሎች ዜጎች ደቂቅ የሙስና ተግባር በሙስና ወደ እስር የምታስግዝ ናት፤ በዚያ ላይ ትንሽ ፖለቲካዊ ጣጣ ካለችባት ክሱ ወደሽርተኝነትም ሊለወጥ ይችላል፡፡ እንደነሱ በሙስና ለመብከትም ቅድመ ሁኔታ ያለው መሆኑን እንግዲህ ልብ ይሏል፡፡ እነሱ ለመብከት ያላቸው ሙስናዊ መብት ሌላው የለውም – በገዛ ሀገሩ ባይተዋርና የበይ ተመልካች ነዋ! እንደዜጋ አይቆጠርማ! ሌላው ዜጋ ቀበጥ አድርጎት ከነሱ እጅግ ባነሰ ሁኔታ እንኳን ሲሞስን ቢገኝ “ድምበር ዘለልክ! ቀስ ብለህ እደግ! ያደረችዋ ባቄላ… እናንተ ፊት ሲያሳዩዋችሁ፣ የዱሮው ይበቃችኋል …” በሚል አደብ እንዲገዛ ያደርጉታል፤ ትግሬ ወያኔ ግን ወያኔ ያልሆነን ሺህ ዜጋ ቢገድል፣ በቢሊዮን የሚገመት ገንዘብ ቢዘርፍ ጠያቂ የለውም – የድርሻውን እንደገደለና የድርሻውን የደም ካሣ እንደወሰደ ይቆጠርለትና እንዲያውም የሚመሰገን ይመስለኛል (በኤርምያስ ለገሠ መጽሐፍ የተገለጸችውንና የሚጣል የበግ ቆዳ ለአንዲት ምሥኪን ጠላ ሻጭ በመስጠቷ ምክንያት ከሥራ የተባረረችውን ሴት እዚህ ላይ ያስታውሷል፤ ያቺ ሴት ትግሬ ብትሆን ኖሮ – በግልጽ እንነጋገርና – አይደለም አንድ ወይ ሁለት የበግ ቆዳ መቶ ሺህ ለዕርድ የተዘጋጁ በጎችን ለፈለገቺው ሰው ብትሰጥ ግፋ ቢል “ምን ነካሽ አንች ልጅ? ዕረፊ እንጂ!” ተብላ በ‹ድርጅቱ› ትገሰጽ እንደሆነ እንጂ ዝምቧን እሽ የሚለው አይኖርም – ምክንያት፡- የአብዮቱ ዋና አንቀሳቃሽ ከሆነው የጠራ ዘር – ምናልባትም ከ“እሽ አትበሉኝ የሹም ዶሮ ነኝ” ምርጥ የዐድዋ ዘር የተገኘች ናታ!)፡፡ እዚህ ላይ የሚታየውን ዐይን ያወጣ ልዩነት ለመግለጽ ያህል እንጂ ለሙሰኞች አቦካቶ መሆን ቃጥቶኝ እንዳልሆነ ማስታወስ እፈልጋለሁ፡፡ ሙሰኛ ሙሰኛ ነው፡፡ የየትኛውም ጎሣ አባል ይሁን፣ በትንሹም ይሞስን በብዙው፣ ሙስና ያው ሙስና (ጥፋት) በመሆኑ በፍጹም ወገንተኝነት ሊያሳዩበት አይገባም፤ ነውርም፣ ኃጢኣትም፣ ወንጀልም ነው፡፡ በፍትህ ሚዛን ጥፋት ሁሉ እኩል የሚለካና እንደየጥፋቱ ቅለትና ክብደት ተገቢውን አንቀጻዊና ኅሊናዊ ፍርድ ማግኘት የሚገባው እንጂ በዘርና በነገድ፣ በትውውቅና በዘመድ አዝማድ እንዲሁም በጉቦና በመማለጃ ገጸ በረከት(በዓይነትም ይሁን በገንዘብ) ፍርድ የሚያዛቡበት ሊሆን አይገባም፡፡ ግን ግን ትግሬ ወያኔ ብቻ የፈለገውን ይዝረፍ ሌላው ግን የተንጠባጠበችዋን እንኳን ሳትቀር መሬት ላይ አግኝቶ ቢልስ ዘብጥያ ይውረድ የሚል ጭፍን ያለ “ፍትህ” ሲበየን እንደ አንድ ሀገር የጋራ ዜግነት ክፉኛ ያማል – የህመሙ ቃንዛ አጥንትን ሰርስሮ መቅኒ ውስጥ እስኪገባ ድረስ፡፡ ለፍርድና ለንግግር ያስቸገረ ሁኔታ እኮ ነው የገጠመን፡፡ ምን ይሻለን ይሆን አሁንስ? ወደፊትስ ይህን ጉዳችንን እንዴት ነው ለሰው የምናወራው? በጣም እኮ ነው የሚያሣፍር! በዚህ የ21ኛው መቶ የ‹IT› ዘመን እንዲህ ያለ ሀገራዊ ውርደት ይግጠመን? እግዜሩን እግዜር ይይለት! ኃጢያታችን ምን ከሰው ቢከፋ እንዴት በዚህ ዓይነት ለወሬ እንኳን በማይመች አሸማቃቂ ቅጣት ይቀጣናል?

እዚህ ላይ አንድ ቁጭት እናንሳ፡፡ የዚህች ሀገር ሀብት በሙስና እንዲህ እየተዛቀ ባይዘረፍ ኖሮ ስንትና ስንት የልማት ሥራ ይሠራ ነበር? ስደትና ሥራ አጥነት በስንት ደረጃ ይቀንስልን ነበር? ከላይ እስከታች ያለው የወያኔ ባለሥልጣን በሚያገኘው አጋጣሚ ሁሉ፣ ራሱም አጋጣሚውን እየፈጠረ የጋራ ሀብታችንን እንዲህ ከቋት ከቋቱ ባይሞጨልፍብን ኖሮ አንድ የአባይ ግድብ አይደለም መቶና ሁለት መቶ ትላልቅ የልማት ዕቅድ አይጠናቀቅም ነበር ወይ? ቁርሱን እንደነገሩ ቀምሶ የምሣና የእራቱ  ነገር ህልም ከሚሆንበት ሲቪል ሰርቫንት (የመንግሥትና የግል ተቀጣሪ ሠራተኛ?) ለአባይ ግድብ ደመወዙን በግዳጅ ከሚቆረጥ በሰፊ ቧምቧ ወደ ግለሰብ ኪስ የሚንዶለዶለው የሀገር ሀብት ቢገደብ የአንድ የአምስት ስድስት ባለሥልጣናት ገንዘብ ብቻ ግደቡን አያሠራም ነበር ወይ? መከላከያን ወደቢዝነስ በመለወጥ በንግድ ስም የሚካሄደው ስርቆት፣ በባለሥልጣናትና ዘመዶቻቸው እንዲሁም በጥገኛ መዥገሮች በሙስና እየተወሰደ የሚቸበቸበው መሬታችንና ሀብታችን፣ በጦርና በፖሊስ ከፍተኛና መካከለኛ መኮንኖች የሚካሄደው ለከት ያጣ ዘረፋ፣ በመሣሪያ ግዢ ሰበብ፣ በስንቅና ትጥቅ፣ ለወንበር ጥበቃ ለተሠለፈው የመከላከያ፣ የደኅንነትና ፀጥታ ተቋማትና አባላት በከንቱ የሚፈሰው የሀገር ሀብት፣ በወያኔው የኢንዳውመንት ተብዬዎቹ የንግድ ድርጅቶች፣ ወዘተ. የሚመዘበረው ከግምት በላይ የሆነ የሀገር ገንዘብ ድህነትን ከኢትዮጵያ በስንት ማይል ያባርር ነበር?  በመለስ ስም – ሊያውም ሳይበላው ለሞተው – ስንት ቢሊዮን ዶላር አለ? ባለሥልጣናት ስንትና ስንት ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀስ ሀብት በሀገር ውስጥና በውጪ አካብተዋል? በመለስ ልጅ በሰምሃል ስም ተቀምጧል የተባለው ከአምስት ቢሊዮን የሚበልጥ ዶላር  ስንት ግድብና ስንት ዘመናዊ ሆስፒታል ያሠራ ነበር? በየምሽት ክበቡ ለምታስታውክበትና ጎረምሣ ለምትቀልብበት ለዚህች አሳዳጊ ለበደላት የመርገምት ውጤት የኢትዮጵያ ሕዝብ ገንዘብ እንደቅቤ በከንቱ የሚቀልጠው የምን ፍርጃ ይሆን? ስንቶቻችን ነን በቀላ ሊድኑ በሚችሉ ጥቃቅን በሽታዎች በየቀኑ እንደቅጠል የምንረግፍ? ስንቶቻችን ነን በርሀብ አለንጋ የምንገረፍ? ለመሆኑ በዚያች ማሕጸን ውስጥ ውኃ ብትሆን በሚሻላት አዜብ በሚሏት መበለት ስም ስንት ዶላር አለ? በእያንዳንዱ ባለሥልጣንና ዘመድ አዝማዶቹ ስም ስንት ገንዘብ በየባንኩ አለምንም ሥራ ታጉሯል? በግለሰቦች እንደተመዘበረ ከተደረሰበትና ውጪ እንደኮበለለ ወይም ወዳገር ሳይገባ በዚያው እንደቀረ ከተነገረው የ8.5 ቢሊዮን ዶላር የአንድ ወቅት ሪፖርት በተጨማሪ በየጊዜው በድብቅ እየወጣ የሚጠፋው ዶላርና ወርቅ ስንት ይሆን? ያ ጋጠወጥ ቀልበ-ቢስ ቱጃርና መሰሎቹ ልበ-ሥውራን ሀብታሞች አለመላው የሚጫወቱበት የሀገር አንጡራ ሀብት በስንት ቢሊዮን ይገመታል? ታዲያ ኢትዮጵያና ሕዝቧ በአጥንታቸው መሄድ ይነሳቸው? የግፋቸው ግፍ ደግሞ ከዚችው ከልደታ እስከባታ እንኳን መድረስ ከማትችለው ደሞዝ ተብዬ አነስተኛ ምንዳ ላይ ከዓለም ሀገሮች በከፍተኛነቱ እጅግ በሚለየው የሥራ ግብርን(income tax) ጨምሮ በፈለጉት ሰበብ መዝረፋቸው ነው( ይገርማችኋል- በዓመት አምስት መቶ ሺህ የተጣራ ገቢ ሊያገኝ የሚችል ነጋዴ አጭበርብሮና ከግብር አስከፋይ ኃላፊዎች ጋር በጥቅም ተሞዳምዶ በዓመት ከአምስት ሺህ ያልበለጠ የገቢ ግብር ሲከፍል እንደኔ ዓይነቱ ደመወዙ ላይ አንድም ድምፅ የሌለው ምሥኪን ሠራተኛ ቫትን ጨምሮ ከደመወዙ 50 በመቶ አካባቢ ይቆረጥበታል፤ ፍትህ የት አለች? ሰሚም ባይኖር አብረን እንጠይቅ፡፡) ዳሩ እነሱ ደሞዛቸውን አያውቁት፤ ዳሩ እነሱ ምን ገደዳቸው በደሞዛቸው አይኖሩ፤ እነሱ ደሞዝን ለስም እንጂ መች ሲጠቀሙበት ፡፡ ይብላኝ ለኛ እንጂ፡፡ እግዜሩ፣ ጨካኙን መንግሥቱ ኃ/ማርያምን ወስዶ እነዚህን አረመኔ ገዢዎች የሰጠን ምን ያህል ክፉ ብንሆንበት ይሆን? ለመልስ ዳተኛ ቢሆንም እሱንም እንጠይቀው፡፡

