Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

አገር እንቁጣጣሽ (ከበወቅቱ ስዩም)

$
0
0

የ’ዳ ክንድሽ አቅፎኝ
ያሳር ክንፍሽ ኣቅፎኝ
እንቁሽን ስመኘው
ጣጣሽ ብቻ ተርፎኝ
መኖርን ስፈራ – መሞትም ስፈራ
ካየር ንብረት በቀር- ንብረት ሳላፈራ
ወሩ ተጠራቅሞ- አንድ ደርዘን ሞልቶ
እንደባለጌ ልጅ – በሩን በግሩ ከፍቶ
አዲስ ዘመን ገባ::
Beweketu Seyoun joke about African leaders summit [Very Funny]
አዲስ ኣመት ገባ
ያለ መስቀል ወፎች – ያለ አደይ አበባ
በግዜር ሰራሽ ማማ
ቁራ ብቻ ሰፍሯል
የመስቀል ወፍማ
ወይ አገር ለውጧል
ወይ ልብሱን ቀይሯል::

አዲስ ኣመት ገባ
በቄጤማ ምትክ- ቡልኬት ጎዝጉዞ
በቅፍ አደይ ምትክ- ጉንጉን ሽቦ ይዞ
በሉባንጃ ምትክ- አቡዋራ እያጤሰ
በፈንድሻ ምትክ- ጠጠር እያፈሰ::
አዲስ አመት ገባ
አዲስ እንዲህ ዋዛ
ተፈጥሮ በውበት -መንፈሴን ሳይገዛ
በመአዛው ሳይዋጅ
መስከረም መግባቱን- በሬድዮ ልስማው?
እንደ መንግስት አዋጅ:

↧

↧

ህዝባዊ እንቢተኝነት ለነፃነት እና ለፍትህ ! (በይድነቃቸው ከበደ)

$
0
0

በአገራችን የፖሊቲካ ሥርዓት ሄደት ውስጥ ስልጣን በሰላማዊ መንገድ ከአንዱ ወደሌላው የተሸጋገረበት አጋጣሚ እጅግ በጣም አናሳነው፡፡ አብዛኛው የስልጣን ሽግግር ጉልበትና ብረትን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የስልጣን ሽግግር ጉልበተኞች ሁሌም አሸናፊ የሚሆኑበት ጉልበቱ አናሳ የሆነ ከስልጣን የሚርቅበት ዓይነተኛ መንገድ ነው፡፡ይህም በመሆኑ በህዝብ ፍቃድ እና ምርጫ ወይም በህዝባዊ እንቢተኝነት የመንግስት የአስተዳደር የስርዓት ለውጥ ወይም ጥገናዊ ማስተካከያ ለውጥ ከዚህ ቀደም እንዲሁም ባሁን ወቅት በአገራችን ስለ መደረጉ ምስክርነት ለመስጠት የሚያስችል አጋጣሚ ስለመኖሩ ያጠራጥራል፡፡ ለዚህም ነው ሰላማዊ ትግል በአገራችን ተስፋ አስቆራጭ እና የማይሞከር መስሎ የሚታየው፡፡

ይድነቃቸው ከበደ

ይድነቃቸው ከበደ


እርግጥነው በሰላማዊ ትግል ሂደት ውስጥ ውጣ ውረዶ የበዛ ነው፡፡ በዓለማችን ላይ የተካሄዱት ሠላማዊ ትግሎች ውጤት ያስመዘገብት መተኪያ የሌለውን የሰውልጅ ሕይወትን እስከመንጠቅ በመድረሰ ነው፡፡ ይበልጥ ደግሞ ትግሉ አስቸጋሪ የሚያስመስለው ውጤቱ የሚፈጀው ጊዜ ነው፡፡ ሠላማዊ ትግል ማለት ታጋዩ የሚታገልለትን ውጤት ሣይመለከት በትግሉ ሂደት የሚሰዋበት ነገር ነው እስከመባል ይደርሳል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ደረጃ ለመድረስ ከሌላ ጋር ሣይሆን ከእራስ አስተሳሰብ ጋር ይህ ቀረሽ የማይባል ትግልን ማካሄድ ይጠይቃል፡፡ ይሁን እንጂ እንዲህ-አይነቱ የአስተሳሰብ ልዕልና ለመድረስ ገፊ ምክንያቶች ካሉ፣ ምክንያቶችሁ በስትራቴጂ ከተነደፉ፣ የገዥው ስርዓት ደካማ ጎኖ በሚገባ ከታወቀና ከተለየ፣ ተምሳሌታዊ እንዲሁም ደረጃ በደረጃ የሚያድግ ሰላማዊት ግሉን የሚመራ ጠንካራ ተቋም ካለ የሰላማዊ ትግል የአስተሳሰብ ደረጃ ማሳያ የሚሆን በአመርቂ ውጤት የተደገፈ ተግባር እውን ሆኖ ማያት የማይቻልበት ምንም ምክንያት የለም ፡፡ በመሆኑም የሠላዊ ትግል መገለጫዎች ከሆኑት ውስጥህ ዝባዊ እንቢተኝነት ከአምባገነን አገዛዝ ወደ ዲሞክራሳዊ ስርዓት ለመሸጋገር አይነተኛ መንገድ ነው፡፡ ስለዚህም ህዝባዊ እንቢተኝነት ወንጀልም አጢያትም አይደለም! ህዝባዊ እንቢተኝነት በተለያዩ አገሮች በተለያየ ወቅት የተተገበር እና ውጤት የታየበት ከአምባገነናዊ ስርዓት የመላቀቂያ ቀጥተኛ መንገድ ነው ብሎ መደምደም ባይቻልም ተመራጭ የሰላማዊ ትግል ስትራቴጂ ነው፡፡ ሁላችንም ሊያስማማን የሚችለው ጨቋኝ የመንግስት ሥርዓት ባለበት ህዝባዊ እንቢተኝነት የቅንጦት ጉዳይ ሣይሆን የህልውናምርጫ ይሆናል፡፡ በዚህም ምክንያት ህዝባዊ እንቢተኝነት የትኛውም አይነት ስም ቢሰጠው ተጨቋኝ እና ጨቋኝ እስካለ ድረስ አይቀሬነቱ እርግጥ ነው፡፡
ጨቋኝነት እራስን በክፉ ልቦና እና በጥላቻ በማስገዛት ከሰውነት በታች በራስ ፍቃድ የሰው መጥፎ መሆንን ወዶ መቀበል ነው፡፡ መጮቀን ግን ማንም የትም ፈልጎ የማይቀበለው ጉልበተኛ ጉልበት በሌለው ላይ የሚያሸክመው የግፍ ክምር ነው፡፡መጨቋን በግለሰብ ደረጃ ሲሆን እዳው ገብስ ነው ተብሎ ቀሎ ባይታይም፣ በአገር እና በመንግስት ሲሆን ግን ልብ ይስብራል የማንነትም ክብር ያሳጣል፡፡ ጭቋና በሃይማኖት፣ በጎሣ፣ በአስተሳሰብ እና በፖለቲካ አመለካከት ምክንያት ሲፈፀም የጭቆና ቀንበር መሸከም ይከብዳል፡፡
በመሆኑም በስልጣን ላይ የሚገኝ የህዝብ ፍቃድ ጨርሶ ያላየው በሃይል እየገዛ የሚገኘ መንግስት፡፡በሃይማኖት፣ በጎሣ፣ በአስተሳሰብ እና በፖለቲካ አመለካከት በዜጎቹ ላይ እያደረሰ ያለው ጭቆና መጠኑ እና አይነቱ እየበዛ ከሄደ ለዜጎች እንቢተኝነት ምላሹ የሥርዓት ለውጥ ብቻ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በጭንጋፍ አምባገነናዊ የመንግስት አስተዳደር ውስጥህ ዝባዊ እንቢተኝነት ያለው ምልክታ እንደሌሎች ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ እና ተቃውሞ የተሸዋረር እይታ አይደለም፡፡
ይሁን እንጂ የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ እኛ ኢትዮጵያዊያን ስለ እዝባዊ እንቢተኝነት ለመነጋገር ሳይሆን ተግባራዊ ለማድረግ በቂ ምክንያቶች አሉን፡፡ የመጀመሪያው እና ወሳኙ በህዝብ መልካም ፍቃድ እና ምርጫ ይሁንታ ባላገኘው ጉልበተኛ መንግስት አማካኝነት ነፃነት እና ፍህት በአደባባይ መነጠቃችን እና በተነጠቅነው ምትክ እየደረሰብን ያለው መንግስታዊ ጭቆና ከልክ በላይ መሆኑ ነው፡፡ የህዝብ ስልጣን ባለቤት ቀማኞች ኢትዮጵያዊ ማንነት እና ክብር በማሳጣት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነት ንእንዲጠፋ ለማድረግ እና እነሱ እንደሚፈልጉት አይነት ሃገር ሆና ማየት የቀን የለሊት ምኞታቸው እንዲሁም ጥረታቸውም ጭምር ነው፡፡ ማንነትን ከማሰናከል እና ከማጥፋት የሚጀምረው መንግስታዊ ውንብድና እጅ ሳይሰጡ ለምን ብሎ መጠየቅ ትልቁ እና የመጀመሪያው የነፃነት ጥያቄ ነው፡፡ የጥያቂው ምላሽ ምንም ይሁን ምን በጀግኖች አባቶቻችን እና እናቶቻችን ተከብራና ታፍራ የኖረችው በፈጣሪ ቃልኪዳን እና እገዛ ሁሌም በክብር ትኖራላች፡፡
በአገራችን ሞልቶ በፈሰሰው የግፍ ፅዋ ያልተነካው ማነው ? 23 ዓመት ሙሉ ነፃነት እና ፍትህ በመነጠቅ የቁም እስረኛ በመሆኑ የተጨነቀው ስንቱ ነው? ጭንቀቱ አላስችል ሲለው አገር ጥሎ በሰው አገር የሚኳትነው ምን-ያህል ነው? በአገዛዙ ስርዓት ምክንያት የስንት ሰው ህይወት ተሰዋ ? የታሰረው እና የቆሰለው ቤት ይቁጠረው፡፡ የኑሮ ውድነቱ ትከሻን ከማስጎበጥ አልፍ የስንቱን ህይወት ቀጠፈ? እኛ ኢትዮጵያዊያን ደሰታችን እና ሀዘናችን ከፈጣሪ ጋር የተቆራኘ ነው፤ ይህን እንጂ የአገዛዙ ሥርዓት የለየለት አምባገነን መሆኑ የሚያመላክተው በሃይማኖት ላይ የሚያደርገው ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት እና ያስከተለው ቀውስ ጭምር ነው፡፡ ለሃይማኖት እና ለታሪክ ግድ የማይሰጠው ገዥው መንግስት በዜጎች መካከል ማህበራዊ ቀውስ በመፍጠር ያለተረጋጋ ማህበረሰብ እንዲኖር ያልተደረገ ነገር ምን አለ ? መሬት ቆርሶ መሸጥ የዕለት ገቢ ያደረገው መንግሰት በተለያየ የአገራችን ክፍል ምትክ መሬት ወይም ተገቢውን ካሳ ሳይሰጣቸው የተፈናቀሉ እና ለከፋ ችግር የተጋለጡ ቤት ይቁጠራቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህ እና መሰል በደሎች በመንግሰት አማካኝነት ያልተፈፀመበት ማነው ?፡፡ ከተገፉ እና ከተበደሉ ጎን ላለመቆም መወሰን ምንም አልተነካውም የሚለው ነገ ላለመነካቱ ምን ማረጋገጫ አለው ፡፡እርግጥነው የስርዓቱ ቀጥተኛ ተጠቃሚ የሆኑ ጥቂት ግለሰቦች እና ሆድ አደሮች ለህዝባዊ ህንቢተኝነት የወንዝ ዳር ሙጃ ሣራ መሆናቸው አይቀርም ፡፡
በመሆኑም ጥገናዊ ለውጥ የሚያመጣ የመንግሰት አስተዳደር ሳይሆን የስርአት ለውጥ ለመፍጠር የሚያስችል ሁሉን አቀፍህ ዝባዊ እንቢተኝነት በሠላማዊ መንገድ ተግባራዊ ማድረግ እንደ-ዜጋ የመኖር ወይም ያለመኖር ምርጫም ጭምር ነው፡፡ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ከግዴለሽነት እና ምን-ያገባኛል ስሜት ተላቆ በገዥው መንግሰት ላይ “ስልጣን የህዝብ ነው!” ከማለት ባለፍ የስልጣን ባለቤት ለመሆን የሚያስችል ቁጭት አዘል ዝግጅት ስለመኖሩ ብዙ አመላካች ነገሮች አሉ፡፡ ስለሆነም ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ያለው የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ፣ እጅግ በጣም ሰላማዊ የሆነ መሪ እና ተመሪ ያለው ጠንካራ ስትራቴጂ በመንደፍ ህዝባዊ ህንቢተኝነት ለነፃነት እና ለፍትህ ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል፡፡
እንዲህ አይነቱ ህዝባዊ እንቢተኝነት በሁለት መንገድ የሚፈፀም ነው፡፡ የመጀመሪያው ዜጎች በራሳቻው ፍቃድ ተነሳሽነት በሚፈጥሩት ተቋማት የሚመራ ሲሆን፡፡ በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ነፃ ማህበራዊ ተቋም ስለመኖሩ እና ይህን ስለማስፈፀማቸው እርግጠኛ ለመሆን አይቻልም፡፡ ሌላው ደግሞ በፖለቲካ ፓርቲዎች አማካኝነት ነው፡፡ ይህ ደግሞ አሁን ባለው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከተለመደው እና ውጤቱ በግልፅ ካልታወቀበትና ካልተመዘነበት የቅርብ ጊዜ የተቃውሞ ሰልፍ ልምድ ጋር ሲነፃፀር አዲስ ምዕራፍ ነው፡፡ ሆኖም ግን ለ8 ዓመታት የተዘጋው የተቃውሞ ሰልፍ በሰማያዊ ፓርቲ ፈር-ቀዳጅነት አደባባይ ወጥተን ድምፃችን ለማሰማት መቻላችን ለፓርቲው አድናቆት የሚያሰጥ ነው፡፡ በተጨማሪ የዚህ ፁሁፍ አቅራቢ በመኢአድ እና በአንድነት እንዲሁም በመድረክ አማካኝነት የተካሄዱትን የተለያዩ የተቃውሞ ሰልፎች ያለው አድናቆት እንደተጠበቀ ነው፡፡ ስለሆነም አገር አቀፍ ህዝባዊ እንቢተኝነት በሰላማዊ መንገድ ተግባሪዊ እንዲሆን የፓርቲዎች ፊት አውራሪነት እና አዝማችነት የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ በህዝብ የተጣለበትን ሃላፊነት የሚወጣ እና የተለያ የሰላማዊ የትግል ዜዴዎችን ተግባሪዊ የሚያደርግ ጠንካራ የተቃዋሚ ፓርቲ የምናይበት ወቅት እርቁ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለው ፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!
↧

የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ከአውሮፓውያን ጋር ያለው ልዩነት መንስኤ እና ትክክለኛ መሰረቱ (የጉዳያችን ጡመራ ልዩ ጥንቅር)

$
0
0

የዘመን መስፈሪያዎች

 

Adeyabebaእግዚአብሔር «ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ፣ ለዕለታት፣ ለዘመናትና ለዓመታት ምልክት ይሆኑ ዘንድ» / ዘፍ.1. 14- 15/ የፈጠራቸውን የፀሐይንና የጨረቃን እንቅስቃሴ መሠረት ያደረጉት መስፈሪያዎች ናቸው፡፡ እነዚህም፤

 

ሀ. ዕለት-

አንድ ዕለት አንድ ቀንን /የብርሃን ክፍለ ጊዜን / እና አንድ ሌሊትን /የጨለማ ክፍለ ጊዜን/ ያካተተ ፀሐይ አንድ ጊዜ ከወጣች በኋላ ተመልሳ እስክትወጣ ድረስ ያለውን ጊዜ የያዘ ነው፡፡ በአሁኑ ዕውቀታችን አንድ ዕለት ምድር በራሷ ዛቢያ አንድ ጊዜ የምትሸከረከርበት ጊዜ ነው፡፡

ለ. ውርኅ-

 

ወርኅ ማለት በግእዝ ጨረቃ ማለት ነው፡፡ አንድ ወርኅ የሚባለው ጊዜ ሙሉ ጨረቃ ከወጣች በኋላ ድጋሚ እስከምትወጣ ድረስ ያለው ጊዜ ነው፡፡ በአሁኑ ዕውቀታችን / በጥንቱም ጨምሮ/ ይህ ጨረቃ መሬትን አንድ ጊዜ ዙራ ለመጨረስ የሚፈጅባት ጊዜ ነው፡፡ አንድ ወር ሃያ   ዘጠኝ ተኩል ዕለታትን ይፈጃል፡፡

 

ሐ. ዓመት-

አንድ ዓመት ማለት መሬት አንድ ጊዜ በፀሐይ ዙሪያ ለመዞር የሚፈጅባት ጊዜ ነው፡፡ ይህም 365 ከ1/4 / ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ቀን ከሩብ/ ዕለታት ይፈጃል፡፡ይህ ከመታወቁ በፊትም ግን የዓመት ጽንሰ ሓሳብ ነበር፡፡ ፕሮፊሰር ጌታቸው ኃይሌ የፅንሰ ሐሳቡን አመጣጥ እንዲህ ያስረዳሉ፡፡

 

ሰዎች ርዝመታቸው እኩል የሆኑ ሁለት  ሻማዎችን ሠሩና ልክ ፀሐይ ስትወጣ /ቀኑ ሲያልቅና ሌሊቱ ሲጀምር/  አንዱን ሻማ አበሩት፡፡ልክ ፀሐይ ስትወጣ እሱን አጠፋና ሌላውን / ሁለተኛውን/ ሻማ አበሩት፤ ጧት ፀሐይ እንደገና ስትወጣ / ሌሊቱ አልቆ ሌላ ቀን ሲጀምር/ ሻማውን አጠፉት፡፡ አሁን እንግዲህ ከየሻማዎቹ /ከሁለቱ ሻማዎች/ ምን ያህል እንደተቃጠለላቸው ሲያስተያዩት ከሁለቱ ሻማዎች የተቃጠለው እኩል አለመሆኑን ተመለከቱ በዚህም የቀኑና የሌሊቱ ርዝማኔ እኩል አለመሆኑን ተረዱ፡፡

 

ቀደም ብለውም የቀኑና የሌሊቱ ርዝማኔ በተለያዩ ወቅቶች የተለያየ መሆኑን ልብ ብለው ነበርና ይህንን ሙከራቸውን ሲቀጥሉ በቀኑና በሌሊቱ ርዘማኔ / በሚቃጠለው የሻማዎቹ መጠን/ መካከል ያለው ልዩነት ከወቅት ወቅት የተለያየ እንደሆነ ተመለከቱ ይህን ሙከራቸውን ሲቀጥሉ ግን በየ182 /ተኩል/ ዕለቱ ቀኑና ሌሊቱ እኩል የሚሆኑባቸው ሁለት ዕለታት በዓመት ውስጥ እንዳሉ ተገነዘቡ፡፡ እነዚህ ዕለታት አንዱ የሙቀት ወራት ከመጀመሩ በፊት የሌላው ደግሞ የቅዝቃዜው ወራት ከመጀመሩ በፊት የሚመጡ ናቸው፡፡ ስለዚህ የቀኑና የሌሊቱ ርዝመት አንድ ጊዜ እኩል ሁኖ ደግሞ በዚያው ወቅት እኩል እስከሚሆን ድረስ ያለውን ጊዜ ማለትም / 182 ተኩል + 182 = 365/ ዕለት አንድ ዓመት አሉት፡፡ አሁን ባለን ግንዛቤ ምድር በራሷ ዛቢያ እንደተሽከረከረች በፀሐይ ዙሪያ ትዞራለች፡፡ ምድር በፀሐይ ዙሪያ የምትዞረው ወደ ጎን 23 ተኩል ዲግሪ ያህል አጋድላ ነው፡፡ ይህ የቀንና የሌሊት ርዝመት መለያየትም የሚከሰተው በዚህ ማጋደል ምክንያት ነው፡፡

 

እንግዲህ በአጠቃላይ ዋናዎቹ የጊዜ / የዘመን/ መስፊሪያዎች ዕለት፣ ወር እና ዓመት ናቸው፡፡ ሦስትቱም ተመላላሽ ክስተቶችን / ለምሳሌ የፀሐይን መውጣት/ መሠረት ያደረጉ ናቸው፡፡ እነዚሀ ተመላላሽ ክስተቶች አንድ ጊዜ ከተከሰቱ በኋላ ደግመው እስኪከሰቱ የሚፈጁት ዘመን ወይም ጊዜ  ዓውድ ይባላል፡፡ ዓውድ ማለት ዙሪያ፣ ክብ፣ እንደ ቀለበት ዙሮ የሚገጥም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ዓውድ ማለት ክስተቶቹ አንድ ጊዜ ከተከሰቱ በኋላ ደግመው እስኪመጡ ድረስ ያለው ጊዜ ማለት ነው፡፡

 

በዚህ መሠረት ከላይ ያየናቸው ሦስት መስፈሪያዎች / ዕለት፣ ወርኀ፣ ዓመት/ ዓዕዋዳት / ዓውዶች/ የሚወጡበት ጊዜ ዓውደ ዕለት፣ ዓውደ ወርኀ፣ ዓውደ ዓመት ይባላሉ፡፡

 

መጀመሪያ ላይ ሰዎች እነዚህን ሦስቱን መስፈሪያዎች /ዓዕዋዳት/ /በተለይም ቀንና እና ወርን/ ለየብቻቸው ይጠቀሙባቸው ነበር፡፡ ከዚህን ያህል ቀን፣ ከዚህን ያህል ወር በኋላ /በፊት/ እያሉ ጊዜን ይለኩ ነበር፡፡

 

እነዚህ ሦስቱን በቅንብር /በቅንጅት/ ለመጠቀም ሲፈለግ ግን የዘመን አቆጣጠር ስሌት ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም አንድ ወር 29 ከግማሽ ቀን ነው፡፡

 

እንዲሁ እንዳለ ለመቁጠር ቢፈለግ የመጀመሪያው ወር ጠዋት ላይ ቢጀመር ሁለተኛው ወር ምሽት ላይ ይጀምራል፣ ሦስተኛው ደግሞ ድጋሚ ጠዋት ላይ ይጀምራል፤ ይህን ለመቅረፍ ወሩን ሙሉ  ሰላሳ ቀን ቢያደርጉት ከትክክለኛው ወር /የጨረቃ ዐውድ/ ግማሽ ቀን ይተርፋል፤ 29 ቀን ብቻ ቢያደርጉት ደግሞ ግማሸ ቀን ይጎድላል፡፡ አንድ ዓመት 365 ከሩብ ዕለታት አሉት፡፡

 

ዓመትን በወራት ለመቁጠር ቢፈለግ፤ ዓመቱን 12 ወር ቢያደርጉት የዓመቱ /የዕለታት ቁጥር /29.5X12=354/ ብቻ ይሆናል፡፡ ይህም ከትክክለኛው ዓመት /365-354=11/ ዕለታት ያህል ያንሳል፡፡ 13 ወር ቢያደርጉት ዓመቱ /365X13=385.5/ ቀናት ይሆናል ይህም ከትክክለኛው ዓመት /383.5-365=19/ ቀናት ያህል ይበልጣል፡፡

 

ስለዚህ እነዚህን መስፈሪያዎች በቅንጅት ለመጠቀም ይህንን አለመጣጣም የሚፈታ ቀመር /የዘመን አቆጣጠር ሥርዓት/ ያስፈልጋል፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ የዘመን አቆጣጠሮች ተዘጋጅተዋል፡፡

 

የአይሁድ ዘመን አቆጣጠር

የአይሁድ ዘመን አቆጣጠር እያንዳንዳቸው 29 እና 30 ዕለታት ያሏቸው 12 ወራት አሏቸው፤

ተ.ቁ የአይሁድ ወራት የዕለታት ብዛት ወራቱ በእኛ
1 ኒሳን 30 መጋቢት/ ሚያዝያ
2 ኢያር 29 ሚያዝያ/ ግንቦት
3 ሲዋን 30 ግንቦት/ ሰኔ
4 ታሙዝ 29 ሰኔ/ ሐምሌ
5 አቭ 30 ሐምሌ/ ነሐሴ
6 አሉል 29 ነሐሴ/ መስከረም
7 ኤታኒም 30 መስከረም/ ጥቅምት
8 ቡል 29/30 ጥቀምት/ ኅዳር
9 ከሴሉ 30/29 ኅዳር/ ታህሳስ
10 ጤቤት 29 ታህሳስ/ ጥር
11 ሳባጥ 30 ጥር/ የካቲት
12 አዳር 1 29 የካቲት/ መጋቢት

እነዚህ የዓመቱ 12 ወራት በአጠቃላይ 354 ያህል ብቻ ዕለታት ይኖሯቸዋል፡፡ ይህም በትክክለኛው ዓመት በ11 ዕለታት ያህል ቢያንስም አዲስ ዓመት ይጀምራሉ፡፡ ልዩነቱ በሁለት ዓመታት 22 ዕለታት፣ በሦስት ዓመት ደግሞ 33 ዕለታት ያህል ይሆናል፡፡ ስለዚህ በየሦስት ዓመቱ ከአስራ ሁለተኛው ወር ጳጉሜን በፊት አንድ ሌላ ወር ይጨምሩና ጨምረው የዓመቱን የወራት ቁጥር ዐሥራ ሦስት ያደርጉና ልዩነቱን ያስተካክሉታል፡፡

 

የኢትዮጵያውያንና የግብጻውያን ዘመን አቆጣጠር

የሀገራችን ኢትዮጵያ እና የጥንት ግብጻውያን /ዛሬም ድረስ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የምትጠቀምበት/ የዘመን አቆጣጠር ተመሳሳይ ነው፡፡ ሁለታችንም እኩል ሰላሳ ቀናት ያሏቸው 12 ወራት አሉን፡፡ እነዚህ 12 ወራት / 12X30=360/ ቀናት አሏቸው እነዚህ ቀናት በትክክለኛው ዓመት በ/365.25-360=5.25/ ቀናት ያንሳሉ፡፡ ይህንንም 5 ቀናት / በ4 ዓመት አንድ ጊዜ 6 ቀናት/ ያሏትን 13ኛ ወር በመጨመር ያስተካክሉታል፡፡ የኢትዮጵያውያን እና የግብጻውያን ወሮች ስም እንደሚከተለው ነው፡፡

 

ተ.ቁ የግብጽ ወሮች የኢትዮጵያ ወሮች
1 ቱት/ዩት መስከረም
2 ባባ/ፓከር ጥቅምት
3 ሀቱር ኅዳር
4 ኪሃክ/ከያክ ታኅሣሥ
5 ጡባ/ቶቢር ጥር
6 አምሺር/ሜሺር የካቲት
7 በረምሃት መጋቢት
8 በርሙዳ ሚያዝያ
9 በሸንስ ግንቦት
10 ቦኩሩ ሰኔ
11 አቢብ ሐምሌ
12 መስሪ ነሐሴ
13 ኒሳ/አፓጎሜኔ ጳጉሜን

/ባሕረ ሐሳብ፣ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ ፣ገጽ.65/

የኢትዮጵያ ዘመን አቈጣጠር

የኢትዮጵያ እምነታዊ ባህል የሚወረሰው በሦስት ዐይነት ጠባይ ነው። አንዱ ሕገ ልቡና ይባላል። ከመጽሐፍ በፊት የነበረ ነው።ከአበው ቃል በቃል የተወረሰ ነው። ሁለተኛው በሕገ ኦሪት ከኦሪት የተቀዳ ነው። ሦስተኛው በሕገ ወንጌል ከወንጌል የተማርነው ነው።እና በሦስት ዐይነት ጠባይ የሚመራ ነው። በዚህ ዐይነት ከወረስናቸው በዓላት ማለት በሦስቱም ጠባያት ከወረስናቸው በዓላትየየራሳቸው መልክ ያላቸው አሉ። ለምሳሌ ልደት፥ ጥምቀት፥ ዕርገት፥ ደብረ ታቦር እነዚህን የመሳሰሉት ከወንጌል የተማርናቸውናቸው፤ በብሉይ የሉም። ፋሲካ፥ በዓለ ጰራቅሊጦስ ደግሞ ከኦሪት የተማርናቸው ናቸው። የዘመን መለወጫ በዓል ግን ከሕገ ልቡናቃል በቃል ተምረን፥ በኦሪት የመጽሐፍ መሠረት አግኝተንለት በወንጌልም አጽንተን ይዘነው የኖርነው ሦስት የሥራ ዘመን ክፍልየተላለፈና እዚህ የደረሰ ነው። እኛ የዘመን መለወጫ ብለን በሀገራችን ባህል የምናከብረው ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር የተገኘበት፥ብርሃን፥ ጊዜ፥ ዕለት፥ ሰዓት የተፈጠሩበት፤ ለብርሃን፥ ለጊዜ፥ ለዕለት፥ ለወር ለዓመት ጥንት መሠረት የሆነ ቀን ነው። ይህንን ሁሉበማስገኘት እግዚአብሔር ራሱን የገለጠበት፥ ዓለምን በመፍጠር ከሃሊነቱን ያረጋገጠበት ቀን ነው ብለን ነው የምናከብረው። ስለዚህምጥንተ ብርሃን፥ ጥንተ ዕለት፥ ጥንተ ጊዜ፥ ጥንተ ፍጥረት ርእሰ ዐውደ ዓመት ብለን ነው የምናከብረው። በዚህ ስያሜ በዓሉ ርእሰ ዐውደዓመት፥ ቅዱስ ዮሐንስ፥ የዘመን መለወጫ ብለን እናከብረዋለን።

 

ቅዱስ ዮሐንስ

የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ በዓል ሌላው ስሙ ቅዱስ ዮሐንስ ይባላል። ቅዱስ ዮሐንስ የሚባልበትም ሁለት ጠባይ አለው። አንዱ፤መጥምቁ ዮሐንስ በሄሮድስ አንቲጳስ ጊዜ ከጳጉሜን ፩ ቀን ጀምሮ ታስሮ ሰንብቶ በመስከረም ፩ ቀን ዐሳብ ስለ ተቆረጠበትናበመስከረም ፪ ቀን እንዲሞት ውሳኔ ስለ ተሰጠበት አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ ስለ ሞተ ሊቃውንት ይህንን በዓል እሱ ራሱ ለኦሪትናለወንጌል መገናኛ መምህር ስለ ነበረ ይህም በዓል ላለፈው ዘመን መሸኛ፥ ለሚመጣው ዘመን መቀበያ እንዲሆን ብለው በመስከረም ፩ቀን እንዲከበር ስላደረጉ በሱ ስም ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል። በሁለተኛው ግን ከአራቱ ወንጌላውያን አንዱ ወንጌላዊ ዮሐንስየተሰየመበት ስለ ሆነ በአቆጣጠርም ተራ ወደ ኋላ ተመልሶ ቢቈጠር ዓለም የተፈጠረበት ዘመን በዘመነ ዮሐንስ እንዳጋጣሚ ሆኖስለሚገኝ ቅዱስ ዮሐንስ ተብሎ ይጠራል።

 

ዕንቍጣጣሽ

በዚያም ጊዜ የነበሩ ኖኅና ልጆቹ ሰማዩ በደመና በመክበዱ ምክንያት ማየ አይኅ እንደገና ይመጣ ይሆን፥ የጥፋት ውሃ እንደገና ይዘንምይሆን እያሉ ሲደነግጡ ከርመው በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ሙሉ የፀሓይ ብርሃን ስላዩ፥ ምድር በአበባ አሸብርቃ ስለ ተገለጠችናበዚህም የእግዚአብሔርን ቸርነት፥ የቃል ኪዳኑን መጽናት ስለ ተረዱ ይህንን በዓል ቀድሞ ከአባቶቻቸው እንደ ወረሱት ያው ጥንተብርሃን፥ ጥንተ ዓመት፥ ጥንተ ዕለት አድርገው አክብረውታል። ሲያከብሩትም እንግጫ ነቅለው፥ አበባ ጐንጕነው መጀመሪያ መሥዋዕትይሠዉነት ከነበረው ቦታ ሄደው ለእግዚአብሔር ገጸ በረከት አቅርበው ከዚያ በኋላ ግን እርስ በርሳቸው የአበባ ስጦታ በመለዋወጥአክብረውታል። ሲያከብሩትም ዕንቍጣጣሽ በሚል ቃል እውነት የመልካም ሞኞታቸውን ይገላለጡበት ነበር። ዕንቍጣጣሽ ማለትንምብዙ ታሪክ ጸሓፊዎች በልዩ ልዩ መልክ ተርጕመውታል። እንዲያውም ንጉሡ ሰሎሞን ለሳባ ንግሥት የዕንቍ ቀለበት ሰጥቷት ነበርና«ዕንቍ ለጣትሽ» ማለት ነው ብለው የጻፉ ብዙ ሰዎችም አሉ፤ የሚናገሩም አሉ። ነገሩ ግን እንዲህ አይደለም። ዕንቍጣጣሽ ማለትተንቈጠቈጠ፥ አንቈጠቈጠ ከሚለው ቃል ተወስዶ ምድር በአበባ አጌጠች፥ ሰማይም በከዋክብት አሸበረቀ እንደ ማለት ሰማይንበከዋክብት ያስጌጠ አምላክ ምድርንም በአበቦች አጎናጸፋት ለማለት የተሰጠ ቃል ነው እንጂ ስለ ሳባ ንግሥት የተሰጠ አይደለም።ሁለተኛም አባቶቻችን ኢትዮጵያን በሙሉ ሀብት ተረክበዋት ነበርና፤ «ዕንቍ ዕጣ ወጣሽ፤» ሲሉ ወደ አገራቸው ሲገቡ ለአገራቸውመታሰቢያ አድርገው የተጠቀሙበት ቃል ነው ይባላል። በመሠረቱ ግን ያ የጥፋት ውሃ ቀርቶ ምድር ጸንታ፥ አበባ ቋጥራ፥ ፍሬለመስጠት ተዘጋጅታ መገኘቷን የሚያበሥር ቃል ነው።

