Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የባለ ራዕይ ወጣቶች ማህበር ከፍተኛ አመራር ታሰረ

$
0
0

ፍኖተ ነፃነት

Birhanu-Tekele-Yaredበኢትዮጵያና በአዲስ አበባ ወጣቶች ስም በተመሰረቱ ማህበራቶችና ፎረሞች ውስጥ ተደራጅተው ከነበሩ ወጣቶች መካከል የተወሰኑት የሚገኙባቸው ማህበራት ‹‹ነጻነት››የማይጨበጥ ሲሆንባቸው ‹‹የባለ ራዕይ ወጣቶች ማህበርን››መሰረቱ፡፡ከመስራቾቹ አንዱም ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድ ነው፡፡ብርሃኑ ማህበሩን በተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንትነትና በህዝብ ግኑኝነት በማገልገል ላይ የሚገኝ ከመሆኑም በላይ በተለያዮ የህትመት ውጤቶች አማካኝነት ሀሳብን የመግለጽ መብቱን ይጠቀማል፡፡

ማህበሩ በየጊዜው የሚያነሳቸው የመብት ጥያቄዎችና አገራዊ አጀንዳዎች ያላስደሰተው አካል የእነ ብርሃኑን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በአይነ ቁራኛ ሲከታተል ቆይቷል፡፡ወጣቱ የመብት ታጋይ ዛሬ ማለዳ ከሚኖርበት ወረዳ 11 በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ከሰዓት በኋላ ለደቂቃዎች በቤተሰቦቹ እንዲጎበኝ የተደረገው ብርሃኑ ‹‹ያሰሩኝ በቅርቡ ሰላማዊ ሰልፍ ለመጥራት አስባችኋል ብለውኛል ፡፡ ነገር ግን እኛ (ባለ ራዕይ ማህበር)ሰላማዊ ሰልፍ አልጠራንም ሰልፉን የጠሩት ሰማያዊ ፓርቲዎች ናቸው ስላቸው ይህንን ወረቀት ታዲያ ለምን በተንክ ብለው ከዚህ በፊት ተመልክቼው የማላውቀውን ወረቀት አሳዮኝ እኛ ሰልፍ ብንጠራ በህቡዕ ሳይሆን በአደባባይ እንደምናደርገው ነግሬያቸዋለሁ፡፡››በማለት የእስሩን ምክንያት ተናግሯል፡፡ የመኖሪያ ቤቱ መፈተሹን የጠቆሙት የፍኖተ ነጻነት ምንጮች ፖሊሶች ግንቦት 7/2005 ተበትኗል ያሉትን ወረቀት ‹‹ የኤርትራ ጉዳይ ›› በተሰኘ የዘውዴ ረታ መጽኀፍ ውስጥ አገኘን ማለታቸውንና ብርሃኑም ተገኘ የተባለው ወረቀት ቤት ፈታሾቹ ሆን ብለው ያስቀመጡት ካልሆነ በቀር እርሱ እንዳላስቀመጠው በመግለጽ ፖሊሶች ‹‹የእኔ ነው ብለህ ፈርም ሲሉት›› እምቢ ማለቱን በኋላም አሁን ፈርምና ፍርድ ቤት በምትቀርብበት ወቅት የአንተ አለመሆኑን ትናገራለህ በሚል ማግባቢያ ቤተሰቦቹን ማስጨነቅ ባለመፈለጉ መፈረሙን ምንጮቻችን ፡፡ብርሃኑ በአሁኑ ሰዓት ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣብያ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡


ግንቦት 7, 97 የታየውን የለውጥ መነሳሳት ለመድገም ጠንካራ ሰላማዊ ትግል የግድ ይላል

$
0
0

2005-kinijit-demonstration-picture

ፍኖተ ነፃነት

ግንቦት በሀገራችን ታሪክ ወሳኝ ፖለቲካዊ ሁነቶች የተከሰቱበት ነው፡፡ ከሌሎቹ ፖለቲካዊ  ሁነቶች መካከል፣ ኢትዮጵያን ከአምባገነኖች መዳፍ ነፃ ለማውጣት የተስፋ ጭላንጭል የታየበት የግንቦት 7, 97 ምርጫ ጎላ ብሎ የሚጠቀስ ነው፡፡ በወቅቱ ገዢው ፓርቲ በአንፃራዊነት ከፍቶት በነበረው የውድድር ሜዳ የተጠቀሙት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ዳር እስከዳር ህዝቡን ለማስተባበር የቻሉበት ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብም ለውጥ እንደሚፈልግና የሰለጠነ ፖለቲካ ለውጥ ማምጣት እንደሚችል ለኢህአዴግም ሆነ ለመላው የአለም አቀፍ ህብረተሰብ ያረጋገጠበት ነው፡፡

ግንቦት 7 ተደርጎ የነበረው ታሪካዊ ምርጫ በኢህአዴግ አምባገነናዊ አፈናና በተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ፖለቲካዊ ብስለት ማጣት ምክንያት ለውጤት አለመብቃቱ የሚያስቆጭ ነው፡፡ ሆኖም ከስምንት አመታት በኋላም የህዝቡ የለውጥ ፍላጎት የመጨመር እንጂ የመቀነስ ሁኔታ አይታይበትም፡፡

ኢህአዴግ በግንቦት 97ቱ ምርጫ ያጋጠመውን ኪሳራ ካሰላ በኋላ በሀገር አቀፍም ሆነ በወረዳና በከተማ ደረጃ ካሄዳቸውን ምርጫዎች ሙሉ ለሙሉ ለውድድር የማይመቹ እንዲሆኑ በማድረግ በህዝቡ የለውጥ ፍላጎት ላይ ቀዝቃዛ ውሀ ቸልሷል፡፡

በዘንድሮው የአካባቢና የከተማ ምክር ቤት ምርጫም ኢህአዴግ በከፍተኛ ውጤት ማሸነፉን ገዢው ፓርቲ እንዳሻው የሚዘውረው ብሔራዊው ምርጫ ቦርድባሳለፍነው ሳምንት ለህዝብ ይፋ አድርጓል፡፡ ኢህአዴግ ያለተፎካካሪ ብቻውን የሮጠበትን የምርጫ ሂደትና ያገኘው ውጤት ከግንቦት 7, 97 ምርጫ ጋር ሲተያይ የሀገራችን የዴሞክራሲ ጉዞ ምን ያክል ወደ ኋላ እንደተመለሰ ያመላክተናል፡፡

የሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ጉዞ የተሳካ እርምጃ እንዲሄድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ማለትም ዜጎች፣መንግስት፣ገዢው ፓርቲ፣ምርጫ ቦርድ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣የሲቪክ ተቋማትና የሌሎች የጋራ ተሳትፎ ወሳኝ ነው፡፡ መንግስት እና ገዢው ፓርቲ ፀረ ዴሞክራሲያዊ እርምጃዎችን ሲያደርጉ፣ ብሔራዊው ምርጫ ቦርድም የድርጊቱ ተባባሪ ሲሆን ሌሎቹ ባለድርሻ አካላት በዝምታ መመልከት የለባቸውም፡፡ በሀገራችን በገሀድ እየታየ ያለው ሀቅ ግን ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት መንግስትና ገዢው ፓርቲ የሚያደርጉትን ፀረዴሞክራሲያዊ ተግባራት ከማውገዝ ያለፈ ተግባራዊ ስራ፣  ሲሰሩ አይታዩም፡፡ ይልቁኑም ገዢው ፓርቲ ያሻውን እንዲያደርግ የተውት እስኪመስል ድረስ ከመግለጫ ያለፈ ተግባራዊ ሰላማዊ ትግል ከማድረግ ተቆጥበዋል፡፡ ይህ ሁኔታ በምንም አይነት መቀጠል የለበትም፤ በመሆኑም የኢህአዴግን በተለይም የገዢውን ቡድን አምባገነናዊ አፈና ከማማረር ባለፈ ግንቦት 7, 97 የታየውን የለውጥ መነሳሳት ለመድገም ጠንካራ ሰላማዊ ትግል ይኖርበታል፡፡ግንቦት 7, 97ቱን የለውጥ እንቅስቃሴ ለመድገም ምቹ ሁኔታዎች እንዳሉ ለመረዳት የሀገራችንን ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታ መመዘን ያስችለናል፡፡

ሀገራችን የገባችበት የማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ምስቅልቅል ከስምንት አመት በፊት ከነበረው እጅግ የባሰ ነው፡፡ ህዝባችን የእምነት፣የመደራጀት፣የመናገር፣በፍትሀዊነት የመዳኘት መብቶቹን ከ1997ዓ.ም በባሰ መልኩ በገዢው ቡድን ተነጥቋል፡፡ የሲቪክ ተቋማትና መንግስት ባወጣው አሳሪ ህግ ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ አስተዋፅኦ እንዳይኖራቸው ተደርገዋል፡፡ ነፃውን ፕሬስ በአፋኝ የፕሬስ ህግ በማዳከም እንዲሁም ጋዜጠኞች በፀረሽብርተኝነት ህግ ሰበብ የሚጠበቅባቸውን ያህል እንዳይሰሩ ተደርገዋል፣ በርካታ ጋዜጠኞች በተቀነባበረ የሽብር ክስ ታስረዋል፣ ጋዜጦች አታሚ በማጣት ከገበያ እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎች ከደጋፊዎቻቸውና ከህዝብ ጋር እንዳይወያዩ አዳራሽ ከመከልከል ጀምሮ አመራሮቻቸውን በተፈበረከ ክስ ታስለውባቸዋል፡፡ እነዚህ ሁሉ ዘርፈ ብዙ አፈናዎች በ1997 ዓ.ም ከነበረው አፈና ጋር ሲተያይ የአሁኑ እጅግ የከፋ ነው፡፡ ይህ ዘርፈ ብዙ አፈና በህዝቡ ውስጥ የፈጠረውን ብሶት ወደ ሰላማዊ ህዝባዊ ዕምቢተኝነት መለወጥ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ በግንቦት 17፥2005 ዓ.ም የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በመደገፍ የተሰጠ አቋም መግለጫ

$
0
0

ከዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ

ቀን፣ 23/05/13

ሰማያዊፓርቲበግንቦት 17፥2005 ዓ.ምየጠራውንሰላማዊሰልፍበመደገፍ ከዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የተሰጠ አቋምመግለጫ!

united we standየሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት ፅ/ቤት ፊት ለፊት ጥቁር በመልበስ እና ፍፁም ሰላማዊ የሆነ ሰልፍ ለማድረግ ማቀዱ ይታወቃል በመሆኑም እንዲህ አይነት ሰላማዊ የህዝብ የመብት፣ የፍትህ እና የዲሞክራሲ ጥያቄን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የሚደግፈው መሆኑን ስንገልጽ::

በተለይ የሰማያዊ ፓርቲ “በአገዛዙ ምላሽ የተነፈጋቸው የተለያዩ አንገብጋቢና መሰረታዊ የሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ የመብት፣ የፍትህ እና የዲሞክራሲ ጥያቄዎችን የዓለም ዓቀፍ ማሕበረሰብ ትኩረት እንዲሰጣቸው በሚል ሃሳብ በአዲስ አበባ የሚከበረውን የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት በዓልን አጋጣሚ በመጠቀም ድምፃቸውን ለአለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ለሃገር መሪዎች እና ለታላላቅ ሚዲያዎች ለማሰማት በማቀዳቸው ከጎናቸው ሆነን ድጋፋችንን እንገልፃለን::

እንደሚታወቀው የወያኔ አገዛዝ ባፀደቀው ህገመንግስቱ ላይ የመሰብሰብ፥ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት የተደነገገ ሲሆን፥ ከ1997 ምርጫ በኋላ በግልፅ በከፍተኛ ደረጃ በውርደት የተሸነፈው የወያኔ አገዛዝ በአቶ መለስ ዜናዊ ትእዛዝ ብቻ ለራሳቸው በሚያመች ሁኔታ ያረቀቁት ህገመንግስቱ ከተሻረ በኋላ የዜጎች የመሰብሰብ፥ ሰላማዊ ሰልፍ የማረግ እንዲሁም ተዛማች መብቶች ከተገፈፈ እነሆ ስምንት አመታት ተቆጥሯል::

በመሆኑም ይህንን አንገብጋቢና መሰረታዊ የሆነ የመብት፣ የፍትህ እና የዲሞክራሲ ጥያቄ ሁሉም ነጻነት የተጠማ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሊደግፈው ይገባል ብለን እናምናለን፣ ሰለሆነም ሙሉ አጋርነታችንን ለማሳየት የየዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዎይ የሥራ አስፈጻሚዎች፣ አባላት እንዲሁም ደጋፊዎች ቀኑን የጥቁር ልብስ በመልበስ ለሰማያዊ ፓርቲ ጥያቄ ድጋፍችንን እናሳያለን፣ በማያያዝም በኖርዌይ ለሚኖሩ መላ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ ቀኑን የጥቁር ልብስ በመልበስ ለሰማያዊ ፓርቲ ጥያቄ ድጋፋችሁን እንድታሳዩ ድርጅታችን ጥሪውን ያቀርባል::

 

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

 

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ

ኖርዌይ፣ ኦስሎ፣ ግንቦት 23፣ 2013

ሰለማዊ ሰልፍ መከልከል??? ከአብርሃ ደስታ

$
0
0

አብርሃ ደስታ

ሰማያዊ ፓርቲ’ የተባለ የፖለቲካ ድርጅት ለአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ለማክበር የአፍሪካ መሪዎች በአዲስ አበባ በሚሰበሰቡበት ግዜ የህዝብ ሰለማዊ ሰልፍ እንደሚጠራ ሰምተን ነበር። የሰልፉ ዓላማ ምንድነው? ለምን አስፈለገ? ለምን ለአፍሪካ መሪዎች ማሳወቅ አስፈለገ (አብዛኞቹ የአፍሪካ መሪዎች ሰለማዊ ሰልፍ አይወዱም ወይ አይፈቅዱም ብዬ) የሚሉና ሌሎች ተዛማጅ ጥያቄዎች አንስተን መከራከር ይቻላል።

እነዚህ መከራከርያ ነጥቦች ለግዜው ወደ ጎን ትተን እነኚህ ‘ሰለማዊ ሰልፍ’ የጠሩ አካላት ምን ይሁን ምን የራሳቸው ምክንያት፣ ዓላማና አሰራር ይኖራቸዋል (ድርጅትን ያህል ምክንያት ሳይኖረው፣ አስፈላጊነቱ ሳይታየው የተቃውሞ ሰልፍ በሚከለከልበት ሀገር ሰለማዊ ሰልፍ ይጠራል ብዬ አላስብም)።

መጠየቅ ያለብን ነገር የሰልፉ ዓላማና አስፈላጊነት ሳይሆን (ምክንያቱም ሰልፉ አስፈላጊ ነው ወይ አይደለም ብለን ለመደገፍ ወይ ለመተቸት የሚከለክለን ሕጋዊ አካል የለም) ዜጎች ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ (ለፈለጉት ዓላማ) ሕገ መንግስታዊ መብት አላቸው ወይ የሚል ነው??? የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀፅ 30፣ “ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሳሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፤ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነትና፤ አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡” ብሎ ይደነግጋል። በሕግ የተደነገገ በተግባር መተርጎም አለበት። የሕግ የበላይነት መረጋገጥ አለበት። ዜጎችም ሕገ መንግስታዊ መብታቸው ሊከበርላቸው ይገባል።

ዜጎች በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸው ‘ሰለማዊ ሰልፍ’ የማድረግ መብት ለመጠቀም ሰልፍ ከመውጣታቸው በፊት የአከባቢው አስተዳደር ማሳወቅ ወይ ፍቃድ መጠየቅ እንደሚኖርባቸው ሕግ ይደነግጋል። የሰለማዊ ሰልፍ ፍቃድ ሲጠየቅ (የተለየ ሁኔታ ካላጋጠመ በቀር) በመንግስት አስተዳደር የሚከለከልበት መንግስታዊ አሰራር የለም። ምክንያቱም ሰለማዊ ሰልፍ ማድረግ የዜጎች መብት መሆኑ በሕገ መንግስቱ ተቀምጧል)።

ትናንት ማታ እንደሰማነው ታድያ ‘ሰማያዊ ፓርቲ’ ‘ሰለማዊ ሰልፍ’ ለማድረግ የሚያስችለው ፍቃድ እንዲሰጠው ለአዲስ አበባ አስተዳደር ማቅረቡና ጥያቄው ተቀባይነት አላገኘም። መንግስት ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ ፍቃድ ለመከልከል የሚያስችል ስልጣን የለውም (ሰልፉ የሚከለከልበት ልዩ አጋጣሚ እስከሌለ ድረስ)።

መንግስት ፍቃድ መከልከሉ የሀገራችን ሕገመንግስት የጣሰ ነው። መንግስት የራሱን ሕገመንግስት በራሱ ከጣሰ ዜጎች መንግስት የጣሰውን ሕገመንግስት እንዲያከብሩ እንዴት ማስገደድ ይቻለዋል? ዜጎች ብቻ ሕገመንግስቱ ቢያከብሩ እንዴት ዉጤት ማምጣት ይቻላል? በዴሞክራሲያዊ ሀገር ሕገመንግስት የበላይ ሕግ ነው፤ በመንግስትም በዜጎችም መከበር አለበት። ሕገመንግስቱን በመጣስ ኢህኣዴግ የሚመራው የኢትዮዽያ መንግስት ከሕግ በላይ እየሆነ ነው። መንግስት ሕግን በሚጥስበት ሀገር ዴሞክራሲ አለ ማለት አይቻልም። ዴሞክራሲ ከሌለ የኢትዮዽያ መንግስት ‘አምባገነን ነው’ ብንል እንዴት ስሕተት ሊሆን ይችላል?

መንግስት አምባገነን ከሆነ ዜጎች ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚገነቡበት አጋጣሚ ለመፍጠር ብንቀሰቅስ ኃጥያት ይሆናል? መሪዎቻችን ለስልጣን ሲታገሉ ለዴሞክራሲ ግንባታ ብንታገል መልካም አይደለምን? ሰለማዊ ሰልፍ ማድረግ ህዝቦች ሓሳባቸውንና ያላቸው ቅሬታ (በመንግስት ይሁን በሌላ) የሚገልፁበት መድረክ እስከሆነ ድረስ የዴሞክራሲያዊ አሰራር መገለጫ ይሆናል ማለት ነው።

ሰለማዊ ሰልፍ ማድረግ የዴሞክራሲ መገለጫ ከሆነ ታድያ ለምን ሰለማዊ ሰልፍ እንፈራለን? ሰለማዊ ሰልፍ ባለመፍቀድ የህዝብን ብሶት ያቃልላል ያለው ማነው? ህዝብን ማፈን የህዝብን ቅሬታ እንዲጨምር እንደሚያደርግና ህዝቡ ሌላ አማራጭ (ሰለማዊ ያልሆነ መንገድ) ተጠቅሞ ፀረ መንግስት ሊነሳ እንደሚችል ኢህኣዴጎች ከደርግ አገዛዝ ትምህርት አለመቅሰማቸው ግርም ይለኛል። ሰለማዊ መንገድ መዝጋት የሃይል ወይ የዓመፅ መንገድ መክፈት ማለት ነው።

እኛ የምንፈልገው ግን የዓመፅ መንገድ ሳይሆን ሰለማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ነው። ኢትዮዽያ በሃይል ስልጣን የመያዝ የብዙ ዓመት ልምድ አላት። እስካሁን ድረስ የኢትዮዽያ ገዢዎች ስልጣን የያዙት በሃይል ነው። ባለስልጣናቱ (ሰዎቹ) ይቀያየሩ እንደሆኑ እንጂ ፖለቲካዊ አገዛዛቸው ተመሳሳይ ነው፤ ስልታቸው ጭቆና ነው። የሚገለገሉበት ስልጣን ከህዝብ ተውሰው የያዙት ሳይሆን በጠመንጃ አፈሙዝ የነጠቁት ነው፤ ለዚህም ነው ለስልጣናቸው እንጂ ለህዝብ ነፃነት ግድ የሌላቸው።

ሰለማዊ ሰልፍ የምንፈራበት አንድ ምክንያት ሊኖር ይችላል። ይሄም ‘ሰለማዊ ሰልፉ’ እንደስሙ ‘ሰለማዊ’ ላይሆን ይችላል። መፍትሔው ግን ቀላል ነው። በሕገ መንግስቱ የተቀመጠ ‘ሰለማዊ ሰልፍ’ ነው። ሰዎቹም የጠሩት ‘ሰለማዊ ሰልፍ’ ነው። ፍቃድ የተጠየቀው ‘ለሰለማዊ ሰልፍ’ ነው። መንግስት ይሄንን ፍቃድ መስጠት ነበረበት። ሰልፉ ሰለማዊ መሆኑ ቀርቶ የዓመፅ መንፍስ ከታየበት ‘ሕገ ውጥ ሰልፍ’ እየሆነ ነው ማለት ነው። በዚህ ግዜ መንግስት ‘ሕገመንግስቱን ለማስከበር’ ጣልቃ ሊገባ ይችላል። ‘ሕገ ወጥ ድርጊት’ የፈፀመ አካል ካለ ወደ ሕግ ቀርቦ በሕግ ይፈረዳል። (የሕግ የበላይነት ይከበራል)።

ገና ለገና ‘ዓመፅ ሊቀሰቅሱ ይችላሉ’ በሚል ስጋት (ይህን ያልኩበት ምክንያት መንግስት ዓመፅ ፈርቶ ካልሆነ በቀር ሰለማዊ ሰልፍ የማይፈቅድበት አሳማኝ ምክንያት ስላልመጣልኝ ነው) ሰለማዊ ሰልፍ መከልከል የዜጎች መብት መጣስ ስለሆነ አግባብነት የለውም። ባጭሩ መንግስት በሕገወጥ ተግባር ተሰማርተዋል ማለት ነው።

ሰለማዊ ሰልፍ መጥራት የመብት ጥያቄ እንጂ የአቋም ጉዳይ አይደለም።

ዓፈና ዓመፅን ይወልዳል።

ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፉን ለማድረግ ከከንቲባው ጽ/ቤት እውቅናን አገኘ (ደብዳቤውን ይዘናል)

አንድነት ፓርቲ የሰኔ አንድ ሰማዕታትን በህዝባዊ ንቅናቄ ሊዘክር መሆኑን ምንጮች ጠቆሙ

$
0
0

ፍኖተ ነፃነት

UDJአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የግንቦት 97ን ምርጫ ተከትሎ ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓ.ም በመንግስት ሀይሎች በግፍ የተጨፈጨፉትን ኢትዮጵያውያን ለመዘከር የተለያዩ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን ለፍኖተ ነፃነት የደረሰው መረጃ አመላክቷል፡፡

