Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

Health: ጓደኛሽ ሸንቃጣ የሆነችባቸው 20 ምስጢሮችን ላስተዋውቅሽ

$
0
0

ሊሊ ሞገስ

1. የሚጠጣ ውሃ ከእጃችሁ አትጡ
በማንኛውም ጊዜ ውሃችሁን ከቦርሳችሁ አውጥታችሁ መጎንጨት፣ ከጠማችሁም ጥማችሁን እስክትቆርጡ ድረስ መጠጣት ጥሩ ነው፡፡ ውሃ ብዙ አማራጭ ያለው መጠጥ ነው፡፡ ባዶውን ከጉሮሯችሁ አልወርድ ብሎ ያስቸግራችሁ እንደሆነ ሎሚ ወይም የሎሚ ጁስ ደባልቃችሁ ልትጠጡ ትችላላችሁ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በቅርበት የምታገኙት ከሆነ ቫይታሚን ውሃ መጠጣትም ሌላኛው አማራጭ ነው፡፡ ንፁህ እና ኩልል ያለ ውሃን የመሰለ ነገር የለም፡፡
Nice ethiopian women body
2. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
የአካል ብቃት እንቅስቃሴን እንደ አንድ አስደሳች ድርጊት እንጂ እንደ አንድ መወጣት ያለባችሁ እለታዊ ግዴታ አትመልከቱት፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሰውነታችሁ እና ህይወታችሁ ላይ ሊያመጣ የሚችለውን አዎንታዊ ለውጥ አስቡት፡፡ ቀጥሎ ምን መብላት እንደሚጠበቅባችሁ ከመጨነቅ ይልቅ ቀጥሎ ምን አይነት እንቅስቃሴ ልታደርጉ እንደምትችሉ አስቡ፡፡

3. የተመጣጠነ ምግብ ብሉ፡፡
አንዳንድ ምግቦች ምንም እንኳ ከስብ ነፃ ሆነው በአንፃሩ የፕሮቲን ይዘታቸው ከፍ ያለ ቢሆንም ዋና የካሎሪ ምንጭ ስለሚሆኑ ክብደት እንድትጨምሩ ሊያደርጓችሁ ይችላሉ፡፡ የምትመገቡት የቱንም ያህል የተመጣጠነ ምግብ ቢሆንም ዞሮ ዞሮ ተጨማሪ ካሎሪ ማለት ተጨማሪ ክብደት መሆኑን አትዘንጉ፡፡

4. የካፌይን አጠቃቀማችሁን ገደብ አበጁለት፡፡
ከሲጋራ በተዘዋዋሪ ከሚመጣ ጢስ እንኳን ቢሆን ራሳችሁን አርቁ፡፡
5. የአጭር ጊዜ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እቅድ ላይ ትኩረት አድርጉ፡፡
ዋናው ትኩረታችሁ መሆን ያለበት የለት ተዕለት ግባችሁን ዳር ማድረስ መሆን መቻል አለበት፡፡
6. በቀን ውስጥ በትክክል ምን ያክል እንደምትመገቡ ለመለየት የሚያስችላችሁን ዝርዝር መረጃ አነስተኛ ደብተር ወይ ማስታወሻ ላይ መዝግባችሁ ያዙ፡፡ በየካፌው የምትመገቡት ቺፕስ፣ ልጆቻችሁ መክሰስ ሲበሉ አብራችሁ የምትጎራርሱትን ነገር ሁሉ አካቶ መመዝገቡ አስፈላጊ ነው፡፡
7. አልፎ አልፎ ለምሳሌ በሳምንት አንድ ቀን እንዳሻችሁ ሁኑ (ሺ ዓመት አይኖር)፡፡ ይሁን እንጂ ሳምንት ሙሉ ወይም አንድ የዓመት ረፍት ጊዜ ሙሉ እንዳይሆን ጥንቃቄ አድርጉ፡፡
8. በዙሪያችሁ የሚገኙ ሌሎች ሰዎችም ጤናቸው የተጠበቀ እንዲሆን የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ፡፡ አብሯችሁ ስፖርት የሚሰራ ጓደኛ ቢኖራችሁ መልካም ነው፡፡ ሌሎች በቅርበት የምታውቋቸውን ሰዎችም ስፖርት እንዲሰሩ አበረታቷቸው፡፡ ጠዋት ተነስቶ የእግር ጉዞ ማድረግ ወይም ዱብ ዱብ ማለት የሚወድ ጎረቤት ካላችሁ እናንተም መቀላቀል ትችሉ እንደሆነ ጠይቁ፡፡
9. መሰልቸት እንዳይገጥማችሁ በየጊዜው የምትሰሩትን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አይነት ቀያይሩ፡፡ ኤሮቢክስ፣ ብስክሌት መንዳት፣ ዋና መዋኘት፣ ዳንስ፣ የእግር ጉዞ ማድረግ ወዘተ እንደየሁኔታው እየለዋወጣችሁ ልትሰሯቸው የምትችሏቸው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አይነት ናቸው፡፡
10. በጤና፣ የአካል ብቃት ወዘተ… ዙሪያ መረጃ የሚሰጡ መጽሔቶች እና ጋዜጦችን ‹‹ሰብስክራይብ›› በማድረግ ቢሯችሁ አሊያም ደግሞ ቤታችሁ ድረስ እንዲመጣላችሁ አድርጉ፡፡
11. አስፈላጊ የሆኑ አዳዲስ ንብረቶች ላይ ገንዘባችሁን አውጡ፤ ለስፖርት ምቹ የሆነ ጫማ፣ ቱታ፣ ሙዚቃ ማዳመጫ ኤምፒስሪ ወዘተ፡፡
12. አንዳንድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አይነቶችን አዘውትራችሁ ለምሳሌ ለስድስት ወይም ለሰባት ቀናት መደዳውን በተከታታይ አንዳንዴም ጠዋትና ማታም ጭምር ለመስራት አቅዱ፡፡
13. ሰውነታችሁን ከሌሎች ሰውነት ጋር አታነጻጽሩ፡፡ በምትኩ የራሳችሁ ምርጥ ለመሆን ጥረት አድርጉ፡፡
14. አመጋገባችሁ ያልተመጣጠነ ከሆነ የተመጣጠነ ለማድረግ ጥረት አድርጉ፡፡ በየዓለቱ ቫይታሚን እና ሚኒራል እየወሰዳችሁ መሆኑን አረጋግጡ፡፡
15. የአካል ብቃት እንቅስቃሴያችሁን ደረጃ እና ክብደት በየጊዜው ለማሻሻል ስራ ስሩ፡፡
6. ዝም ብላችሁ ከጊዜ ለጊዜ እና አጋጣሚ ውሳኔውን ከመተው ይልቅ አንድ ቀን ቀደም ብላችሁ በማግስቱ የምትሰሩትን የእንቅስቃሴ አይነት አቅዱ፡፡ ከኩባንያ መሪዎች እስከ ቤት እመቤቶች እና የሀገር መሪዎች ድረስ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ ጊዜ ይኖራቸዋል፡፡ እናንተም ጊዜ የምታጡበት ምክንያት የለም፡፡
17. ክብደት መቀነስ ከሚለው ክልል ወጥታችሁ ሁለገብ አካላዊ ብቃት መፍጠር ወደሚለው ሽግግር አድርጉ፡፡ ስኬታችሁን ልብሳችሁ ምን ያህል ልክክ እንደሚልባችሁ በመመልከት ወስኑ፡፡
18. ያለማቋረጥ ልትከተሉ የምትችሉት የአመጋገብ ልምድ ይኑራችሁ፡፡ የቱንም ያህል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የምታደርጉ ቢሆንም የ‹‹ካሎሪ›› ይዘታቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን እስከ አዘወተራችሁ ድረስ ሸንቀጥቀጥ ለማለት ፈተና ይገጥማችኋል፡፡
19. በቂ እንቅልፍ ተኙ፡፡ ስፖርት የሚሰሩ ሰዎች በጊዜ የመተኛት እና እጅግ ጥሩ እንቅልፍ የማግኘት ልማድ አላቸው፡፡
20. የአልኮል መጠጥ አወሳሰዳችሁን በተለያዩ የበዓላት እና ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ወቅት ብቻ ወስኑ፡፡


ጫልቱን የገደላት ወያኔ ኢህአዴግ ሆኖ ተገኘ

$
0
0

ገለታው ዘለቀ

የስደተኛው ማስታወሻ ከተሰኘው መጽሃፍ ውስጥ ኣንዲት ምእራፍ መዝዤ በዛ ላይ የሰላ ግምገማ ለማድረግ ነው የዛሬው ኣነሳሴ ። መጽሃፉን የጻፈው ተስፋየ ገብረኣብ ሲሆን በዚህ መጽሃፍ ውስጥ የተለያየ ጭብጥ ያላቸውን ጉዳዮች በየምእራፉ ያነሳ ሲሆን “ጫልቱ እንደ ሄለን” የሚለው የብዙዎችን ትኩረት እንደሳበ ሁሉ የእኔንም ስቦ ነበርና በዚህ ክፍል ላይ ያነጣጠረ ትችት ኣቀርባለሁ።መጽሃፉ ከተለቀቀ ዘግየት ቢልም የጫልቱ እንደሄለን ጉዳይ ግን መወያያነቱ ረዘም ላለ ጊዜ ቆይቶ ስላየሁ ነው ዛሬ የተነሳሁት።
ደራሲው ይህን ክፍል ሲጀምር በፍቃዱ ሞረዳ በተባለ ገጣሚ የተደረሰ ግጥምን በማንበብ ነው። የዚህ ግጥም ይዘት ወይም ጭብጥ ከዘረኝነት ጋር የተያያዘ ነው። በዚህ ግጥም ብእሩን ያሟሽና ኣንዲት ጫልቱ የተባለች ቆፍቱ ተወልዳ ያደገች ውብ፣ የኣስራ ኣራት ኣመት  ልጅ ጋር ያስተዋውቀናል ። ይህቺ ህጻን ቆፍቱ ውስጥ የታወቀች ፈረስ ጋላቢ  እንደነበረች ይናገራል። ከወንዶች ጋር ሁሉ ተወዳድራ ፈረስ ግልቢያ እንዳሸነፈች በዚያም ምክንያት ፈረስ እንደተሸለመች፣በዚህም ስሟ እስከ ዋጂቱ፣ እስከ ወልመራ፣እስከ ሴራ፣ እስከ ደዋራ፣ እስከ በቾ፣ እስከ ጭቋላ፣ እስከ ድሬ፣ እስከ ጊምቢቹ ድረስ ተሰምቶ እንደነበር ያስረዳናል። ይህ የሆነው ከኣስራ ኣራት ኣመቷ በፊት በመሆኑ በርግጥ ይህቺ ህጻን ከቆፍቱ ትላልቅ የታወቁ ፈረስ ጋላቢዎች ጋር ተወዳድራ ኣሸነፈች? የሚለው የተኣማኒነትን ጥያቄ ያስነሳል። ወይ እንደሷ ከሆኑ ታዳጊ ህጻናት ጋር ተወዳድራ  ከሆነ ደራሲው ኣንድ ይበለን እንጂ  የኣስራ ሁለት የኣስራ ሶስት ወይም ከዚያ በታች ህጻን ሆና ከኣካባቢው ወንዶች ጋር ተወዳድራ ኣሸነፈች ቢለን ከመነሻው ተዓማኒነት የሚባለውን ጉዳይ እንድናነሳ ያደርገናል። ይሁን….  እንግዲህ….. ብለን ይህንን ጉዳይ ተወት ኣድርገነው ማንበባችንን ስንቀጥል ጫልቱ ብቻዋን በኣስራ ኣራት ኣመቱዋ ፈረስ ጋልባ ዘመድ ለመጠየቅ ጉዞ ስትጀምር ያሳየናል። ይህቺ ኣንድ ፍሬ ልጅ ብቻዋን ፈረስ ጋልባ ዘመድ እንድትጠይቅ ቤተሰብ መፍቀዱ ሌላው ኣንድ ኣንባቢ የሚጠይቀው ጉዳይ ሆኖ ለማናቸውም መንገድ ላይ ሊጠልፏት የከበቧትን ጎረምሶች በጣጥሳ እንዳመለጠች ይተርክልናል። ጋላቢ ስለነበረች ከዚያ ሁሉ ጎረምሳ ሽምጥ ጋልባ ኣመለጠች ይለናል። ምን ኣይነት ፈረስ ቢሆን? ምን ኣይነት ህጻን ጋላቢ ናት ያሰኘናል። ይሁን ብለን እንቀጥላለን….. ደራሲው ብዙ ሳይቆይ ጫልቱ በኣስራ ኣምስት ኣመቷ ከድሬ ለመጣ ታዋቂ የአድአ ቤተሰብ መዳሯን ያረዳናል። የሚገርመው ደራሲው ይህን መርዶ ለተደራሲያኑ ሲያቀርብ ኣለመከፋቱ ነው። በኣስራ ኣምስት ኣመት ትዳር መጀመርና መደፈር በጣም ኣሰቃቂ ጉዳይ ነበር። ደራሲው ለዚህች ህጻን ኣዛኝ ቢሆን ኖሮ ያለእድሜዋ በመዳሯ ብዙ ሊል ይገባው ነበር። ይህቺ ህጻን ያገባችው በኣስራ ሰባት ኣመቱዋ ኣይደለም። በኣስራ ኣምስት ኣመቷ ነው የተደፈረችው። ይህቺ እህታችን ምን ኣልባትም ገና የሴቶቹን ወግም ኣላየችም ይሆናል። በገጠር የሚወለዱ ሴቶች  ቶሎ የሴቶችን ወግ የሚያዩ ኣይደሉም። ኣካሉዋና ስሜቱዋ(emotion) ለወሲብና ለትዳር ሳይበቃ መዳሩዋ ቀጣይ የህይወት ዘመኑዋን ሁሉ ሊያበላሸው ስለመቻሉ ጥያቄ የለውም።የስነ ልቡና ሰዎች እንደሚሉት ሴቶች ለኣቅመ ህያዋን ሳይደርሱ ወሲብ ሲፈጽሙ ህይወታቸውን ሁሉ የሚከተላቸው የስሜት ችግር ኣለ። ደራሲው ለዚህች ወጣት ስስ   ስሜት እንዳለው እንደራራላት በዚህ ኣካባቢ ሳያሳየን መቅረቱ ለጫልቱ ያለውን ፍቅር ከወዲሁ እንድንመዝን ያደርገናል።

ጫልቱ ብዙም ሳትቆይ ጠፍታ ወደ ቤቷ ተመለሰች። ምነው ትዳር ይሻላል ቢሏት ሰካራም ነው ይደበድበኛል ኣለች። በርግጥ ከዚህ ሌላ በቃል ለመግለጽ የፈራችው ምክንያት እንዳለ ሁሉ ተሰምቶኛል። ችግሩዋን ማስረዳት ስለማትችል ይህንን ምክንያት በመስጠት እንቢኝ ማለት ፈልጋ ይሆናል። ለማናቸውም ይህን ክፍል ሳነብ ኣንጀቴን ያላወሰው ጉዳይ ያለእድሜዋ ምናልባትም የሴቶችን ወግ እንኳን በቅጡ ሳታይ ዘላ ሳትጠግብ የቤተሰብ ሃላፊነት ቀንበር ትከሻዋ ላይ መጫኑ ነው።

ጸሃፊው ወደ ኣዲስ ኣበባ ሊሸኛት ሲል የባህሪ ለውጥ ማምጣቱዋን ቁጡ መሆኑዋን ጥቂት ጠቆም ኣድርጎን እሱን ስላብከነከነው የሄለንና የጫልቱ ስያሜ ጉዳይ ያሮጠናል። ኣንባቢዎች እንከተልና ንባባችንን ስንቀጥል ከብዙ የቤተሰብ ምክር በሁዋላ ወደ ሸገር ሄዳ እንድትማር ተወሰነ ይለናል። ቤተሰብ ወደ ሸገር እንድትሄድ መወሰኑ ስለሸገር መልካምነት የሰማው ጉዳይ ቢኖር ነው ብለን እንድናስብ ያደርገናል። የጫልቱ ዘመዶች የሚወዱዋትን ቆንጆ ልጃቸውን ወደ ክፉ ቦታ ሂጂ ኣይሉም ብለን እናስባለን። ቆፍቱ ከኣዲስ ኣበባ ብዙ የማይርቅ በመሆኑ እነዚህ የጫልቱ ቤተሰቦች ተመላልሰው ኣይተውም ሊሆን ይችላል። ከሁሉም በላይ ኣዲስ ኣበባ  ያለችው የጫልቱ ኣክስት ምስክርነትም ጥሩ ነበር ማለት ነው። የሆነ ሆኖ ጫልቱ ወደ ሸገር እንድትሄድና በዚያ እንድትማር ስምምነት በመያዙ ጫልቱ ሸገር ገባች። ሸገር ስትገባ ያረፈችው በኣክስቷ ቤት ነው። ኣክስቷ ኣዲስ ኣበባ ውስጥ ከኣንድ መሬ ኣማራ ጋር ጋብቻ መስርታ በጥሩ ሁኔታ ትኖራለች። ጫልቱን ኣዲስ ኣበባ ጥሩ ኣርጋ ስተቀበላት ነው የምናየው። የኣክስቷ ባል ሲቆጣት እንኳን ኣናይም። ጫልቱ ኣዲስ ኣበባ ውላ ስታድር ተወደደች።ጎረቤቶች ሁሉ እንዴት ይገልጿት እንደነበር ደራሲው ሲገልጽ። እንዲህ ኣድርጎ በኣክስቷ በኩል ያቀብለናል።

“ሄለን የኔ ቆንጆ፦ ጎረቤቶቻችን ሁሉ ወደውሻል። ግልፅና ልበ ሙሉ ናት ብለው ነገሩኝ። ቁመናሽና መልክሽን የማያደንቅ የለም።”

ይህ የሚያሳየው ቆፍቱ ላይ ወጪ ወራጁ ይላት እንደነበረው ኣዲስ ኣበባም ተቀብላ ጫልቱን እያደነቀች እንደሆነ ነው። የምትኖርበት ኣካባቢ ኣእምሮ ብሩህ ቆንጆ እያለ ውስጥና ውጪዋን ኣድንቋል። በርግጥ ደራሲው ይህን ከነገረን በሁዋላ ኣክስቷ ስሟን መቀየር እንዳለባት፣ ትምህርት ለመማር ኣማርኛ መማር እንዳለባት ገለጸችላት ይለናል። በርግጥ ትምህርት ለመማር ኣማርኛ መማር ያለባት እዚህ ኣዲስ ኣበባ ስለመጣች ብቻ ኣይደለም። ቆፍቱ ሆና ትምህርት ለመማር ብታስብ ኖሮ በዚያን ጊዜ ቁቤ ኣልነበረምና ያው ኣማርኛ መማር ነበረባት። ይህ ጉዳይ ያሳዝነኛል። ሁሉም የሃገራችን ቡድኖች ሁሉ በቋንቋቸው መማር ቢችሉ ኖሮ ጥሩ ነበር። ባይልንጉዋል ሆኖ ማደግ ቀድሞ ቢቻል ኖሮ ጥሩ ነበር።

ለማናቸውም ጫልቱ ኣማርኛ ገና መልመድ መጀመሩዋ ሲሆን በዚህ ጊዜ ኣዲስ ኣበባ ውስጥ ሊስቁብሽ ይችላሉና ቶሎ ቶሎ ኣጥኚ መባሉዋን ይነግረናል። በርግጥ እዚህ ጋር ልገልጸው የምፈልገው ኣለ። ደራሲው በዋናነት ለዚህች ውብ ወጣት የህይወት መጥፋት ተጠያቂ ለማድረግ የሚሞክረው የቋንቋን የስምንና የንቅሳትን ጉዳይ በማመናፈስ ስለሆነ ኣንድ ነገር ማለት እፈልጋለሁ። እርግጥ ነው ኣዲስ ኣበባ  በሄለን ቅላጼ (Accent) መሳቁዋ ኣይካድም። እዚህ ጋር ግን መነገር ያለበት ኣዲስ ኣበባ በቅላጼ የምትስቀው ጫልቱ ኦሮሞ ስለሆነች ኣይደለም። ኣዲስ ኣበባ ከኣዲስ ኣበባ ውጭ ተወልደው በመጡ ኣማሮች፣ ትግሬዎች፣  ዶርዜዎች፣  ጉራጌዎች ወዘተ እንደሳቀች ነው የምትኖረው። ይሄ ጉዳይ ደግሞ በጣም ክፉ (serious) ተደርጎ ኣይታይም ነበር። ከጫልቱ ኣማርኛ ይልቅ ኣዲስ ኣበባ በመንዞች ኣማርኛ ተንፈራፍረው ይስቃሉ። ለምን የራሴን ልምድ ኣልነግራችሁም። ኣዲስ ኣበባ በነበርኩበት ሰዓት ወላጅ እናቴ ከገጠር ኣንዲት የዘመዳችንን ልጅ ወደ ኣዲስ ኣበባ ይዛ መጣች። ይህቺ የዘመዳችን ልጅ ወደ ኣዲስ ኣበባ የመጣችው መሃን የሆነችውን ኣክስታችንን እንድታግዝ፣ በዚያውም ትምህርት እንድትማር ነው። ይህቺ ልጅ ተወልዳ ያደገችበት ቀበሌ ከስልጣኔ በብዙ ርቀት ወደ ኋላ የቀረ ነው። መኪና እንኳን ኣይታ ስለማወቋ እርግጠኛ ኣይደለሁም። ለማናቸውም ኣዲስ ኣበባ መጣችና ትምህርት ቤት እንዳስገባት ታዘዝኩ። ወደ ትምህርት ቤት ልወስዳት ስል ያሳሰበኝ ነገር የስሟ ጉዳይ ነበር። ስሟ በልጌ ነው። በዚህ ስም ልጆች ይስቁባትና ስሜቱዋ ይጎዳል ብየ ረድዔት ኣልኳት። በዚያ ስም ተመዘገበችና ትምህርት ቀጠለች። ኣልፎ ኣልፎ በንግግሩዋና በገርጋራ የገጠር እንቅስቃሴዎቹዋ ህጻናት ይስቁባት እንደነበር ተረድቼኣለሁ። በኣማርኛዋ የትምህርት ቤት ህጻናት ከሚስቁት ይልቅ እኛ ቤት ውስጥ የምንስቀው ኣይረሳኝም። ኣንድ ቀን እንደዚህ ሆነ። ምሳ ልንበላ በዝግጅት ላይ ሳለን ረድዔት ለማስታጠብ ትዘጋጃለች። በወጉ መሰረት ኣባወራ መጀመሪያ ይታጠባልና ማስታጠቢያውን ይዛ ወደ ኣክስቴ ባል ቀረበች። የኣክስቴ ባል ኣሁን ያስታውሱታል ብየ ኣስባለሁ። በዚያን ጊዜ እሳቸው ሬዲዮ ይጎረጉሩ ነበርና ረድዔት መቆሙዋን ኣላዩም። ትንሽ ጠበቀችና

“ኣብባ እጣትሁ ላይ ውሃ ላርግልሁ” ኣለቻቸው። የኣክስቴ ባል ዘወር ኣሉና

“ምን?”

“ጣትኩን ውሃ ኣስነኩት”

የኣክስቴ ባል ፈገግ ኣሉና ሌባ ጣታቸውን ብቻ ወደ ማስታጠቢያው ዘረጉ። ሁላችንም በሳቅ ኣለቅን።  በረድዔት ቤት “ጣትኩን ውሃ ኣስነኩት” ማለት እጅሁን ታጠቡ ማለት ነው። እንዲህ ባሉ ዘየዎች ኣዲስ ኣበባ ትስቃለች። ይሁን እንጂ የምትስቀው መራራ ጥላቻን በሆዷ ይዛ ሳይሆን በቀልድ ነው።

በርግጥ እንደጫልቱ ከተለያየ ገጠር የሚመጡ ሁሉ ኣዲስ ኣበባ ሲገቡ ሊሰማቸው የሚችለውን  ጫልቱም ሊሰማት እንደሚችል ስሜቱዋን ልንረዳላት ይገባል። የሆነ ሆኖ በኣጠቃላይ በጎረቤቶቹዋ ዘንድ ባለ ብሩህ ኣይምሮና ልበሙሉ ቆንጆ የተባለች ስለሆነች የተጋነን ችግር ኣልገጠማትም። እንዴውም መልካም ስም ወጥቶላታል። መልካም ልጅ ተብላለች። ከማሪቱ ጋር ያላት ግንኙነት በጣም ጥሩ ነበር። ብዙ ጊዜ በኣንድ ሰው ቤት ያለውን ንትርክ ሁሉ ጫልቱ ኣላየችም።

ጥሩ በሚባል ቤተሰብና ጎረቤት መሃል ቆየችና ኣማርኛዋ ሲሻሻልላት የማታ ትምህርት ገባች። የማታ ትምህርት በገባችበት ሰዓት ምንም መጥፎ ነገር ኣይገጥማትም። ነፍስ ካወቁ የማታ ተማሪዎች ጋር ምን ኣልባትም በጣም ጥሩ ግንኙነት ነበራት። ኋላ ላይ ለጫልቱ ቤተሰቦች ጫልቱን ወይም ሄለንን ወደ ቀን ማዛወሩ መልካም መስሎ ታያቸውና ወደ ቀን ስትዛወር  ደራሲው በሚገርም መንገድ እንዲህ ሲል ልባችንን ያንጠለጥለዋል።

“የጫልቱ መራር ፈተና የጀመረው በዚህ ጊዜ ነበር።”…….

