Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የኢቲቪ “ያልተገሩ ብዕሮች” ዘጋቢ ፊልምና ያልተገራው አቀራረብ (ነቢዩ ሲራክ)

0
0

ነቢዩ ሲራክ

ከሁለት ሰአቱ የኢቲቪ ዜና አወጃ ተከትሎ የቀረበውን ” ያልተገሩ ብዕሮች ” ዶክመንተሪ በደረቁ ሌሊት ድጋሜ ስርጭቱ ተከታትየ ጨረስኩት … ላፍታ እንደተጠናቀቀ ዝም ፣ ጭጭ አልኩና በሃሳቤ በህዝብ ገንዘብ ከፍተኛ ወጭ እየተደረገባቸው የሚሰራጩትን የመንግስት የህትመት ጽሁፍና የኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙሃንን አሰብኳቸው … በምናብ ብዙ ርቄ ሔጀ በዶደመ ፣ ባልተገራ እና በተባውና በተገራው ብዕር ውስጥ ራሴን አትኩሮት ሰጥቸ የመገናኛ ብዙሃን ውጤቶች በሃሳብ ተመላለስኩባች ! ሰፊ ሽፋን ያለውን ኢቲቪና ራዲዮኑን ፣ በየቀኑ እየታተሙ የሚወጡትን እነ አዲስ ዘመንን ጋዜጣንና የመሳሰሉት እሰብኳቸው …አስቤ አሰላስየ ወደ ደረስኩበት ድምዳሜ ከማቅናቴ በፊት ግን በ”ያልተገሩ ብዕሮች ” ዘጋቢ ፊልም ዙሪያ የታዘብኩትን ቀዳሚ አድርጌ የተሰማኝን ላካፍልዎ ወድጃለሁ…

” ያልተገሩ ብዕሮች ” …

…ስለ ጋዜጠኝነት ስነ ምግባር ከባለ ሙያዎች የቀረበው መግለጫ ዘጋቢ ፊልሙ የተነሳበትን አላማ በሚያሳካ መልኩ የተጠናቀረ ስለሚሸት ፣ ስለሚመስል አልተመቸኝም። ከሙያው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ወገኖች የሰጡት አስተያየት የግል አመለካከታቸው ነውና ብዘለውም ባዕድ በሆኑት ሙያ የሰጡት ግምገማ አልተዋጠልኝም። “ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ” ሆኖብኝ ልቀበለው አልተቻለኝም ፣ አልወደድኩትም ! ምስክርነት ግምገማቸውን ያለወደድኩት “የመገናኛ ብዙሃን ውጤቶች አያጠፉም !” ከሚል እሳቤ ተንደርድሬ ሳይሆን ላጠፉት ጥፋት ቅጣት መቅጫ ወፈር ያለ ህግ ተቀምጦ በህግ መጠየቅ ሲገባ ጅምላ ነቀፋን ማቅረብ ባልተገባቸውን ነበር በሚል ነው ። የመንግስት ሃላፊዎች የሰጡት ገለጻና ማብራሪያም የተጻፈውን ህገ ደንብ ከማብራራት አልፎ ጥፋት እየተካሔደ በሆደ ሰፊ መታለፉንና አሁን ግን መንግስት ማምረሩን የሚያስረዳ ከመሆን ያለፈ ፍሬ ነገር የለውም ።

ብቻ ….ገና ከጅምሩ ዘገቢ ፊልሙ ድምጻቸው በሚስብ ጋዜጠኞችና በምስል ቅንብር ደምቆ ፣ መልዕክቱ ግን በህግ በተያዙና በሚፈለጉ ተጠርጣሪ የመገናኛ ባለሙያዎች ላይ ከፍርድ በፊት ጥፋተኝነትን የሚለድፍ ሆኖ ታይቶኛል። ሳጠቃልለው የ “ያልተገሩ ብዕሮች ” ዘጋቢ ፊልም ፍርድ ቤት ገና እያየው ባለውና ባልወሰነባቸው በጦማሪ ጸሃፍት ፣ በአምደኞች እና በነጻው መገናኛ ብዙሃን የሚቀርበውን ክስ ለማጠናከር የተሰራ መሆኑ ያሳብቃል ፣ ወንጀሉን ለማጠናከርም ለውንጀላው ምስክሮች በመንግስት ቴሌቪዥን የሰማሁትን ያህል ተሰማኝ !

ከዘመነ ጃንሆይ ፣ ዘመነ ደርግና ዘመነ ኢህአዴግ የመንግስትን አቋም እያራመዱ በጣም በወረደ ዋጋ ለነዋሪው በየቀኑ እየታተሙ ይቀርባሉ ። ዳሩ ግን ትናንትም ሆነ ሃገር ምድሩን በሚሞላ ቁጥር የመታተማቸውን ያህል ቁም ነገር አላቸው የሚባሉት ገጾች የስራ ፈላጊዎችን ቀልብ የሚስቡት ማስታወቂያዎችና የጨረታ ማስታወቂያዎች ብቻ መሆናቸውን ቢያንስ በደርግና በኢህአዴግ ዘመን አውቃለሁ ። ብዙሃኑን ነዋሪ እውነትንና ጠቃሚ መረጃን ቢይዙ አንኳ አጓጉተውት አይገዛቸውም !

ወደ ኤሌክትሮኒክስ መገናኛ መስኩም ስናመራ የምናየው እውነታ ተመሳሳይ ነው ። ዘመኑ የመረጃ ነው ፣ ዘመነኛ የመገናኛ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ያንጠለጠለው የታደለው ቀርቶ በስማ በለው ከሚነገሩት መስማት የሚናፍቀው የሃገሬ ሰው ቁጥር የትየለሌ ነው። ጭብጥን መረጃ ከሃላፊት ጋር ይዘው ፈርጀ ብዙ በሆነ መንገድ የሚሰራጩ መረጃዎችን በፍቅር የሚከታተለው ወገን መረጃ እንደ እለታዊ ፍጆታው የቆጠረው ይመስላል። ዛሬ ዛሬ ከስልጡን ለውጥ ፈላጊ እስከ መደዴው የኔ ቢጤ ያለ መረጃ መተንፈስ አይቻለውም።

አትኩሮት ሰጥቶ ከሚከታተለው የራዲዮ ፣ ቲቪ መርጦ ጀሮውን ይሰጣል። ለህትመት ውጤት ለሆኑት ጋዜጣና መጽሄቶችን ያለው እየተጋፋ ገዝቶ ፣ የሌላው እየተከራየ መረጃን ይመገባል። ያሻውን ይመርጣል ፣ ያሻውን አንቅሮ የመትፋት ያህል አይቀርባቸውም !

በ ” ባልተገሩ ብዕሮች ” የቀረቡት ባለሙያዎች ያልመረምሩት እውነታ ይህ ነው ። በጥናታዊው ዘገባ የቀረቡት ባለሙያዎች በዋናነት የህዝቡን ነጻ መረጃ የማግኘት መብት አክብረው ሙያዊ ” የተገራ ያልተገራ ብዕር ” ግምገማ አድገው አላሳዩንም ።

ይልቁንም ቀርበው የደሰኮሩበት የህዝብን ገንዘብ መሰረት አድርጎ ከሚንቀሳቀው ኢቲቪ ይልቅ እየፈራ እየተባም ቢሆን ከጽፈኛ ተቃዋሚዎች ልሳንነት የሚደበውን ኢሳትን ይከታተላል ፣ በመንግስት ደጋፊነት የሚፈረጀውን ኢቢኤስን ደረቱን ገልብጦ ማየት ይፈልጋል። የኢትዮጵያ ራዲዮን ትቶ ጀርመን እና አሜሪካን ብሎም በሃገር ቤት የመንግስት እጅ የለባቸውም የሞላቸውን የተመረጡ የኤፍ ኤም አዳዲስ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ያምናል ፣ ማየትና መስማትን ይመርጣል። የዚህ ሁሉ የነዋሪው ግልጽ ሽሽት ምን ይሆን የሚለው ዳሰሳ መላ ምት ውጤት በዘገባ በቀረቡት ባለሙያዎች ቢነገረን ያምር ነበር ። ” ነበር ባይሰበር “ …

ይህ የሆነው ለምን ይሆን ? ብዙሃን ነዋሪ ምርጫ እንዲህ የሆነው ምን ቢሆን ነው ? እውን ውስጣቸው ባልተገራ ብዕር የታጨቁ መረጃዎች ስለተሞላ ነው ማለት ይቻል ይሆን ? አይመስለኝም በሚል የሚሸፈን ሳይሆን ህዝቡ የፈለገውን ማየት መስማት አይሻምና ነው ባይ ነኝ !…”ያልተገሩ ብዕሮች” ምንጭ እያስተዋለ መርጧልና ያለተገራው ብዕር በሰፊው ያለበትን ቦታ አሳምሮ ተረድቶታል … ! እናም የማይፈልገውን አይቀርበውም ኩሩው ህዝብ እንዲህ ነው !

አይ ” ያልተገሩ ብዕሮች !” ? ጊዜ ደጉ ፣ መስናት ፣ ማየት ፣ መናገር መልካም !

ሰላም ለሁላችሁ !

Comment


አነጋጋሪው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የፖሊሲ ስልጠና [ተማሪዎች የስልጠና ሰነድ በማቃጠል ተቃውሟቸውን አሰምተዋል]

0
0

ተማሪዎችና የፖለቲካ ተቋዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ፖሊሲ ላይ ያተኮረው ለከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ተማሪዎች የሚሰጠውሥልጠና ከጥሪው አንስቶ በግዳጅ የሚካሄድ መሆኑን ነው የሚናገሩት የኢትዮጵያ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሁለት ሳምንታት የፖሊሲ ስልጠና ላይ መሆናቸውን መንግስት አስታውቋል ።

UNiversity students

ነሐሴ የተጀመረው ይኽው ስልጠና ተማሪዎች በግዳጅ የሚሳተፉበት መሆኑን አንዳንድ ተማሪዎችና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይናገራሉ። መንግሥት ግን ይህን ያስተባብላል።

ተማሪዎችና የፖለቲካ ተቋዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ፖሊሲ ላይ ያተኮረው ለከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ተማሪዎች የሚሰጠውሥልጠና ከጥሪው አንስቶ በግዳጅ የሚካሄድ መሆኑን ነው የሚናገሩት። በተለይ በስልጠናው የማይሳተፉ ተማሪዎች በመጪው አመት የትምህርት እድል እንደማያገኙ ይገልፃሉ ።ከዚህ በተጨማሪ የትምህርት ነጻነትና ፖለቲካዊ ሰበካ በመርህ ደረጃ አብረው የማይሄዱ ሆኖ እያለ ተማሪዎችም ይህን አስመልክቶ ቅሬታቸውን እንዳያሰሙ ተቃውሞ እንደገጠማቸው ነው የሚገልፁት። በትምህርት ላይ ሳሉ የኢህአዴግ አባል የሆኑ ተማሪዎች በኩል መመዝገባቸውንና የስልጠና ቅጽ መሙላታቸውን በስልጠናው የሚሳተፉ ተማሪዎች ይናገራሉ። ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ አንድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የስልጠናውን አጀንዳዎች ያብራራል።

ካሁን ቀደም ምላሽ ያላገኘው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጥያቄ በቅድሚያ ምላሽ ሊሰጥበት ይገባል የሚል ተቃውሞ መነሳቱን ይኽው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ተናግሯል። ተማሪው ስልጠና የሚሰጥባቸው አካባቢዎች በፌዴራል ፖሊስ መከበባቸውንና ተማሪዎች ከቅጥር ግቢው መውጣት መከልከላቸውንም ገልጿል። ተማሪው እንዳለው በስልጠናው የሚሳተፉ ተማሪዎች የተሰጣቸውን የስልጠና ሰነድ በማቃጠል ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

semayawi

ካልተመዘገቡና ካልተሳተፉ በመጪው አመት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የጀመሩትን ትምህርት ለመቀጠል እንደማይችሉም ጨምረው ተናግረዋል።

ተቃዋሚው የፖለቲካ ፓርቲ ሰማያዊ ፓርቲ ባለፈው ሳምንት ይህን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በስልጠና አመካኝቶ የራሱን አስተሳሰብና ርዕዮተ ዓለም በተማሪዎች ላይ እየጫነ መሆኑን አስታውቋል። የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ስለሺ ፈይሳ ስልጠናውን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት የትምህርት ተቋማት ከፖለቲካ ጫና ነፃ መሆን እንዳለባቸው ይናገራሉ። እሳቸው እንደሚሉት ከሆነ አገሪቱ ካለችበት አስቸጋሪ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ አኳያ ይህን አይነት ስልጠና ትልቅ ወጪ የሚጠይቅ ስለሆነ ከየትኛው በጀት ተወስዶ እየተካሄደ መሆኑ ግልጽ ስላልሆነ ሃብት ማባከን ነው ።

መንግስት በበኩል ሥልጠናው በግዳጅ የሚስጥ እንዳልሆነና የትምህርት ነጻነትን እንደማይጋፋ ነው ያስታወቀው። በአምቦ፤ ወለጋ፤መዳወላቡና ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች ተቃውሞዎች አሉ ቢባልም አቶ ሬድዋን ሁሴን ግን የፖሊሲ ስልጠናው ያለምንም እንከን እየተካሄደ መሆኑን ይናገራሉ።

በአሁኑ ወቅት በሃገሪቱ ባሉ ከ30 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ከስምንት መቶ ሺ በላይ ተማሪዎች በስልጠናው እንደሚሳተፉ ተገልጿል። (ፎቶ ከፋይል ማህደር)

(ምንጭ: የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ DW: መርጋ ዮናስ እና ነጋሽ መሐመድ)

ያለ መድኃኒት የደም ግፊትን ለመቆጣጠር የሚረዱ10 መንገዶች

0
0

እነዚህን 10 የአኗኗር ዘዬዎች በመከተል ደም ግፊትዎን እና በልብ ህመም የመጠቃት እድልዎን ይቀንሱ!