ፓርቲው በአዲስ አበባ መዋቅሩ ጭፍጨፋው የተፈፀመበትን እለት በህዝባዊ ንቅናቄ ለመዘከር  ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የፓርቲው ምንጮች ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡ ምንጮቹ የህዝባዊ ንቅናቄው ዝርዝር አፈጻፀም በቅርቡ ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን በመግለፅ ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የግንቦት 97ን ምርጫ ተከትሎ ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓ.ም በመንግስት ሀይሎች በግፍ የተጨፈጨፉትን ኢትዮጵያውያን ለመዘከር የተለያዩ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን ለፍኖተ ነፃነት የደረሰው መረጃ አመላክቷል፡፡

ፓርቲው በአዲስ አበባ መዋቅሩ ጭፍጨፋው የተፈፀመበትን እለት በህዝባዊ ንቅናቄ ለመዘከር  ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የፓርቲው ምንጮች ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡ ምንጮቹ የህዝባዊ ንቅናቄው ዝርዝር አፈጻፀም በቅርቡ ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን በመግለፅ ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

እኔ ስለአንድነት/መድረክ እከራከራለሁ

$
0
0

በፍቃዱ ዘ ኃይሉ
BefeQadu Z Hailu

Medrek Andinetሰሞኑን በአንድነት እና አቃፊው መድረክ መካከል የተከሰተውን አለመግባባት የተጋነነ ቨርዥን ጋዜጦች ላይ ያላነበበ ወይም ካነበበ ሰው ያልሰማ አይኖርም ብዬ በመገመት ልጀምር። ባለፈው ሰሞን የማከብራቸው አቶ ቡልቻ አንድነት (በመድረክ) ሕወሓት (በኢሕአዴግ) ማለት ነው የሚል ጽሑፍ (የአማራ ፓርቲ ነው ከሚመስል ነገርጋ) መጻፋቸው አነጋጋሪ ኹኖ ሰንብቶ ነበር አሁን ደግሞ አንድነት መድረክን ገምግሞ ድክመቱን በማሳወቁና ወደውኅደት በፍጥነት እንዲሸጋገር በመጠቆሙ የቃላት ልውውጡ ተበራክቷል። በዚህ መሐል ያስተዋልኩት:–

ሀ)。አንድነት ፓርቲ የመድረክ ትልቁና የበለጠ ተቀባይነት ያለው ፓርቲ መሆኑ አይካድም። ይህ ግን ከሕወሓትጋ አያመሳስለውም። ምክንያቱም አንድነትነ ኅብረብሔራዊ ፓርቲ በመሆኑ ሁሉንም ሕዝብ የሚወክል እንጂ እንደሕወሓት ለአንድ ወገን የቆመ አይደለም።

ለ)。አሁን የተፈጠረውን አለመግባባት ብዙዎች “አይ የተቃዋሚዎች ነገር” ሲሉት ስሰማ ተቃዋሚዎቹ የምንተቸውን ኢሕአዴግን እንዲሆኑ ነውንዴ የምንፈልገው የሚል ጥያቄ ይመጣብኛል። ሕወሓት የበላይነቱን፣ ቀሪዎቹም ደካማነታቸውን እያወቁ ሳይበርዳቸው ሳይሞቃቸው ገዢና ተገዢ ሆነው አሉ። የመድረክ ትንንሽ ፓርቲዎች ጥያቄ ማንሳታቸው የሚያሳየው ትንሹ ትልቁን በጥያቄ መገዳደር እንደሚችል ነው። የአንድነትም መድረክን መገምገምም የሚያሳየው እንደሕወሓት የሌሎቹን አቅመቢስነት ሳይጠናከር እንዳይቀጥል መፈለግ ነው።

ሐ)。አንዳንዶች የሰነዘሩት አስተያየት ደግሞ ሌሎቹ እንደአንድነት መጠናከር አለባቸው የሚል ሳይሆን አንድነት እንደሌሎቹ መድከም አለበት የሚል ይመስላል። አንድ ፓርቲ የበለጠ ጠንካራ በመሆኑ ሲተች አስቂኝና አሳዛኝ ነው። ጥንካሬውን ከጨቋኝነት ቀላቅሎ መረዳትም እንደዚያው።

መ)。ለአንዳንድ የመድረክ አባል ፓርቲዎች አባላት (በተለይ) ወጣቶቹ አባልነታቸውን የአንድነት ፓርቲ የማድረግ ዝንባሌ እየታየባቸው እንደሆነ ሰምቻለሁ። ይህ በፊዚክስ የስበት ማዕከሉ (the center pod gravity) የሚፈጥረው ተፈጥሯዊ ተፅዕኖ ዓይነት የማየቀር እውነት ነው – የስበት ማዕከሉ ትልቁ ሲሆን፣ ትንንሾቹ ወደትልቁ ይሳባሉ። የአንድነት ጥንካሬ የሳባቸው ወጣቶች ወደአንድነት መግባታቸው የሚያሳየው የአንድነትን ጥንካሬ እንጂ ሌላ አይደለም።

አንድን ፓርቲ በጥንካሬው ምክንያት መተቸት አሳማኝ አይደለም።

Sport: ባየር ሙኒክ Vs ዶርትሙንድ –የዳዊትና ጎሊያድ ጦርነት

$
0
0

Borussia-Dortmund-vs-Bayern-Munich
(ምንጭ ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 51 ሚኒሶታ)
ባየርን ሙኒክ ለተጨዋቾች ዝውውር ከፍተኛ ወጪ የሚያወጣ ክለብ ሲሆን ቦሩሲያ ዶርትሙንድ በአንፃሩ ከአካዳሚው በሚያፈራቸው ባለተሰጥኦዎች የብዙዎችን ቀልብ መግዛት ችሏል፡፡ የማሪዮ ጎትዘ በ37 ሚሊዮን ዩሮ ወደ ባቫሪያኑ ክለብ ማቅናት አንዳንድ ቅሬታዎችን ፈጥሯል፡፡ አብዛኞቹ ቅሬታዎች ያነጣጠሩት በባየር ሙኒክ ላይ ነው፡፡ ባየርን የገንዘብ አቅሙን እየተጠቀመ ምርጥና ባለተሰጥኦ ወጣቶችን እያሰሰ ያስፈርማል፡፡ ዶርትሙንድ ደግሞ ዋነኛ ተጠቋሚ ነው፡፡
የሁለቱ ክለቦች ፍጥጫ በትልቁ ባየርን እና በወኔያሞቹ የዶርትሙንድ ወጣቶች መካከል ነው ልንለው እንችላለን፡፡ በጥሩውና መጥፎው አልያም በዳዊትና ጎሊያድ መካከል የሚደረግ ፉክክር ሊባልም ይችላል፡፡ በአውሮፓ መድረክ ታላላቅ ቡድኖችን የሚገነዳድሱ ትንንሽ ቡድኖችን ተመልክተናል፡፡ አፖኤልና ባተ ቦሪሶቭን አይተናል፡፡ አፓኤና ባቴ ሲጠፉ ደግሞ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ መጥቷል፡፡
ባየርን ባለፉት አምስት ዓመታት ለዝውውር ያወጣው የተጣራ ወጪ ከዶርትሙንድ በሶስት እጥፍ ይበልጣል፡፡ ነገር ግን ባየርንን ብቻ ከፍተኛ ወጪ የሚያወጣ የቡንደስሊጋው ክለብ አድርጎ መቁጠር ተገቢ አይደለም፡፡ ታሪክን ወደኋላ መለስ ብለን ከቃኘን ዶርትሙንድም ለዝውውር ብዙ ገንዘብ አውጥቶ እናገኘዋለን፡፡ በወጣቶች የተዋቀረው የአሁኑ ዶርትሙንድ የርገን ክሎፕ በ2008 ወደ ኃላፊነቱ ከመምጣታቸው በፊት እጅግ አስቸጋሪ ዓመታትን አሳልፏል፡፡ ቢጫና ጥቁር በሜዳ ላይ ውጤታቸው ሲዳከም በፋይናንሱ ደግሞ ተንኮታኩተው ነበር፡፡
የቡንደስሊጋው የተጫዋቾች ዝውውር ታሪክ
ባየርን በፋይናንስ በኩል ያለው የፈረጠመ ጡንቻ ሁልጊዜም የቡንደስሊጋው የበላይ ያደርገዋል፡፡ አላማውን ለማሳካት የሚረዳውን የትኛውም ተጨዋች ከማስፈረም ወደኋላ እንደማይል ይገልፃል፡፡ ታሪክ የሚነግረን ግን በቡንደስሊጋው ሪከርድ በሆነ ሂሳብ ተጨዋቾችን ያስፈረሙት ሌሎች ክለቦች መሆናቸውን ነው፡፡ ቬርዴር ብሬመን በ1971 ሪከርድ በሆነ ዋጋ አምስት ተጨዋቾችን አስፈርሞ ነበር፡፡ አምስቱ ተጨዋቾች ግን በጋራ ማስቆጠር የቻሉት 37 ጎሎችን ብቻ ነበር፡፡ ብሬመን ለ10 ዓመታት ከፍተኛ ወጪ ቢያወጣም በ1980 በ34 ጨዋታዎች 93 ጎሎች ተቆጥረውበት ከሊጉ ሊወርድ ችሏል፡፡
ኮሎኝ በቡንደስሊጋው ታሪክ ለአንድ ተጨዋች ዝውውር 1 ሚሊዮን የከፈለ የመጀመሪያው ክለብ ሲሆን ተጨዋቹ ሮጀር ቫን ጎል ይባላል፡፡ በዚህ ወቅት ሙኒክ 200 ሺ ማርክ (የቀድሞ የጀርመን ገንዘብ) ትርፍ አግኝቶ ነበር፡፡ በ1987 ኤይንትራክት ፍራንክፈርት ለሳድስ ዴታሪ ዝውውር 3 ሚሊዮን ማርክ በመክፈል ሪከርዱን አሻሻለ፡፡ በ1995 ሄይኮ ሄርክን ከሞንቼግላድባኽ ለማስፈረም 10 ሚሊዮን ማርክ በመክፈል የመጀመሪያው የጀርመን ክለብ ሆኗል፡፡ ከስድስት ዓመታት በኋላ ዶርትሙንድ ለማርሲዮ አሞሮሶ ዝውውር 50 ሚሊዮን የማርክ (25 ሚሊዮን ዩሮ) በመክፈል ሪከርዱን ደግሞ አሻሽሏል፡፡ ዶርትሙንድ በ1999 ለሄርሊሽና ፍሬዲቦቢች ግዢ የከፈለው 5.75 ሚሊዮን ዩሮ በቡንደስሊጋው በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከተፈፀሙ 50 ከፍተኛ ወጪ የወጣባቸው ግዢዎች ውስጥ ተካተዋል፡፡ የዶርትሙንድ ውድ ዝውውሮች የተካሄዱት ግን ከ2000-2009 ባሉት ጊዜያት ነው፡፡ ቀሪዎቹ ሶስት ውድ ፈራሚዎች ግን ከ2000 በፊት በነበረው ጊዜ የተፈፀሙ ናቸው፡፡
የቡድንስሊጋው ከፍተኛ ወጪ የወጣባቸው ዝውውሮች ስንመለከት ባየርን ሙኒክ ብዙ ገንዘብ አውጥቶ እናገኘዋለን፡፡ የባቫሪያ ውድ ዝውውሮች የተካሄዱት ግን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ነው፡፡ ዶርትሙንድ በ2000ዎቹ መጀመሪያ ላይ የፋይናንስ ውስጥ ሲገጥመው ባየርን ደግሞ አስገራሚ የኮሜርሺያል ገቢ አግኝቷል፡፡ ሙኒክ በ2009 በ30 ሚሊዮን ዩሮ ማሪዮ ጎሜዝን ከስቱት ጋርት በማስፈረም የቀደሙትን ሪከርዶች ሰብሯል፡፡ ባየርን ማኑኤል ኑዌርን በ2011 የቡንደስሊጋው ውዱ ግብ ጠባቂ በማድረግ 22 ሚሊዮን ዩሮ ከፍሎ አስፈርሞታል፡፡ ባለፈው ክረምት ደግሞ 40 ሚሊዮን ዩሮ በማውጣት ሃቪ ማርቲኔዝን ወደ አሊያንዝ አሬና አስመጥቶታል፡፡
የተጠና የቢዝነስ አካሄዱ ባየርን አሁን ለሚገኝበት የማይነቃነቅ የፋይናንስ ጥንካሬው አድርሶታል፡፡ ባየርን ለዝውውር ከፍተኛ ወጪ የሚያወጣው በቂ የፋይናንስ አቅም ስላለው ነው፡፡ ዶርትሙንድን ጨምሮ ቀሪዎቹ የቡንደስሊጋ ክለቦች ዘንድ ግን የባየርን አይነት አቅም የላቸውም፡፡
የዶርትሙንድ የፋይናንስ ቀውስ
ከቡንደስሊጋው መስራቾች አንዱ የሆነው ዶርትሙንድ በሊጉ የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ቡድን ነበር፡፡ በ1966 በአውሮፓ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ ፍፃሜ ሊቨርፑልን በማሸነፍ በኢንተርናሽናል መድረክ ዋንጫ ያነሳ የመጀመሪያው የጀርመን ክለብ መሆን ችሎ ነበር፡፡ በ1970 እና 80ዎቹ ዶርትሙንድ በፋይናንሱ በኩል ተዳከመ፡፡ በአንፃራዊነት በ1960ዎቹ ስኬታማ የነበረ ቢሆንም በ1972 ግን ከሊጉ ወርዷል፡፡ ከአራት ዓመታት በኋላ ደግሞ ወደ ቡንደስሊጋው ቢመለስም በ1986 ወደታችኛው ዲቪዚዮን በድጋሚ ከመውረድ ለጥቂት ተርፏል፡፡
ዶርትሙንድ ደግሞ ወደ ስኬት የተመለሰው በኦትማር ሂትዝፊልድ አሰልጣኝነት በ1991 ነበር፡፡ ሂትዝፊልድ በችግር ውስጥ የነበረውን ቡድን በማጠናከር 1993 ላይ ለአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ዋንጫ ፍፃሜ አደረሱት፡፡ ወቅቱ የጀርመን ቴሌቪዥን ጣቢያዎች የአውሮፓ ውድደሮችን ለማስተላለፍ ገንዘብ ማፍሰስ የጀመሩበት ነበር፡፡ በዚያው ዓመት ክለቦች በሚጓዙበት ልክ ገቢ አግኝተዋል፡፡ ዶርትሙንድ በጊዜው በ16ቱ ቡድኖች ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፈ ብቸኛው ስለነበር ወደ 25 ሚሊየን ማርክ ገቢ አግኝቷል፡፡
ክለቡ የገንዘብ አቅሙን ማጠናከር ጀመረ፡፡ በተለይ ከጣሊያኖቹ ክለቦች ጋር የመፎካከር ኃይል አገኘ፡፡ በወቅቱ በርካታ ጀርመናዊያን ተጨዋቾች በቡንደስሊጋ የሚያገኙት ደመወዝ ዝቅተኛ በመሆኑ ወደ ሌሎች ሊጎች አምርተው ነበር፡፡ ዶርትሙንድ ባገኘው ገንዘብ እንደ ማቲያስ ዘመር፣ ካርል ሄይንዝ ሪድል፣ የርገንኮለር፣ አንድሪስ ሙለር እና ስቴፋን ሬውተር የመሳሰሉትን ወደ ሀገራቸው መልሷቸዋል፡፡ ከእነዚህ ተጨዋቾች በተጨማሪ የጁቬንቱስ ተጨዋቾች የነበሩትን ሁሊዮ ሌዛር እና ፓውሎ ሶዛን አስፈርሟል፡፡
1990ዎቹ የዶርትሙንድ ወርቃማው ጊዜ ነበር፡፡ ቡድኑ በሂትዝፊልድ እየተመራ ሁለት የቡንደስሊጋ እና በ1997 የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን ማሸነፍ ችሏል፡፡ ከ2000ዎቹ በኋላ ደግሞ ቀውስ ውስጥ ለመግባት ተገደደ፡፡ በ1999 በሊጉ አራተኛ ሆኖ ቢያጠናቅቅም በቀጣዩ የውድድር ዘመን ግን ወደ ታችኛው ሊግ ለመውረድ ተቃርቦ ነበር፡፡ ክለቡ ወደ ስኬታማነቱ ጎዳና ለመመለስ ለዝውውር ከፍተኛ ወጪ ማውጣት ምርጫው ሆነ፡፡
ክለቡ ቦቢች (5.8 ሚሊዮን ዩሮ)፣ ቶማስ ሮዚስኪ (145 ሚሊዮን ዩሮ)፣ አሞሮሶ (25 ሚሊዮን ዩሮ)፣ ያን ኮለር (12.75 ሚሊዮን ዩሮ) እንዲሁም ኤቫኒስን (15 ሚሊዮን ዩሮ) ወደ ሲግናል ኤዱና ፓርክ አመጣ፡፡ በ2001/02 የውድድር ዘመን ከፍተኛ ወጪ ያፈሰሰው ዶርትሙንድ የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ከባየር ሌቨርከብን ጋር ከፍተኛ ፉክክር አድርጓል፡፡ በውድድር ዘመኑ የመጨረሻ ጨዋታ በማሸነፍ የቡንደስሊጋውን ክብር ተቀዳጅቷል፡፡ በቀጣዩ የውድድር ዘመን በዶርትሙንድ መልካም ሁኔታ አልተከሰተም፡፡ የፋይናንስ ችግሩ ተባባሰ፡፡
የባየርን በሌሎች መጠላት
ባየርን ሙኒክ በቡንደስሊጋው ታሪክ እጅግ ስኬታማው ክለብ እና የሁልጊዜም የትኩረት ማዕከል ነው፡፡ ከፍተኛ ወጪ በሚያወጣው ክለብ ላይ ብዙዎች ሀሳባቸውን ከመሰንዘር ወደኋላ አይሉም፡፡ ባየርን መልካም ዕድል ያለውና በመጨረሻው ደቂቃ የሚያሸንፍ ቡድን ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ሞንቼግሊድባኽ፣ ዶርትሙንድ፣ ሌቨርከብንና ሼልከ በአንፃሩ በ11ኛው ሰዓት ስኬት የሚርቃቸው በመሆን ይታወቃሉ፡፡ አንዳንድ የቡንደስሊጋ ክለቦች ለባየርን ተጫዋቾቻቸውን ላለመሸጥ ባለመፍቀዱ ተጫዋቹን በአነስተኛ ሂሳብ ለጁቬንቱስ አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ ይሁን እንጂ ባየርን በቅርቡ ያስፈርማቸው ኑዌር እና ጎትዘ የቡንደስሊጋውን ምርጦች ከመውሰድ የሚያቆመው እንደሌለ ያሳያል፡፡ ባየርን ሙኒክ ስኬታማ እንዲሆን ጥሩ እቅድና ግንኙነት ግንባር ቀደምቶቹ ናቸው፡፡ በ1966 ሙኒክ ሮበርት ሻውንን በቡንደስሊጋው የመጀመሪያው ፕሮፌሽናል ቢዝነስ ማናጀር አድርጎ መሾሙ ለወደፊቱ ያለውን ጥሩ ዕቅድ ያመለክታል፡፡ ሮበርት በኡሊ ሆኔሽ ከተተኩ በኋላ የባየርን የዓለም አቀፍ ዝና ይበልጥ ናኘ፡፡ በእርሳቸው ስር 15 የሊግ ዋንጫዎችንና ሌሎች የሀገር ውስጥ ድሎችን አጣጥሟል፡፡
የባየርን ስኬታማነት በሆኔሽ መጎልበቱን ቀጠለ፡፡ የሆኔሽ መምጣት የክለቡን ግንኙነት አስፍቷል፡፡ ሆኔሽ ባየርን ሙኒክ ሆንሽን በተጨዋችነት ያገኘው የ18 ዓመት ልጅ ሳሉ ነው፡፡ ከከተማው ተቀናቃኛቸው 1860 ሙኒክ ጋር ስምምነት ቢኖራቸውም ሆኔሽ ወደ ባየርን አመሩ፡፡ ወደ ባየርን ለማቅናት የወሰኑት በጀርመን ወጣት ቡድን ያሰለጠናቸውን ዑዶ ላዴክ በመከተላቸው ነበር፡፡
በ1979 ሆኔሽ ጫማቸውን ከሰቀሉ በኋላ የክለቡ ጄኔራል ማናጀር ሆነው ተሹመዋል፡፡ ዑሊ ኃላፊነታቸውን እንደጀመሩ ባየርንን ከትክክለኛ ሰዎች ጋር የማቆራኘት ልምዱን አስቀጥለዋል፡፡ ወንድማቸው ዲተር ሆኔሽ ወደ ባየርን እንዲመጣ መንገዶችን አመቻችተውለታል፡፡ ዲተር በባየርን ቆይታው 224 ጨዋታዎች ሲያደርግ 102 ጎሎች አስቆጥሯል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አምስት የቡንደስሊጋ ክብሮችና ሶስት የጀርመን ጥሎ ማለፍ ዋንጫን ማሸነፍ ችሏል፡፡ ኡሊ ሆኔሽ ከሜዳ ውጭ ያላቸው ተፅዕኖ እጅግ ግዙፍ ነው፡፡
የባየርን ሙኒክ ለጋስነት
ባየርን ሙኒክን በ2000 የለቀቀው ማርከስ ባበል ‹‹በአውሮፓ ውስጥ ከሚገኙ ታላላቅ ክለቦች መካከል ባየርን እጅግ ሰብአዊው ነው፡፡ ችግሮችን ሲመለከት እጁን ከመዘርጋት ወደኋላ አይልም›› በማለት ስለቀድሞ ክለቡ አስተያየቱን ይሰጣል፡፡ ባበል አልተሳሳተም፡፡ የተቸገሩ ተጨዋቾችም ሆኑ ክለቦች ባየርን እጁን ይዘረጋላቸዋል፡፡ አለን ማክናሊ በጉልበት ጉዳት ከሜዳ ሲርቅ ባየርን ደመወዙን እየከፈለ ኮንትራቱ እስከሚጠናቀቅ ደግፎታል፡፡ በመኪና አደጋ የተጎዳውን ላርስ ሉንድን ሆኔሽ በግላቸው ረድተውታል፡፡ ገርድ ሙለር ከችግሩ እንዲወጣ ወደ አልኮል ማገገሚያ በማስገባት በኋላም በባየርን ስር ስራ እንዲቀጠር በማድረግ ሆኔሽ የበኩላቸውን ተወጥተዋል፡፡ ክለቦችም የባየርን ድጋፍ ተቋዳሽ ናቸው፡፡ በ2003 ዶርትሙንድ ከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ መግባቱን የተመለከተው ባየርን ሙኒክ ለጥቂት ወራት ለተጫዋቾች ደመወዝ ለመክፈል ይረዳው ዘንድ ለዶርትሙንድ 2 ሚሊዮን ዩሮ ሰጥቷል፡፡ በዚያው ዓመት ባየርን ከሴንት ፖሊ ጋር ባደረገው ጨዋታ የተገኘው ገቢ በመስጠት በደካማ ፋይናንስ ለእገዳ ተቃርቦ የነበረውን ሃምቡርግ አድኖታል፡፡ በ2006 ደግሞ 1860 ሙኒክ በአሊያንዝ አሬና ላይ ያለውን ድርሻ ባየርን 11 ሚሊዮን ዩሮ በማውጣት ገዝቶታል፡፡ በዚህ ምክንያት 1860 ሙኒክ ዕዳ ውስጥ እንዳይገባ ታድጎታል፡፡ ኽርታ በርሊን እና ዳይናሞ ድሬሰደን የባየርን እገዛ ያገኙ ሌሎች ክለቦች ናቸው፡፡ በመጪው ክረምት ሃንሳ ሮስቶክን ለመርዳት ባየርን ገቢ ማሰባሰቢያ ጨዋታ ለማድረግ ተስማምቷል፡፡
የዶርትሙንድ ደጋፊዎች በበኩላቸው የባየርን እገዛ የጠቀማቸው በጥቂቱ መሆኑን ያምናሉ፡፡ ዶርትሙንድ በ2005 መሸጥ የጀመረው ሼር በ80 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን ተከትሎ በተጨዋቾቹ ደመወዝ ላይ የ20 በመቶ ቅነሳ ለማድረግ ተገዷል፡፡ የዶርትሙንድ የፋይናንስ ኦፊሰር ቶማስ ቶስ በወቅቱ እዳቸው 200 ሚሊዮን ዩሮ እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡ ቶሬስ ስለባየርን እገዛ ሲናገሩ ‹‹የባየርን ተግባር ክብር የሚሰጠው ነው፡፡ በአስቸጋሪ ወቅት ሌሎች ክለቦችን መርዳት ድንቅ ተግባር ነው፡፡ የባየርን 2 ሚሊዮን ዩሮ ሁሉንም ችግር ባይፈታም ዶርትሙንድን ደግፏል›› በማለት ያመሰግናሉ፡፡
ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከፋይናንሳዊ ውድቀት በኋላ አካሄዱን በመቀየር ወጣቶች ላይ በማተኮርና ባለተሰጥኦዎችን በማፍራት በአሁኑ ወቅት አውሮፓን ያስገረመ ቡድን ገንብቷል፡፡ ጎትዘ ወደ ባየርን መጓዙና የሮበርት ሌቫንዶቭስኪ መልቀቅ እርግጥ እየሆነ መምጣቱ የዶርትሙንድ ስትራቴጂ በረጅም ጊዜ ምን ያህል እንደሚጠቅመው የሚታይ ይሆናል፡፡ የአሰልጣኝ ክሎፕ በወጣቶች ላይ ያተኮረ ፕሮጀክት ገና እንጭጭ ነው፡፡
የቅርብ ታሪኮችን ተመርኩዘን የዶርትሙንድና የባየርን የቻምፒየንስ ሊግ ፍጥጫ ከተመለከትነው በወጣቶች ላይ ያተኮረውና በከፍተኛ ወጪ ላይ በተመረኮዘ ቡድን መካከል የሚደረግ ጨዋታ ሊባል ይችላል፡፡ ባየርን እና ዶርትሙንድ ታላቅ ክብር የሚገባቸው ቡድኖች ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ጥሩ ታሪክ ተንኮለኛ ገፀ ባህሪ ያስፈልገዋል፡፡ ምርጥ ታሪክ ግን በሁሉም ጎን ጀግና ያኖረዋል፡፡ S
በዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ የስፖርት ዘገባዎችን በየቀኑ ይከታተሉ