ሁሉን ቢያወሩት ራስን ከማሳመም ውጪ ትርፍ የለውምና ስለዶክተር ተብዬው የወያኔ አንዱ መሥፍን ትንሽ እናውጋ፡፡ ነገር እየተጎተተብኝ አንዱን ጀምሬ በቅጡ ሳልቋጭ ሌላውን ማንሳቴን አውቃለሁና ይቅርታችሁን – ወድጄ እንዳይመስላችሁ፡፡

ይህ ሰው ሲቪል ሰርቪስን እንዲመራ ከተመደበ 20 ዓመት ሊሞላው ጥቂት ጊዜ ነው የሚቀረው፡፡ ያን ግቢ እንደፈለገው ያሽከረክረዋል፤ አስፈሪና አስጨናቂ ንጉሥ ነው፡፡ የእናት አባቱ ርስተ ጉልት ይመስል በወያኔ ካድሬነቱ በመኮፈስና ከማንጠልጠያዎቹ ጋር ባለው የጥቅም ትስስር ምክንያት ማንም ምንም ሊያደርገው እንደማይችል በመረዳት መምህራንና ሠራተኞችን ሲያንገላታ አንድም ጠያቂ የለውም፡፡ በድንጋይ ማምረቻነት የሚታወቀውን ይህን ዩኒቨርስቲ ልክ እንደ አንድ ኪንደር ጋርተን (ሙኣለ ሕጻናት) በመቁጠር እንደፈለገው ይዘባነንበታል፡፡ በሰሞኑ የወያኔ የዩንቨርስቲ መምህራን ሥልጠና ግና በስብሰባው መጨረሻ ላይ በተከፈተች አንዲት ጠባብ “የተቋማችሁን ችግሮች አስረዱ” የምትል መድረክ ምክንያት የዚህ ሰውዬ ገመና ተፍረጥርጦ ሊነገር ችሏል፡፡ ደፋር አይጥፋ፡፡ እስከዶቃ ማሰሪያው ነው የነገሩት፡፡ ከሰማሁት በጥቂቱ ላካፍላችሁ እችላለሁ፡፡ የሰውዬው ገመና በተለይ ይህን ተቋም ለሚያውቅ የአደባባይ ምሥጢር ስለሆነ አዲስ ነገር አልናገርም፡፡ (በነገራችን ላይ ዩኒቨርስቲው ካባ (ድንጋይ ማምረቻ) እየተባለ የሚጠራው በመምህራኑ ዕውቀትና ችሎታ ማነስ ሣይሆን በፖለቲካው ቅኝት ተመርጠው የሚገቡት ተማሪዎች “ሀ” ቢሏቸው “ሁ” የማይሉ ደናቁርት በመሆናቸው ነው፡፡ በወያኔ ቡድን ከወረቀትና ከታማኝነት ባለፈ የትምህርት ጥራትና ብቁ የዲግሪ ትምህርት አያስፈልግም፡፡ ስለሆነም እምነት የሚጣልበት ቅን ታዛዥ ይሁን እንጂ ከስምንተኛ ክፍልም ቢሆን ተመልምሎ የሚላክ ካድሬ የላከው ድርጅት የፈለገው ድግሪ በተቋሙ እንዲሰጠው የወያኔ ያልተጻፈ ህግ ያስገድዳል – ዐይኑን ሳያሽ የታዘዘውን የሚፈጽም ሙሰኛ አለቃም ስላለ  ድንጋይ ለማምረት አደናቃፊ ነገር አይኖርም፡፡ የድንጋዮች መጨረሻ አምሮ እንደማያውቅ ብጠቁም ግን ደስ ይለኛል፡፡)

