Quantcast
Are you the publisher? Claim or contact us about this channel


Embed this content in your HTML

Search

Report adult content:

click to rate:

Account: (login)

More Channels


Showcase


Channel Catalog


Articles on this Page

(showing articles 1 to 20 of 12419)
(showing articles 1 to 20 of 12419)


Channel Description:

ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) Latest Ethiopian News Provider

(Page 1) | 2 | 3 | .... | 621 | newer

  0 0

  New Picture (5) ራሱን የትግሬ ሕዝብ ነፃ አውጪ ባዩ ወያኔና አጋሩ ሻዕቢያ በም ዕራባውያን ከፍተኛ ድጋፍና ትብብር በአዲስ አበባና አስመራ ወደ ሥልጣን ኮርቻ ከመጡበት ወራት ጀምሮ በአማራው ኢትዮጵያዉ ማኅበረሰብ ላይ የተቀነባበረ ግልጽና ስውር ሴራ ያለማቋረጥ ቀጥሏል።
  ሙሉውን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


  0 0

  በፍቅር ለይኩን ~ (fikirbefikir@gmail.com)

  ብዕር …፣ ብዕር …፣ የብዕር ኃይል ምንጊዜም ያሸንፋል!!
  (ናይጄሪያዊው የብዕር ጀግና ኬን ሳሮዊዋ)

  Penየቀድሞው አፍሪካ አንድነት ድርጅት የዛሬው የአፍሪካ ኅብረት ተመሠረተበትን የ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ለማክበር በተለይ የኅብረቱ ዋና መቀመጫና ለአፍሪካ አንድነትም ሆነ ለኅብረቱ እውን መሆን በንጉሥ ኃይለ ሥላሴ ብርቱ ጥረት ግንባር ቀደም ሚና በተጫወተችው በኢትዮጵያ፣ በመዲናችን አዲስ አበባ በደማቅ ሁኔታ ለማክበር መጠነ ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡
  የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ከተቋቋመና አብዛኞቹ አፍሪካ አገራትም ነፃነታቸውን ከተጎናጸፉ በኋላ አፍሪካውያን በልባቸው ትልቅ ተስፋንና ራእይን ሰንቀው ነበር፡፡ አፍሪካ በጥቁር አፈሯ የአብራኳ ክፋዮች፣ በልጆቿ መሪነት ወደተሻለ ፖለቲካዊ አስተዳደርና መረጋጋት፣ ማኅበራዊ ተሐድሶ፣ ኢኮኖሚያዊ እምርታና እድገት ትገሠግሣለች ተብሎ ነበር በብዙዎች ዘንድ የተገመተው፣ የታሰበው፣ የታቀደውም፡፡
  ግና ለአፍሪካ ይመጣል ተብሎ የታሰበው፣ ያ ብሩህ ዘመን የተገመተውንና የተጓጓለትን ያህል ብዙም ተስፋ ሰጪና ብሩህ አልነበረም፡፡ እዚህም እዛም የፈነዱት የብዙ አፍሪካውያን ሕይወት የቀጠፉ የእርስ በርስ ግጭቶች፣ ስደትና መፈናቀል፣ በወታደሮችና በጦር ኃይል የታገዘ ደም አፋሳሽ የሆኑ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎች፣ ሙስናና ዝርፊያ አኅጉሪቱን ባልተጠበቀ ፍጥነት ወደ ምድራዊ ገሃነምነት ነበር የቀየሯት፡፡
  በዚህ አጭር መጣጥፌ በብዙ ተስፋ ስለተደረገው የትላንትናው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት፣ የዛሬው የአፍሪካ ኅብረት በአፍሪካ አገራት ውስጥ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊና በሌሎችም ዘርፎች ስላስመዘገበው ስኬቶች፣ ስላጋጠሙት እንቅፋቶችና ውድቀቶች ለመተንተን አይደለም አነሣሴ፡፡
  ይሁን እንጂ የዚህ ጽሑፌ ዋና ትኩረት የኅብረቱን 50ኛው የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ለማክበር ሽር ጉድ እያሉ ባሉት አፍሪካውያን አገሮች ውስጥ የምድሪቱ የብዕር ጀግኖች በየአገራቸው የተነሡትን አምባገነኖችን፣ የሰብአዊ መብት ረገጣዎችን፣ ሙስናን፣ የአስተዳር ብልሹነትን፣ መሪዎቻቸው የተዘፈቁበትን የሞራል ዝቅጠትንና ውድቀትን… ወዘተ በማጋለጣቸው የተነሣ በየጊዜው የተነሡ አፍሪካውያኑ አምባገነኖች የብዕር ጀግኖቻቸውን ያሳደዱበትን፣ ያጋዙበትንና እንዲያም ሲል ሞት ያወጁባቸውን የአፍሪካ የምንጊዜም ምርጥ የብዕር ጀግኖች ስለሆኑ ኃያላኖች ታሪክ ጥቂት ላካፍላችኹ ወድጄ ነው፡፡
  ዛሬም ድረስ የየአገሮቻቸውን አምባገነኖች ለማረም የተነሡትን የከበሩ ምሁራኖችን፣ ጸሐፊዎችን፣ ጋዜጠኞችን፣ የጥበብና ብዕር ሰዎችን ጉሮሮ ለመፍጥረቅ እንደወትሮው ኃይል የማያንሳቸው አፍሪካና አፍሪካውያን አምባገነኖች በየጓዳው በተጽእኖ በትርና በአድርባይነት መርዝ ዛሬም ድረስ ስንቱን የኪነ ጥበብ ሊቅ በግፍ ረግጠው እየገዙ እንዳለ ሊታሰበን ይገባል፡፡ ለአብነትም ያህል በአገራችን በቀደመው ትውልድ ዘመን እነ አቤ ጉበኛና እነ በዓሉ ግርማ የመሳሰሉ ኃያላኖች በብዕራቸው አማካይነት ስለ እውነትና ስለ ፍትሕ በመጮኻቸው ነበር የእብሪተኞችና የአምባገነኖች ሰለባ ለመሆን የተዳረጉት፡፡
  በእኛው ዘመንም በዓለም አቀፍ ደረጃ የብዙ ሽልማቶች ባለቤት የሆነው እንደ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ እንዲሁም ከሰሞኑ እንኳን የመንግሥታቱ ድርጅት ዩኔስኮ ለነፃ ፕሬስና ሐሳብን በነፃነት ለመግለጥ እውን መሆን አምርራ በብዕሯ የታገለች ምርጥ፣ ጀግና ሴት፣ የብዕር አርበኛ ተብላ የተሸለመችው ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙና ሌሎችም በገዛ አገራቸውና መንግሥታቸው ‹‹አሸባሪ›› በሚል ሰበብ በወኅኒ እንዲወረወሩ ያደረጋቸው እምቢ ለእውነት፣ እምቢ ለፍትሕ፣ እምቢ ለነፃነት ባለችው ኃያል ብዕራቸው የተነሣ መሆኑን ማንም ይስተዋል ብዬ አልገምትም፡፡
  መቼም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ሆነ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ማኅበሮች በታሪክ ‹‹አሸባሪዎችንና ሽብርተኞችን›› ሲሸልሙ፣ ሲሾሙና ሲያከብሩ አይተንም፣ ሰምተንም አናውቅም፡፡ ለመሆኑ መንግሥት ይህን እውነት በአደባባይ እያየና እየሰማ ምን እያሰበ፣ ምንስ መከራከሪያ እያዘጋጀ ይኾን?! ለመሆኑ ‹‹አሸባሪነትስ›› በመንግሥታችን መዝገበ-ቃላት ውስጥ ያለው ፍቺስ ምን ማለት ይኾን?!
  ባለፉት ዓመታትም ወጣቱ ከያኒ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በጥበብ ሥራው የዛሬው የትላንቱን ለመቀጣትና ለመበቀል ከሆነ ራእዩና ፍላጎቱ ለኢትዮጵያ የታለመው ሰላም፣ ብልጽግና፣ እድገትና ዲሞክራሲ አድራሻው ወዴየት ነው?! ቂም በቀል ይቅር፣ ለአንድ እናት ምድራችን በማንዴላ የእርቅ መንፈስ እጅ ለእጅ እንያያዝ፣ እንደጋገፍ፡፡ በብሔር፣ በቋንቋ፣ በዘር መለያየታችን ይቅር፣ ኢትዮጵያችን ሁላችንም የጋራ ቤት፣ የጋራ እናታችን ናት፡፡ ሰንደቀ ዓላማችን፣ ቋንቋችን ፍቅርና ፍቅር ብቻ ይሁን!!
  አለበለዚያ ግን የዛሬው መንግሥት በተራው በትላንቱ ላይ በጥላቻ ጥርሱን የሚነክስ ከሆነና የበቀል ሰይፉን የሚያነሣ ከሆነ ‹‹አዲስ ንጉሥ እንጂ መቼ ለውጥ መጣ?!›› ብሎ በማዜሙ የተነሣ ከእውነት፣ ከፍቅር፣ ከፍትሕና ከእርቅ መንፈስ ጋር የተፋቱ ብኩኖችና እብሪተኞች በወጣቱ ከያኒ ላይ ጥርሳቸውን ክፉኛ ነክሰውበት ሲያጥላሉትና ሲያወግዙት ለመስማት የተገደድንበት አጋጣሚ ቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡
  ሌላው ቀርቶ በግሌ የማስታውሰው በኦሎምፒያ አካባቢ ተሰቅሎ የነበረው የወጣቱ ከያኒ ‹‹ጃህ ያሰተሰርያል!›› የሚለው የጥበብ ሥራው ፖስተር ከላይ እስከ ታች ነጭ ቀለም ተረጭቶ ያየኹበትን ትእይንት አሁን ድረስ ሳስታውስ አምባገነኖችና እብሪተኞች በልባቸው ያረገዙትን ክፋታቸውንና በቀላቸውን ለመተግበር ምን ያህል ርቀት ሊጓዙ እንደሚችሉ ነው በሐዘንና በጸጸት ውስጥ ሆኜ እንዳስብ ያደረገኝ፡፡
  አፍሪካውያኑ አምባገነኖች በዚህ አካሄዳቸው አገራቸውን የዕድገት፣ የዲሞክራሲ፣ የነፃነትና፣ የፍትሕ ምች እንዲያጠናግረው የፈቀዱ ማን አለብን ባዮች ዓይኖቻቸውን ሳያርገበግቡ ምን መጠበቅ እንዳለባቸው አሳምረው ያውቁታል፡፡ ለእውነት፣ ለሰብአዊ መብቶች፣ ለፍትሕና ለሕዝብ ብሶት የቆሙ የጥበብ ድምፆችንና ሐቀኛ ብዕሮችን በዋሉበትና ባደሩበት እያደፈጡ ሲያሴሩና ጥበብን አልከስክሰው በእውነት ላይ ለመማገጥ የታቻላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡ እናም ሊደፋፈሩ የሚገባቸውን ጀግኖቻቸውን ያዋክባሉ፣ ያሳድዳሉ፣ ያግዛሉ፣ ይገድላሉ፣ ያስገድላሉ፡፡
  ድንግል አፍሪካ፣ በተፈጥሮ ሀብቷ አቻና አምሳያ የሌላት አፍሪካ… የማርና ወተት መፍለቂያ ምድር እማማ አፍሪካ፣ አውሮፓውያኑ የአፍሪካ በዕዳን ወራሪዎች ካደረሱባት ግፍና መከራ ያልተናነሰ ከማኅፀንዋ የወጡ፣ ጡትዋን ጠብተው ያደጉ ልጆቿ፣ ነፍጥ ማንገታቸው ልባቸውን በእብሪት የወጠረው ወታደራዊ መሪዎቿ ይህ ነው ማይባል የግፍና የመከራ ዘመንን አስቆጥረዋታል፡፡ ለዛሬ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት በነበሩት በጄኔራል ሳኒ አባቻ ዘመነ መንግሥት ለእስራትና ለሞት ስለተዳረገው ስለ ኃያሉና ጀግናው ብዕረኛ፣ ደራሲ ኬን ሳራዊዋ ታሪክ በጥቂቱ ላካፍላችኹ ወደድኹ፡፡
  የናይጄሪያዊው ጁንታ መንግሥት የስቅላት ገመድ በአንገቱ ገብቶ በሕይወቱ ላይ ስለተፈረደበት የነፃነት ታጋይ፣ የጥበብ ፊታውራሪ፣ የሕዝብ ልጅ፣ የናይጄሪያውያኑ የኢጎኒ ጎሳ ተወላጅ፣ የሕዝቡ የቁርጥ ቀን ልጅ ስለሆነው ደራሲ፣ ገጣሚ፣ ሐያሲ፣ ነጋዴ፣ የፖለቲካ ሰው፣ ሃይማኖት ሰባኪ ኬን ሳሮዊዋ፡፡
  የፈላጭ ቆራጩ የሳኒ አባቻ መንግሥት የደህንነትና የፀጥታ ክፍል ኃላፊዎች ኬን ሳሮዊዋ እትብት ከተቀበረበት ቀዬ ነዳጅ ቀድተው እንዳሻቸው መሆን እንደማይችሉ የተረዱት ናይጄሪያውያኑ አምባገነኖች ይህን በሕዝቡ ፍቅር የተነደፈውን ሐቀኛ ሰው ከማጥፋት ውጭ ሌላ አማራጭ አልነበራቸውም፡፡ እናም ይህን የሕዝብ አለኝታ ከምድራቸው ሊያጠፉት መከሩበት፤ መክረውበትም አልቀረ ያን የሕዝባቸውን የንጋት ኮከብ ገና በአፍላ ዘመኑ ብርሃኑን ጨክነው አጨለሙት፣ አጠፉት፡፡
  አምባገነኖቹ ሳሮዊዋን በቁጥጥር ስር ለማዋል ያቀናበሩለት የውንጀላ ሴራም እንዲህ የሚል ነበር፡፡ በዋና ከተማይቱ አቡጃ ትልቁ አደባባይ በጠራራ ፀሐይ በተጠመደ ፈንጅ የታፈሩና የተከበሩ የሚባሉ በሳኒ አባቻ ፊት ሞገስ ያገኙ ሦስት አዛውንቶች በድንገት ተገደሉ፡፡ የእነዚህ አዛውንቶች ግድያ ከኬን ሳሮዊዋ ጋር ሚያገናኘው ምንም ነገር አልነበረም፡፡ በወቅቱ በተደረገው ማጣራትም ግድያው የተፈፀመውም ሆነ አደጋው የተጣለው ወታደራዊውን ጁንታ በሚቃወሙ ወጣቶች መሆኑ ተገልፆ ነበር፡፡
  ይሁን እንጂ ወታደራዊው አምባገነን መንግሥት ድርጊቱን በቀጥታ ከሳሮዊዋ ጋር በማያያዝ ለሳኒ አባቻ መንግሥት የእግር እሳት የሆነው የነፃነት ታጋዩ ኬን ሳሮዊዋ በዚህም አለ በዚያ በሐሰትም ቢሆን ተወንጅሎ ከሚወዳት አገሩና ሕዝቡ መወገድ ነበረበት፡፡ እናም ናይጄሪያዎቹ አምባገነኖች ይኽን ውሳኔ አስቀድመው አቅደውና ወስነው የዚህን ጀግና የብዕር ሰው ሞት/እረፍት ለማፋጠን ተቻኮሉ፡፡
  ናይጄሪያዊው ደራሲና ብዕርተኛ ኬን ሳሮዊዋ በወቅቱ ሰለ አምባገነኖቹ ወታደራዊ መሪዎች እርምጃ እንዲህ ነበር ያለው፡- ‹‹እነዚህ ሰዎች ነፍሰ ገዳዮች ሆነው ሳሉ እኔን በከንቱ ለመወንጀል ይጥራሉ፤ በበኩሌ የመሠረቱብኝን ክስ እንኳን ለመስማት አልፈልግም፡፡ ችሎቱ በሚካሄድበት ወቅት ማለፊያ የሆነውን መጽሐፌን አንስቼ አነባለኹ፡፡ እነዚህ ሰው በላ ጭራቆች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ፍትሕንና እውነትን የተጠየፉ አምባገነኖች፣ በሚያዩት ሁኔታ እርካታ አግኝተው እንዲፈነጥዙ ዕድል አልሰጣቸውም፡፡››
  ጀሽዋ ሐመር የተባለ ጋዜጠኛ ኬን ሳሮዊዋ ያለአግባብ ተወንጅሎ ወኅኒ ከተጣለ በኋላ አግኝቶ ለማነጋገር ብዙ ጥረት አድርጎ ነበር፡፡ የናይጄሪያ ፖሊሶች ጋዜጠኛውን አታክተውና አሰላችተው ለመሸኘት ያደረጉት ጥረት ግን በሰውዬው አይበገሬነትና ብሎም በሳሮዊዋ ጠባቂ ትብብር ከሸፈና በስተመጨረሻ ሊያገኘው ቻለ፡፡ ጋዜጠኛው ጀሽዋ ሳሮዊዋን ባገኘው ጊዜ ብረት ባነገቱ ወታደሮች ተከቦ ነበር፡፡
  ሳሮዊዋ አልጋው ላይ ጋደም ብሎ ፒፓውን እያጨሰ ነበር፡፡ እንዳየኝ ይላል ጋዜጠኛ ጀሽዋ እንዳየኝ ተነሣና ጨበጠኝና ለመሆኑ ከቀናት በፊት የላኩልህ ደብዳቤዬ ደረሰኽ ሲልም ጠየቀኝ፡፡ እኔም ደብዳቤው እንደደረሰኝ አንገቴን በማወዛወዝ ገለጽኩለት፡፡ አብረን በቆየንበት ጊዜ ሳሮዊዋ የአገሩ አምባገነን መንግሥት መሪዎች ፍርደ ገምድሎች፣ ጨካኞችና የሰው ደም የጠማቸው ሆነው ሳለ በከንቱ ሲወነጅሉት የቱን ያህል ልቡ እንደተጸየፋቸው አጫወተኝ፡፡ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ኬን በሠራው ሥራ ሁሉ ፍፁም ጸጸት እንደሌለበትና የአሸናፊነት ስሜት እንደሚሰማውም ነገረኝ፡፡
  በዚህ ጨዋታችን መካከልም የእስረኞቹ መኪና መጣ፡፡ ሳሮዊዋ መኪናው ላይ ከሚጫኑት ዋንኛውና አንዱ ተረሻኝ ነበር፡፡ መኪናው ላይ ከወጣ በኋላ የተለየኝ በአውራ ጣቱ አሸናፊነት/የድል ምልክት እያሳኝ በፈገግታ እንደታጀበ ነበር ይላል ጋዜጠኛው ጆሽዋ፡፡ ኬን ሳሮዊዋ በሕይወቱ ጀምበር ማዘቅዘቂያ የመጨረሻ ሰዓት ላይ ጋዜጠኛው ወዳጁን በዚህ መልኩ ከተለየው በኋላ ሳሮዊዋና ሁለት ሌሎች እስረኞች ጥብቅ በሆነ የጥበቃ አጀብ ወደሚሰቀሉበት ፖርት ሐርኮት እስር ቤት ተወሰዱ፡፡
  ከመገደያቸው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ንስሐ ይቀበሉ ዘንድ አንድ እንግሊዛዊ ካህን ወደ ወኅኒ ቤቱ መጡ፡፡ በስፍራው የነበረ አንድ የዓይን ምስክር እንደገለጸው ሁለቱ እስረኞች ያለ ቅጥ እየተንሰቀሰቁ ሲያለቅሱ ሳሮዊዋ ተመልክቶ ጠጋ በማለት ለእናት ምድራቸው ናይጄሪያና ናይጄሪያውያን መሥዋዕት በመሆናቸው ሊኮሩ እንደሚገባቸው በመንገር በድፍረት የሞትን ጽዋ ይጠጡ ዘንድ ነበር ያበረታታቸው፡፡
  የሞት ፍርዳቸው በሚጸናበት ረፋድ ጠዋት ላይ ኬን ሳሮዊዋ አዘውትሮ ከከንፈሩ የማይነጥላትን ፒፓውን ለአባቱ እንዲሰጡለት ገዳዮቹን ተማጸነ፡፡ ጥያቄውን የተቀበለው ሰው ግን አልነበረም፡፡ ወዲያው የአምባገነኖቹ ቅጥረኛ የሆኑት ወታደሮች የእስረኞችን ዓይን በጥቁር ጨረቅ ሸፍነው ወደ መስቀያው ስፈራ እያጣደፉ ወሰዷቸው፡፡ ኬን ሳሮዊዋ የመጀመሪያው ተሰቃይ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በሚገርም ሁኔታ በኬን ሳሮዊዋ አንገት ውስጥ የተጠለቀው ገመድ ለአራት ጊዜያት ያህልም ቢበጠስም በአምስተኛው ግን እነዛ ጨካኞችና እብሪተኞች ሕይወቱን በስቅላት ከነፍሱ ነጠሏት፡፡
  ግዑዙ ገመድ እንኳን እምቢ ለፍትሕ፣ እምቢ ለእውነት ብሎ በኬን ጎን በቆመበት፣ በመሰከረበትና ባመጸበት በዛች ቅጽበት አምባገነኖቹ ልባቸውም ሆነ ዓይናቸው ታውሮ ይኼን እውነት ለመገንዘብ ሕሊናቸውም አእምሮቸውም ጨለመባቸዋልና ሊምሩት አልወደዱም፡፡ ወታደሮቹ ለጊዜውም ቢሆን ከዚህ እኩይ ድርጊታቸው፣ በክፉው፣ ሸካራና ጠማማ ጎዳና ላይ ከመገሥገሥ የሚያግዳቸው ምንም ምድራዊ ኃይል እንደሌለ ነበር ለናይጄሪያ ሕዝብና ለመላው ዓለም ለማሳየት የሞከሩት፡፡
  ታጋይ፣ ደራሲ፣ ጸሐፊ … የሆነው ኬን ሳሮዊዋ በናይጄሪያ ደቡብ ምስራቅ ጠረፍ በኒጀር ወንዝ ዳርቻ የሚኖር የኢጎኒ ብሔር ተወላጅ ነበር፡፡ በ54 ዓመት ዕድሜው በግፍ በገመድ ተንጠልጥሎ ለሕልፈት የበቃው ሳሮዊዋ በተለያዩት ጊዜያት በጋዜጦች ላይ ባቀረባቸው መጣጥፎች፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ የሰላ ትችቶቹ፣ በቴሌቪዥን ዝግጅቶቹና ዘገባዎቹ በድፍን ናይጄሪያ ከፍተኛ ተወዳጅነትንና ዝናን ለማትረፍ የቻለ ስመ ገናና ጸሐፊና ገጣሚ ነበር፡፡
  ‹‹ሶልጀር ቦይ›› የተሰኘ ወጥ የፈጠራ ሥራው ከአገሩ አልፎ ከበሬታን ያተረፈለትና ተነባቢ ሥራው ለመሆን በቅቶለታልም፡፡ ሳሮዊዋ በኑሮው የተደላደለ ቱጃር ለመሰኘት የሚችል፣ የግሉ የሆነ ፕሬስ መሥርቶ በመንቀሳቀስ ላይ የነበረና ይህ ጎደለው የማይባል ሰው የሚባል ዓይነት ቢሆንም እንኳን ናይጄሪያና ናይጄሪያውያን ዕጣ ፈንታ በአምባገነኖቹና በጨካኙ ወታደራዊ ኃይሎች እጅ መውደቁ እረፍት ስለነሣው አምባገነኖችን በብዕሩ አምርሮ ለመዋጋት ተነሣ ጀግና የብዕር ሰው ነበር፡፡
  ታጋዩና ደራሲው ኬን ከትውልድ ቀዬው በገፍ የሚቀዳው ጥቁር ወርቅ (የነዳጅ ዘይት) የናይጄሪያ 90 በመቶ የገቢ ምንጭ ከመሆኑም በላይ ለሙስናና ለምዝበራ ለተዘፈቁት ወታደራዊ ገዢዎች መንደላቀቂያነት ሲውል ታዝቧል፡፡ ሕዝቡ ይህ ነው በማይባል ድህነትና ጉስቁልና ውስጥ ተዘፍቀው አምባገነኖቹ እንዲህ መቀማጠላቸው የሕሊና እረፍት የነሣው ሳሮዊዋ ይህን ግፍ ለመበቀል ነበር ብዕሩን በድፍረት ያነሣው፡፡ በዚህም አምባገነኖቹንና ሙሰኞቹን ናይጄሪያውያንን ክፉኛ ነበር ያሰጨነቃቸው፡፡
  ደራሲና ታጋይ ኬን ሳሮዊዋ ሙያውን አክባሪና በሙያው ተደሳች እንደነበር ለእንግሊዛዊው ደራሲ ዊሊያም ማድዬ በጻፈው ደብዳቤ እንዲህ በማለት ነበር ማንነቱንና ሥራውን የገለጸው፡-
  በእጅጉ የማከብረውንና የምወደውን የኢጎኒ ሕዝብ እነዚያ አበሳውንና ፍዳውን በሚያስቆጥሩት ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎችን እንዲጋፈጣቸው ለማድረግ የሥነ ጽሑፍ ስጦታዬን እንደ ታላቅ መሳሪያ ለመጠቀም በመቻሌ በሕይወቴ ውስጥ ትልቁ ነገር ሆኖ ይመዘገባል፡፡ ብዕሬን ለወገኖቼ አርነት ማዋሌን ያህል ሚያስደስተኝ ነገር የለም፡፡ ለወገኔ የእኔ ድምፅ፣ የእኔ ጩኸት በጣሙን ወሳኝና አስፈላጊ ነበር፡፡
  በእጅጉ የሚደንቅ ነው!! ፖለቲከኛ ሆኜ እንዲህ ያለ ነገር ማድረግ አልቻልኩም፣ በንግዱ ዓለም ተሰማርቼ በነበር ወቅትም አልሳካልኝ ያለ ነገር ነበር፡፡ ብዕር አንስቼ ከወረቀት ጋር ማዋኻድ ስጀምር ግን ከባዱ ነገር ቀላል ሆነ፡፡ አልሳካ፣ ድምፁም አልሰማ ያለው ነፃነትና የፍትሕ ድምፅም ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ በምድሬ በናይጄሪያ ተሰምቶ አምባገነኖቹንና እብሪተኞችን መግቢያና መውጫ አሳጣቸው፣ እረፍትም ነሣቸው፡፡
  ብዕር …፣ ብዕር …፣ የብዕር ኃይል ምንጊዜም ያሸንፋል፡፡ ለእኔ ከዚህ በላይ ደስታ የለም፡፡ በዚህ ወቅት የፈለገው ነገር ቢመጣም በቆራጥነት ለመጋፈጥ ተዘጋጅቼያለኹ፡፡ እንደሚመስለኝ በዚህ ሰዓት ታላቅ የሆነ የሞራል ድል የተጎናጸፍኩት እኔ ነኝ፡፡ በጠላትነት የተነሡብኝ አምባገነኖች፣ ጠላቶቼ ከዘላለማዊ እፍረትና ጸጸት ከማያመልጡበት የሲኦል ቅርቃር ውስጥ እንደገቡ ሆነው ነው የሚሰማኝ፡፡ ነበር ያለው ያ ጀግና የብዕር ሰው!!
  በእያንዳንዱ ናይጄሪያዊ ሕዝብ፣ የአርነት ታጋዮችና በዓለም ሕዝቦች ሁሉ ዘንድ ብሎም የኪነ ጥበብ ወዳጆችና አፍቃሪዎች ልብ ውስጥ ኬን ሳሮዊዋ ዛሬም ነገም ሕያው ሆኖ ይኖራል፡፡ አባቻና መሰል አምባገነኖች ግን በአረመኔያዊ ግብራቸው ታሪክ በትዝብት ሲያስታውሳቸው ይኖራሉ፡፡
  በመጨረሻም በአገራችን ታላቅ የሆነ ብዕራዊ ተጋድሎ ያደረጉትን እነ ጸጋዬ ገ/መድኅንን፣ እነ አቤ ጉበኛን፣ እነ በዓሉ ግርማን አርአያ አድርገው ዛሬም ስለ እውነት፣ ስለ ፍትሕ፣ ስለ ነፃነት … በጨዋ፣ በታረመና ባላመነዘረ ብዕራቸው ተጋድሎ እያደረጉ ላሉ ኢትዮጵውያን ሁሉ ያለኝን አድናቆትና ክብር ለመግለጽ እወዳለኹ፡፡
  በአቤ ጉበኛና በበዓሉ ግርማ መንፈስ፣ ሌሎችም በዚህ ዘመን የእነርሱን ብዕር ቁርጠኝነትና ወኔ የተቀላቀሉ ኃያላንና ጀግኖች ብዕረኞች ለተገፉ ወገኖቻቸው፣ ለሰው ልጆች መብት፣ ለፍትሕና ለእውነት በመቆም በተባ ብዕራቸው ላደረጉትና እያደረጉት ላለው ታላቅ ተጋድሎ ሊዘከሩ የሚገባቸው የምን ጊዜም የኢትዮጵያ የብዕር ጀግኖቻችን ናቸውና ልናከብራቸው፣ ልንዘክራቸው ይገባናል ለማለት እወዳለኹ፡፡
  ሰላም! ሻሎም!


  0 0

  eppfየኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በዋልድባ አካባቢ ልዩ ስሙ ሰቋር እና አምቦ ጠበል በተባለ ቦታ በተከታታይ ሁለት ቀናት ከወያኔው የፈጥኖ ደራሽ ጋር ባደረገው የፊት ለፊት ውጊያ በጠላት ላይ ወታደራዊ የበላይነትን በመቀዳጀት አኩሪ የአርበኝነት ጀብድ ፈጸምኩ ሲል ለዘ-ሐበሻ በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ።

  የድርጅቱ ጋዜጣዉ መግለጫ “ የግንባሩ ሰራዊት በዋልድባ ልዩ ስሙ ሰቋር በተባለ ቦታ በሚያዚያ 8-2005 ዓ.ም የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ መመኪያ በሆነው የፈጥኖ ደራሽ ላይ በከፈተው የማጥቃት እርምጃ 21 የጠላት ወታደሮችን በመግደል 25 አቁስያለሁ” ካለ በኋላ በተመሳሳይ በሚያዚያ 9-2005 ዓ.ም በዋልድባ ልዩ ስሙ አምቦ ጠበል በተባለው ቦታ ውጊያ መካሄዱንና  በዚሁ እለትም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት 25 የወታደሮችን ገድሎ 39 በማቁሰል ከፍተኛ ድል የተቀዳጀ መቀዳጀቱን ጠቅሶ  በዚሁ አውደ-ውጊያ ላይም የተለያዩ የቡድንና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያዎችንም ከመሰል ጥይቶቻቸው ጋር መማረኩን አትቷል።

  “የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በሁለት ተከታታይ ቀናት ባደረጋቸው አውደ-ውጊያዎች ላይ በድምሩ 46 የፈጥኖ ደራሾችን ከጥቅም ውጭ በማድረግና 64 በማቁሰል የግንባሩ ሰራዊት የተሰለፈበትን ሐገራዊ ተልዕኮውን በመፈፀም በጠላት ላይ ከፍተኛ የሕይወትና የንብረት ኪሳራ በማድረስ አኩሪ የአርበኝነት ጀብድ ፈፅሟል።” ያለው የድርጅቱ መግለጫ “ የግንባሩ ሰራዊት ጥቃቱን በፈፀመበት አካባቢ የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎችም ስርዓቱ በሚያራምደው የግፍ አገዛዝ ከፍተኛ ምሬትና ተቃውሞ በማሰማት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊትም የጀመረውን ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን አስተዋፅዖ በማበርከት ሐገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ወደ ግንባሩ ሰራዊት እየተቀላቀሉ ይገኛሉ” ሲል ጋዜጣዊ መግለጫውን አጠናቋል።

  የአርበኞች ግንባር በበተነው ጋዜጣዊ መግለጫ ዙሪያ የኢሕአዴግ መንግስት የሚሰጠውን ምላሽ ለማካተት ያደርገነው ጥረት ባይሳካም፤ እስካሁን በይፋ የሰጠው ምላሽም የለም።


  0 0

  New Picture (5) ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተባረው ወደ ፍኖተ ሰላም ከተማ፤ ከፍኖተ ሰላም ከተማ ደግሞ እንደገና ወደ መጡበት በግዳጅ እንዲመለሱ የተደረጉት የአማራ ተወላጆች በርሃብ እየተቀጡ መሆኑን ኢሳት ራድዮ ዛሬ በስፍራው ያሉትን በማነጋገር ዘገበ። ለምግብነት የተሰጣቸው ዱቄት ወረርሺኝ እንዳመጣባቸው ያጋለጠው የኢሳት ዘገባ በቤንሻንጉል ጉምዝ ግዙፍ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ ነው ይላል። ያድምጡት።


  0 0

  51197D367BA550D871870C1D732FA_h296_w526_m2_bblack_q100_p100_cLzUgTDNf

  በእውነተኛ ፍቅር ውስጥ መሆንዎን ማወቅ ይፈልጋሉ?

