Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ጋዜጠኛ መልካም ሰላም ሞላ ከሀገር ተሰደደች

$
0
0

melkamበማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ለጥያቄ ትፈለጊያለሽ በሚል ጥሪ የደረሳት የቆንጆ መጽሔት ዋና አዘጋጅ በጥሪው መሰረት የሚደርስባትን እስርና መንገላታት በመስጋት ጷጉሜ 4 ቀን 2006 ዓ.ም ከሀገር መሰደዷ ተረጋግጧል መንግስት በሀገሪቱ የነጻው ፕሬስ ላይ እያደረሰ ያለውን ማሳደድ ተከትሎ በነሐሴ ወር 2006 ዓ.ም ብቻ 21 የግሉ ፕሬስ ጋዜጠኞች ከሀገር መሰደዳቸው ተረጋግጧል።

ከዚህ ዜና ጋር በተያያዘ ቅዳሜ ጷግሜ 1ቀን 2006 ዓ.ም ታትሞ ለንባብ የበቃውን የቆንጆ መጽሔትን ያተመው ማተሚያ ቤት በመንግስት ባለስልጣናት መታሸጉ ለማወቅ ተችሏል:: መንግስት በጋዜጠኞቹ ላይ እያደረሰ ያለውን ማሳደድ አለም አቀፍ ተቋማት እያወገዙት ሲሆን መንግስትም እስራቱንና ማሳደዱን ቀጥሎ የሎሚ፣የፋክት፣የአዲስ ጉዳይ ጋዜጠኞች የፍርድ ውሳኔ ተከሳሾቹ በሌሉበት መስከረም 8 ቀን 2007 ዓ.ም እንደሚሰጥ ታውቋል

↧

↧

በሃገራችን እውነት እና የሚሰራ ሰው አይወደድም፤ መፈራረጅ የትግል ስልት አይደለም

$
0
0

ናትናኤል መኮንን ( NATI MAN ) ስዊዘርላንድ

ኢትዮጵያውያን በያዝነው አምባገነንነትን የማውደም ትግል ውስጥ እያንዳንዱ ዜጋ የራሱ ድርሻ እንዳለው የማይካድ ሃቅ ነው ። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በእኛ ሰዎች ዘንድ አንድ ችግር አለ ፡ አንድ ሰው በራሱ አስተሳሰብ የሚሄድ ከሆነ እውነታን ይዞ አንገቱን ሰብሮ የሚታገል ከሆነ አንዱ ለአንዱ ለምን አላጎበደደም እንደኛ ለምን አላሰበም ለምን አስተሳሰቡን ጻፈ በሚል በከፍተኛ ፍጥነት ጥላቻ ይንጸባረቅበታል ይፈረጃል። እያንዳንዳችን ሰዎች የራሳችን አስተሳሰቦች እና አመለካከቶች አሉን፡፤ አስተሳሰቦቻችንን እና አመለካከቶቻችንን ደሞ የማንጸባረቅ መብት አለን፡፤ የግዴታ ለማንም ተገዢ አንሆንም አሁን እየታገልን ያለነው በ እምቢተኝነት ጭቆናን ነው። ሌላ ጭቆና በነጻው የማህበራዊ ድህረገጽ ላይ እንዲግውጥመን አንፈልግም፡፤ ሌላው ደም ሰዎች ከኛ በመረጃም ይሁን በአጻጻፍ ዘይቤ በልጠውን ሲገኙ አይናችን ደም የሚለብስበት ምክንያት አይገባኝም ። መከባበር ሲገባን የሰውን አስተሳሰብ ማክበር እና መተራረም ሲገባን ብድግ እያልን ሰውም መጠራጠር መፈረጅ መሳደብ መዝለፍ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት አሊያም የትግል ስልት አይደለም።
Tensaye
በየድህረገጹ የሚጽፉ ሰዎችን ቃላት እየሰነጠቁ ነገር እየፈለፈሉ ለማሳጣት መሞከር እና መታገል ለየቅል የሆነ እና የማይገናኝ ነገር ሆኖ ሳለ የፖለቲካ እውቀቱ እና ብስለቱ የሚያጥራቸው ጥቂት ሰዎች የማይታወቅ ጅራፋቸውን ታግለው በሚያታግሉ ሰዎች ላይ ሊሰነዝሩ ሲንደፋደፉ ይታያሉ። ሰዎች ሁሉ እንደ ተቃዋሚ ድርጅት አሊያም እንደ ተቃውሚ ግለሰብ ሆነን ስንሽከረከር እንደና ካላሰበ እኛን ካልተከተለ የኛን ካለጠፈ እሱ ተቀብሮ እኛ ካልታየን የሚሉ ከሆነ ይህ ትግል ለሃገር እና ለህዝብ ሳሆን ለስም እና ለዝና የሚደረግ መሆኑን በግልጽ ያሳያል። ሰዎች የራሳቸውን መረጃም ይሁን ጽሁፍ ይዘው ሲመጡ ልናከብርላቸው ሲገባ ባንቀበለውን ባንስማማበትም መፈረጅ እና ማሳጣት አሊያም ትግሉን ሽፋን በማድረግ መዝለፍ አያዛልቅም። በአሁን ሰአት የሚደረጉ ዝባዝብንኪ የዘለፋ እና የትችት ተግባራት የትም የማያደርሱ እና ጭራሽ ትግሉን የሚገሉ መሆኑን ልናውቅ ይገባል። በተጨማሪም ሰዎች በጃቸው ያለውን የፖለቲካ መረጃ ደራርበው የሚያወጡት ከሆነ ትግሉን እንደሚገል እና እንደሚያጠፋ በግልጽ ለመመስከር የምንገደድበት ወቅት ላይ መድረሳችን በማይረቡ ሰዎች ትግሉን የማኮላሸት ሂደትን መጋበዝ አንዱ ስህተት ሆኖ ይሰማኛል። ፖለቲካ ማለት ጥንቃቄ የሚፈልግ እና የትግል ስልትን የማያዳከም ታላቅ ድል የሚሻ ጉዳይ ነው።

ይህንን ከግንዛቤ የማያስገቡ ሰዎች የግለሰቦችን ዱካ እና አረፍተ ነገር እየተከተሉ በቃላት ስንጠራ ላይ ከተሰማሩ ትግሉን ማን ይታገል ? ዘለፋ ላይ ካተኮርን ትግሉን ማን ይታገል ? በቂ ማስረጃ እና መረጃ ሳንይዝ እከሌ ላይ እንዲህ ይሁን እከሌ እንዲህ ነው ምናምን እየተባለ በስም ማጥፋት ላይ የምንሰማራ ከሆነ ህዝቡ በነቃ ጊዜ መግቢያ ቀዳዳ እንድሚጠፋን ካሁኑ ማሰብ ያስፈልጋል። ተቃዋሚ ነን የሚሉ ሁሉ በአጋር ተቃዋሚዎች ላይ የከፈቱት ዘመቻ እስካሁን ምን ያህሉ እንደተሳካ በተቃዋሚ ግለሰቦች ላይ የከፈቱት ስም ማጥፋት ምን ያህሉ እውነት እንደሆነ በቂ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እውነተኛ ሰው የለም። ያሌለ ነገር ከመዘባረቅ እና የግለሰብ ማንነትን በሃሰት ከመበከል እንዲሁም ባልበሰለ የፖለቲካ ግምት ሰዎችን ከማሳጣት ውጪ ለትግሉ ምንም አልፈየደም። ምንም እድገት አላመጣም።

ትግሉን እንዴን ማሳካት እንችላለን? አሁን ካለበት እንዴት ልናሳድገው እንችላለን ? ምን መርዳት አለብን ? ምን መተባበር አለብን ወዘተ የሚሉ ተመሳሳይ ጥያቄዎችን ይዘን ህዝብን ማነቃቃት ህዝብን ማስተማር ለለውጥ ማነሳሳት ሲገባን የግለሰቦችን ዱካ እየተከተልን ስም ማጥፋት እና መነካከስ መፈራረጅ በህዝቡ ዘንድ ያለውን ተቃዋሚዎች አይረቡም ተነካካሾች ናቸው እርስ በርሳቸው ሳይስማሙ እኛን እንዴት ይመሩናል የሚለውን አስተሳሰብ እያሰፋ እንጂ እያጠበብ አይሄድም። ስለዚህ የግለሰቦችን ስም ማጥፋት እና መዘርጠጥ የማይሆን ስም መስጠት ታፔላ መለጠፍ ለትግሉ ምንም አይፈይድም።የሚሰደቡት ሰዎች በጥንካሬ በርትተው እያየናቸው እንጂ እንድ ተስአድቢዎች ሲከስሙ አላየንም ፡፤ የሚሰደቡ ሰዎች መረጃዎቻቸው እውነት ሆነው ሲገኙ እንጂ ሲያፍሩ አላየንም። ስለዚህ ይህ መፈራረጅ እና መዘላለፍ ቆሞ በጋራ ለትግሉ አስታውጾ ማበርከት አለብን ። ሊታሰብበት የሚገባ አቢይ ጉዳይ ነው።

↧

“የይቅርታ ልብ ያስፈልገናል”–አዲሱን ዓመት በማስመልከት በስደት ከሚገኘው ሲኖዶስ የተላለፈ መልዕክት

$
0
0

holy sinod excileበፓትሪያሪክ አቡነ መርቆርዮስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ አዲሱን ዓመት በማስመልከት ባስተላለፈው መልዕክት አዲሱን ዘመን አዲስ መፍትሄ የምንፈልግበት ዘመን ልናደርገው ይገባል አለ። ቅዱስ ሲኖዶሱ ለዘ-ሐበሻ በላከው የአዲስ ዓመት መግለጫው “ብዙዎቻችን በልዩነቶቻችን ምክንያት በጥላቻ ስሜት ውስጥ ነን። ለዚህ የይቅርታ ልብ ያስፈልገናል። የቀድሞ አባቶቻችን በይቅር ለእግ ዚአብሔር ላይ የተመሰረተ ይቅርባይነት ብዙ ለውጥ ያመጡ ነበር። ‘በቀል የኔ ነው ያለውን አምላካዊ ቃል መሰረት አድርገው ጥላቻን ሳይውል ሳያድር ከመካከላቸው እያስወገዱ አንድነታቸውን ጠብቀው ኖረዋል” ብሏል።

ሙሉ መል ዕክቱን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

↧

“2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ መፃዒ እድል የሚወሰንበት ዓመት በመሆኑ ሁላችንም በተነሳሳ የአርበኝነት መንፈስ እንቀበለው”–ግንቦት 7

$
0
0

2007 ወሳኝ የትግል ዓመት!!!

የግንቦት7 በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የበተነው ጽሑፍ

ሁለት ሺህ ስድስት ዓመተ ምህረት ለኛ ለኢትዮጵያዊያን በአብዛኛው በመጥፎ የሚታወስ ዓመት ነው። 2006፣ በመካከለኛው ምስራቅም ሆነ በአፍሪቃ በስደት ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ስቃይ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰበት ዓመት ነበር። 2006፣ ቀደም ባሉ ዓመታት አገራቸዉን ለቅቀዉ የተሰደዱ ሳይደላቸው በርካታ አዳዲስ ስደኞች ከአገር ወጥተው በበረሃዎችን ቀልጠው፤ በባህር ሰጥመው ያለቁበት አሳዛኝ ዓመት ነው። 2006፣ ጥንቃቄ በተሞላበትና በተቆጠበ መንገድም ቢሆን የተቃውሞ ድምጽ ያሰሙ ወገኖቻችን ወደ እስር ቤቶች የተጋዙበት ዓመት ነው። 2006፣ በአምቦ፣ በለቀምት፣ በጅማ በሀረር በርካታ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተገደሉበት፤ በአስር ሺዎች የሚገመቱት ደግሞ የታሰሩበት ዓመት ነው። 2006፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በቤንሻንጉል፣ በጋምቤላ፣ በአዲስ አበባና አካባቢው በ100 ሺዎች የሚገመት ኢትዮጵያዊ የተፈናቀለበት ዓመት ነው። 2006 ቁጥራችው ቀላል ያልሆኑ የነፃነት ታጋዮች ከጎረቤት አገራት ታፍነው ወደ እስር ቤቶች የተጋዙበት ዓመት ነው። 2006 የንቅናቄዓችን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በጉዞ ላይ እያለ በትራንዚት አውሮፕላን ለመቀየር ባረፈበት በየመን ዋና ከተማ ሰንዓ በየመን መንግሥት ወንበዴዎች ታፍኖ ለሸሪካቸው ህወሓት በህገወጥ መንገድ አስተላልፈው ለስቃይ እንዲዳረግ የተደረገበት ዓመት ነው። በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ነው 2006 “ጥቁር ዓመት” የሚል ስያሜ ያገኘው።
ginbot 7
ጭንቅላት የሚባል ነገር ያልፈጠረባቸው ድኩማን ሰላዮችና ፈንጋዮች የመጨረሻውን የመንግሥት ሥልጣን የያዙበትና ውሳኔያቸው “እሰረው፣ ክሰሰው፣ ግረፈው፣ ግደለው …” ብቻ የሆነበት ዓመት መሆኑ የ2006 ልዩ መታወቂያው ሆኖ ይቆይ ይሆናል። ይሁን እንጂ በ2006 ጨለማ ውስጥ የታዩ የብርሃን ጨረሮችም እንደነበሩና እንዳሉም መርሳት አይገባም።

በሁለት ሺህ ስድስት ዓመተ ምህረት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመቸውም በላይ በህወሓት አገዛዝ አምርሯል፤ በሁለገብ ትግል የህወሓትን አገዛዝ ለመፋለም የቆረጡ ወገኖች ትብብር ተጠናክሯል። በ2006፣ ኢትዮጵያ ዉስጥም ከኢትዮጵያም ውጭም የንቅናቄዓችን የግንቦት 7 ድርጅታዊ መዋቅር ተጠናክሯል። በ2006፣ ከህወሓት አገዛዝ ጋር ያለው መፋጠጥ ከሯል። እነዚህ ሁኔታዎች 2007 አገራችን በለውጥ ማዕበል የምትናጥበት ዓመት ሊሆን እንደሚችል ያመለክታሉ።

በአዲሱ ሁለት ሺህ ሰባት ዓመተ ምህረት፣ የግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎች ትልቁ ሥራ ድርጅታዊ አቅምን ማጎልበት ነው። በተለይ ወጣቶች በአምባገነን ሥርዓቶች ውስጥ ሕዝባዊ የትግል ድርጅቶችን እንዴት መመሥረት እንደሚቻል ማጥናት እና መፈተሽ ይኖርባቸዋል። ትናንሽ የግንቦት 7 ድርጅታዊ ቋጠሮዎች በመላው አገሪቱ መሠራጨት ይኖርባቸዋል። ወጣቶች ትናንሽ ኢ-መደበኛ ስብስቦችን ቶሎ መፍጠር እና አደጋ ሲያጋጥም ቶሎ ማፍረስ መልመድ ይኖርባቸዋል። ይህንን ክህሎት ደግሞ በቀጥታ ከሌሎች አገራት ከመዋስ ሀገር በቀል ቢሆን ይመረጣል።

በሁለት ሺህ ሰባት ዓመተ ምህረት፣ የጽዋ ማኅበሮች፣ መድረሳዎችና ጀማዎች፣ የስፓርት ቡድኖችና ደጋፊዎች፣ የመንደር ደቦዎችና የቡና ተርቲቦች፣ ስም ያላቸውም፣ ስም የሌላቸውም ስብስቦች የግንቦት 7 አባላት መገናኛዎች ይሆናሉ። በ2007 የግንቦት 7 አባል መሆን የምርጥ ዜግነት ምልክት መሆኑ በስፋት ተቀባይነት የሚያገኝበት ዓመት ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። በ2007 በህወሓት ካድሬዎች “ሽብርተኛ” መባል የሚያስደስትና እንደ ሽልማት ተደርጎ የሚወሰድበት ዓመት ይሆናል ብለንም ተስፋ እናደርጋለን። በ2007 እስር ማስፈራሪያ መሆኑ ያከትማል። በ2007 የኢትዮጵያ ወጣቶች በአርበኝነታቸው ይታወቃሉ። በ 2007 እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የህወሓት ሹማንምትን ዘረፋ የሚያጋልጥበት ዓመት ይሆናል። 2007 ዳኞች “እንቢ፣ በሀሰት አንፈርድም”፤ የመንግሥት ጋዜጠኖች “እውነቱን ደብቀን አንዋሽም”፤ ፓሊሶች “ወገናችንን አንደበድብም፣ አናስርም፣ አንገርፍም”፤ ወታደሮች ደግሞ “በወገናችን ላይ አንተኩስም” የሚሉበት ዓመት ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

በዚህም ምክንያት 2007ን የምንቀበለው በታላቅ ተስፋና ዝግጅት ነው። በ 2007 ነፃነትና አምባገነንነት፤ ዘረኛነትና አንድነት፤ እውነትና ውሸት፤ አድርባይነትና አርበኝነት፤ ዝርፊያና ንጽህና፤ ድህነትና ብልጽግና የሚፋጠጡበት ዓመት ይሆናል ብለን እንጠብቃለን። በአጭሩ 2007 የወሳኝ ትግል ዓመት ይሆናል።

ሁለት ሺህ ሰባት ዓመተ ምህረት፣ የኢትዮጵያ መፃዒ እድል የሚወሰንበት ዓመት በመሆኑ ሁላችንም በተነሳሳ የአርበኝነት መንፈስ እንድንቀበለው ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ጥሪ ያደርጋል።

መልካም አዲስ ዓመት!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !

↧

የማለዳ ወግ …በዓሉ በጆሲ ደምቆ ተሸኘ ! * ዝክረ አለባቸው ተካ እና የጆሲ ድንቅ ስራ …

$
0
0

ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ

* ዝክረ አለባቸው ተካ እና የጆሲ ድንቅ ስራ …
* የልጅ አዋቂው ጆሲ እናመሰግንሃለን …
ጆሲ በ2007 ዓም አዲስ አመት ልዩ ዝግጅቱ ታዋቂው ድንቅ ኮሜዲያን አለባቸው ተካን በተገቢ መንገስ አዘከረው ። አርቲስት አለባቸው ተካ ድንቅ ኮሜዲና የመጀመሪያ ቶክ ሾው አቅራቢ ነበር ። አለቤ በተለይም በኢቲቪ የቶክ ሺው ዝግጅቱ በርካታ አርአያነት ያለው ስራዎችን የሰራ ታላቅ ወንድም ነበር ። አርቲስት አለባቸው ተካ ሰርግ ሰርጎ ከአቅመ ደካማ ድሃ ወገኑን በማብላት በማጠጣት ደስታ አለኝታነቱን አሳይቶ ፣ አርአያነት ያለው ስራ ሰርቶ ያሳየን ብቻኛ አርቲስትም ነበር። ለራሱ ሳይኖር ለሌሎች ኢትዮጵያን ለሚወዱ በተለይም ለድሆችና ለከፋቸው የቆመ ወንድም ነበር ። በድንገተኛ አደጋ አለፈ ፣ አዘንን ! እሱ ካለፈ በኋላ ግን እሱን የሚያስታውስም ሆነ የእሱን ቤተሰቦች የሚደግፋቸው አልነበረም ።

ጆሲ ግን አለቤን አልረሳውም ። በወዳጆቹ አማካኝነት ቀን ዘንበል ያለባትን የአለባቸው ተካ ቤተሰቦች አገኘ። በመጀመሪያ ያገኛት ታናሽ አህቱን አህት የሻሸወርቅን ነበር ። ጆሲ ፕሮግራሙን ሲጀምር በተረካው እንደሰማነውና እንዳየነው የአለቤ እህት የሽዋወርቅ በአነ ድምጻዊ ግርማ ተፈራ ድጋፍ በአንድ መዝናኛ ቡና ማፍላት ስራ ወደ ጀመረችበት ቦታ ሄዶ ተዋወቃት !
alebachew teka

alebachew teka 2
ይህ እየተከታተልኩ ፣ አሁን የአዕምሮ በሽተኛ የሆነው ሌላው ከልታማ ታዋቂ ኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ ታወሰኝ ! ልመንህ አሜሪካ በስደት ሲኖር አዕምሮው ተነክቶ ፣ ሀገር ቤት ከገባ አመታት መቆጠራቸውን ሰምቻለሁና የዚያ ዘመኑ ፈርጥ ጥርስ የማስከድነው ፣ ዛሬ ከንፈር የሚመጠጥለት ኮሜዲያን ልመንህ ታወሰኝ ! ልመንህ አሁንም አዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎች እየተንከራተተ ይሆን? … ሰብሳቢ ደራሽ አጥቶ እንደነበር ባውቅም ዛሬ ሰብሳቤ ደጋፊ አግኝቶ እንደሁ አላውቅም … በልመንህ ህይወት የጀመርኩት በተመሳሳይ ሁኔታ የሚነወከራተቱ ደራሽ ደጋፊ ያጡ ቀን የዘነበለባቸው ጋዜጠኛ ሰሎሞንን ጋዜጠኛ ዳሪዮስ ሞዲን ፣የጥበብና የስፖርት ሰዎች አሰብኳቸው ! ሁሉም ለዚህች ሃገርና ህዝብ የድርሻቸውን ሲወጡ አጨብጭበንላቸው ፣ ሲደካክሙና ቀን ሲዘነብልባቸው የረሳናቸው ግፉአን ናቸው!

… እንዲህ የተረሱ ወገኖችን ከያሉበት እያስታወሱ ድጋፍ ትብብር እንድናደርግ ትልቁን ስራ አየሰራች ያለችው የኢቢኤስ “አርአያ ሰብ ” ዝግጅት መሪ ጋዜጠኛ ህሊና አዘዘ ብዙ የተረሱና በአዲሱ ትውልድ የማይታወቁ የሃገር ባለውለታዎች የማስተዋቀቋን ድንቅ ስራ አስታወስኩ ። ጋዜጠኛ ህሊና እንዲህ ህይወትና የቀደሙ የተደበቁ ማንነቶችን እያሳየች ማስተማሯን በቀጠለችበት አጋጣሚ የጆሲ ኤንድ ሃውስ አስደማሚ ዝግጅት ቀጥሏል! በዛሬው ዝክረ አለባቸው ተካ ዝግጅት ቀልቤን ከነጎደበት መለሰው …አናም ቀልቤን ከሄደበት መልሸ ወደ የጆሲ ልዩ የዓውዳመት ልዩ ዝግጅት አቀናሁ … !
ጆሲ ባማረው መኖሪያ ቤቱ ባቀረበው ዝግጅት ከእህት የሻበወርቅ ተካ ጋር ሰፋ ያለ ውይይት ስለአለባቸው የልጅነት ህይወት አስተሳደግ ፣ ለወገኖቹና ለቤተሰቦቹ ሲደግም እስከተቀጠፈበት ድረስ የራሱ መኖሪያ ቤት አለመስራቱን ሃብት አለማካበቱን ፣ በሚወደው መኪና መንዳት አደጋ በመጨረሻው በድንገት ማለፉን መራራ መርዶ ፣ በህልፈቱ መርዶ ይደግፍ ይረዳው የነበረ ወንድሙ በድንጋጤ መሞቱን ድርብ ሃዘን ፣ ከዚያም የቤተሰቡ ደጋፊ አልባ መሆን ፣ የሚረዳቸው የወንድሙ ልጆች ትምህርት ሳይቀር ማቆማቸውን ፣ የአንዱን ወጣት የታክሲ ደላላ መሆን ፣ ለአቅመ አዳም የደረሰቸው ያንዷ ጉብል በድህነት የተደቆሱ ቤተሰቦችን ለመደገፍ አረብ ሃገር ለመሄድ አስባ መንገዱ በመዘጋቱ ትምህርቷን በችግር ተከባ መቀጠሏን ፣ የአለባቸው የወዳጅ የስራ ባልደረቦች የተባሉትን ይህ ሁሉ ሲሆን ይህ ነው የሚባል ደጋፍ አለማድረጋቸውን ፣ እንደ ወ/ሮ አሚና ያሉት ጎረቤቶች ለየሽወርቅ ያደረጉት ድጋፍ ሁሉንም ልባችን በሃዘን እየተሰበረው አሳዛኝ ያልሰማነውን ታሪክ ከእህቱ ጋር በአቤቱ ከአለቤ ወንድም ባለቤት ጋር ቁርቁስ ካለው ቤት ደጃፍ የሆነውን ሰማን !

አጠር ላድርገው …ጆሲ ከሃዘን ትካዜው ያወጣነወ ዘንድ እንደዋዛ ወደ ሙዚቃው ዝግጅት ልውሰዳችሁ ብሎ በአስገራሚና ባልተጠበቀ አቀራረብ ለአለቤ እህት አለ የተባለ የኮስሞቲክ ሱቅ ቁልፍ አስረከባት ! ስጦታው ጎረፈ …ያዘነ የተከዘ ልባችን ትፍስህት አገኘች …እኒያን የጨለመባቸው የአለቤን ወንድም እናት ሳናስበው አመጣና እሳቸውንም በሚያስደንቅ ስጦታ አንበሻበሻቸው! በችጋር የተጠበሱ ፣ ያዘኑ ፣ የተከዙ ፣ ተስፋ የጨለመባቸውና የተጨነቁት የአለባቸው ቤተቦች ብቻ ሳይሆን እኛም የጆሲ ታዳሚዎች በጆሲ በጎ ምግባር የምንይዝ የምንጨብጠው አጣን !
jossy gebre
ጆሴ ሌላም እንግዳ ነበረው … ሌሎች ያደገችው ሃገር ግፉአን ! አበባና ሮቤል ድሃ አደግነታቸው ሳያንስ ኤች አይ ቪ ተጠቂዎች ናቸው ፣ የደሃ የጀርባ አጥንቱን ያሳየን የጆሲ የክበር እንግዶች ሆኑ ! ልዩ የድጋፍ ገጸ በረከት ተበረከተላቸው። ዝርዝሩን ለወተወው … ትምህርት ያቆመችው አበባ ትምህርት እንድትቀጥል ስጦታ ተበረከላት ፣ ለሮቤልም እንዲሁ : ) ጆሲ ከሜሪ ጆር ፣ ከዳሸን ፣ ከመድሃኒአለም ሞል እና ከቀሩት በጎ አድራጊዎች ጋር በመተባበር ጆሲ ድጋፉን በማቀናጀት በስጦታና በተቆራጭ ሁሉንም ተገፊወች አንበሸበሿቸው: ) ልዩ የአውደ አመት ስጦታ: )
ጆሲ ስለተደረገው ነገር ሁሉ አመሰገነ ! የድጋፍ ትብብር ሲጠይቅ አሻፈረኝ ስላሉት ሲናገር አንረዳም አንሰጥም ማለታቸውን ባይኮንነውም “ለካስ ለመስጠትም መሰጠት አለበት!” ሲል የተናገረው ታላቅ መልዕክት ንፉጎች ልብ ብለን ልንሰማው የሚገባ ቀዳሚ ቁምነገር ነበር ! ከገባን …
ዝግጅቱ ወደ መጠናቀቁ ተቃረበ …ክብር እንግዶቹ የአውደ አመቱን ኬክ ቆረሱ ፣ አልቅሰው ታሪካቸውን ነግረው ልባችን ሰብረው ያሳዘኑን የአለቤ ቤተሰቦ በአሉን በደስታ እየጨፈሩ ብሩሁን መጭ ጊዜ ይቀበሉ ቀን ከፈጣሪ በታች ብልሁ ጆሱ የአንበሳውን ድርሻ ያዘ ፣ ዝግጅቱ ተከወነ ! …
እንዲህም አልኩ ..ጆሲ ጧሪ የሌላቸውን በሚደግፈው መቅዶንያን ባቋቋመው ወጣት እና በመሰሎቹ እጹበ ድንቅ ምግባር ስንደመም ለከረምነው ባሳየህን ፋና ወጊ በጎ ምግባር ኮርተናል : ) በጥቁቷ እንኳ ለበጎ ምግባር ሳይሰለፉ “ሃብታችን ህዝብ ነው! ” እያሉ በሚያደነቁሩን በሃገሬ ጥበብ ባለሙያዎች የታመምን ብዙዎች ባንተ በወጣቱ ድምጻዊና የተዋጣልህ ቶክ ሾው አዘጋጅ እውነተኛ የህዝብ ሃብትነትም ኮራን! ይብላኝ ለሆዳሞች … በእጅጉ እንኮራን እወቀው አልሃለሁ !

እንዲህም ሆነ …ዝግጅትህ እየተላለፈ እያለ በርካታ መልዕክቶች ደረሱኝ …በምኖርበት አረብ ሃገር ሳውዲና በቀረው አለም የሚገኙ ወዳጆቸ በሰራህው ድንቅ ሰብአዊ ስራ ተማርከው እርዳታና ድጋፍ የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸውልኛል! በጎ ሃሳብ ነው አልኳቸው ! ዳሩ ግን ያንተን አላማ ለመደገፍ እሰክንደራጅና እስኪሳካ ቢያንስ የተሳካልን በአረቡ አለም ያለን ወገኖች በአጠገባችን ከአፍንጫችን ስር የሚንከራተቱ የተቸገሩትን የኮንትራት ሰራተኞች በመደገፉ ሰብዕናችን እናሳይ ማለት ወደድኩ! ብቻ በአመት በአሉ ልዩ ዝግጅት ጆሲ ባንተ ደምቀናል !
በአሉ በአንተ በጆሶ ኤንድ ሾው ልዩ ዝግጅት ደምቆ ተሸኘ !

የልጅ አዋቂው ጆሲ እናመሰግንሃለን !
መልካም በዓል!

