Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በጄ/ል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ በሚኒሶታ ሕዝባዊ ስብሰባ ጠራ

$
0
0

olf ethiopia
(ዘ-ሐበሻ) በብርጋዲየር ጄነራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ ዓመታዊ ስብሰባውን በሚኒሶታ ጁላይ 7 ቀን 2013 እንደሚያደርግ ለዘ-ሐበሻ በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ። ድርጅቱ ጁላይ 7 በሚያደርገው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ዘርና ጾታ ሳይለይ ማንኛውም ኢትዮጵያውያን እንዲታደሙ ጋብዟል።
ድርጅቱ በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የዘንድሮውን ስብሰባ ልዩ የሚያደገውን ምክንያት ሲገልጽ “ይህንን ስብሰባ ካለፉት ልዩ የሚያደርገው ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ ወይም ብሔር እና ብሔረሰቦች እንዲሁም ሕጋዊ ከሆኑ ተቃዋሚዎች ጋር በመተባባር የወደፊት የኢትዮጵያን ህልውና እውነተኛ የዲሞክራሲ የሕግ በላይነት የማንኛውም ግለሰብና ድርጅት መብት የሚከበርባት አገር ለመመስረት እንደሆነ ከኦነግ የፖለቲካ ለውጥ መረዳት ይቻላል” ብሏል።
“በዚህ ስብሰባ ላይ የሚገኙ ፡ የሐይማኖት አባቶች ፡ የፖለትካ ድርጅቶች ፡ መካሪ አዛውንቶችና ፡ ታዋቂ ግለሰቦች በወቅታዊ ኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ለመመካካር በዚሁ ታሪካዊ ጥሪ ላይ ይገኛሉ፡፡” ያለው ኦነግ “ስለዚህ ፡ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ፡ ይህ ጉዳይ ይመለከተኛል የሚል ሁሉ ጁላይ 7 2013 ከቀኑ 1፡00 ፒኤም እንድገኙልን በትህትና እንጋብዛለን። ብሏል።
በብርጋዲየር ጀነራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ ሕዝባዊውን ስብሰባ የሚያደርግበት አድራሻ የሚከተለው ነው።
አድራሻ : Best Western / Kelly Inn
161 St. Anthony Ave.
St. Paul , MN , 55103

July 7 , 2013 @ 1:00 Pm
አዘጋጅ ኮሚቴ
ጁላይ 7 የኦሮሞ ሰሜን አሜሪካ የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል በሚኒሶታ የሚደረግበት ሰሞን በመሆኑ ከሌሎች ስቴቶች እና ሃገራት የሚመጡ እንግዶች በዚህ ስብሰባ ላይ እንዲታደሙ እድሉን ይፈጥርላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።


ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 51 (PDF)

ጸረ ሙስና የዝቋላ ብረታ ብረት ፋብሪካን አስተዳደር በምክር ማለፉ አነጋጋሪ ሆኗል

$
0
0

321589_109993089111063_1484315227_a(ፍኖተ ነፃነት) በዝቋላ ብረታ ብረት ማምረቻ ፋብሪካ ንብረት አስተዳደር ከፍተኛ ሙስና መኖሩን አስመልክቶ የደረሳቸውን ጥቆማ በመንተራስ የጸረ ሙስና ኮሚሽን አጣሪዎች በፋብሪካው ምርመራ ሲያደርጉ ቢቆዩም የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አሊ ሱሌይማን ለፓርላማው አቅርበውት በነበረው የአስር ወራት የኮሚሽኑ ሪፖርት በዝቋላ ብረታ ብረት የታየው ክፍተት ማሻሻያ ሊደረግበት ይገባል በሚል ምክር ማለፋቸው በፋብሪካው እየተፈጸመ የሚገኘውን ብክነት በቅርበት የሚያውቁ ሰዎችን አስገርሟል፡፡
የፍኖተ ነፃነት ምንጮች እንደጠቆሙት ከሆነ ግልጽ ጨረታ ባልተደረገበት ሁኔታ 2.5 ሚልዮን ዩሮ ወጥቶባቸው የተገዙ የማምረቻ ማሽኖች ያለ አገልግሎት ተቀምጠዋል፡፡ ጸረ ሙስና ኮሚሽን በሪፖርቱ ከፍተኛ የምርትና የስራ ሰዓት ብክነት እንዲሁም ተመሳሳይ ችግሮች እንደሚስተዋሉ ከመጠቆም አልፎ ለፋብሪካው መሰረታዊ አገልግሎት ይሰጣሉ ተብለው የተገዙት ማሽኖች የሚፈለገውን አገልግት በመስጠት ላይ እንደማይገኙ ማረጋገጡን ይፋ አድርጓል፡፡ለፋብሪካው ስራ አስኪያጅ አቶ ጥበበ አየለ በፍኖተ ነፃነት ተደውሎላቸው በስልክ አለ ስለሚባለው ከፍተኛ ሙስና እና ተያያዥ ችግሮች በሰጡት ምላሽ ‹‹በመጀመሪያ ደረጃ ጸረ ሙስና ኮሚሽን የእኛን ፋብሪካ በሚመለከት በፓርላማ ሪፖርት ስለማቅረቡ የማውቀው ምንም ነገር የለም፡፡ ምርመራ ተደርጓል መባሉም ከኛ እውቅና ውጪ ነው፡፡ ማሽኖቹን የገዛናቸው ግልጽ የሆነ ጨረታ በማውጣት ሲሆን አስፈላጊነታቸውም በፋብሪካችን ባለሞያዎች ታምኖበታል በዚህ ላይ ማሽኖቹ ያለ አገልግሎት አልተቀመጡም አስፈላጊውን አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ›› ብለዋል፡፡
ተመሳሳይ ጥያቄ የቀረበላቸው የፋብሪካው ኃላፊ አቶ በፍቃዱ ዘውዴ በበኩላቸው ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ የዝቋላ ብረታ ብረት ፋብሪካ በመንግስት ቁጥጥር ስር የሚገኝ ሲሆን የተመሰረተው ከደቡብ አፍሪካው የብረታብረት አምራች ፋብሪካ (ISCOR)ብረት ለማምረት የሚያስችል ንጥረ ነገር ተገዝቶ በ1990
መገንባቱ አይዘነጋም፡፡

ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ 2ኛ ዓመት ቅጽ 2 ቁ 77

$
0
0

Fnote 77 pic

ብአዴን ‹‹ሰለሞናዊ›› ስርወ መንግስት!? – (ሊያነቡት የሚገባ የአደባባይ ምስጢር)

$
0
0

የብርሐኔ አበራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ቤተሰብ አባላት አቶ በረከት እና አዲሱ

የብርሐኔ አበራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ቤተሰብ አባላት አቶ በረከት እና አዲሱ

በአንድ ወቅት ዜጋ መጽሔት ላይ ታትሞ የነበረና ለግንዛቤዎ ይጠቅምዎታል ብለን እንደገና ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች አቅርበናል።
በአንዳንድ የአገዛዝ ሥርዓቶች በሀብት፣ በመደብ፣ ወይም ዴሞክራሲያዊ ምርጫ፣ አልያም በዘር የተዋቀረ ሥርዓት ይኖራል፡፡ ለምሳሌ በአፄ ኃይለ ስላሴ ጊዜ የነበረው የስልጣን ፍልስፍና ከሰለሞን ስርዎ መንግስት የሚመዘዝ የዘር ሀረግ ባለቤት መሆንን ይጠይቅ እንደነበረ ሁላችንም የምናስታውሰው ነው፡፡ ከሰለሞን ስርዎ (Solomon Daynasty) መንግስት ውጭ ላሉና በዚያ የስልጣን ዘር ሀረግ ውስጥ ያሉ ሆነው በጉልበትም ይሁን በብልሃት ስልጣን ላጡት ስልጣን የሚሰጣቸው በጋብቻ ትስስር እንደነበረ ለማስታወስ የአፄ ኃይለስላሴ ልጆች ከማንና የት ተጋብተው እንደነበረ ማስታወሱ በቂ ምሳሌ ነው፡፡
ከፍ ብዬ የጠቀስኩትን የታሪክና የንድፈ ሀሳብ ማነፃፀሪያ ይዘን የኢህአዴግ አባል ድርጅት ስለሆነው ብአዴን የስልጣን ድልድልና ከሕወሓት በሚሰጣቸው መመሪያ ድርጅቱን በሞኖፖል አንቀው የያዙትን ግለሰቦች የጋብቻ ትስስር፣ በትጥቅ ትግል ዘመን ጊዜ የነበራቸው ተሳትፎን እንዲሁም ዛሬ ያሉበትን ሁኔታ እንደሚከተለው ላቀርብ ተከታተሉ፡–
በክልል ሶስት በዋግ ህምራ ዞን ብርሃኔ አበራ ስለሚባሉ ባልቴት ታጋይ ነው የማወጋችሁ፡፡ ለስሙ የዋግህምራ ዞን ኃላፊ (ሊቀመንበር) ልጃለም ወልዴ ሆኑ እንጅ የዞኑ ህቡዕ መሪ ብርሃኔ አበራ ናቸው፡፡ ይታሰር ያሉት ይታሰራል፤ ይፈታ ያሉት ይፈታል፤ ይባረር ያሉት ሁሉ ከስልጣን ላይ ይባረራል፡፡
ወይዘሮ ብርሃኔ አበራ ለመሆኑ ይኀን ሁሉ ገበሬ ኩሉ ስልጣን ከየት አገኙት? የስልጣን ምንጫቸውን የጨበጡት ከዚህ ቀጥሎ ዝርዝራቸውን በማቀርባቸው ‹‹ታጋይ›› ልጆቻቸው፣ እህቶቻቸውና አማቾቻቸው ወዘተ ነው፡፡
የብርሃኔ አበራ ልጆች
1. መዝሙር ፈንቴ የብአዴን ማ/ኮ አባል የነበረ አሁን የተባረረ፤
2. አሰፋ ፈንቴ፡- የበረከት ስምኦን ሚስት/ሲቭል ሰርቪስ ኮሌጅ የምትማር፤
3. ገነት ፈንቴ፡- አንድ የሕወሓት የደህንነት ባለስልጣን ያገባች፤
4. የሺሀረግ ፈንቴ
5. አሸናፊ ፈንቴ
6. መላኩ ፈንቴ
7. አበባ ፈንቴ፡- የሟቹ ሙሉአለም አበበ ሚስት የነበረች፤ በአገር ውስጥ ጉዳይ የኢሚግሬሽን ቪዛ ኃላፊ የነበረች፤ (የብርሃኔ አበራ እንጀራ ልጅ)
8. አለሚቱ ፈንቴ፡- በክልል ሶስት የምክር ቤት አባል የነበረች፤ አሁን እንግሊዝ አገር ያለች (የብርሃኔ አበራ የእንጀራ ልጅ)
9. ኃይሉ ፈንቴ፡- የጢጣ ት/ቤት አስተዳደር
10. አድና ፈንቴ (የተሰዋች)
የወይዘሮ ብርሃኔ አበራ ታጋይ እህቶች
1. የሺ አበራ የጄኔራል ኃይሌ ጥላሁን ሚስት፣ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል በኃላፊነት ቦታ የምትሰራ፤
2. ነጻነት አበራ፡- የታደሰ ጥንቅሹ (ካሳ) ሚስት ክልል ሶስት በፕሮፖጋንዳ ክፍል ውስጥ የምትሰራ፤
የብራሃኔ አበራ ታጋይ የልጅ ልጆች
1. ውዲቱ አጋዡ፤- መከላከያ ውስጥ የነበረች፤
2. ፍሬህይወት አጋዡ፡- የኢህአዴግ ቢሮ ውስጥ ያለች፣ የውዲቱ አጋዡና የፍሬህይወት አጋዡ እናት የብርሃኔ አበራ ታላቋ ልጃቸው ዋርቃ ናት፡፡
የብርሃኔ አበራ የእህት ልጆች
1. እንወይ ገብረመድህን የጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር (የአዲሱ ለገሰ ሚስት የነበረች)
2. ቢያድጎ፤
3. የዋግህምራ አቃቢ ህግ ሹም-ወይዘሮ እንወይ ገ/መድህን የአንድ ወንድ ልጅና የሁለት ሴት ልጆች እናት ናቸው፡፡ የወ/ሮ እንወይ ልጆች አባት አቶ ብርሃኑ ነጋሽ ዛሬ ነዋሪነታቸውን አሜሪካ አገር ያደረጉ ሲሆን፣ ከባለቤታቸው ጋር የተለያዩት ወ/ሮ እንወይ ገና ወደትግል ሜዳ ከመግባታቸው በፊት ነበር፡፡ ወ/ሮ እንወይ
የብርሃኔ አበራ ቤተሰብን በጋብቻ የተዛመደው ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ)

የብርሃኔ አበራ ቤተሰብን በጋብቻ የተዛመደው ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ)

ወደ ትግል ከገቡ በኋላ ከአቶ አዲሱ ለገሰ ጋር አንድ ወር ላልበለጠ ጊዜ ጋብቻ መስርተው ነበር፡፡ የአሁኗ የአዲሱ ለገሰ ሚስት የሰቆጣዋ ታምር ተሻለ ነች፡፡ ወ/ሮ እንወይ በአሁን ሰዓት ትዳር የላቸውም፡፡ ወ/ሮ እንወይ ትግሉን ሙሉ በሙሉ የተቀላቀሉት ከ1978 ዓ.ም ወዲህ ነው፡፡ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ኢህዴን ወደ ብአዴን ከተለወጠ በኋላ ነው፡፡ ምንም እንኳ በበረሃው ዘመን የነበራቸው የፖለቲካ ንቃት የኢህዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ሊያደርጋቸው የሚችል የነበረ ቢሆንም፣ ኢህዴን ከሕወሓት የፖለቲካ ፕሮግራም የገለበጠውን ‹‹ፊውዳሊዝም አስፈጊ ጠላታችን በመሆኑ (Threa-tening enemy) በፕሮግራማችን ውስጥ መስፈር አለበት›› የሚለውን አመለካከት ወ/ሮ እንወይ ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያ አብዮትና ደርግ ጠራርገው የጣሉት ስርዓት የሌለ ስለሆነ፣ ስለሌለ ፊውዳሊዝም መሰረታዊ የኢትዮጵያ ህዝቦች ጠላት ነው ብሎ ፕሮግራማችን ውስጥ ማስፈር የለብንም›› የሚል አቋም ነበራቸው፡፡ ይህ አቋማቸው እንዲያውም የኢህአፓን ፕሮግራም ተከታይ አስብሏቸው ስለነበረ ነው በጣባው ኮንፍረንስ የኢህዴን ማ/ኮ አባል ሆነው ሳይመረጡ የቀሩት፡፡
4. ሌላኛዋ የብርሃኔ አበራ የአክስት ልጅ፡- የአቶ ታምራት ባለቤት ሁለት ልጆቿን አሜሪካ ይዛ የገባችው ወ/ሮ ሙሉ ግርማይ ናት፡፡
የዚህ ቤተሰብ የእርስ በእርስ ግንኙነት ሁኔታ
በትጥቅ ትግሉ ዘመን ይህ ቤተሰብ እርስ በራሱ በጣም ይደጋገፍ ነበር፡፡ ከእንወይ ገ/መድህን በስተቀር እስከ 1983 እንወይ ገ/መድህን ከዚህ ቤተሰብ እንዲገለሉ ያደረጋት ታደሰ ጥንቅሹ ነበር፡፡ በ1975 ዓ.ም የኢህዴን የህቡዕ አባላት ተጋልጠው የህይወትና የአካል አደጋ ደርሶባቸው ነበር፡፡ ይህን የህቡዕ አባላት እንቅስቃሴ በጊዜው ይከታተለው የነበረው ታደሰ ጥንቅሹ ነበር፡፡ የእቡዕ አባሎቻችንን ያጋለጠችው እንወይ ነች ብሎ ስላስወራባት ነው እስከ 1983 በመጠኑም ቢሆን ከዚህ ቤተሰብ የተገለሉት፡፡
ሌላኛዋ የዚህ ቤተሰብ አባል ሆና ይኸን ያህል የጎላና እፍ እፍ የቤተሰብ ፍቅር ያልነበራት ወ/ሮ ሙሉ ግርማይ ነች፡፡ እንዲያውም ወደመጨረሻው አካባቢ የአንድ ቤተሰብ አባል ሆነው በባሎቻቸው የስልጣን ከፍና ዝቅ ማለት፣ በአኗኗርና በአለባበስ በወ/ሮ ሙሉ ግርማይና በሌላው ቤተሰብ አባላት ከፍተኛ አለመግባባት ተከስቷል፡፡
አቶ ታምራት ላይኔም ከብርሃኔ አበራ ቤተሰብ ጋር ይዛመዳሉ

አቶ ታምራት ላይኔም ከብርሃኔ አበራ ቤተሰብ ጋር ይዛመዳሉ

ከዚህም በላይ አቶ ታምራት የግንቦት 20 ትምህርት ቤት ይማሩ በነበሩ የዚህ ቤተሰብ አባላት ዘንድ ከፍተኛ ፈንጠዝያ ተፈጥሮ ነበር፡፡
ዘ-ሐበሻ ድረገጽን ሁልጊዜ ያንብቡ። በየሰዓቱ አዲስ ነገር አያጡም።
በትጥቅ ትግሉ ወቅት የዚህ ቤተሰብ ተሳትፎና መስእዋትነት
በመግቢያዬ የዘረዘርኳቸው የዚህን ቤተሰብ አባላት ዋና ዋናዎቹን ነው፤ እንጂ ጠቅላላ በብአዴን ውስጥ ያሉትን ኢህዴን ውስጥ የታገሉት በቁጥር 60 ናቸው፡፡ በትጥቅ ትግሉ ውስጥ የነበራቸውን ተሳትፎ በትክክል ማየት እንድንችል ከዚህ ቀጥዬ ስም ዝርዝራቸውን የማቀርብላችሁ በኢህአዴን ውስጥ እንደታጋይ ታቅፈው ጊዜው ይጠይቅ የነበረውን የትጥቅ ትግል ምላሽ ለመስጠት እንዲችሉ የወታደራዊ ስልጠና (ተአለም) ያልወሰዱትን ነው፡፡
1. እንወይ ገ/መድህን
2. ኃይሉ ፈንቴ
3. የሺሀረግ ፈንቴ
4. ገነት ፈንቴ
5. አሸናፊ ፈንቴ
6. አለሚቱ ፈንቴ
7. ብርሃኔ አበራ ከማስታውሳቸው የዚህ ቤተሰብ አባላት ከፊሎቹ ናቸው፡፡
ሁሉም ሰው መገንዘብ እንደሚችለው በአንድ የሽምቅ ውጊያ ስልታዊ ንቅናቄ ውስጥ የሚገኙ የድርጅት አባላት በሙሉ ትግሉ የሚጠይቀውን የወታደራዊ ስልጠና ወስደው ቢያንስ ራሳቸውን መከላከል በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መገኘት አለባቸው፡፡ ሙያና ምንም አይነት የመጀመሪያ ደረጃ የውጊያ እውቀት የሌለው ታጋይ ጠላት ኃይሉን አጠናክሮ ወደ ድርጅቱ ቤዝ አምባ ሊገባ በሚዘጋጅበት ጊዜ ከእቃ ጋር አብሮ መሸሽ ነበር የመጨረሻ እጣ ፈንታው፡፡ ይህ በደፈናው የሚቀርብ የንድፈ ሀሳብ ትንተና ሳይሆን ኢህዴን ውስጥ በተግባር የታየ ሀቅ ነው፡፡ ይህ ቤተሰብ በትጥቅ ትግሉ ዘመን መሽጎ የኖረው ጠላት ይደርስበታል ተብሎ በማይገመተው የኢህዴን ቤዝ አምባ ውስጥ ነው፡፡ የትጥቅ ትግሉ የሚጠይቀውን የውዴታ ግዴታ ይህ ቤተሰብ ሊፈፅም ባለመቻሉ በተለይ በ1978 አካባቢ በሌላው የድርጅቱ አባላትና ይኸን ቤተሰብ ጉያው ውስጥ በሸጎጠው የኢህዴን ማ/ኮ አባል መካከል ከፍተኛ አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር፡፡
በወቅቱ ይነሱ የነበሩ ጥያቄዎች ይህ ቤተሰብ ለመስእዋትነት ዝግጁ አይደለም፤ የሌላውን የድሀ ገበሬ ልጅ ላብና ደም እየጋጠ መኖር የሚፈልግ ነው፤ የኢህዴን ማ/ኮ ለዚህ ቤተሰብ (የነማዘር ቤተሰብ) አባላት ልዩ እንክብካቤ ያደርጋል የሚሉ የሰላ ሂሶች ነበሩ፡፡
ከላይ ስለዚህ ቤተሰብ የገለፅኳቸውና ያነታርኩ የነበሩ ጥያቄዎች ምን ያክል ትክክል መሆናቸውን ለማየት ከ60 የቤተሰብ አባላት ውስጥ ስንቶቹ የህይወት፣ ስንቶቹ የአካል መስእዋትነት ከፈሉ የሚለው ጥያቄው በትክክል ይመልሰዋል፡፡ ከዚህ ቤተሰብ ውስጥ የህይወት መስእዋትነት የከፈለችው አድና (ታሪክ) ፈንቴ ብቻ ነች፡፡
በጥይት የቆሰሉ
1.ነፃነት (አምራየ) አበራ በ1977 ዓ.ም ቀስታ ውስጥ ልዩ ስሙ አቡነይ ጋራ በተባለ ቦታ በተካሄደ ውጊያ ዳሌዋ ላይ መጠነኛ የመቁሰል አደጋ የገጠማት ሲሆን በሌላ ውጊያ በጌምድር ክፍለ ሀገር ደጎማ ከተማ በተካሄደ ውጊያ ቀኝ እጇን በብርቱ ቆስላለች፡፡
2.መዝሙር ፈንቴ በ1977 ዓ.ም ዋግ አውራጃ ልዩ ስሙ ተላቁዝቁዛ ይገኝ ከነበረው የኢህዴን ቤዝ አምባ ከራሱ ከመዝሙር ፈንቴ ቤተሰብ ጥይት እግሩ ላይ የመቁሰል አደጋ ገጥሞታል፡፡ ሲጠቃለል ከስድስት ግለሰቦች ውጪ በዚህ ቤተሰብ ላይ የደረሰበት የአካልም ይሁን የህይወት መስእዋትነት የለም፡፡ ስለዚህ የኢህዴን አባላት ለዚህ ቤተሰብ መስእዋትነት ከፈሉ እንጂ ይህ ቤተሰብ ለኢህዴን የከፈለው መስእዋትነት ኢምነት ነው፡፡ እንዲያውም በደም ጎጆ በተገነባ ቤት ውስጥ ተንደላቀው ኖሩ እንጂ ስለነ ‹‹ማዘር›› (ብርሃኔ አበራ) ቤተሰብ ሲነሳ እኔም ጆሮ ዳባ ልበስ ብዬ የማሳልፈው ሀቅ አለ፡፡ የዚህ ቤተሰብ አንድ የእህል ወፍጮ ከቤተሰቡ በላይ እንዳገለገለ መርሳት እኔም የበላሁትን ቂጣ መካድ ይሆንብኛል፡፡