ምን ይሆን የሚገጥማት? ኣስተማሪ ምን ሊላት ነው?  ምን ትሆን ይሆን? ………. ብለን ልባችን ይሰቀላል:: ደራሲው መጨረሻ ላይ ለደረሰበት ድምዳሜ ትልቅ ኣስተዋጾ ያደረገው ኣሁን በዚህ በትምህርት ቤት የምታሳልፈው የህይወት ልምዱዋ ነው ማለት ነው። ደራሲው ለጫልቱ ህይወት መመሰቃቀል ተጠያቂ የሚያደርገው ስርአታዊ ሽብር (systemic Violence) ነው ብሎ ያምናል። በራሱ ቋንቋ እንዲህ ይገልጸዋል።

“የሆነችውን አፍርሶ፣ ያልሆነችውን እንድትሆን ያደረጋት ማነው? ይህ ስርአታዊ ሽብር (systemic Violence) ስለመሆኑ ጫልቱ ግንዛቤው አልነበራትም።”

የሚገርመው ግን ለዚህ ስርዓታዊ ሽብር (systemic violence)ና ለጫልቱ ስሜት መጎዳት ዋና ተጠያቂ የሚያደርገው ህጻናትን ነው። ከፍ ሲል እንዳልኩት ጫልቱ ኣዲስ ኣበባ ስትመጣ ብዙም የሚያስከፋ ነገ ኣልገጠማትም። ነፍስ ካወቁ የማታ ተማሪዎች ጋር ስትማር የከፋ ችግር የመረረ ነገር የለም። ትልቁ ችግር የመጣባት ወደ ቀን ስትዛወር የሰባተኛ ክፍል ተማሪ የሆኑት በትምህርታቸው ኣርባ ኣንደኛ የወጡ ሰነፎች እንደነ ሳምሶን ኣይነት ህጻናት ማብሸቃቸው ነው። የሚገርመው በትምህርት ቤቱዋ ውስጥ መምህራኖቹዋም ለጫልቱ ያደሉ ነበር። ይወዱዋት ነበር። ችግሩ የነበረው እነዚያ የኣስራ ሶስትና የኣስራ ኣራት ዓመት ህጻናት ጋር ነው። እነዚህ ህጻናት በጫልቱ ንቅሳትና ቋንቋ መሳቃቸው ጫልቱን ሊጎዳ የሚችል መሆኑ ኣያጠያይቅም። ነገር ግን ጫልቱ በነዚህ ህጻናት መጎዳቷ ስርዓታዊ ሽብር(Systemic Violence) ለሚል መደምደሚያ ኣያደርስም። ጫልቱ እኮ ወደ ማታ ተመልሳ በዚያ ትምህርቱዋን መቀጠል ትችል ነበር። ለምን ከነዚያ ህጻናት ጋር እያበሸቁዋት ትኖራለች።

እነዚህ ህጻናት ጫልቱን በማብሸቃቸው ከስርዓት ጋር ምንም የተያያዘ ነገር የለውም። ቤተሰብ ኣላስተማራቸው፣ ኣስተማሪ ኣላስተማራቸው ይህንን መሳቅ ከየት ኣመጡት። እነዚህ ህጻናት ከኣዲስ ኣበባው ዘየ ለየት ያለ ኣማርኛ ሲሰሙ መቀለዳቸው ኣይቀርም። ጫልቱ ኦሮሞ ስለሆነች ኣይደለም።

ደራሲው ኣንዲህ ይላል። ኣንድ ጋጠ ወጥ ተማሪ የሚለውን ይመስለኛል የሚገልጸው።

“ ቆንጆ ነሽ የሆንሽ ኒቂሴ ገላ ሆንሽ እንጂ”

በርግጥ ኣንድ የኣስራ ሶስት ኣመት ሕጻን “ቆንጆ ነሽ” ይላል? ኣይመስለኝም። ንቂሴ ገላ…. ሊል ይችላል። በርግጠኝነት ግን ጫልቱ ኦሮሞነቱዋን ሳትገልጽ ስሟንም ደብቃ “ሄለን ነኝ” ያለች ሲሆን ኣንድ የኣስራ ሶስትና ኣስራ ኣራት ኣመት ህጻን

“የጋላ ነገር ይህን የመሰለ ውበት ቸክችከው ቸክችከው ኣበላሹት”  ኣይልም።

እንዴ?…. ህጻናት እኮ ናቸው:: ህጻናት የጠሉትን ንቅሳት ኣልፈው ሌላ ውበት በጫልቱ ፊት ላይ ማየት ኣይችሉም። ከሁሉ በላይ ደግሞ “የጋላ ነገር….” ኣይሉም።ይህንን ያለው ራሱ ተስፋየ ነው። ደራሲው ራሱ የፈለገውን መልእክት ለማስተላለፍ እነዚህን ህጻናት ለምን ወንጀል እንደሚያናግራቸው ኣልገባኝም። በደርግ ጊዜ እንኳን የኣስራ ሶስትና የኣስራ ኣራት ኣመት የኣዲስ ኣበባ ህጻን ይቅርና እኔ ራሴ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆኘም ስለ ብሄር  ብዙ ኣላውቅም። ትላልቅ የሆኑ ሰዎችም  ብዙ ኣያውቁም ነበር።  ሌላው ቀርቶ መንግስቱ ሃይለማርያም ኦሮሞ ይሁን ኣማራ ወይ ወላይታ ኣይታወቅም ነበር። ሁዋላ ላይ ዚምባብዌ ሳለ ኧረ ኣገሩ ሁሉ ዘሩን እየተጠየቀ ነው እርስዎ ከየት ነዎት? ተብሎ ነው ኦሮሞና ኣማራ መሆኑን ለ VOA ተናግሮ የታወቀው። ይህንን ስናይ በፍጹም ከእውነታው የራቀ ነገር  እነዚህን ህጻናት ደራሲው እንዲናገሩ ያደርጋቸዋል። በዚህ ኣዝኛለሁ። ከሁሉ የሚያሳዝነው ጎረቤቱን፣ ኣስተማሪውን ሁሉ ለጫልቱ ጥሩ ኣድርጎ፣  የማታ ተማሪዎችን እንከን ሳያወጣ፣  የሰባተኛ የቀን ተማሪዎችን ለጫልቱ መሰበር ዋና ተጠያቂ ማድረጉ ብሎም የስርዓቱን ሽብር የፈጠሩት ዋና ተጠያቂ እነዚህ ህጻናት እንደሆኑ ኣይነት ድምዳሜ ማሳየቱ በጣም ገርሞኛል።

ከፍ ሲል እንዳልኩት ደራሲው የሚያሳየን እነዚህ ህጻናት ጫልቱ ኦሮሞ መሆኑዋን ያወቁት በንቅሳቷ ነው። ይሄ ደግሞ በጣም ይገርማል።በመጀመሪያ ደረጃ ንቅሳት የሚነቀሱት ከፍ ሲሉ ነው። ጫልቱ በስንት ኣመቷ ደረቷን ሁሉ ሳይቀር እንደተነቀሰች ኣላውቅም። ይሁን…. ኣልፎ ኣልፎ በኣስራ ኣንድ በኣስራ ሁለት ኣመት ጊዜ የሚነቀሱ ይኖሩ ይሆናልና ይህን እንለፈው። በመሰረቱ የኣስራ ሶስትና ኣስራ ኣራት ኣመት የኣዲስ ኣበባ ህጻን በዚያን ጊዜ ንቅሳት የኦሮሞ መገለጫ መሆኑን ኣያውቅም። ኣይደለምም።  ንቅሳት ያለው  እንዴውም በብዛት የሚታየው በኢትዮጵያ ኣይሁዶች፣ በዎሎዎች፣ በትግሬዎች፣ በመንዞች ኣካባቢ ነው። እነዚያ ህጻናት ንቅሳትን በማየት ሄለን ኦሮሞ ናት ሊሉ ኣይችሉም። ደራሲው ሊደርስበት ለፈለገው መደምደሚያ የወሰዳቸው መንደርደሪያዎች(premisis) ተዓማኒነት የጎደላቸው ከመሆናቸውም በላይ ህጻናት መራሽ ስርዓታዊ ሽብር የተፈጠረ ኣስመስሎ ማቅረቡ ይህን ክፍል ባዶ እንዳያስቀርበት እሰጋለሁ።ደራሲው ኣጥብቆ የሚታገለው ጫልቱ ስሟን መቀየሩዋ ከማንነት መምታታት(identity confusion) ጋር እንዲያያዝለት ነው። በመሰረቱ በቋንቋ ሳይንስም ቢሆን በስምና በተሰያሚ መካከል ምንም ዓይነት ተፈጥሮኣዊ ግንኙነት የለም።

እኔ ራሴ ስሜ ከኦሮሞ የተወሰደ እንደሆነ ብዙ ሰው ይነግረኛል። በዚህ ደስተኛ ነኝ። ወላጅ እናቴ ኦሮሞ ኣገር ደራ የተባለው ቦታ ኣድጋ ስለነበር ስለ ኦሮሞዎች ጥሩነት ኣውርታ ….ኣውርታ ….ኣውርታ……..ኣትጠግብም ነበርና በልጅነት ጊዜየ እኔም ኦሮሞ በሆንኩ ብየ ኣስቤ ኣውቅ እንደነበር ትዝ ይለኛል።

የስም ጉዳይን ይዘን ወደ ኣዲስ ኣበባ ስንመጣ ብዙ ኣስቂኝ ጉዳዮችን ማንሳት ይቻላል። እርግጠኛ ነኝ እነዚያ የጫልቱ የክፍል ጓደኞች ከኣማራ ኣካባቢ የሄደች ኣንድ ንቅሳት ያላት ወጣት ክፍሉ ውስጥ ብትኖር ስሟ ደግሞ ቁንጥሬ ጭንቅል ቢሆን በስሟም በንግግር ዘየዋም መሳቃቸው ኣይቀርም። ኣንድ ኣምታታው ውርጋጥ የሚባል ወንድ ተማሪ ቢኖርም ክፍሉ በሳቅ ማለቁ ኣይቀርም። በዚህ በስም ኣካባቢ ብዙ ነገር ኣይቻለሁ። እዚህ ስማቸውን ብጠቅስ ጓደኞቼ ይቆጡኛል ብየ እንጂ የማውቃቸው ሰዎች ኣዲስ ኣበባ ሲገቡ ዘመንኛ ስም ለውጠው ኣይቻለሁ። ይሄ ደግሞ መራራ ከሆነ ስሜት ጋር የተያያዘ ሳይሆን ሸገርን ለመምሰል ነው።እነዚያ ህጻናት ሃጎስ በሚለውም ስም መሳቃቸው ኣይቀርም። ሸምሱ በሚባል የጉራጌ ልጅም መሳቃቸው ኣይቀርም።ይህ ነገር መልካም ኣይደለም። ሕጻናቱ የሚስቁት ከብሄር ከደም ሃረግ ጋር ኣያይዘው ሳይሆን ኣዲስ ኣበባ ሰለጠንኩ ስትል ዘመንኛ ያለቻቸውን ስሞች ዘርዝራለች። ከጥንት ጀምሮ በገጠሩና በከተሜው መካከል ሰፊ ምጣኔ ሃብታዊና ማህበራዊ ክፍተቶች ተፈጥረው እየሰፋ በመምጣቱ ኣዲስ ኣበባ ለየት ማለቱዋን በስም ኣወጣጥ፣ በኣነጋገር ዘየ  ለማሳየት ፈልጋ ነው። ይሄ ደግሞ እጅግ መራራ ነገር ኣይደለም። የገጠሩን ወንድሙዋና እህቱዋን ኣትጠላም።

ጸሃፊው የኣተቴን ነገር ኣንስቶ ጫልቱ በዚህም እንዳዘነች ይገልጻል። ያለችው እኮ ኣዲስ ኣበባ ነው።ርቃ ሄዳለች እኮ።  የተለየ ባህል የተፈጠረበት፣ ኣዲስ ኣገር ነው ያለችው።ጫልቱ ለመልቲ ካልቸራሊዝም ክፍት መሆን ኣለባት እኮ። ቆፍቱ ያለው ኣተቴ እዚህ ባለመጠራቱ  ልታዝን ኣይገባትም። እዚያው ኦሮሚያ ክልል ያሉ ብዙ የኦሮሞ ልጆች ኣይቀበሉትም። ወለጋ ያሉ ፕሮቴስታንት ኦሮሞዎች በየሱስ ስም እያሉ ነው የሚረግሙት። እዚያው ኦሮሞዎች መካከል ስትሄድም ልትጎዳ ነው ማለት ነው። ርቃ ስድትሄድ በተውጣጣ ማህበረሰብ ውስጥ ስትኖር በቀበሌዋ የነበረውን ባህል ሁሉ ታገኘዋለች ማለት ኣይደለም። ይህቺ ልጅ ይህን  የኣተቴ ባህሉዋን እዚያው ቆፍቱ እያለች እንዳትንከባከበው የሚያደርግ ኣካል ቢፈጠርና  ኣዘነች ቢባል ስሜት ይሰጣል። ይህንን መገንዘብ ያስፈልጋል። በተረፈ ግን ኣተቴ ያለው ኦሮሞ ጋር ብቻ ኣይደለም። ወሎና መንዝ ብንሄድ ብዙ ኣለ። ኣዲስ ኣበባ መጥታ ተይ ልጆቹን ስለ ኣተቴ ኣታስተምሪ መባሉዋ የመጨረሻ ስሜት ሰባሪ ነገር ተደርጎ መቅረቡ ትክክል ኣይደለም።

በመሰረቱ ማህበራዊ ለውጥ ኣይጠላም። ጫልቱ ጂንስ መልበሷ፣ ቦርሳ መያዟ፣ ከተሜ መምሰሏ ምንም ችግር የለውም። ዋናው ነገር ለለውጥ ስትዘጋጅ ኣንዳድ ጠቃሚ የሆኑ ባህሎቹዋን እንዳትጥል መምከር ነው። ስልጣኔ ሲመጣ ማህበራዊ ለውጥም ይመጣል። በዚህ ጊዜ ኣዳዲስ ባህሎችን ለመማር መዘጋጀት ማለት ነው እድገት ማለት።ይሄ ደግሞ ከማንነት መምታታት ጋር የተገናኘ ኣይደለም። ማንነት በነገራችን ላይ የሚቀየር፣ የሚያድግ ነገር ነው። ትናንትና ሙስሊም የነበር ዛሬ ክርስቲያን ቢሆን ማንነቱን ቀየረ ማለት ነው። ባህላዊ ማንነትም እየተቀየረ ሊሄድ ይችላል። ዜግነትም ይቀየራል። በመሆኑም እግራችን ሲርቅ ያለንበት ኣካባቢ ባህል ሲውጠን ስሜታችን ሁሉ ስብርብር ይላል ማለት ኣይደለም።

ወደ ጫልቱ የሰባተኛ ክፍል ብሽሽቅ ጉዳይ እንመለስና መምህር ጽጌ ያን ዱርየ ሳምሶንን ኣንዴ ሲዠልጡት  ኣልቅሶ ቆይ ሰኔ ሰላሳ እንገናኛለን ነው ያለው። ጫልቱ ማድረግ የነበረባት ይህንን ነው። የሚሰድቧትና የሚያበሽቋት ህጻናት በኣስተማሪዎች የተላኩ ኣይደሉም። ስለዚህ ማድረግ የነበረባት ለመምህር ጽጌ መናገርና  ጸጥ ማሰኘት ነው።

ደራሲው ጫልቱን ከሚገባው በላይ ስሜቷን ለመስበር ይሞክራል።ኣንባቢን ከንፈሩን ለማስመጠጥ ይሞክራል። ይሁን እንጂ የሄለንን ህይወት የወሰደበት መንገድ እሱ እንዳሰበው ኣንባቢ እንዲሰማው የሚያደርግ ኣይደለም። ራሱ ደራሲው እነዚያ የኣንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ስሜቱዋን ሁሉ ዖሮሞ ከመሆኑዋ ጋር ኣያይዞ እንዲሰብሩዋት ያደርግና በተሰበረ ስሜት ወደ ቆፍቱ ለእረፍት ይልካታል። በዚያ ደግሞ ስሟን በመቀየሯ መሳቂያ ያደርጋታል። ቆፍቱ ስትሄድ ኣክስቷ ኣማርኛ ብቻ ተናገሪ ኦሮምኛ ኣልችልም በይ ኣለቻት ይለናል። እንደዚህ ይባላል? ለማናቸውም እረፍት ጨርሳ ወደ ኣዲስ መጣች።ወዲያው ደግሞ በትምህርቷ ብዙ ሳትገፋ ከዘጠነኛ ክፍል ኣካባቢ ኣቋርጣ ትዳር መሰረተች ይለናል።

የሚገርመው ሄለን ያገባችው ኣውራጃ ኣስተዳዳሪ ነው። ስርዓቱ ምን ያህል ተቀብሏታል ማለትነው? ኣዲስ ኣበባ ውስጥ ያለ ኣውራጃ ኣስተዳዳሪ ጫልቱን ከነንቅሳቷ በፍቅር ወድቆ፣ ብዙ ቆንጆ ባለበት ኣዲስ ኣበባ ጫልቱ ኣሸናፊ ሆና ኣውራጃ ኣስተዳዳሪ ማግባቷ የሚያሳየው ከነዚያ ከህጻናት ከነሳምሶን ውጭ ከፍተኛ ከበሬታና ተቀባይነት ኣላት ማለት ነው። ባሏም ደስ ብሏት ኣብራው እየኖረች ነበር። ኣገር ዘመድ ኣውራጃ ኣስተዳዳሪ ኣገባች ብሎ ሳይኮራ ኣልቀረም። በዚያን ጊዜ ኣውራጃ ኣስተዳዳሪ መወሸም እንኳን ለሴቶች እንደ ትምክህት እንደነበር ኣይዘነጋም።

ከዚህ ተነስተን የሄለን ህይወት ሰመረላት ኣለፈላት ወደሚባል የህይወት መስመር ውስጥ እንደገባች መረዳት ያስችላል። ይህቺ ልጅ ገረድ ኣይደለም የሆነችው። ኣውራጃ ኣስተዳዳሪ ነው ያገባችውና።

ደራሲው ሄለን ኣውራጃ ኣስተዳዳሪ ኣግብታ እያለ በመሃል ኢህዓዴግ ኣዲስ ኣበባን እንደተቆጣጠረ ይነግረናል። ከዚህ በሁዋላ ኣውራጃ ኣስተዳዳሪው ባሏ ወደ ወህኒ ሲወርድ ምን ኣልባትም ሃብትና ንብረቱንም ኣጣ። የዚህን ጊዜ ሄለን ወይም ጫልቱ ትልቅ ችግር ላይ ወደቀች። ለባለቤቷ ስንቅ እንኳን ማቀበል ተሳናት። ትዳሯ ፈረሰ። ጎጆዋ ዘመመ። ከሁሉ የሚያሳዝነው ደራሲው በራሱ ኣንደበት

“ለባሏ ስንቅ ማቀበያ ቀርቶ ለራሷም የምትመገበው አልነበራትም።” ይላል።

ይልቅ ይሄ ኣንጀቴን በላው። የኣንድ ኣውራጃ ኣስተዳዳሪ ሚስት ያላትን ሁሉ በኣጭር ጊዜ ውስጥ ኣጥታ የምትበላው ሁሉ ስታጣ የለውጡን ኣስከፊነት ያሳያል። የምትበላው ብቻ ሳይሆን ማደሪያም በመቸገሩዋ ኣንድ ካፌ ውስጥ እየሰራች መተዳደር ጀመረች። ትንሽ ቤት ተከራይታ መኖር ጀመረች። ቤታቸውም ተወረሰ ማለት ነው። ይህ ኑሮ ለኣንድ ኣውራጃ ኣስተዳዳሪ ሚስት ከባድ ነበር። ስሜትን ይጎዳል።

ደራሲው ቀድሞ ለወሰነውና ሊያስተላልፍ ላሰበው ጭብጥ ሲል ሄለንን እንደፈለገው ሲያናግራት እናያለን። ወደ መጨረሻ ወጉን ሲቀጥልልን ይህቺ የኣውራጃ ኣስተዳዳሪ ሚስት ደርግ ወድቆ ኢህዓዴግ በገባ ሰሞን ቴለቪዥን ትከታተል ነበር ይለናል። ከዚያ ኣንድ ቀን  “ጭቆና” የሚለውን ቃል በቴሌቪዥን ስትሰማ ጊዜ ለመረዳት ጥረት አድርጋ ነበር ይላል ደራሲው። ይሄ ኣይመስልም። ይህቺ ልጅ በስርዓት ደረጃ ጭቆናን በህይወቷ ኣላየንም።ማነው የጨቆናት። የት ቦታ ጭቆናን ኣየች። እንዴውም ኢህዓዴግ ራሱ የጨቋኝ ሚስት ብሎ  ኣለማሰሩም ኣንድ ነገር ነው። የኣንደኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ ያውም እነሳምሶን ኣበሸቋት ማለት ወደዚህ ከፍ ያለ ማህበራዊ ጉዳይ ኣያመጣንም። ከሁሉ በላይ ማህበራዊ ለውጥ እንዲህ ቀላል ነገር ኣይደለም። በኣንዴ በቴለቪዥን ስታይ ኣሃ! ብላ ጭቆናን ተገነዘበች ለማለት ኣይቻልም።በቀጥታም ባይሆንም የኣውራጃ ኣስተዳዳሪ ባል ኣግብታ ያለፈውን ስርዓት የቀመሰች ሴት በትምህርት ቤት ብሽሽቅ “ጭቆና!” ትላለች ለማለት እኛ እራሳችን ልጅ መሆን ሊኖርብን ነው።

ደራሲው እነዚህን የማይመስሉ ነገሮች ሁሉ ኣንስቶ ጫልቱ የማንነት መምታታት ውስጥ እንደገባች ሊያሳየን ይሞክራል። በመሰረቱ የብሄርን ማንነት ከስም ጋር ኣያይዞ የማንነት   መምታታት ውስጥ ለመግባትና ለመጨነቅ እውቀት ይጠይቃል። ስለብሄር ፖለቲካ መማር በዚያ መጠመቅ የመንፈስን መረበሽ ሊያመጣ ይችላል። ይህቺ ለግላጋ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ በስም ለውጧ ምክንያት ተጨንቃ፣ ኣሁን እኔ ሄለን ነኝ……. ጫልቱ ነኝ……..ጫልቱን ፈልጌ ኣጣሁት ከውስጤ…….. ብላ በመጨነቅ ሰውነቷ ከስቶ ለሞት ደረሰች ማለት በሬው ወለደ ከሚለው ጠብደል ፈጠራ ኣይተናነስም:: ታዲያ ጫልቱን ምን ገደላት? ካልን  ወያኔ ኢሃዲግ ኣዲስ ኣበባ ሲገባ ትዳሯን ኣፍርሶ ሜዳ ላይ ጥሏት ስለነበረ፣ የሚበላ ስላጣች፣ ተስፋ ስለመነመነባት፣ በብስጭት ኩርምት ብላ ነው የሞተችው። ማን ገደላት ካልን ወያኔ ኢህዓዴግ ኣበሳጭቶ ተስፋ ኣሳጥቶ ለበሽታ ሰጥቶ ነው የገደላት ለማለት ጠንካራ መረጃ ኣለን። ይህቺ ልጅ የሁዋላ ታሪኳ ማለትም ያለእድሜዋ ማግባቱዋ፣ ሁዋላም ኣዲስ ኣበባ ስትመጣ ለባህል ግጭት (culture shock) መጋለጧ  በተለያየ ደረጃ የጎዱዋት የህይወት ልምዶች ቢሆኑም ከዚያ በሁዋላ ኣግብታ ኣካባቢውን ለምዳ ትኖራለች ተብሎ ነው የሚታሰበው።

የዚህ ጽሁፍ ደራሲ በቅርቡ በኣንድ ስብሰባ ላይ ሲናገር ለጫልቱ ሃውልት ይገባታል ሲል ሰምቻለሁ። በዚያ ኣልከራከርም።ለሃውልት የሚያበቃ ነገር ካለ ችግር የለውም። በሚሰራው ሃውልት ላይ ግን የሚጻፈው የሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች ብሽሽቅ ሳይሆን ወያኔ ኢሃዴግ ትዳሯን ኣፍርሶ ሜዳ ላይ ስለጣላት ለሞት የተዳረገችው ጫልቱ ተብሎ መሆን ኣለበት።

 

ማጠቃላያ

“ጫልቱ እንደ ሄለን” ጭብጡ በጣም የቀለለብኝ የኣንድን ሰው ህይወት ኣንስቶ ማህበረሰብን ወክሎ ለማሳየት ስለሞከረ ኣይደለም። ደርሶ ማጠቃቃለል (hasty generalization) የሚባለው እዚህ ጋር ኣይሰራም። የኣንድ ሰውን ይወት እየተረኩ የማህበረሰብን ህይወት ቁልጭ ኣድርጎ ማሳየት ይቻላል። ዋናው ግን የተሳሉት ገጸ ባህርያት ያንን ልናሳይ  የምንፈልገውን ማህበረሰብ ህይወት የሚወክል ባህርይ ስንፈጥርላቸው ይመስለኛል። ጫልቱ እንደ ሄለን በሚለው ውስጥ የኦሮሞ ወገኖቼን ብሶት ማሳየት ኣይቻልም። ከሁሉ በላይ ደራሲው የሲስተም ሽብር ያለውን ጉዳይ ለማሳየት ህጻናት ዋናውን ድርሻ መያዛቸው ልቦለዱ እንዲወርድብኝ ኣድርጓል።