 

መስከረም

መስከረም የሚባለው ወርም ኖኅ በመርከብ ውሥጥ በነበረ ጊዜ እንደ ዕብራውያን አቈጣጠር ሰባተኛ በሆነው በመስከረም ወርመጀመሪያ ላይ መርከቢቱ አራራት ከሚባለው ተራራ ላይ ዐርፋ ምድር ጨብጣለች። በግእዝ ቋንቋ መርከብ መስቀር ይባላል። ከዘመንብዛት በኋላ «ቀ» ወደ «ከ» ተለውጦ መስከረም ተባለ እንጂ መስቀርም ምድር አገኘች፥ መርከብም ምድር ነካች ለማለት የተሰጠ የወሩስያሜ ነው።

 

ርእሰ ዐውደ ዓመት

የምንለው፤ ዐውድ ማለት በግእዙ ቋንቋ ዙሪያ፥ ክብ የሆነ ነገር ማለት ነው። የዓመት ጠቅላላ ቀኖች መሠረታውያን ቀኖች የሚባሉትሦስት መቶ ስድሳ አራት ቀኖች ናቸው። እነዚህም በኀምሳ ሁለት ሱባዔ ተከፍለው ለእያንዳንዱ ቀን በዓመት ውስጥ ለሰባቱ ዕለታትኀምሳ ሁለት ኀምሳ ሁለት ቀን ይደርሳቸዋል። ከነዚህ ቀኖች የተሳሳበ የሴኮንድ፥ የደቂቃ፥ የሰዓት ዕላፊ ተጠራቅሞ ሦስት መቶ ስድሳዐምስተኛዋን የዘመን ማገጣጠሚያ ቀን ያስገኛል። ይህቺ ቀን እንግዲህ ዙሪያ፥ ክብ መግጠሚያ ናት ማለት ነው። በዚህች ቀንአማካይነት ወደ ዐዲሱ ዘመን መጀመሪያ እንተላለፋለን። ይህቺ ቀን ዕለት አዕዋዲት፥ ዕለተ ምርያ የመዘዋወሪያ ቀን ወይም የመጨረሻቀን ተብላ ትጠራለች። በአራት ዓመት ደግሞ ከዚህች መሳሳብ የምትገኝ አንዲት ቀን ትመጣለች። ሦስት መቶ ስድሳ ስድስተኛ። ይህቺቀን ዕለተ ሰግር ትባላለች። መረማመጃ ማለት ነው። አንድ ቀን ታስተላልፋለች። እንግዲህ እነዚህን ሁለቱን ቀኖች ተከትሎየሚመጣው ቀን የዘመን መጀመሪያ፥ የዘመን ክብ መነሻና መድረሻ ተብሎ ርእሰ ዐውደ ዓመት ተብሎ በግእዙ ይጠራል። እነዚህ ቀኖችበኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ተጠቃለው አንድ ጊዜ የሚገኙ ናቸው።

 

የኢትዮጵያ ቍጥር መሠረቱ መጽሐፈ ሔኖክ የሚባለው ነው። መጽሐፈ ሔኖክ በ፲፱፥ ፳፥ ፳፩ እና ፳፪ ምዕራፎች የሚሰጠን የፀሐይን፥የጨረቃን ጉዞ መነሻ አድርጎ የወሮችን፥ የዕለታትን፥ የዓመታትን መነሻ፥ መድረሻ፥ መዘዋወሪያ ብተታቸውን፥ ጥንታቸውን ነውየሚያሳየው። ስለዚህም በሔኖክ ቍጥር የወር ቀኖች ቍጥር ሠላሳ ናቸው። በሦስት በሦስት ወር ግን አንድ ቀን ትከተላቸዋለች። እናዓመቱ ለአራት ይከፈላል። በዘጠና አንድ በዘጠና አንድ ቀን። ጠቅላላው ይሄ ድምር ሦስት መቶ ስድሳ ስድስት ቀን ይመጣል። ይህካለቀ በኋላ አንዲት ቀን ለዘመን ማገጣጠሚያ ዕለተ ምርያ የምትባለው ትመጣለች። እንግዲህ በኢትዮጵያውያን ቍጥር ወሩ ከሠላሳአያንስም፤ ከሠላሳ አይተርፍም። ለዓመቱም ሦስት መቶ ስድሳ ዐምስት ቀን መደበኛው አቆጣጠር ነው ማለት ነው። ይህ ነገርበአውሮፓውያን ቍጥርም አለ። ግን እነሱ ከዓመት ወሮች ሰባቱን ሠላሳ አንድ ሠላሳ አንድ አድርገው አራቱን ደግሞ ሠላሳ ሠላሳአድርገው አንዷን ወር ሦስቱን ዓመት ሃያ ስምንት፥ በአራተኛው ዓመት ሃያ ዘጠኝአድርገው ያጣጧታል።

 

እንግዲህ የአቀማመጡ ለውጥ ካልሆነ በስተቀር በቍጥር አካሄድ ዞሮ ዞሮ የዓመት ቀኖች ሦስት መቶ ስድሳ ዐምስት ወይም ሦስት መቶስድሳ ስድስት በመሆን አንድ ሆነዋል ማለት ነው። ልዩነቱ ግን የአቀማመጥ ለውጥ ነው። በኢትዮጵያ አቈጣጠር ግን ጠቅላላውን ፲፪ወሮች መደባቸው ሠላሳ ብቻ ነው። እነዚያ በሔኖክ መጽሐፍ በጣልቃ ገብነት የነበሩት አራት ቀኖች ተጠቅለው ጳጉሜን በሚባልበዓመቱ መጨረሻ ላይ ተገኝተዋል። ዐምስተኛዪቱ ቀንም ከእነሱ ጋር ተገኝታለች። ይህም ለቍጥር ተራ ቅምር መቅናት የተደረገ እንጂቀኑን የሚለውጥ ምንም ነገር የለበትም። እና ከእነዚህ ቀኖች በኋላ የምናገኘው ቀን ርእሰ ዐውደ ዓመት ይባላል። ይህንን በዓል ከአዳምጀምሮ እስከ ኖኅ ድረስ የነበሩ ዐሥሩም አበው በዐሥሩ ትውልድ እስከ ማየ አይኅ ድረስ ሲያከብሩት እንደ ቆዩና ኋላም የኖኅ ልጆችከአባታቸው ተቀብለው ሲያከብሩት እንደ ነበረ ኩፋሌ የተባለው መጽሐፍ በምዕራፍ ፯ ያስረዳናል። እንግዲህ ኢትዮጵያ ይህንን ቀንየወረሰችው ከአበው ነው የምንለው በዚህ ምክንያት ነው።

 

  

  የዘመን ቁጥር ልዩነት

ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ የዘመን አቆጣጠር መለያየትን መነሻ እንዲህ በማለት ያብራራሉ፤ «ክብ የሆነ ነገር ሲከብ ከየትኛውም ቦታ መጀመር ይቻላል፤ የዘመን አቆጣጠር /ዓውደ ዓመትም/ ይኸው ነው፡፡ ዋናው ነገር አንድ ታላቅ ታሪካዊ ድርጊት ፈልጎ እርሱን መነሻ ማድረግ አንድ ታላቅ ታሪካዊ ድርጊት ፈልጎ እርሱን መነሻ ማድረግ ነው፤ የዘመን አቆጣጠሮቹም ልዩነት መንስኤው ይኸው ነው» ይላሉ፡፡ ባሕረ ሐሳብ፣ ጌታቸው ኃይሌ፣ ገጽ.65/ ለምሳሌነትም ሮማውያን የሮም ከተማ የተቆረቆረችበትን ጊዜ መነሻ ማድረጋቸውን/ በኋላም ታላቁ እስክንድር የነገሠበት ዘመን የዘመን ቆጠራ መነሻ ሆነው እንደነበር ይጠቅሳሉ፡፡ መሐመድና ተከታዮች ከመካ ወደ መዲና ያደረጉትን ስደት መነሻ የሚያደርገው ኢስላማዊ  የዘመን አቆጣጠርም ሌላው ተጠቃሽ ነው፡፡

 

የአይሁድን አቆጣጠር ትተን ከላይ ያየናቸው ሁለቱ የዘመን አቆጣጠሮች /የምዕራባውያኑ የጁልየስ ጎርጎርዮሳዊ አቆጣጠርና የኢትዮጵያና የግብጽ አቆጣጠር/ ሁለቱም ዘመንን የሚቆጥሩት ከክርስቶስ ልደት መነሻ አድርገው ነው፡፡ ይሁን እንጂ እኛ ዛሬ 2006ዓ.ም ነው ስንል እነርሱ ደግሞ 2014 ዓ.ም ነው ይላሉ፡፡ በመካከሉ የ7/8 ዓመታት ልዩነት አለ፡፡ እንግዲህ ጥያቄው ትክክለኛው የትኛው ነው? የሚለው ነው፡፡

 

ጉዳዩ መጻሕፍትን ሊያጽፍ የሚችልና በእርግጥም የተጻፉበት ቢሆንም ለማሳያ ያክል ሁለት ነገሮች እንመልከት፤

  1. አሁን ባለው የምዕራባውያን አቆጣጠር ሄሮድስ የሞተው 4 ዓመት ቅ.ል.ክ ነው፡፡ ሄሮድስ የሞተው ጌታ ተወልዶ በስደት ሦስት ዓመት ያህል በግብጽ ከቆየ በኋላ ነው፡፡ ይህ ማለት በእርሱ አቆጣጠር ጌታ የተወለደው በ7 ዓመት ቅ.ል.ክ ነው ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ጌታ በትክክል በተወለደበት በአንድ ዓ.ም እነርሱ ጌታ ሰባት ዓመት ሆኖታል ይላሉ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ትክክለኛውን ቁጥር ለማግኘት አሁን ካላቸው ቁጥር ላይ ሰባት ዓመት መቀነስ አለባቸው፡፡
  1. ፍላቪየስ ጆሴፈስ የተባለው የአይሁድን ታሪክ የጻፈው ሊቅ እንደመሰከረው ጌታ የተወለደበት ዓመት ነው ተብሎ በወንጌል ላይ የተጻፈው የቆጠራ ዓመት /ሕዝቡ ሁሉ የተቆጠረበትን ዘመን /ሉቃ.2.1/ በጎርጎሪያን ዘመን አቆጣጠር «7 ዓመተ እግዚአ /A.D/ ላይ ነው፡፡» በማለት መረጃ ትቶልናል ይህ ማለት ደግሞ ከምዕራባውያኑ ዘመን አቆጣጠር ላይ 7 ዓመቶች የግድ መቀነስ አለበት ማለት ነው፡፡ ያ ሲደረግ ደግሞ የኛን ዘመን አቆጣጠር ያመጣል፡፡

የዘመን መለወጫ ቀን ልዩነት

ሁለተኛው ጉዳይ የዘመን መለወጫ ወርና ዕለት ልዩነት ነው፡፡ እኛ መስከረም  1 አዲስ ዓመት ስንጀምር እነርሱ በ January 1 / በእኛ ታኅሣሥ 23/ አዲስ ዓመት ይጀምራሉ፡፡ ይህ ከየት የመጣ ልዩነት ነው?

የእኛ እና የግብጻውያን አቆጣጠር እዚህ ጉዳይ ላይ ከአይሁድ አቆጣጠር ጋር ይስማማል፡፡ በአይሁድ አቆጣጠር የመጀመሪያው ወር ኒሳን የሚባለው /በእኛ መጋቢት/ ሚያዝያ/ ነው፡፡

«ይህ ወር የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ይሁናችሁ፣ በዚህም ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የአንድ ዓመት ተባዕት ላይ ወስደው ይረዱ፡፡ . . .»/ዘፀ.12.1-14/ ተብሎ የተሰጣቸውን የፋሲካ በዓል የሚያከብሩት በዚህ ወር ነው፡፡

ይሁን እንጂ አዲስ የዓመት በዓል አድርገው የሚያከብሩት «የሰባተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን ዕረፍት ይሁናችሁ፡፡ በዚሁ በመለከት ድምጽ የሚከበር የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ መስዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርቡ እንጂ የተለመደ ተግባራችሁን አታከናውኑበት» /ዘሌ.13.23-25/ ተብሎ የተሰጣቸው የሮሽ ሆሻና፣/የመለከት በዓል ወይም በዓለ መጥቅዕ/ ተብሎ የሚጠራው በዓል ነው፡፡ ይህም ማለት አዲስ ዓመት የሚያከብሩት በሰባተኛው ወር በኢታኒም ወር /በእኛ መስከረም ጥቅምት/ ነው፡፡

በቤተክርስቲያናችንም ትምህርት ዓለም የተፈጠረው መጋቢት 29 ቀን ነው፡፡ መስከረም ደግሞ ከመጋቢት ጀምሮ ሲቆጠር ሰባተኛው ወር ነው፡፡ ይህም ከአይሁድ ዘመን አቆጣጠር ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡

አይሁድስ ቢሆኑ የመጀመሪያው ወር እያለ አዲስ ዓመትን ለምን በሰባተኛው ወር ያከብራሉ ለሚለው ጥያቄ ሁለት ዓይነት ምላሾች /ምክንያቶች/ ይሰጣሉ፡፡ የመጀመሪያው ምክንያት «ሰባተኛው ወር ኖኅ ከመርከብ የወጣበት ወር በመሆኑ ይህ የአዲስ ዓመት መጀመሪያ ተደርጎ መከበር በመጀመሩ ነው» የሚል ነው፡፡ በዘመን መለወጫ ዕለት ልጃገረዶች አበባ እና ለምለም ሣር መያዛቸው ርግቢቱ ለኖኅ ካመጣችው ለምለም ወይራ /ቄጠማ/ ጋር ተያይዞ የተጀመረ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

ሁለተኛው ደግሞ መስከረም የቀንና የዕለቱ ርዝመት እኩል የሚሆኑበት ወር በመሆኑ ነው የሚል ነው፡፡ የመስከረም 1 ቀን ስንክሳር «የተባረከ የመስከረም ወር የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመታት ወሮች ርእስ ነው፤ የቀኑ ሰዓትም ከሌሊቱ ሰዓት የተስተካከለ ዐሥራ ሁለት ነው» ይላል፡፡

እዚህ ላይ ማስተዋል የሚገባው ሌላው ጉዳይ በቤተክርስቲያናችን ትምህርት እመቤታችን ጌታን የጸነሰችው መጋቢት 29 ቀን ነው፡፡ ይህም ቅዱስ ጳዉሎስ ፣የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት ተወለደ» /ገላ.4.4/ እንዳለው የ5500 ዘመኑ ፍጻሜ /ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ/ ነው፡፡

ጽንሰትን መጋቢት 29 ካልን በኋላ ልደትን ታህሣሥ 29 ቀን እናከብራለን፡፡ ከመጋቢት 29 እስከ ታህሣሥ 29 ድረስ 9 ወር ከ5 ቀን ነው፡፡ /ጳጉሜን ጨምሮ/፡፡ ጳጉሜ 6 በምትሆንበት ጊዜ ደግሞ ታህሣሥ 28 ቀን ልደት ስለሚከበር አሁንም በመሐሉ ያለው ጊዜ 9 ወር ከአምስት ቀን ይሆናል፡፡

ማጠቃለያ

በመጨረሻም የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ፍፁም መፅሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያለው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የሚቆጥር መሆኑን እንጂ እንደ ዘመኑ ነገስታት ፍላጎት በታሪክ ክስተትን መሰረት ያደረገ አለመሆኑን ከተረዳን ይህንን ሃሳባችንን የሚያጠናክርልን የሳምንታንት እና የወራት ስያሜዎቻችንን እንዲሁም የልሎቹ የቀን አቆጣጠር ምንጭን ከ እዚህ በታች ባሉት ሰንጠረዦች እንመልከት።ለምሳሌ እነኚህ የሳምንታንት ልዩነቶች አውሮፓውያን ከጥንት ከነበረ አምልኮት ጋር የትዛመደ ሲሆን የእኛ ግን እግዚአብሔር አለምን መፍጠር ከጀመረ የመጀመርያ ቀን ስንል እሁድ ማለታችንን ሁለተኛ ቀን ስንል ሰኑይ (ሰኞ) ማለታችንን ወዘተ እንረዳለን።

ማኅበረ ቅዱሳን አውደ-ርዕይ 2000 ዓም

ማኅበረ ቅዱሳን አውደ-ርዕይ 2000 ዓም

ማኅበረ ቅዱሳን አውደ-ርዕይ 2000 ዓም

አሮጌው ዘመን 2006 ዓም ተጠናቆ አዲሱን 2007 ዓም ልንቀበል ሰዓታት ቀርተውናል። የሮማ ካቶሊክ ፓፓ ቤኔዲክት 16ኛ ”የናዝሬቱ እየሱስ” በተሰኘ መፅሐፋቸው አሁን አውሮፓውያን የሚጠቀሙበት የክርስቶስ የልደት ዘመን ትክክለኛ እንዳልሆነ ሲገልጡ እንዲህ ብለዋል-“The calculation of the beginning of our calendar—based on the birth of Jesus—was made by Dionysius Exiguus, who made a mistake in his calculations by several years,”  ”ከጅምሩ የቀን አቆጣጠራችን ክርስቶስን ተወለደ ያለበት ዘመን መሰረት (በእክስጉሥ የተቀመረው) የብዙ አመታት የስሌት ስህተት አለው” ብለዋል።

(http://www.charismanews.com/world/34714-pope-says-jesus-birth-date-is-wrong)

ይህ ከአንድሚልዮን ኮፒ በላይ እንደተሸጠ የተነገረው መፅሐፍ ላይ ፓፓው ይህንን ይበሉ እንጂ ስህተቱን

 ለማረም እና ወደ ትክክለኛው ወደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ለመምጣት የደፈረ እስካሁን አልታየም።ወደፊት

 ግን ይጠበቃል። 

 

ጉዳያችን ጳጉሜን 2/2006 ዓም

ምንጮች  -

1/ መስከረም 2004 አዲስ ጉዳይ መፅሄት እትም
2/ አለቃ አያሌው ታምሩ ትምህርት http://www.aleqayalewtamiru.org/new_year_2003.html

3/ ማኅበረ ቅዱሳን ድህረገፅ http://www.eotc-mkidusan.org/site/-mainmenu-24/–mainmenu-26/30—-

 4/ደጀ ሰላም መስከረም 11/ 2011 http://www.dejeselam.org/2011/09/blog-post_11.html#more

  5/ማኅበረ ቅዱሳን 2000 ዓም አውደ ርዕይ

 

 

Source:: gudayachn

↧

የ 2007ዓ/ም አዲሰ ዓመት የመልካም ምኞት መግለጫ (ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉእላዊነት )

$
0
0

Arena-Tigray-logoዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉእላዊነት የ 2006 ዓ/ም ዘመነ ማርቆስ ተገባዶ ወደ 2007 ዓ/ም ዘመነ ሉቃስ እንካን በሰላም አሸጋገረን በማለት አዲሱ ዘመን የሰላም ‘የደስታና የብልፅግና ኣመት እንዲሆንል በማለት ለመላ የኢትዮåያ ህዝቦች የመልካም ምኞት መግለጫውን ያቀርባል ፡፡

ኣዲሱ ኣመት የሰላም ‘የደስታና የብልፅግና ኣመት እንዲሆንልን ማደረግ በኛው ኢትዮåያውያን ዜጎች እጅ ነው፡፡ አዲሱ ዓመት የሰላም ፣ የደስታና የብልፅግና ዓመት እንዲሆንልን መመኘት የመጀመርያው እርምጃ ቢሆንም ምኞቱ ክውን ሆኖ ለማየት ግን በግልም ሆነ በቡድን ከእያንዳንዳችን ኢትዮጵያዊያን ዜጎች የሚጠበቅ ሃገራዊ ግዴታ አለብን፣፣ ስለሆነም መጪው ኣዲስ ኣመት የሰላም ‘የደስታና የብልፅግና ኣመት ይሆንልን ዘንድ ከመመኘት ወደ እውነታ ለመብቃት ከገ¸ው ፓርቲ ‘ከመንግስትና’ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲሁም ከሲቪል ማሕበራትና ከእያንዳንዱ ዜጋ የሚጠበቀው ሚና ወሳኝነት ኣለው፡፡
የፍላጎት’የሃሳብና የእምነት ልዩነት መኖር የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ባህሪ ሆኖ ለየተለያየ ፖሊሲ የሚያራምዱ ፓርቲዎችን መፈጠር ምክንያት ሆኖ ብሎም የህዝቦች የሰላም ፍላጎትና የህዝቦች ፍላጎት የበላይነት መከበር ሲባል የሰላማዊ ‘ሕጋዊና ዴሞክራሲያዊ ውድድር መኖር የግድ ማለቱ፣ ይህ ባልተቻለበት ወይም የሚቻል እያለ ባልተጠቀምንበት ደግሞ ለ የእርስ በርስ ጦርነቶች ማቆጥቆጥ ምክንያት እንደሚሆንና ይህን ለሃገር ሰብኣዊና ቁሳዊ ሃብት ውድመት ዓይነተኛ ምክንያት እንደሆነ ከታሪክ የምንማረው ብቻ ሳይሆን በህይወታችን ያየነው እውነታ ነው፡፡

ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉእላዊነት ፓርቲ /ዓረና / መጪው አዲሱ ዓመተ 2007 የሰላም ፣ የደስታና የብልፅግና ዓመት እንዲሆንልን የሚያግዙት የ 3 ዓመት የሰላማዊ ውድድር ስትራተጂ ረቂቅ ሰነድ በማፅደቅና የ2007 ዓ/ም ምርጫን ማእከል ያደረግ የተግባር እቅድ ነድፎ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን ለመላ የኢትዮጵያ ህዝብና ለነፃነትና እኩልነት ወዳጁ የትግራይ ክልል ህዝብ ሲያበስር ደስታ ይሰማዋል ፡፡

እናም ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት ስንሸጋገር በአሮጌው አመት ያየናቸውና ያጋጠሙን ችግሮች ወደ አዲሱ አመት እንዳይሸጋገሩና አዲሱ ዐመት የሰላም ፣የደስታና የብልፅግና አመት እንዳይሆን የሚያውኩ መልከ ብዙ ችግሮቻችን ይወገዱ ዘንድ በግልም ሆነ በቡድን የዜግነት ሃላፊነታችን መወጣት የገድ የሚሉን አሉ፡፡
1. መላው ኢትዮጵያዊ ዜጎች ፣ ገዥው ፓርቲና ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ችግር ያለ ልዩነት መላው ኢትዮጵያዊያንን ያቆሰለ እንጂ አንዱን ሸልሞ ሌላው የጎዳ ባለ መሆኑና የችግሩ መፍትሄም በሁሉም ኢትዮጵያዊያን የጋራ አsምና የጋራ መስዋእትነት ብቻ መሆኑን መገንዘብና ፣ እንዲሁም የአገራችን እጣ ፈንታ ለማስዋብና የሃገራችን ፖለቲካ ለማዘመን ከማናቸውም መልኩ ከዘር ፖለቲካ መራቅ የሚጠበቅብን መሆኑን፣

2. ሰላማዊ የትግል አማራጭን የመረጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዘመቻ ማሳደድ ፣የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን በግድ አባልነታቸው እንዲሰርዙ ማስገደድ/ ለምሳሌ ፣በራያ ፣ አፅቢ ፣ ወልቃይት፣ አኩሱም / ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከህዝብ የሚገናኙበት እንደ ህዝባዊ ፖለቲካዊ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይደረግ ማፈን / መቐለ/፣ ከሁሉም ጥፋች የከፋ ጥፋትና የሰላም ጠንቅ በመሆኑ በተለይ በተለይ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች የሃገር እጣ ፈንታ ከፖለቲካ ፍላጎት እንደሚቀድም ተገንዝበው የበኩላቸውን ሃገራዊ ሃላፊነት እንዲወጡ ፣

3. ሰብአዊ መብትና ነፃነት በገዛ ትግልና ጥረት የምታመጣው እንጂ በገፀ በረከት የሚሰጥ ፀጋ ባለመሆኑ እያንዳንዱ ዜጋ የገዛ ራሱ መብትና ነፃነት ለማስከበር የሚያሳየው ድፍረትና ቆራጥ አsም መጪው አዲሱ አመት የሳላም ፣የደስታና የብልፅግና ሆኖ እነዲከወን የማድረግ ወሳኝ ሃላፊነት ያለው መሆንና ይህንኑ ሃላፊነቱ ለፖለቲካ ፓርቲዎች በመተው በገዛ መብቱ ባይተዋር ለመሆን መፍቀድ እንደማይጋበው፣ፍርሃት በማናቸውም መስፈርት ሰብአዊ መብትና ነፃነት አሳልፎ ተቀባይነት ሊኖረው የማይችል መሆኑንና እንዲያውም መፍራት ያስፈልጋል ከተባለ ከሁሉም ባላይ መፍራት ያለብን እየፈሩ መኖር መሆኑን መገንዘብ ፍርሃትን በማስወገድ አዲሱ ዓመት የሰላም ፣ የደስታና የብልፅግና ዓመት ማድረግ የሚጠበቅብን መሆኑን፣

4. በፖለቲካ ፓርቲዎች የፖሊሲ ልዩነት እንዳለ ሆኖ በሃገራችን የሰላም ፣የደስታና የብልፅግናና ራኢ ሊተገበር የሚቻለው የኢትዮጵያ ህዝቦች እኩልነት በመቀበልና በመተግበር ፣ብሄርነትና ብሄረሰብነት እንዲሁም የተለያዩ ባህላዊና ማንነታዊ ማሕበረሰብነት ተፈጥሮአዊ ፀጋና የሃገሪቱ ውበት አድርጎ መቀበልና የሁሉንም ፍላጎት ያካተተ የፖሊሲ አቅጣጫ ብቻ የሃገራችን የሰላምና የብልፅግና መነሻና መድረሻ አድርጎ መቀበልና መተግበር አስፈላጊ መሆኑን ፣

መገንዘብና ለጉዳዩ ቁርጠኛ አsም መሳየት እንደሚጠበቅብንና በጋራ እንድንቆም ዓረና ጥሪውን እንሆ አዲሱ ዓመት የሰላም ፣ የደስታና የብልፅግና ዓመት እንዲሆንልን ምኞቱን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ያቀርባል፡፡

ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉእላዊነት /ዓረና /
ጳጉሜን 2/2006 ዓ/ም
መቐለ

↧

በአዲስ አበባ በየሰፈሩ ዲሽ የሚገጥሙ ወጣቶች “ኢሳትን እየቀጠላችሁ ነው በሚል ወከባ ይደርስባናል”አሉ

$
0
0

Dish addis ababaአዲስ አበባ ውስጥ በየ ቤቱ እየዞሩ ዲሽ የሚገጥሙ ወጣቶች ‹‹ኢሳትን እየቀጠላችሁ ነው›› በሚል ወከባ እንደሚደርስባቸው ገለጹ፡፡ ወጣቶቹ ከኢሳት ውጭ ያሉ ጣቢያዎች የሚተላለፉበት ዲሽ በሚገጥሙበት ወቅትም ‹‹ኢሳትን እየቀጠላችሁ ነው፡፡ ህዝቡ ኢሳትን እንዲያይ ታደርጋላችሁ›› በሚል በደህንነቶች ወከባ እንደሚደርስባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ ከወራት በፊት መርካቶ አካባቢ ዲሽ የሚገጥሙ ወጣቶች ‹‹ኢሳትን ለህዝቡ እያሳያችሁ ነው›› ተብለው በፖሊስ ተይዘው እንደነበር ተጠቁሟል፡፡ ያም ሆኖ ግን በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ኢሳትን እንደሚገጥሙ የሚያሳዩ የዲሽ ማስታወቂያዎች ይታያሉ፡፡ ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ

↧
↧

Hiber Radio: በአንዋር መስጊድ ያለ ሀባሽ ፈቃድ ሃይማኖታዊ ትምህርት መስጠት የሚከለክል መመሪያ ወጣ፤ በጅጅጋ የክልሉ ታጣቂዎች ኦብነግን ተቀላቀሉ

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ጳጉሜ 2 ቀን 2006 ፕሮግራም

እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!

<...>

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ አሮጌውን በአዲሱ ዓመት ዋዜማ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት እአ የሌሎች አዲስ ዓመት አከባበር (ልዩ ዘገባ)

ጭንቀትና መዘዙ ብሎም የማህበረሰባችን ምልከታ ሰናይት አድማሱ የስነ ልቦና ባለሙያ ጭንቀት ስለሚያስከትለው የጤና ቀውስ(ስለ > ካደረግነው ውይይት ሙሉውን ያዳምጡት)(የመጨረሻ ክፍል)

>

ጋዜጠኛ ሔኖክ ዓለማየሁ በሚኒሶታ ስለተከበረው የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት ከሰጠን ማብራሪያ

በቬጋስ የኢትዮጵያዊነት ቀን በመጪው ወር ይከበራል በይድነቃቸው ተሰማና በጋዜጠኛ ሰለሞን ተሰማ ስም ውድድሮች ተዘጋጅተዋል(ክፍል ሶስት ልዩ ዘገባ)

ዜናዎቻችን

– ጅጅጋ ላይ የክልሉን ፕሬዝዳንትለማንሳት የሚደረገው እኢቅስቃሴ ውጥረት አስከተለ

– የክልሉ ልዩ ሀይል ፖሊሶች የኦብነግን ታጣቂዎች ተቀላቀሉ

– በአገር ቤት የኑሮ ውድነቱ የበዓሉን ገበያ አቀዝቅዞታል

– በአንዋር መስጊድ ያለ ሀባሽ ፈቃድ ሃይማኖታዊ ትምህርት መስጠት የሚከለክል መመሪያ ወጣ

– በዴንቨር የሚገኙ ኢትዮጵያን ድምጻዊ ሕብስት ጥሩነህን በአገዛዙ ደጋፊዎች መድረክ እንዳትገኝ ጥሪ አስተላለፉ

– ከሊቢያ ትሪፖሊ አየር ማረፊአ የጠፉት 11 አውሮፕላኖች ስጋት ደቀኑ

– የኢትዮጵያው ዋሊያ በአልጀሪያው የበረሃ ተኩላዎች ተሸነፈ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

↧

በብሶት የታፈነው ህዝብ አመፅ ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት ወያኔ አድሮበታል።

$
0
0

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) 2007 ለለውጥ !