↧
↧

Health: ለወሲብ ህይወትዎ ፀር የሆኑ 5 የጤና ችግሮች

$
0
0

አገርና ድንበር ሳይወስነው በሰው ልጆች ሁሉ የሚፈፀመውንና የትልቅ ጉድኝት መገለጫ የሆነውን ወሲብ አስቸጋሪ የሚያደርጉ እና የደስታና እርካታ ምንጭ እንዳይሆን የሚያደርጉትን የጤና ችግሮች ከነመፍትሄያቸው የቅርብ ጊዜ ጥናቶችን ዋቢ አድርገን አሁን እንቃኛለን፡፡

- ጥናቶቹ ምን አሉ?
– ስኳር ህመም እና ሴክስ
– ከፍተኛ የደም ግፊት ከወሲብ ይገፋዎታል
– ከፍተኛ የደም ግፊት ሴቶችንም ከእርካታ ያርቃል
– ኮሌስትሮል የሴክስ ጠር ይሆን?
– የህይወት ውጣ ውረዶች እና የወሲብ ህይወትዎ


‹ጤንነት› ሲባል የሁሉንም የሰውነት ስርዓት እና አካላቶቻችን እንደመሆኑ የወሲብ ህይወታችን ጤንነትም ገሸሽ የሚደረግ አይደለም፡፡ የተሰካ የወሲብ ህይወት የሌላቸው ጥንዶች ደስታቸው ሙሉ ይሆናል ማለት አስቸጋሪ መሆኑም ሀቅ ነው፡፡ የሰዎችን የወሲብ ህይወት አስቸጋሪ የሚያደርጉና ከተጣማሪያቸው ሊያራርቋቸው የሚችሉ በርካታ የጤና ችግሮችን ባለሞያዎች ያነሳሉ፡፡ እነዚህ ችግሮች አዕምሮ መልካም ሁኔታ ላይ ካለመገኘቱ አሊያም በአካላዊ ህመሞች ምክንያት የሚመጡ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በርከት ላሉ ሰዎች የተቃና የወሲብ ህይወት ማጣት እና እርካታ የለሽ ጉድኝት በሚዳርጉት ችግሮች ላይ ትኩረት አድርገናል፡፡

ጥናቶቹ ምን አሉ?

sexual-problems
‹‹የበርካቶችን የወሲብ ህይወት የሚያናጉ በርካታ የጤና ችግሮች በመላው ዓለም የታወቁ ቢሆንም ችግሩን ወደ ሐኪም ቀርበው የሚያስረዱና መፍትሄው የሚፈልጉላቸው ሰዎች በጣም ጥቂት በመሆናቸው የየሰዉ የጓዳ ችግር ሆነው ቀርተዋል›› ይላሉ በኒው ኢንግላንድ ጆርናል ኦፍ ሜዲስን ይህንን በተመለከተ ጥናታቸውን ያሰፈሩት ዶ/ር ስቴሊ ቴስለር፡፡
በዚህ የምርምር መፅሔት በቀረበው ጥናት 3 ሺህ ሰዎች ላይ በተደረገ ምልከታ በወሲብ ህይወታቸው ላይ ጤናቸው ችግር ማስከተሉን ከሐኪም ጋር ለመወያየት የፈቀዱ ወንዶች 38 ከመቶ ያህሉ ሲሆኑ 22 በመቶ ሴቶችም ወንዶቹን ተቀላቅለዋል፡፡ ‹‹ችግር አለ›› ሲሉም ምክር ፍለጋ ሄደዋል፡፡
በተለያዩ ጥናቶች ከተገኙና የአብዛኛዎቹ ሰዎች አስደሳች ወሲብ የመፈፀም ብቃት ከፈተኑ የጤና ችግሮች መካከል በደም ቧንቧ ላይ የሚከሰቱ ህመሞች፣ የስኳር በሽታ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት፣ ከመጠን ያለፈ ኮሌስትሮል፣ ድብርት እንዲሁም የሴቶች ማህፀንን የሚያጠቁ የካንሰር አይነቶች በበርካቶች ተጠቅሰዋል፡፡ ለተለያዩ በሽታዎች ተብለው የሚወሰዱ መድሃኒቶችም ከሚያስከትሏቸው የጎንዮሽ ጉዳቶች መካከል አንዱ ወሲብን አስቸጋሪ ማድረጋቸው በባለሞያዎቹ የሚጠቀስ ነው፡፡ ከእነዚህ ሌላ በስራ የተወጠረ እና ለትዳር አሊያም ፍቅር ጓደኛ ጊዜን የማይሰጥ ሰው በወሲብ የመደሰት እድሉ ዝቅተኛ ነው ተብሏል፡፡ ሰላም የሌለው እና በጭቅጭቅ የተሞላ ጉድኝትም የወሲብ ህይወትዎ ፀር ተደርጓል፡፡

ስኳር ህመም እና ሴክስ

የስኳር ህመም በተለይ ሁለተኛው አይነት የስኳር ህመምን ተከትለው ከሚመጡ ተያያዥ ችግሮች መካከል የልብ ህዋሳትን መጉዳቱ፣ አይን፣ ኩላሊት እና የሌሎች አካላት ነርቮችን ማጥቃቱ በዋናነት ይነሳሉ፡፡ የወሲብ ህይወትዎስ ላይ? አዎን ችግር ያመጣል፡፡ በስኳር ህመም ምክንያት በደም ውስጥ የሚገኘው የስኳር መጠን በሚጨምርበት ወቅት በሚመጣው የነርቮች ጉዳት የወሲብ አካላትም የችግሩ ቀማሽ ይሆናሉ፡፡ ይህም የሚሆነው ለወንዶች በቂ የደም አቅርቦት ወደ ብልት እንዳይደርስ ይሆናል፡፡ ብልት በደም ካልተሞላ ደግሞ ሊወጠርና ሊቆም አይችልም፣ ለወሲብም አይዘጋጅም፡፡ በሳይንሳዊ አጠራሩ ‹‹ኤሬክታይል ዲስፊንክሽን›› ተብሎ የሚጠራው የብልት መወጠርና መቆም አለመቻል ችግር የስኳር ህመም ባለባቸው ወንዶች ላይ በበለጠ መታየቱን በርካታ ጥናቶች ማውሳታቸውም ይህን ያስረዳል፡፡

በደቡብ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የዩሮሎጂ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ዴቪድ ፔንሰን የጤና ችግሮች በወሲብ ላይ የሚያደርሱትን ተፅዕኖ ለወንዶች በመንገር ለጤናቸው የተሻለ እንክብካቤ እንዲያደርጉ መምከር ጥረታቸውን የበለጠ ውጤታማ እንዳደረገላቸው ይናገራሉ፡፡ ‹‹ወሲብ መፈፀም መከልከል ወይም ደባሪ ሴክስ መፈፀም የሚፈልግ ወንድ የለም፡፡ ስለሆነም ይህን ለማስቀረት ሲል የምትመክሪውን ሁሉ ይቀበላል›› ይላሉ፡፡ ‹‹ስኳር ህመም የአይን ብርሃንህን ሊያጠፋው ይችላል፣ ኩላሊትህ ይጎዳል የሚል ማስጠንቀቂያ ከሰጠኸው ታማሚ ይልቅ የስኳር መጠንህን ካልተቆጣጠርክ ከአሁን በኋላ ወሲብ መፈፀም አትችልም ብትለው ደንግጦ ጥንቃቄውን መተግበር ይጀምራል›› ሲሉ አክለዋል፡፡
የስኳር ታማሚ ከሆኑ በደምዎ የሚገኘውን ስኳር መጠን ከሐኪም ምክር ጋር ይቆጣጠሩ፡፡ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ይመገቡ፣ የአካል እንቅስቃሴም ያደርጉ፡፡ በሐኪም የተከለከሉትን ምግብም አይውሰዱ፡፡ ያለዚያ የወሲብ ህይወትዎ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሊወድቅ ይችላል፡፡ የወሲብ እርካታ በረከትንም መቋደስ አይችሉም፤ ያስቡበት፡፡

ከፍተኛ የደም ግፊት ከወሲብ ይገፋዎታል

ከመደበኛው በላይ የሆነ የደም ግፊት ለልብ ህመምና ስትሮክ አጋላጭ መሆኑን መቼም ያውቃሉ ብለን እንገምታለን፡፡ ወሲብ ከመፈፀም ጋር በተያያዘ ችግር ያመጣብኛል ብለው አስበውስ ያውቃሉ? በዚህ ዙሪያ ጥናቶችን ያደረጉ ባለሞያዎች ግንኙነታቸውን ይተነትናሉ፡፡ ‹‹ከፍተኛ የደም ግፊት የወሲብ ህይወትዎን ጤናማ ፍሰት ያደናቅፋል››
ከፍተኛ የደም ግፊት በወንዶች በሚኖርበት ጊዜ በሂደት የደም ቧንቧዎችን ግድግዳ ሽፋን በማጥቃት ቧንቧዎቹ (አርተሪዎች) እንዲጠጥሩ እና እንዲጠቡ ደም የማሳለፍ ብቃታቸውም በእጅጉ እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ በቂ ደም ወደ ብልት ካልሄደ ብልት መቆም ይቸግረዋል፡፡ ቢቆምና ወሲብ ቢፈፀም እንኳ የዘር ፈሳሽ (ስፐርምን) በመርጨት እና እርካታ በማግኘት በኩል አሉታዊ ተፅዕኖን ያሳድራል፡፡ ለተወሰኑ ጊዜያት በዚህ ሁኔታ ወሲብ ከፈፀሙ ከእርካታ ይልቅ የነበረው ችግር ይሆናል የሚታሰብዎት፡፡ በዚህ በመሳቀቅ ወሲብን ነፃ ሆነው ከመፈፀም ገሸሽ ይላሉ፡፡ ብዙም አይደፋፈሩም፡፡ ይህ ደግሞ በፈንታው ከፍቅር ጓደኛዎ አልያም የትዳር ጓደኛዎ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ቅሬታ ውስጥ መጣሉ አይቀርም፡፡

ከፍተኛ የደም ግፊት ሴቶችንም ከእርካታ ያርቃል

ከፍተኛ የደም ግፊት ሴቶችን የወሲብ ህይወት በምን መልኩ እንደሚጎዳ ጥርት ያለ የጥናት ውጤትን ማግኘት ባይቻልም እስካሁን የተደረጉ ምልከታዎች የደረሱባቸውን ውጤቶች እና ምክንያታዊ ግምቶች ያስቀምጣሉ፡፡ ከፍተኛ የደም ግፊት የደም ቧንቧዎች ላይ ተፅዕኖ በማሳደር በቂ የደም መጠን ወደ ብልታቸው እንዳይደርስ ያደርጋል፡፡ ይህ በአንዳንድ ሴቶች ላይ ለወሲብ የመነሳሳት ፍላጎታቸው እንዲቀንስ፣ ብልታቸውም እንዲደርቅ እና የእርካታ ጫፍ ያለመድረስ ችግር እንዲገጥማቸው አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡
‹‹በመሆኑም›› ይላል በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የሚታተመው ሃርቫርድ ኸርት ሌተር መፅሔት፡፡ ‹‹በመሆኑም ደም ግፊት ልክዎን መቆጣጠር እና በጤናማ ልኬት ውስጥ መሆኑን ማረጋገጥ የወሲብ ህይወትዎን ከችግር ያድናል፡፡ ለደም ግፊት መቆጣጠሪያ ብለው የሚወስዷቸው መድኃኒቶችም አንዳንድ ጊዜ ተመሳሳይ አሉታዊ ተፅዕኖ በወሲብ ህይወትዎ ላይ የማሳደር ዕድል ስላላቸው መድኃኒቱ ሲወስዱ የሚሰማዎትን፣ በወሲብ ፍላጎት እና አፈፃፀም ጭምር የገጠመዎትን ችግር ከሐኪምዎ ጋር ተመካክረው ለእርስዎ ተስማሚ የሆነውን መድሃኒት ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡›› ከሐኪሞች ጋር ስለ ወሲብ ማውራት በተለይ ለኛ ኢትዮጵያውያኑ በጣም ያልተለመደ እና እፍረት ላይ የሚጥል ቢመስልዎትም ከእርስዎ አይብስም፡፡ ለማን ነው የሚኖሩት?

ኮሌስትሮል የሴክስ ጠር ይሆን?

ኮሌስትሮል የቅባት ዘር የሆነ እና ለበርካታ ሆርሞኖች መስሪያነት የሚያገለግል የመሆኑን ያህል ከተገቢው መጠን በላይ በተለያዩ ‹‹መጥፎ›› የሚባለው የኮሌስትሮል አይነት በደም ውስጥ ሲጠራቀም አርተሪዎችን (የደም መተላለፊያ ቧንቧዎችን) ተጠራቅሞ በመዝጋት ለተለያዩ በሽታዎች ያጋልጣል፡፡ የልብ ድካም፣ ስትሮክ እና መሰል የደም ቧንቧ ህመሞችን ከማስከተሉ በተጨማሪ ጤናማ ወሲብ እንዳይፈፅሙ እና በእርካታውም እንዳይደሰቱ ከሚያደርጉ ችግሮች ተመድቧል፡፡ ግና የደም እና ንጥረ ነገር አቅርቦቶች ወደ ወሲብ ብልቶችና አካባቢያቸው እንዳይደርሱ በማድረግ መሆኑን ባለሞያዎች ይገልጣሉ፡፡ በመሆኑም የቅባት (ኮሌስትሮል) ልክዎን መቆጣጠር ስራዬ ብለው ይያዙት፡፡ ቅባት ነክ ምግቦች እንዲወዳጁም አይመከርም፡፡ በሴክስ ፈርደው ከሆነ ይግቡበት!

የህይወት ውጣ ውረዶች እና የወሲብ ህይወትዎ

ህይወት ሁል ጊዜ በተቃና ሁኔታ አትጓዝምና አንዳንድ ጊዜ የሚያሳስቡን እና የሚያስጨንቁን ሁኔታዎች ይከሰታሉ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎችን ለጭንቀት ውጥረት እና ድብርት ሊዳርጉት የመቻል እድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ አዕምሯችን በዚህ ሁኔታ ባለበት ጊዜ ውስጥ ወሲብ የመፈፀም ፍላጎት አይኖረንም፡፡ የሆነ የጎደለ ነገር እንዳለ ቢሰማንም ወሲብ ካለመፈፀማችን ጋር የተያያዘ ይሆናል ብለን የምንገምት ብዙ አይደለንም፡፡ በመሆኑም ሁልጊዜም ስሜታችን ጥሩ ያልሆነ እንደሆነ እና አዕምሮአችን የተጨናነቀ ከመሰለን ምክንያቱን ፈልገን እናውጣ፣ መፍትሄ እንፈልግ፡፡ ነፃ ያልሆነ እና ዘና ያላለ አዕምሮ በወሲብ የመዝናናት እና እርካታ የማግኘት፣ የመደሰት እድሜ ዝቅተኛ በመሆኑ አዕምሮዎትን ከሚያስጨንቀው ነገር ያፅዱት፣ ለጓደኞች ሀሳብዎን ያካፍሉ፣ ባለሞያ እርዳታ ከመፈለግም አይቆጠቡ፡፡ ለተለያዩ በሽታዎች የሚወስዷቸው መድኃኒቶችም የወሲብ ህይወትዎን አጓጉል የማድረግ መጥፎ የጎንዮሽ ጉዳት ስለሚኖራቸው ይህን ያስቡበት ከባለሞያም ይመካከሩ፡፡

– See more at: http://www.tenaadam.com/amharic/archives/1930#comment-1315

↧

ቪኦኤ አማርኛ፣ ከድጡ ወደ ማጡ? –በአበበ ገላው (ጋዜጠኛና አክቲቪስት)

$
0
0

የዛሬ ወር ገደማ የቪኦኤ አማርኛ ሪፖርተር የሆነውና አወዛጋቢና የተዛባ መረጃ በማቅረብ በስፋት የሚታወቀው ሄኖክ ሰማእግዜር ሙሉ በሙሉ ሃሰት የሆነ ዘገባ በአሜሪካን ሬድዎ አማካኝነት አሰራጨ። የዘገባው አላማ በካሊፎርኒያ የሚገኘው አዙሳ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲ ለአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሰጥቶ የነበረውን የክብር ሽልማት መልሶ መንጠቁንና ዝግጅቱ መሰረዙን በማስመልከት የቀረበው ዘገባ ሃሰት ነው ብሎ ለማስተባበል እና እኔን፣ አለማቀፉን የኢትዮጵያዊያን መብት የጋራ ህብረት እንዲሁም ኢሳትን በሃሰተኝነት ለመወንጀል የታለመ ነበር።

አበበ ገላው

አበበ ገላው


ይሁንና ለእርምጃው ምክንያት የሆነው በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት ዩኒቨርሲቲው እንዲመረምርና ሽልማቱን መልሶ እንዲያጤን ስለተደረገ መሆኑ በግልጽ የተነገረ እውነታ ነበር። ዩኒቨርሲቲውም ለክብሩ ስነ ስርአት መሰረዝ የሰጠው ዋነኛ ምክንያት ይሄው የሰብአዊ መብት ጥሰት ጉዳይ መሆኑን በይፋ ደጋግሞ ገልጿል።

አልተሳካም እንጂ ሄኖክ በተለይ በእኔ ላይ ያነጣጠረ በተንኮል የተሞላ ጎጂና የተዛባ ዘገባ ሲያቀርብ ይሄኛው ሶስተኛው ነው። በግንቦት 10, 2004 (May 18, 2012) በአቶ መለስ ዜናዊ ላይ የተቃውሞ ድሞጽ ሳሰማ ሄኖክ በአይኑ ያየው በጆሮው የሰማው ሃቅ ቢሆንም ድምጼን ሳንሱር አርጎ ዘገባውን አዛብቶ ለስርጭት አበቃው። በዚህም ምክንያት ቪኦኤ ከአድማጮቹ ከፍተኛ ተቃውሞ ስለቀረበበት በሳምንቱ ዘጋባውን እንደገና በሌላ ሰው አስተካክሎ ተቆርጦ የቀረውን ድምጼን አስገብቶ ሌላ ዘገባ ለማስተላለፍ ሞከረ። ይሄን በጋዜጠኝነት ስም የተሰራ እርካሽ የፖለቲካ ቁማር ታዝበን አለፍነው።

ከዛም ግኡሽ አበራ የሚባል አንድ የቦስተን ነዋሪ በእኔ ላይ የግድያ ወንጀል ለመፈጸም ሲዶልት ገና ከጥንስሱ በFBI ተደርሶበት ምርመራ እንደተደረገበት ተዘገበ። በዚህ ላይ ወያኔ የተቀናጀ ስራ በመስራት፣ አንዳንድ ድህረ ገጾችን፣ ፓልቶኮችን እና ቪኦኤን በመጠቀም እኔ ግኡሽ አበራን ልክ በሃሰት የወነጀልኩት ለማስመሰል ሌላ ያልተሳካ ጥረት ተደረገ። እንደተለመደው ሄኖክ አሳፋሪ የካድሬ ስራውን በመቀጠል ከፍተኛ መዛባት ለመፍጠር ሞከረ። ትንሽ ብዥታ ቢፈጥሩም ያሰቡትን ያህል ግን አልተሳካም። ፈጽሞ ያላናገረውን የFBI ቃል አቀባይ ጠቅሶ እንደለመደው ድምጽ ሳያስገባ “የጥቅሱ መጀመሪያ፣ የጥቅሱ መጨረሻ” በማለት አድማጭን ግራ የሚያጋባ ዘገባ ለቀቀ። እኔ እንደ ጋዜጠኛ ባይሆንም እንደ ጉዳዩ ባለቤት ከቦስተን FBI ቃል አቀባይ ግሬግ ኮምኮዊች ጋር ያደረኩት ንግግር የድምጽ መረጃ እስካሁን በእጄ ላይ አለ። በተጨማሪም እንደነ ግኡሽ ስራ ቦታው ድረስ ሄደው የFBI መርማሪዎች ካፋጠጡት ግን በሴራው አለመሳተፉ ከተረጋገጠው ቤዛ ጥላሁን ያገኘሁት ዝርዝር መረጃ ጭምር በእጄ ይገኛል።

ዘፋኝና የግኡሽ ደባል የነበረችው አበራሽ የማነ በግዜው የቤዛ ወዳጅ የነበረች ሲሆን አሁን ትዳር መስርተዋል። በወቅቱ ለአበራሽ የማነ መርማሪዎቹ ጥያቄ ቢያቀርቡም ምንም አይነት ውንጀላ ማንም ባያቀርብባትም ፓልቶክ ላይ ብቅ ብላ በሃሰት አበበ ገላው ወነጀለኝ እንድትል ተደረገ። እነ አውራምባ ታምስም ወገንተኛ የሆነና የሚያስተዛዝብ ስራ ሰሩ። ይህንንም በወቅቱ ታዝበን አለፍነው።
peter
FBI በዋነኛነት ትኩረት ያደረገው ግኡሽ ላይ ነበር። ለዚህም ምክንያት ደግሞ እንዳወሩት በፌስቡክ ስለተሳደበ ወይንም ስለዛተ ሳይሆን በግድያ ወንጀል ዱለታ ሊያስጠይቅ የሚችል መረጃ መርማሪዎች እጅ በመግባቱ ነበር። በቀጣይነት በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ እርምጃ የመውሰድና ያለመውሰድ መብት የመርማሪዎቹ ሲሆን የዘገባው እውነታ ግን ከላይ የተጠቀሰው ነው።

በግልጽ አፍቃሪ ወያኔ የሆነው ሄኖክ ሰማእግዜር ግን ጥቅስ ብሎ ያነበበውን ብዥታ የሚፈጥርና ከዋናው ጭብጥ ውጭ የሆነና አዛብቶ ያቀረበውን ሃተታ በተውሶ የወሰደው ከሶስተኛ ወገን፣ እንደውም እንደሰማሁት ከሆነ፣ ከትግሪኛ ዝግጅት ክፍል ነበር። ይሁንና ጥረቱ እውነቱን አልቀየረውም። ግኡሽ አበራ እኔን በስም ማጥፋት በፍርድ ቤት እንደሚከስ ወያኔዎች ደጋግመው ከመናገር አልፈው ከፍትኛ ገንዘብ ቢያዋጡም እስካሁን የተሰማ ክስ የለም።

እኔ በወቅቱ ወንጀል ሲዶልት የተደረሰበት ሰው ማንንም በስም ማጥፋት መክሰስ አይቻለውም ያልኩት እውነትን በመተማመን ነበር። አሁንም ፍርድ ቤቶች ክፍት ስለሆኑ ግኡሽ ብቻ ሳይሆን የውሸት ዘገባ በማሰራጨት እጅ ከፍንጅ በመያዝ አደባባይ ያወጣሁት ሄኖክ ሰማእግዜር (እስከ እረዳቶቹ) ዶሴውን ጠርዞ ፍርድ ቤት መሄድ ይችላል። ይሁንና ውሸት ታጥቆ አየር ላይ መውጣትም ይሁን የውሸት ዶሴ ጠርዞ ፍርድ ቤት መሮጥ ፈጽሞ እንደማያዋጣ ከወዲሁ መጠቆም እወዳለሁ።

የአሁኑ ይባስ እንዲሉ ሄኖክ አቶ ሃይለማሪያም አሜሪካ ሳይደርሱ ላስቸኳይ ስራ ተመለሱ፣ ያልደወሉትን ስልክ ደውለው ክብሩ ይቅርብኝ አሉ፣ እኔ ያልጻፍኩትን ደብዳቤ እያነበበና እያጠቀሰ፣ ያልተናገርኩትን ተናገረ፣ ያልዘገብኩትን ዘገበ እያለ ፈጽሞ ያላናገራቸውን ቃል አቀባይ ያላሉትን አሉ እያለ፣ አደባባይ ወጣ። በሁዋላ ስናጠያይቅ እንደውም የተረዳነው አሳፋሪው የቪኦኤ የሃሰት ዘገባ የተሰራው በቡድን ለሶስት መሆኑን ነው።

ታዲያ ምነው ይሄ ሁሉ የቪኦኤ ሰራዊት አንዲት ቅንጣቢ መረጃ ማውጣት ተሰናው? ከሁሉ የሚገርመው ደግሙ ውሸታችን “ቢቢጂ” የተባለ ቦርድ አጸደቀልን ብለው አይናቸውን በጨው አጥበው አደባባይ መውጣታቸው ነው። በእውነቱ በጣም ያሳዝናል። ቢቢጂም ቢሆን በመረጃ የተደገፈ ማስተባበያ ይዞ እስካልመጣ ድረስ አድማጭም አክባሪም በቀላሉ ማግኘት ይችላል ብዬ አላምንም። የተራዳሁት አንድ ጉዳይ ቪኦኤ ውስጡን ለቄስ ነው። ማንንም የመውደድም ይሁን የመጥላት ግላዊ መብታቸውን ብናከብርም ውሸት ታጥቀው አየር ላይ ከወጡ ግን ችላ ሳንል ደግመን በእውነት ሚሳኤል አናወርዳቸዋለን።

እኛ ለህዝባችን ነጻነትና መብት ከመከራከርና ከመታገል አንቆጠብም። ለዚህም ደግሞ ከማንም ፍቃድ አንጠይቅም። አንዳንድ የቪኦኤ አማርኛ ክፍል ባልደረቦች የእነ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ክብር ተነካ ብለው እኛን ለማጥቃት መነሳታቸው ባያስገርምም ያሳዝናል። በከንቱ ይደክማሉ እንጂ አቶ ሃይለማርያምም ሆኑ አዙሳ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲ በዙ ተቀጣሪዎች አሏቸው። ሁለቱም ወገኖች ቪኦኤን በቃል አቀባይነትይሁን በጥብቅና አለመቅጠራቸውን በርግጠኝነት መናገር ይቻላል።
VOA 1
እንኳን በሜድያ ስራ የተሰማራ ጋዜጠኛ ነኝ ባይ ይቅርና ማንም እንደሚያውቀው አንድ ሚድያ ስተት ሲሰራ ባግባቡ እርማት እንዲያደርግ ይጠየቃል። ስህትት ተሰርቶ ከተገኝም አግባብ ባለው መንገድ እርምት አድርጎ ይቅርታ ይጠይቃል።። ቪኦኤን የሚያህል ግዙፍ ተቋም የሌሎችን ስራ ከማኮሰስ አልፎ በውሸት ጭብጦ የእውነትን ተራራ ለመናድ ጥረት ማድረጉ በጣም ግራ የሚያጋባ ጉዳይ ከመሆን አልፎ የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ የሚለውን አባባል ያስታውሰናል።

ሌላው አሳዛኝ ጉዳይ በዚህ የሀሰት ዘገባ ቁልፍ ሚና የተጫወተው ፒተር ሃይንላይን በአጠያያቂ መስፈርት ባለፈው ሳምንት ለሄኖክ ሰማ እግዜር “ሽልማት” ማቀበሉ ነው። ሄኖክም ይህንኑ ሽልማት ከአፍሪካ ክፍል ሃላፊው ከአቶ ንጉሴ መንገሻ እጅ ተቀብሏል። በርግጥ ሄኖክ ለማዛባትና ሃሰትን በይፋ በማሰራጨት ተወዳዳሪ ስላልተገኘለት ታላቅ ሽልማት ይገባው ይሆናል። ለጋዜጠኛነቱ ሽልማት መስጠት ግን ጋዜጠኝነትን መስደብ ነው።

በዚህ አይን ከፋች በሆነ አጋጣሚ ከእነ ሄኖክና ፒተር ሃይህላይን ይልቅ የአማርኛው እና የአፍሪካ ክፍል ሃላፊ የሆኑ ሁለት አንጋፋ ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞችን በጣም ታዘብኩ።። ክብር ወደ ትዝብት ያለ ምክንያት እንደማይቀየር ለማንም ግልጽ ነው። ለምን ታዘብከን ብለው ከጠየቁኝ ምላሹን በዝርዝር በአደባባይ ላስረዳቸው ዝግጁ ነኝ። እስከዛው ሆድ ይፍጀው በማለት ለዛሬው የኢሳቱ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን የቪኦኤን ከድጡ ወደ ማጡ የሆነውን የሰሞኑን ጉዞ አስመልክቶ ያዘጋጀውን ምርጥ ዝግጅት ካልሰሙት አያምልጥዎ።

መልካም አዲስ አመት ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ!