ግልጽ ደብዳቤ ለዶ/ር በያና ሱባ (የኦዴግ አመራር) –ከዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ ጂግሳ

$
0
0
ዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ

ዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ

ይድረስ ለተከበሩ ዶ/ር በያና ሱባ፣ የኦሮሞ ዲሞክራሲ ግንባር አመራር በአሉበት።

ይህን ደብዳቤ እንድጽፍልዎ ያነሳሱኝ ምክንያቶች ርስዎ በቅርቡ ለኢሳት ሬድዮ የሰጡት ቃለመጠይቅና አሁን ርስዎ የሚመሩት ከሳምንታት በፊት የተቋቋመው “የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ግንባር የወሰዳቸው አቋሞች ናቸው። ….

ሙሉውን ለማንበበብ እዚህ ይጫኑ
 

Download (PDF, 87KB)

የቶሮንቶ ኢትዮጵያዊያን የዜጎችን መፈናቀል አወገዙ፤

$
0
0

By Tekelmichael Abebe

ብሄርን መሰረት ያደረጉ መፈናቀሎችንና ሀይማኖትን መሰረት ያደረጉ ሰብአዊ ግፎችን ለመዋጋትም ቃል ገቡ

Toronto ethiopian 3
Toronto ethiopian 2
በቶሮንቶና አካባቢዋ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን፤ በኢትዮጵያ በተለያየ ስፍራ የሚደረገውን ብሄርን መሰረት ያደረገ መፈናቀልና ሀይማኖትን የዘመረኮዘ የሰብአዊ መብት ገፈፋ በጽኑእ አወገዙ።
ባለፈው እሁድ ሜይ 19 ቀን ብሉር መንገድ ላይ በሚገኘው በትሪኒቲ ቅዱስ ጳውሎስ ቤተክርስቲያን አዳራሽ፤ በሁለቱ ዋና ዋና ሀይማኖት መሪዎች አስተባባሪነት በተደረገው ስብሰባ ላይ፤ ተሰብሳቢዎቹ በያዝነው ግንቦት ወር ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግና ጉዳዩን ለአለም መንግስታት ለማሳወቅም ወስነዋል።
በዚህ፤ ከአጼ ሀይለስላሴ ዘመን ጀምሮ በሕዝብ እንደራሴነትና በተለያዩ ሀላፊነት ኢትዮጵያን ሲያገለግሉ የቆዩት ሀጂ መሀመድ ሰይድ በምክትል ሊቀመንበርነት፤ እንዲሁም በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ ቃል አቀባይ፤ ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ፤ በሊ/መንበርነት የሚመሩት የፖለቲካ ድርጅቶች ተወካዮችን የያዘው ስብስብ ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ፤ የስብስቡ ምክትል ሊ/መ ሀጂ መሀመድ ከህመማቸው እንዲፈወሱ ጸሎት በማድረግ ተጀምሮ፤ ሶስት ሰዓታት ያህል በመምከር፤ በወቅቱ አንገብጋቢ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የውሳኔ ሀሳቦችን አሳልፏል።
የስብሰባው ሊቀመንበር ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ ባደረጉት የመግቢያ ንግግር፤ ፖለቲካ ውስጥ አንገባም የሚሉ ሰዎች ሰዎች መሆናቸውን እንደሚጠራጠሩ፤ ክርስትናም ከፖለቲካ ጋር ተቃርኖ እንደሌለው፤ እንዲያውም፤ ክርስቶስም ይሁን ነቢያትና ሀዋርያት ነጻነትን እንደሰበኩና፤ የዚህ ዘመን ክርስቲያኖችም ነጻነታቸውን ለማስከበር ከመታገል ወደሁዋላ ማለት እንደሌለባቸው ተናግረዋል።
ሊቀ ካህናት ጨምረውም፤ ቤተክርስቲያን የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ እንደማትታገል፤ እንዲሁም ማናቸውንም የፖለቲካ ቡድኖች ወይንም ፓርቲዎች ለይታ እንደማትደገፍ፤ ይሁን እንጂ ለነጻነት የሚደረግን ትግል የመምራት የሞራል ግዴታ እንዳለባት፤ ለነጻነት ትግል የሀይማኖት ተቋማትና ተከታዮቻቸው ቀዳሚ መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል።
ወደወቅታዊው አንገብጋቢ የአገር ጉዳይና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ማድረግ ስለሚገባቸው ነገር ሲናገሩም፤ “ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር የሚቀረፈው የስርአት ለውጥ ሲመጣ እንደሆነና ሁላችንም ለዚያ ዓላማ መሳካት በትጋት መስራት እንዳለብን አሳስበው፤ እስከዚያው ግን ይሄንን የመከራ ግዜ በድርጅትና በሀይማኖት በብሄርና በግል ጸብ ሳንለያይ በአንድነት መጋፈጥ አለብን ሲሉ መክረዋል።
ከረጅም ውይይት በሁዋላም ከክርስቲያኖችና ከሙስሊሞች፤ ከሴቶች እንዲሁም ከፖለቲካ ድርጅቶች የተወጣጡ 13 አባላት ያሉበት የቶሮንቶ ኢትዮጵያዊያንን የሚያስተባብር ግብረ ሀይል ተቋቁሟል።
ተሰብሳቢው ህዝብ፤ ይህ ግብረ ሀይል፤ በቀጣዩ አንድ ወር ውስጥ፤ ሶስት አበይት ስራዎችን እንዲያከናውን ሀላፊነት ሰጥቶታል። አንደኛ በካናዳ ዋና ከተማ ኦታዋ የሚካሄድ የተቃውሞ ስልፍ እንዲያዘጋጅ፤ ሁለተኛ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ለካናዳ መንግስት የሚቀርብ የውሳኔ ሀሳብ እንዲያሰናዳ፤ ሶስተኛም ለተጎዱት ወገኖች የገንዘብ ማሰባሰብ የሚደረግበት መንግድ እንዲጠና ወስኗል።
ከአፋር እስከቤኒሻንጉል፤ ከጅጅጋ እስከ ጉራፈርዳ በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሰውን መፈናቀልና ሰቆቃ በጽኑ ያወገዘው ስብሰባ፤ በሜይ 25 በኢትዮጵያ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ ለጠራው ሰልፍ ጥቁር ልብስ በመልበስ አጋርነቱን ለማሳየትም መግባባት ላይ ደርሷል።

ከቶሮንቶ ካናዳ ለተጠናከረው ዘገባ፤ ሀብታሙ ስለሺ

አባ መላ ልብ ሲበላ ! በእንግዳ ታደሰ

$
0
0

በእንግዳ ታደሰ

Aba Mela

Aba Mela (Ato Birhanu Damte)

ተረት ሲጀምር ከዕለታት አንድ ቀን ተብሎ አይደል የሚጀመረው ? በኔ እና በአባ መላ የወጣትነት ዘመን  አንድ ድምጻዊ ዘፋኝ ነበር ፡፡  በሃይሉ እሸቴ የሚባል ፡፡  « ገሳጭ እንበለው ? ወይስ  ነቃፊ ዘፋኝ ? »  ብቻ ልማታዊ ዘፋኝ አልነበረም ፡፡ ምጸተኛ ዘፋኝ ብለው ይሻላል ፡፡ ውሻን ወደ ግጦሽ … የዋኋን እንስሳ ደግሞ ወደ ሊጥ ቡሃቃ ያስጠጋ ፡፡ አባ መላ ደግሞ እንደሰማሁት ከሆነ ትውልዱ መርካቶ ዙርያ ስለነበር ፣ ኮልፌ አካባቢ ያለውን የፖሊስ ሠራዊት ሙዚቃ ሰፈር ጠንቅቆ ስለሚያውቀው በሃይሉ እሸቴንም ያውቀዋል የሚል እምነት አለኝ ፡፡

በሃይሉ በዘፈኑ ሲሸነቁጥ የተሰደቡትም ሳይቀር  በዘፈኑ እየሳቁ እንደገናም ከምር ይጠሉት ነበር ፡፡ አባ መላ ልክ እንደ በሃይሉ እሸቴ ፣ ከሰሞኑ የወያኔን ሰፈር ፣ በብላኔ*  ይሁን ወይም በዉነት ስላደበላለቀው ፣ እንስሶቹ ሰፈራቸው ሁሉ ተደበላልቆባቸው የግጦሹ እንስሳ ወደ ሊጥ ወረዳ ፥ የሊጡ እንስሳ ደግሞ ወደ ግጦሽ መንደር ገብተው እየተተራመሱ፣ አንዴም በአባ መላ የአራዳ ቋንቋ ሲስቁ ፣ በሌላም በኩል በጥላቻ እየወረዱበት ይገኛሉ ፡፡ ብላኔ የመርካቶ ቋንቋ ናት- ዕውነተኛ ያልሆነች ሲሉ የሚጠቀሙባት ፡፡

አንድ የቡሽ ጥቅስ ትዝ አለኝ ፡፡ የአባትየው ሳይሆን ፣ የጀርጀራው የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ፡፡ ልክ እንደ አገራችን ቀዳማዊት እመቤት አፉ እንዳመጣለት የሚዘባርቀው ጆርጅ ቡሽ ፣ ሁሌም ባይሆን አንዳንዴ ፣ ጥሩ ጥቅሶች ተብለው ከተመዘገቡለት ውስጥ የመስከረም አስራ ሃንድን የሽብርተኞችን ጥቃት አስመልክቶ የተናገረው ንግግር ነበር ፡፡

« ሽብርተኞች ላይ ርምጃ በምወስድበት ወቅት ፣ አስር ዶላር ለሚያወጣ ባዶ ድንኳንና  በድንኳን ውስጥ ለተጎለቱት ግመሎች  ስል የሁለት ሚልዮን ዶላር ሚሳይል እንዲተኮስ አላደርግም ፡፡ ወሳኝ የሆነ ርምጃ ነው የምወስደው ብሎ  ነበር » ፡፡ ”When I take action, I’m not going to fire a $2 million missile at a $10 empty tent and hit a camel in the butt. It’s going to be decisive.”

በጥሩው ፍቅራቸው ጊዜ ፣ ከአቶ መለስ ጥሩ አቀባበልና ፣ መስተንግዶ ይደረግለት ነበር የሚባለው አባ መላ ፣ አሁን ፥ አሁን ግን በአስር ብር ድንኳን ውስጥ ለተጎለቱት የመለስ ግመሎች ሚሳይሌን ከማስወነጭፍ ፣ ከትላልቆቹ ልጀምር ብሎ የጀመረው ሚሳይል የማስወንጨፍ ርምጃ – ከገዛ ተጋሩ እስከ እነ ግርማ ብሩ ኤምባሲ ግቢ ውስጥ ያሉ ወያኔዎችን ሁሉ አበሳጭቶ ፣ አባ መላን ይሄ ከሃዲ እያስባለው  ነው ፡፡

ከአባ መላ ጋር ያደጉና ቅርሌ የለጉ አብሮ አደጎቹ ፣ አባ መላ ከልጅነቱም ጀምሮ ፣ ባህላተ ቃላት ያለው ወይም አፈ ቀና እንደሆነ ይመሰክሩለታል ፡፡ አባ መላንም ፣ በቦታ ፥ በጊዜ ፥ እንደሁኔታው መሆን የሚችልም ነው ይሉታል ፡፡ እሱም አልካደ ! በአራዳ ቋንቋ ፖለቲካን ማን ነው እንደተርኪስ ባቡር አንድ ቦታ ላይ ያቆመው ? ተለዋዋጭ ነው ብሎናል ፡፡አባ መላ ይህን እንደ ተርኪስ ባቡር  ማን ነው አንድ ቦታ ያቆመው ያለውን ፖለቲካ ፣ አቶ መለስ ከሞቱ  በኋላ ማድረጉ ነው አጠያያቂው ጉዳይ ? አራዳ ሁሌ ሲወሳ ! ያውም ፒያሳ- ያውም ፒያሳ የሚል ዘፈን የሰማሁ ይመስለኛል ፡፡ ዉነቱን ነው አባ መላ ! በአቶ መለስ ለሳኝነት በአህያ ቆዳ የተሰራው ቤት ፣ ጅብ ሲጮኽበት ፈረስኩ ፣ ፈረስኩ ሲል እያየ ! ማን አብሮ እዚያ ቤት ይከርማል ? አራዶቹ እነ አባ መላ ድሮ « ላስ እንደ አየር ላንስ ይሉ አልነበር መርካቶ ! »

ግን አባ መላ ! ይህ ፖለቲካ ተለዋዋጭ ነው ! አንቀጹ መሻሻል አለበት ! የዘር ፖለቲካውም ጦዘ ! በየኤምባሲዎቻችንም አንገቱ ላይ ከረባት ያንጠለጠለ ገበሬ በዛበት ፥ ሻንጣ ተሸካሚውም በዛ ፣ የተባለውን ፊልም ያየውና የባነነው አቶ መለስ ከሞቱ  በኋላ ነው ወይስ ድሮም በብልጥጤ አይ ነበር ሊለን ነው ? ዉነቱን ነው አራዳው ሁሉ ወረዳ በሆነበት ዘመን ! አባ መላ ፊልም ቢሠራብን ሊደንቀን አይገባም ፡፡

ባለፈው ፕሮፌሰር መስፍን ፓል ቶክን በሚመለከት በጻፉት ጽሁፍ ላይ ያላስተዋልኩትን ነገር እንደገና ሄጄ እንዳይ አድርገውኛል ፡፡ የዚህ ፓልቶክ ሰለባ የሆኑት የምስራቅ አፍሪቃ አገሮች ሰዎች ሲሆኑ ፣ ከፍተኛውን ቁጥር ሱማልያ ስትዘግን ሁለተኛውን ደግሞ ኢትዮጵያ ታፍስና ፣ ሶስተኛውን ደግሞ ኤርትራ ትቆነጥራለች ያሉትን በትክክል አየሁ ፡፡

ናይጄርያ በአፍሪቃ ከፍተኛውን የህዝብ ቁጥር ያላት አገር የከፈተችው የፓልቶክ ክፍል አንድ ነው ፡፡ እሱም ሙዚቃ ብቻ ነው የሚያሰማው ፡፡ ከዚያም ከዘለለ ምናልባት ቢያስተዋውቅ የፉፉ ዱቄት ሊሆን ይችላል ፡፡ እንደ አፍሪቃ ቀንዱ የፖለቲካ ዲዲቲ አይረጭም ፡፡

ከዘጠና ሰባት ምርጫ ወዲህ ፓልቶክ የሚባለውን ጣቢያ ከኮምፒዩተሬ ውስጥ አውጥቼ  በሰላም እኖር ነበር ፡፡ ከሰሞኑ አንድ ጸሃፊ ለዚህ ፓልቶክ ጥሩ ስም አውጥቶለት አንብቤአለሁ – ቡል ቶክ ! ብሎታል ፡፡ አንድ ወዳጄ ኧረ እባክህ አባ መላን ግባና አድምጠው ብሎ ቢጨቀጭቀኝ ፣ ይህን ፓልቶክ የሚባል ጭነት ኮምፒዩተሬ ውስጥ ጭኘ  እንደ ቦኖ ወሃ ጠባቂ ሴት ተራዬን ጠብቄ ውዬ ፥ ውዬ እድሉን አገኘሁና አባ መላ ድንኳን ጎራ አልኩ ፡፡

ዉነትም አባ መላ ! አፉ እንደ አሜሪካን ዶላር ነው ፡፡ ይለዋል ! ይመነዝረዋል ፡፡ አበባ ይረጭለታል ! በርታ የሚልም የጅ ጠአት ይቀሰርለታል- ኧረ ስንቱ ! እጅግ የገረመኝ አባ መላ የማረከው የሚመስል የእጅ ምስል ለመናገር ተራ እየጠበቀ እጁን የሰቀለው ሰው መብዛቱ እጅግ ድንቅ የሚል ነው ፡፡ በዚህ መሃል አንድ እጅግ ከልቤ ያሳቀኝ አንድ ተረበኛ ሰው ከጽሁፍ ገበታው ላይ አንድ የሚያስቅ ጽሁፍ ከተበ ፡፡ አቤት ! አቤት ! ይሄ ሁሉ እጅ ፣ አንዳንድ ጠብመንጃ ቢይዝ ኖሮ ወያኔ የሚባል አይኖርም ነበር ፡፡ ወሬኛ ሁላ አለ ! አባ መላም የሚስቅ ምስል ለቀቀለት ፡፡ አባ መላ ውነትም የፓልቶክ አባባ ታምራት ገለታ ነው ፡፡

እጅግ የሚገርመው እዚያው አዲስ አበባ ላይ ሆኖ  ወያኔን በተባ ብዕሩ እንቅልፍ የሚነሳውን ፣የተመስገን ደሳለኝን ጽሁፍ የማያነብ ዲያስፖራ ! አሳጥረህ ብቻ አንቆርቁልኝ የሚል ብዙ ሰው በአባ መላ ተሞለቀቀ ፡፡ ሞለቀቀ በከሳቴ ብርሃን መዝገበ ቃላት ብዙ ትርጉሞች ቢኖሩትም ፣ በዚህ አግባብ ግን ብዙ ሰው በአንድነት አብሮ ሄደ ነው ትርጉሙ ፡፡ እስከዛሬ ግንባራቸውን ሳያጥፉ የወያኔንን ካምፕ ሲያራውጡ የነበሩ የፓልቶክ ክፍሎች ሁሉ ሳይቀር ቀፎአቸውን ነቅለው አብረው ሊቀላቀሉ እስኪመስል ድረስ ቤታቸውን አቀዘቀዙ ፡፡ አባ መላም አለ ! በሶስት ክፍል የከፈትኩትን ክፍል ለወደፊት በሬድዮ ጣቢያም አጎለብተዋለሁ አለ ፡፡ ማን ያውቃል ፟? ቀጥሎም ኢሳትን የሚገዳደር ቴሌቪዥንም ሊከፍት ይችላል ፡፡

ይህን ሞገደኛ የዲያስፖራ ኃይል በአራዳ ስልትና በወያኔ ቆረጣ ለመሰንጠቅ ፣ የሚደረግም ጨዋታ ሊሆን ይችላል ብሎ መገመትም የዋህነት አይመስለኝም ፡፡ በእባብ የደነገጠ በልጥ ሆኖብን ብንጠራጠር  አባ መላ ይቀየመን ይሆን ?

ልደቱ ሸዋ ሮቢት ታስሮ ወያኔ  በአይነ ምድር ላይ በባዶ እግሬ እንደ ጭቃ ረጋጭ አስረገጠኝ ሲለን አዝነን ማንዴላችን አልነው ፡፡ ቀጥሎም በምርጫ ዘጠና ሰባት ወቅት ወያኔ ቢሮዬ ውስጥ ቆልፎብኝ ፣ ይኽው ሶስተኛ ቀኔ ብሎ ፣በአሜሪካን ድምጽ የአማርኛ ፕሮግራም በስልክ ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ ! እንዴት ወያኔ ስልኩን ሳይቆርጥበት ባዶ ቢሮ አስቀመጠው  ብለን ሳንጠይቅ ልደቱ ልባችንን በላው ፡፡ ይህ ሁሉ ደርሶብን ! አባ መላ አንተንም እንደ ታምራት ገለታ ብንጠረጥር ትቀየመን ይሆን ?