 

 (ከጤና ይስጥልን የተወሰደ)

ከዚህ ቀደም በደም ግፊት ህመም ተጋልጠው (ከ 140/90 ወይም ከዛ በላይ) ሆኖ አስጨንቆት ነበር? ይህን ቁጥርም ለመቀነስ በተደጋጋሚ የህክምና ተቋም ደጅ ረግጠውም ይሆናል፡፡

doctor-suprised-high-blood-pressureጤናማ የአኗኗር ዘዬዎች ይሄን ከፍ ያለ የደም ግፊት ለመቀነስ ይህ ነው የማይባል ሚና ይጫወታሉ፡፡ በእነዚህ አስር የአኗኗር ዘዬዎች የደም ግፊትዎን ይቆጣጠሩ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሃኪም ቤት የሚመላለሱበትን ጊዜም ሊቀንሱ ብሎም ፈፅሞ ሊያስቀሩ ይችላሉ፡፡

‹‹›እንዴት ተደርጎ?›› ካሉ

እስቲ እነዚህን አስር የህይወት ዘዬዎች ይሞክሯቸው፡፡

  1. ክብደትዎን ይቀንሱ

አብዛኛውን ጊዜ የደም ግፊት የክብደት መጨመርን ተከትሎ ሽቅብ ይምዘገዘጋል፡፡ ሌላው ቀርቶ 4.5 ኪሎ ብቻ መቀነስ እንኳን የደም ግፊትን ይቀንሳል፡፡ ብቻ ምን አለፋዎ ክብደትዎን በቀነሱ መጠን በተጓዳኝ የደም ግፊትንም እየቀነሱ ነው፡፡ ሃኪምዎ ጋርም ጎራ ካሉ በምን ያህል ጊዜ ምን ያህል መቀነስ እንደሚኖርብዎት ስለሚያማክርዎ ውጤቱ የተሻለ አመርቂ ይሆንልዎታል፡፡

ክብደት የመቀነሱ ነገር ላይ ተፍ ተፍ ሲሉ ታዲያ በወገብዎ ዙርያ ያለውንም ቦርጭ ችላ አይበሉት፡፡ እሱ ነገር ለከፍተኛ የደም ግፊት የማጋለጥ እድሉ ሰፋ ያለ ነው፡፡ ለመሆኑ የወገብዎ ስፋት ምን ያህል ሴንቲ ሜትር ይሆናል? የማይጠየቅ ጠየቅን ይሆን? እስቲ ይለኩት፡፡  ወንድ ከሆኑ  የወገብዎ ስፋት 102 ሴንቲ ሜትር፤ ሴት ከሆኑ ደግሞ 89 ሴንቲ ሜትርን ከዘለለ የደም ግፊት በዙርያዎ እያንዣበበ ነውና ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ የተቻለዎትን ያህል የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃ ይውሰዱ፡፡

  1. መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ

ቢያንስ ከ30-60 ደቂቃ ከየሳምንቱ ቀናት አብዛኛውን የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማድረግ ከ4-9 ያህል millimetres of mercury የደም ግፊትዎን ይቀንሳል፡፡ ልዩነቱንም በአጭር ጊዜ ያስተውሉታል::ፈጣን ባይሆኑም እንኳን የአካል ብቃትእንቅስቃሴ አያቋርጡ፣ በጥቀቂት ሳምንታት ውስጥ የደም ግፊትወ መቀመስ ይችላሉ፡፡

ከፍተኛ የደም ግፊት ካለብዎት የላይኛው ከ120-139 የታችኛው ደግሞ ከ80-89 ከተመዘገበ ጉዳት  እንዳያደርስብወትና ወደ ከፍተኛ የደም ግፊት እነዳይሸጋገር መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴውም ቢሆን በእቅድና ከሀኪሞ ጋር በመመካከር ቢያደርጉት የተሻለ ይሆናል፡፡ ምናልባትም ሊደፍሩት የማይገባ እንቅስቃሴን በዘፈቀደ አድርገው ነገሩ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዳይሆን፡፡ ምን አይነቱን እንቅስቃሴ ለምን ያህል ሰአት ማድረግ እንዳለብዎት መመካከሩ አይከፋም፡፡ ጂም ገብተው ኤሮቢክሱን ምኑን ከአቅምዎ በላይ ሲያጣድፉት ምናልባትም የ20 ደቂቃ የእግር ጉዞ ይበቃወት ይሆናል፡፡ የእረፍት ቀናትን ተከትሎ የሚመጣ የበዛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ያስወግዱ፡፡ የሳምንቱን ሁሉ በአንድ ቀን እወጣዋለሁ በሚል ስልት አንድ ቀን የሚደረግ የእቅስቃሴ ጋጋታ አያዋጣም፡፡ እንዲያውም ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡

 

  1. ጤናማ አመጋገብ ይኑርዎት

በጥራጥሬና ፍራፍሬ እንዲሁም አትክልት የበለፀጉ እና አነስተኛ የቅባት መጠን ያላቸውን የወተት ተዋፅኦ መመገብ፣ ቅባት የበዛባቸውን እና ኮሌስትሮል ነክ ምግቦችን መቀነስ የደም ግፊትን እስከ 14 millimetres of mercury ያህል ይቀንሳል፡፡ ይህ የአመጋገብ አይነትም dietary approaches to stop hypertension (DASH) ወይም የደም ግፊትን ለማቆም የሚረዳ አመጋገብ ዘዴ በመባል ይታወቃል፡፡ እርግጥ ነው የአመጋገብ ልማድን መቀየር ቀላል አይደለም፡፡ የሆነ ሆኖ ግን በሚከተሉት ሃሳቦች በመታገዝ ጤናማ አመጋገብን መለማመድ ይቻላል፡፡

  • የምግብ መዝገብ ይኑርዎት፡-  የሚመገቡትን ይፃፉ፡፡ ቢያንስ ለሳምንት ይሄን ያድርጉ፡፡ ያኔ በርግጥ የአመጋገብ ልማድዎ ምን እንደሚመስል በመገረም ይገነዘባሉ፡፡ ምን እንደሚመገቡ፣ ምን ያህል እንደሚመገቡ፣ መቼ እና እንዴት እንደሚመገቡም መቆጣጠር ይችላሉ፡፡
  • ፖታሽየም ያብዙ፡- ፖታሽየም ሶዲየም በደም ግፊት ላይ ያለውን ተጽእኖ ይቀንሳል፡፡ ፖታሺየምን ፍራፍሬና አትክልት ከመሳሰሉ ምግቦች ውስጥ እናገኘዋለን፡፡ ለእርስዎ ተመታጣጣኝ የሆነ ፖታሺየም ምን ያህል መሆኑን ለማወቅ ታዲያ ሃኪምዎን ማማከርዎን እንዳይረሱ፡፡
  • ብልህ ገበያተኛ ይሁኑ፡- ‹‹ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት›› ተብሎ እንዳይተረትብዎ ወደ ገበያ ሲወጡ ለመግዛት የሚፈልጉትን መዝግበው ይያዙ፡፡ ይህን ማድረግዎ ፊት ለፊትዎ ያገኙት ሁሉ ቦርሳ ወይም የኪስዎ አቅም እስከፈቀደ ከማጋበስ ይድናሉ፡፡ በተጨማሪም የታሸጉ ምግብ ነክ ነገሮችን ሲገዙ እላያቸው ላይ የተፃፈውን ማስረጃ አገላብጠው ያንብቡና ከእርስዎ ጤናማ አመጋገብ ጋር የማይጣረስ መሆኑን ያረጋግጡ፡፡ ይህን የሚደርጉ ‹‹ብለህ ገበያተኛ›› ይባላሉ፡፡
  • አንዳንዴም ላላ ያርጉት፡- ‹‹ምኑን?›› ይህ የደም ግፊትን ለማቆም የሚረዳ አመጋገብ ዘዬ dietary approaches to stop hypertension (DASH) ለእድሜ ልክ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን እጅግ ከሚወዷቸው ምግቦች ጨርሶ ይቆራረጡ ማለት አይደለም፡፡ አልፎ አልፎ ለአምሮት ያህል ከዚህ የአመጋገብ ስርአት ውጪ የሆነ ከረሜላም ሆነ የተፈጨ ድንች ያለበት መረቅ ቀመስ ቀመስ ቢያደርጉ ክፋት የለውም፡፡

 

  1. ሶድየምን ከምግብዎ ይቀንሱ   

ሌላው ቀርቶ  መጠኑ ትንሽ የሆነ ሶድየም ከምግብዎ ሲቀነስ የደም ግፊትን ከ2-8 millimetres of mercury ያህል ይቀንሳል፡፡

  • በቀን 2300 ሚሊ ግራም በታች ሶድየም ብቻ ይውሰዱ፤
  • በተለይ እድሜያቸው ከ51 ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች፤ በየትኛውም የእድሜ ክልል ለሚገኙ አፍሪካ-አሜሪካውያን ከፍተኛ ደም ግፊት ላለባቸው እንዲሁም ደግሞ ስኳርና ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ላለባቸው ሰዎች በቀን 1500 ሚሊ ግራም በላይ ሶዲየም እንዲመገቡ አይመከርም፡፡
  • ሶዲየምን ለመቀነስ በምግብዎ ውስጥ ምን ያህል የጨው መጠን እንዳለ ይድረሱበት፡- የምግብ መዝገቡ በየእለቱ ምግባችንና መጠጣችን ውስጥ ምን ያህል ሶዲየም እንደተጠቀምን ለማወቅ ያግዛል፡፡
  • የታሸጉ ምግቦች የተለጠፈባቸውን ማስረጃ ያንብቡ፡-  ከቻሉም የሶዲየም መጠናቸው አናሳ የሆነ ምግቦችን እና መጠጦችን መርጠው ይግዙ፡፡
  • ብዙም በምግብነት ሂደት ውስጥ ያላለፉ ምግቦችን ይመገቡ፡- የድንች ጥብስ ስጋዎች እና የመሳሰሉት . . . በምግብነት ሂደት ባለፉት መንገድ ከፍተኛ ሶዲየም ይይዛሉ፡፡
  • ጨውን ያስወግዱ፡-  አንድ የሻይ ማንኪያ ጨው 2300 ሚሊ ግራም ሶዲየም አለው፡፡ ለምግብዎ ጣዕም ለመስጠት ከጨው ይልቅ ቅጠላ ቅጠል እና ቅመማ ቅመሞችን ይጠቀሙ፡፡

ይመችዎት፡- በምንም ተአምር ሶዲየምን በአንድ ጊዜ ከምግብዎ ማስወገድ ካልቻሉ አይጨነቁ፤ በጊዜ ሂደት ሊጠፋ ይችላል፡፡ ጉሮሮዎትም ቢሆን ቀስ በቀስ ጣእሙን ይለምደዋል፡፡

 

  1. የሚወስዱትን የአልኮል መጠን ይቀንሱ

እርግጥ ነው አልኮል በጤና ላይ የራሱ የሆነ ተፅእኖ ይኖረዋል፡፡ በጥቂቱ ከተወሰደ በተወሰነ መልኩ የደም ግፊትን የመቀነስ አቅም አለው፡፡ ከመጠን በላይ መውሰዱ ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናልና አይመከርም፡፡ ሴቶች እና እድሜያቸው 65ን የተሻገሩ ወንዶች በቀን አንድ ብርጭቆ በቂ ሲሆን እድሜያቸው ከ65 በታች ለሆኑ ወንዶች 2 ብርጭቆ እንዳይዘሉ ይመከራሉ፡፡ አልኮልን የመጎንጨት ልማድ ፈፅሞ ከሌለዎ ግን ‹‹ደም ግፊቴን አስተካክላለሁ›› በሚል ምክኒያት እንዳይሞክሩት አደራ! ያንን ቢያደርጉ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናልና ኋላ ማጣፊያው እንዳያጥር፡፡ ከመጠን ከማለፉም የደም ግፊትዎ ለመጨመሩ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከቱለት መሆኑን አይዘንጉ፡፡ የመድኃኒቶቹንም ፈዋሽነት አዳክሞ ለከፋ ጉዳትም ይዳርጋል፡፡

  • የአጠጣጥ ልምድዎን ይቆጣጠሩ፡- ( ይሄ ነገር ሜኑ መሰለ ካላሉ) ከምግብ መዝገብዎ ጎን ለጎን የመጠጥ ዝርዝርዎንም ያሰፍሩ ጤናማ አጠጣጥን ሊቀይሱ ይችላሉ፡፡ አንድ ጊዜ ሊጠጡ የሚፈልጉት ቢራ ከሆነ 355 ሚሊ ሊትር፣ ዌን ከሆነ ደግሞ 148 ሚሊ ሊትር ሌሎች የአልኮል ይዘት ያላቸውን ከ45 ሚሊ ሊትር በላይ የሚወስዱ ከሆነ ይቀንሱ፡፡
  • ቀስ በቀስ ይቀንሱ፡- ከአሎኮል በእጅጉ ተቆራኝተው ከነበረ በአንድ ጊዜ እርግፍ አድርጎ መተው ለቀናት የሚዘልቅ የደም ግፊትን ሊያስነሳ ይችላልና አቀናነሱ ብልሃት የተሞላበት እንዲሆን የባለሙያ እርዳታን ይሻል፡፡ ከሃኪምዎ ጋር በመመካከር ከቀን ወደ ቀን ከሳምንት ወደ ሳምንት በሂደት ይቀንሱ፡፡
  • መጠንዎን አይለፉ፡- ከ4 ብርጭቆ በላይ አልኮል መጠጣት ለሌሎች የጤና ችግሮች ከማጋለጡ በተጨማሪ የደም ግፊትዎን ባልተጠበቀ እና ከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምረው ይችላልና አይሞክሩት፡፡

 

  1. አያጭሱ፤ በአጫሾች ዙርያም አይገኙ

ትንባሆ ሌሎች በርካታ ጉዳቶች እንዳሉት ሆኖ በውስጡ የያዘው ኒኮቲን የተባለ ንጥረ ነገር አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የደም ግፊትዎን ከፍ ያደርጋል፡፡ በተለይ በየቀኑ የሚያጨሱ የለየልዎት አጫሽ ከሆኑ የደም ግፊትዎ ከከፍታው ሳይወርድ እንደገነነብዎ ይቆያል፡፡ ብዙዎቻችን አለማጨሳችንን እንጂ ለሲጋራ ጭስ አለመጋለጣችንን ትኩረት አንሰጠውም፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ሲጋራ በሚጨስባቸው አካባቢዎች መገኘትም ከአጫሹ እኩል የኒኮቲን መጠንን ወደ ሰውነት ማስገባት ሊያስከትል ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ የደም ግፊትን እና የልብ ህመምን ጨምሮ ለሌሎች የጤና ችግሮች ሁሉ ያጋልጣል፡፡

 

  1. ካፌን ቀንሱ

በቡና እና መሰል መጠጦች ውስጥ የሚገኘው ካፌይን ተባለው ንጥረ ነገር በደም ግፊት ላይ ያለው አስተዋፅኦ እስካሁን ድረስ አወዛጋቢ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ካፌይን ያለባቸውን መጠጦች መጠጣት የደም ግፊትዎን ለጊዜውም ቢሆን በአስደንጋጭ ሁኔታ ሊጨምረው ይችላል፡፡ አወዛጋቢው ነገር ይህ ተፅእኖው ‹‹ለጊዜው ብቻ ነው? ወይስ ‹‹ለእድሜ ልክ?›› የሚለው ነው፡፡ እርስዎ ሄንን ይሞክሩ እስቲ. . .

ቡና በጠጡ በ30 ደቂቃ ውስጥ የደም ግፊትዎን ይለኩ፡፡ቁጥሩ ከወትሮው ከ5-10 ጨምሮ ከተገኘ ካፌን ለደም ግፊትዎ አሉታዊ ተፅእኖ ይኖረዋልና ባያዘወትሩት ደግ ነው፡፡

 

  1. ጭንቀትዎን ቀንሱ

ጭንቀት ለጊዜውም ቢሆን የደም ግፊትን ይጨምራል፡፡ ምን ይሆን የሚያስጨንቆት? ስራ፣ ቤተሰብ፣ የገንዘብ እጥረት ወይስ ጤና ማጣት? እስቲ ጊዜ ወስደው የስቡበት፡፡ አንዴ የጭንቀትዎ መንስኤ ምን እንደሆነ ካወቁት እንዴት መቀነስ ወይም ማስወገድ እንዳለብዎ ይረዳሉ፡፡ ያንን ማድረግ ካልቻሉ ግን ቢያንስ ችግሮቹን መቀበል እና በጤናማ መንገድ እንዴት አብሮ መቀጠል እንደሚቻል መላ ማበጀቱ አያቅትዎም፡፡ የትልቅ አተነፋፈስ ልምምድ በማድረግ ፋታ ይውሰዱ፡፡ ማሳጅ ይደረጉ ወይም ዮጋ እና ተመስጥዎ ለዚህ ጥሩ መፍትሄ ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡ በዚህ መንገድ ራስን የመርዳቱ ሙከራ ካልተሳካ በሙያው የሰለጠኑ አማካሪዎችን መጎብኘት ያሻል፡፡

 

  1. የደም ግፊትዎን ከቻሉ በቤትዎ ይቆጣጠሩ፣ በመደበኛነት የሀኪም ክትትል ይኑርዎት   

ከፍተኛ የደም ግፊት ካለብዎት የደም ግፊትዎን በቤትዎ መቆጣጠር ሳያስፈልግዎ አይቀርም፡፡ በላይኛው የክንድ ክፍል የሚታሰረው መቆጣጠሪያም ጥቂት ቢማሩት የራስዎን ደም ግፊት ራስዎ ቢቆጣጠሩት የማያስቸግር ነው፡፡ ከሁሉ በፊት ሃኪምዎን ያናግሩና ይጀምሩ፡፡

  • በቋሚነት የሚከታተልዎ ሀኪም ይኑርዎት
  • ሐኪምዎን በቋሚነት ይጎብኙ (የደም ግፊትዎ ባግባቡ በቁጥጥር ስር ካልዋለ፣ ተጓዳኝ ህመሞች ካብዎት በየወሩ ሀኪምዎን ማግኘት ያስፈልግዎታል፡፡ የደም ግፊትዎን በአግባቡ መቆጣጠር ከቻሉ ደግሞ ከ6-12 ወራት ባሉት ጊዜ ውስጥ ቢጎበኙ በቂ ይሆናል፡፡

10. ከቤተሰብና ከጓደኞች እርዳታ ይቀበሉ

በዙሪያዎ ያሉ ጓደኞችና ቤተሰቦች ለጤናዎ መሻሻል ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታሉና ችላ አይበሏቸው፡፡ እራስዎን እንዲንከባከቡ ሊያበረታቱዎት፤ ሐኪም ቤት ሲሄዱና ሌሎች የደም ግፊት የሚቀንሱ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ አብሮዎት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ጤናዎትን ይጠብቁ!!!