↧

በሽብርተኝነት የተከሰሱት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ወደ ማዕከላዊ ተዛወሩ

$
0
0

በሽብርተኝነት ተከሰው አርባምንጭ ታስረው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞ ጎፋ ዞን አመራሮች ከነበሩበት የአርባ ምንጭ እስር ቤት አዲስ አበባ ወደሚገኘው የፌደራል ወንጀል ምርመራ መዘዋወራቸው ታወቀ፡፡
news
ከዞኑ አመራሮች መካከል የአርባ ምንጭ ምክትል ሰብሰቢ አቶ በፍቃዱ አበበ እና ደርጅት ጉዳይ ኃላፊው ኢንጅነር ጌታሁን በየነ ጱግሜ 5 ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ ወደ ማዕከላዊ የተዘዋወሩ ሲሆን ቀሪዎቹ አሁንም አርባምንጭ ውስጥ ታስረው ይገኛሉ፡፡

ወደ ማዕከላዊ የተዘዋዋሩትን የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞጎፋ አመራሮች ምግብና ልብስ ከማቀበል ውጭ መጠየቅ እንደማይቻል የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

↧

የማይዝሉ ጀግኖች! (በላይ ማናዬ)

$
0
0

ጫማ ማውለቅን ጨምሮ እጅግ አሰልቺና አሳቃቂ የሆነውን ፍተሻ አልፈን ወደ ውስጥ ዘለቅን፡፡ በጋራ ሰብሰብ ብለን ወደ ስፍራው ካቀናነው ወጣቶች መካከል ግማሻችን በዞን አንድ ሌሎቻችን በሌላኛው ዞን ተከፋፍለን ወደ ወዳጆቻችን ገሰገስን፡፡

አሁን ያለነው በፌደራል መንግስቱ ስር ከሚተዳደሩት እስር ቤቶች መካከል አንዱ በሆነው ቂሊንጦ ውስጥ ነው፡፡ እዚህ እስር ቤት ውስጥ ልናያቸው የናፈቅናቸው የአርነት ታጋዮች፣ የብዙሃን ድምጾች አሉ፡፡ ከሁለቱ ቡድኖች ከአንደኛው ጋር በመቀላቀል ወደጀግኖቹ አመራሁ፡፡ ከፊት ያሉት ቀድመው አስጠርተዋቸው ኖሯል፡፡ ሁሉም በፈገግታ ታጅበው ከአጥሩ ማዶ ሰላምታ ሰጡን፡፡ ውብ በሆነ ፈገግታና የናፍቆት ስሜት ውስጥ መሆናችን ከጠያቂዎችም ከተጠያቂዎችም በኩል በጉልህ ይታያል፡፡

10616558_581452168647112_4041948437710460738_n

በቀጭን ሰውነቱ ላይ ስስ ነጭ ቲሸርት ለብሶ ሲታይ በእድሜ በጣም ለጋ አስመስሎታል፡፡ ረጂም ቁመቱ ደግሞ ቅጥነቱን አጉልቶታል፡፡ ፍልቅልቅ ነው፤ ሙሉ ደስተኛ ገጽታው ማንንም ቢሆን በፍጥነት የሚያላምድ ይመስላል፡፡ ሲናገር የሚደመጥ፣ ሲናገሩ የሚያደምጥ ግሩም ወጣት ነው፡፡ ይህ ወጣት የዞን 9 ጦማሪያን ቡድን አባልና በ2006 ዓ.ም የቡድኑ አስተባባሪ የሆነው ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ ነው፡፡ ሌሎች አብረውኝ የነበሩት ወጣቶች ከሌሎች ሁለት ታሳሪ ጋዜጠኞች ጋር እያወሩ ሳሉ እኔ ከናቲ ጋር አንዳንድ ጉዳዮችን እያነሳን እያለ ስለወቅታዊ አያያዛቸውና ስላለፈው ሁኔታ ወደ ኋላ መለስ ብዬ ጥያቄዎችን አነሳሁለት፡፡ ‹‹ሀገሬ ላይ እርግጠኛ የሆንሁበት ጉዳይ ቢኖር እኔን እንደ ዜጋ የሚጠብቀኝ መንግስት የሌለኝ መሆኑን ነው፡፡ ህገ-መንግስቱ አልጠበቀኝም፡፡ ህገ-መንግስቱ ጥሩ ቢሆንም አልተከበረም›› አለኝ ወጣቱ ጦማሪ፡፡

በ2006 ዓ.ም ሚያዚያ ወር አጋማሽ ላይ ነበር መንግስት የዞን 9 አባላትን ለቃቅሞ ወደ ማዕከላዊ ማጎሪያ ያጋዛቸው፡፡ የጡመራ ቡድኑ አባላት በሽበር ወንጀል ተጠርጥረው እንደታሰሩ ተገልጾላቸው ለረጂም ጊዜያት በምርመራ ላይ መደበኛ ክስ ሳይመሰረትባቸው ከቆዩ በኋላ፣ መደበኛ ክሱ ሲመሰረት ‹ከሽብር ቡድኖች ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ ህገ-መንግስቱን በኃይል ለመናድ…› በሚሉ ‹ወንጀሎች› ተከሰው በቂሊንጦ እስር ቤት ሆነው የፍርድ ሂደታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡ ከቡድኑ አባላት መካከል ናትናኤል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላ፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ አጥናፍ ብርሃኔ እና ዘላለም ክብረት እንዲሁም አብረው በተመሳሳይ ክስ የተያዙት ሁለቱ ጋዜጠኞች ተስፋለም ወልደየስ እና አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ በዚሁ በቂሊንጦ ሲገኙ ጦማሪት ማህሌት ፋንታሁን እና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ ደግሞ ቃሊቲ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

እነዚህን እና ሌሎች ቀደም ብለው በእስር ላይ የሚገኙትን ጋዜጠኞች፣ የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኪሚቴ አባላትን፣ ፖለቲከኞችን እና ሌሎችንም ታሳሪዎች 2007 ዓ.ም አዲስ አመት መባቻን አስመልክተን ወጣቶች ሰብሰብ ብለን በዋዜማውና በበዓሉ ዕለት ጠይቀናቸው ነበር፡፡ በተለይ ባለፈው ሳምንት በማህበራዊ ሚዲያው ‹‹ጥቁር ሳምንት›› (black week) በሚል ለአምስት ቀናት ዘመቻ (campaign) በተካሄደ ጊዜ በዘመቻ መጨረሻው ቀን የዘመቻው አስተባባሪዎች አዲስ አመትን በማስመልከት ‹አዲስ አመት በዓልን ከነጻነት ታጋዮች ጋር› በሚል የታሰሩ የነጻነት ታጋዮችን እንድንጠይቅ ጥሪ ማስተላለፋቸውና ጥሪውን የተቀበሉ ወጣቶች መበርከት የእስረኞችን የጥየቃ ፕሮግራም ልዩ አድርጎት ነበር፡፡

እስር ቤት ታጉረው የሚገኙ የነጻነት ታጋዮችም በወጣቶቹ ድርጊት እጅግ መደሰታቸውን በመግለጽ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ እኒያ የማይዝሉ ጀግኖች እስክንድር ነጋና አንዱዓለም አራጌ በቃሊቲ በተገኘንበት ወቅት በወጣቶቹ ድርጊት እንደኮሩና ትግሉ እንዳልቆመም ማሳያ መሆኑን ከመግለጽ አልተቆጠቡም፡፡ ‹‹እኛ ገና በሰላማዊ ትግሉ ጅማሮ ላይ ነው የታሰርነው፡፡ ትግሉ ገና መጀመሩ ነው፡፡ ትግሉ በተግባር የሚፈትናቸው በርካታ ጀግኖች አሉ›› ሲል ነበር ትንታጉ ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ ወጣቶችን ያበረታታው፡፡

እስክንድር የታሰረ አይመስልም፡፡ አልታሰረምም! በእስር ቤቱ ፖሊሶችና በአንድ ሲቪል በለበሰ ጆሮ ጠቢ ታጅቦ ወደ እኛ ቢቀርብም እስክንድር ፍጹም ነጻ ሆኖ ነበር የሚያወራን፡፡ እስክንድር ነጋን ይፈሩታል እንጂ እሱ አይፈራቸውም፡፡ ይህንን ደግሞ በተግባር ያሳየ ጀግና ነው፡፡ ‹‹አንተ እኮ የምንግዜም ጀግናችን ነህ፤ እንኮራብሃለን!›› አለው ከመካከላችን አንዱ፡፡ እስክንድር መለሰ፤ ‹‹ለእኔ ደግሞ እናንተ ከውጭ ያላችሁ ወጣቶች ናችሁ ጀግኖቼ!››

የእስክንድር መንፈስ ወደ ሌሎች የመጋባት ኃይል አለው፡፡ የዞን 9 የጡመራ ቡድን አባላት የጥንካሬ ምንጭ ይህ የማይዝል ጀግና እስክንድር ነጋ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ቂሊንጦ በነበርንበት ወቅት ፍልቅልቁ ወጣት ናትናኤል የሚያረጋግጠውም ይህንኑ ነው፡፡ ‹‹ያኔ ወደ እስር ቤት ሳንገባ በፊት እስክንድር ነጋን ልንጠይቅ ቃሊቲ ስንሄድ እስክንድር ሁሌም ይገርመን ነበር፡፡ ሁሌም ጠንካራ፣ ደስተኛና አስተዋይ ሆኖ ነበር የምናገኘው፡፡ እና፣ እሱን እያየን መታሰር፣ መስዋዕትነት መክፈል ሌላውስ ለምን ይፈራል ታዲያ ስንል ራሳችንን እንጠይቅ ነበር፡፡ እስክንድር ልዩ ሰው ነው፤ የሚጋባ መንፈስ ያለው ጀግና!››

ተስፋለም፣ ናትናኤል፣ አስማማው እና ሌሎችንም ወጣቶች ‹‹እስክንድር አክብሮቱን ገልጾላችኋል እኮ፤ ሰምታችኋል?›› ሲባሉ በደስታ አወንታዊ ምላሽ ሰጡ፡፡ እስክንድር ጀግኖችን የሚያፈራ ጀግና ነው፡፡ ዛሬ ሌሎች ወጣት የአርነት ንቅናቄው የማይዝሉ ጀግኖች የአርዓያቸው እስክንድርን ቃል ለሌሎች ሲናገሩ ይደግሙታን፡፡ ወጣቱ ጦማሪ ናትናኤል ከቂሊንጦ ተናገረ፣ ‹‹ለሀገር የሚያስቡ ብዙ ወጣቶች በየጊዜው ማበባቸው አይቀሬ ነው፡፡ እየታየ ያለውም ይሄው ነው፡፡ ምንግዜም የሚበረቱ ሰዎች ለውጥ ያመጣሉ ብዬ አምናለሁ፡፡››

የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የሆነው ያሲን ኑሩ ደግሞ እዛ ቂሊንጦ እስር ቤት ልንጠይቅ ለሄድነው ወጣቶች እንዲህ አለን፤ ‹‹መንግስት በኃይማኖቶች መካከል ልዩነት መፍጠር ይፈልጋል፡፡ እናንተ ክርስቲያኖች የኃይማኖት ድንበር ጥሳችሁ ከእኛ ከሙስሊም ወንድሞቻችሁ ጋር መቆማችሁን እናደንቃለን፡፡ እኛን ለመጠየቅ እስር ቤት ድረስ ስለመጣችሁ በጣም እናመሰግናለን፡፡ ትግሉ ከዚህም በላይ መስዋዕትነት ያስከፍላልና በርቱ፡፡››

ከሁሉም ታሳሪዎች አንደበት የሚወጣው መልዕክት አስገራሚ ነው፤ ሊያበረታቸው ወደ እነሱ የሚሄደውን ጠያቂ ሁሉ መልሰው አበርትተው ይልኩታል፡፡ እነሱ የማይዝሉ ጀግኖች ሆነው የዛለውን የሀገሬ ወጣት ‹‹በርታ!›› ይሉታል፡፡ አጠር ቀጠን ያለ ቆፍጣና ወጣት ነው፤ ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ፡፡ ‹‹በጥቁሩ ሳምንት ዘመቻ ያደረጋችሁትን ነገር ሰምተናል፡፡ በጣም ደስ የሚል ስራ ሰርታችኋል፡፡ መጥታችሁ ስለጠየቃችሁን ደስ ብሎናል፡፡ እስሩ ቀጣይነት እንደሚኖረው ቢታወቅም፣ በየትኛውም ሁኔታ በርታትችሁ እንድትቀጥሉ እፈልጋለሁ›› ሲል እሱም የማበረታቻ ቃሉን ተናገረ፡፡

ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌ በበኩሉ የማሃተመ ጋንዲን የሰላማዊ ትግል አስተምሮ በምሳሌነት ሲያነሳ ከቆየ በኋላ፣ እሱን አብነት አድርገን በሰላማዊ ትግላችን እንድንበረታ አሳሰበን፡፡ ‹‹የሁላችንም ተስፋ ያለው እዚህ እስር ቤት አይደለም፡፡ ከዚህ ውጭ ካላችሁት ነው ሁሉም ነገር ያለው፡፡ በርቱ! ኢትዮጵያ እንደ እናንተ ያሉ እጅግ ብዙዎችን ትፈልጋለች፡፡ ደግሞም አሉ! በበዓል ቀን ስለመጣችሁና ስለጠየቃችሁን ኮርተንባችኋል፡፡››

ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የባለሙያ እጥረት እጅጉን እንደሚያሳስበው ይናገራል፡፡ በእስር ላይ ካለ ጀምሮ የሚያየው የባለሙያ እጥረት ሳይታሰር በፊት ከሚያውቀው በላይ ሳይሆንበት አልቀረም፡፡ ‹‹ታስሬ ባለሁባቸው ቀናት ሁሉ የታዘብኩት ነገር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የባለሙያ እጥረት በሁሉም ዘርፍ መኖሩን ነው፡፡ አቅም ያላቸው ዜጎች ከስርዓቱ በመገፋታቸው ክፍተቱ እንዲሰፋ ሆኗል፡፡ በጣም ነው የሚያሳዝነው፤ የሚሰሩ ሰዎች በተገቢው ቦታ ላይ አለመኖራቸውን አይቻለሁ፡፡ የሚያሰራ ስርዓት ስለሌለ ብዙዎች ህሊናቸውን መርጠው በመራቃቸው ይመስለኛል አቅም ያላቸው ሰዎች የራቁት፡፡ ይህ ለሀገር አሳሳቢ ነው፡፡››

ለመሆኑ በተለየ ሳላከናውነው (ወይም እንደ ቡድን ሳናከናውነው) በመታሰሬ እቆጫለሁ የምትለው ነገር ይኖር ይሆን ስል ጥያቄ አነሳሁለት፡፡ ‹‹የሚቆጨኝ ነገር በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና በሌሎች ተቋማት በእንግሊዝኛ የተሰሩ የጥናት ስራዎችን በመምረጥ አሰባስበን በአማርኛ ቋንቋ በጆርናል መልክ ለመስራት አስበን ያን ሳንሰራ በመታሰራችን ነው›› አለኝ ትክዝ ባለ ስሜት፡፡ ሆኖም አለ ናትናኤል፣ ሆኖም ‹‹አሁን በተለያዩ ሁኔታዎችና ጉዳዮች ላይ ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያው በኩል የሚሰሩ ስራዎች እንዳሉ ስሰማ በጣም ነው ደስ ያለኝ፡፡ እኛን አስረው ሌላው ዝም እንዲል ፈልገው ኖሮ ከሆነ እንዳልተሳካላቸው የሚያሳይ ነው፡፡ ለሀገር የሚያስቡ ብዙ ወጣቶች በየጊዜው ማበባቸው አይቀሬ ነው፡፡ እየታየ ያለውም ይሄው ነው፡፡ ምንግዜም የሚበረቱ ሰዎች ለውጥ ያመጣሉ ብዬ አምናለሁ›› አለ ቀጭኑ ቁምነገረኛ ወጣት፡፡

በግሌ እንደዘንድሮ አይነት አዲስ ዓመት በማይረሳ መልኩ ያሳለፍኩ አይመስለኝም፡፡ ከእነዚህ ባለብሩህ አዕምሮ ባለቤቶች፣ ሰላማዊ ታጋዮች፣ ሀገር ወዳዶች ጋር በዓልን ከማሳለፍ የበለጠ ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር ይኖራል!

እናንተ የማትዝሉ ጀግኖች…የእናንተን ፈር በሚከተሉ እልፍ ኢትዮጵያውያን ነገ ብሩህ ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊና የዘመነ አስተዳደር ይገባታል!

↧
↧

(ድብቅ ስትራቴጂ) የህወሓት ሥርዓት የአፋር ህዝብን መሬት የትግራይ ነው አለ

$
0
0

(በአኩ ኢብን አፋር )

በሰሜናዊው የአፋር ክልል የሚገኙ የአፋር ክልል ወረዳዎች ዳሉልን ጨምሮ «የትግራይ መሬት ነው!» በማለት አፋቸው ሞልተው የሚናገሩ የህዋሓት መሪዎች ይደመጣሉ!! እሱም አብዓላ፣ ደሉል፤ ኮናባ፣ ባራህሌ፣ የትግራይ መሬት ነው ከሚባሉ ቦታዎች ይጠቀሳሉ። በኮናባ ወረዳ ከሁለት ሳምንታት በፊት በትግራይ ነዋሪዎችና በአፋር ነዋሪዎች መካከል ግጭት ተፈጥሮ አንድ የአፋር ወጣት ሲሞት 3 ደግሞ መቁሰላቸው ዘግበን ነበር። ችግሩ በሁለት ነዋሪዎች መካከል የሚፈጠር ግጭት አይደለም! የህዋሓት መንግስት የአፋር መሬትን ለመቀራመት የሚያደርገው ሆን ተብለው የሚደረጉ ትንኮሳዎች መሆናቸው ግልፅ ነው! «የኮናባ ወረዳ እና የአፅቢ ወረዳ የድምበር ወዝግብ የቆየ ቢሆንም የዛሬው በመንግስት ሆን ተብሎ የተፈጠረ በመሆኑ አሳስቦናል።» ይላሉ የኮናባ ነዋሪዎች።
afar region
የህዋሓት መንግስት ባለስልጣናት «መሬቱ የእኛ ነው እስከ ዳሉል የትግራይ መሬት ነው ብትፈልጉም ባትፈልጉም መንግስት እርምጃ ይወስዳል» ብለው ይናገራሉ። የአፋር የአገር ሽማግሌዎችን ጨምሮ ብዙ ወጣቶች በነገሩ በመገረም «በመሬታችን እየሞተን ነው! ገና አሁንም እንሞታለን!» በማለት ባለፈው ሳምንት በውቅሮ የተደረገው ስብሰባ ያለ ምንም መፍተሄ ተበትኗል! በስብሰባው የትግራይ ክልልን ወከለው የተገኙት የውቅሮው የዞን አስተዳደር የዞኑ የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የአፅቢ ወረዳ መስተዳደርና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ በአፋር በኩልም እንደዛው። ለእነርሱ ታማኝ የሆኑት የዞን 2 የመንግስት ባለስልጣናትና በርካታ የአገር ሽማግለዎች ተገኝተዋል!! በዚህ ስብሰባ በባለፈው ውግያ የንፁሃን ሰዎችን ህይወት ያጠፉትን ሰዎች የአፅቢ ወረዳ የፀጥታ ኃይሎች ለህግ እንዲያቀርቡ በአፋር ሽማግሌዎች የተጠየቁ ቢሆንም ሰሚ አላገኙም!! «ካሁን በኋላ» ይላሉ የኮናባ ወጣቶች «ካሁን በኋላ ሁላችን በተጠንቀቅ እንቆማለን እንሞታለን!»

ከመንግስት የምንጠብቀው ፍትህ የለም!!

↧

በቦረና ዞን ነዋሪ የሆኑት አቶ ጎንፋ አበራ ከፖሊስ በተተኮሰ 4 ጥይት ሕይወታቸው አለፈ

$
0
0

Car ethiopia

Car ethiopia1
አስከሬኑ ሽኝት ላይ የነበሩ የአባያ ገላና ወረዳ ሰብሳቢ አቶ በድሉ መንግሥቱ በፖሊስ ተደብድው በእስር ላይ ናቸው

(ፍኖተ ነፃነት) በቦረና ዞን ገላና ወረዳ ቶሬ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጎንፋ አበራ ጳጉሜ 4 ቀን 2006 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ወታደር ዋቆ ሁቃ በተባለ ፖሊስ በተተኮሰ 4 ጥይት ህይወታቸው ማለፉን የቦረና ዞን የአንድነት አስተባባሪ አቶ ጌታቸው በቀለ ለፍኖተ ነፃነት ገለጹ፡፡ የአቶ ጎንፋ አስከሬን ወደ ቶሬ ከተማ ጤና ጣቢያ ተወስዶ ሐሙስ መስከረም 1 ቀን 2007 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ቤተሰባቸው ወደሚገኝበት አምቦ ከተማ ሲሸኝ የቶሬ ከተማ ነዋሪዎች አሸኛኘት ያደረጉ ሲሆን የአባያ ገላና ወረዳ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ በድሉ መንግሥቱ ከሽኝቱ ሲመለሱ በፖሊስ ተይዘው ድብደባ ከተፈጸመባቸው በኋላ በእስር ላይ መሆናቸውን አስተባባሪው ገልጸዋል፡፡ አቶ በድሉ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል በመሆናቸው ብቻ በተደጋጋሚ በገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ድብደባና እስር ይፈጸምባቸው የነበረና ባሳለፍነው ዓመትም ይሰሩበት የነበረ የግል ታክሲያቸውን በድንጋይ የሰባበሩባቸው ሲሆን አቶ በድሉና በአካባቢው ያሉ የፓርቲው አባሎች ግን እየደረሰባቸው ያለው ዛቻ፣ ማስፈራሪያና እስር ከትግሉ ፈቀቅ እንደማያደርጋቸው ሰላማዊ ትግሉንም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡ ወደ ቶሬ ወረዳ ፖሊስ ደውለን ሁኔታውን ለማጣራት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፡፡

↧

የዩክሬይን ክራሚያና የሩስያ ጉዳይ ስለኢትዮጵያና ኤርትራ ያልተዘጋ አጀንዳ ምን ያሰተምረናል?

$
0
0

(አክሊሉ ወንድአፈረው – የግል አስተያየት)

መስከረም 2, 2007 (ስፕተምበር 12 2014  )

 

ukrባለፉት ጥቂት ወራት በዩክሬንና ክራሚያ ውስጥ የተቀሰቀሰው ሁኔታ እና አሁን የደረሰበት ደረጃ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር አንጻር ብዙ ዕድምታዎች አሉት፡፡ እነዚህን ዕድምታዎች መመርመር  በሀገራችን ውስጥ ያለፉና የወደፊት ጉዞ ላይ የተከሰቱ፤ እና ሊከሰቱም የሚችሉ ጉዳዮችን  ከወዲሁ በግምት ውስጥ በማስገባት  ሀገራዊ ራዕያችንን ፣ የትግል አቅጣጫችንን አና አጋርና ተቀናቃኝ ሊሆኑ የሚችሉትን ሃይሎች ለይቶ ለማወቅ ያግዛል ብዩ አሰባለሁ።  ይህን ማወቁ ደግሞ በሀገራችን እና በብሑራዊ  ጥቅማችን ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ከሚችሉ ተግባሮች እንድንቆጠብ ዕድል ይሰጠናል። የዚሀ ጽሁፍ ዓላማም በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት ለመጫር ነው።

 

ለመንደርደሪያ ያህል፦ ለመሆኑ በታሪክ ክራሚያ ዩክሬን ወይስ ሩሲያ ነበረች?

ጠቅለል ባለ ሁኔታ የክራሚያን ያለፉት 200 ዓመታት ታሪክ ስንመለከት በዋናነት የሩሲያ አካል ሆና መቆየቷን እናያለን። በሌኒን የሚመራው የሶሻሊስት አብዮት ከተቀጣጠለ ከ 1917 በሁዋላም ቢሆን ክራሚያ በሶቭየት ህብረት ዕቅፍ ውስጥ አንድ ራስ-ገዝ አስተዳደር ሆና ቆይታለች።

 

ክሬሚያ የዩክሬን አካል የሆነችው ባውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1954 በወቅቱ የራሽያ ኮሚኒስት ፓርቲና ያገሪቱ መሪ በነበሩት በኒኪታ ክሩስቼቭ ሲሆን፤ እኘህም ሰው የትውልድ ቦታቸውና የፖለቲካ አጋራቸው ለሆነችው ዩክሬን በስጦታ መልክ ከሰጡ በሁዋላ ነበር፡፡ በወቅቱ ይህ ጉዳይ ለሶቭየት ፖለቲካ መሪዎችም ሆነ ለክራሚያ ነዋሪዎች አስጨናቂ ጉዳይ አልነበረም፡ ለምን ቢሉ ዩክሬን የሶቭየት ህብረት አንድ ክፍለ ሀገር (ሪፐብሊክ) የነበረች ሲሆን የክራሚያ ዩክሬን ውስጥ መግባት ለአስተዳደር አመቺነት ካልሆነ በስተቀር በጊዜው ሌላ ሰፊ የፖለቲካ እንደምታ አልነበረውምና ነው። ከዚያም አልፎ በተለይ በምስራቅ አውሮፓ ይገኙ የነበሩት ሁሉም ሶሻሊሰት ሀገሮች  በሶቭዬት ሶሻሊስት ሪፐብሊክ የበላይነት ጥላ ስር  እንዳንድ ሀገር ሆነው  (በሶሻሊስት ዓለማቀፋዊነት መርህ) ይመሩ ስለነበርም እንኳንስ በአንድ ሀገር ስር ያሉ ያስተዳደር ክልሎች በተለያዩ ሶሻሊስት ሀገሮችም መካከል ቢሆን ድንበርና ድንበርተኘነት ታላቅ ቁምነገር ያለው ተደርጎም ይወሰድ እንዳልነበር ማሰታወስ ያስፈልጋል።

 

የክራሚያ ነዋሪዎች በማንነት አንጻር ራሳቸውን እንዴት ይመለከታሉ?

ይህ ጉዳይ አጅግ አወዛጋቢና በዪከሬን ግጭት ውስጥ ተፋላሚ የሆኑ ክፍሎችም የግል አቌማቸውን የብዙሃኑን ፍላጎት እንደሚንጸባርቅ አድርገው የሚሟገቱበት ዕውነታ ነው::

 

በዩክሬይን ስልጣኑን የጨበጡት ክፍሎች እና ደጋፊዎቻቸው “የክራሚያ ነዋሪዎች ራሳቸውን የሚያዩት ከሁሉም በላይ  ከራሽያ የተለዩና ዩከሬንያዊ አድርገው ነው የሚቆጥሩት”  የሚለውን አመለካከት ሁሉም ስው እንዲቀበለው ይፈልጋሉ:: ክራሚያ የዩክሬን አካል ሆና የቆየችበትን ጊዜ በማጣቀሰም በተለይም አዲሱ ትውልድ የተማረውም፤ ያደገውም ስለዩክሬን እየተነገረው ስለሆነ ስለ ራሽያዊነት የሚሰማውም የሚያውቀውም  ቅንጣት ያህል ነገር እንደሌለና ይህም በመሆኑ  ከራሽያ ጋር  የሚያገናኝው ስንሰለት እንደተበጣጠስ ደጋግመው ሲናገሩ ይደመጣሉ::

 

በክራሚያ ውስጥ የሚታየውና የሚጨበጠው  እውነታ ግን ሌላ ነው:: ከ 60 ዓመታት የዩክሬን አካልነት እና ከ23 አመታት ሙሉ ለሙሉ መለያየት በሁዏላም የከሬሜያም ሆነ ሌላው የምሥራቅና ደቡብ ምሥራቅ ዩክሬን ነዋሪዎች የሚሰማችው ስሜት ግን ከሩሲያ ጋር ያላችው የቀደመ ትስስር አንጅ የዩክሬን አካልነት ሆኖ አልተገኘም:::

 

ከዚህ በታቸ የሚታየውና በቅርቡ የተካሄደ  አንድ ጥናት  እንደሚያሳየው  ከ 70%  (ሰባ ከመቶ) የማያንሱ ክራሚያዎች ራሳቸውን የሚቆጥሩት ብቻ ሳይሆን ትስስርንም ቢሆን የሚሹት ከሩሲያ ጋር እንደሆነ ያመለክታል::

 

Data: Razumkov Center; Figure: Grigore Pop-Eleches and Graeme Robertson/The Monkey Cage

 

ይሀ ሁኔታ የሚያሳየው ከአቅመቢሷ ዩክሬን ጋር ከመዳበል ይልቅ ሰፋና ጠንከር ካለችው ሩሲያ ጋር መሆኑ ምን ያህል ጠቀሜታ እንዳለው መገንዘብን ብቻ ሳይሆን የረጅሙ ጊዜ ትስስር የፈጠረውን ማንነትንም በቀላሉ መበጣጠስም  እንደማይቻል ነው::

 

በዚህም ምክንያት ይመስላል ክራሚያዎች በተለያየ ሁኔታ በዩክሬን ውስጥ ማንነታቸውን ሊያሰከብሩ ሲጥሩ ቆይተውና ሳይሳካላቸው ባሉበት ሁኔታ ዩክሬን ጓዟን ጠቅልላ በአውሮፓ ማህበረሰብ ዕቅፍ ስር ለመግባት ርምጃ መውሰድ ስትጀምር ሁኔታው ስላልጣማቸው ከገቡበት ፈተናና አጣብቂኝ እንድትታደጋቸው ሩሲያን የተማጸኑት።

ቀደም ሲል በምዕራቡ ዓለም ፖለቲካ ተንታኞች  ክራሚያወች ወደ ራሽያ መዋሀድን አይፈልጉም፤  ፍላጎታቸው ከሌላው አውሮፓ ጋር ይበልጥ መተሳሰር ነው በማለት ደግመው ደጋግመው ይናገሩ ወይም ያስተጋቡ እንጂ በማርች 2014  ሬፈረንደም ሲካሄድ ግን  97%  የሆነው ህዝብ ነበር ዩክሬንን ትቶ ወደ ራሽያ መቀላቀልን የመረጠው። ይህ ሁኔታ የክራሚያ ተወላጆች ከሩሲያ ጋር  ለረጅም ዘመናት ከነበራቸው የታሪክ፣ የፖለቲካ፤ የቤተሰብ፣ የባህል፣ የስነ ልቦናና፣የማሕበራዊ ግንኙነት   ሙሉ በሙሉ  መለያየት ችለናል፤  በራሸያና በክራሚያወች  መካከል የነበረውን የአንድነትና የትስስር ስሜት አጥፍተነዋል፤  ብለው ሲያስቡ ለነበሩ ሁሉ መርዶና የራስ ምታት ነው የሆነባቸው::

ክራሚያውያን ከሩስያ ጋር መልሶ ለመቀላቀል ከ 90 በመቶ በላያ በሆነ ድምጽ  ፍላጎታቸውን ገልጸው ደስታቸውን ሲገልጹ )  Mike Collett-White and Ronald Popeski SIMFEROPOL/KIEV Sun Mar 16, 2014 SIMFEROPOL/KIEV (Reuters) – Russian)

ባሁኑ ሰአት በክሬሚያ የሚታየው ሁኔታ በሻቢያ ስር የወደቀውን ህዝብ የማንነት ጥያቄ በተመለከተ ብዙ ጉዳዮችን እንድናገናዝብ ያስገድዳል። ላለፉት 23 አመታት “የኛ ሀገር ነች; የማንነታችን  መግለጫ ነች”; ብለው ከሚመለከቷት እና ከሚወዷት ኢትዮጰያ ተነጥለውና በኤርትራ ውስጥ ከነመሬታቸው ተገደው ከሚገዙት የአፋር፤ ኩናማ፤ ኢሮብ፤ የሀማሴን፣አካለጉዛይ እና ሌሎችም ወገኖቻችን ሁኔታ ጋር እጅግ ይመሳሰላል። ታላቁ የአፋር ተወላጅ የተከበሩት ቢትወደድ ዓሊ ሚራህ፣ “እንኳንስ ህዝቡ ግመሎቻችንም ቢሆኑ የኢትዮጵያን ባንዲራ ያውቃሉ” ሲሉ የተናገሩት ታላቅ መሪ ቃል  ስለአፋር ህዝብ የማይናጋ ጥልቅ ኢትዮጽያዊነት በቂ ማስረጃ ነው። ከዚህም ሌላ ቅድመ ሻቢያ/ወያኔ ከኢትዮጵያዊነት ውጭ ምንም አናውቅም ብለው ስለቆሙ በሻቢያ ሰራዊት በተደጋጋሚ የተደበደቡት የኩናማ፤ የሳሆ ወዘተ ወገኖች ታሪክ  ኢትዮጰያዊነትንና የትዮጵያዊነትን ስሜት ከነዚህ ህዝቦች መለየት እንደማይቻል ወይም እጅግ ረጅም ጊዜ እንደሚወስድ ያመላክታል።

በመሀል ብዙ ቅሬታ እንደተከሰተ አጠያያቂ ባይሆንም ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር ለማሰተሳሰር ስለታገሉትና ስለወደቁት አርበኞች፣በልጆቻችውና በልጅ ልጆቻቸው አዕምሮ ውስጥ በአሁኑ ሰአት ምን አይነት ስሜት እንደሚመላለስ  የክራሚያ ተመክሮ ፍንጭ ሊሰጥ ይችላል:: በተለይም ደግሞ የክሬሚያ አዲስ ትውልድ አሁንም ከአማሪጮች ሁሉ ወደ ራሸያ ማዘንበሉን እንደመረጠ ስንመለከት አበረታች ሁኔታ ቢፈጠር በሻቢያ ስር በምትገኘው ኤርትራ ውስጥ ሊከሰት የሚችለውን ዕውነታ መገመት አይከብድም::

 

የክራሚያን ሁኔታና ዕውነታ ስንመለከት፤ የህወሀት መሪወች ሲሰብኩት የቆየውና አሁን ደግሞ ባንዳንድ  ተቃዋሚወች ውስጥም እየሰረጸ ያለው “የኤርትራ ጉዳይ ያለቀለት ጉዳይ ነው” የሚለው  አመለካከት የህዝብን ሰነልቦናዊ ጥንካሬ ወደሚቦረቡር እና ብሄራዊ ጥቅምንም ወደሚጎዳ ተግባር እንዳያነጉደን ያሰጋል። የሀገር ጥቅም የሚጠበቀው ጽናት እና ጥራት ባለው ራዕይ ላይ በተመሰረተ ትግል እንጂ  ጊዚያዊ ጥቅምን ለማሳደድ ሳያላምጡ በመዋጥ ወይም ደግሞ መሰረታዊ የሀገር ጥቅምን “እሱን አሁን እርሱት”  በሚል  ራእይ የለሽ አካሄድ ከቶውንም ሊሆን አይችልም::

 

ሩሲያ ስለ ክራሚያ ምን ያስጨንቃታል?