  ከሊሊ ሞገስ

  ‹‹ጋብቻ ክቡር ነው መኝታውም ቅዱስ ነው››
  ሰዎች በህይወት ዘመናቸው ውስጥ ማከናወን ከሚገባቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ እና አብይ የሆነው ጋብቻ ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል ብዙ ቁጥር ያላቸው ሙሽሮችን የምንመለከተው፡፡ ይሁን እንጂ በተመሳሳይ መልኩ ባማረና በደመቀ ስነ ስርዓት ባይሆንም፣ በቁጥር /በብዛት/ የበለጠው ቡድን ከፍተኛ የሆነ ሽልማት ያገኛል የተባለ ይመስላል ክቡር የሆነውን ጋብቻ ረግጠውና ጥለው ትስስራቸውን ለመበጣጠስ የየፍርድ ቤቱን ችሎት የሚያጨናንቁ ባለትዳሮች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ሲሆን በሌላ በኩል የፈጠሩት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ሚዛኑን ደፍቶ መፍታት ሳይችሉ በመካከላቸው ሰላም፣ ፍቅርና ደስታ ጠፍቶ እንዲያው ለይስሙላ አብረው የሚኖሩት ቁጥር ደግሞ ከተፋቱት የሚበልጠው ነው፡፡ ይህንንም የሚያረጋግጠው ጥናታዊ መግለጫ ነው፡፡
  ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ ከተመሰረቱ ትዳሮች 1/3ኛው በጥንዶች መካከል እውነተኛ ፍቅር ሰላምና ደስታ በመጥፋቱ ትዳር በፍቺ ሊቋጭ ችሏል በማለት ሰሞኑን የገለፀው በተለያዩ የዓለማችን ክፍል በጋብቻ ዙሪያ ጥናት የሚያደርግ አንድ የተመራማሪዎች ቡድን ሲሆን፣ በተመሳሳይ ወቅት በዚሁ ጉዳይ /በጋብቻ/ ዙሪያ የሚያጠና ቡድን ከስድስት ጥንዶች /ባለትዳሮች/ መካከል ደስተኛና ሰላማዊ በመሆን የትዳር ህይወታቸውን ማስቀጠል የቻሉት /የቻለው አንዱ ትዳር መሆኑን ማረጋገጥ ችያለሁ ብሏል፡፡
  እንግዲህ ይህ በገሀዱ ዓለም የሚታየው እውነታ ለሁሉም ባይሆንም ለብዙዎች የጋብቻችን ክቡርነት የመኝታውም ቅዱስነት ማርከስ ማለት አይደለም ትላላችሁ?
  ይሁን እንጂ የጋብቻን ክቡርነት የመኝታውንም ቅዱስነት ጠብቆ መጓዝ የጥንዶቹ የውዴታ ግዴታ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህንን ግዴታ ለመወጣት ደግሞ ሰው ሆነን በመፈጠራችን የተሰጠን ትልቅ ብቃትና ፀጋ አለን፡፡ ነገር ግን ይህን ብቃታችን ተጠቅመን በጋብቻ ውስጥ መኖር ያለበትን ሰላም፣ ፍቅርና ደስታ እያጣጣምን ለመኖር ስላለንበት ዘመን እውነታ፣ ስለ እውነተኛ ፍቅር ምንነት እና ስለ ትዳር ጠንቅቀን ማወቅ ግድ ይለናል፡፡ ለዛሬ በዚህ ዙሪያ ጥቂት ለማለት ወደድን፡፡
  መልካም ንባብ

  በእርግጥም ሁሉም ጥንዶች /ተጋቢዎች/ በወግ በማዕረግ ተውበውና ተሞሽረው በደመቀ የሠርግ ስነ ስርዓት ትዳራቸውን መመስረት መፈለጋቸው የማይታበል ሀቅ ነው፡፡ በመሆኑም ሁሉም እንደየአቅሙ ወይም እንደ ገቢ መጠኑ ወይም እንደየአስተሳሰቡ ከእወቁልኝ ካርድ እና በጣት የሚቆጠሩ ታዳሚዎች ከማሳተፍ ጀምሮ አገር ጉድ የሚያሰኝ ድል ያለ ሠርግ በመሰረግ የትዳር ህይወቱን አንድ ብሎ ይጀምራል፡፡ ይሁን እንጂ እዚህ ጋር ልብ ሊባል የሚገባው ትልቁ ነገር የትኛውም አይነት የሠርግ ስነ ስርዓት በተጋቢዎች መካከል ዘላቂነት ያለው እርካታና የደስተኝነት ስሜት ለማምጣት ምንም አይነት አስተዋፅኦ እንደሌለው ወይም ለዘላቂ ደስተኝነታቸው ዋስትና ሊሆን እንደማይችል ነው፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ከፍተኛ የገንዘብ ወጪ የተደረገባቸውና ብዙ የተደከመባቸው ሠርጎች ተጋቢዎቹ /ጥንዶቹ/ የሽርሽር ጊዜያቸውን ሀኒሙኒያቸውን ሳይጨርሱ በመካከላቸው ሰላምና ደስታ እየራቀ ሲሄድ ይስተዋላል፡፡
  ምንም እንኳ እውነታው ይህ ቢሆንም፣ ማንኛውም ትዳር ዘላቂነት ያለው ደስታ፣ ፍቅርና ሰላምን በውስጡ እንደያዘ ለሁልጊዜም መጓዝ ይችላል የሚሉት የዘርፉ ተመራማሪ ሊቃውንቶች፣ ይህ ሊሆን የሚችለው ግን ጥንዶቹ በተናጥልም ሆነ በጋራ ለትዳራቸው የጋራ ጥቅም በእውነተኛ ስሜትና ፍላጎት ሲያስቡና ሲሰሩ ነው ይላሉ፡፡ አክለውም ነገር ግን እዚህ ጋር ሊሰመርበት የሚገባው ጉዳይ ጥንዶች ወደ ትዳር ህይወት ከመግባታቸው በፊት አንድ አስደሳች እና ማራኪ ትዳር ለመመስረት የሚጠይቀውን መስፈርት አስቀድመው ማሟላት የቻሉ እንደሆነ ነው ብለዋል፡፡
  በእርግጥ በባለ ትዳሮች መካከል ዘላቂነት ያለው አስደሳችና ሰላማዊ የትዳር ህይወትን ሊያስገኝ ወይም ሊያመጣ የሚችል አንድ አይነት የሂሳብ ቀመር ወይም መመሪያ ባይገኝም፣ ምናልባት በእውነታው ዓለም ውስጥ ያለ የየራስ መሻታቸውን ለማርካት ትዳሩ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ካበረከተ በጥንዶቹ መካከል ቀጣይነት ያለው ደስተኝነትና ፍቅር ሊኖር ይችላል፡፡ ይህን እንደ መመሪያ ወይም ቀመር መውሰድ ሁላችንንም ሊያስማማ ይችላል፡፡ ማለትም አንድ ሰው በትዳሩ ወይም በትዳር አጋሩ ደስተኛ መሆን የሚችለው በትዳሩ ውስጥ የኑሮ እና የአጋርነት ዋስትና የማግኘት ፍላጎቱ፣ የሁልጊዜ ተወዳጅና ተፈቃሪ የመሆን ፍላጎቱ፣ በተጓዳኙ ዘንድ አስፈላጊና ጠቃሚ ሰው ስለመሆኑ እውቅና የማግኘት ፍላጎቱ /recognition/ እና ሌሎች መሰረታዊ ፍላጎቶቹ ሁሌም መርካት የቻሉ እንደሆነ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ፍላጎቶችን ማሟላት በራሱ ፈታኝ መሆኑ እንዳለ ሆኖ እነዚህ ፍላጎቶች በተሟሉበት ሁኔታ ውስጥ በባለ ትዳሮች ሰላማዊና አስደሳች የፍቅር ሕይወት ላይ ጥላውን የሚያጠላው አሁን የሚታየው ዘመናዊ አኗኗር /Modern living/ የፈጠረው ችግር መሆኑ ይታመናል፡፡
  ማለትም ዘመኑ በወለደው ዘመናዊ አኗኗር ውስጥ የተፈጠረው ያልተረጋጋ ኢኮኖሚ /የገቢና ወጪ አለመመጣጠን/ ከፍተኛ ውጥረትና ጭንቀት፣ የጊዜ እጥረት፣ የሰላም መጥፋት፣ ከፍተኛ የጥሎ ማለፍ ውድድርና ሌሎች ለዘመናችን ባለትዳሮች አስደሳች የትዳር ህይወት መጥፎ መሰናክል እንደሆኑ ይታመናል፡፡
  ይሁን እንጂ እነዚህ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ወይም መሰናክሎች ለዘመናችን ባለትዳሮች ፈታኝ መሆናቸው የማይታበል ሀቅ ቢሆንም ማንኛውም ሰው በየዘመኑ የሚያጋጥሙትን አስቸጋሪና ፈታኝ ሁኔታዎች በጣጥሶ በድል በማለፍ ካሰበውና ካለመው ለመድረስ የሚስችል ተፈጥሯዊ ብቃት ባለቤት ስለመሆኑ የቀደሙትም ሆኑ የዘመናችን ስኬታማ ባለትዳሮች ህያው ምስክሮች ናቸው፡፡ በመሆኑም ወጣቶች የግልም ሆነ የጋራ ፍላጎታቸውን የማሳካት ጽኑ እምነትና የተቀራረበ ስብዕና ወይም ስነ ልቦና ባለቤት ከሆኑ ዘላቂ ደስታ፣ ፍቅርና ሰላም የሰፈነበት የትዳር ህይወት መምራት እንደሚችሉ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡
  እንግዲህ ስለ ትዳር ወይም ጋብቻ ስናነሳ በጥንዶቹ መካከል የሚፈጠረው ፍቅር መሰረታዊና ቀዳሚ ጉዳይ ስለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ በመሆኑም በአጠቃላይ ስለ ፍቅር ወይም ስለ ፍቅር ትርጓሜ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ለማየት እንሞክር፡፡

  ፍቅር
  ፍቅር ማለት አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር ጠንካራና የጠበቀ የግል ግንኙነት እንዲኖረው እና ያፈቀረውን ሰው ደስታና ደህንነት እንዲሁም ሌሎች ፍላጎቶች የማሟላት ብሎም የበለጠ የማሳደግ ከፍተኛ ፍላጎትና ኃላፊነት እንዲያድርበት የሚስችል እውነተኛ ስሜት ማለት ነው፡፡ በፍቅር ውስጥ ያለ ሰው የውዴታ ደረጃው፣ የጠለቀ ፍላጎት፣ የተቆርቋሪነት ስሜት እና ሌሎቹ መልካም ፍላጎቶችን በየጊዜው እየገነባ እና እያዳበረ ይሄዳል፡፡
  ፍቅር ማለት ያፈቀሩትን ሰው መርዳት ወይም ማወቅ ማለት ነው፡፡ ከጠለቀ እውቀት፣ ከአስተዋይነት እይታ እና ከዳበረ ልምድ የፈለቀ ጥልቅ መረዳት፡፡ ያፈቀሩትን ሰው መረዳት ወይም ጠንቅቆ ማወቅ ማለት ስለ ግለሰቡ ስሜት፣ ፍላጎት፣ ባህሪ፣ ጉድለትና ሌሎች በቂ እውቀት ማግኘት ማለት ነው፡፡
  ስላፈቀረው ሰው በቂ መረዳት ያለው አፍቃሪ፣ ያፈቀረውን ሰው ስሜት የሚጎዳ ድርጊት የመፈፀም አጋጣሚም ሆነ የሚያስቀይም ቃል የመናገር እድል አይኖረውም፡፡ በመሆኑም በእውነተኛ ፍቅር ውስጥ ባሉ ጥንዶች መካከል የሚኖረው አለመግባባት /misunderstanding/ አነስተኛ ወይም ከቁጥር የማይገባ መሆን ይችላል፡፡
  ፍቅር ማለት እምነት ወይም መተማመን ማለት ነው፡፡ ፍቅር ማለት ፍቅረኛሞች እርስ በእርሳቸው በሚኖራቸው ውህደት ወይም ቁርኝት፣ ታማኝነት እና ፍትሀዊነት ወይም ሚዛናዊነት ላይ እርግጠኝነት እንዲሰማቸው የሚያደርግ እምነት ወይም መተመመን ማለት ነው፡፡ ይህም አፍቃሪው ለተፈቃሪው የገባውን ቃል አክባሪነቱንና ታማኝነቱን ስለሚያረጋግጥ ተፈቃሪው በአፍቃሪው ላይ ሙሉ እምነትና መተማመን እንዲያሳድር ከማድረጉም ባሻገር የራሱንም ታማኝነትና እውነተኝነት ጠብቆ እንዲዘልቅ ያስገድደዋል፡፡ በዚህም ተፈቃሪዎች ሙሉ እና እውነተኛ የርስ በርስ መተማመን መፍጠር ይችላሉ፡፡
  ፍቅር ማለት አንደኛው ለሌላኛው ቅድሚያ የሚሰጥበት እና አንድነትን በመፍጠር ወገናዊነቱን የሚያሳይበት መድረክ ነው፡፡ ያፈቀሩትን ሰው መሻትና ፍላጎት እውን ይሆን ዘንድ የራስን /የግልን/ ፍላጎት፣ ደስታና ስሜት አሳልፎ መስጠት ወይም መስዋዕት ማድረግ ጎልቶ የሚታይበት መድረክ ነው፡፡ ይህ መድረክም ተፈቃሪው የራሱን ስሜትና ፍላጎት ለአፍቃሪው አሳልፎ የመስጠት ዝንባሌና ፍላጎት እንዲያድርበት ያደርጋል፡፡ በዚህም ለተፈቃሪዎች የየግል ፍላጎትና መሻታቸውን አንደኛው ለሌላኛቸው አሳልፈው ለመስጠት ወይም መስዋዕት ለማድረግ ፈቃደኝነት እና ዝግጁነት እንዲኖራቸው ማድረግ ያስችላል፡፡ እንግዲህ ይህ ደረጃ በደረጃ በጥንዶች መካከል የሚፈጠረው ህብረት ወይም አንድነት የሚገለፅበት የላይኛው እርከን ነው፡፡
  ፍቅር ማለት በትልቅ ስሜት መዋደድ ወይም የፍቅርን ስሜት በተዋበና ባማረ መልኩ መግለፅ ማለት ነው፡፡ የፍቅር ስሜትን ወይም በግንኙነት የሚፈጠር ደስታና እርካታና ላፈቀሩት ሰው የሚገልፁበት ማራኪና ቀልብ ገዢ ድርጊታዊ እንቅስቃሴ ወይም አርት ማለት ነው፡፡
  አፍቃሪው ከተፈቃሪው ሰው ጋር ሲገናኝ የሚተቃቀፍበት አስተቃቀፍ የወደደውንና የተመኘውን ገላ የሚደባብስበት አደባበስ፣ አብረው የእግር ጉዞ ሲያደርጉ /ሲንሸራሸሩ/ እጆቿን/ቹን የማይዝበት/የምትይዝበት አያያዝ፣ ወገቧን/ወገቡን የሚያቅፍበት/የምታቅፍበት አስተቃቀፍ፣ ከንፈር ለከንፈር የሚሳሳሙበት አሳሳም በቃ ምን አለፋችሁ አጠቃላይ እንቅስቃሴና ድርጊቱ/ቷ ውበትና አርት የተላበሰ መሆኑ የተፈቃሪውን ልብ በሀሴት ጮቤ ከማስረገጡ ባሻገር ተመሳሳይ ወይም የበለጠ ምላሽን እንዲሰጥ ያደርገዋል፡፡ እንግዲህ ይህ ሁኔታ በፍቅረኛሞች መካከል ያለውን ጥልቅ ፍቅር በተለየ መልኩ ማስኬድ የሚቻልበት ሂደት ነው፡፡
  እንግዲህ በፍቅረኛሞች መካከል የሚፈጠረው እውነተኛ ፍቅር ማለት ከላይ እንዳየነው ሲሆን፣ ለትዳር ህይወት መቀዝቀዝ ምክንያት የሚሆኑ ተጨማሪ ነገሮችን ለማየት እንሞክር፡፡ ፍቅረኛሞች ደስተኛና ስኬታማ የትዳር ህይወት ለመምራት ሁለቱም ግለሰቦች በየግላቸው ፍቅር መስጠትና መቀበል ወይም ከላይ የተገለጡትን መግለጫዎች መተግበር ይኖርባቸዋል፡፡ አለበለዚያ በአንድ ወገን ብቻ የሚደረግ ጥረት/ፍቅር መስጠት ውጤታማ ሊሆን አይችልም፡፡ ማለትም አልፎ አልፎ አንዳንድ ተፈቃሪዎች ፍቅርን የመስጠት ብቃታቸው ወይም ስሜታቸው በእጅጉ የተጎዳ የሚሆኑበት አጋጣሚ አለ፡፡ ምናልባትም በአስተዳደጋቸው ወይም በሆነ ወቅት የደረሰባቸው በደል እንደ አስገድዶ መድፈር ያለ መጥፎ ጠባሳ ወይም በሌላ ተመሳሳይ ምክንያት የተፈጠረባቸው ችግር ሊሆን ይችላል፡፡ በመሆኑም እነዚህ ሰዎች ፍቅርን መስጠት እና መቀበል በተለይም ፍቅር የመስጠት/የፍቅር ስሜታቸውን መግለፅ ብቃትና ችሎታቸውን መልሰው ማምጣት የሚችሉበትን የስነ ልቦና ህክምና ከማግኘታቸው በፊት ወደ ትዳር ህይወት መግባት እንደሌለባቸው ይመክራል፡፡ ምክንያቱም ስኬታማ የትዳር ህይወትን ለመምራት ፍቅርን መስጠትና መቀበል ወይም ሌላውን የማፍቅር ፍላጎት መሰረታዊ በመሆኑ ነው፡፡
  ሌላው ለትዳር መፍረስ ወይም ደስተኛ የትዳር ህይወት ላለመምራት ተጠቃሽ ምክንያት የሚሆነው ተፈቃሪዎች ወደ ትዳር ከመግባታቸው በፊት የሚመሰርቱት ፍቅር እውነተኛ ወይም ፍቅር የሚመስል ነገር ፍቅር ያልሆነ ጊዜያዊ ስሜት (infatuation) መሆን አለመሆኑ ለይተው ላያውቁ ወይም እውነተኛ ፍቅር መስሏቸው መጀመራቸው ነው፡፡ በእርግጥ አንድ በፍቅር ስሜት ውስጥ ያለ ‹‹ያፈቀረ ሰው›› የያዘው ፍቅር ከእውነተኛ ስሜት የመነጨ ፍቅር ይሁን ከተመለከተው አካላዊ ቁመና ወይም ከተፈጠረበት የወሲብ ስሜት የመነጨ የፍቅር ስሜት ይሁን በቀላሉ ለመለየት ያዳግተዋል፡፡ ይሁን እንጂ እውነተኛ ፍቅር ማለት ከላይ ለማየት እንደሞከርነው፣ ያፈቀሩትን ሰው የማወቅ፣ የመተማመን፣ የመተባበር ወይም አንድነትን የመፍጠርና ሌሎች እውነታዎች በውስጡ የያዘና ጊዜ የሚጠይቅ ነው፡፡ በመሆኑም እውነተኛ ፍቅር ረዘም ያለ ጊዜ የሚጠይቅ እንጂ በአንድ ቀን ወይም ሳምንት ወይም ወር ውስጥ የሚፈጠር አይደለም፡፡ በአይናችን አይተን ስለተማረክን ወይም በወሲብ ስሜት (መሻት) የሚፈጠር ፍቅር ብዙ ጊዜ ፍቅር የሚመስል ጊዜያዊ ስሜት ሲሆን ተፈቃሪዎች ወደ ትዳር ካመሩ አልፎ አልፎ ግንኙነታቸው ወደ እውነተኛ ፍቅር የመሸጋገር እድል ቢኖረውም በአብዛኛው ግን በሰላም እና ደስታ ማጣት ብሎም በመለያየት (በፍቺ) የሚደመደም ይሆናል፣ እንዲሁም ወሲብን (ከወሲብ መጣጣምና እርካታን) ብቻ መሰረት በማድረግ የሚመሰረት ጋብቻም ተመሳሳይ እጣ ፈንታ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡
  በአጠቃላይ ለአንድ ትዳር ዘላቂ ሰላም፣ ደስታ እና እርካታ የጎላ ድርሻ ያለውን እውነተኛ ፍቅር ሁሉም እንዲኖረው የሚመኘው፣ ነገር ግን ጥቂቶች ብቻ የሚያጣጥሙት ቢሆንም ሀቁ ይህ ሊሆን የቻለው ከራሳችን ድክመት እንጂ ከእውነተኛ ፍቅር ባህሪ እና መገለጫ ወይም ተአምራዊነት አለመሆኑን ሁላችንም አምነን ልንቀበለው ይገባል፡፡ እንዲያውም ማወቅና መገንዘብ የሚገባን እውነተኛ ፍቅር ማለት ለሁሉም የሰው ልጅ የተሰጠ ተፈጥሯዊ ፀጋ እና በጊዜ ሂደት ውስጥ በቀላሉ ማግኘት የሚቻል ቅዱስ ነገር እንደሆነ ነው፡፡

  በእውነተኛ ፍቅር ውስጥ መሆን አለመሆንዎን ማወቅ ይፈልጋሉ?
  እንግዲያውስ ከታች የተዘረዘሩትን ጥያቄዎች በጥንቃቄ መርምረው ይመልሱ

  ከፍቅረኛዎት ወይም ከትዳር አጋርዎት ጋር አንድ ላይ በሚሆኑበት ወቅት ወይም በሆነ ርዕስ በሚነጋገሩበት ወቅት ወይም የሆነ ስራ በጋራ በሚያከናውኑበት ወቅት የደስታ ስሜት ይሰማዎታል?

  ከፍቅረኛዎ ወይም ከትዳር አጋርዎ ጋር ረዘም ላለ ሰዓት በሆነ ጉዳይ በሚወያዩበት ወቅት እርስ በርስ ከመሰለቻቸት ውጭ መሆን ይችላሉ? መሰረታዊ ፍላጎቶቻችሁ በተቀራራቢ ወይም በተመሳሳይ ነገሮች ላይ ነው? ብዙ ጊዜ ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ ሀሳቦች /እና አላማዎች ይኖራችኋል? እርስ በርስ በጥልቀትና በእርግጠኝነት እንተዋወቃለን፤ ወይም ፍቅረኛዬን አውቀዋለሁ እረዳዋለሁ ይላሉ?

  ከትዳር አጋርዎ የያዞት ፍቅር ከማንነታቸው እንጂ ከላይ ካዩት አካላዊ ውበት ወይም ካገኙት ወሲባዊ እርካታ ስላለመሆኑ እርግጠኛ ነዎት?

  አልፎ አልፎ ለሚያጋጥማችሁ የሀሳብ ልዩነቶች እና አለመግባባቶች መፍትሄ ለመስጠት ወይም ወደ ጋራ ስምምነት ለመምጣት ተስማሚ /ተደራዳሪ/ ይሆናል?

  አልፎ አልፎ የሚፈጠሩ ንትርክና ጭቅጭቆች የተሻለ መፍትሄ በማግኘት ይቋጫሉ?

  አንድ ነገር ሲያስቡም ሆነ ሲያቅዱ እኔ በሚል ሳይሆን /እኔና ፍቅረኛዬ/ በሚል ስሜትና መንፈስ ነው?

  ፍቅረኛዎን ወይም የትዳር አጋርዎን ሁሌም ለማስደሰት ይሞክራሉ?

  ሰዎች በሚሰበሰቡበት ስፍራ ከፍቅረኛዎ ወይም ከትዳር አጋርዎ ጋር ሆነው መታየትዎ የኩራትና የደስታ ስሜት ይፈጥርቦታል?

  በመካከላችሁ ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ የተለያዩ ጥናቶችን በማካሄድ ለተግባራዊነቱ በሙሉ አቅምዎ ይጥራሉ?

  ልብ ይበሉ፡-
  ከላይ ለተዘረዘሩት ጥያቄዎች መልስዎ ‹‹አዎ›› በትክክል የሚል ከሆነ በእውነተኛ ፍቅር ውስጥ ለመሆንዎ ምክንያታዊ ማረጋገጫ አገኙ ማለት ነው፡፡
  መልካም የትዳር ህይወት


  0 0

  sewenet Bishaw
  ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሠውነት ቢሻው የተወሰኑ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች በተለያዩ ጊዜዎች እያደረሱባቸው የሚገኘው ጫና ሥራቸውን በአግባቡ ለማከናወን እንዳይችሉ እንዳደረጋቸው በመግለጽ ጫናው በእርሳቸውና በቤተሰባቸው ላይ ጉዳት ይደርሳል የሚል ስጋት ስለፈጠረባቸው « መንግሥት ጥበቃ ያድርግልኝ » ሲሉ መጠየቃቸውን መንግስታዊ ሚዲያዎች ዛሬ ዘገቡ።
  አሰልጣኙ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጻፉትና ለመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፣ ለፌዴራልና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ፣ለስፖርት ኮሚሽን ፣ ለኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እንዲሁም ለመንግሥትና ለግል የመገናኛ ብዙኃን በግልባጭ ባሳወቁት ደብዳቤያቸው ላይ እንደገለጹት የተለመደ ስራቸውን ለማከናወን ስቴዲየም በሚገኙባቸው አጋጣሚዎች ከተወሰኑ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች እየደረሰባቸው የሚገኘው ከስፖርቱ ስነ ምግባር ውጪ የሆነ ድርጊት በስራቸው ላይ ጫና ፈጥሮባቸዋል። ይህ ድርጊት በእርሳቸውና በቤተሰባቸው ላይ አደጋ ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት ስለፈጠረባቸው መንግሥት ጥበቃ እንዲያደርግላቸው ለመጠየቅ አስገድዷቸዋል።
  አሰልጣኝ ሰውነት በፊርማቸው አስደግፈው በላኩት መግለጫ ፤ እነኝህ «የተወሰኑ » ሲሉ የገለጿቸው የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች የካቲት 26 ቀን 2005ዓ.ም ብሔራዊ ቡድኑ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከቤኒን አቻው ጋር በአዲስ አበባ ስቴዲየም በተጫወተበት ወቅት የእርሳቸውንና የቡድኑን ተጫዋቾች ስብዕና የሚነካ ስድብና ዘለፋ በመሰንዘራቸው ተጫዋቾቻቸው ውጤት እንዳያስመዘግቡ እንቅፋት ሆነዋል ብለዋል።
  በተመሳሳይ መጋቢት 15 ቀን 2005ዓ.ም ብሔራዊ ቡድኑ ከቦትስዋና አቻው ጋር በአዲስ አበባ ስቴዲየም ባደረገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ እነዚሁ ደጋፊዎች « ሠውነት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ገዳይ፤ ሠውነት ጋዳፊ » እያሉ የስራ ነጻነታቸውን ፣ ሞራላቸውንና ስብዕናቸውን የሚፈታተኑ አጸያፊ ቃላት እንደወረወሩባቸው በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።
  «ይህ ድርጊት በስሜታዊነት የተሰነዘረ ነው ብዬ ለማለፍ ብሞክርም ሁኔታው ከመቆም ይልቅ ፍጹም በተደራጀ መልኩ ተከስቷል » በማለት በመግለጫቸው የጠቀሱት አሰልጣኝ ሠውነት ፤ ሚያዚያ 5 ቀን 2005 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቡና እና የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለቦች ባደረጉት ጨዋታ ላይ ድርጊቱ ከቀድሞው በበለጠ መልኩ መከሰቱን አስታውቀዋል።
  ይህ ሁኔታ በማንኛውም ጊዜ በእርሳቸውና በቤተሰባቸው ላይ አደጋ ይደርሳል የሚል ስጋት እንዲያድርባቸው እንዳደረገ በመግለጫቸው ገልጸዋል። በመሆኑም ስራቸውን ተረጋግተው እንዲሰሩ መንግሥት ሁኔታውን ተከታትሎ የማያዳግም መፍትሔ እንዲሰጣቸውና ፣ ለእርሳቸውና ለቤተሰባቸው ጥበቃ እንዲደረግላቸው በመግለጫቸው ጠይቀዋል።
  የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት ምላሽ ክለባቸው ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ እንደሚሰጥ በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ ሚዲያዎች መዘገባቸውን የዘሐበሻ ወኪሎች አስታወቀዋል።


  0 0

  በታምሩ ገዳ (ጋዜጠኛ)

  በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው አስከፊ የሰብአዊ መብት ረገጣ ይቆም ዘንድ እያንዳንዱ ዜጋ የበኩሉን አሰተዋጽኦ ሊያበረክት እንደሚገባው እና ከራሱ ጋር መነጋገር እንዳለበት ተገለጸ፡፡ይሄ የተገለጸው እርቲስት እና እክቲቬስት ታማኝ በየነ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን ኢሳት የተመሰረተበት 3ኛ አመት እና ጣቢያውን ለማጠናከር ባለፈው ቅዳሜ ሚያዚያ 13 2013 እኤአ በ አሜሪካው የካሊፎርኒያ ግዛት በሎሳንጀለስ ከተማ በተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ በመገኘት ለተሰበሳቢዎች እና ለኢሳት አጋሮች በሰጠው አሰተያየቱ ነው፡፡

  በተለይ አርቲስት ታማኝ የህብር ራዲዮ ዘጋቢ ከሆነው ከዚህ ጸሃፊ (ከታምሩ ገዳ )ጋር ከገቢ የማሰባሰብ ፕሮግራሙ በሁዋላ ባደረገው ቃለምልልስ “ሌላው ቢቀር ልጆቻችን አገራቸውን ጥለው እንዳይሰደዱ እና በአገራቸው ተደላድለው እንዲኖሩ ለማድረግ በአገር ቤት በመካሄድ ላይ ያለውን የግፍ ቀንበር ልንሰብረው ይገባናል፡በሶስት ሺህ ዘመን አለም በተለያዩ የኢኮኖሚ እድገት ላይ ሲገኝ እኛ ግን ከሁሉ አገር በታች በደመ ነፍስ በሚነዳ እና ህግ በሌለበት ብቸኛ አገር ውስጥ እንገኛለን፡፡” ያለው አርቲስት ታማኝ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ጥረት ማድረግ እንዳለበት አስረግጦ የተናገረ ሲሆን አስተያየቱን ሲያራዝምም “እኛ እናልፋልን ነገር ግን ቢያንስ ልጆቻችን ተድላድለው እንዲኖሩ ይህን በደል የማስቆም የሞራል ግዴታ አለብን፡ እነ ታማኝ ወይም እነ እገሌ ምን አደረጉ? የሚባልበት ወቅት ሳይሆን ለምንድን ነው አገሬ ውስጥ ዘወትር ችግር ብቻ የምሰማው? እንደሌሎች አገሮች መሆን የተሳነን ለምንድን ነው? ሲል እያንዳንዱ ዜጋ እራሱን እንደዜጋ ሊጠይቅ ግዴታ አለበት፡፡”ብሏል፡፡