 

ግምቴን ላስቀምጥ ፡፡ አባ መላ አሁንም የኢሃዴግ ደጋፊ ነኝ ይለንና ፣ የተማረኩት በወያኔ ፎቅና መንገድ ነው ይለናል! እኛም እንለዋለን ! ጥልያንም ጣዝማ በርንም ፥ ጅማንም ፥የቀበና ድልድይንም ገንብቶልናል እና ጥላያን ተመልሶ ይግዛን ማለትህ ነው እንለዋለን ? ፡፡ ስለ ሃብት ክፍፍሉ ፍትሃዊ አለመሆንና ፣ ባዶ አንገታቸው ላይ ክራባት ያሰሩ የአንድ ክልል ተወላጅ  ገብሬዎች ፣ ኤምባሲያችንን ሞልተውታል እያለን ፣ በዘረኝነትና በሙስና የተበከለን መንግስት እደግፈዋለሁ ሲለን ሃሳቡ አይጋጭም  ?

 

አባ መላ! ምናልባት አቶ መለስ ያዋቀሩት በአህያ ቆዳ የተለበጠው ቤታቸው ከርሳቸው ህልፈት በኋላ እንደማይቆይ ቀድሞ ነቄ ስላለ ፣ፖለቲካ ዳይናሚክ ነው ፣ መገለባበጥ ነው በሚልም እሳቤ ይህን ርምጃ እንደወሰደ በገሃድ ነግሮናል ፣የአባ መላን አመል ለማወቅ ራጅ ወይም ኤክስሬይ እስካላገኝንለት ድረስ ከአባ መላ ጋር አብሮ ለመሥራት ከሌሎች ፓልቶክ ቤቶች የአድሚንነት ስራ ለማግኘት cv ያቀረቡ አድሚኖች የአባ መላን ዘላቂነት የት ያህል ተረድተዉታል ?

 

አባ መላ እንደሚለው ብዙ ሰነዶች በእጁ እንዳሉና ፥ በራሱ በኢሃዴግም ውስጥ ጥገናዊ ለውጥ የሚፈልጉ አመራሮች እንዳሉ ስለነገረን ፣ ይህን ነውጠኛ የዲያስፖራ ህዝብ ፣አባ መላ ከሚያውቀው የጥገና ለውጥ አቀንቃኝ የኢሃዴግ መስመር ጋር ለማዛመድ የሚወሰድ ርምጃ እንደሚሆን መገምት ቢቻልስ ፥

 

በመጨረሻም በወያኔያዊ ቆረጣ ፣ ይሄ አልበገር ያለውን ፣ የአባይ ቦንድን ገንዘብ አትበሏትም ብሎ ባዶ አቁማዳዎቻቸውን ይዘው እንዲመለሱ ያደረጋቸውን የዲያስፖራ ህዝብ ፣ በሚጥመውና ፥ ደስ በሚለው አራዳዊ ቋንቋ እንደ ታምራት ገለታ አነሁልሎ ፣ የወያኔን ቀላል ሚዛን ቦክሰኞች እና የገዛ ተጋሩን ሰዎች አስደንብሮ ከክፍሉ ካስወጣ በኋላ ! ኑ የሌሎች ፓልቶክ ቤት አድሚኖች ፣ እንደውም ታላቅ የፈውስ ኮንፍረንስ ለመጀመርያ ጊዜ ፣ በሳይበር አለም ከአዲስ አበባና ክምድረ አሜሪካ ያሉ ታዋቂ ተቃዋሚዎችን ስለጋበዝኩ  ዛሬና እሁድን ከኔ ጋር አሳልፉ የሚለው ግብዣ ስንቱን ጠርጎ ይወስደው ይሆን ፟? ጠርጥር ከጥህሎም አይጠፋም ስንጥር ሆኗል ተረቱ ተቀይሮ አባ መላ ! ለማንኛውም ፖለቲካ ዳይናሚክስ ነው ! አባ ድሉን ግን ትወዳቸዋለህ እንጂ ! እሳቸው እንኳ የሚከረበቱ አይመስለኝም…ለቀልድ ነው

ከአንተ ቀጥሎ በፓልቶክ ንግግር የምወዳቸው አባት ናቸው ፡፡ በተለይ ከግዕዙ ጋር ሲያዋዙት አቤት ደስ ሲል፡፡

 

እንግዳ ታደሰ

 

ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ግንቦት 25 ቀን 2005 ይደረጋል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው የተቃውሞ ሰለፍ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም እንደሚደረግ ታወቀ። ፓርቲው እንደገለጸው “ከአዲስ አበባ አስተዳደር ም/ከንቲባ በዛሬው እለት በተሰጠ ገለጻ መንግስት 50ኛውን የአፍሪካ ህብረት በአል ለማክበር በአሁኑ ግዜ ከፍተኛ የጸጥታ ሰራተኞች መድቦ በመስራት ላይ በመሆኑ ከፓርቲው የቀረበልንን ጥያቄ ለማስተናገድ የጸጥታ ሰራተኞች እጥረት አለብን። ይህም በመሆኑ የተቃውሞ ሰልፉ ቀንና ቦታ እንዲለወጥ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲም የዚህን ጥያቄ ተገቢነት ከሰላማዊ ሰልፍና የፖለቲካ ስብሰባ ስነስርአት አዋጅ ቁጥር 3/1983 አንጻር በመመርመር ተገቢ ሁኖ ስላገኘው የተቃውሞ ሰልፉ ግንቦት 25/ 2005 አ.ም. በኢትዮ-ኩባ አደባባይ ከጠዋቱ 4 ሰአት- 8 ሰአት እንዲሆን በመወሰን ከመንግስት የእውቅና ማሳወቂያ ደብዳቤውን ተቀብሏል፡፡”

በዚህም መሠረት ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው የተቃውሞ ሰለፍ ግንቦት 25 በአዲስ አበባ ስለሚደረግ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንዲገኝ መጋበዙን ፓርቲው አስታውቋል። ፓርቲው ለሰላማዊ ሰልፉ ባገኘው እውቅና መሠረት በከፍተኛ ሁኔታ ቅስቀሳ እያደረገ ሲሆን እየበተነ ያለው ፍላየርም የሚከትለው ነው።

semayawi party

ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

በየፊናችን እየተማረርን መማራችን ለበጎ ነው –ከይነጋል በላቸው

$
0
0

ይነጋል በላቸው

እቲ ናይ ቀደም ሰላም ዘመን ክምለስ፤
ሰላም ኢልና ንዝመር ብሃደ መንፈስ፡፡…
(ከኤርትራው ተወላጅ ድምጻዊ ርዕሶም ገ/እግዚአብሔር የዘፈን ግጥም የተወሰደ)