በሳሞራ የኑስ እና በጌታቸው አሰፋ የሚመራ ልዩ የኮማንዶ እና የደህንነት ሃይል አዲስ አበባ ባህር ዳር እና ድሬዳዋን መቆጣጠር የሚችልበትን ስልት እየነደፈ ነው።

- በሳሞራ የኑስ የሚመራው የኮማንዶ ጦር ህገመንግስታዊ ጥያቄ ማንሳቱ ታማኝነቱ ጥርጣሪ ውስጥ ገብቷል
- መጪው ጊዜ በመላው ኢትዮጵያ የአንድነት እና የዲሞክራሲ ሃይሎች ገነው ይወጣሉ።
- ዲያስፖራው ከምንም ጊዜ በበለጠ ለወያኔ የጎን ውጋትና ራስ ምታት ሆኗል።
- ተቃዋሚ ሃይሎች በአሁን ወቅት ከባድ ጥንካሬ እና የትግል ስልት ሊኖራቸው ይገባል።ጊዜው ነው።

unityምንሊክ ሳልሳዊ ፦ በብሶት የታፈነው ኢትዮጵያዊ በቀጣዮቹ ጊዜያት ከፍተኛ አመጽ ያስነሳል በሚል ስጋት ያደረበት እና አመፁ ከመንግስት ሃይሎች ቁጥትር ውጪ ይሆናል በሚል ከፍተኛ ውጥረት በስጋት የተደባለቀበት የወያኒው ጁንታ በከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ ስብስባ የተቀመጠ ሲሆን ካለፉት ሳምንታት ተከታታይ ስብሰባዎች በተገኙ የውይይት ፍሬ ሃሳቦች መሰረት በሳሞራ የኑስ እና በጌታቸው አሰፋ የሚመራ ልዩ የኮማንዶ እና የደህንነት ሃይል አዲስ አበባ ባህር ዳር እና ድሬዳዋን መቆጣጠር የሚችልበትን ስልት እየነደፈ ነው።

በአዲስ አበባ የከፍተኛ ለሕወሓት ባለስልጣናት ቅርብ የሆኑት ምንጮች እንደተናገሩት የሚነደፈው ስልት የሕወሓት ባለስልጣናት እምነት ያልጣሉባቸውን የፖሊስ እና ወታደራዊ ሃይሎችን ጨምሮ ህዝቡን መቆጣጠር በሚቻልበት ሁኒታ ልላ ያተኮረ ሲሆን የፖሊስ እና ወታደሩ ክፍል በባለስልጣናት ላይ እርምጃ ይወስዳል በሚል ከፍተኛ ስጋትም እንዳደረባቸው ታውቋል ። የትግራይ ተወላጆች የሆኑትም ፊታቸውን እንዳዞሩባቸው የጠቆሙት ምንጮቹ በከፍተኛ ገንዘብ ከደቡብ ሱዳን ምስራቃዊ ክፍል የሚገኙ እና በስደተኝነት በኢትዮጵያ የኖሩ አማርኛ ቋንቋን የሚናገሩና የሚሞክሩ እንዲሁም ከኑባ ደማዚን ቅጥረኞችን በመግዛት ከቢንሻንጉል ጉምዝ በማምጣት እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ የቀድሞ ታጋዮችን በፖሊስ መልክ በመመልመል በጥሩ ክፍያ በአዲስ አበባ ባህር ዳር እና ድሬዳዋ ላይ ለማስፈር መታቀዱን ተጠቁሟል። በተለይ በአዲስ አበባ እና በባህር ዳር ይመደባሉ የተባሉ እናበተለያየ ጊዜ በሳሞራ የኑስ የተመረቁ እና በስሩ የሚታዘዙ ኮማንዶዎች እንዲዘጋጁ የተነገራቸው ቢሆንም ባለፈው ሳምንት በነበርቸው ስብሰባ ላይ ህገመንግስታዊ ጥያቂዎችን እንዳነሱ ከታወቀ በኋላ ታማኝነቱ ጥርጣሬ ውስጥ በመግባቱ የወያኒ ስጋቶች ሰፍተው እና ተወጥረው መታየታቸውን ምንጮቹ ተናግረዋል።

የሕዝብ አመጽ ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ይሆናል የሚሉት ባለስልጣናት ወታደሩ ክፍል እና የፖሊስ ሰርዊቱ ስለ ተቃዋሚዎች በጎ አመለካከት እንዳይኖረው ከፍተኛ ፕሮፓጋንዳ በየ ክፍሉ እየረጩ ሲሆን የፖለኢስ እና የጦር ሰራዊቱ ግን ጥያቂዎችን ከማንሳቱም በላይ ከካድሬዎች ጋር ፊት ለፊት እስከመሟገት መድረሱ ከቀረበልቸው ሪፖርት የተረዱት ወያኔዎች እንዲሁን ይህን ሰሞን በተለያየ መልኩ አብዮታዊ ዲሞክራሲ በልማት ስም ሽፋን በማድረግ በስልተና መልክ ሲሰጡ የገጠማችው ተቃውሞ ካድሬዎች ፖሊሰና ሰርዊቱ ሕገመንግስታዊ ጥያቄ እንዲያነሳ ማድረጉን የሚያስገነዝብ ሪፖርት በስፋት እንደቀረበ እና ይህንን ሪፖርት ተገትሎ የህዝብ ብሶት ይፈነዳል የሚል ስጋት ወያኒን እያሯሯጠው እንደሆነ ታውቋል።

ምንጮቹ አያይዘውም መጪው ጊዜ በመላው ኢትዮጵያ የአንድነት እና የዲሞክራሲ ሃይሎች ገነው ይወጣሉ። የሚልው የወያኒ ዋና የስብሰባ ነጥብ ገነው እንዳይወጡ በተለይይ የማምከን ስራ ለመጠቀም ቢያስብም ካሁን በፊት የተጠቀመብት ስልት እንዳላዋጣው እና ተቃዋሚዎች ገነው እንዳይወጡ የሚያደርግ የመጨረሻ እርምጃ ለመውስድ የሚያስችል ጥናት በአቶ በርክት ስምኦን በኩል በአስቸኳያ እንዲጠና ሲል ዲያስፖራው ከምንም ጊዜ በበለጠ ለወያኔ የጎን ውጋትና ራስ ምታት እንደሆነና የሀገር ውስጥ ተቃዋሚዎችን በማደረጀት ረገድ ትልቁን ሚና እየትጫወተ እንደሆነ መወሳቱን እና ይህንን ወያኔ መቆጣጠር እንዳቃተው እንደቀጠለ እንዳለ ተነግሯል። ምንጮቹ አያይዘውም ተቃዋሚ ሃይሎች በአሁን ወቅት ከባድ ጥንካሬ እና የትግል ስልት ሊኖራቸው ይገባል ፤ጊዜው ነው። ሲሉ መረጃውን አድርሰውናል።

በሃገር ውስጥ እና በውጪው ህገር የምንገኝ ተቃዋሚዎች ወያኒ በገባበት ስጋት እና ውጥረት ውስጥ ራሱን በራሱ እንዲቀብር ና በኢትዮጵያ ለአንዲና ለመጨረሻ ጊዜ አምባገነንነት እንዲያከትም የዜግነት ድርሻችንን በጋራ የምንወጣብት ጊዜ አሁን በመሆኑ በጋራ ልዩነቶችን በማቻቻል አንዱ አንዱን ሳይወንጅል እና ሳይፈርጅ በተባበረ ክንድ በተገኘው የትግል ስልት ልይ ሁሉ በተገኘው ድርጅት ጋር ሁሉ በመሳተፍ ለነጻነትችን የምንችለውን አስታውጾ ሁሉ እንድናደርግ ይጠበቅብናል። ነጻነት በእጃችን ነው !!!‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

↧

በፕሬሱ ላይ የተመዘዘው ሰይፍ

$
0
0

ነገረ ኢትዮጵያ
re4መረጃ የማግኘት ነጻነት ከዋነኞቹ የዴሞክራሲ መገለጫዎች ወይም እሴቶች መካከል ይጠቀሳል፡፡ መረጃ የማግኘት ነጻነቱ የተከበረለት ህዝብ በሀገሩ የስልጣን መንበሩ ላይ የተቀመጠውን አስተዳደር (መንግስት) የመቆጣጠር ኃይሉ ከፍተኛ ነው፡፡ ሙስና፣ ብልሹ አስተዳደርና ሌሎችን ንቅዘቶች በማጋለጥ የመንግስትን ተጠያቂነት በማስፈን ሂደት ውስጥ ህዝብ ንቁ ተሳታፊ ይሆን ዘንድ መረጃ የማግኘት ነጻነቱን ሊጎናጸፍ ይገባዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ መረጃ የሚያደርሱት ሚዲያዎች በስፋት መኖር የግድ ነው፡፡ ለዚህም ነው በዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ውስጥ የሚዲያ (ፕሬስ) ሚና እንዲጎላ የሚደረገው፡፡

በተቃራኒው በአምባገነን ስርዓት ውስጥ ገዥዎች የሚዲያ (ፕሬስ) ነጻነትን በማፈን ህዝብ መረጃ እንዳያገኝ የተለያዩ እርምጃዎችን ሲወስዱ ይስተዋላል፡፡ አምባገነኖች ስርዓቱን የሚተቹ የፕሬስ ውጤቶችን ይዘጋሉ፣ ጋዜጠኞችን ያስራሉ፣ ያሳድዳሉ፣ አለፍ ሲልም ይገድላሉ፤ ያስገድላሉ፡፡ አምባገነኖች ለይስሙላ የሚዲያ ነጻነት መረጋገጡን የሚያሳዩ ህጎችን በማውጣት በውጭ ሆኖ ለሚመለከታቸው አካል ዴሞክራት በመምሰል በውስጥ ተግባራቸው ግን ካወጧቸው ህጎች ፍጹም ተቃራኒ በመሆን የአፈና ስራ ያከናውናሉ፡፡ የግል ፕሬሶችን በቀጥታም ሆነ በእጃዙር ጨምድዶ በመያዝ፣ ፕሬሶች ህጉን ተከትለው በፈቃዳቸው ያሻቸውን እንዳይሰሩ ያደርጋሉ፡፡ እንዲህ አይነቶቹ የአምባገነኖች ተግባራት በበርካታ ሀገራት ተመሳሳይነት ያላቸው ናቸው፡፡
ለአብነትም ለረጂም አመታት ቻይናን እየገዛ ያለው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ በሀገሩ የሚንቀሳቀሱ የሚዲያ ውጤቶች ላይ ባሻው ጊዜ ሁሉ ህገ-ወጥ እርምጃዎችን በመውሰድ ይታወቃል፡፡ ይኸው የቻይና ገዥ በ2012 ብቻ ከ16 በላይ ዌብሳይቶችንና ብሎጎችን ከርችሟል፡፡ ይህ አምባገነን ስርዓት በምድረ ቻይና የመረጃ መረብ እቀባ በማድረጉ ምክንያት፣ ሀገሪቱ በተለያየ ጊዜ ከታዋቂዎቹ ዓለም አቀፍ የመረጃ ምንጮች ጎግልና ያሁ ድረ-ገጾች ጋር አተካራ ውስጥ ስትገባም ይታያል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ቻይና በሀገሯ የሚታተሙ ጋዜጦችንና መጽሔቶችንም በመክሰስና በመዝጋት ስሟ በአሉታ ይነሳል፡፡

ቻይና ዲንግ ዲያን የተሰኘውን ከፍተኛ ተነባቢ ሳምንታዊ ጋዜጣ እ.ኤ.አ በ2006 መዝጋቷንም እዚህ ጋር እንደምሳሌ ማንሳት ይቻላል፡፡ የቻይና ገዥዎች ጋዜጣውን የዘጉት በሀገሪቱ ያለውን የማህበራዊ ቀውስ፣ በሙስና የተጨማለቀውን አስተዳደር፣ በከተሞች ያለውን የከፋ የአየር ብክለት፣ ያልተመጣጠነ የዜጎች የደመወዝ ክፍያን፣ ልቅ የመሬት ይዞታን እና ሌሎች ችግሮቹን በተከታታይ ማጋለጡን ተከትሎ እንደነበር ይወሳል፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ የቻይና መሪዎች ትችትን ለመቀበል አለመፍቀድ እንዲህ አይነት እርምጃዎችን እንዲወስዱ አድርጓቸዋል፡፡ ቻይናውያን ጋዜጠኞች በቻይና መንግስት የሚወሰደው እርምጃ ፍጹም ህጋዊ መሰረት የሌለው ነው ሲሉ ቢከራከሩም ሰሚ አግኝተው የሚያውቁ አይመስሉም፡፡

በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ያለው እውነታም ተመሳሳይነት ያለው ነው፡፡ በእነዚህ አምባገነን ስርዓቶች ገዥዎች ፕሬሱ በተቋም ደረጃ ጎልብቶ በሁለት እግሩ እንዲቆም የሚፈልጉ አይደሉም፡፡ ስለሆነም የራሳቸውን የግል ስልጣን ጠብቆ ለመቆየት ነጻ ፕሬሶችን ሰለባ ያደርጓቸዋል፡፡ በእርግጥም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ፣ አምባገነኖች በነገሱባት ሀገር ፕሬሱና ሙያተኛው በነጻነት ተደራጅቶና ጎልብቶ ተቋም እንዲመሰርት አይፈቀድለትም፡፡ ለዚህም ይመስላል የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በ2009 አፍሪካን ሲጎበኙ ጋና አክራ ላይ ‹‹አፍሪካ ጠንካራ ሰዎችን (መሪዎችን) ሳይሆን ጠንካራ ተቋማትን ነው የምትሻው›› ሲሉ ሀቁን የተናገሩት፡፡

በእርግጥም አፍሪካ ጠንካራ ተቋማት የላትም፡፡ በኢትዮጵያ ያለው የጠንካራ ተቋማት እጦት ችግር ደግሞ ከብዙ የአፍሪካ ሀገራትም የከፋ ነው፡፡ በተለይ ለሌሎች ተቋማት መጎልበት አይነተኛ ሚና የሚጫወተው የሚዲያ ተቋም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት ምንም በሚባል ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ አምባገነኖቹ ገዥዎች ድክመቶቻቸውን በሚያጋልጥባቸው ሚዲያ ላይ የሚወስዱት ህገ-ወጥ እርምጃ አሉታዊ ሚና አለው፡፡

ፕሬሱ ላይ የተመዘዘው አዲሱ ሰይፍ

የኢህአዴግ ገዥዎች ፕሬሱን በማዳከም ሂደት ላይ ከቻይና ‹‹ምርጥ ተሞክሮ›› ሳይወስዱ አልቀሩም፡፡ ልክ እንደ ቻይና ሁሉ ጋዜጦችን፣ መጽሔቶችን፣ ዌብሳይቶችን…ይዘጋሉ፤ ይከስሳሉ፡፡ በእርግጥ በኢትዮጵያ ያለው የፕሬስ ነጻነት ህገ-መንግስታዊ እውቅና አግኝቷል፤ ዋስትና ግን የለውም፡፡ ምክንያቱም ህገ-መንግስታዊ እውቅና ያገኘው የፕሬስ ነጻነት በተለያዩ አፋኝ አዋጆች ዋስትናውን አጥቷል፡፡ የፕሬስ ተቋማትም ሆነ ሙያተኞች (ጋዜጠኞች) ህገ-መንግስቱ ላይ በሰፈረው መሰረት ለመስራት ሲንቀሳቀሱ በተለያዩ ተልካሻ ምክንያቶች በህገ-ወጥ እርምጃ በተደጋጋሚ ተደናቅፈዋል፤ እየተደናቀፉም ይገኛሉ፡፡ በዘመቻ መልክ የግሉን ፕሬስና ጋዜጠኞችን የማሳደድ ስራ ከተከናወነበት ምርጫ 97 ጀምሮ ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ይህን ህገ-መንግስታዊ እውቅና የተቸረውን ነጻነት ሲገረስስ ታይቷል፡፡

አስገራሚው ጩኸት ደግሞ ኢህአዴግ እነዚህን የአፈና ስራዎች ሲሰራ ‹ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ለመጠበቅና ለማስጠበቅ› በሚልና በልማት ሽፋን መሆኑ ነው፡፡ ህግን እየጣሱ ህግን ለማስከበር ስል ነው የሚለው የኢህአዴግ መንግስት ከሰሞኑ ደግሞ ሌላ የአፈና መስመርን ዘርግቷል፡፡ ይኸውም ‹‹ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በአመፅ ለመናድ በማሴር የተጠረጠሩ የህትመት ውጤት አሳታሚዎችና ድርጅቶች›› ላይ በ‹ፍትህ ሚኒስቴር› አማካኝነት ክስ መመስረት ነው፡፡

ተጠርጣሪ ተከሳሽ አሳታሚዎችና ድርጅቶች የክስ ቻርጅ ሳይደርሳቸው እንደማነኛውም ሰው የስርዓቱ አፍ በሆነው በኢቴቪ መስማታቸውን የገለፁት የክስ ይዘት፣ ለብዙዎቻችን ግርምትን የሚያጭር ነው፡፡ የፍትህ ሚኒስቴር መግለጫ ስለጉዳዩ ሲያትት እንዲህ ይላል፤ ‹‹በየጊዜው ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ የአመፅ ቅስቀሳና የሀሰት ወሬዎችን በመንዛት፣ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ በኃይል እንዲፈረስ እና ህዝብ በመንግስት ላይ ያለአግባብ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርጉ የወንጀል ተግባራትን በመፈፀም ተጠርጥረዋል፡፡››

ተጠርጣሪዎቹ ከፍተኛ ተነባቢነት እንዳላቸው የሚታወቁት አምስት መጽሔቶችና አንድ ጋዜጣ ናቸው፡፡ እነዚህም ፋክት፣ ጃኖ፣ ሎሚ፣ አዲስ ጉዳይ እና እንቁ መፅሄቶችና አፍሮ ታይምስ የሚባል ጋዜጣ አሳታሚዎችና ድርጅቶች ናቸው። ምናልባትም ኢህአዴግ ክሱን ለመመስረት መስፈርቱ ፕሬሶቹ ከፍተኛ ተነባቢነት ማግኘታቸው ሳይሆን አይቀርም፤ አለበለዚያም በምንም አይነት መልኩ ምንም ባደርግ አትተቹኝ ባይነት መሆኑ ነው፡፡ እዚህ ላይ፣ ለመሆኑ ‹‹…ህዝብ በመንግስት ላይ ያለአግባብ አመኔታ እንዲያጣ በማድረግ…›› ማለት ምን ማለት ነው? ሲጀመርስ ስርዓቱ በህዝብ ዘንድ አመኔታ አለው ወይ? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል፡፡

ይህን መሰሉ የመንግስት እርምጃ የግሉ ፕሬስና ጋዜጠኞቹ ላይ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽዕኖ ኢህአዴግ ጠንቅቆ የሚያውቀው ይመስላል፡፡ ከአሁን በፊት እንደታየው ከሆነ መንግስት እነዚህን መሰል አሳታሚዎች ክስ ሲመሰርትባቸው ጋዜጠኞቹና አሳታሚዎቹ ወዴት ሊያመሩ እንደሚችሉ የበፊት ተሞክሮው ማህደር የሚነግረው እውነታ አለ፡፡ የኸውም ጋዜጠኞቹና አሳታሚዎቹ ክሱ በሚያሳድርባቸው ጫና ሀገር ጥለው መኮብለል፣ አልያም ስራቸውን እርግፍ አድርገው መተው እንደሆነ አይቶታል፡፡ ይህን አይነት በፍትህ ሚኒስቴር በኩል የሚወጣ ‹መረጃ› እነ አዲስ ነገርና አውራምባ ታይምስን የመሳሰሉ ጋዜጦችን ከህትመት ውጭ አድርጓቸው እንደነበርና ጋዜጠኞችንም ለስደት እንደዳረጋቸው ኢህአዴግ ጠንቅቆ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ የዚህኛው ክስ ጉዳይም ከዚህ ጋር የተመሳሰለ ምላሽን እንዲያስገኝለት በማሰብ የመሰረተው ክስ ሊሆን ይችላል፡፡

የራሷ ሲያርባት…

አንዳንዴ ከራስ ግዙፍ ጉድፍ ይልቅ የሌላን ጥቃቅን ችግር ማየት የተለመደ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ መንግስት በእነዚህ አምስት መጽሔቶችና አንድ ጋዜጣ ላይ የመሰረተው ክስ ተገቢነት የሚኖረው ከሆነ ኢህአዴግም በተመሳሳይ የሚከሰስባቸው አግባቦች መኖራቸውን ልብ ያለው አይመስልም፡፡ ይኸውም መንግስት በራሱ ቁጥጥር ስር በሚገኙ ሚዲያዎች ዘወትር ህዝብን ባዶ ተስፋ እየመገበ ከማወናበዱ በተጨማሪ፣ በተቃውሞው ጎራ ያሉትን ኃይላት ከህዝብ ለማራቅ የሚያደርሰው የስም ማጥፋትና ማጥላላት አልታወሰውም፡፡ መቼም በዶክሜንተሪ ፊልም ስም በተለያዩ አካላት ላይ የሚሰራው ስራ ምን ያህል ጤነኛ እንዳልሆነ ከራሱ ከኢህአዴግ ሰዎች የተሰወረ ሊሆን አይችልም፡፡

ስለሆነም መንግስት አሳታሚዎችንና ድርጅቶችን ‹‹…የሀሰት ወሬዎችን በመንዛት ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ በኃይል እንዲፈረስ እና ህዝብ በመንግስት ላይ ያለአግባብ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርጉ የወንጀል ተግባራትን በመፈፀም…›› ከጠረጠረና ከከሰሰ፤ እሱ ህጋዊና ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ‹‹ከአሸባሪ ቡድኖች ጋር ግንኙነት በመፍጠር›› እያለ ስማቸውን ሲያጎድፍ እንዴት አያፍርም ያስብላል፡፡

ያም ሆነ ይህ ግን መንግስት ምርጫ 2007 ዓ.ም ሳይደርስ ህዝብ መረጃ የሚያገኝባቸውን ፕሬሶች ከወዲሁ ከመስመር እንዲወጡ ማድረጉን ተያይዞታል፡፡ ቀደም ብሎ በተለያዩ ፕሬሶችና ጋዜጠኞች እንዲሁም ጦማሪያን ላይ ሲወስደው የቆየውን እርምጃ አሁንም ገፍቶበታል፤ ገናም ይቀጥልበታል፡፡ ለዚህ ማሳያ ምልክቶች የሚሆኑት ደግሞ በአሳታሚዎችና ድርጅቶቹ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ቀጣይ መሆኑን ፍትህ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ በግልጽ መናገሩ ነው፡፡ ‹‹በህገ-መንግስቱ የተበጁትን ገደቦች በማን አለበኝነት በመጣስ ስራዬ ብለው ብሄራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ በሚጥል መልክ አመፅና ሁከትን የሚቀሰቅሱ፣ አክራሪነትንና ሽብርተኝነትን የሚያወድሱ እንዲሁም የሚያበረታቱ፣ በህዝቡ መሃከል የዘርና የሃይማኖት ጥላቻን የሚቀሰቅሱ፣ የህዝብ መሪዎችንና የተቋማትን መልካም ስምና ዝና በሀሰት የሚያጠፉና የሚወነጅሉ አንዳንድ ህትመቶች እንዳሉም ሊታወቅ ይገባል›› ሲል ማስፈራሪያ አዘል መግለጫውን አሰምቷል፡፡

‹አያ ጅቦ…›

አሁን በአምስቱ የመጽሔት እና አንድ ጋዜጣ አሳታሚዎች ላይ የተመሰረተው ክስ ብዙ የተንሸዋረሩ ምክንያቶችና ሰበቦችን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡ ለምሳሌ ከወራት በፊት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ባስጠናው ‹የአዝማሚያ ጥናት›፣ መሰረት ‹‹አብዛኛዎቹ በህትመት ላይ ያሉ መጽሔቶች የጽንፈኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች ልሳኖች ናቸው›› ሲል ድምዳሜ ላይ መድረሱ ሲነገር ቆይቷል፡፡ ይህም የኢህአዴግ መንግስት በ‹ጥናት› አረጋግጠናል በሚል ‹‹አያ ጅቦ ሳታማሃኝ ብላኝ›› ማለቱ እንደሆነና በቀጣዩ እርምጃ ሊወሰድባቸው የተመረጡ ፕሬሶች መኖራቸውን ያሳየ ነበር፡፡ በዚህም አሁን ክስ የተመሰረተባቸው የፕሬስ አሳታሚዎች በዚያ ‹ጥናት› ስማቸው በክፉ ተነስቶ ጥርስ የተነከሰባቸው እንደነበሩ ማየቱ በቂ ነው፡፡

ሌላው ማመሃኛ ወይም ማደናገሪያ ደግሞ መንግስት ‹ይኽን ክስ እንድመሰርት የተገደድኩት በህዝብ ግፊት ነው› ለማለት የሞከረበት ድንግርግሮሽ ነው፡፡ ‹‹የጥቃታቸው ሰለባ የሆነው ህዝብ በእነዚህ የህትመት ውጤቶች የህግ ከለላ በተሰጣቸው ጥቅሞቹ ላይ ያለማቋረጥ የሚደርሰውን ጥሰት ለማስቆም መንግስት ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ በተለያዩ መንገዶች ሲጠይቅ ቆይቷል›› ይላል መንግስት በፍትህ ሚኒስቴር በኩል በሰጠው መግለጫው፡፡

በእርግጥ የኢህአዴግ መንግስት ከረጂም ጊዜ ተሞክሮው እንደታየው አካሄዳቸው ያላማረውን (የሚተቹትን፣ ድክመቶቹን የሚያጋልጡትን) ማናቸውንም የግል ህትመት ውጤቶች በተለያዩ ዘዴዎች ከመስመር ማስወጣቱን ልብ ማለት ይቻላል፡፡ መንግስት አዲስ ዘመንን፣ ኢቴቪንና አይጋ ፎረም የመሳሰሉ ሚዲያዎችን በመጠቀም ሰፊ ማጥላላት ሲከፍትባቸው የነበሩትንና ያሉትን ፕሬሶችና ጋዜጠኞች ስንመለከት ኢህአዴግ ህግ የማይገዛው፣ በአንጻሩ ግን ህግን በማስከበር ስም ሌሎች ላይ ጥቃት እያደረሰ የሚገኝ መሆኑን እናያለን፡፡

ተቋም እንዳይኖር ማድረግ

ኢህአዴግ ፕሬሱ በተቋም ደረጃ እንዲጎለብት አይፈቅድም፡፡ ስለሆነም የግል ፕሬሱ እንደ ፕሬስም ሆነ ጋዜጠኞቹ በነጻነት ተደራጅተው ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ አይደረግም፡፡ በዚህ አመት ላይ ራሳቸውን በማህበር ለማደራጀት የሞከሩ ጋዜጠኞች እንኳ እጣፈንታቸው ከመበታተን ያለፈ አልሆነም፡፡ ለዚህ ደግሞ የመንግስት ጫና አሉታዊ ሚና አለው፡፡ ለምሳሌ ሁለቱ አመራሮች (የማህበሩ ፕሬዚዳንት ጋዜጠኛ በትረ ያዕቆብ እና የህዝብ ግንኙነት የነበረው ጋዜጠኛ ዘሪሁን ሙሉጌታ) ስርዓቱ ባደረሰባቸው ጫና ሀገር ጥለው ተሰድደዋል፡፡

ኢህአዴግ መደራጀት መብት ነው ሲል፣ በራሱ ማዕቀፍ ጥገኛ እስከተሆነ ድረስ ማለቱ እንደሆነ በተደጋጋሚ የታየ ጉዳይ ነው፡፡ አሁን ላይ ነጻና ገለልተኛ ማህበራትን ማየት ብርቅ ሆኗል፡፡ ምክንያቱም በየማህበራቱ የኢህአዴግ እጅ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አለ፡፡ ስለሆነም የፕሬሱን ጉልበት ማዳከሚያ ዋና መሳሪያው ያገባኛል የሚሉ አካላት በነጻነት እንዳይደራጁ ማድረግ ነው፡፡

እስካሁን ድረስ የግል ፕሬሱ አንድ የጋራ ጠንካራ ማተሚያ ቤት እንኳ ሊኖረው አልቻለም፡፡ ፕሬሱ የአንጋፋ የመንግስት ማተሚያ ድርጅት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ጥገኛ ነው፡፡ ሌሎች የንግድ ማተሚያ ቤቶችም ቢሆን አንድም አቅማቸው የሚያወላዳ አይደለም፤ ሁለትም በተዘዋዋሪ መንገድ በስርዓቱ ተጽዕኖ ስር የወደቁ ናቸው፡፡

የተመዘዘውን ሰይፍ ለማጠፍ…

በአጠቃላይ አሁን ያለው የሀገራችን የፕሬስ ነጻነት እጅግ አሳሳቢና አደገኛ ሁኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑ ግልጽ ሆኗል፡፡ እስካሁን ከተለመደው የጋዜጠኞቹ እስርና ድብደባ እንዲሁም ስደት በከፋ ሁኔታ አሁን ደግሞ አሳታሚዎች ላይ ክስ መመስረት መቻሉ መንግስት ምን ያህል የግል ፕሬሱን ማሽመድመድ እንደፈለገ ጉልህ ማሳያ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ይህን በፕሬሱ ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለማቃለል የተደራጀ ርብርብ በሚመለከታቸው ተቆርቋሪ አካላት ዘንድ መደረግ ይኖርበታል፡፡ መንግስት ህገ-መንግስቱን አክብሮ ፕሬሱ በነጻነት እንዲቀሳቀስ መፍቀድ ግዴታው መሆኑን በተለያዩ ስልቶች (ለምሳሌ የፕሬሱ አባላት የሚያስተባብሩት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ፣ የተዘጉ ፕሬሶችን የቀደሙ ኮፒዎች ይዞ በአደባባዮች በህብረት መታየት፣ አፍን በጥቁር ፕላስተር አሽጎ ተቃውሞን መግለጽ…) በመሳሰሉት ማስገደድም የተገባ ይሆናል፡፡

source: ነገረ ኢትዮጵያ

↧

አዲሱ የዳያስፖራ የትግል ስልት (ጌታቸው ሺፈራው )

$
0
0

ጌታቸው ሺፈራው

105አምባገነኖችን በሰላማዊ መንገድ ለማንበርከክ ይውላሉ የሚባሉ ከ180 በላይ የትግል ስልቶች እንዳሉ ይጠቀሳል፡፡ ከእነዚህ መካከል አንዱ በተለያዩ መንገዶች ግለሰብ ላይ ጫና ማሳደር ነው፡፡ በዚህ የትግል ስልት ውስጥ የሚጠቀሰው ደግሞ መሪዎች በስራቸው እንዲሸማቀቁ ማጋለጥ ይገኝበታል፡፡ አንዳንዶቹ ባለስልጣናትን ማሸማቀቅ፣ ማጋለጥ ባለፉት አስርት አመታት እንዳልተጀመረ ያስረዳሉ፡፡ ሮማውያንና ቻይናውያን ስር የነበሩ ተገዥ ህዝቦች የድሮዎቹ ገዥዎችን ንግግር በማቋረጥ፣ የእነዚህ አገዛዞች ወረራ፣ ፖሊሲ አላግባብ የሆነ ግብር አሊያም በግለሰብ ደረጃ ለመሪዎቻቸው ያላቸውን ተቃውሞ በመጮህ ይገልጹ እንደነበር ይገለጻል፡፡ ይህ መሪዎችን የማሸማቀቅ የሰላማዊ ትግል ስልት ከድሮዎቹ በበለጠ ባለፉት በተለይም የሶቬትን መፈረካከስ ተከትሎ የሰላማዊ ትግል ስልቶች ይበልጡን የህዝብ መሳሪያ በሆኑበትና አምባገነኖች ስልጣናቸውን በመልቀቅና ባለመልቀቅ መሃል ሲወዛገቡ በነበሩበት ዘመን ጀምሮ በስፋት እየተሰራበት ይገኛል፡፡

የሙታድሃር አልዛይዲ መንገድ

ሙንታድሃር አል ዛይዲ የኢራቅ የመንግስት ቴሊቪዥን ውስጥ የሚሰራ ጋዜጠኛ ነው፡፡ ይህ ጋዜጠኛ ኢራቅ ውስጥ የነበረው የአሜሪካ ሰራዊት በኢራቃውያን ህጻናት፣ እናቶችና ወጣቶች ያደርሰው የነበረውን ግፍ በቀዳሚነት ተመልክቷል፡፡ ኢራቃውያን በአሜሪካ ሰራዊት ፍዳቸውን ማየታቸውን ይፋ ለማውጣት የተቀጠረበት የመንግስት ሚዲያ ባያመቸውም በግሉ ግን የቡሽ አስተዳደር የሚፈጽመውን ግፍ በሰላማዊ መንገድ ማጋለጥ ችሏል፡፡ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ጥር 14/2008 ላይ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ደብሎው ቡሽ በኢራቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤተ መንግስት ውስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጡ በመሆኑ ሁኔታውን እንዲዘግብ ሲላክ ይህን ትግሉን የሚያካሂድበት አመች ሜዳ አግኝቷል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የኢራቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ሆነው የአሜሪካ መንግስትና ህዝብ ኢራቅን ለመታደግ የወሰዱትን ፖሊሲ፣ የአሜሪካ ሰራዊት ለኢራቃውያን የሚያሳየውን ርህራሄና ደጀን አስመልክተው ድስኩር እያሰሙ በነበረበት ወቅት አንድ በአሜሪካ ፕሬዝንት ላይ፣ ያውም በኢራቅ ቤተ-መንግስት ውስጥ ይሆናል ተብሎ የማይታሰብ፣ አንድ የመንግስት ሚዲያ ውስጥ የሚሰራ ጋዜጠኛ ይፈጽመዋል የማይባል አስደንጋጭ ነገር ተከሰተ፡፡ ከቡሽ ዲስኩር ይልቅ ‹‹ይህ ከኢራቅ ህዝብ የተላከ የመሸኛ ሰላምታ ነው!›› የሙንታድሃር አል ዛይዲ ድምጽ አስተጋባ፡፡ ድምጹን አጅቦት የጋዜጠኛው ጫማ የአሜሪካኑን ፕሬዝዳንት ለጥቂት ሳተው፡፡ ለጋዜጠኛው ይህ ሌላ ጊዜ የማያገኘው ጦር ሜዳው ነውና ‹‹ይህኛው ደግሞ ኢራቅ ውስጥ ለሞቱት፣ ባል አልባና አባት አልባ ለቀሩት ኢራቃውያን ማስታወሻ›› ይሁን በሚል ሁለቱንም ጫማዎች ወደ ቡሽ በመወርወር የኃያሏን አገር አሜሪካ ፕሬዝደንት በጫማ አስጨነቃቸው፡፡ ቡሽ በሚያዙት የአሜሪካ ሰራዊትና ይሁንታ ስልጣን ላይ የነበሩት የኢራቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ‹‹እኔን ይምታኝ›› ብለው ለተደናገጠው ቡሽ ሲደረቡ ታዩ፡፡