  1. ሰውዬው ፍጹም አምባገነን ነው፡፡ በግቢው ውስጥ ያሉ ትላልቅና ንዑሳን የሥራ ክፍል ኃላፊዎች በፕሬዝደንቱ በኩል ሳያልፍ ከማንም ጋር ምንም ዓይነት መደበኛም ይሁን ኢ-መደበኛ ግንኙነት እንዲያደርጉ አይፈቀድላቸውም፡፡ ለዚህም ሳይሆን አይቀርም ምንም ደብዳቤ መጻፍና መላላክ እንዳይችሉ አንዳቸውም ቢሮ የሥራ ክፍሉ ማኅተምና የኃላፊው ቲተር እንዳይኖር የተደረገው፡፡ እንኳንስ በአንድ ትልቅ ዩኒቨርስቲ በአንዲት ትንሽ ተቋም እንኳን፣ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች እዚህ የተጠቀሱት የመደበኛ ደብዳቤ መላኪያ ማኅተምና ቲተር ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይህ አፄ መለስ ዳግማዊ ግን ይህን አልፈቀደም፡፡ ሁሉንም በርሱ ሥር ማሳለፍና መቆጣጠር ይፈልጋል፡፡ ተቋሙ የግሉ ንብረት እንደሆነ ያህል ስለሚሰማው በንብረቱም ሆነ በገንዘቡ ያሻውን ያደርጋል፤ እንደብዙዎቹ ወያኔዊ የመንግሥት ተቋማት ሁሉ በዚህ ግቢም ቁጥጥር ብሎ ነገር የለም፡፡ ሠራተኞችንና መምህራንንም አባቱ የቀጠሩለት የዱሮ ዘመን ባሪያዎች የሆኑ ያህል ሳይቆጥራቸው አልቀረም፡፡ የሚገርም ‹ዶክተር› ነው እባካችሁ!
  2. ሠራተኞችንና መምህራንን ደስ ባለው ጊዜ እየተነሣ ከሥራ ያባርራል – ይህም ጠባይ ሀገሪቱን እንደግል ርስት የያዙ የሚመስላቸው የብዙ መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች የሥራ ኃላፊዎች የሚጋሩት ነው፤ ወያኔን አይንኩ እንጂ በሌላው ጎሣና ነገድ ላይ እንደዐይጥ እንዲጫወቱበት ዘረኛ ሥርዓቱ ይፈቅድላቸዋል – በትግሬ ላይ ቢያደርጉት ግን የአለቃ ገ/ሃናን “እዚያም ቤ እሳት አለ!” የሚለውን ብሂል ሊያስታውሱ የግድ ነው (መለስ ስለሚስቱ ሲናገር እሳት የሚተፋ ምን ነበር አላት ያለው?) ፡፡ ሰውዬው – ዶፍተሩ – ከመጠን በላይ አሉቧልታና ሀሜት እንደሚወድ ይነገርለታል፤ በትንሹም በትልቁም እያኮረፈ ታዲያን ሠራተኞችን ከሕግ ውጪ ከሥራ ያግዳል፤ ያባርራል፡፡ ባለፈ አንድ ወቅት አንዳችም መሠረታዊ አሳማኝ ምክንያት ሳይኖረው ስምንት መምህራንን አባርሮ እንደነበርና ኋላ ላይ ግን ብዙዎቹ በፍርድ ቤት ተከራክረው መመለሳቸው ታውቋል፤ ይህም በስብሰባው ላይ ተገልጾኣል፡፡ አምባገነን ግለሰብ ከአምባገነን የመንግሥት ሥርዓት ጋር ሲጎዳኝ የዜጎች የመኖር ዋስትና እንዴት እንደሚጨፈለቅ ከዚህ ሰውዬ ነውረኛ ድርጊት መገንዘብ ይቻላል – ተምሮ ያልተማረ ማይም፡፡ በአንድ የምረቃ መጽሔት የመጨረሻ ቃል ማስፈሪያ የፎቶዋ ግርጌ ላይ አንዲት ተመራቂ “ሣይማሩ ላስተማሩኝ መምህሮቼ ምሥጋና ይድረሳቸው” የሚል አስደንጋጭ ሐረግ ማስቀመጧን አሁን ሳስበው የዚህ ‹ዶክተር› ትምህርትም ውኃ እንደበላው ገባኝ፡፡ ግን ግን ሞኝ አትበሉኝና መማር ለመደደብ በር ከፋች ዘበኛ(doorman) ይሆን እንዴ?
  3. አምስት መቶ ሺህ ብር እንኳን በማትፈጅ ትንሽዬ ድልድይ ስምንት ሚሊዮን ብር እንደፈጀ አድርጎ ማወራረዱ ተሰብሳቢን በሣቅ ባፈነዳ ሁኔታ ጉባኤው ላይ በግልጽ ተነግሯል፡፡ በዚህ ትንሽ ሰው ይህን ያህል የሀገር ሀብት ከተዘረፈ እሱን መሰሎች በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የወያኔ ካድሬዎች ምን ያህል የሀገር ሀብት ሊመዘብሩ እንደሚችሉ ይታያችሁ፡፡ አሁንም ከፍ ሲል የጠቀስኩትን እዚህ ልድገመው – እናም እኛ ኢትዮጵያውያን በችጋርና በችግር ያላከክን ማን ሊያክ ኖሯል? ድልድይቱን እኔም በዐይኔ በብረቱ አይቻታለሁ፡፡ ዩኒቨርስቲውን በስተጀርባ በኩል ካለው መንገድ የምታገናኝ በጣም ትንሽ ድልድይ ናት፡፡ የሚገርመው “ስምንት ሚሊዮን”ም ፈጅታ ከተሠራች ስድስት ወር ሳይሆናት ተሰነጣጥቃለች፡፡ ምን ይታወቃል – ለማሳደስ በሚል ሰበብ ደግሞ አንድ አሥር ሚሊዮን ብር ወጪ ይደረግባት ይሆናል፡፡ የተዓምራት መገለጫ በሆነች ሀገራችን ምን የማንሰማው ድንቅ ነገር አለ?
  4. ይቺኛዋ ታሪክ ደግሞ ትንሽ ቆየት ያለች እውነተኛ ዘገባ ናት፡፡ አንድ ጊዜ ነው – ብዙ የሕዝብ ማመላለሻ የቻይና ሃይገር አውቶቡሶች ወደዩኒቨርስቲው ይመጣሉ፡፡ ሹፌሮቹም አቶ ማንን ነው እቴ – ዶክተር እንጂ፣ ዶክተር ኃይሌን ጥሩልን ይላሉ፡፡ ዶክተሩ ተጠርቶ ሲመጣ ሾፌሮቹንና መኪኖቹን ባዬ ጊዜ በድንጋጤ ተውጦ “ለምን እዚህ መጣችሁ? ለምን በስልክ አታናግሩኝም?” በማለት ይጮህባቸዋል፡፡ እነሱ ደግሞ የገጠማቸውን ችግር ያስረዳሉ – የመጡት ከመኪና መሳደሪያ ሒሳብ ጋር በተያያዘ በገጠማቸው እሰጥ አገባ ምክንያት የደረሰባቸውን ጊዜ የማይሰጥ ችግር ለማስረዳትና በወቅቱ መፍትሔ ለማግኘት ነበር፡፡ ለካንስ እነዚያ መኪኖች የዶክተሩ የግል ንብረቶች ናቸው! አንድ የዩንቨርስቲ ፕሬዚደንት ይህን ያህል ሀብትና ንብረት ማፍራት እንዴት ይችላል? አዎ፣ የኛ ሀገር የወያኔ ካድሬዎች የሆኑ “ምሁራን” ሙስና እንደማይዘወተርበት በሚታመነው የትምህርቱ መስክ ሣይቀር ይህን የመሰለ ዘረፋ ያካሂዳሉ – በሌሎች መስኮች የሚገኙትማ እንዴቱን ያህል አይዝቁት፤ የየባለሥልጣኑ ሆድ እንዴት ነው እንዲህ እንደፊኛ እየተለጠጠ የሀገርን ሀብት የሚያግበሰብሰው ጃል! ታዲያ እኛ ያልከሳን ያልጠቆርን ማን ይክሳ፣ ማንስ ይክሰል? አክስቴ ማንጠግቦሽ አሥሯን አሥራ አምስት አደርጋለሁ ብላ በየጉሊቱ የሃምሣ ብር ቃሪያና ሽንኩርት በአንድ ብርና በሁለት ብር ትቸረችራለች – እነወያኔ ደግሞ በየቀኑ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ከድሃዋ ኢትዮጵያ በሰበብ አስባቡ ይዘርፋሉ፤ እነሱ እየዛቁ ወደግል ካዝናቸው ሲከቱ ሀገሪቱ ለደሞዝ መክፈያ እንኳን እጅ እያጠራት ከቀን ወደ ቀን እየደኸየች ትሄዳለች፤ የነዚህን ወያኔዎች ቀዳዳ ሆድ ለመሙላትም ብሔራዊ ባንክ በየቀኑ የወረቀት ግፋፎ እያተመ ገበያውን ያጨናንቀዋል፡፡ ሠራተኛው በዚህ መሀል ጭዳ ይሆናል – ግራሟ(ክብደቷ) የአንድ ጆሮ ጌጥ ለምታህል አንዲት ጉርሻ ፎርኖ አንድ ብር ከሠላሣ ሣንቲም እየገዛን ልጆቻችንን ቁርስ ማቅመስ አቅቶን ባዶ ሆዳቸውን ትምህርት ቤት የምንልክ ብዙ ነን – ሊያውም ለዚህም የታደልን እንጂ ዩኒፎርምና ደብተር መግዛት እያቃተው ስንቱ ወላጅ መሰላችሁ ልጆቹ በረንዳ ሲያሞቁ ውለው ማታ ሲገቡ ወይም በየጎዳናው ሲርመሰመሱ እያዬ አንጀቱ የሚቃጠለው፡፡ በዓይነቱ የተለዬ ዕንቆቅልሽ ገጥሞናል፡፡ ፈጣሪ ይሁነን እንጂ በዚህ ከቀጠልን በጥቂት ዓመታት ውስጥ ስሊያችንን አንቀው እንደተራበ ነብር ደማችንን በጠራራ ፀሐይ ሳይመጡት አይቀሩም፡፡ እነዚህ መዥገሮች ቀላል እንዳይመስሏችሁ፡፡
  5. አንድ መምህር ለትምህርት ወደ ውጭ ሀገር ይሄዳል፡፡ ባለቤቱና ሕጻን ልጁ በግቢው በተሰጣቸው ቤት ይኖራሉ፡፡ ይህ ዶክተር ሕጻን ይመስል ከመምህሩ ጋር በተጋባው እልህ ምክንያት ሴትዮዋን ከቤቱ ውጪ ይላታል፡፡ ቤት አፈላልጋ ልትወጣ ወደግቢው ስትገባ ዘበኞቹ አትገቢም ይሏታል፡፡ የሚገርመው በፊት ስትወጣም አትወጪም ተብላ በመከራ ነው የወጣችው፤ አትወጪም – አትገቢም፡፡ የወያኔ ነገር “ያውጡብሽ እምቢ፣ ያግቡብሽ እምቢ” መሆኑ አይገርምም? ምን ዓይነት ትዕዛዝ ነው? ከዛም የምታደርገውን ስታጣ ፖሊስ ይዛ መጣችና የምታጠባው ሕጻን ልጅ ስለነበረ እንድትገባ ተደረገ፡፡ ሰውዬው – ዶክተሩ – ግራ የሚያጋባ ስብዕና ባለቤት ነው – እንደብዙዎቹ ወያኔዎች፡፡ ወያኔዎች ሥራቸው ሲታይ የሕጻንነት ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ ይመስለኛል ትልቅ የሚሆኑት፡፡ እልሃቸው ይገርማል፤ ቂም በቀልን የሚወጡበት ሥልት ይገርማል፤ የሚጠሉትን ለማጥቃት የሚሄዱበት አስቂኝ መንገድ ሁሉ ይገርማል፡፡ አሁን እስኪ ይታያችሁ “ከስምንት ዓመት በፊት የገዛሃት መኪና የቀረጥ ችግር ነበረባት” ብሎ ከተሸጠችና ከተረሳች ዘመን ያለፋትን መኪና ታሪክ – ችግሩ እውነት ነው ብለን ብናምንላቸውም እንኳን – ከመቃብር አውጥቶ ሰውን መክሰስ ሕጻንነት እንበለው ወይንስ መጃጃል? በርግጥም ለሀገር የሚቆረቆሩ ከሆነ እስኪ የዶክተር ኃይሌን ድልድይ ወጪ ያጣሩና ከዚያች መኪና የበለጠ ገንዘብ ለ“መንግሥት” ለማስገባት ይሞክሩ፡፡ እንዴ! ምንድናቸው እነዚህ “ሰዎች”?
  6. አንድ ወቅት ለሰባት መምህራን ቤት ሊሰጥ ከሃያ መምህራን መካከል በተቀመጡ መሥፈርት አማካይነት የማጣራት ሥራ ይካሄዳል፡፡ ከሃያዎቹ መካከልም ሰባቱ ነጥረው ይወጡና ከአንድ እስከ ሰባት በደረጃ ይቀመጣሉ፡፡ ሰውዬው ይህን ሲመለከት ከሰባቱ ውስጥ በተለይ አንደኛና ሁለተኛ የወጡትን ሁለት ግለሰቦች አይወዳቸውም ነበርና ውጤቱን ለመገለባበጥ አዲስ መስፈርት ይጨምራል፡፡ ያም መመሪያ የአስተዳደር ግምገማ ከ20 በመቶ እንዲያዝ የሚል አዲስ ትዕዛዝ ነው፡፡ በአዲሱ “መመዘኛ” መሠረት ሰውዬው የሚፈልጋቸው በፊተኛው የማጣራት ሂደት የወደቁ ሁለቱ ግለሰቦች አንደኛና ሁለተኛ እንዲወጡ ሆኖ የፊተኞቹ አንደኛና ሁለተኛ የወጡ መምህራን ፎሪ ይደረጋሉ፡፡ የሚገርመው ዝርዝሩ ብዙ ስለሆነ እዚህ ላይ መጥቀሱ ይከብደኛል እንጂ በአዲሱ መመዘኛም እነዚያ ቤት እንዳገኙ የተደረጉ ሁለት መምህራን እነዚህኞቹን በውጤት በልጠዋቸዋል፤ ግን ሞኝ እንዴት ያሸንፋል ቢሉ እምቢ ብሎ እንዲሉ ሆኖ በድርቅና ብቻ እንዲያሸንፉ ተደረገ፡፡ ይህን ዐይን ያወጣ የመድሎ ሥራ ሁሉም የግቢው ሰው ያውቀዋል፡፡ ነገር ግን ዘረኝነት ያሳወረውን ሰው መጋፈጥ ለበለጠ ጥቃት ማጋለጥ በመሆኑ ገፍቶ የሄደበት ሰው የለም፡፡ በቀደም ዕለት ግን ይህ አስነዋሪ ተግባር በአደባባይ በስብሰባው ወቅት ተጋለጠና ሰውዬው የሀፍረት ጃኖ ለበሰ፤ ግን ማፈርስ ሲያውቅበት አይደል?
  7. በዚህች የመጨረሻ ድሃ ሀገር ይህ ሰውዬ ለመሥሪያ ቤት ሥራ የሚጠቀምባቸው መኪኖች ቁጥር አራት ናቸው፡፡ “ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት” እንደምንለው ወያኔዎች ካሉባቸው መጥፎ ጠባዮች አንዱ ሁሉንም ነገር የመቆጣጠር አባዜ ነው፡፡ በአንዲት ድሃ ሀገር የአንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ኃላፊ አንድ ዐይን የማይገባ መኪና ቢጠቀም የትኛው ክብሩ ይቀነስበታል? የዚህ ሰውዬ መኪኖች ዋጋ ደግሞ ሰማይ ነው፡፡ እንደሚባለው ድምር ዋጋቸው ከአምስት ሚሊዮን አያንስም፡፡ የመኪኖቹ ዋጋ ራሱ በአንድ መንደር አንድ አነስተኛ ክሊኒክ ሊያሠራ ይችላል፡፡ የአንድ ሀገር ባለሥልጣን የሚያስተዳድረውን ሀገር ሕዝብ ኢኮኖሚያዊ አቅምና የአገሩን የዕድገት ደረጃ ካላወቀ ዓለም እስክትታዘበው ድረስ ትልቅ ችግር ይፈጠራል፡፡ ለምሳሌ በሚከፈለው ደሞዝ የወር ቀለቡን መሸፈን ሳይችል በርሀብ የሚንጠራወዝ የመንግሥት ሠራተኛን በሥሩ ያቀፈ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ለፕሮቶኮሉ ሣይሆን ለደኅንነቱ ሲባል በእግሩ እንዲመላለስ ባይጠበቅበትም በአምስትና ስድስት ሚሊዮን ብር በሚገዛ ተሸከርካሪ እንዲጓዝ ኅሊናው ሊፈቅድለት አይገባም፡፡ አእምሮ የተፈጠረው አዙሮ ለማየት ነውና የሚያስተዳድሩትን ሕዝብ ኑሮና አጠቃላይ ሁኔታ ወረድ ብሎ ማየትና ባጭር ታጥቆ የሕዝብን ችግር ለመጋፈጥ መነሣት ከአንድ ሀገር ወዳድ ባለሥልጣን የሚጠበቅ ነው – እንደወያኔ የድሆችን ገንዘብ እየመዘመዙ በድሃ ላይ መንቀባረር ሳይሆን “እንዲህ ከምቀናጣ ለሕዝቤ ስል ይህን ይህን ነገር ልተው” ማለት ይገባል – “ሆድ” ደግሞ “እንዳሳዩት ነው” ይባላል፡፡ በመሠረቱ ሀገርን ለማስተዳደር በቅድሚያ ሀገራዊና ብሔራዊ ስሜት ያስፈልጋል፡፡ አሁን የምንጮኸው ጅብንና ዓሣማን እንደሰው አስቡ የማለት ያህል ነው፡፡ ከንቱ የቁራ ጩኸት፡፡ ምን ይሻለን ይሆን ግን?