በየፊናችን እየተማረርን መማራችን ለበጎ ነው – ከይነጋል በላቸው ይሄ ኢሣት የሚባል ቴሌቪዥን በትዝታ ባህር እያስዋኘ ጊዜየንም ዕንባየንም እያስጨረሰኝ ነው፡፡ በግማሽ ሜትር ርቀት እሱው ጋ – እቲቪው አጠገብ – ከተደቀንኩ የሚያስነሳኝ የለም፡፡ ቤቴ ሁሌ በአምባጓሮ እንደታመሰ ነው፡፡ ቤተሰብ የሚፈልገውና እኔ የምፈልገው ለየቅል በመሆኑ ትንሹ አምባገነን ሆኛለሁ፡፡ ለነገሩ አምባነንነት የሚጀምረው ከቤት ነውና ይቺ ተፅዕኖየ እየተሰማችኝ መጥታለች፡፡ ምን ላድርግ?
ትናንትና ጧት ላይ ሲሳይና ተወልደ ይበልጡን በግንቦት ወር ዙሪያ የሚያጠነጥንና እልህና ቁጭት ውስጥ የሚከት ዝግጅት እያቀረቡ ሳለ አንድ ሙዚቃ ጋበዙን፡፡ የዚህ ሙዚቃ አዝማች በመግቢያየ ላይ ያስቀመጥኩት ነው፡፡ የአማርኛንና የትግርኛን ቋንቋዎች ተቀራራቢነት የምገልጽላችሁ ይህን እላይ ያስቀመጥኩትን የሁለት ስንኞች ዘለላዎች ወዳማርኛ ላለመተርጎም በመፈለግ ነው – ተቻችሏልና – ከዚህ በላይ እንደምን ይነገር – ያው ነው፡፡ ስልቻ ቀልቀሎ ቀልቀሎ ስልቻ፤ (እኛን የሚያለፋን ክፉ መንፈስ ብቻ፡፡)
በተለይ ከ1960ዎቹ የመጨረሻ ዓመታት አንስቶ በኢትዮጵያ ውስጥ የተለቀቀው የአውሬው ክፉ መንፈስ በሀገራችን የሠለጠነው ክፉ አውሬ ያላደረገን ነገር የለም፡፡ ኢትዮጵያችንን እንደገና መሥራት እጅግ አስቸጋሪ እስከሚሆንብን ድረስ የአጋንንት ኃይል ተጫውቶብናል፡፡ ተመሳሳይ የባህልና የኢኮኖሚ እንዲሁም የሃይማኖትና የሥነ ልቦና ቀመር ባላቸው የአንዲት ሀገር ሕዝብ መካከል በሌሎች ሀገራት ያልታዬ የመከፋፈልና የዘረኝነት አባዜ ታይቶብናል፡፡ የታዩብንን ኆልቁ መሣፍርት የሌላቸውን ጉድፎች ከመግለጽ ይልቅ ያልታዩልንን ጥቂት መልካም ገጽታዎች መናገሩ ሳይቀለን አይቀርም – እነሱም ካልደበዘዙ፡፡
ለዐይን ይበጃል ተብሎ የተቀቡት ኩል ዐይንን እንደሚያጠፋ ሁሉ የነበሩንን አነስተኛ ችግሮች ለማስወገድ ብለን አንዳንዶቻችን በወሰድናቸው እርምጃዎች የጋራ የትስስር ገመዶችን (social fabrics) ከመበጣጠስ ጀምሮ አጠቃላዩ ማኅበረሰብኣዊና ሀገራዊ ኅልውናችን ጥያቄ ውስጥ እስኪገባ ድረስ ረጂም የጥፋት መንገድ ተጉዘናል፡፡ የሀብትና ሥልጣን ሱስ እንዲሁም አጥንትን ሰርስሮ የገባው የቂም በቀል ልክፍትና የጥላቻ መንፈስ ከደም ዝውውር ሥርዓታችን በቀላሉ ስለማይወጡ እንጂ አሁን ሰዓቱ የንስሃ ነበር፡፡ ንስሃው ቀርቶ ከምንሠራቸው ተጨማሪ ጥፋቶች መቆጠብ በራሱ ትልቅ መልካም ዋጋ የሚያሰጠው ነበረ፡፡ ‘Better late than never’ ይላሉ ፈረንጆች – አርፍዶም ቢሆን አንድን (መልካም) ሥራ መሥራት የሚገባ መሆኑን ለማጠየቅ፡፡ ግን ማን ዐውቆት? የዘመኑንስ መቃረብ ማን ተረድቶት? …
ርዕሶም ገ/እግዚአብሔር ለአንድ ድሃ ዘመዴ የሚሆነኝን ዕንባ ሊያውም በጧቱ አስነባኝ፡፡ እግዚአብሔር ይባርከው፡፡ የብዙ ልጆች አባት የነበረውና በሻዕቢያ ሠርጎ ገቦች የተገደለው የነምሥግና ደግ መንፈስ፣ የነዶክተር ፍስሐጽዮን መንግሥቱ ደግ መንፈስ፣ የሌሎቹም የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ግዛት የኤርትራ ዕንቁ ልጆች ደገኛ መንፈስ ከመለኮት ጥበቃ ጋር በነፍስና በሥጋው አይለዩት፡፡ ልጅነቴን አሳየኝ፡፡ የደጉን ዘመን አሻራዎች በዘፈኑ አስቃኘኝ፡፡ አዲስ አበባ ላይ በተወሰኑ ቦታዎች ፈልጌ ስላጣሁት ይህን ዘፈኑን በኢሜሌ ለሚልክልኝ ወገን – ምን ሽልማት ላዘጋጅ እባካችሁን – አዎ – አዲስ አበባ አሥመራ የደርሶ መልስ የመኮንን ነጋሽ ወይም የሀጂ አብዱ አሊያም የወሎ ፈረስ ሀገር አቋራጭ ትኬት በአድራሻው እልክለታለሁ፡፡ በእነዚህ አልሄድም ለሚል የንሥር አሞራ ትኬትም አለኝ፡፡ (እነዚህንና ሌሎችን የሕዝብ ትራንስፖርት ማኅበራት የሚያስታውስ ይኖር ይሆን? ዘመኑ እኮ እየራቀ ሄደ!)
ርዕሶምን ወደድኩት፡፡ እንዲህ ይላል – ጦርነት ይብቃን፤ እንደ ቀድሞ ሠናይ ዘመን ወደ አንድነታችን እንመለስ፤ የአንድ ቤተሰብ ልጆች ተበታትነን አንቅር፤ በአክሱም በአድዋ በጎንደር በጎጃም ባህር ዳር አድርገን በአውቶቡሶችቻችን ልክ እንደዱሮው በፈለግነው አቅጣጫና ወደፈለግነው ቦታ እንደርሱ አገላለጽ ወዳፈተተን የኢትዮ-ኤርትራ ግዛት እንዳሻን እንመላለስ፤ ከሸዋ ወደ አሥመራ ያላንዳች ኮንቮይና ያላንዳች የጉዞ ሰነድ በአንድ ሀገር ልጅነት እንዘዋወር፤ በምፅዋ በሃሰብ በአውሣ በደሴ በኮምቦልቻ ከሚሴ አድርገን ትሬንታ ኳትሮዎቻችን፣ ኤን ትሬዎቻችን፣ ሎንቺናዎቻችን እንደቀድሞው ደጉ ዘመን ሰውም ሆነ ዕቃ እየጫኑ ይመላለሱ፤ (በተንኮለኞችና በመሠሪዎች) ከሸልቶው የተለየው ሪሞርኪ ይቀጠልና መኪናው የተሟላ አቋም ይኑረው – የተበጠሰው ግንኙነት ይቀጠል፤ በሃይማኖትና በቋንቋ ልዩነቶች መቆራቆስ ይብቃ… ይለናል – ሰሚ ከተገኘ የርዕሶም ዘፈን ታሪካዊ ነው፡፡ የቀድሞውን ዘመን በጨረፍታም ቢሆን ላዬ ለእንደኔ ዓይነቱ ከርታታ ዜጋ ይህ ዘፈን ካላስለቀሰው ሌላ ምንም ሊያስለቅሰው የሚችል ነገር የለም – አለበለዚያም ራሱ አስለቃሽ ነው ማለት ነው፡፡
የደረስንበት ዘመን ለወሬ ብዙም የሚያምር አይደለም፡፡ ከአሁን ወዲያ ወሬና የፖለቲካ ትንተና ሳይሆን ተግባራዊ እንቅስቃሴ ብቻ ነው ሀገራችንን ከወረሯት መዥገሮችና ገሃነማዊ የእሳት ትሎች ነጻ ሊያወጣት የሚችል፡፡ በመቶዎች የአስተሳሰብና የአመለካከት ጎራዎች እየተቧደኑ በነገር ጅራፍና በአሽሙር ጦር መተጋተጉ፣ በመቶዎች የሲቪል ማኅበረሰብ ተቋማት እየተደራጁ በቃላትና በተቃውሞ ሰልፍ ጠላትን በምናብ ‹ማደባየቱ›፣ ወጡ ሳይወጠወጥ በርቀትም በቅርበትም በህልማዊ ሥልጣን ነፍዞ መቆራቆሱ፣ ተመሳሳይ በሽታን ለማከም ተመሳሳይ የዘረኝነት ክትባትን ተከትቦ በዚያ ያረጀ ያፈጀ የጎጠኝነት ፈሊጥ ተሰባስቦ የ‹እገሌ ብሔር ነጻ አውጪ ድርጅት› እያሉ በወያኔዊ ቅኝት መጓዙ፣ ከአንዱ እያኮረፉ ወደሌላው በመግባት ከነባሩ የበሰበሰና የገማ ስብዕና መገለጫ ጋር አዲስና የቆዩ እንቅስቃሴዎችን ማጨንገፉ፣ ለሥልጣንና ገንዘብ ሲባል በሕዝብ የማቴሪያልና የሞራል ሕይወት መጫወቱ… ላለፉት 22 ዓመታት ተሞክሮ ‹እነሱ›ን ከመጥቀም ባሻገር ‹እኛ›ን ጨምሮ ሁላችንንም የሚጠቅም አንዳችም ለውጥ ባለማምጣቱ ከዚህ በኋላ በዚህ የተበላ ዕቁብ መንገድ መራመዱ ዋጋ የለውም – የሕዝብን የነጻነት ፍለጋ መንፈስ በማቀጨጭና አለኝታን በማሳጠት ረገድ የተጫወተው ሚናም ቀላል አይደለም – ሕዝቡን ሰጥ ረጭ ያደረገውም ይሄው ነው (‹አገባሻለሁ ያለ ላያገባሽ ከባልሽ ሆድ አትባባሽ› የሚባለው ይህን ዓይነቱን መጥፎ አጋጣሚ ለመግለጽ ነው)፡፡ ከአሁን በኋላ ማድረግ የሚገባን ‹እነሱ›ንም ‹እኛ›ንም በእኩል የሚጠቅም፣ ሀገራችንን ከውርደት የሚያድን፣ ሕዝባችንን ካለመኖር ወደመኖር የሚያመጣ አዲስ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመር እንጂ የሞኝ ዘፈን ሁልጊዜ አበባየ እንዲሉ በጀመርነው የንግግርና የጽሑፍ እንካስላንትያ መቀጠሉ ብዙም ፋይዳ ያለው አይመስለኝም፡፡ ከነተረቱ የወሬ የለውም ፍሬ ነው፡፡ ሕዝቡ የሚፈልገው ዜና ‹ እንደዚህ የሚባል ጠንካራ የተቃዋሚ ኃይል እነዚህን ጠቅላይ ግዛቶች ተቆጣጥሮ ወደመናገሻዋ ከተማ ወደ አዲስ አበባ በከፍተኛ ፍጥነት እየተጓዘ ነው› የሚል እንጂ የነገር ወንጭፍ ሰልችቶታል፡፡ የዚያ ዓይነት ዜና በተነገረ ማግሥት – ለዚያ ዓይነቱ ዜና ያብቃን እንጂ – በየትኛውም ኢትዮጵያዊ ሥፍራ ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት አይከብድም፡፡ ለማንኛውም ጥቂት ነጥቦችን እንዳመጣጣቸው ላክልና ላብቃ፡፡
1. ቪኦኤ ‹ወጣቱ የፖለቲካ ተንታኝ› እያለ የሚያሞካሸውን የጁሃር ሲራጅ መሃመድን የኢሣት ቃለ መጠይቅ ተከታተልኩ፡፡ እጅግ የሚመስጥ ነው፡፡ ልጁም የዋዛ አይደለም፡፡ ጥሩ አንባቢ ነው፡፡ የልጅ ዐዋቂ ቢባል አያንሰውም፡፡ ይደግ ይመንደግ፡፡ ከዐይን ያውጣው፡፡ እንደልደቱ አያሌው የትንታግ አንደበት ባለቤት ነው – ያነጻጸርኩት አንደበታቸውን ነው፤ አንደበት ደግሞ የእውነተኛ ማንነት መገለጫ አይደለም – ተግባር ነው ዋናው የማንነት ማሳያ፡፡ የተሰማኝን ቅሬታ ግን በእግረ መንገድ ልግለጥ፡፡ እናም ለጁሃር ብቻ ይህችን ጸሎትና አስተያየት ልሰንዝር፡፡
የተሟላ ኢትዮጵያዊ ስብዕና እንድትላበስ፣ ከሌንጮ ለታዊ ሻዕቢያ ተከል ኋላቀር አስተሳሰብ ነጻ የወጣህ እንድትሆን፣ ከአንድ ብሔር ተቆርቋሪነት ወጥተህ የሁሉም ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች አለኝታ እንድትሆን ፈጣሪ ይርዳህ፡፡ ይህን የምለው በቃለ መጠይቁ ከተናገረው ሳይሆን ካልተናገረው ነገር ግን ለኔና መሰል ወገኖቼ ከዐይነ ውኃው ከሚገባን ተነስቼ የተረዳሁትን ነው፡፡
ጉዳዩ እንዲህ ነው፡፡ በእንግሊዝኛው paralanguage ይሉት ነገር አለ፡፡ በቋንቋ የመግባባት ሂደት ቀላል አይደለም – እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡ እየመረቅሁህ የምረግምበት፣ እየሰደብኩህ የማመሰግንበት፣ ፍቅሬን እየገለጥኩልህ ጥላቻየን የማንጸባርቅበት የአነጋገር ሁኔታ አለ፡፡ ወርቃማ ቃላትን፣ ሰውነትን በሃሤት የሚያለመልሙ ሀረጋትንና ዐረፍተ ነገሮችን በአንደበቴ እየተናገርኩ ባለሁበት ሁኔታ የሰውነት እንቅስቃሴየና መላው የአነጋገር ድባቤ ሲጠና ግን ከምናገረው በስተጀርባ የተለያዩ የእውነተኛው ስሜቴ ነጸብራቆች የሆኑ ተቃራኒ መልእክቶች ሊተላለፉ እንደሚችሉ መታወቅ አለበት፡፡ ቋንቋ ብቻውን እውነተኛውን ማንነታችንን አያሳይም ማለት ነው፡፡ ድባብና ዐውድ እንዲሁም ድምፀት ቋንቋ አከል የመግባቢያ ሥልቶች ናቸው፡፡ ሁሉንም እንደወረደ ከወሰድነው ለተሳሳተ ግንዛቤ ልንጋለጥ እንችላለንና ንግግርን ከዐይነ ውኃ ጋር በማዛመድ የሰውን እውነተኛ ማንነትና ስሜት ከተራው ሥነ ልሣናዊ ዐውድ ወጣ ባለ መንገድ ለመረዳት መሞከር ይገባናል፡፡ በዚህ ረገድ ብዙ ማለት ቢቻልም ለአሁኑ ይብቃን፡፡
ጁሃር የኢትዮጵያን ስም መጥራት በልጆች አነጋገር የሚደብረው ይመስለኛል፡፡ በዚያ ቃለ መጠይቁ ጠያቂው ኢትዮጵያን በተደጋጋሚ ለመጥራት ቢሞክርም ተጠያቂው ገሸሽ ሲያደርግና ወደኦሮሚያ ክፉኛ ሲያዘነብል አስተውያለሁ ፤ ከተሳሳትኩ እታረማለሁ፡፡ ግን ለምን እንዲህ ሆነ? ብለን መጠየቅ እንችላለን፡፡ ምክንያቱን ከመገመት በስተቀር በግልጽ ለማወቅ ይከብዳል፡፡
ጁሃር የወያኔ ዘመን ምሁር ነው፤ ያልዘሩት አይበቅልምና የተቃኘበት ዘፈን ሁሉ ከኮዝሞፖሊታኒዝም አነስ ሲልም ከኢትዮፒያኒዝም እጅግ ባፈነገጠ መልኩ የአንድ ብሔር አቀንቃኝ ሊሆን የመቻሉ ምሥጢር ጊዜው ያቀረበለት ምርጫና እርሱም ምናልባትም ሳይወድ በግዱ የተቀበለው አካሄድ ይመስላል፡፡ እናም እንደ ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሣ ጥናታዊ ዘገባ ከ80 በመቶ በላይ በጋብቻና ወሊድ ትስስር እርስ በርሱ ተጋምዶ እንደውሃና ወተት የተዋሃደውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ‹ኦሮሞ፣ አማራ …› እያለ በወያኔ በተቀደደለት ቦይ ለመፍሰስ መሞከሩ ትንሽ አሳስቦኛል፤ ከልጅ አንደበት ይህን መሰል ፍካሬ የማንበቤ ዕድለቢስነቴም አስቆጥቶኛል፡፡ ይህ ብርቅዬ ልጃችን እንደገና ቁጭ ብሎ ማሰብ ይኖርበታል – እኔ እሱን የኔ ብዬ ያለመሻከክ እንድቀበለው እርሱም የጋራ እናታችንን እማዬ እንዲላት እጠብቃለሁ – የእንጀራ እናቱ አይደለችምና፡፡ ገና ወጣት እንደመሆኑ ቅኝቱን ለብልጣብልጥነት ሥልት ሳይሆን ለእውነት ብሎ ካስተካከለ በመለኮታዊ የዕውቀት ትውፊት ታድሏልና ሁላችንንም የሚጠቅም የሁላችንም ተስፋ ሊሆን የሚችልበት ዕድል አለው፡፡ አሁን በያዘው ጎዳና ቢቀጥል ግን አዝናለሁ የትም ይደርሳል ብዬ አላስብም፡፡ ላስፈራራው አይደለም፡፡ እውነትን መናገር ስላለብኝ ነው፡፡ ዘመኑ የጎጥና የሸንተረር፣ የነገድና የአጥንት ጥራት ሳይሆን የሰብኣዊነት ነው፡፡ እንስሳት የዕድገት ደረጃቸው እንደሚፈቅድላቸው ዐይጥ ከዐይጥ ፣ ድመት ከድመት፣ ውሻም ከውሻ… ይሰባሰቡ፡፡ ሰዎች ግን ሰዎች ስለሆንን በደምና በአጥንት ሳይሆን በሰውነታችንና በሀገራዊ የጋርዮሽ ዜግነታችን እንሰባሰብ፡፡ (ከአሁን በኋላ ደግሞ መታወቂያችን ላይ ‹ብሔር› የሚል ነገር መኖር የለበትም፤ ዜግነት የሚለው በቂ ነው፡፡)
‹ከአነጋገር ይፈረዳል፤ ከአያያዝ ይቀደዳል› ነውና ጁሃር የአዲሱ ዘመን ሐዋርያ መሆን ከፈለገ በዘር የታሸውና ኦሮምኛ ተናጋሪን ሕዝብ ከኢትዮጵያ አጀንዳ እየነጠለ ኦሮሚያና ኢትዮጵያ የሚባሉ ልይት ኑባሬዎች ያሉ ያህል መስበኩ አዋጪ ካለመሆኑም በተጨማሪ ሌላ ዋጋ ያስከፍለናል፡፡ አንድን ሕዝብ በዘርና በሃይማኖት እየነጣጠሉ አንዱን ጨቋኝ ሌላውን ተጨቋኝ እያደረጉ ማቅረብ ስህተት ነው፡፡ በመሠረቱና እንደእውነቱም ከሆነ ተጨቋኝ እንጂ ጨቋኝ ሕዝብ የለም፡፡ እርግጥ ነው – ከአንድ ሕዝብ አብራክ የሚገኙና ከዚያ ሕዝብ የተወሰነውን ክፍል አስተባብረው የራሳቸውን ህልምና ቅዠት በሌሎች ላይ የሚጭኑ አሰለጦች እንዳሉ ሩቅ ሳንሄድ እዚሁ ሀገራችን ውስጥ በከባድ ክፍያ ተምረናል – ይህን የፈጠጠ ጠባሳ ለመሻር ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅብንም መገንዘብ አለብን፡፡ ከዚያ ውጭ አማራ/ትግሬ የሚባል ጨቋኝ ኦሮሞ/ደቡብ የሚባል ተጨቋኝ ነበረ/አልነበረም በሚል ጉንጭን ማልፋት ተማርኩ ከሚል ቀርቶ ከደንቆሮም ሰው አይጠበቅም – ከዚያ የተሻለ ፍሬያማ ውጤት የሚያስገኝ ሥራ ባልጠፋበት ዘመን የዱሮ ታሪክ እያነሱ ወርቃማ ጊዜን ማባከንም ሞኝነት ነው፡፡ አማራው በኦሮሞው ውስጥ፣ ትግሬው በአማራውና በኦሮሞው ውስጥ ፣ ጉራጌው በሃዲያውና በሰሜኑ ውስጥ፣ ሰሜኑ በምዕራቡና በምሥራቁ ውስጥ የአንዱ ደም በሌላው ደም ውስጥ እየቀለጠ ሰምና ወርቅ ሆነው ይኖሩ እንደነበር ከዘነጋን የተሸረጠብን አንዳች ክፉ መንፈስ፣ ተዳብሎን ያለ ሸርና ተንኮል አለ ማለት ነውና ራሳችንን እንመርምር፡፡ የጋራ ችግርን በጋራ መፍትሔ ማስወገድ እየተቻለ ሽል ምንጠራ ውስጥ መግባት አስፈላጊም ተገቢም ወቅታዊም አይደለምና በተለይ ምሁራን የተባላችሁ ወገኖች ተጠንቀቁ፡፡ መማር ጥሩ ነው – ነገር ግን ዐወቅሁ ብላ መጽሓፋቸውን ያጠበችውን የቄሱን ሚስት መሆን አይገባም፡፡ ሕዝብ ‹ማን ይምራህ? እንዴት ይምራህ? ችግርህ ምንድን ነው?› ተብሎ ይጠየቃል እንጂ ያላሳከከውን በማከክ ያልነበረና የማይፈለግ ቁስል መፍጠር ነውር ነው፡፡ እኛ እንደሕዝብ አብረን ነው የኖርነውና እየኖርንም ያለነው፡፡
ከኔ ቤት ቀጥሎ ተስፋጋብር አለ፤ ከተስፋጋብር ቤት ቀጥሎ የሻመና ቶቆ ቤት አለ፤ ከርሱ ቤት ፊት ለፊት የደቻሳና የጫልቱ ቤት ይገኛል፤ ከነሱ ቤት በስተኋላ ግደይና ስንሻው ቡና እየተጠራሩ በሀዘኑም በደስታውም እየተገናኙ በሰላም ይኖራሉ፡፡ በአብረኸት ሠርግ ጣይቱና ዘርመጪት ልባቸው እስኪጠፋ ይጨፍራሉ፡፡ በሐጎስ ቤት የክርስትና ድግስ ይነጋልና አበቅየለሽ ታፋቸው እስኪገነጠል ጮቤ ይረግጣሉ፡፡ በፈይሣና በካሣሁን የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ፍትዊና ሃንቆሬ ስቅስቅ ብለው ያለቅሳሉ … እኛ እንዲህ ነበርን፤ ነንም፡፡ ባልና ሚስቶቹ አደፍርስና አምለሰት፣ ዘርዓይና ገመቺሣ፣ ዘርትሁንና ጎይቶም፣ ቦጋለና ትብለፅ ያፈሯቸው ልጆች እነሜሮን ሣሚ ዳኒ ቲቲ … የጋራ ሀገር ይፈልጋሉ፡፡ በዘርና በጎሣ የተሸነሸነች ሳትሆን እንደጥንት እንደጧቱ የዝውውር ነጻነት ያልተገደበባትና በዘር ምክንያት የመፈናቀል ጣጣ የሌለባትን ኢትዮጵያ ይፈልጋሉ፡፡ አሁን ለተጨማሪ ጊዜ ይህንን ሕዝብ እንዴት ነው ኦሮሚያ ጎጃሚያ ጎንደሪያ ወሎዊያ … እያልን እንደደሮ ሥጋ የምንበልተው? ግፍ አይደለም? ትንሽ ማፈር አለብን፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደፍልስጥኤምና ኮሶቮ አይደለም፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሦርያውያን አጥንት ድረስ የዘለቀ የእርስ በርስ ጥላቻ ላይ ገና አልደረሰም – ይህ እውን እንዲሆን የመሪዎች ጥረት ቢኖርም፡፡ የሕዝብ ለሕዝብ ጠብ የለብንም – የብልህ አመራር እጦት እንጂ፡፡ በፍቅርና በመቻቻል የሚኖር ሕዝብ በዘር እየለዬ በር ሳያንኳኳ በየቤቱ የሚገባን ሌባና ቀጣፊ አይቀበልም፡፡ እርግጥ ነው – ይህንን አብሮነት ለመበጣጠስ ብዙ ቢሞከርም እንደምንም ይዘነው እስካሁን ድረስ ዘልቀናል – አሁን ቆም ብለን ማሰብ ይገባናል፤ ምክንያቱም ነገሮች እንዳሉ የማይቀጥሉበት ሁኔታም አለና፤ ለዚህ ደግሞ ምሁራን ትልቅ ድርሻ አላቸው – ከየቀለሱት የግል ጠባብ ዓለም እየወጡ ሰፊ ሜዳ ላይ ይገናኙ፡፡ በቀናነት ይወያዩ፤ የሚበጀንንም ይወስኑና በጋራ ለጋራ ድል ያነሳሱን፡፡ ዘርና ሃይማኖት ደግሞ በትግሉ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ጫና ስለሚያሳድሩ እነዚህ ልዩነቶች በየትኛውም ሚዲያም ይሁን መድረክ ግዘፍ ነስተው መራገብ የለባቸውም፡፡ የሌሎች ሀገሮች መንግሥታት ሕዝባቸውን አንድ አድርገው ለመግዛት ቀና ደፋ ሲሉ በተገላቢጦሽ የኞች የምንላቸው መሠሪ ልጆቻችን እያለያዩ ሲቀጠቅጡን ኖረዋል፡፡ ሰላምና ፍቅር ጠላታቸው የሆኑ ያህል የሕዝብን ሰላምና መረጋጋት አይወዱም፡፡ የብልጽግናቸውና የሥልጣናቸው እርዝማኔ መሠረት የሕዝብ ስቃይና መከራ ነው ማለት ይቻላል፡፡ እነሱም እኛም ዕድለቢሶች ነን፡፡
ጁሃርን በሚመለከት አንድ ነገር ደግሜ ልናገር – ይህ የደስ ደስ ያለው መልከ ቀና ወጣት ‹እኔ መቼ እንዲህ አልኩ? መች ወጣኝ?…› ሊል ይችላል፡፡ እውነቱን ነው፡፡ እኔ ነኝ በጥራዝ ነጠቃዊ የሥነ ልቦና ‹ዕውቀቴ› ልጁን ያነበብኩት፡፡ የምንደሰትበት እንጂ የምናዝንበት አጋጣሚን ፈጣሪ ያርቅልን እስኪ፡፡
2. ልጅ ተክሌ ወይም ተክለ ሚካኤል ከካናዳ በቅርቡ የጻፈውንና ሌላም ጊዜ የሚጽፈውን ሁሌ እከታተላለሁ፡፡ የእውነትን ክኒን እንዳለች ለመዋጥ እጅግ መራር በመሆኗ ለብዙዎች አስቸጋሪ ናት፡፡ ውሸት ግን አንጎልን ወደተፈለገው አቅጣጫ እየጠመዘዘች ስለምታነሆልል እርሷን ለማዳበልና በቤተሰብነት ለመያዝ የማይጣደፍ የለም፡፡ በተለይ በአሁኑ ዘመን የሀሰት ጓደኞች ሥፍር ቁጥር የላቸውም፤ እውነት እየኮሰመነች ናት – መጨረሻዋ ያማረ ቢሆንም፡፡
ተክሌ ሃሳብን በነጻ የመግለጽ ባህል በዳበረበት የምዕራቡ ዓለም ከአሥር ዓመት በላይ የኖረና እውነትን ተናግሮ ከመሸበት ለማደር የቆረጠ ወጣት ይመስላል (ልደቱን እንዴት እንደወደደው ግን አልገባኝም – ወይም ስለመውደድ አለመውደዱም የተሳሳተ ግንዛቤ ይዤ ሊሆን ይችላል፡፡)፡፡ ለሀገራችን ፊት ለፊት የመሞከሻሸት ዞር ሲሉ ግን በሃሜት የመጎሸማመጥ ባህል ይህ የተክሌ ዓይነቱ አካሄድ ታላቅ መፍትሔ ሥራይ ነው፡፡ በቃ – ብዙ ነገሮች ይብቁን፡፡ አየናቸው – ሞከርናቸው – ተጎዳንባቸው እንጂ አልተጠቀምንባቸውም፡፡ ስለዚህ አካፋን አካፋ እንበል፡፡ እናም የእውነትን ዘገር ከያዝን ስለማንም ይሁን ስለምንም የሚሰማንን እንነጋገር፡፡ አነሳሳችን በቀናነት ይሁን እንጂ አለባብሰን መሄድን በመተው ስሜትን በማይጎዱ ቃላት አንገትን በማያስደፉ ውብ አገላለጾች ወዳጅ ዘመድን እንውቀስ፤ እንተች፤ በሳይቃጠል በቅጠል እንተራረም፡፡ እየተሸፋፈነ የሚሄድ ቁስል መጨረሻው ካንሰር ነው፡፡ ‹ጨዋ ሲጋባ የተፋታ ያህል ነው› የሚለውን ብሂል በደንብ እናጢነውና አፍረጥርጠን መነጋገርን እንልመድ፡፡ በጀርባ ከመተማማት በግልጽ ተወያይተን ቅሬታን ማስወገድን ብንለምድ ተጠቃሚዎች እንሆናለን፡፡
በለውጥ ኅልውናም እንመን፡፡ አንድ ሰው ትናንት ሌባ ከነበረ ዛሬ ጨዋ የማይሆንበት ምክንያት የለም፤ ትናንት ወያኔ ከነበረ ዛሬ ፀረ – ወያኔ የማይሆንበት ምክንያት የለም፤ ትናንት ውሸታም ከነበረ ዛሬ እውነት ተናጋሪ የማይሆንበት ምክንያት አይኖርም፤ ዋናው ለውጡ አሳማኝና ትክክለኛ ነው ወይ የሚለው ነው፤ ለውጡ በርግጥ የባሕርይ ለውጥን ያስከትላል ወይ ብለን መፈተሸ ነው ያለብን፤ ያን በጥልቀትና ከተለያዩ አቅጣጫዎች አንጻር መመርመር ይገባናል፡፡ ይህን የምናደርገው መንሸራተት እንዳይኖርና ሠርጎ ገብን ለመከላከል ነው፡፡ ለውጡ ለሥልት ነው ወይንስ ሃቀኛ ነው ብለን እንፈትሽ እንጂ አንድ ለውጥ ስናይ የለውጡ አስፈሪነት እንዳባተተን ወይም እንዳስበረገገን ያህል ድንገት ዱላ እየመዘዝን አናት አናትን መቀጥቀጥ ወይም ብዕር እያወጣን በቃላት እሩምታ ንጹሓንን ድባቅ መምታት ተገቢ አይደለም፡፡ ፀረ ለውጥ ሆነን ትግሎችን ወደኋላ ማስኬድ የነጻነት ጠላት መሆን ነው፡፡ በነገረኛ ብዕርና ፓልቶክም ሰዎችን ከመጠጋታቸው አናባርር፡፡ ብዙ ወገኖቻችን ራሳቸውን ከትግል ያራቁትና እያራቁ የሚገኙት የይሉኝታቢስ ወንድሞቻችንን ይሉኝታቢስና ሚዛን የማይደፋ የስድብና የዘለፋ ዛቻን እየፈሩ እንደሆነ ይነገራልና ከእንግዲህ እነዶኪሾትና እነአያ እንደልቡ ጥንቃቄ ቢያደርጉ ይመረጣል፡፡ ከሁሉም ከሁሉም በቅድመ ሁኔታ ያልታጠረ ቀናነትንና መደማመጥን እንላበስ፤ ከአሉታዊነት ይልቅ አወንታዊነት ጠቃሚ መሆኑን እንገንዘብ፡፡ ለማሰብ ጊዜ ይኑረን፡፡ አንድን ነገር ለማጣራት ጊዜና ትዕግሥት ይኑረን፡፡ በአንድ ቅኝት መጓዝ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናልና ዙሪያ ገባችንን እያየን ራሳችንን በተገቢው መንገድ እናዘምን፡፡ ደግሞም እርስ በርስ በከንቱ አንጠፋፋ፡፡ ለሚያልፍ ዘመን የማያልፍ ትዝብት አናስቀምጥ – እንተማመን ፡- ሕዝቡም ሆነ ታሪክ ሁሉንም ለይቶ ያውቃል፡፡ ማን ለምን ምን እንደሚያደርግ በዚህ ዘመን ለማንም ድብቅ አይደለም፡፡ የ‹ዝምብ ልጃገረድ› በምትታወቅበት ሀገር ውስጥ ዘረኝነት ወይም ይህን መሰል ሌላ ከፋፋይ ሥልት በማታገያነት ለምን ጥቅም ላይ እንደሚውል የማያውቅ ይኖራል ብሎ መገመት ጅልነት ይመስለኛል፡፡ በተጨማሪም ‹እንግዲህ ጀመረው!› ‹አሄሄ… ያ ሰውዬ ያን የነገር ጭቃውን በነእንትና ላይ ሊለጥፍ ተነሣ…› ከመባል ይልቅ በገምቢ አስተያየት ሰጪነት በሰዎች መሃል መወሳት ትልቅ መታደል መሆኑን እንረዳ፡፡…
ስህተትን የማይሠራ የሞተ ብቻ እንደሆነ አምነን ስህተት ከሠራን ያን ስህተት ነቅሶ ለማውጣትና የእርምት እርምጃ ለመውሰድ ማመንታት የለብንም፡፡ ከነባር ሥርዓቶች የወረስናቸውን ፀረ ዴሞክራሲያዊ የትዕቢትና የማንአለብኝነት ባሕርያትን አክ እንትፍ እንበላቸው፡፡ ጎዱን፡፡ አብረውን የሚዘልቁ ከሆነም ገና ብዙ ይጎዱናል፡፡ ትዕቢት ሣጥናኤልን ከክብሩ አውርዶታል፡፡ ትዕቢት ተቆጥረው የማያልቁ ምድራውያን ታላላቅ ሰዎችን ከክብር ሥፍራቸው አዋርዷል፡፡ ዝና ይጠፋል፤ ሀብትም ይበናል፤ ማናቸውም ነገር እንዳለ እንደማይቆይ ተረድተን ትህትናንና መከባበርን መላበስ፣ ትዕቢትን መጠየፍ ይኖርብናል፡፡
ዛሬ ሰዎች የወደዱን ለምንድነው ብለንም እንጠይቅ፡፡ የወደዱን ምክንያት አላቸው፤ ያ ምክንያታቸው ግን ሊጠሉን ሲጀምሩ እየደበዘዘ ይሄድና ለመወደዳችን ያወጣነው ወጪና የተነሳንበት ወረት እንደጤዛ እንደሚረግፍ ዕንወቅ፡፡ ዝናን ማትረፍ ከባድም ቀላልም ነው፡፡ ማቆየቱ ግን ሸክም ነው፡፡ ምክንያቱም አንዳንዴ ክፉ መንፈስ እየገባብን የትዕቢትና የትምክህት ልምሻዎች ይኮደኩዱንና ልባችን በውዳሤ ከንቱ ይማስናል፡፡ ያም ልክ እንደጥንቱ የአፈ ታሪክ ንጉሥ ዕርቃናችንን መሆናችን እስከሚረሳን ድረስ ራሳችን ለራሳችን በምንፈጥረው ዓለም ውስጥ እንዳክራለን – ለተወሰነ ጊዜም በእኛው የዕውር ድንበር ዓለም ውስጥ ሌሎችንም ልናዳክር እንችላለን፡፡ ያኔም እንደገና በተምኔት ከፍ ከፍ እንልና መነሻችንን እንረሳለን – ‹ታሞ የተነሣ ፈጣሪን ረሳ› እንዲሉ ዓይነት፡፡ የምድራችን ትልቁ ችግር እንግዲህ ይህ እዚህ ላይ እያየነው ያለነው ጉዳይ ነው፡፡ ማንንም አላሰብኩም፤ እናንተም ማንንም ሳታስቡ አጠቃላይ እውነታውን ብቻ ተረዱልኝ፡፡
የኢትዮጵያውያን ችግሮች መባቀያ ደግሞ ይሄው ብቻ እስኪመስል ድረስ ሥር ሰድዷል፡፡ የዚህ ሁሉ ወፈ ሰማይ የፖለቲካ ድርጅት ምሥረታ ምሥጢሩ ብዙ ሊሆን ይችላል፡፡ ሀገርን ነጻ ማውጣት ሱቅ በደረቴ ንግድ የመጀመር ያህል ቀላል ይመስል ‹እኔ በእገሌ ድርጅት ሥር ገብቼ የነእገሌ ታዛዥና ተላላኪ ልሆን? እነሱ ደግሞ ብለው ብለው የኔ አለቃ ሊሆኑ? አላውቀውምና ነው…› ከሚል ትዕቢት በመነሣት አዳሜ በውጪም በውስጥም የየራሱን ድርጅት ያቋቁማል – ይህም በትንሹ ከንቱነት ነው – እልፍ ሲልም ድንቁርና ነው፤ ይህ ዓይነቱ ጠባብ ጅማሮ ስንዝር ሳይሄድ ይፈርሳል፡፡ ጨዋታው ፈረሰ ዳቦው ተገመሰ ዓይነት የልጆች ዕቃ ዕቃ ጨዋታ፡፡ … ስለሆነም በማንኛውም ዘርፍ ለሀገር እንታገላለን የምንል ወገኖች ትልቁ ጠላታችን ይሄ ትዕቢት የሚሉት ልብ አሳባጭ የክፉ መንፈስ ውላጅ ነውና መድሓኒቱን ገዝተን ወይም ጠበል ቢጤ አስመጥተን አጠገባችን እናስቀምጥ፡፡ ትዕቢት ራሳችን ላይ መውጣቱ ሲሰማን ወይም ሰዎች ሲጠቁሙን ቶሎ ብለን እንዋጥና ወይም እንጠመቅና እንደወያኔ ብዙ ጥፋት ሳናደርስ እንፈወስ፡፡ አለበለዚያ ይህች ሀገር ለረጂም ጊዜ ትሰቃያለች(ያነበብኩትን ወይም የሰማሁትን የትንሣኤ ዘመን ወሻክቼ ባልተጨበጠ ተስፋ የሰውን ሆድ መቀብተት አልፈለግም እንጂ ሁሉም የክፋት ዘመን እንደሚያበቃ ከነምልክቱ ልጠቁም በወደድኩ ነበር፡፡) ለማንኛውም ትዕቢትና ውድቀት ጓደኛሞች መሆናቸውን እንረዳና መፍትሔ እንፈልግ፡፡
3. በሀገር ቤት የ‹ፀረ ሙስናው ትግል› ተጧጡፏል፡፡ እሰዬው ፣ ይጧጧፍ፡፡ በዚህ ሽኩቻ ውስጥ የተረገዘ ሀገርን የሚጠቅም ነገር ይኖረው ይሆናል፡፡ አለበለዚያማ … ቆይማ ቀጣዩዋን ክስ ባጭሩ እንቃኝ፡፡
ኢየሱስን ጠላቶቹ ሊፈትኑት ፈለጉና አንዲት ሴት ይዘው ወደርሱ በመቅረብ ‹ ኢየሱስ ሆይ፤ ይህቺን ሴት ስታመነዝር አገኘናት፤ በሙሤ ሕግ መሠረት በድንጋይ ተወግራ እንድትሞት ሕጉ ያዝዛል፡፡ አንተስ ምን ትላለህ?› ይሉታል፡፡ ኢየሱስም ‹ከእናንተ ምንም ዓይነት ኃጢኣት ያልሠራ የመጀመሪያውን ድንጋይ ይወርውርባት› ይልና አንገቱን አዘቅዝቆ አፈሩ ላይ ይጫጭር ገባ (ምን እንደጫጫረ እስካሁን አልታወቀም ይባላል፡፡) ቀጥ ሲል ከተከሳሽዋ ሴት በስተቀር ሁሉም አንድ ባንድ ሄደው ማንም የለም፡፡ ‹አንቺ ሴት ከሳሾችሽ ወዴት አሉ?› ብሎ ይጠይቃታል፡፡ ጥለዋት እንደሄዱም ትገልጽለታለች፡፡ … ‹በይ ከአሁን በኋላ ኃጢኣትን አትሥሪ› ብሎም በነጻ ያሰናብታታል፡፡ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከፍርድ ቤት ወደቤት ሄደች እነእስክንድርን የሚያስባቸው ከሰውም ሆነ ከአምላክ ግዛት ጠፋ እንጂ፡፡ በሞራል ትምህርቶች ይህ የክርስቶስ ምሳሌ የሚስተካከለው ያልተገኘ ትልቁ ምሰሶ ነው፡፡ ኃጢኣትን የማይሠራ ማን አለ? ማንም፡፡ ትልቁ መልካም ተስፋ ግና ከኃጢኣት ለመመለስ ያለን የማይገፈፍ መብት ነው፡፡ ይህን መብት ማን ይጠቀምበት? የባከነ መብት! ብዙዎች የናቁት ዘመን የጣለው መብት?
አለበለዚያማ ብዬ ወዳቋረጥኩት ሃሳብ ልመለስ፡፡ አለበለዚያማ ከዝንጀሮ ቆንጆ ተመርጦ አንዱዋ ባሪያ ሌላዋ ሞናሊዛ ሊሆኑ ይቻላቸው ነበርን? እናም የምናውቀውን ሀገራዊ እውነት ስንፈትሸው በወያኔ ሥርዓት ውስጥ ካለሙስና እስትንፋሱ የምትቀጥል አንድም ባለሥልጣን የለም – በየትኛውም መንገድ ይሁን ሙስና ውስጥ መዘፈቁ አይቀርም – በቀጥታም ይሁን በተዛዋሪ፡፡ ሙስና ደግሞ ዓይነቱና መልኩ ብዙ ነው፡፡ ሙስና እንኳንስ በሌሎች መሥሪያ ቤቶች በትምህርት ተቋማትም ሳይቀር ተንሰራፍቶ የማለፊያ ነጥብን ለማሟላት በዓይነት ከሚቀርብ የንብረትና የወሲብ ጉቦ አንስቶ እስከገንዘብ ድረስ ለመምህራንና ለትምህርት ባለሙያዎች እንደሚሰጥ በስፋት ይነገራል – ከዚህ በላይ የሀገር ሞት የለም፡፡ ሙስና እንኳንስ በዓለማዊ የሥልጣን ቦታዎች በሃይማኖት ተቋማት ሳይቀር የወረርሽኝ ያህል ተስፋፍቶ አነስተኛ ገቢ ካለው ደብር ከፍተኛ ገቢ ወዳለው ደብር ለመዛወር፣ እልቅና ለማግኘት፣ በክህነት አገልግሎት ለመቀጠርና ለአነስተኛ የዝውውር ጥያቄዎች በሺዎች የሚገመት ብር እንደሚከፈል እንሰማለን – ከዚህ በላይ የሞራል ዝቅጠት የለም፡፡ ሙስና በቤተ መንግሥት ይቅርና በገዳማትና በአብያተ ክርስቲያን ሳይቀር የዘመኑ ፋሽን በሆነበት ሁኔታ ድንገት ተነስቶ እገሌንና እገሊትን ማሠር ከጎኑ ሌላ የቦካ ቂም መኖሩን ከማመልከት ባሻገር እንዲያም ሲል በቧልታይ ድንቃይ የልጆች ኮሜዲነት ከማሣቅ በተጓዳኝ ሌላ የሚሰጠው ትርጉምም ሆነ ሀገራዊ ፋይዳ የለውም፡፡ እንትን ላይ ተቀምጦ እንትን ገማኝ አይባልም፡፡ ያለሙስና የሚንቀሳቀስ የመንግሥት ባለሥልጣን አለ ማለት መኖር ያቆመ ባህታዊ ሕዝብንና ሀገርን በቅንነት ለማገልገል ቆሎና ደረቅ ዳቦ እየቀመሰ በመንግሥት ሥራ ላይ ተሰማርቷል ማለት ነው፡፡ የፀረ ሙስና ኮሚሽን በተቋቋመ ማግሥት ቢሮውን በቁሣቁሶች ለማሟላት ገበያ የወጣው የግዢ ሠራተኛ ራሱ በሙስና እንደተያዘ በወቅቱ ሰምተናል፡፡ ሙስና የጊዜያችን የኑሮ ማጣፈጫ ቅመም ነው፡፡ ማንም ያለርሱ አይኖርም፡፡ እንኳን ኢትዮጵያ ውስጥ አሜሪካና አውሮፓም ውስጥ ሙስናን ዝምቡን እሽ የሚለው የለም፤ ተንቀባርሮ ይኖራል፡፡ ታየኝ እኮ ‹የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናቱን በሙስና ወንጀል ጠርጥሮ አሠረ!› ሲባልና ሲነገር – ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ፡፡ እንዲያው ጥቂት አያፍሩም ጎበዝ?! የሙስና እናት ባለችበት ሀገር እንዲህ መደረጉ ሕዝብን መናቅ ይመስለኛል፡፡ 80 ሚሊዮኑን ሕዝብ እንደምን ቢቆጥሩት ይሆን? ወይ ጊዜ!
4. የኑሮ ውድነቱ ሕዝቡን እየጨረሰው ነው፡፡ የዕቃዎች ዋጋ በየቀኑ እየጨመረ ብዙ ሰው በሚለብሰው ሳይሆን ቀምሶት በሚያድረው ወይ በሚውለው መጨነቅ ከያዘ ቆዬን፡፡ በተቃራኒው ወደወያኔው ጉያ የተሸጎጡ በርካታ ዜጎች በተለይ በአሥራዎቹና በሃያዎቹ የሚገኙ ገና በቅጡ ያልባለቁ ወጣቶች ገንዘቡን እንዴት እንደሚያገኙት በማይታወቅ ሁኔታ ሌት ከቀን ሲምነሸነሹ ይታያሉ፡፡ ዊስኪና ድራፍት ቤቶች፣ ሥጋ ቤቶችና ሌሎች ንግድ ቤቶች ገዢ አጥተው አይከስሩም፡፡ የወያኔዎቹ ልጆች ብዙዎቹ ትምህርት ስለማይገባቸው አቋርጠው ሌት ከቀን ጭፈራ ላይ ናቸው፤ ከወያኔዎቹ በርካታዎቹ ትምህርት ዋጋ አለው ብለው ራሳቸው ስለማያምኑ በልጆቻቸው ስም በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በባንክ እያስቀመጡላቸው ለአካለ መጠን እስኪደርሱላቸው በዱርይነት ተሠማርተው እንዲኖሩ ፈቃደኞች የሆኑ ይመስላሉ – የ14 እና 15 ዓመት ዕድሜ የወያኔ ኩታራ ልዩ ኢግዝኪዩቲቭ መኪና ይዞ ሃሽሽና ሲጋራ እየማገ በጭፈራ ቤት ሲደንስ እንደሚያድር እሰማለሁ – በዚህ ዙሪያ ራሴ የማውቃቸው ብዙ ጉዳዮችም አሉኝ፡፡ (ውድ ኢየሩሳሌም አርአያ፡- ስለነበረከትና ሰዓረ ልጆች፣ ስለአምባሳደር ጎይቶምና ስለሌሎቹም ዋልጌ ልጆች እየተከታተልክ ብትጽፍልን ልጠቁምህ፡፡)
እርግጥ ነው ብዙዎቹ ወያኔዎች ትዳራቸው የፈረሰና በሞራላዊ ሕይወታቸው ከላይ እስከታች የተበሳበሱ በመሆናቸው ለልጅ አስተዳደግም እንደዚሁ ተገቢውን ቦታ የሚሰጡ አይደሉም፡፡ በዚያም ምክንያት ይመስላል የሕዝብ እርግማን ተጨምሮበት ልጅ እንዳይወጣላቸውና እነሱም ሽንታቸውም ባክነው እየቀሩ የሚገኙት፡፡ ሚስቱን ያልቀየረ ነባር ታጋይ ማግኘት ይከብዳል ይባላል፡፡ አሮጊቶቹን እየጣሉ ሕጻናትን ማግባትና በየቦታው ቅምጥ ማስቀመጥ በነሱ ዘንድ የተለመደ ነው፡፡ ለልጆቻው ገንዘብን ለማውረስ ባንኮችን በብር ከማጨናነቅ ውጪ ለአብራካቻው ክፋዮች የሚሆን ፍቅር የላቸውም ይባላል፡፡ እነሱም ልጆቻቸውም ያልታደሉ፡፡
በአሁኑ ወቅት ልጆቻቸው የሚይዙት መኪና ሌላ ነው – የሚመነዝሩት ረብጣ ረብጣውን ነው፡፡ ሴት ሲያሳድዱ ደግሞ አባቶቻቸውን ያስንቃሉ፡፡ እንደሸሚዝ ነው የሚለዋውጡ ይባልላቸዋል – ዱሮውንስ ያልዘሩት መች ይበቅላል? የወያኔ ቡችሎችና ተለጣፊዎች የሚያሽቃንጡባቸው ተሸከርካሪዎችም ልዩና ውድ ናቸው – የባሕርይ ምስስላቸውም እንከን አይወጣለትም፡፡ ዋጋቸው በብዙ መቶ ሺዎች ምናልባትም በሚሊዮኖች የኢትዮጵያ ብር የሚገመቱ መኪናዎች ሲርመሰመሱ ለማየት ከአውሮፓና አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ሳያስፈልግ አይቀርም፤ ለአንድ ሺህ ሰው ሦስት መኪናዎች ብቻ በሚሰላባት ሀገር ውስጥ እነዚሁ ጥቂት መኪኖች ባብዛኛው የተያዙት በወያኔ ጭፍራዎችና በመንግሥታዊና ግላዊ ድርጅቶች ነው፡፡ ሀገራችን የለየላት የዕንቆቅልሽ ምድር ሆናለች፡፡ አንዱ የሚቀምሰው አጥቶ በጠኔ ሲያጣጥር ታያለህ – አንዱ ጥጋት ላይ፡፡ ሌላው ሐመርን በመሳሰሉ ዘመናዊ መኪናዎች እየተንፈላሰሰ በሺዎች በሚቆጠር ብርና ዶላር የሌሊት ክበባትን ሲያደምቅ ታያለህ – በሌላው ጥጋት፡፡ በአንድ እጅ ጣቶች የሚቆጠሩ የጥቂት ሺህ ብር ደመወዝተኛ ባለሥልጣናት ትላልቅ ሆቴሎች ውስጥ ገብተው በቁርጥና በዊስኪ ሲዝናኑና ለአንድ ጊዜ የመገባበዣ ክፍያ የሦስትና የአራት ወር ደሞዛቸውን ድምር ሒሳብ ከፍለው ሲወጡ የምታየው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ በዚህ አግራሞትህ ላይ ሌላ አግራሞትን እንድትደርብበት ያህል – እነዚሁ ባለሥልጣናት በማታው የቴሌቪዥን ዜና ላይ በሃሳብ ያልተስማሙዋቸውን ሌሎች ባለሥልጣናትን በሙስና ማሰራቸውን የምትሰማውና በለበጣ የምትስቀው እዚህችው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ ለጉድ የፈጠራት የደም ምድር አትልም? ቃየሎች በአቤሎች ላይ የሰለጠኑባት አስገራሚ ኢትዮጵያ!
የዱሮና ዘንድሮን ልዩነት በቃላት እንኳን ለመግለጽ እየከበደን ነው፡፡ የዐርባ ብር ደሞዝተኛ ዱሮ ቤት መሥራት ይችል ነበር፡፡ የአራት ሺህ ብር ደሞዝተኛ ዛሬ ቤት ተከራይቶ እንኳ መኖር ይከብደዋል፡፡ ዛሬ መቶ ሊትር ቤንዚን በሚቀዳበት ገንዘብ ዱሮ ሁለትና ሦስት አሮጌ መኪና ይገዛበት ነበር፡፡ የዛሬ የአንድ ኩንታል ጤፍ ዋጋ ዱሮ ወደ 60 ኩንታል ገደማ ይገዛበት ነበር፡፡ ዘንድሮ ለሐኪም ቤት ካርድ ማውጫ ብቻ የምትከፍለው ገንዘብ ዱሮ መላ ቤተሰብህን ሊያሳክም የሚችል ነበር፡፡ ዱሮ በስሙኒ የምትገዛው 12 ዕንቁላሎች የሚመረቁልህ ሙክት ዶሮ ዛሬ ከነዕንቁላቹ (200 ሲደመር 36) 236 ብር ደርሷል – ነገ ደግሞ ከዚህ ሊያጥፍም ይችላል፡፡ ዘንድሮ ቤትህን ለማደስ የምታወጣው አሥር ሺህ ብር ዱሮ አሥር አነስተኛ ቪላዎችን ሊያሠራህ ይችል ነበር፡፡ በሞራልም፣ በሃማኖትም፣ በሥነ ምግባርም… በሁሉም ዘርፍ ብትቃኝ የደረስንበት የኪሣራ መጠን በምንም ዓይነት ምድራዊ መሣሪያ ሊለካ የማይችልና ለማንሰራራትም ከተዓምር በታች በመፍትሔነት የማይታሰብበት አሳሳቢ ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡ በቃኝ፡፡
የርዕሶምን ያን ሕይወት አለምላሚ ዘፈን እባካችሁን ላኩልኝ፡፡
Yinegale3@gmail.com
Part 1