13 የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣኖችና የጦር መኮንኖች በስዊድን አለማቀፍ የጦር ፍርድ ቤት ክስ ተመሰረተባቸው

0
0

arkabe equbay

አቶ በረከት

አቶ በረከት

Samora Yenuswerekeneh gebeyehuana gomez and aba dula gemeda
አቶ አባይ ጸሐዬ

አቶ አባይ ጸሐዬ


(ኢሳት ሰበር ዜና) 13 የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣኖችና የጦር መኮንኖች በስዊድን አለማቀፍ የጦር ፍርድ ቤት ክስ ተመሰረተባቸው ሲል ኢሳት በሰበር ዜናው ዘገበ።

እንደ ኢሳት ቲቪ ዘገባ አርከበ እቁባይ፣ በረከት ስምኦን፣ አባ ዱላ ገመዳ፣ ሳሞራ የኑስ፣ አባይ ጸሃየ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ፣ ሃሰን ሺፋ፣ ሙሉጌታ በርሄ፣ ነጋ በርሄ፣ ወርቅነህ ገበየሁ፣ ኮማንደር ሰመረ እና አንድ ስሙ ያልተገለጸ ሰው በግድያ፣ በአስገድዶ መድፈር፣ በስቃይ፣ ሰዎችን በማንገላታትና በህገወጥ መንገድ በማሰርና ሌሎችንም ተመሳሳይ ወንጀሎች በመፈጸም በስዊድን አለማቀፍ የጦር ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶባቸዋል።

የስዊድን ታዋቂ ጠበቆች ያዘጋጁት የክስ ቻርጅ የስዊድ የአለማቀፉ ወንጀል መርማሪ ፖሊስ ተረክቧል።

ጉዳት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያንም የ130 ሚሊዮን የስዊድን ክሮነር ካሳ መጠየቁን የዘገበው ቴሌቭዥኑ ከስዊድን አለማቀፍ የወንጀል መርማሪ ፖሊስ የተሰጠው መልስ እጅግ አስደሳች መሆኑን አዘጋጆች ለኢሳት መግለጻቸውን ዘግቧል።

የስዊድን ፖሊሶች ምርመራ መጀመራቸውን ያስታወቁ ሲሆን የክሱ አላማ በምርጫ 97 ወቅት ለተገደሉትና ለቆሰሉት ፍትህ መስጠት ነው።

የኦህዴድ ካድሬዎች የህዝብ ሰብልና ንብረትን እያወደሙ እንደሆነ ተገለጸ

0
0

newsኦሮሚያ ክልል ውስጥ ጫንቃ፣ ሁርሙ፣ ዶረኒ፣ ኃይና፣ ከሚሴጎንደራ፣ በዴሳና ሄና በተባሉ ወረዳዎች የኦህዴድ ካድሬዎች የአማርኛ እና ትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ሰብልና ንብረት እያወደሙ መሆኑን ምንጮች ነገረ ኢትዮጵያ ዝግጅት ክፍል ድረስ በመምጣት ገልጸዋል፡፡

ካድሬዎቹ ሰብሉን ማውደም የጀመሩት ከሀምሌ ወር መጀመሪያ ጀምረው እንደሆነና ማሽላ፣ በቆሎ፣ ቡና፣ ባህር ዛፍ የመሳሰሉትን ሰብሎችና ንብረቶች ጨለማን ተገን በማድረግ በገጀራና በመሳሰሉት መሳሪያዎች በማውደም ላይ መሆናቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ይህ ድርጊት እየተፈጸመ ያለው በአካባቢው የሚኖሩት ከላይ የተጠቀሱት ኢትዮጵያውያን ልቀቁ ሲባሉ ለቀው ለመውጣት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሰብላቸውና ንብረታቸው ከወደመ ይለቃሉ ከሚል ስልታዊ ማፈናቀል ዘዴ መሆኑን ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል፡፡

ከሶስት አመት በፊት በቾ በተባለ ወረዳ ተመሳሳይ ተግባር እንደተፈጸመ የገለጹት ምንጮቻችን፣ በወቅቱ ይህ ሰብል የማውደም ተግባር የተመራው በሚሊሻ ጽ/ቤቱ ኃላፊ እንደነበር እማኝነታቸውን ገልጸውልናል፡፡ ይህን ተግባር የፈጸመው ግለሰብ መልካም ስራ እንደሰራ በአሁኑ ወቅት ትልቅ ስልጣን ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህ ስልታዊ የማፈናቀል ተግባር የኦህዴድ ካቢኔ ለሁለት እንደተከፈለ የገለጹት ምንጮቻችን ንብረት የማውደሙ ተግባር ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ተጠናክሮ መቀጠሉ የነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ንብረታቸው እየወደመባቸው የሚገኙ ዜጎች ሌሊት ሌሊት ተደራጅተው ሰብላቸውንና ንብረታቸውን ለመጠበቅ በዝግጅት ላይ በመሆናቸው ከካድሬዎቹ ጋር ሊጋጩ እንደሚችሉና ይህንንም ካድሬዎች የህዝብ ግጭት አስመስለው ስለሚያቀርቡት በህዝብ መካከል ግጭት ሊያስነሳ ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን አክለው ገልጸዋል፡፡

የጋዜጣ አዙዋሪዎች ስራ ሊያቆሙ ነው

0
0

በቅርቡ መንግስት በፋክት፣ አዲስ ጉዳይ፣ ሎሚ፣ እንቁ፣ ጃኖ መጽሄቶችና አፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ፍትህ ሚኒስትር ክስ መመስረቱን ተከትሎ ሚዲያዎቹ ከህትመት በመውጣታቸው ምክንያት ስራ ሊያቆሙ መሆኑን የጋዜጣ አዙዋሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡

newspaper_ethiopiaበአራት ኪሎ፣ ፒያሳ፣ መርካቶ፣ ሳሪስ፣ ቦሌና ካሳንቺስ የሚገኙ የጋዜጣ አዙዋሪዎች በርካታ አንባቢ የነበራቸው መጽሄቶችና ጋዜጦች ከገበያ በመውጣታቸው፣ ሌሎቹን ጋዜጦችና መጽሄቶች በማዞር ህይወታቸውን መምራት ስለማይችሉ የጋዜጣ ማዞር ስራቸውን አቁመው ሌላ ስራ ለመፈለግ መገደዳቸውን ገልጸዋል፡፡

በተለይ በስርጭት ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘው የነበሩት ፋክት፣ አዲስ ጉዳይና ሎሚን በመሸጥም ሆነ በማከራየት አብዛኛውን ገቢያቸውን ያገኙ እንደነበር የገለጹት የጋዜጣ አዙዋሪዎች አሁን ያሉትን ጋዜጦችና መጽሄቶች በህዝቡ ዘንድ እምብዛም ተነባቢ ባለመሆናቸው በዚህ ስራ ህይወታቸውን መምራት እንደማይችሉ ገልጸዋል፡፡ የፍትህ ሚኒስትር ሚዲያዎቹን ከከሰሰ በኋላ ማተሚያ ቤቶች ቀሪዎቹን ጋዜጦችና መጽሄቶች አናትምም በማለታቸው በርካታ ሚዲያዎች ከገበያ መውጣታቸው ጋዜጣ አዙዋሪዎቹ ስራ እንዲያጡ ምክንያት መሆኑ ተገልጾአል፡፡

አዙዋሪዎቹ በእነዚህ ሚዲያዎች ላይ እርምጃ ከመወሰዱ በፊትም ቢሆን ‹‹የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በመሆናችሁ የእነሱን አቋም የሚያንጸባርቁ ጋዜጣና መጽሄቶች ለህዝብ እንዲደርስ እያደረጋችሁ ነው፣ ከአጥፊ ኃይሎች ጋር እየተባበራችሁ ነው›› በሚል እርምጃ ይወሰድባቸው እንደነበርና አሁን በመጽሄትና ጋዜጦች ላይ የተወሰደው እርምጃ ሰርተው መኖር እንዳይችሉ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል፡፡ የእነዚህ ሚዲያዎች በመዘጋታቸው የገቢ ምንጫቸውን ከማጣታቸው በተጨማሪም በሚዲያው ላይ የተወሰደው እርምጃ በእነሱም ላይ የማይወሰድበት ምክንያት እንደሌለ ባለፉት ጊዜያት የደረሰባቸው በደል ማሳያ መሆኑን በመግለጽ ስራውን ሊያቆሙ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ ከወራት በፊት ገዥው ፓርቲ የሚቀጥለው ምርጫ ተከትሎ ሚዲያዎች ወደ ክፍለ ሀገር እንዳይደርሱ አከፋፋዮችንና አዙዋሪዎችን በማደራጀት ሚዲያዎችን ከስራ ለማስወጣት እንዳቀደ መገለጹ ይታወቃል፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየወጡ ያሉ ስሞች

0
0

1. ልማቱ ፈጠነ
2. ቦንድነህ አባይ
3. ሊግ ይበልጣል
4. አኬልዳማ ታዬ
5. ኑሮ ውድነህ
6. ፌደራል እርገጤ
7. ስልጣኑ በዛብህ
8. ኮንዶሚኒየም ለማ
9. ግምገማ ከበደ
10. ተሳለጭ ሃገሬ
11. መተካካት ተሻለ
12. ባድመ ይበቃል
13. አሰብ ተስፋዬ
14. ቻይና ፍቅሩ
15. መብራት ይታገሱ
16. ቴሌነሽ በዝብዝ
17. አክስዮን ሰብስቤ
18. ቫቱ በዛብህ
19. ግብሩ ጫንያለው
20. ህገመንግስት ጣሴ
21. ነጠፈ ብሩ
22. ፌስቡክ ተመስገን
23. ሀያልነሽ መንግስቴ
24. አምስትለአንድ አደራጀው
25. ግንቦት ሃያ ገብረማርያም

(ምንጭ: Ethio-Sunshine ፌስቡክ)

በአንባቢያን የተጨመሩ:

Gulilat Kasahun የጨመሩት

1. ምርጫዬ ደረሰ
2. ደሞዝ ስሜነህ
3. ይበቃል ገዛኸኝ
4. ብርቅይሁን ምሳዬ
5.ሞላልኝ ጎርፉ
6. ብሩ ባይከዳኝ
http://www.goolgule.com/new-names/

Comment

ዓይናችን ለወቅታችን!  (ሥርጉተ ሥላሴ)

0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 29.08.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

 

Cry-ethiopiaወርቅ ይቀልጣል። ወርቅ ቀልጦ ከፈሰሰ ደግሞ መልሶ ለማግኘት ይቸግራል፤ አበው „ የፈሰሰ ያልታፈሰ“ ያሉን እኮ ለላንቲካ አይደለም። ብሂሉ ተቋም ነው። መርኹ የምክር አገልግሎትን በተመክሮ ያዘመረ ነው። ይህቺ ወቅት አዎን ይህቺ ወቅት የወያኔ …. ማዕከላዊ አካል ተሰቅዞ የተያዘበት ወርቅ …. ወቅት እንዳትሾልክ እንዳታመልጥ … ጥንቁቅ፤ ብልህ፤ ብልጥ፤ ሥልጡን እንሁን። እንብለጠው የወያኔ ሃርነት ትግራይን ደባና ሸር፤ ቂምና በቀል – እንቅደመው።

ወቅቱን እናዳምጠው። ወቅቱን እናጣጥመው። ወቅቱን እንሁነው። ወቅቱን እናዋህደው – በመስተዋድድ። ይነግረናል … ያውጃል …. ይመሰክራል ….. ይጣራል …. ተጋሩኝ እያለ። ተጠቀሙብኝ እያለ። ወቅቱ የቅምጥል ጊዜ አይደለም። የመከራ ጊዜ ነው፤ የሽርሽር ጊዜ አይደለም። በጽሞና መርምረን ወቅቱ ለጠዬቀን ማናቸውም ሁኔታ ወቅቱን በድርጊት አስመችተን ልናስተናግደው በእጅጉ ይገባል። የወቅት ጽናታዊ ተደሞ እኛን እዬቀደመን ነው። የወቅት በሳል ተመክሮ እኛን እዬበለጠን ነው። የወቅት ጽሞናዊ አርምሞ እኛን እያለፈን ነው። እኮ ምን ምን እንጠብቃለን? „አሻምን በተባ ሥራ ለመሞሸር“ አይበቃም እንዲህ በቋሳ ገጀሞ መከትከት …. ሃላፊነት በማይሰማው ወመኔ መታረስ –

አዎን እኔ እላለሁ … ይህ የዘመናዊነት የእናቴ መቀነት የተጨወትነበት፤ ፍላጎታችን ያሾለክንበት ጊዜን መለስ ብለን በመገመገም ቀዳሚወን ጥያቄ ባሊህ እንበለው። ባሊህ ማለት ብቻ በቂ አይደለም – እንቀበለው የዕንባን የጭንቅ ምጥ ጥሪውን። አለሁልህ እንበለው። ጥሪው የደም ዕንባ ጥሪ ነው። ቀንም ፋታም የማይሰጥ። ላሜ ወልዳ ዬት ትታሰር ግብ ግብ በአስቸኮይ ቆሞ ሁሉም እንደ አንድ – አንዱም እንደ ሁሉ ቀዳዳውን በመድፍን፤ ክፍተቱን በሞሙላት ሰባራውን በመጠገን፤ ወለምታውን ወጌሻ በመሆን በመከራ ጊዜ አብረን ሆነን ህዝብና ሀገርን፤ ታሪክና ትውልድን እናድን ዘንድ ዓይናማው ወቅት እያሳሰብን ነው። አስረግጦ እያሳዬን ነው …. ተንበርክክኮ እዬለመነን ነው፤ መሪ ሆኖ እዬመራን ነው …. በሳል ሆኖ፣ ከእኛም ቀድሞ ተመክሮውን እያቀናልን ነው። ሰነፍ አንሁን —

ገለጥ እናድርገው። በተለያዩ ትብትቦች የተሸበቡ ድቡልቡልና ጠፍጣፋ ሙልሙል ፍላጎቶቻችን እናርቃቸው። ወቅቱ እራሱ መሪውን ያዘጋጃል። ለነገም ሻማ ሁኖ ሊቀልጥ ወቅቱ እራሱን አስቀድሞ እዬተጣራ ነው። አቤት እንበለው። ወይ እንበለው። እሺ እንበለው።

ለዛሬም ለነገም ለነገም ለተወዲያም አዎንታዊ ዘላቂ መስመራችን እንዲሆን እንከብክበው። እንወስን። እንቁረጥ። በራሳችን ላይ የማያዳግም የውስጥ ለውጥ አምጥተን፤ አራሳችን ወቅሰን ከወቅቱ ብሄራዊ ጥሪ ጋር አብረን እንሰለፍ … በፈጠራ – በአዳዲስ የለውጥ አብነቶች ፍላጎታችን እናሳምረው – ራዕያችን እናብራው።

አወን ወቅቱ ዓይናችን ሆኗል። መንፈሳችን አብርተን ካለ ቀጠሮ በማናቸውም የትግል መስመር፤ በማናቸውም የነፃነት እንቅስቃሴ በሁለመናነት በመደጋገፍ፤ በመተባበር፤ በመረዳዳት አብረን – አብርን እንሰለፍ።  በአንድ እግሩ የተጠለለውን እንሰሳዊ ሥርዓት ለማሰወገድ …. ዓይናችን – የሃቅ ዓይን እናድርገው …. ልባም እንሁን። ሥልጡን እንሁን። የ97 ድል እዲደገም …. 12 አካላችን እናሰራው …. ድል – ድል ይሆናል። ናፍቆት እውን ይሆናል …. ከሰባራ ሰንጣራ ስንጥቅ እራስን መታደግ ከተቻለ ….