ሩሲያ በኢኮኖሚም ሆን በወታደራዊ ሃይል በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊነትና ተደማጭነት ያላት ታላቅ ሀገር እንደመሆኑዋ በቆዳ ስፋቱዋም ቢሆን አሁንም ባንደኘነት ደረጃ ላይ ትገኛለችል። ባንጻሩ ደግሞ ክራምያ በህዝብ ቁጥርም ሆነ በኢኮኖሚ ለሩስያ እዚህ ግባ የማይባል አስተዋጽኦ ነው የሚኖራት። በኢኮኖሚ አንጻር ብቻ ካየነው በዋናነት ተጠቃሚዋ ከራሚያ እንጂ ሩሲያ አትሆንም፡፡ ሆኖም ግን የዘር ሓረግና ታሪክን የሚገዛው ገንዘብ ብቻ አደለምና  ክራሚያ በሩስያ  (ሩስያም በክሬምያ) በታሪክም ሆነ በህዝቡ ሥነ-ልቦና ላይ እጅግ ቁልፍ ቦታ አላቸው፡፡ይህ ሁኔታ ምን ያህል መሰረት ያለው እንደሆነ ለመገንዘብ የሚቀጥሉትን ታሪካዊ ሁኔታዎች እንመልከት፡

 

  • በጊዜው በመዳከም ላይ የነበረው የኦቶማን ኢምፓየር እና ራሸያ በኦክቶበር 1853 ውጊያ ውስጥ የገቡት በክሬምያ ጉዳይ ነበር፡፡ ውጊያው የተቀሰቀሰው ሩሲያ በክራሚያ የነበሩ የኦርቶዶክስ ክርስትና ተከታዮችን ከጥቃት ለማዳን በወሰደችው እርምጃ ነው ።
  • ይህን ተከትሎ ከ 1853–1856 ባንድ በኩል በራሸያ በሌላ በኩል ደግሞ በፈረንሳይና እንግሊዝ ጥምር ጦር መሀል የተካሄደው ጦርነት በክሬምያ ውስጥ ነበር፡፡
  • የቦልሽቪኮችን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ ነጩ ሰራዊት ( the white army) እየተባለ የሚጠራውና ሶሻሊዝምን በሚቃወሙ የምዕራብ ሃይሎች ይደገፍ የነበረው የተቃዋሚዎች ሀይል በ1920 የመጨረሻውንና ወሳኙን ውጊያ ያካሄዱትም በዚሁ በክሬሚያ ነበር።
  • በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከፍተኛ ደም የፈሰሰበት ጦርነት ከተካሄደባቸው ቦታዎች ውስጥ ክራሚያ አንዷና በዋናነት የምትጠቀስ ነች።
  • የጀርመን ናዚዎች ክራሚያን ለመያዝ ባደረጉት ወረራ ከ 170 ሽህ በላይ የሶቭየት ጦር የተሰዋ ሲሆን በወቅቱ ፋሽስቶችን እስከመጨረሻ የመከተችው ኣና የጀግኖች ከተማ በመባል ልዩ ሽልማት የተሰጣት የክራሚያ ዋና መናገሻ የሆነችው ሴቫስቶፖል ነበረች። በወቅቱ ምዕራብ ዩክሬን የፋሽስቱ ሂትለር ተባባሪ በመሆን በሽዎች የሚቆጠሩትን ጸረ-ፋሽስት ሃይሎች እንደገደሉና እንዲሰደዱ እንዳደረጉ ታሪክ መዝግቦታል።
  • በሁለተኛው ያለም ጦርነት ማጠቃለያ በሦስቱ ተባባሪ ሐያላን ሀገሮች (Allied Forces) መሪዎች ያሜሪካው ፍራንክሊን ሩዝቬልት፣ የሩሲያው ጆሴፍ ስታሊን እና የኢንግሊዙ ዊንስተን ቸርችል መካከል የተደረገው ስብሰባ የተካሄደው በያልታ ፣ ክራሚያ ውስጥ ነበር።

 

ይህ ሁሉ በራሽያውያንና ክራሚያ መካከል ያለውን ከፍተኛ የታሪክና  የሰነልቦና ትሰሰር  አንዱ ሌላውን ለምን እንደሚፈልግ ያሳያል::

 

ይህ ብቻ ሳይሆን ክራሚያ ለሩሲያ የምታስገኘው  ጂኦ-ፖለቲካዊና ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታም እጅግ ትልቅ ነው። ክራሚያ ቀደም ሲል የሶቭየት ህብረት በሁዋላም የሩሲያ ፌዴሬሽን ባህር ሀይል የሆነው ብላክ ሲ ፍሊት የጦር ሠፈር ነች። በዩክሬን ውስጥ የራሽያ ፍቅር የሌለው መንግስት ሥልጣን ቢይዝ የሩሲያን ደህንነት ዛሬም ባይሆን ነገና ከነገ ወዲያ አደጋ ላይ ሊጥለው እንደሚችል ራሸያ ጠንቅቃ ታውቃለች። ይህ አደጋም አፍንጫዋ ስር ሲከሰት እጅ አጣጥፎና ምንም እንዳልተፈጠረ በማስመሰል ማለፍን የራሸያ መሪወችም አልፈለጉም። ስለዚህም ቀልጠፍና ፈርጠም  ያለ እርምጃ መውስድን አስፈላጊ ሆኖ አግኝተውታል። የራሽያው ፕሬዚደንት ፑትን በቅርቡ ለሀገሪቱ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር ክራሚያ ለሩሲያ ምን ያህል ስትራተጂያዊ አስፈላጊነት እንዳላት ሲገልጹ “ ወደ ሜዴትራንያንና ወደ ጥቁር ባህር መሽጋገሪያችን የሆነችው ሶቫስቶፖል በባዕዳን ቁጥጥር ስር ሆና ማየት ከቶውንመ ተቀባይነት የለውም “ ነበር ያሉት።

 

ከላይ ስንደረደርበት የቆየሁት አመለካከት ወዳገራችን ሁኔታ ሲመለስ፤ ኢትዮጵያሰ ስለ ኤርትራ ምን ያስጨንቃታል የሚለውን ጥያቄ ማጫሩ አይቀሬ ነው። ከዚህ አኳያ እያንዳንዱ ሰው የየራሱን ምርምር አድርጎ መደምደሚያ ላይ እንዲደርስ ያስፈልጋል ብዬ አስባለሁ። ሆኖም ግን ኢትዮጵያ በታሪክ፣ በኢኮኖሚ፣ በሀገር ደህንነት ወዘተ አንጻር እጅግ ብዙ ጉዳት እንደደረሰባት  እና ወደፊትም መገመት የሚከብድ አደጋ እንደተጋረጠባት ብዙወች በመረጃ አስደግፈው ጽፈውበታል። በኢኮኖሚ አንፃር ብቻ ሲታይ እንኴ የራሷን ወደብ እንድታጣ የሆነችው ኢትዮጵያ ለጂቡቲ መንግስት ለወደብ ኪራይ የምትክፍለው ገንዘብ በየቀኑ በሚሊዮኖች የሚቆጠር እንደሆነ ይታወቃል:: ይሀ ገንዘብ ለሀገር ልማት ቢውል ኖሮ የምን ያክል ህጻናትን ህይወት ማዳን እንደሚቻል ምን ያህል ተጨማሪ ትምርት ቤት ጤና ጣቢያ ማቌቌም እና ህይወት ማዳን እንደሚቻል ስናስብ የሁኔታውን አንገብጋቢነት ለመገንዘብ ይረዳል::

 

አሁን ካለው አሀዝ ስንነሳ ኢትዮጵያ የራሷን ወደብ አጥታ ለጅቢቲ የምትከፍለው ወጪ  በያመቱ ለአንዳንዱ ወረዳ በሚሊዮኞች የሚቆጠር ተጨማሪ በጀት ለመመደብ የሚያሰችል ነው። ይህ ታዲያ ድህነትን ለመቀነስ፣ ለልማት ወዘተ ምን ያህል አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ማንናውም ጤነኛ አእምሮ የሚገነዘበው ነው።

 

በዚህ አንጻር ሰፋ ያለ ግንዛቤ ለማግኘት ለሚፈልግ ሁሉ የዶ/ር ያዕቆብ ሐይለማርያም “አሰብ የማን ናት”፤ የአምባሳደር ዘውዴ ረታን “የኤርትራ ጉዳይ”፤ ባዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የታተመውን “የአክሊሉ ማስታወሻ” ጥሩ ግንዛቤና መረጃ ሊሰጡ የሚችሉ መጻህፍት መሆናቸውን መጥቀስ እወዳለሁ።

 

የሶቭየት ህብረት መፈራረስ ክራሚያና ኤርትራ

የሲቭየት ህብረት መፈራረስን ተከትሎ በነበረው ያልተረጋጋ ወቅት ክራሚያም በግርግር ከዩክሬን ጋር ተደባልቃ ከራሸያ ተገንጥላ እንድትሄድ አድርገዋል የሚባሉት እንኳንስ ለሀገር ለራሳቸውም ማሰብ ይሳናቸው ነበር እየተባለ የሚነገርላቸው ፕሬዚደንት ቦሪስ ዬልሰን ናቸው:: ግለሰቡ የዚሀ አይነት ውሳኔ ሲወስኑ የክሬሚያን ታሪክ፣ ስትራተጂክ ጠቀሜታ ወዘተ ከቁብ አላስገቡትም፣ የህዝቡንም ስሜት ቦታ አልሰጡትም ነበር። የሳቸው ሩጫ ከምን እንደመነጨ በግልጽ በማይታወቅ መልኩ ጎርባቾቭ የቀደዱትን የለውጥ መንገድ በመለጠጥ ሶቭየት ህብረትን በማፈራረስ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ ክራሚያን በተመለከተም የሶቭየት ህብረት ታላቅ የባህር ሀይል የሆነው ብላክ ሲ ፍሊት ንብረት ሽያጭና ገንዘብ መሰብሰብ ላይ ነበር ትኩረታቸው። ያም ሆኖ  በንግድ አንጻር እንኳ እዚህ ግባ የሚባል ገንዘብ አላገኙበትም።

 

የክራምያን ጉዳይ መደምደሚያ ለመስጠት የተሞከረው በሶቭይት ሕብረት ባጠቃላይ እንዲሁም በራሽያና በተቀሩት  ሶሻሊስት ሀገሮች ታይቶ የማይታወቅ ቀውስ እና አለመረጋጋት በሰፈነበት ወቅት ነበር። በዚያ የቀውስ ወቅት በቂ የሆነ አማራጭና ረጋ ብሎ ለማሰብ ጊዜ ሳይኖር ሬፈረንደም ተካሄደና 58% የሚሆን ህዝብ ደገፈው በማለት ክራሚያ ከሩሲያ ተለይታ የዩክሬን ግዛት ሆና እንድትሄድ ተወሰነ።

 

ይህ ጉዳይ ግን በብዙ ዜጎች ልብ ውስጥ ቁርሾ አስከተለ፤ ጠባሳም ጣለ። የጊዜው ሁኔታ ባይመችና በወቅቱ ማድረግ ስለሚገባቸው ነገር ግራ ቢጋቡም፤ እጅግ ብዙ የክራሚያ ኑዋሪዎች ልባቸው መሸፈቱ አልቀረም፡፡ በዘሩም በታሪኩም ራሽያዊ ነኝ ብሎ የሚያምነው የክሬምያ ሀዝብ የለም ዩክሬናዊ ነህ ሲባል ጥርሱን ነከሰ። ሆኖም ግን በወቅቱ የሚያዳምጠው አላገኝም። ያ ታምቆ የቆየ  ቅሬታ  አሁን በቅርቡ አመጽ ወልዶ እነሆ እየሆነ ያለውንና የሆነውን ዓለም እየመሠከረ ነው።

 

የኤርትራ ከኢትዮጵያ የመገንጠል ዕውነታ ከሶቭየት ህብረት መፈራረስ እና ከቀዝቃዛው ጦርነት “መገባደድ” ጋር በቅርብ የተቆራኘ ነበር፡ “ህዝበ ውሳኔ” (ሬፈራንደም ) የተባለው ሂደትም በሀሪቱ በከፍተኛ ቀውስ ውስጥ በነበረችበት፣ ገና ቋሚ መንግስት እንኳን ሳይኖራት ነበር። በ“ህዝበ ውሳኔ” ሂደት ውስጥም የኢዮጵያዊነት አማራጭ በታፈነበት ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምነውና የሆነውን የአፋርና ኩናማ፣ የሳሆ፤ ወ.ዘ.ተ ህዝብንም ፍላጎት ለማክበር ምንም ጥረት ሳይደረግና ውጤቱም ሳይታይ በግድ ያልሆነውንና ያላመነበትን ማንነት  ተቀበል ተብሎ የተጠናቀቀ የግርግር ሁኔታ ነው። ይህ ስለሆነም እነሆ እስካሁን የቀጠለው ቅሬታ የመሳሪያ ግጭትን ወልዶ ካንድ ቀውስ ወደሌላ በመሽጋገር ላይ ይገኛል።

 

የሚገርመው ከስልሳ አመት በሓላ ሩሲያ በክሩስቼቭ ጊዜ የተጀመረውን ያስተዳደር ክልል ማሸጋሸግ እና በቦረስ ዬልሲን ዘመን የተወሰደውን የረጅም ጊዜ ዕይታ የጎደለውን የፖለቲካ ርምጃ ለማረም የተዘጋጀ ድርጅትና መሪ አግኝታለች። ኢትዮጵያችን ግን በሁሉም መልኩ ሀላፊነት የጎደለውን የመለስ ዜናዊ ለሀገር ደንታ ቢስ የሆነ ውሳኔ ለማረም እና ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ጥቅም በድፍረት የቆመ የመንግስት መሪ ገና አልታደለችም። ያም በመሆኑ መከራውም ቀጥሏል መፍትሄውም እየተወሳሰበ መሄዱ አይቀሬ ሆኗል።

 

የተባበሩት መንግሥታት “የዩክሬንን ሀገራዊ አንድነት ስለማሰከበር” ያካሄደው የድምጽ አሰጣጥ

የክሬሚያ ነዋሪወች በዩክሬን ስር መተዳደርን አንፈልግም ብለው ማጉረምረም ሲጀምሩ ነው ታላላቆቹ የምእራብ መንግስታት ሁኔታውን ለማዳፈን መሯሯጥ የጀመሩት። የክሬምያን ህዝብ ታሪክ፣ ፍላጎትና ማንነት ጠንቅቀው የሚያውቁት ምዕራባውያን ጭንቀታቸው ያነጣጠረው በክሬምያ ላይ ሳይሆን ሩሲያ እንደገና ተጠናክራ በመውጣት ጉዳይ ላይ ስለሆነ ይህንን ለማከሽፍ፣ ባለፈው የካቲት መጨረሻ ገደማ ዩክሬን ውስጥ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠው መንግስት ባመጽ ሲፈነቀል ቃል ያልተነፈሱት ምዕራባውያን፤ በክራሚያ የተደረገውን ሬፈረንደም ተከትሎ ዩክሬን ተወረረ፣ ወዘተ፤ የሚለውን ከበሮ መደለቅ ጀመሩ። ከሁካታው በስተጀርባ ግን አሁን ባለው ሁኔታ ምዕራባውያኑም ሆኑ ራሱ የዩክሬይን መንግስት የክራሚያ ጉዳይ ያለቀለት እንደሆነ የተቀበሉት ይመስላል። ሩጫው ሊፈጠር የሚችለውን ሌላም ምስቅልቅል ሁኔታ ለመቀነስ ምናልባትም ራሱ የዩክሬን እንደሀገር የመቀጠል ጉዳይ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ የመጨነቅ፣ ሰፋ ያለ የርስ በርስ ጦርነት ባውሮፓ ውስጥ እንዳይቀሰቀስ የመፍራት ጉዳይ እንጂ ክራሚያን የማስመለስ ፍላጎት አይመስልም።

 

የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ጥበቃው ምከር ቤት (ድምጽን በድምጽ ሽሮ ጥርስ-አልባ የሆነው) እና ጠቅላላ ጉባኤውም በዚህ ጉዳይ ያስተላለፈውና ከፍተኛ ክፍፍል የነበረበት ውሳኔ “ይህን ብለን ነበር “ ከማለት የማያልፍ ነው። ጠንከር ያለ የማዕቀብ እርምጃ ወሰዱ የተባሉት አሜሪካና የአውሮፓ ማህበረሰብም ቢሆኑ ርምጃቸው ጥቂት ባለስልጣኖችን የሚነካ ከመሆን አላለፈም።

 

ቀረብ ብሎ ሲታይ ደግሞ ያፍሪካ መንግስታት በተለይም የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግስታት የወሰዱት አቋም ትኩረትን የሚስብ ነው፡፡ የሁለቱም ወኪሎች  በተባበሩት መንግስታት ውሳኔ አሰጣጥ ላይ የክሬምያን ከዩክሬን መገንጠል ሳያወግዙም ሳይደግፉም ድምጽ ተአቅቦ (አብስቴን) በማድረግ ማለፉቸውን እንገነዘባላን።

 

ይህ የድምጽ አሰጣጥ ከብዙሀኑ ያፍሪካ ሀገሮች የተለየ አይደለም፤ በተባበሩት መንግሰታት ምክር ቤት ”የዩክሬንን ሀገራዊ አንድነት ማሰከበር “ በሚል ርእስ የክራሚያን መገንጠል ለመቃወም የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ የደገፉ ያፍሪካ ሀገሮች 19 ብቻ ሲሆኑ የተቃውሞ ድምጽ ያሰሙ ሁለት (ሱዳንና ዚምባብዌ ) ድምጸ ተአቅቦ ያደረጉ ደግሞ ወደ 22 ያፍሪካ ሀገሮች ነበሩ። ከነዚህም ውስጥ ኢትዮጰያና ኤርትራ ይገኙበታል። ይህ በሶሰት ቦታ የተከፈለ የድምጵ አሰጣጥ  የሚያሳየው የተባበሩት መንግሥታትም ሆነ ያፍሪካ አንድነት ማህበር በተመሳሳይ ሁኔታዎች ላይ የሚወስዷቸው አቋሞች ከሀገራቸው ፖለቲካ፣ እና ከሚያስገኝላቸው ጥቅም አንጻር እንጂ ከቋሚ መተክልና ዕምነት በመነሳት እንዳልሆነ ነው፡፡

 

ከዚህ ሁኔታ መገንዘብ እንደሚቻለው ለተመሳሳይ ሁኔታወች እያንዳንዱ ሀገር ስለሚወስደው እርምጃ ወሳኙ ጉዳይ “የተባበሩት መንግስታት ወይም ያፍሪካ አንድነት ህግ” ሳይሆን እያንዳንዱ ሀገር የሚያገኘው ጥቅማ ጥቅም እንደሆነ ነው። ባጭሩ የሀይል አሰላለፉን  የሚገዛው መተክል (ፐሪንስፕል) ሳይሆን በጊዜው ሀገራት የሚያገኙት ጥቅም እና የሀይል ሚዛን ይመስላል።

 

ማጠቃለያ

ከዩክሬይን ክራሚያና የሩስያ ጉዳይ የሚገኘውን ትምህርት በከፊል እንደሚከተለው ላጠቃል፡

 

  1. ሀገራዊ ራዕይና አርቆ አሳቢነት ከፖለቲካ መሪዎች (ገዠዎችም ተቃዋሚም ) የሚጠበቅ ተግባር ነው፣

 

  1. ለአጭር ጊዜ ፖለቲካዊ ጥቅም ሲባል የሚወሰዱ ርምጃወች ጦሳቸው እጅግ የተወሳሰበ ይሆናል። ክሬሚያና ዩክሬንን በተመለከተ ፕሬዚደንት ያልሰን የወሰዱት ይህን ያመለክታል፡

 

  1. የህዝብ ታሪክ እንደፈለጉ የሚጽፉት፤ የሚፍቁት ወይም የሚቀያይሩት ኣደለም፡፡ ክራሚያውያን ባገኙት የመጀመሪያ አጋጣሚ ወደ ራሽያ ልመለስ ማለታቸው የሚያሳየውም ይህንኑ ነው፡፡ የክራሚያ ዓይነቱ ጥያቄ በክራሚያ ብቻ አልተወሰነም። አሁን በምሥራቅና ደቡብ ምሥራቅ ዩከሬን 10 ያህል ከተሞች ውስጥ እየተካሄደ ያለውም አመጽና ጥያቄ ባብዛኛው የክራሚያ ነዋሪዎችን ጥያቄ የሚያሰተጋባ ነው።

 

  1. የሀገር መሪዎች ሀገራዊ እና ስትራተጂያዊ ጠቀሜታን ማረጋገጥ ከሁሉም በላይ ግዴታቸው ሊሆን ይገባል። ይህን ሲያደርጉ ደግሞ ዋናው መሠረት የህዝባቸው ፍላጉት፣ ታሪክና እውነታ እንጂ የባዕዳንን ጥቅምና ትዕዛዝ ከማስጠበቅ አኳያ ሊሆን አይገባውም።

 

  1. የሀገሩን ታሪካዊና ስትራተጂያዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚቆም መሪ ደግሞ የህዝብን ድጋፍ የሚያገኝ ለመሆኑ የክሬምያ ሁኔታና የፑቲን ተወዳጅነት ያረጋግጣል። ካውሮፓ፤ ካናዳና አሜሪካ የሚሰማው ተቃውሞ ቢቀጥልም የፕሬዚደንት ፑቲን የህዝብ ድጋፉ እየጨመረ በመሄድ ላይ ይገኛል፡ተጻርረው የቆሙ ደግሞ የተወገዙ ከመሆን እና “የታሪክ ጠባሳ” ተሸክመው ከመጓዝ ሊድኑ አይቸሉም። በቅርብ የተካሄደ አንድ ጥናት እንደሚያሳዪው 85% የራሽያ ህዝብ ፕሬዚደንት ፑቲንን ይደግፋል  http://www.levada.ru/06-08-2014/avgustovskie-reitingi-odobreniya:: በነገራችን ላይ ጥናቱን ያካሄደው ለፑቲን ፍቅር እንደሌለው የሚታወቀው ሊቪዳ የተሰኝው የጥናት ተቌም ነው

 

  1. ባለራዕይ መሪዎች የተለያዩ ታሪካዊ ሁኔታዎች የሚፈጥሩላቸውን አጋጣሚዎች በመጠቀም የትናንት ስህተቶችን ለማረም ቆራጥ እና ፈጣን ርምጃ መውሰድ ይኖርባቸዋል። ይህም ከፖለቲካ ቀኖናና ከአይዲዮሎጂ እሥረኛነት መላቀቅን እና ድፍረትን ይጠይቃል።

 

7.ድርጅቶች ኤርትራን በተመለከተ ያልተዘጋውን አጀንዳ  በጥልቀት በመረዳት የህዝብን ወኔ ከሚሰልብ በሽንፈትና በጨለምተኛነት ከተተበተበ አመለካከትና አካሄድ ራሳቸውን ሊያጸዱ ይገባል እላለሁ:: ወላጆቻችን አያቶቻችንና ቀደምት ትውልዶች  ጠላት የጫነባቸውን ሁሉ “ያለቀለት ነው” ብለው በመንበርከክ ሳይሆን ሀገራዊ ጥቅምን በተመለከተ በጠራ ራእይ ላይ ተመርኩዘው በጽናት በመቆማቸው ነው ያችን ሀገር ለኛ ያወረሱን። እኛስ?