ወያኔ ጋር ለመሥራት ኅሊና ስለማያስፈልግ እነሱን ተጠግቶ ሀገሪቱን ባለ በሌለ አቅሙ የሚግጠው የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ዜጋ ብዙ ነው – ያ የእግር ኳስ አሰልጣኝ እንኳ ግብ በገፍ የሚያስተናግድ ልፍስፍስ ቡድናችንን ለ“ማሠልጠን” የስንትና ስንት ሠራተኛ ደመወዝ ጭማሪ ቢሆን የብዙ ሕጻናትን ወስፋት ይሸነግል የነበረ 500,000.00 ሺህ ብር አይደል በየወሩ የሚከፈለው? በሞኝ ደጃፍ ሞፈር እንደተቆረጠ በኢትዮጵያ ግዛት ፀሐይ ሳትወጣ እስከመቼ እንደምንዘልቅ ሳስበው ግርም ይለኛል – ለዚህ ለዚህማ ሰውነት ቢሻው እንደለመዳቸው እያሰለጠናቸው ደህና ደሞዝ ቢከፈለው ምን ነበረበት? ለምን በቆዳ ይታመናል? ራስን እየናቁና የራስን እያጣጣሉ የት ይደረሳል? ይህን የምለው በሁሉም ዘርፍ ስላለው የጭቡ ሥራ ሁሉ እንጂ የስፖርቱን ብቻ አይደለም፡፡ ለአብነት በትምህርቱ ዘርፍ ዶክትሬት ይኑረው አይኑረው፣ ዶክትሬቱ ሊያስተምር በተቀጠረበት የትምህርት ዓይነት ይሁን አይሁን ሳይታወቅ እንዲሁ በቀለምና በዘር የማምለክ ጠባያችንና ምናልባትም በሙስናዋ ደንዝዘን ለአንድ የሕንድ ዶክተር ተብዬ መምህር ብዙ ሺህ ብር ስንከፍል እሱን ለሚበልጠው ኢትዮጵያዊ ምሁር ግን አንድ አሥረኛውን እንኳን አንከፍለውም፤ ለምንከፍለው አነስተኛ ገንዘብም እንቆጫለን – ወጉ አይቀርምና ሲሉም ተሰምቷልና በሚዲያችን ላይ “brain drain” እያልን እናላዝናለን – የውሸታችንን፡፡ ለመሆኑ በአሁኑ ወቅት ስለሀገር የሚጨነቅ አንድ ባለሥልጣን አለ? ለተማራና ለሠለጠነ የሀገር ልጅ ቅድሚያስ የሚሰጥ ተቋም አለ? የለም፣ ምክንያቱም ብዙዎቻችን የምቀኝነትና የማይምነት ልክፍት ሰለባዎች ነና፤ ፈረንጁ ሲልጠን ደስ ይለናል፤ የኛው ሲያገኝ ግን ይከፋናል፤ ብዙዎቻችንን የተጠናወተንን ጠማማ አስተሳሰብና አመለካከት በአወንታዊ የቀናነት ቅባት ካላሸነው ከዚህ በበለጠ ገና እንጠፋለን፤ ምቀኝነትና ቅናት ፈዋሽ ጠበል ካልፈለቀላቸው ሀገርን የሚያጠፉ አደገኛ መርዞ ናቸው፡፡ እንዲያው ባጭሩ ግን ብዙዎቻችን ፈረንጅ አምላኪዎች ነን – የማንረባ! ስንቱ ጉዳችን ተነግሮ ይዘለቃል እባካችሁ(በተማሪ መግቢያና መውጫ ሰዓት ነጭ ገዋን አልብሰው ባገሩ አትክልተኛ የነበረ ማይም ፈረንጅ በግቢያቸው የሚገትሩ  የግል ትምህርት ቤት ባለቤቶች እንዳሉ ሰምታችኋል? ወላጅ ልጁ በፈረንጅ ሲማርለት እየታየው የተጠየቀውን ገንዘብ ይከፍላላ! መቼ ይሆን ሰው የምንሆነው?)፡፡ እውነቱን ያ ብላቴና “ባለቤት የሌላት ከተማ” ያላት አዲስ አበባን፡፡ ሀገሪቱም ሕዝቧም እንደጠፍ አህያ ማንም እንደፈለው የሚጭነን ባለቤት አልባዎች ሆነናል፡፡(እዚች ላይ ባጭሩ ሳልጠቅሳት ማለፍ የማልፈልጋት የምቀኝነትን ባህላዊ ትክልነት የምትጠቁም ነገር አለችኝ፡፡ በወቅቱ አንድ መጣጥፍ ልጽፍባት አስቤ እየዘነጋሁትና ንዴቴ እየበረደ ሄዶ ተውኩት፤ ቆይቶ ደግሞ ያናደደኝ አንድ በጣም የምወደው ጋዜጠኛ ወገኔ ወደእስር ስለወረደ መጻፌን በገምቢነት አላየሁትም፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡- በስም የማልጠቅሰው ጋዜጠኛ በኤርምያስ ለገሠ መጽሐፍ ላይ ትችት ሲያቀርብ ኤርምያስ እያገኘ ያለውን ዝናና ታዋቂነት መሠረት ያደረገ በሚመስል የምቀኝነት ሊለቀን ያልቻለ አባዜ የወጣቱን ልጅ ሀገራዊ አስተዋፅዖ – ምናልባትም ሳይታወቀው – አንኳስሶ ሲጽፍበት በውነቱ አፍሬያለሁ፤ እንደዚያ ያለ ለጠላት በር የሚከፍት ነገር በወዳጅ ጋዜጠኛ ብዕር ተጽፎ ሳነብ የተሰማኝ የመከፋት ስሜት ወደር አልነበረውም፡፡ … አንድ ሰው የሚኖረው ዝና የኛን ስብዕናና ታዋቂነት የሚሻማብን እየመሰለን አንዳንዶቻችን የምናሳየው ያልተለመደ የመቅበጥበጥና የመወራጨት ባሕርይ ትዝብት ውስጥ ይጥለናልና ጠንቀቅ ማለቱ ደግ ነው፡፡ የጻፍነውን ነገርም ደግመን ማየቱና ‹ኤዲት› ማድረጉ ብዙዎችን ከማስከፋት ያድነናል፡፡ በዚህ ብቻ ልለፈው፡፡ እሱም በአሁኑ ሰዓት እየተሰቃዬ ስለሆነ ፈጣሪ ከርሱና ከመሰሎቹ ጋር ይሁን፡፡)

ወደጀመርኩት አለፍኩ፡፡ በነዳጅ ስም፣ በአበል ስም፣ በወንበር ስም፣ በቤት አበል፣ በትምህርት አበል፣ በግልጽ በሚታወቅም በማይታወቅም ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅም ስም በየቢሮው የሚዘረፈውን ገንዘብ ታሪክ ያስላው ከማለት ውጪ የምናውቀውና የምንለውም የለም፡፡ የሚገርመው ሌላ ነገር በርዕሳችን የተገለጠውን ዶክተር ተብዬ ጨምሮ እነዚህ የወያኔ ባለሥልጣናት አለን የምንለውን ትንሽ ሀብት እንዲህ ሲዘባነኑበት ሕዝቡ ግን መንገድ የለው፣ መብራት የለው፣ ውኃ የለው፣ ስልክ የለው፣ ህክምና የለው፣ ዴሞክራሲ የለው፣ ትምህርት (ቤት) የለው፣ የመኖሪያ ቤት የለው፣ ሠራተኛው ከወር ወር ቀርቶ ለሦስት ቀናት የሚበቃ ደሞዝ እንኳን አይከፈለው…. ኧረ ምን ይሻለናል ገበዝ? በአንድ በኩል የባለሥልጣናቱንና አጃቢዎቻቸው የሆኑ የነጋዴዎችን ኑሮ ስታዩት፣ በሌላ በኩል የአብዛኛውን ሕዝብ የከፋ የድህነት ኑሮና ጉስቁልና እንዲሁም የታህታይና ላዕላይ መዋቅሮች በበቂና ደረጃቸውን በጠበቀ ሁኔታ አለመዘርጋት ስታዩ ወዴት እየሄድን እንደሆነ ግራ በመጋባት ሁሉም ነገር ጨልሞባችሁ ጭንቅላታችሁ ይዞርባችኋል፡፡( የአሁኑ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ብፃይ ቴዎድሮስ አንደሆም አንድ የሐኪሞች ስብሰባ ላይ ለተጠየቀ የጥራት ጥያቄ ምን አለ አሉ – “እኛ የምናሰለጥናችሁ ለዚህ ሀገር ሕዝብ የሚበቃችሁን ያህል መጠነኛ ዕውቀት እንጂ ለዓለም አቀፍ ገበያ የምትሸጡት ከፍ ያለ የሕክምና ዕውቀት አይደለም”፡፡ አሃ! ኢትዮጵያውያንን ለማከም አስፕሪንና ፓናዶል ማዘዝ ብቻ የሚችል ዶክተር ነዋ የሚያስፈልገን! ለዚች ለዚችማ ዳማከሴና አርማጉሳ፣ ሐረግሬሣና ጤናዳም የት ሄደው? ለነገሩ “ራቁቱን ለተወለደ እርቦ ምን አነሰው” ይባል የለም? ጊዜያቸው ነውና ግዴለም እነብፃይ ይጫወቱብን፡፡ “ይደልዎሙ” ይላል ግዕዙ “ይገባቸዋል” ሊል ሲፈልግ፤ እኛም “ይደልዎነ” እንበላ “We deserve!” ለማለት፡፡ አዎ፣ ከችግራችን ለመውጣት የምንጓደድ ከሆነ ችግራችን ድሎታችን እንደሆነ በመቁጠር ተስማምተን ተቀብለናል ማለት ነውና ቢረግጡን ሊከፋን አይገባም፡፡…)

እኛና ፖለቲከኞቻችን እንግዲህ እንዲህ ነን፡፡ ሙስናና ንቅዘት የሌለበት ሀገራዊ ተቋም በፍጹም አይገኝም፡፡ ለአንድ ፕሮጀክት ከሚመደብ በጀት ውስጥ በግምት ከሃምሣና ስልሣ በመቶ በላይ በባለሥልጣናት ይመነተፋል፡፡ በቀሪዋ በጀት ሥራውን እናስጨርሳለን ብለው ሲሞክሩ ደግሞ የሥራው ጥራት ይበላሽና ለምሳሌ ቤት ከሆነ ገና ሥራ ሳይጀምር በባህር ዛፍና በጥድ አጣና የሚደገፍ ወይም ስብርብሩ ወጥቶ ከናካቴው የሚገነደስ ይሆናል፤ መንገድም ከሆነ አንድ ክረምት ሳያልፍ ምናልባትም ርክክቡ ሳይፈጸምና በወጉ ሳይመረቅ ፍርክስክሱ ወጥቶ ወይ አስፋልት ወይ የጠጠር የገጠር መንገድ ሳይሆን የሸማኔ ጉድጓድ እንደሆነ መኪኖችን ሲያረትም ይገኛል – ባለመኪኖችን ለተወደደ የተሸከርካሪ መለዋወጫ ሊያጋፍጥ፡፡ በመጨረሻም…