ይህን ዓይናችን ለወቅታችን!እርእሰ አንቀጽ በድምጽ ማደመጥ ይሻሉን? የ28.09.2014 የጸጋዬ ራዲዮን ዝግጅት በዚህ አድራሻ ያገኙታል። www.tsegaye.ethio.info Aktuell Sendung Radio Lora (Tsegaye Radio)

 

ስንብት – የኔዎቹ አብራችሁኝ ስለቆያችሁ ወደድኳችሁ ፍቅሬንም ሰጠኋችሁ  – አዘናክቼ። መሸቢያ ሰንበት።

 

ድል ለኢትዮጵ ሰፊ ህዝብ! ሞትና ሽንፈት ለወያኔ ሃርነት ትግራይ!

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 


የኢትዮጵያውያን ስደተኞች መበራከት

0
0

አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ

መንግሥት በአንዳንድ የግል ጋዜጦች ላይ ክስ ከመሠረተ እና ባለፈው ግንቦትም ዘጠኝ ጋዜጠኞች እና የድረ ገፅ አምደኞች ከታሰሩ ወዲህ ቁጥራቸው ትንሽ የማይባል ጋዜጠኞች ኢትዮጵያን ለቀው ወጥተዋል።


43f5db4e4
ባለፉት ጊዚያት ሀገር እየለቀቁ የወጡት ግን ጋዜጠኞች ብቻ አይደሉም፣ ብዙ ወጣቶችም በተለያዩ መንገዶች መሰደዳቸውን የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች ያሳያሉ። ለጋዜጠኞች ደህንነት የሚሟገተው ድርጅት፣ የ«ሲ ፒ ጄይ» የምሥራቅ አፍሪቃ ተጠሪ ቶም ሮድስ፣ ኢትዮጵያውያን ሕይወታቸውን ለአደጋ እያጋለጡ የሚወጡበት ጉዳይ ከሰብዓዊ መብት ጋ የተያያዘ ነው ይላሉ።

ብዙ ወጣት ኢትዮጵያውያን በየመን ፣ በኬንያ እና ታንዛንያ፣ እንዲሁም በሱዳን እና በሊቢያ በኩል እያደረጉ አደገኛ በሆነ ጉዞ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ፣ ደቡባዊ አፍሪቃ እና አውሮጳ ለመግባት ይሞክራሉ፣ በዚሁ ሙከራቸው ወቅት በየበረሃው እና በየጫካው ወድቀው የሚቀሩት እና ባህር የሚበላቸው ጥቂቶች እንዳልሆኑ እና የሕገ ወጥ ሰው አሸጋጋሪዎች ሰለባም እንደሚሆኑ በየጊዜው የዜና ምንጮች የሚያወጡዋቸው ዘገባዎች ያሳያሉ፣ ከጥቂት ጊዜ በፊት በዚምባብዌ በኩል አድርገው ደቡብ አፍሪቃ የገቡ 24 ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ፈቃድ ስላልነበራቸው በሀገሪቱ ፖሊስ መያዛቸው የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያውያኑ ራሳቸውን ለዚህ ሁሉ መከራ የሚያጋልጡበት የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን ለጋዜጠኞች ደህንነት የሚሟገተው ድርጅት፣ «ሲ ፒ ጄይ» የምሥራቅ አፍሪቃ ተጠሪ ቶም ሮድስ ገልጸዋል።

« ሁለት ዋነኛ ምክንያቶች ያሉ ይመስለኛል። የመጀመሪያው፣ መንግሥት ማንኛውንም ትችት ወይም ተቃውሞ በቸልታ የማለፍ ልማዱም ሆነ አሰራር በፍፁም የለውም። እና ከማንኛውም ትችት የሚሰነዝር ቡድን ጋ የሆነ ግንኙነት ካለህ፣ ምንም እንኳን ግንኙነቱ ደካማ ቢሆንም፣ የመንግሥት ክትትል ዒላማ ልትሆን ትችላለህ። ሁለተኛው ደግሞ፣ የፍትሑ አውታር በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ነው ፣ እና አንዴ በመንግሥት ክስ ከቀረበብህ ወደ ወህኒ መውረድህ የማይቀር ነው፣ ስለዚህ ብዙዎቹ የረጅም ዓመታት የእስራት ቅጣት እንዳይደርስባቸው መሸሹን መርጠዋል። »

የ«ሲ ፒ ጄይ» ቶም ሮድስ
ለብዙዎች ሀገር እየለቀቁ መውጣት ከሀገሪቱ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ጋር የተያያዘ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት ቶም ሮድስ በሚቀጥለው ዓመት በሀገሪቱ የሚካሄደው ምርጫ ማበርከቱንም ቶም ሮድስ ይናገራሉ።

« ምርጫ በሚቀጥለው ዓመት ግንቦት ወር ይደረጋል። ይህም፣ ምንጮች እንደነገሩኝ፣ በመንግሥቱ ውስጥ ያሉት ፣ ሥልጣን እንደያዙ ለመቆየቱ ስለሚፈልጉ፣ ሊነሳ የሚችል ማንኛውንም ትችት ለማፈን እየሞከሩ ነው። ተመሳሳይ ሁኔታ ካሁን ቀደም አይተናል። እአአ በ2005 ዓም ተቃዋሚው ወገን ምርጫውን ሳያሸንፍ አልቀረበትም የተባለው ምርጫ ውጤት ክርክር ባስነሳበት ጊዜ ተመሳሳይ ሁኔታ ተመልክተናል። እና ከዚያን ጊዜ ወዲህ እምነት ያጣው መንግሥት፣ በሥልጣን ለመቆየት ሲል ጋዜጠኞችን ብቻ ሳይሆን የሲቭል መብት ተሟጋችቾችን እና ጠበቆችንም ጭምር ለመምታት ወደኋላ አላለም። »

ቶም ሮድስ፣ ጋዜጠኞች እና ብዙ ወጣቶችን ከስደት እና በሰበቡ ከሚደርስባቸው መከራ እና ስቃይ ለመታደግ የኢትዮጵያ መንግሥት ፖሊሲውን ሊከልሰው ይገባል ባይ ናቸው።
«መንግሥት አንዳንድ ፣ ለምሳሌ፣ እአአ በ2009 ዓም የወጣውን የፀረ ሽብርን የመሳሰሉትን ሕጎች ዳግም ማጤን ይኖርበታል። ፖሊሲውን በጥሞና ስንመለከተው፣ በሀገሪቱ የሕግ ሥርዓት ውስጥ ፍትሓዊ አሰራር የተጓደለበት ሁኔታ ሰዎች በሕጉ ሥርዓት ላይ እምነት እንዳያድርባቸው አድርጓል። ይህ ባይሆን ኖሮ ብዙ ሰው ሀገር እየለቀቀ ሲሸስ ባልታየ ነበር። እርግጥ፣ ጉዳዩ የተወሳሰበ ነው። የሀገሪቱ መንግሥት ልማትን በተመለከት ጉልህ መሻሻል አድርጓል። በዚህም የተነሳ በኤኮኖሚ ምክንያት መውጣት የሚገደዱት ኢትዮጵያውያን በጣም ትንሽ ነው። ይሁንና፣ የልማቱ እንቅስቃሴ የሚደረገው ለሰብዓዊ መብት መከበር ትኩረት ሳይሰጥ ነው። ይህም ሰዎች ሀገራቸውን እንዲወጡ ያስገድዳል። መንግሥት የሚሰራበት የመሬት መቀራመትን ፖሊሲ ምን ያህል ብዙ ወጣቶችን እንደሚነካ መመልከት ይበቃል። »

የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ መብቱን ይዞታ እንዲያሻሽል እና የፕሬስ ነፃነትን እንዲያከብር ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጫና ሊያሳርፍ እንደሚገባ ድርጅታቸው በተደጋጋሚ ቢያሳስብም፣ እስካሁን ይህ ነው የሚባል የረባ ውጤት ሊያስገኝ የሚችል ግፊት ባለማሰረፉ ቶም ሮድስ አልተደሰቱም

« በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አሰራር ብዙ ጊዜ ቅር ተሰኝቼአለሁ። ምክንያቱም የሚናገሩት እና የሚያደርጉት የተለያየ ነውና። እና ለምሳሌ ዩኤስ አሜሪካ እና ብሪታንያን የመሳሰሉ ዓበይት ለጋሽ ሀገራት ለኢትዮጵያ ሊያቀርቡት ያቀዱትን ግዙፍ ርዳታ፣ የሰብዓዊ መብት ይዞታን ከግንዛቤ ሳያስገቡ ሊሰጡ አይገባም። »

በአዲስአበባ የሞባይልና ኢንተርኔት አገልግሎት መዳከም አሳሳቢ ሆኗል

0
0

ኢሳት ዜና :-  የኢትዮ- ቴሌኮም በአዲስአበባ የኢንተርኔት አገልግሎትን በማሳደግ የ4ጂ አገልግሎት መስጠት የሚችልበት ደረጃ
ደርሻለሁ ቢልም የአገልግሎቱ ጥራት በከፍተኛ ደረጃ እየወደቀ መምጣቱ ተጠቃሚዎች በከፍተኛ ደረጃ ምሬት ውስጥ እየከተተ ነው፡፡

Head-office-Building-of-ETCበ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ወጪ የቻይናዎቹ ሁዋዌ እና ዜድቲኢ የሚባሉ ኩባንያዎች የማስፋፋፊያውን ፕሮጀክት ለመስራት ከኢትዮቴሎኮም ጋር በዚህ ዓመት መጀመሪያ የተፈራረሙ ሲሆን የአዲስአበባው ፕሮጀክት እስከሰኔ ወር 2006 ዓ.ም መጨረሻ ተጠናቆ የተሻለ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ ነበር፡፡ ኢትዮቴሌኮም የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ በስኬት ተጠናቋል በሚል ተደጋጋሚ መግለጫ የሰጠ ሲሆን ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የሞባይል ሒሳብ ለመሙላትና ቀሪ ሒሳብ ለመጠየቅ አለመቻል፣ የፈለጉትን ሰው በቀላሉ ደውሎ ማግኘት አለመቻል፣ ያልደወሉበት ሒሳብ መቆረጥ፣ የሞባይል ኢንተርኔት በተለይ ፈጣን ነው የተባለውን 3ጂ ጨምሮ ደካማ መሆን፣ የፌስቡክ አካውንት አለመከፈት፣ የገመድ አልባ ኢንተርኔትና ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረጥና ደካማ መሆን በስፋት እየታየ ነው፡፡

ያነጋገርናቸው ተጠቃሚዎች የአፍሪካ ህብረትና የሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የሆነችው አዲስአበባ ጥራት ያለው የሞባይልና ኢንተርኔት አገልግሎት ብርቋ መሆኑ እንደሚያሳዝናቸው ተናግረዋል፡፡ አንድ አስተያየት ሰጪ እንዳሉት ኢትዮቴሌኮም የተሻለ ማስፋፊያ አድርጌለሁ እያለ በተግባር ይህ አለመታየቱ ምናልባትም መንግሥት በተለይ በማህበራዊ ድረገጾች እየተሰነዘረበት ያለውን ጠንካራ ተቃውሞና ትችት ለማፈን የተጠቀመበት አዲስ ዘዴ ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ እንደገባው ተናግሮአል፡፡

የኢንተርኔት ኔትወርክ እንደመብራት ብልጭ ድርግም እያለ ብዙዎች በመበሳጨት አገልግሎቱን እየተው ነው ያለው አስተያየት ሰጪያችን መንግሥት በዚህ ሒደት ከሚያጣው ገንዘብ ይልቅ ተቃዋሚዎቹን ለማፈን ትልቅ ግምት ሳይሰጠው እንዳልቀረ አስረድቷል፡፡

ሰማያዊና ቴዲ አፍሮ የስልጠናው የልማታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ትግላችንንን ፈተናዎቹ አጀንዳ ሆነዋል (ሰነዱን ይመልከቱት)

0
0

ምንሊክ ሳልሳዊ

‹‹ኢህአዴግ ራሱ በአኖሌ ስም እየነገደ ለእሱ የሚቀርቡት አካላት ከእነ ቴዲ አፍሮና ሰማያዊ ፓርቲ ጋር አላትሞ መውቀሱ የሚያስገርምና ውይይት ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ያስነሳ ነው›› የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጥቁር ሰው አልበም በስልጠና ሰነዱ ላይ ለአክራሪነት ምሳሌ ተደርጎ የቀረበ ሲሆን ተማሪዎችም ቴዲ አፍሮ ለአገር አንድነት የቆመ መሆኑን በመግለጽ መከራከራቸውን ገልጸውልናል፡፡
10660354_570682683057394_4672553645250217075_nበኢህአዴግ ጽ/ቤትና በትምህርት ሚኒስትር ትብብር ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እየተሰጠ ባለው ስልጠና ሰማያዊ ፓርቲና ቴዲ አፍሮ አጀንዳ መሆናቸውን ሰልጣኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ‹‹የልማታዊ ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ትግላችንና ፈተናዎቹ›› በሚለውና በአሁኑ ወቅት ከአዲስ አበባ ውጭ በየ ክልሉ እየሰለጠኑ ለሚገኙት ተማሪዎች እየተሰጠ ባለው ስልጠና ሰማያዊ ፓርቲና ቴዲ አፍሮ ለልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባታ ፈተናዎች ተብለው ቀርበዋል፡፡ አሰልጣኞቹ ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹መንግስት የእምነት ነጻነት ያክብር!›› እያለ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች በአክራሪነት የፈረጀ ሲሆን ቴዲ አፍሮም ‹‹ጥቁር ሰው›› በሚል ለህዝብ ያደረሰው አልበም ተመሳሳይ ውንጀላ ቆርቦበታል ሲሉ ሰልጣኞቹ ገልጸዋል፡፡

ሰማያዊና ቴዲ አፍሮ በተለይ በውይይት ወቅት ከአሰልጣኞቹ ሰፋ ያለ ወቀሳና ውንጀላ እንደደረሰባቸው ሰልጣኞቹ ገልጸዋል፡፡ ተማሪዎቹ በበኩላቸው ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ እንደ አንድ ለህዝብ እንደቆመ ፓርቲ መንግስት በእምነት ጣልቃ እንዳይገባ መጠየቅና መታገል መብቱ ብቻ ሳይሆን ግዴታው ነው፡፡›› ብለው እንደተከራከሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጥቁር ሰው አልበም በስልጠና ሰነዱ ላይ ለአክራሪነት ምሳሌ ተደርጎ የቀረበ ሲሆን ተማሪዎችም ቴዲ አፍሮ ለአገር አንድነት የቆመ መሆኑን በመግለጽ መከራከራቸውን ገልጸውልናል፡፡ ተማሪዎቹ አክለውም ‹‹ጥቁር ሰው የሚለው ተወዳጅ ዘፈን በገዥው ፓርቲ ቁጥጥር ስር ከሚገኙት ውጭ በአብዛኛዎቹ ሚዲያዎች በስፋት ይለቀቃል፡፡በስልጠናው እያየነው እንዳለነው ግን ገዥው ፓርቲ ቴዲ አፍሮን ብቻ ሳይሆን ሚዲያዎቹንም በአክራሪነት እየከሰሰ መሆኑ አሳዛኝ ነው፡፡›› ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን ገልጸዋል፡፡