Part 2

በሚኒሶታ ለቤተክርቲያን ሰላምና አንድነት ከቆሙ ምእመናን የተላለፈ ጥሪ

$
0
0

በስመ አብ ወወለወድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ፤ አሜን!

ግንቦት ፳፻፭ ዓ.ም

ባለፉት ፳ ዓመታት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የደረሱ ጥፋቶችና በደሎች ባጭሩ እና የምንገኝባትን ቤተክርሰቲያን አንድነትና ሰላም አጽንተን ስለመጠበቅ።
ለቤተክርቲያን ሰላምና አንድነት ከቆሙ ምእመናን
ሚኔሶታ

deb የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ቀኖና በመጣስ በሥርዓትና በምልዐት የተሾሙትን ፓትርያርክ ከመንበራቸው በማውረድና በማባረር
 ወያኔ የራሱን ጉዳይ አስፈጻሚ ጳጳስ በመንበሩ በመሾሙ ምክንያት የቤተክርስቲያኗ አባቶችና ምእመናን በታሪክ ባልታየ ሁኔታ እንዲከፋፈሉ ተደርጓል
 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያ ዳር ድንበር መከበር ለታሪክና ለቅርስ መጠበቅ ያበረከተችው አስዋጽኦ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነበር። ነበር መባሉ ግን እጅግ አሳዛኙ በዘመናችን በምሬት የምንቀበለው እውነታ ሆኗል።
 የወያኔ ባለስልጣናት በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ የጽርፈት ነገር ሲያስተጋቡ ቤተክርስቲያኗን ይመሩና መንጋዋን ይጠብቁ ዘንድ የተሾሙ አባቶች ድርጊቱን ሳይገስጹና ሳያወግዙ በዝምታ አልፈውታል።
 አቶ ተፈራ ዋልዋ፣ አቶ ስብሐት ነጋ፣ አቶ አባይ ጸሐዬና ሌሎችም ባለሥልጣናት በግልጽ የቤተክርስትያኗን ህልውና ሲያንቋሽሹና ሲያዋርዱ ተሰምተዋል። ለምሳሌም ያህል ኦርቶዶክስ የነፍጠኛ ዋሻ ነች፣ መነኮሳትን የተለየ የፓለቲካ አጀንዳ ያላቸው ናቸው፤መለኪያው ኦሮቶዶክስና አማራ የነበረውን ሥርዓት ሰብረነዋል ወዘተ የሚሉ የድፍረትና የማዋረድ ቃላት ሲነገሩ መስማቱ እንግዳ አይደለም።
 በአባቶች መካከል የተፈጠረውን መለያየትና መወጋገዝ በመፍታት ሰላምና እርቅን ለማምጣት ግድ ያላቸው ውድ የቤተክርስቲያን ልጆች ጥረት በከንቱ ሲመክን የአባቶች ዝምታ እና የዚሁ ሰላምንና አንድነትን የማፍረስ የአመጸኝነት ተግባር አካል መሆን እጅጉን አሳፋሪና አስነዋሪ ክርስቲያናዊ ያልሆነ ተግባር ነው። ይህንን የብዙዎችን ተስፋ ያጨለመ ድርጊት አስመልክቶ በሁለቱም ወገኖች ይሁንታን ካገኘ በኋላ የማደራደር/የማስታረቅ/ ወንጌላዊ ተግባር ሲያከናውን የነበረው የኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰላምና አንድነት ጉባዔ ለዓመታት የተለፋበት የሰላምና እርቅ ሂደት አስመልከቶ የካቲት 12/2005 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የእርቅና የሰለም ሂደቱ እንዳይሳካ ያደረጉትን ዋና ዋና ምክንያቶችን ሲገልጽ፦
 1. ‘‘ በኢትዮጵያ ያሉ አንዳንድ አባቶች ከቤተክርስቲያን ሰላምና አንድነት ይልቅ ለሢመተ ፓትርያርክ ቅድሚያ በመስጠታቸውና የላኳቸውን ልዑካን ሪፖርት ሳይሰሙ አስመራጭ ኮሚቴ መሰየማቸው፤
 2. የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰላምና አንድነት ጉባዔ አባላት በልዑካኑ የስምምነት ውሳኔ መሰረት ወደ አዲስ አበባ ቅዱስ ሲኖዶስ ተሰይመው ከሔዱ በኋላ የተላኩበትን ዓቢይ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ለቅዱስ ሲኖዶስ እንዳያቀርቡ እስካሁን ድረስ እንኳን ማንነታቸው ባልታወቁና ባልተረጋገጠ ግለሰቦች ተላለፈ በተባለ ሕገ ወጥ ትእዛዝ ወደ መንበረ ፓትርያርኩ ቅጽረ ግቢ እንዳይገቡ በጥበቃ ሰራተኞች መከልከላቸው፤
 3. ከዚህም በላይ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ አንደኛውን ልዑክ ካለአንዳች ምክንያት በግዳጅ ከሀገር እንዲወጡ መደረጉ ሁለተኛውንም ልዑክ በማጉላላትና ወደ ቤተክህነት ግቢ እንዳይገቡ በማገድ በቀጠሮ እንኳን ለሚጠብቃቸው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ከላይ የዘረዘርናቸውን የመፍትሔ ሃሳቦች የያዘውን የሰላምና አንድነት ጉባዔ ደብዳቤ አቅርበው እንዳያስረዱና ቅዱስ ሲኖዶስ በጉዳዩ እንዳይመክርበት መደረጉ
 4. ገና ከጅምሩ ጀምሩ እርቀ ሰላሙን የማይፈልጉና በግልጽ ይቃወሙ የነበሩ አንዳንድ አባቶች ፈጽሞ የተዛባና ከእውነት የራቀ መሠረተቢስ መረጃ ለመንግስት ባለሥልጣናትም ሆነ ለኅብረተሰቡ መስጠታቸው
 5. በሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያናችን ፍጹም ሰላምና አንድነት እንዲሰፍን ለማድረግ ላለፉት ሦስት አመታት ሲካሔድ የቆየው የእርቀ ሰላም ጥረት ከዳር እንዳይደርስ በሚፈልጉ ጥቂት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አማካይነት ቅዱስ ሲኖዶስ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆኖ የተጀመረው የእርቀ ሰላም ውይይት ለውጤት እንዲበቃ ባለማድረጉ ምክንያት መንግስት በቅዱስ ሲኖዶስ ሉዓላዊ ሥልጣን ላይ ግልጽ ተጽእኖና ጫና በማድረጉ
 6. በመጨረሻም ጥር 8/2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ስድስተኛ ፓትርያርክ ለመሾም በችኮላ መወሰኑ የሰላሙን በር ከመዝጋቱም በላይ የእርቀ ሰላሙን ውጤት በጸሎትና በታላቅ ተስፋ ሲጠባበቅ ለቆየው መላው ሕዝበ ክርስቲያን ታላቅ መርዶ ሆኗል።’’ በማለት በዝርዝር አስረድቷል። ከዚህም ሌላ በቅርቡ በቤተክርሰተያኗ ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ብንመለከት
 የታላቁ ሰማዕት የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ከስፍራው ሲነሳ የአባቶች ዝምታ ወይንም የድርጊቱ ተባባሪ መሆን፣
 የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ተቋም በአንድም በሌላም ምክንያት ሲዘጋ የአባቶች ዝምታ ወይም የድርጊቱ ተባባሪ መሆን
 ከሁሉም በላይ ደግሞ አሁን በቅርቡ ለዘመናት በኢትዮጵያ ሕገ-መንግስትና በፍታብሔር ሕግ ውስጥ እውቅናና ሕጋዊ ሰውነት የተሰጣትን ቤተክርስቲያን ሕጋዊ መብቷን ለመግፈፍና ለማፍረስ እንደ ማንኛውም በኃይማኖት ስም እንደተራጁ ድርጅቶች እንደ አዲስ ተመዝግባ ፈቃድ በማውጣትና በማሳደስ ብቻ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባት የሚገልጽ ረቂቅ አዋጅ ወጥቶ ቀርቧል። ይህም ቤተክርስቲያንን የማዳከሙና የማፍረሱ ታላቁ ሤራ አንዱና ትልቁ እቅድ መሆኑ አያጠራጥርም። ይህ ሁሉ ሲደረግም የቤተክርስቲያናችን አባቶች ዝምታ እጁጉን የሚያስደምም ሆኗል።
 ወያኔ በያዘው የጸረ-አማራነትና ጸረ-ኦርቶዶክስ ፖሊሲ በአርሲ፣በጅማ፣በደቡብ ህዝቦች፣ በጎንደር፣በደሴ፣ በአሰቦት፣በዝቋላ፣በ ዋልድባ ገዳማት፣ቤተክርስቲያናት፣ካህናትና ምእመናን ላይ ሞት፣መቃጠል፣ዝርፊያና ውድመት ሲደርስ የቤተክርስቲያኗን መብትና የምእመናንን ደህንነት ለመጠበቅ የተሾሙ አባቶች በማወቅም ሆነ በቸልተኝነት ዝም ብለው በማየት የዚህ ሁሉ በደል ፈጻሚዎችና አስፈጻሚዎች ደጋፊ እና ተባባሪ ሆነው መገኘታቸው በጣም አሳዛኝና ሐዋርያዊ ተልዕኮን መዘንጋት ነው።
 የዋልድባ ገዳም ወደስኳር ፋብሪካት እየተቀየረ ነው። የአባቶች ዝምታ ወይም በድርጊቱ ተባባሪ መሆን ፣
 ዜጎች በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባላት ያለምንም ወንወጀል ከቤት ንብረታቸው ሲፈናቀሉ፣ለስደትና ለእንግልት ሲዳረጉ የሚያጽናናቸው አባት አጥተው ምስካዬ ኅዙናን የተባለች ቤተክርስቲያንን መጠጊያና መሸሻ ለማድረግ ሲሞክሩ ከቤተክርስቲያን ቅጽር እንዲባረሩ መደረጉ በዘመናችን ያሉ ‘ብጹአን አባቶች’ ታረክ መሆኑ እጅግ ከማሳዘን አልፎ በርግጥም መጽሐፍት እንደሚነግሩን የተመረጡን እስከሚያስት ድረስ ተዐምራትን ያደርጋል የተባለለት የመጨረሻው ዘመን መንፈስ በግልጥ እየሰራ ያለበትን ዘመን መሆኑን የሚያሳስብ ነው።ይህም ለእውነትና ለኃይማኖት፣ለቤተክርስቲያንና ለመንጎቿ የሚገደው አባት ፈጽሞ የጠፋበት ጊዜ ላይ መድረሳችንን የሚያስዳ ነው።
 እንግዲህ በዚህ ሁኔታ ነው በቤተክርስቲያን ላይ ጥቃትና ደባ ከሚፈጽምና ከሚያስፈጽም መንግስት ተብዬ ጎን እንቁም፤ እርሱን ከሚደግፉና የጉዳዩ አስፈጻሚ ከሆኑ አባቶች ጋር አብረን እንሰለፍ እየተባለ የሚሰበከውና የሚነገረው???!!!

