Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በነኡስታዝ በድሩ ሁሴን ላይ የተፈጸመውን ግፍ ”በአፓርታይድ ጊዜ እንኳን ያልተፈጸመ”በማለት ዳኛው መኮነናቸው ታወቀ ‪

$
0
0

news(ቢቢኤን ራድዮ) የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በዛሬው እለት ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም ዳኞች አልተሟሉም በሚል ያልተካሄደ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ለሁለቱ ዳኞች ግን እየደረሰባቸው ያለውን ነገር አህመድ ሙስጠፋና ኡስታዝ በድሩ ሁሴን በዝርዝር ማስረዳታቸው ታዉቐል፡፡ ቁልፍ ባለው ሰንሰለት በጨለማ ክፍል እንዳሰሩዋቸው ምግብም እንደከለከሏቸው የገለጹ ሲሆን ዳኛውም ይህን ሲሰሙ እንዴት እንደዚህ ይደረጋል በዚህ ዘመን ቀርቶ በአፓርታይድ ጊዜ እንኳን አይፈጸምም ነበር በማለት መኮነናቸው ታዉቐል፡፡ ዳኛውም አያይዘው እንኳን በ21ኛው ክፍለ ዘመን ቀርቶ አስርቱ ትእዛዛት በሚፈጸሙበት ጊዜ እንኳን እንዲህ አይነት ነገሮች አይደረጉም ነበር ማለታቸው ታዉቋል፡፡
ኮሚቴዎቹም አሰቃቂ ስቃይ በሚፈጸምበት በማእከላዊ እንኳን የምግብ ክልከላ እንደማይፈጸምባቸው ተናግረዋል፡፡ ኡስታዝ በድሩ ሁሴን የታሰረበት ሰንሰለት ረዥም ጥልፍልፍ ሲሆን ዙርያ ጥምም በማሰር ቆልፈውበት እንደነበር ገልጾ ካቴናውም የተፈታለት ፍርድ ቤት ሊመጣ ሲል ከ85 ሰአታት እስር በሁላ እንደሆነ ገልጽዋል፡፡
ጠዋት ወደ ፍርድ ቤት ሊመጡ ሲሉ ኮሚቴዎቹ የበድሩ ሰንሰለት ሳይፈታ ይሂድ ለፍርድ ቤት ማሳየት እንፈልጋለን ብለው የነበረ ቢሆንም የማረሚያ ቤቱ ሃላፊ በግዳጅ ሰንሰለቱን ፈተው ወደ ፍርድ ቤት እንዲሄድ እንዳደረጉ ለመረዳት ተችሏል።

↧

↧

ዐማራው በመስዋዕትነቱ ባቆያት ኢትዮጵያ ለምን ዘሩ ከምድረ-ገፅ ይጥፋ?

$
0
0

moreshየትግሬ-ወያኔ መሪዎች እነ መለሰ ዜናዊ እና ስብሐት ነጋ ወደ ደደቢት በርሃ የገቡበት ዋና ምክንያት በዐማራው ህዝብ ላይ ካላቸው ፍራቻ እና ጥላቻ በመነጨ የበቀል ስሜት ነው። ይህንኑ በፖሊሲ የተነደፈ የበቀል ስሜት ከበረሃ ጀምረው በረቀቀ መንገድ እና በተቀናጀ ሥልት በተከታታይ ተግባራዊ በማድረግ ዐማራን ከኢትዮጵያ ምድር ለማጥፋት ሌት ተቀን ተግተው በመማሰን ላይ ናቸው። ነገር ግን ዐማራው በምን በደሉ እና ኃጢያቱ፣ በደም ዋጋ አንድነቷን ጠብቆ ካኖራት ውድ እናት አገሩ ፈጽሞ ይጥፋ? ለምን?

ለዚህ መነሻ የሚሆነው የትግሬ-ወያኔን መርኅ፣ የአባሎቹንም ማንነት ጠንቅቆ ማወቅ ሲቻል ነው። የትግሬ-ወያኔ ቡድን ጎጠኛ ትግሬዎች የመሠረቱት፣ ናዚያዊ እና ፋሽስታዊ ባሕርይዎች ያሉት ድርጅት ነው። በመሆኑም ኢትዮጵያን ለማፍረስ የኢትዮጵያዊነት መሠረት እና ምንጭ የሆኑ ተቋሞችን ለማጥፋት ይንቀሣቀሣል። የትግሬ-ወያኔ ዐማራውን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖትን ከሥር መሠረታቸው መንግሎ ለመጣል ፖሊሲ አውጥቶ ሌት ተቀን የጥፋት ዘመቻውን ያጧጧፈ የዐረመኔዎች እና የሠይጣን አማኞች ድርጅት ነው። የዚህ ቡድን እንቅስቃሴ በባሕርይው ከደቡብ አፍሪቃ የአፓርታይድ ሥርዓት አራማጆች እና ከጀርመኖቹ የናዚ ፓርቲ ጋር ተመሣሣይነት አለው። የጀርመኑ ናዚ ፓርቲ መርኃግብርም ሆነ የመሪዎች ጽኑ ምኞት በዘረኝነት እና በፀረ-አይሁዳዊነት የተሞላ ነበር። በትክክለኛ ቅጅም የትግሬ-ወያኔ ከመሠረቱ ሲታይ ፀረ-ዐማራ እና ፀረ-ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖት እንደሆነ በድርጅቱ ማኒፌስቶ ላይ በግልጽ ተቀምጧል። ስለሆነም በዛሬይቱ ስሟ በካርታ ላይ ብቻ በቀረው ኢትዮጵያ፣ ዐማራው በምን ደረጃ ለፈጽሞ ጥፋት እንደተጋለጠ ለማየት ያስችላል።   ( ሙሉውን ከዚህ ላይ ያንብቡ )

↧

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሚድሮክ ያቀረበውን የካርታ መምከን አቤቱታ ተቀበለ

$
0
0

•የአዲስ አበባ አስተዳደር የመከነው ካርታ እንዲመለስ አዘዘ

የአዲስ አበባ አስተዳደር ግንባታ ሳይካሄድባቸው ለዓመታት ታጥረው የተቀመጡ ሁለት ቦታዎች ካርታ ማምከኑን የተቃወመው ሚድሮክ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት ማግኘቱን ምንጮች ገለጹ፡፡

HMDAMUDIየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሚድሮክ ልማት ለማካሄድ ከዓመታት በፊት ተረክቦ ግንባታ ሳያካሂድ አጥሮ ያስቀመጣቸው ቦታዎች ያሉበትን ሁኔታ በከፍተኛ ባለሙያዎች አስጠንቶ ነበር፡፡ ባለሙያዎቹ በተለይ በልደታ ክፍለ ከተማ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ጎንና በየካ ክፍለ ከተማ በሻሌ ሆቴል አካባቢ የሚገኙት ቦታዎች ምንም ዓይነት ግንባታ ሳይካሄድባቸው ለዓመታት የተቀመጡ በመሆናቸው፣ ካርታቸው እንዲመክን የውሳኔ ሐሳብ አቅርቦ ነበር፡፡ የሁለቱ ቦታዎች ካርታ እንዲመክን የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ተቀባይነት በማግኘቱ ካርታዎቹ በክፍላተ ከተሞቹ መክነዋል፡፡ 

ነገር ግን ሚድሮክ በተወሰደው ዕርምጃ ደስተኛ ባለመሆኑ ምክንያት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቤት ብሏል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የቀረቡትን የሚድሮክ መቃወሚያ ሐሳቦች መቀበሉን የሚናገሩት ምንጮች፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር ያመከነውን ካርታ በድጋሚ እንዲሰጥ መመርያ ማስተላለፉን አስረድተዋል፡፡

ከፍተኛ ባለሙያዎች ተካተውበት የሚድሮክ 11 ቦታዎችን ያጠናው ኮሚቴ፣ ካርታቸው መክኖ የነበረባቸው ሁለቱ ቦታዎች ምንም ግንባታ እንዳልተካሄደባቸው አመልክቷል፡፡ ከእነዚህ ቦታዎች በተጨማሪ ለሸራተን ማስፋፊያ ከሦስት ዓመት በፊት ነዋሪዎች ተነስተው ነፃ የሆነው መሬትም ግንባታ እንዳልተጀመረበት ኮሚቴው በጥናቱ አመልክቷል፡፡ በተወሰነ ደረጃ ፒያሳ የሚገኘውና ካዛንቺስ አካባቢ የሚገኙት ቦታዎች መሠረት ለማውጣት የተወሰነ ሥራ መሠራቱንም የኮሚቴው ሪፖርት ጠቁሟል፡፡ 

በቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ የአስተዳደሩ ካቢኔ የማስተማሪያ ዕርምጃ ይወስዳል ተብሎ ሲጠበቅ፣ ሐሳቡን የሚቀለብስ ሥራ መሠራቱ አስገራሚ እንደሆነባቸው የአስተዳደሩ ሠራተኞች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 

ኮሚቴው ከሚድሮክ ቦታዎች በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማ 109 ቦታዎች ያለግንባታ ታጥረው ለዓመታት መቀመጣቸውንና ከእነዚህ ቦታዎች መካከል 56 ያህሉ ዕርምጃ እንዲወስድባቸው የውሳኔ ሐሳብ አቅርቧል፡፡ የውሳኔ ሐሳቡ ከቀረበ በርካታ ወራትን ቢያስቆጥርም ከብዙ መዘግየት በኋላ፣ የከንቲባ ድሪባ ኩማ ካቢኔ በዚህ ሳምንት በውሳኔ ሐሳቡ ላይ ተመሥርቶ የመጨረሻ መመርያ ለመስጠት ፕሮግራም መያዙ ታውቋል፡፡

Source: Ethiopian Reporter

↧

ፍትህ ሚ/ር በጋዜጠኞች ላይ የጀመረውን ዘመቻ ቀጠለ፤ አፍሮ ታይምስና ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው የክስ ቻርጅ ደረሳቸው (ክሱን ይዘነዋል)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ለአዲስ ጉዳይ መጽሔት አዘጋጆች መሰደድ ምክንያት የሆነው የፍትህ ሚ/ር ጋዜጠኞችን ሰዶ የማሳደድ ዘመቻ ቀጥሎ በትናንናው ዕለት ሎሚ መጽሔት እና ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ የክስ ቻርጅ የደረሳቸው መሆኑን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም። ዛሬ በደረሰን መረጃ መሰረት የአፍሮ ታይምስ ጋዜጣ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው ከፍትህ ሚ/ር የክስ ቻርጅ ደርሶታል።

ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው

ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው


የፍትህ ሚ\ር በጋዜጠኛውና በአፍሮ ታይምስ አሳታሚ ድርጅት ላይ የመሰረተው ክስ “የሃሰት ወሬዎችን በማሳተም ሕዝብን ለማነሳሳት በማሰብ ሕዝቡ በህገመንግታዊ ሥርዓቱ ላይ አመኔታ እንዳይኖረው፣ ጥርጣሬ እንዲገባው ለማድረግ በማሰብ” የሚል ነው። ጋዜጠኛ ቶማስ የቀረበበት ክስ በሚያዝያ 21 እና 22 2006 በወጣው አፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ላይ “ልዩ ሃይሎችና መከላከያ ሠራዊት ተፋጠዋል” በሚለው ዜና ሥር “ቀደም ባሉት ጊዜያት በጋምቤላ ክልል ሰፍሮ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት የፈለገውን ሰው ሲያስር፣ ሲገድል፣ ሴቶችን አስገድዶ ሲደፍር ቆይቷል። ይህም የሰራዊቱን ስርዓት አልበኝነትና ሕገወጥ ድርጊት ለማስቆም የሞከረ መንግስታዊ አካል አልነበረም።” በሚል በሰፈረው መረጃ ሲሆን ለዚህም ፍትህ ሚ/ር “አገሩንና ህገመንግስቱን በመጠበቅ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ሕብረተሰብና መንግስታት መልካም ስነምግባር እያከናወነ ያለውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሕዝቡ ዘንድ አመኔታ እንዲያጣ ጥርጣሬ እንዲገባው ለማድረግ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በፈጸሙ ሐሰተኛ ወሬዎችን በመንዛትና ሕዝብን በማነሳሳት ወንጀል ተከሰዋል” ሲል በክስ ቻርጁ ላይ አስፍሯል፡፡

በሃገር ውስጥ የሚታተሙ በርካታ መጽሔቶችን እና ጋዜጦችን እከሳለሁ ሲል የቆየው ፍትህ ሚ/ር ጋዜጠኞችን ለማፈን የሚያደርገውን ተንኮል ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሲተቹት እንደቆዩ ይታወሳል።

thomas ayalew 1

thomas ayalew 2

↧

ኤርትራ የሩሲያን የጦር ልምምድ ልታስተናግድ ነው

$
0
0

በመላኩ ጸጋው

በቅርቡ በተለያዩ አካባቢዎች ተከታታይ የጋራና የተናጠል የጦር ልምምድ ያደረገችውን ሩሲያን በቀጣይ በኤርትራ በቀይ ባህር አካባቢ ልታስተናግዳት መሆኑን “ጊሲካ አፍሪካ ኦንላይን” በአውሮፓ የሚገኙ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን ጠቅሶ ከሰሞኑ ባሰራጨው ዘገባ ገልጿል። የልምምዱ ዋነኛ ዓለማ በአንድ መልኩ የሩሲያን ጦር ዝግጁነት ለማረጋገጥ እንዲሁም በኤርትራ ወደቦች አቅራቢያ ሩሲያ ቋሚ የጦር ሰፈርን (Military base) ለማቋቋም መሆኑን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል። እንደ ዘገባው ከሆነ የሩሲያ የጦር ልምምድ በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።
news
ኤርትራ ከተወሰኑ ጊዜያት ወዲህ በሩስያ እንደ አንድ ስትራቴጂክ አጋር ሀገር እየታየች መሆኗን ዘገባው አመለክቷል። እንደዘገባው ከሆነ አሜሪካ በጅቡቲ ቋሚ የጦር ሰፈር ያላት ሲሆን በተለያዩ ጊዜያትም ከጅቡቲ ወታደሮች ጋር የአየር ኃይልና የባህር ኃይልን ባቀናጀ መልኩ የጦር ልምምድ ታደርጋች። ጅቡቲ የአሜሪካንን ጦር ከማስተናገድ ባለፈ በዋነኝነትም የፈረንሳይ የጦር ሰፈር በመሆን እያገለገለች ነው። ሱዳን በአንፃሩ ኢራን በቀይ ባህር የሱዳን ምዕራባዊ ግዛት የባህር ኃይል ቤዝ እንድትመሰርት ለማድረግ እንቅስቃሴ የጀመረች መሆኗን ቀደም ያሉ የዩናይት ፕሬስ ኢንተርናሽናል UPI ዘገባዎች ያመለክታሉ። ይህ የሱዳን እንቅስቃሴ ግን በእስራኤል አልተወደደም።

ሩሲያ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ አቅጣጫዎች ተከታታይ የጦር ልምምዶችን በማድረግ ላይ ትገኛለች። እንደ ዘጋርድያን ዘገባ ከቀናት በፊት ከሃያ ያላነሱ የጦር መርከቦችንና በርካታ ተዋጊ አውሮፕላኖችን ባሳተፈ መልኩ በደቡብ ምስራቅ አውሮፓ በሚገኘው ጥቁር ባህር ሰፊ የጦር ልምምድ አድርጋለች። ኢተር ታሰ የዜና ወኪል ባሰራጨው ዘገባም ከዚህም በተጨማሪ ሩስያ በተመሳሳይ መልኩ ከቻይና ጋር በጋራ በመሆን 18 የጦር መርከቦችን ባሳተፈ መልኩ በሻንጋይ አቅራቢያ በያዝነው አመት የጦር ልምምድ አድርጋለች። በሌላ አቅጣጫ ሩስያ ከቀናት በፊት አንድ መቶ ተዋጊ አውሮፕላኖችን ባሳተፈ መልኩ በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ጠንካራ የጦር ልምምድ ያደረገች መሆኑን ዘገባዎች ያመለክታል።

ኤርትራ አልሸባብን በሶማሊያ በማገዝ በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ በመግባት አካባቢያዊ ሰላምን እያወከች ነው በሚል በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በኩል ተከታታይ ማዕቀቦች ጥለውበታል። የቀድሞው የቡሽ አስተዳደርም ሆነ የኦባማ አስተዳደር ኤርትራን ሽብርን በሚደግፉ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ እንድትካተት ያደረጓት ሲሆን በቅርቡም በዋሽንግተን በተካሄደው የአሜሪካ አፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ከሮበርት ሙጋቤ እና ከአልበሽር ጋር ኢሳያስ አፈወርቂ በስብሰባው ላይ የሚታደሙበት ጥሪ ሳይደርሳቸው ቀርቷል።

ሩሲያ በአንጻሩ ከዩክሬን ጋር በተያያዘ ፖለቲካ ውዝግብ መግባቷን ተከትሎ በምዕራባውያኑ ሀገራት ተከታታይ ማዕቀብ የተጣለበት ሲሆን የሩሲያ መንግስት በአንፃሩ የአውሮፓና የአሜሪካ የግብርና ምርቶች ወደ ሀገሩ እንዳይገቡ እገዳን ጥሏል። የዩክሬኑን ውዝግብ ተከትሎ ሩሲያ ተከታታይ ወታደራዊ ልምምዶችን እያደረገች ሲሆን የቀይ ባህሩም የጦር ልምምድ የዚህ አካል ነው ተብሎ ይገመታል። ዘገባውን ያሰራጨው ጊሲካ አፍሪካ ኦንላይን የመረጃ ስርጭቱን በዋንኛነት በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሌላድ፣ ኬኒያ እና ኡጋንዳ ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራ የሚዲያ ተቋም ነው። በኢጋድ ዙሪያም ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ሰፋ ያሉ ዘገባዎችን ሲያሰራጭ ቆይቷል።

ዜናው የተገኘው ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ ከወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ ነው።

↧
↧

የትንሳኤ ጥሪ ለኢሕአፓ –ቁጥር 2

$
0
0

የትንሣኤ ጥሪ ነሀሴ 2006
ቁጥር 2

‘’we must accept finite disappointment, but never lose Infinite hope.”
MARTIN LUTHER KING JR

“በትግል መሞት ህይወት” ብለው የተነሱት የኢሕአፓ ልጆች አሁንም እንደትናንቱ የሕዝብን መብት፥ የሀገርን ሉአላዊነት እና ክብር ከማንኛዉም ነገር አብልጠው ይታገሉለታል። ይህንንም ሲያደርጉ በድርጂቱ በኢሕአፓ ውስጥ ያገኙትን ልምድ ለሕዝብ በማካፈል ሕዝብን የስልጣን ባለቤት ለማድረግ ነዉ።

በአሁኑ ወቅት ያለብንን ትልቅ ፈተና ለማለፍና ሕዝብን ለድል ለማብቃት በመጀመራያ ሀገርን ከሁሉም በላይ ማስቀደም፤ በውስጣችን ያለዉን መከፋፈል ማጥፋት፡የድርጅትን ህይወት ከግለሰቦች በላይ ማየት፤ ሌት ተቀን ጠንክሮ መስራትን፡ ብሎም ለራስ ጥቅም ተገዢ እለመሆንን ይጠይቃል። የኢሕአፓ መሪወችም ሆነ አባላት እንደማንኛዉም ታጋይ የድርጂታቸዉና የኢትዮዽያ ሕዝብ አገልጋዮች መሆናቸዉን በመገንዘብ ድርጂቱ በኢሕአፓነቱ ሳይሆን፣ ታጋዩ በታጋይነቱ ሳይሆን በመሪዎቹ ሥም ሲጠራና ሲክፋፈል በግዴለሽለት ከአዩት በታሪክ ፊት ይጠየቃሉ።
ውድ ወገኖቻችን በሚያዝያ ወር ትንሳዔ በሚል የመሰባሰቢያ ርእስ አንድ ጽሁፍ አውጥተን መበተናችን ይታወሳል ከዚህም ጽሁፍ ቦኋላ በአንዳንድ የዜና ማሰራጫዎች በመቅረብ የሰብስባችን አላማ ምን እንደሆነ ማብራሪያዎች ለመስጠት ሞክረናል ሆኖም አሁንም የተነሳንለትን ዓላማ እንደገና ማብራራት አስፈላጊ በመሆኑ ትንሳኤ ቁጥር ሁለትን አውጥተናል።
Tensaye
አላማችን አንድና አንድ ነው ይሄውም በኢትዬጵያ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶችን የሚያከብር ለህግ የሚገዛ በህዝብ ውክልና ያለው ስርአት እንዲገነባ ጠንካራ ትግል ማካሄድ ነው። ለዚህ ትግል በቆራጥነታቸው የተመሰከረላቸውና ከፍተኛ ልምድ ያላቸውን የኢህአፓ ልጆች እንደገና ማሰባሰብ ከፍተኛ ጥቅም ይኖረዋል ብለን እናምናለን። ቅሬታዎቻችንና እና ልዩነታቸውን አስወግደን ስርዓት በአለው መልክ በዴሞክራሲያዊ አሰራር ድርጅታችን አጠናክረን ብንወጣ ትግሉን ለውጤት ለማብቃት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
የትንሳኤ ንቅናቄ ጥረት አንድና ጠንካራ ኢህአፓ እንዲኖር ነው፤ በኢህአፓ ውስጥ የደረሰው መከፋፈል መሰረታዊ በሆኑ የመርህ ልዩነቶች የመጣ ሳይሆን ጓዶች በሰከነ መንፈስ በመግባባትና እንደቀድሞው በመተማመን ባለመወያየታቸው የተፈጠረ ችግር ነው ብለን እናምናለን። ስለዚህ መሰረታዊ ልዩነት በኢህአፓ ታጋዮች ማህል የለም እያልን አስታራቂ ሆነን መቅረብ አንችልም እኛም እራሳችን የሂደቱ አካል ነንና።