(ዘ-ሐበሻን ያንብቡ0

Hiber Radio: አማራው ተደራጅቶ ራሱን ከህወሃት ጥቃት እንዲከላከል ጥሪ ቀረበ

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ዕሁድ  ግንቦት 18  ቀን 2005 ፕሮግራም

<<…በደቡብ አፍሪካ ፣በአንጎላ፣ በሞዛምቢክ እነዚህ ወንድሞቻችን ካሉበት የባርነት ቀንበርነጻ እስኪወጡ ድረስ መላው አፍሪካና  ኢትዮጵያዊያኖች በዓለም ሸኝጎ በዕኩልነት ድምጻቸው እንዲሰማ …የአፍሪካ አገሮች የአዲስ አበባ ጉባዔ…>>ቀዳማዊ አጼ ሀይለስላሴ እ.አ.አ በ1963 ካደረጉት ንግግር የተወሰደ

<<ህወሃት ጣሊያን የሰራውን ነው በአማራ ህዝብ ላይ እያደረገ ያለው። የፋሺስቱ ጣሊያንና አሁን ያለው የህወሃት አገዛዝ ጸረ አማራ አቁዋም አንድ ነው። አማራው ራሱን ማደራጀትና ከዚህ ሊያቀጠፋው ከተነሳ ድርጅት ጥቃት መከላከል አለበት። አማራ ልደራጅ ሲል ለምን ተቃውሞ ይቀርባል?…>>

አቶ ተክሌ የሻው የሞረሽ ወገኔ ሊቀ መንበር በቬጋስ ተገኝተው ካደረጉት ንግግር የተወሰደ

<<… አማራው እየተረገጠ ለመብትህ አትደራጅ ብትለው ማን ይሰማሃል? ማርቲን ሉተርን አትደራጅ ትለዋለህ? ማህተመ ጋንዲን እንግሊዞችን አትታገል ትለው ነበር? ህወሃት ከዚህ የባሰ ነው። አማራው በፖለቲካውም ሆነ በወታደራዊ መስክ ተደራጅቶ ራሱን መከላከል አለበት። አማራ ተደራጅቼ …ልግደል ቢል ግን እንታገለዋለን። ዛሬ ዘመኑ ሰልጥኗል ሰው ልግደል ብለህ ፓርቲ ብታቋቁም ሰው አይከተልህም።ለመብት ተደራጅቶ መታገሉን ግን እደግፋለሁ…>>ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን በቬጋስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ራዕይ ማህበር የቀድሞ ሊቀመንበር ስለ አማራ መደራጀት ከተናገሩት

<<…ወ/ሮ ትግስት ከሲና በረሃ ለሽፍቶቹ ገንዘቡ ተከፍሎ ተለቃለች።ዛሬ ካይሮ ግብጽ ነች።እዚያ ያሉ ግፍ የሚፈጸምባቸው ወገኖቻችንን በተመለከተ እያንዳንዳችን ሀላፊነት አለብን…>> ወ/ሮ ሰብለ ደምሴ ከሱዳን ታፍነው ተሽጠው በሲና በረሃ ሲሰቃዩ የቆዩትን ሴት ለማስለቀቅ ዕርዳታ ማሰባሰቡን ካስተባበሩት አንዷ ለህብር እንደተናገሩት

የአፍሪካ ህብረት እና የ50 ዓመት ክብረ በዓሉ ዳሰሳ  

ሌሎች ቃለ መጠይቆችም አሉን

ዜናዎቻችን

- የግብጹ ፕሬዜዳንት ሙርሲ አዲስ አበባ ላይ በአባይ ግድብ ዙሪያ መከሩ

- አንድነት የሰኔ አንድ ሰማዕታትን በሕዝባዊ ንቅናቄ አከብራሉ አለ

- አማራው ተደራጅቶ ራሱን ከህወሃት ጥቃት እንዲከላከል ጥሪ ቀረበ

- በጉዲፌቻ መልክ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የመጣች ህጻን ልጅ በአደጋ ሞተች

- የኤርትራ ጳጳሳት ለተመድ ዋና ጸሃፊ አቤቱታ አቀረቡ

ሌሎችም ዜናዎች አሉን

“አባይ ይገደብ፤ ኢህአዴግም ይገደብ፤ አባይ ይቀየስ ኢህአዴግም ይቀየስ!” –ከአቤ ቶኪቻው

$
0
0

አቶ በረከት

አቶ በረከት

“የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት ከዚህ በፊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬድዮ ጣቢያ ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ተቆጣጥሮታል፡፡ ጉንቦት ሃያ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት አመተ መህረት!” አለ ታጋዩ…

“የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት ከዚህ በፊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬድዮ ጣቢያ አሁን ደግሞ ለራሱ ጥቅም ተቆጣጥሮታል፡፡ ቆጣጥሮታልም፤ ግንቦት ሃያ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት አመተ መህረት!” አልኩ እኔ…

“ኢህአዴግ ደርግን ደመሰሰ እና ሌላ ቀዳበት” አለ ልጅ ያሬድ! ”ኢህአዴግ ደርግን ደምስሶ በደርግ ዜማ ሌላ ቀዳበት” አልኩ እኔ

ዛሬ ግንቦት ሃያ ነው፡፡

አነዛ ፀጉራቸውን አሳድገው አዲሳባ የገቡ ሰዎች ዲሞክራሲን እና መልካም አስተዳደር ያሳድጉልናል… ብሎ ተስፋ የጣለባቸው ሁሉ በቴስታ ብለው ከጣሉት እነሆ ሃያ ሁለት አመት እንደዋዛ ሆናቸው፡፡

መልካም አስተዳደሯንም ለራሳቸው እያደሯት፤ ዴሞክራሲዋንም ራሳቸው እየኮመኮሟት ህብረተሰቡን እንቁልጭልጭ አሉት፡፡

ዛሬ የግንቦት ሃያ በዓል ሲከበር የአባይ ወንዝን የማስቀየስ ስራ ይሰራል ተብሏል፡፡ ወንዙ ተቀይሶ ምን ላይ ሊሆን ነው… እንዴት ነው ነገሩ በሳፋ ነው እንዴ ግድቡ የሚሰራው… ብዬ ልጠይቅ ወይስ አልጠይቅ…!

አስታውሳለሁ፤ “አባይ ይገደብ በቃ” ብለው ጠቅላዩ የወሰኑት ከሁለት አመት በፊት “በቃ” በሚል ሀይለ ቃል …ኢህአዴግ ይበቃዋል ግንቦት ሃያን ዘንድሮ ለመጨረሻ ጊዜ እናከብራለን ከዛም ለድጋፍ ሰልፍ ወጥተን በዛው እንቀራለን፡፡ ኢህአዴግ እስካልወረደ ድረስም እቤታችን አንገባም…. የሚል እንቅስቃሴ በፌስ ቡክ በኩል ተጀምሮ የነበረ ጊዜ ነው፡፡

በዚህ በ”በቃ” ጦስ እነ ርዮት አለሙ እነ ውብሸት ታዬ እነ አቶ ዘሪሁን ገብረ እግዚአብሄር እነ ሂሩት ክፍሌ ወድያው ለእስር ሲዳረጉ ቀስ በቀስ ደግሞ ሌሎችም ለቃሊቲ እና ለቂሊጦ ተዳርገዋል፡፡ (በተለይ የነዚህ ወዳጆቼን ፍርድ ሂደት ስከታተል ነበር እና አጋነንክ ቢሉኝም ባይሉኝም የአቃቤ ህግ ማስረጃ “በቃ የሚለውን የፌስ ቡክ እና የአደባባይ እንቅስቃሴ ትኩር ብላችሁ አይታችኋል” የሚል ነበር)

እንቅስቃሴው በፌስ ቡክ ተጀምሮ በየአደባባዩም “በቃ” የሚል ሃይለቃል በመፃፍ ተሟሙቆ የቀጠለ ነበር፡፡ በርካቶችም ግንቦት ሃያ መስቀል አደባባይ የሚፈጠረውን ተዓምር እያሰቡ አንድም ደስታ አንድም ፍርሃት ሲፈራረቅባቸው አንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡

ይሄኔ አቶ መለስ ፈርሸው ዘየዱ፤ (ሁል ጊዜ ቁጭ ብለው አሰቡ… እያልንኮ ፍራሽ የሌላቸው አስመሰልናቸው… “ፈርቸው” ማለት ፍራሽ ዘርግተው እጅግ በተመስጦ ማሰብ ማለት ነው…) አስበው አስበውም፤ “ለምን አባይን አንገድበውም…” አሉ እርሳቸው ብለው እምቢ… እንዴት… ለምን… በምን… አይባልምና እሺ እሺ ተብሎ ተጀመረ፡፡ የዛን ጊዜውን ግንቦት ሃያም መንግስታችን ለአባይ ግድብ ድጋፍ ሰልፍ ውጡልኝ፡፡ አለ… በዛውም የህዝቡ የተቃውሞ ሃሳብ ተገደበ፡፡

የአቶ መለስን ብልጠት በመኮረጅ ፈተናዎች ይታለፋሉ ብለው የሚያምኑት አቶ በረከት ደግሞ ዛሬ እነሆ በግንቦት ሃያው አባይ ወንዝን የማስቀየስ ስራ እነደሚሰራ በቴሌቪዥናቸው ብቅ ብለው ነገሩን፡፡

ጥሩ ኮርጀዋል…! አኮራረጃቸው ስም ሁሉ ሳይቀር እንደሚቀዳ አይነት ኮራጅ ነው፡፡

ህዝቡ ይህንን ዜና ሲሰማ ምን አላቸው… የሚለውን ቤት ለቤት ሄደን መጠየቅ ብንችል ጥሩ ነበር፡፡ መጠየቅ ባንችል ግን መጠርጠር እንችላለን እና አንዲህ እንጠረጥራለን፤

“አባይ ይገደብ፤ ኢህአዴግም ይገደብ፤ አባይ ይቀየስ ኢህአዴግም ይቀየስ!” ሳይላቸው አይቀርም፡፡

እየተስተዋለ – በወንድስን ገ/ህይወት (ቪ.ሚ)

$
0
0

ላለፉት 22 ዓመታት በትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር ሀገራችን በጉልበት መመራት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በህዝባችንና በሀገራችን ላይ በመፈጸም ላይ የሚገኘው እጅግ አሰቃቂና ዘግናኝ ሁኔታዎች ተባብሰው ይገኛሉ።

ይህ የወንበዴ ስብስብ ይህን ሁሉ ግፍ እየፈጸመ የሚገኘው በሀገራችን ውስጥ ምንም ዓይነት ነጻ የፍትህና የነጻ ፕሬስ ተቋማት እንዳይኖሩ በማድረጉ ነው።የህዝባችን መብት መረገጥ፣የሀገራችን ህልውና እጅግ ያሳሰባችው ቆራጥና ደፋር ጥቂት ኢትዮጵያውያን ይህን ዘረኛ የወንበዴ መንግስት ፊት ለፊት በመጋፈጥ ታግለዋል፣ህዝቡን በማስተባበር ሥርዓቱን ለመጣል ሞክረዋል፣ለዓለም ህብረተሰብ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ ለማስረዳት ጥረዋል።ይህን በማድረጋቸው በገዢው የትግሬ ነጻ አውጭ ቡድን መታሰር፣መደብደብ፣የአካል መጉደል፣መሰደድና መገደል ደርሶባቸዋል።በተለይም ዛሬ በሀገራችን ውስጥ በነጻነት ተምሮ ሰርቶ መኖር የማይቻልባት ሀገር በመሆንዋ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ወገኖቻችን ጨምሮ ህዝባችን በብዛት እየተሰደደና ሀገሩን እየተወ በመሸሽ ላይ ይገኛል።
የሀገራችን ሁኔታ ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሉዓላዊነትዋ አሳሳቢ ደረጃ ደርስዋል።በውጭ ወራሪዎች እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን ያልተደፈረችው ሐገራችን የናት ጡት ነካሽ በሆኑ የማሕጸነ መርገምት ልጆችዋ በውጭ ሐይል እርዳታ በተደራጀ ተገንጣይና አስገንጣይ ቡድን በግልጽ ለጨረታ ቀርባ እየተቸበቸበች ትገኛለች።ይህን ድርጊት ተባብረን ካላቆምነው አባቶቻችን ድማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው በነጻነት ሐገራችንን ጠብቀው ለኛ ያስተላለፉልንን አደራ እኛም ለተተኪው ትውልድ ሣናስተላልፍ ብንቀር ታሪክ ተጠያቂና ተወቃሽ ከመሆን አንድንም።

ይህ ስርዓት ላለፉት 22 ዓመታት ያለ ምንም ተቀናቃኝ በሥልጣን ላይ የቆየው በሱ ጥንካሬና ሀይል ሳይሆን በኛ ያለመተባበር፣ከሁሉም በላይ በፍርሀት፣በሽሽት፣በልዩነትና ሀላፊነትን ለመወጣት መስዋዕትነትን ለመክፈል በመፍራታችን ጭምር ነው።ካለፉት ህዝባዊ እምቢተኝነትና በዘረኝነት ላለመገዛት ህዝብ የወሰደውን የጋራ ትግል ስሜት ትግሉን በሚመሩት አካሎች ቆራጥ አመራር ለመስጠት አለመቻል፣መስዋዕትነትን በመፍራታቸው ምክንያት አሸናፊ ለመሆን አልቻልንም።

በሀገራችን ውስጥ በየክፍለ ሀገሩ፣በየቀበሌው እየደረሰ ያለው በደል መጠኑ ይለያይ እንጂ በሁሉም የሀገራችን ክፍል ተመሳሳይ ነው። በየዕለቱ ከሐገር ቤት የምንሰማው ዜና ሁሉ እጅግ አሳዛኝና የወገን ያለህ የሚያሰኝ ሁንዋል።ገዢው የወያኔ ሐይል ይህንን ሁሉ በደል በሕዝባችን ላይ የሚፈጽመው ባለው መሳሪያ፣መረጃና ገንዘብ ብቻ ሳይሆን የህዝብን ሚድያ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠሩና በነጻው ፕሬስ ላይም እገዳ በማድረግ ሕዝባችን ምንም ዓይነት መረጃ እንዳያገኝ በመዝጋቱ ነው።

በውጭ ሐገር በስደት የሚኖሩ ጥቂት ኢትዮጵያውያን የሐገራቸውን ህልውና ለመታደግና የሕዝቡን ጭቆና ለማስወገድ በድርጅት፣በቡድንና በግል ጭምር ብዙ እየጣሩ ይገኛሉ።በተለይም ሕዝቡ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ ወደ ሐገር ቤት የሚተላለፍ የሬድዮ አገልግሎት ለመስጠት ሲሞክሩ ረጂም ጊዜ አሳልፈዋል።ብዙዎቹ ሬድዮኖች ተጠናክረው መቀጠል ባይችሉም ጥቂቶቹ አሁንም እየሞክሩ ይገኛሉ።እስካሁን ያደረጉት አስተዋጽኦ ቀላል ባለመሆኑ ሊደገፉና ሊመሰገኑ ይገባቸዋል።

በቅርቡ ደግሞ በእድሜ ለጋ የሆነው ኢሳት የቴሌቪዥንና የሬድዮ አገልግሎት ወደ ሐገር ቤት እየሰጠ ይገኛል።ይህ ድርጅት ወደ ሐገር ቤት በተለያዩ መንገድ ለሕዝብ የተጣራ መረጃ በማቀበል በኩል እያደረገ ያለውና በየሰዓቱ ሐገር ውስጥ የሚደረገውን ድርጊት ውጭ የምንገኘው ኢትዮጵያውያን እንድናውቅ የሚደረገው ጥረት ብዙ አድማጭና ተመልካች እንዲኖረው ከማስቻሉም በላይ ድጋፋችንን እንድንሰጠው አድርጎናል።

ይህ ለጋ ድርጅት እስካሁን በሚሰራው እሰይ እደግ ተመንደግ አስብሎታል።በዚህ ሥራ ላይ እውቀታቸውን፣ ጉልበታቸውንና ገንዘባቸውንም እየሰጡ ኢሳት እንዲጠናከር ለሚያደርጉት ኢትዮጵያውያን በግሌ አክብሮትና ምስጋና አቀርባለሁ። ድርጅቱ ገና ወጣት ተቋም በመሆኑ በስራው ሂደት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የሚደረጉ ጥቃቅን ስህተቶች እንደሚኖሩ ብገምትም አንዳንዶቹ ግን ሀገርም ሆነ ህዝብ የማይጠቅሙ ከመሆናቸው በላይ በኢሳት ደጋፊዎች ላይ እምነትን የሚያሳጡ እንዳይሆኑ እሰጋለሁ።

ከነዚህም ውስጥ ቢያንስ ሁለቱን ለመጥቀስ እወዳለሁ።

፩ኛ። ካሁን በፊት በዜና ከተላለፈው ውስጥ አክራሪና ተገንጣይ የፖለቲካ አቋም ለመተግበር ሲል ሀገራችንንና ህዝባችንን ሲጎዳ የነበረው በተለይ በሀረር ጋራ ሙለታና አካባቢው ንጹሀን ዜጎች ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ ያደረገውን የእስላሚክ ኦሮሚያ መሪ ጃራ አባ ገዳን የኦሮሞ ሌጀንድ የሆኑት አረፉ ሲል በእሳት ቲቪ ያቀረበውን ዜና ስሰማ እኔን ያሳዘነኝን ያህል ብዙ ኢትዮጵያውያንን አሳዝኖቸዋል ብዬ እገምታለሁ። እኔም እንደ ኢሳት የሆላንድ ድጋፍ ሰጭ አባልነቴ ለኢዲቶሪያል ቦርዱ ቅሬታየን በወቅቱ በኢ፡ሜይል አሳውቄለሁ።

፪ኛ ሜይ 13 ቀን 2013 በተላለፈው እንወያይ ፕሮግራም በጋዜጠኛ ደረጀ ሀ/ወልድ፣ፋሲል የኔዓለምና አፈወርቅ አግደው የተካሄደው ውይይት ርዕስና በውይይቱም ሂደት የተንጸባረቀው ሀሳብ ፍጹም ግራ የሚያጋባ ሁኖ አግኝቼዋለሁ። ምክንያቱም የውይይቱም ርዕስ እንደሚያስረዳው በሀገር ቤት ውስጥ በሰላማዊ ትግል ለመታገል በህጋዊነት ተመዝግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ በ50ኛው የአፍሪካ ህብረት በዓል ላይ የአ.አ ህዝብ ጥቁር በመልበስ በገዢው ፓርቲ (ወያኔ) በህዝብና በሀገራችን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል በመቃወም የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በመመርኮዝ ነበር።በተደረገው ውይይት የተጠራው ሰልፍ ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት፣የተመረጠው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ከሰላማዊ ሰልፉ ማን ሊጠቀም ይችላል? በሚል አብዛኛው በአፍራሽ እይታ የተሞላ ውይይት ነበር።ለመሆኑ የሁላችንም ፍላጎት የሆነውና ይህንን ሥርዓት ለመጣል በሀገር ቤት ውስጥ መሰረት ያደረገ ህዝባዊ ትግል መኖር ለትግሉ አስፈላጊ መሆኑ እየታወቀ ሀገር ውስጥ ያለውን መነሳሳት የሚያኮላሽና ሰልፍ እንዳይወጣ ጥርጣሬን የሚያጎላ ውይይት ጠቀሜታው ለማነው? የጋዜጠኝነት ሙያ ባይኖረኝም የቅድመ ትንበያው አተናተናዊ ሁኔታ ሰልፍ አትውጡ የሚል አንድምታ ያለው መልክት ለማስተላለፍ የተፈለግ አስመስሎታል።ይህ ሁኔታ ራሱን የህዝብ አይንና ጆሮ ለማድረግ ከሚሰራ ተቋም የማይጠበቅ ማስተዋል የጎደለው ዝግጅት ሁኖ አግኝቼዋለሁ።

በተለይ እንደ ኢሳት አይነት አማራጭ የሌለውና በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ህዝብ በከፍተኛ ትኩረት የሚከታተለው የመረጃ ተቋም ላይ የሚቀርቡ ፕሮግራሞች በሙሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግባቸው ይገባል። አስገራሚው ደግሞ ጋዜጠኛ ፋሲል፣ አፈወርቅና ደረጀ ያደረጉት ውይይት እኛን እንጂ ኢሳትን አይወክልም ሲሉ ይሰማሉ።ግን ማወቅ ያለባቸው እነሱ የኢሳት ባልደረቦችና የሙያ ተጠያቂዎች መሆናቸውን ጭምር ግንዛቤ ውስጥ አለማስገባታቸውና ኢሳትንም ተጠያቂ የሚያደርገው መሆኑን አለመረዳታቸው ነው።

ለግንዛቤ እንዲረዳ አንድ የቆየ በBBC የተላለፈ ዜና ትዝ አለኝ።በቀዝቃዛው ጦርነት ማብቂያው አካባቢ ዓለም ላይ ከፍተኛ ሥጋት ጥሎ የነበረው የኑክሊየር ፍጥጫ አስመልክቶ በመግቢያ ዜና ላይ ሰበር/Breaking news/ በሚል ዜና መሀል አንባቢው አዝናለሁ የእንግሊዝ ህዝብ በማለት ከሩሲያ የተተኮሱ የኑክሊየር ሚሳይሎች ከጥቂት ደቂቃ በሁዋላ ለንደን ይደርሳሉ ብሎ በማስተላለፉ በእንግሊዝ ህዝብ ላይ ምን ያህል መደናገጥ አስከትሎ እንደነበረና ጥቂት ቆይቶ ዛሬ እኮ April the fool ነው በማለት እየሳቀ መናገሩ ብዙ ሰው ያስቆጣ ነበረ። ዜናውን ያነበበው ጋዜጠኛና ፕሮግራሙን ያዘጋጀው ሀላፊ ከሥራ ከመወገዳቸውም በላይ በህግ ተጠያቂ ሁነዋል።

ለማጠቃለል ያህል በዚህ ምክንያት በሚድያ የሚቀርቡ ነገሮች በሙሉ ህዝብ እውነት ናቸው ብሎ ስለሚያምን በጣም ጥንቃቄ ያስፈልጋቸዋል።ይህንን ጽሁፍ በምጽፍበት ሰዓት የኢሳት ጠንካራ ሥራዎች እንዲጎለብቱ ድክመቶች ደግሞ ሊታረሙ ይገባቸዋል ብዬ ስለማምን ነው።

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!