 

አስተያየት ቢኖርወት በሚከተለው ኢሜል አድራሻ ሊልኩልኝ ይችላሉ  ethioandenet@bell.net

 

 

 

↧

ላልተወለድከው ልጄ (በበዕውቀቱ ሥዩም)

$
0
0

ሚስቱ አረገዘችበት ፡ ደነገጠ – እንድታስወርደው ጠየቃት አሻፈረኝ አለች፡፡ በጣም ተቆጣ ! ቁጣው ሲውል ሲያድር ቁዘማ ሆነ ፡፡ ቁዘማው ላልተወለደው ልጁ ደብዳቤ እንዲፅፍ አነሳሳው ፡፡
ሁለት ደብዳቤዎችን እንዲፅፍ አነሳሳው ፡፡ ሁለት ደብዳቤዎችን ፃፈ፡፡ የደብዳቤዎቹ ሙሉ ቃል ይሄ ነው፡፡
አንደኛው ደብዳቤ፡-

lije
ልጄ የወገቤ ክፋይ፡-ከኔ ወገብ ከተለያየንበት እንዲሁም ከእናትህ ማህፀን ከተገናኘህበት ሰዓት ጀምሮ እንደምን አለህልኝ እኔ ትወለዳለህ ከሚለው ሀሳብና ሰቀቀን በስተቀር ደህና ነኝ ልጄ ፡፡
ይሄን ደብዳቤ የፃፍኩልህ የፊደልንና የቋንቋን ጣጣ ከማህፀን እንድትጀምረው ለማስገደድ አይደለም ፡፡
ይልቁንስ ለውሳኔ እንዳትቸኩል ከመምጣትህ በፊት ግራ ቀኙን እንድትመረምር ነው፡፡ አሁን ጨቅላ አይደለህም የ3 ወር ጎረምሳ ነህ ! አውራ ጣትህን መጥባት ጀምረሃል፡፡
ጊዜህን እንደጥንቱ በራስ በመቆም ብቻ እንደማታሳልፈው አውቃለሁ፡፡ ከዚህ በኋላ 6 ወሮች አሉህ ፡፡ በእኚህ ቀሪ ጊዜያት እንድትፋፋባቸው ሳይሆን እንድታስብባቸው እፈልጋለሁ፡፡ ስለሁሉም ነገር አስብ ፡፡
ከመቸኮልህ በፊት አስብ ፡፡ እኔ 40 ዓመት ሞልቶኛል፡፡ ግን በዕውቀትና በጥበብ ካንተ እንደማልበልጥ አውቃለሁ፡፡ ‹‹ ማወቅ ማለት ከውጭ ያለውን መማር ማለት አይደለም፣ ከመወለዳችን በፊት ያለውን ማስታወስ ነው ›› ብሏል ሰውዬው ፡፡
ይህንን ብሂል ያመንኩ ቀን ስቅስቅ ብዬ ነው አለቀስኩ፣ ለካ አባቴ ቄስ ትምህርት ቤት ያስገባኝ ፤ አንደኛ – ሁለተኛ -ሦስተኛ ደረጃ ትምህርት ያስተማረኝ ፤ ባለ ድግሪ ፤ በለ ማዕረግ ያሰኘኝ አልባሌ ቦታ ከምውል ብሎ ኖሯል ፡፡ ስለዚህ ‹‹ የምወለደው ለማወቅ ስለምፈልግ ነው ›› አትበል! ፡፡ እኔ ካንተ አላውቅም ፤ ካንተ አልበልጥም፤ ምናልባት የምበልጥህ በንዴትና በሽበት ብቻ ይሆናል፡፡
ልጄ ወዳጄ የወገቤ ክፋይ እንዳትወለድ የማሳሳብህ ስለምጠላህ አይደለም ! ‹‹እወድሃለው›› – ‹‹እወልድሃለው›› አላልኩም ‹‹እወድሃለው›› ፡፡ ግን የወደድነውን በባዶ ቤት አንጋብዝም ፤ እናትህ ‹‹ ሁላችንም እዚህ ምድር ስንመጣ ዕርቃናችንን ነው ›› ትላለች ፡፡ ብወዳትም አላመንኳትም ፡፡
ጥቂቶች ለብሰው እንደሚወለዱ አውቃለሁ፡፡ ለምሳሌ ከካናዳ የመጣች ጓደኛዬ ስትነግረኝ ካናዶች አንድ ልጅ ሲወልዱ ብዙ ሺህ ብር ከመንግስት ይሰጣቸዋል፡፡ የስካንዲቪያን ሠዎች አርግዘው በታዩ ጊዜ አስተዳደሮቹ ለመጪው ልጅ የሚሆን ቁሳቁስ ፣ ቤት ያሰናዱላቸዋል፡፡
የፈረንጅ ልጆች ስንቅ ሳይዙ ወደዚህች ምድር አይመጡም ! ለፈረንጅ አባቶች ልጅ ክፍት የስራ ቦታ ማለት ነው ፡፡ ሲሳይ ነው ፡፡ ስለዚህ አንድ ካናዳዊት ብታስወርድ እህል የሞላው ጎተራ አቃጠለች ማለት ነው፡፡ እኔ አሁን ውጭ ሀገር ኖሬ አላውቅም ፣ ግን የሰማሁትን ይዤ ብዙ አስባለሁ፡፡
የፈረንጅ ሽማግሎች ጡረታ ሲወጡ በመውለድ የሚጠመዱ ይመስለኛል፡፡ በዕድሜዬ መግፋት ያጣሁትን ደመወዝ በሚስቴ ሆድ መግፋት እመልሰዋለሁ የሚሉ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ የተነሳ እናትህ ‹‹እናትህ ሁላችንም የመጣነው ዕርቃናችንን ነው›› ስትል የባልነቴን ጭንቅላቴን ባወዛውዝላትም አላምናትም፡፡
ከላይ እንዳስነበብኩህ የፈረንጅ ልጆች ለብሰው ይወለዳሉ ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ለወላጆቻቸው ካፖርትና ቀሚስ ይዘው ወደዚህች ዓለም ይመጣሉ ፡፡ የሀበሻ አባት ግን ሚስቱ ስታረግዝ የድሮ ሱሪውን ማሳጠር ይጀምራል፡፡ አለበለዚያ ልጁ ሲወለድ ምን ይለብሳል ? ልጄ ወዳጄ የወገቤ ክፋይ ፡- ይሄ ሁሉ የሆነው በእኔ ጥፋት አይደለም ፤ ጥፋቱ ሁሉ የእናትህ ነው፡፡ እመነኝ ፡፡
የመጀመሪያ ስህተቷ ሴት መሆኗ ነው፡፡ ግዴለም ትሁን ፤ – ለምን ተቆነጃጀች ? – ግዴለም ትቆንጅ ፤ ለምን በደጄ አለፈች ? – ግዴለም ትለፍ፤ ለምን ሠላምታዬን መለሰች ? – ግዴለም ትመልስ፤ ለምን እኔን አመነች ? – ግዴለም ትመን፤ ለምን እሺ ብላ ተሳመች ? – ግዴለም ትሳም፤ ለምን…… ? – ግዴለም አንዴ ሆኗል ! ፡፡ ልወቅሳት አልፈልግም ምክኒያቱም እወዳታለሁ፡፡
እንዲያውም ጥፋተኛው እኔ ሳልሆን አልቀርም ፡፡ የመጀመሪያው ስህተቴ ወንድ መሆኔ ነው ፤ ወንድ ባልሆን ኖሮ ከድንበር አትሻገራትም ነበር ፡፡ ክኒኑን እንደ ቁርስ ምሳዬ ሳላሰልስ እወስደው ነበር ፡፡ የክኒንና የወንድ ዝምድና ግን አይገርምም ? ወንዶች ክኒንን ይሰሩታል – ሴቶች ይውጡታል፡፡ የለም! ስህተቱ የእኔም የእናትህም አይደለም ! ያንተ ነው፡፡ መጀመሪያ ማሰብ ነበረብህ >
እኔና አናትህ መደሰት መብታችን ነው ለመደሰት ቀን መቁጠር የለብንም ! አንተ መወለድ መብትህ ነው ግን መብትህን ለመጠቀም ጊዜና ቦታ መምረጥ አለብህ ፡፡ አሁን ምን አጣደፈህ? ተው እንጂ ልጄ ጥድፊያ በዘራችን የለም ! ምናልባት ‹‹ዕድገት እየታየ ነው›› የሚል ወሬ ከሰማህ አትመነው ፡፡ ከእናት ሆድ በስተቀር እዚህ ሀገር ያደገ ነገር የለም፡፡
ልጄ በርግጥ ካንተ ጋር እደራደራለሁ፡፡ ካልተወለድክ በጣም ብዙ ነገር ላደርግልህ ቃል እገባለሁ ፡፡ ካልተወለድክ ጥሩ አባት እሆንሃለው፡፡ አስብበት!፡፡ የማነበው መፅሀፍ ላክልኝ ባልከው መሰረት የአቤ ጉበኛን ‹‹ አልወለድም›› ን ልኬልሃለው ፡፡ መልስህን በቶሎ እጠባበቃለሁ፡፡
*****
ሁለተኛ ደብዳቤ :
እምቢ አልክ ! መልዕክትህን አንብቤ ደሜ ፈላ! ግትር ነህ ! ቂል ነህ ! ‹‹ የወፎችን ድምፅ መስማት ስለምፈልግ በቅርቡ እወለዳለሁ›› ብለሃል ፡፡ አትጃጃል፡፡
የሞባይልና መኪና እንጂ የወፍ ድምፅ እዚህ አዲስ አበባ ከየት አምጥተህ ነው የምትሰማው ? ፍላጎትህ ይህ ከሆነ አማዞን መሀል ተፈጠር፡፡ በአጠቃላይ መልዕክትህ ሁሉ ግትርነትህን የሚያሳይ ነው ! ፡፡ እናትህ ልዝብ ጨዋ ናት፡፡ ቤተሰቦቿም ለስላሶች ናቸው፡፡
እኔም ትሁትና ተግባቢ ነኝ ታዲያ ይሄ ግትርነት ከየት መጣ ? በሁለታችንም ደም ውስጥ ግትርነት ከሌለ አንተ ከየት ወረስከው ? መቼም ልጄ ነህ ብዬ ለማመን መልክህን የግድ ማየት የለብኝም፡፡ ጠባይህም ከእኔ የተገኘ መሆኑን ማወቅ አለብኝ ፡፡ ባህሪህ የእኔ አይደለም ፡፡ የእናትህም አይደለም፡፡ ስለዚህ የእኔ ልጅ አይደለህም ፡፡ ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ የምነጋገረው ካንተ ጋር አይደለም ፤ ከእናትህ ጋር ነው ፤ ከእርሷ ጋር ሁሉን እንጨርሳለን፡፡
*****
© በዕውቀቱ ሥዩም

↧
↧

ወያኔ፣ ሽብር እና እኛ (ያሬድ ኃይለማርያም)

$
0
0

ያሬድ ኃይለማርያም

ከብራስልስ

መስከረም 3 ቀን 2007 ዓ.ም.

 

Woyanes shoud face justiceበአለም አቀፍ ደረጃ ስለ ሽብርተኝነት ያለው አረዳድ እና ወያኔ ሽብርተኝነትን የሚተረጉምበት መንገድ ለየቅል ናቸው። በአለም አቀፍ ደረጃ የሽብርተኝነት ጉዳይ እንደ ዋና አጀንዳ ተይዞ ለመጀመሪያ ጊዜ መነጋገሪያ የሆነው በ1934 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ነው። በዛሬው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተተካው የሊግ ኦፍ ኔሽን በሽብርተኝነት ዙሪያ ሲመክር ቆይቶ በ1937  ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ሽብርተኝነትን ለመከላከል እና ለመቅጣት የሚያስችል አንድ ድንጋጌ (Convention for the prevention and punishment of terrorism) አጽድቋል። ከዚህ ድንጋጌም በኋላ ከ14 የሚበልጡ አለም አቀፍ ድንጋጌዎችና ስምምነቶች በተባበሩት መንግስታት ጸድቀዋል። የእነዚህ ሕጎች ዋነኛ አላማም መንግሥታት ሽብርተኝነትን በተናጠልም ሆነ በጋራ እንዲዋጉ ለማስተባበር ብቻ ሳይሆን  ሽብርተኝነትን እንዋጋለን በሚል ሽፋን በዜጎቻቸውም ሆነ በተቀረው የሰው ዘር ላይ መድልዎን፣ ግፍና በደሎችን በመፈጸም ሰብአዊ መብቶችን ለማክበርና ለማስከበር የተጣለባቸውን አለም አቀፋዊ ግዴታ እንዳይዘነጉም ለማሳሰብ ነው። ምንም እንኳን ኃያላኖቹ አገራት ሳይቀሩ የጸረ-ሽብር ዘመቻን ለፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞቻቸው ማስገኛ ሲያውሉትና ሲመነዝሩት በግልጽ ቢስተዋልም በሽብርተኝነት ላይ ያላቸው ምልከታና አቋም ግን በአለም አቀፍ ደረጃ ከተቀመጡት መመዘኛዎች የራቁ አይደሉም።

በወያኔ መንደር ሽብርተኝነት ለየት ያለ መልክ ነው ያለው። የወያኔ የሽብርተኝነት መስፈርትም ሆነ ትርጓሜ ብዙ ሃገሮች፤ አንባገነን የተባሉት ሳይቀሩ ስለሽብርተኝነት ካላቸው ግንዛቤም ሆነ ከአለም አቀፉ መመዘኛዎች የተለየ ነው። የሽብርተኝነት ተግባር እየተተረጎመ ያለው በወያኔ ባልሥልጣናት የመሸበር መንፈስና ሰለራሳቸው ሥልጣን ብቻ በማሰብ ከጭንቀት በመነጨ የፍርሃት ስሜት ላይ የተመሰረተ ነው:: ባለሥልጣናቱን ጭንቅት ወስጥ የሚጥል፣ የሚያስደነብር፣ የሚያስቀይም፣ የሚያስቆጣ ወይም የሚያሰፈራራና እንቅልፍ አጥተው እንዲያድሩ የሚያደርግ ተግባራትን የፈጸመ ሁሉ በሽብርተኛነት ይፈረጃል:: ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ቀይ መስመር አስምረውና አዋቅረውት የሄዱትን የወያኔን አጥር የሚነቀንቅ ብቻ ሳይሆን ጠጋ የሚልም ሁሉ በአሸባሪነተ ሊፈረጅ፣ ሊታሰርና ሊከሰስ እንዲሁም ሊፈረድበት እንደሚችል እየታየ ነው:: ለአገዛዝ ሥርዓቱ የሥልጣን ዘመን መራዘም ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ የሚሉዋቸውን አካላትና ግልሰቦች ሁሉ አሸባሪ አያሉ መክሰስ የተለመደ ሆኗል። ብዕራቸውን አንስተው በመንግሥት ላይ የሰሉ ትችቶችን በመጻፍ ተቃውሟቸውን የገለጹ፣ የሃይማኖትና የተለያዩ ማህበራዊ ተቋማትን በመወከል የመብት ጥያቄዎችን አንስተው የተሟገቱ የሕዝብ ወኪሎች፣ በወያኔ በባለሥልጣናት የተፈጸሙ ወንጀሎችን፣ ሙስናዎችን፣ አገርና ሕዝብን ያዋረዱ ተግባራትን ያጋለጡና ባደባባይ ሥርዓቱን የሞገቱ ጋዜጠኞች፣ የማህብራዊ ድረ-ገጽ ገተሳታፊዎች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ጭምር የሽብርተኝነት ካባ እያከናነቡ ማጎርና መወንጀል የሥርዓቱ ዋና ስልት ሆኗል። ይህም ወያኔ አለም በሚሸበርበት ጉዳይ ሳይሆን ራሱ በፍርሃት በፈጠረው የሽብር ዓለም ወሰጥ መሆኑን ያሳያል::

ከግለሰብ (ከሟቹ ጠ/ሚ መለስ) አንባገነናዊነት ወደ ቡድን አንባገነናዊነት የተሸጋገረው የወያኔ-ኢሕአዴግ ሥርዓት ከመቼው ጊዜ በከፋ ሁኔታ በፍርሃት መዋጡን የሚያመላክቱ በርካታ ክስተቶችንም እያስተዋልን ነው። ፍጹም አምባገነንና ፈላጭ ቆራጭ የነበሩትን አቶ መለስ በብዙ ትናንሽ መለሶች ለመተካት ተጥሯል። ምንም እንኳን በበቂ ማስረጃ ማረጋገጥ ባይቻልም የሥርዓቱ ተዋናይ ከነበሩ እና አሁንም በሥልጣን ላይ ካሉ የአመራር አባላት እየሾለኩ የሚወጡት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በድርጅቱ ውስጥ ባሉት ጎሣን መሰረት ያደረጉት ክፍልፋዮች መካከል ከሚስተዋለው ጤናማ ያልሆነ የፖለቲካ ፉክክር እና ሽኩቻ ባሻገር በግለሰቦች ዙሪያ የመቧደን ስሜት እየጎላ በመምጣቱም ድርጅቱ ውስጥ ፍርሃት እንዲነግስ አድርጓል። ይህንን ክፍተት በመጠቀም በሰላማዊም ሆነ በነፍጥ ኃይል የሥርዓት ለውጥ ለማምጣት የተደራጁ የፖለቲካ ኃይሎችና ቡድኖች መነቃቃትም በፍርሃት ውስጥ ያለውን የወያኔን ሥርዓት የበለጠ እንዲደነብር አድርጎታል።

በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰላማዊ ትግል አምነው ከተደራጁት የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የተወሰኑት  በተከታታይ ያካሄዷቸው የተቃውሞ ሰልፎችና የሕዝብ ምላሽ፣ አፈና እና ስቃዩን ተቋቁሞ ለአመታት የዘለቀው የሙስሊሙ ማኅበረሰብ እንቅስቃሴ፣ ልማትን ሽፋን አድርጎ ሥር እየሰደደ ያለው የኑሮ ዋስትና መታጣትና የከፋ ድህነት፣ በሃያ አመት ውስጥ የተዘራው የዘር ፖለቲካና በአዲሱ ትውልድ አእምሮ ውስጥ ፍሬውን አፍርቶ በሥርዓቱ ላይ ጭምር የዘር ጥላቸቻን ማሳየቱ እና ሌሎችም ውጫዊ ምክንያቶች ተደማምረው ገዢውን ኃይል እንዲፈራና የፈሪ ዱላውንም እንዲያነሳ አስገድደውታል። ዛሬ የወያኔ አመራሮች ሕዝብን ብቻ ሳይሆን የሚፈሩት እራሳቸውንም ጭምር ነው። ድርጅቱ አባላቱን ይፈራል፣ በአወራውና አጃቢ ድርጅቶች መካከል መፈራራት አለ፣ አባላቱ እርስ በርስ ይፈራራሉ፣ አባላቱ መሪዎቻቸውን ይፈራሉ፣ መሪዎች ተከታዮቻቸውን (ተራ ካድሬውን) ይፈራሉ፣ በአመራር ላይ ያሉት ሰዎችም እርስ በርስ ይፈራራሉ። የአንድ ላምስት የስለላ መዋቅር ምንጩም ይህ ነው። አንድ ሥርዓት ጭልጥ ወዳለ አንባገነናዊነት (totalitarianism) ሲገባ ሕዝብን ብቻ ሳይሆን እራሱንም ይፈራል:: በደርግ ዘመንም የሆነው የሄው ነበር:: ለዚህም ነው በእንዲህ ያሉ ሥርዓቶች ውስጥ አባላቱና ደጋፊዎች ከሚሰሩበት ይልቅ እርስ በርስ የሚገማገሙበት ጊዜ ሳይበልጥ አይቀርም የሚባለው።  ሕዝብን እና ራስን መፍራት የሽብር መንፈስ ውስጥ ይከታል።

የፖለቲካ ተቀናቃኞችንና የሰላ ትችት የሚሰነዝሩበትን ሁሉ አሸባሪ እያሉ የጥቃት ዒላማ ማድረጉም ዋነኛ አላማው አነሱን ከትግሉ ሜዳ ለማሸሽ ብቻ ሳይሆን የቀረውንም ሕዝብ ለማሸማቀቅና በፍርሃተ ውስጥ ሆኖ ጸጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛም ለማድረግ ነው::  ሥርዓቱ የሕዝብ ስላልሆነ ሕዝብን ይፈራል። ለነገሩ ሕዝብን ብቻ ሳይሆን ለጥቅም ሲሉ በዙሪያው የተኮለኮሉትን ሹማምንት፣ አባላቱን እና ‘የአባቴ ቤት ሲዘረፍ አብሬ ልዝረፍ’ በሚል ሕሊና ማጣት ወይም አይን ያወጣ ሌብነት የከበቡትን ‘መሁራን’ና ባለሃበቶች ጭምር ይፈራል:: በመሆኑም የሥርዓቱ ደጋፊዎችና አባላቱ ከሌላው የህብረተሰብ ክፍል በከፋ ሁኔታ የአፈና መዋቀሩ ዋነኛ ሰለቦች ናቸው:: አንድ የወያኔ-ኢህአዴግ አባል የሆነ ሰው በአባልነቱ የተለያዩ ቁሳዊ ጥቅሞችን በብቸኝነት ወይም በቅድሚያ ከሌላው ሰው ተለይቶ የማግኘት እድል ይኖረዋል:: ይሁን እንጂ ይህ እድል በነጻነት ማሰብን፣ ሃሳቡን በነጻነት መግለጽን፣ ያመነበትን የፖለቲካም ሆነ ሌሎች አስተሳሰቦቹን ባደባባይ ማንጸባረቅን ወይም ባመነበት ጉዳይ አቋም የመያዝን፣ በመንግሥት ፖሊሲዎችና አፈጻጸሞች ላይ የሰሉ ትችቶችን የመሰንዘር ባጠቃላይ የፖለቲካና የሲቪል መብቶቹንና ነጻነቶቹን አያጎናጽፈውም:: በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ ሰዎች የነጻነትን ጣእም አያቁትም።

ጥልቅ በሆነ ፍርሃት ወስጥ ሆኖና ውሉ በማይታወቅ የሸብር ስጋት ተሸብሮ ሕዝብን ማሸበር፣ በጎሣ ፖለቲካ የሰበጣጠሩትን ሕዝብ የቡና ማህበር ድረስ ሥር የሰደደ የአፈና መዋቅር ዘርግቶ በመጠርነፍ የልቡን እንኳን ቡና እየጠጣ እንዳይተነፍስና በሌሎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቹም እንዳይተዛዘንና እንዳይረዳዳ ማድረግ ሥርዓቱ አገሪቱን እና ሕዝቡን ይዞ ሊገባ እየተንደረደረ ያለበትን ጥልቅ ገደል ያመላከታል:: በቅርቡ የኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች ያነሱዋቸው ጥያቄዎች ባህሪያት እና የሥርዓቱ ምላሽ የዚህን አደጋ ቅርበት ጥሩ አድርጎ ያሳያል:: እንግዲህ የሁሉም ሰው ጥያቄ እንዲህ ፈርቶ እያስፈራራ፣ ተሸብሮ እያሸበረ፣ ሕዝብንም አገልጋዮቹንም አፍኖ አገሬውን ሁሉ የቁም እስረኛ፤ ቀሪውንም በየማጎሪያው ካምፑ ከርችሞ እያሰቃየ ያለውን ክፉና በአጉል ቀን የተጣባንን ሥርዓት በምን መላና ዘዴ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከትከሻችን ላይ አውርደን እንገላገለው የሚል ይመስለኛል:: ለዚህ ጥያቄ መልስ ማግኘት እንዲህ ቀላል ባይሆንም ወደ መልሱ የሚያመሩ መንገዶችን ግን መጠቆም ይቻል ይሆናል::

 

እኛስ?

ሥርዓቱ ዕለት ተዕለት በአገርና በሕዝብ ላይ የሚፈጽማቸውን ወንጀሎችና ደባዎች፤ እንዲሁም የሰብአዊ መብት ረገጣዎች እየተከታተሉ በማጋለጥና ሕዝብ እንዲያውቀው በማደረግ ረገድ የግል ሚዲያውና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ትልቁን ሚና ተጫውተዋል:: ይሁንና ጥረታቸውን የሚያግዝና ሥርዓቱን ሊያርቅ የሚችል ሌላ የተጠናከራና አገራዊ ዕራይ ያነገበ ኃይል ሊፈጠር ወይም ከተፈጠረም በዘላቂነት ሊቆይ ባለመቻሉ የተቆለሉት ወንጀሎችና ጥፋቶች የወያኔን ገጽታ ወደ አስፈሪ ጭራቅነት አግዝፈውታል:: በተቃዋሚ ጎራ ውስጥ ያሉ ቡዙዎቹ የውይይት መድረኮችና ሚዲያዎች ወያኔን ለማዋረድ በማሰብ ብቻ በየቀኑ የሚያዥጎደጉዱት ፕሮፓጋንዳ ብዙዎች ወያኔን የማይደፈር ኃይል አድርገው እንዲያስቡት እስተዋጾ አድርጓል:: ከዚያም በላይ ከጥላቻ ያልዘለለው የአንዳንድ ሚዲያዎች ያላቋረጠ የጸረ-ወያኔ ፕሮፓጋንዳ ተደማምሮ ደርግ አላሸቆት የሄደውን የሕዝብ ወኔና የመንፈስ ጥንካሬ እንዳያገግምና የፖለቲካ ምህዳሩን እንደ ፈንጂ ቀጠና እንዲያየው አድርጎታል:: ወያኔ ባያወቀው ነው እንጂ እነዚህን ሚዲያዎች ለማፈንና ከሕዝብ ዘንድ እንዳይደርሱ ለማድረግ የሚጥረው እነዚህ ሚዲያዎች ባለውለተኞቹ ናቸው:: በግምት 95% በሚሆነው ዘገባቸው የወያኔን ወንጀል የመፈጸም ችሎታ፣ አቅምና የአፈጻጸም ሥልቱን፣ ስለ ተደራጀው የአፈና መዋቀሩ፣ ወደር ስለሌለው ጭካኔው፣ ከሕግ በላይ ሰለመሆኑ እና ያሻውን ቢያደርግ የሚመልሰው አንዳችም ኃይል አለመኖሩን ነው ነጋ ጠባ የሚዘከዝኩት:: ወያኔ እነኚህን መድረኮች ከሚያፍናቸው ይልቅ ሕዝብን የማስፈራራቱን ሥራ እየሰሩለት ስለሆነ በእጅ አዙርም ቢሆን ገንዘብ እየደጎመ ቢያጠናክራቸው አድሜውን ለማራዘም ይረዱታል::

በእነዚህ መድረኮች እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ስላለው እምቅ ኃይል፣ በሰውነቱ ሰለተጎናጸፋቸው መበቶችና ነጻነቶች፣ ከሌሎች ጋር በጋራ አብሮ ሲቆም ሊፈጥር ስለሚችለው ኃያል ጉልበትና ተአምር፣ ሕዝብ እንዴት የሥልጣን ባለቤትነቱን ማረጋገጥ እንደሚችል፣ የሰላማዊ እመቢተኝነት ኃያልነትን ማወራትና ማሰተማር የተለመደ አይደለም:: ወያኔን ለመታገል በተቃራኒው ተደራጅቶ ሰለቆመውም የፖለቲካ ኃይል ከሚናገሩት ውስጥ አመዛኙ መርዶ ነው:: አንጃ ተፈጠረ፣ ኅብረት ፈረሰ፣ ውህደቱ መከነ፣ እገሌ ከዳ፣ እገሌ የተባለው ፓርቲ ‘እገሌ-ዲ’ የተባላ ደባል አፈራ የሚሉና አዳዲስ ግንባሮችና ውጥኖች መጠንሰሳቸውን ሰምቶ የሚቦርቀው ሰው ላቡን ሳያደርቅ ደም እንባ የሚያስለቅሱ የክሸፈት መርዶዎችን ያበስሩናል:: እንደ እኔ እምነት እነዚህ ሚዲያዎችም ሆኑ የሚዲያዎቹ ተሳታፊዎች የሳቱት ትልቁ ነገር የኢትዮጵያ ሕዝብ ዝምታ የወያኔን ደባና ወንጀል በደንብ ካለማወቅ ነው ከሚል መነሻ ላይ ሆነው ሥራቸውን መጀመራቸው ይመስለኛል:: ተደበደብክ፣ ታሰርክ፣ ታፈንክ፣ በላይህ ላይ ሞሰኑብህ እያሉ ለተደበዳቢው፣ ለታፋኙ፣ ለታሳሪው፣ ሌት ከቀን የግፍ እንቆቆውን ለሚጋተው ሰው ለራሱ ‘ሰበር’ ዜና እያሉ ማደንቆር ተበዳዩን አያጀግነውም፣ ለትግልም አያነሳሳውም፣ ብርታትም ሊሆነው አይችልም:: የማይካደው ቁምነገር ግን ቢያንስ በደሌን ሕዝብ አውቆልኛል ብሎ አንዲጽናና እና አሱም የሌሎችን በደል እያደመጠ በደልን እንዲላመድ ይረዳው ይሆናል::  ለዛም የምስለኛል ይህ ሁሉ መከራ ቢሚወርድበት አገር ከ90 ሚሊዮን ሕዝብ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ብቻ ለራሳቸውና ለሕዝብ ነጻነትና ከብር ባደባባይ ወጥተው የሚታገሉት:: ለዚህም ይመስለኛል ሃዲዱን የሳተውን የአገሪቱን የፖለቲካ አቅጣጫ ለማስተካከልና መረን የለቀቀውን የወያኔን ባህሪ ለማረቅ ዕዳው በጣት በሚቆጠሩ ግለሰቦችና ደርጅቶች ላይ የተጫነው:: እዚህ ላይ ለማሳሰብ የምወደው ሥርዓቱ የሚፈጽማቸው ወንጀሎችና ጠፋቶች አይነገሩ፣ ሕዝብ እንዳይሸበር ተሸፋፍነው ይቅሩ እያልኩ አይደለም::

ሕዝቡ የሚደርስበትን በደል ጠንቅቆ ሰለሚያወቅ እሱኑ ነጋ ጠባ አያወጡና እያወረዱ ማብጠልጠል መፍትሄ አይሆንም:: ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ ጋዜጠኞችም ሆኑ ሌሎች የለውጥ ኃይሎች በሕዝቡ ውስጥ የሰረጸውን ጨለምተኝነት ለመግፈፍና ሕዝቡም የትግሉ አካል እንዲሆን፤ እንዲሁም የአገሬ ጉዳይ ያገባኛል፣ ባለድርሻም ነኝ፣ ኃላፊነትም አለብኝ፣ ለውጥ ለማምጣትም የሚያስችል አቅም አለኝ በሎ ማሰብ እንዲጀምር ሊያስተምሩትና አቅሙን አጉልተው ሊያሳዩት ይገባል:: መልካም ዜጋን የመገንባት ሥራ ላይ ልናተኩር ይገባል:: የአገዛዝ ሥርዓቱን አያገዘፉ ሕዝብን ማኮሰስና ማስፈራራት ወያኔ እንደተፈራ ሌሎች አስርት ዓመታትን እንዲቆይ ይረዳዋል:: ሸነጥ ሲያደርገን በቻ እየተነሳን ሥርዓቱን የገለባ ክምር አድርጎ በማቅለል በስድስት ወር እንንደዋለን፣ የመሪዎቹን ጉሮሮ አንቀን ከምድረ ገጽ እናጠፋለን አያሉ መፎከርና ለአመታት ይህንኑ እየደጋገሙ መማልና መገዘት በጭንቅ ውስጥ ያለውን ሕዝብ በቀቢጸ ተሰፋ እንዲቆይና በአገር ላይ የተጋረጠውንም አደጋ በቅጡ እንዳያይ በማድረግ መዘናጋትን ይፈጥራል እንጂ ግዴታውን እንዲወጣ አያነሳሳውም:: ፉከራና ቀረርቶውም እየተስተዋለ ይሁን::

በቸር እንሰንብት!