  አርቲስት እና አክቲቬስት ታማኝ በየነ

  አርቲስት እና አክቲቬስት ታማኝ በየነ


  ኢሳትን የመሳሰሉ ነጻ የመረጃ ምንጮች ይስፋፉ ዘንድ ምን መደረግ እንዳለበት የሚያስተላልፈው መልእክት ካለ ተብሎ ከህብር ራዲዮ ለቀረበለት ጥያቄ አርቲስት እና አክቲቬስት ታማኝ ሲመልስ” ይህ አይነቱ ሃሳብ ነው ሊበረታታ የሚገባው ከዛሬ ሶስት አመት በፊት ኢሳት አልነበረም:: ዛሬ ግን ጋምቤላ ውስጥ ችግር ሲፈጠር በኢሳት አማካኝነት ትሰማዋለህ :፡የአማራ ክልል ተወላጆች ከተለያዩ እካባቢዎች በግፍ ሲባረሩ ኢሳት ላይ ወዲያውኑ ትሰማዋለህ:: በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ በደል ሲደርስ እንደዚሁ ኢሳት ላይ መረጃውን ትሰማዋለህ፡፡በመረጃ የተደገፈ ዜና ለማግኘት ህዝቡ አስተዋጽኦ ማድረግ አለበት፡፡የህቺ እንግዲህ በሶስት አመት ውስጥ የተገኘ የሁላችን የጥረት ውጤት ነው ፡፡ ሶስት አመት በጣም ትንሽ ጊዜ ነው ፡፡ኢሳት የሶስት አመት ልጅ ነው ፡፡ ልጅን ስናሳድግ ደግሞ ይታመምብናል: ምግብ አይስማማውም፡ብርጭቆ ይሰብራል ይሄን ሁሉ እየተከታተልክ አይደል ልጅህን የምታሳድገው?ኢሳትም እንዲሁ ደካማ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ሁሉም ሰው በመተባበር የተሟላ የሚዲያ ተቋም ሊያደርገው ይችላል፡፡ለዚህ መሰሉ በጎ ተግባራት አስተዋጽኦ ማድረግ የእያንዳንዱ ዜጋ ግዴታ ነው፡፡” ብላል፡፡ በስተመጨረሻም የተጠናከረ ስራ ለማካሄድ ምን መደረግ አለበት? ለሚለው ጥያቄ ሲመልስ “ አያንዳንዱ ዜጋ ከራሱ ጋር ይነጋገር:: ወደዚህ ምድር ላይ የምጣሁበት ተልኮዮ ምንድን ነው ? ምን አድርጌ ነው የምሄደው? በእየ ወሩ ለቤተሰቤ 300 ወይም 400 የአሜሪካ ዶላር መላክ? በ ተሻለ ቤትውስጥ ለመኖር ወይም ዘመናዊ መኪና ለማሽከርከር የተሻለ ልብስ ለመልበስ ነው ወደዚህ አለም የመጣነው? እንደእኔ እምነት አገራችን ወደ ተሻለ ደረጃ እንድትሸጋገር ጥረት ማድረግ እያንዳንዱ ዜጋ በሚችለው እና አቅሙ በፈቀደው መጠን ብሄራዊ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል ፡፡ቁጭ ብሎ መተችት ለውጥ አያመጣም፡፡አስተዋጽኦ ማድረግ አለብን፡፡በምናምንበት መንገድ በምንም ይሁን የእኔ ፍላጎት እና ስሜት የሚያደላው በዚህ ላይ ስለሆነ እስተዋጽኦ ማድረግ እፈልጋለሁ ብሎ በጉልበት ይሁን በእውቀት በምክር ሊሆን ይችላል ፡፡ይሄ የጥቂት ወገኖች እህላፊነት ተደርጎ መወስድ የለበትም ፡፡ የሁሉም ወገን እርብርቦሽ ሊሆን ይገባል ፡፡” ብሏል::

  በዚህ የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም ላይ ለተገኙ በመቶዎች ለሚቆጠሩ የሎሳንጀለስ ከተማ ነዋሪዎች የገዢው የኢሃአዲግ መንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያዎች የሆኑት የመገናኛ ብዙሃናትን ጨምሮ ከተለያዩ የአገር አቀፍ እና የአለማቀፍ የዜና አውታሮች ያሰባሰባቸው በምስል እና በጽሁፍ የተደገፉ ማስረጃዎችን ለታዳሚዎቹ በማቅረብ በኢትዮጵያ ወገኖች ላይ በ ሀገር ውስጥ ሆነ በውጪ ሀገራት የደረሱት እና በመድረስ ላይ ያሉትን ዘግናኝ የሆኑ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ለግንዛቤ ማስጨበጫነት ይረዳ ዘንድ ያቀረበ ሲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለአንድ አፍታ ቆም ብሎ የት ላይ እንደሆንን እና በወገኖቻችን ላይ ምን አይነት ግፍ እየትፈጸመ እንደሆነ ሊያስተውል ይገባል ሲል ወገናዊ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

  ወጣት ሄኖክ የሼጥላ ግጥሙን ለታዳሚዎች ሲያሰማ (ከግራ ወደ ቀኝ ሃጄ ነጂብ መሃመድ እና አርቲስት ታማኝ በየነ)

  ወጣት ሄኖክ የሼጥላ ግጥሙን ለታዳሚዎች ሲያሰማ (ከግራ ወደ ቀኝ ሃጄ ነጂብ መሃመድ እና አርቲስት ታማኝ በየነ)


  በገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን በመወከል ንግግር ያደረጉት እውቁ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሃጂ ነጂብ መሃመድ “ ህገመንግስታዊ መብታችን ይከበር ያሉ ሙስሊም ወገኖቻችን ካለፈው አንድ አመት ትኩል ጀምሮ በአገዛዙ የጸጥታ ሃይሎች ለእስራት ፡ ለግርፋት እና ለስደት የተዳረጉበት የመብት ጥያቄያቸው ስር ሰዶ እና የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ድጋፍ አግኝቶ አሁን ካለንበት ደረጃ ደርሷል፡፡ከዚህ በሁዋላ ወደ ሁዋላ መመለስ ትልቅ ስህተት ስለሚሆን በተያያዝነው ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ክርስቲያኑ እና ሙስሊሙ ማህበረሰብ እጅ ለእጅ ተያያዞ አገዛዙን በቃህ ሊለው የግድ ይላል፡፡” ብለዋል፡፡ ሃጂ ነጂብ ንግግራችውን በማራዘም “ነብዩ መሃመድ ተከታዮቻቸው በ1034 አመት በፊት በመካከለኛው ምስራቅ ግድያ እና እንግልት በበዛባቸው ወቅት ሴት ልጃቸውን ጨምሮ ወደ ኢትዮጵያ (ሃበሻ መሬት) ሄዱ በዚያ ማንንም ሰው የማይበድል ክርስቲያን መሪ አለ በማለት ጎረቤት አገሮች የሆኑትን አነ ሶሪያ እና የመንን ትተው ወደ ኢትዮጵያ እንዲሰደዱ አዘዋል ፡፡ ታዲያ የተገፉ ወገኖችን በመቀበል ለአለም አርያ የነበረች አገር ኢትዮጵያ ዛሬ በኛ ዘመን እንዴት አላህ ዋክበር!!( እግዜአብሄር ታላቅ ነው!!) ያሉ ዜጎች መብታቸው ተንፍጎ ይታሰሩባታል?” ሲሉ የወቅቱን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ሁኔታን ከቀድሞው እንግዶችን እንድ ራስ አድርጎ የመቀበል ጥሩ ባህል ጋር በማነጻጸር በጥያቄ መልክ ለመግለጽ የሞከሩ ሲሆን በቀርቡ የገዢው ፓርቲ ለፕሮፓጋንዳ መሳሪያነት የሚጠቀምበት ኢቲቪ “ጀሃዳዊ ሃራካት” በሚል ርእሱ እና መልእክቱ የማይጣጣም ፕሮግራም በማዘጋጀት በሙስሊም ወገኖች ላይ ለማላገጥ የተጠቀመበትን ዘዴ እርቃኑን መቅርቱን አጋልጠዋል፡፡ በአሁን ወቅትም የእገዛዙ የጸጥታ ሃይሎች የታሳሪዎች ቤተሰቦችን በመቅረብ ታሳሪዎቹ ይቅርታ እንዲጠይቁ የማግባባት ዘመቻ መጀመራቸውን ገልጸው “ ለመሆኑ የተበደለ እና መብቱን የተገፈፈ ሰው በየት አገር ነው ይቅርታ የሚጠይቀው ? ይህ አይነቱ አካሄድ በራሱ የአገዛዙ ኤፍትሃዊነትን ነው የሚያመላክትነው ፡፡ “ብለዋል፡፡

  ሄኖክ የሺጥላ የተባለ በሎሳንጀለስ ከተማ የሚኖር ወጣት “ናፍቆት” በሚል ግጥሙ በአገዛዙ የጸጥታ ሃይሎች ለእስራት የተዳረገው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ህጻን ልጁ ናፍቆትን የውስጥ ስሜትን በሚኮረኩር መልኩ በምናባዊ ግጥሙ አወድሷቸዋል፡፡ በተጨማሪም ወጣት ሄኖክ “ለምንድን ነው ዛሬ የምናደደው?” በሚለው በሁለተኛው ግጥሙ የአገዛዙ ቁንጮ የነበሩት መለስ ዜናዊን ኮንኗል፡፡

  የጨረታ ስነስርአቱ ከመካሄዱ በፊት የሚያሳይ ፎቶ

  የጨረታ ስነስርአቱ ከመካሄዱ በፊት የሚያሳይ ፎቶ


  ለኢሳት ማጠናከሪያ ይሆን ዘንድ መነሻ ዋጋው 500 ዶላር ሆኖ ለጨረታ የቀረበ አንድ ታብሌት ዘመናዊ ላፕቶፕ ከሰባት ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ የተሸጠ ሲሆን አሸናፊው ግለሰብም በሳንዴያጎ ከተማ ለሜድረገው ተመሳሳይ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ይውል ዘንድ ታብሌት ላፕቶፑን መልሰው ሰጥተዋል ፡፡አንዲት የሎሳንጀለስ ከተማ ነዋሪ በበኩላቸው ኢሳትን ለምደገፍ በሚደረገው ረብርቦሽ ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ሲሉ በእጃቸው የፈተሉትን ዘመናዊ ሙሉ የአገር ልብስ ለጨረታ እንዲቀርብላችው ለአዘጋጆቹ ሰጥተዋል፡፡ በሎሳንጀለስ ከተማ የኢሳት ድጋፍ ሰጪ አባላትም በስፍራው የተገኙት ሁሉንም ተሳታፊዎችን በማመስገን ኢሳትን በሁሉም መልኩ የመደገፍ ርብርቦሹ እንዲቀጥል ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ ( tamgeda@gmail.com)

  0 0

  በገ/ክርስቶስ ዓባይ  ሚያዝያ 6 ቀን 2005 ዓ/ም

  አንድን  ታላቅ ሀገራዊ እንቅስቃሴ ከአጥናፍ  እስከ አጥናፍ ማለትም ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ፤  ወጥ በሆነ መልኩ እንዲዳረስ የሚገፋፋና የሚያስገድድ፤ አሁን እንዳለንበት ወቅት ያለ ፈታኝ ሁኔታ ሲከሰት፤ በቅድሚያ መታወቅ ያለባቸውንና ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች ለይቶና አበጥሮ ደረጃ በደረጃ ማስቀመጥ ግድ ይላል ።

  ስለሆነም ከጸጸት ለመዳን የሚያስችለንን ሐቀኛና ፍትሐዊ የሆነ መመዘኛ ጊዜ ወስደን  አስበንና አሰላስለን ማስቀመጥ ይኖርብናል። በዚህ አጋጣሚ ለሰላም፤ ለፍትሕ፤ ለዲሞክራሲና ለዕኩልነት እንዲሁም ሐሳብን በነፃነት የመጻፍና የመግለጽ መብት፤ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ተዘዋውሮ የመሥራት፤ ሀብት የማፍራትና በመረጠው የአገሪቱ ክፍል የመኖር መብት ሊኖረው ይገባል በማለት የሚያምን፤ ፍትሐዊ አስተሳሰብ ያለው ዜጋ ሁሉ፤ በሃይማኖት፤ በቋንቋ፤ በጎሣ፤ በክልልም ሆነ በጎጥ እንዲሁም በድርጅትም ቢሆን ሳንከፋፈል፤ በዚህ መርህ እስማማለሁ፤ ለዚህም መከበር እታገላለሁ፤ የሚል አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ለዚህ የጋራ ዓላማችን  እውን መሆን፤ የምንኖርበት የቦታ ርቀትም ቢሆን ሳይበግረን በየአለንበት  በአንድ ላይ ሆነን መቆም አለብን።

  እንዴት ?ብሎ መጠየቅ ይቻላል።

  eprdfከሁሉም በፊት ቅድሚያ ልንሰጠው የሚገባን ነገር የአገራችን ጉዳይ መሆን ይኖርበታል። አገር ማለት ደግሞ ወገን ማለት ነው። እዚህ ላይ ግልጽ ማድረግ የሚገባን ጉዳይ ይኖራል። በተለይ ሀገርና አገር የተለያዩ መሆናቸውን ልናስተውል ይገባል። ሀገር ማለት በተደረሰበት የጋራ ስምምነት ወይም በኃይል የተሰመረ ድንበር፤ ወይም ለግዛት እንዲያመች የተዘጋጀ (Political Boundary)ራሱን የቻለ መጠሪያ ያለው የፖለቲካ ክልል ሲሆን፤ ይህም በአብዛኛው የሚያተኩረው በዱር በገደሉ ፤ በጫካውና በሸለቆው፤ እንዲሁም በተራራውና በሜዳው ላይ ነው። ከዚህም የተነሣ በተለይ አምባገነኖች ሁሉንም ነገር ትተው አገር የሚለውን ሳይሆን ሀገር የሚለውን አጉልተው ለማሣየትና አገር የሚለውን ጽንሰ ሐሳብ አሳንሰውና አኰስሰው ለማሳየት ያላደረጉት ጥረት የለም። ለምሳሌም ብናነሳ የወያኔው ዋና ጠርናፊ የነበሩት በቅድሚያ ሁሉን ሲጠቀልሉ ቆይተው አሁን የተጠቀለሉት መለስ ዜናዊ የአዲስ አበባን ዩኒቨርስቲ ምሁራንን አስመልክቶ እነዚህ ምሁራን ያለአግባብ ከሥራ ሲባረሩ ማን ሊያስተምር ነው ሲባሉ “መንገዱን ጨርቅ ያድርግላቸው” ማለታቸው አይዘነጋም።  በተጨማሪም ለሱዳን ወደ 65 ኪሎሜትር እርዝመት ያለው በአገር(በወገን) ያልተመከረበት መሬት ከልለው፤ የሱዳን መንግሥት በትግል ጊዜ ላደረገላቸው እገዛ እንደ ካሣ መስጠታቸው ይታወቃል። ሌላም መጨመር ይቻላል።

   

  የትግራይን ክልል ለማስፋት እና የአማራውን ክልል ለማሳነስ ሲባል ራያን ከወሎ ፤ ጠለምትንና፤ ቆላ ወገራንና፤ ወልቃይት ጠገዴን ከጎንደር እንደ ዳቦ በመቁረስ ወደ ትግራይ አድርገዋል፤ ቤንሻንጉልን ግማሹን ከወለጋ ግማሹን ከጎጃም በውሰድ አዲስ ከልል ፈጥረዋል። ድቡብንም እንዲሁ ከሸዋ፤ ከሲዳሞ ከጋሞ ጎፋ እና ከከፋን ከጂማ በመቀናነስ ፈጥረዋል። በአጠቃላይ ይህ ዓይነቱ አከላለል ለሕዝብ እንዲጠቅም ታስቦ ሳይሆን ቀደም ሲል የነበረውን ሥር የሰደደ የማንነት ጥንካሬና በራሥ የመተማመን  አንድነት በመሸርሸር ፍጹም ያልነበረና ከቶ በኢትዮጵያዊ አእምሮ ሊታሰብ የማይችል የመከነና የያንዳንዱን ዜጋ ህልውና የሚፈታተን ሰይጣናዊ የሆነ እርምጃ ነው። በእነርሱ አባባል ለሌላው ኢትዮጵያዊ “የመቶ ዓመት የቤት ሥራ” በመስጠት በዚህ ግርግር ውስጥ ግን እነርሱ ያሻቸውን እንዲያደርጉና እንደፈለጉ የአገርን ሐብትና ንብረት እንዲዘርፉ መንገዳቸውን አስተካክለው ጨርሰው የአስፓልት ንጣፍ ሊያነጥፉ በተዘጋጁበት ወቅት ሕዝቡ ያለፉትን የሃያ ሁለት ዓመታት ቆይታውን እንደገና መረምር ሲጀምር ነው፤ በተለይ የነፃ ሚዲያ የሆነው ተወዳጁ ኢሳት አገልግሎቱን በማስፋፋት አስተማማኝ መረጃዎችን ማሰራጨት ከጀመረ በኋላ ነው ሕዝቡ ከዕንቅልፉ እንደነቃ ሁሉ መባነን የጀመረው።  በተለይ ወያኔ መራሹ የትግሬ ባንዳዎች ስብስብ  ዘራፊ ሥርዓት ብዙ የዋሃንን አጭበርብሮ በትረ መንግሥቱን ሲቆናጠጥ የወሰዳቸውን በማር የተሸፈኑ አንዳንድ እርምጃዎች ማስታወሱ ተገቢ ይሆናል።

  ለምሳሌም ያህል የኦሮሞ ሕዝብ ታላቅ እንደመሆኑ መጠን ለዚህ ሕዝብ የሚሆን የቤት ሥራ ወዲያውኑ ነበር የተሰጠው።  ይኸውም ለሥልጣንና ለገንዘብ ጥቅም ያጎበደዱ አንዳንድ ከሐዲ የኦሮሞ ተወላጆችን አቶ ሐሰን አሊን ጨምሮ የተወሰኑ ሰዎችን በማሰልጠን የኦሮሞን የተከበረውን ባህልና የገዳ ሥርዓት ከፊት ለፊት በማስቀደም እየሰበኩ፤ የግዕዝ ፊደል ለኦሮምኛ ቋንቋ አይሆንም ከእንግዲህ በኋላ ኦሮምኛ የሚጻፈው በላቲን ነው በማለት ማስተማር መጀመራቸውን በቁጭት የምናስታውሰው ነው።፤

  በወቅቱ አንድ የማውቀው የቅርብ ጓደኛየ ኦሮሞ በመሆኑ በሚሠራበት መ/ቤት ይህንኑ “ቁቤ” ብለው የሰየሙትን የላቲን ፊደል አጠቃቀም እንዲሠለጥን የደረሰውን ትዕዛዝ ቀመስ  ግብዣ ተቀብሎ ሄዶ ነበር፤ ነገር ግን ሥልጠናውን ሳይጨርስ እሳት ለብሦ እሳት ጎርሦ እየተናደደ  አቋርጦ በመመልሱ፤ ምነው የከፋህ ትመስላለህሳ ? ብለው ጓደኞቹ ሲጠይቁት የመለሰው መልስ የሚረሳ አይደለም።

  እነዚህ ሰዎች ዓላማቸው ምን እንደሆነ አልገባኝም፤ የሚሠሩትንም የሚያውቁ አይደሉም። የኦሮሞ ሕዝብ የሚፈልገው የሥርዓት ለውጥ እንጂ የፊደል ለውጥ አይደለም ደግሞስ ቢሆን የተለያዩ ድምፅን በመወከል የላቲን ፊደል እንደ የኛው የግዕዝ ፊደል የበለጸገ አይደለም።ለምሳሌም እንደ ቀ፤ ቸ፤ ኘ፤ ዠ፤ ጠ፤ ጨ፤ ጸ፤ ጰ የመሳሰሉ ፊደላት እንኳ የሉትም ታዲያ በምን መስፈርት ነው የላቲን ፊደል አጠቃቀም ተማሩ ተብሎ የኦሮሞ ሕዝብ የተወሰነበት ?በማለት ጠይቋል።

  አየይዞም በሦስት መስመር በግዕዝ ፊደል የሚጻፈው ኦሮምኛ በላቲን ከሆነ ሲቸከችኩ መዋል ነው፤ አንድ ገጽ ገደማ ይፈጃል ስለዚህ አጠቃላይ ሁኔታው የኦሮሞን ሕዝብ ዕድገት ሆነ ተብሎ ለመግታት፤ ወይም ደግሞ ምስጢሩ ያልታወቀ የቤት ሥራ ሳይሆን አይቀርም  እኔ ግን በዚህ በማይረባ ጉዳይ ጊዜየን አላጠፋም፤ ሌላውም  የኦሮሞ ሕዝብ ቢሆን በዚህ ተታሎ ጊዜውንና ገንዘቡን ማጥፋት የለበትም፤ በማለት በመናገሩ የት እንደደረሰ አይታወቅም።

   

  ለማንኛውም አገር ግን ከዚህም በላይ ታላቅ ትርጉም ያለው ጉዳይ ነው። ቀደም ሲል እንዳየነው ሀገር ሕዝብን አይጨምርም። አገር ስንል ግን ቅድሚያ የሚመጣው ሕዝቡ፤ ቀጥሎም ያ ሕዝብ የሚኖርበት መሬት (ሀገር) እና የአኗኗሩ ሁኔታ፤ የአስተዳደሩ ፤የባህሉ ፤የኢኮኖሚው፤ የሃይማኖቱ፤ የፖለቲካውና የጤናውን ሁኔታ ሁሉ ያጠቅልላል።

  እንግዲህ እስከዚህ ድረስ በተደረገው ማብራሪያ የምንግባባ ከሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ላለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት በቀጥታም ሆን በተዘዋዋሪ ትግራይ በቀል በሆኑ ጥቂት ደቂቀ ባንዳ ስብስቦች ከዘር ባገኙት አስነዋሪ የአገር ክህደት ውርስ የደረሰባቸውን የበታችነት ስሜት ተንተርሰው በጀግኖች አባቶቻችን መስዋዕትነት ዳር ድንበሯ ተከብሮ ለብዙ ሺህ ዓምታት ታፍራና ተክብራ የቆየችውን ኢትዮጵያን ለማፈራረስና ለመበታተን ያልፈነቀሉት ድንጋይና ያልሸረቡት ሤራ የለም።

  እዚህ ላይ የወያኔን አንዱን የማስመሰያ መሠሪ ተንኰል የሆነውን የብሄር ተዋጸዖን የተመለከትን እንደሆነ ዓላማው  ለሀገርና ለወገን የሚጠቅም ሊመስለን ይችላል። ሐቁ ግን በብሄር ተዋጽዖ ሲባል የችሎታ መለኪያ ዋጋውን ያጣል። ያም የሚወከል ሰው ቢማር ባይማር ግድ የለም ቢቻል እንዲያውም ባይማር ይሻላል። ምክንያቱም የቀረበለትን ሁሉ ያለምንም ጥያቄ የተጻፈውን ይፈርማል፡ የታዘዘውን እንዳለ ተቀብሎ ይፈጽማል ያስፈጽማል። ሌላው ቀርቶ ወንድሙን ግደል ቢባል ይገድላል። አውቀው ደግሞ በተለያዬ የጥቅም መረብ ውስጥ እንዲገባ ያደርጉትና ከዚያ በኋላ በሰው አእምሮ ሊታሰብ የማይችል ነገር እንኳ ቢሆን እንዲሠራ ይገደዳል። ለምሳሌ ም/ጠ/ሚ/ርና የትምህርት ሚ/ር ደመቀ መኰንን የኢትዮጵያን ግዛት ለሱዳን ለማስረክብ ኢትዮጵያን ወክለው የፈረሙ መሆናቸው በስፋት ይወራል።  ይህ ጉዳይ እውነት ከሆነ ግለሰቡ ቢታሠሩ፤ አለበለዚያም ከነ ክብራቸው ቢሞቱ ይሻላቸው ነበር ። ግን ወያኔ እርሳቸውን በጊዜያዊ መቅቡጥ አታሎ እንደሮቦት ወይም እንደ ለማዳ ውሻ ተጠቅሞባቸዋል።

  የ97 ዓ/ም ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረው የምርጫ ውጤት አይደግ (ኢሕአዴግ) በዝረራ መሸነፉ አይዘነጋም። ይሁን እንጂ አይደግ በጠመንጃ ያገኘሁትን ሥልጣን በካርድ ልነጠቅ አልችልም በማለት የሕዝቡን ድምጽ ዋጋ አሳጥቶታል ። ይህንኑ ተከትሎ በተፈጠረው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ አሁንም አይደግ ሆዬ በዚህ አጋጣሚ ሕዝቡን ለመበቀል በድብቅ የነፃ እርምጃ ትዕዛዝ አስተላልፎ ኖሮ ይህንኑ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አነጣጥሮ ተኳሾችን አሠማርቶ እንደነበር ይነገራል።

  ታዲያ ነፍሰ ገዳዮች ተብለው የተመደቡት የመጀመሪያውን ዙር ትዕዛዝ አከናውነው እንደተመለሱ በተደረገ ግምገማ፤ አንዳንዶቹ ባደረጉት ገለጻ “እኔ ይህን ያህል ጥይት ተኩሼ ይህን ያህል ሰው ገድያለሁ፤ እገሌ ግን እንኳን ሰው ሊገድል  አንዲት ጥይትም አልተኰሰም” በማለት እነዚሁ ሮቦቶች ድርጊታቸውን እንደጀግንነት ሲያቀርቡ ሌሎች ግን “በማን ላይ ነው ጥይት የምተኩሰው? ጠላት ላይ ቢሆን እሺ፤ ያ ሌላ ጉዳይ ነው ግን በሰላማዊ ሕዝብ ላይ ያውም በወገን ላይ እንዴት ተደርጎ”  ይላሉ። ጥይት የተኮሱት ወደ ሌላ ክፍል እንዲሄዱ ይደረጋል ።ከዚያም ጥይት ያልተኮሳችሁ እዚሁ ቆዩ ተጨማሪ ገለጻ ይደረግላችኋል ይባሉና እንግዲህ ተጨማሪ ዙር ስላለ በዚያን ጊዜ ትታያላችሁ ይህ የመንግሥት ተዕዛዝ እስከሆነ ድረስ ግዳጃችሁን መፈጸም ይጠበቅባችኋል ተብለው ይሰናበታሉ።

  ጥይት ተኩሰናል እያሉ ለተገመገሙት ነፍሰ ገዳዮች የተሰጣቸው መመሪያ ደግሞ የተለዬ ነበር። እናንተ ለመንግሥት ያላችሁን ታማኝነት በግልጽ አስመስክራችኋል፤ አይደግም ለእናንተ ያለው ክብር ከፍተኛ መሆኑን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።

  ይሁን እንጂ እነዚህ ከሐዲዎች የተሰጣቸውን ግዳጅ በብቃት አልተወጡም ስለሆነም ከዛሬ ጀምሮ ለድርጅታችን ብቻ ሳይሆን ለእናንተም ጠላቶች ስለሆኑ መወገድ አለባቸው።

  አሁን ለሁለትኛው ዙር ስትወጡ ከኋላቸው በመሆን ጭንቅላት ጭንቅላታቸውን እንድትሏቸው፤ የሚል ቀጭን ትዕዛዝ መሰጠቱና በኋላም ተፈጻሚ እንደሆነ ይነገራል። ይህም እንደገና ለአይደጎች እንደ መከራከሪያ ነጥብ ሆኖ መቅረቡ ይታወቃል። ይኸውም ከሰላማዊው ሕዝብ በተተኮሰ ጥይት የመንግሥት ወታደሮች ተገድለውብናል የሚል ነው ። እንግዲህ እንደዚህ ያለ ጅብ የሆነን መንግሥት በዘርና በጥቅማ ጥቅም እየተሸነገሉ ሕሊናን በመሸጥ መደገፍ የሞት ሞት ነው።

   

  እዚህ ላይ ርዓዬ ቢሱ፤ ሟቹ ጠ/ሚር በአንድ ወቅት የተናገሩትን ለመጥቀስ እገደዳለሁ። እኛ የምንፈልገው ታማኝነት ብቻ ነው እንጂ ባይማርም  ታማኝ እስከሆነ ድረስ ጄኔራልም መሆን ይችላል ማለታችውን ሐቀኛ ኢትዮጵያውያን በቁጭት የምናስታውሰው ነው። እዚህ ላይ ዋናው ጉዳይ ያዘዝነውን ብቻ ሳይሆን ያስብነውን የሚሠራ ማለታቸው እንደሆነ ግልጽ ነው።  ይህንን የመሰለውን ግልጽ የሆነ የዘቀጠና፤ በትዕቢት የተወጠረ አነጋገር ሲጠቀሙ የነበሩትን ሰው የ… ራዕይ እናስቀጥላለን እያሉ ሲደሰኩሩ ዝም ብለን እያዳመጥናቸው ነው። እነርሱማ መያዣው መጨበጫው ቅጥ አምባሩ ስለጠፋባቸው ቢሉም አይደንቅም ፤ ምክንያቱም ካፈሩና ከደነገጡ ውለው አድረዋል።

  እኛ ግን ከነርሱ የባሰ የህሊና ስብራት ደርሶብናል። ምክንያቱም ስለ እነርሱ  መጥፎነት ብቻ ስናወራ ይኸው ድፍን ሃያ ሁለት ዓመት ሆነን። ወገናችንም አቅጣጫና መሥመር አስይዞ የሚመራው ቁርጠኛ ድርጅት እስኪመጣ ድረስ በተጠንቀቅ እየተጠባበቀ ይገኛል።

  ስለሆነም በአሁኑ ወቅት መቅደም ያለበት ምን እንደሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠንቅቆ አውቆታል። ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች ለአገር ዕድገትና ብልጽግና እንዲሁም ለዲሞክራሲና ስብዓዊ መብት መከበር የተቋቋሙ እንደመሆናቸው መጠን ከሁለት ጥቃቅን ጉዳዮች በስተቀር ሊታረቁ በሚችሉ መርህ ላይ የተመሠረቱ እንደሆነ ይታወቃል።

  እነርሱም አንደኛው ያቋቋሙት ፓርቲ መጠሪያና፤ ለሥልጣን ያላቸው የጉጉት መጠን ናቸው። መቼም ቢሆን በዲሞክራሲ እናምናለን የሚሉና ለዚህም መከበር እንታገላለን የሚሉ ከሆነ ለሥልጣን ያላቸው ፍላጎት በሕዝብ ዘንድ ባላቸው ታማኝነትና ክብር ላይ የተመሠረተ እንዲሁም በሕዝበ ውሳኔ የሚረጋገጥ በመሆኑ የሥልጣን ጉጉት እዚህ ላይ ያከትማል። የድርጅታቸውን መጠሪያ ግን ከፈለጉ እንደያዙ በዚያው በጀመሩት የዕዝ ስንሠለት መቀጠል ይችላሉ ግን ማየት የሚገባቸው ጉዳይ አለ።

   

  በተናጥል ብዙ ቢደክሙም ለውጥ ማምጣት ያለመቻላቸውን የተገነዘቡ ስለሆነ ከሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ተቀናጅቶ መሥራትና ይህን ራሡ ላወጣው ሕግ እንኳ የማይገዛ አምባገነን ሥርዓት ከሕዝብ ጫንቃ ላይ አውርዶ በመቅበር በምትኩም በሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘንድ የሚናፈቀውን ሰብአዊ መብት የሚከበርበት፤ ሕግና ፍትህ የሠፈነበት መንግሥት እውን እንዲሆን ሌት ተቀን መሥራትን ይጠይቃል። ከዚያ በኋላ ችሎታውና ፍላጎቱ እስካለ ድረስ ሥልጣኑም በአስተማማኝነት ሊመጣ ይችላል። ምክንያቱም የሕዝብ ድምፅ ተቀባይነት ስለሚኖረው ተወዳድረው ካሸነፉ ሥልጣንም ሊይዙና ለወገን የሚጠቅም ራዕያቸውን ተግባራዊ ከማድረግ የሚያግዳቸው አንዳችም መሰናክል አይኖርም።