የዚህ ጋዜጠኛ ተግባር ሰላማዊ ለመሆኑ ቡሽ በወቅቱ የሰጡት አስተያየት በግልጽ አሳይቷል፡፡ ከስድብ ጋር በጫማ ባራወጣቸው ጋዜጠኛ ተግባት ተበሳጭተው ‹‹ተደፍረናል፣…›› አላሉም፡፡ ይልቁንስ ‹‹ይህ ጉዳይ ምንም አያስጨንቀኝም፡፡ ሰዎች ትኩረት ለማግኘት የሚወስዱት ስልት ነው›› በማለት ሰላማዊ እንደሆነ ተገንዝበው አልፈውታል፡፡

በእርግጥ የኢራቁ ጋዜጠኛ የወሰደውን እርምጃ ቡሽ ‹‹ይህ ጉዳይ ምንም አያስጨንቀኝም›› ቢሉም በቡሽ ይሁንታ ስልጣን ላይ የነበሩት የአገሪቱ ገዥዎች እንዲሁ ሊያልፉት አልቻሉም፡፡ በወቅቱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠባቂዎች ጋዜጠኛውን እየደበደቡ ለስርዓቱ መከላከያ ሰራዊት አሳልፈው ሰጥተውታል፡፡ ከፍተኛ ደብደባ እንደደረሰበትም ታውቋል፡፡ በዛች የወደቀች አገር የስርዓቱ እጅ የሆነ ፍርድ ቤት የሶስት አመት እስር ወስኖበታል፡፡ በተቃራኒው ህዝብ ጋዜጠኛው ጀግና መሆኑን በመግለጽ እንዲለቀቅ ጎዳና ላይ ወጥቶ ጭምር ጠይቋል፡፡ ተወሰደበት የተባለውን እርምጃ ተቃውሟል፡፡ የኋላ ኋላ ጋዜጠኛው ከ9 ወር በኋላ መልካም ጸባይ ያለው ሰው ነው ተብሎ ተለቅቋል፡፡ በዛች በፈራረሰችውና በአሜሪካ ስር በምትተዳደር ኢራቅ ውስጥ ያውም በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ላይ ጫማ የወረወረ ኢራቃዊ ጋዜጠኛ የወሰደው እርምጃ ሰላማዊ በመሆኑ ሰላማዊ ነው ተብሎ ተለቋል፡፡ አገሪቱ ያለችበት ሁኔታ እንጂ ለአንድም ቀን የሚያሳስት አልነበረም፡፡ በኋላ ላይ የወረወረውን ጫማ ቅርጽ የሚያሳይ ሀውልት የተቀረጸለትም ትግሉ ሰላማዊና አርዕያ የሚሆን ስለነበር ነው፡፡

የዚህ ኢራቃዊ ጋዜጠኛ ስምና ዝና እንዲሁም የትግል ስልት ኢራቅ ብቻ ተወስኖ አልቀረም፡፡ ጫማ መወርወር አንድን ሰው ምን ያህል እንደሚጠሉት ለማሳየት በአረቡ ዓለም የተለመደ ባህል ነው፡፡ ከዓረቡ ዓለም ውጭም በመላው ዓለም አዲስ አምባገነኖችን የማሸማቀቂያ ስልት ሆኖ የታየ ሲሆን ሙንታድሃር በፕሬዝዳንት ቡሽ ላይ ጫማ ከወረወረ በኋላ በፖለቲከኞችና በሌሎች ታዋቂ ሰዎች ላይ ቢያንስ 44 ያህል ጊዜ ጫማ ተወርውሮባቸዋል፡፡

ቡሽ ከተወረወረባቸው በኋላ ጦርነቱን የተቃወሙ የአሜሪካ ዜጎች በሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው ወደ ዋይት ሃወስ ጫማቸውን በመወርወር የኢራቁን ጋዜጠኛ ተግባር አሜሪካ ውስጥ ደግፈውታል፡፡ በተመሳሳይ ካናዳ ውስጥም ሰላማዊ ሰልፈኞች ከአሜሪካ ቆንጽላ ፊት ለፊት በርካታ ጫማዎችን በመወርወር ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡ እ.ኤ.አ 2008 ጥር ወር መጨረሻ ላይ የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ወይንጃባው ካምብሪጅ ዩኒቨርሰቲ ውስጥ ከጎርደን ብራውን ጋር ስለ ኢኮኖሚ ትብብር እያወሩ በነበረበት ወቅት ከአንድ ጀርመናዊ ተሳታፊ ወጣት ጫማ ተወርውሮባቸዋል፡፡ በወቅቱ ስለ ቻይና እድገት ሲደሰኩሩ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ አምባገነንነታቸውና ውሸታቸው ተቃውሞውን ካቀረበው ወጣት ውርጅብኝ ተርፈዋል፡፡ ጀርመናዊው ወጣት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቻይናውያን ላይ የሚያደርሱትን በደል በመቃወም ጫማ መወርወርን ዓለም አቀፋዊ የሰላማዊ ትግል ስልት አድርጎ ተጠቅሞበታል፡፡

የቻይና ባለስልጣናት ወጣቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩንና የሁለቱን አገር ግንኙነት ለመጉዳት ነው በሚል ቅጣት እንዲጣልበት ጫና ቢያደርጉም ወጣቱ ግን ይህን ለማድረግ የሚያሳይ መረጃ በመታጣቱ ተለቅቋል፡፡ በተመሳሳይ አመት ስዊድን ውስጥ ይገኙ የነበሩ የእስራኤል አምባሳደር ስለ ጋዛ በሚያወሩበት ወቅት ‹‹ገዳይ›› በሚል ድምጽ ንግግራቸውን በማቋረጥ ጫማ ተወርውሮባቸዋል፡፡ ሄላሪ ክሊንተን ግብጽን እየጎበኙ በነበሩበት ወቅት ‹‹ሞኒካ›› ከሚል የማሸማቀቂያ መዝሙር ጋር ግብጾች ጫማቸውን ወርውረውባቸዋል፡፡ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር በሌላ ቀንም እየተናገሩ በነበረበት ወቅት አንድ ተማሪ ‹‹ዘረኛ›› ከሚል ማሸማቀቂያ ጋር በጫማ ተስተዋል፡፡ አህመዲን ኒጃድ ግብጽና አገራቸው ውስጥም ጫማ ተውርውሮባቸዋል፡፡

ከእነዚህ በተጨማሪ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማንሞናህ ሲንህ፣ የዓለም ገንዘብ ድርጅት ዳይሬክተር ዶሚኒኩ ስትራውስ ካህን፣ በሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር (ካርቱም ውስጥ)፣ የቱርኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርዶጋን፣ የፓኪስታኑ ፕሬዝዳንት አሲፍ አሊ ዛርዳሪ፣ ቶኒ ብሊየር (ጫማና እንቁላል)፣ የቀድሞ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔርቬዝ ሙሻራፍና ሌሎችም የጫማ ውርወራ ተቃውሞ ሰለባና የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ መነጋገሪያ ሆነው ተሸማቅቀዋል፡፡

ይህ ጫማ በመወርወር ባለስልጣናትን ማሸማቀቅ አንዳንዶች ሰላማዊ አይደለም ቢሉትም የተወረወረባቸው አካላት ሳይቀሩ እንዲሁ ሲያልፉት ተስተውሏል፡፡ በባለስልጣናት ጫማ ከወረወሩት መካከል ከበድ ያለ ቅጣት የተጣለበት ሰው እምብዛም አይነገርም፡፡ የኢራቁ ጋዜጠኛ ጫማ በወረወረበት ወቅት እውቅ የሆኑ የሰላማዊ ትግል ጠበብቶች ‹‹ጋዜጠኛው ቡሽን ለመጉዳት ሳይሆን ጫማ መወርወር በዓለቡ ህዝብ ዘንድ ለሚጠላ ሰው የሚደረግ ተግባር በመሆኑ ነው›› ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ ጋዜጠኛው ለ9 ወር ከታሰረ በኋላም መልካም ስነ ምግባር ያለው ሰው ነው ተብሎ ከመለቀቁም ባሻገር በአሁኑ ወቅት ለኢራቃዊያን ሰብአዊ እርዳታ በመስጠት ላይ የሚገኝ መሆኑ ይህን ሰላማዊነቱን የሚያሳይ ነው፡፡ በቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ ጫማ የወረወረው ጀርመናዊ ወጣት ‹‹የወረወርኩት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለመምታት ብዬ አይደለም፡፡ ጫማውን መድረኩ ላይ ስጥለው የጋራ መግባባት እንደሚፈጥር አውቃለሁ፡፡ ይህ አንድ የተቃውሞ ምልክት ለመሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ሰው ለመጉዳት ፍላጎት የለኝም›› በሚል የተቃውሞውን ሰላማዊነት ገልጾ ነበር፡፡

የአበበ ገላው (የዲያስፖራው መንገድ)

የባለስልጣናትን ንግግር በማቋረጥ የሚፈጽሙትን በደል ለሚዲያና ለዓለም ማህበረሰብ ማሰማት አንዱ የሰላማዊ ትግል ስልት ነው፡፡ በህዝብ ላይ በደል በፈጸሙ ባለስልጣናት፣ የኩባንያ ባለሃብቶች፣ ግለሰቦች ለሚዲያ በቀረቡበት ወቅት አሊያም በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ አሜሪካ ውስጥም ጮኸት እንደተደረገባቸው ይነገራል፡፡ ለአብነት ያህል በምርጫ ክርክሮች መሃከል በመናር ላይ የነበሩ ባለስልጣናት በፖሊሲያቸው የማይስማሙ ዜጎች ንግግራቸውን በማቋረጥ መቃወም፣ ማሸማቀቅ ተደርጎባቸዋል፡፡

በግንቦት ወር 2004 ዓ.ም በባራክ ኦባማ ግብዣ ወደ አሜሪካ ያቀኑት የወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊም በሌሎች የአፍሪካ መሪዎች፣ የአሜሪካ ተወካዮችና የዓለም ሚዲያ ፊት ተመሳሳይ እጣ ፈንታ ገጥሟቸዋል፡፡ ልክ እንደ ኢራቁ ጋዜጠኛ የውይይት መድረኩን እንደ ሰላማዊ የጦር ሜዳ የተጠቀመው ጋዜጠኛ አበበ ገላው ‹‹መለስ ዜናዊ አምባገነን ነው፣ ነጻነት እንፈልጋለን፣ እስክንድርና ሌሎች የህሊና እስረኞች ይፈቱ›› የመሳሰሉትን መፈክሮች ሲያስተጋባ መለስ ዜናዊ አቀርቅረው ታይተዋል፡፡ ጋዜጠኛው ያደረገው ነገር ሰላማዊ በመሆኑ የውይይቱ አስተባባሪዎች አበበ ገላው መፈክሩን እንዲያቆም ‹‹ሰምተናል፣ እናመሰግናለን›› ከማለት ውጭ ሌላ እርምጃ አልተወሰደበትም፡፡

የኢራቁ ጋዜጠኛ ካደረገውም በበለጠ እጅግ ሰላማዊ በሆነና የዓለም ማህበረሰብ በሰፊው በሚሰማበት አጋጣሚ በኢትዮጵያ ዲያስፖራ የተጀመረው ተቃውሞ በአንድ ወቅት መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ ምንም እንኳ ሰላማዊ ትግልን ይህን ያህል ለውጥ እንደማያመጣ በሚያምነው ማህበረሰብ ውስጥ የአንድን ባለስልጣን ንግግር ማቋረጥ ባንዳንዶቹ ከዚህ ግባ የማይባል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ብልግና ተደርጎ ቢወሰድም በስርዓቱ ደጋፊዎችና ባለስልጣናት ላይ ከፍተኛ መደናገጥን መፍጠሩ የሚታወስ ነው፡፡ ሰላማዊ ትግል ለውጥ ያመጣል ብለው በሚያምኑት ዘንድም እንደ ድል የተቆጠረ ሲሆን ሌሎች መንገዱን እንዲመርጡት አድርጓል፡፡ አበበ አቶ መለስ ‹‹አምባገነን ነው!›› ከተባሉ ከሁለት አመት በኋላ አርብ ሜይ 9/2014 እ.ኤ.አ በፕሬዝዳንት ኦባማ ላይ ዳግመኛ ተግብሮታል፡፡

‹‹ሚስተር ኦባማ እኛ ኢትዮጵያውያን እንወድወታለን፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ነጻነት እንፈልጋለን›› በማለት የጀመረው ጋዜጠኛ አበበ ገላው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ጨቋኝ ስርዓት መደገፍ አቁመው ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እንዲቆሙ አሳስቧል፡፡ ከጋዜጠኛ አበበ ገላው ጋር እንደሚስማሙ የተናገሩት ፕሬዝደንት ኦባማ ስለ ጉዳዩ ከአበበ ጋረ እንደሚያወሩበት በዓለም ሚዲያ ፊት ቃል ገብተውለታል፡፡ በስተመጨረሻ አበበ ለፕሬዝዳንቱ ደብዳቤ ሰጥቷቸዋል፡፡ የአበበ ገላው ተቃውሞ ሰላማዊ በመሆኑ ፕሬዝዳንት ኦባማ ከመበሳጨትና እንደ አቶ መለስ አንገታቸውን ከመድፋት ይልቅ ‹‹እኔም እወድሃለሁ!›› ብለው ሰላማዊነቱን ገልጸውለታል፡፡

አበበ ገላው የአቶ መለስን ንግግር ካቋረጠ ከሁለት አመት እንዲሁም ፕሬዝዳንት ኦባማን ካቋረጠ ከሁለት ወር በኋላ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት በተመሳሳይ የትግል ስልት የኢትዮጵያን ባለስልጣናት ማሸማቀቅ፣ ጉዳዩን የሚዲያ መነጋገሪያ ማድረግና ሌሎችም በተመሳሳይ ሰላማዊ ትግል ስልት እንዲሳተፉ ማነቃቃት ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ ለአብነት ያህል ከአንድ ወር በፊት ወደ አሜሪካ አቅንተው የነበሩት የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ ዋሽንግተን ውስጥ በሚገኝ አንድ የኢትዮጵያ ሪስቶራንት ውስጥ በነበሩበት ወቅት በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ እንዳሰሙባቸው ታውቋል፡፡

በተመሳሳይ የአሜሪካ መንግስት የአፍሪካን መሪዎች በጋበዘበት ወቅት በአሜሪካ የተገኙ የኢትዮጵያ ባለስልጣናትም ከዳያፖራው ቀላል የማይባል ተቃውሞ ገጥሟቸዋል፡፡ ለአብነት ያህል የኮሚኒኬሽ ሚኒስትሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን በአንድ የገበያ ማዕከል ውስጥ በነበሩበት ወቅት ‹‹ገዳይ ነህ! ተላላኪ!›› የሚሉትን ጨምሮ ስድብና ተቃውሞ ሲደርስባቸው ተመልክተናል፡፡ ምንም እንኳ በአቶ ሬድዋን ላይ ከተቃውሞም ባለፈ ተራ ስድብ ጭምር የተሰነዘረባቸው ቢሆንም ምንም ቢሆንም እንቁላልና ጫማም በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞን መግለጫ በሚያገለግሉበት በአሁኑ ወቅት ሰላማዊ አይደለም ለማለት አይቻልም፡፡ ከቪዲዮው ማየት እንደተቻለው ተቃውሞውን ያቀረቡት ኢትዮጵያውያን አቶ ሬድዋን ጋር ከነበራቸው የአካል ቅርርብ አንጻር ከሰላማዊ መንገድ በሆነ መልኩ እርምጃ ሊወስዱ የሚያስችል አጋጣሚ ነበራቸው፡፡ በመሆኑም ተቃዋሚዎቹ ሰላማዊ የሆነውን መንገድ መምረጣቸውን ያሳያል፡፡

ሱቅ ውስጥ ሲዋከቡ አቶ ሬድዋን ሁሴን የመጀመሪያው ፖለቲከኛ አይደሉም፡፡ የሰለጠኑት አገራት ባለስልጣና ያውም አገራቸው ውስጥ ጭምር ተመሳሳይ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል እ.ኤ.አ በ2012 የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አገራቸው ላይ ተመሳሳይ ተቃውሞ ደርሶባቸዋል፡፡ በአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ደስተኛ ያልሆኑ ዜጎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገቡበት ሱቅ ውስጥ ጩኸታቸውንና ተቃውመዋቸውን አሰምተዋል፡፡ ይህ አውስትራሊያ ውስጥ ተገለልን በሚሉ ህዝቦች የተደረገ ጮኸት አሜሪካንና አውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ከአውስትራሊያ ውጭ ያለውን የዓለም ህዝብ አነጋግሯል፡፡ ከዚህ በኋላም በእነዚህ ህዝቦች ላይ ተፈጸመ በተባለው ወንጀል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይቅርታ እስከመጠየቅ ደርሰዋል፡፡ አቶ ምንም እንኳ አቶ ሬድዋን ሁሴን በገጠማቸው ተቃውሞ ሲሸማቀቁ ቢታዩም እንዲህ እንዲሸማቀቁ ላደረጋቸው ተግባር ግን ይቅርታ ይጠይቃሉ ብሎ መጠየቅ የዋህነት ይሆናል፡፡

ከአቶ ሬድዋን በተጨማሪ ኢትዮጵያውያን ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ያረፉበት ሆቴል በመሄድ ተቃውሞ ለማሰማት ጥረት እንዳደረጉና ዶክተር ቴዎድሮስን ደብቀዋል ያሏቸውን ሰዎች ለይ ጫና ሲያደርጉ የሚያሳይ ቪዲዮም ተለቅቋል፡፡ በተመሳሳይ ዳያስፖራው ተቃውሞ እንደሚያቀርብባቸው አውቀዋል የተባሉት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እነ አበበ ገላውና ‹‹Global Alliance for the Rights of Ethiopians›› የተባለ አካል እያደራጁት በነበረ ተቃውሞ ምክንያት አዙሳ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በሌሎች በተያዘላቸው ፕሮግራም መገኘት አለመቻለቸው የዳያስፖራው አዲስ መንገድ ምን ያህል ባለስልጣናቱን እያሸማቀቀ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡

የሌሎች የአፍሪካ አገራት በመኪናቸውና በአረፉበት ሆቴል ላይ የየአገራቸውን ሰንደቅ አላማ ሲያውለበልቡ አቶ ኃይለማርያምን ጨምሮ ሌሎች የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በመኪናቸውም ሆነ ባረፉበት ሆቴል ላይ ሰንደቅ አላማ አለማድጋቸውንና ዳያስፖራው በተጠናከረ መንገድ ከሚያደርግባቸው ተቃውሞ ለመደበቅ ያደረጉት መሆኑን የዳያስፖራው ሚዲያዎች ‹‹Ethiopia: Prime Minster Hailemariam in Hiding›› ሲሉ ተቀባብለውታል፡፡ በአቶ ሬድዋን ሁሴን ላይ ተቃውሞ ያደረሱት ኢትዮጵያውያን ከተናገሩት መረዳት እንደሚቻለው ዳያስፖራው ስለ ባለስልጣናቱ መረጃ በመስጠትና በየግሉ ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ መደራጀቱን ነው፡፡ ይህ የዳያስፖራ ተቃውሞ በሰላማዊነቱና በተጠናከረ መልኩ ከቀጠለ አሜሪካ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ሊያቀኑባት የሚፈሯት አገር እንድትሆን ያደርጋታል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አፈና፣ የባለስልጣኑ ተደራሽነትና በመሳሰሉት ምክንያቶች ይህ የትግል ስልት እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ይህ ነው የሚባል ሚና ባይኖረውም የዳያስፖራው የትግል ስልት አገር ቤት መለመድ አለመለመዱ ወደፊት የሚታይ ይሆናል፡፡

↧
↧

Health: ያለ መድሃኒት! የደም ግፊትን ለመቆጣጠር የሚረዱ 10 መንገዶች

$
0
0

እነዚህን 10 የአኗኗር ዘዬዎች በመከተል የደም ግፊትዎን እና በልብ ህመም የመጠቃት ዕድልዎን ይቀንሱ

ከዚህ ቀደም በደም ግፊት ሕመም ተጋልጠው (ከ140/90 ወይም ከዛ በላይ) ሆኖ አስጨንቆዎት ነበር? ይህን ቁጥርም ለመቀነስ በተደጋጋሚ የህክምና ተቋም ደጅ ረግጠውም ይሆናል፡፡
ጤናማ የአኗኗር ዘዬዎች ይህን ከፍ ያለ የደም ግፊት ለመቀነስ ይህ ነው የማይባል ሚና ይጫወታሉ፡፡ በእነዚህ አስር የአኗኗር ዘዬዎች የደም ግፊትዎን ይቆጣጠሩ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሐኪም ቤት የሚመላለሱበትን ጊዜም ሊቀንሱ ብሎም ፈፅሞ ሊያስቀሩ ይችላሉ፡፡
‹‹እንዴት ተደርጎ?›› አሉ?
እስቲ እነዚህን 10 የህይወት ዘዬዎችን ይሞክሯቸው፡፡
highbloodpressure
1. ክብደትዎን ይቀንሱ
አብዛኛውን ጊዜ የደም ግፊት የክብደት መጨመርን ተከትሎ ሽቅብ ይምዘገዘጋል፡፡ ሌላው ቀርቶ 4.5ኪሎ ብቻ መቀነስ እንኳን የደም ግፊትን ይቀንሳል፡፡ ብቻ ምን አለፋዎ ክብደትዎን በቀነሱ መጠን በተጓዳኛ የደም ግፊትዎንም እየቀነሱ ነው፡፡ ሐኪምዎ ጋርም ጎራ ካሉ በምን ያህል ጊዜ ምን ያህል መቀነስ እንደሚኖርብዎት ስለሚያማክርዎ ውጤቱ የተሻለ አመርቂ ይሆንለዎታል፡፡
ክብደት የመቀነሱ ነገር ላይ ተፍ ተፍ ሲሉ ታዲያ በወገብዎ ዙሪያ ያለውንም ቦርጭ ችላ አይበሉት፡፡ እሱ ነገር ለከፍተኛ የደም ግፊት የማጋለጥ ዕድሉ ሰፋ ያለ ነው፡፡ ለመሆኑ የወገብዎ ስፋት ምን ያህል ሴንቲ ሜትር ይሆናል? የማይጠየቅ ጠየቅን ይሆን? እስቲ ይለኩት፡፡
ወንድ ከሆኑ የወገብዎ ስፋት 102 ሴንቲ ሜትር፣ ሴት ከሆኑ ደግሞ 89 ሴንቲ ሜትርን ከዘለለ የደም ግፊት በዙሪያዎ እያንዣበበ ነውና ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ የተቻለዎትን ያህል የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃ ይውሰዱ፡፡

2. መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ
ቢያንስ ከ30-60 ደቂቃ ከሳምንቱ ቀናት አብዛኛውን የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማድረግ ከ4-9 ያህል Millimeters of Mercury የደም ግፊትዎን ይቀንሳል፡፡ ልዩነቱንም በአጭር ጊዜ ያስተውሉታል፡፡ ፈጣን ባይሆኑ እንኳን የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎን አያቋርጡ፣ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የደም ግፊትዎ መቀነስ ይችላሉ፡፡
ከፍተኛ የደም ግፊት ካለብዎት የላይኛው ከ120-139 የታችኛው ደግሞ ከ80-89 ከተመዘገበ ጉዳት እንዳያደርስብዎ እና ወደ ከፍተኛ የደም ግፊት እንዳይሻገር መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴው ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ ታዲያ የአካል ብቃት እንቅስቃሴውም ቢሆን በእቅድ እና በሐኪምዎ ጋር በመመካከር ቢያደርጉት የተሻለ ይሆናል፡፡ ምናልባትም ሊደፍሩት የማይገባ እንቅስቃሴን በዘፈቀደ አድርገው ነገሩ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዳይሆን፡፡ ምን አይነቱን እንቅስቃሴ ለምን ያህል ሰዓት ማድረግ እንዳለብዎት መመካከሩ አይከፋም፡፡ እርስዎ ጂም ገብተው ኤሮቢክሱን ከአቅምዎ በላይ ሲያጣድፉት ምናልባትም የ20 ደቂቃ የእግር ጉዞ ይበቃዎት ይሆናል፡፡
የእረፍት ቀናትን ተከትሎ ከሚመጣ የበዛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ያስወግዱ፡፡ የሳምንቱን ሁሉ በአንድ ቀን እወጣዋለሁ በሚል ስልት አንድ ቀን የሚደረግ የእንቅስቃሴ ጋጋታ አያዋጣም፡፡ እንዲያውም ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡

3. ጤናማ አመጋገብ ይኑርዎት
በጥራጥሬ እና ፍራፍሬ እንዲሁም አትክልት የበለፀጉ እና አነስተኛ የቅባት መጠን ያላቸውን የወተት ተዋፅኦ መመገብ፣ ቅባት የበዛባቸውን እና ኮሌስትሮል ነክ ምግቦችን መቀነስ የደም ግፊትን እስከ 14 Millimeters of mercury ያህል ይቀንሳል፡፡ ይህ የአመጋገብ አይነትም “Dietary Approaches to stop Hypertension (DASH)” ወይም ‹‹የደም ግፊትን ለማቆም የሚረዳ የአመጋገብ ዘዴ›› በመባል ይታወቃል፡፡ እርግጥ ነው የአመጋገብ ልማድን መቀየር ቀላል አይደለም፡፡ የሆነ ሆኖ ግን በሚከተሉት ሐሳቦች በመታገዝ ጤናማ አመጋገብን መለማመድ ይቻላል፡፡
– የምግብ መዝገብ ይኑርዎት፡- የሚመገቡትን ይፃፉ፡፡ ቢያንስ ለሳምንት ይህንን ያድርጉ፡፡ ያኔ በእርግጥ የአመጋገብ ልማድዎ ምን እንደሚመስል በመገረም ይገነዘባሉ፡፡ ምን እንደሚመገቡ፣ ምን ያህል እንደሚመገቡ፣ መቼ እና እንዴት እንደሚመገቡም መቆጣጠር ይችላሉ፡፡
– ፖታሺየም ያብዙ፡- ፖታሺየም ሶዲየም በደም ግፊት ላይ ያለውን ተፅዕኖ ይቀንሳል፡፡ ፖታሺየምን ፍራፍሬ እና አትክልት ከመሳሰሉ ምግቦች ውስጥ እናገኘዋለን፡፡ ለእርስዎ ተመጣጣን የሆነ ፖታሺየም ምን ያህል መሆኑን ለማወቅ ታዲያ ሐኪምዎን ማማከርዎን እንዳይረሱ፡፡
– ብልህ ገበያተኛ ይሁኑ፡- ‹‹ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት›› ተብሎ እንዳይተረትብዎ ወደ ገበያ ሲወጡ ለመግዛት የሚፈልጉትን መዝግበው ይያዙ፡፡ ይህን ማድረግዎ ፊት ለፊትዎ ያገኙት ሁሉ የቦርሳዎ ወይም የኪስዎ አቅም እስከፈቀደ ከማጋበስ ይድናሉ፡፡ በተጨማሪም የታሸጉ ምግብ ነክ ነገሮችን ሲገዙ እላያቸው ላይ የተፃፈውን ማስረጃ አገላብጠው ያንብቡና ከእርስዎ ጤናማ አመጋገብ ጋር የማይጣረስ መሆኑን ያረጋግጡ፡፡ ይህን የሚያደርጉ ‹‹ብልህ ገበያተኛ›› ይባላሉ፡፡
– አንዳንዴም ላላ ያድርጉት፡- ‹‹ምኑን?›› አሉ፤ ይህ የደም ግፊትን ለማቆም የሚረዳ አመጋገብ ዘዬ ‹‹Dietary approaches to stop hypertension›› ለዕድሜ ልክ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን እጅግ ከሚወዷቸው ምግቦች ጨርሶ ይቆራረጡ ማለት አይደለም፡፡ አልፎ አልፎ ለአምሮት ያህል ከዚህ የአመጋገብ ስርዓት ውጪ የሆነ ከረሜላም ሆነ የተፈጨ ድንች ያለበት መረቅ ቀመስ ቀመስ ቢያደርጉ ክፋት የለውም፡፡

4. ሶድየምን ከምግብዎ ይቀንሱ
ሌላው ቀርቶ መጠኑ ትንሽ የሆነ ሶዲየም ከምግብዎ ሲቀነስ የደም ግፊትን ከ2-8 Millimeters of mercury ያህል ይቀንሳል፡፡
– በቀን ከ2300 ሚሊ ግራም በታች ሶዲየም ብቻ ይውሰዱ፡፡
– በተለይ ዕድሜያቸው ከ51 ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች፣ በየትኛውም የዕድሜ ክልል ለሚገኙ አፍሪካ- አሜሪካውያን፣ ከፍተኛ ደም ግፊት ላለባቸው እንዲሁም ደግሞ ስኳር እና ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ላለባቸው ሰዎች በቀን 1500 ሚሊ ግራም በላይ ሶዲየም እንዲመገቡ አይመከርም፡፡
ሶዲየም ለመቀነስ…
በምግብዎ ውስጥ ምን ያህል የጨው መጠን እንዳለ ይድረሱበት፡- የምግብ መዝገቡ በየዕለቱ ምግባችን እና መጠጣችን ውስጥ ምን ያህል ሶዲየም እንደተጠቀምን ለማወቅ ያግዛል፡፡
የታሸጉ ምግቦች የተለጠፈባቸውን ማስረጃ ያንብቡ፡- ከቻሉም የሶዲየም መጠናቸው አናሳ የሆነ ምግቦችን እና መጠጦችን መርጠው ይግዙ፡፡
ብዙም በምግብነት ሂደት ውስጥ ያሳለፉ ምግቦችን ይመገቡ፡- የድንች ጥብስ እጅግ የቀዘቀዙ ምግቦች፣ በእንፋሎት የደረቁ ስጋዎች እና የመሳሰሉት… በምግብነት ሂደት ባለፉበት መንገድ ከፍተኛ ሶዲየም ይይዛሉ፡፡
ጨውን ያስወግዱ፡- 1 የሻይ ማንኪያ ጨው 2300 ሚሊ ግራም ሶዲየም አለው፡፡ ለምግብዎ ጣዕም ለመስጠት ከጨው ይልቅ ቅጠላ ቅጠል እና ቅመማ ቅመሞችን ይጠቀሙ፡፡
ይመችዎት፡- በምንም ተአምር ሶዲየምን በአንድ ጊዜ ከምግብዎ ማስወገድ ካልቻሉ አይጨነቁ፣ በጊዜ ሂደት ሊጠፋ ይችላል፡፡ ጉሮሮዎትም ቢሆን ቀስ በቀስ ጣዕሙን ይለምደዋል፡፡