ከያሬድ ኃይለማርያም

↧

ቅድመ ምርጫ 2007 እና የተቃውሚዎች እጣ ፋንታ (ሀይለሚካሄል ክፍሌ ከኖርዌይ ኦስሎ)

$
0
0

ሀይለሚካሄል

Election2007መቼም የምርጫ ነገር ሲነሳ በኢትዮጵያ ታሪክ የጎላ ቀለም ያለው ምርጫ 97 ነው ምክንያቱም ከዚ በፊት የነበሩት ምርጫዎች በኢህአዲግም ሆነ በደርግ መንግስት የነበሩት የይስመላ ምርጫዎች ነበሩ ምርጫ 97ም ቢሆን የዲሞክራሲ ጭላንጭል የታየበት በአዲስ አበባ እስከ ምርጫው እለት ሲሆን በክልሎች ግን ምርጫው አንድ ወር እስኪቀረው ነበር በክልሎች ገዝው ኢህአዲግ ቀሪውን አንድ ወር አፈናውን እናወከባውን አጠናክሮ ከመቀጠሉም በላይ አልፎ አልፎ ጠንካራ ተፎካካሪዎች ባሉበት ክልል ግድያም ይፈፅም ነበር በአዲስ አበባም ቢሆን ከምርጫው ውጤት በዃላ የምርጫውን ውጤት በመቀልበስ የዲሞክራሲ ጭላንጭሉን አጨልሞታል ከዚያም በዃላ የምርጫውን ውጤት ተከትሎ በሃይል ገንፍሎ የወጣውን የህዝብ ቁጣ በሃይል ከመቀልበስ ውጭ አማራጭ ያጣው ኢህአዲግ አፈናውን እና ግድያውን አጠናክሮ በመላ ሃገሪቱ ቀጠለ እናም ተቀዋሚ ጎራው እጣ ፋንታውግማሹ እስር ቤት ግማሹም ኢህአዲግ ባሰመረለት መንገድ መሄድ ብቻ ሆነ እናም የምርጫ 97 ድራማ በዚህ መልኩ ተጠናቀቀ ቀሪው አምስት አመት ቀጣዩ ምርጫ እስኪመጣ ግምት ሰጥቶት የነበረውን የምክር ቤቱን ከ540አካባቢ መቀመጫ አንድ አራተኛ ለተቀዋሚ በመስጠት ያለውን የውጭ ጫና በማቅለል የተዘጉትን የእርዳታ ማእቀብ ለማስለቀቅ የሰራው የሂሳብ ስሌት ባለመሳካቱ እራሱን እንዲፈትሽ ምርጫው ትልቅ ማሳያ ሆኖታል በምርጫው ማግስት ኢህአዲግ ውጤቱን በሃይል መቀልበሱ በብዙዎች ቢታመንም ለኢህአዲግ ግን ውጤቱ ያልጠበቀው እና ያልተዘጋጀበት በመሆኑ በቀጣዩ የምርጫ ጊዜ ኢህአዲግ ካለፈው ተምሮ ብዙ ነገሮችን እንደሚያስተካክል የብዙዎች ግምት ቢሆንም ፓርቲው ግን ካለፈው ተምሬአለሁ የሚለውን የምፀት አባባል በአደባባይ እየተናገረ ለቀጣዩ 2002 የምርጫ ዘመን የሚከተለውን መዋቅር ዘረጋ
ከምርጫ 97 በዃላ በዋነኛነት የተወሰዱ እርምጃዎች

1 በህትመት እና በህትመት ውጤቶች ላይ ጫና መፍጠር እና አፋኝ የሆኑ የፕሬስ ህግ አዋጆችን መተግበር

2 በፀረ-ሽብር እንቅስቃሴ ከአሜሪካ ጋር በህብረት ፀረ-ሽብርተኝነትን መከላከል መርህ ሰበብ በምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካ ዋነኛ አጋር በመሆን ጠቀም ያለ ወታደራዊ የቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ ኢህአዲግ መራሹመንግስት እንደሚያገኝ ይታወቃል መንግስት ይሄንን የሽብር ጥቃት መከላከል  በብ በመጠቀም በሃገርውስጥ የፀረ- ሽብር አዋጅ በማቋቋም ብሎም በመተግበር በሃገርውስጥ በሰላማዊ ትግል የተደራጁትን ፓርቲዎችን እና የነፃነት እና ዲሞክራሲ እጦት ተቋውሞ እንቅስቃሴዎችን በሽብርተኝነት በመፈረጅ አዋጁን በመጠቀም ብዙዎችን ለእስር በመዳረግ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴዎችን መድረክ ማጥበብ ማቀጨጭ እና ብሎም ማጥፋት

3 በምርጫ 97 ከታዩት ጉልህ የኢህአዲግ ስህተቶች ወጣቱን በተለይ ሰራአጥ ወጣቶችን በአደገኛ ቦዘኔነት መፈረጅ እንዲሁም የተማረውን ሃይል ማግለል ስለነበር ይህንን እንደፓርቲው ስህተት በመቁጠር የሙሁሩን ጎራ በከፊልም ቢሆን መተካካት በሚል መርህ ጥቂት ጥቅማጥቅሞችን በማጋራት ብሎም ሙያዊ ሹመቶችን በመስጠት ልማታዊ ሙህር ልማታዊ ጋዜጠኛ ልማታዊ ዶክተር ወ.ዘ.ተ እያለ ወደዱም ጠሉም የፓርቲው አባል ማድረግ

4 ስራ አጥ ወጣቶችን በየቀበሌው እንዲደራጁ በማድረግ ባቋቋማቸው የማታለያ ገንዘብ ብድር ተቋማት ብድር በመፍቀድ እንዲደራጁ በመፍቀድ ሲደረግ ለዚህም የመጀመራያው መስፈርት የድርጅቱ አባል መሆን ሲሆን ለዚህም ዋናው አላማ ለተቀዋሚው ጎራ አባል ለመሆን እየሄደ የለውን ወጣት በጥቅማጥቅም ማስቀረት

5 ቀሪውን የህብረተሰብ ክፍል በተለይ ቀበሊ ነዋሪዎችን አንድ ለአምስት መርህ በኢህአዲግ ቋንቋ(መጠርነፍ)መያዝ እና በህዝቡ ቁጥር ልክ የሚመስል የደህንነት ሃይል ማሰማራት ይሄውም ተቀዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በህዝቡውስጥ ገብተው ምንም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ማድረግ

6 ልማታዊ መንግስት በሚል መርህ በየመንደሩ በእርዳታ ድርጅቶች የተሰሩትን የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በኮብል እስቶን በመቀየርለዚሁም በአብዛኛው ሰራ የሌላቸውን ወጣቶችን በማሰማራት አላማው ጥሩ ቢሆንም ከህብረተሰቡ የሚጠየቀው ገንዘብ ግን የተጋነነ ነው::

ኢህአዲግ ግን በዚህ ሲስተም በአንድድንጋይ ሁለት ወፍ የሚለውን የአባቶች አባባል ተጠቅሞበታል ይሄውም በልማት ሰበብ ለአባላቱ ጠቀም ያለ ገንዘብ ማስገኘት እና ሌላው አዳዲስ አባሎችን ማብዛትነው እንግዲህ እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን የኢህአዲግ የ2002 የምርጫ ዝግጅት ማስቀየሻ ስልቶች ሲሆኑ እንደእቅዱ ሲተገበር ያተረፈው ነገር እጅግ ብዙ ቁጥር ያለው ደጋፊ ማፍራት ቢሆንም እውነታው ግን ኢህአዲግ ያፈራው እውነተኞቹን ደጋፊዎችን ሳይሆን በጥቅም የታሰሩትን እና ለሆዳቸው የተገዙ ደጋፊዎችን ሲሆን የዚህም የመጨረሻ ውጤት የደጋፊው ቁጥር በጨመረ ቁጥር የሁሉንም ጥቅም መጠበቅ አይቻልም ደጋፊዎችም ጥቅመኞች ስለሆኑ ልማታዊ ሳይሆኖ በተቃራኒው ሙሰኞች እና ዘራፊዎች ናቸው እናም የኢህአዲግ ጠላቶች የሚመነጩት ከራሱ ደጋፊዎች ሲሆን እነሱም እነዚህ በጥቅም የመጡቱ ጥቅማቸው በተቋረጠ ጊዜ የኢህአዲግ የመጨረሻ ጠላቶች ናቸው እንግዲህ ከላይ በጠቀስናቸው የማስቀየሻ ስልቶች ኢህአዲግ ምርጫ 2002ን ያለምንም ተቀናቃኝ ምርጫውን 99ፐርሰንት አሸንፌአለሁ ለማለት አስችሎታል ለዚሁም በአሸነፈ ማግስት የቀድሞው ጠ/ሚኒስት ሲናገሩ‹‹ ይህ ህዝብ ኢህአዲግ ካለፈው ስህተቱ የሚማር ፓርቲ መሆኑን ተገንዝቦ ለ5አመት ኮንትራቱን ሰጥቶናል ይህ ለኛ ትልቅ ማስጠንቀቂያ ነው ቃላችንን ካልጠበቅን በድምፁ የሰጠንን ካርድ መልሶ ይነጥቀናል›› ሲሉ አቶ መለስ የንቀት ንግግር አድርገዋል በአንፃሩ ግን እንዴት እንዳሸነፉ እራሳቸውም ህዝቡም ያውቃል እናም የ2002 ምርጫ እንከን የለሽ ምርጫ በሚል ድራማ ተጠናቋል በቀጣዩ መጣጥፍ በምርጫ 2007 ዘገባ ላይ ያተኮረ የዚህን መጣጥፍ ክፍል ሁለት ይዤ እቀርባለው እስከዚያው ቸር ይግጠመን

↧

ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 17 የውጭ ዜጎች ክስ ተመሠረተባቸው

$
0
0

• ከ95 ሚሊዮን ብር በላይ የገቢ ንግድ ግብርና ቫት ባለመክፈላቸው ተከሰዋል • ከ716 ሚሊዮን ብር በላይ ምንጩንና ዝውውሩን ደብቀዋል ተብሏል • ከ104 ሚሊዮን ብር በላይ በሕገወጥ መንገድ መገኘቱ ተገልጿል

newsየፀና የንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው የንግድ ሥራ በመሥራት፣ የንግድ ትርፍ ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ባለመክፈል፣ በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብና ሐሰተኛ ሰነዶችን በማቅረብ ወንጀል የተጠረጠሩ የሲሪላንካ፣ የህንድ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ፣ የጂቡቲ፣ የኒውዚላንድና ኢትዮጵያውያን 17 ግለሰቦች ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

የገቢ ግብርና ቫት ባለመክፈል፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ምንጭና ዝውውር በመደበቅና በሕገወጥ መንገድ በመያዝ ተከሰዋል፡፡

የፌዴራል ግለሰቦች ዓቃቤ ሕግ ጳጉሜን 4 ቀን 2006 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት ክስ የመሠረተባቸው፣ ተጠርጣሪዎች ኢትዮጵያውያን አሽረፍ አወል አብዶና በሥራ አስኪያጅነት የሚመሩት አካፔ ኢምፔክስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ የሲሪላንካ ዜጋ የሆኑት ሂትራጅግ ያሳንታ ሱሬንድራናታ፣ ፕላንዋታጅ አሲታ፣ ቦፒ ጊድራ አጅት፣ አሳንታ ኡዳያ፣ ኩሩፑ አራችችግ፣ የህንድ ዜግነት ያላቸው አንኪት ሙኪሽ መሂታ፣ አሾክ ሞሃንላል፣ ኩማር ኤም፣ ቪሻል ኩማርና ሙኒሽ ኩማር፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ዜግነት ያላቸው መሐመድ ሽፋን መሐመድ፣ ኦቶ ወርልድ ኢንተርናሽናል ፍሪዞን ኩባንያና ዱባይ ኦቶ ጋላሪ ኤልኤልሲ፣ የኒውዚላንድ ዜጋ ሱሀስ ፓራሳድና የጅቡቲ ዜግነት ያላት ሲና መሐመድ መሐሙድ ይባላሉ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በተለይ ዱባይ ኦቶ ጋለሪ ኤል.ኤል.ሲና ኦቶ ወርልድ ኢንተርናሽናል ፍሪዞን ኩባንያዎች፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን አካፔ ኢምፔክስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር እንደ ሽፋን በመጠቀም የወንጀል ድርጊት መፈጸማቸውን ክሱ ያብራራል፡፡
የሲሪላንካ ዜግነት ያላቸው ሂትራጅግ ያሳንታ ሱሬንድራናታ ሂትያራጅጅ (ሱሬንድራ)ና ፕላን ዋታጅ አሲታ ሳራናታ ፔሬር (አሲታ) ድርጅቶችን በሚመለከት ሁለት የሲሪላንካ ዜጐች በኢትዮጵያ የዱባይ ጋለሪ መሪና ረዳት መሪ በሚል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውንም ክሱ ያስረዳል፡፡ ዱባይ ኦቶ ጋለሪና ኦቶ ወርልድ ኢንተርናሽናል ኩባንያዎች፣ በኢትዮጵያዊው አሽረፍ አወልና የጅቡቲ ዜግነት ባላት ሲና መሐመድ ባለቤትነት የተቋቋመውን አካፔ ኢምፔክስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርን በሽፋንነት በመጠቀም፣ ሐሰተኛ የሥራ ውል መፈራረማቸውም በክሱ ተጠቅሷል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ምንም ዓይነት የፀና የሥራ ፈቃድ ሳይኖራቸው፣ ለኢትዮጵያውያን ብቻ የተከለለና ለውጭ ዜጎች ባልተፈቀደ የንግድ ሥራ ዘርፍ በመሰማራት፣ የባጃጅ ምርትና መለዋወጫ በቀጥታ ከዱባይ ወደ አገር ውስጥ ሲያስገቡ እንደነበር ክሱ ያስረዳል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ጂቡቲ ውስጥ ከሚገኝ የንግድ ድርጅት ኤስዲሲ በርበራ ፍሪዞን ኩባንያን በመጠቀም በጂቡቲ በኩል ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት፣ በኢትዮጵያ በሚገኙ ክልሎች፣ ዞኖችና የወረዳ ከተሞች በመዘዋወር የገበያ ጥናትና ሌሎች ተያያዥ የንግድ ሥራዎችን በመሥራት ለዱባይ ኦቶ ጋለሪ ኤልኤልሲ ሪፖርት ሲያደርጉ መገኘታቸውን ክሱ ያብራራል፡፡

ሌሎቹ ተጠርጣሪዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በተቋቋመው አካፔ ኢምፔክስ ተቀጣሪ ሠራተኞች በመምሰል፣ ሐሰተኛ የሥራ ቅጥር ውል በመፈራረምና በድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ኢትዮጵያዊው አቶ አሽረፍ አወልና በድርጅቱ ተጠያቂነት በሌላ የሥራ መደብ ፈቃድ በማውጣት ሲጠቀሙ እንደነበርም ክሱ ይገልጻል፡፡

ህንዳዊው አሾክ ሞሃንላል ሻርማና ኒውዚላንዳዊው ሱሀስ ፓራሳድ በቱሪስት ቪዛ ወደ አገር ውስጥ ገብተው፣ ያለምንም የሥራ ፈቃድ የባጃጅ መለዋወጫ ሽያጭ ንግድ ሥራ ውስጥ በመሰማራት በክልሎች በሚገኙ የዞንና የወረዳ ከተሞች በመዘዋወርና የገበያ ጥናት በማድረግ፣ ለዋና ድርጅታቸው ሪፖርት ሲልኩ መገኘታቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ያቋቋሙትን አካፔ ኢምፔክስ በሽፋንነት በመጠቀም ለኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች ብቻ የተከለለና ለውጭ ዜጎች በማይፈቀድ የአስመጭነት፣ የጅምላና የችርቻሮ ንግድ ሥራ ውስጥ ተሰማርተው መገኘታቸውንና ምንም ዓይነት የሥራ ፈቃድና የፀና የንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው ሽፋን በመስጠት፣ በቱሪስት ቪዛ ብቻ የባጃጅ ንግድ ሥራ እንዲሰማሩ መደረጋቸውን ክሱ ያብራራል፡፡

አካፔ ኢምፔክ፣ ዱባይ ኦቶ ጋለሪ ኤልኤልሲና ኦቶ ወርልድ ኢንተርናሽናል ፍሪዞን ኩባንያዎች ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሮችን የወሰዱ ቢሆንም፣ የፀና የንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው ለውጭ ባለሀብት የማይፈቀድ ሥራ ላይ በመሰማራት ካገኙት ገቢ ግብር አለመክፈላቸውን ክሱ ያብራራል፡፡ በመሆኑም ሐሰተኛ ሰነድ በማቅረብ ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ የገቢ ንግድ ግብርና ተጨማሪ እሴት ታክስ አለመክፈላቸውን ክሱ ይጠቁማል፡፡ ከ416 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን ገንዘብ ምንጩንና ዝውውሩን መደበቃቸው ተጠቅሷል፡፡ እንዲሁም ከ104 ሚሊዮን ብር በላይ በኢትዮጵያዊው አሽረፍ አወልና በድርጅቱ አካፔ ኢምፔክስ ስም በተለያዩ ባንኮች በማስቀመጥ፣ በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስለው ማቅረባቸውን ክሱ ይዘረዝራል፡፡

ህንዳዊው ቪሻል ኩማር ላክሃኒ ደግሞ የባጃጅ መገጣጠሚያና ማምረቻ ንግድ የሥራ ዘርፍ፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ የኢንቨስትመንት ፈቃድና የንግድ ፈቃድ በማውጣት፣ እንዲሁም ኤሽያ አፍሮ አውቶሞቢልስ በሚል ከንግድ ሚኒስቴር በተሰጠው የንግድ ስያሜ ቪሻል ኩማር ላክሀኒ የሚል ድርጅት ማቋቋሙን ክሱ ይጠቁማል፡፡ ነገር ግን የመገጣጠሚያ ፋብሪካውን ሳያቋቁምና ምንም ዓይነት የአስመጪነት፣ የአከፋፋይነትና የችርቻሮ የፀና የንግድ ፈቃድ ሳይኖረው፣ ባጃጅ ከውጭ አገር በማስመጣት ሳይገጣጠም በጅምላና በችርቻሮ ሲሸጥ እንደነበር በክሱ ተካቷል፡፡ ተጠርጣሪው ከ84 ሚሊዮን ብር በላይ የገቢ ግብርና ተጨማሪ እሴት ታክስ ካለመክፈሉም በላይ፣ በሕገወጥ ንግድና ግብር ሲሠራ ያገኘውን ከ330 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ገንዘብ፣ ከወንጀል ተጠያቂነት ለማምለጥ በማሰብ የገንዘቡን ምንጭና ዝውውር መደበቁን ክሱ ያብራራል፡፡

የጂቡቲ ዜግነት ያላት ተጠርጣሪ ሲና መሐመድ መሐሙድ በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ በዱባይ የኢትዮጵያ ቆንሲላ ጽሐፈት ቤት ቀርባ፣ ‹‹የቤት እመቤት›› የሚል ሐሰተኛ መረጃ በመስጠት መታወቂያ በማግኘት ስትገለገልበት በመክረሟና ሐሰተኛ የሆነ ኦፊሴላዊ ሰነድ በማጭበርበር ማግኘት ወንጀል መከሰሷን የዓቃቤ ሕግ ክስ በዝርዝር ያሳያል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በአጠቃላይ ከ95 ሚሊዮን ብር በላይ የገቢ ንግድ ግብርና ቫት ባለመክፈል፣ ከ716 ሚሊዮን ብር በላይ ምንጩንና ዝውውሩን በመደበቅ፣ እንዲሁም ከ104 ሚሊዮን ብር በላይ በሕገወጥ መንገድ በመያዝ ክስ ተመሥርቶባቸዋል፡፡

የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ለደንበኞቻቸው የዋስትና መብት እንዲጠበቅላቸው በጽሑፍ ለፍርድ ቤቱ በማቅረባቸው፣ ዓቃቤ ሕግ ለጥያቄው በጽሑፍ ምላሽ እንዲሰጥ ለመስከረም 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

↧

የቪኦኤ አማርኛ ሪፖርተር የሆነውና አወዛጋቢና የተዛባ መረጃ በማቅረብ በስፋት የሚታወቀው ሄኖክ ሰማእግዜር

$
0
0

በአበበ ገላው

የዛሬ ወር ገደማ የቪኦኤ አማርኛ ሪፖርተር የሆነውና አወዛጋቢና የተዛባ መረጃ በማቅረብ በስፋት የሚታወቀው ሄኖክ ሰማእግዜር ሙሉ በሙሉ ሃሰት የሆነ ዘገባ በአሜሪካን ሬድዎ አማካኝነት አሰራጨ። የዘገባው አላማ በካሊፎርኒያ የሚገኘው አዙሳ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲ ለአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሰጥቶ የነበረውን የክብር ሽልማት መልሶ መንጠቁንና ዝግጅቱ መሰረዙን በማስመልከት የቀረበው ዘገባ ሃሰት ነው ብሎ ለማስተባበል እና እኔን፣ አለማቀፉን የኢትዮጵያዊያን መብት የጋራ ህብረት እንዲሁም ኢሳትን በሃሰተኝነት ለመወንጀል የታለመ ነበር።Peter-Heinlein-Henok-Semaezer-Fente

ይሁንና ለእርምጃው ምክንያት የሆነው በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት ዩኒቨርሲቲው እንዲመረምርና ሽልማቱን መልሶ እንዲያጤን ስለተደረገ መሆኑ በግልጽ የተነገረ እውነታ ነበር። ዩኒቨርሲቲውም ለክብሩ ስነ ስርአት መሰረዝ የሰጠው ዋነኛ ምክንያት ይሄው የሰብአዊ መብት ጥሰት ጉዳይ መሆኑን በይፋ ደጋግሞ ገልጿል።

አልተሳካም እንጂ ሄኖክ በተለይ በእኔ ላይ ያነጣጠረ በተንኮል የተሞላ ጎጂና የተዛባ ዘገባ ሲያቀርብ ይሄኛው ሶስተኛው ነው። በግንቦት 10, 2004 (May 18, 2012) በአቶ መለስ ዜናዊ ላይ የተቃውሞ ድሞጽ ሳሰማ ሄኖክ በአይኑ ያየው በጆሮው የሰማው ሃቅ ቢሆንም ድምጼን ሳንሱር አርጎ ዘገባውን አዛብቶ ለስርጭት አበቃው። በዚህም ምክንያት ቪኦኤ ከአድማጮቹ ከፍተኛ ተቃውሞ ስለቀረበበት በሳምንቱ ዘጋባውን እንደገና በሌላ ሰው አስተካክሎ ተቆርጦ የቀረውን ድምጼን አስገብቶ ሌላ ዘገባ ለማስተላለፍ ሞከረ። ይሄን በጋዜጠኝነት ስም የተሰራ እርካሽ የፖለቲካ ቁማር ታዝበን አለፍነው።

ከዛም ግኡሽ አበራ የሚባል አንድ የቦስተን ነዋሪ በእኔ ላይ የግድያ ወንጀል ለመፈጸም ሲዶልት ገና ከጥንስሱ በFBI ተደርሶበት ምርመራ እንደተደረገበት ተዘገበ። በዚህ ላይ ወያኔ የተቀናጀ ስራ በመስራት፣ አንዳንድ ድህረ ገጾችን፣ ፓልቶኮችን እና ቪኦኤን በመጠቀም እኔ ግኡሽ አበራን ልክ በሃሰት የወነጀልኩት ለማስመሰል ሌላ ያልተሳካ ጥረት ተደረገ። እንደተለመደው ሄኖክ አሳፋሪ የካድሬ ስራውን በመቀጠል ከፍተኛ መዛባት ለመፍጠር ሞከረ። ትንሽ ብዥታ ቢፈጥሩም ያሰቡትን ያህል ግን አልተሳካም። ፈጽሞ ያላናገረውን የFBI ቃል አቀባይ ጠቅሶ እንደለመደው ድምጽ ሳያስገባ “የጥቅሱ መጀመሪያ፣ የጥቅሱ መጨረሻ” በማለት አድማጭን ግራ የሚያጋባ ዘገባ ለቀቀ። እኔ እንደ ጋዜጠኛ ባይሆንም እንደ ጉዳዩ ባለቤት ከቦስተን FBI ቃል አቀባይ ግሬግ ኮምኮዊች ጋር ያደረኩት ንግግር የድምጽ መረጃ እስካሁን በእጄ ላይ አለ። በተጨማሪም እንደነ ግኡሽ ስራ ቦታው ድረስ ሄደው የFBI መርማሪዎች ካፋጠጡት ግን በሴራው አለመሳተፉ ከተረጋገጠው ቤዛ ጥላሁን ያገኘሁት ዝርዝር መረጃ ጭምር በእጄ ይገኛል።

 http://youtu.be/Zv1LtuLEFIU

ዘፋኝና የግኡሽ ደባል የነበረችው አበራሽ የማነ በግዜው የቤዛ ወዳጅ የነበረች ሲሆን አሁን ትዳር መስርተዋል። በወቅቱ ለአበራሽ የማነ መርማሪዎቹ ጥያቄ ቢያቀርቡም ምንም አይነት ውንጀላ ማንም ባያቀርብባትም ፓልቶክ ላይ ብቅ ብላ በሃሰት አበበ ገላው ወነጀለኝ እንድትል ተደረገ። እነ አውራምባ ታምስም ወገንተኛ የሆነና የሚያስተዛዝብ ስራ ሰሩ። ይህንንም በወቅቱ ታዝበን አለፍነው።

FBI በዋነኛነት ትኩረት ያደረገው ግኡሽ ላይ ነበር። ለዚህም ምክንያት ደግሞ እንዳወሩት በፌስቡክ ስለተሳደበ ወይንም ስለዛተ ሳይሆን በግድያ ወንጀል ዱለታ ሊያስጠይቅ የሚችል መረጃ መርማሪዎች እጅ በመግባቱ ነበር። በቀጣይነት በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ እርምጃ የመውሰድና ያለመውሰድ መብት የመርማሪዎቹ ሲሆን የዘገባው እውነታ ግን ከላይ የተጠቀሰው ነው።

በግልጽ አፍቃሪ ወያኔ የሆነው ሄኖክ ሰማእግዜር ግን ጥቅስ ብሎ ያነበበውን ብዥታ የሚፈጥርና ከዋናው ጭብጥ ውጭ የሆነና አዛብቶ ያቀረበውን ሃተታ በተውሶ የወሰደው ከሶስተኛ ወገን፣ እንደውም እንደሰማሁት ከሆነ፣ ከትግሪኛ ዝግጅት ክፍል ነበር። ይሁንና ጥረቱ እውነቱን አልቀየረውም። ግኡሽ አበራ እኔን በስም ማጥፋት በፍርድ ቤት እንደሚከስ ወያኔዎች ደጋግመው ከመናገር አልፈው ከፍትኛ ገንዘብ ቢያዋጡም እስካሁን የተሰማ ክስ የለም።

እኔ በወቅቱ ወንጀል ሲዶልት የተደረሰበት ሰው ማንንም በስም ማጥፋት መክሰስ አይቻለውም ያልኩት እውነትን በመተማመን ነበር። አሁንም ፍርድ ቤቶች ክፍት ስለሆኑ ግኡሽ ብቻ ሳይሆን የውሸት ዘገባ በማሰራጨት እጅ ከፍንጅ በመያዝ አደባባይ ያወጣሁት ሄኖክ ሰማእግዜር (እስከ እረዳቶቹ) ዶሴውን ጠርዞ ፍርድ ቤት መሄድ ይችላል። ይሁንና ውሸት ታጥቆ አየር ላይ መውጣትም ይሁን የውሸት ዶሴ ጠርዞ ፍርድ ቤት መሮጥ ፈጽሞ እንደማያዋጣ ከወዲሁ መጠቆም እወዳለሁ።

የአሁኑ ይባስ እንዲሉ ሄኖክ አቶ ሃይለማሪያም አሜሪካ ሳይደርሱ ላስቸኳይ ስራ ተመለሱ፣ ያልደወሉትን ስልክ ደውለው ክብሩ ይቅርብኝ አሉ፣ እኔ ያልጻፍኩትን ደብዳቤ እያነበበና እያጠቀሰ፣ ያልተናገርኩትን ተናገረ፣ ያልዘገብኩትን ዘገበ እያለ ፈጽሞ ያላናገራቸውን ቃል አቀባይ ያላሉትን አሉ እያለ፣ አደባባይ ወጣ። በሁዋላ ስናጠያይቅ እንደውም የተረዳነው አሳፋሪው የቪኦኤ የሃሰት ዘገባ የተሰራው በቡድን ለሶስት መሆኑን ነው።

ታዲያ ምነው ይሄ ሁሉ የቪኦኤ ሰራዊት አንዲት ቅንጣቢ መረጃ ማውጣት ተሰናው? ከሁሉ የሚገርመው ደግሙ ውሸታችን “ቢቢጂ” የተባለ ቦርድ አጸደቀልን ብለው አይናቸውን በጨው አጥበው አደባባይ መውጣታቸው ነው። በእውነቱ በጣም ያሳዝናል። ቢቢጂም ቢሆን በመረጃ የተደገፈ ማስተባበያ ይዞ እስካልመጣ ድረስ አድማጭም አክባሪም በቀላሉ ማግኘት ይችላል ብዬ አላምንም። የተራዳሁት አንድ ጉዳይ ቪኦኤ ውስጡን ለቄስ ነው። ማንንም የመውደድም ይሁን የመጥላት ግላዊ መብታቸውን ብናከብርም ውሸት ታጥቀው አየር ላይ ከወጡ ግን ችላ ሳንል ደግመን በእውነት ሚሳኤል አናወርዳቸዋለን።

እኛ ለህዝባችን ነጻነትና መብት ከመከራከርና ከመታገል አንቆጠብም። ለዚህም ደግሞ ከማንም ፍቃድ አንጠይቅም። አንዳንድ የቪኦኤ አማርኛ ክፍል ባልደረቦች የእነ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ክብር ተነካ ብለው እኛን ለማጥቃት መነሳታቸው ባያስገርምም ያሳዝናል። በከንቱ ይደክማሉ እንጂ አቶ ሃይለማርያምም ሆኑ አዙሳ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲ በዙ ተቀጣሪዎች አሏቸው። ሁለቱም ወገኖች ቪኦኤን በቃል አቀባይነትይሁን በጥብቅና አለመቅጠራቸውን በርግጠኝነት መናገር ይቻላል።

እንኳን በሜድያ ስራ የተሰማራ ጋዜጠኛ ነኝ ባይ ይቅርና ማንም እንደሚያውቀው አንድ ሚድያ ስተት ሲሰራ ባግባቡ እርማት እንዲያደርግ ይጠየቃል። ስህትት ተሰርቶ ከተገኝም አግባብ ባለው መንገድ እርምት አድርጎ ይቅርታ ይጠይቃል።። ቪኦኤን የሚያህል ግዙፍ ተቋም የሌሎችን ስራ ከማኮሰስ አልፎ በውሸት ጭብጦ የእውነትን ተራራ ለመናድ ጥረት ማድረጉ በጣም ግራ የሚያጋባ ጉዳይ ከመሆን አልፎ የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ የሚለውን አባባል ያስታውሰናል።

ሌላው አሳዛኝ ጉዳይ በዚህ የሀሰት ዘገባ ቁልፍ ሚና የተጫወተው ፒተር ሃይንላይን በአጠያያቂ መስፈርት ባለፈው ሳምንት ለሄኖክ ሰማ እግዜር “ሽልማት” ማቀበሉ ነው። ሄኖክም ይህንኑ ሽልማት ከአፍሪካ ክፍል ሃላፊው ከአቶ ንጉሴ መንገሻ እጅ ተቀብሏል። በርግጥ ሄኖክ ለማዛባትና ሃሰትን በይፋ በማሰራጨት ተወዳዳሪ ስላልተገኘለት ታላቅ ሽልማት ይገባው ይሆናል። ለጋዜጠኛነቱ ሽልማት መስጠት ግን ጋዜጠኝነትን መስደብ ነው።

በዚህ አይን ከፋች በሆነ አጋጣሚ ከእነ ሄኖክና ፒተር ሃይህላይን ይልቅ የአማርኛው እና የአፍሪካ ክፍል ሃላፊ የሆኑ ሁለት አንጋፋ ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞችን በጣም ታዘብኩ።። ክብር ወደ ትዝብት ያለ ምክንያት እንደማይቀየር ለማንም ግልጽ ነው። ለምን ታዘብከን ብለው ከጠየቁኝ ምላሹን በዝርዝር በአደባባይ ላስረዳቸው ዝግጁ ነኝ። እስከዛው ሆድ ይፍጀው በማለት ለዛሬው የኢሳቱ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን የቪኦኤን ከድጡ ወደ ማጡ የሆነውን የሰሞኑን ጉዞ አስመልክቶ ያዘጋጀውን ምርጥ ዝግጅት ካልሰሙት አያምልጥዎ።

መልካም አዲስ አመት ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ!