123

በሰነዱ ‹‹ጠባብና ትምክተኛ ተብለው የተፈረጁ ኃይሎች ተመጋጋቢ ናቸው›› ተብለው የቀረቡ ሲሆን ‹‹የትምክት አስተሳሰብ የተጠናወተው ሚዲያ ‹‹ጥቁር ሰው›› በሚል ዘፈን ሚኒሊክን ሲያሞካሽ በጠባብነት የተለከፈው ሚዲያ የአኖሌን ግፍ ህዝብን ለመለያየት ይጠቀምበታል›› ሲል ሁለቱንም በጅምላ ይወቅሳል፡፡ ይህን ስልጠና እየወሰዱ ያሉ ተማሪዎች ‹‹ኢህአዴግ ራሱ በአኖሌ ስም እየነገደ ለእሱ የሚቀርቡት አካላት ከእነ ቴዲ አፍሮና ሰማያዊ ፓርቲ ጋር አላትሞ መውቀሱ የሚያስገርምና ውይይት ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ያስነሳ ነው›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ‹‹እራሱ ህዝብን በተለያዩ መንገዶች ህዝብን እየነጣጠለና የከፋፍለህ ግዛ ስርዓት አስፍኖ በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምኑትን አካላት በማይገባቸው ክስ መክሰሱ የዪኒቨርሲቲ ተማሪዎች አላዋቂ አድርጎ መውሰዱንና ንቀቱን የሚያሳይ ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ ሰልጣኝ ተማሪዎች የላኩልንን የሰነዱን አካል እንደሚከተለው አያይዘነዋል፡፡

New sened

 

 

እስር ቤት የሚገኙት የሽዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታና ዳንኤል ሺበሽ በጠበቃቸው እንዳይጎበኙ ተከለከሉ

0
0

Habtamu abrhayeshiwas danielእነ የሽዋስ በጠበቃቸው እንዳይጎበኙ ተከለከሉ በማዕከላዊ እስር ቤት የሚገኙት የሽዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታና ዳንኤል ሺበሽ በጠበቃቸው እንዳይጎበኙ መከልከላቸውን የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ከበደ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ የማዕከላዊ ምርመራ ታሳሪዎቹ በሳምንት ሁለት ቀን (ረዕቡና አርብ) በጠበቃቸው እንዲጎበኙ ፈቅዶ የነበር ቢሆንም ጠበቃ ተማም አባ ቡልጉ ደንበኞቻቸውን ለማግኘት በተደጋጋሚ ወደ ማዕከላዊ አቅንተው ሳያገኟቸው ቀርተዋል ተብሏል፡፡ ተማም አባ ቡልጉ ወደ ማዕከላዊ ባቀኑባቸው ቀናት ‹‹ሌላ ቀን ታገኛቸዋለህ፣ ስብሰባ ላይ ነን›› እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች እያቀረቡ ቀኑን ሙሉ ሲያስጠብቋቸው እንደነበርና በተለይ በዛሬው ቀን ነሃሴ 23 ደንበኞቻቸውን ለማግኘት እየጠበቁ ከዋሉ በኋላ ‹‹ከፈለክ ችሎት ላይ ታገኛቸዋለህ፡፡ ከዚህ ማግኘት አትችልም›› ተብለው እንደተመለሱ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ‹‹ታሳሪዎች በጠበቃቸው፣ በኃይማኖት አባታቸው፣ በጓደኛና በዘመድ የመጎብኘት መብት አላቸው፡፡ በሳምንት ይህን ቀን ተብሎ በህግ አልተወሰነም፡፡›› በሚል በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ ነው የሚጎበኙት መባሉም ስህተት ነበር ያሉት አቶ ይድነቃቸው ‹‹ጭራሹን እንዳይጎበኙ መደረጉ ደግሞ ሆን ተብሎ የተፈጸመ ህገ ወጥ ድርጊት ነው›› ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ስልጠና ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ተማሪዎች ጠንከር ያሉ ጥያቄዎችን ማንሳት መቀጠላቸውን ሰልጣኞቹ ገለጹ፡፡

0
0

‹‹ለግራዚያኒ ዘብ የቆመው ኢህአዴግ እንዴት ኢትዮጵያዊ ይባላል?››
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) Via ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia

• ‹‹ተቃዋሚዎችን እያሰራችሁ እንዴት ተቃዋሚ የለም ትላላችሁ››
• ተማሪዎቹን በፖሊስና ደህንነት እያሸማቀቁ ነው
• ‹‹ብሄራዊ ቋንቋ የሌላት አገር ሉዓላዊ ልትባል አትችልም››
• ‹‹አንቀጽ 39 ከህገ መንግስቱ ይውጣ››
• ‹‹ለግራዚያኒ ዘብ የቆመው ኢህአዴግ እንዴት ኢትዮጵያዊ ይባላል?
• ተማሪዎቹን በፖሊስና ደህንነት እያሸማቀቁ ነው


addis-ababa-universityኢህአዴግን ደግፈው የሚከራከሩ ተማሪዎች ቁጥር በማነሱ ፖሊስና ደህንነቶች ሲቪል መስለው እንደሚከራከሩና የሚጠይቁትንና ጠንካራ አስተያየት የሚሰጡትን ተማሪዎች ለብቻቸው እየጠሩ እያሸማቀቁ መሆኑ ታውቋል፡፡ ሰልጣኝ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስልጠና ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ተማሪዎች ጠንከር ያሉ ጥያቄዎችን ማንሳት መቀጠላቸውን ሰልጣኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ባለፉት የስልጠና ጊዜያት ኢህአዴግን ላለፉት 23 አመታት አይተነው ለውጥ ስላላመጣ ስልጣን ሊለቅ ይገባል፣ የአሰብ ወደብ ለኤርትራ መሰጠቱ ስህተት ነው፣ የሸክ ኑሩ ግድያ ሴራ ነው፣ የባህርዳሩ ግጭት የብአዴን ሴራ ነው የመሳሰሉት ጥያቄዎች መነሳታቸው ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ጠንከር ያሉ ጥያቄዎች እየተነሱ መሆናቸውን ሰልጣኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የህገ መንግስት ማሻሻያ በደብረማርዎስ ከተማ የሚሰለጥኑ ተማሪዎች ህገ መንግስቱ ማሻሻያ እንዲደረግበት ጠይቀዋል፡፡

በተለይም አንቀጽ 39 ‹‹የኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ልዩነት ለመፍጠር ህገ መንግስቱ ላይ የተቀመጠ አንቀጽ በመሆኑ ህገ መንግስቱን ለማሻሻል የተቀመጡት ውጣ ውረዶች ሳይገድቡት ከህገ መንግስቱ ሊወጣ ይገባል›› ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ‹‹አንቀጽ 39 እንዲሁ ከሚቀየር የኢትዮጵያ ህዝብ ህዝበ ውሳኔ አድርጎበት ከህገ መንግስቱ ቢወጣም የተሻለ ነው፡፡›› የሚል ሀሳብ ያቀረቡ እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡ ብሄራዊ ቋንቋ ተማሪዎቹ ‹‹ኢትዮጵያን ያህል አገር ለምን ብሄራዊ ቋንቋ አይኖራትም?›› ብለው የጠየቁ ሲሆን አሰልጣኞቹ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ የሌላት መሆኑን ተናግረው ከማለፍ ውጭ ለጥያቄው መልስ መስጠት እንደተቸገሩ ሰልጣኞቹ ገልጸዋል፡፡

ተማሪዎቹ በበኩላቸው ‹‹ህገ መንግስቱ ሲረቀቅ የብሄራዊ ቋንቋ ጉዳይ የተረሳው ሆን ተብሎ ነው፡፡ ብሄራዊ ቋንቋ የሌላት አገር ከሌሎች ብሄራዊ ቋንቋ ካላቸው አገራት ጋር እኩል ሉዓላዊ ልትሆን አትችልም›› ሲሉ አስተያየት መስጠታቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ኢህአዴግ ኢትዮጵያዊ ነው? መጋቢት 6/2005 ዓ.ም ሰማያዊ ፓርቲ፣ ባለራይ ወጣቶችና በአቶ ታዴዎስ ታንቱ የተመራ የአገር ተቆርቋሪ አካል ለግራዚያኒ የቆመውን መታሰቢያ ተቃውሞ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የሰማዕታቱ ሀውልት ጀምሮ ወደ ጣሊያን ኤምባሲ የሚያመራ ሰልፍ ጠርቶ ነበር፡፡ ይሁንና ሰልፉ ከመጀመሩ በፊት ፖሊስ ሰልፉን በኃይል በመበተን ተሳታፊዎቹን ማሰሩ ይታወቃል፡፡

በስልጠና ላይ የሚገኙት ተማሪዎቹም ‹‹ኢትዮጵያውያንን የቀጠፈውን የቅኝ ገዥ ጀኔራል ላይ ተቃውሞ እንዳይነሳ የፈለገና፣ በእሱ ላይ ተቃውሞ ሰልፍ ለመውጣት የሞከሩትን የደበደበና ያሰረው ኢህአዴግ እንዴት ኢትዮጵያዊ ሊባል ይችላል? ኢህአዴግ ለግራዚያኒ ጠበቃ ቆሞ እንዴት ኢትዮጵያዊ ይባላል?›› ይባላል የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡ ተቃዋሚዎቹን እያሰራችሁ አሰልጣኞች ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሰላማዊ ሰልፍም ሆነ በሌሎች አጋጣሚዎች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ትክክል አለመሆናቸውን የገለጹ ሲሆን ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ እንደሌለም ተገልጾአል፡፡ በተቃራኒው ተማሪዎቹ በተቃዋሚዎቹ ላይ የሚደርስባቸውን ጫና እና የታሰሩትንም በምሳሌነት በማንሳት ‹‹ተቃዋሚዎቹን እያሰራች እንዴት ተቃዋሚ የለም ትላላችሁ? የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡

ኢህአዴግ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱን ለማሳካት አቅም እንደሌለውና አፋኝ እንደሆነ የሚገልጹ አስተያየቶችንም ተነስተዋል፡፡ ተማሪዎቹን ማሸማቀቁ ቀጥሏል በተለያዩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ጥያቄ እንዳይጠይቁ ማሸማቀቁ እንደቀጠለ ነው ተባለ፡፡ በተለይ በልደታ ግቢ በመሰልጠን ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ጥያቄ ሲጠይቁም ሆነ አስተያየት ሲሰጡ ስለማንነታቸው አላስፈላጊ ዝርዝር ጥያቄዎችን እየተጠየቁ እንደሆነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ኢህአዴግን ደግፈው የሚከራከሩ ተማሪዎች ቁጥር በማነሱ ፖሊስና ደህንነቶች ሲቪል መስለው እንደሚከራከሩና የሚጠይቁትንና ጠንካራ አስተያየት የሚሰጡትን ተማሪዎች ለብቻቸው እየጠሩ እያሸማቀቁ መሆኑ ታውቋል፡፡

ከአፈናው በተጨማሪ በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች የሚሰለጥኑትን ተማሪዎችን በመደለያነት ሙዚቃ፣ ከፍተኛ ወጭ የወጣበት ምግብና የመዝናኛ ምሽቶች እየተደረጉላቸው መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል በመላ አገሪቱ በስልጠና ላይ ለሚገኙት ተማሪዎች ስልጠና የሚሰጡት ከወራት በፊት በመቀሌ ስልጠና የተሰጣቸው የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

 

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያንን/ብሔራቸውን ነጻ ለማውጣት በኤርትራ የሚንቀሳቀሱ የነጻ አውጪ ድርጅቶች ዝርዝር

0
0

Eriteria1- የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ደምሕት )
2 -የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦነግ – ዳውድ )
3- የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦነግ – ከማል )
4- የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ)
5- የግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ሃይል
6- የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አርበኞች ግንባር
7- የድቡብ የእኩልነት እን የፍትህ ግንባር
8- የጋንቤላ ነጻ አውጪ ግንባር
9 – የቤንሻንጉል ነጻ አውጪ ግንባር
10 – አርዱፍ የአፋር ነጻ አውጪ
11- ጋደሌ የአፋር ነጻ አውጪ
12 -የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች ንቅናቄ
13 – የአፋር ሕዝቦች ንቅናቄ
14 -የአፋር አንድነት ዲሞክራቲክ ፓርቲ
15 – ትንሳኤ አርበኞች ግንባር
16 – የአፋር ነጻ አውጪ የጋራ ሕብረት

እርስዎ የሚያውቁት ካለ ይጨምሩበት ።

 

የአቢሲኒያ ባንክ ፕሬዚዳንት ከኃላፊነታቸው ለቀቁ

0
0

002a8b24df33f103d3de8d882e515849_Lባለፉት አምስት ዓመታት አቢሲኒያ ባንክን በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የቆዩት አቶ አዲሱ ሃባ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ፡፡ ከነሐሴ 26 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ኃላፊነታቸውን ያስረክባሉ፡፡ ያልተጠበቀ ዕርምጃ ነው የተባለው የአቶ አዲሱ ከኃላፊነት መልቀቅ የተለያዩ ምክንያቶች እየተሰነዘሩበት ቢሆንም፣ አቶ አዲሱ ግን፣ ‹‹ከኃላፊነቴን የለቀቀሁት ራሴ ባቀረብኩት የሥራ መልቀቂያ ጥያቄ መሠረት ነው፤›› ይላሉ፡፡

‹‹ወደ አቢሲያ ባንክ ስመጣ ለሦስት ዓመታት ላገለግል ነበር፡፡ ሆኖም ለአምስት ዓመታት አገልግያለሁ፡፡ በዚህ ወቅት መሥራት የሚገባኝን ሥራ ለባንኩ በማበርከት ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡ አሁን የምለቅበት ጊዜ በመሆኑ ኃላፊነቴን ለቅቄያለሁ፤›› በማለት ገልጸዋል፡፡ የመልቀቃቸው ጉዳይ ድንገተኛ ሳይሆን ቀደም ብሎ የነበረ እንደነበርም ጠቅሰዋል፡፡

ባንኩ እሳቸው ወደ ኃላፊነት ከመምጣታቸው በፊት ይጎሉታል የተባሉትን ነገሮች በሙሉ እንዲስተካከሉ በማድረግና ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶችን በማስጀመር የሠሩት ሥራ ጥሩ በመሆኑ፣ ቀደም ብሎ በነበራቸው ሐሳብ መሠረት መልቀቂያ ማስገባታቸውን ተናግረዋል፡፡ አቶ አዲሱ የሥራ መልቀቂያ ነሐሴ 12 ቀን 2004 ዓ.ም. አስገብተው ቦርዱ አሥር ቀናት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ጥያቄውን እንደተቀበላቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

የሥራ መልቀቂያው ድንገተኛና ግፊት ያለበት ስለመሆኑ የሚልጹ ወገኖች ግን፣ የአቶ አዲሱ መልቀቅ እሳቸው ባቀረቡት ጥያቄ ብቻ መሆኑን ይጠራጠራሉ፡፡ ከግል ባንኮች በተለየ የተለያዩ ፕሬዚዳንቶችን በመቀያየር ስሙ ለሚነሳው አቢሲኒያ ባንክ አቶ አዲሱ አምስተኛ ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡

የአቶ አዲሱ መልቀቅ ድንገተኛ ነው የሚለውን እምነት ያጠናከረው ደግሞ፣ አቶ አዲሱ ከጥቂት ወራት በፊት በአገሪቱ ውስጥ በሥራ ላይ ያሉትን አሥራ ዘጠኙንም ባንኮች በአባልነት ያቀፈው የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸው ነው፡፡

አቶ አዲሱ ማኅበሩን እንዲመሩ ከሰባት ወራት በፊት ሲመረጡ የምርጫ ዘመናቸው እስኪጠናቀቅ ማኅበሩን ለማገልገል ቃል ገብተው የነበሩ በመሆናቸው፣ ከአቢሲኒያ ባንክ ፕሬዚዳንትነት መልቀቃቸው ያልተጠበቀ ነው የሚለውን ግምት ያጠናክረዋል የሚሉም አሉ፡፡ ቀደም ሲል ከአቢሲኒያ ፕሬዚዳትነት የመልቀቅ ዕቅድ ከነበራቸው የማኅበሩ ፕሬዚዳነት ሆነው ለመሥራት ፈቃደኛ አይሆኑም ነበር በማለትም ይናገራሉ፡፡