5. የሚወስዱትን የአልኮል መጠን ይቀንሱ
እርግጥ ነው አልኮል በጤና ላይ የራሱ የሆነ አዎንታዊ እና አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል፡፡ በጥቂቱ ከተወሰደ በተወሰነ መልኩ የደም ግፊትን የመቀነስ አቅም አለው፡፡ ከመጠን በላይ መውሰዱ ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናልና አይመከርም፡፡ ሴቶች እና ዕድሜያቸው 65ን የተሻገሩ ወንዶች በቀን 1 ብርጭቆ በቂ ሲሆን ዕድሜያቸው ከ65 በታች ለሆኑ ወንዶች 2 ብርጭቆ እንዳይዘሉ ይመከራሉ፡፡ አልኮልን የመጎንጨት ልማድ ፈፅሞ ከሌለዎ ግን ‹‹ደም ግፊቴን አስተካክላለሁ›› በሚል ምክንያት እንዳይሞክሩት፡፡ አደራ፡፡ ያንን ቢያደርጉ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናልና ኋላ ማጣፊያው እንዳያጥር፡፡ ከመጠን ካለፉም የደም ግፊትዎ ለመቸመሩ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከቱለት መሆኑን አይዘንጉ፡፡ የመድሃኒቶቹንም ፈዋሽነት አዳክሞ ለከፋ ጉዳትም ይዳርጋል፡፡
– የአጠጣጥ ልምድዎን ይቆጣጠሩ፡- (ይሄ ነገር ሜኑ መሰለ ካላሉ) ከምግብ መዝገብዎ ጎን ለጎን የመጠጥ ዝርዝርዎንም ቢያሰፍሩ ጤናማ አጠጣጥን ሊቀይሱ ይችላሉ፡፡ አንድ ጊዜ ሊጠጡ የሚፈልጉት ቢራ ከሆነ 355 ሚሊ ሊትር፤ ወይን ከሆነ ደግሞ 148 ሚሊ ሊትር ሌሎች የአልኮል ይዘት ያላቸውን ከ45 ሚሊ ሊትር በላይ የሚወስዱ ከሆነ ይቀንሱ፡፡
– ቀስ በቀስ ይቀንሱ፡- ከአልኮል በእጅጉ ተቆራኝተው ከነበረ በአንድ ጊዜ እርግፍ አድርጎ መተው ለቀናት የሚዘልቅ የደም ግፊትን ሊያስነሳ ይችላልና አቀናነሱ ብልሃት የተሞላበት እንዲሆን የባለሙያ እርዳታን ይሻል፡፡ ከሐኪምዎ ጋር በመመካከር ከቀን ወደ ቀን ከሳምንት ወደ ሳምንት በሂደት ይቀንሱ፡፡
– መጠንዎን አይለፉ፡- ከ4 ብርጭቆ በላይ አልኮል መጠጣት ለሌሎች የጤና ችግሮች ከማጋለጡ በተጨማሪም የደም ግፊትዎን ባልተጠበቀ እና ከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምረው ይችላልና አይሞክሩት፡፡
አያጭሱ፣ በአጫሾች ዙሪያም አይገኙ
ትንባሆ ሌሎች በርካታ ጉዳቶች እንዳሉት ሆኖ በውስጡ የያዘው ኒኮቲን የተባለ ንጥረ ነገር አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የደም ግፊትዎን ከፍ ያደርጋል፡፡ በተለይ በየቀኑ የሚያጨሱ የለየልዎት ከከፍታው ሳይወርድ ይቆያል፡፡
ብዙዎቻችን አለማጨሳችንን እንጂ ለሲጋራ ጭስ አለመጋለጣችንን ትኩረት አንሰጠውም፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ሲጋራ በሚጨስባቸው አካባቢዎች መገኘትም ከአጫሹ እኩል የኒኮቲን መጠንን ወደ ሰውነት ማስገባት ሊያስከትል ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ የደም ግፊትን እና የልብ ህመምን ጨምሮ ለሌሎች የጤና ችግሮች ሁሉ ያጋልጣል፡፡

7. ካፌይን ይቀንሱ
በቡና እና መሰል መጠጦች ውስጥ የሚገኘው ካፌይን የተባለው ንጥረ ነገር በደም ግፊት ላይ ያለው አስተዋፅኦ እስካሁን ድረስ አወዛጋቢ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ካፌይን ያለባቸውን መጠጦች መጠጣት የደም ግፊትዎን ለጊዜውም ቢሆን በአስደንጋጭ ሁኔታ ሊጨምረው ይችላል፡፡ አወዛጋቢው ነገር ይህ ተፅኖው ‹‹ለጊዜው ብቻ ነው?›› ወይስ ‹‹ለዕድሜ ልክ?›› የሚለው ነው፡፡
እርስዎ ይህንን ይሞክሩ እስቲ…
ቡና በጠጡ በ30 ደቂቃ ውስጥ የደም ደግፊትዎን ይለኩ፡፡ ቁጥሩ ከወትሮው ከ5-10 ጨምሮ ከተገኘ ካፌን ለደም ግፊትዎ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋልና ባያዘወትሩት ደግ ነው፡፡

8. ጭንቀትዎን ይቀንሱ
ጭንቀት ለጊዜውም ቢሆን የደም ግፊትን ይጨምራል፡፡ ምን ይሆን የሚያስጨንቅዎት? ስራ? ቤተሰብ? የንዘብ እጥረት? ወይስ ጤና ማጣት? እስቲ ጊዜ ወስደው ያስቡበት፡፡ አንዴ የጭንቀትዎ መንስኤ ምን እንደሆነ ካወቁት እንዴት መቀነስ ወይም ማስወገድ እንዳለብዎት ይረዳሉ፡፡ ያንን ማድረግ ካልቻሉ ግን ቢያንስ ችግሮቹን መቀበል እና በጤናማ መንገድ እንዴት አብሮ መቀጠል እንደሚቻል መላ ማበጀቱ አያቅትዎም፡፡ የጥልቅ አተነፋፈስ ልምምድ በማድረግ ፋታ ይውሰዱ፡፡ ማሳጅ ይደረጉ ወይም ዮጋ እና ተመስጥኦ ለዚህ ጥሩ መፍትሄ ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡ በዚህ መንገድ ራስን የመርዳቱ ሙከራ ካልተሳካ በሙያው የሰለጠኑ አማካሪዎችን መጎብኘት ያሻል፡፡

9. የደም ግፊትዎን ከቻሉ በቤትዎ ይቆጣጠሩ፤ በመደበኛነትም የሐኪም ክትትል ይኑርዎት
ከፍተኛ የደም ደግፊት ካለብዎት የደም ግፊትዎን በቤትዎ መቆጣጠር ሳያስፈልግዎ አይቀርም፡፡ በላይኛው የክንድ ክፍል የሚታሰረው መቆጣጠሪያም ጥቂት ቢማሩት የራስዎን ደም ግፊት ራስዎ ለመቆጣጠር የማያስቸግር ነው፡፡ ከሁሉ በፊት ግን ሐኪምዎን ያናግሩና ይጀምሩት፡፡ ምናልባት በቋሚነት ሐኪምዎን መጎብኘትዎ መደበኛ ክንውንዎ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ጉብኝትም የደም ግፊትዎ ያለበትን ደረጃ በግልፅ ለማወቅ እና ለመረዳት ይረዳዎታል፡፡
– በቋሚነት የሚከታተልዎት ሐኪም ይኑርዎት
እንዲህ ያለ ሐኪም የሌላቸው ሰዎች የደም ደግፊታቸውን መቆጣጠር አስቸጋሪ ሆኖ ያገኙታል፡፡ ቢቻል በቋሚነት አንድ የህክምና ተቋምና ሐኪም ለአስፈላጊው የጤንነት እንክብካቤ ቢጎበኙ ይመረጣል፡፡
– ሐኪምዎን በቋሚነት ይጎብኙ፡- የደም ግፊትዎ በአግባቡ በቁጥጥር ስር ካልዋለ፤ ተጓዳኝ ህመሞች ካሉብዎ በቋሚነት በየወሩ ሐኪምዎን ማግኘት ያስፈልግዎታል፡፡ የደም ግፊትዎን በአግባቡ መቆጣጠር ከቻሉ ደግሞ ከ6-12 ወራት ባሉት ጊዜ ውስጥ ቢጎበኙ በቂ ይሆናል፡፡ ይህ ታዲያ ባሉበት ሁኔታዎች ላይ የተወሰነ ይሆናል፡፡

10. ከቤተሰብ እና ከጓደኞች እርዳታ ይቀበሉ
በዙሪያዎ ያሉ ጓደኞች እና ቤተሰበቾች ለጤናዎ መሻሻል ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታሉና ችላ አይበሏቸው፡፡ ራስዎን እንዲንከባከቡ ሊያበረታትዎት፣ ሐኪም ዘንድ ሲሄዱና ሌሎች የደም ግፊትዎን ለመቀነስ በሚረዱ እንቅስቃሴዎች ሲያደርጉ አብሮዎት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስለ ህመሙ አስከፊነት መከላከያ እና መቆጣጠሪያ መንገዶችን መወያየትም ቀላል ነገር አይደለም፡፡

↧

Sport: “ምትሃተኛው!!”–በክርስቲያኖ ሮናልዶ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ የተዘጋጀ ልዩ የጽሁፍ ዶክመንተሪ

$
0
0

የውድድር ዘመኑ የጎል ሪከርድ ያስመዘገበበት፣ የዓለም ኮከብ የሚያስብለውን ‹‹የባሎን ዶር››ን ክብር የተጎናፀፈበት፣ ሀገሩ ፖርቹጋልን በዓለም ዋንጫ ላይ በአምበልነት የመራበት እና ክለቡ ሪያል ማድሪድ በቻምፒዮንስ ሊጉ ለ10ኛ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮን እንዲሆን ያስቻለበት ዘመን ነበር፡፡ በዚያች የፀደይ ዕለት ግን በማድሪድ ከተማ አንዳች ነገር አስከፍቶታል፡፡

በልምምድ ማዕከሉ ከሚገኘው ህንፃ ፎቅ ላይ ሆነው እንኳን ፊቱን ተመልክቶ ቅሬታውን ማስተዋል አያቅትም፡፡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ተከፍቷል፡፡ አንዳንድ የቡድን ጓደኞቹ ‹‹ኤልአንሲያ›› (ጭንቀታሙ) በሚል ቅጽል ያውቁታል፡፡ በዚያች ዕለት ንዴትና ጭንቀት ይታዩበታል፡፡ አንድ ያልተመቸው ነገር አለ፡፡ በፈጣን እግሮቹ ጭን ላይ ያሉት የጡንቻ ጅማቶች ጤነኛ አይደሉም፡፡ ህመም ይሰማዋል፡፡ እንደልብ የማያንቀሳቅስ እክል ቀስፎ ይዞታል…፡፡
cristiano-ronaldo-09
የሪያል ማድሪድ የልምምድ ማዕከል ከእንቅልፉ ነቅቷል፡፡ የሜዳውን ሳር ውሃ የሚያጠጡት ቧንቧዎች ገና መዘጋታቸው ነው፡፡ ባዶ የነበረው የማዕከሉ የመኪና ማቆሚያ በቅንጡ ስፖርት አውቶሞቢሎች ተጨናንቋል፡፡ ቱጃሮቹ ተጫዋቾች ለዕለታዊው ልምምዳቸው በማዕከሉ ተሰባስበዋል፡፡ የሮናልዶ የቡድን ጓደኞች 260 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ አላቸው፡፡ ጋሬት ቤል፣ አንሄል ዲ ማሪያ፣ ሰርጂዮ ራሞስ እና ማርሴሎ በልዩ እንክብካቤ በተያዘው አረንጓዴ ሜዳ ላይ ፈሰሱ፡፡ የውድድር ዘመኑ ማብቂያ ላይ ነው፡፡ ሪያል ማድሪድ የላ ሊጋው የመጨረሻ ጨዋታን መጫወት ይቀረዋል፡፡

ጥርት ባለው ሰማይ አዕዋፍ እንደ ሮኬት ከወዲያ ወዲህ ይተኮሳሉ፡፡ የማድሪድ የሰማይ አድማስ በግንባታ ክሬኖችና ባለመስተዋት ህንፃዎች ታጅቦ ይታያል፡፡ ልምምዱ ግን ለሁሉም ክፍት አይደለም፡፡ በኤሌክትሮኒክ ፍተሻ መሳሪያ ስር ያለፉ ጥቂቶች ብቻ የታደሙበት ዝግ ልምምድ ነው፡፡ ከተፈቀደለት ጋዜጠና ሌላ በልዩ ስምምነት በሪያል ማድሪድ አካዳሚ እንዲሰለጥኑ ከሩቅ ምስራቅ የመጡ ቻይናዊያን ወጣቶች በማዕከሉ ደርሰዋል፡፡ ሮናልዶ በሮጠ ቁጥር ጎረምሶቹ ስሙን ይጠራሉ፡፡ ኳስ ሲመታም ‹‹ሮናልዶን ተመልከተው›› እያሉ ያወራሉ፡፡ በመላው ዓለም እንደሚገኙት ታዳጊዎች ሁሉ እነዚህም ልጆች ሮናልዶ የሚያደርገውን ሁሉ በራሳቸው ለመስራት ይሞክራሉ፡፡ የፖርቹጋላዊው መለያ የሆኑትን አብዶዎች ይኮርጃሉ፡፡ የቅጣት ምት ዓመታት ልማዱን ይደጋግማሉ፡፡ ታዳጊዎቹ ስሜታቸውን ቢቆጣጠሩም ወጣቱን ኤልቪስ ፕሪስሌይ እንዳዩ ኮረዶች በደስታ መቁነጥነጣቸው አልቀረም፡፡

ሮናልዶ ለግማሽ ሰዓት ያህል ከቡድኑ ጋር ልምምዱን ሰራ፡፡ ግን ያለ እንከን መቀጠል አልቻለም፡፡ በድንገት በአንዱ ንስር አይን አሰልጣኝ እይታ ውስጥ ወደቀ፡፡ ወደ ሜዳው ጠርዝ ለይቶት በግራ እግር ጡንቻዎቹ ላይ የጤና ማረጋገጫ ሙከራዎች አደረገለት፡፡ በልምምድ የሚሰራ የጤና ምርመራ እንደማለት ነው፡፡ ለ15 ደቂቃዎች በዚሁ ሂደት ውስጥ አለፈ፡፡ ውጤቱ ግን አስደሳች አልነበረም፡፡ ሮኒ የግድ ልምምዱን ማቋረጥ አለበት፡፡

ካርሎ አንቾሎቲ በውዱ ልጃቸው ላይ ሪስክ መውሰድ አልፈለጉም፡፡ ለተባባሰ ጉዳት ከሚዳረግ ልምምዱን አቁሞ በህክምና ክትትል እንዲቆይ ይሻላቸዋል፡፡ እንዲህ አይነቱ አጋጣሚ የማዴይራውን ልጅ የሚያስደስት አይደለም፡፡ ከቡድኑ ገለል ብሎና ለምቦጩን ጥሎ ተቀመጠ፡፡ ሲያናግሩት እጁን በማወዛወዝ ይመልሳል፡፡ መጫወት ቢፈልግም ወደ መልበሻ ቤት ማምራት ዕጣው ሆነ፡፡ በሜዳ ላይ ሳይሆን በወጌሻ ወንበር ላይ ጊዜውን ለማሳለፍ ተገደደ፡፡

ለአንድ ሰዓት ያህል ያስጠበቀውን ጋዜጠኛ ያገኘው ከዚህ በኋላ ነው፡፡ ላቡን ለመታጠብ ሻወር ወስዶ ድብርታም ገጽታ ካላቸው አጃቢዎቹ ጋር በማዕከሉ አንደኛው የፕሬስ ክፍል ብቅ አለ፡፡ በዳይመንድ ሎቲው አጊጧል፡፡ እጅግ ተውቦ ለመታየት ፀጉሩን በቄንጥ አበጥሮ በጄል ሸብቦታል፡፡ በጆሮ ግንዱ አካባቢ ብቅ ያለው ፀጉሩ እንደ ጩቤ ጫፍ ስል መስሏል፡፡ ጃኮብ ኤንድ ኮ የተባለው እጅግ ውድ ብራንድ ሰዓቱ በእጁ አንጓ ላይ ያብረቀርቃል፡፡ ጀነን ብሎ ጥቂት ከተራመደ በኋላ ተቀመጠ፡፡

ሮናልዶ ራሱን በማስጌጥና ተውቦ ለመታየት ጊዜ የሚያጠፋ ሰው ስለመሆኑ ይነገርለታል፡፡ ኮራ ያለው ጉብል ግን በቀላሉ የሚሰበር ደካማ ጎን አለው፡፡ ነገሮች ባልፈለገው መንገድ ሲጓዙበት በብስጭት የሚሸነቁጥር ውስጣዊ ስሜት አለው፡፡ በዚያ ዕለት የተረጋገጠበት ጉዳት ከቀሪው የሪያል ማድሪድ ጨዋታዎችና ከብራዚሉ የዓለም ዋንጫዎች ውጭ ሊያደርገው እንደሚችል በመታወቁ ብስጭት ሁሉ ጓዙን ጠቅልሎ ሰፍሮበታል፡፡ ይህ ለመሆኑ ሌላ ማረጋገጫ አያስፈልግም፡፡ በ2009 ወደ ሪያል ማድሪድ ከመጣ ጊዜ ጀምሮ ሮናልዶ ለስፔኑ ዋና ከተማ ክለብ 240 ጎሎችን አስቆጥሯል፡፡ በእነዚህ የማድሪድ ዓመታት በእግርኳሱ ዓለም ያሉ ውድድሮችንና ዋንጫዎችን ከሞላ ጎደል አሸንፏል፡፡ በ2014 ብቻ ለሪያል ማድሪድ 51 ጊዜ ኳስና መረብን አገናኝቷል፡፡ እንዲህም ሆኖ ሮኒ ገና አልረካም፡፡ ወደ ፊትም የሚረካ አይደለም፡፡

ሮናልዶን በቅጡ የሚያውቁ ሰዎች ገና በመጎልበት ላይ ያለ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ራሱን ወደ ፍፁማዊ የብቃት ጠርዝ ለማድረስ የመትጋት ልክፍት ተጠናውቶታል፡፡ የስኬት ረሃቡም ፈፅሞ የሚጠግብ አይደለም፡፡ በዚህ አስተያየት ክርስቲያኖ ይስማማል፡፡ ‹‹ዘወትር ራሴን ለማሻሻል እሰራለሁ›› የሪያል ማድሪዱ ሰባት ቁጥር ይናገራል፡፡ ‹‹ከዛሬ ይልቅ ነገ የተሻልኩ ተጨዋች እሆናለሁ፡፡ ከዘንድሮ ይበልጥ ለከርሞ ተሽዬ እቀርባለሁ፡፡ ሰዎች በሜዳ ላይ ሲበዛ ኮስታራ እንደሆንኩና ፈገግታ እንደማይታይብኝ ይናገራሉ፡፡ ምክንያቴ መቶ በመቶ በስራዬ ላይ ትኩረት ማድረጌ ነው፡፡ ሁልጊዜ በቃኝ አላውቅም››
ሮናልዶን መሆን ቀላል ነገር አይደለም፡፡ የብቃት ጽንፍ ላይ ለመድረስ ያለው ትጋትና የክብሮችን ሁሉ ክብር የመጎናፀፍ ልክፍቱ ይደንቃል፡፡ ራስን የመውደድና ራስን የመተቸት ተቃራኒና ኃይለኛ ስሜቶች ተጣምረው ይታዩበታል፡፡ ‹‹ልዩ ውስጣዊ ጉልበት›› ብሎ በሚጠራው ስሜት ተገፋፍቶ ይሮጣል፡፡ በመላ የእግርኳስ ህይወቱ ለወጣበት እጅግ ከፍተኛ ዋጋ ብቁ ምላሽ መስጠቱን ከማሳየት ከባድ ትግል ጋር ግብግብ ሲፈጥር ኖሯል፡፡ ይህም በቀላሉ ስሜቱ የሚጎዳ፣ ድንጉጥና በስኬት ጊዜም ከልክ ባለፈ የሚደሰት ሰው አድርጎታል፡፡

አንዳንድ ጊዜ ሮናልዶ ምጡቅ ችሎታን እንዲያሳይ በሚወተውት የገዛ ስሜቱ የሚገፋ ይመስላል፡፡ ሁልጊዜም በተቻለው ሁሉ የላቀ ደረጃ ላይ ለመድረስ መድረሻውን ያስቀምጣል፡፡ ከዚያም ካሰበው ጣሪያ የላቀ ስሜት ያስመዘግባል፡፡ ብሪታኒያዊው የእግርኳስ ጋዜጠኛ ባርኒ ሮናይ እንደገለፀው ‹‹ሮናልዶ ሲጫወት በባለጋራ ተጨዋቾች ብቻ ሳይሆን በስታዲየሙ ታዳሚ ሁሉ ሳይቀር የሚሳደድ ይመስላል››
Ronaldo Christiano
ስለ ሮናልዶ ተሰጥኦ ታላቅነት ጥርጣሬ የለም፡፡ ከቀንደኛ ተፎካካሪው ሊዮኔል ሜሲ ጋር የዓለም ምርጡ ተጨዋች መሆኑ ማስረጃ የማይፈልግ እውነት ነው፡፡ ከእነ ፔሌ እና ማራዶና ጋር ከስፖርቱ ታሪካዊ ተጨዋቾች ተርታ ሊሰለፍም ይችላል፡፡ ሁሉን ብቃት ያሟላ ተጨዋች ነው፡፡ በሁለቱም እግሮቹ ተጋጣሚን ይገድላል፡፡ ጥበብ የተሞላበት ድሪብሊንጉ ይለያል፡፡ መረብ በጣሽ የጎል ሙከራዎቹ ኃይልና ጮሌነትን ደባልቀዋል፡፡ እንቅስቃሴው የተከላካዮችን ትኩረት ይበታትናል፡፡ ቅጣት ምቶቹ በግርምት አፍ ያስይዛሉ፡፡ ክፍተት ከሰጡት ፍጥነቱ ለንፅፅር አይቀርብም፡፡
‹‹የዘመኑ እግርኳስ በአካላዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ጥንካሬ፣ እና ኢንዱራንስ የላቀ ቦታ አላቸው›› ይላል የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን አማካይ ማይክል ብራድሌይ- በዓለም ዋንጫው ላይ ከፖርቹጋል ጋር ከመጫወታቸው ቀደም ብሎ፡፡ ‹‹ሮናልዶ ደግሞ እነዚህን ሁሉ ያሟላ ተጨዋች ነው፡፡ ስለ ቴክኒካዊ ተሰጥኦው ስታነሳ ደግሞ -የአየር ላይ በቃቱ- በማንኛውም ሰዓት ልዩነቱን መፍጠር የሚችል መሆኑን ትገነዘባለህ››

ብራድሌይ አልተሳሳተም፡፡ በጨዋታው 95ኛው ደቂቃ ላይ ሮናልዶ በሚሊ ሜትር መጥኖ ያሻገራት ኳስ ለፖርቹጋል ማሸነፊያ ጎል መገኘት ምክንያት ሆናለች፡፡ ‹‹ሮናልዶ ኳስ ይዞ ወደ ክንፍ ሲጠጋ ማየት ለተጋጣሚ ተከላካዮች የአደጋ ማስጠንቀቂያ ደወል ነው፡፡ የትኛውም ተከላካይ ሊያየው የሚወድ አጋጣሚ አይደለም›› ይላ የኢኤስፔኤኑ ኮሜንታተር እና የቀድሞው የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ አሌክሲስ ላላስ፡፡ ‹‹ይህ ሲሆን እኔም ትንፋሼን ዋጥ አደርጋለሁ፡፡ ምክንያቱም አንድ ምትሃታዊ አጋጣሚ ይፈጠር ዘንድ የሚጀምረው ከዚያ ነውና››
አሰልጣኝ ጆዜ ሞውሪንሆ ለሮናልዶ አድናቆት ለማግኘት ከዚህ ዓለም ወጥተዋል፡፡ ‹‹እነርሱ ከሌላ ፕላኔት ነው፡፡ እኔ ካሰለጠንኳቸው ተጨዋቾች ሁሉ እንደ ክርስቲያኖ በተሰጥኦ የታደሰ አላየሁም›› ብለውታል፡፡ የማንችስተር ዩናይትዱ የቀድሞው አሰልጣኝ ደግሞ ‹‹ምትሃተኛው›› ሲሉ ይገልፁታል፡፡ ‹‹እርሱ ሲጫወት መመልከት ፕሌይስቴሽን ጌምን እንደመጫወት ይቆጠራል›› ያለው ደግሞ የቶተንሃሙ አጥቂ አማኑኤል አዴባየር ነው፡፡

የሮናልዶን የእግርኳስ ህይወት በማናጀርነት የመራው የተጨዋቾች ወኪል ጆርጌ ሜንዴዝ የኮከቡን ህይወት ሲገልፅ ከአንድ ኢንጂነሪንግ ፕሮጀክት ጋር ያመሳስለዋል፡፡ ‹‹ለመጪዎቹ 500 ዓመታት ክርስቲያኖ ሮናልዶ መሳይን ለመገንባት ፈፅሞ የማይቻል ነው›› ሲል ይተነብያል፡፡
የሮናልዶ ብቃት ባለፈው ኖቬምበር ወር በስቶክሆልም ከተማ በይለብጥ ተገልጧል፡፡ ለዓም ዋንጫ ለማለፍ የመጨረሻ ማጣሪያ ጨዋታ ፖርቹጋል ስዊድንን ገጠመች፡፡ የባለሜዳው ቡድን ደጋፊዎች ‹‹ሜሲ! ሜሲ!›› እያሉ ይጮሁ ነበር፡፡ ሮናልዶን ለማበሳጨት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ እርሱ ግን አልተሸበረም፡፡ በሶስት ድንቅ ጎሎቹ ተበቀላቸው፡፡ ሁለተኛው ጎል ሲያስቆጥር ወደ መሬት እየጠቆመ ‹‹እነሆኝ!›› አላቸው፡፡ የስዊድን የዓለም ዋንጫ ህልምም ቅዠት ሆኖ ቀረ፡፡

‹‹ምርጥ እንድትሆን በስራህ ላይ ትኩረት ማድረግ አለብህ›› ይላል ሮናልዶ፡፡ ‹‹አዕምሮህን ማሰልጠን በጣም አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ሽንፈት ሽንፈት መስሎ አይሰማህም፡፡ በራስህ የምትተማመን ከሆነ መረጋጋትህን የሚያውክ ነገር አይኖርም፡፡ ጠንክረህ በሰራህና ራስህን ለስራህ ባስገባህ ቁጥር ይበልጥ በራስህ ትተማመናለህ››

ከስፖርታዊ ክህሎቱ በተጨማሪ ሮናልዶ በመሮ የተቀረፀ የሚመስል ሰውነት ባለቤት ነው፡፡ አካላዊ ቅርፁና ውበቱ ስፖንሰሮችን ምራቅ ያስውጣል፡፡ በሞዴልነቱ መስክም ክርስቲያኖ ሌላው ዴቪድ ቤካም ነው፡፡ ሮናልዶ ታላቅ ስፖርተኛ ብቻ አይደለም፡፡ ታላቅ ስፖርተኛ ሊኖረው የሚገባ አካል ተምሳሌትም ጭምር እንጂ፡፡ በእግርኳሱ ዓለም እጅግ ታዋቂውና ተወዳጁ ተጨዋች ሲሆን ናይኪ፣ ሳምሰንግ፣ ሄርባልላይፍን ከመሳሰሉት ግዙፍ ኩባንያዎች ጋር ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው የስፖንሰርሺፕ ኮንትራት አለው፡፡ ዓመታዊ ገቢውን 73 ሚሊዮን ዶላር ያደረሱትም እነዚሁ ስምምነቶቹ ናቸው፡፡ ‹‹በህዝብ መካከል ከብዙ ተጨዋቾች ጋር ዞሬያለሁ፡፡ የሮናልዶ ያህል ድጋፍ ጩኸት የሰማሁበት ግን የለም›› ይላል የቢኢን ስፖርት የእግርኳስ ኮሜንታተር ሬይ ሃድሰን፡፡ ‹‹መነኩሴዎችን ሳይቀር ሊያስጮህ የሚችል ሰው ነው›› ሲል የኮከቡን ተወዳጅነት ይገልፀዋል፡፡ በእንስቶች የመወደዱን ያህል ህይወቱ በልቅ ግንኙነት የተሞላ አይደለም፡፡ ከእውቋ ራሺያዊት ሱፐር ሞዴል ኢሪና ሻይክ ጋር በፍቅር ተጣምሯል፡፡

የሮናልዶን የታይታ ህይወት የማይወዱለት ወገኖች የሉም ማለት አይቻልም፡፡ እዩኝ እዩኝ የሚለው ባህሪዩን የሚጠሉለት ብዙ ናቸው፡፡ በሜዳ ላይ በንዴት አኩርፎ መታየቱን፣ ብሎም ማልቀሱ የጥላቻቸው ምክንያት የሆነላቸውም አሉ፡፡ ቅንጡ ጌጣጌጡንና ብርቅርቅ ፎቶግራፎቹን በደስታ ያልተቀበሉም አይጠፉም፡፡ ነገር ግን ከተቺዎቹ መካከል ለራሱ ባለው ከፍ ያለ ግምት ምክንያት የጠሉት ይበዛሉ፡፡

በራሱ ምስል ያጌጡ የቅልጥም መከላከያዎችን ያደርጋል፡፡ 7 ቁጥሩ ማሊያው ምትሃታዊ ኃይል አለው ብሎ ያምናል፡፡ ከዲዛይነር ሪቻርድ ቻይ እና ከዴንማርኩ የቡቲክ ብራድ ጂቢኤስ ጋር በመተባበር በራሱ ስም ያመረተው ሙታንታ አለው፡፡ ላ ፊንቻ በተሰኘው የማድሪድ ከተማ ባለፀጋዎች ሰፈር በሚገኘው ቤቱ ውስጥ ወንበርና ጠረጴዛው ሳይቀር ‹‹ሲአር 7›› የተሰኘው የግል ብራንዱ ያረፈባቸው መሆኑ ተዘግቧል፡፡ በአንድ ወቅት እርሱን ሲመለከቱ ሰዎች ስለምን እንደሚጮሁ ተጠይቆ ‹‹ቆንጆ፣ ታዋቂና ሃብታም በመሆኔ ስለሚቀኑ ነው›› ሲል የሰጠው መልስ አስተችቶታል፡፡ ባለፈው ዓመት ዲሴምበር ወር ላይ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ 540 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የትውልድ ደሴቱ ማዴይራ ፉንቻል ከተማ የራሱን መታሰቢያ ሙዚየም ከፍቷል፡፡ በማዕከሉም ‹‹በሲአር7›› ብራንድ የተሰሩ ቁሳቁሶች፣ በግል በቡድን ያሸነፋቸው ዋንጫዎች፣ ፊርማው ያረፈባቸው ማሊያዎች እና ኳሶች ሁሉ ተሰብስበው ለእይታ ተቀምጠውበታል፡፡ በስሙ የተቀረፀ የተጫዋቹ ሀውልት ሳይቀር እዚያ ይገኛል፡፡ በተለያዩ ስፖርቶች ላይ የተሳካላቸው ከዋክብት የዋንጫ መሰብሰቢያ ሙዚየሞችን መስራታቸው የተለመደ ቢሆን ክርስቲያኖ ግን ለየት አድርጎታል፡፡ በራሱ መንገድ እየተጓዘ እንደ አርማታ የጠነከረ በራስ መተማመን ገንብቷል፡፡ ‹‹እናቴ ሁል ጊዜ ራሴን መስዬ እንድኖር እየመከረች አሳድጋኛለች፡፡ ይህን ባህሪዬን ሰዎች ሊወዱትም ሆነ ሊጠሉትም ይችላሉ፡፡ ችግር የለውም፡፡ለእኔ ግን ጠንካራ ሰብዕና እንዲኖረኝ አግዞኛል›› ይላል ሮናልዶ፡፡

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ዶ ሳንቶስ አቬዬሮ ከእግርኳስ ጋር በፍቅር የወደቀው የእሳተ ገሞራ ኮረብቶች በበዙባት ፉንቻል ከተማ ነው በሜዴይራ ደሴት፡፡ ወላጆቹ የቀድሞው አሜሪካው ፕሬዝዳንት ሮናልድ ሬገን አድናቂ በመሆናቸው ለአብራካቸው ክፋይ ስሙን አውጥተውታል፡፡ ከደሃ ቤተሰብ የተገኘ ሲሆን ታዳጊው ሮናልዶ ያደገው በደሳሳ ጎጆ ከሁለት ልጆች ጋር በጋራ በሚጠቀምባት አንድ ክፍል ውስጥ ነበር፡፡ ዕቃ ለማስቀመጫ በቂ ቦታ ስላልነበር የልብስ ማጠቢያ ማሽናቸውን በቤቱ ጣሪያ ላይ እስከማኖር ደርሰዋል፡፡ እናቱ ዶሎሬስ የጽዳት ሠራተኛ፣ አባቱ ዲኒስ ደግሞ አትክልተኛ ነበሩ፡፡ አባት በመጠጥ ሱሰኝነትና በእግርኳስ አፍቃሪነታቸው ይታወቁ ነበር፡፡

በወላጆቹ አበረታችነት ትንሹ ክርስቲያኖ በመኖሪያ ቤታቸው ዙሪያ በተገኘው ጠባብ ቦታ እግር ኳስን መጫወት ጀመረ፡፡ እግሮቹ የፉትቦልን ጥበብ ማዳበርን የጀመሩት በዚህ ጊዜ ነበር፡፡ ለትንሹ ልጅ የኳስ ፍቅር ደንቃራ የሆነ አንድ ሰው ቢኖር ሚስተር አጎስቲኖ ይሰኛል፡፡ ሰውዬው በልጆች ቅሪላ የአትክልት ቦታው እየተበላሸ ቢቸግረው አንድ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ወደ አትክልት ቦታው የገባ ኳስ ሁሉ ለባለቤቱ ከመመለስ ይልቅ ተቀዶ ይጣላል፡፡ የሚስተር አጎስቲኖ ነገር ሮናልዶን አንድ አብይ ትምህርት አስተማረው፡፡ ያለማቋረጥ ኳስን ለመጫወት ሲል ስህተት መፈፀም የለበትም፡፡ ተሳስቶ ኳስ ወደ አትክልት ቦታው ከገባች ያበቃላታልና፡፡