  ነገር ግን ቁምነገርኛ መዥገር ቆርበት  ነክሶ ይሞታል እንዲሉ በዚያው ባለሁበት እቀጥላለሁ ቢሉ ሕዝብ ከጎናቸው ከሌለ ብቻቸውን እንደሚቀሩ ከአሁኑ ማወቅ አለባቸው። የሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና ዓባላት መነጋገርና መወያየት ያለባቸው የወቅቱ ሁኔታ ከየትኛው ፓርቲ ጋር ብንቀናጅ ተስማምተንና ተግባብተን፤ በመረዳዳት ሥራችንን አንድ እርምጃ ወደፊት ማስኬድ እንችላለን በሚለው ላይ ጊዜና ትኩረት ሰጥተው  መነጋገር ይጠበቅባቸዋል። አስፈላጊ ከሆነም ከተለያዩ ፓርቲዎች የተለያዩ ሰዎችን በመጋበዝ ስለእነርሱ ፓርቲ ገለጻ እንዲያደርጉላቸው ማድረጉ ተገቢ ነው።

  ያሉትን የተቃዋሚ ፓርቲዎች በማሰባሰብ ወደ አንድ የሚመጡበትን ዘዴ መቀየስ ካልሆነ በስተቀር ከእንግዲህ ወዲህ ሌላ አዲስ ድርጅት ወይም ፓርቲ ማቋቋም ማለት፤ የጠላትን ዕድሜ ለማሳጠር ሳይሆን ለማስረዘም ብሎም በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ መቀለድ ስለሚሆን ከቶ መታሰብ እንኳ የለበትም እላለሁ።

  አሁን የሚያስፈልገው ሁሉም ተቀራርቦ መሥራትና፤ ለዚህ ችግሩና ኑሮው  ላንገፈገፈውና በተጠንቀቅ ለሚገኘው ወገናችን አቅጣጫ በማስያዝ መንገዱን መምራት ብቻ ነው። ነገር ግን የተባና ወጥ የሆነ አመራር ለመስጠት የግድ ማዕከል መፈጠር አለበት።

  ለምሳሌም ክርስቲያኑ ሕዝብ በወያኔ ጣልቃ ገብነት ለተመረጠው ፓትሪያርክ ያለውን፡ተቃውሞ ለመግለጽ ሁኔታዎች እስከሚስተካከሉ ድረስ ሙዳዬ ምጽዋት የሚባል ነገር ለቤተክርስቲያን መስጠቱን እንዲያቆም መቀስቀስ፤ ትልቅ ሚሳይል እንደመትኰስ ይቆጠራል። በአንፃሩ ግን መለመን ለአፈሩ ችግረኛ ሰዎችና በቤተ ክርስትያን ዙሪያ ወድቀው ለሚለምኑ ወገኖች እንዲመጸውቱ  ማስተማር። ጠንከር ያለ አቅም ያላቸውን ደግሞ ድርጅቶን እንዲረዱ ማበረታት።

   

  በተለይ ወጣቱ ክፍል በአብዛኛው፤ አይደግ ሥልጣን ሲይዝ የ10 እና የ8 ዓመት የነበሩ ሁሉ በአሁኑ ሰዓት የ30 ዓመት ዕድሜና ከዚያም በላይ በመሆናቸው እነርሱን በከፍተኛ ደረጃ እየተጠቀመባቸው ይገኛል። ስለሆነም ይህ ወጣት ትውልድ አገሩ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ በትክክል እንዲያውቅና ዘመኑ ያመጣቸውን የመገናኛ ዘዴዎች ማለትም ኢንተርኔት፤ ዩቲዩብ፤ ኢሜይል፤ ፌስ ቡክ፤ ትዊተር፤ ስካይፕና ቫይበር የመሳሰሉ የመገናኛ ዘዴዎችን እንዲጠቀም በማስተማር በመርዳትና በማደፋፈር መረጃዎችን የመቀበል፤ የመዘገብ፤ የማስተላለፍና የማሠራጨት ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ ማስተማር ይጠበቅባቸዋል።

  ከዚያም በተጨማሪ ከልባቸው አምነውበት ሳይሆን ለዕለት ጉሮሮአቸው ማለትም ቤተሰባቸውን ችግር ላይ ላለመጣል ብለው በሥርዓቱ ታቅፈው ያሉትን በዘዴ በመቅረብና በማግባባት አይደግ በቀጣይ ሊተገብራቸው ያሉትን ምስጢራዊ ዕቅዶች በማወቅ ለመገናኛ ብዙኃን እንዲደርሱና በወቅቱ ለሕዝብ ይፋ የሚሆኑበትን መንገድ ማመቻቸት። ነገር ግን በዚህ ሁኔታ የማይተባበሩትን የአገር ከሐዲ ባንዳዎች ከየትኛው ቅርንጫፍ ማለትም፤ ከብአዴን፤ ከኦሕዴድ፤ ወይንም ከደሕዴግ መሆናቸውን ለይቶ፤ ዕድሉም የተሰጣቸውን ዕለትና ቀን  ጭምር፤በጥንቃቄ በልዩ ሠነድ መዝግቦ መያዝ።

  እንደሚታወቀው የመጀመሪያው የቅርብ ጠላታችን ከላይ በተጠቀሱት የአይደግ ቅርንጫፎች ውስጥ ተሰግስገው ለጊዜያዊ ጥቅም ሲሉ ወገናቸውን የሚያሰቃዩ የመጀመሪያ ጠላት መሆናቸው መታወቅ አለበት። ምንም እንኳ ትዕዛዙንና መመሪያውን የሚያወጣው ወያኔ ቢሆንም ይህንን መመሪያ የሚፈጽመውና በወገኑ ላይ አሰቃቂ ሥቃይ፤ ዘረፋና ግድያ የሚፈጸመው፤ በኦሮሞው ላይ ኦሕዴድ፤ በአማራው ላይ ብአዴን፤ በደቡብ ሕዝብ ላይ ደሕዴን እንዲሁም በቀሩት ኢትዮጵያውያን ላይ የአጋር ድርጅቶች ዓባላት ስለሆኑ ባለፈው ሥራቸው ተጸጽተው ስማቸውን ለማደስ ከወገናቸው ጎን ካልተሰለፉ በስተቀር፤ እነዚህ አካላት ከወያኔ በከፋ መልኩ ከሞራል አኳያ የእኛነት ስሜት የሌላቸው ጨካኝና አረመኔዎች ስለሆኑ ምንም ዓይነት ይቅርታ ሊደረግላቸው ከቶ አይገባም።

  ስለዚህ እነዚህ የወያኔ ፍርፋሪ ለቃሚ ውሾች በአንደኛ ደረጃ በጠላትነት መታየት አለባቸው። ምክንያቱም ወያኔ የወጣው ከትግራይ እንደመሆኑ መጠን እነዚህን ጥቂት አገር ከሐዲዎች በመርዳት የሥርዓቱ ደጋፊና አስፈጻሚ ባይሆኑ ኖሮ እንኳን ሃያ ሁለት ዓመት አንድ ዓመትም ሊቆዩ ባልቻሉም ነበር።

  ጠላትማ ሁልጊዜም ጠላት ነው፤

  አስቀድሞ መግደል አሾክሿኪውን ነው።

  ብለው አባቶቻችን ከልምዳቸው ያገኙትን ተሞክሮ እንደ መመሪያ እንድንጠቀምበት ትተውልን አልፈዋል። በዚህ ፈታኝና ወሳኝ ወቅት ከተራ አገልጋይ እስከ ከፍተኛ የአሻንጉሊሊትነት ሥልጣን ደረጃ ላይ ያለ ፍርፋሪ ለቃሚ ሁሉ በክብር ወደ ወገኑ ወደ ሠፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ መመለስ አለበት።

  ይህን የማያደርግ ግን በቅርቡ የነበረው እንዳልነበረ ሲሆን መድረሻው የት ይሆን?

  አዎ ቢያንስ ከሁለት አንዱ መሆኑ አይቀርም፤ አንድም ንጹሃን አገር ወዳዶች ያለአግባብ በሚሰቃዩበት በቃሊቲ ወይም ወደ ጠርናፊያቸው መቀላቀል በፍጹም አይቀርም።

  ባንዳን ጊዜ ከዳው! ድል ለሠፊው ሕዝብ!

  ኢትዮጵያ እንደ ቀድሞ አባቶቻችን ሁሉ በሐቀኛ ልጆቿ አንድነቷ ጸንቶ ይቀጥላል!


  0 0

  ታደለ መኩሪያ

  tekeleስለ ሙስሊም ኢትየጵያውያን መሪዎች  ለኢሳት ገንዘብ ማሰባስብ ዝግጅት ላይ  መገኘትና ስለታማኘ በየነ የዋህ አነጋገር ተክለማካኤል አበበ  ለአቀረበው ጹሑፍ ማስተባበያ የቀረበ ነው።

   

  ወደ ዘርዝር ሐሣቡ ከመግባቴ በፊት ስለአንድ ገጠመኝ ጀባ ልበላችሁ፤ ጊዜው ቢረዘምም አይረሳም፤ በ1969 ዓ ም ነበር። ሻለቃ ዮሐንስ ምስክር ብቻውን በምኒልክ ቤተ መንግሥት የከተመውን የደርግ ፣ የካድሬ ጎራ የጦር ሜዳ ቀጠና አድርጓት መዋሉ ምንጊዜም ይወሳል። በዕለቱ እምድር ቁና ትሆናለች፤ ሻለቃ ፣ኮሌኔል፣ ጅንራል ፣ ሊቀመበሩ ሳይቀሩ ከታንክ ውስጥ እንደተጠለሉ ይነገራል። የካድሬው መንጋማ እንደ አሻሮ ተቆላ ተብሎለታል።

   

  ታዳንስ አንድ ሻለቃ ዮሐንስ ምስክርን  ኮፍጣና ወታደር መሆኑን የሚያውቅ የዘብ ሃለፊ ሻለቃ ባሻ እሱ መሆን አለበት በማለት ሁኔታውን ያጣራል። እርሱ እንደሆነ ይደርሰበታል።  ‘ሻለቃ ዮሐንስ  ምስክር ነው! ተረጋጉ!’ እያለ ከአንዱ ማዕዘን ወደሌላው ይሯሯጣል። ምድረ  ሻለቃ፡ ኮሌኔል ጅንራል ፡  የደርግ አባል፣ የአብዮት አራማጅ ካድሬ  ሳይቀር፤ በየጠረጴዛው፣ ቁም ሳጥኑ ተሸሸጓል። ሊቀመበር መንግሥቱም  በታንኩ ውስጥ ኩሼ ብለዋል። የዘብ አላፊው ሻለቃ ባሻ፤ ሻለቃ ዮሐንስ ምስክር ብቻውን ይህን ሁሉ ቀውጤ እንደፈጠረ ሲያውቅ እራሱ ከሻለቃው በላይ ጀግና ለመሆነ ቃጣው። ወታደራዊ ሰላምታ እየሰጣቸው ሁሉንም  ከተሸሸጉበት እንዲወጡ አደረገ። ‘አንዱ ሻለቃ ዮሐንስ ምስክር ነው እንደብርጌድ የዘመተብን ደርሸበታለሁ በማለት ተኩራራ፣ ልቡንም አሣበጠ። ከዚያ በኋላማ ማን ይቻለው? የደርጉም ሊቀመበር የሻለቃነት ማዕረግ ሰጡት። ከእርሳቸው በመለስ ለማንም አልታዘዝም አለ። በደርግ ጽፈት ቤት ግቢ እንደልቡ ይፏልል ጀምረ። ጸረ አበዮተኛ እያለ መግደሉን አጧጣፈ።ለትንሹም ለተልቁም መሣሪያ መምዘዙን ጀመረ።  ቀደም ያሉት ካፈጸሙት ግድያ በልጦ ለመገኘት የብዙሃንን ነፍስ አጠፋ። ለእርሱ ግን መልካም ሥራ ይመስለው ነበር። ሌሎችም እንደሱ ሰው መሆናቸው ተረሳው።    ኮሌኔል አጥናፉ አባተን እርሱ እራሱ እደገደላቸው ይናገራል። የበላዮቹን በሥልጣናቸው እየገባ  በእርሱ ብሶ በሥልጣኔ ገባችሁብኝ  እያለ በራ ከረዩ ይል ጀመር። እንዲህ ነው ለሕግ ያለመገዛት እንደፈለጉ መፏለል።

  ሁለተኛው በቅርብ የሆነ ነው።ነፍሳቸውን ይማረውና ዶክተር ዮናስ አድማሱ ወንደማቸው ዮሐንስ አድማሱ ስለታዋቂው ጻሐፊ ዮፍህታይ ንጉሴ ሥራዎች ጀምረውት የነበረውን ከፍፃሜው ደርሱ ለሕዝብ ይቀርባል።ሥነሥረዓቱን የመሩት ግለሰብ ያሳዩት የሥነምግባር ግድፈት ትዝብት ላይ እንደጣላቸው ተቺው ጠቀስ አድርገው አልፈውታል። መነሻቸው ለሥራው ያላቸውን አድናቆትና ምስጋና ለማቅረብ  ነበር።ርዕሳቸውም ያተኮረው ‘ ሦስቱ ዮዎች’ ላይ ነበር። ዮናስ አድማሱ፣ ዮሐንስ አድማሱና ዮፍህታይ ንጉሤ። የነዚህን ታላቅ ዮዎች በመድረክ ላይ ያስተዋውቅ የነበሩት ግለስብ  ባለታሪኮቹ በሕይወት ሰለሌሉ እራሳቸው የታሪኩ ፈጣሪ ሆነው መቅረባቸው ነው ያናደዳቸው።ይህ ዓይነቱን መጥፎ ባህል መቼ ነው የምናስወግደው በማለት ነበር ስሜታቸውን የገለጹት።

   

   

  ልጅ ተክለማርያም አበበ ጹሑፉን በቅርብ በሚያውቀው በሰባአዊ መብት ተከራካሪ ታማኝ በየነ ይጀምራል።ይሄውም የክርስቲያኑ ባዓል ሲከበር የዕስልምና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን አለመከበሩን  ታማኝ በየነ በመናገሩ እንደየዋህነት ቆጥሮታል። አበው ሲተርቱ ‘ከጥምጥሙ ይቅደም መማሩ’ ይላሉ።

   

  በ1966 ዓ ም ነበር። የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት የተከበሩ እንደልካቸው መኮንን ነበሩ። በአዲስ አበባ ከተማ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ሃይማኖታችን ተገቢውን እውቅና ይሰጠው ብለው ሰላማዊ ሰልፍ ይወጣሉ። መሳ ለመሳ  የክርስትና ሃይማኖት በሰልፉ ላይ ነበር። በወቅቱ የ ቀ ኃ ሥ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዋናኛዎቹ ሰልፉን አስተባባሪዎች ነበሩ።ጥያቄው የፍትህ መሆኑን ይረዳሉ። የኢትዮጵውያን ተማሪዎች ከሚደነቁበትና አክብሮት ከሚቸርበት ተግባራቸው አንዱ ወግተኛ አለመሆናቸው ነው። አቶ ተክለሚካኤል  አበበ በእርሱ አስተሳሰብ የአቶ ታማኝን  የዋህነት ሲገልጽ ፣ብልህነቱ  ስለፍትህ የማያውቁ እሲኪያውቁ ቆሞ ያለመጠበቁ ይሆን?።

   

  ሁለተኛው ደግሞ ለኢሳት ለሚደረገው የገንዘብ አሰባሰብ ዝግጅቶች ላይ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መድረኩን ተቆጣጠሩት ፖለቲካውንም ይቆጣጠሩታል የሚል ሥጋት ነው። ልጅ ተክሌ በመላ ምት ላይ ተሞርክዞ ስለ ዘጠና ሚለዮን ሕዝብ ትንተና አይስጥም፤ ነውር ነው። እንዴት ነውር እንደሆነ ወርድ ብዬ አሣያለሁ።

   

  ልጅ ተክሌ  ጠላት ወዳጅ ከሚያከበረው ከአበበ ገላው በኢትዮጵያን ስሙ ሲጠራ የማይውለው ታማኝ በየነን አጅብህ  በትልልቅ የአሜሪካና የካናዳ ከተማዎች በመድረክ ላይ  ሰለታየህ እነርሱን ነህ  ማለት አይደለም። የልጅ ተክሌንም ሃይማኖት የጠየቀ አልነበረም።  ተክሌ  ከሃይማኖቱ በፊት ሰው መሆኑን የኢሳት ሰዎች እንደሚያውቁ እረዳለሁ። እስልምና ተከታይ ወንድሞቻችንም ከሃይማኖታቸው በፊት ሰው መሆናቸውን አይዘነጉም። የሰው ልጅና ፍተህ ሊነጣጠሉ ስለማይችሉ ለፍትህ የሚታገል ሁሉ ሰው ለመሆኑ የሚታገል ነውና ዘር፣ ሃይማኖት፣ ቋንቋ ፣ሞያ ወዘተ ሰው ከሆንን በኋላ የሚመጡ ናቸው። ለልጅ ተክሌ ይህ ይጠፋዋል አልልም፤ በኮታ እንደ ዘር ፓለቲካ  ሃይማኖትን ለመመድብ  መሞከር በአሁኑ ጊዜ የእስልምና ተከታዩን ወገናችንን የፍትህ ጥያቄ ዳር እስከ ዳር  ማጥለቅለቁን ያለማውቁን  ያለማቁ ይመስላል።

   

  እንደሻለቃው ባሻና እንደመድረክ አስተዋዋቂው ከዚህም ከዚያም ተሯርጠው ስለነገሩ ጥቂት ካወቁ በኋላ በድንገት በአጋጠሚ ራስን አንድ ቦታ አስቀምጦ ከሌሎች ጋር መላተሙ አይጠቅምም። ይህ ድርጅት እቀፉ ያንን ሃይማኖት አትቀፉ ፣ እንዲህ አድርጉ ለማለት  አንተ ማነህ? የሚል ጥያቄ ያጭራልና ከወዲሁ ሰብሰብ ማለቱ አይከፋም። የቁጥጥር ኮሚቴ በኢሳት ውስጥ ይቋቋም ከሆነ መቀበልም ያለ መቀበልም የቦርዱ ነው።ያስተምራል ወይስ ያደናግራል ምርጫው የእነርሱ ነው።

   

  ከዮፍህታይ ንጉሤ ስንኝ አንድ፣ ለመንገድ፤

  ለጌሾው ወቀጣ አንደ ሰው አልመጣ፤

  ለመጠጡ ጊዜ ከየጎሬው ወጣ።

  ምስጋና ይግባቸው ለሦስቱ ‘ዮዎች’ ብዙ ከዚህ እንማራለን።

   

  ታደለ መኩሪያ

  tadele@shaw.ca

   

   

   

   

   

   


  0 0

  በሦስት ኀይሎች የተደራጀው የጨለማው ቡድን ‹‹የኣባይ ፀሃዬን አመራር›› ያቀናጃል
  መመሪያው÷ የልዩ ጽ/ቤት፣ የውጭ ግንኙነት መምሪያ፣ ፕሮቶኮል፣ ጥበቃ ሓላፊዎችን ምደባዎች ይመለከታል ተብሏል

  (የሐራ ተዋሕዶ ዘገባ እንደወረደ)

  ‹‹ኣባይ ፀሃዬ ከስኳር ኮርፖሬሽን በተጨማሪ ጠቅላይ ቤተ ክህነትን በበላይነት እንዲመሩ ከመንግሥት ትእዛዝ ተላልፏል፡፡ የትግራይ ተወላጆች የግቢውን አመራር ሙሉ በሙሉ እንረከበዋለን፡፡ ከዚህ በኋላ ቤተ ክርስቲያን በትግራዎት እንጂ በአማራ አትመራም፡፡ ለሚኒስትሮች የሚፈለገውን ጥቅም እያቀረብን እናስፈጽመዋለን፡፡››
  /ኣባይ ፀሃዬ ለፓትርያሪኩ የሚሰጡትን ‹‹አመራር›› ከእነ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ጋራ ያስተባብራሉ የተባሉት በምሥራቅ ትግራይ የደብረ ኣላማ አሲራ መቲራ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም አበምኔት አባ ገብረ መድኅን ገብረ ጊዮርጊስ ዛሬ ጠዋት የተናገሩት/

  ፓትርያሪኩ ‹‹አባ›› ነኝ ባዩን ከግቢው እንዲያርቁላቸው መመሪያ ሰጥተዋል፤ ተፈጻሚነት ይኖረው ይኾን?
  መንግሥት፣ የቤተ ክርስቲያን አመራር፣ ካህኑና ምእመኑ ጉዳዩን ከምር አጢነው አቋም እንዲወስዱ ተጠይቋል፡፡

  አቡነ ማቲያስ

  አቡነ ማቲያስ

  ከአምስተኛው ፓትርያሪክ ኅልፈተ ሕይወት በኋላ፣ የመንበረ ፓትርያሪኩን ላዕላይ መዋቅሮች በመቆጣጠርና ለተቋማዊ ለውጥ የታቀዱትን ተግባራት በማምከን÷ 1)ቡድናዊና ግለሰባዊ ጥቅሙን አስጠብቆ ለመቆየት፣ 2)ኦርቶዶክሳዊ ማንነትን በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ደብዛውን ለማጥፋት በልዩ ኹኔታ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የጨለማው ቡድን÷ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን በጎጠኝነት፣ በፖሊቲካዊ ታማኝነትና በጥቅም ስቦ እና አቅርቦ ማሰለፍ መጀመሩ ተዘገበ፡፡

  በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መምሪያዎችና ድርጅቶች ውስጥ በሓላፊነት ደረጃ የተቀመጡ ጥቅመኞችን ጨምሮ የታወቀ ሹመት የሌላቸውን ነገር ግን የሁሉ ፈጣሪና ገባሪ ለመኾን ‹‹ሥልጣን›› ያገኙ ግለሰቦችን የሚያካትተው የጨለማ ቡድኑ÷ በፓትርያሪኩ እና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ላይ ማሰለፍ የጀመረው ‹‹የህወሓት ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ነው›› ተብሏል፡፡ ቡድኑ በዚህ ስትራተጂው የህወሓት/ኢሕአዴግን ባለሥልጣናት ተጽዕኖ በመጠቀም በማንኛውም ቦታ በተለይም በቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ አመራር ላይ ተጽዕኖውን ለማጠናከርና ያሻውን ለመፈጸም ማቀዱ ነው የተነገረው፡፡

  ይኸው ስትራተጂ ባለፉት ኻያ ዓመታት መንበረ ፓትርያሪኩ ለክፍፍልና ትርምስ የተዳረገበት፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ለጥቃትና ድብደባ የተጋለጡበት እንደነበር ያስታወሱት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች፣ ስልቱ በመልኩ አዲስ ባይሆንም በይዘቱ ግን ቡድኑ የተለየ ቁመና ይዞ የተደራጀበት መኾኑን ያስረዳሉ፡፡ እንደ ምንጮቹ ገለጻ፣ ፅልመታዊ ቡድኑ ለሦስት ኀይል ተከፍሎ በተለያዩ ግለሰቦች የሚመራ ሲሆን የተመረጡ የመንግሥት ባለሥልጣናትን እየተፈራረቀ በመወትወት/በማግባባት ተመሳሳይ ጉዳይን ከተለያየ አቅጣጫ እያስተነተነ ስለጉዳዩ አንድ ዐይነት ቀለም/ሥዕል ለመፍጠር ግፊት ያሳድራል፤ ለኾነ ርምጃ የሚያበቃ ውሳኔ እንዲተላለፍ ያደርጋል፡፡ በዚህም ቡድኑና አባላቱ ለመንግሥት ቀራቢና ተቆርቋሪ፣ ለቤተ ክርስቲያን አሳቢ መስለው ጋርዮሻዊና ግለሰባዊ ጥቅማቸውንና ሥልጣናቸውን ያስጠብቃሉ፡፡

  ለሦስት ኀይል የተከፈለውን ‹‹የጨለማ ቡድን›› የሚመሩት ግለሰቦች፡-

  አባ ገብረ መድኅን ገብረ ጊዮርጊስ – በምሥራቅ ትግራይ የደብረ ኣላማ አሲራ መቲራ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም አበምኔት
  አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል – በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ የትምህርትና ሥልጠና መምሪያ ዋና ሓላፊ
  ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ – በመዋቅር የማይታወቀው የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ
  በአሁኑ ወቅት በሦስት ኀይል የተደራጀው የጨለማ ቡድን ከውጭ ኀይል ያገኘዋል በተባለ አመራር፣ የመንበረ ፓትርያሪኩን ከፍተኛ መዋቅሮች ለመቆጣጠር በሚያደርገው መፍጨርጨር፣ ለዓላማዬ ዕንቅፋት ናቸው ብሎ በሚያስባቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሓላፊዎችና በቀናዒ ኦርቶዶክሳውያን ላይ መጠነ ሰፊ የስም ማጥፋት ዘመቻ እያካሄደ ነው፤ ለዚህም የፓትርያሪኩ ድጋፍ እንዳለው አስመስሎ ነው መቀሳቀስ የያዘው፡፡ እንዲያውም ከመረጃው ምንጮች አንዳንዶቹ÷ አዲሱ ፓትርያሪክ ‹‹ሳያውቁ በቡድኑ ቁጥጥር ውስጥ ገብተው በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመሥርተው ለመወሰንና የውሳኔያቸውን አፈጻጸም ለመከታተል በማይችሉበት አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል›› እስከማለት ደርሰዋል፡፡

  ምንጮቹ ለዚህ ድምዳሜያቸው በአብነት የሚጠቅሱት፣ ከየካቲት ወር አጋማሽ አንሥቶ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የቀን መደበኛ መርሐ ግብር ደቀ መዛሙርት እና በአስተዳደሩ መካከል የተነሣውን ውዝግብና አያያዙን ነው፡፡ እንደ ምንጮቹ ገለጻ፣ ውዝግቡ በአጭር ጊዜ እልባት እንዲሰጠው አይፈለግም፡፡ ለዚህም ጣታቸውን የሚቀስሩት ‹‹ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በደብዳቤ የተሠየመኹትና የሚመለከተኝ እኔን ብቻ ነው፤›› በሚሉት የትምህርትና ሥልጠና መምሪያው ሓላፊ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ላይ ነው፡፡

  ከደቀ መዛሙርቱም ከሓላፊዎቹም መካከል ምንጮቹ በስም የሚጠቅሷቸውን ግለሰቦች በማቅረብ ውዝግቡን ሳብ ረገብ እያደረጉ ይዘዋል የተባሉት አባ ሠረቀ ብርሃን፣ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ጣልቃ ገብቶ ፓትርያሪኩን እንዲያነጋግር ከስኳር ኮርፖሬሽኑ ኣባይ ፀሃዬ ጋራ መክረዋል ተብሏል፡፡ አባ ሠረቀ ብርሃን ታዲያ ይህን የሚያደርጉት፣ በርግጥም አካዳሚያዊ መብታቸውንና መልካም አስተዳደርን በመጠየቃቸው በረኀብ እየተቀጡ ላሉት ደቀ መዛሙርት ከአንጀት በማዘን አይደለም፡፡

  አባ ሠረቀ ብርሃን ችግሩም መፍትሔውም በግልጽ የሚታወቀውን የደቀ መዛሙርቱንና የአስተዳደሩን ውዝግብ ከዐውዱ ውጭ እያወሳሰቡ በስም የተጠቀሱትን ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን ወትውተዋል፡፡ በዚህም ጥንተ ጠላታቸው ማኅበረ ቅዱሳን እንደ ተቋም እና ‹‹የማኅበሩን ተልእኮ የሚያስፈጽሙ ናቸው›› የሚሏቸውን የኮሌጁን ሓላፊዎች እንደ ግለሰብ በከፍተኛ ደረጃ ወንጅሎ (አንዱ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ብሎግ እንደወሸከተው) ፖሊቲካዊም አስተዳደራዊም ርምጃ እንዲወሰድባቸው የማድረግ ፍላጎታቸው የናረ ኾኗል፡፡ እስከ መጪው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በማሰንበትም ጉዳዩ ተለጥጦና ዐቢይ አጀንዳ ኾኖ የፈለጉት ውሳኔ እንዲተላለፍበትም ነው ዕቅዳቸው፡፡
  ሳይገባቸው በተቀመጡበት መምሪያ ረብ ያለው ቁምነገር ለመፈጸም አቅሙም ዝግጁነቱም የሌላቸው አባ ሠረቀ ብርሃን፣ ለዚህ አካይስት አድራጎታቸውና ዕቅዳቸው ተባባሪ አላጡም፤ በቀደሙት ዘገባዎቻችን እንዳስነበብነው የደቀ መዛሙርቱን ጥያቄ አጥንቶ የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያቀርብ የተቋቋመው ኮሚቴ ሥራውን እንዳይጀምር በማሰናከል የሚያግዟቸው የፅልመታዊ ቡድኑ የበላይ ተቆጣጣሪ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ አሉላቸው፡፡ ንቡረ እዱ የፓትርያሪኩ አማካሪ መስለውና ራሳቸውን በአማካሪነት ሾመው በቀጣይ የፓትርያሪኩን ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ግንኙነት መመሪያ ለመቆጣጠር አቶ ኣባይ ፀሃየ ለፓትርያሪኩ ‹‹የሚሰጡላቸውን መመሪያ›› የሚጠባበቁ ናቸው፡፡

  ለሐራዊ ምንጮች በደረሰው ጥቆማ መሠረት፣ አቶ ኣባይ ፀሃየ ለፓትርያሪኩ መመሪያ እንዲሰጡ ማግባባት ያደረጉት በምሥራቅ ትግራይ የደብረ ኣላማ አሲራ መቲራ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም አበምኔት ነኝ የሚሉት አባ ገብረ መድኅን ገብረ ናቸው፡፡ ‹‹አባ›› ነኝ ባዩ ገብረ መድኅን አበምኔት ነኝ በሚል በስሙ ከሚነግዱበትና ለሀ/ስብከቱ ከማይታዘዙበት ገዳም ‹‹አበምኔትነት›› በቀር በመንበረ ፓትርያሪኩ ይህ ነው የሚባል ሹመት የሌላቸው ናቸው፤ በገዳማት ርዳታ ስም ከፍተኛ ፈንድ ለማጋበስ የቋመጡባትን የገዳማት አስተዳደር መምሪያ ዋና ሓላፊነት ለቀም እስኪያደርጓት ድረስ!!
  የአሲራ መቲራው ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን በሽግግሩ ወቅት ፊት በሰጧቸውና አለመጠን ባቀረቧቸው ዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ ተሸጋግረው ከቀድሞም ባደለቡት የዝርፊያ ሀብት ላይ አያሌ የግል ሀብት ለማካበት ኹኔታዎችን አመቻችተዋል፤ ራሱን በዳግም አደረጃጀት ባጠናከረው ፅልመታዊ ቡድን ውስጥም በቅድመ ግንባር የተሰለፉ፣ ስንኳን ለመነኲሴ ለሰብአ ዓለም አጸያፊ በኾኑ የድፍረት ኀጣውእ ተሰነካክለው በማሰነካከል የታወቁ፣ በሄዱበት የማይለዩትን ሽጉጥ በሠባራ ሰንጣራው ምክንያት ባገኙት ላይ (በሀ/ስብከታቸው ሊቀ ጳጳስ ላይ ሳይቀር) እየመዘዙ የሚደነፉ ግልፍተኛ ናቸው፡፡

  ንቡረእድ ኤልያስ አብርሃ

  ንቡረእድ ኤልያስ አብርሃ

  ዝርዝሩ ለኋላ ይቆየንና ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን ባለፉት ሦስት ቀናት በአቶ አባይ ፀሃየ ላይ አካሂደውታል በሚባለው ውትወታ÷ በፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጭ ግንኙነት መምሪያ፣ የፓትርያሪኩ መጋቤ ሥርዐት (ፕሮቶኮል)፣ የመንበረ ፓትርያሪኩ(የግቢ) ጥበቃ ሓላፊ መኾን የሚገባቸውን ሰዎች መልምለውና አሳምነው እንደጨረሱ ከራሳቸው አንደበት በዛሬው ዕለት ሲነገር ተደምጧል፡፡ ካለፉት ኻያ ዓመታት ልምድ ለመገንዘብ እንደሚቻለው እኒህ የሓላፊነት ቦታዎች (በቀጣይ እስካልተስተካከሉ ድረስ)÷ ፓትርያሪኩን በመቆጣጠር፣ ባለጉዳዮችን በማጉላላትና የቤተ ዘመድ ሰንሰለት በመዘርጋት አስከፊ ሙስናና በቤተ ክርስቲያን ስም ሕገ ወጥ ተግባራት የሚፈጽምባቸው እንደነበሩ አሌ አይባልም፡፡