በሌላ በኩል ግን አቶ አዲሱ በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን የሚያምኑ ወገኖች ደግሞ፣ አቶ አዲሱ ከኃላፊነት መልቀቅ ግፊት ያለበት ቢሆን ኖሮ የሽኝት ፕሮግራም እንደማይዘጋጅ ጠቅሰው፣ በጥያቄያቸው መሠረት የተፈጸመ እንጂ ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት ሰላማዊ ክንውን ነው ይላሉ፡፡

ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምክንያቶች ከባንኩ የለቀቁ ፕሬዚዳንቶች ይህንን ዕድል አለማግኘታቸውን በማስታወስ፣ የአቶ አዲሱ ከሥራ መልቀቃቸውና በክብር መሸኘታቸው፣ ከሥራ የለቀቁት በፈቃዳቸው ለመሆኑ ማረጋገጫ እንደሆነ ያመለክታሉ፡፡ የባንኩ ቦርድና ማኔጅመንት ለአቶ አዲሱ ሽኝት ነሐሴ 24 ቀን 20006 ዓ.ም. ምሽት በሒልተን ሆቴል ፕሮግራም አዘጋጅቶ ነበር፡፡

አቶ አዲሱ በአቢሲኒያ ባንክ ፕሬዚዳንትነታቸው ውጤት ማስመዝገባቸው ይነገራል፡፡ እንደ ምሳሌ የሚቀርበውም እሳቸው የፕሬዚዳነትነት ኃላፊነቱን ሲረከቡ 46 የነበረውን የባንኩ ቅርንጫፍ ብዛት 106 ማድረሳቸው፣ የባንኩን ካፒታል ከ315 ሚሊዮን ብር ወደ 1.5 ቢሊዮን ማሳደጋቸው፣ 100 ሚሊዮን ብር አካባቢ የነበረውን ትርፍም ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ማድረስ መቻላቸውን በአስረጅነት ያቀርባሉ፡፡

ከባንኩ የተገኘው ሌላ መረጃ ደግሞ አቶ አዲሱን ተክተው ባንኩን በተጠባባቂ ፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ የባንኩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አስማረን ቦርዱ መሰየሙ ታውቋል፡፡

የአቶ አዲሱ ከአቢሲኒያ ባንክ መልቀቅ ከጥቂት ወራት በፊት የተረከቡትን የባንኮች ማኅበር ፕሬዚዳንትነታቸውን እንዲለቁ ያደርጋል፡፡ በሌላ በኩል አቶ አዲሱ ከአቢሲኒያ ባንክ ለቀው በዚሁ ኢንዱስትሪ ውስጥ ሆነው የሚቀጥሉ ከሆነ፣ የባንኮች ማኅበር ፕሬዚዳንትነታቸው ሊቀጥሉ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ስለዚህ ጉዳይ የተጠየቁት አቶ አዲሱ፣ ‹‹በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ የምቆይ ከሆነ በፕሬዚዳንትነቴ እቀጥላለሁ፤›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የማይቀጥሉ ሆነ ግን ማኅበሩን በምክትል ፕሬዚዳንትነት የሚያገለግሉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ፣ አዲስ ምርጫ እስኪደረግ የአቶ አዲሱን ቦታ ተክተው ሊሠሩ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡ አቶ አዲሱ በባንክ ኢዱስትሪው ውስጥ ከ36 ዓመታት በላይ ያገለገሉ ሲሆን፣ በተለይ የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክን ለስምንት ዓመታት በፕሬዚዳንት መምራታቸው ይጠቀሳል፡፡ በዚሁ ባንክ ውስጥ በምክትል ፕሬዚዳንትነትና በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ማገልገላቸው ይታወሳል፡፡

 

Source:: Ethiopian Reporter


ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ያወጣው መመርያ ደንብ የጣሰ ነው የሚል ተቃውሞ ገጠመው

0
0

‹‹መመርያው የወጣው ክልሎች ተገቢውን ዕርምትና ጥበቃ ሊያደርጉ ስለማይችሉ ነው››

የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር

የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የሕግ ታራሚዎች ዝውውርን በሚመለከት ያወጣውና ከሰኔ 12 ቀን 2006 ዓ.ም. ተግባራዊ መደረጉ የተገለጸው የአፈጻጸም መመርያ ቁጥር 2/2006 ተቃውሞ ገጠመው፡፡


ተግባራዊ መደረግ የጀመረውን የማረሚያ ቤቱን የአፈጻጸም መመርያ የተቃወሙት፣ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ታራሚዎች ናቸው፡፡ ታራሚዎች በተለይ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት የሕግ ታራሚዎችን በሚመለከት በአንቀጽ 21 (2) ሥር ባሰፈራቸው ድንጋጌዎች፣ በጥበቃ ሥር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ከትዳር ጓደኞቻቸው፣ ከቅርብ ዘመዶቻቸው፣ ከሃይማኖት አባቶቻቸው፣ ከሐኪሞቻቸውና ከሕግ አማካሪዎቻቸው ጋር የመገናኘትና እንዲጎበኟቸው ዕድል የማግኘት መብት እንዳላቸው ስለተደነገገ ደንብ መውጣቱን አስታውቀዋል፡፡ 

የሕገ መንግሥቱን የመብት ድንጋጌ ተከትሎ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በደንብ ቁጥር 138/99 አንቀጽ 19 ላይ የሕግ ታራሚዎችን የዝውውር ጥያቄ በሚመለከት እንደገለጸው፣ ማንኛውም ታራሚ የመጨረሻ ውሳኔ ተሰጥቶት በሌላ ክስ የማይፈለግ ከሆነ፣ ቤተሰቦቹ በሚኖሩበት አካባቢ ወደሚገኝ ማረሚያ ቤት እንዲዛወር ካመለከተ፣ ሊፈቀድለት እንደሚችልና ቤተሰቦቹም እንዲያውቁ እንደሚደረግ የተደነገገውን ደንብ መመርያው እንደሚጥስና ታራሚዎቹንም መብት እንደሚያሳጣ አስረድተዋል፡፡

መመርያ ደንብን ሊጥስ ወይም ሊያርም እንደማይችል የሚናገሩት ታራሚዎቹ፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣውን ደንብ ማረሚያ ቤቱ ምንም ሳይሸራረፍ ተፈጻሚ ማድረግ ሲገባው፣ አስተዳደሩ መመርያ እያወጣ መሠረታዊ መርሆዎችን መጣስ እንደማይችልና ተገቢም አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

ማረሚያ ቤቱ ተግባራዊ ባደረገው ደንብ የሚጥስ የአፈጻጸም መመርያው ‹‹የሚኒስትሮች ምክር ቤት በደንብ ቁጥር 138/1999 አንቀጽ 19 ስለታራሚዎች ዝውውር የተደነገገ ቢሆንም›› ካለ በኋላ፣ ዝውውር የማይፈቀድባቸውን የወንጀል ዓይነቶች በዝርዝር ማስቀመጡን ታራሚዎቹ ተናግረዋል፡፡ በሰው ዘር ማጥፋት ወንጀል፣ በሽብርተኝነት፣ በሃይማኖት አክራሪነት፣ በአገር ክህደት፣ የአገሪቱን ሚስጥር አሳልፎ መስጠት፣ በከባድ ውንብድና፣ በጦር መሣሪያ ንግድ፣ በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በሙስና፣ ገንዘብ ማሳተምና ዝውውር፣ በሴቶች፣ በሕፃናትና በአካል ጉዳተኞች ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎችና ሌሎች በርካታ የወንጀል ዓይነቶችን አስተዳደሩ በመመርያው በመዘርዘር፣ በእነዚህ ወንጀሎች የተፈረደባቸው ታራሚዎች ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ወደ ክልሎች ማረሚያ ቤቶች መዘዋወር እንደማይችሉ ማስታወቁን ታራሚዎቹ ጠቁመዋል፡፡ አስተዳደሩ የወንጀል ዓይነቶቹ አዲስና ውስብስብ እንደሆኑ የገለጸ ቢሆንም ለዘመናት የነበሩና አዲስ አለመሆናቸውን ገልጸው፣ በአሁኑ ጊዜ ለዚያውም ደንብ ጥሶ ለመከልከል የፈለገበት መንገድ አሳማኝ አለመሆኑን ተቃውመዋል፡፡

ማረሚያ ቤቱ ያወጣው አዲስ የአፈጻጸም መመርያ በታራሚዎች ላይ ከፍተኛ ችግር የሚፈጥር ከመሆኑም በላይ፣ ሕገ መንግሥታዊ መብት የሚጋፋና በመታሰራቸው ምክንያት ንብረታቸው እንዲወድም፣ ቤተሰቦቻቸውን እንዳያገኙና እንዳይጠይቋቸው፣ በራሳቸውና በቤተሰቦቻቸው ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ፣ ሥነ ልቦናዊና ማኅበራዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድርባቸው ሥጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

አንድ ታራሚ በመሠረታዊ መርህ ደረጃ በሕግ የተጠበቀ መብቱ ሊገደብ የሚችለው፣ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ በሚያሳየው ያልተገባ ባህሪና የማረሚያ ቤቱን ሕግና ደንብ ንዶ ሲገኝ እንጂ፣ ከዓመታት በፊት በተቀጣበት ወንጀል መሆን እንደሌለበት ታራሚዎቹ ተናግረዋል፡፡ የክልል መንግሥታት የፌዴራል መንግሥቱ ያወጣቸውን ሕጐች የማስፈጸም ሕገ መንግሥታዊ መብት እንደተሰጣቸው የጠቆሙት ታራሚዎቹ፣ በመመርያው የዝውውር ዕገዳ የተጣለባቸው የወንጀል ዓይነቶች 90 በመቶ የሚሆኑት በክልሎች ፍርድ ቤትም የሚታዩና ውሳኔ የሚሰጥባቸው መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ያወጣው የታራሚዎች የዝውውር መመርያ፣ ባጠፉት ጥፋት ተፀፅተው በመታረም ብቁ ዜጋ በመሆን ላይ ለሚገኙ ታራሚዎች በሕግ የተሰጣቸውን መብት የሚገድብ ከመሆኑም በላይ፣ የሕገ መንግሥቱን ድንጋጌና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 138/1999ን የሚቃረን በመሆኑ እንዲስተካከልላቸው ጠይቀዋል፡፡

ታራሚዎቹ የተቃወሙትን የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ያወጣውን የአፈጻጸም መመርያ በሚመለከት ማብራሪያ እንዲሰጡ የማረሚያ ቤቱን የሕዝብ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት ረዳት ኃላፊ አቶ አዲሱ ጴጥሮስን ሪፖርተር አነጋግሯቸው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

አቶ አዲሱ በሰጡት ምላሽ፣ እንደገለጹት ‹‹የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስለፌዴራል ታራሚዎች አያያዝ ባወጣው ደንብ ቁጥር 138/1999 ማንኛውም ታራሚ የመጨረሻ ውሳኔ ካገኘና በሌላ ክስ የማይፈለግ ከሆነ፣ ቤተሰቦቹ በሚኖሩበት አካባቢ ወደሚገኘው ማረሚያ ቤት እንዲዛወር ካመለከተ ሊፈቀድለት ይችላል፤›› ሲል ‹‹ላይፈቀድለትም ይችላል ማለቱ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ማረሚያ ቤቱ በመመርያው ላይ ዘርዝሮ ዝውውር የከለከላቸው የወንጀል ድርጊቶች ፈጻሚ ታራሚዎች ወደ ክልል ማረሚያ ቤቶች ቢላኩ፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶችን ያህል ጥበቃ ሊደረግላቸውና ሊታረሙ ይችላሉ የሚል እምነት ባለመኖሩም ጭምር መሆኑን አቶ አዲሱ አስረድተዋል፡፡

በዚህ ጊዜ የታራሚዎች ዝውውር ዕግድ እንዲጣልበት የተደረገበትን ምክንያት እንዲያስረዱ የተጠየቁት አቶ አዲሱ፣ ምክንያቱ የሽብርተኝነት ወንጀል እየተስፋፋ በመምጣቱና ከሃይማኖት አክራሪነት ጋር የተያያዘ ወንጀል እየተስፋፋ መምጣቱና ሌሎችም ምክንያቶች እንዳሉ ገልጸዋል፡፡ ደንቡ ሲወጣ ደግሞ በመመርያ የሚወጣውን ዝርዝር ጉዳይ ታሳቢ በማድረግ በመሆኑ፣ የወጣው መመርያ ሊነቀፍ እንደማይገባው የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊው አቶ አዲሱ ገልጸዋል፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው የሕግ ምሁራን ግን በወንጀል ሕጉም ሆነ በሌሎች የወንጀል ኃላፊነት የሚያስከትሉ ሕጎች ውስጥ የሃይማኖት አክራሪነት የሚባል ወንጀል እንደሌለ በመግለጽ፣ መመርያው ምን ለማት እንደፈለገ ግልጽ እንዳልሆነ አስረድተዋል፡፡

newspaper_ethiopia

እውነት አብርሃ ደስታ አሸባሪ ወይስ ህወሓት? ኢህአዴግ ነው ለሰላማዊ ትግል ፈሪ?

0
0

ክብሮም ብርሃነ (መቐለ)

Free Abreha Desta አብርሃ ደስታ ይፈታ

Free Abreha Desta አብርሃ ደስታ ይፈታ

ነሐሴ 1 ቀን 2006 ዓ.ም የአረና ትግራይ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚና የመቀሌ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር አብርሃ ደስታ በሽብር ተጠርጥሮ በተከሰሰበት ልክ በወሩ ፍ/ቤት እንደሚቀርብ በፌስ ቡክ አይቼ እኔም እንደ ዜጋና እንደ አድናቂው የሚቀርቡለትን የድራማ ክስ ለመስማት ጓጉቼ ፍ/ቤቱ ስደርስ እንደ እኔ አብርሃ ደስታን በአይናቸው ለማየትና የክሱን ድራማ ለማወቅ እንዲሁም ለቆራጡ ወጣት ፖለቲከኛ አብርሃ ደስታ የሞራል ድጋፍ ለመስጠት የተሰባሰቡ የተለያዩ የክልላዊና ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ አባላት፣ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች እንዲሁም የወጣቱ ፖለቲከኛ አድናቂዎች ሽማግሌዎችና ወጣቶች ተደማምረው ያልገመትኩት የሕዝብ ብዛት በቡድን በቡድን ሰብሰብ ብለው የአብርሃ ቆራጥነትና የሀገራችን የፖለቲካ ሁኔታ ሲወያዩ አገኘኋቸው፡፡
የክሱን ሁኔታ ለመመልከት የመጡ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች
*******************************************
1. የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ተቀዳሚ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ተክሌ በቀለ
2. የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ም/ፕሩዚዳንት አቶ በላይ ፍቃዱ
3. የሰማያዊ ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ስለሺ ፈይሳ
4. የመድረክ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጥላሁን እንደሻው
5. የጌድኦ ሕዝብ ዴሞክራስያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኣቶ ኣለሳ መንገሻ እንዲሁም ጋዜጤኞች፣ ብዙ የታወቁ ሰዎችና ወጣት አድናቂዎቹ ተገኝተዋል፡፡