ይህንን ካልኩኝ በሁዋላ ግን የኦሮሞ ህዝብ ብሶትና እንግልት  ባለፉት ስርዓቶች ሁሉ ያሳለፈው ጉዳት ከስም ለውጥ ከኣተቴ ልምድ ያለፈ ነው። የኦሮሞን ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ክፍፍል፣ የፖለቲካ ውክልና ጥያቄዎች እንዲህ ባሉ በስያሜ በምናምን ማውረድ ተገቢ ኣይደለም።ኢትዮጵያን ከኦሮሞ ውጭ ማየት ኣይቻልም። ይህ ህዝብ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ታላቅ ታሪክ ያለው ከሌሎቹ ወንድሞቹ ጋር ለሃገሩ መስዋዕት ሲሆን የኖረ ልበ ሰፊ ህዝብ ነው። ይሁን እንጂ በመጡት ስርዓቶች ሁሉ ተጠቅቱዋል። በኢኮኖሚው፣ በማህበራዊው መስክ ተጎድቱዋል። ይህ ማለት ግን ሌላው ወገኑ ኣልተጎዳም ማለት ኣይደለም። ሁሉም ቡድኖች በተለያየ ቅርጽና ይዘት ተጎድተዋል። የኦሮሞው ህዝብ ኣሁን ያለው ፍላጎት ብሄርን ነጥሎም ይሁን በጅምላ የሚደረግ ጭፍጨፋ ይቁም እኩልነት በሃገራችን ይስፈን ነው። ይህ ጥያቄው ደግሞ ተገቢና እውነተኛ ነው። በቋንቋው በኩል ኦሮምኛ ኣንዱ ዋና መግባቢያ ቋንቋ መሆን ኣለበት። ከዚያ ውጭ ግን ከሌሎች ወገኖቹ ጋር ሲኖር ኣንዳንድ የኦሮሞ ተወላጆች የኣማራ ስም ወይ የትግሬ ስም ወይ የወላይታ ስም ኣውጥተዋል ብሎ የሚከፋ ኣይደለም።  ኣማራ ሆነው የኦሮሞ ስም ያላቸው ብዙ ኣሉ። የደቡብ ተወላጅ ሆነው የኦሮሞ ስማ ያላቸው ሰዎችና ቦታዎች ብዙ ናቸው። በመሆኑም የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ ከፍ ኣርጎ ማየትና ከፍትሕ ከዴሞክራሲ ኣንጻር መመለስ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው። በኢትዮጵያ የሚኖሩ ብሄሮች ሁሉ ኣንዱ የኣንዱን ብሶት በመረዳትና እውቅና በመስጠት ተከባብረው ሲኖሩ ጥያቄዎቻቸው ይፈታሉ። ከዚህ ውጭ ግን ባህል ለመካፈል፣ ባህልን ሰጥቶ ለመቀበል፣ ለዘመናዊነት ክፍት መሆን በጣም ኣስፈላጊ ነው።

 

እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ

 

geletawzeleke@gmail.com

EPRDF

በጎንደር አዘዞ አካባቢ 1250 ኮንደሚኒየም ቤቶችን የተረከቡ አባወራዎች ላለፉት 3 ዓመታት መብራት ማጣታቸውን ገለጹ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በሰሜን ጎንደር አዘዞ አካባቢ ከ3 ዓመት በፊት የኮንደሚኒየም ቤት የተረከቡ ወገኖች ላለፉት 3 ዓመታት ኮንደሚኒየሞቹ መብራት ያልገባላቸው በመሆኑ በከፍተኛ መጉላላት ላይ እንደሚገኙ ለዘ-ሐበሻ በላኩት አቤቱታ አስታወቁ።

የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)

የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)

ከ3 ዓመት በፊት 1250 የኮንደሚኒየም ቤቶች ተሰርተው መብራት ሳይገባላቸው ተሰጥቶናል ያሉት ነዋሪዎቹ ገንዘባችንን ከወሰዱ በኋላ መብራት ሳይገባላቸው ይኸው በስቃይ ላይ ነን ብለዋል። “ስጋ ሰጥቶ ቢለዋ እንደመከልከል ነው” የሚሉት ነዋሪዎቹ አካባቢያችን አቋርጦ የሚያልፍ የመብራት ገመዶችን ከማየት ውጭ በመኖሪያ ቤታችን መብራት አትጠናል ይህም “የበይ ተመልካች…” የሚለውን ያስተርታል ይላሉ።

“በአካባቢው የሚገኘውን የመብራት ኃይል ጠይቃችሁ ነበር ወይ ለምን መብራቱ እንደዘገየ?” በሚል ዘ-ሐበሻ ለነዋሪዎቹ ጥያቄ ያቀረበች ሲሆን ነዋሪዎቹ ጥያቄውን በተደጋጋሚ ቢያቀርቡም፤ የሚሰጣቸው ምላሽ ላለፉት 3 ዓመታት ሰበብ ብቻ እንደሆነ ገልጸውልናል።

ዘ-ሐበሻ የአካባቢውን የመብራት ሃይል ባለስልጣን ለምን ባለፉት 3 ዐመታት እነዚህ ኮንደሚኒየም ቤቶች መብራት እንዳላገኙ ለመጠየቅ ሙከራ አድርጋ የነበረ ቢሆን ያገኘችው ምላሽ “ለሚድያ መግለጫ አንሰጥም” የሚል ነው።

ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በዋሽንግተን ዲሲ –ለማክሰኞ ኦክቶበር 7 ጠዋት 9፡00 ሰዓት

$
0
0

ማክሰኞ October 7 ከጠዋቱ 9:00 ሰአት ጀምሮ በዋሸግተን ዲሲ State Department ፊት ለፊት 22 C ST NW WASHINGTON DC 20018.
All freedom Loving Ethiopians are Invited.
Date October 7, 2014 Time 9:00am
Place US department of state
Washington DC
Organizer Dc Joint Task Force

ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በዋሽንግተን ዲሲ – ለማክሰኞ ኦክቶበር 7 ጠዋት 9፡00 ሰዓት

ለህወሃት/ኢህአዴግ ሥርዓት እድሜ መራዘም ዋና ዋና ምክንያቶች፦ (አንተነህ ገብርየ)

$
0
0

 

EPRDFየዛሬው እድሜ ጠገብ አንጋፋ ፖለቲከኛና ምሁር በየካቲት 1966 እና ከዚያም በፊት የፖለቲካ አፈንፋኝ የነበረው ትውልድ ድርጅት መሥርቶ በድርጅት ደረጃ የታገለና ያታገለ እንደነበረ ይታወቃል። ያ ትውልድ በለስ ቀንቶት ሥልጣን የያዘበትና በለስ ሳይቀናው ቀርቶ ደግሞ ዛሬም የድርጅቱን ስም ሳይቀይር መሠረታዊ ለውጥ ሳያሳይ ቀጥሎበት ይገኛል።የዚያ ጊዜ አመራሮች ዛሬም የእነዚያ ድርጅቶች አመራር ሆነው ቀጥለዋል።አብዛኛው በኢትዮጵያ መንግሥትና የሕዝብ ሀብት ለመማር እድል ገጥሞት ወደ ውጭ ሄዶ ዓላማውን በመቀየር የመንግሥት ሥልጣንን ለመጨበጥ አልሞ የነበረው ሲሆን የቀረው ደግሞ ከየዩኒቨርስቲዎችና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችና አስተማሪዎች የወጣ የየካቲት ሕዝባዊ አብዮት ያነሳሳው፤ የኃይለሥላሴ መንግሥት ቤተሰብና ባለሥልጣናትን ያካተተውና ከወታደራዊ ካምፕ ውስጥ የነበረው ነው።(በስም ሲገለጡ፦ ሻእብያ፤ ህወሃት፤ ጀብሐ፤ኢዲዩ፤ደርግ፤መኢሶንና ኢህአፓ ማለት ነው)

እነዚህን ድርጅቶች የኢትዮጵያ ህዝብ ተገፍቼና ተደፍቻለሁ ዋስ ጠበቃ ሁኑኝ በደል በዛብኝ ብሎ ተማጽኖ እንዲታገሉለት አልመረጣቸውም በመንፈሳዊና ብሔራዊ ሞራል ለሕዝብ በመቆርቆር አለመሆኑም ይታወቃል ዋና ዓላማውና ግቡ የነበረው የሥልጣን ባለተራ ከመሆን ውጭ የሚታሰብ አልነበረም አሁንም ከዚያ የተሻለ ራእይ አላቸው ማለት በፍጹም አዳጋች ነው።እነዚህ ኃይሎች ወይም የድርጅት አመራሮችና አባላት ይበልጡ በየሥርዓቱ አገልጋይና ሹመኛ የነበሩ ባለሥልጣናት ቤተሰብ እንደነበሩ ግልጽ ነበር።አንግበውት የተነሱት መፈክር ግን የሕዝቡ ቁስል የነበረውንና ዛሬም እልባት ሊያገኝ ያልቻለውን ጥያቄ ነበር፡፡

በኋላ ላይ እርስ በርሳቸው ተባልተው ጀብሓ ቢከስምም የሻእብያና ጀብሓ አነሳስ ኤርትራ በጣሊያን ግዛት ሥር ለ50፤በእንግሊዝ ግዛት ሥር ለ10ዓመታ የቆየችበትን ምክንያትና ችግር ወደ ጎን በመተው ከዚያ በፊት ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል አልነበረችም ብሎ ሸምጥጦ በመካድ ኢትዮጵያ ኤርትራን ከእንግሊዝ ግዛት ወደ ራሷ በማድረግ እንደ አንድ የኢትዮጵያ ክፍለሀገር(ጠቅላይ ግዛት)ማስተዳደር በጀመረችበት ወቅት ኢትዮጵያ ኤርትራን በቅኝ ግዛት ነው ይዛ ያለች በሚል ደረቅ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ተነሳስተው ኤርትራን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ታገሉ ተሳካላቸው።ዛሬ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ሕዝብ እያመሰ ያለው በሻእብያ  ፊታውራሪነት በዐረብ ፊውዳሎችና ምዕራባውያን ተኮትኩቶ ያደገው ህወሃትም የሻእብያ ጉዳይ አስፈጻሚና ተላላኪ በመሆን ጠንክሮ የሰራ ሲሆን እንደ መነሻ ያደረገው ግን የትግራይ ሕዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለየ ሁኔታ በአማራው ገዥ መደብ የተጨቆነ ስለሆነ ነፃ ማውጣት አለብን የሚል መፈክር ይዞ የተነሳ ሲሆን ሌሎች ሕብረ-ብሔራዊ ድርጅቶችን ከሻእብያና ጀብሓ ጋር በመሆን ያዳከመና በ1976 ዓ/ም ትግራይን ከኢትዮጵያ በመገንጠል “ ታላቋን ትግራይ ትግርኝት ሪፐብሊክ” መመሥረት ይገባል በማለት በማነፌስቶ (manifesto)ላይ ይፋ በማድረግ የተንቀሳቀሰና ዛሬም ከዚያ ጭንብል አስተሳሰብ ያልተላቀቀ ድርጅት ነው። አንዳንድ ወገኖች ህወሃት የመንግሥትን ሥልጣን በመያዙ ከመገንጠል አባዜው ድኗል ብለው ሳይሞግቱኝ አልቀሩም ጥሬ ሀቁ ግን የህወሃት አመራርና አባላቱ በኢትዮጵያ የሚገኘው የፖለቲካ ምሕዳር ሲጠብ የህወሃት ምርጫ መገንጠል ሊሆን እንደሚችል በአራት ነጥብ መደምደም ይቻላል።ለዚያ ሲባልም ነው ህወሃት የኢትዮጵያ ሕዝብ በጎሣ ተለያይቶ የየራሱ የተከለለ መንደር ተበጅቶለት አንዱ ሌላውን እንዳያምነውና በጥርጣሬ ዓይን እንዲተያዩ ለዘመናት አብሮ ያኖራቸውን ባሕላዊና ታሪካዊ ትሥሥር የአንድነታቸውን ማሰሪያ ገመድ ለመቁረጥ አዛዥና አናዛዥ በመሆን እየሠራ የሚገኘው።

ሌሎች የየካቲት 1966 ሕዝባዊ አብዮት ያስገኘውን ድል ነጥቆ ሥልጣን የጨበጠውን የወታደራዊ ጁንታ ጨምሮ ኢህአፓና መኢሶን የማርክሳዊ ሌሊናዊ ርዕዮትን የተከተሉ ሲሆን ማሌን በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታው ሳይፈቅድ ለማስረጽ ነበር የተንቀሳቀሱት በውጤቱ ምን እንዳተረፉ ተመልክተናል።ከዚህ ለየት የሚለው የየካቲት ሕዝባዊ አብዮት የተናደውን የፊውዳላዊ ሥርዓት ለማስመለስ የተንቀሳቀሰው ኢዲዩ ጉዳይ ነበር።ኢዲዩ ከላይ እስከ ታች ያለው መዋቅሩ አንድ ወጥ የሆነና በሥነ-ሥርዓት የታነጸ አመራርና አባላት የነበረው ባይሆንም ከሌሎች ባልተናነሰ መልኩ ሕዝብን የማነሳሳትና ደርግን የማደናገጥ አቅም ፈጥሮ ነበር። ህወሃትና ኢህአፓ ከውስጡ ሠርጎ በመግባትና በውጊያም አዳክመው እንዲንኮላሽ አደረጉት።

እንደመግቢያ ወደ ኋላ ሄጀ አንዳንድ ቅድመ ሁኔታዎችን የነካካሁት በብዙ መንገድ ምክንያታዊ ነው ህወሃት በለስ ቀንቶት የመንግሥት ሥልጣን ከጨበጠ በኋላ አካሄዱ ያላማራቸው ተደራጅተው ትግል የጀመሩትን በሚመለከት ጊዜ ወስዶ ስለሁኔታቸው ማየት የሚያስፈልግ በመሆኑ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ ግድፈቶች ናቸው ብየ የማምንባቸውን በዚህ ጹሑፌ  ስለነሱ የምለው አይኖረኝም።የታገሉኝንና ያታገሉኝን ድርጅቶች ግን ከታች በነበረው የአባላቱ እርከን ሆኘም ስለማውቃቸው ለምን እርስ በርስ ከመናከስና ከመዘረጣጠጥ እርቀ-ሰላም አውርደው(ይቅር-ለእግዚአብሔር)ተባብለው በአንድነት ጠንካራ ክንድ ፈጥረው ይህን “ተውሳክ የኅዳጣኖች ድርጅት ህወሃትን”አይታገሉም?በሚለው ጉዳይ ዙሪያ የተጠየቅ ሀሳቤን ከመሰንዘር ወደ ኋላ እንደማልል ልገልጽላቸው እወዳለሁ።

ሁላችንም የምንስማማበት የሁላችን የሆነ የጋራ ችግር እንደገጠመን ግልጽ ነው። ይኸውም “ውሃ እያሳሳቀ ይወስዳል” እንዲሉ ቅጥረኝነትን እንደ ሥልጣኔ ቆጥረው በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የጥፋት ዘመቻ የሚካሄዱና እያካሄዱ ያሉ የዘር ሀረገጋቸው ኢትዮጵያዊ የሆኑ በተልዕኮ ግን ድርቡሽ (መሐዲስት)፤ ዮዲት ጉዲት፤ግራኝ መሐመድና ጣሊያን በቅርቡም ደርግ ከፈፀመው ፀረ-ሕዝብ ተግባር የከፋ አመለካከትና ዓላማ አንግበው አጀንዳቸውን ደብቀው በኢትዮጵያዊነት ስም የመንግሥት ሥልጣን በመጨበጥ ሀገርንና ሕዝብን እያጠፉ የሚገኙ ከአንድ ነገድ የተሰባሰቡ ጠባብና ጎጠኛ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች የሚመሩት  እንዲሁም ከሌሎች ነገዶች የተሰባሰቡ አድርባዮችና ሆዳሞች የያዙት ሥልጣን እያደረሰብን ያለው ጉዳይ ነው።

ይህን ዓይነቱን ችግር በምን ሁኔታ ማስወገድ እንደሚቻል እንኳን እንደ ድርጅት ቆመውና የፖለቲካ ፕሮግራም ነድፈው የሚንቀሳቀሱት በግብርና የሚተዳደር የትግራይ ወይም ወለጋ የሚገኝ አርሶ አደር እስከ መፍትሔው ሊያስቀምጠው ይችላል። ለዚያም ነው ሕዝባችን አንድ ሆናችሁ ተጋሉ እኛንም አታግሉን የሚለው። ልብ አድርጉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ታገሉልን አላለም አታግሉን ነው ያለው።ይህ እጅግ በጣም የባሰ ችግር እንዳለና ሕዝብ ለትግል ቆርጦ መነሳቱን ሲያሳይ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ግን አንድ ርምጃ ወደፊት ሄደው መገኘት ሲገባቸው አንድ ርምጃ ወደ ኋላ ሄደው ጭራ ሆነው የሚገኙበት ወቅት ነው። ሀገሬንና ሕዝቤን እወዳለሁ የሚል ግልጽ ዓላማና ፕሮግራም ያለው ድርጅት ቅድሚያ ማድረግ ያለበት የሕዝብ ተገዥነቱን ፤ ተአማኒነቱን ማረጋገጥ ነው። ይህን ማድረግ ሲቻል ነው ያ ድርጅት ወይም እነዚያ ድርጅቶች በሰው ኃይል ሊጠናከር ወይም ሊጠናከሩ የሚችሉት። በሰው ኃይል የተጠናከረ ድርጅት ደግሞ ድል ማድረጉ የማይቀር ነው።እንግዲህ ይህን መራራ እውነት ለመቀበል አለመድፈር የሚያመላክተው እያንዳንዱ ድርጅት ያነገበው ድብቅ አጀንዳ አለ ወይም በድርጅት ደረጃ መንቀሳቀስ አንድምታው ምን እንደሆነ ሳያውቁ የተዘፈቁበት ጉዳይ ነው ማለት ይቻላል።

በርግጥ በርከት ያሉት ድርጅቶች እንደ የካቲቱ ዓይነት ሕዝብ የሚያስገኘውን ድል ለመንጠቅ የሚጠባበቁና በአቋራጩ የሥልጣን ማማ ላይ ለመቀመጥ የሚያስቡ ናቸው። አንዳንዶቹ ደግሞ የህወሃቱ አይነት የውሸት ግንባርና ህወሃት የተጠቀመባቸውን አይነት አሻንጉሊት ድርጅቶችን በማስመራት ህወሃት በሄደበት መንገድ ሄዶ በኃይል ገብቶ ሥልጣን ለመጨበጥ የሚጓዙም አሉ። ሌሎች ደግሞ ትክክለኛ የሕዝብና ሀገር ፍቅር ያላቸው በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት፤ ነፃነት ፤ እኩልነት፤ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን የሚዋደቁ ሞልተዋል።ቢሆንም ግን ሕዝብ ምን እያለን ነው? ነባራዊ ሁኔታው ምንን እያሳየ ይገኛል? የሕዝቡ ለትግል የመነሳሳት ጉዳይ እለታዊ ነው ወይስ ሥር ነቀል ለውጥ እስኪመጣ ድረስ የሚዘልቅ ነው? በሚለው ዙሪያ መግለጫ ከማውጣትና በተደጋጋሚ ከማውራት ተሻግሮ ተገቢ እንቅስቃሴ ማድረግ የተሳናቸው ናቸው።

ዲሞክራሲ የሰፈነበት፤የሕዝቦች ነፃነትና እኩልነት የተከበረበት፤የሕግ የበላይነት የሰፈነበት ሥርዓት ሲገነባና በተገነባበት አገር በሕዝብ ላይ የግድያ የእሥራት፤የድብደባና የአፈና ወንጀል፤የሕዝብን ሀብት የዘረፈ የሀገርን ሉዓላዊነት ያስደፈረ በወንጀል ወይም በፍትሐብሔር ሕግ ይጠየቃል። የወሰደውን ይመልሳል፤ የበደለውን ይክሳል እንደ ጥፋቱ ክብደት እየታየ የእሥራትና የሞት ቅጣት እስከመውሰድ የሚያደርስ ሕጋዊ ርምጃ በመንግሥት ይወሰዳል።የትኛውም ዜጋ በዜግነቱ ተከብሮ የሕግ ጥበቃ ይደረግለታል።ሕጉን ጥሶ በዜጋ ላይ አግባብ የሌለው ርምጃ የወሰደ ማንኛውም ባለሥልጣን ይከሰሳል ፤ ይቀጣል፤ሥራውን እንዲያጣ ይደረጋል።በኢትዮጵያችን እንዲህ ያለውን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት፤ የሕዝቦች በጋራ መፈቃቀድና መከባበር የተገነባ ነፃነትና እኩልነት፤ የሕግ የበላይነት ታይቶ አያውቅም። ግለሰቦች ከሕግ በላይ ሆነው በቡድን ተደራጅተው የሕግ ከለላ የሌላቸውን ሲያሰድዱ ሲገድሉ፤ሲያስሩ፤ሲዘርፉ ኖሩ አሁንም ይህ የሰብአዊ መብት አፈናና ረገጣ፤ፋሽስታዊ ዱላ በዜጎች ላይ እየተፈፀመ ይገኛል። የዘውዳዊው ሥርዓት መጥፎ ባህሪያት ደርግ አሻሽሎና አጠናክሮ ቀጠለ፤ከዚያ የተረከበው የህወሃት ቡድን ደግሞ እጅግ በጣም አጠናክሮ ሕዝብና አገር እያጠፋ ይገኛል። እዚህ ላይ ቁም ድምበሩን ዘለሃል የሚል በመጥፋቱ በማናለብኝነት አካላዊ ግፍ ከመፈፀማቸው ባሻገር ስነ-አእምሮን የሚያውኩ አፀያፊ ቃላትን በመጠቀም በአንድ ነገድና የክርስትና እምነት ተከታይ ሕዝብ ላይ ሰፊ ዘለፋ አካሄዱ አሁንም እየገፉበት ሄደዋል።

በዘውዳዊ አገዛዝ ዘመን የነበሩ የመንግሥት ባለሥልጣናት ላይ ደርግ በወሰደው ፋሽስታዊ ርምጃ ያበቃ በመሆኑ በዚህ ዙሪያ የምለው አይኖረኝም። በደርግ ዘመን የነበረው የመንግሥት ባለሥልጣን፤ካድሬ፤ደህንነት ወደ ዘመነ ወያኔ(የትግራይ ወመኔዎች) ተላልፏል።በወመኔዎች የሥልጣን ዘመን ደግሞ ለየት ባለና ባልተለመደ መልኩ በአንድ ጐሣ ጥርቅሞች የሚመራው ደህንነት፤ፖሊስ፤ካድሬ ከላይ እስከ ታች ባለው የመንግሥት መዋቅር የሚገኘው ኃይል ሕዝብን እያስለቀሰ ፤እየዘረፈና እየገደለ ይገኛል።የሰላማዊ በሩ ተዘግቷል።የወጣቱን ትውልድ እጣ ፈንታ አጨልመነዋል። የእነዚህ ሁሉ ማጠንጠኛው በቡድንም ሆነ በተናጠል በሕዝብ ላይ የፈጸሙት ግፍ በኃይል ተጠናክረው ካልቆሙ በስተቀር በሰላም ቀን የተጠያቂነት ጉዳይ ስለሚነሳ እየተረበሹ እንዲኖሩ የግድ ሆኗል።ሕብረት ፈጥረው በጋራና በአንድነት የማይታገሉት የተቃዋሚ ኃይሎችም ተመሳሳይ ቁስል ያላቸው ስለሆኑ እርቀ- ሰላም ማውረድና ይቅር ለእግዚአብሔር ተባብሎ የበደሉትን ሕዝብ ይቅርታ ጠይቀው ወደ ድሮው ሰውነታቸው መመለስ አልፈለጉም።ችግራችን ያለው እዚህ ላይ በመሆኑ ሁላችንም ተባብረን መፍትሄውን ልናበጅለት ይገባል የሚል እምነትና አመለካከት ስለአለኝ ከሕዝቡ ይሁንታና መሠረታዊ ፍላጎት ውጭ የሚሄዱትን የተቃዋሚ ኃይሎች በጋራ እንዲታገሉ ማድረግ የወመኔዎችን ቡድንም የፕሮፓጋዳ፤የኢኮኖሚና የፖለቲካ ሥሩ የሚደርቅበት ሥራ እንሥራ እነዚህ የደደቢት ወመኔዎች እቤትህ ድረስ ሳይመጡ አንተ እቤታቸው ሂድባቸው።

                        

 

                       

ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ ተገልብጦ የ17 ሰዎች ሕይወት አለፈ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚያሰቅቅ ሁኔታ እየደረሰ ያለው የመኪና አደጋና በዚሁ ጉዳትም የሚያልቀው ሕዝብ ብዛት እጅጉን አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው። ዛሬም ወደ አዲስ አበባ 65 መንገደኞችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ አውቶቡስ ተገልብጦ 17 ሰዎች ወዲያውኑ መሞታቸው ታውቋል።
Car accident
በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንኳ በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ ከዘገብናቸው ዘግናኝ የመኪና አደጋዎች ውስጥ፦

ከሞያሌ ወደ ሻሸመኔ የሚጓዝ አገር አቋራጭ አውቶቡስ ተገልብጦ 17 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ፤
ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር የሚጓዝ አውቶቡስ ተገልብጦ 41 ሰዎች ማለቃቸው፤
በአዲስ አበባ ከካራ ወደ መርካቶ የሚጓዝ አውቶቡስ 15 ሜትር ጥልቀት ካለው ገደል ገብቶ የሰዎች ሕይወት ማለፉ፤
ወደ ደብረማርቆስ የሚጓዝ አውቶቡስ ተገልብጦ የ13 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱና ሌሎችም ይገኙበታል።

ዛሬ ከሃገር ቤት የተሰማው ዜና እንደሚያስረዳው ከደባርቅ ወደ አዲስ አበባ 65 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ተገልብጦ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል። አደጋው የደረሰው ዛሬ ከቀኑ 6:30 ላይ አውቶብሱ በአማራ ክልል፣ ደጀን ወረዳ፣ ባልበሌ ቀበሌ አካባቢ በሚገኝና 50 ሜትር ጥልቀት ባለው ገደል ገብቶ ነው።

መንግስታዊ ሚድያዎች እንደዘገቡት በዚህ አደጋ የ17 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ 37 ሰዎችም ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የማለዳ ወግ …ትኩረት የሚሻው የአረብ ሃገሩ ስደት ጉዳይ ! (ነቢዩ ሲራክ)

$
0
0

መስከረም 25, ቀን 2007 ዓ.ም በምሽቱ የ EBC ዜና እወጃ የፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ የኢምሬት ጉብኝት ተከትሎ አንድ ቀልቤን የሳበ መረጃ ሰማሁ ። ፕሬዘደንት ዶር ሙላቲ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሜሬት ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር  መመካከራቸውንና ስለ ተቋረጠው የኮንትራት ሰራተኞች ጉዞ ተጠይቀው የዜጎችን ሰብአዊ መብት ለማስጠበቅ የሚችል ህግና ደንብ እየተሰራበት መሆኑን ጠቁመዋል። መልካም ነው!  የ EBC ዘገባ የአምናው የሳውዲ ” ህገወጦች ውጡልኝ! ” እወጃ ተከትሎ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን በደል ተከትል ዜጎችን በአፋጣኝ ወደ ሃገር ለማስገባት በዘመቻ መልክ ከኢምሬት የጅዳን ቆንስል ለመርዳት መጥተው የነበሩትን የኢምሬትን አምባሳደር  አብዱልቃድርን ማብራሪያም አሰምቶናል ። ይህም መልካም ነው  !