  ለአስረጅነት እንዲኾን ከሙስናውም ከሕገ ወጥ ተግባሩም አብነት እንጥቀስ፡፡ ፓትርያሪኩ እንደተሾሙ ሰሞን ‹‹አላምዳለኹ፤ አማክራለኹ›› በሚል ተጠግተው ቢሯቸውን በዚያው በጽርሐ መንበረ ፓትርያሪኩ ያደረጉት ንቡረ እድ ኤልያስ በቤተ ክርስቲያኗ ስም በሚደረግ ትብብር ሁለት ሰዎችን ገንዘብ ተቀብለው ወደ አሜሪካ ለመላክ ያደረጉት ሙከራ ተይዞባቸዋል፡፡

  በመለያ ስሙ ‹‹ሃይለ ሰይጣን›› የሚባለውና በቀድሞው ፓትርያሪክ እገዛ በዋሽንግተን ዲሲና ካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት ሕገ ወጥ ሹመቶች የተደራረቡለት ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን ከፓትርያሪኩ ምርጫ ወቅት ጀምሮ በአዲስ አበባ ይገኛል፡፡ ሃይለ ሰይጣን የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ግንኙነት የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ በኾኑት አቡነ ገሪማ አማካይነት ከአዲሱ ፓትርያሪክ ጋራ ዕውቂያውንና መቀራረቡን ማጠናከሩ ይነገራል፡፡ የሥራ አስኪያጅነት ሥልጣኑ ኦርቶዶክሳዊነት በሌለው ፕሮቴስታንታዊ ማንነቱ ያገኘው ሕገ ወጥ ሹመት ኾኖ ሳለ፣ በልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ግንኙነት የበላይ ሓላፊው ሊቀ ጳጳስ አስፈጻሚነትና በእነ ንቡረ እድ አስተናባሪነት የቀድሞው የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስና ቀናዒ ኦርቶዶክሳውያን ሠራተኞቻቸው የደከሙበትን ሀ/ስብከትና መንበረ ጵጵስና ሳይገባው ለመረከብ የሚያስችለውን ደብዳቤ ሰሞኑን አጽፎ ወደዚያው ለመብረር ተዘጋጅቷል፡፡

  ሃይለ ሰይጣን ለመልስ ጉዞ ሲዘጋጅ የያዘው ሰለባ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ በቆይታው በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የታገደውንና ደርሶ ማኅበረ ቅዱሳንን እገዳደራለኹ ባዩን ‹‹የጉባኤ አርድእት›› ጉዳይ ከግንባር ቀደም የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አራማጆችና ሌሎች ግብረ አበሮቹ ጋራ በመኾንለማንቀሳቀስ መሞከሩ ተዘግቧል፡፡ በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በአዲስ መልክ እንደተዘጋጀ በተገለጸው የሃይማኖት ማኅበራት ምዝገባ አዲስ አሠራር አግኝቶ ነገር ግን በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ለመንቀሳቀስ ከመሰሎቹ ጋራ ጅር ጅር ሲል ሰንብቶ ነው የሚሄድ፡፡
  ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ፡፡ ሰሞኑን ‹‹አባ›› ገብረ መድኅንና ፅልመታዊው ቡድን በሚያካሂዱት ውትወታ ታዲያ የውጭ ግንኙነት መመሪያውንና የልዩ ጽ/ቤት ሓላፊነቱን ጠቅልለው በመረከብ ይመራሉ የሚባሉት ‹‹ሰይጣንን በዘመን እንጂ በተንኰል እንደሚወዳደሩት›› የሚነገርላቸው ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ናቸው፡፡ የፓትርያሪኩ መጋቤ ሥርዐት (ፕሮቶኮል) እንዲኾኑ አሳምኜ መልምያቸዋለኹ የሚሏቸው ደግሞ አቶ ተወልደ በኀይሉ የተባሉ ግለሰብ ናቸው፡፡ አሁን በዜግነትና ኤሚግሬሽን ጉዳይ ሠራተኛ መኾናቸው ይነገራል፡፡ ግለሰቡ በ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን ምልመላና ማግባባት የመንግሥት ሥራቸውን ለቀው የፓትርያሪኩ ፕሮቶኮል ለመኾን እንደተስማሙ ከራሳቸው ከአባ ገብረ መድኅን በዛሬው ዕለት ተሰምቷል፡፡ ሌላው የአባ ገብረ መድኅን ምልምል ለጊዜው ስማቸው ተለይቶ ያልተገለጸና በወቅቱ የግቢው ጥበቃ ሓላፊ አቶ ብርሃኔ ኀይሉ ላይ/ምትክ የሚሾሙ ሰው ናቸው፡፡
  በ‹‹አባ›› ገብረ መድኅንና በጨለማው ቡድን ዕቅድ መሠረት፣ እኒህ ሦስት የሓላፊነት ቦታዎች ተይዘው ሲያበቁ በቀጣይ ካነጣጠሩባቸው የአስፈጻሚው አካል (የጠቅላይ ቤተ ክህነት) የሓላፊነት ቦታዎች አንዱ የበጀትና ሒሳብ መምሪያው ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በዚህ መምሪያ ላይ እየሠሩ የሚገኙት ሓላፊዎች የማኔጅመንትና አካውንቲንግ ሥልጡኖች ናቸው፡፡ ከትውፊታዊውም ከዘመናዊውም ትምህርት የሌሉበት እነአባ ገብረ መድኅን ግን እኒህን ባለሞያዎች አስወግደው በምትካቸውመመለስ የሚፈልጉት ገብረ መስቀል ድራር የተባሉ የአስተሳሰብና ተግባር መሰላቸውን ነው፡፡ ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የበጀትና ፋይናንስ መመሪያ ከተነሡ በኋላ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የቁጥጥር ሓላፊው ገብረ መስቀል ድራር የሁለት ቪላዎች ባለቤት ከመኾናቸውም በላይ ለዓመታት ያካበቱት ገንዘብ ‹‹ባንኩን አጣቦታል›› በሚል ይወራባቸዋል፡፡
  እንግዲህ እነ ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን÷ ‹‹የትግራይ ተወላጆች የግቢውን አመራር ሙሉ በሙሉ እንረከበዋለን፡፡ ከዚህ በኋላ ቤተ ክርስቲያን በትግራዎት እንጂ በአማራ አትመራም፡፡ ለሚኒስትሮች የሚፈለገውን ጥቅም እያቀረብን እናስፈጽመዋለን›› የሚሉት በእኒህ ስንኩል ግለሰቦች በሚዘወሩ የቤተ ክህነቱ ከፍተኛ መዋቅሮች አማካይነት ነው፤ ትግራዎት በእኒህ የአስተሳሰብና የተግባር ስንኩላን ሊወከሉም ሊጠሩም አይችሉም፤ አይገባቸውም እንጂ!

  የዜናው ምንጮች፣ ‹‹አባ›› ገብረ መድኅንና የጨለማው ቡድን በዛሬው ዕለት አቶ ኣባይ ፀሃዬን ከፓትርያሪኩ ጋራ በማገናኘትና ፓትርያሪኩን በማግባባት ይህንፍላጎታቸውን ከዳር ለማድረስ ዕቅድ ነበራቸው፡፡ አልያዘላቸውም እንጂ!
  በእነ ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን ፕሮግራም መሠረት፣ አቶ ኣባይ ፀሃዬ ዛሬ፣ ሚያዝያ 10 ቀን 2005 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡15 ላይ ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ ገብተው በደጃፉ ቆመው ወዲያ ወዲህ ሲሉ ታይተዋል፤ እየመሯቸው የገቡትም ሲወተውቷቸው የሰነበቱት ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን ናቸው፡፡ አመጣጣቸው ግን በመንገደኛው ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን ቀጠሮ እንጂ እንደ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን ወጉን (ፕሮቶኮሉን) የጠበቀ አልነበረምና የፈለጓቸውን ‹‹መመሪያ ተቀባይ›› አላገኟቸውም፤ ‹‹መመሪያ ተቀባዩም ለስብሰባ ወጥተው በቢሯቸው አልነበሩም፤›› ይላሉ ምንጮቹ፡፡ በርግጥ አቶ ኣባይ ‹‹መመሪያ ሊሰጧቸው ተዘጋጅተውባቸዋል›› በተባሉት ቅዱስነታቸው ምትክ እዚያው በቆሙበት በአልፎ ሂያጅ ካገኟቸው ሁለት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ተቀብለዋል፡፡ ከዚህ በቀር ጨዎታቸው ከግቢው ጥበቃ አባላት ጋራ ነበርና ከቆይታ በኋላ በመጡበት አኳኋን ተመልሰዋል፡፡

  ይህም ስለሆነ የስኳር ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ኣባይ በዛሬ ዕለት ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ መጥተው ከደጃፍ ስለተመለሱበት ጉዳይ በግልጽ የተረጋገጠው፣ ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን በተመለደ ግልፍተኝነታቸው ድምፃቸውን አሰምተው ሲናገሩ ካደመጧቸው እማኞች ነው፡፡ እማኞቹ ለሐራዊ ምንጮች እንደመሰከሩት፣ ኣባይ ፀሃየ በዛሬው ዕለት ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ የመጡት ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ መመሪያ ለመስጠት እንደነበር ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን በበስጭት ተናግረዋል፡፡ በአጭሩ በብዙ እማኞች የተረጋገጠው፣ የትግራዎትን አስተሳሰብና ፍላጎት ፈጽሞ ሊወክልና ሊያስጠብቅ የማይችለው አሳፋሪውና አሳዛኙ የ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን ቀጥተኛና አሳዛኝ አነጋገር የሚከተለው ይዘት ነበረው፡፡

  ‹‹ለፓትርያሪኩ አመራር ሊሰጡ ነበር የመጡት፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከዚህ በኋላ በትግራዮች እንጂ በአማራ አትመራም፡፡ የፓትርያሪኩን ፕሮቶኮል በቅርቡ አስመጥቼ ጨርሻለኹ፡፡ የጥበቃ ሓላፊውንም አስመጥቼ ጨርሻለኹ፡፡ ከዚህ በኋላ በኣባይ ፀሃዬ መሪነት ቤተ ክርስቲያን ትመራለች፡፡ መንግሥት ኣባይን ከስኳር ኮርፖሬሽን በተጨማሪ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱን በበላይነት እንዲመሩ ትእዛዝ ተላልፏል፡፡ የትግራይ ተወላጆች የግቢውን አመራር ሙሉ በሙሉ እንረከበዋለን፡፡››

  አቶ አባይ ጸሐዬ

  አቶ አባይ ጸሐዬ

  በዕሥራ ምእቱ መባቻ ሙስናን፣ የዘመድ አዝማድና ዐምባገነናዊ አስተዳደርን ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ለማስወገድ ተደርጎ የነበረው ትግል ብፁዓን አባቶችን በመከፋፈል፣ ከዚያም አልፎ በማንገላታት መምከኑን ያስታወሱ የዜናው ምንጮች ‹‹አሁን ደግሞ አቶ ኣባይ ምን ቀራቸው?›› በማለት ይጠይቃሉ፡፡ ጉዳዩን መንግሥት፣ የቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ አመራር፣ ካህናትና ምእመናን ሁሉ የምር ሊያዝኑበት እንደሚገባም ያሳስባሉ፡፡

  በርግጥ በሐራዊ ግምገማ፣ ፓትርያሪኩ በጨለማው ቡድን አጣብቂኝ ውስጥ እንደገቡ መደምደሙ ከጊዜው የቀደመ ይመስላል፡፡ ለምን? ፓትርያሪኩ የቅ/ሲኖዶሱን አቋምና የቤተ ክህነቱን አሠራር በጣልቃ ገብነት የሚያበላሹትን ‹‹ድሮም አሁንም እቃወማለኹ›› ሲሉ አረጋግጠዋልና፡፡
  ‹‹ሰውን መጥላትም መውደድም የምንችለው በዘሩ ሳይሆን በግብሩ ነው፤ አንድ ሰው ሊመሰገንም፣ ሊሾምም ሊሻርም ሊወቀስም የሚገባው በጠባዩ፣ በግብረ ገብነቱ፣ በትምህርቱ ብቻ እየተመዘነ መኾን አለበት፤›› በማለት ጎጠኝነትን በዐደባባይ አውግዘዋልና፡፡

  ‹‹የተሟላና የተቃና ሥራ ለመሥራት ከሁሉ አስቀድሞ ብቃትና ጥራት ያለው ሥራ መሥራት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ ሰው በሰው ላይ መደራረብ ሳይሆን ትምህርትና ችሎታ ያለው፣ ለተመደበበት ሥራ የሚመጥን ሰው መቀመጥ አለበት፡፡ ለዚህች ታላቅ መንፈሳዊ ተቋም የሚመጥኑ ሰዎች መቀመጥ አለባቸው፡፡ ቅ/ሲኖዶስ ለዚህ ጉዳይ ትልቅ ትኩረት ይሰጠዋል የሚል እምነት አለኝ፤›› በማለት ትክክለኛውን ሰው በትክክለኛው ቦታ በማስቀመጥ ተቋማዊ ለውጡን ወደፊት ለማራመድ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋልና!!


  0 0

   
  Abrham Destaባለፈው የትግራይ ህዝብ በምርጫ ወረቀቶች የተለያዩ ኣስተያየቶች (ኣብዛኞቹ ስድቦች) በመፃፍ ህወሓትን ማስጠንቀቁ ፅፌ ነበር። ያኔ ባስቀመጥኳቸው ቁጥሮች ታድያ ‘ማኖ የነካሁ’ መሰለኝ።

  የህወሓት መሪዎች በሰጠሁት ስታትስቲክስና የቀበለ መረጃ ተንተርሰው በማጣራት መረጃ የወጣባቸው የምርጫ ጣብያዎች እየለዩ ይገኛሉ። ይህን ያህል መረጃ የወጣበት መንገድና መረጃው የሰጡ ሰዎች ለማወቅ ‘ኣውጫጭ’ ጀምረዋል። በተጠቀሱት አከባቢዎች የነበሩ የምርጫ ታዛቢዎችና አስተባባሪዎች (ሁሉም የህወሓት አባላት ናቸው) ‘hard ዉስጥ’ ናቸው። (ወይኔ ድሮ ለኣውጫጭ ቅኔ ነበር መድሃኒቱ።)

  በተያያዘም ህወሓቶች እኔ ለምፅፋቸው መረጃዎች ምንጮቹ እነማን እንደሆኑ (የራሳቸው አባላት ወይ የዉስጥ ሰዎች እንደሚሆኑ ጥርጥር የላቸውም) ለማወቅ ‘ኣብርሃ ደስታ የሚባል ልጅ ከነማን ጋር እንደሚንቀሳቀስ ከድሮ በበለጥ ክትትል’ እንዲደረግበት ተወስነዋል። በዚህ መሰረት ድሮ እንዲከታተሉኝ ከተመደቡት ‘የደህንነት ሰዎች’ ኣሁን በሁለት እጥፍ ይጨምራሉ። እኔም ደስ አለኝ፤ አጃቢዎቼ (ዞምቢዎቹ) በዝተውልኛላ።

  ይሄ ስልክ መጥለፍ ምናምን ተዉት እንዴ? ወይስ ብዙ …… መጠቀም እንደሚቻል ተገንዝበዋል? ለማንኛውም ሁለቱ የህወሓት/ ኢህኣዴግ ከፍተኛ ‘የደህንነት ሓላፊዎች’ ከፍተኛ ጠብ ላይ ናቸው። በሁለቱ መካከል የከረረ ጠብ ኣለ (ስም መጥቀስ ኣያስፈልግም)። እርስበርሳቸው የሚጣሉት ያህል እኔን ኣይጠሉኝም።

  የደህንነት ሰዎች ሰለማዊ ግለ ሰዎችን ከመከታተል ይልቅ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ነገሮች ቢያተኩሩ ጥሩ ነው። የገዢው ፓርቲ ህልውና ለማስቀጠል የዜጎች መብት ከመጣስ ይልቅ የህዝብን ሁለንተናዊ ደህንነት ለማስጠበቅ ቢጥሩ መልካም ነው።

   


  0 0

  በ ይሄይስ አእምሮ

  Penርዕሴ በጣም እንዳይጮኽብኝ ፈርቼ እንጂ ላደርገው አስቤና ፈልጌም የነበረው “ሰይጣንና ሰይጣናዊነት እንዴት ይታወቃሉ?” የሚል ነበር፡፡ ይህ ጽሑፌ በዚሁ ተመሳሳይ ጉዳይ ዙሪያ ባለፈው ሰሞን በአንዳንድ ድረ ገፆች የወጣውን በሴቴኒስቶች የሰላምታ መለዋወጫ ምልክቶች ምስል የተደገፈ አነስተኛ መጣጥፍ የተከተለ  ነው፡፡ ከሁሉ በፊት ግን ቀጣዩን ሥነ ቃላዊ ትውፊት ለነገሬ መነሻነት ባስቀድም ደስ ይለኛል፡፡

  የቸገረው ሰው ከገባበት የችግር ማጥ ለመውጣት የማያደርገው ነገር የለም፡፡ አንዲት ሴት፣ ልጅ መውለድ እምቢ ይላትና ለዐርባ አራቱም ታቦት ትሳላለች፤ በዚያም አልሆነላትም፡፡ በየጠንቋዩና በየደብተራው ቤትም ደጅ ትጠናለች፤ በዚያም አልሆነም፡፡ በየጠበሉና በየሀኪም ቤቱም ትንከራተታለች፤ አሁንም በዚያም አይሆን ይላታል፡፡ ቢጨንቃት ለሰይጣን ትሳላለች፡፡ ስለቷም “አንተ እንደኔው የእግዜር ፍጡር የሆንክ ሰይጣን ሆይ! ልጅ እወልድ ብዬ ብዙ ተሳልሁ፤ ወጣሁ ወረድሁ ግን አልሆነልኝም፡፡ አሁን ደግሞ ባንተ በኩል ልሞክር ወስኛለሁ፡፡ ስለዚህ እስከዛሬ ዓመት ድረስ ወንድ ልጅ ከነቃጭሉ ከሰጠኸኝ ራሴው ፈትዬ አንድ ቡልኮ በስለት አስገባልሃለሁ” የሚል ነው፡፡

  የአጋጣሚ ነገር ሆነና ልክ ባመቱ የሰማ ሰምቷት አንድ ወንድ ልጅ ከነቅጭልጭሉ ትወልዳለች፡፡ ደስታዋም ከጣሪያ በላይ ይሆናል፡፡ ከአራስ ቤት ጀምራ ትፈትልና በክርስትናው ማግሥት ለሰይጣን የተሳለችውን ቡልኮ በዕውቅ ሸማኔ አሠርታ ዝግጁ ታደርጋለች፡፡ ነገር ግን ያላሰበችው ችግር ይገጥማታል፡፡ ሰይጣንን የት አግኝታ ትስጠው? ችግር እኮ ነው፤ አንዱ ሲሟላ አንዱ አይሟላም፡፡

  በየመንደሩና በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እየዞረች “የሰይጣንን ቤተ ‹ክርስቲያን› ያያችሁ ነይ ወዲህ በሉኝ” ብትል ማን ዐውቆት ያሳያት? ብዙ ትለፋለች፤ ትደክማለችም፤ ነገር ግን በክንዷ አንጠልጥላ የምትዞረውን ቡልኮ ወይም ጋቢ የሚረከባት አንድም ሰይጣን ይጠፋል፡፡

  ችግሯን ያስረዳቻቸውና የገባቸው አንድ ብልህ ሽማግሌ ግን እንዲህ ሲሉ ይመክሯታል፡፡ “አንቺ ሴትዮ፣ ልጅ ለመውለድ ያደረግሽው ጥረት በውነቱ የሚገርምና ታይቶም ሆነ ተሰምቶ የማያውቅ ነው፡፡ አሁን ሰይጣንን ካላገኘሽውና ቤቱንም ካጣሽው በአማራጭነት እንዲህ አድርጊ፡- እሁድ ቀን ወደ አንዱ ቤተ ክርስቲያን ሂጂ፡፡ ከዚያም ማርገጃው አካባቢ ሽማግሌዎች ተሰብስበው የተጣሉ ወይም የተቀያየሙ ሰዎችን በሚያስታርቁ ጊዜ የሽማግሌ ቃል አልሰማም ብሎ ንቋቸው ከጉባኤው እመር ብሎ የሚወጣ ሰው ስታገኚ ‹በስምህ የተሳልሁትን ልሰጥህ ስፈልግህ ኖሬ ዛሬ ገና አገኘሁህ፤ ይሄውልህ ቡልኮህ› በይና ትከሻው ላይ ጣይለት፤ ሰይጣን ማለት ዕርቅና ሰላምን የማይወድና የማይፈልግ ነውና እዚያ ማርገጃው ላይ በሰው ተመስሎ ታገኝዋለሽ፡፡” ይላታል፡፡

  ‹ሞኝ የነገሩትን፤ ብልህ የመከሩትን› ነውና ያቺ ሴት እንደተባለችው ቤተ ክርስቲያን እየሄደች ያን መሳይ ሰው ታጠምድ ያዘች፡፡ አንድ ቀንም እንደድንገት ሃሳቧ የሚሣካበት ምቹ አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡ አንድ ደመ ሞቃት ሰው የሽማግሌዎችን ምክርና ተግሣጽ እንዲሁም የማስታረቂያ ሃሳብ ንቆ “ደግሞ እናንተን ብሎ አስታራቂ! ቀልማዳ ሁላ፤ እኔ ነኝ ደግሞ ‹በድየሃለሁና ይቅር በለኝ ብዬ እሱ እግር ላይ የምወድቅ?› የወሬ ቋቶች! …” በማለት ተስፈንጥሮ ከጉባኤው ሲወጣ ታየዋለች፡፡ ይሄኔ በደስታ እየተፍነከነከች አፈንጋጭ ጎልማሣውን ጠጋ ትልና “እሰይ! እንኳን አገኘሁህ! አሁን ገና ገበያየ ሞላ! ለስንት ጊዜ ስፈልግህ ኖሬ ዛሬ ገና ተሳካልኝ፡፡ በል ስለትህን ተረከበኝ” ትልና ቡልኮውን እሰውዬው ትከሻ ላይ ትጥልለታለች፡፡

  ሰውዬውም ይደነግጥና ‹እንዴ? ምንድነው እሱ – ምን አድርጌልሻለሁ?…› በማለት ምክንያቱን ይጠይቃታል፤ እሷም በተመከረችው መሠረት ነገሩን ከሥሩ ታስረዳዋለች፡፡ ይሄኔ ያ ሰው ‹ሰይጣንነቱ› ይከሰትለታል፤ እሱ ሰው እንጂ ሰይጣን እንዳልሆነ በማስረዳት ጋቢውን ይመልስላትና ወደጉባኤው ተመልሶ ሽማግሌዎቹንም ይቅርታ ጠይቆ ቀድሞ በተነገረው የማስማሚያ ቃላዊ ሠነድ መሠረት ከባላንጣው ጋር ይታረቃል፡፡

  ብልሁ መካሪ ሽማግሌ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ መምታታቸውን ልብ ይሏል፡፡ መግቢያየ ይህን ይመስላል – አሁን ወደዋናው መስመር ልመልሳችሁ፡፡

  ሰይጣን እንዴት ይታወቃል? ተከታይ ጋሻ ጃግሬዎቹስ እንዴት ይለያሉ? በጣም ቀላል ነው፡፡ በቅድሚያ ግን እንደመነሻ ከአሥራ አንዱ ሰይጣናዊ መመሪያዎች ሦስቱንና(4ኛውን፣ 7ኛውንና 11ኛውን) ዘጠኙን ሰይጣናዊ ኃጢኣቶች ቀጥለን እንመልከት፡፡

  4.  በቤትህ የመጣ እንግዳ ካበሳጨህ ያለአንዳች ርህራሄ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ አጸፋውን መልስለት፡፡ (ዐይንን ላጠፋ ዐይንን ማጥፋት ከሚለው የሀሙራቢ ሕግ ጋር የሚመሳሰል)

  7. ፍላጎቶችህን ለማሳካት ጥንቆላና መተት ተጠቅመህ ከሆነ ለዚህ (ሰይጣናዊ) አበርክቶ ዕውቅና ስጥ፤ ምሥጋናም አቅርብ፡፡ ይሁንና በጥንቆላና በምትሃት ስኬት ጫፍ ላይ ከደረስክ በኋላ የበላህበትን ወጪት ሰባሪ ሆነህ ሰይጣንን ብትክድ ያገኘኸውን ሁሉ ታጣለህ፤ የሰይጣን በረከትም ይለይሃል፡፡

  11. በየትኛውም ግዛት ስትጓዝ ስለምንም ነገር ሃሳብ አይግባህ፤ በጉዞህ ላይ የሚያስቸግርህ ሰው ቢገጥምህ በቅድሚያ እንዲተውህ አስጠንቅቀው፤ ካልተወህ ግን ድራሹን አጥፋው፤ ድባቅ ምታው፡፡

   

  ዘጠኙ ኃጢኣቶች (ሴቴኒስቶች ሊተላለፏቸው የማይገቡ የሃይማኖቱ መሥራች አንቶን ሌቪ የቀመራቸው)

  1. ደደብ መሆንና በሌሎች ተበልጦ መገኘት (ኃጢኣት ነው!)
  2. እውነትን እንዳመጣጧ በኃይልም በዘዴም በተገኘው ሥልት ሁሉ ከመጋፈጥ ይልቅ እንደቀሪው ማኅበረሰብ በአስመሳይነትና በነባር ባህል ለመመሳሰል መሞከር
  3. የኃይል ግብረ መልስ የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች በታጋሽነት ማለፍ
  4. የሆነን እንዳልሆነ ወይም ያልሆነን እንደሆነ አድርጎ ራስን ማታለል
  5. የራስን ስሜት ከመከተል ይልቅ በይሉኝታና በሀፍረት ታስሮ የሌሎችን ፍላጎት ተቀብሎ በየዋህነት ከጎጋው ሕዝብ ጋር መንከርፈፍ
  6. ወደተፈለገው ግብ የሚያደርስ (ማንኛውም ዓይነት) ራዕይና ዓላማ አለመያዝ
  7. ያለፈን የሃይማኖትና የማኅበረሰብ ትውፊት መርሣት ሲገባ ያን ማስታወስ
  8. አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በራስ ስኬት መኩራት ያለመፈለግና ያለመቻል
  9. በሁሉም ዘርፍ ሁሉንም ቀድሞ ለመገኘት በማንኛውም መንገድ የተቻለውን ሁሉ ጥረት አለማድረግ

   

  ሰይጣናዊነትና ተከታዮቻቸው (Satanism and Satanists) በይፋ ቤተ አምልኮ (Church of Satan) አቁመው ሰይጣንን ማምለክ የጀመሩበት ዘመን የቅርብ ጊዜ ክስተት ቢሆንም ይህ ሃይማኖት በድብቅም ይሁን ሲቻል በግልጽ፣ በሰይጣን ስምም ይሁን በሌሎች መጠሪያዎች በዚህች ዓለም ውስጥ ኅልውናውን ያገኘው ከሰው ልጆች መፈጠር ጋር እንደሚያያዝ መገመት አይከብድም፡፡ “ሊበሉት የፈለጉትን አሞራ ስሙን ይሉታል ጅግራ” እንዲሉ ሆኖ በስያሜ ለሰይጣን የቀረበም ይሁን የራቀ በተግባር ግን ሰይጣናዊ የሆነ የእምነት አካሄድ በዓለማችን ከረጂም ዘመን ጀምሮ በገሃድ ይታይ እንደነበር ለማንም መዝገብ አገላባጭ እንግዳ ነገር አይሆንም፡፡ ባገራችን የቆሌ ባዲገዝና የቦረንትቻ ባህል፣ ‹እነዚህ ባለውቃቢዎች ለካንስ ክርስቲያኖች ናቸው› በሚል የዋህነት ሰው እንዲከተላቸው ‹ገብርኤልንና አቡየ ፃዲቁን ዘክሪ፣ የሚካኤልን ጠበል ለሦስት ሰባት ጠጪ…› የሚሉትን አጭበርባሪ ባለአውሊያዎች፣ ሌሊት ቅኔ ማኅሌት ላይ ቃለ እግዚአብሔርን በዕዝልና በአራራይ እያንበለበሉ ቀንና ባሳቻ ሥፍራ ግን መጥሐፍ የሚገልጡ ደባትርና ታላላቅ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት… በሙሉ የአጋንንት ጭፍራዎች መሆናቸውንና ይህም ዕኩይ ተግባር ከጥንት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ማኅበረሰብኣዊና ሃይማኖታዊ ክዋኔ እንደሆነ መገንዘብ አይቸግርም – የሁለት ጌቶች አሽከር መሆን የሚፈልግ ሰው ሁሉ የእግዚአብሔር ሣይሆን የሰይጣን አሽከር ነው፡፡ በዚህ መስመር መጓዙ ብዙ ያደክመናልና ባጭሩ እንመለስ፡፡

  መጽሐፍ ቅዱስ “ጣፋጭ ፍሬ ከዛፍ ላይ እንዳለ ያስታውቃል” ይላል፡፡ የክርስትና እምነት ቁንጮ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስም እዚህ የምናነሳቸውን ሰዎች “በሥራቸው ታውቋቸዋላችሁ” ይለናል፡፡ አዎ፣ የማን ማንነት በሥራው ይታወቃል፡፡ አዋዋላችንም የሚናገረው ብዙ ነው፡፡ ከነተረቱ “ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን ልንገርህ” ይባላል፡፡ ስለዚህ ከየትኛው ወገን እንደሆንን ለመለየት ቀላሉና ብቸኛው መንገድ በሥራችን ማለትም በዘወትር ተግባራችን የምንገልጠው የዕኩይነት ወይም የደግነት መገለጫ ምግባራችን እንጂ የአነጋገራችን ለዛና መስህብ ወይም የአለባበሳችን ማማር ወይም የፂማችን መንዠርገግ አይደሉም፡፡ የምንከተለው ሃይማኖትም ምናልባት ጠቋሚ እንጂ ትክክለኛው የመጽደቃችን ዋስትና አመላካች ሊሆን አይችልም፡፡ በአላህ ስም አንገት እየቀሉ፣ በእግዚአብሔር ስም ግድያን ጨምሮ ሕዝብ ላይ ሰይጣናዊ ቁማር እየተጫወቱ፣ ኩነኔ ካልሆነ ጽድቅ ይገኛል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡ ሰይጣን ደግሞ ብልጥ ነው፤ የምታደርገው ነገር እንጂ የምትከተለው ሃይማኖት ጉዳዩ አይደለም፤ በሥራህ ካከበርከው ፓትርያርክም ሁን ኢማምም ሁን ራባይም ሁን ኮርተህ የመንግሥቱ ወራሽ ነህ፤ እርሱም የአንተን ነፍስ ካለተቀናቃኝ ተረካቢ ነው፡፡ ምሥጢሩ ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ያለው ነገር ሁሉ ለ‹ምሁራዊ› ፍልስፍናና ለጉንጭ አልፋ ክርክር ፍጆታ የሚውል እንቶፈንቶ ነው፡፡

  ከዚህ በተያያዘ ግን በቅድሚያ የጋራ መግባባት እንዲኖረን የሚያስልግ ጉዳይ አለ፡፡ እሱም ዕኩይ ስንል ምን ማለታችን ነው? ደግ ስንልስ? ለሁለቱም መለኪያችን ምንድነው? በማንስ ዕይታ? ለአንተ ዕኩይ የሆነ ነገር ለእኔ ደግ ከሆነ ዳኛችን ማን ሊሆን ነው? በአንድ ሀገር ወንጀል የሆነ ነገር በሌላ ሀገር ፍቁድ ከሆነ የጋራ መግባቢያው የወል ስምምነት እንዴት ሊፈጠር ይችላል? ነገሩ ቀላል አይደለም፡፡ ብዙ ክርክር ያለው ነገር ነው፡፡