አብርሃ ደስታ ወደ ፍ/ቤት ሲገባ
**********************************
አብርሃ ወደ ፍ/ቤቱ ግቢ ከመድረሱ በፊት ቁመቱ ትንሽ ረዘም ያለ የፊቱ ቀለም አብርሃን የሚመስል አንድ የትግራይ ተወላጅ ደህንነት (ለራሱ ያልዳነ) ከኋላው ሶስት ጠመንጃ ያነገቡ የፌዴራል ፖሊስ አስከትሎ ሲገባ አብርሃ ደስታን ለማየት ጓጉቶ የነበረ የአዲስ አበባ አድናቂዎቹ ‹‹ መጣ ……. መጣ…….. ›› ማለት ጀመሩ፡፡ ደህንነቱና የፌዴራል ፖሊሶቹ ልክ እንደገቡ ፊታቸውን ከሰል አስመስለው “ገለል በሉ …. ዞር በሉ ……!” እያሉ ትዕዛዝ ስለሰጡ ራቅ ብለን ተሰለፉ ሳንባል ፊታችን ወደ ዋናው መንገድ አድርገን ራሳችን ተሰለፍን
አንድ የፌዴራል ፖሊስ ከፊቱ ሆኖ እየመራው አብርሃ በኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በሙስሊሙና በክርስቲያኑ ያለውን የመልካም አስተዳደር እጦት እንዲሁም የፖለቲካ ጣልቃ ገብነትና አፈና ለመግለጽ ቀለም የሚያንጠባጥብ ብዕር መያዝ ብቻ የለመዱ እጆቹ በብረት ሰራሽ ካቴና ክርችም ብሎ እልህ የሚነበብበት ፊቱ ጠቆር ብሎ፣ ሰውነቱ ከሳ ብሎ ሁለት የፌዴራል ፖሊስ አስከትሎ ገባ፡፡ ልክ ሙሽራ ሲመጣ እንደምናደርገው አቀባበል ወደ ፍ/ቤቱ ግቢ እንደገባ ያ ሁሉ ሕዝብ ግቢውን በጭብጨባ ቅውጥ አደረገው ያኔ አብርሃ ደስታ ግራ ገባው፡፡ ያ ሁሉ ሰው በሰልፍ ቆሞ ሙሽራ እንደመጣ ሲያጨበጭብ ይሆናል ብሎ ስላልጠበቀ መሰለኝ ጭብጨባው ለራሱ አልመሰለውም፡፡ አንድ ሁለት እርምጃ እንደሄደ ቀና ብሎ ሲያይ ብዙ የሚያውቃቸው ሰዎች ሲያይና ‹‹ አይዞህ!……. አይዞህ!……. አብርሃ የኛ ጀግና! ከጎንህ ነን! ›› እያሉ እጃቸውን እያወዛወዙ ሰላምታና ሞራል ሲሰጡት ለሱ መሆኑን ሲያውቅ ፊቱን ፈገግ በማድረግ የታሰሩ እጆቹን ከፍ በማድረግና ከወቡ ጎንበስ በማለት በተደረገለት አክብሮትና ሞራል የጨዋ ምላሽ እየሰጠ ወደ ችሎቱ ገባ፡፡
የግቢውን በር ከረገጠበት ጀምሮ ችሎት እስከሚገባ ድረስ ባለማቋረጥ በኃይለኛ ጭብጨባ ታጀበ፡፡ ያኔ ይዞት የመጣው ደህንነት በጣም ስለበሸቀ ‹‹ ስነስርዓት አድርጉ!…. ስነስርዓት አድርጉ!…. ›› ቢልም ሀሳቡ ስነስርዓት የሚያሲዝ ስላልነበረ መሰለኝ ጆሮ የሚሰጠው አልነበረም፡፡ አስከትሎም ምንም እንኳ በግልጽ ለማን መሆኑ ባይታወቅም “ቆይ አሳይሃለሁ!…. ኋላ ይቆጭሃል!…. ” እያለ ማስፈራራት ጀመረ፡፡ ይህን የሚገልጽ አንድ የትግርኛ አባባል አለ፡፡ ምን ይላል መሰላችሁ “ሰበይቱያ ዝለአኸቶስ ደገአፍ ቤተመንግስቲ አይፈርሕን ” በአማርኛም እንደዚህ “ሚስቱ የላከችው ሞት አይፈራም ” ይባላል፡፡ ያ ያልዳነ ድህንነትም ያመነው ነገር ባይኖር ህግ ባለበት ሀገር ደህንነት በመሆኑ ብቻ እንዲህ ብሎ ሰው ማስፈራራት አይችልም ነበር፡፡
“ቆይ አሳይሃለሁ!… ኋላ ይቆጭሃል!….” ማለቱ አንተም በሽብር ከስሼህ አሰቃይሃለሁ ማለቱ ይሆን?
በነገራችን ላይ አብርሃ ወደ ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሎ የተቀጠረው በ8፡00 ሰዓት ነበር፡፡ አብርሃን ለማየት የተሰበሰበ የሕዝብ ቁጥር አላምር ስላላቸው መሰለኝ ምናልባት ተሰላችተው ይሄዱ ይሆናል በሚል ታሳቢ እስከ 10 ሰዓት ከ25 አላቀረቡትም ነበር፡፡ ሕዝቡም ይሄን ተረድቶ እስከ 12 ሰዓትም ቢሆን እንቆያለን ብሎ በመረጋጋቱ እንደማይሆንላቸው አውቆ 10 ሰዓት ከ25 ሲል ነው ያመጡት፡፡ ይህ ግን በአብርሃ ብቻ ሳይሆን በእነ ሀብታሙ አያሌውም እንዲህ ተደርጓል፡፡ የሆነው ሆኖ ከግማሽ ሰዓት የችሎት ቆይታ አብርሃ እንደገና ታጅቦ ከችሎት ወጣ፡፡ ሲወጣም እንደገና ቅልጥ ያለ ጭብጨባና ሞራል ሲሰጠው ፈገግ እያለ አፉ ባይናገርም በታሰሩ እጆቹ አይዟችሁ እያለ እጅ እየነሳ ወጣ፡፡

የአብርሃ ደስታ ክስ በፖሊስ ሲነበብ
********************************

ክብሮም ብርሃነ

ክብሮም ብርሃነ

አብርሃ ችሎት ከገባ በኋላ አጠገቡ የነበረው በሙያውና በስነምግባሩ የታወቀ እንዲሁም ከብር ይልቅ ለፍትህ ቅድሚያ የሚሰጥ ጠበቃው ተማም አባቡልጉ ብቻ ነበር፡፡ ኋላ ግን ሁለት የአረና አመራርና አንድ የአክስቱ ልጅ ገብተው የክሱን ሁኔታ እንዲከታተሉ ስለተፈቀደላቸው ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ተከታትለዋል፡፡
አጠቃላይ የክሱ ጭብጥ
***********************
1. አረና ትግራይ ሽፋን በማድረግ ከግንቦት 7 አመራሮች እየተገናኘና ገንዘብ እየተቀበለ ሽብርን ለመፍጠር ተንቀሳቅሷል፡፡
2. ሽብር ለመፈጸም 60 ሰዎች መልምሏል፡፡
3. በቤቱ ሽብር ለመፈጸም የሚያስችል ዶክመንት በፍተሻ ተገኝቷል የሚሉ ነበሩ፡፡
መቼም ቢሆን አብርሃ ደስታ ይህን የፈጠራ ክስ ፈጽሞት ይሆን? ብሎ የሚጠራጠር ካለ የዘመኑ በጣም የዋህ ወይም የህወሓት/ኢህአዴግ መሰሪ ሴራና ተንኮል የማያውቅ ብቻ ነው፡፡ አብርሃ ህወሓት የሚፈጽማቸውን አፈናዎችና የህግ ጥሰቶች በየቀኑ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እያሳወቀ በመሄዱና ሕዝብ በጽናት ታግሎ በሚቀጥለው ምርጫ ከትከሻው አሽቀንጥሮ መጣል እንዳለበት በድህረ ገጾችና በመጽሔቶች እየጻፈ ለብዙ ወጣቶች አርአያ እየሆነ በመሄዱና የትግራይ ሕዝብ የህወሓት ክህደትን አውቆ ለዳግም ሰላማዊ ትግል በሁሉ አቅጣጫ እንዲነሳሳ ማድረጉ ለህወሓት ትልቅ የራስ ምታት ስለሆነበት ነው እንጂ አብርሃ ደስታ የተከሰሰበትን የፈጠራ ክስ እንደማይፈጽምና እንዲህ አይነት ተልካሻ ስራ በሚወዳት ሀገሩና በሚወደው ሕዝብ ላይ ለመስራት የሚያዘው ጭንቅላት እንደሌለው አብርሃን በቅርበት የሚያውቁት ሁሉ ይመሰክሩለታል፡፡

አብርሃ ደስታ ለፍ/ቤቱ ካቀረባቸው አቤቱታዎች
1. በጣም ቀዝቃዛና ጨለማ በሆነ ቤት ብቻውን እየታሰረ እንዳለ
2. ፍ/ቤት እስከቀረበበት ጊዜ 8 የተለያዩ ግለሰቦች ከለሊቱ ከ7 እስከ 8 ሰዓት በየተራ እየመጡ እንደሚደበድቡት
(እንደሚያሰቃዩት)
3. በጭለማ ቤት ሆኖ የማያውቀውንና ያላነበበውን ጽሑፍ (ዶክመንት) እየተደበደበ እንዲፈርም እንደተደረገ
4. የቆየ የጨጓራ ህመም ስላለው እንጀራ ብዙም እንደማይማይበላና ሆኖም ግን አሁን ያለ ፍላጎቱ እያመመው እንዲበላ ስለተገደደ በከፍተኛ የጨጓራ ህመም እየተሰቃየ እንዳለ፣ በማዕከላዊ (ታስሮ ባለበት ቦታ) በሚደረግለትን የህክምና ዕርዳታ ሊያገግም እንዳልቻለ እነዚህና ሌሎች እየደረሱበት ያሉ ስቃዮች ምንም እንኳን ሰሚ ባያገኝም በአቤቱታ መልክ አቅርቧል፡፡
የተከበራችሁ አንባቢዎች እውነት አብርሃና መሰሎቹ ሽብርን ለመፈጸም በተጨባጭ መረጃና ማስረጃ ተይዞ ከሆነ እመኑ እየተባሉ ያ ሁሉ መደብደብ፣ መሰቃየትና ሳያነቡ ጽሑፍ እንዲፈርሙ መደረጉ ለምን አስፈለገ? የተገኘ እውነተኛ መረጃ ለሕዝብ ግልጽ አይደረግም? ፍርዱን ሕሊና ላለው ሰው ይሁን፡፡

በጠበቃው ተማም አባቡልጉ የቀረበ ክርክር
አንድ ሰው በወንጀል ተጠርጥሮ ሲየዝ በቂ የሆነ መረጃና ማስረጃ መኖር አለበት (ሕገ መንግስት እያጣቀሰ) አለበለዚያ ሰውን አስረህ ፖሊስ መረጃና ማስረጃ ላሰባስብ ጊዜ ይሰጠኝ ስላለ ብቻ ከበቂ በላይ ጊዜ እየተሰጠ ሰው ማሰቃየት ከህግ በላይ መሆን ነው፡፡ ወይም ሰው በእምነቱ እንዳይጓዝ ለመገደብ የሚደረግ ህገ መንግስቱን የጣሰ አካሄድ ነው፡፡ ስለዚህ አሁንም ፖሊስ ከዚህ ቀደም በቂ ጊዜ ተሰጥቶት እያለ ትርጉም ያለው መረጃና ማስረጃ ሊያቀርብ ስላልቻለ አሁንም እንደገና ጊዜ ይሰጠኝ ብሎ መጠየቁ ደንበኛዬ ከስራው ለማስተጓጎልና ለማሰቃየት ካልሆነ ሌላ ዓላማ ስለሌለው ደንበኛዬ የዋስ መብቱ እንዲከበርለትና በዋስ ተፈትቶ ክሱን በውጭ ሆኖ እንዲከታተል ይወሰንልኝ ብሎ ህገ መንግስቱን ተንተርሶ ተከራክሮዋል፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው ከሳሹና ፈራጁ አንድ በሆነበት ሀገር ፍትህ እንዴት ይገኛል? ድሮም እኮ ፍትህ ቢኖር በፈጠራ ክስ ሰው አይከሰስም ነበር፡፡ እንዲህ ስለሆነ እንደገና ከ28 ቀናት በኋላ ነሐሴ 29 ፍርድ ቤት ይቀርባል ተባለ፡፡

በዛን ቀን የታዘብኩት ነገር
ህወሓት/ኢህአዴግ በቋንቋ፣ በብሔርና በጎጥ ከፋፍሎ ሲገዛን የራሱና ለራሱ ብቻ የሚሆን ምክንያት አለው፡፡ ነገር ግን ያን ቀን የታዘብኩት ነገር ካለ በህወሓት/ኢህአዴግ ሴራ ኢትዮጵያዊነታችን አሁንም ጨርሶ እንደማይናድ ነው፡፡ ምክንያቱም ህወሓት/ኢህአዴግ አብርሃን መቐለ ይዘው አዲስ አበባ ፍ/ቤት ሲያቀርቡት የፍርድ ሂደቱን የሚከታተል ብዙ ሰው ስለማይኖር የአብርሃ ሞራል ይጎዳል ብለው ይሆንናል፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችን እኩል አይቶ በእኩል የሚቆረቆር፣ ከግላዊ ጥቅምና ክብር የሕዝብ ጥቅምና ክብር የሚያስቀድም እንዲሁም የሀገርና የሕዝብ መብትና አንድነት ይከበር ብሎ በፅናት በአደባባይ የሚከራከር ኢትዮጵየዊ ከየትኛውም ብሔር ወይም ክልል ይምጣ፣ የፈለገውን ቋንቋ ይናገር በኢትዮጵያውያን ዘንድ የተለየ ክብርና ሞገስ እንዳለውና ሁሌም ኢትዮጵያውያን ከጎኑ እንደሆኑ በደንብ ተረድቻለሁ፡፡ አሳሪዎቹም ጭንቅላት ካላቸው ሳይረዱት አይቀርም፡፡ እንዴት ብትሉኝ አብርሃ የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ቢሆንም ህወሓት/ኢህአዴግ እርስ በእርሳችን በጥላቻ አይን ከመተያየት አልፈን እንዳንተባበር የሚያደርጋቸውን የተለያዩ ሴራዎችን ሰብሮ የአብርሃ ጉዳይ የሁላችን ጉዳይ ስለሆነ ያሳስበናል ብሎ ብሔር፣ ቋንቋ እንዲሁም የህወሓት/ኢህአዴግ የመከፋፈል ሴራ ሳይገድባቸው የትግራይ፣ የአማራ፣ የኦሮሞና የደቡብ ተወላጆች ኢትዮጵያውያን በአንድነት የግል ስራቸውን ትተው የወጣት ፖለቲከኛና መምህር አብርሃ ደስታ የፍርድ ሂደት ሲከታተሉ መዋላቸውና ከፍተኛ ሞራል መስጠታቸውን ሳይ ኢትዮጵያዊነታችን በህወሓት/ኢህአዴግ ሴራ ጨርሶ እንደማይሸረሸር አረጋግጫለሁ፡፡ በኢትዮጵያዊነቴም ኩራት ይሰማኛል፡፡ አሁንም ገዢዎች በሚያደርጉት ሴራ እኛ ኢትዮጵያዊያን መለያየትና መቀያየም የለብንም፡፡ ለጋራ ዓላማና ጥቅም በጋራ መንቀሳቀስ አለብን፡፡ ስንተባበር ክንዳችን ይጠነክራል ሞራላችን ከፍ ይላል፡፡
ቸር እንሰንብት!

አንድ ቀን የፍትህና የነፃነት ባለቤቶች እንደምንሆን አልጠራጠርም!