በፉንቻል የታዳጊዎች ውድድር ላይ ክሪስቲያኖ ተለይቶ ለመታየት ጊዜ አላስፈለገውም፡፡ አባቱ የቡድኑ ትጥቅ ያዥ ነበሩ፡፡ የመጫወቻ ትጥቆችን ከመያዙም በተጨማሪ ክርስቲያኖን ለክብር ያዘጋጁታል፡፡ ያን ጊዜ በሜዳ ላይ ለሚያሳየው ጉልበተኛ አጨዋወት ሰዎች ‹‹አቤሊንሃ›› ብለው ይጠሩት ነበር፡፡ ‹‹ትንሹ ንብ›› እንደማለት ነው፡፡ ለመሸነፍ ፈጽሞ ዝግጁ አልነበረም፡፡ ቡድኑ ካላሸነፈ ወይም የቡድን ጓደኛው ኳስ ካልሰጠው ያለቅሳል፡፡ 12 ዓመት ሲሞላው ደሴቲቷን ለቅቆ በስፖርቲንግ አካዳሚ ሙከራ ላይ ሊገኝ ወደ ሊዝበን በረረ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን የተጓዘው በዚያች ዕለት ሲሆን ከቤተሰብ ናፍቆትና በጉዞው ላይ በነበረው የበረራ ጩኸት ምክንያት አልቅሷል፡፡

የወደፊቱን ኮከብ እምቅ ብቃት ለማወቅ ግን ደጋግሞ ማየት አስፈላጊ አልነበረም፡፡ ገና ከጅምሩ በሙከራው ላይ የነበረው አሰልጣኝ ‹‹ኧረ ይሄስ ልጅ ይለያል›› ሲል ለሌላው ባልደረባው በጆሮው ላይ አንሾካሾከ፡፡ ጊዜ ሳይፈጅ ክርስቲያኖ ሜዴይራን ተሰናብቶ ሊዝበን የሙሉ ሰዓት መኖሪያው ሆነች፡፡ በመጀመሪያ ላይ የደሴቲቱ ህዝቦች የሚያወሩበት የንግግር ቅላፄው ለሌሎች ሰልጣኞች ቀልድ ምክንያት ሆኖ ነበር፡፡ ‹‹ገና ለመናገር አፌን ከመክፈቴ›› ይላል ሮናልዶ ‹‹ሞመንትስ›› በተሰኘው የግል ማስታወሻ መጽሐፉ ላይ ዘመኑን ሲያስታውስ፡፡ ‹‹ልጆቹ ይስቃሉ፣ ያሾፋሉ፡፡ እኔም ሞኛሞኝ የሆንኩ ያህል ይሰማኛል››

ህይወት በሊዝበን አልተመቸችውም፡፡ ከቤተሰብ ርቆ መኖር ለክርስቲያኖ ፈተና ሆነ፡፡ ናፍቆት ሁሉን ሊያሳጣው ቀረበ፡፡ ኳሱን ትቶ ጠቅልሎ ወደ ማዴይራ እስከ መመለስ ድረስ አሳሰበው፡፡ በተደጋጋሚ በዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ቢቃረብም ጨክኖ አላደረገውም፡፡ ደጋግሞ ማልቀስ ግን ሥራው ሆነ፡፡ የ14 ዓመት ልጅ ሳለ በመምህሩ ላይ ወንበር ወርውሮ ከትምህርት ቤት በመባረሩ ሙሉ ትኩረቱን በእግር ኳሱ ላይ አደረገ፡፡ ደግሞ ደጋግሞ ልምምዱን ይሰራል፡፡ በክለቡ ውስጥ ዝናው እያደገ ሄደ፡፡ የ17 ዓመት ልጅ ሳለ የመጀመሪያ ፕሮፌሽናል ጨዋታውን ተጫወተ፡፡ ለስፖርቲንግ ሊዝበን የመጀመሪያ ጎሉን ሲያስቆጥር እናቱ ከልክ ባለፈ ከመደሰታቸው የተነሳ የህክምና እርዳታ አስፈልጓቸዋል፡፡

የማንቸስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ አሌክስ ፈርጉሰን ለልጁ ችሎታ ትኩረት ሰጡ፡፡ ካዩዋቸው ወጣት ተጨዋቾች ሁሉ እጅግ የተደነቁበት ሆነ፡፡ ስለዚህ በተጠየቀው ተመን ሊያስፈርሙት ቆረጡ፡፡ ለእኩዮቹ ተከፍሎ በማያውቅ 12 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ ኦልድትራፎርድ አመጡት፡፡ ወደ እንግሊዙ ክለብ ሲዛወር ክርስቲያኖ የጥርሱን ብሬስ አልጣለም፣ ፊቱም ከመጥፎ የቆዳ በሽታ ጋር በተያያዘ ከመጣ ብጉር አልፀዳም ነበረ፡፡ ፈርጉሰን ግን በችሎታው ተማመኑ፡፡ በማንቸስተር ዩናይትድ ታሪክ ከፍ ያለ ቦታ የሚሰጠውን የክዋክብቱን 7 ቁጥር ማሊያ አለበሱት፡፡ በጆርጅ ቤስት፣ ኤሪክ ካንቶና እና ዴቪድ ቤካም ቦታ ሌለው ባለጊዜ ተተካ፡፡ ‹‹7 ቁጥር ማሊያን መልበስ›› ይላል ሮናልዶ ‹‹ክብርና ታላቅ ኃላፊነት ነው››

ኦገስት 16 ቀን 2003 ክርስቲያኖ ሮናልዶ በኦልድ ትራፎርድ የመጀመሪያውን ጨዋታ አከናወነ፡፡ ሰር አሌክስ በግለ ታሪክ መጽሐፋቸው ላይ እንዳሰፈሩትም ‹‹ደጋፊዎች አዳኝ እንደመጣላቸው ወዲያውኑ ተረዱ፡፡ ልዩ ተሰጥኦውም ሳይውል ሳያድር ታወቀ››

ሮናልዶ ግን ያልተጠረገ አልማዝ ነበር፡፡ በሜዳ ላይ የሚያሳያቸው አንዳንድ የጨዋታ ባህሪያት አሰልጣኙን ሊያስደስቱት አልቻሉም፡፡ ይጮሃል፤ ከኳስ ጋር አላስፈላጊ ጊዜ ያባክናል፡፡ ለታታ የሚሆኑ አብዶዎችን ለመፈፀም ይሞክራል፡፡ ይህ በፈርጉሰን አይን ተገቢ ያልሆነና ውጤታማም አይደለም፡፡ ምን ያህል ጥሩ ተጨዋች መሆኑን ለህዝብ ለማሳየት የሚያደርገው ጥረት የማደጊያው መንገድ አልነበረም፡፡ ሰር አሌክስ ሊገሩት ተነሱ፡፡ ሮናልዶም ደካማ ጎኑን እየጣለና ጠንካራውን ጎኑን እያጎለበተ በመሄዱ ላይ አተኮረ፡፡

የማንቸስተር ዩናይትድ ህይወቱ ተጀምሮ የዝናውን መንገድ እንደጀመረ በግል ህይወቱ ሀዘን ገጠመው፡፡ ለእግርኳስ ስኬቱ ብዙ የለፉት አባቱ በሞት ተለዩት፡፡ ዲኒስ በጉበት በሽታ ለህልፈት ሲበቁ የ20 ዓመቱ ሮኒ ልብ በሀዘን ተሰበረ፡፡ የአባቱ ሞት በህይወቱ የማይሽር ጠባሳ ትቶ አለፈ፡፡ በግለ ማስታወሻ መጽሐፉ ላይም እንዳሰፈረው እስካሁንም ድረስ ያልሻረ ቁስል ፈጥሮበታል፡፡ የአባቱን ጤና ያቀወሰውና በኋላም ለህልፈት ያደረሰ በመሆኑ ሮናልዶ እስካሁንም አልኮል እንደማይጠጣ ይናገራል፡፡ ‹‹አባቴ አሁንም በህይወት ያለና አብሮኝ ያለ ያህል ይመስለኛል፡፡ አስበዋለሁ፡፡ እንዴት እንደሆነ ልገልፀው ባልችልም እስካሁን ድረስ አንዳንድ ጊዜ ምክሩን እሰማለሁ››
ሀዘኑ ጥሎት ያለፈው ቀዳዳ በብዙ መልኩ በሰር አሌክስ ተሞልቷል፡፡ 7 ቁጥሩ በማንቸስተር ዩናይትድ በቆየባቸው ሰባት ዓመታት አጨዋወቱን አጎልብቷል፣ በስሏል፡፡ በርካታ ጎሎችን አስቆጥሯል፡፡ ክለቡ ተደራራሚ ዋንጫዎችን እንዲያነሳ አስችሎታል፡፡ በግሉም በ2008 የመጀመሪያውን ባሎን ዶሩን አግኝቷል፡፡ የሮናልዶ ታላቁ ጥንካሬ አዕምሮውና የትኛውንም አይነት ተጋጣሚ ከኳስ ጋር መጋፈጥ መሆኑን ሰር አሌክስ ተገነዘቡ፡፡ ‹‹ጉብዝና በተለያዩ መልኮች ይገለጣል፡፡ (የሮናልዶ አይነቱ የአዕምሮ ጉብዝና) ግን እጅግ ምርጡ ነው፡፡ በግንብ አጥር መሀል የሚሮጡ ሰዎች፣ ከባድ ሸርተቴዎችን ተጋፍጠው የሚጫወቱ፣ ጭንቅላታቸው ተፈንክቶ ትግላቸውን የማያቆሙ ተጨዋቾች አሉ፡፡ ሁል ጊዜ ኳስን ይዞ ለመሄድ የሚያስችል ድፍረት ግን ከሁሉም የላቀው ጉብዝና ነው››

ከፍ ያለ የስኬት ደረጃ ላይ ለመድረስ እንደሚመኝ ማንኛውም ወጣት በመጨረሻ ሮናልዶ የአባት ያህል ከሆኑለት ሰው መለየት ነበረበት፡፡ በ2009 ማንቸስተር ዩናይትድ ከሪያል ማድሪድ የቀረበለትን 133 ሚሊዮን ዶላር ለመቀበልና ኮከቡን ልጁን ወደ ስፔን ለመላክ ተስማማ፡፡ በወቅቱ ለአንድ የእግርኳስ ተጨዋች ዝውውር ያን ያህል ገንዘብ ተከፍሎ አያውቅም፡፡ ከዚያ ዋጋ ጋር ቢመጣም ሮናልዶ የተጠበቀውን ያህል ከመሆን ያገደው ነገር አልነበረም፡፡ ጎሎችን በጎሎች ላይ ማዝነቡን ቀጠለ፡፡ የበለጠው ሮናልዶ በሪያል ማድሪድ ማሊያ ታየ፡፡ ለሪያል የመጀመሪያ የውድድር ዘመን 33 ጎሎችን አገባ፡፡ በቀጣዩ ዓመት 55፣ ከዚያም 55…፡፡

የሮናልዶ የሪያል ማድሪድ ህይወት የስኬት ጣሪያን የነካው ባለፈው ግንቦት በሊዝበን የከተማ ተቀናቃኛቸውን አትሌቲኮ ማድሪድን ድል በማድረግ ቻምፒዮንስ ሊግን ሲያሸንፉ ነበር፡፡ ሮናልዶም ሪል ማድሪድን ለፍፃሜ ለማብቃት 16 ጎሎች አግብቷል፡፡ በውድድሩ ላይ ያሳየው ብቃት አድናቆት የሚያንሰው ነበር፡፡ በፍፃሜውም ጨዋታ ውጤቱ 3-1 ሳለ ወደ መጨረሻ በፍፁም ቅጣት ምት አንድ ጎል አስቆጥሯል፡፡ ጎሉ የተለየ ትርጉም ባይኖረውም ሮናልዶ ማሊያውን በማውለቅ፣ ጡንቸውን በማሳየትና እንደ ሃልክ ሆገን ኃይል የተሞላበትን የደስታ አገላለፅ ከጩኸት ጋር በማሳየት መወያያ ርዕስ ፈጥሯል፡፡ ትዕይንቱ ጥንካሬውንና አንዳንድ ሰዎች የማይወዱለትን የእዩኝ እዩኝ ባህሪውን በአንድ ጊዜ ያሳየበት ትክክለኛው የሮናልዶ መገለጫ ነበር፡፡ ሪያል ማድሪድ የአውሮፓ ሻምፒዮን በሆነበት ምሽት ከእርሱ በቀር ንጉስ በዚያ ስታዲየም ውስጥ አልነበረም፡፡

ሊጋን የሚከታተሉ ባለሙያዎች ሮናልዶ ወደ ሪያል ማድሪድ ከመጣ ወዲህ እንደ ተጨዋች ብቻ ሳይሆን እንደሰውም እጅጉን መጎልበቱን ይመሰክራሉ፡፡ በማንቸስተር ዩናይትድ ሳለ አብረውት ከነበሩት መጥፎ ልማዶቹ ብዙዎቹ ተወግደዋል፡፡ የተጫዋቹ የረጅም ጊዜ ፊዚዮቴራፒስት አንቶኒዮ ጋስፐር ‹‹ሮናልዶ የላቀ ስፖርተኛና በሜዳ ላይም እውነተኛ መሪ ሆኗል›› ይላል፡፡ ‹‹መሻሻሉን ሳይ እደሰታለሁ፡፡ አሁንም ጠንካራ እና ፈጣን ነው፡፡ የቴክኒክ ችሎታው አስደናቂ ቢሆንም ከቀድሞ የበለጠ በብልጠት ይጫወታል፡፡ ጠንካራ ጎኖቹን በተሻለ ሁኔታ የመተቀም ብስለትንም አዳብሯል›› በማለት የማዴይራውን ልጅ ይገልፀዋል፡፡ አካላዊ ብቃቱና ተሰጥኦው የብቃት ጣሪያን በነኩበት ሰዓት ላይ ይገኛል፡፡ በኢስፔኤን ቴሌቪዥን በላ ሊጋ ላይ የሚሰራው ግራሃም ሃንተር በበኩሉ ‹‹የላቀ ክህሎት የተፈጥሮ ስጦታ ሳይሆን የጥረት ውጤት መሆኑን ያሳየ ስፖርተኛ ሆኗል›› ባይ ነው፡፡

በእርግጥ ከዚህ በተቃራኒ አንዳንዶች የሮናልዶ በራስ መተማመንና በፍፁምነት ጽንፍ ላይ ለመድረስ ያለው ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ላይ ለመድረስ ያስቻለው ስለመሆኑ ይከራከራሉ፡፡ ‹‹ፍፁም ለመሆን የሚያደርገውን ጥረት ያቆመ ዕለት ብቃቱ ማሽቆልቆል ይጀምራል›› ይላል የቢኢን ስፖርቱ ሃድሰን፡፡ ‹‹በውስጡ ለሚቀጣጠለው የስሜት እሳት ነዳጁ እብሪቱ ነው፡፡ ለስኬት የሚያተጋውን ውስጣዊ ኃይል ያባብስለታል፡፡ ጫና ታላላቅ ተጨዋቾችን ሳይቀር ያጠፋል፡፡ ሮናልዶ ግን እንደ አልማስ ሃብሉ ለብሶት ተላምዶታል››

በሪያል ማድሪድ የክርስቲያኖ ህይወት በልዩ የተፎካካሪነት ስሜትም የሚገለፅ ነው፡፡ በዚሁ ዘመን እግርኳስ ሌላውን አብሪ ኮከብ አግኝቷል፡፡ ‹‹ቁንጮው›› በሚለው ቅጽል የሚታወቀው ሊዮኔል ሜሲ ከሮናልዶ የተለየ አካላዊ ተፈጥሮ፣ የጨዋታ ዘይቤና ሰብዕና ያለው ተጨዋች ነው፡፡ የባርሴሎናው አጥቂ በክለብ እግርኳስ ላይ ባለ ተፅዕኖ ሲሆን ሮናልዶ በብቃቱ ልቆ እንዳይታይ የራሱን የፉክክር ጥላ አጥልቶበት አራት ጊዜ ባሎን ዶርን በተከታታይ አሸንፏል፡፡ የሜሲን የበላይነት ሰብሮ ልቆ መገኘትም የሮናልዶ አላማ ሆኖ ቆይቷል፡፡

አሁን ሮናልዶ ከሜሲ ጋር መነጻፀሩ ሰልችቶታል፡፡ ስለ ንፅፅሩ ሲጠየቅ ‹‹እኔ የምወዳደረው ከሜሲ ጋር አይደለም፡፡ ከራሴ ጋር እንጂ›› የሚል ምላሽ ይሰጣል፡፡ ‹‹ከሌሎች ጋር ከመፎካከር ይልቅ በራሴ ጨዋታ ላይ ማተኮርን እመርጣለሁ››

የሮናልዶ የሜዳ ላይ ብስለት ከሜዳ ውጭም ባለው ህይወቱም ይበልጥ ይደፋል፡፡ ዛሬ ክርስቲያኖ የልጅ አባት ነው፡፡ ጁላይ 3 ቀን 2010 ሮናልዶ በፌስቡክና በትዊተር ገፆቹ ላይ አዲስ ዜና አስነበበ፡፡ የወንድ ልጅ አባት መሆኑ ደስተኛ እንዳደረገው ገለፀ፡፡ የሮናልዶን ዙሪያ ለሚከታተሉ ዜናው ፈጽሞ ያልተጠበቀ ነበር፡፡ ሳይታሰብ ይፋ የሆነው መረጃ ግን ጥያቄን ማስከተሉ አልቀረም፡፡ ዕድለኛዋ ሴት ማን ትሆን? የፍቅር ጓደኛው ኢሪና ሻይክ ነፍሰ ጡር ሆና አልታየችም፡፡ ታዲያ የልጁ እናት ማን ናት? ተባለ፡፡

ሮናልዶ ‹‹ምስጢሩን ለእኔ ተዉት›› ቢልም ዓለም ዝም ማለትን አልመረጠም፡፡ ታብሎይድ ጋዜጦች የተለያዩ መረጃዎችን እየመዘዙ ዘገቡ፡፡ የህፃኑ ስነ ህይወታዊ እናት ካልሆነች ሴት በማህፀን ኪራይ ብቻ የተወለደ ነው የሚለው መረጃ አንደኛው ነው፡፡ በአንድ ምሽት ድንገተኛ ወሲብ የተረገዘ ነው የሚለው ሌላኛው ጥርጣሬ ነው፡፡ ለዚህ መረጃ እንደ ማጠናከሪያ የሚቀርበው እናት በድጋሚ ልጄ ብላ መብቷን እንዳትጠይቅና ማንነቷን ይፋ እንዳታደርግ በስምምነት አፍ ማስያዣ ከተጨዋቹ 10 ሚሊዮን ፓውንድ ተቀብላለች መባሉ ነው፡፡ በ2007 ባሳተመው መፅሐፉ ለይ በጋብቻ ከመተሳሰሩ በፊት የልጅ አባት የመሆን ምኞት እንዳለው ገልጿል፡፡ ‹‹ወንድ ከሆነ እኔኑ እንዲመስል እመኛለሁ፡፡ ተመሳሳይ የመልክ ቅጂ እንዲሆን ሳይሆን እንደኔ የእግርኳስ ዘረመል በውስጡ ያለው መሆን ይኖርበታል፡፡ መመሳሰሉ በቀላሉ የሚለይ እንዲሆንም እፈልጋለሁ›› ብሏል፡፡

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ጁንየር ዛሬ አራት ዓመት ሞልቶታል፡፡ ሪያል ማድሪድ የላሊጋውን የመጨረሻ ጨዋታ ባከናወነበት ዕለት ልጁ በሳንቲያጎ ቤርናቢዩ የመስታወት ትሪቡን ተቀምጦ በሜዳ ላይ አባቱ ያልተሰለፈበትን ጨዋታ ተመልክቷል፡፡ በዲዛይነሮች በተሰሩ የህፃናት ልብሶች ዘንጦና ፀጉሩንም በዘይቤ ተበጥሮ አስተናጋጆች ጭማቂዎችንና የኢቤሪያን ሳንድዊች በሚያቀርቡበት ትሪቡን ወዲያ ወዲህ ሲል ታይቷል፡፡ በዕለቱ ልጁን የመጠበቁ ኃላፊነት ለሮናልዶ እና ዶሎሬስ የተተወ ጉዳይ ነበር፡፡ ልጁ አባቱን ይመስላል፡፡ ሮናልዶም ለል የተሰጠ ሰው ነው፡፡ ‹‹አባትነት እጅግ ደስ የሚል ነገር ነው›› ይላል፡፡ ቀጥሎም ‹‹ልጄ ዘወትር ደስታን ይሰጠኛል፡፡ ዘወትር ህልምን የመኖር ያህል ነው›› በማለት የትንሹ ሮናልዶ ወደዚህ ዓለም መምጣት በህይወቱ ላይ የጨመረለትን ዋጋ ይገልፃል፡፡

በዙሪክ ስዊዘርላንድ አንድ ብርዳማ ምሽት ብራዚላዊው ፔሌ ከተሰበሰቡ እንግዶች ፊት በመድረክ ላይ ቆመ፡፡ የ2014 ፊፋ ባሎን ዶር ሽልማት ስነ ስርዓት ነበር፡፡ የብራዚል እግርኳስ ፓትሪያክ በመድረኩ ላይ የተገኘው የዓመቱን የዓለም የእግር ኳስ ኮከብ አሸናፊን ሊናገር ነው፡፡ በተጠናቀቀው የካሌንደር ዓመት የላቀ ብቃት ያሳየ ተጨዋች ይሸለማል፡፡ ፔሌ ኤንቬሎፑን ሲከፍት የቴሌቪዥን ካሜራዎች በሶቱ ዕጩዎች ፊት ላይ አረፉ፡፡ ፍራንክ ሪቤሪ፣ ሊዮኔል ሜሲና ክርስቲያኖ ሮናልዶ፡፡ የፖርቹጋሉ ኮከብ ፍቅረኛውን ከጎኑ አድርጎ በልዩ ሙሉ ልብስ ዘንጧል፡፡ የፔሌ ድምፅ ተሰማ፡፡ ‹‹…ክርስቲያኖ ሮናልዶ››
ሮናልዶ ኢሪናን ሳመና ከመቀመጫው ተነስቶ ፔሌን ለማቀፍ ወደ መድረኩ አመራ፡፡ ከዚያ ዘናጭ ልጁ ወደ መድረኩ ተከተለው፡፡ ሮናልዶ ከእንባ ጋር እየታገለ ‹‹ሁላችሁንም አመሰግናለሁ›› አለ፡፡ በአይኑ ላይ እንጥፍጣፊ እብሪት እንኳን አልቀረም፡፡ ትህትና እና ብስለት ቦታቸውን ይዘዋል፡፡ ድምፁ በስሜት እንቅፋት ይቆራረጣል፡፡ ቤተሰቡን አመሰገነ፡፡ እናት በኩራት ፊታቸውን በመረሃረብ ሲጠራርጉ እንኳን አይኖቻቸውን ከልጆቻቸው አልተነቀለም፡፡ ሮናልዶ ሽልማቱን ሁሉም እንዲያየው ከፍ አደረገው፡፡ የወርቅ ኳሱ የኋላ ማረፊያው በፉንቻል በሚገኘው የግል ሙዚየሙ መሆኑ እርግጥ ነበር፡፡ ‹‹እኔን የሚያውቁ ሰዎች ሁሉ ስንት ሰዎች እንደረዱኝ ያውቃሉ፡፡ የረሳሁት ካለ ይቅርታ እጠይቃለሁ››

የሜሲ ዘመን (ቢያንስ ለዘንድሮ) ፍፃሜ ለማግኘቱ የታወጀ አዋጅ ነበር፡፡ ህይወት ግን በ2013 ብቻ አትገደብም፡፡ ፉክክሩ ይቀጥላል፡፡ በቅርቡም የ2014 15 ላሊጋ ይጀምራል፡፡ ‹‹ጭንቀታሙ›› ሮናልዶም ‹‹ከቁንጫው›› ጋር ባላንጣነቱን ያድሳል፡፡ አሁንም ከሜሲ በላይ ሆኖ ለማጠናቀቅ የብቃትን ፅንፍ ለመጨበጥ ይተጋል፡፡

↧

የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት 400 ሰዎች በተገደሉበት የጋምቤላ ጭፍጨፋ የሕወሓት ባለስልጣናት መሳተፋቸውን አጋለጡ

$
0
0

የቀድሞው የጋምቤላ መሪ በክልሉ ለደረሰው ጭፍጨፋ የህወሃት ባለስልጣናትን ተጠያቂ ማድረጋቸውን ኢሳት ዘገበ። የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ ኦሞት ኦባንግ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ 400 ሰዎች የተገደሉበት የጋምቤላው ጭፍጨፋ እንዴት እንደተከናወነ በዝርዝር ሁሉን ነገር ተናግረዋል።
omot obang
እንደ ኦሞት ገለጻ የህወሃት ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ አባይ ፀሐዬ ግድያውን በተመለከተ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል ያሉ ሲሆን በክልሉ ስለሚፈጸመው ሙስናና የመሬት ወረራ የቀድሞው ባለስልጣን በዝርዝር በዝርዝር ተናግረዋል።

የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኦሞድ ወደ ውጭ ከወጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሰጡት በተነገረው በዚህ ቃለምልልሳቸው ላይ 400 ሰዎች በግፍ በአባይ ፀሐዬ ከፍተኛ ሚና መገደላቸውን መዘርዘራቸው ወደፊት በነዚህ ባለስልጣናት ላይ ለሚከፈተው ክስ ጥሩ ምስክር ሊሆን ይችላል ተብሏል።

↧

የዘ-ሐበሻ አንባቢያን የዓመቱ ምርጥ ሰው ይፋ ሆነ

$
0
0

ነጻነት፣ ፈጣሪ ለሰው ልጆች ሁሉ በነጻ የሰጠን ገጸ በረከት ነው። ነገር ግን በአገራችን ኢትዮጵያ፣ ጥቂቶች፣ የያዙትን መሳሪያና ያላቸዉን ጡንቻ በመጠቀም፣ ነጻነታችንን ሰርቀዉን፣ በባርነትና በፍርሃት እንድንኖር አድርገዉናል። ከፍርሃት የተነሳ ብዙዎቻችን ከአገር ተሰደናል። ብዙዎቻችን በአገራችን እንደ ሁለተኛና ሶስተኝ ዜጎች ተቆጠረን፣ አንገታችንን ደፍተን፣ በሉ የምናብለውን እያልን፣ ሰልፍ ዉጥ ስንባል ሰልፍ እየወጣን፣ ከፍቃዳችን ዉጭ የጥቂቶችን ፍላጎት ብቻ እየፈጸምን የምንኖር አለን። በፍርሃት ተተብትበንና በጥቅም ታስረን።
person of the year
በሌሎች ትግልና መስዋእትነት ነጻነታችንን ማግኘት የምንፈልግ ጥቂቶች አይደለንም። ነጻነትን ፈልገናት፣ ግን ለነጻነት የሚከፈለዉን ዋጋ ለመከፈል ፍቃደኝነት አይታይብንም። ከታሰርንበት ፍርሃት ለመላቀቅ አልቻልንም።
ነገር ግን ከመቼውም ጊዜ የበለጠ፣ የፍርሃትን ቀንበር በመስበር፣ ለራሳቸው ነጻነትን አዉጀው፣ ለሌሎች መብት የተሰለፉ ብዙ አኩሩ ልጆችን ኢትዮጵያ እያፈራች ነው። እስራትን፣ እንግልትን የማይፈሩ፣ ለአገራቸዉን ለሕዝባቸው መስዋእትነት ለመክፈል የተዘጋጁ፣ ጠመንጃና ጥይት ሳይዙ ጀግንነት ምን ማለት እንደሆነ ያስመሰከሩ ልጆች !

ከነዚህ አኩሪ የኢትዮጵያ ልጆች መካከል፣ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር የሆነው፣ ታዋቂው ጦማሪ፣ ወጣት አብርሃ ደስታ ይገኝበታል። ወጣት አብርሃ ፣ ከሕወሃት አፍንጫ ሥር ሆኖ ፣ ብዙዎች ያላወቁትንና ያላዩትን፣ በትግራይ ባሉ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለዉን ግፍና ጭቆና ሲታግልና ሲያጋልጥ የነበረ ወጣት ነው። ብዙ ጊዜ በሕወሃት ካድሬዎች ተደብድቧል። ተሰድቧል። ዛቻና ማስፈራራት ደርሶበታል። ነገር ግን አብርሃ አልተበገረም። አንዳንዶች እንደሚያደርጉት፣ የሕወሃት አባልና ካድሬ ሆኖ በግሉ የተለየ ጥቅም ሊያገኝ ይችል ነበር። በጥቅም ሊደልሉት ሞክረዋል። ነገር ግን ራስ ወዳድ አልሆነም። ከግል ጥቅም ይልቅ የአገርን እና የሕዝብን ጥቅም አስቀደመ። የህዝቡን ብሶት እያነሳ ጮኸ።

አገራችን ኢትዮጵያን ትልቅ ስጋት ላይ ከጣሉት ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል አንዱ፣ በሕወሃት/ኢሕአዴግ የተዘረጋው የዘር ፖለቲካ ነው። አገዛዙ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ አማራ … እያለ ዜጎችን በመከፋፈል ፣ አንዱን ከአንዱ ጋር በማጣላት፣ ለብዙ ወገኖች እልቂትና መፍናቀል ምክንያት ሆኗል። አብርሃ ደስታ « ብሄሬ(ዘሬ) ኢትዮጵያዊነት ነው» በሚል ዜጎችን በዘራቸው ሳይሆን በስራቸው ብቻ መመዘን እንዳለባቸው የሰበከ፣ በነአጼ ዮሐንስ እና ራስ አሉላ አባ ነጋ መንፈስ፣ የኢትዮጵያዊነትን ደውል ያቃጨለ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጅ ነው።

ሐሳብ፣ ጽሁፍን መመከት የማይችሉ፣ የጫካ ፖለቲካ የሚያራምዱ ሕወሃቶች ግን ፣ ትችቶችን ተቀብለው ማሻሻያዎችን ከማድረግና የሕዝብ ጥያቄ ከማዳመጥ ይልቅ፣ እንደለመዱት የሚቃወሟቸውን መጨፍለቅ መረጡ። ሐምሌ አንድ ቀን 2006፣ አብርሃ ደሳታን እየደበደቡ አሰሩት። ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ማእከላዊ ወሰዱት። በሽብርተኝነት ክስ ከሰሱት። ፖሊስ «መረጃ እስካሰባሰብ» ብሎ የ28 ቀን ቀጠሮ ጠየቀ። «ፍርድ ቤቱ» ግን መረጃ ሳያይ፣ የፖሊስን ጥያቄ ተቀበሎ፣ የአብርሃን የዋስታና መብት ረግጦ፣ ለነሐሴ 29 ቀጠሮ ሰጠ። በቀጠሮ ቀን፣ አሁንም ፖሊስ ማስረጃ ያቀርባል ተብሎ ሲጠብቅ እንደገና ተጨማሪ 28 ቀን መረጃ ለማሰባሰ ጠየቀ። ፍርድ ቤቱ እንደገና ሁለተኛ ቀጠሮ ለመስከረም 22 ሰጠ። አብርሃ ደሳታ፣ ምንም አይነት መረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ ይኸው ፣ በማእከላዊ እሥር ቤት እየማቀቀ ይገኛል።

አብርሃ ደስታ ሊታሰር እንደሚችል ያውቅ ነበር። ነገር ግን የዜጎችን የነጻነት ጥያቄ፣ ጥቂቶች አፍነው ማቆየት እንደማይችሉ በመረዳቱና፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች፣ ምሳሌ አግኝተው፣ ይበረታቱ የዘንድ፣ የትግል ቁርጠኝነትን ያሳየው።
የኢትዮጵያን ትንሳኤ ለማየት፣ እንደ አብርሃ ደስታ ያሉ በየክልሉና በየቦታው በብዛት መነሳታቸው አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት፣ ኢትዮጵያዉያን ሁሉ በያለንብት የአብርሃ ደስታን ፈለግ ተከትለን፣ ለሕግ የበላይነት ፣ ለሰብአዊ መብት መከበር፣ ለነጻነት፣ ለኢትዮጵያነት እንቆም ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን። ላባረከተው ትልቅ አስተዋጾ፣ ላሳየው ቁርጠኝነት፣ ከአንባቢያኖቻችንም ብዙ ባገኘው ብዙ ድምጽ መሰረት፣ አብርሃ ደስታን የ2007 የዘ-ሐበሻ አንባቢያን የዓመቱ ሰው መሆኑን ስናሳወቅ በታላቅ አክብሮት ነው።

በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የምንኖር ኢትዮጵያዉያን ሁሉ መልካን እንቁጣጣሽ እየተመኘን ፣ 2007 የለወጥ፣ የሰላም፣ የነጻነት አመት እንዲሆንልን ምኞታችንን እንገልጻለን።