  ምሳሌ ወስደን ማየት እንችላለን፡፡ በአንዳንድ የክርስትና ሃይማኖት ዘርፎች የተመሳሳይ ፆታዎች ወሲባዊ ግንኙነት ከቀሲስ እስከ ሊቃነ ጳጳሣት ድረስ እንደሰደድ እሳት የተዛመተ በመሆኑ “የኔ ሶዶማዊ መሆን እግዚአብሔርን በ‹ቅንነት› ከማገልገል ጋር ምን ያገናኘዋል?” በማለት በምድራዊ መንግሥቶቻቸው ሕጎች ብቻ ሳይሆን በቀኖና ቤተ ክርስቲያንም ውስጥ በቃለ ዐዋዲነት እንዲጽድቅላቸው የሚታገሉ ‹የእግዚአብሔር ቤተሰቦች› በብዛት መታየት ከጀመሩ ቆይተዋል፡፡ በሌላ በኩል ከሰይጣን አምላኪዎች አካባቢ ለዘብተኛ የሚባሉት ይህን እኛ ብዙዎቻችን በሰይጣናዊነት የምንፈርጀውን የግብረ ሶዶም ተግባር የሚቃወሙና እንዲያውም ‹ሰው ካልተነኮሰህ አንተ ቀድመህ አትተንኩሳቸው› ብለው የሚያምኑ “ደጋግ” ሰይጣናውያን አሉ፡፡ በክርስትና ሃይማኖት መስጠት (በብቸኝነት ባይሆንም) እንደሚያጸድቅ ይሰበካል፤ በሌላም በኩል በዚሁ ሃይማኖት አንዳንድ የተማሩ ተከታዮች ዘንድ መስጠት ሰውን ስለሚያሰንፍ ከአጽዳቂነቱ ይልቅ አስኮናኝነቱ ይበዛል የሚሉ ወገኖችም አሉ፡፡ የክርክሬ አካሄድ ለሁሉም ግልጽ ይሆናል ብዬ አምናለሁ፡፡

  ስለዚህ ዕኩይነትና ደግነት እንደቁንጅና ሁሉ የተመልካቹን ፍርድ የሚጠባበቅ ዋጋው በታሳቢነት የሚሰላ ሊሆን ነው ማለት ነው፡፡ ነገሩን ብዙ አናራቅቀውና ሰይጣናዊነትንና ሰይጣን አምላኪነትን እስካሁን ብዙዎቻችን የሚገባንን ያህል አድርገን እንውሰደው፡፡ በነገራችን ላይ በግርድፍ ግምት አራት ዋና ዋና ቅርንጫፎች እንዳለው ከሚገመተው የሰይጣናዊነት እምነት ውስጥ ‹አማፂ ሰይጣናዊነት/Rebel Satanism›ን ያህል የከፋ የክፋትና የአመፃ ድርጊት የሚፈጽም እንደሌለ በዘርፉ ዕውቀት ያላቸው ሰዎች ይናገራሉ፡፡ በተለይ በአሁኑ ወቅት ዓለምን ከጽንፍ እስከ አጽናፍ እያመሳት ያለው አፍራሽ ኃይል (Negative Energy) እንግዲህ ይሄኛው ነው ማለት ነው፡፡ ተከታይ የጥፋት ኃይሎቹም በሀገራቱ መንግሥታትና በኅቡዕም ይሁን በግልጽ በሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ቡድኖች ውስጥ የተሰገሰጉ በደም የሚነግዱ ጨካኝ ዜጎች ናቸው፡፡ የነሱ ጭካኔ በጨለማው ንጉሥ በዲያብሎስ ዘንድ የሚያሸልምና የሚያሾም ድንቅ ሥራ ነው፡፡ በገደሉ ቁጥር ደስታቸው ይበዛል፤ ባሰቃዩ ቁጥር የመንፈስ መነቃቃትን ያገኛሉ፡፡ የደግነት ምግባር የሚያስከፋቸው፣ የክፋት ሥራ ጮቤ እሚያስረግጣቸው የተንኮልና ሸር አምባሳደሮች ናቸው፡፡ በግዛታቸውና በዘመነ ሥልጣናቸው የተገኘን ምሥኪኖች ግን እናሳዝናለን – ከልባዊ በስማምና አቡነ ዘበሰማያት ሌላ ምንም ጦር የሌለን ድሃ ወገኖች ይህ ዘመነ ሰልቢያኖስ ክፍላችን አይደለም፡፡

  ጉንጭ አልፋ ክርክራችንን ትተናል፡፡ ክፉ ማለት ሆን ብሎና አለ አንዳች ምክንያት – ለሥጋዊ ጥቅምና ፍላጎቱ ሲል የሚገድል፣ የሚያሥር፣ የሚያሰቃይ፣ የሚጠላ፣ የሚያዳላ፣ ሆን ብሎ የሚጎዳ፣ የማይስማማ፣ የሚያስርብ፣ የሚያስጠማ፣ የሚያሰድድ፣ የሚያሳድድ፣ የሚከፋፍል፣  … ነው ብለን ለጊዜው እንስማማ – እንደወያኔዎች፡፡ እነዚህንና ሌሎች ብዙዎቻችን በክፉ ሥራነት የምንስማማባቸውን የክፋተኝነት ድርጊቶች የሚፈጽም ዐወቀውም አላወቀውም – ወደ ቤተ ሣጥናኤል ሄዶ ጸለየ አልጸለየ – የቤተ ሰይጣን ተከታይ (ሴቴኒስት) ነው፡፡ እርግጥ ነው ከሴቴኒስቶችም ‹ዘመናዊ ሴቴኒስቶች(Modern Satanists)› የሚባሉት በስም ብቻ ሣይሆን በተግባርም ‹ክርስቲያን ነን› ከሚሉ አንዳንድ አስመሳይ ወገኖች ጋር የተቀራረበ እንዲያውም የተሻለ ባሕርይና አመለካከት እንዳላቸው በዘወርዋራም ቢሆን ከፍ ሲል ዐይተናል፡፡ ትልቁ ቁም ነገር ስማዊው የየሃይማኖቶቻችን መጠሪያ ሳይሆን ዋና የማንነት መገለጫችን ተግባራችን ነው፡፡ እናም እንደኔ እንደኔ ክፉኛ ግራ ከመጋባቱ የተነሣ በሰይጣን ግዛት ሥር አድሮ ነገር ግና መልካም ሥራ የሚሠራ ሰው በእግዚአብሔር ግዛት ሥር ሆኖ በማወቅ ክፉ ሥራ ከሚሠራ ሰው ያነሰ ዋጋ ያገኛል ብዬ አልገምትም፡፡ ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዋጋችንን የሚተምነውና የየመክሊታችንን የሚሰጠን በሰው – ሠራሽ የልዩነቶች ጎራ ተመሥርቶ ሳይሆን በግብር በምናሳየው መልካም ሥራችን ላይ ተመሥርቶ መሆኑን አምናለሁ፡፡ የሆነው ቢሆን ግን “ዕብድ ቢጨምት እስከ ዕኩለ ቀን ነው” እንዲሉ ነውና በተለይ ሰይጣናዊነትን በምንም መንገድ የማላበረታታ መሆኔን በዚህ አጋጣሚ ላሰምርበት እወዳለሁ፡፡

  ዓለማችንን የሠይጣን መፈንጫ ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ እጅግ በጣም የቆዬ እንደሆነ ይነገራል፡፡ እንደዚህ ዘመን ግን ሰይጣናዊነት በምልዓት የተገለጠበት ዘመን ታይቶ አይታወቅም ነው የሚባለው፡፡ በተለይ የፊልምና የሙዚቃው ኢንዱስትሪ ግዘፍ ነስቶ እንዲህ ጫፍ በደረስ ሁኔታ የዓለም ወጣት ዜጎችን መጫወቻ ማድረግ ከተጀመረ ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ወዲህ የእግዚአብሔር ስም እንዳይጠራ እንኳን እዬተደረገ ያለው ሰፊ ዘመቻ በታላቅነቱ ወደር የሚገኝለት አልሆነም – እውነቱን ለመናገር የእግዚአብሔርን ስም መጥራት በርሱም ማመን ፋራና ኋላ ቀር እያስባለ፣ ብዙዎችንም እስከማሣፈር በደረሰ ሁኔታ ከእውነተኛው መንገድ እያሰናከለ የምንገኝበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ በተቃራኒው ግን ዱሮ ያሣፍር የነበረ ጠንቋይና ደብተራ ቤት እየሄዱ መጎናበስና የሰዎችን ጫማ መላስ ዛሬ ዛሬ የሚያኮራ የዘመኑ ፋሽን ሆኗል፡፡ ጎረቤትህን፣ ጓደኛህን፣ ሀብታምን፣ ታማሚን፣ ምቀኛ ድሃን… ተመልከትና ይህ የምልህ ነገር እውነት ሀሰትነቱን አጢን፡፡ የጠፋንበት ዘመን ላይ እንደምንገኝ አትጠራጠር፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም ባለፀጋና የተደላደለ ኑሮ የሚኖር አብዛኛው ሰው አንድም የሰይጣን አምላኪ ነው፤ አንድም በተለያዩ ወንጀሎች የሚታማ ነው – ሁሉም ግን የሰይጣናዊነት መገለጫ በመሆኑ ሰውዬው ያው ሴቴኒስት ነው – እንደአካሄድ ቅዱስ ሰይጣንና እርኩስ መልአክ የሉም – ምርጫው አንድና አንድ ብቻ ነው፤ እግዚአብሔር ወይ ሰይጣን – ብርሃን ወይ ጨለማ፡፡ የምልህ ነገር የምቀኛ ወሬ እንዳይመስልህ፡፡ አንተም ብልጥ ከሆንክ ሰይጣን የመሆንና እንደነሱ የመክበር ቦርቃቃ ዕድል አለህ፤ አለበለዚያ ለፍተህና ጥረህ ግረህ በወዝህ መኖር፡፡ በበኩሌ ሰይጣን የመሆን ዕድሉ ነበረኝ፤አለኝም፡፡ ግን አልተጠቀምኩበትም፤ወደፊትም የምጠቀምበት አይመስለኝም፡፡ ስለወደፊት እርግጠኛ መሆን ስለማይቻል ነው የተጠራጠርኩ የመሰልኩት፡፡ እንጂ የሰይጣን ሀብት ምኑ ሊያስቀና! በአፍንጫየ ይውጣ!

  ከፍ ሲል እንደተገለጸው ወጣቱን ማግኘት የሚቻለው በአብዛኛው በሙዚቃና በፊልም እነዚህንም ዋነኛ መደላድል በሚያደርገው በወሲብ አማካኝነት ነው፡፡ እነዚህን ነገሮች ለማሣካት ደግሞ የገንዘብ አስፈላጊነት አማራጭ የለውም፡፡ ለዚህም ነው መጽሐፉ “ገንዘብ የኃጢኣት ምንጭ ናት” የሚለው፡፡ በእያንዳንዱ ሀብት በስተጀርባ ወንጀል ስለመኖሩ በተደጋጋሚ የሚወሳውም የገንዘብን የነፍስ አማሣኝነት አጉልቶ ለማሳየት ነው፡፡ አሁን በዘመናችን ከፈጣሪ ይልቅ ቤተ አምልኮ አልቆመለትም ጽላትም አልተበጀለትም እንጂ ገንዘብ እስከመመለክ የደረሰው ሰው ራሱ በሠራው የምድር ንዋይ ፈጣሪን መለወጡን የሚያሳይ የዝቅጠት ምልክት ነው፡፡ በዚህ ዘመን እጅግ ብዙ ሰዎች ሁሉንም የሃይማኖትና የሞራል ድንበሮች ጥሰው አቅላቸውን በመሳት ገንዘብን የሚያሳድዱት የዓለም ብልጭልጭ ነገሮች ካለገንዘብ እንዲሁ በምኞት ብቻ ሊገኙ ስለማይችሉ ነው፡፡ እዚህ ላይ ምርጫው ሁለት ነው – ከጤናማ ኅሊና ጋር በእውነተኛው ገቢ በድህነት እየኖሩ መቸገር ወይም በሰይጣናዊ ቀድዶ ሕክምና ኅሊናን ከጭንቅላት አውጥቶ በ‹ጅብ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ› ዘይቤ በተገኘው መንገድ ሁሉ ለቁሣዊ ሕይወት ብልፅግና መጣር፡፡ በዚህኛው አቅጣጫ ለሚመራ ሰው ገንዘብ እስካስገኘ ድረስ ማንኛውም እንቅስቃሴ በሕግ ቢከለከልም በተግባር የተፈቀደና ያልተከለከለ ያህል የሚቆጠር ነው፡፡

  መንግሥታዊ ሥርዓቶችም የዚሁ የንቅዘት ሥርዓት አባላት በመሆናቸው እነሱም የበኩላቸውን ይሞስናሉ፤ ከቢጤዎቻቸውም ጋር ይተባበራሉ፤ ያስተባብራሉ፡፡ የማይሞስን የነሱ ፀር መስሎ ስለሚታያቸው ባገኙት ዘዴ ሁሉ ያጠፉታል – በ‹የምዬን እከክ ወዳብዬ› ሥልት ሙሰኛ ነው ብለውም ዘብጥያ ሊያወርዱትና በፈጠራ ክስ ሊያሰፈርዱበትም ይችላሉ፡፡ ስለሆነም ሞሳኝና አስሞሳኝ፣ በራሱ አንጡራ ገቢ የማይኖር፣ ያልተፈቀደለትን ማንኛውንም ነገር ከሰው የሚቀማ፣ ሥልጣኑን ለመጨቆኛ እንጂ ባግባቡ የማይጠቀም፣ ሕዝብን በሥልጣኑ የሚበድልና የሚያጉላላ ሁሉ የሰይጣን ወገን ነው፡፡ በዚህም የሰይጣን ወገን ይታወቃል፡፡

  ወደሰይጣናዊ ተቋማትና አመራሮቻቸው እንመለስ፡፡ ብዙዎቹ ምናልባትም ሁሉም የነዚህ ዓለም አቀፍ ታላላቅ ተቋማት ባለቤቶች በኢኒሼሽን ፒራሚዳዊ የደረጃ ሠንጠረዥ ከፍተኛውን ዲግሪ በያዙ የዚህኛው ወይም የዚያኛው ምሥጢራዊ ሰይጣናዊ ድርጅት አባላት ናቸው፡፡ (ለጠቅላላ ዕውቀት፣ የቤተ ሣጥናኤል አመራር መዋቅር ዲግሪ ከ1-5 ሲሆን ‘the Skull and Bones’ን የመሳሰሉ ከዓለማችን ሀብትና ሥልጣን ጀርባ የሚገኙና ወደጥልቁ የጥፋት ባህርም እያዳፉን የሚገኙት የምሥጢራዊ ድርጅቶች ዲግሪ ደግሞ ከ1-33 እንደሚደርስ ይነገራል፡፡ ይህ ዲግሪ ለነሱ እንደማዕረግ የሚቆጠር ነው – በልፋት(በጥፋት?) የሚገኝ!)

  የሚደነግጥ እንዳይኖርብኝ እሰጋለሁ እንጂ በአሁኑ ወቅት ሴተኒስቶች ሁሉንም የዓለም ነገር ተቆጣጥረዋል፡፡ የቀራቸው ያለ አይመስልም፡፡ አንተንም አንቺንም እኔንም ተቆጣጥረውናል፡፡ በምትበላው፣ በምትጠጣው፣ በምትለብሰው፣ በምትጓጓዝበት… ይመጡብሃል – በዕቃዎች ላይ በግልጥም ይሁን በሥውር በሚለጥፉብህ የ666 ምልክታቸው ብቻ እንዳይመስልህ – እስትንፋስህን ሳይቀር ተቆጣጥረውታል እያልኩህ ነው ወንድሜ (ፈገግ በል አስኪ፡- ሽንት ቤት ገብተህ ወደዋናው ጉዳይ ከመግባትህ በፊት በእንትንህ ሙዚቃ ስንቴ እንደተዝናናህ ሳይቀር እነሱ ከፈለጉ ያውቁታል፡፡ አዲዮስ ‹privacy›፣ ገባህ? አትታዘበኝ – አዲስ ነገር የለም፡፡ )

  በተለይ ኢትዮጵያን በመሰሉ ድሃ ሀገሮች ውስጥ የሚገኘውን የድሃ ገበሬ ማሣ በማዳበሪያ አፈር ድሜ አብልተውታል፤ በኬሚካላቸው የገበሬውን መተዳደሪያ የተፈጥሮ ማዕድን ሲያቃጥሉት በውድ ከሚገዛው የነሱ ማዳበሪያ ውጪ አፈሩ ዘር ማብቀሉን ተወ – ኬሚካሉን ልግዛ ሲል እነጉናና አምባሰልን በመሰሉ የሀገር ውስጥ ወያኔያዊ ሼሪኮቻቸው አማካኝነት ዋጋውን ሰማይ ሰቀሉት፤ እኛንም ገበሬውንም ለችግር ዳረጉንና ሁላችንም ኤሎሄ እንል ጀመር፡፡ በግብርናውም ሆነ በኢንዱስትሪውና በፖለቲካው መስክ ከነሱ ቁጥጥር እንዳትወጣ የማያደርጉት ነገር የለም፡፡ ድመት የገደለቻትን ዐይጥ እስክትበላት ድረስ እንደምትጫወትባት ሁሉ እነዚህ ጥቂት የአጋንንት ውላጆች እንዳሳሁርታ በቅጽበቶች እየተራባ የሰባት ቢሊዮንን ጉበን በቅርቡ ያለፈውን የዓለም ሕዝብ ጢባጢቤ እየተጫወቱበት ናቸው፡፡ በቁራጭ አሞሌ ጨው በሬ ወደመታረጃው እንደሚሄድ እነዚህ ገብጋቦች የዓለምን ሀብትና ፖለቲካ በቀጥታና በእጅ አዙር ተቆጣጥረው ወደ አጠቃላይ ውድመት እየመሩን ናቸው፡፡ በዚህም ሰይጣኖችን ታውቃለህ!

  የትም ሂድ የትም ግባ ቤተ ክርስቲያንን ሳይቀር በአለቃቸው የሰይጣን መንፈስ ተቆጣጥረዋል – ኢትዮጵያ ውስጥ ለምሳሌ እስከቅርብ ሩቅ ድረስ ዋልድባ ገዳምን ሰይጣን እምብዝም አይደፍርም ነበር (ይባላል)፤ አሁን ግን ገዳሟ መንፈላሰሻቸው ሆናለች – የነደብረ ሊባኖስና የሌሎች ደብረዎች ነገር ተከድኖ ይብሰል፡፡ እነዚህ ገዳማትና አድባራት ዋና መሥፈሪያ ቆጣቸው ናቸው፤ ጸሎቱ የማያርገው፣ ስብከቱ የደነደነ ልብን አሟምቶ ከኃጢኣት መንገድ የማይመልሰው፣ ሕዝበ ክርስቲያን የዳነ እየመሰለው ሃይማኖቱን እንደሸሚዝ የሚቀያይረው ከዚህ የተነሣ ነው – ሀሰት ከተናገርኩ … ዳሩ አይማልም ለኬ፡፡ የምለው ግን እውነቴን ነው!

  ዘመኑ የጭንቀትና የጥበት ነው፡፡ መዳን በዚህ ወይ በዚያ አለ የሚባልበት ድኅነት ግን የሌለችበት እጅግ አስጨናቂ ዘመን ላይ ልንገኝ የቻልነው አእምሮኣችንን የስንግ በያዙን ሴቴኒስት መሪዎቻችን አማካይነት ራሱ ዲያቢሎስ የፊጥኝ ስላሰረን ነው፤ አሳዳጃችን ሰይጣን በምንሄድበት ቦታ ሁሉ ቀድሞ ይጠብቀናል፡፡ እሥረኞቹ ደግሞ በጎቹ ብቻ ሣንሆን እረኞቻችንም ናቸው፡፡ አዲስ አበባን ተመልከት፡፡ በዲኤክስና በቪታራ… የሚዝመነመነውን የደብር አለቃና የሀገረ ስብከት ባለሥልጣን ካህን ስታይ፣ የየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ታዋቂ ቀሣውስትና መዘምራን ወሰባኪያን በምቾት አብጠው እንደ እምቧይ ሊፈርጡ ተቃርበው ስታይ ያቺ ካላት ሳይሆን ያላትን ከመቀነቷ ፈትታ ወደ ሙዳየ ምጽዋት የምትጨምር ሴት በዐይነ ልቦናህ ትታይሃለች፡፡ እኛ እየኮሰመንን እነሱ እየተነፉ፣ እኛ እየደኸየን እነሱ እየከበሩ፣ እኛ እየፆምን እነሱ እየፈሰኩ፣ … መኖር ተብሎ አለሃይማኖትና አለመሪ የአጋንንት ወጀብ እያላጋን ተገትረን አለን፡፡ ዘመኑ ቀርቧል የምንለው እንግዲህ ከነዚህ ነገሮች አንጻርም ነው፡፡ ሁሉም የውሸት ነው – የታይታ፡፡ ይህን ግን አስብ፡- ‹የእግዚአብሔርና የሰይጣን ሰዎች በሥራቸው ይታወቃሉ፤ የታይታ ፆምና ስግደት ወይም የፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ዓይነቱ የአለባበስና የአነጋገር ላህይ ሳይሆን – እምነት፣ ሥራና ፍቅር የሰውን ምግባር ይገልጣሉ፡፡› በቃ፡፡

  የሌሎችን የእምነት ቤቶችም ተቆጣጥረዋል፡፡ ሚዲያውም በነሱው ቁጥጥር ሥር ነው፡፡ እነሱ የሚፈልጉት ዜናም ሆነ ሀተታ ይነገራል፤ ሌላውና ከነሱ ፍላጎት ውጪ የሆነው ግን ይታፈናል፡፡ የየሀገራቱ መሪዎች ሴቴኒስት ካልሆኑ ከሥልጣን የሚወርዱበት መንገድ ይጠናና ተግባራዊ ይደረጋል፤ ምክንያቱም እንደኃያላኑ መንግሥታት መሪዎች ሌሎቹም ሴቴኒስቶች ካልሆኑ እንደልብ አይታዘዟቸውም – ሰይጣንና መልአክ – እርኩስና ቅዱስ ውሃና ዘይት ናቸውና፡፡ የሆሊውድንና የሌሎች -ውዶችን ፊልሞችና ሙዚቃዎች ቃኙ፤ ከሞላ ጎደል ሁሉም ማለት በሚቻል ሁኔታ አገልግሎታቸው በሰይጣናዊው አዲሱ የዓለም ሥርዓት [The New World Order] መሠረት የተቃኘ ነው፡፡ ለነሱ የማይስማማ ይወገዛል – ተጠርጎ ይጣላልም፤ ለነሱ የሚስማማ ጨካኝና አውሬም ቢሆን እንደጫጩት ጉያ ውስጥ ይታቀፋል(ሳዑዲንና ባሕሬይንን ያስቧል)፤ (የቬንዞላ ሕዝብ አሜሪካ የምትፈልገውን ካፒሪሌን ትቶ ማዱሮን መምረጡ ስህተት ነው፤ እና አሜሪካ የምርጫውን ውጤት አትቀበልም፡፡ የኢትዮጵያው የ97 ምርጫ ግን – ዌል – እንደዴሞክራሲያዊ ተሞክሮ ስለሚቆጠር – ተቃዋሚ በዝረራ ቢያሸንፍም – እርግጥ ነው – ወያኔ አሸንፏል ማለት ይቻላል፡፡ ተቃዋሚዎች የተሰጣቸውን ወንበር መቀበልና በመናጆነት በወያኔ ፓርላማ በረት ገብተው ማንቀላፋት ነበረባቸው፡፡ … የጉዶች ምድር፣ የምፀት ዓለም… “ሥራ ለሠሪው እሾህ ላጣሪው…”ይብላኝ ለንጹሑ ሰላማዊ ሕዝብ! ዐይጥ በበላ ዳዋ ተመታ …

  በነገራችን ላይ ሁለት ወጣቶች ብቻ አሜሪካውያንን በ‹ጦር ሜዳ ውሎ›ና በፕሮፓጋንዳ እንዲህ ‹ሽንት በሽንት› ያደረጉ፣ የዓለምን ሚዲያ በመሪና በሰበር ዜናነት ከዳር እዳር ያጥለቀለቁ፣ ፕሬዝደንት ኦባማን ሣይቀር እንቅልፍ አሳጥተው ያስጨነቁና ዕንባ በዕንባ ያስደረጉ አሥርና አሥራ አምስት ቢሆኑ ምን ያሳዩ ይሆን? በዛሬዋ ቀን እያዘንኩም ቢሆን ሁለት ዜናዎች ፈገግ አድርገውኛል፡፡ አንደኛው እነኢራንንና ሰሜን ኮሪያን ፌሽታ በፌሽታ የሚያደርገው ምናልባትም በሣቅ የሚያፈነዳው የቦስተኑ ክስተት ሲሆን ሁለተኛው ያ ሙሻራፍ የሚባል ገልቱ ሰውዬ በሀገር ክህደትና በሌሎች ወንጀሎች ዘብጥያ ሊወርድ ከሞቀ የስደት ኑሮው መመለሱና ዛሬ በፖሊስ መያዙ ናቸው – የሥልጣን ፍቅር አነሁልሎት እውነቱ ተሸፈነበትና ጉድ ተሠራ፡፡ በጊዜያችን ብዙ ነገሮች ከመግረም እያለፉ እንደጅል በሞኝነት ማሣቅ ይዘዋል፡፡ ፈገግ ብትሰኙልኝ አንድ አስቂኝ ታሪክ እዚች ላይ ባጭሩ ላስታውሳችሁ፡፡(የአሜሪካው ትዕይንት ግን ሆሊውድ በቦስተን የቀረጻ ልምምድ እያደረገ አልመሰላችሁም?)

  በዱሮ ጊዜ ነው አሉ፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት አንድ የጦር ቡድን ወደ አንድ ጫካ ይልካል፡፡ ያስቸገረ አስቸግሮ ነበርና፡፡ ከጦርነቱ መልስ አንድ ሰውዬ የጦር አዛዡን ጠጋ ይልና እንደሚከተለው ይጠይቀዋል፡፡

  ጠያቂ፡- ውጊያው እንዴት ነበር? በቀላሉ ቀናችሁ ወይንስ ጉዳት ደረሰባችሁ?

  አዛዥ፡- ኧረ ምኑ ይወራል! በጣም ኃይለኛ ጦርነት ነበር፤ ያልጠበቅነው ብዙ ጉዳት ደረሰብን…

  ጠያቂ፡- እንዴ? ብዙ የጠላት ኃይል ነበር እንዴ የገጠማችሁ? ማለቴ ከእናንተ የሚበልጥ…

  አዛዥ፡- አሄሄ… እንደሱማ ቢሆን በማን ዕድላችን፤ የገጠመን አንድ ሰው ብቻ ሆኖ ውር ውር እያለና         እየተሽሎከለከ ፈጀን እንጂ፡፡ በስንት መስዋዕትነት መሰለህ መጨረሻ ላይ የገደልነው …

   

  ኢትዮጵያችን በሰይጣን ግዛት ከገባች ቆይታለች፡፡ በፊትም ግማሽ እግር በሰይጣን ግዛት ግማሽ እግር በእግዜር ግዛት ውስጥ በጨለማና በብርሃን በሚመላለስ የአገዛዝ ሥርዓት ውስጥ ነበረች፡፡ እየቆዬ ደግሞ በለዬለት ሁኔታ እዚያው እጨለማው ግዛት ገባችና አሁንም ድረስ በዚያው አለች፡፡ እግዚአብሔር ይርዳት፡፡

  በእስልምና ስም እየታዬ ያለውም የሚዘገንን ነው፡፡ ሰሞኑን ከድረ ገፆች ስለአንዲት ኢትዮጵያዊት ልጃችን ያነበብኩት ሰቅጣጭ ታሪክ ወደውስጤ አስለቅሶኛል – ወደ ውጪ የማፈስሰው ዕንባ የለኝም፤ ለጊዜው ጨርሻለሁ፡፡ ይህች ልጅ እንደብዙዎቹ ከርታታ ወገኖቻችን ሁሉ ያልፍልኛል ብላ ወደዐረብ ሀገር ትሄዳለች፡፡ ሦርያ ውስጥ ገብታ ሥራ ትይዛለች፡፡ ነገር ግን ‹አንበሣን ፈርቼ ዛፍ ላይ ብወጣ ነብር ጠበቀኝ› እንዲሉ ሀገሯ ያስወጣት ችግር መልኩን ቀይሮ ሦርያ ላይ ጠበቃት – ጦርነት፡፡ ከርሀብ ስትሸሽ ጦርነት አፉን ከፍቶ ጠበቃት፡፡ በዚህ የርስ በርስ ውጊያ ሰበብ ቀጣሪዎቿ ቤቱን ጥለውላት ወደዉጭ ይሰደዳሉ፡፡ ዝርዝሩን ከነዚያው ድረ ገፆች አንብቡ፡፡

  ሳላነሳው ማለፍ የማልፈልገው ግን ለዚህ መጣጥፍ መነሻ የሆነኝ የዚህች ልጅ ስቃይ ነው፡፡ ይህች ልጅ ደማስቆስ የመሬት ለመሬት የውስጠኛ ክፍል ውስጥ በመሸጉ አሸባሪዎች እጅ ትወድቃለች፡፡ በነዚህ የእስላም አክራሪ ሰይጣኖች ቁጥጥር ከገባች በኋላ የምታየው አበሳ በቃላት የሚገለጽ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የሰይጣኑን የመለስ ዜናዊን ነፍስ ተገቢ ዋጋዋን ይስጣትና በሱ የተንሸዋረረና በዘረኝነት የበከተ አገዛዝ ምክንያት ወደዉጭ የሚሰደዱ ወገኖቻችን ምን ዓይነት መከራና ስቃይ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ይህች ልጅ አብነት ናት፡፡ በብዙ ሺዎች የሚገመቱ ወገኖቻችንም በዚህ ዓይነት አሰቃቂ ሁኔታ እንደሚኖሩ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህ ለቤት ቀጋ ለውጭ አልጋ የሆነ ሥርዓት በቶሎ ካልተወገደ በሀገራችን ምን ያህል ውድመት እየደረሰ እንዳለና ወደፊትም የሚመጣብን መከራ በዚህች ልጅ አማካይነት ቁልጭ ብሎ ይታያልና ወደየኅሊናችን ተመልሰን ለጋራ ጉዳያችን በጋራ እንድናስብ ይህ ዓይነቱ አስከፊው ተሞክሮኣችን ያስተምረን፡፡ በፈጠረን ይሁንብን!