ወንድስን ገ/ህይወት (ቪ.ሚ)


Health: 10 የእንቅልፍ ፀሮችና መፍትሄያቸው

$
0
0

getting-out-of-bed-clipartእንቅልፍ በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ ልክ እንደምግብና አየር ሁሉ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው፡፡ ሰዎች ጥሩ ምግብን እንደሚመርጡ ሁሉ ጥሩ እንቅልፍንም ሊያገኙ ይገባል፡፡ ከጤንነትም ሆነ የስራ ሂደትን በብቃት ከመወጣት አንጻር እንቅልፍ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ለህይወታችን አስፈላጊ ስለሆነም ነው ስንፈጠርም አብሮን ለእንቅልፍ የሚሆነን ጊዜም እንዲኖረን የተደረገው፡፡ ተፈጥሯዊ ሂደት ነው ማለት ነው፡፡ ታዲያ በመልካም እንቅልፍ ማረፍ በምንፈልግበት ጊዜ ለእንቅልፋችን እንቅፋት የሚሆኑ ችግሮችም አልጠፉም፡፡ በዋናነት የሚጠቀሱና ለእንቅልፋችን መረበሽ ምክንያት የሆኑ 10 አስገራሚ ክስተቶችን እስከነመፍትሄያቸው ቀጥለን እናያቸዋለን፡፡

1. በእንቅልፍ ልብ ተነስቶ መጓዝ

ብዙ ሰዎች ካሉባቸው የጤናና የቀን ውሎ ችግሮች የተነሳ በተለይም ከአንጎል ጋር ተያያዥ የሆኑ ችግሮች ሲፈጠሩ በእንቅልፍ ልባቸው ከአልጋቸው ተነስተው ሲጓዙ ይስተዋላል፡፡ እንደዚህ አይነት የእንቅልፍ ችግር የተለመደውን ጤናማ የእንቅልፍ ውህደት በማዛባትም ሆነ በእንቅልፍ የሚገኝን ረፍት በማሳጣት መልካም እንቅልፍም ሆነ የቀጣይ ቀን ውሎ እንዲስተጓጎል ያደርጋሉ፡፡ በተለይ ስለዚህ እያሰቡ የሚተኙ ሰዎች የበለጠ የችግሩ ተጋላጭ ከመሆናቸውም አልፎ ሲጀምሩም እንቅልፍ አልመጣ ብሎ ሊያስቸግራቸው ይችላል፡፡

እንደመፍትሄ በዚህ ችግር ውስጥ ያለ ሰው ወደ ሌላ ችግር ለሚፈጥሩ የሚችሉ ነገሮች ውስጥ ከመግባቱ በፊት በቀላሉ ሊወስዳቸው የሚችሉ እርምጃዎች አሉ፡፡ በእንቅልፍ ልቡ እየነቃ የሚቸገር ሰው የሚተኛበትን ክፍል ጨለማ ወይም በጣም ደብዛዛ ብርሃን በማድረግ ቢጠቀሙና ወደ መታጠቢያ ክፍል መጓዝ ቢለምዱ፣ ቴሌቪዥንን ወይም ኮምፒዩተርን ሳያጠፉ ቢተኙ ድንገት በመንቃት ቶሎ ወደ እንቅልፍ እንዲመለሱ ማድረግ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ድንገት በነቁ ሰዓት ቶሎ ወደ እንቅልፍ እንዳይመለሱ የሚያደርጉ ምግቦችን ወደ መኝታ ሲሄዱ አለመመገብ፣ ከአልጋ አጠገብ ብዕርና ወረቀት ማስቀመጥና በነቁ ሰዓት ራስን ወደ ማወቅ ቶሎ ሲመለሱ መጻፍን መልመድ፣ እግር፣ እጅንና ጭን አካባቢ ለቀቅ የሚያደርጉ ቀላል የማላቀቂያ ስፖርቶችን መስራት የመሳሰሉት ወዲያው ወደ ጥሩ እንቅልፍ እንዲመለሱ ለማድረግ ያግዛሉ፡፡ በየጊዜው እየተከሰተ ሌላ የጤና ችግር የሚፈጥር ከሆነ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል፡፡

2. በእንቅልፍ ውስጥ ሆኖ ጥርስን ማፋጨት

በእንቅልፍ ውስጥ ሆኖ ጥርስን ማንገጫገጭ በህክምናው አጠራር ብሮክሲዝም (Bruxism) ይባላል፡፡ ይህ ችግር ሰዎች ረዥም ሰዓት ሲጋራ ከማጨስ፣ ጫት ከመቃም፣ ከስራ መደራረብና ከመጨናነቅ፣ በመጥፎ ስሜት ውስጥ ሲሆኑና በውስጣዊ የጤና ችግሮች በመሳሰሉት ሊከሰትባቸው ይችላል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ልማዶች መተውና የጤና ምርመራ ማካሄድ እንደ ግራይንድ ኬር የመሳሰሉ የተለያዩ መፍትሄዎችን መውሰድም ያስፈልጋል፡፡

 3. የእንቅልፍ አውደ ስርዓት መዛባት

ሰርካዲያን ራይትም በመባል የሚጠራው በውስጣችን ያለ የእንቅልፍ የመንቂያ ሰዓታችንን የሚቆጣጠር ስርዓት ነው፡፡ ይህ የእንቅልፍ ሂደትን የሚቆጣጠረው ስርዓት በብርሃን፣ በጨለማ በስራ ብዛት በእንቅልፍ ሰዓት መቀያየር፣ በምንበላቸው ምግቦችና መጠጦችም ሊዛባ የሚችል ነው፡፡  ይህን ለመቅረፍ የእንቅልፍ ሰዓትን ወጥና ከብዙ መጨናነቆች ነፃ ከማድረግ ጀምሮ ቀን ላይ በቂ ብርሃን ባለበት ቦታ ስራን መስራትና ዘና የሚያደርጉ ቀላል የኤሮቢክስ ስፖርታዊ እንቅ ስቃሴ ማድረግ ምሽት ላይም የመኝታ ክፍልን ለእንቅልፍ የሚ መች ድባብ እንዲኖረው ማድረግ ተጠቃሽ መፍትሄ ናቸው፡፡

4. ሽንትን በተደጋጋሚ ከእንቅልፍ እየተነሱ መሽናት

ሽንትን በተደጋጋሚ መሽናት በሳይንሱ አጠራር ኖክቱሪያ (Nocturia) ሲባል በተለይም ሰዎች ዕድሜያቸው ሲገፋና ሰውነታቸው ፈሳሸ መያዝ ሲያቅተው በብዛት የሚታይ ነው፡፡ ይህ ችግር በፕሮስቴት ዕጢ አካባቢና በሽንት መውረጃ ቱቦዎች ላይ በሚከሰቱ ኢንፌክሽኖች ምክንያቱ ከፍተኛ የአልኮልና የአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚነት የመሳሰሉት በዋናነት የሚጠቀሱ ሲሆነ በእንቅልፍ ሰዓት ከእንቅልፍ በመቀስቀስም እረፍት የሚነሳ ነው፡፡ ወደ እንቅልፍ ሲሄዱ ካፌይን ያለባቸውን እንደ ቡናና ሻይ አለመጠጣት፣ ፈሳሽ አለማብዛት፣ አልኮል አብዝቶ አለመጠጣትና የሽንት ቧንቧና የሽንት ፊኛን ተመርምሮ ጤንነቱን መጠበቅ በዋናነት እንደ መፍትሄ ይጠቀሳሉ፡፡

5. ማንኮራፋት

ማንኮራፋትን በአጠቃላይ የእንቅልፍ ችግር ተደርጎ ባይወሰድም በከባድ ሁኔታ የሚፈጠር ማንኮራፋት ግን የእንቅልፍ ችግር ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ከመተንፈሻ አካል ችግሮች ጀምሮ የአተኛኘት ሁኔታና የሰውነት ክብደት፣ የምንወስዳቸው መጠጦች ለከፍተኛ ማንኮራፋት ሊዳርጉ ይችላሉ፡፡ ስለዚህም በመተንፈሻ አካላት አካባቢ ችግሮች ካሉ የህክምና መፍትሄ መውሰድ፣ ክብደትን መቀነስ፣ የመተኛ አቅጣጫን መቀያየር፣ የአልኮል መጠጥን መተው (በተለይም ድርቀትን በማምጣቱና ድርቀት ደግሞ ማንኮራፋትን የሚያነሳሳ በመሆኑ)፣ የእንቅልፍ መድሃኒቶችንና አደንዛዥ ኬሚካሎችን አለመጠቀም (በጉሮሮ አካባቢ ያሉ ጡንቻዎችን ዘና በማድረግ ማንኮራፋት እንዲባባስ ያደርጋሉ) እንደ መፍትሄ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

6. የትንፋሽ እጦት

በጉሮሮ ወይም በአፍ አካባቢ ባሉ ስስ ቲሹዎች ላይ በሚከሰቱ ጫናዎችም ሆነ የጤና ችግሮች የተነሳ ትንፋሽ እተቆራረጠ እንዲወጣ ማድረጉ በተለይም በእንቅልፍ ሰዓት ከፍተኛ ድምፅ ያላቸው ነገር ግን እየተቆራረጠ በቆይታ የሚሰማ ማንኮራፋት እንዲሰከት የሚያደርግ ነው፡፡ በአጠቃላይ የእንቅልፍ እጦት ችግር ተደርጎም ይቆጠራል፡፡ ይህ ጠለቅ ያለ የህክምና መፍትሄ የሚሻ ስለሆነ በእንቅልፍ ሰዓት ያለውን ችግር ከመከታተል ጀምሮ ቀጣይ የአየር ግፊትን የሚጥር መሳሪያን (CPAP) እስከመጠቀምና እስከ ቀዶ ህክምናም ሊያደርስ ይችላል፡፡ ካርቦንዳይኦክሳይድ ሊዘር የተባለ መሳሪያም በመጠቀም በቶንሲል አካባቢ ጡንቻዎች እንዲሸበሸቡም ማድረግ ሌላኛው መፍትሄ ነው፡፡

7. የላይኛው የመተንፈሻ አካል ችግር

አንዳች ባዕድ ነገር ወይም ውስጣዊ የጤና እክል የላይኛውን የመተንፈሻ አካል አየር እንደልብ እንዳያስተላልፍ ሲያደርግ የሚከሰት ችግር ነው፡፡ ይህ ችግር በቂ የአየር ዝውውር እንዳይኖር ከማድረግ አንፃር ምሽት ላይ የእንቅልፍ ሰዓቶች እንዲረዝሙ ያደርጋል፡፡ በእንቅልፍ ሰዓት የምላስ አቀማመጥና ጉሮሮ አካባቢ ያሉ የመተንፈሻ አካላት አፍን ጨምሮ በአክታ መሰል ሙከስ መሞላትም ችግሩ እንዲከሰት ያደርጋል፡፡ ሰፋ ያለ ፊት፣ ትናንሽ አገጮች፣ ቀጭን አንገት ያለውና ለትራስ ማስተካከያ ተብሎ ብሬስ በሚያደርጉ ላይ ችግሩ የበለጠ ሲከሰት ይታያል፡፡ በጀርባው ሲተኛ የማንኮራፋት ችግር ያለበት ሰውም ይህ የመተንፈሻ ችግር እንዳለበት ሊጠረጥር ይገባል፡፡ በአብዛኛው መፍትሄዎቹ የህክምናዊ መፍትሄዎች ይሆናሉ ማለት ነው፡፡

8. እግርን ያለ እረፍት ማንቀሳቀስ

ከሰዎች ቁጥጥር ውጪ በሆነ መልኩ በእንቅልፍ ውስጥ እግርን ድንገት ማወራጨት ወጥ የሆነ ጥልቅ እንቅልፍን የሚረብሽ ሌላኛው ችግር ነው፡፡ ለችግሩ በዋናነት የስኳር ህመም፣ የደም ስር ችግር፣ የነርቭ ውጫዊ ክፍል መጎዳት፣ የብረት ማዕድን እጥረት (Anemia) የቫይታሚን ቢ እጥረት፣ የእንቅርት ህመም፣ የኩላሊት ህመም እንደዚሁም እንደ አንቲ ዲፕረሰንት፣ አንቲሂስታሚን እና ሊቲየምን የያዙ መድሃኒቶችና የጎንዮሽ ጉዳቶች በዋናነት የሚጠቀሱ ምክንያቶች ናቸው፡፡ እነዚህን ህመሞችና ችግሮች መቅረፍም በእንቅልፍ ሰዓት የሚከሰተውን የእግር እንቅስቃሴ መቀነስ ይቻላል፡፡

9. የእጅና የእግር መወራጨት

ይህም ቅጽበታዊ በሆነና ከቁጥጥር ውጪ በሆነ መልኩ የሚከሰት ነው፡፡ ከላይ ከጠቀስነው ጋር የሚመሳሰል ሲሆን የሚለያየው እጅንም ሆነ እግርንም በእንቅልፍ ሰዓት ሲወራጭ ይህን ድርጊት በፍፁም አለማወቃችንና አለመንቃታችንም ነው፡፡ 90 በመቶ የሚሆኑ በላይኛው ችግር የተጠቁ ሰዎች በዚህም ተጎድተው ይገኛሉ፡፡ ይህ ችግር ግን በእንቅልፍ ውስጥ ያሉ ሰዎች ወጥ የሆነ የተረጋጋ እንቅልፍ እንዳልወሰዳቸው ሲነቁ የሚያወቁት ክስተት ነው፡፡ ከላይ ያነሳነው ህክምናዊ መፍትሄም እዚህም ላይ የሚሰራ ነው፡፡

10. ኢንሶሚንያ

በተለያዩ ምክንያቶች እንቅልፍ በተከታታይ ሲያጡ ወይም ለተከታታይ ጊዜያት ለረዥም ሰዓታት መተኛትን የሚያመለክት ነው ኢንሶሚኒያ፡፡ ለረዥም ሰዓት ለቲቪ/ኮምፒዩተር ስክሪን ብርሃን መጋለጥ፣ ምሽት ላይ ቆይቶ መመገብ፣ አልኮል መጠጥ ማብዛት፣ የመኝታ ክፍል ምቹ አለመሆን፣ የሚረብሹ ድምፆች መኖር፣ የሚያጨናንቁና ድብርት ውስጥ የሚከቱ የስራ ጫናዎችና የጤና ችግሮች ተጠቃሾቹ ምክንያቶች ናቸው፡፡ ለጤና ችግሮች መፍትሄ ከመስጠት ጀምሮ ዘና ያለ አኗኗርን ማዘውተር፣ የመኝታ ክፍሎችን ለእንቅልፍ ምቹ እንዲሆን ማድረግ፣ ንጽህናን መጠበቅ፣ ወደ መኝታዎ ሲሄዱ ላብቶፑን ይዘው አይግቡ ጫና የሚፈጥሩ ነገሮችን ማስወገድ ያስፈልጋልና፡፡

በአጠቃላይ ከላይ ላየናቸው የእንቅልፍ ችግሮቻችን ሁሉ መፍትሄው ከራስ ይጀምራና በራሳችን ላይ እየፈጠሩ ያሉትን ችግር መለየትና ወዲያው መፍትሄ መውሰድ ይገባል፡፡S

በጥላሁን ገሠሠ ሥም እየነገደ ያለው ሰው ምነው ተው ባይ አጣ?

$
0
0

tlahoun_gessesse
ከአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ አፍቃሪዎች አንዱ!

በሰሜን አሜሪካ ነዋሪ የሆነ አንዴ ግለሰብ (የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ ባለቤት ወንድም ነኝ የሚል) በሙዚቃው ንጉስ ስም አንዴ የቴሌቪዥን ጣቢያ መክፈቱን ከሰማሁ ቆየሁ። ለጥልዬ አይደለም አንዴ የቴሌቭዥን ጣቢያ ሌላም ሌላም ይገባዋል። የሚያሳዝነውና የሚያሳፍረው ግን የተከፈተው ቴላቭዥን ጣቢያ የፕሮግራም ጥንጥኑና ቅንብሩ የሙዚቃውን ንጉስ ገድለ-ጥበብ ከመዘከር ይልቅ ዘረኛውን የወያኔ መንግስት ከተቃዋሚ ወገን ጥቃት ለመከላከል ሲተጋ መገኘቱ ነው።

የጥላሁን ገሠሠ ባለቤት የወ/ሮ ሮማን ወንድም ነው የሚባለው ሰው የሚመራው ይህ ቴሌቭዥን ጣቢያ በብርቅዬው አርቲስት ስም ይህን ርካሽ ተግባር ሲፈጽም፤ ተው ባይ ማጣቱ ላሊው በግርምት ያስደመመኝ ጉዳይ ነው።

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ኢትዮጵያዊቷ ወጣት በአትላንታ 25 ዓመት እስር ተፈረደባት