በመጨረሻም ፈገግ ልታሰኛችሁ ብትችል  አንዲት  ሙስና ቀመስ ቀልድ ልንገራችሁና እንሰነባበት – ዛሬ መቼስ አሰለቸኋችሁ፡፡ ከአንድ ከፍተኛ ተቋም በምህንድስና ሙያ የተመረቁ ሁለት ጓደኛሞች ዘወትር እየተገናኙ ይጨዋወታሉ፡፡ ከሁለቱ አንደኛው በአጭር ጊዜ ውስጥ እያለፈለት ሲሄድ ሌላኛው ግን እግረኛና የሚቀይረውም ልብስ የሌለው ናቸው፡፡ በኑሮው ያለፈለት መሃንዲስ መኪና እንደሸሚዝ ይቀያይራል፤ አለባበሱና አመጋገቡ እንዲሁም ቆነጃጅትን አለዋወጡም ሌልኛ ነው፡፡ ይህን የታዘበው ጓደኛው “ደሞዛችን ተመሳሳይ ነው፤ አንተ ግን በኑሮህ በጣም እየተለወጥክ ነው፤ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?” ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ እንዴት እንዳለፈልኝ ልንገርህ? ይለውና አዎንታውን ሲያገኝ እንዲህ ያጫውተዋል፡፡ በተውኔት መልክ እናቅርበው መሰለኝ፡፡ ስማቸውንም ወደሌላ ቅኔ ውስጥ ሳንገባ እንዲሁ በዘፈቀዳዊ አሰያየም ያለፈለትን መሃንዲስ አበበ፣ ያላለፈለትን ደግሞ ደበበ እንበላቸው፤

 

አበበ፤ ያን ድልድይ ታየዋለህ?

 

ደበበ፤ እዚያ ወዲያ ያለው?

 

አበበ፤ አዎ፣ እሱ፡፡ እሱን ሳሠራ ለርሱ ከተመደበው በጀት 30 በመቶውን ለራሴ ውስድ፡፡

 

ደበበ፤ እሺ …

አበበ፤ ያ እዚያ ጋ የተገተረው ሕንፃስ ይታይሃል?

 

ደበበ፤ በሁለቱ ቪላ ቤቶች መሃል ያለው?

 

አበበ፤ እህሳ! ከርሱ በጀት ደግሞ 35 በመቶውን ቅርጥፍ!

(ከጥቂት ወራት በኋላ ደቤ ጀግናው ፕራዶ ሚካናውን ይዞ ሱፉን ከነሚያምር ክራቫቱ ገጭ አድርጎ ሲሄድ                            መብራት ያቆመውና አቤን ያገኘዋል፡፡ መብራ ተለቅቆ ዳር ይዘው ከቆሙ በኋላ …)

 

አበበ፤ እንዴ! በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ምን አግኝተህ እንዲህ ተለወጥክ?

 

ደበበ፤ ዕድሜ ላንተ፡፡

 

አበበ፤ እኔ ደግሞ ምን አደረግሁልህ?

 

ደበበ፤ ይልቁናስ እንዴት እንዳለፈለኝ እንዳሳይህ ና ተከተለኝ፡፡ (ምንም ቤትና መንገድ እንዲሁም ሕንፃና ድልድይ                                      ወደሌለበት  ገላጣ የከተማ ዳርቻ ሥፍራ ይወስደዋል – ደበበ አበበን፡፡)

 

ደበበ፤ ያ ድልድይ ይታይሃል ?

 

አበበ፤ የትኛው ድልድይ? ( ምንም ነገር ወደሌለበት ባዶ ጫካ እየተመለከተ)

 

 

ደበበ፤ ባይታይህ አይፈረድብህም፤ ብቻ ለሱ ሥራ የተመደበውን በጀት 100 ፐርሰን ልቅሙጭ!

 

አበበ፤ እሺ…

 

ደበበ፤ ያ እዚያ ታች ከዛፎቹ መሃል የተገተረው ሕንፃ ይታይሃል?

 

አበበ፤ የቱ ሕንፃ? (አሁንም ከዛፍና ቁጥቋጦ ውጭ አንዳችም የቤት ዘር ወደሌለበት ደን እየተመለከተ)

 

ደበበ፤ ባይታይህ አይፈርድብህም፤ ብቻ የርሱንም በጀት መቶ ፐርሰነት ልቅሙጭ!

 

ማብራሪያ የሚያስፈልግ አይመስለኝም፡፡ ትምህርት ማለት እንዲህ ነው፡፡ ከራሱ የሚበልጥ ተማሪ የማያፈራ አስተማሪ እንዳስተማረ አይቆጠርም ይሉ ነበር ግሪካውያን የጥንት ፈላስማዎች በዘመነ አሪስጣጣሊስ ወአፍላጦን፡፡ ግሩም ሀገር ገምቢ ወጣትና ጎልማሣ በብዛት እያፈራን ነው፡፡ ለሀገርና ለወገን ተቆርቋሪ ቴክኖራት በገፍ እያመረትን መላ የወያኔ ኢትዮጵያን እያጥለቀለቅናት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ በጥራትም በብዛትም እጅግ የላቁ የተማሩ ልጆች ሕዝብሽን ወደታላቅ የሥልጣኔ ማማ ሊያደርሱት ቀን ከሌት እየተጉልሽ ናቸው፡፡ አዲዮስ ፓስታ ነበር ያለው ያ ጣሊያን? አዲዮስ ሀገር! አዲዮስ ሕዝብ! አዲዮስ ዕውቀት! አዲዮስ ትምህርት! አዲዮስ ኅሊና!… ራስ ብቻ ጤና፡፡

ዘጠኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

$
0
0

ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ከአዲስ አበባ እንዘገበው ዘጠኝ የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ዛሬ ጥቅምት 11/2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
semayawi party
ፓርቲዎቹ ለረዥም ጊዜ ስለ ትብብር ሲመካከሩ የቆዩ መሆኑ የታወቀ ሲሆን፣ ዛሬ ሰባት ገጽ ያለው ሰነድ ላይ የትብብር ፊርማቸውን በማኖር ትብብሩን ሊመሩ የሚችሉ አመራሮችንም መምረጣቸው ታውቋል፡፡

ዘጠኙ ፓርቲዎች የትብብር ስምምነቱ ያስፈለገበትን ምክንያት በሰነዱ ላይ ገልጸዋል፤ በዚህም ‹‹ነጻ አሳታፊና ታአማኒ ምርጫ እንዲካሄድ በትብብር ለመስራት፣ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋትና የዜጎችን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ በጋራ መታገል››ን በተመለከተ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

በዚህም መሰረት ፈራሚዎቹ ፓርቲዎች የሚከተሉትን አመራሮች ትብብሩን እንዲመሩ መርጠዋል፡-
1. ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ከሰማያዊ ፓርቲ
2. ምክትል ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርጌሎ ከከንባታ ህዝቦች ኮንግረንስ
3 ዋና ፀኃፊ አቶ ግርማ በቀለ ከኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
4. ምክትል ፀኃፊ አቶ ካሳሁን አበባው ከመኢአድ
5. ገንዘብ ያዥ አቶ ኑሪ ሙደሂር ከመኢዴፓ ሆነው ተመርጠዋል፡፡
በትብብር ለመስራት ሲወያዩ ከነበሩት 14 ፓርቲዎች መካከል አንድነትና መድረክ ውስጥ የታቀፉት ፓርቲዎች ትብብሩን ለመፈረም በየ ድርጅቶቻቸው ውሳኔ ባለመተላለፉ ያልፈረሙ ሲሆን ትብብሩ እስከ ቅዳሜ እንዲጠብቃቸው ጠይቀዋል፡፡ በመሆኑም በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ትብብሩ ስለ ቀጣይ የትግል ሂደትና ስለ ትብብሩ አጠቃላይ ሂደት ላይ ነገ ጥቅምት 12/2007 ዓ.ም ከጠዋቱ አራት ሰዓት በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

“አንዳርጋቸውን አስገድደው በማናገር ሌላ የፊልም ቅንብር ለመስራት ተፍ! ተፍ! እያሉ እንደሆነ መረጃ ደርሶናል”–ታማኝ በየነ

$
0
0

አሻራ፦ ጤና ይስጥልኝ አርቲስና አክቲቪስት ታማኝ በየነ፤ በቅድሚያ ስለ ጊዜህ በአንባቢያን ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ። አቶ አንዳርጋቸውን ለምን ያህል ጊዜ ታውቃቸዋለህ ? እንዴትስ ትገልጻቸዋለህ?

andargacew ashara magazine cover page

ታማኝ፦ አንዳርጋቸውን የማውቀው ከምርጫ 97 ጀምሮ ነው።በምርጫ 97 ቅንጅትን ተቀላቅሎ በሚንቀሳቀስበት ወቅት ማለት ነው። ያኔ መቼም ሁላችንም ልባችን የምርጫው እንቅስቃሴ ላይ ስለ ነበር በየእለቱ እየደወልን ሁኔታውን እንከታተል ነበር። እኔም ራሴ ሃገሬ ገብቼ እንደልቤ በነጻነት ለመኖር የምችልበት ጊዜ አሁን ነው ከሚል እምነት የመግባት እቅድ ነበረኝ። አንዳርጋቸውን የማውቀው እንግዲህ በዛ ግዜ በነበረን የስልክ ግንኙነት ነው። እስኪታሰር ድረስ ማለት ነው። በነገራችን ላይ ከመታሰሩ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ያናገረኝ እኔን ነበር። ከኔ ጋር አውርተን ስልክ እንደዘጋ ነው የታሰረው።

ከንግግራችን የማስታውሰው እኔ እዚህ ሆኜ በስልክ ብቻ ከምከታተል ልምጣ እያልኩት ነበር። እሱ ደግሞ በዚህ ደረጃ መምጣት የለብህም እዛው ብትሆን ነው የምትጠቅመን እያለኝ ተነጋግረን እንደጨረስን ታሰረ። ከዚያም ተፈቶ ወደ እንግሊዝ አገር ተመለሰ። በኋላም በቅንጅት ኢንተርናሽናል ተመርጦ ሲሰራ በስልክም በአካልም እንገናኝ ነበር። ከአንዳርጋቸው ጋር የነበረን ትውውቅ ይህን ይመስል ነበር፡፡

እንዴት ትገልጸዋለህ? ላልከኝ፦በጣም አስቸጋሪ በሆነበት ጊዜና መንገድ ህልሙን ሊያሳካ የደከመ ሰው ነው!። በተማሪዎች እንቅስቃሴ ወቅት የውጭውን ዓለም ዘመናዊ ህይወት የለመዱ ከአውሮፓና ከአሜሪካ እየሄዱ የኢህአፓን ትግል ተቀላቅለው በርሃ የቀሩ ወጣቶች እንደነበሩ አንብቢያለሁ። በንባብ የምታውቀውን ታሪክ በአካል የምታውቀው ሰው ሲያደርግ ስታይ ደግሞ በጣም ከባድ ነው። በአውሮፓና አሜሪካ ህይወት ፤ ምግብ፤ አልባሳት፤መኝታ፤ መዝናኛ፤

ብቻ እያንዳንዷን ነገር በምርጫና በፍላጎት የምታደርግበትን ህይወት ለምደህ በርሃ ገብተህ፤ ድንጋይ ለመንተራስ፤ አሸዋ ለመልበስ፤ ላለመታጠብና ያልታጠበ ለመልበስ መወሰን እጅግ በጣም ከባድ ነው። አስበው ከእንግሊዝ አገር ከንግስቲቷ ከተማ ሄዶ አሸዋ ላይ መተኛት ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ!።

ባጠቃላይ አንዳርጋቸው ከልጅነቱ ጀምሮ ከራሱ ህይወት አልፎ ቤተሰቡ የከፈለውን መስዋዕትነት ሳይ የሚሰማኝ ስሜት ሃዘን ሳይሆን ይህን ሥርዓት በተለያየ መልኩ እንታገላለን ለምንል ወገኖች ትልቅ ምሳሌና አርአያ የሆነ ሰው መሆኑን ነው።

አሻራ፦ የወያኔ መንግስት አንድን ግለሰብ ለመያዝ ይህን ያህል ተጨንቆና ተጠቦ፤ ቀደም ሲል የግድያ ሙከራ ማድረጉ አሁን ደግሞ ከፍተኛ ወጪ አፍስሶ፤ ሁለተኛ አገር(የመን) የተሳተፈችበት ድንበር ዘለል አፈና መፈጸሙ ምን የፖለቲካ ፋይዳ አገኝበታለሁ ብሎ ይመስልሃል?