↧
↧

የቀጣዩ መንግሥታችን ሸክም (ይሄይስ አእምሮ)

$
0
0

ይሄይስ አእምሮ

 

(ይህ ጽሑፍ የተጻፈው ግንቦት ውስጥ 2006 ዓ.ም ነው፤ ትቼው ከርሜ ሳበቃ አሁን ምን በል እንዳለኝ አላውቅም ደግሜ ቃኘሁትና ላክሁት፡፡)

 

“እሳቸው በመጡና ድንጋይ በበሉ” አለች አሉ አንዷ የዳግም ዘማች ባለቤትና የቤት ሙሉ ልጆች እናት፡፡ በደርግ ጊዜ ነው፤ ወጣት-ሽማግሌ ባሏ ለዳግመኛ ሀገራዊ ወታደራዊ ግዳጅ ተጠርተው ወደሰሜን ጦር ግምባር ሄደዋል – የሆነው ሁሉ መሆኑ ላልቀረው አውዳሚ ጦርነት፡፡ ያቺ ሴት “አባታችን ናፈቀን” የሚሉ ብዙ ልጆች አሏት፡፡ ከልጆቿ ጋር የሚኖሩት በድህነትና በጠባብ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ሰው ሊጠይቃት በመጣ ቁጥር የባለቤቷን ከዘመቻ መመለስ አጥብቃ እንደምትሻ ትናገራለች፡፡ አንዱ ጠያቂ ታዲያ “ይምጡ፣ ይምጡ፣ የምትይው ቢመጡ ምን ልታበያቸው ነው?” ሲል ይጠይቃታል፡፡ እሷም በወቅቱ ያጣቻቸው ባለቤቷ መመለስ እንጂ ቀጣዩ ነገር የሚያሳስባት እንዳልሆነ ለመግለጽ “በመጡና ድንጋይ በበሉ!” የሚል መልስ ሰጠች ይባላል፡፡ ዋናው የሰውዬው መምጣት ነው፤ ሌላው ቀስ ብሎና በሂደት ይታሰብበታል፡፡

አዎ፣ የኛ የምንለው መንግሥት ይምጣ እንጂ የሸክሙ ነገር ሊያሳስበን አይገባም እያልኩ መሆኔን መጠርጠር ከነገር ዐዋቂ አንባቢ ይጠበቃል፡፡ ግን ግን እውነት ለመናገር በእጅጉ ፈራሁ! የፍርሀቴ መሠረትም የቀጣዩ መንግሥታችን ታሪካዊ ኃላፊነት መክበድ ነው፡፡ ወያኔ ሀገራችንን በቁሟ እንጦርጦስ ያወረዳት በመሆኑ መልሶ የመገንባቱ ነገር ሲታሰብ ከምንም ነገር በላይ ያስጨንቃል፡፡ እንዲያውም አለማሰቡም ሳይሻል አይቀርም፤ ቢሆንም ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም – እንዲሁም እስላም – ይባላልና ሁሉን ነገር ማድረግ የማይሳነው ታላቁ የሰማይና የምድር ፈጣሪ በቅርቡ መልካም ነገርን እንደሚያደርግልን፣ እነዚህን መዥገሮችም በኪነ ጥበቡ እንደሚነቅልልን መጠበቁ በተለይ የትንቢቱን ፍጻሜ ከሥር መሠረቱ ስንከታተል ለነበርንና በዳግም ትንሣኤያችን የብሥራት ጫፍ ላይ እንደምንገኝ ለምናምን ጥቂት ወገኖች አግባብነት አለው፤ ይገባናልናም ያደርግልናል፡፡ እንግሊዝኛ አማረኝ – So I shall sincerely suggest that we deserve both independence and freedom; as a nation, we are not independent and as people we are not free. Understandably, Ethiopia is under colonial apartheid system, a system led by few Tigrian mercenaries who are clandestinely supervised by anti-Ethiopian foreign forces who crave to see the over-all downfall of Ethiopia and her historic people. In light of this, it is quite right to say that the country is neither independent nor the people ር free from oppression and ethnic segregation run and sponsored by TPLF and its international supporters. For instance, the Amharas have been exposed to genocide and ethnic cleansing since the time TPLF came to existence some 40 years back, first in Tigray and later in all parts of the country, while other ethnics are stifled or even victimized if they don’t blindly obey this crooked ruling junta.

ከአእምሮየ ሰሌዳ ሳትሰወርብኝ አሁን ትዝ ያለችኝን አንዲት በጣም የምታውቋትን ነገር ላስታውሳችሁ፡፡ በአፄው ዘመን አንዷ ትንሽዬ የቤተ መንግሥት ልዕልት ፣ የአሁኑን አያድርገውና “የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር እኮ በአስደንጋጭ ሁኔታ 20 ሚሊዮን ደረሰ፡፡” እያሉ መኳንንት መሣፍንቱ ሲያወሩ ብትሰማ ጊዜ “ለመሆኑ 500 እንሆናለን እንዴ?” ብላ በአግራሞት ጠየቀች አሉ፡፡ እኔም አሁን ማንም ሊመልስልኝ የማይችል ከባድ ጥያቄ – እንዲያው ለላንቲካው ያህል – ልጠይቅ “በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ስንት ይሆን?” 90 ሚሊዮን? 70 ሚሊዮን? 50 ሚሊዮን? 30 ሚሊዮን? አንድ ሚሊዮን? ወደ ዜሮ የሚጠጋ ሚሊዮን? ስንት ነን በውነቱ? አካላዊ ዐይናችሁን ለአፍታ ዝጉና በኅሊናዊ ዐይናችሁ ራሳችሁን ጠይቁ፤ መልስ ለማግኘትም ሞክሩ፡፡ አንድ ሕዝብ፣ በሕዝብነት ታውቆ ሊመዘገብ የሚችለውስ ብዛቱ ስንት ሲሆን ነው? አንድ ማኅበረሰብ በዕውቀት፣ በጥበብ፣ በአስተሳሰብ፣ በሃይማኖት፣ በባህል፣ … ምን ዓይነት የልኬት ደረጃ ላይ ሲደርስ ይሆን “ሕዝብ” የሚባለውን ዓለማቀፍ መጠሪያ የሚያገኘው? በእውነቱ አሁን እኛ ‹ሕዝብ› ነን? የአንድ ሀገር ሕዝብ ሲባል ምን ማለት ነው? ቀጣዩ መንግሥት ሕዝብ የመፍጠር ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት አለበት – ሀገርና ሕዝብ የመፍጠር ግዴታና ኃላፊነት ደግሞ እጅግ ፈታኝና እልህ አስጨራሽ ነው፡፡ ጠፍተናል፡፡

በመሠረቱ መልካም አስተዳደርና ለሀገርና ለሕዝብ የሚቆረቆር መንግሥት ካለ፣ እንደወያኔ ለጥቂቶች የሚያደገድግና በብዙኃን ሥቃይ የሚደሰት መንግሥት ሣይሆን እውነተኛ የመንግሥት መዋቅር ቢኖር ሕዝብ አንደኛውና ትልቁ የሀገር ሀብት ነው፤ የጥራት ጉዳይ ግን በሚኖረው መንግሥትና በሕዝቡ በራሱ የመማር፣የመመራመርና የመሰልጠን ፍላጎት የሚወሰን መሆኑን በታሳቢነት መያዝ ይገባናል፡፡ አለበለዚያ ብዛት ጥራትን ስለማያመለክት ለምሳሌ አንድ ቢሊዮን ሕዝብ ያለው ሀገር 500ሺህ ሕዝብ ካለው ሀገር ያነሰ የቁሣዊና መንፈሣዊ የዕድገት ደረጃ ላይ ሊገኝ እንደሚችል ተግባራዊ አብነቶችን በማጣቀስ መረዳት እንደሚቻል ለማንም ወገን ግልጽ ሊሆን ይገባል፡፡

በመሠረቱ የሕዝብ ብዛት እንደችግር የሚቆጠረው በአንድ ወገን ጥቂት አምራችና ብዙ በላተኛ ሲኖር መሆኑ ይታወቃል፡፡ በሌላ ወገን ደግሞ ከትምህርትና ከሥልጣኔ ርቆ በጥንታዊ የአኗኗር ዘይቤ የሚዳክር ሕዝብ ካለ ሳይወለድ እንደጨነገፈ ሽል ሊቆጠር ቢችል ተጠያቂውን አካል በማፈላለግ ወቀሳን ማዥጎድጎድ እንጂ ሌላ አማራጭ የሚኖር አይመስለኝም፡፡ ሀገር ወዳድ መንግሥትና ብሔራዊ ስሜት የተላበሱ የመንግሥት ባለሥልጣናት ካሉና ሁሉንም ዜጋ እንደችሎታውና እንደዬአቅሙ በአግባቡ በማስተማርና በማሰልጠን ለሥራ ካሰማሩት መጽዋችም ተመጽዋችም አይኖሩም፡፡ ልመናና ስርቆት፣ ሙስናና ንቅዘት ይቀንሳሉ ወይም ከነአካቴውም ሊጠፉ ይችላሉ እንጂ መንገዶችና የአምልኮት ሥፍራዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ በለማኞችና ባጡ በነጡ ድሆች አይሞሉም፡፡ የማጭበርበርንና በአቋራጭ የመክበርን ጎጂ ልማድ ሣይሆን በሥራና በመልካም ሥነ ምግባር የታነፀ ትውልድን የመገንባት ባህል የሚያዳብር የሕዝብ ወገን የሆነ አምባገነንም ይሁን በሕዝብ የሚመረጥ መንግሥት በአንድ ሀገር ውስጥ ካለ አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ፈጥጦ ያለው ችግር አይኖርም፡፡(በነገራችን ላይ አምባገነን መንግሥት በህዝብ ምርጫም ሊመጣ እንደሚችል ያሜሪካውን ትንሹን ጆርጅ ቡሽና የግብጹን ሞሀመድ ሙርሲን ማስታወስ በቂ ነው)፡፡  ሕዝብና ሀገር ሲባል ደግሞ ተጨባጩ የሀገር ሁኔታና ተጨባጩ የሕዝብ ኑሮ እንጂ በታሪክ ካባ ተጀቡኖ የአሁን ስቃይንና ኋላቀርነትን ለመርሳት መሞከር አይደለም፡፡ ወንዞችና ተራሮች፣ ሸለቆዎችና ዋሻዎች፣ ባህሮችና ኩሬዎች እንዲሁም በቱሪስት መስህብነት የሚያገለግሉ የታሪክ አሻራዎችም ወቅታዊ የሕዝብ ኑሮ መገለጫዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡ “በቅሎ አባትሽ ማን ነው?” ቢሏት “እናቴ ፈረስ ነች” አለች እንደተባለው እንዳይሆን መጠንቀቅ ተገቢ ነው፡፡ እዚህ ላይ ለኢሳቷ እሳት ለመታሰቢያ ቀፀላ አክብሮቴን መግለጥ እፈልጋለሁ፡፡ በቅርብ በተከታተልኩት አንድ ውይይት እውነቱን አፍረጥርጣ በመናገር ይህን ቆሎ የማያበላንን የቀድሞ ብሔራዊ የኢትዮጵያዊነት ኩራት አላግባብ እንዳንለጥጠውና በከንቱ እንዳንኮፈስ ወይም በከንቱ መኮፈሳችንን እንድንቀንስ በመረጃና በማስረጃ በተደገፈ ገለጻዋ በልጅነት አንደበቷ መክራናለች፡፡ እውነትን ብትመርም ብትጎመዝዝም መቀበል ይኖርብናል፡፡ ዘፈንንና ሽለላን ለተወሰነ ጊዜና ለተወሰነ ዓላማ ይጠቀሟል እንጂ ራስን ለማነሁለልና ምንም ያልተነኩ መስሎ ምናባዊ መቼት ውስጥ በሥነ ልቦናዊ የተደላደለ ጉዝጓዝ ላይ ለመዘርፈጥ ልንገለገልበት አይገባም፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ምን አለ? በሚፈለገው የጥራት ደረጃና የአገልግሎት መጠን ባይሆንም የአስፋልቱና የመንገዱ ግንባታ፣ የኤልክትሪኩና የስልኩ ዝርጋታ፣ የሕንፃና ኢንዱስትሪው ጋጋታ፣ የትምህርትና ጤና ኬላዎች ‹ተደራሽነት›፣ … በጥቅሉ ይህ አሁን የምናየው የዕድገትና ብልጽና ምልክት ሁሉ እሰዬው የሚያስብል ነው፡፡ ግን “ሰው አለ ወይ?” ብለን ከመጠየቅ የሚያግደን ነገር በእስካሁኑ ሁኔታ ሊታይ አልቻለም፡፡ ለዚህም ነው ታዋቂው መንግሥቱ ለማ ቀጣዩን ዘመን የማይሽረው ሥነ ግጥም የቋጠረው፤ ግጥሙን ደግመን ደጋግመንም ቢሆን እናስታውሰው፡-

 

ምን ሕንፃው ቢረዝም ቢንጣለል አስፋልቱ፤

ሰው ሰው ካልሸተተ የታለ ውበቱ፡፡

 

በተለይ ለዚህ ዘመን ተለክቶ የተሰፋ ልጨኛ ሥነ ግጥም ነው፡፡

 

ወጣም ወረደ፣ ግራም ነፈሰ ቀኝ፣ የኛ የምንለው መንግሥት ሊያውም በቅርቡ ይኖረናል፡፡ በግሌ ቆሜም ተኝቼም የሚያስጨንቀኝ ግን የመንግሥታችን ሸክም ነው፡፡ እንደኔ ኢትዮጵያ ውስጥ አንዲት ሽርንቁላ ውስጥ ተወትፎ ኢትዮጵያን ከነአጠፋፏ ጭምር እየታዘበ ለሚገኝ ዜጋ ኢትዮጵያን ከነዚህ ደም መጣጭ መዥገሮች ነፃ ለማውጣት ከሚደረገው ትግል ይልቅ ከሙታን ሀገራት ተርታ ፈልቅቆ ለማውጣትና ትንሣኤዋን ለማብሠር የሚደረገው ግብግብ ይበልጥ ያስጨንቀዋል፡፡ በቁማችን እኮ ሞተናል!

ወጣቱም በለው ጎልማሳው ከየኅሊናው ጋር ተኮራርፎ ለሥጋው ብቻም አድሮ ሌት ከቀን ሲባዝን የምታየው በባሌም ይሁን በ”ቦሌ” እንዴት አድርጎ ገንዘብ እንደሚያጋብስና በአንድ አዳር እንደሚከብር ነው፡፡ “ቦሌ”ን ያላገጥኩባት በአሁኑ ሰዓት በባሌ እንጂ በቦሌ መክበር እንደብርቅና እንዲያውም ከነአካቴው የሌለ መሆኑን ለመጠቆም ፈልጌ ነው፡፡ ባሌን እንደህገ ወጥ፣ ቦሌን እንደህገኛ መንገድ ካሰብነው ዛሬ ዛሬ በህገኛ መንገድ የሚያልፍለት ዜጋ የለም ቢባል ከእውነቱ አልራቅንም፡፡ ሕግ በጉልበተኞች መዳፍ ሥር ወድቃ እያቃሰተችና ለይቶላት እየሞተች ናት፡፡ በህጋዊ መንገድ መነገድ፣ በህጋዊ መንገድ ተሟግቶ ፍትህን ማግኘት፣ በህጋዊ መንገድ ሥራ ማግኘት፣ በህጋዊ መንገድ ተምሮ ሥራ መያዝ፣ በህጋዊ መንገድ ተከራክሮ መርታት፣ በህጋዊ መንገድ ጉዳይህን ማስፈጸም፣ በህጋዊ መንገድ የዜግነትና የሰብኣዊ መብቶችህን ማስከበር፣ በህጋዊ መንገድ የንብረትህ ባለቤት መሆን፣ ወዘተ. ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ፈጽሞ አይታሰብም፡፡ የሁሉም ነገር መሠረት ዘርህና እንዲያም ሲል አድርባይነትህ ወይም ሆዳምነትህና ኅሊናቢስነትህ ነው፡፡ የወደፊቱ መንግሥታችን – የኛ የምንለው መንግሥታችን – ሸክሙ እንደሚበዛ የምንረዳው ይህን የተንሸዋረረ የአሁን አካሄዳችንን ለማስተካከል የሚጠበቅበትን ከፍተኛ ትግል ስናስብ ነው፡፡

አሁንና ዛሬ ወያኔና አጫፋሪዎቹ የሀገሪቱን ቁልፍ ለብቻቸው ይዘውና ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረው ሁሉን ነገር ማድረግ ይችላሉ፡፡ ለቃሉ አጠራር ይቅርታ ይደረግልኝና ኮንዶሙ ደሳለኝ ኃ/ማርያም በሰሞኑ የግንቦት 20 (2006ዓ.ም) ንግግሩ – ያን ንግግርም ጌቶቹ አዘጋጅተው የሰጡት መሆኑን ማስታወስ አያስፈልግም ብዬ ነው – አንሻፍፌም ቢሆን እጠቅሳለሁ – “በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ‹ኢትዮጵያውያን› ዜጎች ሚሊዮኔሮችና ቢሊዮኔሮች መሆን የቻሉት በኢሕአዴግ አመራር ነው” ብሎ የተናገረው ማንን እንደሚያካትት ግልጽ ነውና ወደዚያ መግባት አይገባም፡፡ ለነገሩ ቢገባስ ምን ክፋት አለው? የዐዋጁን በጆሮ እንዲሉ ነው፡፡

ሀብታሞቹ በኔ ግርድፍ ግምት 95 ከመቶው በላይ ወያኔ ትግሬዎች ናቸው፡፡ የትም ይኑሩ የትም ከነሱ ውጪ ሀብታም ወይም እነሱ ሀብቱን የማይቆጣጠሩትና በፈለጉ ጊዜ ሊያደኸዩት የማይቻላቸው ኢትዮጵያዊ ሀብታም የለም፡፡ በቀላሉ ላስታውስ – የአማልጋሜትዱ ገ/የስ ቤኛ፣ የአያት ቤቶች ኮንስትራክሽን ባለቤት አያሌው (ተሰማ?)፣ ኤርምያስ አመርጋ፣ ብርሃነ መዋ፣ ያለምዘውድ (ጎጃሜው ሀብታም) … ስንቱን ዘርዝሬው … በዚህች ጠባብ ቅንጭላቴስ ስንቱን አስታውሼው … እነዚህ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከሀብትም ከሀገርም ሣይሆኑ የቀሩት ሌላ ወንጀል ፈጽመው ሣይሆን “ኢኮኖሚውን የማይቆጣጠር ዘውግ ፖለቲካውንም ሊቆጣጠር አይችልም፤ ስለሆነም ከኛ ሌላ ሀብታምና ከኛ ሌላ ተፅዕኖ ፈጣሪ ነጋዴ መኖር የለበትም ” በሚል ያረጀና ያፈጀ የአገዛዝ ፈሊጥ እስከዕለተ ሞቱ ድረስ በዕውር ድንብር የሚነዳው ወያኔ ባሳረፈባቸው ዱላ ነው፤ ወደድንም ጠላንም መራር እውነቱ መላው ኢ-ትግራዋይ በወያኔ የቁጥጥር ራዳር ውስጥ የሚገኝ መሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ የተጋቦት ወያኔ ሆንክም አልሆንክም ወደሀብትና ሥልጣን ማማዎች ልትወጣ ካሰብክ እንደመናጆ ሊጠቀሙብህ እንጂ የእውነት ከመሰለህ ጊዜህን ጠብቀህ ቁልቁል ስትፈጠፈጥ ያኔ የእንሥራ ጆሮነትህ – ባዳነትህና ለኮንዶምነት አገልግሎት መዋልህ ይታወቅሃል፡፡ ይህን እውነት ለመረዳት የቅርብ ጊዜ መረጃ ልጠቁምህ – ኤርምያስ ለገሠ የተባለ ወጣት የቀድሞ የተጋቦት ወያኔ  በቅርብ ለኢሳት የሰጠውን ቃለ ምልልስ አድምጥና ዕርምህን አውጣ፡፡ ሀገሪቱ አልቆላታል ወደሚል አሳዛኝ ደረጃ ትደርሳለህ – እስካሁን ተስፋ አለኝ የምትል ከሆንክ ነው ሊያውም፡፡ የኤርምያስን ቃለ ምልልስ ያዳመጠ ሰው፣ ወያኔ – ትግሬ ምን ያህል ቅሌታም፣ ምን ያህል ዐይኑን በጨው ያጠበ ዘረኛ እንደሆነ በቀላሉ መረዳት ይችላል፡፡ ይህ ለቅጣት የመጣ የአንበጣ መንጋ – የሰንበት ጽንስ ጥርቃሞ – ኢትዮጵያን እንዴት እንዳዋረዳትና ዜጎቿን ከመጤፍ ባለመቁጠር እንዴቱን ያህል እላያቸው ላይ እንደሚጸዳዳ ማንም መገንዘብ አይከብደውም፡፡ አሣሪዎቹ እነሱ፣ ገራፊዎቹ እነሱ፣ መርማሪዎቹ እነሱ፣ ደብዳቢዎቹ እነሱ፣… አንድም ቅልቅል ሳይኖርባቸው ኢትዮጵያውያን ላይ የሰለጠኑ አልቃኢዳዎችና የአዲሶቹ የእስላሚክ ስቴት ካሊፌቶች እነሱ ናቸው፡፡ ሙስሊሞቹ ፀረ-ምዕራባውያን አሸባሪዎች በተቆጣጠሩት ነፃ ግዛት በምዕራባውያን ጋዜጠኞችና የረድኤት ሠራተኛ ላይ ሲፈጽሙ በቅርቡ እንደታዘብነው፣ ወያኔዎች አንድን ኢትዮጵያዊ ዜጋ በቢላዎ ጭንቅላቱን ከአንገቱ ቆርጠው ጀርባው ላይ ሲያስቀምጡ በበኩሌ አላየሁም እንጂ የነዚህ ትግሬ ወያኔዎች የጭካኔ ደረጃ ከነዚህ አረመኔ ፍጡራን ቢበልጥ እንጂ አያንስም፡፡ የሚገርመኝ ይህን ሁሉ አረመኔያዊ ባህርይ ከየት እንዳገኙት ነው፡፡ ለሆድ ቅድሚያ ከመስጠት በተጓዳኝ አንድ ኢትዮጵያዊ እስከዚህን ዘግናኝ የጭካኔ ደረጃ እንደምን ሊወርድ እንደቻለ ለመገመት የዘወትር ዕንቆቅልሽ እንደሆነብኝ አለ፡፡ በውነቱ ሰዎች ናቸው? ማታ ማታ ቤታቸው ሲገቡ ከቤተሰብ ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት እንዴት ይሆን? ለመሆኑ እንቅልፍስ ይይዛቸዋል? … ይህንን መሰሉን የተበላሸ ስብዕና መለወጥም የወደፊቱ መንግሥታችን አስቸጋሪው የኃላፊነት ሸክም ነው፡፡

በነገራችን ላይ “ዘባራቂ” አትበሉኝና በብርሃኑ ነጋ ቃለ ምልልስ ላይ ብርሽ ሸፋፍኖ ያለፋትን አንዲት ጥያቄ “እኔ ብሆን” እንዲህ አድርጌ እመልሳት እንደነበር በዚህ አጋጣሚ ልጠቁም፡፡ ጥያቄውን ለማስታወስ ያህል – “ወያኔ ሲወርድ በወያኔያውያን የተዘረፈው የሀገር ሀብትና ሥልጣን እንዴት ወደ ሕዝብ ይመለሳል? በትግሬዎች የተያዘው ቢሮክራሲና ቤትና ቦታ ሁሉ ለሕዝብ የሚሆነው በምን ዓይነት አግባብ ነው? አሁን እንደሚታየው የኢትዮጵያውያን ቤት ስደትና ከርቸሌ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ ጊዜ ሲገለበጥ አሁን የሚታየው ሀገርንና ሕዝብን እያስለቀሰ ያለ የዝርፊያና የውንብድና ጎርፍ አመጣሽ ዐይን ያወጣ የዘመን ክስተት እንዴት ይስተካከላል?” (የሲሳይ አጌናን ጨዋነት በኔ ግልጽነት ለማካካስ መሞከሬን ልብ ብትሉልኝ ደስ ይለኛል – ለማለት የፈለገ የመሰለኝን ግን በቀጥታው ያላለውን ብያለሁና!) የኔ መልስ ባጭሩ – “ያንተ ያልነበረ ያንተ አይሆንም፤ ከአፈር ነውና የተፈጠርከው ወዳፈር ትመለሳለህ” የሚል ነው፡፡ ቀኑ መምጣቱ አይቀርም፤ ቀኑም ቀርቧል፡፡ ያኔ የተዘረፈው ሁሉ ወደየቦታው ይሄዳል እንጂ አለበለዚያማ ትግል ለምን አስፈለገ? ሰው ሀኪም ቤት የሚሄደው ታክሞ ለመዳን አይደለምን? ነቀርሣ ያለበት ሰው ሀኪም ቤት ሄዶ “ነቀርሣየን በጣም እወደዋለሁ፤ እሱንና ያደረሰብኝን ጉዳት አትንኩብኝ፡፡ ነገር ግን ከአሁን በኋላ እንዳይጎዳኝ ምከሩልኝ፡፡” ሊል ይችላልን? እንዴት ተድርጎ! አዎ፣ ፍትህ ለተጎዱ ይበየናል እንጂ ማለባበስ የሚነግሥበት ነፃነት አይኖርም፡፡ ሁሉም እንደዬሥራው፡፡

ሊሆን የሚችለው – ያድርሰንና በቻልነው ሁሉ የምንጥረውም ፍትህ እንድትገኝ ነው፡፡ የቀማ የቀማውን ነገር ለተቀማው ወገን ይመልሳል – መመለስ ብቻም አይደለም፤ ከነኪሣራውና ከነሞራል ካሣው እንዲከፍል በህግ አግባብ ሊበየንበት ይገባል፡፡ ከየትኛው ጊዜ ጀምሮ ምን በነማን እንደተደረገ ይታወቃል፡፡ ሕዝብ ደግሞ መዝገብ ነው፡፡ ሐጎስ የቀማኝን ንብረት ለማስመለስ የሚያስፈልገኝ ነገር የሕዝብ ውሳኔ የደገፈው የመብት ማስከበሪያ ቀላጤ እንጂ ይሉኝታ አይሆንም፡፡ እንደዚያ ከሆነ ነፃነትም የነፃነት ትግልም አያስፈልግም፡፡ አምባቸው በተላላኪነትና በሙስና ያካበተው መቶ ሚሊዮን ብር የሕዝብ ገንዘብ ወደመጣበት ካዝና የማይመለስ ከሆነ በጥፊ አቀርንቶ ይቅርታ እንደመጠየቅ ነው፡፡ ጥፋትን ማስተካከልና ይቅርታ ለዬቅል ናቸው፡፡ የተዘረፈ ወደተዘረፈበት ቦታ ይመለሳል እንጂ አንዴ ተዘርፏልና በዘረፈው ገንዘብ እየተንፈላሰሰ ይኑር ብሎ በፍርደ ገምድልነት መበየን ዝርፊያን ቅድስና መስጠት ነው፡፡ ይህ ሁሉ ግን የወደፊቱ መንግሥታችን ሸክም ነው፡፡