ይህ የአንድነት እንቅስቃሴ ሁሉንም የኢህአፓ ልጆች በማሰባሰብ ጠንካራ የሃገርና የህዝብ ሃይል እንዲሆኑ የማድረግ ጥረት በመሆኑ በትግሉ ውስጥ ያለፋችሁ ሃይሎች ሁሉ የኔ ጉዳይ ነው ብላችሁ ልትሳተፉበት ይገባል። ይህ ጥሪ ሀገራችን የገጠማት ችግር እንዲወገድላትና የሰላም፤ የፍትህ፤ የእኩልነትና የብልጽግና ሃገር እንድትሆን ለሚመኙ ወገኖች ሁሉ የሚቀርብ ጥሪ ነው። እንደገና እንዳንሰባሰብ ተጠናክረንም እንዳንወጣ ያልሆነ ቀለም የሚቀቡ ግለሰቦች ካሉ እባካችሁን ወደ ህሊናችሁ ተመለሱ ሁላችንም የምንኮራባቸው የተሰውት ጔዶች አጽም እና ደም ይፋረደናል እንላቸዋለን።
የኢሕአፓ መዳከምና መከፋፈል ለዘረኞችና ለጎጠኞች የልብ ልብ ሰጥቷል። ጠባቡም የወያኔ በድን ኢትዮጲያን እንደዘመነ መሳፍንት በጎሳና በጎጥ ከፋፍሎ ለማጥፋት ታጋዮችን ያስራል፡ይገድላል፡ይደበድባል፡ያሳድዳል፡ሲያስፈልግም ከጎረቤት አገሮች ጋር በመመሳጠር በማንአለብኝነት እስሮ ይወስዳል። ከዚህ በፊት ሱዳን በነበሩ ታጋዮች ላይ ያደረገውን በቅርቡ የመን ላይ በአቶ አንንዳርጋቸዉ ጽጌ ላይ አድርጎታል። የኢሕአፓ ልጆች ከተመክሮ እንደተማርነዉ አንድ ታጋይ መሰዋእትነት ሲከፍል በሺ ታጋዮች እንደሚተካ ስለምናውቅ የብዙሀን ድል ይገኛል በቆራጥ ትገል እያልን ድርጊቱንም በጥብቅ እናወግዛለን። እንዲያዉ ነገርን ነገር ያነሰዋልና በአረመኔዉ የደርግ መንግስት የታጋይ ጓዶቻችን እሬሳ መንገድ ላይ ዘርረዉ የዝንብ መጫወቻ ያደረጉትን ታላቁን ታጋይ ዮወሴፍ አዳነን አይኑን እየሸነቆሩ ቁዋንጃዉን እየቆረጡ የገደሉትን የፋሺስቱን ደርግ አባሎች ህይወት ወያኔ ሲያተርፍ ህይወታቸዉን በሙሉ ለህዝብ ሥልጣን ባለቤትነት እና ለዴሞክራሲ ሲታገሉ ሲወድቁ ሲነሱ የቆዩት ታጋዮች እነፀጋዬ ገ/መድህንን(ደብተራዉ)፡ እነ አበራሺ በርታን፡ እነ ስጦታዉ ሁሴንን ,,,ወዘተ የት እንዳደረሳቸዉ እስከ አሁን እንኩዋን አናዉቅም። ወያኔና የወያኔ መሪወችም ይህን ሚስጥር እንደያዙ አንዳንዶቹ እየሞቱ ቢሆንም ቀሪዎቹ ነገ በህዝብና በህግ ፊት ይጠየቁበታል።

አዎን የኢሕአፓ ጀግኖች ሙሾ ተወርዶላቸዉ፡ ደረት ተመቶላቸዉ፡ የስርዓተ ቀብር ተደርጎላቸዉ ባያዉቅም ያሞራ ቀለብ የዝንብ መጫወቻ ቢሆኑም፡ሰልፋቸዉ ከህዝብ ጋር ነዉና ሕዝብ ሲያሸንፍ ያን ግዜ ያን ቀን ታሪካቸዉ ይዘከራል። አሁንም ቢሆን ቀሪዉና ቀጣዩ ትዉልድ ሰንደቃቸዉን አንስቶ፡ መፈክራቸዉን አንግቦ በመታገል ከዓለሙት እና ከተሰዉለት ግብ ይደርሳል። በሕዝብ ሀይል የሚያምን ሁሉ ይህን አይጠራጠርም።ለዚህ ነዉ ትንሥኤ ኑ በቤታችን እንሰባሰብ ኑ እንታገል የትግላችን ጉዞ እንደ ኩሬ ዉሀ አንድ ቦታ ላይ ተገድቦ መንቀሳቀስ አልቻለምና መፍትሄ እንፈልግለት እያለ ጥሪውን የሚያቀርብ።
መሪነት ታላቅ ሀላፊነት እንደመሆኑ መጠን እንደ ሺልማት የሚሰጥ ገፀ በረከት አይደለም።ታግሎ ማታገልን ቀድሞ መገኛትን ከቂም ነጻ ሆኖ አርቆ አስተዋይነትን ይጠይቃል። “ከሊቀመንበር መንግሥቱ ጋር ወደፌት” ያሉትን ወይም በሙት መለስ “ራዕይ” የሚመሩትን ስናወግዝ ወደ ራሳችንም ዘወር ብለን እራሳችን ልንፈትሽ ይገባል። ከዚህ አንጻር በየትኛውም እርከን የታገላችሁና በመታገል ላይ ያላችሁ ጔዶች ሃላፊነታችሁን በአግባቡ እንድትወጡ አጥብቀን እንጠይቃለን።

ከዚህም ባሻገር የትንሥኤ ቡድን ህልም ኢሕአፓን አጠናክሮ ማውጣት ብቻ ሳይሆን ድርጂቱ እሱን ከመሳሰሉ ጠንካራ ድርጂቶች ጋር በመቀናጀት የጋራ ትግል እንዲያደርግም ይገፋፋል።ወቅቱ በጋራ መሥራትን አጥብቆ ይጠይቃልና።ሕዝቡም “ተባበሩ ወይም ተሰባበሩ” የሚለውን ጥሪ አሁንም እያቀረበ ነው፤ ለሕዝብ የሚሰራ ሁሉ የሕዝብን ድምፅ መስማት አለበት።በህዝብ ያልታቀፈና የሕዝብን ቃል የማያከብር ድርጂት ብቻዉን እነደቆመ ግንድ ነዉ። የሳለ መጥረቢያ በቀላሉ ይቆርጠዋል ለሕዝብ ለመቆም የሕዝብን ድምፅ መስማት፡የሕዝብን ፍላጎት ማወቅ፡ ያንንም ተግባራዊ ማድረግን ይጠይቃል። ያለሕዝብ ድጋፍ ድርጂት ሊኖር አይችልም።ድጋፉን የሚሰጥ ሕዝብ ድምፁን የማሰማት መብት አለዉ የድርጂት መሪወች ይህንን ተገንዝበዉ መተባባር አለባቸዉ እልህ ግትርነትና በድርጅት ውስጥ ለራስ ከፍተኛ ቦታ መስጠት የተከፈለውን መስዋእትነት ያበላሻል። ልዩነትን በነጻ መድረክ ተወያይቶ መፍታት የግድ ባህልና የውዴታ ግዴታ መሆን አለበት። አባላትም መሪዎቻቸውን መከታተል የድርጅታቸውን ፖሊሲ መመርመር ልዩነትን ከማራገብ ይልቅ አንድነትን ማጠናከር ይኖርባቸዋል። በዚህ ዙሪያ ያሉትን ድክመቶቻችን ካስወገድን ኢህአፓን በማጠናከር ተባብሮ በመስራት የሕዝብን ትግል ከግብ ማድስ እንችላለን ብለን እናምናለን።

ለዚህም የተቀደሰ አላማ ኢህአፓ የከፈለውን መስዋእትነት የምናከብር በኢሕአፓ ዙሪያ እንደገና ለመሰባሰብና ኢህአፓን አጠናክሮ እንደቀድሞዉ ቆራጥና የተባበረ ትግል ለማካሄድ ለምትፈልጉ ሁሉ የትንሥኤ ቡድን በድጋሚ ጥሪዉን ያቀርባል። ይህንም እንቅስቃሴ ተካፋይ ለመሆን የምትፈልጉ ሁሉ በነዚህ ኢሜል አድራሻወች ልትገናኙን ትችላላችሁ

TINSAE64@GMAIL.COM
ስለ ሀገር ፍቅራችሁ እና ቅን አመለካከታችሁ አስቀድመን እናመሰግናለን
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

↧

2007ን ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ ሲባል እስከ ምርጫ ወይስ እስከ ዴሞክራሲያዊ መንግስት (ዳንኤል ተፈራ)

$
0
0

ዳንኤል ተፈራ

ዳንኤል ተፈራ — የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ

ዳንኤል ተፈራ — የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ

በጣም በቅርቡ አንድ ስላልነገርኩት ስሙን የማልጠቅሰው ጉምቱ የሚባል ጋዜጠኛ ወዳጄና ሌላ አንድ ጎልማሳ ጋር ኢ-ወጋዊ በሆነ መንገድ ስለተቃዋሚ ጎራው ማውጋት ይዘናል፡፡ የጨዋታችን መነሻ ደግሞ አንድነትና መኢአድ ከብዙ ውጣ ውረድና ድርድር በኋላ ከፍፃሜ ለማድረስ ደፋ ቀና እያሉበት ያለው ውህደት ነው፡፡ የተቃውሞ ፖለቲካውን በቅርበት እንደሚከታተሉ አንዳንድ ግለሰቦች አስተያየት ‹‹ውህደቱ መሳካት አዎንታዊ ጎን ቢኖረውም ዘግይቷል፡፡ በዚህ ጊዜ የውህደቱ ጣጣ አልቆ፣ የሚተባበሩት ተባብረው ወደ ሰፊ ህዝባዊ ንቅናቄ የሚገቡበት ነበር›› ይላሉ፡፡ የውህደቱ መሳካት ጥሩ ሆኖ ውህደቱም ሆነ ትብብሩ ዘለቄታ ላለው ዴሞክራሲያዊ ለውጥ ለማምጣት ወይስ ምርጫ ስለደረሰ ብቻ? የሚል ጥያቄ አንስቶ መመለስ ተገቢ ነው፡፡

ጎልማሳው ሰው ቀበል አድርጎ ለተቃዋሚው ጎራ ቅርበት አለው ብሎ ስላመነ ይመስለኛል አይኖቹን እንደ ቆመህ ጠብቀኝ መሳሪያ ፊቴ ላይ ወድሮ ‹‹በተቃውሞ ጎራው በኩል ተቀራርቦ፣ ተባብሮና ተዋህዶ የመስራቱ ነገር እምብዛም ባለመለመዱ ወይም እስካሁን ባለመሳካቱ ይመስለኛል ውህደት እንዳንድ አደረጃጀትን የሚያጠነክር የፖለቲካ ስራ ሳይሆን እንደግብ ይታያል፡፡ ከፖለቲካ ጠቀሜታ አንፃር ሳይሆን ከምርጫ፣ ከግል ጥቅምና ዝና አንፃር ይታል፡፡ ውህደት እንዳንድ የለውጥ ማምጫ ስትራቴጅ ባለመታየቱ በህዝቡ ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ ነው፡፡ መጠላለፍና ሴራ በብርቱ የሚያጠቃው የፖለቲካ ባህላችን ግን ‹‹እኔ ብቻ አዋቂ፣ እኔ ብቻ ንጉስ›› ከሚል ጨፍላቂ ሰርዓት ጋር ሲደመር ግራ ማጋባቱ ላይገርም ይችላል፡፡ በአጠቃላም የተቃውሞ ጎራውን ከአሮጌና ምርጫን ግብ ካደረገ አስተሳሰብ አላቅቀው የራሱ መነሻና መድረሻ ያለው ስትራቴጅ የሚነድፉ መሪዎች ያስፈልጉታል›› አለ፡፡

ጎልማሳው ሁለታችንም ዝም ብለን የልቋጨውን ሀሳብ እንዲጨርስ እየጠበቅነው እንደሆነ ሲረዳ፡- ‹‹ለነገሩ መምራት የሚችሉ ግለሰቦች ለመምጣት ቢሞክሩም በጥርጣሬና በሴራ ፖለቲካ ተስተካካይ የሌላቸው ግለሰቦች እንዲርቁ ያደርጓቸዋል፡፡ ከነሱ ተረፉትን ደግሞ ኢህአዴግ ‹‹አሸባሪ›› ብሎ ያስራል፡፡ ስለዚህ ውህደት ብቻ ሳይሆን ውህደቱን የሚመራ ጥብቅ መሪ ያስፈልጋል፡፡ ምርጫ ሞክሮ የሚሄድ ሳይሆን ከምርጫ ባሻገርም ለውጥ የሚመጣበትን መንገድ የሚቀይስ ብርቱ ሰው›› በማለት ሃሳቡን ጠቀለለ፡፡

ያነሳው ሃሳብ ጥቅል ቢሁንም ለውይይታችን ማጠናከሪያ መሆኑ አልቀረም፡፡ የጨዋታችንም ጭብጥ ሰፋና የተለያዩ ጋዜጦች ላይ ስለተቃዋሚው የሚፃፉትን አሉታዊ ትንታኔዎችን እያነሳን ነበር፡፡ የተቃዋሚ ጎራው መተቸት አለበት ወይስ የለበትም፤ ትችቱ ምን አይነት ቢሆን ለሀገር ይጠቅማል፤ ገዥው ፓርቲ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ምን አይነት ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል፤ ለምን? የሚሉ ጉዳዮችም ተነሱ፡፡ መቼስ ተቃዋሚው መተቸት የለበትም የሚል ድምዳሜ ላይ መድረስ አይቻልም፡፡ ኢህአዴግ ካቴና ይዞ የሚመጣው ‹‹ለምን ነካችሁኝ፤ ለምን ተቻችሁኝ›› ብሎ አይደል እንዴ? ታዲያ እንዴት አሁን ካለው ስርዓት የተሻለ ሀገር መምራት እችላለሁ ብሎ እየታገለ ያለውን ተቃዋሚ አይነካ ማለት ይቻላል? እያልን ስናነሳ ጋዜጠኛው ወዳጄ የተቃውሞ ጎራ አሁን ባለበት አቋም የሚያስፈልገው ገንቢ ትችት ነው የሚል ነገር ዱብ አደረገ፡፡ በድማሜ ውስጥ ሆኜ ‹‹ለምን?›› የምትል ቤሳ ጥያቄ ማቅረቤ አልቀረም፡፡ እሱም እንዲህ መለሰልኝ፡፡

‹‹አየህ ተቃዋሚው ባጠቃላይ ከአፈጣጠሩ በርካታ ችግሮች ያሉበት ነው፡፡ ኢህአዴግ የሚፈጥረው ችግር ደግሞ ብዙ ነው፡፡ ለባለፉት 23 ዓመታት ተቃዋሚው በተበታተነ አሰላለፍ፣ ምርጫን ብቻ ግብ አድርጎ ቆይቷል፡፡ ይህ አሰላለፍም ዘላቂነት ላለው ድልና የማይናድ የተቃዋሚ ግንብ ለመገንባት አላስቻለውም፡፡ ግልፅ ራዕይና ስትራቴጅ በማስቀመጥ፣ ተተኪ ፖለቲከኞችን በማፍራትና በውስጡ ተሰግስገው እንደ አሜባ የሚራቡትን ሰርጎ ገቦች ማጥራት አልቻለም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ኢህአዴግ ‹‹ተቃዋሚዎች እግር እስከሚያወጡ መጠበቅ ተገቢ አይደለም›› በሚለው የተበላሸ አመለካት የተነሳ ከፍተኛ ወጭ መድቦ ተቃዋሚ ጎራውን በአይነ ቁራኛ ይጠብቃል፡፡ ከተራ ስም ማጥፋትና በውስጥ ክፍፍል ለመፍጥር ከመስራት ጀምሮ እስከ ‹‹ሽብርተኛ›› ብሎ እስከማሰር የደረሰ መዋቅር ዘርግቷል፡፡ ስለዚህ አሁን መሆን ያለበት ተቃዋሚውን ሃይል መተቸት ሳይሆን  መደገፍ ነው፡፡ በህጋዊ መንገድ ተመዝግቦ፣ በሰላማዊ ትግል አምኖ እየታገለ ያለን ሃይል እንደ ጠላት የሚቆጥር መንግስት ባለበት ሀገር፤ ተቃዋሚው የስብሰባ አዳራሽ፣ የሚከራይ ቢሮ ለማግኘት በሚቸገርበት ሁኔታ፤ አባሎቹን እየተከታሉ ‹‹ወይ ከስራህ አሊያም ከተቃውሞህ አንዱን ምረጥ›› በሚባልበት ስርዓት ውስጥ ቀዳሚው ነገር ተቃዋሚውን መተቸት ሳይሆን ተቃዋሚው እግር እንዲያወጣ ማገዝ ነው፡፡ እግር አውጥቶ የቡጢ ሚዛኑ ሲስተካከል ግን ገንቢ ትችት ብቻ ሳይሆን አሁን ኢህአዴግ በሚተችበት ደረጃ መተቸት ነው›› የሚል ትንሽ ትንታኔ አቀረበ፡፡

በርግጥ በጋዜጠኛው ወዳጄ በጎ ሃሳብ የሚስማሙም የማይስማሙም ይኖራሉ፡፡ አንዳንዶች መጠንከርም ሆነ መልፈስፈስ የተቃዋሚው የራሱ ምርጫ ነው የሚሉ አጋጥመውኛል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ተቃዋሚው ጠንካራም ሆነ የተልፈሰፈሰ እንዲሆን የሚያደርገው ህዝቡ ሊሆን ይገባል የሚሉም አሉ፡፡ የፖለቲካ ፓርቲ የሚቋቋመው ለህዝብና ለሀገር አገለግላለሁ ተብሎ ነው ስለዚህ ባለድርሻው ህዝብ ከሆነ ጠንካራ ለሚለው ድጋፍ በመስጠትና በአጉል አቅጣጫ ለሚነጉደው ትብብር በመንፈግ ለተቃዋሚው አቅም ሊፈጥር ይችላል፡፡ እኔም አዳምጨ ሳበቃ ይህንን ሃሳብ ተመርኩዤ የራሴን ምልከታ ለመሰንዘር ወደድሁ፡፡

‹‹ጋንግስተሪዝም››

አስቀድሞ ትውስ ያለኝ ጋንግስተሪዝም ነው፡፡ ለሀሳቤ መነሻ ሆነኝ ጋዜጠኛ ዮናስ በላይ በቅርቡ ያሳተመው ‹‹የትግራይ ሕዝብ፤ ወያኔዎቹና ሽፍቶቹ›› የሚለው መፅሀፍ ነው፡፡በመፅሐፉ በ1993 ህወሃት ለሁለት ስትሰነጠቅ መሰረታዊ ልዩነቶች ምን እንደነበሩ ስብሃትን ጠይቋቸው ሁለት ነገር አስቀምጠዋል፡፡ በተለይም በኤርትራ ጉዳይ አንደኛው እነ ስየ መለስን ‹‹ተንበርካኪ ሆናችኋል›› የሚል ሲሆን የነ መለስ ቡድን በበኩሉ በመልሶ ማጥቃት ተንበርካኪነትን ባለመቀበል ዴሞክራሲያዊ አመለካከት ጠፍቷል ‹‹ጋንግስተሪዝም›› እያደገ ነው በማለት ለመመከት ተገድደዋል፡፡ የፖለቲካ ጉዳይ ስለሆነ እንጅ እነ መለስ ለዴሞክራሲ ተጨንቀው እንዳልሆነ አሁን ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ምስክር ነው፡፡ ጋንግስተሪዝም በተገላቢጦሽ በክፍፍሉ አሸናፊ ሆኖ የወጣው የነ መለስ ቡድን መለያ መሆኑ ፈገግ ያሰኛል፡፡

ጋንግስተሪዝም (ቦዘኔነት) ዋናው የተቃዋሚ ጎራ ችግርም ነው፡፡ ቦዘኔዎች ዋና ተግባራቸው ስራ መስራት አይደለም የሚሰሩትን እየተተከተሉ ማጥቃት እንጅ፡፡ አሁን ያለው ወጣት ትውልድ ግን ከጋንግስተሪዝም ይልቅ ዴሞክራሲ ልዩ መለያው እንደሆነ መመስከር ይገባኛል፡፡ ጋንግስተሪዝም በዋናነት የአባቶቻችን ትውልድ መለያ ነው ብሎ መከራከር ይቻላል፡፡ የሃሳብ ልዩነትን በውይይት ከመፍታት ይልቅ ማጥፋት የተለመደ ነው፡፡ በተቃዋሚው ጎራም አባራሪና ተባራሪ አለ፡፡ ‹‹የተቃዋሚዎች እናት አንድ ናት›› እንዲል አስራት አብርሃም በቅርቡ እንኳን ታዋቂውን ፀሃፊና ፖለቲከኛ አስገደንና ሌሎችን አረና አባሯል፡፡ አረና ወደ ማባረሩ የገባው ሌላው በአጭር ጊዜ በፖለቲካ ስራውና በሚያቀርባቸው ፅሁፎቹ እውቅና ያተረፈው አብርሃ ደስታ ከታሰረ በኋላ ነው፡፡ ታዲያ የተያዘው ማጠናከር ወይስ ማላላት? ፕሮፌሰር እንዳሉት የስላሴዎች እርግማን ይሆንን? አደህይቶ መግዛት፤ አጎሳቁሎ ተስፋ ማሳጣት፤ ባዶ ማድረግ፡፡ ጋንግስተሪዝም፡፡ ይሄ የትውልድ ውልቃት መጠገን አለበት፡፡ ቅድሚያ ለውጥ ፈላጊነት ጋንግስተሪዝምን ማሸነፍ አለበት፡፡