$
0
0

rodas teklu ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ሮዳስ ተክሉ እዚህ አትላንታ ከተማ በዋለው የወንጀል ጉዳዮች ችሎት ቀርባ ጉዳይዋ ሲታይ ከቆየ በኋላ ባለፍው ሰኞ MAY 20/2013 ….. 25 ዓመት እስር ተፈረደባት። ሮዳስ ተክሉ ይህ የተፈረደባት የሰው ነፍስ በማጥፋቷ ወንጀሉንም መፈጸሟን በማመኗ ነው።
የኋላ ታሪኩ እንዲህ ነው። ፌብሩዋሪ 5 ቀን 2009 አመሻሽ ላይ በአትላንታ የተፈጸመው ወንጀል መላው የአትላንታ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን በቅርብ፣ ነገሩን የሰሙና በሌሎች ከተሞች ያሉትን ደግሞ በሩቅ ያስደነገጠ ነበር። 3754 ቢፈርድ ሃይዌይ የሚባለው የአትላንታ መንገድ ላይ የጸጉር መከርከሚያ ሱቅ ከፍቶ በመስራት ላይ የነበረው ኤርሚያስ አወቀ ፣ ማምሻውን ጭምር አምሽቶ እየሰራ ነበር። ከምሽቱ 8 ፒ ኤም አካባቢ ሮዳስ ተክሉ ሱቁ ድረስ መጣች።
የፖሊስ ሪፖርት እንደሚያሳየው ሮዳስ ሱቁ ድረስ ከመጣች በኋላ ጭቅጭቅ ተጀመረ። እሱ እንድትወጣለት ቢጠይቃትም አልወጣችም። ይልቁኑ በእጇ ሽጉጥ ይዛ ስለነበር ፣ ስልኩን አንስቶ 911 ደወለ፣ ስልኩን ላነሳችው ኦፕሬተር “አንዲት ሴት ሱቄ ድረስ መጥታ ልትገለኝ እያስፈራራችኝ ነው፣ መሳሪያ ይዛለች .. እያለ ገና ተናግሮ ሳይጨርስ ስልኩ ተቋረጠ። ከዚያ በኋላ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች የጥይት ድምጽ መስማታቸውን ይናገራሉ።
rodas tekluፖሊስ ካለበት፣ ነገሩን የሰሙም በጸጉር ቤቱ አካባቢ ሲደርሱ ኤርሚያስ በደም ተነክሮ ወድቋል፣ ወዲያው ወደ ሆስፒታል ተወሰደ ፣ ሆስፒታል ሲደርስም ህይወቱ አለፈ። በወቅቱ አንዲት ሴት ከቤቱ ወጥታ ስትሄድ አይተናል ከሚል ጥቆማ ውጪ ማን ገደለው የሚለው ጥያቄ እንቆቅልሽ ሆነ።
በማግስቱ ፌብሩዋሪ 6 ግን ፖሊስ ሮዳስ ተክሉ የተባለችና የቀድሞ ፍቅረኛው ነች የተባለች ሴት በጥርጣሬ መያዙን አስታወቀ። እሷም ወደ እስር ቤት ተወሰደች። ኤርሚያስም የፖሊስ ምርመራ ከታወቀና ዶክተሮች የሞቱን መንስኤ ካስታወቁ በኋላ ፌብሩዋሪ 11 ቀን በርካታ የአትላንታ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በጸጉር ቤቱ ደጃፍ የሻማ ማብራት ሰነ ስር ዓት ተካሄደ፣ በማግስቱ ፌብሩዋሪ 12 ጸሎተ ፍትሃት ከተደረገለት በኋላ አገር ቤት ተወስዶ እንዲቀበር በተያዘለት ፕሮግራም ይሄዳል ሲባል ፣ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ ያስፈልገኛል በማለቱ እስከ ፌብሩዋሪ 24 ሳይላክ ቆየ። ፌብሩዋሪ 24 ቀን ግን አስክሬኑ ወደ አገር ቤት ለቀብር ተላከ።
ከዚያ በኋላ ዜናው በአድማስ ሬዲዮም ሆነ አትላንታ ባለው ድንቅ መጽሔት ከወጣ በኋላ በወቅቱ የወጣት ሮዳስ ተክሉ ቤተሰቦች “እሷ በግድያው የለችበትም፣ ይህንን ድርጊት እሷ ትፈጽማለች ብሎ ማሰብ ትክክል አይደለም” ሲሉ ተናግረው ነበር። ሆነም ቀረ ላለፉት አራት ዓመታት ነገሩ ከፍርድ ቤት እስር ቤት ፣ ከ እስር ቤት ፍርድ ቤት ሲንከባለል ቆየ፣ የ ኤርሚያስ አወቀ የቅርብ ቤተሰብ የሆኑት አቶ ላቀው ለአድማስ ሬዲዮ እንደገለጹት በመካከል ተጠርጣሪዋ ልጅ፣ በጠበቆቿ አማካኝነት “አእምሮዋ ትክክል አይደለምና ለፍርድ ልትቀርብ አይገባም” ብለው ሲከራከሩ የቆዩ ሲሆን፣ ዳኞቹም የ አ ዕምሮዋ ነገር በሃኪሞች እንዲታይ ፈቅደው ቆይተዋል። በኋላ ግን ችሎት መቆም እንደምትችል በመታመኑ ፣ ጉዳዩ በከሳሽ አቃቤ ህግ እና በተከሳሽ ሮዳስ ተክሉ ጠበቆች መካከል ክርክሩ ቀጥሎ አራት ዓመት ከፈጀ። እንደ አቶ ላቀው ገለጻ ፣ በመጨረሻ ላይ ሮዳስ ወንጀሉን መፈጸሟን እንድታምን ተጠይቃ “አዎ ፈጽሜያለሁ፣ ነገር ግን በደም ፍላትና ሳላስበው ያደረኩት ነው” ስትል በማመኗ ዳኛዋ 25 ዓመት ጽኑ እስራት ፈርደውባታል። ምናልባት ጥፋቷን ባታምን እና ነገሩ በክርክሩ ብትሸነፍ የሞት ፍርድ ሊጠብቃት ይችልም ነበር ብለዋል።
ዳኛዋ በፍርድ ውሳኔያቸው እንደገለጹት “ ኤርሚያስ ገበየሁን በ 10 ጥይት መግደል ሳይታሰብ፣ ባጋጣሚ የተደረገ አይደለም” ሲሉ ውሳኔያቸውን አጽንተዋል።
በተያያዘ ሁኔታ ሮዳስ ተክሉ እዚያው እስር ቤት እያለች አንዲት ሴት ልጅ መውለዷም ታውቋል። የወለደችው ግሬዲ ሆስፒታል በፖሊስ ታጅባ ሄዳ ሲሆን፣ ባሁኑ ሰአት ህጻኗን አንዲት ነርስ እዚያው ግሬዲ እያሳደገቻት መሆኑ ሲታወቅ፣ የህጻኗን አባት በተመለከተ ዳኛዋ “የቀረበልኝ የዲ ኤን ኤ ምርመራ ስለሌለ፣ በልጅቷ አባት ጉዳይ የምሰጠው አስተያየት የለም” ሲሉ መናገራቸውም ታውቋል። (ምንጭ አድማስ ሬዲዮ አትላንታ)

ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር የአመራሩን ህገወጥ እስር አወገዘ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር “በአምባገነኖች የሀሰት ውንጀላ እስርና እንገግልት አንንበረከክም” በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ የማህበሩ ን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በመንግስት የደህንነት ሀይሎች በህገወጥ መንገድ መታሰርና እንዳይጎበኝ ክልከል መደረጉን በጥብቅ አወገዘ።
ለሥር ዓቱ ራስ ምታት እየሆነበት መጥቷል እየተባለ የሚነገርለት ባለራ ዕይ ወጣቶች ማህበር የታሰረው የሕዝብ ግንኙነት ሃላዲ በሕግ አማሪካዎች እንዳይጎበኝ መከልከሉና በቀጣይ የማህበሩ አመራሮች ላይ ሊወሰድ የታሰበው እርምጃ የስርዓቱን አፋኝነት የሚያረጋግጥ ነው ብሏል።
“ዜጎችን በ እስርና በድብደባ ማንበርከክ እንደማይቻል ለማረጋገጥ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ተቋማትና የፖለቲካ ፓርቲዎችን በማስተባበር ወደ ሰፊ ህዝባዊ ንቅናቄ በመግባት አምባገነናዊና አፋኝ የሆነውን ይህን ስራዓት በጽናት እንደምንታገል እንገልጻለን” ያለው ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር በቅርቡም ዝርዝር የተቃውሞ ፕሮግራሙን ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል።
መግለጫውን ለማንበብ ፎቶው ላይ ይጫኑ
bele Rayu

ትግሉ ጥራት እንዲኖረው -በቶኩማ አሸናፊ

$
0
0

በቶኩማ አሸናፊ

አቅጣጫንና ግብን አለማወቅ ልዩነትን፡ መከፋፈልን ፡

አለመተማመንንይፈጥራል:: እርስዎስ የትነው ያሉት ?

Penእንደ አንድ  ዜጋ  በሃገራችን ጉዳይ ላይ በሚነሱ ማንኛውም ጥያቄዎች ላይ ነገሮችን በችላ ባይነት ለማለፍ ብዙ ጊዜ አልሞክርም ። ያም በመሆኑ ያቅሜን ያህል  የማበረክተው ድርሻ ካለ ቀዳዳዋን ለመጠቀም እሞክራለሁ። በተለይ በአሁኑ ጊዜ በሃገራችን ጉዳይ ላይ በርካታ “ምሁራን” በየቀኑ የመያወጡአቸውን የተለያዩ ጽሁፎች አነብና ፡ በየቀኑ የሃገሬ ልጆች በየፓልቶኮቹ የሚያደርጉትን ውይይት ክርክር ስድብ እሰማና ማታ ጋደም ብዬ ሳብሰለስለው አንዱም ነገር ውስጤ ሳይቀር ሲሰማኝ በመብሰልሰል ብቻ እኖራለሁ።

ዛሬ በሃገራችን ያለውን ችግር የምንገዘብበት የግንዛበቤ መነጽራችን  እጅግ የተለያየ ከመሆኑም በላይ ለመፍትሄውም ዝብርቅርነት ዋነኛውን አስተዋጽኦ አድርጎኦል ብዬ ስለምገምት እነሆ ወገኞቼ በተለይም በሃገራችን ጉዳይ ላይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ ቀጥዬ በማቀርበው መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ በሚኖረን አቅዋም ልዩነቶቻችን ሊጠቡ ወይም ሊሰፉ ልንግባባ ወይም ላንግባባ በጋራ ለሃገር እንድንቆም ወይም ያለመፍትሄ ስንረጋገም እድሜያችንን እንድንፈጅ እንገደዳለን ብዬ አምናለሁ።

በወያኔ/ ኢህአዴግ ላይ በሚኖር አመለካከት ላይ ያለ ልዩነት/ተቃዋሚዎች

የአመለካከት አንድ ስብስቦች

ወያኔ/ኢሃዴግ ፋሸስታዊ መንግስት ነው

ወያኔ/ኢሃዴግ ኢትዮጰያን በኮሎኒ የያዘ መንግስት ነው

ወያኔ አፓርታይድ መንግስት ነው

ወያኔ የሽፍቶች ቡድን እንጂ መንግስት አይደለም

ወያኔ ጸረ ኢትዮጵያ የሆነ መንግስት ነው አላማውም ኢትዮጵያን ማፈራረስ ነው።

በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የአንድ ዘር የትግሬን በላይነት የሚጠብቅ መንግስት ነው

ወያኔ ሁሉም ነው

*የአመለካከት ሁለትንም ያጠቃልላል

ከላይ ለሚጠቀሱት የወያኔ/ኢሃዴግ መገለጫዎች  የሚቀርቡት መፍትሄዎች

ኢትዮጵያውያን ድርጂቶች እንደግንቦት 7 አርበኞች ግንባር  ተደራጅተው ታጥቀው ጦር መስርተው በሃገር ውስጥ ቤዝ ፈጥረው ትጥቅ ትግል መጀመር አለባቸው።

ስር ነቀል ለውጥ እንጅ ጥገናዊ ለውጥ አያስፈልግም

ኢትዮጰያዊ አጅንዳ ባይኖራውቸም ወያኔን እስካስወገዱ ድረስ ከሌሎች ሃይሎች ጋር ለምሳሌ እንደኦነግ እንደኦብነግ ከዚያም ከሻቢያም ጋር ህብረት ፈጥሮ ትጥቅ ትግል መካሄድ አለበት

ሁለገብ ትግል መጠናከር አለበት። ሰላማዊ ትግሉ በሃገር ቤት ትጥቅ ትግሉ ከውጭ መፋፋም አለበት።

ሰላማዊ ትግሉ ከግንቦት ምርጫ አሁንም ከ2002 ምርጫ ስላበቃለት ትጥቅ ትግሉ ብቻ ነው መፍትሄ የሚሆነው።

ትጥቅ ትግሉ በሃገር ቤት የራሱን የህቡእ ማደራጀት ስራ ሰርቶ ህዝባዊ አመጽ ማስነሳት አለበት።

ወያኔ በማንኛውም አይነት የትጥቅ ትግል ከተሸነፈ በሁዋላ የሽግግር መንግስት ተመስርቶ የኢትዮጵያን የወደፊት እጣ ይነጋገርበታል።- ሰላማዊ ትግሉ እያስመዝገበ ያለው ውጤት ወያኔን ከስልጣን የሚያወርድ ብቃት ያለው አይደለም። – በሰላማዊ ትግሉ መጉዋዝ ወያኔን እድሜውን ማራዘም ነው ። እንዲዬወም አንዳንዶቹ  በብሄረ ሰብ የተደራጁ ድርጅቶች እራሳቸው የወያኔ ተቀጥላዎች ስለሆኑ ሰላማዊ ትግሉ እነሱንም ማቀፉ ትግሉን ይጎዳዋል።

* በአመለካከት አንድ በአካሄድ ልዩነቶች አሉ። ከዚህ ውሰጥ ዋነኛው  ለምሳሌ በኢህአፓና  ግንቦት ሰባት መካከል ወያኔን ለማስወገድ የትግል አጋሮችን ወይም ህብረትን  በሚመለከት

የአመለካከት ሁለት ስብስቦች

ወያኔ/ኢሃዴግ በብሄረ ሰብ መብት ስም ህዝብን በጎሳና በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ክልል ከፋፍሎአል። ስለዚህም ዘረኝነትን አስፋፍቶአል

ወያኔ ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፎ የሰጠና እየሰጠም ያለ መንግስት ነው ለምሳሌ የአሰብ ጉዳይ የሱዳን ዳር ድንበር ጉዳይ ላይ በወሰዳቸው እርምጃዎች ይገለጻል።

መንግስቱ ኢሃዴግ ይባል  እንጂ የጥቂት አምባገነኖች ቡድን መንግስት ነው

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ያዳከመ መንግስት ነው

ዲሞክራሲን ፍትህን የመናገር የመጻፍ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን የግለሰብ ነዻነትን እያፈነ ያለ አምባገነን መንግስት ነው

ኢሃዴግ ዋናው ችግሩ እርሱ ያረቀቀውንና ህዝብ ያጸደቀውን ህገ መንግስት የጣሰ የሚጥስ አምባገነን መንግስት በመሆኑ ህገ መንግስቱ ከተከበረ ሊለወጥ የሚችል መንግስት ነው

 

 ለተጠቀሱት መገለጫዎች የሚቀርቡ መፍትሄዎች

- በወያኔ የተለያዩ ጥፋቶች  ቢኖሩም ጥፋቶቹን ለማስተካከል በህዝብ ውሳኔ ላይ የቆመ መንግስት ያስፈልጋል ።ስለዚህ ይህንን መንግስት ለማምጣት የሚያስችሉ የሰላማዊ ትግል ስልቶች ሁሉ መፈተሽ አለባቸው።

- ወያኔ ኢሃዴግ እነዚህ ባህርያት ቢኖሩትም ለሰላማዊ ትግል በሩን ፈጽሞ ያልዘጋ መንግስት በመሆኑ ትጥቅ   ሊመዘዝበት አይገባም ። ወያኔ ኢሃዴግን የማስወገድ ሳይሆን የማሳተፍ ፖለቲካ እንደድርጅት ህልውናው ሊኖር ይገባል ኢሃዴግን የሚያጠፋ ፖለቲካ ሳይሆን በምርጫ የሚያስወግድ ፖለቲካ መሆን አለበት

- በሃገር ውሰጥ ሰላማዊ ትግል የማይታገዝ የትጥቅ ትግል ሕዘባዊ መሰረት የሌለውና ኢትዮፕያንም የበለጠ አደጋ ውስጥ የሚከት አካሄድ ነው።

_ የፈጀውን ጊዜ ቢፈጅም  ከእንግዲህ የኢትዮጵያ ህዝብ በጠመንጃ ስልጣን መያዝን ማስወገድ አለበት ። በጠመንጃ  የሚመጣ ስልጣን በህዝብ ንብረትና ህይወት ላይ ከሚያስከትለው ውድመት ባሻገር ዘለቄታ ለውጥ አያመጣም።

አመጽ አይመረጥም ። ይሁን እንጂ  ህዝባዊ አመጽ ሊነሳ ይችላል ። ለዚህ ተጠያቂው ወያኔ ኢሃዴግ ነው የሚሆነው

ሰላማዊ ትግሉ የሚያስፈልገው ወያኔ ኢሃደግንም ጭምር የሚያሳትፍ የፖለቲካ ስርአት ለመዘርጋት መሆን አለበት

ብሄራዊ መግባባትን መሰረት ያደረገ ብሄራዊ እርቅ ሊፈጠር ይገባል

ዋና ዋና  ጥያቄዎች በህዝበ ውሳኔ መፈታት አለባቸው።ስለዚህም ተጠናክሮ ለመውጣት በሰላማዊ ትግል የሚጉዋዙ  ድርጅቶች ተባብረው መውጣት አለባቸው።

ኢሃዴግ የመለሳቸው አንዳንድ ጥያቄዎች ለምሳሌ የብሄረሰብ ጥያቄዎች በዘረኝነት ሽፋን መታለፍ የሌለበትና አግባብ ያለው መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል።

*በአመለካከት ሁለት ባካሄድ ልዩነቶች አሉ፡ ለምሳሌ በመድረክ በመኢአድና በኢዴፓ ህብረብሄራዊነትና በብሄር መደራጀትን አስመልክቶ

 

የአመለካካት ሶስት ስብስቦች/ የወያኔ ኢሃዴግ ደጋፊዎች

ኢህአዴግ ካለፉት መንግስታት የሚሻል መንግስት ነው

ኢህአዴግ የኢትዮጰያን መሰረታዊ ችግር የብሄረሰብ እኩልነትን ያረጋገጠና ዲሞክራሲን ያሰፈነ ወይም መሰረት የጣለ ድርጅት ነው።

ኢህአዴግ ወያኔ ሳይሆን እንደስሙ ኢህአዴግ የሆነ  መንግስት ነው

ኢህአዴግ አንድም የሃገርን ጥቅም አሳልፎ የሰጠበት ሁኔታ የለም።

ኢሃዴግ ልማታዊ መንግስት ነው።

በኢህአዴግ አመራር ዲሞክራሲያዊ መብቶች ተከብረዋል። ጥቃቅን ቺግሮች ግን አሉ

በሃገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ጎረቤት አገሮች ጋር ሰላምን አስፍኖአል።

 

ለተጠቀሱት  ባህርያቱ የሚሰጡ መፍትሄዎች

-ኢህአዴግ ካለፉት መንግስታት የሚሻልና ብዙ ለውጥም ያመጣ መንግስት ስለሆነ የምንታገለው መንግስት       ሳይሆን የምንንከባከበው መንግስት ሊሆን ይገባል። ስህተቶቹን እንዲያርም ማድረግ ነው ከተቃዋሚ የሚፈለገው።

- ተቃዋሚው መቃወም ብቻ እንጂ በሀገራዊ ጉዳዮች ጭምር ተሳትፎ  የለውም/

-ተቃዋሚ የተሻለ ራእይ ይዞ አልቀረበም። የረባ ተቃዋሚም የለም።

-ተቃዋሚው የድሮ መንግስታት ርዝራዦች እንጂ ስርአቱ የፈጠረው ብሶት የወለደው አይደለም። ስለዚህ የዲሞክራሲ ገደቡም ሆነ ተጽእኖው የተደረገው በአጥፊው ላይ ነው። ይህም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።

- የረባ ተቃዋሚ እስከሌለ ኢህአዴግ 40ም 50 አመትም ሊገዛ ይችላል።

ኢህአዴግ/ህወሃት መስዋትነትን ከፍሎ የመጣ ሃይል በመሆኑ ሌላውም ኢህአዴግን ለማስወገድ መስዋእትነት መክፈል አለበት ። ጫካ መግባት አለበት

ኢህአዴግን መቃወም ያለፈ ስርአትን መናፈቅ ነው።

እንግዲህ እነዚህ ከላይ የጠቀስኩዋቸው ሃሳቦች በሀገራችን ፖለቲካ ዙሪያ የሚያጠነጥኑና  በተቃዋሚውም በኩል ሆነ በኢሃዴግና ደጋፊዎቹ  የትግሉን አቅጣጫ የሚያመላክቱ አንዳንዶቹ በውስጣዊ ይዘታቸው የሚመሳሰሉና የጋራ ባህርይ ያላቸው አንዳንዶቹ ደግሞ ፈፅሞ የማይቀራረቡና አንዱ አንዱን ካላስወገደ ሊመለሱ የማይችሉ ተቃራኒ አመለካከቶች መሆናቸውን ማየት ቀላል ጉዳይ አይደለም።

ለጊዜው ሶስተኛውን አመለካከት እናቆየውና በተለይም በተቃዋሚው ክፍል ባሉ ሃይሎች ነጋ ጠባ የሚጮህለት  የህብረት  ጥያቄ በነዚህ የአመለካከት ልዩነቶች ላይ የጠራ አቁዋም እስከሌለ ድረስና በልዩነቶቹ ላይ የመስጠትና የመቀበል ፖለቲካ እስካልታከለበት ምንም አይነት የተጠናከረ ትግል ለማካሄድ እንደማይቻል ያለፉት አመታት ልምዶች ያስገነዝቡናል።

በተለይም ወያኔ /ኢሃዴግ በየጊዜው በሚወስዳቸው አስከፊ እርምጃዎች የአመለካከት መሸጋሸግ ሊኖር እንደሚችል ቢታመንም አሁን ባለንበት ሁኔታ እነዚህን አመለካክቶች ሊቀይሩ የሚችሉ መሰረታዊ ጉዳዮች አይታዩም

-አንዳንዶቹ አመለካከቶች ኢሃዴግ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ የተነሱ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ በሂደት የተፈጠሩ መሆናቸው ለምሳሌ የማስወገድ ፖለቲካ ገኖ የወጣው ከምርጫ 97 በሁዋላ መሆኑ ከምርጫው በፊት የነበረውን አመለካከት የቀየሩ ባህርያትና የሃይል አሰላለፍን ያደበላለቁትን ምክንያቶች ለይቶ ማውጣት ያስከተለው ችግር።

- ስለ አንድ መንግስት ባሀርይና ማንነት ገላጭ የሚሆኑ ጉዳዮች በተወሰነ የፖለቲካ ሂደት ውሰጥ በሚፈጠር የአንድ ወቀት ክስተት ላይ በመመርኮዝ ይሁን ወይም ስልጣን ላይ ከወጣ በሁዋላ በየጊዜው በሚወስዳቸው  የተሳሳቱ የፖለቲካ ውሳኔዎች ላይ መሆኑን በቂ ግንዛቤ የማግኘት ችግር

-ኢሃዴግ እንደ ማንኛውም መንግስት ለህልውናው ብሎም ቢሆን የሚተገብራቸው በጎ ተግባራትን የመቀበልና በጎ ባልሆኑት ላይ ህብረተሰቡን የማንቀሳቀስ ልምድ ያለመዳበር ችግርና ሌሎችም ብዙ ምክንያቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ።

እርስዎስ የትኛው አመለካከት ለሃገራችን ይበጃል ይላሉ?