   አጽንኦት ሰጥቶ ላዳመጠው አምባሳደሩ በገደምዳሜ ሳይሆን በግልጽ ከዚህ በፊት በመንግስት ደረጃ የሰራተኛ ልውውጥ  ስምምነት እንዳልነበርና አሁን በዚያ ዙሪያ  እየተሰራበት እንደሆነ አስረድተዋል። በመንግስት ደረጃ ስምምነትም ሆነ ቅድመ ዝግጅት ሳይኖር ለደረሰው የዜጎች ጉዳት ተጠያቂ ማነው ? ብለን  ስላለፈው ከፍ ያለ ጉዳት ባንሞግትም በቀጣይ ሌላ አደጋ እንዳይከሰት ስለ እውነት ሲባል መነጋገሩ ተገቢ ነው። የሳውዲን ጉዳይ ካነሳን ከምንም በላይ የኢምሬቱ አምባዳደር ለስደተኛው መከራ እያደር መክፋት ከሚረቀቀው ህግ ባለፈ በሙያው የተካነ ፣ ለዜጎች መብት የተጋ ተጠሪ እጥረት መኖሩን በቦታው ተገኝተው እንዳዩትና በብዙዎቻችን ተግልጾላቸው እንደነበር አስታውሳለሁ ።

   መቸም ስደቱን ማቆም ቢገድ “እየተሰራ ነው” ከተባለው ህግና ደንብ ጎን ለጎን በእጅጉ ስለጎዳን የአረቡ ሃገር ስደት እንነጋገር ከተባለ የአረቡ ሃገር ስደተኛ ዜጎቻችን መብት ለማስከበር የተጉ ሃላፊዎች የሉንም ። ለችግሩ መፈታት የምንሻ ከሆነ ይህ የመብት አዴሰከባሪ እጦት መመለስ ያለበት ቁልፍ ጥያቄ መሆኑ ችላ ሊባል አይገባም ። ሌላው አሁንም በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ከዚህ በፊት ያለ ህግ ማዕቀፍና በቂ ዝግጅት የተላኩት ዜጎች በየአረብ ሃገራቱ መብታቸውን አስከባሪ አጥተው ሞልተው ተርፈዋል።  አሁን ድረስ በአደጋ ተከበው ኑሮን እየገፉ ላሉት ዜጎች መብት ጥበቃ በቂ ምላሽና መፍትሔ ሳይገኝ ዜጎችን እንደገና ወደ አረብ ለመላክ የተያዘው ጅምር በግል የስደተኛውን መከራ በቅርብ እንደሚመለከት ዜጋ ያሳስበኛል። በማያውቁት ሃገር ፣ ባህልና የስራ ጸባይ ለስራ ባልደረሰ ለጋ እድሜያቸው በአፈ ጮሌ ደላላ አማካኝነት በአረብ ሃገራት እንደ ጨው የተበተኑት ዜጎች ጉዳይ በውል ሊጠና ይገባል።   የወገናችን ጉዳይ ያገባናል ብለን መረጃ ጨብጠን የምናቀርበው የሰላ ሂስ የምናቀርበውን ፣ እኛ የምንለው ቀርቶ  ያን አምና ሳውዲ በዘመቻ መጥተው የስደተኛውን አበሳ በአካል አይተው የሚያውቁት እንደ ኢምሬቱ አንባሳደር አብድልቃድር ያሉ የመንግስት ከፍተኛ  ሃላፊዎች  እውነቱን ገላልጠው ለበላይ አካላት በማሳወቅ  መፍትሔ ሊያፈላልጉ ይገባል ባይ ነኝ !   ከልብ ካዘኑ እንባ አይገድምና  …

ቸር ያሰማን  !

ነቢዩ ሲራክ

የማለዳ ወግ …ትኩረት የሚሻው የአረብ ሃገሩ ስደት ጉዳይ ! (ነቢዩ ሲራክ)

ለባቡር ፕሮጀክት ሊሰጥ የነበረው 1.4 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንዲዘገይ ተደረገ

$
0
0

በስዊዘርላንድ ባንክ ክሬዲት ስዊዝ የሚመራው የአውሮፓ አበዳሪ ባንኮች ጥምረት፣ ኢትዮጵያ ላቀደችው የአዋሽ – ወልዲያ የባቡር ፕሮጀክት ለማቅረብ የተስማማውን 1.4 ቢሊዮን ዶላር ብድር አዘገየ፡፡

ባንኩ የተጠቀሰውን ብድር ያዘገየው የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ያቀረበው የአካባቢና ማኅበራዊ ተፅዕኖ ጥናት ክሬዲት ስዊዝ ከሚከተለው ‹‹ኢኳቶሪያል ፕሪንሲፕል›› ከተሰኘ የአካባቢና ማኅበራዊ ተፅዕኖ መመዘኛ ደረጃ ጋር፣ ሙሉ በሙሉ መጣጣም ባለመቻሉ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

hd0002የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በምሥራቅ የአገሪቱ ክፍል ከምትገኘው አዋሽ አርባ በኮምቦልቻ በኩል ወልዲያ ሃራ ገበያ የሚደርስ 447 ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር በመዘርጋት፣ የሰሜኑን የአገሪቱ ክፍል በቀጥታ አዲስ አበባን ሳይረግጥ ወደ ምሥራቁ የአገሪቱ ክፍል የሚደርስበትን የትራንስፖርት አማራጭ ለመዘርጋት አቅዷል፡፡

ይህ የባቡር መስመር በአጠቃላይ 1.7 ቢሊዮን ዶላር የሚፈጅ ሲሆን፣ የውጭ ብድሩን ለማግኘት የውጭ አበዳሪዎች የሚጠይቁትን ሰነድ ለማሟላት የሚያስችል የአካባቢና ማኅበራዊ ተፅዕኖ ጥናት፣ የፕሮጀክቱ ርዝመት፣ በአራት ተከፍሎ በአራት ኩባንያዎች ጥናቱ መሠራቱንና ይህ ጥናትም ከብድር ጥያቄ ሰነዱ ጋር አብሮ በክሬዲት ስዊዝ ባንክ መቅረቡን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በክሬዲት ስዊዝ መሪነት ሥር የተጣመሩ የተለያዩ የአውሮፓ ባንኮች ለአብነትም የስዌድሽ ኤክስፖርት ክሬዲት ጋራንቲ ቦርድ (EKN)፣ EKF፣ SERV፣ OEKB እና ሌሎችም በጋራ በመሆን 1.4 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለማቅረብ በተስማሙት መሠረት፣ የፕሮጀክቱ ባለቤት ያቀረበው የአካባቢና ማኅበራዊ ተፅዕኖ ጥናት በገለልተኛ ኩባንያ እንዲጠና አድርገዋል፡፡

በዚህም መሠረት ፕራይስ ወተርሐውስ ኩፐር (PWC) የተሰኘ አማካሪ ድርጅት በመቅጠር ጥናቱ እንዲገመገም አድርገዋል፡፡ በግምገማው ውጤት መሠረትም የስዊዝ ባንክና ሌሎች የአውሮፓ አገሮች በሚጠቀሙበት ‹‹ኢኳቶሪያል ፕሪንሲፕል›› መመዘኛ መሠረት፣ በአካባቢና ማኅበራዊ ተፅዕኖ ጥናቱ 17 ንዑስ መገምገሚያ ርዕሶች የ‹‹ኢኳቶሪያል ፕሪንሲፕል›› ደረጃዎችን እንደማያሟሉ ግምገማውን የሠራው ድርጅት ማረጋገጡን ምንጮቹ ገልጿል፡፡

በአጠቃላይ የአካባቢያዊና የማኅበራዊ ተፅዕኖ ጥናቱ በ37 ንዑስ ርዕሶች ተገምግሞ 17 ንዑስ ርዕሶች የአውሮፓ ደረጃን እንደማያሟሉ፣ የተቀሩት በከፊል ወይም ከሞላ ጐደል የሚያሟሉ መሆናቸውን ምንጮች አስረድተዋል፡፡

‹‹የፕሮጀክቱ ባለቤት የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ያቀረበው የአካባቢያዊና ማኅበራዊ ተፅዕኖ ጥናት በአሁኑ ወቅት ክሬዲት ስዊዝ ባንክ የሚከተለውን ‹‹ኢኳቶሪያል ፕሪንሲፕል›› ሆነ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ፐርፎርማንስ ስታንዳርድ አያሟላም፡፡ ይህ ማለት ግን የፕሮጀክቱ ዲዛይን ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ደረጃዎቹን የማያሟሉት 17 ንዑስ ርዕሶች ላይ ማስተካከያ ቢደረግ ደረጃውን አያሟሉም ማለት አይደለም፤›› የሚል ምክረ ሐሳብ ለባንኩ እንደቀረበለትና ባንኩም መረጃውን ለብድር ጠያቂው እንዳስተላለፈ ምንጮቹ አስታውቀዋል፡፡

የአውሮፓ ደረጃን እንደማያሟሉ ከተጠቀሱት 17 ንዑስ ርዕሶች መካከል ዜጎችን የሚያፈናቅልና የመሬት ይዞታቸውን የሚነካ፣ የብዝኃ ሕይወት ጥበቃ፣ የፕሮጀክቱ አካባቢ ነዋሪዎችን ባህል፣ አኗኗርና ጥቅም የማይጐዳ መሆኑ አለመረጋገጡ ይገኙበታል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደረጀ ተፈራ ከላይ የተባለው ነገር እንደሌለና ብድሩም እንደተገኘ ገልጸዋል፡፡ ለዚህ አባባላቸው ግን ዝርዝር መረጃ አልሰጡም፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት የአዋሽ – ወልዲያን የባቡር መንገድ ለመገንባት ያፒ መርከኒ የተሰኘ የቱርክ ኩባንያን በኢንጂነሪንግ ፕሮኪዩርመንት (ግዥ) እና ግንባታ (EPC) ስምምነት መሠረት ከሁለት ዓመት በፊት የቀጠረ ሲሆን፣ የቱርክ ኤክስፖርት ኢምፖርት ባንክም 300 ሚሊዮን ዶላር ለፕሮጀክቱ ለማበደር ተስማምቷል፡፡

ፕሮጀክቱ የሚጠይቀውን ገንዘብ ማግኘት ባለመቻሉ እስካሁን ፕሮጀክቱ መጀመር እንዳልተቻለ የሚገልጹት ምንጮች፣ የቱርክ መንግሥት 300 ሚሊዮን ዶላር ብድር ቢለቅ ፕሮጀክቱን አስጀምሮ ቀሪውን እየገነቡ መጠባበቅ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡

ይህ ከቱርክ መንግሥት የሚጠበቅ ገንዘብ እስካለፈው ሳምንት አለመለቀቁ ተረጋግጧል፡፡ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ አሜሪካ የነበሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ ከቱርኩ አቻቸው ጋር ተገናኝተው ብድሩ በፍጥነት እንዲለቀቅ ተነጋግረው መግባባታቸውን በትዊተር ማኅበራዊ ገጻቸው ላይ ይፋ አድርገዋል፡፡

አንዳንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ባለሙያ ግን፣ ፕሮጀክቱ በይፋ በዚህ ሳምንት ሊጀመር እንደሚችል ይናገራሉ፡፡

የፕሮጀክቱ ብድር ተፈቀዶ ስምምነት ሳይፈጸም ወደ ሥራ መግባት አስቸጋሪ እንደሆነ የሚገልጹ የሪፖርተር ምንጮች፣ ይህ ዓይነቱ አሠራር ኢትዮጵያ ውስጥ እየተለመደ መምጣቱን፣ ለአብነትም በመገንባት ላይ ያለው የአዲስ አበባ – ጂቡቲ አዲስ የባቡር መስመር ዝርጋታ ብድር ከቻይና ባንክ ሳይለቀቅ ፕሮጀክቱ መጀመሩን ይናገራሉ፡፡ ፕሮጀክቱ የተጀመረው የቻይና ባንክ ብድሩን አይከለክልም በሚል ግምት የኢትዮጵያ መንግሥት ከራሱ ካዝና የመጀመሪያ ክፍያ ለኮንትራክተሩ በመክፈል መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ ነገር ግን ኮትራክተሩና የኮንትራክተሩ የቀድሞ ተቆጣጣሪ የነበረው የስዊድን ኩባንያ ባለመግባባታቸው፣ የቻይናው ኤግዚም ባንክ ብድሩን መያዙንና የቻይና ተቆጣጣሪ ኩባንያ ካልተቀጠረ ብድሩን እንደማይለቅ ማስታወቁን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በዚህም መሠረት የስዊድኑ ኩባንያ ከተቆጣጣሪነቱ ተነስቶ ሌላ የቻይና ኩባንያ ተተክቶ ብድሩ መለቀቁን፣ ብድሩ ሙሉ በሙሉ ሳይገኝ ፕሮጀክቱ በመጀመሩ መንግሥትን ጫና ውስጥ ከቷል ሲሉ ምንጮች አስረድተዋል፡፡

በዚህም ምክንያት አንድ የቻይና ኮንትራክተርን ሌላ የቻይና ኩባንያ እየተቆጣጠረ የአዲስ አበባ – ጂቡቲ የባቡር መስመር እየተዘረጋ ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑም ብድሩ ሳይገኝ ፕሮጀክቱ በሚጀመርበት አግባብ ላይ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

Source- Ethiopianreporter


የአዜብ ዱላ በሰሎሞን አስመላሽ ላይ…

$
0
0

ከአርአያ ተስፋማሪያም

hqdefaultጋዜጠኛ ሰሎሞን አስመላሽ ለብዙዎች እንግዳ አይደለም። የ120 መዝናኛ አዘጋጅ ነበር። ከኢቲቪ ከወጣ በኋላ ሜጋ አመራ። (በ1989ዓ.ም ከሳምሶን ማሞ ጋር በታዋቂ አትሌት ላይ የሞከሩት የፔፕሲ ማስታወቂያ ማጭበርበር ድርጊት ነበር፤ ጉዳዩን ለጊዜው እንለፈው) የሜጋ ሃላፊዎች እግር ስር ወድቀው ከወጡ በኋላ ሰሎሞን አስመላሽ የራሱን ማስታወቂያ ድርጅት ከፍቶ መስራት ቀጠለ። በአደባባይ የገዢው ፓርቲ ደጋፊና አቀንቃኝ መሆኑን የሚናገረው ጋዜጠኛ ሰሎሞን ከአራት አመት በፊት በምሽት መዝናኛ ውስጥ መጠጥ እየተጐነጨ ነበር። በድንገት መብራት ድርግም ይላል።

ሰሎሞን ጮክ ብሎ « አዜብ መስፍን ያስገባቸው ጄኔሬተር ተቸበቸበ! ሆን ተብሎ ነው መብራት የሚጠፋው..የአዜብን ጄኔረተር ለመሸጥ!» እያለ ተናገረ። በሚገርም ፍጥነት ይህቺ ቃል አዜብ መስፍን ጆሮ ደርሳለች። አዜብ ወዲያው በቀጭን ትእዛዝ ወደ መዝናኛው ደህንነቶች አዘመቱ። በዛው ሰሞን ሰሎሞን በውድ ዋጋ እጅግ ዘመናዊ አውቶሞቢል ሸምቶ ነበር። በስፍራው የደረሱት ደህንነቶች የመኪናዋን መስተዋት በመሰባበርና ጐማዎቿን በማስተንፈስ ተልእኳቸውን ጀመሩ። ሰሎሞን አስመላሽ ከመዝናኛው ሲወጣ አንድም የሰውነት አካሉ ሳይቀር በዱላ ቀጥቅጠው መንገድ ዳር ዘርረውት ሄዱ።

አዜብ « እንዳትገድሉት ግን ሰባብራችሁ ጣሉት» በማለት አዘው ስለነበረ ያንን ደህንነቶቹ እንደፈፀሙ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቅ ከፍተኛ የደህንነት ምንጭ አጋልጦዋል።…በነገራችን ላይ መስከረም 1 ቀን 1995ዓ.ም ፒያሳ ትግራይ ሆቴል በገዢዎቹ ተቀነባብሮ የተፈፀመው የፈንጂ ጥቃት በአሰቃቂ ሁኔታ ከሞቱት 60 ንፁህ ሰዎች አንዱ የሰሎሞን አስመላሽ ታናሽ ወንድም ይገኝበታል። ይህ ዘግናኝ ድርጊት እንዴት እንደተፈፀመ ጋዜጠኛው ካወቀ በኋላ ሞቅ ሲለው ይናገር ነበር።..በ1990 ዓ.ም ሰሎሞን አስመላሽ እጅግ ውብ የሆነች ፍቅረኛውን ተነጥቋል። በአሜሪካ ትኖር የነበረችው ፍቅረኛውን አንድ ለባለሃብቱና ለገዢው ባለስልጣናት ቅርብ የሆነ ግልገል “ቱጃር” የግሉ አድርጓታል። .. ጋዜጠኛው አሁንም የገዢው ደጋፊ ነው።

– See more at: http://satenaw.com/amharic/?p=1923#sthash.BkvSoF7l.dpuf

ነገረ ህወሓት: ህወሓትና ‹‹ወያኔ›› ምንና ምን ናቸው? –ጌታቸው ሺፈራው (ጋዜጠኛ)

$
0
0

‹‹ህ.ወ.ሓ.ት›› የተሰኘው የፖለቲካ ቡድን ሙሉ ስሙ ሲዘረዘር ‹‹ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ›› መሆኑ ለማንም ግራ የሚያጋባ አይደለም፡፡ በተለይ በርሃ በነበረበት ጊዜ ከረዥም ስሙ ይልቅ ‹‹ወያኔ›› መጠሪያው ሆኖ አገልግሏል፡፡ መጀመሪያ አካባቢ ይህን ስም ህወሓት ከዚህ በፊት የነበረ ታሪክ ቀጣይና የትግራይ ህዝብ ታሪካዊ እንቅስቃሴ አስቀጣይ (ወራሽ) ለመምሰል ተጠቀመበት፡፡ ህወሓት ‹‹ወያኔ›› የተሰኘ ስሙን በመጀመሪያዎቹ ለጥቂት ጊዜያት በተለይ ውስጥ ለውስጥም ሆነ በቀጥታ ካስተዋወቀ በኋላ ይህን ስሙን ሌሎችም እንዲለምዱት አደረገ፡፡ ይህን ያደረገበት ምክንያቱ ደግሞ ስሙ በታሪካዊነቱም ሆነ ትርጉሙ የህወሓትን ሰብዕና የሚገነባ በመሆኑ ነው፡፡
tplf-rotten-apple-245x300
‹‹ወያኔ›› ማለት በትግርኛ አብዮት ወይንም አመጽ እንደ ማለት ነው፡፡ ህወሓት ይህን መልካም መጠሪያ የወሰደው ደግሞ በ1935 ዓ/ም አካባቢ ተነስቶ ከነበረው ‹‹ወያኔ›› ከተባለው የአርሶ አደሮች አመጽ የቀጠለ ታሪካዊና አልጋ ወራሽ ለመምሰል ነው፡፡ ሆኖም በ1930ዎቹ መጨረሻ ትግራይ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የአገራችን ክፍሎችም ተመሳሳይ የአርሶ አደሮች አመጽ ተቀስቅሶ እንደነበር ይታወቃል፡፡ የ‹‹ወያኔ›› አመጽ የፊውዳሉ ስርዓት ከነበረው ብልሹነት የመነጨና በኋላም ለተማሪዎች አብዮትም ጭምር እንደ እርሾ እንዳገለገለ ከታሪክ መረዳት ይቻላል፡፡ የወቅቱ አማጺያን ህዝብ ይቀሰቅሱበት ከነበረው መፈክር መካከል ቀዳሚው ‹‹ሰንደቃችን የኢትዮጵያ ነው›› የሚል ነበረበት፡፡ በአጠቃላይ እንቅስቃሴው በኢትዮጵያ አንድነትን መሰረት ያደረገ እንጂ ህወሓት ‹‹ወያኔ››ን በቅጽል ስምነት አንጠልጥሎ ይከተለው ከነበረው ‹‹ተገንጣይነት›› ፖሊሲ ጋር በእጅጉ የሚቃረን ነው፡፡ የመጀመሪያው እንቅስቃሴ ‹‹ወያኔ›› ወይንም አመጽ ከስርዓት እንጂ ከአገር ‹‹ነጻ›› መውጣት ወይንም መገንጠልን ጋር የተገናኘ አልነበረም፡፡

ህወሓት ከአርሶ አደሮቹ አመጽ ብቻ ሳይሆን በነ መንግስቱ ንዋይ ከተሞከረው የመንግስት ለውጥ ሙከራ በተጨማሪ ‹‹መሬት ለአራሹ›› የሚል መፈክርን አንግቦ ለተነሳው የተማሪዎች አብዮት እርሾ እንደነበር ከሚነገርለት የአርሶ አደሮች እንቅስቃሴ እጅጉን ተቃራኒ ነው፡፡ ህወሓት ‹‹እየሱስ አምላካችን ነው›› የሚል መፈክር ካነገቡት አርሶ አደሮች ይልቅ የወቅቱ የማርክሲዝም አንድ መርህ ከነበረው ስለ መሬት ለአራሹ፣ ስለ ዓለም ላብ አደሮች ትብብር ከሚያወራው የተማሪው አብዮት ቅርብ ነበር፡፡ ሆኖም ከአርሶ አደሮቹ ይልቅ ለተማሪው እንቅስቃሴ አንድ አካል ነበር የሚባለው ህወሓት ከመሬት ለአራሹ ይልቅ ‹‹ስለ ትግራይ ህዝብ›› መሬት እንደሚጨነቅ አስመሰለ፡፡ ስለ ዓለም ላብ አደሮች ትብብር ሲያወራ ከነበረው የ1960ው አብዮት ወርዶ ለአንድ ብሄር ተወላጆች ትብብር፣ መገንጠል…የመሳሰሉት ተገንጣይ ጉዳዮች ቅድሚያ ሲሰጥ ነው ከተማሪዎች አብዮትም ያፈነገጠው፡፡ ሁለተኛው ‹‹ወያኔ››ነት (አብዮት) ይህኔ ነው ያከተመው፡፡ ከዚህ በኋላ ህወሓት ‹‹ወያኔ›› የሚያሰኘውን ነገር ሁሉ አጥቷል፡፡ ምክንያቱም ከአርሶ አደሮችም ሆነ ከተማሪው አብዮት አፈንግጧልና ነው፡፡
ከተማሪዎች እንቅስቃሴ እንኳን ያፈነገጠው ህወሓት የቀዳማዊ ወያኔ ወራሽ ነኝ በሚል ዳግማዊ ‹‹ወያኔን›› በመጠሪያነት መጀመሪያ አካባቢ ተጠቀመበት፡፡ ህወሓት በደርግ ላይ ድል እያስመዘገበ ሲመጣ ‹‹ወያኔ›› በተለይ በወቅቱ ተቃዋሚዎች ዋነኛ መጠሪያው ሆነች፡፡ ስሙ ከመለመዱ የተነሳ እነ መንግስቱ ኃ/ማርያም ሳይቀሩ ተግባሩን ሲያወግዙ ከህወሓትና ከረዥም ዝርዝሩ ስሙ ይልቅ ‹‹በወያኔ››ነት መጥራቱን ተያያዙት፡፡ ይህ ለህወሓት መልካም ስም ነበር፡፡ እሱ ቢጀምረውም ትርጉምና ታሪካዊ ተያያዥነቱን ሳያጤኑ ያጋነኑለት የሚቃወሙትና የሚጠሉት አካላት ናቸው፡፡

የአርሶ አደሮች አመጽ በተቀሰቀሰበት ወቅት በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ተመሳሳይ አመጾች የነበሩ ቢሆንም ከህወሓት ጋር የተማሪው አብዮት አካል የነበሩት ወደ ትጥቅ ትግል ሲገቡ ‹‹ዳግማዊ፣ ሳልሳዊ…›› ብለው ስማቸውን አልወሰዱም፡፡ ወያኔ የአርሶ አደሮቹ አመጽ ኢትዮጵያዊ አላማ የነበረው ቢሆንም ልክ እንደ ህወሓት አሻፈረኝ ብለው ዱር የወጡትና ከእሱም የተሻለ አገራዊ አላማ እንደነበራቸው የሚነገርላቸውና ከተማሪዎች እንቅስቃሴ ያፈነገጡት እንኳን ‹‹ወያኔ›› ነን አላሉም፡፡ በእርግጥ ህወሓት የአርሶ አደሮቹን ቀደምት አመጽ ከራሱ ጋር በማዛመድ ‹‹ዳግማዊ››ነቱን ያወጀው ከመርህና አላማ አንጻር ሳይሆን ከአርሶ አደሮቹ ጋር ‹‹በብሄር›› ግንኙነት እንዳለው ለመግለጽ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህም በአብዛኛው መርህና አላማ ከተማሪዎች አብዮትም ሆነ ከአርሶ አደሮቹ አብዮት የራቀና ያፈነገጠ ያደርገዋል፡፡ አሁንም አብዛኛዎቹ የህወሓት/ኢህአዴግ ተቃዋሚዎች ‹‹ወያኔ›› የምትለዋን ስም አሉታዊ አድርገው በስፋት ይጠቀሙባታል፡፡ እኔ በበኩሌ ይህ ስም ለህወሓት ኢህአዴግ አይገባውም ባይ ነኝ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ህወሓት ራሱን ኢትዮጵያዊ አቋም ከነበራቸው አርሶ አደሮች የቀጠለ መሆኑን ለመግለጽ ‹‹ዳግማዊ ወያኔ›› ብሎ የሚጠራበት አላማም ሆነ ታሪካዊ ትስስር ስለሌለው ነው፡፡