በውጪ አገራት ያሉ ቤተክርስቲያናትን አስተዳደርና አመሰራረት በተመለከተ

 በውጪ አገራት ያሉ ቤተክርስቲያናት የሚቋቋሙበት ሕግና ሥርዐት በሚገኙበት አገር የቤተክርስቲያናትና ሌሎች ከታክስ ነጻ ለመሆን የሚመሰረቱበት ሕግና ደንብን ተከትሎ መሆኑን ባለመረዳት በቤተክርስቲያናት መካከል ልዩነት ያለ ይመስል እኛ ከቤተክርስቲያን ተገልለናል እነዚያ በዚህኛው እነዚያ በዛኛው ሲኖዶስ ሥር ናቸው ሲባል ይሰማል።
 ነገር ግን ሁሉም ቤተክርስቲያናት የሚተዳደሩት ባሉበት አገር ህግና ተቀባይነት ባለው መተዳደሪያ ደንብ ወይንም ባይ ሎው መሰረት በቦርድ አመራር ሰጪነት ከቀረጥ ነጻ የሚያደርጋቸውን ሕግ የሚያከብሩ ሲሆኑ ነው። ቤተክርስቲያናቱም ያለልዩነት በቦርድ ኦፍ ትረስቲስ ነጻ አገልጋዮች ብቻ የሚመሩና በየአመቱ ከቀረጥ ነጻ የሚያደርጋቸውን ቅጽ እየሞሉ የእድሳት ፈቃድ እያወጡ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው። አሁን ያለውን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ቃለ-አዋዲ የውጪ አገር መንግስታትና ሕጎቻቸው የማያውቁትና በውጪ አገር ሊሰራበት የማይችል ነው። ስለሆነም ወደ እናት ቤተክርስቲያን ይሁን በስደት ባለው ሲኖዶስ ሥር እንሁን የሚለው አካሔድ ከምኞት የማያልፍ ነባራዊ ሁኔታን ያለመረዳት ነው። ምክንያቱም ሁሉም በአንድ አይነት ሕግ ብቻ የሚመሰረቱና የሚተዳደሩ በመሆናቸው።
ስለሆነም ልዩነት ያለው ወገንተኝነትን ከመግለጽ አኳያ ብቻ ነው። ይህም ከመንበራቸው የተባረሩትን ወይም በወያኔ የተሾሙትን ፓትሪያርኮች ስም በመጥራትና ባለመጥራት የሚገለጽ ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ ጉዳዩን በመረጃ በተደገፈ ማጣራት የጉዳዩን ወይም የልዩነቱን መንስዔ በትክክል አውቆ ለመወሰን አስቸጋሪ ሁኔታ በመፈጠሩ ምክንያት ሁለቱ ወገኞች በሰላምና በእርቅ ሂደት ወደ አንድነት እስካልመጡ ድረስ እንደ ክርስቲያን የችግሩን ውል በሚገባ ሳያውቁ ለዚህኛው ወይንም ለዛኛው ወገን ወግኖ መገኘት ኢክርስቲያናዊ በመሆኑ የሁለቱንም ወገኖች/ፓትርያርኮች ስም ከመጥራት በመቆጠብ ወደ ሰላምና አንድነት የሚመጡበትን መንገድ መደገፉ ትክከለኛ አማራጭ መሆኑ የታመነ ነው።
 በየደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሁሉም ወገኖች የቤተክርስቲያኑን አቋም እስካከበሩ ድረስ መጥተው መባረክ፣ ማስተማርና መቀደስ አልተከለከሉም።
 በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ ሲኖዶስ ስር ያሉም ሆኑ በውጪው ያሉ እንዲሁም ከሁለቱም ወገን ያልሁ አባቶች በተለያየ ጊዜ መጥተው ቀድሰዋል፣ አስተምረዋል ፣ቡራኬ ሰጥተዋል።
 ከላይ እንደተጠቀሰው መለያየቱ ያሳሰባቸው ውድ የቤተክርስቲያኗ ልጆች በከፍተኛ ጥረት የሰላምና እርቅ ኮሚቴ አቋቁመው ለሦስት ዙር ያህል ጥረት አድርገው ውጤቱም በግልጽ በዚሁ ኮሚቴ እንደተገለጸው ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ አንዳንድ ለስልጣን በቋመጡ አባቶችና አይዟችሁ ባዩ መንግስት ተብዬ እንዲጨናገፍ ሆኗል። በእግዚአብሔር ተስፋ አይቆረጥምና አሁንም ቢሆን ወደዚሁ የእርቅና ሰላም ሒደት እንደሚመለሱ ተስፋ እናደርጋለን።
 ይህም በእግዚአብሔር ፈቃድ እስኪፈጸም ድረስ ወገንተኝነትን ለቤተክርስቲያን ብቻ በማድረግ በእውነትና በእምነት መጽናት አማራጭ የሌለው መንገድ ነው። በጭፍን ከዚህኛው ወይንም ከዚያኛው ወገን መወገን ግን ለሥርዓተ ቤተክርስቲያን መጣስ፣የእርቅና ሰላም ሒደት እንዳኖር፣ ለሕሊናና ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለጥቅምና ለወገኔ ይድላው በማለት ከኃይማኖት መውጣት ነው።
 ስለዚህ የምንገኝበትን ቤተክርስቲያን ሰላምና አንድነት አጽንተን በመጠበቅ በተስፋ እየኖርን ለእግዚአብሔር መንግስት ለመብቃት እንዘጋጅ።

የሰላም አምላክ ሰላምን ያድለን
አንድነታችንን ይጠብቅልን አሜን!


እኛና ገዥዎቻችን –በቢርደያ ይሃማክ

$
0
0

ጫርጫር ማረግ አምሮኛል፡፡ ‹እኛና ገዥዎቻችን› በሚል  ርዕስ ሥር ተከታታይ ጽሑፎችን ለማቅረብ ወስኛለሁ፤ ልጀምር ነው፤ ቀጠልኩ፡፡

ቀጥያለሁ—–

(ፀሐፊ፡- ቢርደያ ይሃማክ   e-mail: aklilhabte@gmail.com)

ሰኞ ነሐሴ 28 ቀን 2004 ዓ.ም. 5 ሰዓት አካባቢ ወደ ደንበል ለመሄድ ከጥቁር አንበሳ ሼል ስነሳ በየቀኑና በየቦታው እንደተለመደው ታክሲ አጣሁ፡፡ ሞልተው የሚያልፉ ታክሲዎችን በመሸኘትና የመለስ ዜናዊ ፎቶ የተለጠፈበትን ጥቁር ከነቲራ የለበሱ አንዳንድ ባልቴቶችን በማየት ብዙ ደቂቃዎችን በክብር ከሰዋው በኋላ በእግር ጉዞዬን ጀመርኩ፡፡ እነዚህን ባልቴቶች ሳይ የወጣቶች ሊግ፣ የሴቶች ሊግ እና የቀበሌ ሸማቾች ማህበር ትዝ አሉኝና ተናደድኩ፤ ለምን እንደተናደድኩ የገመተ አለ@ በጣም ጥሩ፤በደርግ ጊዜ የነበረው የአገልግሎት ሱቅ (የቀበሌ ሱቅ) ስኳር፣ አሻቦ፣ ቡና የሚሸጥበት ዋጋ ውጭ በገበያ ላይ ከነበረው ዋጋ ምን ያህል ይቀንስ እንደነበርና ከቀበሌ መግዛት በርግጥ ሰውን እንዴት ይገላግል እንደነበር ያየሁ ሰው ዛሬ የወያኔ ባላባቶችና ቁልፍ ነጋዴዎች ዋጋን እንቆጣጠራለን በማለት የሆነ ውዥንብር ፈጥረው ወይም የነሱ ብቻ በሆኑት ግዙፍ ጅምላ አከፋፋይ ድርጅቶቻቸው ምርትን ሆን ብለው ደብቀውና አከማችተው የዋጋ ንረት እንዲፈጠር ካደረጉ በኋላ ጅንአድ፣ ሸማቾች ወዘተ በሚሏቸው ቱቦዎቻቸው በኩል ገበያ ላይ ካለው ዋጋ አንድ ብር ወይም ሁለት ብር ብቻ በመቀነስ በውድ እየቸበቸቡ ሲከብሩ አያለሁ፡፡ የሚገርመው የአንድ ብር ቅናሽም ተስፋ የሆነችበት ይህ ምስኪን ሕዝብ ከነሱ ለመግዛት ቀኑን ሙሉ በቀበሌዎችና በሸማቾች ደጃፍ ተሰልፎ ይውላል፡፡ በነፍስም በሥጋም የሞተው የሟቹ የለገሰ ዜናዊ የሞተ መንግሥት ለምን በህዝቤ እንደሚጫወት አይገባኝም፡፡ ለምንስ የህዝቤን ሰዓት ያቃጥላል@ ይኸ እኮ ነው ወገኖቼ የዛሬ ሸማቾች፣ ቀበሌ፣ሊግ ትዝ ሲሉኝ በቶሎ የሚያናድደኝ፡፡

ጥቁር አንበሳን ሆስፒታል በስተቀኝ እያየሁ ቁልቁል ስወርድ በስደተኞችና ዜግነት ጉዳይ መሥሪያ ቤት (ኢሚግሬሽን) ለመስተናገድ የሚተራመስ ሕዝብ ታየኝ፡፡ አቤት ብዛቱ! የሰማይ ኮከብ፣ የባህር አሸዋ ወይስ ምን@ ይኸ ሁሉ ሰው ነው@ ውጭ ለመሄድ የተሰለፈ ሰው! ‰ረረ በዚህ ከቀጠለ ወደፊት ወያኔ የሚገዛው ሕዝብ እንዳያጣ ያሰጋዋል-ሰው ሁሉ ሄዶ ያልቅበታላ!

ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ 21 ዓመት ሙሉ ኢትዮጵያ በጎሣ ትሸንሸን በሚለው ከሰሜናዊው አባቴ ከኢሳያስ አፈወርቂ በቀሰምኩት አስተሳሰቤ ለምን ከክርስቶስ አሳንሳችሁ ታዩኛላችሁ በማለት ሲሰድበን፣ሲያዋርደንና ሲገድለን የኖረው የወያኔ አምበል ፈርኦን ለገሰ ዜናዊ በመሞቱ የተደናበሩት የሱ ደቀ-መዛሙርት ዛሬ በአደባባይ በሬዲዮና በቴሌቪዥን አንደሚነግሩን በአንድ ግለሰብ ብቻ ሲነዱ የባጁ፣ የኖሩ፣ ያረጁ የአንድ አውራጃ (የአድዋ) ሰፋ እናርግላቸው ካልንም የ3 አውራጃዎች (አሽአ-አክሱም፣ሽሬ፣ አድዋ) ዘመናዊ ነገሥታት የሥልጣኑን ቁልፍ ጨብጠው በፈጠሩት ውጥንቅጥ ኢህአዲግ የሚባለው ጭራቅ ድርጅት አባል የሆኑ ሰዎች በየቀበሌው ተደራጅተው፣ በተለያዩ የመንግሥትና የግል መሥሪያ ቤቶች ተቀጥረው እየጨፈሩ፣ እየሰከሩ አንዳንድ ጊዜም አንዳንዶቹ ምስኪኑን እያሰሩ ሲኖሩ፤ እየተራቡ የበይ ተመልካች የሆኑትና አገሬ ላይ በራብ ከምሞት፣ ቤተሰቦቼና ዘመዶቼ በራብ ሲሞቱ ከማይ፤ አረብ አገር ሄጄ ከፎቅ ተወርውሬ፣ በፖሊስ ተደብድቤ ወይም ትንሽ ካየሁትና ለውጥ ከሌለ ታንቄ ልሙት፤ ፈጣሪ ብሎልኝ ካልሞትኩም ለራሴና ለቤተሰቤ ትንሽ ገንዘብ አገኛለሁ በሚል በሕይወታቸው ፈርደው ወደውጭ ለመሄድ ሰልፍ የያዙትን ምስኪንና ቆነጃጅት ያገሬ ልጆች ከብዛታቸው የተነሳ ማየትና መቁጠር አቅቶኝ እግዚኢ-አቤት የፈጣሪ ያለህ፣ የመንግሥት ያለህ፣ ያገር ያለህ፣ የሕዝብ ያለህ እያልኩ ከግፊያው በመከራ ወጥቼ ቸርችል ጎዳና ገባሁ፡፡ በዐይኔ ይኸን እያየሁ አሁን ይህን ጊዜ የወያኔ ሬዲዮዎች (ቱልቱላው ፋና 98.1፣ የቀንደኛዋ ካድሬ ንፋው ዛሚ 90.ምናምን፣ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1) ስለ መለስ ተዐምራትና ገድል ያወሩ ይሆናል፡፡ ምን ዐይነት ዓለም! ይህን ጊዜ እኮ በጥበብ፣ በዕውቀት፣ በሥልጣኔ የተራቀቁት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲየን ቁንጮ ላይ ዶላር ጎዝጉዘው የሚደንሱት የአሽአ (አክሱም-ሽሬ-አድዋ) ቀሳውስት፣ ሊቃውንት፣ኤጲስ ቆጶሳት፣ ጳጳሳት – - በአስደናቂ ራዕይ እየተመሩ፣ ክንፎቻቸው እያበሩ ስለ ቅዱስ፣ ሰማዕት- በስመ ድንጋጤ ወአንቅጥቅጤ፣ ልክፍተ ቡዳ በአበበ ገላው ዘጎጃም ወጎንደር ዘነገደ ይሁዳ – ለገስ መለስ – ገድል በወርቅ ብዕር እየፃፉ ይሆናል፡፡ አዎ፣ ይሁን ያርገው ይገባል፡፡ የቅዱስ ለገስ አባ መለስ ገድል ተፅፎ በስማቸው ለሚቀረፀው ታቦት ማደሪያ- ማህደር በሚሆነው ደጀ-ሰላም ውስጥ ቅዳሴ ይቀደስበታል፡፡ ውዳሴ ይወደስበታል፡፡ ልጋሴ ይለገስበታል፡፡ ህዳሴ ይኸደስበታል፣ ይታደስበታል፡፡ አሃሃሃሀ—እውነቱን ለመናገር ርካሴ፣ ርኩሰት ይረከስበታል፡፡

እየተጓዝኩ ነው፡፡ በቸርችል ጎዳና ትንሽ ከወረድኩ በኋላ ዋናው ፖስታ ቤት አካባቢ ስደርስ ወደ ግራ በመታጠፍ ወደ አምባሳደር ሲኒማ ቤት ወረድኩ፡፡ በስተቀኝ የመከላከያ ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት አላሳልፈኝ አለ፡፡ በሕንፃው ላይ የተለጠፉትን የመለስ ፎቶዎችና አብረው የተፃፉትን ተዐምራት እንደምንም ተቋቁሜ ቀጠልኩ፡፡መስቀል አደባባይማ የኢትዮጵያውያን አደባባይ መሆኑ ቀርቶ የመለስ ዜናዊ አደባባይ ሆኗል፡፡ ወይ የባንዳ ዘመን! ጸረ-ኢትዮጵያ የሆነን ሰው ፎቶ በአደባባይ በመስቀል ኢትዮጵያዊያንን አንገት ማስደፋት ምን የሚሉት ኢትዮጵያዊነት ነው@ እህህህ!! ቀንደኛ የኢትዮጵያ ጠላት የሆነን ሰው ፎቶውን በመስቀል ከሞተ በኋላ ኢትዮጵያዊ ማድረግ የሚቻል መስሏቸው ይሆን@ ምስኪን አጎብዳጆች!

ከጥቁር አንበሳ እስከ ኦሎምፒያ ድረስ ያየሁትን ነገር ሳሰላስል አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሳይሆን የመለስ ቤተሰቦች ለሟቹ መታሰቢያ ባሰሩት ትልቅ መቃብር ቤት ውስጥ ያለሁ መስሎኝ ደገነጥኩ፡፡ መቃብር ቦታ ሰይጣን አይጠፋም፣ መቃብር ቦታ ይከብዳል እየተባልኩ ያሳለፍኩት አስተዳደጌ ትዝ ብሎኝ በድንጋጤ ላማትብ ስል አበሩስ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ወዳለው ጉዳዬ ለመውጣት የደረጃውን የመጀመሪያ መካን መርገጥ እንደጀመርኩ ተገነዘብኩ፡፡

በደርግ መንግሥት የመጨረሻ ዘመን አካባቢ የሚዘወተረው ወቅታዊ ዜና የሚከተለውን መልዕክት የያዘ ነበር- ‹‹ ገንጣዩ ሻዕብያ እና በአምሳሉ የፈጠረው ውላጁ ወያኔ በሀገራችን ታሪካዊ ጠላቶች መሣሪያና ገንዘብ ሰክረው፤ ኤርትራን ከእናት አገሯ ኢትዮጵያ ለመገንጠል፣ የሃገራችንን ታሪክና ቅርስ ለማጥፋት፣ የባህር በራችንን ለመዝጋት፣ ዳር ድንበራችንን ለመቆራረስና ባጠቃላይ አንድነታችንን ለመናድ እንዲሁም ሕዝቡን በጎሣና በዘር ከፋፍለው ርስበርስ እያናቆሩ አዳክመው ለመግዛት የከፈቱብንን ጦርነት ሕዝቡ በቆራጥነት እየመከተ ይገኛል›› ዛሬ ዘይት ከከተማ ሲጠፋ በቴሌቪዥን ጀሪካን ይዘው ‹‹ዘይት ሞልቷል››፣ ሕዝቡ ትራንስፖርት አጥቶ ሲሰቃይ ‹‹የትራንስፖርት ችግር የለም›› እያሉ የወያኔን የፈጠራ ወሬ በማስተጋባት የውሸት ምስክርነት የሚሰጡ ግፈኛ ፍርፋሪ ለቃሚ ካድሬዎች የሚያቃጥሉኝን ያህል በደርግ ዘመን ከያንዳንዱ ዜና ጋር የምንትሴ አስተዳደር ክልል የኢሰፓ ዋና ፀሐፊ፣ ምንትሴ እያሉ በሃገሪቱ ያለ ኢሰፓ አባል ሰው የሌለ ሲያስመስሉ ያተክኑኝ ነበር፡፡

ይሁንና ያኔ በደርግ ጊዜ ለመገንጠልና ለማስገንጠል፣ ዳርድንበር ለመቆራረስ፣ እንዲሁም የባህር በራችንን ለመዝጋት ይታገሉ ስለነበሩት ጎጠኛ ቡድኖች ይባል የነበረውን ዛሬም ስመዝነው ውሸት ላገኝበት አለመቻሌ ይገርመኛል፡፡ ርግጥ አልፎ አልፎ ጊዜ በራሱ የሚፈጥረው ተዐምር መኖሩ አይቀሬ በመሆኑ አስገንጣዩ ቡድን (ወያኔ) ፈጣሪውና አለቃው የነበረውን ቡድን (ሻዕብያን) ካጣ በኋላ ከሻዕብያ ሌላ በምድር በሰማይ ጠላት የለኝም በማለት አገር ይያዝልኝ ሲልና ተስፋ በማጣት ከመሸ በኋላ ኢትዮጵያዊ ለመምሰል በተወነው የ10 ዓመታት አድካሚ ትያትር ሲወድቅ፣ ሲነሳ፣ ሲንፈራገጥ ጀርባው ሲገጣጠብ ለማየት በመብቃታችን ወይ ዕድሜ ደጉ ብለናል፡፡ የትያትሩ ደራሲ ራዕይ ይቅርና አቋም የሚባል ነገር ያልተፈጠረበት ለፖለቲካ ጥቅምና ለሥልጣን ሲል ዛሬ በግራ ነገ በቀኝ መሰለፍ የማያሳፍረው መለስ ዜናዊ እንደነበር ‹‹ገድለ-መለስ ወለገስ የህዳሴው መሀንዲስ›› በሚለው መጽሐፍ መለሲዝም የሚለው እምነት ተከታዮች በሆኑት አብዮታዊ ካድሬዎች ተተርኮለታል፡፡ እባካችሁ ለጊዜው መሳቅ ክልክል ነው፤ እሺ@ ከሞተ ገና ዓመቱ እኮ ነው-አይሳቅም፡፡

የሆነ ሆነና በ2004 ዓ.ም. መጨረሻ አካባቢ የሞተው መለስ ዜናዊ በርግጥ ኢትዮጵያን ሊወክል የሚችልና ለኢትዮጵያዊያን የመጣ ሰው ነበርን@@@   ይህ ጥያቄ እንቅልፍ ባይነሳኝ ኖሮ ይህን ፅሑፍ መጻፌን ትቼ አርፌ በተኛሁ ነበር፡፡

(ክፍል አንድ በሚቀጥለው ይቀርባል)

መላኩ ፈንታ መታመማቸውን ጠበቃቸው ፍ/ቤት ተናገሩ፤ ኦ! ኦ! ርዕዮት ዓለሙ ጡቷን ታማ የጮኸ የለም!