ክጭፍን  ደጋፊነት ወይም ነቃፊነት ለመውጣት ከቻልን አንድ እርምጃ ወደፊት እንራመዳለን።

 

 

 

ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ በሚጠራው ሰልፍ ላይ 100ሺህ ሰው ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል

$
0
0
semayawi partyበመስከረም አያሌው
የፊታችን ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም በሚካሄደው እና ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለፁት፤ ፓርቲው ባለፈው ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያራዝም መንግስት በጠየቀው መሰረት የፊታችን እሁድ ያካሂዳል። መንግስት በፀጥታ እና ሰላም ማስከበር ሂደት ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሲያጋጥመው ሰልፉን ለሌላ ጊዜ እንዲዛወር መጠየቅ ይችላል የሚል ህግ በመኖሩ ሰልፉ ከአንድ ሳምንት በኋላ እንዲደረግ መወሰኑን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
ሰላማዊ ሰልፉን በአፍሪካ ህብረት በዓል ወቅት ማካሄድ የተፈለገው ኢትዮጵያ በአሉን ስለምታዘጋጅ እና መንግስት ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራው ስራ በመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብና ሚዲያው እንዲሁም አለም አቀፍ ሚዲያዎች ስለሚሰሙት ጥያቄው ከፍ ብሎ ይሰማል ከሚል አስተሳሰብ መሆኑን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ፤ የሰላማዊ ሰልፉ ቀን መራዘም ምንም የተለየ ነገር እንደማይፈጥር ገልፀዋል። “የችግሩ ባለቤትም ሆነ መፍትሔ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። የሚጨቁነንም መንግስት እዚህ ነው ያለው” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ ሰልፉ በታሰበለት ቀን ቢካሄድ ጥሩ እንደነበር ገልፀው ቀኑ መቀየሩም ያን ያህል ለውጥ እንደሌለው ተናግረዋል።
የሰላማዊ ሰልፉ በመራዘሙ በፊት ይሳተፋል ተብሎ ከታሰበው በላይ ሰው ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ሰላማዊ ሰልፉን በህጉ መሰረት ማስፈቀዱ እና ህዝቡም ጊዜ ወስዶ እንዲወያይበት በመደረጉ ከ100ሺ በላይ ሰዎች በሰልፉ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። በሰልፉ የሚነሱት አራት ጥያቄዎች በመሆናቸው ህዝቡ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እና የተነሱ ጥያቄዎችን የተመለከተ ብቻ እንዲሆንም ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል። በሰላማዊ ሰልፉ ወቅትም የታሰሩ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች እንዲለቀቁ፣ የእስልምናን እምነት ነፃነት በመጠየቃቸው የታሰሩት የሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ፣ የተፈናቀሉ ሰዎች ወደሚኖሩበት አካባቢ በሰላም ተመልሰው ካሳ እና ድጎማ ተደርጎላቸው ህይወታቸውን እንዲቀጥሉ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ እና በስራ አጥነት እና በሙስና ላይ መንግስት አፋጣኝ መፍትሔ እንዲፈልግ የሚሉ ጥያቄዎችን አንግበው ሰላማዊ ሰልፉን እንደሚያካሂዱም ተገልጿል።
ከጠዋቱ 4 ሰዓት ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፉ መነሻውን ግንፍሌ አካባቢ ከሚገኘው የፓርቲው ጽ/ቤት በማድረግ በአራት ኪሎ፣ ፒያሳ እና ቸርቸል ጎዳና አልፎ እስከ ድላችን አደባባይ ወይም ኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት አደባባይ የሚደረግ ሲሆን፤ በእለቱም አጠቃላይ የሀገሪቱን ሁኔታ የሚገልፁ ንግግሮች እና መፈክሮች ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።¾
(ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ የረቡዕ ሜይ 29 ዕትም)

ከሙስና ተጠርጣሪዎች እሥር በኋላ የጥቆማ ቁጥር በእጥፍ ጨመረ፤ ሕጉ ይሻሻላል ተባለ

$
0
0
አቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ

አቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ

ከሙስና ተጠርጣሪዎች እሥር በኋላ የጥቆማ  ቁጥር በእጥፍ ጨመረ

በጋዜጣው ሪፖርተር
የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች ተጠርጣሪ ግለሰቦች በሙስና ወንጀል ጠርጥሮ ከያዘ በኋላ ለኮሚሽኑ የሚደርሰው የሙስና ጥቆማ ቁጥር መጨመሩ ታወቀ።
ኮሚሽኑ በድረገፁ ይፋ እንዳደረገው በተለይ ከግንቦት 2 ቀን 2005 ዓ.ም በኋላ ባሉት አስር ቀናት ብቻ ከዚህ ቀደም ከነበረው ጋር ሲነፃፀር የጥቆማ ቁጥር በእጥፍ በልጦ መመዝገቡን ገልጿል።
ኀብረተሰቡ ሙስና አስከፊ ድርጊት መሆኑን ተገንዝቦ ለማጋለጥና ሙስናን ለመዋጋት እያሳየ ላለው ጥረት ኮሚሽኑ ምሥጋና አቅርቧል። ሆኖም ምን ያህል ጥቆማ እንደቀረበለት በቁጥር ከመግለፅ ተቆጥቧል።
የፌዴራሉ የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በ2005 በጀት ዓመት አስር ወራት የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትን ጨምሮ 3001 ጥቆማዎችና አቤቱታዎችን መቀበሉን ከነዚህ ውስጥ በኮሚሽኑ የሥልጣን ክልል ሥር የሚወድቁት 1ሺ 335 ወይም 44 በመቶ ያህሉ ሲሆን የተቀሩት 56 በመቶ ከሥልጣኑ ክልል ውጪ መሆናቸውን ኮሚሽነር ዓሊ ሱሌይማን ከሳምንት በፊት ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መግለፃቸው ይታወሳል።n
በሌላ ዜና
የፀረ-ሙስና ሕግ ሊሻሻል ነው
·        የአክሲዮን ማኅበራት፣ ባንኮች፣ ኢንሹራንሶችና የልማት ማኅበራት
በአዲሱ የሙስና ሕግ ይካተታሉ
በዘሪሁን ሙሉጌታ
321589_109993089111063_1484315227_aየፌዴራል የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሕግ በወንጀል ሕጉ የተደነገጉ የሙስና ወንጀሎች እንደገና የሚደነግግ አዋጅ በማዘጋጀት አሁን እያስቀጣበት ያለውን ሕጋዊ ወሰን በማስፋት አዋጁን ሊያሻሽል ነው።
አዲስ እየተዘጋጀ ባለው ረቂቅ ሕግ በዋናነት የግል ዘርፍ አካላትን በሙስና ወንጀል ተጠያቂ የሚያደርግ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። በተለይም በመቶ ሚሊዮኖች ገንዘብ የሚገመት ሀብት እያንቀሳቀሱ ያሉ፣ የሕዝብ ሀብት የሚያስተዳድሩ የግል ዘርፍ አካላት ላይ ረቂቅ ሕጉ አተኩሯል። እነዚህ አካላት በማንኛውም አግባብ ከአባላቶቻቸው ወይም ከሕዝብ የተሰበሰበ ወይም ለሕዝባዊ አገልግሎት እንዲውል የተሰበሰበ ገንዘብ፤ ንብረት ወይም ሌላ ሀብትን የሚያስተዳድሩ ወይም የሚያንቀሳቅሱ አክሲዮን ማኅበራት በማኑፋክቸሪንግ፣ በእርሻ፣ በንግድ፣ በኮንስትራክሽን፣ በትራንስፖርት፣ በፋይናንስ እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት መካከል በአክሲዮን የተቋቋሙ ባንኮች፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሐዋላ ተቋማት የሙያና የብዙሃን ማኅበራት ፌዴሬሽኖችና ኮንፌዴሬሽኖች፣ የኅብረት ሥራ ማኅበራትና ዩኒየኖች፣ ኢንዶውመንቶችና የልማት ማኅበራት (ለምሳሌ አልማ፣ ኦልማ፣ ወዘተን) ያካትታል።
ሕጉን እንደገና ለማሻሻል ያስፈለገው ሙስናን የሚፀየፍ ኅብረተሰብ እንዲፈጠር የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር፣ በዓለም አቀፍ ደረጃም፤ በግል ዘርፍ የሚፈፀም ጉቦኝነትና ምዝበራ በሙስና ወንጀል የሚያስቀጣ በመሆኑ ሲሆን፤ አዲሱ ረቂቅ ሕግም ከሲንጋፖር፣ ከስዊዲንና ከደቡብ አፍሪካ ተመሳሳይ ሕጎች በመቀመር መዘጋጀቱም ታውቋል።
በአዲሱ ሕግ መሠረት ለሕዝብ ተብሎ የተሰበሰበ ሀብት የሚያንቀሳቅሱ እና የሚያስተዳድሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ የፖለቲካ ድርጅቶችና የዓለም አቀፍ ድርጅቶችን በሙስና ወንጀል እንዲጠየቁ ማድረጉ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ስለሚያመዝን በሕጉ ያልተካተቱ ሲሆን፤ ሌሎች የሕዝብን ገንዘብና ሀብት የሚያስተዳድሩ ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት፣ እድር እና ተመሳሳይ ባህላዊ ወይም ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው ማኅበራት አባላቱ እርስ በርስ የሚተማመኑና ለሙስና የመጋለጥ ዕድላቸው ዝቅተኛ በመሆኑ፣ በሙስናውም ቀጥተኛ ተጠቂ የሚሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጥቂቶች በመሆናቸውና ከሚያንቀሳቅሱት ሀብት አነስተኛነት የተነሳ በሙስና ተጠያቂ በማድረግ ከሚድነው ሀብት ይልቅ ተጠያቂ ለማድረግ የሚባክነው ሀብት ከፍተኛ በመሆኑ ከሕጉ ውጪ ተደርገዋል።
በአዲሱ የሙስና ወንጀል ረቂቅ ሕግ በግለሰብ ባለሀብት ወይም ባለሀብቶች የተቋቋመ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በሙስና ወንጀል አይጠየቅም።¾
በሌላ የሙስና ዜና
በእነ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ መዝገብ ስር የተዘረዘሩት 12 ተጠርጣሪዎች ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው
-    በእነ መላኩ ፈንታ መዝገብ ያሉ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ ዛሬ ይታያል
-    አቶ ነጋ ገ/እግዚአብሔር ድብደባ ተፈፅሞብኛል አሉ
በአሸናፊ ደምሴ
Addis Gudayየፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የምርመራ ቡድን ተጨማሪ ጊዜ በተጠየቀባቸው በእነ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ መዝገብ ስር የሚገኙ አስራሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ የ14 ቀኑ ጊዜ ቀጠሮ ሲፀናባቸው፤ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ በሦስት የተለያዩ መዝገቦች የተዘረዘሩትን 22 ተጠርጣሪዎች ጉዳይ ለመመርመር ደግሞ ዛሬን ጨምሮ ሐሙስና አርብ ተለዋጭ ቀጠሮዎችን ሰጥቷል።
ችሎቱ በዕለቱ ሲሰየም ኮሚሽኑ የደረሰበትን የምርመራ ውጤት ለመስማት እንደሆነ ፍርድ ቤቱ አስታውሶ፤ ለፌዴራሉ ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የምርመራ ቡድን ተወካዮች ሀሳባቸውን እንዲያስረዱ ዕድል በመስጠት ጀምሯል። በችሎቱ የተገኙት የመርማሪ ቡድኑ ተወካይም ቡድኑ ያሳካቸውንና ያላሳካቸውን የምርመራ ውጤቶች በሁለት ከፍለው ለፍርድ ቤቱ አሰምተዋል። በዚህም በዘጠኝ ተጠርጣሪዎች መኖሪያ ቤት በመድረስ የኤሌክትሮኒስ መሳሪያዎችን፣ የተደበቁ ሰነዶችንና በህገወጥ መንገድ የተገኙ ገንዘቦችን (መኒ ላውንደሪ) መሰብሰቡን ጭምር ገልጿል። አክሎም የ28 ተጠርጣሪዎች ክስ መቋረጡን የሚያስረዱ ሰነዶችን፣ ስምንት በቫት ማጭበርበር ተጀምረው የተቋረጡ ክሶችን፣ ኦዲት ያልተደረጉ ሰነዶችን እና የ15 ምስክሮችን ቃል ስለመቀበሉ ካጠናቀቃቸው ውጤቶች አንኳሮቹ ናቸው ሲል አስረድቷል።
በአንፃሩ ደግሞ የኮሚሽኑ የምርመራ ቡድን አላጠናቀኳቸውምና ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ጥያቄ ያቀረበባቸው ጉዳዮች መካከል፤ ተጨማሪ የሙስና ወንጀሎች የታገዱባቸው ሰነዶች፣ የታገዱ ንብረቶችን ማጣራት፣ ከአራጣ ብድር ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ማጥራት፣ የምርመራ ስራው ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ቦታዎች የሚካሄድም ጭምር መሆኑን እና በምርመራ ቡድኑ አማካኝነት የተገኙ ሰነዶችን መርምሮ ከክስ መዝገቡ ጋር እንዲያያዙ ለማድረግ ይረዳ ዘንድ ተጨማሪ 14 ቀናትን ፍርድ ቤቱ እንዲፈቅድ ጠይቀዋል።
ሰኞ ከሰዓት በኋላ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት በቀዳሚነት ጉዳያቸው በችሎቱ መሰማት የጀመረው በሁለተኛ የክስ መዝገብ ስር የተዘረዘሩት 12 ተጠርጣሪዎች ሲሆን፤ በዚህም ስር የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ ጨምሮ ሌሎችም ባለስልጣናት እና ነጋዴዎች በሙስና ወንጀሉ ተሳታፊ ሆነዋል የተባሉ ቤተሰቦች በችሎት ቀርበው በጠበቆቻቸው በኩል ጉዳያቸውን አስረድተዋል።
አብዛኞቹ ተጠርጣሪዎች በጠበቆቻቸው በኩል ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት ጥያቄና አቤቱታ መሠረት፣ መርማሪ ቡድኑ በቂ ማስረጃዎችን ሰብስቤያለሁ ያለ መሆኑን በመጥቀስ፤ አንዳንድ ተጠርጣሪዎችም አሁን ድረስ የተጠረጠሩበትን ወንጀል ክስ አለማወቃቸውን እና በጤናና በቤተሰብ ጉዳይ ላይ ተንተርሶ የዋስትና መብታቸው እንዲከብር ጥያቄ አቅርበዋል።
የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ በጠበቃቸው አማካኝነት የምርመራ ቡድኑ አገኘሁት ያለው መረጃ በቂ ሆኖ ሳለ ሁለት ህፃናት ልጆቼ በችግር ላይ ስለሚገኙ የዋስ መብቴ ተጠብቆ ከእስር ልለቀቅ ይገባል የሚል ሀሳብ አቅርበዋል።
አቶ ገብረዋህድ አክለውም፤ ሁለት ህፃናት ልጆቼ የሚንከባከባቸው በሌለበት መልኩ እንዲኖሩ ተገደዋል። ባለቤቴም ሆነች እህቷ የተመሠረተባቸው ክስ ሰነድ መደበቅ ቢሆንም ተደብቋል የተባለው ሰነድ ግን ቀድሞም በኮሚሽኑ እጅ የገባ መሆኑን በማስታወስ፤ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች በዚህ ክስ ስር መጠቃለላቸው አግባብ አይደለም ብለዋል። ይህም በመሆኑ ፍ/ቤቱ ሁለቱን የቤተሰብ አባላት በዋስ መብታቸው ተጠቅሞ እንዲያሰናብታቸው ጠይቀዋል።
በሌላም በኩል በተለይም በሁለተኛው የክስ መዝገብ ስር 5ኛ ተከሳሽ ሆነው የቀረቡት የነፃ ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ነጋ ገ/እግዚአብሔር በምርመራ ወቅት ከፍተኛ ድበደባ እንደተፈፀመባቸውና ለሁለት ጊዜያት ያክል ራሳቸውን ስተው እንደነበር በማስታወስ፤ “በእስር ቆይታዬ አገሬ ምን እንደምትመስል አውቄያለሁ” ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። አቶ ነጋ ገ/እግዚአብሔር የልብ፣ የደምና የስኳር ህመምተኛ መሆናቸውን ጭምር በማስረዳት የዋስትና መብት ጠይቀዋል። በዚሁ መዝገብ 3ኛ ተጠርጣሪ ሆነው የቀረቡት አቶ ጥሩነህ ባልቻ በበኩላቸው ሕገመንግስቱንና ሰብዓዊ መብትን በሚቃረን መልኩ በዱላ የታገዘ ምርመራ ተፈፅሞብኛል ሲሉ ቅሬታቸውን ለፍርድ ቤቱ አሰምተዋል።
በመዝገቡ ስር ሁለተኛ ተጠርጣሪ ሆነው የቀረቡት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣና ዋና ኦዲተር አቶ በላቸው በየነ፤ በጠበቃቸው አማካኝነት በቂ ማስረጃና ኤግዚቢት ይዘናል፤ ሠነድ ሰብስበናል ካሉ በኋላ የደንበኛዬን የዋስትና መብት በመገደብ ተጨማሪ የ14 ቀናት ቀጠሮ ሊጠይቅ አይገባም ሲሉ ተከራክረዋል። ለ27 ዓመታት በመንግስት መስሪያ ቤት ማገልገላቸውን ያስረዱት ተጠርጣሪው፤ እኔ የምተዳደረው በወርሐዊ ደመወዜ ነው ሲሉ በእርሳቸው መታሰር ምክንያት ቤተሰባቸው ችግር እንደገጠመው በመጥቀስ ፍርድ ቤቱን የዋስትና መብት ይከበርልኝ ሲሉ ጠይቀዋል።
በድምሩም በችሎቱ ለመርማሪ ቡድኑ ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል ፍርድ ቤቱ አፅንኦት የሰጡባቸው ሦስት አበይት ጉዳዮች ሲኖሩ፤ ይኸውም ቡድኑ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜን ሲጠይቅ ምንን እንደሚጠይቅ ቢታወቅም ማንን እንደሚጠይቅ በግልፅ አለመቀመጡን፣ የሚሰሙት ምስክሮች በማን ላይ ምስክርነታቸውን የሚሰጡ ስለመሆናቸውና የትኛው ተከሳሽ በየትኛው ክስ ስር ተጠያቂ እንደሆነ በግልፅ አለመስፈሩ ተጠቁሟል።
የምርመራ ቡድኑ ተወካዮች በበኩላቸው ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዱ፤ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የተጠየቀው ወንጀሉ እጅግ ውስብስብና ሰንሰለታማ መሆኑን በመጥቀስ፤ ተጠርጣሪዎቹ ባለስልጣናትና ባለሃብቶች ከመሆናቸው አንፃር ከእስር በዋስ ቢለቀቁ ማስረጃዎችን ከማጥፋትም በላይ ምስክሮችን ሊያሸማቅቁ አሊያም ሊያግባቡ የሚችሉ ናቸው ሲል አስረድቷል።
በምርመራ ሂደት ውስጥ ተፈፅሟል ለተባለው ሕገ-መንግስቱን የጣሰ የሰብዓዊ መብት ችግር አስመልክቶ በሰጡት ምላሽ፣ ጉዳዩ ለፍርድ ቤት ሲደርስ ተጠርጣሪዎቹ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ነገር ግን እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ችግሮች ካሉ እናርማለን የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
የህክምናና የቤተሰብ ጉዳዮችን አስመልክቶ ለተነሱት ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡም፤ ታማሚዎች ካሉ ማረሚያ ቤቱ የራሱ የሆነ ክሊኒክ መኖሩን በመጥቀስ ከክሊኒኩ በላይ ለሆኑ ህመሞች በሪፈራል ደረጃና ከዚያም በላይ ለማሳከም የሚያስችል አቅም መኖሩን ጠቅሰዋል። ቤተሰብን በተመለከተ በተለይም 1ኛ ተጠርጣሪ በሰጡት አስተያየት ላይ ተመርኩዘው ሲያስረዱ ከቤተሰቡ የተገኘው ሰነድ እንዳለ ሆኖ መርማሪ ቡድኑ የሚፈልጋቸው ሌሎች ሰነዶችም ስለመኖራቸው በመግለፅ ተጠርጣሪዎቹ በዋስ መብት ከእስር ቢለቀቁ አስቸጋሪ ይሆንብናል ብለዋል።
በጥቅሉም ለተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብት መስጠትን በሚመለከት በወንጀለኛ ሕጉ ላይ፤ የተፈፀመው ወንጀል በሀገር ሀብት ላይ ከሆነና ከ10 ዓመት በላይ ሊያስቀጣ የሚችል መሆኑ ከግምት ከገባ ዋስትና እንደማይሰጥ ይደነግጋል ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።
የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ችሎቱም፤ ተከሳሾቹ የተጠረጠሩበት ወንጀል ከባድና ውስብስብ መሆኑን በመጠቆም የዋስትና መብታቸውን ውድቅ አድርጐ ለመርማሪ ቡድኑ ተጨማሪ የ14 ቀናትን የጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል። አያይዞም በሰጠው ትዕዛዝ፤ የተጠርጣሪዎችን ሰብዓዊ መብት በሚመለከት ጥንቃቄ መደረግ እንደሚገባው አሳስቦ የምርመራ ሂደቱም ግልፅ ይሁን ሲል ትዕዛዝ በመስጠት ለሰኔ 3 ቀን 2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በተያያዘ ዜና በሙስና ወንጀል የተጠርጣሪዎቹን ቁጥር ወደ 54፤ የክስ መዝገቡን ደግሞ ወደ ሰባት ያደረሰው የእነመልካሙ እንድርያስ ጉዳይ በመርማሪ ቡድኑ የተጨማሪ ቀነ ቀጠሮ በመጠየቁ ለግንቦት 23 ቀን 2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል። በዚህ መዝገብ የተዘረዘሩት ግለሰቦች መልካሙ እንድርያስ የናዝሬት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ሰራተኛ፣ ወ/ሮ አልማዝ ከበደ የባሕር ትራንዚት ስራ አስኪያጅ፣ አቶ ዳዊት መኮንን ደላላ እና አቶ ዳዊት አብተው ሠራተኛ ናቸው። እነዚህ ግለሰቦች የተጠረጠሩት ከትራንዚት ድርጅቶች ጋር በመመሳጠር እቃዎች የጉምሩክን ስርዓት ባልጠበቀ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ በማድረግና ያልተገባ ሀብትን ማካበት በሚሉ ወንጀሎች ነው።¾
ምንጭ፡ ሰንደቅ ጋዜጣ የረቡዕ ሚርይ 29 ዕትም አዲስ አበባ