በነገራችን ላይ በእንግሊዘኛው ‹‹Tigray People Liberation Front›› ከተባለው ስሙ ውስጥ ‹‹ወያኔ›› ለሚባለው እኩያ ትርጉም አይገኝለትም፡፡ በቀጥታ እንተርጉመው ከተባለ ‹‹የትግራይ ህዝቦች ነጻ አውጭ ግንባር›› ነው የሚሆነው፡፡ Tigray ትግራይ ነው፡፡ People ህዝብ የሚለውን ይወክላል፡፡ Liberation አርነት (ኃርነት) ነው፡፡ Front ደግሞ ግንባር እንጂ አብዮት ሊሆን አይችልም፡፡ ስሙን እንዲሁ ለክብር ሲባል አገናኘው እንጂ ተያያዥ ትርጉም የለውም፡፡ ቃል በቃል ሲተረጎም ‹‹Front››ን ‹‹ወያኔ እንዳሉት እንረዳለን፡፡ ወያኔ የተሰኘው የአርሶ አደሮች እንቅስቃሴ የራሱ የሆነ እንቅስቃሴ እንጂ ‹‹ግንባር›› ወይንም ‹‹Front›› የሚባል አልነበረም፡፡ ከህወሓት ውጭ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር (‹‹Tigray Liberation Front››) የሚባል ታጣቂ ቡድንም ነበር፡፡ ግን እንግሊዘኛ ስሙ ላይ ‹‹Front› የሚል ስላለው ብቻ ‹‹ወያኔ›› በሚል የሌሎችን ታሪክ ለመጋራት አልተንጠራራም፡፡

ምንም እንኳ በማርክሲሳዊ እይታ አብዮታዊ ባይሆንም ከህወሓት ይልቅ ኢዲዩ ራሱን ወያኔ ብሎ ቢጠራ ከህወሓት የተሻለ መሰረት ነበረው፡፡ ምክንያቱም አብዛኛዎቹ የኢዲዩ አባላት ከአማጺያኖቹ አርሶ አደሮች ጋር የሚያመሳስል የርዕዮተ ዓለማዊም ሆነ ሌሎች ትስስሮች ስለነበራቸው ነው፡፡ የተገንጣይ አላማም ሆነ በአገራቸው ላይ ጥላቻ አልነበራቸውም፡፡ ይህን ስንመለከት ህወሓት በበርካታ ምክንያቶች ‹‹ወያኔ›› የሚለው ስያሜ እንደማይገባው መገንዘብ ይቻላል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ‹‹ልማታዊ መንግስት››፣ ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ››፣ ‹‹ዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ››…..የሚባሉትን ስሞች ዝም ብሎ በሌሉበት የመለጠፍ ታሪኩ የሚጀምረው ‹‹ወያኔ››ን በመጠሪያነት ያለ አግባብ ከቀላቀለበት ጊዜ የጀመረ ይመስለኛል፡፡

ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ በኋላ ያነሳው ሁሉ በስፋት እንደሚጠላ ያውቀዋል፡፡ ይህን የማይገባውን የክብር ስምም ገና በርሃ እያለ አስተዋውቆ ዘወር በማለቱ በአብዛኛው አሉታዊ መስሏቸው ሌሎች ናቸው መጠሪያው ያደረጉት፡፡ በተለይ በተቃዋሚዎቹ ዘንድ የማይወደው መስሎ ሳይታያቸው አይቀርም፡፡ ስለሆነም አብዛኛዎቹ ተቃዋሚዎች ህወሓት/ኢህአዴግን ‹‹ወያኔ›› ብለው ሲጠሩት ግን ከሚገባው በላይ እንዳጋነኑለት፣ የማይገባውን ታሪክ እንዳወረሱት፣ አገር ወዳድና ቀናኢ አላማ እንዳለው አድርገው እየቆጠሩት መሆናቸውን መገንዘብ ይገባቸዋል፡፡ በተለይ ህወሓትን ጠበብ ብለው እየከሰሱ ቢሆን ህወሓትን ከትግራይ ህዝብ ጋር የማይነጣጠል፣ ለትግራይ ህዝብ የሚሰራ አድርገው የሚቆጥሩት ‹‹ወያኔ›› ብለው ሲጠሩ ህወሓትን ከሚከሱበት ጠባብነት አልወጡም ማለት ነው፡፡

‹‹ወያኔነት›› በገዥዎች ላይ እምብይ ባይነት ነው፡፡ የድሮዎቹ አርሶ አደሮች ይህን ስም የራሳቸው ያደረጉት በበዝባዡ ፊውዳል ስርዓት ላይ አምጸው ነው፡፡ አሁን ‹‹ወያኔ›› የሚባለው ህወሓት ዘመናዊ ፊውዳል ሆኗል፡፡ ራሳቸውን ‹‹ወያኔ›› ባይሉም የህወሓትን ዘመናዊ ብዝበዛ የሚቃወሙ እምብይ ባዮች አሉ፡፡ እነዚህ እምብይተኞች ህወሓት አሸባሪዎች ይላቸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ወያኔ የሚባል አካል መባል ካለበት ግን ያለ ምንም ጥርጥር ከበዝባዡና ከዘመናዊ ፊውዳሉ ከህወሓት ይልቅ ይህን አፋኝ ስርዓት በመቃወም ላይ ለሚገኙት ደፋሮች የሚመጥን ስም ይሆናል፡፡ ችግሩ ግን ተቃዋሚዎች ራሳቸው ለራሳቸው የሚገባውን ስም ለበዝባዥ አሳልፈው የሚሰጡ መሆናቸው ነው፡፡ ይህ ለህወሓት መልካም ነገር ነው፡፡

እኔ በበኩሌ ‹‹ወያኔ›› ብዬ ጠርቼው አላውቅም፡፡ አይገባውማ! ያለ ታሪኩ!? ያለ አላማው!?

Hiber Radio: በኢትዮጵያ ሁለት አሜሪካውያን ባልታወቁ ኃይሎች ጥቃት ደረሰባቸው፤ በቬጋስ የተከሰተው ቀላል የመሬት አደጋ ምንም ጉዳት አላደረሰም

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በ1340 ኤ.ኤም የአየር ሞገድ ወይም በድህረ ገጽ በቀጥታ በአይቱን www. KRLV1340AM.com ይደመጣል። በስልክ ለማዳመጥ ለሚቀናችሁ በቀጥታ በአዲስ ቁጥር 712 432 8451 ያለ ኮድ በቀላሉ ማዳመጥ ይቻላል። (9፡30 በዋሽንግተን ሰዓት ጀምሮ ) የቀድሞ ቁጥር 610-214-0200 አክሰስ ቁጥር 729369# ክፍት ነው። ህብር ሬዲዮ_የወቅታዊ መረጃ ምንጭ።
የህብር ሬዲዮ መስከረም 25 ቀን 2007 ፕሮግራም

ለእስልምና ዕምነት ተከታይ አድማጮቻችን እንኳን ለኢድ አልአድሀ በአል በሰላም አደረሳችሁ!

ሁለት አሜሪካዊያን በኢትዮጵያ ባልታወቁ ታጣቂዎች ጥቃት ደረሰባቸው

አሜሪካ ባለፈው ሰኞ በኢትዮጵያ ውያን ላይ የተኮሰውን ዲፕሎማት ከአገሯ ማባረሯን አረጋገጠች

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደራደሩት ሱዳኖች ድርድሩ ተቋርጦ ወደ ኬኒያ እንዲዛወር ጠየቁ

መኢአድ በጋምቤላ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት አስመልክቶ በነገው እለት ዓለም አቀፍ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል

የኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ቢሮ ጋዜጠኞቹ ለምሳ በወጡበት በፀጥታ ሀይሎች ታሸገ

በቬጋስ ዛሬ የተከሰተው ቀላል የመሬት መንቀጥቀጥ ምንም ጉዳት እንዳላደረሰ ተገለፀ

የዙምባቤዋ ቀዳማዊ ዕመቤት ባለቤቴን ከስልጣን ለማውረድ አሜሪካና ከፍተኛ ሹማምንቱ ያሴራሉ ሲሉ ወቀሱ

በኢትዮ ጵያውያን ላይ በአገር ውስጥና በውጭ ግፍ ሲፈፀም አንድም ቀን ድምፃቸውን አሰምተው የማያውቁ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደረገውን ጭፍጨፋ የሚደግፉ የስርዓቱ ደጋፊዎች ትላንትና ባንዲራ ጨርቅ ነው እያሉ እንዳላዋረዱ ዛሬ የባንዲራ ተቆርቋሪ መስለው በሰኞ ተቃውሞ ሳቢያ ተኩስ በከፈተው ዲፕሎማት የደረሰባቸውን ውርደት ለማካካስ ለተቃውሞ ሊወጡ ነው

እኛም ማክሰኞ የአፀፋ ተቃውሞ እናደርጋለን >>

አክቲቪስት መኮንን ጌታቸው ማክሰኞ ስለሚደረገው የአፀፋ ተቃውሞ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ

ኢቮላ በአሜሪካ ልዩ ዘገባ

የአረፋን በአልን አስመልክቶ በሳውዲ ጅዳ ከሚገኘው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ጋር ቆይታ

> ዶ/ር መረራ ጉዲና ለህብር ከሰጡት ቃለመጠይቅ ክፍል አንድ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

ማዕተቤን አልበጥስም

$
0
0

በአንድ ወቅት በጨካኝነቱ ተወዳዳሪ ያልነበረው የታላቋ ሩስያ መሪ የነበረው ስታሊን በአገዛዝ ዘመኑ የሩስያ ኦርቶዶቶዶክስን ለማጥፋት ያልወሰደው አረመኔአዊ ድርጊት አልነበረም ። ከእነዚህም መካከል የቤተክርስቲያኒቱን አማኞች በጥይት መግደሉ ጥይት ማባከን ነው ብሎ በማሰቡ ከፓትርያርኩ ጀምሮ እስከ አራስ ህፃናት ድረስ ያሉትን ኦርቶዶክሳውያን በግዙፍ መርከቦች እየጫነ ውቅያኖስ ውስጥ በመጨመር ለአሳነባሪዎች ቀለብ እስከማድረግ ደረሰ ። ይህን የመሰለው ግፍ ግን ኦርቶዶክሳውያኑን ከማጥፋት ይልቅ ይበልጥ ሃይማኖታቸውን እንዲያጠብቁ አደረጋቸው ። እንዲያውም በሩሲያ ታሪክ እንደዚያን ዘመን የኦርቶዶክሳውያን አማኞች ቁጥር በዝቶ የታየበት ዘመን እንደሌለ የታሪክ ፀሐፊዎች ይናገራሉ ።

የሁኔታውን አደገኛነት የተገነዘበው ስታሊን ፓርላማውን ሰበሰበና እንዲህ አለ ።” ጓዶች ይሄ አካሄዳችን አላማረኝም ከሃይማኖቱ ሰባኪዎች ይልቅ የእኛ ግድያ የሩስያ ኦርቶዶክስን እያለመለመ እና እያጠነከረ ይገኛል። እናም ግድያው ይቁም ። ምክንያቱም ከዚህ አይነቱ አካሄዳችን የተማርኩት ነገር ቢኖር ክርስቲያን እና ምስማር በመቱት ቁጥር እየጠበቀ መሄዱን” ነው ብሎ የሩሲያን ኦርቶዶክስ ማጥፋት ድክም ብሎት አቆመ ይባላል ።

ትናንት ከግሸን እንደተመለስኩ ለ 10 ቀናት ያህል የተለየሁትን የማኅበራዊ ድረገፆችን ለማየት ብከፍተው አንድ ደስ የማይል ዜና ብዙዎች ሲቀባበሉት ተመለከትኩ ። ብዙዎች የሚያወሩት በስሜት እንዳይሆን ብዬ ወደ አንድ ወዳጄ ጋር ብደውል ወሬ አለመሆኑን አረጋገጠልኝ ። እኔም ምንም ከሌሎች የተለየ ነገር ማለት ባልችልም የአቅሜን ታህል ድምፄን ላሰማ አልኩና ይኸው ብቅ አልኩኝ።

ክቡር ሚንስትሩ በሲቪል ሰርቪስ ስልጠና ላይ ግልፅ በሆነ አማርኛ ” የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ይሄን የኦርቶዶክሳውያን ማዕተብ መበጠሳችን አይቀርም ” ብለው መናገራቸውን ሰማን ። አንድን ሰው ወንጀለኛ አድርጎ ከባድ ፍርድ እንዲፈረድበት የሚያደርገው ደግሞ ምቹ ጊዜ ሰዓትና በተገቢው ሁኔታ ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ወንጀል መፈፀሙ ሲረጋገጥ መሆኑን የህግ ባለሙያዎች ይናገራሉ ። አንዳንድ ሰዎች የሰው ህይወት በእጃቸው ጠፍቶ 3 እና 4 ዓመት የሚፈረድባቸው እና ሌሎች ደግሞ በተመሳሳይ መንገድ የሰው ሕይወት አጥፍተው ከ ዕድሜ ልክ እስከ ሞት ፍርድ ድረስ የሚያደርስ ቅጣት የሚወሰንባቸው ከ3 እና የ4 ዓመት ፍርደኞቹ በተለየ መልኩ በስህተትና በአጋጣሚ ሳይሆን ሆን ብለው አቅደው ፣ቅድመ ዝግጅትም አድርገው ሆን ብለው የፈፀሙት ወንጀል በመሆኑ ነው ቅጣታቸውን ከባድ የሚያደርገው ።

እኝህ ክቡር ሚንስትር በዚህች ጥንታዊት ቤተክርስቲያን ላይ ደስ የማይሉ ንግግሮችን ቀን እየጠበቁ መናገራቸውን ከጀመሩ ቆየት ብለዋል ። እኝህ ሰው ዛሬም ሲናገሩ እግዚአብሔር በሰማያት ብዙዎቻችን በምድር እየሰማን ነው። ከሰመነው ሰዎች መካከልም፦

1. ቅዱስ ፓትርያርካችን ሰምተዋል ።
2. መላው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ሰምተዋል።
3. ካህናት እና ዲያቆናቱም ሰምተዋል።
4. መነኮሳቱና ባህታውያኑም ሰምተዋል።
5. የሊቃውንት ጉባኤ አባላትም ሰምተዋል።
6. የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት በሙሉ ሰምተወል።
7. ዘማሪዎቻችንም ለዚህ የሚሆን ዜማ ባይደርሱም ሰምተዋል።
8. ፀሐፍያን ነን ብለው በየአጋጣሚው መከራ የሚያሳዪን ፀሐፍትም ሰምተዋል።
9. ከሁሉም በላይ ከየመንፈሳዊ ኮሌጆቻችን ተመርቀው የወጡና የአውደምህረት ላይ የስቱዲዮና የሲዲ ላይ አንበሶቻችንም በደንብ ሰምተዋል ። ግን ሁሉም ይስሙ እንጂ ምንም ሊሉን አልፈቀዱም።

ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ክቡራን ሊቃነ ጳጳሳቱ ከጥቂቶች በቀር ብዙሃኑ በእርግና ማእረግ ላይ የሚገኙ ያውም መቃብራቸው የተማሰ ልጣቸው የተራሰ ቢሆንም ዝም ብለዋል ። አረ ተዉ ውኃ ሽቅብ አይፈስም ነው እኮ የሚባለው። እናንተ ዝም ስላላችሁ እኮ ነው ፓስተር ዳዊት ነኝ የሚል ፍንዳታ ወጠጤ ተነስቶ እንደፈለገ ቅድስት ቤተክርስቲያንን የሚሰድባትን ሰው ነው እኮ እንዲያው ሰው የላትም ተብሎ ከሚቀር ከማለት እነ መምህር ምህረተአብ የአቅማቸውን ያህል የሚፍጨረጨሩት ። ሌሎችም እንዲሁ በየአቅጣጫው እየተነሱ የፈሪ በትራቸውን ሲያወርዱባት ምነው ዝምታችሁ በዛ ።

ሰባኪዎቻችንም እንደሁ ከጥቂቶች በቀር ብዙሃኑ እኛን ኢትዮጵያን አትልቀቁ ዲቪም አትሙሉ እያሉን እነሱ ግን በቦሌም በባሌም ፣ በሚስትም በሲስተምም እልም እያሉ መኖርያቸውን ከኢትዮጵያ ውጪ ከማድረግ በቀር ፣ ንግድ ሚንስቴር በማያውቀው ነፃው አውደምህረት ላይ በየ ስቱድዮው በመቀረፅ ያልበላንን በማከክ ከሚያራግፉብን ሸቀጦች ሌላ እና ለእርድ እንደተዘጋጀ የሐረር ሰንጋ ራሳቸውን ከማደለብ በቀር ምንም ሲፈይዱ አይታዪም ።

እስቲ ጥሩልኝ ኢትዮጵያ ውስጥ የቀረ ኑሮውን በምእራብ ሀገራት ያላደረገ ሰባኪ ። ከ ምህረተአብ በቀር እንደው በቤተክርስቲያን ላይ የሚወረወሩ ቀስቶችን ለመመከት የሚፍጨረጨር ማን አለ ? ንገሩኛ እከሌ በሉኝ ። ወይኔ ዛሬ እንኳን ሰው ይጥፋ ? እነ አትናትዮስን እነ ቅዱስ ጊዮርጊስን የወለደችው ቅድስት ቤተክርስቲያን የወላድ መካን ሆና ትታይ።

እኔ የምለው ክቡር ሚንስትር ይሄ አሁን ግዜ እየጠብቅንለት ነው ብለው የነገሩን ማዕተብ ከኦርቶዶክሳውያን አንገት ላይ የመበጠሱ ነገር የምእራብ ኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ባለፈው ዓመት ከምእራብ የሀገራችን ክፍል መጥተው ለቅዱስ
ሲኖዶሱ እንደተናገሩት …… ” ፖሊሶች በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች በራፍ ላይ በመቆም ከኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች አንገት ላይ እየበጠሱ ነው ያሉትን አቤቱታ መነሻ በማድረግ በዚያ የታየው ማዕተብ የማስበጠስ ስራ ተሞክሮው አበረታች ሆኖ በመገኘቱ ነው ለዚህ አዋጅ መሰል ዛቻ ያበቃዎት ?

ሲቀጥል ደግሞ እርስዎ የሚከተሉት ሃይማኖት ምን ይሆን ?

እኔ ግን እላለሁ

1. ባለፈው ጊዜ ማኅበረ ቅዱሳንን የመጎነታተል ነገር ቢሞከር ከታሰበው በላይ ከማኅበሩ በተለያዪ ምክንያቶች የራቁትን ጨምሮ ሌሎች አዳዲስ አባላትን ወደ ማኅበሩ በማምጣት ማኅበሩን በሰው ኃይልእንዲጠናከር አድርጎታል።

2. በሻሻ የሚባል ቦታ በሀገራችን መኖሩን የሚያውቅ ከአካባቢው ሰው በቀር የሚያውቅ ብዙ ሰው አልነበረም ። ነገር ግን ጥቂት ብዙኃኑን የእስልምና እምነት ተከታዮች የማይወክሉ አሸባሪዎች ማዕተባችንን አንበጥስም ባሉ የተዋህዶ ልጆች ላይ በፈፀሙት ግድያ ምክንያት በሻሻ በዓለም ላይ ታወቀች። ዛሬ በሻሻ ልክ እንደ አክሱም ፅዮን ፣ ግሸን ማርያም ፣ ቅዱስ ላሊበላ ፣ ቁልቢ ገብርኤል ከመላው ዓለም በሚመጡ ምእመናን ይጨናነቃል ። በአክራሪዎቹ የወደመችዋ ደሳሳዋ የበሻሻ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያንም ዛሬ በሚገርም ካቴድራል ተተክቷል ። ለዚህ እውቅና ደግሞ ሀገረ ስብከቱ ምንም ያደረገው አስተዋፅኦ የለም ። የሰማዕታቱ መሰየፍ እንጂ ።
mahtebe
ይገርምዎታል ክቡር ሚኒስትር የበሻሻ ጉዳይ መች በዚህ ብቻ ያበቃል መሰልዎ ። አሁን መላውን ዓለም እያስደመመ የሚገኘው የወጣቶች የጥምቀት በዓል አከባበርን የወለደው እኮ የበሻሻ ሰማእታት ደም ነው። በዚህ ጉዳይ የአንድም ሰባኪ እጅ የለበትም ። ከግሪሳዎቹ የተሃድሶ ርዝርራዦች መካከል አንዱ ግሪሳ ብቻ ነው የእኛ የአገልግሎት ነው ወጣቱን እንዲህ እንዲነሳሳ ያደረገው ሲል የተሰማው። ይህ ግን ሀሰት ነው ግሪሳዎቹ ኪሎና የባንክ አካውንታቸውን ከመጨመርና ከማብዛት በቀር አንድም ምእመን ወደ ቤተክርስቲያን ጉያ አልጨመሩም ።

አሁን ደግሞ ምን እየሆነ መሰልዎት እርስዎ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ማዕተብ ማስበጠሳችን እንደሁ አይቀር አሉ ከተባለ ወዲህ ይገርምዎታል የኦርቶዶክሳውያኑን አንገት ቢመለከቱ ቀድሞ የሀብት መግለጫ የነበሩትን የወርቅና የብር ሐብሎች በሚያምሩና በወፋፍራም የማዕተብ ክሮች ተተክተው እየታዩ ነው ። የብዙኀኑ የፌስ ቡክ ፕሮፋይል ፒክቸሮችም በማዕተብ ክሮች እየተለወጡ ነው ። የማዕተብ ክር ነጋዴዎችም ገበያ ድርት ብሏል። ምነው ደግሞ ቅዳሴ ማስቀደስ ፣ ንስሀ መግባት ፣ ስጋወደሙ መቀበል ፣ ፆም መፆም የሚከለክል በመጣና ተአምር ባየን ። ከዘመኑ ሰባክያን ይልቅ ምእመናን ወደ ቅድስት ቤተክርስትያን ለመመለስ እግዚአብሔር ባወቀ በአንድም በሌላም መንገድ የአህዛብና የመናፍቃን መነሳሳት ሳይሻል አይቀርም ። እንደውም የዘመኑን ግሪሳ ሰባክያን እና ዘማርያን ልብ ብላችሁ አንገታቸውን ብታዩት ማዕተብ የለውም።

በመጨረሻም ክቡር ሚንስትር እኔ ማዕተቤን በአንገቴ የማስረው ለጌጥ ሳይሆን ጌታ በማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ 10 ፣ 32 – 33 ላይ የተናገረውን አምላካዊ መመርያ መሰረት በማድረግ ነው። ” ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ ይላል። ይህ ማለት በአፌ ማንነቴን መግለፅ የማልችል ብሆንም እንኳን ማዕተቤን በአንገቴ ላይ ማሰሬ ብቻውን የክርስቶስ መሆኔን እርርሪሪ እያለ በመጮህ ይመሰክርልኛል ።

ግን ቆይ የማዕተብ ክር በአንገታቸው ላይ ያለውን እናቆይ እና ሌሎቹን በትግራይ ፣ በአማራ ፣ በኦሮምያ ፣ በደቡብና በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ያሉትን በግንባራቸዉ ፣ በአንገታቸው ፣ በክንዳቸው ላይ የተነቀሱ ኦርቶዶክሳውያን ዕጣ ፈንታስ እንዴት ሊሆን ነው ? ለዛሬ አበቃሁ ።

ዘመድኩን በቀለ ነኝ
ከግሸን ደብረ ከርቤ መልስ
መስከረም 26/ 1 /2007 ዓም
አዲስ አበባ – ኢትዮጵያ

ከአቶ ገብሩ አስራት ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

$
0
0

የትግራይ አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ገብሩ አስራት “ሉአላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ” በሚል ርእስ ሰፋፊ ነጥቦችን የዳሰሰና ስህተቶች ነበሩ ያልዋቸውንም ያካተተ አዲስ መጽህፍ መጻፋቸው ይታወቃል። መጽሀፉን መሰረት በማደርግ አቶ ገብሩን አነጋግረናል።

VOA News

Gebru Asrat

 

ፖሊሶች ዩኒፎርም ለብሰው ቤተክርስቲያን ሲሳለሙ ከተገኙ ይገመገማሉ፤ ማዕተባቸው ከዩኒፎርማቸው በላይ እንዲታይ አይፈቀድም

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባና በአካባቢዋ የሚገኙ ፖሊሶች የፖሊስ ዩኒፎርም ለብሰው ቤተክርስቲያን ሲሳለሙ ከተገኙ እንደሚገመገሙና እንደሚቀጡ፤ ማዕተባቸውም ከዩኒፎርማቸው በላይ እንዳይታይ እንደሚገደዱ ታወቀ። በሌላ በኩል ዛሬ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዩኒቨርሲቲዎች ሃይማኖታዊ ስነስርአትና አለባበስን በሚመለከት ያወጡትን የስነምግባር ደንብ በመቃወም የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር በሽብር ድርጊት ውስጥ የተሳተፉ 13 ግለሰቦች የጥፋተኝነት ፍርድ ተላለፈባቸው ሲሉ ዘገቡ።
police1
በአዲስ አበባ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ ያሉ የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች እንደገለጹት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም “የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ይሄን የኦርቶዶክሳውያን ማዕተብ መበጠሳችን አይቀርም” በሚል መናገራቸውን ተከትሎ ዜናው እጅጉን መናገገሪያ ቢሆንም ፖሊሶች የደንብ ልብስ ለብሰው ቤተክርስቲያን መሳለም ከተከለከሉ ቆይተዋል። እንደምንጮቹ ገለጻ የደንብ ልብስ ለብሰው ቤተክርስቲያን በሚሳለሙ ፖሊሶች ላይ ከግምገማ አንስቶ እስከ ሥራ መባረር የሚደርስ ቅጣት የሚጣልባቸው ሲሆን የደንብ ልብስ ሲለብሱም የሚያደርጉት መስቀል ከዩኒፎርማቸው በላይ እንዳይታይ እንደሚከለከሉ እነዚሁ ምንጮች ጠቅሰው በዚህ የተነሳ ሥራቸውን ያጡ በርካታ መሆናቸውን አስታውቀውናል።

ማህተባችን ከሚወልቅ የፖሊስ ዩኒፎርማችን ይውለቅ በሚል በርካታ ፖሊሶች ሥራቸውን ለመልቀቅ እንደተገደዱ የሚገልጹት እነዚሁ የዘ-ሐበሻ ምንጮች የመንግስት አካሄድ ምን እንደሆነ የራሱን አባላት ግራ እንዳጋባ ይገልጻሉ።

የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሃይማኖታዊ ስነስርአትና አለባበስን በሚመለከት የስነምግባር ደንብ ማውጣታቸውን ተከትሎ ማንኛውም የቢሮ ሰራተኛ በቢሮው ውስጥ የቁርአን ጥቅስ፣ ሃይማኖታዊ ምስሎችን እንዳይለጥፍ የሚከለከል ሲሆን በተለይ ዩኒቨርሲቲዎች በተማሪዎች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል። በዚህም መሠረት ዛሬ እንኳን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት እስማኤል ኑር ሁሴን፣ ፈትያ መሃመድ፣ ኑርዬ ቃሲም፣ ያሲን ፈያሞ፣ መሃመድ አሚን፣ መሃመድ ሰይድ፣ የሱፍ ከድር፣ ጣሂር መሃመድ፣ መሃመድ ሰይድ፣ ሰይድ ኢብራሂም፣ አብደላ መሃመድ፣ አብዲ መሃመድ እና ኢብራሂም የሱፍ ኢብራሂም የተባሉ ኢትዮጵያውያን “የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ሃይማኖታዊ ስነስርአትና አለባበስን በሚመለከት ያወጡትን የስነምግባር ደንብ በመቃወም የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር በሽብር ድርጊት ፈጽመዋል” በሚል ውሃ በማይዝ ክስ ጥፋተኛ መባላቸውን ዘግበዋል።

እንደመንግስታዊ ሚዲያዎች ዘገባ “ተከሳሾቹ በ2005 ዓ.ም በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ሃይማኖታዊ አለባበስን በሚመለከት የወጣውን ደንብ ተከትሎ በጥቂት ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች የተጀመረው አመጽና አድማ በተናጠል ከሚሆን ሃገር አቀፍ መሆን አለበት በማለት በየዩኒቨርስቲዎች በስልክ፣ በማህበራዊ ድረ ገጾችና በአካል በመንቀሳቀስ ቀስቅሰዋል።” የሚል ክስ ቢቀርብባቸውም ታዛቢዎች ግን ተከሳሾቹ ሃይማኖታቸው የሚያዛቸውን ነው የተከተሉት በሚል የተላለፈባቸውን ውሳኔ ፖለቲካዊ ሲል ይቃወሙታል።

የኢትዮጵያ መንግስት “ሃይማኖታዊ ስነስርአትና አለባበስን በሚመለከት ያወጣው የስነምግባር ደንብ” ሙስሊሙንም ሆነ ክርስቲያኑን እጅግ እያስቆጣ ሲሆን በተለይ ክርስቲያኑን ወገን መስቀል እናስወልቃለን ብለው ዶ/ር ሽፈራው ከተናገሩ በኋላ በሶሻል ሚዲያዎች ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ሲደርስባቸው ወዲያው “አላልኩም” ብለው ለማስተባበልና ነገሩን ለማብረድ ቢጥሩም ጉዳዩ የተሳካ አይመስልም። ልክ የክርስቲያኑን መስቀል እናስወልቃለን አላልንም በሚል ለማስተባበል የተጠቀሙትን ቃል ለሙስሊሙም ሂጃብ ጥያቄ ምላሽ መስጠት ይኖርባቸዋል በሚል ዶ/ር ሽፈራው በሶሻል ሚዲያዎች ከፍተኛ ውተወታ እየደረሰባቸው ነው። በተለይም ዶ/ር ሽፈራው መንግስት በሃይማኖት አለባበስና ስነ ስር ዓት ውስጥ እንደማይገባ በሚዲያዎቻቸው በዋሹ በሰዓታት ውስጥ የመንግስት ሚዲያዎች 13 ሙስሊሞች በተመሳሳይ ክስ ጥፋተኛ ተባሉ ተብሎ መፈረዱ አነጋጋሪ ሆኗል።

የግንቦት 7 ወታደራዊ ጉዳዮች ቡድን የሕወሓት/ኢሕአዴግ ጀነራል መኮንኖችን ብቃት የገመገመበት ሰነድ ወጣ

$
0
0

nega berehanu

የሕወሓት/ኢህአዴግ መንግስት በ23 ዓመት ው ያፈራቸው ጄኔራል መኮንኖች  ከወታደራዊ አመራር ይንስ ትምህርት እና ስልጠና አን

ሲመዘኑ

 

በግንቦት 7  የወታደራዊ ጉዳዮች ቡድን

የተዘጋጀ ጥናታዊ ፅሁፍ

ክፍል 1

መስከረም 2007 ዓ..

የርዕስ ማውጫ

መግቢያ. 2

1…… የወታደርዊ አመራር ምንነትና ዋና ዋና የአመራር እርከኖች፤. 3

2…… የወታደራዊ አመራር የስልጠና እርከኖችና ወደ ወታደራዊ የትምህርት አካዳሚዎች መግቢያ መስፈርቶች.. 3

2.1. ወታደራዊ አካዳሚ፡ 4

2.2. ሰታፍ ኮሌጅ.. 4

2.3. የአዛዥነት እና የመምሪያ መኮንንነት አካዳሚ… 5

2.4 የጦር ኋይሎች ዋር ኮሌጅ(Armed Forces War College) 6

3…… የመኮንኖች የማዕረግ ዕድገት ሂደት.. 7

4…… የጄነራል መኮንንነት የማዕረግ ዕድገት.. 8

5…… የቀድሞው የሀገር መከላከያ ሠራዊት አመራሮች የሥልጠና ሂደት፤. 10

6…… የአሁኑ  የሀገር መከላከያ መኮንኖች ከወታደራዊ አመራር ሳይንስና ጥበብ አንፃር. 11

7…… ማጠቃለያ. 13

8…… አባሪ ሰነድ- ፩ (Annex-1) 15

 

የሕወሓት/ኢህአዴግ መንግስት በ23 ዓመት ጉዞው  ያፈራቸው ጄኔራል መኮንኖች

ከወታደራዊ አመራር ሳይንስ ትምህርት እና ስልጠና አንፃር ሲመዘኑ

 

መግቢያ

የኢትዮጵያ ሠራዊት በዘመናዊ መልክ ከተቋቋመበት ከ1927 ጀምሮ  እስክ 1983 ዓ/ም ድረስ ጊዜው በሚጠይቀው ወታደራዊ ሳይንስ የተማሩ፣  ዘመናዊ ክህሎትንና  ሥንምግባርን የተላበሱ እና  በተግባር የተፈተነ ጀግና  የምድር ጦር፣ የባህር ኃይልና የአየር ሃይል ሠራዊትና መሪዎችን  ለማፍራት የቻለ ነበር::  በሂደቱም ሰራዊቱን  ፈታኝ በሆኑ የተለያዬ አውደ ፍልሚያዎች መርተው ለድል ያበቁ ከፍተኛ ወታደራዊ ምሁራንና መኮንኖችን አፍርቶ ማለፉ የሚታወስ ነው::  የማእረግ አሰጣጡም እንዳሁኑ ዘርን መሰረት በማድረግ ሳይሆን የትምህርት ዝግጅትን፣ ወታደራዊ ዲስፕሊንና ሥነምግባርን እንዲሁም በእየእርከኑ ያሳየው ብቃትና ተገቢውን የመቆያ ጊዜ መፈፀሙ ተረጋግጦ፤ ይህንን እንዲያስፈፅም በተዋቀረ ገለልተኛ አካል አቅራቢነት በሀገሪቱ መሪዎች ሹመት ሲሰጥ ኖሯል።
Samora Yenus
ቀደም ሲል በተገለፀው የማዕረግ እድገት አሰጣጥ ሂደት መሠረት በአጠቃላይ ከ1927 እስክ 1983 ሀገሪቱ 293 ጄኔራሎችን አፍርታ ነበር። በሌላ መልኩ ወያኔ የመንግሥት ሥልጣን ከወሰደበት ከ1983 ጀምሮ ዘርንና ታማኝነትን በቻ መሰረት በማደረግ ለ130  የቀድሞ ሽምቅ ተዋጊ መሪዎቹ ከብርጋዲየር እስከ ሙሉ ጄኔራልነት ማዕረግ አድሎአቸዋል። ከትምህርት ዝግጅት አንፃር 97 በመቶ (126ቱ) የሚሆኑት መደበኛ የወታደራዊ ሳይንስ እውቀትና ከህሎት የሌላቸው ሲሆን ቀሪዎቹ 3 በመቶ የሚሆኑት ተገቢውን የወታደራዊ ሳይንስ የተማሩና በቂ ሙያዊ ክህሎትን ያዳበሩ አራት የቀድሞ ጦር አባላት ብቻ ነበሩ (አሁን ሦስቱ በጡረታ ሲገለሉ አንዱ በፖለቲካ ጉዳይ የተባረሩ ናቸው)። በአጠቃላይ ከነዚህ 130 ጄነራሎች ውስጥ 67ቱ የሆኑ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የሕወሓት አባላት ናቸው።

 

የዚህ ፅሁፍ አጠቃላይ ዓላማ ባለፉት 23 ዓመታት የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ያፈራቸውን ጄኔራል መኮንኖች ከወታደራዊ ሳይንስና ሙያዊ ክህሎት አንፃር መፈተሽና መገምገም ነው። በዚህም መሰረት ይህን መግቢያ (Introduction) ጨምሮ

1ኛ፡ የወታደራዊ አመራር ምንነት እና ዋና ዋና የጦር  አመራር እርከኖች፣

2ኛ፡ የወታደራዊ አመራር የስልጠና እርከኖችና ወደ ወታደራዊ የትምህርት አካዳሚዎች የመግቢያ መስፈርቶች፣

3ኛ፡ የመኮንኖች የማዕረግ እድገት፣

4ኛ፡ የጄኔራል መኮንኖች የማዕረግ እድገት፣

5ኛ፡ የቀድሞው የሀገር መከላከያ ሠራዊት አመራሮች ትምህርትና የሥልጠና ሂደት፣

6ኛ፡ አሁን ያለው የጦር ሃይል መኮንኖች የአመራር ሥልጠናና ብቃት፣

7ኛ፡ ማጠቃለያ ሲሆኑ ከዚህ እንደሚከተለው በቅደም ተከተል ይቀርባሉ።

 

1.    የወታደራዊ አመራር ምንነትና ዋና ዋና የአመራር እርከኖች

 

ወታደራዊ አመራር በተፈጥሮው የሳይንስንና የጥበብን (both Science and Art) ዘርፍ አጣምሮ የያዘና የተከበረ የሙያ መስክ ነው። ይህም በመሆኑ ማንኛውም የጦር ኃይል አባል በአመራር ቦታ ላይ ከመቀመጡ በፊት ዘመኑ የሚጠይቀውን ለየሥልጣን እርከኑ ተገቢ የሆነውን ወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ በመማርና እና ስልጠና በመውሰድ (Military Education and Training) በአጥጋቢ ሁኔታ ማጠናቀቅ ይጠበቅበታል።

 

የወታደራዊ አመራር (Military Leadership) ትምህርትና ሙያዊ ስልጠናውም በወታደራዊ የአመራር ንድፈ ሀሳብ ፣ ስትራቴጅና ታክቲክ ትምህርትና የተግባር  ሥልጠናን የሚያካትት ሆኖ መደራጀት ይኖርበታል።

meles and his millteryበጦር ሀይሎች ውስጥ አመራር የሚሰጡ የአመራር አካላት በሁለት ዋና ዋና ደረጃዎች ይከፈላሉ:: እነሱም:-

1.1.   የበታች ሹም (Non Commissioned Officer/NCO)

1.2.  መኮንኖች ናቸው (Commissioned Officers) ናቸው::

የበታች ሹም (Non Commissioned Officer/NCO)፦ የሚባሉት ሰራዊቱን በቅርብ የሚቆጣጠሩ፣ የሚያደራጁ፣ የሚያሰለጥኑ፣ የሚመሩትን ሀይል ለውጊያ የሚያዘጋጁ ከፍተኛ ሀላፊነት ያለባቸው የሰራዊቱ የጀርባ አጥንት ሆነው የሚያገለግሉ መሪዎች ናቸው:: በሰራዊቱ ውስጥ በግንባር መስመር ከበላይ አካል የሚሰጣቸውን ትእዛዝ ተቀብለው በተዋረዱ የሚያዙ የሚያዋጉ እና በየትኛውም የሰራዊቱ ጠቅላይ መምሪያ ውስጥ የስታፍ ስራዎችን በኃላፊነት የሚሰሩ ናቸው:: የአመራር ብቃታቸውንም ለማጎልበትም የወታደራዊ የአመራር ስልጠናም ይወስዳሉ:: በአጠቃላይ የበታች ሹሞች በተዋጊው ሰራዊትና በአመራር መኮንኖች መካከል እንደ ድልድይ ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው::

 

መኮንን (Commissioned Officer/CO)የሚባለው የወታደራዊ አመራር ጥበብን እና የወታደራዊ ስልት ስልጠናን ወስዶ በምድር ጦር፣ በአየር ሀይል (Pilot Officer) በባህር ኃይል (Ensign) በምክትል መቶ አለቃነት ማዕረግ የተመረቀ(ች) ወይም ከዚያ በላይ እስከ ከፍተኛ ፊልድ ማርሻል ማዕረግ የደረሰ ሁሉ መኮንን ይባላል:: ስልጠና ያልወሰደ ግን መኮንን አይባልም፡፡ አንድ መኮንን በህግ የተሰጠውን ማዕረግና ሀላፊነት ከተቀበለ በኋላ በተመደበበት የጦር ክፍል የሚመራቸውን ክፍሎች ወይም ኃይሎች  በትዕዛዝ፣ በማነቃቃት እና በማግባባት ግዳጃቸውን እንዲፈጽሙ ተጽዕኖ የማድረግ ሀላፊነት አለበት::

 

2.   የወታደራዊ አመራር የስልጠና እርከኖችና ወደ ወታደራዊ የትምህርት አካዳሚዎች መግቢያ መስፈርቶች

 

ማንኛውም የሠራዊቱ አባል መኮንን ለመሆን ከዚህ እንደሚከተለው በተዘረዘሩት መሠረታዊ  የመኮንኖች የአመራር ሳይንስና ጥበብ ሥልጠና ተቋማትና እርከኖች ውስጥ በመግባት ተገቢውን እውቀትና ክህሎት በማዳበር የሚሰጠውን የተግባርና የንድፈ ኃሳብ መመዘኛ በጥሩ ሁኔታ ማለፍና መመረቅ ይኖርበታል።የወታደራዊ አመራር የስልጠና እርከኖችም የሚከተሉት ናቸው፦

2.1.   የእጩ መኮንኖች መሰረታዊ የአመራር ስልጠና

2.2.  የስታፍ ኮሌጅ

2.3.  የአዛዥነትና የመምሪያ መኮንንነት

2.4. የጦር ኮሌጅ ናቸው::

2.1. ወታደራዊ አካዳሚ፡

ይህ አካዳሚ የዕጩ መኮንኖች ማሰልጠኛ ሲሆን ተቋሙ እንደ የሀገሩ እና አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ በጦር ኃይሎች ውስጥ እጩ መኮንኖችን መልምሎ ወታደራዊ የአመራር ጥበብና ሳይንስ በማስተማር ሠራዊቱን ለመምራት እና ለማገልገል የሚያዘጋጅና አጥጋቢ ውጤት ያመጡትን  አስመርቆ ወደ ተለያዩ የሠራዊቱ ክፍሎች እንዲሰማሩ የሚያስችል ተቋም ነው፡፡ ወደ አካዳሚው የእጩ መኮንነት ኮርስ መግባት የሚቻለው ከዚህ የሚከተሉት መስፈርቶች ተሟልተው ሲገኝ ብቻ ነው፡፡

ሀ. እድሜያቸው 17 እስክ 23 ዓመት የሆነ (የሆነች)፣

ለ. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን በሚገባ ያጠናቀቁ ሆነው በትምህርት ቤት ቆይታቸው ወቅት ከክፍል ወደ ክፍል በሚሸጋገሩበት ጊዜ በክፍል ውጤት ደረጃቸው ከ1ኛ እስከ 5ኛ የወጡ፣

ሐ. ከፍተኛ የትምህርት ተቋም/ኮሌጅ በዲፕሎማ በጥሩ ሁኔታ የተመረቁ፣

መ. ከዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ወይም የሁለተኛ ዓመት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ፣

ሠ. ከሰራዊቱ ውስጥ ከበታች ሹማምንት ውሰጥ ፲ አለቃ እና ከዛ በላይ ሆነው በአካዳሚ እውቀታቸውና ወታደራዊ አመራር ብቃታቸው የተረጋገጠላቸው፡;

ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች አሟልተው የተመለመሉ እጩ መኮንኖችም በአካዳሚው ውስጥ ከሦስት እስከ አራት ዓመት ለሚሆን ጊዜ  የአካዳሚክ፣ የወታደራዊ ስልቶች፣ መሰረታዊ የአመራር ሳይንስና ጥበብ፣ የአካል ብቃት፣ የሞራል እና የስነ ምግባር ትምህርቶችና የተግባር ሥልጠናዎችን በመማር የብቃት መመዘኛ ፈተናዎችን በአጥጋቢ ሁኔታ ሲያሟሉ እንዲመረቁ ይደረጋሉ፡፡ የብቃት ደረጃ የሚለካባቸው መስፈርቶችም፦ የአካዳሚ ብቃት 55% ፤ የወታደራዊ ብቃት 30% እና የአካል ጥንካሬና የአትሌቲክስ ብቃት 15% ይይዛሉ፡፡ ኮርሱን ሲጨርሱና በምዘናው አጥጋቢ ውጤት ሲያመጡ በመጀመሪ ደረጃ የሳይንስ (Bachelor of Science / B.Sc) ዲግሪና በምክትል መቶ አለቃነት ማዕረግ  ይመረቃሉ፡፡ በአጠቃላይ አካዳሚው ተመራቂ መኮንኖችን በቆይታቸው ወቅት በሠራዊቱ ውስጥ የአንድ የመቶ ጦር (ኃይል) ለማዘዝ የሚያስችላቸውን  ወታደራዊ የአመራር ጥበብ ትምህርት እና የአካዳሚክስ እውቀት በሚገባ ታጥቀው እንዲወጡና በብቃት እንዲያገለግላሉ ያስችላቸዋል፡፡

2.2. ሰታፍ ኮሌጅ

 

ስታፍ ኮሌጅ ማለት የመካከለኛ መኮንኖች የአመራር ሳይንስና ጥበብ የሚማሩበት ተቋም ነው፡፡ በዚህ ኮሌጅ ውስጥ የሚሰጠው ትምህርት የወታደራዊ አመራር ትምህርት፣ የአስተዳደር እና የስታፍ መምሪያ መኮንንነት ተግባር እና ሀላፊነት፣ የወታደራዊ ሥነምግባር፣ የወታደራዊ ሙያ ፖሊሲ እና የአካል ብቃት ትምህርቶች ይሰጣሉ፡፡ በኮሌጁም ውስጥ በሁለት ደረጃ የተከፈሉ ሥልጠናዎች ማለትም ጁኒየር እና ሲኒየር ኮርሶች ይሰጣሉ። ወደ እዚህ ኮሌጁ ለመግባት የግድ ማሟላት የሚገባቸው መሰፈርቶች በሲኒየር የሻምበልነት ወይም በሻለቃነት ማዕረግ ሰራዊቱ ውስጥ ግዳጅን መወጣትና  ማገልገል ናቸው፡፡

ሀ. የጁኒየር ኮርስ፡ ይህ ኮርስ ሲኒየር የሆኑና የሻምበል ማዕረግ ያላቸው መኮንኖች ገብተው የሚማሩበት ፕሮግራም ነው። የሚሰጠውም የኮርስ ይዘት የወታደራዊ አመራር እና የስታፍ መኮንንነት ተግባራትን፣ የወታደራዊ ሥልቶችን እና የአካል ብቃት ሥልጠናን ያካተተ ነው፡፡ ኮርሱም የሚፈጀው ጊዜ ሃያ ሳምንት ሲሆን ኮርሱንም ሲጨርሱ የሻምበል አዛዥ ወይም በሻለቃ መምሪያ ውስጥ በስታፍ መኮንንነት የኃላፊነት ቦታ ይሰራሉ፡፡

ለ. የሲኒየር ኮርስ፡ ይህ ኮርስ ጁኒየር የሆኑ የሻለቃ ማዕረግ ያላቸው መኮንኖች የሚሳተፉበት ኮርስ ነው፡፡ ትምህርትና የሥልጠናውም ይዘት ወታደራዊ የአመራር ሳይንስና ጥበብ፣ የወታደራዊ ሥልጠናዎች፣ የአስተዳደር እና የሎጂስቲክ ትምህርቶች፣ የስታፍ መኮንንነት ተግባር እና ኋላፊነት እና የአካል ብቃት ሥልጠናዎችን ያካትታል፡፡ የኮርሱም የቆይታ ጊዜ አንድ ዓመት ነው፡፡

መኮንኖቹ ኮርሱን ሲጨርሱ የሻለቃ አዛዥ ወይም በብርጌድ መምሪያ ውስጥ የስታፍ መኮንን ሆነው ያገለግላሉ፡፡ በአጠቃላይ የስታፍ ኮሌጅ ሥልጠና የጨረሱ መኮንኖች የሚሰጣቸው የትምህርት ማስረጃ  ዲፕሎማ ነው፡፡

2.3. የአዛዥነት እና የመምሪያ መኮንንነት አካዳሚ

 

ይህ አካዳሚ ሲኒየር ሻለቃዎች እና ሌ/ኮሌኔሎች በመቀበል ለከፍተኛ አመራር ሰጭነት  የሚያስተምር ተቋም ነው፡፡ ወደ አካዳሚው የመግቢያ መስፈርቱም  የጁኒየር እና የሲኒየር ስታፍ ኮሌጅ ኮርሱን ካጠናቀቁ መኮንኖች ውስጥ በአመራር ስጭነታቸውና በስነምግባራቸው የሚመረጡ ይሆናል፡፡ ኮርሱም በዋነኝነት  በወታደራዊ የአመራር ጥበብ፣ ፍልስፍና፣ በወታደራዊ ታሪክ፣ በወታደራዊ ሥልቶች፣ እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት እና የአካል ብቃት ትምህርቶች ያተኮረ ሆኖ ከ10-12 ወራት የሚሆን ጊዜን ይፈጃል፡፡ ኮርሱን አጠናቅቆ ለመጨረስ እንዲያስችላቸው  የመመረቂያ ጥናታዊ ፅሁፎችን አዘጋጀቶ ማቅረብና አጥጋቢ ውጤት ማምጣት ያስፈልጋል፡፡ መኮንኖቹም ትምህርታቸውን ሲጨርሱ በወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ የማስተርስ (Master of Military Arts and Sciences) ዲግሪ ይሰጣቸዋል፡፡ ከሥልጠናው በኋላም የሥራ ኋላፊነታቸውም የሻለቃ ወይም የብርጌድ አዛዥ ወይም በክ/ጦር (በዕዝ) መምሪያ ውስጥ የመምሪያ መኮንን በመሆን ያገለግላሉ፡፡ መኮንኖቹ ከተመረቁና በያዙት ማዕረግ የተወሰነ አገልግሎት ከሰጡ በኋላ በዚሁ አካዳሚ ውስጥ እንደገና ሁለት ኮርሶችን ይወስዳሉ፡፡

እነዚህም፦

ሀ/ ከፍተኛ ወታደራዊ ጥናትና

ለ/ የዕዝ አዛዥነት

እነዚህ ኮርሶች በዋናነት የሚያተኩሩት በወታደራዊ ስትራቴትጂክ ጉዳዮች እና የዕዝ አዛዥነት ንድፈ ሀሳብ ላይ ነው፡፡ ኮርሱንም ሲጨርሱ የወታደራዊ ዕቅድ ነዳፊዎች (Strategic Military Planners) ሆነው ይመደባሉ፡፡

 

2.4 የጦር ኋይሎች የጦር ኮሌጅ (Armed Forces War College)

 

ይህ ተቋም  በወታደራዊ የሥልጠና እርከን ውስጥ የመጨረሻው የስትራቴጂክ አመራር ሥልጠና (Strategic Leadership Training) የሚሰጥበት የጥናት እና የምርምር ማዕከል ነው፡፡ በዚህ ተቋም ውስጥ የኮርሱ ተሳታፊዎች የሚሆኑት በምድር ኋይል፣ በአየር ኋይል፣ እና በባህር ኋይል ውስጥ ስትራቴጂክ አመራር (Strategic Level Leaders) እየሰጡ ከሚገኙት እና   ከከፍተኛ ስቪል የመንግስት ባለስልጣናት ውስጥ ቢያንስ ማስተርስ ዲግሪ ያላቸውን ፖሊሲና እስትራቴጂ አውጪ ሊሆኑ ይችላሉ የሚባሉትን በመቀበል ለከፍተኛ የሥልጣን ቦታ እና ሀላፊነት የሚያዘጋጅ የፖሊሲ እና የስትራቴጂ ጥናት እና ምርምር ተቋም ነው፡፡

እንደ ተለያዩ ሀገሮች ተጨባጭ ሁኔታ በጦር ሀይሎቻቸው ውስጥ እራሳቸውን የቻሉ የምድር ሀይል የጦር ኮሌጅ፣ የአየር ሀይል የጦር ኮሌጅ እና የባህር ሀይል የጦር ኮሌጅ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ሆኖም በወታደራዊ የሥልጠና እርከን መሰረት ሁሉም ሀይሎች አመራር መኮንኖቻቸውን በየራሳቸው የጦር ኮሌጅ ትምህርታቸውን ካስጨረሱ በኋላ ወደ ዋናው የጦር ኃይሎች የጦር ኮሌጅ ገብተው እንዲሠለጥኑ ያደርጋሉ፡፡

ወደ ጦር ኋይሎች የጦር ኮሌጅ ለመግባት በቅድሚያ መሟላት ያለበት፦

  1. የአዛዥነትና የመምሪያ መኮንንነት ኮርስን መጨረስ፣
  2. በጦር ኃሎች የጦር ኮሌጅ የሚሰጠውን ኮርስ መጨረስ፣
  3. በሠራዊቱ ውስጥ በአመራር ሰጭነት ከ 22 ዓመት በላይ ማገለገል፣
  4. በወታደራዊ ሥነምግባር ምንም ችግር የሌለበትና፣
  5. የአካል ብቃቱ በሀኪም የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል፡;