በመቀጠል የተቃውሞ ጎራው ከተከላካይነትና ከተጠቂነት ወደ አጥቂነት የሚሸጋግርበትን የፖለቲካ ስትራቴጂ የሚነድፍ መሪ ያፈልገዋል፡፡ ትግሉን ከምርጫ ፖለቲካ በላይ አሻግሮ የሚመለከትና የኢህአዴጋውያኑን የጠቅላይ አምባገነንነት አባዜ ተረድቶ የመስበሪያ ስልት የሚቀይስ የፖለቲካ ማሃንዲስ መፍጠር ይገባል፡፡ የተቃውሞ ጎራው እስካሁን በመጣበት መንገድ ከፍተኛ መስዋዕትነት ተከፍሎበታል፡፡ አሁንም ስለለውጥ ከፍተኛ ዋጋ ዕየተከፈለ ነው፡፡ ነገ ትልቅ መሪ የሚሆኑ የኢትዮጵያችን ተስፋዎች ጨለማ ክፍል ውስጥ ተጥለዋል፡፡ እነ አንዷለም አራጌ፣ ኦልባ፣ በቀለ ገርባ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ናትናኤል መኮንን፣ የሽዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ፣ ዳንኤል ሺበሺና ሌሎች በፖለቲካ እምነታቸው ብቻ ወደ ጨለማ ክፍል የተወሰዱ ዜጎች የከፈሉት ዋጋ ፍሬው መታየት አለበት፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ደግሞ ምርጫ ስለደረሰ ብቻ ሱፋቸውን አሳምረውና ጫማቸውን ወልውለው ከተቻለ ፓርላማ፤ ካልተቻለ ደግሞ ሌላ አምስት አመት እስከሚመጣ እቤታቸው በሚቀመጡ ፖለቲከኞች አይደለም፡፡ ለውጡ ሊመጣ የሚችለው ያለ ፋታ በሚሰሩ ለውጥ ፈላጊ ሃይሎች እንጅ፡፡

ጋንግስተሪዝምን (ቦዘኔነትን) አሸንፎ ምርጫ ካለና በአግባቡ ከተጠቀሙበት የለውጥ ማምጫ መሳሪያ ነው፡፡ አሁን ያለው ገዥ ፓርቲ ፍትሃዊ ምርጫ ለማካሄድ ቁርጠኝነቱ አለው ተብሎ አይገመትም፡፡ ነገርግን የተቃዋሚው ስራስ ምን መሆን አለበት? አፋኝነቱን ከመተንተን ያለፈ የማስገደድ ሃይል ያለው ጡንቻ ያስፈልገዋል፡፡ በምርጫው መሳተፍ ይገባል ወይስ አይገባም፤ ብንሳተፍ ምን ምቹ ሁኔታዎች አሉ፤ ምን ተግዳሮቶች አሉ፤ በአማካይ ስንት ወንበር አሸንፈን ስልጣን መያዝ እንችላለን፤ ምርጫው ኢፍትሃዊ እንዳይሆን ምን ምን ርምጃዎች መወሰድ አለባቸው፤ ህዝቡን የማንቂያ ስትራቴጅዎች፣ ህዝባዊ ንቅናቄ የመፍጠሪያ ስልቶች፣ የችግር አፈታት ስልቶችና የታሰሩ አመራሮች ለምርጫው ያላቸው አጋርነት መፈተሽ ይገባል፡፡

በአመራር ደረጃም በምርጫው ተቃዋሚ ጎራው ሞካሪና አዳማቂ ሆኖ ሳይሆን አሸናፊ ሆኖ የሚወጣበትን ስትራቴጅ የሚነድፉ፤ የተነደፈውን ስልት ወደ ውጤት የሚቀይሩ የኦፕሬሽን ሰዎች፤ ይህንን የሚደግፉና የሚያሰርፁ አባላት በብዛት ያስፈልጋሉ፡፡ የዚህ ፅሁፍ አቅራቢዎ አንደታዘበው ግን በተቃውሞ ጎራው ስለ ግልፅ የማሸነፊያ ስትራቴጅና ስለ ስልት እምብዛም አይወራም፡፡ ሕዝቡ ካለበት የኑሮ ጫና፣ የነፃነት እጦትና የስርዓቱ ሹማምንት ከሚያደርሱበት ምሬት አንፃር የተቃውሞ ጎራውን በስፋት ይደግፋልና ይመርጣል የሚለውን ግምት በተግባር መፈተሽና በአግባቡ የዚህን የተገፋ ህዝብ ይሁንታ የሚያገኙበትን ተክለ ቁመና መፍጠር ያስፈልጋል፡፡

ዞሮ ዞሮ ከላይ ለመግለፅ በሞከርኩት መንገድ የተቃውሞ ጎራው ከውህደት ባሻገር ከአመራር አንፃርና አጠቃላይ ትግሉ ያለበትን ነባራዊ ሁናቴ ፈትሾ፤ የሚፈለገውን ቁርጠኝነት አሳይቶ ለውጥ ከማምጣት አንፃር መሰራት እንዳበት አንስተን የኢ-ወጋዊ ውይይታችን ማጠቃለያ የሆነው በሚቀጥለው ዓመት ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው ሃገራቀፍ ምርጫ ነበር፡፡ (በነገራችን ላይ ምርጫ፣ ምርጫ ስል ምርጫ አለ እንዴ! በ2002 ምርጫ ተደርጎ ነበር እንዴ! በማለት ታማኝነትን ያተረፈ ምርጫ ካልተደረገ እንደተደረገ አይቆጠርም በማለት ጠንከር ያለ መከራከሪያ የሚያቀርቡ እንዳሉ ሳይዘነጋ ማለት ነው) በአንፃራዊነት ጠንካራ የሚባሉ ፓርቲዎች 2007ን እንዴትና ለምን ግብ ሊጠቀሙበት እያሰቡ ነው? ምርጫውን ለመሞከር ወይስ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ ላለው ዴሞክራሲያዊ ለውጥ ለማምጣት? የሚለው ዋና ጥያቄ ነው፡፡

የምርጫ ጊዜ ወፎች

ከጋንግስተሪዝም ለጥቆ የሚመጣው የምርጫ ግርግር ፈጣሪው ነው፡፡ ስለ ሰላማዊ ትግል ስናስብ ስለ ውጤትም ማሰብ ይገባል፡፡ ኢህአዴግን ብቻ ሳይሆን እንደ መስቀል ወፍ ምርጫና የምርጫ ወሬ ሲሰማ የሚሉትን የምርጫ ጊዜ ወፎች መታገል ይገባል፡፡ የነዚህ ወፎች ግብ ከላይ እንደገለፅኩት ዘለቄታዊ ለውጥ በማምጣት የሚፈለገውን ዴሞክራሲ መገንባት አይደለም፡፡ ዘላቂነት ያለው የለውጥ ስሜትም ሆነ ስትራቴጅ ስለሌላቸው በምርጫ ጊዜ ብቻ ብቅ ይሉና ‹‹ሲያቃጥል በማንኪያ ከበረደ በእጅ›› የምትል የጮሌ ስትራቴጅ በመያዝ ምርቻ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉት ናቸው፡፡ እነዚህ ሃይሎች ካራባት በማሳመር ምርጫ ማሸነፍ ይቻል ይመስል ‹‹የ2007ን ምርጫማ መሞከር አለብን›› ይላሉ፡፡ መሞከር ብሎ ትግል፡፡ ሰው የሚወዳደረው ለመሞከር ሳይሆን ለማሸነፍ ነው፡፡ የምርጫ ጊዜ ወፎች ግን ‹‹ኸረ እባካችሁ ህዝብና ሃገር መሞከሪያ አይደለም፤ ኢህአዴግ በዚህ ጭቁን ህዝብ ላይ የሞከረበት ይበቃል፤ ዘላቂነት ያለው ስትራቴጅና ራዕይ ካላችሁ ወዲህ በሉ›› ሲባሉ ያኮርፋሉ፡፡ ይፈርጃሉ፡፡ ያችኑ የሚውቋትን የሴራ ጨዋታ ከች ያደርጓታል፡፡ ያ የፈረደበት ምርጫ 97 ይጠቀስና ‹‹ስንት ዋጋ ከፍለን፤ ደማችን ፈስሶ አጥንታችን ተከስክሶ…›› የምትል ‹ፉከራ› በማምጣት ጉዞ ወደ ምርጫ ሙከራ ይሆናል፡፡

ዋናው ቁምነገር የተከፈለውን ዋጋ ለማሳነስ አይደለም፡፡ በ97 ደግሞ የስርዓቱን አስከፊ ገፈት ያልቀመሰና ዋጋ ያልከፈለ የለም፡፡ ዳሩ ግን ከታሪክ መማር እንጅ በታሪክ መኖር አይቻልም፡፡ በታሪክ መኩራት እንጅ በታሪክ ማሸነፍ አይቻልም፡፡ ማሸነፍ የሚቻለው ዛሬ ላይ አቅዶ፣ እቅዱን ወደ ተግባር ለውጦ፣ ህዝቡን አሳትፎ መጓዝ ሲቻል ነው፡፡

አንድነትና መኢአድ ጀምረውታል፡፡ ቢያንስ የሁለቱን ትላልቅ ፓርቲዎች ሃይል በአንድ መስመር ማስገባት የሚቻልበት ታሪካዊ ስራ ነው፡፡ ግን በቂ አይደለም፡፡ አሁንም ዳርላይ የቆሙ ፓርቲዎች አሉ፡፡ የተናጠሉ ጉዞ አያዋጣም እየተባለ ነው፡፡ 2007ን በአግባቡ ለመጠቀም የተሰባሰበ አንድ የተቃውሞ ሃይል መፍጠር አንዱ ነው፡፡ ለዚህ ትልቅ የተቃውሞ ሃይል የሚመጥንና ወደ ፊት የሚያራምድ አመራርም ያፈልገዋል፡፡ የምርጫ ጊዜ ወፎች ምርጫ መግባትን እንደ ግብ ስለሚያዩ ከተቻለ ትግሉ ምርጫ የመሞከር ሳይሆን ትግሉ እየተካሄደ ያለው ለውጥ ለማምጣትና ለትልቋ ሀገራችን የሚመጥን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የማስፈን ስለሆነ ወደ ትክክለኛ መስመር እንዲገቡ ማድረግ ነው፡፡ አልገባም ካሉ እነሱንም መታገል ነው፡፡

የዚህ ፅሁፍ አቅራቢዎ በድጋሚ እንደታዘበው አሁን በተቃውሞ ፖለቲካው ውስጥ ሁለት አይነት የውስጥ ትግል እየተካሄደ ነው፡፡ ይሄ ትግል የሚካሄደው በለውጥ ፈላጊ ሃይሎችና (ይሄ በብዛት የወጣቱን ቀልብ የሳበ ይመስላል) በቀደመው መንገድ ማዝገም በሚፈገልጉ፣ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ከእኛ በላይ ላሳር ብለው የሚምኑ፤ ነገርግን በተግባር ውጤት ያላስመዘገቡ ሃሎች መካል ነው፡፡ በዚህ መልኩ መታገል መብት ነው፡፡ ፖለቲካ ውስጥ የውስጥ ትግልና የውጭ ትግል መኖሩ የተለመደ ነው፡፡ የሚዳኘው ግን አባላትና ህዝቡ ይሆናል፡፡

የግል ይዞታነት

በመጨረሻ ማንሳት የምፈልገው ትግሉን ፍሬያማ ለማድረግ እንቅፋት እንደሆነ የሚታመነው የግል ዞታ አመለካከት ነው፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ከምርጫ ባለፈ የምንመለከት ከሆነ በተቃዋሚ ጎራው የሚታየውን ፓርቲን እንደግል ንብረት የመመልከት ዝንባሌ ማጥራት ያስፈልጋል፡፡ በትግል ውስጥ ዋጋ መክፈል ማለት ፓርቲውን የግል ንብረት ማድረግ ማለት አይደለም፡፡ ከላይ እንደጠቀስኩት ፓርቲ የሚቋቋመው ለህዝብና ለሀገር የሚጠቅም ርዕዮተ ዓለምና የማስፈፀሚያ ስልት ይዞ እሱን ተግባራዊ ለማድረግ እንጅ የግል ዝናና ሞገስ ለማግኘት አይደለም፡፡

እኔ አይነኬ ነኝ የሚሉ እንዳንድ ግለሰቦች ‹‹እኔ አንደዚህ፣ እንደዚህ አድርጌ በመሰረትኩት ፓርቲ…›› የምትል መከራከሪያ ሲያቀርቡ ይሰማል፡፡ ፓርቲ ውስጥና ፖለቲካ ውስጥ ‹‹እኔ›› የምትል የግለኝነት ሃሳብ መነሳት ከጀመረች ህዝብና ሀገር ተዘንግቷል ማት ነው፡፡ ፓርቲን እንደ ግል ዞታ መመልከት የሚመጣው እኔ ከሚል ያልተባረከ ሃሳብ ነው፡፡ ማንም ሰው ማወቅ የሚገባው ወደ ኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ የሚመጣው ሊሰጥ እንጅ ሊቀበል አይደለም፡፡ ፖለቲካ ውስጥ ገብቶ መስጠት ሳይሆን መቀበል የሚፈልግ ካለ ወደ ኢህአዴግ ዘንድ ቢሄድ ውጤታማ ይሆናል፡፡ ተቃዋሚው ጎራ ያለው ግን መስጠት ብቻ ነው – ያውም ክቡር የሆነውንና የመጨረሻ ውዱን ህይወት፡፡ ስለዚህ በተቃውሞ ጎራ ያለውን የግል ይዞታ አመለካከት መታገል ወደሚፈለገው የለውጥ ግብ ያደርሳል፡፡

ለማጠቃለልም አሁንም ከፊት ለፊታችን የሚጠብቀን ሀገራቀፍ ምርጫ አለ፡፡ በኢህአዴግ በኩል ግልፅ የሆነ  የመጠቅለል አካሄድ እየታየ ነው፡፡ ይህንን የአፈና አካሄድ መስበር የሚቻለው የምርጫ ግርግር ውስጥ በመግባት ወይም ለመሳተፍ በመጓጓት ብቻ አይደለም፡፡ በቅድሚያ ምርጫ እንዲኖር መታገል ያስፈልጋል፡፡ 2007ን ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ መጠቀም የሚቻለው እስከ ምርጫ ብቻ በማሰብ አይደለም፡፡ ከምርጫ ባሻገርም ተቃውሞ ጎራው ላይ አስተማማኝ መሰረት ጥሎ ዴሞክራሲያዊ መንግስት መመስረቱም ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ሁለንተናዊ ችግሮችን ፈትሾ፣ አካዶችን በግልፅ ተችቶ መድረሻ ጎል ማስቀመጥ፡፡ አዎ ጊዜው እየሮጠ ነው፡፡ ህዝቡም የተጫነበት ቀንበር ከብዶታል፡፡ ስለዚህ በዚህ ልክ መሮጥ ያስፈልጋል፡፡ ጎበዝ እንሩጥ፡፡

↧

“ያልተሄደበት መንገድ” –ሊነበብ የሚገባው ድንቅ መጽሐፍ! (ነፃነት ዘለቀ)

$
0
0

ነፃነት ዘለቀ
freeandualemaragie.org

ይህን የአንዱአለም አራጌን በራሱ አገላለጽ ከጠባቧ የቃሊቲ እስር ቤት የተጻፈ ግሩም መጽሐፍ ሳነብ የተሰማኝን ስሜት ባጭሩ ለመግለጽ እንጂ ሥነ ጽሑፋዊ ደንብ የተከተለ ሂስ ወይም የመጽሐፍ ግምገማ ለመስጠት አለመነሳቴን መግለጽ እፈልጋለሁ – መሆኑን እንዴት ከረማችሁ?

ከሁሉ በፊት ግን ከሰሞነኛ ጉዳዮች መካከል ቂላቂሉ ወያኔ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የሠራውን አስቂኝ ድራማ ስመለከት እያዘንኩ የታዘብኩትን በዓለም ወደር የማይገኝለት ምርጥ የምርመራ ውጤት በሚመለከት ትንሽ ልበል፡፡

Yeltehedebet Menged

የኢትዮጵያን ቴሌቪዥን በውነቱ አልመለከትም፤ አለመመልከቴ ስህተት መሆኑ ቢገባኝም ጤንነቴን አጥብቄ ስለምፈልገው ይሁነኝ ብዬና ቁም ነገር አገኝበታለሁ ብዬ ኢቲቪን አላየውም – ብዙዎች እኔን መሰሎች ስላሉ “የዐዋጁን በጆሮ” እንዳትሉኝ እንጂ፡፡ የሆኖ ሆኖ በቀደምለታ ከሰዎች ጋር የሆነ ቦታ ቁጭ ብዬ ቁርስ ቢጤ ስንቀምስ በፖሊስ ፕሮግራም የተከታተልኩት በዓይነቱም ሆነ በይዘቱ ድንቅ የሆነ የወያኔ የወንጀል ምርመራ ቴክኒክና ውጤት ያጫረብኝን ልዩ ስሜት በዚህ አጋጣሚ ሳላነሳው መቅረት አልፈለግሁም፡፡ ከእውነት ሰው መሆኔን ጠላሁ፡፡

“መርማሪው” ወያኔ አይታይም፤ ይህን የለመድነው ነው፡፡ ወያኔዎች ራሳቸውን እንደወንጀለኛ አድርገው ስለሚቆጥሩና ከአልቃኢዳ ጋር የሚያመሳስሏቸውን ድርጊቶች የሚፈጽሙ መሆናቸውን ሕዝቡ የተረዳው መሆኑን ስለለተገነዘቡ ይመስለኛል የመንግሥትን ሥልጣንና ኃይልም የጨበጡ “ምሁራኑ መርማሪዎች” በግልጽ በሚዲያ መታየትን የሚወዱ አይመስሉም ፤ እነዚህ ጭራቅ ገራፊዎችና ሀዘን አምላኪዎች (ሳዲስቶች) በራሳቸውም በመንግሥታቸውም የሚተማመኑ እንዳልሆኑና በሆዳቸውና በዘረኝነት ቁርኝታቸው ብቻ ተለክፈው በስሜት ፈረስ የዕውር ድምብር ግልቢያ ዜጎችን የሚያሰቃዩ ናቸው – ቀናቸው ሲደርስ ምን እንደሚውጣቸው ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው፤ አሣር አለባቸው – የቁናው ሥፍር እየተንደረበበ ይጠብቃቸዋል – እዚህ ወይም እዚያ፡፡ ከሞራል ዕሤቶቻችንና ከምርመራ ህግ በወጣ ሁኔታ አቡበከር የሚባለውን የሙስሊም ተቃውሞ አመራር አባል እጆቹን በእጀሙቅ አስረው የሚያካሂዱትን “ምርመራ” በአደባባይ በቲቪ ለዓለም ሕዝብ ሲያሳዩም “መርማሪው ሊቅ” መታየትን አልወደደም – አስጠሊታ ሣቁ ግን ከአንጀቱ ጥርስ ሳይሆን ከማተብ የለሽ አንገቱ ይሰማ ነበር፡፡ ስለዚህ የአንዲ ልዩነት እጆቹ አለመታሰራቸው እንጂ ሂደቱ ልክ እንደአቡቦከር ነው፡፡ ይህ የምርመራ ሂደትና ውጤቱ የሀገራችን የለየለት ውርደትና የወያኔን ማንአለብኝነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ ወያኔዎች ከግዑዝ ድንጋይ የማይሻሉ የመጨረሻ ደደቦች መሆናቸውን ምናልባትም ለሚሊዮንኛ ጊዜ የገለጡበት ማፈሪያ ድርጊት ነው፡፡ የሚታዘነው በተመርማሪዎቹ ሳይሆን በመርማሪ ተብዬዎቹ ነው፡፡ ከመነሻው የዘረኝነት ልክፍት ያሽመደመደውና ከዘር ማዕቀፍ ውጭ የማያስብ ደንቆሮ ማይምና ሳዲስት እንዴት አንድን የተማረን ሰው ይመረምራል? እንዲያው ትንሽም ቢሆን የተማረ ዘረኛ ወያኔ ጠፍቶ ነው ወይ? ይህ ዓይነቱ የአደባባይ ግፍ ሄዶ ሄዶ የሚያስከትለውን መዘዝ እንዴት አጡት? ድንቁርና ይህን ያህል በጀብደኝት ያሳውራል?