↧
↧

የዘ-ሐበሻ አንባቢያን የዓመቱ ምርጥ ሰው መምህር አብርሃ ደስታ ሆነ (የ36ቱን እጩዎች ዝርዝር ይዘናል)

$
0
0

person of the year
(ዘ-ሐበሻ) እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን። የዘ-ሐበሻ አንባቢያን ከሦስት ዓመት በፊት መምህር የኔሰው ገብሬን የዓመቱ ምርጥ ሰው ሲሉ በ2004 ዓ.ም መርጠው ነበር። ቀጠሉና በ2005 ዓ.ም የዓመቱ ምርጥ ሰው አድርገው የሰየሙት እድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት የሚገኘውውን አንዷለም አራጌን ነበር። ዘንድሮም እንዲሁ ዘ-ሐበሻ ለአንባቢዎቿ የአመቱን ምርጥ ሰው ምረጡ በሚል ባቀረበችው መጠይቅ መሰረት የተለያዩ ምርጥ ታጋይ ኢትዮጵያዉያን የአንባቢዎቻችንን ድምጽ አግኝተዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ መራጮች በሰጡት ድምጽ መሰረት ለአመቱ ምርጥ ሰውነት የታጩት የሚከተሉት ናቸው።

1ኛ. ቴዲ አፍሮ
2ኛ. አበበ ገላው
3ኛ. ታማኝ በየነ
4ኛ. አብርሃ ደስታ
5ኛ. ጥሩነሽ ዲባባ
6ኛ. መሠረት ደፋር
7ኛ. ሔኖክ ዓለማየሁ
8ኛ. አንዷአለም አራጌ
9ኛ. እስክንድር ነጋ
10ኛ. አንዳርጋቸው ጽጌ
11ኛ. ሌንጮ ለታ
13ኛ. ጄነራል ከማል ገልቹ
14ኛ. ታጋይ ሞላ አስገዶም
15ኛ. ርዕዮት ዓለሙ
16ኛ. አቡበከር አህመድ
17ኛ. ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ
18ኛ. ኃይለማርያም ደሳለኝ
19ኛ. ካፒቴን ኃይለመድህን አበራ
20ኛ. ሊያ ከበደ
21ኛ. የሺዋስ አሰፋ
22ኛ. በቀለ ገርባ
23ና ኦልባና ሌሊሳ
24ኛ. ፕ/ር ተካልኝ ማሞ
25ኛ. ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
26ኛ. ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም
27ኛ. ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ (በወህኒ ቤት ያረፉ)
28ኛ. ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት
29ኛ. ዶ/ር መረራ ጉዲና
30ኛ. ሃብታሙ አያሌው
31ኛ. የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ምዕመናን
32ኛ. ኦባንግ ሜቶ
33ኛ. ቴዎድሮስ አድሃኖም
34ኛ. በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵዮጵያውያን
35ኛ. ጃዋር መሐመድ
36ኛ. እና ሌሎችም

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ገልሰቦች ድምጽ ያግኙ ኢትዮጵያውያን ሲሆኖ ክነዚህ ውስጥ 624 ድምጾችን ያገኘው ታዋቂው ታጋይና በአሁኑ ወቅት በእስር ቤት የሚገኘው አብርሃ ደስታ ነው። ከሱ በመቀጠል ተቀራራቢ ድምጽ ያገኘው ታጋይ በወያኔ እስር ቤት የሚገኘው አንዳርጋቸው ጽጌ ነው። 601 ድምጾችን ያገኘው አንዳርጋቸው ጽጌ በቀጣይ ሲቀመጥ 534 የሚሆን ድምጽ ያገኘው ደግሞ ታጋይ ሃብታሙ አያሌው ነው። የዓመቱ ምርጥ ዘፋኝ የሚለውን የአንባቢዎቻችንን ክብር ያገኘው ቴዲ አፍሮ ሲሆን 369 ድምጾችን አግኝቶ ከሌሎች አርቲድቶች የተለየ ሆኗል።

ጥቂት ስለ አብርሃ ደስታ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

↧

ኢህአዴግ የመልካም አስተዳደር ችግር በማንም የማይላከክ ነው አለ

$
0
0

በ  አሸናፊ ደምሴ

eprdfባለፉት ሃያ ሶስት ዓመታት ውስጥ የተጓዝኩባቸው የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ መንገዶች ውጣ ውረድ የበዛባቸው ናቸው የሚለው ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ፤ በተለይም የመልካም አስተዳደር ችግሮቼ በማንም ላይ አይላከኩም ሲል ላለፉት ሁለት ሳምንታት በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ለሚማሩ ተማሪዎች በመንግሥት ፖሊሲና ስትራቴጂ ሥልጠና ላይ ባሰራጨው ሰነድ ጠቆመ።

በሐምሌ 2006 ዓ.ም ታትሞ ለተማሪዎች በተበተነውና “የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ትግላችንና ፈተናዎቹ” በሚል የቀረበው ሰነድ የመልካም አስተዳደር ችግሮቹን ተከትሎ ትምክህትና ጠባብነት፤ የሃይማኖት አክራሪነትና የዚህ ሁሉ መንስኤ የሆነው አለአግባብ የመጠቀም ዝንባሌ የሥርዓቱ አብይ ፈተናዎች መሆናቸውን ገልጿል።

“የህዝቡን መሠረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ እየወደቅን እየተነሳን ነው” ያለው ፅሑፉ፤ ከደረስንበት የእድገት ደረጃን ከህዝቡም ፍላጎት አንፃር ሲታይ ገና ብዙ እንደሚቀረውም ይጠቁማል። በተለይም በከተሞች አካባቢ ከህዝቡ የሚነሱትን ጥያቄዎች በየደረጃው ባሉ አመራሮች በጊዜና በፍጥነት ውሳኔዎች አለመስጠታቸው፤ በዚህም የልማት እንቅስቃሴዎች መጓተታቸውና በቂና አሳማኝ ምላሽ የመስጠት ችግሮች መኖራቸውን እንደማሳያ ጠቅሷል። አክሎም ዜጎች በመንግስት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ያለአንዳች አድልኦና መጉላላት መጠቀም ሲችሉና ሲገባቸው አላስፈላጊ አድልዎና ውጣ ውረድ ያጋጥማቸዋል ሲል በሰነዱ ላይ ያትታል።

በሰነዱ እንደተጠቀሰው ዜጎች ከመንግሥት ማግኘት የሚገባቸውን ተገቢ አገልግሎቶች ባለማግኘት እጅ መንሻ ከሚጠየቅባቸውና ችግር አለባቸው ተብለው ከተጠቀሱት ተቋማት መካከል የኤሌክትሪክ፣ የቴሌኮም፣ የውሃና የመንገድ አገልግሎቶች በምሳሌነት በሰነዱ ተጠቅሰዋል። በመጨረሻም ሰነዱ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን በተመለከተ ህዝቡ በስርዓቱ ላይ እምነት እንዲኖረው በየጊዜው የሚያማርርባቸውን ችግሮች በየጊዜው በአስተማማኝ ሁኔታ መቅረፍ ይገባል፤ ሲል ምክረ ሃሳብ አቅርቧል።

ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ለተውጣጡ ተማሪዎች በመንግሥት ፖሊሲና ስትራቴጂ ዙሪያ የተሰጠው የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ባሳለፍነው ቅዳሜ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ በቀጣዩ መስከረም 2 ቀን 2006 ዓ.ም ደግሞ ሁለተኛ ዙር ሥልጠና እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል።

↧

የአመት በዓል ገበያ በአዲስ አበባ – (የዶሮ፣ የበግ፣ የሽንኩርት፣ የቂቤ…. ዋጋዎችን ይዘናል)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የዘ-ሐበሻ የአዲስ አበባ ዘጋቢዎች እንደሚናገሩት ከሆነ የዘንድሮው አዲስ ዓመት በዓል ገበያን የዋጋ ውድነቱ አቀዝቅዞታል። በአዲስ አበባ የተለያዩ የገበያ ቦታዎች እየተዟዟሩ ገበያውን የተመለከቱት ዘጋቢዎቻችን እንደሚሉት አንድ ከትንሽ ትልቅ በግ ከ1500 እስከ 3000 ብር ድረስ የሚሸጥ ሲሆን ዶሮ ከ150 ብር እስከ 200 ብር ድረስ እንደሚሸጥ ዘግበዋል።
???????????????????????????????
doromarket
ቂቤ እስከ 180 ብር ድረስ እየተሸጠ እንደሚገኝ የነገሩን ዘጋቢዎቻችን ሽንኩርት በኪሎ ከ12 ብር ጀምሮ ይሸጣል ብለዋል። ቲማቲም በኪሉ ከ12 ብር ጀምሮ ዘይት በሊትር ከ60 ብር ጀምሮ የሚሸጡ ሲሆን የቃሪያ ገበያ በእጅጉ እንደናረ ነግረውናል። 5 ፍሬ ቃሪያ እስከ 5 ብር ድረስ እንደሚሸጥ የዘገቡት የዘ-ሐበሻ ወኪሎች ለወጥ የሚሆን ሥጋ በኪሎ ከ120 ብር ጀምሮ፣ ለቁርጥ የሚሆን ሥጋ ከ200 ብር ጀምሮ እንደሚሸጥ ዘግበዋል። በተጨማሪም ፍየል ከ5 ሺህ ብር ጀምሮ የሚሸጥ ሲሆን ምስር ክክ በኪሎ ከ30 ብር ጀምሮ ይሸጣል ብለውናል።

↧

Art: የድፍረት ፊልም ድፍረት –አበራሽ በቀለ ስንት ጊዜ ትደፈር?

$
0
0

በድንበሩ ስዩም

ልክ የዛሬ ሣምንት ነሐሴ 28 ቀን 2006 ዓ.ም ከ10 ሰዓት ጀምሮ ብሔራዊ ቴአትር ቤት አካባቢ በከፍተኛ የፀጥታ ቁጥጥር ስር ዋለ። በቁጥጥር ስር የዋለበት ምክንያት “ድፍረት” የተሰኘ ፊልም ስለሚመረቅ በዚህም ምረቃ ላይ ባለሥልጣናት፣ አምባሳደሮችና ታላላቅ ሰዎች ለመታደም ወደ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ስለተጓዙ ነው። እነዚህ ሁሉ ትልልቅ ስብዕናዎች ወትሮም ባልተለመደ ሁኔታ ለድፍረት ፊልም እንዲህ ከያሉበት ነቅለው መምጣታቸው ራሱ አነጋጋሪ ነገር ነበር። ምክንያቱም ፊልም ስለሚወዱ ነው ወይስ በሌላ ምክንያት እያልኩ ሳሰላስል ነበር። ብቻ ቴአትር ቤቱ ከተለመደው ሁኔታ ለየት ባለ መልኩ በእጅጉ ደምቋል። ቀይ ምንጣፍ ተዘርግቷል። ቆነጃጅት ሞዴልስቶች እንግዶችን ሲቀበሉ ቆዩ። አዳራሹ ሞላ። ታዳሚዎች ቦታቸውን ያዙ። ያ በጉጉት የሚጠበቀው ድፍረት ፊልም ሊጀመር ሆነ።
Art1470
ይህን ድፍረት የተሰኘውን ፊልም ፕሮዲዩስ እንዳደረገችው የሚነገርላት በአለማችን ላይ እጅግ ዝነኛ ከሆኑት የፊልም ተዋናይቶች መካከል በግንባር ቀደምነቷ የምትታወቀው አንጀሊና ጆሊ ነች። አንጀሊና የድፍረት ፊልም ኤግዝኪቲቭ ፕሮዲውሰር ወይም አንጡረ ገንዘቧን አውጥታ ያሰራች ነች ተብሎ ሲነገር ቆይቷል። ስለዚህ ፊልሙ በባለቤትነት የአንጀሊና ጆሊ ነው ተብሎ ይታሰባል። የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር ደግሞ ኢትዮጵያዊው ዘረሰናይ ብርሃኔ መሀሪ ነው።

ስለዚህ የአንጀሊና ጆሊ ስም እና ዝና በአለም ላይ የናኘ በመሆኑ ድፍረት የተሰኘ ፊልም ፕሮዲዩስ አደረገች እየተባለ በመነገሩም የፊልሙ ስምም እንደዚያው ገነነ። የተለያዩ ሁለት አለማቀፍ ሽልማቶችንም አገኘ ተባለ። በየድረ-ገፁ ሰፊ ሽፋን ተሰጠው።
የዚህ ፊልም ርዕሰ ጉዳይ ደግሞ የኢትዮጵያ ጉዳይ በመሆኑ አያሌ ኢትዮጵያዊያንም ሊመለከቱት ወደዱ፤ ናፈቁ። ለዚህም ነው ፊልሙ በሀገሩ ኢትዮጵያ ለመታየት ቀነ ቀጠሮ የተያዘለት። በዚህ ቀን አንጀሊና ጆሊ እና ባለቤቷ ብራድ ፒት ይመጣሉ ተብሎ ወሬ የተናፈሰ ቢሆንም በመጨረሻም ሁለቱም ከያኒዎች አልመጡም። ለዚህ ደግሞ የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር በሰጠው መልስ ኢቦላን ፈርተው ነው ያልመጡት ብሏል።

ነሐሴ 28 ቀን 2006 ዓ.ም በብሔራዊ ቴአትር ቤት ይህን ፊልም ለመመረቅ ከ1200 ታዳሚያን በላይ ቁጭ ብለዋል። የፊልሙ ባለቤት አንጀሊና ጆሊ ከምትኖርበት ከዩናይትድ ስቴትስ በስካይፒ ለብሔራዊ ቴአትር ቤት ታዳሚያን በድምጿ መልዕክት እያስተላለፈች ነው። ይህን ያልተነገረለት የኢትዮጵያ ታሪክ እዩት እያለች ተረከች። መልካሙንም ተመኘችልን። በመጨረሻም ያ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ድፍረት ፊልም ተጀመረ። ትንሽ እንደተጓዘ ድንገት ፊልሙ ቆመና ጨልመው የነበሩት የአዳራሹ መብራቶች በሩ። ያልተለመደ ሁኔታ ስለነበር ሁሉም ድንግጥ አለ። የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር ዘረሰናይ ወደ መድረኩ መጣ። ምን ሊናገር ነው ተብሎ ሲጠበቅ አንድ ያልተለመደ ጉዳይ ተናገረ። “ፖሊሶች መጥተው ፊልሙ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ታግዷል ብለዋል። ስለዚህ እዚህ ላይ ማቋረጥ እንገደዳለን። ነገሮች ሲስተካከሉ በሌላ ጊዜ እንገናኛለን” ብሎ ይቅርታ ጠይቆ ታዳሚውን አሰናበተ።

ብዙ የተወራለት፤ በየቦታው በሽልማት መንበሻበሹ የተነገረለት ድፍረት ፊልም የከፍታ ጣሪያ ላይ ከወጣ በኋላ ድንገት ሽምድምድ አለ። ለመሆኑ ፊልሙ ለምን ታገደ? ከድፍረት ፊልም በስተጀርባ ምን ችግር አለ? የሚሉትን ነጥቦች ለማየት እሞክራለሁ።

ድፍረት የተሰኘው ይኸው (የአንጀሊና ጆሊ) ፊልም የታሪኩ መሠረት እና የጀርባ አጥንት ወይም የታሪኩ እስትንፋስ የሆነው የዛሬ 18 ዓመት እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተ አንድ አስገራሚ ታሪክ ነው። ታሪኩ ሙሉ በሙሉ እውነት ነው። ድፍረት ፊልምም የዚህን እውነተኛ ታሪክ ሁኔታ ነው ወደ ፊቸር ፊልምነት ቀይሮት የሰራው። ታሪኩ እንዲህ ነው።

የዛሬ 18 ዓመት አንዲት አበራሽ በቀለ የምትባል የ14 ዓመት ታዳጊ ወጣት አርሲ ውስጥ ቀርሳ በምትባል ከተማ ከቤተሰቦቿ ጋር ትኖር ነበር። አንድ ቀን ወደ ትምህርት ቤት ደብተሯን ይዛ ስትሔድ ድንገት በፈረሰኞች ትከበባለች። ከዚያም በፈረሳቸው ላይ አፈናጠዋት ይዘዋት ይነጉዳሉ። ሰዋራ ቦታ ወደሚገኝ ቤት ያስገቧትና ከፈረሰኞች መካከል አንደኛው የ14 ዓመቷን አበራሽን ይደፍራታል፤ ክብረ-ንፅህናዋን ይወስዳል። አበራሽም በማታውቀው ሰው እንደተጠለፈች ትገነዘባለች። ይህ ሰው በተደጋጋሚ የወሲብ ጥቃት ይፈፅምባታል። አበራሽ በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ በዚያች ቤት ትቆያለች። በመጨረሻም ከዕለታት በአንዱ ቀን ታግታ ከምትደፈርበት ቤት ታመልጣለች። ስታመልጥ ደግሞ በቤት ውስጥ ያገኘችውን ጠመንጃ ይዛ ነበር። ታዲያ ባመለጠችበት ሰዓት ጠላፊዎቿ ነቁ። እንደገና ሊይዟት ወደ አበራሽ በቀለ ዘንድ መሮጥ ጀመሩ። እሷም እንዳይዟት ለማምለጥ እግሬ አውጭኝ እያለች ትበራለች። እነሱም እንደሚታደን አውሬ ያዛት እያሉ ይከተላሉ። በመጨረሻም ድጋሚ ሊይዟት፤ ሊጠልፏት ተቃረቡ። አበራሽ በቀለ ስንት ጊዜ ትጠለፍ? ስንት ጊዜ ትደፈር? ስንት ጊዜ ካለ ፍላጎቷ፣ ካለ ፈቃዷ ትጠቃ? አበራሽ ከዚህ ጉድ የሚያላቅቃት አንድ አማራጭ በእጇ አለ። ጠመንጃ! ቆም አለች። በእጇ ላይ ያለውን ጠመንጃ ሊይዛት ወደተቃረበው ሰው ላይ ተኮሰች። ሊይዛት የነበረው ሰው ወደቀ። ሕይወቱም አለፈች። ያ ሰው የጠለፋት፣ ያለፍላጎቷ የደፈራት፣ ክብረ-ንፅህናዋን የገሰሰው ሰው ነበር። አበራሽ በቀለም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለች።

ከዚያም የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ይህን ጉዳይ ሰማ። ማህበሩ ለአበራሽ በቀለ ጥብቅና ቆመ። ከብዙ ጊዜ ክርክር በኋላ አበራሽ ነፃ ወጣች። ነፃ የወጣችበት ምክንያት ራሷን ለመከላከል በወሰደችው እርምጃ ነበር።

ይህ ከላይ የሰፈረው ታሪክ እውነተኛው የአበራሽ በቀለ ታሪክ ነው። ወደ ዝርዝሩ ስንገባ አበራሽ በቀለ ብዙ መከራ የደረሰባት የ14 ዓመት ጉብል ነበረች። ከምትኖርበት ቀርሳ እስከ ዛሬ ድረስ በስደት ነው ተሸሽጋ ያለችው። አበራሽ አሳዛኟ የዚህ ማህበረሰብ አካል ነች። የመደፈርን እጣ ፈንታ ተሸክሜ አልኖርም ብላ ለህሊናዋ ነፃነትና አርነት የቆመች የሴቶች ተምሳሌት ነች።

የዚህችን ልጅ ሙሉ ታሪክ የዛሬ 15 ዓመት አለማቀፉ ቴሌቭዥን ጣቢያ BBC የ50 ደቂቃ ግሩም የሆነ ዶክመንተሪ ፊልም ሰርቶ ለአለም አሰራጨው። አበራሽ ከ15 ዓመታት በፊት ከገጠሯ ቀርሳ ተነስታ የአለም ህዝብ የመነጋገሪያ አጀንዳ የሆነች የጥቃትና የነፃነት አርአያ ሆነች። የBBCቴሌቭዥንም በሰራው School Girl Killer በተሰኘው ዶክመንተሪ ፊልም ምክንያት ለአበራሽ በቀለ ድጋፍና እርዳታ ያደርግላት እንደነበር ባለታሪኳ ራሷ ሰሞኑን በሬዲዮ ፋና አዲስ ጣዕም ተብሎ በሚጠራው የሬዲዮ ዝግጅት ክፍል ከ18 ዓመታት በኋላ መግለጫ ሰጥታለች።
አሁን ደግሞ ወደ መነሻችን እና ዋና ርዕሰ ጉዳያችን ወደሆነው ድፍረት ፊልም እንምጣ። ድፍረት የተሰኘው ፊልም ታሪኩ የተፃፈውና ዳይሬክት የተደረገው በዘረሰናይ ብርሃኔ መሀሪ ነው። “በዚህ ፊልም ውስጥ ያለው ታሪክ ሙሉ በሙሉ የኔ ነው። የኔን ታሪክ ሳያስፈቅደኝ ፊልም ሰርቶበት ማሳየት አይችልም። እኔ በታሪኩ ምክንያት ላለፉት 18 ዓመታት ተሸሽጌ ነው የምኖረው። በከፍተኛ ችግር ውስጥ ነኝ። እንደገና ካለኔ እውቅና ታሪኬ ፊልም ሆኖ ሲወጣ የተረሳው ነገር ደግሞ መነጋገሪያ ሆነ። እኔን በበቀል የሚፈልጉኝ የሟች ቤተሰቦች አሉ። ይሔ ፊልም ደግሞ ደህንነቴም እንደገና አደጋ ላይ እንዲወድቅ ያደርገኛል” የሚል ሃሳብ ያለው ንግግር በአዲስ ጣዕም የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ስትናገር ተደምጣለች።

በዚህ ምክንያትም ፍርድ ቤት ከሰሰች። ፍርድ ቤቱም ፊልሙ ለህዝብ እንዳይታይ፣ እንዳይመረቅ የእግድ ትዕዛዝ ሰጠ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነው ከብሔራዊ ቴአትር ቤት የምረቃ ስነ-ሥርዓት ላይ ድፍረት ፊልም እንዲቆም የተነገረው። እናም ድፍረት ቆመ። ታገደ።
የድፍረት ፊልም ደራሲና ዳይሬክተር ዘረሰናይ ብርሃኔ መሀሪ ለአዲስ ጣዕም አዘጋጅ በሰጠው መግለጫ ይህ ታሪክ የአበራሽ ብቻ አይደለም። የብዙ የኢትዮጵያ ሴቶች ታሪክ ነው። በወቅቱ በልዩ ልዩ ሚዲያዎች ስለቀረበ የሕዝብ ታሪክ ነው። ይህን ታሪክ ወስጄ እንደፈለኩ ልፅፍበት ላስተምርበት መብት አለኝ የሚል ሃሳብ ሰንዝሯል።

ባለታሪኳ አበራሽ በቀለ ደግሞ ይህን አባባል ትሞግታለች። ይህ ታሪክ የሕዝብ ታሪክ አይደለም። የኔ ታሪክ ነው። በ14 ዓመቷ የተጠለፈች። በ14 ዓመቷ የተደፈረች፤ በ14 ዓመቷ ጠመንጃ ይዛ ከጠላፊዋ ቤት ያመለጠች፤ በ14 ዓመቷ ጠላፊዋ ደግሞ ሊደፍራት፣ ሊጠልፋት ሲል እምቢኝ ብላ ጠመንጃ ተኩሳ የደፈራትን የገደለች ሌላ ባለታሪክ ካለች ትምጣ። የዚህ ታሪክ ባለቤት እኔ ነኝ፤ ብላለች አበራሽ በቀለ።
ጉዳዩ የመነጋገሪያ አጀንዳ ከፍቷል። ዘረሰናይ እንደሚለው ከሆነ የአበራሽን ታሪክ ማንም ሰው እንደልቡ በነፃነት ካለ እሷ ፈቃድ ፅፎ ሊጠቀምበት፣ ፊልም ሰርቶ ሊያገኝበት፣ ሊሸለም ሊሞገስበት ይችላል ወይ? የአበራሽ ታሪክ ራሱ ያልተፃፈ ድንቅ ስክሪብት ነው። እሷ ሳትፈቅድ ይህን የሕይወት ስክሪብቷን መውሰድ ይቻላል ወይ?

በድፍረት ፊልም ዙሪያ በርካታ አነጋጋሪ ጉዳዮች አሉ። ዘረሰናይ ብርሃኔ መሀሪ ከአበራሽ ሌላም ክስ መጥቶበታል። ከሳሹ ደግሞ አቶ ፍቅሬ አሸናፊ የተባሉ ሰው ናቸው። ሰውየው የሕግ ባለሙያዋ የወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ወንድም ናቸው። እርሳቸው ደግሞ የስክሪብቱ መነሻ ሃሳብ የኔ ነው የሚል ክስ ይዘው ፊልሙ እንዲታገድ ከአበራሽ በቀለ ጋር ሆነው ዘረሰናይን ከሰዋል።

ድፍረት ሌላም አነጋጋሪ ነገሮች አሉት። በፊልሙ ውስጥ በዋናነት ታሪኩ የተሰራው ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ አበራሽ በቀለን (የፊልም ስሟ ሂሩት) እሷን ከእስር ለማስፈታት የሚጥሩትን፣ የሚዳክሩትን ውጣ ውረድ የሚያሳይ ነው። በድፍረት ፊልም ውስጥ ወ/ሮ መአዛ፣ የአበራሽ በቀለ (የሂሩት) ጠበቃ ሆነው ነው የሚታዩት። ፊልሙ መአዛ አሸናፊን በአበራሽ ሕይወት ውስጥ አግንኖ ሲያወጣ የሚያሳይ ነው። እውነታው ግን ይሄ አይደለም። የዛሬ 18 ዓመት የአበራሽ ጠበቃ ሌላ ሴት ናቸው። ዛሬ በህይወት የሉም። ወ/ሮ መአዛ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ሊቀመንበር እንጂ የአበራሽ ጠበቃ እንዳልሆኑ ይነገራል። ድፍረት ፊልም ላይ ግን ጠበቃ ሆነው ቀርበዋል።

ድፍረት ፊልም ወደ አንድ ሚሊዮን ዶላር እንደወጣበት ዘረሰናይ ብርሃኔ መሀሪ ይገልጻል። የፊልሙ ፕሮዲዩሰር አንጀሊና ጆሊ ነች እየተባለ ሲነገር ቆይቷል። አሁን አሁን ደግሞ ዘረሰናይ ሲናገር አንጀሊና ለፊልሙ ምንም ሳንቲም አላወጣችም። ፊልሙን ስለወደደችው ስሟን እንድንጠቀምበት ጠየቅናት፤ ፈቀደችልን። ስለዚህ በስሟ ለመጠቀም እንደ ኤግዝከቲቭ ፕሮዲዩሰር አድርገን ተጠቀምንበት ሲል ከፊልሙ ምርቃት አንድ ቀን በፊት ዘረሰናይ እንደተናገረ የአዲስ ጣዕም የሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጆች ገልጸዋል። እውነት አንጀሊና ጆሊ ብሯን ሳታወጣ፣ በባዶ ሜዳ ነው ሕዝብ የምታሳስተው? ብለን እንድንጠይቅም ያደርጋል። ይህን ዘረሰናይ የሚናገረውን ነገር እንዴት መቀበል ይቻላል? በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠት ያለባት ራሷ አንጀሊና ጆሊ ነች። ፊልሙን እሷ ፕሮዲዩስ እንዳደረገችው በየአደባባዩ ሲነገር ቆይቶ አሁን ደግሞ ሸራፋ ሳንቲም አላወጣችበትም እየተባለ ነው። ይህ የአመቱ ሌላው አስገራሚ ታሪክ ነው። እውነት ከሆነ ደግሞ አንጀሊና ጆሊ አጭበርባሪ እና ዋሾ ሴት መሆኗ ነው።

ይህ የሰሞኑ ትልቅ መነጋገሪያ አጀንዳ የሆነው ድፍረት ፊልም ገና ተመዘው ያላላቁለት ጉዳዮች አሉ። አበራሽ በቀለ እና ፍቅሩ አሸናፊ የክሳቸው መጨረሻ ምን ይሆን? ድፍረት ፊልም ስንት ብር ወጣበት? ስንት ብርስ አገኘ? አንጀሊና ጆሊ እና ድፍረት ፊልም እውነተኛ ግንኙነታቸውን ማነው የሚያስረዳን? አበራሽን ሳያስፈቅዳት ታሪኳን የደፈረው ማን ነው? እነ አበራሽ በቀለ መክሰስ ያለባቸው አንጀሊና ጆሊን ነው ወይስ ዘረሰናይን? የፊልሙ ባለቤት ማን ነው? በነዚህና በሌሎች አስገራሚ ጉዳዮች ላይ ሳምንት እመለስበታለሁ።

↧
↧

አዲሱን ዓመት በማስመልከት ከነጻነት ታጋዮች ጋር በቂሊንጦ እስር ቤት

$
0
0

ባለፈው ሳምንት በማህበራዊ ሚዲያው ‹‹ጥቁር ሳምንት›› (black week) በሚል ለአምስት ቀናት ዘመቻ (campaign) መካሄዱ ይታወሳል፡፡ በዚያ የጥቁር ሳምንት ዘመቻ ወቅት በመጨረሻው ቀን አስተባባሪዎቹ አዲስ አመትን በማስመልከት ‹አዲስ አመት በዓልን ከነጻነት ታጋዮች ጋር› በሚል የታሰሩ የነጻነት ታጋዮች እንዲጠየቁ ጥሪ መተላለፉ አይዘነጋም፡፡ በመሆኑም የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችና የነገረ ኢትዮጵያ ዝግጅት ክፍል ጳጉሜ 5 ቀን 2006 ዓ.ም በቂሊንጦ የሚገኙ የዞን 9 የጡመራ ቡድን አባላትንና የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በመጠየቅ የዘመቻውን አካል አከናውነዋል፡፡ ቀጥሎም የጥቂት እስረኞችን መልዕክት በአጭር በአጭሩ አቅርበናል፡፡
kiliminto jail

ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ

‹‹ሀገሬ ላይ እርግጠኛ የሆንሁበት ጉዳይ ቢኖር እኔን እንደ ዜጋ የሚጠብቀኝ መንግስት የሌለኝ መሆኑን ነው፡፡ ህገ-መንግስቱ አልጠበቀኝም፡፡ ህገ-መንግስቱ ጥሩ ቢሆንም አልተከበረም፡፡ ይህ ሁሌም የሚያሳዝነኝ ጉዳይ ነው፡፡

ታስሬ ባለሁባቸው ቀናት ሁሉ የታዘብኩት ነገር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የባለሙያ እጥረት በሁሉም ዘርፍ መኖሩን ነው፡፡ አቅም ያላቸው ዜጎች ከስርዓቱ በመገፋታቸው ክፍተቱ እንዲሰፋ ሆኗል፡፡ በጣም ነው የሚያሳዝነው፤ የሚሰሩ ሰዎች በተገቢው ቦታ ላይ አለመኖራቸውን አይቻለሁ፡፡ የሚያሰራ ስርዓት ስለሌለ ብዙዎች ህሊናቸውን መርጠው በመራቃቸው ይመስለኛል አቅም ያላቸው ሰዎች የራቁት፡፡ ይህ ለሀገር አሳሳቢ ነው፡፡

የሚቆጨኝ ነገር በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና በሌሎች ተቋማት በእንግሊዝኛ የተሰሩ የጥናት ስራዎችን በመምረጥ አሰባስበን በአማርኛ ቋንቋ በጆርናል መልክ ለመስራት አስበን ያን ሳንሰራ በመታሰራችን ነው፡፡

አሁን በተለያዩ ሁኔታዎችና ጉዳዮች ላይ ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያው በኩል የሚሰሩ ስራዎች እንዳሉ ስሰማ በጣም ነው ደስ ያለኝ፡፡ እኛን አስረው ሌላው ዝም እንዲል ፈልገው ኖሮ ከሆነ እንዳልተሳካላቸው የሚያሳይ ነው፡፡ ለሀገር የሚያስቡ ብዙ ወጣቶች በየጊዜው ማበባቸው አይቀሬ ነው፡፡ እየታየ ያለውም ይሄው ነው፡፡ ምንግዜም የሚበረቱ ሰዎች ለውጥ ያመጣሉ ብዬ አምናለሁ፡፡››

አይመዲን ጀበል፣ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል

ልትጠይቁን ስለመጣችሁ በጣም እናመሰግናለን፡፡ በተለይ ወጣቶቹ እያደረጋችሁ ያለው እንቅስቃሴ እንሰማለን፡፡ በጣም ደስ ይላል፡፡ እስካሁን በአገር ጉዳይ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ የቆዩት የ1960ው ትውልድ አባላት ናቸው፡፡ አሁን ወጣቶች እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው፡፡ ይህ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ነገር ግን በቂ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ስለሆነም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡

ያሲን ኑሩ፣ የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል

‹‹እስር፣ እንግልትና ሌሎችም በደሎች የአምባገነኖች እርምጃ መለያ ባህሪያት ናቸው፡፡ አምባገነኖችን አንድ የሚያደርጓቸው እነዚህ ባህሪያት ናቸው፡፡ አምባገነኖች ከታሪክ አይማሩም፡፡ የዛሬ 20 አመትም ሆነ 50 አመት ወደ ስልጣን የሚወጣ አምባገነን ይህን ነው የሚደግመው፡፡