$
0
0

ከሮቤል ሔኖክ

ጀግናዋ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ

ጀግናዋ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ

ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣውን ሪፖርተር ጋዜጣ ሳነብ ከሰሞኑ ከወረተኛዋ ኢሕአዴግ በፍቅር ሲቆሉ ከከረሙት ባለስልጣናት መካከል አንዱ የሆኑት አቶ መላኩ ፈንታ ታመው እንደነበር የሚገልጽ ዜና አንብቤ በዜናው ቀናሁ። የሙያ ባልደረባችን ርዕዮት ዓለሙ በጡቷ ላይ እብጠት ወጥቶባት ሕክምና ስትፈልግ፤ ለህክምና ራይድ የሚሆን መኪና የለም ተብላ ወራትን ስትጠብቅ ይህን ዜና እንደዘ-ሐበሻ የመሳሰሉ ነፃ ሚድያዎች ሲዘግቡት እነ ሪፖርተር ሆዬ ጆሯችን አልሰማም ብለው አልዘገቡትም። ዛሬ የአቶ መላኩን ዜና ሲጽፉት ትዝ አለኝና ር ዕዮት ዓለሙ ትዝ አለችኝ። የቅናቴ መነሻም ይሄው ነው።

ስለ ር ዕዮት ዓለሙ የጡት ህመም ለመዘገብ አንጀት ያልነበረው ሪፖርተር ስለ መላኩ ፈንታ መታመመ ጠበቃቸውን ጠቅሶ እንዲህ አለ፦

በተጠረጠሩባቸው የተለያዩ የሙስና ወንጀሎች ግንቦት 2 ቀን 2005 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ በቁጥጥር ሥር ውለው በእስር ላይ የሚገኙት በሚኒስትርነት ማዕረግ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ መታመማቸውን ጠበቃቸው ግንቦት 16 ቀን 2005 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበው አስታወቁ፡፡

ጠበቃው አቶ መላኩ በአስቸኳይ ሕክምና እንዲደረግላቸው ጠይቀው፣ “እኚህ ሰው በጠና ስለታመሙ የታሪክ ተወቃሽ እንዳንሆን፤

የአቶ መላኩን ጤንነት በሚመለከት ጠበቃው በዝርዝር ጠይቀው የሕመማቸው ዓይነትና ደረጃ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ባይረዱም፣ መልካቸው ቢጫ ሆኖ እንዳዩዋቸው ገልጸዋል፡፡ ለምን እንዳላነጋገሩዋቸው ሲጠየቁ በቂ ጊዜ እንዳልነበራቸው የገለጹት ጠበቃው ከእሳቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘታቸውን፣ ነገር ግን ሆስፒታል ይሂዱ ወይም አይሂዱ አለማወቃቸውንም አስረድተዋል፡፡

በአጃቢ ሆነው ሕክምና እንዲያገኙ ጠበቃው ላነሱት ጥያቄ፣ ስለመታመማቸው የሚገልጽ ማስረጃ ከክሊኒክ ወይም ከሆስፒታል እንደሚያስፈልግ በመግለጽ ያለማስረጃ ትዕዛዝ መስጠት እንደማይቻል ፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡

አቶ መላኩ መንግሥት የሚያውቀውና በአገር ውስጥ ሕክምና የማይድን ሕመም እንዳለባቸውና በውጭ አገር እየታከሙ እንደነበር፣ ለፍርድ ቤቱ ራሳቸውና ጠበቃቸው ማስረዳታቸው የሚታወስ ነው፡፡ ” ብለዋል

አንድ በሙስና የበሰበሰና የሰዎች ሰብአዊ መብት ሲገፈፍ አቤት ሳይል የከረመ ሆዳም ባለስልጣን ምንስ ቢሆን የምን ታሪክ ይመጣል? ይልቅ የታሪክ ተወቃሽ የሚያደርገን የመናገርና የመጻፍ መብቷን ተገፋ ታስራ ህክምናም እንዳታገኝ በወህኒ የተወረወረችው ር ዕዮት ጉዳይ ነው የታሪክ ተወቃሽ ሊያደርግ የሚችለው።

 

 መላኩ ፈንታ እኚህ ናቸው።

መላኩ ፈንታ እኚህ ናቸው።

እኔን የገረመኝ ከሰሞኑ በስርቆት ወንጀል የታሰሩት እነዚህ የወያኔ ተላላኪዎች በፍርድ ቤት ‘ይታዘንልን’ ሲሉ ያቀረቡት ማስተዛዘኛ ሁሉ ህመምን ነው።

- አንዱ የልብ ህመም

- አንዱ መናገር የማልፈልገው በሽታ

- አንዱ ሌላ

- ሌላው ሌላ በሽታ ጠርተዋል: ርዕዮት ዓለሙ ጡቷን ታማ ሲሳለቁ፤ ውስኪያቸውን ሲጨልጡ የነበሩ ተላላኪዎች  ይህን “ይታዘንልን?” ምክንያት ሲያቀርቡ እኛ እንቀበል ይሆን?

 

 

 

ድምጻዊ አበበ ከፈኒና ኤርሚያስ አስፋውን ሳስታውሳቸው

$
0
0

ድምጻዊ አበበ ከፈኒና ኤርሚያስ አስፋውን ሳስታውሳቸው(በግርማ ደገፋ ገዳ)
ድምጻዊ አበበ ከፈኒ (ጄኔቭ) የሚገኝ እና ኤርሚያስ አስፋው ናዝሬት የሚኖር፤ የእነዚህን ሁለት የናዝሬት ድምጻውያንን ሙዚቃ ስሰማ አንድ ትዝ የሚለኝ ሁኔታ አለ። እ.ኤ.አ. 1998 በናዝሬት (አዳማ) ከተማ፣ ፋሲል ሆቴል ውስጥ በከተማዋ የሚገኙ ድምጻውያንን ለውድድር በአንድ መድረክ ላይ አቀረብናቸው። ሃሳቡ የዳንኤል ክፍሌና የመስፍን አስገዶም ነበር። ዳንኤል በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ ምክንያት አንድ ዓመት ከስድስት ወራት ከርቸሌ ከርሞ የመጣ ጋዜጠኛ ነው።
በእለቱ በናዝሬት ከተማ ይደረግ የነበረውን የመኪና ውድድር ኮካኮላ ፋብሪካ ስፖንሰር አድርጎ ስለነበር፣ እኛንም ስፖንሰር እንዲያደርገን አድርገን፤ ከአዳማ የመምሕራን ማሰልጠኛ ተቋም ውስጥ የሙዚቃ አስተማሪ የነበሩት መምህር ጉልቴ በመሃል ዳኝነት ውድድሩን ዳኙልን። ለመምህር ጉልቴ መምህራን ማሰልጠኛ ተቋም ድረስ ሄጄ የትብብር ጥየቃ ደብዳቤያችንን የሰጠዋቸውም እኔ ነበርኩ። ወደ ዝግጅቱ ለመግባት አቅም ያለው እየከፈለና በነጻ እንዲታደም በደብዳቤ የጋበዝነውና አክብሮን የመጣው ብዙ በመሆኑ፤ መቀመጫ ጠፍቶ ዝግጅቱ ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ ለመቆም የተገደደ እድምተኛ ነበረን።
“የሆዴን አውጥቼ ልንገርሽ” የሚባለውን ምርጥ የጥላሁን ገሰሰን ዘፈን የተጫወተውና በውድድሩ አንደኛ የወጣው፤ ኤርሚያስ አስፋው ነበር። አበበ ከፈኒና ሰለሞን ዘሥላሴ ሁለተኛና ሶስተኛ ወጡ። ያን ጊዜ አበበ ባገኘው ውጤት አልተደሰተም ነበር። ይሁንና ከትንሽ ጊዜያት በኋላ አውሮፓ የሚወጣበት አጋጣሚ ተፈጠረና ለማሳተም ያዘጋጀውን ካሴት ናዝሬት ለሚገኙ ሙዚቃ ቤቶች አድሎ በዚያው ድምጹ ጠፍቶ ቀረ።
ዛሬ፤ አበበ ተቀማጭነቱን አውሮፓ አድርጎ ከአውሮፓውያን ሙዚቀኞች ጋር ልዩ ልዩ ዝግጅቶቹን ለፈረንጅም ይሁን ለአፍሪካውያን ከማሳየቱም ባሻገር ሲዲም ለገበየ ካቀረበ ሰነባበተ። “ናዝሬት አዳማዬ” የተባለ የናዝሬት ልጆችን ልብ የሰበረ ዘፈን ተጫውቷል። “ያርግልህ በሉኝ” በጥሩ ሙዚቃው የሚጠቀስ ነው። በቅርብ ጊዜ የአሊ ቢራን “ሂያዲኒ” የተሰኘ የኦሮምኛ ዘፈን ተጫውቷል፤ ዩቱብ እና የሙዚቃ ነገር ይመለከተናል ያሉ ዌብ ሳይቶችም አስተናግደውለታል። በቅርብ ቀን የሚወጣ የነጥላሁን ዘውገ የኮመዲ ቪሲዲ ላይም የራሱ የሆነ ድርሻ እንዳለው ከተለጠፈው ፖስተር ላይ እያየን ሲሆን፤ በኮመዲው ላይ ድርሻው ምን ሊሆን እንደሚችል ቪሲዲው ገበያ ሲወጣ የምናውቀው ይሆናል። የዚህ ቪሲዲ አሳታሚና አከፋፋይ ዘውገ አርት ፕሮሞሽን ነው።
ኤርሚያስ አስፋውም ጥሩ ዘፈኖች የተሰባሰቡበት ሲዲ ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት ገደማ ለገበያ አውሏል። በተለይ “ልረሳሽ አልቻልኩ” በጣም ጥሩ ዘፈኑ ነች። ዩቱብ ላይም ትገኛለች። የግጥም ደራሲውም ዳንኤል ክፍሌ ነው። ኤርሚያስ አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ባላውቅም ጥሩ የሙዚቃ ሰው በመሆኑ በዚያው የቀጠለ ይመስለኛል።
በእለቱ አንጋፋ ጋዜጠኛ የነበሩትን አቶ ያለው በለውን በክብር እንግድነት ጋብዘን ስለጋዜጠኝነት ለታዳሚው የሚሉትን ብለዋል። ድራማ፣ አስቂኝ ጭውውቶችና ግጥሞች ቀርበዋል። የፋሲል ሆቴል ባለቤት ልጅ የነበረው ወጣቱ ፋሲል ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ እጅግ ሰነባበተ። ብዙ የረዳን እሱ ነበር።
ዛሬ እንደዚህ ዓይነት ነገር ናዝሬት (አዳማ) ላይ አለ ወይ? አበበ ከፈኒ ለሥራ ጉዳይ ወደ ናዝሬት መመላለሱ አልቀረም፤ ስለዚህ ከኔ የተሻለ የሚያውቀው ይኖራል።
http://www.youtube.com/watch?v=2zu28SQFyfQ “የሆዴን አውጥቼ ልንገርሽ”
http://www.youtube.com/watch?v=aGkfV63IEdI “ናዝሬት አዳማዬ”
http://www.youtube.com/watch?v=QGH-0PmvD2k “ያርግልህ በሉኝ”
http://www.youtube.com/watch?v=t6ivqTKyLtI “ሂያዲኒ”
http://www.youtube.com/watch?v=04CGqQliWaY “ልረሳሽ አልቻልኩ”

እርማት ለጃዋር መሐመድ፡ በነጭ ውሸት ላይ የተመሰረተ ትንተና የት ያደርሰን ይሆን?

$
0
0

በቴዎድሮስ በላይ

በየፊናችን እየተማረርን መማራችን ለበጎ ነው – ከይነጋል በላቸውአቶ ጁዋር ሲራጅ መሃመድ በቅርቡ ከአቶ ደረጀ ደስታ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ (http://ethsat.com/video/esat-yehager-lij-activist-juwar-mohamed-10-may-2013/) በአጽንኦት ተከታትያለሁ። የሰውየው ግለ ታሪክና ያደረጋቸው ጉዞዎች መሳጭ ቢሆኑም አንዳንድ እርማት የሚያስፈልጋቸው የተሳሳቱና የተዛቡ ታሪኮችን እንደገና እንዲፈትሽ፤ ሆን ብሎ እያራገበው ከሆነም ቆም ብሎ እንዲያስብበት ለመጠቆም ወደድኩ። የተሳሳተ መረጃ መረጃ ራስንም ሌላውንም ክፉኛ ይጎዳል። ሊዘህ መነሻ የሆነኝ፤ ስለ ኦሮሞ ጭቆና መነሻውን ሲገገልጽ፤ አማራዎቹ የአውሮፓን መሳሪያ ቀድመው ስላገኙ የሚል፤ መሰረት የለሽ ውንጀላው ነው።
ጋዜጠኛ ደረጀ ስለ ኦነግ አመሰራረት ሲጠይቀው፤ ጁዋር እንዲሚከተለው መለሰ። “እንግዲህ በመቶ አመታት ወደዃላ ሂደን ስናይ አካባቢው በቡድን ግጭት የተሞላ ነበር-በተለይ ከ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ። ከዚያ በፊት አብዛኛው የሐይማኖት ነበር። በሐይማኖት ስር የተደራጁ መንግስታት ነበር ሲጋጩ የነበሩት። ከዚያ በዃላ ግን የብሔር ግጭቶች ነበሩ። ይህ የብሔር ግጭት፤ በአማራ፣ በኦሮሞና በትግሬ የተካሄደው ነው-ኢትዮጵያን የወለደው። በዚህ ግጭት ውስጥ ቀድሞ የአውሮፓን መሳሪያ ሊያገኝ የቻለው የአማራው ሀይል አሸንፎ፤ በበላይነት አሁን የምናውቃት ኢትዮጵያን ፈጠረ። “ እጅግ በጣም የገረመኝ መልስ ነው። በእርግጥ አቶ ጁዋር ብቻ አይደለም ፤ በቅርብ ጊዜ የምሰማው ከመሰሎቹ የኦሮሞ ወንድሞቼ የዕለት ከዕለት ውንጀላ ሆኗል። ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል፤ እንዲሉ የዚህ አይነቱን ነገር እንደ እውነት ሳይወስዱት አልቀረም።
ይሄ መልስህ፤ ብዙ ጥያቄዎችን አጭሮብኛል፡
• በውኑ ኢትዮጵያን የወለደ ከ14ኛው አመት በዃላ ያለው የብሔር ግጭት ነው?
• ከ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በነበሩት የሐይማኖች ግጭቶች፤ የኦሮሞ ሕዝብ የት ይሆን የነበረው?
• በውኑ አማራው ነው የውጭዎቹን መሳራያውን ቀድሞ ያገኘው? ማረጋገጫ ልትሰጠኝ ትችላለህ? እኔ ያነበብሁትና የማውቀው ሌላ ነው።
ለምን የፈጠራ ውንጀላ ውስጥ በተለይ ማንበብና መጻፍ ከምንችል ሰዎች መካከል እንደምንዘፈቅ አይገባኝም። ሁለቱን ጥያቄዎች ለአቶ ጁዋር ትቼ፤ ለውንጀላ የተጠቀምህበትን ሶስተኛውን ጥያቄ እኔው ካነበብሁት እመልሳሃለሁ። ስህተት ከሆነ ማስረጃ ያቅርብና እንከራከርበት። ኢትዮጵያውያን እርስ በራሳቸው፤ በአካባቢያቸው በሰሩት መሳሪያ ይዋጉና አሸናፊው ይገዛ እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። በዚህ እርሱ እና እኔም እንስማማለን። እንዲህ አይነቱ ልማድ በሌሎቹም አለም ሲደረግ የኖረ ሃቅ ነው። ነገር ግን የአለም ሁኔታ ተቀይሮ፤ አንዱ የሌላውን ሃብት ድምበር አቋርጦ ለመዝረፍ ሲባል፤ ጠመንጃ መሳሪያን ይዘው ብቅ አሉ። በመሰረቱ የጠመንጃ መሳሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠረው በ14ኛው ክፍለ ዘመን በቻይናዎች ነው። ወዲያውኑም ወደ ሩቅ ምስራቆችና አውሮፓዎቹ ተዛመተ። አውሮፓውያንና ሩቅ ምስራቆች፤ በሐይማኖት ሰበብ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭትን አስነሱ፤ የጠበንጃ መሳሪያውንም ይዘው ተነሱ። በኢትዮጵያም ይኸው ሆነ። በወቅቱ፤ ከክርስቲያኖች ጋር ለተጣላው ግራኝ አህመድ፤ ቱርኮቹ ልዩ ሰልጠና ሰጥተው የጦር መሳሪያ አስታጥቀው፤ ከሰለጠነ ወታደር ጋር ወደ ኢትዮጵያ አስገቡት፤ በ11529 ጀምሮ ኢትዮጵያን በይፋ ወረረ። በጦርና በጨበጣ ብቻ የመዋጋት ልምድ የነበራቸው ኢትዮጵያውያን፤ የጠመንጃ መሳሪያ የታጠቀውን መሃመድን በምንም መልኩ ሊቆጣጠሩት አልቻሉም። ብዙ የሰው ህይወትና የአገር ሃብት አወደመ። በወቅቱ የነበሩ ገዥዎች፤ እርሱን ለመቋቋም፤ ክርስቲያን ክፍል የሆኑትን ፓርችጋሎችን በመማጸን የመሳሪያና የሰው ሃይል እርዳታ አግኘተው፤ ተዋግተው አሸነፉ። ይህ ነው የጠመንጃ መሳሪያ ወደ ኢትዮጵያ አመጣጡ። ይሄን እውነታ ቀይሮ አማሮቹ መሳሪያ ቀድሞ ስላገኑ የሚለው አካሄድ፤ ምን አይነት የፓለቲካ ትርፍ ያመጣ ይሆን? በመሰረቱ፤ የግራኝ ጦርነትን ተከትሎ ሰሜኑን የወረረው ማን ነው። የኦሮሞዎች ወረራና በቀላሉ ሰፊውን የሃገሪቱ ክፍል የመያዝ ውጤቱ፤ በግራኝ አማካኝነት የተካሄደው ጭፍጨፋ ከፍተኛ የሆነውን የአማራ ሕዝብ ስለጨረሰ ነው። ለዚህ መከራከሪያ ምላሹን ከአቶ ጁዋር እፈልጋለሁ። የኦሮሞ ማህበረሰብ በወቅቱ የተፈጠረውን አጋጣሚ በመጠቀም፤ የሰሜኑን ክፍል ወርሮ ያሸነፈው ብቸኛው ምክንያት ይሄው ነው። የጦር መሳሪያ ወደ ኢትዮጵያ መግባት የጠቀመው፤ አቶ ጁዋር እንደጠቀሰው አማራውን ሳይሆን ኦሮሞውን ነው። ከቆላማው ወደ ደጋማውና ለም የሃገሪቱ ክፍል እንዲገቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጎላቸዋል። ይሄን ጥሬ ሃቅ ክዶ፤ በወቅቱ የተሰራን ግፍ ወደ ሌላው መለከክ፤ ከአንድ የፓለቲካ ተንታኝ፣ ያውም ሌሎቹን እያሰለጠነ ካለ በፍጹም አይጠበቅም።
በወንድሜ፤ በአቶ ጁዋር አካሄድ ቢተነተን፤ እስላምና በኢትዮጵያ ምድር ለመስፋፋት አስተዋጽኦ ያደረገው፤ የጠመንጃ መሳሪያ የሙስሊሞቹ መሪ የነበረ በመጀመሪያ በእጁ በቱርክ በኩል ከልዩ ስልጠና ጋር ስለገባ፤ ብዙውን ሰው አሰለመ ወደሚለው ያደርሰናል። እናም፤ ሙስሎሞች ጥፋት ስላጠፉ…..የሚል ጭልጥ ያለ ውንብድና ውስጥ ይከተናል። እኔ ግን ይሄን አልቀበለውም። ምንም ይሁን ምን፤ ደካማ ጎናችንን በመጠቀም፤ የውጭ ሃይሎች የጫኑብን መከራ ነበር ብዬ ነው የማልፈው። ለዛሬ ችግራችንም መጥቀስን አልፈልግም። ምክንያቱም፤ በእነሱ ተንኮል ስር እንደገባሁ ስለምቆጠርው። እናም ጁዋር፤ የኦሮሞ ችግር በውኑ በአማራው የደረሰብት መከራ ነበርን ለማት ታሪኩን፤ መሳሪያ ከመግባቱ በፊት የነበረውን ሁኔታ በጥልቅ እንዲያነቡና ለሁላችን የሚያስማማ፤ እያንዳንዱ ዜጋ የተከበረባት ኢትዮጵያን ለማዬት እጅግ ወሳኝ ነው እላለሁ።
አበቃሁ።

የአሊ ቢራ 50ኛ ዓመት የሙዚቃ አገልግሎት ሊከበር ነው

$
0
0

ali birra(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚኛ ሙዚቃ ታሪክ ላይ ግዙፉን ቦታ የሚይዘው ድምጻዊው አሊ ቢራ በሙዚቃው ዓለም የቆየበት 50ኛ ዓመት በዓል እዚህ ሚኒሶታ ውስጥ ጁላይ 4 ቀን 2013 እንደሚከበር ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ጋዜጣ አስታወቁ።
በሚኒሶታ የሚደረገውን የዘንድሮውን የኦሮሞ ስፖርት ፌስቲቫል ተከትሎ ከሚደረጉ በርከት ያሉ ዝግጅቶች መካከል አንዱ እንደሚሆን የሚነገርለት ይህ የአሊቢራ የሙዚቃ ሕይወቱ የቆበት 50ኛ ዓመት በዓል የሚከበረው በራት ግብዣ እንደሚሆን ተገልጿል። በእለቱ ድምጻዊው ሥራውን እንደሚያቀርብ የሚናገሩት ምንጮቹ በተለይም በኦሮሚኛ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ከማህበራዊ ሕይወት አንስቶ እስከ ፖለቲካ ጉዳዮች በማንሳት የተጫወታቸው ሥራዎች ይዘከራሉ ተብሏል።
አሊ ቢራ ሜይ 26 ቀን 2048 በድሬደዋ ተወለደ። ለእናቱና ለአባቱም ብቸኛ ልጅ ነው።S

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live