ወደአስቂኙ ድራማ ልለፍ፡፡ አንዳርጋቸው በ“ነፃ ኅሊናው” የሰጠውና ለኢትዮጵያ ሕዝብ በደናቁር የወያኔ ወንበዴዎች እሳቤ ሊተላለፍ የተፈለገው መልእክት ይህን ይመስላል፤ “የግንቦት ሰባት ኅልውና ከእንግዲህ ግፋ ቢል ለሁለት ወራት ቢዘልቅ ነው፤ ወዲያም አለ ወዲህ ዕድሜው ከሁለት ወር አይበልጥም፡፡ የአውሮፓና አሜሪካ ምቾቱን ትቶ እንደኔ በረሃ ወርዶ የሚያታግል ቆራጥ ሰው አይኖረውም፡፡…”  የግንቦት ሰባት ቀሪ ዕድሜ ሁለት ቀንም ይሁን ሁለት ወር እሱ ሌላ ጉዳይና ወደፊትም የሚታይ ሆኖ ይህን የተናገረው ግን አንዳርጋቸው ጽጌ መሆኑን ልብ ይሏል – አንዲን በሚዲያም ቢሆን ባላውቀው ኖሮ ከአሁን በፊት “የተናገረውን”ና ገና ወደፊት “እንደሚናገረው በጉጉት” የሚጠበቀውን ሁሉ በበኩሌ ሳላንገራግር በሙሉ ልቤ አምኜ በተቀበልኩና ከወያኔ የሸፈተውን ልቤን ወደወያኔ በመለስኩ ነበር – ይህ ሁሉ ድካማቸው ታያ የማንን ቀልብ ለመሳብ ? በመሠረቱ እስካሁን ወያኔ የነበረ በአንዳርጋቸው ንግግር ምክንያት የወያኔነት ደረጃው አይጨምርም – በተቃራኒውም እስካሁን ወያኔ ያልነበረ በዚሁ የአንዲ ንግግር ምክንያት ንዴቱና ቁጭቱ ይጨምርና ወደድርጊት ይገባ እንደሆነ እንጂ ከተቃዋሚነቱ የሚያፈገፍግ አይመስለኝም፤ እናም የወያኔዎች የጅልነት ምጥቀት ያሳዝነኛል ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንንና ዓለምን በጠቅላላው እስከዚህን ያህል መናቃቸው ምን ያህል ወራዳዎች – እደግመዋለሁ ምዕመናን – ምን ያህል ወራዳዎች መሆናቸውን ከማሳየት በስተቀር የአንዲ ስቃይና የሙሌት ኑዛዜ የሚጨምርላቸው አንዳችም አወንታዊ ነገር የለም – ይህን ነባራዊ እውነት ለመናገር ደግሞ የክር ወይም የሃቂቃ ጉዳይ እንጂ የግንቦት ሰባት አባልም ሆነ ደጋፊ መሆንን አይጠይቅም፡፡ የወያኔዎችን ውስጠ ምሥጢርና የግፍ ታሪክ በየመድረኮች ሲዘከዘክ ሚሊዮኖችን በዕንባ ሲያራጭና በትካዜ ባህር ሲያሰምጥ የምናውቀው አንዳርጋቸው ጽጌ በምትሃታዊ ፍጥነት ወደማፊያው መንግሥት ተገልብጦ ተናገረው የተባለውን እንዲያ ሲናገር ይታያችሁ፡፡ የምናውቀው አንዳርጋቸው የምናውቅለትን ጽኑ ፀረ-ወያኔ አቋሙን በሻጥርና በብዙ ገንዘብ ክፍያ በየመኖች ተይዞ በወያኔዎች እጅ በገባ በሁለት ሣምንታት ጊዜ ውስጥ ሲለውጥ በዐይነ ኅሊናችሁ ይታያችሁ፡፡

ግሩም የምርመራ ውጤት! ዓለምን የሚያስደምም ሣይንሳዊ የወንጀል ምርመራ ግኝት! በዚህ በአንዳርጋቸው ቃልና የመከራ ኑዛዜ ማፈር ያለበት ቀደም ሲል ለመጠቆም እንደሞከርኩት ወያኔ ብቻ ነው፡፡ ከወያኔ ውጭ ማንንም ሊያሳፍር አይችልም፡፡ እንዲያውም እኔ ብሆን ኖሮ “ግንቦት ሰባት የሚባል ድርጅት ከነአካቴው በሕይወት አለ እንዴ? አሁን እናንተ ስትሉ ሰማሁ፡፡ ማን ተናገር እንዳለኝ አላውቅም ዝም ብዬ ነበር እኮ በኢሳት ያንን ሁሉ ንግግር የምዘባርቀው፡፡ ደግሞ ብርሃኑን ብሎ ግንቦት ሰባት! ከመነሻው ግንቦት ሰባት ብሎ ነገር ሲኖር አይደለም ወርቆቼ! …” ብዬ አስደስታቸው ነበር እንጂ የሌለን ምሥጢር ለመደበቅ በመሞከር ሰውነቴን ለስቃይ አልዳርግም – ሊያውም በዚያ ኑዛዜየም ስቃዩን ቢቀንሱልኝ አይደል? ግን አይቀንሱልኝም – ስለዚህ ብናገርም ባልናገርም ለውጥ የለውም፤ ጠባችን በደም የሚጠራ እንጂ በውሃ ታጥቦ የሚጸዳ አይደለምና፡፡

እንደውነቱ ታዲያ አንዳርጋቸው ሊሰጠው የሚችለው የማይታወቅ የተከደነ አዲስ ምሥጢር ሊኖር ይችላል? ሁሉም ነገር እኮ ግልጽ ነው፤ ወያኔ የሚባል ሀገር አጥፊና ፀረ-ሕዝብ የሆነ የማፊያዎች ቡድን አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ውስጥ መሽጎ አለ – እሱን ለማስወገድ ደግሞ ዜጎች በተበታተነ ሁኔታም ቢሆን በየፊናቸው ጥረታቸውን እያደረጉ ነው፤ ምሥጢር ከተባለ ይህ ነው ምሥጢሩ፡፡  አንዳርጋቸው የትግል መስመሩ ስላበሳጫቸውና እየሠራ ያለው ነገር ለኅልውናቸው አስጊ ሆኖ ክፉኛ የሚያሳስባቸው በመሆኑ እርግጥ ነው እሱን ከመድረክ ገለል እንዲል ማድረግ ቢፈልጉ ያንን መቀበል ይቻላል – ሰይጣናዊ ፍላጎታቸውን ለማርካት የሄዱበት ርቀት ብዙ የሕግና የሞራል ችግር ማስነሳቱ እንዳለ ሆኖ፡፡ ከዚያ ውጪ ምሥጢር አውጣ ብሎ የዓለማችን ቤት ባፈራው የማሰቃያ ዘዴ ሁሉ ሰውን ማሰቃየት፣ በዚያም ሂደት ራስን ለትዝብትና ለስላቅ የሚያጋልጥ ነውረኛ የምርመራ ሂደት ማካሄድና ተመርማሪዎች የማያምኑበትን ነገር እንዲናገሩ ማድረግ በእግረ መንገድም “በሰላም አንገዛም፣ አንገብርምም ያሉንንና ሕዝብን የሚያሳምጹብንን ቀንደኛ ጠላቶቻችንን ‹እንዲህ አሸናናቸው!›፣ የወንዶች ወንዶች መሆናችንን ብልታቸውን እየቆረጥን አሳየናቸው…” በማለት ስብዕናን ለማዋረድ መሞከር ወደራስ የሚዞር አሉታዊ ውጤትን መጋበዝ መሆኑን መረዳት ይገባቸው ነበር፡፡ ለነገሩ ወያኔ ልብሱም ጉርሱም ቅሌትና ውርደት በመሆኑ በዚህ ረገድ የሚሰማው አንድም የሀፍረትም ሆነ የይሉኝታ ስሜት የለም፡፡ ጃዝ ብለው የለቀቁት 13 እና 33 ቁጥሮችም እየሳቁበትና እየተዝናኑበትም ቢሆን ወያኔ ለሚሠራው ግፍና በደል ሁሉ ቡራኬያቸውን አይነፍጉትም፡፡ እነሱስ ቢሆን በጭፍሮቻቸው አማካይነት በጓንታናሞና ኢራቅ ውስጥ አስከሬኖች ላይ እስከመሽናት በሚዘልቅ ኢሰብአዊነት ስንትና ስንት ግፍ ይፈጸሙ የለም? ልጅ ከአባት ቢማርና የጭካኔ ደረጃውን አዘምኖ ምሥኪን ኢትዮጵያውያንን ምድራዊ ገሃነም ውስጥ ቢዘፍቃቸው ዋኖቹ ሀዘን አምላኪዎች ይደሰታሉ እንጂ ከከንፈር ሽንገላ ባለፈ ሕዝቡን ሊታደጉት አይፈልጉም – ይህንንም አሳምረን እናውቃለን፡፡ ጭምብሉን ፖለቲካዊ የተለሳለሰ የሚመስል አካሄድም አንዘነጋም – አገም ጠቀሙን፡፡

በነገራችን ላይ 13 እና 11 ወይም 33 ደግሞ ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ለሚያምንበት ሁሉም የትልቁ ቁጥር የአውሬው መገለጫ የ666 ቅንስናሾች ናቸው፡፡ አሥራ አንዶች በ110 የለበጣ ቀመር ቢያላግጡም እውነቱ ቀፎ የመለዋወጥ – የትሮይን ፈረስ ቅርጽ የማሻሻል ጉዳይ እንጂ ሲሙ ያው ነው – አሥራ አንድ፡፡ ለነገሩ ዝናር ባንገቴም ይሁን 11 ወይም ዜሮም ይሁን አንድ ሽንትር ዋናው ነገር ተግባር ነው፡፡ ሌላው ትርፍና ጨዋታን ለማሳመር ያህል በአጃቢነት የገባ ነው፡፡ እናም በሀገራችን ሁኔታ የሰውዬው ማንነት ምንም ይሁን ምን በስቃይና በግድያ የሚያምን ሁሉ እናት ክፍሉና ጥንተ አመጣጡ ከአውሬው መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ክፉና ደግ መንፈሶች ኅብረት የላቸውም፡፡ ሩህሩህ መሐሪና አረመኔ/ጨካኝ ገዳይ አንድነት የላቸውም፡፡ መጽሐፉም ጣፋጭ ፍሬ በዛፍ ላይ ሳለ ይታወቃል እንደሚል ማን የማን ወገን መሆኑ በተለይ በዘመናችን በግልጽ ይታወቃል፡፡ ማን ነው የበሽታ ሕዋሳትን በቤተ ሙከራ እየፈለሰፈና እያራባ ለዓለም በተለይም ለኋላቀር ሀገሮች እንደ ዕርዳታ ስንዴ የሚያከፋፍል? ማን ነው የዓለማችንን የአየር ንብረት እያዛባና ዕድሜዋን በብርሃን ፍጥነት እያሳጠረ የሚገኘው? የዓለምን ጠቅላይ ገዢነት በትረ መንግሥት በጉልበት የተቆጣጠረውና “ለኔ ካልሰገዳችሁ ሀብትና ሥልጣን አይኖራችሁም” ብሎ ሁሉን እያስደገደገ የሚገኘውና በትዕምርተ ኅቡኣታዊ ባለአንድ ዐይን ፒራሚዳዊ ቅርጽ ወይም በፔንታጋራማቲን የኮከብ ቅርጽ የሚታወቀው ምሥጢራዊ ኃይል ማን ነው? ማን ነው አሁንም ሆነ ከአሁን በፊት መካከለኛውን ምሥራቅ እያተራመሰ ያለው? መፍለቂያው የሆነችን የአንዲት ትንሽዬ ሀገር ኅልውናና የበላይነት ለማስጠበቅ ሲል ድምጽን በድምጽ የመሻር መብቱ የዓለምን የመንግሥታት ኅብረት እንደአሽከር ሰጥ ለምበጥ አድርጎ የሚገዛ ማን ነው? አይኤም ኤፍ፣ ዩኤን፣ ወርልድባንክ፣ ኔቶ፣ ሲአርኤፍ፣ … የማን አድቃቂ ክንዶች ናቸው? ለመሆኑ የዚህ ሞገደኛ የወቅቱ የዓለማችን ገዢ ዋና መሥሪያ ቤትና ቅርንጫፍ ቢሮዎቹ የት የት ናቸው? ጽዮንና ሀማስ የማን ልዑካን ናቸው? የግጭቶች መንስኤና የምክንያታዊነት ሚዛኑ ለማንም ያጋድል ዋናው የሁለቱም ተልእኮ ግና ለአውሬው ግብር የሚሆን ብዙ የደም ባህር ማቆር መሆኑን መዘንጋት የዓለም ነገር አያገባኝም ብሎ እንደመመነን ይቆጠራል፡፡ በየትኛውም የዓለም ክፍል – ማን ነው የጦር ኃይሎችን በሁለት ጎራ እየከፈለ በተፃራሪነት በማሰለፍ የሚሊዮኖችን ደም በከንቱ እያፋሰሰ ያለው? ኢራንና አሜሪካ በርግጥም ባላንጣዎች ይሆኑ እንዴ? በፍጹም፡፡ ጠላቶች መስለው ትያትር በመከወን ለአንድ ዓላማ ስኬት የሚተጉ የአንድ ገዢ አንድ አምሳል አንድ አካል ናቸው፡፡  ማን ነው በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከአፍ እስከገደፋቸው በንጹሃን ተሣፋሪዎች ጢም ብለው የሞሉ የሲቪል አውሮፕላኖችን(የማሌዥያን) ባልታወቀ ዕፀ መሠውርና በሚሳኤይል ድራሻቸውን ያጠፋው? ምን ዓይነት ወያኔያዊ ጨካኝ አንጀት ያለው ፍጡር ይሆን ይህን ያደረገ? ለምን ዓላማ? ቫቲካንንና መለስተኛ አውሮፕላን የምታህል የነጭ እርግብ ምስል ለማስመሰል ያህል በሰላም ምልክትነት በዋና የፓትርያርክ ጸ/ቤቱ በር ላይ ያቆመውን የኛኑ ኦርቶዶክስ ሳይቀር ከሞላ ጎደል ሁሉንም የሃይማኖት ተቋማት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ተቆጣጥሮ ሁሉንም ሃይማኖት አለኝ ባይ በአውሬው ትዕዛዝ ሥር ያደረገው ማን ነው? ለመሆኑ በአሁኑ ሰዓት ቅዱስ ሊባል የሚችል ቦታና ሰው አለ ወይ? ፖፕ ጆን ፖል አንደኛ፣ ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ፣ ‹አቡነ› ጳውሎስ የኛ… ሌሎችም የማን ወኪል ነበሩ? ፍየሎች በበጎች ጋጣ ውስጥ መሽገዋል፡፡ በጎች እያለቁ ነው፡፡ አውሬው ሆሊውድና ቦሊውድን ብቻ ሳይን ገዳማትንና ካቴድራሎችንም ከተቆጣጠረ ምዕተ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ጭካኔን በሚያስተምሩ ፊልሞች፣ በልቅና ባልተገሩ ኢ-ሞራላዊም በሆኑ ፖርኖግራፊዎች በተለይ የዓለምን ወጣት ትውልድ ጡጦ ከመጣሉ በእንጭጩ ለማምከን  ይህችን ዓለም ማንና ከየትስ ሆኖ እየገዛት እንዳለ መች አጣነው? የዚያ ‹ታላቅ› የጨለማ ንጉሥ የእጅ ሥራዎች የሆኑ ወያኔዎችም ባቅማቸው ቅድስቲቱን ሀገር ድራሽዋን ቢያጠፏት ከድጋፍ በስተቀር ማን ከልካይ አላቸው? በጎችስ ቢጮኹ አለጊዜው ማን ይደርስላቸዋል? ግን ግን አይዞን፤ የፍየሎችና የበጎች የመጨረሻ ዕድል ተለይቶ የሚታወቅበት የፍርድ ቀን በፍጥነት እየመጣ ነው፡፡ ብሎም ቢሆን ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ድል በምኞት ሊገኝ እንደማይችል ልብ ማለት ይገባናል፡፡ ብቻ ይህን መሰሉን ነገር በሆድ ይፍጀው ለሌላ ቀን በይደር ማቆየቱ ሳይሻል አይቀርም፡፡ ለነገሩ እኛን ምን አገባን? ሁሉም ከልኩ አይዘል፡፡

 

ከሰው ተውሼ እያነበብኩት ነበር – “ያልተሄደበት መንገድ”ን፡፡ በቅርብ ካነበብኳቸው በሀገር ችግር ዙሪያ ከሚያጠነጥኑ የቅርብ ጊዜ መጻሕፍት ውስጥ በኔ ዕይታና ለኔ ፍጆታ ይሄኛውን ወደር አላገኘሁለትም፡፡ አንዱአለም አራጌ ዋለ የተዋጣለት መጽሐፍ በመጻፉ – ሊያውም በዚህ አፍላ የጎልማሳነት ዕድሜውና በመከራ ውስጥ ሆኖ – ባለበት አድናቆቴ ይድረሰው፡፡ ወላድ በድባብ ትሂድ የሚባለው በዚህ ዓይነት አጋጣሚ ነው፡፡ ሚሊዮኖች ፈርተንና ለሥጋችን አድረን በየሽርንቁላው ተወትፈን በፍርሀት ቆፈን ስንርድ ሊያውም በእስር ቤት ውስጥ ሆኖ ይህን የመሰለ አብሪ መጽሐፍ ካለበቂ ማጣቀሻና ዋቢ መጻሕፍት በአዩኝ አላዩኝ ሰቀቀን ሌሊት ሌሊት እየተደበቁ መጻፍ ልዩ ጀግንነትና ተሰጥዖም ነው፡፡ አንዱአለምና መሰል የብዕርና የፖለቲካ ታጋዮች ለነፃይቱ ኢትዮጵያ በሕይወት እንዲደርሱ እግዚአብሔር ይታደገን፤ ይታደጋቸው፡፡ ቤተሰባቸውንም ይባርክ፡፡ ለእኛም ለባከንነውና ለራሳችን ጥቅምና ፍላጎት ስንል በ‹እስኪያልፍ ያለፋል› ተረት ራሳችንን እያታለልን የወያኔ ባርያ ሆነን ለጠፋነው ዜጎችም ፈጣሪ ረድኤቱንና ወኔውን ይስጠን፡፡ እንደዚህ ያሉ ዜጎች ባይኖሩን ኖሮ ሕይወት በጠቅላላው ለይቶላት ጨለማ በሆነች ነበር፡፡ ከዚህ አንጻር እግዜር የተመሰገነ ይሁን፡፡ እርሱን መሰል ሌሎች ጸሐፊዎችንና ታሳሪዎችንም ጭምር እግዜር ይባርክልን፡፡ ለቤታቸውም ያብቃልን፡፡ የሚሳነው ነገር የሌለው የኢትዮጵያ አምላክ የመከራ ደብዳቤያችንን የሚቀድድና ሃራ የሚያወጣን አንዳች ኃይል ይዘዝልን፡፡ አሜን፡፡

ይህ መጽሐፍ የዋቢ መጻሕፍትን ገጽ ጨምሮ በጠቅላላው 320 ገጾች አሉት፡፡ በአራት ዋና ዋና ክፍሎች ሥር የተካተቱ 18 ርዕሶችንም ይዟል፡፡ ጠቅጠቅ ብሎ የተጻፈ በመሆኑ እንደሌሎች በርካታ መሰል መጻሕፍት በቀላሉ አይገፋም፡፡ የሆኖ ሆኖ በተለይ እስከማገባደጃው ድረስ ስሜትን ቆንጥጦ በመያዝ መነበብ የሚያስችለው ሥነ ጽሑፋዊ ውበትና ይዘታዊ ግርማ ሞገስ አለው፡፡ እናም አንብቡት፡፡ በነገራችን ላይ ይህን መጽሐፍ እያነበብኩ ወደ ገጽ 100 አካባቢ ስደርስ የተዋስኩትን እንደምመልስ ገባኝና ወዲያውኑ ከተማ ወጥቼ ገዛሁት፡፡ ተውሼ ያነበብኩትን ወይም እያነበብኩት ያለሁትን መጽሐፍ ስገዛ ይህ የመጀመሪያ ጊዜየ ነው፡፡ አንጡራ ሀብቴና የመጻሕፍት መደርደሪያየ አንዱ ፈርጥ እንዲሆን ተመኘሁ፡፡ ተመኝቼም አልቀረሁ፡፡ ለልጆቼ ውርስ ይሆናል፡፡ እናንተም አሁኑኑ ግዙና ንብረታችሁ አድርጉት፡፡ መጽሐፉ “ኩሎ አመክሩ ወዘሰናየ አጸንዑ” እንዲል፡፡

አመስጋኝ አማሳኝ እንዳልባል በዚህ መጽሐፍ የታዘብኳቸውን አንዳንድ ግድፈቶችም በዚሁ አጋጣሚ ብጠቁም ደስ ይለኛል፡፡ ጥቂት የማይባሉ የአርትዖት ችግሮች አሉበት፡፡ አሉታዊ መሆን ያለበት በአወንታዊ ወይም የዚህ ተቃራኒ ሆኖ የሚጻፍበት አጋጣሚ አልፎ አልፎ ይስተዋላል፡፡ አማርኛ ላይ ብዙውን ጊዜ የምታስቸግር ነገር አለች – ለምሳሌ “እኔን እንደሚያገባኝ እንዴት ረሳኸው?” በሚለው ዐረፍተ ነገር ውስጥ “ሚ”ን “ማ” ብናደርጋት ትርጉሙ ሙሉ በሙሉ ይለወጣል፡፡ “ጽንፍ” ለማለት “ቅንፍ” ብንል አንዳንዶችን ግር ሊያሰኝ ይችላል፡፡ የአርትዖት ሥራ ሽንፍላ እንደማጠብ ነው፡፡ በተቻለ መጠን ብዙ ሰዎች በብዙ አዳዲስ ዐይኖች ሊተባበሩበት የሚገባው አስቸጋሪ ሥራ ነው፡፡ እንዲያም ሆኖ የማይጠራበት ጊዜ አለ፡፡ ከዚህ አኳያ ይህን ቆንጆና ለታሪክ የሚቀመጥ መጽሐፍ ዐዋቂ ሰው እንደገና “ኤዲት” ቢያደርገው የበለጠ ማለፊያ ይሆናል፡፡ የግሌ አስተያየት ነው፡፡ (አንድ ወዳጄ የነገረኝ አንድ አርትዖታዊ ስህተት በጭንቅላቴ ብልጭ እያለ ‹እዚህ ላይ ካልጻፍከኝ ሞቼ እገኛለሁ!› ብሎ አስቸገረኝ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ የመሥሪያ ቤቱ የብድር ኮሚቴ ስብሰባ ይጠራል፡፡ ለተሰብሳቢዎችም “ከብድር ኮሚቴ…. ለጠቅላላ አባላት” የሚል ጽሑፍ ተበትኗል፡፡ ሁሉን ያስፈገገው ግን ጸሐፊዋ “ከብድር ኮሚቴ” ከሚለው ሐረግ ውስጥ የአንዱን ቃል የመጨረሻ ፊደል ሳትጽፈው መቅረቷና እስከዚያን የስብሰባ ጊዜ ድረስ ማንም ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ስህተቱን ልብ አለማለቱ  ነበር፡፡ ያቺ “ነገረኛ” ጸሐፊ የትኛዋን ሆሄ እንደዘነጋቻት እኔም አሁን ዘነጋኋት፡፡ )