  አሸባሪዎቹ ይህችን ልጅ በሚስቶቻቸው ፊት ሳይቀር ይደፍሯታል፤ ሌሎችን በኮረንቲ እንድትጠብስ ያደርጓታል፤ ሽንታቸውን እንድትጠጣ – የርሷንም ሽንት ሌሎችን እንድታጠጣ ያደርጓታል፤ ሬሣ መሀል እንድታድርና አእምሮዋን ስታ ወደአውሬነትም ተለውጣ ለአጥፍቶ መጥፋት ተልእኮ ፈቃደኛ እንድትሆን ያስገድዷታል፡፡ ዝርዝሩ ብዙ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል የዚህችን ልጅ ስቃይ ያላነበበ ከአንዱ ድረ ገጽ ቢያነብ ደስ ይለኛል (በዚህ በኩል ልምዱ ያላችሁ የዘሀበሻ ድረገፅ ሰዎች እባካችሁን እዚህች ቦታ ላይ የዚያን ጽሑፍ አድራሻ አጣቅሱት – እኔ ያነበብኩት በኢትዮሚዲያ ላይ ነው፤ ርዕሱ ‹ኢትዮጵያዊቷ በሦርያ ያሳለፈችውን ስቃይ…› የሚል ነው – ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ነው የወሰዱት)፡፡ የእርሷ ስቃይ የኛ ስቃይ ነው፡፡ ይህች ልጅ የኔንም ምስል የምታሳይ ሴት ክርስቶስ ናት፡፡ የገማና የሻገተው ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ሥርዓታችን ነፀብራቅ ናት፤ የመለስ ራዕይ ውጤት ያስገኘልን ድል መገለጫ የኅሊና ጸጸታችንና የጋራ ቁጭታችንም መንስኤ ናት፡፡ ያንዳችን ቁስል ላንዳችን ካልተሰማን ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳንሆን ሰዎችም አይደለንም ማለት ነው፤ ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ አንዳችን ለአንዳችን እንተዛዘን፡፡ በነገራችን ላይ ይህች ልጅ ፈጣሪ በሰዎች አማካይነት ረድቷት ከዚያ የቁም መቃብር ተርፋ አሁን በሕይወት አለች፡፡

  እንግዲህ ሰይጣን ማለት ከፍ ሲል እንደተመለከትነው ነው – ዕልቂትና ትርምስ የሚወድ፡፡ በሦርያ፣ በኢራቅ፣ በአፍጋኒስታን፣ በፓኪስታን፣ በሕንድ፣ በሶማሊያ፣ በግብጽ፣ በፍልስጥኤም፣ በበርማ፣ በኢንዶኔዥያ፣ በአሜሪካዎች፣ በማሊ፣ በሴንትራል አፍሪካ ‹ሪፓፕሊክ›፣ በጊኒ፣ … ሠይፉን መዝዞ ሕዝበ አዳምን እያንቆራጠጠ የሚገኘው ሰይጣን በሰዎች ተመስሎ ነው – (በነገራችን ላይ ሰይጣንም ሆነ እግዚአብሔር – በጨለማና በብርሃን በሚመሰል የመንፈስ ኃይል እንጂ የራሳቸው ቁሣዊ መገለጫ እንደሌላቸው የታወቀ ነው፡፡) ቦስተን ላይ የፈነዱት ሁለት ቦምቦች የሰይጣን ናቸው፤ ኢራቅ ውስጥ በየቀኑ የሚፈነዱ ቦምቦችና የአጥፍቶ ጠፊ ተልእኮዎች ከሰይጣን የሚላኩ ናቸው፡፡ ሶማሊያ ውስጥ የሚፈነዱ ቦምቦች የሰይጣን ናቸው፡፡ እስላም እማሬያዊ ትርጉሙ ‹ሰላም› ሆኖ ሳለ ሰይጣን አእምሮኣቸውን የሠረራቸው ሰዎች በዚህ ሰላምን በሚሰብክ ሃይማኖት ሽፋን ስም ገብተው ዓለምን ወዴት እያቀጣጯት እንደሆነ ልብ እንበል፡፡ የዕብድ ገላጋይ ድንጋይ እንደሚያቀብል ሁሉ በሌላው ጫፍ ያሉ የሰይጣን ሎሌዎችና ደንገጡሮችም የጠቡን አድማስ ከማጥበብ ይልቅ እዬለጠጡና ነገር እየተነኮሱ አለይዞታቸውም በሰው ግዛት ጥልቅ እያሉ በሚያቀጣጥሉት የ‹አሸባሪነትና ተሸባሪነት› አሸናፊ የሌለው ጦርነት ውስጥ የስንቶች ንጹሓን ዜጎች ሕይወት በየቀኑ እንደሚረግፍ እናስተውል፡፡ አስቂኝ ቀልድ – አሸባሪነትን በአሸባሪነት ለማሸነፍ የመሞከር ልዩ የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ትራጂኮሜዲ ድራማ፡፡ በሰዎች ዕልቂት ሰዎች የሚጨፍሩበት አሣዛኝ ተውኔት፡፡ ዓሣሞችና አጋሰሶች – ማነው – ዝኆኖች ሲጣሉ ሣሮች የሚረጋገጡበት ክፉ ዘመን፡፡ ምን ይሻለናል? ጊዜው አያስፈራም? የኔ ስሜት ድብልቅ ነው – ያስፈራል ፤ አያስፈራምም፡፡

  የእንቅስቃሴውን ስም አልቃኢዳም እንበለው አልሻባብ፣ አል ኑስራም እንበለው አል ዛዋሪ – ሃይማኖቱ እስልምናም ይሁን ክርስትና ቡድሂዝምም ይባል አይሁድ ተግባሩ ሰዎችን መጨረስ ከሆነ ያው ሰይጣን ነው፡፡ ሰይጣናዊነት ሰብኣዊነት የሌለው በግድያ እንድትዝናና የሚያደርግ የጭካኔ አምልኮት ነው፡፡ በሰው ስቃይ የሚደሰት ሁሉ ሰይጣን ነው፡፡ የተቀደሰ ግድያ የለም፡፡ ግድያ በማንም ይሁን በማን፣ ማንም ላይና ለምንም ዓይነት ዓላማ  ይፈጸም አስከፊ ነገር ነው፤ አስተማሪነትም የለውም፡፡ የሞተም አልተማረም፤ የተመለከተም ኅሊናውን በሚያሰቃይ ቁስል አነፈረቀ እንጂ ትምህርት አልቀሰመም፡፡ በተጨማሪም ግድያን ምንም ዓይነት ሕጋዊም ይሁን ሞራላዊ ልባስ ቢሰጡት ያው ግድያ እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡ ሞትን አፈጠንከው አዘገየኸው መቼም ቢሆን ለማንም አይቀርም፡፡ እናም የፈጠረ ይግደል፤ ያልፈጠረ ያልፈጠራትን ነፍስ ከሥጋዋ አለጊዜዋ ለምን ይለያል? “አትግደል” የሚለውን የፈጣሪ ሕግና ትዕዛዝ የሚተላለፍ ሁሉ ኃጢኣትን አደረገ፡፡ ስለዚህም ሰውን በመግደልም ይሁን በማሰቃየት የሚደሰቱ ሁሉ ምድባቸው ከሰይጣን መሆኑን በመረዳት ምርጫችንን እናስተካክል፡፡ ከሁለቱ አማራጮች ውጪ ሌላ አማራጭ የለም፤ አንድም የፍቅርና የሰላም የእግዚአብሄር መንፈስ ያለን መሆን ወይም በተቃራኒው የጠብና የአምባጓሮ፣ የግድያና በሰው ስቃይ የመደሰት ሰይጣናዊ መንፈስ ያለን መሆን፡፡ ምርጫው በእጃችን ነው፡፡ መሆን ወይም አለመሆን – በግዛታችን ያለ ነጻ ምርጫ፡፡

   


  0 0

  (ዘ-ሐበሻ) በአባይ ቦንድ ስም የወያኔ አምባሳደር በኖርዌይ የጠራችው ሕዝባዊ ስብሰባ እዚያው በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተሰናከለ። አዳራሹን የሞሉት ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን “ከአባይ በፊት የሰው መብት ይከበር” በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ በማሰማት ስብሰባው እንዲቋረጥ ተደርጓል። በስብሰባው ለመገኘት የመጣቸው አምባሳደርም በፖሊስ ታጅባ ወጥታለች። ቪድዮውን ይመልከቱ።


  0 0

  በኖርዌይ ስታቫንገር ከተማ የተደረገው የአባይ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ ወያኔ የተከራየውን አዳራሽ ተቃዋሚዎቹ  ተቆጣጥረውታል!!

  Norway demo1

  ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት ጭቅጭቅ ነበር። ተቃዋሚዎች አይገቡም በማለት የተጀመረው መክፈቻ በኋላ ላይ ግን ፖሊስ ከመጣ በኋላ እንዲገቡ ተፈቀደ ። ስብሰባው በጥያቄ ተጀምሮ ነበር።  ተቃዋሚዎቹ ጥያቄውም እንዲ በማለት ጀመሩ፥

  1 በመጀመሪያ እስከዛሬ እናንተ ከገባችሁ ጅምሮ ለገደላችሁት ሰዎች  የህሊና ፀሎት ይደረግ በማለት ነበር የተጠየቀው በመቀጠል

  2 እስከዛሬ እናንተ ያደረጋችሁትን የዘር ማጥፋት በአማራ፣ በኦሮሞ እንዲሁም በሕዝባችን ላይ የተደረገው ነገር ሳያንስ ዛሬ ደግሞ በአማራው ላይ የዘር ማፅዳት ዘመቻ እየፈፀማችሁና እየገደላችሁ እዚህ መጣችሁ ገንዘብ መጠየቅ ለኛ ድፍረት ነው በማለት በስብሰባው አዳራሽ በጩወትና በመፈክር ተናወጠ የወያኔ የስዊዲን አገር ቆንፅላም እንዲሁም ጀሌዎቹም በመፍራት አዳራሹን ለተቃዋሚዎች  በማስረከብ ለቀው ወተዋል ! ።

  ሌባ ነው ሌባ ወያኔ ሌባ በማለት የተጀመረው በመፈክር  በጭወትና በዝማሪ አዳራሹ ተደበላልቋል!

  ከገንዘብ በፊት ነፃነት ይቅደም!

  ከገንዘብ በፊት  ሰብኣዊነት ይቅደም!

  ኢትዮጵያ አገራችን የደፈረሽ  ይውደም! በማለት ተቃዋማቸውን ሲያሰሙ ነበር።

  የወያኔ/ ህውሃትና ጀሌዎች በአለም ላይ የሚያደርጉት የአባይ ገቢ ማሰባሰብያ በየአለማቱ ተቋውሞ እየደረሰበት ይገኛል።

  በደቡብ አፍሪካ የተጀመረው ገቢ ማሰባሰብያ ሳይሳካ እንደውም ወያኔ የተከራየውን አዳራሽ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር በማስወጣት ያሳዩትን ጀግንነት ቀጥሎ በሌሎች አገርም  በአሜሪካ፣ በሳውዲ አረቢያ( ጅዳ) ፣በጀርመን ተቀጣጥሎ በቀጠለበት ሁናቴ  በኖርዌይ

  Norway demo2

  ከፍተኛ የሆነ ተቋውሞ ደርሶበታል ።በኖርዌይ የተጀመረው ገቢ ማሰባሰብያ ስብሰባ በመቃወም  ወያኔ የተከራየውን ገቢ ማሰባሰብያ  አዳራሽ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር በማስወጣት የወያኔን ባንዲራ በማውረድ  የኢትዮጵያን ትክክለኛውን ባንዲራ በመስቀል በማውለብለብ ወያኔዎችንና ጀሌዎችን በማባረር አዳራሹን ተቃዋሚዎቹ ተቆጣጥረውታል ። በአለማቱ ያሉቱ የወያኔ ቅጥረኛ አምባሳደር ተብዬዎች አንገታቸውን ያስደፋና እንደ ቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስተራቸው አንገትን አስደፍቶ፣አስደንግጦ ወደ መጡበት ያስመለሰ ነበር።አዳራሹ ውስጥ የነበሩት ተቃዋሚዎች ሙሉ በሙሉ ይበልጣሉ።ታሪክ በውጪ ባሉ ኢትዮጵያዊያን እየተሰራ ይገኛል!

  Norway demo3

  ኢትዮጵያውያን አንድነታቸው ተጠናክሯል ። የወያኔ የመገነጣጠል አላማ ስትራቴጂ የወደመበት ሆኗል።የሕዝቡም አንድነት የታየበት ነበር።ይህ በእንዲህ እንዳለ በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍም ሚያዚያ 18 2013 መካሄዱ ይታወሳል።

  ኢትዮጵያውያን በአንድ ላይ በመሆን በመዘመርና በመፍክር ብሶታቸውን አሰምተዋል።

  ተቃዋሚዎቹ በአንድነት በመሆን ያሰሙት ቃል ነበር

  (( ገና ይቀጥላል ሁላችንም ነፃ እስከምንወጣ ድረስ ))

  ሞት ለአንባገነን!

  ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

   


  0 0

  ከዓለማየሁ ገበየሁ

  bealu girma 1

  ሰሞኑን ለስራ ወደ ሰሜን ስጓዝ በውስጤ ግዘፍ ነስቶ የቆየው የበዓሉ ግርማ ጉዳይ ነበር ፡፡ በቂ ግዜ ካገኘሁ ‹ የፌስ ቡክ ሰራዊት › ሲወያይበትና ሲከራከርበት ለከረመው አጀንዳ ቢቻል የተጠጋጋ ካልሆነም እንደነገሩ የቆመ መረጃ አሰባስቤ እመለሳለሁ ስል አሰብኩ ፡፡

  የዜናው መነሻ ፤

  ‹‹ ከወደ ባህር ዳር አካባቢ የተሰማው ወሬ በርካቶችን እያስገረመና እያስደነገጠ ይገኛል … ደራሲ በዓሉ ግርማ በዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ውስጥ አለም በቃኝ ብሎ ሞንኩሶ እግዚአብሄርን እያገለገለ መሆኑ ታውቋል … በይስማዕከ ወርቁ ደራሲነት የምናውቃቸው ዴርቶጋዳ ፣ ራማቶሃራ ፣ ዣንዣራ እና ተልሚድ የተሰኙ ስራዎች የደራሲ በዓሉ መሆናቸው ተረጋግጧል … ይህ ወሬ ከተሰማ በኃላ በርካታ የባህር ዳር ነዋሪዎች የዳጋ ደሴትን ያጨናነቁ ሲሆን የአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ነዋሪዎችም በአስገራሚ መልኩ ወደ ስፍራው እየተመሙ ናቸው … ››

  ይህን ዜና ያለማመንታት ‹‹ የማይታመን ›› ያሉ የመኖራቸውን ያህል ‹‹ ትክክለኛ ነው ›› እንዲሁም ‹‹ ትክክል ሊሆን ይችላል ›› የሚሉ ግምቶችን ያስቀመጡ ጥቂቶች አልነበሩም ፡፡ እኔም ‹‹ የደራሲዎች እየሱስ ! ›› የምለውን የበዓሉን ብዕር ከአድማስ ባሻገር እስከ ኦሮማይ እንደ ማስቲካ እያላመጥኩ ፣ ድዴ ሲደክም ደግሞ ወሬውን ለስራ ባልደረቦቼ በማካፈል መቋጫ የሌላው ክርክር እንዲነሳ ማድረጌ አልቀረም ፡፡

  ከዚህ ቀደም ባለው አነጋገር ለመሞቱ ፣ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ደግሞ ለመጥፋቱ ምክንያት የሆነው ኦሮማይ የተባለውን መጽሀፍ … የማላቀውን የዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም … እንደ አብርሃም ቤት የለኝ እንደ ሙሴ መቃብሬ አይታወቅ የሚለውን የደራሲው ገጸ ባህሪ… ጽሁፍ ህይወት ነው ከዚያ ውጪ ሌላ የህይወት ምኞት የለኝም የሚለውን በዓሉንና በሰበቡ የተነሱትን እነ ዴርቶጋዳ … ወደ ገዳም ለመጓዝ ሁከትና ጉጉት የሚታይበትን የባህርዳር ህዝብ… ተራ በተራ እየሳልኩ ነበር ባህርዳር የደረስኩት ፡፡

  የማጣሪያ ወሬ ፤

  በበዓሉ ግርማ ዙሪያ የተነሳውን ዜና ወይም ወሬ ለማጣራትና ወደ አንድ አቅጣጫ ለማምጣት በጉዳዩ ዙሪያ የሚወዳደሩ ክፍሎችን ወይም የሊግ አባላትን ማብዛት ያስፈልጋል ፡፡ ጋዜጠኛም ጸሀፊም በመሆኔ ነው መሰል አስቀድሜ የጨዋታውን ንድፍና ህግጋት / sketch / ለመሳል ያልቦዘንኩት ፡፡ በዚህ ፍትጊያ መሃል ነው ለእውነት የተጠጋ መረጃ ሊገኝ የሚችለው ወይም የተሰወረ መንገድን ማወቅ የሚቻለው ፡፡

  እናም የባህርዳር ነዋሪዎች ፣ የተለያዩ የመንግስት መዋቅሮች / ፖሊስ ፣ ባህልና ቱሪዝም ፣ ጋዜጠኞች / ፣ ቀሳውስት ፣ መጽሀፍት ሻጮች ፣ አንባቢዎች ፣ የጀልባ አከራዮችና የዳጋ እስጢፋኖስ አስተዳደሮች በማጣሪያው እንዲሰለፉ አቀድኩ ፡፡ የትኛው ቡድን ወይም የትኛውም መንገድ ለፍጻሜ እንደሚደርስ ለመተንበይ ግን አልሞከርኩም ፡፡

  በጉዳዩ በጣም ተጨናንቋል የተባለውን የባህር ዳር ነዋሪ እኔ ያገኘሁት በሁለት መልኩ ነው ፡፡ አንደኛውና በጣም የሚበዛው ጭራሽ ስለ ርዕሰ ጉዳዩ ያልሰማና ምንም መረጃ የሌለው ነው ፡፡ ሁለተኛው ክፍል ስለ ጉዳዩ የሚያውቅ ነገር ግን የተለያዩ መላምቶችን ደርዝ በሌለው መልኩ ያዘለ ነው ፡፡ አንዳንዶች ‹‹ እስካሁን ይወራል እንጂ የታመነ ዜና አልተገኘም ›› ይላሉ ፡፡ ሌሎች ‹‹ ተጨባጭ መረጃ ባይገኝም በዓሉ ግርማ ገዳሙ ውስጥ ሊኖር እንደሚችል ይሰማናል ›› ብለዋል ፡፡ ወሬው ሀሰት ነው ከሚሉት ውስጥ ዜናው ተቀነባብሮ የተፈጠረው በጀልባ አከራዮች ነው ያሉት ጥቂቶች አይደሉም ፡፡ ለምን ለተባለው ጥያቄ ደግሞ ‹‹ ገበያ ለመፍጠር ›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ደራሲው ገዳም ውስጥ ሊኖር ይችላል የሚሉ ወገኖች ዋነኛ መከራከሪያ ደግሞ በዓሉ በደርግ ተይዞ ተሰወረ ተባለ እንጂ ስለመሞቱ ማረጋገጫ ያለመገኘቱን ጉዳይ ነው ፡፡

  በርግጥ የበዓሉ ግርማ ወሬ በፌስ ቡክ ከተለቀቀ በኃላ በባህርዳር የሚገኙ የመንግስት አካላት ጉጉትና ውጥረት ገኖ ቆይቷል ፡፡ አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ የመንግስት ሰራተኛ የተለያዩ ከፍተኛ ኃላፊዎች ወሬው እውነት ይሁን ሀሰት እንዲጣራ በተለያዩ መንገዶች በገዳሙ ውስጥ ፍለጋ እንዲከናወን አድርገዋል ፡፡ ይህም ጥረት የገዳሙን ነዋሪ ከማጨናነቅ የዘለለ ተጨባጭ ፋይዳ ያስገኘ አልነበረም ፡፡ አንዳንድ የፖሊስ ሰራዊት አባላትም ወሬውን ሊያረጋግጥ የሚችል መረጃ ባለመገኘቱ እውነት ነው የሚል እምነት የለንም ብለዋል ፡፡

  ርዕሰ ጉዳዩ ጋዜጠኞችም ሰፈር ደርሷል ፡፡ ጋዜጠኞችም ወሬው ህብረተሰቡ ምርጫውን በአግባቡ እንዳያከናውን ለማደናቀፍ ወይም ለማዘናጋት የሚደረግ ጥረት እንደሆነ ገለጻ ተደርጎላቸዋል ፡፡

  በባህርዳር ከተማ ጥቂት የማይባሉ መጽሀፍት መሸጫ መደብሮች ይገኛሉ ፡፡ በዚህ ወሬ ምክንያት የበዓሉ ግርማ መጽሀፍት ከወትሮው በተለየ መልኩ ሊሸጡ እንደሚችሉ ገምቼ ነበር ፡፡ ይህን ግምት ይዤ አራት ከሚደርሱ ነጋዴዎች ጋር ተወያየሁ ፡፡ ሁሉም ስለ ወቅታዊው ወሬ ከበቂ በላይ መረጃ ቢኖራቸውም በዚሁ ሰበብ የበዓሉ ግርማ መጽሀፍት እንዳልተሸጡ ተናግረዋል ፡፡ ሁለቱ ሚያዚያ ውስጥ የተሰማው ወሬ ‹ የአፕሪል ዘ ፉል › ውጤት መሆኑን ሲናገሩ ሁለቱ ደግሞ ማንኛውም ወሬ ውስጥ ጥቂት የእውነት ፍሬ ሊገኝ እንደሚችል ጠቋቁመዋል፡፡ በየግዜው ለገዳሙ በርካታ መጽሀፍት እየተገዙ መግባታቸው የትላልቅ ሰዎች መናኀሪያ መሆኑን ለማስረዳት በመሞከር ፡፡

  ሰው በሰው ያገኘኃቸው ቀሳውስት ወሬው ከተማው ውስጥ እንጂ በገዳሙ እንደማይሰማ ተናግረዋል ፡፡ ለብዙ ዓመታት በገዳም ውስጥ ህይወታቸውን ያቆዩ አባቶችን የትናንት ማንነት ለማወቅ ከባድ መሆኑን ብቻ ሳይሆን ብዙም ጠቃሚ እንዳልሆነም አስረድተዋል ፡፡ አለም በቃኝ ብሎ ከፈጣሪ ጋር ለመገኛኘት የሚተጋ ህብረተሰብ የቀደመውን ማንነት ማስታወስ ምን ይረባዋል በማለትም ጫጫታውን ለማርገብ የሞከሩም ይመስላሉ ፡፡

  ይህ የጥቂት ቀናት አሰሳ ከጥሩ አንባቢያን ጋርም አገናኝቶኛል ፡፡ በተለይ አንድ አንባቢ ‹ ጥሩ ቀልድ ናት › ነው ያለኝ ፡፡ ይህ ሰው ወሬው ሆን ተብሎ ተቀነባብሮ የተፈበረከው የመቀበል ጸጋ በተሳናቸው ጠማማ ሰዎች ምክንያት እንደሆነ ነው የሚያምነው ፡፡ እሱ ጠማማ ሰዎች የሚላቸው የይስማዕከ ወርቁን ችሎታ ለመቀበል የተናነቃቸውን ነው ፡፡ ወጣቱ ደራሲ ያልተጠበቁ ስራዎች መስራቱ የቅናትና የመበለጥ ስሜታቸው እንዲቆጣ ምክንያት ፈጥሯል ፡፡ እናም ህያው ውብ እጅን ከማድነቅ ይልቅ ለሰበብነት የሞተ ማንነትን እንደ ምክንያት መጠቀም ተመርጧል ፡፡

  ወሬውን መንግስት ራሱ ሆን ብሎ ያሰራጨው መሆኑን በልበ ሙሉነት የሚናገሩም አጋጥመውኛል ፡፡ ይህ ዓይነት አከራካሪና በቀላሉ እልባት ሊያገኝ የማይችል መረጃ የሚለቀቀው ወቅታዊ ጉዳዮችን ወይም ውጥረቶችን ለማርገብ ሲፈለግ ነው ፡፡ መንግስት ከሙስሊሙ ህብረተሰብ ጋር መጋጨቱ ፣ ከተለያዩ ክልሎች የተፈናቀለው የአማራ ብሄረሰብ ጉዳይ መነጋገሪያ መሆኑን እንደ ምክንያት ያነሳሉ ፡፡ በተቃራኒው የበዓሉ ግርማ በዳጋ እስጢፋኖስ የመታየት ጉዳይ ለገዢው ክፍል የሚመች ዜና ያለመሆኑን ያስረዱ አሉ ፡፡ እንዴት ሲባሉ የበዓሉ በህይወት መገኘት የደርግን ገዳይነትና ጨካኝነት እንዲለዝብ ስለሚያደርግ በኢህአዴግ አይን መታየት ያለበት ጉዳይ አያደርገውም ፡፡ በመሆኑም ለገዳሙም ሆነ ለደራሲው ቀጣይ ስጋት እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል ፡፡

  መንገዶች ሁሉ ወደ ጣና ይወስዳሉ ፤

  ከሰማኃቸው መረጃዎች መካከል ዳጋ እስጢፋኖስ የዶክተሮች ፣ የምሁራኖችና በንባብ የመጠቁ በርካታ ሰዎች ስብስብ ገዳም ነው የሚለው አስተያየት ከፍ ብሎ ይሰማኛል ፡፡ በገዳሙ ለሚገኙ ሰዎች አንዳንድ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት በጎ አድራጊዎች መጽሀፍና ቁሳቁስ የሚረዷቸው ከምን አንጻር ነው ? የሚለውም ጥያቄ የጥርጣሬ ሚዛን ወደታች ዝቅ ብሎ እንዲመዝን የሆነ አስተዎጽኦ ሊያደርግ ይችላል ፡፡ በርግጥ ዳጋ እስጢፋኖስ ጥቅጥቅ ባለ ደን የተሸፈነና ከሌሎቹ ገዳማትም ልዩ ገጽታ እንዳለው ይታወቃል ፡፡ የገዳሙ ህንጻ የጀልባ ቅርጽ ያለው ሲሆን የዚህ ተምሳሌትም የኖህ ጀልባ የሰው ዘርን ከጎርፍ ጥቃት የማዳኑን ምስጢር ይጠቁማል ፡፡

  በዓሉ ግርማ በዚህ ደንና ዋሻ ውስጥ ተደብቆ ይሆን ? ‹ ተፈጸመ › ን ለንባብ አበርክቶ የፍጻሜው ማረፊያ ትሆን ዘንድ በኖህ ጀልባ ተሳፍሮ ይሆን ? ሽቅርቅሩና ታጋዩ ደራሲ በርግጥ ጭምተኛና ገዳማዊ መሆንን መርጧል ? ከሆነ እንዴት ከባድ ምርጫ ነው ፡፡ ምክንያቱም አንድ ገዳማዊ ጤዛ ልሶ ፣ ድንጋይ ተንተርሶ ፤ ድምጸ አራዊትን ግርማ ሌሊትን ታግሶ ነው የሚኖረው ፡፡ አንድ ገዳማዊ ከዓለማዊ ኑሮ ርቆ ፣ ራሱን በራሱ እየረዳ ዘወትር በጾምና ጸሎት ፣ በገድልና ትሩፋት ተጠምዶ የሚኖር የእግዚአብሄር ሰው ነውና ፡፡

  እንደ ጣና ማዕበል ግራና ቀኝ የሚላተመውን ሀሳብ ይዤ ወደ ጣና ኃይቅ የግል ጀልባ ማህበር አመራሁ ፡፡ እዚህ ወደ ዳጋ እስጢፋኖስ የሚቀዝፉ ጀልባዎች ይገኛሉ ፡፡ እዚህ ወደተለያዩ ገዳማት የሚጓዙ ሰዎችን ሀሳብና ፍላጎት እንዳልሰሙ ሆነው የሚሰሙ የጀልባው ካፕቴኖች ይገኛሉ ፡፡ እዚህ ስለገዳማቱ የቀረበ መረጃ ያላቸው ሰዎች አይጠፉም ፡፡ እዚህ የሀሰት ፈጠራ ሊፈበረኩ ይችላሉ ተብለው የሚታሙ ሰራተኞችም አሉ ፡፡

  ሰላምታ ሰጥቼ ወደቢሮው ከዘለቅኩ በኃላ ስለ ስራ ጉዳይ ማውራት ጀመርኩ ፡፡ የማህበሩ ኃላፊ የሞቀ አቀባበል አደረገልኝ ፡፡ ሞተሬን ካሞቅኩ በኃላ ስለ ርዕሰ ጉዳዩ መጠየቅ ጀመርኩ ፡፡

  ‹‹ በዓሉ ግርማ በዳጋ እስጢፋኖስ ሊኖርም ላይኖርም ይችላል ›› በማለት ማጋደል ያቃተው ምላሽ ወረወረልኝ
  ‹‹ እንዴት ነው ሊኖር የሚችለው ? ››
  ‹‹ ገዳሙ የምሁራን አምባ ስለሆነ ››
  ‹‹ እንዴት ነው የማይኖረውስ ? ››
  ‹‹ ምክንያቱም እስካሁን እኔ አይቸዋለሁ የሚል ሰው ስላልተገኘ ››
  ‹‹ ወሬው ከተሰማ በኃላ ወደ ዳጋ የሚሄደው ጎብኚ ቁጥር በዝቷል ? ››
  ‹‹ እንግዶች ይሄዳሉ ፡፡ ግን ደራሲውን ፍለጋ ነው ብለው አይናገሩም ››
  ‹‹ ይህ ወሬ ታዲያ ከየት መጣ ? ››
  ‹‹ ከፌስ ቡክ ነው ! ››
  ‹‹ ከእናንተ ነው የሚሉም አሉ ፡፡ ማለትም ገበያ ለመፍጠር ››
  ‹‹ ዉሸት ነው ! እኛ ያልተረጋገጠ ወሬ ለደንበኞች አንናገርም ፡፡ ይኀው እንዳንተ በርካታ ሰዎች እየመጡ በዓሉ ካለ ልሄድ ነው መረጃ ንገረኝ ይሉኛል ፡፡ እኔ ገንዘብ ብፈልግ አደርገዋለሁ ፡፡ በግልጽ የምነግራቸው ምንም መረጃ እንደሌለኝ ነው ፡፡ የምመክራቸውም መሄድ ያለባቸው ገዳሙን የመጎብኘት ፍላጎት ካላቸው ብቻ መሆኑን ነው ››
  ‹‹ እውነት ስለ በዓሉ ምንም አላውቅም ነው የምትለኝ ? ››

  ኃላፊው የሚያውቀውን በትክክል እንደገለጸልኝ ደጋግሞ ነገረኝ ፡፡ ትንሽ ቆይቶ ግን የአንድ ሰው ስም ጠራና የተሻለ መረጃ ሊገኝ እንደሚችል ጠቆመኝ ፡፡ ወጣቱ የሚሰራው በዳጋ እስጢፋኖስ ጀልባ ላይ ነው ፡፡ ጀልባዋ ሁለት ጥቅም ትሰጣለች ፡፡ አንደኛው የገዳሙን አባላት ካሉበት ወደ ከተማ ፣ ከከተማ ወደ ገዳም ማመላለስ ሲሆን ሁለተኛው ጎን ለጎን ወደ ገዳሙ የሚጓዙ ሰዎችን በተለመደው ታሪፍ ታጓጉዛለች ፡፡ የጀልባዋ ካፕቴን አንተሁን ጥበቡ በገዳሙ የሚኖር ሲሆን የማስጎብኘትም አገልግሎት ይሰጣል ፡፡

  ቀጠሮ ለመያዝ ስደውልለት ወደ ክብራን ገብርኤል እንግዶችን ይዞ እንደሄደ ገለጸልኝ ፡፡ ሌላ እድል ስላልነበር የስልክ ቃለ መጠይቁን ማድረግ አንደሚገባኝ ወዲያው ወሰንኩ ፡፡ ዳጋ ውስጥ ከመቶ በላይ መነኮሳት እንደሚገኙ የገለጸው አንተሁን ወደ ገዳሙ የገባ ሰው ራሱን ደብቆ የሚኖር በመሆኑ ተፈላጊውን ለይቶ ለማወቅ ያስቸግራል ባይ ነው ፡፡ በዓሉ ግርማን በፎቶ እንኳ እንደማያውቀው ፣ በቦታው ኖሮ ቢያየው እንኳ ትርጉም እንደሌለው አስረድቷል ፡፡ ብዙዎቹ የበሰሉና ምሁራን ሆነውም ራሳቸውን ምንም እንደማያውቅ መሃይም አድርገው ለመኖር የሚያደርጉት ጥረት ምስጢራዊው ህይወት ምን ያህል ከባድ መሆኑን የሚያስረዳ ነው ፡፡ በዚህም ምክንያት እስካሁን ለጠየቁኝ ሰዎች የሰጠሁት ምላሽ አላውቅም የሚል ነው ብሏል ፡፡ ደራሲውን በአካል የሚያውቀው ሰው ለአዳር መጥቶ መፈለግ እንደሚኖርበትም ሃሳብ ሰጥቷል ፡፡

  የገዳሙን ሰው አመስግኜ ወደ ጣና ዳር ተጠጋሁ ፡፡ አያሌ ጀልባዎች ወታደራዊ ሰልፍ ይዘው እንግዶቻቸውን ይጠባበቃሉ ፡፡ ጀልባዎቹ ከተደገፉበት ግንብ አናት ላይ ጉዞን የተመለከተ መረጃ የሚሰጥ ታፔላ ቆሟል ፡፡ የአጭርና ረጅም ጉዞ ታሪፍ ነው ፡፡ ዳጋ እስጢፋኖስ የአጭር ጉዞ ዝርዝር ውስጥ የለም ፡፡ በረጅሙ ጉዞ ውስጥ በሁለተኛ ረድፍ ላይ ግን ጎልቶ ይታያል ፡፡ በብረት ጀልባ ለመሄድ 1700 ብር ፣ በፋይበር ጀልባ ከሆነ ደግሞ 2200 ብር ያስጠይቃል ይላል መልዕክቱ ፡፡
  bealu girma 2

  ካፒቴኑ እንደነገረኝ ዳጋ ለመድረስ አራት ሰዓት ይፈጃል ፡፡ ማደር ካለ ደግሞ ክፍያው ከፍ ይላል ፡፡ የቀረኝ እንጥፍጣፊ መረጃ ቢኖር ገዳሙ ራሱ የሚነግረኝ ነው ፡፡ በሁለት ምክንያት ግን ወደ ምሁራኑ አምባ ለማቅናት አልችልም ፡፡ የመጀመሪያው ወደ ደባርቅና ሁመራ ቀሪ መንገድ ስለሚጠብቀኝ የሚያወላዳ ግዜ የሌለኝ መሆኑ ነው ፡፡ ሁለተኛው ገንዘብ ነው ፡፡ ግዜን ከመንግስት ስራ ቀነጫጭቤ ማትረፍ ብችል እንኳ ገንዘብን ከራሴ ኪስ ለመስረቅ አልቸልም – ከባዶ ኪስ ፡፡

  ባዶነት ተሰማኝ ፡፡ ውጤቱ ምንም ሆነ ምን ገዳም ላይ የሚደረገውን የመጨረሻ ፍለጋዊ ውድድር መመልከት ነበረብኝ ፡፡ እንደ ሀገሬ ብሄራዊ ቡድን እያለቃቀስኩም ሆነ እየዘፋፈንኩ ስፖንሰር ለመጠየቅ ዕድል አልነበረኝም ፡፡ ለብሄር ብሄረሰቦች በዓል የተገዛችውን ህብር የተባለች የክት መሳይ ጀልባ እየቃኘሁ ሀይቅ ላይ ወደቆመው ጣይቱ መዝናኛ በዝግታ አመራሁ ፡፡ የኔ አሰሳ በዚሁ ተፈጸመ ፡፡ ‹ ተፈጸመ › የሚባለው የበዓሉ ግርማ ጀግና ወይም ‹ ጦሰኛ › መጽሀፍ ግን እንዲህ ይላል ‹‹ ህይወት አንድ ቦታ ላይ አትቆምም … ትቀጥላለች ያንዱን ህይወት ከሌላው ጋር ድርና ማግ እያደረገች … ››

  ኦሮማይ !!!