ታማኝ፦ በመጀመሪያ የአንዳርጋቸውን የዓላማ ጽናት (ኮሚትመንት) አብሯቸው በሰራ ጊዜ አይተውታል። ያውቁታል። ከወጣትነት ዕድሜው ጀምሮ በኢ.ህ.አ.ፓ በኋላም ከነሱ ጋር ሲሰራ ለራሴ የሚል ሰው እንዳልሆነ፤ ስልጣን ይዞ ለመንደላቀቅ፤ ቤት ለመስራት፤ መኪና … የመሳሰሉት ቁሳዊ ፍላጎት የሌለው ሰው እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቁታል። የአንዳርጋቸው የዘወትር ቁጭት ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ብዙ ያልተሟሉ ጉዳዮች ስላሏት እነሱን ለማሟላት መሆኑንም ያውቃሉ። ከቅርብ ጊዜው ብናይ እንኳ በምርጫ 97 ቅንጅትን ተቀላቅሎ በአጭር ግዜ ውስጥ ምን ያህል ህዝብን የማሰባሰብና የማደራጀት ስራ እንደሰራ እናስታውሳለን።

ባለፈው አስመራ ድረስ ቅጥር ነፈሰ ገዳይ ልከው ሊያስገድሉት መሞከራቸውን ኢሳት በዘገበበት ጊዜ እንዴት ሊሆን ይችላል?ይሄ የኢሳት ወሬ ነው ያሉኝ ሰዎች ነበሩ። እነሱ(ወያኔዎች) ግን በየት በኩል ጉዳት ሊመጣ እንደሚችል በደንብ ገብቷቸዋል።በኔ ግንዛ አንዳርጋቸው የማስተባበሩን ስራ ጥሩ አድርጎ እንደሚሰራ ስላወቁ ይመስለኛል ይህን ያህል ክትትል አድርገው ሊይዙት የቻሉት።
Tamagn

አሻራ፦ እንዳልከው አቶ አንዳርጋቸውን መያዝ ማለት የተቃዋሚውን አከርካሪ እንደመስበር ሳይቆጥሩት የቀሩ አይመስልም።ይሁንና አቶ አንዳርጋቸውን የመን ላይ ይዘው መውሰዳቸው ለግዜው ጮቤ ቢያስረግጣቸውም፤ ውጤቱ ግን “ አሳ ጎርጓሪ….” ሆኖባቸዋል የሚሉ ብዙ ናቸው፡፡ አንተስ በዚህ ሃሳብ ትስማማለህ?

ታማኝ፦ በጣም እንጂ የምስማማው።እኔ እንግዲህ ህወሃት አገሪቷን ከተቆጣጠረበት ጊዜ አንስቶ በተቃዋሚነት አብሬ ኖርያለሁ። በውጭው ዓለምም አውሮፓ ፤ አውስትራሊያ ፤ አሜሪካ …ያለውን የተቃዋሚውን ወገን እንቅስቃሴ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን አውቃለሁ እላለሁ። እናም ከቅንጅት በኋላ “የምን ፖለቲካ?…ፖለቲካ በቃኝ!” እያለ የሸሸው ሰው ሁሉ በፈቃደኝነት “ምን እናድርግ?” ብሎ የመጣበት ወቅት ነው አሁን።

የአንዳርጋቸውን ነገር የተለየ የሚያደርገው ደግሞ፦ አንዳርጋቸው በየመድረኩ የሚታይ ሰው አይደለም። ከሱ በበለጠ እኔ በብዙ መድረክ እታያለሁ።

እሱ ግን የሚሰራ እንጂ የሚታይ ሰው አልነበረም፡፡ ይሁንና ህውሃት ይህን ያህል ሊያጠፋው የፈለገው አንዳርጋቸው ምን አይነት ሰው ቢሆን ነው? የሚለውን ነገር እንድት ጠይቅና እንድታገናዝብ ያደርግሃል። ለዚህም ይመስለኛል በውጭም በሃገር ቤትም የሚገኘው ህዝብ በሚያስደንቅ መልክ የተንቀሳቀሰው።

በዚሁ ጉዳይ ላይ ከአንድ ኢትዮጵያዊ ምሁር ጋር ስንወያይ “በታሪክ ውስጥ አንዳንድ ሰዎች ለለውጥ ምክንያት ይሆናሉ” ነበር ያለኝ። እኔም አንዳርጋቸው የለውጥ ምክንያት እንደሆነ ነው የሚሰማኝ። በርግጥ በዚህ መልክ መሆኑና እየደረሰበት ያለውን ስቃይ ስታስብ ቢያምህም በህዝብ ውስጥ የፈጠረው የመተሳሰብና የአብሮነት ስሜት ግን ቀላል አይደለም። ፊት ለፊት የማይተያዩና መነጋገር የማይፈልጉ ተቃዋሚዎች ያወጡትን ተመሳሳይ ቁጭት፤ እልህና ንዴት የተንጸባረቀበትን መግለጫ ስታየው ህወሃቶች እራሳቸው ምነው በቀረብን ሳይሉ የሚቀሩ አይመስለኝም። አንዳርጋቸውን መያዛቸው በርግጥም “አሳ ጎርጓሪ..” ሆኖባቸዋል በሚለው ሃሳብ እስማማለሁ።

አሻራ፦ አሁን ደግሞ በቅርቡ ለእይታ ወዳቀረብከው “ተላላኪው ማነው?” ወደሚለው የምስል ዘገባ ልመልስህ፦ ይህን ስራ ለማቅረብ ምክንያት የሆነህ ወይም መነሻ ሃሳቡን ያጫረብህ ጉዳይ ምንድነው?

ታማኝ፦ እእ …! ሁሌም በአይምሮዬ የሚመላለሱ ጥያቄዎች አሉ፦ የህወሃት መሪዎች ከሟቹ ጠ/ሚንስትራቸው ጀምሮ “እነዚህ የሻቢያ ተላላኪዎች” የሚሉት ነገር አለ። እናም ሁሌ እነኝህ ሰዎች እውነት ሰው አያውቅብንም ብለው ያስባሉ? እያልኩ እራሴን እጠይቃለሁ። አንድ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር “እነኚህ የሻቢያ ….” ሲሉ እየቀለዱ ነው? እላለሁ።

አሁን ደግሞ አንዳርጋቸውን ከያዙ በኋላ ይህንኑ አባባላቸውን ደጋግመው ሲጠቀሙበት …. አልበዛም? የሚል ስሜትና የነሱ መሬት የለቀቀ ውሸት ነው ለሥራው ያነሳሳኝ።

አሻራ፦ አቶ አንዳርጋቸውን ለሁለተኛ ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮ ያቀረቧቸው “ተላላኪው ማነው?” የሚለው የታማኝ የምስል-ዘገባ በኢሳት እንደሚቀርብ ከማስታወቂያው በማወቃቸው ሳይቀደሙ ለመቅደም አስበው ነው ሲሉ ብዙዎች አስተያየት ሰንዝረዋል። በተለይ ያቀረቡት የፊልም ዘገባ የሚጀምረው “የሻቢያ ተላላኪዎች” በሚሉ ቃላት መሆኑ የአስተያየቱን ትክክለኝነት ያጎላዋል ይላሉ…በዚህ መልክ ታይቶሃል?

ታማኝ፦ እንዳልከው የተሰነዘሩ አስተያየቶችን ሰምቻለሁ። ምንድነው ከባዱ ነገር መሰለህ ? የኔ ስራ ከመውጣቱ በፊት ለመቅደም ሲሉ አዘጋጁት ብል የኔ ከፍታ ሊጨምር ነው፤ መንጠራራት ሊሆንብኝ ነው። ከኔጋ እየተከራከሩ ነው ማለት በጣም በጣም ይከብዳል። ከተለያዩ ሰዎች የተሰነዘሩ አስተያየቶችን ስትመለከት፤ የቪዲዮው ያለ ጥንቃቄ ተከታትፎ (በአግባቡ ኤዲት ሳይደረግ) በችኮላ መቅረብ፤ የተጠቀሙበት ቃልና ከኔ ሥራ ጋር በአንድ ቀን መልቀቃቸው እነኚህን ነገሮች እንድታስብ ያደርግሃል። ጥድፊያቸው ደግሞ ከአንዳርጋቸው ቃል ጀርባ ያለውን የጣር ድምጽ እንድንሰማ እስከማድረግ ያደረሳቸው ነው። ይህን ይህን ደማምረህ ስታይ አንተ ከምትለው ጋር ይቀራረባል ። እኔ ግን ለኔ መልስ ሰጡ ብዬ ማለት ይከብደኛል።

አሻራ፦ እንደ መንግስት አስበሃቸው ይሆን ለኔ መልስ እየሰጡኝ ነው ማለት ይከብደኛል ያልከው?