ከሆሄያት ግድፈትና ሞክሼ ፊደላትን  በነባሩ ሰዋስዋዊ ልማድ ከመጠቀም አኳያ ከሚታዩ አንዳንድ ጥቃቅን “ስህተቶች” በተጓዳኝ ጥቂት የመረጃ መዛባትና የዘይቤና ፈሊጥ አጠቃቀም እጅግ አነስተኛ ችግር ሳይኖር እንደማይቀር እገምታለሁ፡፡ ለምሳሌ “ኢሕአፓ” የሚለው ምሕጻረ ቃል ሲፈታ እኔ የማውቀው “የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ” በሚል ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ግን “የኢትዮጵያ ሕዝብ አደራጅ ፓርቲ” በሚል ከአንዴም ሁለቴ ገደማ ቀርቧል፡፡ ፈሊጥን በተመለከተ “ለያዥ ለገራዥ” ለማለት “ለያዥ ለገናዥ” ተብሏል፡፡ በተጨማሪም የሃሳብ ድግግሞሽ በስፋት ይታይበታል፡፡ በዚያም ምክንያት አንድ አንባቢ በጀመረበት የስሜት ሞቅታ መጨረስ ባይችል ችግሩ ከዚህ የሃሳቦች መደጋገም የሚመነጭ ይመስለኛል፡፡ የሆኖ ሆኖ የመጽሐፉ አጻጻፍና ለኅትመት መብቃት በብዙ ችግር የታጠረ በመሆኑ የአሁኑ ይዘቱ ራሱ ከሚጠበቀው በላይና በአንጻራዊ ሁኔታ ከሌሎች በርካታ መሰል ጸሑፎች(እኔ ካነበብኳቸው) በጣም የተሻለ መሆኑን በበኩሌ ልገነዘብ ችያለሁ፡፡ በመሆኑም ይህ ጥረቱ ደራሲውን በእጅጉ ያስመሰግነዋል፡፡ እዬዬም ሲደላ ነው ጓዶች፡፡ እነኚህንና መሰል ሌሎች እንከኖችን አስተካክሎ በቀጣይ ኅትመት ለንባብ የሚያበቃው ወገን ከተገኘ መልካም ነው፡፡ ደግሞም የማይቻል አይመስለኝም፡፡

 

አንዱአለምን በዚህ መጽሐፉ ደርቤ እንዳነበብኩት የፕሮፌሰር መስፍን ደቀ መዝሙር ይመስለኛል፡፡ ይህን የምለው ፕሮፌሰሩ አንድ ወቅት እነብርሃኑ ነጋ “ሁለገብ ዘዴን በመጠቀም ወያኔን እንታገላለን” ባሉ ወቅት ክፉኛ ይተቿቸውና “እኛ ወደዚህ ‹የማይረባና ውዳቂ› የአስተሳሰብ ደረጃ አንወርድም”  ማለታቸውን በማስታወስና አንዱአለምም በዚያው ቅኝት አሁንም ድረስ በዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ ወንዝ ቀርቶ የደረቀ ምንጭ በማያሻግር የሰላማዊ ትግል ሥልት ወያኔን እንጥላለን ብሎ የሚያምን በመሆኑ ነው፡፡ እርግጥ ነው አንዱአለም አሁን ባለበት ሁኔታ በኃይል ወይም በጦር መሣሪያ ወያኔን እንታገል ብሎ ቢጽፍ የሚደርስበትን ተጨማሪ መከራና ፍዳ ስለምንገነዘብ ይህን አቋም ያርምድ ብለን በሰው ቁስል እንጨት አንሰድም፡፡ ይሁንና ቢያንስ ዝም ማለት ሲገባ ወያኔ የፈጠረው የኢትዮጵያ ውጥንቅጥ ችግር የሚፈታው ወያኔን በሰላማዊ መንገድ በመታገል ብቻ ነው የሚል እምነት በጭፍን ማራመዱን አልወደድኩለትም፡፡ (በነገራችን ላይ ኤርምያስ ለገሰ ቅድም በኢሳት አንድ ውይይት ላይ ሲናገር እንደሰማሁት የአንዳርጋቸውን በወያኔዎች መያዝ ኔልሰን ማንዴላ በኢዲያሚን ዳዳ እንደተያዘ ያህል እቆጥረዋለሁ ማለቱን እኔም በጣም እደግፋለሁ፡፡) ሰው ከሰው ጋር ቢታገል አሸናፊውና ተሸናፊው ይለያል፡፡ ከአውሬ ጋር ግን እንዴት መታገል ይቻላል? ውሾች በ“አስተሳሰብ” ከሚበልጡት ወያኔ ጋር እንዴት ስለሰላም መወያየት እንደሚቻል አንዱአለም ቢያስረዳኝ ደስ ባለኝ፤ ውሾ ሲሸናነፉ በሚያሳዩት ተፈጥሯዊ ምልክት ይግባቡና ጦርነቱን ያቆማሉ፤ ከዚያም በመካከላቸው ሰላም ይሰፍናል፡፡ ሁኔታዎችም ወደጥንቱ (statusquo ante) ይመለሱና ማኅበረከልባዊ ሕይወት ትቀጥላለች (“ከልብ” ውሻ ማለት ነው – “ል” ጠብቃ አትነበብም)፡፡ ወያኔ ግን ያሸነፈውን ሁሉ በሕይወት ያለውን ብቻም አይደለም የሞተውን ሳይቀር እስከመቃብር ድረስ የፕሮፓጋንዳ ሠራዊት እያዘመተ የቅርብ አጥንቶችንና የሩቅ አፅሞችን የሚፋለም ዶንኪሾት ነው፡፡ ይህን ባሕርዩን ለማወቅ በግድ እንደነአሥራት ወ/የስ መሞትና እንደነእስክንድር ነጋ መታሰር አያስፈልግም፡፡ ዛሬ ላይ ቁጭ ብሎ ወያኔን በሰላማዊ መንገድ ከሥልጣን አስነሳለሁ ብሎ መቃዠት በርግጥም ቅዠትና ሲያንስም የዋህነት እንጂ አንዱአለምን ከመሰለ በሳል የፖለቲካ ሰውነት የሚጠበቅ አይመስለኝም፡፡ ከዚህ ውሱን ነጥብ አኳያ ምን እንደነካው ሊገባኝ አልቻለም፡፡

አክራሪ ኦርዶቶክሳውያን እንዳይቀየሙኝ እንጂ የአንዱአለም የዋህነት (naivety?) ከ‹ቅድስት› ክርስቶስ ሠምራ ጋር ይመሳሰልብኛል፡፡ ‹ቅ.› ክርስቶስ ሠምራ – በገድሏ ላይ ተጽፎ እንደሚነበበው – ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ለማስታረቅ ዕቅድ ትነድፋለች አሉ፡፡ … እርሱ ወዳለበት ሲዖል በቀጥታ ትሄዳለች፡፡ “ስፈልግሽ ኖሮ እዚሁ መጣሽልኝ?” ይላትና የክርስቶስ ሠምራን ነፍስ ይዞ ወደግዛቱ ሊያስገባት ሲል መላእክት ደርሰው ወደመጣችበት ወደገነት ይወስዷታል፡፡ በአጋጣሚው ግን 78 ሺህ የተኮነኑ የሲዖል ነፍሳት በቅድስቲቷ መንፈሳዊ አካል ላይ በመጣበቅ ወደገነት ይገባሉ፡፡ እምነት ነው፡፡ በየዘመናቱ በገዢዎችና በሃይማኖት መሪዎች ፈቃድ እንዲካተቱ የተደረጉና እነዚህን አሳሳች ይዘት ያላቸውንና እርስ በርስ የሚቃረኑ፣ “በእግዚአብሔር መንፈስ የተነዱ” ሰዎች ስለመጻፋቸው የሚጠቁም አንዳችም ማስረጃም የሌላቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ የተካተቱ አንዳንድ ጽሑፎችንና ሰይጣናዊ ሳጋዎችን ሳይቀር ላለመቀበል አንድ ሰው መብት ያለው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ይህን ኢትዮጵያዊ ሃይማኖታዊ ድርሰት ማመን አለማመን የማንም ውዴታ እንጂ ግዴታ ሊሆን አይገባም – እዚያው ውስጥ በሚገኙት ዘንድም ቢሆን፡፡ ታርጋ ሳይለጠፍብኝ ስለሃይማኖቴ ልናገር እንዴ? አይ፣ ለማንም አይጠቅምም፡፡ ግን ማንኛውንም ሃይማኖታዊ አክራሪነትና ጽንፈኝነት የምጠላ አማኝ(theist) መሆኔን ብገልጽ ደስ ይለኛል፡፡ አነሳሴ ወዳልሆነ ነገር በመንሸራተቴ ይቅርታ – ምን ላድርግ ሁሉም ነገር አንሸራታች ሆኖ ዐረፈው እኮ፡፡ ብቻ አንዱአለም የዚህችን ቀና ሴት ባሕርይ የተላበሰ ግን በአፀደ ሕይወት የሚገኝ የማይቻልን ነገር ለመሞከር የሚተጋ የወንድ ክርስቶስ ሠምራ ይመስለኛል፡፡  

ሰላማዊ ትግል የራሱ መደላድል አለው፡፡ በቅድሚያ የሀገርህ ሰው ከሆነ ሰው ጋር፣ ዜጋህ ከሆነ ሰው ጋር፣ እንደዜጋው ከሚቆጥርህ ወይም ከሚመለከትህ የአገዛዝ ኃይል ጋር፣ በትንሹ ደግሞ ሰው መሆንህን አምኖ ከሚቀበል ሰው ጋር እንጂ ከአውሬና ከለዬለት የዲያብሎስ መንጋ ጋር በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ ብለህ ወርቃማ የመቶዎች ዓመታት ጊዜህን አታባክንም – አንዱአለም የሚለው ግን ዝንታለሙን እየታሰርንና እየተገደልን ነፃነታችንን ከወያኔ በችሮታ እንቀበል ነው – ምናልባትም በወዲያኛው የምፅዓት ዘመን፡፡ ሰዎች ወያኔን መረዳት እንዴት እንዳልቻሉ ወይም እንደማይችሉ ሳስበው ይገርመኛል፤ እንዲያውም ወያኔዎች፣ ሰዎች እንዲህ እንዲሆኑ – ማለትም በሰላማዊ መንገድ ከነሱ ጋር መታገል እንደሚቻል እንዲያምኑና እንዲያሳምኑ – የሚያደርግ ድግምት ቢጤ ሳይኖራቸው የሚቀር አይመስለኝም፡፡ አለበለዚያስ የሰላማዊ ትግልን ገፈት ቀማሽ ከሆነ አንዱአለምን ከመሰለ ብርቅዬ ዜጋ እንዲህ ያለ ተሳስቶ የሚያሳስት አነጋገርና እምነት ሊደመጥ ባልተገባ ነበር፡፡ ይቅርታ ይደረግልኝና ዝምታ ማንን ገደለ? በከንቱ መነቃቀፍ ከትዝብት በስተቀር ምን አወንታዊ ውጤት ያስገኛል? እንዳለመታደልና እንደርግማንም ሆኖ በኅብረት መታገል ቢያቅት ሁሉም ባመነበት ቢንቀሳቀስ ምን ክፋት አለው? ከአድማስ ማዶ ሊኖር ይችላል ተብሎ በሚታሰብ ሥጋት ከወዲሁ መቆራቆስ አግባብ ነው ወይ? ለዚህማ ወያኔ አለ አይደል? ይህን ስል አንዱአለማውያንና መስፍናውያን – በተወሰነ ደረጃ እኔንም ጨምሮ – ስሜታችን እንደሚጎፈንን ይሰማኛል፡፡ ግን ምርጫ የለኝም፡፡ የሚሰማኝን መናገሬ እንደወንጀል ሊቆጠርብኝ አይገባም፡፡ አውቃለሁ – አንዱአለም እሳት ውስጥ ነው፡፡ አልክድም – እኔም ከርሱ ባልተናነሰ ሁኔታ እሳት ውስጥ አለሁ፡፡ ልዩነታችን እርሱ ባመነበት ገብቷል፡፡ “ደስ”ም ያለው ይመስላል፡፡ የኔ ግን ከሁሉ ያጣ ሆኜ በዕብደትና በስክነት መካከል አንዴ ሰው አንዴ ዐፈር በመሆን እየተቀያየርኩ መረጋጋትና ሰላም የሌለው ሕይወት እገፋለሁ፡፡ ኅሊናህን አፍነህ መኖር ከመታሰር በበለጠ እንደሚጎዳ አውቄያለሁ፡፡ ሰው እንኳን ሳያውቅልህ በአእምሮ ስቃይ ምክንያት ከቤተሰብህም ከጓደኞችህም ‹እየተናጀስክ› ሰላምህን አጥተህ በትልቁ እስር ቤት መኖር በትንሹ እስር ቤት ከመኖር የበለጠ እንደሚያሰቃይ ተረድቻለሁ፡፡ መብላት፣ መጠጣት፣ መዳራትና በሰፊ ጎዳና መመላለስ ትርጉም የሚያጡበትና አንጎልህ ተቀፍድዶ ተይዞ ሰዎችን ሰላም በምትነሳበት ሁኔታ ለመኖር ያህል ብቻ መኖር ከለዬለት ከርቸሌ ያልተሻለ መሆኑን ከተረዳሁ ቆይቻለሁ፡፡ ስለሆነም ከአንዱአለም ባልተናነሰ የኔም እስረኝነት የዋዛ አይደለምና ሁላችንም አንድ ነን፡፡ እንዲህ የምለው ስለኔ ብቻ አይደለም – ስለሌሎች እኔን መሰሎችም እንጂ፡፡ እንዲህ የምለው ግን ለምንድነው? የማንን አንጀት ለማላወስ? ማንስ ነው ሆዴ ላይ ቆሞ ያናዘዘኝ? ሆ!   

በውሸት መከሰሱን፣ በውሸት ምሥክር (አዳፍኔ በሚላቸው) ዘብጥያ መውረዱን፣ በውሸት የግንቦት ሰባት አባልና የሽብር ጥቃት ሊፈጽም ከምንደኞች ጋር እያቀነባበረ ነው መባሉን፣ …. ሁሉንም ዘንግቶ ከእባብ ዕንቁላል እርግብ እንደሚፈለፈል ሊያስረዳን መሞከሩ አንዱአለም ወያኔን ለማወቅ ገና ብዙ ጊዜ የሚፈጅበት መሆኑን አመልክቶኛል – ጠሊቅ ሀገራዊና ታሪካዊ ዕውቀት ያለው መሆኑ ተይዞልኝ፡፡ እናም እላለሁ – ሰማይ ዝቅ መሬት ከፍ ቢሉ ወያኔ በሰላማዊ ትግል ሥልጣን አይለቅም፡፡ ይህን ፀሐይ የሞቀውንና ሀገር ያወቀውን ሃቅ በመካድ ከዚህ የተለዬ ህልም ማለም – እንደአካሄድ ባይከለከልም – ትዝብት ላይ ይጥላል፡፡ በነገራችን ላይ ክርስቶስም ለትግስቱና ለፍቅሩ ገደብ ነበረው፤ ለዚህም ነው በመሳም አሳልፎ የሰጠውን ይሁዳን የረገመው – በአንገቱ የወፍጮ መጅ ታስሮ ወደጥልቅ ባህር ቢወረወር እንደሚሻለው በምሬት በመናገር፡፡

ይቅርታችሁንና በዚህስ አንዱአለምን ተናድጀበታለሁ፡፡ ምን ነካው ግን? እንግዲያውስ ያበጠው ይፈንዳ በኢትዮጵያ እንደእስካሁኑ የስግብግብነትና ራስ ወዳድነት በሽታችንና የሥልጣን አራራችን ከሆነ በሰላማዊ መንገድ እንኳንስ ወያኔ ኢንጂኔር ግዛቸው ሽፈራውም ሥልጣን አይለቅም፤ እንኳንስ ወያኔ ኢንጂኔር ኃይሉ ሻውልም አይለቅም (በጤና ምክንያት …ካልሆነ)፤ እንኳንስ ወያኔ ፕሮ. በየነ ጴጥሮስም አይለቅም፤ እንኳንስ ወያኔ ዶር. መረራ ጉዲናም አይለቅም፤ እንኳንስ ወያኔ ዶር. ፍስሐ እሸቱም አይለቅም፤ እንኳንስ ወያኔ በቁሙ የሞተው ከሃዲው ልደቱ አያሌውም አይለቅም … (ዝርዝሩ ብዙና ብዙ ነው – ስንተዋወቅ? ግን እባብ ልቡን ዐይቶ እግሩን ነሣው ሆነና …)፡፡ የኢትዮጵያ መሬት አዲስ በሚፈልቅ ፍቱን ጠበል ካልተረጨ ይሄ የሥልጣንና የገንዘብ እንዲሁም የሴሰኝነት ጠንቆች በቀላሉ አይለቁንም – በኛ ባሱብን እንጂ እርግጥ ነው እነዚህ መሰናከያዎች የአጠቃላዩ የሰው ዘር መደናቀፊያዎች መሆናቸው የታወቀ ነው (ለምሳሌ የሰሞኑንና የቅርብ ሩቅ ጊዜውን የኢራቁን አልማሊኪንና የግብጹን አልሲሲን የሥልጣን ሱስ ብናይ በሰው ልጅ ራስ ወዳድነት መገረማችን አይቀርም – ይህ ነገር ወደኛ መጥቶ ከማይምነታችን፣ ከሥልጣን ወዳድነታችንና ከቦክሰኛው አስተዳደጋችን ጋር ሲደመርማ ምን ያሳይ፡፡) በኛ ሀገር ለሁሉም ነገር በተለይም ለጥላቻችንና ለራስ ወዳድነታችን ልጓም አጣን፤ ለከት ጠፋ፤ በቃኝን ተጸየፍን፤ ጠገብኩን ጠላን፤ ከይሉኝታና ሀፍረት ተፋታን – ስንገርም፡፡ እናም ለነዚህ ነገሮች ያለን ጥብቅ ቀረቤታ ከሌሎች የጥፋት ሰበዞች ጋር ተደማምሮ እንደሀገርም እንደሕዝብም ከናካቴው ከምድረ ገጽ ልንጠፋ – መለኮታዊ ጣልቃገብነት በቅርብ ጊዜ ውስጥ ካልተከሰተ –  ዘመኑ ቀረበ፡፡ ውሸት ነው? ውሸት ነው ካልክ እውነት ነው ማለት ነው፡፡ “አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም” የሚል መጽሐፍ ዱሮ አነበብኩ ልበል? አዎ፣ ‹ፀጉራም ውሻ አለ ሲሉት ይሞታል› እንዲሉ ካልሆነ ለይቶልን ጠፍናል፡፡ አንወሻሽ፡፡

አንዱአለም ወያኔ በሰላማዊ መንገድ ሥልጣን እንደማይለቅ አሳምሮ ያውቃል፡፡ መጽሐፉ ላይ በገደምዳሜ ገልጾታል፡፡ እንደመፍትሔ በየገጾቹ የሚያቀርበው ግን ያንኑ የሰላማዊ መንገድ የትግል ሥልት ነው፡፡ “የሰላማዊ መንገዱ ካልሠራ” ይላል አንዱአለም ፈገግ ባደረገኝ ሁኔታ “የሰላማዊ መንገዱ ካልሠራ ሌላ የሰላማዊ መንገድ መሞከር ነው፡፡” ከመሰነባበታችን በፊት በመጽሐፉ መጨረሻ አካባቢ ገጽ 312 ላይ የሚገኘውንና ወያኔን በሰላማዊ መንገድ ማስወገድ ባይቻል በማስከተል ምን ማድረግ እንደሚገባ አንዱአለም የመጨረሻ መፍትሔ ብሎ የሚሰነዝረውን እንመልከት – ወጣቱ ፖለቲከኛ አይፈረድበትም፡፡ የት ነው ያለውና? አያድርስ ነው – እነዚህ ሰዎች አስጨንቀው ያዙንና እምንለውንም እያሳካሩ ግራ አጋቡን እኮ፡፡ አንዱ ለጓደኛው “ያዋስኩህን ዕቃ ባትመልስ ዋልህ! አሳይሃለሁ!” ይለዋል፡፡ “ምናባህ ልታደርገኝ አንት የውሻ ልጅ!” ብሎ ቢያፈጥበት “አይ፣ ምን አድርግሃለሁ ያው ታዝቤህ እቀራለሁ እንጂ” አለው ይባላል፡፡ እርግጥ ነው መናገር የማድረግን ያህል እንደማይከብድ አውቃለሁ፡፡ “አይ መሬት ያለ ሰው!” ብሏል አሉ የሚጋልበው ፈረስ የደነበረበት አንድ ሰው – “እንዲህ አድርገው፤ እንዲህ ያዘው” ባሉት ጊዜና፡፡ አሁንም እርግጥ ነው – ለተቀማጭ ሰማይ ቅርብ ነው፡፡ እርግጥ ነው – አታሞ በሰው እጅ ስታምር በገዛ እጅግ ግን ልታደናግር ትችላለች፡፡ ቢሆንም የሚሰማኝን ብናገር ቢያንስ ዴሞክራሲያዊ መብቴን “ባልተሸራረፈ” መልኩ እንደተጠቀምኩበት ከመረዳቴም በተጨማሪ የተወሰነ እፎይታን አገኛለሁ፡፡ ለማንኛውም ወደአንዱአለም የመጨረሻ የችግሮቻችን መፍትሔ እናምራና ለአፍታ እንመልከትለት፤

 