አሁን ገንዘቡንም በባንክ በፈለጉት ስም ያከማቹ፡፡ ሕንፃውንም የትም ይገንቡት – በማንምም ስም ይገንቡት፡፡ ግን ግን ነገ ይህ ሀብትና ንብረት የሀገርና የቀጣዩ መንግሥት ሀብትና ንብረት ይሆናል፡፡ የህግ ዐዋቂዎች አንድ ጥፋት  በሁለት መንገድ ይታያል ይላሉ – በፍትሐ ብሔርና በወንጀል፡፡ ስለዚህ ወያኔም ይሁን ግብረ በላው ሁላ በሚሠራው የፍትሐ ብሔር ነክም ይሁን የወንጀል ድርጊት ይጠየቅበታል እንጂ ዝም ብሎ የሚታለፍ ሊሆን አይገባም፡፡ ከፍ ሲል እንደተጠቀሰው ከሕዝብ ዐይን የሚሠወር ደግሞ ምንም ነገር የለም፡፡

የቀጣዩ መንግሥት ሸክም ብዙ ነው፡፡ አንደኛው እየመረረውም ቢሆን ከዚህ ከፍ ሲል የጠቀስኩትን የሕዝብ ብሶት በፍትህ አደባባይ ቆሞ በደለኞች ተበዳዮችን እንዲክሱ የማድረጉ ጣጣ ነው፡፡ ጥፋት እንዳይደገም ማድረግ የሚቻለው አጥፊነት የሚያሳድግ ሳይሆን የሚያቀጭጭ፣ የሚያለማ ሳይሆን የሚያኮስስ መሆኑን በገሃድ በማሳየት ነው፡፡ አለበለዚያ “እንዲህ ባደርግም ምንም አልሆንም” የሚል ስሜት በአጥፊዎች ዘንድ እየፈጠረ ጥፋት መሥራት ባህል እንደሆነ ይቀጥላል፡፡

አንድ ችግር ግን አለ፡፡ ፍትህን ለማስፈን ማን ነው የሞራል ብቃት የሚኖረው? የክርስቶስን ቃል እዚህ ላይ ያስታውሷል፡፡ የዚያችን በአመንዝራነት የተከሰሰች ሴት ታሪክ ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ ኃጢኣት ያልሠራ የመጀመሪያውን ድንጋይ እንዲወረውርባት ክርስቶስ ሲናገር ሁሉም ሹልክ ሹልክ እያሉ ጠፉና ተከሳሹዋ ብቻ ቀረች፡፡ ማን ይድፈር? … ለመሆኑ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ስንት ነን? ራሳችንን እንጠይቅ፡፡ ማን ነው በማን ላይ መፍረድ የሚችል? ማን ነው ንጹሕ? ማን ነው ዕድፋም? በሰው ዐይን ውስጥ የሚገኝን ስንጥር የሚያህል ጉድፍ ለማውጣት ከመሞከራችን በፊት በራሳችን ዐይን ውስጥ እርፍ እሚያህል ጉድፍ ላለመገኘቱ እርግጠኞች ልንሆን ይጠበቅብናል፡፡ ትግል ከራስ ብላለች ዘፋኟ፡፡

የነገዎቹ መሪዎቻችን አሁን የት ነው ያሉት? ምን እያደረጉ ነው? ከደሙ ንጹሕ ናቸውን? እየተጠላለፉ ነው ወይንስ ምቹ ሁኔታ እስኪፈጠር በአርምሞ እየተጠባበቁ ናቸው? ራሳቸውን ከወንጀልና ከሙስና አጽድተው በጥሩ ድህነት እየኖሩ ነው ወይንስ በ“ሲሞቅ በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በእጅ” ዓይነት እንደአየሩ ጠባይ ድርጊታቸውንም አነጋገራቸውንም እያስተካከሉ በእስስታዊ ባሕርይ ቀን ይጠብቃሉ? አሮጌው ወይን በአዲስ አቅማዳ ይገለበጥና ከአንዱ የመከራና የሥቃይ አዙሪት ወደሌላው እንዛወር ይሆን ወይንስ ፈጣሪ በቃችሁ ይለናል? የአዲሱ መንግሥታችን ሰብኣዊና መዋቅራዊ ቅርጽና ይዘት ከአሁኑ ያስጨንቀኛል፡፡ ለምን ቢሉ እባብን ያዬ በልጥ ይበረያልና፡፡ ስንቱ ቂጣ ይረረብን? ምጣዱስ፣ ማገዶ እንጨቱስ፣ ጊዜውስ፣ ትውልዱስ … አያሳዝኑምን? ኧረ ወደቀልባችን እንመለስ! የተከፋፈለች መንግሥት አትጸናም ይል ‹ነበር› መጽሐፉ፡፡

ስለሆነም ቀጣዩ መንግሥት ብዙ ዕዳ አለበት ነው ባጭሩ፡፡ ቀዳሚው ዕዳው ራሱን የማወቅና ካለፉት በርካታ እንቶ ፈንቶ ሰይጣናዊ አገዛዞች የተለዬ መሆኑን በተግባር የማሳየት ኃላፊነት ነው፡፡ ጨካኝ መሆን ሩህሩህ ከመሆን ያነሰ ወጪ እንዳለው ግልጽ ነው – የዞረ ድምሩ ግን ብዙ ኮተት አለው፡፡ ከሞላ ጎደል የሁሉም ጨካኝ ገዢዎች የመጨረሻ ዕድል ተመሳሳይ ነው፤ ቢያንስ በታሪክ ስማቸው ሲወቀስ ይኖራል፡፡ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው በሀፍረት እየተሸማቀቁ አንገታቸውን ደፍተው እንደነገሩ ለመኖር ይገደዳሉ፡፡ ለአብራኮቻችን ክፋዮች የማናስበው ታዲያ ለምን ይሆን? ምን ዓይነት ርኩስ መንፈስ ተጋብቶብን ይሆን በጥላቻና በቂም በቀል ተለክፈን አንዳችን የአንዳችንን ውድቀት የምንመኘው?

በተረፈ የቀጣዩ መንግሥታችንን ሸክም የሚያበዙ ሀገራዊ ጉዶችን ዘርዝረን አንጨርሳቸውም፡፡ በትምህርት ረገድ “ A,B,C,D” ን በቅጡ ያልለዩና ስማቸውን እንኳንስ በእንግሊዝኛ በሀገርኛ ቋንቋም መጻፍ የማይችሉ ወይም የሚከብዳቸው የቢኤና ኤምኤ ዲግሪ ተመራቂዎችን እንደገና ለማስተማር ራሱ ትልቅ ሥራ ይጠብቀዋል፤ ለነገሩ የትምህርት ጥራት ውድመትን በሚመለከት የምርጫ ቦርዱ ፕሮፌሰራችን ያኔ በ97 ዓ.ም “EPRDF has winned the election!” በማለት የጌቶቹን “ድል አድራጊነት” በገለጸበት ወቅት የሀገሪቱን ምሁራን የዕውቀት ደረጃ ፍንትው አድርጎ አሳይቶ የለምን? ለአሻንጉሊትነትም የማይበቃው “ጠ/ሚኒስትር” ደሳለኝም ያቺን የፈረደባትንና በተናገረ ቁጥር ከአንደበቱ የማይለያትን የእንግሊዝኛ ቃል (unequivocally የምትለዋን) ካለቦታዋ በመደንቀር መንግሥታዊ የዕውቀት ብቃትን ማስመስከሩንም በቅርቡ በአበበ ገላው ልዩ የዶኩመንታሪ ዝግጅትንና በራሳችን ገጠመኝም ታዝበናል፡፡ ጉድ ነው ምዕመናን – የዛሬው እንዲህ ከሆነ የነገውን መገመት አይከብድም – ታዲያ አልጠፋንም ትላላችሁ? ብቻ በውጭ ሀገራት ያላችሁ ወገኖቻችን አደራችሁን – የሀገራችን ተስፋዎች በአብዛኛው እናንተ ናችሁና ገንዘብ ላይ ብቻ ሣይሆን ዕውቀት ላይም እንድታተኩሩና ሀገራችሁ በምትፈልጋችሁ ጊዜ ከገባችበት አዘቅት ለማውጣት በሚደረገው ርብርብ የበኩላችሁን አስተዋፅዖ እንድታደርጉ ከአሁኑ ዝግጁ ሁኑልን – በሀገር ቤት ብዙም አስተማማኝ ነገር ያለ አይመስለኝምና ሀገራችሁ ከእናንተ ብዙ እንደምትጠብቅ በበኩሌ ይሰማኛል፡፡ በሁሉም አቅጣጫ ጠፍተናል፡፡

በዜግነትህና በሰውነትህ ብቻ ተንቀባርረህና “ጎይታይ እምበይተይ” ተብለህ ሊፈጸምልህ ለሚገባ አንድ ጉዳይ እጅ እጅህን  የሚመለከት ሲቪል ሰርቫንት የሚዋኝበትን የመንግሥት ቢሮክራሲ ለማጽዳት የፈጣሪ ተዓምር ካልታከለበት በስተቀር መቶ ዓመትም የሚበቃ አይመስለኝም፡፡ ወደ ሆድ ወርዶ የተሸጎጠውን የሚሊዮኖች ጭንቅላት ከቦርጭ አውጥቶ ወደ ትክክለኛ ሥፍራው ለመመለስና በአንጻራዊ አነጋገር እንደቀድሞው ያለ የመተሳሰብና የመተዛዘን ዘመን ለማምጣት 90 ሚሊዮን ሕዝብን እንደገና የመፍጠር ያህል ከባድ ሥራ ነው፡፡ ግን ግን ኢትዮጵያውያን ስንት እንሆን ይሆን?(እኔ በበኩሌ ከቁጥር የማልገባ ቦቅቧቃ መሆኔን ከአሁኑ እቅጩን መናገር እፈልጋለሁ – ለከንቱ ውዳሤ እንዳይመስላችሁ!! ከእውነት ፈሪና ሀገሬ የኔን አስተዋፅዖ በምትፈልግበት ወቅት ተደብቄ የምኖር ወሬ ጠራቂ ነኝ፡፡ ተደብቆ ማውራት ደግሞ ማንም ሊያደርገው የሚችለው ቀላል ነገር ነው፡፡ ስለዚህም ምድቤ ከጠፉት ነው፡፡)

በአንድ ወይ በሌላ ነገር ያልጠፋን ዜጎችን ለማግኘት አይቻልም፤ እንዲያ ባንሆን ኖሮ ቢያንስ ሀገር በኖረን ነበር፡፡ ትልቁ የመጥፋታችን ምልክት በጥቂት ወንበዴዎች መቶ ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ መቅኖ አጥቶ መቅረቱ ነው፡፡ የሎጥን ታሪክ አስታውስ፡፡ “ጌታ ሆይ አምሳ ሰው እንኳን ባገኝ ቁጣህን አትመልስልኝምን?” – ከተሳካልህ እሺ ይሁንልህ፡፡ ፈለገ፡፡ አጣም፡፡ … “ጌታ ሆይ! አምስት ባገኝስ?” – ከተሳካልህ እሺ ይሁንልህ፡፡ አሁንም ፈለገ፤ ግን አጣ፡፡ ታሪኩን ራስህ ጨርሰው፡፡ የሆነውንም አስብ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ደረጃውን የጠበቀ ጥሩ ዜጋ ለማግኘት እግርህ እስኪነቃ ብትሄድ የምታገኝ አይመስለኝም፡፡ ከሞላ ጎደል ሁላችንም በፍርሀት ተሸብበን ከላይ እንጂ ከራሳችን ምንም ነገር የማንጠብቅ የፈጣሪ ድውያንና የተፈጥሮ ምርኮኞች ሆነናል፡፡ ፍርሀት ብርቱ ጠላት ነው፡፡ ከሰውነት ደረጃ ያወጣል፤ ወደእንስሳነት ደረጃም ያወርዳል፡፡ እኛ በዚህ ሂደት ውስጥ አለን – ‹እስከመቼ?› ለሚለው ወቅታዊ ጥያቄ ግን መልስ የሚያስፈልገው ነው፡፡ እንደወትሮው ሁሉ እግዚአብሔር ይህችን ሀገር ጥሎ የማይጥላት መሆኑ ከታሪክና ከተሞክሮ የምንረዳው ቢሆንም የኛን ሚና መጫወት እንደሚገባን ማስታወስ አለብን፡፡ ለራሳችን ደግ ደጉን ስናስብና ስናደርግ ፈጣሪ ይጨመርበታል – ሁሉንም ከርሱ መጠበቅ ግን የስቃይ ዕድሜን ማራዘም ነው፡፡ …

ነጋዴው ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር እየተመሣጠረ በየቀኑ በሚቆልለው የሸቀጦች ዋጋ ኑሮው የሰማየ ሰማያትን ድምበር ጥሷል፡፡ ለጠቅላላ ዕውቀትህ ያህል የቀዳማዊ ኃ. ሥላሴ ዘመን አንድ ብር በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ ዕቃዎች 30 እና 40 ብር ሲሆን በአንዳንድ ውድ ዕቃዎች ደግሞ ከ500 ብር የሚበልጥባቸው ምንዛሬዎችም አሉ፡፡ ሆድ ተምቦርቅቆ ጤናማ ኅሊና ቁልቁል በመውረድ ቦርጭ ውስጥ ተወሽቆ ሕዝብ ደም እያለቀሰ ነው፡፡ በሕዝቡ መካከልም ፍቅርና መተሳሰብ ጠፍቶ፣ መተዛዘንና መከባበር ተረት ሆነው፣ በተለይ ወጣቱና ጎልማሳው ጫትና መጠጥን እንዲሁም ሀሽሽና ወሬኛነትን በመሳሰሉ ሱሶች ተለክፎ፣ ሙሰኝነት እግር አውጥቶ፣ ብሔራዊ ስሜት በጎጠኝነት ተተክቶ፣ ኢትዮጵያዊነት አብቅቶለት ሊቀበር ተገንዞ፣ ሆዳምነት ነግሦ፣ ታታሪ ሠራተኝነት በዳተኝነት፣ በግዴለሽነትና በስንፍና ተቀይሮ፣ ሃይማኖት በፍቅረ ንዋይ ተለውጦ፣ ቄሱና ጳጳሱ ሳይቀሩ ከዓለማውያን በበለጠ ሥጋውያን ሆነው የደም ግብር ለለመደውና ካለደም ግብር እስትንፋሱ ለማትቀጥለው የደራጎን መንግሥት አድረው ለዲያብሎስ መንግሥት እየሰገዱ፣ ሞራልና ትውፊት ባህልና ወግ ልማድ አጥራቸው ተደረማምሶ ዜጎች ወደ አውሬነትና ወደ እንስሳነት እየተለወጡ፣ መስጊድና ቤተ ክርስቲያናት ለግብር ይውጣ ካልሆነ በሃቅ አምልኮት የማይካሄድባቸው የአጋንንት መፈንጪያ ሆነው፣ ከህገ አምላክና ከህገ ተፈጥሮ ባፈነገጠ ሁኔታ ልቅ ወሲባዊነትና አመንዝራነት እንዲሁም አፈንጋጭ የሴሰኝነት ልማዶች ሀገር ምድሩን ሞልተውትና ይህንን ሰይጣናዊ አፈንጋጭነትም በህግ ለማስረገጥ በሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ ለማቅረብ የማያፍሩ ዜጎች ከተሞችን እያጥለቀለቁ፣ ቅድስቲቷን ሀገር ለማርከስ ዓለም አቀፍ ዘመቻ ተከፍቶ ለብልግና ሥራዎች ማስፋፊያ የውጭ የገንዘብ ድጎማና በክፋት ሥራ የሰለጠነ የሰው ኃይል ድጋፍ እየተደረገ፣ ዘረኝነት ሀገሪቱን እንደብል እምሽክ አድርጓት ሁሉም ነገር በወያኔዎች ቁጥጥር ሥር ገብቶ… ባለበት በዚህ አስጨናቂ ሁኔታ አዲሱ መንግሥታችን ቢመጣ የሚገጥመውን ሁለንተናዊ እንቅፋትና የሥራ ብዛት ከአሁኑ አስቡት፡፡ ጓዶች – የአዲሱ መንግሥታችን ሸክም እጅግ ከባድና ካለፈጣሪ ዕርዳታም የማይሞከር ነው፡፡ በሰው አምሳል የሚንቀሳቀስን አገር ሙሉ አውሬና ነቀዝ ወደሰውነት ለመለወጥ ብዙ ትግስት፣ ብዙ መንፈሣዊና ሥጋዊ መልካም ዕውቀት፣ ብዙ ጥበብ፣ ብዙ ልምድና የአስተዳደር ችሎታ፣ ብዙ ትምህርት፣ ብዙ ተሞክሮ፣ ብዙ መለኮታዊ እገዛና ብዙ የእምነት ጥንካሬ … ያስፈልጋል፡፡ ማይማኑና ደናቁርቱ ወኔያዎች ከ23 ዓመታት ለሚበልጥ ጊዜ ያበለሻሹትን የመንግሥት ቅርጽና ይዘት ለማስተካከል ባጭር ታጥቀውና አንጀታቸውን አሥረው ሌት ከቀን የሚሠሩ ሀገር ወዳድና ሆዳምነትን፣ ዘረኝነትን፣ ሙሰኝነትንና ስንፍናን የሚጸየፉ ቆራጥ ዜጎች ያስፈልጉናል፡፡ እንዲሁ ስለማይገኙ በየምነታችን ወደዬምናመልከው እንጸልይ ምዕመናን፡፡

ግን ግን ካንጀቴ ልጠይቃችሁና በአሁኑ ወቅት እኛ ኢትዮጵያውያን ስንት እንሆን ይሆን? ጥያቄዬ የሚመለከተው በትልቁ እሥር ቤት ማለትም በ“ዞን ዘጠኝ” ውስጥ የምንገኘውን እንጂ በጠባቡ የቃሊቲና መሰል ኢትዮጵያውያን የወያኔ ኦሽቲዊዞች ውስጥ እየተሰቃዩ የሚገኙትን ብርቅዬ ዜጎች እንዲጨምርብኝ አልፈልግም፡፡ በነዚህ እሥር ቤቶች ውስጥ የሚማቅቁ ዜጎች የኔን ፍርሀት በነሱ ወኔና ጀግንነት አሸንፈው የኔንም የነሱንም ስቃይ እየተሰቃዩ የሚገኙ ዳግማዊ ክርስቶሶች ናቸውና በነገይቱ ኢትዮጵያ የድል አክሊል የሚቀዳጁ የነፃነት አርበኞች ናቸው፡፡

(ዲባቶዎች መሣይ ከበደ፣ ብርሃኑ ነጋና ተስፋዬ ደምመላሽ በግዛው ለገሰ የኢሳት ቲቪ ውይይት ላይ ስከታተላቸው ከመሣይ አስተሳሰብ የፈለቀ አንድ አመለካከት ገረመኝ፡፡ ሌላ ቦታ ስለማላገኝ አሁኑኑ ባጭሩ ልተች፡፡ መሣይ የሚለው  “ወያኔዎች ጋር ሰላምና ዕርቅ ለመፍጠር መከላከያውንና ፀጥታውን በነሱው ቁጥጥር ሥር እንደሆኑ ትተን በሌሎች የፖለቲካ መስኮች አብረን መካፈል እንድንችል ለድርድር እንጋብዛቸው” የሚል ነው፡፡ መሣይ ውስጥ በእንግሊዝኛው የቃላት አጠቃቀም naivety ቁልጭ ብሎ ይታየኛል፡፡ ዋናዎቹ የወያኔ መሣሪያዎች ምን ምን ሆኑና ነው? እነዚህን ጡንቻዎች የያዘ አካል ምን ዓይነት መብት ነው ለሕዝብ የሚሰጥ? ዋናው የተቃዋሚም ሆነ የህዝብ ትግልስ እነዚህን የወያኔ እንደልብ መፈንጠዣ ተቋማት ለመቀማትና ለሕዝባዊና ሀገራዊ ዓላማ ለማዋል አይደለምን? ለዚህ ለዚህማ ምን ድርድር ያስፈልጋል? ልክ እንደነልደቱ አያሌውና አሁን አሁን ደግሞ እንደግዛቸው ሽፈራው መሰል የወያኔ አጫፋሪዎች ከወያኔ ጋር አብሮና ተባብሮ የሕዝብን ሰቆቃ ማራዘም የሚቻለው ወያኔ ጉያ ውስጥ በመወተፍ ነው – ልክ እንደነልደቱና ሽፈራው ግዛቸው – ማነው እቴ – ግዛቸው ሽፈራው፡፡ ብርሃኑ እንዳለው አምባገነኖች በምንም ዓይነት መንገድና ሁኔታ ለድርድር አይቀርቡም፡፡ ሞተውም ሞታቸውን የማያምኑ ገልቱዎች ናቸው፡፡ ጋዳፊ በሰደፍ እየተወገረና ሣንጃ በእንትኑ እየገባበት የሀገሩ መሪ እርሱ እንደሆነና እስከዚያን ቅጽበት እንኳን በሊቢያ እየተካሄደ ያለውን ሕዝባዊ አመፅ ለማመን ባለመፈለግ እንዲያውም ምን እንደተፈጠረም ለማወቅ በሚመስል የልብ መደፈን “ጠባቂዎቼ የት አሉ? ምን ሆናችኋል? ግርግሩ ምንድንነው?…” ይል ነበር አሉ፡፡ አምባገነኖች እስከዚህን ድፍን ቅል ናቸው፡፡ እናም የመሣይ የቀቢፀ ተስፋ ንግግር አስገርሞኛል፤ አስቆኛልም፡፡ (ለካንስ ይህን የዋህነቱን ይዞ ኖሯል በዘመነ ደርግ የቀበሌያችን ሊቀ መንበር የነበረው?)  “ራስዋ ሄዳ ጣፊያ የከለከሏት ‹ምላስ ሰምበር ላኩልኝ› አለች” ይባላል፡፡ ወያኔ እንዴትና መቼ እንደሚወድቅ ለምንገምት ወገኖች የመሣይ ሃሳብ ምን ያህል ሞኝነት እንዳለበት መረዳት አይከብደንም፡፡)

ለማንኛውም እንኳን ለ2007 ዓመተ ፍዳ በሰላም አደረሳችሁ፡፡ እንዳይመስልህ – ይህም ያልፋል ደግሞ፡፡

 

Comment

 

↧

የደቡብ ሱዳን ድርድር በባሕር ዳር

$
0
0

ካለፈው ነኀሴ 22 ጀምሮ ተቋርጦ የቆየው በተለያዩ የደቡብ ሱዳን ወገኖች መካከል ይካሄዳል የተባለ ድርድር ሰኞ – መስከረም 5/2007 ዓ.ም ባሕርዳር ላይ ይጀመራል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡

Source:: voanews

ካለፈው ነኀሴ 22 ጀምሮ ተቋርጦ የቆየው በተለያዩ የደቡብ ሱዳን ወገኖች መካከል ይካሄዳል የተባለ ድርድር ሰኞ – መስከረም 5/2007 ዓ.ም ባሕርዳር ላይ ይጀመራል ተብሎ እየተጠበቀ ነው ተደራዳሪዎቹ ኢትዮጵያ የገቡ ሲሆን የድርድሩ እንደተባለው ከተጀመረ ዋናው የመነጋገሪያ ነጥብ የሚሆነው የሽግግር መንግሥት ምሥረታ ጉዳይ እንደሚሆን ተገምቷል፡፡

ምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች የጋራ ልማት ባለሥልጣን – ኢጋድ ቀደም ሲል ወገኖቹ የሁለት ዓመት ተኩል ዕድሜ የሚኖረው የሽግግር መንግሥት እንዲመሠርቱ ሰጥቷቸው የነበረው ቀነ-ገደብ ያለውጤት ከተቃጠለ በኋላ የ45 ቀናት ሌላ ቀነ-ገደብ ቆርጦላቸው እንደነበረ ይታወሣል፡፡

ኢጋድ አቅርቦ በነበረው ሃሣብ የአሁኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በሽግግሩ ወቅት በሥልጣናቸው እንዲቀጥሉ፤ ተቃዋሚዎች ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሰይሙና ስዩሙ ጠቅላይ ሚኒስትርም የፕሬዚዳንቱን ይሁንታ ማግኘት እንዲኖርበት የሚጠይቅ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ይህ ሃሣብ አሁን በሃገሪቱ ውስጥ ያለው ሁኔታ እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው ሲሉ ተቃዋሚዎቹ ደስተኛ እንዳልሆኑበት የገለፁ ሲሆን የመንግሥቱ ወገን ግን ተስማምቶ ለድርድሩ ዝግጁ መሆኑን ማስታወቁን ባሕርዳር የሚገኙትን የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትርና የተደራዳሪዎቹን ቃል አቀባይ ማይክል ማኩዬይን ያነጋገረው እስክንድር ፍሬው ዘግቧል፡፡

ከእስክንድር ጋር የተደረገውን ጥያቄና መልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

VOA 1

 

↧

በህወሀት እና በአጋር ፓርቲዎቹ መካከል አለመተማመን እየተፈጠረ ነው

$
0
0

1231607_10151872226524743_661233572_nእስከ ጳጉሜ 4 2006 ዓ.ም ድረስ የተካሄደው የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ በርካታ እንግዳ ክስተቶችን ይዞ የተገኘ እንደነበር ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል:: በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ለሶስተኛ ጊዜ በተካሄደው በዚሁ የድርጅቱ ስብሰባ ብአዴን እና ኦህዴድ ድርጅታዊ ተልእኮዎችን የማስፈጸም ውስንነት እንደታየባቸው አልፎ ተርፎም የኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎች በተለይም ከኦሮሚያ ክልል ወለጋ ኢሊባቡር እና አምቦ የኦነግ ምሽግ የሆኑ ሲሆን በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር በአርበኞች ግንባር ቁጥጥር ስር ለመዋል እንደተቃረበ፣ በአመራሩ እንዝህላልነት ህዝቡ ከኢህአዴግ እየራቀ እና ለድርጅቱ ጀርባውን እንደሰጠ ከመድረክ ተገልጽዋል:: በዚህ ጉዳይ ላይ የተናገሩት የብአዴን እና የኦህዴድ አመራሮች የተቀሰው አካባቢ ገብቶ ለመስራት ፍቃደኛ የሚሆኑ አባላት እጥረት እንዳለ፣ ህዝቡ በተደጋጋሚ በአካባቢው አመራሮች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እንደሚያደርስ ገልጸው ይህም ሊሆን የቻለው በአካባቢው ያለው የሀይል እጥረት እንደሆነ ገልጸዋል::

በሌላ በኩል በብኣዴን እና በኦህዴድ ውስጥ የሚገኙ አባላት ድርጅታዊ ታማኝነታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ እየመጣ እንደሆነ በርካታ አባላት በየሄዱበት ሀገር ጥገኝነት በመጠየቅ ላይ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን መጪው የ2007 ምርጫ በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድ ሁሉም መሰረታዊ ድርጅቶች አባላታቸውን ጠንክረው እንዲያንቀሳቅሱ በተጨማሪም የሚዲያው ክፍል ልማታዊ አርቲስቶች ወደ ህዝቡ ልብ እንዲገቡ መሰራት እንዳለበት ለዚህም እቅድ ተነድፎ በቅርቡ ለሚዲያው ክፍል ገቢ እንደሚሆን እና ስራው ተግባራዊ እንደሚሆን ከመድረክ ተገልጹአል::

በሌላ በኩል ህወሀት በ2007 ቴዎድሮስ አድሀኖምን የድርጅቱ ኮከብ በማድረግ ላቅ ብሎ ለመታየት የሚያደርገው ሙከራ በአንዳንድ የኦህዴድ እና የብአዴን አባላት ተቃውሞ ሊያስነሳ እንደሚችል የተገመተ ሲሆን ከዚህ ሁሉ ነገር ጸድቶ ትክክለኛ የህወሀት ስራ አስፈጻሚ ሆኖ እየሰራ የሚገኘው ደህዴን እንድሆነ ለማወቅ ተችሉአል::

በተያያዘ ዜና ህወሀት እና የተቃዋሚው ቡድን ለእርቀ ሰላም ይቀመጡ ዘንድ በአፍቃሪ ህወሀቶች ዘንድ ውስጥ ውሰጡን ስራ እየተሰራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣ ይህንንም ስራ በበላይነት ይዘው እየሰሩ ያሉት አቶ መነገሻ ስዩም እንደሆኑ በተጨማሪም አሜሪካን ሀገር ሜሪላንድ ውስጥ ነዋሪ የሆኑት ዶ/ር ጥላሁን በየነ በቡድኑ ውስጥ እንደሚገኙም ለማወቅ ተችልዋል::

የእርቀ ሰላሙ ጉዳይ ከየትኛው ወገን እንደተነሳ ባይታወቅም የተለያዩ አስተያየት ሰጪ የኢህአዴግ አባላት ህዝቡ ከኢህአዴግ በተቃራኒ በመቆሙ በተለይም በሐገር ውስጥ በትግራይ ክልል የአረና ፓርቲ ተቀባይነት ማግኘት በመሀል ኢትዮጵያ ደግሞ የሰማያዊ እና የአንድነት ፓርቲዎች መጠናከር በሚጠሩት ሰልፍ ላይ የሚገኘው የህዝብ ቁጥረ ከእለት ወደ እለት መጨመር በውጪ ሀገራት ደገሞ ግንቦት ሰባት እና የአርበኞች ግንባር ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው ወደ አንድ መስመር መምጣት በህወሀት ነባር አመራሮች ለድርጅታቸው እንደ አደጋ በመታየቱ የእርቀ ሰላሙ ጉዳይ ከህወሀት አመራሮች ሊነሳ እንደሚችል ይገመታል፣ በተቃዋሚው በኩል በእርቀ ሰላሙ ዙሪያ ያለው ምላሽ ምን ሊሆን እንደሚችል የታወቀ ነገር የለም።

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live