ከላይ የተጠቀሱት መሠረታዊ መስፈርቶች እንደተጠበቁ ሆነው ወደ ጦር ኋይሎች የጦር ኮሌጅ የሚገቡት ለብርጋዲየር ጄኔራልነት የሚታጩ ስለሆነ በምድር ኃይል በሙሉ ኮሎኔል ማዕረግ በአየር ኋይል ተመጣጣኝ በሆነው Group Captain እና በባህር ሀይል ደግሞ ካፒቴን (Captain) በአጠቃላይ ሁሉም በኮሎኔል ማዕረግ ደረጃ ሆነው በማገልገል ያሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

የኮርሱም ተሳታፊዎች መጠንም 75 በመቶ ከጦር ኋይሎች ከሦስቱም ኃይሎች ተመጣጣኝ ቁጥር ያላቸው ከፍተኛ መኮንኖችን እና 25 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከሲቪል የመንግስት ባለስልጣናት፣ ከሀገር ውስጥ ጉዳይ፣ (በአሁኑ የፌደራል ጉዳዮች)  እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ተመርጠው እንዲሣተፉ ይደረጋል፡፡ ኮርሱም የሚያተኩርባቸው ርዕሰ ጉዳዮችም የስታራቴጂክ አመራር ጥበብ፣ የብሔራዊ ደህንነት ስትራቴጂ ጥናት (National Security Strategy)፣ የግጭት ማስወገድ ጥናቶች (Conflic Resolution Research)፣ የህብረት ጥምር ውጊያ ፍልስፍና (War Games) እንዲሁም የጥናት እና ምርምር ንድፈ ሀሳብ ትምህርት የሚሰጥበት ማዕከል ነው፡፡ መኮንኖቹ ትምህርቱን ሲጨርሱም በስትራቴጂ ጥናት የማስተርስ ዲግሪ (Master Degree in Strategic Studies) ደረጃ  ይመረቃሉ፡፡ በጦር ኋይሎች ውስጥም የኮር ወይም የዕዝ አዛዥ ወይም በሀገር መከላከያ ጠቅላይ መምሪያ የመምሪያ መኮንነት የሥራ ኋላፊ ሆነው እንዲሠሩ ይደረጋል። በጦር ሀይሎች የጦር ኮሌጅ ውስጥ ትምህርታቸውን ጨርሰው የተመረቁ መኮንኖች ምንም አይነት የዲሲፕሊን ችግር ሪከርድ የሌለባቸው ከሆነ በቀጥታ የብርጋዴር ጄኔራልነት ማዕረግ ይሰጣቸዋል፡፡ በአጠቃላይ ከላይ የተቀመጠው  መሠረታዊ የሆነው የመኮንኖች የአመራር ጥበብ ስልጠና ሂደት ከዕጩ መኮንነት ኮርስ እስከ ጦር ኮሌጅ የሚዘልቅና መንገዱም ሌላ አቋራጭ  የሌለው ረዥም እና አስቸጋሪ ውጣ ውረድ የበዛበት መሆኑን ለማሳየት ተሞክሯል፡፡ ይህንን ረጅም መንገድ ያለፉ መኮንኖች ሁሉ የተሰጣቸውን ግዳጅ በብቃት የተወጡ ስለመሆናቸው ያለፉት ታላላቅ አውደ ውጊያዎች(በምስራቅና በሰሜን ኢተዮጵያ) ምስክርና ማስረጃዎች ናቸው፡፡

 

3.    የመኮንኖች የማዕረግ ዕድገት ሂደት

 

የመኮንኖች የማዕረግ ዕድገት መነሻውም ሆነ መድረሻው ወታደራዊ ትምህርትና ሥልጠና ነው፡፡ የወታደራዊ አመራር ሳይንስ ጥበብ ደግሞ ለመኮንነት ማዕረግና ዕድገት የማዕዘን መሰረተ ድንጋይ ሲሆን በአጠቃላይ የመኮንነት የማዕረግ  ዕድገት በሥልጠና እየታገዘ የሚከናወን ቀጣይነት ያለው ሂደት  ነው፡፡ መኮንን ለመሆን በቅድሚያ የዕጩ መኮንንነት ኮርስ ወስዶ በሚገባ ማጠናቀቅን ይጠይቃል። የአንድ መኮንን የመጀመሪያው ማዕረግም በምድር ሀይል ምክትል መቶ አለቃ (Second Lieutenant) በአየር ሀይል ፓይለት መኮንን (Pilot Officer) በባህር ሀይል ደግሞ ኢንሳይን (EnSign ) ይባላል፡፡ ምክትል መቶ አለቃ ሆኖ የተመረቀ መኮንን ወደ ሚቀጥለው የማዕረግ ዕድገት ለማለፍ የግል ሪፖርቱ ተገምግሞ ምንም ዓይነት የዲሲፕሊን ችግር ከሌለበት በምድር ሀይል ሙሉ መቶ አለቃ (Lieutenant) በአየር ሀይል በራሪ መኮንን (Flying Officer) በባህር ሀይል ምክትል ሊዩተናንት (Sub – Lieutenant) ይሆናል ፡፡ በሙሉ መቶ አለቃ ማዕረግ ደግሞ አምስት ዓመት ካገለገለ በኋላ የሻምበልነት ማዕረግ ያገኛል፤ በሻምበል ማዕረግ ደግሞ አራት ዓመት ማገልገል አለበት፡፡ በአራት ዓመት የቆይታ ወቅትም የስታፍ ኮሌጅ ኮርሱን ካጠናቀቀና በቆይታ ጊዜ ውስጥ ያስመዘገበው የወታደራዊ ዲሲፕሊን እና የሙያ ብቃቱ ተረጋግጦ በበቂ ሁኔታ ከአለፈ የሻለቃነት ማዕረግ ዕድገት ይሰጠዋል፡፡

በሻለቃ ማዕረግ የቆይታ ጊዜ አራት ዓመት ሲሆን  በአራት ዓመት ውስጥም የአዛዥነትና የመምሪያ መኮንንነት ኮርስ ይወስዳል፡፡ የሻለቃ የማዕረግ ቆይታውን ሲጨርስ በሠራዊቱ ሕገ ደንብ መሰረት በዋንኛነት የወታደራዊ ዲሲፕሊኑ፣ የአመራር ብቃቱ፣ በተዋረድ የወሰደው የወታደራዊ አመራር ስልጠና እና በቆይታው ጊዜ ባስመዘገበው ሪፖርት ተመስርቶ ይገመገምና ወደ ሚቀጥለው የማዕረግ ዕድገት የሚያልፍ ከሆነ የሌ/ኮሎኔል ማዕረግ ይሰጠዋል፡፡ የሌ/ኮሎኔል ማዕረግ ቆይታ አራት ዓመት ሲሆን በአራት ዓመት ቆይታው ወቅት የሚወስዳቸው ኮርሶች የአዛዥነትና የመምሪያ መኮንንነት ኮርስ እንዲሁም የምድር ኃይል ወይም የአየር ኃይል የጦር ኮሌጅ የአመራር ጥበብ ሥልጠናን ወስዶ ከጨረሰና በቆይታ ጊዜውም ውስጥ ምንም ዓይነት የዲሲፕሊን ችግር ከሌለበት የሙሉ ኮሎኔልነት ማዕረግ እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡

ከሙሉ ኮሎኔልነት ማዕረግ ወደ ቀጣዩ ማዕረግ ለማደግ ቢያንስ የአራት ዓመት የቆይታ ጊዜ ያስፈልጋል ፡፡ በአራት ዓመት የቆይታ ጊዜ ውስጥም የጦር ኃይሎች የጦር ኮሌጅ በመግባት የስትራቴጂክ የአመራር ጥበብ መውሰደና መመረቅ ይኖርበታል:: ኮርሱንም ከጨረሰ በኋላ በቀጥታ የወሰደው የአመራር ሥልጠና እርከን፣ የአመራር ብቃቱ እና አጠቃላይ የ22 ዓመት የአገልግሎት የቆይታ ሪፖርት ተገምግሞ ከአለፈ የብ/ጄነራልነት የማዕረግ ዕድገት ይሰጠዋል፡፡ ትክክለኛ የመኮንኖች የማዕረግ እድገት አሰጣጥ ሂደትና ይዘት ከላይ በተጠቀሰው የትምህርት፣ የስልጠና፣ የሥነምግባር አፈፃፀም ግምገማ  ውጤትን መሠረት ባደረገ መንገድ የሚከናወነው ብቻ ነው፡፡

 

4.    የጄነራል መኮንንነት የማዕረግ ዕድገት

 

የጄነራል የመኮንነት የማዕረግ ዕድገት መሰረታዊ የትምህርትና ሥልጠና ዝግጁነቶች እንደተጠበቁ ሆኖ በየሀገሩ ተጨባጭ ሁኔታ  መሰረት  ይሰጣል፡፡ ለምሳሌ ያህል በአሜሪካ የጦር ኋይሎች ውስጥ የጄነራልነት ሹመት በፕሬዘዳንቱ አቅራቢነት በህግ መወሰኛው ምክር ቤት ይጸድቃል፡፡ በሌሎች ሀገሮች ግን የጄነራልነት ሹመት የሚካሄደው በመከላከያ ሚኒስቴር በሚቋቋመው የማዕረግ ዕድገት ቦርድ ወይም በመከላከያ ካውንስል በተቋቋመው በሰራዊቱ ህገ ደንብ መሠረት መመዘኛውን ያሟሉ ተመርጠው ለሀገሪቷ ፕሬዘዳንት ቀርቦ ይጸድቃል፡፡

የጄነራል መኮንንነት ማዕረግ ከፍተኛው የወታደራዊ ማዕረግ እርከን ሲሆን በጦር ኋይሎች ( በምድር ኃይል፣ በአየር ኃይል እና በባህር ኃይል) ከፍተኛውን ኃይል የሚመሩ ወይም የሚያዙ፣ ሠራዊቱን የሚያደራጁ፣ የሠራዊቱን ህግ ደንብ የሚያወጡ፣ ሠራዊቱ የሚዋጋበትን የጦርነት ህግ እና ሠራዊቱ የሚሰለጥንበትን የሥልጠና ፖሊሲ፣ የወታደራዊ ዶክትሪን እና ስትራቴጂ የሚቀርጹ፤ በአካዳሚም ሆነ በወታደራዊ ሳይንስ እና ጥበብ የተካኑ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለባቸው የጦር ኃየሎች ጄነራል መኮንኖች ናቸው፡፡

 

ሰንጠረዥ-ሀ፦ የጄነራል መኮንኖች የማዕረ አጠራር በተለያዩ የጦር ኃይል ክፍሎች

ተ.ቁ

በምድረ ኃይል

በአየር ኃይል

በባህር ኃይል

1

Brigadier General Air Commodore Commodore

2

Major General Air Vice Marshal Rear Admiral

3

Lieutenant General Air Marshal Vice Admiral

4

Full General Air Chief Marshal Admiral

5

Marshal or Field Marshal Marshal Air Forces Admiral of the fleet

 

ሀ. ብርጋዴር ጄነራል፡ ይህ ማዕረግ ከሙሉ ኮሎኔል ቀጥሎ የሚሰጥ ሲሆን የጄነራል መኮንኖች የመጀመሪያ ማዕረግ ነው፡፡ ከሙሉ ኮሎኔልነት ወደ ብርጋዴር ጄነራልነት ለመሸጋገር መመዘኛዎቹ፡

1)    በኮሎኔልነት ማዕረግ የአገልግሎት ዘመን፣

2)   የወታደራዊ የአመራር ጥበብ በተዋረድ የወሰደ፣

3)   በአገልግሎት ዘመኑ ያሳየው ዲሲፕሊን፣

4)   የወታደራዊ አመራር ብቃቱ እና ልምዱ፣

5)   በብ/ጄነራልነት ማዕረግ ሊሰራበት የሚችልበት የሥራ ቦታ ክፍት ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡

ብርጋዲር ጄነራል ማዕረግ ያለው መኮንን በጦር ኃይሎች የብርጌድ ወይም የክፍለ ጦሩ አዛዥ እንዲሁም የኮር እስታፍ ይሆናል፡፡ በያዘው ማዕረግም ከሁለት እስከ አራት ዓመት ያገለግላል፤ የጡረታ ጊዜውም በያዘው ማዕረግ አምስት ዓመት ከቆየና 30 ዓመት የአገልግሎት ዘመን ከሞላው ጡረታ ይወጣል፡፡ የጡረታ የዕድሜ ጣራውም 62 ዓመት ይሆናል፡፡

 

ለ.ሜጀር ጄነራል፡ ይህ ማዕረግ ከብ/ጀኔራል ማዕረግ ቀጥሎ ያለ ባለ ሁለት ኮከብ ማዕረግ ነው፡፡ ከብ/ጀ ወደ ሜ/ጀኔራል የማዕረግ ዕድገት ለመሸጋገር በቅድሚያ ፡-

  • ክፍት የስራቦታ መኖሩ (Number of Open Positions) ፣
  • በአመራር ብቃት የፈጸማቸው ግዳጆች፣
  • በወታደራዊ ሥነ ምግባር ምንም ችግር የሌለበት፣
  • የአመራር የሥልጠና እርከን በተዋረድ የወሰደ፣
  • የአገልግሎት የቆይታ ጊዜውን (Years of Services) የጨረሰ መሆኑ መታየት ይኖርበታል።

መኮንኑ ሜ/ጀኔራል ከሆነ በኋላ የሥራ ኃላፊነቱም የክፍለ ጦር ወይም የዕዝ አዛዥ ወይም በጦር ኃይሎች ጠቅላይ መምሪያ ውስጥ የመምሪያ መኮንን ሆኖ መሥራት ነው፡፡ በያዘው ማዕረግም እስከ አምስት ዓመት ከአገለገለ በኋላ ወይም 35 ዓመት በጦር ኃይሎች ውስጥ አገልግሎት ከሰጠ ጡረታ ይወጣል፡፡ የጡረታ ዕድሜውም 62 ዓመት ነው፡፡ ከዕድሜው ጣራ ውጭ በተለየ ሁኔታ በሥራ አስፈላጊነት አራት ዓመት በተጨማሪ የመስራት አማራጭ አለው፡፡ እድሜውም እስከ 64 ዓመት ሊዘልቅ ይችላል፡፡

 ሐ. ሊዩተናንት ጄኔራል፡ ይህ ማዕረግ በሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ባለ ሦስት ኮከብ ከፍተኛ የጀኔራልነት ማዕረግ እርከን ነው፡፡ አንድ መኮንን ወደ ሌ/ጀኔራልነት ማዕረግ ከመድረሱ በፊት በጦር ኃይሎች ውስጥ በአመራር ከ 20 ዓመት ያልበለጠ አገልግሎት መስጠት አለበት፤ ከሜ/ ጀኔራል ማዕረግ ወደ ሌ/ጄነራል ማዕረግ ለመሸጋገር መሟላት ያለበት የአመራር ብቃቱ፣ በያዘው ማዕረግ የቆይታው ጊዜ፣ በወታደራዊ ሥነ-ምግባር ምንም አይነት ችግር የሌለበት፣ የአመራር የሥልጠና እርከኖችን ያለፈ፣ እና ክፍት የሥራ ቦታ መኖሩ ናቸው፡፡ ሌ/ጀኔራል ከሆነ በኋላ የሥራ ኃላፊነቱም የኮር ወይም የግንባር ወይም የህብረት የጥምር ጦር አዛዥ እና በሀገር መከላከያ ጠቅላይ መምሪያ፣ የመምሪያ መኮንን ሆኖ ማገልገል ነው፡፡ መኮንኑ በያዘው ማዕረግ ቢያንስ ሦስት ዓመት ማገልገል አለበት ነገር ግን በያዘው ማዕረግ አምስት ዓመት ከአገለገለ እና በጦር ሀይሎች ውስጥም 40 ዓመት ካገለገለ በጡረታ ይገለላል፤ የዕድሜ ጣሪያውም 62 ዓመት ይሆናል፡፡

 

መ. ጄኔራል፡ ይህ ማዕረግ ከሌ/ጄነራል ቀጥሎ ከፊልድ ማርሻል  ዝቅ ያለ ባለ አራት ኮከብ ማዕረግ ሲሆን በጦር ኃይሎች ማዕረግ አሰጣጥም ከፍተኛው የሹመት እርከን ነው፡፡ ከሌ/ጀኔራልነት ወደ ሙሉ ጀኔራልነት የማዕረግ እድገት ለመሸጋገር በቅድሚያ ክፍት የስራ ቦታ ሲኖር፣ በጦር ሀይሎች ውስጥም 20-23 ዓመት ያገለገለ፣ የአመራር ብቃት እና ልምዱ ስኬታማ የሆነ፣ በወታደራዊ ሥነ ምግባሩም ምንም ዓይነት እንከን የሌለበት፣ ለአመራርነት የሚሰጠውን ከፍተኛ የሳይንስና የጥበብ ሥልጠና እርከኖችን በተዋረድ የጨረሰ መሆን ይኖርበታል፡፡ የሙሉ ጀኔራል የኋላፊነት ቦታም በጦር ኃይሎች ውስጥ የምድር ጦር ወይም የአየር ኃይል አዛዥ ወይም የህብረት ዕዝ አዛዥ ወይም የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ወይም የጦር ኃይሎች አዛዥ ሆኖ መሥራትን ያጠቃልላል፡፡ በያዘው ማዕረግ ቢያንስ አምስት ዓመት ያገለገለ ሆኖ በጦር ሀይሎች ውስጥ ያበረከተው የአገልግሎት ጣራ  40 ዓመት ከሞላ ጡረታ ይወጣል፡፡ የዕድሜ ጣሪያውም 64 ዓመት ይሆናል፡፡

የአንድ ሀገር የጦር ኃይል (የምድርኃይል፣ የአየር ኃይል፣ የባህር ኃይል) ከዚህ በታች በተጠቀሱት  ሦስት አይነት የአመራር ደረጃዎች  ማለትም፦

  1. በቀጥተኛ የግንባር መስመር አመራር መኮንኖች
  2. በከፍተኛ አመራር መኮንኖችና
  3. በስትራቴጂክ አመራር መኮንኖች የተደራጀ መሆን ይኖርበታል፡፡

በሰራዊቱ ውስጥ ጄነራል መኮንኖች የሆኑ ሁሉ የሥትራቴጂክ አመራር አካል ናቸው፡፡ አንድ መኮንን የብ/ጄነራል ማዕረግ ለመድረስ 22 ዓመት ማገልገል አለበት ከዚህ ውስጥ ከ7-8 ዓመታት ያለው ጊዜ የወታደራዊ የአመራር ጥበብ ሳይንስ የሚቀስምበት የዕውቀት ጉዞ መንገድ ነው፡፡

በአጠቃላይ የጄነራል መኮንኖች የወታደራዊ አመራር ጥበብ ሥልጠና መነሻው መሰረታዊ ከሆነው ከዕጩ መኮንንነት የሥልጠና እርከን ተነስቶ እስከ መጨረሻው የፖሊሲ እና ስትራቴጂ ትንተና ጥናት እና ምርምር ተቋም እስከ ሆነው የጦር ኮሌጅ ድረስ ይዘልቃል፡፡ የአመራር የሥልጠና እርከኖችን ያላለፈ ጄኔራል የተሟላ ተክለ ሰውነት እንደሌለው ይታሰባል ወይም ይቆጠራል፡፡

 

5.    የቀድሞው የሀገር መከላከያ ሠራዊት አመራሮች የሥልጠና ሂደት፤

 

በሀገራችን የመከላከያ ሠራዊት ታሪክ ውስጥ የወታደራዊ ትምህርትና ሥልጠና ከፍተኛ ቦታ እና ትኩረት ነበረው፡፡ በቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት የነበረው የመከላለከያ ሚኒስቴር ሁለት የጦር አካዳሚ ትምህርት ቤቶች ነበሩት፡፡ እነዚህም የሐረር ጦር አካዳሚና የሆለታ ገነት ጦር ትምህርት ቤቶች ናቸው፡፡ የሆለታ ገነት ጦር ትምህርት ቤት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በትንሽ ዓመት ቆይታ የተቋቋመ በርካታ ብርቅዬ የጦር መኮንኖችን በጥራት ያስመረቀ ተቋም ነው፡፡ ትምህርት ቤቱ ከ1ኛ ኮርሰ እስከ 54ኛ ኮርስ ድረስ መኮንኖችን ያስመረቀ ቢሆንም በደርግ ጊዜ በነበረው የርስ በርስ ጦርነት ምክንያት የማሰልጠን ሥራውን ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ማካሄድ ተስኖት ነበር፡፡

የሐረር ጦር አካዳሚ እ.ኤ.አ 1957 ከተቋቋመ አንስቶ እስከ ተዘጋበት 1977 ድረስ በርካታ መኮንኖችን አስመርቋል። አካዳሚው ለጎረቤት ሀገሮች ጭምር መኮንኖችን ያሰለጥን ነበር፤ ሁለቱም የጦር ትምህርት ቤቶች አለም ዓቀፍ የአመራር ስልጠና መመዘኛ ስታንዳርድን በጠበቀ መልኩ ተደራጅተው ብዙ አመራሮችን አሰልጥነው በማስመረቅ ለሃገሪቱ አበርክተዋል፡፡ ከእነዚህ የጦር አካዳሚ ት/ቤቶች ከተመረቁ መኮንኖች ውስጥ ከምክትል መቶ አለቃነት  እስከ ሌ/ጀኔራልነት ማዕረግ የደረሱ ይገኙበታል፡፡እነዚህ ጄኔራል መኮንኖች በወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ የተካኑና በሥነምግባር የታነፁ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የተማሩ ከፍተኛ ብቃት እና ችሎታ ያላቸው ሀገራቸውን በወታደራዊ መስክ ያስጠሩ ብርቅዬ የኢትዮጵያ የሀገር መመኪያ ልጆች ነበሩ፡፡ የሐረር ጦር አካዳሚ  ከ1ኛ ኮርስ እስከ 21ኛ ኮርስ ድረስ በማስተማር አስመርቋል፡፡

 

በወቅቱ የነበሩት የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ጦር ኃይሎች የመከላከያ ሥልጠና ፖሊሲ በሚያዘው መሠረት ወታደራዊ የአመራር ጥበብና ሳይንስ በተገቢው ሁኔታ ከዕጩ መኮንን ሥልጠና እስከ ስታፍ ኮሌጅ ድረስ የዘለቁ 293 ጄነራል መኮንኖች ነበሩት(ሰንጠረዥ-ለን ይመልከቱ)።

ሰንጠረዥ–ለ፦ በሦስቱም መንግሥታት የተሾሙ ጄነራል መኮንኖች (1927–2007 ዓ/ም)

.