ካርቱም ለምትገኙ ስደተኞች በሙሉ –በሱዳን የሚገኙትን 5ቱን የወያኔ ሰላዮች/ ተላላኪዎች ይወቁ

0
0

በሱዳን ከሚገኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የተላለፈ ጥሪ፦

በሱዳን ሀገር ለምትገኙ ኢትዮጽያውያን በሙሉ መብታችን ሰብአዊ ክብራችን ለዘመናት በስደት በምንኖርበት ሀገረ ሱዳን በ ዩን ኤች ሲ አር በኩል ከፍተኛ አድሎ በደል እንደሚደረግብን ለማንም ግልፅ ነው። ይሂም የኛ ዝምታና አንድነት አለመኖር እረሳችንን እንደጎዳን በማንም ይታወቃል በሕብረት በአንድነት ቆመን መብታችን ለማስከበር እንዳንታገል ያደረግን የወያኔ ረቂቅ ተንኮል መሆኑ ለማንም ግልፅ ነው። ይህንን አሳዛኝ ሕይወት ማንም በየቤቱ ይናገራወል በቅርብ በሚያውቀው ጓደኛ ጎረቤት ይወያይበታል የስደተኛ መብታችንም እንዳናስከብር እንደኛው የስደተኛ መታወቂያ የያዙ ለረዥም ዓመት በጉርብትና በመሀበር በእድር የምናውቃቸው ሁለት አይነት መታወቂያ ያላቸው እስስት ሰላዮችን ስደተኛው ማህበረሰብ በይሉኝታ እስከ ዛሬ በዝምታ ሲያልፋቸው ኖረዋል። እነሆ እሰከ ዛሬ የስደተኛ መብታችን ከመጋራት አልፎ እኛን መስለው ሲሰልሉን እያየን እየሰማን አንድ ለአምስት በሚባል በስለላ ስራ ተሰማርተው በቤተክርስትያን በእድር በጉርብትና በየፀበል ፀዲቁ በዩ ኤን ኤች ሲ አር በኮር ስደተኛው በሚገኝበት በስውር ተመድበው ሰርገው በመግባት በከፍተኛ ደረጃ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። እነዚህ ከሀዲ ባንዳዎች ሰርቶ የሚኖረውን ስደተኛ እለት በእለት እየተከታተሉ ለወያኔ ኢንባሲ ዘርፈው ለማይጠግቡ ኢትዮጽያን ሸጠው ለማይረኩ ቅጥረኞች ማንኛውንም እንቅስቃሴ ሪፖርት ያደርጋሉ። ከዚህ በኋላ ዝምታችን ሰብረን ዝምታ ለበጓም አልባጃት እንዲሉ ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩትን ወራዳ እንደ ሚሸጥ ስጋ ምንግዜም እራሳቸውን በፍርፋሪ የሚሸጡ በፍፁም ኢትዮጽያዊ ክብር
የለላቸውን በስደተኛ ስም ስደተኛ ነን የሚሉትን ከሀዲ ባንዳዎችን ከዛሬ ጀምሮ በካርቱም በተለያዩ ቦታዎች በበሀሪ በእምድሩማን በጅሬፍ በሰሀፋ ሸሪክ በሰሀፋ ዘለጥ በጀብራ በጎዝ በዴም ውስጥ የሚገኙትን ተራ በተራ እናጋልጣለን ለግዜው።……..

የካርቱም ከተማ ከፊል ገጽታ (ፎቶ ፋይል)

የካርቱም ከተማ ከፊል ገጽታ (ፎቶ ፋይል)


1ኛ. አየልኝ ተድላ መኮነን (ኰከቤ)፡− ይህ ግለሰብ በ2005 የተቋቋመው የስደተኞች ኮሚቴ ውስጥ አባል ሆኖ እየሰራ እያለ በኮሚቴ አባላት መካከል ጠንካራ እንቅስቃሴ ያደርጉ የነበሩትን ወያኔ ሆነዋል ብሎ በማስወራትና ክፍፍል በመፍጠር ኰሚቲው እንዲፈራርስ ትልቅ ሚና ተጫውቶዋል። በዚህ ሳይቆም ከኢትዮጵያ ሸሽቶ የመጣ አንድ የግንቦት 7 ዓባል አቶ አንዱአለም የተባለ ሰውየ እዚህ ካርቱም እንዲታፈንም ከፍተኛ አስተዋጾ ካደረጉት ሰዎች አንዱ ነው። COR እና UNHCR ሲሄድ ተቃዋሚ መስሎ የሚቀርብ በተግባር ግን የወያኔ ቅጥረኛ የሆነ ግለሠብ ነው።

2ኛ. ወርቁ አለባቸው (ባሪያው) ፡− ግለሰቡ የወያኔው የማፍያ ቡድን መሪ የነበረው የመለሰ ዜናዊ የሃዘን ቀን በሚከበርበት ቀን የሟቹን ፎቶ ይዞ ምሾ ሲወርድ እና ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል ባጋጣሚ ፎቶው ይቀደዳል ወያኔ ለመሆን ይረዳኛል ብሎ ያሰበው እለቅሶ ወያኔ በሆኑት ሆን ብለህ ነው የቀደድከው አንተ ሆዳም ዓማራ ተብሎ ተዋረደ እና ተደበደበበት። ከዛን ቀን በሆላ ጠቅልሎ እንደገባ በአደባባይ አስመሰከረ።

3ኛ. ተስፉ የሽወንድም ፡− በዘመነ ደርግ በጎንደር ውስጥ በኢሰፓ ውስጥ ሲሰራ የነበረ ሲሆን ስደት ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በየሄደበት ወሬ በመለቃቀም ለኢንባሲው የሚያቀብል አደገኛ ወሬ አነፍናፊ የሆነ ግለሰብ ነው።

4ኛ. ሽዋየ ሲሳይ ፡− በባሏ መሞት አማራነቷን ያወቀችው ቀዳማዊ ዕመቤት እየተባለች ስትሞካሽ የነበረችው አዚብ መስፍን ሱዳን ስትመጣ በቤቷ ተቀብላ በማስተናገድ ብቻ ሳትወሰን የስለላም ስራ በመስራት ሪፖርት የምታቀርብ ናት።

5ኛ. መኪ ጉራጌው ፡− በመባል የሚታወቀ ኦምዱሩማን የሚኖር ይሂው ግለሰብ ኦምዱሩማን የሚኖሩ ስደተኞችን በማማበል ስደተኞች በኢንባሲው ውስጥ በተዋቀረው እድር እንዲሳተፉ እና የተለያየ ጥቅማጥቅም እንደሚያገኙ በማሳመን የአባላት ምልመላ ያካደርጋል። እግረመንገዱንም ለኢምባሲው በመሰለል መረጃ ያቀብላል።

ወድ ኢትዮጽያዊ እነዚህ ለሆዳቸው ያደሩ አሳልፈው እንደሰጡህ ይታወቃል ሌሎችም አንድ ለአምስት በሚል በወያኔ የስላላ መረብ የተጠረነፉ እንደተለከፈ ውሻ በየስደተኛው ቤት የሚክለፈለፉ በአማራ በትግሬ በኦሮሞ በጉራጌ በደቡብ መሀበራት ስም የተደራጁ እንዳሉ ይታወቃል እነዚህ ወገን ሀገርን የሚሸጡ ደላለዎችን በማንኛውም መልኩ ከማንኛወም ማህበራዊ ግንኙነት እንዲገለሉ ማድረግ አለብን። ከአሁን በሆላ በስደተኛው ስም መነገድ እንዲያቆሙ ልንነግራቸው ይገባል። እንደማይራሩሉልህ ይታወቃልና ስለዚህ በይሉኝታ መብታችን ና የኢትዮጽያን ክብር ከአሁን በፊት አሳልፈን የሰጠነው ይብቃል እንበላችው ! በጋራ እንዋጋቸው !!!

ይህንን በረሪ ወረቀት ኮፒ እያደረክ ያላነበበው እንዲያነበው ትብብርህን አንጠይቃለን !
ለመብትህ ለክብርህ ተነስ !!!

አቶ አባይ ፀሐዬ ቤተክርስቲያን የግል ፕሬሶች ላይ እየተከታተለች ክስ እንድታቀርብ መመሪያ መስጠታቸው ተጋለጠ

0
0

(ዘ-ሐበሻ) ከሁለት ወራት በፊት አቶ አባይ ጸሐዬ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ በፕሬሶች ላይ እየተከታተለች ክስ እንድታቀርብ መመሪያ ማስተላለፋቸውን የዘ-ሐበሻ የቤተ-ክህነት ምንጮች አጋለጡ። እንደምንጮቹ ገለጻ ቤተክርስቲያኗ ይህን መመሪያ ከተቀበለች በኋላ የተለያዩ ክሶችን በፕሬሶች ላይ አዘጋጅታ የነበረ ሲሆን ከነዚህም መካከል በሎሚ መጽሔት ላይ የታሰበው ክስ ጋዜጠኞቹ በመሰደዳቸው የተነሳ ክሱ ሊቀር ችሏል።

(ሎሚ መጽሔት ሊከሰስበት የነበረው ጽሑፍ ይህ ነበር)

(ሎሚ መጽሔት ሊከሰስበት የነበረው ጽሑፍ ይህ ነበር)


የቤተክህነት ምንጮቻችን ዜናውን ሲያደሱን “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በተክርስቲያን በሎሚ መጽሄት ላይ ልትመሰርት የነበረውን ክስ ሰረዛዋለች።” ካሉ በኋላ “ከትላንትና በስቲያ በንብረኡድ ኤሊያስ አብርሃ ለሕግ ክፍል በደረሰ የስልክ ትእዛዝ መሰረት የሎሚ መጽሄት ባልደረቦች ስለተሰደዱ እና ጹሁፉን ጻፈ የተባለው ግለሰብም የሚኖረው በአውሮፓ ሞናኮ መሆኑን የመንግስት አካላት ባደረስን መረጃ ክሱ ዝግጅቱ ቢጠናቀቅም እንዲሰረዝ በስልክ በንበሩድ ኤሊያስ ተነግሮናል።” ብለዋል። እነዚሁ ምንጮች እንዳሉት “ክሱ እንዲመሰረት የተፈለገው “ዜጎችን ያልታደጉ ቆባቸውን ያውልቁ ” በሚል ርእስ ስር የተጻፈው የሃይማኖት መሪዎችን መብት ይጋፋል እንዲሁም የእምነት ነጻነትን በማደፍረስ ሕዝቡ በሃይማኖት መሪዎች ላይ ታማኝነት እንዳይኖር ያደርጋል ..ወዘተ በሚሉ ተያያዥነት ካላቸው ጉዳዮች ጋር ሰበብ እና አቃቂር በመፍጠር መጽሄቱን እና ጸሃፊውን ለመክሰስ ታስቦ ለሕግ ክፍሉ ተጠንቶ ክሱ እንዲዘጋጅ ትእዛዝ ተላልፎልን የነበረ ቢሆንም ከመንግስት በተገኘ በሚል መረጃ መሰረት በንብረኡድ ኤሊያስ አብርሃ ተሰርዟል።” ብለዋል።

ምንጮቹ ጨምረውም ከሁለት ወራት በፊት በቤተክርስቲያኗ ጉዳይ ሁሌም ጣልቃ የሚገቡትና በአንድ ወቅትም ቤተክርስቲያን አንድ ልትሆን በተቃረበችበት ወቅት “ውጭ ያለውን ሲኖዶስ በቅርብ ቀን በአሸባሪነት እንከሳለን፤ ስደተኛው ሲኖዶስ ሀገር ቤት የሚመጣው መንግስት ለመገልበጥ ነው” በሚል አባቶችን ማስፈራራታቸው በሚዲያ የተለቀቀባቸው አቶ አባይ ጸሃዬ ቤተክርስቲያኗ በፕሬሶች ላይ እየተከታተለች ክስ እንድታቀርብ የሰጡትን መመሪያ ተከትሎ በሌሎች ፕሬሶች ላይም ክስ ለመመስረት ዝግጁ ናቸው።

Health: የደም መርጋት (Thrombosis) መንስኤውና መከላከያው

0
0

በማስረሻ መሀመድ

የደም መርጋት ወይም ትርምቦሲስ የሚባለው አንድ የደም ስር ውስጥ የደም መርጋትን በመፍጠር በደም መዘዋወሪያ ሲስተም ውስጥ የደም ፍሰትን ሲያውክ ነው፡፡ አንድ ትሮምቦስ ደም ከልብ የሚያጓጉዘውን የደም ስር አካባቢ ከ75 በመቶ በላይ ሳይዝ ወደ ቲሹ የሚፈሰው የደም መጠን አቅርቦት በጣም ስለሚቀንስ ህመም ይፈጥራል፡፡ በዚህ ብቻ ሳይወሰን እንደ ላክቲክ አሲድ የመሳሰሉ የሜታል ውጤቶች ይከማቻሉ፡፡ እንቅፋቱ ከ9ዐ በመቶ በላይ ከሆነ እኔክስያን /Anoxia/ ያስከትላል፡፡ ይህ ሙሉ በሙሉ ኦክሲጅን እንዳይገኝ ያደርጋል፡፡ በዚህ ብቻ ሳይወሰን የሴል መሞትን ወይም Infraction ያስከትላል፡፡
የደም መርጋት Thrombosis
መንስኤዎቹ

በህክምናው ረገድ ትሮምቦሲስ የሚከሰተው ባልተለመደ ሁኔታ ከዚህ በታች ካሉት በአንዱ ወይም በብዙዎቹ ምክንያት ነው፡፡
• የደሙ ሁኔታ /Hypercoaguiabity/
• የደም ስሩ ጥራት /Endothelial cell injury/
• የደም ግፊት ባህሪ /Hemostasis/ ናቸው፡፡
ብዙውን ጊዜ ትሮምቦስ የሚፈጠረው በቫሪስኮቬንነው፡፡ ይህ ሲብራራ ለምሳሌ ለረጅም ጊዜ የአውሮፕላን በረራ ከተደረገ የደም ፍሰቱ የዘገየ ወይም የታገደ ይሆናል፡፡ ወይም በጅን /ህዋስ/ ጉድለት ይህ በሽታ ሊከሠት ይችላል፡፡

አከፋፈል
ሁለት የተለያዩ የትሮምቦሲክ ዓይነቶች አሉ፡፡
1. ቬነስ ትሮምቦሲስ
ቬነስ ትሮምቦሲስ አንድ ደም ወደ ልብ በሚያጓጉዘው የደም ስር ውስጥ የደም መርጋት ሲፈጠር ነው፡፡ በዚህ ምክንያት የሚመጡ ብዙ በሽታዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ የልብ ድካምና ስትሮክ
2. ዲፕ ሼን ትሮምቦሲስ
ዲፕ ሼን ትሮምቦሲስ አንድ ጥልቅ በሆነ ወደ ልብ ደም በሚያጓጉዘው ስር ውስጥ የደም መርጋት ሲከሰት ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ የሚያጠቃው የእግር የደም ስሮችን ማለትም እንደፊሞረስ የደም ስር የመሳሰሉትን ነው፡፡ አንድ ጥልቅ የደም ስር ውስጥ የደም መርጋት ከመፍጠር ሶስት ምክንያቶች ወሳኝ ናቸው፡፡ ይህም የደም ፍሰቱ መጠን፣ የደሙ ውፍረትና የደም ስሩ ግድግዳ ኳሊቲ ናቸው፡፡ የዲፕ ቬይን ትሮምቦሊስ ዓይነተኛ ምልክቶች ውስጥ እብጠት ህመም የሚያጠቃው አካባቢ መቅላት የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

መከላከያ

የደም መርጋትን በከፊል መከላከል ይቻላል፡፡ በጣም በሰፊው ከሚታዩት የደም መርጋት አይነቶች ውስጥ አንዱ ዲፕ ሼን ትሮምቦሲስ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በከፊል ወይም በሙሉ የረጋው ደም ከመጀመሪያ ሳይቱ በመነሳት ወደ ዋናው የደምቋት ሊመጣ ይችላል፡፡ ይህ ከተከሰተ የረጋው ደም ሌላ ሰውነት ክፍል ውስጥ ይከማቻል፡፡

ሆስፒታል እንዲተኙ ከተደረጉ ሰዎች ውስጥ ትሮምቦሲስ የኮምፕልኬሽኖች እና አልፎ አልፎም የሞት ዋና መንስዔ ነው፡፡ ስለዚህ መከላከያ ዘዴው በሆስፒታል ውስጥ ተኝቶ ከህክምና ባለሞያ ተገቢው የጤና እንክብካቤ በመስጠት ሲሆን ለበሽታው በሐኪሞች አማካኝነት የሚታዘዙ መድኃኒቶችን በተገቢው መጠቀም ነው፡፡

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live