ማንዴላ በመጨረሻዋ የፍርድ ቀን ለዘረኞች ያለው. በሉሉ ከበደ

$
0
0

ሉሉ ከበደ

comment_stage_5ኢትዮጵያን በቁጥጥሩ ስር ያዋላት የትግራይ ዱር አራዊት ቡድን ዛሬ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየጫነ ያለውን የአፓርታይድ አይነት ስራት እነ ኒልሰን ማንዴላ ከደቡብ አፍሪካ ምድር ከስሩ መንግለው ለመጣል እጅግ ብዙ መስዋእትነትና ምእተ አመት የሚጠጋ ጊዜ ነበር የወሰደባቸው።

ምእራቡም ሆነ ምስራቁ አለም ለአፍሪካውያኑ የነጻነት ትግል ፈጥኖ እውቅናና ድጋፍ አለመስጠቱና በተለይ ምእራቡ ከነጮቹ ጋር ተመሳጥሮ በተዘዋዋሪ እነሱን መደገፉ ትግሉ ረጅም ጊዜ እንዲወስድና የነጻነቱም ቀን እንዲርቅ ቢያደርገውም፤ በትግሉ መሪዎች ፍጹም ቆራጥነትና ለሞት መዘጋጀት እንዲሁም በህዝቡ አንድነትና ጽናት አፓርታይድ ተወግዶ የደቡብ አፍሪካ ህዝብ መሪ መሾምና መሻር ችሏል በነጻነት።

እርግጥ  በኢትዮጵያ የበላይነቱን የተቆጣጠሩት የህውሀት ዘረኛ ሰዎች ከደቡብ አፍሪካ ነጮች ጋር ሊያነጻጽራቸው የሚያስችል ስልጣኔና ለነጩ አለም ቀረቤታ አላቸው ባንልም፤ ለሀያላኑ መንግስታት በሎሌነት እስከቀረቡና የሚታዘዙትን እስከፈጸሙ ድረስ ድጋፋቸውን እንደማይነፍጓቸው ባይናችን እያየነው በመኖር ላይ ነን። ይሁንና ከሁሉም በላይ ለወያኔ መቅበጥና ከልከ ማለፍ፤ ለነሱ የልብልብ ማግኘትና በላያችን ላይ መግነን ተጠያቂው እራሳችን ነን። አንድ ሆነን በቶሎ እነሲህን የኢጣሊያ ጣእረመንፈስ ነጋሲያን ፋሺሽቶች ማስወገድ ተስኖን የህዝቡን ደም እየጠቡ፤ የሀገሪቱን ሀብት እየዘረፉ መወፈራቸውን ቀጥለዋል።

የደቡብ አፍሪካውን የጥቂት ነጮች አፓርታይ መንግስት ለማስወገድ ኤ ኤን ሲ በ1912 ዓም ኢ ኤ አ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ከአርባ አመት በላይ ሰላማዊ የትግል ስልት ነበር ሲከተል የቆየው። ህዝባዊ እንቢታ፤ እቤት የመዋል አድማ፤ የሥራ ማቆም አድማ፤ ይለፍ ወረቀት ሳይዙ በጅምላ ሆ ብሎ የተከለከለ ቦታ ሄዶ መታሰር፤ ወዘተ…. ያሁሉ ግማሽ ምእተ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ የተካሄደው ሰላማዊ ትግል የህዳጣኑን መንግስት ጭቆናና ጭካኔ አባባሰው እንጂ ለደቡብ አፍሪካ ህዝብ የፈየደው ነገር አልነበረም።

ኋላ ላይ ግን እነማንዴላ ሀሳባቸውን ለመቀየር ተገደዱ። ሰላማዊው ትግል በትጥቅ ትግል መደገፍ እንዳለበት አመኑ። ይህንንም ወሰኑ። የሽምቅ ውጊያ ለመጀመር በርካታ የ ኤ ኤን ሲ ታጋዮች ማንዴላን ጨምሮ ወደተለያዩ ሀገሮች ለወታደራዊ ስልጠና ተሰማሩ። ማንዴላም ወደ ኢትዮጵያ አቀና። እናም እ ኤ አ በ1961 ዓም የ ኤ ኤን ሲ ወታደራዊ ክንፍ በማንዴላ መሪነት ተመስርቶ በመንግስቱ የኢኮኖሚና ወታደራዊ ተቋማት ላይ አደጋ መጣል ጀመረ።

የነጮቹ መንግስት የትግሉ ትኩሳት እየተሰማው በመጣ ቁጥር ወያኔ እንደሚያደርገው በየጊዜው አዳዲስ ህግ ማውጣትና ድርጅቶችን ሁሉ ማገድ፤ ህዝቡንና ታጋዮቹን ማሳደድ፤ ማሰርና ማዋከቡን በሙሉ ሀይሉ ቀጠለ። የትግሉን መሪዎች የደረሰበትን በቁጥጥር ስር አዋለ ያልተያዘውም ከሀገር መሰድድና ትግሉን ከጎረቤት ሁኖ መምራት ግድ ሆነበት። የታሰሩት መሪዎች የሀገር ክህደትና መንግስትን በሀይል ለማስወገድ መሞከር  በሚል ክስ ለሞትና ለድሜልክ እስራት ያዘጋጃቸው ጀመር አፓርታይድ ።

እ ኤ አ አቆጣጠር 1962 ዓም ማንዴላ ያለፍቃድ ከሀገር ወተሀል፤ ህዝብን ለአድማ አነሳስተሀል ተብሎ አምስት አመት ተፈርዶበት እስር ላይ እንደነበረ ነበር ይህ አዲሱ ክስ የተደረበለት። ከዘረኞች ፍርድ ቤት ለነጻነት ታጋዮች ፍትህ የለምና ከረጅም ጌዜ ከንቱ ክርክር በኋላ እነማንዴላ ጥፋተኞች ናቸው ብሎ ነጩ ዳኛ ፈረደ። የፍርዱን ልክ ከመበየኑ በፊት ተካሳሾች የፍርድ ማቅለያ ክርክራቸውን እንዲያሰሙ በታዘዙት መሰረት ማንዴላ አራት ሰአት የፈጀ ታሪካዊና ድፍረትና ሀቅ የሞላበት ንግግር  በጽሁፍ  አቅርቦ ነበር።

በዚያ የመጨረሻዋ የፍርድ ቀን ለችሎቱ የተናገረውን ማንዴላ በጻፈው መጽሀፍ ውስጥ አሳጥሮ አቅርቦታል። ያ የአላማ ጽናትና ቆራጥነት የተሞላበት ንግግር አንዷለም አራጌን እስክንድር ነጋን ያስታውሳል። በሀገራችን ካለው ሁኔታ ጋር ምን ያህል እንደሚመሳሰል ለማስገንዘብ ወደ አማርኛ መልሸዋለሁ።

ማንዴላ ተከሳሽ ሳጥን ውስጥ ቆሟል። ተራው ደርሶ የክርክሩን ማክተሚያ ያነብ ጀመር።

አንደኛ ተከሳሽ ነኝ። በባችለር ኦፍ አርት የመጀመሪያ ዲግሪ አለኝ። ጆሀንስበር ውስጥ ከሚስተር ኦሊቨር ታንቦ ጋር በሽርክና ሆነን ለተወሰኑ አመታት የጥብቅና ሙያ ሰርቻለሁ። በ 1961 ግንቦት መጨረሻ ላይ ህዝብን ለአድማ ማነሳሳት እና ካለፍቃድ ከሀገር መውጣት በሚሉ ክሶች የአምስት አመት ፍርድ ተፈርዶብኝ በእስር ላይ የምገኝ ፍርደኛ ነኝ።

ነሀሴ ወር 1962 ለእስር እስከተዳረኩበት ድረስ በጉዳዩ ከፍተኛ ሚና የተጫወትኩና ኡምኮንቶ ሱዚዌ፤ የኤ ኤን ሲን ወታደራዊ ክንፍ ለማደራጀት ከረዱት መካከል አንዱ መሆኔን እቀበላለሁ።

ከሁሉ በፊት መንግስት በመግቢያው ላይ በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው ትግል፤በውጭ ሀይሎች ወይም  በኮሙኒስቶች ተጽእኖ ስር ያለ ነው የሚለውን ሀሳብና ግምት ባጠቃላይ ስህተት ነው ለማለት እሻለሁ። ያደረኩትን ነገር አድርጌአለሁ። እንደ ግለሰብም እንደ ህዝብ  መሪነትም። ይህንን ሳደርግ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ባለኝ ተሞክሮና በፍጹም አፍሪካዊ ኩራትና ክብር እንጂ የውጭ ወገኖች ባሉትና በሚሉት ተመርቼ ተነሳስቼ አይደለም።

በወጣትነት ዘመኔ ትራንስኪ ውስጥ የጎሳችን  አረጋውያን ስላለፈው የጥንት ዘመን ታሪክ ወግ ሲነግሩን እሰማ  ነበር። ሽማግሌዎች ከሚያወሷቸው የሗላ ታሪካችን ከኔ ጋር የሚያመሳስሉት የነበረው “ ያባትን ሀገር “ ለመከላከል ያደረጓቸውን ጦርነቶች ሲያነሱ’ የእነ ደንጌ እና ባንባታ፤ ሂንሳና ማካና፤ ኩንቲና ዳላሲል፤ ሞሾሾና ሲሁሁኔ ስሞች ሲጠቀሱ፤ የመላው አፍሪካ ክብርና ኩራት ሆነው ይሞገሱ ይወደሱ ነበር። ያኔ ያን ታሪክ ሥሰማ ተስፋ አደርግ  ነበር። ለህዝባችን የነጻነት ትግል የበኩሌን ጥቂት አስትዋጾ እንዳበረክት፤ ህይወት አንድ አጋጣሚ ትቸረኝ ይሆናል እያልኩ። በዚህ ጉዳይ ላይ ክስ ሲመሰረትብኝ እንደጥፋት የተጠቀሰውን ሁሉ እንዳደርግ መነሻና ግፊት የሆነኝ ይኸው የኋላ ታሪካችን ነበር።

ይህን እያልኩ የአመጹን  ጥያቄ አነሳና ፈጥኜ ጥቂት ዘለግ ላለ አፍታ ያለውን  ነገር ላስረዳ ግድ ይለኛል። እስካሁን ለችሎቱ ከተነገሩት ነገሮች ገሚሱም እውነት ገሚሱም እውሸት ናቸው። የሆነው ይሁንና ሻጥር ( በመንግስት የኢኮኖሚ ተቋማት ላይ አደጋ መጣል) ማቀዴን አልክድም። ይህንንም ሳቅድ በግዴለሽነትና በዘፈቀደ መንፈስ ተሞልቼ ወይም ደግሞ አመጽን የምወድ ሰው ሁኜ አይደለም። የረጅም ዘመን አንባገነንነት ያስከተለውን የነጮች  ብዝበዛና ጭቆና የተንሰራፋበትን የፖለቲካ ሁኔታ በሰከነ  አእምሮና  በተረጋጋ ሁኔታ ስገመግም ከኖርኩ በኋላ ነው በውጤቱ ይህን እርምጃ ለማቀድ የወሰንኩት።

ለችሎቱ ለማስረዳት የሞከርኩት ይህን የአመጽ እርምጃ ስንወስድ ሀላፊነት ሳይሰማንና ያልተጠበቀ ውስብስብ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል  ሳናስብ ቀርተን እንዳልነበር ነው። አንድም አይነት ጉዳት በሰው ህይወት ላይ እንዳይደርስ ለማድረግ መወሰናችንን አጽንኦት ሰጥቼ ነበር።

እኛ ኤ ኤን ሲዎች ምንጊዜም የቆምነው ከዘረኝነት የጸዳ ዲሞክራሲ  እንዲሰፍን ነው። ጎሳዎችን እስካሁን ካሉበት ሁኔታ  በባሰ መልኩ ከሚያራራርቅ ማናቸውም ድርጊት እንታቀባለን። ጠጣሩ እውነታ ወይም ሀቅ ግን የሀምሳ አመት ሰላማዊ ትግል ለአፍሪካውያን ያተረፈው ያስገኘው ነገር ቢኖር እየበዛ እየበዛ የመጣ የመጨቆኛ ህግና እያነሰ እያነስ የሄደ መብት ብቻ ነው። ለዚህ ችሎት ይህን መረዳት ቀላል ላይሆን ይችላል። ህዝቡ ለረጅም ዘመን ሀይል ስለታከለበት አመጽ ሲነጋገር መኖሩ እሙን ነው። የአመጽን አማራጭ ተተው በሰላማዊ ትግሉ እንዲቀጥሉ እኛ የ ኤ ኤን ሲ መሪዎች ብንመክርም፤  ከነጮች ጋር ተዋግተው የሀገራቸው ባለቤት ስለሚሆኑባት ቀን ይወያያሉ። ግንቦትና ሰኔ 1961 ዓም ገሚሶቻችን ይህን እየተነጋገርን በነበረ ወቅት ከዘረኝነት የጸዳ መንግስት እንዲኖረን ለማድረግ የሰላማዊ ትግሉ ፖሊሲ ምንም ውጤት እንዳላመጣ መካድ አልተቻለም ነበር። ተከታዮቻችን በዚህ ፖሊሲ ላይ መተማመን እያቃታቸው፤ የሀይልን አመጽ እንደአማራጭ በአእምሮ ውስጥ ማጎልበት ጀመሩ። የሚረብሽ የአሽባሪነት እሳቤ።

የ ኤ ኤን ሲ ወታደራዊ ክንፍ ህዳር 1961  ዓም ተመሰረተ። ይህን ውሳኔ ስናስተላልፍና በተከታታይ እቅዳችንን ስንነድፍ የ ኤ ኤን ሲ ሌጋሲ ከአመጽ  በጸዳ ትግል ህብረ ዘርነት እውን የሚሆንበት ሀሳብ አብሮን እንዳለና እንደያዝነው ነበር። ሀገሪቱ በጥቁሮችና   በነጮች መካከል ወደሚቀሰቀስ የርስበርስ ጦርነት በሚያስኬድ ጎዳና ላይ እየተጓዘች እንዳለች ይሰማናል። ነገሩን የምንመለከተው በማስጠንቀቂያ ደወል ነው። የርስ በርስ ጦርነት ማለት ኤ ኤን ሲ የቆመለትን እሴት ማውደም ማለት  ነው። የርስ  በርስ ጦርነት ከተነሳ ማናቸውም ዘር ሰላም የማግኘት እድሉ እጅግ የከፋ ይሆናል። ጦርነት የሚያስከትለውን የከፋ ነገር ለማወቅ በደቡብ  አፍሪካ ታሪክ ውስጥ በቂ ምሳሌ አለን። በደቡብ አፍሪካ አንግሎ – ቦር  ጦርነት ያስከተለው ጠባሳ ለመሻር ከሀምሳ አመት በላይ ወስዷል። ዘር በዘር ላይ ተነስቶ ከሁሉም በኩል በቀላል የማይገመት ህዝብ በሚያልቅበት ሁኔታ ጦርነት ቢካሄድ ጠባሳው ለመሻር ምን ያህል ዘመን ይፈጃል?

በተግባር አይተን እንዳመነው፤ አመጽ፤ ለመንግስት፤ ህዝባችንን በጅምላ መጨረስ የሚያስችል ገደብ የሌለው እድል ይሰጠዋል። በርግጥም የደቡብ አፍሪካ ምድር፤ አፈር፤ ዱሮ በንጹሀን አፍሪካውያን ደም ጨቅይቷል። ሀይልን በሀይል መክተን ራሳችንን ለመከላከል የመዘጋጀት የረጅም ጊዜ ስራ መስራት ተግባራችን እንደሆነ ይሰማናል። ጦርነት አይቀሬ ከሆነ ጦርነቱ መመራት ያለበት ለህዝባችን ሁኔታ በተመቸ መልኩ እንዲሆን እንሻለን። ለኛ አንድ ነገር ያጎናጽፋል፤ እናም በሁለቱም ወገን አነስተኛ የህይወት መስዋእትነት የሚያስከፍል ይሆናል  ብለን ያልነው የሽምቅ ውጊያ ነው። ለዚሁ ዝግጅት ለማድረግ ወሰንን።

ነጮች  በሙሉ የግዴታ ወታደራዊ ስልጠና ይሰጣቸዋል። ለጥቁሮች ይህ ነገር አይደረግም። የሽምቅ ውጊያውን ሊመሩ የሚችሉ፤ ወታደራዊ ስልጠና ያላቸው ሀይሎችን መገንባት መሰረታዊ እሳቤአችን ነው። ሳንዘገይ ለዚህ መዘጋጀት አለብን።

ውይይታችን በዚህ ደረረጃ ላይ እንዳለ በአፍሪካ ሀገሮች ልዩ ልዩ ጉባኤዎችን ለመካፈልና ወታደራዊ ስልጠና ለመውሰድ ካገር እንደወጣሁ አስረዳሁ። የሽምቅ ውጊያ ቢጀመር ከህዝቤ ጋር አብሬ ለመቆም ለመዋጋት እንድችል፤ ወታደራዊ ስልጠና መውሰዴን ተናገርኩ።( ማንዴላ ወታደራዊ ስልጠና የወሰደው ኢትዮጵያ ነበር ) በ ኤ ኤን ሲና በወታደራዊ ክንፉ መካከል ያለውን የሚለያቸውን መስመር ለችሎቱ ገለጽኩ። ሁለቱ እንዴት የተለያዩ መሆን እንዳለባቸው እንዳደረግን ተናገርኩ። ፖሊሲያችን  ነበር። ተግባር ላይ ለማዋል ቀላል አልነበረም። በህግ መታገድ መታሰር ሁሉ ስለነበረ ሰዎች በሁለቱም ውስጥ መስራት  ነበረባቸው። የኮሙኒስት ፓርቲውና ኤ ኤን ሲ አንድ ዓላማ አላቸው የሚለውን የመንግስት ክስ ተከራሬዋለሁ።

የ ኤ ኤን ሲ ርእዮተ ዓለም መርህ ምን ጊዜም አፍሪካዊ  ብሄረተኝነት ነው። “ ነጭን ወደ ባህር ንዳው “ የሚለው አይነት የአፍሪካ ብሄረተኝነት ጩኽትም አይደለም። ኤ ኤን ሲ የቆመለት አፍሪካዊ ብሄረተኝነት፤ አፍሪካውያን በምድራቸው ምሉእ ሆነው በነጻነት እንዲኖሩ የሚያስችል ጽንሰ ሀሳብ ነው። የ ኤ ኤን ሲን ዓላማና አቋም የሚያንጸባርቀው ሰነድ በ ኤ ኤን ሲ የጸደቀው የነጻነት ቻርተር ሰነድ ነው። በምንም መልኩ የሶሻሊስት መንግስት እቅድ አይደለም። ለሀገሪቱ ታሪክ  ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ መዋቅር ኤ ኤን ሲ መቼም አብዮታዊ ለውጥን ደግፎ አያውቅም። እስከማውቀው የካፒታሊዝምንም ስራት አውግዞ አያውቅም።

ከኮሙኒስት ፓርቲው በተለየ መልኩ ኤ ኤን ሲ በአባልነት አፍሪካውያንን ብቻ ነው የሚቀበለው። ዋና አላማውና ግቡም አፍሪካውያን አንድነትና የተሟላ የፖለቲካ መብት እንዲቀዳጁ ማድረግ ነው። የኮሙኒስት ፓርቲ ዋና አላማ  በሌላ መልኩ ካፒታሊስቶችን ማስወገድና በሰራተኛው መደብ መንግስት መተካት ነው። የኮሙኒስት ፓርቲ ለመደብ ልዩነት አጽንኦት ሲሰጥ ኤ ኤን ሲ በህብር አብረው የሚጓዚበትን ሁነት ይፈልጋል።