ትልቁ ጥያቄ ኢሕአዴግ የብሔራዊ ዕርቁን ጥያቄ አሁንም “የባልና የሚስት ፀብ አይደለም” ብሎ ቢያጣጥለው ምን ማድረግ ይቻላል? የሚለው ነው፡፡ በእኔ እምነት ኢሕአዴግ ከዚህ በኋላም (እስካሁን) ለ21 ዓመታት የዳከረበትን መንገድ የሚመርጥ ከሆነ ተቃዋሚዎች ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ሆነው የሚጓዙ(በ)ት የራሳቸው አዲስ መንገድ መፈጠሩ አይቀሬ ይመስለኛል፡፡ ኢትዮጵያን በአስተማማኝ መሠረት ላይ ለመገንባት (የ)ሚያስችለውን የብሔራዊ ዕርቅ መንገድ በመጓዝ ለፍትሃዊ ነፃና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንገድ መጥረግ የማይፈልግ ኃይል በኢትዮጵያ ሕዝብ ሰቆቃ ላይ የራሱን ግላዊ ወይም ቡድናዊ ጥቅም ብቻ የሚያስቀድም መሆኑን ያመለክታል፡፡ ኢሕአዴግም ይሄን መንገድ እስከመረጠ ድረስ የኢትዮጵያን ሕዝብ በኃይል ረግጦ የመግዛት ፍላጎቱን አሁንም ለመቀጠል እንደሚፈልግ ያሳያል፡፡ የማንወጣው መንገድ ቢሆንም ከተገደድን ግን ኢትዮጵያውያን በፀና ሰላማዊ ትግል ኢሕአዲግን ልኩን እንዲያውቅ ብሎም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ፈቃድ እንዲገዛ ማድረግ አማራጭ የለውም፡፡ … (መስመር የተጨመረ) 

 

 

ወያኔ ልኩን የሚያውቀው በሰላማዊ ትግል ነውን? ይህ ነገር እውነት ይሆን? ይህች ነገር አጭር የክበበው ገዳን ቀልድ ትመስለኛለች፡፡

 

 

በመሠረቱ ጥሩ መመኘት በራሱ መጥፎ አይደለም፡፡ ነገር ግን የምኞትን ገደብ ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ አንዱአለም ከዕድሜ አንጻርም ይሁን ከገጠመኝ ማጠጥ/ማጠር የተነሣ በኢትዮጵያ ምድር አይመኙትን ምኞት በመመኘት እርሱን መሳይ የዋሃንን በተስፋ ዳቦ ለመቀብተትና በከንቱ ለማስገሳት ሲጥር እንመለከታለን፡፡ እዚህም ላይ ወያኔን አለማወቁ ያሳዝነኛል፡፡ ማንበብ ጥሩ ነው፤ ማወቅና መመራመርም ጥሩ ነው፡፡ ተስፈኝነት መልካም ነው፡፡ ተስፋ አለመቁረጥና ሩቅ ማሰብም ደግ ነው፡፡ ይሁንና ጓዳችን ውስጥ እንደመዥገር ተለጥፎ በመርዘኛ ጥርስና ምላሱ እያንገበገበን የሚገኘውን ወያኔ በሰላማዊ ትግል ይወገዳል ብሎ ማሰብና መስበክ አንድም ባለማወቅም ቢሆን የወያኔን ዓላማ የማራመድ ያህል ነው አለዚያም ሞኝነት ነው፡፡ ቢሆን በወደድን፡፡ ግን ፈጽሞ አይሆንም – ተምኔታዊነት (ዩቶፒያን መሆን) ነው፡፡ ኔልሰን ማንዴላ ለኢትዮጵያ አብነት ሊሆን አይችልም፤ ማኅተመ ጋንዲ ለኢትዮጵያ አብነት ሊሆን አይችልም፡፡ እነዚህ ምርጥ የዓለማችን ዜጎች የታገሉት ከሰዎች ጋር ነው፡፡ የኛን የሚለየው ትግላችን ከድፍን ቅል ዘረኞችና መቼም በማይበርድ እንዲያዉም እየሰላ በሚሄድ የጥላቻና የቂም በቀል አባዜ ከተሞሉ የባንዳ ልጆች ጋር ነው፡፡ ምናልባት አንዱአለም ያልተገነዘበው ይህንን ሃቅ ሊሆን ይችላል ብዬ እገምታለሁ፡፡ በዚያ ላይ በሰላማዊ ትግል ቀርቶ በመሣሪያም የሚነቀንቃቸው እንዳይኖር ሕዝቡን በማይምነት ጋርደው፣ ፍጹም ከደረጃ በታች በሆነና “A,B,C,D”ን በቅጡ በማያስለይ እንዲሁም ዜጎችን በሚከፋፍል የትምህርት ሥርዓት ትውልድን አደድበው፣ ጥቂት የማይባሉ ኢትዮጵያውያንን በማይረባ የጥቅም ፍርፋሪ ከፋፍለው፣ በዘረኛ የፌዴራል ፖሊስ፣ በደንቆሮ ካድሬና መከላከያ አፍነው፣ በቅንድብ ጥቅሻና በስልክ ቀጭን ትዕዛዝ ወንበዴዎቹ የሚፈልጉትን ፍርድ በሚያስተላልፍ ኮንዶም ዳኞችና ፍርድ ቤቶች ሀገር ምድሩን ሞልተውት፣ ዜጎችን በጎጠኛ የፀጥታና ደኅንነት መዋቅር ቀፍድደው፣ በድህነት ኮድኩደው፣ በተለይ ወጣቱን በልዩ ልዩ ሱሶችና በወሲብ የአዶከብሬ ዛር ዳንኪራ አስረግጠው፣ በመርዘኛ የጎሰኝነትና የዘረኝነት በሽታ ሕዝበ አዳምን በክለው፣ … ከጠማማ ጎጆው ባለፈ – የሰኞን ነፍሱን ወደማክሰኞ በማሳደሩ ከመደሰት በዘለለ ለሀገርና ለወገን የሚቆረቆር ዜጋ እንዳይኖር አድርገው የሀገሪቱን ኅልውና ገደል ጫፍ ላይ ጥለውታል፡፡ ይህን ኃይል በሰላማዊ መንገድ እጥላለሁ ብሎ ማሰብ ዕብደት ነው የምለውም ለዚህ ነው፡፡ የደቡብ አፍሪካው አፓርታይድ ሥርዓት የመጨረሻ ፕሬዝደንት ኤፍ ደብልይው ደክለርክ ጭንቅላቱ ውስጥ ተሸክሞት ይዞር የነበረው ሊማር የሚችል ጤናማ ነጭ አንጎል እንጂ እንደወያኔ በድንቁርና የታጀለ ከመግደልና በሰው ስቃይ ከመደሰት ውጪ ምንም የማያውቅ የገማና የበሸቀጠ ጥቁር ጭቃ አልነበረም፡፡ ወያኔን በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ ማለት ለወያኔ አዲስና ለራሳቸው ለአባላቱም ቢሆን ግርታን የሚፈጥር ልዩ ተፈጥሮን እንደማላበስ ይቆጠራል፡፡…     

አፄ ኃ/ሥላሴ ለጉብኝት ይሁን ለሥራ ወዳንድ ቦታ ሲሄዱ አንዲት ችግረኛ ሴት ከነልጆቿ መንገድ ዳር ቆማ “ወድቃ በተነሳችው ባንዲራችን፣ በልዑል እግዚአብሔር ይሁንብዎ…” በማለት ባንዴራ ዘርግታ ታስቆማቸዋለች፡፡ ያኔ እንደዛሬው ዘመን መሪ ሲወጣና ሲገባ ግድግዳ እያስደገፉ (የሚገርም እኮ ነው!) ለገዢዎች የኅለውና መሠረት ከመሆናቸው አንጻር ውድና ብርቅ ሊሆኑ የሚገባቸውን ዜጎች በኢሰብአዊነት ማሰቃየት አልነበረምና ጃንሆይ መኪናቸውን አስቁመው በመውረድ “ችግርሽ ምንድነው?” ብለው ይጠይቋታል፡፡ ሴትዮዋም፣ “ጃንሆይ፣ ለምግብ ያላነሱ ለሥራ ያልደረሱ ስድስት ልጆችን ጥሎብኝ ባለቤቴ ሞተ…” ብላ ችግሯን መናገር ስትጀምር በቀልደኛነት የሚታወቁት የቀድሞው ንጉሣችን አጠገባቸው አጅበዋቸው ወደቆሙ መኳንንት ዘወር ብለው “አግባኝ ነው የምትለው?” ብለው እንደዋዛ ጣል ያደረጓት ቀልድ በሴትዮዋ ጆሮ ገብታ ኖሮ ድሃ መቼም ሞኝ ነውና “ጃንሆይ! ሆኖልኝ ነው! አ’ርጎት ነው!” አለች ይባላል፡፡ ቀልድ በአግባቡ ጥሩ ነው፡፡ ኃ/ሥላሴ ሴትዮዋን እንደማያገቧት ግልጽ ነው – ሴትዮዋ ግን ድሃና በዕውቀትም ዝቅተኛ ናትና በጣለችው ተስፋ አንፈርድባትም፡፡ ከወያኔ ጉያ ሕዝባዊ ሥልጣን በሰላማዊ መንገድ ይገኛል ተብሎ ተስፋ ማድረግ ግን ከሴትዮዋ የበለጠ ጅል መሆንን የሚያመለክት እንጂ የወያኔን ተፈጥሮ ከመገንዘብ የሚመነጭ ገምቢ ዕውቀትና ጥበብ አይመስለኝም፡፡ ይህን የሚመር ቀልድ የሚቀልዱ ሰዎች ራሳቸውን ቢመረምሩ የተሻለ ነው፡፡ ሰላማዊ ትግል ደግሞም በኢትዮጵያ – ሆ!

በጦርነት የሚገኝ ነገር መልካም ነው እያልኩ እንዳልሆነ ግን ይመዝገብልኝ፡፡ ምርጫ ከጠፋ ግና ምን ይደረጋል? ከሁለት መጥፎዎች የተሻለውን መምረጥ የምንገደድበት ጊዜ ይኖራል፡፡ እናም ሰው ካልሆነ አውሬ ጋር እየታገሉ ከማለቅ ቢያንስ የራሴ ነው ከሚሉት ጨካኝና አምባገነን መሪ ጋር መፋለም ይመረጣል – ለዚያም መብቃት እኮ መታደል ነው፡፡ እንደሚመስለኝ አሁን ሰዎችን እያሳሰባቸው ያለው የማያሳስብ ነገር ነው፡፡ ቀድሞ የመቀመጫየን ያለችው ፍጡር ወድዳ እንዳልሆነ መረዳት ተገቢ ነው፡፡ “ሌላውን እሾህ በመቀመጫየ ተቀምጬ ራሴው እነቅለዋለሁ” ማለቷ ነው፡፡ እና ያልበላንን የሚያኩልን ወገኖች አደብ ቢገዙልን ብዙ እንደረዱን ይቆጠራል፡፡ ለነገሩ ወያኔን ማንም ደገፈው ማን – በማወቅም ይሁን ባለማወቅ -  ወቅቱን ጠብቆ ወረደ መቃብሩን ሳይወድ በግዱ መቀበሉ አይቀርም፡፡ አንድዬ በመንበሩ ካለ – አለም- ይህን ሁሉ ግፍና በደል የፈጸሙ ሰው መሳይ “ሰዎች” የቁናቸውን ሳይከፈሉ ይቀራሉ ብሎ ማሰብ የታሪክንና የፈጣሪን ፍርድ አለመረዳት ነው፡፡ የሞተ ይነሳል፤ የተኛ ይነቃል፤ የቆመ ይቀመጣል፤ የተጋደመ ይቆማል፡፡ ለሁሉም ጊዜ እንዳለው ዛሬ አይደለም የምናውቀው፡፡ ታሪክና እግዜሩ ወያኔ ላይ ሲደርሱ ሥራቸውን ያቆሙ ይሆን? ለጅላጅሎቹ ወያኔዎች እንዲያ ሳይመስላቸው የሚቀር አይመስለኝም፡፡ ለኔ ግን በፍጹም! ጊዜው ቀርቧል፡፡

አገባቤና አወጣጤ የተምታታ ነገር ያለበት መሆኑ ይሰማኛል፡፡ ለዚህ የተምታታ ነገሬ ማንን ይቅርታ መጠየቅ እንዳለብኝ ግን አላውቅም፡፡ የሆኖ ሆኖ የዚህ ዘመን እውነት ባብዛኛው የተዘበራረቀ በመሆኑ አላግባብ ሊፈርድብኝ የሚቃጣ እንደማይኖር እገምታለሁ፡፡ ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራልና ወደማይቀረው ድል እየተጠጋን ስንመጣ እንጫወታለን፡፡ ማርቲን ሉተር ባይቀድመኝ እኔም “ህልም አለኝ!” ብል በወደድኩ፡፡

 

“ቀኒቷን ማንም አያውቅም፡፡ ከጥቂቶች በስተቀር ብዙኃኑ ጎጋም እንኳን የምፅዓትን የመጨረሻ ቀን አያውቃትም፡፡ እናንተ የሚገባችሁ ታጥባችሁ ታጥናችሁ መጠበቅ ነው – ከሙስናና ከዕድፍ ርቃችሁ፤ ከዘረኝነት አረንቋና ከሆዳምነት ተቆጥባችሁ፤ አስተዋይነትን ተላብሳችሁ፣ በወረተኛ ወጀባዊ ንፋስ እንዳትወሰዱ ተጠንቅቃችሁ … ፡፡ ይሁንና ምልክቶቹን ስታዩ የቀኒቷን መቅረብ ትረዳላችሁ፡፡ ምልክቶቹን ያዬ ትውልድ ከምፅዓት በፊት የምትገለጠዋን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ቀን ያያታል፡፡ …” (‹መጽሐፈ ትንሣኤ ኢትዮጵያ› ፣ ምዕራፍና ቁጥር የማይነበብ!)  

በየነ

 More on —-http://www.freeandualemaragie.org/?p=359

↧

የኢትዮጵያና የሱዳን የጦር ስምምነት

$
0
0

ትዮጵያና ሱዳን የጋራ የመከላከያ ኃይል ለመፍጠር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የሁለቱም ሃገሮች የመከላከያ ሚኒስትሮች አስታውቀዋል፡፡
ኃይሉ ሥራ የሚጀምረው የፊታችን መስከረም ላይ እንደሚሆን የኢትዮጵያው የመከላከያ ሚኒስትር ሲራጅ ፈጌሣ ተናግረዋል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Source: voanews

Ethiosudan

↧
↧

ባዕት ዕንባ በልታ። (ከሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 13.08.2014 ( ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

xxe

በትቢያ – ድሪቶ

በቋሰኛው – ጉቶ

ተመተረ ዘመን – በቅንቅን ተበልቶ፤

በበደል ተቁላልቶ

በግለት ተወግቶ

በቁርሾ ተሰልቶ።

ሲናሳ መራራ – የአስተሳሰብ ንቅዘት

ሲሰነብት እሬት – የባንዳነት ስባት

- ብነት።

ትናትን – ገደለ

ዛሬን – ረሸነ

ነገን – አተነነ

ዬበነነ።

ዞጋማ ቁሌቱ

ቅብረት ነው ስሌቱ

የወያኔ ማቱ

ጥፋቱ።

ዬት ሳውቅህ – በምንህ!?

ቃር=== ማ —- ነው ቃርሚያህ

የደም ሲቃ ግብርህ።

ዘረፋ – ሰርዴታህ

ዕበለትም – አትራፊህ፤

ሲካዳህ – ዕለትህ

የቆዬ ሰው፤ – ይይህ

ትነቱ ዘመድህ – የዘለአለም ስንቅህ

ፍልሰትህ —።

ኤሉሄ! ትላለች እናት ልጇን አጥታ፣

ኤሉሄ! ትላለች ባዕት ዕንባን በልታ፣

ኤሉሄ! ይለዋል ምጣድ የድርቅ ዋልታ

ኤሉሄ ትላለች – እንሥራ ተጠምታ፤

የሲሳዩ ማሳ በዕንባ እዬተፈታ

በጫካ -  ገበጣ።

ሸንተረር አነባ – በጉልበት ሲመታ

ወንዙም ሆዱ ባባ – በእርግጫ ሲለጋ

አፈር አለቀሰች – ተግርፋ በአለንጋ ….

… በበቀል ተወራ – ለድርቡሽ ተሰጥታ

ከውስጧ – ተራቁታ።

ጥንት – ከጥዋቱ፤ ልጇ ተቆላምጦ

የሚፈልገውን እንዳዬው መራርጦ …

ታዬ በወያኔ – ቀኑ ተገልብጦ —-

…. ተቀማ ዕህሉን፤  ወገን በወረንጦ

አምጦ።

ወያኔ የሚሉት —- የመከራ ጥሪት

ወያኔ የሚሉት —  የአሳሩ ስሌት

ወያኔ የሚሉት —- የመጋኛ ሌሊት

ወያኔ የሚሉት — የአሲድ እፉኝት

ህማማት።

የዋህነት – ቀብሮ

ቅንነትን – ቀብሮ

አብሮነት – ተቀብሮ

ትህትናንም – ቀብሮ

መተዛዘን – ቀብሮ

ነፃነት ተባሮ

መርዛማው ወያኔ – ውሳጣችን – ቆፍሮ

አዬነው እራሱን በጥፋት ተቀብሮ፤

በመንደር ተዋቅሮ

እሮ!

አመዳማ — ጉዞ

ጎርብጥባጣ — አዞ

ሳጥናኤል — ተመዞ

ለጥፋትም — ታዞ፤

ታሪክን – አንቅዞ

ትውፊትን – አፍዝዞ

ባህልን – ጠምዝዞ

መንፈስ –  ተገንዞ

ናውዞ።

ሞት ቢሞት ሞቱ ነው

ቢኖርም ሞቱ ነው

ሰኔልና ቹቻ

ስለት ለቋቁቻ።

 

 

28.06.2014 ሲዊዘርላንድ ቪንቱርቱር ተጣፈ።

 

መከራን ሳዳምጠው ደሜን አገኘዋለሁ!

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

 

 

↧

ወያኔ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ የሚያደርሰው ቅጥ ያጣ አፈናና በደል

$
0
0

ፋሲል አያሌው

 

cartoon_HMD

አሁን በስልጣን የሚገኘው የወያኔው ስርአት ላለፉት 22 አመታት የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ እያለ ጆሮአችንን ቢያደነቁረውም እሱ የሚለው የዲሞክራሲ ስርዓትና ትክክለኛው ዲሞክራሲያዊ ስርአት አራምባና ቆቦ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ዲሞክራሲያዊ ስርአትን በገመድ ለክቶና መጥኖ የናንተ መብትና ነጻነት እስከመጨፈር እንጂ የኔን ስልጣንና ጥቅም የሚነካ ከሆነ ቢላ ባንገቴ ካለን ሰነባበተ:: ለዚህም ይመስላል በተለይም ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው የተቃውሞ ድምጻቸውን ለሚያሰሙ ጋዜጠኞችም ሆነ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምንም አይነት መፈናፈኛ እንዳያገኙ ሌት ተቀን ደፋ ቀና የሚለው::


ከዚህም የነጻነት እጦት እና ፍጹም አምባገነናዊ አፈናዎች መካከል እንደ አንድ ማሳያ የሚሆነው በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ የሚያደርሰው ቅጥ ያጣ አፈናና በደል ሲሆን ዛሬ በወያኔው ስርዓት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚታዩት እንደ ተፎካካሪ ፓርቲ ሳይሆን ሃገርን ለማፍረስ እንደተዘጋጁ አሸባሪዎች ተደርገው ነው:: በጣም የሚያሳዝነውነና አደገኛው አካሄዱ ደግሞ ይህን እምነቱን ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያምንና እንዲቀበል ፍጹም ህገወጥ በሆነና ከዕውነት በራቀ ውንጀላ ተቃዋሚዎችን ለማጠልሸት የሚያደርገው እልህ አስጨራሽ ትግሉ ነው::


ስርዓቱ በተለይም ከ1997 ዓ.ም ወዲህ ተቃዋሚዎችን ለማዳከምና ለማጥፋት ፍጹም ኢ-ፍትሃዊና ህገወጥ በሆነ መልኩ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በሁለት ስትራቴጂዎች የተዋቀረ ነው::
የመጀመሪያውና ቀጥተኛው ስትራቴጂ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን አሸባሪና እሱ ራሱ አሸባሪ ናቸው ብሎ ከፈረጃቸው ድርጅቶች ጋር ማያያዝ (ማዛመድ) ነው:: ይህንንም ለማሳካት የተቃዋሚ ድርጅት አባሎችን ከአሸባሪ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል የፈጠራ ክስ መወንጀል ሲሆን በጣም በሚያሳፍርና በሚያሳዝን መልኩ በዚህ ስትራቴጂ ውስጥ ይቃወሙኛል ብሎ ያሰባቸውን የነጻው ሚዲያ ጋዜጠኞችንም ይጨምራል:: እንግዲህ ይህ ስትራቴጂ የተወሰኑ ግለሰቦችን በአሸባሪነት ክስ ወደ ዘብጥያ በማውረድ ብቻ የተገታ ወይም የተቋጨ ነው ብሎ የሚያስብ የዋህ ይኖራል ብዬ አላስብም ዋናው አላማ አማራጭ ሚዲያና እውነተኛ መረጃ የተነፈገው ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ በፍርሃት ውስጥ እንዲሸማቀቅና ለትክክለኛ የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ የሚኖረውን የጋለ የህዝብ ስሜት ጥቁር ጥላ እንዲያጠላበት የሚያደርግ እንጂ::


በዚህ ስትራቴጂ የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔውን ስርአት የሃሰት ውንጀላ ጠንቅቆ የሚያውቅ ቢሆንም ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል እንዲሉ አንድ ለናቱ በሆነው የገዢው ስርአት ሚዲያ በየቀኑ የሚቀርበው የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ህዝቡ ለተቃዋሚዎች፣ ለገዢው ፓርቲም ይሁን ለጠቅላላ የፓለቲካው ድባብ የሚኖረው ስሜት በፍራቻ፣ በጥርጣሬና ቀላል በማይባል ሁኔታ በፓለቲካው ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ውስጥ እንዲገባ የማድረግ ሃይሉ እጅግ ከፍተኛ ነው::