ታማኝ፦ በጭራሽ!! እንደ መንግስት ቢያስቡና እኔም እንደ መንግስት ባስባቸውማ በወደድኩ ነበር። ዋናው ችግር እንደ መንግስት አለማሰባቸው ፤ እንደ መንግስት አለመስራታቸው አይደል እንዴ?እንዴት አድርጌ ነው እንደ መንግስት የማስባቸው? እኔ ይህን የምለው ሕዝብን ከማክበር ነው። በግለሰብ ደረጃ የሰጠሁት አስተያየት ወይም ያቀረብኩት ስራ ሊታይ የሚገባው በዛው ደረጃ መሆኑን ስለማምንበትና ከዛ በራቀ እንዳይታይብኝ ነው።
Fezralizm – By Tamagn Beyene Part 2
አሻራ፦ በቅርቡ በጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና አወያይነት አንተ፤ አቶ ኤርሚያስ ለገሰና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ወንድማገኝ ጋሹ በኢሳት ቀርባችሁ ባደረጋችሁት ውይይት ብዙዎችን ያስገረመ ነገር አስደምጠሃል። ያስደመጥከው ነገር፦ ጥቂት የወያኔ ባለስልጣናት በተገኙበት ውይይት ላይ አቶ በረከትና አቶ አዲሱ የተናገሩትን ነው። ይህ ውይይት በኢሳት መደመጡ ተቃዋሚው ወያኔ ጉያ ውስጥ ለመግባቱ አመላካች ሆኗል የሚሉ ብዙዎች ናቸው። ትግሉ የደረሰበትን ደረጃም ያሳያል የሚሉም አሉ፡፡ እንደ ጥያቄ ማንሳት የምሻው ይህን አይነት ጥብቅ ሚስጥር ኢሳት እጅ ሊገባ መቻሉ የተቃዋሚው የመረጃ ክፍል ጥንካሬ ወይስ ወያኔ ውስጡ ከመቦርቦሩ ጋር በተገናኘ እየሆነ ያለ …?

ታማኝ፦ ህዝቡ እኮ ታፍኖ የመጨረሻ ግፍ እየተቀበለ ነው ያለው። ደርግ ክፉ ነገሮችን ሁሉ ጨርሶ አድርጓቸው ሄዷል፤ ከደርግ በላይ ማንም ምንም አይነት ግፍ ሊፈጽም አይችልም የሚል እምነት ነበርን፡፡ እነዚህ ግን እኮ ሁሌም የሚሰሩት ግፍና ክፋት እያስደነቀን ነው።

ክፋታቸውን ቢያሳይ አንድ ምሳሌ ልንገርህ፦ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ፍርድ ቤት ቀርበው በነበረበት ጊዜ፤ በርሃብ ምክንያት መናገር እንኳ አቅቷቸው፤ ለዳኛው ምግብ በልተን አናውቅም ብለው ሲናገሩ፤ ዳኛው ደንግጦ ምግብ አምጡላቸው ብሎ ፍርድ ቤት ውስጥ እኮ ምግብ ተበላ! እነኚህ ሰዎች እኮ ያሰሩትን ሰው በርሃብ የሚቀጡ ናቸው ! እረ ስንቱን…… ዘርዝሬ እችለዋለሁ?

የህዝብን ስሜት በጥቂቱም ሊያሳይ ከቻለ አንድ ነገር ልንገርህ፦ በቅርቡ ለኢሳት አራተኛ አመት ወደ ጀርመን ሄጄ ነበር፡፡ በዝግጅቱ ላይ አንድ ሰው እጁን አውጥቶ እንዲህ ሲል ተናገረ፦ “ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ሄጄ ነበር፡፡ በክፍለ ሃገር ቤተሰቤ በሚገኝበት አካባቢ ለሚኖሩ አንድ አዛውንት ለቡና መግዣ ብዬ 50 ዩሮ ሰጠኋቸው። ተቀብለው ካመሰገኑኝ በኋላ፤ ሰማህ ወይ ልጄ ከዚህች 50 ብር ላይ ዘርዝርና 10 ብሩን ለዛ ለታማኝ በእጁ ስጥልኝ፤ ለኢሳት ገቢ እንዲያረግልኝ ብለው ሰጥተውኛል።” ነበር ያለው፡፡ ተመልከት በዚህ አይነት የኑሮ ደረጃ ያሉ ኢትዮጵያዊ እንኳ ከተሰጣቸው 50 ዩሮ 10 ለኢሳት ይሰጥልኝ አሉ።ይሄ እኮ ሌላ ምንም ማለት አይደለም። ህዝቡ ምን ያህል ነጻነት እንደናፈቀ የሚያሳይ ነው። የሰውን ፍላጎት ነው የምነግርህ፡፡

በመረጃ በኩልም ህዝቡ ለትግሉ የሚጠቅም መረጃ ለመላክ በሚገርም መልኩ ፍቃዱና ፍላጎቱ አለው። ባገኘው ቀዳዳ ሁሉ ሳይፈራና መስዋዕትነት ከፍሎም ቢሆን መረጃዎችን ለመላክ ይፈልጋል።

ኢሳት አሁን አብዛኛውን መረጃ የሚያገኘው ከህዝብ ነው። እኔ በግለሰብ ደረጃ ነው መረጃዎቹ የሚደርሱኝ፡፡ አንድ ጠንካራ ድርጅት ተፈጥሮ በዚህ ረገድ ስራ ቢሰራ ደግሞ ምን ያህል እንደሚተባበር መገመት ከባድ አይሆንም።

አሻራ፦ ወደ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ልመልስህ፦ አቶ አንዳርጋቸው ላይ አፈናው በተፈጸመበት ሰሞን በለንደን በተደረገ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ተገኝተህ በነበረበት ወቅት አቶ አንዳርጋቸው የአንበሳ ምስል በልዩ ሽልማት መልክ ሲሰጡህ ከሚያሳይ ክሊፕ ጋርአዳብለህ “ አንዳርጋቸው አንበሳውን መልሰህ ተቀበለኝ፤ ለኔ አይገባኝም!” የሚል መልዕክት አስተላልፈሃል። ይህን ያዩ ሰዎች ለአንድ ሃገር አንድ አንበሳ ብቻ ነው የሚያስፈልጋት እስካልተባለ ድረስ ታማኝም አንዳርጋቸውም ለሃገራችን አንበሶች ናቸውና ታማኝ ለምን ያንን አደረገ? ሲሉ ይጠይቃሉ። በርግጥ ለአቶ አንዳርጋቸው ያለህን ክብር ለመግለጽ የተጠቀምክበትን አገላለጽ ብዙዎች ወደውታል ። እስቲ ይህን ልትል ያስቻለህን …. ግለጽልን፡፡

ታማኝ፦ ያንን ያልኩት በስሜታዊነት ወይም በግብታዊነት አይደለም። ከልቤ የተሰማኝንና የሚሰማኝን ነው የተናገርኩት። አንዳርጋቸው አንበሳውን ለኔ ሲሸልም ስለኔ የተናገረው ራሱ በጊዜውም ከብዶኛል። እኔ ቀደም ሲል እንደ ገለጽኩልህ ራሴን የማየው እንደ አንድ ለህዝብ ነጻነትና ለሃገሩ ሰላም ፤ ….የሚናፍቅ ዜጋ ነው። አንዳርጋቸው በዚህ እድሜው ለህዝቡና ለሃገሩ ሲል የወሰደው እርምጃ በጣም ያስደንቀኛል። ሊከፍል የተዘጋጀው መስዋእትነት ሳያንስ እንደገና አፈናው ሲፈጸምበት ልንላቸው ይገባል፡፡

እነሱ (ገዢው ፓርቲ) በፍርሃት ዓለም ውስጥ ስለሆኑ ሁሉንም ነገር ለመቆጣጠር ነው ሩጫቸው፡፡ ወደፊት መቼም ቻይና የማትሰራው ነገር የለምና አገር ስትገባ ኤርፖርት ላይ ለመንግስት ክፉ -ልብ ያለውን ስካን የሚያደርግ መሳሪያ ሁሉ ሊያሰሩ ይችላሉ ….(ሳቅ)። ምርጫውንም ቢሆን ከዚህ በተለየ አይደለም የማየው። ፍርሃት ውስጥ ያለ አካል እውር ድንብሩን ብዙ ነገር ሊያደርግ ይችላል።

አሻራ፦ አንዳንድ ሰዎች ታማኝ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝን የራራላቸው ይመስላል። አቶ መለስን የተነፈሷትን ቃል ተከትሎ ወዲህ ወዲያ ያደርጋቸው እንዳልነበር ለአቶ ሃይለማሪያም ምነው ዝም አለ ይላሉ?

ታማኝ፦ ሳቅ…………! ይህን የሚሉ ሰዎች እውነት ከልባቸው እኔ በአቶ ኃይለማሪያም ላይ ግዜ እንዳጠፋ ፈልገው ነው? አይመስለኝም፡፡ አቶ መለስ እኮ የራሳቸው ተረት ፤የራሳቸው ስድብ ፤የራሳቸው፤ ውሸት የራሳቸው ምናምን…የነበራችው ሰው ነበሩ። አቶ ኃይለማሪያም ደግሞ ሳይዛቸው አልሆን ብሎ እንጂ የአቶ መለስን ልብስ ሊለብሱ የሚፈልጉ ነው የሚመስለኝ።

የአገር መሪዎች ከስራ ውጭ መጽሄት ማገለባበጥ፤ የአለም ዜና መከታተል …. እንዲህ እንዲህ አይነት ነገር እደሚያደርጉ ነው የማስበው፡፡ አቶ ኃይለማሪያም ግን ሌሊት ሁሉ ቁጭ ብለው የአቶ መለስን ቪዲዮ የሚያዩ ነው የሚመስለኝ፡፡ “ እስኪ የ 94ቱን አምጪልኝ የ93ቱን ጨርሻለሁ እያሉ…” እና በእኝህ ሰው ላይ ነው ግዜ እንዳጠፋ የሚፈለገው? ለሳቸው የሚሆን ግዜ እንኳ የለኝም፡፡ በቁምነገር ልወስዳቸው አለመፈለጌ እንጂ አቶ ኃይለማሪያም እንዴት ያለ ኮሜዲ ሊሰራባቸው የሚችሉ መሰሉህ?

አንተ ኮ! ስትኮርጅ የሰውን ሃሳብ፤ ወይም ሻል ያለ ነገር ትኮርጃለህ ። ማዛጋት ትኮርጃለህ?…..(ሳቅ) እሳቸው እኮ የአቶ መለስን ማዛጋት ሁሉ እየኮረጁ ነው! (ሳቅ)……! እኔ እንደ መዝናኛና ኮሜዲ ሾው ነው የማያቸው። ከዚህ ባለፈ አላያቸውም። አይ የግድ ይሰራባቸው ከተባለም ለቁምነገር ሳይሆን ለትርፍ ግዜ መዝናኛ ሊሰራባቸው ይችላል፡፡ከዚያ ውጭ ግን በሳቸው ላይ ግዜ ማጥፋት ያለብኝም ያለብንም አይመስለኝም።

ደግሞ ምን መሰለህ..? እኔ ጠ/ሚ/ር ስትለኝ የሚመጣብኝ ምስል እንደ አክሊሉ ሃብተወልድ አይነት ሰው ነው፡፡ ….እና በዚህ ስም ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሲጠራበት ……(ፋታ) ልክ አይሆንም፡፡

አሻራ፦ የወያኔን ከፍተኛ ባለስልጣናት በስልክም ቢሆን ለማግኘት ሞክረህ አታውቅም? ሞክረህ ከሆነ ውጤቱ ምን ነበር?