  0 0

  negaso gidadaየአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ዋና ጸሀፊ አቶ ትግስቱ አወሉ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት እንደተናገሩት የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በዚሁም መሰረት የአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ በመጪው አመት መስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ላይ እንዲደረግ በፓርቲው ስትራቴጂክ እቅድ መሰረት አድርጎ እንደሚያካሂድ አስረድተዋል፡፡ በፓርቲው ደንብ ለሊቀመንበሩ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የነበሩትን ኢ/ር ዘለቀ ረዲን በስራ አፈፃፀም ብቃት ማነስ ምክንያት አንስተው በቦታው አቶ ስዩም መንገሻን መተካታቸውን ለምክር ቤቱ አሳውቀዋል፡፡ ምክር ቤቱም ሹመቱን አፅድቋል፡፡ አቶ ትግስቱ ጨምረውም ባለፈው ረቡዕ በሰንደቅ ጋዜጣ ለአንድነት ፓርቲ አሉታዊ አመለካካት ባለቸው አካላት የወጣውን መሰረተ ቢስ ውንጀላና በፓርቲው ስራአስፈፃሚ አባል በነበሩት ኢንጅነር ዘለቀ ረዲ በተሰጠው የሀሰት መረጃ ዙሪያ ኢንጅነር ዘለቀ በተገኙበት ሰፊውይይት መደረጉን አብራርተዋል፡፡
  ምክር ቤቱ በሰጠው ውሳኔ መሰረትም ነገ ሰኞ ሰንደቅ ጋዜጣ ያወጣውን ሀሰተኛ መረጃ የሚያስተካክል መግለጫ እንዲሰጥ ኢ/ር ዘለቀን በሚመለከትም ጉዳዩ ለብሔራዊ ዲሲፕሊን ኮሚቴ እንዲመራ መወሰኑን የምክር ቤቱ ጸሀፊ ገልፀዋል፡፡

  የሰንደቅ ጋዜጣ ዘገባን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

  ከጥቂት ወራት በፊት በኢሳት ላይ ቀርበው “መለስ ዘረኛ አልነበረም” ሲሉ የካዱት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በቅርቡ ከወያኔው የራድዮ ጣቢያ ፋና ጋር አድርገውት የነበረውን አወዛጋቢ ቃለ ምልልስ ካላደመጡት እንዲያዳምጡት ለትዝብት እዚህ አቅርበነዋል።


  0 0

  Penበደቡብ ክልል በቤንች ማጂ ዞን በሚገኘው ሚዛን 2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት በተነሳው ግጭት ሶስት ተማሪዎች መቁሰላቸውና ከሚያዚያ 10 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ ትምህርት መቋረጡን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ ፡፡ እንደ ፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለፃ ከሆነ ከሚያዚያ 7 ቀን 2005ዓ.ም. ጀምሮ
  በትምህርት ቤቱ ተማሪዎችና አስተዳደር አካላት በተነሳ አለመግባባት ከፍተኛ እረብሻ በመፈጠሩ እንደሆነ ተገልጧል፡፡ ለረብሻው መንስኤው ለትምህርት ቤቱ ከአሜሪካ በተሰጠው የትምህርት ዕድል የ12ኛ ክፍል የመሰናዶ ተማሪዎች መካከል በተደረገው ውድድር ከሴቶች ተማሪ መድኃኒት ስታሸንፍ ከወንዶች ደግሞ በጀመሪያ
  ተማሪ ጌታመሳይ ማሸነፉ ከተጠቆመ በኋዋላ በተደረገ የውጤት ማጣራት ሂደት ተማሪ ዮሐንስ ማለፉ መለጠፉ ነው፡፡
  ይህንንም ተከትሎ በተለይ የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ በወንዶች ተማሪ ዮሐንስና ተማሪ ጌታመሳይ ውድድር ላይ የውጤት አሰራር ስህተት በመኖሩን በተማሪዎችና በትምህርት ቤቱ መምህራንና አስተዳደር አካላት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት መማር ማስተማሩ ሂደት መቋረጡ ተጠቁሟል፡፡
  በመጨረሻም በተደረገው የውጤት ማጣራት መሰረት በውድድሩ ያለፈው ተማሪ ዮሐንስ መሆኑንም ምንጮቻችን አስታውሰዋል፡፡


  0 0

  “ፓርቲው ህዝብ ለምርጫ ያልወጣው በጠርናፊዎች ድክመት
  ነው የሚል አቋም ላይ ደርሷል” ውስጥ አዋቂ ምንጮች

  ባለፈው ሳምንት ሚያዝያ 6 በመላው ሀገሪቱ በተካሄደው የአካባቢና የከተማ ምክር ቤት ምርጫ እጅግ ጥቂት መራጭ በመሳተፉ ኢህአዴግ ተደናግጦ ግምገማ እንደጀመረ ለፓርቲው ቅርበት ያላቸው ውስጥ አዋቂ ምንጮች ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡

  eprdfምንጮቹ ለፍኖተ ነፃነት እንዳስረዱት ኢህአዴግ አንድ ለ አምስት ህዝቡን እንዲያደራጁ ያሰማራቸውን ጠርናፊዎች በግምገማ እያተራመሳቸው ነው፡፡ እንደምንጮቹ መረጃ ኢህአዴግ በመላው ሀገሪቱ የጥርነፋ መዋቅር አደራጅቷል፤ መዋቅሩ የግለሰቦችን ዝርዝር መረጃ ለደህንነት አካላት ማስተላለፍ፣ በምርጫ ወቅት ኢህአዴግ እንዲመረጥ ማስገደድ እና ፓርቲውና መንግስት ላይ የሚነሱ ተቃውሞዎችን ለመቆጣጠር ተብሎ የተደራጀ ነው፡፡ ሆኖም ባለፈው ሳምንት በተደረገው ምርጫ አንድ ለአምስት የተጠረነፈው አብዛኛው ህዝብ ለምርጫ አለመውጣቱ ኢህአዴግን አስደንግጦታል፡፡ በዚሁ ምክንያትም ጠርናፊዎቹን “የምርጫ ሰራዊት በአግባቡ አላንቀሳቀሳችሁም” በማለት ጥብቅ ግምገማ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
  የፍኖተ ነፃነት የመረጃ ምንጮች እንደሚያስረዱት በተለይ በአዲስ አበባ በሁሉም ወረዳዎች ያሉት የኢህአዴግ ካድሬዎችና የህዋስ አመራሮች አንድ ለ አምስት የጠረነፏቸውን ግለሰቦች ስም ዝርዝር ለአለቆቻቸው ከቃለመሀላ ጋር አስመዝግበዋል፤ ፓርቲውም ከተጠረነፈው ህዝብ መሀከል ቢያንስ 80 በመቶ እንደሚመርጠው በካድሬዎቹ
  ማረጋገጫ ተሰጥቶታል፡፡ ለኢህአዴግ በደረሰው ዝርዝር መሰረት ለምርጫ ያልወጡ ተጠርናፊዎችን ዝርዝር ከፍተኛ በመሆኑ ጠርናፊዎችን መገምገም ጀምሯል፡፡ ጠርናፊዎቹና ሌሎች የኢህአዴግ ካድሬዎችም ቤት ለቤት እየዞሩ የተጠረነፉ ሰዎች ለምን እንዳልመረጡ እንዲጠይቁና እንዲያስጠነቅቁ ኢህአዴግ ትዛዝ አውርዷል፡፡
  በተያያዘ ዜና ባለፈው ሳምንት በተደረገው ምርጫ በርካታ መራጮች ድምፅ ያልተሰጠበት ወረቀት ኮሮጆ ውስጥ በመክተታቸው የምርጫ አስፈፃሚዎች እየተመለከቱ ባዶ ወረቀቱ ላይ ለኢህአዴግ ምልክት እየተደረገ እንደተቆጠረና የተለያዩ የተቃውሞ መልዕክቶች የተፃፉባቸው ወረቀቶችም በብዛት መገኘታቸውን ከተለያዩ አካባቢዎች ተጠናቅረው ለፍኖተ ነፃነት የረደሱ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡


  0 0

  nebese turወ/ሮ ሰፊያን እንደዋጋው የተባሉት የቤት እመቤት የህክምና ባለሙያዎች ተገቢውን ኃላፊነት ባለመወጣታቸው ህይወታቸው ማለፉን ቤተሰቦቻቸው ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል አስታወቁ፡፡ የሟች ቤተሰቦች በሠነድ አስስደግፈው ለዝግጅት ክፍላችን እንዳስታወቁት የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታ የዕለቱ ተረኛ ሐኪሞች በፈጠሩት ኃላፊነት የጎደለው አገልግሎት አሰጣጥ የእህታቸውን ህይወት ሊያጡ ችለዋል፡፡የሟች ቤተሰቦች እህታችን አጣን የሚሉበት ሁኔታ ሲያስረዱ “እህታችን መንታ ማርገዟ ተነግሯት ተገቢውን የህክምና ክትትል እያደረገች የእርግዝና ጊዜዋን ጨርሳለች ፡፡ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ/ም ለሊት ምጥ ያዘኝ አለች፡፡ እያማጠችና እየተሰቃየች ነጋ በማግስቱ ጠዋት ነተስተን ሳሪስ ጤና ጣቢያ ወስደናት፤ ጤና ጣቢያው የደረሰነው 4 ሰዓት ነው፡፡ ለጊዜው ምንም ዕርዳታ ሳይደረግ 6 ሰዓት ሆነ፡፡ የጤና ጣቢያው ሠራተኞች ለምሳ ወጡ፡፡ 7 ሰዓት ሲመለሱ የላብራቶሪ ምርመራ አድርገው ከአቅማችን በላይ ስለሆነ ብለው ለጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፖታል ሪፈር ተጻፉልን፡፡
  ከቀኑ 8 ሰዓት ሲሆን ጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል ደረስን፡፡” በማለት ይገልጻሉ፡፡
  ቤተሰቦቿም በመቀጠልም ሲያብራሩ “8 ሰዓት ሆስፒታሉ ብንደርስም ከ8-11 ሰዓት ድረስ ከሆስፒታሉ ምንም ዓይነት እርዳታ ማግኘት አልቻለችም፡፡ ከ11 ሰዓት በኃላ ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ሪፈር ጻፉልን፡፡ 12 ሰዓት ሲሆን ዘውዲቱ ሆስፒል ደረስን፡፡ የዘውዲቱ ሆስፒታል የዕለቱ ተረኞች ምንም እርዳታ ሳያደርጉ ተኝታ መታከም
  አለባት፡፡ እኛ አልጋ የምንሰጠው እኛ ጋ ክትትል እያደረጉ ለቆዩ ታካሚዎች ነው፡፡ ስለዚህ ወደ መጣችሁበት ሆስፒታል ተመለሱ፤ ብለው ጻፉልንና ተመልሰን ወደ ጥሩነሽ ቤንጂንግ ሆስፒታል ሄድን፡፡ የዕለቱ ሐኪሞች ተመልሰን ስንመጣ ተቀብው ሊያስተናግዱን አልቻልንም፡፡ የደረስነው ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ነው፡፡ ሐኪሞች በአንድ ክፍል ተሰብስበው “ሰው ለሰው” ድራማ ይመለከቱ ነበር፡፡ ቀን የተመለከተቻት ሐኪምም ቆማ ድራመውን ትመለከታለች እህታችን ህመሙ ጨምሮባት የስቃይ ድምጽ ታሰማለች፡፡ ደም ይፈሳታል፡፡ ኸረ እባካችሁ ልትሞትብን ነው! እርዳታ ስጡልን ብለን ለመንን፤ ከውጪ የጥበቃ ሠራተኞች ጠርተው ሆስፒታሉን እየረበሹ ስለሆነ አስወጧቸው ብለው አስወጡን፤ ባለሞያዎቹ እኛ ነን እንጂ እናንተ አይደላችሁም ምታውቁት መውለጃ ጊዜዋ ገና ነው ብሎን አግዳሚ ላይ አስቀምጠዋት እነሱ ወደ ድራማቸው ሄዱ፡፡ እኛም አላስችል ብሎን እየተመላለስን በቀዳዳ ስንመለከት ስትሰቃይ ተመልክተናል፡፡” ሲሉ በለቅሶና በቁጭት ሁኔታውን ይገልጹታል፡፡

  የሟች ቤተሰቦች በማያያዝም ሲናገሩ “እስከ ለሊቱ 6 ሰዓት ድረስ ምንም እርዳታ አላገኘችም:: ከሌሊቱ 6 ሰዓት አልጋ ተገኝቶላታል ገንዘብ ክፈሉ ተባልን ለጊዜው ደስ ብሎን ከፍለን አልጋ ይዛ ተኛች፡፡ ከቀን ጀምሮ እንደተመለከትነው አሁንም ደም ይፈሳትል የምጥ ስሜት የተናነቃታል፡፡ መርዳት ባለመቻላችን እያየን አዝነን
  ጥለን ወጣን፡፡ ከዚያ በኋላ መግባት እንደማንችልም ተነገረን፡፡ እስከ ለሊቱ 9፡15 ድረስ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለች ማወቅ አልቻልንም በትግስት ተቀምጠን ጠበቅን፡፡ ዘጠኝ ሰዓት ከሩብ ሲሆን ንድ ወንድና አንድ ሴት ልጅ በሠላም መገላገሏን ለእሷ የተመደበችውና ቆማ ድራማውን የምትከታተለዋ ሐኪም አበስረችን፡፡ ለልጆቹ ልብስ ጠየቀችን፤
  ይዘን ስለነበረ ሰጠናት፡፡ ማየት እንችል እንደሆነ ጠየቅን ቆይ አሁን ትረጋጋ ብላን ሄደች፡፡ ከንጋቱ 12 ሰዓት ሲሆን አሁንም ማየት እንድንችል ጠየቅን አሁን የሚያስፈልጋት አጥሚት ስለሆነ አምጡላት አሉን፤ ሰጠናት፡፡ እኛ ደግሞ አንድ ቀን ሙሉ ደም ሲፈሳት ስለዋለች ልባችን ሊረጋጋ ባለመቻሉ ማየት ፈለግን አልፈቀዱልንም የሰጠናትን አጥሚት ትጠጣም አትጠጣም ያወቅነው ነገር የለም፡፡ ሀኪሟ ተመልሳ መጥታ በጣም በጥሩ ሁኔታ ላይ ናት ከ2-7 ሰዓት ትወጣለች አለችን፡፡ ሁላችንም በጣም ደስ አለን፡፡ በየአቅጣጫው እየደወልን ለዘመድ አዝማድ ተናገርን፤ ይዘናት ለመውጣት ስንዘጋጅ ትንሽ ደም ስለፈሰሳት ደም ያስፈልጋታል አሉን፡፡ ሁላችንም የእህታችንን ህይወት ለማትረፍ ወደ ስታዲየም አካባቢ ደም ለመስጠት ቀይ መስቀል ሄድን ፡፡” በማለት ያስረዳሉ፡፡ አክለውም “ሟች እህታችን ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ በቤት ውስጥ ወልዳለች፡፡ የመጀመሪያ ልጇ 17 ዓመት ከሁለት ወሩ ሲሆን ሁተኛዋ ልጇ 16 ዓመቷ ነው፡፡ ሁለተኛዋ ልጇ ተደብቃ ገብታ እናቷን ስትመለከት በጀርባዋ ተንጋላ ተኝታለች
  አያኗም ተጫፍኗል፡፡ ብላ ነገረችን፡: እኛ ደም ለመለገስ ስንሯሯጥ የ17 ዓመት ከሁለት ወር የሆነውን ልጇን አስፈርመው አፕራሲዮን አደረግን አሉን፡፡ ከኦፕራሲዮን በኃላ መሞቷ ተነገረን፡፡ በምን ምክንያት ኦፕራስዮን ልትሆን እንደቻለች ሊያስረዱን አልቻሉም ዕድሜው 18 ዓመት ያልሞላ ልጅ ለምን ማስፈረም ፈለጉ?፡፡ አስክሬን ለማስረከብ
  እና ገንዘብ ለመቀበል ይህ ነው የማይባል በደል ደርሶብናል፡፡ አስክሬን ለማውጣት ገንዘብ ለመክፈል በሊፍት ውስጥ የገባውን ባለቤቷን መብራት ጠፍቶ ለ30 ደቂቃ በአየር እጥረት ተዳክሞ በብረት ታግለንና ሊፍቱን ፈልቅቀን ስናወጣው የሊፍት ሠራተኛው እረፍት ሄዷል መብራት ስለጠፋ ነው ብለው አላግጠዋል፡፡
  አስክሬኑን ከወሰድን በኋላ ከፍተን ስንመለከተው የተከፈተው አካሏ በአግባቡ አለመሰፋቱን ማየት ችለናል፡፡ እህታችን የሞተችው በሐኪሞች ጥፋት ነው፡፡ የተፈጸመብንን በደል ህዝብና የሚመለከተው የመንግስት አካል ይወቅልን፡፡” ሲሉ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍላችን ድረስ በመምጣት አስረድተዋል፡፡
  በጉዳዩ ላይ የጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል  ኃላፊዎች አስተያየት እንዲሰጡበት ተመላልሰን ጥያቄ አቅርበን ነበር፡፡ በተሰጠን መልስም “በዚህ ጉዳይ መልስ መስጠት የሚችሉት ኃላፊ የሉም፤ ጥያቄውን በደብዳቤ መጠየቅ አለባችሁ፤ ከመምጣታችሁ በፊት ስልክ ደውሉልን” በሚል ምክንያቶች የሆስፒታሉን አስተያየት ማካተት አልቻልንም፡፡ በጉዳዩ
  ላይ አስተያየት መስጠት የሚችል አካል ቢኖር አሁንም መግለጽ እደሚችል ዝግጅት ክፍሉ ያሳውቃል፡፡


  0 0

  man 1

  man 2

  man 3

  man 4

  man 5

  man 6ማን.ዩናይትድ ዛሬ ኦልትራፎርድ ላይ አስቶንቪላን በሮበን ቫንፐርሲ 3 ጎሎች በዜሮ አሸንፎ ፕሪምየር ሊጉን ለ20ኛ ጊዜ አሸንፏል። የማን.ዩናይትድን ሲዝን በትንሹ የሚዳስስ አጭር ዝግጅት ከዘ-ሐበሻ ተዘጋጅቷል ይከታተሉት።
  ማንቸስተር ዩናይትድ ከሰንደርላንድ ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ ሮቢን ቫን ፔርሲ ጎሉን ለማስቆጠሩ እርግጠኛ ነበር፡፡ በስታዲየም ኦፍ ላይት የውጤት መመዝገቢያ ላይ ግን ጎሉ የተቆጠረው በተጋጣሚው ተጫዋች ታየተስ ብራምብል መሆኑ ተፃፈ፡፡ በራስ ላይ የተቆጠረ ጎል ተደርጎ መውሰዱ ቫን ፔርሲ ያለ ጎል አልባ ደቂቃዎች መጨመራቸውን ቀጠለ፡፡ ሆላንዳዊው በክለቡ ማሊያ በመጨረሻ በተጫወተባቸው 10 ሰዓታት አንድ ጎል ማስቆጠር ተስኖታል፡፡ ለ594 ደቂቃዎች ማለት ነው፡፡ በዚህ ወቅት ላይ ማንቸስተር ዩናይትድ ከኤፍ.ኤ.ካፕ እና ከቻምፒየንስ ሊግ ውጭ ቢሆንም በፕሪሚየር ሊጉ ላይ ሰንደርላንድን ድል በመንሳት ለሰባተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸንፎ ወጥቷል፡፡ የቡድኑ የውድድር ዘመን የሊጉ ምርጥ ብቃት በታየበት ሰሞን ኮከቡ ጎል አግቢያቸው በጎል ድርቅ መመታት አስገራሚ ቢሆንም የሚነግረን ነገር አለ፡፡ ቡድኑ በሌሎች ቦታዎች ብቃቱን ማሳደጉን ያረጋግጥልናል፡፡
  ቻምፒየንስ ሊግ እጅግ አጓጊ በሆነ ደረጃ ላይ ባለበት በዚህ የሩብ ፍፃሜ ወቅት አንድም የእንግሊዝ ክለብ አይገኝበትም፡፡ ይህ ሲሆን ከ1996 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ቡድናቸው የማይዋዥቅ ብቃቱን የሚያበረክት ጎል አስቆጣሪ አለመያዛቸው ያስቆጫቸዋል፡፡ ከሪያል ማድሪድ ጋር በተደረጉት የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ላይ ጎል ማስቆጠር የቻለው የዩናይትድ ተጨዋች ዳኒ ዌልቤክ ብቻ ነው፡፡ ቫን ፔርሲ ከስፔኑ ኃያላን ጋር አልቀናውም፡፡ ከዚህም በኤፍ.ኤ.ካፑ በደርሶ መልሱ የቼልሲ ግጥሚያ ቫንፔርሲ በተጠባባቂነት ተቀይሮ ገብቶም የፈየደው ነገር የለም፡፡ በውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ላይ አላቋርጥ ብሎ የነበረው የጎል ፍሰት በዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ ሊመለስለት አልቻለም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቀድሞው የአርሰናል አጥቂ ለ622 ደቂቃዎች በሜዳ ላይ ቆይቶ አንድ ጎል ብቻ አግብቷል፡፡ ከዚያ ፊት ግን በአማካይ በየ99 ደቂቃው አንድ ጊዜ ኳስና መረብን ያገናኘ ነበር፡፡ ምናልባት ለሁለት ተከታታይ የውድድር ዘመናት ለየክለቦቹ ከሞላ ጎደል በሁሉም ጨዋታዎች ላይ የመሰለፉ ነገር አድክሞት ሊሆን ይችላል፡፡ አምናም ሆነ ዘንድሮ አርሰናል እና ማንቸስተር ዩናይትድ በቫን ፔርሲ ላይ ተመርኩዘው መቅረባቸው ግልጽ ነው፡፡
  በተለይ አርሰናል ለውጤታማነት በተለይ ቫን ፔርሲ ላይ የተንጠላጠለ መሆኑ ጉልህ ነበር፡፡ ዘንድሮ ያለ እርሱም ምን ያህል ጥንካሬው እንደላሸቀ ታይቷል፡፡ በማንቸስተር ዩናይትድ ዌይን ሩኒ ጎል የማስቆጠር ሸክሙን አግዞት 12 ጎሎችን አስቆጥሯል፡፡ ስምንት ጎሎችን ያገባው ሃቪዬር ሄርናንዴዝም የሸክሙ ሌላው ተካፋይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሺንጂ ካጋዋ በቅርቡ በኖርዊች ሲቲ ላይ ሃት ትሪክ ከመስራቱ በፊት ከቫን ፔርሲ ቀጥሎ የዩናይትድ ከፍተኛው ጎል አግቢ ፓትሪክ ኤቭራ (4)፣ ጆኒ ኢካንስ (3) እና ራፋኤል ዳ ሲልቫ (3) ነበሩ፡፡ አማካይ ክፍሉ ጎል የማስቆጠር እጥረት ገጥሞት ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ቫን ፔርሲ በድርጊቱ ተመቷል፡፡ በተለይ አንቶኒዮ ቫሌንሲያ፣ ሉዊስ ናኒ እና አሽሊ ያንግ ለችግሩ ኃላፊነት ሊወስዱ ይገባል፡፡ ሶስቱ አማካዮች ባለፈው የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ ላይ በድምሩ 18 ጎሎችን አስቆጥረው ጎል የሆኑ 30 ኳሶችን አቀብለው ነበር፡፡ ዘንድሮ ግን ሶስቱ በድምሩ አንድ ጎል ብቻ ያስቆጠሩ ሲሆን ያቀበሏቸው ጎል የሆኑ ኳሶቻቸው ብዛት ዘጠኝ ብቻ ናቸው፡፡ ሪያል ማድሪድ እና ቼልሲ ማንቸስተር ዩናይትድን ከቻምፒየንስ ሊግና ከኤፍ.ኤ.ካፑ ሲያስወጡት የፕሪሚየር ሊግ ተጋጣሚዎች ግን የኦልድትራፎርድ ክለብ ለ20ኛው ዋንጫ እንዲተም ፈቅደውለታል፡፡ ቡድኑ በዚህ ወቅት በፕሪሚየር ሊጉ ላይ እጅግ ደካማ ብቃት ካላቸው ቡድኖች መካከል ሁለቱን (ሬዲንግ እና ሰንደርላንድ) ገጥሞ ከብዙ ልፋት በኋላ ሁለቱንም ማሸነፍ የቻለው 1-0 ብቻ ነው፡፡ ሬዲንግ ከዩናይትድ ጋር ከመጫወቱ በፊት ባደረጋቸው ስድስት ግጥሚያዎች ሁሉ የተሸነፈ ቡድን ሲሆን ሰንደርላንድ ደግሞ ከስምንት ተከታታይ ጨዋታዎች አንድም ድል ያልተቀዳጀ ነበር፡፡
  በውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ማንቸስተር ዩናይትድ ከሚቆጠሩበት ጎሎች ይልቅ በእጥፍ ለሚበልጡ ጊዜያት ጎል ያስቆጥር ነበር፡፡ ከቫን ፔርሲ ብቃት መቀዝቀዝ በኋላ ግን ይህ ሊሆን አልቻለም፡፡ የሚያስቆጥራቸው ጎሎች ቢያሽቆለቁልም (በሊጉ ላይ) ሽንፈት አልገጠመውም፡፡ የዚህ አብይ ምክንያት የቡድኑ የተከላካይ መስመር ጥንካሬ መጨመር ነው፡፡ ሰር አሌክስ አጥቂያቸው ጎል ማምረት ሲያቆም ተከላካያቸው ብቃቱን አሳድጎ ከሽንፈቶች ታድጓቸዋል፡፡ ለ627 ደቂቃዎች አንድም ጎል ሊቆጠርበት አልቻለም፡፡
  በግብ ጠባቂነቱ ቦታ በውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ላይ ዴቪድ ደ ሂያ ቋሚ ተሰላፊነቱን ለአንደርስ ሊንዴጋርድ አሳልፎ ሊሰጥ እንደሚችል የሚያስጠረጥር ብቃት ነበረው፡፡ ሆኖም በራስ መተማመኑ ከውጤታማነት ጋር በማሳደግ አሁን ቋሚነቱን በአስተማማኝነት ይዟል፡፡ በጨዋታዎቹ ላይ የሚፈጽማቸው ስህተቶች ቁጥር ቀንሰዋል፡፡ አሁንም በራስ መተማመኑ ረገድ ከዚህም በላይ መጎልበት ያለበት ሲሆን በተለይ በክሮሶች ወቅት ያለው በቃላት የሚታማ መሆኑ ቀጥሏል፡፡ የጎል ሙከራዎችን በማዳር ረገድ ያስመዘገበው አሃዛዊ ብቃት በሊጉ በአንደኛ ደረጃ ላይ አስቀምጦታል፡፡ ወጣቱ ስፔናዊ ላይ ከሚሞክሩት የጎል ሙከራዎች 78% በመቶ ያህሉን ያድናል፡፡ በሊጉ ክለቦች በቋሚ ተሰላፊነት ከሚጫወቱት በረኞች ሁሉ ምርጡ ንፀሬ መሆኑነው፡፡ ብዙ የእግርኳስ አፍቃሪዎች በዴ ሂያ ላይ ተስፋ ሲቆርጡ ሰር አሌክስ ግን በእርሱ ፀንተው ቀመራቸው በመጨረሻ ፍሬውን ማፍራት ጀምሯል፡፡
  በተከላካዩ መስመር ሪዮ ፈርዲናንድ ተደናቂ ብቃቱን መልሶ አግኝቶታል፡፡ የኔማኒያ ቪዲች ከጉዳት መመለስ በመሀል ተከላካይነት ቦታ ላይ ከአቫንስ ጋር ለተሰላፊነት ከባድ ፉክክር ውስጥ አስገብቷቸዋል፡፡ የዚህ ጤናማ ፉክክር ውጤት ደግሞ የማንቸስተር ዩናይትድን የኋላ መስመር በቀላሉ የማይጣስ አድርጎታል፡፡ በርካታ ጨዋታዎችን ምንም ጎል ሳይቆጠርባቸው መውጣት ችለዋል፡፡ ይህም ሰር አሌክስ ፈርጉሰን የሊጉን ንግስና መልሶ ወደ ኦልድ ትራፎርድ ያመጡ ዘንድ ምክንያት ሆኗቸዋል።

  የዩናይትድ አጥቂዎች የዘንድሮ የጎል ስታቲስቲክስ
  ቫን ፔርሲ ሩኒ ሄርናንዴዝ ዌልቤክ ማን ዩናይትድ
  - ጎሎች 22 12 8 1 66
  - አንድ ጎል ለማግባት ስንት ጊዜ ኳስ ጋር ይገናኛል? 68.26 104.66 38.87 656 329.93
  - በየስንት ደቂቃዎች አንድ ጊዜ ጎል ያስቆጥራል? 126.47 132.66 85.5 1113 450
  - የመጨረሻ የሊግ ጎሉን ካስቆጠረ በኋላ የተቆጠሩት ደቂቃዎች 332 69 113 702 69
  የጎል ዕድልን ወደ ጎልነት የመቀየር ንፃሬ 17.27% 15.78% 24.24% 2.77% 14.53%


(Page 1) | 2 | 3 | .... | 621 | newer