እርግጥ ነው በ ኤ ኤን ሲና  በኮሙኒስት ፓርቲው መካከል የቅርብ ትብብር አለ። ትብብሩም የጋራ የሆነ ግብ  መኖሩን የሚያረጋግጥ ነው።  ጉዳዩ የነጮችን የበላይነት ማስወገድ  ነው። ይህ ማለት በሁሉም አቅጣጫ የጋራ አቋምና የጋራ ግብ እንዳለ ያረጋግጣል ማለት አይደለም። የአለም ታሪክ በተመሳሳይ ምሳሌዎች የተሞላ ነው። ምናልባትም ስሜት የሚሰጠው ስዕል፤ ታላቋ ብሪታንያ፤ አሜሪካና ሶቬት ህብረት ናዚ ሂትለርን ለመውጋት ያደረጉት ትብብር ነው። ሂትለር ብቻ ካልሆነ በስተቀር፤ ቸርችልን ወይም ሩዝቬልትን ወደ ኮሙኒስትነት ተቀየሩ ብሎ ማንም ሰው ለመናገር የሚደፍር አይኖርም። ወይም ደግሞ አሜሪካና እንግሊዝ የኮሙኒዝምን ስራት ለማስፈን እየሰሩ ነው የሚል አይኖርም። ልምድ ያላቸው አፍሪካውያን ፖለቲከኞች ኮሚኒስቶችን ለምን ጥሩ ወዳጅ አድርገው እንደሚቀበሏቸው ስር የሰደደ መጥፎ አመለካከት በነሱ ላይ ላላቸው የደቡብ አፍሪካ ነጮች መረዳት በጣም ሊከብዳቸው ይችላል። ለኛ ግን ምክንያቱ ግልጽ ነው። በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ለብዙ አስርት አመታት ጥቁሮችን እንደሰው ለማስተናገድ የተዘጋጁ፤ ኮሙኒስቶች ብቻ ነበሩ። እኩልነታቸውን የተቀበሉ፤ አብረውን ለመብላት ለመጠጣት የተዘጋጁ፤ አብረውን ለማውጋት፤ አብረውን ለመስራትና ለመኖር የተዘጋጁ። በዚህም ምክንያት ዛሬ ብዙ አፍሪካውያን ናቸው ኮሙኒዝምን ከነጻነት ጋር እኩል አድርገው የማየት ዝንባሌ ያላቸው።

እኔ ምንጊዜም ራሴን እንደአፍሪካዊ አርበኛ የምመለከት እንጂ ኮሙኒስት አለመሆኔን ለችሎቱ አስረዳሁ። መደብ አልባ ስራት  በሚል አስተሳሰብ መማረኬን ወይም ደግሞ የኮሙኒስት አስተሳስብ ተጽእኖ እንዳሳደረብኝ አልካድኩም።

ካነበብኳቸው የኮሙኒዝም ጽሁፎችና ከተወያየሗቸው ማርክሲስት ግለሰቦች እንደተረዳሁት ኮሙኒስቶች የምእራባውያንን የፓርላማ ስራት ኢዲሞክራሲያዊና አድሀሪ እንደሚሏቸው ተገንዝቤአለሁ። በተቃራኒው ግን እኔ የዚያ አይነቱ አሰራር አድናቂ ነኝ።

ማግና ካርታ ( መሰረታዊ መብት ማረጋገጫ ሰነድ)፤ ፔቲሽን ኦፍ ራይት፤ ቢል ኦፍ ራይትስ፤ የሚባሉት ሰነዶች  በመላው ዓለም የሚገኙ ዲሞክራቶች ዘንድ በክብር የሚያዙ ሰነዶች ናቸው። ለብሪታንያ የፖለቲካ ተቋማት ታላቅ አክብሮት አለኝ። ለሀገሪቱ የፍትህ ተቋማትም እንደዚያው። የብሪያንያን ፓርላማ በዓለም ከፍተኛው ዲሞክራሲያዊ ተቋም አድርጌ  ነው የምመለከተው። የፍትህ ተቋማቷ ራስ ገዝነትና ያለ ወገንተኝነት መስራት አድናቆቴን ሳያጭሩ የቀሩበት ጊዜ የለም። የአሜሪካን ኮንግረስ፤ የሀገሪቱ ስልጣን ክፍፍል፤ የፍትህ ተቋማቷ ራስ ገዝነት ተመሳሳይ አድናቆት በውስጤ ያጭራሉ።

በደቡብአፍሪካ ውስጥ በጥቁሮችና  በነጮች ህይወት መካከል ያለውን አስደንጋጭ ልዩነት ዘረዘረኩ። በትምህርት፤ በጤና፤ በገቢ፤ በየፈርጁ ጥቁሮች በህይወት ለመቆየት ብቻ  በሚያስችል ደረጃ ሲኖሩ፤ ነጮች በአለም ያለውን ከፍተኛ ደረጃ  ይኖራሉ። እናም ህይወት በዚሁ መልኩ እንድትቀጥል የማድረግ ዓላማ አለ። “ ነጮች” አልኩ። ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ያሉት ጥቁሮች በሌላው አፍሪካ ካሉት ጥቁሮች የተሻለ ኑሮ የሚኖሩ ናቸው ብለው ያስባሉ። የኛ እሮሮ አልኩ፤ ከሌላው የአፍሪካ ህዝብ ጋር ስንነጻጸር ድሆች ነን አይደለም። በሀገራችን ውስጥ ካሉት ነጮች ጋር ስንነጻጸር ድሆች ነን ነው። ይህንን የተዛባ ሁኔታ እንዳናርም እንዳናስተካክል በህግ ተከልክለናል ነው።

አፍሪካውያን በሀገራቸው ክብር ያጡበት ሁኔታ ነጮችን የበላይ የማድረጉ ፖሊሲ ቀጥተኛ ውጤት ነው። የነጮች የበላይ መሆን የጥቁሮችን የበታችነት ያስከትላል። የነጩን የበላይነት ለመጠበቅ የሚወጣው ህግ ይህን እምነት ስር እንዲሰድ ያደርገዋል። በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ማናቸውም ዝቅተኛ ስራ  በጥቁሮች ነው የሚሰራው። አንድ ነገር መነሳት ወይም መጽዳት ካለበት  ያን ስራ እንዲሰራለት ነጩ ጥቁሩን ገልመጥ ገልመጥ ብሎ ይፈልገዋል። አፍሪካዊው የርሱ ተቀጣሪ ሆነም አልሆነም።

ድህነትና የቤተሰብ መፍረስ የሚያስከትሉት ነገር አለ። የሚሄዱበት ትምህርት ቤት ስለሌላቸው፤ ወይም ትምህርት   ቤት እንዲውሉ የሚያስችል ገንዘብ  ወላጆቻቸው ስለሌላቸው፤ ህጻናት በየጎዳናው ሲንከራተቱ ይውላሉ። እቤት ውስጥም ተገኝተው ልጆቻቸው የት እንደሚውሉ ሊያዩ የሚችሉ ወላጆች የሉም። እናትም አባትም ያውም ሁለቱም ካሉ ቤተሰቡን በህይወት ለማቆየት ስራ  ብለው ውጭ መዋል አለባቸው። ይህ የወደቀ የሞራል ደረጃን ያስከትላል። በፖለቲካ  ብቻ ሳይሆን  በየአቅጣጫው ህገወጥነት፤አመጽና ሁከት እንዲንሰራፋ ያደርጋል።

አፍሪካውያን   በመላዪቱ ደቡብ አፍሪካ እኩል ድርሻ እንዲኖራቸው ይሻሉ። በህብረተሰቡ ውስጥ የደህነነት ዋስትናና ድርሻ እንዲኖራቸው ይሻሉ። ከሁሉም በላይ እኩል የፖለቲካ መብት እንዲኖረን እንሻለን። ያለዚህ መብት ስንኩልነታችን ዘለአለማዊ ነው የሚሆነው። በዚህች ሀገር ውስጥ ላሉት ነጮች ይህ አብዮታዊነት እንደሚመስላቸው አውቃለሁ። ምክንያቱም ብዙሀኑ መራጭ የሚሆነው ጥቁሩ አፍሪካዊ ስለሚሆን ነው ነጩ ዲሞክራሲን እንዲፈራ የሚያደርገው።

ይህ ኤ ኤን ሲ የሚዋጋለት ጉዳይ ነው። ትግላቸውም እውነተኛ ብሄራዊነት ነው። ባፍሪካውያን በራሳቸው ተሞክሮና በደረሰባቸው ስቃይ የተቀሰቀሰ የአፍሪካ ህዝቦች ትግል ነው። በህይወት የመኖር መብት ትግል ነው።

ንግግሬን አነበብኩ። እዚህች ነጥብ ላይ እንደደረስኩ ወረቀቶቼን ተከላካይ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጥኩና ፊቴን ወደ ዳኛው መለስኩ። ችሎቱ ፍጹም ጸጥ እረጭ አለ። የመጨረሻዋን ንግግር ከትውስታዬ ስናገር ፊቴን ከዳኛ ዴዊት ላይ ዘወር አላደረኩም ነበር።

በህይወት ዘመኔ ለዚህ የአፍሪካ ህዝብ ትግል ህይወቴን አሳልፌ ሰጥቻለሁ። የነጮችን የበላይነት እየተዋጋሁ ነው። የጥቁሮችን የበላይነት እየተዋጋሁ ነው። ሁሉም ሰው ተዋህዶ፤ ሰምሮና አብሮ እኩል እድል እየተጋራ አንድ ላይ መኖር አለበት የሚል አስተሳስብ አለኝ። የምኖርለትና እንደግብም ልለቀዳጀው ተስፋ የማደርግበት አስተሳሰብ  ነው። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም ለመሞት የተዘጋጀሁለት አስተሳሰብ ነው።

አሁን  በችሎቱ ፍጹም ጸጥታ ሆነ። የመጨረሻዋን ከተናገርኩ  በኋላ ቁጭ አልኩ። በችሎቱ ውስጥ የነበሩ ታዛቢዎች ሁሉ አይናቸው እኔ ላይ ያረፈ መሆኑ  ቢሰማኝም ቤቱ ውስጥ ወዳለው ህዝብ ዘወር ብየ አላየሁም። ጸጥታው ለበርካታ ደቂቃዎች የዘለቀ  ቢመስልም ግን ምናልባትም ከሰላሳ ሲኮንድ በላይ አልቆየም ነበር። በረጅሙ የሚተነፍስ፤ ቁናቁና የሚተነፍስ፤ የሕብር ጉምጉምታ፤ የሴቶች ለቅሶ ተከትሎ በፍርድ ቤቱ ውስጥ ይሰማ ጀመር….

“ LONG WALK TO FREEDOM”- NELSON MANDELA ( PAGE 432-438 )

lkebede10@gmail.com

 

 

 

 

 

 

 

ኮለኔል ጎሹ ወልዴ እና ዶር ታዬ ወ/ሰማያት ወዴት ገቡ?

$
0
0

ኮለኔል ጎሹ ወልዴ እና ዶር ታዬ ወ/ሰማያት ወዴት ገቡ?

ዛሬ ካልወጡሰ መቼ?        

ከሎሚ ተራ 

ዝነኛውና የማይጠገበው ድምጻዊ (ዶ/ር) ጥላሁን ገሠሠ፤ ሲያንጎራጉር፤ እንዲህ ብሎ ነበር፤

“ጩኸቴን ብትሰሙኝ ፤ ይኸው አቤት አቤት እላለሁ በደል ደርሦብኝ እጮሃለሁ ብያለሁ”

 

ኮለኔል ጎሹ ወልዴ

ኮለኔል ጎሹ ወልዴ

እያለ ያንጎራጎረውን  እኔም አቤት አቤት የ ( የመሪ ያለህ!!! ) በዪ እኔም እጮሀለሁ። ምንም እንኳን ሰለኮነሬል ጎሹም ሆነ ሰለ ዶክተር ታዬ ታላቅ ሰራና አገር ወዳድነታቸው አገር የሚያወቀው ያደባባይ ሚሰጥር ቢሆንም  ቅሉ፤ ሰሞኑን ግን የተለያዩ የሀገርኛ ጉዳይን የሚያሳዩ ቪዲዩዎችን ሰመለከት ድንገት የኮነሬል ጎሹን ብዙዎችን ያሰደነቀና ያኮራ ሃገር አቀፍ የጥብቅና ንግግር (On the fate of Ethiopia and Eritrea’s Referendum) አየሁና  በቁጭት ምን ተብሎ፤ ማን አሰከፍቶት ይሆን ኮነሬሉ ጥግ የያዙት ? ዶክተር ታዬ ወልደሰማያትሰ ? የት ገቡ ? በማለት በቁጭት ለመጠየቅ ብዕሬን አነሳሁ።

መቼም እንዲህ ያለውን አንገብጋቢ ሃገራዊ ጥያቄ የሚጠይቁ በርካታዎች እንደሚሆኑ ባምንም ጥቂቶች ደግሞ  የ ምርጫ 97 ቱን ምሳሌ በማድረግ የሞተ ዘመድ የለውም ወይ?  ይኸ ሰው ምን ነካው የሚሉ እንደማይጠፉም አምናለሁ። መልሴ ግን የሞቱ ዘመዶች በርካቷች አሉኛ፤ ተሰፋዪ ግን አይሞትም።ተሰፋ ላንድም ሰከንድ አጥቼ አላውቅም ነው ።

 

እንዲህ አይነቱ ጥያቄ አገራችን የምትገኝበትን የፖሎቲካ ሂደትና ቀውሰ በሰፊው እንድንጠይቅና ከሰኸተታችንም ታርመን ይቅርም ተባብለን፤ በሃገር ጉዳይ እኔ ማን ነኝ ? ምንሰ ማድረግ ይጠበቅብኛል ? የሚለውን ጥያቄ በቅንነት በመጠየቅ አንተ ትብሰ፤ አንቺ ትብሸ በመባባል እንደገና እጅ ለእጅ ተያይዝን አገራችን እንድትገባበት ከተቆፈረላት ጥልቁ ጉድጓድ የማውጣት አገራዊ ግዴታ አለብን በዬ አምናለሁ።

 

taye_wsemayatከገጠመን እና ከተጋረጠብን የፖሎቲካ ውጥንቅጥ አኳያሰ እባክህ፤ እባክሽ ያሰፈልጋል ወይ ? ብቃት ያላቸው የፖሎቲካ መሪዎችሰ እባካችሁ እሰኪባሉ መጠበቅ አለባችው ወይ ? በሚል የተለያዩ እሣት የሚተፉ እንጉርጉሮዎች ከየጎራው ሊነሱ እንደሚችሉ የሚጠበቅ ቢሆንም ከተጋረጠብን ከፍተኛ አደጋ ባሻገር ምንሰ ብናደርግ አገር ትዳን እንጂ ነው መልሴ።

ሥለዚህ  ሰለጠንካራ የፖሎቲካ አመራር ብቃታቸውና፤  ሰራቸው በርካታ አገር ወዳዶች የሚመሰክሩላቸውን ጠንካራ መሪዎች ዳግም ወደ ፈጠጠው የትግል ጎዳና እንዲመጡ የማይደረግበት ምክነያት ምንም ሊኖር አይችልም።  እነ ኮነሬል ጎሹንም እነ ዶክተር ታዬ ወ/ሰማያትንም ሌሎችም አሉ የሚባሉትን ከየ አካባቢያችን ውጡ፤ አገራችን ኢትዮጲያ ትጮሃለች፣ የመሪ የለኸ እያለችም ትጣራለች ብለን የማውጣት ሃገራዊ ግዴታ አለበን። እከሌ ከከሌ ሳንል ጩኸታችንን እናሰማና አገራችንን ተባብረን ከውድቀት እናድን።

 

“ይሄ – መሪ ትግሉ ይወልዳል የሚለውም ባዶ ጩኸታችን ለ 22 አመት ወልዶ አላሳየንም እና ሁላችንም ቆም ብለን እናስብ፡

የሚዲያ ክፍሎችም በሙሉ፤-  እነ ቪ. ኦ. ኤም፣ ዶቼ ቬሌም ፤ እሣትም፣ ሌሎች ሚዲያዎች ሁሉ ካሜራችሁን ወደ አራቱም ማዕዘናት አዟዙሩት ፤ምክነያታቸውንም አሰሙን እያልኩ ጩኸቴን ብትሰሙኛ እላለሁ። በቸር ይግጠመን!!

 

ሎሚ ተራ፦Tuesday, May-28-13

ይድረስ ለዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ ጂግሳ፦ “ዘመድ መስላ ቀርባ አሞራ ዶሮ በላች”

$
0
0

ODFያጀማል (B.B)

ሰሞኑን ለአንዱ የኦዲኤፍ አመራር አባል ብለው የጻፉትን ደብዳቤ በአንድ ድረ-ገጽ (ዘ-ሐበሻ) ላይ ለማንበብ እድል ገጥሞኝ ነበር። ደብዳቤውፕ የተላከለት ባለቤት ቢኖረውም የደብዳቤው ይዘት ግን በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ በመሆኑ እንደ አንድ የኦሮሞ ታጋይና ብሄረተኛ ምላሽ ልሰትዎት ተገድጄ ብእሬን አነሳሁ።
(ሙሉውን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ)

ለደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን መዕመናን የቀረበ ጥሪ (ሚኒያፖሊስ –ሚኒሶታ)

$
0
0
የፊታችን እሁድ ጁን 2 ቀን በደብረሰላም  መድሃኔዓለም ቤ/ክ ምርጫ ይደረጋል ተብሏል።

የፊታችን እሁድ ጁን 2 ቀን በደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ምርጫ ይደረጋል ተብሏል።

ሚኒያፖሊስ ሚኒሶታ

ግንቦት ፳፻፭ (May 2013)

የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች ይኸውም ለሥልጣን ያቆበቆቡ እሾም ባዮች ፣ ለጥቅማቸው የቆሙ ግለሰቦች እና ሆድ አደሮች የሀገራችው ፣ የሕዝባቸው፣ የቤተ ክርስቲያኗ ገዳማውያን እና መናንያን ሐዘንና ሰቆቃ ሳይገዳቸው እኔ ከሞትኩኝ ስርዶ አይብቀል እንዳለችው አህያ የግል ቀቢጸ ተስፋቸውን (ego) ላማሟላት ብቻ ቤተ ክርስቲያኗን ለወያኔ አሳልፈው ለመስጠት መሰናዶአችውን ጨርሰውና ወገባቸውን ጠበቅ እድርገው ተነስተውልህ June 2, 2013ን በትልቅ ጉጉት እየተጠባበቁ ይገኛሉ (በነገራችን ላይ ስለ June 2, 2013 ለማታውቁ ወይንም ላልሰማችሁ ለማሰማት ይረዳ ዘንድ….. June 2, 2013 የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ወደ ኢትዮጵያ ሲኖዶስ ትቀላቀል ወይንስ አትቀላቀል የሚለው ውሳኔ ይሰጥ ዘንድ የቤተ ክርስቲያኗ የአስተዳደር ቦርድ ስብሰባ የጠራበት ዕለት ነው፤ ስብሰባውም ከቅዳሴ አገልግሎት በኋላ ይከናወናል)።

በኢትዮጵያ ገዳማት እና አድባራት በመነኮሳት እና በመናንያን ወገኖቻችን ላይ የህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት የሚፈጽመውን የዘር ማጥፋት እና ማፅዳት፣ የገዳማት እና አብያተ ክርስቲያናት መቃጠል፣ መፍረስ፣ መዘረፍ እና መታረስ ሳይገዳቸው፤ በኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ላይ በተለያዩ ቦታዎችና ግዜያት ለምሳሌ ያህል ከቡዙ በጥቂቱ በሐረር፣ በእርሲ አርባጉጉ፣ በጉራ ፈርዳ፣ በአፋር፣ በጋንቤላ፣ በደቡብ ህዝቦች ከልል፣ በጂማ፣ በአሶሳ፣ በጎንደር፣ በአዲስ አበባ በ1997 ከተካሔደው ምርጫ በኋላ፣ በአዋሳ፣ በበደኖ፣ በአርባጉጉ፣ በአርሲ አሳሳ፣ በቤኒሻንጉል ህዝባችን ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ፣ የተናጠል ግድያ፣ አማራው ወልዶ ከሳመበት አርሶ ከቃመበት ቀዬው/ሠፈሩ የዘር ሐረጉ እየተመዘዘ ሲባረር፣ እስራት፣ መከራ፣ ስቃይ፣ ግርፋት፣ እርዛት እና ረሐብ ሲቆላው እያዩ እና እየሰሙ የወገናቸው እና የህዝባቸው ሥቃይ፣ መከራ፣ ሰቆቃ እና ዋይታን ወደጐን በማለት በሌላው ላይ የሚደርሰው ግፍ የማይሰማቸው ካህናት እና መዘምራን የደንቆር ለቅሶ መልሶ ቀልሶ ይሉ ዘንድ አባት ያስፈልገናል በሚል የሐሰት ቅጥፈታቸው፣ የግል ፍላጐታቸውን ለማሟላት እና በወያኔ የተሰጣቸውን የቤት ሥራ ለመስራት ሲሉ ብቻ ቤተ ክርስቲያኗን፣ አንተን እና አንቺን አሳልፈው ሊሸጡህ/ሊሰጡህ የተዘጋጁ ሥለሆነ አንተም ጠንቅቀህ እውነታውን ተረድተህ እና ነቅተህ ቤተ ክርስቲያኗን ልትጠብቅ ይገባሃል።