ታማኝ፦ እምምም.. አዎ! አንድ ሶስት ግዜ ሞክርያለሁ፡፡ አንዴ የቤንሻንጉል መፈናቀል ጊዜ …ሌላው ደግሞ አርሲ ውስጥ ሙስሊሞች የተገደሉ ጊዜ ይመስለኛል…አንዱን ዘነጋሁት። ብቻ ለ3 ጊዜ ያህል አቶ በረከት ጋ ደውዬ ነበር።መጀመሪያ የደወልኩ ጊዜ አነሳ፤ ጤና ይስጥልኝ ከአሜሪካ ነው የምደውለው አልኩት። “ማን ልበል? ” አለኝ። አይ እኔ የመንግስትዎ ተቃዋሚ ነኝ፤ ነገር ግን አሁን እየሆነ ባለው ጉዳይ መረጃ ይሰጡኝ እንደሁ ብዬ ነው የደወልኩት አልኩት።

እሱም “ማንነትክን ካልገለጽክልኝ ምንም መረጃ መስጠትም ሆነ ማውራት አልችልም” አለኝ።

መልሼም፦ማንነቴን ከነገርኩዎት አያናግሩኝም አልኩት። “ግዴለህም አናግርሃለሁ!” አለኝ።

ታማኝ በየነ ብዬ ሳልጨርስ ስልኩ ላዬ ላይ ተዘጋ፡፡በሌላም ጊዜ የሆነው እንዲሁ ነው፡፡ ታማኝ በየነ ነኝ ስለው ስልኬን ይዘጋዋል።

አሻራ፦ ለማነጋገር ፈቃደኛ ቢሆን ኖሮ በምን አይነት ስሜት ነበር የምታናግረው? ምንስ ነበር የምታናግረው?

ታማኝ፦ ለነገሩ በተለይ በመጀመሪያ የደወልኩለት ጊዜ አልተዘጋጀሁም ነበር፡፡ አሁን ስልኩን ሲያነሳ እንዴት ብዬ ነው የማናግረው? ንዴትም ቁጣም ፤ እልህም ይኖራል እና እንዴት እንደማናግረው አላውቅም ነበር፡፡ ሰዎችም አብረውኝ ነበሩ። ለማንኛውም የምለውን ሳልል እሱም ስልኩን ዘጋው። ሁለተኛ ስደውል ግን አስቤበት ነበር፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው ስልኩ ይነሳና ራሴን ሳስተዋውቅ ይዘጋል።

አሻራ፦ ምን ትለው ነበር ?

ታማኝ፦ሁሌ ራሴን የምጠይቀውን ነገር ነበር ልጠይቀው የፈለኩት። እንደው መጨረሻችሁ ምንድነው? እውነት እናንተ ሰዎች የምታደርጉትን ነገር ሁሉ የምታደርጉት የምር!! ለሃገርና ለህዝብ ጥሩ እየሰራን ነው ብላችሁ አምናችሁበት ነው? ልጆቻችሁን ትወዳላችሁ? ልጆቻችሁ ከሌሎች ልጆች ጋር በፍቅር እዲኖሩ አስባችሁ ታውቃላችሁ? ብዬ ጠይቄ ከራሳቸው አንደበት ብሰማው ፈልጌ ነበር አልሆነም ዘጋብኝ፡፡

አሻራ፦ ወደ ወቅቱ ጉዳይ ልመልስህ፦ የአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ኢትዮጵያዊውን ሁሉ አስቆጥቷል፡፡ በወያኔ መንግስት ላይ ያለው ተቃውሞና ለለውጥ ያለው ተነሳሽነት ከመቼው ጊዜ በተለየ ጠንክሯል። ይህን ተነሳሽነት ወደ ውጤት ለመለወጥ ምን መደረግ አለበት ትላለህ?

ታማኝ፡- አንድ ነገር አለ! በአሁኑ ሰአት በሃገራችን እየሆነ ያለው ነገር በጣም የሚያስፈራ ነው፡፡ እኛ የምንቃወማቸው ስለምንጠላቸው አይደለም፡፡ የምንቃወማቸው እያደረጉ ያሉት ነገር በጣም የሚያስፈራ፤ ሃገራችን እንደ ሃገር ህልውና እንዳይኖራት፤ ህዝባችንም አብሮ መኖር እንዳይችል የሚያደርጉ ሥራዎችን እየሰሩ በመሆኑ ነው። በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በተደጋጋሚ የዘር ቅራኔዎችን እያየን ነው። እገሌ ከዚህ ክልል እገሌ ከዚህ ክልል ውጣ እየተባለ ህዝብና ህዝብ እየተቂያቂያመ እንዲሄድ እየተደረገ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ያስፈራል፡፡

የህክምና ባለሙያ ባልሆንም አንድ ዶክተር ወደ ካንሰር ሊለወጥ የሚችል በጣም ከባድ የጤና ችግር ያለበትን በሽተኛ ፡ በአግባቡ መርምሮ ዘለቄታዊ መፍትሄ ይፈልግለታል እንጂ ህመም አስታጋሽ (ፔይን ኪለር) የሚሰጠው አይመስለኝም፡፡ የሃገራችን ወቅታዊ ጉዳይም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው። ዛሬ አንድ ዘላቂ መፍትሄ ነገር ካላደረግን ችግሩ ሊድን ወደማይችል ካንሰርነት መለወጡ አይቀርም።

ኢትዮጵያን ሃገሬ የምንላት ሁሉ አትሌቶቻችን ባንዲራዋን ለብሰው ትራክ ላይ ሲያሟሙቁ፤ ማን በ10 ሺህ ተሰለፈ ? ማን ለወርቅ ተስፋ አለው? …. እያልን እንጨነቃለን ። በውጤቱም እንደሰታለን። አሁን ደግሞ አትሌቶቿ ወርቅ ሲያስገኙላት የምንቦርቅላት ሃገር እንደ ሃገር መቀጠሏ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው። ይህ ደግሞ በኛና በኛ ትከሻ ላይ ብቻ ያረፈ ችግር ነው። ስለሆነም ከዚህ በፊት በተቃዋሚነት ሲንቀሳቀስ የቆየውም ሆነ ያልተንቀሳቀሰው ዜጋ፤ ብቻ ሁሉም ሁሉም ባመነበትና ታግሎ ያታግለኛል ባለው በአንዱ መስመር ገብቶ መታገል አለበት እላለሁ፡፡ ዛሬ አንዱ ተመልካች አንዱ ሯጭ የሚሆንበት ጊዜ አይደለም። ማንም ለምንም ጥሪ የሚያደርግበት ጊዜም አይደለም። ዛሬ አንድ ነገር ካላደረግን ለልጆቻችን የምናስተላልፈው “ነገ” የለም፡፡በዚህ ደረጃ ነው መታየት ያለበት የሚመስለኝ።

አሻራ፦ በተነሳንበት እንቋጭና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለህዝብ ነጻነት በጽናት ሲታገሉ ጠላት እጅ ወድቀዋል ፤ ህዝብስ ለሳቸውም ሆነ ለሃገር ነጻነት በመታገል ረገድ ምን ይጠበቅበታል ትላለህ?
Andargachew Tsige
ታማኝ፡- አንዳርጋቸው በወያኔ እጅ እስከወደቀበት ጊዜ ድረስ የራሱንና የቤተሰቡን ህይወት ሰውቶ፤ በርሃ ገብቶ የቻለውን ሁሉ አድርጓል። የአንዳርጋቸው የትግል ጉዞ እዛ ጋ አብቅቷል። ዓለም ላይ ያሉ ሰውን የማስቃያ ቴክኒኮችን ሁሉ በእጁ ያስገባው የወያኔ መንግስት ደህንነት ባለፉት ሁለት ወራት አንዳርጋቸው ላይ ምን ሲፈጽምበት እንደቆየ ለመገመት የካፒቴን ተሾመ ተንኮሉን ቃለ ምልልስ ማድመጡ በቂ ይመስለኛል፡፡ አንዳርጋቸው ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሏል። እየከፈለም ነው።

የወያኔ መንግስትን ባህሪ መለስ ብለን ብናይ ሕዝብ የሚያከ ብራቸውን ሰዎች አዋርዶና አቅልሎ ለማሳየት የማይፈነቅለው ድንጋይ እንደሌለ እንረዳለን፡፡

በአቶ አንዳርጋቸው መታፈን የተቆጣውን ህዝብ ተስፋ ለማስቆረጥ በተለመደው መልክ አቶ አንዳርጋቸውን አስገድደው በማናገር ሌላ የፊልም ቅንብር ለመስራት ተፍ! ተፍ! እያሉ እንደሆነ መረጃ ደርሶናል። ዋናው ቁምነገር ግን ህዝባችን ለዚህ መሰሉ የወያኔ ተደጋጋሚና አሰልቺ ህዝብን የማሳሳት፤ ጉምቱ የህዝብ ወኪሎችን የማዋረድ ሴራ አዲስ ስላልሆነ ምንም ይበሉ ምንም ይስሩ ፕሮፓጋንዳው ውጤት እንደማይኖረው አልጠራጠርም፡፡

ዋናው ቁም ነገር የነሱን ፕሮፓጋንዳ ማክሸፍ ብቻ ሳይሆን ለዘመናት ስንታገልለት የቆየነው ዘረኛውን መንግስት ከሕዝብ ጭንቃ ላይ የማውረድ ዓላማ በውጤት እንዲቋጭ ሁላችንም አንድ ሆነን መነሳት ነው!!!።

አሻራ፡ ስለ ጊዜህ በድጋሚ እናመስግናለን! ታማኝ፡ እኔም ስለተሰጠኝ እድል አመሰግናለሁ::

በአውስትራሊያ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለማስታወስ ከታተመችው አሻራ መጽሄት የተወሰደ::

ደቡብ ጎንደር ደብረታቦር ለሰዓታት በጥይት እሩምታ ስትታመስ ቆየች

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በደቡብ ጎንደር ደብረታቦር ከተማ ለሰዓታት በጥይት ስትታመስ መቆየቷን ምንጮች ለዘ-ሐበሻ አስታወቁ::
news
ከግብር ጋር በተያያዘ ተነሳ በተባለው በዚሁ የጥይት ተኩስ ሶስት አርሶ አደሮች መቁሰላቸው የተዘገበ ሲሆን የሞተ ሰው ግን እንደሌለ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::

በሌላ በኩል ምኒልክ ሳልሳዊ በደቡብ ጎንደር ደብረታቦር ከተማ ከግብር ጋር በተያያዘ ክፈል ሌላው ቀደም ሲል ከፍያለሁ በሚል በተነሳው ጸብ ፓሊሰ በአሰቃቂ ሁኔታ አርሶአደሩን በመደብደቡ ገበያ ላይ የነበረው ሰው ህግ ፊት አቅርበህ እንዲቀጣ ታደርጋለህ እንጂ አትገድለውም በማለቱ የተነሳ ደብረታቦር ከተማ ለሰዓታት መናወጧንም ዘግቧል::

በዛሬው ዕለት በተነሳው በዚሁ ግጭት የአንድ አርሶ አደር እጅ መቆረጡን የዘገበው ምኒልክ ሌሎች ሶስት አርሶአደሮችም በጽኑ መቁሰላቸውን ዘገቧል:: ተኩስ ያነሳው ፖሊስም ወደ ደበረታቦር ሆስፒታል የተወሰደ መሆኑን የሚናገሩት የአይን እማኞች ሕይወቱ በአስጊ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ጠቁመዋል::

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live