ከዚህም በተጨማሪ ይህንን አደገኛ አካሄድ የከፋ የሚያደርገው ደግሞ ተቃዋሚዎች ምንም አይነት ሃሳባቸውን የሚገልጹበት ነጻ ሚዲያ ሰለሌላቸው (ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ እንኳን እንደታፈነች ነች)በፈጠራ ክስ ለታሰሩ አባሎቻቸውም ሆነ ለደረሰባቸው የመልካም ገጽታ (Good Will) መበላሸት ማስተባበያ የመስጠትም ሆነ የመከላከል አቅሙ የሌላቸው መሆኑ ነው::
ሁለተኛውና ቀጥተኛ ያልሆነው ስትራቴጂ ከመጀመሪያው ስትራቴጂ ጋር የሚያያዝ ሲሆን ተቃዋሚዎች የመሰብሰብ፣ የመደራጀት ከህዝቡና ከደጋፊዎቻቸው ጋር የመገናኘትና የመቀስቀስ ስራዎቻቸውን እንዳይሰሩ በእጃዙርም ይሁን ባስ ሲልም በቀጥታ የማፈንና የማሰናከል ተግባር ነው::


ይህንን እቅዱን እውን ለማድረግም ተቃዋሚዎች የመሰብሰቢያ አዳራሾችን እንዳያገኙ የተለያዩ መሰናክሎችን መፍጠር፣ ራሳቸውን በገቢም ይሁን በተለያዩ ነገሮች ለማጠናከር የሚደረጉ ዝግጅቶችን ማስቆም፣ ማሰናከል፣ ተቃዋሚዎች የሚጠሩትን ሰላማዊ ሰልፎች አለመፍቀድ ወይም መሰረዝ፣ ምንም አይነት ነጻ ሚዲያ እንዳያገኙ መዝጋትና ሌሎችንም ዘዴዎች ይጠቀማል:፡


ሌላውን ሁሉ ትተን ዛሬ በጣም በሚሳዝን ሁኔታ በሃገራችን ለተቃዋሚዎች አንዱ ከባዱ ስራ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ማግኘት ነው:: ከተወሰኑ ጊዚያቶች በፊት ሰማያዊ ፓርቲ የመመስረቻ ጠቅላላ ጉባኤውን የሚያደርግበት አዳራሽ አጥቶ ምን ያህል እንደተቸገረ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው::ዛሬ ለአንድ ህጻን ልጅ ልደት ለማክበር እንኳን አዳራሽ በሽ በሆነበት ሃገር ተቃዋሚዎች መሰብሰቢያ አዳራሽ አጥተው በሰው ቤት ጓሮ ዳስ እየጣሉ ግማሹ ተሰብሳቢ ጸሃይ እየበላው ነው ስብሰባቸውን የሚያካሂዱት:: የሆቴል ቤት ባለቤቶችና አዳራሽ አከራዮች በወያኔው ስርዓት በሚደርስባቸው ከባድ ተጸዕኖ ለተቃዋሚዎች አዳራሾቻቸውን ለማከራየት ፈቃደኞች አይደሉም::


የሃገሪቷ ሃብት በወያኔዎች እጅ በወደቀበት በዚህ ሰዓት ኣንድ የሆቴል ቤት ባለቤት አዳራሹን ለተቃዋሚዎች ቢያከራይ በህብረተሰቡ ውስጥ በዘሩት የተቃዋሚዎችን ስም በሀሰት የማጠልሸት ተግባር፣ ፍራቻና የስጋት ድባብ እንዲሁም ወያኔዎችና ደጋፊዎቻቸው በሆቴሉ ላይ በሚጀምሩት የሃሰት አሉባልታ ሆቴሉ ቀስ በቀስ ከገበያ ውጭ ሊሆን ስለሚችልና ምናልባትም ካስፈለገ ሆቴሉን እስከማሳሸግ ሊደርሱ እንደሚችሉ ስለሚታወቅ ነው ( በ1997 ዓ.ም ምርጫ ወቅት የመርካቶው ምዕራብ ሆቴልና ሌሎችም ሆቴሎች ተቃዋሚዎችን ትረዳላቹ ተብለው ታሽገው እንደነበር አይዘነጋም::)


እንግዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ በተቃውሞው ጎራ መሰለፍ እንደ ሃገር ጠላት የሚታይበት ደረጃ ላይ መድረስ ብቻ ሳይሆን ባስ ካለም አሸባሪ የሚል ታርጋ አስለጥፎ ወህኒ ሊያስወረውር የሚያስችልበት ሁኔታ ኢትዮጵያውያኖችን በነጻነት የሚፈልጉትን ደግፈው ወይም ተቃውመው መኖር እንዳይችሉ ብቻ ሳይሆን በፍርሃት እንዲሸማቀቁና እንዲሰጉ ምክንያት ሆኗል:: ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ የወያኔን ስርዓት መቃወም ስትጀምር በዚያውም ወደ እስር ቤት መቃረብህን ትረዳለህ:: አንተን ለመክሰስ የማስረጃ ጉዳይ ብዙም አያስጨንቅም በኢ- ማይልህ ላይ አንዳንድ መረጃዎችን ወይም ሞባይልህ ላይ ጥቂት መልእክቶችን መላክ (SMS) ማድረግ አንተን ዘብጥያ ለማውረድ በቂ ናቸው:: ( ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ከወንድሙ ጋር በኢ-ሜይል ስለአባታቸው የህክምና ኦፕሬሽን (Operation) የተጻጻፉትን ኦፕሬሽን የሚለው ቃል ሌላ አላማ ተብሎ እንደማስረጃ የቀረበበት ሁኔታን ልብ ይሏል::)


በተጨማሪም እስር ቤቶቻችን ጥፋተኛን ወይም ወንጀል የሰራን ጸባዩን ከማረም ይልቅ በፓለቲካ አቋማቸው በግፍ የታሰሩ ወገኖቻችንን ቅስምና ሞራል ለመስበር በእስረኞች ላይ የሚደረገው ግፍ ለማመን የሚከብድ ነው:: ለዚህም ይመስላል ሁለቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች እንዲህ ያለ የእስር ቤት ግፍ በአሜሪካዊው ፊልም ዳይሬክተር ስቴቨን ስፒልበርግ ፊልሞች ላይ እንጂ በእውን በዚህ ምድር ላይ ያለ አይመስለንም ነበር ያሉት::

↧

በጋዜጠኞች ላይ የተከፈተው የክስ ዘመቻ ቀጠለ፤ እንቁ እና ጃኖ መጽሄቶችና አዘጋጆች ተከሰሱ (የክስ ቻርጁን ይዘናል)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የሕወሓት አስተዳደር የፍትህ ሚ/ር ሃሳብን የመግለጽ መብታቸውን ተጠቅመው በመሥራት ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች ላይ የክስ ፋይል መክፈቱን ተያይዞታል። ከትናንት በስቲያ በሎሚ መጽሔትና በአዘጋጁ ግዛው ታዬ፣ ትናንት በአፍሮ ታይምስ እና በአዘጋጁ ቶማስ አያሌው ላይ የተከፈተው ክስ ዛሬ ቀጥሎ በእንቁ መጽሔትና አዘጋጁ አለማየሁ ማህተመወርቅ እና በጃኖ መጽሔትና በአዘጋጁ አስናቀ ልባዊ ላይ ክስ ተመስርቶ የክስ ቻርጅ ደርሷቸዋል።

የክስ ቻርጆቹን ተመልከቷቸው።

ምርጫ እየደረሰ ባለበት በዚህ ወቅት በጋዜጠኞች ላይ እንዲህ ያለው አፈና መፈጸሙ ብዙዎችን እያስቆጣ ይገኛል።

enqu 1

enqu 2

enqu 3

jano 1

jano 2

↧

ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰው የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የአፍ ወለምታ ስለሙስሊም ታሳሪዎች –የጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ልዩ ትንታኔ

$
0
0

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ቴዎድሮስ ስለሙስሊም ታሳሪዎች ምን አሉ ? ድንበር የለሹ የህወሃት ፕሮፖጋንዳ ሲፈተሸ የዶ.ር ቴዎድሮስን ንግግር አስመልክቶ ሳዲቅ አህመድ ልዩ ዝግጅት አሰናድቷል
ሳዲቅ እዉነታዎችን በመፈተሽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ንግግር የ አፍ ወለምታ ሳይሆን ሚኒስቴሩ ሆን ብለዉ የፈጠሩት ብዥታ በመሆኑ ኦፊሴላዊ መግለጫ ሊሰጡ ይገባል ሲል ይደመድማልና ፕሮግራሙን እንከታተለዉ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የአፍ ወለምታ ስለሙስሊም ታሳሪዎች – የጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ልዩ ትንታኔ

↧
↧

Health: የዘር ፈሳሼን ቶሎ ማፍሰስ /Premature Ejaculation/ የትዳሬን መፍረስ ምክንያት ሊሆን ደርሷል፤ እባካችሁ እርዱኝ (የዶ/ሩ ምላሽ)

$
0
0

እባካችሁ የዘር ፈሳሼን ቶሎ የመጨረስ ወይም የወሲብ ፈሳሽ ቶሎ የማፍሰስ ችግር አለብኝ እና በዚህ ምክንያት ትዳሬም ሊፈርስ ነው፡፡ እኔም በከፍተኛ ችግር ውስጥ ነኝ ከአሁን ከአሁን ይሻላል ብልም ያተረፍኩት ልክ እንደ ሩጫ ውድድር በየጊዜው የቀድሞውን ሪኮርዴን ማሻሻል ብቻ ነው፡፡ ምን ይሻለኛል ከጉድ አውጡኝ፡፡
እውን አበበ

Premature Ejaculation 1
ብዙ ወንዶች አንዳንድ ጊዜ ራሳቸውን ወይም የወሲብ ጓደኛቸውን ከምትፈልገው ቀደም ብለው ሊጨርሱ/Ejaculate/ ይችላሉ፡፡ አንዳንዴ ብቻ ከተከሰተ ብዙም የሚያሳስብ ችግር አይደለም፡፡ ነገር ግን በተደጋጋሚ ወይም ሁልጊዜ የሚከሰት ከሆነ እንደ ጠያቂያችን አቶ እውን አበበ በህክምና ቋንቋ ፕሪ ማቹር ኢጃኩሌሽን/premature ejaculation/ ወይም ወቅቱን ያልጠበቀ እርካታ ችግር አለ ማለት ነው፡፡

ወቅቱን ያልጠበቀ እርካታ/ማፍሰስ/ በጣም በስፋት የሚታይ የወሲብ ችግር ነው፡፡ ግምቱ ቢለያይም ከሶስት ወንዶች መካከል አንዱ የዚህ ችግር ተጠቂ እንደሆነ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ምንም እንኳን ብዙ ወንዶች አፍረት ስለሚሰማቸው ስለዚህ ችግር ከሐኪሞቻቸው ጋር አይነጋገሩም፡፡
በፊት በፊት ይህ ችግር የሳይኮሎጂ ችግር ብቻ ተደርጎ ይታይ ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን የውስጥ ችግርም የዚህ ችግር ምንጭ እንደሆነ ጥናቶች ጠቁመዋል፡፡ በአንዳንድ ወንዶች ይህ ችግር በብልት መነሳሳት ችግር ምክንያት እንደሚመጣም ታውቋል፡፡
አንድ ወንድ ለማፍሰስ ምን ያክል ጊዜ መውሰድ አለበት የሚል የወጣ ስታንዳርድ በህክምና የለም፡፡ ነገር ግን የዚህ ችግር ዋናው ምልክት ሁለቱ የወሲብ ጓደኞች ከሚፈልጉት በፊት የሚከሰትና ለሁለቱ አሳሳቢ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ ይህ ችግር በማንኛውም የወሲብ ጨዋታዎች ሊከሰት ይችላል ማለትም ራስን በማዝናናት ወይም ከወሲብ ጓደኛ ጋር በሚደረግ መዝናናት ወቅትም ሊከሰት ይችላል፡፡

በህክምና ይህ ችግር ፕራይመሪ ፕሪማቹር ኢጃኩሌሽን/Primary premature ejaculation/ ሲባል ይህ ማለት አንድ ሰው ወሲብ ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ ይህ ችግር የሚታይበት ሲሆን ነው፡፡
ሌላው አይነት ደግሞ ሰከንደሪ ፕሪማቹር ኢጃኩሌሽ Secondary Primary premature ejaculation ሲባል በፊት ጥሩ የወሲብ ሁኔታ ያለው ወንድ የኋላ ኋላ የመጣ ቶሎ የማፍሰስ ችግር ሲገጥመው ማለት ነው፡፡
የዚህ ችግር መንስኤ ገና እየተጠና ሲሆን በፊት በፊት የሳይኮሎጂ ችግር ብቻ ነው ተብሎ ሲታሰብ የቆየ ሲሆን አሁን ግን መንስኤው ውስብስብና የሳይኮሎጂክና የአካላዊ /ባየሎለጂካላዊ/ ችግሮች ጋር በጥምረት የመጡት ችግሮች ነው፡፡ ወደዚህ መላምት በመግባት አንባቢን ግራ ከማጋባት እቆጠባለሁ፡፡
በርካታ ሁኔታዎች የዚህን ችግር መከሰት ያባብሳሉ፡፡ ከዚህም ውስጥ የወሲብ አካል አለመነቃቃት ለምሳሌ የተነቃቀው የወሲብ አካል ሊቀዘቅዝ ይችላል ብሎ ከመስጋት ቶሎ ወደ መጨረስ መሯሯጥ ሊከሰት ይችላል፡፡ ቶሎ የማፍሰስ ችግር ካላቸው ሶስት ሰዎች መካከል አንዱ የወሲብ ንቃታቸውን እንዲነቃቃ ማቆየት ያቅታቸዋል፡፡ በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ ችግር ይፈጠራል ተብሎ የሚገመት በሽታ ለምሳሌ የልብ በሽታ ችግሩ ያለበት ሰው ተጣድፎ የመጨረሽ አዝማሚያ ሊያሳይ ይችላል፡፡ የአዕምሮ መዳከም ወይም ጭንቀት ቶሎ ለማፍሰስ ሊያጋልጥ ይችላል፡፡ ይህም በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ ዘና ብሎ ተመስጦ መተግበርን በመቀነስ ነው፡፡ አንዳንድ መድሃኒቶችም ለዚህ ሊያጋልጡ ይችላሉ፡፡

ሐኪም ጋር ሲቀርብ ሐኪሙ የተሟላ የግብረ ስጋ ግንኙነት ታሪክ ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡ አካላዊ ችግር የለም ብለው ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡ አካላዊ ችግር የለም ብለው ከገመቱ ወይም የሳይኮሎጂ ችግሩን ድርሻ ለማወቅ ከፈለጉ በዚህ ችግር ላይ ሰፋ ያለ ግንዛቤ ወዳላቸው ባለሙያዎች ተጨማሪ ትንተና ለማግኘት ሊልኩዎት ይችላሉ፡፡ ሌሎችም ምርጫዎች ሊያዙ ይችላሉ፡፡

በዚህ ችግር ማለትም ቶሎ በማፍሰስ ችግር ምክንያት እንኳን ሌላ የጤና ችግር ባይመጣም በግል ህይወት ውስጥ ጭንቀት ይፈጠራል፡፡ ዋና ዋና የዚህ ህመም ተጓዳኝ ችግሮች በትዳር ላይ ልክ ጠያቂያችን ያስቀመጡት አይነት ጭንቀት መከሰት ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ለህክምና ሲመጡ ከባለቤትዎ ወይም ከወሲብ አጋርዎ ጋር ቢመጡ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡

ቶሎ የማፍሰስ ችግር አንዳንድ ጊዜ የመውለድ ችግር ሊፈጥር ይችላል፡፡ ስለዚህ ቶሎ የማፍሰስ ችግሩ ካልተቀረፈ ምን አልባት ለመውለድ ሌላ የህክምና ዘዴ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡
የዚህ ችግር ህክምና በሶስት ዘርፎች ይመደባል፡፡ እነዚህም ሴክሽዋል ቴራፒ፣ የመድሃኒት ህክምና፣ እና የሳይኮ ቴራፒ ናቸው፡፡

የመድሃኒት ህክምናው የድብርት መድሃኒት በመስጠት የዚህ የድብርት መድሃኒት የጎንዮሽ ጉዳት ዘግይቶ ማፍሰስ ስለሆነ ከጎንዮሽ ጉዳቱ ተጠቃሚ ለመሆን የታቀደ ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህ መድሃኒቶችም ሌሎች ተጨማሪ የጎንዮሽ ጉዳቶች አላቸው፡፡ ሌላው መድሃኒት በብልት ላይ የማደንዘዣ ክሬም በመቀባት ስሜቱን በመቀነስ ቶሎ ማፍሰስን ለመዘግየት የሚሞክር ነው፡፡ ባይኮቴራፒው ከሳኮቴራፒስት ጋር በማውራት ጭንቀት በመቀነስ የሚሰራ ነው፡፡ አብዛኛው ባልትዳሮች ሁለቱም አብረው ሲኖሩ የተሻለ ውጤት አለው፡፡ ይህም በመካከላቸው ስለ ችግሩ በግልፅ ማውራትን እድል ይፈጥራል፡፡
የሴክሽዋል ቴራፒ/Sexual therapy/ ለምሳሌ ከግንኙነት በፊት አንድ ወይም ሁለት ሰዓት ቀደም ብሎ ማስተርቤት ማድረግ/ራስን አዝናንቶ መጨረስ/ ወይም ለረጅም ጊዜ ግንኙነት ሲያደርጉ በሌላ አይነት የወሲብ ጨዋታዎች ላይ ፎከስ በማድረግ በዋናው የወሲብ ግንኙነት ላይ ያለውን ጫና መቀነስ፡፡

ሌላው ጠቃሚው መንገድ የመጭመቅ ዘዴ ይባላል ሐኪምዎ ይህንን ዘዴ እንዲጠቀም ሊመክሩዎት ይችላሉ፡፡ አሰራሩ እንደሚከተለው ነው፡፡

ደረጃ አንድ፡- የግብረ ስጋ ግንኙነት ጨዋታ መጀመር/በተለመደው አኳኋን/ ይህ ብልትን በእጅ ማነሳሳትን ይጨምራል እስከ ፈሳሽ መምጫ ድረስ ይቀጥላል፡፡
ደረጃ ሁለት፡- የወሲብ ጓደኛህ ከማፍሰስህ በፊት በእጇ ክርክሩ ላይ ለበርካታ ሰከንዶች እንድትይዘውና የማፍሰስ ፍላጎቱ እስኪሞት በዛው መቀጠል፡፡
ደረጃ ሶስት፡- ጓደኛህ ጭምቅ አርጋ የያዘችውን ትልቀቀውና ለ30 ሰከንዶች መቆየት ከዚያም ወደ ጨዋታው መግባት በጨመቀው ቁጥር ደግሞ ያለው በድጋሚ የወሲብ ጨዋታ ወይም ማነሳሳት በድጋሚ ይነቃቃል፡፡
ደረጃ አራት፡- አሁንም የማፍሰስ ስሜት ሲመጣ የወሲብ ጓደኛህ በድጋሚ ክርክሩ ላይ ጨምቃ እንድትይዘው ማድረግ፡፡
ይህንን ቴክኒክ ደጋግሞ በማድረግ ከጓደኛ ጋር በሚደረግ ትክክለኛው ወሲብ ጊዜ ወዲያው ማፍሰስ ይቀርና አዲስ የመቆየት ልማድ ይፈጠራል፡፡ ይህንን ደጋግሞ ለብዙ ጊዜ ሳይታክቱ በማድረግ ይህንን ችግር ለመፈታት ይቻላል፡፡ መልካም ዕድል፡፡ መልካም የትዳር እና የወሲብ ዘመን፡፡

↧

ነቀርፉኝት! ነቀርፉኝት ማነው?