ህዝበ ክርስቲያኑን እኛ እናውቅልሀለን፣ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ቆመናል፣ አባት ያስፈልግሃል እኛም አባትህ ነን የምንልህን ስማ ካላችሁ ምነው ታዲያ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ተባረው ወደ ጐጃም ሲጋዙ የተጫኑበት አይሱዙ ተገልብጦ አባይ በረሃ ላይ ከ 60ዎቹ 59ኙ ያለቀባሪና ያለአንሺ አስክሬናቸው የአውሬና የአሞራ ሲሳይ ሲሆን በደብረ ሰላም ቤተ ክርስቲያን ፀሎት አልተደረገላቸው፣ የዝቋላ ገዳማት ሲጋዩ፣ የዋልድባ መናንያን ከገዳማቸው ሲባረሩ ምነዋ የኛዋ ደብረ ሰላም በፀሎት አላሰበቻቸውም??? ባለፈው ቦስተን ላይ በደረሰው የሽብርተኞች ጥቃት ለሞቱት ፀሎት ሲደረግላቸው የኛን ግን ረሳናቸው!! ነው ወይንስ የዋልድባ አሳዳጆች የኛን ካህናትም ወዮላችሁ አሏችሁ፤ ካሏችሁ መቼስ ምን ይደረጋል
ፈሪ ለእናቱ ያገለግላል፣
ምጣድ ስትጥድ እንሰቅስቅ ይላል፣ ይባል የለ፤ ለማንኛውም የምንኖረው በ21ኛው ክፍለ ዘመን ስለሆነ በሃገራችን እና በቤተ ክርስቲያንናችን ላይ የሚደርሰውን ጥፋት፣ ውድመት እና ዘረፋ በስማ በለው ሳይሆን በቀጥታ በየእለቱ መከራውን ቀማሽ ከሆነው ህዝባችን ስለምንሰማው ልትሸነግሉን ባትሞክሩ መልካም ነው፤ ይልቁንስ ለእውነት ስለእውነት ቆማችሁ ሃገራችንን እና ቤተ ክርስቲያንናችንን በጋራ ብንታደጋት ለወደፊቱ ይበጀናል ይበጃችኋል።
አንዳንድ ካህናት በቤተ ክርስቲያኗ ዓውደ ምህረት ስብከታቸው ላይ ወደ ኢትዮጵያ ሲኖዶስ (ሀገር ቤት ያለው በአባይ ፀሐይ እና የፌድራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ ዶ/ር ሺፈራው ተ/ማርያም የሚመራውን ሲኖዶስ (በነገራችን ላይ ዶ/ር ሺፈራው ተ/ማርያም የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ናቸው) ከፓትሪያርክ ምርጫ በፊት ሲኖዶሱን ሲመሩት እንደነበረ የሚዘነጉት አይመስለንም) እንግባ እያሉ የሚያደነቁሩን ከቤተ ክርሲቲያን ውጪ ደግሞ የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎችን ሲኖዶሱ/የኮሌጁ አስተዳደር ከመኖሪያና መማሪያ ግቢ ባባረራቸው ወቅት ተማሪዎቹ የሚበሉት የሚጠጡት የላቸውምና እባካችሁን ለእነርሱ እንድረስላቸው እያሉ የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎችን የገንዘብ መለመኛ ያደርጓቸዋል። ነገሩ ለበጎ ቢሆነ ባልከፋ ነበረ ነገር ግን በአደባባይ ትክክለኛው ሲኖዶስ ኢትዮጵያ ነው ያለው፣ ሲኖዶስ አይሰደደም እያሉ የሚሰብኩ ነገር ግን ለገንዘብ መለመኛ ሲሆን ሲኖዶሱን ከሰውና ወቅሰው ከስንቶቻችሁ ገንዘብ አንደሰበሰቡ ቤት ይቁጠረው ገንዘቡም ይድረስ አይድረስ ለሰብሳቢው ካህን ትልቅ የጥያቄ ምልክት ? እያኖርኩኝ፤ ከቤተ ክርስቲያኗ አውደ ምህረት ውጪ ሲሆን ግን የተማሪዎቹ መባረር ስህተት ነው፣ ሲኖዶሱም የሚሠራው ሥራ ትክክል አይደለም፣ ጥፋት እየተፈፀመ ነው ብለው ካመኑ፤ ሲኖዶሱንም እያወገዙ ገንዘብ ከለመኑ ታዲያ ምነው ሲኖዶስ አንድ ነው፣ አይሰደድም፣ እሱም ኢትዮጵያ ያለው ነው፣ ትክክልም እየሠራ ነው፣ እሱን ልንከተል ይገባናል አያሉ አውደ ምህረት ላይ ለምን ይሰብካሉ (ባንድ ራስ ሁለት ምላስ ይሏል ይህ ነው)።

እውነታውን አንነጋገር ከተባለ ምነው የአቡነ ጴጥሮስ ኃውልት ሲነሳ በዓውደ ምህረት ላይ አንድ ካህን አልተነፈሰም ያውም የአቡነ ጳውሎስ ኃውልት በሲኖዶስ ውሳኔ እንዲፈርስ ተወስኖ ሳለ፣ የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ከትምህርት ቤቱ ግቢ ሲባረሩ ያውም ምግብ ተከልከለው የእለት ጉሮሮአቸውን አንኳን ለምነው አንዳይዳፍኑ በፖሊስ እየተሳደዱ ባሉበት፣ የዋልድባ መናንያን ቋርፍ በልተው ከሚኖሩባት ገዳማችው እየተባረሩ ወደ ነበሩበት ገዳም ለመመለስ ሲጠይቁ ወደ እዚህ ከምትመለሱ አናታችሁ ማሕፀን ብትመለሱ ይሻላችሗል ሲባሉ፣ በሰደፍ ተደቅትው ሜዳ ላይ ሲጣሉ፣ እንደ ሕፃን በአለንጋ ሲገረፉ በልምጭ ሲለመጡ፣ ከወፍጮ ቤት ገቢ ያሰባሰቧትን 60, 000 (ስልሳ ሺህ ብር) በአደባባይ በመንግስት ታጣቂዎች በጠራራ ፀሐይ ሲዘረፉ፤ ዝቋላ፣ የአሰቦት ገዳም፣ ታሪካዊ መጽሐፍት አና ቅርሶች ያሉባችው ደብሮች እና ገዳማት ሲጋዩ፣ በምዕራብ ጎጃም ጣና በለስ አካባቢ ያሉ አብያተክርስቲያናት እንዲፈርሱ በወያኔ ሲወሰን ምነው አንድም ቀን በቤተ ክርስቲያኗ ዓውደ ምህረት ላይ አልሰበኩ መልሱን ለአንባቢያን እና ለሰባኪያኑ እተወዋለሁ። የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በተባረሩ ሰሞን አዲስ የተሾሙት ፓትሪያርክ በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ (VOA http://amharic.voanews.com) ተጠይቀው ይህ ጉዳይ እኔን አየመለከተኝም ሲሉ የሲኖዶሱ ፀሐፊም ተመሳሳይ መልስ ለኢሳት (Ethiopian Satellite TV/Radio www.ethsat.com) ሲሰጡ እንዲያውም ይባስ ብለው በሌላ ቃለ መጠይቅ እኚሁ የሲኖዶሱ ፀሐፊ ተብዬው አቡነ ህዝቅኤል ስለ ዋልድባ ገዳማውያን እንግልት ጥያቄ ቀርቦላችላቸው “ማርያምን አልሰማሁም” ሲሉ መስማቱ አያሳዝንም። ታዲያ የቤተ ክርስቲያኗ የበላይ ተብዮዎች አያገባንም ካሉ ማ ሊጠየቅ ኖሯል በቅጥፈት እውነትን ለመሸሸግ መሞከሩ ከተጠያቂነት አያድንም፤ ነው ወይንስ የተሾሙት አባት ተብዮዎች ወንበር ለማሞቅ የተቀመጡ ጉዶች ናቸው?? ለነገሩማ ከአነጋገራቸው ለመረዳት እንደቻልነው ምንም ነገር ከመተንፈሳቸው በፊት ከመንግስት አካል ትዕዛዝ/መመሪያ መጠበቅ አለባቸው፣ እህህህ ከማለት ውጪ ምን ይባላል የሚሰብኩትን ወንጌል ሰባኪ ብቻ ሳይሆኑ ፈፃሚም ያድርጋቸው።

ታዲያ የደብረ ሰላሞቹም ካህናት እራሳቸውን አዋቂ ሌላውን አላዋቂ ለማስመሰል ስለ ዮዲት ጉዲት፣ ግራኝ መሀመድ አና ስለ ሌሎችም በቤተ ክርስቲያኗ ላይ ስለደረሱት ጥፋቶች በተደጋጋሚ ሰበኩን፤ አዎ በጣም ብዙ ብዙ ጥፋቶች እና ውድመቶች በዮዲት ጉዲት እና በግራኝ መሀመድ ተፈጽመዋል ይህንን የካደ በደብራችን ማንም ሰው የለም ወይንም አላጋጠመንም ነገር ግን አሁንም ከዛ ባልተናነሰ መልኩ ቤተ ክርስቲያኗን እያጠፏት እና እያወደሟት ስለሆነ ከእነርሱ ጋራ አንተባበርም፣ ከእነርሱ ጋራ ቤተ ክርስቲያኗን አናጠፋም ነው እያልን ያለነው፤ ካህናቶቹ እያላችሁ ያላችሁት ግን ከአጥፊዎች ጋር ተባበሩ፣ ከአጥፊዎች ጋር እጥፉ ነው፣ ዮዲት ጉዲትም መጥታ ስለ አንድነት እየሰበከች ቤተ ክርስቲያንን ብታጠፋ ከእርሷ ጋር ተባበሩ እያለችሁ ነው፤ አሁንም ደግመን ደጋግመን የምንለው ከአጥፊዊች ጋር አንተባበርም ነው።

ይሁዳ ጌታን አሳልፎ በመስጠቱ ያገኘው ፀፀትና ሐዘን እንጂ ፍሰሐ እና ደስታ አልነበረም እናንተስ እኛን አሳልፎ በመስጠት የምታገኙት ደስታ ምን ይሆን??? መልሱን ለእናንተው እተወዋለሁ። ለማንኛውም ለሹመቱ ጉጉት ያሎት ጠቀም ያለ ገንዘብም ያዘጋጁ በቅርቡ ሐራ ተዋህዶ አንደዘገበችው ከሆነ ለደብር እልቅና በአነስተኛ ግምት እስከ ብር 80,000 (ሰማኒያ ሺህ) ፣ ለፀሐፊነት አስከ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር ጉቦ መስጠት ይጠበቃል (ለዝርዝሩ ይህን ሊንክ ይክፈቱ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/3506)፤ አሁን አሁን ደግሞ ሰውን አሳልፎ በመስጠት ብቻ ጵጵስና የሚገኝበት ዘመን ላይ አይደለንምና!!! ያውም ካገኙ፤ በቅርቡ ከቤተ ክህነት እንዳፈተለከው ወሬ ከሆነ ሦስተኛ መመዘኛም ተመዟል (መቼም የትግራይ ህዝብ ፈርዶበት በስሙ ይነገዳል) ከትግሬ በቀር ሌላው ቤተ ክህነትን አይረግጥም እየተባለ ነው፤ ታዲያ የኛዎቹ ጉዶች ሌላውን መመዘኛ ብታልፉ ይሄኛው ሳይጥላችሁ አይቀርም (አበስኩ ገበርኩ) ።

አንድነት አንድነት እያሉ የሐሰት ነጋሪታቸውን የሚጐስሙና የውሸት ጥሩንባቸውን የሚነፉ ግለሰቦች ስለ እውነተኛው አንድነት ቢለፉና ቢደክሙ ምንኛ መልካም ነበረ፤ በቅርቡ በአዳባባይና በሚዲያ ወጥተው አማራና ኦርቶዶክሱን አከርካሪውን ሰብረነዋል እያሉን አንዴትስ ነው ከአከርካሪ ሰባሪዎች ጋር አንድ የምንሆነው፤ ይልቁንም የእነርሱ የገደል ማሚቶ ሆኖ የሐሰት ጩኸታችውን ከማስተጋባት ቤተ ክርስቲያናችንን በህብረት ብንሰራ ምንኛ በተሻለ ነበር ይልቁንም በአስራ አንደኛው ሠዓት ላይ የራሳቸውንም ሆነ የቤተ ክርስቲያኗን ሠላምና አንድነት ከሚነሱ አርፈው ቢቀመጡ እንመክራቸዋለን። ለመሆኑ እስቲ አንድነት አንድነት የሚሉትን አንድ ጥያቄ ልጠይቃቸው፤ ባለፈው በዳላስ ቴክሳስ የነበረውን የአንድነት ጉባኤ የበተነው ማነው፣ ጉባኤው ሳያልቅ ከኢትዮጵያ መግለጫ ያወጣው ማነው፣ በሰላም ጉባኤው ላይ የተካፈሉትን ቄሶች መስቀል ነው ያለውስ የህወኃት መስራች የየትኛው አካል ይሆን???? እኛማ የኢትዮጵያን አንድነት እና የቤተ ክርስቲያናችንን አንድነት አጥብቀን እንሻለን እናንተ የምትድግፏቸው ግን ወገኖቻችንን አሳደዷቸው የኢትዮጵያ አንድነት እና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ስላሉ ገደሏቸው፣ ተከብሮና ተፈርቶ የኖረውን ገዳም አትንኩብን ባሉ ገረፏቸው፣ ቀጠቀጧቸው፣ የቤተ ክርስቲያኗን ሀብት እና ቅርስ ዘርፈው ሸጡ፣ ገዳማትን አቃጠሉ፤ ታዲያ አንድነቷን ያሳጣ ሰላሟን የነሳ የትኛው አካል ይሆን???? ጉድ ሳይሰሙ መስከረም አይጠባ ይባል የለ……

እሁድ May 19, 2013 አቡነ ዘካሪያስ በራችስተር ሚኒሶታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ንግስ እና የአዲስ ቤተ ክርስቲያን ግዢ ምርቃት ላይ ተገኝተው በነበረበት ወቅት በተደረገው ስብከት ላይ ባካበቢያችን ሦስት ቤተ ክርስቲያናት ብቻ እንዳሉ እና ሶስቱም በኢትዮጵያ ሲኖዶስ ስር እንዳሉ አድርጐ የተሰበከውን ስብከት አንቀበለውም። አቡነ ዘካሪያስ የጐጃም ክፍለ ሃገር ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ወቅት እናቶችና አባቶች ከልጆቻቸው ጉሮሮ ነጥቀው ለቤተ ክርስቲያን የሰጧትን ምፅዋት ዘርፈው ወደ አሜሪካን በአቡነ ጳውሎስ የተላኩ ናቸው። ይህንንም ከጎጃም አካቦቢ የመጣነው ጠንቅቀን እናውቀዋለን፣ እርሳቸውም ቢሆኑ ሳይክዱ በኤሚሪካን ድምፅ ራዲዬ ቀርበው በማመን ከልጆቻቸው ለምነው እንደሚከፍሉ ለአቶ አዲሱ አበበ በቃለ መጠይቁ ወቅት የእምነት/ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል። አቡነ ዘካሪያስን፤ አባታችን አባታችን ለሚሉት አንድ ጥያቄ እናስቀምጥላቸው፤ እንደተባለው እና እንዳመኑት የወሰዱትን ከ 1.5 ሚሊየን ብር በላይ ከምን ከተቱት፤ ቤት ሰርተውበት እያከራዩት ይሆን ወይንስ???? እርሳቸውን ብትጠይቁልን?? ሌላው እኚሁ አቡነ ዘካሪያስ በራችስተር ሚኒሶታ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ ንግስ በኋላ በዕለቱ በበዓለ ንግሱ ላይ የነበሩትን ካህናት እና መዘምራንን ሰብስበው በርቱ የምትሰሩትን መልካም ሥራ እየተከታተልን ነው በማለት ተጨማሪ የቤት ሥራ ሰጥተዋቸዋል፣ ያቺ June 2 ደርሳ ማን ከኢትዮጵያዊያን ማን ከወያኔ እና ከቤተ ክርስቲያን ዘራፊዎች ጋር አንደሚወግን እንተዛዘባለን።
እነሆ ሀገር ወዳድ የሆንከው ኢትዮጵያዊ በሙሉ ይህችን ቤተ ክርስቲያን ከጥፋት ትታደጋት ዘንድ ጥሪያችንን ስናቀርብ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የወያኔን በስመ አባይ ቦንድ ሽያጭን (እዚህ ላይ ወገኔ እንድትገነዘብ የምንፈልገው ሀገር ብትለማ የሚጠላ ማንም እንደሌለ ልብ ይሏል፤ ይሁን እንጂ የሚሰበሰበው ገንዘብ የሚውለው ያንተኑ ወገን ለማፈናቀያ እና ለማሰቃያ እንጂ ለሀገር ልማት ቢውልማ ማን ይጠላ ነበረ!!!) በደቡብ አፍሪካ፣ ሒውስተን ቴክሳስ፣ ሳንዲያጎ ካሊፎርኒያ፣ በኖርዌይ ስታቫንጋር አሳፍረህ እንደመለስክ ዛሬም ይህንኑ እንድትደግም አንቢ ቤተ ክርስቲያኔን ለወያኔ መፈንጫ ገንዘቤን ወገኔን ለማፈኛ አሳልፌ አልሰጥም የምትል ሁላ June 2, 2013 በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን (4401 Minnehaha Ave S. Minneapolis MN) ተገኝተሽ/ህ ድምፅሽን\ህን እንድታሰሚ\ማ።
በመጨረሻም ከአንድ ድረ ገጽ ያገኘነውን ቀንጨብ አድርገን እናካፍላችሁ እና ፅሑፋችንን ለዛሬው በዚሁ እንግታ “ወያኔ መራሹ ዘረኛ መንግስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ለማጥፋት ኢላማውን ካነጣጠረ እነሆ 21 ዓመታትን አስቆጠረ። ወያኔ ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት በግልፅ የግድ ወታደር ማዝመት አይጠበቅበትም ለምን ቢባል ገና በደደቢት እያለ ያሰለጠናቸውን ልዩ ሃይል መነኩሴ በማስመሰል አሰልጥኖ በመላክ ተልዕኮውን እያሳካ ይገኛል” (ከጥላ መጽሔት http://www.ethiomedia.com/abc_text/tila_sixth_edition_2013.pdf)

For general knowledge please read the below article

http://www.ethiofreedom.com/tplf-is-appying-the-nazi-model-to-exterminate-the-amhara-people/

 

ሠላም ሠንብቱ የከርሞ ሰው ይበለን

ውበት ኢትዮጵያዊነት – ከሚኒያፖሊስ

የሰለማዊ ትግል ፋይዳ (ከአብርሃ ደስታ)

$
0
0

አብርሃ ደስታ

 

“ምንም ቢሆን ምንም (ለኩፉም ለ ደጉም) ወታደራዊ እርምጃ ተጠቅመህ ስልጣን መያዝ ለኣንድ ወገን ሃሴት ለሌላ ብሶት መሆኑ ኣይቀርም:: ጨቋኙ ደርግ ለሰላማዊ መንገድ ዕድል የሚሰጥ ቢሆን ነሮ ፤ ኣንድነታችን ማስጠበቅ ያልቻለ ኢህወዴግም የጦርነቱ ውጤት የሚያስከትለው ተረድቶ በሰላማዊ ትግል ጨቃኙ ስርዓት ለመጣል ቢችል ነሮ( በነገራችን ላይ ኢህወዴግ እንኳንስ ያኔ ኣሁንም በሰላማዊ ትግል ኣላሸነፈም፤ አረ የሚስበውም ኣይመስለኝም::) ይህ ሁሉ ብሶት ላይፈጠር እሰከዘለዘለሙ ሊያከትም ነበር::

ነገር ግን ለሰላማዊ ትግል ዕድል የማይሰጥ ሃይል መጠቀም ግድ ይላልና ጦርነቱን ኣፋፍመው እርሰ በራሳችን ኣፋጁን:: የተሸነፍነው እኛ ፤ ያሸነፈነው እኛ:: የሞትን እኛ፤ ያለን እኛ:: ጦርነቱ ኣባቶቻችን ና እናቶቻችን ኣሳጣን:: በዚህ ብቻ ኣላቆመም ኣንድነታችን ኣሳጣን:: ( የምን ኣንድነታችን ብቻ ፍቅራችን ጭምር እንጂ::) የጠበቅነው ኣሳጣን ( መብታችን፣ ፍተሃውነት ወዘተ) :: እና ኢህወዴግም በታራው ብሶት ኣሰረገዘን:: በዚህ ኣጋጣሚ እኔም እንደ ኣንድ መሰረታዊ ለውጥ ፈላጊ ስው ኣብራሃና መሰሎቹ የማድረጉት ጥረት ኣደንቃሉሁ::

ሰላማዊ ትግል ኣማራጭ የሌሎው መንገድ ነው ስንል ኢህወዴግን የመሰለ ድርጅት በሃል ኣናሸንፍም ብለን ፈርትን ሳይሆን ሃይል ለሃገርና ህዝብ ሊጠቅም እንደማይችል በማመን፤ እንዲያውም ኢህወዴግ በኛ ተቋዋሚ ፓርቲዎች ሊፈጥሩ የሚችል ኣደጋ እንደ ኪሳራ ሳናስብ ነው:: ገዢዎቻችን ኢህወዴጎች ደሞ በራሳቹ የሰላም መንገድ ኣትዝጉን:: ሰላማዊ ሰልፍ ይፈቀድ:: ተቋዋሚ ፓረቲዎች የልማት ኣጋሮች እንጂ ጠላቶች እንዳልሁኑ ክልብ እመኑ:: የተቋሚ ፓርቲዎች መንገድ ሲዜጋ የህዝብ መብት ና ፍላጎት መንፈግ መሆኑ የሚረዳ የሰከነ ኣስተሳሰብ ይኑርባቹ::

ለፖለቲካ ኣላማ የምትጠቀሙ ሃገር ና ህዝብ የማይጠቅሙ ከንታክንቱ ብልጣብልጥንት ኣቋርጡ:: ከሁሉም በላይ የልማት ቡድን የምትሉ ሽፋኑ ልማት ውስጡ ግን የፖሎቲቻ ካንሰር የሆነ ትስስር ( ፖለቲካዊ ቡድን ) መሆኑ ተከሽፋቹዋልና (ዋጋ እነዳያስከፍላቹ ብየ ነው) ኣሱቡበት::

ሰላማዊ ትግል የማይፈቅድ ሃይልን ለመጥቀም ያስገድዳልና ለሰላም ቅድሚያ እንስጥ!!!”

ሽሻይ ክንፈ ከፃፈው የተወሰደ

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live