የማ ደረጃ

1927 እስከ 1983

ከ1983 ጀምሮ

ጠቅላላ ድምር

ኃይለ ሥላሴ

ርግ

ህወሓት/ ኢህአዴግ

1

ጄኔራል

0

0

1

1

2

ሌ/ጄኔራል

15

3

6

24

3

ሜ/ጄኔራል

6

32

24

62

4

ብ/ጄኔራል

63

174

99

336

ጠቅላላ ድምር

84

209

130

423

 

 

በአጠቃላይ እነዚህ ጄኔራል መኮንኖች በዚህ ጽሁፍ ዋና አካል ላይ የተቀመጡትን የወታደራዊ አመራር ሥልጠና እርከኖች ይዘት እና ሂደት አሟልተው የተመረቁና በተግባር በጦር ሜዳ ውሎአቸውም አመርቂ ውጤት ያስመዘገቡ እንደነበሩ ድርሳናቸው ያስረዳል፡፡

6.    የአሁኑ  የሀገር መከላከያ መኮንኖች ከወታደራዊ አመራር ሳይንስና ጥበብ አንፃር

 

የዛሬው የሕወሓት ሰራዊት ከሽምቅ ተዋጊነት በቀጥታ መደበኛ የሀገሪቱ ሠራዊት እንዲሆን በምድር ሀይልና በአየር ሀይል ተከፋፍሎ  እንዲደራጀ የተደረገ ሲሆን ሠራዊቱን እንዲመሩ የተመደቡት የበታች ሹሞችና መኮንኖች በሙሉ በምንም ዓይነት ወታደራዊ የአመራር ስልጠና ውስጥ ሳያልፉና ከወታደራዊ ሙያ ሳይንስና  ሕግጋት ውጭ በዘርና በፖለቲካ ወገንተኝነት ላይ በመመሥረት ማዕረግ በጅምላ የተሰጣቸው ናቸው:: ይህ ደግሞ በሀገሪቷ መጥፎ የታሪክ ጠባሳ እየጣለ ይገኛል።

በወታደራዊ የአመራር ስልጠና ታሪክ ያለምንም የአመራር ስልጠና የጄነራል መኮንነት ማዕረግ የሰጠች የመጀመሪያ አፍሪካዊት አገር ኢትዮጵያ ነች:: ሕወሓት/ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ከ1983 ጀምሮ እስከ 2006 ዓ.ም. ድረስ ለ130 አባሎቹ (ለዝርዘሩ አባሪ ፩ን ይመልከቱ)  የጄኔራል መኮንነት ማዕረግ የሰጠ ሲሆን 97 በመቶ የሚሆኑት ተሿሚዎችም በምንም ዓይነት የወታደራዊ አመራር ሳይንስና ጥበብ ስልጠና ውስጥ ያላለፉ ናቸው። ወደ 52 በመቶ (67ቱ) የጄኔራል መኮንንነት ቦታም የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የህወሓት አባላት ተቆጣጥረውታል (ሰንጠረዥ-ሐን እና ሥዕል-አንድን ይመልከቱ)::

 

በአጠቃላይ ከላይ በሥዕሉና በሠንጠረዡ እንደተመለከትነው፤ ሂደቱ የሀገሪቱን የወታደራዊ ስልጠና ገጽታን ከማበላሸቱም በላይ መጥፎ የታሪክ ጠባሳ እየጣለ ይገኛል:: በሚገርም ሁኔታ የሀገር መከላከያ የስትራቴጂክ አመራር እንዲሰጡ በህዋሓት የተሾሙ ጄነራል መኮንኖች  መሰረታዊ የሆነውን የአመራር ስልጠና እንኳን ያልወሰዱ እና የአካዳሚክስ እውቀታቸው በጣም ዝቅተኛና በአብዛኛው ከ5ኛና ከ9ኛ ክፍል ያላለፈ መሆኑን የግል ሕይወት ታሪካቸው ያሳያል።

አንድን ሠራዊት ለመምራትም ሆነ ለማሰልጠን ቀድሞ ሰልጥኖ መገኝት ጥያቄ ውስጥ ሊገባና ሊጣስ የማይችል መርህ ነው:: የህወሓት መንግስት ከፈጸመው አስከፊ ወንጀል አንዱ ምንም ዓይነት የወታደራዊ አመራር ትምህርትና ስልጠና ሳያገኙ ጄነራል ብሎ በመሰዬም ሠራዊት እንዲመሩ ማድረጉ ነው:: የአሁኑ ጄኔራል መኮንኖች በአካዳሚክስም ሆነ በወታደራዊ ሳይንስና የአመራር ጥበብ ድህነት የተጎዱ፣ ጫካ በነበሩበት ወቅት መደበኛ ባልሆነ የሽምቅ ውጊያ ዕውቀት ብቻ ተኮፍሰው የኖሩ አሁንም በዚያው መንገድ የሚጓዙ ናቸው::

የህወሓት ጄነራል መኮንኖች  ስለወታደራዊ አመራር ጥበብ ስልጠና ምንነትና ይዘት እንዲሁም  ሂደት  ምን እንደሆነ ግንዛቤ የሌላቸውና የማወቅ ፍላጎት የሌላቸው ናቸው፡፡ በአንድ ወቅት በአስተርጓሚ እንዲማሩ ተሞክሮ ነገር ግን ሳይሳካ መቅረቱ በተጨባጭ የሚታወቅ ነው፡፡ ምክንያቱም “አሁን እኛ ጄነራል መኮንኖች ስለሆንን አንማርም ምን ያደርግልናል” በሚል ነበር።  በአሁኑ ወቅት ሠራዊቱ እየተመራ ያለው በእነዚህ ዓይነት ሰዎች ነው! የሚገያስርመው ነገር በሚመሩት ሰራዊት ወስጥ የሚገኙ የመካከለኛ እና የዝቅተኛ አመራር መኮንኖች በወታደራዊ የአመራር ስልጠና ንድፈ ሀሳብም (Theory) ሆነ ተግባራዊ ስራዎች አለቆቻቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ይበልጧቸዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት እድሉ ቢሰጣቸው እነዚህን ጄኔራሎች በብቃት መልሰው ሊመሯቸው የሚችሉ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የወታደራዊ ሳይንስ ንድፈ ሀሳብ (theory) እንደሚያሳየው አንድ ወታደር መኮንን የሚባለው የአመራር ጥበብ በመውሰድ በተገቢ ሁኔታ ካጠናቀቀ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ንድፈ ሀሳብ  አንፃር ለህወሓት ጄኔራል መኮንኖች ምን ስም ቢሰጣቸው ይመጥናቸዋል? የበታች ሹም ቢባሉ፣ ለበታች ሹምነት ማዕረግ የሚያበቃውን የአመራር ስልጠና አልወሰዱም፡፡ ከበታች ሹም ቀጥሎ ወደታች ያለው ማዕረግ ቢሰጣቸው ደግሞ እሱንም እንኳን ለማሟላት መደበኛ የሆነውን መሠረታዊ የወታደራዊ  ስልጠናም አልወሰዱም፡፡ በዚህ ነባራቂ ሐቅ በመንተራስ ከተራ ወታደር በስተቀር ሊሰጣቸው የሚችል ምንም ዓይነት መጠሪያ ስም የለም፡፡ ሕወሓቶች ጫካ እያሉም ሆነ አሁን የሚጠራሩበት “ተጋዳላይ እከሌ” “ወዲ እከሌ” የሚለው መጠራሪያቸው የሚመጥናቸው ይመስላል፡፡ ለምሳሌ ሌ/ጄነራል ብለው የሾሙትን ከፍተኛ መኮንን ወዲ ወረዳ እያሉ ይጠራሉ፡፡ ይህ ባጠቃላይ ሲታይ ሠራዊቱ የአንድ መደበኛ ሠራዊት አካልነት ባህሪም ሆነ ተግባር አይታይበትም።

የህወሓት ጄኔራል መኮንኖች የወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ፣ ዕውቀትና አመራር አናሳና ደካማነት በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በተጨባጭ በግልጽ የተከሰተበት የታሪክ አጋጣሚ ታይቶ አልፏል:: ይህ ጦርነት እልፍ አዕላፍ የሆኑ የደሃው ኢትዮጵያዊውያን/ት ልጆች ህይወት የተቀጠፈበትና የሀገሪቷ አንጡራ ሀብት የወደመበት አስከፊ ጦርነት ነበር:: ለዚህ ደግሞ ተጠያቂዎቹ:-

1ኛ፡ የሕወሓት ከፍተኛው አመራር እና

2ኛ፡ የህወሐት ስትራቴጂክ አመራር ሰጭ ጄኔራሎች ናቸው

ከላይ የተጠቀሱት የሕወሓት ጄኔራል መኮንኖች  የወታደራዊ ትምህርትና ስልጠና ሳይወስዱ ወይንም ሳይቀስሙ ሠራዊቱን እንዲመሩ በመደረጋቸው ከፍተኛ ጉዳትና አደጋ ደርሷል:: ይህ ሁኔታ ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ ውስጥ መኪና ያለመብራት መንዳት ወይም መኪናን ያለመሪ ለመንዳት እንደሚደረግ ሙከራ ያህል ይቆጠራል::

በአጠቃላይ የመኮንኖች የወታደራዊ አመራር ጥበብ ሥልጠና ምንነትና ይዘት እንዲሁም ሂደቱን እና የመኮንኖች የማዕረግ ዕድገት አሰጣጥ መነሻውም ሆነ መድረሻው የወታደራዊ ትምህርትና ስልጠና መሆኑን በሚገባ ከተጨባጭ ሁኔታ ጋር አይተናል፡፡

2.    ማጠቃለያ

 

ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ በአጠቃላይ የወታደራዊ ትምህርት እና ስልጠና ይዘትና ሂደት ምን እንደሚመስልና  አሁን ያለውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚመሩትን ጄኔራል መኮንኖችን  ዓለም ከደረሰበትና  ተቀባይነት ካለው የወታደራዊ ትምህርትና ስልጠና ስታንዳርድ እንፃር የሙያ ብቃት ደረጃቸውን በመመዘንና በመተንተን  በጥልቀት ለመዳሰስ ሙከራ አደርጓል። የወታደራዊ ሳይንስና የአመራር ጥበብ ሥልጠና በተዋረድ ከመሰረታዊ ሥልጠና ወደ ቀጣዩ ስልጠና እንዴት እንደሚሸጋገርና እንደሚገባ፣ ሥልጠናው የሚያካትታቸው የትምህርት ዓይነቶች ፣ ከሥልጠናም በኋላም በኃላፊነት ሊመሩት የሚችሉት ኃይልና የወታደር ብዛት፣ የሥልጠናው የቆይታ ጊዜ፣ እንዲሁም ሥልጠናውን ሲጨርሱ የሚሰጠው የትምህርት ማስረጃ እና ከተወሰነ አገልግሎት በኋላ ከአንዱ የአመራር ሥልጠና ወደ ሌላው የአመራር ሥልጠና እርከን እንዴት እንደሚሸጋገሩ ሥዕላዊ በሆነ መለኩ በማቅረብ ሳይንሳዊ የሆነ የአመራር ሥልጠና ሂደት ዋነኛው እና ትልቁ መንገድ መሆኑን ያመለክታል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ አንድ ጀኔራል መኮንን በሚያዝዘው  ኃይል ውሰጥ ለየእርከኑ አመራር ሰጭ ሊሆኑ  የሚገባቸውን ማዕረጋቸውን፣ የኃላፊነት ቦታና ሠራዊቱ የሚዋጋበትን የጦርነት ህግ፣ ሰራዊቱ የሚሰለጥንበትን የስልጠና ፖሊሲ፣ የወታደራዊ ዶክትሪንና ስትራቴጂ  መቅረጽ መቻል ያለበት መሆኑን ያስረዳል:: አሁን መሬት ላይ ያለው ሐቅ የሚያሳየው ግን ተሿሚዎቹ ክህሎቱ እና ችሎታው የሌላቸው በመሆኑ ከላይ የተዘረዘሩትን አንድ ብቃቱ የተረጋገጠለት ጀኔራል መኮንን ሊፈፅማቸው የሚገባ ተግባራት በብቃት ማከናወን እንደማይችሉ ጥናቱ ያስረዳል:: የእነሱ ዶክትሪንና ስትራቴጂ ቀረጻ መሬት ወረራ ፣ ዝርፊያ፣ ምዝበራ፣ አፈናና ዜጎችን በውጭ ሀገራት ሳይቀር እንዴት መጥለፍ እንደሚቻል ያተኮረ ላቅ ያለ ተንኮል ብቻ ነው:: በአንድ ወቅት ሟች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ጄነራል መኮንኖቹን ሲገመግሙ ያስቀመጡትን ድምዳሜ በመጥቀስ ፅሁፍን እናበቃለን። “እናንተ በቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴም ሆነ በደርግ ዘመነ መንግስት ከነበሩት ጄኔራል መኮንኖች ጋር ስትነፃጸሩ የሰማይና የምድር ያህል ትራራቃላችሁ:: የእናንተ ችሎታ አንድ ሻለቃ  ወይም 400 መቶ ሰው ያለው ሀይል ከማዘዝ  ያለፈ አይደለም!’’

በመጨረሻም ከዚህ በታች በተቀመጠው አባሪ ሰነድ ሰንጠረዥ ፩፤ ሕወሓት/ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ከ1983 ዓ.ም. አንስቶ እስካሁን ድረስ የጦር ኃይሉ የተዋቀረው በአንድ ብሔር (በትግራይተወላጆች) የበላይነት፣ ያለአንዳች የወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ ሥልጠና መሆኑን ማንም ሊያስተባብለው በማይችል መልኩ ጥሬ ሐቁ ተቀምጧል። ይህ በራሱ ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ለምን በዚህ አሳዛኝ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና፣ የማኅበረሰባዊ ዝቅጠት ላይ እንደምትገኝ ቁልጭ አድርገው ከሚያሳዩት ተግዳሮቶች (Factors) አንዱ ሊሆን ይችላል።

3.    አባሪ ሰነድ- ፩ (Annex-1)

 

ginbot 7 1 ginbot 7 2 ginbot 7 3 ginbot 7 4 ginbot 7 5 ginbot 7 6

ginbot 7 7 ginbot 7 8 ginbot 7 9 ginbot 7 10 ginbot 7 11 ginbot 7 12


በዋሽንግተን ዲሲ ጥቂት የወያኔ ኢምባሲ ሠራተኞች እና ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በየፊናቸው ሰልፍ ወጡ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ጥቂት የሕወሓት የዋሽንግተን ዲሲ ኢምባሲ ሠራተኞች እና አንዳንድ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጉሮሮ ተነጥቆ በሚሰጣቸው የስኮላርሺፕ ገንዘብ የደለቡ የስርዓቱ ደጋፊዎች በሰለሞን ተካልኝ መሪነት በስቴት ዲፓርትመንት ደጃፍ ዛሬ ሰልፍ ወጡ። በተመሳሳይም የአሜሪካ መንግስት በዋሽንግተን ዲሲ የሕወሓት ኢምባሲ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ ጥይት የተኮሰውን የስርዓቱን ተላላኪ ከሃገሩ በማባረሩ ለዚህም ምስጋና ለማቅረብ ኢትዮጵያውያን በስቴት ዲፓርትመንት ተመሳሳይ ሰልፍ አድርገዋል።


ሃገር ወዳዱ ኢትዮጵያውያን ልሙጡን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ በመያዝ እንዲሁም የሕወሃት ደጋፊዎች በመሃሉ ላይ ሰማያዊ ኮከብ ያለብትን እና ብዙዎች አይወክለኝም የሚሉትን ባንዲራ ይዘው ሰልፍ የወጡ ሲሆን በስቴት ዲፓርትመንት ደጃፍ በየፊናቸው ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ አርፍደዋል። የሕወሓት ደጋፊዎች “ኢምባሲያችን ተደፈረ፣ ባንዲራችን ተዋረደ” በሚል ሰልፍ የጠሩ ሲሆን ኢትዮጵያውያኑ በበኩላቸው ሃገራችንን ከነክብሯና ባንዲራዋ ያዋረደው ገዢው የሕወሓት መንግስት ነው በማለት የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያውያኑ ላይ ጥይት የተኮሰውን ግለሰብ ወደሃገሩ በማባረሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ቀድሞ ከተቃዋሚዎች ጋር የነበረውና ተገልብጦ የሕወሓት ደጋፊ ሆኖ ቁጭ ያለው ሰለሞን ተካልኝ የሕወሓት ደጋፊዎችን ሰልፍ የመራ ሲሆን፤ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያኑም ሰለሞን የሕወሓትን መንግስት ይቃወምበት የነበረውን “ሁሉም ዜሮ ዜሮ” የሚለውን ዘፈኑን ከፍተው ለምስጋናው ሰልፍ ማድመቂያ አድርገውታል። ሰለሞን ጥቂት የኢምባሲ ሠራተኞችን ሰብስቦ ራሱን በራሱ በማይክራፎን “ሰለሞን እንዲህ የሚሆነው ለሃገሩ ለባንዲራው ነው፤” ያስባለ ሲሆን የሕወሃት ሰልፍ አላማውን ስቶ እንደተባለው የአሜሪካ መንግስትን መቃወሚያ ሳይሆን የሰለሞን ተካልኝ ሞራል መገንቢያና ማወደሻ ሆኖ አልፏል ሲሉ በአካባቢው የነበሩ ኢትዮጵያውያን ለዘ-ሐበሻ ዘጋቢ ተናግረዋል።

በዋሽንግተን ዲሲ መንግስትን የሚደግፍም ሆነ የሚቃወመው በአንድ ቦታ ቆሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጉ ለራሳቸው ለወያኔ ደጋፊዎች ሊያሳፍራቸው ይገባል የሚሉት አንድ አስተያየት ሰጪ “እኛ እንዲህ ያለው ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ነው ትግላችን። ሕወሓትን የሚደግፍም የሚቃወምም በእኩል እንዲታይ። ሆኖም በሃገራችን መንግስትን መቃወም የማንችል መሆኑን የወያኔ ደጋፊዎች እያወቁት ሰሜን አሜሪካ ላይ ከእኛ እኩል ሰልፍ መውጣታቸውና የአሜሪካ መንግስት የመናገር መብትን መፍቀዱ የሚደግፉት መንግስት የሚሰራው ስህተት እንደሆነና እንዲማሩበት ትልቁን ሚና ይጫወታል: ሆኖም ግን ደጋፊዎቹ በአሜሪካ ሃገር ያገኙትን ነጻነት እኛ ሃገራችን ላይ እንድናገኝ ስለማይፈልጉ ከኛ እኲል ዲሞክራሲያዊ መንግስት እየደገፍን ነው ብለው መውጣታቸው ሊያሳፍራቸው ይገባል። ልክ እንደአሜሪካ መንግስት ሁሉ የሚደግፉት የሕወሓት መንግስት ተቃራኒ ሃሳብ ያላቸውን ወገኖች እኩል የመናገር መብት ሊሰጥ እንደሚገባ ከዚህ ሰልፍ ሊማሩ ይገባል” ብለውናል።
washington dc 1

washington dc 3

በአማራ ክልል በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች አብድራፊ ወደ ትግራይ ክልል ሊካተት ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ገለጹ

$
0
0

መስከረም ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአሁን ቀደም ከትርፍ አምራች የአማራ ክልል ወረዳዎች ወደ ትግራይ ክልል የተካለሉ ቦታዎች አሁም ድረስ በሁለቱ ክልሎች መካከል የውዝግብ ምክንያት ሆኖ በቀጠለበት በዚህ ወቅት የአብደራፊ ከተማን

ethiopia-mapወደ ትግራይ ክልል ለመጠቅለል የሚደረገው ቅድመ ዝግጅት ስጋት አሳድሮብናል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ገልጸዋል።

የክልሉ መሪዎች ለአጎራባች ክልል ኢንቨስተሮችና ከፍተኛ ባለስልጣናት የሚሆኑ የእርሻ መሬቶችን በገጸ በረከትነት ለመስጠት መሯሯጣቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ለክልሉ ርእሰ መስተዳድር ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና ለሌሎች ከፍተኛ አመራሮች

ተናግረዋል፡፡ አንድ ተናጋሪ አብደራፊ ወደ ክልል አንድ ትሄዳልች ‘ የሚለው ወሬ በስፋት መሰራጨቱ በህዝቡ ውስጥ ስጋት መፍጠሩን ጠቁመው ፣ በአሁኑ ሰአት የሚታየው የመንገድ ግንባታ ይህንን ያጠናክራል ብለዋል።

ተናጋሪው አክለውም በ ሰሮቃ ከተማ አካባቢ በትግራይና በአማራ ክልል ነዋሪዎች መካከል በየጊዜው ግጭት እየተከሰተ ጉዳት ቢደርስም፣ የሁለቱ ክልሎች ባለስልጣናት ግጭቶችን በየጊዜው ችላ በማለታቸው ወደ ባሰ ውስብስብ ነገር እየገባን ነው ብለዋል።

ሌላ ቅሬታ አቅራቢ ደግሞ በአካባቢው የሚታየው የመንገድ አሰራር አብድራፊን ሆን ብሎ ከአማራ ክልሎች እንዳትገናኝ በማድረግ ከቆይታ በኋላ ወደ ትግራይ ክልል ለመጠቅለል እየተሰራ ያለ ስራ መኖሩን ይጠቁማል ይላሉ።

“ቀደም ብላችሁ በመምጣት ልትጎበኙን ይገባ ነበር “በማለት በምርጫ ወቅት የሚደረግ የተለመደ ጉብኝት መሆኑን ነካ አድርገው ያለፉት ሌለው ተናጋሪ፣ በአካባቢው በሚከሰቱ ችግሮች ዙሪያ የወረዳ አመራሮች መፍትሄ የማይሰጡት በበላይ አመራሮች በሚደርስባቸው

ተጽዕኖ የተነሳ ነው ይብለዋል፡፡ ተናጋሪው “ከማይካድራ የተነሳው መንገድ አብርሃጅራ በመግባት አብደራፊን ማግኘት እያለበት አብደራፊን ሳይገባ ተጠምዝዞ ወደ ክልል አንድ ዳንሻ የተመለሰው መንገድ በምን ምክንያት ነው ?” የሚል ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፣ “አብደራፊ

ወደ ክልል አንድ ትሄዳለች ወይስ አትሄድም? ቁርጥ ያለ መልስ ዛሬውኑ ንገሩን በማለት አመራሮችን አፋጠዋል፡፡ ከተለያየ አቅጣጫ የቀረቡትን የአብደራፊን ዕጣ ፈንታ የተመለከቱትን ጥያቄዎች በተመለከተ የክልሉ መሪ የተብራራ መልስ ባለመስጠታቸው ተሰብሳቢው

ቅሬታውን ገልጿል፡፡ የምእራብ አርማጮሆ ህዝብ ለሚያቀርባቸው የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መልስ እንደማያገኝ አንድ አስተያየት ሰጪ የሃገር ሽማግሌ ለዘጋቢያችን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው ብሄር ተኮር የፌደራል ስርአት በክልሎች መካከል የድንበር ውዝግብ እንዲነሳ ማድረጉን ታዛቢዎች ይገልጻሉ። በአማራ እና በትግራይ ፣ በትግራይና በአፋር፣ በአማራና በኦሮምያ፣ በኦሮምያና በደቡብ፣ በኦሮምያና በሶማሊ፣ በጋምቤላና

በደቡብ ክልሎች መካከል ያልተፈቱ የድንበር ውዝግቦች አሉ ። ኢህአዴግ በበኩሉ የፌደራል ስርአቱ የብሄር ግጭቶች እንዲቀንሱ አድርጓል በማለት ይከራከራል።

Source:: Ethsat

ለመላው የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያየድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አባላት እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያውያን በኖርዌይ በሙሉ!!

$
0
0
dr_tedros_adhanomኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ /“INVEST IN ETHIOPIA”/ በሚል ርእስ በኦክቶበር 16/2014 ኦስሎ ላይ ሴሚናር ይካሀዳል፥፥ ዝግጅቱቱን ያዘጋጀው Norwegian-African Business Association /NABA/ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የአምባገነኑ የወያኔው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ ቴዎድሮስ አድሃኖም ገብረየስ፥ እንዲሁም የኖርዌይ አምባሳደር በኢትዮጵያ ሚ/ር አንድሪያስ ጋርደር እና አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ የተለያዩ የኖርዌጂያን የንግድ ድርጅቶች ጋር ተገናኝተው ለመወያየትና ፓሮግራም ተይዟል፥፥
ዝግጅቱ የሚደረገው በሃሙስ ኦክቶበር 16/2014 ከ 09:00-11:30 ሲሆን ከ11፥30—12፥30 የምሳ ፕሮግራም ይኖራቸዋል፥ በመሆኑም ውድ ኢትዮጵያውያን በኖርዌይ በሙሉ እንድታውቁትና በንቃትእንድትከታተሉ እናሳስባለን፥፥
አድራሻው Confederation of Norwegian Enterprise (NHO) ማለትም Næringslivets Hus
Middelthuns gate 27
Majorstuen, Oslo ሲሆን ተጨማሪ መረጃ በቅርብ ቀን
ለበለጠ መረጃ፥ http://norwegianafrican.no/news/16th-of-october-invest-in-ethiopia-seminar-in-oslo
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

”እናመሰግናለን አሜሪካ!” Thank you America! ኢትዮጵያውያን ዛሬ በዋሽግተን ዲሲ በሰልፍ ወጥተው ያሰሙት ድምፅ

$
0
0

የጉዳያችን አጭር ጥንቅር

Ethio-America flag 1ኢትዮጵያውያን ዛሬ መስከረም 27/2007 ዓም (ኦክቶበር 7/2014) ዋሽግተን ላይ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር (ስቴት ዲፓርትመንት ) ፊት ለፊት ተሰለፉ።ሰልፉ ባለፈው በዋሽግተን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኢትዮጵያውያን ላይ የተኮሰውን የኤምባሲ ሰራተኛ ከሀገር በማስወጣቷ አሜሪካንን ለማመስገን ሲሆን በሰልፉ ላይ ግለሰቡ የተኮሰበት ሽጉጥ አሁንም በኤምባሲው ውስጥ መገኘቱ እና ምርመራው ወደ አምባሳደር ግርማም እንዲዞር ይጠይቃል።በሌላ በኩል በወገኖቹ ላይ የተኮሰው ግለሰብን በመደገፍ እና ወደ ኤምባሲ የገቡትን ተቃዋሚዎች በመቃወም የተሰለፉትን ከዋሽግተን አትዮጵያ ኤምባሲ እና ከሌሎች ቦታዎች የአውቶብስ ተከፍሎላቸው የመጡ ሰልፈኞች ታይተዋል።በተለይ የስርዓቱ ደጋፊዎች ተሰላፊዎች ለመፈክር መፃፍያ እና ለአውቶብስ ከ2000 ዶላር በላይ ወጪ መደረጉን መረጃ እንደደረሳቸው በተቃዋሚ በኩል ከተሰለፉ ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያ ወቅታዊ የመወያያ መድረክ (ECADF) የቀጥታ ስርጭት ገልፀዋል።

በሰልፈኞች ላይ የተኮሰውን ደግፎ የሚሰለፍ የሰው ልጅ ይኖራል ብለው ያልገመቱት የአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት ሰራተኞች በወገኖቹ ላይ የተኮሰውን ግለሰብ በመደገፍ የወጡትን በመገረም ተመልክተዋቸዋል።በአሜሪካ ሕግ ጠለላ ውስጥ ያለ ሰው እንዲህ በወገኖቹ ላይ የተኮሰ ሰውን ደግፎ ይወጣል ብለው አሜሪካኖቹ ፈፅመው ያልገመቱት የስቴት ዲፓርትመንት ሰራተኞች ቢገረሙ አይገርምም።በነገራችን ላይ በወገኖቹ ላይ የተኮሰው የኤምባሲ ሰራተኛ ላይ የአሜሪካ አቃቢ ሕግ የክስ ወረቀት ማውጣቱን ዛሬ ”ዘሀበሻ” በድረ-ገፁ ገልጧል።

በመጨረሻም ሰልፈኞቹ በመጪው ቅዳሜ የዓለም ባንክ ፊት ለፊት ለሌላ ሰልፍ ለመገናኘት ተቀጣጥረው ተለያይተዋል።በዓለም ባንክ ፊት ለፊት በመጪው ቅዳሜ የሚደረገውን ሰልፍ ዓላማ ለኢትዮጵያ ወቅታዊ የመወያያ መድረክ (ECADF) የገለፁት አንድ የሰልፉ አስተባባሪ እንደተናገሩት ” እኛ ለኢትዮጵያ ብድር አይሰጥ አንልም።ብድሩ ይሰጥ። ነገር ግን ወያኔ እጅ እንዳይገባ እና ለሙስና እንዳይጋለጥ ከፍተኛ ቁጥጥር ይደረግ” የሚል ጥያቄ ነው ለዓለም ባንክ የምናቀርበው ብለዋል።

ጉዳያችን
መስከረም 27/2007 ዓም (ኦክቶበር 7/2014)

በዋሽንግተን ዲሲ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የአሜሪካ መንግስት የወያኔውን ባለስልጣን ከሃገሩ በማባረሩ የተሰማቸውን ደስታ ለመግለጽና ለማመስገን ከወጡት ሰልፍ (ቪድዮ)

$
0
0

በዋሽንግተን ዲሲ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የአሜሪካ መንግስት የወያኔውን ባለስልጣን ከሃገሩ በማባረሩ የተሰማቸውን ደስታ ለመግለጽና ለማመስገን ከወጡት ሰልፍ ተጨማሪ ቪድዮ

wee

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live