$
0
0

መግቢያ
ተወደደም ተጠላም ያለነው በጦርነት ላይ ነው፥፥ የመሣሪያ ድምፅ ኣለመሰማት የሰላም ምልክት!!አይደለም። የሕዋሃት ግፍና በደል ሞልቶ በፈሰሰበት፥ መከራችን በተራዘመበት በዚህ ወቅት፤ እነሱም አዋርደው መግዛትን እንደዋነኛ መገለጫቸው አድርገውታል። እኛም ውርደትን እንደ ኒሻን አጎንብሰን እንድንቀበላቸው፤ እንደውሻ የተፉትን አጎንብሰን እንድንልስላቸው ብቻ አይደለም የሚፈልጉት ከተቻለ ለዘላለም እነሱን ወደማናይበት ወደ ጥልቁ የሞት ሸለቆ ብንወርድላቸው እንጂ ።[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—

Comment

↧

ፍርድ ወይስ ፍዳ ! (ይድነቃቸው ከበደ)

$
0
0

በይድነቃቸው ከበደ

ይድነቃቸው ከበደ

ይድነቃቸው ከበደ

ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም በአናዋር መስጊድ በተነሳው ግጭት ምክንያት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙት፤ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባል አቶ ኢብራሂም አብዱልሰላም እና ወ/ሪ ወይንሸት ሞላ እንዲሁም የአዲስ ጉዳይ መፅሔት ፎቶ ግራፈር አዚዛ መሐመድ ከህግ አግባብ ውጪ ለተጨማሪ 48 ሰዓት በእሰር ቤት እንዲቆዩ ተደረገ፡፡


ሚክሲኮ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የቂርቆስ ምድብ ችሎት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባቀረበው የክስ አቤቱታ መሠረት በተለያየ ቀናት ከሳሽን እና ተከሳሽ መካከል ክርክር ሲደረግ ቆይቶ ሐምሌ 29 እና 30 ተከሳሾች (እነ ወይንሸት) እያንዳንዳቸው 5000 ሺህ ብር የሚገመት የንብረት ዋስ አሲዘው እንዲለቀቁ ውሳኔ አስተላልፎ ነበር፡፡ይሁን እንጂ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጉዳዩ ላይ ይግባኝ በመጠየቅ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲሻር በማድረግ 30 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የ7 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲፈቀድለት አስደርጓአል፡፡ይህን የህግድ ውሳኔ የሰጠው የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ነው፡፡ይሁን እንጂ የዚህን ትህዛዝ በክስ መዝግብ ውስጥ ፖሊስ ሳያካት ወይም ቀድሞ ውሳኔ ለሰጠው ፍርድ ቤት ሳያሳውቅ እነ ወይንሸትን ፖሊስ በራሱ ፍቃድ ብቻ እስር ቤት ሊያቆያቸው ችሎአል፡፡


በመሆኑም በተሰጠው የህግድ ትህዛዝ መሠረት በ07/12/06 ይግባኝ ባይ ፖሊስ በተሠጠው የጊዜ ቀጠሮ ለፍርድ ቤት ቀርቦ “የሚቀረን ተጨማሪ የሰው ማስረጃ ማሰባሰብ ፣ያልተያዙ አባሪዎችን መያዝ ነው፡፡ሆስፒታል ተኝቶ የነበረው ፖሊሲ የጤናው ሁኔታ ከነበረበት የተሸለ ስለሆነ የህክምና ማስረጃዎችን ጨርሰን ለአቃቢ ሕግ አስታየት ማሰጠት ነው” በማለት ለፍርድ ቤት ያስረዳ ሲሆን ፡፡ፍርድ ቤቱ “ ይግባኝ ባይ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀ ይሁን እንጂ ቀደም ሲል በተሰጠው የህግድ ትህዛዝ መሠረት የተጎጂዎች የህክምና ማስረጃ በማቅረብ ወይም የምርመራ መዝገቡን በመያዝ በአግባቡ አላስረዳም በመሆኑ የህግድ ትህዛዙን አንስተናል” በማለት በትላንትናው ዕለት ውሳኔ አስተላልፏአል፡፡ይሁን እንጂ ይህ ውሳኔ ከተላለፈ በኋላ ቀደም ብሎ ትዕዛዝ ወደተሰጠበት ፍርድ ቤት ታሳራዎችን በዋስ ለማስለቀቅ የተደረገው ጥረት ዳኞች እና የፍርድ ቤት እረዳት ሰራተኞች ስብሰባ ላይ ናቸው በመባሉ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡


ይህ በሆነ በማግስቱ ማለትም በዛሬው ዕለት በ8/12/06 ጠዋት 2፡30 ሚክሲኮ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የቂርቆስ ምድብ ችሎት በመቅረብ ቀድሞ የተወሰነው ውሳኔ ሰበር ሰሚ ፍ/ቤት አፅድቆታል በመሆኑም የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ታሳሪዎች እንዲለቀቁ ዋስ በማዘጋጀት ፍ/ቤቱ የማስፈቻ ትህዛዝ እንዲሰጥ ቢጠየቅም ፡፡ጉዳዩን የተመለከቱት ዳኛ በሰበር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ ግልብጭ ያስፈልጋል ይህም በመሆኑ ግልባጭ አምጡ በማለት ትህዛዝ ሰጡ፡፡ ህንዲህ አይነቱ ትህዛዝ በወቅቱ አስፈላጊ ባይሆንም ምን አይነት አማራጭ ባለመኖሩ ወደተጠቀሰው ፍርድ ቤት በመሄድ የውሳኔ ግልባጭ የተጠየቀ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት “እንዲ አይነት ትህዛዝ ከዚህ ቀደም ተሰጥቶ አያቅም በአሰራር ሂደትም ገጥሞን አያውቅም ” በማለት ለተጠየቁት የውሳኔ ግልባጭ ምላሽ ለመስጠት እጅግ በጣም መቸገራቸውን በመግለፅ የሁኔታው አሳሳቢነት ተረድተናል በማለት የተጠየቀውን የውሳኔ ግልባጭ ለመስጠት ችሎአል፡፡

semayawi 101
ይውሳኔ ግልባጭ የጠየቀው የታችኛው ፍርድ ቤት የጠየቀውን ትህዛዝ የቀረበለት ሲሆን ቀድሞ ትህዛዙን የሰጡት ዳኛ ምክንያቱ ባልታወቅ ሁኔታ የስራ ገበታቸው ላይ ሊገኙ አልቻሉም፡፡ይህ በመሆኑ የትህዛዝ ችሎት ዳኛ ለሆኑት ለተለዋጭ ዳኛ ጉዳዩን እንዳዲስ በማስረዳት የታሳሪዎች የዋስትና መብታቸው ተከብረሮ ከእስር ቤት እንዲወጡ የማስፈቻ ትህዛዝ እንዲሰጡ የተጠየቁ ሲሆን እሳቸውም በተራቸው “ እኔ ውሳኔ መስጠት የምችለው የሰበር ሰሚ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ መሠረት ብቻ ሳይሆን ቀድም ብሎ ሰበር ሰሚ ፍ/ቤት የእኛን ውሳኔ ያገደበት የህግድ ትዛዝ ግልባጭ ሲደርሰን ነው፡፡በመሆኑም ከሰበር ሰሚ ፍ/ቤት የህግድ ትህዛዙን ማምጣት አለባችሁ በማለት ውሳኔ አስተላለፉ፡፡ይህ ሲሆን ጉዳዩን በፍርድ ቤት በመገኘት በቅርበት ስንከታተል ለነበርነው የሰማያዊ ፓርቲ የምክ/ቤት ዋና ሰብሳቢ አቶ ሰኢድ ኢብራሂም፣የሰማያዊ ፓርቲ የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ አቶ እያስፔድ ተስፋዬ እንዲሁም የወይንሸት ሞላ እህት ወ/ሪ መልካም ሞላ እና አቶ አፍወርቅ በደዊ፡፡በተጨማሪም እያንዳንዱን ጉዳይ ፍጥነት በተሞላበት መልኩ በስልክ ልውውጥ ሲከታተሉ ለነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንብር ኢ/ር ይልቀል ጌትነት እና የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ኢ/ር ጌታነህ ባልቻ እጅግ በጣም ከማስገረሙም አልፎ ቁጭት እና በስጭት እንዲሰማን አድርጓአል፡፡ሆኖም ግን ልክ እንደቅድሙ አሁንም ምንም ማድረግ ስለማይቻል ወደተጠቀሰው ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለማመልከት ግድ ሆኖአል፡፡


በመሆኑም የታችኛው ፍርድ ቤት የጠየቀውን ትእዛዝ ለመጠየቅ የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመቅረብ ከስር ፍርድ ቤት የተጠየቅነውን አስረድተን ሳንጨርስ “ የዛሬው ምን ጉድ ነው ? ምን አይነት ዳኞች ናቸው ፣እንዲ አይነት ትእዛዞችን እየጠየቁ የሚያጉሏሏችሁ ! የቅድሙ ሲገርመን ይሄን ይጠይቃሉ” በማለት በታችኛው ፍ/ቤት ሲገረሙ እና ሲሣሣቁ ለመታዘብ የተቻለ ሲሆን፡፡በሆነው ነገር አብዛኛው የመዝገብ ቤት ሰራተኞች እና የዳኞች ፃፊዎች በማዘና እና በመገረም የታችኛው ፍርድ ቤት የጠየቀውን የህግድ ትህዛዝ በማዘጋጀት በሚደንቅ ትብብር ሊሰጡ ችለዋል፡፡በዚህም መሠረት የታችኛው ፍርድ ቤት የጠየቅውን የህግድ ትህዛዝ በመያዝ የህግድ ትህዛዙ እንዲቀርብላቸው ለጠየቁት ዳኛ በዲጋሚ ለመቅረብ የተቻለ ሲሆን ጉዳይ የተመለከቱት ዳኛ “አሁን ሁሉም ነገር ተሟልቷአል በጉዳዩ ላይ ውሳኔ መስጠት የሚችለው ጉዳዩን በመጀመሪያ ሲያየው የነበረ ዳኛ ነው፤አሁን እሱ ስለሌለ ነገ ጠዋት መጥታችሁ ጉዳያችሁ ማቅረብ ትችላለችሁ” በማለት ምንም እንዳልተፈጠረ አድርገው ውሳኔ አስተላለፉ፡፡


የአገራችን የዳኝነት ስርአት በተለያየ ወቅት እና በተለያየ ተበዳዮች እውነተኛ ፍትህ ሳያገኙ እየቀሩ በእንዲ መልኩ ከስር ከስሩ እየታጨደ ሌጣ ሜዳ ሆኖ መቅረቱ ያስቆጫል፡፡እኔ በሆነው ነገር እጅግ በጣም ነው ያዘንኩት፤ በእንዲህ አይነቱ ግዴለሽነት እና በእጅ አዙር መንግስትን የሚጠቅም ውሳኔ የሚያስተላልፍ ፍርድ ቤት እና የዳኝነት ስርአት መታየቱ የገዥውን የአምባገነን መንግስት ስርአት አደገንኘቱን ከማመላከት ባለፈም ስርአቱ በህዝብ ተሳትፎ ከወደቀም በኋላ ወደፊት ዜጎች በፍትህ ስርአት ላይ አመኔታ እንዲያጡ ሆን ተብሎ የሚቀበር ፈንጂ ስለመሆኑ አርቆ አሳቢነትን አብዝቶ የሚጠይቅ አይደለም፡፡


ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!  

 

 

↧

የኪዳነምህረት ዓመታዊ ክብረ በዓል በሚኒሶታው ቅዱስ ዑራኤል ቤ/ክ

↧
↧

“አሸባሪነት” በወያኔ አገዛዝ ሥር ባለችው ኢትዮጵያ

$
0
0


በአገራችን፣ በወያኔ አገዛዝ መደበኛ ትርጉማቸውን ከሳቱ በርካታ ቃላት መካከል “የሽብር ድርጊት“ እና ”አሸባሪ“ የሚሉት ግንባር ቀደሞቹ ናቸው። ሰፊ ተቀባይነት ያለው የአሸባሪ ትርጉም “የሽብር ድርጊቶችን የሚፈጽም ሰው ወይም ድርጅት” ማለት ነው። “የሽብር ድርጊቶች” የሚባሉት ደግሞ የተለመዱ ጥቃቶችን ሳይሆን የሀይማኖት፣ የፓለቲካ ወይም የርዕዮተዓለም ግብ ለማሳካት ሲባል በሰዎች ላይ ፍርሀትን ለማንገስ፤ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሱ አስከፊ ጥቃቶችን ነው። የሽብር ድርጊቶችን ሰላማዊውን ሕዝብ ጭዳ የሚያደርጉ በመሆኑ በጥብቅ ሊወገዙ ይገባል። ዓላማን በሽብር ድርጊቶች ማስፈፀም ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው።

በወያኔ መዝገበ ቃላት ግን “ሽብርተኛ” እና “የሽብር ድርጊቶች” በዘፈቀደ የሚነገሩ ተራ ቃላት ሆነዋል። ስለአገራቸው እና ስለትውልድ የሚጨነቁ፤ ሀሳባቸው በነፃነት የሚያራምዱ፤ የወያኔን ፕሮፖጋንዳ እንደ በቀቀን የማይደግሙ ዜጎች “አሸባሪዎች” እየተባሉ ወደ እስር ቤቶች እየተወረወሩ ነው። ጋዜጠኞች፣ ጦማርተኞች፣ ፍጹም ሰላምተኛ አማኞች እና ሰላማዊ ፓለቲከኞች በሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ ቀዳሚውን ሥፍራ የያዙ ናቸው።

በአንፃሩ ደግሞ እውነተኛው አሸባሪ ህወሓት፣ የመንግሥትን ሥልጣን ይዞ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ማሸበሩን በስፋት ተያይዞታል። ህወሓት ዘረኛ ርዕዮተ ዓለሙን ለማስፈፀም ሲል ባለፉት ሠላሳ አምስት ዓመታት ውስጥ የፈፀማቸው የሽብር ድርጊቶች ተዘርዝረው አያልቁም። የህወሓት የሽብር ድርጊቶች ዓላማ የኢትዮጵያን ሕዝብ በፍርሀት አደንዝዞ መግዛት ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ “አሸባሪ” የሚለውን ቃል ራሱ በማሸበሪያ መሣሪያነት እያዋለው ነው። ይህ የውስጥም የውጭም ታዛቢዎችን የሚያሳስት በመሆኑ ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ ነው።

“የፀረ-ሽብር አዋጅ” የሚባለው ህገ-አልባነትን ህጋዊ ያደረገው ሰነድ የመንደር ካድሬዎች ሳይቀሩ አንድን ሰው በሽብርተኝነት “ጠርጥረው” ማሳሰርና ማስደብደብ አስችሏቸዋል። የአስተሳሰብ ድህነት ያጠቃቸው የህወሓት ካድሬዎች ብቻ ሳይሆኑ ኃላፊነት የጎደላቸው ፓሊሶችም የፀረ-ሽብር ህጉን ጉልበታቸውን ማሳያ እና ተፎካካሪዎቻቸውን ማጥቂያ አድርገውታል። በፀረ-ሽብር ህጉ ተከስሰው ወህኒ የወረዱ ዜጎችን ያጤነ ማንኛውም ሰው ኢትዮጵያ አገራችን በዚህ ህግ ሰበብ ምርጥ ዜጎቿን እያጣች እንደሆነ ይገነዘባል።

በሽብርተኝነት ለመጠርጠር የሚያበቁ ምክንያቶች እጅግ አሳዛኝ ናቸው። ለካድሬ ሰበካ እውነተኛነት ጥርጣሬውን የገለፀ አስተዋይ ሰው መሆን ብቻውን እንኳን በሽብርተነት ያስጠረጥራል። በዚህም ምክንያት ነው በእውቀትም በአስተሳሰብም የበሰሉ ዜጎቻን በአሸባሪነት የመፈረጅ እድላቸው ከፍተኛ የሆነው። የንቅናቄዓችን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ በርካታ የሀገራችን ምርጥ ዜጎች የዚህ የተዛነፈ ትርጓሜ ሰለባ ሆነዋል። ተስፋ የሚጣልባቸው በርካታ ወጣቶች በዚህ ህገ-ወጥ ህግ እና የተሳሳተ ትርጓሜ ምክንያት የወጣትነት እድሜዓቸውን በእስር ቤት እንዲያሳፉ ተገደዋል። ከዚያ የበዙት ደግሞ በቃሉ ተሸማቀው፤ በሚያስከፍለው ዋጋ ተሸብረው ራሳቸውን እንዲደብቁ ተደርገዋል።

ለመሆኑ ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው ምርጥ ዜጓቿ በአሸባሪነት ስም ወህኒ እየተወረወሩ ሲሰቃዩ ምላሻችን ምን ሊሆን ይገባል? እስከመቼ አስተዋይ፣ አርቆ አሳቢና አመዛዛኝ የሆኑ መሪዎቻችንን ለወያኔ ፋሽቶች እየገበርን እንኖራለን? ሀገራችን ይህን ኪሳራ የመሸከም አቅም አላት?

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔን ለማስወገድ የተሻለ ነው ብሎ ያመነበት የትግል ስልት – ሁለገብ የትግል ስልት ነው። በዚህ የትግል ስልት መሠረት ሕዝባዊ ተቃውሞ፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነት እና ሕዝባዊ አመጽ ተደጋግፈውና ተናበው መሄድ አለባቸው ብሎ ያምናል። ስለሆነም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በአመቸውና በሚያምንበት መንገድ ለትግሉ አስተዋጽኦ የማበርከት እድል አለው።

በዚህም መሠረት ለሀገር፣ ለትውልድ ድህንነት ዋጋ ለመክፈል እና ለገዛ ራሳችን ህሊና ታማኝ ለመሆን በወያኔ “አሸባሪ” ለመባል መድፈር የትግላችን አንዱ አካል አድርገን መቁጠር ይኖርብናል። በወያኔ “አሸባሪ” መባል የሚያሸማቅቅ ሳይሆን የሚያኮራ፤ ለታላቅ ኃላፊነት እና ሕዝባዊ አደራ በእጩነት የሚያቀርብ መሆኑን በራሳችንም በማኅበረሰባችንም ውስጥ ማስረጽ ይኖርብናል። “አሸባሪ” የሚለው ቃል በወያኔ ተግባር መሠረት ሲተረጎም “ለሀገርና ለትውልድ ደህነት የሚጨነቅ ምርጥ ዜጋ“ ማለት እንደሆነ ማስተማር ይገባናል።

ወያኔ ወደ ሕዝብ የሚወረውረውን ጦር መልሰን ወደ ራሱ መወርወር ይኖርብናል። ወያኔ አሸባሪነት ዜጎችን ለማጥቂያ እያዋለው መሆኑ ተረድተን እኛ በዚህ ስያሜ መሸማቀቅ ሳይሆን፣ መኩራትና መልሰን ወያኔን ማሸማቀቅ ይኖርብናል። በውጭ አገራት እየተስፋፋ የመጣው የወያኔ ሹማምንትን የማሸማቀቅ ዘመቻ በኢትዮጵያ ውስጥም መጀመር ይኖርበታል።

ሕዝባዊ ተቃውሞ፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ሕዝባዊ አመጽ ሲቀናጁ ድላችንን ያፈጥናሉ። በወያኔ “አሸባሪ” መባል የመልካም ዜግነት ምስክርነት እንደሆነ በሙሉ ልባችን እንቀበል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

G7

↧

“ውሸታም”!

$
0
0

Pen

እመ-ሰብ፣ እምዬ – ደጓ ያልታደሉ፣
ቆንጥጠው ያሳደጉህ – “አትዋሽ” እያሉ፣
የአደይ ምክር፣ ተግሳጽ.. ባክኖ ሲቀር ቃሉ፣
እናትህ ምን ይሉ?!
“ኮትኩቼ ያሳደግሁት፣ ክብሬን የሚጠብቅ..” የሚሉህ ልጃቸው፣ “አሳዳጊ የበደለው..” በሚሉት እርግማን ሲነሳ ስማቸው፣
አባ-ወራ፣ አባትህ – የቤቱ ምሰሶ ምንድን ይሰማቸው?!
ባለቤትህ ምን ትል? – የኑሮህ “ተጋሩ”፣ “ያ! ውሸታም ባልሽ..” – ስትባል በ”ዕድሩ”፤
በብሩህ ተስፋ ስንቅ ጉዞ የጀመሩ – ልጆችህ ምን ይሉ?!
አንገት እሚያስደፋ – አባት ሲታደሉ፤
ባልንጀሮችህስ፣ ወይ አብሮ አደጎችህ፣ ወይ ባልደረቦችህ.. ህሊና ያላቸው፣
ከጎንህ ለመቆም እሚሸማቀቁ – ጊዜ ፈርዶባቸው፤
ህሊናስ ወዴት ነው? – ማተብስ ምን ዋጠው?!
ሲወርድ-ሲወራረድ – ከትውልድ የመጣው፤
ምን ዓይነት “ባህል” ነው? – ከወዴት የመጣ፣
ሰብዕናን ሽሮ – ይሉኝታን ያሳጣ፤
እግዚኦ! ያሰኛል – እኔስ ላነተ አፈርኩ፣
አምላክ ይታረቅህ – ኧረግ! አበስኩ-ገበርኩ!

ጌታቸው አበራ
ነሐሴ 2006 ዓ/ም
(ኦገስት 2014)

——
የሕዝብን መሰረታዊ የነጻነት፣ የፍትህና የዴሞክራሲ ጥያቄዎችን በቀጥታ መመለስ ሲሳናቸው፣ (ወጣቱ ሀገር ተረካቢ ትውልድ በመልካም ስነ-ምግባር ታናጾ እንዳያድግ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ እስከሚፈጥር ድረስ) በግልጽ ባደባይ፣ በእጅጉ ዘቅጠው በውሸት ለተዘፈቁ የወያኔ ባለሥልጣኖች እና ለተላላኪዎቻቸው።

↧

አቶ ሙሼ ሰሙ ከኢዴፓ አባልነታቸው ለቀቁ

$
0
0

mushe semuከዳዊት ሰለሞን

ከአቶ ልደቱ አያሌው ጋር በመሆን ፓርቲው ከተመሰረተበት 1992 ጀምሮ በህዝብ ግኑኝነት፣ በጸሀፊነትና በፕሬዘዳንትነት ያገለገሉት አቶ ሙሼ ሰሙ ከሁለት ሳምንት በፊት ለፓርቲው ጽ/ቤት ባስገቡት ባለ ሶስት መስመር ደብዳቤ ከፓርቲው የማእከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸውና ከተራ አባልነት ጭምር ኢዴፓን ለመልቀቅ መወሰናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሙሼ ለ14 ዓመት ያህል የተጓዙበትን ፓርቲ ለመልቀቅ የወሰኑት በምን ምክንያት እንደሆነ በደብዳቤያቸው ያልገለጹ በመሆኑ የፓርቲው አመራሮች ምክንያቱን ለመግለጽ መቸገራቸውን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ ደብዳቤውን ስለማስገባታቸው በስልክ የተጠየቁት ሙሼ ‹‹በራሴ መንገድ ምክንያቴን ይፋ አድርጋለሁ››ብለዋል፡፡

ሙሼ ኢዴፓን ለመጨረሻ ግዜ ያገለገሉት በፕሬዘዳንትነት ሲሆን አንድ ተርም ብቻ በቦታው ካገለገሉ በኋላ በድጋሚ የመመረጥ ዕድል እያላቸው በፈቃዳቸው ራሳቸውን ከዕጩነት ማግለላቸው አባላቱን ሲያነጋግር ቆይቷል፡፡

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live