መንግስት በኃይማኖቶች መካከል ልዩነት መፍጠር ይፈልጋል፡፡ እናንተ ክርስቲያኖች የኃይማኖት ድንበር ጥሳችሁ ከእኛ ከሙስሊም ወንድሞቻችሁ ጋር መቆማችሁን እናደንቃለን፡፡ በተለይ ሰማያዊ ፓርቲ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ መብት በመቆም የሚያደርገውን ጥረት እናደንቃለን፡፡ እኛን ለመጠየቅ እስር ቤት ድረስ ስለመጣችሁ በጣም እናመሰግናለን፡፡ ትግሉ ከዚህም በላይ መስዋዕትነት ያስከፍላልና በርቱ፡፡››

ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ

‹‹ማዕከላዊ የገባነውን የመጀመሪያ ሰሞን ለእኛ አስቸጋሪ ነበር፡፡ በማንኛውም ጊዜ እስር ሊኖር ይችላል በሚል ማዕከላዊ የሚደረጉትን ነገሮች ለማሳወቅ እንጥራለን፡፡ በተለያዩ ጊዜያት የጻፍናቸው ጽሁፎች ለዚህ ያግዛሉ ብየ አምናለሁ፡፡ በመሆኑም በእኛ ላይ ከደረሱብን ነገሮች ሌሎች ይማሩባቸዋለን ብለን እናምናለን፡፡ ይህ ሲሆን የሚታሰሩ ሰዎች የሚደርስበት ችግር አዲስ እንዳይሆን ያደርጋል፡፡ ወደ ቂሊንጦ ከመጣን በኋላ የተሻለ ነገር ቢኖርም አሁንም ድረስ መጽሃፍና ጋዜጣ አይባልንም፡፡

በጥቁሩ ሳምንት ዘመቻ ያደረጋችሁትን ነገር ሰምተናል፡፡ በጣም ደስ የሚል ስራ ሰርታችኋል፡፡ መጥታችሁ ስለጠየቃችሁን ደስ ብሎናል፡፡ እስሩ ቀጣይነት እንደሚኖረው ቢታወቅም፣ በየትኛውም ሁኔታ በርታትችሁ እንድትቀጥሉ እፈልጋለሁ፡፡

በየቀኑ ጋዜጠኞች በሚደርስባቸው ጫና አገራቸውን ጥለው መሰደዳቸውን እንሰማለን፡፡ ይህ በጣም ያሳዝናል፡፡››

ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ

‹‹ከመታሰሬ በፊት ማዕከላዊ ውስጥ ስለሚፈጸሙ በደሎች በተለያዩ ሪፖርቶች ላይ ማንበብ ችዬ ነበር፡፡ ማዕከላዊ ከገባሁ በኋላ ያየሁት ግን ሰፊና ከጠበኩት በላይ ነው፡፡ በተለይ ትጥቅ ትግልን የመረጡ ተቃዋሚዎች አባላት ናቸው የተባሉ አሊያም በሚዲያው የማይታወቁና ጠያቂ የሌላቸው አካላት ላይ የሚደርሰው በደል ዘግናኝ ነው፡፡ በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ተመሳሳይ ድብደባ ደርሶባቸዋል፡፡ ድሮ ማዕከላዊ ውስጥ ይደረጉ እንደነበር ሰምቼ ነገር ግን ይሆናሉ ብዬ የማላምናቸውን ነገሮች ሁሉ እንደሚፈጸሙ ለመገንዘብ ችያለሁ፡፡

የማዕከላዊ መርማሪዎች አስቸጋሪዎች ናቸው፡፡ ምርመራ ማድረግ ሳይሆን ጥፋተኛ መሆናችንን እንድናምንላቸው ነው ሁሌም ተመሳሳይ ጥያቄ የሚያነሱልን፡፡ አንዳንዶቹ ጥያቄዎች በጣም የሚገርሙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል በምርመራ ወቅት ‹‹እከሌ ጋር ሻይ እየጠጣን›› ብለን የተናገርነውን ነገር እነሱ ‹‹ስብሰባ አድርገን›› ብለው ይጽፉታል፡፡ ሻይ መጠጣት በእነሱ ስብሰባ ተብሎ ይተረጎማል፡፡ አንድ ጋዜጠኛ የሚሰራው ህጋዊ ስራ ህገወጥ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ለአብነት ያህል ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25/2004 ዓ.ም ባደረገው ሰልፍ ተገኝቼ ፎቶ አንስቼ ነበር፡፡ ይህ ፎቶ ግራፍ በክስ ቀርቦብኛል፡፡ አስቡት በዚህ ሰልፍ ኢቲቪና ሌሎች የመንግስት ሚዲያዎችም ፎቶ አንስተዋል፣ ቪዲዮ ቀርጸዋል፡፡ መርማሪዎቹን ‹‹ይህ ስራዬ ነው፡፡ አያስወነጅለኝም›› ብትል አያምኑልህም፡፡ ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስም ሰማያዊ ፓርቲ ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ ተገኝተሃል የሚል ጥያቄ ቀርቦለታል፡፡

በተመሳሳይ ዩጋንዳ እያለሁ ባቋቋምኩት ጋዜጣ ላይ ሙሃመድ ሰልማን ‹‹ፒያሳ ሙሃመድ ጋ ጠብቂኝ›› በሚል ከጻፈው መጽሃፍ ላይ ያሉ ጽሁፎችን ጋዜጣው ላይ አውጥቻቸው ነበር፡፡ ሆኖም ይህም በክስ ቀርቦብኛል፡፡ ‹‹መጽሃፍ ላይ ነው የወሰድኩት፡፡ መጽሃፉ ህጋዊ ሆኖ አገር ውስጥ ይሸጣል›› ብትል ማንም አይሰማህም፡፡ ፖሊስ ህዝብን ለመጠበቅ የቆመ አካል ተደርጎ ነው የሚወሰደው፡፡ ነገር ግን ከገባንበት ጊዜ ጀምሮ ገና ሳይፈረድብን ‹‹እናንተስ ለምን ሽብር ትፈጥራላችሁ?›› ያሉን ፖሊሶች አጋጥመውናል፡፡ ቀድመው ፈረዱብን ማለት ነው፡፡

በምርመራ ወቅት በጣም የሚያስገርሙ ነገሮች ተነስተዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል ጆን ኬሪ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ወቅት መርማሪዎቹ የሚገርም ጥያቄ አንስተውልን ነበር፡፡ ‹‹ጆን ኬሪ ጓደኛችሁ ነው?›› ብለው ጠይቀውናል፡፡ በጣም የሚገርም ነው፡፡ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣን የእኛ ጓደኛ እንደሆነ አድርገው አቅርበውታል፡፡ ደግሞም ይህንንም ህገወጥ አድርገው ነው የሚያቀርቡት፡፡ በሌላ በኩል አንዴ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር፣ ሌላ ጊዜ ከግንቦት ሰባት ሌላ ጊዜ ደግሞ ከኦነግ ጋር ግንኙነት እንዳለን ይገልጹልናል፡፡ እነዚህ ድርጅቶች በምንም መልኩ የሚገናኙ አይደሉም፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ጋዜጠኛ የሚከሰሰው በመጻፉ አይደለም፡፡ በጋዜጠኝነት ብትከሰስ አንድ ነገር ነው፡፡ እነሱ ግን የሚያነሱብህ ክስ ሌላ ነው፡፡

ፌስቡክና ሌሎች ሚዲያዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ የነበርን ሰዎች ያለመረጃ ስንቀመጥ ከባድ ነው፡፡ በተለይ በመጀመሪያዎቹ 75 ቀናት ነገሮች አስቸጋሪ ነበሩ፡፡ ከዛ በኋላ ግን ቢያንስ ኢቲቪን መመልከት ችለናል፡፡ ኢቲቪ በሚያቀርባቸው ጉዳዮች ላይ የየራሳችን ትርጉም እየሰጠን አገራችን ውስጥ በጥቂቱም ቢሆን ምን እየተካሄደ እንዳለ መረዳት እንችላለን፡፡ ወደ ቂሊንጦ ከመጣን በኋላ ነገሮች የተሻሉ ናቸው፡፡ ከጠያቂዎቻችን መረጃዎችን ማግኘት እንችላለን፡፡››

ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ

↧

አንድነት ኃይል ነው፤ መበታተን ጥቃት ነው (ዶ/ር. አክሎግ ቢራራ)

$
0
0

 አስተያየት

 ዶ/ር. አክሎግ ቢራራ 

unityበመሳሪያ ኃይልና በውጭ መንግሥታት ድጋፍ የስልጣን እርካብ የተቆናነጠጠው፤ በጠባብ ብሄርተኛው በህወሓት ፍጹም የበላይነት የሚመራው፤ የኢህአዴግ መንግሥት ከተመሰረተበት ጀምሮ የኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት፤ ደህንነትና ነጻነት፤ የዘጠና አራት ሚሊዮን ሕዝቧ ሉአላዊዊነት፤ እውነተኛ እኩልነት፤ ማህበራዊ ጥቅም፤ መሰረታዊ ትብብር፤ ነጻነትና ዲሞክራሳዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ ተናግተዋል፤ ተገፈዋል። በማንኛውም የዘመናዊነት መስፈርት ቢፈረጅ፤ ኢትዮጵያን ከባሰ አደጋ፤ ሕዝቧን ከከፋ ድህነት እና የእርስ በርስ ግጭት፤ ወጣቱን ትውልድ ለሁላችንም ከሚያሳፍር ስደተኛነትና ውርደት ሊያድነው የሚችለው ተተኪ የአገዛዝ ስርአት (አማራጭ) በሕግ የበላይነት፤ በእውነተኛ የኢትዮጵይያውያን እኩልነት፤ በሕዝብ ስልጣን የተመሰረተ ዲሞክራሳዊ አገዛዝ ብቻ ነው። ሰፊ ለም መሬት፤ ዝናብ፤ ወንዝ፤ ተስማሚ አየር፤ ከመሬት በታች ገና የማይታወቅ ሃብት ያላት አገር ለሁሉም አስተናጋጅ ለመሆን እንደምትችል አልጠራጠርም። ፍትህ-ርትእ ከሌለ ይኼን የማይገኝ ሃብት የሚጠቀሙበት የውጭ ኢንቬስተሮችና አጋር የሆኑ የውስጥ ሃብታሞች ሆነው ይቆያሉ። ገዢው ፓርቲና ተቃዋሚዎች የሚስማሙበት አንድ አበይት ጉዳይ አለ። ይኼውም ዲሞክራሳዊ አማራጭ አስፈላጊ ነው የሚል። ከጽንሰ ሃሳብ ባሻገር ግን ሁለቱም ወገኖች ዲሞክራሳዊ አሰራርን በተግባር አላሳዩም፤ ለማሳየትም የተዘጋጁ አይመስልም። አንዱ በሌላው እያመኻኘ ሃያ ሶስት ዓመታት አልፈዋል። የሚቀጥለው ምርጫ ዘጠኝ ወሮች ቀርተውታል። ሑኔታው ከቀጠለ የሚቀጥለው ምርጫ ከአሁኑ ተወስኗል ለማለት እንችላለን፤ የገዢው ፓርቲ የበላይነት ብቻ ይሆናል። መቶ በመቶ አሸነፍኩ ቢል አንገረም። የሚወዳደረው ከራሱ ጋር ይሆናል።

ገዢው ፓርቲ መከፋፈልን ወደ ሳይንስ ለውጦታል። ተቃዋሚው ይኼን ሳይንስ አልቀበም በማለት ፋንታ እርስ በርሱ መናከሱን ቀጥሎበታል። በተደጋጋሚ የሚታየው የራእይ፤ የግብ፤ የአደረጃጀትና የአመራር ደሃነት በቀላሉ አለመፈታቱ ተቃዋሚውን ፍሬ ቢስ አድርጎታል። በአገር ውስጥ ብቻ ያለው ሳይሆን በውጭም ያለው፤ በነጻነት ለመወያየትና አብሮ ለመስራት ገዢው ፓርቲ ሊቆጣጠረው የማይችለው። ቢቀበለውም ባይቀበለውም ተቃዋሚው የገዢው ፓርቲ አገልጋይ ሆኗል ለማለት ያስችላል። የምናውቀው የሃገሪቱን አስተዳደር በቋንቋ የቀየሰው አምባገነን መንግሥት ቆይታውንና የኢኮኖሚ ጥቅሙን ለማጠናከር ህዝብን እርስ በርሱ እንዲጋጭ፤ ተቃዋሚዎች እርስ በርሳቸው እንዲናከሱ በማድረግ ላይ ይገኛል። ይኼ የመከፋፈልና ስልጣንና ሃብትን የማስተማመኛ ስልት ከታወቀ፤ በአገር ቤትም ሆነ በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎች በሰከነ መንገድ አስበው፤ ተፈላልገው፤ ተከባብረው፤ “ተናበው”፤ በዋናው ዓላማ ላይ ተስማምተው ለመስራት የገዢው ፓርቲ ፈቃድ አያስፈልጋቸውም ነበር። ችግሩ ጥበባዊና ዘመናዊ በሆነ መንገድ የማደራጀትና የመምራት ድክመትና ክፍተት መኖሩ ነው። ስርዓቱ  የራሱን መቆያ ያጠናከረውና የሚያጠናክረው የሃገሪቱን ባጀት፤ የተፈጥሮ ሃብትና ሌላ ጥሪት ለጥቂቶች አገልጋይ የሆነ ተከታታይ የብልጭልጭ እድገት በማሳየት፤ “እኔ እስካለሁ የእድገቱ ተጠቃሚዎች ትሆናላችሁ፤ እኔ ከሌለሁ፤ ትበላላችሁ” በሚል ዘዴ ነው።

ስርዓቱ የሚሰራውን ያውቃል ማለት ነው። የሚሰራውን የማያውቀው ተቃዋሚው ሆኗል። የተበታተነው ተቃዋሚ የሚለው በኢትዮጵያ እድገት የለም አይደለም። ፍትህ የለም። የአብዛኛው ሕዝብ ኑሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ታች በመሄድ ላይ ይገኛል፤ የኑሮ ውድነት የተራውን ዜጋ የመግዛት አቅም አስጊ በሆነ ደረጃ ቀንሶበታል። የወጣቱ ትውልድ እድል ተምሮ መሰደድ ሆኗል። በዘመነ ኢህአዴግ የሃገሪቱ ለም መሬትና ወንዝ ለውጭ ኢንቬስተሮች በእርካሽ ዋጋ ሲሰጥ ቆይቶ በአሁኑ ጊዜ አላሙዲ ብቻ የሚያመርተው በዓመት አንድ ሚሊዮን ቶን ሩዝ ለሳውዲ ገበያ ይቀርባል። እንደ ካሩቱሪ ያሉ የህንድ ኢኒቨስተሮችም የጋምቤላን ለም መሬት ተረክበው ምርታቸውን ለውጭ ገበያ ያቀርባሉ። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ እየተነገደባት ነው። ሳውዲዎች እየተመገቡ  ብዙ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ይራባሉ፤ አገሪቱ በዓመት ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ለምግብ ግዢ ታወጣለች። ህይወቱ የተናጋው አብዛኛው ሕዝብ መብቱ ሰለታፈነ፤ ድምፁን ለማሰማት ስላልቻለ መከራውን ተቀብሎ ይኖራል ወዘተ የሚሉ ናቸው።

ስለሆነም፤ ተቃዋሚው የጠራ አማራጭ ለማቅረብ ነባራዊው ሁኔታ ይፈቅድለታል። የሚጎድለው የዓላማ አንድነትና የአመራር ብልሃት ነው። እርግጥ ነው፤ የገዢው ፓርቲ አቅም ከፍተኛ ነው። መንግሥትን ከተቆጣጠረ ባጀትንም እንደፈለገው ፈሰስ ለማድረግ ይችላል።

 

ስንቅ ብቻውን አቅም አይሆንም

የተቃዋሚው ክፍል አቅም ጠንካራ ሊሆን የሚችለው ከሕዝብ ከሚያገኘው ድጋፍ፤ ከመተባበሩ፤ ያለውን የቁሳቁስ አቅም በጋራ ከመጠቀሙ፤ በብልሃት ከመስራቱ፤ በአንድ ድምፅ ከመነሳቱ፤ ለዓላማው ጠንክሮ፤ በውስጥ አመራር ሳይበከል መስዋት ለመክፈል ፈቃደኛ ከመሆኑ ላይ ነው። በውጭ ያለው አገር ወዳድ፤ ዲሞክራትና የሰብአዊ መብቶች ጠበቃ ኃይል ያልተቆጠበ ድጋፍ ለማድረግ አቅምና ፍላጎት አለው። “ተባበሩ ወይንም ተሰባበሩ” እያለ ሲመክር ቆይቷል። ገንዘቡን፤ እውቀቱን፤ ድጋፉን ችሯል። ወደፊትም ይችራል የሚል እምነት አለኝ። ሆኖም፤ ስንቅ አቀባይነት ያለ ድርጅትና አመራር ብቃት ኢትዮጵያን አይለውጥም። ለዚህ ነው፤ ደጋፊዎች ተስፋ እየቆረጡ “ተቃዋሚ ነኝ” ማለቱን ቀልድ አታድርጉት፤ “ጩኸቱን ወደ ተግባር ለውጡት፤ በፍርሃትና በመጠላለፍ ዓለም መኖራችሁን አቁሙ፤ ነጻነት፤ ፍትህና ዲሞክራሳዊ ስርአት ያለ መስዋእትነት ስኬታማ ሊሆኑ አይችሉም። የእርስ በርስ ጦርነቱን አቁሙ። በውጭ ኃይሎች ማምለኩን አቁሙ። ድርጅት አፍርሳችሁ በድርጂት መተካቱን ተውት። አትጠላለፉ። መገናኛ ብዙሃኖችን ለእርስ በርስ ጦርነት አትጠቀሙ፤ አትወነጃጀሉ፡  የራሳችሁን የውስጥ አመራር ሳታጠናክሩ ሁሉን ነገር በገዢው ፓርቲና በሌላው ላይ አታመኻኙ፤ ተቃውሞ ብቻውን የማህበራዊ ጥቅም አይኖረውም” ወዘተ፤ ወዘተ የሚሉት።

በጀ፤ ታዲያ መፍትሄው ምንድን ነው?

ይኼ አጭር የፖለቲካ ኢኮኖሚ ስእል በተደጋጋሚ ያሳየው የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች ጥቃቅን ልዩነቶችን ወደ ጎን ትተው ለሃገሪቱ ዘላቂነት እና ለመላው ሕዝቧ ደህንነት ሲባል መተባበር፤ ቢቻል መዋሃድ አለባቸው የሚለውን ባለፉት አስር አመታት በተደጋጋሚ ሁሉን በሚመለከት ያቀርብኩትን ምክርና ጥሪ ነው። ምክር እንጅ ትእዛዝ አይደለም። ማንም ግለሰብ ወይንም ቡድን ከውጭ ሆኖ ትእዛዝ ለመስጠት አይችልም። ትግሉ በአገር ቤት ካልተጠናከረ፤ አገር አቀፍና አሳታፊ ካልሆነ የፈለገው ጥረት ቢደረግ ዲሞክራሳዊ መሰረት ለመጣል አይቻልም። የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገው አብሮና ተሳስቦ መኖርን ነው። ቂም በቀልነትን አይፈልግም። አንዱን አምባገነን በሌላ አምባገነን መተካት አይደፈልግም። ይኼማ ከሆነ ኢህአዴግ ምን አደረገ፤ የተካው ደርግ ምን አደረገ፤ አጼ ኃይለ ሥላሴስ ምን አደረጉ? የኢትዮጵያ ሕዝብ ራሱ የስልጣኑ፤ የመንግሥቱ፤ የመሪዎቹ ባለቤት ለመሆን ይፈልጋል። ለዚህ ብዙ መስ ዋት ከፍሏል። ስለሆነም፤ ሁሉም ተቃዋሚ ኃይሎች በዓላማ እንድነት በመንቀሳቀስ ታሪክ የሚጠይቀውን ሃላፊነት መወጣት አለባቸው። ሕዝብን ካጎለመሱ ተመጣጣኝ አቅም ይኖራቸዋል። ወሳኙ ሕዝብ ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ በምርጫ ዘጠና ሰባት ለቅንጅትና ለህብረት የሰጠው ያልተቆጠበ ድጋፍና የከፈለው መስዋእት እንዲያንሰራራ ከተፈለገ በአገር ቤትና ከአገር ውጭ የሚገኙ የፖሌቲካና የማህበረሰብ ድርጅቶች፤ የሞያ ስብስቦች፤ ግለሰሶብችና ሌሎች ከቡድን፤ ከፓርቲ፤ ከግል ዝናና ጥቅም በላይ ለኢትዮጵያ ዘላቂነትና ለመላው ስብጥር ሕዝቧ ደህንነት አብረው መነሳትና አምባገነኑን መንግሥት ማንበርከክ፤ ቢያንስ ለድርድር እንዲስማማ ማድረግ ይኖርብናል። ከሁሉም በላይ የተቀነባበረ የሕዝብ አመፅ አገር አቀፍና ዘላቂነት ባለው ደረጃ ከተካሄደ ገዢው ፓርቲ ለመደራደር ይገደዳል።

ይኼን ትንተና ለማዘጋጀት የተገደድኩበት ዋና ምክንያት የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት የለመደውን መንገድ እየተጠቀመ፤ ከመጭው ምርጫ በፊት በሰላማዊ መንገድና በሁለገብ ትግል የሚንቀሳቀሱና ተባብረው ለመስራት ፈቃደኛ የሆኑትን ተቃዋሚዎች ሁሉ ተባብረው እንዳይሰሩ በማሰብ በመከፋፈል ላይ ይገኛል። ይኼ አዲስ ነገር አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋ ጥሎበት የነበረው የመኢአድና የአንድነት ውህደት ሂደት አሳዛኝና ተስፋ በሚያስቆርጥ መልክ ስኬታማ አለመሆኑ ለገዢው ፓርቲ ቆይታ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርጓል። ይኼ ችግር የገዢው ፓርቲ ሳይሆን የተቃዋሚው ነው። በቅርቡ የተከሰተም ሌላ የተቃዋሚውን ክፍል ከጥያቄ ውስጥ ያስገባ አከራካሪ ጉዳይ አለ።

እንደማንኛውም አገር ወዳድ በ August 28, 2014 ሶስት በውጭ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ድርጅቶች በዜናና በድህረገጾች ያሰራጩትን፤ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ትኩረት የሰጡትን የጋራ መግለጫ በሰከነ መንገድ ተመልክቻለሁ።  መግለጫው እንዲህ ይላል። “ኢትዮጵዮጵያንና ሕዝቧን ካሉበት አዘቅት በማውጣት ሕዝቡ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግልና መስዋእትነት የግድ የሚለን ደረጃ ላይ መድረሳችንን፤ የወያኔን ቡድን በሁለገብ ትግል እየተፋለምን ያለን ድርጅቶች ተጣምሮና አንድ ሆኖ መታገል እንዳለብን ካመንን ዓመታት አስቆጥረናል። ስለሆነም፤ ወደፊት ለመዋሃድ የተሰማማነው ድርጅቶች፤

  1. የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር
  2. የግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ
  3. የአማራ ዲሞክራሳዊ ኃይሎች ንቅናቄ ነን” የሚል መግለጫ ወጥቶ ሲያነጋግር ቆይቷል።

ከአንድ ሳምንት በኋላ በ September 6, 2014, በኮሎኔል አለበል የሚመራው የአማራ ዲሞክራሳዊ ኃይሎች ንቅናቄ ማስተባበያ አውጥቶ “ከግንቦት 7 ጋር አልተዋሃድኩም” ብሏል።

በእኔ ግምትና እምነት ምንም እንኳን የጋራ ስምምነቱ በምን አጀንዳ ላይ እንደተቀረጸ ባላውቅም፤ አሰራሩ በግልፅነት፤ በሃላፊነት፤ በዲሞክራሳዊነት፤ በዘላቂነትና ሌሎችን በሚያበረታታ መንገድ የውህደቱ ድርድር እንዲካሄድ ያለኝን ተስፋና ምኞት ለማቅረብ እፈልጋለሁ። በተመሳሳይ፤ በአንድነትና በመኢአድም በውስጥና በመካከላቸው መካከል የተከሰቱ ልዩነቶችም በውይይት፤ በግልፅነት፤ በሃቀኝነት፤ በብልሃት፤ በዲሞክራሳዊ ስልት እንዲፈቱ የታሪክ አደራ እሰነዝራለሁ። ዛሬ ለፍትህ- ርትእ፤ ለህግ የበላይነት፤ ለሰብአዊ መብቶች መከበር፤ አገርን ከአደጋ ለመከካለክ፤ ለእውነተኛ እኩልነትና ለዲሞክራሲ የሚታገሉ ኃይሎች “ኢህአፓ፤ መኤሶን፤ እሴፓ፤ ፓሪስ አንድ፤ ፓሪስ ሁለት፤ ኢዲዩ፤ እዴፓ፤ ቅንጅት፤ ህብረት፤ ታንድ፤ ኦነግ፤ መድረክ፤ አሬና፤ ግንቦት 7፤ አርበኞች፤ የአማራ ዲሞክራሳዊ ኃይሎች፤ አንድነት፤ ሰማያዊ፤ መኢአድ፤ አንድ ሁለትና ሶስት ወዘተ የሚሉበትና እርስ በርስ የሚወቃቀሱበት ዘመን አልፏል ለማለት የሚያስችሉ ብዙ ክስተቶች አሉ። የኼን ስል፤ ሁላችሁም ተዋሃዱ ማለቴ አይደለም፤ ብዙ ተሞክሮ አለተቻለም። ዲሞክራሳዊ ለውጥ ከተፈለገ ለመተባበርና ለመደጋገፍ ይቻላል። ይኼም ፈቃደኛነት ካለ ብቻ ነው። “አገር ትሸጥ ሲባል ስንት ታወጣለች” የሚል አዲስ ባህልና አዲስ ባለሃብት መደብ መፈጠሩን እያየን እርስ በርሳችን የምንናከስ ከሆነ ከትግሉ ዓለም መውጣት አለብን። አዲሱ ትውልድ ለራሱ ህይወት ሲል ይታገልበት ለማለት መድፈር አለብን። በምትካችን አዲስ ትውልድና አዲስ ዓመራር እየታገለ አመራሩን እንዲይዝ ቦታውን እንልቀቅለት። መሰናክል አንሁን። መቀበል ያለብን፤ እኛ ራሳችን ለመምከር ወይንም ለመመከር ስለማንፈልግ ሌሎች፤ በተለይ ፈረንጆች ለእኛ ተናጋሪ ሆነዋል። ለምሳሌ፤ ለኢትዮጵያ የሚለግሱ መንግሥታትና ድርጅቶች ደጋግመው የሚነግሩን በአንድ ላይ፤ በአንድ ድምፅ ለመናገርና አግባብ ያለው አማራጭ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማቅረብ እስካልቻላችሁ ድረስ ማንም አያዳምጣችሁም ነው። ሃቁ፤ ያለውን መንግሥት እንደግፋለን ነው የሚሉት። የተበታተነ ተቃዋሚ ውጤቱ ይኼው ነው። አንፈረድባቸው። የሚያኮራ ታሪክ እያለን የራሳችን ህብረተሰብ ለመታገድ ካልቻልን ሌሎች ያዙብናል። እያዘዙብን ነው። ከዚህ የበለጠ የጠነከረ ምክር መጠበቅ ራስን ማታለል ነው።

ለማጠቃለ፤ በሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጭ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎች እንዲያስቡበት የምመኘውና አደራ የምለው የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት እድሜውን ለማራዘም ለሚያደርገው ያልተቆጠበ ሴራና ሰለባ ምርኮኛ መሆን የለባችሁም/የለብነም የሚል ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገውና የሚመኘው የእርስ በርስ መጠላለፍና ለስልጣን መሻማትን አይደለም፤ አብሮና ተባብሮ አምባገነኑን ስርዓት በዲሞክራሳዊ ስርዓት መተካትና ዘላቂነትና ፍትሃዊነት ያለው የእድገት በርና መሰረት እንዲከፈትለት ነው። ስለሆነም፤ የተቃዋሚዎች ሙሉ እምነት በኢትዮጵያ ሕዝብ አቅም ላይ ይሁን አላለሁ።

9/10/2014

 

↧

የሕወሓቱ ታጋይ ሌተናንት ጀነራል ዮሐንስ ገ/መስቀል በ95 ሚሊዮን ብር ቦሌ ላይ ህንፃ አስገንብተዋል

$
0
0

ከኢየሩሳሌም አረአያ

ሌተናንት ጀነራል ዮሃንስ ገብረመስቀል ከባንኪሙን ጋር

ሌተናንት ጀነራል ዮሃንስ ገብረመስቀል ከባንኪሙን ጋር

የሕወሐት ሌተናንት ታጋይ ጄ/ል ዮሃንስ ገ/መስቀል ቦሌ ቴሌ መድሃኒያለም ባለ6 ፎቅ ህንፃ እንዳስገነቡ የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። ከ95ሚሊዮን ብር በላይ በሚደርስ ወጪ እንደተገነባ የተነገረለት ይኸው ባለ6 ፎቅ ዘመናዊ ህንፃ ለተለያዩ የግልና የመንግስት ባንኮች፣ ኢንሹራንስ ድርጅቶች፣ ንግድ ቤቶችና የተለያዩ ድርጅት ቢሮዎች እንደተከራየ የጠቆሙት ምንጮቹ በወር ከ2.1 ሚሊዮን ብር የሚገመት ኪራይ ጄኔራሉ እንደሚሰበስቡ አስታውቀዋል። ሌ/ጄ ዮሃንስ በግላቸው ባለ6 ፎቅ ዘመናዊ ህንፃ በከፍተኛ ወጪ በማስገንባትና ከፍተኛ የኪራይ ሂሳብ በየወሩ በመሰብሰብ ከሌሎቹ በቢዝነስ ከተሰማሩ የሕወሐት/ኢህአዴግ ጄኔራል መኮንኖች የተለየ እንደሚያደርጋቸው ምንጮቹ አመልክተዋል። በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የመረጃ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሆነው ለረጅም አመታት ሲሰሩ የቆዩት የህወሐቱ ጄኔራል ዮሃንስ ገ/መስቀል ከ1995ዓ.ም ጀምሮ ከጄ/ል ሳሞራ የኑስ ጋር የከረረ ቅራኔ ውስጥ ገብተው እንደቆዩና በሁለቱ የህወሀት ጄኔራሎች መካከል የተፈጠረው ቅራኔ እየተባባሰ ሄዶ ጄ/ል ዮሃንስ ከሃላፊነት እንዲነሱ መደረጉን ያስታወሱት ምንጮቹ የሁለቱ ቅራኔ ሙስናን መሰረት ያደረገ እንደነበረ አስረድተዋል። (በወቅቱ ስለግጭታቸውና መለስ ዜናዊ ዘንድ ቀርበው ስለተነጋገሩት በኢትኦጵ ጋዜጣ መረጃው ይፋ ተደርጐዋል)

ጄ/ል ዮሃንስ ከመከላከያ ሃላፊነታቸው እንዲነሱ የተደረጉት በጄ/ል ሳሞራ መሆኑን ያስታወሱት ምንጮቹ በወቅቱ “ጡረታ” በሚል እንደተነሱና ሲነሱም በሜ/ጄኔራል ማእረግ እንደነበሩ አስታውቀዋል። በሙስና ባገኙት በመቶ ሚሊዮን የሚገመት ገንዘብ ሕንፃ ወደማስገንባት የግል ቢዝነስ የተሰማሩት ጄ/ል ዮሃንስ ከአራት አመት በኋላ በመከላከያ የሌተና ጄኔራልነት ማእረግ ባሳለፍነው ሰኔ ወር ተሰጥቷቸው በደቡብ ሱዳን የሚሰማራውን የተመድ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት በጦር አዛዥነት እንዲመሩ መመደባቸው አስገራሚ ነው ያሉት ምንጮቹ ምክንያቱም ጡረታ ተብለው የተሰናበቱት ዮሃንስ የሌተና ጄኔራል ማእረግ እድገት ተሰጥቷቸው መመለሳቸው በመከላከያ ታሪክ የመጀመሪያው ሊያደርጋቸው ስለሚችል ግርምት ሊፈጥር ችሏል ብለዋል። ዮሃንስ የአገር መከላከያ ሚ/ር የሌ/ጄኔራል ማእረግ እንዲሰጣቸውና በተመድ እንዲመደቡ የተደረገው በአሜሪካ ትእዛዝ መሆኑን ምንጮቹ አመልክተዋል። በቦሌ ለንደን ካፌ ፊት ለፊት ዘመናዊ መኖሪያ ካስገነቡት ጄኔራሎች አንዱ ናቸው።

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live